id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
41948042
https://www.bbc.com/amharic/41948042
በመቱ ዩኒቨርስቲ ብሔር ተኮር ውጥረት ነግሷል
የትግራይ ክልል ተማሪዎች የሚደርስባቸውን ዛቻ እና ማስፈራሪያ በመሸሽ ከዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ መውጣታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የመቱ ዩኒቨርስቲ ኃላፊዎች በበኩላቸው ተማሪዎቹ ከግቢ መውጣታቸውን አረጋግጠው ''ትምህርትን ጥሎ ለመሸሽ የሚያበቃ በቂ ምክንያት ግን የለም'' ብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የትግራይ ክልል ተማሪዎች ''በእኛ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ፍተሻ በሌሎች ተማሪዎች ይካሄድብናል'' ሲሉ ተናግረዋል። ይህም ስጋት ያሳደረባቸው ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲው በ150 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው የጋምቤላ ከተማ አቅንተው ለአንድ ሳምንት ያህል በዚያው ቆይተዋል። ተማሪዎቹ እንደሚሉት የዩኒቨርስቲው ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እና የጋምቤላ ክልል አስተዳደር ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተደርጎ ረቡዕ ዕለት ወደትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ወስነው በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ቢደርሱም የመጡበት አውቶብሶች በድንጋይ ጥቃት ስለደረሰባቸው ተመልሰው ወጥተዋል። ''ችግሩን ለመቅረፍ ከዩኒቨርስቲው ጋር እየሰራን ነው'' የሚሉት የመቱ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ መክብብ ተማሪዎቹ ከጋምቤላ ሲመለሱ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ደረሰብን ያሉትን ጥቃት እውነትነትም አረጋግጠዋል። የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ድርጊቱን '' የአብዛኛውን ተማሪ አቋም አይወክልም፤ በኦሮሞ ባህል እና ወግ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው'' በማለት የኮነኑት ሲሆን ተማሪዎቹ ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡም አስጠንቅቀዋል። የጥርጣሬ እርሾ በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባቦራ ዞን ውስጥ የምትገኘው መቱ ከተማ የተለያዩ ብሔሮች ተስማምተው የሚኖሩባት መሆኗን ከንቲባዋ አቶ ኃይሉ አፅንዖት ሰጥተው ይናገራሉ። አቶ ኃይሉ'' በከተማዋ የብሔር መልክ ያላቸው ግጭቶችም ሆነ ቅራኔዎች አልነበሩም'' ይላሉ። ይሁን እንጂ ''ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች ላይ በተነሱ ጥቆማዎች መሰረት የግለሰቦች ቤት ላይ ፍተሻ ተካሂዷል'' ሲሉ ያስረዳሉ። በከተማው የተካሄዱት ፍተሻዎች በኦሮሞ እና በትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች መካከል ጥርጣሬ እና ስጋትን ሳይፈጥሩ አልቀረም የሚሉት አቶ ኃይሉ፤ የኦሮሞ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ስጋት አለብን በማለት የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎችን ማደሪያ ክፍሎች ሲፈትሹ እንደነበረ ይገልጻሉ። ጋምቤላ ደርሶ መልስ የዩኒቨርስቲውን ግቢ ለቅው ከወጡት ተማሪዎች መካከል ከትግራይ ክልል የመጣው አብረሃ ዘውዱ (ለደህነነቱ ሲባል ስሙ የተቀየረ) ይገኝበታል። ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ከመቱ ወጥቶ ወደጋምቤላ ከተማ ያቀናው አብረሃ ''ሰልፎች በተካሄዱ ቁጥር የትግራይ ተወላጆች ከዩኒቨርስቲው ይውጡ የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ይነሳል'' ሲል ያስረዳል። "ወደማደሪያ ክፍሎቻችን እየመጡ 'እናንተ ተጠርጣሪዎች ናችሁ፤ ቦምብ ይዛችኋል፣ እንድንፈትሻችሁ ተፈቅዶልናል' ይሉናል'' ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። አብረሃ ''በግቢው ውስጥ የቀረ የትግራይ ተወላጅ ተማሪ የለም'' ይላል። የዩኒቨርስቲው የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኦልቀባ አሰፋ ግን በዚህ አይስማሙም። አቶ ኦልቀባ ከግቢው የወጡ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች ከመቶ እንደማይበልጡ በመግለጽ ግቢውን ጥለው ለመውጣት የሚያደርስ "በቂ ምክንያት አልነበረም፤ ለስጋት የሚዳርግ ምንም እንቅስቃሴ አልነበረም፤ አሁንም የለም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አብረሃ እንደሚለው ከሆነ አስራ አምስት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲው አንመለስም በማለት ወደ አዲስ አበባ አቅንተዋል። የዩኒቨርስቲው ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ችግሩን ለመፍታት እየተወያዩ ቢሆንም አብረሃ ግን "እኛ ከሁሉም በላይ ሕይወታችንን ነው የምንፈልገው፤ ለእኛ ትምህርት ሁለተኛ ነገር ነው፤ መመለስ ነው የምንፈልገው'' ሲል ይናገራል። የዩኒቨርስቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኦልቀባ "ከመጀመሪያውም አንስቶ ግቢውን ጥለው እንዳይሄዱ ጥረት ስናደርግ ነበር፤ አሁንም ወደ ዩኒቨርስቲው ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ ከመምህራንም ከተማሪዎች ጋር ምክክር እያደረግን ነው" ይላሉ። በትናንትናው ዕለት ሰልፍ የወጡ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው አመራሮች ላይ የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙ ሲሆን፤ ከሰልፈኞቹ መካከል ተማሪው ቶሎሳ ጋሪ (ስሙ የተቀየረ) ይገኝበታል። ቶሎሳ ሁሉም ተማሪ ወደ ዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ከመግባቱ በፊት ይፈተሻል፤ ''የትግራይ ክልል ተማሪዎች ግን አይፈተሹም ይህም ጥርጣሬ አሳድሮብናል'' ሲል ይናገራል። "የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ለተቋሙ መርህ ታማኝ መሆን ባለመቻላቸው፥ በአመራራቸው ላይ እምነት እንዳይኖረን አድርጓል" ይላል ቶሎሳ፤ "በመሆኑም ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጥያቄ አቅርበናል'' ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። የዩኒቨርስቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኦልቀባ ተቃዋሚ ተማሪዎቹ የበላይ አካል መጥቶ እስኪያነጋግረን ድረስ ትምህርት አንጀምርም ባሉት መሰረት መማር ማስተማሩ ከትናንት ጀምሮ መቋረጡን ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ አዲሱ አረጋ አርብ ማምሻውን በፌስቡክ ገጻቸው ከተማሪዎቹ ጋር ባደረጉት ውይይት የመማር ማስተማሩ ሂደት ሰኞ ህዳር አራት እንዲቀጥል፣ ማንኛውም ተማሪ የሚኖረውን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እንዲያቀርብ እና የሚመለከተው አካል ለጥያቄው ምላሽ እንደሚሰጥ በመስማማት ተጠናቋል ብለዋል። አቶ አዲሱ ተማሪዎቹ ወደ ግቢው ለመመለስ ስለመስማማታቸው ያሉት ነገር የለም።
57345859
https://www.bbc.com/amharic/57345859
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን እየተንደረደሩ የሚገኙት ናፍታሊ ቤኔት ማን ናቸው?
ቀጣዩ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን እያኮበኮቡ የሚገኙት ናፍታሊ ቤኔት በቀድሞው የኮማንዶ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተሰማርተው ሚሊየነር ናቸው።
ናፍታሊ ቤኔት ከቤንያሚን ኔታንያሁ ይበልጥ ወደ ቀኝ የሚያዘነብሉ እና የፍልስጤም መንግሥት ፅንሰ ሐሳብን የማይቀበሉ ናቸው፡፡ የቤኔት ጠቅላይ ሚንስትር የመሆን ምኞት ረዥም ጊዜ የቆየ ነው። ቀኝ ዘመሙ ብሔርተኛ ፓርቲያቸው ያሚና ባለፈው አገር አቀፍ ምርጫ ጥቂት መቀመጫዎችን ብቻ በማግኘቱ ሹመቱን መጠበቃቸው አስገራሚ ነው፡፡ ፓርቲያቸው ሰባት የፓርላማ መቀመጫዎችን በማግኘት አምስተኛ ሆኖ አጠናቋል። ከሁለቱ ተቀናቃኞች ወደ አንዱ ካዘነበሉ መንግሥት የመመስረት ዕድል በመኖሩ ቤኔት 'ንጉሥ ሰያሚ' ለመሆን በቁ። እአአ ከ2009 ጀምሮ በሥልጣን ላይ በነበሩት ኔታንያሁ እና በተቃዋሚው መሪ ያይር ላፒድም የፕሪሚየርነቱ ቦታ እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸው ነበር። ቤኔት ሰፊ የርዕዮተ ዓለም ልዩነት ቢኖራቸውም ከላፒድ ጎን ለመቆም መረጡ፡፡ የ49 ዓመቱ ናፍታሊ ቤኔት ከ2006 እስከ 2008 ድረስ ከኔታንያሁ ጋር መሥራታቸውን ተከትሎ ደጋፊያቸው ተደርገው ይወሰዱ ነበር፡፡ በኋላ ግን ተለያዩ። የኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲን ለቀው ወጡ። ቀኝ ዘመሙን ጄዊሽ ሆም ፓርቲን በመቀላቀል እአአ በ2013 በተካሄደው ምርጫ አሸንፈው ፓርላማ ገብተዋል፡፡ እስከ 2019 ድረስ በእያንዳንዱ ጥምር መንግሥት ውስጥ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡ በዚያ ዓመት ግን ፓርቲያቸው ምንም መቀመጫ ማግኘት አልቻለም ነበር። ከ11 ወራት በኋላ ቤኔት ሽኝቱን በመቀልበስ የያሚና ሊቀ መንበር በመሆን ወደ ፓርላማው ተመለሱ፡፡ ከኔታንያሁ የበለጠ "ቀኝ ክንፍ ነው" ሲሉ ራሳቸውን የሚገልጹት ናፍታሊ ቤኔት፤ የአይሁድ ብሔረሰብ የአይሁድ ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ የይገባኛል ጥያቄዎች የሚያነሱባቸውን ዌስት ባንክ፣ ምሥራቅ ኢየሩሳሌም እና የሶሪያንጎላን ኮረብቶች ባለቤትነት ይደግፋሉ። ምንም እንኳን እስራኤል በጋዛ ላይ ምንም ዓይነት የይገባኛል ጥያቄ እንደሌላት ቢናገሩም በዌስት ባንክ የአይሁዶችን የሰፈራ መብት ሲደግፉ ቆይተዋል። በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሕገ ወጥ ቢባልም እስራኤል ከ600,000 በላይ አይሁዶች በዌስት ባንክ እና በምሥራቅ ኢየሩሳሌም በሚገኙ ወደ 140 ገደማ ሰፈሮች ማስፈሯ ትክክለኛ ነው ትላለች፡፡ የሰፈራዎቹ ዕጣ ፈንታ ከእስራኤል እና ፍልስጤም ያለመግባባት ምክንያት አንዱ ነው። የሰፈራ እንቅስቃሴን ማቆም ይቅርና ጣልቃ መግባቱን ቤኔት አይቀበሉትም። ሥራውን የሚደግፉት ኔታንያሁን በጉዳዩ ላይ እምነት የሚጣልባቸው አድርገው አይቆጥሯቸውም፡፡ እንግሊዘኛ እና መገናኛ ብዙሃንን ጠንቅቀው የሚያውቁት ቤኔት በተደጋጋሚ በውጭ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ ተገኝተው የእስራኤልን ውሳኔ ደግፈዋል፡፡ አንድ ጊዜ በአገር ውስጥ የቴሌቪዥን ጣቢያ ክርክር ላይ እስራኤላዊ-አረብ የፓርላማ አባል አይሁዶች በዌስት ባንክ የመኖር መብት የላቸውም ማለታቸውን ተከትሎ "እናንተ ከዛፍ ዛፍ ስትዘሉ እዚህ የአይሁድ መንግሥት ነበረን" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ . ቤኔት ከእስራኤል ጎን ለጎን የፍልስጤም መንግሥት መመስረት የሚለውን ሐሳብ አይቀበሉም። ለእስራኤል-ፍልስጤም ግጭት መፍትሔ እንዲሆን የሁለት-መንግሥት ተብሎ የሚጠራውና በአሜሪካ እና በጆ ባይደን እንዲሁም በብዙ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሚቀርበውን መፍትሔ አይቀበሉም። እአአ በየካቲት 2021 በሰጡት ቃለ መጠይቅ "እኔ ማንኛውም ኃይል እና ቁጥጥር እስካለኝ ድረስ ከእስራኤል ምድር አንድ ሴንቲ ሜትር አሳልፌ አልሰጥም" ብለዋል። ይልቁንም ቤኔት የእስራኤልን የዌስት ባንክ ይዞታ በጉልበት ማጠናከርን ይደግፋሉ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የዕብራይስጥ ስሙ ጁዲያ እና ሰማርያ በሚለው ስማቸው ይጠሯቸዋል። ቤኔት የፍልስጤም ታጣቂዎችን ስጋት ለመቋቋም ከባድ አቋም በመውሰድ የሞት ቅጣትን እደግፋለሁ ብለዋል፡፡ እአአ በ1961 በኢየሩሳሌም ተፈርዶበት በቀጣዩ ዓመት ከተሰቀለው የኖዚ እልቂት መሐንዲሱ አዶልፍ ኢክማን በስተቀር ይህ ቅጣት በእስራኤል በጭራሽ አልተተገበረም፡፡ በ2018 ከጋዛ የሃማስ ገዥዎች ጋር የተካሄደውን ውዝግብ ያስቆመውን እርቅ ተቃውመዋል። ግንቦት 2021 ላይ ከጋዛ የተተኮሱትን ሚሳኤሎች ተከትሎ እስራኤል በወሰደችው ምላሽ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸውን በጅምላ አስገድለዋል በሚል ይከሷቸዋል፡፡ የቤኔት የፖለቲካ ከፍታ ቀደም ሲል በወታደራዊ እና በንግድ ውስጥ ያስመዘገቡትን ይከተላል፡፡ በሠራዊቱ አገልግሎት ወቅት በእስራኤል ልዩ ኃይል ሁለት ቅርንጫፎች ውስጥ አገልግለዋል። የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን በማቋቋም እና በመሸጥ ሚሊየነር ለመሆን ችለዋል፡፡ በ2014 በቃለ መጠይቅ ወቅት ስለ ሀብታቸው ሲናገሩ፤ "17 ስቴኮች አልበላም፣ የግል አውሮፕላን ወይም ጀልባም የለኝም። [ሀብቱ] በቃ የፈለግኩትን ለማድረግ ነጻነት ገዝቶኛል" ብለዋል፡፡
46121041
https://www.bbc.com/amharic/46121041
በአሜሪካ ምርጫ ዲሞክራቶች የምክር ቤት መቀመጫዎችን የተቆጣጠሩ ሲሆን ይህም ትራምፕን አስደንግጧል
በአሜሪካው "ሚድ-ተርም" ምርጫ ዲሞክራቶች 435 የሕዝብ እንደራሴዎች ያሉትን ምክር ቤት (ሀውስ ኦፍ ሪፕረዘንታቲቭስ) ማሸነፋቸው እየተዘገበ ነው። ይህም ለሪፓብሊካኑ ትራምፕ ትልቅ ሽንፈት ነው።
ዲሞክራቶች የታህታዩ ምክር ቤት (ሀውስ ኦፍ ሪፕረዘንታቲቭስ) ከስምንት ዓመታት በኋላ ማሸነፍ መቻላቸው የፕሬዚዳንቱን አጀንዳዎች እንዳሻቸው መቀያየር ያስችላቸዋል። በሌላ በኩል 100 አባላት የሚኖሩትን የሴኔቱን ምርጫ ሪፐብሊካኖች እንደሚያሸንፉት ተገምቷል። • ትላልቅ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች "አዋጭ አይደሉም" • በኢትዮጵያ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ 10 ሰዎችን ገደለ • ቢቢሲ ከእንግሊዝ ቀጥሎ ግዙፉን ቢሮውን አስመረቀ ሪፓብሊካኖች ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ተቀናጅተው አሜሪካን የመዘወር ዘመን ያበቃለት ይመስላል። ላለፉት ሁለት ዓመታት ዶናልድ ትራምፕ 'ወዳጃቸው' ነው የተባለው ኮንግረስ ፖሊሲያቸውን አጽድቋል፤ ድጋፍም አድርጎላቸዋል። ከሁለት ወራት በኋላ ግን ተመራጮቹ ከዋሺንግተን ሲከትሙ ይህ ሁሉ ይቀራል። በሌላው በኩል ዲሞክራቶች በሴኔቱ ዘንድ የፈቀዱትን ማስፈጸም ዳገት ነው የሚሆንባቸው። የምርጫው ውጤት ለትራምፕ እና ሪፓብሊካን ምን ትርጉም አለው? በሴኔቱ አብላጫውን ወንበር አሸንፈዋል። ይህም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛን ጨምሮ የዳኞችን ሹመት እንዲያጸድቁ ያስችላቸዋል። ትራምፕ እንዳለፉት ሁለት ዓመታት ቀሪውን የስልጣን ዘመን መምራት ቀላል አይሆንላቸውም። ከሁለቱም ወገን ጋር በመሆን መስራት ይጠበቅባቸዋል። ዲሞክራቶች ትራምፕ ከግብር ጋር ተያይዞ የሚነሳባቸውን ክስ ምርመራ ለማስጀመር አቅም ተፈጥሮላቸዋል። ይህ ብቻም ሳይሆን ዲሞክራቶች ትራምፕን ከሰው ከስልጣን ሊያስወርዱ ይችላሉ። የምርጫው ውጤት ለዲሞክራቶች ምን ትርጉም አለው? ዲሞክራቶች የሃውስ ኦፍ ሪፕረዘንታቲቭስ አብላጫ ወንበር በማግኘታቸው በአሜሪካ የፌደራል መንግሥት ሰልጣን ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ይሆናሉ። ይህም ፕሬዚዳንቱን እንዲቆጣጠሩ እድል ይፈጥርላቸዋል፤ የማይስማሙበትን ፖሊሲም ውድቅ እንዲያደርጉ አቅም ይፈጥርላቸዋል። የ"ሚድ-ተርም" ምርጫ ምንድነው? 'ሚድ-ተርም' የተባለው መሀል ላይ ስለሚካሄድ ነው። ለአራት ዓመት እንዲያገለግል የተመረጠው ፕሬዚዳንት ሁለት ዓመት እንደቆየ የሥራ ዘመኑ ይጋመሳል። በዚህ ወቅት "ሚድ-ተርም" ምርጫ ይከሰታል። ምርጫው ታዲያ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ በወርሃ ኖቬምበር (ኅዳር) ነው የሚካሄደው። ምን ዓይነት ምርጫ ነው? የአሜሪካ ምክር ቤት ላዕላይና ታህታይ ምክር ቤቶች አሉት። ታህታዩ ምክር ቤት 435 የሕዝብ እንደራሴዎች ሲኖሩት 'ሀውስ ኦፍ ሪፕረዘንታቲቭስ' ይባላል፤ ላዕላዩ ምክር ቤት 100 አባላት ሲኖሩት ተመራጮቹ ሴናተሮች ተብለው ይጠራሉ። የኅብረት ስማቸው ኮንግረስ ነው። ይህ ሕግ አውጪ ምክር ቤት በድምሩ 535 አባላት ይኖሩታል። በደፈናው አንድ ረቂቅ ሕግ ከላዕላዩም ከታህታዩም ምክር ቤት ሊመነጭ ይችላል ማለት እንችላለን። የዘንድሮ ምርጫ ለምን አጓጊ ሆነ? ምርጫ በዶናልድ ትራምፕ ላይ የሚካሄድ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል። ለምን? አንዱ ምክንያት ሁለቱም የምክር ቤት ወንበሮች በሪፐብሊካን ወኪሎች አብላጫ ተይዘው መቆየታቸው ነው። የዚህ ምርጫ ውጤት ግን የሚያሳዩት ወንበሮቹ ከሪፐብሊካን እጅ እንደወጡ ነው። ይህ ማለት ትራምፕ ለትራምፕ ትልቅ ሽንፈት ነው። ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔዎቻቸውን ለማጸደቅ ምጥ ይሆንባቸዋል።
news-56170353
https://www.bbc.com/amharic/news-56170353
ወደ 7 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከቤኒሻንጉል ወደ ሱዳን ሸሽተዋል ተባለ
በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ወደ 7 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ተሰደው ወደ ሱዳን መግባታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
የመተከል ዞን ተፈናቃዮች በቻግኒ። የመተከል ዞን ባለፉት ሶስት አመታት የተለያዩ ጥቃቶችን ያስተናገደ ሲሆን በተለይም ከመስከረም 2013 ጀምሮ ተደጋጋሚ ማንነነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን በዞኑ ተፈጽመዋል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እንዳለው ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከምዕራባዊው የኢትዮጵያ ከፍል የመተከል ዞን ተፈናቅለው ወደ ጎረቤት ሱዳን መሸሻቸውን ገልጿል። የኤጀንሲው ቃል አቀባይ ብባር ባሌክ ትናንት በጄኔቫ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለፁት፤ ከኢትዮጵያ ወጥተው ወደ ሱዳኗ የብሉ ናይል ግዛት የገቡት ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ ይደርሳል ተብሎ ይገመታል። እስካሁን 3 ሺህ የሚሆኑትን መመዝገብ መቻሉን ጠቅሰው፤ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቅለው የመጡ ሰዎችን መመዝገብ ሲቻል ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል የኤጀንሲው ቃል አባይ ተናግረዋል። ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ብቻ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በመሆን ወደ 1 ሺህ ለሚጠጉ ተፈናቃዮች እርዳታ አቅርቧል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ድጋፉ ምግብ፣ ህክምና፣ ውሃ እና የንፅህና መጠበቂያዎችን እንዲሁም ሌሎች የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቶችን ያጠቃለለ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ቀሪዎቹን ጥገኝነት ጠያቂዎች የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሱዳናዊያን ተቀብለው እያስተናገዷቸው እንደሚገኙ ተገልጿል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ባለፉት ሦስት ዓመታት የተለያዩ ጥቃቶች በነዋሪዎች ላይ ተፈጽሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በተለይም ከመስከረም 2013 ጀምሮ ተደጋጋሚ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ተከስተዋል። በተለይ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ውስጥ በሚገኘው የመተከል ዞን የአማራ፣ የኦሮሞ እንዲሁም የሺናሻ ተወላጅ የሆኑ ነዋሪዎች ላይ በተፈጸሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ተከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞትና መፈናቀል ማጋጠሙ ይታወቃል። በዚህም ሳቢያ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እንዲሁም የማፈናቀል ተግባራት ተደጋግመው እንደተፈጸሙ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በተደጋጋሚ ገልፀዋል። በአሁኑ ጊዜ የክልሉና የፌደራል መንግሥት በጋራ ያወቀሩት የዕዝ ማዕከል ተደጋጋሚ ችግር ባጋጠመባቸው አካባቢዎች ሠላምና መረጋጋት ለማስፈን የእርዳታና የመልሶ ማቋቋም ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑ መገለጹ ይታወሳል። የክልሉ ፖሊስ ከፌደራል የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ጥቃት ፈጽመዋል በተባሉ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአገር ውስጥ መገናና ብዙሃን ከዚህ በፊት የዘገቡ ሲሆን፤ በመተከል ዞን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ አመራሮችን በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው መገለጹ አይዘነጋም።
49027426
https://www.bbc.com/amharic/49027426
በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ የዓለም የጤና ስጋት ነው ተባለ
የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ "በአስቸኳይ የዓለምን ትኩረት የሚሻ የጤና ቀውስ" ሲል በይኖታል።
ይህ የጤና ድርጅቱ ውሳኔ ሐብታም አገራት ወረርሽኙን ለመዋጋት የሚረዳ ገንዘብ እንዲሰጡ ያስችላቸው ይሆናል ተብሏል። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅት አሁንም አገራት ድንበራቸውን እንዲዘጉ ያለው ምንም ነገር የለም። ለዚህ ምክንያት ብሎ ያቀረበው በሽታው ከክልሉ ወጥቶ የመዛመት እድሉ አናሳ ነው በሚል ነው። • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢታደል ችግሩ ምንድነው ? በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እስካሁን ድረስ በወረርሽኙ ምክንያት 1ሺህ 600 ሰዎች ሞተዋል። በዚህ ሳምንት ሚሊየኖች በሚኖሩባት ጎማ በበሽታው የተያዘ ቄስ መሞቱ ተሰምቷል። ጎማ በዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ሩዋንዳ ድንበር የምትገኝ ከተማ ስትሆን፤ ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ያለባት ስፍራ ነች። ወረርሽኙ በዚች ከተማ መከሰቱን የዓለም ጤና ድርጅት "ሁኔታውን ሊቀይር የሚችል" ያለው ሲሆን፤ ከጎማ ውጪ ግን ስለመዛመቱ እስካሁን የተሰማ ነገር የለም። ይህ የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጠው የአስቸኳይ ምላሽ ጥሪ ከፍተኛው ሲሆን፣ ድርጅቱ ከዚህ በፊት ሦስቴ ብቻ እንዲህ አይነት ጥሪዎችን አስተላልፏል። • በአዲስ አበባ ቢያንስ 3.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ትራንስፎርመሮች ተሰረቁ ከእነዚህም መካከል አንዱ ከ2014 እስከ 2016 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በምዕራብ አፍሪካ የኢቦላ ወረርሽኝ ተከስቶ 11ሺህ ሰዎችን በገደለበት ወቅት ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በጄኔቫ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅትና አስቸኳይ ትኩረት እንደሚሻ ባወጁበት መግለጫ ላይ "ጊዜው ዓለማችን ማስጠንቀቂያውን የሚወስድበት ነው" ብለዋል። የጉዞ ገደብ ሊደረግ እንደማይገባ የተሰጡ ምክረ ሀሳቦችን ድርጅቱ መቀበሉን የተናሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ አክለውም ንግድ፣ እንዲሁም ወረርሽኙ በተከሰተበት አካባቢ ከሚገኙ አገራት ውጪ በአየር መንገድና ወደብ መግቢያዎች ላይ የሚደረግ የጤና ፍተሻም መኖር የለበትም ሲሉ ተናግረዋል። የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ድርጅቶች ይህንን ውሳኔ በመልካም ጎኑ የተቀበሉት ሲሆን፤ " በወረርሽኙ የተጠቁ ግለሰቦችንና ቤተሰቦቻቸው ሕይወት ላይ ለውጥ ባያመጣም ዓለም ለዚህ የጤና ቀውስ ተገቢውን ትኩረት መስጠት ይኖርበታል" ብለዋል በመግለጫቸው። የኢቦላ ወረርሽኙ በዓለማችን ታሪክ ከተከሰቱት ሁለተኛው ሲሆን በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሁለት አውራጃዎች በስፋት ተከስቷል። እስካሁን ከ2500 ሰዎች በላይ የተያዙ ሲሆን ከዚህም አብዛኞቹ ሞተዋል። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች በየእለቱ 12 አዳዲስ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ይገኛሉ። በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1ሺህ ለመድረስ 224 ቀናት ብቻ የፈጀበት ሲሆን 2ሺህ ለመድረስ ግን ተጨማሪ 71 ቀናት ብቻ ናቸው የወሰደበት። ከዚህ ቀደም ከተከሰተው ወረርሽን ወዲህ እጅግ ውጤታማ የሆነ ክትባት የተገኘ ሲሆን በበሽታው የተያዙ አልያም ከተያዘ ሰው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 161 ሺህ ሰዎችም ክትባቱ ተሰጥቷቸውከበሽታቸው ተፈውሰው ነበር። ነገር ግን ሁሉም ሰው ስላልተከተበ ወረርሽኙ በድጋሚ ሊከሰት ችሏል። የዓለም ጤና ድርጅት ወረርሽኙ በተከሰተበት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዙሪያ ወደሚገኙ ሀገራት የመዛመት እድሉ ከፍተኛ ነው ያለ ሲሆን እስካሁን ኡጋንዳና ሩዋንዳ ውስጥ በሽታው መከሰቱ ታይቷል።
news-52818879
https://www.bbc.com/amharic/news-52818879
ጆርድ ፍሎይድ፡ የጥቁር አሜሪካዊው ግድያ ተከትሎ በሚኒያፖሊስ ተቃዋሚዎች እና ፖሊስ ተጋጩ
በሚኒያፖሊስ ከተማ ነጭ ፖሊስ ያልጣጠቀ ጥቁር አሜሪካዊ አንገትን በጉልበቱ እረግጦ ለሞት ማብቃቱን ተከትሎ በአሜሪካ ቁጣ ተቀስቅሷል።
ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ለመተኮስ ተገዷል በሜኒሶታ ግዛት ሚኒያፖሊስ ከተማ ፖሊስ እና ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ተጋጭተዋል። በብስጭት አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች ፖሊስ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመበተን አስልቃሽ ጭስ ተኩሷል። በማኅበራዊ ሚዲያ በአስደንጋጭ ፍጥነት በተሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ ነጭ ፖሊስ እጁ ወደኋላ የታሰረውን ጥቁር አሜሪካዊ አንገት በጉልበቱ ተጭኖት ፊቱን ከመሬት አጣብቆ ይዞት ይታያል። ጥቁር አሜሪካዊው በበኩሉ "መተንፈስ አልቻልኩም እባክህን አትግደለኝ" እያለ ሲማጸነው ይሰማል። ይህ ነጭ ፖሊስን ይህን ሲፈጽም ሌሎች ሦስት ፖሊሶች ከጎኑ ቆመው ነበር። ሟቹ የ46 ዓመት ጎልማሳ ጆርጅ ፍሎይድ ይባላል። አራቱ ፖሊሶች ከሥራ መባረራቸው ተነግሯል። ይህ ዘግናኝ ክስተት ከዓመታት በፊት በተመሳሳይ ቁጣን የቀሰቀሰውና በነጭ የፖሊስ አባላት ጭካኔ የሞተውን ኤሪክ ጋርነርን ያስታወሰ ሆኗል። ኤሪክ በወቅቱ በፖሊስ አንገቱ ተቆልፎ "እባካችሁ መተንፈስ አልቻኩም" እየለ ነበር የሞተው። በተቋሞ ሰልፉ ምን ተፈጠረ? የታቀውሞ ሰልፎቹ የጀመሩ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ማክሰኞ ከሰዓት ነው። ሰዎች ነጩ ፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊውን አንቆ የያዘበት ስፍራ ለተቃውሞ ተሰባስበዋል። የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጆቹ ሰዎች ርቀታቸውን እንዲጠበቁ እና የታቀውሞ ሰልፉ ሰላማዊ እንዲሆን ሲጥሩ ነበር። ለሰልፍኞቹ "መተንፈስ አልቻለኩም" እና "እኔ ልሆን እችል ነበር" የሚሉ መፈክሮችን ደጋግመው ሲያሰሙ ነበር። አንድ ለተቃውሞ ሰልፍ የወጣች ሴት ለሲቢኤስ "ይህ እጅግ አስቀያሚ ነገር ነው። ፖሊስን ይህን አይነት ሁኔታ የፈጠረው እራሱ መሆኑን ማወቅ አለበት" ብላለች። ሌለኛው ሰልፈኛ ደግሞ "ተንበርክኬ የሰላም ምልክት እያሳኋቸው አስልቃሽ ጭስ ተኮሱብኝ" ብሏል። ፖሊስ ለተቃውሞ ከወጡት መካከል አንዱ በጥይት መመታቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ ግለሰቡ የደረሰበት ጉዳት ህይወቱን አደጋ ላይ የሚጥል አይደለም ከማለት ውጪ ዝርዝር መረጃ ሳይሰጥ ቀርቷል። የሆነው ምን ነበር? ሰኞ በሚኒሶታ ሜኒያፖሊስ ያጋጠመው ክስተት ለ10 ደቂቃ ያህል የቀረጹ የአይን እማኞች ፖሊሱ ጉልበቱን ከተጠርጣሪው አንገት እንዲያነሳ ሲጠይቁት በተንቀሳቃሽ ምሥሉ ይታያል። በምሥሉ ላይ ሟችም "መተንፈስ አልቻልኩም ከማለቱም በላይ እባክህን አትግደለኝ" እያለ በተደጋጋሚ ሲማጸን ያሳያል። ሌላ የዐይን እማኝ "እባክህን አፍንጫውን እየነሰረው ነው" ሲል ፖሊሱን ይማጸነዋል። ፖሊሱ ምንም ምላሽ አይሰጥም፤ ሆኖም ሌላ የፖሊስ ባልደረባ ቀረጻውን በመከለል ለማስተጓጎል ሲሞክር ይታያል። በቪዲዮው ላይ ሌላ የዐይን እማኝ "አሁን የገደልከው ይመስለኛል፤ ይህ ድርጊትህ ሕይወትህን ሙሉ ይከተልሃል" ሲል ይሰማል። ከዚህ በኋላ ተጠርጣሪው እንቅስቃሴ አልባ ሆኖ ይዝለፈለፋል። አምቡላንስ መጥቶም ይወስደዋል። ምናልባት ግለሰቡ በዚያው ቅጽበት ሞቱ እንደሆነም ተጠርጥሯል። ፖሊስ ግን ግለሰቡ የሞተው ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ነው ይላል። ጆርድ ፍሎይድ
sport-50890496
https://www.bbc.com/amharic/sport-50890496
"የዘረኝነት ጥቃቱ ከዚህም በላይ ሊከፋ ይችላል" ንጎሎ ካንቴ
ትናንት ምሽት በነበረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቶትንሃም ከቼልሲ ጋር ሲጫወቱ በጥቁር ተጫዋቾች ላይ በተለይም በቼልሲው ተከላካይ አንቶንዮ ሩዲገር ላይ ያነጣጠረ የዘረኝነት ስድብ ከደጋፊዎች በኩል ተሰምቷል።
የቶትንሃምና የቼልሲ ተጫዋቾች ሜዳ ውስጥ ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር መንግሥት ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ የሚከሰቱትን የዘረኝነት ድርጊቶች መርምሮ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል። የቶተንሃም ቡድንም በክስተቱ ላይ ጥልቅ ምርመራ እንደሚያደርግና "ጠንከር ያለ እርምጃ" እንደሚወስድም አሳውቋል። በጥቁር ተጫዋቾች ላይ የተሰነዘረውን የዘረኝነት ድርጊት ተከትሎ ጨዋታው ለአጨር ጊዜ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ በስታዲየሙ ውስጥ ባሉ የድምጽ ማጉያዎች በኩል "የዘረኝነት ባህሪ በጨዋታው ላይ እንቅፋት" እየሆነ መሆኑ ለተመልካቾች ተገልጾላቸዋል። • "እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" መሠረት ማኒ • "በአንድ ጨዋታ ሰባት ግቦችን በማስቆጠር ታሪክ መስራቴ አስደስቶኛል" ሎዛ አበራ • «እግር ኳሰኞች ከማሕበራዊ ሚድያ እራሳቸውን ማግለል አለባቸው» ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረገው የቼልሲው የመሃል ሜዳ ተጫዋች ንጎሎ ካንቴ "የእግር ኳሱ የበላይ ኃላፊዎች ጉዳዩን በአንክሮ ካልመረመሩት የዘረኝነት ጥቃቱ ከዚህም በላይ የከፋ ሊሆን ይችላል" በማለት የጉዳዩን አሳሳቢነት ተናግሯል። በጉዳዩ ላይ ከዚህም በላይ መነጋገር ለተጫዋቾች የግድ አስፈላጊ ነው ብሎ ያምናል ካንቴ። በሁለተኛው አጋማሽ ደጋፊዎች ሲናገሩት የነበረው ነገር "አጸያፊ ነው፤ በእግር ኳስ ውስጥ ይህ መኖር አልነበረበትም። ነገር ግን ጤናማ እግር ኳስ ይኖረን ዘንድ እኛም ተገቢውን ምላሽ ሰጥተን ማስተካከል የሚኖርብን ይመስለኛል" ብሏል የቼልሲው ኮከብ። በእርግጥ "የተባለውን ነገር አልሰማሁም ነበር" የሚለው ካንቴ የቡድኑ አምበል አዝፒሊኬታ ጉዳዩን ለዳኛው ሲያመለክት ነበር "ጥቃት እየሰነዘሩብን እንደነበር የገባኝና እኔም ማዳመጥ የጀመርኩት" በማለት በጨዋታው የደረሰባቸውን የዘረኝነት ጥቃት እንዴት እንደተረዳ ለቢቢሲ አስረድቷል። ይህንን ድርጊት ለማስተካከል በየደረጃው የሚገኙ የእግር ኳሱ የበላይ ጠባቂዎች የመፍትሔ አማራጮችን እንዲያስቀምጡም ካንቴ ጥሪውን አቅርቧል። "ዳኞች አሉ፣ የፕሪሚየር ሊጉ የበላይ አካል አለ፤ ስለዚህ እነሱ መፍትሔ ያመጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። መፍትሔው እንዲመጣ ግን የሆነውን ነገር ለሚመለከታቸው አካላት ማመልከት ከእኛ የሚጠበቅ ነው" ያለው ካንቴ "ችግሩን ለመቅረፍ እየሞከሩ እንደሆነ አምናለሁ፤ ነገር ግን እንዴት ሊያስተካክሉት እንደሚችሉ በጋራ የምናየው ይሆናል ብሏል የፈረንሳይና የቼልሲው የመሃል ሜዳ ተጫዋች ንጎሎ ካንቴ።
news-54157750
https://www.bbc.com/amharic/news-54157750
ኢራን የጄነራል ሱለይማኒን ደም ለመበቀል የአሜሪካ አምባሳደርን ለመግደል እያሴረች ነው?
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ማንኛውንም የአሜሪካ ዲፕሎማት ከገደለች አይቀጡ ቅጣት እቀጣታለሁ ሲሉ ዛቱ፡፡
ይህን ያሉት ኢራን በደቡብ አፍሪካ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑትን ላና ማርክስን ለመግደል ኢራን እያሴረች ነው የሚል መረጃ መውጣቱን ተከትሎ ነው፡፡ ኢራን በማንኛውም መንገድ በየትኛውም የአሜሪካ ዲፕሎማት ላይ ጥቃት ከፈጸመች "የእጇን እንሰጣታለን" ያሉት ትራምፕ" ቅጣቱ ደግሞ የድርጊቷን 1ሺ እጥፍ የሚበልጥ ይሆናልም" ብለዋል፡፡ ይህን ያሉት ሰኞ በትዊተር ሰሌዳቸው በጻፉት ማስታወሻ ነው፡፡ ኢራን ግድያ እያሴረች ነው የሚለውን መረጃ ይፋ ያደረገው ፖለቲኮ የተባለ ጋዜጣ ነው፡፡ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሰኢድ ካቲብዛድ የጋዜጣውን ዘገባ "ቅጥፈት" ብለውታል፡፡ የፖለቲኮ ጋዜጣ እንደሚያወሳው ኢራን በደቡብ አፍሪካ የአሜሪካ አምባሳደርን ለመግደል የመረጠችው አምባሳደሩ የዶናልድ ትራምፕ የረዥም ጊዜ ወዳጅ በመሆናቸው ነው፡፡ የግድያው ዓላማም ባለፈው ጥር በአሜሪካ የተገደለባትን የተወዳጁን ጄኔራሏን ቃሲም ሱለይማኒን ደም ለመመለስ ነው፡፡ ጄኔራል ሱለይማኒ በጥር ወር በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን የተገደለው በባግዳድ አየር መንገድ አውሮፕላን ሊሳፈር በነበረበት ቅጽበት ነበር፡፡
news-51541563
https://www.bbc.com/amharic/news-51541563
በኮሮናቫይረስ ምክንያት የግል አውሮፕላን ተፈላጊነት በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የግል አውሮፕላኖች ተፈላጊነት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
የግል አውሮፕላኖችን የሚያከራዩ ኩባንያዎች ከመንገደኞች በርካታ ጥያቄ እየቀረበላቸውም ነው ተብሏል። በርካታ የአየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ መሰረዝ እንዲሁም ቁጥሩን መቀነሳቸው ወደየአገራቸው መሄድ የሚፈልጉ መንገደኞችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። •''ኮሮናቫይረስን ወደ አፍሪካ መውሰድ አልፈልግም'' •ኢትዮጵያውያን፡ የአስወጡን ድምጽ በጎሉባት የቻይናዋ ዉሃን ወደ ቻይና መሄድ የሚፈልጉ እንዲሁም ከቻይና መውጣት የሚፈልጉ ግለሰቦች በረራዎችን በመፈለግ በተጠመዱበት ሰዓት በግላቸው አውሮፕላን መከራየት የሚችሉት ደግሞ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከፍለው ባመቻቸው ቀንና ሰዓት መጓዝ እንደቻሉ እየተዘገበ ነው። ነገር ግን ምንም እንኳን ግለሰቦቹ "ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ" በሚለው እየተመሩ ቢሆንም ጥያቄያቸው ግን በአንዳንድ ኩባንያዎች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም። ለዚህም ደግሞ እንደ ምክንያትነት የተቀመጠው የአውሮፕላን ሠራተኞች በስጋት ምክንያት ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ነው። በአውስትራሊያ ተቀማጭነቱን ያደረገው ዳሪን ቮይልስ እንዳስታወቀው በእነዚህ ጥቂት ሳምንታት አውሮፕላኖቻቸውን ለመከራየት ከፍተኛ ፍላጎት ያለ ቢሆንም፤ አብዛኛዎቹን በአውሮፕላንና በሠራተኞች እጥረት ለመመለስ ተገደዋል። •ሆንግ ኮንግ፡ በኮሮና ምክንያት በተከሰተ እጥረት አንድ ቡድን የሶፍት ጥቅሎችን ዘረፈ •ኮሮና ቫይረስ መጠሪያ ስሙን አገኘ ብዙዎች አውሮፕላኖቻቸውንም ሆነ ሠራተኞቻቸውን ወደ ቻይና መላክ አይፈልጉም። ሠራተኞች በቫይረሱ ይያያዛሉ ብሎ ከመስጋት በተጫማሪ ለቢዝነሱም አዋጭ አይደለም፤ ምክንያቱም ቻይና ደርሰው ከተመለሱ በኋላ ለሁለት ሳምንታት ያህል ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጋቸው ነው። ይህም ማለት በእነዚህ ቀናት አውሮፕላኖቻቸው ሥራ ፈትተው ይቆያሉ ማለት ነው። በሲንጋፖር ተቀማጭነቱን ያደረገው ማይሌት ኤዥያ በበኩሉ ባለፈው ወር ብቻ ከ80-90 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። "የቻይና አዲስ ዓመት በዓል በሚከበርበት ወቅት ብዙዎች ከቻይና ወጥተው ነበር አሁን ደግሞ ወደ ቻይና ለመመለስ ትግል ላይ ናቸው" በማለት የማይሌት ኤዥያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተናግረዋል። ብዙዎቹንም ወደ ቤይጂንግ፣ ሻንጋይና ሆንግ ኮንግ አድርሰዋቸዋል። "ምንም እንኳን ወደ ቻይና ብንበርም አንዳንድ ቦታዎች አይፈቀደልንም፤ መንገደኞች ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ቢሆኑም አንዳንድ አየር መንገዶች በነፃነት እንድንቀሳቀስ አይፈቅዱልንም" ብለዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች ከቻይና ለመውጣት ቀን ተሌት ትግል ላይ ናቸው። ከደቡብ አሜሪካ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ በመቶዎች የሚቆጠሩ መንገደኞችን ከዉሃን እንዲወጡ የግል አውሮፕላኖችን እንዲከራዩለት ጥያቄ እንደቀረበላቸው የፕራይቬት ፍላይ ሥራ አስፈፃሚው አዳም ቲዊደል ገልፀዋል። በእንግሊዝ ተቀማጭነቱን ያደረገው ኩባንያ በበኩሉ ከግለሰቦች እንዲሁም በቡድን አውሮፕላን እንፈልጋለን የሚሉ ጥያቄዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚመጡለት ነው። ቀለል ያለ አውሮፕላን ከ2 እስከ አራት መንገደኞችን የሚያሳፍር ሲሆን በሰዓት 77 ሺህ ብር የሚገመት እንደሚያወጣ ፖራማውንት ቢዝነስ ጄትስ የሚባል ኩባንያ አስታውቋል። •ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች •የጤፍ ባለቤትነት መብት ከኢትዮጵያ እጅ እንዴት ወጣ? መካከለኛ የሆኑ አውሮፕላኖች ደግሞ ከ8- 10 ሰዎችን የመያዝ አቅም አላቸው፤ በሰዓትም 192 ሺህ ብር ያስከፍላሉ። ግሎባል ፕራይቬት የተባለው ኩባንያም ምንም እንኳን ምንም ወደ ቻይና የሚያደርጋቸውን በረራዎች በሙሉ የሰረዘ ቢሆንም ጥያቄዎች ግን በእጥፍ እንደጨመሩ ነው። ምንም እንኳን ፍላጎት በከፍተኛ መጠን ያሻቀበው በተወሰነ መልኩ ከቻይና አዲስ ዓመት ጉዞዎች ጋር የተያያዘ ቢሆንም በዋነኝነት ግን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ግለሰቦች ከሌሎች መንገደኞች ጋር ለመጓዝ አለመፈለጋቸውን ቪስታ ጄት የተባለው ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ይናገራሉ። በጎርጎሳውያኑ 2003 ከተነሳው ሳርስ ጋር በተያያዘም የግል አውሮፕላኖች ጥያቄ ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም በዚያን ጊዜ መውጣት መግባትም ቀላል ስለነበር እንዳሁኑ በርካታ አልነበሩም ተብሏል። በአሁኑ ወቅተት መንግሥታት ከፍተኛ ቁጥጥርም እያደረጉ ያሉበት ጊዜ ነው።
news-52878990
https://www.bbc.com/amharic/news-52878990
ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ዝሆኖች በታጣቂዎች ተገደሉ
ባለፈው ሳምንት በደቡብ ክልል በሚገኘው የማጎ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ከዚህ ቀደም አጋጥሞ በማያውቅ ሁኔታ ስምንት ዝሆኖች መገደላቸው ተገለጸ።
የማጎ ብሔራዊ ፓርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጋናቡል ቡልሚ እና የደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ፍሬሕይወት ዱባለ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት በአንድ ቀን ውስጥ ስምንት ዝሆኖች ለጥርሳቸው ሲባል በታጠቁ ሰዎች ተገድለዋል። የማጎ ብሔራዊ ፓርክን በደንብ የሚያውቀው የቱሪዝምና ጉዞ ጋዜጠኛው ሄኖክ ስዩም እንደሚለው ይህ ግድያ እጅግ የከፋና ከዚህ ቀደም አጋጥሞ የማያውቅ በእንስሳቱና በአገር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ነው ብሏል። ማክሰኞ ግንቦት 18/2012 ዓ.ም በዝሆኖቹ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው በፓርኩ አቅራቢያ ባለው ኦሞ ወንዝ ላይ ውሃ በሚጠጡበት ጊዜ በርካታ ጥይት ተተኩሶባቸው እንደሆነና ጥርሳቸውም እንደተወሰደ የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ ገልጸዋል። በዝሆኖቹ ላይ ጥቃቱን ከፈጸሙት ሰዎች መካከል ሁለቱ በዝሆኖቹ አማካይነት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ወ/ሮ ፍሬሕይወት አንደኛው ከዚህ ቀደም በወረዳ አመራር ውስጥ የነበረ ግለሰብ እንደሆነ ጠቅሰው መንግሥት በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል ብለዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በተደረገ ቆጠራ በማጎ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ 175 ዝሆኖች ይገኙ አንደነበረ የገለጹት አቶ ጋናቡል በስምንቱ ዝሆኖች ላይ የተፈጸመው ግድያ ከዚህ በፊት ያልታየ "ጭፍጨፋ" ነው ሲሉ በምሬት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዝሆኖቹ ላይ ግድያውን የፈጸሙት ሰዎች አስበውና ተዘጋጅተው ለጥርሳቸው ሲሉ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ጋናቡል አንድ ዝሆን ከ30 በላይ በሆነ ጥይት መመታቱን እንዳረጋገጡ ገልጸው ድርጊቱን "ዘር ማጥፋት ነው" ሲሉ ገልጸውታል። በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች አርብቶ አደሮችና የታጠቁ በመሆናቸው በፓርኩ ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠርና በእንስሳቱ ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም አስቸጋሪ እንዳደረገው የሚናገሩት የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ ይህ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ጠቁመዋል። ሄኖክ ስዩም እንደሚለው ተጎራብተው በሚገኙት በማጎና በኦሞ ብሔራዊ ፓርኮች በአጠቃላይ 600 ያህል ዝሆኖች የሚገኙ ሲሆን በተለያዩ ወቅቶች በሚፈጸሙ ግድያዎች የዝሆኖቹ ቁጥር ሳያንስ እንደማይቀር ይናገራል። ሄኖክ ጨምሮም ጥቃቱ በዝሆኖቹ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሳይሆን የፓርክ ጠባቂዎችም ኢላማ ናቸው ይላል። "ዝሆኖቹን ለማደን የሚመጡት ሕገወጦች የፓርኩን በሚጠብቁ ስካዉቶች ላይ ጥቃት ይፈጽማሉ።" የማጎ ብሔራዊ ፓርክ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጋናቡል ቡልሚም ይህ ስጋት እውነት እንደሆነ ጠቅሰው ጠባቂዎቹ ዝሆኖቹን ለመከላከል እርምጃ ሲወስዱ እንደሚጠየቁ እንደዚሁም ለአደጋ እንደሚጋለጡ ጠቅሰው፤ " ባለፈው ዓመት አንድ አባላችን ሲገደል እስካሁን ከአስር በላይ በሕገ ወጦች ጥቃት ተገድለዋል።" እንዲህ አይነት በሰዎችና በእንስሳቱ ላይ ወንጀሎች ሲፈጸሙ ጉዳዩ የአገር ሽማግሌዎች ተይዞ ያለተገቢ ቅጣት ስለሚታለፍ ድርጊቱ እንዲደገም ይበረታታል። ለፓርኮቹና ጠባቂዎቹ ተገቢው ከለላና አስፈላጊ የመከላከያ መሳሪያ ካልተሰጠ ተመሳሳይ ነገር ማጋጠሙ አይቀርም ይላል ሄኖክ። ለአሁኑ ጥቃትም ያለው አለመረጋጋትና የመንግሥት ትኩረት በኮናቫይረስ ወረርሽኝ ላይ መሆኑን ተገን ተደርጎ እንደሆነ በመግለጽ ጥብቅ እርምጃና ትኩረት ለፓርኮቹ እንዲሰጥ አሳስቧል። ወ/ሮ ፍሬህይወት እንደሚሉት የክልሉና የዞኑ መስተዳደር አጥቂዎችን ለይቶ ለሕግ ለማቅረብ አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። "ወንጀለኞቹን አጋልጦ ለሕግ በማቅረብ ቀጣይ ጥቃቶችን በማያዳግም እርምጃ ለማስቆም እየሰራን ነው" ብለዋል። በዝሆኖቹ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ክፉኛ ያዘነው ሄኖክ ስዩም፤ "ኢትዮጵያ ዝሆኖችን ለመጠበቅ ስምምነት ፈርማለች ቀላል የማይባል ድጋፍም እያገኘች ነው። ነገር ግን በማጎ እና በባቢሌ ፓርኮች ውስጥ በዝሆኖች ላይ ተደጋጋሚ ችግር እየደረሰ ነው" በማለት የጉዳቱን አሳሳቢነት አመልከቷል። ዝሆኖቹ ላይ የሚደርሰው ጉዳት በዚህ ከቀጠለ ሊጠፉ እንደሚችሉ የሚሰጋው ሄኖክ አገሪቱ ለእንስሳቱ ጥበቃና ከጎብኚዎች የምታገኘው ገቢ ከመቆሙ ባሻገር ለትውልድ ተጠብቀው መተላለፍ ያለባቸውን ሐብቷን ታጣለች ይላል። ከሁሉ ያሳዘነው ደግሞ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ዝሆኖች ተገድለው "የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል ኃላፊዎች የወሰዱት ፈጣን እርምጃ ያለመኖሩ ነው።"
news-54001763
https://www.bbc.com/amharic/news-54001763
የእስራኤሉ ወታደር የፍልስጤማዊው አንገት ላይ መቆሙ ቁጣን ቀሰቀሰ
የእስራኤል ጦር አባል ለተቃውሞ የወጡት ፍልስጤማዊ አዛውንት አንገትን በጉልበቱ አፍኖ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ከወጣ በኋላ ቁጣን ቀስቅሷል።
የእስራኤሉ ወታደር ፍልስጤማዊ ተቃዋሚ አንገት ላይ ቆሞ ካሂሪ ሃኑን የተባሉት ዝነኛው ተቃዋሚ አዛውንት እጆቻቸው ወደኋላ ታስሮ፤ ፊታቸው ከመሬት ጋር ተጣብቆ የእስራኤል ወታደር አንገታቸው ላይ በጉልበቱ ቆሞ የሚያሳየው ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። ምስሉ የተቀረጸው ትናንት ፍልስጤማውያን በዌስት ባንክ ለተቃውሞ በወጡበት ወቅት ነው። ወታደሩ በጉልበቱ የካሂሪ ሃኑን አንገት ላይ ለ50 ሰከንዶች ያክል ተጭኖ ቆይቷል። ይህም በፍልስጤማውያን ዘንድ ሌላ ታቃውሞን ቀስቅሷል። የእስራኤል ጦር ግን የጦር አባላቱ የነበረውን ሁኔታ ለመቆጣጠር ተመጣጣኝ እርምጃ ነው የወሰዱት ብሏል። ተንቀሳቃሽ ምስሉም የግጭቱን ሙሉ ምስል አያሳይም፤ በጦር አባላቱ ላይ ሲደርስ የነበረውን ጥቃትም አያስመለክትም ብሏል። ጦሩ ጨምሮ ወደ 200 ሰዎች ግጭት በተስተዋለበት የተቃውሞ ስልፍ ላይ መሳተፋቸውን እና በጦሩ አባላት ላይ ድንጋይ መወርወሩን አሳውቋል። የእስራኤል ጦር በመግለጫው ካሂሪ ሃኑን በእስራኤል ጦር አባሉ ላይ ተደጋጋሚ ትንኮሳ መፈጸማቸውን እና አባላቱ በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጥረት ተባባሪ ሳይሆኑ በመቅረታቸው እርምጃው እንዲወሰድባቸው ግድ መሆኑን አብራርቷል። ካሂሪ ሃኑን ጥቃቱ ከደረሰባቸው በኋላ ለአንድ የእስራኤል ጋዜጣ “በቁጥር አስተኛ የሆንን በእድሜ የገፋን አዛውንቶች ወታደሮቹ ጉዳት አያደርሱብንም ብለን ተሰባስበን ለተቃውሞ ወጣን። ልክ እንደ ሌባ ጉዳት አደረሱብን” ሲሉ ተናግረዋል። ካሂሪ ሃኑን ክስተቱን ከአሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ጋር አዛምደውታል። ግንቦት ወር ላይ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ነጭ የፖሊስ አባል በጉልበቱ አንገቱ ላይ ለረዥም ደቂቃዎች ከቆመ በኋላ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል። “ያን አይነት ስሜት ነው የተሰማኝ። አፍኖኝ ነበር” ብለዋል ካሂሪ ሃኑን።
news-49875116
https://www.bbc.com/amharic/news-49875116
ካዱና ትምህርት ቤት፡ "ማሰቃያ ቤቱ እንደ ሲኦል ነው"
በናይጀሪያ አንድ ማሰቃያ ቤት ታጉረው የነበሩ በርካታ ሰዎች ፖሊስ ባደረገው ክትትል ነፃ መውጣታቸው ይታወሳል። ከእነዚህ ፖሊስ ከታደጋቸው ግለሰቦች አንዱ የሆነው ኢሳ ኢብራሂም ሁኔታው በገሃነመ እሳት ውስጥ እንደመኖር ነው ሲል ይገልፀዋል።
የ15 ዓመቱ ሕፃን በድብደባው የደረሰበትን ጠባሳ አሳይቷል። "ስትፀልይም፤ ስታነብም ይበድቡሃል" ሲል የ29 ዓመቱ ኢሳ ለቢቢሲ ተናግሯል። ሕፃናትን ጨምሮ ቁጥራቸው 500 የሚሆኑ ወንዶች በናይጀሪያ ካዱና በሚገኝ እና ለእስልምና ትምህርት ቤት ያገለግል ከነበረ ሕንፃ በፖሊስ እርዳታ ነፃ ወጥተዋል። ፖሊስ እንዳስታወቀው ቦታው ሰዎች በባርነት የተሰቃዩበትና አብዛኞቹ በእግረ ሙቅ ታስረው ነበር የተገኙት። • 500 ወንዶች ታጉረውበት ከነበረው ህንጻ ነፃ ወጡ • ናይጀሪያዊቷ ልጆቿን ልትሸጥ ስትል ተያዘች አንዳንዶቹ ተጠቂዎች የተሰቃዩ ሲሆን የወሲብ ጥቃትም የደረሰባቸው መኖራቸውን የአገሪቷ ባለሥልጣን አስታውቋል። የማጎሪያ ህንፃውን የጎበኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ኢሳቅ ካሊድ እንዳለው ተመሳሳይ ድርጊቶች የሚፈፀሙባቸው ሌሎች ተቋማት ሊኖሩ እንደሚችል ጥርጣሬ አላቸው። በናይጀሪያ አብዛኛው ቤተሰብ ልጆቻቸውን ወደ ትምርት ቤት ለመላክ አቅማቸው ስለማይፈቅድ በቂ ክትትልና ቁጥጥር የማይደረግባቸው ወደ እንደዚህ ዓይነት ተቋማት ይልካሉ። በዚህ ተቋም ፊት ለፊት 'አህመድ ቢን ሃምበል የእስልምና ትምህርት ማዕከል' የሚል ማስታወቂያ ተሰቅሎ የሚታይ ሲሆን መጥፎ ሥነ ምግባር ያላቸውን ወጣት ወንዶች በባህሪ ለማረቅ ይጠቀሙበትም እንደነበር ተመልክቷል። የካዱና ግዛት ፖሊስ ቃል አቀባይ ኩቡ ሳቦ "ይህ የሰብዓዊ ጥሰት የተፈፀመበትን ቦታ የእስልምና ትምህርት ቤት ነው ለማለት ያስቸግራል" ብለዋል። ቦታው ከወላጆች ክፍያ ሲቀበል የነበረ ቢሆንም እንደ ትምህርት ቤትም ሆነ እንደ የባህሪ ማረሚያ ተቋም የተመዘገበ አለመሆኑን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የተወሰኑ የተቋሙን ሠራተኞች ጨምሮ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊት የሚፈፀምባቸው ተቋማት ካሉ ለማጣራት ተጨማሪ ምርመራ እያደረኩ ነው ሲል መንግሥት አስታውቋል። በተለይ በሰሜን ናይጀሪያ ክፍል የፀባይ ማረሚያ ትምህርት ቤቶች ጥቃት እንደሚፈፀም የተለያዩ መረጃዎች ይወጣሉ። አንዳንድ ጊዜ ተማሪዎቹ በትርፍ ጊዜያቸው በጎዳና ላይ ለልመና እንዲወጡ ይገደዳሉ ብሏል ሪፖርቱ። ኢሳ ኢብራሂም ባህሪውን ለማረቅ ሲሉ ወላጆቹ ወደ ትምህርት ቤት የላኩት ከሁለት ሳምነንታት በፊት ነበር። እርሱ እንደሚለው ፖሊሶቹ ከመድረሳቸው አንድ ቀን አስቀድሞ ለማምለጥ ሞክሮ ነበር። እግሮቹ በሰንሰለት ታስረው ከአንድ አሮጌ ጀኔሬተር ጋር አቆራኝተውት ስለነበር ማምለት አልቻለም። ኢሳ ጭካኔ የተሞላበት ድብደባም ይፈፀምበት እንደነበር ይገልፃል። ቅጣቱ 'ታርኪላ' ይሰኛል እጃቸው ወደላይ ታስሮ ከጣሪያ ላይ እንዲንጠለጠል በማድረግ ነው የሚፈፀመው። • ቀነኒሳ 'ከሞት እንደመነሳት' ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ "በጣም ብዙ ጉዳቶች ደርሰውብኛል፤ ሁሉም የሰውነት ክፍሌ ተጎድቷል፤ ብንተኛ እንኳን ከእንቅልፋችን እየቀሰቀሱ ይደበድቡናል" ይላል። ኢሳ እንደሚለው ምግብ ይሰጧቸው እንዳልነበርና ከሰጧቸውም ነጭ ሩዝ ብቻ እንደነበር ይናገራል። በሕንፃው ውስት የነበሩት ሰዎች ምግብ ስለማይሰጣቸው አቅማቸው ተሟጦ አልቆ ነበር። ከአምስት ዓመት የሚያንሱ ሕፃናት ነፃ ከወጡት የሚገኙበት ሲሆን አብዛኞቹ ከናይጀሪያ ሲሆኑ ሁለቱ ግን ከቡርኪና ፋሶ የመጡ እንደሆኑም ተዘግቧል። የካዱና ባለሥልጣናት በግዛቷ የሚገኙ ሌሎች የእስልምና ትምህርት ቤቶች ላይ ፍተሻ እንደሚደርጉ አስታውቀዋል።
news-49575767
https://www.bbc.com/amharic/news-49575767
ፍልስጤማዊው የሃርቫርድ ተማሪ ወደ አሜሪካ እንዲገባ ተፈቀደለት
ጓደኞቹ ፌስቡክ ላይ በለጠፉት ጽሑፍ ምክንያት ብዙ ባወዛጋቢ መልኩ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ተከልክሎ የነበረው ፍልስጤማዊው ተማሪ ሰኞ ዕለት ወደ አሜሪካ እንዲገባ ተፈቀደለት።
በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ለመከታተል አሜሪካ ቦስተን አየር ማረፊያ ከደረሰ በኋላ ለረዥም ሰዓታት በአሜሪካ ድንበር ተቆጣጣሪዎች ምረመራ እንደተደረገበት እስማኤል አጃዊ ተናግሯል። • ተማሪው 'በማህበራዊ ሚዲያው ፅሁፎች' አሜሪካ እንዳይገባ ታገደ • የእንግሊዝ ወላጆች በትምህርት ቤት ስልክ እንዲታገድ ለምን ይፈልጋሉ? የ17 ዓመቱ ተማሪ እስማኤል ሰኞ ዕለት ወደ አሜሪካ እንዲገባ ፍቃድ ማግኘቱን ተከትሎ ትምህርቱን መከታተል ጀምሯል። ከወራት በፊት የአሜሪካ መንግሥት ወደ አሜሪካ ማቅናት የሚሹ ሰዎች ቪዛ ሲያመለክቱ የሚጠቀሙትን የግል የማህበራዊ ሚዲያ አድራሻ እንደሚጠየቁ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የአሜሪካ የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ ባለስልጣን ለቢቢሲ እንደተናገረው ተማሪ እስማኤል አጃዊ ''ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ሊያስከለክሉ የሚችሉ ምክንያቶች ባለመኖራቸው ኤፍ1 ቪዛ ተሰጥቶታል'' ብሏል። በቅድሚያ ተማሪው ወደ አሜሪካ እንዳይገባ የተከለከለበት የሕግ አግባብ የቱ እንደሆነ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠበው ባለስልጣኑ፤ ''በወቅቱ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ከውሳኔ ላይ የተደረሰው የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ ባለስልጣናት ባገኙነት መረጃ ነው'' ብሏል። የተማሪው ወላጆች ''በስተመጨረሻም ቢሆን በተሰጠው ውሳኔ ደስተኛ ነን'' ሲሉ ተናግረዋል። ''ያለፉት 10 ቀናት በጣም አስጨናቂ ነበሩ። አሁን ግን ደስተኞች ነን። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለላኩልን የማጽናኛ መልዕክት ከልብ እናመሰግናለን" ብለዋል የተማሪው ወላጆች። ሃምዛ ራዛ የተባለ የሃርቫርድ ተማሪ እስማኤል ሃርቫርድ ከደረሰ በኋላ ፎቶግራፍ አብረው ተነስተው በትዊተር ገጹ ላይ ለጥፏል። እስማኤል እንደሚለው የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ቦስተን አየር ማረፊያ ከደረሰ በኋላ ላፕቶፕ እና የእጅ ስልኩን ከመረመሩ በኋላ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ እንደከለከሉት ተናግሯል። • የአይኤስ አባል የነበረችው አሜሪካ እንዳትገባ ተከለከለች ከሳለፍነው ሰኔ ጀምሮ የአሜሪካ መንግሥት ቪዛ አመልካቾች የሚጠቀሙትን የማህበራዊ ሚዲያ ድረ-ገጾች፣ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲጠቀሙበት የነበረውን የስልክ እና የኢሜይል አድራሻ መጠየቅ ጀምሯል። ይህ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሕግ በየዓመቱ ከ14.7 ሚሊዮን በላይ ከሚሆኑ ሰዎች መረጃዎችን እንደሚሰበስብ ታውቋል።
51577396
https://www.bbc.com/amharic/51577396
በአወዳይ በመንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ግጭት ተፈጠረ
በአወዳይ ከተማ በመንግሥት እና በተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች መካከል ግጭት መከሰቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
አወዳይ በኦሮሚያ ክልል በድሬ ዳዋ እና ሐረር ከተሞች መካከል ትገኛለች። ዛሬ ጠዋት (የካቲት 12/2012) የጠቅላይ ሚንስርት ዐብይ መንግሥት እና ፓርቲን ለመደገፍ የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ የወጡ ሲሆን፤ በተቃራኒው ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩን መንግሥት በመቃወም መፈክር እየሰሙ የወጡ ሰዎች እንደነበሩ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ የፖሊስ ባልደረባ ለቢቢሲ እንደተናገረው "ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ለመደገፍ ሰዎች ሰልፍ ወጡ። ከዛ ለምን ለድጋፍ ወጣችሁ የሚሉ ሌሎች ሰዎችም መውጣት ጀመሩ። ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚያወግዝ መፈክር በማሰማት ድንጋይ መወርወር ጀመሩ" በማለት የግጭቱን አጀማመር ያስረዳል። በድንጋይ ተመተው እና በዱላ ተደብድበው ጉዳት የደረሰባቸው ብዙ ሰዎች መኖራቸውን የፖሊስ አባሉ ተናግረዋል። ይህ የፖሊስ ባልደረባ እንደሚለው ከሆነ፤ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተከሰተውን ግጭት ለመበትን ፖሊስ በርካታ ጥይት ወደ ሰማይ መተኮሱን ተናግረው፤ በፖሊስ ኃይል በተተኮሰ ጥይት ጉዳት የደረሰበት ሰው ስለመኖሩ የማውቀው የለም ብለዋል። ሌላው የከተማዋ ነዋሪ "ባለፉት ቀናት የአከባቢው የመንግሥት ባለስልጣናት 'ለጠቅላይ ሚንስትሩ ድጋፋችሁን ለመግለጽ ሰልፍ ውጡ' እያሉ ነዋሪዎችን ሲያስጨንቁ ነበር" ይላል። ይህ የአወዳይ ከተማ ነዋሪ እንደሚለው ከሆነ ዛሬ ጠዋት ላይ ሰዎች ለድጋፍ ሲወጡ እነሱን የሚቃወሙ ሌሎች ሰዎችም አደባባይ መውጣት ጀመሩ። "በዚህ መካከል ከየት መጡ ሳይባል በርካታ የጸጥታ ኃይል አባላት ከተማዋን ወረው ግርግር ተፈጠረ ከዚያም ወደ ግጭት ተገባ" በማለት ይናገራል። ይህ የከተማዋ ነዋሪ እንደሚለው ከሆነ ድጋፍ ለመስጠት አደባባይ ወጡ የተባሉት ሰዎች ወደው እና ፍቅደው ሳይሆን በደረሰባቸው ጫና ነው ይላል። ቢቢሲ በሠልፉ ከተካፈሉ ሰዎች ነበረ ስለተባለው ጫና ለማረጋገጥ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካለትም:: በዚህም 'ለምን ያለ ፍላጎታችሁ ድጋፍ መስጠት አስፈለጋችሁ' ከሚሉ ሰዎች ጋር መጋጨታቸውን ያስረዳል። ይህ ነዋሪ እንደሚለው ከሆነ የጸጥታ ኃይሎች በሰዎች ላይ ድብደባ ፈጽመዋል። ሌላው የአከባቢ ነዋሪ ግጭቱ የተከሰተው ጠቅላይ ሚንስትሩን ለመደገፍ በወጡ እና እነሱን በተቃወሙ መካከል መሆኑን ያረጋግጣል። "መንገድ ዝግ ነበር። አሁን ላይ መኪኖች በመከላከያ እየታጀቡ ነው እያለፉ ያሉት" ሲል ያለውን ሁኔታ ያስረዳል። በዛሬው ዕለት (የካቲት 12 2012) በከተማዋ ስለተከስተው ነገር ከአካባቢው ባለስልጣናትና ከፖሊስ ለማጣራት ቢቢሲ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው ሳይሳካ ቀርቷል:: በተከሰተው ግጭት ሳቢያ በሰውና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ቢነገርም በትክክል ለማረጋገጥ አልተቻለም።
56485879
https://www.bbc.com/amharic/56485879
እነ አቶ ጀዋር መሐመድ የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ
አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ አምስት ተከሳሾች ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ. ም. የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ።
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት የፀረ ሽብርና የሕገ መንግስት ወንጀል ጉዳዮች አንደኛ ምድብ ችሎት በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር ካሉት 24 ተከሳሾች መካከል ባለፈው ሳምንት የ16ቱን የእምነት ክህደት ቃል ሰምቶ ነበር። ዛሬ ደግሞ የአምስት ተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ተቀብሏል። እነዚህም አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ፣ አቶ ሸምሰዲን ጠሀ እና አቶ ዓለማየሁ ገለታ ናቸው። ተከሳሾቹ በክስ መዝገቡ ውስጥ የተጠቀሱትን ድርጊቶች አንዳልፈጸሙና ምንም ጥፋት አንደሌለባቸው ለፍርድ ቤቱ መናገራቸውን ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ ኢብሳ ገመዳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ጀዋር፤ "እነዚህን የተባሉትን ድርጊቶች ለመፈጸም የሚያስችል ማንነት የለኝም" በማለት የተከሰሱበትን ድርጊቶች እንዳልፈጸሙ ለፍርድ ቤቱ መናገራቸውን ጠበቃቸው አስረድተዋል። በአቶ ጀዋር ላይ ከቀረቡት ክሶች አንዱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አባቶች (አምስት ጳጳሶች እና ሁለት አገልጋዮች) እንዲገደሉ ማስተባበር የሚል ነው። አቶ ጀዋር ቤተሰቦቻቸው የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ መሆኑን ጠቅሰው "በሃይማኖት አባቶች ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚያስችላቸው ሁኔታ አንደሌለ" ተናግረዋል። በተጨማሪም "የኦርቶዶክስ አባቶች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አድርገሀል ተብዬ መከሰሴ ግማሹን የሰውነት ክፍሌን ከላዬ ላይ ቆርጬ እንደመጣል ስለሚቆጠር ይህን ለማድግ የምችል ሰው አይደለሁም " ማለታቸውን ጠበቃው ተናግረዋል። አቶ ጀዋር ብሔሮችን ለማጋጨት በሚል የቀረባቸው ክስ ትክክል እንዳልሆነና "ይልቁንም ብሔሮችን ለማቀራረብ እንደሰሩ" ለፍርድ ቤቱ መናገራቸውን አቶ ኢብሳ ለቢቢሲ ገልጸዋል። አቶ ሸምሰዲን ጠሀ በምን ጉዳይ ተከሰው ከዘጠኝ ወራት በላይ በእስር ላይ እንዳሉ እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ መናገራቸውን ጠበቃው ጨምረው ገልጸዋል። ከተከሰሱባቸው ድርጊቶች "አንደኛውም እሳቸውን እንደማይገልጽ እና ጥፋት እንደሌለባቸው" ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ከሰማ በኋላ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ቀጠሮ ይዟል። በዚህም መሠረት እነዚህ ምስክሮች ቃላቸውን የሚሰጡት በግልጽ ነው ወይስ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው የሚለውን ብይን ለመስጠት ለመጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ. ም. ቀጠሮ ሰጥቷል። በተጨማሪም የዓቃቤ ሕግን ምስክሮች ለመስማት ለመጋቢት 29 እና 30 እንዲሁም ለሚያዝያ 5፣ 6፣ 7፣ 12፣ 13 እና 14፣ 2013 ዓ. ም ቀጠሮ ይዟል። እነ አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች መካከል ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር ወር ላይ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ፣ የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሣሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ ሲሆኑ፤ በወቅቱ ውሳኔ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ መሆናቸውም የሚታወስ ነው። የቀሩት አራት ክሶች በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርን እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድረግ፣ የፀረ ሽብር አዋጅ 1176/2012 እና የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅን 7061/2004 የሚመለከቱ ናቸው።
news-50034450
https://www.bbc.com/amharic/news-50034450
የ'ፍሬንድስ' ፊልም ተዋናዮች እንደገና ቢመለሱስ?
የፍሬንድስ ተዋናዮች እንደገና ቢመለሱስ? ተመልሰው አዲስ ተከታታይ ፊልም ቢሰሩስ?
የተወዳጁ ተከተታይ ሲትኮም የ'ፍሬንድስ' አድናቂዎች የመጨረሻው ክፍል ከታየበት ከአስራ አምስት ዓመታት ጀምሮ የሚጠይቁት ጥያቄ ቢኖር የፍሬንድስ ተዋናዮች እንደገና እንዲሰባሰቡ ነው። ለአስር ዓመታት ያህልም ብዙዎች የስድስቱን ጓደኞች ውጣ ውረድ በፍቅር ተመልክተውታል። ከተሰራበት ከአሜሪካ ውጪ ወጥቶ የተለያዩ ትውልዶችን፤ ዘሮችንና ህዝቦችንም ማገናኘት ችሏል። አሁንም ብዙዎች በናፍቆት ይጠብቁታል፤ እንደገና ቢሰባሰቡስ? የሚሉ ጥያቄዎችም ይሰማሉ። በቅርቡም ይህንን ሃሳብ እውን የሚያደርግ ነገር ተከስቷል፤ ተዋናዮቹ ኮርትኒ ኮክስ (በፍሬንድስ ገፀ ባህርይ ስሟ ሞኒካ) ቤት ተሰባስበው ነበር። በአሜሪካ ብቻ ሳይሆን በእንግሊዝም ለሁለት ዓመታት ያህል የከፍተኛ ቁጥር ያለው ተመልካችን ከመሳብ አንፃር ብዙዎችን የመሰባሰባቸው ዜና አስደስቷቸው ነበር። •የሆሊውዱን ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? •"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ በተመልካቾች ቁጥር ብቻ አይደለም ፊልሙ የሚመራው፤ በፊልሙ ዙሪያ ዲዛይን የተደረጉ አልባሳትም ሆነ ሌሎች ቁሳቁሶች በከፍተኛ ደረጃ ይቸበቸባሉ። ይህ ማለት የፍሬንድስ መመለሻ ጊዜ አሁን ይሆን? ፍሬንድስ ፊልም እንደገና ቢመለስም ከፍተኛ የሆነ እይታም ሆነ ተወዳዳሪነት እንዳለው ሳይታለም የተፈታ ነው። ፊልሙ 25ኛ ዓመት ክብረ በዓልም እየተከበረ ባለበት ወቅት ኔትፍሊክስ ፊልሙን እያሳየ መሆኑ አዳዲስ ተመልካቾችን ማምጣት ችሏል። •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ ቀልዶቹም በአዲሶቹ ተመልካቾች ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት መቻላቸው፤ የተለያዩ ትውልዶችን ማገናኘት የቻለ ተብሎለታል። በተለይም ከኔትፍሊክስ ጋር በብዙ ሚሊዮን ፓውንዶች ስምምነት መድረስ መቻሉ ያለው ተፈላጊነትን ማሳያ እንደሆነ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያሉ ሰዎች ይናገራሉ። ፊልሙን የሰራው ዋርነር ብራዘርስ ቲቪ ስቱዲዮ ሰዎች ለሬዲዮ 1 ኒውስ ቢት እንደተናገሩት "ይህ ማለት ፊልሙ እንደገና ይመለሳል ማለት አይደለም፤ ለዓመታትም ሳይቋረጥ ታይቷል" ማለታቸው ተሰምቷል። የተመልካቾች ቁጥር አዘጋጆቹ ላይ ተፅዕኖ ማሳረፍ ካልቻለ፤ ምናልባት በፊልሙ ስም የሚመረቱ አልባሳትና ቁሶች እንደገና ሊያመጡት ይችሉ ይሆን? በእንግሊዝ ውስጥ ከፊልሙ የተወሰዱ ሃረጎች ለምሳሌ ጆዊ የተባለው ገፀባህርይ በተደጋጋሚ የሚላቸውን "ሃው ዩ ዱይን" ፅሁፍ የሰፈረባቸው ሹራቦች እንዲሁም ቲሸርቶች በከፍተኛ ደረጃ ተፈላጊነት አላቸው። ታላላቅ ዓለም አቀፍ የአልባሳት ኩባንያዎችም በዚህ ዘርፍ ተሳታፊ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ዘርፉን ዘግይቶ የተቀላቀለው ኤችኤንድ ኤም ነው። ኤች ኤንድ ኤም ለቢቢሲ እንደገለፀው ከፍተኛ ሽያጭም አላቸው። ችሎ ኮሊንስ ዓለም አቀፉን የአልባሳት ሽያጮችን መረጃ ተንታኝ ናት፤ በተለያዩ አልባሳት ሱቆች ውስጥ ዘርፉን እየመሩ ያሉት የትኞቹ ናቸው ብላም በምትመለከትበት ወቅት በፍሬንድስ ፊልም ዙሪያ የተሰሩ አልባሳት ገበያውን ቀዳሚ እንደሆነ ትናገራለች። •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም ከእነዚህም ውስጥ ታዋቂዎቹ የአልበሳት ምርት ምልክቶች ኤችኤንድኤም፣ ቶፕሾፕ ኤስኦኤስ ይገኙበታል። "አሁንም ቢሆን ሰዎች በየቀኑ የሚያዩት ፊልም ነው፤ አያረጅም፤ ጊዜም አያልፍበትም" ትላለች። ያልተጠበቀ መሰባሰብ የተመልካች ቁጥር ወይም ፍላጎት ሳይሆን ዋናው ጥያቄ ተዋናዮቹ እንደገና ተሰባስበው መስራት ይፈልጉ ይሆን ወይ የሚለው ነው። ኮርትኒ ኮክስ (ሞኒካ) ቤት በተሰባሰቡበት ወቅት እንደገና አንድ ላይ ሊሰባሰቡ ይችላሉ የሚለው ተስፋ አንሰራርቶ ነበር። ከፍሬንድስ ተዋናዮች ጄኔፈር አኒስተን (ሬቸል)፣ ማት ለብላንክ (ጆዊ) ጋር አብረው የተነሱትንም ፎቶ "ያልተለመደ ምሽት፤ በጣም ነው የወደድኩት'' በማለት ሞኒካ በኢንስታግራም ገጿ አጋርታለች። በተለይም ጄኔፈር አኒስተን በተገናኙበት በነገታው ከአሜሪካው ሬድዮ ጋር ባደረገችው ቃለ መጠይቅ ስድስቱም መገናኘታቸውን ይፋ ማድረጓን ተከትሎ ብዙዎችም ደስታቸውን ገልፀው ነበር። አሁን ባሉበት እድሜ ተሰባስበው እንደገና የመስራት እቅድ አላችሁ ወይ ተብሎ ለቀረበላት ጥያቄ የሚያቅማማ የሚል ምላሽ ሰጥታለች። •''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" "እንደገና ተሰባስበን ብንሰራ እንደቀድሞው ጥሩ አይሆንም፤ ያበላሸዋል" ብላለች። ምንም እንኳን በጭራሽ አይሆንም የሚል መልስ ባትሰጥም የቴሌቪዥን ፊልሞች ላይ ሂስ በመስጠት የሚታወቀው ስኮት ብርያን ሊሰባሰቡ እንደማይችሉ ይናገራል "ዋናው ጉዳይ ተዋናዮቹ ናቸው" ይላል። ፊልሙን እንደገና መስራትም አደጋ እንዳለውም አልደበቀም። "ፊልሙ ከተመለሰ በትዝታ ብቻ መሄድ አይችልም፤ እሱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይጠፋል። አሁን ያለንበትን ጊዜ ሊያንፀባርቅ የሚችል ታሪክና ገፀባህርያት ያስፈልጋሉ" ይላል። ሆነም ቀረም ፊልሙን እንደገና የመስራት ውሳኔ የአዘጋጆቹና የፀሃፊዎቹ ቢሆንም የተዋናዮቹም እንደገና መገናኘታቸው ብዙ ያነሳሳቸው አይመስልም።
news-56473770
https://www.bbc.com/amharic/news-56473770
በኡጋንዳ ሳይመረዙ አልቀረም የተባሉ አንበሶች ሞተው ተገኙ
በኡጋንዳ ከሚገኙ ፓርኮች በአንዱ ሳይመረዙ አልቀረም በሚል የተጠረጠሩ ስድስት አንበሶች ሞተው አካላቸው ተቆራርጦ ተገኝቷል፡፡
አንበሶቹ በንግስት ኤልሳቤጥ ብሔራዊ ፓርክ ጭንቅላታቸውና መዳፎቻቸው ተቆርጠው አስከሬናቸውም በአሞራዎች ተከቦ ተገኝቷል ሲሉ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ የኡጋንዳ የዱር እንስሳት ባለስልጣን "ህገ-ወጥ የዱር እንስሳት ዝውውርን ከግድያው ጀርባ ሊሆን ይችላል" ብሏል፡፡ የጥበቃ ባለሙያዎች ከአከባቢው ፖሊሶች ጋር በቦታው በመገኘት ምርመራው ጀምረዋል፡፡ አንበሶቹ ዛፎችን በመውጣት ልዩ በሆነው ችሎታቸው ይታወቃሉ፡፡ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ በሽር ሃንጊ በሰጡት መግለጫ በግድያው "ማዘናቸውን" ተናግረዋል፡፡ የተፈጥሮ ቱሪዝም ለኡጋንዳ ኢኮኖሚ አስፈላጊ ሲሆን ለእንስሳት ጥበቃም ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ "የኡጋንዳ የዱር እንስሳት ባለስልጣን የዱር እንስሳትን ህገ-ወጥ ግድያ አጥብቆ ያወግዛል። ምክንያቱም እንደ ሀገር በቱሪዝማችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖን ስላለው ብቻ ሳይሆን አካባቢዎችን ለመጠበቅ እና የህብረተሰቡን ሥራ የሚደግፍ የገቢ ማስገኛ ጭምር ነው" ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት በንግስት ኤልሳቤጥ ብሔራዊ ፓርክ አንበሶች ተመርዘዋል ተብሎ የታመነባቸው በርካታ ክስተቶች ነበሩ፡፡ በ2018 ተመርዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ ስምንት ደቦሎችን ጨምሮ 11 አንበሶች ሞተው ተገኝተዋል፡፡ ተመሳሳይ ክስተት በግንቦት 2010 ለአምስት አንበሶች ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡
45494884
https://www.bbc.com/amharic/45494884
ቪየትናም ነዋሪዋቿ የውሻ ሥጋ እንዳይበሉ እያሳሰበች ነው
የቪየትናም ባለሥልጣናት የሃገሪቱ ነዋሪዎች፤ በተለይ የርዕሰ መዲናዋ ሃኖይ ሰዎች የውሻ ሥጋ እንዳይበሉ በማሳሰብ ላይ ይገኛሉ። የከተማዋን ስም ያጠለሻል የሚል ነው ምክንያታቸው።
የሃኖይ ሕዝቦች ኮሚቴ እንዳስታወቀው የውሻ ሥጋ መብላት ዘመናይ የሆነችውን ከተማ ስም ከማቆሸሹም በላይ ለበሽታ ሊዳርግ ይችላል። በሃኖይ ከተማ የሚገኙ አንድ ሺህ ያህል ሱቆች የውሻ እና የድመት ሥጋ በሰልፍ ይሸጥባቸዋል። • ትራምፕ ቪየትናም ገብተዋል ኮሚቴው የውሻ ብቻ ሳይሆን የድመት ሥጋ መብላትም እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል፤ ምንም የውሻን ያህል ተወዳጅነት ባይኖረውም። ከስም ማቆሸሹና ከበሽታው በዘለለ የቤት እንስሳቱ በግፍ መገደል ድርጊቱ እንዲቆም ለማድረግ ያስገድደናል ብሏል ኮሚቴው። የቢቢሲ ቪየትናም ዝግጅት ክፍል ባልደረባ የሆነው ሊን ጉየን «ምንም እንኳ አብዛኛው የሃገሪቱ ሰው ውሻ መብላትን ባይቀበለውም አሁንም ተመጋቢው በርካታ ነው» ሲል ስለሁኔታው ይናገራል። • ለማነፍነፍ የሰነፈችው ጥሩ ውሻ ወሬውን የሰሙ ብዙዎች 'መልካም ዜና' ነው ቢሉም የተቃወሙት ግን አልጠፉም፤ 'ባህልችንማ' በሚል። «የውሻ ሥጋን አትብሉ ብሎ መከልከል ነፃነትን እንደመግፈፍ ነው» ሲል እንድ ቪየትናማዊ ሃሳቡን በፌስቡክ ገልጿል። «ባይሆን ቀረጥ መጨመርና በተወሰኑ ሥፍራዎች ብቻ እንዲሸጥ ማድረግ» ሲልም አማራጭ ሃሳብ አቅርቧል። የቪየትናም ዋና ከተማ ሃኖይ 490 ሺህ ያህል ውሾችና ድመቶችን በቤት እንስሳነት ታስተዳድራለች። • ካለሁበት 27፡ 'እንጀራ ከበላሁ ዓመት አልፎኛል'
46734174
https://www.bbc.com/amharic/46734174
በ2019 በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው?
የዲጂታል ሥራዎችና መሰል ተግባራት ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታዋቂ እየሆኑ መጥተዋል።
ባደጉት ሃገራት ላፕቶፖቻቸውን በጀርባቸው ተሸክመው ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱና ጥሩ የኢንተርኔት አገልግሎት አለበት በተባለ ቦታ ሁሉ የሚገኙ ወጣቶች በርክተዋል። ሃሳባቸው ደግሞ የግድ ቢሮ ውስጥ ገብተን ሥራ መስራት የለብንም፤ ካለንበት ቦታ ሆነን ለምን ትርፋማ ሥራዎች መስራት አንችልም? ነው። • ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች ሁሉንም የሚያመሳስላቸው ደግሞ በይነ መረብን በአግባቡ ማወቃቸውና የዲጂታል ኢኮኖሚ ጥቅም የገባቸው መሆኑ ነው። በዲጂታል የሥራ ብቃት ላይ ትኩረት ያደረጉ ብዙ ትልልቅ ድርጅቶችም ፊታቸውን ወደ እነዚህ ወጣቶች እያዞሩ ያመስላል። በያዝነው የፈረንጆች አዲስ ዓመት የትኞቹ የዲጂታል ሥራ ዘርፎች የበለጠ ውጤታማ ሆነው በብዙዎች ዘንድ ተፈላጊ ይሆናሉ? ባለሙያዎችን አናግረን አምስት የሥራ አይነቶችን ለይተናል። 1. ሳይበርሰኪዩሪቲ ስፔሻሊስት (የመረጃ መረብ ባለሙያ) በታህሳስ ወር ይፋ በተደረገ አዲስ ጥናት መሰረት በ2019 እጅግ በጣም ብዙ ሰራተኞች የሚፈለጉበትና ትርፋማ ሊሆን የሚችለው የዲጂታል የሥራ ዘርፍ የሳይበርሰኪዩሪቲ ስፔሻሊስትነት ነው። የመረጃ ደህንነት እንዲሁም ኔትወርኪነግ ደህንነት በብዙ ድርጀቶች አሳሳቢ ነገሮች እየሆኑ መምጣታቸውን ተከትሎ ይህ የሥራ ዘርፍ ተፈላጊ እንደሚሆን ይጠበቃል። • በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? የሳይበርሰኪዩሪቲ ስፔሻሊስቶች ዋነኛ ሥራ የድርጅቶች መረጃና አዳዲስ ፈጠራዎች ከውጪና ከውስጥ ከሚሰነዘሩ የበይነ መረብ ጥቃቶች መከላከል ነው። አሁን ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ የፈጠራ ውጤቶችን ቶሎ ቶሎ መከታተልና ወደፊት ሊመጡ የሚችሉ ስጋቶችን ቀድሞ ማወቅ ደግሞ ግዴታቸው ነው። 2. ብሎክቼይን ዴቨሎፐር (በበይነ መረብ ውስጥ ዋጋ ያላቸውን መገበያያዎች የሚፈጥሩ) በጥናቱ መሰረት ይህ የሥራ ዘርፍ በአዲሱ ዓመት በዲጂታሉ ዓለም በሁለተኝነት ተፈላጊ ሊሆን ይችላል። 'ሊንክድኢን' የተሰኘው ሥራ አፈላላጊ ተቋም እንዳስታወቀው በቀጣሪዎችም ሆነ በሥራ ፈላጊዎች ዘንድ ይህ ዘርፍ በጥብቅ ይፈለጋል። የብሎክቼይን ዴቨሎፐሮች ፍላጎት በአሜሪካ ብቻ በአስገራሚ ሁኔታ በ33 እጥፍ እንደጨመረ ተቋሙ ገልጿል። • የስልክዎን ባትሪን ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም የባለሙያዎቹ ዋነኛ ተግባር ደግሞ 'ክሪፕቶከረንሲ' ማርቀቅ ነው። ለዚህ ደግሞ በቀዳሚነት የሚቀመጠው 'ቢትኮይን' የተሰኘው 'ክሪፕቶከረንሲ' ነው። ባሳለፍነው ዓመትም 'ቢትኮይን' ምንድነው ብለው ጉግል ላይ መረጃ የጠየቁ ሰዎች ቁጥርም ከፍተኛ ነበር ተብሏል። 3. አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ገና ጅምሩ ላይ ያለ የሥራ ዘርፍ ይመስላል። ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሲወራ፤ ሮቦቶች አልያም ሌላ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ሥራችንን ሊወስዱብን ነው ብለው የሚሰጉ ብዙ ሰዎች አሉ። ይህ የሥራ ዘርፍ ግን ብዙ ባለሙያዎችን ለመቅጠር ትልቅ ዕድል ያለውና ጀማሪ በሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው። በቅርቡ የተሰራው ጥናት እንደሚያመለክተው ከእያንዳንዱ 15 ተስፈኛ የሥራ እድሎች መካከል ስድስቱ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር የተያያዙ ናቸው። ከ2015 እስከ 2017 ባሉት ዓመታት ብቻ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር የተያያዙ እውቀቶችና ሥራ ልምዶች 190 በመቶ አድገዋል። • ራስዎን ካላስፈላጊ የስልክ ጥሪ እንዴት ይታደጋሉ? እንደ አፕልና ኢንቴል ያሉ በአሜሪካ የሚገኙ የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ባለሙያዎችን ዋነኛ ፈላጊ እንደሆኑ 'ሊንክድኢን' የተሰኘው ድርጅት ጠቁሟል። 4. ክላውድ ኮምፒዩቲንግ (የበይነ መረብ የመረጃ ቋት) የተለያዩና ብዙ ቦታዎችን የሚይዙ መረጃዎችን በበይነ መረብ የመረጃ ቋት (ክላውድ ኮምፒዩቲንግ) ማስቀመጥ ተመራጭ ተግባር እየሆነ መጥቷል። ለዚህም ነው የክላውድ ኮምፒዩቲንግ ባለሙያዎች በዲጂታሉ ዓለም በጣም ተፈላጊ እየሆኑ የመጡት። የትልልቅ ድርጅቶችን መረጃዎች በቋቶቹ ውስጥ ማንም ሰው ሊያገኘው በማይችለው መልኩ ማስቀመጥና ማጠራቀም ደግሞ የእነዚህ ባለሙያዎች ዋነኛ ተግባር ነው። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት በዚህ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦች ብዙ ጊዜ ጠቀም ያለ ደሞዝ የሚከፈላቸው ሲሆን፤ በዓመት እስከ 125 ሺህ ዶላር ያገኛሉ ተብሎ ይገመታል። እስካሁን የጠቀስናቸው የዲጂታል ዓለም የሥራ ዘርፎች በሙሉ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ መጠቀም ግድ ይላቸዋል። 5. የንግድ መረጃ ተንታኝ አምስተኛውና በጣም ተፈላጊ የሆነው የዲጂታል ሥራ ዘርፍ ደግሞ የንግድ መረጃ ተንታኝነት ነው። ነገር ግን ምንድነው የሚሰሩት? ልትሉ ትችላላችሁ። ዋነኛው ሥራቸው ብዙ ሰዎች በቀላሉ ማከናወን የማይችሉትን የብዙ ዓመታት መረጃዎች ማሰባሰብና ለውሳኔ እንዲያግዙ አድርጎ ማዘጋጀት ነው። ማንኛውም አይነት መረጃ ጠቃሚ ነው ብለው ያምናሉ እነዚህ ሰዎች። የኮምፒዩተር ሳይንስ እውቀታቸው ከፍ ያለ ሲሆን፤ ከንግድ ተጋር የተያያዙ ማኛውንም አይነት መረጃዎች አያመልጧቸውም። አንድ ንግድ ትርፋማ ይሆናል ወይስ አይሆንም የሚለውን ጥያቄ በቀላሉ መመለስ ይችላሉ። ትርፋማ መሆን ያልቻለ የንግድ ዘርፍንም ማነቃቃትና ትርፋማ እንዲሆን ለማድረግ እነዚህ ባለሙያዎች እጅግ ወሳኝ ናቸው።
news-46915239
https://www.bbc.com/amharic/news-46915239
ከናይሮቢው የሽብር ጥቃት ጋር በተገናኘ 9 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
21 ሰዎች ከተገደሉበት የናይሮቢው የሽብር ጥቃት ጋር በተገናኘ 9 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
የኬንያ ፖሊስ አምስቱን አሸባሪዎች ገድሎ የዱሲትዲ2ናይሮቢ ህንጻን ለመቆጣጠር የ19 ሰዓታት ኦፕሬሽን ማካሄድ ነበረበት። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፤ ''አሸባሪዎቹ በሙሉ ተገድለዋል፤ ኦፕሬሽኑም ተጠናቋል'' ሲሉ አሳውቀል። ፖሊስ እንዳስታወቀው፤ የሽብር ጥቃቱን በማቀነባበር እና በገንዘብ የደገፉ ግለሰቦችን ማደኑን ተያይዞታል። አል ሸባብ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ባለው የሽብር ጥቃት የሟቾች ቁጥር 21 መድረሱ ይታወሳል። • ከሽብር ጥቃቱ በኋላ ምን ተከሰተ? ስለ ጥቃት አድራሾቹ ምን እናውቃለን? የኬንያ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት፤ ከጥቃት አድራሾቹ መካከል የአንደኛው ታጣቂ ሚስት ኪያምቡ ተብሎ በሚጠራው ግዛት ውስጥ በቁጥጥር ሥር ውላለች። ጥቃት አድራሾቹ ወደ ሆቴሉ የመጡበት መኪና የአንደኛውን አሸባሪ ማንነት እንድለይ ረድቶኛል ሲል ፖሊስ አስታውቋል። መኪናዋ ከሆቴሉ አቅራቢያ ቆማ በቴሌቪዥን መስኮት የተመለከቱ ነዋሪዎች ለፖሊስ ስለመኪናዋ ባደረሱት ጥቆማ ከጥቃት አድራሾቹ መካከል እንዱ አሊ ሳሊም ጊቹንጌ መሆኑ ታውቋል። የአሊ ሳሊም ጊቹንጌ ጎረቤቶች 'ዘ ስታንዳርድ' ለተሰኘ ጋዜጣ በሰጡት ቃል፤ ጥቃት አድራሹ እና ባለቤቱ ከጥቂት ወራት በፊት በስፍራው መኖር መጀመራቸውን እና ሚስጥራዊ መሆናቸውን ተናግረዋል። ጎረቤቶቹ ጨምረውም 'በዚህ ሳምንት ከናይሮቢ ልንወጣ ነው' በማለት የቤት እቃዎቻቸውን ለሽያጭ አቅርበው ነበረ ብለዋል። • ከሽብር ጥቃቱ በኋላ ምን ተከሰተ? ሮይተርስ እንደዘገበው፤ አል ሸባብ "ይህን ጥቃት የሰነዘርኩት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርገው በመቁጠራቸው ምላሽ እንዲሆን ነው" ብሏል። በጥቃቱ ከተገደሉት 21 ሰዎች መካከል የፖሊስ አባል እንደሚገኝበትም ታውቋል። የሽብር ጥቃቱ ማክሰኞ ከሰዓት 9 ሰዓት ገደማ ነበር የጀመረው። ፖሊስ እንደሚለው ታጣቂዎቹ ወደ ሆቴሉ እንደተቃረቡ ወደ መኪና ማቆሚያ ስፍራ የእጅ ቦንቦችን ወረወሩ፤ ከዚያም አንዱ ታጣቂ እራሱን አፈነዳ። የሲሲቲቪ ካሜራ ምስሎች አራት ታጣቂዎች ተኩስ ሲከፍቱ አሳይተዋል። እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ጥቃት አድራሾቹ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ወደ ሆቴሉ ተጠቃሚ በመምሰል ይመላለሱ ነበረ። ባለ አምስት ኮከቡ ሆቴል 101 ክፍሎች ያሉት ሲሆን፤ ህንጻውም ከሆቴል በተጨማሪ የቢሮ አገልግሎቶችንም ይሰጣል።
news-55359760
https://www.bbc.com/amharic/news-55359760
ኬንያ፡ የናይሮቢው ገዢ በቀረበባቸው የሙስና ክስ ከስልጣናቸው ተነሱ
የኬንያ ዋና መዲና ናይሮቢ ገዢ የሆኑት ማይክ ሶንኮ ምቡቪ በክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ የቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ተቀባይነት በማግኘቱ ከሥልጣን እንዲሱ ተደረገ።
የምክር ቤቱ አባላት የናይሮቢ ከተማ ገዢን ከቀረበባቸው አራት ክሶች በተጨማሪ፣ ሕገመንግሥቱን በመጣስ፣ ሥልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም፣ ያልተገባ ጠባይ በማሳየት እንዲሁም ሌሎች የአገሪቱን ሕጎች በመጣስ ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸውን ገልፀዋል። ማይክ ሶንኮ ላይ ከቀረቡባቸው ክሶች መካከል አንዱ የሕዝብ ገንዘብን ተጠቅመው በ2018 ልጃቸው ወደ ኒውዮርክ እንድትጓዝ አድርገዋል የሚል ሲሆን፣ እንዲሁም በናይሮቢ ለተለያዩ ጉዳት ለተጋለጡ ሕጻናት የተመደበውን ፈንድ ለግል ጥቅም አውለዋልም ተብለዋል። የናይሮቢ ከተማ ገዢ የነበሩት ማይክ ሶንኮ እጅጉን ተሽቀርቅረው መታየት የሚወዱ፣ የወርቅ ጌጣጌጦችን የሚያዘወትሩ መሪ የነበሩ ሲሆን የቀረበባቸውን ክስም አስተባብለዋል። እንደ እርሳቸው ከሆነ በናይሮቢ ከተማ በሙስና በተዘፈቁ ቡድኖች የሕዝብ ገንዘብ እንዳይዘረፍ የሚያደርጉትን ትግል ለማስቆም የተሰራ ሴራ ነው። የናይሮቢ ከተማ ገዢ የነበሩት ሶንኮ ባለፈው ዓመት ሕዳር ወር ላይ ነበር በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት። ማይክ ሶንኮ ከተለያየ እሰጥ አገባዎች ጀርባ በተደጋጋሚ ስማቸው ይነሳል። በቅርቡ የኬንያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ባለስልጣናት ሶንኮ ከ20 ዓመት በፊት ከጥብቅ እስር ቤት ውስጥ በማምለጥ ወንጀል ስማቸውን አንስተው ከስሰዋቸዋል። ማይክ ሶንኮን በቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ እየተደረገላቸው ባለበት ሰዓት ከማረሚያ ቤት ማምለጣቸውን እውነት መሆኑን ተናግረዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኬንያ ከተከሰተ ወዲህም ለናይሮቢ ነዋሪዎች በሚከፋፈል የእርዳታ እህል ውስጥ ሄኔሲ ቢራ እንዲካተት ያደረጉ ሲሆን ለዚህም ምላሽ ሲሰጡ “በቢራው ውስጥ ያለው የአልኮል መጠን ኮሮናቫይረስን ያስቆመዋል” ብለው ነበር። ሶንኮ የናይሮቢ ገዢ ሆነው የተመረጡት በ2017 በፕሬዝዳንት ኡሁሩ ጁቢሊ ፓርቲ ስር ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ሁለቱ ግለሰቦች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ሶንኮ ወደ ሌላ ፓርቲ እንዲሄዱ ሆኗል። ፕሬዝዳንት ኬንያታ ከተማዋን የሚያስተዳድር ከዚህ በፊት በውትድርና ሙያ ላይ ያገለገለ ግለሰብ በመመደብ ማይክ ሶንኮ ለይስሙላ በቦታው እንዲቀመጡ አድርገው ቆይተዋል። ማይክ ሶንኮ ከአዲሱ ተሿሚ ጋር የስልጣን ርክክብ ካደረጉ በኋላ፣ በሰጡት ቃለምልልስ ላይ ሰነዶቹ ላይ ስፈርም ጠጥቼ ነበር ብለዋል። ማይክ ሶንኮ የፖለቲካ ስልጣናቸውን የጀመሩት ኢስትላንድ በሚባል አካባቢ ሲሆን ከፍተኛ ድጋፍ ያገኙት ደግሞ ዝቅተኛ ኑሮ ከሚመራው ሕብረተሰብ ክፍል እና ከወጣቱ ነበር። ሶንኮ የራሳቸው የሆነ የንግድ ተቋም ያላቸው ሲሆን “ሶንኮ ሬስኪው ቲም” በመባል ይታወቃል። ይህ ድርጅት አምቡላንሶች፣ የእሳት አደጋ መኪኖች፣ ለሰርግ የሚከራዩ ሊሞዚኖችንና የቀብር ማስፈፀሚያ መኪናዎች ያከራያል። ተቺዎቻቸው ግን የሕዝብ ገንዘብ በመመዝበር እና ያልተገባ ጥቅም በማካበት ይኮንኗቸዋል። የናይሮቢ ከተማ ነዋሪዎች በስድሳ ቀናት ውስጥ ወደ ምርጫ መሄድ እና የከተማቸውን ገዢ መምረጥ ይጠበቅባቸዋል። ሶንኮ በኬንያ በስልጣን ላይ እያለ በቀረበበት ውንጀላ ከኃላፊነቱ የተነሳ ሁለተኛው ሰው ናቸው። ከዚህ ቀደም በታሕሳስ ወር የኪያምቡ ካውንቲ ገዢ ፈርዲናንድ ዋይቲቱ በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ክስ ቀርቦባቸው ከሥልጣናቸው እንዲነሱ የተደረገ ሲሆን እርሳቸው ግን እኔ ንፁህ ነኝ ሲሉ ተከራክረዋል።
news-55516805
https://www.bbc.com/amharic/news-55516805
ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዳይሰጥ ፍርድ ቤት ወሰነ
የመንግሥታትን ምስጢር ሲያጋልጥ የነበረው የዊኪሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዳይሰጥ አንድ የለንደን ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ።
ጁሊያን አሳንጅ የፍርድ ቤቱ ዳኛ አሳንጅ በጥብቅ ለምትፈልገው አሜሪካ ተላልፎ መሰጠቱን የከለከሉት በግለሰቡ የአእምሮ ጤና ላይ ባላቸው ስጋት የተነሳ መሆኑ ተገልጿል። የ49 ዓመቱ ጁሊያን አሳንጅ በወንጀለኝነት እየተፈለገ ለመሳደድ የበቃው ከአስር ዓመት በፊት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥታትን ጥብቅ የምስጢር ሰነዶች በድረ ገጹ ላይ በማተሙ ነው። አሜሪካ በአሳንጅ ላይ ባቀረበችው ክስ ግለሰቡ ይፋ ያደረጋቸው ምስጢራዊ ሰነዶች ሕግን የሚጣሱ እንዲሁም የሰዎችን ሕይወት ለአደጋ የሚያጋልጡ በመሆናቸው ነው ብላለች። የምስጢራዊ መረጃዎች አሹላኪ የሆነው 'ዊኪሊክስ' መስራች ጁሊያን አሳንጅ የቀረቡበትን ክሶች ፖለቲካዊ አላማ ያላቸው ናቸው በማለት ተላልፎ እንዳይሰጥ ተከራክሯል። አሳንጅ ተላልፎ እንዳይሰጥ የወሰኑት ዳኛ ቫኔሳ ባሬይስትር በውሳኔያቸው ላይ እንዳመለከቱት ግለሰቡ እራስን ለማጥፋት የማሰብና እራሱ ላይ ጉዳት ማድረስን የሚያመለክቱ ማስረጃዎችን ጠቅሰዋል። "አጠቃላይ ግምገማው የሚያመለክተው መደበትና አንዳንድ ጊዜም ተስፋ መቁረጥ የሚታይበት የወደፊት ሕይወቱ የሚያሰጋው ሰው ነው" ሲሉ ስላለበት ሁኔታ ተናግረዋል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ግን ውድቅ የተደረገባቸው ውሳኔን ለማስቀልበስ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል። ጁሊያን አሳንጅ በአሜሪካ ፍርድ ቤት ቀርቦ ጥፋተኛ ከተባለ አስከ 175 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ሊበየንበት እንደሚችል ጠበቆቹ የተናገሩ ቢሆንም የአሜሪካ መንግሥት ግን ቅጣቱ ከአራት አስከ ስድስት ዓመት እንደሚሆን አመልክቷል። አሳንጅ በዊኪሊክስ ድረ ገጽ ላይ የታተሙ ከአፍጋኒስታንና ከኢራቅ ጦርነቶች ጋር የተያያዙ ምስጢራዊ መረጃዎችን ወታደራዊ የመረጃ ቋት ሰብሮ በመግባት ለመውሰድ ከማሴር ጋር በተያያዘ በአሜሪካ መንግሥት በርካታ ክሶች ቀርበውበታል። አሳንጅ እንደሚለው ይፋ የወጡት መረጃዎች በአሜሪካ ሠራዊት የተፈጸሙ ግፎችን የሚያጋልጡ ናቸው በማለት ይከራከራል። ነገር ግን የአሜሪካ ዐቃቤ ሕግ ይፋ የወጡት ምስጢራዊ ሰነዶች የሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ በመሆናቸው በአሁኑ ጊዜ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ቤልማርሽ በሚባል እስር ቤት የሚገኘው አሳንጅ ተላልፎ እንዲሰጣት ትፈልጋለች። አሳንጅ ለእስር የተዳረገው በዋስት ከእስር ውጪ እንዲቆይ የተሰጠውን ዕድል በመተላለፍ ለንደን ውስጥ በሚገኘው ኢኳዶር ኤምባሲ ውስጥ ተደብቆ በመቆየቱ ነው። አሳንጅ ከ2012 (እአአ) አንስቶ ወደ ኤምባሲው በመግባት ጥገኝነት ጠይቆ ለሰባት ዓመታት የቆ ሲሆን፤ ከኤምባሲው በ2019 ሲወጣ ነው በፖሊስ የተያዘው። ወደ ኢኳዶር ኤምባሲ ገብቶ ከለላ በጠየቀበት ጊዜ ወሲባዊ ጥቃት ፈጽሟል በሚል ክስ ስዊዲን ግለሰቡ ተላልፎ እንዲሰጣት ጠይቃ ነበር። አሳንጅ ክሱን ያስተባበለ ሲሆን በኋላ ላይ ደግሞ ክሱ ውድቅ ተደርጓል።
news-54970746
https://www.bbc.com/amharic/news-54970746
ትግራይ፡ ግጭቱን ፈርተው ወደ ሱዳን የገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር ከ30 ሺህ በላይ መድረሱ ተገለፀ
ወደ ሁለት ሳምንት ባስቆጠረው የፌደራል መንግሥትና ትግራይ ክልል ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሺህ እንደበለጠና ከቀን ወደ ቀንም እየጨመረ መሄዱን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ ዩኤንኤችሲአር አስታውቋል።
ግጭቱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ መባባሱን የገለፁት በካርቱም የዩኤንኤችሲአር ድንገተኛ ምላሽ አስተባባሪ ጀንስ ሄዝማን ሁኔታውን "አስጊ ነው" ብለውታል። በድንጋጤ የተዋጡ፣ እራፊ ጨርቅ ላያቸው ላይ ጣል ያደረጉና በፍርሃት የተሞሉ ተፈናቃዮች ወደ ሱዳን ያቀኑ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ታዳጊዎች እንደሆኑም መረጃዎች ይጠቁማሉ። ኢትዮጵያን በትግራይ ክልል በኩል ከሱዳን ጋር የሚያዋስነው ድንበር የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች ሁኔታ እየተከታተሉ ያሉት አስተባባሪው፤ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ በምሥራቃዊዋ የሱዳን ግዛት በሦስት ቦታዎች የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር መጨመር አሳሳቢ ነው ብለዋል። በተለይም በሃምዳያት በኩል ከፍተኛ የሆኑ ተፈናቃዮች ቁጥርም እየተመዘገበ ነው፤ በየቀኑም "አስገራሚ" በሚባል ሁኔታም እየጨመረ መሆኑን አስተባባሪው ይናገራሉ። በትናንትናው ዕለት፣ ህዳር 7/ 2013 ዓ.ም ብቻ 2 ሺህ 300 አዲስ ተፈናቃዮች ሱዳን ገብተዋል። ከትናንት በስቲያ እንዲሁም ከ 5 ሺህ በላይ አዲስ ተፈናቃዮች መግባታቸውንም አስተባባሪው አስረድተዋል። ከዚህ ለየት ባለ ሁኔታም በደቡባዊ ሱዳን በኩል በርካታ ተፈናቃዮች እየገቡ መሆናቸውን ዩኤንኤችሲአር ተመልክቷል። አካባቢው ከዚህ በከፍተኛ ርቀት ከመገኘቱ አንፃር "ወደ ተለያዩ የድንበር አካባቢዎች እየተስፋፋ ለመሆኑ ምልክት ነው" ይላሉ። ሃምዳያት የድንበር አካባቢ መሸጋገሪያ ስትሆን በቦታው ያለው የመጠለያ ማዕከል በዩኤንኤችሲአር ቢቋቋምም ትንሽ ቁጥር ያላቸውን ተፈናቃዮች ለማስተናገድ የተከፈተ ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለማስተናገድ የተቋቋመው ማዕከል በሺህዎች በሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ተጨናንቋል። ማዕከሉ ማስተናገድ ከሚችለው በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ተጨናንቆ የሚገኝ ሲሆን ተፈናቃዮች በአካባቢው እንዲሁም ወደ ሃምዳያት ከተማም ለመሄድ መገደዳቸውንም አስተባባሪው ይናገራሉ። ተፈናቃዮቹ ባገኟቸው መጠለያዎች ሁሉ ተጠልለው እንደሚገኙም አክለዋል። የአካባቢው ማሕበረሰብ ለተፈናቃዮቹ ደግነትን በማሳየት ያላቸውንም እያጋሯቸው እንደሚገኙም ይናገራሉ። የአካባቢው ባለስልጣናት በተመሳሳይ መልኩ ተፈናቃዮቹን በበጎ መልኩ ተቀብለው እያስተናገዱ ሲሆን ስደተኞቹ የሚያርፉባቸው ስፍራዎችን በመለየት ላይ ይገኛሉ። የተፈናቃዮቹን ህይወት ከማዳንና ድንገተኛ ሥራ ከመስራት በተጨማሪም ዩኤንኤችሲአር በዋነኝነት ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራበትም ስደተኞቹ መጠለያ እንዲያገኙ ማድረግም ነው። "ተፈናቃዮቹ በድንጋጤና በፍርሃት ተውጠው ይገኛሉ። በርካቶቹ ለደኅንነታቸው ይሰጋሉ። ከደረሱም በኋላ ጥላቸውን አያምኑም። ብዙዎቹም እዚህ ደህና ነን ወይ እያሉ ይጠይቃሉ? አሁንም ህይወታችን ከአደጋ ወጥቷል ብለው አያምኑም" ይላሉ አስተባባሪው። አንዳንዶቹም ቀጥታ ጦርነት ከሚደረግባቸው ቦታዎች የሸሹ ሲሆን ስለደረሰባቸውም ጥቃትና እንግልት ለዩኤንኤችሲአር አስረድተዋል። በተለይም በአሁኑ ወቅት ለዩኤንኤችሲአር ፈተና የሆነበት የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከቀን ወደ ቀን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ጋር ተያይዞ በሺህዎች ለሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በአፋጣኝ የድጋፍ እርዳታ ማድረግ ነው። ማዕከሉ በዚህ ደረጃ ስደተኞችን ለመቀበል የአቅርቦት ማዕከል ባለማዘጋጀቱም ጭምር እክል ሆኗል። በሱዳንም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃም እርዳታም ለማሰባሰብ ጥረት እየተደረገም እንደሆነ ይናገራሉ። የተፈናቃዮቹ ሁኔታ ለዩኤንኤችሲአር እንዲሁም ለአጋር ድርጅቶቹ በዓለም ምግብ ፕሮግራምና በዩኒሴፍ ዋነኛ ኃላፊነት በመሆኑም የድንገተኛ ቡድኖችን በመላክ ይገኛሉ። የተለያዩ እርዳታዎችንም በማሰባሰብ ጭምር እንደሚገኙ የገለፁት አስተባባሪው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ከሱዳን መዲና ካርቱም እንዲሁም ከውጭ አገራት እየገቡ ነው ብለዋል። የፌደራል መንግሥት ሕግን የማስከበር ሂደት በሚለው ዘመቻ ከትግራይ ክልል ልዩ ኃይል የተቀሰቀሰውን ግጭት በመሸሽ በርካታ ሰዎች ወደ ሱዳን ለመሰደድ መገደዳቸው ተነግሯል።
news-50167138
https://www.bbc.com/amharic/news-50167138
". . . ጦርነት ታውጆብን ነበር" ምክትል ፕሬዝደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ትናንት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል። ስለፕሬዝዳንት ኢሳያስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ወደ መቀሌ መምጣትን በተመለከተ "የትግራይ መንግስት የኤርትራ እና የትግራይ ህዝቦች ዝምድና እንዲጠናከር፣ ግንኙነቱ ወደ ንግድና ትብብር እንዲሸጋገር ከፍተኛ ፍላጎት" እንዳለ ጠቅሰው "የፌደራል መንግሥት ያላደረገው ነው እያደረግን ያለነው፤ የፌደራል መንግሥት ከሚሰራው ሥራ አንጻር ሲታይ እኛ እልፍ እየሰራን ነው" ብለዋል ዶክተር ደብረጽዮን። • ዶዶላ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት የ4 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በሌሎች ከተሞችም ተቃውሞው ቀጥሏል • በኦሮሚያ ከተሞች በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች 6 ሰዎች ተገደሉ የተዘጉ የድንበር መተላለፊያዎችን በተመለከተ "ፕሬዝደንቱ በመኪና ነው ወይስ በአውሮፕላን የሚመጡት የሚለው ትተን፤ መንገዱ ሳይከፈት ግን እንዴት ነው የሚመጡት? ብለን እንጠይቅ። እኛ የተዘጋው መንገድ እንዲከፈት እንፈልጋለን፤ መጥተው ለማስተናገድም ዝግጁ ነን። ግን መንገድ ተከፍቶ በመኪና እንጂ በአውሮፕላን እንዲመጡ አንጠብቅም" በማለት የፕሬዝደንት ኢሳይያስን ወደ መቀለ መምጣት እንደሚደግፉት ገልጸዋል። ዶክተር ደብረጽዮን ጨምረውም ከዚህ በፊት ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር እንዲገናኙ ተፈልጎ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ መቅረቱን አንስተዋል። 'የትግራይ ህዝብ አደጋ ላይ ነው' 'የትግራይ ህዝብ አደጋ ተደቅኖበታል' በማለት የክልሉ መንግሥት ህዝብ የሚያነሳቸው ጥያቄዎችን ላለመመለስ ሰበብ እያቀረበ ነው የሚል ትችት ይቀርባል ተብለው የተጠየቁት ዶክተር ደብረጽዮን "ህዝቡ ላይ የተጋረጠ የህልውና አደጋ አለ፤ ለዚህ ነው አንድ እንሁን የምንለው። ህዝቡ በህልውናው የመጡበት ስጋቶች አሉ። የዚህ ህዝብ ደህንነት ካልተጠበቀ ደግሞ" የመልካም አስተዳደርና የመሬት ጥያቄዎች ትርጉም አይኖራቸውም" ሲሉ መልሰዋል። "በመሆኑም በማንኛውም ጊዜ የትግራይ ህዝብ ሰለምና ደህንነት መጠበቅ ቀዳሚ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው" ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፤ ከዚህ በፊት ወደ መቀሌ የአየር ማረፊያ መጥተው የነበሩት የፌደራል ፖሊስ የጸረ ሽብር አባላትን ጉዳይ አንስተው ያን ድርጊት "ጦርነት እንደታወጀብን ነው የምንቆጥረው" በማለት "ቃታችንን ያልሳብነው እኛ እንጂ በእነሱማ ጦርነቱ ታውጆብን ነበር" ሲሉ ተናግረዋል። የኢህአዴግ ውህደት በኢህአዴግ የውህደት ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት የትግራይ ምክትል ፕሬዝደንት ዶክተር ደብረጽዮን "ህወሓት በውህደቱ ላይ የተለየ አቋም እንደሌለውና እንዲተገበር እንደሚፈልግ" ተናግረዋል። "የአራቱ ድርጅቶች የፖለቲካ ፕሮግራም አንድ አይነት ነበር፤ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነበር። አሁን ግን አንድ አይደለንም። ልዩነታችን አደባባይ ላይ ወጥቷል። ስማቸውን የቀየሩት ድርጅቶችም ፕሮግራማቸውን ለመቀየር አስበው ነበር፤ ከተቀየረው ፕሮግራማቸው ጋር ወደ ሃዋሳ ቢመጡ ኖሮ ያን ጊዜ እንለያይ ነበር" ብለዋል። • የትግራይ ክልል አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ አማራ ክልል አንደማይልክ አስታወቀ • ዛሬ በመቀሌ ሊካሄድ የነበረ ሠላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ አሁን ያለው ልዩነት የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነት መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ደብረጽዮን "ህወሓት ሳይሆን ቃሉን ያላከበረው፤ ከሃዋሳው ጉባኤ በኋላ ክዳችሁናል ነው እያልናቸው ያለነው" በማለት ኢህአዴግ ፕሮግራም የመቀየር ፍላጎት ካለው አስቸኳይ ስብሰባ መጥራት እንዳለበት ገልጸዋል። ስለ ተከለከሉ ሰልፎች "መንግሥት የሴቶች ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው። ሰልፍ ተከልክሏል መባሉን ሰምቻለሁ፤ ለምን ያላሟሉት ነገር ካለ አሟሉ አትሉም? ለምን ትከለክላላችሁ? ጠርታችሁ አናግሯቸው ብያቸዋለሁ። ለትግራይ ይጠቅማል ያለ ሁሉ፤ እኛን ለመስደብም ቢሆን ሰልፍ መውጣት አለበት" ብለዋል። "ሰልፍ ይጠቅማል ወይ ካላችሁኝ? በእኔ እምነት አይጠቅምም" ያሉት ምክትል ፕሬዝደንቱ "መዋቅራዊ ጽዳት ላይ ባለንበት ወቅት አይደለም ሰልፍ ወሬም አያስፈልግም። እንዴት ወደፊት እናምራ በሚለው ግን መነጋገር እንፈልጋለን" ብለዋል። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በሚመለከት ይካሄዳል ስለተባለው ሰልፍ ደግሞ "መንግሥት በተግባር ሥራ በሚሰራበት ወቅት፤ መንግሥት ላይ ሰልፍ ማካሄድ አስፈላጊ አይደለም" ሲሉ ተችተዋል።
news-53373006
https://www.bbc.com/amharic/news-53373006
የዊል ስሚዝ ባለቤት ስለነበራት የፍቅር ግንኙነት በቀጥታ ስርጭት ላይ ተናገረች
ጃዳ ፒንኬት ስሚዝ ኦውገስት አልሲና ከተሰኘ የራፐ ሙዚቀኛ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንደነበራት በቀጥታ የፌስቡክ ስርጭት ለባለቤቷ ዊል ስሚዝ ይፋ ማድረጓ አነጋጋሪ ሆኗል።
ሬድ ቴብል ቶል በተሰኘው የፌስቡክ ቀጥታ ስርጭቷ ላይ ነው ወ/ሮ ፒንኬት ለባለቤቷ ምስጢሩን የዘረገፈችው። ነገር ግን፤ ጃዳ ፒንኬት ከአልሲና ጋር ግንኙነት የነበራት ከዊል ስሚዝ ጋር ተቆራርጠው ሳለ እንደነበር ይፋ አድርጋለች። "ከዚያ በኋላ ተለያይተናል" ስትል ነገሩ በጊዜው እንደተቋጨ አሳውቃለች። "ከዚያ በኋላ ባለው ጊዜ ከኦውገስት ጋር የተለየ ግንኙነት ነው ያለን" ብላለች። "በወቅቱ ጥሩ ሁኔታ ላይ አልነበርኩም። ልቤ ተሰብሮ ነበር" ስትል የነበረችበትን ሁኔታ ገልፃለች። ዊል እና ጃዳ ፒንኬት ስሚዝ ከአውሮፓውያኑ 1997 ጀምሮ በትዳር ኖረዋል። ሁለት ልጆችም አፍርተዋል። ጥንዶቹ በቅርቡ ተለያይተው እንደገና እንደተጣመሩ ይፋ አድርገው ነበር። ጥንዶቹ፤ ማኅበራዊ ድር-አምባዎች ላይ እየተነዙ የተለያዩ አወዛጋቢ ወሬዎችን ለማጥራት ነው ሐቁን ለመናገር የወሰንነው ብለዋል። የማኅበራዊ ድር-አምባ ተጠቃሚዎች ስለ ጥንዶቹ ትዳር ማውራት የጀመሩት ኦውገስት የተሰኘው 'ራፐር' አንድ የራድዮ ዝግጅት ላይ ቀርቦ ፍንጭ የሚሰጥ ነገር ከተናገረ ወዲህ ነው። ኦውገስት አልሲና ከጃዳ ፒንኬት ጋር የነበረውረውን ግንኙነት ዊል ስሚዝ እንደሚያውቅና ይህ ደግሞ ጥንዶቹ በይፋ ከሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል የተዛባ ነገር ፈጥሮ እንደነበር ተናግሯል። ጃዳ ፒንኬት ስሚዝ የአጭር ጊዜ የፍቅር ጓደኛዋ ኦውገስት ትዳሯ ላይ ችግር እፈጥራለሁ የሚል ስጋት እንነበረው ትናገራለች። ነገር ግን "እኔና አንተ በፈቃደኝነት ስለሆነ የተለያየነው እሱ ምንም አላጠፋም" ስትል ለባለቤቷ ተናግራለች። ዊል ስሚዝ፤ ምንም እንኳ ተለያይተው የነበረ ቢሆንም በወቅቱ ባለቤቷ ለምን ወደ ሌላ ወንደ እንደሄደች ጠይቋታል። "በቃ ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ እፈልግ ነበር" ብላ ስትመለስ ዊል ስሚዝ በመስማማት ፊቱን ሲነቀነቅ በምስሉ ላይ ይታያል። ጥንዶቹ ወደ ትዳራቸው ከተመለሱ በኋላ ፍቅራቸው "ገደብ የለሽ" መሆኑን ወ/ሮ ስሚዝ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ አስታውቃለች። በስርጭቱ መጨረሻ ላይ ጥንዶቹ አይበሉባቸው ካገጫጩ በኋላ "አብረን እንጓዛለን፤ አብረን እንሞታለን። ትዳር እስከ መቃብር" ሲሉ ተደምጠዋል።
news-55629203
https://www.bbc.com/amharic/news-55629203
አንበጣ ወረራ ፡ በምስራቅ አፍሪካ አዲስ የአንበጣ ወረራ ስጋት እንዳለ ፋኦ አስጠነቀቀ
በደቡብ ኢትዮጵያና በሰሜን ኬንያ የተከሰተው አዲስ የአንበጣ መንጋ በምሥራቃዊ አፍሪካ አካባቢዎች እየተዛመተ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የምግብና እርሻ ድርጅት [ፋኦ] አስጠነቀቀ።
ድርጅቱ ሰኞ ዕለት ባወጣው መረጃ፤ አዲስ የተፈለፈሉ የአንበጣ መንጋዎች ከዚህ ቀደም ከተከሰተባቸው ምሥራቅ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ሶማሊያ በመሰደድ ወደ ኢትዮጵያ ደቡብ ክልል እና ወደ ሰሜን ኬንያ እና የባህር ዳርቻዎች አካባቢ እየተስፋፋ ነው ብሏል። እስካሁን ድረስ በአራት የኬንያ ግዛቶች ማለትም በዋጂር፣ ጋሪሳ፣ ማርሳቢት እና በቅርቡ ደግሞ ኢሲኦሎ ግዛቶች የአንበጣ መንጋው መከሰቱን ድርጅቱ ጠቅሷል። "የአንበጣ መንጋው መራባቱን ቀጥሏል። በኬንያ ደቡብ ምስራቅ ታይታ ታቬታ እና በባህር ዳርቻዎች አካባቢ ደግሞ እድገቱን ያልጨረሰ የአንበጣ መንጋ ይገኛል" ብሏል ድርጅቱ። የተወሰነው የአንበጣ መንጋ በዚህ ወር ወደ ሌሎች የኬንያ አካባቢዎች እንዲሁም ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳ ሊደርስ እንደሚችል ድርጅቱ አስጠንቅቋል። የአንበጣ ወረራ በቀጠናው ለምግብ ዋስትና ትልቅ ስጋት መሆኑን የጠቀሰው ድርጅቱ፤ ባለፈው ዓመት በቀጠናው የተከሰቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ አንበጣዎች በሰብል ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጿል። በመሆኑም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቱ፤ አገራት ጥናት ለማካሄድ፣ የአንበጣ መንጋውን ፍልሰት ለመቀነስ እና የነፍሳቱን እርባታ ለመቆጣጠር አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርጉ አሳስቧል። ድርጅቱ አክሎም የአንበጣ መንጋው በማዕከላዊ ኬንያ ምን አልባትም ደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ምስራቅ ታንዛኒያ፣ ምስራቃዊ ኡጋንዳ እና በደቡብ ምስራቅ ደቡብ ሱዳን በተያዘው ወር ሊደርስ እንደሚችል ትንበያውን አስቀምጧል። በሰሜን ምሥራቅ ታንዛኒያ ምዋንጋ አካባቢ እድገቱን ያልጨረሰ የአንበጣ መንጋ መታየቱን ሪፖርቶች እንደሚያመልክቱ ድርጅቱ ገልጿል። "የአንበጣ መንጋ የሚመቸው ቦታ ላይ ከደረሰ፤ በማደግ፣ እንቁላል በመጣልና በመፈልፈል በየካቲትና መጋቢት ወር ላይ እድገቱን ያልጨረሰ የአንበጣ መንጋ ይፈጠራል" ሲል አሳስቧል ድርጅቱ። በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።
news-45588933
https://www.bbc.com/amharic/news-45588933
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ወላጆች በሌላ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሄደው ለመማር ስጋት እንዳለባቸው ገለፁ
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣት ብቻ ሳይሆን የት ዩኒቨርሲቲ ይደርሰኝ ይሆን? የት ይመደቡ ይሆን? የሚለው የተማሪዎችም የወላጆችም ስጋት ከሆነ ቆይቷል።
በአዲስ አበባ የሚኖረው በቃሉ ሰንዳፋ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አምጥቶ፤ ምደባ እየተጠባበቀ ይገኛል። እንደ አዲስ ተማሪነቱ ቀደም ብለው ሲማሩ ከነበሩ ጓደኞቹ ጋር ስለተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ሁኔታ ሃሳብ ተለዋውጧል። ከእነርሱ የሰማውና ከዚህ በፊት በተለያዩ ቦታዎች እየተፈጠሩ ያሉ አጋጣሚዎች እርሱን ብቻ ሳይሆን ወላጆቹንም በተለይ እናቱን ስጋት ውስጥ እንደጨመረ ይናገራል። "ብጥብጥ ነበረባቸው የሚባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ብመደብ የምፈራ ይመስለኛል" ይላል። በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ልጅ ያለቸው አባት በበኩላቸው "ባለፉት ዓመታት የተፈጠረውን አይተናል፤ ብዙዎች ለመማር ሄደው ሞተዋል። ይህ ችግር አሁንም እየቀጠለ ነው። በዚህ ሁኔታ ልጆቻችን የኛን ተስፋ እንዲሞሉ ብለን ሬሳቸውን መቀበል አንፈልግም፤ ለመላክም ፍቃደኛ አይደለሁም" ሲሉ እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተገደዱ ይናገራሉ። • በእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች ያነጋገርናቸው ተማሪዎችና ወላጆች ከተናገሩት በተጨማሪ በቅርቡ በመቀሌ የሚገኙ የትግራይ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች በአገሪቱ በሚገኙ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ሄዶ ለመማር ደህንነት አይሰማንም ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቃቸው ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው። ይህ ስሜት በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች የሚገኙ ተማሪዎችና ወላጆችም ይጋሩታል። ብሔርን መሰረት ያደረጉ ናቸው የተባሉ ጥቃቶች በተለያዩ አካባቢዎች መሰማታቸውም ጭንቀታቸው እንዲባባስ አድርጎታል። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ ዓመት ተማሪ የሚያስተምሩት አቶ ሰለሞን ዮሐንስ ከዚህ ቀደም በዩኒቨርሲቲው አጋጥመው የነበሩ ብሔርን መሰረት ያደረጉ እንግልቶችን ጠቅሰው "የአሁኑ ደግሞ የባሰ ነው፤ እንኳን ብዙ ርቀት ለመላክ ይቅርና እዚህም ሆነን እየሰጋን ነው፤ እርሷ መመረቅ ብትፈልግም እኔ ግን ጨክኜ ለመላክ አልወሰንኩም" ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር አብዱልዋሴ ሁሴን በየዓመቱ ሁሉንም በሚፈለገውና በተሳካ ሁኔታ ለማስፈፀም የሚያስችል አደረጃጀት እንዳላቸው ይናገራሉ። ዘንድሮም በቂ ዝግጅት እንዳደረጉ በመግለፅ "ወደዚህ የሚመጣ ተማሪ የኛም ልጅ ነው፤ ከምንም በላይ ደግሞ የሰላሙ ዘብ ተማሪው ራሱ ስለሆነ ምንም ዓይነት ስጋት ሊገባቸው አይገባም" ብለዋል። • ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን? ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪም "ደህና ናቸው የሚባሉ አካባቢዎችም ወደ ረብሻና ግርግር እየገቡ ነው፤ ባለፉት ዓመታት የነበረው አገራዊ ሁኔታ ሊቀየር ስላልቻለ፤ ወደ ሌላ ክልል መሄድ ያሰጋኛል" ሲል ይናገራል። በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ዳይሬክቶሬት ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ይዳኝ ማንደፍሮ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለመቀበል በተለያየ ዘርፍ በቂ ዝግጅት አድርጓል ይላሉ። "ተማሪዎቹ ገና ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲገቡ ጀምሮ ህግና ደንቡ ስለሚነገራቸውና ትምህርት ስለሚሰጣቸው ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ችግር ገጥሞን አያውቅም። ዩኒቨርሲቲው አምስት ግቢ ሲኖረው በቂና አስተማማኝ ፀጥታ አላቸው፤ ምንም ስጋት ሊገባቸው አይገባም" ሲሉ ያብራራሉ። ከዚህ ቀደም ከሌላ ቦታ ወደ ዩኒቨርሲቲው መጥተው የሚማሩ ተማሪዎች የሚያሰጋቸው የደህንነት ጉዳይ አልነበረም የሚሉት በዲላ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ሔኖክ ንጉሴ ናቸው። አሁንም ከየትኛውም አካባቢ የሚመጣ ተማሪ ደህንነት እንዲሰማው የተማሪዎች አደረጃጀቶችና የዩኒቨርሲቲው አካላት የቅርብ ክትትል እንዲቀጥል ተማሪዎች ከመግባታቸው አስቀድሞ እየሰሩ እንደሚገኙ ዳሬክተሩ ገልፀዋል። "ክልሉ የተለያዩ ብሔረሰቦች የሚኖርበት ነው፤ ድሮም ከሁሉም አካባቢ መጥተው ይማራሉ፤ አሁንም ለየት ያለ ዝግጅት የሚያስፈልገው አይደለም" የሚሉት ደግሞ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ዱንኳና ንጉሴ ናቸው። "የፀጥታ ስጋት የለም፤ በግቢው ውስጥም በቂ የሆነ ክትትልና ጥበቃ ይደረግላቸዋል" ብለዋል። የተማሪዎችንና ወላጆችን ስጋት አንስተን ያነጋገርናቸው በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክፍል ኃላፊ ዶክተር ሳሙዔል ክፍሌ ያለፉት ዓመታት ተመሪዎችን ብቻ ሳይሆን ወላጆችንና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያሰጋ እንደነበር ያወሳሉ። ይሁን እንጂ አሁንም አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ ችግሮች መኖራቸውን አልካዱም። "በዚህ ዓመት የተሻለ ሁኔታ እየተፈጠረ ስለሆነ ስጋት ላይ የሚጥል ነገር የለም። መንግሥትና የፀጥታ ኃይሉ ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ ጥሩ አቅም ላይ ይገኛል" ይላሉ ዶክተር ሳሙዔል። አንድ አገር እስካለን ድረስ በተወለድንበት ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ካልሆነ መማር አንችልም የሚለው ጥያቄ ግን ተቀባይነት እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል። ማንኛውም ዜጋ በአገሪቱ ባሉ አካባቢዎች የመማር ብቻ ሳይሆን የመኖርና የመስራት ህገ መንግሥታዊ መብት እንዳለው የገለፁት ኃላፊው "እንደ አገር ሰላም ከሌለ፤ በክልላችን ብቻ ስለተመደብን ሰላም እንሆናለን ብሎ ማሰብ ስህተት ነው" በማለት ሃሳቡን ተቃውመውታል። • ከአንታርክቲካ በስተቀር ስድስቱን አህጉሮች ያዳረሰችው ኢትዮጵያዊት • ፍኖተ ካርታው ወደ ቀድሞ የትምህርት ፖሊሲ ሊመልሰን ይሆን ? በመሆኑም ተማሪዎቹ በተመደቡበት ቦታና እጣ መሰረት መሄድ አለባቸው፤ ለደህንነት በሚል ሰበብ በክልላቸው የሚመደቡበት ሥርዓትም አይኖርም፤ መፍትሔም አይሆንም ብለዋል። በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩት ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ ሌሎች ነዋሪዎችም በመሆናቸው የሚበጀው የሁሉንም ሰላም ማረጋገጥ ብቻ ነው ሲሉ አስረድተዋል። የዩኒቨርሲቲ መምህራንና አመራሮች በፍኖተ ካርታው ላይ የሚያደርጉት ውይይት እንደተጠናቀቀ እንደ የራሳቸው ዝግጁነት ተማሪዎችን ለመቀበል ከመስከረም 28 በኋላ ጥሪ ማድረግ እንደሚጀምሩ ገልፀዋል። ዶክተር ሳሙዔል ባለፉት ሁለት ዓመታት የነበሩት ችግሮች በትምህርት ዘርፉ ላይ ብቻ ሳይሆን፤ በዲፕሎማሲው፣ በልማቱ ዘርፍ፣ በማህበራዊ ጉዳይ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በአገር ገፅታ ላይ ኪሳራ ማሳደራቸውን አስታውሰዋል።
news-44908118
https://www.bbc.com/amharic/news-44908118
በምሥራቅ ወለጋ የአራት ቀን ሬሳ አስነሳለሁ ብሎ መቃብር ያስቆፈረው 'ነብይ' በቁጥጥር ሥር ዋለ
አቶ በላይ ቢፍቱ የሊሙ ወረዳ ገሊላ ከተማ ነዋሪ ነበሩ። ባሳለፈነው ሰኞ ነበር በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው።
እራሱን ነብይ የሚለው ግለሰብ ሟችን ለማስነሳት ሲጥር ቤተሰብ ሃዘን ተቀምጦ ሳለ ጌታያውቃል አየለ የሚባል ግለሰብ ለሟች ቤተሰቦች የመጽሐፍ ቅዱሱን አልአዛር ታሪክ ከነገራቸው በኋላ ሟቹ በላይን እንደሚያስነሳ ይነግራቸዋል። ከዚያም በላይን ከሞት እንደሚያስነሳ የቤተሰብ አባላቱን ካሳመነ በኋላ በላይ ወደተቀበረበት ወደ ሙሉ ወንጌል የመቃብር ስፍራ ይዟቸው ሄደ። • ሰባኪው አውሮፕላን ግዙልኝ አለ • በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው በአዞ ተገደሉ በቤተክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ የነበሩት የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ሰራተኛ የሆኑት አቶ ዲንሳ ደበላ ''ከመቃብሩ ስፍራ በላይ ከሞት ይነሳል የሚል ተደጋጋሚ ድምጽ ሰምቼ ምን እየተከናወነ እንደሆነ ለማጣራት ወደ ስፍራው ሄድኩ'' ይላሉ። እሳቸው እንደሚሉት ድርጊቱ የቤተክርስቲያኒቷን ስርዓት እንደሚጻረር በመንገር ድርጊቱ እንዲቆም ሲያሳስቡ ከግለሰቦቹ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው ሲል ሸሽተዋል። ከዚያም ጌታያውቃል የተባለው ግለሰብ መቃብሩን አስቆፍሮ የሬሳ ሳጥኑን ከከፈተ በኋላ በተደጋጋሚ ''በላይ ተነስ'' እያለ ሲጮህ ነበር። በዚህ ብቻ ያልተቆጠበው ይህ ግለሰብ የሬሳ ሳጥኑ ላይ ተዘርግቶ በመተኛት 'ተነስ' እያለ በተደጋጋሚ ድምጹን አሰማ። ራሱን ነብይ እያለ የሚጠራው ይህ ግለሰብ ከላይ የተጠቀሰን ድርጊት ሲፈጽም የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ በርካቶች ሲቀባበሉት ውለዋል። በመጨረሻም መልስ ያጣው ግለሰብ ''ምንም ማድረግ አይቻልም'' ብሎ ከመቃብሩ ጉድጓድ ውስጥ ወጥቶ ሊሄድ ሲል ጉዳይን በአትኩሮት ሲከታተሉ የነበሩ የአካባቢው ሰዎች እና የቤተሰብ አባላት በግለሰቡ ድርጊት በመበሳጨታቸው ሊደበድቡት ተነሱ ሲሉ አቶ ዲንሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዘግይቶ በአካባቢው የተገኘው ፖሊስ አቶ ጌታያውቃልን ከመደብደብ አትርፎት በቁጥጥር ስር አውሎታል። ''አሁን በቁጥጥር ስር ይገኛል'' ሲሉ የሊሙ ወረዳ የፖሊስ አባል የሆኑት ኮማንደር ታደሰ አማኑ ነግረውናል። ''ግለሰቡ የፈጸመውን ድርጊት እያጣራን ነው። ነብይ ነኝ የሚለው ይህ ሰው በአካባቢው ያሉ የየትኛውም ቤተክርስቲያን አባል እንዳልሆነ አረጋግጠናል'' ሲሉ ለቢቢሲ ጨምረው ገልፀዋል። ይህ ግለሰብ የወረዳው ጤና ቢሮ ባልደረባ ስለመሆኑም ከምንጮቻችን መረዳት ችለናል።
news-48374310
https://www.bbc.com/amharic/news-48374310
በገላን የጋራ መኖሪያ ቤቶች አሰሪዋን በዘነዘና የደበደበችው እየታደነች ነው
ከትላንት በስትያ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ገደማ በገላን ኮንደሚኒየም አንዲት የቤት ሠራተኛ አሠሪዋና ሓፃናት ልጆቿ ላይ በስለት እና በዘነዘና ጉዳት አድርሣ ተሰውራለች።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለቢቢሲ እንደገለፁት የመግደል ሙከራው የተከሰተው ከትናንትና ወዲያ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ገላን ኮንደሚኒየም ነው። የቤት አሰሪዋ የ25 አመት ዕድሜ ያላቸው ቅድስት ሀብቴ ከልጆቿና አሁን ከተጠረጠረችው ሰራተኛ ፅጌ ምናቡ ጋር አብራ ትኖር ነበር። "አሰሪዋ በተኛኝበት ጭንቅላቷን በዘነዘና በመምታት እንዲሁም የሶስት አመት ህፃን ልጅ በቢላዋ አንገቷንና እንዲሁም የአንድ አመት ጨቅላም በደረሰባት ጉዳት በአፏና በአፍንጫዋ አካባቢ ደም ፈሷታል" ብለዋል። •"የከተማ መስፋፋት የኢትዮጵያን ብዝሀ ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል" ዶ/ር መለሰ ማርዮ •በጉጂ አስር ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ •ኬንያዊው ፀሀፊ ቢያንቫንጋ ዋይናይና ሲታወስ ጉዳቱን ካደረሰች በኋላ የተሰወረች ሲሆን ፖሊስ አለችበት የምትባለው አካባቢ ፍለጋ እያደረገ መሆኑን ነው። አሰሪዋም ሆነ ልጆቹ ለህይወታቸው የሚያሰጋ ምንም ነገር እንደሌለ ጤናቸው እያገገሙ መሆኑንም ተናግረዋል። የፀቡ መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን ድረስ እንዳልታወቀም ምክትል ዳይሬክተሩ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
news-53635577
https://www.bbc.com/amharic/news-53635577
አረብ ኤሜሬቶች የአረቡ ዓለም የመጀመሪያ የሆነውን የኒውክሌር ማብላያ ጣቢያ ሥራ አስጀመረች
የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የአረቡ ዓለም የመጀመሪያ የሆነው የኒውክሌር ማብለያ ጣቢያ ሥራ አስጀምረች።
በአውሮፓውያኑ 2017 ላይ ለማስጀመር እቅድ ተይዞለት የነበረው የኒውክሌር ጣቢያ ከሶስት ዓመታት መዘግየት በኋላ የደቡብ ኮሪያ ቴክኖሎጂ ይዞ ወደ ሥራ ገብቷል። ባራካሃ የሚል ስያሜ የተሰጠው የኒውክሌር ጣቢያው በነዳጅ ሃብቷ ለበለጸገችው የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች (ዩኤኢ) ሌላ የገቢ አማራጭ ይሆናታል ተብሏል። ዩኤኢ ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ ማርስ በማቅናት በባህረ ሰላጤው አገራት በህዋ ምርመራ ፈር ቀዳጅ መሆኗ ይታወሳል። ዩኤኢ ከዚህም በተጨማሪ ከጸሃይ ብርሃን ኃይል ለማመንጨት ከፍተኛ ገንዘብ መድባ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። በርካቶች ግን የባርካሃ ኒውክለር ማብለያ ጣቢያ አስፈላጊነት ላይ ጥያቄያቸውን እያነሱ ይገኛሉ። ይህን የኒውክለር ጣቢያ ለመመስረት፣ ለማንቀሳቀስ እና የሚያስገኘውን ጥቅም ከጸሃይ ብርሃን ኃይል ጋር በማነጻጸር የኒውክሌር ማብላያ ጣቢያ ፕሮጄክቱን የሚተቹ በርካቶች ናቸው። ኳታር ግን ከጸሃይ ብርሃን የሚገኘው ኃይል በአነስተኛ ዋጋ ከኒውክለር የተሻለ ኃይል ያስገኛል በማለት ግንባታው አስፈላጊ አይደለም ስትል ትከራከራለች። በቀጠናው የዩኤኢ እና ሳኡዲ አረቢያ ተቀናቃኝ የሆነችው ኳታር፤ ባራካሃ የኒውክለር ጣቢያ “ለቀጠናው ሰለም፣ ደህንነት እና ከባቢያዊ አየር ስጋት ነው” ብላ ነበር። ዩኤኢ ይህን የኒውክለር ማብላያ ጣቢያ እየገነባች ያለችው ከኳታር ድንበር አቅራቢያ ላይ ነው። ሌላኛዋ ከባህራ ሰላጤ አገራት በቅርበ ርቀት ላይ የምትገኘው ኢራን ነች። ኢራን በኒውክለር ማብለያ ጣቢያዋ ምክንያት በአሜሪካ ማዕቀብ ተጥሎባት እንደምትገኝ ይታወቃል። የዓለም አቀፉ የኒውክለር አማካሪ ቡድን ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር ፖል ዶርፍማን ከአንድ ዓመት በፊት “ኒውክለር ማብላያ ጣቢያ በባህረ ሰላጤው አገራት መካከል የሚኖረውን ፖለቲከዊ ግነኙነት ከባድ ያደርገዋል። አዲስ የኒውክለር ማብላያ ጣቢያ የኒውክለር ጦር መሳሪያ ባለቤት ማድረግ ይችላል” ብለው ጽፋው ነበር። ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ፕሮጄክት በባህረ ሰላጤው አገራት የሬዲዮ አክቲቭ ብክለት ሊያስከትል እንደሚችልም ተነግሯል። ይሁን እንጂ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ የኒውክር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን ባወጣው መግለጫ፤ በከባቢያው አየር ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ “ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ጥንቃቄዎችን እተገብራለሁ” ብሏል። ኮርፖሬሽኑ ጨምሮ እንዳለው፤ ፕሮጄክቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ የዩኤኢን 25 በመቶ የኤሌክትሪክ ፍላጎት ይሸፍናል፤ 21 ሚሊዮን ቶን የካርበን ልቀትን ይቀንሳል። ይህ ማለት በየዓመቱ 3.2 ሚሊዮን መኪኖችን ከመንገድ ማንሳት ነው። ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የዩኤኢን ባርካሃ ፕሮጄክት ሲደግፍ መቆየቱ ተነግሯል። የአቡ ዳቢ መሪ ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ዛይድ በትዊተር ገጻቸው የፕሮጄክቱ ሥራ መጀመሩን በማስመልክት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
news-49260745
https://www.bbc.com/amharic/news-49260745
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ለምን ተስተጓጎለ?
በመላው ሃገሪቱ ባሉት ቅርንጫፎችና በትልቅነቱ ቀዳሚ እንደሆነ የሚነገርለት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአራት ተከታታይ ቀናት ተስተጓጉሎ የነበረውን አገልግሎት አስተካክሎ መደበኛ አገልግሎቱን መስጠት እንደጀመረ የባንኩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የአብሥራ ከበደ ለቢቢሲ ገለፁ።
• በሴት ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ • የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ስለ ንግድ ባንክ እርዳታ ምን ይላሉ? ከሰሞኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የተለመደውን አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ ተገልጋዮች ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ22 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችና ከ1450 በላይ ቅርንጫፎች እንዳሉት የገለፁት ኃላፊው፤ ከባለፈው ሳምንት አርብ ጀምሮ ሲስተሙ የመዘግየት ችግር እንዳጋጠመውና ሙሉ በሙሉ ተስተጓጉሎ እንደነበር አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ባሳለፍነው እሁድ ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሶ የኤትኤም ማሽኖች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ገልጸዋል። ይኽው አገልግሎት እንደገና ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በድጋሚ መስተጓጎል ገጥሞት የነበረ ቢሆንም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መደበኛ አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። "በአጠቃላይ ለአንድ ቀን ተኩል ያህል ነበር አገልግሎቱ የተቋረጠው" የሚሉት ኃላፊው አገልግሎቱ ከተስተካከለ በኋላ በየቅርንጫፎቹ የደንበኞች ቁጥር ጨምሮ ነበር ይላሉ። ስለ ሲስተሙ መጨናነቅ የተጠየቁት አቶ የአብሥራ "እንዲህ ነው ተብሎ የሚገለፅ ነገር የለም፤ ግን ቴክኖሎጂ በባህሪው ድንገት የሚፈጠሩ ችግሮችን ያስተናግዳል" ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የሲስተም መጨናነቅ በባንኩ ውስጥ አሊያም በውጭ በሚፈጠሩ የኢንተርኔትና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት ሊፈጠር እንደሚችል የሚያስረዱት ኃላፊው፤ አሁን ያጋጠመው ችግር ግን በራሱ በባንኩ ሲስተም መጨናነቅ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ባንኩ ለሚመጡት 10 ዓመታት የሚያገለግል ዘመናዊ የመረጃ ቋት ያለው ቢሆንም ያጋጠመው እክል አንዳንድ ጊዜ በቴክኖሎጂ ላይ በሚፈጠሩ ጊዜያዊ ችግሮች ነው። በነበረው መስተጓጎል የደረሰውን ኪሳራ አስመልክተን ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ የአብሥራ "ባንኩ የደንበኞች አገልግሎት ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ ነበር እንጂ፤ ባጋጠመው መስተጓል ያጋጠመው ኪሳራ ስሌት ውስጥ አልገባም"ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ወደፊት ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። የደንበኞች ቁጥር በጨመረ ቁጥርም እንዲህ ዓይነት መጨናነቆች እንዳይከሰቱ ባንኩ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ፣ የኢንተርኔት፣ ሲቢኢ ብር፣ በካርድ አገልግሎት ክፍያ መፈፀሚያ ማቅረቡን በመግለፅ ደንበኞች ሳይንገላቱና ሳይደክሙ አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚችሉ ጠቁመዋል። እንደ አማራጭ የቀረቡት መንገዶች ከኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በኢትዮጵያ ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነትና ፍጥነት በርካቶች የሚማረሩበት ነው። እንዲያም ሲል በተለያዩ ምክንያቶች በተለያዩ ጊዜያት መዘጋቱ ጉዳዩን የከፋ ያደርገዋል። በመሆኑም እነዚህ ንግድ ባንክ ያስቀመጣቸው አማራጭ አገልግሎቶች የበለጠ ጫናው ላይ አይወድቁም ወይ? ስንል ለኃላፊው ጥያቄ አንስተን ነበር። ኃላፊውም ችግሮች መኖራቸውን አምነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለችግሮቹ እልባት ለመስጠት ሃገሪቱ ውስጥ ያለውን እንዲሁም የራሱንም መሠረተ ልማት አጣምሮ እንደሚጠቀም ገልፀዋል። በዚህ መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ደንበኞች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል። "እስካሁን ከ5 ሚሊዮን በላይ የኤትኤም ካርድ ተጠቃሚዎች እና ከ2 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎች አሉ" የሚሉት ኃላፊው በኢትዮጵያ ካለው የሕዝብ ብዛት ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ በአገሪቱ የሚፈጠሩ ክፍተቶቹን ባንኩ እየሞላ አገልግሎት መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያጋጠመው መስተጓጎል ተፈታ ካለ በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ ተጠቃሚዎችና የባንኩ ሠራተኞችን በመጠየቅ ለማረጋገጥ ባደረግነው ሙከራ የነበረው ችግር መፈታቱን የገለጹ ሲሆን በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የሲስተም ዘገምተኛ መሆን እንዳለ ገልጸዋል። ስለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊው እንደነገሩን... • ከ22 ሚሊየን በላይ ደንበኞች አሉት • የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 542 ቢሊየን ብር ደርሷል • አጠቃላይ ሃብቱ ከ660 ቢሊየን ብር በላይ ነው • ከ5 ሚሊየን በላይ የኤ ቲ ኤም ካርድ ተጠቃሚዎች አሉት • ከ2 ሚሊየን በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎችን ያስተናግዳል • 38 ሺህ ሠራተኞች አሉት • ከ1450 በላይ ቅርንጫፎች አሉት • የደበኞች ቁጥር በየዓመቱ በ2 እና 3ሚሊየን ብልጫ ያሳያል።
48796515
https://www.bbc.com/amharic/48796515
አብን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከ100 በላይ አባላቶቼ ታስረዋል አለ
ሰኔ 15 አመሻሽ ላይ በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና በከፍተኛ የመከላከያ ጄነራሎች ላይ ግድያ ከተፈፀመ በኋላ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሰዎች እየታሰሩ መሆናቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ተናገሩ።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ "አባላቶቻችንና አመራሮቻችን በተለያዩ አካባቢዎች እየታሰሩብን ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የጅምላ እስር የሚመስል ነገር ነው ያለው" ያሉት አቶ ክርስቲያን "የአብን አባሎችና አመራሮች ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ንቃተ ህሊናቸው ከፍ ያሉ ናቸው ተብለው የሚገመቱ ግለሰቦችንና ነዋሪዎችንም ጭምር ዝም ብሎ የማሰር ሁኔታ ነው የሚታየው" ሲሉ ተናግረዋል። • "መደናገጥ ባለበት ወቅት ስህተቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ" አቶ ንጉሱ ጥላሁን • በቤንሻንጉል ክልል በሽፍቶች በደረሰ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ • የኤርትራ መንግሥት፡ 'የካቶሊክ ጤና ተቋማትን መውሰዴ ትክክል ነው' አለ 56 የሚደርሱ የክፍለ ከተማና የወረዳ አባላትና አመራሮች በአዲስ አበባ ታስረውብናል ያሉት አቶ ክርስቲያን ወደ 50 የሚደርሱ ደግሞ ወለጋ ላይ መታሰራቸውን ይናገራሉ። አዳማ አንድ፣ ጅማ ሰባት ወለንጪቲና ሱሉልታ አካባቢዎች ደግሞ 25 የሚደርሱ አባላት፣ አመራሮች እንዲሁም ንፁሃን ዜጎች ታስረዋል ያሉት አቶ ክርስቲያን ይህ መረጃ እስከ ትናንት ምሽት ድረስ ብቻ የተጠናቀረ ነው በማለት የታሳሪዎች ቁጥሩ ከዚህም ሊጨምር ይችላል ብለዋል። አባላቶቻቸው የታሰሩባቸውን ምክንያቶች ለማጣራት ስላደረጉት ሙከራ አቶ ክርስቲያን ሲገልጹ አዳማ የታሰረው የአብን ቅርንጫፍ አስተባባሪ ፍርድ ቤት መቅረቡንና ክሱ "ምንጃር አረርቲ ላይ የነበረውን ግጭት በገንዘብ ደግፈሀል" የሚል እንደሆነ አስረድተዋል። በአዲስ አበባ በተለምዶ ሦስተኛ የሚባለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ታስሮ የሚገኘው የብሔራዊ ምክር ቤት አባላችን ያሉት ግለሰብ ደግሞ ከሰሞኑ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ግንኙነት አላችሁ በሚል መታሰሩ እንደተነገረው አስረድተዋል። በአጠቃላይ በተለያየ አካባቢ የታሰሩ አባላቶቻቸውና አመራሮች "ለሰላምና ደኅንነት እንዲሁም መረጋጋት ስጋት ናችሁ" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው እንደነገሯቸው አቶ ክርስቲያን ገልጸዋል። ወለጋ ላይ የአብን አባል ያልሆኑ፣ ድሬዳዋ ላይ የአብን አባላት ብቻ ሳይሆኑ የአዴፓ አባላት የአብን ደጋፊ ናችሁ በሚል ተይዘዋል ያሉት አቶ ክርስቲያን አንዳንዶቹ ከሌሎች እስረኞች በተለያ ስፍራ መታሰራቸውን ሰምተናል ይህ ደግሞ ስጋት ውስጥ ይከተናል ብለዋል። "በመሰረታዊነት ሕግ መተላለፍ ካለ ለማንኛቸውም ወንጀለኛ አብን መደበቂያ ዋሻ እንዲሆን አንፈልግም" የሚሉት አቶ ክርስቲያን ንፁሀን ዜጎችና አባሎቻቸው በምን ምክንያት እንደታሰሩ ሳይነገር ለሰላምና ደህንነት ስጋት ናችሁ ብሎ ማሰር "አንድም ወንጀል ነው አንድም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሊቀ መንበርነት የሚመሩት ፓርቲ በሚያስተዳድረው ክልል ውስጥ እንዲህ አይነት ነገር መፈጠሩ ምናልባትም እዚያ አካባቢ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማጥበብና በተለይም አማራ መደራጀት እንዳላስደሰታቸው የሚያመላክት ሆኖ አግኝተነዋል" ብለዋል። ከአንድ አባላቸው በስተቀር ሌሎች የታሰሩ አባላትና አመራሮች ላይ ምንም አይነት ክስ አልቀረበም ያሉት አቶ ክርስቲያን አባላቶቻችን ከህግ አግባብ ውጪ በፖለቲካ አባልነታቸው ብቻ ማሰር የማሸማቀቅ ተግባር እየተፈፀመ ነው ሲሉ ይከስሳሉ። ሰሞኑን በሃገሪቱ ያጋጠመውን ችግር በተመለከተ መግለጫ የሸጠው የፀጥታና ፍትህ የጋራ ግብረ ኃይል ትናንት ባወጣው መግለጫ በአማራና በአዲስ አበባ ውስጥ ከድርጊቱ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርከታ ሰዎች እንደተያዙ አመልክቷል።
news-56547974
https://www.bbc.com/amharic/news-56547974
የሱዊዝ መተላለፊያ ለመርከቦች እንቅስቃሴ ክፍት ሆነ
ለሳምንት ያህል የስዊዝ ቦይን ዘግታ የነበረችው መርከብ ከቦታው ላይ መነሳቷንና መስመሩም ለእንቅስቃሴ ክፍት መደረጉን የግብጽ ባለሥልጣናት ተናገሩ።
መተላለፊያውን የዘጋችው ኮንቴይነር የጫነችው ኤቨርግሪን የጭነት መርከብ ከማክሰኞ ጀምሮ በአንዲት መርከብ የተዘጋው የሱዊዝ መተላለፊ መስመር ለመክፈት የተደረገው ጥረት ውጤት አስገኝቶ መርከቧ ከመተላለፊያው ላይ እንድትንቀሳቀስ ተደረጓል። ባለስልጣናት ለቀናት የተዘጋው የሱዊዝ ቦይ ቅዳሜ ወይም እሁድ ይከፈታል በማለት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቆይቶ ዛሬ ጠዋት መስመሩን ለማስከፈት ችለዋል። በዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ መስተጓጎልን ያስከተለው የመተላለፊያው መዘጋት ለተጨማሪ በርካታ ቀናት ሊቆይ ይችላል ተብሎ ቢሰጋም በተደረገው ጥረት ግዙፏ የጭነት መርከብ እንድትንቀሳቀስ ተደርጎ መተላለፊያው ሊከፈት ችሏል። ከማክሰኞ ጀምሮ የባሕር መተላለፊያ መስመሩን በአግድሞሽ ዘግታ የቆመችውን ግዙፏን የጭነት መርከብ ለማንቀሳቀስ ጥረት ሲደረግ ነበር። በዚህም ሳቢያ በመተላለፊያው የሰሜንና የደቡብ መግቢያ መስመር ላይ የሱዊዝ ቦይ መከፈትን በሚጠብቁ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው መርከቦች መጨናነቅ መፈጠሩ ተገልጿል። ጆ ሬይኖልድስ የታዋቂው የመርከብ እቃ አመላላሽ ድርጅት ሚርስክ ዋና ኢንጂነር ናቸው። ለቢቢሲ ሲገልጹ ''በቦዩ ደቡባዊ መግቢያ በኩል መንገዱ በመዘጋቱ በርካታ መርከቦች ለማለፍ እየተጠባበቁ ነው። ይህ ደግሞ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ፈጥሯል'' ብለዋል። ''በመላው ዓለም የተዘረጋው የመርከቦች የጉዞ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል'' ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ማክሰኞ ጠዋት አካባቢ 400 ሜትር ርዝማኔና 59 ሜትር ስፋት ያለው መርከብ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አሁንም ድረስ መንገድ እንደዘጋ ይገኛል። የሱዊዝ ቦይ በመባል የሚታወቀው የግብፅ መተላለፊያ ሜድትራኒያን እና ቀይ ባሕርን በማገናኘት በእስያና አውሮፓ መካከል አጭሩ የሚባለውን የውቅያኖስ መንገድ ይፈጥራል። በታይዋኑ ኤቨርግሪን ማሪን ሥር ያለው ኤቨር ጊቭን መርከብ በዓለም ትልቁ ኮንቴነር ጫኝ ሲሆን፤ 200,000 ቶን የሚመዝን እንዲሁም 20,000 ኮንቴነር ማጓጓዝ የሚችል ነው። ኤቨር ግሪን የተሰኘው ግዙፍ መርከብ ከቻይና ተነስቶ ወደ ኔዘርላንድስ እያቀና ነበር። የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት መርከቡ ባጋጠመው ቴክኒካዊ ችግር ምክንያት ነው መሀል ላይ ቆሞ የቀረው። በፈረንጆቹ 2018 የተሠራው ይህ የፖናማ መርከብ ኤቨርግሪን ማሪን በተሰኘው የትራንስፖርት ኩባንያ ባለቤትነት ነው የሚንቀሳቀሰው። በእንደዚህ አይነት ችግሮች ብዙ ልምድ አላቸው የተባሉ ድርጅቶች የሱዊዝ ቦይ ትራፊክ መጨናነቅን ለመፍታት ቢጥሩም እስካሁን መፍትሄ አልተገኘም። ከ230 በላይ መርከቦች የመተላለያውን መከፈት እየጠበቁ ነው የግብፅ ፕሬዝዳንት አማካሪ ችግሩ በቀናት ውስጥ እንደሚፈታ ገልጸው ነበር። ነገር ግን ባለሙያዎቹ ትልቋን መርከብ ለማንቀሳቀስና ወደቀደመው እንቅስቃሴ ለመመለስ ሳምንታት ሊፈጅ እንደሚችል ሲሉ ቆይተዋል። መተላለፊያው በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ምርቶች የሚተላለፉበት ሲሆን፤ የጦፈ ንግድ የሚካሄድበት መስመር ነው። ከመላው ዓለም የባሕር ንግድም 12 በመቶው የሚያልፈውም በዚሁ የግብፅ የባሕር ላይ ማቋረጫ መስመር በኩል ነው። በሱዊዝ ቦይ ምትክ እንደ አማራጭ የቀረበው የኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ መንገድ ደግሞ ከሱዊዝ ቦይ ጋር ሲነጻጸር ተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ይፈጃል። ይህ ደግሞ ለበርካታ የመርከብ ድርጅቶች አዋጪ አይደለም። የግብፅ ሱዊዝ ቦይ በመዘጋቱ ምክንያት እስካሁን በየቀኑ 9.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መተላለፍ አልቻሉም። ሎይድስ ሊስት የተባለው የመርከብ ጉዞ ድርጅት እንደሚለው፤ በቀን ውስጥ ከምዕራብ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩ 5.1 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መጓጓዝ አልቻሉም። ከምሥራቅ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩና የተስተጓጎሉ ምርቶች ደግሞ 4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ናቸው። ሎይድስ ሊስት ባወጣው አሃዝ መሠረት፤ በአሁኑ ጊዜ 160 መርከቦች በሱዊዝ ቦይ በኩል ለማለፍ እየጠበቁ ነው። ከእነዚህ መካከል 41 የሚሆኑት የተለያዩ ምርቶች ሲይዙ 24 ደግሞ ነዳጅ ጫኝ ናቸው። ቢአይኤምሲኦ የተባለው ዓለም አቀፍ የመርከበኞች ማኅበር እንደሚለው መተላለፊያው ተዘግቶ ከቆየ የምርት አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። በተጨማሪም በሱዊዝ የመተላለፊያ መስመር ላይ ቆማ የባሕር ላይ ጉዞን ባስተጓጎለችው መርከብ የተነሳ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል። በመተላለፊያ መስመሩ መዘጋት ሰበብ የድፍድፍ ነዳጅ አቅርቦት ሊስተጓጎል ይችላል በሚል ስጋት ነው ረቡዕ ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የታየበት። በሰሜናዊ ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘውን ወሳኝ የባሕር ላይ መተላለፊያን ዘግታ የምትገኘው የጭነት መርከብ ባለቤት የሆነው ጃፓናዊ በመርከቧ ምክንያት በዓለም የንግድ ልውውጥ ላይ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ መጠየቁ ተነግሯል። በከባድ ንፋስ ምክንያት መስመሯን ስታ መተላለፊያውን የዘጋችውን መርከብ ለማንቀሳቀስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ የገለጸው የመርከቧ ባለቤት "ነገር ግን የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ" ላይ መሆናቸውን ገልጿል።
news-48279043
https://www.bbc.com/amharic/news-48279043
ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች
በዓለም ዙሪያ በእያንዳንዱ 40 ሰከንድ አንድ ሰው ራሱን ያጠፋል። ብዙ ጊዜ ራሳቸውን የሚያጠፉት ወንዶች ሲሆኑ ምክንያቱ ደግሞ ያጋጠሟቸውን ችግሮች የማውራት ወይም እርዳታ የመጠየቅ ባህል ስለሌላቸው ነው።
ታዲያ ወንዶች በግልጽነት ሊያወሯቸው የሚገቡ ጉዳዮች ምንድናቸው? • ከ27 ዓመታት በኋላ ከ'ኮማ' የነቃችው ሴት • 'ቅሽለት' ስለሚባለው የአእምሮ ጤና ችግር ያውቃሉ? የማህበራዊ ሚዲያ ሕይወትና እውነታው መጋጨት ማህበራዊ ሚዲያ የአዕምሮ ጤና ላይ ከፍተኛ ጫና የማሳደር አቅም አለው። የአሜሪካው ፔንስሎቬንያ ዩኒቨርሲቲ በሰራው አንድ ጥናት ማህበራዊ ሚዲያን አብዝተው የሚጠቀሙ ግለሰቦች ለአዕምሮ በሽታና ጭንቀት የተጋለጡ እንደሆኑ ያሳያል። ውጤቱ የተገላቢጦሽ ሊሆንም ይችላል። ከሌላ ጊዜ ባነሰ መልኩ ማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም የጀመሩ ሰዎች ይሰሟቸው የነበሩ የብቸኝነትና የድብርት ስሜቶች እንደቀነሱላቸው በጥናቱ የተሳተፉ ሰዎች ገልጸዋል። የጥናቱ ዋና አስተባባሪና የሥነ አዕምሮ ጤና ባለሙያ የሆኑት መሊሳ ሃንት እንደሚሉት ወንዶች በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚያዩዋቸውን ነገሮች ማድረግ አለመቻላቸው ከፍተኛ ጫና ያሳድርባቸዋል። በማህበራዊ ሚዲያ የምንመለከታቸው አስደሳችና አስገራሚ የሰዎች አጋጣሚዎች አብዛኛውን ጊዜ ከእውነታው የራቁና ሰዎች መሆን አልያም ማድረግ የሚፈልጓቸውን ነገሮች የሚገልጹ ናቸው። በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የሥነ አዕምሮ ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ኦስካር ይባራ እንደሚሉት ሰዎች ሰው እንደመሆናቸው መጠን እነሱ ያላቸውን ነገር ከሌሎች ሰዎች ጋር ማወዳደር ይወዳሉ። '' ራሳቸው እንኳን በማያውቁት ሁኔታ ነው ማወዳደር የሚጀምሩት። ሰዎች ሲዝናኑ ሲመለከቱ እኔስ መቼ ነው የምዝናናው? ሰዎች ከሃገር ውጪ ለሥራ ሲሄዱም ተመሳሳይ ጥያቄ ይጠይቃሉ። ይህ ደግሞ ለድብርትና ጭንቀት ስሜት ተጋላጭ ያደርጋል። ብቸኝነት ቢቢሲ 'ዌልካም ኮሌክሽን ፈንድ' ከተባለ ተቋም ጋር በመተባባር በሰራው በዓይነቱ ትልቅ የሆነ የሙከራ ጥናት መሠረት ከ16 እስከ 24 ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ብቸኝነት ይሰማቸዋል። በአውሮፓውያኑ 2017 በተሰራ አንድ ጥናትም በተለየ መልኩ ወንዶች ከብቸኝነት መላቀቅ እንደሚከብዳቸው ተመልክቷል። • ደስታና እንቅልፍ- የፀሃይ ብርሃን ለህይወት አስፈላጊ የሆነባቸው ምክንያቶች • ስለ እንቅልፍ የተሳሳቱ አመለካከቶች ሴቶች ጓደኝነታቸውን ለማስቀጠል የግድ መገናኘት አይጠበቅባቸውም። ስለቀኑ ውሏቸው በስልክ ማውራት ብቻ በቂ ሊሆን ይችላል። ለወንዶች ግን ለረጅም ሰዓት ስልክ ማውራትና ስለ ቀን ውሎ መወያየት የማይታሰብ ነው። እንደውም ወንዶች ጓደኝነታቸውን ለማስቀጠል የግድ መገናኘት አለባቸው። ሰብሰብ ብለው እግር ኳስ ይመለከታሉ አልያም ወደ መጠጥ ቤት ጎራ ይላሉ። እነዚህና ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችን የማያደርጉ ከሆነ ግን ለብቸኝነትና ጭንቀት የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ ነው። ብቸኝነት ከዚህ ባለፈ ለእንቅልፍ እጦትና ከፍ ሲል ደግሞ ራስን እስከማጥፋት ሊያደርስ ይችላል። ማልቀስ ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ማልቀስ ለጭንቀትና ድብርት ፍቱን መድሃኒት ነው። ነገር ግን ወንዶችና ማልቀስ ብዙ ጊዜ አይዋደዱም። በወንዶች ዘንድ ማልቀስ እንደመሸነፍና ደካማነት ተደርጎ ይቆጠራል። እንግሊዝ ውስጥ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት 55 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 24 የሆኑ ወጣቶች ማልቀስ ወንድነትን ዝቅ ማድረግ ነው ብለው ያምናሉ። ራስ ማጥፋት ላይ በትኩረት የሚሰራው የአውስትራሊያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ኃላፊ የሆኑት ኮልማን ኦድሪስኮል እንደሚሉት ወንዶች ከልጅነታቸው ጀምሮ ውስጣዊ ስሜታቸውን መግለጽ እንደሌለባቸውና ማልቀስ ደካማነት እንደሆነ እየተነገራቸው ነው የሚያድጉት። ''ማልቀስ በሚገባን ሰዓት ማልቀስ፤ ሁሌም ቢሆን ጭንቀትንና ድብርትን የመቀነስ ከፍተኛ አቅም አለው።'' ይላሉ ኮልማን ኦድሪስኮል። አባወራነት እንግሊዝ ውስጥ ከሚኖሩ ወንዶች 42 በመቶ የሚሆኑት ከፍቅር ጓደኞቻቸው አልያም ከሚስቶቻቸው ከፍ ያለ ገቢ ሊኖራቸው እንደሚገባ ያምናሉ። ወንዶች ሙሉ የቤታቸውን ወጪ መሸፈን እንዳለባቸው የሚያስቡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ጥቂት የሚባል አይደለም። በአሁኑ ሰዓት ገንዘብና ከገንዘብ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጭንቀቶች ከሚታሰበው በላይ እየተስተዋሉ ነው። በአውሮፓውያኑ 2015 የተሰራ አንድ ጥናት እንዳመላከተው የሥራ አጥነት መጠን አንድ በመቶ በጨመረ ቁጥር ራስን የማጥፋት ቁጥር በ0.79 በመቶ ከፍ ይላል። አካላዊ መገለጫዎች ብዙ ጊዜ ሰዎች ሴቶች ብቻ ስለ አካላዊ ቁመናቸው የሚጨነቁ ይመስላቸዋል። ነገር ግን እውነታው ከዚህ በጣሙን ራቀ ነው። ጆሽ እንግሊዝ ውስጥ በሚገኝ አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በሚቀርብ የቴሌቪዥን ውድድር ላይ ሦስተኛ ሆኖ ነው ጨረሰው። አካላዊ እንቅስቃሴ አብዝቶ መስራቱና ስለ ሰውነቱ መጨነቁ አስተዋጽኦ እንደነበረው ያምናል። "በባህር ዳርቻዎችና በተለያዩ ቦታዎች ከወገቤ በላይ እራቁቴን ሆኜ ስንቀሳቀስ ከሴቶች አልፎ ወንዶች እንዴት እንደሚመለከቱኝ አያለው። ምናለ እንዳንተ ዓይነት ሰውነት ቢኖረኝ ብለው የሚያወሩኝም አሉ። '' ብሏል። ወንዶች ሁሌም ቢሆን ከሌሎች ወንዶች በሁሉም ነገር የተሻሉ ሆነው መገኘት ይፈልጋሉ ። አካላዊ ገጽታቸው ደግሞ ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል።
news-48102088
https://www.bbc.com/amharic/news-48102088
ዕጽ በማዘዋወር የተጠረጠረችው ናይጄሪያዊት ከሳኡዲ እስር ቤት ተለቀቀች
ባለፈው ዓመት ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ በእጽ ማዘዋወር ተጠርጥራ በእስር ላይ የነበረች አንዲት ናይጄሪያዊት ተማሪ በነጻ መሰናበቷን የሃገሪቱ መንግሥት አስታወቀ።
ዛይነብ አሊዩ 2000 እሽግ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ወደ ሳኡዲ አረቢያ ይዘሽ ገብተሻል የሚል ክስ ነበር በወቅቱ የቀረባበት። የናይጄሪያ ባለስልጣናት ግን በምርመራ ደረስንበት ባሉት መረጃ መሰረት የአሊያ ሻንጣ ውስጥ መድሃኒቶቹን በስውር ያስቀመጠው በህገወጥ የእጽ ዝውውር ላይ የተሰማራ አንድ የወንጀለኞች ቡድን ነው። • ከ27 ዓመታት በኋላ ከ'ኮማ' የነቃችው ሴት • ሰላሳ ሰባት ማዳበሪያ ዕፀ ፋርስ ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል ተያዘ በኢስላማዊ ህግ በምትተዳደረው ሳኡዲ አረቢያ የእጽ ዝውውር ከባድ ወንጀል ሲሆን ይህንን ሲፈጽም የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ የሞት ፍርድ ነው የሚጠብቀው። ባሳለፍነው ወርም አንዲት ናይጄሪያዊ የፓኪስታንና የየመን ዜግነት ካላቸው ሰዎች ጋር በዚሁ ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው በመካ ከተማ የሞት ፍርዱ ተግባራዊ ተደርጎባቸዋል። ዛይነብ አሊዩ ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ከዋለችበት ቀን ጀምሮ ብዙ ናይጄሪያውያን ተቃውሟቸውን ሲገልጹ የነበረ ሲሆን ዛይነብ ነጻ ትሁን የሚል እነቅስቃሴ በማህበራዊ ሚዲያዎችም ጀምረው ነበር። ማክሰኞ ዕለትም በመቶዎች የሚቆጠሩ የማይታማ ሱሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ካኖ በተባለችው ከተማ በመሰባሰብ ዛይነብ ትለቀቅ የሚል የተቃውሞ ድምጻቸውን ካሰሙ በኋላ ነው የመለቀቋ ዜና የተሰማው። ሰኞ ዕለትም የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሞሃመዱ ቡሃሪ የሃገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጉዳዩን እንዲከታተሉት ትእዛዝ አስተላልፈው ነበር ተብሏል። ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ ዛይነብ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ ሳኡዲ ተጉዛ ሆቴላቸው ውስጥ እያሉ ነበር በሳኡዲ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለችው። እስከ ማክሰኞ ድረስም በእስር ላይ ነበረች። የሳኡዲ ባለስልጣናት እንደገለጹት የአሊዩ ስም ያለበት ሻንጣ ኤርፖርት ውስጥ የተገኘ ሲሆን 2000 እሽግ ትራማዶል የተባለ የህመም ማስታገሻ በውስጡ ተገኝቷል። በቅርቡ የናይጄሪያ የእጽ ቁጥጥር ኤጀንሲ እንደገለጸው በእጽ ማዘዋወር ስራ ላይ የተሰማሩ ብዙ የወንጀለኛ ቡድኖች ያሉ ሲሆን ባላወቀችው መንገድ ዛይነብም የነዚህ ቡድኖች መጠቀሚያ ሆናለች። • የካናዳ ፓርላማ ዕፀ-ፋርስን ለመዝናኛነት ህጋዊ አደረገ የዛይነብ ወላጅ አባት በሳኡዲ ስለተፈጠረው ነገር ለናይጄሪያ ፖሊስ ባሳወቁ ወቅት ልጃቸው ከናይጄሪያ ስትወጣ በተጠቀመችው ማላም አሚኑ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ ምርመራ ተጀመረ። በምርመራውም ስድስት የአየር መንገዱ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ ሲሆን በከፍተኛ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል ተብሏል። ዛይነብ አሊዩም ወንጀለኛ አይደለሽም ወደቤትሽ መመለስ ትችያለሽ ተብላ በነጻ ተሰናብታለች።
news-41751628
https://www.bbc.com/amharic/news-41751628
የአይንስታይን ማስታወሻ በ1.6 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ
አንድ ሰው በሕይወቱ ደስተኛ ለመሆን እኒህን መመሪያዎች ተግባራዊ ቢያደርግ ብሎ አልበርት አይንስታይን በምክር መልክ ያሰፈረበት ማስታወሻ ሰሞኑን በ1.6 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ በእየሩሳሌም ከተማ ተሽጧል።
አይንስታይን ማስታወሻውን በአውሮፓውያኑ 1992 ለአንድ መልዕክተኛ በጉርሻ መልክ ነበር የሰጠው። ወቅቱ አይንስታይን በፊዚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ያገኘበት ነበርና ለመልዕክተኛው ማን ያውቃል ወደፊት ጥሩ ዋጋ ያለው ዕቃ ይሆናል ብሎት ነበር። በማስታወሻው አይንስታይን የረጅም ጊዜ ዕቅድን ማሳካት ማለት ደስታ መግዛት እንዳልሆነ ማስፈሩም ታውቋል። ጀርመን የተወለደው ሳይንቲስት አይንስታይን በወቅቱ ወደ ጃፓን ለትምህርታዊ ጉዞ ሄዶ ነበር። መልዕክተኛው አይንስታይን ወዳረፈበት ክፍል የተላከውን ለማድረስ ሲመጣ አይንስታይን ለጉርሻ የሚሆን አንዳች ገንዘብ አልነበረውም ነበር። በምትኩም ለመልዕክተኛው ማስታወሻውን ሰጠው። መመሪያው ባረፈበት ሆቴል ማስታወሻ ደብተር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድ ዓረፍተ-ነገር በጀርመንኛ ቋንቋ የተፃፈም ነበር። "የተረጋጋ እና ትህትና የተመላበት ሕይወት ላቅ ያለ ደስታ ያመጣል። የስኬት ምንጭም ነው፤ እርጋታ የሰፈነበት ሕይወትም ይሆናል" ሲል ይነበባል ማስታወሻው። ሌላኛውና በተመሳሳይ ወቅት አይንስታይን የፃፈው ማስታወሻ በ240 ሺህ ዶላር የተሸጠ ሲሆን "መልካም ፍቃድ ባለበት ሁሉ መንገድ አለ" የሚል ዓረፍተ-ነገር ያረፈበት ነው። አጫራቾቹ ማስታወሻውን ለሽያጭ ካቀረቡበት ዋጋ እጅግ ልቆ እንደተሸጠ አሳውቀዋል። ገዢው ማንነቱ እንዲታወቅ ያልፈለገ አንድ አውሮፓዊ ሲሆን፤ ሻጩም የመልዕክተኛው የቅርብ ዘመድ መሆኑም ታውቋል።
news-56797853
https://www.bbc.com/amharic/news-56797853
ምርጫ 2013፡ ኦብነግ እና ኢዜማ በሶማሌ ክልል የምርጫ እንቅስቃሴያችንን እናቆማለን አሉ
ኦብነግ እና ኢዜማን ጨምሮ አራት በሶማሌ ክልል ውስጥ በምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎችና የግል ተወዳዳሪዎች በምርጫ ሂደቱ ላይ ያላቸው ቅሬታ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ በክልሉ የምርጫ እንቅስቃሴ አይኖረንም ብለዋል።
ይህን ጥያቄ ያቀረቡት የኦጋዴን ነጻነት ግንባር (ኦብነግ)፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ አንዲሁም የሱማሌ ክልል የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች ናቸው። ፓርቲዎቹና ግለሰቦቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ ላይ የምርጫ ሕጎች እና ፓርቲዎች የፈረሙት ቃለ መሃላ በሱማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ተጥሰዋል ብለዋል። የኦብነግ ሊቀመንበር አብድራህማን ሞሐመድ መሃዲ አራቱ አካላት ይህን መግለጫ ያወጡት ትናንት (እሁድ) በጅግጅጋ ከተማ ውይይት ካካሄዱ በኋላ መሆኑን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ሊቀመንበሩ አቶ አብድራህማን የክልሉ አስተዳዳሪዎች የድምጽ ሰጪዎችን ካርድ አግተው ወስደዋል፤ ለፈቀዱት ግለሰቦችም በመቶዎች የሚቆጠሩ ካርዶች ሰጥተዋል ሲሉ ይከስሳሉ። ሊቀመንበሩ ይህን ያሳያል ያሉትን በአንድ ግለሰብ በርካታ የድምጽ መስጫ ካርዶችን ይዞ የሚያሳይ ምስልም ለቢቢሲ አጋርተዋል። የኢዜማ ቃል አባይ ናትናኤል ፈለቀም፤ ፓርቲያቸው በውይይቱ ከተሳተፈ በኋላ የጋራ መግለጫው መውጣቱን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አራቱ ፓርቲዎች ባወጡት የጋራ መግለጫ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ አስፈጻሚዎች በክልሉ አስተዳዳር ጫና ሥር ወድቀዋል፣ የድምጽ ሰጪዎች ምዝገባ ሂደት እና የድምጽ ሰጪዎች ካርድ ስርጭት ከምርጫ ቦርድ ይልቅ በክልሉ አስተዳዳሪዎች ቁጥጥር ሥር ወድቋል ሲሉ ከስሰዋል። ጨምረውም ለሶማሌ ክልል የተመደበው የመራጮች ምዝገባ ካርድ ቁጥር አልታወቀም፣ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች የምርጫ ካርድ ስርጭት እንዲታዘቡ አልተጋበዙም የሚሉ እና ተያያዥ ቅሬታዎችን ቀርበዋል። እነዚህ አራት አካላት በዚህ ሁኔታ ፍትሃዊ እና ነጻ ምርጫ ማካሄድ ስለማይቻል ማስተካከያ እንዲደረግ አሳስበዋል። ስለዚህም ተዓማኒነት ያላቸው፣ ገለልተኛ የሆኑ እና ኃላፊነታቸውን መወጣት የሚችሉ የምርጫ ቦርድ ምርጫ አስፈጻሚዎች ወደ ክልሉ እስኪመጡ ድረስ፣ እንዲሁም ግልጽ እና ተዓማኒነት ያለው የመራጮች ምዝገባ ሂደት እስኪኖር ድረስ በሶማሌ ክልል ለመሳተፍ የሚያስችለን የምርጫ ስርዓት ባለመኖሩ የምርጫ ተሳትፏችንን ለጊዜው እናቆማለን ሲሉ ገልጸዋል። የምርጫ ቦርድ ቃል አቀባይ ሶሊያና ሽመልስ በበኩላቸው በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ላይ ከኦብነግ ፓርቲ ቅሬታ መቀበላቸውን አረጋግጠው፤ በቀረቡት ቅሬታዎች ላይ ብሔራዊ ቦርድ ዛሬ እንደሚወያይ ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ከኦብነግ ቅሬታው ደርሶናል። የጋራ መግለጫው ግን አልደረሰንም። የመራጮች ምዝገባ ገና መጀመሩ ነው፣ ሁለት ወይም ሦስት ቀን ቢሆነው ነው። የምርጫ ቁሳቁሶችም ተጓጉዘው እዚያ የደረሱት ባለፈው ሳምንት ነው" በማለት የተነሱ ቅሬታዎችን መርምሮ ምላሽ ለመስጠት በቂ ጊዜ እንዳልነበረ አመልክተዋል። የኢዜማ ቃል አቀባይ አቶ ናትናኤል ፈለቀም በሶማሌ ክልል የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች አና በምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች መካከል ዛሬ ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል። በውይይቱ ላይም በክልሉ ከምርጫ ሂደት ጋር በተያያዘ የተስተዋሉ ችግሮች ተቀርፈው የምርጫው ሂደት በአስቸኳይ ይቀጥላል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል። በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻ ላይና በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እንደሚካሄድ በሚጠበቀው ምርጫ ላይ በድምጽ ሰጪነት የሚሳተፉ መራጮች መዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተላለፈው ስድስተኛው ዙር አገራዊ ምርጫ ላይ በመራጭነት ለመሳተፍ ባለፉት ሳምንታት የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር የተጠበቀውን ያህል እንዳልሆነ ምርጫ ቦርድ አስታውቆ ነበር። የሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ ከሌሎች አካባቢዎች ዘግይቶ ከቀናት በፊት መጀመሩን ፓርቲዎች ገልፀዋል።
54445181
https://www.bbc.com/amharic/54445181
አእምሮ ጤና፡ ለዓመታት ወላጆቻቸው በሰንሰለት ያሰሯቸው ናይጄሪያውያን
ለዓመታት በወላጆቻቸው ታስረው የነበሩ ሰዎች ነጻ የመውጣታቸው ዜና መላው ናይጄሪያን አስደንግጧል።
ለዓመታት በወላጆቻቸው ታስረው የነበሩ ሰዎች ነጻ የመውጣታቸው ዜና መላው ናይጄሪያን አስደንግጧል አንዳንዶቹ የአዕምሮ ህሙማን ሲሆኑ፤ በብረት ካቴና ቁርጭምጭሚታቸውን ለዓመታት ታስረዋል። በጠባብ ቦታ እንዲበሉ፣ እንዲተኙና እንዲጸዳዱም ተገድደዋል። ከእነዚህ አንዱ የ32 ዓመት ጎልማሳ ነው። በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያዋ ካኖ ግዛት ቤተሰቦቹ ቤት ለሰባት ዓመታት ታስሮ ነበር። የእንጀራ እናቶቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ያሰቃዩዋቸው ልጆችም ተገኝተዋል። . በኢትዮጵያ የአዕምሮ ህሙማን ሰብዓዊ መብት እየተጣሰ ይሆን? . የኮሮናቫይረስ ፅኑ ህሙማን እንዴት ያገግማሉ? መስከረም ላይ አንድ የሰባት ዓመት ታዳጊን በመግደል እንጀራ እናቱ በቁጥጥር ስር ውላለች። እስካሁን ክስ አልተመሰረተባትም። በዶሮ ጎጆ የታሰረው ታዳጊ በመላው ናይጄሪያ ታዳጊዎች ጉልበታቸው እንደሚበዘበዝ ሪፖርት ይደረጋል። አሁን ግን ዋነኛው ትኩረት ያለው በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ላይ ነው። ነሐሴ አጋማሽ ላይ በኬቢ ግዛት የ11 ዓመት ታዳጊ በዶሮ ጎጆ መታሰሩ ተሰምቷል። በቅንጡ ቤት እየኖሩ የነበሩት አባቱና እንጀራ እናቱ ለፍርድ ቀርበዋል። ከዶሮዎች አጠገብ ተኮማትሮ የተቀመጠው ታዳጊ ምስል በርካቶችን አስቆጥቷል። ከዶሮዎች አጠገብ ተኮማትሮ የተቀመጠው ታዳጊ ምስል በርካቶችን አስቆጥቷል የሰብዓዊ መብት ተቋም ኃላፊው ሀሩና አያጊ፤ የታዳጊው ሁኔታ ይፋ ከተደረገ በኋላ ሌሎችም ጥቆማዎች እንደደረሷቸው ይናገራሉ። ተቋም 12 ሰዎችን ነጻ አውጥቷል። ከነዚህ ሰባቱ ልጆች ናቸው። "ብዝበዛ የደረሰባቸው ልጆች ከእናታቸው ጋር አይኖሩም ነበር" ይላሉ ሀሩና። በናይጄሪያ መዲና አቡጃ ሁለት ልጆች በእንጀራ እናቶቻቸው መጸዳጃ ቤት ታስረው ተገኝተዋል። መደብደብ፣ መቃጠል፣ መራብ በካኖ ግዛት አንድ የሰባት ዓመት ልጅ በእንጀራ እናቷ መደብደቧ፣ መቃጠሏና ምግብም መከልከሏ ተዘግቧል። አሁን ታዳጊዋና ሌሎችም ልጆች በመንግሥት ማቆያ ይገኛሉ። ህክምና እና የሥነ ልቦና ምክርም እየተሰጣቸው ነው። ከልጆቹ ወላጆች መካል የታሰሩ፣ ገና ፍርድ ያልተላለፈባቸውም አሉ። . 13 ልጆች በቤታቸው ውስጥ በሰንሰለት ታስረው ተገኙ . በስዊድን ያሉ የስደተኛ ልጆች ሚስጥራዊ ህመም እአአ 2003 ላይ የወጣ ሕግ፤ በአግባቡ ያልተያዙ ልጆችን መንግሥት እንዲወስድ ይፈቅዳል። ሆኖም ካኖን ጨምሮ 11 የናይጄሪያ ደቡባዊ ግዛቶች ሕጉን አላጸደቁም። ሕጉ አለመጽደቁ ብዝበዛ የሚደርስባቸውን ልጆች መንግሥት እንዳይታደግ እንቅፋት ሆኗል ሕጉ ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ማግባት አይችሉም ስለሚል ተቃውሞ ገጥሞታል። አንዳንድ የሙስሊም ማኅበረሰብ ለአቅመ አዳምና ሔዋን የደረሱ ልጆች መዳር አለባቸው ይላል። ሕጉ አለመጽደቁ ብዝበዛ የሚደርስባቸውን ልጆች መንግሥት እንዳይታደግ እንቅፋት ሆኗል። በአካባቢው ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት የተለመደ ነው። ይህ ማለት በርካታ ልጆች ከእናቶቻቸው ጋር አይኖሩም ማለት ነው። ከወላጅ እናታቸው ተነጥነው ለእንግልት ይዳረጋሉ። የሴቶችና ሕፃናት መብት ታጋይ ተቋም መሪዋ ላማቦግ ላዲፖ "ልጆችን ማሰቃየት እየተለመደ ነው። ሰብዓዊ መብትን ይጋፋል። ጭካኔም ነው" ይላሉ። የታሰሩት የአዕምሮ ህሙማን በካኖ ግዛት ቤተሰቦቹ ቤት ታስሮ የተገኘው የ30 ዓመት ግለሰብ ጎረቤቶች እንደሚሉት፤ የአዕምሮ ህመምተኛ በመሆኑ ሰባት ዓመት ታስሯል። ግለሰቡ ሲገኝ መራመድ አይችልም ነበር። ሌላ የ55 ዓመት የአዕምሮ ህመምተኛም በርና መስኮት በሌለው ክፍል ታስረው ተገኝተዋል። አንደኛው እግራቸው ከብረት ዘንግ ጋር ታስሮ ለ30 ዓመታት ኖረዋል። የአዕምሮ ህሙማን ስለሚገለሉ ተገቢው እንክብካቤ አይደረግላቸውም። ቤተሰቦቻቸውም ስለማይቀበሏቸው ያረጀ ልብስ ለብሰው ከቆሻሻ መጣያ ሲመገቡ ይስተዋላል። ዶ/ር ታይዎ ላቲፍ እንደሚሉት፤ የአዕምሮ ህሙማን ይታሰራሉ፣ እንግልትም ይደርስባቸዋል። ምን ያህል ሰዎች የአዕምሮ ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው መረጃው የለም። ነገር ግን ከ200 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ያላቸው ከ300 ያነሰ የሥነ ልቦና ሀኪም ነው። የአዕምሮ ህመምተኛ በመሆኑ ሰባት ዓመት ታስሯል የክርስትና እና እስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ባህላዊ ህክምናን ይመርጣሉ። የአዕምሮ ህመምን ከክፉ መንፈስ ጋር የሚያስተሳስሩትም በርካታ ናቸው። የናይጄሪያ ጤና ሚንስትር 2013 ላይ ያወጣው አሐዝ፤ ቢያንስ ዓሥር በመቶ የሚሆነው ዜጋ የአዕምሮ ህመም እንደሚገጥመው ይጠቁማል። . በርካቶች መርሳት ያልቻሉት ጦርነት ሲታወስ . 500 ወንዶች ታጉረውበት ከነበረው ህንጻ ነፃ ወጡ የዓለም ጤና ድርጅት ከነዚህ ህክምና የሚያገኙት ከ10% በታች ናቸው ይላል። በተለይ በገጠር የሚኖሩ ሰዎች ህክምና ለማግኘት ይቸገራሉ። ሆኖም የአዕምሮ ህክምና መስጫ ባለባቸው ቦታዎችም ሳይቀር ህሙማን ይገለላሉ። "ብዙ ሰዎች የአዕምሮ ህክምና መስጫ ሲገቡ መታየት አይሹም። ብዙ የተዛቡ አመለካከቶች ከአዕምሮ ህመም ጋር ተያይዘዋል። ሰዎች የአዕምሮ ህመም እንዳለባቸው መካድን ይመርጣሉ" ይላሉ ዶ/ር ታይዎ።
news-41480232
https://www.bbc.com/amharic/news-41480232
ስቴፈን ፓዶክ : ቁማርተኛና የቀድሞው የሂሳብ አያያዝ ባለሙያ
የላስ ቬጋስን ጥቃት የፈጸመው የቀድሞው የሂሳብ አያያዝ ባለሙያ ስቴፈን ፓዶክ ሃብታምና በጡረታውም የተመቻቸ ሕይወት የነበረው ሰው ነው።
የ64 ዓመቱ ፓዶክ የአውሮፕላን አብራሪነት ፈቃድ ሲኖረው የሁለት አነስተኛ አውሮፕላኖች ባለቤት ነበር። ለአደንም ህጋዊ ፈቃድ ተሰጥቶታል፤ ከዚህ ቀደም ግን ምንም አይነት የወንጀል ሪከርድ እንዳልነበረበት ፖሊስ አስታውቋል። አንድ የቀድሞ ጎረቤቱ ተጠርጣሪውን ቁማርተኛና ወጣ ያለ ባህሪ የነበረው ሲሉ ገልጸውታል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ለሮይተርስ እንዳሉት ግለሰቡ ስነልቦናዊ ችግር እንደነበረበት የሚያሳዩ ሁኔታዎችም አሉ። ጥቃቱ በኦርላንዶ 49 ሰዎች ከሞቱበትና በወቅቱ የከፋ ከተባለው አደጋ ልቆ በአሜሪካ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ከተፈጸሙት ሁሉ በላይ ደም አፋሳሽ ሆኗል። ''ከሌለው ጎረቤትህ ጋር የመኖር ያህል ነበር'' የቀድሞ ጎረቤቱ ፓዶክ ማንዳላይ ቤይ ሆቴል ላይ ሆኖ በከፈተው ተኩስ ቢያንስ 59 ሰዎችን ገድሎ ከ 500 በላይ የሚሆኑት ካቆሰለ በኋላ ራሱን አጥፍቷል። ፖሊስ የላስ ቬጋሱ ታጣቂ ጥቃቱን ለመፈፀም ምን እንዳነሳሳው እያጣራ ነው። ፖሊስ ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ባረፈበት የሆቴሉ 32ኛ ፎቅ ላይ በሚገኝ ክፍል ውስጥ 23 መሣሪያዎችን አግኝቷል። በመኖሪያ ቤቱም ተጨማሪ 19 የጦር መሳሪያዎች፣ በግቢውና በመኪናው ውስጥ ደግሞ ፈንጂዎች ተግኝተዋል። መሣሪያዎችን የሸጠለት ሰውም ፓዶክ የአሜሪካን የምርመራ ቢሮ የማንነት ማጣሪያ ጨምሮ ሁሉንም የመግዣ መስፈርቶች አሟልቶ ስለተገኘ እንደሸጠለት ተናግሯል። ''ሆኖም ከኔ የገዛቸው መሣሪያዎች ማሻሻያ ሳይደረግላቸው በቪዲዮ የተመለከትናቸውና የሰማናቸውን አይነት አቅም ሊኖራቸው አይችልም '' ብሏል። አይ ኤስ ለጥቃቱ ኃላፊነትን ቢወስድም የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ( ኤፍ ቢ አይ) ግን እስካሁን ፓዶክ ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንደነበረው የሚያሳይ ምንም መረጃ አላገኘም። ጥቃቱ የተፈጸመበት አካባቢ አባቱም የባንክ ቤት ዘራፊ እንደነበር፣ በምርመራ ቢሮ እጀግ ተፈላጊ ወንጀለኞች ዝርዝር ውስጥ ሰፍሮ እንደነበረና በአንድ ወቅትም ከእስር ቤት ማምለጡን ታናሽ ወንድሙ ኢሪክ ፓዶክ ለጋዜጠኞች ተናግሯል። ፓዶክ በ 2016 ነበር ከ62 ዓመቷ የሴት ጓደኛው ማሪሎ ዳንሌይ ጋር በአሁኑ መኖሪያ ቤቱ መኖር የጀመረው። ማሪሎ ከጥቃቱ በኋላ በፖሊስ ስትፈለግ ቆይታ በጃፓን ብትገኝም እጇ እንዳለበት የሚያሳይ ምንም ማስጃ አልተገኘባትም። መጀመሪያ በግብረ አበርነት ተፈላጊ የነበረችው ማሪሎ ዳንሌይ ከአሜሪካ ውጭ ተግኝታለች ሆቴሉን ሲከራይም ከእርሱ ጋር አልነበረችም ብሏል ፖሊስ። እንዲያውም ፓዶክ መታወቂያዋን ለአላማው ሲጠቀምበት ነበር። የቀድሞ ጎረቤታቸው ዳያን ማኬይ ለዋሽንግተን ፖስት ጥንዶቹን ሁልጊዜም ነገሮችን በምስጢር ማድረግ የሚያዘወትሩ በማለት ገልጸዋቸዋል። " ወጣ ያለ ባህሪ ነበረው ፤ሁሉንም ነገር በምስጢር ይይዝ ነበር ፤ ከሌለው ጎረቤትህ ጋር የመኖር ያህል ነው'' ብለዋል።
56813072
https://www.bbc.com/amharic/56813072
በተለያዩ የአማራ ከተሞች ግድያና ጥቃቶችን በመቃወም ሰልፎች ተካሄዱ
በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች በንሑሃን ዜጎችን ላይ የሚፈጸሙ ግድያና ጥቃቶችን በመቃወም ሰልፎች ተካሄዱ።
ደብረ ማርቆስ የተቃውሞ ስልፍ ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል የክልሉ መዲና ባህር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ወልዲያ፣ ደሴ፣ ሐይቅ እና ሰቆጣ ከተሞች ይገኙበታል። ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱት ደሴ እና ደብረ ማርቆስ ከተሞችም በተመሳሳይ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ወልዲያ በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ በዋናነት በንሑሃን ዜጎች ላይ የሚደርሱትን ግድያ እና ጥቃቶች የሚያወግዙ ድምጾች ተሰምተዋል። ሰልፈኞች በቅርቡ በሰሜን ሸዋ የንሑሃን ዜጎችን ሕይወት መታደግ ባለመቻሉ ክልሉን እያስተዳደረ የሚገኘውን ብልጽግና ፓርቲ እና መንግሥትን አውግዘዋል። የክልሉ መገናኛ ብዙሃን በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች፤ ተቃዋሚዎች በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግድያና መፈናቀል አውግዘዋል ሲል ዘግቧል። ባህር ዳር በተመሳሳይ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በባሕር ዳር፣ በደብረ ማርቆስ እና ወልደያ ከተሞች በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ማንነትን መሠረት ያደረገ ግድያ የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል ብሏል። ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት መውደሙን ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች እና በቤኒሻንጉል ክልል ማንነትን መሠረት ባደረጉ ጥቃቶች የበርካቶች ሕይወት አልፏል። በተለይ ማክሰኞ ዕለት ለተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያት የሆነው በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈጸመው ጥቃት ሲሆን አስካሁን በዚህ ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ በውል ባይታወቅም ሮይተርስ የዜና ወኪል ነዋሪዎችን ተቅሶ እንደዘገበው ቢያንስ 50 ሰዎች ሞተዋል ብሏል። ቢቢሲ ያናገራቸው የአካባቢው አስተዳዳሪ እንደተናገሩት በዞኑ ውስጥ ባሉ ከተሞች ከባድ ንብረት ማውደም መፈጸሙንና በተለይ አጣዬ ከተማ በጥቃቱ ክፉኛ መጠቃቷን ገልጸዋል። በአማራ ክልል ውስጥ በሚገኙት የሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞኖች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶችና ባጋጠሙ ግችቶች በሰውና በንብረት ላይ ተደጋጋሚ ጉዳት ደርሷል። ባለፈው መጋቢት ወር ባጋጠመ ተመሳሳይ ሁኔታ ከ300 መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት መጥፋቱን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም ኃላፊ የሆኑትን አቶ እንዳለ ኃይሌን ጠቅሶ ዘግቧል።
news-52384393
https://www.bbc.com/amharic/news-52384393
ኮሮናቫይረስን ለመፈወስ ተስፋ ያለው መድኃኒት የቱ ነው?
ከ150 ሺህ በላይ ሰዎች ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህመም አልቀዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ለቫይረሱ ተጋልጠው ይገኛሉ። እስካሁን ግን ከቫይረሱ እንደሚፈውስ የተረጋገጠለት መድኃኒት አልተገኘም።
ግን ግን ከኮቪድ-19 ጨርሶ የሚፈውስ መድኃኒት ለማግኘት ምን ያህል ተቃርበናል? ከቫይረሱ የሚፈውስ መድኃኒት ለማግኘት ምን ተከናወነ? በመላው ዓለም የሚገኙ ተመራማሪዎች ከ150 በላይ የሆኑ የተለያዩ መድኃኒቶች ላይ እየተመራመሩ ሙከራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ። ምርምር እና ሙከራ እየተደረገባቸው የሚገኙት አብዛኞቹ መድኃኒቶች በገበያ ላይ ያሉ ወይም ከዚህ ቀደም የሚታወቁ ናቸው። ከበሽታው ሊፈውሱ የሚችሉት መድኃኒቶች ምን አይነት ሊሆኑ ይችላሉ? ከበሽታው ሊፈውሱ የሚችሉ መድኃኒቶችን ለማግኘት እየተደረገ ያለው ምርምር በሦስት ከፍሎ መመልከት ይቻላል። እነዚህም፤ 2. በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የሰውነትን በሽታን የመከላከል ሥርዓት ለኮሮናቫይረስ የተመጠነ ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርግ መድኃኒት ማግኘት ነው። ምክንያቱም የሰውነት የበሽታ መከላከል ሥርዓት፤ አካላችን በበሽታ ሲጠቃ ከመጠን በላይ ምላሽ ሲሰጥ ታማሚው በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚታመም መድኃኒቱ ተዛማጅ ጉዳትን ለመቆጣጠር ይረዳል። 3. ሦስተኛው ደግሞ በላብራቶሪ የተዘጋጀ ወይም ከኮሮናቫይረስ ካገገሙ ሰዎች 'አንቲቦዲ' በመጠቀም ለኮቪድ-19 መላ መፈለግ የሚለው ነው። ኮቪድ-19ን ሊፈውስ ይችላል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት መድሃኒት የቱ ነው? የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባ ዶ/ር ብሩስ አለዋርድ ከቻይና ጉብኘታቸው በኋላ ኮሮናቫይረስን ያድናሉ ተብለው ከተሞከሩ መድኃኒቶች መካከል ውጤታማ ስለመሆኑ ምልክት ያሳየው ሬምዴሲቪር (remdesivir) ብቻ ነው ብለዋል። ይህ መድኃኒት ከዚህ ቀደም ይውል የነበረው በኢቦላ የተያዘን ሰው ለማከም ነበር። መድኃኒቱ ከኢቦላ በተጨማሪ ሌሎች የኮሮናቫይረስ አይነቶችን ለማከም በእንስሳት ላይ ተሞክሮ አመርቂ ውጤት አሳይቷል። በዚህም ኮቪደ-19ን ሊያክም ይችላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። አንድ ሾልኮ የወጣ መረጃ እንደጠቆመው በቺካጎ ዩኒቨርስቲ በተመራ የላብራቶሪ ሙከራ መድኃኒቱ በኮቪድ-19 የተያዘን ሰው ለማከም ውጤታማ መሆኑ ተደርሶበታል። ይህ መድኃኒት የዓለም ጤና ድርጅት በ'ሶሊዳሪቲ ትሪያል' ማዕቀፍ ውስጥ ከያዛቸው አራት መድኃኒቶች መካከል አንዱ ይህ ነው። የዚህ መድኃኒት አምራች የሆነው ጊሊድ የተሰኘው ተቋምም በመድኃኒቱ ላይ ምርምር እያካሄደ ይገኛል። የጸረ ኤችአይቪ መድሃኒቶች ኮሮናቫይረስን ሊያክሙ ይችላሉ? ሎፒናቪር (lopinavir) እና ሪቶናቪር (ritonavir) የተባሉ የጸረ ኤችአይቪ መድኃኒቶች በኮቪድ-19 የተያዘን ሰው ለማከም ይውላሉ የሚሉ መላምቶች በስፋት ቢኖሩም ለዚህ ማረጋገጫ አልተገኘም። በላብራቶሪ ደረጃ መድኃኒቶቹ ውጤታማ ስለመሆናቸው ማረጋገጫዎች ቢኖሩም በሰዎች ላይ የተደረጉ የሙከራ ውጤቶች ግን አጥጋቢ ሳይሆኑ ቀርተዋል። መድኃኒቶቹ በኮቪድ-19 ተይዘው በጠና ለታመሙ ሰዎች ቢሰጡም የመጨረሻ ውጤታቸው፤ ታማሚዎቹ ከበሽታው አላገገሙም፣ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም አልቀነሰም አልያም በሰውነት ውስጥ የሚገኘው የቫይረስ መጠን አልቀነሰም። ጸረ-ወባ መድኃኒቶችስ ኮሮናቫይረስን መግታት ይቻላቸዋል? የጸረ-ወባ መድኃኒቶች የዓለም ጤና ድርጅት እና ዩናይትድ ኪንግደም የሚያደርጓቸው ምርምር አካል ናቸው። ክሎሮኪን እና ሃይድሮክሎሮኪን የተባሉ የጸረ-ወባ መድኃኒቶች ፕሬዝድነት ትራምፕ ኮቪድ-19ን ለማከም ሊውሉ እንደሚችሉ መጠቆማቸውን ተከትሎ መድኃኒቶቹን የመጠቀም ዝንባሌ በስፋት ተይቷል። ይሁን እንጂ መድኃኒቶቹ ከኮቪድ-19 ስለመፈወሳቸው ማረጋገጥ አልተቻለም። የዓለም ጤና ድርጅትም የመድኃኒቶቹ ውጤታማነት ላይ እስካሁን ማረጋገጫ አልተገኘም ብሏል። የበሽታ መከላከል አቅምን ከፍ የሚያደርጉ መድኃኒቶችስ? የሰውነት የበሽታ መከላከል ሥርዓት ቫይረሱን ለመዋጋት ከተገቢው በላይ ምላሽ ከሰጠ፤ ሰውነታችን ይቆጣል። ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሰውነት የበሽታ መከላከል ሥርዓት ላይ መመርኮዝ ጠቃሚ ቢሆም፤ ይህን ሥርዓት ከተገቢው በላይ ከፍ ማድረግ ግን አደጋ ሊያስከትል ይችላል። የዓለም ጤና ድርጅት እያከናወነ ያለው 'ሶሊዳሪቲ' የተባለው ሙከራ 'ኢንፌርኖ ቤታ' የሚባል ኬሚካልን እየመረመረ ይገኛል። 'ኢንፌርኖ ቤታ' የንጥረ ነገሮች ስብሰብ ሲሆን ሰውነታችን በቫይረስ ሲጠቃ ቫይረሱን ለመከላከል በሰውነታችን ውስጥ ይለቀቃሉ። የሰውነት መቆጣትንም ይቀንሳሉ ተብሏል። ዩናትድ ኪንግደም ደግሞ የሰውነት መቆጣትን የሚቀንስ የመድኃኒት አይነትን እየመረመረች ትገኛለች። ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ደም በሽታውን ለማከም ይውል ይሆን? ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቫይረሱን የሚዋጋ አንቲቦዲ ይኖራቸዋል። ሃሳቡ ከበሽታው ያገገመ ሰው አንቲቦዲ ያለበት ደም በመውሰድ በበሽታው የሚሰቃይን ሰው ለማከም ጥቅም ላይ ማዋል ነው። አሜሪካ እስካሁን 500 ሰዎችን በዚህ መንገድ እክማለች። ሌሎች አገራትም የአሜሪካንን ፈለግ እየተከተሉ ነው። መድኃኒት እስኪገኝ ምን ያክል ጊዜ እንጠብቅ? በቅርቡ ከኮቪድ-19 የሚፈውስ መድኃኒት መቼ ተግባር ላይ እንደሚውል እንሰማለን። ከዚያ በፊት ግን በቀጣይ ጥቂት ወራት የመድኃኒቶቹ ውጤታማነት ላይ የላብራቶሪ ግኝቶችን እንሰማለን። በትክክል መናገር የሚቻለው ግን ከክትባት ቀድሞ መድኃኒት ተግባር ላይ ይውላል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ተመራማሪዎች እና ዶከተሮች የሚመራመሩበት ወይም ለታማሚዎች የሚሰጡት የመድኃኒት አይነቶች ደህንነታቸው የተረጋገጠና ከዚህ ቀደም የሚታወቁ ወይም የነበሩ መድኃኒቶች በመሆናቸው ነው። ክትባት ለማግኘት ምርምር የሚያደርጉት ተመራማሪዎች ግን ሥራቸውን ከዜሮ ነው የጀመሩት፤ ይህም ምናልባት ወራትን ወይም ዓመታትን ሊጠይቅ ይችላል። አሁን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች የሚታከሙት በየትኛው መድኃኒት ነው? በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ በሽታው ካልጠናባቸው በቤት ውስጥ እራሳቸውን ለይተው በመቀመጥ እረፍት እንዲያደርጉ፣ የህመም ማስታገሻዎችንና በርከት ያለ ፈሳሽ እንዲወስዱ ይመከራል። በጽኑ የታመሙ ደግሞ በሆስፒታል አልጋ ላይ ሆነው ለመተንፈስ የሚያግዛቸው ቬንቲሌተር ተገጥሞላቸው እንደየ ሃገሩ መመሪያ መሠረት መድኃኒቶች ሊሰጣቸው ይችላል።
news-52478110
https://www.bbc.com/amharic/news-52478110
ሰሜን ኮሪያ ያለ ኪም ጆንግ ኡን ማን አላት?
የሰሜን ኮሪያው ጠቅላይ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጤናቸው እንደተቃወሰ መነገር ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል። ቢሆንም ጉዳዩ ከወሬ የዘለለ አይደለም ሲሉ የሃገሪቱ ባለሥልጣናትና የጎረቤት ሃገር ደቡብ ኮሪያ መሪዎች አሳውቀዋል።
ወሬው ውሃ የሚያነሳም ሆነ አልሆነ ኪም ጆንግ-ኡንን ማን ነው የሚተካቸው ለሚለው ጥያቄ መልስ ማፈላለግ ተጀምሯል። ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው ያላቸውን ሰዎች አነጋግሯል። የኪም ቤተሰብ ሰሜን ኮሪያን መምራት ከጀመረበት 1940 ጀምሮ ሃገሪቱን የገዙ ሁሉም ግለሰቦች ወንዶች ናቸው። የኪም ቤተሰብ ዝና በሕብረተሰቡ ውስጥ የናኘ ነው። የቤተሰብ ታላቅነት ከልጅነት ጀምሮ ይሰበካል። ሕፃናት 'መሪያችን ኪም ጆንግ-ኡንን ማየት እፈልጋለሁ' እያሉ ይዘምራሉ። ታድያ እንዴት ሆኖ ሰሜን ኮሪያና ካለዚህ ምስሉ ጎልቶ ከሚታይ ቤተሰብ ውጭ ማሰብ ይቻላል? ሁሌም ኪም አለ ኪም ጆንግ-ኡን ሥልጣል ሊጨብጡ ሲዘጋጁ በእንግሊዝኛው 'ፓየክቱ ብለድላይን' [የፓየክቱ ዘር ግንድ] የሚል ቃል አብዝቶ መሰማት ተጀመረ። ይህ የሆነው የኪምን ወደ ሥልጣን መምጣት ሕጋዊነት ለማስጠበቅ ነው። ፓየክቱ የተቀደሰ የሚባል ተራራ ነው። ኪም ሱንግ ሁለተኛ እዚህ ተራራ ላይ የጎሪላ ውጊያ እንዳደረጉ ይታመናል። ኪም ጆንግ ኢልም እዚህ ነው የተወለዱት ተብሎ ነው የሚነገረው። የአሁኑ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን አስፈላጊ የፖሊሲ ውሳኔ መስጠት ሲሹ ወደዚህ ተራራ ይሄዳሉ። በሰሜን ኮሪያ ታሪክ ሁሌም ኪም አለ። ኪም የሃገሪቱ ልብ ትርታ ናቸው ማለት ይቻላል። ሰሜን ኮሪያ ያለ ኪም ጁንግ-ኡን ማን አላት? የ36 ዓመቱ ኪም ልጆች እንዳላቸው ይታመናል፤ ሥልጣን ለመረከብ ግን ገና ለጋ ናቸው። የኪም ልጆች ሶስት እንደሆኑ ጭምጭምታ አለ። ትልቁ የ10 ዓመት ታዳጊ፤ ትንሹ ደግሞ የ3 ዓመት ጨቅላ። ኪም ጆንግ-ኡን ራሳቸው ሥልጣን ሲረከቡ የ27 ዓመት ወጣት ነበሩ። የሰሜን ኮሪያን ውሎ የሚከታተሉ ማን ምን ሥልጣን እንዳለው ያውቃሉ። ትዕዛዝ ከየት እንደሚመነጭ ግን ቁርጡን መናገር ይከብዳል። አንዳንድ ጊዜ ምክትሎች ከዋና ኃላፊዎች የላቀ ኃይል አላቸው። ይህ ደግሞ ሃገሪቱ ወዴት አቅጣጫ እንደምትሄድ ለመገመት እጅግ አዳጋች ያደርገዋል። የኪም ጆንግ-ኡን ታናሽ እህት ኪም ዮ-ጆንግ የቀሩት ሶስቱ ኪሞች አሁን ሶስት ኪሞች ቀርተዋል። ኪም ጆንግ-ኡን ወደ ሥልጣን መመለስ ባይችሉ ሊተኳቸው ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ። የቤተሰቡን ሌጋሲ ማስቀጠል ግን ቀላል አይደለም። የመጀመሪያዋ ኪም ዮ-ጆንግ ናት። የኪም ጆንግ-ኡን ታናሽ እህት። የአባቷ ተወዳጅ ልጅ እንደሆነች ይነግርላታል። ገና ከልጅነቷ ፖለቲካ ውስጥ ለመግባት ፍላጎት ታሳይ ነበር ይባላል። ታዛቢና መልካም ፀባይ ያላት እንደሆነች ብዙዎች ይመሰክራሉ። ከወንድሟ ጋር ቅርብ እንደሆነችም ነው የሚታመነው። ትራምፕና ኪም ሲንጋፖር ሲገናኙ እስኪርፕቶ ያቀበለችው እሷ ናት። ሃኖይ በነረበው ስብሰባ ላይም ታይታለች። የሃኖይ ስብሰባ ባለመሳካቱ ምክንያት በጊዜያዊነት ከእርከናቸው ከተቀነሱ ባለሥልጣናት መካከል ነበረች የሚባል ወሬ ተሰምቷል። ማረጋገጥ ግን አልተቻለም። የፖሊት ቢሮ አባል ብትሆንም ውሳኔ በመስጠየት የሚታወቀው የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ኮሚሽን አባል ግን አይደለችም። የኮሪያ ሠራተኞች ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ ክፍልን በምክትልነት የምትመራው እሷ ናት። ፓርቲው በሃገሪቱ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ነው። ሴት መሆኗ ግን ከፍተኛ ሥልጣን ለመያዝ ያከብድባታል። ሰሜን ኮሪያ ጥብቅ የሆነ አባታዊ ሥርዓት ያላት ሃገር ናት። ጠቅላይ መሪ መሆንም ሆነ ወታደራዊ ሥርዓቱንም መምራት ለሴቶች የሚታሰብ ቦታ አይደለም። ሁለተኛው ኪም ጆንግ-ቹል ነው። የኪም ጆንግ-ኡን ታላቅ ወንድም። በፖለቲካ ጨዋታው ሜዳ የማይታይ። ከፖለቲካ ይልቅ የኤሪክ ክላፕተን [እንግሊዛዊ የሮክ ሙዚቃ ተጫዋች] ጊታር ድምፆች የሚመሰጡት እንደሆነ ይነገርለታል። የመጨረሻው ኪም ፒዮንግ-ሁለተኛ - የኪም ጆንግ ኡን ግማሽ ወንድም። እናቱ የኪም ጆንግ ኡን እንጀራ እናት ነበሩ። ሥልጣን እንዲይዝ አብዝተው ይሹ ነበር ይባላል። ኪም ፒዮንግ-ሁለተኛ በ1971 ወደ አውሮፓ ተልኮ በተለያዩ ሃገራት አምባሳደር ሆኖ ካገለገለ በኋላ ባለፈው ዓመት ነው ወደ ሃገሩ የተመለሰው። በፒዮንግያንግ ፖለቲካ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ አይጠበቀም። በኪም ጁንግ አስተዳደር ትልቅ ሚና ያላቸው ሌሎች ሰዎች ቢኖሩም ለሥልጣን ዕድል ይኑራቸው አይኑራቸው የሚታወቅ ነገር የለም። አንደኛው ኮዊ ሪዮንግ-ሄ ናቸው። ሰውዬው የፖሊት ቢሮ ፕሬዝዳንትና የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ተቀዳሚ ሊቀ-መንበር ናቸው። ባለፈው ዓመት ደግሞ ከ20 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝደንት ሆነው ተሹመዋል። ኪም ዮንግ-ቾል የተባሉት የውጭ ጉዳዮች ዲፕሎማት፣ የካቢኔ መሪው ኪም ጄ-ሪዪንግ፣ የፀጥታ ጉዳዮች ኃላፊው ጆንግ ኪዮንግ-ታየክ እና ከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጣን ያላቸው ህዋንግ ፒዮንግ-ሶ በኪም አመራር ከፍተኛ የሚባል ቦታ ያላቸው ናቸው። ማን ለሥልጣን ይጋደላል? የኪም ወዳጆችና ተቀናቃኞች የሚባል ነገር ይኖር ይሆን? ሃገሪቱ እንዳትፈራርስ በመስጋት ተቀናቃኞች ድምፃቸውን ከማሰማት ይቆጠቡ ይሆን? ሰሜን ኮሪያ እንዳይሆን ሆና በደቡብ ኮሪያ አልያም በቻይና እጅ ስትወድቅ ማየት የሚሻ ሰሜን ኮሪያዊ ይኖራል ብሎ ማሰብ አዳጋች ነው። እውነት ለመናገር አሁን ኪምን ማን ይተካቸዋል የሚለው ጥያቄ ጥርት ያለ ምላሽ የለውም። እህቱ አባታዊ ሥርዓቱን ሰንጥቃ ማለፍ ይጠበቅባታል። ሌሎች ደግሞ የፓየክቱ ዘር ግንድ የላቸውም። ወጣም ወረደ ሰሜን ኮሪያውያን ሃገራቸውን ከዓለም አቀፍ ጫና ለመጠበቅ ሁሉን እንደሚያደርጉ ይታመናል። ሰሜን ኮሪያ ለምን ኑክሊዬርን መረጠች?
44979022
https://www.bbc.com/amharic/44979022
ልጆችዎ ጤናማ ምግብ እንዲመገቡ ማድረጊያ መላዎች
ልጆችዎ ጤናማ ሆነው ያድጉ ዘንድ ይሻሉ? ኧረ ምን በወጣኝ እንዳማይሉ ሙሉ እምነት አለን። በተለይ ልጆች ጤናማ ሆነው ያድጉ ዘንድ ፍራፍሬን የመሰለ ነገር የለም ይላሉ የሥነ-ምግብ ባለሙያዎች።
ልጆች በባሕሪያቸው ያልመዷቸውን ምግቦች ወደአፋቸው ማስጠጋት እንኳን አይፈልጉም፤ ባለሙያዎቹ ማሙሽ ወይም ሚሚ ጤናማ ምግቦችን ከመመገብ ቢያፈገፍጉ መላ አለና ማጣፊያው አይጠሮት ይላሉ። ቀጣዮቹ አምስት መላዎች ሕፃናት ጤናማ ምግቦችን እንደመገቡ የሚያስችሉ ናቸው ተብለው በአዋቂዎቹ የተቀመጡ ናቸው። • “መሸ መከራዬ”፡ የታዳጊዎች ስቃይ • ፈር ቀዳጅ የታይፎይድ ክትባት ተገኘ ፩. 20 ጊዜ ይሞክሩ ልጆችዎ አዲስ የሆነባቸውን ምግብ አልቀምስም ቢሉ በትንሽ በትንሹ ደጋግመው መሞክረዎን አያቁሙ። ይመኑን ልጆችዎ እንዲመገቡ የሚሹትን ጤናማ ምግብ ቢያንስ ለ20 ቀናት ቆንጠር ቆንጠር እያደረጉ መመገብ ውጤቱ ሸጋ ይሆናል ተብሏል። አንድ ጥናት እንዳመለከተው ልጆች በተደጋጋሚ ያንን ምግብ የሚያዩትና የሚቀምሱት ከሆነ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደዱት ይመጣሉ። ፪. ግማሽ በግማሽ መቼም ልጆችዎ እርስዎን መስለው መውጣታቸው አይቀሬ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ዶክተር ሌዌሊን እንደሚሉት «ልጆችዎ እንዲመገቡ የሚሹትን ምግብ አብረዋችው ይመገቡ። ከማሙሽ ወይም ከሚሚ ፊት ቁጭ ብለው ቢመገቡ ይመኑኝ ልጆችዎ ያንን ምግብ ባህል ያደርጉታል።» «ለምሳሌ አንድ ካሮት አንስተው ለሁለት በመክፈል 'አቤት ሲጣፍጥ' በማለት ግማሹን በልተው ግማሹን ለልጅዎ ቢሰጡ የማሙሽና ሚሚ የመብላት ፍላጎት ይጨምራል።» ፫. አይጫኗቸው አንድን ምግብ ወደአፋቸው አላስጠጋ ብለው ልጆች ቢያስችግሩ ከ15 ደቂቃ በኋላ ወደማስፈራራት ቢገቡ አይፈረድብዎትም። ''ይኸውልህ ይህን ካሮት አትብላና ውጪ ወጥተህ ምትጫወት መስሎሃል'' ብለው አቡቹን ቢያስፈሩርት የሚደንቅ አይደለም፤ ግን ይህ ነገርን ከማባባስ ውጭ ጥቅም የለውም። ኧረ እንደውም ሁለተኛ ያንን ምግብ ማየት አይፈልጉም ሲሉ ባለሙያዎች አፅንዖት ይሰጣሉ። እናማ ትንሽ ትዕግስት ቢጤ. . .ትንሽ ብቻ ሳይሆን ሞቅ ያለ ትዕግስት ያስፈልጋል ስንልዎ በታላቅ ትህትና ነው። ፬. ድለላ 'ዱላውን ወዲያ ካሮቱን ወዲህ'. . .ባለሙያዎቹ ናቸው የሚሉት። ሐፃናት መንቆለጳጰስ መውደዳቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። ጥናቱም የሚጠቁመው ሕፃናት አንድ ነገር እንዲያደርጉ በምላሹ ጉርሻ ይፈልጋሉ። ታድያ ዶክተር ሌዌሊን እንደሚሉት ድለላው ልጆች አዲስ ነገር ስለሞከሩ እንደሽልማት ሊቀርብ ይገባል። የሕፃናት ምግብ በማዘጋጀት የምትታወቀው እንግሊዛዊቷ አናቤል ካርሜል ለቢቢሲ ስትናገር ሌላኛው መላ ምግቡን ውብ አድርጎ ማቅረብ ነው። ፭. ሽልማቱ ምን ይሁን 'ሚሚዬ ይህችን ከበላሽ ኬክ እገዛልሻለሁ'. . .የሚሉት አይነት ማባበልን 'ታጥቦ ጭቃ' ይሉታል የዘርፉ ሰዎች። ልጆች ጤናማ ምግብ እንዲበሉ አባብለው መጨረሻው ጤናማ ያልሆነ ከሆነ ለፍቶ መና ሆነ ማለት ነው። ለዚህ ነው ሽልማትዎ ጤናማ ካልሆኑ ምግቦች የተጠበቀ ይሁን በማለት ባለሙያዎቹ ምክራቸውን የሚለግሱት። ሳይንቲስቶች ህፃናት ራሳቸውን መቼና እንዴት እንደሚያውቁ ጥናት እያደረጉ ነው።
news-46481228
https://www.bbc.com/amharic/news-46481228
አሜሪካ ውስጥ ለየት ያለ ደም ላላት ህፃን ለጋሽ ለማግኘት ዘመቻ ተጀመረ
በካንሰር ህመም እየተሰቃየች ያለችው የሁለት ዓመት ህፃን በሽታውን ለመግታት የሚያስፈልጋትን በርካት ያለ መጠን ያለውን የተለየ የደም ዓይነት ከለጋሾች ለማግኘት ዓለም አቀፍ ዘመቻ ተጀመረ።
ዘይነብ ሙጋል አሜሪካ ፍሎሪዳ ውስጥ ያለችው ህፃኗ ዘይነብ ሙጋል በዓለም ላይ ለየት ያለ የደም ዓይነት ካላቸው ጥቂት ሰዎች መካከል አንዷ ናት። ይህም የሚያስፈልጋትን የደም አይነት የሚለግሳት ሰው ለማግኘት አስቸጋሪ አድርጎታል። • በዩቲዩብ 22 ሚሊዮን ዶላር የሚያገኘው የሰባት ዓመቱ ህፃን እስካሁን አንድ ሺህ የሚደርሱ የደም ናሙናዎች ቀርበው ቢመረመሩም ከእሷ ደም ጋር ተዛማጅ ሆነው የተገኙት ሦስቱ ብቻ ናቸው። ሃኪሞች እንደሚሉት ለህፃኗ 10 ተመሳሳይ ደም ያላቸው ለጋሾችን ማግኘት ያስፈልጋል። ለዘይነብ ደም ለማግኘት ዘመቻውን እየመራ የሚገኘው 'ዋንብለድ' የተሰኘው የበጎ አድራጎት የደም ባንክ የላብራቶሪ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ፍሬዳ ብራይት እንደሚሉት፤ የህፃኗ ደም የተለየ ነው ምክንያቱም በብዙ ሰዎች ደም ውስጥ የሚገኘውና ኢንብ ተብሎ የሚታወቀው አንድ የደም ክፍል የላትም። ስለዚህም የህፃኗን ህይወት ለመታደግ በተመሳሳይ ይህ አይነቱ የደም ክፍል የሌላቸው ለጋሾችን ማግኘት የግድ አስፈላጊ ነው። ሌላ አይነት ደም ከተሰጣት ደግሞ ሰውነቷ ፈጽሞ ሊቀበለው አይችልም። • "ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም ይህ አይነቱ የደም አይነት ያልተለመደ መሆኑን የሚናገሩት የላብራቶሪው ሥራ አስኪያጅ ብራይት "ከ20 ዓመታት በላይ በዚህ ሙያ ላይ ተሰማርቼ የቆየሁ ቢሆንም እንዲህ አይነቱ ነገር ሲያጋጥመኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው" ብለዋል። ለህፃኗ ደም ለጋሽ ለማግኘት የሚደረገውን ዘመቻ እየመሩ ያሉ ባለሙያዎች እንደሚሉት ለጋሾች ተመሳሳይ የደም አይነት እንዲኖራቸው ከመፈለጉ በተጨማሪ በተለይ የፓኪስታን፣ የሕንድ ወይም የኢራን ዝርያ ያላቸውና የደም አይነታቸው ደግሞ ኦ ወይም ኤ ሊሆን ይገባል። የሦስቱ ሃገራት ዝርያ ያላቸው ለጋሾች ብቻ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ተፈላጊው የደም ዓይነትን ከነዚህ ሃገራት ውጪ ካሉ ሰዎች የማግኘቱ እድል ከሞላ ጎደል ዜሮ በመሆኑ ነው ተብሏል። ተመሳሳይ የደም አይነት አላቸው ከሚባሉት ሰዎች መካከልም ከህፃኗ የደም አይነት ጋር የሚዛመድ ደም ያላቸው የሰዎች ቁጥር ከአራት በመቶ ያነሰ ነው። • "ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ የዘይነብ አባት እንደተናገሩት ልጃቸው ኒዩሮብላስቶማ ተብሎ የሚታወቀውና በአብዛኛው ህፃናት ልጆች ላይ የሚያጋጥመው የካንሰር አይነት እንዳለባት የታወቀው ባለፈው ጥቅምት ላይ ነበር። ቤተሰቧ ይህንን አስደንጋጭ ዜና ሲሰማ ክፉኛ ነበር በሃዘን የተመታው የበለጠ ሃዘናቸውን ያበረታው ደግሞ የዘይነብ ደም ለየት ያለ መሆኑና የሚያስፈልጋትን ደም ለማግኘት አስቸጋሪ መሆኑ ነበር። ህፃኗን እያከሙ ያሉት ሃኪሞች እንደሚሉት በኬሞቴራፒ ህክምና የካንሰሩ እጢ መጠን እየቀነሰ ቢሆንም፤ ዘይነብ ተጨማሪ ህክምናና በርከት ያለ ደም ያስፈልጋታል። "እየተፈለገ ያለው ደም ዘይነብን ከህመሟ ባያድናትም፤ ለካንሰር የሚሰጣትን ህክምና ለመቋቋም ግን እጅግ አስፈላጊ ነው" ይላሉ ብራይት።
46154717
https://www.bbc.com/amharic/46154717
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ ወደ ሶማሊያ በረራ ጀመረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ ወደ ሶማሊያ በረራ አድርጎ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ አረፈ።
ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ ሰንደቅ አላማ የተሰራ ኬክ በቦይንግ 737 የተደረገው በረራ የተመራው በሴት አውሮፕላን አብራሪ ሲሆን፤ 50 ሰዎችን አሳፍሮ ነበር። • በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር ላይ የጅምላ መቃብር ተገኘ • አሜሪካ ለህገ ወጥ ስደተኞች ጥገኝነት መስጠት ልትከለክል ነው አውሮፕላኑ ሞቃዲሾ የደረሰው ከአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ሁለት ሰአት ገደማ ከበረረ በኋላ ነበር። ከተሳፋሪዎቹ መካከል በኢትዮጵያ የሶማሊያ ኤምባሲ ፈርስት ካውንስለር አቶ አብዱላሂ መሀመድ ዋርፋ ይገኙበታል። አቶ አብዱላሂ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በረራው መጀመሩ የሁለቱን ሀገሮች የንግድ ግንኙነት ያጠናክራል። አውሮፕላኑ ከአዲስ አበባ ሲነሳ፣ በበረራው እኩሌታ እንዲሁም ሞቃዲሾ ካረፈ በኋላ ልዩ ልዩ መሰናዶዎች ተካሂደዋል። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? • "የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኞች ከሌሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው" ጄኔራል አሳምነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊያ በረራ ማድረግ ያቋረጠው እንደ አውሮፓውያኑ በ1970ዎቹ በሁለቱ ሀገሮች የድንበር ግጭት ከተከሰተ በኋላ ነበር። በአሁን ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆና ከኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ይገኛሉ። የኬክ ቆረጣ ስነ ስርዓት ተካሂዷል ጋዜጠኞች ተገኝተው ነበር አቶ አብዱላሂ መሀመድ ዋርፋ አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ የሶማሊያ ባህላዊ ሙዚቃ ቀርቧል
news-52103777
https://www.bbc.com/amharic/news-52103777
ከ50 በላይ የካንሰር አይነቶችን ቀድሞ የሚለይ የደም ምርመራ ተገኘ
ምንም አይነት የካንሰር ህምም ምልክቶች ከመታየታቸው በፊት በሚደረግ ቀላል የደም ምርመራ ከ50 በላይ የካንሰር አይነቶችን መለየት እንደተቻለ ተመራማሪዎች አሳወቁ።
በዚህም በሰውነት ውስጥ የሚከሰቱ ካንሰር አምጪ ሴሎችን በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እያሉ ለመለየት ያስችላል። ባለሙያዎቹ እንደሚሉትም ይህ ምርመራ ካንሰርን በወቅቱ ለማከም ከፍ ሲልም ለማዳን ተስፋን እንደፈጠረ አመላክተዋል። በሥራው ላይ የተሳተፈው ቡድን እንደጠቆመው በምርመራው የተገኙት ካንሰርን አመልካች ውጤቶች ውስጥ ከ99 በመቶ የሚበልጡት ትክክለኛ መሆናቸው ተመልክቷል። ነገር ግን ውጤቱ ስህተት እንዳይኖረው ማረጋገጥ ያስፈልገዋል ተብሏል። ሐኪሞች ምርመራውን በህሙማን ላይ እየሞከሩት ሲሆን ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልገው በካንሰር ህክምና ላይ የሚያተኩረው መጽሔት ገልጿል። ምርመራው ከካንሰር አምጪ ህዋሳት በመውጣት በደም ስሮች ውስጥ የሚገኝንና በዘረ መል ውስጥ የሚከሰትን ኬሚካላዊ ለውጥ የሚዳስስ ነው። ከተለያዩ የህክምና ምርምር ተቋማት የተወጣጡት አጥኚዎች ካንሰር ያለባቸውና የሌለባቸው ከ4 ሺህ የሚበልጡ የህሙማን ናሙናዎችን በመውሰድ ሙከራ አድርገዋል። በዚህ የሙከራ ምርመራ ወቅትም የአንጀት፣ የሳንባና የማህጸን ካንሰርን ጨምሮ ከ50 የሚበልጡ የካንሰር አይነቶች ተካተዋል። ሙከራው ከተደረገባቸው ናሙናዎች ውስጥ 96 በመቶው የሚሆኑት ላይ የተገኘው የመርመራ ውጤት በትክክል ያለባቸውን የካንሰር አይነት የመለከተ እንደሆነም ተገልጸወል። የጡት ካንሰር 12 ምልክቶች
news-54613280
https://www.bbc.com/amharic/news-54613280
ፓራጉዋይ፡ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ኮኬይን በከሰል ጭነት ውስጥ ተደብቆ ተገኘ
በፓራጉዋይ 23 ኩንታል ኮኬይን በከሰል ጭነት ውስጥ ተደብቆ ተገኘ።
ጭነቱ ወደ እስራኤል እየተጓዘ እንደነበር ፖሊስ የገለፀ ሲሆን 500 ሚሊዮን ዶላርም ያወጣል ተብሏል። በደቡብ አሜሪካዋ ፓራጉዋይ የተያዘ ትልቁ አደንዛዥ የእፅ ዝውውርም ክምችትም መሆኑ ተገልጿል። የኮኬይኑ ክምችት የተገኘው በመዲናዋ አስዩኒኮን አቅራቢያ በምትገኘኝ ቪሌታ ከተማ በሚገኝ የግል ወደብ ውስጥ ባለ መጋዘን ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ሁለት ሰዎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን አንደኛው ግለሰብ የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ የቀድሞ ዳይሬክተር ነው። ኮኬይኑ ተጠቅልሎ በአንደኛው መጋዘን ውስጥ በከሰሎች መካከል የተገኘ ሲሆን ቀሪ አምስት መጋዘኖችም እንደሚፈተሹ ፖሊስ አስታውቋል። የአገር ውስጥ ሚኒስትር ኡስሊደስ አክቬዶ እንዳሉት በአጠቃላይ የኮኬይን መጠኑም ወደ 30 ኩንታል ሊሆን እንደሚችልም አመላክተዋል። በላቲን አሜሪካ አገራት መካከል ወደ ውጪ ከሚላኩ ምርቶች መካከል ዋነኛ የሆነው የከሰል ምርት በአለም አቀፍ ድንበሮች ላይ ኮኬይንን ለማዘዋወር ሽፋንም ሆኖ በማገልገል ላይ ነው። የምርቱ የመጨረሻ መዳረሻ እስራኤል ቢሆንም በመካከል ግን በአርጀንቲናዋ መዲና ቦነስ አይረስና በቤልጂየሟ ከተማ አንትወርፕ ለማቆም እቅድ ይዞ የነበረ መሆኑን ሚኒስትሩ ኡስለደስ አስታውቀዋል። ጭነቱን በተመለከተ ከቤልጂየም ጥቆማ እንደደረሰውም የፓራጉዋይ ፖሊስ አስታውቋል። ኮኬይኑ ከቦሊቪያ በአውሮፕላን ተጭኖ ሳይመጣ እንዳልቀረ የፓራጉዋይ ፀረ-አደንዛዥ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ቦሊቪያ በአለም ላይ ሶስተኛ አደንዛዥ እፅ አምራች አገር ናት። ፓራጉዋይ በአመታትም ውስጥ ቁልፍ የአደንዛዥ እፅ መሻገገሪያ ሆና ቆይታለች። ለምሳሌም ያህል የብራዚሉ ፈርስት ካፒታል ኮማንድ የተባለው ቡድን በፓራጉዋይም ክንፉን ዘርግቶ ተንሰራፍቶ ይገኛል። ከዚህ ቀደም በፓራጉዋይ ትልቁ የተባለው የኮኬይን ክምችት የተገኘው ከአመት በፊት ሲሆን ይህም 22 ኩንታል ነበር።
news-42828895
https://www.bbc.com/amharic/news-42828895
ትራምፕ ለ1.8 ሚሊዮን ስደተኞች ዜግነት ሊሰጡ ነው
የትራምፕ አስተዳደር ሁለት ሚሊዮን ለሚጠጉ በሃገሪቱ ለሚገኙ ሰነድ ለሌላቸው ስደተኞች የአሜሪካ ዜግነትን ለመስጠት እቅድ አዘጋጀ። ለእነዚህ ሰዎች ዋይት ሀውስ ዜግነት የሚሰጠው በአወዛጋቢው የሜክሲኮ ድንበር ላይ አጥር ግንባታ በጀት የሚመደብ ከሆነ በምላሹ ነው።
ከፍተኛ የትራምፕ አማካሪዎች እዚህ ወሳኔ ላይ የደረሱት ከዲሞክራቶች ጋር ድርድር በሚያደርጉበት ዋዜማ ነው። ስለዚህም በመደራደሪያነት የሚያቀርቡት ለስደተኞቹ ዜግነት መስጠትን ሲሆን የግንባታ በጀት ደግሞ ከድርድሩ ማትረፍ የሚፈልጉት ይሆናል። ይህ መደራደሪያቸው ሰኞ ይፋ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን ለድንበር አጥር ግንባታው የሚጠይቁት በጀት 25 ቢሊዮን ዶላር ነው። ሜክሲኮ ድንበር ላይ አጥር መገንባትን የሚቃወሙ ዲሞክራቶች አጠቃላይ እቅዱን ተቃውመዋል። ስለዚህ እቅድ የተሰማው የዋይት ሃውስ ፖሊሲ ሃላፊ ስቴፈን ሚለርና የሪፐብሊካን አማካሪዎች ትናንት ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ቃለ ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ነበር። ሚለር ይህን የዋይት ሃውስ ፕላን አስገራሚም ብለውታል። እቅዱ 1.8 ሚሊዮን ስደተኞች ከ10-12 ዓመት ጊዜ ውስጥ ዜግነት የሚያገኙበትን ደረጃ ያስቀምጣል። ቁጥሩ ትራምፕ 'ድሪመርስ' የሚሏቸው ህፃናት ሳሉ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ የገቡ፤ ነገር ግን በኦባማ አስተዳደር ዘመን በጊዜያዊነት አገሪቱ ላይ እንዲማሩና እንዲሰሩ የተፈቀደላቸውን ሰባት መቶ ሺህ ስደተኞችን ይጨምራል። ሌሎቹ 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑት በተመሳሳይ መልኩ ወደ አገሪቱ የገቡ ነገር ግን በኦባማ አስተዳደር ከለላ ለማግኘት ሳያመለክቱ የቀሩ ናቸው። በስደተኞች ጉዳይ የሪፐብሊካኖች አክራሪ ድምፅ የሆኑት የምክር ቤት አባል ቶም ኮተን የትራምፕን እቅድ ለጋስና ሰብዓዊነትን የተከተለ ብለውታል። በተቃራኒው ዲሞክራቶች በእቅዱ ብዙም ደስተኞች አይደሉም። ይልቁንም እነዚህ ስደተኞች ትራምፕ ቤተሰብን ለመነጣጠል በሚከፍቱት ጦርነት መያዣ መሆን አይገባቸውም እያሉ ነው። ሜክሲኮ ድንበር ላይ ግንብ ለመገንባት የሚወጣው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የታክስ ከፋዮችን ገንዘብ የሚያባከን ነው እያሉ ነው።
news-54456862
https://www.bbc.com/amharic/news-54456862
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ 30 'ሽፍታዎች' ሲገደሉ 3 ተማረኩ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ረቡዕ መስከረም 27/2013 ዓ.ም በርካታ ሰዎች በከተገደሉበት ጥቃት ጋር በተያያዘ 30 የሚሆኑ 'ሽፍታዎች' መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ለቢቢሲ ገለጹ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ እንደገለጹት ሰሞኑን በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት አንድ ቻይናዊን ጨምሮ 13 ሰዎች በታጣቂዎቹ ተገድለዋል። ይህንን ተከትሎ የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ጥቃቱን ፈጽመዋል የተባሉ 30 የሚሆኑ የክልሉ ፖሊስ ሽፍታዎች ያላቸው ላይ እርምጃ ተወስዶባቸው ሲገደሉ ሦስቱ ደግሞ መማረካቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። ከባለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ ማንነታቸው በይፋ ያልተገጹ ታጣቂዎች በክልሉ ውስጥ ባሉ ወረዳዎች በፈጸሟቸው ጥቃቶች ሳቢያ በርካታ ሰዎች መገደላቸውና ንብረት መውደሙ ይታወሳል። ባለፈው ረቡዕ በተፈጸመው ጥቃትም ታጣቂዎቹ ግድያውን የፈጸሙት ግለሰቦቹ ሲጓዙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች አስቁመው እንደሆነ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ ገልጸዋል። ኮሚሽነሩ ጨምረው እንዳብራሩት ጥቃቱ የተፈጸመባቸው መንገደኞች በአካባቢው ካለው የጸጥታ ሁኔታ አንጻር መከላከያ ሠራዊትና የፀጥታ ኃይሎች የመንገዱን ደኅንነት እስኪያረጋግጥ ድረስ ባሉበት እንዲቆዩ ተጠይቀው እንደነበር ተናግረዋል። ነገር ግን ቻይናዊው መንገደኛ የነበረበት ተሽከርካሪ የተሰጠውን የጥንቃቄ መመሪያ ችላ ብሎ ጉዞውን መቀጠሉን ተከትሎ ሌላ አውቶብስ በተመሳሳይ ሁኔታ መንገዱን መቀጠሉን አመልክተው፤ በእነዚህ በሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ሰዎች መገደላቸውን አስረድተዋል። ከዚህ ቀደም የተከሰቱ ጥቃቶችን በተመለከተ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ጸረ ሰላም ኃይሎች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ጥቃት አድራሾቹ በአገር ውስጥና በውጭ ኃይሎች የሚደገፉ መሆናቸውንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። የአካባቢውን ፀጥታ ለመጠበቅ ሕዝቡ ከፀጥታ ኃይል ጎን ሆኖ ሽፍቶቹን እየተዋጋ መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፤ በአካባቢው ሕብረተሰቡን የማጠናከር ሥራ እንዲሁም የፀጥታ ኃይሎችም በተጠናከረ ሁኔታ ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም በክልሉ ከጳጉሜ 2 ጀምሮ ለሳምንት በዘለቀ ጥቃት፤ ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ኃይሎች በተለያዩ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢዎች በፈጸሟቸው ጥቃቶች ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መገደላቸውና ንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን ይታወሳል። በወቅቱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በጥቃቱ እስከ 50 የሚደርሱ ሰዎች መሞታቸው ሲገልጹ፤ የወደመውና የተዘረፈውን ንብረት መጠን ግን ማወቅ እንዳልቻሉ ተናግረው ነበር። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም ባወጣው መግለጫ በክልሉ በአንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የፀጥታ መደፍረሶችን ተከትሎ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከተፈጸሙ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ እጅግ አሳሳቢ መረጃዎች እየደረሱት መሆኑን ባወጣው መግለጫ አመልክቶ ነበር። በወቅቱ እነዚህ መረጃዎች እየደረሱት ያለው በክልሉ ውስጥ ከሚገኘው መተከል ዞን፣ ከቡለን ወረዳ አጳር ቀበሌ እንዲሁም ከወንበራ ወረዳ መልካን ቀበሌ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል። በክልሉ ጳጉሜ 1/2012 ዓ.ም እንዲሁም ከመስከረም 4 እስከ መስከረም 10/2013 ዓ.ም መካከል ባሉት ቀናት ውስጥ ቢያንስ ሁለት ጥቃቶች ማጋጠማቸውን ከክልሉ መንግሥት ለማረጋገጥ መቻሉንም በዚያው መግለጫ ላይ አመልክቷል። ቢያንስ በሁለት ዙር በተፈጸሙት ጥቃቶች ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያዎች መፈፀማቸውን እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን በስፍራው ከሚገኝ አንድ መንግሥታዊ ምንጭ መረዳት እንደቻለ ኮሚሽኑ መግለፁ ይታወሳል። በክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር በመከላከያ ሠራዊት፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልል የጸጥታ ኃይሎች ሰላምን ለማስጠበቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንደሚያበረታታም አስታውቋል። ኮሚሽኑ አገሪቱ በተቀበለቻቸው ሕጎችና ሰነዶች መሰረት የሰዎች በሕይወት የመኖር መብቶች እንዲከበሩ የጠየቀ ሲሆን፣ በክልሉ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ጥቃቶች በተደጋጋሚ ማጋጠማቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ገለልተኛ፣ ፈጣን ምርመራዎችን በማካሄድ ግድያው በተከሰተባቸው ሁኔታዎች ላይ የጥፋተኞችን ተጠያቂነት እንዲያረጋግጡ አሳስቦ ነበር። በተጨማሪም የክልሉ መንግሥት አካላት ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ወደ ቀደመ ሕይወታቸው የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻቹ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል። ከዚያም በኋላ በክልሉ ማንዱራ ወረዳ በንገዝ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ሐሙስ መስከረም 14/2013 ሌሊት ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ በድጋሚ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ የ15 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጾ፤ ሁኔታው አሳሳቢነቱ በእጅጉ እንደጨመረ ማመልከቱ ይታወሳል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተደጋጋሚ ያጋጠሙ ጥቃቶችን ተከትሎ ክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በኮማንድ ፖስት ስር እንዲተዳደሩ የተወሰነ ሲሆን የመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ በአካባቢዎቹ ሰላም እንዲያስከብሩ ተሰማርተዋል።
news-48554519
https://www.bbc.com/amharic/news-48554519
ትኩረት እየሳበ የመጣው የሴቶች እግር ኳስ የዓለም ዋንጫ
የዘንድሮው የሴቶች የዓለም ዋንጫ ከሌሎቹ ጊዜያት በተለየ ሁኔታ በርካታ መሻሻሎችን አድርጎ ዛሬ በፈረንሳይ ይጀመራል።
ስኬታማ ከሆኑት የሴት እግር ኳስ ቡድኖች መካከል ቀዳሚዎቹ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ውድድሩ በ1991 (እአአ) ከጀመረ ወዲህ በማስታወቂያ፣ በቴክኖሎጂና በሌሎች ነገሮች ጉልህ መሻሻልን በማሳየት የወንዶቹን ያህል እንኳን ባይሆንም ያለውን ሰሪ ልዩነት በተወሰነ ደረጃ በማጥበብ ይካሄዳል። የሚከተሉት ስድስት ጉዳዮች የሴቶች የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ያሳየውን ዕድገት ያሳያሉ። ተሳታፊዎችና ተመልካቾች ከአራት ዓመታት በፊት ካናዳ ውስጥ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ የተደረጉትን 52 ግጥሚያዎች 1.35 ሚሊዮን ሰዎች ተመልክተውታል። የዓለም እግር ኳስ የበላይ አካል የሆነው ፊፋ፤ ፈረንሳይ የምታስተናግደው የዚህ ዓመቱ የሴቶች እግር ኳስ የዓለም ዋንጫ ውድድርን ከባለፈው ጋር ተመሳሳይ አሊያም የበለጠ ቁጥር ያለው ሰው ይመለከተዋል ብሎ ይጠብቃል። ጨምሮም በቴሌቪዥን ውድድሩን የሚመለከተው ሰው ቁጥር ከባለፈው የዓለም ዋንጫ ከፍ እንደሚልም አመልክቷል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ይህ የሴቶች የዓለም ዋንጫ በ1995 (እአአ) ኖርዌይ ውስጥ ሲካሄድ እያንዳንዱን ጨዋታ በአማካይ 4500 ሰዎች ብቻ ነበር የተመለከቱት። በአጠቃላይ ውድድሩን የተመለከቱት ሰዎች ደግሞ ከ112 ሺህ ያህል ብቻ ነበሩ። አዲሱ የኔዘርላንድስ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ማሊያ አመቺና ተመራጭ የስፖርት አልባሳት በዚህ ዓመቱ የሴቶች የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ ከሌላው ጊዜ በተለየ ተጫዋቾቹ ለወንዶች የተዘጋጀ የስፖርት ትጥቅን ሳይሆን ለሴቶች ተብለው የተዘጋጁ ትጥቆችን ይለብሳሉ። ለዚህም በውድድሩ ከሚሳተፉት 24 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የሦስተ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊዋን አሜሪካንን፣ አስተናጋጇን ፈረንሳይን፣ የአውሮፓ ሻምፒዮናን ኔዘርላንድስ እና ብራዚልን ጨምሮ 14 ቡድኖችን ስፖንሰር ያደረገው የስፖርት ትጥቆች አምራች ድርጅቱ ናይኪ ነው። • ''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ የድርጅቱ የምርምርና የዲዛይን ቡድን የሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ፍላጎትን ከግምት በማስገባት ረጅም ጸጉር ላላቸው በቀላሉ የሚለበስና የሚወልቅ ማሊያዎች እንዲሁም ሰውነትን የማያጋልጡ ነገር ግን እንቀስቃሴን የማይገድቡ ቁምጣዎችን አዘጋጅቷል። የኔዘርላንድስ ቡድን ማሊያም የሃገሪቱ ወንድ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች ደረት ላይ ይደረግ የነበረውን የወንድ አንበሳ ምስል በመቀየር ለሴቶቹ ምስሉ የሴት አንበሳ እንዲሆን ተደርጓል። እራሷን ከዓለም ዋንጫ ያገለለችው አዳ ሄገርበርግ ዝቅተኛ ክፍያ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር አሁንም ድረስ በገቢና በክፍያ በኩል ከወንዶቹ አቻቸው በእጅጉ ዝቅ ያለ ነው። ከሴቶች እግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል ከፍተኛውን ክፍያ የምታገኘው የኖርዌይ ዜጋዋ አዳ ሄገርበርግ ስትሆን በዓመት የሚከፈላት 450 ሺህ ዶላር ነው። ይህም ከአርጀንቲናዊው አጥቂ ሌዮኔል ሜሲ ጋር ሲነጻጸር በ325 እጥፍ ያነሰ መሆኑን ፍራንስ ፉትቦል የተባለው መጽሔት ያካሄደው ዓመታዊ ጥናት ያመለክታል። የዚህ ዓመቱ የሴቶች የዓለም ዋንጫ ውድድር 30 ሚኒዮን ዶላር በሽልማት መልክ ለውድድሩ ተሳታፊዎች ይሰጣል። ይህም ቀደም ባለው ውድድር ላይ ከቀረበው እጥፍ ሲሆን በውድድሩ ታሪክም ከፍተኛው ነው። • ሞ ሳላህ ለሊቨርፑል መፈረሙ በከተማዋ ሙስሊም ጠልነት ቀነሰ ነገር ግን ለውድድሩ አሸናፊ ብድን 4 ሚሊዮን ዶላር የሚሰጥ ሲሆን ይህ በወንዶቹ ውድድር ላይ ከ16ቱ የዙር ፉክክር የሚሰናበቱ ቡድኖች ከሚያገኙት ገንዘብ ግማሹ ነው። ይህ በወንዶችና በሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት ኖርዌያዊቷ ሄገርበርግ ከዓለም ዋንጫ አራሷን እንድታገል አድርጓታል። ተጫዋቿ ከሀገሯ ብሔራዊ ቡድን ውጪ እንድትሆን ያደረጋትን ከፍ እያለ የመጠው ተስፋ መቁረጥና ለሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ያለው አክብሮት ዝቅተኛ መሆን ለውሳኔዋ ምክንያት እንደሆነ ገልጻለች። በተመሳሳይ የአውስትራሊያ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ቅሬታቸውን ለፊፋ ያቀረቡ ሲሆን አሜሪካ ሴት እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች ደግሞ በሚከፈላቸው ከወንዶች ያነሰ ክፍያ ምክንያት በሃገራቸው የእግር ኳስ ማህበር ላይ ክስ መስርተዋል። የኔዘርላንድስ አሰልጣኝ ሳሪና ዊግማን ከቡድኗ አባላት ጋር ሴት አሰልጣኞች የአውሮፓ እግር ኳስ ውድድር የበላይ አስተዳዳሪ የሆነው ዩኤፋ እንደሚለው በአህጉሩ ካሉ የእግር ኳስ ቡድን የአሰልጣኝነት ሥራዎች ውስጥ 80 በመቶው በወንዶች የተያዙ ናቸው። በተጨማሪም 97 በመቶው የአሰልጣኝነት ፈቃድ የተሰጠው ለወንዶች ነው። ከዚህ በመነሳትም በዚህ ዓመቱ የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ ከሚወዳደሩ 24 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ስምንቱ ሴት አሰልጣኞች አሏቸው። እነሱም ዋነኞቹን የውድድሩ ተፎካካሪዎች የሆኑትን ጀርመንና አሜሪካን መጨመሩ አውንታዊ ነው ተብሏል። ብዙዎች እግር ኳስ መጫወት ይፈልጋሉ በፊፋ ግምት መሰረት ከ30 ሚሊዮን የሚበልጡ ሴቶችና ልጃገረዶች በዓለም ዙሪያ እግር ኳስን ይጫወታሉ። ባለፉት አስር ዓመታትም በአማተርነት እግር ኳስን የሚጫወቱ ሴቶች ቁጥር ከ15 በመቶ በላይ በሆነ አሃዝ አድጓል። ነገር ግን ይህ ቁጥር በዓለም ዙሪያ ከተመዘገበው እድገት አንጻር ከ10 በመቶ በታች ነው። • ፌዴሬሽኑ፡ «የቡና እና መቀለ ደጋፊዎች ባሉበት ጨዋታ ሊካሄድ አይችልም» በዓለማችን ካሉ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል ከግማሽ የሚበልጡት በአሜሪካና ካናዳ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ይህ በደቡብ አሜሪካ ላሉት መልካም ምሳሌ በመሆን ሊያነሳሳ ይችላል ተብሏል። በወንዶች እግር ኳስ በዓለም ዙሪያ ስማቸው ዘወትር የሚነሱት የደቡብ አሜሪካ ሃገራት በሴቶች ዘርፍ ያላቸው ቁጥር ዝቅተኛ ነው። በደቡብ አሜሪካ ያሉት ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ቁጥር ከ250 ሺህ በጥቂቱ አለፍ ያለ እንደሆነ የፊፋ መረጃ ያመለክታል። በዓለማችን እግር ኳስ ከሚጫወቱ ሰዎች መካከል ሴቶች ከ10 በመቶ ብቻ ናቸው ፉክክሩ ከባድ ይሆናል አሜሪካ ከዚህ በፊት የተካሄዱ ሦስት የሴቶች የዓለም ዋንጫን በማሸነፍና አራት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን በመውሰድ የውድድሩ ንግሥት ስትሆን፤ የዚህ ዓመቱን ዋንጫ ለማንሳት ትፎካከራለች። ቢሆንም ግን ተሳታፊ ቡድኖቹ በተቀራራቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው ፉክክሩ ቀላል እንደማይሆን ይታመናል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ስፖርታዊ መረጃዎችን የሚሰበስበው ግራሴኖት የተባለው ድርጅት እንዳለው የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ ለማንሳት አዘጋጇ ፈረንሳይ በ 22 በመቶ ከፍተኛውን ግምት አግኝታለች። • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' የውድድሩ አሸናፊ ይሆናሉ ተብሎ ግምት ከተሰጣቸው መካከል አሜሪካ (በ14 በመቶ) የሁለት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ጀርምን (በ12 በመቶ) እና እንግሊዝ (በ11 በመቶ) እድል እንዳላቸው ተገምቷል። ባልተጠበቀ ሁኔታ የውድድሩን ዋንጫ ያነሳሉ ተብለው የሚታሰቡት ደግሞ የወቅቱ የአውሮፓ ሻምፒዮን የሆኑት የኔዘርላንድ ሴት ብሔራዊ ቡድን አባላት ናቸው።
news-56066791
https://www.bbc.com/amharic/news-56066791
ቢል ጌትስ "ኮቪድ-19 ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል ችግር አይደለም"
51 ቢሊዮን ለዜሮ!
ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥን ሲያስቡ እነዚህን ሁለት ቁጥሮች እንዲያስታውሱ ያሳስባሉ፣ ቢሊየነሩ ቢል ጊትስ። እርሳቸው እንደሚሉት የሰው ልጅ የአየር ንብረት ለውጥን መቆጣጠር ከቻለ በሰው ልጅ ዝርያ ታሪክ ትልቁ ስኬት ሆኖ ይመዘገባል። የአየር ንብረት ለውጥን መቆጣጠር ከባድ እንደሆነ ሲያስረዱም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ማቆም እጅግ ተራ ጉዳይ እንደሆነ በአንጻራዊነት በማስረዳት ነው። የቢል ጌትስ አዲሱ መጽሐፍ ርእሱ "How to Avoid a Climate Disaster" ይሰኛል። የአየር ንብረት ለውጥ ጥፋትን እንዴት መከላከል ይቻላል? የሚል ትርጉም አለው። መጽሐፉ ዓለማችን ወደ አየር ንብረት ውጥንቅጥ ጨርሶዉኑ ከመግባቷ በፊት መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ያትታል። በሚቀጥሉት 30 ዓመታት ዓለም የሚገጥማትን ፈተና በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቀው ነው ይላሉ ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ። ይህን በድጋሚ ሲያስረዱም ሁለት ቁጥሮችን ያነሳሉ። 51 ቢሊዮን ለዜሮ! የእነዚህ ቁጥሮች ትርጉም ዓለም በዓመት ወደ ከባቢ አየር የምትለቀው የግሪንጋስ መጠንን የሚያሳይ ነው። 51 ቢሊዮን ቶን የግሪንጋስ በካይ ልቀት ሲሆን የሰው ልጆች ይህን ቁጥር ወደ ዜሮ ማውረድ ይኖርባቸዋል። የሰው ልጅ ይህን ካሳካ በሰው ልጆች ፍጥረት ታሪክ ትልቁ ስኬት ይሆናል ይላሉ ቢል ጌትስ። የቢል ጌትስ ትኩረት አሁን ቴክኖሎጂዎች ወደ ዜሮ ግስጋሴን እንዴት ሊያግዙ ይችላሉ የሚለው ነው። እንደ ንፋስ ኃይልና የጸሐይ ብርሃንን የመሰሉ ታዳሽ ኃይሎችን መጠቀም የካርቦን ልቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳሉ። ይህ ግን ከልቀቱ 30 ከመቶ ብቻ ነው መቀነስ የሚያስችለው። የዓለም ኢኮኖሚን 70 ከመቶ በሌላ ታዳሽ ኃይል እየተኩ መሄድ ያስፈልጋል። አለበለዚያ ዓለም ቅርቃር ውስጥ ትገባለች ይላሉ ቢልጌትስ። 70 ከመቶ የዓለም ኢኮኖሚ በተለይም የብረት፣ የሲሚንቶ፣ የትራንስፖርት ዘዴዎች እንዲሁም የማዳበርያ ምርት በሙሉ አዲስና ከካርቦን ነጻ የሆነ ዘዴ ሊተካቸው ይገባል ነው የሚሉት ቢል ጌትስ። ይህ ሥራ በፍጹም ለሰው ልጅ ቀላል ነው ተብሎ አይገመትም ባይ ናቸው። ቢል ጌትስ እንደሚሉት ይህን የዓለምን 70 ከመቶ ኢኮኖሚ የያዘ ዘርፍ ብድግ ብለን በአዲስ ለመተካት አቅሙም ሐሳቡም የለንም፤ ቀላልም አይሆንም ይላሉ። አሁን የሰው ልጅ የነዳጅና ናፍጣ መኪና በማሽከርከሩ፣ ኤሌክትሪክ በመጠቀሙ እየከፈለ ያለው ዋጋ አይታየውም። መንግሥታት ግን ዓለምን ከጥፋት ለመታደግ ሥራ መጀመር አለባቸው ሲሉ ይወተውታሉ ቢል ጌትስ። ተራ ዜጋ በዓለም የአየር ንብረት ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት፣ እየደረሰበት ያለውንም ጉዳት ለማየት፣ ሕመሙ ሊሰማው አይችልም። ለዚህም ነው መንግሥታት ጣልቃ መግባት ያለባቸው ብለው ይከራከራሉ። የግል ዘርፉ ታዳሽ ኃይል ላይ ብቻ እንዲያተኩርና የአካበቢ ብክለትን እንዲያቆም ከባድ ቅጣቶችን በመንግሥታት ሊጣልበት ይገባልም ይላሉ። የሪፐብሊካን ፓርቲ በአሜሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ የሰጠውን ዝቅ ያለ ግምትም ማስተካከል ይገባዋል ባይ ናቸው። ቢል ጌትስ በ1975 ማይክሮሶፍትን በሽርክና የፈጠሩ ሰው ሲሆኑ አሁን በ124 ቢሊዮን ዶላር ሀብት የዓለም 4ኛው ሃብታም ሰው ናቸው። ከሀብታቸው 50 ቢሊዮኑን ለበጎ አድራጎት በመስጠት በሜሊንዳ ፋውንዴሽን በርካታ የጤና ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ ያደርጋሉ። ቢል ጌትስ በአሁን ሰዓት በጤናና በትምህርት ዘርፍ በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ትልቅ ተሰሚነት ያላቸው ባለሀብት ናቸው። ቢልጌትስ በዓለም ላይ ኮቪድ-19ኝን የመሰለ የጤና እክል እንደሚከሰት ቀደም ብለው መተንበያቸውን ተከትሎ ተህዋሲውን እሳቸው ናቸው የፈጠሩት የሚሉ የሴራ ፖለቲከኞች ትኩረት ሆነው ቆይተዋል። ሐሳዊ መረጃዎችን በመገጣጠም የሴራ ፖለቲካ የሚያራምዱ ቡድኖች ቢል ጌትስ ኮቪድ-19ኝ ወረርሽኝን ፈጥረው የዓለም ሕዝብን ቁጥር ለመቀነስ ይፈልጋሉ ብለው ያሟቸዋል።
news-44354792
https://www.bbc.com/amharic/news-44354792
የወር አበባ ለምን በአንዳንድ ሴቶች ላይ ህመም ያስከትላል?
የወር አበባ ተፈጥሯዊ ጸጋ ነው።
የመተንፈስ ወይም የመመገብ ያህል ከተፈጥሮ ሂደቶች አንዱ ነው። የምድርን እኩሌታ የያዙት ሴቶች ወርሀዊ ዑደትም ነው። ሆኖም ስለ ወር አበባ ማውራት እንደ ሀጢያት ይቆጠራል። ከወር አበባ ጋር የተያያዙ የተዛቡ አመለካከቶችም የትለሌ ናቸው። ከደቡብ እስያ ሴቶች አንድ ሦስተኛው የወር አበባ ከማየታቸው በፊት ስለ ወር አበባ ምንነት እንደማያውቁ ዩኒሴፍ እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 የሰራው ጥናት ያመለክታል። ከኢራናውያን ሴቶች 48 በመቶዎቹ እንዲሁም ከህንዳውያን ሴቶች አስር በመቶ የሚሆኑት የወር አበባ በሽታ እንደሆነ ያስባሉ። በዓለም ላይ በሚልዮን የሚቆጠሩ እንስቶች የወር አበባ በሚያዩበት ወቅት ይገለላሉ። ሀፍርትም ይሰማቸዋል። የግንዛቤ ክፍተቱን ከግምት በማስገባት ዋሽ ዩናይትድ የተባለ የተራድኦ ድርጅት በየአመቱ ግንቦት 28 ዓለም አቀፍ የወር አበባ ንጽህና ቀን እንዲከበር አድርጓል። ስለ ወር አበባ ርዕሰ ጉዳይ ማውራትን ለማስለመድ ስለ ሂደቱ ማወቅ የመጀመሪያ እርምጃ ሊሆን ይችላል። የወር አበባ ዑደት እንዴት ይፈጠራል? ስለ ወር አበባ ምንነት ማስገንዘብ ስለ ዑደቱ ያለው አመለካከት እንዲቃና መንገድ ይከፍታል። የወር አበባ ከአስር እስከ 14 ዓመት አንስቶ ከ45 እስከ 50 ዓመት የሚዘልቅ ዑደት ነው። የወር አበባ ወርሀዊ ዑደት የሚፈጠረው በየ28 ቀን ልዩነት ሲሆን፣ ወደ ጽንስነት ያልተለወጠ እንቁላል ፈርሶ በደም መልክ የሚወጣበት ሂደት ነው። የ28 ቀን ዑደቱ ሁለት ደረጃዎች አሉት። የመጀመሪያው የወር አበባ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ያሉትን ሁለት ሳምንታት ያካትታል። በዚህ ወቅት ከሴቶች መራቢያ ህዋስ በአንዱ እንቁላል ማደግ ይጀምራል። የእንቁላሉን እድገት የሚያፋጥን ሆርሞንም ይመረታል። ወደ አስራ አራተኛው ቀን አካባቢ እንቁላሉ ሲያድግ በማህጸን ቧምቧ አድርጎ ወደ ማህጸን ይወርዳል። እንቁላሉ ከወንድ ዘር ጋር ከተዋሃደ የእርግዝና ሂደት ይጀመራል። ውህደቱ ካልተፈጠረ እንቁላሉ ከሁለት ወይም ከሦስት ቀናት በኋላ ሞቶ ይወገዳል። የዑደቱ ሁለተኛ ደረጃ በአስራ አራተኛው ቀን ጀምሮ በሀያ ስምንኛው ቀን ይጠናቀቃል። በሀያ አምስተኛው ቀን በማህጸን ውስጥ የሚመረተው የሆርሞን መጠን ቀንሶ ከሦስት እስከ ሰባት ቀን ደም ይፈሳል። በዚህ መንገድ የሚፈጠረው የወር አበባ ወርሀዊ ሂደትን ይከተላል። ለምን በወር አበባ ወቅት ህመም ይከሰታል? በወር አበባ ወቅት ምቾት የማይሰማቸው ሴቶች አሉ። አንድ ሦስተኛ ያህሉ ሴቶች ደግሞ ያማቸዋል። ከህመሞቹ ራስ ምታት፣ የጀርባ ህመም፣ ሆድ ቁርጠትና ማቅለሽ ይጠቀሳሉ። ለ24 ሰዓት ሊቆዩም ይችላሉ። ምክንያቱን ለማብራራት ቢያስቸግርም አቅም ማነስ የሚከሰትበትም ጊዜ አለ። የወር አበባ ህመም መጠን ያለፈ የማህጸን ውስጥ የደም እጢ ውጤት ነው። ይህም የማህጸን ጡንቻ መወጠርና መላላት የሆድ ቁርጠት ያስከትላል። ህመሙ ከወር አበባ አንድ ወይም ሁለት ቀናት በፊት ጀምሮ ለቀናት ይዘልቃል። አንዳንድ ሴቶች ላይ ከቀናት ሊያልፍም ይችላል። ዲስሜኖሪያ የተሰኘው ከወር አበባ ጋር የተያያዘ ፍተኛ የሆድ ቁርጠት እድሜ ሲጨምር ሊከሰት ይችላል። በዘር የመተላለፍ ባህሪም አለው። በማህጸን ውስጥ መሆን ያለባቸው ህዋሶች ከማህጸን ውጪ ሲሆኑ ኢንዶሜትርዮሲስ ይባላል። ከአስር ሴቶች በአንዷ ሊከሰትም ይችላል።
news-48862811
https://www.bbc.com/amharic/news-48862811
"ብ/ጄኔራል አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ" ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ
ሰኔ 15 ምን ይመስል ነበር?
ጋዜጣችን የእሑድ ጋዜጣ ነው፤ ቅዳሜ ምሽት ሁልጊዜም ቢዚ ነው። ጋዜጣውን ቅዳሜ ማታ ነው ማተሚያ ቤት የምናስገባው። ቅዳሜ ሁልጊዜ የሩጫ ቀን ነው። በዚህ ሩጫ ውስጥ ሆነሽ የባሕርዳሩን ክስተት ለመጀመርያ ጊዜ ስንት ሰዓት ላይ ሰማሽ? ምንድነው የሰማሽው? ከማንስ ነው የሰማሽው? በትክክል ሰዓቱን አላስታውስም። ግን ከ1፡30 እስከ 2፡00 ሰዓት ባለው ይመስለኛል። ቢሮ ነበርኩ፤ ያው ጋዜጣውን ጨርሰን ወደ ማተሚያ ቤት ለመላክ እየተሯሯጥን ነበር፤ ስለ ባሕርዳር የሰማንበት ሰዓት። ከአለቃዬ ተደውሎ ነው የተነገረኝ። ባህርዳር ላይ ችግር አለ እየተባለ ነው እስኪ አጣሪ ተባልኩ። •የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ ከዚያስ? ያው ክልሉ ላይ አንዳንድ ነገሮች ሲኖሩ የምናጣራው ወደ ክልሉ ኮሚኔኬሽን ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ ጋ [በመደወል] ነው። አጋጣሚ እሱ ጋ ስንደውል እኔም ባልደረቦቼም፤ የሱ ስልክ አይሰራም ነበር። ፖሊስ ኮሚሽን፣ ጸረ ሙስና... ብቻ ሰው እናገኛለን ብለን የምናስባቸው ሁሉ ጋ ስንደውል ነበር። •የጄኔራሎቹና የአዴፓ አመራሮች ግድያ፡ ሙሉ እውነቱን ማን ይንገረን? ከክልሉ ባለሥልጣናት መሀል በስም የሚታወቁ ሰዎች ጋ ደውለሻል። አንድ ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ የሚባል ሰው አለ በክልሉ፤ እሱ ጋ፣ አቶ አሰማኸኝ ጋ ሌላ በስም የማላውቃቸው ጋ፣ [እንዲሁም ደግሞ] አማራ ክልል ያሉ ጋዜጠኞች እነዚህ ጋ ብትደውይ ያሉኝ ሰዎች [ዘንድ] አንድ አራቱ ጋ ደውያለሁ... ሁሉም አያነሱም? የአቶ አሰማኸኝ አይሠራም ነበር። የፖሊስ ኮሚሽን ያለው ልጅም አይሠራም። ሌሎቹ ግን ስልክ አያነሱም። ዶ/ር አምባቸው ጋ ደውለሽ ነበር? አልደወልኩም፤ የርሳቸው ኮንታክትም የለኝም። ከዚያ ጄኔራል አሳምነው ጋ ደወልሽ? አዎ መጨረሻ ላይ «ቆይ... ለምን የክልሉ ጸጥታ ክፍል ኃላፊ ጋ አልደውልም?» ብዬ ወደርሳቸው ጋ ደወልኩኝ። ከዚህ በፊትም ለአንድ ጉዳይ ደውዬላቸው ነበር። ስልካቸውም ነበረኝ። ለምን ቆየሽ ግን? ከዚያ በፊት ትደዋወሉ ከነበረና በዚያ ላይ ጉዳዩ የጸጥታ ጉዳይ በመሆኑ በቀጥታ እሳቸውን የሚመለከት ሆኖ ሳለ ለምን እርሳቸው ጋ መጀመርያ አልደወልሽም? እርግጠኛ አይደለሁም ለምን ቀድሜ እሳቸው ጋ እንዳላሰብኩኝ። መጀመርያ የመጣልኝ ኮሚኔኬሽን ቢሮው ኃላፊ ጋ ነበር። ከቆየሁ በኋላ ነው እርሳቸው ጋ መደወል የመጣልኝ። በመሀልም የከተማውን ነዋሪዎች ለማነጋገር እየሞከርን ነበር። «የት አካባቢ ነው ተኩስ ያለው? የተጎዱ ሰዎች አሉ ወይ?... እሱንም ለማጣራት እየሞከርን ነበር በመሀከል። መጨረሻ ላይ ግን እርሳቸው ጋ ነው የደወልኩት። ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ተገለጸ እርሳቸው ወዲያው አነሱት? ወዲያው። [እንዲያውም] ሁለት ጊዜ ይመስለኛል የጠራው። በዚያ ሰዓት ተጠርጣሪ እንደሆኑ ታውቂያለሽ? ምንም የማውቀው ነገር የለም ምን ተባባላችሁ? ደወልኩኝ አነሱ። እራሴን አስተዋወቅኩ። ከአዲስ አበባ እንደምደውልላቸው የምሠራበትን መሥሪያ ቤትና ለምን እንደደወልኩ አስረድቼ ክልሉ ላይ ያለውን ነገር ምን እንደሆነ አንዲያስረዱኝ ነበር የጠየቅኳቸው። ምን አሉ? ባህር ዳር ከተማ ላይ አንድ አንድ ግጭቶች እንዳሉ እና ጉዳቶችም እንደደረሱ ነገሩኝ። 'ስፔሲፊክ' እንዲሆኑልኝ ስለፈለኩኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የፕሬስ ሴክሬቴሪያት ኃላፊው አቶ ንጉሡ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ነው ብለው መግለጫ ሰጥተዋል እና እርስዎ ግን ግጭት ነው ያሉኝ ስላቸው «መፈንቅለ መንግሥት ብሎ ነገር የለም። መፈንቅለ መንግሥት በየመንደሩ አይደረግም። መፈንቅለ መንግሥት ሊደረግ የሚችለው ማዕከላዊ መንግሥት ላይ ነው፤ እና ይህ ከእውነት የራቀ ነው። ምናልባት የምጠረጥረው የፌዴራል መንግሥት ወደ ክልሉ ለመግባት ፈልጎ የሰጠው ምክንያት ይሆናል ብዬ ነው የምገምተው» አሉኝ። ከዚያ «መፈንቅለ መንግሥት ካልሆነ [ታዲያ] ምንድነው 'ስፔሲፊካሊ' ያለው ነገር ስላቸው «እሱን አሁን መናገር አንችልም፤ ምክንያቱም እኛ ምርመራ ላይ ያለነው፤ እያጣራን ነው። እሱን እንደጨረስን እናሳውቃችኋለን» አሉን። "ብ/ጄነራል አሳምነው በባጃጅ ለማምለጥ ሲሞክሩ ነው የተገደሉት'' መቼ ነው የምታሳውቁን ስላቸው [ደግሞ] «ነገ ጠዋት በተወሰነ መልኩ ምርመራውን ስለምንጨርስ መግለጫ እንሰጣለን» አሉኝ ከዚያ ተሰነባብተን። ከዚያ በፊት ግን የመጨረሻ ጥያቄ ብዬ «ተኩስ አለ ይባላል፤ አሁንም ድረስ አልተረጋጋም ወይ?» ስላቸው «እኔም አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማኛል» አሉኝ። «መከላከያ ገብቷል ስለሚባለውስ ነገር?» ስላቸው «እሱ ላይ ኮሜንት ማድረግ አልችልም፤ የማውቀው ነገር የለም አሉኝ፤ ከዚያ በኋላ ብዙም ጥያቄ ለመመለስ ፍላጎት አልነበራቸውም። የሚሉኝ የነበረው «ምርመራ ላይ ነን፤ እያጣራን ነው፤ አልጨረስንም፤ እሱን እንደጨረስን ነገ ጠዋት መግለጫ እንሰጣለን» የሚል ምላሽ ነበር የሰጡኝ። ያወራሽው እርሳቸውን ስለመሆኑ ምን ያህል እርግጠኛ ነሽ? ከርሳቸው ድምጽ ጋ 'ፋሚሊያር' ነኝ። [ድምጻቸው ለኔ አዲስ አይደለም] ለምን እንደዛ አልሽ? ከዚያ በፊት አውርቻቸው አውቃለሁ፤ እንደነገርኩህ። ክልሉ ላይ በነበሩ ጉዳዮች በጸጥታ ጉዳዮች አውርቻቸው አውቃለሁ'ኮ አንቺ ግን ያውቁኛል ብለሽ ታስቢያለሽ? ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱ [ከዚህ ክስተት በፊት] የስልክ ልውውጦች ነበሩን። 'ሜሴጄም' አድርጌላቸው አውቃለሁ። ከዚያ በፊት በነበሩ ሁኔታዎች ማለቴ ነው። ምክንያቱም [ከዚህ ክስተት በፊት በነበሩ አጋጣሚዎች] ቴክስት ሳደርግላቸው ስብሰባ ላይ ነኝ እያሉ ይመልሱልኝ ስለነበር ስደውልላቸውም ራሴን አስተዋውቄ እንደዚህ ዓይነት ዜና እየሠራሁ ስለሆነ [ላናግርዎት ፈልጌ ነው] ብዬ ጽፌላቸው ስለማውቅና ስለመለሱልኝም ያውቁኛል ብዬ አስባለሁ፤ ላያውቁኝም ይችላሉ።እርግጠኛ አይደለሁም ግን። አንቺ ግን አርሳቸው ስለመሆናቸው ይቺን ታህል ጥርጥሬ የለሽም ማለት ነው? አዎ! አርግጠኛ ነኝ፤ ድምጻቸውን በደንብ አውቀዋለሁ። ስልካቸውም የርሳቸው ነው፤ የተሳሳተ ስልክ አይደለም። ብዙ ጊዜ ድምፅ ስሜትን የመግለፅ ጉልበት አለው ብዬ አምናለሁ። እንዳው በደወልሽላቸው ሰዓት እሳቸው ላይ መረበሽ ተሰምቶሻል? ከጀርባ የሚሰማ የተኩስ ድምፅስ ነበር? በጣም ፀጥ ያለ ቦታ። በቃ ድምፅም ጩኸትም ተኩስም የሌለበት ቦታ ነበር የነበሩት። ድምፃቸውም በጣም የተረጋጋ፤ሲያናግሩኝም ተረጋግተው ነበር። ከሰማናቸው ነገሮች አንፃር መረጋጋታቸውና ፀጥታው የሚጠበቅ አይደለም። እንዴት እንደዚያ የተረጋጋ ድምፅ ሊኖራቸው የቻለ ይመስልሻል? ግምትሽ ምንድን ነው? እርግጠኛ አደለሁም ግን የጦር ሰው ናቸው አደል። ብዙ ጊዜ የእንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ስሜት ከድምፃቸው መረዳት የምንችል አይመስለኝም። የተባለው ነገር በእርግጥም ሆኖ ከነበረ መደናገጥና መረበሽ ያልሰማሁባቸው ወታደራዊ ሰው በመሆናቸው ነው ብዬ እገምታለሁ። ግን አሁንም እርግጠኛ መሆን አልችልም። በደወልሽላቸው ሰዓት የክልሉ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ሌሎችም ሰዎች ተገድለዋል። እና ያንን ጉዳት አደረሰ የሚባል ሰው በዚያ መረጋጋት ማውራትና የክልሉን የፀጥታ ሁኔታ ማብራራት፤ በማግሥቱም መግለጫ እንሰጣለን ሲሉ ከድምፃቸው ምንም ነገር መረዳት አለመቻል ለማመን አይከብድም? አንቺ ራስሽ አሁን ላይ ስታስቢው አይገርምሽም? በርግጥ ግልፅ ቃለምልልስ ስለነበር ድምፃቸውን እቀርፅ ነበር። በሰዓቱ ከሰማሁት ነገር አንፃር እኔም ተረጋግቼ አልሰማኋቸው ይሆናል ብዬ በኋላም ደጋግሜ ሰምቼው ነበር፤ ድምፁን ግን አሁንም በጣም የተረጋጋ ድምፅ ነው ያላቸው። ድምፃቸውን ቀድተሻል ብዬ አላሰብኩም ነበር። የስልክ ንግግራችሁ የስንት ደቂቃ ነበር? ሶስት ደቂቃ ከ18 ሰከንድ መሰለኝ። አንዴ ቆየኝ እንዳላሳስትህ ቼክ ላድርገው።[ከአፍታ ቆይታ በኋላ] አዎ በትክክል ሦስት ደቂቃ ከ18 ሰከንድ ነው። የደወልሽላቸው ስንት ሰዓት ነበር? 2፡29 ላይ ነበር። በዚህች ደቂቃ ነው ያን ሁሉ ሐሳባቸውን የሰጡት? አዎ ንግግራችሁን ለመቋጨት ይሞክሩ ነበረ? ጋዜጠኛ ስለሆንሽ ተጨማሪ ጥያቄዎችን እንደምታከታትይባቸው እገምታለሁ? አዎ እንደዛ ነበረ። አንድ ሁለት ሦስት ጥያቄ መጀመሪያ ከመለሱ በኋላ ምርመራ እያደረግን ነው። እሱን ስንጨርስ ነው መናገር የምንችለው ነበር መልሳቸው። እኔ ግን በተደጋጋሚ ያለኝን ጥያቄ ሁሉ እጠይቃቸው ነበር። ምላሻቸው ያው እያጣራን ነው ነበር። ለምሳሌ ስሞች ጠቅሼ እነ እገሌ ጉዳት ደርሶባቸዋል እላቸው ነበር። ሌላ [ቅድም]ያልነገርኩህ ነገር የደረሰ ጉዳት? ስላቸው የክልሉ መስተዳደር አካባቢና የፓርቲ ጽ/ቤት ላይ ነው ጥቃት የደረሰው የሚል መልስ ሰጥተውኝ ነበር። እሳቸው ግን በስም የጠቀሱልሽ ግለሰብ የለም? እኛ ዜና ሰርተን ስለነበር እነ ዶ/ር አምባቸውን ስም ጠርቼ እነሱ ላይም ጉዳት ደርሷል ይባላል ስላቸው «ሊደርስም ላይደርስም ይችላል፤ እሱን እርግጠኛ ሆኜ መናገር አልችልም። እሱን የምናውቀው ምርመራችን ሲያልቅ ነው ነበር ያሉኝ። ለምን እንደዛ ያሉሽ ይመስልሻል? የምትገምቻቸው ነገሮች አሉ? ብዙ ነገር ሊሆን ይችላል ግን ይሄ ነው፣ ይሄ ነው ብሎ መገመትና መናገር ይከብደኛል። ነገሩ ገና በምርመራ ላይ ያለና ያልተቋጨ ነው። በምርመራ ሂደት ላይ ያለ ነገር ላይ [analysis and hypothesis ] መሥራት ከባድ ነው። ሁልጊዜ የስልክ ንግግርሽን የመቀርጽ ልምድ አለሽ? ይሄን የምጠይቅሽ ከዚህ በፊትም የእሳቸው ተብሎ የወጣ ድምፅ ስላለ ነው። እሱ ቅንብር ነው፤የመንግሥት የስለላ መዋቅር ያሰናዳው ነው የሚሉ ነገሮች ተነስተውበታል። ምናልባት አንቺም በተመሳሳይ ልትጠረጠሪ የምትችይበት ዕድል ይኖራልና እንዴት ነው የምናምንሽ? በፊትም የመቅዳት ልምድ ነበረሽ ወይ? ስልክሽ ላይ የተጫነ ሶፍትዌር ነው ወይስ ስቱዲዮ ገብተሽ ነበር የደወልሽላቸው? አይ ስልኬ ላይ [recorder]አለኝ። ለሥራ ቃለምልልስ በማደርግበት ጊዜ [on]አደርገዋለሁ። የግል ስልኮችን አልቀርጽም። ብዙ ጊዜ ለሥራ መደበኛ የቢሮ ስልኮችን ነው የምንጠቀመው። ግን የግል ስልኬን ስጠቀም እቀርፃለሁ። የዚያን ዕለት እንዲያውም የቢሮ ስልክ ነበር ልጠቀም የነበረው፤ ግን ሌሎችም ልጆችም ስለጉዳዩ እያጣሩ ስለነበር ነው ስልኬን የተጠቀምኩት። ከድምፅ ጋር ተያይዞ በቅርቡ የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ከብርጋዲየር ጀነራል አሳምነው ጋር ያደረጉት ንግግር ወጥቷል። ያንን ድምፅ ጥያቄ ውስጥ የሚከቱት ሰዎች አሉ። አንቺ እሳቸውን በድምፅ እለያቸዋለሁ ስላልሽን ስለዚህ ድምጽ ምን ልትይን ትችያለሽ? የሳቸው ድምፅ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። እንዳልኩህ ድምፃቸውን አውቃለሁ ሰምቼ፤ ደጋግሜ ስለሰማሁት እለየዋለሁ። እንዳልኩህ የሳቸው ድምፅ ይመስለኛል። "ኦዲዮው" ትክክል ነው፣ አይ ትክክል አይደለም፣ ተሰርቶ ነው በሚለው ላይ አስተያየት ባልሰጥ ደስ ይለኛል።... ስትሰሚው ግን ላንቺ የተሰማሽ ስሜት ምንድን ነው? ጄኔራል አሳምነው ናቸው ነው ያልሽው? የመጀመሪያ ስሜትሽ ምንድን ነው? ይቅርታ እዚህ ላይ በጭራሽ ምንም ኮሜንት ባላደርግ ደስ ይለኛል። አወዛጋቢ ስለሆነ ነው? አዎ ! የምልህ ጉዳዩ (ኬዙ) በደንብ ያልለየለት ነገር ነው፤ በዚህ ወቅት ምንም ብል የአንድን ሰው ሐሳብ እንደ መከራከሪያ ተደርጎ ፒክ ይደረጋል እና ቢቀር ነው የሚሻለኝ፤ እርግጠኛ ሆኜ ኮሜንት ማድረግ አልችልም። እርሳቸውን ካናገርሻቸው በኋላ በምን ፍጥነት ነው ፌስቡክ ላይ ፖስት ያደረግሽው? በጣም ቆይቻለሁ! ካናገርኳቸው "አይ ቲንክ" ሰላሳ አርባ ደቂቃ የቆየሁ ይመስለኛል። ምክንያቱም የጋዜጣውን ሥራ መጨረስ ስለነበረብን እሱን ጨርሰን ልክ ወደ ማተሚያ ቤት ከተላከ በኋለ ነው፤ ያንን ፖስት ያደረግኩት፤ አንድ ሰዓት ወይ እንደዚህ ! ፌስቡክ ላይ ስትለጥፊው ተጠርጣሪ እንደነበሩ ታውቂ ነበር? በፍፁም አላውቅም፤ ከቢሮ ከወጣሁ በኋላ ፌስቡክ አካውንቴ ላይም ያንን ነገር «አብዴት» ካደረግኩ በኋላ አጋጣሚ ወደ መንገድ ነው የወጣሁት። ወደ አዳማ እየነዳሁ ነበር። በመሀሉ ብዙ ስልኮች ይደወሉ ነበር። የምሄድበት ቦታ ስደርስ ሌሊት ነው። ኢንተርኔት ተቋርጦም ስለነበር ምንም የሰማሁት ነገር የለም። በማግስቱ ጥዋት ነው አማራ ቴሌቪዥን ላይ እሳቸው ተጠርጣሪ ናቸው መባሉን የሰሙ ልጆች ደውለው የነገሩኝ። አጋጣሚ ያለሁበት ቦታ መብራት አልነበረምና ተጠርጣሪ ናቸው ወይም አሉበት ብሎ መንግሥት እንደሚጠረጥራቸው የሰማሁት ከሰው ነው። ከክስተቱ በኋላ በጣም ብዙ ጥያቄዎች ይነሱ ነበር። ብዙ ግልፅ ያልሆኑ ነገሮች ነበሩ። ምናልባትም ብቸኛው መረጃ ከገለልተኛ ወገን በሳቸው ጉዳይ ላይ የፃፍሽው አንቺ ነሽ። ይሄ ጽሑፍ ሕይወትሽ ላይ ብዙ ተፅእኖ እንደፈጠረ እገምታለሁ። ከዛ ባሻገር ግን የደህንነት መዋቅሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ሊያናግርሽ አልሞከረም ወይ? ምርመራ አልተደረገብሽም? በፍፁም! ከዚያ በኋላ ማንም የትኛውም አካል ያናገረኝም የጠየቀኝም የለም። አንተም የምታውቀው ይመስለኛል ሶሻል ሚዲያ (ማህበራዊ ሚዲያ) ላይ ታፍና ተወስዳለች፤ ከዚያ ቀደም ብሎ ደግሞ ባልታወቁ ሰዎች ተገድላ ተጥላለች አይነት ዜናዎች ይሰሙ ነበር። ግን እንደሚባለው ምንም የደረሰብኝም ሆነ የጠየቀኝም፤ አፍኖ የወሰደኝ የለም። ይህንን ቃለ ምልልስ እንድትሰጪና ምንም አልሆንኩም እንድትይ ማንም ግፊት አላደረገብሽም፤ ከመንግሥት? ከዛ በፊት ከቀናቶችም በኋላ ምንም የደረሰብኝ ግፊት የለም። ማንም ጠርቶኝም፣ አናግሮኝምና ጠይቆኝም አያውቅም በዚህ ጉዳይ.... በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊያገኙሽና ስለዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሞከሩ ሰዎች የሉም በቀጥታ የፀጥታ አካላት ባይሆኑም.... የሉም! አንዳንድ የማቃቸው ሰዎች ፌስቡክ 'አብዴት' ያደረግኩትን ነገር ያዩ "እርግጠኛ ነሽ እሱን ነው ያናገርሽው? እሱ ስለመሆኑ ምን ያህል እርግጠኛ ነሽ" አይነት ጥያቄዎች ይጠይቁኛል። እነዚህ የማቃቸው ሰዎች ናቸው። ከዛ ውጭ የማላቃቸው ሰዎች በተዘዋዋሪ ጠይቀውኝ አያውቁም። ለምን ዝምታን መረጥሽ? ባንች ጉዳይ ላይ ብዙ ሲባል ነበር። አንደኛ ከፌስቡክ ገፅሽ ላይ የፃፍሽውን አላወረድሽም፤ ሁለተኛ ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው ዝምታሽን የሰበርሽው። ለምንድን ነው? ኢንተርኔቱ ቅዳሜ ቀን ተቋረጠ። ስለዚህ ቅዳሜ፣ እሑድ፣ ሰኞ፣ ማክሰኞ እስከ ረቡዕ ድረስ ኢንተርኔት አልነበረም። አለሁ ብዬ ለመፃፍም የኢንተርኔት አገልግሎት [access] አልነበረኝም። ያንንም የሰማሁት ከአገር ውጪ ያሉ ሰዎች ሲደውሉልኝ ነበር። እንደዚህ ተብሎ ተፅፏል ብለው ነገሩኝ። አለሁ ለማለትም ኢንተርኔት ስላልነበር መመለስ አልቻልኩም። ከዛ በኋላ ግን በቢሮ ስልክ ደውለው ያገኙኝ የሚዲያ ተቋማት [Media House] አሉ። ለምሳሌ አቤ ቶኪቻው ሳቅና ቁምነገር [ካልተሳሳትኩ] እሱ ደውሎ አናግሮኛል 'አለሁ' ብየዋለሁ። ዶይቼ ቬለ እንደዛው ደውለው አግኝተውኝ እንዳልታሰርኩ አረጋግጨላቸዋለሁ። ግን ኢንተርኔት እንዳገኘሁ እንዳለሁ 'ስታተሴን አብዴት' አድርጌያለሁ። አለመታሰሬን atleast የሚያሳውቅ ነገር። ከማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጽሑፉን ያላነሳሁት That's ...That's fact ነው። Fact means እውነት ነው ሳይሆን፤ ቃለምልልስ አድርጌ ያገኘሁት ነገር ነው። ለእርሱ ደግሞ ማስረጃ አለኝ። የቀዳሁት [Record] ያደረኩት መረጃ አለኝ። የተቀዳው ድምጽ እንዲወጣ ፍቃደኛ ነሽ? ለምሳሌ ከፈቀድሽ እኛም ልናወጣው እንችላለን ወይም በራሳችሁ ሚዲያ። እንደሱ ዓይነት ፍላጎት አለሽ? አሁን ባይወጣ እመርጣለሁ። ምክንያቱም ያለቀለት፤ የተዘጋ ነገር አይደለም። ምርመራ ላይ ያለ ነገር ነው። ስለዚህ በዚያ መካከል ማውጣቱ ተገቢ ነው ብዬ አላስብም። ከዚህ ክስተት በኋላ ሕይወትሽ ላይ ወይም በቤተሰቡ የፈጠረው መረበሽ አለ? ምንም ነገር። ማንም ጠይቆኝ ስለማያውቅ ምንም ነገር የለም። አንዳንድ የሚነግሩኝ ሰዎች አሉ። አደጋ [Risk] አለው እኮ... ለምን እንደዚህ አደረግሽ? እንደዚህ ቢሆን... እንደዚህ ቢከሰት ... ዓይነት ነገሮች አሉ። ግን ከቤተሰብ በኩል የመጀመሪያ ሰሞን ይጨነቁ ነበር። ሰው እንደዛ ሲል ታስራለች ... እንዲያውም ማክሰኞ ዕለት የነበረው ሞታ ተገኝታለች ሲባል ነበር። ግን ወዲያው ነው የቆመው እሱ ወሬ። ረቡዕ ዕለት ተመልሶ ታስራለች መባል ተጀመረ። የዚያን ጊዜ ይደነግጡ ነበር። የእውነትም ይመስላቸዋል። ደውለው እስከሚያጣሩና ድምፄን እስከሚሰሙ ድረስ የእውነት ይመስላቸው ነበር። ምክንያቱም አሁን ነው የታሰረችው...ከሰዓታት በፊት ነው ዓይነት ነገር ይባላል እና ደጋግመው ይጠይቁኝ [Check] ያደርጉኝ ነበር ሥራ ቦታ ላይ ስለነበርኩኝ። ከዚያ በኋላ ግን ከረቡዕ ዕለት በኋላ ነገሮች ሁሉ የተረጋጉ መሰለኝ። አልፎ አልፎ ነው አንዳንድ ሰዎች 'ታስራለች' የሚሉት እንጂ ግልፅ የሆነ መሰለኝ እንዳልታሰርኩኝ። አንች ግን የሆነውን ሁሉ ተመልሰሽ ስታይው ምነው ያን ቀን ባልደወልኩ የሚል ስሜት ይፈጠርብሻል? በፍፁም አይፈጠረብኝም፤ በፍፁም አልተፈጠረብኝም፤ አይፈጠርብኝም። ሥራ ላይ ነበርኩ ሥራዬን እየሰራሁ በነበረበት ሰዓት ነው አጋጣሚ የደወልኩት እና ምንም የተለየ ነገር እንዳደረኩም አይሰማኝም። የመንግሥት የፀጥታ አካላት እስካሁን አንች ጋ አለመምጣታቸው ወይም ቃል ለመቀበልም አለመሞከራቸው ግን ይገርምሻል? እ... No! አይ አይገርመኝም። ለምን? ጋዜጠኛ ነኝ። ጋዜጠኛ ነገሮችን ይጠይቃል፤ ያጣራል። ሶ እኔም ያደረኩት ያንን ነው። በዛ ሰዓት የደወልኩላቸው መረጃ ለመጠየቅ ነው። መረጃ ወስጃለሁ። መረጃ ያገኘሁትን ነገር አውጥቻለሁ ወይ ፅፌያለሁኝ። ያንን ማድረጌ ያስጠይቀኛል ብዬ አላስብም። ስጋትም አላደረብኝም። ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ከእርሳቸው ጋር በተያያዘ የሚፃፉ ነገሮችን ትከታተያለሽ? አልፎ አልፎ ይህንን ነገር ለማጥራት እጅሽ ላይ ያለውን ድምፅ ለመልቀቅ ጊዜው አይደለም ብለሽ እንድታስቢ ያደረገሽ ምንድን ነው? እ... አንደኛ ይህን ነገር ማጥራት የእኔ ኃላፊነት ነው ብዬ አላስብም። ይሄንን ኃላፊነት ያለው ክፍል አለ። በዛ ላይ አሁንም ደግሜ የምልህ ያለቀ ነገር አይመስለኝም። ምርመራ ላይ ያለ ነገር ነውና ምርመራ ላይ ያለ ነገር ላይ ጣልቃ ገብቶ እንደዚህ ነው እንደዛ ነው ማለት ትክክል አይመስለኝም፤ የሕግም ተጠያቂነት ያለበት ይመስለኛል።
news-42622642
https://www.bbc.com/amharic/news-42622642
አምስቱ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጎዳናዎች በ2018
ስህተት አልባ የመሬት ምዝገባ
በአፍሪካ አብዛኛውን ጊዜ ማስረጃዎች በአግባቡ ስለማይያዙ የመሬት ይዞታ ጉዳይ ሁሌም ያጋጫል።አሉ ተብለው የሚቀርቡ ማስረጃዎችም ብዙ ጊዜ የተሳሳቱ ሆነው ይገኛሉ።ነገር ግን የማይሰረዝና የማይሳሳት ማስረጃ ብሎክቼን በተሰኘ መንገድ ሊዘጋጅ ይችላል።ብሎክቼን መሬትን የሚመለከቱ መረጃዎች የሚደራጅበት ዲጂታል አሰራር ነው።ይህ በብሎክቼን የተደራጀ መረጃ ደግሞ በጥቂት ኮምፒውተሮች ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን በሺዎች ወደ ሚቆጠሩ ኮምፒውተሮች የሚላክ ነው።ከዚህ አሰራር ጋር ግንኙነት ያለው ኮምፒውተር ሁሉ በየጊዜው የተሻሻለ መረጃ ይደርሰዋል።ስለዚህ አሰራሩ ግልፅና ተአማኒነት ያለው ነው።ይህን ቴክኖሎጂ በሩዋንዳ ተግባራዊ የሚያደርገው ዋይዝኪ የተሰኘ የመረጃ መረብ ደህንነት ኩባንያ ነው።እንደ አውሮፓውያኑ 2017 ላይ የሩዋንዳ መንግስትን የብሎክቼን ተጠቃሚ ለማድረግ ከማይክሮሶፍት ጋር መፈራረሙን ዋይዝኪ አስታውቋል።የመጀመሪያው እርምጃ በሩዋንዳ የመሬት ምዝገባና ስነዳን ዲጅታላይዝ ማድረግ ነው።ኩባንያው በሩዋንዳ የብሎክቼን ማእከል ያቋቋመ ሲሆን በ2018 እንደ ቢትኮይን የሩዋንዳን ክሪፕቶከረንሲ(ምናባዊ የኢንተርኔት መገበያያ)ለመስራት እቅድ አለው። የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለአፍሪካ ማስተላለፍ አለም የሶፍትዌር ሰሪዎች እጥረት አለባት።በሌላ በኩል አፍሪካ ደግሞ በወጣት ህዝብ የተሞላች ነች።አሜሪካና አውሮፓ አፍሪካዊ ሶፍትዌር ሰሪዎችን ቢያሰለጥኑ በዚህ የሰው ሃይል ይጠቀማሉ።አንዲላ ሶፍትዌር ሰሪዎችን ናይጄሪያ ውስጥ አሰልጥኖ በአለም አቀፍ ድርጅቶች የሚያስቀጥር ኩባንያ ነው።በዚህ መልኩ አንዲላ እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት ያሰለጠናቸውን በማስቀጠር 40 ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል።በ2016 ደግሞ ከፌስቡኩ ማርክ ዙከርበርግ 24 ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል።በ2018 ደግሞ አንዲላ በግብፅም ማዕከል እንደሚከፍት ይጠበቃል። ማንኛውንም ክፍያ ቀላል ማድረግ በአፍሪካ ብዙ ሰዎች የባንክ ሂሳብ የላቸውም።በሌላ በኩል የሞባይል ክፍያ ስርአት ውጤታማ እንደሆነ ታይቷል።በጥናት እንደታየው አፍሪካ መቶ ሚሊዮን ሰዎች የሞባይል የገንዘብ ሂሳብ የከፈቱባት አህጉር በመሆን አለምን ከሚመሩ ተርታ ተሰልፋለች።በአሁኑ ወቅት የሞባይል የፋይናንስ አገልግሎት ብድርና ቁጠባን፣መድህንንና ሃዋላን ያካትታል።ችግሩ በዚህ መልኩ የሚሰሩ ስርአቶች በርካታ መሆናቸውና አንድላይ አለመስራታቸው ነው።ይህ ማለት ደግሞ አፍሪካ ውስጥ እቃዎችን በኢንተርኔት መግዛት አለመቻል ነው።ለምሳሌ ፍለተርዌቭ የተባለው ስርአት በመላ አፍሪካ ለባንኮችና ለሌሎች ኩባንያዎችም የሞባይል ክፍያ ስርአት ዝርጋታን እውን አድርጓል።በአውሮፓውያኑ 2017 የመጀበሪያው ሶስት ወር ውስጥ ፍለተርዌቭ 444 ሚሊዮን ዶላር በናይጄሪያ፣ጋናና ኬንያ አዘዋውሯል።ከመጀበሪያው ጀምሮ ኩባንያው በአስር ሚሊዮን ዝውውሮች 1.2 ቢሊዮን ዶላር አስተላልፏል።በዚያው ዓመት ኩባንያው ከአሜሪካ የአስር ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አግኝቷል።ይህ ድጋፍ ለኩባንያው ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለት የሚጠበቅ ሲሆን በአፍሪካ ሰዎች በኢንተርኔት በቀላሉ የፈለጉትን መግዛት የሚችሉበትን ስርዓት እንደሚዘረጋ ይጠበቃል። በድሮን መልዕክት ማድረስ አለም ላይ በድሮን አነስተኛ ነገሮችን ከቦታ ወደ ቦታ የማመላለስ አገልግሎት የመስጠት ከፍተኛ ፍላጎት አለ።በርግጥ በአቬሽን ህግ ምክንያት ይህ በአሜሪካና በአውሮፓ ተከልክሏል።በተወሰኑ የአፍሪካ አገራት ለምሳሌ በሩዋንዳ ሃሳቡ ተቀባይነት አግኝቷል።የገጠር መንገዶች ምቹ አለመሆንና የበረራዎች ሰፊ ቦታዎችን አለመሸፈን ለድሮን መልዕክት አገልግሎት አፍሪካን ምቹ ያደርጋታል።ዚፕላየን የተሰኘው ኩባንያ እንደ ደም፣ክትባትና ሌሎች መድሃኒቶችን አይነት ቀላል ነገሮችን የሚያደርሱ ድሮኖች አሉት።የአለም የመጀመሪያው የድሮኖች ወደብ የተከፈተው እንደ አውሮፓውያኑ በ2017 በሩዋንዳ ነበር።በወቅቱ ወደቡ በታንዛኒያም እንደሚከፈት ተገልፆ ነበር።በ2018 የታንዛኒያው ዶዶማ ድሮን ወደብ ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።በአብዛኛው የሚያመላልሰውም መድሃኒት ነክ ነገሮችን ይሆናል።ፎርብስ እንዳለው ይህ በአለም ትልቁ የድሮን መልዕክት ማድረስ ስርአት ይሆናል። ያለ ኤሌክትሪክ ሃይል ማሰራጫዎች መብራት እንዲኖር ማድረግ ፔግ አፍሪካ ከኤሌክትሪክ ማሰራጫዎች ሃይል ለማይደርሳቸው ሶላር ፓኔሎችን የሚሸጥ ድርጅት ነው።ሶላር ፓኔል መግዛት ለብዙዎች ውድ በመሆኑ ሰዎች በአነስተኛ የሞባይል ክፍያዎች ኤሌክትሪክ ሃይል ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታም ኩባንያው አመቻችቷል።በዚህ መልኩ እንደ አውሮፓውያኑ 2017 ላይ ፔግ 13.5 ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል።ፔግ አፍሪካ በጋናና በአይቮሪኮስት እየተስፋፋ ነው።
45298819
https://www.bbc.com/amharic/45298819
እነ አንዷለም አራጌ ህይወት እንደገና
"ልጄ ድምፄን ሲሰማ አለቀሰ"
የአንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲ መሪ የነበረው አቶ አንዱአለም አራጌ ካለፉት 12 ዓመታት ስምንት ተኩል የሚሆነውን ያሳለፈው በእስር ነው። የታሰረው ሁለት ጊዜ ሲሆን በሽብርተኝነት ተከሶ እንደ አውሮፓውያኑ 2011 ላይ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ከስድስት ዓመት በላይ በእስር አሳልፏል። በቅርቡ ከዓመታት እስር በኋላ ከተለቀቁ እስረኞች መካከል አንዱ የሆነው አንዱአለም ከተፈታ አምስት ወራት አልፎታል። ከዓመታት እስር በኋላ ህይወትን ፤ኑሮን ዳግም እንዴት ጀመርከው ስንል ጠይቀነው ነበር። •"እንደምፈታ ያወቅኩት ባለፈው መስከረም ነበር" አንዷለም አራጌ •እስክንድር ነጋና አንዷለም አራጌ በይቅርታ ሊፈቱ ነው ተባለ •"ህልም አለኝ":-በቀለ ገርባ ነገሮች በጣም ከባድ እንደነበሩ የሚናገረው አንዱአለም "ባልወደውም እስር ህይወቴ ሆኖ ነበር እና ከዚያ ህይወት ወደዚህ ስመጣ ነገሮች ፈታኝ ሆነውብኝ ነበር"ይላል። እንግዳ ስለሆነባቸው ልጆቹ ሊቀርቡት ተቸግረው ነበር።በመግለፅ አንድ የተለየ አጋጣሚን ያስታውሳል። "ተፈትቼ የመጀመሪያው እለት መብራት ጠፍቶ ነበር እና ልጄ ድምፄን ሌሊት ሲሰማ ልክ ሌባ እንደገባ አይነት ነገር ማነው እያለ አለቀሰ" በማለት ከልጆቹ ጋር መቀራረብ ተቸግሮ እንደነበር ይናገራል። •እስር በአዲስ አበባ እና በባህር ዳር ማህበራዊ ትስስሩ ከሰዎች ጋር መቀራረቡም ሌላ አስቸጋሪ የሆነበት ነገር ነው። ለአመታት ብቻውን መኖሩ አሁን በሰው መሃል መገኘት ፣ እንደ ካፍቴሪያ ያሉ ቦታዎች ላይ ብዙ ድምፆችን መስማት ምቾት እንዲነሳው አድርጓል። አንድ አካባቢ ላይ የብዙ ሰዎች መገኘትም ይረብሸዋል። "ሁሉም ነገር ለእኔ እንግዳ ስለሆነ የተንሳፈፍኩ ያህል ይሰማኛል። እውነቱን ለመናገር ገና መሬት አልረገጥኩም"ይላል አንዱዓለም። መንገድ ላይ መንቀሳቀስ ፣ ሻይ ቤቶች ውስጥ ከሰዎች ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መጫወት ይደሰትባቸው ነፃነት እንዲሰማው ያደርጉ የነበሩ ነገሮች ነበሩ። "እስር ቤት ሆኜ ሁሌም ይናፍቀኝና ከህይወቴ አጣሁት የምለው ጠዋት ከሶስት እስከ አራት ሰዓት ላይ ፀሃይ እየሞቅኩ አንድ ጥግ ላይ ሆነ እያሰብኩ ወይም ጋዜጣ እያነበብኩ ማኪያቶ መጠጣት ነበር" በማለት በትዝታ ወደ ኋላ ይመለሳል። የሚያዘወትረው አራት ኪሎና ከአራት ኪሎ መገናኛ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ ቤሊየር ተብሎ የሚጠራ አካባቢ ያለ ካፍቴሪያን ነበር። ዛሬ የቅርብ ወዳጆቼ የሚላቸው አገር ውስጥ ባይኖሩም አሁንም ከተወሰኑ ሰዎች ጋር ሻይ ቡና ቢልም አሁን መሄድ ስለማይፈልግ አራት ኪሎ ግን ትዝታው ሆና ቀርታለች። "አራት ኪሎ ስሄድ ድሮ የማውቃቸውን ሰዎች አላይም።ከዘመኑ ጋር ሰዎች አልፈዋል ቦታዎቹም ተቀያይረዋል።ያለ እነሱ ደግሞ ስሜት አይሰጥም ባይተዋርነትም ይሰማኛል"ይላል። ቀድሞም ለቴክኖሎጂ እምብዛም ነበርኩ ለሚለው አንዱዓለም እንግዳ የሆነበት ሌላው ነገር ሰዎች ከስልካቸው ጋር ያላቸው ቁርኝት ነው። ከዓመታት በፊት ቤትም ይሁን ካፍቴሪያ ውስጥ ሰብሰብ ተብሎ ማውራት መጫወትም ነበር። "የትም እንደ ድሮ ከቦ ማውካካት የለም።አንድ ላይ ተቀምጦም ሁሉም ከስልኩ ጋር ነው የሚያወራው።በዚህ የዘመኑን መፍጠን መለወጥ አይበታለው"ብሏል። "መግቢያ ስላልነበረኝ የ87 ዓመት እናቴ ቤት ነው የገባሁት" የአራት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ በሽብር ተፈርዶባት ከዘጠኝ ዓመታት እስር በኋላ የተፈታችው በቅርቡ ነው። ከእስር ስትለቀቅ የአዲስ አበባውን ቤቷን እንደነበር አላገነችውም። "መሳሪያ ደብቃለች ተብሎ ቤቴን አፍርሰውት ነው የጠበቁኝ"በማለት ቤቷ ፈርሶ ልጆቿም ስለተበተኑ ጎንደር የሚገኙት የ87 ዓመት ወላጅ እናቷ ቤት ልትገባ ግድ እንደሆነባት ትናገራለች። ከደረጀ ኑሮና ቤቷ ወጥታ በዚህ እድሜዋ የእናቷ ጥገኛ መሆን ከባድ እንደሆነ ነገር ግን እናቷ የእድሜ ባለፀጋ ሆነው መጠጊያ ስለሆኗት ፈጣሪዋን እንደምታመሰግን እማዋይሽ ትገልፃለች። አንዱ ልጇ እሷን እስር ቤት አጥር ውስጥ ማየትን መቋቋም ባለመቻሉ መሰደዱን ትናገራለች። "አንደኛዋ ልጄ ለዲፕሎማ እየተማረች ነበር።በትምህርቷ ትገፋለች ብዬ አምን የነበረ ቢሆንም ትምህርቷን አቋርጣ ወልዳ ነው ያገኘኋት። ስታሰር የ11 ዓመት የነበረች ልጄ ደግሞ በስደት ኬንያ ትገኛለች" በማለት ልጆቿ እንዴት እንተበተኑባት ትገልፃለች። በሽብር ስለተከሰሰች መጀመሪያ ላይ ኬሎች እስረኞች ጋር እንድትቀላቀል አይፈቀድላትም ነበር። ኋላ ግን እየሩሳሌም ተስፋው፣ቀለብ ስዩምና በሽብር ታስራ የነበረች ፈቲያ የምትባል ሙስሊም ጓደኞቿ እንደነበሩ ትናገራለች። "ከሪኦት አለሙ ጋር የነበረኝ ጓደኝነት ግን የተለየ ነበር።ሁሉን ተካፍለን ነበር የምንበላው" በማለት ታስታውሳለች። የቀድሞ የስራ ባልደረቦቿ ጓደኞቿም ከተፈታች በኋላ እንገናኝ የሚሏት ቢሆንም "በደከምኩበት የሞትኩበት በመሆኑ በብዛት የማገኘው የእስር ቤት ጓደኞቼን ነው" ትላለች። "የእስር ቤት ጓደኝነት ስሜት የሚነካ ነው" ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ በሽብር ተፈርዶበት ሰባት ዓመታትን በእስር አሳልፏል። ከተፈታ አምስት ወር የሆነው ውብሸት አብዛኛው እስረኛ በህክምና እጦትና በድብደባ የጤና ችግር እንደሚያጋጥመውና እሱም ከእስር ህመም ይዞ እንደወጣ ይናገራል። ብዙዎች ከእስር በመለቀቃቸው ተደስተው ሳይጨርሱ ከዘመድ ወዳጅ ጋር ሆነው ያላወጡት የእናት የአባት እንዲሁም የእህት የወንድም ሞት እርምን ለማውጣት አንብተዋል ልባቸውም ተሰብሯል። አባቱ የሞቱት በእስር ላይ እያለ በመሆኑ ውብሸትም በዚህ የሚሰብር ስሜት ውስጥ ሊያልፍ ግድ ሆኖበታል። "እኔ እድለኛ ስለሆንኩ ትዳሬ አልፈረሰም ሚስቴ ሸክሜን ተሸክማልኝ ኖራለች"የሚለው ውብሸት የሚያውቃቸው ብዙዎቸ ከስር ሲወጡ ትዳራቸው ፈርሶ ማግኘታቸውን ይናገራል። ወደ ኑሮ ለመመለስ ወይም አዲስ ነገር ለመጀመር አሲስ አለም አዲስ አገር ላይ ያሉ እስኪመስል ድረስ ነገሮች በጣም ፈታኝ እንደሆኑ "ሲስተም ውስጥ መግባት በጣም ከብዶኛል" በማለት ስሜቱን ይገልፃል። ከሁሉም በላይ ሲታሰር የሁለት አመት ከሰባት ወር ልጅ ከነበረውና አሁን 10 ዓመት ከሆነው ልጁ ጋር መቀራረብ ከብዶታል። "ልጄ በጥርጣሬ ነው የሚያየኝ"የሚለው ውብሸት እንደ አባት ሳይሆን እንደ እንግዳ እንደ ውጭ ሰው የገዛ ልጁን አባብሎ እንደሚቀርበው ይናገራል። እንደሚለው እስር ላይ እያለ ምንም እንኳ ባለቤቱ ልጁ እንዲያየው ቢያደርግም ልጁን መንካትም ሆነ ማቀፍ አይፈቀድለትም ነበር።ስለዚህም ባለፉት አመታት ሁሉ ልጁ አባቱን ከአጥር ጀርባ መመልከቱ ለዛሬው ስሜቱ ምክንያት ሆኗል። ብዙ ጓደኞቹ በመሰደዳቸው ከቀድሞ ጓደኞቹ የሚያገኛቸው ጥቂት ናቸው። የእስር ቤት ጓደኝነት ስሜት የሚነካና ጥልቅ እንደሆነ የሚናገረው ውብሸትበ በአሁኑ ወቅት አብረውት ታስረው ከነበሩ ጋር እንደሚገናኝ ይናገራል።
news-41325316
https://www.bbc.com/amharic/news-41325316
ለከባድ አውሎ ነፋሶች ማነው ስም የሚያወጣው?
ለምን ስም እንዲኖራቸው አስፈለገ ?
ስለከባድ አውሎ ነፋሶች ብዙ ጊዜ ዜና ላይ ይነገራል፤ ነገር ግን ለምን ስም እንደሚሰጣቸውና ስያሜው እንዴት እንደሚወሰን ጠይቀዉ ያውቃሉ? ለከባድ አውሎ ነፋሶች ስያሜ መስጠት ሰዎች የበለጠ እንዲያውቋቸውና የአደገኝነት መጠናቸውንም እንዲረዱት ያደርጋል በትሮፒካል አካባቢ የሚከሰቱ ሄሪኬን፣ ሳይክሎን ወይም ታይፉንን የመሳሰሉ ከባድ አውሎ ነፋሶች ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ በመሆናቸው ተመራማሪዎች ለሚያደርጉት ክትትል እንዲረዳ ስም ይሰጣቸዋል። ቀደም ሲል አውሎ ነፋሶቹ የተከሰቱበትን ዓመት መሰረት በማድረግ ይከታተሏቸው ነበር። ነገር ግን በአንዳንድ አካባቢዎች በዓመት ውስጥ 100 የሚደርሱ አውሎ ነፋሶች ሊከሰቱ ስለሚችሉ ስም መስጠቱ ለአጥኚዎቹ አንዱን ከአንዱ ለመለየት በጣም ቀላል አድርጎላቸዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የሚትዮሮሎጂ መሥሪያ ቤት እንደሚለው ለከባድ አውሎ ነፋሶች ስያሜ በመስጠት ሰዎች የበለጠ እንዲያውቋቸው ከማድረጉ በተጨማሪ የአደገኝነት መጠናቸውንም እንዲረዱት ያደርጋል። ማነው የአውሎ ነፋሶቹን ስም የሚወስነው? በቀጣይ ዓመት ሊከሰቱ ለሚችሉ አዳዲስ ከባድ አውሎ ነፋሶች ስያሜ ለመስጠት ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ የአየር ሁኔታ ሳይንቲስቶች መደበኛ ስብሰባዎችን ያካሂዳሉ። በርካታ ውድመትን ያስከተሉ የከባድ አውሎ ነፋሶች ስም ፈፅሞ በድጋሚ ለስያሜነት ጥቅም ላይ አይውሉም። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ሕዝቡ አማራጭ ስሞችን እንዲጠቁም በሚትዮሮሎጂ መሥሪያ ቤት በኩል ጥያቄ ይቀርባል። አውሎ ነፋሱ ስም እንዲያገኝ ምን ያህል ከባድ መሆን አለበት? ሁሉም አውሎ ነፋሶች ስም ለማግኘት የሚያስችል ጉልበት የላቸውም፤ ከባድ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱት ብቻ ናቸው ስያሜን የሚያገኙት። የትኛው የአውሎ ነፋስ ስያሜ በመጀመሪያ ይመረጣል? አውሎ ነፋሶች ስያሜን የሚያገኙት በእንግሊዝኛ ፊደላት ቅደም ተከተል ነው። ስለዚህም የዓመቱ የመጀመሪያዎቹ አውሎ ነፋሶች በ'ኤ' የሚጀምር ስያሜ ሲሰጣቸው፤ ሃሪኬን አሊስ ወይም ታይፉን አንድሩ ይባላሉ። ቀጣዮቹ ደግሞ በ'ቢ' የሚጀምር ስም ሲያገኙ ሌሎቹ በዚሁ መሰረት ቀጣዮቹን ፊደላት እየተጋሩ ይሄዳሉ። በእያንዳንዱ የእንግሊዝኛ ፊደላት የሚጀምሩ ስሞች ሲኖሩ 'ኪው'፣ ዩ፣ ኤክስ፣ ዋይ እና ዜድ ግን አልተካተቱም። ስያሜው የሴት ወይም የወንድ ስም እንዲሆን ማነው የሚወስነው? አውሎ ነፋሶች የሴት ወይም የወንድ ስም በየተራ እየተፈራረቀ ይሰጣቸዋል። ለአውሎ ነፋሶች መጀመሪያ ላይ የሴት ስም ብቻ ነበር የሚሰጣቸው። የወንድ ስም መስጠት የተጀመረው ከ1979 (እአአ) ጀምሮ ነው።
news-46444359
https://www.bbc.com/amharic/news-46444359
ኤርትራዊያን በጋዜጠኛ ማርቲን ፕላውት ጉዳይ ለምን ይቋሰላሉ?
ማርቲን ፕላውት ጋዜጠኛ ነው።
ደቡብ አፍሪካ የተወለደ እንግሊዛዊ ይሁን እንጂ በሚያነሳው ርዕሰ ጉዳይ ለኤርትራዊያን ይቀርባል። ሁልጊዜም ታዲያ በኤርትራዊያን ፖለቲካ ውስጥ የውዝግብ ምንጭ እንደሆነ አለ። ጀግናችን የሚሉት እንዳሉ ሁሉ ደመኛችን የሚሉትም ጥቂት አይደሉም። ከነዚህ 'ጥቂት አይደሉም' ከሚባሉት ውስጥ ያዕቆብ ገብረመድኅን ይገኝበታል። ባለፈው ዓርብ 8፡00 ሰዓት ስለሆነው ነገር ማርቲን ለቢቢሲ ሲያስረዳ እንዲህ የይላል "ያዕቆብ ነኝ ከሚል ሰው ጥሪ ደረሰኝ፤ ከኤርትራ የወጡ ጠቃሚ መረጃዎች አሉ፣ ላቀብልህ አለኝ። መረጃዎቹ ይጠቅሙኛል ብዬ ስላሰብኩ ቀጠሮ አደረግን። ብሪቲሽ ላይብረሪ እንድንገናኝ ተነጋገርን። መልሶ ደወለና ከላይብረሪው ውጭ ብንገናኝ ይሻላል አለኝ። ከአቅራቢያ ባለች ካፌ ተገናኘን። ቡና አዘዘ። ትንሽ ቆይቶ ተነሳና በቅርብ ርቀት አስቀምጦት የነበረን አንድ ባልዲ አንስቶ እላዬ ላይ ደፋብኝ..." ማርቲን ለቢቢሲ ጨምሮ እንዳስረዳው ጥቃት አድራሹ ኤርትራዊ ድርጊቱን በሚፈጽምበት ወቅት "አንተ ከሃዲ፣ በእንግሊዝና በአሜሪካ የተገዛህ! የኤርትራ ጠላት..." እያለ ይጮኸ ነበር። ይህ ኤርትራዊ ወጣት ለዚህ ድርጊት ምን አነሳሳው? አቅዶ፤ እንቁላል በወተት ሊጥ አቡኪቶ፣ በባልዲ ጭኖ እንዲህ ዓይነት ድርጊት ለመፈጸም ያበቃው ቁጣ ከየት መጣ? የማርቲንና የኤርትራ ዕውቂያ ማርቲን ፕላውት አምስት መጻሕፍትን አበርክቷል። ከእነዚህ ውስጥ ምዕራቡ ዓለም "የአፍሪካ ሰሜን ኮሪያ" ስለሚላት ኤርትራ የጻፈው 'Understanding Eritrea' ይጠቀሳል። በምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይና የኮመንዌልዝ ቢሮ አማካሪም ነበር። ለግዙፍ መገናኛ ብዙኃን በደቡብና በምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ጉዳዮች እንደ ተቀዳሚ ተንታኝ የሚታየው ማርቲን ከኤርትራ ጋር ያለው ዕውቂያ ሩብ ክፍለ ዘመንን የሚሻገር ነው። እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ በ1984 ለቢቢሲ ይዘግብ ነበር። ከዚያ በፊት ግን በብሪታኒያ ሌበር ፓርቲ ውስጥ የአፍሪካ ተመራማሪና ጸሐፊ ኾኖ አገልግሏል። ከኤርትራና ከኤርትራዊያን ጋር ያስተዋወቀውም ያ ዘመን ነው። • የአንስታይን ደብዳቤ በ84 ሚሊዮን ብር በፈረንጅ በ70ዎቹ መጨረሻና በ80ዎቹ መባቻ ሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ቅልጥ ያለ ትግል ላይ ነበር። ያን ጊዜ የግንባሩ የአውሮፓ ተወካይ ኤርሚያስ ደበሳይ (ፓፓዮ) ማርቲንን አፈላልጎ ያገኘዋል። ማግኘት ብቻም ሳይሆን የኤርትራ በረሃን እንዲጎበኝ ይጋብዘዋል። የሌበር ፓርቲው ማርቲን ፈራ ተባ እያለ ግብዣውን ተቀበለ። በሱዳን በኩል አሳብሮ ኤርትራ ገባ፤ ሻዕቢያ በረሃ ይዞት ወረደ። በረሃ ብዙ ተመለከተ። የመጀመርያውን የኤርትራ የሴቶችና የሠራተኞች ጉባኤን ጭምር ሌበር ፓርቲን በመወከል ተሳተፈ። ከ1984 ወዲህ ለቢቢሲ መሥራት የጀመረው ማርቲን ኤርትራን በድጋሚ የመጎብኘት ዕድሎች አጋጥመውታል። ነጻ የወጡ የሻዕቢያ የሚቆጣጠራቸውን ግዛቶችን ቃኝቷል። የከረን ምሽጎችን ተሽሎክሉኮባቸዋል። ኤርትራ ቤቱ ሆነች። ያኔ በዚያ ዘመን ታዲያ ማርቲን ከሻዕቢያ የላዕላይ አመራር ጋር የቅርብ ወዳጅነት እንደፈጠረ ይገመታል። እሱም ቢሆን በቆይታዬ "በርካታ ወዳጆችን አፍርቻለሁ' ይላል። ፓፓዮና ማርቲን በትግል ስሙ ፓፓዮ (ኤርሚያስ ደበሳይ) ከሕዝባዊ ኤርትራ ሓርነት ግንባር ጎምቱ አመራሮች አንዱ ነበር። በትግሉ ወቅት የግንባሩ የአውሮፓ ተወካይ ሆኖ ሠርቷል። ከትግሉ በኋላም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና በድኅረ ነጻነት ኤርትራ በመወከል በኡጋንዳና በቻይና አምባሳደር በመሆን ለአጭር ጊዜ አገልግሏል። ፓፓዮ ከዕለታት በአንዱ ቀን ወደ አገረ ኤርትራ ተጠራ። ታሰሮ ለአጭር ጊዜ ከእስር ተፈታ። በድጋሚ ከእህቱ ከሰናይት ደበሳይ ጋር ወደ እስር ቤት ተወረወረ። ከዚያ ወዲያ አልተመለሰም። ይሙት ይኑር አይታወቅም። ፓፓዮ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የቅርብ ወዳጅና ምስጢረኛ እንደነበረ በስፋት ይነገራል። ማርቲን ፕላውት ታዲያ የዚህ ኤርትራዊ ወዳጁ ለሁለት ዐሥርታት መታሰር በኤርትራ ጉዳይ ዝም እንዳይል ጉልበት ሳይሰጠው አልቀረም። 'ከአርብ ዕለቱ ጥቃት ወዲህ የኤርትራን ጉዳይ ታነሳለህ ወይ?' ተብሎ ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ፣ "... ፓፓዮ እስኪፈታ፣ የኤርትራ ሕዝብ የሚናፍቀውን ነጻነቱን እስኪቀዳጅ ድረስ በፍጹም ዝም አልልም" ሲል መልሷል። • የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ፊታቸውን ወደ ሶማሊያ አዞሩ ጥቃት አድራሹ ማን ነው? ያዕቆብ ድርጊቱን ሲፈጽም የሚያሳየው የተንቀሳቃሽ ምስል ባለፉት ቀናት በከፍተኛ ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያ ተዛምቷል። ፖለቲካ ግድ የሚላቸው ኤርትራዊያንም እንደተለመደው በሁለት ጎራ ተሰልፈው ሲቆራቆሱ ታይተዋል። አበጀህ ያሉትን ያህል ዐይንህን ላፈር የሚሉትም በርካታ ናቸው። ያዕቆብ ለዚህ ጥቃት ምን እንዳነሳሳው ለማወቅ ቢቢሲ እርሱን አግኝቶ ለማናገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ኾኖም ማርቲን በትዊተር ገጹ በኔዘርላንድስ የኤርትራ ኤምባሲ በጉዳዩ እጁ እንዳለበት የሚጠቁም መረጃ መስማቱን ጠቁሟል። በኤርትራ ጉዳዮች ሐሰተኛ ዜናዎችን ያሰራጫል የሚል ተደጋጋሚ ክስ የሚቀርብበት ማርቲን "በመጀመሪያ ደረጃ ይህን ክስ የሚያቀርቡት የትኞቹ ኤርትራዊያን ናቸው?" ሲል ጥያቄውን በጥያቄ ይመልሳል። የሆነስ ሆኖ ዲሞክራሲ ባለባት እንግሊዝ ጥገኝነት የጠየቀ አንድ ኤርትራዊ ይህንን ጥቃት በአገሬው ዜጋ፣ ለያውም በጋዜጠኛ ላይ ማድረሱ ምን ስሜት ሰጥቶት ይሆን? "እኔ ጋዜጠኛ ነኝ፣ ሰው ነኝ፤ ልሳሳት እችላለሁ፤ በቻልኩት አቅም ሁሉ ግን መረጃን አቀርባለሁ። ሰዎች እኔ በማቀርበው መረጃ ላይስማሙ ይችላሉ፤ የመተቸት መብት አላቸው። ጥቃት የማድረስ መብት ግን የላቸውም" ይላል ማርቲን። ጥቃት አድራሹ ወጣት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ በዋስ ተለቋል። በዚህ የፈረንጆች ወር መጨረሻ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብም ይጠበቃል። • በዩቲዩብ 22 ሚሊዮን ዶላር የሚያገኘው የሰባት ዓመቱ ህፃን
news-42490536
https://www.bbc.com/amharic/news-42490536
2017: ያልተጠበቁ ቁጥሮች የተመዘገቡበት ዓመት
37,993
ባለፉት 12 ወራት ማለት ከፈረንጆቹ 2017 መባቻ እስከ መገባደጃው በርካታ ክስተቶች ዓለምን ጎብኝተዋል። እነሆ ከበርካታ ክስተቶች በጥቂቱ ከቁጥሮች ጋር እንመልከት . . . ከጥር እስከ ጥቅምት ባለው ጊዜ በአሜሪካ የሚመራው ጥምር ኃይል ኢራቅ እና ሶሪያ ላይ የጣላቸው ቦምቦችና ሚሳዔሎች ብዛት። ሩስያም በርካታ የጦር መሣሪያ በተጠቀሱት ቦታዎች ብታዘንብም ቅሉ ቁጥሩ ይፋ አልተደረገም። ዋሽንግተን እና ሞስኮ በጥቃቱ የተጎዱ የሰላማዊ ዜጎች ቁጥር ብለው ካሳወቁት በላቀ ደረጃ ሰው ተጎድቷል ቢባልም ተልዕኮው አይ ኤስን ከሞላ ጎደል ከኢራቅና ሶሪያ አስወጥቷል። 127 የተጠቀሰውን ቁጥር ያህል ንቁ እሣተ ገሞራ በኢንዶኔዥያ ይገኛል። ይህም ሃገሪቱን በዓለማችን በርካታ የእሣተ ገሞራዎች ያሉባት ሃገር ያደርጋታል። ወርሃ ኅዳር ላይ ከእሣተ ገሞራዎቹ አንዱ ፈንድቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል። 1.7 ሚሊዮን በአሜሪካው የፊልም ዓለም 'ሆሊውድ' እየተከናወነ ያለውን ፆታዊ ጥቃት በመቃወም '#me too' የተሰኘውን ቃል በመጠቀም የማህበራዊ ሚድያ ዘመቻውን የተቀላቀሉ ሰዎች ቁጥር። በሃገራችን ኢትዮጵያም '#እኔም' በሚል መሪ ቃል በርካቶች ፆታዊ ጥቃትን ሲያወግዙ ተስተውለዋል። ቢያንስ በ85 ሃገራት የሚገኙ ሴቶች በማህበራዊ ሚድያው ዘመቻ መሳተፋቸው ተነግሯል። ዜሮ በሰላም ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዋ የበርማ መሪ ኦንግ ሳን ሱ ኪ በምያንማር ያሉ የሮሂንጃ ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ያወገዙበት ክስተት። ምንም እንኳ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መሪዋ በሃገራቸው እየተከናወነ ያለውን ድርጊት እንዲያወግዙ ተፅዕኖ ቢያሳድርባቸውም፤ ሳን ሱ ኪ ይህን ሊያደርጉ አልቻሉም። ይልቁንም ሁኔታውን "ሐሰተኛ ዜና" ሲሉ አጣጥለውታል። የዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ ኃኪሞች ማህበር በ2017 ብቻ 6 ሺህ የሚሆኑ የሮሂንጃ ሙስሊሞች መገደላቸውን ዘግቧል። 812 የእግር ኳስ ሜዳዎች በፈረንጆቹ 2017 ሐምሌ ወር ላይ ከአንታርክቲክ ላይ የተደረመሰው የበረዶ ግግር። የበረዶ ግግሩ በእግር ኳስ ሜዳ ቢታሰብ 12 የዓለም ዋንጫዎችን በአንድ ጊዜ ማጫወት የሚችል ስፋት ያለው ነው። ሳይንቲስቶች ክስተቱ እየጨመረ ካለው የዓለም ሙቀት መጠን ጋር ተያያዥነት እንዳለው ይናገራሉ። 44 ጊዜ በየቀኑ ከህንዷ ኒው ደልሂ የሚወጣው ጭስን መተንፈስ በቀን 44 ሲጋራ ከማጨስ ጋር እኩል ነው ሲሉ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በዓለም ካሉ 20 በጣም የተበከሉ ከተሞች መካከል አስሩ በህንድ ይገኛሉ። 60 ሚሊዮን የኦሎምፒክ መዋኛ ገንዳ ሃሪኬን ሃርቪይ የተሰኘው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ 150 ትሪሊዮን ሊትር የሚለካ ውሃ በአሜሪካ ላይ ጥሏል። በነሐሴ ወር በሂዩስተን ቴክሳስ የጣለው ዝናብ ልኬት ከ60 ሚሊዮን የኦሎምፒክ መዋኛ ገንዳዎች ውሃ ጋር እኩል ነው። አንደ የኦሎምፒክ መዋኛ ገንዳ 50 ሜትር ርዝማኔና 25 ሜትር ስፋት ሲኖረው ጥልቀቱ 2 ሜትር ይለካል።
news-48049276
https://www.bbc.com/amharic/news-48049276
ዓለም አቀፍ የወባ ቀን፡ ወባ ምንድን ነው? እንዴትስ እናስቁመው?
ወባን እንዴት እናስቁመው?
ወባ የሚተላለፈው በታመሙ ቢምቢዎች ነው ወባን መከላከል ቀላል ሆኖ ቢታይም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለ በሽታ ነው። የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት ወባ በየሁለት ደቂቃዎች አንድ ሕፃን ሲገድል በየዓመቱ ከ200 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በወባ እንደሚያዙ ያሳያል። ባለፉት አሥርት ዓመታት ውስጥ ለውጦች ቢመዘገቡም እ.አ.አ ከ2015 ወዲህ ግን ወደፊትም ወደ ኋላም እየሄድን አይደለም ይላል ያለፈው ዓመት የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት። ቁጥሩ ባለፉት ሦስት ዓመታት ምንም ዓይነት ለውጥ እንዳላሳየ ሪፖርቱ ያመለክታል። ወባን መከላከል እና ማዳን ቀላል ነው ዛሬ ዓለም አቀፍ የወባ ቀን ነው። ስለ ወባ ምን ማወቅ አለብዎት? ምልክቶች ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ የሚል ስሜት እና እራስ ምታት የወባ ምልክቶች ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ የሚል ስሜት እና እራስ ምታት ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ በቢምቢ ከተነከሱ ከ10 እስከ 15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ነው ምልክቶቹ የሚታዩት። ምልክቶቹን ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም በታዩ በ24 ሰዓታት ውስጥ ካልታከመ ፕላስሞድየም ፋልሲፓረም የተሰኘው ፓራሳይት ወደ ከባድ፣ የማይታከምና ለሞት የሚዳርግ በሽታ የመሸጋገሩ ዕድል ሰፊ ነው። ማንን ሊያጠቃ ይችላል? የታመመች ሕፃን እ.አ.አ በ2017 የዓለም ግማሽ ያህል ነዋሪዎች በወባ ተይዘው ነበር። ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት ተጠቂ የመሆናቸው ዕድል በጣም ሰፊ ነው። በፈረንጆቹ 2017 ብቻ በዓለም 61% ወይም 266 000 ሕፃናት በወባ ሞተዋል። እርጉዝ ሴቶች እና የተፈጥሮዓዊ መከላከያቸው የተዳከመ ሰዎችም በወባ የመያዝ ዕድለቸው ከፍተኛ ነው። ወባ በየት አካባቢዎች ይበዛል? ከምድር ወገብ በታች ያሉ ሃገራትና በተለይ አፍሪካ ተጋላጭ ናቸው ብዙውን ጊዜ ከሳሐራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት ተጋላጭ እንደሆኑ ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት ይገልፃል። በተጨማሪ ደቡብ ምሥራቅ እስያ፣ ምሥራቅ ሜዲትራኒያዊ፣ ምዕራብ ፓስፊክ ውስጥ እና በአሜሪካዎቹ ያሉ ሰዎች ተጋላጭ መሆናቸውንም ይገልፃል። እ.አ.አ በ2017 ከተመዘገቡት በወባ ከተጠቁ ሰዎች መካከል ግማሹን ያስመዘገቡት አመስት ሃገራት ብቻ ነበሩ። እነርሱም ናይጄሪያ (25%)፣ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ (11%)፣ ሞዛምቢክ (5%)፣ ሕንድ (4%) እና ዩጋንዳ (4%) ናቸው። እንዴት ይተላለፋል? ፓራሳይቱን ተሸካሚ የሆነች አስተላለፊ ቢምቢ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎችን ማላሪያ የሚይዛቸው ፓራሳይት ተሸካሚና አስተላላፊ በሆነች ሴት አኖፌሌስ በተሰኘች ቢምቢ ሲነከሱ ነው። የአኖፌሌስ ቢምቢ ብቻ ከ400 ዘር በላይ ሲሆን ከእነሱ መካከል 30ዎቹ ብቻ ናቸው ወባ የሚያስተላልፉት። ሁሉም የማላሪያ ተሸካሚና አስተላላፊ የሆኑ ቢምቢዎች ሌሊቱ ሊነጋጋ ሲል የሚናከሱ ናቸው። አኖፌሌስ የተሰኙት ቢምቢዎች እንቁላሎቻቸውን በውሃ ላይ የሚወልዱ ሲሆኑ፤ እንቁላሎቹ ወደ እጭ ተቀይረው ሰብረው ሲወጡ ሙሉ በሙሉ ያደገ ቢምቢ ሆነው ይወጣሉ። ወላጅ ቢምቢዎች እንቁላሎቻቸውን ለማሳደግ ደም ይመግቧቸዋል ማለት። መከላከያ ብዙዎች የወባ መድሃኒት በተረጩ አጎበሮች መትረፍ ችለዋል ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት መድሃኒት በተረጩ አጎበሮች ሥር መተኛት ከቢምቢዎቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ስለሚቀንስ በጣም ውጤማ መሆኑን ይናገራል። ከአጎበሩ በተጫመሪ ደግሞ የመኖሪያ ስፍራዎችን መድሃኒት መርጨትም ጠቃሚና አንደኛው የመከላከያ መንገድ መሆኑን ይናገራል። በተለያየ ጊዜ መድሃኒቱን ከመርጨት ባሻገር ለሚጓዙ ሰዎች የሚዋጡ መድሃኒቶችን መውሰዱም በጣም ጠቃሚ የሆነ የወባ መከላከያ መንገድ እንደሆነ ይገለፃል። ሕክምናው በሽታውን ቶሎ መለየትና መታከም ጠቃሚ ነው ጥርጣሬ ካለ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ በግማሽ ሰዓት ውስጥ ውጤቱን ማወቅ እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ። አንድአንድ የሕክምና ማዕከላት ደግሞ ተገቢው መሣሪያ ካላቸው ከዚያም በታች እንደሚወስድባቸው ይናገራሉ። በሽታውን በፍጥነት ለይቶ ማወቁ ወባው ከፍ ወዳለ ደረጃ ወይም ሞትን ወደ ማስከተል ሳይደርስ መከላከል ይቻላል። ፕላስሞድየም ፋልሲፓረም ለተሰኘው ፓራሳይት አርቴሚሲኒን ያለው መድሃኒት ጥሩ መሆኑንም ይገልፃሉ። መድሃኒት ተቋቋሚ ፓራሳይቶች ማላሪያ የያዘ ደም ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት አኖፌሌስ የተሰኘው ቢምቢ የተባዮች መከላከያ መድሃኒቶችን ከመለማመዳቸው የተነሳ እየጠነከሩ መምጣታቸውን አስጠንቅቋል። ይህ ደግሞ ወባን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት እያኮላሸ መሆኑን አስታውቋል። በቅርብ ጊዜ የወጣ ሪፖርት በ68 የተለያዩ ሃገራት ያሉ ቢምቢዎች በተለምዶ አገልግሎት ላይ ይውሉ የነበሩ አምስት መድሃኒቶች ተላምደው እንደማይሞቱ ይነግራል። ከዚያም በተጨማሪ ፀረ-ወባ የሆኑ መድሃኒቶችም በልምምድ ምክንያት ሃይላቸው እየቀነሰ ነው። ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት ወባን ለመከላከልና ለማዳን ያላቸው አቅም ሰፊ በመሆኑ መድሃኒቶች ላይ ብዙ ሥራ መሠራት አለበት ይላል። የመድሃኒቱ መዳከም እንደታወቀ ጥናት ቢደረግ በፍጥነት ሌላ ውጤት የሚያመጣ ሊሠራ እንደሚችል ይናገራል።
news-57278888
https://www.bbc.com/amharic/news-57278888
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 'የተወለደው' በቻይና ቤተ ሙከራ ውስጥ በተፈጠረ ስህተት ይሆን?
እነሆ ዓመት ተኩል!
ዉሃን ውስጥ የሚገኘው የቫይረሶች ምርምር ተቋም ኮቪድ ዓለምን ካመሰቃቀለ ዓመት ከመንፈቅ ነው። ጊዜው እንዴት ይነጉዳል? በሰውና በተህዋሲው መካከል ጦርነቱ አሁንም ቀጥሏል። ኮቪድ-19 እየረታም እየተረታም ይገኛል። እስከ አሁን በጦርነቱ ከ3 ሚሊዮን በላይ ሙት፣ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ደግሞ ቁስለኛ አድርጓል። አንድ በዓይን የማይታይ ተህዋሲ፣ ከሰማይ ይዝነብ ከምድር ይፍለቅ የማይታወቅ፣ እዚህ ግባ የማይባል ደቃቃ ተህዋሲ የሰው ልጆችን እንዲህ ልክ ያስገባል ያለ ማን ነበር? የሆነስ ሆነና፣ ተህዋሲው ከየት መጣ? ይህ ቁልፍ ጥያቄ እስከዛሬም እየተጠየቀ ነው። እስከዛሬም እየተመለሰ ነው። ነገር ግን አልተቋጨም። ምናልባትም አይቋጭም። ተህዋሲው ቢረታ እንኳ ወደፊት የሚጻፍለት የሕይወት ታሪክ በዚህ ዐረፍተ ነገር ሊጀምር ይችላል። "ኮቪድ-19 በቻይና አገር፣ በሁቤይ አውራጃ፣ በዉሃን ከተማ ተወለደ…። ዕድሜው የሰውን ልጅ ለመጨረስ እንደደረሰ…።" በእርግጥ በዉሃን ከተማ ተወልዷል። ግን የት ቤት ውስጥ ተወለደ? እንደሚባለው 'ሁውናን' በሚባለው የባሕር እንሰሳት ጉሊት [ዓሣ ተራ] ነው የተወለደው? ማንስ አዋለደው? ከሰሞኑ አዲስ መላ ምት ጠንክሯል። ከዓሣ ተራ ሳይሆን ከቤተ ሙከራ ነው ኮቪድ-19 ያፈተለከው የሚለው መላ ምት ድጋሚ እያነጋገረ ነው። ይህ መላምት እንዴት የባይደንን ትኩረት ዘግይቶ ሊስብ ቻለ? የዚህ ጽሑፍ ነገረ-ብልት ይኸው ነው። መላ ምቱ ምን ይላል? የኮቪድ-19 ተህዋሲ በድንገት ከቻይና የቫይረሶች ጥናት ተቋም አፈትልኳል ይላል መላምቱ። ለምን ሲባል፣ ምናልባት ቻይና ሆን ብላ ዓለምን ለመቆጣጠር ያደረገችው ይሆን? ምናልባት የባዮሎጂካል መሣሪያ ፈጥራ ምድርን ልታሸብር አቅሙ እንዳላት ማሳያ ይሆን? ምናልባት ምዕራቡ ዓለም ምን ያህል ሰው ሠራሽ ተህዋሲዎችን ሊመክት ይችላል የሚለውን ልትለካበት ይሆን? እነዚህ መላ ምቶች ስሜት ይሰጣሉ? ለአንዳንዶች አዎ! ለምሳሌ ቻይና ከአሜሪካ ጋር ባላት ሁሉን አቀፍ ባላንጣነት አዲሱ የውጊያ ግንባር በባዮሎጂካል ሳይንስ ልትከፍት አስባ ሊሆን ይችላል። በቤተ ሙከራ ተህዋሲዎች የሚመረቱትም ለዚሁ ተግባር ሊሆን ይችላል። ኮቪድ-19 አፈትልኮ ወጥቶበታል የተባለው የምርምር ማዕከል ሁለተኛው የመላምቱ ማጠናከሪያ በቻይና ሁቤት አውራጃ፣ ዉሃን ከተማ የባሕር እንሰሳት ገበያ አካባቢ የቫይረሶች ምርምር ቤተ ሙከራ መኖሩ ነው። ይህ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል? ምናልባት! ሦስተኛው የመላምቱ ማጠናከሪያ ቻይና የተህዋሲው ምንጭ ሆና ተህዋሲውን የተቆጣጠረችበት ፍጥነት የሚታመን ባለመሆኑ ነው። የተቀረው ዓለም ሥርጭቱን ለመቆጣጠር አሁንም እየተንደፋደፈ ነው። ቻይና ግን ገና ሳይቃጠል በቅጠል ብላ ነው ጸጥ ያሰኘችው። ቻይና ያላት፣ ሌላው የሌለው ጥበብ ምንድነው? ምናልባት አምጣ የወለደችውን ተህዋሲ ባሕሪ አሳምራ በማወቋ ይሆን? ሌሎች ደግሞ ቻይና ተህዋሲውን ሆን ብላ አሠራጭታው ላይሆን ይችላል ይላሉ። ሆኖም በቤተ ሙከራ ተመርቶ በአጋጣሚ አፈትልኮ በቅርብ ኪሎ ሜትር የሚገኘውን የባሕር ምግቦች ጉሊት በክሎስ ቢሆን? ሌሎች ግግሞ ተህዋሲው በቤተ ሙከራ ምሕንድስና የተዋለደ ሳይሆን ለምርምር ከባሕር እንሰሳት ወደ ቤተ ሙከራ ተወስዶ ከዚያ አፈትልኮ የወጣ ነው ይላሉ። እነዚህ መላምቶች ተህዋሲው ዓለምን ማሸበር በጀመረ ሰሞን እየተናፈሱ መጥተው በኋላ ላይ ዶናልድ ትራምፕ እያጠናከሯቸው የመጡ ግምቶች ናቸው። ኃያላን ወደፊት እግረኛ ጦር የሚልኩበት ጦርነት ላይኖር ይችላል። ኃያላን 3ኛውን የዓለም ጦርነት ከጀመሩ ውጊያው የሚሆነው ወይ በኮምፒውተር ቫይረስ ነው ወይ ደግሞ በባዮሎጂካል ቫይረስ ነው። ይህ መላምት ሲጠናከር አገራት በቤተ ሙከራ ውስጥ ተደብቀው የሚቀጥለውን እጅግ ከባዱን የጦር መሣሪያቸውን እየፈበረኩ ይሆናል የሚል ነው። የዚህ ድብብቆሽ የጦር መሣሪያ ውድድር አንዱ መገለጫ ደግሞ ይህ አፈተለከ የተባለው ተህዋሲ ቢሆንስ? ከዚህ ወዲያ የሚታጠቁት ቦምብ፣ የሚሸከሙት ምንሽር መቼስ አይኖር። የመሣሪያዎች ረቂቅነት ልቆ በዓይን ወደማይታይ ተህዋሲ መውረዱ አይቀርም። ብዙ የሳይንስ አዋቂዎችና የሚዲያ ተንታኞች እንዲህ ያሉ መላምቶችን ከቁብ ባይቆጥሯቸውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ነገሩ "አይሆንም አይባልም" እየተባለ ነው። ለምን? ፕሬዝዳንት ባይደን ስለቫይረሱ መነሻ በሦስት ወር ሪፖርት እንዲቀርብ ጠይቀዋል የባይደን ጥርጣሬ? ከሰሞኑ የአሜሪካ ሚዲያ ጉዳዩን ነክሶ ይዞታል። ይህ ተህዋሲ ከቤተ ሙከራ ያፈተለከ ነው የሚሉ ሐሳቦች እየተብላሉ ነው። ይህን ቸል ተብሎ የነበረ መላምት እንደ አዲስ የቀሰቀሱት ደግሞ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ናቸው። ለሳይንቲስቶቹ መነሻ የሆነው ደግሞ በምስጢር ተይዞ የነበረ አንድ የአሜሪካ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ሰነድ ነው። ሰነዱ ምን ይዟል? በዉሃን ቤተ ሙከራ ውስጥ በኅዳር ወር 2019 አካባቢ ሦስት የቤተ ሙከራው ተመራማሪዎች አመም አድርጓቸው ሆስፒታል ሲታከሙ ነበር። ይህ የጊዜ ስሌት ወዴት ይወስደናል? ጊዜውን ተህዋሲው ከባሕር እንሰሳት ጉሊት ተነሳ ከተባለለት ጊዜ ጋር ስናገጣጥመው ተመራማሪዎቹ ታመው የታከሙት ከዚያ ትንሽ ቀደም ብሎ እንደሆነ እንረዳለን። ይህም መረጃ ነው ሳይንቲስቶቹን ምናልባት ተህዋሲው ከጉሊት ሳይሆን ከቤተ ሙከራ የወጣ ነው እንዲሉ ያስቻላቸው። ይህን መላምት ተመሥርቶም ትራምፕ አንድ ምርመራ እንዲጀመር አዘው ነበር፣ ያኔ። ባይደን ሲመጡ ምርመራው ቆመ። ዝነኛው የተላላፊ በሽታዎች ሐኪምና አሁን የጆ ባይደን የጤና ጉዳዮች ልዩ አማካሪ ዶ/ር አንቶኒዮ ፋውቺ ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴዎች ሲናገሩ "ይህ መላምት ውሃ የማይቋጥር የሚባል አይደለም፤ ምርመራው መቀጠል አለበት" ብለው ነበር። የእሳቸውን ንግግር ተከትሎ ምርመራው ቢቀጥልም ውጤቱ እስከዛሬ ይፋ ሳይደረግ ቆይቷል። ባይደን አሁን የዚህ ምርመራ ውጤት በአስቸኳይ ይቅረብልኝ፣ ምርመራውም ተጠናክሮ ይቀጥል እያሉ ነው። በዚህን ጊዜ ዶናልድ ትራምፕ ደስ አላቸው። ለኒውዮርክ ፖስት ጋዜጣም "ነግሪያችሁ ነበር እኮ…" የሚል ደብዳቤ ጻፉ። "ገና ድሮ ተናግሬ ነበር። እኔ ገና ነገሩ ሲጠነሰስ ጀምሮ አውቄዋለሁ። ሰው ሁሉ ግን ወረደብኝ፤ አብጠለጠለኝ፤ አሁን ሁሉም ሰው 'ለካንስ ትራምፕ እውነቱን ነበር' እያለኝ ነው" ሲሉ ማስታወሻ ቢጤ ለጋዜጣው ከትበዋል። በዉሃን የሚገኘው የባሕር ምግቦች መሸጫ ገበያ ሳይንቲስቶች ምን አሉ? ሳይንቲስቶች ብዙ እያሉ ነው። ነገሩ በእነርሱ መካከልም ትልቅ መነጋገርያ ሆኗል። የዓለም ጤና ድርጅት ምርመራ ነገሩን ሁሉ ያጠራዋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ነገር ግን ድርጅቱ የላከው ቡድን ከብዙ መልስ ይልቅ ብዙ ጥያቄ ይዞ ነው የተመለሰው። ቡድኑ 12 ቀናትን በዉሃን ከተማ ካሳለፈ በኋላ "ከቤተ ሙከራ ተህዋሲው አፈተለከ ለማለት የሚያስችል ጠንካራ ነገር አላገኘሁም" ብሏል። ነገር ግን ብዙዎች የቡድኑን አጠራጣሪ ድምዳሜ ተጠራጥረውታል። ቡድኑ ኮቪድ-19 ከቤተ ሙከራ አምልጦ ይሆናል የሚለውን መላምት በቁም ነገር ወስዶ ምርመራ አላደረገም እየተባለ ይተቻል። ራሳቸው የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ሳይቀሩ ሁሉም መላምቶች ለምርመራ ክፍት መሆን አለባቸው፤ አዲስ ምርመራ ሊጀመር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። ዶ/ር ፋውቺ አሁን እያሉ ያሉት ተህዋሲው በተፈጥሮ የመጣ ነው የሚለውን ለመቀበል እንደሚቸገሩ ነው። ዶ/ር ፋውቺ ቀደም ባሉት ጊዜያት ከዚህ በተቃራኒው ነበር የሚያስቡት። አሁን ሐሳባቸውን ምን እንዳይስቀየራቸው እንጃ። ምናልባት ለሕዝብ ይፋ ያልተደረገ ሰነድ ከደኅንነት ቢሮ አግኝተው ይሆን? ቻይና ምን አለች? ቻይና ከሰሞኑ ይህን ተህዋሲ በቤተ ሙከራ አምርተሻል መባሏ አስቆጥቷታል። አብግኗታል። የቃል አጸፋ መመለስ ይዛለች። ይህ እኮ የምዕራባዊያን የተለመደ ስም ማጥፋት ዘመቻ ነው ብላለች። በነገራችሁ ላይ፣ ቻይና ተህዋሲውን በቤተ ሙከራ ሠራሽው የሚለውን ክስ ብቻ ሳይሆን ተህዋሲው ከአገሯ እንደተነሳም አታምንም። ምናልባት የባሕር ምግቦች በማቀዝቀዣ በኮንቴይነር ከእሲያ አገሮች ወደ ቻይና ሲጓጓዙ አብሮ የገባ ተህዋሲ ይሆናል ነው የምትለው። የተህዋሲው መነሻም የደቡብ ምዕራብ እሲያ አገራት ሊሆኑ ይችላሉ ነው የምትለው። የቻይና ቁልፍ የሥነ ተህዋሲያን ሊቅ የሆነችው ፕሮፌሰር ሺ ዘንግሊ [በቅጽል ስሟ የቻይናዋ ባትዎማን ይሏታል] ባለፈው ሳምንት አዲስ ግኝት አሳትማለች። ይህቺ ታላቅ ቻይናዊት ሳይንቲስት በዉሃን ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ናት። የምርመራ ውጤቷ እንዳመላከተው የተህዋሲው 'መልክና ቁመና' ከሩቅ አካባቢ የማዕድናት ማውጫ ሰፈር ከመጣ የሌሊት ወፍ ላይ ከተገኘ ተህዋሲ ናሙና ጋር ምስስሎሽ አለው። ሌላ መላምት አለ? አዎን አለ። በዚህ ገለልተኛ ጎራ የሚገኙ ሳይንቲስቶች ተህዋሲው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ከእንሰሳት ወደ ሰው የተላለፈ ነው ብለው ያምናሉ። ኮቪድ-19 ከሌሊት ወፍ ነው የመጣው። የሌሊት ወፍ ምናልባት ለሌላ እንሰሳ አስተላለፈችው፤ ሌላኛው እንሰሳ በውክልና ራሱ ጋር አቆይቶት ሲያበቃ ወደ ሰው አዛመተው ብለው ይገምታሉ። ይህ መላምት ተህዋሲው መዛመት በጀመረ ሰሞን በስፋት ይታመን የነበረና በጊዜ ሂደት ግን እየተሸረሸረ የመጣ ነው። ከየትስ ቢመጣ እኛ ምናገባን? ይህ ተህዋሲ በዓለም ላይ 3 ሚሊዮን ተኩል ሕዝብ ጭጭ አድርጓል። ምናገባን የሚባል ሊሆን አይችልም። በቀጣይ ሌላ የሰው ልጆችን እልቂት እንደዋዛ የሚያመጣ ተህዋሲ ሊኖር ይችላል። ያ ከመምጣቱ በፊት የሰው ልጅ ስለዚህ ተህዋሲ ድብን፣ ጥርት አድርጎ ሊያጠና ይገባዋል። የሰው ልጅ እንደሚታሰበው በጣም አልተራቀቀም። ወይም በጣም ተራቋል። መቆያውንም መጥፊያውንም በማምረት የተጠመደ የሰው ዘር ተራቋል ነው የሚባለው? ተህዋሰው እንደሚባለው ቻይና በቤተ ሙከራ አምጣ-ወልዳው ከሆነ ደግሞ አጥፊያችንም አዳኛችንም ወይ ቻይና፣ ወይ ባላንጣዎቿ ኃያላን ናቸው።
news-54970749
https://www.bbc.com/amharic/news-54970749
ኬንያ፡ አራስ ልጅ የሚሸጡባቸው የናይሮቢ ጉሊቶች- ልዩ የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ
የርብቃን ልጅ ያያችሁ!
በኬንያ መዲና ናይሮቢ ሕጻናት ይሸጣ። ልክ እንደ ኩንታል ስንዴ። ለዚያውም በጥቁር ገበያ ነው የሚቸበቸቡት። የቢቢሲው የምርመራ ጋዜጠኞች ቡድን ይህንን አሰቃቂ የሕጻናት የገበያ ሰንሰለት ደርሶበታል። የአንድ ሕጻን ዋጋም በአማካይ 300 ፓውንድ መሆኑን ተረድቷል። በማታ ልጇ የተመነተፈባት ርብቃ የርብቃ ልጅ 10 ዓመት ይሆነዋል። የት እንዳለ እናቱ ርብቃ አታውቅም። ናይሮቢ ውስጥ ሊሆን ይችላል። አውሮፓም ሊሆን ይችላል። አውስራሊያም ሊሆን ይችላል። ብቻ የሆነ ቦታ ግን አለ። አይበለውና ሞቶም ሊሆን ይችላል። እንዲያውም እናቱ ርብቃ ውስጧ የሚነግራት እንደዚያ ነው። "የሞተ የሞተ ይመስለኛል" ትላለች እንባ እየተናነቃት። እርሟን ግን አላወጣችም። ማውጣትስ ትችላለች? እንዲያውም የ10 ዓመት ልጅ በናይሮቢ ጎዳና በሀብታም ቤተሰቦች ታጅቦ ስታይ ልቧ ይርዳል። የእኔው ሎውረንስ ቢሆንስ? ትላለች። ርብቃ መቼ ነው ልጇን ለመጨረሻ ጊዜ ያየችው ቢባል የዛሬ 9 ዓመት አካባቢ ነው መልሷ። ገና አንድ ዓመቱ እያለ ነው ከእጇ ያመለጠው። ያኔ እሷ 16 ዓመቷ ነበር። ያን መጥፎ ሌሊት አትረሳውም። መጋቢት 2011 ዓ.ም። ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት አካባቢ ነበር። ርብቃ ጎዳና ነበር የምትኖረው። ብርዱ እንዳይሰማት ቤንዚን ስባ ነበር የተኛችው። ርብቃ ይሄን ቤንዚን የምታጨሰው ድፍረት ለማግኘት ነው። አለበለዚያ ሰዎችን ሄዶ መለመን ያሳፍራታል። ልክ 15 ዓመት ሲሞላት እናቷ የትምህርት ቤት መክፈል አቃታቸው። እሷን ማኖር አቃታቸው። ከቤት ወጣች። የጎዳና ልጅ ሆነች። ከዚያ የሆነ ትልቅ ሰውዬ "እረ ጣጣ የለም፤ እኔ አገባሻለው" አላት። ደስ ብሏት አብራው ሆነች። እንዳረገዘች ሲያውቅ ጠፋ። የበኩር ልጇ ሎውረንስ ታዲያ ከዚህ ትልቅ ሰውዬ የወለደችው ነው። ጥሏት ከጠፋው ሰውዬ። እና በዚያች መጥፎ ሌሊት ምን ሆነ? በቤንዚኒ በ'ጦዘችበት' እንቅልፍ ይዟት እልም። ሞተ የመሰለ እንቅልፍ። ስትነሳ ልጇ ከእቅፏ የለም። ገና 1 ዓመቱ ነበር ያኔ። ለ9 ዓመታት ፈለገች። አስፈለገች። የትም የለም። ያልሄደችበት የልጅ ማሳደጊያ፣ ያልገባችበት ፖሊስ ጣቢያ የለም። ኪያምቦ፣ ካዮሌ፣ ሞያሌ…ሎውረንስ ከየት ይገኝ? እምጥ ይግባ ስምጥ አልታወቀም። ርብቃ ከዚያ በኋላ ሌሎች ልጆችን ወልዳለች። የሎውረንስ ነገር ግን ያንገበግባታል። "ለመጀመርያ ጊዜ እናት ያደረገኝ እኮ እሱ ነው። እወደዋለሁ፣ እናፍቀዋለሁ" ትላለች። ርብቃ አሁንም ጎዳና ነው ቤቷ። 3 ልጆችን ወልዳ የጎዳና ሕይወቷን አጠናክራ ቀጥላበታለች። ርብቃ ከሴት ልጇ ጋር ርብቃ በድጋሚ ልትሰረቅ ነበር? የሚገርመው ከ3ቱ አዳዲስ ልጆቿ ጋር ጎዳና እየኖረች አንድ ቀን ጨቅላዋን ልጇን አንድ ሰውዬ ብድግ አድርጎ አቀፋት። ሰውየው እሷ በምትኖርበት ሰፈር ሲያውደለድል ታየዋለች። "ምናባክና ነው ልጄን የምታዝላት" ብላ ስታንባርቅበት ጊዜ "…ኧረ ልጅሽ የሚጠጣ ነገር ግዛልኝ ብላኝ ነው! ሆ ሆ ምነካሽ አንቺ ሴትዮ! ተረጋጊ" አላት። "ውሸቱን ነው። እንዴት እንዳወቅኩ ልንገርሽ፤ አስቢው እስኪ! እንዴት ነው የአንድ ዓመት ልጅ አንድን መንገደኛ የሚጠጣ ግዛልኝ ልትል የምትችለው? ሌባ ነው፤ የልጅ ሌባ…።" ከዚያ በኋላ ርብቃ ቀስ ብላ ይህንን ሰውዬ መከታተል ጀመረች። በእግሩ ሄዶ ሄዶ የሆነ መኪና ውስጥ ገባ። የገባበት መኪና ውስጥ ደግሞ የሆነች ሴትዮ ነበረች። ኤስተርና ካሮል ልጆቻቸውን ተሰርቀዋል እንደ ርብቃ ዓይነት ብዙ ታሪኮች እሷ በምትኖርበት ጎዳና ላይ ይሰማሉ። ለምሳሌ የኤስተር የ3 ዓመት ልጅ በተመሳሳይ መንገድ ነበር የጠፋው። "ልጄን ካጣሁ ጀምሮ ልክ አይደለሁም፣ አእምሮዬ ታሟል" ትላለች ኤስተር። ከናይሮቢ እስከ ሞምባሳ በእግሯ ሄዳ ልጇን ፈልጋለች። የለም። በጭራሽ የለም። ሌላኛዋ ካሮል ናት። የ2 ዓመት ወንድ ልጇን ካጣች አሁን 5 ዓመት ሊሆናት ነው። "ከነፍሴ አስበልጬ የምወደው ልጄ ነበር። የምኖረውም ለሱ ነበር" ትላለች። "እንዲያውም ሌቦቹ ልጄን መልሰው ቢሰጡኝ ከልቤ ይቅር እላቸዋለው፤ ክስም አልመሰርትም" ትላለች ልጇን የማግኘት ጉጉቷ ሲያይልባት። አሁን እነ ኤስተር፣ ርብቃና ካሮል በናይሮቢ የሕጻናት ጥቁር ገበያ እንዳለ እየተረዱ መጥተዋል። ጭራውን መያዝ ነው ያልቻሉት። ቢቢሲ የምርመራ ጋዜጠኞች ቡድን ከአንድ ዓመት በላይ አድብቶ የዚህን ጥቁር ገበያ ጭራ ለመያዝ ጥረት አደረገ። ተሳክቶለታል። ህፃናትን የሚሰርቁ ግለሰቦችን የምታጋልጠው ኤማ ሕጻናት የሚሸጡባቸው ሆስፒታሎች የልጆች መሸጫ ጥቁር ገበያ ሰንሰለቱ ከመንገድ ላይ ጊዜያዊ የድንኳን ክሊኒክ እስከ ደላሎች ብሎም የመንግሥት ሆስፒታሎች ጋር የተያያዘ ነው። የመርማሪ ቡድኑ አንድ ጋዜጠኛ ማንነቱን ደብቆ ልጆች ይሸጣል ወደሚባል ሆስፒታል ሄደ። ሀብታም የልጅ ገዥ መስሎ። ይህ ሆስፒታል በመንግሥት የሚተዳደር ነው። ልጆችን ለጉዲፈቻ በሕጋዊ መንገድ ለሁለተኛ ወገን ይሰጣል። ውስጥ ለውስጥ ግን ሕገ ወጥ ሽያጭም እንዳለ ይጠረጠራል። ሆስፒታሉ በደላላ ሰንሰለት የተተበተበ ነው። ሆስፒታሉ ልጆችን እንዴት እንደሚሸጥ እንመለስበታለን። ከዚያ በፊት ግን ልጆችን በችርቻሮ ስለሚሸጡ ከበርቴዎች ጥቂት እናውራ። እነዚህ ከበርቴዎች አቅራቢና ሰራቂ ደላሎች አሏቸው። ከእነሱ አንዷ አኒታ ናት። አኒታ ከባድ ጠጪ ስትሆን የአደገኛ ዕጽ ሱሰኛም ናት። የምትተዳደረው ልጅ በመስረቅ ነው። እንደ ርብቃ ካሉ ጎዳና ላይ ከሚኖሩ እናቶች ልጆችን መንትፋ ለደላሎች ታስረክባለች። ወይም ራሷ ትሸጣቸዋለች። የምትመርጣቸው ሕጻናት ከ3 ዓመት በታች የሆኑትን ነው። "እነሱ ጥሩ ዋጋ ያወጣሉ" ትላለች። የቢቢሲ ጋዜጠኞች ስለ አኒታ የሰሙት ከቅርብ ጓደኛዋ ኢማ ነው። ኢማ ስለ አኒታ በርከት ያለ መረጃን አቀበለች። ሕጻናቱን የምታጠምድባቸው ዘዴዎችን ጭምር አብራራች። ፍሬድ ሌፕራን ከማማ ሉሲ ሆስፒታል ልጅ ለመስረቅ 300 ሺህ የኬንያ ሺልንግ ተቀብሏል አኒታ ልጆች የምትሰርቀው ከየትና እንዴት ነው? መጀመርያ ከእናቶቻቸው ጋር ትቀራረባለች። እናቶቹን ታግባባቸዋለች። ስለሷ ማንነት እንዳይጠረጥሩ ታደርጋለች። ይዘናጉላታል። ልጆቻቸውን ከሰረቀች በኋላም ወዳጅነቷን አታቋርጥም። የጎዳና እናቶች የጠረጠሯት ከመሰላት ደግሞ አዘናግታ አፍዝ አደንግዝ መድኃኒት ታበላቸዋለች። ምግብ ላይ ነስንሳ፣ መጠጥ ላይ ቀምማ ትሰጣቸዋለች። ድብን ያለ እንቅልፍ ላይ ሲወድቁ ልጃቸውን አንጠልጥላ ትሰወራለች። አኒታን ለማግኘት የቢቢሲ ጋዜጠኞች ከወዳጇ ኢማ ጋር ተመሳጠሩ። አንዷ ጋዜጠኛም የልጅ ገዥ መስላ ቀረበቻትና ተቀጣጠሩ። በአንድ የናይሮቢ የገበያ ቦታ የልጅ ሻጭ ደላሎች ይበዙበታል በሚባል ጠባብና ድብቅ መጠጥ ቤት ነበር የተገናኙት። አኒታና ጋዜጠኛዋ ተግባቡ። የምትሸጣቸው ልጆች ምን ዓይነት እንደሆኑ፣ ለጊዜው እጇ ላይ ያሉትን ልጆች መልክና ሁኔታ፣ እንዲሁም ዕድሜ ወዘተ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ አጋራች። አኒታ ዝርዝሩን ስትናገር ኮንዶሚንየም ቤት የምታከራይ እንጂ ልጅ የምትሸጥ አትመስልም። አኒታ ስለ ሥራዋ ሳትሳቀቅ ተናገረች። በምስጢር እየተቀረጸች እንደሆነ ግን አታውቅም። የልጆች ከበርቴ የሚባለው አለቃዋ ብዙ ልጆች እንድትሰርቅ ጫና እንደሚያደርግባት አብራራች። "ብታዪ እናትየው ለጎዳና ሕይወት አዲስ ነበረች። ግራ የተገባች እንደሆነች ገና ሳያት አወቅኩ። ስቀርባት ወዲያው አመነችኝ። ልጇን መንትፌያት ጠፋሁ…።" አኒታ አለቃዋ የልጆች ቢዝነስ ከበርቴ እንደሆነና ከእሷና ከሌሎች የወንጀለኛ ቡድኖች ጋር በመመሳጠር ልጆችን በጥሩ ዋጋ እንደሚረከብ አብራራችላት። አለቃዋ የተረከባቸውን ልጆች ለማን እንደሚሸጣቸው ስትናገር፣ "ብዙውን ጊዜ መውለድ የማይችሉ ሴቶች ናቸው የሚገዙት። ለእነሱ ልክ እንደ ጉዲፈቻ ማለት ነው። ነገር ግን ለሌላ ሰይጣናዊ ተግባርም ልጆቹን የሚገዙ ሰዎች አሉ" ብላለች። "ለምሳሌ ልጆችን ከጥንቆላ ጋር በተያያዘ እንደ ዶሮ ለመሰዋት።" አኒታ ልጆቹን ትሸጣቸዋለች ወይም ለአለቃዋ ታስረክባቸዋለች እንጂ ከዚያ በኋላ በሕጻናቱ ላይ ምን ይድረስ ምን የምታውቀው ነገር የለም። ደንታም አይሰጣትም። እሷን የሚያስጨንቃት የልጅ መሸጫ ዋጋ መውጣትና መውረድ ነው። ሰሞኑን ዋጋ ጨምሯል። ገበያውም ደርቷል። በዚህ ቢዝነስ ለተሰማራች አንዲት የተሰረቁ ሕጻናት ተረካቢ በቅርቡ የሸጠችበትን ዋጋ በድብቅ እየተቀረጸች ስትናገር፣ "ሴት ሕጻን 50 ሺህ ሺሊንግ ወንድ ደግሞ እስከ 80 ሺህ የኬንያ ሺሊንግ አስረክቢያለሁ" ብላለች። ይህ በብር 15 ሺህ አካባቢ ይሆናል። "ልንገርሽ አይደለ? እኔ ሕጻናቱ ለጥንቆላ ይዋሉ ለማደጎ ምን ገዶኝ? ገንዘቤን ካገኘሁ እልም ብዬ እጠፋለሁ" ብላታለች፤ ማንነቷን ለደበቀችው የቢቢሲ ጋዜጠኛ። ድብቋ ጋዜጠኛ አኒታን ለሁለተኛ ጊዜ ቀጠረቻት። ልጅ ገዥ ሆና ስለቀረበቻት አኒታ አልጠረጠረችም። በሁለተኛው ቀጠሯቸው አኒታ ብቻዋን አልነበረችም። ገና 5 ወር ካልሞላት እንቦቀቅላ ጋር ነበረች። "አሁን ገና ሰርቂያት መምጣቴ ነው፤ አታምርም?" ሕጻኗ ለሌላ ገዥ ነው የተሰረቀችው። 50 ሺህ ለመክፈል እንደተስማሙ ነግራታለች። በዚህ መሀል የአኒታ ጓደኛ ኢማ ጣልቃ ገባች። ያን ቀን አብራቸው ነበረች። "እንዴ አኒታ! እኔ 80 ሺህ የሚከፍል ሰው አገናኝሻለሁ፤ በሃምሳማ እንዳትሸጫት" አለቻት። በዚሁ ተስማምተው ለ3ኛ ጊዜ ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ። አኒታ ከቢቢሲ ህቡዕ ጋዜጠኛ ጋር ለሦስተኛ ጊዜ የተቀጣጠሩት ምሽት 11 ሰዓት አካባቢ ለመገናኘት ነበር። የቢቢሲዋ ጋዜጠኛ ባለፈው ጊዜ አኒታ እጅ ላይ ያየቻት የ5 ወር ሕጻን ልጅ ሕይወት ደኅንነት አስግቷታል። ሕይወቷን ለመታደግ ቆረጠች። ለሦስተኛው ቀጠሮ ከሲቪል ፖሊሶች ጋር በሰዓቷ የተገኘችውም ለዚሁ ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ አኒታ በሦስተኛው ቀጠሮዋ ላይ ሳትገኝ ቀረች። በተደጋጋሚ አኒታን ለማግኘት ሙከራ ተደረገ። አልተሳካም። ከሳምንታት ቆይታ በኋላ በጓደኛዋ ኢማ በኩል ወሬ ተሰማ። ኢማ እንደምትለው አኒታ መጨረሻ ላይ በሰረቀቻት ልጅ ጥሩ ብር ስላገኘች ባለ ሁለት ክፍል የቆርቆሮ ቤት ለመሥራት ብላ ነበር የጠፋችው። ፖሊስ አኒታን አሁንም እየተከታተላት ይገኛል። በኬንያ በእርግጥ የሕጻናት ጥቁር ገበያ አለ? በኬንያ በሚሰረቁ ልጆች ዙርያ ምንም አስተማማኝ መረጃ የለም። መንግሥትም ሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የማያወላዳ አሐዝ የላቸውም። አንዳንድ የጠፉ ልጆችን በማግኘት ሥራ የተሰማሩ ድርጅቶች በቂ የሚባል በጀት የላቸውም። የሰው ኃይልም የላቸውም። ልጆቻቸው ከተሰረቁባቸው እናቶች ጋር በቅንጅት ከሚሰሩ ድርጅቶች አንዱ "ሚሲንግ ቻይልድ ኬንያ" ይባላል። መሥራቿ ማሪያ ሙንየንዶ ናት። ላለፉት 4 ዓመታት በሥራ ላይ ነበረች። 600 እናቶች ልጆቻቸው ተሰርቀውባቸው እሷ ዘንድ ሪፖርት አድርገዋል። "የልጆች ሰርቆት በኬንያ ትልቅ መነጋገርያ ነው። ነገር ግን ሪፖርት አይደረግም" ትላለች ማሪያና። ብዙውን ጊዜ ልጆቻቸው የሚሰረቁባቸው እናቶች ሀብታሞች አይደሉም። የጎዳና ዜጎች ናቸው። ስለዚህ ጉዳያቸውን ለመከታተልም ሆነ ሪፖርት እንኳ ለማድረግ ጉልበቱ የላቸውም። የሚዲያና የመንግሥትን ትኩረትም ለመሳብ አይችሉም። የብልጹግ ዜጎች ልጆች እየተሰረቁ ቢሆን ግን ነገሩ አገራዊ መልክ ይኖረው ነበር። "ድሆች ናቸው። ታክሲ ተሳፍረው እንኳን ሪፖርት ለማድረግ አቅሙና ጉልበቱ የሌላቸው ናቸው። የልጆቻቸውን መሰረቅ የሕግ አካላት ዘንድ እየሄዱ ለመከታተል እንዴት ችለው? በየት በኩል?" ትላለች ማሪያና። እንዴት በኬንያ ይህ የልጆች ጥቁር ገበያ ሊፈጠር ቻለ? ማርያና ምላሽ አላት። "የባሕል ጉዳይ ነው" ትላለች። "…ሴት ልጅ ቆሞ ቀር መሆን አትፈልግም። በትዳር ውስጥ ያለች ሴት ደግሞ ካልወለደች ለእሷ ሞት ነው። በአፍሪካ ይሄ የተለመደ ነው። "ሴት ልጅ ማግባት አለባት፣ ካገባች መውለድ አለባት፣ ከወለደች ወንድ ልጅ መሆን አለበት። ይህን ማሳካት ያልቻለች ሚስት ከትዳሯ ትፈናቀላለች። ስለዚህ ያላት አማራጭ አራስ ልጅ መስረቅ ይሆናል።" መውለድ ያልቻሉ ሴቶች እንደ አኒታ ዓይነት የልጅ ደላሎችን በእግር በፈረስ የሚፈልጉትም ለዚሁ ነው። ከሆስፒታል በነርሶች በኩል የሚሸጡ ሕጻናት የቢቢሲ የህቡዕ ጋዜጠኛ ወደ ማማ ሉሲ ኪባኪ ሆስፒታል ሄደ። እዚያ ፍሬድ ሊፓራን የሚባል ሠራተኛ አለ። የልጆች ጤና ተንከባካቢ ነው። ራሱን የደበቀው ጋዜጠኛ ፍሬድን አንድ ምሽት አገኘው። አንዲት የሚያውቃት ሴት ጓደኛው፤ ልጅ በጣም እንደምትፈልግ አግባብቶ ነገረው። "እንዴት ልትተባበራት ትችላለህ?" "እንግዲህ ነገሩ ትንሽ አስቸጋሪ ነው። ጥንቃቄን ይሻል። ለጊዜው አንድ ወንድ ልጅ እጄ ላይ አለ። እናቱ ከሁለት ሳምንት በፊት እኛ ጋር ጥላው ጠፍታለች" አለው ፍሬድ ለህብዑ የቢቢሲ ጋዜጠኛ። የቢቢሲ ጋዜጠኛ በድብቅ ፍሬድን እየቀረጸው ነበር። "ማናችንንም ችግር ውስጥ በማይከት መልኩ ጓደኛህን ባለ ልጅ ልናደርጋት እንችላለን።" የመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ የሚጣሉ ሕጻናት በሕጉ መሠረት ለተገቢው አሳዳጊ ድርጅት ይሰጣሉ። ወይም ደግሞ ሕጋዊና ዘለግ ያለ የጀርባ ጥናት ከተደረገ በኋላ ለሕጋዊ ጉዲፈቻ ይሰጣሉ። ደንቡ የሚያዘው ይህንን ነው። የሆስፒታል ሠራተኞች ግን ይህን ቀዳዳ በመጠቀም ልጆቹን አውጥተው በደላሎች በኩል ለጥቁር ገበያ ያቀርቧቸዋል። ማንነቱን የደበቀው የቢቢሲ ጋዜጠኛ ለሁለተኛ ቀጠሮው ባልደረባውን ሮዛን ይዟት ሄደ። ሮዛ ልጅ የምትፈልግ ሴት ሆና ቀረበች። ፍሬይድ ሮዛን አንዳንድ ጥያቄዎችን ጠየቃት። ትዳር እንደመሰረተችና ነገር ግን ለመፀነስ እንደተቸገረች፤ በዚህም ጭንቀት እንደገባት ነገረችው። "ጉዲፈቻ ሞክረሻል?" አላት። "ከባለቤቴ ጋር ተማክረንበት ነበር፤ ነገር ግን ውስጥብ ስለሆነ ትተነዋል" አለች። እንግዲያውስ ሌላው ዘዴ ሕጻናትን መግዛት እንደሆነ ገልጾ የእሱ የመጨረሻ ዋጋው 300 ሺህ ሺልንግ እንደሆነ ገለጸላት። 80 ሺህ ብር አካባቢ ማለት ነው። "በዚህ ከተስማማሽ ስለ ጉዳዩ የምናውቀው እኔ፣ አንቺና ይህ ያመጣሽ ሰው ብቻ ይሆናል።" ከዚህ በኋላ ሽያጩን ለማካሄድ ቀጠሮ ያዙ። በድንኳን ክሊኒኮች ውስጥ የሚሸጡ ልጆች እንደ አኒታ ልጅ ከመንገድ የሚሰርቁ አሉ። እንደ ፍሬይድ ሁሉ ልጅ ከሆስፒታል የሚያሻሽጡ አሉ። ሦስተኛው የልጅ ገበያ በኬንያ ጭርንቁስ ሰፈር በሚቀለሱ የጎዳና የድንኳን ክሊኒኮች ውስጥ የሚካሄድ ነው። እነዚህ ክሊኒኮች የማዋለድ አገልግሎት ለድሆች ይሰጣሉ። የቢቢሲ ጋዜጠኛ ካዮሊ ወደሚባለው ጭርንቁስ ሰፈር ሄደች። ጋዜጠኛዋን ወደዚህ የወሰደቻት የጌቶ ራዲዮ አቅራቢ ጁዲዝ ናት። ካዮሌ የልጅ ጉሊት ያለበት ሰፈር ነው ማለት ይቻላል። ጁዲዝ ወደ አንዱ ክሊኒክ ልጅ ገዥ መስላ ቀረበች። የዚህ ክሊኒክ አስተዳዳሪ ሜሪ ኦማ ትባላለች። በኬንያ ትልልቅ ሆስፒታሎች ነርስ ሆና ማገልገሏን ትናገራለች። ማንነቷን የደበቀችው ጋዜጠኛ ወደተጠቀለሰው ክሊኒክ ስትገባ ሁለት ሴቶች በማማጥ ላይ ነበሩ። አዋላጇ ከሚያምጡት ሴቶች ሌላ ወረፋ ወደሚጠብቁት እየጠቆመች፣ "ያቺ የ8 ወር ተኩል ነፍሰ ጡር ናት። ደርሳለች። ልጇን 45 ሺህ ሺሊንግ ልሸጠልሽ እችላሁ" ስትል ገና ሆድ ውስጥ ያለን ጽንስ ማሻሻጥ ጀመረች። "አታስቢ፣ እናትየው ልክ ገንዘቧን እንደሰጠሻት ከዚህ እልም ብላ ነው የምትጠፋው።" "ለሁሉም እናቶች እቅጩን ነግረናቸዋል። በዚህ ድርድር የለም። ልጄን፣ ማቄን ጨርቄን ብለው መመለስ አይችሉም፤ ተሸጠመ፣ ተሸጠ ነው።" ይቺ ሆዷ ውስጥ ያለውን ጽንስ ትሸጣለች የተባለችው ሴት አዳማ ትባላለች። አዳማ ቤሳቤስቲን የላትም። ልክ እንደ ርብቃ ለአንድ ሰውዬ አረገዘችለትና ሰውየው ብን ብሎ ጠፋ። እርጉዙ ስትሆን ከሥራ ተባረረች። በአንድ ተቋራጭ ውስጥ ሲሚንቶ ተሸካሚ ነበረች። ለወራት ያህል ቤት አከራይዋ ታገሳት። ከዚያም ግን አውጥቶ ጣላት። አዳማ እጇ ላይ ያለው ሀብት ሆዷ ውስጥ ያለው ጽንስ ብቻ ነው። ለመሸጥ ወሰነች። እዚህ የጎዳና የዳስ ውስጥ ክሊኒክ የመጣችውም ዋጋ ለመደራደር ነው። የክሊኒኩ ባለቤት 45ሺ ሺሊንግ ብትደራደርም ለአዳማ የምትሰጣት ግን 10 ሺህ ሺሊንጉን ብቻ መሆኑ ያማል። ርብቃ የጽንስና የልጅ ገበያ ለጥንቆላ ነርሱ ፍሬይድ በመጨረሻ ደወለ። ልጁ ዝግጁ ነው ኑና ውሰዱ ብሎ ደወለ። ከሆስፒታሉ አንዳንድ የወረቀት ፎርሞች ከሞላላ በኋላ ውጭ መኪና ውስጥ ወደምትጠብቀው ሮዛ ሄደ። ለባልደረቦቹ ሮዛ ሕጻናት ተንከባካቢ ድርጅት ውስጥ የምትሰራ ሴት ናት ብሎ ዋሻቸው። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሮዛ ገንዘቡን አቀበለችውና የገዛችውን ልጅ ይዛ ከሆስፒታሉ ወጣች። በእርግጥ መኪናዋ ውስጥ ከገዛችው ልጅ ሌላ ተጨማሪ ሁለት ጨቅላዎች ነበሩ። እነሱ ወደ ማደጎ የሚወሰዱ ናቸው። ሆን ተብሎ ሕጋዊነት ለማላበስ ነው አብረው እንዲወጡ የተደረገው። እናቶቹ ልጆቻቸውን ከሸጡ በኋላ ስቃይ ውስጥ ይገባሉ። ገንዘቡን ሲጨርሱ የሚተርፋቸው ጸጸትና ድህነት ነው። እንደ ርብቃ የተሰረቁት ግን ዕድሜያቸውን ሙሉ እንደባተቱ ነው። ርብቃ ባለፈው ዓመት አንድ የሰፈሯ ሰው ልጅሽን የሆነ ሰፈር አየሁት አላት። እንቅልፍ ባይኗ አልዞረም። ተቅበጠበጠች። "እንዴት ልጄ እንደሆነ አወቅክ?" ስትለው "ቁጭ ላውረንስን የሚመስል ልጅ ነው ያየሁት" አላት። ሀብታም ሰፈር ውስጥ ነው ያየው ልጁን። ሄደች። ፈለገችው ተንከራተተች። ጠብ ያለ ነገር አልነበረም። ስቀይዋ ግን በዛ። "ብዙ ሰዎች የጎዳና እናቶች ለልጃቸው ብዙም ስሜት ያላቸው አይመስለውም፤ ድህነታቸው ስሜታቸውን የቀማቸው ይመስለዋል። ድህነት እናትነታቸውን አልነጠቀም" ትላለች ማሪያና። ርብቃ የሚገርማት ግን ሌላ ነው። "የተሰረቀ ልጅ ገዝተው የሚያሳድጉት እናቶች ግን እንዴት እናት ሊሆኑ ይችላሉ? የሆነ ቦታ የልጁ እናት ስቃይ ላይ መሆኗን ሲያስቡ አይረበሹም?" እያለች ትገረማለች። ኤስተርና ካሮል ግን እዬዬም ሲደላ ነው ባይ ናቸው። የፎቶ ባለሙያ ብሪያን ኢንጋንጋ