id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
56547520
https://www.bbc.com/amharic/56547520
ማኅበራዊ ሚዲያ፡ የቲክቶክ እና የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች እየገጠማቸው ያለ ጫና
ቲክቶክ እና ኢንስታግራም ላይ የሰውነት አካልን እንዴት መለወጥ እንደሚቻል የሚያስተዋውቁ መተግበሪያዎች ይቀርባሉ።
የማኅበራዊ ሚዲያዎቹ ተጠቃሚዎች የሆኑና የአመጋገብ ሥርዓት መዛባት ያለባቸው ሰዎች በእነዚህ ማስታወቂያዎች ጫና ሥር እንደወደቁ የመብት ተሟጋቾች እገለጹ ነው። ወገብን እንዴት ማቅጠን እንደሚቻል፣ በምን መንገድ ጡንቻ ማውጣት እንደሚቻልና ሌላም ሰውነት ላይ ስለሚደረግ ለውጥ መተግበሪያዎቹ ይገልጻሉ። እነዚህን መተግበሪያዎች [አፕ] የሚያስተዋውቁ ገጾች ደግሞ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተስፋፍተዋል። እነዚህ መተግበሪያዎች አፕል እና አንድሮይድ ላይም አሉ። ተጠቃሚዎች በፎቶ ወይም በቪድዮ የሚታይ ሰውነታቸው ላይ የፈለጉትን አይነት ለውጥ እንዲያደርጉ እንደሚችሉ የሚገልጹ ናቸው። ይህም ቆዳን ማለስለስ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ ጡንቻ ማሳደግን ያካትታል። የአመጋገብ ሥርዓት መዛባትን በተመለከተ ንቅናቄ የሚያደርጉ ድርጅቶች፤ ማኅበራዊ ሚዲያዎቹ እየተፈጠረ ያለውን ጫና ከግምት እንዲያስገቡ ጠይቀዋል። የቴክኖሎጂ ተቋሞቹ እንደሚሉት፤ እነዚህ መተግበሪያዎች የማኅበራዊ ሚዲያዎቹን የማስታወቂያ ደንብ አልጣሱም። ነገር ግን ቲክቶክ በበኩሉ የማስታወቂያ ፖሊሲውን ለመከለስ ፍቃደኛ ሆኗል። "ሰዎች ስለ ሰውነታቸው በጎ አመለካከት እንዲኖራቸው ከማበረታታት ወደ ኋላ አንልም" ብሏል ቲክቶክ። ምግብ ስለመቀነስ እና ክብደትን ለመቆጣጠር ስለሚወሰዱ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች የሚያስተዋውቁ ጽሑፎችን ባለፈው ዓመት ማገዱ ይታወሳል። "ጤናማ ያልሆነና የተዛባ መልዕክት ማስተላለፍ አይገባም" የአመጋግብ ሥርዓት መዛባት ተሟጋቿ ሆፕ ቪርጎ "ጤናማ ያልሆነና የተዛባ መልዕክት ማስተላለፍ አይገባም" ትላለች። ማኅበራዊ ሚዲያዎች ተጠያቂ መደረግ እንዳለባቸው ትናገራለች። ባለፈው ዓመት የአመጋገብ ሥርዓት መዛባት ያለባቸው ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ትናገራለች። የአመጋግብ ሥርዓት መዛባት ከሚከሰትባቸው ምክንያቶች አንዱ ለሰውነት ቀና አመለካከት ማጣት ነው። ቲክቶክ እና ኢንስታግራም ላይ ሰውነትን ስለመለወጥ የሚያሳዩ መተግበሪያዎች መተዋወቃቸው ደግሞ ችግሩን እንዳያባብሰው ተሰግቷል። ሲድ የተባለው የአመጋግብ ሥርዓት መዛባት ላይ የሚሠራው ድርጅት ባወጣው አሀዝ መሠረት፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ይህ መዛባት የገጠማቸው ከ10 እስከ 19 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ቁጥር በ68 በመቶ ጨምሯል። የጤና ጉዳዮች ጋዜጠኛ ሆነችው ዴኒ ሜሲር ከዚህ ቀደም የአመጋገብ ሥርዓት መዛባት ገጥሟት ነበር። ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ላይ ሰውነትን በመልካም መንገድ ማየትን የሚያበረታቱ መልዕክቶች ታጋራለች። "እነዚህ መተግበሪያዎች ችግሩን እንደሚያባብሱ በራሴ አይቼዋለሁ። ከተፈጥሯዊ ሰውነቴ የቀጠነ ምስል ያሳያሉ። የሚያሳዩት ነገር በተፈጥሮ ሊፈጠር የማይችል ነው" ትላለች። መተግበሪያዎቹ ያሳደሩት ጫና ከፍተኛ እንደሆነ ገልጻ "ተጽዕኖውን ገና ለዓመታት እናየዋለን" በማለት ተናግራለች። በቀላሉ ተጽዕኖ ሥር ሊወድቁ የሚችሉ ታዳጊዎች በዋነኛነት ተጎጂ እንደሆኑም አያይዛ አስረድታለች። "ታዳጊዎች ነገሩን ለማገናዘብ እድሜያቸው ገና ነው። የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ስለሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች ለሕፃናት ማስታወቂያ እንደማይሠራው ሁሉ እነዚህ መተግበሪያዎችም መታገድ አለባቸው" ስትልም አስተያቷን ሰጥታለች። ኃላፊነት መውሰድ የሲድ ኃላፊ ጀማ ኦተን በወረርሽኙ ወቅት ብዙዎች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያሳልፉት ጊዜ መጨመሩን ትናገራለች። ሰዎች ትክክለኛ ገጽታቸውን ለውጠው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መቅረብ የሚችሉበት መተግበሪያ መፈጠሩ በጊዜ ሂደት ሥነ ልቦናዊ ቀውስ እንደሚያስከትልም ታስረዳለች። በተለይም ዓለም ወደ መደበኛው ሕይወት ሲመለስ እንደ አሁኑ ከስክሪን ጀርባ መደበቅ ስለማይቻል ነገሮች ይባባሳሉ። ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሰውነት ላይ ስለሚደረግ ለውጥ የሚያስተዋውቁ መተግበሪያዎችን በማገድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ታሳስባለች። ቢት የተባለው የአመጋገብ ሥርዓት መዛባት ላይ የሚሠራው ተቋም የውጭ ጉዳዮች ዳይሬክተር ቶም ክዊን "መተግበሪያዎቹን የሚሠሩ ሰዎች ምን ያህል ጎጂ ነገር እያመረቱ እንደሆነ እንዲያውቁት እንፈልጋለን" ይላል።
news-51346277
https://www.bbc.com/amharic/news-51346277
ከቻይና ውጪ የመጀመሪያው ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ሞተ
ኮሮና ቫይረስ የዓለም ስጋት መሆኑ ቀጥሎ ፊሊፒንስ ውስጥ አንድ ግለሰብ በቫይረሱ ህይወቱ ማለፏ ተረጋግጧል። ከቻይና ውጪ በቫይረሱ ሰው ሲሞት ይህ የመጀመሪያው ነው።
የ 44 ዓመቱ ቻይናዊ ግለሰብ በሁቤ ግዛት በምትገኘው ዉሃን ከተባለችው ከተማ የመጣ ሲሆን ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘውም በዚችው ከተማ ነበር። የዓለምአቀፉ ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው ግለሰቡ ፊሊፒንስ ከመድረሱ በፊት በቫይረሱ ተይዞ ነበር። • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? • ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ከ 300 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን አብዛኛዎቹ ደግሞ ከሁቤ ግዛት ናቸው። በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 14 ሺ በላይ እንደደረሰም ታውቋል። አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎች በርካታ ሀገራት ከቻይና የሚመጡ በረራዎችን አግደዋል። ከቻይና ተጉዞ ፊሊፒንስ ውስጥ ህይወቱ ያለፈችው ግለሰብ ከእሱ በተጨማሪ አብራው የነበረችው የ 38 ዓመቷ ቻይናዊ ባለቤቱ በቫይረሱ እንደተያዘች ማረጋገጣቸውን የሀገሪቱ የጤና ኃላፊዎች አስታውቀዋል። በፊሊፒንስ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ የሆኑት ራቢንድራ አቤያሲንግ ዜጎች እንዲረጋጉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። '' ከቻይና ውጪ በቫይረሱ ሰው ሲሞት ይህ የመጀመሪያው ነው። መርሳት የሌለብን ግን ግለሰቡ በሽታውን ከቻይና ይዞት መምጣቱን ነው'' ብለዋል። ሁኔታው በቻይና ምን ይመስላል? የቻይና ባለስልጣናት እንደገለጹት ትናንት (ቅዳሜ) ብቻ በሁቤ ግዛት 45 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። ይህም ቁጥር የሟቾችንም ቁጥር ወደ 304 ከፍ አድርጎታል። በተጨማሪ 2590 አዲስ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በአጠቃላይም ቻይና ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 14 ሺ 380 ደርሷል። ምንም እንኳን የቻይና ባለስልጣናት ይህን ይበሉ እንጂ ቁጥሩ ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችል በርካቶች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። በእነሱ ግምት መሰረትም ቫይረሱ መጀመሪያ በተገኘባት ዉሃን ከተማ ብቻ ከ75 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሳይያዙ አልቀረም። ከዉሃን ከተማ በስተምስራቅ የምትገኘውና ስድስት ሚሊየን ሰዎች የሚኖሩባት ሁዋንግጋንግ ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው በከተማዋ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በመጪዎቹ ቀናት ሊጨምር እንደሚችል ገልጸዋል። አክለውም ከዉሃን የሚገቡ መንገደኞች ላይ እገዳ ከመጣሉ በፊት እንኳን እስክ 700 ሺ የሚደርሱ ሰዎች ከዉሃን ወደ ሁዋንግጋንግ ገብተዋል ብለዋል። ኮሮና ቫይረስ ምንድነው? የቻይና ባለስልጣናት እንዳረጋገጡት በአገራቸው የተከሰተው በሽታ መንስኤው ኮሮና በሚባል ቫይረስ ምክንያት ነው። ቀደም ሲል ሰዎችን የሚያጠቁ ከዚህ ቫይረስ ጋር ዝምድና ያላቸውና የሚመሳሰሉ የታወቁ ስድስት አይነት የቫይረሱ ቤተሰቦች አሉ፤ አሁን የተገኘው አዲሱ ሰባተኛ እንደሆነ ተነግሯል። • አንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ ኬንያ ውስጥ ተገኘ • በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በአዲስ አበባ ተገኙ በሽታው ሲጀምር በትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ተከትሎት ይከሰታል፤ከዚያም ከሳምንት በኋላ የትንፋሽ ማጠርን በማስከተል አንዳንድ ህሙማንን የሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያስፈልጋቸው ሊያደርግ ይችላል። በአራት ሰዎች ላይ ከሚከሰተው ይህ በሽታ አንዱ እጅግ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ። በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ማስነጠስና የአፍንጫ ፈሳሽ ላይታይበት ይችላል። የኮሮና ቫይረስ ቀለል ካለ የጉንፋን ምልክቶች አንስቶ እየከፋ ሲሄድ እስከሞት ሊያደርስ ይችላል። ከሰሞኑም የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ የወቅቱ አሳሳቢ የምድራችን የጤና ስጋት ነው ሲል አውጇል። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክትር ዶክትር ቴድሮስ አድሃኖም ይፋ እንዳደረጉት ለዚህ ውሳኔ ዋነኛው ምክንያት "በቻይና የተከሰተው ነገር ሳይሆን በሌሎች አገሮች እየሆነ ያለው ነው" ብለዋል። የዓለም የጤና ድርጅት የበሽታ ወረርሽኝ ተከስቶ ከዚህ አይነት ውሳኔ ላይ ሲደርስ ይህ ስድስተኛው ሲሆን ከዚህ ቀደም ኤችዋን ኤን ዋን የተባለው ኢንፍሉዌንዛ፣ ኢቦላ፣ ፖሊዮ፣ ዚካና በድጋሚ የተከሰተው ኢቦላ ምክንያት ነበሩ። በሽታው የተያዙ ሰዎችን ለሞት እስኪያደርሳቸው የተወሰነ ጊዜን ስለሚወስድ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች መካከል የተወሰኑት እስካሁንም ሊሞቱ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል። በተጨማሪም ምን ያህል እስካሁን ያልተመዘገቡ በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ አስቸጋሪ በመሆኑ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።
news-51665122
https://www.bbc.com/amharic/news-51665122
አሜሪካ ከህዳሴ ግድብ አደራዳሪነት እንድትወጣ የሚጠይቀው የዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ
ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙርያ የሚያደርጉትን ድርድር የአሜሪካ መንግሥት ቀደሞ በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት መግባቱን በመቃወም በአሜሪካ፣ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ የሰልፉ አስተባባሪ እና የዲሲ ግብረ ኃይል ተወካይ አቶ ጣሰው መላከሕይወት ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ዋነኛ ጥያቄያቸው አሜሪካ ከአደራዳሪነት እንድትወጣ ነው። አሜሪካ እንዲሁም የዓለም ባንክ ከአደራዳሪነት ወደ ታዛቢነት እንዲመለሱ እንደሚፈልጉም አክለዋል። "ሰልፉን የጠራነው የአሜሪካ መንግሥት ቀደም ሲል በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት ለመግባት ኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ተጽዕኖ እየፈጠረ ስለሆነ፤ ያንን ተጽዕኖ ከኢትዮጵያ እንዲያነሳ ለመጠየቅ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • ትራምፕ ህዳሴ ግድብ ሲያልቅ እመርቃለሁ ማለታቸው ተሰማ • ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ላይ በቅርቡ ስምምነት እንደሚደረስ ተናገሩ • ኢትዮጵያ በዋሽንግተኑ የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ አሳወቀች በተጽዕኖ የሚመጣ ስምምነትን እንደማይቀበሉ ለማሳወቅና የኢትዮጵያ መንግሥትም የበርካቶች ህልውና የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይን በተመለከተ በተጽዕኖ ስምምነት እንዳይፈርም ለመጠየቅ ሰልፉ እንዳስፈለገም አብራርተዋል። አቶ ጣሰውን ያነጋገርናቸው ሰልፉ መካሄድ በጀመረበት ሰዓት ሲሆን፤ ወደ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ እንደተገኙ ለቢቢሲ ገልጸው እየጨመረም ይመጣል ብለዋል። ሰልፈኞቹ ዋነኛ ጥያቄያቸው አሜሪካ ከአደራዳሪነት እንድትወጣ መሆኑን ገልጸዋል "አገር ውስጥ ባለው ፖለቲካ የተለያየ አቋም ቢኖረንም በአገር ህልውና ላይ በተመሰረተው በአባይ ጉዳይ በጋራ እንደምንቆም፣ በጋራ ድምጻችንን እንደምናሰማ የሚገልጹ መፈክሮች አሉን" ሲሉ አስተባባሪው ተናግረዋል። መንግሥት በግድቡ ጉዳይ ከማህበረሰቡ ጋር እንዲወያይና ያሚካሄደውን ነገር ለሕዝብ እንዲያሳውቅ የሚያሳስቡ መፈክሮች የሰላማዊ ሰልፉ አካል እንደሆኑም አቶ ጣሰው አክለዋል። አሜሪካንም ትሁን ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዳያሳድሩ ለመጠየቅ ከሰልፍ ባሻገር በየአካባቢያቸው ያሉ የሕዝብ ተወካዮችንና የመንግሥት ተቋሞችን የመድረስ እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል። ሰልፉን ያስተባበሩት ዲሲ ግብረ ኃይል፣ መደመር በተግባር፣ ኢትዮጵያን-አሜሪካን ሲቪል ካውንስል የተባሉ ስብስቦች እንዲሁም የመብት ተሟጋቾችም ጭምር ናቸው። በየአካባቢያቸው ያሉ የሕዝብ ተወካዮችንና የመንግሥት ተቋሞችን የመድረስ እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል ኢትዮጵያ በዋሽንግተን የመጨረሻ ቀጠሮ ተይዞለት በነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀጣይ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ ለአሜሪካ ማሳወቋ ይታወሳል።
47980286
https://www.bbc.com/amharic/47980286
የካቢኔው ሽግሽግ ምን ያመላክታል?
በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በካቢኔያቸው ላይ ያደረጉትን ሹም ሽር ፓርላማው አፅድቋል።
በዚህም መሰረት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ ኢንጂነር አይሻ መሀመድን በመተካት የመከላከያ ሚኒስትር፣ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)ን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። .“ኢትዮጵያ አዲስ የጥላቻ ንግግር ህግ አያስፈልጋትም” አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ ከመከላከያ ሚኒስትርነት የተነሱት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ፣ አቶ ጃንጥራር ዐብይን ተክተው በቀድሞው ቦታቸው ማለትም በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትርነት ተመድበዋል። ምክር ቤቱም ሹመታቸውን በአንድ ተቃውሞ፣ በአምስት ድምፀ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል። ከዚህም በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአቶ ለማ መገርሳ ምትክ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ የዛሬውን ጨምሮ ሦስተኛ ሹም ሽር ወይም የካቢኔ ሽግሽግ አድርገዋል። የዛሬው ሹም ሽር ይፋ ከተደረገ በኋላ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል አዲሶቹ ተሿሚዎች በተሰጣቸው ቦታ በአግባቡ ለማገልገል ሙያዊ ብቃት አላቸው? ከሹመታቸው ጀርባ ያለው ፖለቲካዊ አንድምታስ ምንድን ነው? የሚሉት ይገኙበታል። •ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ? በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግና ፌደራሊዝም መምህር የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ በአንድ ዓመት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የካቢኔ ሽግሽግ መደረጉ ስለሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ የሚጠቁመው አለ ይላሉ። "ፖለቲካዊ ትርጉሙ አለመረጋጋት መኖሩን የሚያሳይ ነው። ኢህአዴግ ግንባር እንዲሁም የተለያዩ የብሔር ተኮር ፖለቲካ ድርጅት ስብስብ በመሆኑ የነሱን ይሁንታ የማግኘት ነገር በጣም ወሳኝ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻቸውን የሚወስኑት ወይም ደግሞ ለሳቸው የሚረዷቸው ብለው የሚያስቧቸውን ሰዎች በራሳቸው መንገድ መሾም የማይችሉበት ሁኔታ ነው ያለው። ወጣ ገባነቱ እየታየ ያለው በዚህ ምክንያት ነው" ይላሉ። በመቐለ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር መኮንን ፍስሐ፣ የአዲሶቹ ሚንስትሮች ሹመት ከሙያዊ ብቃት ይልቅ ፖለቲካዊ አንድምታው ያመዝናል ይላሉ። ረዳት ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታ ትልቅ እንዲሁም የኢኮኖሚና የፖለቲካ ዲፕሎማሲ እውቀት የሚያስፈልገው እንዲሁም የሀገር ደህንነትንም ጥያቄ የያዘ ቦታ ነው። የአሁኑን ተሿሚ በማየም "ለቦታው ይመጥናሉ ብዬ አላስብም። በአቅም ሳይሆን በፖለቲካዊ ኃይል አሰላለፍ ነው" ይላሉ። በተቃራኒው የመከላከያ ሚኒስትሩ የኤታማዦር ሹም ስላለው፤ የሚመራው ያው አካል በመሆኑ እንደ ትልቅ ቦታ ባይቆጥሩትም "በኢትዮጵያ የማይናቅ ቦታ ነው" ይላሉ። ዶ/ር ሲሳይና ረዳት ፕሮፌሰር መኮንን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስትሯ ኢ/ር አይሻ በሙያቸው ስለመሾማቸው ይስማማሉ። •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ አቶ ገዱ በውጪ ጉዳይ እንዲሁም በዲፕሎማሲ ዘርፍ ልምድ እንደሌላቸውም ይናገራሉ። በመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ለማ ጉዳይ ዶ/ር ሲሳይ ከረዳት ፕሮፌሰር መኮንን የተለየ ሀሳብ አላቸው። "ቀደም ሲል በፀጥታ ቦታዎች ላይ በኃላፊነት እንዲሁም በባለሙያነት እንደመሥራታቸውና የቆዩ እንደመሆናቸው መጠን የመከላከያ ሚኒስትሩን በብቃት ይይዛሉ ብዬ አስባለሁ" ብለዋል። በሚንስትሮች ሹም ሹር ወቅት በተደጋጋሚ የሚሰነዘረው ትችት አንድ ሚንስትር የተሾመበትን ዘርፍ አውቆና ተደርቶ መሥራት ሳይጀምር ወደሌላ መሥሪያ ቤት ሲዘዋወር በሥራው ላይ ተጽዕኖ የማሳደሩ ነገር ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚደረገው ሽግሽግ ዛሬ ከሕዝብ እንደራሴዎች ጥያቄም ተነስቶበታል። •ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ "ቢያንስ ቢያንስ አንድ ሚኒስትር አንድ ተርም መቆየት አለበት። ሹመቱ ጎርፍ ሆነ" አንድ የፓርላማ አባል የሰጡት አስተያየት ነበር። ምሁራኑም ስለሽግሽጉ ጉዳይ አስተያየታቸውን ሰጥተውናል። ዶ/ር ሲሳይ እንደሚናገሩት አንድ ተሿሚ ሥራውን ለመምራት ተዘጋጅቶ ሳለ፣ ከተሰጠው ቦታ ተነስቶ ወደ ሌላ ቢሸጋሸግ እንደገና አዲሱን ሹመት ለመልመድ ጊዜ ያስፈልገዋል። በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚደረግ ሽግሽግ መቼ እነሳ ይሆን? የሚል ጥያቄ በማጫር አለመረጋጋት ይፈጥራልም ብለዋል። ረዳት ፕሮፌሰር መኮንን አመራሮች ሳይገመገሙና የተወሰነ ጊዜ ሳይቆዩ በተደጋጋሚ እንዲለዋወጡ መደረጋቸው "በአገሪቱ ትልቅ አለመረጋጋት እንዳለ ያሳያል" ይላሉ። ሀሳባቸውን የሚጋሩት ዶ/ር ሲሳይም በአንድ ዓመት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የካቢኔ ሽግሽግ መደረጉ "አለመረጋጋት መኖሩን ያሳያል" ይላሉ።
news-50633123
https://www.bbc.com/amharic/news-50633123
የወላይታ ዞን ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር በምን ተስማሙ?
የወላይታ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከወላይታ ሕዝብ ተወካዮች ጋር ትናንት ሕዳር 21/2012 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
ከውይይቱ በኋላ ያነጋገርናቸው የወላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር የወጣቶች ክንፍ አመራር አቶ አሸናፊ ከበደ ፤ በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ካቀኑት አባላት መካከል ይገኙበታል። • የወላይታ ዞን ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ሊወያዩ ነው • የሲዳማ ሕዝበ-ውሳኔ፡ አዲስ ክልል፤ አዲስ ፈተና? አቶ አሸናፊ እንደገለፁልን ውይይቱ በአጠቃላይ የወላይታን ሕዝብ የክልል እንሁን ጥያቄን የተመለከተ ነበር። ውይይቱ በዋናነት ከዚህ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወላይታ ሶዶ በሔዱበት ወቅት "ተወያዩበት፤ ምከሩበት" ባሉት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በዚሁ መሠረት ውይይት ያደረጉበትን ሃሳብ ይዘው ወደ ውይይት መቅረባቸውን አቶ አሸናፊ ያስረዳሉ። ከዚህ ቀደም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ያደረጉትን ውይይት የሚያስታውሱት አቶ አሸናፊ፤ በወቅቱ የነበሩት አጀንዳዎች ሦስት እንደነበሩ ያወሳሉ። "የወላይታ ሕዝብ ብቻውን ክልል መሆን ነው ወይ?፣ ሌሎችን ይዞ ከአጎራባች ዞኖች ጋር ክልል መሆን ነው ወይ? አጠቃላይ ሌሎች 55ቱን ይዞ ሠፊ ሕዝብና መሬት፣ ሰፊ የተማረ ሰው ያለበት በመሆኑ አንደ ዋና መቀመጫ እንዲያገለግል በሚል ዙሪያ ነበር የተወያየነው" ይላሉ። በእነዚህ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ካደረጉ በኋላ አቋማቸውን ማስቀመጣቸውን ይገልፃሉ። • ሲዳማ: 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል በመሆኑም ክልል የመሆንን ጥያቄ የወላይታ ሕዝብ ብቻውን የሚወስነው ባለመሆኑ፤ ተጨባጭነቱም ሊረጋገጥ ስለማይችል በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር እንደማይችል እንዲሁም አጎራባች ያሉ ዞኖች ጋር አንድ ክልል መሆንንም አንደ አማራጭ የወላይታ ሕዝብ ተወያይቶበት፤ ሌሎች ከመጡ ማቀፍ እንደሚችል ከዚያ ውጭ ግን በሌሎች እጣ ፈንታና መብት ውስጥ ገብቶ መወሰን የወላይታ ሕዝብ ሥልጣን አለመሆኑን ተነጋግረውበታል። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ውይይት መነሻነት ወላይታ ራሱን ችሎ የወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፤ ወላይታ ሶዶን ደግሞ ማዕከል አድርጎ የራሱን ክልል እንዲመሠርት የሁሉም ሕዝብ ድምፅ በመሆኑና ሕገ መንግሥታዊ መብት ስለሆነ ሌሎች አማራጮች እንዳማይሠሩና እንደማያዋጡ ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን ያስታውሳሉ። የወላይታ ሕዝብ ተወካዮች ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባደረጉት ውይይት የደረሱባቸውን ሃሳቦች አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጥያቄው ሕገ መንግሥታዊ ከሆነ ጥያቄውን እርሳቸው እንደማይመልሱት በመግለፅ፤ በሕጉ መሠረት እንዲሄድ ከምርጫ ቦርድ ጋር እንደሚነጋገሩ እዚያው ምላሽ በመስጠት ለቀሪ ጉዳዮች በተወካዮች በኩል ሰፋ ያለ ምላሽ እንደሚሰጡ እንደገለፁላቸው አቶ አሸናፊ ነግረውናል። "የወላይታ ሕዝብ ፍላጎትና ጥያቄ ራሱን በክልል አደራጅቶ መምራት መሆኑን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀን ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሌሎች አማራጮችን አይታችኋል ወይ ተማክራችኋል ወይ?" የሚል ጥያቄ አቅረበውላቸው እንደነበር ይጠቅሳሉ። ይሁን እንጅ የቀረቡት አማራጮች ሁሉ የሕዝብ ጥያቄ ባለመሆናቸው፤ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄም ባለመሆናቸው በሕገ መንግሥቱ መሠረት የወላይታ ሕዝብ የሚጠይቀው የራሱን በሕገ መንግሥት የተቀመጠውን መብት እንጅ የሌሎችን እጣ ፈንታ በሚወስን መልኩ መጠየቅ አይችልም በሚል ውሳኔ ላይ የተደረሰበትን የሕዝብ አቋም አንፀባርቀው መውጣታቸውን ይናገራሉ። ወላይታ ክልል እሆንበታለሁ ያለውን ቀነ ገደብም ታህሳስ 10/2012 ዓ.ም አድርጎ አስቀምጧል። ቀነ ገደብ ማስቀመጡ ምን ያህል ያስኬዳል? ያልናቸው ተወካዩ፤ "በሕገ መንግስቱ መሠረት አንቀፅ 47/42 በተቀመጠውና በሌሎች አንቀፆች የፌደሬሽን ምክር ቤት፣ የምርጫ ቦርድ በአንድ ዓመት ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ ያደራጃል ይላል" ሲሉ አንቀፅ ይመዛሉ። በመሆኑም ሕዝበ ውሳኔውን እንዲያደራጁ ታህሳስ 10 አንድ ዓመት ይሞላል፤ ከዚህ በኋላ ጥያቄው መመለስ ካልተቻለ ሕዝቡ ቀኑን ጠብቆ የራሱን ሉዓላዊ ሥልጣን ይጠቀማል ብለዋል። ይሁን እንጅ በሲዳማ የተፈጠረውን ስህተት ለመድገም እንዳማይፈለግ ገልፀዋል። "ሰላማዊ በሆኑ መንገዶች በሙሉ ታህሳስ 10 ሕዝበ ውሳኔው የሚካሄድበት ቀን ካልታወቀ፤ የራሱን ውሳኔ አሳውቆ አቋሙን ገልፆ ፤ቀጣይ ሰላማዊ ትግሎች በሌሎች መንገዶች ይሄዳሉ" ብለዋል። በዚህ ሒደት የሚያጋጥሙ ችግሮች ካሉም የክልሉ መንግሥትና የፌደራል መንግሥት ኃላፊነቱን መውሰድ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
news-46028024
https://www.bbc.com/amharic/news-46028024
በእንግሊዝና በጋምቢያ የሚገኙ ተመራማሪዎች ውሾች ወባን በማሽተት እንደሚለዩ አስታወቁ
ውሾች በአፍንጫቸው የማሽተት ችሎታ ብቻ የወባ በሽታን መለየት እንደሚችሉ በእንግሊዝና በጋምቢያ የሚገኙ ተመራማሪዎች አስታወቁ።
አጥኚዎቹ በወባ በሽታ የተጠቃ ሰው ልብስ ለውሾቹ በማስሸተት ለረጅም ወራት አሰልጥነዋቸዋል። በተለይ በአፍሪካና በእስያ በየዓመቱ የብዙ ሰዎችን ህይወት የሚቀጥፈው የወባ በሽታን ለመከላከልና ለማጥፋት በሚደገረው አለምዓቀፍ ርብርብ ይሄኛው ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል። ምንም እንኳን የምርምር ውጤቱ ገና በሙከራ የሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም፤ የወባ በሽታን ለመርመር እንደ አዲስ መንገድ ሊያገለግል ይችላል። • የወባ በሽታ ያለ ደም ምርመራ ሊታወቅ ነው • ሐረር በፈረቃ ውሃ ማግኘት ጀምራለች ጥናቶች እንሚያሳዩት በወባ በሽታ ስንጠቃ የሰውነታችን ጠረን የሚቀየር ሲሆን፤ የወባ ትንኞች ደግሞ በዚህ ጠረን ስለሚማረኩ የተጠቂውን ሰው ደም ቀድመው በመምጠጥ በሽታውን ያስተላልፋሉ። አሁን ደግሞ ውሾች ይህንን ጠረን በማሽተት በሽታውን መከላከል ይችላሉ። የተመራማሪዎቹ ቡድን በጋምቢያው 'አፐር ሪቨር' ክልል የሚገኙ ህጻናት የለበሷቸውን ካልሲዎች አሰባስበው ወደ እንግሊዝ በመላክ ነው ጥናቱ የተጀመረው። ከተላኩት 175 ካልሲዎች ደግሞ 30 የሚሆኑት በወባ በሽታ የተጠቁ ህጻናት የለበሷቸው ነበሩ። ምንም እንኳን ውሾቹ አብዛኛውን በበሽታው የተጠቁ ህጻናትን ካልሲዎች ቢለዩም፤ ከአስር ህጻናት አንዱ በሽታው ሳይኖርበት እንደ ተጠቂ ቆጥረውታል። ይሄ ደግሞ ውሾቹን እስከመጨረሻው ከማሰልጠን ጋር የተያያዘ ነው። የተመራማሪ ቡድኑ መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ስቲቭ ሊንዲሴይ በጥናቱ ውጤታማነት እጅግ መደሰታቸውንና ለጊዜው ውሾቹ የምርመራ አገልግሎት ላይ እንደማይውሉ ገልጸዋል። • በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ ውሻዎቹ በሽታውን ሙሉ በሙሉ መለየት የሚችሉበት ደረጃ ለማድረስ የማሰልጠን ስራው እንደሚቀጥልና፤ ሌሎች በሽታዎችንም መለየት እንዲችሉ ለማድረግ እንደሚሰሩ ፕሮፌሰር ስቲቭ ጨምረዋል። በሙከራ ደረጃም በአየር መንገዶችና ሌሎች ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች ውሻዎቹን በማሰማራት ውጤታማኑትን ለመፈተሽም ታስቧል።
53104052
https://www.bbc.com/amharic/53104052
ፌስቡክ የዶናልድ ትራምፕን የምረጡኝ ቅስቀሳ አገደ
ፌስቡክ አንድ የዶናልድ ትራምፕን የድጋሚ ምረጡኝ ማስታወቂያ ቅስቀሳ መልእክት ከገጹ ላይ ማንሳቱን አስታወቀ፡፡ ምክንያቱም ደግሞ መልእክቱ የፌስቡክን ደንብና ሁኔታዎች ስለሚጥስ ነው ብሏል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ለቅስቀሳ የተጠቀሙበት ምልክት የናዚ ጀርመን አርማ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ይህን ደግሞ ፌስቡክ ሊታገሰው የሚችለው አልሆነም፡፡ የተገለበጠ ሦስት ማዕዘን ቅርጽ ያለውና መደቡ ቀይ የሆነው ይህ ምልክት በናዚ እንደ አርማ ካገለገለው ምልክት ጋር ተቀራራቢነት ያለው ነው፡፡ የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን አባላት በበኩላቸው ምልክቱን የተጠቀምነው በአሜሪካ ግራ ዘመም እንቅስቃሴን እያፋፋመ ያለውን አንቲፋ የተባለውን ቡድን ለመተቸት ነበር ሲሉ ፕሬዝዳንቱን ተከላክለዋል፡፡ ፌስቡክ ግን ምንም ይሁን ምን ማስታወቂያው ጥላቻን የሚሰብክ በመሆኑ አስወግደነዋል ብሏል፡፡ ይህ የፌስቡክ እርምጃ በግዙፍ የማኅበራዊ ሚዲያ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችና በዋይት ሃውስ መካከል ያለውን ፍጥጫ ወደ አዲስ ምዕራፍ ይወስደዋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ባለፈው ወር ትዊተር ኩባንያ በተመሳሳይ ዶናልድ ትራምፕ የሚኒያፖሊሱን ክስተት ተከትሎ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ ያሰፈሩት ጽሑፍ ነውጥን ያበረታታል በሚል አንስቶባቸው ነበር፡፡ ይህን የትዊተር እርምጃን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ ቁጣቸውን ገልጸው ፕሬዝዳንታዊ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ‹ተጠያቂነትን የሚጨምር የሕግ ማጥበቂያ ሸምቀቆ› ማሰራቸው አይዘነጋም፡፡ ፌስቡክ በወቅቱ ትዊተር የወሰደውን ርምጃ በፕሬዝዳንቱ ላይ መውሰድ ነበረበት በሚል ከፍተኛ ውግዘት አስተናግዶ ነበር፡፡ አሁን ፌስቡክ የፕሬዝዳንቱን የምረጡኝ ቅስቀሳ መልእክት ማንሳቱ ዶናልድ ትራምፕን ክፉኛ እንደሚያስቆጣ ይጠበቃል፡፡ ትራምፕ ከትዊተር ይልቅ ፌስቡክን ለምርጫ ቅስቀሳ እጅግ አድርገው ይፈልጉታል፡፡ ትልቁ የፕሬዝዳንቱ የምረጡኝ ቅስቀሳ በጀት የሚፈሰውም ወደ ፌስቡክ ገጽ ነው፡፡ የጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ በተነሳው ነውጥ ዙርያ ትራምፕ ‹‹ዘራፊዎችን ዘረፋ ሲጀምሩ፣ ተኩሱም ይቀጥላል›› የሚል መልእክት በትዊተርና ፌስቡክ አስፍረው ነበር፣ ያኔ፡፡ ትዊተር በወቅቱ በመልእክቱ ላይ እርምጃ ሲወስድ ፌስቡክ ቸል በማለቱ የፌስቡክ ኩባንያ ሰራተኞች ‹‹በድርጅታችን አፍረናል›› ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
news-54076907
https://www.bbc.com/amharic/news-54076907
የአውሮፓ ሕብረት ፡ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ከ8 ሰዎች አንዱ ይሞታል
በአውሮፓ ሕብረት አገራት ውስጥ ከሚሞቱ 8 ሰዎች መካከል የአንድ ሰው ሞት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር እንደሚያያዝ የአውሮፓ ሕብረት የአካባቢ ጥበቃ አጀንሲ ሪፖርት ጠቆመ።
በሕብረቱ አገራት ውስጥ ለሚሞቱ ሰዎች የአየር ብክለት፣ የውሃ ንጽህና ጉድለት እና የኬሚካል ተጋላጭነት ምክንያት እንደሆነና ይህም የ13 በመቶ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት እንደሆነ ሪፖርቱ አመልክቷል። ሪፖርቱ ጨምሮ እንዳለው ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ የማኅብረሰብ ክፍሎች ለአየር ንብረት ለውጥ የበለጠ ተጋላጮች ናቸው። በዚህም ምክንያት "በአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑ ማኅብረሰቦችን ለመጠበቅ ጠንከር ያለ እርምጃ ያስፈልጋል" ብሏል ኤጀንሲው። የሕብረቱ የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ ኮሚሽነር ቪርጂኒጅስ ሲነኬቪሲየስ እንዳሉት የሰው ልጆች ጤና እና ከባቢያዊ አየር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው። "እያንዳንዱ ሰው ሊረዳው የሚገባው ነገር የአካባቢያችንን ሥነ-ምህዳር መንከባከብ ቻልን ማለት የሰዎችን ህይወትን እየታደግን ነው ማለት ነው" ብለዋል። መቀመጫውን ኮፐንሃገን ያደረገው ኤጀንሲው ትናንት ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ እአአ በ2012 በአውሮፓ ሕብረት አገራት ውስጥ ለ630 ሺህ ሰዎች ሞት የአየር ንብረት ለውጥ አንዱ ምክንያት ነው ብሏል። የአየር ብክለት ለ400 ሺህ ሰዎች ሞት እንደ አንዱ ምክንያት ሆኖ የቀረበ ሲሆን፤ የድምጽ ብክለት ደግሞ ከ12 ሺህ ሰዎች ሞት ጋር ተያይዟል። የተቀሩት ደግሞ እንደ ከፍተኛ ሙቀት ካሉ የአየር ሁኔታዎች ጋር ተያይዘዋል። ሪፖርቱ የሰው ልጆች በየትኛው ጊዜ ለአየር፣ ለውሃ፣ ለድምጽ ብክለት ወይም ለኬሚካል ተጋላጭ ናቸው ይላል። እነዚህም በተናጠልም ሆነ በድምሩ በሰው ልጆች ጤና ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደሩ ነው ብሏል። ኤጀንሲው በሪፖርቱ እንደገለጸው ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ከአውሮፓ አገራት ብዙ ጉዳት እያስተናገዱ የሚገኙት የምሥራቅ አውሮፓ አገራት ናቸው። እንደምሳሌ የኖርዌይ እና የአይስላንድ ዜጎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርስባቸው ጉዳት ከአልባኒያ አንዲሁም ከቦስኒያ እና ሄርዜጎቪና ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። የዓለም ጤና ድርጅትም ከዚህ ቀደም የአየር ብክለት በመላው ዓለም ለሚሊዮኖች ሞት ምክንያት እየሆነ ነው ብሎ ነበር። የአየር ብክለት ከስትሮክ፣ ከሳምባ ካንሰር እና ከልብ ሕመም ቀጥሎ የበርካቶችን ሕይወት ይቀጥፋል ይላል ድርጅቱ። ሌላ የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት እንደጠቆመው ደግሞ የድምጽ ብክለት የደም ግፊት መጠንን ከፍ በባመድረግ እና የጨንቀት ሆርሞኖች እንዲመነጩ በማደረግ ለልብ ሕመም ያጋልጣል ብሏል።
news-56708103
https://www.bbc.com/amharic/news-56708103
በኮሮናቫይረስ ፅኑ ህሙማን ክፍል ያለጊዜያቸው የተወለዱት መንትዮች አንድ ዓመት ሞላቸው
በእንግሊዟ በርሚንግሃም ባለፈው ዓመት እናታቸው በኮሮናቫይረስ በጠና ታማ በሰመመን እያለች በፅኑ ህሙማን ክፍል ያለጊዜያቸው የተወለዱት መንታ ህፃናት አንድ ዓመት ሞላቸው።
ልክ የዛሬ ዓመት እንደ አውሮፓውያኑ ሚያዚያ 10/2020 መንትያዎቹ የተወለዱት በ26ተኛ ሳምንታቸው ነው። መደበኛ የእርግዝና ጊዜ 38 ሳምንታት ሲሆን በበርሚንግሃም የተወለዱት መንትዮች ከዚህ 12 ሳምንታትን ቀድመዋል። የህፃናቱ እናት ዶክተር ዩክ አሁን ላይ የእሳቸውም ሆነ የልጆቹ ሁኔታ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በነበሩት ጊዜያት "እየጠነከርን እና እየተሻሻልን" ነው ብለዋል። ይህ ቀን "ሁላችንም የደስታ ዘውድ የደፍንበት ቀን ነው። ምክንያቱም ሁላችንም እዚህ አለን" ሲሉም ተናግረዋል። ነገሩን ወደ ኃላ ሰንቃኘው ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ የበርኒግሃም ሆስፒታል የሩማቶሎጂ አማካሪዋ ዶ/ር ዩክ ጤንነት አይሰማቸውም ነበር። እናም ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል እንዲገቡ ተደረገ። በመተንፈሻ ማገዣ መሳሪያ/ቬንትሌተር ታግዘው ኮማ ውስጥ እንዲገቡ ተደረገ። በወቅቱ ከመትዮቹ ልጆች ሴቷ 77 ወንዱ 80 ግራም ነበር የሚመዝኑት። ከ16 ቀናት በኃላ ከሰመመን የነቁት እናት መንትዮቹ ልጆች የኔ መሆናቸውን "አላመንኩም ነበር" ብለዋል። "ወደ ኃላ መለስ ብሎ ከዋሻው ጫፍ ያለውን ብርሃን ማየት መልካም ነው! ሲሉ ተናግረዋል ዶ/ር ዩክ ሴቷ ልጅ ወደ ምድር ስትመጣ ከነበራት ጥንካሬና ፈጣን የጤንነት ለውጥ በተቃራኒ ወንዱ ልጅ በአስቸጋሪ የጤንነት ሁኔታ ሰለማለፉ ተናግረዋል። አንደኛ ዓመታቸውንም በበይነ መረብ ራቅ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር በማክበር ያሰቡት ሲሆን "ባለፈው ዓመት ባለፉበት ሁኔታ ማለፍ ዕድል ሊሆን እንሰሚችል ዶክተር ዩክ" ገልፀዋል። "ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ጊዜ ኮማ ውስጥ ነበርኩ። ልጆቼንም አላገኘዋቸውም ነበር። የትም እንዳለሁ አላውቅም ነበር። በህይወትና ሞት ግብግብ ውስጥ ነበርኩ።" ሲሉ የገለፁት ዶክተር ዩክ "ከፈጣሪና ከህክምና ቡድኑ ዕርዳታ ባይኖር እዚህ አንሰርስም ነበር። በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነበር [ለመንትዩቹ] እኛም ከነሱ ሁኔታ ጋር ከፍ ዝቅ ብለናል። አሁን ጠንካራ ነን። ተስፋ እንዳርጋለን ካሰብንበት እንደርሳለን።" በማለት ተናግረዋል።
news-55329580
https://www.bbc.com/amharic/news-55329580
ኡጋንዳ ከሙዚቀኛው ተቃዋሚ ጋር ግንኙነት ያላቸው የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲታገዱ ጠየቀች
የኡጋንዳ መንግሥት ከታዋቂው ሙዚቀኛና ተቃዋሚ ቦቢ ዋይን ግንኙነት ያላቸው የዩቲዩብ ቻናሎች እንዲታገዱ ጠይቋል።
በኡጋንዳ የኮሚዩኒኬሽን ዘርፉን በዋነኝነት የሚቆጣጠረው አካል አስራ አራት የዩቲየብ ቻናሎች እንዲዘጉ ጠይቋል። ተቆጣጣሪው አካል ደብዳቤውን የፃፈው የዩቲዩብ ባለቤት ለሆነው ጉግል ሲሆን በባለፈው ወር ከደረስው ነውጥም ጋር ግንኙነት ያላቸውና ለ50 ሰዎችም መሞት ተጠያቂ ናቸው ያላቸው እንደሆነም አስፍሯል። በአገሪቱ ውስጥ ዋነኛ ተቃዋሚ የሚባለው ሮበርት ካያጉላንይ ወይም ቦቢ ዋይን እስር ተከትሎም በመዲናዋም ካምፓላም ሆነ በዋነኞቹ ከተሞች ነውጥ ተከስቷል። ሙዚቀኛው ቦቢ ዋይን የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን ጥሷል በሚልም ነው ለእስር የተዳረገው። እንዲታገዱ የተወሰኑት የዩቲዩብ ቻናሎች ከሙዚቀኛው ጋር ግንኙነት አላቸው ቢባልም የኡጋንዳ ኮሚዩኒኬሽን የህግ ጉዳዮች ኃላፊ በበኩላቸው "የአጋጣሚ ጉዳይ ነው" ማለታቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል። ኮሚሽኑ ለጉግል በፃፈው ደብዳቤ የዩቲብ ቻናሎቹን ነውጡን ለማነሳሳት ተጠቅመውበታል፤ ከህግ ውጭ ያላቸውንም ይዘቶች አሳይተዋል በማለትም ዴይሊ ሞኒተር ጋዜጣ ፅፏል። ኡጋንዳ በጥር ወር ምርጫዋን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ናት። አገሪቷን ከሶስት አስርት አመታት በላይ የመሯት ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪንም በምርጫው ይወዳደራሉ።
news-56756414
https://www.bbc.com/amharic/news-56756414
አሜሪካ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ጣለች
የአሜሪካ መንግሥት ሩሲያ ባደረሰችው የሳይበር ጥቃትና ሌሎች "ጠብ አጫሪ" ድርጊቶች ምላሽ የሚሆን ማዕቀብ እንደጣለ አስታውቋል።
ማዕቀቡ መጠነ ሰፊ እንደሆነ የገለፀው ዋይት ሃውስ ከእርምጃዎቹም መካከል የሩሲያ ተቋማትና ባለስልጣናት ኢላማ ናቸው ተብሏል። አላማውም "የሩሲያ በጥላቻ የተሞላ ተግባራትን" መግታት ነው ብሏል ዋይት ሃውስ በመግለጫው። መግለጫው አክሎም በባለፈው አመት በነበረው የሶላር ዊንድ የሳይበር ጠለፋ ጀርባ የሩሲያ ደህንነት አለበት ከማለት በተጨማሪም በባለፈው የአሜሪካ ምርጫ ሞስኮ ጣልቃ ገብታለች ብሏል። ሩሲያ በበኩሏ ይሄንን አልፈፀምኩም ብላ የተናገረች ሲሆን ለዚህ ማዕቀብም አፀፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች። ትናንትና ሃሙስ የታወጀው ማዕቀብ ዝርዝር እርምጃዎችን የያዘ ሲሆን የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፍፁማዊ ትእዛዝ ፊርማ አርፎበታል። በከፍተኛ ሁኔታ ቅራኔ ውስጥ የገቡት ሁለቱ አገራት አሁን ደግሞ ወደባላንጣነት በሚባል ሁኔታ እየተሸጋገሩ ነው። ባለፈው ወር አሜሪካ ሰባት የሩሲያ ባለስልጣናትንና በርካታ የሩሲያ መንግሥት ተቋማትን መንግሥትን በሚተቸው አሌክሴ ናቫልሊ መመረዝ ምክንያት ኢላማ አድርጋቸው ነበር። ሩሲያ በበኩሏ በአሌክሴ መመረዝ እጄ ከደሙ ንፁህ ነው ትላለች። ጆ ባይደንና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ማክሰኞ እለት ባደረጉት የስልክ ልውውጥ ባይደን አገራቸው ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር "ቆፍጠን ያለ እርምጃ ትወስዳለች" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ ሁለቱ አገራት አብረው ሊሰሩባቸው የሚችሉ ሁኔታዎችን እንዲመቻችም ለሩሲያ አቻቸው ጥሪ አቅርበዋል። ፕሬዚዳንት ባይደን በሩሲያ ላይ የተደረገው የማዕቀብ ውሳኔ "ተመጣጣኝ ነው" ብለውታል። "ከፑቲን ጋር ባደረግረው ንግግርም የአሜሪካን ውሳኔ አሳውቄያቸዋለሁ። ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ወደፊት መግፋት እንችል ነበር ነገር ግን እሱን አልመረጥኩም" በማለት ፕሬዚዳንት ባይደን ለሪፖርተሮች ተናግረዋል። አክለውም "አሜሪካ ማለቂያ የሌለው ውጥረትና ግጭት ውስጥ ከሩሲያ ጋር መግባት አትፈልግም" ብለዋል።
news-48442246
https://www.bbc.com/amharic/news-48442246
የትራምፕ ደጋፊዎች የአሜሪካ - ሜክሲኮ ድንበር ግንብ መገንባት ጀመሩ
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች አሜሪካ እና ሜክሲኮን ድንበር የሚለያየውን ግንብ ባገኙት የገንዘብ ድጋፍ መገንባት መጀመራቸውን አስታውቀዋል።
በአሜሪካና በሜክሲኮ ድንበር ግንብ መጀመሩን ቡድኑ አስታውቋል የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋም የቀድሞ አባል ብሬን ኮልፋጅ በኒው ሜክሲኮ ግዛት የተጀመረውን ግንባታ የሚያሳይ ፎቶግራፍ አጋርተዋል። ኮልፋጅ አክለውም የግንባታው መሠረት የያዙት ብረቶች የቆሙት በእርዳታ በተገኘ 22 ሚሊየን ዶላር ሲሆን ገንዘቡን በበይነመረብ አማካኝነት ባካሄዱት ዘመቻ እንደሰበሰቡት ተናግረዋል። • የትራምፕ አማካሪ፡ የግንቡ ውጥን ውድቅ ከተደረገ ሰነባብቷል ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ግንቡን ለመገንባት ያቀረቡትን ሃሳብ ምክር ቤቱ ውድቅ ካደረገባቸው በኋላ ገንዘብ የማሰባሰብ ሥራውን እንደጀመሩ ገልፀዋል። ባለፈው እሁድ የቀድሞው የአየር ኃይል አባል ኮልፋግ አዲስ እየተገነባ ያለውን ግንብ ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶግራፍ በትዊተር ገፃቸው ላይ ለቀውታል። "ታሪክ ሰርተናል! በመጀመሪያው የተሰበሰበው ገንዘብ ዓለም አቀፉን ድንበር ለመገንባት ውሏል" ሲሉ ኮልፋግ በትዊተር ገፃቸው ላይ ደስታቸውን ገልፀዋል። ግንቡ የሚሰራው 'ዊ ቢዩልድ ዘ ዎል ኢንክ' በተሰኘ ለትርፍ ባልተቋቋመው ድርጅታቸው ሲሆን ድርጅቱ የተመሰረተው ከገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻው በኋላ ነው። የቀድሞ የዋይት ሃውስ ባለሥልጣን ስቴቭ ባነን የዚህ ድርጅት አማካሪ ቦርድ ኃላፊ ናቸው። የቦርዱ ኃላፊ ባነን ለሲ ኤን ኤን እንደተናገሩት አዲስ እየተገነባ ያለው 21 ማይል ርዝመት ካላቸው ሁለት ግንቦች ጋር የሚያያዝ ነው ብለዋል። የቀድሞ ካንሳስ ሃገረ ገዢ የነበሩትና በአሁኑ ሰዓት የድርጅቱ አማካሪ ክሪስ ኮባች በበኩላቸው ግንባታው 8 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ እንደሚፈጅ ገልፀዋል። ግንባታውን እያካሄዱ ያሉት ቡድኖች በሰሜን ዳኮታ ግዛት የዓሳ አምራቾች ተቀጥረው የሚሰሩ ተቋራጮች ሲሆኑ ፕሬዚደንት ትራምፕ ግንባታውን እንዲያካሂዱ አሳስበዋቸው ነበር። • ትራምፕ 'ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አዋጅ' ሊያውጁ ነው ከትራምፕ ደጋፊዎች አንዱ የሆነው የ56 ዓመቱ ጄፍ አለን ግንቡ የተገነባው በሰን ላንድ ፓርክ በኒው ሜክሲኮ ግዛት ሲሆን ከሜክሲኮ ሲዩዳድ ጁዋሬዝ በተቃራኒው አቅጣጫ የሚገኝ ነው። ጄፍ አለን እንዳለው ግማሽ ማይል የሚሆነው የግንቡ ክፍል በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይጠናቀቃል። "ግንቡን ራሳችን እንገነባዋለን፤ ይህ አውሮፓ አይደለም፤ ይህ አሜሪካ ነው፤ ድንበራችችንን ራሳችን እንጠብቃለን" ሲልም ለኤ ኤፍ ፒ ተናግሯል። ይሁን እንጂ ይህንን የሚያደርጉት ስደተኞችን በመጥላት እንዳልሆነ በመናገር ሚስቱ ሜክሲኳዊት ስትሆን ሴት ልጁም የተወለደችው ሲዩዳድ ጁዋሬዝ ውስጥ መሆኑን ጠቅሷል። ውሳኔው ላይ የደረሰው ዘረኛ ስለሆነ ሳይሆን ራሱንና አሜሪካን ለመጠበቅ ደህንነቱ የተረጋገጠ ድንበር እንዲኖራት ስለሚፈልግ እንደሆነም አክሏል። "ሰዎች አገራቸውን ትተው ለመሰደድ ካሰቡም በቀጥታ በመሄድ ማመልከት ይችላሉ" ብሏል -ጄፍ አለን። በመጨረሻም ግንባታውን እያካሄደ ያለው ድርጅት "ይህ ጅምር ነው፤ በአሜሪካ ደቡባዊ ክፍል ያለውን ድንበር መጠበቅ ዓላማችን ነው"ሲል አስታውቋል። ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ግንቡን ለመስራት ያቀረበውን የገንዘብ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
44037099
https://www.bbc.com/amharic/44037099
የኒውዮርኩ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፈፀሙት በተባለ ጥቃት ሥራ ለቀቁ
የኒውዮርኩ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኤሪክ ሽኔይደርማን አራት ሴቶች ጥቃት አድርሰውብናል ብለው በመወንጀላቸው በደረሰባቸው ጫና ከሥራ ለቀዋል።
ሥራቸውን የለቀቁት ኒውዮርከር የተባለው መፅሄት ሴቶቹን አናግሮ ዘገባውን ካወጣ በኋላ ነው። ጥቃት አድርሶብናል ካሉት ሴቶች መካከል ሁለቱ የጠቅላይ አቃቤ ህጉ የቀድሞ ፍቅረኞች እንደሆኑ ተነግሯል። ኤሪክ ሺንደርማን ጥቃቱን ያስተባበሉ ሲሆን ወሲባዊ ጥቃቶችን በማውገዝ የሚታወቀው "ሚቱ" የሚባለው እንቅስቃሴም ከፍተኛ ደጋፊ ናቸው። "የፍቅር ግንኙነቴ ግላዊ ቢሆኑም፤ ማንም ላይ የወሲባዊ ጥቃት አድርሸም አላውቅም፤ በፈቃድ ላይ ያልተመሰረተ ግንኙነትም ኖሮኝ አያውቅም። መቸም አይኖረኝም" በማለት ሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ምንም እንኳን ውንጀላውን ቢቃወሙም ከስልጣን እለቃለሁ ብለዋል። "ምንም እንኳን እነዚህ ውንጀላዎች ካለኝ ሙያ ወይም ከሥራዬ ጋር የማይገናኙ ቢሆንም አሁን ካለው እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ቢሮዬን ለመምራት ተፅእኖ እንደሚፈጥርብኝ የማይካድ ነው" ብለዋል። የኒውዮርክ ገዥ አንድሪው ኩሞም የዘገባውን መውጣት ተከትሎ ሺንደርማን ከሥልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። "የኒውዮርክ ከፍተኛ የህግ አስፈፃሚ ቢሆኑም፤ ሁሉም ሰው ከህግ በታች ነው" በማለት የተናገሩ ሲሆን "ኤሪክ ሺንደርማን በጠቅላይ የአቃቤ ህግነታቸው ሊቀጥሉ አይገባም" ብለዋል። ኩሞ በበኩላቸው ውንጀላው እንዲመረመር አቃቤ ህጉን እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል። ሚሼል ማኒንግ ባሪሽና ታንያ ሴልቫራትናም የተባሉት ሴቶች ለኒውዮርከር እንደተናገሩት ሺንደርማን "መጠጥ ጠጥቶ ደብድቦናል" ብለዋል። ከአካላዊ ጉዳት በተጨማሪ ግንኙነታቸውን ቢያቋርጡ ለመግደል እንዳስፈራራቸውም ሁለቱም ገልፀዋል። "በህይወቴ አስቸጋሪ ከምላቸው ወራቶች በኋላ ተናገርኩ" በማለት መፅሄቱ ለህትመት ከበቃ በኋላ ማኒንግ ባሪሽ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። "ለሴት ልጆቼም ሆነ በዓለም ላሉ ሴቶች ስል በዝምታዬ ልቀጥል አልቻልኩም። ሌሎች ሴቶችም ብርታት እንዲያገኙ ይሆናቸዋል" ብለዋል። በባለፈው ወር ኒውዮርከርና ኒውዮርክ ታይምስ ሆሊውድ ውስጥ የሚከሰቱ ወሲባዊ ጥቃቶችን በማጋለጥ የፑሊትዘር አሸናፊ ሆነዋል። ይህ ዘገባም በሆሊውድ የብዙ ፊልም ባለቤቶች የሆኑትን አይነኬውን ሀርቬይ ዌይንስቴይንን ያጋለጠ ነው። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ወሲባዊ ጥቃቶችንም አላደረስኩም ሲሉ ሀርቬይ ዌይንስቴይን መካዳቸው የሚታወስ ነው። በወቅቱም ሺንደርማን በዌይንስተን ላይ ክስን አቅርበው ነበር። ይህ ክስም ሴት ሰራተኞች ላይ ጥቃት በማድረስና እንዲሁም ለመግደል በማስፈራራት የሚል ነው። ለረዥም ጊዜ የሴቶችን መብት በመደገፍ የሚታወቁት ሺንደርማን ክሱን ካቀረቡ በኋላ ወሲባዊ ጥቃቶችን አውግዘዋል።
51717026
https://www.bbc.com/amharic/51717026
የተማሪዎቹ መታገት ከተሰማ 90 ቀናት አለፉ
ሕዳር 24፤ 2012 ዓ.ም. - ወላጆች ልጆቻቸው እንደታገቱ ሰሙ። ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ መኖሪያ ቀያቸው በማምራት ላይ የነበሩ ተማሪዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ታገቱ።
ዜናው ቀስ በቀስ ሃገሪቱን ያዳርስ ጀመር። መረጃው የደረሰው ቢቢሲም የተማሪዎቹን ማንነት ማጣራት ያዘ። በዚህ መካከል ከአጋቾቿ ማምለጥ የቻለች አንዲት ተማሪ የተፈጠረውን አንድ በአንድ አስረዳች። ተማሪ አስምራ ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንዷ ነበረች። «ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንዷ ነኝ። መጀመሪያ በአጋቾቹ የተያዝነው 18 ተማሪዎች ነበርን። እኔ ማምለጥ ስለቻልኩ አሁን ታግተው ያሉት ተማሪዎች ቁጥር 17 ነው። ከእነዚህ መካከል 4ቱ ወንዶች ሲሆኑ 13ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው» ስትል ተናገረች። ተማሪዋ አከጋቾቹ እንዴት እንዳመለጠችም ለቢቢሲ እንዲህ አስረዳች - «እየጮህን ነው ይዘውን የሄዱት። የጫካውን ግማሽ እንደተራመድን የተወሰኑት ሴቶች መራመድ አቃታቸውና ወደቁ። ታዲያ እነርሱን 'ተነሱ፤ አትነሱ' እያሉ ለማንሳት ሲሞክሩ ነበር እኔ ከአይናቸው የተሰወርኩት። በጫካው ውስጥ ለሁለት ቀናት ያህል ካደርኩ በኋላ፤ በሦስተኛው ቀን ወደ ዋናው የመኪና መስመር መውጣት ቻልኩ። እንደምንም ብዬ ወደ መስመር ስወጣ አንድ አማርኛ በትንሹም ቢሆን መናገር የሚችሉ አባት አገኘሁ። 'የት ነው መሄድ የምትፈልጊው' አሉኝ። 'ደምቢ ዶሎ ለፌደራል ፖሊሶች ስጡኝ' አልኳቸው። ከዚያም መኪና ለምነው አሳፍረው ላኩኝ። መረጃውንም ለፌደራል ፖሊሶቹ ተናግሬያለሁ። ፌደራል ፖሊሶቹ 'ቦታው እንኳን ለተማሪ ለወታደርም አስጊ ነው፤ እንከታተላለን' አሉኝ።» የተማሪዋ ሙሉ ታሪክ፦ "የታገቱት 17ቱ ተማሪዎች፡ "ከታገቱት መካከል አንዷ ነበርኩ፤ በሦስተኛ ቀኔ አምልጫለሁ" ተማሪዎች መታገታቸው እንደተሰማ ስልክ የመታንላቸው የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ "ምንም አይነት መረጃ የለኝም። እኔ የሰማሁት ነገር የለም" ሲሉ ምላሽ ሰጡን። በዚያኑ ወቅት መረጃ ይኖራቸው እንደሆን የጠይቅናቸው የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በበኩላቸው "ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ የለም" ከማለት ውጪ ማብራሪያ መስጠት አልፈለጉም። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የተወሰኑ ተማሪዎች ቤተሰቦች ተማሪዎቹ ከታገቱ በኋላ ለሁለት ሳምንታት ያክል ይደውሉላቸው እንደነበር ነገር ግን ያሉበትን አድራሻ እንደማያውቁት ያስረዳሉ። የተማሪዎቹ መታገት ዜና ከአፅናፍ አፅናፍ ከተሰማ በኋላ የሀገር መነጋገሪያ ሆነ። ብዙዎች መንግሥት አንድ እንዲልና ታገቱ የተባሉ ተማሪዎችን እንዲያስለቅቅ አቤት አሉ። ይሁን እንጂ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች በጊዜ ምላሽ አልሰጠም። በዚህ መካከል ቀናት ቀናትን እየወለዱ ሄዱ። ተማሪዎቹን አየሁ የሚል ጠፋ። ጥር 02/2012 በዚህ መሃል ጥር 2/2012 በብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣብያ የቀረቡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል-አቀባይ አቶ ንጉስ ጥላሁን 'ከታገቱት ተማሪዎች መካከል 21 ተለቀዋል፤ የቀሩ አሉ፤ እነሱንም እናስለቅቃለን' ሲሉ መግለጫ ሰጡ። ተማሪዎቹን ያገታቸው ማነው? ከተለቀቁ የት ነው የሚገኙት? ከወላጆቻቸው ጋር ለምን እንዲገናኙ አልተደረገም? ለሚሉ እና ለሌሎች ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ አልነበረም። ተማሪዎችን ታገቱ ከተባለ ከ50 ቀናት በኋላ የተወሰኑ ተማሪዎች ቤተሰቦች ወዳሉባት አዲስ ዘመን ከተማ ያቀናው የቢቢሲ ዘጋቢ ከተማዋ ሃዘን አጥልቶባታል ይላል። የታጋች ቤተሰቦች ፊታቸው ጠቁሮ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነው ነው ያገኘኋቸው የሚለው ዘጋቢያችን ቤተሰቦችን ማነጋገር እጅግ አሳዛኝ እንደነበር ያስረዳል። ወ/ሮ ማሬ አበበ የተማሪ በላይነሽ መኮንን ወላጅ ተማሪዎች መታገታቸው ከተሰማ 50 ቀናት ካለፉ በኋላ መግለጫ የሰጡት በወቅቱ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ላቀ አያሌው ከታገቱ ተማሪዎች ወላጆች መካከል የተወሰኑትን አነጋግሬአለሁ ብለው ነበር። "እንደ አገር ተማሪዎችን ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት አናሳ በመሆኑ ፈጥኖ መፍትሔ ማግኘት አልተቻለም" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተውም ነበር። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንም ሃገሪቱ ከገጠሟት ፈተናዎች አንዱ የተማሪዎች እገታ ነው ሲሉ መግለጫ ሰጡ። ይህንን የተማሪዎች ዕገታ ጉዳይ "በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድ የተጨበጠ ውጤት ላይ ለማድረስ መንግሥት ሙሉ ኃይሉን አሰባስቦ እየተረባረበ ነው" የሚል መግለጫ ከሰጡ ከወር በላይ ቢሆነውም ከመንግሥት የተሰማ ምንም አዲስ ነገር የለም እስካሁን። እስከዛሬ ተማሪዎቹን ማን አገታቸው በሚለው ጉዳይ ላይ ውል ያለው መረጃ ባይገኝም በርካታ መላ ምቶች ይሰጣሉ። ተማሪዎቹ ከታገቱ ሁለት ወራት በኋላ ከቢቢሲ ጋር ቃለ-ምልልስ አድርጎ የነበረው በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የቀድሞ የኦነግ ጦር አዛዥ ዲሪባ ኩምሳ ወይም ጃል መሮ ተማሪዎቹ የታገቱት እሱ በሚመራው ቡድን እንደሆነ እንደሚነገር ተጠይቆ "ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ከእናንተ ነው። የትግል ዓላማችን ከተማሪዎች ጋር አይገናኝም። በተማሪዎቹ ላይም ይህን የተባለውን አይነት ተግባር አልፈጸምንም። እንደተለመደው የእኛን ስም ለማጉደፍ የተወራ ነው እንጂ በፍጽም እንዲህ አይነት ተግባር አሁንም ወደፊትም እንፈጽምም'' ሲል ማስተባበሉ አይዘነጋም። ቢቢሲ ተማሪዎቹ መታገታቸው ከተሰማ ጀምሮ ያላቸውን መረጃ እንዲያካፍሉ የጠየቃቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ጀምሮ ያሉ የመንግሥት ባለሥልጣናት መረጃ እንደሌላቸው ከመናገር ውጭ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም። 90 ቀናት የተማሪዎቹ መታገት ከተሰማበት ኅዳር 24 ጀምሮ እስከዛሬ የካቲት 12/2012 ባሉት 90 ቀናት የተማሪዎችን መታገት በተመለከተ በርካታ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ መረጃዎች ወጥተዋል። ዜናው ከሃገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰምቷል። መንግሥት ስለ ጉዳዩ የተረጋገጠ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የወጡ መረጃዎች የተጣረሱ ይመስላሉ። የክልል አስተዳዳሪዎችም እርስ በርስ መወቃቀስ ይስተዋልባቸዋል። መሪጌታ የኔነህ አዱኛ የተማሪ ግርማሽ የኔነህ አባት ናቸው። መሪጌታ የኔነህ አዱኛ የተማሪ ግርማሽ የኔነህ አባት ናቸው። «ሞተውም ከሆነ እውነቱን ነግረውን ቤተሰብ ጋር ተሰባስበን አልቅሰን እርማችንን ብናወጣ ይሻለናል፤ እንዲህ በየቀኑ ምን ሆነው ይሆን እያልን በሰቆቃ ከምንኖር» ይላሉ። ሌሎችም የተማሪ ቤተሰቦች በሰቀቀን ውስጥ እንዳሉ ይናገራሉ። ቀን አልፎ ቀን ቢመጣም የታገቱት ተማሪዎች አሁን ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም። የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዊያን ስለታገቱት ልጆች መጮህ ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችም ዘመቻውን መቀላቀላቸው አይዘነጋም። በተለይ ትዊተር በተሰኘው ማሕበራዊ መድረክ ላይ #Bringourgirlsback #Bringourstudentsback #WhereAreTheStudents? የተሰኙ ዘመቻዎች ተስተውለው ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የታገቱት ተማሪዎች ጉዳይ የተዘነጋ መስሏል። አልፎ አልፎ ብልጭ ብልጭ ከሚሉ የማሕበራዊ ሚድያ ዘመቻዎች ውጭ ስለታገቱት ወጣቶች የሚያወራ እምብዛም አይስተዋልም። የተማሪዎቹ ወላጆች ለቅሶ ግን እንደቀጠለ ነው። ጥያቄው አሁንም አልተመለሰም - የታገቱት ተማሪዎች የት አሉ?
news-56757465
https://www.bbc.com/amharic/news-56757465
ኮሮናቫይረስ፡ ጾም ላይ ያሉ ሙስሊሞች የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ ይችላሉ?
የእስልምና አስተማሪዎችና የጤና ባለሙያዎች ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ጾም ምክንያት የኮቪድ-19ን ክትባት ሳያገኝ እንዳይቀር ማሳሰቢያ እየሰጡ ነው።
በረመዳን ጾም ወቅት በርካታ ሙስሊሞች በቀን ምግብና መጠጥ ከመውሰድ ይቆጠባሉ። የእስልምና አስተምህሮ ሕዝበ ሙስሊሞ ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መጥለቂያ ድረስ ባለው ጊዜ "ማንኛውም ወደ ሰውነት የሚገባ ነገር ከመውሰድ እንዲቆጠብ" ያስተምራል። ነገር ግን በሊድስ ከተማ ኢማም የሆኑት ቃሪ አሲም ክትባቱ በጡንቻ በኩል የሚገባ እንዲሁም ምንም ዓይነት የምግብም ሆነ የመጠጥ ንጥረ ነገር ስለሌው ጾም እንደ መግደፍ አይቆጠርም ይላሉ። "በርካታ የእስልምና አስተማሪዎች በረመዳን ወቅት መከተብ ጾምን መግደፍ እንዳልሆነ ነው የሚገነዘቡት" ሲሉ የብሔራዊ መስጅዶችና ኢማሞች አማካሪ ቦርድ መሪ የሆኑት አሲም ለቢቢሲ ይናገራሉ። ነገር ግን በምሥራቅ ለንደን የሕክምና ዶክተር የሆኑት ፋርዛና ሁሴን ሙስሊሞች በቀንም ቢሆንም መጥተው መከተብ ይችላሉ ይላሉ። "በርካታ ሙስሊሞች በጾም ወቅት የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ይገባናል ወይ የሚለው ጉዳይ እንዳሳሰባቸው እንረዳለን" ይላሉ ዶክተሯ። "በርካታ ጿሚዎች በረመዳን ወቅት መርፌ መወጋት ጾምን መግደፍ እንደሆነ ያምናሉ። ነገር ግን ይህ እውነት አይደለም። ምክንያቱም ክትባት ምንም ዓይነት የምግብ ይዘት የለውም።" ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ያሉ አንዳንድ መስጂዶች ጾም ላይ ሙስሊሞች በረመዳን ወቅት ክትባት ማግኘት እንዲችሉ በማሰብ ክትባት በቅጥር ግቢያቸው መስጠት ጀምረዋል። በርካታ ብሪታኒያዊያን በክትባት ላይ ያላቸው እምነት ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ኢፕሶስ ሞሪ የተሰኘ መረጃ ሰብሳቢ ድርጅት ባሰባሰበው ቁጥር መሠረት ነጭ ያልሆኑ ብሪታኒያዊያን በክትባት ላይ ያላቸው እምነት ባለፈው ጥር ከነበረው 77 በመቶ አሁን ወደ 92 በመቶ ጨምሯል። በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ሥፍራ ያለው የረመዳን የጾም ወር ባለፈው ሰኞ ጨረቃ በመካ መዲና ላይ ከታየች ጀምሮ ገብቷል። ወሩ ከንጋት እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ በሚደረግ ጾም እንዲሁም ሰብሰብ ተብሎ በሚደረግ ፀሎትና ስግደት ይታሰባል። ከዚያም ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ ጾሙና በምግብና በመጠጥ ይፈታል። ረመዳን ለወትሮው እንዲህ ባለው ባሕል ነበር የሚዘከረው። ነገር ግን ዘንድሮና አምና በኮሮናቫይረስ ምክንያት ነገሮች ተቀያይረዋል። ምንም እንኳን ተሰባስቦ መስገድ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ይፈቀድ እንጂ ሰዎች ተራርቀው እንዲሰግዱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። አልፎም በሽታው እንዳይዛመት በመስጋት የአንድ ቤተሰብ አባላት ከሌሎች ጋር እንዳይቀላቀሉ ተከልክሏል። የብሪታኒያ ኢስላሚክ ሜዲካል ማኅበር በረመዳን ወቅት መስጂዶች እንዴት ሰዎችን ማስተናገድ እንዳለባቸው የሚጠቁም መመሪያ አውጥቷል። ማኅበሩ ታራዊህ [የአመሻሽ ፀሎት] እንዲቀጥል ያሳሰበ ሲሆን ነገር ግን አየር በሚገባት ሁኔታ ያልተራዘመ እንዲሆን መክሯል። አልፎም ማኅበሩ ኢማሞች ሕዝበ ሙስሊሙን ለመጠበቅ ሲባል ሁለት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ደርበው እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።
news-55301963
https://www.bbc.com/amharic/news-55301963
የአሜሪካ ግምጃ ቤትና የንግድ ተቋማት የሳይበር ጥቃት ተፈጸመባቸው
የአሜሪካ ግምጃ ቤትና ንግድ ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች የሳይበር ጥቃት ተፈጸመባቸው።
ይህንንም ተከትሎ አሜሪካ ሎሎች የሲቪል ፌዴራል ኤጀንሲዎች በአስቸኳይ "ሶላርዊንድስ" ተብሎ ከሚጠራው ኮምፒዩተር ኔትዎርክ መሣሪያን መጠቀም እንዲያቆሙ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። ይህ "ሶላርዊንድስ" የተባለው ኮምፒዩተር ኔትዎርክ መሣሪያ በጠላፊዎች እጅ ወድቋል ተብሏል። አሜሪካ ከጥቃቱ ጀርባ ማን እንዳለ እስካሁን ምንም ያለችው ነገር የለም። 'ፋየርአይ' የተሰኘ የሳይበር ደህንነት ኩባንያ ለደህንነት ማረጋገጫ የሚጠቀምበት የኮምፒዩተር መገልገያ በበይነ መረብ ጠላፊዎች መጠለፉን ካስታወቀ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው ይህ ክስትት ያጋጠመው። የአሜሪካ ሳይበር ደህንነት እና መሰረተ ልማት ደህንነት ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የአሁኑ ጠለፋ የመንግሥት መረጃ ስርዓትን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያጋልጥ የሚችል ነው። ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሶላርዊንድስ እነዚህ የአሜሪካ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙትን የኮምፒዩተር ኔትዎርክ መገልገያ የሰራ ሲሆን በትዊተር ገጹ ላይ አገልግሎቱን የሚያገኙ ተጠቃሚዎች ሊደርስ የሚችለውን የደህንነት ስጋት ለመቀነስ ወደተሻሻለው አዲስ ስርዓት ሊቀይሩ ይገባል ብሎ ነበር። ፋየርአይ የተሰኘው ኩባንያ ጥቃቱ ከፍተኛ የመንግሠዕት መዋዕለ ንዋዮችን እና መሠረተ ልማቶቸን ኢላማ ያደረገ መሆኑ እና ምናልባት በሌላ መንግሥት የሚደገፍ ሊሆን ይችላል የሚለን ሀሳብ ያጠናክረዋል ብሏል። እንደዚህ አይነት መሰል ጥቃቶችን በመመርመር የሚታወቁ ሶስት ግለሰቦች ጥቃቱ የተፈጸመው በሩሲያ ሊሆን ይችላል ሲሉ ለሮይተርስ የዜና ወኪል መናገራቸው ተገልጿል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በበኩሉ በፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት ''ምንም መሰረት የሌለው ውንጀላ ነው'' ብሏል።
news-56506555
https://www.bbc.com/amharic/news-56506555
ትግራይ፡ በአክሱም የተከሰተው 'ሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀል ወይም የጦር ወንጀል ሊሆን ይችላል'-ኢሰመኮ
በአክሱም ከተማ በኤርትራ ወታደሮች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀል ወይም የጦር ወንጀል ሊሆን ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።
ኮሚሽኑ በአክሱም ከተማ ውስጥ ስለተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ያካሄደው የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ ሪፖርቱ ላይ እንዳመለከተው የተፈጸሙት ድርጊቶች "ተራ ወንጀሎች ሳይሆኑ የዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችና መርሆዎችን የሚጥሱ ናቸው" በማለት በአጠቃላይ በክልሉ ውስጥ የተሟላ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ምርመራ ማካሄድ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል። በዚህም በኤርትራ ሠራዊት በአክሱም ከተማ ውስጥ የፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት "ምናልባት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ወይም የጦር ወንጀል ሊሆን ስለሚችል" ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያስፈልግ አመልክቷል። በከተማዋ በግጭቱ ተሳታፊ ያልነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ሆን ተብሎ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸሙን አመልክቶ በወታደራዊ ኢላማነት አስፈላጊነታቸው ሊገመገሙ የማይችሉ የሰላማዊ ሰዎች ንብረቶች፣ በሐይማኖት ተቋማትና በሆስፒታሎች ላይ ጭምር ሆን ተብሎ ዝርፊያና ጉዳት መድረሱን ገልጿል። ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች ሲያወጡ መቆየታቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎም የተለያዩ አገራት እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽንን ጨምሮ የሰብአዊ መብት ጥሰቶቹ እጅጉን እንደሚያሳስባቸው በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ኮሚሽኑ በምርመራው እንደደረሰበት በተለይ ከኅዳር 19 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም በነበሩት ሁለት ቀናት ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንደተፈጸሙ ጠቅሶ "ከአንድ መቶ በላይ ሰላማዊ ሰዎች በወቅቱ በአክሱም ከተማ በነበሩ የኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውን" ገልጿል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው በዚህ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ላይ እንዳመለከተው ያነጋገራቸው የአክሱም ከተማዋ ነዋሪዎች፣ የተጎጂ ቤተሰቦችና የአይን እማኞች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች "ልጆቻቸው፣ ሚስቶቻቸውና እናቶቻቸው ፊት ጭምር በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ አስረድተዋል" ብሏል። በዚህ ጥቃት የተገደሉት የአክሱም ከተማ እና አከባቢው ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ጦርነት ሸሽተው በከተማዋ የተጠለሉ ተፈናቃዮች እንዲሁም የኅዳር ፅዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓልን ለማክበር ከተለያየ ቦታዎች የመጡ ሰዎች ጭምር እንዳሉበት ሪፖርቱ አመልክቷል። ኮሚሽኑ ጨምሮም በዚህ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ላይ የጠቀሳቸው አሃዞች በከተማው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር የሚያመላክት ሳይሆን በምርመራው ወቅት ለማረጋገጥ የቻለውን የሰላማዊ ሰዎች ጉዳት ብቻ የሚጠቁም መሆኑን ገልጿል። ከየካቲት ወር አጋማሽ በኋላ የምርመራ ባለሞያዎቹን ወደ አክሱም ከተማ በማሰማራት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የዓይን ምስክሮችንና የሐይማኖት መሪዎችን በማነጋገር በከተማዋ ስለተፈጠረው ክስተት መረጃዎችን እንዳሰባሰበ ኢሰመኮ ገልጿል። ሪፖርቱ ጨምሮም በክልሉ የተጣለውን የሰዓት እላፊ ገደብን ለማስከበርና በደኅንነት አጠባበቅ ምክንያት በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የሚወሰደው የኃይል እርምጃ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ በሰዎች ላይ ሞትና የአካል ጉዳትን ማስከተሉን ጠቅሶ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል። የኢትዮጵያ መንግሥትም በበኩሉ ተከሰቱ የተባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ በእራሱ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጾ የአፍሪካ ሕብረትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት በምርመራው ውስጥ እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። ይህንንም የመንግሥት ውሳኔ "ትክክለኛ እርምጃ" ሲሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ገልጸውታል። ጨምረውም "አብዛኛው የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በሕይወት መስዋዕትነት ጭምር አገራቸውንና ሕዝቡን የሚያገለግሉ ቢሆንም፤ በተወሰኑ የሠራዊቱ አባላት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ምርመራ ተገቢውን እገዛ ማድረግ ይገባል" ብለዋል። ከኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጥምረት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን እንዲመረምር ጥሪ የቀረበለት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በመርመራው ሂደት ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆኑንና ለዚህም እየተዘጋጀ መሆኑን ባለፈው ሳምንት አሳውቆ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መጋቢት 14/2013 ዓ.ም በአገሪቱ ምክር ቤት ቀርበው እንደተናገሩት ግጭቱ ከተጀመረ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በዚህ ወቅትም በትግራይ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙ ገልጸው ነገር ግን እንዚህ ድርጊቶች መንግሥታቸው ችላ እንደማይላቸውና ምርመራ በማድረግ ጥፋተኞች ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። ከወራት በፊት በታሪካዊቷ የአክሱም ከተማ በኤርትራ ወታደሮች አማካይነት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች ከተለያዩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በኩል መውጣቱ ይታወሳል። የኤርትራ መንግሥት ግን ወታደሮቹ ፈጽመውታል በሚል ስለቀረቡ በይፋ የሰጠው ምላሽ ባይኖርም የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረ መስቀል ግን በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሯቸው መልዕክቶች ክሶቹን ማጣጣላቸው ይታወሳል። የግጭቱ የተቀሰቀሰው በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ላይ የህወሓት ኃይሎች ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ አዘው የፌደራል ሠራዊቱ ወደተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች መሰማራቱ ይታወሳል። በዚህም ሠራዊቱ በሦስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ዋና ዋና የትግራይ ከተሞችን በመቆጣጠር የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን ሲቆጣጠር ለ30 ዓመታት ያህል ትግራይን ሲያስተዳድር የቆየው ህወሓት ከስልጣኑ ተወግዶ ከአመራሮቹ መካከል የተወሰኑት ሲገደሉ ሌሎች ደግሞ የተያዙ ሲሆን የቀሩት የት እንዳሉ አይታወቅም። ወታደራዊ ግጭቱን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ ግድያን፣ ጾታዊ ጥቃትንና ዘረፋን ጨምሮ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች የወጡ ሲሆን በዚህ ድርጊት ውስጥም የኤርትራ ወታደሮች በስፋት ስማቸው ሲጠቀስ ቆይቷል። ከተፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በተጨማሪ በግጭቱ ሳቢያ በርካታ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ከ60 ሺህ በላይ ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ተሰደዱ መሆናቸውንና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው በተለያዩ ቦታዎች እንደሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች ገልጸዋል።
news-51527770
https://www.bbc.com/amharic/news-51527770
ሆንግ ኮንግ፡ በኮሮና ምክንያት በተከሰተ እጥረት አንድ ቡድን የሶፍት ጥቅሎችን ዘረፈ
በሆንግ ኮንግ አንድ ቡድን በመቶዎች የሚቆጠሩ የሶፍት ጥቅሎችን መዝረፉ መነጋገሪያ ሆኗል። ጥቅሎቹ አራት ሺ ሁለት መቶ ብር የሚያወጡ መሆናቸውም ታውቋል።
የኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝን ተከትሎ ብዙዎች እጥረት ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት የሶፍት ወረቀት ጥቅሎችን በመሸመታቸው ገበያ ላይ ከፍተኛ እጥረት አጋጥሟል ተብሏል። • ቻይና፡ በኮሮና የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው ተባለ • ''ኮሮናቫይረስን ወደ አፍሪካ መውሰድ አልፈልግም'' ዝርፊያው የተፈፀመው ሞንግ ኮክ ግዛት በሚገኝ ሱፐር ማርኬት በር ላይ ሲሆን የሶፍት ጥቅሎችን ለማድረስ አንድ ተላላኪ በሚንቀሳቀስበት ወቅት እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ ሁለቱን ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሎ የተወሰነውን የሶፍት ጥቅልም ማስመለስ እንደቻለ የሃገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል። ግለሰቡ የሶፍት ጥቅሎችን ወደ ሱፐር ማርኬቱ ለማስገባት ከመኪና ላይ ሲያወርድ በነበረበት ወቅት እንደዘረፉት ተገልጿል። አንድ የሃገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው 7 ሺ ብር እንደሚያወጡ የመሚገመቱ 600 የሚሆኑ የሶፍት ጥቅሎች ተዘርፏል ብሏል። በግዛቷ የሶፍት ጥቅሎች በሚደርስበት ወቅት ረዥም ሰልፎችም ተስተውለዋል። ምንም እንኳን መንግሥት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የአቅርቦት እጥረት አይኖርም የሚል ማስተማመኛ ቢሰጥም ነዋሪዎች የሶፍት ጥቅሎችን በማከማቸት ላይ ናቸው። የሶፍት ጥቅሎችን ብቻ ሳይሆን ነዋሪዎች ሩዝ፣ ፓስታና የቤት ማፅጃ ቁሳቁሶችንም በፍራቻ ምክንያት በማከማቸት ላይ ናቸው ተብሏል። • ኢትዮጵያውያን፡ የአስወጡን ድምጽ በጎሉባት የቻይናዋ ዉሃን ከዚህም በተጨማሪ የፊት ጭምብልም ሆነ የእጅ ማፅጃ ማግኘት በጣም አዳጋች ሆኗል። ባለስልጣናቱ በበኩላቸው ሃሰተኛ የሆኑ ዜናዎች በድረገፅ በመሰራጨታቸው ነዋሪዎች እጥረት ይከሰታል በሚል መሸመትና ማከማቸታቸውን ቀጥለዋል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ገበያው እንደተረጋጋ ነው ይላሉ። በሆንግ ኮንግ ብቻ ሳይሆን በሲንጋፖርም ነዋሪዎች እጥረት ይከሰታል በሚል ፍራቻ የሶፍት ጥቅሎችን፣ የእጅ ማፅጃና የፊት ጭምብል እየሸመቱ ሲሆን፤ እስካሁን ባለው 75 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።
news-44397984
https://www.bbc.com/amharic/news-44397984
አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጉብኝት
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሁለት ቀናት በግብጽ ያደረጉትን ቆይታ አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ በተለያየ ምክንያት ግብጽ ውስጥ ከነበሩ 32 ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ ገብተዋል።
''ለጉብኝት የዛሬ አምስት ዓመት ወደ ግብጽ የመጣው ኢትዮጵያዊ አንድ ወዳጁ እቃ እንዲያደርስለት ይጠይቀዋል። እንደተባለውም እቃውን ወደ ግብጽ ይወስዳል። ይዞት ወደ ግብጽ የመጣው እቃ (ጫት) ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ሰው እንደልቡ የሚጠቀመው ነገር ቢሆንም ግብጽ ውስጥ ግን ክልክል ነው ተብሎ በፍተሻ ወቅት በቁጥጥር ሥር ይውላል።" የዚህ ኢትዮጵያዊ ታሪክ እጅጉን አሳዝኖኛል ያሉት በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ታዬ አጽቀሥላሴ፤ እስከሚፈታባት ቀን ድረስ ለአምስት ዓመታት በእስር ላይ እንደነበር ገልጸዋል። ''ይህ ሰው ሥራውን አጥቷል፤ ሕይወቱ ተመሰቃቅሏል። በዚህ ሁሉ ዓመት የእስር ቤት ቆይታው፤ ፍርድ ቤት የቀረበው የዛሬ ሦስት ወር ነበር።" በማለት በእስር ቤት ውስጥ ብዙ እንግልት እና ስቃይ እንደደረሰበት አምባሳደሩ ተናግረዋል። መፈታቱን እስካሁን ድረስ እንዳላመነ እና ከመፈታቱ ባለፈ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በአንድ አውሮፕላን ወደ ሃገሩ መመለስ በመቻሉ ደግሞ እጅግ መደሰቱን ገልጸዋል። ከእስር ከተፈቱት ሰዎች በተጨማሪ ኤርትራ ውስጥ የነበሩ እና በቅርብ ወደ ግብጽ የገቡት የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት ኮሎኔል አበበ ገረሱ እና የኦህዴድ መሥራችና ሥራ አስፈጻሚ አባል የነበሩት አቶ ዮናታን ዲቢሳ ወደ ሃራቸው ተመልሰዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በግብጽና ከፕሬዝዳንት አብዱልፈታ አልሲሲ ጋር የነበራቸው ውይይት ምን እንደሚመስል አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴን ቢቢሲ አነጋግሯቸዋል። በውይይቱ ወቅት በመሪዎቹ መካከል የነበረው የእርስ በእርስ መግባባት እና መከባበር በጣም አስገርሞኝ ነበር በማለት የጀመሩት አምባሳደር ታዬ፤ ''እስካሁን ባየሁት ነገር የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ብዙ ርቀት እንደሚጓዝ ተሰፋ አደርጋለሁ'' ብለዋል። ከተነጋገሩባቸው ጉዳዮች መካከልም አንዱ፤ ሁለቱን ሃገራት ያስተሳሰረው የአባይ ወንዝ እና ኢትዮጵያ እየገነባቸው ያለው የህዳሴ ግድብ በተመለከተ ነው። ኢትዮጵያ ግድቡን የምትገነባው የግብጽ ሕዝብን ለማስራብ እንደሆነ አብዛኛዎቹ ግብጻውያን ያምናሉ ያሉት አምባሳደሩ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝትም ይህንን አስተሳሰብ ለመቀየር እና የግብጽ ሕዝብን በቅርብ ለማግኘት ነበር ብለዋል። የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የኢትዮጵያ እድገት የግብጽ ልማት ነው በማለት ኢትዮጵያ ለልማቷ በምታደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ የግብጽ ትብብር እንደሚኖር እና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ለማድረግ ዝግጅትም ፍላጎትም እንዳላቸው አረጋግጠዋል። እንደ አምባሳደሩ ከሆነ ሌላኛው መሪዎቹ የተወያዩበት ጉዳይ ሁለቱን ሃገራት ሱዳንንም ጨምሮ በመሠረተ ልማት የማገናኘቱ ሂደት ነበር። ''በውይይቱ መሠረት በባቡር መስመር፤ በአስፋልት መንገድ እና በውሃ ትራንስፖርት ሃገራቱን የማስተሳሰሩ ሥራ እንዴት ማጠናከር እንደሚቻል ተወያይተዋል''። ከዚህ በፊትም ተቋቁሞ የነበረውን የመሰረተ ልማት ፈንድ የበለጠ ለማጠናከር ደግሞ በመጪው ሃምሌ በካይሮ ስብሰባ ለማድረግ መስማማታቸውን አምባሳደሩ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም በትምህርት፤ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስልጠና እንዲሁም በግብርና ሥራ ላይ ለመተባበርም ተስማምተዋል። እስካሁን የግብጽ ባለሃብቶች 900 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ወጪ ፈሰስ በማድረግ በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ተሰማርተዋል ያሉት አምባሳደሩ፤ ተሳትፏቸውን ለመጨመር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይም ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በሚያዚያ 2015 በሊቢያ በረሃ ላይ አይ ኤስ በተባለው ቡድን የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ሌላኛው የመወያያ ርዕስ ነበሩ። የኢትዮጵያውያኑን አጽም ካለበት ፈልጎ ማግኘት እና ቅሪታቸው ወደ ሃገር ቤት እንዲመለስ የማድረጉን ሥራ ማስጀመር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የሐሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን አምባሳደሩ ጨምረው ተናግረዋል። ''በትክክለኛ መስመር ላይ ያለ ጉዳይ ስለሆነ በጠንካራ ሥራ እና ብርታት፤ እልባት እንደሚያገኝ ተስፋችን የበረታ ነው'' በማለት ያላቸውን እምነት አምባሳደሩ ገልጸዋል። በግብጽ ውስጥ የሚኖሩ እና በተለያዩ ምክንያቶች እስር ቤት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተወያዩበት እንደሆነ አምባሳደር ታዬ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጥቃቅን በሚባሉ ጉዳዮች ለብዙ ዓመታት በፍርድም ሆነ ያለፍርድ እስር ቤት ውስጥ የቆዩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ የገለጹት አምባሳደሩ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፤ 32 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሌሊቱን ሙሉ መጓጓዣ ሰነዳቸው ሲዘጋጅ ቆይቶ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል ብለዋል። በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ ኃላፊነት የነበራቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች ሃገራቸውን ጥለው በግብጽ የተቀመጡ ዜጎች አሉ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወኑ ባሉ የተለያዩ የልማት መስኮች መሳተፍ እንፈልጋለን ያሉትም ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ወደ ኤርትራ መግባት ቀላል ሊሆን ይችላል፤ መውጣት ግን እጅግ ከባድ ነበር ያሉት" አምባሳደሩ ከብዙ ጥረት በኋላ ወደ ግብጽ መምጣታቸውን ይናገራሉ። እነዚህን ሰዎች ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ ምን ዓይነት ድርድር ተደርጎ ነበር ተብለው የተጠየቁት አምባሳደሩ፤ መንግስት ምንም አይነት ድርድር ውስጥ እንዳልገባ እና ኢትዮጵያውያኑ ራሳቸው ወደ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በመምጣት ጥያቄያቸውን እንዳቀረቡ ገልጸዋል። ግብጽ ውስጥ 6000 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩ ሲሆን አብዛኛዎቹም ሴቶች ናቸው። እነዚህ ሴቶች የተሰማሩበትም የሥራ መስክ የቤት ሠራተኝነት፤ የልጅ ተንከባካቢነት እና በሱቆች ውስጥ ተቀጥሮ መሥራት እንደሆነ አምባሳደር ታዬ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-43326929
https://www.bbc.com/amharic/news-43326929
አባቶች ወደ ሴት ልጆቻቸው የዘር ከረጢት ካንሰር የማስተላለፍ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው
የዩናይትድ ስቴትስ ሳይንቲስቶች የዘር ከረጢት ካንሰር የሚያመጣ ከአባት ወደ ሴት ልጅ የሚተላለፍ አዲስ የጅን መለወጥ ሂደት መኖሩን አረጋገጡ።
ይህ 'ኤክስ ክሮሞዞም' ከሚባለው የሚመጣ ሲሆን በተለምዶ ሴቶች በሚያደርጓቸው ምርመራዎች የማይገኝ ነው። ባለሙያዎች የጅኑን ሥራ ለማወቅ ብዙ ጥናት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። የቅርብ ጊዜ ግኝቶች 'ፒሎስ ጌኔቲክስ' የተሰኘው ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ። PLoS Genetics የቤተሰብ ችግር በአሁን ወቅት በቤተሰባቸው የካንሰር ሕመምተኞች የነበሩ ሴቶች ካሉ ቢ ሲ አር ኤ የሚባለውን የጅን ምርመራ እንዲያደርጉ የሚደረግ ሲሆን ፣ ይህ ጅን በጡትና በዘር ከረጢት ካንሰር የመያዝ ዕድላቸውን ከፍ የሚያደርግ ነው። አንጀሊና ጆሊ የተሰኘችው ታዋቂ የፊልም ተዋናይ ከእናቷ ቢአርሲኤ 1 የተሰኘውን ጅን በመውሰዷ ዶክተሮች በጡት ካንሰር የመያዝ ዕድሏ 87 እንዲሁም በዘር ከረጢት የመያዝ ዕድሏ ደግሞ 50 በመቶ መሆኑን ሲነግሯት የመከላከያ ቀዶ ሕክምና አድርጋ ነበር። ነገር ግን ተመራማሪዎች ያልታሰቡ የዘር ከረጢት ካንሰሮች በ ኤክስ ክሮሞዞም የሚተላለፉ በመሆናቸው ሴት ልጆች ከአባታቸው የሚወርሱት መሆኑን አሳውቀዋል። አንጀሊና ጆሊ የመጀመሪያ መከላከያ ቀዶ ሕክምና ያደረገች አ.አ.አ በ2013 ነበር ወንዶች አንድ ኤክስ ክሮሞዞም ወደ ሴት ልጃቸው ያስተላልፋሉ። ዶ/ር ኬቪን ኤንግ እና የሮዝዌል ፓርክ የካንሰር ኢንስቲትዩት የሥራ ባልደረቦቹ በአባቶች ኤክስ ክሮሞዞም ላይ ያገኙትንና የጠረጠሩት ጅንን ለይተው በማጥናት ኤም ኤጂ ኢሲ 3 ብለው ሰይመውታል። የዘር ከረጢት ካንሰር በእናት ጅን ከመተላለፍ ይልቅ ከአባት እና በአባት እናት ዘር በሚወረስ ጅን የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው ይላሉ። በተጨማሪም ይህ ጅን ከአባት ወደ ወንድ ልጅ የወንድ ዘር ካንሰር እንደሚያስተላልፍ ደርሰውበታል። በኒው ዮርክ ባፋሎ በሚገኘው ሮዝዌል ፓርክ የተሟላ የካንሰር ሕክምና ማዕከል የተደረገው ጥናት መሪ ኬቪን ኤንግ ''ቀጥለን ማድረግ የሚጠበቅብን ትክክለኛውን ጅን ማግኘታችንን ማረጋገጥ ነው። በመሥሪያ ቤታችን ይህ ግኝት ብዙ ውይይቶችን አስከትሏል፤ ምክንያቱም የተያያዙትን ኤክስ ክሮሞዞምን ቤተሰብ ማግኘት ያስፈልጋል'' ብለዋል። ''ሦስት ሴት ልጆች ያሉበትን ቤተሰብ ብንወስድ የዘር ከረጢት ካንሰር ሊያጠቃ የሚችለው ከቢ አር ሲ ኤ ጅን ይልቅ የኤክስ ክሮሞዞም መለዋወጥ ያለባቸውን ነው'' በማለት ተናግረዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የካንሰር ምርምር ማእከል ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ካትሪም ፒክወርት ''ይህ ጥናት አንዳንድ ሴቶች በዘር ከረጢት ካንሰር የመጠቃት ዕድላቸው ከአባታቸው የሚመጣ ሲሆን በእናትም ሊተላለፍ ይችላል።'' ብለዋል። ''ይህ ምርምር ወደፊት ይህ የዘር ከረጢት ካንሰር በቤተሰባቸው ያለባቸውን ሴቶች ሊረዳ ይችላል። ምክንያቱም የበሽታውን እድገትና ለውጥ በቅርብ መከታተል ይቻላል።የዘር ከረጢት ካንሰር ብዙ ጊዜ የሚታየው በጣም ካደገና ለማዳን ከባድ ከሆነ በኋላ ነው። አሁን ግን ብዙ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል በተለይ ችግር ያለበትን ለይቶ አጥንቶ እንዴት የዘር ከረጢት ካንሰር እንደሚያስከትል ማወቅ ይገባል።'' አንዌን ጆንስ፥ ታርጌት ኦቫሪያን ካንሰር በተሰኘው ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሲሆኑ '' እነዚህ ግኝቶች በተጨማሪ ጥናትና ምርምር መረጋገጥ አለባቸው። ይህም የዘር ከረጢት ካንሰርን የማሰወገድ ሥራው ላይ ትልቅ አስተዋጽዖ ከማድረጉም ባሻገር በሺህ የሚቆጠሩ ሴቶችን ሕይወት ሊያድን ይችላል'' ብለዋል።
news-42262187
https://www.bbc.com/amharic/news-42262187
እየሩሳሌም፡ የትራምፕን ውሳኔ ዓለም እያወገዘው ነው
በአሜሪካ አጋርነታቸው የሚታወቁት ሃገራት ጭምር የፕሬዚዳንት ትራምፕን እየሩሳሌምን በእስራኤል መዲናነት እውቅና የመስጠት ውሳኔን አውግዘውታል።
ሳዑዲ የትራምፕን ውሳኔ "ምክንያታዊ ያልሆነና ሃላፊነት የጎደለው" ስትለው ፈረንሳይና እንግሊዝ በበኩላቸው ውሳኔውን እንደማይደግፉት አስታውቀዋል። በዌስት ባንክና በጋዛ ሰርጥ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ሀሙስ ዕለት የሥራ ማቆም አድማና የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። በተቃራኒው የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታኒያሁ ውሳኔው የተላለፈበትን ቀን "ታሪካዊ እለት" ብለውታል። ዋይት ሃውስ ውስጥ ባደረጉት ንግግር እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ናት ከማለታቸው ባሻገር፤ በቴል አቪቭ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ እየሩሳሌም እንዲዘዋወር መመሪያ መስጠታቸውንም ተናግረዋል። የዚህች ከተማ እጣ ፈንታ ለዘመናት እስራኤልንና ፍልስጤምን ሲያሟግት ኖሯል።ይህ የትራምፕ እርምጃ ደግሞ በጉዳዩ ላይ ላለፉት አስርት አመታት የቆየውን የአሜሪካ ፖሊሲ የቀየረ ነው። ትራምፕ ውሳኔው የመካከለኛው ምስራቅን የሰላም ስምምነት ወደ ቀጣይ ደረጃ የሚያሻግርና የተጠና እርምጃ እንደሆነም ይገልፃሉ። እስራኤል ውሳኔውን ታሪካዊ ስትለው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግን በፅኑ ወቀሳውን እየሰነዘረ ነው። የፍልስጤሙ ፕሬዚዳንት ሙሃሙድ አባስ ደግሞ የትራምፕ ውሳኔ አሜሪካን መቼም በጉዳዩ አደራዳሪ የሚያደርጋት እንዳልሆነ ተናግረዋል። በመላው ፍልስጥኤም የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው ትራምፕ ግን አሜሪካ አሁንም በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ ከተደረሰ በአከራካሪዋ ምድር ሁለት-አገር የመፍጠር መፍትሄ በማምጣት ከእስራኤል ጎን ለጎን ፍልስጤም የምትባል አገር ልትኖር እንደምትችል ይናገራሉ። የትራምፕን ውሳኔ ተከትሎ አስራ አምስት አገራት አባል የሆኑበት የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። ምክንያቱም ይህን ውሳኔ ማስተላለፍ በጉዳዩ ላይ አሜሪካን ከሌላው ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ይለያታል።
news-54409378
https://www.bbc.com/amharic/news-54409378
ናጎርኖ-ካራባህ ግጭት፡ የአዘርባጃን ሁለተኛ ከተማ በአርሜኒያ ኃይሎች መመታቷ ተገለፀ
በናጎርኖ-ካራባህ ግዛት ይገባኛል በቀድሞ ሶቪየት ሪፐብሊክ አካል በነበሩት አዘርባጃንና አርሜኒያ መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ቀጥሎ የአዘርባጃን ሁለተኛ ከተማ የሆነችው ጋንጃ በአርሜኒያ ኃይሎች መመታቷ ተገለፀ።
የአዘርባጃን ኃይሎች የግዛቷን ዋና ከተማ ስቴፓናከርት ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ የራስ ገዝ አስተዳደሯ ባለሥልጣናት የአዘርባጃን የጋንጃን የጦር አየር ማሪፊያ መምታታቸውን አስታውቀዋል። ከሳምንት በፊት ግጭቱ ከቀሰቀሰ አንስቶ እስካሁን ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። በሁለቱም ወገን የደረሰው ጉዳት በገለልተኛ ወገን ስላልተጣራ የሟቾቹ ቁጥር ከተገለፀው በላይ ሊሆን እንደሚችል ስጋት አለ። አርሜኒያና አዘርባጃን ከ2016 ወዲህ ለተቀሰቀሰው ከባድ ግጭት እርስ በርሳቸው ይወቃቀሳሉ። የአዘርባጃን ጦር ከእሁድ ዕለት ጀምሮ ሰባት መንደሮችን እንደገና መቆጣጠሩን አስታውቋል። ናጎርኖ-ካራባህ ደግሞ ወታደሮቿ የፊት አሰላለፋቸውን ማሻሻላቸውን ተናግራለች። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አርሜኒያ በፈረንሳይ፣ ሩሲያና አሜሪካ አሸማጋይነት ተኩስ አቁም ስምምነት ምክክር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆን አስታውቃ ነበር። በቱርክ የምትደገፈው አዘርባጃን ግን የአርሜኒያ ወታደሮች ከናጎርኖ -ካራባህና ሌሎች አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ ጠይቃለች። ሁለቱ የቀድሞ የሶቭየት ሪፐብሊክ አገራት በግዛቷ ላይ ከጎርጎሮሳዊያኑ 1988-94 ድረስ ጦርነት አካሂደዋል። በኋላ ላይ የተኩስ አቁም ስምምነት ያደረጉ ቢሆንም ስምምነት ላይ ደርሰው አያውቁም። ናጎርኖ-ካራባህ ግዛት በይፋ የሚታወቀው የአዘርባጃን አካል እንደሆነ ቢሆንም፤ የሚተዳደረው ግን በአርሜኒያዊያን ነው። ስለ ናጎርኖ- ካራባክህ
news-57118264
https://www.bbc.com/amharic/news-57118264
የእስራኤልና ፍልስጥኤምን ግጭት ለማርገብ ለሚደረገው ውይይት አሜሪካ ልዑኳን ላከች
በእስራኤልና ፍልስጥኤም መካከል ያለው ግጭት ከፍ ወዳለ ጦርነት ሊያመራ ይችላል በተባለበት ወቅት ግጭቶቹን ለማርገብ ለሚደረገው ውይይት አሜሪካ ልዑኳን ልካለች።
ሃዲ አሚር ከእስራኤል፣ ከፍልስጥኤምና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከተውጣጡ ኃላፊዎች ጋር በሚደረገው ውይይት ይሳተፋሉ። ውይይቱም የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ተስፋ ተጥሎበታል። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በእስራኤልና በፍልስጥኤም ግጭት ላይ በነገው እለት የሚወያይ እንደሆነም ተጠቅሷል። በእስራኤል የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ እንዳስታወቀው የልዑኩ ጉዞ "ዘለቄታዊ ሰላም እንዲመጣ የሚሰሩ ስራዎችን ለማገዝ" እንደሆነ ቢያትትም የእስራኤልና የፍልስጥኤም ባለስልጣናት ተኩስ እንዲያቆሙ የቀረበላቸው ተማፅኖ ፍሬ አላፈራም። ዛሬ በጥዋት እስራኤል በጋዛ ላይ የአየር ጥቃት የፈፀመች ሲሆን ፍልስጥኤማውያንም በምላሹ ሮኬቶችን አስወንጭፈዋል። በባለፉት አምስት ቀናት በግጭት እየተናጠ ያለው ይህ ግዛት በባለፉት አመታት በቀጠናው ከተከሰተው የከፋ ነው ተብሏል። በምስራቅ ኢየሩሳሌም በእስራኤልና በፍልስጥኤማውያን መካከል ለሳምንታት የዘለቀው ውጥረት ወደ ግጭት ያመራው በያዝነው ሳምነት መጀመሪያ ሰኞ እለት ነው። በእስልምናና በአይሁድ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅድስት ተብላ የምትጠራው ስፍራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ መጋጋል ተፈጥሮ ነበር። ጋዛን የሚያስተዳድረው ታጣቂው ሃማስ እስራኤል ከቅድስቲቷ ስፍራ ለቃ እንድትወጣ ካስጠነቀቀ በኋላ ሮኬቶ ማስወንጨፉ ተገልጿል። እስራኤልም በምላሹ የአየር ጥቃቶችን ፈፅማለች። ግጭቱ ከተጀመረባት እለት ጀምሮ በጋዛ እስካሁን ድረስ 133 ሰዎች እንዲሁም በእስራኤል ስምንት ሰዎች ተገድለዋል። የፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት እንዳሳወቁት በዛሬው ዕለት ጥዋት እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ቢያንስ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። ጥቃቱ የደረሰው በምዕራባዊቷ ጋዛ ከተማ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ማዕከል ውስጥ ነው። የሃማስ ታጣቂዎች በምላሹ ሮኬቶችን ወደ እስራኤሏ ከተማ ቤርሼባ አስወንጭፈዋል። በትናንትናው ዕለት ግጭቶች ወደ ዌስት ባንክ ተዛምተው አስር ፍልስጥኤማውያን ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጎድተዋል።
news-55526508
https://www.bbc.com/amharic/news-55526508
ትግራይ ፡ ከውቅሮ ወጣ ብሎ በሚገኙ የእምነት ስፍራዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተገለፀ
በትግራይ ክልል ከውቅሮ ከተማ የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ወጣ ብሎ በሚገኘው ጥንታዊው የአል ነጃሺ መስጅድ እንዲሁም በአንድ ቤተክርስቲያን ላይ ጉዳት እንደደረሰ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።
አል ነጃሺ መስጂድ የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በውቅሮ አል ነጃሺ መስጂድ እና በአማኑኤል ምንጉዋ ቤተክርስትያን ላይ ጉዳት መድረሱን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ጄይላን ከድር በመስጂዱ ላይ ስለደረሰው ጉዳት መረጃ እንዳልደረሳቸውና ከሁለት ቀናት በኋላ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ረዳት ፕሮፌሰር አበባው ለቢቢሲ እንደተናገሩት የአል ነጃሺ መስጂድ ጉዳት እንደደረሰበት መስማታቸውን ገልጸው፤ መስሪያ ቤታቸውም ወደ ሥፍራው የሚሄድ ሁለት የጥናት ቡድን እንዳዘጋጀ አመልክተዋል። ይህ የጥናት ቡድን ወደ ትግራይ ወደ ስፍራው የሚሄደው በዕምነት ቤቶቹ ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን አጣርቶ ለጥገና የሚሆን መረጃ ለማሰባሰብ እንደሆነ ገልፀዋል። የእስልምና ጉዳዮች ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአካባቢው ካሉ የሐይማኖት አባቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ ስላለው ሁኔታ ለማወቅ ባለመቻሉ ስለጉዳቱ ለማረጋገጥ እንዳልቻለ ዶ/ር ጄይላን ለቢቢሲ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጄላን ለቢቢሲ እንዳሉት ይህ የአምልኮ ስፍራ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ቅርስ በመሆኑ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ የደረሰው ጉዳት ይገለፃል ሲሉ ተናግረዋል። እነዚህ የሐይማኖት ስፍራዎች ከቅርስ ባሻገር የአምልኮ ስፍራዎች ናቸው ያሉት ምክትል ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው ተጠግነው ወደ አገልግሎት መመለስ አለባቸው ሲሉ ያስረዳሉ። ወደ ትግራይ ውቅሮ የሚሄደው ቡድን ሁለት መሆኑን የሚናገሩት ምክትል ዳይሬክተሩ አንደኛው የትግራይ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮን የሚያካትት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከፌደራል መንግሥቱ ተዋቅሮ የሚሄድ ቡድን ነው። ጨምረውም ለቢቢሲ ስለጉዳዩ ሲያስረዱ ባለሙያዎች ቀደም ብሎ ሊሄዱ አስበው አለመሳካቱን በመግለጽ፣ አሁን ግን የባሕል ሚኒስትሯ የሚያዋቅሩት ቡድን መኖሩንና ከቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ከሚያዋቀረው ቡድን ጋር በመሆን ወደ ሥፍራው በማቅናት አል ነጃሺ መስጂድን እንዲሁም ሌሎች ስፍራዎችን ተመልክቶ እንደሚመጣ ተናግረዋል። እንደ ረዳት ፕሮፌሰር አበባው ከሆነ በውቅሮ አል ነጃሺ መስጂድ ላይ ብቻ ሳይሆን አማኑኤል ምንጉዋ የተባለ ቤተክርስቲያንም በተመሳሳይ መንገድ ጉዳት እንደደረሰበት መስማታቸውን ገልፀው፤ መጀመሪያ በውቅሮ አካባቢ ባሉት እነዚህ የእምነት ተቋማትና ቅርሶች ላይ የደረሰውን ጉዳት ተመልክቶና አጣርቶ የሚመጣ ቡድን እንደሚላክ አሳውቀዋል። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከወጡት ፎቶዎች መካከል ሁለተኛው ቡድን ደግሞ በስፍራዎቹ ስላሉ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ባለው መረጃ መሠረት፣ በቦታቸው አሉ ወይስ የሉም የሚለውን መረጃ ለማጣራት እንደሚላክም ገልፀዋል። "በእንዲህ አይነት ግጭት ወቅት ከቋሚ ቅርሶች በበለጠ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ላይ ጉዳት ይደርሳል" ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ እነዚህን ቅርሶች አጣርቶ የሚመጣ ቡድን እንደሚላክ አረጋግጠዋል። የመጀመሪያው ቡድን ወደ አካባቢው የሚሄደው ጥር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። ብሔራዊው ቴሌቪዥን ኢቲቪ ሰኞ ምሽት በነጃሺ መስጂድና በአቅራቢያው በሚገኘው አማኑኤል ቤተክርስቲያን ላይ ስለደረሰው ጉዳት የአካባቢውን ነዋሪዎች በማናገር ባቀረበው ዘገባ የህወሓት ኃይሎች በስፍራው ምሽግ መስራታቸውንና ለደረሰው ጉዳት ምክንያት መሆናቸውን አመልክቷል። በትግራይ ክልል የተካሄደውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በአብዛኛው የክልሉ አካባቢ ለረጅም ጊዜ መረጃ ለማግኘት አዳጋች ሆኖ የቆየ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ታሪካዊው የአል ነጃሺ መስጂድ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት የሚያሳዩ ፎቶግራፎች በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ በስፋት ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። በዚህ ዙሪያ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርም ሆነ ፌደራል መንግሥቱ እስካሁን በይፋ ያሉት ነገር የሌለ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በጉዳዩ ላይ መግለጫ አውጥተዋል። ኢዜማ ባወጣው መግለጫ በአል ነጃሺ መስጂድ ላይ የደረሰው ጥቃት በገለልተኛ አካላት በፍጥነት እንዲጣራና ጥንታዊ ቅርስነቱን ሳይለቅ ወደነበረበት ሁኔታ በፍጥነት እንዲመለስ ጥሪ አቅርቧል። አብንም በበኩሉ አል ነጃሺ መስጅድ ላይ የደረሰው ጥቃት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በገለልተኛ መልኩ በጥልቀት መመርመር እንዳለበትና እንዲጣራ ጠይቋል። ከትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለ በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ጥንታዊው የአል ነጃሺ መስጂድ ከሁለት ዓመት በፊት በቱርክ መንግሥት ድጋፍ ጥገና ተደርጎለት እነደነበር ይታወሳል። በ4 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው አል ነጃሺ መስጂድ ዋነኛ የፀሎት ቦታ እና ሁለት የቀብር ስፍራን መያዙ ይነገራል። ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም ከባሕር ማዶ ስፍራውን ለማየት፣ መውሊድንና ረመዳንን ለማክበር የሚመጡ ሰዎችን ለማሳረፍ በማሰብ ማረፊያ ክፍሎችም ተገንብተዋል።
news-52893029
https://www.bbc.com/amharic/news-52893029
ታዋቂው ቦክሰኛ ሜይዌዘር ለጆርጅ ፍሎይድ የሐዘን ሥነ ሥርዓት ወጪን እሸፍናለሁ አለ
ታዋቂው የዓለም ቦክስ ሻምፒዮን ፍሎይድ ሜይዌዘር በቅርቡ በነጭ ፖሊስ የተገደለውን የጆርጅ ፍሎይድን የሐዘን ሥነ ሥርዓት ወጪውን ሙሉ በሙሉ እንደሚሸፍን አስታውቋል።
በሚኒያፖሊስ ከሚገኝ መደብር ውጪ በፖሊስ ህይወቱ ያለፈው ጆርጅ ፍሎይድ፤ ነጭ ፖሊስ አንገቱን መሬት ላይ አጣብቆ ለአስር ደቂቃ ያህል በመንበርከኩ ትንፋሽ አጥሮት ህይወቱ አልፏል። አሟሟቱንም ተከትሎ የፖሊስ ጭካኔን የሚያወግዙ ቁጣዎችና ተቃውሞች ተቀጣጥለው በአገሪቱ ቀጥለዋል። አንገቱን በጉልበቱ መሬት ላይ በማጣበቅ ያነቀው ነጩ ፖሊስ፣ ዴሪክ ቾቪንም በግድያ ወንጀል በቁጥጥር ስር ውሏል። በርካታ የአሜሪካ ሚዲያዎችም እንደዘገቡት የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰቦችም የቦክሰኛውን ችሮታም በፀጋ ተቀብለዋል ተብሏል። በሁኔታው ልቡ እንደተሰበረ የተገለፀው የ43 አመቱ ቦክሰኛ በጆርጅ ትውልድ ቦታ ሂውስተን እንዲሁም ሚኒሶታና ቻርሎት ለሚደረጉ የኃዘን ስርአቶች ወጪውን ይሸፍናል ተብሏል። የጆርጅ ቤተሰቦች አራተኛ የኃዘን ስነ ስርአት ለማድረግ መፈለጋቸውን መግለፃቸውን ተከትሎም ከሶስቱ በተጨማሪ አራተኛውንም እሸፍናለሁ ማለቱን ሆሊውድ አንሎክድ ዘግቧል። "ይህንን በመናገሬ ሜይዌዘር ብዙ ደስተኛ ላይሆን ይችላል ነገር ግን ለሚደረጉት የሐዘን ስርአቶች በሙሉ ወጪያቸውን ይሸፍናል" ማለቱን ኢኤስፒኤን የፍሎይድ ሜይዌዘር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። አክሎም "ፍሎይድ ለባለፉት ሃያ አመታት እንዲህ አይነት ተግባራትን ሲፈፅም ነበር" ብሏል።
41159589
https://www.bbc.com/amharic/41159589
የበርማ ሙስሊሞች ጩኸት!
ከምያንማር ወይም በቀድሞ አጠራሯ በርማ ተሰደው ወደ ባንግላዲሽ የሚገቡ የሮሂንጃ ሙስሊሞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነው። እንደ ተባባሩት መንግስታት መግለጫ ከሆነ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ወደ 35 ሺህ የሚሆኑ በርማውያን ሙስሊሞች ወደ ባንግላዲሽ ገብተዋል።
እ.አ.አ. ከነሃሴ 25 ጀምሮ ባለው ጊሴ ውስጥ ብቻ ወደ 123 ሺህ የሚሆኑ የሮሂንጃ ምሰሊሞች በርማ ሸሽተው መሰደዳቸው ተነግሯል። የሮሂንጃ ታጣቂዎች በምያንማር ፖሊሶች ላይ በከፈቱት ተኩስ ምክንያት የተቀሰቀሰው ግጭት የሮሂንጃ ሙስሊሞች ቀየአዘውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል። የሮሂንጃ ሙስሊሞች ሀገር አልባ አናሳ የሕብረተሰብ ክፍሎች ሲሆኑ ከምያንማር ቡድሂስቶች ጭፍጨፋ እና ግድያ እየደረሰባቸው ነው። ሮሂንጃዎችን ከሀገራቸው ጠራርገው ለማስወጣት በሚል የምወያንማር ጦር የሮሂንጃ ምሰሊሞችን ቤት እያቃጠለ እና ሰውም እየገደለ እንደሚገኝ ተዘግቧል። የምያንማር ጦር እየተዋጋሁ ያለሁት የሮሂንጃ ነፃ አውጪዎችን ነው በማለት ጉዳዩን መፈፀሙን ይክዳል። ጉዳዩን በገለልተኛነት ለማጣራት ወደ ቦታው መግባት ከሚያመጣው አደጋ አንፃር እጅጉን ከባድ ነው። ነገር ግን ወደ ባንግላዲሽ ዕቃቸውን ጠቅልለው ወደባንግላዲሽ የሚገቡ የሮሂንጃ ሞስሊሞች ቁጥር እጅጉን አሻቅቧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምግብ እና መጠለያ የሚያሻቸው የሮሂንጃ ምሰሊሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመሩ ጉዳዩ ኣሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል። ድርጅቱ ስደተኞቹን ለመቀበል ያዘጋጃቸው ሁለት መጠለያዎች መሙላታቸውን አስውቋል። የተቀሩት ሰዎች ውጭ ላይ እነዲሁም መንገድ ዳር እየተኙ ይገኛሉ። "ግድያው ሲጀመር ወደ ተራራው ሮጠን ወጣን። ከዛም ጦሩ ቤታቸንን አቃጠለብን" ሲል ለሬውተርስ ዜና ወኪል የተናገረው በግብርና ስራ ይተዳደር የነበረው የሮሂንጃ ሙስሊሙ ሳሊህ ኡላህ ነው። "እናቴን፥ ሚስቴን እና ሁለት ልጆቼን ይዤ ከሌሎች አራባ ሰዎች ጋር በጀልባ ተሳፍሬ ወደዚህ ተሰደድኩ። ጀልባው ውስጥ 25 ሴቶች እንደነበሩ ትዝ ይለኛል' በማለት ያክላል ሳሊህ። የተባበሩት መንግስታት መረጃ እንደሚጠቁመው አሁንም ግጭቱ ረካይን በተሰኘችውና የሮሂንጃ ሙስሊሞች በሚበዙባት ቦታ ቀጥሏል። በባንግላዲሽ ወደብ አካባቢ እንኳን 15 የሚሆኑ የቃጠሎ ጭሶች እንደታዩ ዘገባው ይጠቁማል። በሌላ በኩል ደግሞ በመልሱ ማጥቃት ድርጊት የተሰማሩት የሮሂንጃ ነፃ አውጪዎች የበርማ ቡዲሂስቶችእ እየገደሉ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል። ለቢቢሲ በርማ አገልግሎት ድምጿን የሰጠች አንዲት ግለሰብ እንደተናገረችው ነፃ አውጪዎቹ በጎራዴ ሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ ናቸው። በጉዳዩ ላይ እስላማዊ ሀገራት ያሳዩት ቸልተኝት ለትችት ዳርጓቸዋል። እርግጥ ዘግይቶም ቢሆን ኢንዶኔዢያ በጉዳዩ ላይ ድምጿን በማሰማት ቀዳሚ ሆናለች። ፓኪስታን እና ማሌዢያም ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው አሳውቀዋል። ማልዲቭ ደግሞ ከምያንማር ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቃለች። የቱርክ ፕሬዝደንት ጣይብ ኤርዶዋን በበኩላቸው የበርማዋ መሪ ኣውንግ ሳን ሱ ኪ ለግጭቱ መፍትሄ እንዲያበጁ አሳስበዋል። ሰኞ ዕለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ባለስልጣን የሮሂንጃ ሙስሊሞች ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል። ለዲሞክራሲ በመታገል የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የሆኑት የበርማ መሪ ኣውንግ ሳን ሱ ኪ ስለጉዳዩ አስተያየት እንደሚሰጡም ይጠበቃል። መሪዋ የምያንማር ጦር እየፈፀመ ያለው ግፍን ማስቆም እንዳለባቸው እየተነገረ ቢሆንም የሮሂንጃ ሙስሊሞች ከሀገራቸው እንዲወጡ ከሚፈልጉት በርማውያን እና ከጦሩ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊገጥማቸው እንደሚችልም እየተነገረ ነው። ባለፈው ወር የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ 43 ሺህ የሚሆኑ የሮሂንጃ ሙስሊም ስደተኞችን ህገ-ወጥ በመሆናቸው ምክንያት ከሀገራቸው ለማስወጣት ማቀዳቸውን ይታወሳል። ምያንማር የሮሂንጃ ሙስሊሞችን እንደዜጋ አትቀበላቸውም። በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ስደተኞቸው መጠለያ የሰጠችው ባንግላዲሽም ተመሳሳይ አቋም ይዛለች። በዚህ ሁኔታ የሮሂንጃ ሙስሊሞች ሀገር አልባ ሆነው በስደት እና ስቃይ ላይ ይገኛሉ።
51217775
https://www.bbc.com/amharic/51217775
የኬንያ ጦር በሽብር ጥቃት ጊዜ 'ወታደሮቹ ሳር ውስጥ ተደብቀው ነበር' መባሉን አጣጣለ
የኬንያ ጦር 'ኒው ዮርክ ታይምስ' ኢስላማዊ ታጣቂ ቡድን አልሸባብ የማንዳ ቤይ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ሲፈፅም ወታደሮቹ ሳር ውስጥ ተደብቀው ነበር ሲል የፃፈውን ሪፖርት አጣጣለ።
ማንዳ ቤይ ካምፕ የኬንያና የአሜሪካ ጦር ኃይል ፀረ ሽብር ሥልጠናና 'ኦፕሬሽን' ለማካሄድ ይጠቀሙበታል • በላሙ ሶስት አሜሪካውያን ከተገደሉ በኋላ የሰዓት እላፊ ታወጀ • በአልሸባብ ጥቃት ሶስት አሜሪካውያን ተገደሉ የኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ እንደሚያትተው በወቅቱ የኬንያ ወታደሮች ሁኔታ ባልደረቦቻቸው የሆኑትን የአሜሪካ ወታደሮች አስፈርቷቸው ነበር። ጋዜጣው አክሎም የአልሻባብ ታጣቂዎች በካምፑ በነበሩ ኬንያውያን የተሰጣቸው መረጃ ሳይጠቀሙ እንዳልቀረም ገልጿል። ይሁን እንጅ የኬንያ ጦር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ፖል ንጁጉና፤ የተፈፀመው የሽብር ጥቃት ዝርዝር መረጃ ይህንኑ ለማጣራት የተሰማራው ቡድን የሚያመጣቸው ውጤቶች ሲታወቁ ግልፅ ይሆናል ብለዋል። "የጋዜጣው ዘገባ ከምን እንደተነሳና የምርመራ ውጤቱ እስከሚጠናቀቅ እየጠበቅን ባለንበት ሰዓት መውጣቱ እንግዳ ነው፤ ምን እንደተፈጠረ ትክክለኛና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ሪፖርት የሚኖረን ምርመራው ሲጠናቀቅ ነው" ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ዘ ደይሊ ኔሽን የተሰኘው ጋዜጣም "ካምፕ ሲምባ በኬንያ ምድር ላይ አሜሪካ የደህንነት ኦፕሬሽን የምትሰራበት ቦታ ነው" ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የጦሩን ባለሥልጣን ጠቅሶ ዘግቧል። የጦሩ ባለሥልጣን እንደተናገሩት "በካምፑ ውስጥ የሆነው ነገር ምስጢራዊ ነው፤ እስካሁን አሜሪካዊያን ጥቃቱ በተፈፀመበት ጊዜ በርካታ ሠራተኞቻቸው መገኘታቸውን በተመለከተ ዝምታን መርጠዋል። በካምፑ ላይ ትዕይንቱን ሲያካሂዱ የነበሩት ራሳቸው ናቸው" ሲሉ ጣታቸውን ወደ እነርሱ ቀስረዋል። ካምፕ ሲምባ በኬንያ የባህር ዳርቻ ከተማ ላሙ የሚገኝ ሲሆን የኬንያና የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይሎች ይጠቀሙበታል። ባለፈው የፈረንጆቹ ጥር 5 በተፈፀመው ጥቃት አንድ የአሜሪካ ጦር አባል እና ሁለት ኮንትራክተሮች መገደላቸው ይታወሳል። የኬኒያዋ ላሙ የባህር ዳርቻ ለሶማሊያ ድንበር ቅርብ ነች። • በአሜሪካ ወታደራዊ ካምፕ ላይ አልሻባብ ጥቃት መሰንዘሩ ተነገረ
news-52796609
https://www.bbc.com/amharic/news-52796609
በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ ያለባት እናት ከበሽታው ነጻ የሆነ ልጅ ወለድች
የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ህክምና እያገኙ ባሉበት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በኮሮናቫይረስ መያዟ የተረጋገጠች እናት ከኮቪድ-19 ነጻ የሆነ ልጅ መገላገሏን የጤና ሚንስቴር አስታወቀ።
የኮሮናቫይረስ በላብራቶሪ ምርምራ ተገኝቶባት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የለይቶ ህክምና ማዕከል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት የምትገኝ የ34 ዓመት እናት አርብ ግንቦት 14 ቀን ወንድ ልጅ በቀዶ ህክምና በሰላም መገላገሏ ተገልጿል። ከህጻኑ የተወሰደው ናሙናም ጨቅላው ከቫይረሱ ነጻ መሆኑን አረጋግጧል ብሏል የጤና ሚንሰቴር። ሚንስቴሩ እናቲቱ ከቫይረሱ ነጻ የሆነ ወንድ ልጀ በሰላም የመገላገሏ ዜና መስማት ተስፋ ሰጪ ነው ብሎታል። እናቲቱ ልጇን በሰላም እንድትገላገል ለረዱ የህክምና ባለሙያዎች ጤና ሚንስቴር ምስጋናውን አቅርቧል። እስካሁን ባለው መረጃ ኮቪድ-19 በእርግዝና፣ በምጥ ወይም ከምጥ በኋላ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ እድል አነስተኛ ቢሆንም፤ ከዚህ ቀደም ቫይረሱ ከሚገኘባቸው እናቶች የተወለዱ ህጻናት በቫይረሱ ተይዘው ተገኝተዋል ብሏል ጤና ሚንስቴር በፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ። "ከወሊድ በኋላ በጡት ማጥባት ወቅት እና ዘወትር በሚኖር ንክኪ ቫይረሱ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ስለሆነ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይመከራል። እነዚህም ጥንቃቄዎች ጡት ከማጥባት ወይም ማንኛውም ንክኪ ከማደረግዎ በፊት እና በኋላ እጅዎትን በሳሙና እና በውሃ መታጠብ፣ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣ የሚኖሩበትን ክፍል በቂ አየር እንዲኖረው እና እንዲናፈስ ማድረግ እንደሚገባ አሳስቧል። በተጨማሪም ወላጆች ለክትባት የሚኖራቸውን ቀጠሮ በአግባቡ መከታተል፣ በቂ የፀሐይ ብርሀን እንዲያገኙ ማድረግ፣ የተለያዩ በሽታዎች ምልክትን ማወቅ እና የህጻናትን ጤና ማስተዋል ይኖርባቸዋል ብሏል።
48973751
https://www.bbc.com/amharic/48973751
በክረምት ሲዘንብ የመሬት ሽታ ለምን ያስደስተናል?
ክረምትም አይደል? አገሪቱ በዝናብ ርሳለች። ለመሆኑ ዝናብ ሲጥል ያለው ሽታ ለምን ደስ እንደሚልዎ ያውቃሉ?
ለወራት ዝናብ አጥቶ የደረቀ መሬት በዝናብ ሲርስ ደስ የሚለንና ሽታው የሚያውደን ያለምክንያት አይደለም። ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ ባክቴሪያ፣ እፅዋትና ብርሀን ተደማምረው ዝናብ ሲጥል ደስ የሚል ሽታ እንዲፈጠር ያደርጋሉ። • ደስታን አጥብቀን ስለፈለግን ለምን አናገኘውም? ዝናብ ሲጥል ያለው አስደሳች መአዛ 'ፐትሪኮር' ይባላል። ሽታው ዘለግ ላለ ጊዜ ይቆያል። ይህም የተመራማሪዎችና የሽቶ አምራቾችንም ቀልብ ገዝቷል። 'ፐትሪኮር' የሚለውን ስም ያወጡት ሁለት አውስትራሊያውያን ተመራማሪዎች ናቸው። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1960ዎቹ ገደማ። ባክቴሪያ ዝናብ ደረቅ መሬት ሲነካ የሚፈጠረው ሽታ ምክንያቱ ባክቴሪያ ነው። ፕሮፌሰር ማርክ በተር እንደሚሉት፤ ዝናብ ሲዘንብ ብዙዎች በተለምዶ "መሬቱ ሸተተኝ" የሚሉት ባክቴሪያ ሞለኪውል ሲሠራ ያለውን ጠረን ነው። • የዓለማችን 'ጭንቀታም' እና 'ደስተኛ' ሃገራት ደረጃ ይፋ ሆነ ይህ ሞለኪውል (ጂኦዝሚን) ጤናማ አፈር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ ጸረ ባክቴሪያ (አንቲባዮቲክ) ለመሥራትም ያገለግላል። ጠብታ ውሀ መሬት ሲነካ ጂኦዝሚን አየር ውስጥ ይለቀቃል። ዝናብ ሲዘንብ ደግሞ የሽታው መጠን ይንራል። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት ሰዎች በቀላሉ ሽታው ያውዳቸዋል። በ1960ዎቹ ሕንድ ውስጥ እጣን ለመሸጥ ይህ ሽታ ጥቅም ላይ ይውል ነበር። አሁንም ሽቶ አምራቾች ከጂኦዝሚን ሽቶ ይሠራሉ። ሽቶ አምራቿ ማሪና ባርሴኒላ "ዝናብ ደረቅ መሬትን ሲነካ ያለው ሽታ ድንቅ ሽቶ ይወጣዋል፤ ከብዙ ንጥረ ነገር ጋር ቢዋሀድ እንኳን ሰዎች ሽታውን ይለዩታል" ትላለች። • ፍየሎችም «ከፍትፍቱ ፊቱ» ይሉ ይሆን? 'ፐትሪኮር' በግሪክ ቋንቋ በአማልክት የደም ሥር የሚዘዋወር ፈሳሽ የሚል ትርጓሜ አለው። እፅዋት ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ የእፅዋት መአዛ ከጂኦዝሚን የሚመነጭ ሊሆን ይችላል። ዝናብ ሲዘንብም ሽታው ጎልቶ ይወጣል። ፕሮፌሰር ፊሊፕ ስቴቨንሰን የተባሉ ተመራማሪ እንደሚሉት፤ እፅዋት ጥሩ ሽታ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ንጥረ ነገር የሚመነጨው በእፅዋት ቅጠል ውስጥ ነው። ዝናብ ይህንን ንጥረ ነገር የሚያጠፋበት እድል እንዳለ ሁሉ፤ የደረቁ እፅዋትን አርሶ ኬሚካል እንዲያመነጩ ያደርጋል። ዝናብ ሲጠፋ የእፅዋት ሜታቦሊዝም ይጓተታል። ሲዘንብ ሂደቱ ይታደስና እፅዋቱ አስደሳች ሽታ ይፈጥራሉ። ብርሀን በዝናብ ወቅት የሚከሰት መብረቅ፤ ልዩ ሽታ እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል። ከመብረቁ የሚወጣው ብርሀን የሚፈጥረው ንጥረ ነገር አየር ውስጥ ሲሰራጭ የሰው ልጆችን የሚያስደስት ሽታ ይፈጥራል። ፕሮፌሰር ማርቢት ስቶልዝበርግ፤ መብረቅ፣ ከመብረቅ የሚፈጠረው ብርሀንና ዝናቡ በጋራ የአየሩን ሽታ ይለውጡታል። አቧራ ተወግዶም በንጹህ አየር ይተካል። እንግዲህ ተመራማሪዎች ዝናብ ሲዘንብ የሚፈጠረው ሽታ የሚያስደስታችሁ በባክቴሪያ፣ በእፅዋትና በብርሀን ምክንያት ነው ብለዋል። ይህን መረጃ ካገኙ በኋላ ክረምትን በተለየ ሁኔታ ያጣጥሙት ይሆን. . .
47465735
https://www.bbc.com/amharic/47465735
360 ብር ለአንድ ሕጻን
ህሊና ጸጋዬ የአዲስ አበባ ነዋሪ ስትሆን ባንክ ቤት ተቀጥራ ነው የምትሠራው። የምትኖረው ደግሞ ከቤተሰቦቿ ጋር እንደሆነ ትናገራለች። በሜሪጆይ ''ስፖንሰርሺፕ'' ፕሮግራም ላይ የምትሳተፍ ሲሆን በየወሩ 360 ብር ድጎማ በማድረግ አንዲት የአራት ዓመት ሕጻንና እናቷን ትረዳለች።
ከልጅነቴ ጀምሮ ማኅበረሰባዊ ግዴታዬን የመወጣት ፍላጎት ቢኖረኝም ትምህርቴን ጨርሼ ሥራ እስክይዝ ድረስ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር ትላለች። ''በአጋጣሚ አብሮኝ ሥራ የሚሠራ ጓደኛዬ በፕሮግራሙ እንደሚሳተፍ ነገረኝና ስልክ ተቀብዬ ሙሉ መረጃ ማግኘት ቻልኩ። አሁን ሌላው ቢቀር የአንዲት ሕጻን ሕይወት ላይ አስተዋጽኦ እያደረግኩ ነው።'' • በህክምና ስህተት የመከነው ህፃን • በጾታ እኩልነት የሚያምኑ ወንዶች የትኞቹ ናቸው. . .? በመጀመሪያ አንድ ልጅ አምጥታ ለመርዳት ብታስብም ስለፕሮግራሙ ከሰማች በኋላ ግን ሐሳቧን ቀይራ ሕጻኗን ከወላጅ እናቷ ሳትነጥል ለመርዳት እንደወሰነች ትናገራለች። በዓላትን ጠብቃም ይሁን በሌላ ጊዜ ሕጻኗንና ቤተሰቧን እንደምትጎበኝና በቤቱ ውስጥ ሌሎች ሕጻናትም ስላሉ የቻለችውን ያክል እርዳታ እንደምታደርግላቸው ነግራናለች። ''እንደውም አንዳንድ ጊዜ ወደ ቤታቸው ስሄድ ሕጻኗ እኔን መለየት ጀምራለች። ታጫውተኛለች፤ ልሄድ ስል አትሄጂም ብላ ታስቸግራለች፤ አንዳንዴም እስከ በር ድረስ ትሸኘኛለች።'' የሜሪጆይ ውጥን በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2005 ዓ.ም ሜሪጆይ 10ኛ የምሥረታ በዓሉን ሲያከብር ነበር ''ፐብሊክ ፕራይቬት ፓርትነርሺፕ'' የሚባል ፕሮግራም ያስተዋወቀው። በሥሩ ከያዛቸው ፕሮግራሞች መካከል ዋንኛው ደግሞ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ከችግረኛ ቤተሰብ ለተገኙ ሕጻናት በበጎ ፈቃድ እጃቸውን የሚዘረጉበት መርሐግብር ነው። በዚህ ሂደት በጎ ፈቃደኞች የችግረኛ ልጆችን ወጪ በየወሩ ይጋራሉ። ይህም ''ስፖንሰርሺፕ'' በመባል ይታወቃል። ፕሮግራሙ ከተዋወቀበት ጊዜ ጀምሮም ወላጆቻቸውን ያጡና ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ እስከ 2000 የሚደርሱ ሕጻናት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን፤ ከ700 በላይ ድርጅቶችና ግለሰቦች ደግሞ ተሳታፊዎች ናቸው፤ በሜሪጆይ ከፍተኛ ፕሮግራም ኦፊሰር የሆኑት አቶ ወንድወሰን መሰለ እንደገለጹት። አንድ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ለአንድ ሕጻን ድጋፍ አደርጋለው ብሎ የስፖንሰርሺፕ ፕሮግራሙ አካል መሆን ከፈለገ በየወሩ 360 ብር ብቻ መክፈል በቂ ነው። 350 ብር ምን ምን ይሸፍናል? 350 ብር በጣም ትንሽ ሊመስል ይችላል የሚሉት አቶ ወንድወሰን ፕሮግራሙን ሲጀምርም ከዛ ባነሰ የነበረ ሲሆን መጀመሪያ 140 ብር በመቀጠል 280 ብር እና በመጨረሻም 360 ብር ሆኗል። ወርሃዊ መዋጮው ይህን ያክል ያነሰበት ምክንያት በአገሪቱ ያለውን የኑሮ ውድነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ይላሉ አቶ ወንደወሰን። ''360 ብሩም የተጠቃሚዎቹን ችግር በዘላቂነት እንደማይፈታ እናውቃለን፤ ነገር ግን ዋናው ትኩረታችን በሕጻናቱና በተረጂዎቻቸው መካከል ቅርርብ መፍጠርና እንዲተዋወቁ ማድረግ ነው።'' • አራት ህጻናትን በአንዴ ያገኘው ቤተሰብ ተጨንቋል • ምግብ ማብሰልና ማጽዳት የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለመቀነስ ከዚህ ምክንያት በተጨማሪ ወላጆቻቸውን አጥተው ከዘመድ ወይም ጎረቤት አልያም ከችግረኛ ወላጆቻቸው ጋር የሚኖሩት ሕጻናት ድጋፉ ከመጀመሩ በፊት ኑሯቸውን የሚመሩበት የራሳቸው የሆነ መንገድ ስላላቸው፤ ሙሉ በሙሉ የተረጂነት ስሜት ውስጥ እንዲገቡ አይፈለግም። አብዛኛዎቹ ቤተሰቦችና ሕጻናት የዕለት ጉርሳቸውን ለማግኘት የሚፍጨረጨሩና አርፈው የማይቀመጡ ሰዎች በመሆናቸው፤ ይህን የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ስሜታቸውን አዳክመን እርዳታ ጠባቂ እንዳይሆኑ የምንቆጣጠርበትም መንገድ ነው ብለዋል አቶ ወንደወሰን። ድጋፍ ሰጪዎቹ በየወሩ ከሚያደርጉት የ360 ብር ድጋፍ በተጨማሪ በዓላትን ምክንያት በማድረግና የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም አልባሳት መግዛትና የትምህርት መሣሪያዎችን በስጦታ መልክ መስጠት አይነት ድጋፎችን ያደርጉላቸዋል። ''እነዚህን ነገሮች ሁሉ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንጂ 360 ብር በቂ እንዳልሆነ በደንብ እናውቃለን።'' ህሊና በአቶ ወንድወሰን ሐሳብ ትስማማለች። እሷ እንደምትለው 360 ብር ለአንድ ሰው ቀላል ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ሕጻናቱ ሌላው ቢቀር የሚበሉት ምግብ በትክክል ማግኘት ከቻሉና የትምህርት ቤት ወጪያቸው ከተሸፈነ ቀሪውን እራሳቸውና ቤተሰባቸው ተፍጨርጭረው ይሞሉታል ባይ ናት። ከዚህ በተጨማሪ የገንዘቡ አነስተኛ መሆን አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በአቅሙ ብዙ ሕጻናትን በያሉበት እንዲረዳ ዕድል ለመፍጠርም አልሟል። "ምናልባት የልጆቹን ሁሉንም ዓይነት ፍላጎት ለማሟላት በሚል ገንዘቡ ከፍ ቢል፤ ብዙ ሰዎች መርዳት እየፈለጉ ጀምሬ ከማቋርጠው እያሉ ሊተዉት ይችላል" ትላለች። ገንዘቡ ትንሽ ነው ብለው የሚያስቡም ካሉ ተጨማሪ ልጆችን መርዳት የሚችሉበት ወይም ደግሞ ከወርሃዊ ድጋፉ በተጨማሪ ለልጆቹ ብዙ ነገር ማድረግና ቤተሰቡንም ከመደገፍ የሚከለክላቸው እንደሌለም ትናገራለች። የግለሰብ 'ስፖንሰሮች' ቁጥር ለምን አነሰ? የመርሐ ግብሩ አስተባባሪ እንደሚሉት ብዙውን ጊዜ 100 እና ከዛ በላይ ሕጻናት በየወሩ የሚረዱት ትልልቅ ድርጅቶች ናቸው። ፕሮግራሙ ሲጀመር ጀመሮ የነበሩ ስፖንሰሮች ከጊዜ ብዛት ድጋፋቸውን እያቆሙ መጥተዋል። ከእነዚህ ድርጅቶች መካከል አንዱ ደግሞ ዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ይገኝበታል። የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ ትህትና ሙሉሸዋ እንደሚሉት በዚሁ ፕሮግራም ስር ላለፉት ሰባት ወራት አስር ችግረኛ ህጻናትን ከቤተሰባቸው ሳይርቁ እርዳታ እያደረገ እንደሆነ ይናገራሉ። • የአከርካሪ ቀዶ ጥገና ባልተወለዱ ልጆች ላይ • መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች ሌሎች ድርጅቶችም በመሰል ተግባራት ቢሰማሩ ብዙ ተስፋ ያላቸውና ተተኪ ሕጻናትን በሌሉበት መርዳት ይቻላል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። አቶ ወንድወሰን ለቁጥሩ ትንሽ መሆን ያነሱት ዋንኛ ምክንያት ግን ከሰው ኃይል እጥረትና አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ መድረስ አለመቻላቸውን ነው። በተለይ ደግሞ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎችን እንዲሁም የመንግሥትና የግል ድርጅቶችን ለመድረስ ሰፊ የሆነ የሰው ኃይልና የማስተዋወቅ ሥራ እንደሚጠይቅም አልደበቁም። እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ እንዳንደርስ አድርጎን ነው እንጂ ብዙ መርዳት የሚፈልጉ ዜጎች እንዳሉ እናውቃለን በማለት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
news-55103341
https://www.bbc.com/amharic/news-55103341
በኬንያ ሐሰተኛ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ያቀረቡ መንገደኞች ታሰሩ
ከኬንያ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሊጓዙ ከነበሩ መንገደኞች መካከል 21ዱ ሐሰተኛ የኮቪድ-19 ምርመራ መረጃ ማቅረባቸውን ተከትሎ ለእስር መዳረጋቸው ተገልጿል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከዚህ ቀደምም ከኬንያ የሚገቡ መንገደኞች ሐሰተኛ የኮቪድ-19 መረጃ አቅርበዋል በሚል የቪዛ እገዳ ጥላለች። ተጠርጣሪዎቹ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በተወሰነ መልኩ መቀነስ አሳይቶ የነበረው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለሁለተኛ ዙር ማገርሸቱን ተከትሎ ኬንያ በርካታ ሕዝብ የሚሰባሰብባቸው ሁነቶች ላይ ገደብ ጥላለች። በሳምንቱ መጀመሪያ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሊቢያ፣ ቱኒዝያና አልጀሪያን ጨምሮ 13 አገራት ላይ የቪዛ እገዳ ጥላለች። በትናንትናው ዕለት፣ ኅዳር 17/ 2013 ዓ.ም በቁጥጥር ስር የዋሉት 21 መንገደኞች መነሻቸውን ከኬንያዋ መዲና ናይሮቢ አድርገው ወደ ዱባይ ለመሄድ ሲሉ የተያዙትም በኬንያ አየር ማረፊያ ነው። የተያዙት ሐሰተኛ የህክምና ማስረጃ ከኮቪድ- 19 ነፃ መሆናቸውን ያሳያል። በቅርቡም በተመሳሳይ ከኬንያ ወደ ዱባይ ከበረሩ መንገደኞች መካከል 100 የሚሆኑ ኬንያውያን ሐሰተኛ መረጃ ይዘው የነበሩ ሲሆን አየር ማረፊያው ላይ በተደረገላቸውም ምርመራ ግማሹ ቫይረሱ እንደተገኘባቸውም ናይሮቢ ኒውስ የተባለው የኬንያ ድረ ገፅ ዘግቧል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮም ኬንያ 80 ሺህ 102 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን 1 ሺህ 427 ግለሰቦችም በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል። በትናንትናው ዕለት ተጨማሪ 780 ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን ይህንን ተከትሎም በርካታ ሰዎች በሚታደሙባቸው ሥነ ሥርቶች ላይ አዲስ እገዳ ወጥቷል። በሠርግ ላይ መገኘት የሚችሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 50 የቀነሰ ሲሆን በቀብር ላይም 100 ሰዎች ብቻ እንዲታደሙ ታዟል። አብያተ ክርስቲያናትም የአገልግሎት ሰዓታቸውን ወደ 90 ደቂቃ እንዲቀንሱ ተደርገዋል።
news-51424992
https://www.bbc.com/amharic/news-51424992
"ጠባቂዎቼ ከእኔ ጋር ይቆያሉ" ጃዋር ሞሐመድ
በመንግሥት ተመድበው ለረጅም ጊዜ ለጃዋር ሞሐመድ ጥበቃ ሲያደርጉ የነበሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት በእራሳቸው ፈቃድ ከእርሱ ጋር ለመቆየት መወሰናቸው ተነገረ።
በቅርቡ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) በመቀላቀል ከመብት ተሟጋችነት ወደ ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የገባው ጃዋር ሞሐመድ ለቢቢሲ እንደተናገረው መንግሥት የመደባቸውን ጠባቂዎቹን እንደሚያነሳ እንዳሳወቀውና ይህንንም ተከትሎ ጠባቂዎቹ ከመደበኛ ሥራቸው ይልቅ "እኔ ጋር መቅረትን መርጠዋል" ብሏል። የኦሮሚያ ክልል የቴሌቪዥን ጣቢያ የፌደራል ፖሊስን ጠቅሶ ለጃዋር ሞሐመድ ተመድበው የነበሩት ጥበቃዎች እንዲነሱ መደረጉን መዘገቡን ተከትሎ ጃዋር በፌስቡክ ገጹ ላይ "ሰላም ነው። ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተወያይተን ከስምምነት ላይ ደርሰናል። አታስቡ" ሲል ለደጋፊዎቹ መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ጃዋር ለቢቢሲ እንደተናገረው የጥበቃዎቹን መነሳት በተመለከተ ከፌደራል ፖሊስ ኮማንደር ጋር መነጋገሩንና አባላቱ ለስልጠና እንደሚፈለጉና ወደ ተቋማቸው እንዲመለሱ መጠየቁን አመልክቷል። ይህንንም ተከትሎ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ጋር በተነጋገሩበት ጊዜ የእሱ ብቻ ሳይሆን በመንግሥት ጥበቃ የተመደበላቸው ሰዎች ጠባቂዎችን ማንሳት እንደጀመሩና የእሱንም ጥበቃዎች እንደሚያነሱ እንደነገሩት ገልጿል። ይህ ከመሆኑ ቀደም ብሎ ለረጅም ጊዜ አብረውት ከቆዩት ጠባቂዎቹ ጋር ስለዚሁ ጉዳይ ተነጋግሮ እንደነበር የሚናገረው ጃዋር "አነሱም ወደ ፌደራል ፖሊስ መመለስ እንደማይፈልጉና ከእኔ ጋር መቆየት እንደሚፈልጉ ነግረውኛል" ምክንያታቸውም ስምና ፎቷቸው በስፋት ሲሰራጭ ስለነበር ለደህንነታቸው በመስጋት እንደሆነ ነግረውኛል በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል። ይህንንም የጠባቂዎቹን ውሳኔ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ እንደተናገረና ኮሚሸነሩም የጠባቂዎቹ ፍላጎት ይህ ከሆነ የፖሊስ አባልነታቸውን በመተው ሊሆን እንደሚገባ ተነጋግረው፤ "በእጃቸው ላይ የነበረውን የጦር መሳሪያና የመንግሥት ንብረት መልሰው ከእኔ ጋር ቀርተዋል" ሲል ጃዋር ተናግሯል። ለጃዋር ከፌደራል ፖሊስ ተመድበውለት ጥበቃ ሲያደርጉ የነበሩት የሠራዊቱ አባላት አራት ሲሆኑ አራቱም የፖሊስ አባልነታቸውን ትተው ከእሱ ጋር ለመሆን መወሰናቸውንም ተናግሯል። የፌደራል ፖሊስ ቀደም ሲል ለተለያዩ ታዋቂ ፖለቲከኞች መድቧቸው የነበሩትን ጥበቃዎች የማንሳት እርምጃ እየወሰደ መሆኑ እንደተገለጸለት የሚናገረው ጃዋር "የእኔን ያንሱ ችግር የለብኝም፤ ብዙ ሕዝብ ነው ያለኝ። እርምጃው ግን ትክክል አይመስለኝም" ይላል። በሌሎች አገሮች አሰራር መሰረት አከራካሪና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆነው የደህንነት ስጋት ያለባቸው ሰዎች ጥበቃ ይደረግላቸዋል በማለት "ለጃዋር ብለው ሌሎችን አደጋ ላይ መጣል የለባቸውም" በማለት በግሉ ጠባቂዎች መጠበቅ እንደሚችል ገልጿል። ባለፈው ጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ በድንገት እኩለ ሌሊት ላይ ጠባቂዎቹን ለማንሳት ሙከራ እንደተደረገና ይህንንም ጃዋር በማህበራዊ መድረኮች ላይ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በተከሰተ ውዝግብና ግጭት ከ80 በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ይታወሳል።
55706108
https://www.bbc.com/amharic/55706108
ስደት፡ ጓቲማላ ወደ አሜሪካ ሊያቀኑ ያሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አገደች
ወደ አሜሪካ የሚጓዙ የመካከለኛው አሜሪካ ስደተኞች ቡድን በጓቲማላ የፀጥታ ኃይሎች ዱላ እና አስለቃሽ ጭስ መንገዳቸው መዘጋቱ ተገለጸ፡፡
እሁድ ዕለት ከሆንዱራስ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ጎዳና ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታግደዋል። መንግስት "ሕገ ወጥ የጅምላ እንቅስቃን" አንቀበልም ሲል ገልጿል፡፡ ከቅርብ ቀናት ወዲህ ከሆንዱራስ ወደ 7000 የሚገመቱ ስደተኞች ድህነትን እና ሁከትን በመሸሽ ወደ አገሪቱ ገብተዋል፡፡ ወደ ሜክሲኮ ቀጥሎም ወደ አሜሪካ ድንበር ለመጓዝ ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ በየአመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመካከለኛው አሜሪካ ስደተኞች "ካራቫን" በመባል በሚታወቁ ቡድኖች በእግር ጭምር በመጓዝ አሜሪካን ለመድረስ ይህን አደገኛ ጉዞ ይጀምራሉ፡፡ ዲሞክራቱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕን ጥብቅ የስደተኞች ፖሊሲ ለመለወጥ ቃል ገብተዋል፡፡ ሆኖም ረቡዕ ሥልጣን የሚረከቡት ባይደን፤ ፖሊሲዎች በአንድ ሌሊት አይለወጡም በማለት ስደተኞች ጉዞውን እንዳያደርጉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ቡድኑ ጓቲማላ ሲገባ ምን ተፈጠረ? ስደተኞቹ ጓቲማላን አቋርጠው ወደ ሜክሲኮ ድንበር ሲጓዙ በደቡብ ምስራቅ ቫዶ ሆንዶ መንደር አቅራቢያ በፀጥታ ኃይሎች ፍጥነታቸውን እንዲቀንሱ ተደርጓል፡፡ የተወሰኑ ወታደሮች እና የፖሊስ መኮንኖች መንገድ በመዝጋት ብዙዎቹን እንዳይንቀሳቀሱ አግደዋቸዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች አሁንም በኃይል ለማለፍ የሞከሩ ሲሆን በፀጥታ ኃይሎች ወደኋላ ተገፍተዋል፡፡ በርካታ ሰዎችም ቆስለዋል፡፡ ብዙ ስደተኞች ወደኋላ አፈግፍገዋል፤ የተወሰኑት ደግሞ አዲስ ሙከራ ለማድረግ በአቅራቢያው እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በአቅራቢያው ወደሚገኙ ተራሮች ሸሽተዋል፡፡ የጓቲማላ ፍልሰት ድርጅት ኃላፊ ጊልርሞ ዳያዝዝ "እንደመታደል ሆኖ የፀጥታ ኃይሎች የመቋቋሚያ ዕቅድ አውጥተዋል። በዚህም ውጤታማ ሆነዋል" ብለዋል፡፡ ከጓቲማላን ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በተሰጠ መግለጫ "የጓቲማላ መልእክት ግልፅ ነው። እንደዚህ አይነቶች ሕገ ወጥ የጅምላ እንቅስቃሴዎች ተቀባይነት የላቸውም። ለዚህም ነው ከጎረቤት አገራት ጋር ይህንን ክልላዊ ጉዳይ ለመፍታት በጋራ የምንሰራው" ብሏል፡፡ ኋላ ላይ መንግሥት የህክምና እርዳታ የፈለጉ 21 ስደተኞች የኮቪድ-19 ምርመራ እንዳደረጉ አስታውቋል፡፡ ለምን ብዙ ሰዎች አሁን ይመጣሉ? ስደተኞቹ በአገራቸው ስደት፣ ዓመጽ እና ድህነት የዕለት ከዕለት ሕይወታቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ባለፈው ኅዳር ማዕከላዊ አሜሪካን በጎዶት ሁለት ግዙፍ አውሎ ነፋሶች የፈጠሩት ጥፋት ሁኔታዎች አባብሰዋል፡፡ እስማኤል ኤላዛር ለአሶሺዬትድ ፕሬስ የዜና ወኪል እንደተናገረው "አሁንም እዚያው ቦታ ጭቃ አለ። ሁሉም ነገር ተደምስሷል። ሁሉንም አጥተናል" ብሏል፡፡ ሆንዱራኖች ወደ አሜሪካ ባቀኑበት ጉዞ ውስጥ በመሳተፍ ቫዶ ሆንዶ፣ ጓቲማላ ውስጥ ዕረፍት አድርገዋል። የተሻለ ሕይወት፣ ሥራን እና ደህንነትን ለማግኘት ወደ አሜሪካመሄድ ይፈልጋሉ፡፡ ከልጇ ጋር የምትጓዘው የ23 ዓመቷ ዳኒያ ሂንስትሮሳ ለኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል እንደተናገረችው "ሥራም ሆነ ምግብ የለንም። ስለሆነም ወደ አሜሪካ ለመሄድ ወሰንኩ" ብላለች፡፡ የባይደን አስተዳደር አዲስ ፖሊሲዎችን ለመተግበር ቃል መግባቱ አንዳንድ ስደተኞችን ወደ አሜሪካ ድንበር ለመድረስ ያነሳሳቸዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡
49725563
https://www.bbc.com/amharic/49725563
ያለ ዛፎች መኖር እንችላለን?
ዛፎች ለምንኖርባት ምድር ካርቦንን ከማጠራቀም እስከ አፈር ጥበቃ፤ የውሃ ዑደትን ከመቆጣጠር በቀላሉ ጥላ አስከመሆን ድረስ አገልግሎት ይሰጣሉ። የአካባቢያችንንና የሰዎችን የምግብ ስርዓት ይደግፋሉ፤ ለብዙ ሺ እንስሳት መጠለያም ይሆናሉ።
ነገር ግን በሚያስገርም ሁኔታ ስለዛፎች ያለን አመለካከት የተዛባና ጎጂ የሚባል አይነት ነው። በአንድ ዓለማ አቀፍ ተቋም የተሰራ ጥናት እንደሚጠቁመው የሰው ልጅ እርሻ ከጀመረበት ከዛሬ 12ሺ ዓመታት በፊት በምድር ላይ ከነበሩት ዛፎች ግማሾቹ ወይም 5.8 ትሪሊየን የሚሆኑት ተጨፍጭፈዋል። • ወደ ጫካነት የተቀየረው ስታዲየም • የማዉ ጫካን ለማዳን 60 ሺ ኬንያውያን ከመኖሪያቸው ተባረሩ ኢንደስትሪያል አብዮት ከተጀመረ ወዲህ ደግሞ የዓለማችን 32 በመቶ የሚሆነው የዛፍ ሽፋን ጠፍቷል። በተለይ ደግሞ በምድር ወገብ አካባቢ ከሚገኙ ዛፎች መካከል በየዓመቱ 15 ቢሊየን የሚሆኑት ይቆረጣሉ። እያንዳንዱን በዓለማችን ላይ የሚገኙትን ዛፎች ሁሉ ጨፍጭፈን ብንጨርሳቸው ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል? በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዌልስ የኢንቫይሮመንታል ዳታ መምህር የሆኑት ኢዛቤል ሮዛ እንደሚሉት ሁሉም ዛፎች ከምድረ ገጽ ቢጠፉ የሰው ልጅ ህይወቱን ማስቀጠል በእጅጉ ከባድ ይሆንበታል። ''ምድርም የሰውን ልጅ ፍላጎቶች ማሟላት ያቅታታል'' ይላሉ። ምድር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ በረሃነት ትቀየራለች። ድርቅና ረሃብ ደግሞ ተከትለው የሚመጡ ክስተቶች ይሆናሉ። እንደው ምናልባት ዝናብ ቢመጣ እንኳን ውሃውን የሚቋጥሩ ዛፎች ባለመኖራቸው በጎርፍ እንጥለቀለቃለን። ከዚህ ባለፈ ምድር ከዛፎች ውጪ ስትሆን ለውቅያኖሶች መስፋፋት ትልቅ እድል ይፈጥራል። ምድርም ቀስ በቀስ ጨዋማ በሆነው የባህር ውህ እየተሞላች ትመጣለች። ዛፎች ካርቦንን በቅጠሎቻቸው አምቀው በመያዝና ከአባቢያቸው ደግሞ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን በማስወገድ በአየር ጸባይ ለውጥ ከሚመጣው ከፍተኛ ሙቀት ይጠብቁናል። የደን ምንጣሮ እስካሁን በዓለማችን ላይ እየጨመረ ለመጣው የካርቦን ልቀት 13 በመቶ አስተዋጽኦ አድርጓል። ዛፎች ከምድራችን ጠፍተው ሲያልቁ ደግሞ ወደ ከባቢ አየር ስንለቀው የነበረው የካርቦን መጠን ከእጥፍ በላይ ጨምሮ 450 ጊጋቶን ካርቦን ወደ ምንተነፍስው አየር ውስጥ ይለቀቃል። ከዚህ ባለፈ ከፍተኛ መጠን ያለው ካርቦን ወደ ውሃ አካላትም ጭምር ስለሚገባ በባህርና ውቂያኖሶች ውስጥ ያሉት እንስሳት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ይጠፋሉ። በዚህ ምክንያት የአሳ ምርት ቆመ ማለት ነው፤ አንድ የምግብ ምንጫችን በአጭሩ ተቀጨ። ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል? የመጨረሻውና እጅግ አስፈሪው የሚባለው የምድር ሙቀት ከፍተኛ የመሆን ደረጃ ላይ እንኳን ሳንደርስ በቢሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችና እንስሳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሞተው ያልቃሉ። በአሜሪካ የሚገኙ ተመራማሪዎች በሰሩት ጥናት መሰረት በአሜሪካ ብቻ ዛፎች 17.4 ሚሊየን ቶን የተበከለ አየር የሚያስወግዱ ሲሆን በገንዘብ ቢተመን እስከ 6.8 ቢሊየን ዶላር ወጪ ሊያስደርግ ይችላል። ከጤና ጋር በተያያዘ ደግሞ እንደ ኢቦላ፣ ኒፓ ቫይረስ እና ወባ ያሉ በሽታዎች በቀላሉ ተስፋፍተው የሰው ልጅን ህይወት አጭር ያደርጉታል። በተጨማሪም እስከዛሬ አይተናቸው የማናውቃቸውና ገና መድሃኒት ያልተገኘላቸው ብዙ ወረርሽኞች ትልቅ ፈተና መሆናቸው አይቀርም።
news-41592924
https://www.bbc.com/amharic/news-41592924
የህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያለ ዕድሜ ጋብቻን መደፈር ነው ብሎ ደነገገ
የህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንዶች በዕድሜ ካልደረሱ ሚስቶቻቸው ጋር ግንኙነት መፈፀምን ይፈቅድ የነበረውን አንቀፅ ውድቅ አድርጓል።
ይህ አከራካሪ የተባለው አንቀፅ የመደፈር ህግ አካል ሲሆን በጋብቻ ውስጥ አንድ ወንድ 15 ዓመት ዕድሜ ካላት ሴት ጋር ግንኙነት ማድረግን ይፈቅዳል። ምንም እንኳን በህንድ ህግ የጋብቻ እድሜ 18 ዓመት ቢሆንም በጋብቻ ውስጥ መደፈር እንደ ወንጀል (ጥፋት) አይታይም። ይህ ውሳኔ የተለያዩ የሴት መብት ተሟጋቾችን ያስደሰተ ቢሆንም፤ አንዳንድ ታዛቢዎች ትዕዛዙን ለማስፈፀም አስቸጋሪ እንደሆነ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ውሳኔውም እንደሚያትተው ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ሴቶች ባሎቻቸውን በመድፈር ለመክሰስ የሚያስችላቸው ሲሆን፤ በአንድ ዓመት ውስጥም ተገደው ግንኙነትን እየፈፀሙ መሆናቸውን ማሳወቅ አለባቸው። "ይህ ምሳሌያዊ ውሳኔ ለዓመታት በሴት ልጆች ላይ ተጭኖ የነበረውን ታሪካዊ ኢ-ፍትሀዊነትን የቀየረ ነው። እንዴት ጋብቻ እንደ መስፈርት ሆኖ ሴት ልጆች ላይ አድልዎ መፈፀሚያ መሳርያ ይሆናል?" በማለት ለቢቢሲ የተናገሩት ቪክራም ሲርቫስታቫ አንቀፁን ለማስቀየር ፊርማ ሲያሰባስቡ ከነበሩት አንደኛው ናቸው። ነገር ግን በደልሂ የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳለቸው፤ በርካቶች ዜናውን በደስታ ቢቀበሉትም የህፃናት ጋብቻ በአገሪቷ በተስፋፋበት ሁኔታ ህጉን ማስፈፀም አስቸጋሪ ነው በማለት አስተያየቷን ሰጥታለች። "ፍርድ ቤትም ሆነ ፖሊስ በእያንዳንዱ ግለሰብ መኝታ ክፍል እየገቡ ሊቆጣጠሩ ይችሉም። እንዲሁም በቤተሰቦቿ ፈቃድ የተዳረች ሴት ልጅ ፖሊስ ወይም ፍርድ ቤት ሄዶ ባሏን ለመክሰስ ድፍረቱ አይኖራትም" በማለት የቢቢሲ ዘጋቢ ትናገራለች። የህንድ መንግስት በበኩሉ የህፃናት ጋብቻ ለልማት፤ ረሃብና ድህነትን በማጥፋት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን በማሳደግ፣ የፆታዎች እኩልነትን በማስፈን፣ የህፃናትን ደህንነት መጠበቅ እንዲሁም የሴቶችን ጤና በማሻሻል በኩል መሰናክሎችን እየፈጠረ ነው በማለት ይናገራሉ።
news-47399819
https://www.bbc.com/amharic/news-47399819
የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት
ጣሊያናዊቷ ቲዚአና ካንቶን ራሷን እንድታጠፋ ያስገደዷት ሁነቶች በቅጽበት የተከሰቱ ናቸው።
ቲዚአና እንደ አውሮፓውያኑ መጋቢት 2007 ላይ የ31 ዓመቱ ጣሊያናዊ በርካታ የወሲብ ቪዲዮዎችን በዋትስአፕ ለአምስት ሰዎች አጋራ። • 100 ሺህ ብር፤ ብልትን ለማወፈር የወሲብ ቪዲዮዎቹ ከተላከላቸው ሰዎች መካከል የቲዚአና የቀድሞ ፍቅረኛ ሰርጂዎች ዲ ፓሎ ይገኝበታል። ሰርጂዮ እና ቲዚያና በፍቅራቸው ዘመን ጥሩ ግንኙነት አልነበራቸውም። በዋትስአፕ የተላኩት ቪዲዮዎች ቲዚያና ማንነታቸው ካልታወቁ የተለያዩ ሰዎች ጋር ወሲብ ስትፈጽም ያሳያሉ። ቪድዮዎቹ በፍጥነት ተሰራጩ ቪዲዮዎቹ በፍጥነት ተሰራጩ። በተለያዩ ልቅ የወሲብ ድረ ገጾች ላይም ተጫኑ። ሰዎች ቪዲዮዎቹን ይመለከቱ፣ ይጋሩም ጀመር። ቲዚአና ግን ይህ እንዲሆን አልፈቀደችም ነበር። • 'የሴቶች ቫያግራ' በአፍሪካዊቷ ሃገር የቲዚአና የ15 ዓመት ጓደኛ ቴሬሳ ፔተሮሲኖ ''እጅግ ውብ እና ስሜቷ በቀላሉ የሚጎዳ ሴት ናት'' በማለት ትገልጻለች። ''ትክክለኛ ባልሆነ ሰዓት፣ ትክክል ካልሆኑ ሰዎች ጋር ነበረች'' ትላለች። ቲዚአና ''ቪዲዮ እየቀረጽክ ነው?'' ስትል ወሲብ እየፈጸሙ ሳሉ ካሜራ የያዘውን ሰው ትጠይቃለች። ከዚያም ''በጣም ጥሩ'' ትላለች። ይህ ንግግር ወሲብ እየፈጸመች በቪዲዮ መቀረጽ "ያስደስታታል" በሚል በርካቶችን አስማማ። ቪዲዮን ለመመልከት እና ለማጋራትም ምክንያት ሆናቸው። ሰዎች ቪዲዮዎቹን ከመመልከት እና ከማጋራትም አለፉ። የቲዚአና ምስል በካናቴራዎች ላይ ይታተ ጀመር። ስሟም ማፌዣ ሆነ። • የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? "ወዳ እና ፈቅዳ የፈጸመችው ነው" ተብሎ ስለታሰበ ቪዲዮዎቹን ማየትና ማጋራት በቲዚአና ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ማንም አላሰበም። "ወዳ እና ፈቅዳ የፈጸመችው ነው" የሚለው አስተሳሰብም ስህተት ነበር። ቲዚአና ቪድዮው ሲቀረጽ በአደንዛዥ ዕጽ ተጽዕኖ ስር ወድቃ ነበር። ቪዲዮዎቹን መቀረጽ የሚያስከትልባትን ጉዳት ማገናዘብ የማትችልበት ሁኔታ ውስጥ ነበረች። ''ከቲዚአና ጋር ስለ ቪዲዮቹ በዝርዝር አላወራንም።'' ስትል ጓደኛዋ ቴሬሳ ትናገራለች። ''በቪዲዮዎቹ ምክንያት ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብታ ነበር'' ትላለች ቴሬሳ። ጉዳዩን ፍርድ ቤት ወሰደችው ቲዚአና ቪዲዮዎቹን ለማስጠፋት ቆርጣ ተነስታ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወሰደችው። ቪዲዮዎቹ በተለያዩ ድረ ገጾች ላይ የተጫኑት ያለፍቃዴ ነው ስትል አቤቱታ አቀረበች። ነገሮች ግን ጉዳዩን እንዳሰበችው ቀላል ሆኖ አላገኘችውም። • ግብጽ 'የፒራሚድ የእርቃን ምሰል' ላይ ምርመራ ጀመረች ''የሆነ ደረጃ ላይ ስትደርስ የምትወጣው ነገር እንዳልሆነ ተረዳች። እኚህ ቪዲዮዎች እንደማይጠፉ እርግጠኛ ሆነች። ወደፊት ባለትዳር ስትሆን ባሏ እኚህን ቪዲዮዎች መመልከቱ አይቀርም። የልጆች እናት ስትሆንም ልጆቿ የእናታቸውን የወሲብ ቪዲዮ ማየታቸው አይቀርም'' በማለት ጓደኛዋ ቲዚአና የገባችበትን ጭንቀት ታስረዳለች። የቲዚአና እናት ማሪያ ቴሬሳ ቲዚአና ካንቶን ሽሽትን መርጣ ከከተማ ርቃ ወደ ቤተሰቦቿ መኖሪያ መንደር አቅንታ ከእናቷ ጋር መኖር ጀመረች። የቲዚአና እናት ''ልጄ በጣም መልካም ሰው ነች'' ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወላጅ እናት ጨምረውም፣ ቲዚአና ያለ አባት ማደጓን እና ይህም በህይወቷ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳሳደረባት ይናገራሉ። ቲዚአና በደስታ ትኖር በነበረበት ጊዜ ሙዚቃ ማድመጥ እና ፒያኖ መጫወት ታዘወትር ነበር። ቪዲዮዎቹ የአደባባይ ሚስጥር ሲሆኑ ግን ይህን ሁሉ ማድረጓን አቆመች። • አር ኬሊ ሴቶችን አስክሮ በመድፈር ውንጀላ ቀረበበት ለፍርድ ቤት ያቀረበችውን አቤቱታ ተከትሎ ቪዲዮዎቹ ከበርካታ ድረ ገጾች ላይ እንዲነሱ ቢደረግም፣ ፍርድ ቤቱ ለሂደት ማስፈጸሚያ በሚል 20 ሺህ ዩሮ እንድትከፍል ውሳኔ አስተላልፎ ነበር። በወቅቱ እየሆነ የነበረው ነገር ከአቅሟ በላይ የሆነ ይመስል ነበር። ''እሷ የሞተች እለት የእኔ ህይወት የፍጻሜ ቀን ነበር" መስከረም ላይ የቲዚአና እናት በሥራ ገበታቸው ላይ ሳሉ የሰልክ ጥሪ ደረሳቸው። ''የደወለችው የወንድሜ ሚስት ነበረች። በተረጋጋ ድምጽ ወደቤት እንድመጣ ጠየቀችኝ። ወደ መኖሪያ ቤቴ ስቃረብ የፖሊስ መኪኖች እና አምቡላንስ ስመለከት ወዲያው መጥፎ ነገር እንደከሰተ ተረዳሁ'' ይላሉ የልጃቸውን መሞት የተረዱበትን ቅጽበት ሲያስረዱ። ''ጎረቤቶቼ ከመኪናው ውስጥ እንዳልወጣ አደረጉኝ። ትንፋሽ አጠረኝ። እራሴን ልስት ተቃረብኩ። ወደ ቤት ውስት ዘልቄ እንዳልገባ ስለከለከሉኝ ለመጨረሻ ጊዜ እንኳ ሳላያት ቀረሁ።'' የተዚአና ጓደኛ ቴሬሳ ''እሷ የሞተች እለት የእኔ ህይወት የፍጻሜ ቀን ነበር'' ትላለች ። ጣሊያናውያን በቲዚአና ሞት እጅጉን ተደናግጠው ነበር። የቲዚያና ቀብር በበርካታ መገናኛ ብዙሃን ሽፋን ተሰጥቶ ነበር። ''ሆነ ተብሎ ይህችን ምስኪን ልጅ ለማዋረድ የተቀነባበረ የወንጀል ተግባር ነው'' ቲዚአና እነዚያን የወሲብ ቪዲዮዎች ሰዎች አንዲረሷቸው ስትል ራሷን ብታጠፋም፣ ይልቁንም በርካቶች ቪድዮዎቹን እንዲመለከቷቸው ምክንያት ሆነ። እናቷ ሳይቀሩ ቪዲዮዎቹን ለመመልከት ተገደዱ። • ፈረንሳያውያን ልጆቻቸውን እንዳይመቱ የሚከለክል ህግ ወጣ ''ቪዲዮዎቹን መመልከት ምን አይነት ስሜት ሊፈጥር እንደሚችል መገመት ከባድ አይሆንም። እውነታውን ማወቅ ስለፈለኩ ቪዲዮዎቹን በዝርዝር ተመለከትኳቸው።'' በማለት ቴሬሳ ትናገራለች። እናቷ እንደሚሉት ቲዚአና ቪዲዮዎቹን የተቀረጸችው በአደንዛዥ እጽ ተጽእኖ ስር ሳለች ነበር። ቪዲዮዎቹ በስፋት የተሰራጩትም በአጋጣሚ አልነበረም። ''ሆነ ተብሎ ይህችን ምስኪን ልጅ ለማዋረድ የተቀነባበረ የወንጀል ተግባር ነው።'' እናትየው፣ የቲዚአና ፍቅረኛ የነበረው ዲ ፓሎ ምን እንደተፈጠረ በዝርዝር እንዲያስረዳቸው ይፈልጋሉ። ቲዚአና እና ወላጅ እናቷ ቴሬሳ ቪዲዮዎቹን ማን አሰራጫቸው? ቲዚአና ከሞተች ከሁለት ወራት በኋላ መርማሪዎች የቀድሞ ፍቅረኛዋን ለአስር ሰዓታት ምርመራ አድርገውበት ነበር። ለሞቷ ተጠያቂ ሰው ካለ በሚል ተጨማሪ ምርመራም አድረገዋል። ቲዚአና ካንቶን ራሷን ካጠፋች በኋላ በጣሊያን የወሲብ ግንኙነት ስለሚያሳዩ ቪድዮዎች ያለው አመለካከት ተቀይሯል። በግዴለሽነት ይዘግቡ የነበሩ ጋዜጠኞች ሳይቀሩ ጥንቃቄ ማድረግ ጀምረዋል። የቲዚአና ቪዲዮዎች አሁንም ከኢንተርኔት ላይ አልወረዱም። የቲዚአና እናት ጣሊያን እና የአውሮፓ ህብረት ግላዊ የሆኑ ምስሎች ላይ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ግፊት አደርጋለሁ ብለዋል።
news-53747872
https://www.bbc.com/amharic/news-53747872
ፊልም፡ ዲዝኒ በመዝናኛው ዓለም ስሙን የተከለውን የ20 ሴንቸሪ ፎክስን ስም ቀየረ
ትዌንቲ ሴንቸሪ ፎክስ የሚባለውና በመዝናኛው ዓለም ስሙን በተመልካቾችና በፊልም ባለሙያዎች ውስጥ የተከለው ኩባንያ ከአሁን በኋላ በይፋ እንደማይኖር ዲዝኒ አስታውቋል።
ዲዝኒ ይህንን ውሳኔውን ያሳወቀው ከቴሌቪዥን ስቱዲዮዎች መካከል አንዱ የሆነውን፤ ትዌንቲ ሴንቸሪ ፎክስ ቴሌቪዥንን (20th Century Fox Television)፣ 20 ቴሌቪዥን (20th Television) በሚል መቀየሩን ባሳወቀበት ወቅት ነው። ይህ ውሳኔ የመጣው ዲዝኒ ከትዌንቲ ሴንቸሪ ፎክስ የፊልም ብራንድ ላይ ፎክስ የሚለውን ቅጥያ መተዉን በታህሳስ ወር ማስታወቁን ተከትሎ ነው። የፊልም ስቱዲዮው በሆሊውድ ታሪክ ተወዳጅ ፊልሞችን አበርክቷል። ካበረከታቸው ፊልሞች መካከል "ስታር ዋርስ"፣ "ዘ ሳውንድ ኦፍ ሚዩዚክ"፣ "ዳይ ሃርድ" እና "ሆም አሎን" ይገኙበታል። ባለፈው ዓመት ከ71 ቢሊየን ዶላር በላይ በማውጣት የፎክስን ንብረቶች የገዛው ዲዝኒ ለረዥም ጊዜ የስቱዲዮ መጠሪያ የነበረውን ወደ ትዌንቲ ሴንቸሪ ስቱዲዮስ ቀይሮታል። ባለፈው ዓመት ዲዝኒ የሩፐርት መርዶክ ፎክስ ሚዲያ ንብረቶችን 71.3 ቢሊየን ዶላር በመግዛት መጠቅለሉ ይታወሳል። ዲዝኒ የቲቪ ስቱዲዮዎቹንም ስም የቀየረ ሲሆን አዲስ ስምና ዓርማ ይኖራቸዋል ብለዋል። ይህም ኤቢሲ ስቱዲዮስ፣ ኤቢሲ ሲግኔቸር ስቱዲዮስ ወደ ኤቢሲ ሲግኔቸር እንዲሁም ፎክስ 21 ቴሌቪዥን ወደ ተችስቶን ቴሌቪዥን ተቀይረዋል። የዲዝኒ ቴሌቪዥን ስቱዲዮስ ፕሬዝዳንት ክሬግ ሁኔግስ አዲሶቹ የፊልምና የቴሌቪዥን ስቱዲዮዎች የድርጅቱን ነባር ስምና ዝና እንዲሁም የፈጠራ ብቃት እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል። 20 ሴንቸሪ ፎክስ ቴሌቪዥን የተመሰረተው እኤአ በ1949 ሲሆን በርካታ ዝነኛ የቴሌቪዥን ትርዒቶች ወደ ሕዝብ እንዲደርሱ አድርጓል። ከእነዚህም መካከል ዘ ሲምፕሰንስ፣ ማሽ (M*A*S*H ) እንዲሁም ቀዳሚው የባት ማን ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ፣ ሞደርን ፋሚሊ ይገኙበታል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ትዌንቲ ሴንቸሪ ስቱዲዮ ዳግም ስሙ ሲቀየር ዲዝኒ ከመርዶክ ስምና ተጽዕኖ ራሱን ለመነጠል እየሞከረ ነው ተብሎ ነበር። ዲዝኒ በአሜሪካ የመገናኛ ብዙሃን ውስጥ በኤቢሲ ኔትወርክ አማካኝነት ከፍተኛ ስምና ዝና አለው። አሁን ደግሞ ከኔትፍሊክስ ጋር በመፎካከር የራሱን የፊልም እና ተከታታይ ድራማዎች ለማሰራጨት ዲዝኒ ፕላስ የሚል ከፍቷል (Disney+)። ትዌንቲ ሴንቸሪ ፎክስ ፊልም ስቱዲዮ እንደ አቫተርና ታይታኒክ ያሉ የምንጊዜም ምርጥ ፊልሞችን ፕሮዲውስ ያደረገ ኩባንያ ነው። ትዌንቲ ሴንቸሪ ፎክስ የተመሰረተው (እኤአ) በ1935 ቴዌንቲዝ ሴንቸሪ ፒክቸርስና ፎክስ ፊልምስ ሲቀላቀሉ ነው። ዲዝኒ ፊልሞች በበኩላቸው በፊልም አፍረቃሪያን ልብ ውስጥ መኖር የጀመሩት (እአአ) በ1937 ስኖው ዋይት እና ሰቨን ድዋርፍስ ከሥራ በኋላ ሲሆን አሁን ደግሞ የስታር ዋርስ ተከታታይ ፊልሞችን እንዲሁም ማርቭል ስቱዲዮስ በመያዝ ዝናውን እና ተመራጨነቱን እንዳስጠበቀ ይገኛል።
50328127
https://www.bbc.com/amharic/50328127
የማርቲን ሉተር ኪንግ ስም ከመንገድ ላይ እንዲነሳ ተደረገ
የካንሳስ ከተማ ነዋሪዎች በጥቁር መብት ተሟጋቹ ስም እንዲጠራ ከተደረገው መንገድ ላይ ስያሜው እንዲነሳ አድርገዋል።
መንገዱ በማርቲን ሉተር ኪንግ ስም የተሰየመው ከወራት በፊት ቢሆንም የከተማዋ ነዋሪዎች ባደረጉት ምርጫ ስሙ እንዲነሳ ድምፃቸውን ሰጥተዋል። 'ዘ ፓሴዎ' በመባል ይታወቅ የነበረው የ16 ኪሎ ሜትር መንገድ በርካታ ጥቁር አሜሪካውያን የሚኖሩበት ሥፍራ ላይ የተዘረጋ ነው። በዓለም ዙሪያ በማርቲን ሉተር ኪንግ ስም የሚጠሩ 1000 ያህል መንገዶች እንዳሉ ይታመናል። የዘጠኝ መቶ ሃምሳ አምስቱ መንገዶች መዳረሻ ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ነው። ካንሳስ ከአሜሪካ ዋና ዋና ከተሞች በዶ/ር ኪንግ የሚጠራ መንገድ የሌለባት ብቸኛዋ ከተማ ልትሆን ነው። ምንም እንኳ በከተማዋ ብዛት ያላቸው ጥቁር አሜሪካውያን ቢኖሩም መንገዱ ቅድሚያውንም ዘ ፓሴዎ ከተሰኘው ስም ወደ ማርቲን ሉተር ኪንግ የተቀረበት ሂደት ፍትሃዊ ነው ብለው አያምኑም። አልፎም ማርቲን ሉተር ኪንግን በዚህ መንገድ አይደለም መዘከር ያለብን ያሉ በርካታ ጥቁር አሜሪካውያን እንዳሉ ተሰምቷል። የካንሳስ ነዋሪዎች የማርቲን ሉተር ኪንግ ስም የተለጠፈበት የመንገድ ምልክት ይወርድልን ብለው ይመርጣሉ ተብሎ ባይታሰብም 70 በመቶ ያህል ድምፅ ሰጭዎች ስያሜው እንዲሳ ሲሉ ድምፃቸውን ሰጥተዋል። የዶ/ር ኪንግ ስም እንዲነሳ መወሰኑ ያንገበገባቸው ጥቁር አሜሪካውያን ግን አልጠፉም። ስያሜው በከተማዋ ለሚኖሩ ጥቁር አሜሪካዊ ታዳጊዎች ምሳሌ ይሆን ነበር ሲሉም ቁጭታቸውን ይገልፃሉ። ጉዳዩን እንደ መልካም አጋጣሚ ያዩትም አልጠፉም። አሁን ዶ/ር ኪንግን በመንገድ ስያሜ ሳይሆን በተሻለ ይዘት መዘከር እንችላለን ይላሉ።
news-47849678
https://www.bbc.com/amharic/news-47849678
የሊቢያ ቀውስ፡ በትሪፖሊ አቅራቢያ በተደረገ ውጊያ የ21 ሰዎች ሕይወት ጠፋ
በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው የሊቢያ መንግሥት በዋናው ከተማ አቅራቢያ በተደረገ ጦርነት የ21 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና 27 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታወቀ።
የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ውጊያው በአስቸኳይ ቆሞ ሁሉም ወገኖች ወደ ንግግር እንዲመጡ ጠይቀዋል። ጀነረራል ካሊፍ የሚመሩት አማፂ ቡድን በምስራቅ በኩል ትሪፖሊን በቁጥጥራቸው ስር ለማዋል እየገፉ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አል ሲራጅ ቡድኑን መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ ሙከራ በማድረግ የወነጀሉት ሲሆን አማፂያንን በኃይል ነው የምናናግረው ሲሉ ተናግረዋል። • አወዛጋቢው ግጭት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር • የ737-8 ማክስ መከስከስ ለቦይንግ ምን ማለት ነው? • ጄፍ ቤዞስ በ35 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ ትዳሩን ለማፍረስ ተስማማ ሕይወታቸውን ካጡት መካከል የቀይ ጨረቃ ዶክተር ሲገኝበት የአማፂ ቡድኑ ባወጣው መግለጫም 14 ተዋጊዎቹን አጥቷል። ቀደም ብሎ የተባበሩት መንግሥታት ለሁለት ሰዓት ያህል የተኩስ ማቆም እንዲደረግና ሰላማዊ ዜጎች ስፍራውን ለቀው እንዲወጡ የጠየቀ ቢሆንም ነገር ግን ይህ ጥያቄው ሰሚ አላገኘም። የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው ላይ "በትሪፖሊ አቅራቢያ የሚደረግ ውጊያ ያሳስበኛል" ሲል ገልጸዋል። በመግለጫው ላይ አክሎም " በአንድ ወገን የሚደረግ የጦርነት ዘመቻ የንፁኃንን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል እና የሊቢያውያንን መፃኢ እድል ተስፋ የሚያቀጭጭ ነው" ብሏል። የአለም አቀፍ ተቋማት ሰራተኞቻቸውን ፀጥታዋ እያሽቆለቆለ ከመጣው ሊቢያ እያስወጡ ነው። ሐሙስ ዕለት ጀምሮ ጀነራል ካሊፍ ሃፍተር የሚመሩት ጦር ከደቡብና ከምዕራብ በኩል ጦርነቱን አፋፍሞታል። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ እንዲያስችለው ያቀረበው የተኩስ አቁም ጥሪ ሰሚ ጆሮ አለማግኘቱን የጠቀሰ ሲሆን ሌሎች የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደ ጦርነት ቀጠናው ለመግባትና ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ እንዳልቻሉ ተናግረዋል። ነገር ግን የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አሁንም ቢሆን በጎ ምላሽ እንደሚያገኙ ተስፋ አላቸው። እሁድ እለት የአማፂ ቡድኑ የመጀመሪያውን የአየር ላይ ጥቃት ማድረጉን አስታውቋል። ይህ የሆነው ደግሞ በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው መንግሥት ቅዳሜ እለት የአየር ላይ ጥቃት ካደረሰባቸው በኋላ ነው። ሊቢያ ለረዥም አመት ያስተዳደሯት ሙሀመድ ጋዳፊ በ2011 ከስልጣን መውረድና መገደል በኋላ ሰላምና መረጋጋት ርቋት ትገኛለች።
news-50357377
https://www.bbc.com/amharic/news-50357377
"ሴት ተማሪዎችን ባጠቃላይ ተመርመሩ ማለት መፈረጅ ነው" የሕግ ባለሙያ ወ/ሮ ሰብለ አሰፋ
ትላንት በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ፤ ሴት ተማሪዎች በመንግሥት ሆስፒታል የእርግዝና ምርመራ አድርገው በ48 ሰዓት ውስጥ ለፕሮክተራቸው (ለተቆጣጣሪዎች) እንዲያስገቡ የሚያሳስብ ማስታወቂያ መውጣቱ በርካቶችን አነጋግሯል።
ዩኒቨርሲቲው "ማስታወቂያው የወጣው በስህተት ነው" ሲል ማስተባበያ ቢያወጣም፤ ማስታወቂያው ለምን እና እንዴት ወጣ? ተማሪዎች እንዲመረመሩ ማስገደድ ሕጋዊ አግባብ አለው? በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በተደጋጋሚ ስለመውለዳቸው እና ህጻናት ተጥለው ስለመገኘታቸው የሚናፈሰው እውነት ነው? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች እየተሰነዘሩ ነው። • የተነጠቀ ልጅነት • "አትግደሉን!"፡ የቱርክ ሴቶች ማስታወቂያው የወጣው በተማሪዎች ኅብረት እንደሆነ የሚገልጸው የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዘዳንት ዳንኤል ጌታቸው፤ "ጠዋት ላይ [ሕዳር 28 ቀን 2012 ዓ. ም.] ውይይት ሳይኖር [በተማሪዎች ኅብረትና በዩኒቨርስቲው መካከል] በስሜታዊነት የተደረገ ነው፤ ስህተት መሆኑን አምነን ይቅርታ ጠይቀናል" ሲል ተናግሯል። በእለቱ ጠዋት ልጅ ወልዳ መንገድ ዳር ጥላ የሄደች ተማሪ እንደነበረች የሚናገረው ዳንኤል፤ ክስተቱ ስሜታዊ እንዳደረጋቸው ገልጾ፤ ይህን ተከትሎ ማስታወቂያው የወጣው "ነገሩ ስላሳሳበን ነው" ይላል። የተባለው ችግር በዩኒቨርስቲው አለ ቢባል እንኳን፤ የእርግዝና ምርመራ ይደረግ ብሎ ማስገደድ እንዴት መፍትሔ ይሆናል? ብለን ላቀረብንለት ጥያቄ፤ "ሌሎች ሴቶች ላይ እንዳይከሰት አስበን ነው፤ ባለማስተዋል የተደረገ ነው" ሲል መልሷል። • የሴቶች ዘብ የነበሩት ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ • የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በተደጋጋሚ ይወልዳሉ? ህጻናት ተጥለው ስለመገኘታቸው የሚናፈሰው ወሬስ እውነት ነው? ብለን ጥያቄ ያቀረብንላቸው የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ት መቅደስ ካሳሁን "ምን ያህል አለ? እስከዛሬ ምን ተሠራ? የሚለው መረጃ ተሰብስቦ እየተሠራ ነው። ሠርተን ይፋ እናደርጋለን" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። የተማሪዎች ኅብረት፣ የተማሪዎች ዲን እና ፕሮክተሮች፤ ዩኒቨርስቲው ላይ እውን ይሄ ነገር ይደጋገማል ወይ? ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ምን የተለየ ነገር አለ? የሚለውን መረጃ በመሰብሰብ እየሠሩ መሆኑንም አክለዋል። ትላንት የወጣውን ማስታወቂያ በተመለከተ "ማስታወቂያ ወጥቷል። ግን የወጣው ኦፊሻል አይደለም። እኛ አስተባብበለን በኦፊሻል ገጻችን ላይ አውጥተናል" ብለዋል ወ/ት መቅደስ። የሕግ ባለሙያዋ ወ/ሮ ሰብለ አሰፋ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርስቲው ማስታወቂያው ኦፊሻል አይደለም ሲል ቢያስተባብልም፤ የተማሪዎች ኅብረት የአስተዳደሩ አካል በመሆኑ ይህን ማለት አይችልም ይላሉ። "አስተዳደሩ በሥሩ ያሉ ተማሪዎችን ያለ ፍቀዳቸው አገድዶ የህክምና ምርመራ እንዲያደርጉ የማድርግ ሥልጣን የለውም። ተማሪዎቹ በአንድ ማስታወቂያ ይህን እንዲያድረጉ በማዘዝ ያወጣው ነገር ሥልጣንን ያላግባብ መጠቀም ነው" ሲሉ ያስረዳሉ። • ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ • የጋዜጠኛዋ መገደል ቁጣ ቀሰቀሰ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕግም፤ አንድ ግለሰብ ያለፈቃዱ የህክምና ምርመራ እንዲያደርግ እንዳይገደድ በሕግ ጥበቃ የማግኘት መብት እንዳለው ጠቅሰዋል። "አስተዳደሩ ተማሪዎች ምርመራውን እንዲያደርጉ ያወጣው ማስታወቂያ ግልጽ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው። ግልጽ የሆነ የሕግ ድንጋጌዎችን የሚጻረርም ነው" ብለዋል። የትኛውም ምክንያት ቢኖር ሰውን አስገድዶ ምርመራ ማስደረግ ኢ-ሰብአዊ እና ጭካኔ የተሞላበት እንደሆነ ወ/ሮ ሰብለ ይገልጻሉ። ዩኒቨርስቲው ውስጥ ተማሪዎች ወልደው ልጅ ስለመጣላቸው ቢነገርም፤ የተረጋገጠ መረጃ አለመሆኑን ጠቅሰውም፤ ይህ ተከስቶ ቢሆን እንኳን አደረጉ የተባሉ ተማሪዎችን በአግባቡ አጣርቶ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ይናገራሉ። መላው የዩኒቨርስቲውን ሴት ተማሪዎች አስገድዶ ተመርመሩ ማለት "ሴት ተማሪዎችን መፈረጅ ነው" ሲሉም ያክላሉ። የሕግ ባለሙያዋ "በመረጃ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ባናውቅም ሆነ የተባለው ነገር ሲሰማ ከባድ ነው። ግን ሴት ተማሪዎችን ባጠቃላይ ተመርመሩ ማለት፤ ሁሉም ሴቶች ያላግባብ፣ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ እያረገዙ መሬት ላይ ልጅ ይጥላሉ በሚል የሚፈርጅ ነው። ሴት ተማሪዎች ሆነው እዚያ በመገኘታቸው ብቻ በቡደን፣ በመጥፎ ሁኔታ የሚፈርጅ ነው" በማለትም ያብራራሉ።
news-57313048
https://www.bbc.com/amharic/news-57313048
ኬንያ የሶማሊያ የሰብዓዊ እርዳታ በረራዎችን አግዳለሁ ስትል አስጠነቀቀች
ኬንያ የሰብዓዊ እርዳታ ተልዕኮ ያላቸውን ጨምሮ ማንኛውንም ከሶማሊያ የሚደረጉ ማንኛውንም በራራዎችን እንደምታግድ አስጠንቅቃለች።
የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴ የሰብዓዊ ተልዕኮ ያላቸው በረራዎች ለማይሆን ተግባር ውለዋል ሲል ለዲፕሎማቶች በፃፈው ደብዳቤ አስታውቋል። ኬንያ የሶማሊያን የንግድ በረራዎች ብታግድም ነገር ግን ለሰብዓዊ ተልዕኮ የሚውሉ በረራዎችን ከማገድ ታቅባ ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ደብዳቤ መሰረት ሰብዓዊ ተልዕኮ ያላቸው በረራዎች ለፖለቲካ ጉዳዮች መጠቀሚያ ሆነዋል ብላለች። ኬንያ በቅርቡ ከጎረቤት አገር ሶማሊያ የሚመጡ በረራዎችን ያገደች ሲሆን እግዱ ተግባራዊ አይሆንባቸውም ተብለው የነበሩት ለአስቸኳይ ህክምና የሚደረጉ በረራዎችና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰብዓዊ ተልዕኮዎችን ነበር። የሰብዓዊ እርዳታ በረራዎች ለሰብዓዊ አገልግሎት ብቻ መዋል አለባቸው በማለት ያስጠነቀቀችው ኬንያ ካለበለዚያ ግን እነዚህንም በረራዎችን በማገድ ሙሉ በሙሉ እግዱ ተፈፃሚ ይሆናል ብላለለች። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማንኛውም የሰብዓዊ እርዳታ በረራዎች መጀመሪያ ፈቃድ ሊያገኙ እንደሚገባና የሚያጓጉዟቸውን ግለሰቦችም ሆነ ቁሳቁሶች ዝርዝርም ማሳወቅ አለባች። ከጊዜ ወደጊዜ ግንኙነታቸው እየሻከረ የመጣው ኬንያና ሶማሊያ በተለይም አገራቱ የሚያወዛግባቸው ጉዳይ መነሻ የሆነው በባህር ላይ አዋሳኝ የሆነው ስፍራ ነው። ሶማሊያ ጉዳዩ በአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እንዲፈታ በማለትም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤቱ የወሰደችው በአውሮፓውያኑ 2014 ነው። በቅርቡ ደግሞ ኬንያ ራስ ገዝ አስተዳደር የሆነችውን የጁባላንድ አስተዳዳሪዎችን በመርዳት በውስጥ ጉዳዬ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ጣልቃ እየገባች ነው ስትል ሶማሊያ ግንኙነቷን ያቆመችው በህዳር ወር ነበር። በግንቦት ወር በኳታር አሸማጋይነት የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተሻሽሏል ቢባልም ኬንያ በሳምንቱ ከሶማሊያ የሚደረጉ በረራዎችን እንዳገደች አስታወቀች። ኬንያ እንደምትለው ከሶማሊያ ጋር የምትጋራው የበረራ መስመር ዝግ መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን ይህም ሁኔታ የሁለቱንም አገራት ግንኙነትም ወደ ባላንጣነት ቀይሯል ተብሏል።
48579638
https://www.bbc.com/amharic/48579638
የታንዛንያ ፖሊስ ሴቶችን በደቦ በመድፈር የተጠረጠሩትን በቁጥጥር ስር አዋለ
በሰሜን ምዕራብ ታንዛንያ ሴቶችን በደቦ በመድፈር የተጠረጠሩ ዘጠኝ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ ከሶስት አመት በፊት ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብሏል። ኪጎማ ተብሎ በሚጠራው የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ ሴቶች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ራሳቸውን "ተሌዛ" ብለው የሚጠሩ ወንዶች ሴቶችን በደቦ በመድፈር ለህይወታቸው አስጊ ሁኔታ መፍጠራቸውን ነው። •ፆታዊ ትንኮሳን ደርሶብኛል በማለቷ ተቃጥላ እንድትሞት የተደረገችው ወጣት •"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" ግለሰቦቹ በመድፈርና በስለት ጥቃት በማድረስ ወንጀል ተጠርጥረዋል። በአካባቢው ያሉ የሴቶች መብት ተሟጋች ቡድን ለቢቢሲ እንደገለፁት በሶስት አመታት ብቻ አርባ ሶስት የመደፈር ጥቃቶች ተከስተዋል። ብዙ ሴቶችም ለደህንነታቸው በመስጋት በቡድን መኖር መጀመራቸውም ተገልጿል። •የተነጠቀ ልጅነት "ከኪጎማ መውጣት እፈልጋለሁ" በማለት ጥቃት የደረሰባት አንዲት ሴት ጠባሳዋን በማሳየት ለቢቢሲ ስዋሂሊ ገልፃለች። ቴሌዛ ተብሎ የሚጠራው ቡድን አባላት ስያሜያቸውን ያገኙት ጥቃት ከማድረሳቸው በፊት በቆሻሻ ዘይት ፊታቸውን ስለሚቀቡ ነው ተብሏል።
52195578
https://www.bbc.com/amharic/52195578
ኮሮናቫይረስ፡ በአህጉረ አፍሪካ 10 ሺህ ገደማ ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል
እስካሁን ድረስ 52 የአፍሪካ አገራት በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች እንደሚገኙባቸው ታውቋል። የአፍሪካ ሕብረት በሽታ መቆጣጠርያና መከላከያ ማዕከል እንዳስታወቀው በአፍሪካ 9,457 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
በአፍሪካ እስካሁን ድረስ 442 ሰዎች ሲሞቱ 800 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል። በሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ ሶስት ሰዎች መያዛቸው ከታወቀ በኋላ፣ በአፍሪካ እስካሁን ድረስ አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው መገኘቱን ያላስመዘገቡ አገራት ኮሞሮስ፣ ሌሴቶ ብቻ ሆነዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሐመት እንዳሉት ከሆነ አፍሪካ የኮሮናቫይረስን ለመዋጋት 100 ቢሊየን ዶላር ትፈልጋለች። እኚህ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ከፍራንስ 24 ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ እንደገለፁት፣ አፍሪካ በማህበራዊና በምጣኔ ሐብታዊ ጉዳዮች በርካታ ጥረት ብታደርግም አሁንም ግን " አቅሟ ደካማ ነው" ብለዋል። አፍሪካ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ በትናንትናው ዕለት ቻይናዊው ባለሃብት ጃክ ማ ሁለተኛ ዙር እርዳታው መላኩን አስታውቋል። የአፍሪካ መንግሥታት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተለያዩ እርምጃዎችን ቢወስዱም ከዕለት ዕለት ግን በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። በጋና 73 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተገኙ ሲሆን ይህም በአገሪቱ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን አጠቃላይ ቁጥር 287 አድርሶታል። በደቡብ አፍሪካም በርካታ ሰዎች መንግሥት የጀመረውን ምርመራ ሲሸሹ ተስተውሏል። ይህም የሆነው መንግሥት ቫይረሱን ለመመርመር የሚጠቀምበት መሳሪያ ራሱ ተበክሏል የሚል ሐሰተኛ ዜና በመሰራጨቱ እንደሆን ተገልጿል። የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት እንዲህ አይነት ሐሰተኛ ወሬዎች መንግሥት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያደርገውን ጥረት ያኮላሻል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። በአፍሪካ የኮሮናቫይረስን የመዋጋቱን ጥረት ሐሰተኛ ዜና ብቻ ሳይሆን ፍርሃትም እየገጎዳው እንደሆነ እየታየ ነው። በኮትዲቯርም ቢሆን በትናንትናው ዕለት በምንኖርበት አካባቢ የኮቪድ-19 ምርመራ አይደረግም፤ ቫይረሱን ወደ ቀያችን ያመጣብናል ያሉ ነዋሪዎች መመርመሪያ ጣቢያውን አውድመዋል። በማላዊ ሁለት ሞዛምቢካውያን ቫይረሱን እያሰራጩ ነው በሚል ሐሰተኛ ዜና ጥቃት እንደ ደረሰባቸው ተዘግቧል። ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብዛት በአፍሪካ ቀዳሚዋ ስትሆን ካሜሮን ደግሞ 658 ሰዎችን በማስመዝገብ ትከተላታለች።
news-44889794
https://www.bbc.com/amharic/news-44889794
የትረስት ፈንድ ሃሳብ በዲያስፖራው እና በባለሙያዎች ዕይታ
ከሁለት ሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የ2011 ዓ.ም ረቂቅ በጀትን በሙሉ ድምፅ ባፀደቀበት ስብሰባ ላይ አዲስ ምክረ-ሃሳብ አቅርበው ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአገር እድገት ይበጃል ያሉት ይህ ምክረ-ሃሳብ፤ የትረስት ፈንድ ማቋቋምን ይመለከታል። ''በቦርድ የሚመራ እና ወጪ እና ገቢው በትክክል የሚታወቅ 'ትረስት ፈንድ' በማቋቋም ዲያስፖራው በየቀኑ አንድ ዶላር እንዲለግስ እንጠይቃለን'' ብለዋል። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱ ቢያንስ በየቀኑ 1 ሚሊየን ዶላር ልታገኝ እንድምትችል ተስፋ አድርገዋል። • ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ? • ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት የሚልኩት ገንዘብ ህጋዊ መንገድን የተከተለ በማድረግ ''ህገ-ወጥነትን በመከላከል አገራችሁን ጥቀሙ'' ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጡን ለማደናቀፍ የሚሞክሩትን አስጠነቀቁ ትረስት ፈንድ ምንድነው? ትረስት ፈንድ ህጋዊ አካል የሆነ ለግለሰቦች፣ ለቡድን ወይም ለድርጅት ጥሬ ገንዘብን ወይም ንብረትን የሚያስተዳድር ፈንድ ማለት ነው። የተለያዩ የትረስት ፈነድ አይነቶች ያሉ ቢሆንም ሁሉም ሦስት ተመሳሳይ መሰረታዊ ይዘት አላቸው። እነዚህም ጥሬ ገንዘብ ወይም ንብረትን የሚለግስ፣ የሚያስተዳድር እና የፈንዱ ተጠቃሚ አካላት ናቸው። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳብ መሰረት የሚቋቋመው ትረስት ፈንድ መቀመጫውን በኢትዮጵያ ወይም ከኢትዮጵያ ውጪ ያደርጋል። ከዚያም ፍቃደኛ የሆኑ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በተወሰነ የጊዜ ልዩነት ለትረስት ፈንዱ መዋጮ ይፈጽማሉ። • "ለዋጋ ግሽበት የውጪ ምንዛሪ ማሻሻያው ምክንያት ነው" • የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች ከሁለት ቀናት በፊት የትረስት ፈንዱ የሂሳብ ቁጥር ይፋ የተደረገ ሲሆን ፍቃደኛ የዲያስፖራ አባላት በቅርቡ ይፋ በሚደረገው የትረስት ፈንዱ ድረ-ገጽ አሊያም ወደ 22 የሚጠጉ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን በመጠቀም ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚችሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ሃሳብ ይፋ ሲያደርጉ ''ዲያስፖራዎች ለአንድ ማኪያቶ እሰከ 5 ዶላር ድረስ ያወጣሉ። ከማኪያቶ ወጪያቸው ላይ ለአገራቸው 1 ዶላር በየቀኑ ቢያዋጡ በወር 30 ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ ያስገኛል ማለት ነው'' ብለዋል። ዲያስፖራው ምን ይላል? አቶ ሃብታሙ አበበ አሜሪካን አገር ሜሪላንድ ግዛት ውስጥ ይኖራሉ። ''በእድሜዬ በኢትዮጵያ ውስጥ አያለው ብዬ ያላሰብኩትን አይነት ለውጥ እየታዘብኩ ነው። በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ፤ የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ'' ይላሉ። አቶ ሃብታሙ ጨምረውም ''ጠቅላይ ሚንስትሩ የዲያስፖራው አስተዋጽኦ ምን መሆን እንዳለበት በትክክል አስቀምጠዋል፤ እኔም ሆንኩ ባለቤቴ ትረስት ፈንዱ ተቋቁሞ ግዴታችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን'' ሲሉ ሃሳባቸውን አጋርተውናል። በሌላ በኩል ነዋሪነታቸውን በእንግሊዝ አገር ያደረጉት አቶ ጳውሎስ አያሌው ''ያለምንም ዲሞክራሲ እና የህግ የበላይነት ሲመራ የቆየ መንግሥት አሁን ፊቱን አዙሮ ገንዘብ አዋጡ ማለቱ ለእኔ ታዓማኒነት የለውም። ከውጪ የሚመጣውን ገንዘብ የማስተዳደሩ አቅም የላቸውም፤ ህዝብም አልመረጣቸውም። አንዲያውም በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ሙስና ከማባባስ ውጪ ለህዝቡ ፋይዳ አይኖረውም'' በማለት ትረስት ፈንድ የማቋቋም ሃሳቡን አጣጥለዋል። በተቃራኒው ደግሞ ነዋሪነቷን በአሜሪካን አገር ቨርጂኒያ ግዛት ያደረገችው ፀደይ ብዙአየሁ ''ጠቅላይ ሚንስትሩ ያሉትን ለመፈጸም በጣም ዝግጁ ነኝ፤ እኔ የምፈልገው እኛን የሚወክሉ ግለሰቦች የትረስት ፈንዱ አካል ሆነው አፈጻጸሙን የሚያሳዩ ወቅታዊ የሆኑ ሪፖርቶችን እንዲያደርሱን ብቻ ነው'' ትላለች። በአሜሪካን አገር ሚኒሶታ ግዛት የሚኖረው እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆነው ያሬድ ገብረወልድ የጠቅላይ ሚንስትሩን ሃሳብ በአዎንታዊ መልኩ ይቀበላል። ''ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ሃሳብ ከማንሳታቸው በፊትም አገራችንን አንዴት መርዳት እንዳለብን በቤተሰብ ደረጃ የምንወያይበት ርዕሰ ጉዳይ ነው'' ይላል። ያሬድ ጨምሮም ''በርካታ ሰው አገሩን በገንዘብ መርዳት ይፈልጋል ይሁን እንጂ የሚያዋጣው ገንዘብ ለጦር መሳሪያ ግዢ ይውላል፣ የሙሰኞች ሲሳይ ይሆናል የሚሉ ስጋቶች ናቸው ከመለገስ እንድንቆጠብ የሚያደርጉን። ተጠያቂነት እና ግልፅነት የሰፈነበት አሰራር ካለ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነን'' ብሏል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ዕይታ የቀድሞ የአዲስ አበባ እና የኢትዮጰያ ንግድ ምክር ቤቶች ፕሬዝዳንት የነበሩት እና የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ክቡር ገና የጠቅላይ ሚንስትሩ ሃሳብ የሚዋጥላቸው አይመስልም። አቶ ክቡር ''የትረስት ፈንድን የማቋቋም ሃሳብ ከውጪ የሚመጣውን ገዘንብ አጠናክሮ ከማስቀጠል ያለፈ ሌላ ፋይዳ አይኖረውም'' ይላሉ። ''ስለ ትልቅ ገንዘብ ነው እያወራን ያለነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚሉትን አይነት ገንዘብ ከማኪያቶ ወጪ ላይ በመቆጠብ የሚመጣ አይነት አይደለም። አሁን በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የፋይናንስ ቀውስ ለመቅረፍ ታስቦ የመጣ ሃሳብ ከሆነ፤ ይህ ሃሳብ የሚያስኬድ ስላልሆነ እንደገና ቢታሰብበት እለላሁ'' ሲሉ ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ። አቶ ክቡር ''በግሌ በዲያስፖራ አላምንም። ዲያስፖራው በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው እገነዘባለሁ። ይሁን እንጂ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አገር ውስጥ ላለው ሃብት ነው'' በማለት ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ሌላው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ኑሩ ሰይድ (ዶ/ር) ግን የዲያስፖራውን አቅም ሲያስረዱ ''ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገሪቱ የሚልኩት የገንዘብ መጠን አገሪቱ ወደ ውጪ ነግዳ ከምታገኘው በሁለት እጥፍ ይበልጣል'' ይላሉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ የዲያስፖራውን አቅም ስለሚረዱ ነው ይህን አይነት ጥሪ ያደረጉት የሚሉት ዶ/ር ኑሩ ''ከዚህ በፊት መንግሥትን ለመጉዳት ታስቦ ዲያስፖራው ወደ አገር ውስጥ ዶላር እንዳይልክ የተለያዩ ቅስቀሳዎች ይደረጉ ነበር፤ እንዲሁም ህጋዊ መንገዶችን ባልተከተለ መልኩ ገንዘብ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ይደረግ ነበር። አሁን ግን የጠቅላይ ሚንስትሩ ሃሳብ ይህን እንኳን ማስቀረት የሚያስችል ከሆነ አገሪቱ በእጅጉ ልትጠቀም ትችላለች'' ይላሉ። ነገር ግን ዶ/ር ኑሩም ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚሉትን የገንዘብ መጠን በትረስት ፈንዱ በኩል ማግኘት ቀላል ሊሆንላቸው አይችልም ይላሉ። ''ይህ ሃሳብ በየትኛውም አቅጣጫ የሚገኘውን የዲያስፖራ ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማግኘት የተደረገ የቅስቀሳ አካል አድርጌ ነው የምመለከተው እንጂ እሳቸው የሚሉትን ያክል ገንዘብ ከዲያስፖራው ለመሰብሰብ የሚቻል አይደለም'' በማለት ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ።
news-50157443
https://www.bbc.com/amharic/news-50157443
"ክስተቱ 'የግድያ ሙከራ' እንደሆነ ነው የምረዳው" ጀዋር መሐመድ
ትናንት ሌሊት በአክቲቪስት ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተነግሯል።
ጀዋር ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ትናንት እኩለ ለሊት ላይ በመኖሪያ ቤቱ ተፈጽሟል ስላለው ጉዳይ እና ምልከታውን ለቢቢሲ አጋርቷል። ጃዋር እኩለ ሊሊት ላይ የተፈጸመውን ሲያስረዳ "ተኝቼ ነበር፤ በፌደራል ፖሊስ ተመድበውልኝ የነበሩት ጠባቂዎች 'በአስቸኳይ መሳሪያችሁን ይዛችሁ ውጡ' ተባሉ። ይህ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ" ይላል። • "ኢትዮጵያ የኢህአዴግ አባት እንጂ፤ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ አባት አይደለም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ድንጋጤ የፈጠረበትን ምክንያት ሲያስረዳ፤ "አንደኛ እኩለ ለሊት ነው። ሁለተኛው ደግሞ 'ጀዋር ሳይሰማ ውጡ' ነው የተባሉት። በዚያ ላይ የሚተኩ ጠባቂዎች የሉም" ይላል። በሁኔታው የተደናገጡት ጠባቂዎች ሁኔታውን ለእርሱ እንደነገሩትና እሱም በስም የሚጠቅሳቸው ጉዳዩ የሚመለከታቸው ግለሰብ ጋር ስልክ መደወሉን ያስረዳል። "በሰልክ ሳፋጥጠው 'ጌታዬ እኔ ደሃ ነኝ። የተሰጠኝ ትዕዛዝ ልጆቹን አስወጣቸው ነው እንጂ ማን ይተካ? ምን ይሁን የተባለ ነገር የለም' አለኝ" ይላል። ግለሰቡም ይህን ትዕዛዝ ማን እንደሰጣቸው ከነገሩት በኋላ፤ አሁንም በስም ወደሚጠቅሳቸው የበላይ አለቃ ጋር ቢደውልም ሊያገኛቸው እንዳልቻለ ያስረዳል። "የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋር ወደልኩ። ስልክ አያነሱም። ምክትላቸውም ጋር ደወልኩ፤ እሳቸውም ስልክ አያነሱም። ከዚያ አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን ጋር ደውዬ ምክትል ኮሚሽነሩ ስልክ እንዲያነሱ አስደረኩ። ምክትል ኮሚሽነሩ ትዕዛዙ ትክክለኛ መሆኑን ሲናገሩ በጣም ተገርምኩ" ይላል። ከዚህ የስልክ ጥሪ በኋላ በሦስት ፓትሮል መኪና ተጨማሪ ጸጥታ አስከባሪ ኃይል መምጣቱን ጃዋር ይናገራል። "ይህ በልጆቹ ላይ [በእርሱ ጠባቂዎች] ከፍተኛ ጫናን ፈጠረ፤ ፍጥጫም ሆነ። ይህ ሲሆን ከለሊቱ 7 ሰዓት ነበር። የተፈጠረውን ውጥረት ሊያረጋጋ የሚችል እና ኃላፊነት የሚወስድ የመንግሥት ባለስልጣን ማግኘት ስላልቻልኩ ይህን ጉዳይ ህዝብ ማወቅ አለበት ብዬ አስተዋወኩ" በማለት በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ እየሆነ ያለውን ለማሳወቅ መገደዱን ያስረዳል። • "በመንግሥትም በፖሊስም በኩል ምንም ዓይነት እርምጃ አልተወሰደም" ፌደራል ፖሊስ ጃዋር ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ ጥበቃ እንደሚያስፈልገው በመታመኑ በመንግሥት ተነሳሽነት ጥበቃ የሚያደርግለት ኃይል መመደቡን ያስረዳል። "ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የደህንነት ኃይሎች በአጽንኦት የተናገሩት 'ብዙ ባላንጣዎች ስላለህ ጥቃት ቢሰነዘርብህ በሃገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ስለዚህ የደህንነት ጥበቃ ሊኖርህ ይገባል' ነው የተባልኩት። እኔ ወደ የግል ሴኪዩሪቲ መግባት ፈልጌ ነበር ግን ግዴታ የመንግሥት ጥበቃ ያስፈልግሃል ተባልኩ" በማለት ይናገራል። "እኔን ማሰረ ከተፈለገ በፈለጋቸው ጊዜ ቢጠሩኝ የምገኝላቸው ሰው ነኝ። 'ና ታሰር' ቢሉኝ እንኳ ክሱ አሳማኝ እስከሆነ ድረስ እምቢ የምልበት ምክያት የለም።" "በውድቅት ለሊት በጣም አጣራጣሪ በሆነ መልኩ የተሞከረው ምን እንደሆነ አልገባኝም። የእስርም አይመስለኝም። ከውስጥ እንደምሰማው ሰሞኑን የነበረን ክርክር እየጦፈ ስለመጣ ሴኪሪቲውን በማስነሳት እንዲፈራ እና እንዲሸማቀቅ እናደርጋለን' የሚል የውስጥ ንግግር እንደነበረ፤ ከዚያም በገፋ መልኩ በዱርዬዎች ቤቴ ላይ ጥቃት በማድረስ ለማሳበብ እንደታሰበ ነው ያሉኝ መረጃዎች የሚያሰዩት" ይላል ጃዋር። በፌደራል ፖሊሰ ኮሚሸን ኮሚሽነር መግለጫ ላይ ያለው አስተያየት "በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ ወይ አንድ አደገኛ ሴራ አለ ወይም የሚያሳፍር ልፍስፍስነት አለ። ኮሚሽነሩ ዛሬ የተናገረው ነገር ከአንድ ከፍተኛ የደህንነት ኃላፊነት ካለበት የፖሊስ መሪ የማይጠበቅ እና አሳፋሪ ነው። ... ሴራ ያለበት ኦፕሬሽን ሞክረው ስለከሸፈባቸው ነው። ምንም አልተሞከረም የሚለው ነገር ነጭ ውሸት ነው። ይህም ሊታረም የሚገባው ነው" ከመንግሥት ጋር ስላለው ግንኙነት ጃዋር ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ስላለው ግንኙት ሲያስረዳ ''ከፌደራል መንግሥት ጋር በቅርበት ነው የምሰራው። እዚህ አገር የመጣሁት ባለኝ ልምድ እና እውቀት ልረዳቸው ነው። ከፖለቲካል ማኔጅመንት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሥራን ነው የምሰራው። ችግር በተፈጠረ ቁጥር ይጠይቁኛል ተንቀሳቅሼ አረጋጋለሁ። ከአንዳቸውም ጋር የግል ቁርሾ የለኝም፤ አዎ እተቻለሁ። አሁን ያለው አያያዝ ወደ አህዳዊ ሥርዓት እየተቀየረ ስለሆነ፣ የሕብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝሙን አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ፣ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በጣም ያሳሰበኝ ድርጅቶቹ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ሥራ አስፈጻሚ አባላት በፕሮጄክቱ እንደማያምኑ በግል እየገለጹልኝ፤ ነገር ግን ደግሞ ካላቸው ፍራቻ የተነሳ የሚደግፉበት ሂደት ስላለው ይህ መተቸት አለበት።" • በዓለማችን የተበራከቱት የተቃውሞ ሰልፎች የሚያመሳስላቸው ነገር ይኖር ይሆን? 'የግድያ ሙከራ' "የእኔ ጽሁፍ እና ትችት ትናንት ለተፈጸመው የግድያ ሙከራ የሚጋብዝ አይደለም" ያለ ሲሆን፤ ትናንት በመኖሪያ ቤቱ ተፈጸመ ስላለው ክስተት እስካሁን ያለው መረጃ የሚጠቁመው በእርሱ ላይ የተደረገ 'የግድያ ሙከራ' እንደሆነ መደምደሚያ ላይ መድረሱን ተናግሯል። የተጋነነው የጀዋር ተጽእኖ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ 20 ለዓመት ሲሳተፍ እንደቆየ የሚናገረው ጃዋር፤ ተጽዕኖ የመፍጠር አቅምን እንደገነባ ይናገራል። "እኔ በተለያዩ የዓለም አገራት ፖለቲካን ተምሬና ብዙ ጽሑፍ ጽፌ፤ ወጣቶችን አሰልጥኜ የዚህ ለውጥ ዋና ቀያሽ ሆኜ ስሰራ ነበር" ይላል። "እውቀቴንና ጉልበቴን ለእዚች አገር ለግሼ መንግሥት ሳይናድ ሃገር ሳይፈርስ ለውጥ እንዲመጣ ረዳሁ። ይህም ተዋቂ እና ተጽእኖ ፈጣሪ እንድሆን ረድቶኛል።" "ከፍተኛ ተጽእኖ እንዳለው ሰው ስልጣን አካፍሉኝ ማለት እችል ነበር። እኔ ግን አልፈለኩም። እንደ ግለሰብ በደሎችን ሳይ ግፎችን ሳይ እናገራለሁ እጽፋለሁ። ... ለዚች ሃገር በጎ እንጂ መጥፎ አላደረኩም" ሲል ይናገራል። ጀዋር ለሁሉም ነገር እኔ ተጠያቂ የማድረግ አባዜ በዝቷል ያለ ሲሆን "... ባል እና ሚስት ከተጣሉ ተጠያቂው እኔ፣ ዝናብ ከጠፋ ተጠያቂው እኔ፤ እኔ ዲዛይን ያደረኩትና እኔ እስትራቴጂስት የሆንኩለት ንቅናቄ ጠቅላይ ሚንስትር እንደዛ አይነት ትችቶችን ፓርላማ ፊት ሲያቀርብ በጣም ነው ያሳዘነኝ" ሲል ቅሬታውን ገልጿል። "ህዝቡ ሊረጋጋ ይገባል። ሰላማዊ ትግል ማድረግ አለበት። በንብረት ላይ ምንም አይነት ጥቃት ማድረስ የለበትም። ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ሊተበበር እና ሊስማማ ይገባል" ያለ ሲሆን ጨምሮም "ሰዉ ህገ-መንግሥታዊ መብቱን ተጠቅሞ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ድምጹን ማሰማቱ ትክክል ነው። መንግሥት እራሱን ከጸብ በመቆጠብ ነገሮችን ተረጋግቶ መፍታቱ ለመንግሥትም ለህዝብም ጠቃሚ ይመስለኛል" ብሏል። ጃዋር ባነሳቸው ጉዳዮች ላይ የጸጥታ ጥበቃው የሚመለከተው አካል ከሆነው ከፌደራል ፖሊስ በኩል ምላሽን ለማግኘት ያደግነው ሙከራ አልተሳካልንም።
news-53084316
https://www.bbc.com/amharic/news-53084316
ኮሮናቫይረስ፡ ለመሆኑ ምን ያህል ነው መራራቅ ያለብን? 1 ሜትር? ወይስ 2?
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ሰዎች ሁለት ሜትር መራራቅ አለባቸው የሚለውን መርህን ይደግፋሉ።
በተቃራኒው የሕዝብ እንደራሴዎቻቸውና የመስተንግዶ ዘርፉ ሠራተኞች ሁለት ሜትር ተራርቆ መሥራት የማይታሰብ ነው ይላሉ። የአገሪቱ መንግሥት አማካሪዎች በበኩላቸው 1 ሜትር ብቻ መራራቅ ለበሽታው የመጋለጥ እድልን በአስር እጥፍ ይጨምራል ሲሉ ይከራከራሉ። ታድያ ሰዎች ምን ያህል ነው መራራቅ ያለባቸው? አንድ ሜትር ወይስ ሁለት ሜትር? ሳይንሱ ምን ይላል? በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር በተቀራረብን ቁጥር ለበሽታው የመጋለጥ እድላችን እንደሚጨምር ሳይንስ ያስረዳል። የዓለም ጤና ድርጅት የሚመክረው አንድ ሜትር መራራቅን ነው። አንዳንድ አገራት የሚተገብሩትም ይህንን መርህ ነው። በእርግጥ ዜጎቻቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ ያስገድዳሉ። በሰዎች መካከል ምን ያህል ርቀት መኖር አለበት? የሚለውን በተመለከተ የተለያዩ አገራት ያወጡትን መመሪያ እንመልከት፦ 1 ሜትር መራራቅ- ቻይና፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ሆንክ ኮንግ፣ ሉቴኒያ፣ ሲንጋፖር 1.4 ሜትር መራራቅ- ደቡብ ኮርያ 1.5 ሜትር መራራቅ- አውስትራሊያ፣ ቤልጅየም፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ጣልያን፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖርቹጋል 1.8 ሜትር መራራቅ- አሜሪካ 2 ሜትር መራራቅ- ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ስፔን ‘ዘ ላንሴት’ በተባለ የሕክምና መጽሔት ላይ የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ቢያንስ አንድ ሜትር ከሰዎች መራቅ ራስን ከበሽታው ለመከላከል ይረዳል። አንድ ሜትር ከሰዎች ሲራቅ በቫይረሱ የመያዝ እድልን 13 በመቶ ይሆናል። ከአንድ ሜትር በላይ መራቅ ደግሞ ወደ 3 በመቶ ያወርደዋል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት እስከ ሦስት ሜትር ድረስ ከሰው ጋር ያለን ርቀት በጨመረ ቁጥር የበሽታው ተጋላጭነት በግማሽ እየቀነሰ ይሄዳል። አካላዊ ርቀት የመጠበቅ መርህ ከየት መጣ? አካላዊ ርቀት የመጠበቅ መርህ በ1930ዎቹ የተሠራ ጥናትን የተመረኮዘ ነው። ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ ስንስልና ስናስነጥስ የሚወጣው ፈሳሽ አየር ውስጥ ይተናል ወይም መሬት ላይ ይወድቃል። ፈሳሹ ከአንድ እስከ ሁለት ሜትር ባለው ርቀት ነው የሚወድቀው። ሰዎች ሲስሉ ወይም ሲያስነጥሱ በሽታውን የሚያስተላልፉትም ለዚያ ነው። በቫይረሱ የተያዘ ሰው የሳለባቸው (ወይም የነካቸው) ቁሳ ቁሶችን መንካትም ለበሽታው በግንባር ቀደምነት ያጋልጣል። ቫይረሱ በአየር መጓጓዝ ይችላል? በሽታው ከያዘው ሰው ጋር መቀራረብ ወይም በቫይረሱ የተያዘ ሰው የተጠቀመባቸውን ቁሳ ቁሶች ነክቶ ፊትን መንካት ለበሽታው ያጋልጣል። አንዳንድ ተመራማሪዎች ኮሮናቫይረስ በጥቃቅን የፈሳሽ ቅንጣቶች (ኤሮሶልስ) አማካይነት በአየር ላይ ይጓጓዛል ብለው ይሰጋሉ። ይህ እውነት ከሆነ ከአንድ ሰው የሚወጣ ትንፋሽ ቫይረሱን ብዙ ርቀት ይዞት ይጓዛል ማለት ነው። በማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ፕሮፌሰር የሆኑት ሊድያ ቦሩባ፤ በከፍተኛ ፍጥነት ፎቶ የሚያነሳ ካሜራ ተጠቅመው፤ አንድ ሰው ሲስል የሚወጣው የፈሳሽ ቅንጣት እስከ 6 ሜትር እንደሚሄድ አሳይተዋል። ቻይና በሚገኙ የኮቪድ-19 ህሙማን ማከሚያ ክፍሎች ውስጥ የተሠራ ጥናት፤ 4 ሜትር መራቅ የተሻለ መሆኑን ጠቁሟል። በሌላ በኩል የአሜሪካ የበሽታዎች ቁጥጥር ተቋም፤ ጥቃቅን የፈሳሽ ቅንጣቶች (ኤሮሶልስ) ቫይረሱን ስለማሰራጨታቸው ገና አልታወቀም ብሏል። ከርቀት ውጪ ያሉ ነገሮች ስለበሽታው ስርጭት ሲነሳ ከግምት የሚገባው ርቀት ብቻ አይደለም። በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ለምን ያህል ጊዜ ቆይተናል? የሚለውም መታየት አለበት። ቫይረሱ ካለበት/ካለባት ሰው ጋር ዘለግ ላለ ጊዜ መቆየት ለበሽታው የመጋለጥ እድልን ያሰፋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥትን የሚያማክሩ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ፤ ከአንድ ሰው ጋር ለስድስት ሰከንድ በአንድ ሜትር ርቀት መቆየት እና በሁለት ሜትር ርቀት ለአንድ ደቂቃ መቆየት እኩል ናቸው። ሳል ካለበት ሰው ጋር መቀራረብ ደግሞ የበለጠ አስጊ ነው። ከሚያስል ሰው 2 ሜትር መራቅና 2 ሜትር ርቆ መነጋገር እኩል ለበሽታው ያጋልጣሉ። በሰዎቹ ያሉበት ቦታ ምን ያህል ነፋሻማ ነው? የሚለውም መታየት አለበት። የተጨናነቀ ቦታ ለቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ያጋልጣል። አየር በየትኛው አቅጣጫ ይነፍሳል? የሚለውን ስንመለከት ደግሞ፤ ቫይረሱ ካለበት ሰው አቅጣጫ ወደሌለበት ሰው የሚነፍስ ከሆነ (ወይም ቬንትሌተር ትንፋሹን ከገፋው) ግለሰቡ ለበሽታው ይጋለጣል። ስለዚህም ክፍት ቦታ ላይ ወይም ንጹህ አየር በሚናፈስበት ቦታ መሆን ይመከራል። ለምሳሌ ቻይና በአንድ ሬስቶራንት ውስጥ ዘጠኝ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ነበር። በሬስቶራንቱ ግድግዳ ላይ ያለው የቤት ውስጥ አየር ሁኔታ መቆጣጠሪያ (ኤር ኮንዲሽኒንግ) ለበሽታው መዛመት ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል። በጃፓን በኮቪድ-19 በተያዙ 110 ሰዎች ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ቤት ውስጥ መሆን አደባባይ ከመሆን 19 ጊዜ በበለጠ ለቫይረሱ ያጋልጣል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅ መፍትሔው ምንድን ነው? የዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች 2 ሜትር መራራቅ ከተቻለ እሰየው፤ ካልተቻለ ግን ከአጭር ደቂቃ በላይ ሰዎች ባይጠጋጉ መልካም ነው ይላሉ። ሰዎች ፊት ለፊት እንዳይቀመጡ ማድረግና በተመሳሳይ ሰዓት አንድ የሥራ ቦታ ወይም ቢሮ የሚገቡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ይመክራሉ። በተለይም በሕዝብ ማመላለሻና የተጨናነቁ ቦታዎች የአፍን አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ያስፈልጋል። ኮሮናቫይረስ መሰራጨት ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ተመራማሪዎች ስለ ቫይረሱ ብዙ መረዳት ቢችሉም፤ አሁንም መመለስ ያልቻሏቸው በርካታ ጥያቄዎች አሉ። ገና ምላሽ ካልተገኘላቸው ጉዳዮች አንዱ ደግሞ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ምን ያህል ቫይረስ ይወጣል? የሚለው ነው። ታዲያ ለዚህ ግልጽ መልስ እስኪገኝ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ይመከራል።
news-52692170
https://www.bbc.com/amharic/news-52692170
ኮሮናቫይረስ፡ የወባ መድኃኒት ምን ያህል ኮሮናቫይረስን ለማከም ይችላል?
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለወባ ህመምተኞች ማከሚያ የተሠሩ መድኃኒቶች ለኮቪድ-19 ህክምና ይውላሉ ማለታቸውን ተከትሎ ጉዳዩ የበርካቶች መነጋገሪያ ከሆነ ሳምንታት ተቆጥረዋል።
ክሎሮኩዊን የወባ በሽታን ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል በእርግጥ እንደ ክሎሮክዊን ያሉ መድኃኒቶች ኮቪድ-19ኝን ያክሙ እንደሆነ ገና ምርምር እየተደረገባቸው ነው። ሆኖም አንዳንዶች ይህን መድኃኒት ራሳቸውን ለማከም መሞከራቸው የዓለም ጤና ድርጅትን አስግቷል። ከአሜሪካ የክትባት ምርምር መሪነታቸው የተነሱት ዶክተር ሪክ ብራይት እንዳሉት፤ ትራምፕ በዚህ መድኃኒት ላይ ማተኮራቸው ብዙ ሳይንቲስቶችን አወዛግቧል። መድኃኒቱ በስፋት እየተነገረለት ስለሆነም በዓለም ገበያ ተፈላጊነቱ ጨምሯል። ስለመድኃኒቱ ምን እናውቃለን? ትራምፕ በሚሰጧቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች ላይ ሀይድሮክሲክሎሮክዊንን ደጋግመው ያነሳሉ። እንዲያውም “ብትወሰዱ ምን ይጎልባችኋል?” ብለዋል። የብራዚሉ ፕሬዘዳንት ዣይር ቦልሶናሮ “ሀይድሮክሲክሎሮክዊን በየቦታው እየሠራ ነው” ቢሉም፤ ፌስቡክ የሐሰተኛ መረጃ ደንብን የተላለፈ ነው ብሎ መልዕክቱን አጥፍቶታል። ትራምፕ መጋቢት ላይ ስለመድኃኒቱ መናገራቸውን ተከትሎ፤ የሀይድሮክሲክሎሮክዊን እንዲሁም የክሎሮክዊን ፍላጎት ጨምሮ ነበር። ክሎሮክዊን የያዙ እንክብሎች ወባን ያክማሉ። ትኩሳት የሚቀንሱ ሲሆን፤ ኮቪድ-19ኝ የሚያስከትለውን ቫይረስ ሊያክሙ ያስችላሉ የሚል ተስፋ አለ። አሁን ላይ ይህ እውነት ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ የለም። ሰዎች ላይ የኩላሊትና ሳምባ ጉዳትን ጨምሮ ሌሎችም የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ እተባለ ነው። የወባ መድኃኒት ለኮቪድ-19 የሚውል ስለመሆኑ ሪፖርት የሠሩት የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ተመራማሪ ኮሜ ጊንጊኔ እንደሚሉት፤ መድኃኒቱ ውጤታማ መሆኑን ለማረጋገጥ ሰፊ የሙከራ ሂደቶችን ማለፍ አለባቸው። በዩናይትድ ኪንግደም፣ አሜሪካ፣ ስፔን እና ቻይና ከ20 በላይ ሙከራዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ። በአሜሪካ በክሎሮክዊን፣ በሀይድሮክሲክሎሮክዊን እንዲሁም አዚትሮሚሲን በተባለ ፀረ ተህዋስን (አንቲባዮቲክ) በማዋሃድ ኮቪድ-19ን ለማከም ሙከራ እየተደረገ ነው። መድኃኒቶቹ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የፈቀዱት የትኞቹ አገራት ናቸው? መጋቢት መጨረሻ ላይ የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ተቋም መድኃኒቶቹ ለተወሰኑ ሰዎች ህክምና እንዲውሉ ‘የአስቸኳይ ጊዜ ፍቃድ’ ሰጥተዋል። ይህ ማለት ግን መድኃኒቶቹ ይሠራሉ ማለት እንዳልሆነ ግን ተቋሙ ገልጿል። ለተወሰኑ የኮቪድ-19 ምርመራዎች ሆስፒታሎች መድኃኒቶቹን ማዘዝ ይችላሉ። በአንዳንድ ህሙማን የልብ ምት ችግር መታየቱን ተከትሎ፤ ሚያዝያ ላይ ተቋሙ መድኃኒቶቹ አደገኛ እንደሆኑ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ጀርምን አየሚገኝ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ 30 ሚሊዮን ሀይድሮክሲክሎሮክዊን ለአሜሪካ ብሔራዊ የመድኃኒት ክምችት መለገሱም ተገልጿል። ፈረንሳይ ለኮቪድ-19 ታማሚዎች መድኃኒቱ እንዲሰት ብትፈቅድም የህክምና ባለሙያዎች ተቆጣጣሪ ተቋም ስለ መድኃኒቱ የጎንዮሽ ጉዳት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የሕንድ መንግሥት መድኃኒቱ ጥቅም ላይ እንዲውል መክሯል። የአገሪቱ የምርምር ተቋም ግን መድኃኒቱ ገና በሙከራ ላይ ያለ እንደመሆኑ ለአስቸኳይ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል አለበት ብሏል። በርካታ የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት መድኃኒቱ ጥቅም ላይ እንዲውል የፈቀዱ ሲሆን፤ ሙከራ ላይ የሚገኙም አሉ። ከእነዚህ መካከል በሀይድሮክሲክሎሮክዊን ኮቪድ-19ኝን ካከሙ አገሮች አንዷ መሆኗን የምትገልጸው ባህሬን ትገኝበታለች። ሞሮኮ፣ አልጄሪያና ቱኒዝያም ይቀሳሉ። አሜሪካ ውስጥ መድኃኒቶቹ ኮሮናቫይረስን ማከም እንደሚችሉ ለማወቅ ጥናት አዕተደረገ ነው በቂ ሀይድሮክሲክሎሮክዊን አለ? መድኃኒቱ ኮቪድ-19ኝን ለማከም ሊውል ይችላል ከተባለ በኋላ የበርታ አገራት ፍላጎት ጨምሯል። በተለይም በታዳጊ አገራት ክሎሮክዊን እና መሰል መድኃኒቶች በየፋርማሲው ይገኛሉ። በእርግጥ ወባ እየጠነከረ ስለመጣ የመድኃኒቱ ውጤታማነት እየቀነሰ ነው። ዮርዳኖስ ሰዎች ሀይድሮክሲክሎሮክዊን ገዝተው እንዳያከማቹ በሚል የመድኃኒቱን ሽያጭ አግዳለች። ኩዌት ደግሞ በሆስፒታሎችና የጤና ማዕከሎች ብቻ እንዲሸጥ ወስናለች። ከአፍሪካ አገራት ደግሞ ኬንያ መድኃኒቱ ያለ ሐኪም ማዘዣ ለማንም እዳይሸጥ አግዳለች። ሕንድ መድኃኒቱን በዋነኛነት ታመርት ነበር። በአንድ ወቅት ግን ለውጪ ገበያ እንዳይቀርብ ማዕቀብ ጥላ የነበረ ቢሆንም፤ ትራምፕ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲን በግል ካነጋገሩ በኋላ ማዕቀቡ ተነስቷል። መድኃኒቱን ያለ ትዕዛዝ መውሰድ ለአደጋ ያጋልጣል በናይጄሪያ ክሎሮክዊን ያላቸው እንክብሎች ወባን ለማከም ይውላሉ። እአአ 2005 ላይ የመድኃኒቱ ውጤታማነት በመቀነሱ ታግዶ ነበር። ክሎሮክዊንን ለኮቪድ-19 ስለመጠቀም ቻይና ውስጥ የተሠራ ጥናት በናይጄሪያዋ ሌጎስ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ሰዎች መድኃኒቱን ማጠራቀምም ጀምረዋል። ትራምፕ በሽታውን ለማከም ይውላል ሲሉ ደግሞ የመድኃኒቱ ፍላጎት በእጥፍ ጨምሯል። ከመድኃኒት መደብሮች ተሽጦ ለማለቅም ጊዜ አልወሰደበትም። የናይጄሪያ የበሽታ ቁጥጥር ተቋም በበኩሉ ሰዎች መድኃኒቱን እንዳይወስዱ አስጠንቅቋል። በሌላ በኩል የናይጄሪያዋ ባውቺ ግዛት አገረ ገዢ ባላ ሞሐመድ፤ መድኃኒቱን ከወሰዱ በኋላ ሌሎች ሰዎችም እንዲጠቀሙበት መክረዋል። የሌጎስ ባለሥልጣናት እንደሚሉት፤ መድኃኒቱን ከመጠን በላይ ወስደው ሰውነታቸው የተመረዘ ሰዎች በርካታ ናቸው።
53963769
https://www.bbc.com/amharic/53963769
ካናዳ ፡ የመጀመሪያው የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐውልት በተቃዋሚዎች ተገረሰሰ
በሞንትሪያል ካናዳ ተቃዋሚዎች የሰር ጆን ኤ ማክዶናልድን ሐውልት ገረሰሱ፡፡
ሰር ማክዶናልድ የካናዳ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስተር ናቸው፡፡ ሰውየው በሥልጣን በነበሩበት 19ኛው ክፍለ ዘመን የአገሬውን ነዋሪ ሰዎች በመጨፍጨፍ ታሪክ ይጠቀሳሉ፡፡ አንድ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያለ ቪዲዮ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሐውልት ከነበረበት ማማ በአፍጢሙ ሲተከልና ወደ መንገድ ተንከባሎ ሲሄድ የሚያሳይ ነው፡፡ የኩቤክ የመንግሥት ተጠሪ ድርጊቱን "ተቀባይነት የሌለው" ብለውታል፡፡ ‹የታሪካችንን አካል ማጥፋት መፍትሄ አይደለም› ብለዋል የኪቤት አስተዳደር ፍራንኮይስ ሊጎት፡፡ የካናዳዊ ሲቢኤስ እንደዘገበው እስካሁን ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋለ የለም፡፡ ሰር ማክዶናልድ እንደነሱ አቆጣጠር ከ1860ዎቹ እስከ-1890ዎቹ በአመራርነት የቆየ ሲሆን በአገር ግንባታ ፖሊሲዎቹ የሚታወስ ነው፡፡ ሆኖም ሪዚደንሻል ስኩል ሲስተም የሚባል የአዳሪ ትምህርት ቤት አሰራርን በመቅረጽ አግላይ ፖሊሲን ተግባራዊ አድርጓል ተብሎ ይተቻል፡፡ ለመቶ ዓመት ያህል ተግባራዊ በሆነው በዚህ ፖሊሲ 150ሺ ነባር የአገሬው ተወላጅ ቤተሰብ ልጆች ከቤታቸው ተፈናቅለው በመንግሥት የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርገዋል፡፡ የነባር አገሬው ልጆች በዚህን ጊዜ በቋንቋቸው እንዳይናገሩ፣ ባህላቸውን እንዲጫኑ ተደርገዋል፡፡ በርካቶችም በዚህ ወቅት ለሞት ተዳርገዋል፡፡ መንግሥት በ2015 ራሱ እንዳመነው ያ የትምህርት ፖሊሲ ‹‹የባሕል ጭቆናና የባህል ዘርፍ ፍጅት›› ተብሎ መጠራት ያለበት ስሁት ተግባር ነበር፡፡ ማክዶናልድ በዚያ ዘመን ነባር የአገሬው ሰዎችን ሆን ብሎ በማስራብ እንዲሁም በበሽታ እንዲያዙ በማድረግ ከዚያ አገር እንዲጠፉ አድርጓል በሚል ይከሰሳል፡፡ ሐውልቱን የገረሰሱት የመብት ተቆርቋሪዎች የመጀመርያው የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር የነጭ አክራሪ ብሔርተኛ፣ ባሕል ጨፍላቂና የዘር ፍጅትን የፈጸሙ ወንጀለኛ ናቸው ይላሉ፡፡ ለሞንቴሪያል ከንቲባ ከዚህ ቀደም ሀውልቱ እንዲፈርስ ፊርማ ተሰብስቦ ተግባራዊ ሊያደርጉት ስላልቻሉ ግዴታችን ተወጥተናል ብለዋል ተቃዋሚዎቹ፡፡ የጆርጅ ፍሎይድን የግፍ ግድያ ተከትሎ በዓለም ላይ በባርነትና ዘረኝነት የሚታወቁ ‹ጀግኖች› ሐውልቶች በበርካታ ከተሞች እንዲፈርሱ ሆነዋል፡፡ በአሜሪካ የክርስቶፎር ኮሎምቦስ ሐውልት እና የኮንፌዴሬት ባሪያ አሳዳሪ የነበሩ መሪዎች ሐውልቶች የፈረሱ ሲሆን በዩኬ የባሪያ ንግድ ያስፋፉ መሪዎች ሐውልቶች ተገርስሰዋል፡፡ በቤልጂየምም ተቃዋሚዎች በተመሳሳይ የንጉሥ ሊዮፓርድ ዳግማዊን ሐውልት ጉዳት አድርሰውበታል፡፡ ሊዮፓርድ ዳግማዊ በአሁኗ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባደረሰው ግፍ ነው ተቃውሞው የተነሳበት፡፡ ኮንጎ ያን ጊዜ የንጉስ ሊዮፓርድ ዳግማዊ የግል ሀብቱ ነበረች፡፡
news-48979428
https://www.bbc.com/amharic/news-48979428
ትራምፕ የኢራን ኒውክሌር ስምምነትን ያፈረሱት ''ኦባማን ለማበሳጫት'' ነው
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከኢራን ጋር ደርሳ የነበረውን የኒውክሌር ስምምነት ያፈረሱት ባራክ ኦባማን ለማበሳጨት መሆኑን በአሜሪካ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር የነበሩት ሰር ኪም ዳሮች መልዕክት አጋለጠ።
የሰር ኪም ዳሮች አፍትልኮ የወጣው መልዕክት፤ የትራምፕ አስተዳደርን ውሳኔን በቅድሞ ፕሬዝደንት የተደረሱት ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ማፈራረስ ላይ ያተኮረ ነው ሲሉ መተቸታቸውን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ''ግላዊ በሆኑ ምክንያቶች' ስምምቱን ችላ ብለውታል፤ ምክንያቱም ስምምቱ የተደረሰው ከእርሳቸው በፊት በነበሩት ፕሬዝድንት ነውና" ሲሉ የቀድሞ አምባሳደር ጽፈዋል። • የእንግሊዝ አምባሳደር የትራምፕ አስተዳደርን 'የፈረሰ እና የተከፋፈለ' ሲሉ ወረፉ • ኒው ዮርክ መብራት መጣ ጋዜጣው እንደ ዘገባው ከሆነ ይህ መልዕከት የተጻፈው በወቅቱ የዩናይድት ኪንግደም የውጪ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ቦሪስ ጆንሰን አሜሪካ ከኢራን ጋር የተደረሰውን የኒውክለር ስምምነት እንዳታፈርስ የትራምፕ አስተዳደርን በጠየቁበት ወቅት ነው። የአሜሪካ እና ኢራን የኒውክለር ስምምነት ኢራን ዩራኒያም የማበልጸግ እንቅሳቃሴዎቿን እንድተገድብ የሚያስገድድ ነበር። በተጨማሪም ኢራን ላይ ተጥለው የቆዩት መጣኔ ሃብታዊ ማዕቀቦች እንዲነሱ፣ ዓለም አቀፍ የኒውክለር እንቀስቃሴን የሚያጠኑ ቡድን አባላት በኢራን ክትትል እንዲያደርጉ የሚፈቅድ ነበር። ከቀናት በፊትም ዴይሊ ሜይል ኪም ዳሮች የትራምፕ አስተዳደርን 'ደካማ፣ በራሱ የማይተማመን፣ ክህሎት የሌለው' ሲሉ ወርፈዋል ሲል መዘገቡ ይታወሳል። ከቀድሞው የእንግሊዝ አምባሳደር አፈትልከው በወጡ ኢሜይሎች ላይ ዋይት ሃውስ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሥር ''የፈረሰ'' እና ''የተከፋፈለ'' ነው ብለውት ነበር። ፕሬዝደንት ትራምፕ አና ሰር ኪም ዳሮች የብሪታኒያ የውጪ ጉዳይ ቢሮ አፈትልከው የወጡት ኢሜይሎች ''ከባድ ችግር ፈጥረዋል'' በማለት ሃሰተኛ አለመሆናቸውን አረጋግጧል። ሰር ኪም ዳሮች ከመንግሥታቸው ጋር የተለዋወጧቸው መልዕክቶች አፈትልከው ከወጡ በኋላ በገዛ ፍቃዳቸው አምባዳሰርነታቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ሰር ኪም ዳሮችን የአገር መሪ ይለዋል ተብሎ በማይጠበቅ ሁኔታ ''በጣም ደደብ ሰውዬ ነው...' ማለታቸው ባለፈው ሳምንት የዓለም መገናኛ ብዙኃንን ትኩረት የሳበ ጉዳይ ነበር።
news-56506557
https://www.bbc.com/amharic/news-56506557
የኢትዮጵያ የዝናብ ቴክኖሎጂና የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ድጋፍ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ማክሰኞ ዕለት በተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት በጎጃም እና በሸዋ አካባቢዎች በሰው ሠራሽ ቴክኖሎጂ አማካይነት ዝናብ ማዝነብ እንደተቻለ መናገራቸው መነጋገሪያ ሆኗል።
አንዳንዶች በኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ሊሆን አይችልም ከሚል ግምት የተነሳ በተለያዩ መልኮች ጥርጣሬያቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ሲያንጸባርቁ ነበር። ቀሪዎቹ ደግሞ የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በማንሳት የጉዳዩን ሳይንሳዊነት እየገለጹ ነው። የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ድርጅት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክንፈ ኃይለማርያም ጉዳዩ አዲስ ነገር እንዳልሆነ ጠቅሰው "በብዙ አገራት ውስጥ ተሞክሯል" ብለዋል። ክላውድ ሲዲንግ ወይም "እኛ ደመና ማበልጸግ ልንለው እንችላለን" የሚሉት አቶ ክንፈ "ሳይንሱ በብዙ አገራት ተሞክሯል። ደመና የተፈለገውን ዝናብ የማይሰጥባቸው ምክንያቶች ስላሉ የደመና አቅምን የመጨመር ሂደት ነው። በዚህም ተጨማሪ ዝናብ እንዲፈጠር ያደርጋል" ይላሉ። በተፈጥሯዊ ሂደት ደመና የተለያዩ ዑደቶችን አልፎ ዝናብ ይሆናል። ዑደቱ ተጠናቆ ወደ ዝናብ ለመቀየር በቂ ንጥረ ነገርም ያስፈልገዋል። ይህ ካልሆነ ዝናብ አይኖርም። ሳይንሱም አስፈላጊውን ተጨማሪ ንጥረ ነገር በመጨመር ደመናን ወደ ዝናብ የሚቀይር ነው። ይህ ሂደት ነው ክላውድ ሲዲንግ ወይም ደመና ማበልጸግ የሚባለው። ደመና እንዴት ዝናብ ይሆናል? በአንድ ደመና ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወደ ዝናብ ያልተቀየሩ የዝናብ ነጠብጣቦችን ይኖራሉ። እነዚያም መጠናቸው አድጎ በመሬት ስበት ዝናብ ሆነው እንዲመጡ መሰባሰብ አለባቸው። "በሂደቱ ነጠብጣቦቹን የሚሰበስብ ኬሚካል ነው የሚደረገው። የጨው ዝርያ ያላቸው እንደ ሶዲየም፣ ፖታሺየም፣ ክሎራይድና ናኖ ቴክኖሎጂ ለዚህ ተግባር ይውላሉ" ሲሉ አቶ ክንፈ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ስለዚህም ደመናው ኖሮ፣ በቂ እርጥበት ኖሮት፣ በበቂ ደረጃ አድጎ ወደ ዝናብ የማይቀየር ደመና የተጠቀሱት ንጥረ ነገሮችን ሲያገኝ በዓይን የማይታዩት የዝናብ ጠብታዎች ተሰብስበው ወደ ዝናብነት እንዲያድጉ ያደርጓቸዋል። ይህ ተግባር እውን መሆን ከጀመረ ከሰባ ዓመታት በላይ የሆነው ሲሆን፤ ለዚህም በዓለም በሜትሮሎጂ ድርጀት የሚታወቁ ከ50 በላይ የዝናብ ማበልጸጊያ መንገዶችም አሉ። እነዚህን ንጥረ ነገሮች ወደ ደመና ለማድረስ የተለያዩ አገራት የተለያዩ ዘዴዎች የሚጠቀሙ ሲሆን፤ ለምሳሌም ቻይና ሮኬት ስትጠቀም ኢራን ደግሞ በሰው አልባ አውሮፕላኖች (በድሮን) ወደ ደመና ትደርሳለች። እንደ ኢትዮጵያ ተራራማ የሆኑ አገራት ከተራራዎች ላይ በመሆን ንፋስ በሚመጣበት አቅጣጫ ከመሬት ንጥረ ነገሮቹን በጭስ መልክ በመልቀቅ ወደ ደመናው እንዲደርስ ያደርጋሉ። ለዚህ አገልግሎት በዋነኝነት የሚውለው ግን በአውሮፕላን አማካይነት የሚደረገው የንጥረ ነገሮቹ ርጭት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥም ተግባራዊ የተደረገው በአውሮፕላን መሆኑን የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ድርጅት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ክንፈ እንደሚሉት ደመናን ወደ ዝናብ በመቀየር በኩል "ከአፍሪካ እንደ ኒጀር፣ ማሊ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሮኮ ያሉ አገራት የሚጠቀሱ ሲሆን፤ ከእስያ በቻይና በስፋት ጥቃም ላይ ውሏል። እስራኤልም በዚህ የታወቀች ነች። በጠቃላይ ከ40 በላይ አገራት ዘዴውን ይጠቀማሉ" ይላሉ። "ስለዚህም ለእኛ ነው እንጂ ለሌላው ዓለም ጉዳዩ አዲስ አይደለም። ለዚህ ደግሞ የደመናው ዓይነት ይለያል። ጊዜና ቦታውም ይለያል። የሚደረገውም ለመዝነብ የማይችል ደመናን ማበልጸግ ነው። በብዙ አገራት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፤ እኛ አገርም እየተሞከረ ነው" ሲሉ በተጨባጭ መሞከሩን አረጋግጠዋል። ይህም ተግባር ኢትዮጵያ ውስጥ በሙከራ ደረጃ ላይ መሆኑን የሚገልጹት ምክትል ሥራ አስፈጻሚው፤ ለዚህ የሚሆኑ አካባቢዎችም በተለያዩ መስፈርቶች አማካይነት እንደሚመረጡም ገልጸዋል። "ቦታዎቹ የሚመረጡት በአየር ንብረት ራዳር የሚካለሉ እና ለሙከራው የሚሆን ደመና መኖሩ ሲረጋገጥ ነው። የአሁኑ ሙከራም የመጀመሪያ ነው" ብለው ከዚህ በመነሳትም ሰፋ ያለ ፕሮግራም እንደሚኖር አስረድተዋል። ደመናን ወደ ዝንብ የሚለውጠው ንጥረ ነገር ከአውሮፕላን ክንፍ ላይ የሚረጭበት መንገድ ድርቅን ለማስወገድ ሊውል ይችላል? ደመናን ወደ ዝናብ ለመቀየር ጥቅም ላይ የሚውለው ቴክኖሎጂ የዓለም አገራትን በተለያዩ ጊዜያት የሚያጠቃውን የድርቅ ችግር በመቅረፍ በኩል አስተዋጽኦ ሊኖረው ይችል እንደሆነ የበርካቶች ጥያቄ ነው። ድርቅ የረዥም ጊዜ የዝናብ እጥረት መሆኑን የሚናገሩት አቶ ክንፈ "ደመናው ካልመጣ ዝናቡን ማበልጸግ አይቻልም። ደመናውን ደግሞ አንፈጥርም። ለመበልጸግ ዝግጁ የሆነ ደመና በተፈጥሮ መምጣት አለበት" ይላሉ። ይህ ዝናብን የማዝነብ ዘዴ ድርቅን ለመከላከል አስተዋጽኦው ዝቅተኛ ነው። ምክንያቱም ደመና በሌለበት ቦታ ተግባራዊ ሊሆን ስለማይችል ነው። "ደመና ኖሮ ከደመናው የሚገኘውን ዝናብ የመጨመር ዘዴ ነው እንጂ፤ ሙሉ ለሙሉ በረዥም ጊዜ ድርቅ ደመና የማይፈጠር ከሆነ ድርቅን መቀየር አይደለም" ብለዋል አቶ ክንፈ። ይህ ዝናብን የማግኘት ዘዴ በተለይ በአንድ ወቅት የሚጠበቀው የዝናብ መጠን ሳይገኝ ቀርቶ ደረቃማ ሁኔታ ሰፍቶ ሲገኝ በሰብሎች ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል። ስለዚህም በዚያ ወቅት የተወሰኑ ቀናት እንዲዘንብ በማድረግ መስክ ላይ ያሉትን የአዝዕርቶች የማገዘዝ ዕድልን ይፈጥራል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ ተራራማ መሆኗ ደመናን በማበልጸግ በኩል የራሱ ጠቀሜታ እንዳለው የሚጠቅሱት አቶ ክንፈ፤ "በአንዳንድ ወቅቶች ደመና እያለ የማይዘንብባቸው ቦታዎች አሉ። ተራራማ ቦታዎች ደመናን በማበልጸግ ከሜዳማ አካባቢዎች ይልቅ በተሻለ ሁኔታ የዝናብ መጠን ለመጨመር ያስችላሉ" ብለዋል። ኢትዮጵያ ከየት ድጋፍ አገኘች? ኢትዮጵያ ዝናብ የማበልጸጉን የሙከራ ተግባር እያከናወነች ያለችው ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ መንግስት እና የሜትሮሎጂ ማዕከል ጋር በመተባበር ባገኘችው የቴክኖሎጂና የባለሙያዎች ድጋፍ እንደሆነ አቶ ክንፈ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህንን ሥራ በዋናነት የሚያስተባብረውና የሚመራው ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሲሆን የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ፣ ብሔራዊ ሜትሮሎጂ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም፣ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየተሳተፉበት ይገኛሉ። ሥራው አስካሁን በሙከራ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን ለዚህም አገሪቱ የነበራት አንድ የአየር ንብረት መከታተያ ራዳርን ወደ በሦስት ለማሳደግ እየተሰራ ነው። ከዚህ አንጻርም አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ሳተለይት እንዳመጠቁ የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ድርጅት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክንፈ ጠቅሰዋል። ከደመና ዝናብ የማግኘቱ ሙከራ እንደሚቀጥልም ጠቅሰው በተከታይነት "ከአዲስ አበባ እስከ ሻውራ የተሻለ ደመና በተገኘበት አካባቢ ሙከራ ይደረጋል። ጥሩ ደመና ካገኘን ቅድሚያ ሰጥተን የምንሞክርበት ከሻውራ ወደ ወልዲያ ባለው አቅጣጫ ሰሜን እና ደቡብ ወሎን ጨምሮ ነው" ብለዋል። ይህ ሙከራ ግን የሚወሰነው ከአየር ሁኔታ መከታተያ ራዳር የሚገኘው የደመና ዓይነቶች ይዘት እና መጠንን በሚያመለክተው መረጃ ላይ ይሆናል። "በዚህም ምክንያት ሙከራው የሚደረግበትን ትክክለኛ ቀንና ቦታ ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው" ሲሉ አስረድተዋል።
53441799
https://www.bbc.com/amharic/53441799
ጥላቻን፣ ጥቃትንና ጠብ አጫሪነትን የያዙ የፌስቡክ መልዕክቶች እንዴት ይታያሉ?
በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሆነ ተብሎም ይሁን በስህተት ሌሎችን ሊጎዱ የሚችሉ መልእክቶች ይተላለፋሉ።
በኢትዮጵያም በተለይ ፌስቡክን በመጠቀም የሚተላለፉ መልዕክቶች ጥላቻንና ንጹሃንን በተለያየ መልኩ ለጉዳት እየዳረጉ ነው ሲሉ መንግሥትን ጨምሮ አንዳንዶች ወቀሳ ይሰነዝራሉ። የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሩ ፌስቡክም መሰል መልዕክቶች በሌሎች ላይ የሚያሳድሩትን ጫና ለመቅረፍ በማሰብ ማንኛውም የፌስቡክ ተጠቃሚ በገፁ ላይ ሰፍረው የሚመለከታቸው ነገሮች መልዕክቶች (Facebook posts) በሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ ብለው ካመኑ ጉዳዩን ለፌስቡክ ሪፖርት የሚያደርጉበት ቀላል አማራጭ አለው። በዚህም ፌስቡክ በድረገጹ ላይ የተላለፉት መልዕክት ይዘቶች የማኅብራዊ ሚዲያውን ሕግጋት ያልተከተሉ ከሆነ ከገጹ ላይ ያስወግዳል። ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ የፌስቡክ መልዕክቶች የትኞቹ ናቸው? የሚከተሉት አይነት ይዘት ያላቸው መልዕክቶች በተጠቃሚዎች ላይ ቀጥተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ፌስቡክ ሪፖርት ሊደረጉልኝ ይገባል ይላል። መልዕክቶቹ በጽሁፍ፣ በፎቶ ወይም በቪዲዮ መልክ ሊቀርቡ ይችላሉ። እነሱም የጥላቻ ንግግሮች ፌስቡክ የጥላቻ ንግግርን ሰዎችን በብሔራቸው፣ በቆዳ ቀለማቸው፣ በሐይማኖታቸው፣ በጾታቸው እና በአካል ጉዳተኝነታቸው በመለየት ከሰዋዊ ክብራቸው ዝቅ የሚያደርግ እና የሚያዋርድ ጥቃት ሲል ይገልጸዋል። በዚህም ምክንያት ፌስቡክ የጥላቻ ንግግሮችን ከገጹ ላይ ያስወግዳል። ሐሰተኛ ዜናዎች ሐሰተኛ ዜና ሆነ ተብሎ የፖለቲካ ወይም የገንዘብ ፍላጎትን ለማሟላት ሲባል የሚሰራጭ የውሸት መረጃ ማለት ነው። በርካቶች የግል ጥቅማቸውን ለማሳካት ሐሰተኛ መረጃዎችን እውነት በማስመሰል ያሰራጫሉ። በኢትዮጵያና በተለያዩ አገራት ውስጥ ፌስቡክን በመጠቀም የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለተለያዩ ጥፋቶችና ጉዳቶች መንስዔ መሆናቸው ከዚህ በፊት መዘገቡ ይታወሳል። ፌስቡክም ከተጠቃሚዎቹ በሚደርሱት ሪፖርቶች መሠረት አስፈላጊውን ማጣራት ካካሄደ በኋላ ሐሰተኛ መረጃዎቹን ከገጹ ላይ ያነሳል። ልቅ የሆኑ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ፌስቡክ ልቅ የሆኑ የግብረ ሥጋ ግነኙነትን እና እርቃንን የሚያሳዩ ምስሎችን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ያግዳል። ለዚህም እንደምክንያት የሚቀርበው እንደዚህ አይነት የአደባባይ መልዕክቶች ከማኅበረሰቡ እሴት ጋር አብሮ አይሄድም የሚለው አንዱ። በተጨማሪም ቪዲዮዎቹ እና ምስሎቹ የተገኙት ተገቢው ፍቃደኝነት በተሰጠበት ሁኔታ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ስለማይገኝላቸው ነው። ሽብር የሚነዙ መልዕክቶች የሸብር ጥቃትን ወይም ሽብርተኛን የሚያወድሱ፣ የሽብር ጥቃቶች እንዲፈጸሙ ወይም ለሽብር ቡድን አባልነት ጥሪ የሚያደርጉ፣ በሽብር ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ላይ የሚያፌዙ የፌስቡክ መልዕክቶች በፍጥነት እንዲጠፉ ይደረጋሉ። ተጠቃሚዎች ይህን አይነት ይዘት ያላቸውን መልዕክቶችን ሪፖርት እንዲያደርጉ ፌስቡክ ይጠይቃል። የኃይል ጥቃትን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶች ፌስቡክ የኃይል ጥቃትን የሚያሞግሱ እና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የሚያዋርዱ መልዕክቶችን ያስወግዳል ወይም ተጠቃሚዎቹ ምስሎቹን ከመመልከታቸው በፊት ምስሉ/ቪዲዮው ስሜት የሚተብሽ ይዘት እንዳለው በመግለጽ ያስጠነቅቃል። ከዚህ በተጨማሪም ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በፌስቡክ ፈጽሞ ተቀባይነት የላቸውም። ከላይ የተጠቀሱትን አይነት ይዘት ያላቸውን የፌስቡክ መልዕክቶች እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል? ቀላል ነው። ለምሳሌ በምስሉ ላይ የሚታየው መልዕክት ይዘት በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይ ጉዳት ያደርሳል ብለን እናስብ። ይህን መልዕክት ለፌስቡክ ሪፖርት ለማድረግ ከመልዕክቱ በስተቀኝ አናት የሚገኙትን ••• (ሦስት ነጥቦችን) መጫን። ሦስቱን ነጥቦች ስንጫን የተለያዩ አማራጮችን ይሰጠናል። ከዚያም እርዳታ ያግኙ ወይም ፖስቱን ሪፖርት ያድርጉ (Find Support or report post) የሚለውን አማራጭ ይጫኑ። ከዚያም እርዳታ ያግኙ ወይም ፖስቱን ሪፖርት ያድርጉ (Find Support or report post) የሚለውን ሲጫኑ ከታች የሚታየውን አይነት ሌላ አማራጭ ይሰጥዎታል። ለምሳሌ የተመለከቱት የፌስቡክ ፖስት ወይም መልዕክት የጥላቻ ንግግር ይዘት ካለው፤ 'Hate Speech' የሚለውን ይጫኑ። ከዚያም ጉዳዩን ሪፖርት በማድረግዎ ከፌስቡክ ምላሽ ያገኛሉ። የፌስቡክ ፖስትን ሪፖርት ካደረኩ በኋላ ምን ይከሰታል? እርሶ ወይም ሌሎች አንድን የፌስቡክን ፖስት ሪፖርት ስላደረጉ ብቻ ፌስቡክ ከገጹ ላይ ያስወግደዋል ማለት አይደለም። ፌስቡክ የራሱ የሆነ 'ኮሚኒቲ ስታንዳር' ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መመሪያ አለው። ሪፖርት የሚደረጉለትን ይዘቶችንም የሚመረምረው እና ከውሳኔ የሚደርሰው 'ኮሚኒቲ ስታንዳርዱን' መሠረት በማድረግ ነው። እርስዎ ሪፖርት ያደረጉት ይዘት የትኛውም አይነት እርምጃ ይወሰድበት፤ እርሶ ይዘቱን ለፌስቡክ ሪፖርት ማድረጎ በሚስጥር የሚጠበቅ ነው የሚሆነው። የጥላቻን፣ ጥቃትና ግጭት ቀስቃሽ እንዲሁም የኅብረተሰብን እሴቶች የሚቃረኑ በማንኛውም መልኩ የቀረቡ መልዕክቶችን የፌስቡክን ሥርዓት ተጠቅሞ ሪፖርት በማድረግ ሊደርሱ የሚችሉ አሉታዊ ውጤቶችን መቀነስ ይቻላል።
news-56901134
https://www.bbc.com/amharic/news-56901134
የኤርትራ ወታደሮች መውጣት 'ቴክኒካዊና ወታደራዊ ጉዳይ ነው'- አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መውጣትን በተመለከተ የሚቀረው ወታደራዊ እና ቴክኒካዊ ጉዳይ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሁለቱም አገራት በአመራር ደረጃ የወታደሮቹን መውጣት የተስማሙበት ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ ፤ ቀሪው ቴክኒካዊ ጉዳይ ነው ብለዋል። አምባሳደር ዲና "የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ በሁለቱም አገራት ስምምነት ተደርሷል" ያሉት ማክሰኞ ዕለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ይሁን እንጂ ወታደሮቹ ከኢትዮጵያ ግዛት የሚወጡበት ሁኔታ "የቴክኒክ ጉዳይ ነው፤ የወታደራዊ ጉዳይም ነው። እንዴት ይወጣሉ? ምን ያህል ይወጣሉ? በምን ዓይነት ሁኔታ ይወጣሉ? እንዴትስ ይረጋገጣል? የሚሉት ጉዳዮች የቴክኒካዊ ጉዳዮች ናቸው" ያሉት አምባሳደር ዲና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጡም። በትግራይ ክልል ስላለው ግጭት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር መወያየታቸው የገለጹት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን "ትግራይ ውስጥ ያሉት የኤርትራ ወታደሮች በፍጥነት እና መረጋገጥ በሚቻል አኳኋን" ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ጠይቀዋል። የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የኤርትራ እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ እንቅፋት በመሆን ድርሻ አላቸው ብሏል። አክሎም እነዚሁ አካላት የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገውን የሦስትዮሽ ድርድር በቅርቡ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል። አምባሳደር ዲና የሦስትዮሽ ድርድሩ በቅርቡ እንደሚቀጥል ኢትዮጵያ ጽኑ እምነት አላት ብለዋል። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሕብረት ካላት አክብሮት አንፃር ድርድሩ በሕብረቱ እንዲቀጥል ፅኑ አቋም እንዳላት ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የሆነችው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ድርድሩ እንዲጀመር ትሰራለች የሚል እምነት እንዳላትም ተናግረዋል። ሱዳን እና ግብጽ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ወደ አሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት ለመውሰድ ፍላጎት ቢኖራቸውም በኢትዮጵያ በኩል ግን ተቀባይነት እንደሌለው በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል። በሌላ በኩል ሦስቱም አገራት ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ኢትዮጵያ ግድቡን ውሃ የምትሞላ ከሆነ ሱዳን እከስሳለሁ ማለቷን በተመለከተ የተጠየቁት አምባሳደር ዲና "ከዚህ በፊትም ብዙ ነገር ሲባል ቆይቷል፤ ይህንን ግድብ እናፈርሳለን ሲባል ቆይቷል" በማለት "ይህ ጉዳዩ ጊዜው ሲደርስ ቢመለስ ይሻላል" ሲሉ አክለዋል። በተጨማሪም አምባሳደሩ "ብዙ ጊዜ ለፉከራ መልስ መስጠት ጥሩ አይደለም፤ ለፉከራ መልስ መስጠት ለፉከራው እውቅና መስጠት ነው። ሁለተኛ ደግሞ የማይሆን ጨዋታ ይሆናል ስለዚህ የሚመከር አይደለም፤ የሚሆነውንም መጠበቅ ይሻላል" በማለት ሱዳን እከስሳለሁ ባለችው ላይ መልስ ሰጥተዋል። ከቀናት በፊት ሱዳን ኢትዮጵያ ግድቡ መሙላት የምትቀጥል ከሆነ ግድቡ ግንባታ ላይ የተሰማራውን የጣልያኑን ሳሊኒ ኩባንያንና የኢትዮጵያ መንግሥትን እከስሳለሁ ማለቷ ይታወሳል።
47113334
https://www.bbc.com/amharic/47113334
በአሜሪካ ሀሰተኛ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች መታሰር በሕንድ ቁጣን ቀሰቀሰ
በአሜሪካ 129 የህንድ ተማሪዎች መታሰራቸዉን ተከትሎ ደልሒ በሚገኘዉ የአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ ተቃዉሞ ተካሔደ።
ባለፈዉ ረቡዕ የአሜሪካ መንግስት ህጋዊ ካልሆነ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ አገኘኋቸዉ ያላቸዉን 129 ሕንዳዉያን ተማሪዎችን አስሯል። ሚቺጋን ግዛት የሚገኘዉ ፋርሚንግተን የተባለዉ ዩኒቨርሲቲ የሀገር ዉስጥ የደህንነት መስሪያ ቤት ዉክልና አለኝ በማለት በህገወጥ መልኩ ወደ አሜሪካ የገቡ ተማሪዎችን ሲመዘግብ መቆየቱን መንግስት ደርሸበታለሁ ብሏል። •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ •ሴት እስረኞችና የማዕከላዊ ምርመራ በተለይ ተማሪዎቹ በአሜሪካ እንዲቆዩ "ለመኖር መክፈል" በሚል እሳቤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን 8500 እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን 11000 ዶላር አመታዊ ክፍያ ያስከፍል ነበር። የሀሰት ዩኒቨርሲቲዉ በህገወጥ መልኩ ከተለያዩ ሀገራት ወደ አሜሪካ የገቡ ዜጎችን ታላሚ አድርጎ በጎርጎሳያውያኑ 2015 የተቋቋመ ነዉ። እናም ባለፈዉ ረቡዕ የአሜሪካ መንግስት ከዚሁ የሀሰት ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ አገኘኋቸዉ ያላቸዉን 129 ሕንዳዉያንን ጨምሮ 130 ተማሪዎችን አስሯል። •"ከሞቱት አንለይም" የሶማሌ ክልል እስረኞች ተማሪዎቹን ለማስፈታት ቅዳሜ ህንድ ደልሂ በሚገኘዉ የአሜሪካ ኤምባሲ በመሰባሰብ ህንዳዉያን ተቃዉሟቸዉን አሰምተዋል። ኤምባሲዉ በበኩሉ የተካሄደዉን የተቃዉሞ ሰልፍ እዉቅና ቢሰጥም ስለጉዳዩ ግን ያለዉ ነገር የለም። የህንድ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰልፉ የታሳሪዎቹን ደህንነት እና አማካሪ የማግኘት መብታቸዉን ለማስከበር ታስቦ የተደረገ መሆኑን ገልጿል። ራሱን እንደህጋዊ ተቋም በተለያዩ አማራጮች የሚያስተዋዉቀዉ ፋርሚንግተን ዩኒቨርሲቲ በድረ ገፁ ተማሪዎች ክፍል ዉስጥ ሲማሩ ፤ ቤተመጽሃፍት ሲያነቡ እና በሳራማ ግቢ ሲዝናኑ በፎቶ ያሳያል። ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚያስተዋዉቅበትም የሀሰት የፌስቡክ ገጽ አለዉ። ነገር ግን ባለፈዉ ሳምንት ከፍርድ ቤት የወጣ መረጃ እንደሚያሳዉ የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኞች የኢምግሬሽንና የጉምሩክ ሰራተኞች እንጂ መደበኛ ሰራተኞች እንዳልሆኑ አረጋግጧል። መንግሥትም ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲዉ ህጋዊ አለመሆኑን እያወቁ የተመዘገቡ በመሆናቸዉ በህግ እንዲጠየቁ አደርጋለሁ ብሏል። የህንድ መንግሥት ግን ዜጎቼ በፍጹም ይህን አያደርጉም በወንበዴዎች ተታልለዉ በመሆኑ ምህረት ሊደረግላቸዉ ይገባል በማለት ተማጽኗል። በተለይ ተማሪዎቹ ያሉበት ሁኔታ እንዲገለጽ፤ ቀድመዉ ከእስር እንዲለቀቁ እና ከአሜሪካ እንዳይባረሩ የአሜሪካን መንግሥት መጠየቁን የህንድ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አስታዉቋል። ከተማሪዎች በተጨማሪ 8 ሰዎች ስደተኞችን ለትርፍ በመጠቀም እና በቪዛ ማጭበርበር ወንጀል ተከሰዋል። እነዚህ ግለሰቦች በተለይ ተማሪዎችን በመመልመልና በማግባባት ከፍተኛ ሚና ነበራቸዉ ተብሏል። በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት በስደተኞች ጉዳይ ጥብቅ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። በተመሳሳይ ከሶስት አመት በፊት ስደተኞችን መሰረት ያደረገ የሃሰት ዩኒቨርስቲ በመገኘቱ ብዙዎቹ ከቻይና እና ከህንድ የሆኑ 21 ሰዎች በሰሜን ኒዉ ጀርሲ ታስረዉ ነበር። ባለፉት ሁለት የትራምፕ የአስተዳደር አመታት ደግሞ የብዙዎቹ ሰነድ አልባ እና ቪዛ ጠባቂዎች ጉዳይ እንዲዘጋ ተደርጓል። በዚህ ሂደትም በርካታ የስራ ቦታዎች የእስረኞች መገኛ ሆነዉ ቆይተዋል። በሁለቱ የትራምፕ አመታት ብቻ የኢምግሬሽንና የጉምሩክ መስሪያ ቤት ኦሃዮ ዉስጥ ከሚገኝ አንድ የስጋ አቃራቢ ድርጅት 146 ሰዎችን እና ቴክሳስ ዉስጥ ከሚገኝ ሌላ ፋብሪካ ዉስጥ ደግሞ 150 ስደተኞችን በዚሁ ምክንያት አስሯል።
41199222
https://www.bbc.com/amharic/41199222
በግንባታዎች ምክንያት እየጨመረ የመጣው የአሸዋ ፍላጎት ወንዞችን እያጠፋ ነው
እርግጥ ያለ አሸዋ ኮንክሪት አይሰራም። በብዙ የአፍሪቃ ሃገራት የሚገኙ ወንዞች ለአሸዋቸው ሲባል እየተሟጠጡ ይገኛሉ። በዚህ በኩል በአሸዋ ሕንፃ ይገነባል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የወንዞች ህልውና አደጋ ላይ እየወደቀ ይገኛል።
አሸዋ የወብ ወሃ ዳርቻዎች ማሳመሪያ፤ የምዕተ ዓመታት የአየር ንብረት ለውጥ የፈጠራቸው ደቂቅ እና አንፀባራቂ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ድንጋዮች ስብስብ፤ አሸዋ። አባባሉም እንደ አሸዋ ያብዛችሁ ነውና አሸዋ ቁጥር ስፍር የሌለው ነገር ቢመስለንም አሁን ላይ አደጋ ከተጋረጠባቸው የምድራችን ሀብቶች አንዱ ሆኗል። ቆም ብለን ብናስብበት እውነታው ሊገለጥልን ይችላል። ሁሉም የሕንፃ መሰረታዊያን ማለትም እነኮንክሪት፣ ጡቦች፣ እንዲሁም መስተዋት ከአሸዋ ነው የሚሰሩት። እጅጉን እየጨመረ የመጣው የሰው ልጅ ቁጥር እና በፍጥነት በማደግ ላይ ያለው የግንባታ ዘርፍ አሸዋን ከውሃ ቀጥሎ በምድራችን ላይ በጣም ተፈላጊው ተፈጥሯዊ ሀብት አድርጎታል። በቢሊዮን ቶን የሚቆጠር አሸዋ በየቀኑ በዓለም ዙሪያ ጥቅም ላይ ይውላል። የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት እንደሚያሳየው እ.አ.አ. ከ2012 ጀምሮ በዓለማችን ጥቅም ላይ የዋለው አሸዋ በምድር ወገብ ዙሪያ 27 ሜትር ከፍታ እና 27 ሜትር ስፋት ያለው የኮንክሪት አጥር መስራት ይችላል። በአሸዋ ለመከበብ የባህር ዳርቻዎች ጋር መሄድ አይጠበቅብንም። ዙሪያችንን የከበቡን መኖሪያ ቤቶች እና መሰል ሕንፃዎች በኮንክሪት መልክ የቆሙ አሸዋዎች ናቸው። ለግንባታ የሚውለው አሸዋ በዋነኛነት ከወንዞች ስር እና ከውቅያኖሶች ግርጌ የሚመጣ ነው። የበረሃ አሸዋ ከሌሎች የግንባታ ምርቶች ጋር ለመቀላቀል በጣም አመቺ የሆነ ተፈጥሯዊ ሀብት ነው። ትላልቅ የዱባይ የግንባታ ዕቅዶች በሀገሪቱ ዙሪያ የሚገኙ አሸዋዎችን ከማራቆታቸው የተነሳ በአሸዋ ላይ የተገነባችው ከተማ ዱባይ አሁን ላይ ከአውስትራሊያ አሸዋ ማስመጣት ጀምራለች። የአሸዋ ፍላጎት በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከመድረሱ የተነሳ በሥነ ምህዳር ላይ ከሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ባለፈ ለሰው ሕይወት መጥፋት መንስኤ መሆን ጀምሯል። በህንድ በነውጠኛ ማፊያዎች እየተመራ የአሸዋ ጥቁር ገበያ ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅጉን ደርቷል። በቻይና የሀገሪቱ ትልቁ የንፁህ መጠጥ ውሃ ምንጭ የሆነው የፖያንግ ሀይቅ በአሸዋ ቁፋሮ ምክንያት መድረቅ ጀምሯል። በወንዙ አከባቢ የሚኖሩ እና በዓሳ ማጥመድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች እና በወንዙ ዙሪያ የሚኖሩ ወፎች ሕይወት አደጋ ላይ ወድቋል። የሀገሪቱ የሕዝብ ቁጥር ዕድገት በ2040 በእጥፍ እንደሚያድግ በሚጠበቅባት ኬንያ እንደ የባቡር መንገድ ዝርጋታ ያሉ ትላልቅ የግንባታ ዕቅዶች በብዙ ቶን የሚቆጠር አሸዋ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል። የኬንያ የባህር ዳርቻዎች እና ወንዞች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአሸዋ ቁፋሮ ምክንያት እጅጉን መራቆት ጀምረዋል። ነገር ግን እንደ ማኩዌኒ ባሉ ዝቅተኛ ኑሮ በሚገፉ አከባቢዎች የአሸዋ ቁፋሮ ነዋሪዎችን ያለመጠጥ ውሃ እያስቀረ ይገኛል። ለግማሹ አሸዋ ሕይወት ሲሆን ለግማሹ ደግሞ ገንዘብ ነው። በማኩዌኒ ፖሊስ ጣቢያ አፊሰር የነበረው ጄዎፍሪ ካስዮኪ በአካባቢው የአሸዋ ቁፋሮን በመከላከል በጣም የተመሰገነ ስራ የሰራ ግለሰብ ነበር። በየካቲት 2011 ግን በጠራራ ፀሀይ አሸዋ ቆፋሪ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው ሬሳውን ጥለውት ሄዱ። ባለቤቱ አይሪን ስትናገር ''ወጣቶቹ ይህን ያደረጉት ሌሎች አሸዋ ቁፋሮን በማገድ ድርጊት ላይ ለተሰማሩ ሰዎች መልዕክት ለማስተላለፍ በማሰብ ነው'' ትላለች። በማኩዌኒ በግብርና ስራ ላይ የተሰማራው አንቶኒ በአከባቢው በአሸዋ ቁፋሮ ምክንያት የጠፋውን ኪሎሜ ኢኮልያ ወንዝን በትካዜ እየቃኘ ይሄንን 'የሞተው ወንዝ' እንለዋለን ይላል። ''ከጥቂት ዓመታት በፊት ይህ ወንዝ እንደልብ የሚፈስ ነበር። አሁን ግን አስር ሜትር ይህል ገብቶ ባዶውን ቀርቷል'' ባይ ነው አንቶኒ። አንቶኒ በደረቀው ወንዝ ዙሪያ በሚንቀሳቀስበት ወቅት በጠራራ ፀሀይ በቡድን በአሸዋ ቁፋሮ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ተመለከተ። ሰዎቹ የቆፈሩትን አሸዋ ወደጭነት መኪና ለመጫን ዝግጅት ላይ ነበሩ። አሸዋ የልጅነት የወንዝ ዙሪያ ትዝታ ሆኖ ሊቀር ይሆን ብለን በምንጭነቅበት ወቅት ሌሎች ግን በጣም የሚያሳስባቸው ጉዳይ አለ። እንደተባለው አሸዋ ለግማሹ ሕይወት ሲሆን ለግማሹ ደግሞ ገንዘብ ነው። በልቶ በማደር እና በመራብ መካከል፤ የመጠጥ ውሃ በማግኘት እና ባለማግኘት መካከል ያለ፤ ባጠቃላይ አሸዋ በሕይወት እና በሞት መካከል ያለ ጉዳይ መሆን ጀምሯል።
news-55905197
https://www.bbc.com/amharic/news-55905197
ጃክ ፓላዲኖ፡ የቢል ክሊንተን የትዳር መማገጥ ዜናን ያድበሰበሰው ሰው አስገራሚ አሟሟት
ዕውቁ የዝነኞች የግል መርማሪ በካሜራው ምክንያት ገዳዮቹን አጋለጠ።
ጃክ ፓላዲኖ ይባላል፡፡ ትናንትና 76 ዓመቱ ነበር፡፡ ዛሬ እንኳ የለም፡፡ በአሜሪካ ዕውቅ የግል ወንጀል መርማሪና ጉዳይ አስፈጻሚ ነበር፡፡ ባለፈው ሐሙስ ለታ ወንበዴዎች ድንገት ያዙት፡፡ ሳንፍራንሲስኮ በሚገኘው ቤቱ ደጅ ላይ ነው ማጅራቱን የቆለፉት፡፡ ታገላቸው፡፡ ጣሉት፡፡ ድንገት ግን አንዲት የድሮ ካሜራውን ይዟት ነበር፡፡ እነሱ ሊቀሙት ይታገሉት ነበር፡፡ ካሜራዋን። እንደምንም ብሎ ተጫናት፡፡ ፎቶ አነሳች፡፡ ወንደበዴዎቹ ጭንቅላቱ ላይ ባደረሱበት ጉዳት ኋላ ላይ ነፍሱ ከሥጋው ብትለይም ፖሊስ ጥፋተኞቹን ደርሶባቸዋል፡፡ ገዳዮቹ ሊደረስባቸው የቻለው ደግሞ ፓላዲኖ ከመሞቱ በፊት ፎቶ ስላነሳቸው ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ከ2 ሳምንታት በፊት ነው፡፡ ፓላዲኖ ሥመ ጥር የግል ወንጀል መርማሪ ሲሆን ከዋና ዋና ደንበኞቹ መሀል የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች እና ዕውቅ የሆሊውድ ተዋናዮች፣ ሙዚቀኞችና ጸሐፊ ተውኔቶች እና ሌሎች ገናናዎች ይገኙበታል፡፡ የፓላዲኖ ካሜራ የወንበዴዎቹን ምሥል በማስቀረቱ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን አድኖ ቢይዝም በነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ሆስፒታል የነበረው ፓላዲኖ ግን ትናንትና ሰኞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ዝነኛው ፓላዲኖ ዘመናትን ባስቆጠረው የግል መርማሪነት ሥራው አነጋጋሪ የነበሩ ጉዳዮችን በመያዝ ገናና ነበር፡፡ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን፣ ሞዛቂና ተዋናይት ከርትኒ ላቭ፣ በቅሌት ማጥ ውስጥ የሚገኘው ዝነኛው ፕሮዲዩሰር ሐርቬይ ዊኒስተን የፓላዲኖ ደንበኞች ነበሩ፡፡ ባለፈው ሐሙስ ፓላዲኖ ጥቃት ሲደርስበት ሳንፍራንሲስኮ ከሚገኘው ቤቱ ደጅ ላይ የነበረ ሲሆን 2 አደገና ቦዘኔዎች ናቸው የተባሉ ወጣቶች ናቸው በእጁ ይዞት የነበረውን ካሜራ ሊቀሙት የታገሉት፡፡ ይህን ተከትሎ ፓላዲኖ ወደኋላ ወድቆ ጭንቅላቱ ስለመታው ራሱን ወዲያውኑ ሳተ፡፡ በሚደንቅ ሁኔታ ታዲያ አጥቂዎቹ ከመሸሻቸውና እሱ ራሱን ከመሳቱ በፊት በነበረች ቅጽበት ፓላዲኖ የካሜራውን ጉጠት ተጭኖት ነበር፡፡ ፓላዲኖ ቢሞትም ፖሊስ ግን ያን ምሥል ተጠቅሞ ነው ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው፡፡ የፓላዲኖ ባለቤት ሳንድራ ሱተርላንድ የወንጀለኞቹን መያዝ ስትሰማ፣ ‹‹ምነው የሰራው ሥራ ወንበዴዎቹ እንዲያዙ ማድረጉን መርማሪ ሆኖ የኖረው ባለቤቴ ባወቀ›› ብላ ተናግራለች፣ ለአሶሲየትድ ፕሬስ፡፡ ሕይወቱን ሙሉ የወንጀል መርማሪ ሆኖ የኖረ ሰው ገዳዮቹ በዚህ መልክ መያዛቸው የሕይወት ግጥምጥሞሽ በሚል ብዙዎቹን አስደንቋል፡፡ ፓላዲኖ ሕግ የተማረ ሲሆን የግል መርማሪ ሆኖ መሥራት የጀመረው በ1970ዎቹ ነበር፡፡ ያን ዘመን የግል መርማሪ በፊልሞች ውስጥ ገዝፎ ይሳል ስለነበር ሥራውም ገናና ያደርግ ነበር፡፡ በ1977 ፓላዲኖ በአንድ የግል የወንጀል ምርመራ ቡድን ውስጥ ከባለቤቱ ጋር ተቀጠረ፡፡ እሱና ባለቤቱ ለዓመታት ወንጀል ምርመራ ውስጥ አብረው ሰርተዋል፡፡ እነ ፓላዲኖ በተለይም ለሆሊውድ ዝነኞች ስማቸው እንዳይጎድፍ የሚዲያ ዘመቻ በመክፈት፣ ወይም የሚዲያ አፍ በማዘጋት ሥራ ይሰማሩ ነበር፡፡ ለምሳሌ ሙዛቂዋ ከርተኔይ ባሏ ከሞተ በኋለ በሱ ዙርያ ይወሩ የነበሩ የሚዲያ ሐሜቶችን እንዲያከስምላት ፓላዲኖን ቀጥራው ነበር፡፡ ፓላዲኖ በተለይ ቢል ክሊንተን ከትዳራቸው ውጭ ወጣ ይሉ ነበር የሚለውን ሐሜት እንዲቀብርላቸው ክሊንተን ቀጥረውት ውጤታማ ሥራ ሰርቶላቸዋል፡፡ በ1999 ዓ/ም ሳንፍራንሲስኮ ኤክዛሚነር ጋዜጣ ፓላዲኖን ሲገልጸው፣ ‹አስጨናቂ መርማሪ፣ የጎደፈ ስም ወልዋይ፣ ለሙያው ሟች› ብሎት ነበር፡፡
55246624
https://www.bbc.com/amharic/55246624
ኮሮናቫይረስ፡ ሀብታም አገራት ክትባት ያላግባብ እያከማቹ መሆኑ ተገለጸ
ሀብታም አገራት ያላግባብ የኮሮናቫይረስ ክትባት እያከማቹ እንደሆነና ይህም ድሀ አገራት ክትባቱን የሚያገኙበትን እድል እንደሚያጠበው ተገለጸ።
ለክትባት ፍትሐዊ ስርጭት የቆመው "ዘ ፒፕልስ ቫክሲን አልያንስ" የተባለው ስብስብ እንዳለው፤ ወደ 70 የሚጠጉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራች ከአስር ዜጎቻቸው ለአንድ ሰው ብቻ ነው ክትባት መስጠት የሚችሉት። ኦክስፎርድ እና አስትራዜንካ በጥምረት ከሚሠሩት ክትባት 64 በመቶውን በታዳጊ አገራት እንደሚያከፋፍሉ አስታውቀዋል። ክትባቱ በፍትሐዊ መንገድ ለመላው ዓለም እንዲከፋፈል እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። ኮቫክስ የተባለው ጥምረት 700 ጠብታ ለ92 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት ለማከፋፈል ተስማምቷል። "ዘ ፒፕልስ ቫክሲን አልያንስ" ውስጥ አምንስቲ፣ ኦክስፋምና ሌሎችም የመብት ተሟጋቾች ይገኙበታል። ይህ ስብስብ እንዳለው፤ ከሆነ በቂ ክትባት ባለመኖሩ መድኃኒት አምራቾች በርካታ ክትባት እንዲመረት የቴክኖሎጂ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ሁሉም ክትባቶች ፍቃድ ካገኙ፤ ሀብታም አገራች ለመላው ዜጎቻቸው ከሚበቃው ሦስት እጥፍ ጠብታ ለመግዛት ከወዲሁ መስማማታቸው ተጠቁሟል። ለምሳሌ ካናዳ ለእያንዳንዱ ዜጋዋ አምስት እጥፍ ክትባት ለማግኘት አስቀድማ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። ሀብታም አገራች ከመላው ዓለም 14% ብቻ ቢሆኑም 53% ክትባት ገዝተዋል። የኦክስፋም የጤና ፖሊሲ ኃላፊ አና ማርዮት "ማንም ሰው ሕይወቱን የሚያተርፍ ክትባት ሊከለከል አይገባም። ክትባት ማግኘት እና አለማግኘት በአገር የገንዘብ አቅም መወሰን የለበትም" ብለዋል። አሁን ያለው ሁኔታ ካልተለወጠ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት ላያገኙ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። "ዘ ፒፕልስ ቫክሲን አልያንስ" ሁሉም መድኃኒት አምራቾች የኮቪድ-19 ክትባት ሂደትና ቴክኖሎጂውን በማጋራት ጠብታው በቢሊዮኖች እንዲመረት ጥሪ አቅርቧል። የዓለም ጤና ድርጅት የመረጃ ልውውጡን ማሳለጥ እንደሚችልም ተጠቁሟል። አስትራዜኒካ ለታዳጊ አገራት ከክፍያ ነጻ ክትባቱን እንደሚያቀርብ አስታውቋል። የአስትራዜኒካ ክትባት ከሌሎቹ ርካሽ ነው። ማቀዝቀዣ ውስጥ ለማስቀመጥ ምቹ ስለሆነም በቀላሉ ማከፋፈል ይቻላል። ሆኖም ግን አንድ ተቋም ብቻውን ለመላው ዓለም ክትባት ማዳረስ እንደማይችል የመብት ተሟጋቾች ይናገራሉ። የፋይዘር እና ባዮንቴክ ክትባት በዩናይትድ ኪንግደም ፍቃድ አግኝቷል። ለበሽታው በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች እየተሰጠም ነው። ክትባቱ በቅርቡ በአሜሪካ እና የአውሮፓ አገሮች ፍቃድ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ማለት ደግሞ ለድሀ አገራት እስኪከፋፈል ጊዜ ሊወስድ ይችላል ማለት ነው። በተጨማሪም የሩስያው ክትባት (ስፑትኒክ) ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስመዝገቡ ተገልጿል። ሌሎች አራት ክትባቶች የመጨረሻ የሙከራ ደረጃ ላይ እንደደረሱም ተዘግቧል።
news-51016945
https://www.bbc.com/amharic/news-51016945
በጀነራል ሶሌይማኒ ቀብር ላይ ከ35 በላይ ሰዎች ተረጋግጠው ሞቱ
በጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ በተፈጠረ መረጋገጥ ቢያንስ 35 ሰዎች መሞታቸውን የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።
እንደ መገናኛ ብዙሃኑ ዘገባ ከሆነ፤ ተጨማሪ 48 ሰዎች በጀነራሉ የትውልድ ከተማ ኬርማን ተረጋግጠው ጉዳት ደርሶባቸዋል። በፕሬዝደንት ትራምፕ ትዕዛዝ የተገደሉት ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ በትውልድ ከተማቸው ግብዓተ መሬታቸው እየተፈጸመ ይገኛል። በኢራቅ ባግዳድ ባሳለፍነው ዓርብ የተገደሉት ጀነራሉ፤ አስክሬናቸው ከኢራቅ ወደ ኢራን ሲጓዝ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራቃውያን አደባባይ ወጥተው ሸኝተዋል። ኢራቃዊያን የጀነራሉን አስክሬን ሲሸኙ ''ሞት ለአሜሪካ'' ሲሉ ተደምጠዋል። ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ። ፕሬዝደንት ትራምፕ ጀነራሉ መገደላቸው ከተሰማ በኋላ ''የሶሌይማኒ የዓመታት የሽብር አገዛዝ አብቅቶለታል" ብለዋል። "ሱሊማኒ በማንኛውም ሰዓት ሊቃጣ የሚችል የሽብር ሴራ በአሜሪካ ዲፕሎማቶች እና የጦር መኮንኖች ላይ ሲያሴር ነበር። ይህንን ሲፈጽም ያዝነው፤ አስወገድነው" ሲሉም ተደምጠዋል። በተያያዘ ዜና ቃሲም ሱሊማኒ ማን ነበሩ? ከእ.አ.አ. 1998 ጀምሮ ሜጀር ጀነራል ሱሊማኒ የኢራን ኩድስ ኃይልን ሲመሩ ቆይተዋል። ይህ ኃይል ከሃገር ውጪ የሚፈጸሙ ሚስጥራዊ ኦፕሬሽኖችን የሚያከናውን ነው። ጀነራሉ በኢራቅ ውስጥ አይኤስ እና አል-ቃይዳን በመዋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ ነበራቸው። ከዚህ በተጨማሪም፤ እኚህ የሽብር ቡድኖች እግራቸውን በኢራን እንዳይተክሉ ተከታትለው ድባቅ የመቷቸው ጀነራል ሱሊማኒ ነበሩ ተብሏል። ጀነራሉ የሚመሩት ኃይል በሶሪያ ግጭት ውስጥ ተሳትፎ እንዳለው አምኗል። ለፕሬዝደንት በሽር አል-አሳድ ታማኝ ለሆኑ ወታደሮች የጦር ምክር ይሰጣል። እንዲሁም ለባሽር አል-አሳድ ታማኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሺያ ሙስሊሞችን አስታጥቋል። በኢራቅ ደግሞ አይኤስን እየታገሉ ለሚገኙ ለሺያ ሙስሊም ሚሊሻዎች ድጋፍ ያደርጋል። በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የተከሰቱት ግጭቶች ጀነራሉ ኢራን ውስጥ እጅግ ዝነኛ ሰው እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ጀነራል ሱሊማኒ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት የኢራን ከፍተኛ የጦር ሽልማት ተቀብለዋል። አሜሪካ በበኩሏ ጀነራሉ የሚመሩት የኩድስ ኃይል በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ አሜሪካን በጠላትነት በመፈረጅ በሽብር መናጥ ለሚፈልጉ ኃይሎች ፈንድ፣ ሥልጠና እና የጦር መሳሪያን ጨምሮ የቁስ ድጋፍ ያደርጋል ስትል ትወነጅላለች። አሜሪካ እንደምትለው ከሆነ ይህ የኩድስ ኃይል ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ኃይሎች መካከል፤ የሌባኖሱ ሄዝቦላ እንዲሁም የፍልስጤሙ እስላማዊ ጅሃድ ተጠቃሽ ናቸው። የቀድሞ የሲአይኤ አለቃ የአሁኑ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ የኢራንን አብዮታዊ ጥበቃ እና ኩድስ ኃይሉን "የሽብር ቡድን" ሲሉ ከወራት በፊት ፈርጀውት ነበር።
news-55285691
https://www.bbc.com/amharic/news-55285691
በሳዑዲ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች አሁንም በአስከፊ ሁኔታ ላይ መሆናቸው ተነገረ
በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የስደተኞች የማቆያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አስከፊ በሆነ አያያዝ ውስጥ እንደሚገኙ ሂዩማን ራይትስ ዋች ገለጸ።
የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪው ድርጅት እንዳለው ሕጋዊ ሰነዶች ሳይኖራቸው ሥራ ፍለጋ ወደ ሳዑዲ የገቡት እነዚህ ስደተኞች ተይዘው የሚገኙበት ማዕከል የተጨናነቀ ከመሆኑ ባሻገር በጥበቃዎች ማሰቃየትና ድብደባ እንደሚፈጸምባቸውም አመልክቷል። የማዕከሉ ጥበቃዎች በጎማ በተሸፈነ ብረት በሚፈጸምባቸው ድብደባ ጉዳት እንደሚደርስባቸው የገለጸው ሂማን ራይትስ ዋች፤ በጥቅምትና ኅዳር ወራት ውስጥ ቢያንስ ሦስት ለሚሆኑ ስደተኞች ሞት ምክንያት መሆኑን በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። ከዚህ ቀደም በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ባሉ የስደተኞች ማቆያ ውስጥ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረስውን ሰቆቃ በተመለከተ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን መዘገባቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥትም በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቹን ወደ አገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያትም በርካታ ሰዎች ከሳዑዲ እንዲወጡ ማድረጉ ይታወሳል። የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ በማቆያ ማዕከሉ ያሉት ስደተኞች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ፣ ድብደባ እንዳይፈጸምባቸውና ያሉበት የአያያዝ ሁኔታ በተገቢው መንገድ እንዲሻሻል ጠይቋል። "ሃብታም ከሚባሉት የዓለም አገራት መካከል አንዷ በመሆኗ ስደተኞችን በዚህ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ለወራት በከፋ ሁኔታ መያዟ በምንም መልኩ አሳማኝ አይደለም" ሲሉ የሂማን ራይትስ ዋች የስደተኞች መብት አጥኚ ናዲያ ሃርድማን ተናግረዋል። በዘራቸው ላይ የተመሰረቱ ማጥላላቶችና ስድቦች እንደሚሰነዘሩባቸው የገለጹት ስደተኞቹ በኮሮናቫይረስ የመያዝ ስጋት እንዳላቸውና በሚታመሙ ጊዜ ህክምና ለማግኘት በሚጠይቁበት ጊዜ በማቆያው ጠባቂዎች ድብደባ እንደሚፈጸምባቸው ገልጸዋል። በድብደባ ምክንያትም የሞቱ ሦስት ሰዎች እንዳሉ ስደተኞቹ እንደነገሩት የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ገልጿል። በእነዚህ የማቆያ ማዕከላት ውስጥ ስላለው አስከፊ አያያዝ በተመለከተ ለረጅም ጊዜያት ቅሬታ ሲቀርብ የነበረ ሲሆን፤ በእነዚህ ቦታዎች ለሥራ ወደ ሳዑዲ የሄዱ በርካታ ስደተኞች ያለበቂ ምግብና መጠለያ በችግር እንዲቆዩ መደረጋቸውን ኢትዮጵያውያን ለሂዩማን ራይትስ ዋች ተናግረዋል። የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ያናገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደነገሩት በማቆያ ማዕከሉ ውስጥ የቻድ፣ የጋና፣ የኬንያ፣ የናይጄሪያና የሶማሊያ ዜጎች ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያውያን በቁጥር በርካታ ናቸው። በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የወጣ ሪፖርት እንዳመለከተው በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ባሉ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው የሚሰሩ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ የውጭ አገራት ዜጎች ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥም ተገቢው የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ የሌላቸውን ሰራተኞችን የማሰር ተግባር በተለያዩ ጊዜያት በመደበኝነት ሲካሄድ ቆይቷል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንዳለው በፈረንጆቹ ግንቦት ወር 2017 እና መጋቢት 2019 መካከል ባላው ጊዜ ውስጥ በየወሩ በአማካይ 10 ሺህ በአጠቃላይ 260 ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ እንዲወጡ ተደርጓል። የኢትዮጵያ መንግሥት በስደተኛ ማቆያ ውስጥ ያሉ ዜጎች ጉዳይን እንደሚከታተል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ለቢቢሲ ከዚህ ቀደም ገልጸው፤ በተጨማሪም ጉዳዩን ለሳዑዲ ባለስልጣናት በማሳወቅ ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ ከመጠየቅ ተቆጥበው እንደማያውቁ ተናግረዋል። ሂዩማን ራይትስ ዋች በሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ የስደተኞች ማቆያ ማዕከላት ውስጥ እየተፈጸሙ ናቸው ያላቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ሕገ ወጥ ግድያን በተመለከተ መንግሥት ምርመራ እንዲያደርግና ጥፋተኛ በሆኑት ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
news-46719274
https://www.bbc.com/amharic/news-46719274
አራት ህጻናትን በአንዴ ያገኘው ቤተሰብ ተጨንቋል
ከዚህ በፊት የአንድ ልጅ እናት የነበሩት ወይዘሮ እቴናት ሲሳይ ባለፈው አርብ ምሽት ምጥ ጀምሯቸው ቅዳሜ ጠዋት ወደ ሃኪም ቤት ተወስደው አራቱን ልጆቻቸውን ተገላግለዋል።
አቶ ፈንታ ሰገድ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ባለቤታቸው ከወራት በፊት የእርግዝና ክትትል ሲያደርጉ በአካባቢያቸው ባሉ ባለሙያዎች እርግዝናቸው መንታ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯቸው እንደነበር አስታውሰዋል። ባለፈው አርብ እኩለ ሌሊት አካባቢ ምጥ የጀመራቸው እናት ቅዳሜ ጠዋት ወደ ቆቦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተወስደው እንዲወልዱ ሲደረግ የህክምና ባለሙያዎቹ ጭምር አራት ልጆች ይወልዳሉ ብለው አልጠበቁም ነበር። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች • የኮንጎ ምርጫ መጓተት ህዝቡን አስቆጥቷል ወይዘሮ እቴናት ወደ ሆስፒታሉ ከመጡ በኋላ በባለሙያዎች ድጋፍ ያለችግር በተፈጥሯዊ መንገድ አራቱን ልጆች ተገላግለዋል። እናትየውና ሦስቱ ህፃናት በመልካም ጤንነት ላይ ሲሆኑ፤ አንደኛው ጨቅላ ግን የህክምና ክትትል የሚያስፈልገው እንደሆነ በሃኪሞች እንደተነገራቸው አባትየው አቶ ፈንታ ተናግረዋል። በአንድ ጊዜ ሦስት ሴቶችና የአንድ ወንድ ልጅ አባት የሆኑት አርሷደር ፈንታ ሰገድ ተጨማሪ የህክምና ክትትል ከሚያስፈልገው አንደኛው ጨቅላ በተጨማሪ ልጆቹንና እናትየውን ለመንከባከብ ያላቸው አቅም ስለማይፈቅድላቸው እጅጉን እንደተጨነቁ ይናገራሉ። ህጻናቱ ቅዳሜ ዕለት የተወለዱበት የቆቦ ሆስፒታል ተወካይ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ካሳሁን አዲሱ እንደሚሉት ከተወለዱት ህጻናት መካከል ሦስቱ ሴቶች በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ አንደኛው ልጅ ግን ህክምና እየተከታተለ ነው። ችግሩ የሆድ እቃዎቹ ሽፋን አለመኖር /ኢምፕሎሲ/ እነደሆነ በህክምና ስለተረጋገጠ ወደ ተሻለ ሆስፒታል ሄዶ በስፔሻሊሰት ሃኪሞች መታየት አለበት ብለዋል። ነገር ግን ይላሉ አቶ ካሳሁን፤ ቤተሰቡ ወደሌላ ቦታ ሄዶ ህክምና ለማድረግ አይደለም እናትየውንና ጨቅላዎቹን ለመንከባበከብ የሚሆን ገንዘብ ስለሌለው ሁኔታው በጣም አስቸጋሪ ነው። ልጆቹ ከተወለዱ በኋላ እናትየው ምንም አይነት የጤና ችግር እንዳላገጠማትና አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝም ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እናትየው ከወሊድ በፊት ክትትላቸውን በሆስፒታሉ ባለማድረጋቸው ቤተሰቡ አራት ልጅ እንደሚወለድ አያውቅም ነበር፤ ይህ ደግሞ ያልታሰበ ዱብዳ እንዲሆንባቸው አድርጓል ብለውናል ተወካይ ሥራ አስኪያጁ። የራያ ቆቦ ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ተወካይ ሃላፊ የሆኑት አቶ ዝናቤ እያሱ በበኩላቸው ቤተሰቡ አራቱን ልጆች ለማሳደግ አቅም የሌለው ሲሆን፤ ወደፊት ልጆቹ የሚፈልጉትን ነገር በሙሉ ሟሟላት አስቸጋሪ ሊሆንባቸው ይችላል ይላሉ። በአሁኑ ሰአት ልጆቹን ማጥባትና እናትየውን መንከባከብ በራሱ በግብርና ሥራ ለሚተዳደረው ቤተሰብ አዳጋች እንደሆነ አቶ ዝናቤ ነግረውናል። • የትራምፕ አማካሪ፡ የግንቡ ውጥን ውድቅ ከተደረገ ሰነባብቷል • "በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ቤተሰቡን ለመርዳት እስካሁን የአካባቢው ነዋሪዎች መዋጮ እያደረጉ እንደሆነና የወረዳው አስተዳደር ቢሮም አቅሙ ያላቸው ሰዎች ለቤተሰቡ የቻሉትን እርዳታ እንዲያደርጉ ለማስተባበር ጥረት እያደረገ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በቆቦ የሚገኝ 'ካቶሊክ' የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ለህጻናቱ አልባሳትና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ለማሟላት እንዲሁም በወር 500 ብር ለመስጠት ቃል እንደገባም ተናግረዋል። ''ከተወለዱት አራት ህጻናት መካከል አንዱ የጤና ሁኔታው ጥሩ ስላልሆነ የተሻለ ቦታ ተወስዶ ህክምና ማግኘት የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸትም እየሰራን ነው'' ብለዋል አቶ ዝናቤ። ''ችግሩ የተለመደና ተገቢውን ህክምና ካገኘ ህጻኑ ወደ ሙሉ ጤንነቱ እንደሚመለስ ከሆስፒታሉ ስለተነገረን ይህንን ለማሳካት እየተሯሯጥን ነው'' ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ያስረዳሉ። ምንም እንኳን አራት ህጻነት በአንድ ጊዜ ማግኘታቸውን እንደ ጸጋ ቢመለከቱትም፤ አቶ ፈንታ ግን ልጆቹን እንዴት እንደሚያሳድጉ ሲያስቡ ከባድ ፈተና እነደሚሆንባቸው ያምናሉ። ከቤተሰቦቻቸው ባገኟት ትንሽ መሬት ላይ እርሻ በማረስ ለሚተዳደሩት ባልና ሚስት ይህ ክስተት ከጥሩ ዜናነቱ ይልቅ አሳሳቢነቱ ጎልቶ ታይቷቸዋል።
51788576
https://www.bbc.com/amharic/51788576
ኮሮናቫይረስ፡ ጣልያን ውስጥ በአንድ ቀን ብቻ 133 ሰዎች ሞተዋል
በየዘመኑ ወረርሽኞች የሚሊዮኖችን ሕይወት ቀጥፈዋል። ሕክምና በዘመነበት ዘመን በመፈጠራችን በሽታዎች እንደተፈለፈሉ በአጭሩ ስለሚቀጩ የቀድሞ ትውልድ ወረርሽኝ እንደሚያስጨንቀው እኛን ላያስጨንቀን ይችላል።
ኮሮናቫይረስ ግን አሁን ዓለምን ሰቅዞ ይዟል። አገራት ምጣኔ ሐብታቸው ብርክ ይዞታል። የዓለም 'የምርት ፋብሪካ' የምትባለው ቻይና እንኳን ኮሮና ፍዳዋን እያበላት ነው። በቁጥር ከዩናይትድ ኪንግደምን ሕዝብ የሚልቀውን የሁቤ ግዛት ነዋሪ ከቤትህ ንቅንቅ እንዳትል ብላዋለች። 60 ሚሊዯን የሚጠጋው የግዛቲቱ ነዋሪ አምራች ሕዝብ ቤቱ ሲቀመጥ ቻይና በድምሩ የምታጣው ገንዘብ የዋዛ አይሆንም። ለመሆኑ ኮሮናቫይረስን በተመለከተ ምን አዳዲስ መረጃ አለ? በጀርመን ተያዙ የተባሉ 800 ሰዎች አሉ። በሰሜን ጣሊያን ሎምባርዲ ክልል 16 ሚሊዮን ሰዎች ገለል ተደርገው እንዲቀመጡ አድርጋለች። ይህ ቁጥር የሕዝቧ አንድ አራተኛ ይጠጋል። በነዚህ የእንቅስቃሴ እቀባ በተደረገባቸው 14 አውራጃዎች አይደለም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሰርግና ቀብር እንኳ በሰዎች ስብስብ መሀል እንዳይከወን ተወስኗል። ይህ ደንብ የቱሪስት መዳረሻ የሆኑትን ሚላንና ቬነስን ይመለከታል። የጣልያን ሴሪ-አ ጨዋታዎችም በባዲስ ስታድዬም ተከናውነዋል። ቫይረሱ ለዓለማችን ትንሿ አገር ቫቲካንም አልራራላትም። በቻይና ጉዋንዡ ከቫይረሱ የሚያገግሙ ሰዎች የሚጠለሉበት ባለ አምስት ፎቅ ሆቴል ተደርምሶ 10 ሰዎች ሞተዋል፤ 28ቱ ፍለጋ ላይ ናቸው። 70ዎቹ ፍርስራሽ ተጭኗቸዋል። የሕንጻው ባለቤት በፖሊስ ቁጥጥር ውሏል።
news-46819689
https://www.bbc.com/amharic/news-46819689
የእንግሊዝ ፓርላማ አባላት የረሃብ ሚኒስቴር ይሾምልን እያሉ ነው
ጥቂት የማይባሉ የእንግሊዝ ፓርላማ አባላት በሃገሪቱ እየጨመረ የመጣውን የምግብ እጥረት የሚከታተልና በተለይም ህጻናት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሚኒስትር መስሪያ ቤት እንዲቋቋም አንፈልጋለን ብለዋል።
በፓርላማው የአካባቢ ጉዳዮች ኦዲት ኮሚቴ እንደገለጸው 19 በመቶ የሚሆኑት ከ15 ዓመት በታች እንግሊዛውያን ህጻናት ምግብ ለመግዛት እጅግ ከሚቸገሩ ቤተሰቦች ጋር ነው የሚኖሩት። ይህ ቁጥር ደግሞ በአውሮፓ ከፍተኛው ነው ተብሏል። • ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ • ዓለምን ሊመግብ የሚችለው የስንዴ ዘር • የአገልግል ምግብ አምሮዎታል? ኮሚቴው እንደሚለው በተለያዩ ዘርፎች የሚገኙ ሚኒስትሮች ችግሩን ለመለየትና መፍትሄ ለመስጠት አልቻሉም። የእንግሊዝ መንግሥት ግን ስራ ከሌላቸው ቤተሰቦች ጋር የሚኖሩ ህጻናት ቁጥር ከሌላ ጊዜው በተለየ ዝቅተኛ ነው ሲል ይከራከራል። እንግሊዝ ውስጥ የተመጣጠኑና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኙ ምግቦችን መግዛት የማይችሉ ዜጎች ቁጥር በአስፈሪ ሁኔታ እየጨመረ እንደመጣ የፓርላማ አባላቱ የጠቆሙ ሲሆን ስራ አጥ የሆኑትና ህጻናት ደግሞ ዋነኞቹ ተጎጂዎች ናቸው ብለዋል። አባላቱ እንዳሉትም ዋነኛ ሃላፊነቱ ረሃብና የምግብ እጥረትን መከታተል የሆነ ሚኒስትር መስሪያ ቤት በአፋጣኝ ሊቋቋም ይገባል። የረሃብና ምግብ እጥረት መንስኤዎች፣ መጠን፣ የሚያስከትሉትን ጉዳትና የመከላያ መፍትሄዎች ማቅረብ ደግሞ ዋነኛ የስራ አትኩሮቱ አድርጎ መስራት አለበት ብለዋል።
42081941
https://www.bbc.com/amharic/42081941
ጃማይካዊው የአማርኛ ቋንቋ አስተማሪ
ስቲቨን ዶኖቫን ልዊስ እባላለሁ። የጃማይካ ዋና ከተማ ከሆነችው ኪንግስተን ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ከዛሬ አስር ዓመት በፊት ነበር።
ስቲቨን ዶኖቫን ልዊስ፡ ጀማይካዊው የአማርኛ ቋንቋ አስተማሪ ወደዚህ ካመጡኝ ጉዳዮች መካከል አንዱ እምነቴ ነው። ከተመረጡት ከአብርሃም ልጆች መካከል አንዱ በሆኑት በንጉስ ኃይለሥላሴ ውስጥ አንድ ነገር በማየቴ ነው። ኃይለሥላሴ ከአብርሃም ልጆች መካከል ናቸው። የእግዚያብሔር ልጆች እንደማለት ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ሁላችንም የአብርሃም ልጆች ነን። እኛ ጃማይካዊያንም የአብርሃም ልጆች መሆናችንን እናውቃለን። ስለዚህም ኃይለሥላሴ ወደ ጀማይካ ሲመጡና 'ከይሁዳ ነገድ መካከል ነኝ' ሲሉ ይህንን ተቀብለናቸዋል። ኃይለሥላሴን እንደ ፈጣሪ አናመልካቸውም። አምላክ መንፈስ ስለሆነ። ፈጣሪ ዳዊትን እውነተኛ ንጉስ እንዲሆን ነው የመረጠው። ይህም ክርስቶስ በንጉስ አምሳያ ምድር ላይ አለ ማለት ነው። ዳዊት ማለት ይህ ነው። ከእምነቴ በተጨማሪ ወደ ኢትዮጵያ ያመጣኝ ሌለው ነገር አማርኛ ቋንቋ ለመማር ያለኝ ጥልቅ ፍላጎት ነው። ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ቋንቋውን የመማር ዕድል እንደማገኝ ትልቅ ተስፋ ነበረኝ። ቋንቋውን አቀላጥፌ ለመናገር ብዙ ጥረት እያደረኩ ነው። በቅድሚያ አዲስ አበባ ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ ባህር ዳር ሄጄ ተምሬያለሁ። በኢትዮጵያ የሚገኙ ራስ-ተፈሪያውያን አማርኛ ቋንቋን መማር እንዳለባቸው ይሰማኛል። ይህን ለመደገፍ የአማርኛን ቋንቋ መማር ለሚፈልጉ ፊደላቱን እያስቆጠርኩ ነው። እስካሁን ድረስ አስራ አምስት ተማሪዎችን አስተምሬያለሁ። አማርኛ ከእንግሊዝኛ በበለጠ ለሰው የቀረበ ቋንቋ ነው፤ ለምሳሌ ከወንድ ጋር ስታወሩ፥ ዓረፍተ ነገሩ ወንድን የሚያመለክት ነው። ከሴት ጋር ስታዋሩም እንደዚያው። ቋንቋው ለትልቅ ሰዎችም ክብር እንድንሰጥ ያስችለናል። በእነዚህ ምክንያቶች አማርኛ ብልህ ቋንቋ እንደሆነ ይሰማኛል። ወንድ እና ሴት አብረው ቆመው ቢሆንና ለአንዳቸው ብቻ ሰላምታ መስጠት ቢያስፈልግ ያንን ማድረግ ይቻላል። ለሁለቱም ሰላምታ ማቅረብ ካስፈለገም እንደዚያው ማድረግ ያስችላል። ለእኔ አማርኛን መማር ወደሰው ልብ በዚያውም ወደአምላክ እንደመቅረብ ነው። ግዕዝም በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አውቃለሁ። ምናልባትም ወደፊት ግዕዝ መማሬ አይቀርም። እንግሊዝኛ ግን እንደዚያ አይደለም። በእንግሊዝኛ 'ሰላም' ማለት በቃ 'ሰላም' ብቻ ነው። ስቲቨን ዶኖቫን ልዊስ፡ ጀማይካዊው የአማርኛ ቋንቋ አስተማሪ የሀገሬ ይፋዊ የሥራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ቢሆንም ለኔ ግን እንግሊዝኛ የኔ ቋንቋ እንደሆነ አይሰማኝም። ለእኔ እንግሊዝኛ የአባቶቼ ቋንቋ አይደለም። አባቶቼ አፍሪካዊያን ናቸው። እንግሊዝኛ የሚነገርበት ሀገር ረጅም ዓመት ስለኖርኩ የማንነቴን ቋንቋ አጥቼ ነበር። አሁን ግን ተመልሼ መጥቼ አማርኛ ተማርኩ። አማርኛ በመማሬም በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ቋንቋውን ማወቄ ኃይማኖቴን የበለጠ እንድገነዘበው ይረዳኛል። አንድ ኢትዮጵያዊ አሁን ወደጃማይካ ቢሄድ ስለሥራ ምንም ጭንቀት አይገባውም፤ አስተማሪ መሆን ብቻ ይበቃዋል። አማርኛ የመማር ፍላጎት ያላቸው በጣም ብዙ ሰዎች አሉ። ፊደል ከማስቆጠር በተጨማሪ ጨርቅን በመጠቀም የተለያዩ ጌጣጌጦችን እሰራለሁ። ለሴቶች የሚሆኑ ልብሶችን፣ የፀጉር ማስያዣ እና የአንገት ጌጦችን እሰራለሁ። ከአሁን በኋላ ወደ ጃማይካ ተመልሶ የመሄድ ፍላጎት የለኝም። ይልቁንም ተጨማሪ ጃማይካዊያን ወደዚህ እንዲመጡ ነው የምፈልገው።
news-47437583
https://www.bbc.com/amharic/news-47437583
የ82 ዓመቱ የአልጀሪያ መሪ አብደላዚዝ ቡተፍሊካ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል
የአልጄሪያው መሪ አብደላዚዝ ቡተፍሊካ ከዜጎቻቸው እየደረሰባቸው ያለውን ተቃውሞ ወደጎን በማለት ለአምስተኛ ጊዜ ለስልጣን መወዳደር እንደሚፈልጉ ያስታወቁ ሲሆን ሙሉ አምስት ዓመት ግን አልጨርስም ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ባስነበቡት ደብዳቤ በመጪው ሚያዚያ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚያሸንፉ ከሆነ ብሔራዊ መድረክ በማቋቋም እሳቸው የማይሳተፉበት አዲስ የምርጫ ስርአት እንደሚዘረጉ ገልጸዋል። ነገር ግን ለአምስተኛ ጊዜ ስልጣን ለመያዝ ማሰባቸው ብዙሃኑን አልጄሪያዊ ከማስቆጣት አልፎ ላለፉት ቀናት ትልቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ምክንያት ሆኗል። • ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ • መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ የ82 ዓመቱ ቡተፍሊካ ከፈረንጆቹ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸዋል። እሳቸው ግን ምንም አይነት ነገር ፕሬዝዳንት ከመሆን አያግደኝም እያሉ ይመስላል። አሁንም ቢሆን ፕሬዝዳንቱ በሃገረ ስዊዘርላንድ የህክምና ክትትል እያደረጉ ሲሆን በአዛውንት አንመራም ያሉ በርካታ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ወጣቶች ትናንት በዋና ከተማዋ አልጀርስ ከባድ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ስድስት ተፎካካሪዎች ተቀባይነት ያገኙ ሲሆን የቀድሞው ጀነራል አሊ ጌድሪ አንዱ ናቸው። እሳቸውም በአልጄሪያ ታይቶ የማይታወቅ አይነት ለውጥ አመጣለው እኔን ምረጡኝ ሲሉም ተደምጠዋል። የንግድ ሰው የሆኑት ራሺድ ኔካዝ ደግሞ ባልተለመደ መልኩ ብዙ ' የፌስቡክ' ተከታዮች ያሏቸው ሲሆን በአልጄሪያውያን ወጣቶች ዘንድ ተቀባይነትና ፍቅርን ማትረፍ ቢችሉም ለፕሬዝዳንትነት መወዳደር እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል። ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግሞ የሃገሪቱን ሁኔታ በመቃወም ከምርጫው እራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል። በፈረንጆቹ 1999 ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ ከሚታወቁባቸው ጉዳዮች መካከል በሃገሪቱ ተከስቶ የነበረውንና የ100 ሺ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን የእርስ በርስ ጦርነት ማስቆማቸው ነው። • ኢራቅ ከአሜሪካ የበለጡ ሴት እንደራሴዎች አሏት • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? ከ2011 ጀምሮ ደግሞ በአልጄሪያ የምግብ ዋጋ መጨመሩና የስራ አጦች ቁጥር ማሻቀብ ከባድ ተቃውሞ አስነስቶ ነበር። ምንም እንኳን ብዙዎች ፕሬዝዳንቱ አርጅተዋል አሁን ካለው የፖለቲካ ስርአት ጋር አብረው መሄድ አይችሉም ቢሉም ሰሚ ያገኙ አይመስልም። ቡተፍሊካ በመጪው ሚያዚያ ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ከሆነ የማሸነፋቸው ነገር እርግጥ ነው የሚሉም አልጠፉም።
news-55695116
https://www.bbc.com/amharic/news-55695116
ኮሮናቫይረስ፡ ጆ ባይደን የትራምፕን ትዕዛዝ በመተላለፍ የኮቪድ-19 ጉዞ ገደብ እንደሚቀጥል አስታወቁ
በነገው ዕለት ስልጣን የሚረከቡት የአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቃል አቀባይ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአውሮፓ ህብረትና በብራዚል የተጣለው የጉዞ ገደብ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ተመራጩ ፕሬዚዳንት ይህንን ውሳኔ ያስተላለፉት የጉዞ ገደቡ ይነሳ የሚለውን የተሰናባቹን ፕሬዚዳንት ትራምፕን ትዕዛዝ በመተላለፍ ነው። በያዝነው ሳምንት ሰኞ ዋይት ሃውስ የጉዞ ገደቡ ጥር 18፣ 2013 መነሳት አለበት የሚል ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ይህም ማለት ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስልጣን ከያዙ ከስድስት ቀናት በኋላ ማለት ነው። ነገር ግን የጆ ባይደን ቃለ አቀባይ ጄን ፕሳኪ በበኩላቸው ወቅቱ የጉዞ ገደብ የሚላላበት አይደለም በማለት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። የ ጆ ባይደን በዓለ ሲመት በነገው እለት ጥቅምት 12፣ 2013 ዓ.ም ይፈፀማል። አሜሪካ የኮሮናቫይረስ ወረርሽን ለመግታት በሚል አውሮፓ ላይ የጉዞ ገደብ የጣለችው በባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ሲሆን በብራዚል ደግሞ ግንቦት ወር ላይ ነበር። "የጤና ባለሙያዎቻችን በመከሩን መሰረት አዲሱ አስተዳደር የተጣለውን የጉዞ ገደብ በጥር 18 አያነሳም" በማለትም ቃለ አቀባይዋ የፕሬዚዳንት ትራምፕ የጉዞ እገዳ ይነሳ የሚለው ውሳኔ እንደተላለፈው ወዲያውኑ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። "በመሰረቱ የማህበረሰቡን ጤንነት ለመጠበቅ ከፍተኛ እቅድ አለን። የኮቪድ-19 ስርጭትንም ለመግታት አለም አቀፍ ጉዞዎችን በጥብቅ እንቆጣጠራለን" ያሉት ቃለ አቀባይዋ አክለውም " በተለይም የተለያዩ አይነት አዳዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች እተከሰቱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት አለም አቀፍ ጉዞዎች የሚላሉበት አይደለም" ብለዋል። ቃለ አቀባይዋ ይህንን መልዕክት ከማስተላለፋቸው ከደቂቃዎች በፊት ዋይት ሃውስ በዩናይትድ ኪንግደም፣ አየር ላንድ፣ የአውሮፓ አገራትና ብራዚል ላይ የተጣለው የጉዞ ገደብ ጥር 18 እንዲነሳ የሚያዘውን የተሰናባቹን ፕሬዚዳንት ትራምፕ ውሳኔ በመግለጫው አውጥቶ ነበር። ውሳኔው አክሎም በቻይናና በኢራን ላይ የተጣለው የጉዞ ገደብም ይቀጥላል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ የአሜሪካው የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት ከጥር 18 ጀምሮ ማንኛውም አለም አቀፍ መንገደኛ ነፃ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ሊያሳይ ይገባል።
news-55883638
https://www.bbc.com/amharic/news-55883638
ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በመጪው ሚያዚያ ወር እንደምታስገባ ገለጸች
ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በመጪው ሚያዚያ ወር ወደ አገር ውስት እንደምታስገባ ገለጸች።
ክትባት የሚገባው የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ቢያንስ 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚዳረስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህንን የክትባት ሥራ የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙም ተገልጿል። በጤና ሚኒስቴር የክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ሙሉቀን ዮሃንስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት መረጃ መሰረት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር እና ከፕሬዚዳንት ፅ/ት ቤቶች ጋር በመቀናጀት የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡ ክትባቱን ለመውሰድ ቅድሚያ የሚያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መስፈርት መሰረት የጤና ባለሙያዎች፣ እድሜያቸው የገፉ፣ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎችና መጪውን ምርጫ ተከትሎ ተደራራቢ ስራና ሃላፊነት ያለባቸው የጥበቃ ኃይሎች መሆናቸውን ተገልጿል። የክትባቱ ብዛት እየታየም ለአውቶብስና የባቡር አሽከርካሪዎች እንዲሁም በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚሰሩ መምህራን እንዲዳርስ የሚደረግ መሆኑን ተመልክቷል። ኢትዮጵያ ክትባቱን ወደ ሃገር ውስጥ የምታስገባው ‹‹ኮቫክስ›› በተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ሸማች ማህበር መሆኑንም ዶክተር ሙሉቀን ተናግረዋል። የመጀመሪያው ዙር ክትባት እስከ መጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባና በፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2021 መጨረሻ ድረስ ደግሞ ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባም አማካሪው ጠቁመዋል። ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ ነው። ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ኢኒሼቲቭ ተቀብለውታል። ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ኢኒሼቲቭ በኩል ክትባቱ ፍቃድ ካገኘና ከፀደቀ በኋላ፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች። እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል።አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ ተገለፀ። አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሕብረቱ መሪ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተዋል። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው። አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ መገለፁ ይታወሳል። አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሕብረቱ መሪ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተዋል። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው።
news-41106160
https://www.bbc.com/amharic/news-41106160
ሕንድ ውስጥ ህንፃ ተደርምሶ ሰባት ሰዎች ሞቱ
ሙንምይ ውስጥ በደረሰ የህንፃ መደርመስ ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሲሞቱ በፍርስራሽ ውስጥ የተቀበሩ በርካታ ሰዎችን ለማዳን የነፍስ አድን ሰራተኞች በፍለጋ ላይ መሆናቸውን ፖሊስ ገልጿል።
አምቡላንሶች፣ የእሳት አደጋ መኪኖችና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደጋው ሥፍራ ነፍስ ለማዳን ጥረት ሲያደርጉ። የሕንድ የንግድ ከተማ በሆነችው ሙምባይ ባለስድስት ፎቅ ህንፃ የተደረመሰው ሃሙስ ዕለት ነው። ብዙ ህዝብ በሚኖርበት ብሄንዲ በተባለው አካባቢ ይገኝ ነበረው ይህ ህንፃ መቶ ዓመታት የሚደርስ እድሜ ነበረው ተብሎ ይታመናል። አምቡላንሶች፣ የእሳት አደጋ መኪኖችና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደጋው ሥፍራ ነፍስ ለማዳን ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ሙምባይ ካጋጠማት ከባድ ዝናብና ጎርፍ ገና በማገገም ላይ ትገኛለች። የመኖሪያ ህንፃው የመፍረስ አደጋ የደረሰበት በህንድ ሰዓት አቆጣጠር ጠዋት ሁለት ሰዓት ከአርባ ገደማ እንደሆነ ሪፖርቶች አመልክተዋል። ''አርባ የሚደርሱ ሰዎች በፍርስራሾች ውስጥ አሉ ተብሎ የሚታመን ሲሆን፤ አርባ ሶስት አባላት ያሉት የነፍስ አድን ቡድን በፍለጋ ላይ ተሰማርቷል'' ሲሉ አንድ የህንድ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል ኃይል ባለሥልጣን ለኤኤፍፒ ተናግረዋል። አንድ ወር በማይሞላ ጊዜ ሙምባይ ውስጥ ከተደረመሱ ህንፃዎች መካከል ይህ ሦስተኛው ነው። ፖሊስ እንደሚጠረጥረው ማክሰኞ ዕለት የጣለው ከባድ ዝናብ የህንፃውን መዋቅር በማዳከም እንዲፈርስ አድርጎት ሊሆን ይችላል። ምክንያቱ ትክክል ይሁንም አይሁን፤ ዋናው ጥያቄ በዚህች እያደገች ባለች ከተማ ስለምን በርካታ ሰዎች ባረጁና ለአደጋ በተጋለጡ ህንፃዎች ውስጥ እንዲኖሩ እንደሚፈቀድ ነው። ሙምባይ ውስጥ ቤቶችን የመግዣም ሆነ የመከራያ ዋጋ እስያ ውስጥ ካሉት ውድ ከተሞች መካከል የሚመደብ ነው። ጥራታቸው በተጠበቀ ሁኔታ የተገነቡ ህንፃዎች አቅርቦት ውስን ነው፤ በመሆኑ በርካታ ሰዎች አማራጭ በማጣት ደረጃቸውን ባልተበቁና በተጨናነቁ ህንፃዎች ውስጥ ለመኖር ይገደዳሉ። የተደረመሰው ህንፃ ምንም እንኳን 100 ዓመታትን በማስቆጠሩ ፈርሶ ስፍራው ለመልሶ ግንባታ እንዲዘጋጅ የተለየ ቢሆንም ሰዎች እየኖሩበት ነበረ። ነዋሪዎችን ለአደጋ ከተጋለጡ ህንፃዎች ለማስወጣት የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ባለሥልጣናት ጥረታቸውን ቢያጠናክሩም በሚፈለገው ፍጥነት ግን እየተከናወነ እንዳልሆነ ይናገራሉ። ሕንድ ውስጥ በህንፃዎች ላይ የመደርመስ አደጋ የሚደጋገም ሲሆን፤ በተለይ በዝናባማ ወቅቶች ይከሰታል። ደካማ የግንባታ ጥራት ደረጃና የህንፃዎች ማርጀት የዘወትር ምክንያቶች ናቸው። ሕንድ ውሰጥ በየዓመቱ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በህንፃዎች መደርመስ ሳቢያ ለሞት ይዳረጋሉ። ባለፈው አንድ ወር ብቻ ሙምባይ ውስጥ ሦስት የህንፃዎች መፍረስ አደጋ አጋጥሟል። ባለፈው ሃምሌ ወር ጋትኮፓር በተባለ ሥፍራ ባለአራት ፎቅ ህንፃ ተደርምሶ 17 ሰዎች ሞተዋል።
news-52690057
https://www.bbc.com/amharic/news-52690057
ኮሮናቫይረስ ያጠላባቸው በየጎዳናው የሚለምኑ የናይጄሪያ ታዳጊዎች
በሰሜናዊ ናይጄሪያ ቁርዓን ይማሩ የነበሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎች ወደየቤታቸው እንዲመለሱ በጭነት መኪና የተከተቱት በቅርቡ ነበር። እርምጃው የተወሰደው የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ነው።
የጭነት መኪና ቢታገድም፤ ታዳጊዎቹን የጫኑ መኪኖች ግን ልዩ ፍቃድ ተሰጥቷቸው ነበር። በመንግሥት አስተባባሪነት ታዳጊዎች በብዛት የተንቀሳቀሱበት እርምጃ ሳይሆን አይቀርም። ናይጄሪያ 200 ሚሊዮን ዜጎች አሏት። ገሚሱ ሙስሊም ገሚሱ ደግሞ ክርስቲያን። በሀውሳ ቋንቋ ታዳጊዎቹ ‘አልማጅሪ’ ይባላሉ። ከአረብኛ ቃል የተወረሰ ነው። ከታዳጊዎቹ መካከል ምን ያህሉ ወደቤታቸው እንደተመለሱ አይታወቅም። ነገር ግን ካዱና ግዛት 30 ሺህ ልጆች አስመልሻለሁ ብላለች። ከታዳጊዎቹ መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት በኮቪድ-19 ተይዘዋል። ወደየቤታቸው አንዲመለሱ ትዕዛዝ የተላለፈው የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት ቢሆንም፤ ውሳኔ ወረርሽኙ አንዲዛመት መንገድ ከፍቷል። ችላ የተባለው ማስጠንቀቂያ ከታዳጊዎቹ መካከል በትውልድ ቀዬያቸው ሲደርሱ ለይቶ ማቆያ ገብተው የተመረመሩ አሉ። በካንዱ ግዛት ከተመረመሩት 196 ታዳጊዎች 65 ያህሉ ላይ በሽታው ተገኝቷል። በጎምቤ ግዛት ደግሞ ከ168 ታዳጊዎች 91ዱ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የሌሎች ታዳጊዎች የምርመራ ውጤት አሁንም እየተጠበቀ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎች እስካሁን አልተመረመሩም። ናይጄሪያ በበቂ ሁኔታ ምርመራ እያካሄደች አይደለም በሚል ትተቻለች። የናይጄሪያ የኮቪድ-19 መከላከያ ግብረ ሀይል ኃላፊ፤ ታዳጊዎቹን ወደቤታቸው መመለስ አደገኛ ነው ቢሉም ሰሚ አላገኙም። በሰሜናዊ ናይጄሪያ የሚገኙ አገረ ገዢዎች ወረርሽኙን የቁርዓን ትምህርትን ለማቆም ተጠቅመውበታል። ትምህርቱ በአብላጫው ሙስሊሞች በሚኖሩበት ሰሜናዊ ናይጄሪያ የትምህርት ሥርዓት አካል ነው። የካዱና አገረ ገዢ ናሲር ኤልሩፊያ የትምህርት ሥርዓቱ ታዳጊዎቹንም ናይጄሪያንም እየጠቀመ ስላልሆነ ማስወግድ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ታዳጊዎቹ ዘመናዊ ትምህርት ቢማሩ ይሻላልም ብለዋል። “ታዳጊዎቹ በየጎዳናው የሚበሉትን ከሚለምኑ አልማጅሪን ማዘመን ይቻላል” ብለዋል አገረ ገዢው። አብዛኞቹ ታዳጊዎቹ ከአቅመ ደካማ ቤተሰብ የተገኙ ናቸው። ከአምስት እስከ አስር ዓመት በቁርዓን መምህር ሥር ይሆናሉ። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው ከአምስት እስከ 14 ዓመት የሞላቸው 10.5 ሚሊዮን ናይጄሪያውያን ትምሀርት ቤት አልገቡም። ድርጅቱ የአልማጅሪን ሥርዓት እንደ ትምህርት ቤት አይቆጥረውም። በየጎዳናው የሚለምኑ ታዳጊዎች በአልማጅሪን ትምህርት ቤቶች አምስት ዓመት የሞላቸው አዳጊዎች ለመምህራቸው በየሳምንቱ እሮብ 100 ናይራ መስጠት ይጠበቅባቸዋል። ማላማ በመባል የሚባሉት መምህራን ክፍያው ለትምህርት ቤቱ እድሳት እንጂ ለግል ጥቅማችን አይውልም ይላሉ። አብዛኞቹ አዳጊዎች ገንዘቡን ለማግኘት በየጎዳናው ይለምናሉ። የሚኖሩበት ሁኔታ ምቹ አይደለም። በተጨናነቀና ንፅህናው ባልተጠበቀ ቦታ የሚኖሩት አዳጊዎቹ፤ ላሳምንታት ሰውነታቸውን ላይታጠቡ ይችላሉ። ይህም ከእስልምና አስተምሮት ውጪ ነው። መምህራኑም ድሃ ናቸው። በቂ የማስተማር ስልጠናም አልወሰዱም። ትምህርት ቤቶቹ ከሁለት ወር በፊት እንዲዘጉ ሲወሰን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳጊዎች መጠለያ ስሌላቸው በየጎዳናው መለመናቸውን ቀጥለዋል። መንግሥት ታዳጊዎቹ በሽታውን ሊያሰራጩ ይችላለሉ ብሎ በየቤታቸው እንዲመለሱ ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም፤ ውሳኔው ዘግይቷል። የቀድሞ አልማጅሪን የነበሩት ኢምራን ሞሐመድ እንደሚሉት፤ ታዳጊዎቹ በበሽታው የተያዙት ሲለምኑ ሊሆን ይችላል። ላለፉት ዓመታት ይህንን የትምህርት ሥርዓት ለማቆም ውይይቶች ሲካሄዱ ነበር። ሆኖም ግን ከትምህርት ቤቶቹ ደጋፊዎች የእስልምና ትምህርትን ልታጠፉ ነው የሚል ተቃውሞ ቀርቧል። ተስፈኛው አባት የቀድሞው ፕሬዘዳንት ጉድላክ ጆናታን በቢሊዮን የሚቆጠር የናይጄሪያ ገንዘብ አውጥተው ነበር እነዚህን ትምህርት ቤቶች ያስገነቡት። ፕሬዘዳንቱ ክርስቲያንና ከደቡብ ናይጄሪያ የተገኙ መሪ ነበሩ። እሳቸውን ተከትለው ሥልጣን የያዙት የሰሜን ናይጄሪያው ሙስሊም መሪ ሙሐመዱ ቡሐሪ ትምህርት ቤቶቹ እንዲዘጉ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ከተማሪዎቹ መካከል ጎዳና የወጡም አሉ። ሻይፉ ያዩ የተባሉ አባት፤ “ትምርት ቤቶቹ የገነት በር ናቸው” ይላሉ፤ እንዲዘጉም አይፈልጉም። የ15 ዓመት ልጃቸው አሁንም ድረስ በካኖ ግዛት አልማጅሪን ነው። “አሁን ሁለተኛ ዓመቱ ነው። ከአምስት ዓመት በኋላ ስለ ቁርዓንና ስለ ኃይማኖቱ እውቀት አካብቶ እንደሚመጣ ተስፋ አፈርጋለሁ” ይላሉ ሻይፉ። ሐሳባቸውን የማይቀበሉም አሉ። ሼክ አብዱላሂ ጋራንግማዋ፤ የትምህርት ሥርዓቱ ተበዝብዟል ይላሉ። በሰሜን ናይጄሪያ የሚገኝ መስጅድ ኢማም ሲሆኑ፤ “አሁን ላይ ትምህርት ቤቶቹ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ግዞት ነው። መንግሥት ማመንታቱን ትቶ ቶሎ ሊዘጋቸው ይገባል” ሲሉም ያስረዳሉ። “ታዳጊዎቹ የእስልምና ትምህርት እየተሰጣቸው አይደለም። ብዙዎቹ ወንጀለኛና የፖለቲከኞች የወንጀል ድርጊት አስፈጻሚ ቅጥረኛ ነው የሚሆኑት” ይላሉ ሼክ አብዱላሂ።
news-51836937
https://www.bbc.com/amharic/news-51836937
የኬንያው የደኅንነት ሚኒስትር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር መከሩ
በአገራቸውና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ ያለውን ውጥረት በተመለከተ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር አዲስ አበባ ላይ መወያየታቸውን የኬንያው የደኅንነት ሚኒስትር ተናገሩ።
ከሶማሊያና ከኬንያ ጋር ድንበር የምትጋራው ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፈውንና ከእስላማዊው ቡድን አል ሻባብ ጋር የሚፋለመውን የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት ለመደገፍ ተሰማርቶ ለሚገኘው የአፍሪካ ኅብርት ሠራዊት አዋጥታለች። የደኅንነት ሚኒስትሩ ፍሬድ ማትያንጊ "በድንበር አካባቢ ያሉትን ችግሮች በመቅረፍ የቀጠናውን መረጋጋት ለማጠንከር በአገራቱ መካከል የትብብር መንገድ ለመፈለግ ያቀደ ውይይት" መሆኑን በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ አስፈረዋል። ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ያደረጉት ውይይት የተካሄደው የሶማሊያ ኃይሎች ከፊል እራስ ገዝ ከሆነችው የሶማሊያዋ ጁባላንድ ግዛት ከመጡ ኃይሎች ጋር በኬንያ ግዛት ውስጥ ከማንዴራ አቅራቢያ ባለ ቦታ ላይ ከተጋጩ ከሳምንት በኋላ ነው። ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ የኬንያው የደኅንነት ሚኒስትር ፍሬድ ማትያጊ ወደ ሶማሊያ አቅንተው ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሒ ፋርማጆ ሞሐመድ ጋር በመገናኘት የድንበር አካባቢ ጸጥታን ለማጠመናከር ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን አድርገዋል። ቀደም ሲልም ሶማሊያ ኬንያን በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ እየገባች ነው በማለት የከሰሰች ሲሆን ጨምራም በድንበር አካባቢም ያለውን መስፋፋት እንድታቆም አስጠንቅቃ ነበር። በሁለቱ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት በሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ ባላቸው የጋራ የውሃ ድንበር ይገባኛል ውዝግብ ምክንያት ከሻከረ ቆየት ብሏል። ይህም የባሕር ድንበር ይገባኛል ውዝግብ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት በመጪው ሰኔ ወር ላይ ይሰማል።
news-49246584
https://www.bbc.com/amharic/news-49246584
ኦባማ አሜሪካዊያን ጥላቻን ለሚሰብኩ መሪዎች ጆሮ እንዳይሰጧቸው ተማፅነዋል
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ አሜሪካዊያን ጥላችና ዘረኝነት የሚሰብኩ መሪዎቻቸውን እንዲያወግዙ ጥሪ አቅርበዋል።
ምንም እንኳ ኦባማ ይህ ነው ያ ነው ብለው ስም ባይጠቅሱም አስተያየታቸው በተከታታይ ቀናት ከተከሰቱ የጅምላ ግድያዎች በኋላ መምጣቱ ትችቱ ዶናልድ ትራምፕ ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን አይቀርም አስብሏል። ቴክሳስ ኦሃዮ ውስጥ 31 ሰዎች በጅምላ ጥቃት ከተገደሉ በኋላ ዶናልድ ትራምፕ ጥላቻ እና የነጭ የበላይነትን ማስወገድ አለብን ሲሉ ተደምጠው ነበር። • ሚሼል ኦባማ በአሜሪካ እጅግ ተወዳጇ ሴት ተባሉ ኦባማ ሥልጣን ላይ የጦር መሣሪያ ግዥ ቁጥጥር እንዲደረግበት ቢታገሉም ሳይሳካላቸው መቅረቱ አይዘነጋም። በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2015 ላይ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ የጦር መሣሪያ ላይ ቁጥጥር ማድረግ የሚያስችል ሕግ ማፅደቅ አለመቻላቸው እንደሚከነክናቸው ገልፀው ነበር። ኦባማ፤ ትራምፕ ስደተኞችን አስመልክቶ ስላሰሟቸው አጨቃጫቂ ንግግሮች ምንም ዓይነት አስተያየት ለመስጠት ቢቆጠቡም ሰኞ ዕለት በለቀቁት መግለጫ 'ጥላቻን የሚሰብኩ መሪዎችን እናውግዝ' ብለዋል። «ጥላቻን የሚሰብኩ፣ ፍራቻን የሚነዙ፣ ዘረኝነት የሚያበረታቱ፣ እነሱን የማይመስሉ ሰዎችን [ስደተኞችን ጨምሮ] የሚያገሉ፣ አሜሪካ ለተወሰኑ ዓይነት ሰዎች ብቻ ነች የሚሉ መሪዎችን አምርረን ማውገዝ አለብን።» በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል። • ኦባማ ፍርድ ቤት ሊያገለግሉ ቢመጡም አገልግሎትዎ አያስፈልግም በሚል ተሰናበቱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው ወቅት የሜክሲኮ ዜጎች ደፋሪዎች እና ገዳዮች ናቸው ማለታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ከሁለት ተከታታይ የጅምላ ጥቃቶች በኋላ ፕሬዝደንት ትራምፕ፤ "የአዕምሮ ጤና እና የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ሕጉ ላይ ማሻሻያዎች ያስፈልጋሉ፤ የጅምላ ጥቃት አድራሾች ከበድ ያለ ቅጣት ያስፈልጋቸዋል" የሚል መግለጫ አውጥተዋል። የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ያቀረበውን የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ሕግ ይደግፉ አይደግፉ ግን ያሉት ነገር የለም። • ኦባማ እና ቡሽ ትራምፕን ተቹ
news-42538583
https://www.bbc.com/amharic/news-42538583
የናይጄሪያ ጦር በቦኮ ሃራም ታግተው የነበሩ 700 ሰዎችን ማስለቀቁን ገለፀ
የናይጄሪያ ጦር በቅርቡ ባደረገው ዘመቻ በሃገሪቱ ሰሜን ምስራቅ ክፍል በቦኮ ሃራም ታግተው የነበሩ 700 ሰዎችን ማስለቀቁን ገለፀ።
ጦሩ በቦኮ ሃራም ታግተው የተለቀቁ ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶ ይፋ አድርጓል የጦሩ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ቲሞቴ አንቲጋ እንዳሉት ታጋቾቹ በቻድ ሐይቅ ላይ ከሚገኙ ደሴቶች ለቀው የቦርኖ ክፍለ ሃገር ከተማ ወደ ሆነችው ሞንጉኖ ደርሰዋል። የጦሩን መግለጫ ከገለልተኛ ወገን ማጣራት ግን አልተቻለም። የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳለው የታገቱት ሰዎች የተለቀቁት በአንዴ ሳይሆን ቀስ በቀስ ሊሆን ይችላል። እንደጦሩ መግለጫ ከሆነ በቅርቡ በተደረገ 'ዲፕ ፐንች 2' ዘመቻ ቦኮ ሃራምን ማዳከም ተችሏል። ፕሬዝዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ በአዲስ ዓመት ለህዝባቸው ባደረጉት ንግግር ቦኮ ሃራም ''አከርካሪው ተሰብሯል'' ብለዋል። የናይጄሪያ ጦር ታግተው የነበሩት ግለሰቦች ገበሬዎች፣ አሳ አስጋሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው እንደሆኑ ገልጧል በናይጄሪያ ጦር ፌስቡክ ገፅ ላይ ኮሎኔል አንቲጋ 700ዎቹ "ገበሬዎች፣ አሳ አስጋሪዎች፣ እና ቤተሰቦቻቸው ሲሆኑ በግብርና ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ተገድደው ነበር" ብለዋል። በቅርቡ የተደረገው ዘመቻ "የቦኮ ሃራም መገናኛ ማዕከላቱን፣ ማሰልጠኛ ጣቢያውን፣ ቦምብ መስሪያ ቁሳቁሱን፣ መኪኖቻቸውን እና ቀለባቸውን የያዙ መሰረተ-ልማቶችን ማውደምን ታሳቢ ያደረገ ነበር " "የማዘዣ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ እንዲወድም እና እንዳያንሰራራ፣ ደሴቶቹን ከሌላው አካባቢ በመነጠል እንዲሁም ታግተው የነበሩት እንዲያመልጡ ማድረግ" ችለናል ሲሉ ፅፈዋል። ኮሎኔል አንቲጋ ከተለቀቁት ግለሰቦች መካከል የቦኮ ሃራም አባላት ሰርገው እንዳይገቡ ጥንቃቄ መደረጉንም ተናግረዋል። በተጨማሪም ከተለቀቁት መካከል ሁለት ሴቶች በጦሩ የሕክምና ማዕከል ውስጥ በሰላም ወልደዋል። ከስምንት ዓመታት በላይ ቦኮ ሃራም ከ20ሺህ ሰዎች በላይ ገድሏል፤ 2.6 ሚሊዮን ሰዎችን አፈናቅሏል። ባለስልጣናት ቦኮ ሃራም እየተንኮታኮተ እንደሆነ መግለጫ ቢሰጡም የቦኮ ሃራም ተዋጊዎች ግን ጦሩ ላይ እና ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አድርሰዋል።
news-56648761
https://www.bbc.com/amharic/news-56648761
ወንዶች ላስረገዟቸው ሴቶች የእርግዝና ወጪ እንዲጋሩ የምታስገድደው ግዛት
በአሜሪካ ዩታህ ግዛት እርግዝና ከተከሰተ በኋላ ወንዶች እንደ ጭስ ብን ብለው መጥፋት አይችሉም። እያንዳንዷን የእርግዝና ወጪ ይጋሯታል።
ይህ ግዴታ አባቶችንም፣ የፍቅር ተጣማሪዎችንም፣ የአንድ ጊዜ የከንፈር ወዳጆችንም ለጽንሱ መፈጠር ምክንያት እስከሆኑ ድረስ የሚመለከታቸው ነው። የወጪ መጋራቱ ታዲያ ከእያንዳንዱ በእርግዝና ወቅት ከሚያስፈልገው መድኃኒት ጀምሮ፣ ለ9 ወራት የሚዘልቁ የምግብ፣ የጤናና ተያያዥ ጉዳዮችን ያካትታል። የወሊድ ወጪንም አባት የግድ ይጋራል። ይህ አዲስ ሕግ በአሜሪካ ሲተገበር ዩታህ ግዛት የመጀመሪያዋ ናት። የዚህ ሕግ ደጋፊዎች አዲሱን ሕግ "የአሜሪካ ሴቶች የሚደርስባቸውን መከራና ፍዳ በትንሹ የሚያቀል" ሲሉ አሞካሽተውታል። ይህ ደንብ የጸደቀው በሪፐብሊካንም በዲሞክራቶችም የጋራ ድጋፍ አግኝቶ ነው። ሕጉ ከጸደቀ በኋላ ግን በአሜሪካ የወላጆች ወጪ ላይ አዲስ ውይይት እንዲከፈት ምክንያት ሆኗል። በተለይም ዩታህ ግዛት ጽንስን የማቋረጥ መብትን ተፈጻሚ ለማድረግ ሴቶች ማሟላት ያለባቸውን ዝርዝር ሁኔታ እያጠበቀች ከመምጣቷ ጋር ተያይዞ አዲሱ ሕግ ብዙ እያነጋገረ ነው። ሕጉ ምን ይላል? የዩታህ የእርግዝና ወጪ መጋራት ሕግ ማንኛውም የተፈጥሮ አባት ለልጁ እናት ጽንሱ ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ግማሽ ወጪን እንዲሸፍን ያስገድዳል። ይህም የኢንሹራንስ ወርሃዊ ክፍያን እና ሌሎች ማናቸውም የሕክምና ወጪዎችን የሚጨምር ነው። ይህ ቀጥታ ወጪ መጋራቱ የተረገዘው/ችው ልጅ ከ9 ወር እርግዝና በኋላ የሚመጣውን የማዋለጃ ዋጋንም ይጨምራል። ለአንዲት አሜሪካዊት እርጉዝ ሴት አንድ ልጅ አርግዞ መውለድ በገንዘብ ደረጃ በአማካይ 4 ሺህ 500 ዶላር ያስወጣታል። ይህ የኢንሹራንስ ወጪን ሳይጨምር ከኪሷ ብቻ የምታወጣው የገንዘብ መጠን ነው። ኢንሹራንስ ለሌላቸው እርጉዝ ሴቶች ይህ ወጪ እጥፍ ይሆናል። እንደ ፌይር ሔልዝ ጥናት ከሆነ ብዙውን ጊዜ የመድኅን ሽፋን አልባ እርጉዝ ሴቶች አርግዘው እስኪወልዱ 10 ሺህ ዶላር አይበቃቸውም። በዚህ ጊዜ ፍቅረኛ/ባል መጠርያው ማንም ይሁን ማን 'የጽንሱ አባት' ከዚህ ቀደም ወጪውን ለመጋራት አይፈቅዱ ስለነበር ሁኔታው ሴት አሜሪካዊያን ላይ ከባድ ጭናን ያሳርፍ ነበር። በአዲሱ ሕግ ግን ይህ ወጪ የባል/የፍቅረኛ ወይም የአንድ አፍታ ወዳጅም ሊሆን ይችላል 'የጽንሱ አባት' ይጋራዋል። ለሴቷ እርግዝና ምክንያት የሆነው ወንድ ቢክድ ወይም ማንነቱ ለጊዜው የማይታወቅ ከሆነና በምርመራ ሂደት ላይ ካለ ወጪ መጋራቱ ለጊዜው እንዲዘገይ ተደርጎ የጽንሱ ባለቤት ሲታወቅ፣ ወይም ጽንሱ ሲወለድ ወጪዎች ተሰልተው ይቀርቡለታል። ሆኖም እርጉዝ ሴቶች የልጁን ባል እገዛ የማይሹ ከሆነ ለአባት ይህ ጨርሶዉኑ እንዳይነገረው፣ ወጪም እንዳይነካው ሊያደርጉ መብቱ አላቸው። ይህ ሆኖ ሳለ ግን እርጉዝ ሴቶች ጽንሱን ማቋረጥ ቢፈልጉ ወጪው አባትን አይመለከተውም። ሴቷ ጽንስ እንዲቋረጥ ስትወስን 'የጽንሱ አባት' ወጪ ሸፍን ተብሎ አይገደድም። ለጽንስ ማቋረጡም የሚሆን ገንዘብ ክፈል ተብሎ በሕግ አይገደድም። ሆኖም የእናትዬው ሕይወት አደጋ ላይ ከሆነ ወይም ጽንሱ የተፈጠረው በእናት ፈቃድ ካልሆነ ወጪውን ወንዱ እንዲሸፍነው ሊደረግ ይችላል። ይህ ወጪ የመጋራት ሕግ ከመጪው ግንቦት 5 ጀምሮ በዩታህ ግዛት ተግባራዊ ሆኖ ይሠራበታል። በአሜሪካ አሁን ባለው አማካይ ዋጋ ለአንዲት ሴት ጽንስ ማቋረጥ ብቻ በትንሹ 1ሺህ ዶላር ያስወጣታል። ይህንን ሕግ በማስተዋወቅና ሕግ እንዲሆንም ከፍተኛ ድጋፍ ካደረጉ እንደራሴዎች መካከል ብራዲ ብራመር ይገኙበታል። "ስለ ጽንስ ማቋረጥ ጉዳይ ሳንጨቃጨቅ እርጉዝ ሴትና ልጇን ማገዝ እንደሚቻል ያሳየ ሕግ ነው" ብለዋል ብራመር ለቢቢሲ። እንደራሴ ብላመር የጽንስ ማቋረጥን የሚቃወሙ ሪፐብሊካን ናቸው። የጽንስ ማቋረጥ ደጋፊዎች ግን ይህን ይኮንናሉ። ጽንስ የምታቋርጥ ሴት የግድ ተስፋ በመቁረጥ አይደለም ድርጊቱን የምትፈጽማው። ጽንስ ማቋረጡ ምርጫዋ ስለሆነ እንጂ ይላሉ። በአሜሪካ 24 ከመቶ የሚሆኑ ሴቶች ዕድሜያቸው 45 እስኪደርስ ድረስ የጽንስ ማቋረጥ ተግባር ይፈጽማሉ ይላል አንድ ጥናት። ከነዚህ መሀል ግማሾቹ የሚሆኑት ከድህነት ወለል በታች ባለ ሁኔታ የሚኖሩ ናቸው። ጽንስን ማቋረጥ መብት ነው ብለው የሚከራከሩ ይህን አዲሱን የዩታህ ግዛት ሕግ በበጎ ይመለከቱታል። ሆኖም ይህ ሕግ ነገሩን የተመለከተበትን መንገድ አልወደዱትም። ከዚህ ይልቅ የተሻለ የጤና መድኅን አቅርቦት፣ የጋራ የቤተሰብ ጤና አገልግሎት፣ ተከፋይ የቤተሰብ የእረፍት ፍቃድ የመሳሰሉት በፖሊሲ ደረጃ ቢተኮርባቸው ለሴቷ ሰፊ አማራጭ የሚሰጡ ናቸው ይላሉ። ይህ ወንዱ የእርግዝና ወጪን እንዲጋራ ማድረግ ሕግ ብቻውን ለሴቷ የሚፈይድላት ነገር እምብዛምም ነው ባይም ናቸው። የአሜሪካ የእርሻና ቤተሰብ ኤጄንሲ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ በአሜሪካ አንድ ቤተሰብ አንድ ልጅን ለማሳደግ (ልጁ/ልጅቷ 17 ዓመት እስኪደርሱ ድረስ) እስከ 233 ሺህ ዶላር ድረስ ያስፈልጋቸዋል። ይህ ስሌት የ2015 ዓ.ም የኑሮ ሁኔታ ላይ ተመሥርቶ የተሠራ ነው። ይህ ወጪ የኮሌጅ ትምህርት ክፍያን የማይጨምር ነው። ዩታህ ጽንስ ማቋረጥን በእጅጉ የማታበረታታ ግዛት ናት። ይህ አዲሱ ሕግም ለዚሁ ተብሎ የተቀመመ ዘዴ ነው ይላሉ የጽንስ ማቋረጥ መብት ተሟጋቾች። ሜሪሊ ቦያክ ከነዚህ አንዱ ናቸው። "የዚህ ሕግ ዓላማ ጽንስ ማቋረጥን ከሴቷ አእምሮ እንዲፋቅ ማድረግ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ አስተያየት ሰጥተዋል። በአሜሪካ በርካታ ግዛቶች ጽንስ በማቋረጥ መብት ላይ ሁሉን አቀፍና መልከ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ነገሩን ለሴቶች ከባድ እያደረጉት ይገኛሉ። ዩታህ በ2019 ያሳለፈችው ሌላ ሕግ በተለዩ ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር ልጅ ከተረገዘ ከ18 ሳምንት በኋላ ጽንስ ማቋረጥን ይከለክላል። ለማቋረጥ የፈለጉ ሴቶች ከባለሙያ ተከታታይ ምክር ማግኘት አለባቸው ሲልም ያስገድዳል። ሴቶች ጽንሱን በማቋረጥ ከጸኑ ድርጊቱን ከመፈጸማቸው በፊት 72 ሰዓት ሐሳባቸውን እርግፍ አድርገው እንዲተዉ የሚያደርግ ሌላ የምክር አገልግሎት የማግኘት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ይህንን ሲያሟሉ ብቻ ነው 72 ሰዓት ጠብቀው ጽንስ ማቋረጥ የሚችሉት። ባለፈው ዓመት ደግሞ 'ትሪገር ባን' የሚል ስም ያለው አዲስ ሕግ ጸድቋል። ይህም ጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ጥቂት ክሊኒኮች ጽንሱን የመቅበር ግዴታን ጥሎባቸዋል። ሴቶች ጽንስ ማቋረጥ የሚችሉባቸውን ዕድሎችም በእጅጉ የሚያጠብ ሕግ ወጥቷል። ከ18 ዓመት በታች ያሉ ሴቶች ጽንስ ለማቋረጥ ወላጆቻቸው ስምምነት መፈረም አለባቸው። በ2017 ብቻ በአሜሪካ ከ800 ሺህ በላይ ሴቶች በጤና ተቋማት የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት አግኝተዋል። ከእነዚህ ውስጥ 3 ሺህ የሚሆኑት የዩታህ ግዛት ነዋሪዎች ናቸው።
news-46285799
https://www.bbc.com/amharic/news-46285799
የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞች በየዓመቱ 8 ቢሊዮን ዶላር ለቤተሰቦቻቸው ይልካሉ ይላል
በእንግሊዝ በተለያዩ ስራዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ስደተኞች ካጠራቀሙት ገንዘብ በዓመት የሚልኩት እስከ 8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ድርጅት አስታወቀ።
አብዘኛው ገንዘብ ለህጻናት ትምህርት ቤት ክፍያ የሚውል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ በጣም ደሃ ወደ ሆኑ ሃገራት ነው ተብሏል። ድርጅቱ እንዳስታወቀው እነዚህ ስደተኞች ከሚልኩት ገንዘብ ውስጥ ትንሽ የማይባል መጠን ያለው ገንዘብ ለአለማቀፍ ገንዘብ አዘዋዋሪዎች ይከፈላል። ምንም እንኳን ዓለማቀፍ ህጉ ለገንዘብ ዝውውር ከ3 በመቶ በላይ መከፈል የለበትም ቢልም፤ ስደተኞቹ እስከ 7 በመቶ ድረስ እንዲከፍሉ እንደሚደረግ የተባበሩት መንግስታት ገልጿል። • ወሎ በነዳጅ 'ልትባረክ' ይሆን? • 85 ሺ የየመን ህጻናት በምግብ እጥረት ሞተዋል በእንግሊዝ የሚገኘው የክፍያ ስርዓት ማዕከላት ሕብረት እንደሚለው የዓለምአቀፍ ማዘዋወሪያ ክፍያዎች በጣም እየናሩ የመጡት አገልግሎቱን የሚሰጡ ድርጅቶች ቁጥር ትንሽ በመሆኑ ነው ይላል። እንግሊዝ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን በማስተናገድ ትልቅ ድርሻ ያላት ሲሆን፤ ናይጄሪያውያን፣ ህንዳውያንና ፓኪስታናውያን በቢሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ ወደ ሃገር ቤት በመላክ ቀዳሚዎቸ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ፓውንድ ደግሞ ወደ ፖላንድ፣ ቻይና፣ ኬንያ፣ ፊሊፒንስ፣ ባንግላዲሽና ጋና ይላካል። ከአሜሪካ የሚላክ ከፍተኛ መጠን ያለው ዶላር ደግሞ መዳረሻው የማዕካለዊ አሜሪካና ደቡባዊ አሜሪካ ሃገራት ናቸው። ምንም እንኳን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ያደጉት ሃገራት ገንዘብ ወደ ደሃ ሃገራት ቢላክም፤ በጣም ብዙ ሊባል የሚችል ገንዘብ ደግሞ በአዘዋዋሪዎችና ባንኮች ይወሰዳል። ስደተኞቹ ለዓለማቀፍ የገንዘብ ዝውውር የሚከፍሉት ገንዘብ እስከ 3 በመቶ ድረስ ዝቅ ቢል በየዓመቱ የሚላከው ገንዘብ ላይ ተጨማሪ 25 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት ይቻላል። ይህ ማለት ደግሞ ተጨማሪ 1 ቢሊዮን ዶላር የህጻናት ትምህርት ላይ ይውላል ማለት ነው። የተባበሩት መንግስታት እንደገለጸው ሁኔታው ባስ ሲል አንዳንዴ ስደተኞቹ ከሚልኩት ገንዘብ 25 በመቶውን ለገንዘብ ተቋማቱ እንዲከፍሉ የሚገደዱባቸው ሁኔታዎች ብዙ ናቸው። ከውጪ ሃገራት የሚላከው ገንዘብ በአፍሪካና በእስያ በሚገኙ 18 ሃገራት ትምህርት ላይ የሚውለውን ወጪ በ35 በመቶ ያሳደገው ሲሆን፤ በደቡብ አሜሪካ በሚገኙ ሃገራት ደግሞ 50 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጎታል። • ትራምፕ ውግዘት ከደረሰባት ሳዑዲ ጎን ቆመዋል • ዌል የተባለው የባህር እንስሳ 6 ኪሎ ያህል ኩባያ ውጦ ተገኘ ፊሊፒንስ ውስጥ ከውጪ ሃገራት ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ላኩ ማለት ህጻናት ለጉልበት ስራ ከመሰማራት ተላቀው ወደ ትምህርት ቤት ይሄዳሉ ማለት ነው። ምንም እንኳን ስደተኞች በውጪ ሃገራት ሲቀጠሩ በጣም ዝቅተኛ ክፍያ ያላቸው ስራዎችን ቢሆንም የሚያገኙት፤ ካላቸው ላይ ቆጥበው ግን ልጆቸቸውን ማስተማር እንዲሁም ቤተሰባቸውን መርዳት ግዴታቸው ይመስላል። እነዚህ ስደተኞች ወደ ሃገራቸው የሚልኩት 8 ቢሊዮን ዶላር የእንግሊዝ መንግስት ለውጪ እርዳታ ከሚያውለው ገንዘብ ይበልጣል።
news-48472488
https://www.bbc.com/amharic/news-48472488
ትራምፕ ወደ እንግሊዝ ምን ይዘው ይሄዳሉ?
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ እንግሊዝ የሚያደርጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማስመልከት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ ወጪ እየተደረገና ከፍተኛ የሆኑ የደህንነት ሥራዎችም እየተከናወኑ ነው።
በንግሥት ኤልሳቤጥ ጋባዥነት ከሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት ለሚደረገው የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት፤ እስከ 18 ሚሊዮን ፓውንድ (666 ሚሊዮን ብር) ድረስ ወጪ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። • ዶናልድ ትራምፕ ተከሰሱ የኋይት ሃውስ የደህንነት ሰዎች ወደ እንግሊዝ መግባት ጀምረዋል። ትራምፕን ተከትለው ወደ እንግሊዝ የሚሄዱት የደህንነት ቁሶችና የመጓጓዥ አይነቶች የትኞቹ ናቸው? ትራምፕን አጅበው የሚመጡትስ እነማን ናቸው? ፕሬዝዳንቱ ወደ እንግሊዝ የሚሄዱት በልዩ ሁኔታ የተሠራውን 'ኤር ፎርስ ዋን' ተሳፍረው ነው። 'ኤር ፎርስ ዋን' በሰሜን ለንደን አቅጣጫ በሚገኘው ስታንስቴድ አየር ማረፊያ ያርፋል ተብሎ ይጠበቃል። 'ኤር ፎርስ ዋን' ተብለው የሚጠሩት ሁለት በልዩ ሁኔታ የተሠሩ ቦይንግ 747-200B አውሮፕላኖች ናቸው። ትራምፕ በእንግሊዝ በሚኖራቸው ጉብኝት ወቅት ሁለቱንም አውሮፕላኖች ጥቅም ላይ ሊያውሉ እንደሚችሉ ይገመታል። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? የአሜሪካ ዜና ወኪሎች ዘገባ እንደሚጠቁመው፤ ትራምፕ በእንግሊዝ ጉብኝታቸው ወቅት ያገቡ ልጆቻቸውን ከነመላው ቤተሰቦቻቸው ስለሚወስዱ ሁለተኛው 'ኤር ፎርስ ዋን' ያስፈልጋቸዋል። ጥንቅቅ ያለው የ 'ኤር ፎርስ ዋን' አሠራርና አጨራረስ በጦር አውሮፕላን ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት ያደርገዋል። አውሮፕላኑ ከአየር ላይ ጥቃቶች ራሱን መከላከል ይችላል። የጠላት ራዳርን ማፈን ይችላል። የሚሳዔል ጥቃት ቢሰነዘርበት ፍንዳታ የማያስከትል ከፍተኛ ብርሃንና ሙቀት ያለው ጨረር በመልቀቅ የተቃጣውን የሚሳዔል ጥቃት አቅጣጫ ያስቀይራል። 'ኤር ፎርስ ዋን' አየር ላይ ሳለ ነዳጅ መሙላት ይችላል። ይህም ላልተወሰኑ ሰዓታት በረራውን እንዲቀጥል ያሰችለዋል። አውሮፕላኑ ላይ የተገጠሙት ሞባይል የመገናኛ ቁሳቁሶች ፕሬዝደንቱ በየትኛውም የዓለም ክፍል ላይ ትዕዛዝ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል። የ 'ኤር ፎርስ ዋን' ተሳፋሪዎች 4,000 ካሬ ጫማ በሚሰፋው አውሮፕላን ውስጥ ዘና ማለት ይችላሉ። አውሮፕላኑ ውስጥ ሦስት ወለሎች አሉ። እነዚህ ሦስት ወለሎች የፕሬዝዳንቱ ቅንጡ ማረፊያ፣ የህክምና አገልግሎት መስጫ፣ የስብሰባና የመመገቢያ ክፍል፣ ሁለት ኩሽና እንዲሁም የክብር እንግዶች፣ የመገናኛ ብዙሃን አባላት፣ የደህንነት ሰዎች እና የፕሬዝዳንቱ ረዳቶች መቀመጫ ስፍራዎችን ይዘዋል። በርካታ እቃ ጫኝ አውሮፕላኖችም ከጉብኝቱ ቀን በፊት የፕሬዝዳንቱን መኪኖች፣ ሄሊኮፕተሮች እና ሌሎች ቁሶችን ያደርሳሉ። እንደ ዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ከሆነ ፕሬዝዳንቱ ሁሌም በሄዱበት የሚከተላቸው ''ፉትቦል'' ተብሎ የሚጠራ ቦርሳ አለ። ይህ ቦርሳ በውስጡ ኒውክለር ለመተኮስ የሚያስችል ማዘዣ እና የይለፍ ቃላትን እንደያዘ ይታመናል። ፕሬዝዳንቱ የጦር ኃይሉ ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆናቸው መጠን፤ የኒውክለር ጥቃት መፈጸም አስፈላጊ ሆኖ ቢገኝ በፍጥነት ትዕዛዙን ይሰጡ ዘንድ እንዲያመቻቸው ይህ ቦርሳ ሁሌም ከጎናቸው አይለይም። ፕሬዝዳንቱ የሚንቀሳቀሱበት መኪኖችን ጨምሮ የሚያጅቧቸው ተሽከርካሪዎች በሙሉ ከእርሳቸው ቀድመው እንግሊዝ ይደርሳሉ። ዶናልድ ትራምፕ የሚጓጓዙበት 'ዘ ቢስት' ተብለው የሚጠሩ ሁለት ተመሳሳይ ጥቁር ካዲላክ መኪኖች አሏቸው። ሁለቱም መኪኖች ተመሳሳይ የሆነ ዋሽንግተን ዲሲ 800-002 የሚል ታርጋ ቁጥር አላቸው። የመኪኖቹ አካል እና መስታወት ጥይት የማይበሳው ሲሆን፤ አስለቃሽ ጭስ መልቀቅ የሚያስችል ስርዓት እና በምሽት ማየት የሚያስችል ካሜራ እንደተገጠመላቸው ይታመናል። በመኪኖቹ ጎማ ላይ የተገጠመው ቸርኬ የመኪኖቹ ጎማ አየር ባይኖረው እንኳን እንዲሽከረከሩ ያስችላል። የነዳጅ ቋቶቹም የእሳት ጉዳት እንዳይደርስባቸው በእሳት መከላከያ ፎም ተሸፍነዋል። እያንዳንዳቸው 7 ሰዎችን የመጫን አቅም ያላቸው መኪኖቹ፤ በውስጣቸው የህክምና ዕቃ አቅርቦቶች ተሟልቶላቸዋል። ኤን ቢ ሲ እንደሚለው ከሆነ አንድ ፍሪጅ ሙሉ የፕሬዝዳንቱ የደም አይነት በመኪኖቹ ውስጥ ይቀመጣል። ዶናልድ ትራምፕ በመኪና መንቀሳቀስ ሲጀምሩ በርካታ ተሽከርካሪዎች ያጅቧቸዋል። ከሚያጅቧቸው መካከል ሞተረኛ ፖሊሶች፣ የደህንነት አባላት መኪኖች፣ የታጠቁ የደህንነት አባላትን የያዙ መኪኖች፣ የህክምና አገልግሎት ሰጪ ቡድን አባላትና ጋዜጠኞች ይገኙበታል። ትራምፕ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ሳይሆን ሄሊኮፍተሮችንም ይዘው ወደ እንግሊዝ ያቀናሉ። ፕሬዝደንቱን የምትጨነው ሄሊኮፍተር 'መሪን ዋን' ትሰኛለች። በዚህ ስም የሚጠራው ሂሊኮፍተር አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ናቸው። 'መሪን ዋን' ሄሊኮፍተሮችም ሚሳዔል መቃወሚያ እና የግንኙነት ስርዓቶች የተገጠሙላቸው ናቸው። ፕሬዝዳንቱን በሄሊኮፍተር ሲጓዙ 'መሪን ዋን' ጋር ተመሳሳይ ቅርጽ ያላቸው ሄሊኮፍተሮች ለደህንነት ሲባል አብረው እንዲበሩ ይደረጋል። በእነዚህ ተመሳሳይ አውሮፕላኖች ውስጥም ቢሆን የደህንነትና የህክምና ቡድን አባላት ይሳፈራሉ። ከትራምፕ ጋር ወደ እንግሊዝ የሚሄዱ ሰዎች 1000 ያህል ሊሆኑ እንደሚችል ተገምቷል። የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት የሚጀመረው በበርኪንግሃም ቤተ-መንግሥት በሚደረገው የእንኳን ደህን መጡ የምሳ ግብዣ ይሆናል። ትራምፕ ከጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ ጋር በሴንት ጀምስ ቤተ-መንግሥት እና በ10 ዶውኒንግ ስትሪት ይወያያሉ። የለንደን ከተማ ፖሊስ ጉብኝቱን በማስመልከት ''በርካታ ኤጀንሲዎች እና ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ አባላት የሚሳተፉበት ኦፕሬሽን ይሆናል'' በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። የከተማዋ ፖሊስ ጨምሮም በፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ወቅት ለንደን በርካታ ግዙፍ የተቃውሞ ሰልፎችን ልታስተናግድ አንደምትችል ይጠበቃል ብሏል። ጸረ-ትራምፕ የሆኑ ቡድኖች የተቃውሞ ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ ከወዲሁ አስታውቀዋል።
news-52657883
https://www.bbc.com/amharic/news-52657883
ሱዳን ለምን የኢትዮጵያን የስምምነት ሃሳብ ተቃወመች?
ሱዳን የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያቀረበችው አዲስ የስምምነት ሃሳብ የሚቀሩት ነገሮች አሉ በማለት እንዳልተቀበለችው ተሰምቷል።
በዚህ የስምምነት ሃሳብ ላይ ግብጽም አለመስማማቷ የተገለፀ ሲሆን፤ ከአሜሪካ ጋር በአቋም በመመሳሰል በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ስምምነት ሳይደረስ ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት እንደሌለባት ቀደም ሲል የተደረጉ ስምምነቶችን በመጥቀስ አቋሟን ገልጻለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ በዕቅድ የያዘችውን ግድቡን በውሃ የመሙላት ተግባር ከሁለት ወራት በኋላ እንደምትጀምር አስታውቃለች። ለመሆኑ ሦስቱ አገራት 2008 ዓ. ም ላይ የፈረሙት የመርሆች ስምምነት ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት በመጀመር በኩል ሊፈጥር የሚችለው እንቅፋት እንዳለ የምሥራቅ ናይል አካባቢ ቀጠናዊ የቴክኒክ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን ለአቶ ፈቅ አህመድን ጠይቀናል። እርሳቸውም ይህ ስምምነት "ኢትዮጵያ ያለሌሎች አገራት ስምምነት ግድቡን ውሃ መሙላት እንዳትጀምር የሚል ግዴታ አይጥልባትም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ግድቡን ውሃ እንዳትሞላ የሚከለክላት የገባችውም ግዴታ እንደሌለና የኢትዮጵያ መንግሥት የታላቁን የሕዳሴ ግድብ በእቅዱ መሠረት ውሃ መሙላት እንደሚችል ይጠቅሳሉ። በአባይ ጉዳይ ዙሪያ በርካታ ምርምሮችን ያካሄዱት ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖም በ2008 ተፈርሞ የነበረው የጋራ አቋም መግለጫ ኢትዮጵያ ግድቡን በውሃ ከመሙላት እንደማያግዳት ያስረዳሉ። የኢትዮጵያን ሃሳብ አልቀበልም ያለችው ሱዳን ከሳምንታት በፊት የአረብ ሊግ አገራት የግብጽን ፍላጎት በሚያስጠብቅ መልኩ የአቋም መግለጫ ባወጡበት ወቅት መግለጫውን ተቃውማ እራሷን አግልላ ነበር። ሱዳን በህዳሴ ግድብ የምታገኘው ጥቅም በርካታ እንደሆነ በዝርዝር የሚጠቅሱት ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ፤ "አንደኛ ጎርፍ ለመቆጣጠር፣ ሁለተኛ ደለልን በመቀነስ፣ ሦስተኛ የተረጋጋ ውሃ ዓመቱን ሙሉ አግኝታ ሠፊ መሬቷን በመስኖ ማረስ በመቻል፣ አራተኛ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል የምታገኝበትን ዕድል ይፈጥርላታል" ይላሉ። ስለዚህም ነው ሱዳን በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለውን ግዙፍ ግድብ በተለያዩ አጋጣሚዎች ስትደግፍ የቆየችው። ቢሆንም ግን ዋሽንግተን ላይ በተደረጉት ድርድሮች ወቅት አንዳንድ ጊዜ ወደ ግብጽ የሚያዘነብሉ አቋሞችን ታንጸባርቅ እንደነበረ ሲነገር ቆይቷል። አሁን ግን በይፋ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ሃሳብ ላይ ተቃውሞዋን አቅርባለች ለምን? እንደ ዶክተር ያዕቆብም ሆነ አቶ ፈቅ አህመድ ሱዳን ከተጽዕኖ ነጻ አገር ልትሆን አትችልም። በተለይ የሱዳን መንግሥት አዲስ መሆኑና ገና መሰረቱ ያልፀና መሆኑ ለተጽዕኖ በቀላሉ እጅ እንዲሰጥ ያደርገዋል ባይ ናቸው። "ብዙ ተጽዕኖ ስላለባት ሊሆን ይችላል። የሱዳን መንግሥት አዲስ ነው ከተለያዩ ኃይሎች ጋር በመሆን በጥምረት የተመሰረተ አስተዳደር ነው። የሚገላምጣቸው ብዙ ነው። አሜሪካም የጣለችውን ማዕቀብ ላንሳ አላንሳ እያለች ነው" ይላሉ ዶ/ር ያዕቆብ። አክለውም "ታዲያ ከዚህ ሁሉ የተነሳ ሱዳን ላይ የሚደርሰውን ተጽዕኖ አናውቅም" በማለት በዚህ ምክንያት የተነሳ አቋሟን ቀይራ ሊሆን ይችላል ይላሉ። አቶ ፈቅ አህመድም ይህንኑ ሃሳብ ካረጋገጡ በኋላ "አዲሱ የሱዳን መንግሥት መሠረቱ ወደ ውስጥ በደንብ ዘልቆ ስላልገባ ማንንም ማስከፋት አይፈልግም። ሌላው ደግሞ በዚህ ዘርፍ ላይ የነበሩና ቀድሞ ከኢትዮጵያ ጋር ሲሰሩ የነበሩ ከፍተኛ ባለሙያዎች አሁን በቦታቸው ላይ የሉም" ይላሉ። "ያሉት ሹማምንት አዳዲስ መሆናቸው የሱዳን ባለስልጣናት በቂ መረጃ እንዳይኖራቸው ሳያደርጋቸው አልቀረም" በማለት ሱዳን ከውጪ ከሚደረግባት ጫና በተጨማሪ የተካሄደው የመንግሥት ለውጥ የፈጠረው ክፍተት እንዳለ አመልክተዋል። አሜሪካ እና ግብጽ ኢትዮጵያ ስምምነት ሳይደረስ ውሃ መሙላት የለባትም ብለዋል። ሱዳን በበኩሏ ኢትዮጵያ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ያቀረበችውን አዲስ የስምምነት ሃሳብ አልቀልም ብላለች። ኢትዮጵያ ደግሞ በያዘቸው ዕቅድ መሰረት ግድቡን ውሃ መሙላት እጀምራለሁ ብላለች። ታዲያ መጪው ጊዜ ምን ይዟል? አቶ ፈቅ አህመድ አሜሪካ በዚህ ድርድር ውስጥ ስትሳተፍ መጀመሪያውኑ የገንዘብ ሚኒስትሯን መመደቧ ስለጉዳዩ ስለማይመለከታቸው፣ በቂ ልምድና እውቀት ስለሌላቸው ተገቢ አልነበሩም ይላሉ። "ምናልባት የፖለቲካ ጫና ሊኖር ይችላል" የሚሉት አቶ ፈቅ "ከዚያ ውጪ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ታበላሻለች ብዬ አላስብም" ብለዋል። ዶ/ር ያዕቆብ ደግሞ "ግድቡ ውሃ መያዝ ሲጀምር ማንም መሸበር ያለበት አይመስለኝም" ይላሉ። "ጦርነትና ግጭት ሊፈጠራል ይችላል የሚሉ አካላትንም የተሳሳተ ግምት ነው" በማለት "ይህ ከሆነም በውሃ ምክንያት ወደ ግጭት በመግባት የመጀመሪያዎቹ እንሆናለን" ይላሉ። አገራቱን በማሸማገል ባለፉት ወራት ወደ ጉዳዩ የገባችው አሜሪካ ሲካሄደው የነበረው ድርድር መልሶ እንዲጀመርና ስምምነት ላይ እንዲደረስ እየወተወተች ትገኛለች።
news-50371535
https://www.bbc.com/amharic/news-50371535
ኢራን 53 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ማግኘቷን አሳወቀች
የኢራንን የነዳጅ መጠን በሶስት እጥፍ ያሳድጋል የተባለለት 53 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ማግኘቷን ፕሬዝደንት ሃሰን ሩሃኒ አሳወቁ።
በደቡብ ምዕራቧ ኩዝስታን አውራጃ የተገኘው ድፍድ ነዳጅ 2400 ስኩዌር ኪሌሜትር የሚሸፍን ነው ብለዋል ፕሬዝደንቱ። ኢራን ከአሜሪካ በተጣለባት ማዕቀብ ሳቢያ ነዳጅ ወደ ውጭ ልካ ለመሸጥ እየተቸገረች ትገኛለች። ማዕቀቡ የተጣለባት አምና ሲሆን አሜሪካ ከሌሎች የዓለም ኃያላን ጋር የነበራትን የኒውክሌር ስምምነት አልፈልግም ብላ ከወጣች በኋላ ነው። «ድፍድፍ ነዳጁ 80 ሜትር ወደታች ጥልቀት ያለው ነው። የኢራን ነዳጅ ላይ ማዕቀብ ብትጥሉም የሃገሪቱ ኢንጂነሮች 53 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ አጊንተዋል። ይህን ለኃይት ሃውስ መናገር እፈልጋለሁ» ብለዋል ሲል የዘገበው ፋርስ የዜና ወኪል ነው። አዲስ የተገኘው ድፍድ ነዳጅ በሃገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ የነዳጅ ክምችት ያለበት ስፍራ ይሆናል ተብሎለታል። አህቫስ የተሰኘው ስፍራ በ65 ቢሊዮን በርሜል ትልቁ ነው ይላል አሶሼትድ ፕሬስ። ኢራን በዓለማ ካሉ አበይት ነዳጅ አምራች ሃገራት አንዷ ናት። ከነዳጅ ሽያጭ የምታገኘው ዓመታዊ ገቢም በቢሊዮን ዶላሮች ይገመታል። ፕሬዝደንት ሩሃኒ አሁን ላይ ሃገራቸው ያላት የድፍድፍ ነዳጅ ክምችት 150 ቢሊዮን በርሜል እንደሆነ ተናግረዋል። ይህ ደግሞ በዓለም አራተኛው ነው። ከኳታር ጋር የምታጋራው ውቅያኖስ ሥር ያለ የተፈጥሮ ጋዝ ባለቤትም ነች። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን እና ሌሎች ስድስት ሃገራት የገቡትን የኒውክሌር ስምምነት አፍርሰው ኢራን ላይ ማዕቀብ ከጣሉ በኋላ የቴህራን ምጣኔ ሃብት እያሽቆለቆለ ይገኛል።
news-57127675
https://www.bbc.com/amharic/news-57127675
እውቋ አሜሪካዊት አሪያና ግራንዴና ዶልተን ጎሜዝ 'አነስ ባለ' ሰርግ ተሞሸሩ
አሜሪካዊቷ አቀንቃኝና ተዋናይት አሪያና ግራንዴና ከእጮኛዋ ዶልተን ጎሜዝ ጋር "በጣም የቅርብ ሰዎች ብቻ በተገኙበት አነስተኛ" የሰርግ ስነ ስርዓት ተሞሽረዋል።
ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ የ27 ዓመቷ ድምጻዊቷ ስትሞሸር ታዳሚዎቹ 20 ሰዎች ብቻ እንደነበሩ ነው የተዘገበው። በታህሳስ ወር ግራንዴ በሁለት ዓመት ከሚያንሳትና በሎሳንጀለስ የሪል ኢስቴት ወኪል ከሆነው የ25 ዓመቱ ዶልተን ጎሜዝ 'እጮኛዬ ሆኗል' ስትል ይፋ ያደረገችው። ታዲያ ጥቂት ታዳሚያንን የያዘው ሰርግ በካሊፎርኒያ በሚገኘው በድምጻዊቷ መኖሪያ ቤት ነበር የተካሄደው። የድምጻዊቷ ተወካይ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት አስተያየት "ጥንዶቹ ተጋብተዋል። ሰርጉ አነስተኛና ከ20 የማይበልጥ የቅርብ ሰዎችን ያሳተፈ ነበር" ብለዋል። "ክፍሉ በፍቅርና በደስታ የተሞላ ነበር"ም ብለዋል። ጥንዶቹ የተሞሽሩበትን የደቡባዊ የካሊፎርኒያ አከባቢ በቅርቡ መነጋገሪያ የነበረው የእንግሊዙ መስፍን የሚኖርበትም ነው። የድምጻዊቷ ባለቤት ጎሜዝ በደቡባዊ ካሊፍርኒያ ያደገ ሲሆን ለ5 ዓመታት በቅንጡ ሪል ኢስቴት ሽያጭ ላይ የሚሰራ መሆኑ ተገልጾል። ጥንዶቹ ከጋብቻ በፊት ከአንድ ዓመት ለሚበልጥ ጌዜ በፍቅር ቆይተው ነው ትዳር የመሰረቱት።
45125152
https://www.bbc.com/amharic/45125152
ዛምቢያ የተቃዋሚ ፓርቲው ፓለቲከኛ የጥገኝነት ጥያቄ አስተባበለች
የዚምባብዌ ተቃዋሚ ኤምዲሲ ጥምረት ከፍተኛ አመራር ቴንዳይ ቢቲ ዛምቢያ ጥገኝነት ሊጠይቁ ነበር መባሉን አስተባበሉ።
ቴንዴይ ቢቲ የምርጫውን ውጤት ቀድሞ በመተንበይ እና ግጭትን በማነሳሳት ይወነጀላሉ የዚምባብዌ ፖሊስ ቴንዳይ ቢቲን ባለፈው ሳምንት የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ አለመረጋጋትና ግጭት እንዲሰፍን ቀስቅሰዋል ሲል ይወነጅላቸዋል። የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆይ ማላንጂ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቴንዳይ ቢቲ ጥገኝነት ጠይቀዋል የሚለው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ታጭተዋል? • ሙጋቤ የማይሳተፉበት የመጀመሪያው የዚምባብዌ ምርጫ • ዚምባብዌ እንዴት ሰነበተች? ወደ ዚምባብዌ እስኪመለሱ ድረስ "ደህንነታቸው ተጠብቆ በጥበቃ ስር" ይቆያሉ ብለዋል ሚኒስትሩ። ቀደም ብሎ የተቃዋሚው መሪ ቴንዳይ ቢቲ ጠበቃ ደንበኛቸው በዛምቢያ ድንበር ላይ በዚምባብዌ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረው ነበር። የዛምቢያ ፖሊስ ሪፖርት ነው የተባለ ማስረጃ በማህበራዊ ድረገፆች ላይ እየተዘዋወረ ሲሆን የዚምባብዌ ባለስልጣናት ቴንዳይ ቢቲ የዛምቢያ ድንበርን ካቋረጡ በኋላ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው ሞክረው ነበር ይላል። የተቃዋሚ ፖለቲከኛው የድረሱልኝ ጩኸት ካሰሙ በኋላ 300 የሚሆኑ ዚምባብዌያውያን የመንግስት የደህንነት ሰራተኞቹ በቁጥጥር ስር እንዳያውሏቸው ተከላክላለዋል ይላል ሪፖርቱ። ከዛም በኋላ የዛምቢያ ባለስልጣናት ጣልቃ ገብተውና "በዛምቢያ ግዛት ውስጥ ይህንን ቢያደርጉ" የዚምባብዌ ሃላፊዎችን በቁጥጥር ስር እንደሚያውሏቸው ገልፀው እንዳስለቀቋቸው ተገልጿል። • በርካቶችን ግራ ያጋባው ፎቶ የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለቢቢሲ እንደገለፁት የቴንዳይ ቢቲ የጥገኝነት ጠየቁ የሚለው "ተቀባይነት የሌለው " ነው። ከሮበርት ሙጋቤ የ37 ዓመት የስልጣን ዘመን በኋላ ባለፈው ወር የተደረገው ምርጫ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት ነበር። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት በዋና ከተማዋ ሀራሬ ተቃዋሚዎች ሊያደርጉት የነበረውን ሰልፍ ፖሊስ ለመከልከል ጣልቃ ከገባ በኋላ የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች በፍርሃት የተነሳ መደበቃቸውን ዘጋቢዎች ገልፀዋል። በምርጫው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ቢያውጅም ኤምዲሲ የተሰኘው ጥምረት ግን ምርጫው ተጭበርብሯል ሲል ክሱን ያሰማል።
news-57118311
https://www.bbc.com/amharic/news-57118311
የኬንያ ፖለቲከኞች ሕገ-መንግሥቱን ለማሻሻል ያደረጉት ጥረት በፍርድ ቤት ታገደ
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በገዢው መንግሥት ድጋፍ ያገኘውን የሕገ-መንግሥት ማሻሻል ሐሳብ ውድቅ አድርጎታል።
ፍርድ ቤቱ የወሰነው ውሳኔ በፈረንጆቹ 2017 ኡሁሩ ኬንያታ ምርጫውን አላሸነፉም ብሎ ፍርድ ቤት ከሰጠው ፍርድ በኋላ ትልቁ ነው ተብሏል። ዳኛው በተለምዶ ቢቢአይ እየተባለ የሚጠራው የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ዕቅድ ሕገ-መንግሥታዊ አይደለም ሲሉ ብይናቸው ሰጥተዋል። ዳኛው አክለው ማሻሻያው ሕገ ወጥና ቅርፅ አልባ ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ዋነኛ ተቀናቃኛቸው የነበሩት የአሁኑ ጓደቸው ራይላ ኦዲንጋ ሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያው እውን እንዲሆን ደፋ ቀና ሲሉ ነበር የከረሙት። ሁለቱ መሪዎች ማሻሻያው ሕግ አውጪው የመንግሥት ክንፍ እንዲስፋፋና የሃገሪቱ ፖለቲካ የበለጠ አሳታፊ እንዲሆን ያስችላል ሲሉ ይሞግታሉ። ነገር ግን ተቺዎች ማሻሻያው የፖለቲካ ፓርቲዎች እርስ በርስ ለመጠቃቀም ያመቻመቹት ነው ሲሉ ይከራከራሉ። ነቃፊዎቹ አክለው ማሻሻያው የሕዝብ እንደራሴዎች ቁጥርን ከፍ ያደርገዋል፤ ይህ ደግሞ ዕዳ ውስጥ ተዘፍቃ ለምትገኘው ኬንያ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው ይላሉ። ቢቢአይ በተሰኘ ቅፅል ስሙ የሚታወቀው የማሻሻያ ሐሳብ ወደ ብሔራዊው ሸንጎና ሴኔት ተልኮ በአብላጫ ድምፅ አልፎ ነበር። ነገር ግን ወደ ፕሬዝደንቱ ጠረጴዛ ተልኮ የመጨረሻው ፊርማ ከማረፉ በፊት ነው ሐሙስ ዕለት በፍርድ ቤት የታገደው። ማሻሻያው ፀደቀ ማለት ኬንያዊያን በሚቀጥለው ዓመት ከሚደረገው ምርጫ በፊት ለሕዝበ ውሳኔ ድምፃቸውን ይሰጣሉ ማለት ነው። ዳኞች ምን አሉ? ለአራት ሰዓታት በቴሌቪዥን መስኮት ቀጥታ በተላለፈው ችሎት ዳኞቹ ፕሬዝደንት ኬንያታ የሃገሪቱን ሕገ-መንግሥት ጥሰዋል ብለዋል። አክለው ኡሁሩ የመሠረቱት የቢቢአይ ኮሚቴ ሕገ-ወጥ ነው፤ ፕሬዝደንቱ የተሰጣቸውን የመሪነት ሚና በአግባቡ አልተወጡም ብለዋል። ዳኞቹ፤ ፕሬዝደንቱን በግላቸው ሊከሷቸው እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። ፖለቲከኞቹ ማሻሻያውን ለማፅደቅ በሚል የሰበሰቡት 5 ሚሊዮን ድምፅ ይህንን ሐሳብ የዜጎች አያደርገውምም ብለዋል ዳኞቹ። የፍርደ ቤቱ ውሳኔ ፕሬዝደንቱን ከሥልጣናቸው ሊያስነሳቸው የሚችል ቢሆንም ነገር ግን የማሻሻያውን ሐሳብ በአብለጫ ድምፅ ያሳለፈው ፓርላማ ይሄን ያደርጋል ተብሎ አይጠበቅም። ቢቢአይ፤ ኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲኖራት፤ ቢያንስ 70 አውራጃዎችና 300 ተጨማሪ የፓርላማ መቀመጫዎች እንዲጨመሩ ሐሳብ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱ የማሻሻያ ሐሳቡን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ መንግሥት ይግባኝ ይጠይቃል ተብሎ ቢጠበቅም ሕግ አዋቂዎች ግን ውጤቱ ከዚህ የተሻለ ይሆናል ብለው አያምኑም።
news-51798143
https://www.bbc.com/amharic/news-51798143
ኮሮኖቫይረስ፡ እውን ነጭ ሽንኩርት የኮሮናቫይረስ ጠር ነው?
የኮሮናቫይረስ ከአገር አገር እየተስፋፋ ነው። በየቀኑ አዳዲስ አገራት 'ኧረ እኛም አገር ገባ እኮ' እያሉ ነው። እስካሁን ኮሮናን ውልቅ አድርጎ የሚያስወጣ ሐኪሞች ያጨበጨቡለት መድኃኒት አልተገኘም።
'እነ ነጭ ሽንኩርትና ባሕር ዛፍ ምን ሠርተው ይበላሉና' የሚል ምክር ሰምተው ይሆናል። ዓለም በአንድ ስጋት ስትናጥ ተከትሎ የሚመጣ አንድ ፅንሰ-ሐሳብ አለ፤ በእንግሊዝ አፍ 'ኮንስፓይረሲ ቲየሪ' ይሰኛል፤ የሴራ ፅንሰ-ሐሳብ ብለን እንተርጉመው። ወደ ኢንተርኔት ዓለም ብቅ ቢሉ ወሬው ሁሉ ስለኮሮናቫይረስ ነው፤ የወቅቱ የዓለም ስጋት ነውና። ኮሮናን ይከላከላሉ ተብሎ የሚወራላቸው ደግሞ ብዙዎች ናቸው። ነጭ ሽንኩርት ደግሞ የአጥቂ መስመር ላይ ተሰልፋለች። ነጭ ካባ ከደረበ ዶክተር. . . ነጭ ሽንኩርት ዝናዋ በዓለም የናኘ ነው። የፌስቡክ ገፅ ቢኖራት ኖሮ 6 ቢሊዮን ሕዝብ የሚከተላት ነጭ የደረበች ሽንኩርት. . . ። ነጭ ሽንኩርት ፌስቡክ ለመቆጣጠር ገፅ አላሻትም። የኮሮናቫይረስን መፈወሻ ተበለው ፌስቡክ ላይ ዝናቸው ከናኘ ነገሮች መካከል ነጭ ሽንኩርት አንደኛ ነች። ግን ኮሮናን መከላከልም ሆነ ማዳን ትችል ይሆን? ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት የዓለም ጤና ድርጅት ግን እንዲህ ይላል - ነጭ ሽንኩርት ብሉ በውስጡ መልካም ነገር አዝሏልና፤ ነገር ግን ከአዲሱ ቫይረስ ሊከላከል እንደሚችል በሳይንስ አልተረጋገጠም። እርግጥ የዶ/ር ቴድሮስ መሥሪያ ቤት እንዳለው ነጭ ሽንኩርት በልኩ መብላት ይመከራል። ከኮሮናቫይረስ ጋር ግን የሚያገናኘው ነገር የለም። ደቡብ ቻይና ውስጥ ከኮሮናቫይረስ ይታደገኛል ብለው 1.5 ኪሎ ግራም ነጭ ሽንኩርት 'ዱቄት' ያደረጉ አንዲት ሴት ጉሮሯቸው ተቃጥሎ በሕክምና ነው የዳኑት። የዓለም ጤና ድርጅት፤ ፍራፍሬና ጥራጥሬ እንዲሁም አትክልት በልኩ ተመገቡ፤ ውሃም ጠጡ ይላል። ነገር ግን ይላል ድርጅቱ. . . ነገር ግን ኮሮናን ይታደጋል ተበሎ ፈቃድ የወጣለት ምንም ዓይነት ምግብ እስካሁን አልተገኘም። ተዓምረኛ ንጥረ-ነገሮች ዩቲዩበኛው ጆርዳን ሳዘር በተለያዩ ማኅበራዊ ድር-አምባዎች ላይ ብዙ ሺህ ተከታዮች አሉት። ይህ ግለሰብ አንድ 'ኤምኤም የተሰኘ ተዓምራዊ ንጥረ-ነገር የኮሮናቫይረስን ድራሽ ማጥፋት ይችላል' እያለ ይሰብካል። ንጥረ ነገሩ ክሎራይን ዳይኦክሳይድ የተሰኘ አንጭ ኬሚካል አዝሏል። ጆርዳንና መሰሎቹ ክሎራይን ዳይኦክሳይድ ያለበት ኤምኤም የካንሰር ሴልን ያጠፋል እያሉ ይሰብኩ ነበር። አሁን ደግሞ ለኮሮናቫይረስ ፍቱን መድኃኒት ነው ብለው ብቅ ብለዋል። ባለፈው ዓመት የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር ይህንን ኬሚካል መጠጣት ለጤና እጅግ አስጊ ነው ሲል ማስጠንቀቂያ አውጥቶ ነበር። መሥሪያ ቤቱ ይህንን ኬሚካል የምትጠጡ ወዮላችሁ፤ ኬሚካሉ በሽታ እንደሚከላከል የሚጠቁም ጥናት የለም ሲል ነው ያስጠነቀቀው። አልፎም ኬሚካሉ ሰውነት ውስጥ ያለ ፈሳሽን አሟጦ በመጨረስ ለከፍተኛ የውሃ ጥም ሊያጋልጥ ይችላል። 'ሳኒታይዘር' ጨርሰናል የሚሉ ማስታወቂያዎች ማየት እየተለመደ መጥቷል ጓዳ ሠራሽ 'ሳኒታይዘር' «ባለሱቅ፤ ሳኒታይዘር አለ?» «ውይ! አንድ ቀርታ ነበር። እሷን ደግሞ ለእኔ . . .» ከመዳፎቻችን ላይ ባክቴሪያ ነሽ ቫይረስ እንዲሁም ቆሻሻ ያስወግዳሉ የሚባልላቸው 'ሳኒታይዘሮች' [ተህዋሲያን ማጽጃ ፈሳሽ] ከገበያ እየጠፉ ነው። ጣልያን ውስጥ ነው አሉ። የሳኒታይዘር እጦት የወሬ ሟሟሻ ሆነ። ኮሮናቫይረስ ሰቅዞ የያዛት የጣልያን ነዋሪዎች ታድያ ወደ ኩሽና ገቡ። የተገኘውን ነገር መቀላቀል ጀመሩ። በአገሬው ዘንድ ታዋቂ የሆነ አንድ ኬሚካል ግን ቆዳ እንዲያፀዳ ሳይሆን እምነ-በረድ እንዲያፀዳ የተሰናዳ ነው። በተለይ ደግሞ ውስጣቸው በመቶኛ ከፍ ያለ የአልኮል መጠንን ያዘሉ ፈሳሾች ለመቀየጫነት ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ደግሞ የምንጠቀማቸው ሳኒታይዘሮች ቢያንስ ከ60-70 በመቶ የአልኮልነት መጠን ቢኖራቸው ሲል ይመክራል። ነገር ግን ሳይንቲስቶች ኩሽና ውስጥ ቫይረስና ባክቴሪያ የሚገድል 'ሳኒታይዘር' ማምረት ከባድ ነው ይላሉ። ቮድካ እንኳ 40 በመቶ ብቻ የአልኮል ይዘት ነው ያለው። እና ሌሎች. . . ከላይ ከተጠሱት አልፎ የቀለጠ ሲልቨር መጠጣት፣ ውሃ በ15 ደቂቃ ልዩነት መጠጣ [የሞቀ ውሃማ ፍቱን ያሉም አልጠፉም]፣ ሙቀት ማግኘት እና አይስ ክሬም አለመላስ የኮሮናቫይረስን ለመፈወስ ፍቱን ናቸው ተብለው በማኅበራዊ ድር-አምባዎች ማስታወቂያ የተሠራላቸው ናቸው። ሳይንሱ ግን እስካሁን የተረጋገጠ ፈውስ አልተገኘም ይላል። ነገር ግን በሽታውን ለመከላከል ዋናውና ቀላሉ መፍትሔ እጅን በሳሙን በደንብ ፈትጎ መታጠብ፣ የእርስ በርስ ንክኪን መቀነስ፣ ፊትን በእጅ አለመነካካት፣ በሽታው ካለበት ሰው ጋር ንክኪ አለማድረግ. . . ነው። አደራዎትን 1 ኪሎ ነጭ ሽንኩርት ስልቅጥ አድርገው በጠላ ካወራረዱ በኋላ እንደ ዉሃኗ ነዋሪ ርዕሰ-አንቀፅ እንዳይሆኑ። ሐኪም ያላዘዘውን መጠቀም ጠንቅ ነውና!
news-57251123
https://www.bbc.com/amharic/news-57251123
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገለጹ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተባባሰ ነው ያሉት ግጭት እንዲሁም ክፍፍል እንዳሳሰባቸው ገለጹ።
ረቡዕ ምሽት ከጽህፈት ቤታቸው በወጣው መግለጫ ላይ ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት በአገሪቱ በርካታ ክፍሎች ውስጥ የሚፈጸሙ እከፉ የመጡ ጥቃቶች እንዲሁም እየጠነከረ ያለ ክልላዊና የብሔር መከፋፈል በእጅጉ እንዳሳሰባቸው አመልክተዋል። ጨምረውም በትግራይ ክልል ውስጥ የተፈጸሙ "መጠነ ሰፊ ጾታዊ ጥቃቶችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች" ተቀባይነት የሌላቸውና በአስቸኳይ ሊቆሙ የሚገባቸው ናቸው ብለዋል። አሜሪካ በትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ግጭት መፍትሔ እንዲያገኝና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ በተደጋጋሚ ያደረኩት ጥረት ውጤት ስላላስገኘ በሚል ከቀናት በፊት በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ በኩል በኢትዮጵያና በኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች ላይ የቪዛ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል። የአሜሪካ መንግሥት ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ሲለው እንደነበረው ሁሉ አሁንም ፕሬዝዳንቱ በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ ኃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ እንዲሁም የኤርትራና የአማራ ክልል ኃይሎች ከክልሉ እንዲወጡ ጠይቀዋል። በተከሰተው ግጭት ሳቢያ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ አጋጥሞ የነበረው አይነት የረሃብ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ያለውን ስጋት የጠቀሰው የፕሬዝዳንት ባይደን መግለጫ፤ ሁሉም ወገኖች በተለይም የኢትዮጵያና የኤርትራ ኃይሎች እርዳታ ያለገደብ እንዲቀርብ በአስቸኳይ እንዲፈቅዱ ጠይቀዋል። የአገሪቱን የግዛት አንድነት ለማስጠበቅና ሕዝቡን ለመጠበቅ የኢትዮጵያ መሪዎችና ተቋማት ለእርቅ፣ ለሰብአዊ መብት መከበርና ብዝሃነትን ለመረጋገጥ ጥረት እንዲያደርጉ ፕሬዝዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥትና የተለያየ ፖለቲካዊ አመለካከት ያለቸው ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሁሉን አቀፍ ውይይት ፈቃደኛ እንዲሁኑ አሳስበዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን አክለውም በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባትና በአካባቢው ያሉትን ተያያዥ ግጭቶች በሰለማዊ መንገድ መፍትሔ እንዲያገኙ ለማደረግ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካው ልዩ ጄፍሪ ፌልትማን አዲስ ጥረት እንደሚያደርጉ አመልክተዋል። በዚህም ልዩ መልዕክተኛው ወደ አካባቢው በሚቀጥለው እንደሚያቀኑና ስላለው ሁኔታ መረጃ እንደሚያቀርቡላቸው ፕሬዝዳንት ባይደን ገልጸዋል። ይህ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ የወጣው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለውን እገዳ ካሳወቀ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በውሳኔው ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን እርምጃውንም በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ተጽእኖ ለመፍጠር ያለመ ነው ሲል ገልጾታል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ መንግሥት በዚህ እርምጃው "በኢትዮጵያ ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫናን ማድረግ መቀጠሉን" በመጥቀስ አሜሪካ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን የምትቀጥል ከሆነ መንግሥት ከአገሪቱ ጋር ያለውን ግንኙነት መለስ ብሎ ለመመርመር እንደሚገደድ አማስጠንቀቁ አይዘነጋም። የአሜሪካ መንግሥት በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ መፍትሔ እንዲገኝ በከፍተኛ ባለሥልጣናቱ በኩል ጥረት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፤ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ልዩ መልዕከተኞች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ይታወሳል። አሜሪካ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለውን ቀውስና የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ጉዳይን በቅርበት እንዲከታተሉላት አንጋፋውን ዲፕሎማት ጄፍሪ ፌልትማንን በልዩ መልዕክተኝነት ሰይማ ከሳምንታት በፊት በአካባቢው ጉብኝት አድርገዋል። ባለፈው ሳምንትም የአገሪቱ ሴኔት በትግራይ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ወገኖች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወሰድ የሚጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ አሳልፎ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥትም በውስጥ ጉዳዩ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ተጽእኖ ለመሳደር የሚሞክሩ መንግሥታትን ጫና እንደማይቀበለው በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ የህወሓት ኃይሎች የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በተጀመረው ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ኃይሎች በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመፈጸም ሲከሰሱ ቆይተዋል።
news-46041710
https://www.bbc.com/amharic/news-46041710
የፓኪስታን ፍርድ ቤት ሞት የተፈረደባትን ክርስቲያን ነፃ ለቀቀ
በእስልምና ሃይማኖት ላይ ስድብ ሰንዝረሻል ተብላ ሞት ተፈርዶባት የነበረችው የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ በፓኪስታን የሚገኝ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣቱ እንዲነሳላት ወሰነ።
አሲያ ቢቢ የተባለችው ሴት በአውሮፓውያኑ 2010 ነበር ከጎረቤቶቿ ጋር ስትጣል ነብዩ ሞሃመድን ተሳድበሻል ተብላ ክስ የተመሰረተባት። ምንም እንኳን ጥፋተኛ እንዳልሆነች በተደጋጋሚ ብትገልጸም፤ ያለፉትን ስምንት ዓመታት በእስር ቤት ነበር ያሳለፈችው። ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው በሞት አትቀጣም፤ እንደውም በነጻ ትሰናበት የሚለው ውሳኔ ደግሞ በፓኪስታን የሚገኙ ብዙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን አስቆጥቷል። • ስደተኞችን የጠለፈችው የካሜራ ባለሙያ ነፃ ወጣች • የኢትዮጵያ እና የጂ-20 ወዳጅነት ውሳኔውን የተቃወሙ ፓኪስታናውያን ካራቺ፣ ላሆር፣ ፔሽዋርና ሙልታን በተባሉ ከተማዎች ሰልፍ የወጡ ሲሆን ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው እንደነበረም ተገልጿል። በዋና ከተማዋ ኢዝላማባድ የሚገኘው ውሳኔውን ያስተላለፈው ፍርድ ቤት በር ላይ ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ተሰብስበው ወደ ውስጥ እንዳይገቡ በፖለስ እየተጠበቁ ነው። የፍርድ ሂደቱን ሲከታተሉት የነበሩት ዋና ዳኛ ውሳኔያቸውን ለተሰበሰቡት ሰዎች ሲያነቡ ''አሲያ ቢባ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ የሰራችው ወንጀል ከሌለ ሼኩፑራ ውስጥ ከሚገኘው ማረሚያ ቤት ያለምንም ችግር መውጣት ትችላልች'' ብለዋል። ምንም እንኳን ውሳኔው ሲሰጥ በፍርድ ቤቱ መገኘት ባትችልም፤ አሲያ ቢቢ ከማረሚያ ቤት ሆና የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እስካሁን ድረስ ለማመን እንደከበዳት ተናግራለች። ''የሰማሁትን ነገር ማመን አልችልም፤ አሁኑ ከእስር ቤት መውጣት እችላለሁ?'' ብላለች። የዛሬ ስምንት ዓመት አሲያ ከጎረቤቶቿ ጋር በመሆን ፍራፍሬ ለመሰብሰብ ወጣ ይላሉ። ታዲያ ከስራ በኋላ እሷ የነካችውን የውሃ መቅጃ መጠቀም እንደማይፈልጉ ጎረቤቶቿቸ ይነግሯታል። ለምን ብላ ብትጠይቅ በሃይማኖትሽ ምክንያት ውሃ መቅጃው ቆሽሿል ይሏታል። በመቀጠልም ሃይማኖቷን መቀየር እንደለባት ሲነግሯት አጸያፊ የሆኑ ስድቦችን መሰንዘሯን በመጥቀስ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባታል። ወደ ቤቷ ስትመለስም ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባትና በጊዜው ወንጀል መፈጸሟን በማመኗ ለፖሊስ ተላልፋ ተሰጥታለች። •በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ የአሲያ ጠበቃ በውሳኔው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ለደንበኛቸው ደህንነት ግን አሁንም እንደሚፈሩ ገልጸዋል። ምክንያቱም ውሳኔውን የሰሙ ሰዎች በፍርድ ቤቱ አቅራቢያ በመሰባሰብ መሞት እንዳለባት ሲናገሩ ነበር። አሲያ ወደ ማረሚያ ቤት እንደገባች የፍርድ ሂደቱ ትክክል አይደለም ብለው የተከራከሩት የፑንጃብ ግዛት አስተዳዳሪ ሳልማን ታሲር በሰው ተገድለዋል። እሳቸውን የገደለው ሰውም የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ተገድሏል። ገዳዩ ሙምታዝ ቃድሪ ከተገደለ በኋላ የአካባቢው ሰዎች ጀግናችን ነው በማለት በስሙ የጸሎት ቦታ ሰርተውለታል። ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ልጇና ቤተሰቦቿ ለደህንነቷ ስለሚያሰጋት ከፓኪስታን ለቅቃ መሄድ እንዳለባት እየተናገሩ ነው። ከተለያዩ ሃገራትም የጥገኝነት ፍቃትድ እንደተሰጣት ተገልጿል።
50415008
https://www.bbc.com/amharic/50415008
ኒውዚላንድ የፈቃድ ሞት ላይ ሕዝበ ውሳኔ ልታደርግ ነው
የኒውዚላንድ ፓርላማ ሰዎች በፍቃዳቸው ሕይወታቸው እንዲያልፍ የሚፈቅድ ሕግ ላይ ስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን፤ በቀጣዩ ዓመት ሕጉ ላይ ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል።
ጠቅላይ ሚንስትር ጃሲንዳ አርደን በእንግሊዘኛ አጠራሩ Euthanasia የሚባለው ሂደት፤ ሰዎች ፈቃደኛ እስከሆኑ ድረስ ያለ ስቃይ ሕይወታቸው እንዲያልፍ ያግዛል። ሕጉ፤ በጠና የታመሙና በሀኪማቸው ከስድስት ወር ያላለፈ ዕድሜ እንደሚኖራቸው የተነገራቸው ግለሰቦች፤ በሀኪሞች ታግዘው እንዲሞቱ ይፈቅዳል። ረዥም ክርክር የተደረገበት ሕጉ፤ 69 ለ 51 የድጋፍ ድምጽ አግኝቷል። የኒውዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን፤ የፈቃድ ሞትን በተመለከተ ያለው ሕግ እንዲሻሻል ከሚፈልጉ አንዷ ናቸው። • ኒውዝላንዳውያን "ጦር መሣሪያ አንፈልግም" እያሉ ነው • መምህርነት የሚያስከብር ሙያ የሆነው የት ነው? • ሰዎች 'ፖፒ' የተሰኘችውን ቀይ አበባ ለምን ደረታቸው ላይ ያደርጓታል? በቅርብ የተሰራ ጥናት ከኒውዝላንዳውያን 72 በመቶ የሚሆኑት የፈቃድ ሞትን እንደሚደግፉ ያሳያል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2017 ወዲህ የፈቃድ ሞትን በተመለከተ ሦስት ጊዜ በሕዝብ እንደራሴዎች ውይይት ተደርጓል። ሕጉ፤ የስድስት ወር እድሜ የተሰጣቸው ህሙማንን ብቻ ያካት ወይስ ሌሎችም በጠና የታመሙ ግለሰቦች ተጠቃሚ ይሁኑ የሚለው አከራካሪ ነበር። የኒውዚላንዱ 'ፈርስት ፓርቲ'፤ ሕጉ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት ሕዝበ ውሳኔ መካሄድ አለበት ሲል ተከራክሯል። ሕጉ ሰፊ ድጋፍ ቢያገኝም የሚቃወሙትም አልታጡም። የሕዝብ እንደራሴዎች በሕጉ ላይ ውሳኔ ሲያሳልፉ፤ "እንድንሞት ሳይሆን እንድንኖር እርዱን"፣ "የፈቃድ ሞት መፍትሔ አይደለም" የሚሉ መፈክሮች በማሰማት ተቃውሟቸውን ያሰሙ ነበሩ። በሚቀጥለው ዓመት ኒውዚላንድ አገራዊ ምርጫ ስታደርግ የፈቃድ ሞት ላይ ሕዝበ ውሳኔ ይተላለፋል። ከዚህ በተጨማሪ ለህክምና የሚውል እጸ ፋርስን በተመለከተም ምርጫ ይካሄዳል።
57053672
https://www.bbc.com/amharic/57053672
120 የሠላም አስከባሪ ኃይል አባላት ወደ ኢትዮጵያ አንመለስም አሉ
በሱዳን የነበራቸውን ግዳጅ የጨረሱ 120 ኢትዮጵያውያን የሠላም አስከባሪ ኃይል አባላት ወደ አገራችን አንመለስም አሉ።
የሠላም አስከባሪ ኃይል አባላት የሠላም አስከባሪ ኃይል አባላቱ ዓለም አቀፍ ጥበቃ እና በሱዳን ጥገኝነት መጠየቃቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል። የሠላም አስከባሪ አባላቱ በቅርቡ በተጠናቀቀው የተባበሩት መንግስታት የዳርፉር ተልዕኮ አካል ነበሩ። በተመሳሳይ ከወራት በፊት 15 በደቡብ ሱዳን የነበራቸውን ግዳጅ የጨረሱ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ኃይል አባላት ወደ ኢትዮጵያ አንመለስም ማለታቸው ይታወሳል። አገር መከላከያ ሠራዊት ወደ አገር ቤት አንመለስም ያሉት "የጁንታው ተላላኪዎች" ናቸው ብሎ ነበር። አሁን ላይ ወደ አገራችን አንመለስም ያሉት 120 የሠላም አስከባሪ ኃይል አባላት የትግራይ ተወላጆች ስለመሆናቸው ተመድ ያለው ነገር የለም። ስለ ሠላም አስከባሪ ኃይሎቹ ምን ተባለ? በዳርፉር አካባቢ ተልዕኳቸው የተጠናቀቀ 120 የሠላም አስከባሪ ኃይሎች ወደ ሀገራቸው ከመመለስ ይልቅ በሱዳን ጥገኝነት ጠይቀዋል ብሏል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት። ለዚህ ምክንያቱ በሰሜን ትግራይ ክልል የተፈጠረው ግጭት ተከትሎ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰቱት ውጥረቶች ጋር የተቆራኘ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል። ኤፒ የዜና ወኪል በበኩሉ ወደ አገራችን አንመለስም ካሉ የሠላም አስከባሪ ኃይል አባላት መካከል ከ30 በላይ የሚሆኑት ወደ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ መግባታቸውን የሱዳን ባለስልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል። የሰሜን ዳርፉር ግዛት የስደተኞች ድርጅት ኃላፊ የሆኑት አል-ፋቴህ ኢብራሂም ሞሐመድ ወደ መጠለያ ጣቢያ እንዲገቡ ከተደረጉት መካከል ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ፍቃደኛ ያልሆኑት ይገኙበታል ብለዋል። የስደተኞች ድርጅት ኃላፊ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ክስ ይጠብቀናል በሚል ፍራቻ ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆኑት መካከል 14ቱ ሴት የሠላም አስከባሪ አባላት ናቸው ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ፋርሃን ሃክ ባለፈው ወር ለኤፒ እንደገለጹት በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ወደ አገራቸው እየተመለሱ መሆኑን ተከትሎ በድርጅቱ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ስር የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን "ዓለም አቀፍ ጥበቃን እየጠየቁ" ነው። የሱዳን የስደተኞች ኃላፊው ሞሐመድ በበኩላቸው ሱዳን እሁድ በትንሹ 33 የሠላም አስከባሪ ኃይሎችን ከሰሜን ዳርፉር ግዛት በማስወጣት ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ወደሚገኘው ምስራቃዊው የካሳላ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ አስገብታለች ብለዋል። ተጨማሪ 31 ሌሎች የሠላም አስከባሪ ኃይሎች ሰኞ ከሰሜን ዳርፉር ይወጣሉ ብለዋል። በዚህም የሠላም አስከባሪ ኃይሎቹ ከትግራይ ግጭት ሸሽተው ወደ ጎረቤት ሱዳን የተሰደዱ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ይቀላቀላሉ። ቀደም ሲል አንመለስም ስላሉት የሠላም አስከባሪ አባላት ምን ተባለ? ከወራት በፊት 15 የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ አባላት ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አንፈልግም ማለታቸውን መዘገቡ ይታወሳል። እንደ የፈረንሳይ ዜና ወኪል ከሆነ ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሠላም ማስከበር ላይ ተሰማርተው የነበሩ 169 ወታደሮች በሌሎች ተተክተው ወደ አዲስ አበባ መመለስ ነበረባቸው። ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደማይፈልጉ ያሳወቁት 15ቱ የሠላም አስከባሪው ኃይል አባላት የትግራይ ተወላጅ መሆናቸውም ተገልጿል። ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ የሠራዊቱን የኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል መሐመድ ተሰማን በመጥቀስ ባወጣው ዜና ወደ አገር አንመለስም ያሉት የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት መሆናቸውን አመልክቷል። እንደሜጀር ጀነራል ተሰማ ከሆነ ሻለቃው በደቡብ ሱዳን የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ለተተኪው ኃይል ኃላፊነቱን በማስረከብ በመመለስ ላይ እንዳለ አስራ አምስት የሠራዊቱ አባላት ወደ አገር ቤት አንመለስም ብለዋል። "የጁንታው ተላላኪዎች ወደ አገራችን አንሄድም በማለት ጁባ አየር ማረፊያ ላይ በመንከባለልና በመጮህ ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል" ሲሉ ሜጀር ጀኔራል መሐመድ በወቅቱ ተናግረዋል። የመከላከያ ሠራዊቱ በዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ግዳጅ አኩሪ ተግባር እየፈፀመ እንደሚገኝ በመግለጽ በግለሰቦቹ የተፈጸመው ድርጊት "የሠራዊቱን አባላት የማይወክል አሳፋሪ ተግባር" መሆኑን ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ ገልጸው ነበር። የዳርፉር ሠላም ማስከበር ተልዕኮ በተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ ስር ኢትዮጵያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወታደሮችንና የፖሊስ ኃይል ያሰማራችበት የዳርፉር ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ከወራት በፊት ተጠናቋል። ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ስር በተለያዩ አገራት ውስጥ ለሚደረጉ የሠላም ማስከበር ተልዕኮዎች ከፍተኛ የሚባለውን ከ8,300 በላይ ሠራዊት ታበረክታለች። ከእዚህም ውስጥ ከፍተኛው ቁጥር ያላቸው በሱዳን ውስጥ በሚገኙት ዳርፉርና በአብዬ ግዛት ውስጥ የተሰማሩ ናቸው። ዩናሚድ በሚባል የአንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል የሚታወቀው የዳርፉር ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ውስጥ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ወታደሮች ካበረከቱ ቀዳሚ ሦሰት አገራት አንዷ ናት። በምዕራባዊ ሱዳን ለ13 ዓመታት በተባበሩት መንግሥታት አማካይነት ሠላም ለማስከበር ተሰማርቶ ለቆየው ሠራዊት በርካታ የዓለም አገራት ወታደሮቻቸውን አዋጥተዋል ከእነዚህም ውስጥ በርካታ የሠራዊቱ አባላትን በማበርከት ሩዋንዳ፣ ፓኪስታንና ኢትዮጵያ ቀዳሚዎቹ ናቸው። በምጽሀረ ቃል 'ዩናሚድ' (UNAMID) ተብሎ የሚታወቀው በዳርፉር ሰላም ለማስከበር የተሰማራው ኃይል ከዚህ በኋላ በሱዳን እንደማይቀጥል የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ማስታወቁ ይታወሳል። ምክር ቤቱ በሱዳን እና በዳርፉር ያለውን አንጻራዊ ሰላም፣ የሽግግር መንግሥቱ ከአማጺያን ጋር ያደረጋቸውን የሰላም ስምምነቶች እንዲሁም አጠቃላይ ለውጦችን ከግምት በማስገባት እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱ ተገልጿል።
news-57264688
https://www.bbc.com/amharic/news-57264688
አንጀሊና ጆሊና ብራድ ፒት በጋራ ልጆቻቸውን እንዲያሳድጉ ተወሰነ
ከረዥም ጊዜ እልህ አስጨራሽ የፍርድ ክርክር በኋላ ብራድ ፒት ከአንጀሊና ጆሊ ጋር ልጆቻቸውን በጋራ እንዲያሳድጉ ተወስኖለታል።
ታዋቂዋ አሜሪካዊት ተዋናይት ፍቺ የጠየቀችው በአውሮፓውያኑ 2016 ሲሆን ከዚያም በኋላ ጉዳዩን ፍርድ ቤት ይዞት ነበር። አሁን ፍርድ ቤቱ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ብራድ ፒት ከልጆቹ ጋር የሚያሳልፈውን ጊዜ በበለጠ ይጨምረዋል ተብሏል። ታዋቂዎቹ የሆሊውድ ተዋናዮች በማደጎ ከኢትዮጵያ የወሰዷትን የ17 አመቷን ዘሃራን ጨምሮ፣ ፓክስ፣ ሺሎህና ቪቪየንና ኖክስ የተባሉ መንትዮች ወላጆች ናቸው። የ19 አመቱ ማዶክስ እድሜው 19 በመሆኑ ከዚህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አልተካተተም። የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም አንጀሊና ጆሊ ህጋዊ ትግሏን እንደምትቀጥል ፔጅ ሲክስ የተባለ ድረ-ገፅ አንድ ምንጭ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። አንጀሊና ጆሊ የተቃወመችው በአጠቃላይ በጋራ የማሳደጉን ሁኔታ ሳይሆን ሌሎች ስጋቶች እንዳሉባት ተገልጿል። ለወራት ያህልም ፍርድ ቤቱ የተለያዩ የዐይን እማኞችን፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎችን፣ እንዲሁም ሌሎች ይመለከታቸዋል የተባሉ አካላትን ምስክርነት ሰምቷል። አንጀሊና ጆሊ ልጆቻቸው ምስክርነት እንዳይሰጡ ተከልክለዋል በማለት የዳኛውን ውሳኔ ተቃውማለች። ተዋናይቷ ለፍቺ ባስገባችው ጥያቄ ላይ ጥንዶቹ "የማይታረቅ ልዩነት እንዳላቸው" ገልፃ ነበር። ብራድ ፒት በተወሰኑ ልጆቹ ላይ ያልተገባ ቁጣን ማሳየቱን ተከትሎ ጥቃት ያደርስባቸው ይሆን በሚል ምርመራ ቢደረግበትም በኋላ ነፃ ተብሏል። ባለትዳሮቹ በብዙዎች ዘንድ የምርጥ ጥንድነት ምሳሌ ተደርገው ስማቸውን በማጣመር "ብራንጀሊና" የሚል ስያሜ በአድናቂዎቻቸው ተሰጥቷቸው ነበር። ጥንዶቹ የተገናኙት ሁለቱም የተወኑበትና በአውሮፓውያኑ 2005 በተሰራው 'ሚስተር ኤንድ ሚስስ ስሚዝ' ፊልም ቀረፃ ላይ ነው።
41461246
https://www.bbc.com/amharic/41461246
ባርሴሎና ከላስ ፓልማስ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታም ላልታወቀ ጊዜ ተዛውሯል
የስፔን ፖሊስ የካታሎንያን ሕዝበ-ውሳኔን ለማስቆም በወሰደው እርምጃ በትንሹ 337 ሰዎች ተጎዱ።
የስፔን መንግስት ሕገ-ወጥ ነው ያለውን የካታሎንያን ሕዝበ-ውሳኔ ለማስቆም ቃል ገብቶ እንደነበር የሚታወስ ነው። የስፔን ፖሊስ ካታሎንያውያን ወደ ምርጫ ጣቢያ እንዳይሄዱ እያገደ እንዳለም ታውቋል። በየጣቢያው በመዞር የምርጫ ቁሳቁሶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉም ተዘግቧል። ፖሊስ በካታሎንያ ትልቋ ከተማ ባርሴሎና ሕዝበ-ውሳኔውን ደግፈው ሰልፍ የወጡ ሰዎች ላይ የጎማ ጥይት ተኩሷል። የስፔን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር እንደገለጸው በተፈጠረው ግርግር 11 ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የስፔኑ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሳንታማርያ እንደተናገሩት "ፖሊስ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ስራውን እየሰራ ነው።" የካታሎንያ መሪ ካርሌስ ፒዩጅመንት በበኩላቸው ህዝበ-ውሳኔውን ለማስቆም በገፍ ወደ ካታሎንያ የመጡትን የማዕከላዊ ስፔን ፖሊሶች ኮንነዋል። "ሕጋዊ ያልሆነው የስፔን መንግስት ተግባር የካታሎንያ ሕዝብ ያሰበውን ከማሳካት አያግደውም" በማለትም ለጋዜጠኖች ተናግረዋል። የስፔን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሁዋን ኢግናሲዮ የካታሎንያውን መሪ "ረብ የለሽ ዝግጅት ያዘጋጀ" ሲሉ ወቅሰዋል። በተያያዘ ዜና ባርሴሎና ከላስ ፓልማስ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታም ላልታወቀ ጊዜ ተዛውሯል። ባርሴሎና በካታሎንያ በከተከሰተው ግርግር ምክንያት ጨዋታው ወደሌላ ጊዜ እንዲዛወርለት ላሊጋውን ጠይቋል። በዚህም መሠረት ባርሳ ከላስ ፓልማስ ጋር ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ እንዲራዘም ሆኗል።
news-52833584
https://www.bbc.com/amharic/news-52833584
በአሜሪካ እየተበራከተ የመጣው የፖሊስ ጭካኔ እና የተገደሉ ጥቁሮች
ባሳለፍነው ሰኞ አንድ ነጭ የፖሊስ መኮንን አንድ ጥቁር አሜሪካዊን በጉልበቱ አንገቱ ላይ ቆሞ ሲያሰቃየው ከቆየ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ በአሜሪካ ዘርን መሰረት ያደረገ የፖሊስ ጭካኔ ጉዳይ ህዝባዊ ቁጣን ቀስቅሷል።
ጆርጅ ፍሎይድ ሟች የ46 ዓመት ጎልማሳ ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ሲሆን በሐሰተኛ የገንዘብ ኖት ጥርጣሬ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ሊያውለው እንደመጣ ተጠቅሷል። ለአስር ደቂቃ በሚዘልቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ፣ ነጭ ፖሊስ የዚህን ጥቁር አሜሪካዊ አንገት በጉልበቱ ተጭኖት እያለ በጉልህ የሚታይ ሲሆን ተጠርጣሪው በበኩሉ ‹‹መተንፈስ አልቻልኩም እባክህን አትግደለኝ›› እያለ ሲማጸነው ይሰማል፡፡ በዛኑ ቀን ደግሞ አንዲት ነጭ ሴት ኒው ዮርክ በሚገኝ ፓርክ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ለምን ውሻሽን አታስሪውም አለኝ በማለት ለፖሊስ ደውላ ነበር። "አንድ ጥቁር ሰው እኔ እና ውሻዬ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየዛተ ነው ድረሱልኝ" በማለት ለፖሊስ ደውላለች። ጉዳዩ ሲጣራ ግን ሴትዮዋ የፓርኩን ህግ በመተላለፍ ውሻዋን በመልቀቋ ነበር ጥቁር አሜሪካዊው ውሻሽን እሰሪው ያላት። አሜሪካ ውስጥ በጎርጎሳውያኑ 2019 ብቻ ከ1 ሺ በላይ ሰዎች በፖሊስ ተተኩሶባቸው ሕይታቸው አልፏል። የጆርጅ ፍሎይድ ሞት በአሜሪካ ላለው አስፈሪ የፖሊስ ጭካኔ ማሳያ ነው ተብሏል። ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት በ2019፣ 1014 ሰዎች በፖሊስ ተተኩሶባቸው የሞቱ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ጥቁር አሜሪካውያን ናቸው። አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት በሰራው ጥናት መሰረት ደግሞ ጥቁር አሜሪካውያን ከነጭ አሜሪካውያን ጋር ሲነጻጸር በፖሊስ የመገደል እድላቸው በሶስት እጥፍ ከፍ ያለ ነው። የፖሊስ ጭካኔ እንደ ‘ብላክላይቭስማተር’ የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ አድርጓል። ታዋቂዋ ዘፋኝ ቢዮንሴ እና ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ሌብሮን ጄምስ ይህንን እንቅስቃሴ በይፋ ደግፈዋል። እስካሁን ድረስ በአሜሪካ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሱ ተመሳሳይ የፖሊስ ጭካኔዎችን እንመልከት። ትሬይቮን ማርቲን፡ የካቲት 2012 የ 17 ዓመቱ ትሬይቮን ማርቲን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ነበር። ሳንፎርድ ፍሎሪዳ ውስጥ ነበር ጆርጅ ዚምርማን በተባለ የጥበቃ አባል ተተኩሶበት ሕይወቱ ያለፈችው። ማርቲን ዘመዶቹን ለመጠየቅ ጥበቃ ወደሚደረግለት አንድ መንደር ያቀናል፤ በዚህም ወቅት ነበር የስፓኒሽ ዘር ያለው ፈቃደኛ የአካባቢው ጠባቂ ጋር የተገናኘው። በወቅቱ ጆርጅ ዚመርማን በፍርድ ቤት ጥፋተኛ አይደለም ተባለ። ምንም እንኳን በአሜሪካ ሕግ መሰረት ጠባቂው የ 17 ዓመቱን ታዳጊ ራሴን ለመከላከል ነው በማለት መግደሉን እንደ ወንጀል ባያየውም የማርቲን ቤተሰቦችና ጓደኞቹ ግን የግድያ ወንጀል ነው የተፈጸመው ብለዋል። በዚህም ምክንያት ነበር ‘ብላክላይቭስማተር’ የሚባለው ማህበራዊ እንቅስቃሴ የተጀመረው። ኤሪክ ጋርነር፡ ሰኔ 2014 ኤሪክ ጋርነር በወቅቱ ትንባሆ በሕገ ወጥ መንገድ በመሸጥ ተጠርጥሮ ነበር በፖሊስ የተያዘው። ኤሪክ በፖሊስ አንገቱ ተቆልፎ ‹‹እባካችሁ መተንፈስ አልቻኩም›› እያለ በተመሳሳይ ሁኔታ ነበር የሞተው፡፡ ለኤሪክ ሞት ተጠያቂ የነበረው ነጭ የፖሊስ አባል ዳንኤል ፓንታልዮ ከሥራው የተባረረው ከክስተቱ አምስት ዓመታትን ቆይቶ መሆኑ ቁጣን ቀስቅሶ ቆይቷል፡፡ ማይክል ብራውን፡ ነሀሴ 2014 የ 18 ዓመቱ ማይክል ብራውን ዳረን ዊልስን በተባለ ፖሊስ አባል ተተኩሶበት መሞቱን ተከትሎ ደግሞ ‘ብላክላይቭስማተር’ የሚባለው እንቅስቃሴ ከአሜሪካ አልፎ ዓለማቀፍ ተቀባይነትን እንዲያገኝ አድርጓል። ሚሱሪ ፈርጉሰን ውስጥ በተፈጠረው ይህ ክስተት ምክንያት ከባድ አመጽ ተነስቶ የነበረ ሲሆን አንድ ሰው ሕይወቱ ሲያልፍ ሌሎች በርካታ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ነበር። ዋልተር ስኮት፡ ሚያዝያ 2015 ዋልተር ስኮት የ 50 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን በሳውዝ ካሮላይና ከፖሊስ ለማምለጥ ሲሞክር ሶስት ጊዜ በጥይት ተመትቶ ነው ሕይወቱ ያለፈችው። የፖሊስ አባሉ ዋልተር ስኮትን ለማስቆም የሞከረው የመኪናው ፍሬቻ መብራት በመሰበሩ ነበር። በወቅቱ ዋልተር ለልጁ የሚቆርጠውን ወርሀዊ ድጋፍ ባለመክፈሉ በፖሊስ ይፈለግም ነበር። • በምዕራብ ወለጋ የአራት ልጆች እናት የሆኑትን ግለሰብ ማን ገደላቸው? ስላገር የተባለው የፖሊስ አባል ዋልተር ስኮትን በመግደል ወንጀል ተከሶ 2017 ላይ የ 20 ዓመት እስር ተፈርዶበታል። የዋልተር ቤተሰቦችም የ 6.5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ተከፍሏቸዋል። ፍሬዲ ግሬይ፡ ሚያዝያ 2015 ዋልተር ስኮት በፖሊስ ተተኩሶበት ከሞተ ሳምንት እንኳን ሳይሞላው ባልቲሞር ሜሪላንድ ውስጥ ደግሞ ሌላ ቁጣን የቀሰቀሰ የፖሊስ ጭካኔ ተመዝግቧል። ፍሬዲ ግሬይ የ 25 ዓመት ወጣት ሲሆን በኪሱ ውስጥ የስለት መሳሪያ ይዞ በመገኘቱ ነበር በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው። በቦታው የነበረ የአይን እማኝ በቀረጸው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ፍሬዲ እየጮኸ ፖሊሶች ተሸክመው መኪናቸው ውስጥ ሲያስገቡት ይታያል። ከጥቂት ሰአታት በኋላ ፍሬዲ የአከርካሪ አጥንት ችግር አጋጥሞታል ተብሎ ሆስፒታል ገባ። ከሳምንት በኋላ ግን ሕይወቱ አለፈች። ይህ ተከትሎ በተቀሰቀሰ ቁጣም ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው 20 ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸው ነበር። ከፍሬዲ ሞት ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ ስድስቱ የፖሊስ አባለት ግን ጥፋተኛ አይደሉም ተብለው በነጻ ተሰናብተዋል። ፊላንዶ ካስቲል፡ ነሀሴ 2016 ፊላንዶ ካስቲል ሚኒሶታ ውስጥ ጀሮሚኖ ኣኔዝ በሚባል የፖሊስ አባል ነው ተተኩሶበት ህይወቱ ያለፈችው። በወቅቱ የተፈጠረውን ነገር የፊላንዶ የፍቅር ጓደኛ በስልኳ አማካይነት በቀጥታ አስተላልፋው ነበር። ምንም እንኳን የፖሊስ አባሉ ፍርድ ቤት ቢቀርብም አንድ ዓመት ከፈጀ የፍርድ ሂደት በኋላ በነጻ ተሰናብቷል። • ቦታም ጂን፡ መስከረም 2018 የ 26 ዓመቱ ቦታም ጂን፣ አምበር ጋይገር በምትባል የፖሊስ አባል ነበር በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ተተኩሶበት ህይወቱ ያለፈችው። በወቅቱ የፖሊስ አባሏ ቤቷ የገባች መስሏት በሂሳብ ስራ የሚተዳደረው ቦታም ጂን ቤት በስህተት ትገባለች። ልክ ስመለከተው ቤቴን ሊዘርፍ የገባ መስሎኝ ተኮስኩበት ብላለች። ከአንድ ዓመት በኋላም አምበር በወንጀሉ ጥፋተኛ በመባሏ የ 10 ዓመት እስር ተፈርዶባታል። • 119 ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል አቀኑ • አትላንታ ጄፈርሰን፡ ጥቅምት 2019 የ28 ዓመቷ አትላንታ፣ የህክምና ተማሪ የነበረች ሲሆን ዳላስ ውስጥ በመኝታ ክፍሏ ሳለች ነበር አሮን ዲን በተባለ የፖሊስ አባል የተደገለቸው። የፖሊስ አባሉ ከጎረቤት የአትላንታ የሳሎን በር ክፍት ነው የሚል ጥቆማ ደርሶት ነበር የመጣው። በመቀጠልም በመኝታ ቤቷ መስኮት በኩል ተኩሶ ገድሏታል። በግድያ ወንጀል ክስ ቢቀርብትም እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረበም። • ብሪዮና ታይለር፡ መጋቢት 2020 የ 26 ዓመቷ ብሪዮና ታይለር የድንገተኛ ህክምና ባለሙያ ነበረች። ኬንታኪ ውስጥ ፖሊሶች ወደ መኖሪያ ቤቷ ሲገቡ በተፈጠረ ጭቅጭቅ ወቅት ስምንት ጊዜ በጥይት ተመትታ ነው ህይወቷ ያለፈው። ፖሊሶቹ በወቅቱ ዕጽ በቤቷ አለ በማለት ነበር የሄዱት። ነገር ግን በብሪዮና ቤት ውስጥ ምንም አይነት ዕጽ አልተገኘም ነበር። ፖሊስ በበኩሉ አንድ የፖሊስ አባል በጥይት በመመታቱ ነው ተኩስ የተከፈተው ብሏል።
news-46192039
https://www.bbc.com/amharic/news-46192039
በጋዛ የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግጭት እየተባባሰ ነው
እስራኤል እሁድ እለት በጋዛ ያደረገችውን ስውር ወታደራዊ ተልኮ ተከትሎ ሰባት ታጣቂዎችና አንድ እስራኤላዊ ወታደር ሞተዋል። ታጣቂዎቹ 300 ሮኬቶችንና ሞርታሮችን እስራኤል ላይ አስወንጭፈዋል።
አውቶቡስ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት አንድ እስራኤላዊ በፅኑ ተጎደቷል በተለይም አንደኛው ሮኬት አወቶብስ መትቶ በአቅራቢያው የነበረ ወታደርን በፅኑ ማቁሰሉ ተዘግቧል። በአፀፋው ደግሞ እስራኤል የሃማስና የኢዝላሚክ ጂሃድ ይዞታ ናቸው ባለቻቸው ቦታዎች ላይ ከ70 በላይ የአየር ጥቃቶችን ፈፅማለች። በዚህም ሶስት ፍልስጥኤማዊያን የተገደሉ ሲሆን ሁለቱ ወታደሮች ናቸው። ሃማስ የሚያስተዳድረው ይዞታ ጤና ጥበቃ በጥቃቱ ዘጠኝ ሰዎች መጎዳታቸውን አስታውቋል። በእስራኤል በኩልም በተመሳሳይ አስር ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። •አምነስቲ የሳን ሱ ኪን ሽልማት ነጠቀ • እስራኤል የሐማስ ኮማንደርን በጋዛ ገደለች አሽኬሎን በተባለ የእስራኤል ከተማ መኖሪያ ቤት ላይ በደረሰ የሮኬት ጥቃት አንድ እስራኤላዊ መሞቱንም የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የእስራኤሉ ሜጀር ጀነራል ካሚል አቡ ሩካን ሃማስ ቀይ መስመር እያለፈ በመሆኑ እስራኤል በከባዱ አፀፋውን እንደምትመልስ አስጠንቅቀዋል። በፈረንሳይ ጉብኝት ላይ የነበሩት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ለአስቸኳይ ስብሰባ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። እሁድ እለት እስራኤል በጋዛ ያደረገችውን ስውር ወታደራዊ ተልእኮ ተከትሎ ከተገደሉ መካከል የሃማስ ኮማንደርና የእስራኤል ወታደር ይገኙበታል።
news-42165548
https://www.bbc.com/amharic/news-42165548
ስደተኛው የፊልም ባለሙያ
አባቱ በፖለቲካ ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ምክንያት ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት በመሸሽ ነበር ገመዶና ቤተሰቡ ሃገር ጥለው የተሰደዱት። የመጀመሪያ መዳረሻቸው ኬንያ ነበረች፤ ለጥቆም ኡጋንዳ፤ በስተመጨረሻም አሁን ያሉበት የኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ከተሙ።
"መጪው ትውልድ ከእኛ ምን ይወርሳል? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን።" ጅማሮ ወጣቱ ፊልም ሰሪ ገመዶ ጀማል ከልጅነቱ ጀምሮ ለኪነጥበብ በተለይም ለስዕል ትልቅ ፍቅር እንደነበረው ይናገራል። "በማሕበረሰባችን ውስጥ ያለውን የፊልም ጥበብ ክፍተት ለመሙላት በማሰብ ነው የጀመርኩት"ይላል ወደ ፊልም ዓለም የገባበትን ምክንያት ሲያስረዳ። የካሜራ ጥበብ፣ የምስል እና ድምፅ አርትኦት፣ እንዲሁም የአዘጋጅነት ሙያዎችን ኖርዌይ በሚገኝ የስነጥበብ ትምህርት ቤት በመግባት ቀስሟል። "ቤተሰቦቼ በጣም ያበረታቱኝ ነበር" የሚለው ወጣቱ ገመዶ በተለይ አባቱ ፍላጎቱን ከሁሉም በተለየ ይደግፉለት እንደነበረ ያስታውሳል። "ለሕዝቤ በታማኝነት እንድሠራ ይመክረኝ ነበር። 'ላመንክበት ነገር ብቻህን እንኳን ብትቆም ከዳር አድርሰው' ይለኛል" በማለት የአባቱን ምክር ያስታውሳል። ጥበብ በስደት፣ በራስ ቋንቋ "ኦሮምኛ ፊልም ለመሥራት ፈልጌ በርካታ መሣሪያዎች እንዲሁም ዕውቀት ቢኖረኝም ትልቁ ፈተና የሆነብኝ በኦሮምኛ የሚተውኑ ተዋንያንን ማግኘት ነው" ባይ ነው። በአንድ ወቅት ቀረፃ በመጨረሻቸው ወቅት አንድ ተዋናይ አቋርጦ መሄዱን አስታውሶ "በዚህም የተነሳ ፊልሙን ዳግመኛ እንደ አዲስ ለመቅረፅ ተገደን እንደነበር አልረሳም" ይላል። ይህ መሰናከል ባይሆንበት ኖሮ እስከዛሬ ድረስ ብዙ ፊልሞችን መሥራት ይችል እንደነበር ይናገራል። ይህንንና መሰል ውጣ ውረዶችን በፅናት በማለፍ እስካሁን ስድስት የኦሮምኛ ፊልሞችን እና በርካታ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለመሥራት ችሏል። ከነዚህም ውስጥ 'አማና' እና 'ጨባሳ' የተሰኙትን ፊልሞች በበርካታ ተመልካቾች እንደወደዱለት ይናገራል። አብዛኛዎቹ የገመዶ ፊልሞች የሚያጠነጥኑት በወቅታዊ የኦሮሞ ሕዝብ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ከዚህም ባሻገር ገመዶ የፊልም አሰራር ጥበብን የተመለከቱ አጫጭር የቪዲዮ ትምህርቶችን በኦሮምኛ ቋንቋ ድረ-ገፆች ላይ ይጭናል። የሚሰጣቸው ትምህርቶች የፎቶ አነሳስ ጥበብ፣ የፊልም ቀረፃ እና አርትኦት ላይ ያተኩራሉ። ወደጥበቡ መግባት ለሚፈልጉ የኦሮሞ ወጣቶች እንደመንደርደሪያ ሊያገለገላቸው እንደሚችል ገመዶ ይናገራል። '' ላመንክበት ነገር ብቻህን እንኳ ብትቆም ከዳር አድርሰው'' ወደፊት. . . ? ቢሳካልኝ ወደ ሃገር ቤት ተመልሼ ጥበብን ማሳደግ እፈልጋለሁ የሚለው ገመዶ "ሃገር ቤት ያሉ የጥበብ ሰዎችን በሁሉም በኩል ማገዝ እፈልጋለሁ" ይላል። "ትናንት ዛሬ አይደለም ዛሬ ደግሞ ነገን አይሆንም" የሚለው ገመዶ የኦሮሞ ሕዝብ ኪነ-ጥበብ አሁን እያደገ እንደሆነ ይናገራል። በተለያዩ ቋንቋዎች ከሚሰሩ ፊልሞች አንፃር ካየነው ግን አድጓል ለማለት አያስደፍርም ሲል ያትታል ገመዶ። ገመዶ አሁን ላይ አዲስ የኦሮምኛ ፊልም እያዘጋጀ መሆኑን ነግሮናል። "ይሀ ፊልም ከዚህ በፊት ከሠራኋቸው ፊልሞች አንድ ደረጃ ከፍ ያለ እንዲሆን ስለምፈልግ በጥሩ መንገድ እየሠራሁት ነው" በማለት ይገልፃል። የአዕምሮ ነፃነት "በሰው ሃገር በአዕምሮ ባርያ ትሆናለህ ነገር ግን አዕምሮህን ተጠቅመህ ደግሞ ነፃ መውጣት ትችላለህ" የሚለው ገመዶ " የሰው ልጅ ምድር ላይ ሲኖር ሰላም እና ነፃነት ያስፈልጉታል" ሲል ያምናል። ገመዶ አሁን በሚገኝባት የኖርዌይዋ ኦስሎ ከተማ በነፃነት ይኑር እንጂ ሃገሩን መናፈቁ እንዳለቀረ ይናገራል። "የራስ ሃገር ሁሌም እናት ነች፤ በሰው ሃገር አገኘሁ የምለው ነገር 'ስደተኛ' በሚል ስም መጠራት ብቻ ነው።" ገመዶ መቼ ይሆን ሃገሬ የምገባው ዛሬ?. . . ወይስ ነገ? ሲል ይተክዛል። አንድ ቀን ግን እንደሚሳካለት ተስፋ ያደርጋል።
news-53282953
https://www.bbc.com/amharic/news-53282953
ተቋርጦ የነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር ተጀመረ
በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረውና የተቋረጠው ድርድር ትናንት አርብ መጀመሩ ተነገረ።
በደቡብ አፍሪካ ሊቀመንበርነት በአፍሪካ ሕብረት ተሳታፊነት በቪዲዮ የሚካሄደው የሦስቱ አገራት ድርድር መጀመሩን የሱዳን ዜና አገልግሎት ገልጿል። የኢትዯጵያው የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በትዊተር ገጻቸው ላይ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ እንዳሰፈሩት የሦስትዮሽ ድርድሩ አርብ ከሰዓት በኋላ እንደጀመረና ቅዳሜም መቀጠሉን አረጋግጠዋል። ሚኒስትሩ ጨምረውም ከአፍሪካ ሕብረትና ሌሎች ታዛቢዎች ባሉበት እተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ድርድሩ እስከ ሁለት ሳምንተ ለሚደርስ ጊዜ በየዕለቱ እተካሄደ እንደሚቀጥል አመልክተዋል። በሦስቱ አገራት መካከል ከሳምንት በፊት ለቀናት ሲካሄድ ቆይቶ በተቋረጠው ድርድር ላይ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ከስምምነት ላይ መደረሱ የተገለጸ ሲሆን ቁልፍ የሆኑ ሕጋዊና የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ መስማማት ባለመቻላቸው ነው ውይይቱ መቋረጡን አገራቱ አሳውቀው ነበር። በተለይ ኢትዮጵያ ግድቡን በውሃ የመሙላት ሥራ በሐምሌ ወር እንደምትጀመር ዕቅድ በያዘችበት ሁኔታ በቀሪ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ሳይደረስ የውሃ ሙሌት እንዳይጀምር በሚል ከግብጽና ከሱዳን የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ድርድሩ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል። ትናንት አርብ መልሶ ተጀምሮ ዛሬም እንደሚቀጥል በተነገረው በዚህ የሦስቱ አገራት ድርድር ላይ በግድቡ ዙሪያ ያሉ መሰረታዊ የቴክኒክና የሕግ ልዩነቶች የመወያያ ጉዳዮች እንደሚሆኑ የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር መግለጹን አል አህራም ዘግቧል። ሚኒስቴሩ በአዲሱ ዙር የድርድሩ የመጀመሪያ ቀን ውይይት ዙሪያ ባወጣው አጭር መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የጀመሩት በቪዲዮ አማካይነት የሚያደርጉት ውይይት ዛሬ ቅዳሜም ይቀጥላል። ሦስቱ አገራት ባካሄዱት የመጀመሪያ ቀን ድርድር ላይ ደቡብ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ሕብረት ጽህፈት ቤት ተወካዮችና የህግ ባለሙያዎች፣ አሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት በታዛቢነት መሳተፋቸውን የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር አስታውቋል። ቀደም ያለው ከሰኔ 2 አስከ 10/2012 በሦስቱ አገራት መካከል በቪዲዮ አማካይነት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለስምምነት ከተጠናቀቀ በኋላ ጉዳዩ ወደ ተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ቀርቦ ባለፈው ሰኞ ምሽት ውይይት እንደተካሄደበት ይታወሳል። ቀደም ብሎ የተደረገው ውይይት ከተቋረጠ በኋላ በአፍሪካ ሕብረት አማካይነት በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና ግብጽ መሪዎች በተደረገው ውይይት አገራቱ ድርድራቸውን ጀምረው በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል። ግብጽና ሱዳን ድርድሩ ተካሂዶ ከስምምነት ላይ ሳይደረስ በፊት ኢትዮጵያ ግድቡን በውሃ የመሙላት ሥራ እንዳትጀምር ቢወተውቱም ባለፈው ሳምንት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ ግን ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ ሙሌት በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ለመጀመር ዕቅድ የያዘች መሆኑን አመልክቶ በዚህ ጊዜም ቀሪ የግንባታ ሥራዎች እንደሚቀጥሉ ገልጿል። ጉዳዩ ወደ ተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት መሄዱን ያልተቀበለችው ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት በሱዳንና በግብጽ ላይ እንደማያስከትል ለምክር ቤቱ ገልጻ የግድቡ ዋነኛ ግብ ልማት እንደሆነ አጽንኦት ሰጥታ ነበር። ባለፈው ሳምንት የአገራቱ መሪዎች በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ባደረጉት ውይይት ጉዳዩ በአህጉሪቱ የበላይ አካል በአፍሪካ ሕብረት የተያዘ በመሆኑ ይህንኑ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ለማሳወቅ መስማማታቸው ይታወሳል። አስር ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከአፍሪካ ትልቁ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን፣ ከአምሰት ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል አቅም ያለው ግዙፍ ግድብ ነው።
52016659
https://www.bbc.com/amharic/52016659
የጎንደር ከተማ አስተዳደር 'ሕገ ወጥ' ያለውን ቡድን ትጥቅ እንዲፈታ የጊዜ ገደብ አስቀመጠ
የጎንደር ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርቷል ያለውን ታጣቂ ቡድን እስከ መጋቢት 20/2012 ዓ.ም ድረስ ትጥቁን ፈትቶ ለመንግሥት እጁን እንዲሰጥ ጥሪ አቀረበ።
የአስተዳደሩ መግለጫ እንደሚለው ይህ ታጣቂ ቡድን ተደራጅቶ በከተማው ይንቀሳቀሳል፣ ኬላ ጥሶ ከከተማ ይወጣል፣ ይገባል፤ ሰው ያግታል፣ ግድያ ይፈፅማል፣ የግለሰብ ቤት ነጥቆ ካምፕ ያደርጋል፣ ከባለሀብት በግዴታ ገንዘብ ይሰበስባል፣ የከተማ መሬት አጥሮ በመያዝ ቤት ይሠራል በማለት አመልክቷል። ይህም ብቻ ሳይሆን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለ ወንጀለኛ ያስፈታል፣ ከፖሊስ ጣቢያ የጦር መሣሪያ ይዘርፋል ሲል ተፈፀሙ ያላቸውን ሕገወጥ ተግባራትን ዘርዝሯል። ባለፈው ሳምንት መገባደጃ አካባቢ በጎንደር ከተማ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ እንዳደረ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲገለጽ ነበረ ሲሆን፤ ቢቢሲም በወቅቱ የተፈጠረውን ለማወቅ ጥረት ቢያደርግም ሳይሳካለት ቀርቷል። በተለይ ተኩሱ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና "ፋኖ" በተሰኘው ታጣቂ ቡድን መካከል እንደነበር የማኅበረሰብ አንቂዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሲገልጹ ነበር። በወቅቱ የተፈጠረውንና አጠቃላይ ሁኔታና በጎንደር ከተማና በዙሪያዋ የሚስተዋለውን የጸጥታ መደፍረስ አስመልክቶ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ዛሬ [ማክሰኞ] መግለጫ አውጥቷል። የጎንደር ከተማ ያወጣው መግለጫ እንደሚያትተው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው ተኩስ "ሕገ ወጥ" ያላቸው ታጣቂዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ላይ የፈጸሙት ጥቃት ነው ብሏል። በዚህ ጥቃትም የሰው ሕይወት መጥፋቱንና ጉዳት መድረሱን መግለጫው ጠቅሷል። መግለጫው እንዳለው "በከተማው ከዋናው ፋኖ ውጪ፣ በሕገ ወጥ መንገድ በቡድን ተደራጅቶ እየተንቀሳቀሰ ያለው ቡድን በርካታ ሕገ ወጥ ተግባራትን እያከናወነ ነው።" አክሎም "ይህ ቡድን ታጥቆና ተደራጅቶ በከተማው ይንቀሳቀሳል፤ ያለምንም ከልካይ ኬላ ጥሶ ከከተማ ይወጣል፣ ይገባል፤ ሰው ያግታል፣ ግድያ ይፈፅማል፣ ዘር ቆጥሮ የግለሰብ ቤት ነጥቆ ካምፕ ያደርጋል፣ ከባለሀብት በግዴታ ገንዘብ ይሰበስባል፣ የከተማ መሬት አጥሮ በመያዝ ቤት ይሠራል" ሲል የቡድኑን ሕገ ወጥነት በዝርዝር በማስቀመጥ ወንጅሎታል። እንዲሁም ይህ ቡድን በፖሊስ እጅ ያለ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ እስር ቤት ጥሶ እንደሚያስፈታ፣ ከፖሊስ ጣቢያ የጦር መሣሪያ እንደሚዘርፍ፣ አስከሬን አጅቦ በመምጣት ጎንደር ከተማን በተኩስ እንደሚንጥ፣ በአገልግሎት መስጫዎች ተቋማት ውስጥ በመግባት የተጠቀመበትን አልከፍልም እንደሚልም ጠቅሷል። የከተማ አስተዳደሩ የሕገ ወጥ ቡድኑን ተግባራት ሲዘረዝር "ታዋቂ ግለሰቦችን በቡድን ተደራጅቶ፣ የቡድን መሳሪያ ጭምር ታጥቆ፣ ያጅባል፣ ታጥቆና ተደራጅቶ የመንግሥት ተቋማትን፣ የፓርቲ ቢሮዎችን ይከብባል፤ ያስፈራራል" በማለት ቡድኑን ከሷል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር በመግለጫው ላይ ቡድኑ ከዚህ ሕገ ወጥ ድርጊቱ ታቅቦ የመንግሥት ተገዳዳሪ ኃይል ሳይሆን ወደ መደበኛ ሕይወቱ እንዲመለስ ጥሪ አቅርቧል። መግለጫው ላይ እንደተጠቀሰው በታጣቂ ቡድኑ ውስጥ ያሉ አባላት መስፈርቱን የሚያሟሉ ከሆነ ወደ ክልሉ የፀጥታ መዋቅር እንዲካተቱ፣ መተዳደሪያ የሌላቸው በከተማ ብድር፣ መስሪያና መሸጫ ቦታ እንዲያገኙ፣ በኢንቨስትመንትና በእርሻ ለመሠማራት ለሚፈልጉ የእርሻ መሬት እንዲሰጣቸውና በቂ መተዳደሪያ ያላቸው ደግሞ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ የሚሉ የመፍትሔ ሃሳቦች ቀርበዋል። ይህ "ሕገ ወጥ ታጣቂ ቡድን" በተቀመጡት መፍትሔዎች የማይስማማ ከሆነ ግን መንግሥት ሕግን ለማስከበር እንደሚገደድ የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል። በከተማው ሕጋዊ የመንግሥት አስተዳደር እስካለ ድረስ በሕገ ወጥ መንገድ ታጥቆና ተደራጅቶ ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳሪያ አንግቦና ካምኘ መስርቶ መኖር እንደማይቻል መግለጫው አመልክቷል። በተጨማሪም ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ውጪ ሌላ አካል ታጥቆ እንዳይንቀሳቀስ መከልከሉን የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል። "የሕዝቡ ሠላም የሚረጋገጥለትም የፀጥታ መዋቅሩ ከሕዝቡ ጋር በመቀናጀት እንጂ በሌላ በማንም ኃይል አይደለም" ያለው መግለጫው "ማንኛውም ቡድን ወይም ግለሰብ በከተማው ውስጥ ታጥቆ እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ ነው" ብሏል። አስተዳደሩ በመግለጫ ላይ በሕገ ወጥ መንገድ የተደራጀው ቡድን እስከ መጋቢት 20/2012 ድረስ በሠላም እጁን ለመንግሥት እንዲሠጥ፣ ይህንን አልፈፅምም የሚል ከሆነ ግን የፀጥታ ኃይሉ እምቢተኛውን ወገን ለሕግ በማቅረብ የሕግ የበላይነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅሶ፣ ለዚህም "ሕዝባችን ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን" ብሏል። የከተማ አስተዳደሩ አክሎም ለከተማው ነዋሪዎች፣ ለክልሉና ለፌደራል ፀጥታ አካላት የከተማዋን ሠላም በማስጠበቅ በኩል ላደረጉትና ለሚያደርጉት አስተዋጸጽኦ አመስግኖ የጎንደር ከተማ ፀጥታ ወደ ቀድሞ ሰላሙ እስኪመለስ ሁሉም የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
news-46340474
https://www.bbc.com/amharic/news-46340474
የጋና ቅንጡ የሬሳ ሳጥኖች-ፍልስስ እያሉ ወደ መቃብር መሄድ
ጋናዊያን አይደለም የቆመን የሞተን ለማስደሰት የሚተጉ ናቸው። የሬሳ ሳጥን ሲሰሩ ሰው በህይወቱ ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን ህልም፣ ምኞት፣ እና የኑሮ ደረጃ ያገናዘበ ነው።
ይህንን ሀሳባቸውን የሚደግፉላቸው ደግሞ የሟች ቤተሰቦች ናቸው። የሟች ቤተሰቦች የሟችን የመጨረሻ ጉዞ ለማሳመር ይፈልጋሉ።ታዲያ ይህ የመጨረሻ ስንብት ምርጥ ሽኝት እንዲሆን ማድረግ የቀብር አስፈፃሚ ድርጅቶችም ስራ ነው። • "ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ • "የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ" አቶ ሌንጮ ለታ • በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ ጋና ካካዋ በማምረት በአለማችን ቀዳሚ ከሆኑት ሀገራት መካከል አንዷነች። ታዲያ በጋና ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ጋናውያን ጥረው ግረው የቋጠሯትን ጥሪት ሟች ዘመዳቸውን በካካዋ አምሳል በተሰራ ሬሳ ሳጥን ለመቅበር ይከፍላሉ። ይህን አይነቱ የሬሳ ሳጥን 28ሺህ ብር ድረስ ያስወጣል። ታዲያ አብዛኛው ከእጅ ወዳፍ የሆነ ኑሮ የሚገፋው ጋናዊ ገበሬ የቀን ገቢው በቀን 80 ብር ገደማ ነው። የሬሳ ሳጥን ሲዘጋጅ የሟችን ሥራ ያገናዘበ ነበር። በዚህኛው የሬሳ ሳጥን ግን "በቃሪያ ቅርፅ የተሰራው ከገበሬው ህይወት ባሻገር ትርጉም አለው "ይላል ላለፉት 50 አመታት እንዲህ የሬሳ ሳጥን በማበጃጀት ስራ ላይ የተሰማራው አናጢው ኤሪክ አጄቲ። የቃሪያው መቅላት እና ቅመምነት የሰውየውን ሰብዕና ይወክላል። "ቁጡና ሀይለኛ ነበር፣ ማንም ቢሆን ከእርሱ ጋር መጋጨት አይፈልግም።" እንዲህ በሜርሴዲስ ቤንዝ የተመሰሉ የሬሳ ሳጥኖች ዝነኞች ናቸው። ይህ ሟች ሐብታምና ጀርመን ሰራሹን ሜርሴዲስ ያሽከረክር እንደነበር ያሳያል። አሁንም የመቃብር ጉድጓዱ መኪናውን ማስገባት በሚችል መልኩ ተቆፍሯል። "ይህ ከሚዘወተሩ የሬሳ ሳጥኖች መካከል አንዱ ነው። በሐብት ጭምልቅ ያለ እንደነበር ይናገራል" ይላል የሬሳ ሳጥን ሰራተኛው ስቲቭ አንሳህ። በርካታ ሰዎች ቅንጡ የሬሳ ሳጥኖች ብለው ይጠሯቸዋል፤ የሀገሬው ሰው ግን 'አቤዱ አዴኪ' ወይንም "የተምሳሌት ሳጥን" ይላቸዋል። ለዚህ ደግሞ ሰበቡ ከእያንዳንዱ ሳጥን ጀርባ ተምሳሌት የሆነ ነገር ስላለ ነው። አውሮፕላን ከዝነኛ የሬሳ ሳጥኖች መካከል አንዱ ነው። ይህ የተሰራው ለህፃን ልጅ ሲሆን ከሞት ባሻገር ባለው ህይወት መልካም ጉዞ እንዲገጥመው ተምሳሌት የሚያደርግ ነው። አንዳንዴ የአካባቢው ሰዎች የሬሳ ሳጥኑን ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለመሸፈን ያላቸውን ያዋጣሉ። ከቅርብ አመታት ወዲህ የቤት ግንባታ በጋና ተጧጡፏል። ታዲያ ይህ የሬሳ ሳጥን ቤት እየሰራ የሚያከራይና በአካባቢው ማህበረሰብ ተወዳጅ ለሆነ ግለሰብ የተዘጋጀ ነው። "የሬሳ ሳጥን መግዛት የሟች ቤተሰብ ኃላፊነት ነው፤ ለቀብር ማስፈፀሚያ መክፈል፣ ለሟች ልብስ መግዛት እንዲሁም ለለቀስተኞች መሸኛ ምግብና መጠጥ ማቅረብም የቤተሰቡ ወጪ ነው።" "ቀብር የሚፈፀመው ከሐሙስ እስከ ሰኞ ባሉት ቀናት ነው። ሐሙስ ዕለት የሬሳ ሳጥን ይገዛል፣ አርብ ዕለት ሬሳው ካለበት ሆስፒታል ይመጣል፣ ቅዳሜ ቀብሩ ይካሄዳል፤ እሁድ ዕለት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል። ሰኞ ለቅሶ ለመድረስ ከመጡ ሰዎች የተሰበሰበውን ገንዘብ የመቁጠሪያ ቀን ነው" ይላል አጄቴ። አናጢው እንዲህ አበጃጅቶ የሰራውን የሬሳ ሳጥን በአግባቡ ጠርቦ ልጎ ለመቀባት ዝግጁ ያደርገዋል። አሁን ይህን የድምፅ ማጉያ ቅርፅ ያለውን የሬሳ ሳጥን ድምፃዊ ሲሞት የሚቀበርበት ነው። "ሟች የሬሳ ሳጥኑ ይብቃው፣ ይሁን አይሁን የምናውቀው ነገር የለም፤ አንዳንዴ ቤተሰብ እንጠይቃለን ካልሆነም ፎቶ እናያለን" ይላል አናጢው አንሳህ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሌሎች አናጢዎችም የገበያውን ፍላጎት ለሟሟላት በማሰብ የተለያዩ ቅርፆች ያሏቸውን ሳጥኖች መስራት ጀምረዋል። ይህ የሬሳ ሳጥን አይደለም፤ አሜሪካ ፍላደልፊያ ለሚገኝ የጥበብ ማዕከል የተሰራ ነው። ባለፉት አስርት አመታት ከ20 ሀገራት በላይ እነዚህን የሬሳ ሳጥኖች ገዝተዋቸዋል። የሬሳ ሳጥኖቹ ቅርፅ በደቡብ ኮሪያ፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ዴንማርክ የእንጨት ስራ የሆኑ ተማሪዎችን ትኩረት በመሳቡ ጋና ድረስ መጥተዋል። እነዚህ ጋናውያን አናጢዎች ግን የሬሳ ሳጥኑን ለማበጃጀት እና መልክ ለመስጠት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች በአካባቢው የሚገኙ ቀላል መሳሪያዎችን ነው።
news-57265513
https://www.bbc.com/amharic/news-57265513
'የምፅዓት ቀን' እምነት ተከታዮቹ ጥንዶች በልጆቻቸው ግድያ ክስ ተመሰረተባቸው
ከጥንዶች የቀድሞ ትዳር የተወለዱት ሁለት ልጆች ባለፈው ዓመት ህልፈታቸው ከተሰማና ከረዥምና ካልተለመድ የፍርድ ሂደት በኋላ በመጀመሪያ ደረጃ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተከሰዋል።
የ7 ዓመቱ ጆሽዋና የ17 ዓመቷ ታይሊ ሪያን አስክሬን የተገኘው በአንደኛው ተከሳሽ ዴቤል መኖርያ ቤት ሲሆን ተከሳሽ ደራሲ እንደነበር ታውቋል። ከዚህም ባለፈ ጥንዶቹ 'የምፅአት ቀን' የተሰኘ እምነት ተከታይ መሆናቸውና ባል ቻድ ዴቤል እምንቱን በተመለከተ የተለያዩ ድርሰቶች ማዘጋጀቱ ጉዳዩ የመገናኛ ብዙሃንን ቀልብ ስቦ ነበር። ጥንዶቹ የሚከተሉት ይህ እምነት ለዓለም ፍፃሜ መዘጋጀትን በእጅጉ የሚያበረታታ በመሆኑ ምንአልባት ከህፃናቱ ሞት ጋር ግንኙነት ይኖረዋል በሚል ነው ትኩረትን ያገኘው። በተጨማሪም ዴቤል አዲሱን ትዳር ከመሰረተ ከሳምንት በኋላ የቀድሞ ባለቤቱ መሞቷን ተከትሎ በሌላ የግድያ ወንጀልም ተከሷል። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ማስረጃን በመሰወር ነበር የተከሰሱት። ታዲያ ይህ የፍርድ ሂደት ባልተጠበቀ ሁኔታ ተቀይሮ ባለፈው ማክሰኞ ጥንዶቹን በግድያ ወንጀል ተከሰዋል። ጥንዶቹ ከግድያው ክስ ባሻገር በሌብነትና በኢንሹራንስ ማጭበርበር ክስ እንደሚጠብቃቸውም ተገልጿል። የፍሪሞንት ካውንቲ አቃቤ ሕግ ሊንዚ ብሌክ 'የምፅአት ቀን' እምነት ተከታዬቹ ጥንዶች ሆን ብለው 3 ንፁሀንን ገድለዋል ለማለት የሚያስችል በቂ ምክንያት አለን ሲሉ ተደምጠዋል።
news-53334223
https://www.bbc.com/amharic/news-53334223
በመላ ኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች የኩፍኝ ወረርሽኝ ተከሰተ
በኢትዮጵያ ውስጥ የኩፍኝ ወረርሽኝ መከሰቱን የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ባለፉት አራት ወራት በሁሉም ክልሎች የኩፍኝ ወረርሽኝ ታይቷል ብለዋል። በተለያዩ ምክንያቶች የኩፍኝ ወረርሽኝ "የጤና ሚኒስትርንም የፈተነ" እነደሆነ የገልፁት ዶክተር ሊያ ታደሰ፤ ባለፉት አራት ወራት በተለያየ ምክንያት ክትባት መስጠት መቀዛቀዙንም ጠቅሰዋል። በወረርሽኙ የተጠቁት በአብዛኛው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው ያሉት ሚንስትሯ፤ ከእነዚህም መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ክትባቱን ያልወሰዱ ህጻናት መሆናቸውን ገልጸዋል። በሁሉም ክልሎች ለወረርሽኙ መከሰት ምክንያቶች ብለው ሚንስትሯ ሲጠቅሱ፤ ከግንዛቤ ማነስም ሆነ ከአገልግሎት ተደራሽነት አንጻር መደበኛ ክትባቶችን አለመውሰድ፣ ክትባት ጀምረው የሚያቋርጡ ህጻናት ከፍተኛ መሆን፣ እንደዚህም ዘጠነኛ ወር ላይ ከሚሰጠው ክትባት በተጨማሪ አንድ ዓመት ከሦስት ወር ላይ የሚሰጠውን ሁለተኛ ዙር ክትባት አለመውሰድ ለወረርሽኙ መስፋፋት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በመከሰቱ የተነሳ በአገር ውስጥ የመደበኛ ህክምና አገልግሎት ፈላጊዎች ቁጥር መቀነሱን የጠቀሱት ሚንስትሯ፤ ይህም ለወረርሽኙ መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሎ እንደሚገመት ተናግረዋል። የኩፍኝ ክትባት ካለፈው ሳምንት (ከሰኔ 23/2012) ጀምሮ በዘመቻ መልክ በሁሉም ክልሎች መሰጠት መጀመሩን አስታውቀዋል። እስካሁን ድረስ 5.1 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት መከተባቸውን የተናገሩ ሲሆን ባለፈው ሳምንት በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ክትባቱን መስጠት ያልጀመሩ አካባቢዎች ቢኖሩም በቅርቡ ግን እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል። እድሜያቸው ከዘጠን ወር ጀምሮ ያሉ ህፃናት ከዚህ በፊት ክትባቱን ቢወስዱም ባይወስዱም እንደሚከተቡ ሚኒስትሯ ዶክትር ሊያ ታደሰ ጨምረው ተናግረዋል።
news-57045807
https://www.bbc.com/amharic/news-57045807
ሕዋ ሳይንስ: ብዙ የተባለለት የቻይና ሮኬት ስብርባሪ ጉዳት ሳያደርስ ውሃ ላይ ወደቀ
ቻይና ወደ ሕዋ ያስወነጨፈችው ሮኬት ስብርባሪዎች በተዘጋጀላቸው ቦታ ሕንድ ውቂያኖስ ላይ ማረፋቸውን አስታውቃለች።
የሕዋ ምርምር ሮኬት የሮኬቱ አብዛኛዎቹ ክፍሎች ወደ ምድር በሚምዘገዘጉበት ወቅት ተቃጥለው አየር ላይ የቀሩ ሲሆን አንዳንድ ስብርባሪዎች ግን በታሰበው ቦታ ላይ ማረፋቸውን የቻይና ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። የአሜሪካ እና አንዳንድ የአውሮፓ ተቋማት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ያልነበረውን ሮኬት ሂደት ሲከታተሉት ነበር። 'ማርች 5ቢ' የሚል ስያሜ የተሰጠው ሮኬት ባሳለፍነው ወር መገባደጃ ላይ ነበር ቻይና በሕዋ ላይ ለመስራት ላሰበችው ማዕከል የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ይዞ ነው ወደ ህዋ የተወነጨፈው። 18ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሮኬት በአስርት ዓመታት ውስጥ ቁጥጥር ሳይደረግበት ወደ ምድር የሚወድቅ ግዙፍ ቁስ ነው ተብሎ ነበር። የዚህ ሮኬት ስብርባሪ አካላት ደግሞ በትክክል መቼ እና የት እንደሚወድቁ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም መባሉ ስጋትን ፈጥሮም ነበር። የአሜሪካ የሕዋ ማዘዢያ ጣቢያ ባወጣው መግለጫ ማርች 5ቢ በአረቢያን ባህረሰላጤ በኩል ወደ ምድር መግባቱን አረጋግጧል። አክሎም ‘’የሮኬቱ ስብርባሪ ግን የውሃ አካል ላይ ጉዳት ማድረስ አለማድረሱ አልታወቀም’’ ብሏል። አሜሪካ ቀደም ብላ ባወጣችው መግለጫ የሮኬቱን አቅጣጫ እና አካሄድ በቅርበት እየተከታተለች እንደሆነ በመግለጽ ተኩሳ የመጣል እቅድ ግን እንደሌላት አስታውቃ ነበር። የአሜሪካ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን "ሮኬቱ ጉዳት ሳያስከትል እንደሚወድቅ ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል። ነገር ግን የሕዋ ሳይንስ ባለሙያዎች እንደሚሉት የሮኬቱ ስብርባሪዎች ሰዎች የሚኖሩበት አካባቢ የመውደቃቸው ዕድል በጣም ዝቅተኛ ነው። የመሬት አካል አብዛኛው ክፍል በውሃ የተሸፈነ እና አብዛኛው የምድራችን ክፍል ሰዎች የማይኖርቡት መሆኑ ለዚህ መቂ ምክንያት ነው ይላሉ። ከዚህ በፊት በተመሳሳይ አንድ የቻይና መንኩራኩር ስብርባሪ ከታሰበለት ጊዜና ቦታ ውጪ ወደ ምድር ከባቢ አየር በመግባት በአንዲት የአይቮሪ ኮስት የገጠር መንደር ውስጥ ወድቆ ነበር። ቻይና የሮኬቱን ስብርባሪዎች መውደቂያ ቦታ እና ትክክለኛ ሰአት መቆጣጠር አለመቻሏ ግድየለሽነቷን የሚያሳይ ነው የሚሉ ወቀሳዎችን ያስከተለባት ሲሆን አገሪቱ ግን ስብርባሪዎቹ ዓለማቀፍ የውሃ ክልል ውስጥ እንደሚወድቅ አውቅ ነበር ብላለች። በአሁኑ ጊዜ በህዋ ምህዋር ላይ የሚገኘው ብቸኛው ዓለም አቀፍ የህዋ ምርምር ጣቢያ፣ በእንግዝኛ ምሕጻሩ አይኤስኤስ (ISS) ነው። ይሁንና ቻይና በዚህ ጣቢያ ውስጥ አልታቀፈችም። ለዚህም ነው ቻይና በአውሮፓውያኑ 2022 የራሷ የህዋ ጣቢያ ግንባታን ለማጠናቀቅ ደፋ ቀና የምትለው።
news-57035747
https://www.bbc.com/amharic/news-57035747
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተወዳጅነትን አለማግኘት ልጆችን ራሳቸውን እንዲጠሉ እያደረጋቸው ነው
ከሁለት ሳምንት በፊት የ 12 ዓመቱ ታዳጊ ጆሽዋ ኃይለ ኢየሱስ በኮሎራዶ ሕፃናት ሆስፒታል ውስጥ ከፍተኛ እርዳታ ቢደረግለትም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም ።
ጆሽዋ ኃይለ ኢየሱስ በቲክቶክ የተሰራጨ 'ብላክ አውት ቻሌንጅ ' ላይ በመሳተፉ ነበር ሕይወቱ ሊያልፍ የቻለው። ጨዋታው ራስን ለተወሰኑ ጥቂት ደቂቃዎች ሳይተነፍሱ በማቆየት የሚደረግ ፉክክር ነው። በዚህ የቲክ ቶክ ፉክክር ላይ ራስን አንቆ ደምና አየር እና እንዳይተላለፍ በማድረግ ለጥቂት ደቂቃዎች ራስን ከሳቱ በኋላ የመንቃት ውድድር ላይ ሲሳተፍ ራሱን ስለሳተ ሆስፒታል የተወሰደ ቢሆንም ሕይወቱን ማትረፍ ግን አልተቻለም ነበር። ይህም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። እኛም ይህንን መሰረት በማድረግ ልጆች የማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም አለባቸው? ከተጠቀሙስ እንዴት መሆን አለበት የቤተሰብ ክትትልስ ምን መሆን ይገባዋል? የሚለውን የሕጻናት ስነልቦና ባለሙያ የሆኑትን ቴዎድሮስ ጌቴን አጋግረናል። ባለሙያው እንደሚሉት ከሆነ ማህበራዊ ሚዲያ ለአዋቂዎችም ቢሆን መጥፎም ጥሩም ሊሆን ይችላሉ። የሚወስነው ግን አጠቃቀም ላይ ነው። ይኹን እንጂ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ብቸኝነት ሲሰማቸው ከሰዎች ጋር ለመነጋገር ሃሳብ ለመለዋወጥ እንዲሁም ትስስር ለመፍጠር፣ ማህበራዊ ሚዲያን ሊጠቀሙ ይችላሉ ይህም በበጎ ጎኑ መታየት ይኖርበታል ብለዋል። ሆኖም ግን፣ እነዚህ ልጆች የአእምሮ እድገታቸው እና የሚነገራቸውን ነገር የሚቀበሉበት መንገድ በምክንያት እና ውጤት የተደገፈ ስላልሆነ በጥንቃቄ ሊታዩ ይገባል ሲሉ ይመክራሉ። በዚህም መሰረት የማህበራዊ ሚዲያው ያለው ተጽዕኖ ትልቅና ከሚታሰበው በላይ መሆኑን ባለሙያው ያብራራሉ። ለምሳሌ ይላሉ አቶ ቴዎድሮስ፣ "አንድ ቲክቶክ ላይ ያለ ተጠቃሚ አንድ ድርጊት እየፈፀመ የሚያሳይ ቪዲዮ ቢለጥፍ፣ በዚህ ዕድሜ ላይ ያሉ ልጆች እኔ ይህ አያቅተኝም፤ እችለዋለሁ፤ በሚል ድርጊቱን መድገም ይጀምራሉ። ምክንያቱም ይህ እድሜያቸው ሁሉን እንደሚችሉ የሚያምኑበት ጊዜ በመሆኑ ነው።" የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻቸው፣ በእውነት ከእነርሱ ጋር እንዳሉ የሚያስቡበት "በምክንያትና ውጤት ከሚያምነው የአእምሮ ክፍላቸው ይልቅ 'ኢጎ' የሚባለው በስሜት የሚያምኑበት እና ድርጊት የሚፈጽሙበት ጊዜ ይበዛል። በተጨማሪም ይህ ጊዜ እኔ ማን ነኝ? ማለት የሚጀምሩበት እና ጉርምስና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ወቅት ነው። በዚህም ተጽዕኖ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለጥፉት ነገር ብዙ ላይክ እንዳገኘ ለማሳየት ይፈልጋሉ በዚያም መጠን ተከታዮቻቸውን ለማብዛት ይጥራሉ።" ስለዚህ እነዚህ ልጆች የለጠፉት ነገር ምን ያህል ተወደደልኝ ወይንም ደግሞ ምን ያህል ሰዎች ተጋሩልኝ የሚለው እንጂ ምን ዓይነት አደጋ አለው የሚለውን ለመረዳት እንደሚከብዳቸው ይገልጻሉ። መወደድ በማህበራዊ ሚዲያ መንደር ልጆች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የለጠፉት ነገር በበርካቶች ከተወደደላቸው፣ ከዚህ በላይ ምን ብለጥፍ ተወዳጅነት ያመጣልኛል በሚል ስለ ራሳቸው ሳይሆን ተከታዮቻቸው ይወዱታል ብለው ስለሚያስቡት ነገር በመጨነቅ ይለጥፋሉ ሲሉ ባለሙያው ያስረዳሉ። ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የሚለጥፉት ነገር የማይወደድ ከሆነ እና ጥሩ ምላሽ ከሌላው ጥያቄ ያጭርባቸዋል። ምክንያቱም እነዚህ ታዳጊዎች የሚሰጣቸውን አስተያየት የሚመዝኑበት እድሜ ላይ አይደሉም። ይህም ለውጥረት እና ድባቴ ያጋልጣቸዋል። "በአይናቸው አይተዋቸው የማያውቋቸው፤ በሚሰጧቸው አስተያየት ራሳቸውን ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚያስገቡበት ጊዜ ቀላል አይደለም።" ይላሉ እኚህ የሕጻናት ስነልቦና ባለሙያ። የውጪ አገራት መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ ደግሞ ራስን በመጥላት ሕይወታቸውን በገዛ እጃቸው ማጥፋት ላይ የሚደርሱ ታዳጊዎች በርካታ ናቸው። በአገራችንም ከተሞች አካባቢ ይህ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና አስጊ እየሆነ መጥቷል በማለት የዚህን ጉዳይ አሳሳቢነት ይገልጻሉ። ከራሳቸው ተሞክሮ ሲናገሩም፣ ለራሳቸው ቅርብ ከሆኑ ሰዎች አንስቶ በሥራ ምክንያት ስላናገሯቸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ማህበራዊ ሚዲያው እያሳደረ ያለውን ተጽዕኖ እንዲህ ይናገራሉ። "ተማሪዎች፣ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው ፌስቡክ አልያም ኢንስታግራም ላይ ስሚለጥፉት ፎቶ እንደሚያስቡ፣ አንድ ታዳጊ ፎቶ ለጥፎ ብዙ ተከታዮች ካላገኘ እና ሌሎች ካገኙ በተቃራኒው መጨነቅ መኖሩን ያስረዳሉ። ቤተሰብ ምን ያድርግ? አቶ ቴዎድሮስ በዚህ ዘመን ቤተሰብ ያስተዳደር ዘዬ መቀየር ወይንም ማሻሻል ይኖርበታል ይላሉ። "ልጆች ከማህበራዊ ሚዲያ መማር ስለሚችሉ እድሉ ሊሰጣቸው ይገባል። ለምሳሌ ልጆች ከዩቲዩብላይ ምግብ መስራት የተለያዩ የእጅ ስራዎችን እንዲማሩ እና ክህሎቶቻቸውን ሊያሳድጉ ይችላሉ። ሆኖም ይህ በቤተሰብ ቁጥጥር ስር መሆን አለበት።" አቶ ቴዎድሮስ ብዙ ቤተሰቦች መካከል በአሁኑ ጊዜ የሚስተዋለው ግን ከዚህ የተለየ መሆኑን ሲያስረዱም " ልጆች ኢንተርኔት ካገኙ ስለማያስቸግሩ፣ ጥያቄ ስለማይጠይቁ ይህን አድርጉ ያንን አድርጉልኝ ስለማይሉ በዘፈቀደ ይለቅቋቸዋል" ብለዋል። ስለዚህ ቤተሰብ ለልጆቹ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ሲሰጥ፡ እኚህ የስነልቦና ባለሙያ "ቤተሰብ ልጆቻቸውን ከመረዳት እና ከማቅረብ ይልቅ እንዲሁ ከፈረዱባቸው የሚያደርጉትን ደብቀው ስለሚፈጽሙ ለአደጋ መጋለጣቸው አይቀርም" በማለት ቤተሰብ ልጆቻቸውን ማቅረብና በግልጽ መነጋገርን ይመክራሉ።
news-44144427
https://www.bbc.com/amharic/news-44144427
የኢትዮጵያ ተረት ገፀ-ባህሪን በአኒሜሽን
"ተረት ተረት" ሲባል "የላም በረት" ለማለት ከሚፈጥኑ ልጆች አንዷ ነበረች። ከልጅነት ትውስታዎቿ ተረት ትሰማ የነበረበተ ጊዜያት ዋነኞቹ ነበሩ ።
አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው የ26 ዓመቷ ፌበን ኤልያስ በህንጻ ኮሌጅ ኧርባን ዲዛይን ስትማር ከምህንድስና በበለጠ የሶስት አውታር ንድፍና ግራፊክስ ዲዛይን ይስባት ነበር። የእንጀራ ገመዷን የዘረጋችውም በዚህ ሙያ ነው። በአርማ አድቨርታይዚን ውስጥ ንድፍና አኒሜሽን ትሰራለች። "ጎረቤቴ ሚጢጢ የአኒሜሽን መነሻዬ" ያሳደጓት አያቶቿ ናቸው። ሚጢጢ የምትባል የጎረቤት ታዳጊ ነበረች። ሚጢጢ ለየት ያለ ባህሪ ስለነበራት የሰፈሩ ልጆች ባጠቃላይ ይወዷታል። ፌበን ደግሞ ጎረቤቷን ከመውደድ ባለፈ የህጻናት አኒሜሽን ገጸ ባህሪ መነሻ አደረገቻት። "ጠያቂነቷ፣ አልበገር ባይነቷ፣ በራስ መተማመኗ፥ ለማወቅ ካላት ጉጉት ጋር ተደማምሮ ተወዳጅ አድርጓታል" ትላለች ጎረቤቷን ስትገልጽ። ልጆች በጣም ስለሚወዷት የሷን የጸጉር አሰራርና አኳኋንም ይከተሉ ነበር። ፌበን ጎረቤቷን ተመርኩዛ 'ድንቢጥ' የተባለች ገጸ ባህሪ ለመፍጠር የወሰነችው በልጆች ዘንድ ተወዳጅ እንደምትሆን በማመን ነው። ከዪኒቨርስቲ ከተመረቀች በኋላ ለስድስት ወር የሶስት አውታር ንድፍ ስልጠና በድረ ገፅ ተከታታለች። የድንቢጥን ፊልም በቤቷ ኮምፒውተር ትሰራም ጀመር። 'ድንቢጥና አያቷ' "አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ልጆች ከገጸ ባህሪዋ ጋር እንዲተሳሰሩ ለማድረግ ሞክሬያለሁ" ትላለች። ድንቢጥን የምትገልፃት "የልጅነት ተሞክሮዎቼን አንድ ላይ አዋህጄ የፈጠርኳት ገፀ ባህሪ ዘወትር አዳዲስ ነገር ለመሞከር ትነሳሳለች" በማለት ነው። ፊልሙ ላይ ድብንቢጥ የምትኖረው ከአያቷ ጋር ሲሆን፣ ጸጉሯ እንደ ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ልጆች ጥቁርና ከርዳዳ ነው። የምትለብሰውም ጥበብ ቀሚስ ነው። "ድንቢጥና የፕሪሙ ፍሬ" ከአኒሜሽን ክፍሎቹ አንዱ ነው። በድንቢጥ ቤት አቅራቢያ የፕሪም ዛፍ አለ። የፕሪሙ ፍሬ ሳይበስል እንዳትበላ ቢነገራትም አእምሮዋ ከመጠየቅ የማይቦዝነው ድንቢጥ "ያልበሰለ ፕሪም ጣዕም ምን ይሆን?" ስትል ትጠይቃለች። ጠይቃም አትቀር ትቀምሰዋለች። "ታሪኩ ጠያቂ መሆንና በራስ መንገድ መሄድን ለልጆች ያስተምራል።" ትላለች ፌበን። ፌበን የድንቢጥን ታሪክ ዲጂታል ላብ አፍሪካ በተባለ ውድድር ያቀረበችው ከወራት በፊት ነበር። በውድድሩ ከአፍሪካ ሀገሮች የተውጣጡ 750 ሰዎች ተሳትፈው ነበር። ከነዚህ መሀከል አስሩ በሰምስት ዘርፍ አሸንፈዋል። በአኒሜሽን ዘርፍ ያሸነፈችው ፌበን የ3,000 ዪሮ ተሸላሚ ሆናለች። በቀጣይ የድንቢጥ ታሪክ ተከታታይ ፊልም ከዛም የህጻናት መጽሐፍ ይሆናል። ኢትዮጵያዊት ገጸ-ባህሪ ሲንድሬላ በዋልት ዲዝኒ ከተፈጠሩ ልቦለዳዊ ገጸ ባህሪዎች አንዷ ነች። ከአሜሪካ አልፋ በመላው አለም የብዙ ህጻናትን ልብ ማርካለች። የሲንድሬላ አይነት አለባበስና ባህሪ 'ተወዳጅና ተመራጭ' መሆኑን የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሀን ይሰብካሉ። ሁሉም ሕጻናት የየሀገራቸው እውነታ እንዳላቸው የተዘነጋም ይመስላል። "የኛን ታሪክ የሚያሳዪ የልጆች ፊልሞች እምብዛም አይደሉም። ይህ የፈጠረው ክፍተት የአፍሪካ ህጻናት ወደ አውሮፓውያን ፊልሞች እንዲያማትሩ አስገድዷል" ስትል ፌበን ትናገራለች። "ሰውነታቸውን ታጥበው ሲጨርሱ ጸጉሬ ለምን እንደ ሲንድላ አልተኛም የሚሉ ልጆች ገጥመውኛል" ትላለች። የዚህ አመለካከት ለመለወጥ ያስችል ዘንድ ድንቢጥ ከርዳዳ ጸጉርና ወፍራም ከንፈር አላት። ፌበን "ልጆች የፌበንን ጸባይ እና መልክ ከራሳቸው ጋር አስተሳስረው ደስ እንድትላቸው እፈልጋለሁ። በአስተዳደጓ፣ በባህሪዋና በመልኳ እነሱን የምትመስል ገጸ ባህሪ እያዪ እንዲያድጉ እፈልጋለሁ" ስትል ትገልጻለች። ከአፋዊ ታሪክ ነገራ ወደ ዲጂታል አኒሜሽን ታሪክ ነገራ ለኢትዮጵያ እንግዳ አይደለም። ለዘመናት ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል ተሸጋግሯል። በዲጂታል ዘመን አፋዊ ታሪክ ነገራ ወደ አኒሜሽንና ካርቱን እየተለወጠ ነው። ብዙ ባለሙያዎች የህጻናት አኒሜሽንና ካርቱን ይሰራሉ። ፌበን ፊልሞቹ በጥራት ረገድ ብዙ ይቀራቸዋል የሚል አቋም ያላት "ይዘታቸው ጥሩ ነው። አሰራሩ ግን ወደኋላ የቀረ ነው። አለም ከሚሰራው አንጻር መወዳደር አልቻልንም" ትላለች። ትምህርት ቤት አለመኖሩ የእውቀት ክፍተቱን ፈጥሯል። ብቃት ያላቸው ስቱድዮችም ብዙ አይደሉም። የህጻናት ታሪክ በህጻንት ስነ ልቦናዊ እድገት ተመራማሪዎች በህጻናት እድገት ሚና አላቸው ከሚሏቸው ልቦለዳዊ ታሪኮች ይገኙበታል። ፌበንም የህጻንት እድገትና የሚነገራቸው ታሪክ ትስስር ጠንካራነቱን ታምናለች። "ልጆች ከራሳቸው ጋር ማስተሳሰር የሚችሉትና የሚወዱትን ገጸ ባህሪ የማስመሰል ባህሪ ኣላቸው" ትላለች ልጆች የድንቢጥን ጠንካራ ጎኖች እንዲወስዱ የምትፈልገውም ለዚሁ ነው። የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መብዛት የአኒሜሽን ፊልሞችን ተደራሽነት ያሰፋዋል ብላም ታምናለች። "ፊልሙን ቤተሰብና ልጆች በቴሌቭዥን በጋራ እንዲያዪት እፈልጋለሁ" ትላለች።
news-51606312
https://www.bbc.com/amharic/news-51606312
በአምቦ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመደገፍ በወጡ ሠልፈኞች ላይ በተወረወረ ቦምብ ጉዳት ደረሰ
ትናንት እሁድ የካቲት 15/2012 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ እና ለፓርቲያቸው ድጋፋቸውን ለመስጠት ሠልፍ በወጡ ሠልፈኞች ላይ በተወረወረ ቦምብ ቢያንስ 29 ሠዎች መቁሰላቸውን የአምቦ ከተማ አስተዳደር እና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ኃላፊው አቶ ሂንሰርሙ ደለሳ እንዳሉት ቦንቡ የተወረወረው ለድጋፍ ሰልፍ በወጡ ፈረሰኞች ላይ ነው። ጉዳት ካጋጠማቸው መካከል የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸው ከሆሰፒታል የወጡ እንዳሉ ሁሉ የተለያዩ የጉዳት መጠን ያስተናገዱ መኖራቸውን አቶ ሂንሰርሙ ተናግረዋል። • "መንግሥት ጠንከርና መረር ያለ እርምጃ ለመውሰድ ተገዷል" ጄነራል ብርሃኑ ጁላ • የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አባላት በንስሐ እስኪመለሱ ክህነታቸው ተያዘ • በአወዳይ በመንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ግጭት ተፈጠረ ከወንጀሉ ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን የተናገሩት ኃላፊው "በጫካ ውስጥ ታጥቆ የሚንቀሳቀስው ኃይል ወንጀሉን ሳይፈፅም እንደማይቀር እንጠረጥራለን" ብለዋል። በጥቃቱ በርካታ ፈረሶችም መጎዳታቸውን ቢቢሲ ከአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ባገኘው መረጃ ለማወቅ ችሏል። ከቀናት በፊት በአወዳይ ከተማ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ድጋፋቸውን ለመግለጽ በወጡ ሰዎችና በተቃዋሚዎች መካከል ግጭት አጋጥሞ ለሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን መዘገባችን ይታወሳል። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድጋፍ ሠልፍ እና የኦፌኮ ስብሰባ መከልከል በጅማ ሰሞኑን በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስተዳደርና ለአዲሱ ፓርቲያቸው፣ ብልጽግና፣ ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ነዋሪዎች በተከታታይ ሰልፍ እያደረጉ ነው። አርብ እኩለ ቀን ላይ ለአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ቡራዩ ውስጥ የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት ሲገደሉ ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸው ተዘግቧል። ፖሊስ በቡራዩም ሆነ እሁድ ዕለት በአምቦ ከተማ ከተፈጸሙት ጥቃቶች ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሰዎችን መያዙን ያሳወቀ ሲሆን እስካሁን ግን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወገን የለም።
news-53525201
https://www.bbc.com/amharic/news-53525201
ሰሜን ኮሪያ 'የመጀመሪያውን' የኮሮናቫይረስ ተጠርጣሪ ማግኘቷን አስታወቀች
ሰሜን ኮሪያ በአገሪቱ የመጀመሪያው የተባለውን በኮሮናቫይረስ የተጠረጠረ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች።
ሰሜን ኮሪያ ውስጥ ሰው በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ጭምብል ማድረግ ግዴታ ነው የአገሪቱ መንግሥት የዜና አገልግሎት እንደዘገበው በሽታው እንዳለበት የተጠረጠረው ግለሰብ ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ ከድቶ ሄዶ የነበረ ሲሆን በቅርቡ በድንበር በኩል ወደ ሰሜን ኮሪያ ከተመለሰ በኋላ የወረርሽኙ ምልክቶች ታይተውበታል። ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ከፍተኛ በለስልጣኖቻቸውን ሰብስበው ከደቡብ ኮሪያ ጋር በምትዋሰነው የድንብር ከተማዋ ኬሶንግ ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ተደርጓል። ለመረጃ ዝግ የሆነችው ሰሜን ቀደም ሲል በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው እንደሌለባት ስታሳውቅ ብትቆይም፤ ተንታኞች ግን ሊሆን አይችልም ሲሉ ቆይተዋል። "በኬሶንግ ከተማ ድንገተኛ ነገር ተከስቷል፤ ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ ኮብልሎ የነበረ ግለሰብ በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር ተሻግሮ ወደ አገሪቱ ከገባ በኋላ ቫይረሱ እንዳለበት ተጠርጥሯል" ሲል የየአገሪቱ ዜና ወኪል ኬሲኤንኤ ዘግቧል። ትናንት ቅዳሜ በተካሄደው የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አስቸኳይ ስብሰባ መሪው ኪም ጆንግ-ኡን የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር "ከፍተኛ የአስቸኳይ ጊዜ ሥርዓት" እንዲዘረጋ አዘዋል። በተጨማሪም ዜና ወኪሉ እንደዘገበው መሪው ኪም ጆንግ-ኡን በበሽታው የተጠረጠረው ግለሰብ በከፍተኛ ጥበቃ ስር ባለው የድንበር አካባቢ ከደቡብ ወደ ሰሜን ኮሪያ እንዴት አልፎ ሊገባ እንደቻለ እንዲመረመር ያዘዙ ሲሆን፤ ተጠያቂ የሚሆኑ ሰዎች ላይ "ከባድ የቅጣት እርምጃ" እንዲወሰድባቸው አዘዋል። ነገር ግን ደቡብ ኮሪያ በተመሳሳይ ጊዜ ምንም አይነት ሕገ ወጥ የድንበር ማቋረጥ ክስተት እንዳልነበረ አሳውቃለች። ከስድስት ወራት በፊት ቫይረሱ በዓለም ዙሪያ መስፋፋት በጀመረበት ጊዜ ሰሜን ኮሪያ ድንበሮቿን ዘግታ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ወደ ለይቶ ማቆያ ውስጥ አስገብታለች። በዚህ ወር መጀመሪያ ገደማ ላይ መሪው ኪም ጆንግ-ኡን አገራቸው በኮሮናቫይረስ ላይ "አንጸባራቂ ስኬት" እንደተቀዳጀች አሳውቀው ነበር።
news-56379415
https://www.bbc.com/amharic/news-56379415
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት መስጠት ተጀመረ
በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የኮቪድ-19 ክትባት መሰጠት የተጀመረ ሲሆን፤ በዚህም የክትባት መርሃ ግብር ጅማሬ ላይ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ኃላፊዎች ተከትበዋል።
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ክትባቱን ወስደዋል የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ ተገኝተው ክትባቱን በመውሰድ መርሃ ግብሩን አስጀምረዋል። "በመላ አገሪቷ ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ በእድሜ የገፉና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በመጀመሪያ ዙር ክትባቱን በቀዳሚነት ያገኛሉ" ብለዋል ሚኒስትሯ። በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባት መሰጠት የተጀመረበት የዛሬው ዕለት፤ ወረርሽኙ በአገሪቱ ውስጥ መገኘቱ ይፋ በተደረገበት ልክ በአንደኛ ዓመቱ ነው። ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያገለግለውን 2.2 ሚሊየን ብልቃጥ ክትባት የተረከበችው ባለፈው ሳምንት ነበር። ክትባቱ አስትራዜኔካ ሠራሽ ሲሆን ክትባቱ ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት አቅርቦት ጥምረት የተገኘ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ ማስታወቁ ይታወሳል። ይህም በተለያዩ ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች ተከፋፍሎ ነው ዛሬ ቅድሚያ ለተሰጣቸው ሰዎች መሰጠት የተጀመረው። በዚህም በአዲስ አበባ፣ አማራ፣ ሐረሪ፣ ሶማሌ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች የክትባቱን መርሃ ግብር በይፋ ተጀምሯል። ወታደራዊ ግጭት በተከሰተበት ትግራይ ክልልም፤ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በመቀለ በመገኘት የክትባቱን መርሃ ግብር አስጀምረዋል። የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ፣ የክልሉ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋና ሌሎች ባለሥልጣናት ክትባቱን ወስደዋል። ዶ/ር ሊያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የክትባት ውስንነት መኖሩን በመግለፅ፤ ሕብረተሰቡ ክትባት ተጀመሯል ብሎ መዘናጋት እንደሌለበት አሳስበዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የክትባት መርሃ ግብርም፤ የከተማዋ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ፤ ስለ ክትባቱ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን በመግለፅ ለማሳያነት ራሳቸው መከተባቸው ተነግሯል። በአማራ ክልልም በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልም ውስጥ ክትባቱ ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል። በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ፣ የጤና ቢሮ ኃላፊው ዶክተር መልካሙ አብቴ እና ሌሎች አመራሮች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ወስደዋል። ክልሉ በአገር አቀፍ በተሰጠው ኮታ መሰረትም 108 ሺህ ብልቃጥ ክትባት ማግኘቱን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ገልጿል። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድም ክትባቱን በመውሰድ የክትባት ዘመቻውን በክልሉ አስጀምረዋል። አቶ ሙስጠፌ ክልሉ 108 ሺህ ብልቃጥ ክትባት ማግኘቱን ገልፀው፤ "ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሕብረተሰብ ክፍሎች በአፋጣኝ ክትባቱን እንዲያገኙ እናደርጋለን" ማለታቸው ተዘግቧል። ክትባቱ ቅድሚያ ለጤና ባለሙያዎች የሚሰጥ ሲሆን በመቀጠልም ተጓዳኝ ህመም ላለባቸውና እድሜያቸው ለገፋ ሰዎች ይሰጣል ተብሏል። በኢትዮጵያ የቫይረሱ ሥርጭት እየጨመረ ሲሆን በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እያሻቀበ ነው። የቫይረሱ መሰራጨት አቅም ጨምሮ በ12.80 በመቶ በኮቪድ የመያዝ ምጣኔ መድረሱን የሕብረተሰብ ጤና ተቋም አስታውቋል። በትናንትናው ዕለትም እስካሁን ከፍተኛ የተባለው የሞት ቁጥር መመዝገቡን ተቋሙ አስታውቋል። በትናንትናው ዕለት 27 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ይህ የተረጋገጠው ከአስክሬን በተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ ነው ተብሏል። ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ 2 ሺህ 510 ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ወደ ፅኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ ታማሚዎች ቁጥርም እየጨመረ መሆኑን የገለፀው ተቋሙ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል። በኢትዮጵያ ወረርሽኙ ከተከሰተ አንስቶ 172 ሺህ 571 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 2 ሺህ 510 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
news-42410305
https://www.bbc.com/amharic/news-42410305
ሳዑዲ ከየመን የየተኮሰ ሚሳዔል ማክሸፏን አስታወቀች
የየመን አማፂ ቡድን ወደ ሳዑዲ ከተማ ሪያድ የተኮሰው ሚሳዔል ተመቶ መወደቁ ተሰምቷል።
የዓይን እማኞች በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሰማይ ላይ የታየውን ጭስ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው በመቅረፅ በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ አሰራጭተዋል። የሁቲ አማፂ ቡድን ቴሌቪዥን ጣቢያ የሆነው አል-ማሲራህ እንዳስታወቀው ታጣቂዎቹ ወደ ሳዑዲ ምድር 'በርካን-2' የተባለ ሚሳዔል አስወንጭፈዋል። ባለፈው ወር ሪያድ ላይ ተመሳሳይ የሚሳዔል ጥቃት ሙከራ ተደርጎ መክሸፉ ይታወቃል። ሳዑዲ አረቢያና አሜሪካ ኢራንን ለሁቲ ታጣቂዎች የጦር መሣሪያ እያቀረበች ነው ሲሉ ይወቅሳሉ። ኢራን በበኩሏ ከ2015 ጅምሮ በሳዑዲ የሚመራውን ጥምር ቡድን እየተፋለመ ያለውን የየመን ታጣቂ ቡድን አልደገፍኩም ስትል ወቀሳውን ታጣላለች። ሚሳዔሉ በሪያድ አል-ያማማ ቤተ-መንግሥት ስበሰባ ላይ የነበሩትን የሳዑዲ ገዢ መደብ መሪዎች ኢላማ ያደረገ እንደበርም ማወቅ ተችሏል። ቤተ-መንግሥቱ የሳዑዲ ንጉሥ ቢሮና የንጉሣዊ ቤተሰብ ፍርድ ቤት ሆኖ እያገለገለ እንዳለም ይታወቃል። ታጣቂ ቡድኑ ሚሳዔል መተኮሱን ካስታወቀ ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሳዑዲ መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ የሆነው አል-ኢክባሪያ ወደ ሪያድ እያመራ የነበረው ሚሳኤል ተመቶ መውደቁን ዘግቧል። በማሕበራዊ ሚድያ የተሰራጩ ፎቶዎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች የሪያድ ሰማይ ተመቶ ከወደቀው ሚሳዔል በወጣ ጭስ ታፍኖ እንደነበር አሳይተዋል።