id stringlengths 6 6 | term_en stringlengths 3 27 | term_local stringlengths 3 95 | language stringclasses 1
value | category stringlengths 4 20 ⌀ | definition_local stringlengths 78 494 | definition_en stringlengths 83 440 | example_local stringlengths 62 396 | example_en stringlengths 23 260 ⌀ | version stringclasses 1
value |
|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
am-001 | Access Point | የአገልግሎት ነጥብ | am | Channel | ተጠቃሚዎች፤ ክፍያዎችን፣ ገንዘብ መላክ/መቀበልን፣ ወይም እገዛ ማግኘትን የመሳሰሉ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ማከናወን የሚችሉበት ቦታ ሲሆን፤ ቦታውም በአካል (በገጽ-ለገጽ) አሊያም በዲጂታል (በርቀት) ሊሆን ይችላል፡፡ የባንክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ ኤ/ቲ/ኤም ማሽን፣ የፖስ ማሽን፣ የወኪል መደብር፣ የእጅ ስልክ፣ እና ኮምፒዩተር የአገልግሎት ነጥቦች ወይም ቦታዎች ናቸው፡፡ | A physical or digital location where users can interact with digital financial services-such as making payments, sending money, or getting support. Access points can include bank branch offices, ATMs, terminals at the POS, agent outlets, mobile phones, and computers. | አንድ ግለሰብ በሞባይል-ዋሌቱ ውስጥ ያለውን ቀሪ ገንዘቡን ለማወቅ፤ የሞባይል-ገንዘብ ወኪል ሆኖ ወደሚሠራ ሱቅ በመሄድ ወይም በመደበኛ የእጅ ስልኩ የዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድን በማስገባት መጠየቅ ይችላል፡፡ ሁለቱም ዘዴዎች አንደ አገልግሎት ነጥቦች ይቆጠራሉ፡፡ | A mobile money agent kiosk or a USSD code on a basic phone that allows users to check their balance are both considered access points. | 1.0 |
am-002 | Accessibility | ተደራሽነት | am | Concept | በሰዎች የቦታ ርቀት፣ በትምህርት ደረጃ፣ እና በአካል የመገኘት ችሎታ፤ ብሎም ቴክኖሎጂ የመጠቀም ዕድል በመኖር እና ባለመኖር ሳይገደብ፤ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት አቅርቦት ሲኖር እና የሰዎች ተጠቃሚነት የተረጋገጠ ሲሆን ነው፡፡ | The ease with which individuals-regardless of their location, literacy level, physical ability, or access to technology-can use and benefit from digital financial services. | በመደበኛ የእጅ ስልኮች ላይ በአገርኛ ቋንቋ የዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮዶችን በማስገባት የሚያስተናግድ የሞባይል-ገንዘብ አገልግሎት ሰጪ፤ አገልግሎቱ ስማርት የእጅ ስልክ ለሌላቸው የገጠር ተጠቃሚዎች ጭምር ተደራሽ ነው፡፡ | A mobile money service that works via USSD and provides instructions in local languages is considered accessible to rural users without smartphones. | 1.0 |
am-003 | Account | ሒሳብ (እንደ አገባቡ የሒሳብ ቁጥር) | am | Product/Instrument | የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ፤ የአንድ ደንበኛውን ግላዊ መረጃ የሚሰንድበት ዓይነተኛ ቋት ሲሆን፤ ይህም ደንበኛው ገንዘብ ለማስቀመጥ፣ ውርኝትን/የገንዘብ እንቅስቃሴን ለመከታተል፣ ብሎም ገንዘብ መላክ፣ መቀበል፣ እና መቆጠብን የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችለዋል፡፡ | A personal record with a financial service provider where users can store money, track transactions, and access services like sending, receiving, or saving funds. | የሞባይል-ገንዘብ የሒሳብ ቁጥር ያላቸው የገጠር ነዋሪዎች፤ በእጅ ስልካቸው አማካኝነት ለቤተሰባቸው ገንዘብ ለመላክ፣ ዕቃ ሲገዙ ለመክፈል፣ እና ሐዋላን ለመቀበል ይችላሉ፡፡ | A mobile money account lets users in rural areas send money to family, pay for goods, and receive remittances using their phone. | 1.0 |
am-004 | Active User | ህልው ተጠቃሚ | am | Metric | ገንዘብ መላክ፣ ክፍያዎችን መፈጸም፣ ወይም ልዩ ልዩ የፋይናንስ ተግባራትን የመሳሳሉ ውርኝቶችን ለማከናወን፤ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን አዘውትሮ የሚገለገል አካልን (ግለሰብ፣ ድርጅት) ይገልጻል፡፡ | A person that regularly uses digital financial services to perform transactions such as sending money, making payments, or accessing financial products. | በሞባይል-ገንዘብ አማካኝነት በየሳምንቱ ለቤተሰቡ ገንዘብ የሚልክ፣ የአየር ጊዜ የሚገዛ፣ እና ማዳበሪያ የሚሸምት አርሶ-አደር፤ እንደ ‹‹ህልው ተጠቃሚ›› ይቆጠራል፡፡ | A farmer who uses their mobile money every week to send money to family, buy airtime, and pay for fertilizer is considered an active user. | 1.0 |
am-005 | Agent | ወኪል | am | Role/Actor | ከወካዩ ድርጅት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፤ ጥሬ ገንዘብ ገቢ እና/ወይም ወጪ ማድረግን፣ ሒሳብ መክፈትን፣ እና ለደንበኞች እገዛ መስጠትን የመሳሰሉ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን የሚሠራ ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፡፡ | A person or business authorized to provide digital financial services on behalf of a provider—such as cash-in, cash-out, registration, and customer support. | ወኪል የሆነ ባለሱቅ፤ በባንክ ወይም በ[ዲጂታል] ዋሌት አገልግሎት ሰጪ ምትክ ወይም ፈንታ፤ ደንበኞች ገንዘባቸውን ከሞባይል-ገንዘብ ሒሳባቸው እንዲያወጡ ወይም እንዲያስገቡ ያግዛቸዋል፡፡ | A shop owner helps customers deposit or withdraw money from their mobile money on behalf of a bank or wallet provider is an agent. | 1.0 |
am-006 | Agent Network | የወኪል ትስስሮሽ | am | Infrastructure | በአንድ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ሥር ሆነው፤ በተለያዩ ቦታዎች፤ ጥሬ-ገንዘብ ገቢ እና/ወይም ወጪ ማድረግ፣ ሒሳብ መክፈት፣ እና ለደንበኞች እገዛ መስጠት የመሳሰሉ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን የሚሰጡ የወኪሎች ስብስብ ወይም ቡድን ነው፡፡ | A group of agents working under a financial service provider to deliver DFS like cash-in, cash-out, registration, and support across different areas. | በወኪል ትስስሮሽ ከሚታቀፉት ውስጥ አንዱ፤ በእጅ ስልክ ወይም በመታወቂያ አማካኝነት ለአካባቢው ማኅበረሰብ አባላት የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሱቅ ነው፡፡ | An agent network may include, mobile vendors who help people access digital financial services in their communities using phones and ID cards. | 1.0 |
am-007 | Agent Outlet | የወኪል መደብር | am | Channel | አንድ ወይም ብዙ የዲጂታል ፋይናንስ ድርጅቶችን ወክሎ፤ ለደንበኞች የምዝገባ እንዲሁም የጥሬ-ገንዘብ ገቢ እና/ወይም ወጪ አገልግሎት የሚሰጥበት ሥፍራ ነው፡፡ ወኪሉ በተመሳሳይ ወቅት ከአንድ በላይ የዲጂታል ፋይናንስ ድርጅቶችን ወክሎ የሚሠራ ከሆነ፤ ከአንድ በላይ የወኪል ስንቆች አሉት ማለት ነው፡፡ አብዛኛው የወኪል መደብሮች፤ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን ከዋናው ሥራቸው ላይ በተደራቢነት የሚያከናውኑ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው፡፡ | A physical location that carries one or more agent tills, enabling it to perform enrolment as well as cash-in and cash-out transactions for customers on behalf of one or more providers. Agent outlets may have other businesses (typically SMEs) and support functions. | የወኪል መደብር የሚባለው፤ የደንበኞችን የእጅ ስልክ እና መታወቂያ ተጠቅሞ ገንዘብ ማስገባት፣ ጥሬ-ገንዘብ ወጪ ማድረግ፣ አሊያም የሞባይል-ገንዘብን የተመለከቱ እገዛዎችን የሚሰጥ አካል (ለምሳሌ አነስተኛ የችርቻሮ ሱቅ) ነው፡፡ | An agent outlet can be a small retail shop where customers go to send money, cash out, or get help with their mobile money using their phone and ID. | 1.0 |
am-008 | Agent Till | የወኪል ስንቅ | am | Infrastructure | የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ሰጪው/ወካዩ፤ ለወኪሉ የሚከፍትለት የዲጂታል ሒሳብ ወይም ዋሌት ሲሆን፤ ይህም ወኪሉ የደንበኞቹን የገቢ እና የወጪ ጥያቄዎችን የሚያስተናግድበት ወረት (የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ) የሚቀመጥበት ነው፡፡ | A digital account or wallet assigned to an agent by a financial service provider, used to manage float (working capital) for processing customer transactions like deposits and withdrawals. | አንድ ወኪል፤ ወደ ሞባይል-ዋሌታቸው ገንዘብ ማስገባት ከሚሹ ደንበኞች ገንዘብ ተቀብሎ ለማኖር፤ እንዲሁም ጥሬ-ገንዘብ ሲፈልጉ አውጥቶ ለመስጠት፤ እና ለመሳሰለው ጉዳይ የወኪል ስንቅን ይጠቀማል፡፡ | An agent uses their till to receive money from customers who want to deposit into their mobile wallets, and to give out cash when customers withdraw. | 1.0 |
am-009 | Aggregator | ጀማይ | am | Role/actor | በርካታ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪዎችን ከተጠቃሚዎች ወይም ወኪሎች ጋር የሚያገናኝ አማካይ ድርጅት ወይም ፕላትፎርም ሲሆን፤ ውርኝቶችን ያቀባብላል፤ የእርስ በርስ መሰናሰልን ያመቻቻል፤ ተቋም/ፕላትፎርም-ዘለል ተናባቢነትን (interoperability) ያረጋግጣል፡፡ አንድ ጀማይ ለመሥራት የሚፈቀድለት ነገሮች አብዛኛውን ጊዜ በአሠራር ደንቦች ይወሰናሉ፡፡ | A company or platform that connects multiple financial service providers to users or agents, helping to route transactions, manage integrations, and ensure interoperability. Scheme rules often specify what aggregators are allowed to do. | ጀማይ፤ አንድ የሞባይል-ገንዘብ አገልግሎት በሁሉም የተለያዩ ባንኮች እና ቴሌኮሞች ጭምር ላይ መገልገል እንዲቻል የሚያደርግ አማካይ አካል ሲሆን፤ ይህም ተጠቃሚዎች በእያንዳንዱ አገልግሎት ሰጪ ዘንድ በተናጠል ሒሳብ መክፈት ሳያስፈልጋቸው፤ ደንበኛ ከሆኑበት ከአንዱ አገልግሎት ሰጪ ወደሌላው አገልግሎት ሰጪ ገንዘብ መላክ ወይም ቢል መክፈል ያስችላቸዋል፡፡ | An aggregator enables a mobile money to work across different banks and telecoms, so users can send money or pay bills without needing separate accounts for each provider. | 1.0 |
am-010 | App | መተግበሪያ | am | null | መተግበሪያ ማለት፤ ገንዘብ ለመላክ፣ ክፍያዎችን ለመፈጸም፣ ቀሪ ገንዘብን ለማወቅ፣ አሊያም ተቀማጭን ለመቆጠብ የመሳሰሉ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማግኘት፤ ተጠቃሚዎች በስማርት የእጅ ስልኮቻቸው ወይም በታብሌቶቻቸው ላይ የሚጭኑት ሶፍትዌር ነው፡፡ | An app is a software program that users can download on smartphones or tablets to access digital financial services like sending money, paying bills, checking balances, or saving. | የታክሲ ሹፌር [በእጅ ስልኩ ላይ በጫነው] የፋይናንስ መተግበሪያ አማካኝነት፤ ከደንበኞቹ ዲጂታል ክፍያዎችን ይቀበላል፤ የነዳጅ ካርድን ይሞላል፤ ብሎም የየእጅ ስልክ ዳታ ሒሳብን ይከፍላል፡፡ | A taxi driver uses a financial app to receive digital payments from customers, top up fuel cards, and pay for mobile data. | 1.0 |
am-011 | Balance | አሁናዊ ሒሳብ | am | Metric | በተጠቃሚ ሒሳብ ወይም ዋሌት ውስጥ አሁን ላይ ያለው የገንዘብ መጠን ማለት ነው፡፡ ይህም ተጠቃሚው ምን ያህል ገንዘብ መክፈል፣ መላክ፣ ወይም ማውጣት እንደሚችል የሚያሳይ አኃዝ ነው፡፡ | The amount of money currently available in a user's account or wallet. It shows how much the user can spend, send, or withdraw. | ምንም ገንዘብ ያልነበረው የአቶ አበበ የባንክ ሒሳብ፤ በትላንትናው ዕለት 4 ሺህ ብር ገቢ ከተደረገበት በኋላ፤ አቶ አበበ ዛሬ 1 ሺህ ብር ወጪ ስላደረገ፤ የአቶ አበበ አሁናዊ ሒሳብ 3 ሺህ ብር ነው፡፡ | null | 1.0 |
am-012 | Bank Accounts | የባንክ ሒሳብ (እንደ አግባቡ የደንበኞች የባንክ ሒሳብ) | am | Products/Instrument | የደንበኞች የባንክ ሒሳብ ማለት፤ በፋይናንስ ተቋሙ የሚሰነድ የግለሰቦች ወይም የድርጅቶች መረጃ ሲሆን፤ ተጠቃሚዎች ገንዘብ ማስቀመጥ፣ መቀበል፣ ብሎም ገንዘብ ማውጣት፣ ማዘዋወር፣ እና መቆጠብን የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችላቸዋል፡፡ አገልግሎቶቹን በቅርንጫፎች፣ በኤ/ቲ/ኤም/፣ አሊያም በእጅ ስልክ (በዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድ ወይም በመተግበሪያ) ማግኘት የሚቻል ሲሆን፤ አገልግሎቱ የተገኘው በእጅ ስልክ ከሆነ ደግሞ ‹‹የሞባይል ባንክ አገልግሎት›› ይሰኛል፡፡ | A bank account is a personal or business record held by a financial institution where users can store money, receive payments, and access services like withdrawals, transfers, and savings. It can be accessed through branches, ATMs, USSD or mobile apps, in which case it is sometimes referred to as mobile banking. | እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ወ/ት አበበች የቤቷን የኤሌክትሪክ ቢል ክፍያ ትፈጽም የነበረው ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአካል በመሄድ ነበር፡፡ ነገር ግን ኮርፖሬሽኑ የጥሬ-ገንዘብ ክፍያን በማስቀረት ደንበኞች በዲጂታል ፋይናንስ አማራጮች ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ የሚያስችል አሠራር በመጀመሩ፤ ወ/ት አበበች የባንክ ሒሳብ መክፈት አስፈልጓታል፡፡ | null | 1.0 |
am-013 | Bill payment | ቢል ክፍያ | am | Use case | አንድ ተጠቃሚ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት አማካኝነት እንደ ኤሌክትሪክ፣ ውሀ፣ እና ኢንተርኔት/በይነ-መረብ ለመሳሰሉ ግልጋሎቶች (utilities)፤ ብሎም ለትምህርት ቤት እና ለመሰል አገልግሎቶች የሚጠበቅበትን ክፍያ ሲፈጽም የሚኖረው የፋይናንስ ውርኝት ነው፡፡
የቢል ክፍያዎችን፤ በሞባይል-ገንዘብ፣ በባንክ አገልግሎት መተግበሪያዎች፣ በዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድ፣ ወይም በወኪል መደብሮች አማካኝነት መፈጸም ይቻላል፡፡ | A financial transaction where a user pays for services or utilities—such as electricity, water, internet, or school fees-using digital financial services. Bill payments can be made through mobile money, banking apps, USSD, or agent outlets. | አንድ ግለሰብ ወደ ሞባይል-ገንዘብ ወኪል ሄዶ ጥሬ-ገንዘብ ከሰጠው በኋላ፤ የኤሌክትሪክ/የመብራት ካርዱን የዲጂታል ገንዘብ እንዲሞላለት ጠየቀው፡፡ | A person visits a mobile money agent, gives cash, and asks the agent to recharge their electricity card digitally. | 1.0 |
am-014 | Bill Spliting | ቢል መጋራት | am | null | ሁለት እና ከዚያ በላይ ሰዎች፤ እንደ ምግብ፣ መጓጓዣ፣ እና ግልጋሎት (utility) የመሳሰሉ ወጪዎችን በመካፈል፤ እያንዳንዳቸው የየድርሻቸውን በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት አማካኝነት የሚከፍሉበት ሁኔታ ነው፡፡ | Bill splitting is when two or more people share the cost of a payment—such as a meal, transport, or utility- and each person pays their portion using digital financial services. | በቡድን ሆነው በምግብ ቤት የተመገቡ ጓደኛማቾች፤ በቢሉ/በደረሰኙ ከተጠቀሰው ድምር ሒሳብ ለእያንዳንዳቸው በነፍስ-ወከፍ የሚደርስባቸውን መጠን፤ በሞባይል-ገንዘብ አማካኝነት ስለከፈሉ ቢል ተጋርተዋል፡፡ | A group of friends who eat at a restaurant use mobile money to each pay their share of the total bill. | 1.0 |
am-015 | Borrowing | መበደር (እንደአገባቡ ብድር) | am | Product/Instrument | መበደር/ብድር ማለት፤ አንድ ተጠቃሚ እንደ ባንክ፣ አነስተኛ የፋይናንስ ድርጅት፣ ወይም የዲጂታል ብድር አቅራቢ ካሉ ከመደበኛ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪዎች ገንዘብን መውሰድ ሲሆን፤ ይህም ገንዘቡን ቆይቶ ለመመለስ በመስማማት ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ብድሩ ወለድ ይሰላበታል፡፡ ብድሩን በእጅ ስልክ (በመተግበሪያዎች አሊያም በዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድ)፣ ወይም በወኪል-አገዝ አገልግሎት አማካኝነት ማግኘት ይቻላል፡፡ | Borrowing is when a user receives money from a formal financial service provider—such as a bank, microfinance institution, or digital credit platform—with an agreement to repay it later, often with interest. Borrowing can be accessed through mobile apps, USSD, or agent-assisted services. | አንድ ነጋዴ፤ ፈቃድ ባለው የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም በወጣ የእጅ ስልክ መተግበሪያ አማካኝነት ገንዘብ ተበድሮ የሱቁን ዕቃ ያሟላ ሲሆን፤ ብድሩም በየሳምንቱ በተከታታይ ክፍያዎች/ተቆራጮች የሚመመለስ ነው፡፡ | A small shop owner borrows money through a mobile app offered by a licensed microfinance institution to restock goods and agrees to repay in weekly installments. | 1.0 |
am-016 | Bulk payments | ጅምላ ክፍያ | am | Use Case | በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማእቀፍ፤ አንድ ድርጅት ወይም ግለሰብ በአንድ ጊዜ ለብዙ ተቀባዮች ገንዘብ እንዲልክ የሚያስችለው አሠራር ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ደሞዝተኞችን፣ ሻጮች/አቅራቢዎችን፣ እና የማኅበራዊ ዋስትና ተጠቃሚዎችን ለመክፈል የሚውል አሠራር ሲሆን፤ የሚከወነውም በሞባይል-ገንዘብ ዳሽቦርዶች፣ በባንክ ፖርታሎች፣ ወይም በተቀናጁ የሶፍትዌር ማናበቢያዎች (integrated APIs)፤ እና በመሳሰሉት መደበኛ አሠራሮች አማካኝነት ነው፡፡ | Bulk payments refer to a digital financial service that allows organizations or individuals to send money to multiple recipients at once. This is commonly used for salaries, vendor payments, or social transfers, and is processed through formal platforms such as mobile money dashboards, banking portals, or integrated AP... | አንድ ኩባንያ በሞባይል-ገንዘብ ፕላትፎርም አማካኝነት፤ በአንድ ውርኝት ብቻ ለሁሉም ሠራተኞቹ ወርኃዊ ደሞዛቸውን በየግል [ኢ-] ዋሌታቸው እንዲገባ አድርጓል፡፡ ይህ መሰል አሠራር ጅምላ ክፍያ ይባላል፡፡ | A company uses a mobile money platform to send monthly salaries to all its employees’ wallets in one transaction. | 1.0 |
am-017 | Buy Now, Pay Later (BNPL) | የዱቤ ግዢ | am | Product/Instrument | ደንበኞች ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን አሁን ወስደው፤ ነገር ግን ዋጋውን ቆይተው እንዲከፍሉ የሚያስችላቸው አሠራር ሲሆን፤ ብዙውን ጊዜ የአከፋፈሉ ዘዴ ደግሞ ወደፊት ባሉ በተለያዩ የጊዜ እርከኖች ላይ ነው፡፡ አገልግሎቱ ባብዛኛው በዲጂታል ዘዴዎች ወይም መተግበሪያዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ ወለድ ወይም የአገልግሎት ክፍያ ሊጠየቅበትም ላይጠየቅበትም ይችላል፡፡ | A payment option that lets customers buy goods or services immediately and pay for them later, often in installments. It is usually offered through digital platforms or apps and may or may not include interest or fees. | ‹‹መሠረ›› ሱፐርማርኬት፤ ‹‹ሀለሐ›› ከሚሰኝ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ጋር ባለው ስምምነት መሠረት፤ የ‹‹ሀለሐ›› ደንበኞች በወር እስከ 3 ሺህ ብር ድረስ ከ‹‹መሠረ›› ሱፐርማርኬት የዱቤ ግዢ መፈጸም ይችላሉ፡፡ ሸማቾቹ ዕቃውን ከወሰዱ በኋላ እስከ 6 ወራት ድረስ የዕቃውን ዋጋ ከእነወለዱ ለ‹‹ሀለሐ›› ከከፈሉ በኋላ፤ ‹‹ሀለሐ›› ደግሞ ለ‹‹መሠረ›› የዕቃውን ዋጋ ብቻ ያስተላልፍለታል፡፡ | null | 1.0 |
am-018 | Open loop | ክፍት ዑደት | am | Infrastructure | ተጠቃሚዎች ወደተለያዩ ፕላትፎርሞች እና አገልግሎት ሰጪዎች ገንዘብን ለመላክ፣ ለመቀበል፣ ወይም ለመክፈል የሚፈቅድ የዲጂታል ፋይናንስ አሠራር ነው፡፡ ገንዘቡ ወደ ሌሎች ባንኮች፣ የሞባይል-ሙዳዮች፣ እና ሌሎች የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪዎች ማስተላለፍን ይፈቅዳል፡፡ | An open loop is a digital financial system where users can send, receive, or spend money across different platforms and providers. It allows money to move between banks, mobile wallets, and other financial services. | አቶ መንሱር እርሱ ከሚጠቀምበት ውጪ የሞባይል-ገንዘብ ከሚገለገለው ከአቶ ሸምሱ ገንዘብ ለመቀበል ስለቻለ፤ አቶ ሸምሱ ደንበኛ የሆነበት ፕላትፎርም ወይም ድርጅት ክፍት ዑደት ያለው አሠራርን ይከተላል ማለት ነው፡፡ | A merchant accepts payments from customers using different mobile money providers through an interoperable payment system. | 1.0 |
am-019 | Closed loop | ዝግ ዑደት | am | Infrastructure | በአንድ አገልግሎት አቅራቢ/ድርጅት ውስጥ ባሉ ተጠቃሚዎች መካከል ብቻ ገንዘብ ለመላክ፣ ለመቀበል፣ ወይም ለመክፈል የሚያስችል የዲጂታል ፋይናንስ አሠራር ነው፡፡ ገንዘቡ ወደ ሌሎች ባንኮች ወይም የሞባይል-ገንዘብ አገልግሎት ሰጪዎች ሊተላለፍ አይችልም፡፡ | A closed loop is a digital financial system where users can only send, receive, or spend money within the same provider’s platform. The money cannot be transferred to other banks or mobile money services. | ደሞዙን ዝግ ዑደት ባለው ዋሌት የተቀበለ አንድ ሠራተኛ፤ ከዋሌቱ እየቀነሰ የአየር ጊዜ ለመግዛት እና አንዳንድ ቢሎችን ለመክፈል ቢችልም፤ ነገር ግን ደሞዙን ወደ ባንክ ሒሳቡ መላክ አይችልም፡፡ | A worker receives their salary in a closed-loop wallet and uses it to buy airtime and pay bills, but cannot move the money to a bank account. | 1.0 |
am-020 | Commissions | ኮሚሽን | am | Pricing | የተጠቃሚዎችን ገንዘብ ለማስቀመጥ፣ ለማውጣት፣ ወይም ሒሰብ ለመክፈት ላደረጉት አገልግሎት፤ ለወኪሎች ወይም አገልግሎት ሰጪዎች የሚሰጥ ክፍያ ነው፡፡ | Commissions are earnings paid to agents, or service providers for for helping users deposit, withdraw, or register for services (for facilitating financial transactions or services) | አንድ የሞባይል-ገንዘብ ወኪል፤ ገቢ-በጥሬ፣ ቢል ክፍያ፣ ወይም የ[ሞባይል-]ዋሌት ሒሳብ መክፈት የመሳሰሉ አገልግሎቶችን በሚሰጥበት ወቅት፤ ባከናወነው በእያንዳንዱ ስኬታማ ውርኝት የሚሰላ ኮሚሽን ያገኛል ወይም ይወስዳል፡፡ | A mobile money agent earns a commission for each successful transaction they assist with, such as cash-in, bill payment, or wallet registration. | 1.0 |
am-021 | Fees | የአገልግሎት ክፍያ | am | Pricing | የአገልግሎት ክፍያ ማለት፤ አንድ ደንበኛ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ስለተጠቀመ እንዲከፍል የሚጠየቀው አነስተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ነው፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ፤ እንደ ገንዘብ መላክ፣ ጥሬ-ገንዘብ ማውጣት፣ ወይም የቢል ክፍያዎች መፈጸም፣ እና የመሳሰሉ ውርኝቶች ላይ የአገልግሎት ክፍያ ሊጠየቅባቸው ይችላል፡፡ የአገልግሎት ክፍያው፤ አብዛኛውን ጊዜ ከተጠቃሚው ሒሳብ ወይም ዋሌት ላይ ወዲውኑ ተቀናሽ የሚደረግ ነው፡፡ | Fees are small amounts of money charged to users for using financial services. In digital financial services, fees may apply to transactions like sending money, withdrawing cash, or paying bills. These fees are usually deducted automatically from the user’s account or wallet. | አንድ ተጠቃሚ፤ ከራሱ የሞባይል-ዋሌት ወደ ሌላ ሰው ሒሳብ ገንዘብ ሲያስተላልፍ፤ አነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ | A user is charged a small fee when transferring money from their mobile wallet to another person’s account. | 1.0 |
am-022 | Community-Based Finance | ማኅበረሰብ-ሠራሽ ፋይናንስ | am | Concept | ገንዘብ ለመቆጠብ፣ ለመበዳደር፣ ወይም ርስበርስ በገንዘብ ለመተጋገዝ ሰዎች የሚሰባሰቡበት ዘልማዳዊ ወይም አካባቢያዊ የመረዳጃ ሥርዓት ነው፡፡ መሰል ሥርዓቶች በመተማመን እና በማኅበራዊ ትስስር ላይ የተመረኮዙ ናቸው፡፡ | Community-based finance refers to traditional systems where people come together to save, lend, or support each other financially. These systems are based on trust and social ties. | ጎረቤታማቾች በጀመሩት ዕቁብ፤ እያንዳንዱ አባል በቁርጥ የተወሰነ ሳምንታዊ መዋጮ የሚከፍል ሲሆን፤ በየሳምንቱ በሚወጣው ዕጣ መሠረት ለአንድ ባለዕድል የሁሉም አባላት ድምር መዋጮ ይሰጠዋል፡፡ ይህ መሰል አሠራር ማኅበረሰብ-ሠራሽ ፋይናንስ ይሰኛል፡፡ | A group of neighbors form an Equb where each member contributes a fixed amount weekly, and one member receives the total amount in rotation. | 1.0 |
am-023 | Credit | ብድር | am | Product/instrument | ብድር ማለት፤ አንድ ተጠቃሚ ከመደበኛ የፋይናንስ አገልግሎት ወይም ከዲጂታል ፕላትፎርም፤ መልሶ ለመክፈል (አብዛኛውን ጊዜ ከእነ ወለዱ) በመስማማት የሚቀበለው ገንዘብ ነው፡፡ | Credit is money provided to a user by a formal financial institution or digital platform with the agreement that it will be paid back later, usually with interest. | አንድ የሞባይል-ገንዘብ ተጠቃሚ፤ ፈቃድ ካለው የዲጂታል ብድር አገልግሎት ሰጪ ብድር የወሰደ ሲሆን፤ ብድሩንም በአንድ ወር ውስጥ ከጥቂት ወለድ ጋር መልሶ ለመክፈል በመስማማት ነው፡፡ | A mobile money user receives credit through a licensed digital lending service and agrees to repay the amount over one month with a small interest fee. | 1.0 |
am-024 | Credit card | የብድር ካርድ | am | Product/instrument | ባብዛኛው በባንኮች የሚሰጥ እና ከተዘዋዋሪ ብድር ዓይነቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች አስቀድሞ እስከተወሰነው የገንዘብ መጠን ድረስ መበደር እና የተበደሩትን ገንዘብ በቀጥታ ለሸመታ ለመክፈል አሊያም በጥሬ-ገንዘብ ለማውጣት ይችላሉ፡፡ ብድሩ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መልሶ መከፈል ያለበት ሲሆን፤ ወለድ እና/ወይም ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ ሊጠየቅበት ይችላል፡፡ | It is a type of revolving credit, typically issued by a bank, which allows borrowing funds to make purchases or withdraw cash, up to a predetermined limit. The borrowed money should be repaid, plus any applicable interest and fees, later. | አቶ አበበ በባንክ የቁጠባ ሒሳቡ ውስጥ ምንም ገንዘብ ባይኖረውም፤ ከባንኩ የተሰጠው እና በወር እስከ 10 ሺህ ብር ድረስ መበደር የሚያስችለው የብድር ካርድ ተጠቃሚ ነው፡፡ አቶ አበበ አስቸኳይ የጤና እክል ስለገጠመው፤ በብድር ካርዱ አማካኝነት 6 ሺህ ብር ወጪ አድርጓል፡፡ | null | 1.0 |
am-025 | Debit card | ባለስንቅ ካርድ | am | Product / Instrument | ተጠቃሚው በባንክ ሒሳቡ ባስቀመጠው በራሱ ገንዘብ፤ ዕቃ ሲገዛ ለመክፈል ወይም ከኤ/ቲ/ኤም/ ጥሬ-ገንዘብን ለማውጣት ያገለግላል፡፡ | A debit card is a card that lets you use your own money from your bank account to pay for things or take out cash from an ATM. | የአቶ አበበ ባለስንቅ ካርድ፤ በባንክ ሒሳቡ ከተቀመጠው ገንዘብ ሌላ እላፊ ገንዘብ ወይም ብድር ሊሰጠው ስላልቻለ፤ የብድር ካርድ እንዲሰጠው አቶ አበበ ለባንኩ ማመልከቻ አስገብቷል፡፡ | null | 1.0 |
am-026 | Prepaid card | የቅድመ-ክፍያ ካርድ | am | Product/Instrument | አስቀድሞ ገንዘብ የገባበት ወይም የተሰነቀለት የክፍያ ካርድ ነው፡፡ ተጠቃሚው መገልገል የሚችለው፤ ወደ ካርዱ በተሞላው ገንዘብ ልክ ብቻ ነው፡፡ አገልግሎቱን ለመጠቀም የባንክ ሒሳብ መኖርን ግድ አይልም፡፡ | A prepaid card is a payment card that has money loaded onto it in advance. The user can spend only the amount that is already on the card. It is not linked to a bank account and does not require borrowing. | የባንክ ሒሳብ የሌለው አንድ ግለሰብ፤ አቅራቢው ወዳለው ወኪል ሂዶ ወደ የቅድመ-ክፍያ ካርዱ ገንዘብ አስሞላ፡፡ በካርዱ ያሻውን ግብይት ከማድረጉም በላይ፤ ክፍያዎችን ጭምር እየተቀበለበት ይገኛል፡፡ ካርዱ ያለ እጅ ስልክ ወይም ያለ ባንክ ሒሳብ፤ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶችን ማግኘት ያስችላል፡፡ | A person without a bank account loads money onto a card at a nearby agent. They then use the card to pay for goods at a shop or receive payments for services. The card helps them access digital payments without needing a mobile phone or bank account. | 1.0 |
am-027 | Credit history | የብድር ታሪክ | am | Process | የብድር ታሪክ ማለት፤ የአንድ ተጠቃሚ የቀደመ የብድር አወሳሰድ እና የብድር አከፋፈል ጠባይ ነው፡፡ ይህም የፋይናንስ ተቋማት፤ የተበዳሪው ግለሰብን ብድር የመመለስ ዝንባሌ ለመገምገም ይረዳቸዋል፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ፤ የብድር ታሪክ የሚጠናቀረው፤ በእጅ ስልከ ከተደረጉ ውርኝቶች፣ ከተፈጸሙ የቢል ክፍያዎች፣ ወይም ከቀደሙ ብድሮች ሊሆን ይችላል፡፡ | Credit history is a record of a user’s past borrowing and repayment behavior. It helps financial institutions assess how reliable a person is when it comes to repaying loans. In digital financial services, credit history may be built from mobile transactions, bill payments, or previous loans. | አነስተኛ የዲጂታል ብድሮችን በተደጋጋሚ እየወሰደ ነገር ግን ሳይዘገይ ጊዜውን ጠብቆ መልሶ የሚከፍል ተጠቃሚ፤ አዎንታዊ የብድር ታሪክን ይገነባል፤ ይህም ተጠቃሚው ወደፊት መጠኑ የላቀ ብድር ሲጠይቅ በሚደረገው ግምገማ ላይ በጎ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ | A user who regularly repays small digital loans on time builds a positive credit history, which may help them qualify for larger loans in the future. | 1.0 |
am-028 | Credit scoring | የብድር ብቁነት ደረጃ | am | Process | በቀደመ የፋይናንስ ጠባይ ላይ ተመሥርቶ በሚካሄድ ግምገማ አማካኝነትየሚሰጥ ደረጃ ወይም ውጤት ሲሆን፤ የአንድ ተጠቃሚን ብድር የመመለስ አቅም የመመዘኛ ዘዴ ነው፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ፤ ከዚህ ቀደም በእጅ ስልክ የተደረጉ ውርኝቶች፣ የቢል ክፍያዎች፣ እና የቁጠባ ዝንባሌን የተመለከቱ መረጃዎች፤ ስጋትን ለመገምገም እና የአንድ ተበዳሪን ብድር የመመለስ ብቃት ደረጃ ለማውጣት እንደ ግብአት ይውላሉ፡፡ | Credit scoring is the process of evaluating a user’s ability to repay borrowed money by assigning a score based on their financial behavior. In digital financial services, credit scoring may use mobile transaction data, bill payments, and savings patterns to assess risk. | አንድ የዲጂታል ብድር አቅራቢ የብድር ጥያቄን ከመፍቀዱ በፊት፤ [የተበዳሪውን] የሞባይል-ገንዘብ (ዋሌት) እንቅስቃሴ እና የአየር ጊዜ ግዢ ታሪክን በመመርኮዝ የብድር ብቁነት ደረጃን ያወጣል፡፡ | A digital credit provider uses mobile money (wallet) activity and airtime purchase history to generate a credit score before approving a loan request. | 1.0 |
am-029 | Customer Service | የደንበኞች አገልግሎት (እንዳገባቡ የደንበኞች አገልግሎት ክፍል) | am | Process | የደንበኞች አገልግሎት [ክፍል] ማለት፤ ተጠቃሚዎች ችግራቸው እንዲፈታ፣ ጥያቄዎችን እንዲያቀርቡ፣ እና ስለ ሒሳባቸው ወይም ውርኝታቸው እገዛ ለማግኘት እንዲችሉ የፋይናንስ አገልግሎቱን በሚሰጠው አካል የሚሰጥ ድጋፍ ነው፡፡ ድጋፉ የሚሰጠው፤ በጥሪ ማእከላት፣ በእጅ ስልክ መተግበሪያዎች፣ የዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮዶችን በማስገባት፣ ወይም ወደ ወኪሎች በአካል በመሄድ ሊሆን ይችላል፡፡ | Customer service refers to the support provided by financial service providers to help users solve problems, ask questions, and get assistance with their accounts or transactions. It can be offered through call centers, mobile apps, USSD menus, or in-person agents. | የሞባይል-ገንዘብ ተጠቃሚ፤ በነጻ ጥሪ መስመር ወደ ደንበኞች አገልግሎት [ክፍል] በመደወል፤ ያልተሳካ ውርኝትን በማሳወቅ ችግሩ የሚፈታበትን እገዛ ለማግኘት ችሏል፡፡ | A mobile money user contacts customer service through a toll-free number to report a failed transaction and receives help to resolve the issue. | 1.0 |
am-030 | Data Protection | የዳታ ጥበቃ | am | Policy | የተጠቃሚዎች ግላዊ እና የፋይናንስ መረጃዎችን ሳይበላሹ እና ሳይጋለጡ ማስቀመጥ፤ ብሎም በኃላፊነት መገልገል ማለት ነው፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት፤ ዳታን ያልተፈቀደላቸው አካላት እንዳያገኙት፣ ላልተገባ ዓላማ እንዳይውል፣ እና አፈትልኮ እንዳይወጣ መጠበቅ ማለት ነው፡፡ | Data protection refers to the practices and policies that ensure users’ personal and financial information is kept safe, secure, and used responsibly. In digital financial services, this includes protecting data from unauthorized access, misuse, or leaks. | የሞባይል-ገንዘብ አገልግሎት ሰጪ፤ የተጠቃሚዎችን ማንነት እና የውርኝት ታሪክ የሚመለከቱ መረጃዎች ፈቃድ ባልተሰጣቸው ሦስተኛ አካላት እጅ እንዳይወድቁ፤ የተመሰጠሩ መረጃዎችን እና የተቆለፉ ሰርቨሮችን ይጠቀማል፡፡ ይህም የዳታ ጥበቃ ይባላል፡፡ | A mobile money provider uses encryption and secure servers to protect users’ identity and transaction history from being accessed by third parties without consent. | 1.0 |
am-031 | Deposit | ተቀማጭ | am | Use case | ተቀማጭ ማለት፤ አንድ ተጠቃሚ ወደ ሒሳቡ ወይም ወደ ሞባይል-ዋሌቱ የሚጨምረው ገንዘብ ነው፡፡ ተቀማጭን በእጅ ስልክ (በመተግበሪያ ወይም የዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮዶችን በማስገባት) አሊያም በሞባይል-ገንዘብ ወኪል አማካኝነት መጨመር ይቻላል፡፡ | A deposit is when a user adds money to their account or mobile money (wallet). Deposits can be made through mobile apps, USSD, or with the help of a mobile money agent. | አንድ ተጠቃሚ ለሞባይል-ገንዘብ ወኪል ጥሬ-ገንዘብ ሰጥቶ፤ ወኪሉ ገንዘቡን ወደ ተጠቃሚው የሞባይል-ዋሌት ገቢ አደረገለት፡፡ | A user gives cash to a mobile money agent, who then deposits the amount into the user’s mobile wallet for future use. | 1.0 |
am-032 | Digital Financial Services | የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች | am | null | የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ማለት፤ እንደ የእጅ ስልክ፣ የበይነ-መረብ/ኢንተርኔት ፕላትፎርሞች፣ ኤ/ቲ/ኤም፣ እና የወኪል ትስስሮሽ በመሳሰሉ የዲጂታል አውታሮች አማካኝነት የሚሰጡ የፋይናንስ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች፤ ክፍያን፣ ቁጠባን፣ ብድርን፣ መድንን፣ እና የገንዘብ ማዘዋወርን (money transfers) የሚጨምሩ፤ ብሎም ተደራሽ፣ አስተማማኝ፣ እና ለአጠቃቀም ምቹ ሆነው የተሰናዱ ናቸው፡፡ | Digital Financial Services (DFS) refer to financial services delivered through digital channels such as mobile phones, internet platforms, ATMs, and agent networks. These services include payments, savings, credit, insurance, and money transfers, and are designed to be accessible, secure, and convenient. | አንድ ተጠቃሚ ቢል ለመክፈል፣ ገንዘብ ለመላክ፣ እና የአነስተኛ ብድር ጥያቄ ለማቅረብ የሞባይል-ገንዘብን መጠቀም ከቻለ፤ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ለተጠቃሚው ተደራሽ ነው ማለት ነው፡፡ | A user accesses digital financial services by using a mobile money to send money, pay bills, and apply for a small loan - all through their phone. | 1.0 |
am-033 | Digital payment | የዲጂታል ክፍያ | am | null | የእጅ ስልኮችን (በመተግበሪያ ወይም በዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድ) አሊያም የሌሎች ዲጂታል ፕላትፎርሞችን በመጠቀም በኤሌክትሮኒክ አውታሮች አማካኝነት የሚደረግ የፋይናንስ ውርኝት ነው፡፡ የዲጂታል ክፍያ ዘዴ፤ ተጠቃሚዎች ያለ ጥሬ-ገንዘብ ቢል ለመክፈል፤ እንዲሁም ለዕቃ እና አገልግሎት ግዢ ክፍያ ለመፈጸም ያስችላዋል፡፡ | Digital payments are financial transactions made electronically using mobile phones, apps, USSD, or other digital platforms. They allow users to pay for goods, services, or bills without using cash. | አንድ ተጠቃሚ የኤሌክትሪክ ቢሉን ለመክፈል፤ ወደ ክፍያ ጣቢያ በአካል ከመሄድ ይልቅ በዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድ አማካኝነት ከሞባይል-ዋሌቱ ስለከፈለ፤ የአከፋፈሉ ዘዴ የዲጂታል ክፍያ ነው፡፡ | A user pays for electricity using their mobile wallet through a USSD code, instead of going to a physical payment center | 1.0 |
am-034 | Digital transaction | የዲጂታል ውርኝት | am | Use Case | ከጥሬ-ገንዘብ ውጪ ኮምፒዩተሮችን እና ስማርት የእጅ ስልኮችን በመሳሰሉ የኤሌክትሮኒክ ዘዴዎች የሚከናወኑ ማናቸውም ዓይነት የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን ይገለጻል፡፡ ይህም የበይነ-መረብ ግብይትን፣ በዲጂታል ክፍያ ዘዴዎች አማካኝነት ግለሰቦች የሚላላኩት ገንዘብን፣ የብድር ወይም የባለስንቅ ካርዶችን፣ የሞባይል-ዋሌትን፣ እና ቀጥተኛ የባንክ ዝውውሮችን ያጠቃልላል፡፡ | A digital transaction is any financial exchange that occurs electronically, without physical cash, using devices like computers or smartphones. These include online shopping, sending money between individuals through various digital payment methods; using credit or debit cards, mobile wallets, and direct bank transfers... | አቶ አበበ የዳሸን ባንክ ተጠቃሚ ሲሆን፤ በባንኩ ሒሳብ ስላለው የባንኩ ኤ/ቲ/ኤም/ ካርድ አለው፡፡ አቶ አበበ በራሱ በዳሽን ባንክ ኤ/ቲ/ኤም/ ማሽን አማካኝነት አማካኝነት ቀሪ ገንዘቡን ለማወቅ የሚያስችለውን ሂደት አከናወነ፡፡ ባንኩ ለዚህ አገልግሎት ክፍያ ባይጠይቀውም፤ የመረጃ ልውውጥ ተካሂዷል፡፡ ይህም እንደ አንድ የዲጂታል ውርኝት ይታያል፡፡
በዛሬው ዕለት አቶ ከበደ ወደ አቶ አበበ የባንክ ሒሳብ ሁለት ጊዜ ገንዘብ ገቢ አድርጓል፡፡ ላኪው አቶ ከበደ ገንዘቡን ያስገባው በእጅ ስልኩ አማካኝነት ከሞባ... | null | 1.0 |
am-035 | Dispute Resultion | አቤቱታ አፈታት | am | null | አቤቱታ አፈታት ማለት፤ ከፋይናንስ ውርኝቶች ጋር የተያያዙ ችግሮችን ወይም አለመግባባቶችን ማስተናገድ እና መቅረፍ ነው፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ፤ ያልተሳኩ ውርኝቶችን፣ በስህተት የተቆረጡ የአገልግሎት ክፍያዎችን፣ ወይንም በደንበኞች አገልግሎት ክፍል በኩል ያለባለቤቱ ፈቃድ ሒሳቡ በሌሎች እጅ መውደቅን የመሳሰሉ ክሥተቶችን ያጠቃልላል፡፡ | Dispute resolution is the process of addressing and solving problems or disagreements related to financial transactions. In digital financial services, this includes handling failed transactions, incorrect charges, or unauthorized access through customer service channels. | አንድ ተጠቃሚ ያልተሳካ የሞባይል-ገንዘብ ውርኝት እንደገጠመው ለአገልግሎት ሰጪው በማሳወቅ፤ ገንዘቡ ተመላሽ እንዲሆን ወይም በአግባቡ እንዲተላለፍ ጠየቀ፡፡ አቤቱታውን የተቀበለው አገልግሎት ሰጪ ድርጅት፤ ገንዘቡን ተመላሽ በማድረግ አቤቱታውን ፈትቷል፡፡ | A user reports a failed mobile money transfer and receives support from the provider to investigate and resolve the issue, either by refund or correction. | 1.0 |
am-036 | eCommerce | ኢ-ንግድ (ኤሌክትሮኒክ ንግድ) | am | Use Case | ኢ-ንግድ ማለት፤ በበይነ-መረብ/ኢንተርኔት አማካኝነት ሸቀጦችን ወይም አገልግሎቶችን መግዛት እና መሸጥ ነው፡፡ ተጠቃሚዎች የሚሸምቱትን ለማፈላለግ፣ ለማዘዝ፣ እና በዲጂታል ዘዴ ለመክፈል፤ የበይነ-መረብ የመገበያያ ገጾችን፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያሉ ሱቆችን፣ እና የእጅ ስልክ መተግበሪያዎችን ሊጠቀሙ ይችላል፡፡ | eCommerce refers to the buying and selling of goods or services over the internet. It includes online marketplaces, social media shops, and mobile apps where users can browse, order, and pay digitally. | አንድ የአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ባለቤት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ አማካኝነት የዕደ-ጥበብ ውጤቶችን አስተዋውቆ ከሸጠ በኋላ ክፍያውን በሞባይል-ገንዘብ ተቀብሏል፡፡ ስለዚህ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገው የግብይት ዓይነት ኢ-ንግድ ነው፡፡ | A small business owner sells handmade products through a social media page and receives payments via mobile money from customers. | 1.0 |
am-037 | Digital Finance Ecosystem | የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓተ-ምኅዳር | am | Concept | የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓተ-ምኅዳር ማለት፤ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ተባብረው እየሠሩ ባሉ ግለሰቦች፣ ተቋማት፣ ቴክኖሎጂዎች፣ እና ሕገ-ደንቦች መካከል ያለው መስተጋብር ነው፡፡ ይህም፤ የሞባይል-ገንዘብ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ባንኮች፣ ወኪሎች፣ ፊንቴኮች (fintechs)፣ ተቆጣጣሪ አካላት፣ እና ተጠቃሚዎችን ይጨምራል፡፡ ጠንካራ ሥርዓተ-ምኅዳር፤ በፋይናንስ አገልግሎቶች ውስጥ ተደራሽነትን፣ ኢኖቬሽንን፣ እና አመኔታን ይፈጥራል፡፡ | An ecosystem refers to the network of individuals, institutions, technologies, and regulations that work together to deliver digital financial services. It includes mobile money providers, banks, agents, fintechs, regulators, and users. A strong ecosystem enables access, innovation, and trust in financial services. | የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ሥርዓተ-ምኅዳር፤ አካታች-ፋይናንስን ለማስፋፋት ተባብረው የሚሠሩ የሞባይል-ገንዘብ ፕላትፎርሞችን፣ የወኪል ትስስሮሾችን፣ የመንግሥት ፖሊሲዎችን፣ ጀማሪ የፊንቴክ ድርጅቶችን፣ እና ሌሎችንም ይጨምራል፡፡ | A digital financial services ecosystem may include mobile money platforms, agent networks, government policies, and fintech startups working together to expand financial inclusion. | 1.0 |
am-038 | eMoney | ኢ-ገንዘብ | am | Product/instrument | ኢ-ገንዘብ (ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ)፤ በሞባይል-ዋሌት ወይም በበይነ-መረብ የሒሳብ ቁጥር ውስጥ በዲጂታል አምሳያ ወይም መልክ የተቀመጠ ገንዘብ ነው፡፡ ተጨባጩን ወይም እውነተኛውን ገንዘብ የሚወክል በመሆኑ፤ ክፍያዎችን ለመፈጸም፣ ገንዘብን ለመላክ ወይም ለመቀበል፣ እንዲሁም የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለመጠቀም ያስችላል፡፡ ኢ-ገንዘብ ፈቃድ ባላቸው የፋይናንስ ተቋማት የሚወጣ እና ዋጋውም በጥሬ-ገንዘብ ካለው መጠን ጋር መሳ-ለመሳ ነው፡፡ | eMoney (electronic money) is a digital form of money stored in mobile wallets or online accounts. It represents real money and can be used to make payments, send or receive funds, and access financial services. eMoney is issued by licensed financial institutions and backed by equivalent cash value. | አንድ ተጠቃሚ፤ ወደ ሞባይል-ገንዘብ ወኪል ሄዶ ጥሬ-ገንዘብ ሲሰጠው፤ ወኪሉ ደግሞ የተቀበለውን ጥሬ-ገንዘብ በእኩል መጠን ወደ ኢ-ገንዘብ ለውጦ ወደ ተጠቃሚው የሞባይል-ዋሌት ገቢ አደረገለት፡፡ ስለዚህ ተጠቃሚው ከዚህ በኋላ ለተለያዩ ጉዳዮች በዲጂታል ዘዴ ክፍያ መፈጸም ይችላል ማለት ነው፡፡ | A user receives eMoney in their mobile wallet after depositing cash through a mobile money agent, and uses it to pay for services digitally. | 1.0 |
am-039 | eMoney Issuer | የኢ-ገንዘብ አውጪ | am | null | የኢ-ገንዘብ አውጪ ማለት፤ ጥሬ-ገንዘብን በኤሌክትሮኒክ-ገንዘብ አምሳያ ለመፍጠር እና ለማስተዳደር ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ነው፡፡ እነዚህ ተቋማት፤ ኢ-ገንዘቡ እኩል ዋጋ ባለው ጥሬ-ገንዘብ የተደገፈ መሆኑን፤ ብሎም ተጠቃሚዎች ያለስጋት ገንዘባቸውን በዲጂታል ዘዴ ማጠራቀም፣ መላክ፣ እና መቀበል የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ፤ ባንኮች፣ የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አውጪዎች፣ የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት፣ ወይም ልዩ የሆነ የክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ከ... | An eMoney issuer is a licensed financial institution authorized to create and manage electronic money. These institutions ensure that eMoney is backed by equivalent cash value and that users can safely store, send, and receive money digitally. In Ethiopia, eMoney issuers may include banks, Payment Instrunment Issuers, ... | ፈቃድ የተሰጠው እና ቁጥጥር የሚደረግበት የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ፤ የሞባይል-ዋሌት አገልግሎትን የሚሰጥ ሲሆን፤ ለዚህም እንዲያግዘው በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ኢ-ገንዘብን ያወጣል፡፡ ይህም ተጠቃሚዎች በዲጂታል ዘዴ ክፍያዎችን አንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል፡፡ | A regulated company provides mobile wallet services and issues eMoney that users can use for payments, transfers, and savings. | 1.0 |
am-040 | Financial Inclusion | አካታች ፋይናንስ | am | Concept | አካታች ፋይናንስ ማለት፤ አገልግሎት-አነስ (underserved)፣ ባንክ-አልቦ (unbanked) ወይም ባንክ-አነስ (underbanked) የኅብረተሰብ ክፍሎች ወደ መደበኛው የኢኮኖሚ ዘርፍ እንዲቀላቀሉ የሚያግዙ፤ ያልተቋረጡ እና የመክፈል አቅምን ያገናዘቡ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች አቅርቦት መኖር ነው፡፡ | Financial inclusion is the ongoing provision of affordable digital financial services that help integrate the underserved, unbanked or underbanked population into the formal economy. | አንድ ግለሰብ ምንም እንኳ የባንክ ሒሳብ ባይኖረውም፤ ገንዘብ ለመቆጠብ፣ ክፍያዎችን ለመቀበል፣ እና ቢል ለመክፈል የሞባይል-ገንዘብን ወይም የሞባይል-ዋሌትን ከተጠቀመ፤ የመደበኛ ፋይናንስ ሥርዓቱ አካል ሆኗል ማለት ነው፡፡ የእነዚህ መሰል አማራጮች መኖር፤ አካታች ፋይናንስን እውን ለማድረግ ያግዛል፡፡ | A person without a bank account uses a mobile money or wallet to save money, receive payments, and pay bills, becoming part of the formal financial system. | 1.0 |
am-041 | Financial Literacy | የፋይናንስ ግንዛቤ | am | Concept | የፋይናንስ ግንዛቤ ማለት፤ የፋይናንስ አገልግሎቶችን የማወቅ እና በብቃት የመጠቀም ችሎታ ነው፡፡ ይህም አንዴት መቆጠብ፣ መበደር፣ በጀት ማውጣት፣ እና ገንዘብን በተመለከተ መረጃን ያማከለ ውሳኔ አሰጣጥን ማወቅ ይጨምራል፡፡ የፋይናንስ ግንዛቤ ያለው ተጠቃሚ፤ የሞባይል-ዋሌት፣ የዲጂታል ክፍያዎችን፣ እና የብድር አገልግሎት አማራጮችን ያለስጋት ለመዳሰስ እና ለመጠቀም ያስችለዋል፡፡ | Financial literacy is the ability to understand and use financial services effectively. It includes knowing how to save, borrow, budget, and make informed decisions about money. In DFS, it helps users navigate mobile wallets, digital payments, and credit products safely. | የፋይናንስ ግዛቤ ያለው ሰው በልበ-ሙሉነት፤ የብድር አማራጮችን ለማነጻጸር፣ አላስፈላጊ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለማስቀረት፣ እና የሞባይል-ዋሌቱን በብቃት ለማስተዳደር ይቻለዋል፡፡ | A user with financial literacy can compare loan options, avoid unnecessary fees, and manage their mobile wallet confidently. | 1.0 |
am-042 | FinTech | ፊንቴክ | am | Role/Actor | ፊንቴክ የእንግሊዝኛ አሕፅሮ-ቃል ሲሆን፤ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማሻሻል ወይም ለማቅረብ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ድርጅትን ወይም አሠራርን ይገልጻል፡፡ ቴክኖሎጂው፤ የሞባይል-ገንዘብን፣ በዲጂታል ዘዴ ማበደርን፣ በበይነ-መረብ መክፈልን፣ እና የፋይናንስ አስተዳደር አሠራሮችን ይጨምራል፡፡ | FinTech (Financial Technology) refers to companies or solutions that use technology to improve or deliver financial services. This includes mobile money, digital lending, online payments, and financial management tools. | አብዛኞቹ የፊንቴክ ጀማሪ ድርጅቶች፤ ተጠቃሚዎች ወጪዎቻቸውን ለመከታተል እና አነስተኛ ብድሮችን ወዲያውኑ እንዲያገኙ የሚያስችል የእጅ ስልክ መተግበሪያ አላቸው፡፡ | A Fintech startup offers a mobile app that helps users track spending and access small loans instantly. | 1.0 |
am-043 | Fraud | ማጭበርበር | am | Risk | ማጭበርበር ማለት፤ የተጠቃሚዎችን ገንዘብ ወይም የግል መረጃ ለመስረቅ የሚደረግ ማናቸውም ዓይነት የማታለል ወይም ሕገ-ወጥ ድርጊት ነው፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማእቀፍ ውስጥ ሲታይ፤ ሕገ-ወጥ ድርጊቶቹ ሐሰተኛ የስልክ ጥሪዎችን፣ አታላይ አጭር የስልክ መልእክቶችን፣ ወይም ያለባለቤቱ ፈቃድ የሞባይል ዋሌት ሒሳብን ማንቀሳቀስ ይጨምራል፡፡ | Fraud is any dishonest or illegal activity meant to steal money or personal information from users. In digital financial services, this includes fake calls, SMS scams, or unauthorized access to mobile wallets. | አንድ አጭበርባሪ ለአንድ ተጠቃሚ፤ የግል መለያ ቁጥሩን (ፒን) እንዲነግረው የሚጠይቅ መልእክት ደረሰው፡፡ ተጠቃሚው የጠያቂውን ማንነት ሳያጣራ የተጠየቀውን የግል መለያ ቁጥር ለአጭበርባሪው ላከ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በተጠቃሚው የሞባይል-ዋሌት ውስጥ ያለው ገንዘብ ተሰረቀ፡፡ | A user receives a fake message asking for their PIN and loses money after sharing it with a fraudster. | 1.0 |
am-044 | Identity | ማንነት (እንደ አግባቡ የማንነት መለያ) | am | Process/requirement | የአገልግሎት ፈላጊውን ማንነት ለመለየት የሚያስችል አንዳች ዓይነት መታወቂያ ማለት ነው፤ ለምሳሌ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ፡፡ አገር-አቀፍ መታወቂያዎች በማእከላዊ መንግሥታት የሚሰጡ ናቸው፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማእቀፍ ውስጥ ሲታይ፤ ሒሳብ ለመክፈት፣ ለደኅንነት ጥበቃ፣ እና የአሠራር ሂደትን ለማስከበር የተጠቃሚዎች ማንነት የሚለይበት ዘዴ መኖር ወሳኝ ነው፡፡ | A credential of some sort that identifies an end user such as Fayda National ID. National identities are issued by national governments. In digital financial services, identity is essential for account registration, security, and compliance. | አቶ አበበ በቀበሌ መታወቂያው እና በስልክ ቁጥሩ አማካኝነት የሞባይል-ዋሌት ሒሳብ ስለከፈተ፤ የፋይናንስ አገልግሎቶችን መጠቀም ይችላል፡፡ | A user provides their national ID and phone number to register for a mobile wallet and access financial services. | 1.0 |
am-045 | Insurance | መድን | am | Product/Instrument | እንደ ሕመም፣ አደጋ፣ ወይም ውድመት የመሳሰሉ ያልታሰቡ ክሥተቶች የሚያስከትሉትን ጉዳት ለማካካስ የሚያስችል የፋይናንስ አገልግሎት ነው፡፡ የመድን ተጠቃሚዎች ‹ዐረቦን› የሚባል መጠነኛ ክፍያን በቋሚነት አስቀድሞ በመክፈል፤ አደጋ ሲደርስ ካሳ ለመቀበል ያስችላቸዋል፡፡ | Insurance is a financial service that protects users against unexpected events like illness, accidents, or loss. Users pay small amounts regularly (called premiums) and receive support when covered risks happen. | አንድ ተጠቃሚ፤ በሞባይል-ዋሌቱ ወርኃዊ አረቦን ክፍያን ሳያቋርጥ ስለከፈለ፤ ሕመም አጋጥሞት ሆስፒታል ሲገባ የካሳ ክፍያ ለማግኘት ችሏል፡፡ | A user pays a monthly premium through their mobile wallet and receives compensation when hospitalized. | 1.0 |
am-046 | Interoprability | ተናባቢነት | am | null | የተለያዩ የፋይናንስ ሥርዓቶች፣ ፕላትፎርሞች፣ ወይም አገልግሎት ሰጪዎች ተናብበው በአንድነት የሚሠሩበት ሁኔታን ይገልጻል፡፡ ተጠቃሚዎች፤ ከሚገለገሉባቸው ውጪ ባሉ ኔትዎርኮች ወይም ተቋማት ገንዘብን መላክ እና መቀበል፣ እንዲሁም የፋይናንስ አገልግሎቶችን ያለ ክልከላ ማግኘት ያስችላቸዋል፡፡ | Interoperability is the ability of different financial systems, platforms, or service providers to work together seamlessly. It allows users to send, receive, or access financial services across different networks or institutions without restrictions. | አንድ የቴሌ ብር ተጠቃሚ፤ ከዋሌቱ ላይ ቀንሶ ወደ ጓደኛው የዳሽን ባንክ ሒሳብ የላከ ሲሆን፤ ውርኝቱም ወዲያው ተከናውኗል፡፡
የዚህ ምክንያት ደግሞ፤ የላኪው እና የተቀባዩ ድርጅቶች ለየቅል ወይም የተለያዩ ቢሆኑም፤ የአገልግሎት ሥርዓታቸው ግን ተናባቢ ወይም ተቋም-ዘለል ሆኖ ስለተቀየሰ ነው፡፡ | A user with a mobile wallet from one provider sends money to a friend using a different provider’s wallet, and the transaction is completed instantly. | 1.0 |
am-047 | Know Your Customer | ደንበኛህን-ዕወቅ | am | null | ‹ደንበኛህን-ዕወቅ› ማለት፤ የፋይናንስ ተቋማት የተገልጋዮቻቸውን ማንነት ወይም መለያ የሚያጣሩበት ሂደት ነው፡፡ ይህም አገልግሎት መስጠት ከመጀመራቸው በፊት እንደ ስም፣ የመታወቂያ ቁጥር፣ እና አድራሻ የመሳሰሉ መሠረታዊ መረጃዎችን በመያዝ፤ ማጭበርበርን፣ የሕገ-ወጥ ገንዘብ እጥበትን፣ እና ሌሎች የሕግ ጥሰቶችን የመከላከል ሥራ ለማገዝ ነው፡፡ | KYC is the process used by financial institutions to verify the identity of their users. It helps prevent fraud, money laundering, and other illegal activities by collecting basic information like name, ID number, and address before offering services. | አንድ ተጠቃሚ የሞባይል-ዋሌት ሒሳብ ለመክፈት ወይም ለመመዝገብ፤ አገልግሎት ሰጪው ባስቀመጠው ቅድመ-ሁኔታ መሠረት፤ የፋይዳ መታወቂያውን እንዲሁም ራሱን በራሱ ያነሣውን ጉርድ ፎቶውን፤ በእጅ ስልኩ ላይ ባለው መተግበሪያ ላይ ጫነ፡፡ የተጠቀሰው ቅድመ-ሁኔታ፤ አገልግሎት ሰጪው የተጣለበትን ‹ደንበኛህን-ዕወቅ› የሚለውን የሕግ ግዴታ ለመሟላት ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ተጠቃሚው የሞባይል-ዋሌት ሒሳብ ለመክፈት ችሏል፡፡ | A user uploads their national ID and takes a selfie through a mobile app to complete KYC and activate their digital wallet. | 1.0 |
am-048 | Loans | ብድር | am | Product/Instrument | ብድር ማለት፤ ከፋይናንስ ተቋም ወይም ከፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ የሚወሰድ እና ከጊዜ በኋላ መልሶ መከፈል (አብዛኛውን ጊዜ ከእነ ወለዱ) ያለበት ገንዘብ ነው፡፡ ተጠቃሚዎች በእጃቸው ላይ በቂ ገንዘብ ከሌላቸው፤ ብድሩ ወጪያቸውን ለመሸፈን ወይም ለመልካም አጋጣሚዎች ለማዋል ይረዳቸዋል፡፡ | A loan is money borrowed from a financial institution or provider that must be paid back over time, usually with interest. Loans help users cover expenses or invest in opportunities when they don’t have enough money upfront. | አንድ የአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ባለቤት በዲጂታል የብድር መተግበሪያ አማካኝነት ብድር ከወሰደ በኋላ፤ ተመላሽ ብድሩን በሞባይል-ገንዘብ በተከታታይ ወራት ከፍሎ ጨረሰ፡፡ | A small business owner borrows money through a digital lending app and repays it in monthly installments using their mobile money. | 1.0 |
am-049 | Microfinance | አነስተኛ የፋይናንስ ሥራ (as in microfinance business)
አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም (as in microfinance institution) | am | Role/Actor | አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም (ማይክሮፋይናንስ) ማለት፤ መደበኛ የባንክ አገልግሎት ማግኘት ላልቻሉ እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ግለሰቦች ወይም አነስተኛ ነጋዴዎች፤ አነስተኛ ብድር፣ ቁጠባ፣ መድን፣ እና የመሳሰሉ የፋይናንስ አገልግሎቶች የሚሰጥበት አሠራር ነው፡፡ ይህም ተጠቃሚዎች ገቢያቸውን ለማሳደግ እና ፋይናንስ-ነክ ችግሮቻቸውን ለማቃለል ያግዛቸዋል፡፡ | Microfinance refers to financial services like small loans, savings, and insurance provided to low-income individuals or small businesses who typically lack access to traditional banking. It helps users grow their income and manage financial risks. | በገጠር ያለች አንዲት ግለሰብ የአትክልት ንግድ ለመጀመር ከአነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ጥቂት ገንዘብ ከተበደረች በኋላ፤ ተመላሽ ብድሩን በሞባይል-ገንዘብ አማካኝነት በየሳምንቱ ከፍላ ጨረሰች፡፡ | A woman in a rural area borrows a small amount from a microfinance institution to start a vegetable business and repays it weekly through a mobile money agent. | 1.0 |
am-050 | Microinsurance | አነስተኛ መድን | am | Product/Instrument | ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች ተደራሽ እንዲሆን እና የመግዛት አቅማቸውን ባገናዘበ መልኩ የተዘጋጀ የመድን አገልግሎት ዓይነት ነው፡፡ አገልግሎቱ አብዛኛውን ጊዜ፤ እንደ አስቸኳይ የጤና እክል፣ የሰብል ውድመት፣ ወይም አደጋ የመሳሰሉ የትናንሽ ጉዳቶችን ካሣ የሚሸፍን፤ እንዲሁም ባብዛኛው በእጅ ስልክ ወይም በወኪሎች አማካኝነት የሚሰጥ ነው፡፡ | A type of insurance designed to be affordable and accessible for low-income individuals. It usually covers small risks like health emergencies, crop loss, or accidents and is often offered through mobile phones or agents. | አቶ አበበ ጠቅላላ የካሳ ሽፋኑ ከ5 ሺህ ብር የማይዘል የስርቆት መድን አገልግሎት የገዛ ሲሆን፤ የአገልግሎት ዓይነቱ ከአነስተኛ መድን የሚመደብ ነው፡፡ አቶ አበበ፤ በእጅ ስልኩ ላይ በጫነው የመድን ድርጅቱ መተግበሪያ አማካኝነት ለአገልግሎቱ የተመዘገበ ሲሆን፤ ወርኃዊ የአረቦን ክፍያውንም (ማለትም 30 ብር) በሞባይል-ዋሌቱ በየወሩ መባቻ እየከፈለ ይገኛል፡፡ | null | 1.0 |
am-051 | Mobile Banking | የሞባይል-ባንክ አገልግሎት | am | Channel | የሞባይል ባንክ አገልግሎት፤ ተጠቃሚዎች በእጅ ስልካቸው አማካኝነት ወደ ባንክ ሒሳባቸው መግባት እና ማንቀሳቀስ ያስችላቸዋል፡፡ ይህም፤ ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በአካል መሄድ ሳያሻቸው፤ ቀሪ ገንዘብን ማወቅ፣ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ለግልጋሎቶች ክፍያ መፈጸም፣ እንዲሁም የፋይናንስ አገልግሎቶች መጠየቅን/ማመልከትን ይጨምራል፡፡ | Mobile banking is a service that allows users to access and manage their bank accounts using a mobile phone. It includes checking balances, transferring money, paying bills, and applying for financial products without visiting a bank branch. | አቶ ከበደ የዳሽን ባንክ ደንበኛ ሲሆን፤ በእጅ ስልኩ ላይ የዳሽን ባንክን መተግበሪያ ጭኗል፡፡ በመተግበሪያው አማኝነት ቀሪ ገንዘቡን ከተመለከተ በኋላ ለጓደኛው ገንዘብ ላከለት፡፡ ይህንን ሁሉ ያከናወነው በአካል ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ ሳይሄድ በእጅ ስልኩ ብቻ ሰለሆነ፤ አቶ ከበደ የሞባይል-ባንክ አገልግሎትን በአግባቡ መጠቀም ችሏል፡፡ | A user checks their account balance and transfers money to a friend using their bank’s mobile app. | 1.0 |
am-052 | Mobile Money | የሞባይል-ገንዘብ (እንደ አገባቡ የሞባይል-ገንዘብ አገልግሎት) | am | Channel | የሞባይል-ገንዘብ አገልግሎት፤ ተጠቃሚዎች በእጅ ስልካቸው አማካኝነት ገንዘብ ማስቀመጥ፣ መላክ፣ እና መቀበል የሚያስችላቸው አገልግሎት ነው፡፡ ለዚህ አገልግሎት የባንክ ሒሳብ መኖር ግድ የማይል እና አብዛኛውን ጊዜ በሞባይል-ገንዘብ ወኪሎች ወይም በእጅ ስልክ መተግበሪያዎች አማካኝነት የሚከናወን ነው፡፡
ሆኖም የሲም ካር (የስልክ ቁጥር) ሊኖር ያስፈልጋል፡፡ | Mobile money is a service that allows users to store, send, and receive money using their mobile phones. It does not require a bank account and is often used through mobile agents or apps.
But one needs to have a SIM card or a phone number. | የባንክ ሒሳብ የሌለው አንድ ግለሰብ፤ ወርኃዊ ደሞዙ በቀጥታ ወደ ራሱ የሞባይል-ዋሌት ገቢ ስለተደረገለት፤ በዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድ አማካኝነት የኤሌክትሪክ ቢሉን ለመክፈል ችሏል፡፡ | A user without a bank account receives their monthly salary directly into their mobile money wallet and pays for electricity using a USSD code. | 1.0 |
am-053 | Mobile Network Operator | የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ሰጪ | am | null | የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ሰጪ ማለት፤ ድምጽ፣ መልእክት፣ እና ዳታን ጨምሮ የገመድ-አልባ የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎቶችን የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ያሉ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ሰጪዎች፤ የኔትወርክ መሠረተ-ልማታቸውን እና የደንበኞቻቸውን ተደራሽነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፤ ሞባይል-ገንዘብን የመሳሰሉ (ለምሳሌ ቴሌ ብር) በእጅ ስልክ የሚከወኑ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለመጠቀም ያስችላሉ፡፡ | A Mobile Network Operator is a company that provides wireless communication services, including voice, SMS, and data. MNOs such as Ethiotelcom also enable mobile financial services like mobile money by offering the network infrastructure and customer access. | አንድ ተጠቃሚ በሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ሰጪው (ለምሳሌ ኢትዮ ቴሌኮም) የስልክ መስመር (ለምሳሌ 127) ላይ የዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድን በማስገባት ለሞባይል-ገንዘብ አገልግሎት መመዝገብ ስለቻለ (ለምሳሌ ቴሌ ብር)፤ የበይነ-መረብ (ኢንተርኔት) ግንኙነት ሳያስፈልገው በእጅ ስልኩ ገንዘብ መላክ እና መቀበል ጀምሯል፡፡ | A user registers for mobile money through a mobile network operator’s USSD code and uses their phone to send money without needing internet access. | 1.0 |
am-054 | Near Field Communication | የቅርብ-ለቅርብ መገናኛ | am | null | የቅርብ-ለቅርብ መገናኛ (Near Field Communication) ማለት፤ ተቀራርበው ያሉ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ርስበርስ ዳታ ለመቀባባል የሚያስችላቸው፤ የዐጭር ርቀት ገመድ-አልባ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማእቀፍ ውስጥ ሲታይ፤ የቅርብ-ለቅርብ መገናኛ፤ የእጅ ስልክን ወይም ካርድን የክፍያ ተርሚናል ላይ በማስጠጋት ብቻ ወይም ያለ ንክኪ ለመገልገል የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡ | Near Field Communication is a short-range wireless technology that allows devices to exchange data when they are close together. In financial services, NFC is used for contactless payments by tapping a phone or card near a payment terminal. | አቶ ከበደ ለሸመተው አስቤዛ፤ የይለፍ ቃል/ቁጥር ማስገባት ሳያስፈልገው ስማርት የእጅ ስልኩን ወደ ነጋዴው የፖስ ማሽን በማስጠጋት ብቻ ክፍያ ፈጽሟል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት፤ የነጋዴው የፖስ ማሽን የቅርብ-ለቅርብ መገናኛ ቴክኖሎጂ ስለተገጠመለት ነው፡፡ | A user pays for groceries by tapping their smartphone on a merchant’s NFC-enabled point-of-sale device without entering a PIN. | 1.0 |
am-055 | Offline Access | ያለ በይነ-መረብ ተደራሽ/ነት | am | Channel | የበይነ-መረብ ግንኙነት ሳያስፈልግ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን የመገልገል ዘዴ ነው፡፡ ይህም ባብዛኛው በዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮዶች፣ በአጭር የጽሑፍ መልእክት አገልግሎት፣ ወይም በወኪል አማካኝነት ሲሆን፤ ውሱን ሞገድ ባላቸው አካባቢዎች ላሉ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ይበልጥ አካታች ያደርገዋል፡፡ | Offline access refers to the ability to use digital financial services without needing an internet connection. This is often done through USSD codes, SMS, or agent-assisted transactions, making services more inclusive for users in areas with limited connectivity. | ወ/ት ከበደች፤ ያለ በይነ-መረብ በመደበኛ የእጅ ስልኳ አማካኝነት የሞባይል-ዋሌትዋ ላይ ያላትን ቀሪ ገንዘብ ካጣራች በኋላ፤ የዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮዶችን በማስገባት ገንዘብ ላከች፡፡ | A user checks their mobile wallet balance and sends money using a USSD code on a basic phone without internet access. | 1.0 |
am-056 | One-Time Password (OTP) | የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል | am | null | አንድ ተጠቃሚ ወደ ሒሳቡ ሲገባ ወይም ውርኝት ሲያካሄድ፤ ማንነቱን ለማጣራት ለተጠቃሚው በስልክ ወይም በኢሜይል የሚላክ ጊዜያው ኮድ ነው፡፡ ለዐጭር ጊዜ የሚቆይ እና ለአንዴ ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ፤ ተጠቃሚዎችን ከማጭበርበር ድርጊት ይጠብቃቸዋል፡፡ | An OTP is a temporary code sent to a user’s phone or email to verify their identity during a transaction or login. It is valid for a short time and can only be used once, helping protect users from fraud. | አንድ ተጠቃሚ ከሞባይል-ዋሌቱ ገንዘብ እንዲተላለፍለት ካዘዘ በኋላ፤ ትዕዛዙ በእርግጥ የእርሱ ስለመሆኑ ለማጣራት ባለ ስድስት አኃዝ/ዲጂት የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል ያዘለ አጭር የጽሑፍ መልእክት ደረሰው፡፡ | A user receives a 6-digit OTP via SMS to confirm a money transfer from their mobile wallet. | 1.0 |
am-057 | Payee | ተከፋይ | am | Role/Actor | ተከፋይ ማለት፤ በፋይናንስ ውርኝት አማካኝነት ገንዘብ የሚቀበል ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማእቀፍ ውስጥ ሲታይ፤ ተከፋዩ አካል በሞባይል-ገንዘብ፣ በባንክ ሐዋላ፣ ወይም በሌሎች አማራጮች ገንዘብ የሚቀበል ነጋዴ፣ አገልግሎት ሰጪ፣ ወይም ግለሰብ ሊሆን ይችላል፡፡ | A payee is the person or organization who receives money in a financial transaction. In digital financial services, the payee can be a merchant, service provider, or individual receiving funds through mobile money, bank transfer, or other channels. | አንድ ግለሰብ ለቤት አከራዩ በሞባይል-ዋሌት የኪራይ ክፍያ ላከ፡፡ በዚህ ውርኝት ላይ አከራዩ ተከፋይ ነው፡፡ | A user sends rental money to their landlord using a mobile wallet. The landlord is the payee in this transaction. | 1.0 |
am-058 | Payer | ከፋይ | am | Role/Actor | ከፋይ ማለት፤ በፋይናንስ ውርኝት አማካኝነት ገንዘብ የሚልክ ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማእቀፍ ውስጥ ሲታይ፤ ከፋዩ በሞባይል-ዋሌት፣ በባንክ መተግበሪያ፣ ወይም በዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድ እና በመሳሰሉት ዘዴዎች አማካኝነት የክፍያ ሂደቱን የጀመረው አካል ነው፡፡ | A payer is the person or organization who sends money in a financial transaction. In digital financial services, the payer initiates the payment using tools like mobile wallets, bank apps, or USSD codes. | አቶ ከበደ የኤሌክትሪክ ቢሉን በሞባይል-ዋሌቱ ከፈለ፡፡ በዚህ ውርኝት ላይ አቶ ከበደ ከፋይ ነው፡፡ | A user pays their electricity bill using their mobile wallet. The user is the payer in this transaction. | 1.0 |
am-059 | Paying Bills | ቢሎችን መክፈል | am | Use case | ቢሎችን መክፈል ማለት፤ እንደ ኤሌክትሪክ፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ወይም የትምህርት ቤት ክፍያ የመሳሰሉ ቋሚ የፋይናንስ ግዴታዎችን መወጣት ነው፡፡ በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማእቀፍ ሲታይ፤ ተጠቃሚዎች የሞባይል-ዋሌትን፣ የባንክ መተግበሪያን፣ ወይም የዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድን በመጠቀም በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ቢሎችን መክፈል ይችላሉ፡፡ | Paying bills refers to settling regular financial obligations such as electricity, water, phone, or school fees. In digital financial services, users can pay bills electronically using mobile wallets, banking apps, or USSD codes. | ወ/ት አበበች ወርኃዊ የኤሌክትሪክ ቢሏን፤ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ ሳትሄድ፤ የዩ/ኤስ/ኤስ/ዲ/ ኮድ በማስገባት ከሞባይል-ዋሌትዋ አውጥታ ከፈለች፡፡ | A user pays their monthly electricity bill using a USSD code from their mobile money wallet without visiting the utility office. | 1.0 |
am-060 | Payment Gateway | የክፍያ አውታር | am | Technology | የንግድ ድርጅቶች ወይም ነጋዴዎች፤ በካርዶች ወይም በሞባይል-ገንዘብ አማካኝነት ክፍያዎችን በበይነ-መረብ እንዲቀበሉ የሚያግዝ ዘዴ ነው፡፡ የክፍያ መረጃዎችን ከደንበኛው ወደ ደንበኛው የሚገለገልበት ባንክ በሚሥጥር ከላከ በኋላ፤ ክፍያው ይሁንታ ስለማግኘቱ ለነጋዴው ያሳውቀዋል፡፡ | A payment gateway is a tool that helps businesses accept payments online through cards, or mobile money. It safely sends payment information from the customer to the bank and tells the business if the payment was approved. | በበይነ-መረብ ሲሸምቱ እና የካርድ መረጃዎን ሲያስገቡ፤ የክፍያ አውታሩ የእርስዎ ካርድ መሥራት/አለመሥራቱን ካጣራ በኋላ ክፍያውን እንዲፈጽሙ ይረዳዎታል፡፡ | When you buy something online and enter your card details, the payment gateway checks if your card works and helps complete the payment. | 1.0 |
am-061 | Payment Instrunment Issuer | የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አውጪ | am | null | የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አውጪ ማለት፤ እንደ ኢ-ገንዘብ፣ ባለስንቅ ካርድ (debit card)፣ የብድር ካርድ (credit card)፣ ቅድመ-ክፍያ ካርድ (prepaid card) የመሳሰሉ ለክፍያ የሚውሉ መጠቀሚያዎችን የሚሰጥ የፋይናንስ ተቋም ነው፡፡ የተጠቃሚው ገንዘብ በተጠቀሰው አካል ዘንድ ሊቀመጥም ላይቀመጥም ይችላል፤ ሆኖም አውጪው አካል ባሉት የግንኙነት መረቦች አማኝነት የተጠየቀው ገንዘብ መኖሩን በማጣራት የውርኝቱን ጤንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፡፡ | A Payment Instrument Issuer is a financial institution hat issues tools like eMoney, debit cards, credit cards, or prepaid cards used to make payments. These issuers may not hold the user’s funds directly but ensure secure transactions by verifying fund availability through connected systems. | አንድ የፊንቴክ ድርጅት ከተጠቃሚው የሞባይል-ዋሌት ጋር የተሳሰረ የቅድመ-ክፍያ ካርድ (ማለትም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድ) አውጥቶ ለተጠቃሚው ሰጥቶታል፡፡ ተጠቃሚው በቅድመ-ክፍያ ካርዱ ዕቃ ሲገዛ፤ በሞባይል-ዋሌቱ ውስጥ በቂ ገንዘብ ስለመኖሩ አውጪው ካረጋገጠ በኋላ ውርኝቱ እንዲቀጥል ፈቃድ ይሰጣል፡፡ | A fintech company issues a prepaid card linked to a user’s mobile wallet. When the user makes a purchase, the issuer checks if there are enough funds and authorizes the transaction | 1.0 |
am-062 | Payment system | የክፍያ ሥርዓት | am | Concepts | ሰዎች፣ ነጋዴዎች፣ እና ባንኮች ገንዘብን ደኅንነቱ በተጠበቀ አኳኋን እና በፍጥነት ለመላክ እና ለመቀበል የሚያስችላቸው አሠራር ነው፡፡ ይህም ለገንዘብ ዝውውር የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን፣ ሕግጋትን፣ እና አገልግሎቶችን ይጨምራል፡፡ | A payment system is a way for people, businesses, and banks to send and receive money safely and quickly. It includes the tools, rules, and services that make money transfers possible. | የገንዘብ ሥርጭትን የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ፣ የንግድ ባንኮች፣ የፋይናንስ ሕጎች እና ደንቦች፣ ፊንቴኮች፣ ወኪሎች፣ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ሰጪዎች፣ አገር-አቀፍ ስዊች፣ እና ሌሎች አጋዥ ዘርፎች የክፍያ ሥርዓቱ አንድ አካል ናቸው፡፡ አንዳቸው ላይ የሚገጥመው መሰናክል በመላው የክፍያ ሥርዓቱ ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል፡፡ | null | 1.0 |
am-063 | Payment System Operator | የክፍያ ሥርዓት ኦፕሬተር | am | Roles/Players | ገንዘብ በሰዎች፣ በነጋዴዎች፣ እና በባንኮች መካከል እንዲሽከረከር የሚያደርገውን ሥርዓት የሚመራ እና የሚያስተዳድር ድርጅት ነው፡፡ | A payment system operator is an organization that manages and runs the system used to move money between people, businesses, and banks | እንደእነ ኢት ስዊች፣ አሪፍፔይ፣ ቻፓ፣ እና ሳንቲምፔይ የመሳሰሉት የክፍያ ሥርዓት ኦፕሬተሮች ሲሆኑ፤ የክፍያ ትዕዛዞችን ተቀብለው አግባብነቱን ያጣራሉ፤ ክፍያዎችን ያቀባብላሉ ወይም ይፈጽማሉ፤ ሒሳብ ያስታርቃሉ፤ ብሎም የክፍያ ማስረጃዎችን/ደረሰኞችን ይሰጣሉ፡፡ | EthSwitch, PSS, Arifpay, Chapa, Santimpay | 1.0 |
am-064 | Peer to peer lending | የአቻ-ለአቻ-ብድር (እንዳግባቡ አቻ-ለአቻ መበዳደር) | am | Use case | የአቻ-ለአቻ-ብድር/መበዳደር ማለት፤ ያለ ባንክ ጣልቃ-ገብነት አንድ ሰው ለሌላ ሰው የሚያበድረው ገንዘብ ነው፡፡ የዲጂታል ፕላትፎርም አበዳሪውን እና ተበዳሪውን በማገናኘት፤ የብድር ሂደቱን ያግዛል፡፡ | Peer-to-peer lending is when people lend money directly to other people without using a bank. A digital platform connects the lender and the borrower, and helps manage the loan process. | አንድ ባለሱቅ ሸቀጥ ገዝቶ ሱቁን ለማሟላት ፈለገ፡፡ ወደ ባንክ ከመሄድ ይልቅ፤ በዲጂታል ፕላትፎርም ከሰው ተበደረ፡፡ ፕላትፎርሙ ሁለቱ ወገኖች በብድሩ መጠን፤ በመመለሻው ጊዜ፣ እና በወለዱ ላይ አስማምቶ አበዳደራቸው፡፡ | A small shop owner needs money to buy stock. Instead of going to a bank, they borrow from another person through a digital platform. The platform helps both sides agree on the amount, repayment time, and interest. | 1.0 |
am-065 | Platform | ፕላትፎርም | am | Concept | ፕላትፎርም ማለት፤ ሰዎች እንደ ገንዘብ መላክ፣ መበደር፣ መቆጠብ፣ እና ክፍያዎችን መፈጸም የመሳሰሉ የፋይናንስ አገልግሎቶችን መጠቀም የሚያስችላቸው የዲጂታል ከባቢ ወይም ሥርዓት ነው፡፡ በበይነ-መረብ ወይም በእጅ ስልክ ኔትዎርክ አማካኝነት ተጠቃሚዎችን ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር ያገናኛል፡፡ | A platform is a digital space or system that allows people to use financial services like sending money, borrowing, saving, or making payments. It connects users and service providers through the internet or mobile networks. | አንድ የገጠር ነዎሪ ገንዘብ መላክ፣ ቀሪ ገንዘብን ማወቅ፣ ወይም ከሞባይል-ዋሌት ብድር መጠየቅ የመሳሰሉ ጉዳዮችን ለማከናወን፤ የእጅ ስልኩ አስቻይ የዲጂታል ከባቢን ይፈጥርለታል፡፡ ይህ የዲጂታል ከባቢ ፕላትፎርም ይሰኛል፤ ወደ ባንክ ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ ሰዎችን ከፋይናንስ አገልግሎቶች ጋር ያገናኛል፡፡ | A person in a rural area uses their mobile phone to access a digital space where they can send money, check their balance, or apply for a loan. That digital space is called a platform — it connects them to financial services without needing to visit a bank. | 1.0 |
am-066 | Point of Sale Device (POS) | ፖስ ማሽን | am | Technology/Channel | ነጋዴዎች ከደንበኞቻቸው ክፍያ የሚቀበሉበት የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ነው፡፡ ካርዶችን ወይም በእጅ ስልክ የሚደረጉ የክፍያ መረጃዎችን አንብቦ ውርኝቱን ይፈጽማል፡፡ | A Point of Sale (POS) device is a machine used by merchants to accept payments from customers. It reads cards or mobile payment information and helps complete the transaction. | አንድ መደብር ሸመታቸውን በካርድ ወይም በሞባይል-ዋሌት አማካኝነት መክፈል የሚሹ ደንበኞችን የሚያስተናግድበት ፖስ ማሽን አለው፡፡ ማሽኑ ክፍያዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ እና ወዲያውኑ ለመቀበል ያስችለዋል፡፡ | A small shop in a town uses a machine to accept payments from customers who want to pay using a card or mobile wallet. The device helps the shopkeeper receive the money instantly and safely. | 1.0 |
am-067 | Quick Response (QR) Code | ኪው/አር/ ኮድ | am | Technology | በእንግሊዝኛ ምሕፃረ-ቃሉ ኪው/አር/ ኮድ ማለት፤ በማሽን የሚነበብ የዲጂታል ኮድ ሲሆን፤ በውስጡ መረጃዎችን የያዘ ምስል ነው፡፡ ሰዎች በእጅ ስልካቸው ስካን በማድረግ ክፍያ ለመፈጸም፣ ገንዘብ ለመቀበል፣ ወይም ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት ይጠቀሙበታል፡፡ ሰዎችን ከፋይናንስ አገልግሎቶች ጋር በፍጥነት እና በቀላል ለማገናኘት ያግዛል፡፡ | A QR code is a type of digital barcode that stores information. People can scan it using a phone to make payments, receive money, or access services. It helps connect users to financial services quickly and easily. | አንድ መደብር፤ ኪው/አር/ ኮድ አትሞ ሰቅሏል፡፡ ደንበኞች በእጅ ስልካቸው ኮዱን ስካን በማድረግ ብቻ ያለ ጥሬ-ገንዘብ ክፍያ መፈጸም ይችላሉ፡፡ ክፍያውም በቀጥታ ወደ መደብሩ ባለቤት የሒሳብ ቁጥር ውስጥ ይገባል፡፡ | A small business displays a printed QR code at their shop. Customers scan the code with their phones to pay without using cash. The payment goes directly to the shop owner's account. | 1.0 |
am-068 | Recurrent Payment | ቋሚ ክፍያ | am | Process | ቋሚ ክፍያ ማለት፤ ያለ ተጨማሪ ትዕዛዝ ወይም በግብረ-ራስ (automatically) በየተወሰነ የጊዜ ልዩነት (ለምሳሌ በየሳምንቱ፣ በየወሩ፣ በየዓመቱ፣ ወዘተ) የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡ ተጠቃሚው አንዴ ብቻ በሚሰጠው ትዕዛዝ፤ የአሠራር ሥርዓቱ በጊዜ ሰሌዳው መሠረት ጠብቆ ክፍያውን ይፈጽማል፡፡ | A recurrent payment is a payment that happens automatically at regular times — like weekly, monthly, or yearly. The user gives permission once, and the system keeps making the payment on schedule. | አቶ ከበደ እስካሁን ለዩኒቨርስቲ ተማሪ ወንድሙ የሚልክለትን ወርኃዊ ተቆራጭ የሚስገባው፤ በየወሩ መባቻ (በ1) ወደ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል ሄዶ ወደ ተማሪው የባንክ ሒሳብ ጥሬ-ገንዘብ በማስገባት ነበር፡፡
አቶ ከበደ የሞባይል-ባንክ መጠቀም ከጀመረ በኋላ ግን፤ በባንኩ መተግበሪያ አማካኝነት የቋሚ ክፍያ አገልግሎትን በማስጀመር፤ ተቆራጩን ከራሱ ሒሳብ ቀንሶ ወደ ተማሪው ሒሳብ በየወሩ መባቻ ላይ ሁሌ እንዲገባ ማድረግ ችሏል፡፡ ስለዚህ ባንኩ በየወሩ አስታዋሽ ሳያስፈልገው የተመደበውን ክፍያ በታዘዘው ዕለት ለ... | A person subscribes to a service and agrees to pay every month. Instead of sending the money each time, the system takes the payment from their account automatically every month. This is a recurrent payment. | 1.0 |
am-069 | Registration | ምዝገባ (እንደ አገባቡ መመዝገብ) | am | Process | ምዝገባ ማለት፤ አንድ ተጠቃሚ የሚገለገልበትን ሒሳብ የሚከፍትበት እና በፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚነት የሚታቀፍበት ሂደት ነው፡፡ ይህም የተጠቃሚውን ሒሳብ ለመክፈት ወይም ገጸ-ታሪኩን (profile) ለማደራጀት የሚያስፈልገውን ስም፣ የስልክ ቁጥር፣ ወይም መታወቂያ ተጠቃሚው ከሰጠ በኋላ የሚከናወን ነው፡፡ | Registration is the process of of opening a provider account, signing up to use a financial service. It usually involves giving your name, phone number, or ID to create an account or profile. | ወ/ት ከበደች ለመኪናዋ ነዳጅ ለመቅዳት የግድ ቴሌ ብርን መጠቀም ስላስፈለጋት በቅድሚያ የቴሌ ብር መተግበሪያን ወደ እጅ ስልኳ አወረደች፡፡ ቀጥሎም የመተግበሪያውን ትዕዛዝ በመከተል፤ ሙሉ ስሟን፣ አድራሻዋን፣ እና ሌሎች ጥያቄዎችን በቅጹ ላይ ከሞላች በኋላ መታወቂያዋን ፎቶ አንሥታ አባሪ አደረገች፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በተሳካ ሁኔታ ለቴሌ ብር አገልግሎት መመዝገቧን የሚገልጽ አጭር የጽሑፍ መልእክት ደረሳት፡፡ | null | 1.0 |
am-070 | Short Message Service (SMS) | ዐጭር የጽሑፍ መልእክት | am | Technology | ዐጭር የጽሑፍ መልእክት ማለት፤ የተመጠነ ይዘት ያላቸው ጽሑፎችን በእጅ ስልኮች የመላላኪያ ዘዴ ነው፡፡ በተለይ በዲጂታል ፋይናንስ ቴክኖሎጂ ማእቀፍ ሲታይ፤ ባብዛኛው ቀሪ ገንዘብን፣ የውርኝት ማስጠንቀቂያን፣ አሊያም ‹ክፍያ ተፈጽሟል› የሚል ማሳወቂያን የመሳሰሉ መረጃዎችን ለማጋራት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ | SMS is a way to send short text messages between mobile phones. It is often used to share information like account balances, transaction alerts, or payment confirmations. | አቶ አማረ ገንዘብ ከላከ በኋላ በእጅ ስልኩ አጭር የጽሑፍ መልእክት መጣለት፡፡ መልእክቱ ውርኝት ስለመካሄዱ እና ከውርኝቱ በኋላ ያለውን ቀሪ ገንዘብ ይገልጻል፡፡
በስልክ የሚላኩ መሰል አጭር የጽሑፍ መልእክቶች፤ ያለ በይነ-መረብ ግንኙነት እንኳ ሰዎች ስለሒሳባቸው እንቅስቃሴ እንዲያውቁ ያስችላቸዋል፡፡ | A person receives a text message on their phone after sending money. The message confirms the transaction and shows the new balance. This SMS helps them stay informed even without internet access. | 1.0 |
am-071 | Super Agent | ዋና ወኪል | am | Role/Actor | የፋይናንስ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ብዙ ትናንሽ ወኪሎችን የሚመራ እና የሚደግፍ ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፡፡ እሱም በሥሩ ያሉትን ወኪሎች በማሠልጠን፣ ጥሬ-ገንዘብ በማቅረብ፣ እና አገልግሎቱ ያለእንቅፋት እንዲካሄድ እገዛ ይሰጣል፡፡ | A super agent is a person or business that manages and supports many smaller agents who provide financial services. They help with training, cash supply, and making sure services run smoothly. | በአንድ ክልል ካሉ ወኪሎች ውስጥ፤ በክልሉ ወይም በዞኑ መዲና ያሉት አንደ ዋና ወኪል በመሆን በየአቅራቢያቸው ላሉት ወኪሎች ጥሬ-ገንዘብን እና የዲጂታል እገዛዎችን ይሰጧቸዋል፡፡ በገጠር ያሉት ወኪሎች ሥራቸውን ያለችግር እንዲያከናውኑ፤ በከተሞች ያሉ ዋና ወኪሎች አስፈላጊውን ትብብር ያደርጉላቸዋል፡፡ | In a regional town, a business acts as a super agent by supplying cash and digital tools to nearby agents. These agents help people send money, pay bills, or top up accounts. The super agent makes sure the agents have what they need to serve their communities. | 1.0 |
am-072 | Unbanked | ባንክ-አልቦ | am | Concept | የባንክ ሒሳብ የሌላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ለመቆጠብ፣ ለመበደር፣ ወይም ለመክፈል ጥሬ-ገንዘብን ወይም መደበኛ ያልሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ | Unbanked people are those who do not have a bank account. They usually rely on cash or informal ways to save, borrow, or make payments. | በገጠር የምትኖረው አማረች፤ ገንዘቧን የምታስቀምጠው በቤቷ ነው፡፡ ፈጽሞ የባንክ ሒሳብ ከፍታ አታውቅም፤ መደበኛ የፋይናንስ አገልግሎቶችንም አትጠቀምም፡፡ ስለዚህ አማረች ከ‹‹ባንክ-አልቦ›› ጎራ ትመደባለች፡፡ | A woman in a rural village keeps her money at home and uses cash to buy goods. She has never opened a bank account and does not use formal financial services. She is considered unbanked. | 1.0 |
am-073 | Underbanked | ባንክ-አነስ | am | Concept | የባንክ ሒሳብ መክፈት የመሳሰሉ መደበኛ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚችሉ/የቻሉ ሰዎች ቢሆኑም፤ ገንዘብ ለመቆጠብ፣ ለመበደር፣ ወይም ክፍያ ለመፈጸም ባብዛኛው ጥሬ-ገንዘብን ወይም ኢ-መደበኛ ዘዴዎችን የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ ብቻ የባንክ ሒሳባቸውን የሚጠቀሙ ወይም ሌሎች የፋይናንስ አገልግሎቶችን ማግኘት የተሳናቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ | Underbanked people have some access to formal financial services, like a bank account, but they still rely mostly on cash or informal methods for saving, borrowing, or making payments. They may not use their account often or lack access to other financial tools. | በአንድ ትንሽ ከተማ የሚኖር ሰው የባንክ ሒሳብ ቢኖረውም እምብዛም አይጠቀምበትም፡፡ ብሩን በጥሬ-ገንዘብ ያስቀምጣል፤ ሲቸግረው ደግሞ ከወዳጆቹ ወይም ከሠፈሩ የብድር እና ቁጠባ ማኅበር ይበደራል፡፡ መደበኛ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በተሟላ ሁኔታ እየተጠቀመ ስላልሆነ፤ ባንክ-አነስ ሰው ነው፡፡ | A man in a small town has a bank account but rarely uses it. He mostly keeps money in cash and borrows from friends or local savings groups. He is underbanked because he doesn’t fully use formal financial services. | 1.0 |
am-074 | Underserved | አገልግሎት-አነስ | am | Concept | ለመደበኛ የፋይናንስ አገልግሎት ያላቸው ተደራሽነት ውሱን የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡ ምናልባት በሩቅ አካባቢዎች የሚኖሩ፣ መረጃ የሌላቸው፤ አሊያም የተለያዩ ተግዳሮቶች ያሉባቸው (ለምሳሌ የገቢ ማነስ፣ የዕውቀት ማጠር፣ ወይም በፋይናንስ ሥርዓቱ አመኔታ ያጡ) ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ | Underserved people are those who have limited access to formal financial services. They may live in remote areas, lack information, or face challenges like low income, low literacy, or lack of trust in financial systems. | በገጠር ያለ ማኅበረሰብ በአቅራቢያው የሚገኝ ባንክ ወይም ወኪል የለም፡፡ ብዙ ሰዎች የሚጠቀሙት ጥሬ-ገንዘብን እና ኢ-መደበኛ የቁጠባ ዜዴዎችን ነው፡፡ ቀላል እና አስተማማኝ ለሆነ የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ ስላልሆኑ፤ አገልግሎት-አነስ ሆነዋል፡፡ | A community in a rural area has no nearby bank or agent. Most people use cash and informal savings methods. They are underserved because they don’t have easy access to safe and reliable financial services. | 1.0 |
am-075 | Utility Payment | የግልጋሎት ክፍያ | am | Use case | የግልጋሎት ክፍያ ማለት፤ እንደ ኤሌክትሪክ፣ ውሀ፣ ወይም ስልክ ለመሳሰሉት መሠረታዊ አገልግሎቶች የሚፈጸመው ክፍያ ነው፡፡ የእነዚህን ክፍያዎች በጥሬ-ገንዘብ፣ በባንክ፣ ወይም በዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎት አማካኝነት ማከናወን ይቻላል፡፡ | Utility payment is the process of paying for basic services like electricity, water, or phone service. These payments can be made in cash, through banks, or using digital financial services. | አቶ ከበደ የቤቱን ወርኃዊ የኤሌክትሪክ እና የውሀ ቢል፤ እንዲሁም የስልኩን ድኅረ-ክፍያ ቢል፤ በቴሌ ብር አማካኝነት ይከፍላል፡፡ ለአነዚህ መሰል ወሳኝ ወይም መሠረታዊ አገልግሎቶች የሚፈጸመው ክፍያ፤ የግልጋሎት ክፍያ (Utility Payment) ይባላል፡፡ | A household pays its monthly electricity bill using a mobile phone or by visiting a nearby agent. This is a utility payment — it helps keep essential services running. | 1.0 |
am-076 | Vaucher | ቫውቸር | am | null | ቫውቸር ማለት፤ የተወሰነ ገንዘብ ወይም ብድር የያዘ ኮድ ወይም ካርድ ነው፡፡ ሸቀጦችን እና አገልግሎቶችን ለመሸመት፤ ወይም የዲጂታል ሒሳብን ለመሙላት ያገለግላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ቫውቸር የሚያገለግለው፤ ሰዎች የባንክ ሒሳብ ወይም የሞባይል-ዋሌት ሳይኖራቸው ሲቀር ነው፡፡ | A voucher is a code or card that holds a certain amount of money or credit. It can be used to pay for goods, services, or to top up a digital account. Vouchers are often used where people don’t have bank accounts or mobile wallets. | አቶ ከበደ የሞባይል ካርድ ከሱቅ ገዝቶ፤ *805*የሚስጥር ኮዱን# ጽፎ በመደወል የስልኩን ሒሳብ ሞላ፡፡ የገዛው ካርድ ወይም የሚስጥር ኮድ፤ ዋጋ ወይም ገንዘብነት ያለው ስለሆነ፤ ሻውቸር ይባላል፡፡ | A person buys a scratch card from a local shop. The card has a code that they enter into their phone to add money to their digital wallet or pay for a service. This code is a voucher. | 1.0 |
am-077 | E-Wallet | ኢ-ዋሌት (ስለተለመደ ዋሌት ብቻ ይበቃል) | am | null | ገንዘብ በኤሌክትሮኒክ አምሳል የሚጠራቀምበት የዲጂታል ቋት ነው፡፡ ሰዎች ገንዘብን ለመላክ፣ ለመቀበል፣ እና ለመቆጠብ፤ አሊያም ሸቀጦች እና አገልግሎቶችን ለመግዛት ይጠቀሙበታል፡፡ ገንዘቡ በእጅ ስልክ ወይም በካርድ ውስጥ ከመሆኑ በስተቀር፤ ልክ በኪስ ቦርሳ ውስጥ እንዳለው ብር ነው፡፡
ኢ-ገንዘብ የገንዘቡ ዓይነት ሲሆን፤ ዋሌት ግን ኢ-ገንዘብ የሚጠራቀምበት እና የሚንቀሳቀስበት አሠራር ወይም ዘዴ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር፤ ዋሌት ጆንያው/ማኅደሩ፤ ኢ-ገንዘብ ደግሞ እህሉ/ኀዳሪው ነው፡፡
ሞባይል-ዋሌት (በእ... | E-wallet is a digital tool that stores money electronically. People use it to send, receive, and save money, or to pay for goods and services. It works like a physical wallet but on a phone or card.
E-money is the digital form of monetary value itself, while an e-wallet is the application or device used to store and ma... | በትንሽ ከተማ የሚኖር አንድ ግለሰብ በአቅራቢው ባንክ ስለሌለ፤ ገንዘቡን የሚያስቀምጠው በዋሌት ውስጥ ነው፡፡ ከሱቅ ሸምቶ ለመክፈል፣ ለቤተሰብ ገንዘብ ለመላክ፣ አሊያም ለመቆጠብ፤ ጥሬ-ገንዘብ ሳይጠቀም በዋሌቱ ውስጥ ያለውን ገንዘብ በእጅ ስልኩ በማንቀሳቀስ ይፈጽማል፡፡ | A person in a small town uses their mobile phone to keep money in a digital wallet. They can use it to pay for items at shops, send money to family, or save for future needs — all without carrying cash. | 1.0 |
am-078 | Activate/activation | ማስጀመር/ማስጀመሪያ | am | Process | አዲስ፣ ሳይንቀሳቀስ የቆየ፣ ወይም የታገደ የፋይናንስ አገልግሎትን (ለምሳሌ የባንክ ሒሳብ፣ የብድር ካርድ፣ ወይም የዲጂታል-ዋሌትን)፤ ጥቅም መስጠት እንዲጀምር የማድረግ ተግባር ነው፡፡ | The process of making a newly issued, dormant, or restricted financial product (such as a bank account, credit card, or digital wallet) functional and usable by the customer. | አቶ ጌታቸው ጠዋት ከአቢሲኒያ ባንክ አዲስ የሞባይል-ባንክ ሒሳብ ከፈተ፡፡ የባንኩን መተግበሪያ ወደ እጅ ስልኩ ካወረደ በኋላ አገልግሎቱ እንዲጀምር፤ ባንኩ የማስጀመሪያ የይለፍ ቃል (activation key) ላከለት፡፡ | null | 1.0 |
am-079 | Cash-In | ገንዘብ ማስገባት (እንደ አገባቡ ገቢ ገንዘብ) | am | Use Case | ጥሬ-ገንዘብን ሰጥቶ በምትኩ ወይም በእኩሌታው ኢ-ገንዘብን መቀበል ሲሆን፤ ይህም ባብዛኛው ከወኪል ዘንድ በመሄድ የሚፈጸም ነው፡፡ | Receiving eMoney credit in exchange for physical cash - typically done at an agent. | አንድ ደንበኛ ፈቃድ ወዳለው የሞባይል-ገንዘብ ወኪል ሄዶ ለወኪሉ ጥሬ-ገንዘብ ከሰጠው በኋላ፤ ወኪሉ ደግሞ ገንዘቡን በደንበኛው የሞባይል-ዋሌት ውስጥ ገቢ አደረገለት፡፡ ይህ አሠራር ገንዘብ ማስገባት ይባላል፡፡
‹‹ባለሱቅ እባክህ ገንዘብ ማስገባት ፈልጌ ነበር፡፡›› | A customer visits a licensed mobile money agent, hands over cash, and the agent deposits the amount into their mobile wallet. | 1.0 |
am-080 | Cash-Out | ገንዘብ ማውጣት (እንደ አገባቡ ወጪ ገንዘብ) | am | Use Case | ከኢ-ገንዘብ ሒሳብ ላይ ቀንሶ በመስጠት በምትኩ ወይም በእኩሌታው ጥሬ-ገንዘብን መቀበል ሲሆን፤ ይህም ባብዛኛው ከወኪል ዘንድ በመሄድ የሚፈጸም ነው፡፡ | Receiving physical cash in exchange for a debit to an eMoney account - typically done at an agent. | ደሞዙን በሞባይል-ዋሌት የተቀበለ ተቀጣሪ፤ የቤቱን አስቤዛ ለመሸመት ጥሬ-ገንዘብ ስላስፈለገው ወደ ወኪል ሄዶ ከገባለት ደሞዝ ከፊሉን በጥሬ-ገንዘብ ተቀበለ፡፡ ይህ አሠራር ገንዘብ ማውጣት ይባላል፡፡
‹‹ባለሱቅ እባክህ ገንዘብ ማውጣት ፈልጌ ነበር፡፡›› | A salaried worker receives their income in a mobile wallet and cashes out part of it through an agent to cover household expenses. | 1.0 |
am-081 | National Switch | አገር-አቀፍ ስዊች | am | Infrastructure | የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማትን እና የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎችን የሚያገናኝ እና በመካከላቸው ደኅንነቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ ውርኝቶችን እንዲያካሂዱ የሚያስችል የተማከለ ሥርዓት ነው፡፡ ይህም ባንኮች፣ የሞባይል-ገንዘብ አገልግሎት ሰጪዎች፣ እና ሌሎችም የፋይናንስ ፕላትፎርሞች የሚጠቀሙባቸው የክፍያ ሥርዓቶች ርስበርስ ተናባቢ (interoperable) እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ | A National Switch is a centralized system that connects different financial institutions and payment service providers, allowing them to exchange transactions securely and efficiently. It enables interoperability across banks, mobile money providers, and other financial platforms. | አንድ ተጠቃሚ ከሚገለገልበት የባንክ ሒሳብ፤ ደንበኛ ወዳልሆነበት ወደ ሌላ የሞባይል-ዋሌት አገልግሎት ሰጪ፤ በአገር-አቀፍ ስዊች (ኢትስዊች) አማካኝነት ገንዘብ አስላልፏል፡፡ ይህም የላኪው እና የተቀባዩ ድርጅቶች የተለያዩ ወይም ለየቅል ሆነው ሳለ ተጠቃሚው ከአንድ ወገን ብቻ አገልግሎቱን ማግኘት የቻለው፤ አገር-አቀፍ ስዊች (ኢትስዊች ድርጅት) እንደ ድልድይ ሆኖ ስላገለገለ ነው፡፡ | A user transfers money from their bank account to a mobile wallet from a different provider using the national switch (EthSwitch), without needing both services to be from the same company. | 1.0 |
am-082 | Over The Counter Services | የገጽ-ለገጽ አገልግሎት | am | Channel | ሦስተኛ አካልን ሳይጨምር፤ በሁለት ወገኖች መካከል በቀጥታ የሚፈጸም የሸቀጥ፣ የአገልግሎት፣ ወይም የፋይናንስ ልውውጥ ነው፡፡ | It refers to transactions, products, or financial trades that occur directly between two parties, such as in a store, rather than third parties. | አንድ ግለሰብ ወደ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል ሂዶ፤ ወደራሱ ሒሳብ ገንዘብ አስገባ፡፡ ይህም የገጽ-ለገጽ አገልግሎት ነው፡፡ | A user visits a bank branch office in-person and deposits money at his account. This type of service is an Over The Counter Service. | 1.0 |
am-083 | Transaction Limits | የውርኝት ጣራ | am | Use case | አንድ ተጠቃሚ በአንድ ውርኝት ወይም በተወሰነ ክፍለ-ጊዜ (በቀን፣ በሳምንት፣ በወር) መላክ፣ መቀበል፣ ወይም ማውጣት የሚችለው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን ነው፡፡ | The maximum amount of money a user can send, receive, or withdraw in a single transaction or within a set time period (daily, weekly, monthly). These limits are set by financial service providers to manage risk and comply with regulations. | በርካታዎቹ የኢትዮጵያ ባንኮች፤ ከቅርንጫፍ ወይም ከኤ/ቲ/ኤም/ በቀን (እንደ ቅደም ተከተላቸው) ከ50 ሺህ ወይም ከ8 ሺህ ብር በላይ ጥሬ-ገንዘብ ማውጣት የሚከለክል ድንጋጌ አላቸው፡፡ ይህም ከውርኝት ጣራ ውስጥ የሚመደብ አሠራር ነው፡፡ | null | 1.0 |
am-084 | Pull payments | የተከፋይ-ጠሪ ክፍያ | am | Use case | በተከፋዩ (ለምሳሌ ነጋዴ) አነሳሽነት ወይም ጠሪነት የሚጀመር የክፍያ ዓይነት ሆኖ፤ ነጋዴው የሚገለገልበት ባንክ የከፋዩን ባንክ ጠይቆ፤ ገንዘቡን ከከፋዩ ሒሳብ ‹‹ጠርቶ›› ወደ ተከፋዩ ነጋዴ የሚወሰድበት አሠራር ነው፡፡
በሌላ አነጋገር የክፍያውን ፍሰት ወይም አቅጣጫ ያስጀመረው ወገንን (ተከፋዩ መሆኑን) የሚያመላክት ነው፡፡ | A payment type which is initiated by the payee: typically a merchant or payment acceptor, whose provider «pulls» the funds out of the payer's account at the payer's provider | የነዳጅ ክፍያዎች የሚከናወኑት በቴሌ ብር ሲሆን፤ የነዳጅ ማደያው አስተናጋጅ፤ ነዳጅ ወዳስቀዳው ሹፌር የስልክ ቁጥር የገንዘቡን መጠን የሚገልጽ የተከፋይ-ጠሪ ክፍያ ጥያቄ ላከለት፡፡ ሹፌሩ የሚሥጥር ቁጥሩን ሲያስገባ ክፍያው ተከናወነ፡፡
ምንም እንኳ ክፍያው በቴሌ-ብር ቢከናወንም፤ የክፍያ ሂደቱን ያስጀመረው የማደያው አስተናጋጅ ስለሆነ፤ የአከፋፈል ፍሰቱ ዓይነት ‹‹የተከፋይ-ጠሪ ክፍያ›› ነው፡፡ | Fuel payment via Telebirr | 1.0 |
am-085 | Push payments | የከፋይ-ጠሪ ክፍያ | am | Use case | በከፋዩ (ለምሳሌ ሸማች) አነሳሽነት ወይም ጠሪነት የሚጀመር የክፍያ ዓይነት ሆኖ፤ ከፋዩ ለሚገለገልበት ባንክ ወይም የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ‹‹ከሒሳቤ ላይ ተቀንሶ ይከፈል›› ብሎ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት፤ ገንዘቡን ወደ ተከፋዩ ባንክ ይሰደዋል፡፡
በሌላ አነጋገር የክፍያውን ፍሰት ወይም አቅጣጫ ያስጀመረው ወገንን (ከፋዩ መሆኑን) የሚያመላክት ነው፡፡ | A payment type which is initiated by the payer, who instructs their provider to debit their account and «push» the funds to the receiving payee at the payee's provider | አቶ ሸምሱ ምሳውን በልቶ ሲጨርስ አስተናጋጁን ቢል እና በቴሌ ብር የሚከፍልበትን የስልክ ቁጥር እንዲያመጣ ካዘዘው በኋላ፤ ሲመጣለት ሒሳቡን ከፈለ፡፡
የክፍያ ሂደቱን ያስጀመረው አቶ ሸምሱ ስለሆነ፤ የአከፋፈል ፍሰቱ ዓይነት ‹‹የከፋይ-ጠሪ ክፍያ›› ነው፡፡ | QR payment via Telebirr | 1.0 |
am-086 | Off us payments | ሦስተኛ ወገን አገዝ ክፍያ | am | Use case | አንድ ክፍያን ለመፈጸም ብዙ አካላት የሚሳተፉበት ሒደት ሆኖ፤ ተከፋዩ (payee) ደንበኛ የሆነበት የፋይናንስ ድርጅት (የገንዘብ ቋቱ ያለበት) እና ለተከፋዩ ከፍያውን የሚፈጽመው አካል (ክፍያ ፈጻሚ/payer) የተለያዩ ድርጅቶች ሲሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ውርኝቱ ሌሎች አካላትን መጨመር ግድ ስለሚል፤ ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያን ሊያስከትል ይችላል፡፡ | Payments made in a multiple-participant system or scheme, where the payer's provider is a different entity as the payee's provider. These transactions often involve intermediaries and may incur additional fees. | አቶ አበበ ለሸመተው ዕቃ በዳሽን ባንክ የባለስንቅ ካርድ ለመክፈል ይፈልጋል፡፡ ሆኖም የባለሱቁ የባንክ ሒሳብ እና የሚጠቀምበት የፖስ ማሽን ከአቢሲኒያ ባንክ ነው፡፡ አቶ አበበ (1ኛ ወገን)፣ ዳሽን ባንክ (2ኛ ወገን) ሆነው፤ ክፍያውን የሚፈጽመው አቢሲኒያ ባንክ (3ኛ ወገን) ስለሚሆን፤ ይህ መሰል አሠራር ‹‹ሦስተኛ ወገን አገዝ ክፍያ›› ይሰኛል፡፡ | A user with a mobile wallet from Provider A pays for goods at a merchant who uses Provider B’s payment terminal. The transaction is completed through a shared payment switch. | 1.0 |
am-087 | On us payments | ሦስተኛ ወገን የለሽ ክፍያ | am | Use case | አንድ ክፍያን ለመፈጸም ሁለት አካላት የሚሳተፉበት ሒደት ሲሆን፤ ተከፋዩ (payee) ደንበኛ የሆነበት የፋይናንስ ድርጅት (የገንዘብ ቋቱ ያለበት) እና ለተከፋዩ ከፍያውን የሚፈጽመው አካል (ክፍያ ፈጻሚ/payer) ተመሳሳይ ድርጅት ሲሆን ነው፡፡ ስለዚህ ውርኝቱ ሦስተኛ አካላትን ሳይጨምር በአንድ ድርጅት ውስጥ ብቻ ስለሚያልቅ ፈጣን እና ወጪ ቆጣቢ ያደርገዋል፡፡ | Payments made in a multiple-participant system or scheme, where the payer's provider is the same entity as the payee's provider. These transactions are processed internally without involving external networks, making them faster and often cheaper. | አቶ አበበ እና አቶ በለጠ፤ ሁለቱም ተመሳሳይ የሞባይል-ዋሌት፤ ማለትም ቴሌ ብርን ይጠቀማሉ፡፡ አቶ አበበ ለአቶ በለጠ በቴሌ ብር ገንዘብ ሲልክ፤ የገንዘብ ቋቱም ክፍያውም እዚህ ስለሆነ፤ የአገር-አቀፍ ስዊችን ወይም የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ሳያስገባ በአንዱ ድርጅት ስለተከናወነ ውርኝቱ ፈጣን ነበር፡፡ | A user transfers money from their mobile wallet to another user who also uses the same mobile money provider. The transaction is completed instantly without routing through a national switch or third-party system. | 1.0 |
DFS Glossary — Amharic & Afaan Oromoo
Expert-verified glossaries of Digital Financial Services (DFS) terminology in
Amharic (am) and Afaan Oromoo (om), published as structured,
machine-readable, openly-licensed data.
Open language infrastructure for two low-resource Ethiopian languages — for developers, researchers, translators, and the financial-inclusion community.
| Languages | Amharic (am, Ge'ez script) · Afaan Oromoo (om, Latin script) |
| Entries | 87 Amharic + 86 Afaan Oromoo = 173 |
| License | CC BY 4.0 |
| Version | 1.0 |
Usage
from datasets import load_dataset
am = load_dataset("shega/dfs-glossary", "am") # Amharic glossary
om = load_dataset("shega/dfs-glossary", "om") # Afaan Oromoo glossary
print(am["train"][0]["term_local"]) # should print clean Ge'ez, e.g. የአገልግሎት ነጥብ
Data fields
| Field | Type | Description |
|---|---|---|
id |
string | Stable, language-prefixed id (am-001, om-001). Never reused. |
term_en |
string | English term — the join key across languages. |
term_local |
string | Term in the target language (Ge'ez / Latin). |
language |
string | am or om. |
category |
string | null | Domain grouping (e.g. Channel, Concept, Process). Verbatim from source. |
definition_local |
string | Verified definition in the target language. |
definition_en |
string | null | English definition, where available. |
example_local |
string | null | Usage example in the target language. |
example_en |
string | null | English usage example, where available. |
version |
string | Dataset version (1.0). |
The English term (term_en) is shared across the two languages, so the am and
om configs can be joined on it.
Methodology
Translated and verified by domain experts as part of the AKOFADA project, and built under a strict fidelity policy:
- Source is the editable copy decks, never the PDFs. Ge'ez (Amharic) script corrupts when copied out of PDFs; for a terminology dataset a single wrong character destroys trust. PDFs are used only for human spot-checks.
- Text is preserved verbatim — only whitespace tidying is applied. No spelling, wording, casing, or Unicode normalisation of the verified text.
- The two languages are cross-linked on the English term.
Provenance
- Producer: Shega
- Project: AKOFADA
- Funding: Gates Foundation
Citation
@dataset{shega_dfs_glossary_2026,
title = {DFS Glossary — Amharic & Afaan Oromoo},
author = {Shega and AKOFADA},
year = {2026},
version = {1.0},
publisher = {Shega},
note = {DOI pending — to be added on first release},
url = {https://huggingface.co/datasets/shega/dfs-glossary}
}
License
Creative Commons Attribution 4.0 International (CC BY 4.0). Free to share and adapt, including commercially, with attribution.
- Downloads last month
- 15