id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-52726228
https://www.bbc.com/amharic/news-52726228
በፓኪስታን የተገደሉ ታዳጊ ሴቶችን እየሳመ የተቀረፀው ግለሰብ ተያዘ
በፓኪስታን ሁለት የተገደሉ ታዳጊ ሴቶችን እየሳመ ቪዲዮ የተቀረፀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል።
በፓኪስታን በክብር ግድያ' የተገደሉ ሴቶችን ለመቃወም የተጠራ ሰልፍ በፓኪስታንም ሆነ በመካከለኛው ምሥራቅ ባሉ አገራት "ማኅበረሰቡን አዋርደዋል፤ የቤተሰባቸውን ክብር ዝቅ አድርገዋል" ተብለው የሚወነጀሉ ታዳጊ ሴቶች "የክብር ግድያ" (ኦነር ኪሊንግ) ተብሎ በሚጠራው ሁኔታ በቤተሰብ አባላቸው ይገደላሉ። እነዚህም ታዳጊዎች በቤተሰብ አባላት በጥይት ተተኩሶባቸው ነው የተገደሉት። ፖሊስ ባወጣው መግለጫ የ28 ዓመቱ ኡማር አያዝ ቪዲዮውን በማዘጋጀት ወንጀል በቁጥጥር ስር አውሎታል። ቪዲዮውንም ሲቀርፅ የነበረውና ቪዲዮውንም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያጋራውም ሌላኛው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል። ከዚህም በተጨማሪ የአንደኛዋ ታዳጊ አባትና ሦስት ዘመዶች ግድያውን ሪፖርት ባለማድረግና መረጃን በመደበቅ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ግድያውን የፈፀመው መሐመድ አስላም እየተፈለገ እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል። የ16 እና የ18 ዓመት ታዳጊዎቹ የአጎት ልጆች ሲሆኑ ግድያው የተፈፀመባቸውም ባለፈው ሳምንት የድንበር ከተማ በሆነችው ሻም ፕሌይን ጋርዮም ግዛት ነው። የአካባቢው ፖሊስ ኃላፊ ሻፉላህ ጋንዳፑር ለሮይተርስ የዜና ተቋም እንዳሳወቁት ስለ ግድያው ሪፖርት የሰሙት ከማኅበራዊ ሚዲያዎች መሆኑን ነው። ባለስልጣናቱ ግድያው በተፈፀመበት አካባቢ ተገኝተው ባደረጉት ምርመራ "ደምና፤ በደም የተለወሱ አልባሳት" አግኝተዋል። ግድያው የተፈፀመው ታዳጊዎቹ ከአንድ ወንድ ጋር ሆነው የሚያሳይ ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መውጣቱን ተከትሎ ነው ተብሏል። ቪዲዮውን ቢቢሲ እንደተመለከተው ሦስት ታዳጊ ሴቶች ከአንድ ወንድ ጋር ሰው በሌለበት ቦታ ላይ ቪዲዮ ሲቀረፁ የሚያሳይ ነው። ቪዲዮው የተቀረፀው ባለፈው ዓመት ሲሆን በቅርብ ሳምንታት ነው ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ወጥቶ ነው ብዙዎች የተጋሩት። ሦስተኛዋ ታዳጊ ያልሞተች ሲሆን፤ የገዳዪም ሚስት ናት ተብሏል። በአሁኑም ሰዓት ተደብቃ እንደምትገኝም ተገልጿል። ፖሊስ በበኩሉ ህይወቷ ስጋት ላይ በመሆኑ እየፈለጓት መሆኑንም አሳውቀዋል። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች በፓኪስታን በታዳጊና በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች "የክብር ግድያ" በሚባለው ድርጊት በፓኪስታን በየዓመቱ አንድ ሺህ ሴቶች እንደሚገደሉ ይናገራሉ። ብዙዎቹ ግድያዎች ሪፖርት የማይደረጉ ሲሆን፤ ከአራት ዓመታት በፊትም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ዝነኛ የሆነችው ኩዋንዲል ባሎሽ መገደል ከፍተኛ ውግዘትን አስከትሏል። ይህንም ተከትሎ ፓኪስታንን የሚገዛው ወግ አጥባቂው ፓርቲ ህጉን እንዲያጠብቅ አስገድዶታል። የ'ክብር ግድያ' ምንድን ነው? የክብር ግድያ በቤተሰብ ላይ ውርደትን አስከትለዋል የሚባሉ ሴቶች ላይ በቤተሰብ አባል የሚፈፀም ግድያ ነው። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም ሂዩማን ራይትስ ዋች ለግድያው ተብለው ከሚሰጡ ምክንያቶች መካከል ከሰበሰቧቸው መረጃዎች፦ ከዚህም በተጨማሪ አለባበሳቸው 'ያልተገባ' ከሆነ፣ 'የማይሆን' ጠባይ ካሳዩ እንዲሁም 'ታዛዥ' ካልሆኑ ግድያው ይፈፀምባቸዋል ተብሏል።
news-46150597
https://www.bbc.com/amharic/news-46150597
የውልደት መጠን እጅጉኑ እየቀነሰ መሆኑ ታውቋል
ተመራማሪዎች እነሆ 'ጉደኛ ወሬ' ብለዋል፤ በዓለማችን የውልደት መጠን እጅግ በጣም እየመነመነ ነው። የት? ለምን? ትንታኔውን ለእኛ ተውት ይላሉ።
ግማሽ ያህል የዓለም ሃገራት አሁንም ከፍተኛ የሆነ የውልደት መጠን አላቸው ተመራማሪዎቹ ጥናት ካደረጉባቸው ሃገራት ገሚሱ የውልደት መጠናቸው ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀንሷል፤ ይህ ደግሞ የህዝብ ቁጥር ቀውስ ማምጣቱ አይቀሬ ነው። አጥኚዎቹ ውጤቱን 'አስደናቂ' ብለውታል፤ ማንም አልጠበቀውምና። ሌላው ውጤቱን አስደንጋጭ ያደረገው ነገር በእነዚህ ሃገራት መጭው ጊዜ በርካታ ወጣቶች ሳይሆን በቁጥር የበዙ አያቶች የምናይበት መሆኑ ነው። የሮቦት ነገር. . . ወዴት ወዴት? «የወሊድ መቆጣጠሪያን ወዲያ በሉት»፦ ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ላንሴት የተባለ መጽሔት ላይ የወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው በፈረንጆቹ 1950 የውልደት መጠን በአማካይ 4.7 የነበረ ሲሆን አሁን ግን ወደ 2.5 ወርዷል። ወደ አፍሪቃ ስንመጣ ግን ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ እናገኘዋለን። በምዕራብ አፍሪቃዋ ሃገር ኒጀር የውልደት መጠኑ 7.1 ነው፤ ወደ ቆጵሮስ ብናቀና ሴቶች በሕይወት ዘመናቸው በአማካይ የሚወልዱት አንድ ልጅ ነው። ግን ግን. . .'ትክክለኛው' የውልደት መጠን ስንት ነው? አውነት እኮ ነው፤ ትክክለኛው የውልደት መጠን ስንት ነው? እርግጥ ስህተት የሆነ የውልደት መጠን አለ እያልን አይደለም፤ እንደው ተመካሪው ለማለት እንጂ። በዚህ ጉዳይ ከእኛ በላይ ማን ሊቅ? የሚሉ ባለሙያዎች የውልደት መጠን ከ2.1 በታች የሆነ ጊዜ 'ችግር አለ' ይላሉ። ጥናቱ የጀመረው በፈረንጆቹ 1950 ገደማ ነው፤ አዎ! የዛሬ 70 ዓመት አካባቢ። ለዚህ ነው 'ኧረ ጎበዝ ጉደኛ ወሬ ይዘናል' ብለው ብቅ ያሉት። በፈረንጆቹ 1950 የውልደት መጠን በአማካይ 4.7 የነበረ ሲሆን አሁን ግን ወደ 2.5 ወርዷል ከአጥኚዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ክርስቶፈር መሪ «አሁን የደረስንበት ደረጃ አንዳንድ ሃገራት ትውልድ መተካት የማይችለቡት ደረጃ ላይ መድሳቸውን ያመለክታል» ይላሉ። «አስደናቂ እኮ ነው። ውጤቱ እኛ አጥኝዎችንም ጉድ በል. . .ያሰኘ ነው። በተለይ ደግሞ ከዓለም ህዝብ ግማሽ ያህሉ የትውልድ ቁጥር ማሽቆልቆል ሰለባ መሆኑ ዱብ ዕዳ ነው የሆነብን።» ለመሆኑ ሃገራቱ እነማን ናቸው. . .? ምጣኔ ሃብታቸው ጎልበቷል የተባለላቸው አውሮጳ ውስጥ ያሉ ሃገራት፤ አሜሪካ፤ ደቡብ ኮሪያና አውስትራሊያ የውልደት መጠናቸውን እያነሰ የመጡ ሃገራት ናቸው። ልብ ይበሉ፤ የእነዚህ ሃገራት የህዝብ ቁጥር ቀንሷል ማለት ግን አይደለም፤ መሰል ለውጦችን ማየት ቢያንስ የትውልድ ልውውጥን ያህል ጊዜ ይወስዳልና። «በቅርቡ የህዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል እንደ አንድ ትልቅ ችግር ሲነሳ መስማታችን አይቀርም» ሲሉ ፕሮፌሰር መሪ ይተነብያሉ። የማይካደው እውነታ ግማሽ ያህል የዓለም ሃገራት አሁንም ከፍተኛ የሆነ የውልደት መጠን አላቸው። ነገር ግን ዋናው ጉዳይ ወዲህ ነው፤ እኚህ ሃገራት በምጣኔ ሃብት እየጎለበቱ መምጣታቸው ስለማይቀር የውልደት ምጣኔያቸውን እየቀነሱ ይመጣሉ። ለምን. . .? አሁን ወደገለው እንግባ። ለምንድን ነው የውልደት መጠን እንዲህ 'በአስደንጋጭ' ሁኔታ የቀነሰው? አጥኚዎቹ ሦስት ወሳኝ ነጥቦችን ያስቀምጣሉ። ከላይ የተጠቀሱትን ምክንያቶች ለተመለከተ 'እና የውልደት መጠን መቀነሱ መልካም ዜና አይደል እንዴ?' ሊል ይችላል፤ ስህተትም የለውም። ሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነፃነታቸው ካልተከበረ የዕድሜ መግፋትና የህዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል የመጪው ጊዜ ራስምታቶች መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ዶ/ር ጆርጅ ለሰን ሰዎች ከለውጡ ጋር ራሳቸውን ማራመድ ከቻሉ ችግር አይሆንም ይላሉ። ምሁሩ ንግግራቸው ጠጠር ያለ ይመስላል፤ የምሁር ነገር። ቀለል ባለ አማርኛ የሰዎች የመንቀሳቀስ ነፃነት ከተጠበቀና ከጊዜው ጋር መራመድ ከቻልን ማለታቸው ነው። «ስነ-ህዝብ ሁሉንም የሚነካ ነው። እስቲ ወደ መስኮታችን ጠጋ ብለን ውጭውን እንመልከት። ሁሉም ነገር በፍጥነት ነው የሚንቀሳቀሰው፤ ግንባታው፣ መኪኖች፣ ትራፊኩ. . . ይህ ሁሉ ለውጥ የህዝብ ቁጥር መጨመር ያመጣው ነው። ከዚያም ባለፈ የዕድሜው ጉዳይም ትልቅ ተፅዕኖ አለው።» ምሁሩ ሁሉም ነገር ይቀየራል፤ መቀየሩም ግድ ነው ይላሉ። የስራ ቦታዎች መቀየር አለባቸው፤ የጡረታ ጊዜውንም አስቡበት (ይጨመር ማለታቸው ነው) ይላሉ ዶ/ር ለሰን። «ጃፖኖችን ተመልከቱ፤ ዕድሜው የሄደ ትውልድ ስጋት ይዟቸዋል። ወደምዕራብ ስትመጡ ግን ወደሃገራቱ የሌላ ሃገር ዜጎች ስለሚገቡ ይህ ስጋት ብዙ አይታይም።» ምንም እንኳ መሰል ለውጦችን መቀበል ቀላል ባይሆንም ጥቅሙ የላቀ ስለሚሆን መቀበል አዋጭ ነው፤ የምሁሩ ሃሳብ ነው። ቻይናም በ1950 ከነበራት ግማሽ ቢሊየን ህዝብ ወደ 1.5 ቢሊየን ደርሳለች፤ በአንድ ልጅ ፖሊሲ በመታገዝ። የአንድ ልጅ ፖሊሲ ጉዳይ አዋጭ መስሎ ያልታያት ቻይናም 'ፖሊሲው በቃኝ' ብላለች፤ መቼም አርጀት ካለው ጎረምሳው ይሻለኛል በማለት። ወጣም ወረደ የዓለም ህዝብ ተጋግዞ ለችግሩ መላ ካላበጀለት መፃኢያችን በችግር የተተበተበ ነው። ቁምነገሩን በልባችን ያፅናልን!!!
news-45715810
https://www.bbc.com/amharic/news-45715810
ዛምቢያ ህገወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ ቻይናውያንን በቁጥጥር ስር አዋለች
ዛምቢያ ህገ ወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ አግኝቻቸዋለሁ ያለቻቸውን ሁለት ቻይናውያንን አሰረች።
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ሲውሉ የጦር ማሳሪያዎችን ይዘው ነበር የአገሪቱ ፖሊስ እንዳስታወቀው ሁለቱ የቻይና ዜጎች ለእስር የተዳረጉት ለአካባቢው የፀጥታ ሃይል አባላት ህገወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ በመያዛቸው እንደሆነ አስታውቋል። • ከኢትዮ- ቻይና ወዳጅነት ጀርባ • «የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአገሪቱ ጎብኝዎች በብዛት በሚገኙበት ሊቪንግስተን ከተማ እንደሆነ ተነግሯል። ይህንን ተግባር በማቀነባበር ወንጀል ተጠርጥረው የዛምቢያ ዜጎችን ጨምሮ እስካሁን 11 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ፖሊስ አስታወቋል። የአገሪቱ ደቡባዊ ግዛት ፖሊስ ኮሚሽነር ቦኒ ካፔሶ እንዳስታወቁት የዛምቢያ ሊቪንግስተን ከተማ የደህንነት ኃላፊ በድርጊቱ እጃቸው አለበት ተብሎ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ጠመንጃ፣ የእጅ ሽጉጦችንና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን መያዙንም ፖሊስ ጨምሮ ተናግሯል። የደህንነት ተቋሙና ተጠርጣሪዎቹ የቀረበባቸው ክስ ላይ ያሉት ነገር እንደሌለም ተገልጿል።
news-48500959
https://www.bbc.com/amharic/news-48500959
''ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም''
ትናንት ከ120 በላይ የኦርቶዶክስ ማህበራት ስብስብ የሆነው ሰልስቱ ምእት የማህበራት ህብረት በቅርቡ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን በኢትዮጵያ ሊያደርጉ ያሰቡትን ጉብኝት በማስመልከት የተቃውሞ ድምጹን ለማሰማት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በሌላ በኩል የጉብኝቱ አዘጋጅ በኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም እያሉ ነው። የማህበራት ህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ደረጀ ነጋሽ ለቢቢሲ እንደገለፁት ''ቶቶ የሚባል አስጎብኚ ድርጅት በቅዱስ ላሊበላ እና ሌሎች መዳረሻዎች ላይ መጥተው ታሪካዊ አሻራችንን እናሳርፋለን የሚሉትን በመቃወም፤ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣ የሃይማኖት አባቶች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ እና ህዝቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግ ነው መግለጫውን መስጠት ያስፈለገን'' ብለዋል። • በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ታጣቂዎች አምስት ሰዎች ገደሉ • የቱሉ ፈራ ደጋግ ኢትዮጵያዊ ልቦች • የስዊዝ ፍርድ ቤት ለካስተር ሰሜንያ ፍርድ ሰጠ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን የጉብኝት ፕሮግራም በማዘጋጀት የሚታወቀው ቶቶ ቱርስ በኢትዮጵያ ከአራት ወራት በኋላ ለ14 ቀናት የሚዘልቅ የጉብኝት መርኃ ግብር አውጥቶ ጎብኚዎችን እየመዘገበ ይገኛል። በአንድ ሰው 7 ሺህ 900 የአሜሪካን ዶላር የሚጠየቅበት ይህ የጉብኝት ፕሮግራም በሁለት ሳምንት ቆይታው አርባ ምንጭ፣ ደቡብ ኦሞ፣ የጣና ገዳማት፣ ጎንደር፣ ላሊበላ፣ አክሱምን እና ሌሎች የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ለማስጎብኘት መርሃ ግብር ቀርጿል። ሊቀ ትጉሃን ደረጀ የማህበራት ህብረቱ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎቹ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የለባቸውም የተባለበትን ምክንያት ሲያስረዱ፤ ''በሃገሪቱ ህግ ድርጊቱ ወንጀል ነው። ከቀላል እስከ ከፍተኛ እስራት ያስቀጣል። ስለዚህ የኢትዮጵያን ሕግ ተላልፎ መምጣት አይችሉም። ሁለተኛ ድርጊቱ በሃይማኖት የተወገዘ ነው። በባህልም ጸያፍ ነው።'' ብለዋል። ''አርማቸውን ይዘው ላሊበላ ላይ እንገናኝ በማለት የዋጋ ተመን አውጠተው መንቀሳቀሳቸው የድፍረት ድፍረት ነው'' ሲሉም አክለዋል። ይህ "እኩይ ተግባር" ከሃገራችን መውጣት አለበት የሚሉት ሊቀ ትጉሃን ደረጀ፤ ''ሕጉ ተሻሽሎ መጥበቅ አለበት። የግብረ-ገብ ትምህርት መሰጠት አለበት" ብለዋል፤ አክለውም ይህን ጉብኝት ተቃውመን አናቆምም።'' በማለት 'ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም' የሚባል የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነትን የሚቃወም ከኦርቶዶክስ፣ እስልምና፣ ካቶሊክ እና ፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የተውጣጣ ሃገራዊ ማህበር እንደሚቋቋም ጨምረው ተናግረዋል። የቶቶ አስጎብኚ ድርጅት መስራች እና ባለቤት ዳን ዌር በበኩላቸው ''በተፈጠረው ነገር በጣም አዝኛለሁ። ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ ግን አንሰርዝም'' ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ''የየትኛውም የሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰው የሚያስፈራው ነገር ያለ አይመስለኝም። የማንንም ሃይማኖት ልንጋፋም ሆነ የራሳችንን አስተሳሰብ በሰዎች ላይ ለመጫን አይደለም ወደ ኢትዮጵያ የምንሄደው። እንዳውም ባህሉን ለማየትና ለመረዳት እንዲሁም ለማድነቅ ነው የምንፈልገው።'' ጉብኝቱን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተመለከቱት ምላሽ በጣም እንዳሳዘናቸው የሚናገሩት ዳን፤ "የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲከታተለው ማሳሰብ እፈልጋለሁ" ብለዋል። የአስጎብኚ ድርጅቱ ባለቤት በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ እንደማይሰርዙ አስረግጠው ተናግረዋል። ''ወደ ኢትዮጵያ እንሄዳለን። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ለደህንነታችን እንሰጋለን'' ይላሉ። • "ደላላው ወደ ቤቱ ወሰደኝ፤ በዚያው ቀን አስገድዶ ደፈረኝ" ዳን ጉዳዩን ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደሚያሳውቁ፤ በተጨማሪም ስለ ጉብኝቱ ግዙፍ የዜና ተቋማት እንዲያውቁ እናደርጋለን ይላሉ። ''ወደ ኢትዮጵያ ስንሄድ አደጋ ቢደርስብን ዓለም በሙሉ ይመለከተዋል። በዚህም የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ እና ሃይማኖት መጥፎ ስም እንዳይሰጠው መጠንቀቅ አለባቸው።'' ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። በጉዳዩ ላይ የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት አስተያየት ማካተት አልቻልንም።
42389739
https://www.bbc.com/amharic/42389739
በአትላንታ አየር ማረፊያ መብራት በመቋረጡ በረራዎች ተሰናከሉ
በአትላንታዋ ሀርትስፊልድ ጃክሰን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መብራት በመቋረጡ ምክንያት ጣቢያው ግማሽ በግማሽ እንዲዘጋና በረራዎችም በከፍተኛው መዘግየት እንዲያጋጥማቸው ምክንያት ሆኗል።
ይህ አየር ማረፊያ በዓለም ስራ ከሚበዛባቸው አንዱ ሲሆን በቀንም ውስጥ ከ250 ሺ መንገደኞች በላይ እንዲሁም 2500 በረራዎችን ያስተናግዳል። ተጓዦቹ ለሰዓታትም ያህል ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ በተዋጠው አውሮፕላን ማረፊያና በአውሮፕላን ውስጥ ተቀምጠው ነበር። በአየር ማረፊያው እንዲያርፉ እቅድ ተይዞላቸው የነበሩ በረራዎች ወደ ሌላ አየር መንገድ አቅጣጫቸውን እንዲቀለብሱ ወይም መውጫ አየር ማረፊያው ላይ እንዲያርፉ ተደርገዋል። አየር ማረፊያው ባወጣውም መግለጫው እሁድ ዕለት ከ12 ሰዓት በኋላ ያጋጠመ ነው ብለዋል። ለአየር መንገዱ የመብራት አቅርቦት የሚሰጠው ጆርጂያ ፓወር በበኩላቸው በመሬት ስር እሳት ተነስቶ ሳይሆን እንዳልቀረ ያምናሉ። እሳቱ የተነሳበት ምክንያት እንደማያውቁና እሁድ ሌሊትም መብራት ይመለሳል ብለዋል። በረራዎቹን የሚቆጣጠረው ማማ በትክክለኛ መንገድ እየሰራ ቢሆንም ብዙዎቹ አየር መንገዶች እንደ ዩናይትድ፣ሳውዝዌስትና የአሜሪካው አየር መንገድ በዕለቱ ስራ ሙሉ በሙሉ አቋርጠዋል። በተለያዩ ድረ-ገፆችም የታዩ ፎቶዎች መንገደኞች በጨለማ ውስጥ ሲጠብቁ አሳይተዋል። የዴልታ አየር መንገድ በትዊተር ገፁ እንዳሰፈረው ያረፉ መንገደኞችን ለማስወረድ ቢሞክሩም የነበሩት በሮች ትንሽ በመሆናቸው እክል እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል። የአካባቢው ፖሊስ ሁኔታውን ለማረጋጋት ተጨማሪ ፖሊሶች እንደላኩ ገልፀዋል። አትላንታ 80% የሚሆነው ከአሜሪካ ህዝብ በሁለት ሰዓት በረራ መገኘቷ በሀገሪቷ ተመራጭ አየር መንገድ እንዲሁም ከሌላ ሀገር ለሚመጡትም ዋነኛ አየር መንገድ ሆኖም ያገለግላል።
43876448
https://www.bbc.com/amharic/43876448
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ችግር
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች አብረው በሚኖሩ ህዝቦች መካከል የሚቀሰቀሱ ግጭቶች እንዲሁም የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሞት እና ውድመትን ከማስከተላቸውም ባለፈ በርካቶችን ለመፈናቀል መዳረጋቸው በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ተደጋግሞ የሚስተዋል እውነታ ሆኗል።
የተፈናቃዮቹ ቁጥር እጅጉን ከፍተኛ መሆን ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት አዳጋች ያደረገው ይመስላል። ግጭቶች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች ያሉ ቅራኔዎችን የመፍታቱን ያህል መልሶ የማስፈር እና የማቋቋም ኃላፊነቶች ለአገሪቷ ከባድ የራስ ምታት ሆኗል። ባለፈው ጥቅምት ወር ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሼ ዞን የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ አላገኘንም ይላሉ። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሼ ዞን በአካባቢው ተወላጆች እና ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ስፍራው በማቅናት ኑሯቸውን በመሰረቱ አርሶ አደሮች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ ሞትና የንብረት ውድመትን ማስከተሉ ባለፈው ጥቅምት ወር መዘገቡ የሚታወስ ነው። ግጭቱ ካፈናቀላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች መካከል ከአምስት መቶ የሚልቁ አባወራዎች በባህር ዳር ከተማ ተጠልለው ይገኛሉ። ከተፈናቃዮቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ አበባው ጌትነት በምዕራብ ጎጃም ዞን ውስጥ የምትገኘውን የትውልድ ቀያቸው ቋሪት ወረዳን ለቀው ወደ ካማሼ ዞን ደዴሳ ቀበሌ ያመሩት በ1992 ዓ.ም እንደነበር ይናገራሉ። ብዙ አዝመራ በማይሰበሰብበት ጥቅምት ወር ላይ ግጭቱ በመነሳቱ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ጥለው እንደወጡ ይናገራሉ። "ግጭቱንም አላወቅነውም። ትንሽ የተወሰነ ረብሻ ነበር የመሰለን። አዝመራ የሚሰበሰብበት ወቅት ስላልነበር 527 አባወራ ምንም ነገር ሳይዝ ትልቅ ኪሳራ ደርሶበት ንብረቱን አጥቶ ለመሰደድ ተገዷል። በባህርዳር አባይ ማዶ የምግብ ዋስትና ግቢ መጋዘን ውስጥ ነው የምንገኘው" ብለዋል። ግጭቶችም ሆነ መፈናቀል ሲከሰቱ የጥቅምቱ የመጀመሪያው ባይሆንም ከወትሮው ግን በጉዳት መጠን የላቀ እንደሆነ የሚያስረዱት ደግሞ ሌላኛው ተፈናቃይ አቶ ልመንህ መኩሪያ ናቸው። ኑሯቸውን በደዴሳ ቀበሌ ከመሰረቱበት 1999 ዓ.ም አንስቶ በእርሻ፣ በከብት ማርባት እና በአነስተኛ ንግድ ይተዳደሩ እንደነበር የሚገልፁት አቶ ልመንህ፤ አሁን ራሳቸውንም ሆነ የሚያስተዳድሩትን ቤተሰብ ለመደጎም በባህር ዳር ከተማ የተለያዩ የጉልበት ሥራዎችን ከማፈላለግ የዘለለ አማራጭ እንዳጡ ይገልፃሉ። "የሚያሳዝንና የሚያስለቅስ ነገር ነው ያለንበት ሁኔታ። ከዛሬ ነገ ችግራችሁ ይፈታል በማለት እስካሁን ድረስ ህብረተሰባችን እየተንገላታና እየተሰቃየ ይገኛል። መሬት ላይ ነው የምንተኛው፤ ምንም ነገር የለንም። በቃ የቀን ሥራ እየሰራሁ ነው ያለሁት " ብለዋል። ተፈናቃዮቹ ችግሮቻቸውን ይዘው ዘላቂ መፍትሄ ይበጅላቸው ዘንድ ለክልሉ አስተዳደር ፅህፈት ቤቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን ይናገራሉ። ባለፈው እሁድም ከክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ተቀምጠው መወያየታቸውንም ያስረዳሉ። ነገር ግን ክልሉ ያቀረበላቸው ሁለት አማራጮች ፤ ወደተፈናቀሉበት ካማሼ ዞን መመለስ ወይንም ቀድሞ ትተዋቸው በሄዷቸው የትውልድ ቀየዎቻቸው ዳግመኛ መስፈር፤ ያስደሰቷቸው አይመስልም። "ወደ ቀያችን እኮ ተመልሳችሁ ተቀመጡ ሲባል ቦታ፣ መጠለያና መቋቋሚያ እንስጣችሁ አይደለም የተባልነው። ምንም የተመቻቸ ነገር የለም። ወደቀያችሁ ተመልሳችሁ ራሳችሁን በራሳችሁ ማቋቋም ወይም መመለስ የሚል አማራጭ ነው የተሰጠን። ከዚህ በኋላ የፌደራል መንግሥት የሚለንን ሰምተን እግዚአብሄር እንዳደረገን ከመሆን ውጭ ምንም ተስፋ የለንም" በማለት በተስፋ መቁረጥ ይናገራሉ።
news-55472951
https://www.bbc.com/amharic/news-55472951
2020 በፎቶ ፡ ከኮሮናቫይረስ ጨረቃ ላይ ሰንደቅ አላማ እስከማስቀመጥ
ዓለም በኮሮናቫይረስ የተፈተነበት የፈረንጆቹ 2020 ሊያበቃ ነው። ዓመቱን ወደኋላ መለስ ብለን በፎቶ ስብስብ እንዲህ ቃኝተናል። ከጥር ወር እንጀምር። ጥር
ቻይና ዉሃን ውስጥ የተቀሰቀሰው ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ የግድ ነው። ከወራት በፊት በመላው ዓለም የጭምብል እጥረት ተከስቶ ነበር። የካቲት በከዋክብት ሳይንስ እጅግ አስደናቂ የሆነው ሙሉ ጨረቃ ቱርክ በሚገኘው ሰልሚዬ መስጂድ አቅራቢያ የታየው በዚህ ዓመት ነው። መጋቢት አብዛኛው ሰው ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ ለማግኘት እንደ ዙም ያሉ የተለያዩ መተግበሪያዎችን ለመጠቀም ተገዷል። ይህ ፎቶ ሆንግ ኮንግ ውስጥ የሚገኝ መምህር ለተማሪዎቹ በበይነ መረብ ትምህርት ሲያስተላልፍ የተነሳ ነው። ሚያዝያ ወረርሽኙን ለመከላከል አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ መርህ በዓለም ዙሪያ ተግባራዊ ሆኗል። አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ የካቶሊክ ቄስ ጸበል ለመርጨት ፈጠራ የተሞላበት መንገድን ተጠቅመዋል። ግንቦት ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ መገደሉ በአሜሪካና በሌሎች አገራትም ዘረኝነትን የሚቃወም ንቅናቄ አስነስቷል። ሰኔ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ከመጣሉ በፊት ባርሴሎና ውስጥ በሚገኘው ግሬን ቴትሬ ደል ሊሲዮ ከሁለት ሺህ ለሚበልጡ ችግኞች ሙዚቃ ቀርቧል። ሐምሌ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎችም የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች እንዲሁም በሕንድ፣ በፓኪስታን እና በኢራን ውስጥ የተስፋፋው የአንበጣ መንጋ ስጋት የሆነበት ዓመት ነው። በምስሉ ኬንያ ውስጥ አንዲት ሴት ሰብል በአንበጣ መንጋ ተወሮ ስትመለከት ይታያል። ነሐሴ በሊባኖስ መዲና በቤይሩት የተከሰተው ፍንዳታ ኒውክሌር ነክ ካልሆኑ ፍንዳታዎች ሁሉ ትልቁ ነው። ከ200 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፎቶው የሚያሳየው ፒያኖ ተጫዋቹ ሬይመንድ ኢሳያም ከደረሰበት ጉዳት ባሻገር ቤቱን አጥቷል። መስከረም የብራዚል አማዞን ጫካ እጅግ በሚያስፈራ ሁኔታ የእሳት አደጋ ደርሶበታል። የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ቃጠሎው አሳስቧቸዋል። አንድ ጃጓር መዳፉ ተቃጥሎ ከእሳቱ ተርፏል። ጥቅምት ኮሮናቫይረስ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካሳደረባቸው መካከል ነጋዴዎች በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። በጣሊያን መዲና ሮም የሚገኘው ሬስቶራንት የንግዱ መቀዛቀዝ ተምሳሌት እንዲሆን አጽም አስቀምጧል። ኅዳር በታይላንድ ተቃውሞ ከሚሳተፉ አንዱ ሚትሬ ቺቲንዳ ነው። ጸጉሩን የተቆረጠው ተቃውሞውን እንደሚደግፍ በሚጠቁም የሦስት ጣት ምልክት ነው። ይህ ምልክት 'ሀንገር ጌምስ' ከተባለው ፊልም የተወሰደ ነው። ታኅሣስ ቻይና ጨረቃ ላይ ሰንደቅ አላማዋን በመትከል ከዓለም ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። በተጨማሪም ቼንጅ-5 የተባለው የሕዋ ጉዞ ከ44 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጨረቃ አለት አምጥቷል።
42914338
https://www.bbc.com/amharic/42914338
በካሌ ስደተኞች ጣቢያ በተነሳ ግጭት ኤርትራውያን ስደተኞች ጉዳት ደረሰባቸው
በፈረንሳይ የወደብ ከተማ ካሌ በአፍጋናውያንና ኤርትራውያን በተነሳ ግጭት አምስት ስደተኞች ቆሰሉ።
እድሜያቸው ከ16-18 የሚሆኑ አራት ኤርትራውያንም አቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስደው ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው ሲሆን በአስጊ ሁኔታም ላይ እንደሚገኙ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። አምስተኛው ሰው ጉዳቱ የከፋ በመሆኑ ወደ ሌላ ከተማም ተወስዷል። በግጭቱ 13 ሰዎች በብረት ዱላ በመደብደባቸውም እንደቆሰሉ የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል። የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀራርድ ኮሎምብ አካባቢወንም ከጎበኙ በኋላ ከሌላው በተለየ መልኩ አደገኛ ሁኔታ ነው ያለው በማለት ገልፀዋል። አንደኛው በጣም የተጎዳው ሰው አንገቱ ጀርባ በጥይት እንደተመታም ተገልጿል። "ለካሌ ነዋሪዎችም ሆነ ለስደተኞቹ መቋቋም የማይችሉዋቸው ግጭቶች እየበረቱ ነው" በማለት ሚኒስትሩ ገልፀዋል። የመጀመሪያው ግጭት ለሁለት ሰዓታት ያህል የቆየ ሲሆን ስደተኞቹም ለምግብ ተሰልፈው በነበረበት ወቅት ነው ግጭቱም የተነሳው። በዚህ ግጭት ቁጥራቸው 100 የሚሆኑ ኤርትራውያንና 30 የአፍጋን ዜጎችም ተሳታፊ ነበሩ። ግጭቱም የተነሳው አንድ የአፍጋን ዜጋ ሽጉጥ በመተኮሱ መሆኑን የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ያሳያል። "በኤርትራውያን የተከበቡትን የአፍጋኒስታን ዜጎችን ለማዳን ፖሊስ አካባቢውን ከቦት እንደነበርም" የአካባቢው አይን እማኝ ገልጿል። የፈረንሳይ የፀጥታ ኃይልም ወደ አካባቢው ተልከዋል። የካሌይ የስደተኞች መቆያ ወይም በቅፅል ስሙ ጫካው ተብሎ የሚታወቀው ይህ ቦታ ከሁለት አመት በፊት የፈረሰ ቢሆንም አሁንም ቢሆን ወደ እንግሊዝ ማቋረጥ በሚያስቡ ከመቶዎች በላይ ስደተኞች መኖሪያ ነው። የቀሩት ብዙዎቹም ወንዶች ናቸው። በአካባቢው ያሉ የእርዳታ ድርጅቶች የካሌ ስደተኞችን 800 ሲያደርሱዋቸው ባለስልጣናቱ ከ550-600 እንደሚደርሱ ገልፀዋል።
news-54094324
https://www.bbc.com/amharic/news-54094324
"ሀረማያ ሀይቅ ቢመለስም መልሶ ከመድረቅ ነጻ አይደለም" -ባለሙያዎች
እስክንድር የሱፍ ዑመር ተወልዶ ያደገው በሀረማያ ሀይቅ አካባቢ ነው። ሀይቁን በቀደመ ሞገሱና ዝናው ያውቀዋል። በሃይቁ ላይ ጀልባ ቀዝፎ፣ አሳ አጥምዶ ያውቃል።
በዚህ የክረምት የዝናብ ወቅት የሀረማያ ሀይቅ ከነበረው የስፋት መጠን 61 በመቶ ተመልሶ በውሃ ተሸፍኗል "እውነት ለመናገር የሀረማያ ሀይቅ በመድረቁ እናት እና አባት እንደሞተብን ይሰማን ነበር" የሚለው እስክንድር ሰሞኑን የሀይቁን ዳግምም መሙላት ተከትሎ በልጅነቱ በሀይቁ ላ ይዝናና እንደነበረው ለመዝናናት፣ ጀልባ እያሰራ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል። በዚህ የክረምት የዝናብ ወቅት የሀረማያ ሀይቅ ከነበረው የስፋት መጠን 61 በመቶ ተመልሶ በውሃ መሸፈኑን ባለሙያዎች ለቢቢሲ ገልፀዋል። ይህ ደግሞ የእስክንድርንም ሆነ ሌሎች የአካባቢ ነዋሪዎች በደስታ አስፈንጥዟል። የሀረማያን ሀይቅ በቅርበት የሚከታተሉ ባለሙያዎች ግን ሀይቁ ቢመለስም ተመልሶ ከመድረቅ ስጋት ነጻ እንዳልሆነ ይናገራሉ። የዘንድሮው ክረምት፣ የዝናብ ስርጭት እንደ አገር ከፍተኛ መሆኑን የሚናገሩት በሀረማያ ዩኒቨርስቲ ሀይድሮሊክና የውሃ ሃብት መሀንዲስ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ኢንጂነር ተሾመ ስዩም፣ በአካባቢው ዘንድሮ ከፍተኛ ዝናብ በመዝነቡ፣ ሀይቁ ውሃ ለመያዝ ችሏል ሲሉ ገልጠዋል። ይኹን እንጂ ከደረቀበት ከሃያ ዓመት በፊት ጀምሮ በዚህ መልክ ውሃን ሲይዝ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ገልፀዋል። የሀረማያ ሃይቅ ከሁለት ዓመት በፊት በዚህ መልኩ ውሃ ይዞ እንደነበርም ያስታውሳሉ። ነገር ግን ውሃ ይዞ መቆየት አልቻልም ያሉት ዶ/ር ተሾመ፣ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የአካባቢው አርሶ አደሮች ለመስኖ ከሀይቁ ብዙ ውሃ ስለሚጠቀሙ መሆኑን አብራርተዋል። "በሀረር አካባቢ ብዙ የተቆፈሩ ጥልቅ የመጠጥ ውሃ ጉድጓዶች አሉ፤ ስለዚህ ወደ ሀይቁ የገባው ውሃ እና ህዝቡ የሚገለገልበት መጠን ከፍተኛ ልዩነት ስላለው ውሃው ተመልሶ ይደርቃል" ሲሉ ዶ/ር ተሾመ ስዩም የተፈጠረውን ያስረዳሉ። ለሀረማያ ሀይቅ መድረቅ አንዱ ምክንያት የውሃ የአስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓት አለመኖር እንደሆነ ምሁሩ አክለዋል። በሀረማያ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች የውሃ አጠቃቀም ላይ ችግር እንዳለ የሚናገሩት ረዳት ፕሮፌሰሩ፣ ወደ ሀይቁ የሚገባው ውሃ እና ሕዝቡ የሚገለገልበት እንደማይመጣጠን ገልፀዋል። "የሚገባው ውሃ ትንሽ ነው፤ ኀብረተሰቡ ለመስኖ እና ለመጠጥ ውሃ የሚጠቀምበት ብዙ ስለሆነ ውሃ ሊጠራቀም አልቻለም።"ይላሉ በአሁኑ ጊዜ ሀረማያ ሀይቅ ይዞ የሚገኘው ውሃ ትልቅ መሆኑን የሚናገሩት ባለሙያው፣ ውሃው ሀይቁ ውስጥ እንዲቆይ የሚፈለግ ከሆነ "በውሃ አጠቃቀም ላይ ሕግ መኖር አለበት" ሲሉ ይመክራሉ። " በዓመት ምን ያህል ውሃ ወደ ሀይቁ ገባ? ኀብረተሰቡ ደግሞ ምን ያህሉን ይጠቀማል? የሚለውን ለመረዳት ሚዛናዊ የውሃ አጠቃቀምን መኖሩን መፈተሽ ያስፈልጋል።" ይኹን አንጂ የአካባቢው አርሶ አደሮች ሀይቁ የያዘውን ውሃ በሙሉ ለመስኖ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የሀይቁ መቆየት ጥያቄ ውስጥ እንደሚወድቅ ረዳት ፕሮፌሰሩ ይናገራሉ። ይህንን ለመከታተል ደግሞ ኃላፊነት ወስዶ የሚሰራ መኖር እንዳለበት ጨምረው ገልፀዋል። ከዚህም በፊት በውሃ አጠቃቀም ደንብ ላይ ውይይት መደረጉን የሚጠቅሱት ዶ/ር ኢንጂነር ተሾመ፣ በምክክሩ የተሄደበት መንገድ ተገቢ እንዳልነበር ያስታውሳሉ። አንድ ሕግ ሲረቀቅ ከህዝቡ ጋር መወያየት እንደሚያስፈልግ የሚገልፁት ምሁሩ፣ ባለሙያዎችን ብቻ ማወያያት ውጤታማ እንደማያደርግ ይገልፃሉ። በተጨማሪም የውሃ አጠቃቀም ሕግ ከወጣ በኋላም በሰነድነት ብቻ እንዲቀመጥ ሳይሆን፣ ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚያስፈልግም ያብራራሉ። ሀረማያ በውሃ እንደተሞላ አንዲቆይ ምን ይደረግ? የሀረማያ አካባቢ አርሶ አደሮች በሚሰሩት የመስኖ ስራ ብዙ የውሃ ብክነት እንዳለ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለዚህ አርሶ አደሮቹ ውሃ ቆጣቢ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ ኀብረተሰቡን ማስተማር እና ግንዛቤ ማስጨበጥ የመፍትሄው አካል መሆን እንዳለበት ያሳስባሉ። "ይህ ሀይቅ ባለቤት የሌለው ከሆነ ተመልሶ ይደርቃል፤ ይህ መታወቅ አለበት" ይላሉ ዶ/ር ኢንጂነር ተሾመ። ከዚህም ሌላ የሀረማያ ሀይቅ ድንበር የሌለው እንደመሆኑ መጠን ሀይቁ እንዲቆይ በማካለል ህብረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀምበት ማድረግ ያሻል። በሌላ በኩል ደግሞ የሀረማያ ሀይቅ በሕይወት እንዲቆይ ለማድረግ የተፋሰስ ልማትን ማካሄድ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ፣ እየታጠበ ወደ ሀይቁ የሚገባውን አፈርን ለመቆጣጠርና ውሃ በስርዓቱ ወደ ሀይቁ እንዲፈስ ለማድረግ አስራ አምስት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የተፋሰስ ልማት መሰራት እንደሚያስፍልግ ባለሙያዎች ይመክራሉ። ይኹን አንጂ እስከዛሬ የተሰራው የተፋሰስ ልማት በቂ እንዳልሆነ ረዳት ፕሮፌሰሩ ገልፀዋል። ችግኞች መትከልና መንከባከብን አከታትሎ መስራትን እንደሚጠይቅ የሚናገሩት እኚህ ምሁር "ሀይቁ አዋሳኝ አካባቢዎች አፈር ታጥቦ እንዳይገባ ሳር መትከል ላይ መስራት በጣም ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ። የምስራቅ ሐርጌ አካባቢ ጥበቃ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን፣ የአካባቢ ጥበቃና ክትትል ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አብዱላዚዝ አህመድ፣ በበኩላቸው ወደ ሀይቁ የሚጣለው ቆሻሻ ችግር እንደሆነ በማንሳት የአካባቢው ኀብረተሰብ ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ ተማጽነዋል።
news-42162571
https://www.bbc.com/amharic/news-42162571
ስደተኛው የፊልም ባለሙያ
ገመዶ ጀማል ይባላል። ከቤተሰቦቹ ጋር ከሃገር ከተሰደዱ ቆይተዋል። ለዚህ ምክንያቱ አባቱ በፖለቲካ ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ምክንያት ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት በመሸሽ ነው። አባቱን ጨምሮ ከስድስት የቤተሰቦቹ አባላት ጋር በመሆን ኬንያ ገቡ።
"መጪው ትውልድ ከእኛ ምን ይወርሳል? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን።" ከዛም ወደ ኡጋንዳ በመቀጠልም አሁን ያሉበት የኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ገብተዋል። ጅማሮ ወጣቱ ፊልም ሰሪ ገመዶ ጀማል ከልጅነቱ ጀምሮ ለኪነጥበብ በተለይም ለስዕል ትልቅ ፍቅር እንደነበረው ይናገራል። ከዚህም በተጨማሪ "በማህበረሰባችን ውስጥ ያለውን የፊልም ጥበብ ክፍተት ለመሙላት በማሰብ ነው የጀመርኩት"ይላል። የካሜራ ጥበብ፣ የምስል እና ድምፅ አርትኦት መስራት፣ እንዲሁም የአዘጋጅነት ሙያዎችን ኖርዌይ በሚገኝ የስነጥበብ ትምህርት ቤት በመግባት ተምሯል። "ቤተሰቦቼ በጣም ያበረታቱኝ ነበር።" የሚለው ወጣቱ ገመዶ በተለይም አባቱ ፍላጎቱን ከሁሉም በተለየ ይደግፉለት ነበር። " ለህዝቤ በታማኝነት እንድሰራ ይመክረኝ ነበር። 'ላመንክበት ነገር ብቻህን እንኳን ብትቆም ከዳር አድርሰው' ይለኛል።" በማለት የአባቱን ምክር ያስታውሳል። ጥበብ በስደት፣ በራስ ቋንቋ "ከውጭ ሃገር የምታገኛቸው ዕውቀት እና መሳሪያዎች ብዙ ናቸው" የሚለው ይህ ወጣት ትልቁ ፈተናው ግን በኦሮምኛ የሚተውኑ ተዋንያንን ማግኘት ነው። በአንድ ወቅት ቀረፃ ሊጨርሱ ሲሉ አንድ ተዋናይ አቋርጦ ሄደ። "በዚህም የተነሳ ፊልሙን ዳግመኛ እንደ አዲስ ለመቅረፅ ተገደን እንደነበር አልረሳም" ይላል። ይህ መሰናከል ባይሆንበት ኖሮ እስከዛሬ ድረስ ብዙ ፊልሞችን መስራት ይችል እንደነበር ይናገራል። ይህንን እና ይህን የመሰሉ ውጣ ውረዶችን በፅናት በማለፍ እስካሁን ስድስት የኦሮምኛ ፊልሞችን እና በርካታ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ሰርቷል። ከነዚህም ውስጥ አማና እና ጨባሳ በርካታ ተመልካቾች የወደዷቸው ነበሩ። አብዛኞቹ ፊልሞቹ የሚያጠነጥኑት በወቅታዊ የኦሮሞ ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ከዚህም ባሻገር ገመዶ የፊልም አሰራርን በቪዲዮ ድረ-ገፆች ላይ በኦሮምኛ አጫጭር ትምህርቶችን ይሰጣል። የሚሰጣቸው ትምህርቶች የፎቶ አነሳስ ጥበብ፣ የፊልም ቀረፃ እና አርትኦት ላይ ያተኩራሉ። ወደጥበቡ መግባት ለሚፈልጉ የኦሮሞ ወጣቶች እንደመንደርደሪያ እያገለገላቸው ይገኛል ሲል ገመዶ ይናገራል ። '' ላመንክበት ነገር ብቻህን እንኳ ብትቆም ከዳር አድርሰው'' ወደፊትስ? ቢሳካልኝ ወደ ሃገር ቤት ተመልሼ ጥበብን ማሳደግ እፈልጋለሁ የሚለው ገመዶ "ሃገር ቤት ያሉ የጥበብ ሰዎችን በሁሉም በኩል ማገዝ እፈልጋለሁ" ይላል። "ትናንት ዛሬ አይደለም ዛሬ ደግሞ ነገን አይሆንም" የሚለው ገመዶ የኦሮሞ ኪነጥበብ አሁን እያደገ እንደሆነ ይናገራል። በዐዓለም ላይ እንዳሉ እና በተለያዩ ቋንቋዎች ከሚሰሩ ፊልሞች አንፃር ካየነው ግን አድጓል ለማለት አያስደፍርም። ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም በነበሩ ስርዓቶች የኦሮሞን ባህልና ኪነጥበብ ለማሳደግ ተፅእኖ የነበሩ ሁኔታዎች በርካታ ናቸው። ነገር ግን ከዚህ አንፃር ሳየው ያን ያህል ወደ ኋላ ቀርተናል የሚያስብለን አይደለም ይላል። ከዚህም ባሻገር በራሱ በኩል አዲስ የኦሮምኛ ፊልም እያዘጋጀ መሆኑን ነግሮናል። "ይሀ ፊልም ከዚህ በፊት ከሰራኋቸው ፊልሞች አንድ ደረጃ ከፍ ያለ እንዲሆን ስለምፈልግ በጥሩ መንገድ እየሰራሁት ነው" በማለት ገመዶ ይገልፃል። የአዕምሮ ነፃነት "በሰው ሃገር በአዕምሮ ባርያ ትሆናለህ አዕምሮህን ተጠቅመህ ነፃ ትወጣለህ" የሚለው ገመዶ " የሰው ልጅ አለም ላይ ሲኖር ሰላም እና ነፃነት ያስፈልጉታል" ይላል። ገመዶ አሁን በሚገኝበት የሰው ሃገር በነፃነት ይኑር እንጂ ሃገሩን ይናፍቃል። "የራስ ሃገር ሁሌም እናት ነች፤ በሰው ሃገር አገኘሁ የምለው ነገር ስደተኛ በሚል ስም መጠራት ብቻ ነው።" ገመዶ ሃገሬ የምገባው ዛሬ ወይስ ነገ ሲል ይተክዛል። አንድ ቀን ግን እንደሚሳካለት ተስፋ ያደርጋል።
news-41016621
https://www.bbc.com/amharic/news-41016621
ተመራማሪዎች በሞቃታማውና በአሲዳማው የአፋር ክፍል ህይወት ያለው ነገር አገኙ
አ ካ ባቢው በተለያዩ ቀለማት ቢያሸበርቅም የቢጫና የአረንጓዴ ቀለማት ተጽእኖ አለው። አየሩም በመርዛማው ክሎሪን ሰልፈር ጋዝ ተሞልቷል።
በኢትዮጵያ የሚገኘው ዳናክል ዲፕሬሽን ከዓለማችን ሞቃታማ እና ለኑሮ ምቹ ካልሆኑ አካባቢዎች አንደኛው ነው። ሆኖም በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት በአካባቢው ህይወት ያላቸው ነገሮች እንደሚኖሩ አረጋግጧል። ዳናክል ዲፕሬሽን አነስተኛ ጥናት ከተካሄደባቸው የዓለም አካባቢዎች አንዱ ነው። ከኤርትራ ድንበር በቅርብ ርቀት በአፋር ክልል ከባህር ጠለል በታች በ100 ሜትር ላይ በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ ይገኛል። አካባቢው ሶስት አህጉራትን በመክፈል አዲስ ምድር ይፈጥራል ተብሎ በሚገመተው በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ያለ ነው። ያልረጋ የመሬት አቀማማጥ ያለው ይህ አካባቢ እጅግ ደረቅ በመሆንም ይታወቃል። ብዙም ዝናብ የማያውቀው አካባቢው ሙቀቱ በአብዛኛው 45 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል። ሁሌም የሚፍለቀለቁ ሁለት እሳተ ገሞራዎች የሚገኙ ሲሆን አንደኛው ኤርታ-አሌ ነው። ኤርታ-አሌ አሲድ የቀላቀለ በመሆኑም ይታውቃል። የባህሩ ጨዋማ ውሃ እሳተገሞራ ውስጥ ከሚገኘው ማዕድን ጋር ሲዋሃድ የተለያየ ቀለም ይፈጥራል። በአካባቢው ሰልፈርና ጨው ተዋህደው ደማቅ ቢጫ ቀለም ሲፈጥሩ መዳብና ጨው ውሃ ሰማያዊ ቀለም ይፈጥራሉ። የዚህ አካባቢ እጅግ ሞቃታማ አየር አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ዕፅዋትና እንስሳት ብቻ እንዲኖሩ የሚፈቅድ ነው። ዳሎል ለኑሮ አመቺ ባይሆንም በቅርብ ርቀት 'ሃማዴላ' የሚባሉ ጊዜያዊ መኖሪያቸውን ቀልሰው የሚኖሩ ሰዎች አሉ። የሎውስቶን ከሚባለው የአሜሪካው አካባቢ ጋር ቢቀራረብም ዳናክል በጣም ሞቃታማና ውሃው አሲድ የበዛበት ነው። የአካባቢው ውሃ የአሲድ መጠን ከፍተኛ ነው። እአአ ከ2013 ጀምሮ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ጥናት ለዳናክል ትኩረት አሰጥቶታል። ዩሮ ፕላኔት የሚባለው የምርምር ተቋማት ኅብረት ሳይንቲስቶች ከማርስ ጋር ተቀራራቢ ይሆናል የሚሏቸውን የዓለማችን ክፍሎችን እያጠኑ ይገኛሉ። ከ2013 ጀምሮ በአካባቢው ጥናት ከሚያደርጉት ባለሙያዎች መካከል የጣሊያኑ ቦሎኛ ዩንቨርሲቲ ባልደረባ ባርባራ ካቫላዚ ትገኝበታለች። "ሙቀቱ በጣም ከፍተኛ ነው። በምሳ ሰዓት እስከ 48 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል። በአንድ ወቅት 55 ዲግሪ ሴንቲግሬድም ሆኖ ያውቃል" ብላለች። ዳሎል አካባቢ ያለው ውሃ ሙቀት መጠን 100 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው። ሳይንቲስቶቹ ከመርዛማው ሰልፋይድ ጋዝም ራሳቸውን መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ንፋሱ ውስጥ ያለው የክሎሪን ብናኝ ደግሞ ሳንባቸው ላይ ጉዳት ስለሚያደርስ ሁሌም የጋዝ ጭንብል ማጥለቅ ይጠበቅባቸዋል። "የጨው ግግሩ በቀላሉ ሊሰበር ስለሚችል ለመራመድ ጥንቃቄ ይፈልጋል" ትላለች ካቫላዚ። "100 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በሚፈላ እና መርዛማ በሆነ ውሃ ውስጥ ከተወደቀ በኋላ ከሚደርሰው ጉዳት በተጨማሪ ህክምና ለማግኘት በቅርብ የሚገኘው ሆስፒታል መቀሌ በመሆኑ እዛ ለመድረስም ሰዓታትን ይፈጃል። በአካባቢው ስንቀሳቀስ ሁሌም የአካባቢውን ሰው ይዤ ነው። እነሱ የት መሄድ እንዳለብኝና የቱን መርገጥ እንዳለብኝ ይነግሩኛል" ትላለች። ጥናቱ በ2013 ሲጀምር እንዴት በአካባቢው መስራት ይቻላል በሚለው ላይ ያተኮረ ነበር። "ማቀዝቀዣም ሆነ ሌላ ናሙናዎችን ለማቆየት የሚረዳ ኬሚካል ማምጣት ስለማይቻል እንዴት መስራት እንዳለብን በደንብ ማቀድ አስፈላጊ ነበር" ብላለች ካቫላዚ። በ2016 ግን ባለሙያዎቹ በአካባቢው ህይወት ሊኖር ይችላል በሚል ተስፋ ናሙናዎችን መሰብሰብ፥ በአካባቢው የሚገኘውንም የውሃ ሙቀት እና መርዛማነት መጠን መለካት ጀመሩ። በድጋሚ ጥር 2017 ናሙናዎችን ወሰዱ። ከሶስት ወር በኋላ የነካቫላዚ ቤተሙከራ ከባክቴሪያ ላይ ዲ ኤን ኤ በመለየት በዳናክል ህይወት ያለው ነገር እንደሚኖር አረጋግጠዋል። የተገኙት ፖሊኤክስትሬሞፊሊክ የሚባሉት ባክቴሪዎች አሲዳማ፣ ሞቃታማና ጨዋማ በሆነ አካባቢ መኖር የሚችሉ ናቸው። ይህም በዳናክል ህይወት እንደሚኖር የመጀመሪያው ማረጋገጫ ሆኗል። እስካሁን ባልታተመው የምርምር ውጤት ሳይቲስቶቹ በሁለት አካባቢዎች ህይወት ያላቸው ሁለት ዓይነት ባክቴሪያዎችን አግኝተዋል። ይህም በቀለማት ባሸበረቀው የዳሎል አካባቢና በአቅራቢያው በሚገኘው አነስተኛ ሃይቅ ነው። ሃይቁ እንደ ጨዋማው አካባቢው ውሃ ባይሞቅም ሙቀቱ እስከ 55 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርሳል። ጨዋማ ቢሆንም አሲድነቱ ግን አነስተኛ ነው። ከሥሩ ባለው እሳተ ገሞራ የተነሳም ውሃው ከፍተኛ ካርቦንዳዮክሳይድ አለው። "ሃይቁ በተለያዩ ስሞች ይጠራል። የአካባቢው ሰዎች 'ጋት-አሌ' ወይም 'አራት' ይሉታል። ሌሎች ደግሞ 'ዘይታማው' ወይም 'ቢጫው' ሃይቅ ሲሉ ይጠሩታል። በአካባቢው አነስተኛ ነፍሳትና ወፎች ሞተው ስለሚገኙ ሌሎች ደግሞ 'ገዳዩ' ሃይቅ ይሉታል። ነፍሳቶቹና ወፎቹ ወደ ውሃው ቀርበው ሊጠጡ ሲሉ በከፍተኛው ካርቦንዳዮክሳይድ ምክንያት የሞቱ ናቸው" ትላለች ካቫላዚ። ካርቦንዳዮክሳይድ ከመደበኛው አየር ስለሚከብድ ወደ መሬት ይገባል። በዚህም አነስተኛ ፍጥረቶች ይህን አየር ሲስቡ ይበከላሉ። ረዘም ለሚሉ ሰዎች ይህ አደገኛ አይደለም። ሆኖም ከሃይቁ እስከ 30 ሴንቲሜትር ብቻ ርቆ ለሚተነፍስ ህይወት ያለው ነገር ብዙ ካርቦንዳዮክሳይድ በመሳብ ለሞት ይዳርጋል። አንዱ የተመራማሪዎቹ ስራ አዲስ ክብረ ወሰን ለመስበር ከጫፍ ደርሷል። ቡድኑ የመርዛማነት መጠኑ ፒ ኤች ዜሮ በሆነ ቦታ ላይ ህይወት አግኝቷል። (ፒ ኤች የመርዛማነት መጠን መለኪያ ሲሆን መጠኑ ወደ ዜሮ በተጠጋ ቁጠር መርዛማነቱ እጅግ ከፍተኛ ይሆናል። ሰባት ሲሆን ግን መርዛማ አይደለም ማለት ነው።) አካባቢው በከፍተኛ መጠን መርዛማ ሆኖ ህይወት የተገኘበት ነው። ከዚህ ቀደም ክብረ ወሰን የያዘው በስፔን ሪዮ ቲንቶ የተገኘውና በፒ ኤች 2 መርዛመነት መጠን የተገኘው ህይወት ነው። "ማርስ ላይ ከዳናክል ጋር ተመሳሳይ የሆነ የሰልፌትና የማዕድኖች ክምችት ሊኖር ይችላል። ተመሳሳይ ጨዋማ ውሃም ሊኖር ይችላል" ስትል ካቫላዚ ትገልጻለች። ስለዚህ በዳናክል ህይወት እንደሚቀጥልና እንዴት መቀጠል እንደተቻለ በማጥናት የትኛው የማርስ ክፍል ለመኖር አመቺ እንደሚሆን ይጠናል።
51657311
https://www.bbc.com/amharic/51657311
ኮሮና ቫይረስ ከየት መጣ?
በቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተቀሰቀሰውና ወደ ተለያዩ የዓለም አገራት በመዛመት ላይ ያለው ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዴት ከእንስሳት ወደ ሰዎች እንደተላለፈ ለማወቅ ተመራማሪዎች ከባድ ጥናት ላይ ናቸው።
በአሁኑ ወቅት ያለው መላምት በቻይና ጫካ ውስጥ ከተገኘ የሌሊት ወፍ እንጥብጣቢ ፈሳሽ በራሪ ነፍሳትን ወደሚመገቡ እንስሳት ተላልፎ፣ በመጨረሻ ወደ ዱር እንስሳት ተዛምቷል የሚል ነው። ከዚያም በቫይረሱ የተያዘ እንስሳ ሰው እጅ ወደቀ፤ ቫይረሱ ከዚህ ሰው የዱር እንስሳት መሸጫ ገበያ ውስጥ ወደሚሰሩ ሰዎች ተላልፎ በመጨረሻ የዛሬው ዓለም አቀፍ የኮሮና ስርጭት ላይ ተደረሰ። በአሁኑ ወቅት ሳይንቲስቶች በዚህ መላምት ላይ እርግጠኛ ለመሆነ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። በለንደኑ መካነ አራዊት ማህበረሰብ ፕሮፌሰር የሆኑት አንድሪው ከኒግሃም እንደሚሉት ኮሮናቫይረስ ከየት መጣ የሚለውን ነገር ወደ ኋላ ተመልሶ ማየት የወንጀል ምርመራ ያህል ውስብስብ ነው ይላሉ። በርካታ የዱር እንስሳት በተለይም የበርካታ ዓይነት ኮሮናቫይረስ ተሸካሚ የሆነችው የሌሊት ወፍ የዚህኛው ኮሮናቫይረስ አስተላላፊ እንደሆነች ይገምታሉ። በየትኛውም አህጉር የሚገኙትና በቡድን ረዥም ርቀት የሚበሩት አጥቢ ነፍሳት ራሳቸው የመታመም እድላቸው እጅግ አነስተኛ ሲሆን ቫይረሶችን በስፋት የማስተላለፍ እድላቸው ግን ሰፊ ነው። የለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጇ ፕሮፌሰር ኬት ጆንስ እንደሚሉት የሌሊት ወፎች ዘረመላቸው ቢጎዳ መልሰው መጠገን ስለሚችሉ ምንም እንኳ የብዙ ዓይነት ቫይረስ ጫና ቢኖርባቸውም ሳይታመሙ ይቋቋሙታል። እናም ይህ የሌሊት ወፎች ባህሪ ለቫይረሶች መራባትና መሰራጨት ምቹ እንደሆነ ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። የሌሊት ወፎች ቫይረሶችን ወደ ሰዎች የማስተላለፍ እድላቸውም ከፍተኛ እንደሆነ የኖትንግሃም ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ጀናታን ባል ይናገራሉ። ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በዉሃኑ የእንስሳት ገበያ ኮሮና ቫይረስን በመርጨት የተጠረጠረው እንስሳ ፓንጎሊን ነው። ጉንዳን በሊታው ፓንጎሊን በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ በህገወጥ መንገድ የሚሸጥ እንስሳ ሲሆን በመጥፋት አደጋ ላይ ያለ እንስሳም ነው። ይህ እንስሳ እስያ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ለመድሃኒትነት ይፈለጋል። በሌላ በኩል የፓንጎሊን ስጋ ለበርካቶች ምርጥ የሚባል ምግብ ነው። ኮሮናቫይረስ በፓንጎሊኖች ላይ የተገኘ ሲሆን አንዳንዶች ቫይረሱ አሁን በሰዎች ላይ ከተገኘው ኮሮና ቫይረስ ጋር ከፍተኛ መመሳሰል አለው ይላሉ። ምናልባትም የሌሊት ወፍ ኮሮናቫይረስና ፓንጎሊኑ ኮሮናቫይረስና የዘር ቅንጣት ተለዋውጠው ይሆን? ሳይንቲስቶች በችኮላ ድምዳሜ ላይ ላለመድረስ ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ ነው። ከፓንጎሊን ጋር በተያያዘ ያለው ሙሉ ሳይንሳዊ መረጃም እስካሁን ይፋ አልተደረገም። ኮሮናቫይረስ ላይ ምርምር እያደረጉ ያሉ ሳይንቲስቶች እንደሚያመለክቱት የፓንጎሊኖች የተለያዩ ዝርያዎችና እንዲሁም የሌሊት ወፎች የሚሸጡባቸው ገበያዎች ቫይረሱ ከአንዱ እንስሳ ወደ ሌላው ለመተላለፍ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ይህ ለቫይረሱ ወደ ሰዎች መተላለፍም እድል ይፈጥራል። • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? ከኮሮናቫይረስ መቀስቀስ በኋላ የተዘጋው የዉሃኑ የእንስሳት ገበያም እንስሶች እዚያው ታርደው ስጋቸው የሚቀርብበት ነበር። በዚህ ገበያ ግመሎች እና ወፎችም ለእርድ ይቀርባሉ። በዚህ ገበያ ፓንጎሊን እና የሌሊት ወፍ ይሸጣሉ ባይባልም የቻይና ደህንነት ተቋም ግን ምን ዓይነት እንስሶች በገበያው እንደሚሸጡ መረጃ አለው። ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ባለፉት ቅርብ ዓመታት የሰው ዘር የተዋወቃቸው ቫይረሶች ከዱር እንስሳት ወደ ሰዎች የተላለፉ ናቸው። በዚህ ረገድ ኢቦላን፣ ኤች አይ ቪን፣ ሳርስን እና የአሁኑን ኮሮናቫይረስ መጥቀስ ይቻላል። የሰው ዘርን እንዲህ ላለፉ ቫይረሶች የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን በሚገባ ማወቅ ከተቻለ በሽታውን መከላከል እንደሚቻል ያስረግጣሉ ተመራማሪዎቹ።
53823769
https://www.bbc.com/amharic/53823769
አምነስቲ ኢንተርናሽናል፡ «በገፃችን ላይ የለቀቅነው ተንቀሳቃሽ ምስል የውስጥ ሂደትን የተከተለ አልነበረም»
ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቅርቡ በማሕበራዊ ሚድያ ገፁ ላይ የለጠፈውን ተንቃሳቃሽ ምስል 'የአምነስቲን የውስጥ ሂደት ያልተከተለ ነው' አለ።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ተክሌ፤ ባለፈው ዓርብ በአምነስቲ ትዊተር ገጽ ላይ የወጣው የአንድ ደቂቃ ቪዲዮ 'የአምነስቲን የውስጥ ሂደት የተከተለ አይደለም' ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ፍሰሃ የተንቀሳቃሽ ምስሉን ይዘት ሲያስረዱ፤ "ከሃጫሉ ግድያ በኋላ የተፈጠረውን ግርግር የሚመለከት ነው። ስለነበረው ግጭት እና ስለታሰሩ ሰዎች ነው" ይላሉ። ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል ከወጣ በኋላ በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ፤ ሪፖርቱ ወይም ዘገባው ሚዛናዊ አይደለም በሚል ሲተቹት ነበር። አቶ ፍሰሃም የተሰጡ አስተያየቶችን መታዘባቸውን እና ምስሉ ከድርጅቱ ማሕበራዊ ገፅ እንዲወርድ መደረጉን ይናገራሉ። "ተንቀሳቃሽ ምስሉ የኛን የውስጥ ሂደት ሳያሟላ ነበር የወጣው። በዚያ ምክንያት ነው ያወረድነው። ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ ጠይቀናል" ብለዋል አቶ ፍሰሃ። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የተገኘው ስህተት ምን እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ፍሰሃ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። "አንድ ለሕዝብ የሚቀርብ ነገር ማለፍ የሚገባው ሂደት አለ። ይሁን እንጂ ቪዲዮ የተወሰኑትን ሳያሟላ በስህተት ተጭኗል" በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። አምነስቲ ከመንግሥት ውጪ በሌሎች ኃይሎች የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የተጠየቁት አቶ ፍሰሃ፤ ከዚህ አንጻር መንግሥት ግጭቶችን የማስቆም እና የመከላከል ግዴታውን በተመለከተ እንመለከታለን ብለዋል። ከዚህ ቀደም በነበረ ሪፖርትም ከመንግሥት ውጪ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ተመልክተናል ያሉ ሲሆን፤ "አሁንም ከሰኔ 23 በኋላ የተፈጠረውን ብሔር እና ኃይማኖት ተኮር የሚመስሉ ጥቃቶችን እየመረመርን ነው። ጥናታችንን አልጨረስንም። ወደፊት የጥናታችንን ግኝት የምናስታውቅ ይሆናል" ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ፍሰሃ አንዳንድ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አምነስቲ ትናንት ይቅርታ የጠየቀበትን ጉዳይ ድርጅቱ ግንቦት ወር ላይ ካወጣው ሪፖርት ጋር ማያያዛቸው ስህተት መሆኑንም ጠቁመዋል። የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አምነስቲ በግንቦት ወር በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በአንዳንድ ቦታዎች ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ያወጣው ሪፖርት ስህተት መሆኑን ገልጾ ይቅርታ ጠየቀ ሲሉ ዘግበዋል። "ዓርብ ዕለት የወጣው ተንቀሳቃሽ ምስል ከሰኔ 23ቱ ግርግር እና እሱን ተከትሎ ስለሞቱ እና ስለታሰሩ ሰዎች ነው የሚመለከተው። ከዚያ ሪፖርት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። በዚያ ሪፖርታችን ውስጥ ያሉት ግኝቶች እና ምክረ ሃሳቦች አሁንም አሉ። የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘገባ ተገቢ አይደለም" ብለዋል አቶ ፍሰሃ ተክሌ።
news-53216690
https://www.bbc.com/amharic/news-53216690
ኢራን ከጀነራሏ ግድያ ጋር በተያያዘ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች
ኢራን በጥር ወር ላይ ኢራቅ ውስጥ ከተገደሉባት ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ ግድያ ጋር በተያያዘ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲታሰሩ ማዘዣ አወጣች።
የኢራን አቃቤ ሕግ አሊ አልቃስሚር እንዳሉት ፕሬዝዳናት ትራምፕን ጨምሮ ሌሎች 35 ሰዎች የግድያና የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ዓም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖልም ተከሳሾቹን ለመያዝ በሚደረገው ጥረት እንዲተባባራቸው ተጠይቋል። ቢሆንም ግን ኢንትርፖል በሰጠው ምላሽ የኢራንን ጥያቄን እንደማይመለከተው አሳውቋል። የአሜሪካ የኢራን ልዩ ተወካይ በበኩላቸው ኢራን ያወጣችው የእስር ማዘዣ ከፕሮፓጋንዳ የዘለለ ማንም የምር የሚወስደው አይደለም ሲሉ አጣጥለውታል። የኢራን የጦር መሪ የነበሩት ሱሌይማኒ በፕሬዝዳንተ ትራምፕ ትዕዛዝ በተፈጸመ ጥቃት ኢራቅ መዲና ባግዳድ ውስጥ በሚገኘው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ ነበር የተገደሉት። ትራምፕ ጀነራሉን በመቶዎች ለሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ሞትና ወደፊት የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በማቀድ እጃቸው አለበት በሚል ከሰዋቸዋል። የጀነራሉን ግድያ ተከትሎ ኢራን የአሜሪካ ወታደሮች ይገኙባቸዋል በተባሉ ኢራቅ ውስጥ የሚገኙ ጦር ሰፈሮችን በሚሳኤሎች መደብደቧ ይታወሳል። በእስር ማዘዣ ትዕዛዙ ላይ ትራምፕን ጨምሮ 36 የአሜሪካና የሌሎች አገራት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች ተካተዋል። ፕሬዝደናት ትራምፕ በዝርዝሩ ቁጥር አንድ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከስልጣን ከወረዱ በኋላም ቢሆን ተይዘው እንዲቀርቡ የማድረጉ ጥረት ይቀጥላል ሲሉ የኢራን አቃቤ ሕግ ተናግረዋል። የኢራን ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ሞሐሲን ባሓርቫንድ እንዳሉት የአገሪቱ ሕግ አውጪ በጀነራሉ ላይ ለተፈጸመው ግድያ የሰው አልባ አውሮፕላኑን ያንቀሳቀሱትን ሰዎች ጨምሮ ተጠያቂ ሰዎችን በመለየት ክስ ይመሰርታል ብለዋል።
news-52526784
https://www.bbc.com/amharic/news-52526784
ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ 100ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሊሞቱ እንደሚችሉ ትራምፕ አስጠነቀቁ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በአገራቸው በቫይረሱ ሳቢያ 100 ሺህ ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ።
ትራምፕ አስተዳደራቸው የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ዝንጉ ሆኖ ነበር የሚለውን ትችት እንደማይቀበሉም ተናግረዋል። እስካሁን በአሜሪካ ከ67 ሺህ ሰዎች በላይ በወረርሽኙ ሳቢያ ህይወታቸውን ተነጥቀዋል። ትራምፕ አክለውም የፈረንጆቹ ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት ለኮቪድ-19 ክትባት ዝግጁ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የዘርፉ ባለሙያዎች ክትባት ለማግኘት ከ12 እስከ 18 ወራት እንደሚያስፈልግ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። "በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ክትባት እንደሚኖረን እርግጠኛ ነን" ሲሉ ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ ተናግረዋል። በትራምፕ ሃሳብ ከማይስማሙት መካከል ጉምቱ የጤና ባለሙያዎች አሜሪካዊው ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ እና የእንግሊዝ የህክምና ኃላፊ ክሪስ ዊቲይ ይገኙበታል። ዶክተር ፋውቺ ክትባት ለማግኘት ቢያንስ 18 ወራት ያስፈልጋሉ ያሉ ሲሆን፤ ክሪስ ዊቲይ በበኩላቸው በሽተኞችን ለማከም የሚረዳ መድኃኒትም ሆነ ክትባት በዚህ ዓመት የማገኘት እድል በጣም ጠባብ ነው ሲሉ ከአንድ ወር በፊት ተናግረው ነበር። ትራምፕ አስተዳዳራቸው "ትክክለኛውን ነገር በመከውን" የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ጥረት ማድረጉን ተናግረዋል። ይልቁንም ለቫይረሱ ስርጭት የቻይናን መንግሥት ተጠያቂ አድርገዋል። "ትልቅ ስህተት የሰሩ ይመስለኛል [ቻይናውያን]፤ ስህተታቸውን አምነው መቀበል አልፈለጉም። ወደዚያ ማቅናት ፈልገን ነበር ግን አልፈቀዱልንም" ብለዋል ትራምፕ። የአሜሪካ መንግሥት መረጃው እያለው ቫይረሱ በአገሪቱ ስለመከሰቱ ለሕዝቡ ይፋ አላደረገም ለሚለው ክስም ምላሽ ሰጥተዋል። ትራምፕ ለዚህ ክስ የአገራቸው የደኅንነት ቢሮን ተጠያቂ አድርገዋል። ፕሬዝድንቱ እንደሚሉት ከሆነ እስከ ጃነዋሪ 23 (ጥር 24) ድረስ የደህንነት ቢሮ ለአስተዳዳራቸው አለማሳወቁን ተናግረዋል። እንደ ሲኤንኤን እና ኤቢሲ ያሉ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የአሜሪካ የደኅንነት ቢሮ ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ ስለመከሰቱ ጀነዋሪ 3 (ታህሳስ 24) ላይ መረጃው ነበረው።
news-47140620
https://www.bbc.com/amharic/news-47140620
ፖፕ ፍራንሲስ የካቶሊክ ቄሶች ሴት መነኮሳትን የወሲብ ባሪያ ማድረጋቸውን አመኑ
ፖፕ ፍራንሲስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃትን እንደሚፈፅሙና ባሪያ አድርገው አስቀምጠዋቸው እንደነበር አመኑ።
በዚህም ምክንያት ከሳቸው በፊት የነበሩት ፖፕ ቤኔዲክት በካህናቱ ተደጋጋሚ ወሲባዊ ጥቃት ይደርስባቸው የነበሩ የሴቶች መነኮሳት ጉባኤን ለመዝጋት ተገደዋል። ፖፑ አክለውም "ችግሩ ከፍቶ የወሲብ ባሪያ የተደረጉ የሴት መነኮሳትን ጉባኤ መበተናቸው ይበል የሚያሰኝ ስራ ነው" ብለዋል። ፖፕ ፍራንሲስ ሴት መነኮሳቱ በካህናቱ ወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ሲያምኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። •የተነጠቀ ልጅነት •ሴት እስረኞችና የማዕከላዊ ምርመራ ቤተክርስቲያኗ ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ብታደርግም አሁንም ድረስ ጥቃቱ እየተፈፀመ እንደሆነ አልካዱም። ፖፕ ፍራንሲስ ይህንን የተናገሩት ታሪካዊ በሚባለው በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸው ላይ ለሚገኙ ጋዜጠኞች ነው። ካህናቱና ኤጲስ ቆጶሳቱ መነኮሳቱ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውንም ቤተክርስቲያኗ እንደምታውቅና ለመቅረፍም ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል። •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ፖፕ ፍራንሲስ በሴቶች መነኮሳት ላይ የሚደርስ የወሲብ ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ የተንሰራፋ መሆኑን አምነው በተለይም በአዳዲሶቹ ጉባኤዎች ላይ ስር የሰደደ ነው ብለዋል። በባለፈው ህዳር ወር ላይ የአለም አቀፉ የካቶሊክ ሴት መነኮሳት ማህበር በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያለው ጥቃት ላይ ያለውን ዝምታና ሚስጢራዊ ባህሉን ማውገዛቸው የሚታወስ ነው። ከቀናት በፊትም የቫቲካን የሴቶች መፅሄት ጥቃቱን አውግዞ በአንዳንድ አካባቢዎችም በካህናቱ ተደፍረው የፀነሱ ሴት መነኮሳት እንዲያስወርዱ እንደሚገደዱም ዘግቧል።
50135332
https://www.bbc.com/amharic/50135332
በሶሪያና ቱርክ ድንበር የተወሰነ የአሜሪካ ጦር እንዲቆይ ተወሰነ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ እንዲወጡ ታዝዘው ከነበሩ ወታደሮች መካከል የተወሰኑት እንዲቆዩ መወሰናቸውን ተናገሩ።
የተወሰኑት የነዳጅ ያለባቸውን አካባቢዎች ሲጠብቁ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ በእስራኤልና ጆርዳን ድንበር አቅራቢያ ይቆያሉ ብለዋል። ከሁለት ሳምንት በፊት የአሜሪካ ጦር ከድንበር አካባቢ እንዲወጣ መወሰናቸውን ተከትሎ ከደጋፊዎቻቸው ሳይቀር ትችት ቀርቦባቸው ነበር። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ መፅሐፍ ምን ይዟል? • አዲስ አበባ ውስጥ ሲካሄዱ የነበሩ ስብሰባዎች በወጣቶች መስተጓጎላቸው ተነገሯል • "ለውጡ ሐዲዱን ስቷል ብዬ ነው የማምነው" አርቲስት ታማኝ በየነ የአሜሪካ ጦር ለመውጣት መወሰኑን ተከትሎ ቱርክ በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ ኩርዶች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፍታለች። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ምንም እንኳ አይ ኤስን በመዋጋት ረገድ ትልቅ አጋር የነበሩትን ኩርዶች ከድተዋቸዋል በሚል ቢተቹም ውሳኔያቸው ትክክል መሆኑን ሲገልፁ ቆይተዋል። "ስለምን ጦራችንን በሁለት ግዙፍ ተቀናቃኞች መካከል፣ በማንኛወም ወቅት ጦርነት ሊገጥሙ በሚችሉ በመቶዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መካከል እንተዋለን? አይመስለኝም" ካሉ በኋላ " የተመረጥኩት ጦራችንን ወደ ሀገሩ ለመመለስ ነው" ብለዋል። ነገር ግን ትራምፕ አክለው እስራኤልና ጆርዳን የተወሰኑ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች "በሌላ የሶሪያ ድንበር አቅራቢያ" እንዲሰፍሩ መጠየቃቸውን ገልጸዋል። በሀገሪቱ ሌላ ክፍል የአሜሪካ ጦር "ነዳጅ የሚገኝበትን አካባቢ አንዲጠብቅ" መፈለጉን ነው የተናገሩት። ቱርክ ሶሪያ ድንበር ላይ የሚገኙ ኩርዶች ላይ ጥቃት የከፈተችው "ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና" ለመፍጠርና ሁለት ሚሊየን ያህል ስደተኞችን ለማስፈር ነው ስትል ትከራከራለች። በቱርክና ሶሪያ ድንበር ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ 300ሺህ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው መሰደዳቸው ታውቋል። ቱርክ የተወሰኑ በኩርዶች የሚመራ ጦር ስፍራውን ለቅቆ እንዲወጣ ለማስቻል የተኩስ አቁም ለማድረግ የተስማማች ቢሆንም ስምምነቱ ግን ዛሬ ያበቃል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ የተኩስ አቁሙ ስለሚቀጥልበት ሁኔታ ያሉት ነገር የለም። የቀድሞ የአሜሪካ መከላከያ ባለስልጣናት ኤን ቢ ሲ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቀርበው እንደተናገሩት የመከላከያ መስሪያ ቤቱ የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን ጠቅልሎ የሚወጣበትን እቅድ እየተነጋገረበት እንደሆነ ገልፀዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሶሪያ የአሜሪካ ጦር እንዲወጣ በመወሰናቸው ከፍተኛ ትችት አስተናግደዋል። ትችቱ የምክር ቤት አባላት ከሆኑ ሪፐብሊካን ጭምር የቀረበ ሲሆን " ትልቅ ስህተት" ሲሉ ቅሬታቸውን የገለፁም ነበሩ።
news-47126800
https://www.bbc.com/amharic/news-47126800
በማሌዥያ ልጃቸውን አንገላቱ የተባሉ ሩሲያዊያን በፖሊስ ተያዙ
ሁለት ሩሲያዊን ማሌዢያ ውስጥ ጎዳና ላይ የህጻን ልጃቸውን እግር በማንጠልጠል ወደ አየር ላይ እየወረወሩ በፈጸሙት ትርኢት በፖሊስ ተያዙ።
• በስዊድን ያሉ የስደተኛ ልጆች ሚስጥራዊ ህመም ፖሊስ ለኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል እንደተናገረው ጥንዶቹ በአራት ዓመቷ ሴት ልቻቸው ላይ ፈጸሙት በተባለው ማንገላታት ምርመራ ተደርጎባቸዋል። የጥንዶቹን ድርጊት የሚያሳየው ቪዲዮ ባለፉት ቀናት በስፋት ከተሰራጨ በኋላ ነው ፖሊስ ግለሰቦቹን ይዞ ምርመራ ያደረገው። 90 ሰከንድ የሚረዝመው ቪዲዮ ፌስቡክ ላይ ተሰራጭቶ የነበረ ሲሆን፤ የተመለከቱት ሰዎች "ድርጊቱ ኃላፊነት የጎደለውና ጉዳትን የሚያስከትል ነው" በማለት ፖሊስ ጥንዶቹን መያዝ አለበት በማለት ሲጠይቁ ነበር። • ፈረንሳይ ህፃናት በሦስት ዓመታቸው ትምህርት እንዲጀምሩ ወሰነች ቪዲዮው አንድ ሰው የህጻኗን እግር በመያዝ ወደፊትና ወደኋላ በማንዠዋዠው ከፍና ዝቅ ሲያደርጋት የሚያሳይ ሲሆን፤ ህጻኗን ወደ አየር ላይ በመወርወር ሲቀልባትም ይታያል። ፌስቡክ በበኩሉ ቪዲዮውን በተመለከተ በሰጠው ምላሽ ቪዲዮው እንዲወርድና በስፋት እንዳይሰራጭ ያደረገው ድርጊቱ የተፈጸመባትን ህጻን ለመታደግ ይረዳል በሚል እንደሆነ ገልጿል። ቪዲዮው አሁንም ማንም ሊመለከተው የሚችል ሲሆን "በህጻን ወይም በታዳጊ ላይ የሚፈጸምን ጥቃት የሚያሳይ" ማስጠንቀቂያ አብሮት ቀርቧል።
news-52932155
https://www.bbc.com/amharic/news-52932155
ለሥራ ቢሮ መሄድ ብሎ ነገር ከናካቴው ሊቀር ይሆን?
ለብዙዎቻችን ቤታችን ቢሯችን ሆኖ ሰንብቷል፤ በኮሮናቫይረስ ተህዋስ ምክንያት። ይህ ጽሑፍ እየተሰናዳ ያለውም በአንድ ከቤቱ እየሰራ በሚገኝ የቢቢሲ ሠራተኛ ነው።
እንቅስቃሴዎች ውስን ይሆናሉ መኝታን ቢሮ ማድረግ ይቀጥል ይሆን? እርግጥ ነው ከቤት ሆኖ መሥራት በድኅረ ኮሮናቫይረስ ዘመን ደንብ የሚሆንባቸው መሥሪያ ቤቶች እንደሚኖሩ ከወዲሁ እየተነገረ ነው። ይህ ሀቅ ከኩባንያ ኩባንያ ቢለያይም ቅሉ፤ ቀጣሪዎች በዚህ አጋጣሚ ሠራተኞቻቸው ከቤት ሲሰሩ ኩባንያቸው ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ እንደሚሆን በትንሹም ቢሆን ተረድተዋል። በዚህ ሀሳብ ገፍተውበት ቢሮ ድርሽ እንዳትሉ ቢሉንስ? ይህ የማይመስል የነበረ ነገር በብዙ ኩባንያዎች ዘንድ እየተጤነ ነው። "ለምን ቢሮ እንከራያለን?"፣ "ለምን በአንድ ቢሮ ሕንጻ ሺህ ሠራተኞች ይርመሰመሳሉ?" ያሉ የሥራ አስፈጻሚዎችና ቀጣሪዎች ቀስ በቀስ ቢሮዎቻችንን ወደ ሠራተኞቻቸው ሳሎን ሊያመጡት ሽር ጉድ ይዘዋል። ይህ ነገር የከተማን ሕይወት በጠቅላላ ሌላ መልክ ሊያሲዘው ይችላል። ማኅበራዊ ሕይወትና ትዳርም መልኩን ይቀይር ይሆናል። በዚህ ጉዳይ ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉን ሦስት ባለሞያዎችን መርጠናል። ጭር ያሉ መሐል መሀል ከተማዎች ጭር ይሉ ይሆን? ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ሰዎች ማኅበራዊ እንሰሳ ናቸው። ውጤታማ ለመሆን የግድ ፊት ለፊት ከባለጉዳይ ጋር መገናኘት ያሻቸዋል። ለ20 ዓመታት የተደረገ ጥናት ያንን ነው የሚያስረዳው። አንዳንድ ነገሮች አሉ፤ የግድ ከሰው ጋር ስንገናኝ የምናደርጋቸው። ከእነዚያ መካከል አንዱ ዕለታዊ ሥራ ነው። ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር) አዲስ ነገር ልንጀምር ጫፍ ላይ ያለን ይመስለኛል። የሰው፣ የቦታና የጊዜ መስተጋብር ሌላ መልክ በመያዝ እየመጡ ይመስለኛል። ከዚህ ወዲያ አንዳንድ ነገሮች በነበሩበት ይቀጥላሉ ለማለት እቸገራለሁ። ኦዲ ቢኮሌት (የፖሊሲ ጥናት ተመራማሪ) አንዳንድ ግዙፍ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸው ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ እያበረታቱ መሆኑ ግልጽ ነው። ትዊተር ይህን ወስኗል። ፌስቡክም እንዲሁ። የባርክሌይ ባንክ ሥራ አስፈጻሚም "7 ሺህ ሠራተኛ ቢሮ ጠርቶ ማርመስመስ ከዚህ በኋላ ያረጀ ያፈጀ ጉዳይ" እንደሚሆን ጠቁመዋል። ቢሮ ሄዶ የመስራቱ ነገር ጨርሶውኑ ይጠፋል ባይባልም የቢሮ መሄድ ልማድ እየከሰመ ሲሄድ አነስተኛ፣ መካከለኛና ዋነኛ የከተማ አካባቢዎች እንደየደረጃው መልካቸው መለወጡ የማይቀር ጉዳይ ነው። ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር) አንዳንድ ኩባንያዎች "ለምንድነው ሚሊዮን ዶላር ለቢሮ የምንከሰክሰው" ማለታቸው አይቀርም።፡ ከወዲሁ እንደዚያ ማሰብ የጀመሩ አሉ። ይሄ ማለት በትንሹ ሦስት ነገሮችን ጨርሶውኑ ይቀይራል። አንዱ የከተሞችን ማዕከላት፣ ሁለተኛው የልጅ አስተዳደግ፣ ሦስተኛው ደግሞ የትዳር ግንኙነት ናቸው። ይህ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። ኦዲ ቢኮሌት (የፖሊሲ ጥናት ተመራማሪ) እኔ እንደሚመስለኝ በየሰፈራችን፣ ወደ ቢሮ ርቀን ሳንሄድ ሬስቶራንቶች፣ መዝናኛዎች እና ሌሎች የምንፈልጋቸው ነገሮች ወደኛ እየቀረቡ ይሄዱ ይሆናል። ሰዎች በአቅራቢያቸው መገናኘት መጀመር ይፈልጉ ይሆናል። ሌላው ደግሞ ከቤታችሁ ስሩ ስንባል ቦታ ስንሻ በዚያው በሰፈራችን የተሸለ ስፍራ መፈለጋችን አይቀርም። ይህ ሀቅ ሰፈሮች እንዲያብቡ ሊያደርጋቸው ይችላል። ቢሮዎች በስፋት በሚገኙባቸው የከተማ ማዕከላትም ለውጦች መኖራቸው አይቀርም። እነዚያ ሰፋፊ የቢሮ ሕንጻዎች ቆመው አይቀሩም መቼስ። የዲዛይን ለውጥ እየተደረገባቸው ወደ መኖርያ አፓርትመን ይቀየሩ ይሆናል። ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ የኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ከቤት ሥሩ ከተባልን ሁሉም የቤተሰብ አባል ቤት መዋሉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በቤታችን ውስጥ ሰፋፊ ቦታ መሻትን ያስከትላል። ካልሆነም በአቅራቢያችን የተመቻቸ ቦታ እንፈልግ ይሆናል። ለስብሰባ በሳምንት አንድ ሁለት ጊዜ ወደ ዋና ጽሕፈት ቤት መሄድ ሊኖር ይችላል። በሳምንት አንድ ጊዜ መሄድ ብቻ ግዴታ ሲሆን ደግሞ ሰዎች ከዋና ከተማ አቅራቢያ መስፈራቸው ጥቅሙ እየቀነሰ ይመጣል። ሰዎች ከከተማ ማዕከል ወደ ገጠር እየሄዱ መስፈር ይጀምሩ ይሆናል። በርሚንግሃም ውስጥ የሚገኝ ጭር ያለ የባቡር ጣቢያ ትራንስፖርትና የሰዎች እንቅስቃሴን በተመለከተ ምን ይፈጠራል? ማርገሬት ቤል በኒውካስል ዩኒቨርስቲ የትራንስፖርትና ኢንቫይሮንመንት ፕሮፌሰር ሰዎች መኪና መግዛት ይጀምራሉ። ይህም የሚሆነው ሰፋፊ ቦታ ፍለጋ ወደ ገጠር ስለሚያቀኑ ነው። በራቁ ቁጥር መኪና የግድ ይላቸዋል። ይህ ደግሞ የካርቦን ልቀትን ይጨምራል እንጂ አይቀንስም። ማድረግ የሚኖርብን ሰዎች ምንም ይሁን ምን ከሥራ ቦታቸው አቅራቢያ እንዲሰፈሩ ማድረግና ብስክሌት እንዲነዱ ማበረታት ነው። ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል የኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ብዙ ሰዎች ቤት ሲቀመጡ ቤት ማብሰል ግድ እየሆነ ይመጣል። ይህ የኢነርጂ [ኃይል] አጠቃቀማችን ላይ ለውጥ ያመጣል። ከቤት ባለመውጣት ከምናድነው ኢነርጂ የበለጠ ቤት ውስጥ እንጠቀማለን። ጥናቶች ይህንን ነው የሚመሰክሩት። በከተሞቻችን ዙርያ ስለሚኖር ለውጥ ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር) ብዙ ጊዜ ስለዚህ ጉዳይ ስናወራ ከፍ ያለ የቢሮ ሥራ ስለሚሰሩ ሰዎች እያሰብን ነው፤ ለምሳሌ በፋይናንስ፣ በአይቲ ወዘተ። ከተሞች የተሞሉት ግን በእነዚህ ሠራተኞች አይደለም። ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና አገልግሎች ሰጪ ተቋማት ይቀጥላሉ። ደግሞም ከተሞች የመገናኛ ማዕከል መሆናችውን አንርሳ። አገልግሎት ብቻ አይደለም የምንፈልገው። ሰዎች ሌሎችን ማግኘት መተዋወቅ ወዳጅነት መመስረት ይፈልጋሉ። ይህ እነሱን ከማይመስሉ ሰዎች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ይጨምራል። በባህል እኛን የማይመስሉ ሰዎችን በሰፈራችን ስለማናገኛቸው ርቀን ወደ ከተማ ማዕከላት መሄዳችን አይርም። ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ሌላው ጉዳይ መጠየቅ ያለብን ሰዎች ወደ ከተማ ወጥተው ለመቀላቀል ከዚህ በኋላ የኮሮናቫይረስ ፍርሃታቸው ብን ብሎ ይጠፋል ወይ? ሰዎች ወደ ድሮ ባህሪያቸው ለመመለስ ቢያንስ በሽታው በቁጥጥር ሥር ስለመዋሉን እርግጠኞች መሆን ይፈልጋሉ። ቢያንስ ክትባት ሊገኝ ይገባል። ይህ እስኪሆን ደግሞ ረዥም ጊዜ መፈለጉ አይርም። ረዥም ጊዜ!
news-46678614
https://www.bbc.com/amharic/news-46678614
ጣሊያን ውስጥ የሁለት ዓመት ሕፃኑ ሲገረዝ ህይወቱ አለፈ
በጣሊያን ስደተኞች በሚኖሩበት አካባቢ ግርዘት የተፈፀመበት የሁለት ዓመት ህፃን በደም መፍሰስ ምክንያት ህይወቱን አጣ።
የዚህ ብላቴና መንትያ በተመሳሳይ ግርዘት የተፈፀመበት ሲሆን ባጋጠመው ከፍተኛ የደም መፍሰስ ሮም በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ እየታከመ መሆኑ ተነግሯል። እንደ ጣሊያን የወሬ ምንጮች ከሆነ የ66 ዓመት አዛውንት በነፍስ ማጥፋት ተከሰዋል። በነፍስ ማጥፋት ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰብ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ሊቢያዊ እንደሆኑ ማወቅ ተችሏል። • ልብ የረሳው አውሮፕላን • 100 ሺህ ብር፤ ብልትን ለማወፈር • በህክምና ስህተት የመከነው ህፃን በምድረ ጣሊያን በየአመቱ 5ሺህ ግርዛቶች የሚፈፀሙ ሲሆን ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው በህገወጥ ስፍራዎች ደህንነታቸው ባልተጠበቁ መሳሪያዎችና ባለሙያ ባልሆኑ ግለሰቦች የሚፈፀሙ መሆናቸውን በጤና ላእ የሚሰራ በጎ አድራጎት ድርጅት ይናገራል። ሁለቱ ህፃናት ስማቸው ያልተገለፀ ሲሆን በ2017 በጣሊያን ከናይጄሪያዊ እናታቸው የተወለዱ ናቸው። ይህች ናይጄሪያዊ እናት 5 ልጆች ያላት ካቶሊክ ብትሆንም የናይጄሪያውያን ሙስሊሞችን ባሀል በጠበቀ መልኩ ለማስገረዝ ልጆቿን ወደዚያ መውሰዷ ተነግሯል። በጣሊያን ለግርዛት የሚከፈለው ገንዘብ ከ60 ሺህ ብር በላይ ሲሆን ይህንን መክፈል የማይችሉ ዜጎች በህገወጥ ስፍራዎች በ1500 ብር ገደማ ልጆቻቸውን ያስገርዛሉ። በአሁኑ ሰዓት በጣሊያን ግርዛት በህዝብ የጤና ተቋማት አይሰጥም። ግርዛት ቀላል ቀዶ ህክምና ቢሆንም ሁሌም ግን ከስጋትና ከአደጋ ነፃ ነው ማለት እንደማይቻል የጤና ባለሙያዎች ይገልፃሉ። በመላው አውሮፓ የወንድ ልጅ ግርዛት ህጋዊ ቢሆንም ክርክር ግን አያጣውም።
news-49535250
https://www.bbc.com/amharic/news-49535250
የሁዋዌ የወደፊት ስልክ የጉግል መተግበሪያዎች ላይኖሩት ይችላል
ሁዋዌ በቀጣይ የሚያመርተው ስልክ አቅጣጫ አመላካች (ጉግል ማፕ) እና ዩቲዩብን ጨምሮ ሌሎች የጉግል መተግበሪያዎች ላይኖሩት እንደሚችል ተገለፀ።
የጉግል ኩባንያ፤ የአሜሪካ መንግሥት የሁዋዌ ምርቶች በአገሪቷ እንዳይሸጡ በመከልከሉ ምክንያት መተግበሪያዎቹን ለቻይናው ግዙፍ ስልክ አምራች ድርጅት- ሁዋዌ ፈቃድ መስጠት አልችልም ብሏል። • ሁዋዌ አንድሮይድን እንዳይጠቀም ገደብ ተጣለበት • ሁዋዌ የተጣለበት እገዳ የስልኩ ተጠቃሚዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል? በዚህም ምክንያት ሁዋዌ በቀጣይ የሚያመርታቸው ስልኮች ላይ የጉግል መተግበሪያን እንዳይጠቀም ያደርገዋል። በመሆኑም የስልኩ ተጠቃሚዎች በጣም አስፈላጊ የሆኑ መተግበሪያዎችን መጠቀም አይችሉም። ሁዋዌ ያለ ጉግል መተግበሪያዎች ስልኮቹን ለመሸጥ ፈተና ሊያጋጥመው እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል። የአገሪቷን የደህንነት ጉዳይ በማንሳት፤ የአሜሪካ መንግሥት የአሜሪካ ድርጅቶች የሁዋዌ ምርቶችን እንዳይሸጡም ሆነ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እንዳይጠቀሙ የከለከለው ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ነበር። ሁዋዌ ግን ይህንን ክልከላ አልተቀበለውም። ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ወር ክልከላው ሊነሳ እንደሚችል ተናግረው ነበር። ይሁን እንጂ 130 የሚሆኑ ጥያቄዎችን ከመቀበላቸው በስተቀር የአገሪቷ ባለሥልጣናት ከሁዋዌ ጋር ግብይት እንዲደረግ ፈቃድ አልሰጡም። በእርግጥ የአንድሮይድ መተግበሪያ ማንኛውንም ሶፍት ዌር መቀበል የሚያስችል አሠራር ስላለው ማንኛውም ሶፍት ዌር አምራቾች ለዘመናዊ ስልኮቻቸውም ሆነ ታብሌቶቻቸው ሊያቀርቡላቸው ይችላሉ። • የጉግልና የሁዋዌ ፍጥጫ አፍሪካዊያንን የሚያሳስብ ነው? ነገር ግን ይህን የሚያደርጉ ድርጅቶች የተለመዱትን እንደ አቅጣጫ አመላካች (ጉግል ማፕ)፣ የጨዋታ (ጌም)፣ የመፈለጊያ፣ ፎቶግራፎች፣ ፕለይ ስቶር እና ዩቲዩብን ለማካተት ከጉግል ጋር መስማማት ይጠበቅባቸዋል። ጉግል በበኩሉ መተግበሪያውን ለሁዋዌ ለመስጠት ፈቃድ መጠየቅ፤ አለመጠየቁን በተመለከተ ያለው ነገር የለም። ሁዋዌም በመግለጫው "የአሜሪካ መንግሥት ከፈቀደልን ሁዋዌ አንድሮይድ ኦ ኤስን እና ምህዳሩን መጠቀሙን ይቀጥላል፤ ካልሆነ ግን የራሳችንን የመገልገያ ዘዴ መሥራታችንን እንቀጥላለን" ብሏል። ደንበኞቹ ድርጅቱ ከአንድሮይድ ጋር ያለውን ግንኙነት አስመልክቶ የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች ለማስተናገድም 'ሁዋዌ አንሰርስ' በሚል ድረ ገፅ ከፍቷል። "የሁዋዌ ምርት የሆነ ዘመናዊ ስልክ የገዙ አሊያም ለመግዛት ያሰቡ፤ ሁልጊዜ እንደሚያደርጉት ዓለም የሚገለገልባቸውን መተግበሪያዎች መጠቀም ይችላሉ" ብሏል- ሁዋዌ። "ሁሉም ምርቶቻችን ዋስትና ያላቸው ሲሆን ድርጅቱ ሙሉ የአገልግሎት ድጋፍ ያደርጋል" ሲልም ከደንበኞቹ ጎን እንደሆነ ገልጿል።
news-47126596
https://www.bbc.com/amharic/news-47126596
የኮንጎ ሚኒስትሮች እስከ ህይወታቸው መጨረሻ ደመወዝ እንዲያገኙ ተወሰነላቸው
ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሚኒስትሮቿ እስከ ህይወታቸው መጨረሻ ደመወዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች የሚያስገኛቸውን ህግአፅድቃለች።
በዛሬው ዕለት በወጣው መንግሥት ባወጣው መግለጫ ይህ ክፍያ የባለስልጣኖቹን ኃብት ለማካበት አይደለም የሚል ነው። በዚህም መሰረት የቀድሞ ሚኒስትሮች 2ሺ ዶላር (አምሳ ስድስት ሺ ብር) ደመወዝ በየወሩ ይከፈላቸዋል። ብዙ ደሃ ህዝብ ባለባት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ይህ መሆኑ ለሰላ ትችት ዳርጎታል። •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ •"ከሞቱት አንለይም" የሶማሌ ክልል እስረኞች ስልጣንን በቅርቡ የሚያስረክበው ይህ መንግሥት ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ሚኒስትሮቹ መሰረታዊ የሆኑ እንደ ምግብ፣ መጠለያና የጤና ሽፋን ግልጋሎቶችን እንዲሸፍንላቸው እንደሆነ ተገልጿል። •ሴት እስረኞችና የማዕከላዊ ምርመራ መግለጫው ጨምሮ እንደገለፀው ሚኒስትሮቹ ወደ ድህነት እንዳያመሩ ለመከላከል ነው። በወጪው ጠቅላይ ሚኒስትር ብሩኖ ትሻባላ በህዳር ወር የተፈረሙት እነዚህ አዋጆች የሚዲያውን ቀልብም ሆነ ሽፋን ያገኙት በቅርቡ ነው። የመጀመሪያው አዋጅ የቀድሞ ሚኒስትሮች አገሪቷን ከሚያስተዳድረው ጠቅላይ ሚኒስትር በ30% ተስተካካይነት ያለው ደመወዝ፣ በየአመቱ አንድ የቢዝነስ የአውሮፕላን በረራ፣ በየወሩ ለቤት የሚሆን 5ሺ ዶላር ብር ክፍያ እንዲፈፀምላቸው የሚያትት እንደሆነ የሮይተርስ ዜና ወኪል ዘገባ ያሳያል። ሁለተኛው አዋጅ ደግሞ የቀድሞ ሚኒስትሮች አሁን ካሉት ሚኒስትሮች በ30% ተስተካካይነት ያለው ደመወዝ፣ በየወሩ አንድ ሺ ዶላር ለቤት ኪራይ፣በየአመቱ አንድ የቢዝነስ የአውሮፕላን በረራ እንደሆነ ይሄው የሮይተርስ ዘገባ ገልጿል። ይህ ከፍተኛ ትችት የቀረበበት ህግ ከአገሪቷ ማህበራዊና ኢኮኖሚያው እውነታ ጋር የማይጣጣም እንደሆነ ተገልጿል። ለአገሪቷ ብዙ ወጭ የሚያስወጣትና የህዝብ ሀብትንም ማባከንም እንደሆነ በመግለፅ የተቹ አሉ። አዲሱ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊኮ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ትሽኬዲ ቃለ መሐላቸውን የፈፀሙት ባለፈው ወር ሲሆን፤ በስድስት አስር የኮንጎ አመታት ታሪክም ውስጥ ስልጣን በሰላም ሲሸጋገር የመጀመሪያው ነው። ይህም ቢሆን የምርጫው ውጤት ከትችት ያላመለጠ ሲሆን በአዲሱ ፕሬዚዳንትና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ መካከል ሚስጥራዊ ስምምነቶች ተደርሰዋል የሚሉ ውንጀላዎች ተሰንዝረዋል። ሁለቱም ግን ውንጀላውን አጣጥለውታል።
news-53847307
https://www.bbc.com/amharic/news-53847307
ማሊ፡ መፈንቅለ መንግሥቱ ማሊያውያንን ሲያስደስት ጎረቤት አገራትን አስቆጥቷል
በዚህ ሳምንት የተደረገው የማሊ መፈንቅለ መንግሥት በርካታ ማሊያውያንን አስደስቷል፤ ጮቤ የረገጡ ማሊያውያን በየጎዳናው በመውጣት ደስታቸውንም በመግለፅ ላይ ናቸው።
ነገር ግን በመፈንቅለ መንግሥቱ ደስተኛ ያልሆኑት በርካቶች ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የበርካታ አገራት መሪዎች ሲያወግዙት የአፍሪካ ህብረት ደግሞ ከአባልነት አግዷታል። ሰፊ የቆዳ ሽፋን ያላት ማሊ ግዛቷ የሰሃራ በረሃንም የተወሰነ የሚሸፍን ሲሆን የፈረንሳይ ወታደሮችን ጨምሮ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪዎች አክራሪ ፅንፈኝነትን እንዋጋለን በሚልም ሰራዊት አስፍረውባታል። የወታደራዊው ኃይል ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ባውባካር ኬታን ጨምሮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦቡዎ ሲሴ፣ የብሔራዊ ጉባኤ ቃል አቀባይ የሆነው የፕሬዚዳንቱ ልጅ፣ የውጭ ጉዳይና የገንዘብ ሚኒስትሮችም በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። በአሁኑ ሰዓትም ፕሬዚዳንቱን በግዞት ወደ ውጭ አገርም ለመላክ አንዳንድ ድርድሮች እንደተጀመሩ ያልተረጋገጡ ሪፖርቶች እየወጡ ነው። ማሊ አባል የሆነችበትና አስራ አምስት አባላት ያሉት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) በበኩሉ ፕሬዚዳንቱ ወደ ስልጣን እንዲመለሱ ጠበቅ ያለ ማስጠንቀቂያን አስተላልፏል። ከዚህም በተጨማሪ አገራት ድንበሮቻቸውን እንዲዘጉ አድርጓል፤ ማንኛውንም የገንዘብ እንቅስቃሴም የገደበ ሲሆን ከማህበረሰቡም የውሳኔ ሰጭነት ቦታ እንድትገለል ወስኗል። መፈንቅለ መንግሥቱንም ተከትሎ የ75 አመቱ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ከስልጣን መልቀቃቸውንም አጠር ባለው የቴሌቪዥን መግለጫቸው አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህንን መግለጫ የሰጡትም ከመዲናዋ ባማኮ 15 ኪሎ ሜትር ራቅ ብላ በምትገኘው ካቲ የጦር ሰፈር ሲሆን በዚያኑ እለትም ነው በወታደራዊው ኃይል ወደ ስፍራው የተወሰዱት። ለባለፉት ሁለት ወራት ያህል የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከፍተኛ ህዝብ የተሳተፈባቸውን የተቃውሞ ሰልፎች መርተዋል። በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን ሙስና፣ የምጣኔ ኃብት ኢ-ፍትሃዊ ክፍፍልና አወዛጋቢ የምርጫ ህግን በተመለከተ ተቃውሞን ከማሰማት ባለፈ የሁሉም መሰረታዊ ጥያቄ ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲወርዱ ነበር። እነዚህን የተቃውሞ ሰልፎች በዋነኝነት ሲያስተባብሩ የነበሩት ኢማም ማህሙድ ዲኮም ነበሩ። ኢኮዋስ በአሸማጋይነትም በመግባት ህዝቡ የሚጠይቃቸውን ማሻሻያዎች ፕሬዚዳንቱ ተግባራዊ እንዲያደርጉም ሞክሯል። በዚህም ሁኔታ እያለ ነው የወታደራዊውን ኃይል የሚመሩ ኮሎኔሎችና ጄኔራሎች ተሰባስበው የፕሬዚዳንቱን ስልጣን ለማሳጠር የወሰኑት። ሆኖም ኢ-ህገ መንግሥታዊ በሆነ ሁኔታ የስልጣን መገርሰስን ኢኮዋስ አይቀበለውም። የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን መፈንቅለ መንግሥቱን ከመሩት ወታደሮች ጋር ለመወያየትም ወደ ባማኮ ከሰሞኑ ያመራሉ ተብሏል። ውይይታቸውም አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችልም እየተነገረ ነው። ሆኖም ማሊያውያን በተለይም በደቡብና ማዕከላዊ ማሊ የሚኖሩ ማሊያውያን የፕሬዚዳንቱ ከስልጣን መውረድ አስፈንድቋል። አስተዳደራቸው በርካታ የሙስና ቅሌቶችን ማስተናገድ ብቻ ሳይሆን የመስረተ ልማቶች ችግር ብዙዎችን አስመርሯል። በተለይም አርሶ አደሮች የማዳበሪያ እጥረት ማጋጠሙ ቀውስን አስከትሏል። ከዚህም በተጨማሪ የሃገሪቱ ሰራዊት ፅንፈኛ አክራሪዎች ጋር በሚያደርገው እልህ አስጨራሽ ትግል የሚከፈላቸው ክፍያ ትንሽ መሆኑ ቁጣን ፈጥሯል። በተለይም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት የወጡ መመሪያዎች የበርካታ ማሊያውያንን ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ በከተተበት ወቅት የፕሬዚዳንቱ ልጅና የፓርላማው መከላከያ ኮሚቴ ሊቀመንበር ካሪም ኬይታ በቅንጡ መርከብ ሲዝናና የሚያሳይ ፎቶ መውጣቱ ብዙዎችን አበሳጭቷል። ፎቶው የአሁንም ይሁን የቀድሞ ካሪም ኬይታ የህዝብን ገንዘብ አልተጠቀምኩም ቢልም በበርካቶች መሬት ላይ ካለው እውነታን የማይገባውና አገሪቷ ያለችበትን ቀውስ ያልተረዳ ነው በሚልም ውግዘት ደርሶበታል።
49041903
https://www.bbc.com/amharic/49041903
እስራኤል በቁፋሮ መስጂድ አገኘች
በእስራኤል ኔጌቭ በረሀ አርኪኦሎጂስቶች 1200 ዓመት ዕድሜ ያለው መስጂድ በቁፋሮ ማግኘታቸው ተነገረ። መስጂዱ ዓለም ላይ ጥንታዊ ከሚባሉት መካከል እንደሚመደብ ተገልጿል።
መስጂዱ የተገኘው በእስራኤሏ ኔጌቭ በረሃ በምትገነው ራሀት ቤዱዌን ከተማ ነው ወደ ሰባተኛውና ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ዕድሜያቸውን የሚቆጥሩ ቅሪቶች የተገኙት በራሀት ቤድዌን ከተማ ነው። • ከላሊባላ ጥገና ጀርባ ያለው ማን ነው ? የእስራኤል ቅርስ ጥበቃ እንዳለው፤ መስጂዱ ሊገኝ የቻለው በአካባቢው ለግንባታ ተብሎ ቁፋሮ በሚካሄድበት ወቅት ነው። መስጂዱ የተገኘው በአካባቢው ግንባታ ለማካሄድ ቁፋሮ በሚደረግበት ወቅት ነው ሙስሊሞች አዲስ በተገነው ጥንታዊ መስጂድ ውስጥ ሲሰግዱ "በአካባቢው በዚህ ክፍለ ዘመን የነበረ እና በመካ እና እየሩሳሌም ከተገኙት መስጂዶች ጋር በእድሜ የሚፎካከር ቅርስ ነው" ሲል የእስራኤሉ የቅርስ ጥበቃ መሥሪያ ቤት ተናግሯል። ቁፋሮውን የመሩት ባለሙያዎች በበኩላቸው መስጂዱ "በዓለማችን የትኛውም ጥግ ከተገኙት ሁሉ ለየት ያለው ነው" ብለዋል። የመስጂዱ ምዕመናኖችም የአካባቢው ገበሬዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ያላቸውን ግምት ተናግረዋል። የእስራኤል የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ባልደረባ ስለ ግኝቱ ዝርዝር ማብራሪያ ሲሰጡ መስጂዱ ጣሪያ የሌለው ሲሆን፤ በአራት መአዘን ቅርፅ የታነፀ ነው። ፊቱን ወደ ሙስሊሞች ቅድስቷ ከተማ መካ ያዞረ መስገጃ አለው። "ይህ የመስጂዱ አቀማመጥ ከበርካታ መቶ ዓመታት በፊት ሙስሊሞች በዚህ መስጂድ ውስጥ ይሰግዱ እንደነበር ምስክር ነው" ብለዋል የቅርስ ጥበቃ መሥሪያ ቤቱ ባልደረባ። የእስራኤል የቅርስ ጥበቃ መሥሪያ ቤት ባልደረባ በሥራ ላይ የእስልምና ታሪክን እንዳጠኑት ባለሙያዎች ከሆነ ይህ መስጂድ እስልምና ወደ አሁኗ እስራኤል በመጣበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የተገነባ ቀደምት መስጂድ ነው ተብሎ ይታመናል። አክለውም በዚያ ዘመን የነበረውን ሁኔታ የበለጠ ለማወቅ "የዚህ መስጂድ በአካባቢው መገኘት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍ ያለ ነው" ይላሉ። • አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት • የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች?
news-51440268
https://www.bbc.com/amharic/news-51440268
የደቡብ ኮሪያው 'ፓራሳይት' ፊልም በኦስካር ሽልማት ታሪካዊ ሆነ
የደቡብ ኮሪያው ፊልም 'ፓራሳይት' በዘንድሮው የኦስካር ሽልማት በምርጥ ፊልም (ቤስት ፒክቸር) ዘርፍ አሸንፏል።
በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያልተሰራ ፊልም በዚህ ዘርፍ ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ሲሆን ታሪካዊም ነው ተብሏል። ሬኔ ዜልዌገር 'ጁዲ' በሚለው ፊልም የጁዲ ጋርላንድን ገፀ ባሕርይ ወክላ በመጫወት በሴት ተዋንያን ዘንድ የምርጥ ተዋናይነትን ዘርፍ ያሸነፈች ሲሆን፤ ጆዋኩን ፊኒክስ 'ጆከር' በሚለው ፊልሙ በወንዶች ምርጥ ተዋናይ ዘርፍ ሽልማቱን ወስዷል። • የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? • ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም ብራድ ፒት 'ዋንስ አፕ ኦን ኤ ታይም ኢን ሆሊውድ' ላውራ ደርን ደግሞ 'ሜሪጅ ስቶሪ' በሚለው ፊልማቸው በረዳት ተዋናይነት ዘርፍ አሸንፈዋል። ፓራሳይት በአጠቃላይ አራት ሽልማቶችን ያሸነፈ ሲሆን፤ የሰር ሳም ሜንዴዝ ፊልም '1917' ሶስት ሽልማቶችን ወስዷል። ምንም እንኳን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ላይ የሚያጠነጥነው '1917' በምርጥ ፊልም ዘርፍ ቢታጭም፤ ሽልማቶቹ በሙሉ በቴክኒክ ዘርፍ ናቸው። የፓራሳይት ዳይሬክተር ቦንግ ጁን ሆ ቢት በምርጥ ዳይሬክተርነትም ሰር ሳምን አሸንፎ ሽልማቱን ወስዷል። ከዚህም በተጨማሪ ፊልሙ በምርጥ ፅሁፍ ዘርፍም ሽልማቱ ሊያሸንፍ ችሏል። የፊልሙ ታሪክ የሚያጠነጥነው ሁለት ከተለያየ መደብ የመጡ ቤተሰቦችን ህይወት ሲሆን፤ በምፀት መልኩም ያስቃኛል። አንደኛው ቤተሰብ ቁምጥምጥ ያለ ደሃ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የናጠጠ ሃብታም ነው። • እግራቸው አሜሪካ ልባቸው አፍሪካ ያለ የሆሊውድ ተዋንያን • ዶናልድ ትራምፕን ከዝነኛው ፊልም ማን ቆርጦ ጣላቸው? ኦስካር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ 92 አመታት ቢያስቆጥርም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያልተሰራ ፊልም ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ነው፤ ይህም ሁኔታ ብዙዎችን አስደምሟል። የፊልሙ ፕሮዲውሰር ክዋክ ሲን አኤ ሽልማቶቹን ከተቀበለ በኋላ "ቃላት የለኝም። በጭራሽ ይህ ይፈጠራል ብለን አላሰብንም። ይህ ለኛ ታሪካዊ ቀን ነው" ብሏል። በፊልም ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦስካር ሽልማት የተቀበለው ብራድ ፒት በስነስርአቱ ወቅት ባደረገው ንግግር ዶናልድ ትራምፕን እንዲሁም ሪፐብሊካን ፓርቲን ወርፏቸዋል።
news-45248580
https://www.bbc.com/amharic/news-45248580
በሊቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬም እየተሰቃዩ ነው
ህልሟ ባህር አቆራርጦ ጣልያን መግባት ነበር። ከወራት በፊት ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ አቀናች። አስከትላም ወደ መተማ አቅንታ ሱዳን ወስጥ አራት ወራትን አሳለፈች።
እንደሷው ያሉ ስደተኞች በሰሀራ በረሀ ለሚያዘዋውር ግለሰብ ገንዘብ ከፍላ በረሀውን በመኪና አቋረጠች። ሊቢያ አንደደረሰች ደላላ ተቀበላት። ተቀብሎም ለሌላ ደላላ ሸጣት። ሊቢያ ውስጥ ኢምወሊድ የሚባል አካባቢ እሷና ሌሎችም ስደተኞች ታሰሩ። "ገንዘብ ክፈሉ" እየተባሉ ይደበደቡ እንደነበረ ትናገራለች። ከእስር ቤቱ ለመውጣት ከኢትዮጵያ ወይም ከሌላ ሀገርም ገንዘብ እንዲያስልኩ በማስገደድ ያሰቃዩዋቸው እንደነበረም ታክላለች። •"ሶስት ጊዜ ለተለያዩ ነጋዴዎች ተሽጫለሁ" •በሊቢያ የስደተኞች ጀልባ ሰምጦ ተሳፋሪዎቹ የገቡበት ጠፋ • ሊቢያ በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ አወጣች ወጣቷን በስልክ ያነጋገርናት ሊቢያ ውስጥ በሚገኝ ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ሳለች ነው። ከእስር ቤቱ ኢንዛራ ወደሚባል ቦታ ከተወሰዱ በኃላም እንግልቱ እንደቀጠለ ለቢቢሲ ገልፃለች። "ከተደፈሩ ሴቶች አንዷ እኔ ነኝ" ትላለች ከደረሰባት ሁሉ የከፋውን ስትናገር። በርካታ ሴቶች እንደሷ ተደፍረዋል፤ ተደብድበዋል። የተገደሉ እንዳሉም ትናገራለች። ካሉበት መጠለያ ለማምለጥ የሚሞክሩ ግለሰቦች ላይ የሚደርሰው ድብደባ የከፋ ነው። "እንድንፈራ እኛ ፊት ነው እንዳይሞቱም እንዳይድኑ አድርገው ነው የሚቀጠቅጧቸው" ትላለች። ያሉበትን ሁኔታ የሚነግሩት አንዳችም አካል እንደሌለ ገልጻ፤ እንደ ሱዳን ያሉ ሀገሮች ዜጎቻቸውን መታደግ እንደቻሉ በንጽጽር ትናገራለች። ከምትገኝበት መጠለያ ከሶስት ቃለ መጠይቅ በኋላ መውጣት እንደምትችል ቢነገራትም ለስምንት ወር ያህል ከቦታው መውጣት እንዳልቻለች ትገልጻለች። "ሁለት ጊዜ ቃለ መጠይቅ አድርጌ ሶስተኛ ነው የቀረሽ ተብዬ ስምንት ወር ሆነኝ" ትላለች። ጊዜያዊ መጠለያው ውስጥ ከሚገኙ ስደተኞች ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚደርስባቸው እንግልት የከፋ መሆኑን የምትናገረው እሷ ብቻ ሳትሆን ሌሎችም በስልክ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው። ሌሎች ዜጎች ከማቆያው ወደ ኒጀር እንደተሰደዱና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ከማቆያው እንዲወስዳቸው በሚጠባበቁበት ወቅት ምግብና መጠጥ ማግኘት እንደሚቸገሩም ይናገራሉ። ያላቸውን ገንዘብ በፖሊሶች እንደተዘረፉ ያገጋገረችን ወጣት ትገልጻለች። "ስልካችንን ወስደውብናል፤ ከሶማሌዎች ተውሰን ነው እናንተንም ማናገር የቻልነው" ትላለች። በተመሳሳይ መጠለያ ውስጥ የሚገኘው ሌላ ኢትዮጵያዊ "አሁን ራሱ አንዱን ሌላ ቦታ ወስደው እየደበደቡት ነው" ይላል በፍርሀትና በስጋት ተሸብቦ። እሱም ተመሳሳይ የመደብደብ እጣ እንዳይገጥመው ይሰጋል። እሱና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ድብደባና ስቃይ እንደበረታባቸው "ያለሁበት ቦታ ለህይወቴ አስጊ ነው" በማለት ይናገራል። የሚገኙት በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ቢሆንም ከሊቢያ ፖሊሶች ድብደባ እንዳልዳኑ ይናገራል። ሴቶች ይደፈራሉ። በድብደባው ምክንያት አርግዘው ያስወረዳቸውም አሉ። ይህኛው ወጣት የተያዘው ከስምንት ወር በፊት ባህር ለማቋረጥ ሲሞክር ነበር። እሱና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ሊቢያ፣ ትሪፖሊ ውስጥ ኢንዛራ የሚባል ቦታ ይገኛሉ። ሌላ ቢቢሲ ያናገራት ኢትዮጵያዊት ለወራት በመጠለያው ሲቆዩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን መውጣት እንዳልቻሉ ትናገራለች። አንዳንድ ቀን ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው ይቀመጣሉ። "ወንዶቹን 'ስራ አለ' ብለው ወስደው ይገርፏቸዋል፤ አንዱን ደግሞ የት እንዳደረሱት አናውቅም" ስትል መጠለያው ውስጥ ፖሊሶች መስለው የሚገቡ ደላሎች የሚያደርሱባቸውን ትናገራለች። ጨምራም"ሊደፍሩን ሲመጡ እየጮህን ከራሳችን ላይ እያስወረድን ነው እንጂ እነሱ በኛ መጫወት ነው የሚፈልጉት" ትላለች። ደላሎቹ ስደተኞችን ከመጠለያው እያስወጡ ይሸጧቸዋል። ከሊቢያ ወጥተው ባህር ለመሻገር ገንዘብ እንዲከፍሉ በመጠየቅም ያንገላቷቸዋል። ሶስቱ ኢትዮጵያውያን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ከሚገኙበት መጠለያ ሶማሌዎች እየተለዩ ወደ ኒጀር ይወሰዳሉ። ኢትዮጵያውያን ወይም ኤርትራውያን ጥያቄ ሲያቀርቡ ግን ቤት ውስጥ ይቆለፍባቸዋል። ስደተኞቹ ኒጀር ውስጥ ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው በኃላ ወደተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች እንዲሻገሩ ይደረጋል። የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ወደ ጊዜያዊ መጠለያው ሲሄዱ ስደተኞቹን እንዳያናግሩ እንደሚደረጉ ይናገራሉ። ኢትዮጵያኑ "እንድትደርሱልን እንለምናለን" የሚሉትም ለዚሁ ነው። ስለሁኔታው የጠየቅናቸው ተሰናባቹ የግብጽ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በሊቢያ እየተንገላቱ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለማውጣት መጓጓዣ ሰነድ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ። ሰነዱን ለመዘጋጀት የሚያስፈልግ መረጃ ከቦታው የሚልክ ተወካይ ወይም አስተዳዳሪ አለመኖሩ ችግሩን እንዳባባሰው ይናገራሉ። "ማንነታቸውን የሚገልጽ ዝርዝር ማስረጃ ስለሌላቸው አንጠይቅም። ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት ብቻ በቂ ነው" የሚሉት አምባሳደሩ፤ ስደተኞቹ ካሉበት ሆነው ፎቷቸውንና ስማቸውን ከላኩ መጓጓዣ ሰነድ እንደሚያዘጋጁላቸው ተናግረዋል። "በቦታው ሁነኛ ሰው ስለሌለን በቀጥታ ማግኘት አንችልም፤ የበረሀ ጩኸት ነው የሚሆነው፤ ልንደርሳቸው የምንችለው በምናውቃቸው ሰዎች ወይም ተቋሞች አማካይነት ብቻ ነው" ይላሉ።
48263643
https://www.bbc.com/amharic/48263643
ዋትስአፕን በመጠቀም የስለላ መተግበሪያ ተጭኖ ነበር ተባለ
የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች (ሀከርስ) የዋትስአፕ መተግበሪያን ተጠቅመው ስልኮችና ሌሎችም የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ላይ መሰለያ ጭነው እንደነበረ ተረጋገጠ።
መሰለያውን የጫኑት የዋትስአፕ መተግበሪያ ላይ ያለ ክፍተትን ተጠቅመው ነው ተብሏል። • 'ዋትስአፕ' በቻይና እክል ገጥሞታል በፌስቡክ ስር የሚተዳደረው ዋትስአፕ ይፋ እንዳደረገው፤ ጥቃቱ የተመረጡ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረገ ነበረ። የተቀነባበረውም የላቀ ችሎታ ባላቸው ሀከሮች ነው ተብሏል። ፋይናንሽያል ታይምስ እንደዘገበው፤ ጥቃቱ የተሰነዘረው 'ኤንኤስኦ' በተባለ የእስራኤል የደህንንት ተቋም ነው። ባለፈው ሀሙስ ዋትስአፕ የተፈጠረውን ችግር ማስተካከል ችያለሁ ብሏል። • በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት አንዳንድ ስልኮች ዋትስአፕን አያስጠቅሙም ጥቃቱ እንደተሰነዘረ የታወቀው በያዝነው ወር መባቻ ላይ ሲሆን፤ ሰኞ እለት ዋትስአፕ 1.5 ቢሊየን ተጠቃሚዎቹ የተሻሻለውን መተግበሪያ እንዲጭኑ (አፕዴት እንዲያደርጉ) ጠይቆ ነበር። መሰለያ የጫኑት አካሎች በዋትስአፕ መሰለል ወደሚፈልጉት ግለሰብ ይደውላሉ። ከዛም መሰለያውን ይጭናሉ። ግለሰቡ ስልኩን ባያነሳም እንኳን መሰለያውን ከመጫን አያግዳቸውም ተብሏል። ፋይናንሽያል ታይምስ እንዳለው ከሆነ ጥሪ ያደረገው አካል ማንነት ከደዋዮች ዝርዝር (ኮል ሎግ) ይጠፋል። ዋትስአፕ ለቢቢሲ እንዳሳወቀው፤ ለመጀመርያ ጊዜ ይህ ክፍተት መፈጠሩን ያስተዋለው የድርጅቱ የደህንነት ክፍል ነበር። • ወደ ድብቁ የዋትስአፕ መንደር ስንዘልቅ ወዲያው ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እንዲሁም ለአሜሪካ 'ዲፓርትመንት ኦፍ ጀስቲስ' አሳውቀዋል። "ጥቃቱ ከግል ድርጅት መሰንዘሩን የሚያሳይ ምልከት አለ። ከመንግሥት ጋር በመሆን ያልተፈለገ የስለላ ሶፍትዌር (ስፓይዌር) በመጠቀም ስልክ መቆጣጠር የሚያስችል ነው" ሲሉ ለመገናኛ ብዙኀን ገልጸዋል። 'ኤንኤስኦ' ከመንግሥት ፍቃድ የተሰጣቸው ተቋሞች ወንጀልን ለመከታከልና የሽብር ጥቃት እንዳይደርስ ለማድረግ እንዲያውሉት አልሞ የሠራው ነው። ሆኖም አሠራሩ ያላግባብ ጥቅም ላይ ውሎ ከሆነ ምርመራ ይደረጋል ተብሏል። ዋትስአፕ ምን ያህል ሰዎች ጥቃቱ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ጊዜው ገና ነው ብሏል። • ዋትስአፕ በተደጋጋሚ መልዕክት ማጋራትን አገደ ከዚህ ቀደም በኤንኤስኦ ጥቃት ደርሶብኝ ነበር ያለው የመብት ተከራካሪው አምንስቲ ኢንተርናሽናል፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች መሰል ጥቃት ሊደረስባቸው እንደሚችል ስጋት ነበረን ብሏል። የአምንስቲ ኢንተርናሽናል የቴክኖሎጂ ክፍል ዳይሬክተር ዳና ሌግሌቶን እንዳሉት፤ ታዋቂ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞችን ለመቆጣጠር በመንግሥታት ጥቅም ላይ የሚውል አሠራር ነው። የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር የ'ኤንኤስኦ'ን ፍቃድ እንዲቀማ ለመጠየቅ በአምንስቲ ኢንተተርናሽናል የተመራ የፊርማ ስብስብ ቴል አቪቭ ፍርድ ቤት ይቀርባል።
news-53135329
https://www.bbc.com/amharic/news-53135329
በደቡብ ኮሪያ ኮሮናቫይረስ ለሁለተኛ ዙር ሳያገረሽ አይቀርም ተባለ
ምንም እንኳን በበሽታው ተይዘው የተገኙ የህሙማን ቁጥር ዝቅተኛ ቢሆንም የደቡብ ኮሪያ የጤና ባለስልጣናት ወረርሸኙ ማገርሸቱን እንደሚያምኑ ገለጹ።
ደቡብ ኮሪያ የኮሮናቫይረስን በመቆጣጠር በኩል ተሳክቶላታል ተብሎ ሲነገር የነበረ ቢሆንም አሁን እያንሰራራ ያለውን በሽታ ለመቆጣጠር ወራት ሊያስፈልጋት እንሚችል እየተነገረ ነው። የኮሪያ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከላት ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ጂዮንግ ኢዩን-ኪዮንግ እንዳሉት የመጀመሪያው ዙር የወረርሽኙ ክስተት እስከ ሚያዚያ ወር ማብቂያ ድረስ ቆይቶ ነበር። ነገር ግን ከግንቦት ወር ጀምሮ በዋና ከተማዋ ሴኡል ውስጥ የሚገኝን የምሽት ክበብን ጨምሮ በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ በሽታው ተከስቷል። በሽታው በቁጥጥር ስር ውሏል በተባለበት ጊዜ በየዕለቱ ይመዘገብ የነበረው ወደ አንድ ሺህ የሚጠጋ የአዲስ ህሙማን ቁጥር ለተከታታይ ሦስት ቀናት ዜሮ ሆኖ ቆይቷል። ዛሬ ባለስልጣንት እንዳስታወቁት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ የተባለው 17 አዲስ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች በተለያዩ ቢሮዎችና መጋዘኖች አካባቢ መገኘታቸው ታውቋል። ኃላፊዋ የወረርሽኙ መልሶ ማገርሸት አገሪቱ ወደ ሁለተኛ ዙር የቫይረሱ ወረራ እየገባች መሆኑን የሚያመለክት ሳይሆን እንደማይቀር ገልጸው፤ ይህም ለወራት ሊቆይ እንደሚችል ስጋታቸውን ተናግረዋል። ዛሬ ጠዋት ከዋና ከተማዋ በስተደቡብ የምትገኘውና ከትልልቅ የአገሪቱ ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው ዴጆን በአንዳንድ ቦታዎች ላይ በበሽታው ተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትከሎ በሙዚየሞችና በቤተ መጽሐፍት ውስጥ መሰብሰብን ከልክላለች። የዋና ከተማዋ ሴኡል ከንቲባም በሚቀጥሉት ሦስት ቀናት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር 30 ከደረሰና በከተማዋ ባሉ ሆስፒታሎች ከሚገኙ አልጋዎች መካከል የሚያዘው ከ70 በመቶ ከበለጠ ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረው ጥብቅ ማኅበራዊ ርቀትን የመጠበቅ ግዴታ ተመልሶ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ደቡብ ኮሪያ በአገሪቷ ውስጥ የመንቀሳቀስ እገዳ ሳትጥል ሕዝቡ በፈቃደኝነት ማኅበራዊ ርቀትን የመጠበቅ እርምጃን ሲወስድ መንግሥት ደግሞ በሽታው ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ፣ በመመርምርና በመለየት የተሳካ የመቆጣጠር ሥራ ተከናውኗል። ደቡብ ኮሪያ በሽታው በግዛቷ ውስጥ መገኘቱን ሪፖርት ካደረገችበት ከጥር ወር መጀመሪያ ወዲህ በአጠቃላይ 280 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ታውቋል። በአገሪቱ እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን አብዛኞቹ አገግመው በክትትል ላይ የሚገኙት 1,277 ብቻ መሆናቸው ተነግሯል።
news-51569577
https://www.bbc.com/amharic/news-51569577
ቻይና ዘረኝነት ተንፀባርቆበታል ባለችው ፅሁፍ ምክንያት የዋልስትሪት ጋዜጠኞችን ከሃገሯ አባረረች
ቻይና ዘረኝነት ተንፀባርቆበታል ባለችው ፅሁፍ ምክንያት ሶስት የዎል ስትሪት ጋዜጠኞች ከሃገሯ እንዲወጡ አዘዘች።
ከሁለት ሳምንት በፊት የታተመው ይህ ፅሁፍ አገሪቷ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር እያደረገችው ያለውን ጥረት "በአስነዋሪ ሁኔታ" ተችቷል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተደጋጋሚ ጋዜጣው ይቅርታ እንዲጠይቅ ቢጠይቁም ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል። • "ትግራይ ላይ ያለው ጥላቻ ካልተስተካከለ፤ ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር ናት ብላችሁ አውጁ" ዶ/ር ደብረፅዮን • ፖምፔዮ በግድቡ ዙሪያ የሚካሄደው ውይይት በቅርቡ መቋጫ እንደሚያገኝ ጠቆሙ ዎልስትሪት ጋዜጣ እንዳሳወቀው ፅሁፉን የፃፉት ጋዜጠኞች ቻይናን ለቀው እንዲወጡ አምስት ቀናት ተሰጥቷቸዋል። በዎል ስትሪት ጆርናል ላይ የወጣው ፅሁፍ ላይ የቻይና ባለስልጣናት ለኮሮና ቫይረስ የሰጡትን ምላሽ "ሚስጥራዊ" እና መንግሥት ራሱን ያስቀደመበት ነው በማለት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በቻይና ላይ መተማመን አጥቷል በማለት ያትታል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጌንግ ሹዋንግ እንዳሉት ፅሁፉ "ዘረኛ" እንዲሁም ቻይና የኮሮና ቫይረስን ወረረሽኝ እንዳይዛመት እያደረገች ያለችውን ጥረት ሆን ብሎ ለማቅለል ያለመ ነው ብለውታል። ወረርሽኙ እስካሁን የ2ሺ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል። " እንዲህ አይነት የዘረኝነት ፅሁፍን የሚፅፉ እንዲሁም ሆን ብለው በተንኮል ቻይናን ለመተንኮስ የሚፈልጉ ሚዲያዎችን የቻይና ህዝብ አይፈልጋቸውም" በማለት ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ምንም እንኳን የቻይና መንግሥት ከአገር የተባረሩትን ጋዜጠኞች ስም ባይጠቅስም ዎል ስትሪት ጆርናል ሁለቱ፣ ጆስ ቺን (ምክትል ኃላፊ) እና ቻዎ ዴንግ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ሲሆን አንደኛው ደግሞ የአውስትራሊያ ዜግነት ያለው ፊሊፕ ዌን ናቸው። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ የጋዜጠኞቹን መባረር አውግዘውታል። • ውጤት ለማሻሻል ወሲብን ተጠቅመዋል የተባሉት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ታገዱ • ኢትዮጵያዊቷ ከ20 ዓመት በኋላ የኤርትራዊቷን ቤት ሊያስረክቡ ነው ማይክ ፖምፔዮ ነፃ ፕሬስንም ሆነ ንግግርን ማገድ ተገቢ እንዳልሆነና የቻይና መንግሥት ስህተት ነው ብሎ ካመነ መሟገቻ ሃሳብ ማቅረብ ይገባ ነበር ብለዋል ባወጡት መግለጫ። የጋዜጣው አሳታሚ ዊልያም ሉዊስ በበኩላቸው ባወጡት መግለጫ በውሳኔው " ከልብ እንዳዘኑና" በዜና ክፍሉና በአስተያየት ፅሁፎች መካከል ግልፅ ያለ ልዩነት ያስፈልጋል ብለዋል። "ጋዜጣችን ላይ የተለያዩ እይታዎችን የምናስተናግድበት አስተያየት በተለያዩ ሰዎች ይፃፋሉ፤ እነዚህን እይታዎች ብዙዎች ሊስማሙማባቸው ወይም ላይስማሙባቸው ይችላሉ። ዋናው ነገር ግን እንዲህ የሚያስቀይም ነው ብለን አላሰብንም፤ ይሄ የኛም ፍላጎት አይደለም" ያሉት ሉዊስ " ነገር ግን ፅሁፉ የቻይናን ህዝብ በማበሳጨቱ የምንፀፀትበት ጉዳይ ሆኗል" ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ጋዜጠኞች ከቻይና እንዲለቁ ሲወጡ ሲነገራቸው ይህ በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው እንደሆነ የቢቢሲው ጆን ሱድዎርዝ ከቤጂንግ ዘግቧል። ጥያቄ የተነሳበት ፅሁፍ "የታመመው እስያዊ" (ዘ ሲክ ማን ኦፍ ኤዥያ) የሚል ርዕስ የተሰጠው ሲሆን በ18ኛውና 19ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ቻይናን ለመግለፅ ይጠቀሙበት የነበሩ "አስነዋሪ ቀላቶች ተካተዋል ተብሏል። • የህዳሴው ግድብ ድርድር ትኩረቱን ስቶ የውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ ሆኗል ተባለ • በጀርመን በተፈጸመ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ እነዚህ አስፀያፊ ቃላቶች ቻይና ውስጥ ያለውን የውስጥ ክፍፍል ከዓለም ኃያላን ጋር በማወዳደር የሚገልፁ ናቸው። እንደ ኒውዮርክ ታይምስ ከሆነ የዎል ስትሪት ጆርናል ጋዜጠኞች ራሳቸው ርዕሱ አስነዋሪ ስለሆነ እንዲቀየር ጎትጉተው ነበር በሚል ዘግቧል። የውጭ ሃገራት ዘጋቢዎች ማህበር በበኩሉ ውሳኔውን ፅንፈኛና ጋዜጠኞችን ለማስፈራራት የተደረገ ነው ብለውታል። በቅርቡ አሜሪካ በአገሯ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የቻይና መንግሥት ጋዜጠኞች ላይ ያሉ ህግጋትን ጠበቅ በማድረግ "የውጭ መልእክተኞች" በሚል መድባቸዋለች። ዢኑዋን ጨምሮ ለቻይና ግሎባል ቴሌቪዥን ኔትወርክ የሚሰሩ ሰራተኞቻቸውንም ዝርዝር እንዲሰጧቸው የጠየቀች ሲሆን፤ በሚያደርጉት ዘገባ ምንም ክልከላ የለም ተብሏል።
news-55317805
https://www.bbc.com/amharic/news-55317805
ፕሬስ ነፃነት፡ ኢትዮጵያና ቤላሩስ የጋዜጠኞች እስር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረባቸው አገራት ናቸው-ሲፒጄ
የዘንድሮው ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መጠን በርካታ ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ተቋም ሲፒጄ ዛሬ ባወጣው ሪፖርቱ አስታወቀ።
ስለ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ፣ ስለ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሲዘግቡ የነበሩ ጋዜጠኞች መታሰራቸውንም ሪፖርቱ አመልክቷል። "በወረርሽኙ ወቅትም የጋዜጠኞቹ የፍርድ ሂደት ተጓቷል፤ እስር ቤትም በበቂ ሁኔታ እንዳይጠይቁ ሆኗል፤ እስር ቤት እያሉም ጤንነታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ለአደጋ ሊያጋልጥ የሚችሉ ሁኔታዎችን እያዩ ችላ ተብለዋል" በማለት በዚህም ምክንያት ቢያንስ ሁለት ጋዜጠኞች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መሞታቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል። እስከ ኅዳር 2013 ዓ.ም ድረስ ቢያንስ 274 ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል ብሏል። ኢትዮጵያና ቤላሩስ የጋዜጠኞች እስር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ የመጣባቸው አገራት መሆናቸውን ሲፒጄ በሪፖርቱ ገልጿል። ለዚህም በኢትዮጵያ ከነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ጀምሮ ወደ ወታደራዊ ግጭት ያመራውን ክስተት ተከትሎ በርካታ ጋዜጠኞች መታሰራቸውን አመልክቷል። በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ታስሮ የነበረው ጋዜጠኛ አንድ ብቻ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ቢያንስ ሰባት ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንዳሉ ሲፒጄ ገልጿል። በምስራቅ አፍሪካ አገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በኤርትራ፣ ካሜሩን ፣ ሩዋንዳ፣ ብሩንዲ፣ ማሊ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳ እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በአጠቃላይ 45 ጋዜጠኞች ታስረዋል። በምስራቅ አፍሪካ በዘንድሮው ዓመት የታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥር ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ጭማሬ አሳይቷል። በቤላሩስም የጋዜጠኞች እስር ለመጨመሩ ለረዥም ጊዜ በሥልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዚደንት በድጋሜ መመረጥን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ ምክንያት ነው ብሏል። በአገሪቷ እስከ ኅዳር 22 ድረስ ቢያንስ 10 ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል። በርካታ ጋዜጠኞች የታሰሩባቸው አገራት ቻይና፦ቻይና ኮቪድ -19 ወረርሽኝን በተመለከተ የሚዘግቡ በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ለታከታታይ ሁለት ዓመት በርካታ ጋዜጠኞችን ያሰረች አገር ሆና ተመዝግባለች። በቻይና 47 ጋዜጠኞች የታሰሩ ሲሆን አብዛኞቹ ለረዥም ጊዜ በእስር የቆዩና ለምን እንደታሰሩ እንኳን ሳይገለፅ ለእስር የተዳረጉ ናቸው። ቱርክ፦በዋስ የተፈቱ ጋዜጠኞችን ፍርድ ቤት በማቅረብ እንዲሁም አዳዲስ ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛ ሆናለች። ቱርክ በዚህ ዓመት 37 ጋዜጠኞችን አስራለች። ይህ ቁጥር ከ2008 ጋር ሲነፃፀር በግማሽ ያነሰ ቢሆንም ባለሥልጣናት አሁንም ጋዜጠኞችን ማስሩን ቀጥሏል ብሏል ሲፒጄ። ግብፅ፦ ግብፅ ደግሞ በምንም ዓይነት ወንጀል ሳይከሰሱ ጋዜጠኖችን የምታስር አገር ተብላለች። በአገሪቷ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ቁጥር 27 የደረሰ ሲሆን በ2008 ዓ.ም የተመዘገበውን ከፍተኛ ቁጥር ጋር የሚስተካከል ነው።በአገሪቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎም በጋዜጠኞች ላይ የሚፈፀመው እንደቀጠለ ሲፒጄ በሪፖርቱ ጠቅሷል። ሳዑዲ አረቢያም ጋዜጠኞች በማሰር ግብፅን ተከትላ ተቀምጣለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ በእስር ላይ ከሚገኙ ጋዜጠኞች መካከል ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት የተከሰሱት በሽብር እና በሕግ በታገዱ ቡድኖች አባልነት ምክንያት መሆኑንም ሲፒጄ በሪፖርቱ አትቷል። ሲፒጄ በሪፖርቱ የተገለፀው የጋዜጠኞች ቁጥር እስከ ኅዳር 2013 ዓ.ም ድረስ በእስር ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ቁጥር መሆኑን በመጥቀስ ዓመቱን ሙሉ ሲታሰሩና ሲፈቱ የነበሩ የጋዜጠኞችን ዝርዝር አለማካተቱን አክሏል።
news-55074073
https://www.bbc.com/amharic/news-55074073
ፖሊሶች በአንድ ጥቁር ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ፕሬዝዳንት ማክሮን አወገዙ
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሦስት ፖሊሶች ፓሪስ ውስጥ አንድ ጥቁር ሙዚቀኛን ሲደበድቡ የሚያሳይ ቪዲዮ መውጣቱን ተከትሎ ድርጊቱን "ተቀባይነት የሌለውና አሳፋሪ" ሲሉ አወገዙ።
በፖሊሶች የተደበደበው ማይክል ዘክለርን በዚህም ሰበብ በፖሊስና በዜጎች መካከል መተማመንን እንደገና ለማጎልበት ያለሙ ሐሳቦች እንዲቀርቡም ጠይቀዋል። ፈረንሳይ "ለአመፅ መፈጠር፣ ለጥላቻ ወይም ለዘረኝነት መስፋፋት" መንገድ ልትከፍት አይገባም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። በቪዲዮው ላይ ማይክል ዘክለርን ሲደበድቡ የሚታዩት ሦስት የፖሊስ መኮንኖች ከሥራ የታገዱ ሲሆን ቁጥጥር ስር ውለዋል ምርመራም እየተደረገባቸው ነው። የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ዠራልድ ዳርማኒን "የሪፐብሊኩን ዩኒፎርምን ያረከሱ" በመሆናቸው መኮንኖቹ ከሥራ እንዲሰናበቱ ግፊት እንደሚያደርጉ ለፈረንሳይ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በፈረንሣይ ዋና ከተማ የተቀረፀው ቪዲዮ ለሕዝብ ይፋ ከተደረገ በኋላ ቁጣቸውን ከገለጹት መካከል ለፈረንሳይ የዓለም ዋንጫን ያነሱት የእግር ኳስ ኮከቦች ይገኙበታል። የፈረንሣይ መገናኛ ብዙሃን አንድ ባለሥልጣን ጠቅሰው ፕሬዝደንት ማክሮን በተፈጠረው ክስተት እንደተበሳጩ መግለጻቸውን ዘግበዋል። ማክሮን በተከታታይ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሁሉንም ዓይነት አድሎዎችን በተሻለ ሁኔታ ለመዋጋት ሀሳቦች ያስፈልጋሉ ብለዋል። "ሕጉን የሚያስከብሩ አካላት ሕጉን ማክበር አለባቸው። በዕለት ተዕለት ህይወታችን እኛን ለመጠበቅ በድፍረት የሚሰሩትን አንዳንዶች የሚያደርጉት የሚያረክሰው በመሆኑ በጭራሽ አንቀበልም" ብለዋል። ፈረንሳዊው የእግር ኳስ ኮከብ ክሊያን ምባፔ የቅርብ ጊዜውን ክስተት በማውገዝ ከብሔራዊ ቡድኑ እና ከሌሎች ስፖርተኞች ጋር ተቀላቅሏል። "ሊቋቋሙት የማቻል ቪዲዮ፣ ተቀባይነት የሌለው ብጥብጥ። ዘረኝነትን አልቀበልም ይበሉ" ሲል በደም የተሸፈነውን ፕሮዲውሰር ምስል ተጠቅሞ በትዊተር ገጹ ገልጿል። የደኅንነት ካሜራ ቪዲዮው ሐሙስ ዕለት ነበር ይፋ የተደረገው። ግለሰቡ ስቱዲዮው ከገባ በኋላ ሦስት ፖሊሶች ሲረግጡት፣ በቡጢ ሲመቱት እና ሲደበድቡት ይታያል። ግለሰቡ መጀመሪያ ላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ባለመያዙ እንዲቆም ተደርጎ እንደነበር ተገልጿል። ዘክለር በአምስቱ ደቂቃ ድብደባ ወቅት የዘረኝነት ጥቃት እንደደረሰበት ተናግሯል። በእምቢተኝነት ተከሶ በቁጥጥር ሰር ቢውልም ዐቃቤ ሕግ ክሱን ውድቅ አድርገው በፖሊሶቹ ላይ ምርመራ ከፈተዋል። አቤቱታውን ለማቅረብ ከጠበቃው ጋር የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት የሄደው ዘክለር ለጋዜጠኞች "እኔን መጠበቅ የነበረባቸው ሰዎች ጥቃት ሰንዝረውብኛል። ለዚህ የሚያበቃ ምንም ነገር አላደረግኩም። ሦስቱም በሕጉ መሠረት እንዲቀጡ እፈልጋለሁ" ብሏል። የፓሪስ ከንቲባ አን ሂዳልጎ "በድርጊቱ በጣም ደንግጫለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፈረንሣይ መንግሥት አወዛጋቢውን የፀጥታ ረቂቅ አዋጅ እንዲወጣ እየሠራ ሲሆን ተቃዋሚዎች ግን ሕጉ የመገናኛ ብዙሃን የፖሊስ ባህሪን የመመርመር አቅማቸውን ያዳክማል በሚል እየተቹት ነው። የረቂቅ ህጉ አንቀጽ 24 እንደ ግለሰብ ለጥቃት ይጋለጣሉ ተብለው የሚገመቱ የፖሊስ ወይም የጦር ሠራዊት አባላት ምስሎችን በማህበራዊ ድር አምባዎች ላይ መለጠፍ እንደ ወንጀል ይቆጠራል። የሕጉ ተቺዎች እንደሚሉት እንደዚህ ያሉ ምስሎች ይፋ ካልሆኑ ባለፈው ሳምንት እወንደወጡት ካሉት ክስተቶች መካከል አንዳቸውም ይፋ አይወጡም ነበር። መንግሥት አዲሱ ረቂቅ ሕግ የፖሊስ በደሎችን ሪፖርት የሚያደርጉ መገናኛ ብዙሃን እና ዜጎች መብት ላይ አደጋ አያደርስም ሲል ይከራከራል። ትችቱን ተከትሎ መንግስት አንቀፅ 24 ላይ ማሻሻያ በማከል "የፖሊስ መኮንን ወይም የወታደርን አካላዊ ወይም ሥነልቦናዊ ታማኝነትን ለመጉዳት በግልጽ ያነጣጠሩ ምስሎችን ማሰራጨት ላይ ብቻ ያተኮረ" መሆኑን አስታውቋል። ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ሰዎች በአንድ ዓመት እስራት ወይም እስከ 40 ሺህ ፓውንድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
news-50640643
https://www.bbc.com/amharic/news-50640643
ፈጣን ለውጥና ጭቆና በሳኡዲ አረቢያ
በሪያድ ዓለማቀፍ ስታዲየም የብራዚልና አርጀንቲና ብሄራዊ ቡድኖች ግጥሚያቸውን ሲያደርጉ አንድ ያልተለመደ ነገር ተስተዋለ። የሳኡዲ ሴቶች ፊታቸውና እና ጸጉራቸውን የሚሸፍነውን ሂጃብ አውልቀው እያውለበለቡ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።
አይደለም ሳይሸፋፈኑ መውጣት፣ ሴቶች ያለወንዶች አጃቢነት መንቀሳቀስ በማይችሉባት ሃገር እንዲህ አይነቱን ነገር መመለከት እንግዳ ሊመስል ይችላል። • ሳዑዲ ያልተጋቡ ጥንዶች ሆቴል እንዲከራዩ ፈቀደች • ሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ያለ ጠባቂ እንዲጓዙ ፈቀደች የአሁኗ ሪያድ፣ አሁን ካለው ዘመናዊ አስተሳሰብ ጋር ለመቀራረብና የሌሎች ሃገራት ዜጎችን ለመሳብ በከፍተኛ ለውጥ ውስጥ ትገኛለች። ከዚህ በፊት ማንኛውም ሰው ወጣ ብዬ አንዳንድ ነገሮች ልግዛ ቢል እንኳን የጸሎት ሰአት ሲደርስ የሱቆች በር መዘጋት ይጀምራሉ። የሱቆቹ ሰራተኞች ሃይማኖታዊ ፖሊሶችን በጣም ነው የሚፈሩት፤ በጸሎት ሰአት ሲነግድ የተገኘ የማያዳግም ርምጃ ይወሰድበታል። የሳኡዲ ወጣቶችም ቢሆኑ እንደልባቸው እዚም እዚያም ተንቀሳቅሰው ነገሮችን ማከናወን አይችሉም ነበር። ያቺኛዋ ሪያድ አሁን የለችም። በእጅጉ እየተቀየረችም ትገኛለች። ለዜጎች መተንፈሻ የሚሆኑ የህዝብ መዝናኛዎች እዚም እዚያም የሚታዩ ሲሆን ሃይማኖታዊ ፖሊሶችም ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ ተደርገዋል። ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች አንዲት ወጣት ለቢቢሲ እንደገለጸችው ሴቶች በሪያድ ጎዳናዎች ላይ መኪና እንዲያሽከረክሩ መፈቀዱ ለብዙ ነገሮች በሩን ከፍቷል። ምንም እንኳን እሷ ገና የመንጃ ፈቃዷን ባታገኝም ብዙ ሴቶች መኪና ሲያሽከረክሩ መመልከት እንደ ተአምር እንደሆነ ትገልጻለች። ሌላው ቀርቶ ሴት ጓደኞቿ የራሳቸውን ቤት ተከራይተው መኖር መጀመራቸው ከጥቂት ዓመታት በፊት የማይታሰብ እንደነበር ታስታውሳለች። በአሁኑ ሰአት በመላው ሪያድ ለሁለት ወራት የሚቆይ የአደባባይ መዝናኛ ድግስ የተዘጋጀ ሲሆን ክፍት ሲኒማዎች፣ ሰርከስና የሙዚቃ ኮንሰርቶችንም ጭምር ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል። በአስርታት የሚቆጠሩ ምግብ ቤቶች ውስጥ ሴቶችና ወንዶች ያለምንም ገደብ እንደልባቸው ሲዝናኑ ይስተዋላል። • መገደል፣ መደፈር፣ መዘረፍ ማብቂያ የሌለው የኢትዮጵያውያን የስደት ጉዞ በቅርቡ ደግሞ የሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ያለ ወንዶች ጥበቃና ፈቃድ ፓስፖርት እንዲያወጡና ከአገር ውጭ እንዲጓዙ መፍቀዷ የሚታወስ ነው። እስካሁን ድረስ የሳዑዲ ሴቶች ፓስፖርት ለማግኘትና ወደ ሌላ አገር ጉዞ ለማድረግ ከትዳር አጋራቸው፣ ከአባታቸው አሊያም ከሌላ ወንድ ዘመዳቸው ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸው ነበር። ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን የሴቶችን በሥራ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ከነበረው 22 በመቶ ወደ 30 በመቶ ከፍ በማድረግ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በ2030 ለማሳደግ ዓላማ ይዘው እየሠሩ መሆናቸውን ከሦስት ዓመታት በፊት አስታውቀው ነበር።
news-57159217
https://www.bbc.com/amharic/news-57159217
ፍራቻና ኃዘን የተቀላቀለበት የእስራኤል-ጋዛ ሁኔታ በፎቶዎች
በእስራኤልና በፍልስጥኤም የተነሳው ግጭት የሰላማዊ ዜጎችን ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል፤ ምንም እንኳን በርካታ አገራት የተኩስ አቁም ስምምነቶች ላይ እንዲደረስ ግፊት ቢያደርጉም ፍሬያማ አልሆነም። ግጭቱ ከፍ ወዳለ ጦርነት እንዳያመራም ተሰግቷል።
በእስራኤል አየር ጥቃት የወደመ ፋብሪካ በጋዛ በባለፉት ቀናት የተሰነዘሩ የአየር ጥቃቶችና ሮኬት መወንጨፎች የበርካቶችን ህይወት ቀጥፈዋል፤ ህንፃዎችን አውድመዋል፤ በርካቶች መኖሪያ አልባ እንዲሆኑና እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆነዋል። ቤታቸው በአየር ጥቃት የወደመባቸው ፍልስጥኤማውያን ቤተሰቦቻቸውን ከፍርስራሹ ለማውጣት እየሞከሩ ነበር እስራኤል የምታደርገው የአየር ጥቃት ኢላማ ያደረገው የፍልስጥኤም ታጣቂዎችን ነው ብትልም በጥቃቱ የኤሌክትሪክ መስመሮች ተቋርጠዋል፤ ዋና ዋና ጎዳናዎች ፍርስርሳቸው ወጥቷል። ከላይ በሚታየው ምስል ባለፈው ሳምንት እሁድ በእስራኤል አየር ጥቃት ቤቱ የፈረሰበት ፍልስጥኤማዊ እጥፍ ብሎ በሃዘን ተሰብሮ ይታያል። አንዳንድ የቤተሰቦቹ አባላት በህንፃው ፍርስራሽ ተቀብረዋል። በእስራኤል ጥቃት ቤተሰቦቿ የተገደሉባት ፍልስጥኤማዊት ሴት ከሳምንት በፊት ግጭት የተነሰባት ጋዛ በርካታ ሰዎች የሞቱባት እለት በባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ነው። እስራኤል ከሌሊት በኋላ ባደረገችው የአየር ጥቃት እንቅስቃሴ የበዛበት ጎዳንን ኢላማ ያደረገች ሲሆን፤ በርካታ ህንፃዎች እንዳልነበሩ ወደሙ። የበርካቶችም ህይወት ተቀጠፈ። "በጋዛ የፈረሱትን መልሶ ለመገንባት ቢያንስ አስር አመታት ያስፈልገናል" በማለት የህፃናት ዶክተር የሆኑት መሃመብ አቡ ራያ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በግዛቲቱም ለበርካቶች የኃዘን ስነ ስርዓት ተደርጓል። በሃማስ ሮኬት ጥቃት ምክንያት ራሳቸውን ከቦንብ ፍንዳታ ለመከላከል ወደ መጠለያ ካመሩ መካከል ይህች ህፃን አንዷ ነበረች ጋዛን የሚያስተዳድረው ሃማስና ሌሎች የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ሮኬቶችን ወደ ደቡባበዊ እስራኤል በማስወንጨፍ ላይ ናቸው። በዚህም የተነሳ ህንፃዎችና ቤቶች የፈራረሱ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ራሳቸውን ከፍንዳታ ለመከላከል ወደ ቦንብ መጠለያዎች አምርተዋል። ከጋዛ ሰርጥ የተወነጨፈው ሮኬት ቤቷን የመታው እስራኤላዊት የደረሰውን ጉዳት ስትገመግም የእስራኤል መከላከያ እንዳስታወቀው ወደ ግዛታቸው ከተወነጨፉ ሮኬቶች መካከል 90 በመቶ የሚሆነውን ማክሸፋቸውን ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሮኬቶች ከጎረቤት አገር ሊባኖስ ወደ ሰሜን እስራኤል ተወንጭፈዋል። በዌስት ባንክ የተገደለው ፍልስጥኤማዊው ያሲን ሃማድ ቤተሰቦች አስከሬን ሲወሰድ በኃዘን ተሞልተው እየሸኙ ግጭቱ በእስራኤል ቁጥጥር ስር ወዳለችው ዌስት ባንክ ግዛት የተዛመተ ሲሆን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በእስራኤል ወታደሮችና በፍልስጥኤማውያን መካከል ግጭት ተፈጥሯል። ፍልስጥኤማውያን አረቦች በዌስት ባንክ በእስራኤል ወታደራዊ አገዛዝና በተወሰነላቸው የራስ አገዛዝ ስር ይኖራሉ። በጋዛ አየር ጥቃት ከህንፃ ፍርስራሽ የተረፉት ሪያድ ኤሽኩንታናና የስድስት አመት ሴት ልጁ በሆስፒታል ውስጥ ህፃኗ ለሰዓታት ያህል በቤታቸው ፍርስራሽ ውስጥ ተቀብራ የነበረ ሲሆን ከአባቷም ጋር በሆስፒታል እየታከመች ትገኛለች። "ልጄ ይቅር በይኝ። ወደ አንቺ እንድመጣ እየነገርሸኝ ነበር፤ መምጣት አልቻልኩም" በማለት ከልጁ ጋር ሲገናኝ ፍልስጥኤማዊው ሪያድ ተናግሯል። በአስራኤል አየር ጥቃት አባቱና የአጎቱ ልጅ የተገደለበት ፍልስጥኤማዊ ታዳጊ በአል ሺፋ ሆስፒታል እያለቀሰ በእስራኤል አየር ጥቃት የ12 አመት ልጁ የተገደለችበት ራሃፍ አል ዳየር የልጁን የተሸፈነ አስከሬን ይዞ እያለቀሰ ግጭቱ ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን የአየር ጥቃቶችና ሮኬት መወንጨፎች ቀጥለዋል። አሜሪካን ጨምሮ የአለም ኃያል አገራት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲኖር ቢጠይቁም ምንም የተቀየረ ነገር የለም። በጋዛ ድንበር ግጭት የተገደለ እስራኤላዊ ወታደር ቤተሰቦች እያለቀሱ
news-45443683
https://www.bbc.com/amharic/news-45443683
የሶማሌ ክልል የቀድሞው ሰንደቅ አላማ ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውል ተወሰነ
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጠራው ልዩ ስብሰባዉ የቀድሞ የክልሉ ሰንደቅ አላማ ተመልሶ የክልሉ መለያ ሆኖ እንዲያገለግል ወሰነ።
ከዓመታት በፊት ለውጥ ተደርጎበት የነበረው በከፊል የሶማሊያ የሰንደቅ ዓላማ ሰማያዊ ቀለምና ነጭ ኮከብ ያለው ሰንደቅ ተመልሶ እንዲያገልግል ተወስኗል። ቀደም ሲል የነበረው ሰንደቅ አላማ በከፊል ቢጫ ቀለምና የግመል ምስል ይዞ ቆይቶ ነበር። በቅርቡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ዑመር በፌስቡክ ገጻቸው በክልሉ ሰንደቅ አላማ ላይ ለውጥ መደረጉን በተመለከተ በማህበራዊ ገፃቸው ላይ "በሶማሌነታችንና በኢትዮጵያዊነታችን መሀከል ተቃርኖ የለም" ሲሉ አስፍረዋል። • አብዲ ሞሃመድ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ • ሙስጠፋ ኡመር የሶማሌ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ የቀድሞው ሰንደቅ አላማ ተመልሶ ሥራ ላይ መዋል መጀመሩን በተመለከተም "የሶማሌ ክልል ህዝቦች ነን፤ ከፊትም ከኋላም ቅጥያ የለም፤ የቀደመው ሰንደቅ አላማ ተመልሷል" በማለት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በገፃቸው ላይ ገልፀዋል። የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደድር አቶ አብዲ ሙሀመድ ዑመር ከስልጣን ከተነሱ በኋላ የተተኩት አቶ ሙስጠፋ ዑመር፤ "የሶማሌነት መገለጫችንን በኩራት ስንጠብቅ ብሔራዊ ግዴታችንንም ባለመዘንጋት ነው" ብለዋል። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት በዛሬው ልዩ ስብሰባው አዲስ አፈ-ጉባኤ ለምክር ቤቱ የሰየመ ሲሆን ለዳኞችም ሹመት ሰጥቷል።
53996764
https://www.bbc.com/amharic/53996764
"ለ15 ዓመታት ኮንዶሚኒየም እየጠበቅኩ ሁለት ልጆች ወልጃለሁ" የአዲስ አበባ ነዋሪ
"ለ15 ዓመታት ኮንዶሚኒየም እየጠበቅኩ ሁለት ልጆች ወልጃለሁ" ይህ የተሰማው ስሜ አይጠቀስ ካሉ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ነው።
ቤት የመኖር ተስፋቸውን ሰንቀው የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ይደርሰኛል ብለው የተመዘገቡት በ1997 ዓ.ም ነበር። የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሰጣቸው በማህበር ተደራጅተው ከተመዘገቡት የመጀመሪያው ዙር ተመዝጋቢም መካከል ናቸው። ለአስራ አምስት ዓመታትም ያህል ቤት ይደርሰኛል ብለው ጠብቀዋል። በእርሳቸው ማህበር ውስጥ ከሚገኙት ከሃያ አባላቱ በላይ በሙሉ የቤት ባለቤት ቢሆኑም እርሳቸው ግን አልደረሳቸውም። ከእርሳቸው የሚጠበቅባቸውን በየወሩ ምንም ሳያዛንፉ ከመቆጠባቸውም አንፃር ለምን አልደረሰኝም ብለው ሲያስቡም የሚሰጡት ምክንያት "ዕጣው ፍትሃዊ ስላልሆነ ነው" የሚል ነው። "በመተዋወቅና በመጠቃቀም ቢሆን ነው እንጂ ይህንን ያህል ዓመት ጠብቄ የማይደርሰኝ ምክንያት የለውም" ይላሉ። ከዚያም በተጨማሪ ያልተመዘገቡ ሰዎች ቤት እየተሰጣቸው እንደሆነም ሲሰሙ ይህንኑ ጥርጣሬያቸውን አረጋገጠላቸው። ሆኖም ለዓመታትም ቤት ይኖረኛል በሚል ተስፋም የቆጠቡትን ብር ሊነኩም አልፈለጉም "ለሌላ ነገር እንዳላደርገው ሁሉ ይዞኛል" ይላሉ። ሲመዘገቡ ገና ወንደላጤ ነበሩ አሁን ሁሉ ተቀይሮ ትዳር ይዘዋል። የሁለት ልጆች አባት ሆነዋል፤ ሆኖም የተመዘገቡት ኮንዶሚኒየም የውሃ ሽታ በመሆኑ "ላም አለኝ በሰማይ..." ሆኖባቸዋል። ለአመታትም የኮንዶሚኒየም ዕጣ ሲወጣ በጉጉት ይጠብቃሉ። ይከታተላሉ ግን አልሆነም። የሚያውቋቸው ሰዎች ቤት አግኝተው ሳይኖሩበት ወይ ሲሸጡት ሲያዩ እርሳቸው በኪራይ ቤት መንከራተት ያሳዝናቸዋል። በተከታታይም ቤቶች ልማት ሄደው ሲጠይቁም የተመዝጋቢዎች ዝርዝር ውስጥ እንዳሉ ይነግሯቸዋል። "ሌሎች ሰዎች እየደረሳቸው ነው እንዴት ነው ነገሩ ብለን ስንጠይቅም 'ያው ስምህ አለ'" ከማለት ውጭ ሌላ ምላሽ ለዓመታት አልተሰጣቸውም። "ጠብቅ" የሚለውም ምላሽ ተስፋ እያስቆረጣቸው እንደመጣ የሚናገሩት እኚህ ግለሰብ፤ ከሰሞኑ ደግሞ ከህገወጥ መሬት ወረራና ኢ-ፍትሃዊ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ ጋር ተያይዞ በሚሰሙ መረጃዎች የነበረቻቸውም ትንሽ ተስፋ ተሟጠጠች። "በጣም ያሳዝናል፤ ያሳፍራል፤ ከዚህ በኋላ ተስፋ አላደርግም" ይላሉ። ቤት (መጠለያ) መሰረታዊ ጥያቄና መብት ቢሆንም በኢትዮጵያ ባሉ ትልልቅ ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ ሰዎች የግል ቤት መኖር ማለት እንደ ቅንጦት የሚታይበት ነው። በርካቶች በማይቀመስ ኪራይ ብራቸውን እየገፈገፉ ለመኖርም ተገደዋል። ገዝቶ የቤት ባለቤት መሆን የሚታሰብ ባይሆንም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የጥራትና ሌሎች ጉድለቶች ቢኖርባቸውም፤ ለብዙዎች የቤት ባለቤት የመሆን ተስፋቸው ሆኖ ቆይተዋል። ሆኖም ለዓመታት ጠብቀው ቤት ሳያገኙ የቀሩ እንዲሁም ቤቱ ደርሷቸው ያልተቀበሉ በርካቶች አሉ። ሌላኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ በ40/60 የቁጠባ ፕሮጀክት ተመዝግበው በሁለተኛው ዙር የቤት እጣ እድለኛ እንደሆኑ ተነገሯቸው። ከስድስት ዓመታት በፊት ተመዝግበው ዕጣው ወጥቶ ቤቱ ከደረሳቸው በኋላ፤ በድልድሉ መሰረት ውል ቢዋዋሉም ቤቱን ሳይረከቡ አንድ ዓመት አለፋቸው። ሙሉውን መክፈል የሚችሉ መቶ በመቶ እንዲከፍሉ ካለበለዚያ ደግሞ በወጣው እቅድ መሰረት አርባ በመቶ ከፍለው ቀሪውን ደግሞ ከባንክ ጋር ውል ተፈፅሞ ቤታቸውን እንዲረከቡ ነበር። የዛሬ ዓመትም የሚጠበቅባቸውን አርባ በመቶ ክፍያ ከፈፀሙ በኋላ ቁልፍ ለመረከብና ከቤቶች ልማትም ቤታቸውን ሊረከቡ የደረሳቸው ነገርም የለም። በቅርቡ እንዲሁ እጣ የደረሳቸው ሰዎች በማህበር ሲደራጁ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲነገሩም ቤቱ አልቋልና ተረከቡ ተብለው ወደደረሳቸው አካባቢ ሄዱ። በሁለተኛው ዙር 18 ሺህ ያህል እድለኞች መኖራቸውን የሚናገሩት እኚሁ ግለሰብ "ልንረከብ ሄደን ቤቱ አላለቀም፤ ቁልፍ ልንረከብ ሄደን ጭራሽ ቤቱ በር የለውም፤ ይሄ እንዴት ይሆናል? የማይሆን ሥራ ነው እየሰሩብን ያሉት" ብለዋል። የአያት አካባቢ ነዋሪ የሆኑት እኚሁ ግለሰብ በሚኖሩበት አካባቢ የሚገኙ መሬቶች በአስደናቂ ፍጥነት መታጠራቸው ጥያቄያቸውን አጭሮታል። በሳምንቱ መጀመሪያ፣ ሰኞ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተባባሰ የመጣ፣ የመንግሥታዊ መዋቅሮች ድጋፍ ያለው ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ እንዳለ ባካሄድኩት ጥናት ደርሼበታለሁ ሲል ማስታወቁ ይታወሳል። የጋራ ቤቶችን በተመለከተም የከተማው አስተዳደር ባወጣው ደንብ መሰረት "በምንም መስፈርት የቤት ተጠቃሚ ሊሆኑ የማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤትና የነዋሪነት መታወቂያ ተሰጥቷቸዋል" ሲል በጋራ የመኖሪያ ቤቶች በኩል አሉ ያላቸውን የአሰራር ችግሮች ጠቅሷል። ጥናቱ እንዳለው በከተማዋ የተለያየ አይነት ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ ተግባራት እንደተከናወኑ አመልክቶ፤ እነዚህም በጅምር ቤት ስም ከባለ ይዞታዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በመግዛት ግንባታ የማካሔድ፣ ባዶ መሬቶችን በቡድንና በግለሰብ ደረጃ በማጠር የመያዝ እንዲሁም ለሌላ ወገን የማስተላለፍ በተጨማሪም "በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በተዘረጋው ሰንሰለት በጥቅም ተጋሪነትና በዝምድና" ሠፋፊና ቁልፍ ቦታዎችን መያዝ በከተማዋ ውስጥ መታየቱን ገልጿል። የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የአሁኑ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በበኩላቸው፤ በቀጥታ የኢዜማን ጥናት ባይጠቅሱም ማክሰኞ ዕለት በፌስቡክ ገጻቸው ላይ በሰጡት ምላሽ የቀረበውን ሪፖርት " ሐሰተኛ" ብለውታል። አቶ ታከለ እንዳሰፈሩት "የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ስንወስድበት የቆየንበት ጉዳይ ነው" ብለዋል።
51414512
https://www.bbc.com/amharic/51414512
ኮሮናቫይረስ፡ በዉሃን ከሚገኙ ኢትዮጵያውን ተማሪዎች 95 በመቶ መመለስ ይፈልጋሉ
ኮሮናቫይረስ በቀሰቀሰባት ዉሃን ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች መንግሥትን 'ወደ አገራችን' ይመልሰን ሲሉ ለሁለተኛ ጊዜ ጠየቁ።
በዉሃን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች 95 በመቶዎ የሚሆኑት መመለስ እንደሚፈልጉ በበተነው መጠይቅ ማረጋገጡን በዉሃን የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ለቢቢሲ አስታውቋል። የህብረቱ ፕሬዝደንት ዘሃራ አብዱልሃዲ እንደገለፀችው በመጠይቁ ከተሳተፉ ተማሪዎች መካከል 41 በመቶ የሚሆኑት መንግሥት ወጪያችንን ሸፍኖ ወደ አገራችን ይመልሰን ያሉ ሲሆን፤ 54 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በራሳችንም ወጪ እንመለሳለን መንግሥት ግን ጉዟችንን ያመቻችልን ሲሉ ፍላጎታቸውን አስታውቀዋል። ቀደም ሲል የተማሪዎቹን 'ወደ ኢትዮጵያ መልሱን' ጥያቄን ህብረቱ በቻይና ለኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዳቀረበ የምታስታውሰው ዘሃራ፤ አሁንም የተማሪው ጥያቄ እጅግ እየገፋ በመምጣቱ መጠይቅ በትነው የተማሪውን ወደ አገራችን መልሱን ጥያቄ በጥናት ማረጋገጣቸውን ታስረዳለች። ዘሃራ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች፤ እንዲሁም የሟቾችም ቁጥር እየጨመረ መሆኑን በመጥቀስ "ተማሪው ከባድ የስነልቦና ጫና ውስጥ ነው ያለው" ትላለች። በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጥያቄ በቀረበለት ወቅት 'የተማሪዎቹን ጥያቄ ለመመለስ ሁኔታዎችን እያጤንን ነው' የሚል ምላሽ ለቢቢሲ ሰጥቶ ነበር። በዉሃን የተማሪዎች ህብረት በጥናት የተደገፈውን የአሁኑን የተማሪዎች ጥያቄ ለኤምባሲው ያቀረበው ከአራት ቀናት በፊት እንደሆነ ዘሃራ ብትናገርም፤ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሽን መሪ አቶ ገነት ተሾመ ይህ መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። አቶ ገነት ምንም እንኳ ይህ መረጃ የለኝም ይበሉ እንጂ ኤምባሲው በቀደመው ጥያቄው መሠረት ሁኔታዎችን እና ያሉ አመራጮቹን ማጤኑን እንደቀጠለ ተናግረዋል። በዉሃን ሶስት መቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን ከትምህርት ውጭ በሌሎች መስኮች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ይህ ነው የሚባል እንዳልሆነ ቢቢሲ ከኤምባሲው ያገኘው መረጃ ያመላክታል። ኮሮናቫይረስ ከተቀሰቀሰባት የቻይናዋ ዉሃን ከተማ የሚመጡ መንገደኞችን በለይቶ ማከሚያ ለማስቀመጥ መወሰኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ ማስታወቁ ይታወሳል።
news-50285514
https://www.bbc.com/amharic/news-50285514
ማክዶናልድ ከበታች ሠራተኛው ጋር ግንኙነት መሥርቷል ያለውን ዋና ስራ አስፈፃሚ አባረረ
ማክዶናልድ የተሰኘው የፈጣን ምግብ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚውን ከበታች ሠራተኛው ጋር የፍቅር ግንኙነት መሥርቷል በሚል አባሮታል።
እንግሊዛዊው ስቲቭ ኢስተርብሩክ የመሠረተው ግንኙነት በፈቃድ ላይ የተመሠረተ ቢሆንምመ የኩባንያውን መመሪያ በመጣሱ ነው ሊባረር የቻለው ብሏል ድርጅቱ። ሥራ አስፈፃሚውም ቢሆን ድርጊቱን መፈፀሙን አልካደም፤ እንዲያውም ጥፋተኛ ነኝ ሲል የበታች ሠራተኞቹን ይቅርታ ጠይቋል። • አሰልጣኙ ቡድናቸው በሰፊ ውጤት በማሸነፉ ተቀጡ የ52 ዓመቱ ፈት ስቲቭ 1993 [በግሪጎሪ አቆጣጠር] ላይ ነበር ማክዶናልድን የተቀላቀለው። በወቅቱ ሎንዶን የሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ኃላፊ ሆኖ ነበር የተቀጠረው። እስከ 2011 ከሠራ በኋላ ለቆ አንድ ሁለት ድርጅቶችን ሲያገለግል ቆየ። 2013 ግድም ዳግም ሲቀጠር የሰሜን አውሮፓ እና የእንግሊዝ ቅርንጫፎች ኃላፊ በመሆን ነበር። ስቲቭ የማክዶናልድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኖ የተሾመው ከአራት ዓመታት በፊት ነው። በእርሱ ዘመን ማክዶናልድ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል ትርፋማም ሆኗል ተብሎ ይነገርለታል። • ኩዌት በድረገጽ ሰዎችን ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረች ማክዶናልድ ለበታች ሠራተኞች በሚከፍለው እና ለኃላፊዎች በሚከፍለው መካከል ባለው ልዩነት ምክንያት ብዙ ይተቻል። ስቲቭ ኢስተርብሩክ የ2018 ዓመታዊ ገቢው 15.9 ሚሊዮን ዶላር [473 ሚሊዮን ብር ገደማ] ነበር። አማካይ የበታች ሠራተኞች ዓመታዊ ገቢ ግን 7400 ዶላር ነው። ስቲቭ የማክዶናልድ የአሜሪካ ኃላፊ በሆነው ክሪስ ካምፔዝኒስኪ ተተክቷል። • የዓለማችን ትርፋማው ድርጅት አክሲዮኑን ለሕዝብ ሊሸጥ ነው
57173549
https://www.bbc.com/amharic/57173549
የአፍሪካ-ፈረንሳይ ስብሰባ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት አገራት የብድር እፎይታ ሃሳብ በማቅረብ ተጠናቀቀ
ላለፉት ጥቂት ቀናት በፓሪስ ሲካሄድ የቆየው የፈረንሳይ-አፍሪካ ስብሰባ ብድር መክፈል ለተሳናቸው የአፍሪካ አገራት የብድር እፎይታ ሃሳብ በማቅረብ ተጠናቀቀ።
የቀረበው ምክረ ሃሳብ ለኢትዮጵያ፣ ቻድ እና ዛምቢያ የብድር እፎይታ እንዲደረገ የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ምክረ ሃሳብ በቀጣይ ወር ለጂ7 አገራት ይቀርባል ተብሏል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ባለጸጋ አገራት ደሃ አገራት የሚጠበቅባቸውን ብድር የሚከፍሉበትን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ለማራዘም ተስማምተው ነበር። የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ስምምነት ከተደረሰላቸው አገራት መካከል 40 ያክሉ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ናቸው። በስብሰባው ላይ ከ20 በላይ የአፍሪካ አገራት መሪዎች፣ የአውሮፓ አገራት መንግሥታት፣ የአውሮፓ ሕብረት ልዑካን እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ (አይኤምኤፍ) ዳይሬክተር ተሳታፊ ሆነዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በስብሰባው መጠናቀቂያ ላይ የስብሰባው ተሳታፊዎች በኮቪድ-19 የተጎዳውን የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ መልሶ እንዲያንሰራራ ተጨማሪ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማፈላለግ ተስማምተዋል ስለማለታቸው ኤፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከዚህ መካከል አይኤምኤፍ የአፍሪካ አገራት ምርት ወደ አገራቸው እንዲያስገቡ እንዲረዳቸው 33 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል። ይህ ድጋፍ አገራቱ ባላቸው ሃብት ላይ ትኩረት በማድረግ በኮሮናቫይረስ ስርጭት ምክንያት የተጎዳ ምጣኔ ሃብታቸው እንዲያንሰራራ ትኩረት እንዲያደርጉ ያስችላል ተብሏል። ይህ የፈረንሳይ-አፍሪካ ውይይት የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 ክትባት ስለሚያገኙበት አማራጭ ላይም መወያየቱን ሬውተርስ ዘግቧል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን እንደ ኤፒ ዘገባ ከሆነ የውይይቱ ተሳታፊዎች የአፍሪካ አገራት ለዜጎቻቸው የኮቪድ-19 ክትባቶችን በራሳቸው በስፋት ማምረት እንዲቻላቸው ከአእምሮ መብት ጥበቃ ጋር የተያያዙ ክልከላዎች መላላት አለባቸው በሚል ተስማምተዋል ብለዋል ማክሮን። "የአፍሪካ አዲስ ስምምነት" የሚል መጠሪያ የሰጡት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ የአፍሪካ አገራትን ለመደገፍ 100 ቢሊዮን ዶላር በቂ አለመሆኑን ገልጸው፤ "በቀጣይ ዋነኛ ሥራችን የሚሆነው ሌሎች አገራት እንደ ፈረንሳይ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ማግባባት ነው፤ ይህም ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ይጀምራል" ብለዋል። የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂኦርጂቫ አይኤምኤፍ ተጨማሪ 33 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያቀርብ ይፋ አድርገው፤ ከኮሮናቫይረስ ስርጭት በኋላ የአፍሪካ አገራት እንደተቀረው ዓለም በፍጥነት ከገቡበት የምጣኔ ሃብት አጣብቂኝ ፈጥነው መውጣት አለመቻላቸው አሳሳቢ ነው ብለዋል። የተቀረው ዓለም በአማካይ የምጣኔ ሃብት እድገታቸው 6 በመቶ ሲሆን በአፍሪካ አገራት ግን የምጣኔ ሃብት እድገቱ 3.2 በመቶ ብቻ መሆኑን ዳይሬከተሯ ገልጸዋል።
news-55135143
https://www.bbc.com/amharic/news-55135143
የአሜሪካ ምርጫ 2020፡ ጆ ባይደን ከውሻቸው ጋር ሲጫወቱ ወድቀው ተጎዱ
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከውሻቸው ጋር ሲጫወቱ ወድቀው መጎዳታቸውን ዶክተራቸው አሳወቁ።
የ78 ዓመቱ ባይደን ቅዳሜ ዕለት ነው ከውሻዎቻቸው ጋር ሲጫወቱ የወደቁት ተብሏል። ተመራጩ ፕሬዝደንት አዳልጧቸው ከወደቁ በኋላ ጉልበታቸው ላይ ጉዳት ገጥሟቸዋል። ዴሞክራቱ ባይደን በተጎዱ በቀጣዩ ቀን ዴልዌር ውስጥ ያለ የአጥንት ሐኪም መጎብኘታቸው ታውቋል። የግል ሐኪማቸው ኬቪን ኦ'ኮነር ተመራጩ ፕሬዝደንት ኤክስ-ሬይ ተነስተው አጥንታቸው መሰንጠቁን አውቀናል ብለዋል። ዶክተሩ እንዳሉት ባይደን በቀኝ እግራቸው ጉልበት አካባቢ ሁለት ትንናሽ መሰንጠቅ ይታያል። ፕሬዝደንት ትራምፕ "ጨርሶ ይማርዎ" ሲሉ በትዊተር ግድግዳቸው ላይ ፅፈዋል። ሪፐብሊካኑ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕን ረትተው ወደ ሥልጣን እየመጡ ያሉት ባይደን ከሰኞ ጀምሮ ስለሚመሯት አገር ዕለታዊ ገለፃ ማግኘት ይጀምራሉ ተብሎ ነበር። ባለፈው ወር 78 ዕድሜያቸውን የደፈኑት ባይደን በአሜሪካ ታሪክ አዛውንቱ ፕሬዝደንት ሆነው ነው ቀጣይ ጥር ሥልጣን የሚጨብጡት። ይህን ተከትሎ የተመራጩ ፕሬዝደንት ወዳጆችና ተቃዋሚዎች ጉዳዩን ቅርበት እየተከታተሉት ይገኛሉ። ዶክተራቸው፤ ባይደን ወደ ጤናቸው እየተመለሱ ይገኛሉ ብለዋል። ባለፈው ታኅሳስ ዶክተራቸው በለቀቁት መግለጫ ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ለማግልገል ምንም የሚያንሳቸው ነገር የለም ብለው ነበር። ባይደን ቻምፕ እና ሜጀር ሲሉ ስም ያወጡላቸውን ሁለት ውሾች ይዘው ነው ወደ ነጩ የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ ቤተመንግሥት ለመግባት ያቀዱት። ውሾቹ 'ጀርመን ሼፐርድ' የተሰኘ ዝርያ ያላቸው ናቸው ተብሏል። ተመራጩ ፕሬዝደንት እና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ሜጀርን ለማሳደግ ወስነው የወሰዱት። ነገር ግን ቻምፕ ዋይት ሐውስ ብርቁ አይደለም። ጆ ባይደን የኦባማ ምክትል በነበሩ ጊዜ በዋይት ሐውስ የተከረከመ ሳር ላይ ሲቦርቅ ታይቶ ነበር።
news-52977239
https://www.bbc.com/amharic/news-52977239
በራያ ቆቦ በወረዳ አመራሮች ግድያ የሚፈለጉት ተጠርጣሪዎች እጃቸውን ሰጡ
ከሳምንት በፊት በአማራ ክልል በራያ ቆቦ ወረዳ አመራሮች ላይ የግድያ ወንጀል ፈጽመው ተሰውረው የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ለፖሊስ እጃቸውን መስጠታቸው አስታወቀ።
አቶ ስዩም መስፍን እና አቶ መንገሻ ሞላ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስዩም መስፍን እና የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንገሻ ሞላ ህይወታቸው ያለፈው እሁድ ግንቦት 23/2012 ዓ.ም ህግ ለማስከበር ጥረት ሲያደርጉ መሆኑን ጽህፈት ቤቱን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቦ ነበር። የወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የቡድን መሪ የሆኑት አቶ አየነ አማረ ለቢቢሲ እንደገለጹት በግድያ ወንጀሉ ሲፈለጉ የነበሩት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ወንድማማቾች ሲሆኑ፤ ተሰውረው ቆይተው ባለፈው እሁድና ትናንት ሰኞ ወልዲያ ማረሚያ ቤት በመሄድ እጃቸውን ሰጥተዋል። የአካባቢው የጸጥታ አካል ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ጥብቅ ክትትል ሲያደርግ እንደነበር ለቢቢሲ የተናገሩት የቡድን መሪው በመጨረሻም ተጠርጣሪዎቹ እራሳቸውን ለሕግ አካል ሰጥተዋል። "የጸጥታ መዋቅሩ ከመጀመሪያ ጀምሮ ከፍተኛ ክትትል በማድረግ መውጫ መንገድ እና አማራጭ ሲያጡ ነው እጅ የሰጡት" ብለዋል። በቀጣይም ተጠርጣሪዎቹን እስካሁን በሕግ ጥላ ስር እንዳይውሉ ያገዙ እና በወንጀሉ ላይ ተባባሪ የነበሩ አካላት ካሉ በሚል ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉንም አቶ አየነ ተናግረዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው የአካባቢው ያለው የፀጥታ ኃይል ከነዋሪዎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ተጠርጣሪዎች ትናናት ሰኞ መያዙን አስታውቆ አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራ ይገኛል ብሏል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው የአካባቢው ያለው የፀጥታ ኃይል ከነዋሪዎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ተጠርጣሪዎች ትናንት ሰኞ መያዙን አስታውቆ አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራ ይገኛል ብሏል። የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ስዩም መስፍን እና የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ መንገሻ ሞላ ህይወታቸው ያለፈው በወልዲያ ከተማ የነበራቸውን ሥራ አጠናቀው ወደ ቆቦ ከተማ በመመለስ ላይ እያሉ ነበር። ሁለቱ አመራሮች በመንገድ ላይ ሳሉ ከወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በሚጻረር እና ለኮሮናቫይረስ ስርጭት በሚያጋልጥ መልኩ አንድ የባጃጅ አሸከርካሪ ስድስት ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ተመልክተው ሕግን ለማስከበር በሞከሩበት ጊዜ ተተኩሶባቸው እንደተገደሉ መነገሩ ይታወሳል። አመራሩቹን የያዘው አሽከርካሪ እና ሌላ በመኪና ውስጥ የነበሩ ኃላፊ ምን ጉዳት ያልደረሰባቸው ሲሆን የጸጥታ ኃይሎችን ከሮቢት ከተማ ይዘው ሲመለሱ ተጠርጣሪዎቹ ባጃጇን ጢሻ ውስጥ ደብቀው መሰወራቸውን አስታውቀዋል። የወረዳው አመራሮችን ለመተካት በቀናት ልዩነት በውክልና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ እና ሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ባለሙያ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው በመሥራት ላይ መሆናቸው ለማወቅ ተችለወል። በተፈጸመባቸው ጥቃት የተገደሉት ሁለቱ የወረዳው አመራሮች አቶ ስዩም መስፍን እና አቶ መንገሻ ሞላ ሁለቱም ባለትዳርና የአንድ አንድ ልጅ አባት ነበሩ።
50444001
https://www.bbc.com/amharic/50444001
የስዊድን ተመራማሪዎች 'ስብሰባ ህክምና ነው' አሉ
በስዊድኑ ማላሞ ዩኒቨርስቲ የተሠራ ጥናት፤ ስብሰባ እንደ 'ህክምና' ሊወሰድ እንደሚችል ይፋ አድርጓል።
በሥራ ቦታ የሚካሄድ ስብሰባ፣ ውሳኔ በማስተላለፍ ረገድ ካለው ሚና በበለጠ እንደ ህክምና የሚኖረው ዋጋ እንደሚልቅ ተመራማሪዎች በጥናት ደርሰንበታል ብለዋል። ስብሰባ፤ ሠራተኞች ብስጭታቸውን የሚገልጹበት፣ በመሥሪያ ቤቱ ያላቸውን ቦታ የሚያሳዩበት እንደሆነም ተመራማሪዎቹ ያስረዳሉ። • በሳምንት አራት ቀን ብቻ መሥራት ውጤታማ ያደርጋል ተባለ ፕሮፌሰር ፓትሪክ ሆል እንደሚሉት፤ በመሥሪያ ቤቶች የሚካሄዱ ስብሰባዎች ቁጥር ቢጨምርም፤ የውሳኔ መስጫ መድረክ የመሆናቸው ነገር እያሽቆለቆለ መጥቷል። የስብሰባዎች ቁጥር መጨመሩ፤ በሥራ ቦታ ያለው አወቃቀር መለወጡን እንደሚያሳይ ያምናሉ። የሰዎች ውጤታማነት እንደቀነሰና በተቃራኒው አማካሪ፣ ስትራቴጂ ነዳፊ የተሰኙ ቦታዎች እየጎሉ መምጣታቸውንም ይገልጻሉ። "ብዙ ኃላፊዎች ምን መሥራት እንዳለባቸው አያውቁም፤ ሚናቸው ምን እንደሆነ ስለማያውቁ በርካታ ስብሰባ ይጠራሉ" ይላሉ። ሠራተኞችም በስብሰባ ላይ በማውራት ሚናቸው ምን እንደሆነ ለማግኘት ስብሰባውን እንደሚጠቀሙበት የሚገልጹት ተመራማሪው፤ እነዚህ ሰዎች ከሥራ ሰዓታቸው ገሚሱን በስብሰባ እንደሚያጠፉም ያስረዳሉ። • ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት ሌላው የስብሰባ ጥቅም፤ ሰዎች ቅሬታቸውን የሚገልጹበት መድረክ መፍጠሩ ነው። ፕሮፌሰር ፓትሪክ፤ ዘለግ ያሉ ስብሰባዎችን እንደ ሥነ ልቦናዊ ህክምና ይወስዷቸዋል። "ቅሬታ መግለጫ፣ በተቀሩት ሠራተኞች ዘንድ ቦታ ማግኛ መድረክም ነው" ሲሉ ስብሰባን ይገልጻሉ። በእርግጥ ብዙዎች በስብሰባ እንደሚሰላቹ የሚጠቅሱት መራማሪው፤ ምናልባትም እነዚህ ሰዎች የስብሰባን እውነተኛ ጥቅም አልተረዱት ይሆናል ይላሉ። ፕሮፌሰሩ፤ በስብሰባ ወቅት የተሳታፊዎች እኩልነት መጠበቅ እንዳለበት ይናገራሉ። የስብሰባ ተሳታፊዎች ማንሳት የሚፈልጉት አጀንዳ መንሸራሸር እንደሚገባውም ያክላሉ። • የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? ስብሰባ የጥቂቶች የበላይነት የሚንጸባረቅበት ከሆነ፤ በሂደቱ አለመካተታቸው የሚሰማቸውን ሰዎች እንደሚያስቀይም ይናገራሉ።
news-49137218
https://www.bbc.com/amharic/news-49137218
አሜሪካ፡ አዲሷ ሙሽራ ባሏን ከእሳተ ገሞራ አፍ ታደገችው
አዲሶቹ ተጋቢዎች ለጫጉላ ሽርሽር እሳቱ ወደማይንቀለቀልበት ፀጥ ብሎ ከሚያንቀላፋው እሳተ ገሞራ ለሽርሽር ነበር የሄዱት።
ክሌይ ቻስቴይን እና አካሚያ የጫጉላ ሽርሽራቸውን ያካሄዱት በተጋቡ ማግስት ነበር። ጋብቻቸውን በአሜሪካ ኢንዲያና ግዛት ፈፅመው ሊያሙኢጋ የተባለ ተራራን በመውጣት እሳተ ገሞራ የፈጠረውን ውበት እያዩ፣ ፍቅራቸውን ለማጣጣም ነበር ሀሳባቸው። ተራራው ጫፍ ላይ እንደደረሱ አዲሱ ሙሽራ ክሌይ ቻስቴይን፣ ትንሽ የሀሳብ ሰበዝ ብልጭ አለችበት። 'ለምን ወደ እሳተ ገሞራው አፍ ወረድ ብለን አናየውም፣ በዛውም ጥሩ እይታን እናገኛለን' የሚል ነው ሀሳቡ። • "በኤችአይቪ የምሞት መስሎኝ ልጄን ለጉዲፈቻ ሰጠሁ" • "እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ ባለቤቱ የከፍታ ፍርሃት ስላለባት ባለችበት ለመቆየት ትወስናለች። እሱ የልቡን ለማድረስ ቁልቁለቱን ወረደ "ድንገት ከፍተኛ ድምፅ ሰማሁ፤ ከኮረብታው የሚንደረደር ቋጥኝ አይነት" ያለችው አካሚያ የባሏን የድረሱልኝ ጩኸት እንደሰማች ወደ እሱ አመራች። በደም ተለውሶ ሞባይሉ ከእሱ ርቆ ወድቆ አገኘችው። ክሌይ ያለ የሌለ ጉልበቷን አስተባብሯ፣ ሀዘኗን ዋጥ አድርጋ ባሏን አፋፍሳ አነሳችው። እርሷ ላይ ተዝለፍልፎ፣ ወደላይ እያለው፣ በሕመም መላ አካሉ እየተሸቀሸቀ ወደ ተራራው ግርጌ ወረዱ። ጥንዶቹ የተጋቡት አደጋው ከመድረሱ ቀደም ብሎ ባሉት ቀናት ነበር ወደ ተነሱበት ለመመለስ የሚረዳቸው አንድም አካል ስላልነበር ሁለቱ ብቻ ተደጋግፈው ሦስት ሰአት ያህል በመጓዝ እርዳታ የሚያገኝበት ሥፍራ ላይ ደርሰዋል። "በጣም የምትደንቅ ሴት ናት" ብላል እንኳንም ሚስቴ ሆነች በሚል ድምፀት። • "ኦሮሞ እና ማዳጋስካርን የሚያገናኝ ፖለቲካ እንዳለ አላውቅም" የትነበርሽ ንጉሤ ቻስቴይን ተራራው ጋር ሲወርድ የራስ ቅሉ ተፈንክቶ እየደማ ነበር። "ተደግፎኝ እየሄድን ደጋግሞ ምን ያህል ቀረን፣ አንደርስም እንዴ? እያለ ይጠይቀኝ ነበር" የምትለው አካሚያ፤ ወደ ፍሎሪዳ ሄዶ የተሻለ ህክምና እንዲያገኝ የሚያስችል ገንዘብ እንደተሰባሰበለት ጠቅሳለች። የራስ ቅሉ መሰበርና ቀላል የአጥንት መሰበር ቢገጥመውም ከባድ የሆነ ሌላ አደጋ የለውም። ነገር ግን ሐኪሞች ሴሬብራል ስፓይናል ፈሳሽ በአፍንጫው በኩል መፍሰሱን ተናግረዋል። "ያን ያህል ጉዳት ገጥሞት በራሱን ኃይል ህክምና የሚያገኝበት ድረስ መሄዱ ትንግርት ነው" ብላለች ባለቤቱ። አክላም በፌስ ቡክ ገጿ ላይ ፈጣሪን አመስግናለች።
news-54117749
https://www.bbc.com/amharic/news-54117749
አልቃኢዳ ፡ የመስከረም አንዱ ጥቃት ሲታወስ፡ አልቃኢዳ የት ነው ያለው?
9/11 ተብሎ የሚጠራው ጥቃት እአአ መስከረም 11 ኢትዮጵያውያን ደግሞ የአዲስ ዓመት በዓልን በሚያከብሩበት ዕለት በአሜሪካ መንትያ ህንጻዎች ላይ የሽብር ጥቃት ከተፈጸመ ዛሬ ልክ 19ኛ ዓመቱ ነው።
የመስከረም አንዱ የአልቃኢዳ ጥቃት በአሜሪካ ምድር ላይ የተፈጸመ አስከፊው ጥቃት ነው ጥቃቱን የፈጸመው በወቅቱ መቀመጫውን አፍጋኒስታን ያደረገው ጽንፈኛው ቡድን አል-ቃኢዳ ነበር። በጥቃቱም አሜሪካውያን የማይረሱትን ጠባሳ እንዲያስተናግዱ ተገደዋል። በሶሪያ የሚገኘው የአል-ቃኢዳ ክንፍ በተቀናቃኝ ኃይሎች ሰኔ ወር ላይ የተደመሰሰ ሲሆን በየመን የሚገኘው የአል-ቃኢዳ መሪ ደግሞ መሪው በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ከተገደ በኋላ ሌላ ሽንፈትን ገጥሞታል። አል-ቃይዳ በሰሜን አፍሪካም ቢሆን ዋና መሪው በፈረንሳይ ወታደሮች ማሊ ውስጥ የተደገለ ሲሆን እስካሁንም ተተኪ አልተሰየመም። በሌላ በኩል የአል ቃኢዳ መሪ አይማን አል ዛዋሂሪ ላለፉት ተከታታይ ወራት ድምጹ የጠፋ ሲሆን ምናልባትም ከኃላፊነቱ ተነስቶ ሊሆን ይችላል የሚለውን ጭምጭምታ እየተሰማ ነው። ማሊ ውስጥ በተካሄደ ዘመቻ በሰሜን አፍሪካ የአል-ቃኢዳ መሪ የነበረው አብድልማሊክ ድሮክዴል መገደሉን ይፋ ያደረገችው ፈረንሳይ ነበረች። በአሜሪካ "አሸባሪ" ተብሎ ተፈርጆ ነበረው የቀድሞ የአል-ቃኢዳ መሪ የኦሳማ ቢን ላድን ልጅ ሃምዛ ቢን ላደን፣ አሜሪካ ባካሄደችው ዘመቻ መገደሉም ይታወሳል። የአል-ቃኢዳ መሪዎች መገደል አል-ቃኢዳን ማዳከሙ እሙን ይሁን እንጂ፤ በአፍሪካ በማሊና ሶማሊያ ውስጥ አሁንም አል-ቃይዳ እንቅስቃሴ ያደርጋል። ሶሪያ ውስጥ አል-ቃኢዳ በይፋ ባልተገለጸው ሁራስ ሰል ዲን ቅርጫፉ በኩል እዚህ ግባ የሚባል ነገር ማሳካት አልቻለም። ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ምክንያቱ በቀጠናው ያለው የሌሎች ጂሃዳዊ ቡድኖች ከፍተኛ ፉክክር ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የትኞቹም የአል-ቃኢዳ መሪዎችና ከፍተኛ ኃላፊዎች በአሜሪካ ባለስልጣናት በጥብቅ ክትትል ስለሚደረግባቸው ነው። በተጨማሪም አልቃኢዳ ሶሪያ ውስጥ ብዙም ተቀባይነት የለውም። ሶሪያውያን አል-ቃኢዳን እንደ ስጋትና ዓለም አቀፍ ተጽእኖ እና ጫና ይዞ እንደሚመጣ ቡድን ነው የሚያዩት። የቀድሞው በአረብ ባሕረ ሰላጤ የአልቃኢዳ መሪ ቃሲል አል ራይሚ ሁራስ አል ዲን በተቀናቃኝ ጂሃዳዊ ቡድን በተሰነዘረበት ከባድ ጥቃት ምክንያት ላለፉት ሁለት ተከታታይ ወራት ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሲያድርግ አልታየም። ምናልባትም በአሜሪካ የአየር ድብደባ ሳይሞት እንዳልቀረም ተገምቷል። የመን ውስጥ የቡድኑ ቅርጫፍ አል-ቃኢዳ በአረብ ባሕረ ሰላጤ የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን በአካበቢው እጅግ የሚፈራ ቡድን ነበር። ነገር ግን በያዝነው ዓመት በርካታ ጥቃቶችን ማስተናገዱና በተለያዩ ጦርነቶች መሸነፉ ተጽእኖ ፈጣሪነቱን እና ተቀባይነቱን አሳጥቶታል። ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ባደረሱት ጥቃት የዚሁ ቡድን መሪ የተገደለ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ በማዕከላዊ ባይዳ ግዛት በሁቲ አማጺያን ተሸንፎ አካባቢውን እንዲለቅ ተገዷል። በሰሜን አፍሪካም ቢሆን አል-ቃኢዳ አልጄሪያ ውስጥ ለመንቀሳቀስ ያደረገው ጥረት እምብዛም ፍሬ አላፈራለትም። በማሊ ደግሞ ጃማት ኑስራት አል ኢስላም ዋል ሙስሊሚን የሚባል የአል-ቃይዳ ክንፍ 2017 ላይ ተቋቁም የነበረ ሲሆን በቡርኪናፋሶ እና ኒጀርም ይንቀሳቀሳል። ከአል-ቃኢዳ ጋር ወዳጅነት ካለውና በሶማሊያ መቀመጫውን ካደገረው አልሸባብ በመቀጠል ይሄው ቡድን በአፍሪካ ሰፋ ያለ ይዞታዎችን መቆጣጠር ችሏል። ቡድኑም በዋነኛነት መከላከያ ኃይሎችን እና የውጭ አገራት ወታደሮችን ኢላማ በማድረግ ጠጥቃት ይፈጽማል። በተለይ ደግሞ የፈረንሳይ ወታደሮች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃትን ይሰነዝራል። በአሁኑ ጊዜ ለአል-ቃኢዳ እንደ አልሸባብ የሚያስፈራ ተቀናቃኝ የለውም። አልሸባብ ማዕካለዊና ደቡባዊ የሶማሊያ ከተሞችን ከመቆጣጠር ባለፈ ማስተዳደር ላይም ጭምር ይሳተፋል። በሶማሊየም በየቀኑ ሊባል በሚችል መልኩ ቀላልና ከባድ ጥቃቶችን ይሰነዝራል። በርካታ የአል-ቃኢዳ ማዕከላዊ የአመራር አባላት በአፍጋኒስታን እና ፓኪስታን ድንበሮች አካባቢ ላለፉት ተከታታተይ ዓመታት በሰው አልባ አውሮፕላኖች በተሰነዘረባቸው ጥቃት ሞተዋል አልያም ሶሪያ ውስጥ በተከፈተባቸው ጥቃት ሕይወታቸው አልፏል። ባሳለፍነው የካቲት ወር ላይ በአሜሪካና ታሊባን መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነትም ለውጥ እንዳመጣ ይታሰባል። በስምምነቱ መሰረት ታሊባን ማንኛውም አይነት የውጭ ጂሃዳዊ ቡድንን ላለመደገፍና ከለላ ላለመስጠት ተስማምቷል። በሌላ በኩል አልቃኢዳ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን በመጠቀም አሜሪካውያን መንግሥታቸው ላይ አንዲነሱ ጥሪውን አቅርቧል። የአሜሪካ መንግሥት ከዚህ ክፉ ወረርሽኝ ሊታደጋችሁ አልቻለም በማለትም መልዕክቱን አስታልፏል። ነገር ግን አሜሪካውያን እድሜ ልካቸውን የማይረሱት ጥቃት ከሰነዘረባቸው ቡድን ጋር በአንድ ጎራ ይሰለፋሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው።
news-51382624
https://www.bbc.com/amharic/news-51382624
የአፈጉባኤዋ የትራምፕን ንግግር መቅደድ አነጋጋሪ ሆነ
የአሜሪካው ፕሬዝዳናት ዶናልድ ለአገሪቱ ምክር ቤት አመታዊውን ንግግራቸውን ካደረጉ በኋላ አፈ ጉባኤዋ የንግግሩን ቅጂ ሲቀዱ መታየታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
ፕሬዝዳንቱ ንግግር ሲያደርጉ ከኋላቸው ተቀምጠው የሚታዩት የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባልና የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በንግግሩ ማብቂያ ላይ እጃቸው ላይ የነበረውን የፕሬዝዳንቱን ንግግር ቅጂ ሲቀዱ ታይተዋል። ይህም የተከሰተው ፕሬዝዳንት ትራምፕ አፈጉባኤዋን ላለመጨበጥ ካንገራገሩና ረጅሙን ንግግራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ነበር። • ኃይለኛ ንፋስ ትራምፕ በሜክሲኮ ድንበር እያስገነቡ ያሉትን አጥር አፈረሰ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ፕሬዝዳናት ትራምፕ ስልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል በሚል ክስ እንዲመሰረትባቸውና ጉዳያቸው በምክር ቤቱ እንዲታይ ማስደረጋቸው ይታወሳል። የዴሞክራቲክ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አፈጉባኤዋ መነጋገሪያ ከሆነው የፕሬዝዳንቱን ንግግር ቅጂ የያዘውን ወረቀት ከቀደዱበት ድርጊታቸው በኋላ ለምን ይህንን እንዳደረጉ በጋዜጠኞች ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል። • ለምስክርነት የተጠሩት አምባሳደር ትራምፕ አስፈራርተውኛል አሉ አፈጉባኤዋም የፕሬዝዳንቱ ንግግር "ቆሻሻ ንግግር ስለነበረ የፈጸምኩት የሚገባ ነገር ነው" ሲሉ ድርጊታቸውን አወድሰዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለአንድ ሰዓት ከ18 ደቂቃ ስለተለያዩ ጉዳዮች አንስተው ለምክር ቤቱ አባላት ንግግር አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ ዓመታዊ ንግግራቸውን አጠናቀው ከምክር ቤቱ ሲወጡ የፓርቲያቸው የሪፐብሊካን አባላት ከአፈጉባኤዋ ከናንሲ ትችት በተለየ ፕሬዝዳንቱ ያደረጉት ንግር "ድንቅ" እንደነበር ሲናገሩ ተሰምተዋል። ዴሞክራቶች ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር ላይ ከአፈጉባኤዋ ጀምሮ በግልጽ ደስተኛ አለመሆናቸውን አሳይተዋል። አንዳንዶቹ እንዲያውም ፕሬዝዳንቱ እየተናገሩ ምክር ቤቱን ለቀው ሲወጡም ታይተዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ከስልጣን ለማውረድ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይሳካ ይሆን?
news-56737753
https://www.bbc.com/amharic/news-56737753
በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እየወጡ ነው
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈፀመ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ተገለጸ።
ጥቃቱ በአጣዬ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ማጀቴ ፣ ካራ ቆሬ እና ሌሎች አካባቢዎች መፈጸሙ ተገልጿል። የዞኑ የጸጥታ ኃላፊ አቶ አበራ መኮንን ለቢቢሲ እንደገለፁት ጥቃቱ የተፈፀመው በዞኑ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ውስጥ ሲሆን "በጣም ከፍተኛ" ቁጥር ያለው የታጠቀ ኃይል "ወረራ" መፈፀሙን ተናግረዋል። የታጠቀው ኃይል "ቤቶችን ያቃጥላል፤ ሰዎችን ይገድላል" በማለትም ወደ አካባቢው የገባው የፌደራል የጸጥታ መዋቅርና የመከላከያ ሠራዊትም "ከአቅሙ በላይ" መሆኑን ለቢቢሲ አስረድተዋል። የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን ተቋም እንደተናገሩት በጥቃቱ የደረሰው ጉዳት የከፋ መሆኑን አመልክተዋል። ለጥቃቱም "ኦነግ ሸኔ እና ሌላ ተከታይ" ያሉትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል። በጥቃቱ የጸጥታ አካላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አክለዋል። ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ማታ ጀምሮ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና በሰሜን ሸዋ ዞን መካከል በሚገኙ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር መኖሩን ገልጸው፤ ይህ ግን ጋብ ብሎ እንደነበር ኃላፊው አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ ትናንት አርብ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የታጠቀ ኃይል ወደ አካባቢው በመግባት በአጣዬ፣ በአንጾኪያና በኤፍራታ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተናግረዋል። ኃላፊው እንዳሉት በጥቃቱ የጸጥታ አካላት እና የንጹሃን ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ ንብረትም ወድሟል። ከሦስት ሳምንታት በፊት በአካባቢዎቹ በተፈፀመ ጥቃትና ግጭት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል። ነዋሪዎች ምን ይላሉ? ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ጥቃቱ በተፈፀመባቸው አጣዬ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ካራ ቆሬ፣ ማጀቴ እና ሌሎች አካባቢዎች በርካታ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ ቤቶች መቃጠላቸውንና ንብረቶች መውደማቸውን ተናግረዋል። ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የኤፍራታና ግድም ወረዳ ነዋሪ "ትናንት ረፋድ ላይ ጀምሮ በርሃ አርሶ አምባና ብርቂቶ ከሚባለው አገር "ሰው አለቀ፤ ተለበለበ" ሲሉ የደረሰውን ጉዳት ገልጸዋል። እርሳቸው አካባቢውን ለቀው እንደወጡ የገለጹት እኝህ ነዋሪ፤ ጥቃቱን የፈፀሙት "የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ሌሎች የህወሓት ኃይሎች" ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። በርካታ ንጹሃን ሰዎችና የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውንና የቤት እንስሳት፣ የተሰበሰበ ሰብል ሳይቀር መቃጠሉንና ነዋሪዎችም አካባቢያቸውን ለቀው እየወጡ መሆኑን ተናግረዋል። "ሰዉ በእንዲህ ያለ ጥቃት ካለቀ በኋላ መንግሥትም ምኑን የስተዳድራል? ድንጋይ አይገዛ፤ ሰው እኮ ነው የሚገዛው" ሲሉ መንግሥት የነዋሪውን ደኅንነት እንዲጠብቅ ተማጽነዋል። ትናንት ምሽት አርብ ያነጋገርናቸው እኝህ ነዋሪ፤ በአካባቢው የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ሌላኛዋ የአጣዬ ነዋሪም ከዚህ በፊት በነበረው ግጭት የመከላከያና ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ በመግባቱ ተረጋግተው መቀመጣቸውን አስታውሰው፤ የዚህ ቀደሙ ጉዳት ሳይሽር ሌላ ጥቃት መፈፀሙ እንዳሳዘናቸውና የሕግ የበላይነት አለመከበሩ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል። እርሳቸውም ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ መሃል ሜዳ እየሄዱ እንደሆኑ የገለፁት እኝህ ነዋሪ "አሁንም ግጭት አለመቆሙንና የከተማው ነዋሪ በሙሉ ወደ ደብረ ብርሃንና እና መሃል ሜዳ ለቆ ሸሽቷል" ብለዋል። በከተማው የገባው የጸጥታ ኃይልም ጥቃት የሚፈጽመው ኃይል ከአቅሙ በላይ መሆኑንና በከተማዋ ቃጠሎ መኖሩን ነዋሪው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረ ጻዲቅ ለአገር ውስጥ ሬዲዮ እንደተናገሩት በጥቃቱ በርካታ ሰዎች መሞታቸውንና በንብረት ላእ ከባድ ጉዳት መድረሱን አመልክተው "መንግሥት አስቸኳይ እርምጃ ወስዶ ኃይል ካልመደበ ችግሩ ከዚህም በላይ የከፋ ይሆናል" ብለዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ኃላፊ አቶ አበራ "ችግሩ በአጠቃላይ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል" በማለት ሕዝቡን የማረጋጋት አስቸኳይ ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀው፤ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆትበዋል። አቶ ግዛቸው ትናንት ምሽት ለክልሉ ሚዲያ በሰጡት መረጃ፤ ጥቃቱ ያልበረደ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ሆነው ወንጀል ፈጻሚዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። ከሦስት ሳምንታት በፊት በሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች ውስጥ በተከሰተ ግጭት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል። በግጭቱ የደረሰው ጉዳት በዝርዝር ባይገለፅም፤ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋምን ጠቅሶ ኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከ300 በላይ ሰዎች ሕይወት አልፏል። የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በአካባቢው በተደጋጋሚ ስለሚፈፀመው ጥቃት ያሉት ነገር የለም። በወቅተ ግጭቱን ለመቆጣጠርና ነዋሪውን ማረጋጋት የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት ወደ አካባቢው እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። በወቅቱ በአካባቢው ስለተከሰተ ግጭት የገዢው የብልጽግና ፓርቲ የአማራና የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፎች የተለያዩ መግለጫዎችን በማውጣት ሲወዛገቡ ነበር። የአማራ ብልጽግና በወቅቱ ባወጣው መግለጫ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን ለጥቃቱ ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን፤ የኦሮሚያ ብልጽግና በበኩሉ በአካባቢው ኦነግ ሸኔ እንደማይንቀሳቀስ መግለጹ ይታወሳል። በዚያው ሰሞን በምዕራብ ወለጋ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ የአማራ ክልል መንግሥትም በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርስ ጥቃት እንዲቆም የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ እንዲገባና በአስቸኳይ መወያየት እንደሚፈልግ ገልጾ ነበር። ይህንንም ተከትሎ የሁለቱ ክልል አመራሮች በአዲስ አበባ ተገናኝተው ችግሮችን በጋራ ለመፍታት መስማማታቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በምን ጉዳይ ላይ እንደተወያዩ ግን በዝርዝር አልተገለጸም።
news-51764737
https://www.bbc.com/amharic/news-51764737
የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ቢሊየነሩ የዱባይ ገዥ ልጆቻቸውን አግተዋል አለ
ቢሊየነሩ የዱባይ ገዢ ሼክ ሞሃመድ ቢን ራሺድ ሁለት ሴት ልጆቻቸውን ያለፍቃዳቸው አግቶ ወደ ዱባይ እንዲመለሱ በማድረግ እንዲሁም የቀድሞ ሚስታቸውን በማስፈራራት በእንግሊዝ ፍርድ ቤት ቀርቦባቸው በነበረው ክስ ጥፋተኛ ተብለዋል።
ሼክ ሞሃመድ ላይ ክሱ የቀረበው በቀድሞ ባለቤታቸው ልዕልት ሃያ ቢንት አልሁሴን ሲሆን ብይኑ የተሰጠው ትናንት ነው። ላለፉት ስምንት ወራት በፍርድ ቤት ሂደት ላይ የነበረውን ይህን ጉዳይ ለማጣራት ፍርድ ቤቱ እውነት አፈላላጊ ኮሚቴ አቋቁሞ ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቷል። ሼክ ሞሃመድ የቤተሰብና የግል ጉዳያቸው በመሆኑ የፍርድ ሂደቱ ለሕዝብ ይፋ ባልሆነ መልኩ እንዲካሄድ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ የመጨረሻ ውሳኔውንም በይፋ አሳልፏል። መንግሥትን የሚመሩ ሰው በመሆናቸው በእውነት ማፈላለጉ ተግባር ተሳትፎ ማድረግ ባለመቻላቸው፤ የእሳቸው በኩል ያለው ነገር ሳይሰማ ውሳኔው የአንድ ወገን እንደሆነም ተናግረዋል ሼክ ሞሃመድ። የእንግሊዙ ፍርድ ቤት ግን በምርመራ ሂደቱ "ተባባሪም ታማኝም አልነበሩም" ብሏቸዋል። • የዱባይ ልዕልት ከባለቤቷ ሸሽታ ለንደን ተደብቃለች • የዱባዩ መሪና ጥላቸው የኮበለለችው ባለቤታቸው ወደ ፍርድ ቤት ሊያመሩ ነው ነገሩ የግል ጉዳይ እንደሆነ "መገናኛ ብዙሃን በእንግሊዝ የልጆቻችንን ግላዊ ህይወት እንድታከብሩና እንዳትተላለፉ እጠይቃለሁ" ሲሉ ለማስረዳት ሞክረዋል ሼክ ሞሃመድ። ፍርድ ቤቱ ከሌላ ትዳር የተወለዱ ሁለት ሴት ልጆቻቸውን በማገትና ያለፍቃዳቸው ወደ ዱባይ እንዲመለሱ በማድረግ ሼክ ሞሃመድን ተጠያቂ አድርጓቸዋል። ሼካ ሻምሳ በእንግሊዝ ከሚገኘው የቤተሰቡ መኖሪያ ያመለጠችው በፈረንጆቹ 2000 ነበር። ነገር ግን ወዲያው ካምብሪጅሻየር ውስጥ በቢሊየነሩ አባቷ የደኅንነት ሰዎች ተይዛ ወደ ዱባይ እንድትመለስ ተደግጓል። እስካሁንም በዱባይ ነች። የካምብሪጅ ፖሊስ በጉዳዩ ምርመራ ለማድረግ ወደ ዱባይ ለማቅናት ያደረገው ጥያቄም ውድቅ ተደርጓል። ሁለተኛዋ ልጃቸው ሼካ ላቲፋ በ2002 እና በ2018 ከአባቷ ቤተሰቦች ጋር ከምትኖርበት ቤት ለማምለጥ ያደረገችው ሙከራ አልተሳካላትም። ለመጀመሪያው የማምለጥ ሙከራዋ አባቷ በሦት ዓመት እስራት ቀጥተዋታል። ከሁለተኛው ሙከራዋ በኋላ ደግሞ የቤት ውስጥ የቁም እስረኛ እንድትሆን ተደርጓል። ለፖሊስ የላከችውን ቪዲዮ መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤቱ ድብደባና ማሰቃየት እንደደረሰባት አረጋግጧል። ፍርድቤ ቱም ቢሊየነሩ የዱባይ ገዢ ሼክ ሞሃመድ የሁለት ልጆቻቸውን ሰብዓዊ ነፃነት ገፍፈዋል ብሏል። የ45 ዓመቷ የዮርዳኖስ ልዕልት ሃያ የሟች ዮርዳኖስ ንጉሥ ሁሴን ልጅ ሲሆኑ የ70 ዓመቱ የዱባይ ገዢ ሼክ ሞሃመድን ያገቡት በ2004 ነበር። የሼክ ሞሃመድ ስድስተኛ እና በእድሜ ትንሿ ሚስት ነበሩ። የሰባት እና የ11 ዓመት ሁለት ልጆችንም አፍርተዋል። የታገቱት ሁለቱ የሼክ ሞሃመድ ትልልቅ ሴት ልጆችን በሚመለከት አባትየው መጀመሪያ ላይ ለልዕልቷ ልጆቹ ችግር ውስጥ ገብተው እንደነበር፤ በመጨረሻ ግን ከቤተሰቡ ጋር በሰላም መቀላቀላቸውን ነበር የነገሯቸው። ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ላይ ግን ልዕልቷ ነገሮችን መጠርጠር ጀመሩ። ከዚያ ደግሞ ቅሬታቸውን መግለፅ ቀጠሉ። በሌላ በኩል ከእንግሊዛዊው ጠባቂያቸው ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀመሩ። ይህም ሼክ ሞሃመድን ክፉኛ አስቆጣ። ከዚያም ፍርድ ቤቱ ላይ እንደተገለፀው የሰውዬው ጠባቂዎች ልዕልቷን በተለያየ መልክ ማስፈራራት ጀመሩ። ሁለት ጊዜ የተቀባበለ ሽጉጥ ትራሳቸው ስር እንዲቀመጥ ተደርጓል። እሳቸውን በረሃ ውስጥ የሚገኝ ሩቅ እስር ቤት ለመውሰድ ባልታሰበ መልኩ ሄሊኮፕተር ከመኖሪያቸው ቅጥር ተገኝቶም ያውቃል። የዛሬ ዓመት የሼክ ሞሃመድ ባለቤት ልዕልት ሃያ ሁለት ህፃናት ልጆቻቸውን ይዘው ከዱባይ አምልጠው እንግሊዝ መግባታቸው ብዙዎችን ጉድ አስብሎ ነበር። ልዕልቲቱ ለህይወታቸው መፍራታቸውን እንዲሁም ህፃናት ልጆቻቸው በአባታቸው ታግተው ወደ ዱባይ ይመለሱብኛል የሚል ስጋት እንዳለባቸው መናገራቸው ይታወሳል። ሸሽተው ወደ እንግሊዝ ባቀኑ በአንድ ወር ውስጥ ባለቤታቸው ሼክ ሞሃመድ "አንቺም ልጆቹም መቼም እንግሊዝ ውስጥ ደህና ሆናችሁ አትኖሩም" ብለዋቸው እንደነበር ልዕልቲቱ ተናግረዋል። ቢሊየነሩ የዱባይ ገዢ ሼክ ሞሃመድ "ኖረሻል፤ ሞተሻል" የሚል ግጥምም ማሳተማቸውን ልዕልቲቱ ይናገራሉ።
news-52074359
https://www.bbc.com/amharic/news-52074359
ኮሮናቫይረስ፡ የህክምና ባለሙያዎቻቸውን ለመከላከል የሚተጉት ቱኒዚያውያን
150 ቱኒዚያውያን ራሳቸውን በፋብሪካ ውስጥ ዘግተው የፊት መሸፈኛ ጭምብል እያመረቱ ነው።
በቱኒዚያው ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩት እነዚህ ሠራተኞች ራሳቸውን በፋብሪካ ውስጥ በመዝጋት በቀን 50 ሺህ የፊት ጭምብል እንዲሁም ሌሎች ለሕክምና ባለሙያዎች የሚያገለግሉ የመከላከያ ቁሶችን በማምረት ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። ሠራተኞቹ በፋብሪካ ውስጥ ራሳቸውን ነጥለው ለሕክምና ባለሙያዎች የሚያገለግሎ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ማምረት ከጀመሩ ሳመንት ሞልቷቸዋል ተብሏል። እነዚህ 150 ቱኒዚያውያን የፋብሪካ ሠራተኞች አብዛኛዎቹ ሴቶች ሲሆኑ በፋብሪካ ውስጥ ለአንድ ወር ያህል ዘግተው ሊቀመጡ ወስነዋል። • የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የኢትዮጵያ ዝግጁነት ምን ይመስላል? • ሴንጋፖር አካላዊ እርቀትን የማይጠብቁ ሰዎችን በገንዘብና በእስር ልትቀጣ ነው የፋብሪካ ሠራተኞቹ ለዚህ ውሳኔ የበቁት አገራቸው ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት የቻለችውን እያደረገች እንደሆነ በተመለከቱ ጊዜ መሆኑን የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ሐምዛ አሎኒ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በፋብሪካው ውስጥ ሠራተኛ የሆነችው ካዋላ ሬቢ ቤተሰቦቿን መናፈቋን ተናግራ ነገር ግን የባልደረቦቿ ሳቅ ጨዋታ ናፍቆቷን እንደሚያስታግስላት ትናገራለች። "ባለቤቴና የ16 ዓመቷ ልጄ ይህንን እንዳደርግ ገፋፍተውኛል" የምትለው ሬቢ የምርት ክፍሉን እንደምትቆጣጣር ለቢቢሲ ተናግራለች። ፋብሪካው ከዚህ በፊት የሚያመርታቸውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችም ሆኑ ሌሎች ለሕክምና ባለሙያዎች የሚረዱ ቁሳቁሶችን ወደ ባህር ማዶ የሚልክ ቢሆንም አሁን ግን ለአገር ውስጥ ፍጆታ ብቻ እንደሚያውል ታውቋል። የሰሜን አፍሪካዋ አገር ቱኒዚያ እስካሁን ድረስ 227 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ ባለፈው ሳምንት ስድስት ህሙማን መሞታቸው ታውቋል። ፋብሪካው ከዋና ከተማዋ ቱኒዝ በደቡባዊ አቅጣጫ ገጠራማ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ከፋብሪካ ሠራተኞቹ ጋር አብረው ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች፣ የመድሃኒት ባለሙያዎችና ምግብ አብሳዮች ይገኙበታል። ለ110 ሴቶችና ለ40 ወንዶች የሚሆኑ የተለያዩ ማደሪያ ክፍሎች እንዲሁም ለአንድ ወር የሚበቃ መሰረታዊ ፍጆታ ተሟልቷል ተብሏል። ራቢ " ለሴቶች የሚደንሱበት ወንዶች ደግሞ እግርኳስ የሚጫወቱበት የተለየ ስፍራ አዘጋጅተናል" በማለት ለሰራተኞቹ ኢንተርኔት እንዳላቸውና ሁሉም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በቪዲዮ እንደሚያወሩ ታስረዳለች። ፋብሪካው በሁለት ፈረቃ የሚሰራ ሲሆን የከሰአቱ ፈረቃ ላይ የተመደቡት አብዛኞቹ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል። አሉኒ በበኩሏ " እኛ ካልሰራን ህክምና ባለሙያዎቻችን ራሳቸውን ከቫይረሱ የሚከላከሉበት ነገር አይኖርም" በማለት ሠራተኞቹ አሁንም በወኔ እንደሚሰሩ ታስረዳለች።
news-51701969
https://www.bbc.com/amharic/news-51701969
በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ3ሺህ በላይ መድረሱ ተዘገበ
ቻይና ተጨማሪ 42 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መሞታቸውን ሪፖርት ማድረጓን ተከትሎ ወረርሽኙ በዓለም ዙሪያ የገደላቸው ሰዎች ቁጥር ከ3 ሺህ ማለፉ ተነገረ።
በበሽታው ከሞቱት ከሦስት ሺህ በላይ ከሚሆኑ ት ሰዎች 90 በመቶ የሚሆኑት በታኅሳስ ወር መብቂያ ገደማ ወረርሽኙ በተቀሰቀሰባት የቻይናዋ ሁቤይ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ከቻይና ቀጥሎ ብዙ ሰዎች በበሽታው የሞቱት ኢራንና ጣሊያን ውስጥ ሲሆን፤ ከ50 በላይ በኢራን ከ30 በላይ ደግሞ ጣሊያን ውስጥ ሞተዋል። በተጨማሪም በሌሎች 10 አገራት ውስጥ ወረርሽኙ የሰዎችን ህይወትን ቀጥፏል። በዓለም ዙሪያ በሽታው በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ሲሆን እስካሁን ድረስ 90 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል። የበሽታው የመዛመት ፍጥነት ከቻይና ይልቅ በተቀረው ዓለም ውስጥ ከፍተኛ ሆኗል። የዓለም የጤና ድርጅት እንዳለው በወረርሽኙ በተያዙ አብዛኞቹ ሰዎች ላይ የሚታየው ምልክት ቀለል ያለ ሲሆን፤ የሞት መጠኑም በ2 እና በ5 በመቶ መካከል እንደሆነም ተገልጿል። በአሁኑ ጊዜ የበሽታው መነሻ በሆነችው ቻይና ውስጥ የወረርሽኙ መስፋፋት እየቀነሰ ሲሆን በቀረው ዓለም ግን በሽታው በከፍተኛ ፍጥነት እተዛመተ ነው ተብሏል። አውሮፓ ውስጥ ወረርሽኙ በስፋት በተገኘባት ጣሊያን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በ48 ሠዓታት ውስጥ በእጥፍ መጨመሩን መንግሥት ገልጿል። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 36 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በቁልፍ ጉዳዮች ላይ የሚወስኑትን የመንግሥት ተጠሪዎች ለአስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ ጠርተዋል። ከዚህ ቀደም ተከስተው የነበሩት ሳርስና መርስ የተባሉት የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች አሁን ከተከሰተው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ አንጻር ከፍተኛ የሞት መጠን ነበራቸው ተብሏል።
54795923
https://www.bbc.com/amharic/54795923
በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ የሆነው ምን ነበር?
በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 32 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል።
የኦሮሚያ ፖሊስ ከትናንት በስቲያ፣ ጥቅምት 22/ 2013 ዓ.ም የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 32 ነው ሲል የዓይን እማኞች እና አምነስቲ በበኩላቸው የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 54 ነው ይላሉ። የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 32 እንደሆነ ቢጠቀስም ኮሚሽኑ ያገኛቸው መረጃዎች አሃዙ ከዛ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ ብሏል። ይህ ግድያ የተፈጸመው ንጹሃን ዜጎች ለስብሰባ በሚል ምክንያት ተጠርተው በአንድ ስፍራ በኃይል እንዲሰበሰቡ ከተረጉ በኋላ መሆኑን የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ግድያው ማንነትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እንዲሁም አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ የገለፀ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ ሶስቱ ቀበሌዎች ላይ የሚኖሩ የአማራ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ አስታውቋል። አምነስቲም በመግለጫው ከ54 የማያንሱ ብሄራቸው አማራ የሆኑ ሰዎች ተገድለዋል ብሏል ትናንት ባወጣው መግለጫ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም በበኩላቸው ግድያው ማንነትን መሰረት ያደረገ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል። የክልሉ መንግሥት ጥቃቱን ያደረሰው ራሱን ኦነግ ሸኔ በማለት የሚጠራው ቡድን ነው ብሏል። ለመሆኑ ግድያው እንዴት ተፈጸመ? ጥቃቱ ሲፈጸም በስፍራው የነበሩ እና ከጥቃቱ በሕይወት ያመለጡ ሁለት ነዋሪዎችን ቢቢሲ አነጋግሯል። ያነጋገርናቸው አንድ የዓይን እማኝ የተጠራው ስብሰባ ላይ እንደነበሩና ከጥቃቱ አምልጠው አሁን ዲላ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሚገኙ ይናገራሉ። እኚህ አርሶ አደር እንደሚሉት ታጣቂዎቹ በኃይል ሰዎችን ወደ ስበሰባው እንዲመጡ ማድረጋቸውን እና በስብሰባው ላይ "አርሶ አደር ነን የምናውቀው ነገር የለም ስንላቸው ዛሬ ጭጭ ነው የምናደርጋችሁ መውጫ የላችሁም አሉን" በማለት የተፈጠረውን ይገልጻሉ። የዓይን እማኙ እንደሚሉት ነዋሪዎቹ በቅድሚያ በትምህርት ቤት አዳራሽ ውስጥ እንዲገቡ መደረጋቸውን ነው። አዳራሽ ውስጥ ታጣቂዎቹ 'የጦር መሳሪያ አምጡ' እንዳሏቸው ያስረዳሉ። "መሳሪያ የለንም ሌላ ነገር ከፈለጋችሁ እንስጣችሁ" እንዳሏቸውም እኚህ የዓይን እማኝ ይናገራሉ። ከዚያም ከአዳራሹ እንዳስወጧቸው ይናገራሉ። የዓይን እማኙ አክለውም ከአዳራሹ ካስወጧቸው በኋላ፤ "መትረየስ አጠመዱ፣ ክላሽም አጠመዱ። ሽማግሌዎች ኧረ የነፍስ ያለህ ቢሉ አናውቅም አሉ። ጥይት አርከፈከፉብን። ሰው እንዳለ ወደቀ። የሞተው ሞተ። እንዳው ዝም ብለን ደመ ነፍሳችንን ብትንትን አልን" ብለዋል። አክለውም "መጀመሪያ ኮማንድ ፖስት ሲጠብቀን ስለነበረ ነው እንጂ እኛም አንቀመጥም ነበር። እነሱ ልንሄድ ነው ተዘጋጁ ሳይሉን ቅዳሜ ድንገት ወጡ። ባዶ መሆናችንን ሲያውቁ ማታ ገቡ፤ የቤት እቃ፣ ስልክ ወሰዱ። እሁድ ሸኔዎቹ መጥተው አደጋ አደረሱብን" ሲሉም ተናግረዋል። እሳቸው ከ50 በላይ አስክሬን እንዳዩ እንዲሁም ቤት መቃጠሉንም ይናገራሉ። በአሁኑ ሰዓት ዲላ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሚገኙ እና ካምፕ ውስጥ የወረዳው አስተዳደደር ሰብስቦ ቢያስቀምጣቸውም በምግብ ተቸግረናልም ብለዋል። ለስብሰባ በተጠራው ቦታ ነበርኩ ያለች ሌላኛዋ የዓይን እማኝ በበኩላቸው አምና የዳሯት ልጃቸውን፣ አባታቸውን እና የልጃቸው ባል አባት እንደተገደሉባቸው ይናገራሉ። "ስብሰባ ብለው ትልቁንም ትንሹንም ጠሩ። መሣሪያ አስረክቡ አሉን። ገንዘብ፣ በሬ ወይም የፈለጋችሁትን እንስጣችሁ መሣሪያው ተለቅሞ ሄዷል አልን። በመጨረሻ እጃችንን እያርገበገብን እየለመናቸው ስብሰባ ላይ ያለነውን ፈጁ። ልጄን ከኔ ላይ ደፋት። የሷ ደም እኔ ላይ እየፈሰሰ እንደ አጋጣሚ ወጣሁ" ሲሉ ለቢቢሲ የተከሰተውን ገልጸዋል። አሁን ከአራት ልጆቻቸው ጋር ዲላ እንዳሉም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "እህል ውሃ የለም። ሕጻናት እህል ውሃ ከቀመሱ ሦስት ቀናችን ነው" ሲሉም ያሉበትን ፈታኝ ሁኔታ ገልጸዋል። ሁለቱም የዓይን እማኞች ጥቃቱ የተፈጸመው በቦምብ ሳይሆን "በክላሽ እና መትረየስ ነው" ይላሉ። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ሰኞ ረፋድ ላይ አሁን ባለን መረጃ ነዋሪዎቹ የተገደሉት በተወረወረባቸው ቦምብ ነው በማለት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። የጉሊሶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዳግም መልካሙ በበኩላቸው ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የአማራና የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች መገደላቸውን ይናገራሉ። "ሰዎች በአንድ ቦታ ሲገደሉ አማራዎች ብቻ አይደሉም የተገደሉት። ኦሮሞ የሆኑም ተገድለዋል። በአካባቢው ሁሉም በአንድ ላይ ተሰባጥረው ነው የሚኖሩት። በጥቃቱ የሁለቱም ብሔር ተወላጆች ተገድለዋል።" ይላሉ ከዚህም በተጨማሪ የቀበሌ አመራሮችም ሊገደሉ ኢላማ ተደርገው ስለነበር አካባቢውን ጥለው ሸሽተው እንደነበርም ለቢቢሲ አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት የተፈናቀለውን ሕዝብ ወደ ቀዬው እንዲመለስ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዲላ ተብላ በምትጠራ ከተማ ሰፍረው እንደሚገኙም በተጨማሪ ገልፀዋል። "የተገደሉትን መቅበር የተጎዱትን ማሳከም ላይ እንገኛለን። የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎችም ጥቃቱን ያደረሱት ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው" ብለዋል
news-48294427
https://www.bbc.com/amharic/news-48294427
ኬንያ፡ 22 ኢትዮጵያዊያን ናይሮቢ ውስጥ ተያዙ
የኬንያ ፖሊስ በሕገ ወጥ መንገድ በድብቅ ወደናይሮቢ ሊገቡ ነበር ያላቸውን 22 ኢትዮጵያዊያንን መያዙን ገለጸ።
በኬንያ የወንጀል መከላከል ልዩ ፖሊስ አባላት የተያዙት ኢትዮጵያዊያን በሁለት መኪኖች ተሳፍረው ሲጓዙ ነበር ተብሏል። ትናንት ከሰዓት በኋላ በፖሊስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ጋር በተያያዘ ሁለት ሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ገልጿል። • ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች የታሰሩት ኢትዮጵያዊያን ለፖሊስ እንደተናገሩት፤ የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በኬንያ በኩል ከዛም ታንዛኒያን በማቋረጥ ደቡብ አፍሪካ ለመድረስ አቅደው ነበር። ከተያዙት ስደተኞች መካከል 17ቱ ሴቶች ሲሆኑ፤ ሲያጓጉዟቸው የነበሩት ግለሰቦች ደግሞ ኬንያዊያን ናቸው። ኢትዮጵያዊያኑ በኬንያ በኩል ለማቋረጥ እንዲችሉ ለሚረዷቸው አዘዋዋሪዎች ምን ያህል ገንዘብ እንደከፈሉ የታወቀ ነገር የለም። • በሊቢያ የባህር ዳርቻ ስደተኞች ሰጠሙ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር የሆኑት ጆርጅ ኪኖቲ እንደተናገሩት፤ ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ማዘዋዋር በመጠኑ ከፍ እያለ በመሆኑ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። የኬንያ ባለስልጣናት እንደሚሉት፤ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያዊያን በኬንያ በኩል ለማቋረጥ ሲሞክሩ ተይዘው ወደመጡበት እንዲመለሱ የተደረጉ ሲሆን፤ አብዛኞቹ ሥራ ፍለጋ እና ወደሌላ ሀገር መሻገርን ግብ አድርገው ወደ ሃገሪቱ ይገባሉ። ስደተኞቹ ከድንበር ከተማዋ ሞያሌ አንስቶ እስከ ናይሮቢ ድረስ በሚጓዙበት ጊዜ ከሃያ በላይ የፖሊስ ኬላዎችን አልፈው መሆኑ የደህንነት ባለስልጣናትን ጥያቄ ፈጥሮባቸዋል። • ሕይወትን ከዜሮ መጀመር አንዳንድ ባለስልጣናት እንደሚሉት፤ ይህ አይነቱ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የሚፈጸመው በአዘዋዋሪዎቹና በጸጥታ ሰራተኞች መካከል በሚደረግ መመሳጠር ነው። ትናንት ከተያዙት ስደተኞች ጋር በተያያዘ የፖሊስና የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት እንዳሉት፤ የተያዙት ሰዎች እንግሊዝኛም ሆነ ስዋሂሊ ስለማይናገሩ ለመግባባት አልቻሉም። • እስራኤል አፍሪካዊያን ስደተኞች እንዲወጡ አዘዘች የኬንያ ባለስልጣናት በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ወጣቶች በተለያዩ መንገዶች ወደግዛታቸው እንደሚገቡ አመልክተው፤ በቅርቡም 8 የኤርትራ ዜጎች ኬንያ በመግባት ወደ እስያ ለመሻገር ሲሞክሩ መያዛቸውን ገልጸዋል።
49500592
https://www.bbc.com/amharic/49500592
በአፋር 3.8 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ ሙሉ የራስ ቅል መገኘቱ ተገለጸ
በአፋር ክልል 3.8 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ ሙሉ የራስ ቅል መገኘቱን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።
የፕሮጀክቱ መሪ ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለሥላሴ ቅሪተ አካሉ የተገኘው በአፋር ክልል ሚሌ ወረዳ ልዩ ስሙ ሚሮ ዶራ በተባለ አካባቢ ነው። በአካባቢው የወራንሶ ሚሌ የቅድመ ታሪክ ጥናት ፕሮጀክት የተባለ ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችን ያካተተ ቡድን ለሦስት ዓመታት ጥናት እያደረገ ነበር። • የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች? • የሉሲ ታላቅ በደቡብ አፍሪካ ተገኘች በቅሪተ አካሉ ላይ ለሦስት ዓመታት ጥናት እንደተደረገና ዛሬ 'ኔቸር' በተባለው የሳይንስ መጽሔት ላይ ግኝቱ ለዓለም ሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ገልጿል። አሜሪካ በሚገኘው የክሊቭላንድ የተፈጥሮ ሳይንስ ሙዝየም ኪውሬተርና የኬዝ ዌስተርን ሪዘርቭ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት የፕሮጀክቱ መሪ ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለሥላሴ እንደተናገሩት፤ ግኝቱ 'አውስትራሎፒቴክስ አናመንሲስ' በሚባለው የቀድሞው የሰው ዝርያ ውስጥ ይመደባል። ዝርያው ያልታወቁ የፊትና የጭንቅላት ቅርፅን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳየ እንደሆነም ዶ/ር ዩሐንስ ገልጸዋል። የምርምር ቡድኑ • የቀደመው ዘመናዊ ሰው ከአፍሪካ ውጪ ተገኘ ዶ/ር ዮሐንስ እንዳሉት፤ 'አውስትራሎፒቴክስ አናመንሲስ' በመባል የሚታወቀው የቀድሞው የሰው ዝርያ እስካሁን ድረስ ይታወቅ የነበረው ከ4.2 ሚሊዮን እስከ 3.9 ሚሊዮን ድረስ ነበር። ኤምአርዲ በመባል የሚታወቀው የራስ ቅል ዝርያ እስከ 3.8 ሚሊዮን ዓመት ድረስ እንደሚያሳይም አክለዋል። የፕሮጀክቱ መሪ ከዚህ ቀደም ከ3.9 ሚሊዮን ዓመት እስከ 3.6 ሚሊዮን ዓመት ድረስ ምንም አይነት የቅድመ ሰው ዝርያ ቅሪተ አካል እንዳልተገኘና የአሁኑ የመጀመሪያው ግኝት እንደሆነ አስረድተዋል። እስካሁን በመላ ምት ደረጃ የነበረውን የ'አውስትራሎፒቴከስ አናመንሲስ' እና የሉሲ (ድንቅነሽ) ዝርያ የሆነው 'አውስትራሎፒቴከስ አፋረንሲስ' ግንኙነትን በተመለከተ በቂ ደረጃ የሰጠ ግኝት መሆኑንም ዶ/ር ዩሐንስ ተናግረዋል። የተገኘው የራስ ቅል ቅሪተ አካል ከመሆኑ በፊት ይህንን እንደሚመስል ተመራማሪዎች ገልጸዋል • የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ በአየር ፀባይ ይመራ ነበር በአፋር ክልል እንዲሁም በሌሎችም የስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች እስከ 6 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠሩ የቅድመ ሰው ዝርያ ቅሪተ አካላት ተገኝተዋል። ግኝቶቹ ኢትዮጵያን በሰው ዘር አመጣጥ ጥናት ቀዳሚ ቦታ እንደሰጧት ተመራማሪዎች ይናገራሉ። እስካሁን ድረስ ከሚታወቁት ከሀያ የማያንሱ የቅድመ ሰው ዝርያዎች መካከል አሥራ ሦስቱ የተገኙት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። የቅድመ ሰው ዝርያ ለሰው ዘር አመጣጥ ጥናት አዲስ መረጃ ከመስጠት ባሻገር ኢትዮጵያ የሰው ዘር ምንጭ እንደሆነች ተጨማሪ ማረጋገጫ እንደሆነ ዶ/ር ዮሐንስ ተናግረዋል።
news-54862123
https://www.bbc.com/amharic/news-54862123
የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ሴቶችን መግደል ከባድ ወንጀል እንዲሆን ልታደርግ ነው
በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ሴት ልጅ ቤተሰብ አዋረደች በሚል ከወግ፣ ሃይማኖትና ባሕል ያፈነገጡ ተግባራትን ፈጽማለች ተብሎ ሲታሰብ የሞት ቅጣት በገዛ ቤተተሰቦቿ ሊፈጸምባት ይችላል፡፡
በዚህ ረገድ በገዳዮቹ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ልል ሆኖ ቆይቷል፡፡አሁን ግን የተባበሩት ኤምሬትስ የሕግ ማሸሻያ ለማድረግ ዝታለች፡፡ ማሻሻያው ሴቶችን በገደሉ የቤተሰብ አባላት ላይ ዳኞች አነስተኛ ቅጣት ወይም የቅጣት ማቅለያ እንዳያደርጉ የሚያስችል ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቶቹ ወንጀሎች ‹‹የክብር ግድያ›› ወይም ‹‹ኦነር ኪሊንግ› በሚል ተቀጽላ እንደ ትክክለኛ እርምጃ የመውሰድ አዝማሚያዎች ነበሩ፡፡ አሁን ይህ እንዲቀር ይደረጋል ተብሏል፡፡ሰውን ገድሎ የክብር ግድያ ብሎ ነገር የለም የሚሉ የመብት ታጋዮችም መጠርያው ሊቀየር ይገባል ይላሉ፡፡ የኤምሬትስ ባለሥልጣናት በበኩላቸው የቤተሰብን ክብር ለማስጠበቅ በሚል በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች እንደ ማንኛውም ግድያ ወንጀል እንዲታዩ ለማድረግ ቆርጦ ተነስቷል፡፡ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች እንደሚሉት በመላው ዓለም ሴት ልጅን ለቤተሰብ ክብር ማስጠበቂያ በሚል መግደል እጅግ እየተዘወተረ ነው፡፡ በየዓመቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች በዚህ መልኩ ይገደላሉ፡፡ ቤተሰብ አዋረደች በሚል በሴቶች ላይ የሚደረጉ ግድያዎች እንደ ሌሎች ግድያዎች ለማየት የኤምሬትስ መንግሥት መወሰኑ ትልቅ እርምጃ ነው በሚል እየተወደሰ ነው፡፡
43137655
https://www.bbc.com/amharic/43137655
በሻንጣ ውስጥ ተጉዞ ስፔን የደረሰው ልጅ አባት ከእስር ነፃ ሆነ
የአይቮሪኮስት ዜግነት ያለው አባት የስምንት አመት ልጁ በሻንጣ ውስጥ ከሞሮኮ ተጉዞ ስፔን የደረሰ ሲሆን፤ አባትየው በቅርቡ ከእስር ነፃ ተደርጓል።
የመንግሥት ዓቃቤ ህግ አባትየውን አሊ ኡታራን ልጁን በህገወጥ መንገድ ወደ ስፔን አጓጉዟል በሚል እስር ይገባዋል ብለዋል። ነገር ግን አባትየው ልጁ በሻንጣ ውስጥ እንደሚጓጓዝ ስለማወቁ ምንም ማስረጃ ባለማገኘቱ ቀለል ባለ ቅጣት ታልፏል። "እኔም ይሁን አባቴ በሻንጣ እንደሚወስዱኝ አላወቅንም" በማለት አሁን የ10 ዓመቱ ልጁ አዱ ለዳኞች ተናግሯል። ልጅየው ጨምሮ እንደተናገገረው በእስር ለአንድ ወር የቆየው አባቱ የነገረው ጉዞው በመኪና እንደሚሆን ነው። ከሞሮኮ ወደ ስፔን ድንበር በማቋረጥ ላይ ባሉበትም ወቅት በሻንጣው ውስጥም መተንፈስ ተቸግሮ እንደነበር ይናገራል። በአውሮፓውያኑ 2015ም በድንበር ላይ የሚገኙ ኃላፊዎች ከባድ የሆነ ሻንጣ አንዲት ሴት ስትጎትት አይተው ተጠራጥረው አስቁመዋታል። አባትየውም 115 ዶላር የሚጠጋ የብር ቅጣትም እንዲከፍሉ ተደርጓል። ልጅየው ከእናቱ ጋር ከፓሪስ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ የሚኖር ሲሆን ለመመስከርም ወደ ስፔን አቅንቶ ነበር። "አሁንም ሁሉ ነገር ተፈፅሟል። ከአሁን በኋላ ከሚስቴና ከልጆቼ ጋር እንዳዲስ ህይወታችንን የምናቃናበት ጊዜ ነው" በማለት ኦታራ በሰሜናዊ ስፔን አዲስ ህይወት እንደሚጀምሩም ተናግሯል።
news-45277501
https://www.bbc.com/amharic/news-45277501
ሙስጠፋ ኡመር የሶማሌ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ
አቶ ሙስጠፋ ኡመር ጊዜያዊ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።
አቶ ሙስጠፋ ኡመር የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲመሩ የሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደመረጣቸው አዲስ አበባ የሚገኘው የቢቢሲ ሶማልኛ ሪፖርተር አረጋግጧል። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልን ለበርካታ ዓመታት የመሩትን አቶ አብዲ ሙሐመድ ኡመርን በመተካት ላለፉት ሁለት ሳምንታት ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ አህመድ አብዲ ሞሐመድ፤ አቶ ሙስጠፋ የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን አረጋግጠዋል። አቶ አህመድ፤ አቶ ሙስጠፋ የሶማሌ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ተደርገው መሾማቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ የቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል። አዲሱ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት የሶህዴፓ አባል ባይሆኑም ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ የፓርቲው ሕገ-ደንብ እንደሚፈቅድላቸው አክለዋል። አቶ ሙሰጠፋ ከክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነታቸው በተጨማሪ የሶህዴፓ ምክትል ሊቀመንበር ተደርገውም ተሹመዋል። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ሺዴ የሶህዴፓ ሊቀመንበር ተደርገው መሾማቸው ይታወሳል። • አብዲ ሞሃመድ ኡመር ከስልጣናቸው ወረዱ • አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ • አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ማን ናቸው? አቶ ሙስጠፋ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሐመድ ኡመር የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይፈጽማሉ በማለት በተደጋጋሚ በመተቸት ይታወቃሉ። ከሳምንታት በፊት አቶ አብዲ ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ጋር አድርገው የነበረው ቆይታ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በወቅቱ አቶ አብዲ ከተናገሩት የብዙዎችን ቀልብ ይዞ የነበረው፤ የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን በሚመለከት የሰጡት አስተያየት ነበር። ''ጌታቸው ሙሰኛ፣ ሌባ እና ራሰ ወዳድ ነው'' ብለው ነበር። • አቶ አብዲ ስለተናገሩት ጉዳይ እንደማያውቅ ኢህአዴግ ገለፀ ይህን አስተያየታቸውን ተከትሎ ከሳምንታት በፊት አቶ ሙስጠፋን አነጋግረናቸው ነበር። በወቅቱ ራሳቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ብለው የሚጠሩት አቶ ሙስጠፋ፤ አቶ አብዲ በቅርቡ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርነት እንዲነሱ የተደረጉት አቶ ጌታቸውን በከፍተኛ ደረጃ መውቀስ ለምን አስፈለጋቸው? የሚል ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር። አቶ ሙስጠፋ በምላሹ፤ አቶ አብዲ ይህን መሰል ወቀሳን መሰንዘር ያስፈለጋቸው፤ "የአዲሱ የፖለቲካ ለውጥ አካል ሆነው ስልጣን ላይ መቆየት ስለሚፈልጉ ነው። አቶ ጌታቸው እና ሌሎች ግለሰቦች ይፈጽሙ የነበሩትን በይፋ ማውጣት 'ተዓማኒነትን ያተርፍልኛል' የሚል ስሌትን በመያዝ ያደረጉት ነገር ነው'' ብለውን ነበር። "ከቀናት በፊት የክልሉ ምክር ቤት ተሰብስቦ ባለበት ወቅት አቶ አብዲ አንድ ጥቁር ቦርሳ ይዘው መጡ። ከዚያም 'በዚህ ሻንጣ ውስጥ በርካታ ሚስጥሮች አሉኝ። የክልሉ ባለስልጣናት እና የፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት ሚስጥር እዚህ ውስጥ አለ። ገንዘብ የከፈልኳቸው ባለስልጣናት አሉ። እኔን ቢነኩ ይህን ሚስጥር አወጣለሁ' በማለት ሲያስፈራሩ ነበር'' በማለት ተናግረውም ነበር። የቀድሞ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አብዲ ከስልጣናቸው ከተነሱ ሁለት ሳምንታት አልፈዋል። አቶ አብዲ ከክልል ፕሬዚዳንትነታቸው መነሳታቸው ከተሰማ ከሁለት ቀናት በኋላ አህመድ አብዲ ሼክ ሞሃመድ (ኤልካስ) ፕሬዚዳንት ተደርገው ተሹመው ነበር።
news-47112939
https://www.bbc.com/amharic/news-47112939
ደቡብ ጎንደር መካነ እየሱስ ውስጥ ምን ተፈጠረ?
በትናንትናው ዕለት (ዕሁድ) በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር መካነ እየሱስ ከተማ በነዋሪዎች መካከል የተፈጠረ ቅሬታ ሃይማኖታዊ ገጽታን በመያዝ አለመግባባቱ ከቁጥጥር ውጪ ወጥቶ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ችግሩ መነሻ ምን ነበር?
አቶ አደም ጡሃሬ ሴት ልጃቸውን ለመዳር ጥር 26/2011 ዓ.ምን ምርጫቸው አደረጉ። በቀጠሮው መሰረት ሠርግ የሚጠይቀውን ማንኛውንም ነገር ተሰናድቶ ተቆረጠው ዕለት የሠርግ ሥነ ሥርዓቱ መከናወን ጀምሯል። ያልተጠበቀው ነገር የሆነው ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ነበር። ቢቢሲ የመካነእየሱስ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተወካይ ሃላፊ ኢንስፔክተር አወቀ ተሸሽጎን ምን ተፈጠረ ብሎ ጠይቋል። •የጥምቀት በዓል አከባበር በጎንደር •የጦር መሳሪያዎቹ ምንጫቸው የት ነው? ኢንስፔክተሩ እንደገለጹት የሠርጉን ዳስ ለማስዋብ ከማተሚያ ቤቶች የተቆራረጡ ወረቀቶችን አቶ አደም ከባህርዳር በማስመጣት ድንኳን ዉስጥ ነስንሰዋል። በሠርጉ ደግሞ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ታዳሚ ነበር። አስር ሰዓት አካባቢ ግን ከተነሰነሰው የወረቀት ቁርጥራጭ መካከል "የድንግል ማርያም ስዕለ አድህኖ" ሲረገጥ አይተናል በማለት ክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ቅሬታ ያሰማሉ። የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ሁኔታውን በማረጋጋት የሠርጉ ደጋሽ አቶ አደምን ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ በማድረግ ሌሎች ደግሞ ወደየመጡበት ተስማምተዉ እንዲመለሱ ያደርጋል። ይህ ግን ከተወሰኑ ደቂቃዎች በላይ መቀጠል አልቻለም። ወጣቶቹ በመሰባሰብ ተመልሰው ወደ ሠርጉ ቤት በመሄድ የሠርጉን ድንኳንና ሌሎች ንብረቶችን በማቃጠል ግጭቱን ጀመሩ። •"በግጭቱ 'ጀምበሬ' የሚባለው ሰፈር ሙሉ በሙሉ ወድሟል" ነዋሪዎች •ከሁለት ወር በፊት ሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ሰው 'ዳግም' ሞቱ በዚህ ያልተቋጨዉ የወጣቶቹ እንቅስቃሴ በከተማው የሚገኙ ሱቆችንና የሞባይል መጠገኛ ማዕከሎችን ከመዝረፍም በተጨማሪ በከተማዋ የሚገኘውን መስጊድ እስከማቃጠል ደርሷል ብለዋል ኢንስፔክተር አወቀ። ኢንስፔክተሩ አክለውም "ችግሩን ለመቆጣጠር ጥረት ብናደርግም ካቅማችን በላይ በመሆኑ ከዞን ልዩ ኃይል እስኪመጣ ድረስ ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ቆይቷል" ብለዋል። በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት እያጣራን ነው ያሉት ተወካይ ሃላፊው ሁለት ግለሰቦች እና አንድ የመስጊዱ ጥበቃ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል። "የሙስሊሙ ማህበረሰብ ምንም አይነት የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ አልሞከረም። እንዲያውም ቤቱንና ንብረቱን በመተው ወደ ክርስቲያን ወገኑ በመጠለል ችግሩ እንዳይባባስ ያሳየው መልካም ተግባር የሚያስመሰግን ነው" ብለዋል። "ችግሩን ሆን ብሎ ያነሳሳው አካል አለ" ያሉት ኢንስፔክተር አወቀ እስካሁን ስለተወሰደው እርምጃና የምርመራ ውጤት ለጊዜው መናገር እንደማይፈልጉ ገልጸው ወደፊት አጥፊዎቹን በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርጉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኢንስፔክተሩ ጨምረው ዛሬ በአካባቢው መረጋጋት መስፈኑንና ችግሩ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገለጸዋል።
news-45396264
https://www.bbc.com/amharic/news-45396264
በናይጄሪያ አዲሱ የማዋለጃ ቦርሳ የእናቶችን ህይወት እየታደገ ነው
"እንዳንዴ የእኛ ሥራ የማያስፈልግበት አንድ ቀን እንዲመጣ ከልብ እመኛለሁ" ትላለች የናይጄሪያው ብራውን በተን ፋውንዴሽን መስራች አዴፔጁ ጄዬኦባ።
ፔጁ ጄዬኦባ በናይጄሪያ ለጤናማና ንጹህ ወሊድ ጠቃሚ ምርቶችን የያዙ ግማሽ ሚሊዮን ህይወት አድን የማዋለጃ ቦርሳዎችን አሰራጭታለች። ከሰባት ዓመታት በፊት ነበር አዴፔጁ በቁልምጫ ስሟ 'ፔጁ' ለናይጄሪያ የልምድ አዋላጆች የማዋለድ ስልጠና ለመስጠት ስትል ከፍተኛ ክፍያ የምታገኝበትን የሕግ ሥራ የተወችው። ከባክቴሪያ የጸዱ ወሳኝ የህክምና ቁሶችን የያዘ ቦርሳም አዘጋጅታ በናይጄሪያ ገጠራማ አካባቢዎች በአነስተኛ ዋጋ እየተሸጠ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ታድጓል። ጓደኞቿና ቤተሰቦቿ ሥራቸውን እንዳትለቅ ሊያሳምኗት ቢሞክሩም በወሊድ ምክንያት የቅርብ ጓደኛዋን በማጣቷ ሌላ አማራጭ አልታያትም። •"አቶ በረከት ባለሐብቶችን ለቅመህ እሰር ብሎኝ ነበር" አቶ መላኩ ፈንታ •አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" •«ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» "ጓደኞዬ የተማረች ነበረች፤ እናም የገንዘብ ችግር የሌለበት ሰው በወሊድ ምክንያት የሚሞት ከሆነ 'አገልግሎቱ ባልተሟሉባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ምን ሊፈጠር ይችላል?' ብዬ እንዳስብ አስገደደኝ።" "በእጅጉ ተስፋ ቆርጬ ነበር፤ በድጋሚ ሌላ ሰው ማጣት አልፈለግኩም ነበር፤ ለአንዱ ህይወትን የመስጠት ሂደት የሌላኛውን ሰው ሕይወት ማሳጣት አለበት ብዬ አላስም።" ህጻናት በናይጄሪያ በሚሸጠው ቦርሳ ውስጥ በሚገኘው አነስተኛ ምንጣፍ ላይ ይለወዳሉ። የመፍትሄ እርምጃ ከሃኪም ወንድሟ ጋር በመሆን በገጠር የሚኖሩ ሴቶች እንዴት ባለ ሁኔታ አንደሚወልዱ በውል ለመረዳት ከሌጎስ በስተሰሜን ወደ ሚገኝ ስፍራ አቀናች። ያገኘችው ነገርም በእጅጉ የሚረብሽ ነበር። "ሴቶች በባዶ መሬት ላይ ሲወልዱ፣ ነርሶችም ጨቅላዎቹ እንዳይታፈኑ ፈሳሹን በአፋቸው ሲስቡ ተመለከትን" ትላለች። •ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? "አዋላጆች አትብት በዛጉ ምላጮችና ብርጭቆ ስባሪ ስለሚቆርጡ ጨቅላዎች በመንጋጋ ቆልፍ ሲያዙ ብዙዎችም ሲሞቱ አየን።" "እጆችን መታጠብና ጓንት ማጥለቅን የመሰሉ መሰረታዊ ነገሮች እንኳ እዚህ ትልልቅ ጉዳዮች ናቸው።" በናይጄሪያ በየቀኑ 118 እርግዝናዎች በሞት ይቋጫሉ፤ ሀገሪቱ ከወሊድ ጋር የተያያዘ የእናቶች ሞት በከፍተኛ ቁጥር ከሚመዘገብባቸው ሃገራት አንዷ ናት። ሂደቱ በጣም አሳሳቢ ነው የምትለው ፔጁ፤ ብዙዎቹ ወላዶች ወሊድን ከመንፈሳዊ ገፅታው አንጻር ስለሚመለከቱት ንፅህናቸውን ከጠበቁ የህክምና መገልገያዎች ይልቅ ባህላዊ መድሃኒቶችና ጸሎት ጥቅም ላይ ወደሚውሉባቸው የባህል ሃኪሞች ዘንድ መሄድን ይመርጣሉ። የፔጁ ቦርሳዎች ዋነኛ አላማቸው ለባክቴሪያ የመጋለጥ ዕድልን መቀነስ ነው። አስፈላጊውን ማሟላት ፔጁ የልምድ አዋላጆችን በዘመናዊ የማዋለጃ ዘዴዎች ለማሰልጠን ብራውን በተን የተሰኘውን ድርጅትን መስረተች። በወቅቱ ይህ መንገድ ለማዋለጃ ቦርሳው ሁነኛ የስርጭት ሰንሰለት እንደሚያበጅላት ግን ብዙም አልተረዳችውም ነበር። እንዴት ተጀመረ "በሌጎስ የምንገዛቸው ነገሮች በሰሜናዊው የሃገሪቱ ክፍል በጣም ውድ እንደሆኑ ተገነዘብኩኝ። ለምሳሌ ጓንት በሦስት እጥፍ ሊወደድ ይችላል።" አምራቾች በርካሽ ዋጋ ለዚያውም ሌጎስ ከሚሸጥበትም ዋጋ በታች እልፍ ሲልም በገጠራማ አካባቢዎች ከሚሸጥበትም ባነሰ ዋጋ እንዲሸጡላቸው በደንብ ተከራክረው ለመነሻ የሚሆናቸውን 30 እሽጎችን ነበር የገዙት። "እንዲህም ሆኖ አንዳንድ ሰዎች አሁንም ቢሆን ቦርሳውን የመግዛት አቅም እንደሌላቸው ነገሩን" ትላለች ፔጁ። "ነገር ግን ለማዋለጃ ቦርሳው የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማጠራቀም የዘጠኝ ወር ጊዜ አላቸው፤ በእያንዳንዱ የቅድመ ወሊድ ምርመራ ጊዜ መዋጮ ቢያስቀምጡ በመውለጃቸው ጊዜ ክፍያው ይጠናቀቃል።" እናቶች ቦርሳው የሚያወጣውን አራት ዶላር በዘጠኝ ወራት የእርግዝና ጊዜያቸው መክፈል ይችላሉ። ቦርሳው ከባክቴሪያ ማጽጃ ጀምሮ ንጹህ ጓንት፣ የእትብቱ መቁረጫ ምላጭ፣ በምጥ ጊዜ የሚነጠፍ አነስተኛ ምንጣፍና ከወሊድ በኋላ ከፍተኛ ደም መፍሰስን የሚቀንሱ መድሃኒቶችንና ሌሎች 13 አይነት መገልገያዎችን ይዟል። የአንዱ ቦርሳ ዋጋ 4 ዶላር ገደማ የሚያወጣ ሲሆን በውስጡ ከያዛቸው መገልገያዎች መካከል አብዛኞቹ እዚያው ናይጄሪያ ውስጥ የሚመረቱ ናቸው። ባለፉት አራት ዓመታት ብራውን በተን ፋውንዴሽን ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ የማዋለጃ ቦርሳዎችን አሰራጭቷል። ፋውንዴሽኑ እንደሚለው ስልጠናውና የቦርሳው አቅርቦት በጥምረት በተሰጡባቸው አካባቢዎች ከወሊድ በኋላ በሚከሰት ከፍተኛ የደም መፈስሰ የሚሞቱት ወላዶች ቁጥር በአንድ አራተኛ ቀንሷል። "ለጤናማ ወሊድ የሚያገለግሉት እነዚህ ቦርሳዎች በወሊድ ወቅት እናቲቱንም ሆነ ጨቅላውን ከቁስል መመርቀዝ (ኢንፌክሽን) መከላከሉ ጥሩ ሃሳብ ነው ምክንያቱም የቁስል መመርቀዝ ወላዶቹን ለሞት ከሚዳርጉ መንስዔዎች አንዱ ነው" ብለዋል በሌጎስ ዩኒቨርስቲ የማህጸንና የጽንስ ህክምና መምህር የሆኑት ቦሴዴ አፎላቢ። "ንጹህ ጓንት፣ ንጹህ የማዋለጃ ቦታ እና እንግዴ ልጁና እትብቱ የሚለያዩበት ንጹህ መቁረጫ ካለ በባክቴሪያ የመጠቃት ዕድሉን ይቀንሳል።" ፔጁ ከፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ስትገናኝ የሚያሳየውን ፎቶ በጠረጴዛዋ ላይ በክብር አስቀምጣዋለች። ኦባማ ወይስ የስልክ ማጭበርበር? አንድ ቀን ፔጁ ቢሮ ስትገባ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከነበሩበት ኋይት ሃውስ ከሚገኝ አንድ ሰው የስልክ መልዕክት ይደርሳታል። እቤት ሄዳ ስለዚሁ መልዕክት ለባሏ ከነገረችው በኋላም ቢሆን የሆነ ሰው እየቀለደባቸው ሊሆን አንደሚችል ነበር የተስማሙት። "ለማንም የምስጢር ቁጥርሽንም ሆነ የባንክ አካውንት ቁጥርሽን እንዳትሰጪ" አላት። ሆኖም በእርግጥም መልዕክቱ የመጣው ከኋይት ሃውስ ነበር። ከእያንዳንዱ አህጉር የፈጠራ ሰዎችን ሲጋበዙ ፔጁ ከአፍሪካ እንድትሄድ ተመርጣ ነበር። "ወደ ኋይት ሃውስ ስገባ እስታውሳለሁ ህልም ነበር የመሰለኝ" ትላለች። "ስለአፍሪካ የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት እና ስለ ጤና ክብካቤ አወራን፣ በሥራዬም ትልቅ ለውጥ እንዳስመዘገብ አድርጎኛል።" ይህ የቢቢሲ ተከታታይ ዝግጅት የሚቀርበው በቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ ነው። የእናቶችንና የሕፃናትን ህይወት እየታደገ ያለው ቦርሳ
news-48796795
https://www.bbc.com/amharic/news-48796795
"ሌሎችንም ከፍተኛ ባለስልጣናት የመግደል ዕቅድ ነበረ" የፀጥታና ፍትህ የጋራ ግብረ ኃይል
ባህር ዳርና አዲስ አበባ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ ካጋጠመው ግድያ በተጨማሪ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ሌሎች የከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናትን የመግደል ዕቅድ እንደነበራቸው ተገለጸ።
ከተለያዩ የመንግሥት አካላት ተወጣጥቶ ተፈጸመ የተባለውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራና ግድያዎችን ክስተት እየተከታተለ ያለው የፀጥታና ፍትህ የጋራ ግብረ ኃይል ሐሙስ ምሽት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው የድርጊቱ ፈጻሚዎች "ተከታታይ ግድያ በሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ጭምር ለመውሰድ አቅደው ነበር።" ግብረ ኃይሉ አክሎም ከመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ከግድያዎቹ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሁለት መቶ ሃምሳ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስታወቀ ሲሆን፤ እነዚህም 212 ሰዎች በአማራ ክልል እንዲሁም 43 ሰዎች ደግሞ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መያዛቸውንና በተጨማሪም በርካታ መጠን ያላቸው የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመልክቷል። • ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ • የጦር እና ሲቪል መሪዎቹ ግድያ፡ ከቅዳሜ እሰከ ዛሬ ምን ተከሰተ? ከቅዳሜው ክስተት ጋር በተያያዘም ሌሎች ጥቃቶችን ለመፈጸም የሚያስችሉ ዕቅዶችና ሰነዶች በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የፀጥታና ፍትህ የጋራ ግብረ ኃይል አሳውቋል። በባህር ዳር በክልሉ መስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ግድያ በመፈጸም የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መደረጉ ከተገለፀ ሁለት ቀናት በኋላ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ እንደተገደሉ የተነገረው ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌና ግብረ አበሮቻቸው ድርጊቱን እንደፈጸሙ በተጨባጭ መረጃዎች ማረጋገጡን ጠቅሶ "ስልጣንን በኃይልና በመሳሪያ አፈሙዝ ለመያዝ የተደረገ" ያለውን ሙከራንም ግለሰቡ ማቀነባብራቸውን ግብረ ኃይሉ አመልክቷል። በተጨማሪም ግብረ ኃይሉ በመግለጫው ላይ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነውና ግብረ አበሮቻቸው "የመንግሥትን ይቅር ባይነትና ሆደ ሰፊነት ወደ ጎን በመተው፤ ክህደት በመፈጸም እና ከዚህ አልፎ ሕዝብ ከሕዝብ ጋር በማጋጨት፣ ሥልጣን በኃይል እና በአቋራጭ ለመያዝ፣ ሐገራችንን እና ሕዝቦቿን ለመበታተን ተንቀሳቅሰዋል" ሲል ከሷቸዋል። ግብረ ኃይሉ በመግለጫው «ማናቸውም የሽብር እንቅስቃሴዎችን አንታገስም» ሲል አስጠንቅቋል። • የጦር እና ሲቪል መሪዎቹ ግድያ፡ ከቅዳሜ እሰከ ዛሬ ምን ተከሰተ? • “የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ነበር” ከዚህ በተጨማሪም ግብረ ኃይሉ አዲስ አበባ ውስጥ በቤታቸው ውስጥ ግድያ የተፈጸመባቸውን የሃገሪቱን ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንንና ባልደረባቸውን ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራን ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረውን የጄነራሉን የግል ጠባቂ ማንነት ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ግብረ ኃይሉ በመግለጫው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መኮንን ሁለቱን ጄነራሎች በመግደል መጠርጠሩን ከፎቶ ግራፍ ጋር አቅርቧል። አክሎም ተጠርጣሪው ጥቃቱን ከፈጸመ በኋላ ቆስሎ በቁጥጥር ስር እንደሚገኝ አመልክቷል። ግብረ ኃይሉ አክሎም በባህር ዳሩ ከፍተኛ አመራሮች ግድያና በአዲስ አበባው የከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ግድያ መካከል ያለውን ግንኙነት እያጣራ መሆኑን ገልጿል ባለፈው ቅዳሜ ስለተሞከረው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራና የከፍተኛ ሲቪልና ወታደራዊ ባለስልጣናት ግድያን በተመለከተ እስካሁን አገኘሁ ያለውን መግለጫ የሰጠው የፀጸጥታና ፍትህ የጋራ ግብረ ኃይል የሃገር መከላከያ ሠራዊትን፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽህፈት ቤትን፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን እንዲሁም የፌደራል ፖሊስን ያካተተ መሆኑ ተነግሯል።
news-57340435
https://www.bbc.com/amharic/news-57340435
ግዙፉን ስጋ አምራች ያጠቃው የሩስያው መረጃ መዝባሪ ነው ሲል ኤፍቢአይ ወቀሰ
የሩስያ የሳይበር ጥቃት ቡድን የዓለማች ግዙፉ ስጋ አቅራቢ ድርጅት ላይ ጥቃት አድርሷል ሲል ኤፍቢአይ ወቅሷል።
የአሜሪካው የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ድርጅት ኤፍቢአይ የሩስያው ሳይበር አጥቂ ቡድን ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ እየሠራ መሀኑን ይፋ አድርጓል። ጄቢኤስ የተሰኘው ስጋ አቅራቢ ድርጅት ባፈለው ቅዳሜና እሁድ በደረሰበት ጥቃት ምክንያቱ በአሜሪካ፣ ካናዳና አውስትራሊያ የሚገኙ የተወሰኑ ቅርንጫፎቹ ተዘግተው ነበር። ሬቪል አሊያም ደግሞ ሶዲኖኮቢ በመባል የሚታወቀው ቡድን በዓለማችን ካሉ ግዙፍ የበይነ መረብ መረጃ መዝባሪዎች መካከል አንዱ ነው። "ስጋ አቅራቢው ድርጅት ላይ የደረሰው ጥቃት ከሬቪል ጋር ተያያዥነት ያለው ነው። እነዚህን ሰዎች ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ እየተጋን ነው" ይላል ኤፍቢአይ የለቀቀው መግለጫ። ዋይት ሃውስ ረቡዕ ዕለት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከሩስያ አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ሲገናኙ የሳይበር ጥቃት ጉዳይን እንደሚያነሱ አስታውቋል። "ኃላፊነት የሚሰማቸው ሃገራት የሳይበር ጥቃትን አይደግፉም" ብለዋል ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ጄን ሳኪ። ፑቲንና ባይደን ከሁለት ሳምንታት በኋላ ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጄቢኤስ አሜሪካ ውስጥ አምስት ግዙፍ ስጋ ማምረቻዎች አሉት። በጥቃቱ ምክንያት ስራ ያቆመው ድርጅት ሐሙስ ዕለት እንቅስቃሴ እጀምራለሁ ብሏል። ጥቃት እንደደረሰበት እሁድ ይፋ ያደረገው ኩባንያው ለመረጃ መዝባሪዎቹ ገንዘብ ይክፈል አይክፈል ያለው ነገር የለም። ራንሰምዌር የሳይበር ጥቃት ዓይነት ነው። መረጃ ጠላፊዎች ወደ ድርጅቶች ኮምፒውተር ሰርስረው ይገቡና መረጃዎችን ይዘጋሉ አሊያም ሰዎች ኮምፒውተሮቻቸውን እንዳይጠቀሙ ያደርጋሉ። ጠላፊዎቹ ብዙ ጊዜ ይህን የሚያደርጉት ገንዘብ ፍለጋ ስለሆን እስኪከፈላቸው ድረስ ኮምፒውተሮች እንደተቆለፉ ይቆያሉ። በፈረንጆቹ 1953 ብራዚል ውስጥ የተቋቋመው ጄቢኤስ በ15 ሃገራት 150 ስጋ ማምረቻዎች አሉት። በዓለም አቀፍ ደረጃ 150 ሺህ ሠራተኞች የሚያስተዳድረው ግዙፉ ድርጅት ለአሜሪካ አንድ ሶስተኛ የበሬ ስጋ፤ እንዲሁም አንድ አምስተኛ የአሳማ ስጋ ያቀርባል። ሬቪል የተሰኘው የበይነ መረብ መረጃ መዝባሪ ቡድን ከዚህ ስጋ አምራች አልፎ ቴክሳስ ውስጥ ያሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን አጥቅቶ ነበር። ባለፈው ወር በደቡብ ምስራቅ አሜሪካ ነዳጅ በማቅረብ የሚታወቀው ድርጅት ከሩስያ ጋር ግንኙነት ባለው ሌላ መረጃ መዝባሪ ቡድን ጥቃት ደርሶበት ነበር። ነዳጅ አቅራቢው ድርጅት ለመረጃ መዝባሪው ቡድን 4.4 ሚሊዮን ዶላር እንደከፈለ አስታውቋል። የአሜሪካ መንግሥት ድርጅቶች ለመረጃ መዝባሪዎች ድንቡሎ እንዳይከፍሉ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ክፍያው መዝባሪዎችን ያበረታታል የሚል ነው።
42556089
https://www.bbc.com/amharic/42556089
የጣና ሐይቅን ሌሎችም አረሞች ያሰጉታል
ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሳይንስ መምህር እና ተመራማሪ ናቸው። በጣና ዙሪያ መወለዳቸውን የሚገልጹት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ላለፉት 15 ዓመታትም በጣና ሐይቅ ላይ በግላቸውም ሆነ ከተማሪዎቻቸው ጋር የተለያዩ ምርምሮችን አድርገዋል።
ጣና ሐይቅ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ፈተናዎች እየገጠሙት ነው ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በሐይቁ ዙሪያ ከመሥራታቸውም በላይ በጣና ውሃ ብክለት፣ የአካባቢው የውሃ አዘል መሬቶች፣ የጣና የውሃ ውስጥ ብዝሃ-ህይወት በአጠቃላይ በጣና ደህንነት ዙሪያ የተለያዩ ምርምሮችን አካሂደዋል። "ሐይቁ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ፈተናዎች እየገጠሙት ነው። የአፈር መከላት፣ የደለል ክምችት፣ ተገቢ ያልሆነ የሥነ-ሕይወት አጠቃቀም፤ ልቅ ግጦሽ እና የባህር ሸሽ እርሻ ተጠቃሾች ናቸው። በተለይ ደግሞ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በሰሜናዊ ምሥራቅ የሐይቁ ክፍል የተከሰተው የእምቦጭ አረም ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል" ይላሉ ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው። እምቦጭ አረም ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። በ1965 ዓ.ም በቆቃ ሐይቅ ላይ ተከስቶ እንደነበር ፕሮፌሰሩ ይገልጻሉ። የአረሙ ዋነኛ መነሻው ደቡብ አሜሪካ ብራዚል ነው። በጣና ሐይቅ ላይ ከመታየቱ በፊት በ2004 ዓ.ም መገጭ በሚባል ወንዝ ላይ ቀድሞ መከሰቱን ተመራማሪው ለቢቢሲ ተናግረዋል። እጅግ አደገኛ የሆነው ይህ መጤ አረም ግንዱን እና ፍሬውን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች የሚራባ መሆኑ በፍጥነት እንዲስፋፋ አስችሎታል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከመገጭ ወንዝ ላይ በመነሳት እስከ 100 ኪሎ ሜትር በመጓዝ የጣና ሐይቅ በአረሙ እንዲሸፈን አድርጓል ይላሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የአየር ንብረት ለውጥ እና በእምቦጭ አረም ላይ ያለው ዕውቀት አነስተኛ መሆኑን ይገልጻሉ። ከዚህ የከፋው ግን በአካባቢው አርሶ አደሮች እና ብዝሃ-ህይወት ላይ የሚያደርሰው ችግር ነው። በሐይቁ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ደስታ ብርሃን እንዳሉት አረሙ ሐይቁን እያጠፋው ነው። "ከብቶቹ ውሃ የሚጠጡበትን፣ ለልብስ ማጠቢያ እና ለተለያዩ ሥራዎች የምንጠቀምበትን ሃይቅ ልናጣው ነው" ይላሉ በቁጭት። "ከብቶችም አረሙን ሲበሉ ጤናኛ አይሆኑም ሥጋቸውም ሆነ ወተታቸው አይጣፍጥም" ሲሉ ይገልጻሉ። በግብርና ሥራ የሚተዳደሩት አቶ ምትኬ ፈንቴ በበኩላቸው "አረሙ ከብቶቻችን እየገደለ ነው" ብለዋል። ከእምቦጭ በተጨማሪ አዞላ እና ኢፖማ የተሰኙ አረሞችም እየተከሰቱ ነው "ጣና የገዳሙ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱም ሃብት ነው" በጀልባ ሥራ የሚተዳደረው አባይነህ ምናለ አረሙ ለጀልባ ጉዞ የማይመች በመሆኑ የቱሪዝም እንቅስቃሴው ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ይላል። የአሳ ምርትም ቢሆን በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። "ድሮ ከአንድ ታንኳ 80 አሳ ይያዝ ነበር። አሁን ግን ከ15 አሳ በላይ አይገኝም" ሲል በሥራው ላይ ያለውን ችግር ይገልጻል። ጣና ሐይቅን የቱሪዝም መስህብ ካደረጉት ነገሮች መካከል ከ20 በላይ ገዳማትን መያዙ ነው። ከገዳማቱ አንዱ በሆነው እንጦስ እየሱስ ገዳም በተገኘንበት ወቅት እማሆይ ወለተማርያምን "ጣና የገዳሙ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱም ሃብት ነው" ይላሉ። እማሆይ ወለተማርያም፤ አረሙ አንጦስ እየሱስ ገዳም አካባቢ አለ መባሉ ጭንቀት ፈጥሮባቸዋል። "አረሙ ሐይቁን ሊያደርቅብን ይችላል የሚል ስጋት አድሮብናል" ይላሉ። "ምን ዓይነት ፈተና መጣብን ብዬ ነው ያዘንኩት" የሚሉት የገዳሙ አገልጋይ አባ ወልደሰንበት፤ የእርሻ ቦታዎችን የሚይዝ ከሆነ ህዝቡ ሊቸገር ይችላል። ይህ ደግሞ የእኛም ችግር ነው ሲሉ ይናገራሉ። ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው እንደሚሉት የተፈጥሮ ስጦታ ሆነው እምቦጭ በሌላው የተፈጥሮ ሃብት ጣና ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት እምቦጭ በትክክለኛ ቦታው ላይ ባለመገኘቱ ነው። "እጽዋት እንደ እጽዋት የሚቆጠረው በተፈጠረበት ሃገር ሲሆን በዛም እንደ ተፈጥሮ ፀጋም ይቆጠራል። ለምሳሌ ደንገል ለእኛ ተፈጥሮ ስጦታ ነው" ሲሉ ያስረዳሉ። "መጤ ሁሉ መጥፎ አይደለም" የሚሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው እንደምሳሌ የሚያነሱት በቆሎ እና በርበሬን ነው። እነዚህ መጤ እጽዋት በሌሎች የተፈጥሮ ጸጋዎች ላይ ጉዳት ሳያደርሱ ጥቅም በመስጠት ላይ ናቸው። እምቦጭ ግን ከዚህ በተቃራኒ በውሃ፣ ሥነ-ህይወትና በሌሎች እጽዋት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ይላሉ። "ጣና አስጊ ደረጃ ላይ ነው" ችግሩን ለመቅረፍ ሦስት ዘዴዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ ይላሉ ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው። የሠው ወይም የማሽን ጉልበትን በመጠቀም፣ እንደማንኛው አረም ኬሚካልን በመጠቀም ወይንም ደግሞ እምቦጭን ሊያጠፉ የሚችሉ ሌሎች እጽዋትን በማስፋፋት መሆኑን ይጠቁማሉ። ሃገራት እነዚህን ዘዴዎች ለየብቻ ወይንም በጋራ እንደ ችግሩ መጠን ይጠቀሙባቸዋል። እነወይዘሮ ደስታም አረሙን ለማጥፋት እየጣሩ ነው። "የራሳችንን ሥራ በመተው ረቡዕ እና አርብ አረሙን ለመንቀል ወደ ሐይቁ መጥተን እንሰራለን" ይላሉ። "አባቶች እና እናቶች ለዓለም ይፀልያሉ። እምቦጭ አረም እንዲጠፋም እየጸለይን ነው" ሲሉ እማሆይ ወለተማርያም ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጎንደር ዙሪያ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝማች ብርሃኑ እንደሚሉት አረሙን ለማጥፋት በጣና ዙሪያ የሚገኙ አምስት ቀበሌዎች እየተረባረቡ ነው። ችግሩ ስፋት ያለው በመሆኑ የአስር ቀበሌ ነዋሪዎችን ለማሳተፍ እየተሰራ ነው ይላሉ። "ይህ ግን በቂ አይደለም የማሽን ድጋፍ ከሌለ ጣና አስጊ ደረጃ ላይ ነው" ይላሉ። "በቅንጅት አልተካሄደም" አረሙን ለማጥፋት ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ እየተሰራ መሆኑን የጠቀሱት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ተማሎ በበኩላቸው በአንዳንድ አካባቢዎች ውጤታማ መሆን መቻሉን ይገልጻሉ። እንደ ምጥራ አባ ዋርካ ያሉ ቀበሌዎች ነጻ መሆናቸውን በምሳሌነት አንስተዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በሰው ጉልበት የሚደረገው ሥራ በማሽን ካልታገዘ በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ አይሆንም። ይህን ለማድረግም ዩኒቨርሲቲዎች እና የተለያዩ ግለሰቦች እየሰሩ ነው የሚሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ውሃው ለተለያዩ አገልግሎቶች ስለሚውል ኬሚካል ደግሞ ተመራጭ አይደለም ይላሉ። እምቦጭን የሚያጠፉ ሌሎች እጽዋትን ማስፋፋት ደግሞ እነሱም የሚያስከትሉት ችግር ሊኖር ስለሚችል ጥናት እየተደረገባቸው ይገኛል ብለዋል። አረሙን ለማስወገድ በተደረገ ጥረት ውስጥ ህይወቱ የጠፋ ሰው መኖሩን እና በእባብ ተነድፈው ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉም የሚናገሩት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው፤ ሆኖም ሥራው "በቅንጅት አልተካሄደም" የሚል እምነት አላቸው። ከሁሉም የሚያሰጋቸው ግን አሁን ያለው ችግር ሳይቀረፍ ከእምቦጭ በተጨማሪ አዞላ እና ኢፖማ የተሰኙ አረሞችም እየተከሰቱ መሆናቸው ነው።
news-53608236
https://www.bbc.com/amharic/news-53608236
ኮሮረናቫይረስ፡ "በአባታችን ቀብር ላይ ሆነን የእናታችንን ሞት ሰማን"
አዛውንቶቹ ጆን እና ሜሪ ትዳር የመሰረቱበትን 60ኛ ዓመት ባለፈው ሳምንት ነበር የሚያከብሩት። ቤተሰቡ ይህንን ቀን ደመቅ ባለ ሁኔታ ለማክበር ሽር ጉድ ሲል ነበር የሰነበተው።
ጆን እና ሜሪ ከ60 ዓመት በፊት በጋብቻቸው ዕለት ነገር ግን ያልታሰበው ተከስቶ የስድስት አስርት ዓመታት የትዳር ዘመናቸውን የሚዘክሩበት በዓልን ማክበር ሳይችሉ ሁለቱም በቀናት ልዩነት ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። "ሁለቱም በርካታ አባላት ካሉት ቤተሰብ የመጡ ሲሆን ሁለቱም በቤተሰባቸው ካሉት ሰባት ልጆች መመካከል ነበሩ'' ትላለች ሴት ልጃቸው ኢሌይን። "አራት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ስንሆን፤ አባታችን በአንድ ቴሌኮም ድርጅት ውስጥ ነበር የሚሰራው። እናታችን ደግሞ በጽዳት ሥራ ከዚያም ሰንደርላንድ ሮያል ሆስፒታል ውስጥ የምግብ አቅርቦት ተቆጣጣሪ በመሆን አገልግላለች።'' ጥንዶቹ ከልጅነታቸው ጀምሮ ጓደኛሞች የነበሩ ሲሆን በሰሜን ምሥራቅ እንግሊዝ ሰንደርላንድ ውስጥ በአንድ አካባቢ ነበር እድገታቸው። "እናቴ እድሜያችንን በሙሉ አብራን የኖረችው ሴት አያታችንን መንከባበከብ ስለፈለገች ሥራዋን አቁማለች። አያቴ ወደ አዛውንቶች መንከባከቢያ ማዕከል የገባችው በ103 ዓመቷ ነበር፤ ምክንያቱ ደግሞ እናቴ የጤና እክል ስላጋጠማት መንከባከብ ባለመቻሏ ነው" ትላለች ኢሌይን። ኢሌይን እና እህቷ ግሊኒስ የወላጆቻቸውን 60ኛ ዓመት የትዳር በዓል ለማክበር ዝግጅት ላይ ነበሩ። "የበዓል ቀናቸውን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር አዳራሽ ልንከራይና ዘፋኝ የሆነው የባለቤቴ ወንድም ደግሞ በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዲያቀነቅን እያሰብን ነበር" ትላለች ኢሌይን። ''ወላጆቼ የባለቤቴ ወንድም ሲዘፍን መመልከት በጣም እንደሚያስደስታቸው አውቅ ነበር። ልክ የእንቅስቃሴ ገደቡ መሆን ሲጀምር ሲጀምር በዓሉን ለማክበር የምናደርገውን ዝግጅት ለጊዜው ማቆም ነበረብን።'' ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ አዛውንቱ አባት ጆን የጤና እክል አጋጥሟቸው ወደ ሰንደርላንድ ሮያል ሆስፒታል የተወሰዱት በዕለተ ስቅለት ነበር። የሆስፒታሉ ሠራተኞች ምንም አይነት ምልክት ማየት ባለመቻላቸው መልሰው ወደቤታቸው ይልኳቸዋል። ነገር ግን ከሁለት ቀን በኋላ በፋሲካ ዕለት ሚስተር ጆን ወደ ሆስፒታል በመመለስ የኮቪድ-19 ምርመራ ያደርጋሉ። በሁለተኛው ቀን የኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ተረጋገጠ። "ሆስፒታሉ አሁንም ቢሆን በድጋሚ ወደቤት ሊመልሰው ሲል የባለቤቴ ወንድም ሆስፒታል ሄዶ ተቀበለው። መራመድ አይችልም ነበር፤ የስኳርና በሽታና የእንቅስቃሴ ችግር ነበረበት። በተደጋጋሚ ድካም እንደሚሰማውና ሰውነቱ እንደሚዝል ይናገር ነበር'' ትላለች ልጃቸው ኢሌይን። ጆን እና ሜሪ ከልጆቻቸው ግሊኒስ እና ኢሌይን ጋር ጆን የጤና ሁኔታቸው እየተባባሰ በመምጣቱ ሆስፒታል እንዲቆዩ ቢደረጉም ሊሻላቸው አልቻለም። ከሰባት ቀናት በኋላም ህመማቸው እጅግ ስለጠናባቸው ይህችን ዓለም በሞት ተሰናበቱ። ''ማመን አልቻልኩም ነበር፤ ሰኞ እና ሐሙስ ዕለት አውርተን ነበር። እንደተለመደው እየተጫወተና እየሳቀ ነበር'' ትላለች ልጃቸው። አክላም በዚህም ምክንያት ''እናቴ በጣም ከማዘኗ የተነሳ ምግብ መብላት አቆመች'' ብላለች። ኢሌይን የአባቷ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሊፈጸም ቀናት ሲቀሩት እናቷን ለመጎብኘት ወደ እህቷ ቤት መሄድ ነበረባት። "እህቴ ስልክ ደውላ በፍጥነት መምጣት እንዳለብኝ ነገረችኝ። እናታችን ጥሩ ስሜት ላይ እንዳልሆነችና የሰውነቷ የሙቀት መጠንም እንደጨመረ ነገረችኝ። ሳልም ሆነ ሌሎች የኮሮረናቫይረስ ምልክቶች ባይታዩባትም የኦክስጂን መጠኗ ግን ዝቅ ብሎ ነበር።" እናታቸው ሜሪ በዚያው ቀን ከሰዓት በኋላ ላይ ሆስፒታል እንዲገቡ ተደረጉ። በተደረገላቸው ምርመራም ኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው ተረጋገጠ። ሜሪ ሆስፒታል ውስጥ እንዲቆዩ ቢደረጉም ቤተሰባቸው ግን በየቀኑ በቪዲዮ ያገኛቸው ነበር። ኢሌይን ለአባቷ የቀብር ሥነ ሥርዓት ወደ ቤታቸው ተመለሰች። በሴንት ሂሊንዳ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተደረገው የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ መገኘት የቻሉት ሰባት ሰዎች ብቻ ነበሩ። ኢሌይን፣ የፍቅር አጋሯ፣ እህቷ፣ የአባታቸው ታላቅ ወንድምና ሌሎች ተጨማሪ ሦስት ሰዎች ብቻ በተገኙበት የአባታቸው የጆን ግብዓተ መሬት ተፈጸመ። "በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኘነው ሁላችንም ስልካችንን አጥፍተን ነበር። ቀብሩ ከተፈጸመ በኋላ ወደ ቤት ተመልሰን ስልካችንን ስናይ ብዙ ጊዜ ተደውሎልን ነበር። ወዲያው መልሰን ስንደውል ጥሪው እናታችን ትታከምበት ከነበረው ሆስፒታል እንደሆነና እናታችን ሕይወቷ እንዳለፈ ተነገረን።" "ሁላችንም ተቃቅፈን ማልቀስ ጀመርን። ምንም እንኳን እናታችን እድሜዋ እንደገፋና ጤናዋ አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ብናውቅም ሕልፈቷ በጣም አስደንግጦናል። በአባታችን በተቀበረበት ዕለት ማረፏ ደግሞ አስገርሞናል።" የእናታቸው የሜሪ የቀብር ሥነ ሥርዓት ከቀናት በኋላ ሲፈጸም በወረርሽኙ ምክንያት ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ ትንሽ ላልቶ መሰባሰብ የሚችሉ ሰዎች ቁጥርም ከፍ ብሎ ነበር። በዚህም የቀብራቸው ላይ 16 የቤተሰብ አባላት፣ ዘመዶችና ወዳጆች መገኘት ቻሉ። "እናትና አባቴ ሁለቱም በጣም ትልቅ ቤተሰብ ነው ያላቸው። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ በጣም ትንሽ ሰው ብቻ ተገኝቶ አሸኛኘት ማድረጉ በጣም ነው የሚያሳዝነው። "ሁለቱም ላለፉት በርካታ ዓመታት በጣም ብዙ ጥሩ ትዝታዎችን አሳልፈዋል። የ40ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን ለማክበር ወደ አሜሪካ ነበር የሄዱት። በፍሎሪዳና ላስቬጋስ ቆይታም አድርገው ነበር።" መላው ቤተሰብ በአሁኑ ጊዜ በሚቀጥው ዓመት የጆን እና የሜሪን ሕይወት ለመዘከር በዝግጅት ላይ ነው። እነሱ አብረዋቸው ባይኖሩም የ60ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን ቤተሰቡ ተሰብስቦ ለማክበር አቅዷል።
51448717
https://www.bbc.com/amharic/51448717
ከሞት የታደገው ጎሽ ከቤት አልወጣም ብሎት የተቸገረው ኢትዮጵያዊ
ወጣት ጋሻው ደመላሽ ነዋሪነቱ ኢሉ አባቦራ ዞን፤ ዳሪሙ ወረዳ አቡነ ጋሊ በምትሰኝ ቀበሌ ውስጥ ነው።
በግብርና ሥራ የሚተዳደረው ጋሻው፤ ከአራት ዓመታት በፊት በሚኖርበት አካባቢ በጭቃ ተይዞ መንቀሳቀስ ያቃተው የጎሽ ግልገል ባጋጣሚ ይመለከታል። ጥሎት ቢያልፍ የግልገሉ እጣ ፈንታ ሞት መሆኑን በመረዳቱ፤ የጎሹን ግልገል ጥሎ ማለፍ አልቻለም፤ ጎሹን ከጭቃ ለማስለቀቅ ግብግብ ያዘ። ከዚያም ጎሹን ከጭቃ አስለቅቆ ወደ መኖሪያው ይዞት ይሄዳል። • ''የአሰብና ምፅዋ ወደቦችን አገልግሎት ለማሻሻል እየሰራን ነው'' ፕሬዚዳንት ኢሳያስ • መንግሥት ለቀድሞ የኬንያ መሪ ቀብር ቀድመው ለሚገኙ ነጻ ምግብና እና መጠጥ አዘጋጃለሁ አለ • ቻይና ውስጥ በኮሮና ቫይረስ 97 ሰዎች በአንድ ቀን ሞቱ "ወደ ቤት ይዤው ሄድኩ። አባቴን አስፈቅጄ አንገቱ ላይ ገመድ አስሬ የላም ወተት እያጠጣሁት ማሳደግ ጀምርኩ" ይላል ጋሻው። የጎሹን ግልገል በአካባቢው የሚያገኛቸውን የተለያዩ ነገሮች እየመገበ እንዳሳደገ ጋሻው ይናገራል። "... እንጀራ፣ አሞሌ ጨው፣ የአረቄ አተላ፣ ማር ሁሉ አበላው ነበር። ከዛ በፍጥነት አደገ ከዛ ተላመደ" ይላል። በአጋጣሚ ህይወቱን አትርፎ ያሳደገው የጎሸ ግልገል ግን በትላልቅ ቀንዶቹ የሰፈሩን ሰው እና የቤት እንስሳት ለማሸበር የወሰደበት ጊዜ አጭር ነበር። "አሁን ስላስቸገረ ታስሮ ነው የሚውለው። ሰው እና ከብቶችን መውጋት ሲጀምር ነው ማሰር የጀመርኩት። ከዛ በፊት ከከብቶች ጋር ነበር ተሰማርቶ የሚውለው። ከእኔ ውጪ ሁሉንም ሰው እና ከብቶች እየወጋ ሲያስቸግር ለመጣል ወሰንኩ። እርቆ ወደሚገኝ ጫካ ወስጄ ብተወውም ተመልሶ መጣ። እንደገና ብወስደውም ስለተላመደ ተመልሶ መጣ" በማለት ጋሻው ጎሹን ወደ ጫካ ወስዶ ለመጣል ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ ያስረዳል። አመጸኛውን ጎሸ ጠምጄ ለማረስ ሞክሬ ነበር የሚለው ጋሻው፤ የአከባቢው ኃላፊዎች የዱር እንስሳ በመጠቀም ማረስ እንደማይችል በመግለጽ ክልክላ እንዳደረጉበት ይናገራል። "በጣም ነው የሚያርሰው፤ የትኛውም በሬ እንደ ጎሹ አያርስም። ከቀበሌ እየመጡ የዱር እንስሳ አጥምደህ ማረስ አትችልም ሲሉኝ ነው የተውኩት።" ጎሹን መጠቀምም ሆነ ከቤቱ ማስወጣት ያልቻለው ጋሻው፤ ለዱር እንስሳው ቀለብ መስፈር ቢበዛበት፤ ከገባበት ጣጣ መንግሥት እንዲገላግለው በአካባቢ ይመለከታቸዋል ላላቸው የመንግሥት መስሪያ ቤት ኃላፊዎች አቤት ቢልም መፍትሄ አለማግኘቱን ይናገራል። "በዞን እና በወረዳ ላሉት አሳውቂያለሁ። ከብት እርባታ ለሚባሉትም ነግሬያቸዋለሁ። ይሄው ስንት ግዜ ደብዳቤ ይዤ፣ ስንት ቦታ ተመላለስኩ፤ መፍትሄ የሚሰጠኝ ግን ላገኝ አልቻልኩም። እየመጡ ፎቶ አንስተው ይሄዳሉ እንጂ ምንም የረዱኝ ነገር የለም" ይላል። የኦሮሚያ ክልል የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ጨመረ ዘውዴ፤ የዱር እንስሳትን ማልመድም ሆነ በመኖሪያ ቤት ውስጥ አስሮ ማስቀመጥ በህግ የተከለከለ ተግባር ነው ይላሉ። አቶ ጨመረ እንደ ጎሽ ያሉ የምግብ ፍጆታቸው ከፍተኛ እና አደገኛ የዱር እንስሳትን የማላመድ ተግባር ከዚህ ቀደም ገጥሟቸው እንደማያውቅ ይናገራሉ። "በቅድሚያ እንዲህ አይነት ነገር ገጥሞን አያውቀውም። ይሄን ጎሽ እንዴት ማላመድ እንደጀመረ አላወቅንም። ግን ይዘው ካቆዩት በኋላ አድጎ የዱር እንስሳነት ባህሪው ሲመጣ ነው ለእኛ ያሳወቁን። ይህን መሰል ተግባርም የተከለከለ ስለመሆኑ በሃገሪቱ ህግ ላይ ሰፍሯል" አቶ ጨመረ ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ያሉትን ሁለት ሃሳብ ያስቀምጣሉ፤ ጎሹን ወደ ጫካ ለመመለስ ጥናት ማካሄድ አልያም ደግሞ ጎሹ በሰዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀነ ከሆነ እርምጃ መውሰድ። "እንዲህ አይነት የዱር እንስሳ ወደ ጊዜያዊ ማቆያ መውሰድ አይችልም። ከሰዎች ጋር የተላመደን የዱር እንስሳ ወደ ጫካ ይመለስ ከተባለ በጫካ የመኖር ባህሪውን አጥቷል። ስለዚህ ጎሹ ስለሚገኝበት ሁኔታ ማጥናት ግድ ነው። አለበለዚያ ግን ጎሹ በሰዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀነ ከሆነ እርምጃ መውሰድ የመጨረሻው አማራጭ ይሆናል" ይላሉ።
news-55367974
https://www.bbc.com/amharic/news-55367974
አወዛጋቢው የህንዱ ፀረ-እምነት መቀየር "የፍቅር ጂሃድ" ህግ
በቅርቡ አንዲት የሂንዱ እምነት ተከታይ የሆነች ግለሰብ በግድ ከሙስሊም ባለቤቷ ጋር እንድትለያይ መደረጓ እንዲሁም ከዚያ በኋላም በደረሰባት መንገላታት የተሸከመችው "ፅንስ ተጨናግፏል" ማለቷ በቅርብ አገሪቷ ፀረ-እምነት መቀየር ላይ ያወጣችውን ህግ አወዛጋቢ አድርጎታል።
በያዝነው ወር ነው ብርቱካናማ ቀለም ያለው የአንገት ሻርፕ የጠመጠሙ በርከት ያሉ ወንዶች፣ ይህችኑ የሂንዱ እምነት ነበረች ያሏትን ሴት ሲሰድቧት፣ ሲጎነትሏትና ሲያሰቃዩዋትም የሚያሳይ ቪዲዮ ወጥቷል። በሰሜናዊ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት ሞራዳባድ ከተማ ነዋሪ የሆነችውን ይህችን ሴት ከእምነትሽ ውጭ ለምን አገባሽም በሚልም ነው ግለሰቦቹ ሲያንገላቷት የታየው። "እንደ አንቺ ባሉ ሴቶች ምክንያት ነው ይሄ ህግ የወጣው" በማለትም አንደኛው ሲጎነትላት ይታያል። አነዚህ ግለሰቦች ፅንፈኛና አክራሪ ሂንዱዎች ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ናሬንድራ ሞዲ ባህራቲያ ጃናታ ፓርቲ (ቢጄፒ) ቀንደኛ ደጋፊዎች ናቸው። ህጉ በአክራሪ ሂንዱዎች "የፍቅር ጂሃድ" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሙስሊም ወንዶች ሂንዱ ሴቶችን በጋብቻ ውስጥ እምነታቸውን እንዲቀይሩ ያደርጓቸዋል የሚለውንም ለማመላከት የሚጠቀሙበት ነው። የሚያወሩለትም ህግ በቅርቡ የፀደቀና "የፍቅር ጂሃድና የእምነት ቅየራን መታገል ላይ ያነጣጠረ ነው። ክስተቱ የተፈጠረው ከሁለት ሳምንታት በፊት ሲሆን የባጃራንግ ዳል ነዋሪዎች የ22 አመቷን ግለሰብ፣ ባለቤቱንና ወንድሙን ለፖሊስም አሳልፈው ሰጥተዋቸዋል። ፖሊስም እሷን ወደ መንግሥት መጠለያ ካደረሳት በኋላ ባለቤቷንና የባለቤቷን ወንድም አስሯቸዋል። የሰባት ወር ነፍሰ ጡር የነበረችው ይህችው ግለሰብ ፅንሷ እንደተጨናገፈም አስታውቃለች። በዚህ ሳምንትም ፍርድ ቤት ቀርባ የነበረ ሲሆን እሷ እንደምትለው በግድ ሳይሆን በፈቃዷ ሙስሊም ወንድ እንዳገባች አስታውቃለች። ፍርድ ቤቱም ወደ ባሏ መንደር እንድትመለስ በነፃ አሰናብቷታል። ባለቤቷም ሆነ የባለቤቷ ወንድም አሁንም በእስር ላይ ናቸው። ከሚዲያዎች ጋር ባደረገችው ቃለ መጠይቅ በመጠለያው ያሉ ሰራተኞች አያያዝ ለፅንሱ መጨናገፍ ምክንያት ሆኗል ብላለች። በከፍተኛ ሁኔታ ሆዷ ላይ ህመም እንደሚሰማት ብትናገርም ችላ እንዳሏትም አሳውቃለች። መጠለያው በበኩሉ ግለሰቧ የምትለውን አስተባብሏል። "የጤናዬ ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን እየባሰና በከፍተኛ ሁኔታ እየባሰ ሲመጣም ነው ወደ ሆስፒታል የወሰዱኝ። የደም ምርመራ ከተደረገልኝ በኋላ ሆስፒታል አስተኙኝ። በወቅቱም መርፌም ወጉኝ፤ ከዚያ በኋላም ነው ከፍተኛ ደም ይፈሰኝ የጀመረው" ከሁለት ቀናትም በኋላም እንዲሁ ተጨማሪ መርፌዎች እንደወጓት ትናገራለች። ይፈሳት የነበረው ደምም እየጨመረና የጤናዋ ሁኔታም እየከፋ በመጨረሻም የ7ወር ፅንሷም ተጨናገፈ "ልጄንም አጣሁ" በማለት ትናገራለች። ሆን ተብሎ የተከሰተ ይሁን ግልፅ አይደለም፤ ሆስፒታልም ውስጥ የተፈጠረው ነገርም እንደተድበሰበሰ ነው። ግለሰቧ በቁጥጥር ስር እንዳለች ባለስልጣናቱ "ፅንሱ ተጨናግፏል" መባሉ ሃሰት ነው የሚል ሪፖርት አውጥተው ነበር። ሪፖርቱ የባለቤቷን እናት በዋነኝነት አናግሬያለሁ፤ የፅንሱንም ደህንነት ተረድቻለሁ ይላል። የህፃናት ደህንነት ጥበቃ ኮሚሽን ሊቀመንበር ቪሸሽ ጉብታ ፅንሱ ተጨናግፏል የሚሉ ሪፖርቶችን በሙሉ የካዱ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ "ልጁ በሙሉ ጤነንነት ላይ ነው" ለማለትም ደፍረዋል። ግለሰቧ ህክምና ያገኘችበት ሆስፒታል የማሕፀን ህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር "የሰባት ወር ፅንስ" እንደተሸከመች በአልትራሳውንድ ያሳይ ነበር። ነገር ግን ዶክተሩ እንደሚሉት የማህፀን ምርመራ ብታደርግ የህፃኑ ደህና መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል ይላሉ። ነገር ግን ከእስር ከተለቀቀች በኋላ "ፅንሱ ተጨናፈግፏል" በማለት ስለተናገረችው ጉዳይ ባለስልጣናቱ አስተያየት አልሰጡም። በሆስፒታሉ ውስጥ ያደረገጋቸውን የአልትራሳውንም ምርመራዎችን ጨምሮ የተወጋቻቸውን መድሃኒቶች ማስረጃ ሊሰጧት አልቻሉም። ሆስፒታል ከገባች ከአምስት ቀናት በኋላ ግለሰቡ ፅንሱ በህይወት ይኑር አይኑር እርግጠኛ የሆነ ነገር የለም። በርካታ ጥያቄዎችንና ጥርጣሬዎችንም አስነስቷል። ሆኖም ግለሰቧ ፅንሷ ተጨናግፏል የሚሉ ሪፖርቶች መላ ህንዳውያንን አስቆጥቷል። በርካቶችም ለዚህ ህይወት መታጣት ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው ባለስልጣናቱ ናቸው በማለት በማህበራዊ ሚዲያዎች እያወገዙ ይገኛሉ። በህንድ የተለያዩ ሃይማኖት ተከተያዮች በፍቅር መጣመርም ሆነ መጋባት ከፍተኛ ውግዘትን የሚያስተናግድ ሲሆን በተለይም ቤተሰቦች በጭራሽ የሚቀበሉት ሁኔታም አይደለም። ነገር ግን "የፍቅር ጂሃድ" የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ ህግ አንድ ሰው ለማግባት በሚል እምነቱን መቀየር ከፈለገ ከግዛቲቱ ባለስልጣናት መጀመሪያ ፈቃድ ሊያገኝ ይገባል። ይህም ሁኔታ ሰዎች በነፃነት የማፍቀርና የህይወት አጋሮቻቸውን የመምረጥ መብታቸውን የሚጥስና ለመንግሥትም ሙሉ በሙሉ የዜጎችን መብት የመቆጣጠር ሁኔታንም ይሰጣል። በዚህ ህግ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ግለሰብ የዋስ መብቱ አይከበርለትም፤ እስከ አስር አመት የሚያደርስም እስር ይጠብቀዋል። ኡታር ፕራዴሽ ግዛት በግድ ወይም በማጭበርበር የሚደረግን የእምነት ቅየራ ለመታገል በሚል አዲሱን ህግ በማፅደቅ የመጀመሪያዋ ሆናለች። ግዛቷ ግን የመጨረሻ አትሆንም ቢያንስ አራት ግዛቶች "የፍቅርን ጂሃድ" እንዋጋለን በሚል ህጉን ለማፅደቅ እቅድ ይዘዋል። ኡታር ፕራዱሽን ጨምሮ አምስቱ ግዛቶችን የሚመራው ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በፀረ- እስልምና አመላካከቶቹ ወቀሳ ሲደርስበት ነበር። ተችዎች ህጉ አስፀያፊና አስነዋሪ ነው በማለት የጠሩት ሲሆን የተለያየ እምነት ተከታይ ባለትዳሮችን ለማጥቃት ያነጣጠረ ነው ብለውታል። በተለይም የቀኝ ክንፍ አክራሪ ሂንዱ ቡድኖች በሴት የሂንዱ እምነት ተከታዮችና በሙስሊም ወንዶች መካከል የሚደረገውን ጋብቻም ለመቃወም ያለመና ፀረ-ሙስሊምም ነው በማለት ተችዎች ይናገራሉ። ህጉም እንዲቀየር የሚጠይቅም ፊርማም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ገብቷል። ህጉ በፀደቀ በአንድ ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በርካቶች በዚህ አወዛጋቢ ክስ መከሰሳቸውን ሪፖርቶች ያሳያሉ። በፈቃዳቸው የተጋቡ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸውም ጭምር ፈቃድ ያገኙ በርካታ በተለያየ እምነት መካከል የሚደረጉ የትዳር ጥምረቶች በህጉ ከተጠየቁት መካከል ናቸው። ሙስሊም ሙሽሮቹም በቁጥጥር ስር ውለዋል። ዴህራዱን በምትባል ከተማ የምትኖር የ22 አመት ግለሰብ እምነቷን ወደ እስልምና ቀይራ ሙስሊም ባሏን ያገባችው በሃምሌ ወር ነበር። አቅራቢያቸው ወዳለች ሞራዳባድ በምትባል ግዛትም ጋብቻቸውን ለማስመዝገብ በሚመጡበት ወቅት በቁጥጥር ስር ውለዋል። "የእንደዚህ አይነት ህጎች ዋነኛ ችግር በተለያዩ እምነቶች መካከል የሚደረግ የፍቅር አጋርነትንም ሆነ የትዳር ጥምረትን እንደ ወንጀል ነው የሚቆጥረው" በማለት የታሪክ ተመራማሪው ቻሩ ጉብታ ይናገራሉ። "የሴቶችን በራሳቸው የመወሰን መብት የሚጥስ ነው። ነፃ ፈቃዷ ጋርም የሚቃረን ነው። ማግባት የምትፈልገውን ማግባት የሴት ምርጫዋ አይደለም እንዴ? እምነቷን መቀየር ብትፈልግ ወይም ቀይራ ማግባት ብትፈልግ ችግሩ ምኑ ላይ ነው?" በማለት ይጠይቃሉ። "ህጉ በጣም ሰፊና በርካታ አወዛጋቢ ነገሮችንም የሚጠቀልል ስለሆነም የተከሰሱትም ሰዎች ንፁህ መሆናቸውን እንዲያስመሰክሩም ይጠበቅባቸዋል። ይህም አደገኛ ነው" ይላሉ።
news-51886425
https://www.bbc.com/amharic/news-51886425
ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ኢንተርኔት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የተለወጠ ነገር እንደሌለ ኢትዮቴሌኮም አስታወቀ
በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች ለወራት ተቋርጦ የቆየው የቴሌኮም አገልግሎት ከኮሮናቫይረስ ክስተት ጋር በተያያዘ እንዲከፈት እየቀረበ ባለው ጥያቄ ዙሪያ እስካሁን የተለየ ነገር እንደሌለ የኢትዮቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለቢቢሲ ገለጹ።
ይህንን በተመለከተ የወረርሽኙ አሳሳቢነት ከታወቀና በኢትዮጵያ ውስጥም የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ከተሰማ በሗላ በተለይ ምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ አካባቢዎች የስልክና የኢንተርኔት አገልገሎቶች መቋረጣቸው ስለበሽታው ያለውን የመረጃ ተዳራሽነት ያስተጓጉላል በሚል ጥያቄዎች እየተንሱ ነው። ተጨማሪ ሦስት የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸውና በርካታ በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች መኖራቸውን በጤና ሚኒስቴር መገለፁን ተከትሎ የኢንተርኔና የስልክ አገልግሎቶችን የመመለስ ሐሳብ ካለ በሚል ቢቢሲ ለኢትዮቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ትናንት አመሻሽ ላይ ለሥራ ጉዳይ ከከተማ ርቅው ቆይተው እየተመለሱ መሆናቸውን የጠቀሱት ሥራ አስፈጻሚዋ ተቋርጦ ስላለው የቴሌኮም አገልግሎት አዲስ መረጃ አንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናገረዋል። አክለውም "እንደሚታወቀው ቀደም ብሎ አገልግሎቱ የተዘጋው በዚህ ምክንያት አይደለም። ስለዚህ የተለየ የወሰድነው እርምጃ የለም፤ የተለየ ነገር ካለ እናሳውቃለችኋለን" ሲሉ የተናገሩት ፍሬህይወት የኢንተርኔቱ መቋረጥ ከፀጥታ ጋር እንደሚገናኝ፤ በመሆኑም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያየተው የሚወሰን ነገር ካለ እንደሚያሳውቁ ገለፀዋል። የኢንተርኔት መቋረጡ "በትክክል ለምን እንደሆነ እኛም ሌሎችም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ማብራሪያ የሰጡበት ነው" ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት ስልክና ኢንተርኔትን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ስለበሽታው የሚተላለፉ መረጃዎች ኅብረተሰቡ እራሱን እንዲጠብቅ ስለሚያስችለው አገልግሎቱ እንዲከፈት አንዳንድ ሰዎች በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ። ባለፈው ሳምንት የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ የሆነው ሂዩማን ራይትስ ዋች የተሰኘው ድርጅት ባወጣው መግለጫ ለሁለት ወራት በምዕራብ ኦሮሚያ ተዘግቶ የቆየውን የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲከፍት ጠይቆ ነበረ። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው የአገልግሎቶቹ መቋረጥ በቤተሰቦች መካከል ያለውን ግንኙነትንና ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ከማስተጓጎሉ በተጨማሪ መንግሥት በአካባቢው በታጣቂዎች ላይ እያካሄደ ያለውን ዘመቻ በተመለከተ የመረጃ ክፍተት እንዲፈጠር አድርጓል ብሏል። ከታኅሳስ 23/2012 ዓ.ም ጀምሮ የሞባይል ስልክ፣ የመደበኛ ስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙት የቄለም ወለጋ፣ የምዕራብ ወለጋና ሆሮ ጉድሩ ዞኖች ተቋርጦ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል::
42770877
https://www.bbc.com/amharic/42770877
ወልዲያ ውስጥ 7 ስዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆሰሉ
በወልዲያ ከተማ በጥምቀት በዓል ማግስት ቅዳሜ ዕለት የተከበረው የቃና ዘገሊላ ክብረ በዓል ማብቂያ ላይ የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የሰባት ሰዎች ህይወት ሲጠፋ በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በበዓሉ ተሳታፊዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተከሰተው ግጭት አስለቃሽ ጭስና ጥይት እንደተተኮሰ በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል:: ቅዳሜ አመሻሽ ላይ በተከሰተው ግጭት ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካቶች የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው የዓይን እማኞችና የሆስፒታል ምንጮች ገልፀዋል:: ነገር ግን የሟቾቹና የጉዳተኞቹ ቁጥር ከተጠቀሰው እንደሚበልጥ እየተነገረ ነው:: ከአዲስ አበባ 500 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው በወልዲያ ከተማ ቅዳሜ ዕለት ለተከሰተው ግጭት ምክንያት ነው ተብሎ ቢቢሲ ያናገራቸው የበዓሉ ታዳሚዎች የገለፁት፤ ወጣቶች በሚጨፍሩበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎች ለማስቆም በመሞከራቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይህን ሙከራ የተቃወሙ አንዳንድ ወጣቶች በፀጥታ ኃይሎች ላይ ድንጋይ መወርወራቸውን ይህንን ተከትሎም ሕዝቡ ላይ የተኮሱት አስለቃሽ ጭስ ግርግሩን ማባባሱን ከዚያም ተከታታይ የጥይት ተኩስ እንደተሰማና ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል፡፡ የአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ቅዳሜ ምሽት በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በወልዲያ ከተማ በወጣቶች እና በፀጥታ አካላት መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰዎች ህይወት ማልፉን አረጋግጠው ለንፁሀን ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑትን ለህግ ይቀርባሉ ብለዋል:: ግጭቱ ለሁለትኛ ቀን እሁድም ቀጥሎ በሰውና በንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳትን አስከትሏል:: በከተማዋ ያሉ የንግድ ተቋማት ተዘግተው የዋሉ ሲሆን መንግዶችም በተቆጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ተዝግተው ከፀጥታ ኃይሎች ውጪ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ተገተው ነበር:: የተኩስ ድምፅም ከተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ይሰሙ እንደነበር ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ እናት ለቢቢሲ ተናግረዋል:: ወልዲያ ውስጥ የአንድ ካፍቴሪያ ባለቤት ስሙን ሳይጠቅስ ለቢቢሲ እንደተናገረው እሁድ ዕለትም አልፎ አልፎ ከሚሰማው የተኩስ ድምፅ በተጨማሪ ጠዋት ላይ ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በድንጋይ ሲፋለሙ እንደነበር እማኝነቱን ስጥቷል:: በሰው ህይወትና አካል ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በእሳት የውደሙ ንብረቶች እንዳሉ ሌላ የከተማዋ ነዋሪ ገልፀዋል:: የአማራ ክልል ቴሌቪዥን እንደዘገቡው የሟቾች ቁጥር ሰባት ደርሷል:: ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ግን ቁጥሩ ከፍ እንደሚል ያምናሉ:: የካፍቴሪያው ባለቤት እንደሚናገረው "እኔ እንኳን የማውቀው አንድ ታታሪ ወጣት ተገድሏል" ብሏል:: እሁድ እለት ተቃውሞው ከወልዲያ ሃያ ኪሎ ሜትር ርቃ ወደምትገኘው አነስተኛ ከተማ ሀራ ተዛምቶ መንገድ ተዘግቶ የነበረ ሲሆን በንብረት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተነግሯል::
44082103
https://www.bbc.com/amharic/44082103
5 ሺህ ጉርሻዎች!
ነገሩ የተለመደ የሙዚቃ ድግስ ነው። ልዩ የሚያደርገው በማጀቢያ ሙዚቃ 5ሺህ ሰዎች ሊጎራረሱ መሆኑ ነው።
ኩነቱን ማሰብ በራሱ ያስቃል። 5ሺህ እንጀራን የጠቀለሉ መዳፎች ወደ 5ሺህ የተከፈቱ አፎች ሲምዘገዘጉ ማሰብ በራሱ ትን ያስብላል...! የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 4 በጊዮን ሆቴል ነው ይህ እንዲሆን ቀጠሮ የተያዘው። አሰናጆቹ ክስተቱን ከአንድ ቀን የዘለለ ትርጉም እንዲኖረው ጽኑ ፍላጎት አላቸው። ለምሳሌ ቋሚ የጉርሻ ቀን መሰየም ይፈልጋሉ። በኢትዮጰያ የማይቋረጥ ዓመታዊ የመጎራረስ ፌስቲቫል እንዲኖር ያልማሉ። ከፍ ሲልም ጉርሻን በማይዳሰስ ቅርስነት የማስመዝገብ የረዥም ጊዜ ትልምን ሰንቀዋል። "ጉርሻ ግን አይዳሰስም እንዴ!?" ብሎ መጠየቅ የተሰነዘረ ጉርሻን ያስከለክል ይሆን? አዘጋጆቹ የጉርሻ ባሕል በኢትዮጵያ አራት መቶ ዓመታትን ያስቆጠረ ነው ሲሉም ይከራከራሉ። አንድ የሚያደርገንን ፌስቲቫል ፍለጋ ኢትዮጵያ ውስጥ ኮስተር ብሎ የሚቆጥር ካለ እያንዳንዱ ቀን በዓል ሆኖ ሊያገኘው ይችላል። ይህ በቋንቋና በባሕል ሀብታም የሆነ አገር ሁሉ ባህሪ ነው። "እንደ ጉርሻ ግን የሚያግባባን የለም" ይላል ቅዱስ። "...ጉርሻ እኮ አንዱ ለሌላው የማጉረስ ተግባር ብቻ አይደለም፤ በተጠቀለለው እንጀራ ውስጥ ፍቅር አለ፣ መተሳሰብ አለ፣ አክብሮት አለ...።" ይላል ከአሰናጆቹ ፊታውራሪው ቅዱስ አብረሃም። ሐሳቡ እንዴት እንደተጠነሰሰ ሲያብራራም የሌሎች አገሮችን ዕውቅ ፌስቲቫሎች ከመመልከት የመጣ "መንፈሳዊ ቅናት የወለደው ነው" ይላል። "ሕንዶች የቀለም፣ ስፔኖች የቲማቲም፣ ጀርመኖች የቢራ ፌስቲቫል አላቸው። እኛ ግን አውዳመት እንጂ የሚያምነሸንሽ አንድም የጋራ ፌስቲቫል የለንም።" ሐሳቡን ያመነጩት የሥራ አጋሩ አቶ ዘላለም እናውጋው መሆናቸውን ጨምሮ ያስገነዝብና እንዴት አንድ ቀላል የጉርሻ ተግባር አገርን ወደ አንድነት መንፈስ ሊመራ እንደሚችል ማስረዳቱን ይቀጥላል። "ጉርሻ ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት አልያም የገቢ መጠንን አይጠይቅም። ሁላችንንም የሚያግባባን ባሕል ነው፤ ለዚህ ነው ልዩ የሚያደርገው። ደግሞም የኢትዮጵያዊያንና የኤርትራዊያን አንጡራ ባህል እንጂ የማንም አይደለም" ይላሉ ቅዱስ። ለዚህ የጉርሻ አገራዊ ፌሽታ ባሕል ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድጋፍ ማድረጋቸውን አሰናጆቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እንግሊዝ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደብዳቤ በመጻፍ የጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ዋና ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን እንዲከታተለው ማድረጉን ቅዱስ አብራርቷል። ጊነስ እና ጉርሻ ጊነስ እንዲህ ዓይነቶቹን ኩነቶች በማኅደሩ ለማስፈር ከ 7ሺህ እስከ 22ሺህ ፓውንድ ይጠይቃል። እነ ዘላለም ይህን ሂደት በማጠናቀቅ ላይ ነበሩ። ሁለት የጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ቢሮ ተወካዮች ይህንን የ5ሺህ ሰዎች ጉርሻ ለመታዘብ በቀጣይ ቀናት አዲስ አበባ እንደሚገቡም ይጠበቅ ነበር። ሆኖም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ጉዟቸው እክል ሳይገጥመው አልቀረም። "የድጋፍ ደብዳቤዎችን በመላክ ልናሳምናቸው ሞክረን ነበር" ይላል ዘላለም። ሆኖም መልካም ፍቃዳቸው አልሆነም። ይህ ማለት ግን ጊነስ ኩነቱን አይመዘግበውም ማለት እንዳልሆነ ጨምሮ ያብራራል። "አማራጭ አሠራር አለ። ይኸውም ገለልተኛ ተቋም ቀጥሮ፣ ለ50 ጥንዶች በቡድን አንድ-አንድ ታዛቢ በመመደብ፣ ክስተቱን ያለማቋረጥ በቪዲዮ ቀርጾ በጊነስ መዝገብ ይፋዊ ድረ-ገጽ በማኖር ለዕውቅና ሰርተፍኬት ማመልከት ይቻላል። ይህን ካሟላን ዕውቅናው እንደሚሰጡን ቃል ገብተውልናል" ይላል ዘላለም። የጉርሻ ታዛቢዎች ነገር እንግዳ ነው። 50 ሰዎች ሲጎራረሱ ከፊት ለፊት ቆመው እያንዳንዷን ጉርሻ ይቆጣጠራሉ። ልክ የተጫዋቾችን እንቅስቃሴ እንደሚቆጣጠር የእግር ኳስ አራጋቢ ዳኛ፤ ከወዳጅ የተቀባበለው ጉርሻ የተቃራኒ ቡድኑን የአፍ መስመር ማለፍ አለማለፏን ይከታተላሉ። ሂደቱ በራሱ የሚያዝናና ይመስላል። የጉርሻ ክብረወሰን በማን ነው የተያዘው? "ክብረ ወሰኑ ጃፓኖች ጋር ነው ያለው። 850 ጥንዶች ተጎራርሰው የዓለም ክብረ ወሰንን ይዘውታል። እኛ ይህን ክብረወሰን በዕለቱ በቀላሉ እንሰብረዋለን" ይላል ሌላኛው የኩነቱ አሰናጅ ቅዱስ አብረሃም በሙሉ መተማመን። እርሱ ራሱ ክብረ ወሰኑ በጃፓኖች ስለመያዙ ለመጀመርያ ጊዜ የሰማው ግን ከጊነስ ሰዎች ነው። "ይሄ የኛና የኤርትራዊያን ባሕል ነው። እንዴት ጃፓኖች ጋ እንደሄደ አልገባኝም። በ"ስቲክ" ይሁን በእጅ እንዴት እንደተጎራረሱ ራሱ አላውቅም፤ ጊነሶች ናቸው የነገሩኝ" ይላል ቅዱስ፤ ግርምት ከወለደው ፈገግታ ጋር። የጾም ነው የፍስክ? ሙዚቃውን፣ ምግቡን፣ ቀኑን፣ ሰዓቱን በጥንቃቄ ስለመምረጣቸው አዘጋጆቹ ደጋግመው ያስገነዝባሉ። ለምሳሌ በዕለቱ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ጾም እንደማይኖር ማረጋገጣቸውን ይጠቅሳሉ። "የረመዳን ጾም ከመግባቱ ቀደም ብሎ ፌስቲቫሉን ያደረገውን ለዚህ ነው" ይላል ቅዱስ። የሸራተን እህት ኩባንያ የሆነው አዲስ ኬተሪንግ ለጉርሻ የሚቀርበውን ምግብ በመከሸን በአጋርነት እንደተሰለፈና ጥብስ፣ ምንቸት፣ ጥብስ ዝልዝል ከምግብ መዘርዝሩ ከፊት የሚሰለፉ የምግብ ዓይነቶች እንደሚሆኑ ተነግሯል። በፊሽካ ነው በደወል? ተጎራረሱ! የሚለው ይፋ መልዕክት የሚተላለፈው እንዴት ነው? ቅዱስ እንደሚለው መድረኩ ላይ የሚሰቀል ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀ ግዙፍ ሰዓት አለ። ይህ የጉርሻ ሰዓት ልክ 11፡30 ከመሙላቱ በፊት ከላይ ወደ ታች መቁጠር ይጀምራል። '00:00' ሲል አምስት ሺህ ክንዶች ወደ ተከፈቱ አፎች ይወረወራሉ። ምግቡን ማወራረጃ የነዘሪቱ፣ የነ አቤል ሙሉጌታ፣ የነኃይሌ ሩትስ ሙዚቃ ተዘጋጅቷል። ተቃዋሚዎችና መንግሥት ቢጎራረሱስ? "ጉርሻ የፍቅር፣ የእርቅ፣ የአክብሮት፣ የህሊና ትስስርና የሞራል ልዕልናን በእንጀራ ጠቅልሎ የያዘ ስለመሆኑ ደጋግመው የሚናገሩት የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በዕለቱ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ተቃዋሚዎች ተገኝተው ቢጎራረሱ፣ ቢዝናኑ፣ ፍቅር ቢለዋወጡ ደስታንን አንችለውም'' ይላሉ። ለመሆኑ ጉርሻ የማይዳሰስ ቅርስ መሆን ይችላል? ትን የሚያስብል ጥያቄ ነው።
news-47611646
https://www.bbc.com/amharic/news-47611646
አደጋው በአውሮፕላን አብራሪዎች ላይ ምን ስሜት ፈጠረ?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን አደጋ 157 ሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፍ የኢትዮጵያዊያንን፣ የኬንያዊያንን፣ የጣሊያናዊያንን እና ሌሎች የሠላሳ ሃገራትን ልብ ከመስበር አልፎ ዓለምን በጠቅላላ በድንጋጤ ያናወጠ ክስተት ነበረ።
ይህን አደጋ ተከትሎ ከሃምሳ በላይ ሃገራትም ሁኔታው ተጠንቶ፣ ተጣርቶና የመረጃው ሳጥን ውጤት ይፋ እስኪደረግ ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላኖቻቸውን ከመብረር ማገዳቸውም ይታወሳል። በዚህም ወቅት የተለያዩ ሰዎች ሐዘናቸውን የገለፁ ሲሆን ባለፈው እሑድ ኢትዮጵያ ውስጥ ተምሳሌታዊ ቀብር ሥነ-ሥርዓት ሲደረግ በኬንያ ደግሞ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ በሙሉ የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ተዘጋጅቶ ነበር። • የቀብር ሥነ ሥርዓት በባዶ ሳጥኖች ተከናወነ ዜናው በርካቶች ላይ ጥልቅ ሐዘንን የፈጠረ ቢሆንም ለሥራው ቅርብ የሆኑት የአውሮፕላን አብራሪዎች ላይ ተለየ ስሜትን መፍጠሩ አይቀርም። እኛም ሁለት አብራሪዎችን ከአደጋው ጋር ተያይዞ የተፈጠረባቸውን ስሜት እንዲያጋሩን ጠይቀናቸው ነበር። ካፕቴን መኮነን ብሩክ አውሮፕላን አብራሪ ከሆነ ከሦስት ዓመታት በላይ የተቆጠሩ ሲሆን፤ አርሱም ሴስናር ካራቫን 208 የተሰኙ አውሮፕላኖች ያበራል። ትውስታውን ወደዛች አሳዛኝ ዕለት መለስ ባደርገነው ጊዜ መኮነን ጥልቅ ሐዘኑን ገልፆ "በረራ 302 እንደወደቀ እኛ ወደ ጂንካ ለመብረር በመዘጋጀት ላይ ነበርን። በረራ 302 አስቸኳይ ጥሪ ማስተላለፉንና እንደሚመለስ ከበረራ መቆጣጠሪያ ማማው ሞተራችንን አጥፍተን እንድንጠብቅ በራድዮ ትዕዛዝ አስተላለፉልን" ይላል። • ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት ካፕቴን መኮነን የሚያበረው ትንሽ አውሮፕላን ሲሆን፤ የ12 ሰዎችን ነፍስ በአየር ላይ ይዞ መጓዝና ከ170 በላይ ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ መካከል ትልቅ ልዩነት ቢኖርም እንኳን ሁሉም የአየር ጉዞ እራሱን የቻለ ስጋትና ውጥረት እንዳለው ይናገራል። "ከግማሽ ሰዓት በኋላ በራድዮ አውሮፕላኑ ከራዳር እንደወጣና በአየር ኃይል ፍለጋ እንደተጀመረ ሲነገረን መከስከሱ ወዲያውኑ ነበር የገባኝ" የሚለው ካፕቴን መኮነን አክሎ በናሽናል ጂዮግራፊ 'ኤርክራሽ ኢንቬስትጌሽን' ፕሮግራሞች እንደሚያስረዱት አውሮፕላን ከራዳር ጠፋ ማለት መጥፎ ነገር እንደተከሰተ የሚያሳይ የመጀመሪያው ምልክት ነው በማለት ያስረዳል። "መከስከሱን ተረዳን፤ ወዲያውኑ በራድዮ የመብረር ፈቃድ ተሰጠንና ልባችን እንደተሰበረ ወደ ጂንካ አመራን" ይላል። ካፕቴን መኮነን ከሴስናር ካራቫን 208 አውሮፕላን አብራሪዎች ጋር ሜሮን አመሃ በአሜሪካ አየር ኃይል ውስጥ በተንታኝነት የሠራች ሲሆን፤ በሥልጠና ወቅት ለአየር ኃይል አብራሪነት የበረራ ሥልጠና ወስዳ ሰርቲፊኬት ለመውሰድ 100 ሰዓታት የሚቀሯት ቢሆንም "የምይዘውን አውሮፕላን የማላውቀው ከሆነ ምንም ሰላም አይሰጠኝም" ትላለች። "አደጋው በጣም አሳዛኝና ልብ የሚሰብር ስሜት ነው የፈጠረብኝ" የምትለን ሜሮን ብዙውን ጊዜ የአውሮፕላን አደጋ በሚሰማበት ወቅት በእውቀት እጥረት ወይም በቴክኒክ ብልሸት የተፈጠረ ነው ተብሎ እንደሚጠረጠርም ትናገራለች። • አቶ ተወልደ አየር መንገዶች ሁሉ ለጊዜው ቦይንግ 737-8 ማክስን እንዳይጠቀሙ ጠየቁ "እንደዚህ ዓይነት አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ የብዙዎችን አውሮፕላን አብራሪ ችሎታ፣ አቅምና እውቀታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው" የምትለን ሜሮን "ይህም ሙያችንን የሚያሰድብና የሚያስጠይቅ ክስተት" ሊሆን የሚችል ነበር ትላለች። ነገር ግን የአሁኑ አደጋ "የአውሮፕላኑ ችግር በመሆኑ በይበልጥ ልብ የሚሰብር ነገር ነው። ለብዙዎች ሕይወት ኃላፊነት ይዞ ለሚያበር ሰው ብቻ ሳይሆን ለተሳፋሪ እራሱ ለማመን የሚከብድ እውነታ ነው። ምክንያቱም የአውሮፕላን ችግር በማንም ሊፈታ የሚችል አይደለም" ትላለች። አክላም ኃላፊነቱን የሚወስደው ማን እንደሆነም ሊታሰብበት ይገባል ስትል ትጨምራለች። ካፕቴን መኮነን "እኛ የምንይዘው አውሮፕላን አነስ ያለ በመሆኑ በወቅቱ ምንም ብናዝንም የበረራ ጉዟችንን ለመቀጠል ብዙ አልከበደንም ነበር። በዚያን ሰዓት ትልቅ አውሮፕላን የምንይዝ ቢሆን ኖሮ በጣም እንደነግጥ ነበር። ግን ዞሮ ዞሮ እንጀራችን ስለሆነ ምንም ማድረግ አልቻልንም አበረርን" ይላል በሐዘን በተሰበረ ስሜት። በቁጥር ሲታይ፤ ከመንገድ ትራንስፖርት ጋር የተያያዙ አደጋዎች ከአየር አደጋዎች አንፃር እጅግ በጣም ይበዛሉ። በዓለም ዙሪያ በዓመት ቢያንስ 1.2 ሚሊዮን ሰዎች በመንገድ ትራንስፖርት አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን እንደሚያጡ የዓለም አቀፍ የመንገድ ትራንስፖርት ደኅንነት ማኅበር ይገልፃል። • ስለምንጓዝበት የአውሮፕላን አይነት እንዴት ማወቅ እንችላለን? በአየር ትራንስፖረት የሚፈጠሩ አደጋዎችን በምንመለከትበት ጊዜ ደግሞ ከዓመት ዓመት የሚለያይ ሲሆን ለምሳሌ እ.አ.አ በ2016 በዓለም ዙሪያ 325 ሰዎች፣ በ2017 ከ37 ሚሊዮን በረራዎች 13 ሰዎች፣ በ2018 ደግሞ 500 ሰዎች በአውሮፕላን አደጋ ሳቢያ በሞት ተቀጥፈወል። የአየር ትራንስፖርት አደጋዎች ከቁጥር አንጻር ዝቅተኛ ነው። "እኛ ሁሌም በአየር ላይ ነንና ሰው ሠራሽ ነገር ምንጊዜም ዘላቂነት የለውም። አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ሁላችንንም ነው የሚነካን፤ ምክንያቱም እንደ ቤተሰብ ነን" የሚለው ካፕቴን መኮነን "ሰው የቤተሰቡን አካል ሲያጣ ምንም ማለት አይችልም ከማዘን ሌላ። ግን እኔ ማብረሬን አላቆምም" ይላል። ሜሮን ደግሞ "እንደዚህ ዓይነት አደጋ በምሰማበት ወቅት ለማብረር ያለኝ ፍላጎትና ባለሙሉ ልብነት ላይ የራሱ የሆነ ውጤት ይኖረዋል" በማለት አደጋው ከፈጠረባት ሃዘን ባሻገር ያለውን ውጤት ገልፃ፤ ሁሉንም የሚነካ አደጋ እንደመሆኑ "የአደጋው መንስዔ ውጤቱ ቢታወቅ ለአብራሪዎችም ሆነ ለተጓዦች በሙሉ ልብ ለመብረር ተስፋ ይሰጣል፤ ለዚህም ነው በጉጉት ውጤቱን የምንጠባበቀው" ትላለች።
49737785
https://www.bbc.com/amharic/49737785
በሴኔጋል የጡት እና የማህጸን ጫፍ ካንሰር ህክምና ነጻ ሊደረግ ነው
የሴኔጋል መንግሥት በጡትና በማህጸን ጫፍ ካንሰር በሽታዎች ለሚሰቃዩ ሴቶች ከመጪው ጥቅምት ጀምሮ በሁሉም የመንግሥት ሆስፒታሎች ነጻ የኬሞቴራፒ ህክምና ማግኘት እንደሚጀምሩ አስታወቀ።
''በውሳኔው በጣም ተደስተናል፤ ምክንያቱም እነዚህ ሁለት የካንሰር አይነቶ ሴቶችን በብዛት እያጠቁ ያሉ ናቸው'' ብለዋል የሴኔጋል ካንሰር መከላከያ ሊግ ፕሬዝደንት የሆኑት ዶክተር ፋትማ ጉዌኖን። • የማላዊ ሴተኛ አዳሪዎች ህይወታችን ተቀይሯል እያሉ ነው • በወር አበባ ምክንያት መምህሯ ያንጓጠጣት ተማሪ ራሷን አጠፋች ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች የካንሰር አይነቶች የሚጠቁ ደግሞ ለህክምና ከሚያወጡት ወጪ 60 በመቶ የሚሆነው በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል። እርምጃው ለብዙዎች ምሳሌ መሆን የሚችል እንደሆነና ምናልባትም በሃገሪቱ ያለውን የሞት መጠን ለመቀነስና ድህነትን ለመዋጋት ቁልፍ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አንድ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ባለሙያው ዶክተር ባራንጎ ፕሬቦ እንደሚሉት እንደ ሩዋንዳ፣ ናሚቢያ እና ሲሸልስ ያሉ የአፍሪካ ሃገራት ከሴኔጋል ቀድመው ይህንን እርምጃ የወሰዱ ቢሆንም አሁንም ለሌሎች ሃገራት ምሳሌ መሆን ትችላለች። ነጻ የጡትና የማህጸን ካንሰር ህክምናው ፕሮግራሙን ለማስጀመር የሴኔጋል መንግስት 1.6 ቢሊየን ዶላር መድቢያለሁ ብሏል። እ.አ.አ. በ2015 ደግሞ የማንኛውም ካንሰር ህክምና 30 በመቶ ወጪ መንግሥት ለመሸፈን ተስማምቶ ነበር። • በ2050 የወባ በሽታ ከዓለማችን ሊጠፋ ይችላል ተባለ • "የሴቶች የንፅህና መጠበቂያን ከቀረጥ ነፃ እናደርጋለን" ዶ/ር አሚር አማን ነገር ግን ካንሰርን በተገቢውና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማከም ብዙ የአፍሪካ ሃገራት ሲቸገሩ ይስተዋላል። የጡት ካንሰርን ለመመርመር የሚረዳው 'ማሞግራም' የተባለው መሳሪያ በሴኔጋል የሚገኙ ሴቶች በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት ዶክተር ፋትማ ጉዌኖን ይናገራሉ።
news-52041679
https://www.bbc.com/amharic/news-52041679
መንግሥት ታግተው የደረሱበት ስላልተወቁት ተማሪዎች ጉዳይ መረጃ እንዲሰጥ ተጠየቀ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከወራት በፊት ባልታወቁ ሰዎች ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ታግተው የደረሱበት ስላልታወቁት 17 የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ለማስለቀቅ የወሰደውን እርምጃ እንዲያስታውቅ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።
ተማሪዎቹ የታገቱት ከደምቢ ዶሎ ጋምቤላ በሚወስደው መንገድ ላይ ነው የመብት ተቆርቋሪው ድርጅት ይህንን ጥያቄ ያቀረበው በመላዋ አገሪቱ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት መዘጋታቸውን ተከትሎ ነው። ባለፈው ኅዳር ወር ላይ የታገቱት የተማሪዎች ወላጆች ሰቆቃን የበለጠ የከፋ ያደረገው በምዕራብ ኦሮሚያ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ስለልጆቻቸው መረጃ ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት እንዳደናቀፈው አምነስቲ በመግለጫው ላይ አመልክቷል። "በኮሮናቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው ስጋት፤ ተጠልፈው ከተወሰዱ በኋላ የት እንዳሉ ስላልታወቁት ልጆቻቸው መረጃ በሚፈልጉት የተማሪዎቹ ቤተሰቦች ሰቆቃን አበርትቶታል" ሲሉ የአምነስቲ ኢንትርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሰይፍ ማጋንጎ ተናግረዋል። "የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የተማሪዎችን ህይወት ለመጠበቅ ዩኒቨርስቲዎችን ለመዝጋት የወሰዱት እርምጃ የሚደነቅ ቢሆንም፤ ነገር ግን በተመሳሳይ 17ቱ ተማሪዎች ያሉበትን ቦታ በማወቅ ነጻ እንዲወጡ አድርገው ከቤተሰባቸው ጋር እንዲቀላቀሉ የሚያስችል ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ አለበት" ብለዋል። አምነስቲ ኢንትርናሽናል አናገርኳቸው ያላቸው በርካታ የታገቱት ተማሪዎች ቤተሰቦች እየከበደ የመጣ ተስፋ መቁረጥና ደጋፊ የማጣት ስሜት ውስጥ መሆናቸውን እንደገለጹ አመልክቷል። ወደ መጡበት ሲመለሱ ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንዷ የሆነችው የሦስትኛ ዓመት የባዮቴክኖሎጂ ተማሪ የነበረችው ግርማነሽ የኔነህ አባት አቶ የኔነህ አዱኛ ለአምነስቲ እንደተናገሩት "ልጆቻችንን ወደ ዩኒቨርስቲ የላክናቸው የተሻለ ተስፋ ሊኖራቸው ይችላል ብለን ነበ፤ አሁን ግን የት እንዳሉና በህይወት መኖራቸውን አናውቅም" ብለዋል። አባትየው ጨምረውም "መጠለፋቸውን ከነገረችን ዕለት ጀምሮ በለቅሶ ላይ ነው ያለነው፤ እንድንጸልይላት ነግራን ነበር፤ ቄስ እንደመሆኔ ጸሎቴን ሳሰማ ቆይቻለሁ። እናቷ በጣሙን ተጎድታለች፤ አእምሮዋ እየተነካ ነው። ከመንግሥት መንም የሰማነው ነገር የለም።" አጋቾቹ መጀመሪያ ላይ ተማሪዎቹ ለቤተሰቦቻቸው ደውለው እንዲያናግሯቸው ፈቅደው የነበረ ቢሆንም አሁን ወላጆች ስለልጆቻቸው ከሰሙ ሦስት ወራት ተቆጥረዋል ይላል አምነስቲ። "በምዕራብ ኦሮሚያ የግንኙነት አገልግሎት መቋረጡ ተቀባይነት የሌለውና የሰዎችን መረጃ የማግኘትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የመጣስ ድርጊት ነው" ሲሉ ሰይፍ ማጋንጎ ተናግረዋል። የተማሪዎቹን መታገት ተከትሎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ተማሪዎቹ ያሉበትን ቦታ የሚያፈላለግና በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ የሚያደርግ ከተለያዩ የመንግሥት አካላት የተወጣጡ አባላት ያሉት ግብረ ኃይል ተቋቁሙ እየሰራ መሆኑን ገልጸው እንደነበር ይታወሳል።
news-55258556
https://www.bbc.com/amharic/news-55258556
ትግራይ፡ የመጀመሪያው የህወሓት ከፍተኛ አመራር ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተነገረ
የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ ወንጀሎች ጠርጥሬያቸዋለሁ ካላቸው የህወሓት ከፍተኛ አመራር መካከል አንዱ የሆኑት አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ሐሙስ ታኅሳስ 01/2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተነገረ።
በዚህም ትግራይ ውስጥ ከተካሄደው ወታደራዊ ግጭት በኋላ ፍርድ ቤት በመቅረብ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የመጀመሪያው ሆነዋል። በትግራይ ክልል እንዲሁም በፌደራል መንግሥቱ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት የአዲስዓለም ባሌማን (ዶ/ር) ጉዳይ የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። ከአንድ ወር በፊት በትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የእስር ትዕዛዝ ከወጣባቸው የህወሓት አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት አዲስዓለም (ዶ/ር) በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት። ፖሊስ አዲስዓለም ባሌማን (ዶ/ር) የጠረጠረበትን በተለያዩ የተለያዩ ወንጀሎች ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንዲፈፀምና ከባድ የጦር መሳሪያዎች እንዲዘረፉ ሁኔታዎችን በማመቻቸት እንዲሁም በማይካድራ ንፁሀን ዜጎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት በማመቻቸት" መጠርጠራቸውን ፖሊስ ለችሎቱ ማስረዳቱን ፋና ዘግቧል። ፖሊስ በተጨማሪም አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ላይ በርከት ያሉ የተለያዩ ክሶችን ያቀረበ ሲሆን ግለሰቡ አምባሳደር በነበሩበት ዘመን አገሪቱ ከሌሎች አገራት ጋር ያላት ግንኙነት እንዲበላሽና እንዲቋረጥ ተጽዕኖ በማድረግ፣ የመንግሥት መረጃና ምስጢሮችን አሳልፈው በመስጠት እንዲሁም ከኦነግ-ሸኔ አመራሮች ጋር በመገናኘትና የመንግሥትን ምስጢር አሳልፈው እንደሰጡና ከቡድኑ ጋር ሲሰሩ እንደነበር ለችሎቱ ገልጿል። ተጠርጣሪው አዲስዓለም (ዶ/ር) ከህወሓት አመራሮች ጋር በመተባበር የወንጀል ድርጊት ለመፈጸም፣ ሁከትና አመጽ እንዲፈጠር የተለያዩ ድርጊቶችን በማስተባበር መጠርጠራቸው ተነግሯል። የአፍሪካ ሕብረት ባለስልጣናትን በመቅረብ በመንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ግፊት በማድረግ እንዲሁም ከአንድ የቻይና አምባሳደር ጋር በመገናኘት የቻይና እና የህወሓት ኮሙኒስት ፓርቲ እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ሲጥሩ እንደነበርም ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ መግለጹ ተነግሯል። ተጠርጣሪው አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በበኩላቸው የተባሉትን ወንጀሎች አለመፈጸማቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናገረው "ሰኞ ዕለት ከደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ጋር በሽምግልና ጉዳይ ስነጋገር ቆይቼ ረቡዕ በቁጥጥር ስር ውያለሁ" በማለት ከሌሎች አምባሳደሮችንና ባለስልጣናት ጋር የተነጋገሩትም በሽምግልና ጉዳይ ላይ እንደሆነ መግለፃቸውን የፋና ዘገባ አስነብቧል። ፖሊስ ተጠርጣሪው ወንጀሉን ስለመፈፀማቸው የሚያስረዱ በቂ መረጃዎች እንዳሉት ገልጾ፤ ምርመራውን ለማካሄድ ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱንም የፖሊስን ጥያቄ ተቀብሎ ፈቅዷል። በተመሳሳይም ለረጅም ዘመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት የአምባሳደር ስዩም ባለቤትና ልጃቸው በፖሊስ ተይዘው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገልጿል። ሐሙስ ፍርድ ቤት የቀረቡት የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት የስዩም መስፍን ባለቤት የሆኑት ወይዘሮ ፈለገህይወት በርሔና ልጃቸው አጋዚ ስዩም ሲሆኑ፤ ፖሊስም በተለያዩ የወልጀል ድርጊቶች ጠርጥሮ በቁጥጥር ሰር እንዳዋላቸው ለፍርድ ቤት ገልጿል። ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ ለማካሄድ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው በጠየቀው መሰረት ስምንት ቀናት እንደተፈቀደለት ፋና ዘግቧል። የትግራይ ክልልን ያስተዳድር በነበረው ህወሓትና በፌደራል መንግሥቱ መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ወታደራዊ ግጭት መሸጋገሩን ተከትሎ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች እንደሚፈለጉ በተገለጹ የቡድኑ አመራሮች ላይ ፖሊስ የእስር ማዘዣ ማውጣቱ የሚታወስ ነው። ለወታደራዊው ግጭት ምክንያት ከሆነው በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ጨምሮ በበርካታ ከፍተኛ ወንጀሎች ጠርጥሮ መንግሥት እፈልጋቸዋለሁ ካላቸው የህወሓት አመራሮች በተጨማሪ በከፍተኛ ወታደራዊና የፖሊስ መኮንኖችም ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል። አስካሁን በቁጥጥሩ ስር እንደዋሉ በይፋ የተገለጹት ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት የቀድሞው የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና አምባሳደር የነበሩት አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) እንዲሁም የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ናቸው።
news-49421165
https://www.bbc.com/amharic/news-49421165
በአንድ ስም ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች መመዝገብ እንደማይችሉ ምርጫ ቦርድ ገለፀ
በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግና በአባ ነጋ ጃራ የሚመራው ኦነግ ቀደም ሲል ተዋህደው አንድ እንደሚሆኑ አስታውቀው ነበር።
በቅርቡ ግን ሁለቱም በኦነግ ስም ከምርጫ ቦርድ እውቅና ለማግኘት የምዝገባ ሂደት መጀመራቸው ተሰምቷል። ጉዳዩን በማስመልከት ቢቢሲ ያናገራቸው የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ "እኛ የምናውቀው የምርጫ ቦርድ የሚጠይቀውን ሁሉ ህግ አሟልተን መግባታችንን ነው። እንደሕጉ ከሆነ ከመመዝገብ የሚከለክለን ነገር የለም። ውሳኔው የምርጫ ቦርድ ነው። የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር አንድ ለመሆንና ለመዋሃድም እየሰራን ነው። ኦነግን በተመለከተ ግን እኛም የኦሮሞ ሕዝብም የሚያውቀው አንድ ኦነግ ነው ያለው" ብለዋል። •ኦነግ ከመንግሥት ጋር ያደረኩት ስምምነት አልተከበረም አለ •''ኦነግ በሚቀጥሉት ቀናት ወደ አገር ቤት ይገባል'' የሌላኛው ኦነግ መሪ አባነጋ ጃራ ደግሞ "ምርጫ ቦርድ መመዝገብ ሕጋዊ ግዴታችን ነው። መመዝገብ ስላለብንም ነው ሂደቱን የጀመርነው። ኦነግን አንድ ድርጅት የማድረግ ሥራ ግን የፖለቲካ ሥራ ነው። እየተነጋገርንበት ነው። በቅርቡ ጨርሰን አንድ ንግግር እናደርገዋለን" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። "አንድ ድርጅት መዝግቡኝ ስላለ የሚመዘገብ አይደለም፤ ረጅም ጊዜ ይወስዳል። የፓርቲ ፕሮግራምን ማስኬድ፣ ቃለ ጉባኤ ማየትና የጠቅላላ ጉባኤ ማካሄድ የሚባሉት ነገሮች ማለቅ አለባቸው። እነሱ ካለቁ በኋላ ነው ለቦርዱ ለውሳኔ የሚቀርበው" በማለት ሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድ ስም እንመዝገብ ማለታቸው ውሳኔ የሚያገኝበትን መንገድ የምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ አብራርተዋል። •ኦነግ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማወጁን ገለፀ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ሁለቱም እዚህ ደረጃ ላይ አልደረሱም የሚሉት ወ/ሮ ሶሊያና በዚህ ውዝግብ ለማንም የተሰጠ የስም እውቅና አለመኖሩን አረጋግጠዋል። ሁለቱም ግን 'ኦነግ' ነው ስማችን ብለው የምዝገባ ሂደት እንደጀመሩ እናውቃለን የሚሉት አማካሪዋ በአንድ ስም ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች መመዝገብ እንደማይችሉም ተናግረዋል። በስም ይገባኛል ሂደቱም አንደኛው ቀድሞ ሂደቱን ስለጀመረ ሁለተኛውን አንተ አይመለከትህም ማለት እንደማይቻልም አማካሪዋ አረጋግጠዋል። ውሳኔ የሚሰጠውም የሁለቱም አመልካቾች ዝርዝር መስፈርት ከታየ በኋላ መሆኑን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ አረጋግጠዋል።
48263644
https://www.bbc.com/amharic/48263644
በአፋር ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አንድ ሰው ገድለው ሌላ አቆሰሉ
በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ በባጃጅ ይጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ ተኩስ ተከፍቶ አንድ ሰው መሞቱን የአፋር ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሕመድ መሐመድ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ኃላፊው እንደተናገሩት፤ ጥቃቱ የተፈጸመው በባለሦስት ጎማ ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ሲጓዙ በነበሩ የግብርና ኮሌጅ መምህራን ላይ ነው። ታጣቂዎቹ በጥቃቱ አንድ ሰው ሲገድሉ ሌላኛውን አቁስለዋል። • የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች? "ታጣቂዎቹ በአፋርና ኢሳ መካከል ግጭት አስነስተዋል ተብለው በመንግሥት እየተፈለጉ ያሉ ናቸው" ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል። አቶ አሕመድ እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም ታጣቂዎች ገዋኔ ከተማ ገብተው አንድ ሰው ገድለው፤ አንድ ሰው አቁስለዋል። አንድ የስምንት ዓመት ሕፃንም አግተውም ወስደዋል ብለዋል። ሃላፊው ጨምረውም ከሳምንታት በፊት ለአንድ ሰው ሞት ምክንያት በሆነው በትግራይ ፖሊስ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ የተፈጸመው ጥቃትም ከዚሁ ታጣቂ ቡድን ጋር የተያያዘ እንደሆነ አመልክተዋል። ገዋኔ አካባቢ በርካታ ጥቃቶች እየደረሱ በመሆኑ ምን እየተሠራ ነው ስንል ኃላፊውን ጠይቀናቸው ነበር። መንግሥት በጉዳዩ ክትትል እያደረገ እንደሆነና የጸጥታ ኃይል መሰማራቱንም ገልጸው፤ ሕዝቡን ራሱን እንዲጠብቅም አሳስበዋል። • "የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በአካባቢው በተደጋጋሚ ጥቃት እየተሰነዘረ ስለሆነ የመከላከያ ሠራዊት ጥበቃ እንዲያደረግ መሰማራቱን ገልጸው፤ "ጥቃቱን እየፈፀሙ ያሉት መንግሥት እየፈለጋቸው ያሉ ሰዎች ናቸው" ብለዋል።
53075791
https://www.bbc.com/amharic/53075791
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስካሁን አንድ ቢሊየን ዶላር ያህል ገቢ አጥቷል
ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአየር ትራንስፖርት ዘርፉ ላይ በተፈጠረው መስተጓጎል ሳቢያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳጣ ተገለጸ።
የኮሮናቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ በአየር መንገዶች ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ ማምጣቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ይናገራሉ። ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኛ በረራዎች መቆማቸውን ለቢቢሲ የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ያንን ተከትሎ ደግሞ ከየካቲት እስከ ሰኔ መጨረሻ ድርጅቱ መንገደኛ በማጓጓዝ ሊያገኘው ይገባ የነበረው ወደ አንድ ቢሊየን ዶላር ገቢ ሳያገኝ መቅረቱን ገልፀዋል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የዓለም አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ሕዝብ ከቤቱ እንዳይወጣ ከተደረገ ወራት አልፈዋል። ይህ ማለት በአየር የሚደረግ ጉዞ ሙሉ በሙሉ ቆሟል። ይህም በአየር መንገዶች ዓይን በሚታይበት ወቅት በአሁን ሰዓት ብዙ አየር መንገዶች አውሮፕላኖቻቸውን አቁመዋል ይላሉ ይላሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው። "የመንገደኛ በረራ ቆሟል። በኢትዮጵያ አየር መንገድም ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኞች አውሮፕላኖቻችን ቆመዋል።" "ይኼ ለአንድ አየር መንገድ እጅግ በጣም ትልቅ የፋይናንስ ቀውስ ነው የሚያመጣው። ይህም ምንም የሚካድ አይደለም እጅግ ተጎድተናል" በማለትም የዚያን ያህል ደግሞ አየር መንገዱ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ የሚያኮራ ሥራ ሰርቷል ሲሉ ድርጅቱ የሰራቸውን ሥራዎች ዘርዝረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢበርም ባይበርም በወር አምስት ቢሊየን ብር ያወጣል ያሉት አቶ ተወልደ ከመጋቢት ወር ጀምሮ የመንገደኞች ጉዞ በሚቆምበት ጊዜ የድርጅቱን ቋሚ ወጪዎች ለመሸፈን፣ አውሮፕላን ለመግዛት የተበደርውን ብድር ከነወለዱ መመለስ ይተበቅበታል። በተጨማሪም አውሮፕላኖችን የተከራየንበት ወርሃዊ የኪራይ ወጪ ለመክፈል፣ እንዲሁም የሠራተኛ ደሞዝ፣ ጥቅማጥቅም፣ አበል፣ ለመሸፈን የሚያስችለውን "በየወሩ አምስት ቢሊየን ብር በየወሩ እንዴት ነው የምናገኘው? ይህ ወረርሽኝ ከቀጠለስ ምን እናደርጋለን?" በማለት መወያየታቸውን ይጠቅሳሉ። በዚህ ወቅት "መጀመሪያ እድገት የነበረውን ስትራጂያችንን ወደ ሕልውና ማረጋገጥ ለወጥን" በማለትም ከመንገደኛ ማጓጓዝ ባሻገር ያለውን እድል በመፈተሽ የጭነት አገልግሎት መስጠትን በወቅቱ ያገኙት ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰዋል። አየር መንገዱ በዚህ ረገድ አስር 777 በጭነት ትራንስፖርት ምርጥ የሚባሉ አውሮፕላኖች፣ በተጨማሪም ሁለት 737 አውሮፕላኖች ስላሉት፤ እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ቶን ማስተናገድ የሚችልና ከነሲንጋፖር ከነሆንክ ኮንግ ከነአምስተርዳም ጋር ሊወዳደር የሚችል በጣም ዘመናዊ የካርጎ ተርሚናል ስላለው ይህንን እንደ ዕድል መጠቀማቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በዚያ ወቅት የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁሶች በጣም የሚፈለጉበት ጊዜ ነበር ያሉት አቶ ተወልደ ያለውን የገበያ ፍላጎት በመመልከት ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አፍሪካ በርካታ ጭነቶችን ማጓጓዛቸውን ያስረዳሉ። የድርጅቱ ገበያ እየጨመረ ሲመጣም ቁሳቁሶቹን በጭነት አውሮፕላኖች ብቻ ማንሳት ስላልተቻለ በፍጥነት የ25 የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወንበራቸውን በማውጣት ወደ ወደ ካርጎ ማዞራቸውን ይጠቅሳሉ። ይህንን በማድረጋቸው የተገኙ ጥቅሞችን ሲገልጹም ሠራተኛ ከሥራ አለማሰናበታቸውን፣ የሠራተኛ ደሞዝ አለመቀነሱን እና ነጥቅማጥቅሙ መከፈሉን፣ ሶስተኛ ምንም አይነት የገንዘብ ድጋፍ ከማንም አለመጠየቃቸውን ያነሳሉ። አክለውም ለጊዜው ሥራ ማስኬጃ የሚሆን ብድር አልወሰድንም፤ ብድራችንም እንዲራዘምልን አልጠየቅንም በማለት በኮቪድ-19 ወቅት በወሰዷቸው እርምጃዎች ያገኟቸውን ስኬቶች ይዘረዝራሉ። አየር መንገዱ ይህንን ሲያደርግ በዚህ በወረርሽኝ ጊዜ ህይወት የማትረፍ ሥራ መስራቱን ያነሳሉ። "የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ስፔንን ረድቷል። የኮቪድ-19 መከላከያ እቃዎችን በማቅረብ። ያ ማለት ሕይወት አትርፈናል ማለት ነው።" ፖርቹጋል፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ብራዚል እና አፍሪካ ሊደርስ ይችል የነበረውን ቀውስ መከላከል የሚያስችሉ የመከላከያ እቃዎችን ሕክምና መሳሪያዎችን በወቅቱ በማድረሳቸው ምክንያት አገሮችና ሕዝቦች ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ክብርና ውለታ እንዳላቸውም ጠቅሰዋል። "የጃክማ ፋውንዴሽን እርዳታን ከቻይና አምጥተን በስድስት ቀን ውስጥ አፍሪካ ውስጥ አከፋፍለናል" ያሉት አቶ ተወልደ "ፍጥነታችን በጣም ተደንቋል።" ሲሉ የአፍሪካ አገሮችም የአሊባባ ፋውንዴሽንም በሥራው መደነቃቸውን ይጠቅሳሉ። ይህንን ተከትሎም የዓለም የምግብ ድርጅት አዲስ አበባን የተባበሩት መንግሥታት በሙሉ የሰብዓዊ እርዳታ ማከፋፈያ አድርጓታል ሲሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ራሳችንን ጠቅመን፣ አየር መንገዱን አድነን፣ ሠራተኞቻችንን ሳንበትን፣ የሠራተኞቻችንን ደሞዝ ሳንቀንስ እና ሕይወት ማትረፍ በመቻላችን እንደ አንድ ዜጋ ትልቅ ኩራት እንደሚሰማቸው ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ለቫይረሱ ተጋላጭ መሆናቸውን ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስፈላጊውን የግንዛቤ መስጫ ትምህርቶችን በማድረግና ጥንቃቁዎችን በመውሰድ ወደ 17 ሺህ የሚጠጉ የድርጅቱ ሠራተኞች በጤና እንደሚገኙ ገልፀዋል። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም አምስት ሠራተኞቹ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በማስታወስ ሁሉም ማገገማቸውንና አሁን ደግሞ ባለፈው ሳምንት ሁለት ሠራተኞች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸው በድርጅቱ ለይቶ ማቆያና ማከሚያ ውስጥ እንደሚገኙ አብራርተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመከላከል የሚረዱ ሥራዎችን በአግባቡ ተግባራዊ እንደሚያደርግ የገለፁት አቶ ተወልደ "በረራ ባለማቋረጣችን ለዚህ ልምድ አግኝተናል" ብለዋል።
50348475
https://www.bbc.com/amharic/50348475
" 'ፖስት ፒል' ብወስድም አረገዝኩ"
"እስከዛች እለት ድረስ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ (ፖስት ፒል) ላይሠራ ይችላል የሚል ቅንጣት ጥርጣሬ አልነበረኝም።"
ሬቸል (ስሟ ተቀይሯል)፤ አንድ ዓመት ከዩኒቨርስቲ እረፍት ወስዳ ካናዳ በነበረችበት ወቅት ነው የተደፈረችው። ጥቃቱ በደረሰባት በዛው እለት ምሽትም ነው ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንክብል የተሰጣት። • ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት • ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው "ከሁለት ወራት በኋላ ማርገዜን ተረዳሁ፤ በጣም ነው የደነገጥኩት፤ በጭራሽ አረግዛለሁ የሚል ሃሳብ ጭንቅላቴ ውስጥ አልነበረም።" የ34 ዓመቷ ሬቸል ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እርግዝናን ላይከላከል እንደሚችል ፍንጭ የሰጣትም አካል አልነበረም። "ውጤታማ ላይሆን ይችላል የሚለው እሳቤ ሲነሳ ራሱ ሰምቼ አላውቅም" ትላለች። መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያን ከሚወስዱት መካከል ከ0.6-2.6% የሚገመቱት ሴቶች ያረግዛሉ። • "ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" • በፅንስ ማቋረጥ ታስራ የነበረችው ሞሮካዊቷ ጋዜጠኛ ምህረት ተደረገላት ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ (ፖስት ፒል) እንክብል ከተወሰደ በኋላ እርግዝና ሊያስከትል እንደሚችል መነጋገሪያ የሆነው አንዲት ጦማሪ እንክብሉን ብትወስድም እንዳረገዘች መፃፏን ተከትሎ ነው። ፅሁፏ ከፍተኛ የመወያያ ርዕስ የሆነ ሲሆን፤ እንክብሉ አንዳንድ ጊዜም ቢሆን ሊሠራ እንደማይችል በደንብ ሊታወቅ ይገባል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። ጦማሪዋ በፅሁፏ ላይ እንዳሰፈረችውም፤ ከውፃት (ኦቩሌሽን) በኋላ አንዲት ሴት ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ ፈፅማ እንክብሉን ብትወስድ ምንም ትርጉም እንደሌለው የተረዳችው በቅርቡ ነው። ይህንን መረጃ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ የሚያመርቱ ኩባንያዎች በሰፊው የማሳወቅ ሥራ ሊሠሩበት የሚገባ ነው ብላለች። ኮንዶም በመቀደዱ ምክንያት ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ብወስድም ማርገዜ አልቀረም፤ እናም ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ምርመራዬን ጀመርኩ ብላለች። ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ የሚሠራው እንዴት ነው? ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ መድኃኒቶች በእንክብሉ መሥራት አለመሥራት ላይ ተፅእኖ እንደሚያደርሱ የሥነ ተዋልዶና የጤና ባለሙያዋ ዶክተር ካሮሊን ኩፐር ይናገራሉ። "እነዚህ መድኃኒቶች ከጉበት መድኃኒት ጋር ጣልቃ ይገባሉ" በማለት ዶክተሯ ገልፀው፤ እነዚህ መድኃኒቶች የኤችአይቪ፣ የሚጥል በሽታ እንዲሁም አንዳንድ ባህላዊ መድኃኒቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ሙያዊ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ሊሠራ የማይችልበት ሌላኛው ምክንያ፤ የሴቲቷ የሰውነት ክብደት እንደሆነ ዶ/ር ኩፐር ያስረዳሉ። የሰውነት ክብደታቸው በጣም ከፍተኛ የሆነ ሴቶች ድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ቢወስዱም ሊያረግዙ እንደሚችሉ ዶክተሯ ይናገራሉ። • ሻደይ፦ለሴቶች፣ በሴቶች ፌስቲቫል ግን ምን ያህል ሴቶች ስለዚህ ሁኔታ መረጃ አላቸው? የሌቭኔልም ሆነ ኤላዋን በራሪ ወረቀቶች የሚሰጡት መረጃ ውፃትን (ኦቩሌሽን) በማዘግየት እንክብሎቹ እንደሚሠሩ ቢሆንም የማያዩት ብዙዎች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም የመድኃኒቱ መሥራት አለመሥራት በወር አበባ ዑደት ዙሪያ ሊደናቀፍ እንደሚችልም ግልፅ ያለ መረጃ አይሰጥም። ታዲያ ለምንድን ነው ማንኛዋም ሴት ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ (ፖስት ፒል) ስትገዛ ይሄ ሁሉ መረጃ የማይሰጣት? "እንክብሎቹ አይሠሩም ብዬ አልሜ አላውቅም" ትላለች የ26 አመቷ ሃሪየት፤ ኮንዶም ቢቀደድባትም ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ስለወሰደች አረግዛለሁ ብላ አልጠበቀችም። ያልጠበቀችው ሆነና አረገዘች። እሷ እንደምትለው በትክክል እንክብሎቹን ወስዳለች። ሃሪየት እንደተነገራትም እንክብሎቹ ረዘም ያለ ጊዜ ከተጠበቀ እንደማይሠሩ ነው። ነገር ግን እሷ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ስለወሰደች አላስጨነቃትም ነበር። ከሳምንት በኋላ ግን ማርገዟን ተረዳች። ለሬቸል ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ እንደማይሠራ ማወቋ ያለችበትን ሁኔታ ባይቀይረውም፤ የአስራ አምስት አመት ልጅ እንዲኖራት አድርጓል። "እርግዝናዬ በጭራሽ ያልጠበቅኩት ነው። የሆነውን ነገር በፍፁም ባልቀይረውም ልጄን አልወልደውም ነበር" ትላለች። የቢቢሲ ጋዜጠኛ ዶ/ር ኩፐርን የወር አበባ ዑደት በድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ውጤት ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ በፋርማሲስቶች ወይም በህክምና ባለሙያዎች ይነገራቸዋል ወይ? ብላ ለጠየቀቻት ጥያቄ "መንገር አለባቸው፤ ግዴታም ሊሆን ይገባል" ትላለች። ሌላኛው ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ኮፐር ኢንትራዮትሪን ዲቫይስ (አይዩዲ) ነው። ያለ ጥንቃቄ ግብረ ሥጋ ግንኙነት በተፈፀመ በአምስት ቀናት ውስጥ በብልት ውስጥ ይገባል። ፖስት ፒል ውፃትን የሚያዘገዩ ሲሆን፤ ኮፐር አይዩዲ ደግሞ የተመረተ እንቁላል ማህፀን ውስጥ እንዳይቆይ ያደርገዋል፤ ውጤታማነቱም 99% ነው። ኤላዋንን ከሚጠቀሙ 100 ሴቶች መካከል ሁለቱ ያረግዛሉ፤ እንዲሁም ከሌቮኔል ተጠቃሚዎች መካከል በአማካይ 0.6-2.6 ፐርስንቱ የማርገዝ አጋጣሚዎች አሏቸው። ሬቸልም ሆነ ሃሪየት ኮፐር አይዩዲ እንደ አማራጭ እንዳልቀረበላቸው ይናገራሉ። • ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ በወረርሽኝ ደረጃ ነው ያለው የሥነ ተዋልዶ ጤና ባለሙያዋ ዶ/ር ጄይን ካቫንጋህ፤ ለዚህ ሁሉ መፍትሔ የሚሆነው ስለ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያም ሆነ ስለ እርግዝና መከላከያ አወሳሰድ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ሊካተት ሲችል ነው ይላሉ። "እንዴት ነው ሁሉም ተማሪ ስለ እርግዝና መከላከያ የማይማረው? የግብረ ሥጋ ግንኙነት አድርገው ሊያረግዙ የሚችሉበት አጋጣሚ ቢፈጠር ምን ያደርጋሉ? ማወቅ አለባቸው" ይላሉ። በተለያዩ ጊዜዎች ያነጋገረቻቸው ተማሪዎችም ብዙዎቹ ስለ ድንገተኛ እርግዝና መከላከያ እንደማያውቁ ከውይይቱ መረዳት ችለዋል ባለሙያዋ። ስለ ድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንዶችም ሊያውቁ እንደሚገባ ሃሪየት ትናገራለች።
50401663
https://www.bbc.com/amharic/50401663
"በአዲስ አበባና በባህር ዳር የተፈጸመው የሰኔ 15ቱ ግድያ ዕቅድ የጀመረው ከሚያዚያ ወር አንስቶ ነበር" ጠቅላይ አቃቤ ሕግ
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከሰኔ 15ቱ የከፍተኛ ባለስልጣናት እና የጦር መኮንኖች ግድያ ጋር በተያያዘ አጠናቅቄዋለሁ ያለውን መረጃ ይፋ አደረገ።
ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ዛሬ [ረቡዕ] ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ የተለያዩ የቴክኒክ፣ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መጠቀማቸውን ገልፀዋል። በዚህም መሰረት ግድያውን አቀነባብረውታል የተባሉት ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ እና ሌሎች አጋሮቻቸው ይጠቀሙባቸው የነበሩ ኮምፒውተሮችን፣ ፍላሽ ዲስኮችንና አምስት ተሽከርካሪዎችን ፈትሾ የተለያዩ የውጪ ሀገራት ገንዘብና ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎችን መያዙን ገልፀዋል። • ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፡ "ሰኔ 15 አደገኛ ክስተት ነበር" በአጠቃላይ ይህንን መፈንቅለ መንግሥት ለማከናወን ዝግጅት የተጀመረው በሚያዚያ ወር መሆኑን የገለጹት አቶ ብርሀኑ፣ ወንጀሉ በጄነራል አሳምነውና ለክልሉ ተቆርቋሪ ነን በሚሉ አክቲቪስቶች የተጠነሰሰ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ይህንንም ለማሳካት ኢመደበኛ የሆኑ አደረጃጀቶችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራሮችንና እንዲሁም ሽፍቶችን በማደራጀት ተከናውኗል ሲሉ ጨምረው አስረድተዋል። በተለይ የክልሉና የፌደራል መንግሥት የተቃረኑ በማስመሰልና ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ በፓርቲው የተበደሉ በማስመሰል ሕብረተሰቡ የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ ሞክረዋል ያሉትጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ይህንንም ሲሰሩ የክልሉ ስልጣን ያልሆኑ ሥራዎችንም ማከናወናቸውን ገልፀዋል። ለአብነትም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች እንዲሁም ከአማራ ክልል 110 የሚሆኑ ሰዎችን በመሰብሰብ ለሰባት ሳምንታት የስለላ ስልጠና በመስጠት አሰማርተዋል ብለዋል። • "መግለጫ የምንሰጠው ሰዎችም ልንታሰር እንችላለን" የአማራ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ስልጠናው ስውር ጦርነት፣ የሥነ ልቦናና የኢኮኖሚ ጦርነት ላይ የሚያተኩር ነበር ያሉት አቶ ብርሃኑ፤ ለግለሰቦቹ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስልጠናዎችም መሰጠቱን ተናግረዋል። ስልጠናውን የወሰዱ ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ አሶሳ፣ አዋሳና አፋር የተሰባሰቡ መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል። ከሰልጣኞቹ መካከልም ከመከላከያ ሠራዊት በሥነ ምግባር ጉድለት ጭምር የተባረሩት እንደሚገኙበት አስረድተው የልዩ ኃይሉ አባል በማድረግ ለተግባሩ ዝግጁ እንዲሆኑ ተሰርቷል ብለዋል። መፈንቅለ መንግሥቱ በዋናነት የክልሉን ስልጣን ለመቆጣጠር የታቀደ መሆኑን የገለፁት አቶ ብርሃኑ፤ ከተሳካ በኋላ በዞንና በወረዳዎች ላይ ተቃውሞ ሊያስነሱ ይችላሉ የተባሉ ባለሰልጣናት ላይ ተጨማሪ ርምጃ ለመውሰድ የታጠቀ ኃይል ተዘጋጅቶ እንደነበርም ተናግረዋል። • ዶ/ር አምባቸው በሚያውቋቸው አንደበት የጄነራሎቹን ግድያ በተመለከተ በከፍተኛ አመራሮቹ ላይ "እርምጃ ከተወሰደባቸው በኋላ የመከላከያ ሠራዊቱ በየብሔሩ ይበታተናል፣ መፈንቅለ መንግሥቱንም ለማሳካት ቀላል ይሆናል በዚህም የፌደራል ስልጣንን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል" በሚል የተፈፀመ ነው ሲሉ አስረድተዋል። በቅድሚያ ጄነራል ሰዓረ ሲመቱ በቦታው የእርሳቸውን ግድያ ተከትሎ ጄነራል ብርጀሃኑ ጁላ ሊገኙ ስለሚችሉ እርሳቸውም ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወሰድ ተነግሮ እንደነበር ጨምረው ገልጸዋል። ጄነራል ብርሃኑ በስፍራው ባለመገኘታቸው የግድያው ሰለባ ሳይሆኑ ቀርተዋል ያሉት ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ይህንንም ለማድረግ ተመልምሎ ጎንደር ውስጥ የሰለጠነ ወታደር የባህር ዳሩ ድርጊት ከተፈፀመ ከሰዓታት በኋላ ለጄነራል ሰዓረ ጥበቃ መሳፍንት ጥጋቡ፣ ደውሎ እንደነገረው ገልፀው ወታደሩም ጄነራል ሰዓረንና ጄነራል ገዛዒን እንደገደላቸው አብራርተዋል። • የጦር እና ሲቪል መሪዎቹ ግድያ፡ ከቅዳሜ እሰከ ዛሬ ምን ተከሰተ? ለመፈንቅለ መንግሥቱ ማስፈፀሚያ ከመንግሥት በጀትና ከባለሃብቶች ገንዘብ በማሰባሰብ ግልና የቡድን መሳሪያዎች ተገዝተዋል ያሉት አቶ ብርሃኑ፣ በአጠቃላይ ባህር ዳር ላይ 3 ሻምበሎችን ከክልሉ ልዩ ኃይል ውጪ በማደራጀት በርዕሰ መስተዳድሩ፣ በአዴፓና በፓሊስ ጽህፈት ቤቶች፣ በክልሉ እንግዳ ማረፊያ፣ እንዲሁም በፖሊስ ኃላፊዎች ቤት ላይ ጥቃት መፈፀሙን አብራርተዋል። በዚህም 15 ሰዎች ሲገደሉ 20 ሰዎች ደግሞ የመቁደሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። በአጠቃላይ በሰኔ 15 ወንጀል በባህር ዳር 200 በአዲስ አበባ ደግሞ 147 ሰዎች ተጠርጥረው ተይዘዋል ያሉት ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ፣ 70 ተጠርጣሪዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ወጥቶ እየተፈለጉ ሲሆን 31 ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው በማለት ቀሪዎቹ 39 ግለሰቦች ግን አለመያዛቸውን ገልፀዋል። • አዴፓ እነ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌን "የእናት ጡት ነካሾች" አለ በባህር ዳር ደግሞ 47 ተጠርጣሪዎች ላይ ቀዳሚ ምርመራ ተደርጎ በአጠቃላይ 55 ሰዎች ላይ ክስ ሊመሰረት መሆኑ ተናግረዋል። አዲስ አበባ ከተያዙት መካከል 5 ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ወደ መሳሪያ ማዘዋወር የተቀየረ ሲሆን 61 ተጠርጣሪዎች በዋስ እንዲለቀቁ ተወስኗል ያሉት ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ፤ ነገር ግን 13 የሚሆኑት ቅድመ ምርመራ ክስ ስለተዘጋጀ በዚህ ሳምንት ይከሰሳሉ ሲሉ አረጋግጠዋል። ባህር ዳር ላይ 15 ተከሳሾች ኃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት የተከሰሱ ሲሆን እነዚህም የሟቾች አጃቢዎችና የሥራ ኃላፊዎች ናቸው ተብሏል። ምርመራውን ለማካሄድ የፌደራል ፖሊስ፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፣ የኢንፎርሜሽን ደህንነት፣ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት፣ የመከላከያ ሠራዊት ባለሙያዎች፣ የአማራ ክልል ፖሊስና ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ መሳተፋቸው ተገልጿል።
news-50010686
https://www.bbc.com/amharic/news-50010686
ቲማቲም የወንዶችን የዘር ፍሬ ያበረታ ይሆን?
ሊኮፒን የተባለው በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር የወንዶችን የዘር ፍሬ ጥራትና አቅም በእጅጉ ሊጨምረው እንደሚችል አንድ ጥናት ጠቆመ።
በእንክብል መልክ የተዘጋጁ የቲማቲም ተዋጽኦዎችን እንዲጠቀሙ የተደረጉ ጤናማ ወንዶች፤ የዘር ፍሬያቸው የተሻለ ጥራት ማሳየቱን ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች ገልጸዋል። የሥነ ተዋልዶ ባለሙያዎች እንደሚሉት ጥናቱን ለማካሄድ የተለያዩ የመውለድ ችግር ያሉባቸውን ወንዶች ተጠቅመዋል። • ጋናውያኑን ያስቆጣው የስነ ወሲብ ትምህርት • ለሰው ልጅ ምርጡ ምግብ እንቁላል ይሆን? የመውለድ ችግር ያለባቸው ወንዶች ጤናማ የሆነ ሕይወት እንዲከተሉና አጥብቀው የሚይዙ የውስጥ ልብሶችና ሱሪዎችን ከመልበስ እንዲቆጠቡ የእንግሊዝ ጤና አገልግሎት ድርጅት ይመክራል። በተጨማሪም በተቻለ መጠን ጭንቀትን መቀነስና የፍቅር አጋራቸው እንቁላሎችን ማምረት በምትጀምርባቸው ጊዜያት አዘውትሮ ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም የመውለድ ዕድልን ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ነገር ግን የተለያዩ ተፈጥሯዊ ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም የወንዶችን የመውለድ አቅም የመጨመር ሃሳቦች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተቀባይነትን እያገኙ የመጡ ይመስላል። ሊኮፒን ልክ እንደ ቫይታሚን ኢ እና ዚንክ በቅርቡ ብዙ ጥናት እየተሠራበት ነው። ሊኮፒን የወንዶችን የዘር ፍሬ አቅም ከመጨመር ባለፈ ብዙ ጤና ነክ ጥቅሞች እንዳሉት እየተገለጸ ነው። ከነዚህ መካከል የልብ ህመምን ለመከላከልና አንዳንድ የካንሰር ዓይነቶችን ቀድሞ ለመከላከል ያለው ጥቅም ብዙ እየተባለለት ነው። ቲማቲም ውስጥ የሚገኘውን ሊኮፒን ሰውነታችን በቀላሉ ፈጭቶ ጥቅም ላይ ለማዋል ስለሚቸገር ተመራማሪዎቹ ንጥረ ነገሩን በሳይንሳዊ መንገድ ከሰበሰቡ በኋላ በጥናቱ ለተሳተፉት ወንዶች በየቀኑ በእኩል መጠን አከፋፍለዋል። በተጨማሪም በቂ የሆነ ሊኮፒን ሰውነታቸው እንዲያገኝ በየቀኑ 2 ኪሎ የበሰለ ቲማቲም መመገብ ነበረባቸው። ለ12 ሳምንታት በቆየው የሙከራ ጥናት 60 ወንዶች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ከበሰለው ቲማቲም ጎን ለጎን 14 ግራም የሚመዝን በሳይንሳዊ መንገድ የተዘጋጀ የሊኮፒን እንክብል እንዲወስዱ ተደርገዋል። ምርምሩ ሲጀመር፣ በስድስተኛው ሳምንትና በጥናቱ መጨረሻ ላይ የተሳታፊዎቹ የዘር ፍሬዎች ተመርምረዋል። በዚህም መሠረት የዘር ፍሬ ቁጥር ላይ ምንም ጭማሪ ባይታይም የዘር ፍሬዎቹ እንቅስቃሴ ላይ ግን ከፍተኛ ለውጥ መታየቱ ተገልጿል። • በየትኛው አቀማመጥ ቢፀዳዱ ጤናማ ይሆናሉ? • "ሰውነቴ ወሲብ እንድፈጽም አይፈቅድልኝም'' የብዙ ሴቶች የጤና እክል ቲማቲም እንዲመገቡ የተደረጉት ወንዶች የዘር ፍሬዎች ጤናማ ቅርጽ ያላቸው ሲሆን በፍጥነት መዋኘትና ጽንስ መፍጠር የሚችሉ ሆነው ስለመገኘታቸው ደርሰንበታል ብለዋል ተመራማሪዎቹ። ''በዚህ ሰዓት ለወንዶች ልንሰጣቸው የምንችለው ምንም ዓይነት ምክር የለም'' ብለዋል በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሼፊልድ የሥነ ምግብ ባለሙያ የሆኑትና ጥናቱን በዋናነት ሲመሩ የነበሩት ዶክተር ሊዝ ዊሊያምስ። ''ምናልባት የሚጠጡትን የአልኮል መጠን እንዲቀንሱና ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት እንዲከተሉ ልንነግራቸው እንችላለን፤ ነገር ግን ይህ በጣም ጠቅለል ያለ ምክር ነው።'' ብለዋል። ዶክተር ሊዝ አክለውም የምርምር ሥራው ገና ብዙ የሚቀሩት ነገሮች ስላሉ በሰፊው ሙከራ ሊደረግበት እንደሚገባም አሳስበዋል። ነገር ግን እስካሁን የተገኘው ውጤት አበረታችች መሆኑን ግን አልሸሸጉም። ከዚህ በመቀጠል የሚጠበቀው በሙከራው የተሳተፉ ወንዶች የዘር ፍሬዎች ጤናማ ከመሆን ባለፈ ጽንስ እንዲፈጠር የማድረግ አቅማቸው ምን ያክል እንደሆነ መመርመር እንደሆነ ዶክተር ሊዝ ገልጸዋል።
55792459
https://www.bbc.com/amharic/55792459
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት በኮቪድ ተያዙ
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አንድሬ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር ኮቪድ ተመርምረው ተህዋሲው እንደተገኘባቸው ይፋ አደረጉ።
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አንድሬ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር የ67 ዓመቱ ፕሬዝዳንት በትዊተር ሰሌዳቸው እንደጻፉት አሁን የበሽታውን ቀላል ምልክቶችን ማሳየት ጀምረዋል። የፕሬዝዳንቱ በተህዋሲው የመያዝ ዜና የመጣው ሜክሲኮ በወረርሽኝ እየታመሰች ባለችበት ወቅት ነው። ሜክሲኮ እስከዛሬ ከ150ሺህ ባላይ ዜጎቿን በተህዋሲው አጥታለች። ሎፔዝ ኦብራዶር አገሪቱን ከቤቴ ሆኜ መምራቴን እቀጥላለሁ ብለዋል። ሩሲያ ሰራሹን ክትባት ለማግኘትም ከፑቲን ጋር እነጋገራለሁ ብለዋል። ትናንት ሁለቱ መሪዎች ዛሬ ሰኞ በስልክ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙርያ ይነጋገራሉ የሚሉ ዘገባዎች ወጥተው ነበር። ዋናው አጀንዳ የሚሆነውም ሰፑትኒክ የተሰኘውን ሩሲያ ሰራሽ ክትባት ሜክሲኮ የምታገኝበትን ዘዴ መቀየስ ነው። ባለፈው ዓመት ፕሬዝደንት ሎፔዝ ሩሲያ ሰራሹን የኮቪድ ክትባት ፈዋሽነቱ እንደተረጋገጠ 12 ሚሊዮን ጠብታ ወደ አገሬ አስገባለሁ ብለው ተናግረው ነበር። ሜክሲኮ ሩሲያ ሰራሹን ክትባት ፈዋሽነት ለጊዜው አላረጋገጠችም። ሆኖም ግን 128 ሚሊዮን ለሚሆነው ሕዝቧ ክትባቱን ለማዳረስ የፋይዘር ባዮንቴክ መዘግየት ታክሎበት ወደ ሩሲያ ለማማተር ተገዳለች። አሁን ለሩሲያው ስፑትኪን ክትባት አውቅና የሰጡ ዋና ዋና አገራት ብራዚል፣ አርጀንቲናና ሀንጋሪ ናቸው። ጆስ ሉዊስ አሎሚያ ዛጋራ የተባለ አንድ የጤና ረዳት የፕሬዝዳንቱን ጤንነት ከገመገመ በኋላ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ የሚያሳስብ ነገር የለም ብሏል። የጤና ባለሙያዎች ቡድን ለፕሬዝዳንቱ የቅርብ ክትትል እያደረጉላቸው ይገኛሉ። ሜክሲኮ በተህዋሲው የተያዙባት ዜጎች ቁጥር ወደ 2 ሚሊዮን እየተጠጋ ይገኛል። በ150ሺ ሟቾች ቁጥርም ግማሽ ሚሊዮን እየተጠጋ ያለ ሕዝብ ከሞተባት አሜሪካ፣ እንዲሁም ከብራዚልና ሕንድ ቀጥሎ ከዓለም በ4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
news-49167646
https://www.bbc.com/amharic/news-49167646
የዱባዩ መሪና ጥላቸው የኮበለለችው ባለቤታቸው ወደ ፍርድ ቤት ሊያመሩ ነው
በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ስማቸው ከፍ ተደርጎ ከሚጠሩት አለቆች መካከል እንዱ የሆኑት የዱባይ ገዥ ጥላቸው ወደ ለንደን ከኮበለለችው ባለቤታቸው ጋር ስለ ልጆቻቸው አስተዳደግ እጣ ፈንታ ውሳኔ ለማግኘት ወደ ፍርድ ቤት ሊያመሩ እንደሆነ ተነገረ።
ልዕልት ሀያ ቢንት አል-ሁሴን የዱባይ መሪ ከሆነው ባለቤቷ ሞሀመድ አል ማክቱም ጋር ልዕልት ሀያ ቢንት አል-ሁሴን የዱባይ መሪ ከሆነው ባለቤቷ ሞሀመድ አል ማክቱም ሸሽታ እንግሊዝ፣ ለንደን ውስጥ ከተደበቀች ሳምንታት አልፈዋል። ባለቤቷን ጥላ መኮብለሏን ተከትሎ ሕይወቷ አደጋ ውስጥ መሆኑንም ተናግራለች። • የዱባይ ልዕልት ከባለቤቷ ሸሽታ ለንደን ተደብቃለች • የተተከሉት ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ? • ብሔራዊ አገልግሎት መንፈሳዊ ህይወቱን የነጠቀው ኤርትራዊው ዲያቆን የ69 ዓመቱ ቢልየነር ሼህ ሞሀመድ አል ማክቱም ባለቤታቸው ጥላቸው በመኮብለሏ ብስጭታቸውን ገልጸዋል። ልዕልት ሀያ ቢንት አል-ሁሴን ከሼህ ሞሀመድ አል ማክቱም ስተሸሽ ሦስተኛ የቤተሰብ አባል ያደርጋታል። ወደ ፍርድ ቤት የሚሄደው ጉዳይ ልዕልቷ ከባለቤቷ ስትሸሽ ይዛቸው ስለሄደቻቸው ልጆቻቸው ነው ተብሏል። በጆርዳን የተወለደችው ልዕልት ሀያ፤ በአሁኑ ወቅት ጆርዳንን እያስተዳደሩት ያሉት ንግሥት አብዲላሂ ሁለተኛ ወንድሟ ናቸው። ልዕልት ሀያ ትምህርቷን የተከታተለችው እንግሊዝ በሚገኙ ቅንጡ የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሲሆን፤ ልዕልቷ በኦሎምፒክ በፈረስ ግልቢያ ውድድር ተሳታፊም ነበረች። እአአ 2004 ከሼህ ሞሀመድ ጋር ትዳር የመሰረተችው ልዕልቷ፤ የሼሁ ስድስተኛ ባለቤት ሆና ነበር። የ70 ዓመቱ ሼህ ሞሀመድ ከተለያዩ ሚስቶች 23 ልጆች እንደወለዱ ይነገራል። የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የተከታተለችው ልዕልት እስከወዲያኛው እንግሊዝ መቆየት ትፈልጋለች። ይሁን እንጂ ባለቤቷ ወደ ዱባይ እንድትመለስ የሚጠይቅ ከሆነ፤ የዱባይን እና የለንደንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥያቄው ለዩናይት ኪንግደም መንግሥት ከፍተኛ እራስ ምታት እንደሚሆን ዲፕሎማቶች ይናገራሉ። የ70 ዓመቱ ቢልየነር ሼህ ሞሀመድ አል ማክቱም ባለቤታቸው ጥላቸው ከኮበለለች በኋላ በኢንስታግራም ገጻቸው በቁጣ የተሞላ ግጥም አስፍረዋል። ግጥሙን ለማን እንደጻፈፉ ባይናገሩም አንዲት ሴትን "ከዳተኛ" ብለው ገልጸዋል። ልዕልቷ ለምን ኮበለለች? ለልዕቷ የቀረቡ ምንጮች እንሚሉት፤ ልዕልቷ ለመኮብለል የወሰነችው ከሼህ ሞሀመድ ልጆች አንዷ ስለሆነችው ላቲፋ ቢን ሞሃመድ አልማክቱም አስደንጋጭ መረጃ በማግኘቷ ነው። የሼሁ ልጅ ከአንድ ዓመት በፊት ከዱባይ ኮብልላ ነበር። በአንድ የፈረንሳይ ዜጋ በሆነ የቀድሞ ሰላይ ድጋፍ ባህር ተሻግራ ከዱባይ ከሸሸች በኋላ በሕንድ ጠረፍ አካባቢ በሼሁ ወታደሮች ተይዛ ወደ ዱባይ እንድትመለስ ተደርጓል። ከዱባይ ለመሸሽ ሙከራ ከማድረጓ በፊት በተቀረጸ ቪዲዮ ላፊፋ፤ "ሞቻለሁ ወይም እጅግ ከባድ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እገኛለሁ" ስትል የወደፊት እጣ ፈንታዋ ከባድ መሆኑን ጠቁማ ነበር። በወቅቱ ልዕልት ሀያና ላቲፋ ቢንት ሞሃመድ አል ማክቱም በዱባይ ደህንነቷ ተጠብቆ ትገኛለች ብላ ነበር። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላቲፋ ከሕንድ ባህር ዳርቻ ላይ በወታደሮች ያለ ፍቃዷ ታፍና ነው የተወሰደችው በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ይሁን እንጂ ልዕልቷ ዘግይቶ ስለ ላቲፍ አዲስ መረጃዎች ስለደረሷት እንዲሁም ከባለቤቷ ዘመዶች የሚደርስባትን ጫና ምክንያት በማድረግ ከባለቤቷ ሸሽታለች ተብሏል።
news-42408114
https://www.bbc.com/amharic/news-42408114
አሜሪካ 'ዋናክራይ' ለተሰኘው የሳይበር ጥቃት ሰሜን ኮሪያን ጥፋተኛ አደረገች
የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር 'ዋናክራይ' ለተሰኘውና ሆስፒታሎችን፣ የንግድ ተቋማትና ባንኮች ላይ ጉዳት ላደረሰው ዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ ጥቃት ሰሜን ኮሪያ ቀጥተኛ ተጠያቂ እንደሆነች አስታወቀ።
የዋይት ሃውስ ሃገር ደህንነት አማካሪ ቶም ቦሰርት አስተያየቱን አቀረቡ በ150 ሃገራት የሚገኙ 300ሺህ ኮምፒዩተሮች ላይ ጥቃት ያደረሰው ይህ ቫይረስ በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ጉዳት አድርሷል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ ረዳት ቶማስ ቦሰርት 'ዎል ስትሪት' በተሰኘው ጋዜጣ ላይ ነው ይህንን ክስ ያቀረቡት። ይህም ዩናይትድ ስቴትስ ሰሜን ኮሪያን ለቫይረሱ ጥቃት በይፋ ጥፋተኛ ስታደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የፕሬዚዳንቱ በሃገር ደህንነት ጉዳዮች የሚያማክሩት ቶማስ ክሱ በመረጃ የተደገፈ መሆኑን አሳውቀዋል። የእንግሊዝ መንግሥትም ጥቃቱ በሰሜን ኮሪያ መፈፀሙን በእርግጠኝነት ባለፈው ወር ይፋ አድርጎ ነበር። ባለፈው ግንቦት የዊንዶውዝ ኮምፒውተርስ ተጠቃሚዎች በሳይበር ጥቃቱ ምክንያት መረጃዎቻቸውን ማግኘት ባለመቻላቸው ለማስመለስ እንዲከፍሉ ተጠይቀው ነበር። ዩሮፖል የተሰኘው የአውሮፓ ሕብረት የፖሊስ አካል የጥቃቱ ክብደት 'ታይቶ የማይታወቅ' በማለት ጠቅሶታል። አጥቂዎቹ የተጠቃሚዎችን ኮምፒዩተሮች በመቆለፍ (ቢትኮይን) በምናባዊ ገንዘብ ከ300 እስከ 600 ዶላር የጠይቁ ነበር ለጋዜጣው በሰጡት መግለጫ ቶማስ ሰሜን ኮሪያ ለጥቃቱ ተጠያቂ መደረግ እንዳለባትና ዩናይትድ ስቴትስ 'ከባድ ጫና' በመጠቀም የሳይበር ጥቃቶችን ለመፈፀም ያላትን ፍላጎት እንደምታከሽፍ ተናገረዋል። ግኝታቸውን አስከትሎ ግን ዩናይትድ ስቴትስ ምን ዓይነት እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጁ እንደሆነች አላብራሩም። ባለፈው ወር 'የሽብር ድርጊት ተባባሪ መንግሥት' የሚለው ስያሜ በድጋሚ ሲሰጣት ከባድ የኢኮኖሚያዊ እገዳዎች የተጣለባት ሰሜን ኮሪያ፤ እያካሄደች ባለው የኒዩክሌር ሚሳይል ሙከራዎች ምክንያት ውጥረት ተፈጥሯል። ''ሰሜን ኮሪያ ከአስርታት በላይ በተለየ መልኩ ያልተገሩ መጥፎ እርምጃዎችን ወስዳለች፤ እያሳየች ያለው ተንኮል አዘል አካሄድም ዕለት ተለት ከመጠን እያለፈ ነው። 'ዋናክራይ' ሁሉንም የሚያጠቃ ቫይረስ ነበር'' በማለት ቶማስ ተናግረዋል። በመቀጠልም ''በይነ-መረብን (ኢንተርኔት) ከጥቃት ነፃ ለማድረግ እየጣርን ባለንበት ሰዓት፤ ብቻቸውን ሆነ ከሕገ-ወጥ ድርጅት ጋር በመተባበር ወይም ከጠላት ሃገራት ጋር በማበር ጥቃት የሚያደርሱብንንና የሚያስፈራሩንን ተጠያቂ ከማድረግ ወደኋላ አንልም'' ብለዋል። በተጨማሪም ''የአምባገነኖች ማሣሪያ አደገኛ ከመሆናቸው የተነሳ ችላ ማለት አይቻለም'' ሲሉ ገልጸዋል። በዕለተ ማክሰኞም ከዋይት ሃውስ ፒዮንግያንግን ተጠያቂ የሚያድረግ መግለጫ ይጠበቃል። 'ታይቶ የማይታወቅ ጥቃት' የእንግሊዝ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት (ኤንኤችኤስ) በዚህ ሳይበር ጥቃት በይበልጥ ከመጎዳቱ የተነሳ ብዙ ታካሚዎችን ከቀጠሮና ከቀዶ ሕክምና መመለስ ነበረባቸው። ጥቃቱ በዓለም ዙሪያ ተዳርሶ የሩሲያም የፖስታ አገልግሎት ከጥቃቱ ጉዳት አልተረፈም። ዩናይተድ ስቴትስ ባቀረበችው ክስ ላይ ሰሜን ኮሪያ ምላሽ አልሰጠችም እ.አ.አ በ2014 የሶኒ የፊልም አምራች ኪም ጁንግ ኡን የሚገደልበት በልብ ወለድ ላይ የተመሠረተ ፊልም እንደለቀቀ የሳይበር ጥቃት በደረሰበት ጊዜ ዩናይትድ ስቴትስ የሰሜን ኮሪያ ሸር እንደሆነ ተናግራ ነበር። የመዝናኛው ድርጅቱ ፊልም፣ ገንዘብ ነክ መረጃዎችና የግል ኢሜይሎች በበይነ-መረብ ይፋ ሆነው ነበር። በክሱ ዙሪያ ሰሜን ኮሪያ ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምላሽ ቢሰጡም በዋይት ሃውስ ስለ 'ዋናክራይ' ጥቃት ለቀረበው ክስ ግን መልስ አልሰጡም። ባለፈው ጥቅምት ሰሜን ኮሪያ ከእንግሊዝ መንግሥት የቀረባበትን ክስ 'መሠረት የሌለው ግምትና' ዓለም አቀፋዊ እገዳዎችን ለማጠናከር የታሰበ 'የክፋት ሙከራ' ነው ብለው ነበር።
news-52322986
https://www.bbc.com/amharic/news-52322986
ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ ሕይወት እንደገና በድንበር ላይ
ኢትዮጵያና ኤርትራ ለሃያ ዓመታት ድንበሮቻቸውን ዘግተው፤ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ቆይተው ነበር። ጉዞ ተከልክሎ፣ ንግድና የስልክ ግንኙነት ተቋርጦ ነበር፤ ይህ ብቻም ሳይሆን ቤተሰቦች ተቆራርጠው ቆይተዋል።
ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ ሕይወት እንደገና በድንበር ላይ ሁለቱ አገራት የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ግን መስከረም 2011 ዓ.ም ድንበሩ ተከፈተ፤ ይህም በሁለቱም ወገን ያሉት ቤተሰቦች እንዲገናኙና ህይወታቸውን እንደገና እንዲጀምሩ እድል ሰጠ። የዛላምበሳ ድንበር ዳግም ሲከፈት፤ ንግድ፣ ግንባታ፣ የቤተሰቦች ህይወት እንደ አዲስ አንሰራራ። ነገር ግን ድንበሩ ዳግመኛ ለንግድና ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተዘጋ። በእርግጥ የድንበር እንቅስቃሴው በእግርና መደበኛ ባልሆነ መልኩ ቀጥሏል። በድንበሩ አካቢ ያሉ ሕዝቦች ነገን በተስፋ አሻግሮ ይመለከታሉ፤ ነገር ግን የሰዎችና የንግድ እንቅስቃሴው መቀዛቀዝ ተስፋ መቁረጥንም እየጋበዘ ነው። በዚህ ዘጋቢ ፊልም የአንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ ቤተሰብን እና በሁለቱም ወገን የሚኖሩ ዘመዶቹን ሕይወት እንከተላለን። የመጀመሪያ ልጃቸውን ክርስትና ሲያስነሱ አብረናቸው እንሆናለን፤ ስለሥራቸውና ስለመጻዒ ህይወታቸው ያላቸውን ተስፋ እንሰማለን። እድሜውም ሙሉ ፎቶግራፍ ሲያነሳ የኖረ ግለሰብም አብሯቸው አለ፤ በዛላምበሳ ከተማ ለሁለቱም ሕዝቦች መገናኛ ይሆናል በሚል ተስፋ ሆቴል የሚገነባ ኤርትራዊ ነጋዴም አግኝተናል።
55706107
https://www.bbc.com/amharic/55706107
ኮቪድ-19 ፡ የቻይና ምጣኔ ሀብት እያደገ ነው
የቻይና ምጣኔ ሀብት ባለፈው ዓመት ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በዝቅተኛ ፍጥነት ማደጉን ይፋዊ አኃዞች ያሳዩ ሲሆን፤ በጎርጎሮሳዊያኑ 2020 ከባለ ትልልቅ የኢኮኖሚ ባለቤቶች ተርታ ብቸኛውን እድገት ያሳየ ለመሆን ተቃርቧል።
ምንም እንኳን በጎርጎሮሳዊያኑ 2020 መጀመሪያ ወራት የኮቪድ-19 እገዳዎች ምርት እንዲቀንስ ቢያደርጉም ምጣኔ ሀብቱ ባለፈው ዓመት 2.3% አድጓል፡፡ ጥብቅ የኮሮናቫይረስ መከላከያ እርምጃዎች እና ለንግድ ድርጅቶች አስቸኳይ እፎይታ መፈቀዱ ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ አግዞታል፡፡ በዓመቱ የመጨረሻ ሦስት ወራት የዕድገት መጠኑ እስከ 6.5% ደርሷል፡፡ በኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት ዋና የምጣኔ ሀብት ምሁር የሆኑት ዩ ሱ "የአገር ውስጥ ምርት (GDP) መረጃ ኢኮኖሚው መደበኛ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ያሳያል ማለት ይቻላል፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት በሰሜን ቻይና በሚገኙ ጥቂት አውራጃዎች የተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለጊዜው መለዋወጥ ቢያስከትልም ይህ ፍጥነት ይቀጥላል ማለት ይችላል" ብለዋል፡፡ የቻይና ዋና አክሲዮን ገበያዎች እና የሆንግ ኮንግ ሀንግ ሴንግ የቅርብ ጊዜ አሃዞች ላይ መጠነኛ ከፍታን ያሳዩ ሲሆን ይህም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ከሚጠብቁት በላይ ሆኗል ሲል በሮይተርስ የተደረገ ጥናት አመልክቷል፡፡ አሁንም ግን በጎርጎሮሳዊያኑ 2020 የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የኢኮኖሚውን እድገት ሊያስተጓጉል ይችላል የሚል ስጋት አለ። የቻይና የምርት ዘርፍ ወደ ዕድገቱ የተመለሰ ይመስላል። በሰኞ ዕለት መረጃ መሠረት የኢንዱስትሪ ምርት በ 7.3 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ወደ ውጭ የሚላክ ምርትም ቀደሚነቱን ይዟል፡፡ በዓለም ዙሪያ የኮሮናቫይረስ ስርጭት የቻይና ምርትን ፍላጎት በመጨመሩ ባለፈው ታህሳስ የአገሪቱ የወጪ ንግድ ከተጠበቀው በላይ አድጓል። ይህ የሆነው የን ጠንካራ ሆኖ የቻይና የውጭ ንግድ ለውጭ አገራት ገዢዎች የበለጠ ውድ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜዎቹ ቁጥሮች አንጻር ግን መልካም ዜናዎች አይደሉም፡፡ በስታንዳርድ ቻርተርድ ባንክ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ምሁር የሆኑት ሊ ዌ በበኩላቸው ከወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች እና በብድር የሚሸጡ መኪናዎች እና ቤቶች አብዛኛዎቹን ዕድገት ያስመዘገቡ ሲሆን የxር ውስጥ ፍላጎት ግን ወደ ኋላ ቀርቷል ብለዋል፡፡ ምሁሩ ለሮይተርስ እንደተናገሩት "የቤት ውስጥ የምግብ፣ የአልባሳት፣ የቤት ዕቃዎች እና የፍጆታ ቁሳቁሶች ፍላጎት ከቅድመ ወረርሽኝ መጠን በታች ሲሆኑ Yቱሪዝም እና የትራንስፖርት ዘርፎች የአቅም እና የጉዞ ገደቦችን መግጠማቸውን ቀጥለዋል፡፡" የችርቻሮ ሽያጭ በ2020 አራተኛ ሩብ ዓመት በ 4.6 በመቶ ቢያድግም የዓመቱ ግን በ 3.9 በመቶ ቀንሷል፡፡ ብዙ ተንታኞች በጎርጎሮሳዊያኑ 2021 ዕድገቱ እንደሚፋጠን ግምታቸውን እየሰጡ ቢሆንም የቻይናው የስታቲስቲክስ ቢሮ "የወረርሽኙ ከፍተኛ ተጽዕኖ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ከባድና ውስብስብ ሊሆን ይችላል" ሲል አስጠንቅቋል፡፡ ቻይና አሁንም ከአሜሪካ ጋር የምታደርገውን የንግድ ውዝግብን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎች ተጋርጠውባታል፡፡
56027722
https://www.bbc.com/amharic/56027722
ኢሰመኮ በትግራይ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 108 የመደፈር ጥቃቶች ሪፓርት ተደርገዋል አለ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 108 የመደፈር ጥቃቶች ለጤና ተቋማት ሪፓርት መደረጋቸውን ገለጸ።
ኮሚሽኑ በመቀለ ከሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ባገኘው መረጃ መሠረት፤ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ በመቀለ ሆስፒታል 52፣ በአይደር ሆስፒታል 27፣ በአዲግራት ሆስፒታል 22፣ በውቅሮ ሆስፒታል 7 በአጠቃላይ 108 የመደፈር ጥቃቶች ለጤና ተቋማት ሪፖርት ተደርገዋል። "የጾታዊ ጥቃት ተጎጂዎች ወንጀሉን ለማሳወቅና የሕክምና እርዳታ ለማግኘት የሚሄዱባቸው እንደ ፖሊስ ጣቢያ እና ጤና ጣቢያ ያሉ ተቋማት በአንዳንድ አካባቢዎች ፈርሰው በመቆየታቸው፤ ሪፖርት የተደረጉ ጥቃቶች ቁጥር ትክክለኛውን የጉዳት መጠንና ስፋት እንደማያመላክት እና የጾታዊ ጥቃት መጠኑ ከዚህ የበለጠ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል" በማለትም የደረሰው ጥቃት ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ኮሚሽኑ ጠቁሟል። በክልሉ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ የሕክምና እርዳታ ፈላጊዎች በምሽት ወደ ጤና ተቋማት እንዳይሄዱ እንቅፋት እንደሆነም ኮሚሽኑ የጤና ባለሙያዎችን ጠቅሶ ግልጿል። ጉዳት የደረሰባቸው ሕጻናት ኮሚሽኑ እንዳለው በጦርነቱ ሳቢያ የአዕምሮ መረበሽ የገጠማቸው ሕጻናትን አግኝቷል። በአይደር ሆስፒታል የሕፃናት ተኝቶ መታከሚያ ክፍል በመታከም ላይ ከነበሩት 20 ከፍተኛ የአዕምሮ ጭንቀት እና ድንጋጤ ታካሚ ሕፃናት መካከል 16ቱ በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው እንደሆኑ ኢሰመኮ ገልጿል። በሆስፒታሉ በመታከም ላይ ከነበሩ ሕፃናት መካከል እጃቸውን እና አይናቸውን ያጡ፣ በጭንቅላት፣ በሆድ እና በአጥንታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የትግራይ ክልልን ጤና ቢሮ ጠቅሶ "ጦርነቱን ተከትሎ በየገጠሩ ያሉ የጤና ተቋማት አገልግሎት በማቆማቸው ምክንያት እና መቀለን ጨምሮ ህክምና ለማግኘት ወደሚቻልባቸው ከተሞች ለመጓጓዝ የትራንስፖርት እጥረት በመኖሩ የተጎዱ ሰዎች ሕይወት እያለፈ እና ከባድ የአካል ጉዳት እየደረሰ ነው" ብሏል። ከአይደር ሆስፒታል በተገኘው መረጃ መሠረት፤ በተለይ በሕፃናት ላይ ለደረሱት ጉዳቶች አንዱ ምክንያት በመሬት ውስጥ የተቀበሩ እና በሜዳ ላይ የተጣሉ ፈንጂዎች የሚያስከትሉት አደጋ ነው። በተለያየ እድሜ ላይ የሚገኙ ሕጻናትን ያነጋገረው ኢሰመኮ ባገኘው መረጃ መሠረት፤ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ የማያውቁ እንዲሁም በተባራሪ ጥይት ጉዳት የደረሰባቸውም እንዳሉ ገልጿል። በተባራሪ ጥይት ተመትተው ከሞቱ ሕጻናት መካከል ለአራት ቀናት በፅኑ ህሙማን ክፍል ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ያለፈ የአራት ዓመት ልጅ አንዱ ነው። "በሴቶች እና በሕፃናት ላይ የሚፈጸም ጥቃትን በተመለከተ በመንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የአጥፊዎችን ተጠያቂነት ማረጋገጥ ጥቃት ለደረሰባቸው ሰዎች ተገቢውን እርዳታ መስጠት ያስፈልጋል" ብሏል ኮሚሽኑ በመግለጫው። የጸጥታ ጉዳይ የክልሉ መደበኛ የፖሊስ አባላት ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ባለመግባታቸውና ለጸጥታ ጥበቃ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ባለመሟላታቸው በክልሉ ዘረፋና ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎች በከፍተኛ መጠን እንደጨመሩ የኮሚሽኑ መግለጫ ይጠቁማል። "በክልሉ የሚገኙት የፌደራል ጸጥታ ኃይሎች ቁጥር በክልሉ ከሚያስፈልገው የደኅንነት ጥበቃ ፍላጎት አንጻር ሲታይ ውስን መሆኑ የሕግ ማስከበር እና ደኅንነትን የማረጋገጥ ሥራውን ፈታኝ አድርጎታል" በማለትም ያክላል። በተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች ውጊያ ባለመቆሙ መደበኛ የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎች እንደተገደቡና የመሰረታዊ ፍላጎት ሸቀጦች በአግባቡ እንደማይዘዋወሩም ተገልጿል። በተያያዥም የክልሉ የቀድሞ አስተዳደር መዋቅር መፍረሱን ተከትሎ በ10 ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ እስረኞች በሙሉ ከእስር እደወጡና የእስረኞችን መረጃዎች የያዙ ሰነዶች እንደወደሙ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ጠቅሶ ኢሰመኮ ገልጿል። "በተለይ ከባድ ወንጀል ፈጻሚዎችን መልሶ የመሰብሰብና በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራውን እጅግ አዳጋች እንዳደረገው" ኮሚሽኑ አክሏል። አገልግሎት ሰጪ ተቋሞች የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ከሚሽን በተለይም የጤና አገልግሎት ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል። አብዛኞቹ አምቡላንሶች በክልሉ የጤና ቢሮ ሥር እንዳልሆኑና አምቡላንስ ባለመኖሩ ምክንያት አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ለመስጠት ባለመቻሉ ሕይወት እንደሚጠፋም አክሏል። "በክልሉ የጤና አገልግሎትን ለመመለስ አስቸጋሪ የሆነው በተለይ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ በምሥራቅ ትግራይ እና በማዕከላዊ ትግራይ የሚገኙ የተወሰኑ ጤና ተቋማት በግዜያዊ አስተዳደሩ ሥር ባለመሆናቸውና በባለቤትነት ችግር የተነሳ ደመወዝ፣ መድኃኒት እና የሰው ኃይልን በአግባቡ ማቅረብ ባለመቻሉ ነው" ይላል የኮሚሽኑ መግለጫ። መቀለ እና አዲ ጉደም የሚገኙ የጤና ተቋሟት በአንጻራዊነት የተሻለ ሁኔታ ላይ ቢገኙም፤ በተለይ በአድዋ፣ በአክሱም እና በሽረ የጤና ተቋሞች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በእነዚህ አካባቢዎች የጤና ባለሙያዎችም ለአስቸኳይ እርዳታ እንደተጋለጡ፣ እንደተፈናቀሉ እንዲሁም ደመወዝ ወይም ገንዘባቸውን ከባንክ ለማንቀሳቀስ ባለመቻላቸው መሠረታዊ አቅርቦት እንዳጡ መግለጫው ይጠቁማል። ስደተኞች እና ተፈናቃዮች በትግራይ ክልል ከሚገኙ አራት የስደተኛ ካምፖች ውስጥ ሁለቱ ሽመልባ እና ሕፃፅ ይገኙ የነበሩ ኤርትራውያን ስደተኞች እንደተበተኑና ካምፖች እንደወደሙ ኢሰመኮ ጠቁሟል። ከጦርነቱ ቀደም ብሎ ሽመልባ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የነበሩ 8500 የሚጠጉ ኤርትራዊያን ስደተኞች የነበሩ ሲሆን ከጦርነቱ በኋላ በግምት 5000 የሚሆኑት ወደ ሽራሮ እና ሽሬ ከተሞች መበታተናቸው ቀሪዎቹ 3500 በፍቃዳቸውም ሆነ ያለፍቃዳቸው ወደተለያየ ስፍራ መጓዛቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል። በሕፃፅ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ በግምት ወደ 13000 የሚጠጉ ስደተኞች የነበሩ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 8000 የሚሆኑት በሽሬ እና ሽራሮ ከተሞች መበታተናቸውና "አብዛኛዎቹ ስደተኞች መጠለያ እና መሠረታዊ አቅርቦቶችን ለማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ እንደሚገኙ ኮሚሽኑ ያገኛቸው መረጃዎች ያሳያሉ" ሲልም አክሏል። ስምንት የተፈናቃዮች መጠለያ ትምህርት ቤቶችን ተዘዋውሮ ባገኘው መረጃ መሠረት እየቀረበ የሚገኘው መሠረታዊ አገልግሎት አነስተኛ እንደሆነ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
news-51499403
https://www.bbc.com/amharic/news-51499403
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አቃቤ ሕግ አስታወቀ.
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተበራከቱ በመጡ የወንጀል ተግባራት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር በማዋል ክስ መመስረት መጀመሩን አስታወቀ።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በበኩሉ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ 350 አባላቱ እንደታሰሩበት ገልጿል። አቃቤ ሕጉ ትናንት አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ በብሔር ወይም በክልሎች መካካል እንዲሁም በግለሰቦችና ቡድኖች በሚፈጠር ግጭት መነሻነት ወንጀል በተፈጸመባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ዋና ዋና ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ በማድረግ የተደራጀ የምርመራና ክስ የመመስረት ሂደት ተጀምሯል ሲል ገልጿል። በመግለጫው ላይ በግጭቶቹ ላይ ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ከሚገኙባቸው ስፍራዎች መካከልም ምዕራብ ጉጂ፣ አዳማ፣ ምሥራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሸዋ እና አዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ የተጠቀሱ ሲሆን ከደቡብ ክልል ደግሞ ጌዲኦ ዞን፣ ሐዋሳ፣ የቴፒና ሸካ ዞን ተጠቅሰዋልወ። በመግለጫው ላይ ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር የማዋል ሥራ የተጀመረባቸው ሌሎች አካባቢዎችም የተጠቀሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከልም በሶማሌ ብሔራዊ ክልል በጅግጅጋና ሌሎች ዞኖች፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ካማሽ ዞን፣ መተከል ዞን የተጠቅሰዋል። በተጨማሪም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በአዊ ብሔረሰብ ዞን በጃዊ ወረዳ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ በሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም በአንዳንድ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተፈጸመውን ወንጀል ድርጊቶችን መነሻ በማድረግ ተጠሪጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራ መጀመሩ ተጠቅሷል። አቃቤ ሕግ በመግለጫው ላይ አክሎም የመንግሥት ከፍተኛ አመራር ባደረገዉ ግምገማ በየቦታው የሚፈጠሩ የወንጀል ድርጊቶች ዋነኛ ችግር የፖለቲካ አመራሮች እጅ ያለበት መሆኑን በሚገባ መረዳቱን ገልጿል። ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አክሎም ይህን የማይገባ ተግባር ሲያስፈጽም እና ሲፈፅም በዝምታ ሲያልፍ የነበረው አመራር ከድርጊቱ እንዲታረም አሳስቧል። "በአገሪቱ በሚፈለገው መጠን የሕግ የበላይነትን በማስከበር ረገድ የነበረውን ፈተና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የምንሻገረው እንደሚሆን እሙን ነው" ያለው መግለጫው ተጠርጣሪዎች በሕግ ፊት እንዲቀርቡ የሚደረገውን ጥረት በሚያደናቅፉ አካላት ላይ ያለምንም ምህረት በማያዳግም ሁኔታ ተጠያቂ እንደሚደረግ ገልጿል። "የሕግ የበላይነትን የማስከበር እንቅስቃሴ ለድርድር አይቀርብም" ያለው መግለጫው ለአገሪቱ ደህንነትና ለሕዝቦች ህልውና ሲባል ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን እንደማይታገስ ጽኑ አቋም መያዙን በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። ቢቢሲ ከቀናት በፊት በጅማ ሊደረግ ታስቦ በነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሕዝባዊ መድረክ መከልከል ጋር በተያያዘ ያነጋገራቸው የድርጅቱ የጅማ ቅርንጫፍ ኃላፊ አባላቶቻቸው እየታሰሩባቸው መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል። በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎችም ወጣቶች እየታሰሩ መሆኑን ቢቢሲ ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ከሚኖሩ ግለሰቦች መረጃ ደርሶታል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ዛሬ በሰጠው መግለጫው ላይ " በኦሮሚያ የተቃዋሚ ድርጅት አባላትና ንፁኀን ዜጎች በጅምላ መታሰራቸው እጅጉን ያሳስበናል" ያለ ሲሆን፤ የመብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናልም ከሳምንታት በፊት ባወጣው መግለጫ ይህንኑ ጠቅሶ ነበር።
news-42011729
https://www.bbc.com/amharic/news-42011729
የዳቪንቺ ስዕል ክብረወሰንን ሰብሮ ተሸጠ
500 ዓመታትን እንዳስቆጠረና በሰዓሊ ሊዎናርዶ ዳ ቪንቺ እንደተሳለ የተነገረለት ስዕል በ450 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ተሽጧል።
"የዓለም ጠባቂ" የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ ስዕል በጥበብ ሥራዎች የጨረታ ዋጋ ታይቶ በማይታወቅ ገንዘብ ለመሸጥ ችሏል። በአውሮፓውያኑ 1519 ሕይወቱ እንዳለፈ የሚነገርለት ዳ ቪንቺ "የዓለም ጠባቂ" የተሰኘው ሥራውን በ1505 እንደሠራው ይታመናል። በ100 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ የቀረበውን የጥበብ ውጤት ማንነቱ ያልታወቅ ግለሰብ ነው በስልክ ድርድር በጠቅላላ ዋጋ 450 ሚሊዮን ዶላር የግል ንብረቱ ማድረግ የቻለው። ይህ ስዕል በአውሮፓውያኑ 1958 ለንደን በሚገኝ የጨረታ ማስኬጃ ሥፍራ በ45 ዩሮ ተሽጦ ነበር። ነገር ግን የዛኔ ስዕሉ የሌዎናርዶ ሳይሆን የሱ ተማሪ የሆነ ሰው እንደሳለው ተደርጎ ነበር የተሸጠው። የ19ኛው ክፍለ ዘመን ጥበብ ጥናት ምሁር የሆኑት ዶ/ር ቲም ሃንተር ስዕሉ "የ21ኛው ክፍለ ዘመን አስገራሚ ግኝት" ሲሉ ይጠሩታል። "ዳ ቪንቺ 20 የሚሆኑ የዘይት ቅብ ያረፈባቸው ስዕሎች ሠርቷል። ከእነዚህ መካከል በጥሩ ይዘት ላይ ያለ መሰል ጥበብ ማግኘት እጅግ አስደናቂ ነው'' ሲሉ ያክላሉ። ስዕሉ ለጨረታ ከመቅረቡ በፊት በሩስያዊው ቢሊዮነር ዲሚትሪ ሪቦሎቭሌቭ እጅ ነበር የሚገኘው። ቢሊየነሩ ስዕሉን ወርሃ ግንቦት 2013 በ127.5 ሚሊዮን ዶላር ነበር የገዛው። ምንም እንኳ ስዕሉ ጥገናዎችን ቢያልፍም አሁንም በጥሩ ይዘት ላይ ነው የሚገኘው ሲሉ አጫራቾቹ ይከራከራሉ። ከዚህ በፊት ከፍተኛ ዋጋ ያለው የጥበብ ሥራ በጃክሰን ፖሎክ የተሰራው 'ቁጥር 17ኤ' የተሰኘው ስዕል ሲሆን ዋጋውም 200 ሚሊዮን ዶላር ነበር።
news-41938453
https://www.bbc.com/amharic/news-41938453
ተማሪዎችን ያስከፋው የትምህርት ሚንስቴር ፖሊሲ ጉዳይ
በቅርቡ ከትምህርት ሚኒስቴር የወጣው መመርያ እያንዳንዱ የከፍትኛ ትምህርት የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪ ከመመረቁ በፊት አጠቃላይ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ፈተና እንዲወስድ ያስገድዳል።
በመምህራን፣ በህክምናና በጤና የትምህርት ክፍሎች ብቻ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ይህ የምዘና ማረጋገጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እና በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ተግባራዊ እንዲደረግ ተወስኗል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተማሪዎች ውሳኔው እንዳደናገራቸው ሲናገሩ ትምህርት ሚኒስቴር ግን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ቀደም ሲል የወጣን ፖሊሲ ተግባራዊ የማድረግ ጉዳይ እንጂ አዲስ ነገር አይደለም ሲል ይገልፃል። የ5 ዓመት ትምህርት በ1 ቀን ምዘና ? በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ምህንድስና 4ተኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ጌታሁን* "የተማሪዎች ብቃት በመጨረሻ ዓመት በሚሰጥ ፈተና አይረጋገጥም" ሲል ይሞግታል። "ሲጀመር መምህራኑ ጥሩ ትምህርት አያስተምሩም። መመዘን ያለባቸው ተማሪዎች ብቻ ኣይደሉም። መምህራኑ በተሻለ ጥራት ሳያስተምሩ ተማሪ ቢመዘን ባይመዘን ምን ዋጋ አለው?" በማለት ይጠይቃል። ጌታሁን* እንደሚለው "ብዙ ዓመት ለፍቶ ጥሩ ውጤት ይዞ የሚመረቅ ተማሪ መንግሥት አራትና አምስት ዓመት ጠብቆ ብቃት የለህም" ማለቱ አግባብ አይደለም። በያዝነው የትምህርት ዘመን መባቻ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ክፍለ-ትምህርት ተማሪዎች አጠቃላይ ምዘና መውሰድ አለመውሰድ ላይ እሰጣገባ ገብተው እንደነበር ቢቢሲ መዘገቡ ይታውሳል። ጌታሁን* ምዘናውን ቢያልፍም በርካታ ጓደኞቹ በተለይ አንዳንዶቹ 3.8 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ጎበዝ ተማሪዎች ወድቃችኋል መባላቻው ምዘናው ላይ ያለውን ስህተት በምሳሌነት ይጠቅሳል። ሌላኛው የ3ተኛ ዓመት የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ኮምፒውተር ምህንድስና ተማሪው ሲሳይ* በበኩሉ "እንኳን አምስት ዓመት ጠብቀን አሁን የተፈተነውም ኣይመጥነንም" ይላል። በአሁኑ ወቅት ለተግባር ትምህርት ወጥቶ የሚገኘው ይሄው የባህርዳር ዩኒቭርሲቲ ተማሪ ምዘናውን የሚቃወምበት ምክንያት አለው። "ምክንያቱም የትምህርት ጥራት የሚረጋገጠው በፈተና ሳይሆን ትምህርቱ በምን ዓይነት ሁኔታ ነው የሚሰጠው? በምን ዓይነት ሁኔታ ነው እያተማርን ያለነው? የሚሉትን ግምት ውስጥ ማስገባት ሲቻል ነው" በማለትም ይጠይቃል። "ብዙ ልምድ በሌላቸውና ከተማሪዎች ብዙም በማይሻሉ አስተማሪዎች ነው እየተማርን ያለነው። በዛ ላይ ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አልፈን ነው የምንማረው፤ ምክንያቱም ምንም አማራጭ የለንም" በማለትም ያክላል። ይህ የአብዛኛዎቹ ተማሪዎች አስተያየት መሆኑ የሚናገረው ሲሳይ* "አዲሱን መመርያ መውጣት ተከትሎ "ሁሉም ተማሪ 'ምን ታስቦ ይሆን?' በማለት እየጠየቀ ነው" ሲል ይናገራል። "በአጠቃላይ ተማሪው ደስተኛ አይመስለኝም" ይላል። ምዘናና የትምህርት ጥራት . . . ? ትምህርት በኢትዮጵያ ባለፉት አስር ዓመታት በመንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ዘርፍ ሲሆን በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥርና ወደ ተቋማቱ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ጨምሯል። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ ግን "ከዚህ በፊት የሕግ ተማሪዎችን፣ መምህራንና የህክምና ተማሪዎችን ስንመዝን ቆይተናል። በሌሎችም ትምህርት ክፍሎች ይህን አሰራር ነው እንዲቀጥል ያደረግነው፤ አዲስ መመርያ ተደርጎ መወሰድ የለበትም" ሲሉ ለቢቢሲ ይናገራሉ። የማይቀር የመንግስት ፖሊሲ መሆኑ በማስረገጥም "ሌሎችም ስለሚቀጥሉና በቂ ዝግጅት ማድረግ ስላለባቸው ነው እንደ አዲስ መፃፍ ያስፈለገን" ይላሉ። ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በታች የሆኑ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ መምህራንም በተመሳሳይ የብቃት ስርዓት እንደሚመዘኑ አክለው ተናግረዋል። "ከዚህ በኋላ በሙያው ያልተመዘነ መምህር አይሆንም፣ ዳኛም ሐኪምም አይሆንም፤ ፈቃድም አያገኝም።" እንደ ዶ/ር ጥላዬ እምነት የተዘረጋው የምዘና ስራዓት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ መንገድ ነው። ኣቶ ታፈረ ቢጠና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ጥራት ኤጀንሲ ከፍተኛ ባለሙያ እንደሚሉት "ይህ ዓይነቱ አሰራር በተለያዩ የውጭ ሀገራት የተለመደና የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ የሚሰራረበት ነው፤ በአግባቡና በስርዓት ከተተገበረ እጅግ ጠቃሚ ነው" ይላሉ። አዎንታዊ ሚናው እንደሚያመዝን የሚናገሩት አቶ ታፈረ በተጨማሪ በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ እንዲኖር እንዲሁም የእርስ በርስ ፉክክርንም ለማስወገድም ይጠቅማል ብለው ያምናሉ። "አንድ ተማሪ ባዶ ወረቀት ይዞ እንዳይወጣና የሚገባውን እውቀት ሸምቶ እንደወጣ ለማመሳከር ምዘናው ይጠቅማል። እንዲሁም ደግሞ መምህራኖች ሲያስተምሩ ይህንን ታሳቢ ያደረገ የሆነ ግንዛቤ ይፈጥራል" ይላሉ። ፕሮግራሙ ከአንድ ኣመት በኋላ በ2011 ዓ.ም. በሁሉም የትምህርት ክፍሎች ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል።
news-47229218
https://www.bbc.com/amharic/news-47229218
ኬንያዋ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሞታ ተገኘች
በባለፈው ሳምንት ረቡዕ ጠፍታ የነበረችው ኬንያዊቷ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ካሮሊን ምዋታ ሞታ ተገኘች።
በመዲናዋ ናይሮቢ ፖሊስ የሚፈፅመውን ግድያዎችን የመመዝገብና ለህዝብ ይፋ የማድረግ ስራ ትሰራ እንደነበር ተገልጿል። የአስከሬን ምርመራዋ ለሚቀጥለው ሰኞ የተላለፈ ሲሆን ለዚህም እንደ ምክንያትነት የተሰጠው ዋናው የአስከሬን መርማሪው ጆሀንሰን ኦዱር መገኘት ባለመቻላቸው እንደሆነ ሲትዝን ቴሌቪዥን ዘግቧል። •ናይጀሪያዊቷ ባለቤቴን ገድሏል በማለት ሼል ኩባንያን ከሰሰች •በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? ሌላኛው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሁሴን ካሊድ በዛሬው ዕለት የአስከሬን ምርመራ ባለመደረጉ እንዳሳዘነው መግለፁን የሀገሪቱ ጋዜጣ ዘ ስታር ዘግቧል። በጠፋችበት ወቅት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ በህይወት የመገኘቷ ነገር እንደሚያሳስበው በትዊተር ገፁ አስፍሮ ነበር። •"ኦሮሞነትን ከፍ አድርጌ ኢትዮጵያዊነትን የማሳንስ አይደለሁም" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ነገር ግን ፖሊስ እንደገለፀው አደገኛ በሆነ ውርጃ ምክንያት መሞቷንና ከድርጊቱም ጋር ተያይዞ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።
news-53963771
https://www.bbc.com/amharic/news-53963771
በአሜሪካ የትራምፕ ደጋፊዎችና የጥቁር መብት ሰልፈኞች ተጋጩ
በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ሁለት ተጻራሪ ሰልፈኞች ለተቃውሞና ድጋፍ አደባባይ ወጥተው በመጋጨታቸው አንድ ሰው ተተኩሶበት ሞቷል፡፡
ሰልፈኞቹ ግማሾቹ ዶናልድ ትራምፕና የሚደግፉ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ የጥቁር መብት ተሟጋቾች ናቸው፡፡ ግጭቱ የተከሰተው በፖርትላንድ ከተማ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፖርትላንድ ጎዳናዎች ተመሳሳይ ግጭቶች በተደጋጋሚ ሲከሰቱ ነበር፡፡ በተለይም በግንቦት 25 ጆርጅ ፍሎይድ በነጭ ፖሊስ ማጅራቱ ታንቆ ከተገደለ በኋላ የጥቁር መብት ተሟጋቾች በፖርትላንድ ተደጋጋሚ ሰልፎችን አድርገዋል፡፡ በሐምሌ ወር ዶናልድ ትራምፕ የልዩ ኃይል አባላትን ወደዚች ከተማ ፖርትላንድ መላካቸው ይታወሳል፡፡ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ደግሞ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ወደ አደባባይ መውጣት ጀምረዋል፡፡ የዛሬው ሦስተኛ ጊዜያቸው ነው፡፡ የፖርትላንድ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ አንድ ሰው ደረቱ ላይ በጥይት ተመትቶ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ መሞቱ ተረጋግጧል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በፓርቲያቸው በይፋ እጩ ሆነው የተመረጡ ዕለት ባደረጉት ንግግር ፖርትላንድ በዲሞክራቶች የምትመራ ሥርዓት አልበኝነት የነገሰባት ከተማ ሲሉ ጠቅሰው ነበር፡፡ በዊስኮንሰን ባለፈው እሁድ ጃኮብ ብሌክ የተባለ ወጣት ሦስት ልጆቹ መኪና ውስጥ ቁጭ ብለው እየተመለከቱት በ7 ጥይት በፖሊስ መደብደቡ ቁጣን ቀስቅሶ ቆይቷል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ዊስኮንሰን ግዛት ኬኖሻ ከተማ ማክሰኞ ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
54626165
https://www.bbc.com/amharic/54626165
የሳኡዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን በአሜሪካ ክስ ተመሠረተባቸው
የሳኡድ አረቢያ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን በአሜሪካ የክስ ፋይል ተከፍቶባቸዋል።
የሳኡዲው ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን ከሳሾቹ ደግሞ የሟቹ ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ እጮኛ ሃቲስ ሴንጊዝ እና ኻሾግጂ ከመገደሉ በፊት የመሠረተው የመብት ተሟጋች ቡድን ነው። በጥምረት የተከፈተው ክስ ጋዜጠኛ ኻሾግጂ እንዲገደል ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ትእዛዝ ሰጥተዋል ይልላ። የዋሺንግተን ፖስት አምደኛና የመብት ተሟጋቹ ጀማል ኻሾግጂ ከሁለት ዓመት በፊት ነው በኢስታንቡል የሳኡዲ ቆንስላ ውስጥ ዘግናኝ በሚባል ሁኔታ የተገደለው። ግድያውን ያዘዙት የሳኡዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ናቸው የሚል በርካታ ክሶች ይቀርብባቸዋል። ልዑሉ ግን ከደሙ ንጹሕ ነኝ ይላሉ። ኻሾግጂ ከጋብቻ ወረቀት ማሳደስ ጋር በተያያዘ በቱርክ ኢስታንቡል በሚገኘው የሳኡዲ ቆንስላ እንደገባ ነበር በዚያው በኖ የቀረው። ያንኑ ዕለት በፍጥነት ከሳኡዲ በልዩ አውሮፕላን የገባ አንድ ነፍሰ ገዳይ ቡድን እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ጀማል ኻሾግጂን ገድሎ ከአገር መውጣቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ሆነ የቱርክ መንግሥት ደርሶበታል። የጀማል ኻሾግጂ እጮኛ ሃቲስ ሴንጊዝ ልዑሉ ግን እኔ ግድያውን አላዘዝኩም ሲሉ ተከራክረዋል። ጋዜጠኛና የዋሺንግተን ፖስት አምደኛ ጀማል ኻሾግጂ የሳኡዲ መንግሥት የመብት ረጋጭነትን ሲተች በይበልጥ ይታወቃል። ከአገሩ ሳኡዲ ከመሰደዱ በፊትም ንጉሣዊያን ቤተሰቡን ያማክር ነበር። የሟቹ ጀማል እጮኛ የነበረችው ቱርካዊቷ ሴንጊዝ ክሱን እና የመብት ቡድኑ ክሱን የከፈቱት በዋሺንግተን ዲሲ ነው። ጀማል ካሾግጂ መስርቶት የነበረው ‹‹ዲሞክራሲ ፎር ዘ አረብ ዎርልድ ናው›› የመብት ተቆርቋሪ ድርጅት ከመሥራቹ መገደል በኋላ ከፍተኛ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ እንደገባ ተነግሯል። ይህ ድርጅትም ከጀማል ኻሾግጂ እጮኛ ጋር በመሆን ልዑሉን ከሳሽ ሆኖ ቀርቧል። ‹‹ጀማል በሕይወት ሳለ በአሜሪካ ሁሉም ነገር ይቻላል ይለኝ ነበር። እምነቴን በአሜሪካ የፍትሕ ሥርዓት ላይ ጥዬ ነው ክሱን የከፈትኩት›› ብላለች፣ እጮኛው። ጀማል ኻሾግጂ ማን ነበር? ቀድሞ በሳኡዲ ውስጥ ጋዜጠኛ ነበር። አፍጋኒስታን በሶቪየት ኅብረት ስትወረር፣ የኦሳማ ቢን ላደን አነሳስና ሌሎች ትልልቅ ጉዳዮችን ለተለያዩ ሳኡዲ ዜና ጣቢያዎች በመዘገብ ዝናን አትርፏል። ከዚያ በኋላም ከንጉሣዊያን ቤተሰቦች ጋር ቅርብ ግንኙነት ነበረው። የመንግሥት አማካሪም ሆኖ ሰርቷል። አንዳች አለመግባባት በመፈጠሩም በፈረንጆቹ 2017 ከሳኡዲ ተሰዷል። በአሜሪካ መኖር ከጀመረ በኋላም ለዋሺንግተን ፖስት ወርሃዊ አምደኛ ሆኖ ይሰራ ነበር። ሌሎች ተያያዥ የመብት እንቅስቃሴዎችንም በማድረግ ይታወቃል። በሚጽፋቸው ጽሑፎቹ የሳኡዲው ልዑልና የንጉሥ ሰልማን ልጅ የሆኑት መሐመድ ቢን ሳልማን ላይ የሰላ ሒስ ያቀርብ ነበር። ከፍተኛ የመብት ረገጣ ባለባት ሳኡዲ ንጉሡንና ቤተሰቡን መተቸት ለሞት የሚዳርግ ነው። ጀማል በኦክቶበር 2፣2018 በቱርክ ኢስታንቡል ከእጮኛው ጋር ሳኡዲ ቆንስሌት ሄደ። እጮኛውን ለማግባት የሚያስችለው ወረቀት ለማግኘት እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመጨረስ። እጮኛው ከዚህ ቆንሱሌት በር ላይ ጠበቀችው። እሱ ገባ። ከዚያ በኋላ አልተመለሰም። ሬሳውም ቢሆን እስከአሁን የት እንዳለ አይታወቅም። ምናልባት የኻሾግጂ ሬሳ በልዩ ኬሚካል ተቃጥሎ እንደ ንፋስ እንዲበን ተደርጓል የሚል ከፍተኛ ጥርጣሬ አለ።
news-55963183
https://www.bbc.com/amharic/news-55963183
በኢትዮጵያ የዘይት እጥረትን እንደሚቀርፍ ተስፋ የተጣለበት ፋብሪካ ተመረቀ
በኢትዮጵያ የዘይት አቅርቦት ላይ ያለውን እጥረት ሊቀርፍ ይችላል የተባለ ግዙፍ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ፋብሪካውን መርቀው ከፍተውታል። ፋብሪካው በአማራ ክልል ቡሬ ከተማ የሚገኝ ሲሆን 4.5 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበትም ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ አካል የሆነው ፌቤላ ኢንደስቱሪያል ኮምፕሌክስ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን 1.5 ሚሊዮን ሊትር የዘይት ምርቶች ለኢትዮጵያ ገበያ የማቅረብ አቅም አለው ተብሏል። በኢትዮጵያ ያለውን ከፍተኛ የዘይት ምርት ፍላጎት ለማሟላት መንግሥት በውጪ ምንዛሬ፣ የዘይት ምርት ከውጪ ወደ አገር ውስጥ እያስገባ ይገኛል። የኢንደስትሪያል ኮምፕሌክሱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳምጤ ስማቸው ኮምፕሌክሱ የሚያመርተው የዘይት ምርት 45 በመቶ የአገሪቱን ፍላጎት የሚሸፍን ይሆናል ብለዋል። ኮምፕሌክሱ ከቅባት እህሎች የሚመረቱ የዘይት ምርቶችን እና የፓልም ዘይትን ለገበያ ያቀርባል። እንደ አቶ ዳምጤ ገለጸ ከሆነ ከቅባት እህሎች ለሚመረተው ዘይት ግብዓቱን ከአገር ውስጥ ለመሰብሰብ ታቅዷል። በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው በቀን ከ750ሺህ በላይ ሊትር የቅባት እህል ዘይት ለማምረት የሚያስፈልገውን ግብዓት ማቅረብ የሚችል የአገር ውስጥ አቅራቢ አለመኖሩን ይናገራሉ። በዚህም ምክንያት ፋብሪካው ወደፊት ለቅባት እህል ዘይት ምርቱ የሚያስፈልገውን ግብዓት ለማግኘት የራሱን እርሻ እያዘጋጀ መሆኑን አቶ ዳምጤ ተናግረዋል። ለፓልም ዘይት ምርት ግን ድፍድፍ ግብዓቱን ከውጪ በማስገባት በፋብሪካው የማጣራት ሥራ እንደሚሰራ አቶ ዳምጤ አስረድተዋል። ኮምፕሌክሱ የሚያመርታቸው የዘይት አይነቶች ለገበያ የሚቀርቡበት ዋጋ በቀጣይ ቀናት እንደሚተመን የሚናገሩት አቶ ዳምጤ፤ የተሻለ ጥራት ያለውን ምርት በተወዳዳሪ ዋጋ ለሕብረሰቡ ማቅረብ አላማችን ነው ብለዋል። በ30 ሄክታር መሬት ላይ የሰፈረው ፋብሪካ፤ ያመረተውን ዘይት ለማሸግ የተለያየ መጠን እና ቅርጽ ያላቸው ፕላስቲኮች እና ካርቶን እንደሚያመርት ምክትል ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል። ዛሬ በተመረቀው ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ ከዘይት ምርቶች በተጨማሪ የሰሊጥ ምርትን በመቁላት እና በመፈተግ እሴት ጨምሮ ወደ ውጪ አገር ይልካል። ከዚህ በተጨማሪ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክሱ የሳሙና እና የማርገሪን ፋብሪካም አለው። ፌቤላ የኢንደስቱሪያል ኮምፕሌክስ በቡሬ ከተማ በ4.5 ቢሊዮን ብር የተገነባ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለ1ሺህ ሰዎች የሥራ እድልን ፈጥሯል። ኮምፕሌክሱ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ እስከ 3ሺህ ሰዎችን እንደሚቀጥር አቶ ዳምጤ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-55359559
https://www.bbc.com/amharic/news-55359559
አሜሪካ ከሩሲያ ነው ተብሎ የተገመተ ‘ከባድ’ የሳይበር ጥቃት እየተከላከለች መሆኑ ተሰማ
አሜሪካ በዚህ ሳምንት መጀመርያ ከባድ የሳይበር ጥቃት እየዘነበብኝ ነው፤ ጥቃቱ አሁንም አላባራም ብላለች።
የሳይበር ጥቃቱም በተለይ በመንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች ላይ ከባድ አደጋን ሊያደርስ እንደሚችል ሰግታለች። ጥቃቱ በዋናነት የአሜሪካ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ላይ ዒላማ ያድርግ እንጂ ለግዙፍ የግል ተቋማትም አደጋን ጋርጧል። ግዙፉ የአሜሪካ ግምጃ ቤት እና የአሜሪካ የንግድ ሚኒስቴር የዚህ የሳይበር ጥቃት ሰለባ ሆነዋል። የአሜሪካ የበይነ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ሲሳ) እንዳመነው ይህንን ጥቃት ለማክሸፍ እንዲህ እንደሚወራው ቀላል አልሆነም። ሐሙስ ዕለት ይህ መሥሪያ ቤት ባወጣው ሪፖርት ዋና ዋና የመንግሥት መሠረተ ልማቶች በዚህ ጥቃት ዒላማ ተደርገዋል ብሏል። መሥሪያ ቤቱ ጨምሮም፥ "ጥቃቱ የዋዛ አይደለም፥ የአንድ ጊዜ ጥቃት ብቻም አይደለም፣ አሁንም ቀጥሏል" ሲል የጉዳዩን አሳሳቢነትና ውስብስብነት ዘርዝሮታል። ብዙዎች ከዚህ ውስብስብ ጥቃት ጀርባ ሩሲያ ካልሆነች ሌላ አካል ሊሆን አይችልም ሲሉ ይከስሳሉ። ሞስኮ ግን መሠረተ ቢስ ወሬ ነው ስትል ክሱን አስተባብላለች። ከዚህ ጥቃት ጀርባ በዋናነት ትልቅ አገር ልትኖር እንደምትችል የተገመተው መረጃ መንታፊዎቹ ያሳዩት ታጋሽነት፣ ጥቃቱን ለማድረስ የሚሄዱበት ውስብስብ ርቀት እና ዲሲፕሊን፣ ጥቃቱን ሲያደርሱ ማንነታቸው እንዳይታወቅ ያዘጋጁት ከለላ ጥብቅነት ያለው በመሆኑ ነው። ሲሳ እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ሩሲያን በይፋ አልከሰሰም። ለጥቃቱ ኃላፊነትን ለየትኛው አካል አልሰጠም። በተጨማሪም የትኞቹ የመንግሥት መዋቅሮች የትኛው መረጃ እንደተመነተፈባቸው በዝርዝር አልገለጸም። ይህ በአንዲህ እያለ ከአንድ ወር በኋላ ወደ ዋይት ሐውስ የሚገቡት ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ባይደን የሳይበር ደኅንነት ጉዳይ መንግሥቴ እጅግ አንገብጋቢ ከሚላቸው አጀንዳዎች አንዱ ነው ብለዋል። በርካታ የአሜሪካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሰሞኑ የሳይበር ጥቃት ክፉኛ እንደተሸመደመዱ ይነገራል። ይህ የሳይበር ጥቃት አሁንም ድረስ አልቆመም። ሮይተርስ እንደዘገበው በርባሪዎቹ በአሁን ሰዓት በአሜሪካ መከላከያ፥ በአሜሪካ አገር ውስጥ ደኅንነት (ሆምላንድ ሴኩሪቲ)፥ በአሜሪካ ግምጃ ቤትና ንግድ ሚኒስቴር ዳታዎችን በከፊል መቆጣጠር ላይ ናቸው። የአሜሪካ የኢነርጂ ዲፓርትመንት እና የብሔራዊ ኒውክሊየር ደኅንነት አስተዳደር መሥሪያ ቤቶችም በተመሳሳይ መረጃዎቻቸው እንደተበረበሩባቸው ተናግረዋል። ሲሳ እንዳለው በርባሪዎቹ የኮምፒውተር ኔትዎርኮችን ሰብረው መግባት የቻሉት መቀመጫውን ቴክሳስ ባደረገ የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ኩባንያ በሆነው ሶላርዊንድስ ሶፍትዌር ተጠቅመው ነው። 18ሺ የሚሆኑ የሶላር ዊንድስ ኦሪዮን ሶፍትዌር ተጠቃሚዎች ይህንን ሶፍትዌር እድሳት (አብዴት) ሲያደርጉ ነው በዚያው በርባሪዎች ሰተት ብለው መግባት የቻሉት። ይህንን ተከትሎ ሁሉም የመንግሥትና የግል ድርጅቶች የሶላር ዊንድስ ሶፍትዌርን ከኮምፒውተራቸው በአስቸኳይ እንዲያስወግዱ ተነግሯቸዋል። አሁንም ቢሆን የአሜሪካ የበይነ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (Cisa) እና የአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (FBI) ከዚህ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት ጀርባ ማን እንዳለ ከመናገር ተቆጥበዋል። ሆኖም በሳይበር ደኅንነት የመሰሩና የበይነ መረብ ደኅንነት ጉዳይ አዋቂዎች፣ አማካሪዎችና ተመራማሪዎች እንዲህ ያለ አቅም ያላት ሩሲያ ብቻ ናት ሲሉ ጣታቸውን ወደ ክሬምሊን ይጠቁማሉ።
49779670
https://www.bbc.com/amharic/49779670
ግብፃውያን ፕሬዝዳንት አል-ሲሲን በመቃወም ሰልፍ ወጡ
ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ በግብፅ በተካሄደው የመጀመሪያ የተቃውሞ ሰልፍ፤ ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙ ተዘገበ።
ግብፃውያን ፕሬዝዳንት አል-ሲሲን በመቃወም ሰልፍ ወጥተዋል በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በታህሪር አደባባይ ሰልፍ ወጥተው፤ ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2011ዱ ተቃውሞ ማዕከል ከነበረው ታህሪር አደባባይ በተጨማሪ በሌሎች አካባቢዎችም ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል። • መንግሥትን ተሳድቧል የተባለው ደራሲ ተከሰሰ • ግብፅ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሞት ውርጅብኝ እያስተናገደች ነው • በጥቅም ላይ የዋሉ የጥንታዊ ግብፅ የህክምና ጥበባት በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፍ የተካሄደው አል-ሲሲ በሙስና መወንጀላቸውን ተከትሎ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በታህሪር አደባባይ ሰልፍ ወጥተዋል ግብፃዊው ተዋናይና የቢዝነስ ሰው ሞሀመድ አሊ፤ አል-ሲሲ በቅንጡ ቤቶችና ሆቴሎች ላይ በርካታ ገንዘብ እያባከኑ እንደሚገኙ በመግለጽ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቪድዮዎች አሰራጭቷል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በድህነት እየማቀቁ ሳለ ፕሬዝዳንቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እያባከኑ መሆኑንም ተናግሯል። አል-ሲሲ የተባለው ነገር "ውሸት እና የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው" ሲሉ ውንጀላውን አጣጥለዋል። ትላንት በትዊተር ላይ በስፋት ሲሰራጩ የነበሩ መልዕክቶች ሕዝቡ አል-ሲሲ ከሥልጣን እንዲነሱ እንደሚፈልግ የሚጠቁሙ ነበሩ። አል ጀዚራ እንደዘገበው፤ በአሌክሳንድርያ እና ስዊዝ ከተሞችም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። ስፔን ውስጥ በስደት የሚኖረው ግብፃዊው ተዋናይና የቢዝነስ ሰው ሞሀመድ አሊ፤ የመጀመሪያ ቪድዮውን የለቀቀው መስከረም ሁለት ነበር። ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን የሚወርዱበት ቀነ ገደብ አስቀምጦ፤ አል-ሲሲ በተባለው እለት ከሥልጣን ካልወረዱ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ገልጾም ነበር። ሞሀመድ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት፤ አል-ሲሲ ከሥልጣናቸው አለመነሳታቸውን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን ሰልፍ ወጥተዋል። ግብፅ ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት የሆኑት ሞሀመድ ሙርሲን በማስወገድ አል-ሲሲ ስልጣን የጨበጡት 2013 ላይ ነበር። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መታሰራቸውን በማጣቀስ፤ የአል-ሲሲን አስተዳደር በጽኑ ይተቻሉ። 2018 ላይ በተካሄደው ምርጫ አል-ሲሲ ጠንካራ ተቀናቃኝ ሳይኖር 97 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል። አል-ሲሲ እስከ 2030 ስልጣን ላይ እንዲቆዩ ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ የማድረግ ሀሳብ አብላጫ ድምፅ ማግኘቱም ይታወሳል።
53864758
https://www.bbc.com/amharic/53864758
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መጠሪያውን እና የብሮድካስት መብቱን ሊሸጥ ነው
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ እንዲችሉ ጨረታ ማውጣቱን ገለፀ።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ፤ ማህበሩ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን ለመሸጥ አቅዶ ጨረታ ማውጣቱን ተናግረዋል። አንደኛው፤ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን በቴሌቪዥን ለማሰራጨት የብሮድካስቲንግ መብቱን ለመሸጥ በማሰብ የዓለም አቀፍ እንዲሁም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃኖች እንዲወዳደሩ ጨረታ ማውጣቱን ገልፀዋል። ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ኩባንያ የሚጠራበትን ስም ለመሸጥ ጨረታ ማውጣታቸውን አቶ ክፍሌ ሰይፈ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፉ 16 ቡድኖች በጋራ ያቋቋሙትና በንግድ ድርጅትነት የተመዘገበ ማህበር መሆኑን ሥራ አስኪያጁ አቶ ክፍሌ ጨምረው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምከንያት በዝግ ስታድየም የሚታይ ከሆነ፣ እንዲሁም ምርመራ እንዲደረግ ግዴታ የሚቀመጥ ከሆነ ተጨማሪ ወጪ ስለሚጠይቅ እነዚህን ነገሮች ለመሸፈን በማሰብ የተለየ አማራጭ ማሰባቸውን ጨምረው ተናግረዋል። ከሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ የአክሲዮን ማህበሩ አባል ቡድኖች ከመንግሥት ድጎማ ተላቅቀው ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ እንዲሁም በአፍሪካም ሆነ በአውሮፓ ደረጃ ያሉ የስፖርት ቡድኖች እንደሚያደርጉት የስፖርት ኢንቨስትመንት ውስጥ እንዲገቡ መነሻ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ከጨረታው የሚገኘው አብዛኛው ገቢ የሚሰጠው ለእግርኳስ ቡድኖቹ መሆኑን የተናገሩት አቶ ክፍሌ፣ ቀሪው የድርጅቱ ሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል ብለዋል። ማሕበሩ የተቋቋመው የእግር ኳስ ቡድኖቹ ከመንግሥት ድጎማ ነፃ እንዲወጡ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ በፕሪሚየር ሊጉ ከሚሳተፉ 16 ክለቦች መካከል ሁለቱ ቡድኖች ብቻ የራሳቸውን ወጪ በመሸፈን የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ደጋፊ አካላት (ስፖንሰርሺፕ) እንዳላቸው ገልፀዋል። ቀሪዎቹ 14 የእግር ኳስ ቡድኖች የከተማ ክለቦች ወይም ስፖንሰር የሌላቸው መሆናቸውን በመጥቀስ እነዚህን ቡድኖች በገቢ ራስን ማስቻል የዚህ ማህበር ቀዳሚ ዓላማ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቡድኖች ችግሮች እንዳለባቸው የሚጠቅሱት ኃላፊው፣ በአመራር ችግር ደሞዝ የማይከፈላቸው በመኖራቸው ከጨረታው የሚገኘው ገንዘብ አብዛኛው ለክለቦች እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህንን የገቢ ክፍፍልን በሚመለከት የማስፈፀሚያ ሰነድ ተዘጋጅቶ 16ቱም ክለቦች መስከረም ወር ላይ ውይይት ካደረጉበት በኋላ የሚፀድቅ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። ማህበሩ በርካታ ተጫራቾች እናገኛለን ብሎ ያሰበው ከዓለም አቀፍ ተጫራጮች መሆኑንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጨረታው ላይ የአገር ውስጥ ድርጅቶችም እንደሚሳተፉ የገለፁት አቶ ክፍሌ በሚወዳደሩበት ወቅት ምክረ ሃሳብ አዘጋጅተው ገቢ የሚያገኙበትን መልክ እና የድርሻ ክፍፍሉ ምን እንደሚመስል ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፟። በኢትዮጵያ እግርኳስ ረዥም ታሪክ ቢኖረውም፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ከማይሸጥባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት።
news-42309861
https://www.bbc.com/amharic/news-42309861
"ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆን ነው የምፈልገው"
ያዴሳ ዘውገ ሰዓሊ፣ የግራፊክስ ዲዛይን ባለሙያ እና አቀንቃኝም ነው።
የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ ዓለማን የሰራው ያዴሳ ዘውገ ጥበብን የሰው ልጆችን ሰብዓዊ መብቶች ለማስከበርም ይጠቀምባታል። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመውባቸውል በሚላቸው ጉዳዮች ላይና በአሜሪካ የጥቁሮችን መብት ለማስከበር ይሠራል። ወላጅ አባቱ በደርግ መንግሥት መገደላቸውን ተከትሎ በልጅነት ዕድሜው ከትውልድ ስፍራው ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ የሚናገገው ያዴሳ ገና በጨቅላ ዕድሜው የሰው ልጆችን መብት ለማስከበር ፍላጎት እንደነበረው ያስረዳል። ''ወላጅ አባቴ የሰው ልጆችን መብት ለማስከበር ባደረገው ጥረት ነው ሕይወቱን ያጣው። ከልጅነቴ ጀምሮ ስለ ሰብዓዊ መብቶች ጠንቅቄ አውቅ ነበር። በዚህም የሰውን ሰብዓዊ መብት የሚጥሱ ነገሮችን ስመለከት ዝም ማለት አያስችለኝም'' ሲል ይናገራል። ያዴሳ የጥበብ ሥራዎችን በመጠቀም ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥረት ያደርጋል። ''ጥበብ ሰዎችን በማስደሰት እና በመማረክ በቀላሉ የምንፈልገውን መልዕክት ማስተላለፍ እንድንችል ይረዳናል። ለዚህም ነው የጥበብ ሥራዎችን በመጠቀም መልዕክቶችን የማስተላልፈው'' ሲል ይናገራል። ያዴሳ ከበቀለ ገርባ ጋር ''ብዙ ጊዜ መንግሥት ሰዎችን የሚያስረው ተረስተው እንዲቆዩ ነው 'ከዓይን የራቀ ከልብ ይርቃል' እንደሚባለው፤ እኔ ግን የሰው ልጅን ሰብዓዊ መብት ለማስከበር ሲሉ የሚታሰሩት እንዳይረሱ በጥበብ ሥራዎቼ ጥረት አደርጋለሁ'' ይላል። ከዚህም በተጨማሪ አሜሪካ ውስጥ ሲካሄድ በነበረው ''ብላክ ላይቭስ ማተር'' በተሰኘው የጥቁሮች መብት አንቅስቃሴ ላይ ትልቅ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። በቅርቡም በሲያትል በጥቁርነት ሀሳብ ላይ ያጠነጠነ "ትሩዝ ቢ ቶልድ" የሚል ዓውደ-ርዕይ አለው። ያዴሳ ሰዓሊ ብቻ ሳይሆን ሙዚቀኛም ጭምር ነው። በሙዚቃ ሥራዎቹ በርካት ሽልማቶችን ወስዷል። ''ከልጅነቴ ጀምሮ መዝፈን እወድ ነበር። የማዜመው ግን ሰዎችን ለማስደሰት ሳይሆን ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ ለመሆን ነው'' ሲል ያስረዳል። የአፍሪካ ሕብረት ባንዲራ ወደ ጥበብ እንድሳብ ካደረጉኝ ነገሮች እንዱ ወንድሜ ነው። ታላቅ ወንድሜ ስዕሎችን ይስል ነበር። ወደ አሜሪካ ከመጣሁ በኋላም ከሁለት ዩኒቨርሲቲዎች 'በቪዡዋል ኮሚዩኒኬሽን' እና 'ግራፊክስ ዲዛይን' ተመርቄያለሁ ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ከሠራቸው የግራፊክስ ሥራዎች መካከል አንዱ የአፍሪካ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማ ነው። ከ116 ሃገራት የተወጣጡ የዲዛይን ሙያተኞች የሕብረቱን ሰንደቅ ዓላማ ለመሥራት ተወዳድረው ነው ያዴሳ አሸናፊ የሆነው። ''ሥራዬ ከሌሎች ተሽሎ የተገኘበት ዋነኛው ምክንያት የያዘው መልዕክት ነው። አረንጓዴው ቀለም አፍሪካ በተፈጥሮ ሃብት የበለጸገች እንደሆነች ያሳያል፣ ኮኮቦቹ ሃገራትን የሚወክሉ ሲሆን ፀሐይዋ ደግሞ የአፍሪካ ሃገራት ከቅኝ አገዛዝ ወጥተው ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር መጀመራቸውን ያመላክታል" ሲል ይተነትናል። በዚህ ሥራው 10ሺ ዶላር እንደተሸለመና በአህጉረ አፍሪካ የሚገኙ 54ቱንም ሃገራት የመጎብኝት ዕድል እንደተሰጠውም ተናግሯል።
news-56369967
https://www.bbc.com/amharic/news-56369967
ኮሮናቫይረስ፡ የአውሮፓ ሕብረት አስትራዜኔካ የተሰኘው ክትባት የደም መርጋት አያመጣም እያለ ነው
ኮቪድ-19 እንዲከላከል ተብሎ የተሠራው የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት የደም መርጋት አደጋን ይጨምራል የተባለው ሃሰት ነው ሲል የአውሮፓ ሕብረት አስታወቀ።
መግለጫውን ያወጣው የአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ነው። ባለሥልጣኑ እንደሚለው የደም መርጋት የታየባቸው የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ካልተከተቡ ሰዎች ቁጥር ጋር ተመሳሳይ ነው። የአውሮፓ ሕብረት ይህን ማለት ያሻው ዴንማርክና ኖርዌይን ጨምሮ አንዳንድ ሃገራት ክትባቱን ለዜጎቻቸው መስጠት ማቆማቸውን ተከትሎ ነው። ሃገራቱ ክትባቱን መስጠት ያቆሙት ጥቂት ሰዎች ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ምልክት አሳይተዋል ተብሎ ነው። አንድ የ50 ዓመት ጣልያናዊ ክትባቱን ከወሰደ በኋላ 'ዲፕ ቬይን ትሮሞቦሲስ' [ከደም መርጋት ጋር ተያያዥነት ያለው] የተሰኘ በሽታ ታይቶበት ሞቷልም ተብሏል። "በአሁኑ ወቅት ክትባቱና የደም መርጋት ግንኙነት እንዳላቸው የሚያሳይ ነገር የለም። የደም መርጋትም የክትባቱ ጎንዮሽ ጉዳት አይደለም" ብሏል የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ። "ክትባቱ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል። ስለዚህ ታዩ የተባሉትን ጉዳቶች እየመረመርን ክትባቱን መስጠት እንቀጥላለን" ብሏል ኤጀንሲው። ኤጀንሲው እንደሚለው አውሮፓ ውስጥ ክትባቱን ከወሰዱ አምስት ሚሊዮን ሰዎች መካከል 30 ሰዎች የደም መርጋት ምልክት ታይቶባቸዋል። አስትራዜኔካ በቃል አቀባዩ አማካይነት የክትባቱ ደህንነት በብዙ ምርምርና ፈተና የተረጋገጠ ነው ብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም የመድኃኒት ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ክትባቱን ከደም መርጋት ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚያሳይ ምንም መረጃ የለም ብሏል። ስለዚህ ሰዎች በተጠየቁ ጊዜ ሄደው ክትባቱን እንዲወስዱ እንመክራለን ይላል። "የደም መርጋት ክትባት ባይኖርም የሚከሰት ነገር ነው። አዲስ ነገር አይደለም። እስካሁን ድረስ 11 ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶች ዩኬ ውስጥ ተሰጥተዋል" ይላሉ የባለሥልጣኑ ሠራተኛ የሆኑት ፊል ብራያን። በክትባት መዘግየት ምክንያት ችግር ላይ የነበረው የአውሮፓ ሕብረት አሁን ደግሞ አስትራዜኔካ ክትባትን በተመለከተ የሚሰራጩ ያልተረጋገጡ ዜናዎች ማነቆ ሆነውበታል። የአውሮፓ ሕብረት አሁን ፊቱን ወደ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ወደተሰኘውና አንድ ጊዜ ብቻ ወደሚሰጠው ክትባት ማዞር የፈለገ ይመስላል። "ደህንነታቸው ይበልጥ አስተማማኝ የሆኑ ክትባቶች ወደ ገበያው እየመጡ ነው" ብለዋል የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኧርስላ ቮን ደር ለየን። ከዚህ አልፎ ኖቫክስ የተሰኘው ክትባት ዋናውን የኮቪድ ዝርያ በመከላከል ረገድ 96 በመቶ አዲሱን ዝርያ ደግሞ 86 በመቶ ውጤታማነት ማሳየቱ ተነግሯል። ዴንማርክና ናሮዌይ የአስትራዜኔካን ክትባት መስጠት ሙሉ በመሉ ሲያቆሙ ኦስትሪያና ጣሊያን ደግሞ አንዳንድ ብልቃጦችን ማስወገድ ይዘዋል። ኢስቶኒያ፣ ላትቪያ፣ ሊቱኔያ እንደ ላግዘምበርግ ልክ እንደ ኦስትሪያ ለጊዜው የተወሰኑ የአስትራዜኔካ ክትባቶችን መስጠት አቁመዋል።
news-51894637
https://www.bbc.com/amharic/news-51894637
የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ፍለጋና የዋጋ መናር በአዲስ አበባ
አዲስ አበባ ውስጥ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በከፍተኛ ገንዘብ ሲሸጥ እንደነበረና በመደብሮች ውስጥ ማግኘት እንዳልቻሉ ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ።
አርብ ዕለት አዲስ አበባ ላይ የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት የመጀመሪያው የተረጋገጠ የኮሮናቫይረስ ታማሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ በኋላ ስጋት የገባቸው ሰዎች የፊት ጭንብልና ፈሳሽ የእጅ ማጽጃ ውህዶችን በመግዛት ላይ ናቸው። የቢቢሲ ያናገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳሉት በሽታው አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ ሊከላከለው ይችላል የተባሉ ነገሮችን እየገዙ መሆናቸውን ነገር ግን የጭንብሎቹና ፈሳሽ የንጽህና መጠበቂያዎች [ሳኒታይዘር] እንደልብ እንደማይገኙ ከተገኙም ዋጋቸው በሚያስደነግጥ ሁኔታ መናሩን ገልጸዋል። አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ የመድሃኒት መደብሮችም የፊት ጭንብልና ሳኒታይዘር እንደሌላቸው በሚለጥፉት ማስታወቂያም ሆነ በተጠየቁ ጊዜ የሚሰጡት ምላሽ እንደሆነ ቅዳሜ ዕለት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የሚገኙ ፋርማሲዎችን የተመለከተው የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይም በርካቶች የፊት ጭንብል ስለመጥፋቱና ስለመወደዱ ገጠማቸውን በጽሁፍና በምስል እያሰፈሩ ነው። ጭንብሉ ያለባቸው ፋርማሲዎች ረዘም ያሉ ሰልፎች የታዩ ሲሆን ውስን ቁጥር ያላቸውን መሸፈኛዎችን በመደበኛው ዋጋ ሲሸጡ እንደነበር ተገልጿል። ቢቢሲ በስልክ ያናገራቸው በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁለት የመድሃኒት መደብሮች የፊት መሸፈኛ ጭምብል እንደጨረሱና ሲሸጡ የነበረውም ቀደም ሲል በነበረው ዋጋ እንደሆነ ገልጸዋል። የከተማዋ ባለስልጣናትም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ተፈላጊ በሆኑ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ በሚሸጡ የንገድ ተቋማት ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን አመልክተው፤ ኅብረተሰቡም ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የፊት ጭንብል ፍለጋ በርካታ ሰዎች በሽታውን ሊከላከል ይችላል በማለት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን ለመግዛት ወደ መድሃኒት መደብሮች ቢሄዱም ለማግኘት እንደተቸገሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ሰው ሁሉ እየገዛ በመሆኑ ለልጆቼም ሆነ ለእራሴ የሚሆን ማስክ ለመግዛት ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በየደረስኩበት ቦታ ያሉ ፋርማሲዎችን ብጠይቅም ላገኝ አልቻልኩም" ያሉት የሁለት ልጆች እናትና አዲስ አበባ ውስጥ አብነት የሚባለው አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መብራት አስቻለ ናቸው። ወይዘሮ መብራት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጎረቤቶቻቸው ጭንብሉን እስከ 200 ብር በሚደርስ ዋጋ ከሰዎች ላይ መግዛታቸውን እንደሰሙ ነገር ግን ይህን ያህል ገንዘብ በማውጣት ለቤተሰባቸው መግዛት ከባድ ስለሆነባቸው እንደተዉት ገልጸዋል። የጭንብሉን አስፈላጊነት በተመለከተ የሰሙት በዙሪያቸው ካሉ ሰዎች መሆኑን እንጂ ከባለሙያዎች የተነገራቸው ነገር እንደሌለ የሚጠቅሱት ወ/ሮ መብራት "በሸታው አሳሳቢ በመሆኑ የምችለውን ላድርግ በማለት ነው ከአንዱ ፋርማሲ ወደ ሌላው በመሄድ ስጠይቅ የነበረው" ይላሉ። ተለያዩ ሰዎች በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ የሚሰጡት አስተያየቶችም ከዚሁ ጋር የሚመሳሰሉ ናቸው የፊት መሸፈኛ ጭንብል ከ150 እስከ 500 ብር በሚደርስ ዋጋ እየተሸጡ መሆናቸውን የሚያመለክቱ ናቸው። ከፊት መሸፈኛ ጭምብሎች በተጨማሪ የእጅ ማጽጃ ፋሳሾችም ዋጋቸው የጨመረ ሲሆን ተህዋሲያንን ያጠፋሉ ተብለው የሚነገርላቸው ሳሙናዎችም ተፈላጊነታቸው ጨምሯል። ዋጋቸውም በዚያው ልክ መጨመሩን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የከተማው መስተዳደርም "የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ተጠቂ ተገኝቷል" የሚለው መረጃ ከወጣ በኋላ በተለያዩ ሸቀጦች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል አቋቁሞ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አሳወቋል። እጥረት እየተከሰተ ነው ከኮሮናቫይረስ መከሰት ጋር በተያያዘ አፍን አፍንጫን የሚሸፍኑ ጭምብሎች በስፋት በዓለም ዙሪያ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። በዚህም ሳቢያ በበርካታ አገራት ውስጥ የጭንብሎቹ እጥረት እየተከሰተ በመሆኑ አምራቾች የጭንብል ምርታቸውን ከፍ እንዲያደርጉ በዓለም የጤና ድርጅት ተጠይቀዋል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚገምተው በየወሩ 89 ሚሊዮን የሚደርስ የፊት ጭምብሎች ያስፈልጋሉ። በኮሮናቫይረስ ስጋትና በተሳሳተ አመለካከት ሳቢያ እነዚህ ጭንብሎች ያላግባብ ጥቅም ላይ ስለሚውሉ የሚየስፈልገው ቁጥር ከዚህም በላይ እንደሚሆን ይገመታል። ድርጅቱ እንዳለውም የፊት ጭንብሎች በስፋት ጥቅም ላይ በመዋላቸውና ሰዎች በብዛት እየገዙ በማስቀመጣቸው የተነሳ የህክምና ባለሙያዎች በየዕለቱ በሚጠቀሙት አቅርቦት ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን አመልክቶ፤ ይህም በዚህ የወረርሽን ጊዜ ህሙማንን በመርዳት ሥራ ላይ የተጠመዱ የህክምና ባለሙያዎች ለኮሮናቫይረስና ለሌሎች በሽታዎች ተጋላጭ ሊያደርጋቸው ይችላል ሲል ስጋቱን ገልጿል። የፊት መሸፈኛ ጭንብል በእርግጥ ያስፈልገናል? የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው የኮሮናቫይረስን ለመካላከል በሚል ሁሉም ሰው የአፍና የአፍናጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ አያስፈልገውም። ጭንብሉን ማድረግ ያለባቸው የሚያስነጥሱና የሚያስሉ ከሆነ እንዲሁም በበሽታው የተጠረጠረ ወይም የተያዘን ሰው የሚቀርቡና የሚንከባከቡ ሰዎች ብቻ ነው። ለእነዚህ ሰዎች ጭንብሉን ማድረግ ብቻ በቂ አይደለም፤ በውጤታማ ሁኔታ በሽታውን ለመከላከልም በመደበኛነት እጃቸውን በሳሙናና በውሃ መታጠብ ወይም አልኮል ነክ በሆኑ ፈሳሾች እጃቸውን ማጽዳት ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም ጭንብሉን መጠቀም ያለባቸው ሰዎች እንዴት መጠቀምና በተገቢው ሁኔታ እንዴት መወገድ እንዳለበትም ማወቅ ይገባቸዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ይመክራል። ስለዚህም በአዲስ አበባና በሌሎች ስፍራዎች የተጠቀሱት አይነት የበሽታው ስጋቶች ሳይኖሩ ጭምብልን ከሚገባው በላይ ከፍተኛ ገንዘብ እያወጡ መግዛት በሽታውን ለመከላከል የሚኖረው ጠቀሜታ ዝቅተኛ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒሰቴር መክሯል። እነዚህ ለአጭር ጊዜ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉት የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች ጥብቅ ብለው አፍንጫና አፍን የሚሸፍኑ ካለመሆናቸው ባሻገር ረጅም ጊዜን አያገለግሉም። የማስነጠስና የማሳል ምልክት የሚታይባቸውን ወይም በኮሮናቫይረስ ከሚጠረጠሩ ሰዎች ጋር የግድ መቅረብ ያለባቸው ሰዎች የሚጠቀሙባቸው የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች በቀላሉ በላብ ስለሚባላሹ ወዲያው ወዲያው መቀየር አለባቸው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም ሆነ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚመክሩት የተጠቀሱት ምልክቶች እስካልታዩ ድረስ ሁሉም ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ አያስፈልጋቸውም። ከዚያ ይልቅ ግን የበሽታው ስጋት ለማስወገድ ከሚያስሉ፣ ከሚያስነጥሱ ወይም ትኩሳት ካለባቸው ሰዎች ጋር የሚኖርን ንክኪ ማስወገድ፣ እጅን በሳሙናና በውሃ መታጠብ ካልሆንም ተህዋሲያንን በሚያስወዱ ማጽጃዎች እጅን ማጽዳት ከሁሉ በበለጠ ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም እጅን ሳይታጠቡ ዓይንን፣ አፍንጫንና አፍን አለመንካት እንዲሁም መጨባበጥን ማስወገድ የቫይረሱን መስፋፋት ለመግታት መወሰድ ካለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
news-46636926
https://www.bbc.com/amharic/news-46636926
የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት የቁንጅና ውድድር አሸናፊዋ በተፈጥሮ ፀጉሯ ልታጌጥ ይገባል ሲሉ ተቹ
የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የአፍሪካ ቆንጆ ተብላ የተሰየመችውን የዩጋንዳ ቁንጅና ተወዳዳሪ የህንድ ፀጉር ቀጥላለች በሚል ተቹ።
ኩዊን አበንካዮ ካሸነፈች በኋላም የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ፎቶዋን በትዊተር ገፃቸው ላይ አድርገው "የአፍሪካን ቁንጅና በተፈጥሯዊ መልኩ ልናሳይ ይገባል" ብለዋል። ሙሴቪኒ "የህንድ ፀጉር" ሲሉ ምን ለማለት ነው ተብለው ሲጠየቁም ቃል አቀባዩ ዶን ዋንያማ "ፎቶውን ተመልከቱትና ምን ዓይነት ፀጉር እንደሆነ ማየት ትችላላችሁ" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። •"ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ •የኤርትራው ፕሬዚዳንት የሞቃዲሾ ጉብኝት •በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ቃል አቀባዩ ጨምረውም "ተፈጥሯዊ ያልሆነ ዊግ ፀጉር ቀጥላለችና በተፈጥሮ ፀጉሯ ለምን አታጌጥም ነው ያሉት" ብለዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ አበንካዮ ምርጫዋ ሊከበር ይገባል በሚል የደገፏት ሲሆን፤ የህንድ ፀጉር የሚለው የፕሬዚዳንቱ አባባል ከፍተኛ ውርጅብኝን አስተናግዷል። በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንድትሰጥ ቢቢሲ ጠይቋት ነበር። ከፕሬዚዳንቱ ጋር በአንድ ጉዳይ እንደምትስማማ ገልፃ " የምዕራቡ ዓለም የሚያደርገውን ነገር በሙል ኮፒ ልናደርግ አይገባም " ብላለች። ነገር ግን ጨምራም " ለኔ ግን በጉዳዩ ላይ ያለኝ አስተያየት ግማሽ በግማሽ ነው። ስሜቴ እንደመራኝ ነው የማደርገው። በምንሰራው ስራም ሆነ ፀጉራችንን በምን መንገድ እንደምናስጌጥ የማንነታችን አካል መሆን የለበትም። እስከተመቸን ድረስ ማንኛውንም ነገር ልናደርግ ይገባል" ብላለች። በማሸነፏም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማትም ገልፃለች። የተወሰኑትም ጉዳዩን ወደ ትዊተር በመውሰድ በሴቶች ግላዊ ምርጫ ላይ ጣልቃ የሚገባ ነው ብለውታል። የሴቶችን አካላዊም ሆነ በምን መንገድ ራሳቸውን ሊያቀርቡ እንደሚገባ ትዕዛዝ ሊሰጥ አይገባምም ብለዋል። ምንም እንኳን ፕሬዚዳንቱን የደገፉ ቢኖሩም የፕሬዚዳንቱ ፀጉር አልባነትም ላይ አስተያየት የሰጡ አልታጡም። ምዕራባውያንን ማዕከል ያደረገ የቁንጅና እሳቤ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ጥቁር የቁንጅና ተወዳዳሪዎች ምዕራባውያንን ማዕከል ያደረገ የቁንጅና እሳቤን (ዩሮሴንትሪክ) በከፍተኛ ሁኔታ እየተቹት ይገኛሉ። የቆዳ ቀለማቸው ቀላ ያሉ ሴቶችና ፀጉራቸው ዘንፋላ (የተተኮሰ ፀጉር) እንደ ቆንጆ ውበት መለኪያ መታየቱ ስህተት ነው ብለዋል።
45813930
https://www.bbc.com/amharic/45813930
የሰራዊት አባላቱ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይት
በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ በተለያዩ ግዳጆች ላይ ተሰማርተው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት የልዩ ሃይል አባላት ተወያይተዋል።
የሰራዊት አባላቱ የሚያገኙት ዝቅተኛ ክፍያ ህይወታቸውን ለመምራት አዳጋች ስለሆነ በዚህ ረገድ የመከላለከያ ተቋማዊ አሰራር ሊፈተሽ እንደሚገባው አሳስበዋል። •የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ- ትህዴን ማን ነው? •ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ •የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ ከውይይቱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ እንደ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል መወያየት እንደፈለጉና የወደፊት ዕጣፈንታቸውንና በዘላቂነት መፈታት ስላለባቸውና ጉዳዮችም እንደተወያዩ ተናግረዋል። "በውይይታችን ያነሱት ነገር እኛ ለሀገራችን፣ ለባንዲራችን ዛሬም እንደ ትናትናው የገባነውን ቃልም ሆነ ሀገራችንን እንጠብቃለን። ኑሯችን ግን ጉዳት አለበት። የኢትዮጵያ ህዝብ በደላችንን አያውቅም። በየቦታው እየሞትን እየቆሰልን እንደ ጠላት ወታደር እንታያለን። ደሞዛችን አነስተኛ ነው። ህዝባችን ካልረዳን እንቸገራለን" እንዳሉ ገልፀዋል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሰሞኑን በተሰማሩባቸው አካባቢዎች በቡራዩ የአካባቢው ህዝብ በምግብ እንደረዳቸው ገልፀው፤ በሌሎች አካባቢዎች ተሰማርተው የነበሩት ግን ለሀያ ቀናት ያህል በቂ ምግብ እንዳላገኙ እንደነገሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ውይይቱ በአጠቃላይ ጠቃሚ እንደነበረም ተናግረዋል። የሰራዊት አባላቱ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ዘርፎች ላይ በቂ ክፍያ እንደሌለ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ዋናው አላማችን ወጪ ቆጥበን ወደ ልማታዊ ሀብት ማዞር ነው። እኛ ደመወዛችንን ከፍ አድርገን ከበላነው ልማት የሚባል ነገር የለም። ሁለት አማራጭ አለን። ያለንን ሀብት ከፍተኛ ደመወዝ እየበላን ልማታዊ ነገር ማቆም። በዘላቂነት የሚያድግ አገር አንፈጥርም። ትንሽ ተጎድተን ዋጋ ከፍለን የተሻለ አገር መፍጠር ይቻላል። የዚህ ችግር ዳፋ መከላከያንም ይመለከታል" ብለዋል። የሰራዊቱንም ሆነ የሌሎች ዘርፎች አባላት ክፍያ የሚሻሻልበት መንገድ ጥናት እንደሚደረግ የተናገሩ ሲሆን ዋናው ትኩረት ሀብት ሰብስቦ ልማት ላይ ማዋልና የህዝቡን ህይወት ማሻሻል እንደሆነም ተናግረዋል። በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ እውነተኛ እንዳልሆነ ተናግረዋል። "መሳሪያ ይዘዋል። አንድም ጥይት የተኮሰ ሰው የለም። ሰላማዊ ነበር። መከላከያ ማሻሻል የሚገባውን በዝርዝር ጠቃሚ መረጃዎች አጋርተውኛል። ዋና ፍላጎታቸው በኔ መደመጥ ነው" ብለዋል።
news-56816928
https://www.bbc.com/amharic/news-56816928
በኢትዮጵያ በሐሰት ተመስክሮባቸው 20 ዓመት የተፈረደባቸው ሴት ነጻ ሊወጡ ነው
በሰሜን ሸዋ ዞን የሙጃና ወደራ ወረዳ የእንጀራ ልጃቸውን ገድለዋል በሚል 20 ዓመት የተፈረደባቸው ሴት ነጻ ሊወጡ መሆኑን በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የማረሚያ ቤቶች መምሪያ ገለፀ።
የመምሪያው ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ ኮማንደር ደበበ መኩሪያ ለቢቢሲ እንደገለፁት ወ/ሮ አዛለች ቤታ የእንጀራ ልጃቸውን ገድለሻል በሚል የሀሰት ማስረጃ ቀርቦባቸው 20 ዓመት ተፈርዶባቸው ላለፉት 5 ዓመታት በእስር ላይ ነበሩ። ነገር ግን ተገድላለች የተባለችው ወጣት ሴት በሕይወት በመገኘቷ ከአምስት ዓመት በላይ በእስር የቆዩት ወ/ሮ አዛለች ከወንጀል ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል ብለዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በ2007 ዓ.ም በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሙጃና ወደራ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ አዛለች "በ2006 የእንጀራ ልጅሽን ገድለሻል" በማለት ነበር በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት። ኮማንደር ደበበ መኩሪያ አክለውም የሰሜን ሸዋ ዞን የማረሚያ ቤቶች መምሪያ ወ/ሮ አዛለች ቤታ ያለምንም ወንጀል እስር ላይ እንደቆዩ እና እንዲለቀቁ ለክልሉ የይቅርታ ቦርድ ማመልከቻ መጻፉን ገልፀዋል። ይሁን እንጂ ወ/ሮ አዛለች እንዲፈቱ ከክልሉ የይቅርታ ቦርድ የደብዳቤው ምላሽ እስካሁን አለመምጣቱ አስረድተዋል። የይቅርታ ቦርድ "ለእርሷ ብቻ መሰብሰብ አይችልም።" በማላቸውን የሚናገሩት ኮማንደሩ፣ አስፈላጊው ሰነድ ለመስከረም ዝግጁ የሚሆን ከሆነ እንጂ "አሁን ላይ የምንፈታው ነገር አይደለም" በማለት የይቅርታ ቦርድ ምላሽ እንደሰጣቸው ገልጸዋል። ያልተፈፀመ ወንጀል እና የሐሰት ምስክሮች ወ/ሮ አዛለች ቤታ ባለቤታቸው እና ከባለቤታቸው ሦስት ልጆች ጋር እየኖሩ ነበር። ነገር ግን ባለቤታቸው ከሞቱ በኋላ ከሶስት የእንጀራ ልጆቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት እየሻከረ መጣ። በ2006 ዓ.ም ግድያ ተፈጽሟል በተባለበት ቀንም ወ/ሮ አዛለች እና በእንጀራ ልጃቸው መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር። ከአለመግባባቱ በኋላ ልጅቷ ቤት ጥላ ወጣች። ወ/ሮ አዛለችም ልጅቷ መጥፋቷንና እንዲፈልጓት ለአጎቶቿ ቢነግሩም እነርሱ ግን አለመፈለጋቸውን ኮማንደር ደበበ ይናገራሉ። በኋላም የእንጀራ ልጇ ጠፍታለች ከተባለ ከአንድ ዓመት በኋላ በ2007 የወረዳው ፖሊስ ወ/ሮ አዛለች ቤታን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማድረግ ጀመረ። የነበረውን ሁኔታም ሲያስረዱ "ወ/ሮ አዛለች፣ የባለቤታቸውን ልጅ ገድላ ሽንት ቤት ውስጥ ጨምራለች፤ በሚል ተጠርጥረው ምርመራ ተካሄደባቸው" ይላሉ። በዚህም መሰረት ፖሊስ በወ/ሮ አዛለች ግቢ በሚገኘው መፀዳጃ ቤት ባደረገው አሰሳ ተገድላለች የተባለችው ወጣት የትምህርት ቤት ደንብ ልብስ እና የሰው ፀጉር ተገኝቷል። ወ/ሮ አዛለች በሰው ግድያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በሚውሉበት ጊዜ የሞጃ እና ወደራ ሕዝብ ሰልፍ በመውጣት 'እንዲገደሉ' ጠይቆ ነበር ሲሉም ሁኔታውን ያስታውሳሉ። "በቁጥጥር ስር ውላ ለምርመራ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በምትወሰድበት ወቅት ሕብረተሰቡ 'ትገደልልን፤ ይህች ልጇን የገደለች ኃጥያተኛ ናት፤ ልቀቋት እኛ እንገድላታለን' እያለ ነበር ይህ በሚዲያም ተላልፏል።" ነገር ግን ወ/ሮ አዛለች ድርጊቱን እንዳልፈፀሙ እያለቀሱ ይናገሩ አንደነበር ኮማንደር ደበበ ገልፀዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን ፍርድ ቤት በተደረገው የክርክር ሂደት ወ/ሮ አዛለች እንጀራ ልጃቸውን መግደላቸው ሰዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የዞኑ ፍርድ ቤትም የሰዎች እና የፖሊስ ማስረጃን ከመረመረ በኋላ ወ/ሮ አዛለች ግድያ ፈጽመዋል በማለት በዚያው በ2007 ዓ.ም የ20 ዓመታት እስር ፈርዶባቸዋል። 'የሞተችው ልጅ' በሕይወት ተገኘች ወ/ሮ አዛለች ከአምሰት ዓመት በላይ በእስር ከቆዩ በኋላ ከአንድ ወር በፊት የካቲት 2013 ዓ.ም በ2006 ወ/ሮ አዛለች ቤታ ተገድላለች የተባለችው ሴት በዘመዶቿ ቤት ታየች። በወቅቱ ይህች ከስድስት ዓመት በፊት ተገድላለች የተባለችው ሴት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ስትኖር ቆይታ መምጣቷ ተነግሯል። ይህንን መረጃ እንደሰሙ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የፍትህ ጽህፈት ቤት ደብዳቤ መጻፋቸውን የሚናገሩት ኮማንደር ደበበ መኩሪያ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ሞታለች የተባለችውን ወጣት በሕይወት መኖር የማረጋገጥ ስራ መሰራቱን ይናገራሉ። "ይህች ሴት በሕይወት መኖሯ የ19 ሰዎችን ቃል በመውሰድ እንዲሁም ቤተሰቦቿ ልጃችንን አግኝተናል በማለት አረጋግጠዋል።" የዞኑ አቃቤ ሕግ ሞታለች የተባለች ልጅ በሕይወት በመገኘቷ ያለ ጥፋታቸው የታሰሩት ወ/ሮ አዛለች ቤታ የእስረኞች ይቅርታ መመሪያ መሰረት በማድረግ እንድትፈታ ማመልከቻ ለማረሚያቤቱ መጻፋቸውን ኮማንደር ደበበ እናገራል። ሌላ ፈተና ኮማንደር ደበበ በሐሰት ማስረጃ በሰው ግድያ ተከስሰው ከአምስት ዓመታት በላይ በእስር ቤት ያሉት ወ/ሮ አዛለች በአሁኑ ወቅት ከወንጀሉ ነጻ መሆናቸው መታወቁ የተደበላለቀ ስሜት እንደፈጠረባቸው "አሁንም እያነባች ነው ያለችው" በማለት ይናገራሉ። የሰሜን ሸዋ ዞን የማረሚያ ቤቶች መምሪያ ወ/ሮ አዛለች ቤታ ያለምንም ወንጀል እስር ላይ እንደቆዩ እና እንዲለቀቁ ለክልሉ የይቅርታ ቦርድ ማመልከቻ መጻፉን ኮማንደር ደበበ ለቢቢሲ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ወ/ሮ አዛለች እንዲፈቱ ከክልሉ የይቅርታ ቦርድ የደብዳቤው ምላሽ እስካሁን አለመምጣቱ ገልፀዋል። በዚህ መካከል ፍትህ እየታዛባ መሆኑን የሚናገሩት ኮማንደር ደበበ "እርሷም ያለ ጥፋቷ እስር ላይ ነች። ጉዳዩ በጣም ነው የሚያሳዝነው" ብለዋል። በሐሰት ማስረጃ ተፈርዶባቸው እስር ቤት ያሉ ሰዎች ከሌሎች እስረኞች እኩል በይቅርታ ይወጣሉ ወይንስ ጥፋት እንደሌለባቸው በተረጋገጠበት ቅጽበት ይፈታሉ የሚለው በአዋጅ ላይ ምንም የተቀመጠ ነገር አለመኖሩን በመጥቀስም ይህም ችግር መሆኑን ገልፀዋል። የሌሎች አገራት ልምድ ምን ይመስላል? ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገራት ሰዎች በተሳሳተ ክስ ተከስሰው ተፈርዶባቸው ለረዥም ዓመታት በእስር ላይ ቆይተው መፈታታቸው ያልተለመደ ነገር አይደለም። በአሜሪካ እኤአ በ2019 በካሊፎርኒያ በሐሰት ክስ ለ38 ዓመት ታስሮ የተፈታው ሰው የ21 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተከፍሎታል። የ71 ዓመቱ አዛውንት ክሬግ ኮሊ በአሜሪካዋ የካሊፎርኒያ ግዛት በአውሮጳውያን አቆጣጠር በ1978 ዓ.ም የቀድሞ ጓደኛውንና ልጁን ገድሏል በሚል ነበር የተፈረደበት። በ2017 የዲኤን ኤ ምርመራ ከተደረገ ምርመራ ከእስር ተፈትቷል። በዚሁ በተመሳሳይ ወቅት በአውስትራሊያ ውስጥ አንድ ሰው የፖሊስ ኃላፊ ገድለሃል በሚል ለ19 ዓመት በእስር ከቆየ በኋላ የ7 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተከፍሎታል። ዴቪድ ኢስት ማን የተባሉት እኚህ የአውስትራሊያ ዜጋ እኤአ በ1995 ዓ.ም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር የሆኑት ኮሊን ዊንችስተር የተባሉትን ሰው በመግደል ተጠርጥረው ነበር የእድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው።
54091490
https://www.bbc.com/amharic/54091490
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጉዳት ለደረሰባቸው ከ12 ሺህ በላይ ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ አደረገች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተከሰተው አለመረጋጋት በአስር አገረ ስብከት ለተጎዱ ምዕመኖቿ የ40 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚል የተደራጀው ኮሚቴ አባል የሆኑት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ ለቢቢሲ እንዳሉት እርዳታው በአስሩ አገረ ስብከት የሚገኙ 2170 አባወራዎች፣ ወይንም 12 ሺህ 719 ቤተሰብ አባላትን ተጠቃሚ ያደርጋል። ለግለሰቦቹ በዚህ ወቅት ድጋፍ ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲገልፁም በዚህ ሳምነት አርብ ለሚለው በዓል እንዲሁም ተመልሰው ወደ ሥራ መግባት የሚችሉ ከሆነ እንዲገቡ በሚል በአስቸኳይ ወጪ ተደርጎ መሰጠቱን ተናግረዋል። እነዚህን የተለያየ ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ለመደገፍ በአጠቃላይ 44.5 ሚሊየን ብር ከቤተክርስቲያኒቱ ካዝና መውጣቱን እንዲሁም ከምዕመናን በልግስና መሰብሰቡን ገልፀዋል። በአሁኑ ሰዓት ከተሰጠው 40 ሚሊዮን ብር ቀሪው 4.5 ሚሊየን ብር በመረጃ ክፍተት ምክንያት የተዘለሉ ግለሰቦች ካሉ ለመጠባበቂያ መቀመጡን ተናግረዋል። እርዳታው ለግለሰቦቹ የተሰጠው እንደ የጉዳት መጠናቸው መሆኑን የተናገሩት ቀሲስ ሙሉቀን፣ ሞት የገጠማቸው፣ ቋሚ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው፣ በሕክምና ሊመለስ የሚችል ጉዳት የደረሰባቸው በሚል መለየታቸውን ተናግረዋል። አክለውም ድጋፉ በባለሙያ የተሰላው ቤተሰቡ እንዳጋጠመው ጉዳት መጠን መሆኑን በመግለጽ ሙሉ በሙሉ የወደመባቸው፣ በከፊል እንዲሁም መለስተኛ ጉዳት ንብረታቸው ላይ የደረሰው ተለይተው ድጋፉ ተሰልቷል ብለዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ዝርዝር መረጃ እና አድራሻ ተይዞ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመነጋገር የቁጠባ ሒሳብ በስማቸው በመክፈት የገንዘብ ድጋፉ በቀጥታ ገቢ መደረጉንም ተናግረዋል። እነዚህ አስር አገረ ስብከቶች የሚገኙት በምዕራብ እና ምሥራቅ አርሲ፣ በምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ምሥራቅ ሸዋ፣ ኢሉአባቦራ ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እንዲሁም ጅማ መሆኑን ገልፀዋል። ይህ ድጋፍ የመጀመሪያ ዙር መሆኑን የገለፁት ቀሲስ ሙሉቀን፤ በቀጣይ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው አገረ ስብከቶች ላይም ጥናት እየተሰራ በመሆኑ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት በጥናት ላይ ያሉ የአገረ ስብከቶች ከጉጂ እንዲሁም ከመተከል አገረ ስብከቶች ላይ የመጡ መረጃዎች መሆናቸውን ጨምረው አስረድተዋል። እነዚህን ሰዎች በዘላቂነት ለማቋቋም፣ የጠፋባቸውን ንብረት ለመመለስ፣ የወደመባቸውን ቤት በነበረበት ይዘት ለመመለስ የ3 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለማሰባሰብ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም አክለዋል። ቤተክርስቲያኒቱ በእምነታቸው ምክንያት ከጥቅምት እስከ ሰኔ ወር ድረስ በተለያዩ ስፍራዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለማቋቋም መወሰኗን ቀሲስ ሙሉቀን ጠቅሰዋል። በቀጣይም የእምነቱ ተከታይ በመሆናቸው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች፣ "ከየትኛውም አገረ ስብከት መረጃውና ማስረጃው እስከመጣ ድረስ ኮሚቴው የማቋቋም ሥራ" እንደሚሰራ ተናግረዋል።
news-44963100
https://www.bbc.com/amharic/news-44963100
ትራምፕ መማገጣቸውን ለመደበቅ ከጠበቃቸው ጋር ሲመካከሩ የሚያሳይ መረጃ ይፋ ወጣ
ሲኤንኤን ይፋ ያደረገው የድምጽ ቅጂ ዶናልድ ትራምፕ ከጠበቃቸው ማይክል ኮህን ጋር በመሆን ኬረን መክዱጋል የተባለች ሞዴል ከትራምፕ ጋር ስለነበራት ግንኙነት እንዳትናገር በገንዘብ ለመደለል ሲመካከሩ ያስደምጣል።
ከግራ ወደ ቀኝ ማይክል ኮሀን፣ ኬረን መክዱጋል እና ዶናልድ ትራምፕ ድምጹ የተቀዳው እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 ማለትም የአሜሪካ ምርጫ ሁለት ወራት ሲቀሩት ነበር። ትራምፕ ከሞዴሏ ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባለው ደግሞ በ2006 ነበር። የቀድሞ የትራምፕ ጠበቃ ማይክል ኮሀን ግግራቸውን በድብቅ መቅረጸ ድምጽ ቀድተውት ነበር። ፕሬዚዳንቱን በአሁን ወቅት እየተከራከሩላቸው ያሉ ጠበቃ ሩዲ ጊውሊያኒ በትዊተር ገጻቸው የቀድሞው የትራምፕ ጠበቃ በሚስጥር መያዝ ያለበትን ንግግር መቅዳታቸው ከጥብቅና ሙያዊ ስነ ምግባር ጋር ይጻረራል ሲሉ ተችተዋል። •"ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ •የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' •የኤምሬትስና የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ፖለቲካ? ድምጹ ወንጀል ስለመሰራቱ ማስረጃ አይሆንም ብለውም መደለያ ገንዘብ አለመከፈሉንም አስረግጠዋል። የጠበቃው ማይክል ኮሀን ጠበቃ ሌኒ ዴቪስ በምላሹ "ሪቻርድ ኒክሰን ትምህርት እንደወሰደው ሁሉ የድምጽ መረጃ ሀሰተኛ ሊሆን አይችልም" ሲሉ ትዊት አድርገዋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካው መሪማሪ ተቋም ኤፍቢአይ የማይክል ኮሀንን ቤት ሲበረብር ከተነኙ መረጃዎች አንዱ የድምጽ ቅጂው ነበር። ሲኤንኤን ካሰራጨው ቅጂ በተጨማሪ ሌሎችም መረጃዎች ተገኝተዋል። •'ሃሰተኛ ዜና '፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት? •በደሴ ከተማ የሸዋበር መስጂድ ላይ በደረሰ ጥቃት ሰዎች ተጎዱ በድምጽ ቅጂው ምን ይደመጣል? በድምጽ ቅጂው ሞዴሏ ኬረን መክዱጋል ናሽናል ኢንኳየር ለተባለ መጽሔት ታሪኳን ካካፈለች በኃላ ትራምፕ የታሪኳ ባለ መብት ለመሆን የሚያስችላቸው ገንዘብ ለመክፈል ከማይክል ኮሀን ጋር ሲመካከሩ ይደመጣል። በድምጽ ቅጂው ማይክል ኮሀን "ለወዳጃችን ዴቪድ ገንዘብ የማስተላልፍበት ተቋም መክፈት አለብኝ" ሲሉ ይሰማል። ዴቪድ ናሽናል ኢንኳየር የተባለ መጽሔት ፕሬዘዳንት ናቸው። ትራምፕ በምላሹ "ለዚህ መክፈል ያለብን ምን ያህል ነው? መቶ ሀምሳ ያህል?" ብለዋል። ከንግግራቸው በኃላ ለሞዴሏ ኬረን መክዱጋል 150,000 ዶላር ተከፍሏታል ተብሏል። በድምጽ ቅጂው ጥሬ ገንዘብ ይከፈል ወይስ በቼክ በሚል ሲወያዩም መስማት ይቻላል። ትራምፕ የቀድሞ ጠበቃቸው ማይክል ኮሀን መቼም እንደማይከዳቸው የሚጠቁም ትዊት ማስነበባቸው ይታወሳል። ሆኖም ማይክል ኮሀን እጁ ላይ ያሉትን መረጃዎች ለመገናኛ ብዙሀን ማቀበሉን ተያይዘውታል። ከትራምፕ ጋር ለገቡበት ጦርነት መከታ ያደረጉት ደግሞ ጠበቃቸው ሌኒ ዴቪስን ነው። የአሜሪካው ዲፓርትመንት ኦፍ ጀስቲስ እንደ ሞዴሏ ሁሉ መረጃ እንዳያወጡ በገንዘብ የተደለሉ ሴቶች ላይ ለመድረስ ምርመራ መጀመሩ ይታወቃል። ትራምፕና ሞዴሏ ኬረን ኬረን መክዱጋል ማናት? ሞዴሏ ኬረን መክዱጋል ከትራም ጋር የ10 ወር ግንኙነት ነበራት ተብሏል። በወቅቱ ከአሁኗ ባለቤታቸው ሜላንያ ትራምፕ ጋር ትዳር መስርተው ነበር። ናሽናል ኮንከረር የተባለው መጽሔት 150,000 ዶላር ከፍሏት ታሪኳን ለማካፈል ተስማምታ ነበር። በስምምነቱ መሰረት ከትራም ጋር ስለነበራት ግንኙነት በአደባባይ ማውራት አትችልም። ትራምፕ በበኩላቸው ከሞዷሏ ጋር ግንኙነት አልነበረኝም ብለዋል።
52147215
https://www.bbc.com/amharic/52147215
ኮሮናቫይረስ: ሐሰተኛ መረጃ እንዳይስፋፋ ምን ልናደርግ እንችላለን?
ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ሐሰተኛ መረጃዎች በይነ መረብን እያጥለቀለቁት ይገኛሉ። ባለሙያዎች ደግሞ ኅብረተሰቡ "መረጃ ማጥራትን" እንዲለማመድ ጥሪ አቅርበዋል። አሳሳች መረጃ እንዳይስፋፋ ምን ማድረግ ይችላሉ?
1. ቆም ብለው ያስቡ ቤተሰቦችዎን እና ጓደኞችዎን መርዳት ይፈልጋሉ። አዲስ ምክር ባገኙ ቁጥር በኢሜይል፣ በዋትስአፕ ፣ በፌስቡክ ወይም በትዊተር በፍጥነት ሊያካፍሏቸው ይችላሉ። እንደባለሙያዎች ከሆነ የተሳሳተ መረጃን ለማቆም ማድረግ የሚችሉት አንድ ቀላል ነገር ቆም ብሎ ማሰብ ነው። ስለመረጃው ጥርጣሬ ካለዎት ለአፍታ ቆም ብለው በደንብ ይመልከቱት። 2. ምንጭዎን ያረጋግጡ መረጃውን ከማስተላለፍዎት በፊት መረጃው ከየት እንደመጣ ይጠይቁ። ምንጩ "የጓደኛ ጓደኛ" ወይም "የአክስቴ ባልደረባ ጎረቤት" ከሆነ መረጃው ትልቅ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይገባል ማለት ነው። በቅርቡ ከአንድ "ሁለተኛ ዲግሪ ካለው አጎቴ" የሚል አንድ አሳሳች መረጃ በፍጥነት የተዛመተበትን መንገድ ለመመልከት ችለናል። በመረጃው ላይ ያሉት የተወሰኑት ጉዳዮች ትክክለኛ ነበሩ። ለምሳሌ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እጅ መታጠብን ያበረታታል።ሌሎቹ ነገሮች ግን ጎጂ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ያልተረጋገጡና በሽታውን ለመመርመር የሚረዱ ናቸው የተባሉ ዝርዝሮች ቀርበውበታል። "አስተማማኝ የመረጃ ምንጮች እንደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የዓለም ጤና ድርጅት ወይም የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ያሉ የሕዝብ ጤና ተቋማት ናቸው" ሲሉ መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገውና የመረጃዎችን ትክክለኛነት የሚያረጋግጠው 'ፉል ፋክት' የተባለው ድርጅት ምክትል አርታኢ ክሌይር ሚልን ያስረዳሉ። 3. ሐሰተኛ ሊሆን ይችላል? አቀራረቡ አሳሳች ሊሆን ይችላል። የቢቢሲ አማርኛ እና የመንግሥትን ጨምሮ ኦፊሴላዊ አካውንቶችን፣ ድረ ገጾች እና ባለሥልጣኖችን ገጽ ማስመሰል ይቻላል። ፎቶ በማንሳት መረጃው ከታመነ አካል የመጣ እንዲመስልም ሊደረግ ይችላል። የታወቁ እና የተረጋገጡ አካውንቶችና ድረ ገጾችን ይጎብኙ። መረጃውን በቀላሉ ማግኘት ካልቻሉ ምናልባት ሐሰተኛ ሊሆን ይችላል። ጽሑፉ፣ ቪዲዮው ወይም ገጹ አጠራጣሪ ምናልባትም ሐሰተኛ ይሆናል። ካፒታል ሌተርስ (Capital letters) እና ወጥያልሆኑ የፊደላት ቀርጾች (fonts) አጠቃቀም መረጃዎችን ትክክለኛነት በሚያረጋግጡ ባለሙያዎች መረጃው አሳሳች ሊሆን እንደሚችል እንደአመላካች ከሚጠቀሙባቸው ነጥቦች አንዱ መሆኑን የፉል ፋክት ምክትል አርታኢ ክሌይር ሚልን ይገልጻሉ። 4. አውነት ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደሉም? መረጃውን አያጋሩ እውነት "ሊሆን ይችላል" በሚል ብቻ መረጃዎችን አያስተላልፉ። በዚህ ምክንያት መልካም ከማድረግ ይልቅ ጉዳት እያደረሱ ይሆናል። ብዙ ጊዜ መረጃዎችን የምንለጥፈው እንደሐኪሞች ወይም የህክምና ባለሙያዎች ያሉ ባለሙያዎች ባሉባቸው ቦታ ነው። ይህ ጥሩ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ስለጥርጣሬዎ ግልፅ መሆንዎን ያረጋግጡ። ያጋሩት ፎቶ ወይም ጽሑፍ ከአውዱ ውጭ ሊወሰድ ስለሚችልም ይጠንቀቁ። 5. እያንዳንዱን እውነታ በተናጥል ይፈትሹ ዋትስአፕ ላይ እየተሰራጨ ያለ የድምፅ ማስታወሻ አለ። በማስታወሻው ውስጥ የምትናገረው ግለሰብ ሆስፒታል ውስጥ የሚሠራ "ጓደኛ ካለው ባልደረባ" ያገኘቻቸውን ምክሮች እየተረጎመች ስለመሆኑ ትናገራለች። ይህም በደርዘን በሚቆጠሩ ሰዎች አማካይነት ከዓለም ዙሪያ ወደ ቢቢሲ ተልኳል። ሆኖም ትክክለኛ እና ትክክል ያልሆኑ ምክሮች የተደባለቀቡት ነበር። በጣም ጠቃሚ የሆኑ ምክሮችን ዝርዝር በሚያገኙበት ወቅት በመሃል በሚያገኙት አንድ ትክክለኛ ምክር (ለምሳሌ እጅ መታጠብ ጠቃሚ ስለመሆኑ በመገለጹ) ብቻ ሁሉንም ትክክል ነው ብሎ ማመን ቀላል ነው። ግን ሁሌም እንደዚያ አይደለም፤ ይጠንቀቁ! 6. ከስሜታዊ መረጃዎች ይጠንቀቁ እንደእውነቱ ከሆነ ፍርሃት፣ ቁጣ፣ ጭንቀት ወይም ደስታ የሚፈጥሩብን ስሜታዊ ነገሮች ናቸው በብዛት የሚሰራጩት። "ፍርሃት ሐሰተኛ መረጃዎች በበፍጥነት እንዲዛመቱ ከሚያደርጉ ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ ነው" ሲሉ ጋዜጠኞች በበይነ መረብ ሐሰተኛ መረጃዎችን እንዲከላከሉ የሚያግዘው 'ፈርስት ድራፍት' የተባለው ድርጅት ባልደረባ የሆኑት ክሌይር ዋርድል ይገልጻሉ። ድርጊትን የሚያበረታቱ አስቸኳይ ጥሪዎች ጭንቀትን ለማነቃቃት የተቀየሱ በመሆናቸው ይጠንቀቁ። "ሰዎች የሚወዷቸው ሰዎች ደኅንነት የተጠበቀ እንዲሆን ለመርዳት ይፈልጋሉ" ስለዚህ 'ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዱ ምክሮች' ወይም 'ይህን የጤና ተጨማሪ ምግብ ይውሰዱ' የሚሉ መረጃዎችን ሲመለከቱ፤ "የሚወዷቸውን ሰዎች ለመርዳት የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ይፈልጋሉ "ትላለች ክሌር። 7. ስለአንድ ጉዳይ ያለንን ወገንተኝነት አንዘንጋ የሆነ ነገር የሚያጋሩት እውነት እንደሆነ ስላወቁ ነው ወይስ በጉዳዩ ስለተስማሙ? በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ዙሪያ ጥናት የሚሰራ ማዕከል የምርምር ዳይሬክተር የሆኑት ካርል ሚለር እንደሚሉት በአብዛኛውን ጊዜ የምናጋራቸው መረጃዎች ያለንን እምነታችንን የሚያጠናክሩትን ነው። "በንዴት ጭንቅላታችንን በምንወዘውዝበት ወቅት ነው በጣም ተጋላጭ የምንሆነው። በዚህ ወቅት ነው ከምንም ነገር በላይ በይነመረብ ላይ የምንሠራውን በሙሉ ማዘግየት ያለብን" ብለዋል።