Dataset Viewer
Auto-converted to Parquet Duplicate
English
stringlengths
1
1.22k
Amharic
stringlengths
1
892
and it came to pass, that at even the quails came up, and covered the camp and in the morning the dew lay round about the host.
እንዲህም ሆነ፤ በመሸ ጊዜ ድርጭቶች መጡ፥ ሰፈሩንም ከደኑት፤ ማለዳም በሰፈሩ ዙሪያ ጠል ወድቆ ነበር።
and when the dew that lay was gone up, behold, upon the face of the wilderness there lay a small round thing, as small as the hoar frost on the ground.
የወደቀውም ጠል ባለፈ ጊዜ፥ እነሆ በመሬት ላይ እንደ ደቃቅ ውርጭ ሆኖ ቅርፊት የሚመስል ደቃቅ ነገር በምድረ በዳ ታየ።
and when the children of israel saw it, they said one to another, it is manna for they wist not what it was. and moses said unto them, this is the bread which the lord hath given you to eat.
የእስራኤልም ልጆች ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደ ሆነ አላወቁምና እርስ በእርሳቸው። ይህ ምንድር ነው? ተባባሉ። ሙሴም። ትበሉት ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው።
this is the thing which the lord hath commanded, gather of it every man according to his eating, an omer for every man, according to the number of your persons take ye every man for them which are in his tents.
እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው። እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ይልቀም፤ በድኳኑ ባሉት ነፍሶች ቍጥር ለአንድ ሰው አንድ ጎሞር ውሰዱ አላቸው።
and the children of israel did so, and gathered, some more, some less.
የእስራኤልም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ አንዱ አብዝቶ አንዱም አሳንሶ ለቀመ።
and when they did mete it with an omer, he that gathered much had nothing over, and he that gathered little had no lack they gathered every man according to his eating.
በጎሞርም በሰፈሩት ጊዜ እጅግ ለለቀመ አልተረፈውም ጥቂትም ለለቀመ አልጐደለበትም፤ ሁሉ እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ለቀመ።
and moses said, let no man leave of it till the morning.
ሙሴም። ማንም ከእርሱ አንዳች ለነገ አያስቀር አላቸው።
and the whole congregation of the children of israel murmured against moses and aaron in the wilderness
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በምድረ በዳ በሙሴና በአሮን ላይ አንጐራጐሩ።
notwithstanding they hearkened not unto moses but some of them left of it until the morning, and it bred worms, and stank and moses was wroth with them.
ነገር ግን ሙሴን አልሰሙትም፤ አንዳንድ ሰዎችም ከእርሱ ለነገ አስቀሩ፥ እርሱም ተላ ሸተተም፤ ሙሴም ተቈጣቸው።
and they gathered it every morning, every man according to his eating and when the sun waxed hot, it melted.
ሰውም ሁሉ ዕለት ዕለት የሚበላውን ያህል በጥዋት ለቀመ፤ ፀሀይም በተኰሰ ጊዜ ቀለጠ።
and it came to pass, that on the sixth day they gathered twice as much bread, two omers for one man and all the rulers of the congregation came and told moses.
እንዲህም ሆነ፤ በስድስተኛው ቀን ሁለት እጥፍ አድርገው እያንዳንዳቸው ሁለት ጎሞር እንጀራ ለቀሙ፤ የማሀበሩም አለቆች ሁሉ መጥተው ለሙሴ ነገሩት።
and he said unto them, this is that which the lord hath said, to morrow is the rest of the holy sabbath unto the lord bake that which ye will bake to day, and seethe that ye will seethe and that which remaineth over lay up for you to be kept until the morning.
እርሱም። እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው። ነገ ዕረፍት፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩት አላቸው።
and they laid it up till the morning, as moses bade and it did not stink, neither was there any worm therein.
ሙሴም እንዳዘዘ ለነገ አኖሩት፤ አልሸተተም፥ ትልም አልሆነበትም።
and moses said, eat that to day for to day is a sabbath unto the lord to day ye shall not find it in the field.
ሙሴም። የእግዚአብሔር ሰንበት ዛሬ ነውና ብሉት፤ ዛሬ በሜዳ አታገኙትም።
six days ye shall gather it but on the seventh day, which is the sabbath, in it there shall be none.
ስድስት ቀን ልቀሙት፤ ሰባተኛው ቀን ግን ሰንበት ነው፤ በእርሱ አይገኝም አለ።
and it came to pass, that there went out some of the people on the seventh day for to gather, and they found none.
በሰባተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ከሕዝቡ አንዳንድ ሰዎች ሊለቅሙ ወጡ፥ ምንምን አላገኙም።
and the lord said unto moses, how long refuse ye to keep my commandments and my laws?
እግዚአብሔርም ሙሴን። ትእዛዞቼንና ሕጎቼን ለመጠበቅ እስከ መቼ እንቢ ትላላችሁ?
see, for that the lord hath given you the sabbath, therefore he giveth you on the sixth day the bread of two days abide ye every man in his place, let no man go out of his place on the seventh day.
እግዚአብሔር ሰንበትን እንደ ሰጣችሁ እዩ፤ ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሁለት ቀን እንጀራ ሰጣችሁ፤ ሰው ሁሉ በስፍራው ይቀመጥ፥ በሰባተኛው ቀን ማንም ከስፍራው አይሂድ አለው።
and the children of israel said unto them, would to god we had died by the hand of the lord in the land of egypt, when we sat by the flesh pots, and when we did eat bread to the full for ye have brought us forth into this wilderness, to kill this whole assembly with hunger.
የእስራኤልም ልጆች። ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልትገድሉ እኛን ወደዚች ምድረ በዳ አውጥታችኋል፤ በሥጋው ምንቸት አጠገብ ተቀምጠን እንጀራ ስንበላ ስንጠግብ ሳለን በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን! አሉአቸው።
so the people rested on the seventh day.
ሕዝቡም በሰባተኛው ቀን ዐረፈ።
and the house of israel called the name thereof manna and it was like coriander seed, white and the taste of it was like wafers made with honey.
የእስራኤልም ወገን ስሙን መና ብለው ጠሩት፤ እርሱም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ ነው፤ ጣዕሙም እንደ ማር ቂጣ ነው።
and moses said, this is the thing which the lord commandeth, fill an omer of it to be kept for your generations that they may see the bread wherewith i have fed you in the wilderness, when i brought you forth from the land of egypt.
ሙሴም። እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው። ከግብፅ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ያዩ ዘንድ ከእርሱ አንድ ጎሞር ሙሉ ለልጅ ልጆቻችሁ ይጠበቅ አለ።
and moses said unto aaron, take a pot, and put an omer full of manna therein, and lay it up before the lord, to be kept for your generations.
ሙሴም አሮንን። አንድ ማድጋ ወስደህ ጎሞር ሙሉ መና አግባበት፥ ለልጅ ልጃችሁም ይጠበቅ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው አለው።
as the lord commanded moses, so aaron laid it up before the testimony, to be kept.
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ይጠበቅ ዘንድ አሮን በምስክሩ ፊት አኖረው።
and the children of israel did eat manna forty years, until they came to a land inhabited they did eat manna, until they came unto the borders of the land of canaan.
የእስራኤልም ልጆች ወደሚኖሩባት ምድር እስኪመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ።
now an omer is the tenth part of an ephah.
ጎሞርም የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ ክፍል ነው።
then said the lord unto moses, behold, i will rain bread from heaven for you and the people shall go out and gather a certain rate every day, that i may prove them, whether they will walk in my law, or no.
እግዚአብሔርም ሙሴን። በሕጌ ይሄዱ ወይም አይሄዱ እንደሆነ እኔ እንድፈትናቸው፥ እነሆ ከሰማይ እንጀራን አዘንብላችኋለሁ፤ ሕዝቡም ወጥተው ለዕለት ለዕለት የሚበቃቸውን ይልቀሙ።
and it shall come to pass, that on the sixth day they shall prepare that which they bring in and it shall be twice as much as they gather daily.
እንዲህም ይሆናል፤ በስድስተኛው ቀን ያመጡትን ያዘጋጁ፥ ዕለት ዕለትም ከሚለቅሙት ይልቅ ሁለት እጥፍ ይሁን አለው።
and moses and aaron said unto all the children of israel, at even, then ye shall know that the lord hath brought you out from the land of egypt
ሙሴና አሮንም ለእስራኤል ልጆች ሁሉ። እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር እንዳወጣችሁ ማታ ታውቃላችሁ፥
and in the morning, then ye shall see the glory of the lord for that he heareth your murmurings against the lord and what are we, that ye murmur against us?
የእግዚአብሔርንም ክብር ጥዋት ታያላችሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ያንጐራጐራችሁትን ሰምቶአልና በእኛም ላይ የምታንጐራጕሩ እኛ ምንድር ነን? አሉ።
and moses said, this shall be, when the lord shall give you in the evening flesh to eat, and in the morning bread to the full for that the lord heareth your murmurings which ye murmur against him and what are we? your murmurings are not against us, but against the lord.
ሙሴም። እግዚአብሔር ያንጐራጐራችሁበትን ማንጐራጐራችሁን ሰምቶአልና በመሸ ጊዜ ትበሉ ዘንድ ሥጋን፥ ማልዶም ትጠግቡ ዘንድ እንጀራን እግዚአብሔር ይሰጣችኋል፤ እኛም ምንድር ነን? ማንጐራጐራችሁ በእግዚአብሔር ላይ ነው እንጂ በእኛ አይደለም አለ።
and moses spake unto aaron, say unto all the congregation of the children of israel, come near before the lord for he hath heard your murmurings.
ሙሴም አሮንን። ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ። ማንጐራጐራችሁን ሰምቶአልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ በል አለው።
and all the congregation of the children of israel journeyed from the wilderness of sin, after their journeys, according to the commandment of the lord, and pitched in rephidim and there was no water for the people to drink.
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፥ በራፊዲምም ሰፈሩ፤ ሕዝቡም ይጠጡ ዘንድ ውኃ አልነበረም።
so joshua did as moses had said to him, and fought with amalek and moses, aaron, and hur went up to the top of the hill.
ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮንም ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ።
and it came to pass, when moses held up his hand, that israel prevailed and when he let down his hand, amalek prevailed.
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ድል ያደርግ ነበር።
but moses hands were heavy and they took a stone, and put it under him, and he sat thereon and aaron and hur stayed up his hands, the one on the one side, and the other on the other side and his hands were steady until the going down of the sun.
የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሀይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ጠነከሩ።
and joshua discomfited amalek and his people with the edge of the sword.
ኢያሱም አማሌቅንና ሕዝቡን በሰይፍ ስለት አሸነፈ።
and the lord said unto moses, write this for a memorial in a book, and rehearse it in the ears of joshua for i will utterly put out the remembrance of amalek from under heaven.
እግዚአብሔርም ሙሴን። የአማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሀፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ ተናገር አለው።
and moses built an altar, and called the name of it jehovahnissi
ሙሴም መሰዊያ ሰራ፥ ስሙንም ይህዌህ ንሲ ብሎ ጠራው፤
for he said, because the lord hath sworn that the lord will have war with amalek from generation to generation.
እርሱም። እጁን በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ስለጫነ የእግዚአብሔር ሰልፍ በአማሌቅ ላይ ለልጅ ልጅ ይሁን አለ።
wherefore the people did chide with moses, and said, give us water that we may drink. and moses said unto them, why chide ye with me? wherefore do ye tempt the lord?
ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት። የምንጠጣውን ውኃ ስጠን አሉት። ሙሴም። ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ? አላቸው።
and the people thirsted there for water and the people murmured against moses, and said, wherefore is this that thou hast brought us up out of egypt, to kill us and our children and our cattle with thirst?
ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ። እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኸን? ሲሉ በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ።
and moses cried unto the lord, saying, what shall i do unto this people? they be almost ready to stone me.
ሙሴም። ሊወግሩኝ ቀርበዋልና በዚህ ሕዝብ ምን ላድርግ? ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
and the lord said unto moses, go on before the people, and take with thee of the elders of israel and thy rod, wherewith thou smotest the river, take in thine hand, and go.
እግዚአብሔርም ሙሴን። በሕዝቡ ፊት እለፍ፥ ከእስራኤልም ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤ ወንዙንም የመታህባትን በትር በእጅህ ይዘሃት ሂድ።
behold, i will stand before thee there upon the rock in horeb and thou shalt smite the rock, and there shall come water out of it, that the people may drink. and moses did so in the sight of the elders of israel.
እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ።
and he called the name of the place massah, and meribah, because of the chiding of the children of israel, and because they tempted the lord, saying, is the lord among us, or not?
ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር። እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን ወይስ አይደለም? ሲሉ እግዚአብሔርን ስለተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው።
then came amalek, and fought with israel in rephidim.
አማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋር በራፊድም ተዋጋ።
and moses said unto joshua, choose us out men, and go out, fight with amalek to morrow i will stand on the top of the hill with the rod of god in mine hand.
ሙሴም ኢያሱን። ጕልማሶችን ምረጥልን፥ ወጥተህም ከአማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔ ነገ የእግዚአብሔርን በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው ራስ ላይ እቆማለሁ አለው።
and the lord spake unto moses, saying,
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።
and when pharaoh drew nigh, the children of israel lifted up their eyes, and, behold, the egyptians marched after them and they were sore afraid and the children of israel cried out unto the lord.
ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዓይናቸውን አነሡ፥ እነሆም ግብፃውያን በኋላቸው ገሥግስው ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ።
and they said unto moses, because there were no graves in egypt, hast thou taken us away to die in the wilderness? wherefore hast thou dealt thus with us, to carry us forth out of egypt?
ሙሴንም። በግብፅ መቃብር ስላልኖረ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ አወጣኸንን? ከግብፅ ታወጣን ዘንድ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው?
is not this the word that we did tell thee in egypt, saying, let us alone, that we may serve the egyptians? for it had been better for us to serve the egyptians, than that we should die in the wilderness.
በምድረ በዳ ከምንሞት ብንገዛላቸው ይሻላልና። ተወን፥ ለግብፃውያን እንገዛ ብለን በግብፅ ሳለን ያልንህ ቃል ይህ አይደለምን? አሉት።
and moses said unto the people, fear ye not, stand still, and see the salvation of the lord, which he will shew to you to day for the egyptians whom ye have seen to day, ye shall see them again no more for ever.
ሙሴም ለሕዝቡ። አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
the lord shall fight for you, and ye shall hold your peace.
እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ አላቸው።
and the lord said unto moses, wherefore criest thou unto me? speak unto the children of israel, that they go forward
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። ለምን ትጮኽብኛለህ? እንዲጓዙ ለእስራኤል ልጆች ንገር።
but lift thou up thy rod, and stretch out thine hand over the sea, and divide it and the children of israel shall go on dry ground through the midst of the sea.
አንተም በትርህን አንሣ፥ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፥ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ።
and i, behold, i will harden the hearts of the egyptians, and they shall follow them and i will get me honour upon pharaoh, and upon all his host, upon his chariots, and upon his horsemen.
እነሆም እኔ የግብፃውያንን ልብ አፀናለሁ፥ በኋላቸውም ይገባሉ፤ በፈርዖንና በሰራዊቱም ሁሉ በሰረገሎቹም በፈረሰኞቹም ላይ ክብር አገኛለሁ።
and the egyptians shall know that i am the lord, when i have gotten me honour upon pharaoh, upon his chariots, and upon his horsemen.
ግብፃውያንም በፈርዖንና በሰረገሎቹ በፈረሰኞቹም ላይ ክብር ባገኘሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
and the angel of god, which went before the camp of israel, removed and went behind them and the pillar of the cloud went from before their face, and stood behind them
በእስራኤልም ሰራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ፥
speak unto the children of israel, that they turn and encamp before pihahiroth, between migdol and the sea, over against baalzephon before it shall ye encamp by the sea.
ተመልሰው በሚግዶልና በባሕር መካከል፥ በበኣልዛፎንም ፊት ለፊት ባለው በፊሀሒሮት ፊት እንዲሰፍሩ ለእስራኤል ልጆች ተናገር፤ ከእርሱም አጠገብ በባሕር ዳር ትሰፍራላችሁ።
and it came between the camp of the egyptians and the camp of israel and it was a cloud and darkness to them, but it gave light by night to these so that the one came not near the other all the night.
በግብፃውያን ሰፈርና በእስራኤል ሰፈር መካከልም ገባ፤ በዚያም ደመናና ጨለማ ነበረ፥ በዚህ በኩል ግን ሌሊቱን አበራ፤ ሌሊቱንም ሁሉ እርስ በእርሳቸው አልተቃረቡም።
and moses stretched out his hand over the sea and the lord caused the sea to go back by a strong east wind all that night, and made the sea dry land, and the waters were divided.
ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምሥራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፥ ባሕሩንም አደረቀው፥ ውኃውም ተከፈለ።
and the children of israel went into the midst of the sea upon the dry ground and the waters were a wall unto them on their right hand, and on their left.
የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ መካከል በየብስ ገቡ፤ ውኃውም በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ሆነላቸው።
and the egyptians pursued, and went in after them to the midst of the sea, even all pharaohs horses, his chariots, and his horsemen.
ግብፃውያንም፥ የፈርዖን ፈረሶችና ሰረገሎች ፈረሰኞቹም ሁሉ፥ እያሳደዱ በኋላቸው ወደ ባሕር መካከል ገቡ።
and it came to pass, that in the morning watch the lord looked unto the host of the egyptians through the pillar of fire and of the cloud, and troubled the host of the egyptians,
ንጋትም በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዓምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሰራዊት ተመለከተ፥ የግብፃውያንንም ሰራዊት አወከ።
and took off their chariot wheels, that they drave them heavily so that the egyptians said, let us flee from the face of israel for the lord fighteth for them against the egyptians.
የሰረገሎቹንም መንኰራኵር አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አገባቸው፤ ግብፃውያንም። እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ አሉ።
and the lord said unto moses, stretch out thine hand over the sea, that the waters may come again upon the egyptians, upon their chariots, and upon their horsemen.
እግዚአብሔርም ሙሴን። እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ፥ ውኃውም በግብፃውያን በሰረገሎቻቸውም በፈረሰኞቻቸውም ላይ ይመለስ አለው።
and moses stretched forth his hand over the sea, and the sea returned to his strength when the morning appeared and the egyptians fled against it and the lord overthrew the egyptians in the midst of the sea.
ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፥ ባሕሩም ማለዳ ወደ መፍሰሱ ተመለሰ፤ ግብፃውያንም ከእርሱ ሸሹ፥ እግዚአብሔርም ግብፃውያንን በባሕሩ መካከል ጣላቸው።
and the waters returned, and covered the chariots, and the horsemen, and all the host of pharaoh that came into the sea after them there remained not so much as one of them.
ውኃውም ተመልሶ በኋላቸው ወደ ባሕር የገቡትን ሰረገሎችን ፈረሰኞችንም የፈርዖንንም ሰራዊት ሁሉ ከደነ፤ ከእነርሱም አንድ ስንኳ አልቀረም።
but the children of israel walked upon dry land in the midst of the sea and the waters were a wall unto them on their right hand, and on their left.
የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ ውስጥ በየብስ ሄዱ፤ ውኆችም በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ሆኑላችው።
for pharaoh will say of the children of israel, they are entangled in the land, the wilderness hath shut them in.
ፈርዖንም ስለ እስራኤል ልጆች። በምድር ይቅበዘበዛሉ፥ ምድረ በዳም ዘጋቻቸው ይላል።
thus the lord saved israel that day out of the hand of the egyptians and israel saw the egyptians dead upon the sea shore.
እግዚአብሔር በዚያን ቀን እስራኤልን እንደዚህ ከግብፃውያን እጅ አዳነ፤ እስራኤልም የግብፃውያንን ሬሳ በባሕር ዳር አዩ።
and israel saw that great work which the lord did upon the egyptians and the people feared the lord, and believed the lord, and his servant moses.
እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፥ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፥ በእግዚአብሔርም በባሪያውም በሙሴ አመኑ።
and i will harden pharaohs heart, that he shall follow after them and i will be honoured upon pharaoh, and upon all his host that the egyptians may know that i am the lord. and they did so.
እኔም የፈርዖንን ልብ አፀናለሁ፥ እርሱም ያባርራቸዋል፤ በፈርዖንና በሰራዊቱም ሁሉ ላይ ክብር አገኛለሁ፤ ግብፃውያንም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። እነርሱም እንዲሁ አደረጉ።
and it was told the king of egypt that the people fled and the heart of pharaoh and of his servants was turned against the people, and they said, why have we done this, that we have let israel go from serving us?
ሕዝቡም እንደ ኰበለሉ ለግብፅ ንጉሥ ነገሩት፤ የፈርዖንና የባሪያዎቹም ልብ በሕዝቡ ላይ ተለወጠና። እንዳይገዛልን እስራኤልን የለቀቅነው ምን አድርገናል? አሉ።
and he made ready his chariot, and took his people with him
ሰረገላውንም አሰናዳ፥ ሕዝቡንም ከእርሱ ጋር ወሰደ፤
and he took six hundred chosen chariots, and all the chariots of egypt, and captains over every one of them.
ስድስት መቶ የተመረጡ ሰረገሎችንም፥ የግብፅንም ፈረሶች ሁሉ፥ በእያንዳንዱም ሰረገላ ሁሉ ላይ ሦስተኞችን ወሰደ።
and the lord hardened the heart of pharaoh king of egypt, and he pursued after the children of israel and the children of israel went out with an high hand.
እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ልብ አፀና፥ እርሱም የእስራኤልን ልጆች አሳደደ፤ የእስራኤልም ልጆች ከፍ ባለች እጅ ወጡ።
but the egyptians pursued after them, all the horses and chariots of pharaoh, and his horsemen, and his army, and overtook them encamping by the sea, beside pihahiroth, before baalzephon.
ግብፃውያንም የፈርዖን ፈረሶች ሰረገሎቹም ፈረሰኞቹም ሰራዊቱም ሁሉ፥ አሳደዱአቸው፤ በባሕሩ ዳር በበኣልዛፎን ፊት ለፊት ባለው በፊሀሒሮት አጠገብ ሰፍረው አገኙአቸው።
then sang moses and the children of israel this song unto the lord, and spake, saying, i will sing unto the lord, for he hath triumphed gloriously the horse and his rider hath he thrown into the sea.
በዚያም ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ። በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።
thou didst blow with thy wind, the sea covered them they sank as lead in the mighty waters.
ነፋስህን አነፈስህ፥ ባሕርም ከደናቸው፤
who is like unto thee, o lord, among the gods? who is like thee, glorious in holiness, fearful in praises, doing wonders?
አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
thou stretchedst out thy right hand, the earth swallowed them.
ቀኝህን ዘረጋህ፥ ምድርም ዋጠቻቸው።
thou in thy mercy hast led forth the people which thou hast redeemed thou hast guided them in thy strength unto thy holy habitation.
በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤
the people shall hear, and be afraid sorrow shall take hold on the inhabitants of palestina.
አሕዛብ ሰሙ፥ ተንቀጠቀጡም፤
then the dukes of edom shall be amazed the mighty men of moab, trembling shall take hold upon them all the inhabitants of canaan shall melt away.
የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞአብን ኃያላን መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።
fear and dread shall fall upon them by the greatness of thine arm they shall be as still as a stone till thy people pass over, o lord, till the people pass over, which thou hast purchased.
አቤቱ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሃትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በክንድህ ብርታት እንደ ድንጋይ ዝም አሉ።
thou shalt bring them in, and plant them in the mountain of thine inheritance, in the place, o lord, which thou hast made for thee to dwell in, in the sanctuary, o lord, which thy hands have established.
አቤቱ፥ አንተ ታስገባቸዋለህ፥ በርስትህ ተራራም ትተክላቸዋለህ፥ አቤቱ፥ ለማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፥ አቤቱ፥ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ።
the lord shall reign for ever and ever.
እግዚአብሔር ለዘላለሙ እስከ ፍጻሜ ይነግሣል።
for the horse of pharaoh went in with his chariots and with his horsemen into the sea, and the lord brought again the waters of the sea upon them but the children of israel went on dry land in the midst of the sea.
የፈርዖን ፈረሶች ከሰረገሎቹ ከፈረሰኞቹም ጋር ወደ ባሕር ገቡ፥ እግዚአብሔርም የባሕሩን ውኆች መለሰባቸው፤ የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ መካከል በየብስ ሄዱ።
the lord is my strength and song, and he is become my salvation he is my god, and i will prepare him an habitation my fathers god, and i will exalt him.
ጕልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥
and miriam the prophetess, the sister of aaron, took a timbrel in her hand and all the women went out after her with timbrels and with dances.
የአሮን እኅት ነቢይቱ ማሪያምም ከበሮ በእጅዋ ወሰደች፤ ሴቶችም ሁሉ በከበሮና በዘፈን በኋላዋ ወጡ።
and miriam answered them, sing ye to the lord, for he hath triumphed gloriously the horse and his rider hath he thrown into the sea.
ማርያምም እየዘመረች መለሰችላቸው። በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።
so moses brought israel from the red sea, and they went out into the wilderness of shur and they went three days in the wilderness, and found no water.
ሙሴም እስራኤልን ከኤርትራ ባሕር አስጓዘ፥ ወደ ሱርም ምድረ በዳ ወጡ፤ በምድረ በዳም ሦስት ቀን ሄዱ፥ ውኃም አላገኙም።
and when they came to marah, they could not drink of the waters of marah, for they were bitter therefore the name of it was called marah.
ወደ ማራም በመጡ ጊዜ የማራ ውኃ መራራ ነበረና ሊጠጡ አልቻሉም፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም ማራ ተብሎ ተጠራ።
and the people murmured against moses, saying, what shall we drink?
ሕዝቡም። ምን እንጠጣለን? ብለው በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ።
and he cried unto the lord and the lord shewed him a tree, which when he had cast into the waters, the waters were made sweet there he made for them a statute and an ordinance, and there he proved them,
ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔርም እንጨትን አሳየው፥ በውኃውም ላይ ጣለው፥ ውኃውም ጣፈጠ። በዚያም ሥርዓትንና ፍርድን አደረገላቸው፥ በዚያም ፈተናቸው፤
and said, if thou wilt diligently hearken to the voice of the lord thy god, and wilt do that which is right in his sight, and wilt give ear to his commandments, and keep all his statutes, i will put none of these diseases upon thee, which i have brought upon the egyptians for i am the lord that healeth thee.
እርሱም። አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም የሚበጀውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ።
and they came to elim, where were twelve wells of water, and threescore and ten palm trees and they encamped there by the waters.
እነርሱም ወደ ኤሊም መጡ፥ በዚያም አሥራ ሁለት የውኃ ምንጮችና ሰባ የዘንባባ ዛፎች ነበሩባት፤ በዚያም በውኃው አጠገብ ሰፈሩ።
the lord is a man of war the lord is his name.
እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው፥
End of preview. Expand in Data Studio
README.md exists but content is empty.
Downloads last month
30