id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-43312895
https://www.bbc.com/amharic/news-43312895
ሞ ፋራህ የዘር ጥቃት ደረሰበት
አራት ጊዜ የኦሊምፒክ አሸናፊ የሆነው ሰር ሞ ፋራህ በጀርመን ሃገር አየር ማረፍያ ከጥበቃዎች የዘር ጥቃት ደርሶበታል።
አራት ጊዜ የኦሊምፒክ አሸናፊው ሰር ሞ ፋራህ በመጪው ወር ለሚካሄደው የለንደን ማራቶን ልምምድ ለማድረግ የ34 ዓመቱ እንግሊዛዊው ከሙኒክ ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዝ ነበር ይህ የተከሰተው። በሶማሊያ የተወለደው አትሌት ሞ ፋራህ በኢንስታግራም አካውንቱ ይህን ግጭት የሚያሳይ ቪድዮ ለጥፏል። ''ሰውየው እንደጉድ እየነካካኝ ነው ። ይህ ግልጽ ጥቃት ነው። ግልጽ የሆነ ጥቃት ነው'' ሲል ሞ ፋራህ ይታያል። ቆየት ብሎም የ47 ሰከንድ ቪድዮ በማህበራዊ አካውንቱ ላይ ለጥፎ ''በ2018 እንደዚህ ዓይነት የዘር ጥቃት ማየት ያሳዝናል'' የሚል ጽሑፍ ከሥሩ አስፍሯል። ለስፖርት ፕሬስ አሶሴሽን በሰጠው መግለጫ ላይም የሞ ፋራህ ቃል አቀባይ ''በዛሬው ቀን ሞ ፋርህ ወደ ኢትዮጵያ ለልምምድ በሚጓዝበት ጊዜ በጀርመን አየር ማረፍያ ላይ ችግር ተከስቶ ነበር'' ብሎ ተናግሯል። በመቀጠልም ''ይህ ክስተት በዘር የተነሳሳ እንደሆነና የአይር መረፍያ ሠራተኞቹ ተገቢ ባልሆነ መልኩ እንደተቀበሉት ነው ሞ ፋራህ የተሰማው'' ብሏል። ሞ ፋራህ ከወር በኋላ በለንደንን ማራቶን ከመሳተፉ በፊት ባለፈው እሁድ 'ቢግ ሃፍ' የተሰኘውን ሩጫ አሽንፎ ነበር። ቢቢሲ ስፖርት የሙኒክን አይር ማረፍያ ባለሥልጣኖችን ለማነጋገር ሞክሯል።
news-56480524
https://www.bbc.com/amharic/news-56480524
ትራምፕ፡ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት 'በራሳቸው የማሕበር ሚድያ ገፅ' ሊመለሱ እንደሆነ ፍንጭ ሰጡ
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በራሳቸው የማሕበራዊ ሚዲያ አማካይነት ወደ ማሕበራዊ ሚድያ ሊመለሱ መሆኑን አማካሪያቸው ተናገሩ።
"ፕሬዝደንት ትራምፕ በሁለት በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ማሕበራዊ ሚድያ ተመልሰው እንደምናያቸው አስባለሁ" ሲሉ ጄሰን ሚለር ለፎክስ ኒውስ ተናግረዋል። አማካሪው እንደሚሉት ዶናልድ ትራምፕ የሚመለሱበት ማሕበራዊ ገፅ "በገበያው በጣም ተፈላጊው" ይሆናል። አልፎም አዲሱ ማሕበራዊ ሚድያ "ጨዋታውን ይቀይራል" ይላሉ አማካሪው። ባለፈው ጥር ካፒቶል በተሰኘው የአሜሪካ ሹማምንት መቀመጫ ላይ ከደረሰው ጥቃት በኋላ ትራምፕ ከፌስቡክና ከትዊተር መታገዳቸው ይታወሳል። የትራምፕ ደጋፊዎች ባደረሱት በዚህ ጥቃት አንድ የፖሊስ መኮንን እንዲሁም ሌሎች አራት ሰዎች ተገድለዋል። ጥቃቱ የአሜሪካን ዴሞክራሲ መሠረት ያነቀነቀ ተብሎለትም ነበር። ይህ ጥቃት ከደረሰ ከቀናት በኋላ ትዊተር ከ87 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያፈራውን የትራምፕ ገፅ "ሌሎች ጥቃቶች ሊያነሳሳ ስለሚችል እስከመጨረሻው ተዘግቷል" ሲል አግዶታል። ትራምፕ ትዊተርን ላለፉት 10 ዓመታት ደጋፊዎቻቸውን ከባሕላዊው መንገድ በተለየ መልኩ ለመድረስ ተጠቅመውበታል። ወደ ገፁ አምርተው ያሻቸውን ይናገራሉ፤ የፈለጉትን ባለሥልጣን ይወርፋሉ፤ ደጋፊዎቻቸውን ያነሳሳሉ። የትራምፕ አዲሱ ማሕበራዊ ድር ይታወቃል? አይታወቅም። አማካሪው ትራምፕ ለመጠቀም ስላሰቡት አዲሱ የማሕበራዊ ሚዲያ መድረክ ምንም ዓይነት ማብራሪያ አልሰጡም። "ሁሉም ሰው ፕሬዝደንት ትራምፕ ቀጣይ ምን እንደሚያደርጉ በጉገት ይጠብቃል፤ ይመለከታል" ብለዋል። አማካሪው ለቴሌቪዠን ጣቢያው እንደተናገሩት ትራምፕ ፍሎሪዳ በሚገኘው ማራላጎ በተሰኘው ልጥጡ ሪዞርታቸው ውስጥ ወሳኝ ከሚባሉ ሰዎች ጋር ምክክር አድርገዋል። "በርካታ ኩባንያዎች" የቀድሞውን ፕሬዝደንት ቀርበው እንዳናገሯቸው ነው አማካሪው የሚናገሩት። ትራምፕ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደንበኞች ማምጣት ይችላሉ ብለው የሚያስቡት አማካሪው አዲሱ የማሕበራዊ ሚዲያ መድረክ የሚደርሰው የለም ባይ ናቸው። ትራምፕ ወደ ካፒቶል ሄደው ሃገር ያርበደበዱትን ሰዎች "አርበኞች" ብለው መጥራታቸውን ያየው ትዊተር መጀመሪያ ለ12 ሰዓታት ከገፁ አግዷቸው ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ የትራምፕ ደጋፊዎች ወደ ካፒቶል ያመሩት የአሜሪካ ኮንግረስ ጆ ባይደን ምርጫውን ማሸነፋቸውን ለማወጅ ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት ነበር። ትዊተር 'ከዚህ በኋላ ሕግ የሚጥሱ ከሆነ ወየልዎ' ሲል የቀድሞውን ፕሬዝደንት አስጠነቀቀ። ወደ ገፃቸው እንደሚለሱ የተፈቀደላቸው ፕሬዝደንቱ ሁለት መልዕክቶችን አከታትለው ለጠፉ። ግዙፉ ማሕበራዊ ድር አምባ የትራምፕ ትዊቶች የኩባንያውን ፖሊሲ የሚጥሱና አመፅ የሚያነሳሱ ናቸው ሲል እስከወዲያኛው አሰናበታቸው። ትራምፕ ከትዊተር ብቻ ሳይሆን ከፌስቡክ፣ እንዲሁም የጌም ማዕከል ከሆነው ትዊች እና ከስናፕቻትም ታግደዋል።
news-46563246
https://www.bbc.com/amharic/news-46563246
በአሜሪካ በረራ ላይ ሴት የተነኮሰው ህንዳዊ ዘብጥያ ወረደ
የአሜሪካ ፍርድ ቤት በአሜሪካ በረራ ላይ አጠገቡ ተቀምጣ የነበረችውን ግለሰብ የተነኮሰውን ህንዳዊ የዘጠኝ አመት እስር ፈርዶበታል።
ትንኮሳ የተፈፀመባት ግለሰብ በበረራው ወቅት ብራብሁ ራማሞርቲ ከተሰኘው ግለሰብና ባለቤቱ መሀል ተቀምጣ ነበር። በወቅቱ ተኝታ የነበረ ሲሆን ድንገት ከእንቅልፏ ብንን ስትል የሸሚዟ ቁልፍና የሱሪዋ ዚፕ ተፈትቶ የግለሰቡን እጅ ሱሪዋ ውስጥ አግኝታዋለች። ይህ የ34 ዓመቱ ግለሰብ እስሩን ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ህንድ ተጠርዞ እንደሚላክ ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ አስታውቋል። •'ምን ለብሳ ነበር?' •ቄሮ፣ ሴታዊት፣ ፋኖ…የትውልዱ ድምጾች •የሜቴክ የህዳሴ ግድብ ውል ለፈረንሳይና ጀርመን ኩባንያዎች ሊሰጥ ነው አቃቤ ህግ 11 ዓመት እንዲፈረድበት ጠይቆ የነበረ ቢሆንም "ምንም እንኳን ወንጀሉ ከፍተኛ ቢሆንም" ዘጠኝ አመት በቂ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን የዲትሮይት ፍሪ ፕሬስ አስታውቋል። ግለሰቡም በበኩሉ በወቅቱ ተኝቶ እንደነበር በመግለፅ ወንጀሉን ክዷል። በተያዘበት ወቅትም አቃቤ ህግ ሊያመልጥ ይችላል የሚል መከራከሪያ በማንሳቱ የዋስ መብቱን ተከልክሎ ነበር። ጥቃት የደረሰባት ግለሰብ ለአውሮፕላኑ አስተናጋጆች ምን እንደደረሰባትም ሪፖርት አድርጋለች። የግለሰቡ ባለቤት በበኩሏ ሴትዮዋ ጉልበቱ ላይ ተኝታ ነበር ስትል የወነጀለቻት ሲሆን፤ ሴትዮዋ ሌላ መቀመጫ እንዲሰጣት መጠየቋንም ገልፃለች። ነገር ግን የበረራው አስተናጋጆች በበኩላቸው ጥቃት የደረሰባት ግለሰብ ብቻ እንዲቀይሯት የጠየቀች ሲሆን ፤ የግለሰቡ ባለቤት የተናገረችው ሀሰተኛ እንደሆነ ለመርማሪዎች ተናግረዋል። በወቅቱም እያለቀሰች የነበረ መሆኑን ገልፀው የሸሚዟም ሆነ የሱሪዋ ቁልፎች ተፈትተው እንደነበር አስተናጋጆች ጨምረው ለመርማሪዎች አስረድተዋል። ከኋላ ወንበር ፈልገው እንዳስቀመጧትም አክለዋል።
news-50272652
https://www.bbc.com/amharic/news-50272652
ታይላንድ፡ ታዳጊዎች ለ17 ቀናት መውጣት አቅቷቸው የቆዩበት ዋሻ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ
ባለፈው ዓመት 12 ታዳጊዎች አንድ ዋሻን ለመጎብኘት በገቡበት ዋሻው በውሃ በመሞላቱ ለ17 ቀናት መውጣት ሳይችሉ መቅረታቸው ይታወሳል። ታዲያ ይሄው ዋሻ ከአንድ ዓመት በኋላ ተከፍቶ ታይላንዳውያን መጎብኘት ጀምረዋል።
ኳስ ተጫዋቾቹ ልጆችና አሰልጣኛቸው ለዘጠኝ ቀናት ያህል ያሉበት ባለመታወቁ ጠፍተዋል ተብሎ የነበረ ሲሆን፤ በአስረኛው ቀን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በዋሻው ክፍተት በኩል ተመልክተዋቸዋል። • መምህራንን ተክቶ ያስተማረው ወታደር እየተወደሰ ነው • የህጻናትን ዘረ መል ማስተካከል ክልክል ነው? የአደጋ ጊዜ ሠራተኞቹ የሚያስፈልጓቸውን ቁሳቁሶች ለማድረስ ሲታገሉም ነበር። ትናንት (አርብ) ከሰአት ላይ ለጎብኚዎች ክፍት የሆነውን ዋሻ ከአደጋው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኙ ተመልካቾች ለመሆን 2000 ታይላንዳውያን ወደ ስፍራው መጉረፋቸው ተገልጿል። 'ዋይልድ ቦር' የሚል ቅጽል ስም ያለው የእግር ኳስ ቡድን አባላት የሆኑት ታዳጊዎች ከአሰልጣኛቸው ጋር በመሆን ወደ ዋሻው ከገቡ በኋላ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ በማጋጠሙ መውጣት እንዳልቻሉ እንደተሰማ የመላው ዓለምን ቀልብ ስበው ነበር። ከ17 ቀናት በኋላም ከ90 በላይ የውሃ ጠላቂዎች በተሳተፉበት የማዳን ሥራ ከዋሻው መውጣት ችለዋል። ባለፈው ዓመት ብቻ ከአንድ ሚሊየን በላይ ጎብኚዎች ዋሻውን የጎበኙ ሲሆን፤ በአደጋው ምክንያት በመዘጋቱ ግዛቲቱ ከፍተኛ የገቢ መቀነስ እንዳጋጠመ አስታውቃ ነበር። የዛሬ ዓመት ምን ተፈጠረ? ከሳምንት በላይ ጠፍተው የነበሩት 12 ታይላንዳውያን ልጆችና የእግር ኳስ አሰልጣኛቸው በታይላንድ ዋሻ ውስጥ በሕይወት እንዳሉ ታውቆ፤ ዋሻው በጎርፍ በመሞላቱ ጎርፉ እስኪቀንስ ለወራት መጠበቅ፤ ወይም ደግሞ ዘለው በዋና ሊወጡ እንደሚገባም ተገልጾ ነበር። በመጀመሪያ ልጆቹ እንደሚገኙ ያወቁት እንግሊዛውያን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች፤ ልጆቹ ጎርፍ በሞላው ዋሻ አጠገብ በሚገኝ አፋፍ ተቀምጠው እንደታዩና በጣም እንደተራቡ ገልጸዋል። • የወላጆች ራስ ምታት እየሆነ የመጣው የልጆች የጌም ሱስ በመጀመሪያ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ለታዳጊዎቹ ምግብና መጠጥ ለማድረስ ተቸግረው ነበር። በዚህ ሁኔታም ለ17 ቀናት የመላው ዓለም አይን የታይላንዱ ዋሻ ላይ ሆኖ ነበር። ዋሻው የሚገኝበት ሰሜናዊ ታይላንድ በዝናብ ወቅት በጎርፍ የሚጥለቀለቅ ሲሆን፤ ይህም እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል ነው።
news-48999926
https://www.bbc.com/amharic/news-48999926
የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ 'ሊብራ' ጥያቄን አስነሳ
አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ በአሜሪካ ጥያቄ ተነሳበት።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስቲቭ ማንቺን ጋዜጠኞችን ሰብስበው የፌስቡክ አዲሱ ዲጅታል ገንዘብ ''ለሕገ-ወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪዎች እና አሸባሪዎችን ለሚደግፉ መልካም አጋጣሚን ይፈጥራል'' ሲሉ በዲጅታል ገንዘቡ ላይ ያላቸውን ስጋት ተናግረዋል። ''በዚህ ደስተኛ አይደለንም'' በማለት የፌስቡክ አዲሱ እቅድ በአሜሪካ ብሄራዊ የደህንነት ስጋት መፍጠሩን አስታውቀዋል። • አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ አፍሪካን ያጥለቀልቅ ይሆን? • ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው? • በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? ከቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ ፌስቡክ ወደ ሁለት ቢሊዮን ለሚጠጉ ተጠቃሚዎቹ በዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና በፌስቡክ መተግበሪያዎቹ አማካኝነት ግብይትን እንዲፈጽሙ ለማስቻል እየሰራ ይገኛል። ሊብራ ተብሎ በሚጠራው ክሪፕቶከረንሲ ሰዎች በቀላሉ በመተግበሪያዎቹ አማካኝነት ገንዘብ ማስተላለፍ እና ግብይት መፈጸም ይችላሉ ተብሏል። የፌስቡክ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ዛሬ ከኮንግረሱ ፊት ቀርበው ማብራሪያ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዴቪድ ማርከስ የተባሉት የሊብራን ትግበራ የሚከታተሉ የፌስቡክ ባልደረባ የሴኔት ባንክ ኮሚቴ ፊት ቀርበው፤ የድርጅታቸውን አዲሱን እቅድ እንዴት እንደሚተገበር ያስረዳሉ። ''ክሪፕቶከረንሲዮች በጠቅላላው በሕገ-ወጥ ቡድኖች፣ በሳይበር ወንጀሎችን፣ ታክስ ለመደበቅ በሚጥሩ ግለሰቦች፣ የጦር መሳሪያዎች እና እጾችን ለመግዛት እና ለመሸጥ ጥቅም ላይ እያዋሉ ይገኛሉ'' በማለት ስጋታቸውን የገለጹት የግምጃ ቤት ኃላፊው፤ ፌስቡክ ከፍተኛ ደረጃ ያለው የደህነንት ማረጋገጫ ማቅረብ እንደሚኖርበት ጠቁመዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የክሪፕቶካረንሲዎችን ''አድናቂ አይደለሁም'' በማለት ፌስቡክ ምናልባትም የባንክ ፍቃድ ሊያስፈልገው እንደሚችል ጠቁመዋል። የአሜሪካ የፌደራል መንግሥቱ ተቀማጭ ግንዘብ ቤት ኃላፊ ጄሮሜ ፖውል ፌስቡክ ሊተገብረው ያሰበው ሊብራ ብዙ ጥያቄዎች ተነስተውበታል ብለዋል። ፌስቡክ በበኩሉ ከሊብራ አተገባበር ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎች ከመንግሥት ኃላፊዎች እና ተቆጣጣሪዎች ሊነሱበት እንደሚችሉ እንደገመተ እና ለሁሉም ስጋቶች በንግግር ለመቅረፍ ዝግጁ ነኝ ብሏል። • ፌስቡክ 5 ቢሊየን ዶላር ሊቀጣ ነው የፌስቡክ ባልደረባ ዴቪድ ማርከስ ''ሊብራ ከሃገራት የመገበያያ ጥሬ ገንዘብ ጋር ውድድር ውስጥ የመግባት ምንም አይነት ፍላጎት የለውም፤ የሊብራ ማህበረም የሊብራን ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ ይቆጣጠራል። ፌስቡክ ከተቆጣጣሪዎች እና መንግሥታት ይሁንታን ሳናገኝ ወደ ትግበራው አንሸጋገርም'' ብለዋል። ክሪይፕቶ-ከረንሲን ምንድነው? ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት 'ክሪይፕቶ-ከረንሲን'፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደህንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ ሲል ይገልጸዋል። ቢትኮይን ምንድነው? ከክሪፕቶከረንሲዎች አንዱ ነው። ቢትኮይን በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል+ገንዘብ+መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን 'ኦንላይን' የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። ሊብራ ከቢትኮይን በምን ይለያል፡ ሊብራ ልክ እንደ ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባለው ሂደት ነው። ልዩነታቸው ሊብራ በሚታወቁ ኩባንያዎች ቁጥጥር ይደረግበታል። ቢትኮይን እና ሌሎች ክሪፕቶ-ከረንሲዎች በመንግሥታት እና በባንኮች አይታተሙም፤ ቁጥጥርም አይደረግባቸውም። የፌስቡኩ ሊብራ ግን በመንግሥታት እና በማዕከላዊ ባንኮች ቁጥጥር ይደረግበታል በተጨማሪም በጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ ይኖረዋል።
news-50955430
https://www.bbc.com/amharic/news-50955430
የኃይማኖት መፃዒ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን?
ከሞሐመድ በፊት፤ ከክርስቶስ ቀድሞ፤ ከቡድሃም ቀድሞ ዞራስተር ነበረ። ከ3500 ዓመት በፊት፤ በነሃስ ዘመን ኢራን የአንድ አምላክን ርዕይ ይዞ የተነሳ።
ከ1000 ዓመት በኋላ በዓለማችን የአንድ አምላክን ሥርዓት በማስረፅ የመጀመሪያ የሚባልለት ዞራስተር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮችን ማፍራት ቻለ። አብዛኛዎች የፋርስ ባሕረ-ሰላጤ ነዋሪዎች ናቸው። ከ1000 ዓመት በኋላ ግን የፋርስ አገዛዝ ፈረሰ፤ ዞራስተሮችም አናሳ ሆኑ፤ እያሳደደ የሚገድላቸውም በዛ። ይህን አድራጊው ደግሞ አዲሱ የፋርስ ባሕረ-ሰላጤ ኃይማኖት ነው. . . እስልምና። ከ1500 ዓመታት በኋላ አሁን ባለንበት ዓለም የዞራስተር ተከታዮች ቁጥራቸው እጅግ የመነመነ ነው። እየሞተ ያለ ኃይማኖት እየተባለ ይጠራም ይዟል። ኃይማኖት ይወለዳል፤ ያድጋል፤ ከዚያም ይሞታል ተብሎ ቢታሰብም ማንም ይህንን መቀበል የሚፈልግ አይመስልም። አዲስ ኃይማኖት የሚመሠርቱ ሰዎች ይወገዛሉ እንጂ አይሞገሱም። በርካቶቻችን ኃይማኖትን እንደ ጊዜ እና ቦታ የማይገድበው አድርገን እንቆጥረዋለን። ኃይማኖት ሲሞት ተረት ይሆናል። ልክ እንደ ግብፅ፣ ግሪክ እና ኖርስ አማልክት። ዛሬ ኃያል የምንላቸው ኃይማኖቶች በዝግመተ ለውጥ ያለፉ ናቸው። ለምሳሌ ክርስትና አነስ ባለች ቤተ-እምነት እንደ ተጀመረ መዛግብት ይጠቁማሉ። ክርስትና ከሶስት ክፍለ ዘመናት በኋላ በደንቡ እውቅና ማግኘት የቻለው። ከዚያ በኋላ ነው ክርስትና ምስራቃዊ ኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ ተብሎ ለሁለት የተከፈለው [ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ1054 ዓ.ም።] እርስዎ የሚያምኑበት ኃይማኖት የእውነት ጫፍ ላይ ደርሷል ብለው ካመኑ ሊቀየር ይችላል ብለው የሚያስቡበት ምንም ምክንያት የለም። ነገር ግን ታሪክ የሚነግረን ሌላ ነው። ኃይማኖቶች እንደ ትውልዱ ይቀያየራሉ፤ ሊጠፉም ይችላሉ። • የቢላል መስጂድንና ራጉዔል ቤተ ክርስትያንን የሚያሰሩት ካህን ኃይማኖቶች ባለፉት ክፍለ-ዘመናት ብዙ ለውጥ እንዳሳዩ ከመዛግብት ከተረዳን ዘንዳ መጪው ዘመን ምን አዝሏል የሚለውን መጠየቅ ግድ ነው። በአንድ አምላክ ማመን እየጠፋ ይመጣ ይሆን? ቴክኖሎጂስ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ ይኖረዋል? አዲስ መልክ ያለው ኃይማኖት ብቅ ይል ይሆን? የኃይማኖት አስፈላጊነት. . . የ18ኛው ክፍለ ዘመን ፈረንሳዊ ባለቅኔ ቮልቴር «ፈጣሪ ባይኖር እንኳ፤ ልንፈጥረው ግድ ነው» ሲል ተደምጦ ነበር። እርግጥ ቮልቴር የተደራጀ ኃይማኖት ቀንደኛ ነቃፊ ነበር። ቢሆንም ፈጣሪ አለ ብሎ ማመን ለማሕበረሰቡ አስፈላጊ ነው ብሎ ያምናል። ዘመናይ ነን የሚሉ የኃይማኖት አጥኚዎችም በዚህ ያምናሉ። ኃይማኖት የሰፊው ሕዝብ ማደንዘዣ ዕፅ ነው የሚለው እሳቤም የመጣው ከዚህ ነው። ኃይማኖት አስፈላጊነቱ ባይከራክርም ይላሉ ፀሐፊያኑ፤ ባለሥልጣናት ሕዝቡን ለመግዛት ሊጠቀሙበት አይገባም። በርካታ ኃይማኖቶች በየጊዜው ይፈጠራሉ። ነገር ግን መዝለቅ አይችሉም። አሁን በርካታ ተከታይ ያላቸው ኃይማኖቶችም አንድ ሰሞን እንዲሁ ነበሩ። የኃይማኖቶች ዕጣ ፈንታ የሚወሰኑ ለምዕመኑ በሚያቀርቡት ጥቅም ላይ ነው። ለምሳሌ ክርስትና በሮም ሥልጣኔ ወቅት አንድ ተራ ቤተ-እምነት እንደነበር አጥኚ ኮነር ዉድ ይናገራሉ። ነገር ግን በሽታ መጥቶ የሮም ሰዎችን ሲያጠቃ የክርስትና እምነት ተከታዮች እርስ በርስ ተረዳድተው ሲተርፉ ኢ-አማንያን ግን አለቁ። እስልምናም ቢሆን ለክብር እና መረዳዳት የሚሰጠው ቦታ በውቅቱ ለነበሩ ኢ-አማንያን አዲስ ነገር ነበር። • በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ የታገቱት ስድስት ታዳጊዎች ለምን ተገደሉ? • የኢትዮጵያን አፈር ለማከም የሚመራመረው ዶ/ር መሐመድ አባኦሊ ወጣም ወረደ ኃይማኖት ለማሕበረሰብ ከሚሰጣቸው በርካታ ጥቅሞች መካከል አንዱ ሰዎች እርስ በርስ ተቻችለው እንዲኖሩ ማድረጉ ትልቁ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን ኃይማኖት የለንም የሚሉ ሰዎች ቁጥር እጅጉን እየበዛ መጥቷል። አሊያም በኃይማኖታቸው አገዛዝ ሥር ለመውደቅ ብዙም የማይሹ የትየለሌ ናቸው። ኃይማኖትና መንግሥታዊ አገዛዝም እየተራራቁ ናቸው። ሰዎች ለፈጣሪ ሕግ ከመገዛት ይልቅ ለመንግሥታዊ ሕግ መገዛት እየቀናቸው ነው። ይህ ሁሉ ተደማምሮ የኃይማኖት ዕጣ ፈንታ አሳሳቢ ነው ማለት አያስገርምም። እንደ ቻይና እና ሩስያ ያሉ ኮሚኒስት ሃገራት ፈጣሪ የለም የሚለውን ሃሳብ [ኤቴይዝም] እንደ ሃገራዊ ፖሊሲ አፅድቀዋል። በተለይ ቻይና ውስጥ እምነትን ማንፀባረቅ ቀላል አይደለም። ኃይማኖት አልባ ሰዎች የሚገኙት ደግሞ በለፀጉ በሚባሉ ሃገራት ነው። ለምሳሌ ጃፓን እና ስዊድን በርካታ ኃይማኖት የለሽ ሰዎች የሚገኙባቸው ሃገራት ናቸው። በጣም የሚያስደንቀው ግን በላቲን አሜሪካና በአረቡ ዓለም በርካታ ቁጥር ያለው ኃይማኖት የለሽ ሰው መገኘቱ ነው። ሌላው ቀርቶ የኃይማኖት [በተለይ ደግሞ ክርስትና] ተፅዕኖ ጎልቶ በሚታይባት ሃገረ-አሜሪካ ኃይማኖት የለንም የሚሉ ሰዎች ቁጥር ከኢቫንጀሊካል ክርስቲያኖች ቁጥር እየላቀ መምጣቱን የአሜሪካ አጠቃላይ የማሕበረሰብ ጥናት [General Social Survey of US] ይፋ አድርጓል። ቢሆንም ኃይማኖት እየጠፋ ነው ለማለት ፈፅሞ አያስደፍርም። በግሪጎሪ አቆጣጠር 2015 ላይ 'ፒው ሪሰርች' የተሰኘው ያሠራው ጥናት የአማኞች ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ እንማይሄደ ያሳያል። የእስልምና እምነት ተከታዮች ቁጥር እየጨመረ ከክርስትያኖች እኩል ሊሆን እንደሚችልም ጥናቱ ይገምታል።
news-49470328
https://www.bbc.com/amharic/news-49470328
አያቴ ከአምስት የናዚ ግድያ ጣቢያዎች አምልጦ በሕይወት መኖር ችሏል
የቢቢሲዋ ሃና ጌልባርት የአያቷን ታሪክ አስደናቂ ታሪክ እንዲህ ከትባዋለች።
ቤታችን ውስጥ አንድ ጥንታዊ ፎቶ አለ፤ ጥቁርና ነጭ ነው። የትምህርት ቤት ፎቶ ነገር ይመስላል፤ ታዳጊዎች ተደርድረው የተነሱት ፎቶ። ጊዜው 1945 [እ.አ.አ.] ነው። ፎቶው ላይ የሚታዩት ሕፃናት አይሁዶች ናቸው። ቦታው ደግሞ ፕራግ [የቼክ ሪፐብሊክ የአሁን ዋና ከተማ]። ሕፃናት ፕራግ አካባቢ ከነበረ አንድ የናዚዎች ግድያ ጣቢያ [ኮንሴንትሬሽን ካምፕ] የተረፉ ናቸው። ብዙዎቹ እርስ በርስ ተቃቅፈዋል። የግማሾቹ ፊት ላይ ፈገግታ ይታያል። ፍፁም ዝምታ የሚነበብባቸው ፊቶችም አልጠፉም። እኒህ ፊቶች የናዚ ጭፍጨፋን [ሆሎኮስት] በአንዳች ተዓምራዊ አጋጣሚ ያመለጡ ናቸው። ብዙዎቹ ቤተሰቦቻቸውን አጥተዋል፤ ወላጅ አልባ ናቸው። የመልስ ጉዞ ወደ ፕራግ ግንቦት፤ 2019 [እ.አ.አ.] ዓመተ ምህረት። ተመሳሳይ ሃውልት ከጀርባቸው ይታያል። ባለነጭ እና ጥቁሩ ፎቶ ላይ ካሉ ሰዎች ጥቂቶቹ ተገኝተዋል። ከባል፣ ሚስትና ልጅ ልጆቻቸው ጋር ነው እዚህ የተገናኙት። እዚህ የተገኙት አዲስ ፎቶ ለመነሳት ነው። በሕይወት መኖራቸውን የሚዘክር፤ ሞትን ድል መንሳታቸውን የሚያበስር ፎቶ። ይኼው እኔም እዚህ ታሪካዊ ፎቶ ላይ ልገኝ ሆነ። ሌሎች 12 የቤተሰብ አባላት አብረውኝ አሉ። ነገር ግን ጋዜጠኛም ሆኜ ነው እዚህ የተገኘሁት። ይህንን ታሪክ በብዕሬ ከትቤ ላስቀር። አያቴ ዳቪድ ኸርማን፤ የሞትን ጭጋጋ ከገፈፉት እኒህ ሕፃናት አንዱ ነው። አምስት የናዚ የግድያ ጣቢያዎች ውስጥ ኖሯል፤ ኦሽዊትዝን ጨምሮ። ሰቆቃ ጉዞዬ ከማንቸስተር ይጀምራል። ከተረፉትና አያቴን ከሚያውቁት መካከል ሁለት አሁንም በሕይወት አሉ። ወደቤታቸው በሄድኩ ጊዜ እጃቸውን ዘርግተው ተቀበሉኝ። ሻይ እና ብስኩት ቀርቦልኝ ትንሽ ከተጨዋወትን በኋላ ወደ ቁምነገሬ ገባሁ። ያሳለፋችሁት ሰቆቃ ምን ይመስላል ስል ጠይቅኳቸው። ቤቱ ድንገት ዝምታ ዋጠው። ከናዚ ሰቆቃ ከተረፈ ሰው ጋር ቁጭ ብዬ ሳወራ የመጀመሪያ ጊዜዬ ነው። ለዚያም ነው አየሩ በዝምታ ሲዋጥ ምን ማለት እንዳለብኝ ጠፍቶኝ እኔም ከንፈሬን ማንቀሳቀስ ያቃተኝ። ዕድሜዬ 10 እያለ ይመስለኛል ከአያቴ እና ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር ኦሽዊትዝንና ሌሎች 'ካምፖችን' ለመጎብኘት የሄድነው። ሕፃናት የሚላስ ነገር ካልተገዛልን እያሉ ያለቅሳሉ። አስጎብኝው የከተመሩ ጫማዎችና ፀጉሮች አሳየን። ከአያቴ ወዳጆች ጋር ቁጭ ብዬ ሳወራ ግን ነገሩ ሌላ ሆነብኝ። ወደ ታሪኩ እጅጉን የተጠጋሁ መሰለኝ። "ሞትን ሁሌም እናየው ነበር" ሳም ላስኪዬር 91 ዓመታቸው ነው። እጅጌያቸውን ገለጥ አድርገው አንድ ንቅሳት አሳዩኝ። አረንጓዴ ቀለም ያላቸው ቃለትና ቁጥሮች ይታዩኛል። "ሞትን ሁሌም እናየው ነበር" አሉኝ። "በጢስ ማውጫው በኩል ሲወጣ የሚታየው ጢስ የሰው ነበር። አንድ ሰው ከሶስት ወር የዘለለ አይቆይም፤ እኔ ግን ሰባት ወራት ከረምኩ። ከመደርደሪያው ላይ አንድ የፎቶ አልበም አንስቶ ያሳየኝ ጀመር። የሆነውን ሲነግረኝ ጠንቀቅ ባለ ሁኔታ ቢሆንም ውስጣቂ ቁስሉ ይገባኝ ነበር። አሁንም ድረስ ስለ ግድያ ጣብያዎቹ እንደሚቃዥ ግን አልደበቀኝም። ኑሮ በኦሽዊትዝ ካምፕ ውስጥ እንዴት እንደነበረ ሲያጫውተኝ እንዴት አድርጌ ወደ ቃላት እንደምለውጠው ከብዶኝ ነበር። ከሁሉም በላይ ረሃቡን አይረሳውም። ቀጥሎ ስንት ሰዓት ላይ ወይንም በየትኛው ቀን ምግብ እንደሚያገኙ ሳያውቁ መኖር። አይክ አልተርማን፤ ሌላኛው የ91 ዓት ባለፀጋ የአያቴ ጓደኛና የሰቆቃው ዘመን ተቋዳሽ ናቸው። "ጭንቀታችን የነበረው ቀጣዩ ዳቦ የሚመጣው መቼ ይሆን የሚለው ነው። ረሃብ ደህና አድርጎ አሰቃይቶናል።" የነፃነት ጣዕም አይክ፤ አንድ የፎቶ ድርሳን ከፈቱና ታሪክን ከምስል ጋር እያመዛገቡ ያሳዩኝ ጀመሩ። "አየሽ ይሄን ፎቶ፤ ነፃ መሆናችንን ያወቅን ጊዜ የተነሳ ነው። እንዲጠብቁን የተመደቡት ናዚዎች መጥፋታቸውን ያወቅን ወቅት። ይኸው እኔ፤ እጄን እያልበለብኩ። በጣም ረጋ ብሎ የሚያወራው አይክ ቀጠለ፤ "በጢስ እንደተበከልን የገባን በሚቀጥለው ቀን ነው። የትም ሊወስዱን አልቻሉም። ሲቀጥል ደግሞ የምንኖርበት ጣብያ ውስጥ የሬሳ ማቃጠያ ነበር።" ነፃነት. . . የሳም ፊት ፈካ ሲል ታየኝ። "ፕራግ ማለት ለኔ ነፃነት ነች። ነፃ አየር የተነፈስኩት እዚያ ነው።" ነፃነቱ ከተገኘ በኋላ ሁሉም ፊቱን ወደ ዳቦ አዞረ። ብዙዎች ለዓመታት ረሃብ ውስጥ ነበሩ። በጣም ከመመገባቸው የተነሳ ቁንጣን ይዟቸው ሆስፒታል የገቡ በርካቶች ነበሩ። ጥቂቶች ደግሞ ጨጓራቸው አልፈጭ ብሎ ሞተዋል። ታሪካዊው ፎቶ ላይ የሚታዩት በርካቶቹ ቴሬዚን [Theresienstadt] በተሰኘው ፕራግ ውስጥ በሚገኝ የግድያ ጣብያ ውስጥ የነበሩ ናቸው። ከጭፍጨፋው የተረፉ ሰዎች ያዩትን የሬሣ ብዛት ቆጥረው እንደማይጨርሱት ይናገራሉ። አሁን ከተማዋ የቱሪስት መናኸሪያ ናት። ላለፉና ለተረፉ እንዲሆን ተብሎ የተሠራ ማስታወሻ የብዙዎች ዓይን ማረፊያ ነው። የቢቢሲዋ ሃና ከአሬክ [ግራ] እና ሳም [ቀኝ] ጋር ጉዞ ወደ እንግሊዝ አያቴን ጨምሮ ሌሎች 732 የሰቆቃው አምላጮች 1945 [እ.አ.አ.] ነበር ወደ እንግሊዝ የመጡት። ከዚያ በኋላ እንደ ወንድም አና እህት ነው የኖሩት። ማንም የላቸውምና። አዲስ ሕይወት በእንግሊዝ። ከባድ ቢሆንም ተወጥተውታል። ቤተሰብ አፍርተዋል። ልጅ እና የልጅ ልጅ አይተዋል። ፎቶው ላይ ከሚታዩት በርካታ ሕፃናት መካከል ወንዶች ቢበዙም 83 ሴቶችም ነበሩ። ስለ ናዚ ጭፍጨፋ [ሆሎኮስት] እንዳውቅ ተደርጌ ነው ያደግኩት። ነገር ግን አያቴና ጓደኞቹ የደረሰባቸው ሰቆቃ 1945 ላይ እንዳላበቃ የገባኝ በቅርቡ ነው። እናቴ ወጣት እያለች ለአባቷ [አያት] አንድም ቀን ትምህርት ቤት ውስጥ የከፋ ቀን አሳለፍኩ ብላ ነግራው እንደማታውቅ ትነግረኛለች። ሞትን እያሸተቱ ተራን ከመጠበቅ በላይ መቼም የከፋ ቀን የለምና። ዳቪድ ኸርማን [የሃና አያት] ወደ ቡክሴንቫልት ግድያ ጣብያ በ17 ዓመቱ ነበር የመጣው የአያቴ ፎቶ አለኝ። ዕድሜው 17 ነበር። ፀጉረን ላጭተውታል። የተቀደደ ፒጃማ አድርጓል። መለያ ቁጥሩም ጎልቶ ይታያል። ወደ ቡክሴንቫልት ጣቢያ በመጣ ጊዜ የተነሳው ፎቶ ነው። ዓይኖቹ ውስጥ የመኖር ጉጉት ይታየኛል። እናቴ እንዲህ ትላለች፤ ይህ ወጣት ሰው ማለት ወላጆቹ ተቃጥለው እንዲሞቱ ተፈርዶባቸው እየተነዱ ሲሄዱ ያየ ሰው ነው።
news-56778228
https://www.bbc.com/amharic/news-56778228
ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል ስለተባለው ሠራዊቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ምላሽ ሰጠች
ኤርትራ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ገብቷል የተባለውን ሠራዊቷን በተመለከተ በይፋ ምላሽ ሰጠች።
አምባሳደርና ሶፊያ ተስፋማሪያም በተባበሩት መንግሥታት የኤርትራ አምባሳደርና ቋሚ ተወካይ የሆኑት ሶፊያ ተስፋማሪያም ሐሙስ እለት የመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ላይ በተነሱ ጉዳዮች ላይ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ነው ስለኤርትራ ወታደሮች የገለጹት። ትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ግጭት መካሄዱን ተከትሎ የኤርትራ ኃይሎች ድንበር ተሻግረው ወደ ትግራይ ክልል ገብተዋል የሚሉ ሪፖርቶች በተደጋጋሚ ሲወጡ የቆዩ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ የኤርትራ መንግሥት ለወራት ሲያስተባብሉ መቆየታቸው ይታወሳል። በመጨረሻም ባለፈው መጋቢት ወር የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደተናገሩት የህወሓት ኃይሎች በሰነዘሩት የጠብ አጫሪነት ጥቃት ተገፍቶ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ መግባቱን ገልጸው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ወደ አሥመራ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር በመነጋገር የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጣ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን አሳውቀዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የኤርትራ መንግሥት በኢትዮጵያ በኩል የተገለጸውን የኤርትራ ወታደሮች መኖር ያላስተባበለ ከመሆኑም በላይ አንድም ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው ስለመግባታቸው ያለው ነገር አልነበረም። አሁን ግን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ባካሄደው ውይይት ላይ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ባለስልጣን የሆኑት ማርክ ሎውኮክ እና በምክር ቤቱ የአሜሪካ መልዕክተኛ የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ላደረጉት ንግግር ኤርትራ በሰጠችው የደብዳቤ ምላሽ ላይ ስለወታደሮቿ ተገልጿል። አምባሳደር ሶፊያ ተስፋማሪያም ለጸጥታው ጥባቃ ምክር ቤት በጻፉት ደብዳቤ ላይ በዚያ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል። በዚህም ወደ ኢትዮጵያ የኤርትራ ሠራዊትን በሚመለከት "አንዣቦ የነበረው ስጋት በአብዛኛው በመወገዱ ኤርትራና ኢትዮጵያ የኤርትራ ኃይሎችን ለማስወጣትና የኢትዮጵያ ሠራዊት በድንበር ላይ እንዲሰማራ ለማድረግ በከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው አማካይነት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል" በማለት አረጋግጠዋል። አምባሳደሯ ለምክር ቤቱ በጻፉት ደብዳቤ ላይ የኤርትራ መንግሥት በዝግ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የአሜሪካዋ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በሰነዘሩት "ተገቢ ያልሆነ" መግለጫ ላይ ተቃውሞ እንዳለው ገልጸዋል። በተጨማሪም የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ዘርፍም ላይ ቅሬታቸውን በደብዳቤው ላይ ተቋሙ "በተደጋጋሚ ከተሰጠው ድርሻ ባሻገር በመሄድ ተቀባይነት የሌለው ገንቢ ያልሆነ ተግባራት ውስጥ ገብቷል" ሲሉ ከሰዋል። በጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት የአሜሪካ መልዕክተኛ የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድም በዚሁ ጊዜ የአስገድዶ መድፈርና ጾታዊ ጥቃቶችን የተመለከቱ ሪፖርቶችን ተከትሎ የኤርትራ ወታደሮች "በአስቸኳይ" ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ ጠይቀው ነበር። አምባሳደር ሶፊያ በደብዳቤያቸው ላይ በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ በግጭቱ ወቅት "ወሲባዊ ጥቃትና ረሃብ እንደ መሳሪያ ጥቅም ላይ ውሏል" በሚል የቀረበውን ክስ ሐሰተኛ ሲሉ በደብዳቤያቸው የተቃወሙት ሲሆን፤ የኤርትራ ወታደሮች አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ፈጽመዋል መባሉ "የሚያስቆጣ ብቻ ሳይሆን በሕዝባችን ባህልና ታሪክ ላይ የተሰነዘረ የከፋ ጥቃት ነው" ሲሉ ተቃውመውታል። ህወሓት በፈጸመው ጥፋት በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ ንጹሃን በምንም መልኩ ጉዳት ሊደርስባቸው እንደማይገባ የገለጸው የኤርትራዋ አምባሳደር ደብዳቤ የሰብአዊ እርዳታን ማቅረብ የወቅቱ አንገብጋቢ ሥራ መሆን ይገባዋል ብሏል። በትግራይ ውስጥ ስላለው ሁኔታ ሐሙስ ዕለት ለአምስተኛ ጊዜ በተወያየው የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በግጭት ከተጎዳው የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል "የኤርትራ ወታደሮች መውጣታቸውን የሚያመለክት ነገር የተባበሩት መንግሥታት ተቋማትም ሆኑ ሌሎች አብረውት የሚሰሩ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች እንዳላዩ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ባለስልጣን የሆኑት ማርክ ሎውኮክ ተናግረው ነበር። ትግራይ ውስጥ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ድንበር ተሻግረው ገብተዋል የተባሉት የኤርትራ ወታደሮች የተለያዩ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን በተመለከተ ክስ ሲቀርብባቸው ቆይተዋል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ግን ለወራት ወታደሮቹ ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን በተመለከተ ይወጡ የነበሩትን ሪፖርቶች ሲያስተባብሉ የቆዩ ሲሆን፤ በመጨረሻም በመጋቢት ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኤርትራ ወታደሮች መኖራቸውን ለአገሪቱ ፓርላማ ተናግረው ነበር። ከቀናት በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ኤርትራ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከተነጋገሩ በኋላ ወታደሮቹ ከኢትዮጵያ የድንበር አካባቢዎች ለቀው በመውጣት የኢትዮጵያ ሠራዊት ስፍራዎቹን እንዲቆጣጠር ከስምምነት መድረሳቸውን ገልጸው እንደነበር ይታወሳል። በትግራይ ክልል ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከተከሰተ አምስት ወራት የተቆጠሩ ሲሆን በዚህ ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት በጉዳዩ ላይ ለመምከርና መግለጫ ለመውጣት ምክር ቤቱ የሐሙስ ዕለቱን ጨምሮ ለአምስት ጊዜ ተሰብስቦ ተወያይቷል። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ማርክ ሎውኮክ ግጭቱ እንዲቆምና የበለጠ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲመቻች ጥያቄ አቅርበዋል። ትግራይ ውስጥ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በመንግሥት ጦር ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ ነበር። በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሃዙ በበርካታ ሺዎች ሊሆን እንደሚችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገርም በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች ግድያዎች፣ ጾታዊ ጥቃቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ዘረፋና የንብረት ውድመቶች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ አመልክተዋል። በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።
news-56778230
https://www.bbc.com/amharic/news-56778230
በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከሦስት ሚሊዮን አለፈ
በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሦስት ሚሊዮን ማለፉን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ።
በኮቪድ-19 አባቱ የሞቱበት ሕንዳዊ ይህ የተገለጸው የዓለም ጤና ድርጅት "ዓለም ወደ ከፍተኛው የኢንፌክሽን መጠን እየተቃረበ ነው" መሆኑን ባስጠነቀቀ ማግስት ነው። ብዙ ሰዎች በቫይረሱ በመያዝ ሁለተኛ የሆነችው ሕንድ ዛሬ ቅዳሜ ብቻ ከ230,000 በላይ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ ወደ 140 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አርብ ዕለት "በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃዎች እየጨመረ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አክለውም "ባለፉት ሁለት ወራት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳምንት በቫይረሱ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር ችሏል" ብለዋል። ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ እንደገለጸው አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገቡ አገራት ሲሆኑ በሦስቱ አገራት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሞተዋል። ባለፈው ሳምንት በዓለም ዙሪያ በየቀኑ በአማካይ 12,000 ሰዎች መሞታቸውን የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቧል። ይህ ስለወረርሽኙ የሚወጣው አሃዝ በዓለም ዙሪያ በብዙ አገሮች ውስጥ ስላለው የበሽታው ሁኔታ ትክክለኛውን መረጃ ላያንፀባርቅ ይችላል ተብሏል። በሕንድ ምን እየተከሰተ ነው? እስከ ጥቂት ሳምንታት በፊት ድረስ ሕንድ በአንጻራዊ ሁኔታ ወረርሽኙን በቁጥጥር ስር ያዋለች ይመስል ነበር። በጥር እና በየካቲት ወራት በአብዛኛው በቀን ከ20 ሺህ በታች አዳዲስ ታማሚዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ይህም ከ1.3 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ላላት አገር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ሄዶ ቅዳሜ ብቻ ለሦስተኛ ተከታታይ ቀን ክብረ ወሰን የሆነ 234,000 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። ሆስፒታሎች የአልጋና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠማቸው ነው። የታመሙ ሰዎች ወደ ቤት እየተመለሱ ሲሆን አንዳንድ ቤተሰቦች የሚፈልጉትን መድኃኒት ለማግኘት ወደ ጥቁር ገበያ ፊታቸውን አዙረዋል። በቢቢሲ የምርመራ ዘገባ መሠረት በሕንድ ውስጥ መድኃኒት ከመደበኛው ዋጋ በአምስት እጥፍ ለገበያ እየቀረበ ነው። ባለሥልጣናት ወረርሽኙን ለመግታት በዋና ከተማዋ ደልሂ እና በሌሎች አካባቢዎች በሳምንቱ መጨረሻ ላይ የእንቅስቃሴ እገዳዎች ተጥለዋል።
54298116
https://www.bbc.com/amharic/54298116
ኢትዮጵያን ጨምሮ የበርካታ አፍሪካ አገራት ተማሪዎች የአሜሪካ ቪዛ በሁለት ዓመት እንዲገደብ ሃሳብ ቀረበ
አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከበርካታ አፍሪካ አገራት የሚመጡ ተማሪዎችን አስመልክቶ በቅርቡ አንድ ረቂቅ መመሪያን አቅርባለች።
በዚህም ረቂቅ መሰረት የተማሪዎቹ ቪዛ በሁለት አመት እንዲገደብ የሚመክር ነው። ይህም ማለት የትምህርት ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ የቪዛ ጊዜያቸው ያልቃል ማለት ነው። በአሜሪካው ሆምላንድ ሴኩሪቲ ቢሮ የወጣው ይህ መመሪያ ከዚህ ቀደም ተማሪዎች ትምህርታቸውን እስኪያጠናቅቁ ድረስ ይሰጥ የነበረውን የቪዛ ህግም የቀየረ ነው ተብሏል። መመሪያውም ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው። ረቂቁ የአራት አመት ቪዛ የሚሰጣቸው አገራትን ዝርዝር ያካተተ ሲሆን በሁለት አመት ደግሞ የሚገደብበትም አንደኛው ምክንያት "በከፍተኛ ሁኔታ ማጭበርበርና ብሄራዊ ደህንነት ስጋት መፍጠሩን ተከትሎ ነው" ብሏል መረጃው እነዚህ የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ተብለው ከተጠቀሱት አገራት መካከል ሽብርን በመደገፍ የምትጠረጥራቸው እንደ ሱዳን ያሉ አገራት የሚመጡ ተማሪዎች ተፅእኖ ይደርሳል ተብሏል። በዋነኝነት ግን ዝርዝሩ ቪዛው ከሚፈቅድላቸው በላይ የቆዩ ተማሪዎችን አገራትን ያካተተ ነው። ቪዛው ከሚፈቅድላቸው በላይ የቆዩ ተማሪዎችን በአማካኝ አስልቶም 10 ከመቶ በላይ የቆዩ አገራት ዜጎችን በሁለት አመታት እንዲገደብም ይመክራል። የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ተማሪዎች ከ13 በመቶ በላይ እንደቆዩም መረጃው የጎሮጎሳውያኑን 2019 መረጃን አጣቅሶ አስፍሯል። ከነዚህ አገራት በተጨማሪም ቡርኪናፋሶ፣ ቡሩንዲ፣ ካሜሮን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ጋቦን ፣ ዘ ጋምቢያ፣ ላይቤሪያ፣ ማላዊና ኡጋንዳም ተካትተዋል።
news-53083704
https://www.bbc.com/amharic/news-53083704
ኮሮናቫይረስ፡ ያልተመለሱ ብዙ ጥያቄዎች ያሉበት አዲሱ መድኃኒት ዴክሳሜታዞን በበኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ዓይን
በአሁኑ ጊዜ ዴክሳሜታሶን የሁሉን ቀልብ የገዛ መድኃት ሆኗል። ምክንያቱ ደግሞ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በኮቪድ-19 ተይዘው በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ለማከም ሊውል ይችላል ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
ዴክሳሜታሶን የዓለም ጤና ድርጅትም ይህ መድኃኒት በኮቪድ-19 በጸና የታመሙ ሰዎችን ለማከም መዋሉን እደግፋለሁ ብሏል። ድርጅቱ በዩናትድ ኪንግደም ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተደረገው የክሊኒካል ሙከራ በኮቪድ-19 በጽኑ የታመሙ እና በቬንትሌተር ድጋፍ የሚተነፍሱ ሰዎችን የሞት መጠን በአንድ ሦስተኛ ይቀንሳል፤ ኦክስጅን ብቻ የሚፈልጉ ታማሚዎች የሞት መጠንን ደግሞ በአንድ አምስተኛ ይቀንሳል ብሏል። በተጨማሪም እንደተባለው የጥናቱ ውጤት ያሳየው ዴክሳሜታሶን በጠና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ መካከለኛ ምልክት በሚያሳዩት ላይ አመርቂ ውጤት አላመጣም። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም "ይህ ኦክስጅንና የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ለሚያስፈልጋቸው የኮሮናቫይረስ ህሙማን ላይ የሚያጋጥምን ሞት የሚቀንስ የመጀመሪያው መድኃኒት ነው" ሲሉ ገልጸውታል። ዋና ዳይሬክተሩ ይህም ታላቅ ዜና መሆኑን ጠቅሰው የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥትንና በዚህን ህይወትን በሚታደግ የመጀመሪያ ግኝት ላይ በመሳተፍ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ፣ ለሆስፒታሎችና ለህሙማን የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። 'ዴክሳሜታሶን' እንዴት ያለ መድኃኒት ነው? ዴክሳሜታሶን ከ1960ዎቹ (እአአ) ጀምሮ በተለያዩ ህመሞች ምክንያት የሚያጋጥሙ እብጠቶችን ለመቀነስና የተወሰኑ አይነት የካንስር ህመሞችን ለማከም ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። ከ1977 ጀምሮ በተለያየ መልኩ ተዘጋጅቶ አስፈላጊ ከተባሉ የዓለም ጤና ድርጅት የመድኃኒቶች ዝርዝር ውስጥ የገባ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከባለቤትነት መብት ነጻ ከመሆኑ በተጨማሪ በብዙ አገራት ውስጥ በቀላሉ ይገኛል። የፋርማሲ ባለሙያ እና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ መምህር የሆኑት አቶ ሸዋነህ አየለ፤ ይህ መድኃኒት 'ግሉኮኮሪኮይድ' ተብሎ በሚጠራ መድኃኒት ዘርፍ ሥር የሚመደብ መሆኑን ይናገራሉ። አቶ ሸዋነህ ይህ መድኃኒት በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ለበርካታ ዓመታት ከመቆየቱ ባሻገር በስፋት እንደሚገኝ እና የጤና ባለሙያዎችም ታማሚዎችን ለማከም ሲጠቀሙ የቆየ እንደሆነ ያስረዳሉ። ባለሙያው እንደሚሉት ይህ መድኃኒት የሚሰጠውን አገልግሎትን የሚተኩ ሌሎች መድኃኒቶች በስፋት ስለማይገኙ ዴክሳሜታሶን በኢትዮጵያ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል። ይህን መድኃኒት ከአፍንጫ ጀምሮ አስከ ሳምባ ድረስ የሚያጋጥሙ አለርጂዎችን ለማከም ጥቅም ላይ ሲውል መቆየቱን ገልጸው፤ በአሁኑ ሰዓት የጎንዮሽ ጉዳታቸው (ሳይድ ኢፌክት) አነስተኛ የሆኑ መድኃኒቶች በመፈብረካቸው እንጂ ይህ መድኃኒት የአስም ታማሚዎችን ለማከም በስፋት ይውል እንደነበረ የፋርማሲ ባለሙያው ይናገራሉ። በአሜሪካ አገር የድንገተኛ ክፍል እና የኅብረተሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና የጤና ጥበቃ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ጽዮን ፍሬውም በተመሳሳይ፤ መድኃኒቱ አስም ላለባቸው ሰዎች ሊታዘዝ አንደሚችል እንዲሁም ህጻናት እንደተወለዱ መተንፈስ ሲያቅታቸው እንደሚሰጣቸው እና ሰውነታቸውን ለመገንባት ለሚፈልጉ ሰዎች ጡንቻቸውን ለማፈርጠም እንደሚጠቀሙት ይናገራሉ። 'ዴክሳሜታሶን' ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች? የፋርማሲ ባለሙያ አቶ ሸዋነህ ዴክሳሜታሶን በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ለማከም መዋል ይችላል የሚለው ዜና "ለእኔ በጣም አስገራሚ ነው" ይላሉ። ባለሙያው መድኃኒቱ ኮቪድ-19 በሽታ የሚያስከትለውን ቫይረስ እንደማይገደል ይናገራሉ። ይህ መድኃኒት ቀድሞውንም ቢሆን በመተንፈሻ አካላት ላይ የሚከሰቱ አለርጂዎችን ለማከም ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። ኮሮናቫይረስም የመተንፈሻ አካላትን ነው የሚያጠቃው። ይህ ቫይረስ ሰውነታችን ውስጥ ሲገባ፤ የሰውነታችን ተፈጥሯዊ ሥርዓት ቫይረሱን ከሰውነት ለማስወጣት በተደጋጋሚ እናስላለን፤ እናስነጥሳለን። ይህ ተፈጥሯዊ ነው። ይሁን እንጂ በቫይረሱ የተያዘ ሰው በተደጋጋሚ ሲያስል የመተንፈሻ ቱቦዎች ጡንቻ ይሰበሰባሉ መልሰው ይላቀቀሉ፤ ይህ ሲደጋገም አለርጂ ይከሰታል። ይህ መድኃኒት ግን ተደጋጋሚ ማስነጠስ እና ማሳልን በመቀነስ በመተንፈሻ ቱቦዎች ላይ አለርጂ እንዲቀንስ ያደርጋል። ከዚያም ታማሚው በተሻለ መልኩ መተንፈስ እንዲችል ያስችለዋል በማለት ያስዳሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ መድኃኒት ሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅሙን ከፍ የሚያደርጉ ሴሎች ማምረትን ዝቅ እንዲል ያደርጋል። በርካቶች በኮሮናቫይረስ የሚሞቱት ሰውነታቸው ቫይረሱን ለመከላከል በሚያወጣው ከፍተኛ አቅም ምክንያት ነው ይላሉ ባለሙያው። የበሽታ መከላከል አቅምን ከፍ የሚያደርጉት ሴሎች የሚመረቱበት መጠን ዝቅ አለ ማለት ሰውነታችን ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያወጣው ኃይል ቀነሰ ማለት ነው። በዚህም ሳል እና ማስነጠስ ስለሚቀንስ ታማሚው በቀላሉ መተንፈስ ይችላል። ዴክሳሜታሶን ለጽኑ ሕሙማን በደም ስር የሚሰጥ ሲሆን፣ ሕመማቸው ላልፀናባቸው ደግሞ በክኒን መልክ እንዲወስዱት ይደረጋል። መድኃኒቱ የጎንዮሽ ችግር ያስከትላል? መድኃኒቱ በስፋት እና በአነስተኛ ዋጋ ማግኘት መቻሉ መልካም አጋጣሚ መሆኑን የሚጠቅሱት ዶ/ር ጽዮን፤ በመድኃኒቱ አጠቃቀም ላይ ግን ስጋት እንዳላቸው ይናገራሉ። "የጉሉኮስ ቁጥሮችን በመጨመር የስኳር በሽታን ያብሳል፣ ጭንቀት ወይም ድብርት ሊያስከትል ይችላል፣ የአጥንት መሳሳትን ሊያስከትል ይችላል" ሲሉ መድኃኒቱ ሊኖረው የሚችለውን የጎንዮሽ ችግር ይተቅሳሉ። ዶ/ር ጽዮን እንደሚሉት ይህ የምርመር ውጤተ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም ገና ቁንጽል የጥናት ውጤት በመሆኑ ሕብረተሰቡ በዚህ ሊዘናጋ አይገባም በማለት ይመክራሉ። ስለዚህም ከበሽታው ሊጠብቁን የሚችሉት "በቤት መሆን፣ የአፍና የአፍንጫ መሰፈኛ ጭምብል ማድረግ፣ የእጅ ንጽህናን መጠበቅ . . . እነዚህ ነገሮች እንደሚሰሩ እናውቅለን። ለአሁኑ የሚሰሩት ነገሮች ላይ ብናተኩር ጥሩ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ዴክሳሜታሶን በኢትዮጵያ መቼ ጥቅም ላይ ይውላል? በጤና ሚኒስቴር የህክምና ግልጋሎት ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ያዕቆብ ሰማን ለቢቢሲ እንደገለጹት በመድኃኒቱ ላይ ምርመራውን እንዲያደርግ የባለሙያዎች ቡድን ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በዚህ መሰረትም ቡድኑ ይፋ የተደረገውን ሙሉውን ጥናት ከመረመረም በኋላ የደረሰበትን እንዲሁም ይሆናል ያለውን ምክረ ሐሳብ አቅርቧል። ስለመድኃኒቱ አጠቃቅም ይጥናት ቡድኑ ያቀረበው ምክረ ሃሳብ ዝርዝር ይዘት ገና ይፋ አልተደረገም። በቀጣይ ምን እንጠበቅ? ተመራማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ሙከራ ውጤታቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት አሳውቀው በቀጣይ ቀናትን ደግሞ ስለዴክሳሜታሶን ያለው ሙሉ መረጃ ተተንትኖ እንደሚቀርቡ እየተጠበቀ ነው። በቀጣይም ድርጅቱ ስለመድኃኒቱ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደሚያቀርብና ስለመድኃኒቱ አጠቃቀም ያለው መመሪያ ላይ መሻሻል ያደርጋል ተብሏል።
news-52590490
https://www.bbc.com/amharic/news-52590490
ኮሮናቫይረስ፡ቤታቸው እስር ቤት የሆነባቸው ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች
የተባበሩት መንግሥታት መረጃ እንደሚያስረዳው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ መወሰኑን ተከትሎ የቤት ውስጥ ጥቃት ጨምሯል።
የበርካታ የአፍሪካ አገራት መንግሥታት፣ፖሊስና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንደገለጹት ከቤት ያለመውጣት ሕግን ተከትሎ በርካቶች በፍቅር አጋራቸው አልያም በቤተሰብ አባላቸው ጥቃት ይደርስባቸዋል። ጥቃት ከሚደርስባቸው ሰዎች መካከል ደግሞ አብዛኛዎቹ ሴቶችና ህጻናት ናቸው። በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ እራሳችሁን ብታገኙት ምን ታደርጋላችሁ? የዘርፉ ባለሙያዎችንና የቤት ውስጥ ጥቃትን ማምለጥ የቻሉ አነጋግረን ተከታዩን አዘጋጅተናል። ‘’ ጥቃት የሚፈጸመምበት አይነት ግንኙነት ውስጥ ካላችሁ ምን እየሆነ እንዳለ መገንዘብ ይቻላል’’ ትላለች ለብዙ ዓመታት በባለቤቷ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት የደረሰባት ኤስተር። ‘’ የሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ሁሌም አስቸጋሪ ነበሩ ምክንያቱም ሁሉም ሰው ወደየቤቱ ይሰበሰባል። በቤት ውስጥ ሲውል ምንም የሚሰራው ነገር ስለሌለው ይደብረዋል። ሰብብ እየፈለገ እኔን ለማበሳጨትና የሆነ ነገር እንድናገር ወይም እንዳደርግ ይገፋፋኛል።‘’ "አዎ ሁሌም መጨረሻው የቃላት ውርጅብኝና አንዳንዴም ዱላ ነበር። ልክ የታሰርኩ ያክል ነበር የሚሰማኝ።‘’ በሁለት ቀን ውስጥ የሰው ልጅ ያክል ይህንን ያህል ከደበረው ለወራት ቤት ውስጥ ሲቀመጥ ደግሞ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ከባድ አይደለም ትላለች ኤስተር። ጭንቀት ጥቃት አድራሾችን የበለጠ ጠብ ጫሪ ያደርጋቸዋል፤ ለሴቶቹ ደግሞ ማንም እንደማይደርስላቸው ሲያውቁ ደግሞ የበለጠ ጨካኝነት ያጠቃቸዋል። ‘’በኢኮኖሚ በኩል ጥገኛ ስለነበርኩኝና ልጆች ስላሉኝ እንዴት ዝም ብዬ እሄዳለው የሚለው ሀሳብ ሁሌም ወደኋላ ይጎትተኝ ነበር።‘’ የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለበት በዚህ ወቅት ደግሞ ሴቶች አጋሮቻቸውን ጥለው እንዳይሄዱ እንኳን ሕግ ጣሳችሁ ተብለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይውላሉ። እሱን ቢያመልጡ እንኳን ወደፈለጉበት የሚሄዱበት የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የለም። በርካታ አገራት ይህንን ውስጥ በማስገባት በቤት ውስጥ ጥቃት ለሚደርስባቸው አገልግሎት የሚሰጥ ነጻ የስልክ መስመር አዘጋጅተዋል። መስመሩ ሁሌም ቢሆን እንደሚጨናነቅ ነው የሚነገረው። በደቡብ አፍሪካ በመጀመሪያዎቹ የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለባቸው ሳምንታት ብቻ ፖሊስ 2320 ጾታዊ ጥቃቶች እንደመዘገበ ገልጿል። ይህ ደግሞ ከሌላ ጊዜው 37 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በዚምባብዌ ደግሞ የጥቃቶች ቁጥር በሶስት እጥፍ የጨመረ ሲሆን በናይጄሪያም ቢሆን ከሌላጊዜው ከፍ ያለ ጥቃት ተመዝግቧል። አንዳንድ የአፍሪካ አገራት ሴቶችን በዚህ ወቅት ለመርዳት በማሰብ የተለያዩ አማራጮችን እየወሰዱ ነው። ለምሳሌ ቱኒዚያ በዚህ ጊዜ ጥቃት የሚደርባቸው ሴቶችና ህጻናት ማረፊያ የሚሆኑ ስምንት መጠለያዎችን አዘጋጅታለች በሌሎች አገራት ደግሞ ተመሳሳይ መጠለያዎች ተዘጋጅተው በጎፈቃደኞችም ጭምር እየተሳተፉ ይገኛሉ። •በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ በዚምባብዌ የሚገኘው መጠለያ በአሁኑ ሰአት 21 አዋቂ ሴቶችና ሰባት ህጻናትን ተቀብሎ እያስተናገደ ይገኛል። የማዕከሉ ዳይሬክተር ቢየትሪስ ሳቫድዬ እንደሚሉት ሴቶቹና ህጻናቱ አንዳንዶቹ ከቤታቸው ጠፍተው የመጡና በፖሊስ ጥቆማም የተገኙ ናቸው። በኬንያ የምትገኛዋ የማህበበራዊ አገልግሎት ሰራተኛ ዳያና ካማንዴ እንደምትለው ደግሞ እሷ የምትሰራበት ድርጅት 17 ሴቶችን ተቀብሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በናይጄሪያ ጥቃት የሚፈጸምባቸውን ሴቶች ከቤታቸው ለማስወጣት በጎ ፈቃደኞችም ጭምር በመሳተፍ ትብብር እያደረጉ ነው። በአንዳንድ አጋጣሚዎች ሴቶቹን ከአጋሮቻቸው ለማስመለጥ ቤተ ዘመድም ጭምር ይሳተፋል ተብል። በጋና ያለው መጠለያ ደግሞ ከዚህ በኋላ ጥቃት የሚደርስባቸውን ሴቶች ለመቀበል እየተቸገርኩ ነው ብሏል። ምክንያቱም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱና የለይቶ ማቆያዎች በመሙላታቸው ነው። ኤስተር በዚህ ማዕከል ውስጥ ጥቃት ለሚደርስባቸው ሰዎች በተቋቋመው የጥር መስመር ላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ ትገኛለች። ‘’ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን በማህበራዊ ሚዲያ በኩል ለማግኘት ጥረት አድርጉ፤ደውሉላቸውና ያላችሁበትን ሁኔታ አስረዷቸው። ሊረዳችሁ የሚችል ማንኛው ሰው ጋር ከመደወል ወደኋላ አትበሉ’’ በማለት ምክሯን ለግሳለች።
49174921
https://www.bbc.com/amharic/49174921
በጎንደር ከ3ሺህ በላይ የመትረየስ ጥይቶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ባለፈው ሰኞ ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም በጎንደር ከተማ 3217 የሚሆኑ የመትረየስ (አብራራው) ጥይቶች መያዛቸውን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ሰጤ ዘርጋው ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ኮማንደሩ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው ግለሰብ ጥይቶቹን በባጃጅ ጭኖ ሲሄድ በቁጥጥር ስር ውሏል። በወቅቱ ወደ ከተማ የመጡ እንግዶችን ለመቀበል መንገድ ተዘጋግቶ እንደነበር የገለፁት ኮማንደሩ ባጃጁ መንገዱን ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር እንዲቆም መታዘዙን ይናገራሉ። •ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? •የጦር መሳሪያዎቹ ምንጫቸው የት ነው? ይሁን እንጂ ባጃጁን ሲያሽከረክር የነበረው ግለሰብ ከመቆም ይልቅ ለማምለጥ ሲሞክር የጸጥታ ኃይል ተከታትሎ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ኮማንደሩ ተናግረዋል። ግለሰቡ ከአራተኛ ጣቢያ አካባቢ ልዩ ስሙ ፋጭት ከሚባል ቦታ ወደ 'ወጥቶ ባርቶ' የተባለ ሥፍራ እያመራ ነበር ብለዋል። በወቅቱ በባጃጁ ውስጥ አሽከርካሪው ብቻ የነበረ ሲሆን ከሱ ጀርባ ያሉትንም ለማግኘት ምርመራ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል። ጥይቱ እንዴት ተገኘ? ከየት መጣ? የሚለው በምርመራ ላይ መሆኑን ኮማንደር ሰጤ ነግረውናል። ፌደራል ፖሊስ ከጥቂት ወራት በፊት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቀው ከሃምሌ 1፣ 2010 ዓ. ም. እስከ ጥቅምት 20፣ 2011 ዓ. ም. 2,516 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ መያዛቸውንና 7,832 የጦር መሳሪያ ጥይቶችም ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ሲሉ መያዛቸውን አስታውቋል። ይህም ብዙዎችን ምን እየተካሄደ ነው? የሚል ስጋት ውስጥ ከትቷል። መንግሥት ምን እያደረገ ነው ? የሚል ጥያቄም በስፋት እያስነሳ ነው። •በአስር ወራት አማርኛ ማንበብና መፃፍ የቻለው ጀርመናዊ ሕገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውሩ በጉልህ ከታየባቸው ክልሎች የአማራ ክልል በዋነኛነት ይጠቀሳል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው ቢቢሲ ከጥቂት ወራት በፊት ባናገራቸው ወቅት ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩ አሁን ያለበትን ደረጃ ሲያስረዱ ''በአንዳንድ የሃገሪቱ ስፍራዎች የጦር መሳሪያ ዝውውሩ እንደጨመረ እና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በተደረገው ቁጥጥር የዝውውር መጠኑ ቀንሷል" ይላሉ። በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው ሕገ-ወጥ መሳሪያ ዝውውር ምንጩ አንድ ብቻ ሳይሆን በርከት ያለ እንደሆነ ይታመናል። በመንግሥት እጅ የነበሩ ጦር መሳሪያዎችም በዚህ ውስጥ እንደሚገኙ ኮሚሽነሩ ያመለክታሉ ''ሕገ-ወጥ መሳሪያዎች ከውጪ ብቻ አይደለም የሚመጡት። ሃገሪቱ ውስጥ ካሉ የመሳሪያ ግምጃ ቤቶች ውስጥ በተለያዩ ኃይሎች ተዘርፈው የተወሰዱም ይገኙበታል።'' እንደ ኮሚሽነሩ ከሆነ፤ ከሃገር ውስጥ ከተዘረፉ መሳሪያዎች ውጪ ከደቡብ ሱዳን፣ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሕገ-ወጥ መሳሪያዎችም መጠናቸው ቀላል የሚባል አይደለም።
news-48376620
https://www.bbc.com/amharic/news-48376620
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፡ የ6ኛ ዓመት እጩ ሐኪሞች ግቢውን ለቅቀው ወጡ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እጩ ሐኪሞች በተደጋጋሚ ያቀረቡት ጥያቄ ባለመመለሱ ያደረጉትን የሥራ ማቆም አድማ ተከትሎ ከዩኒቨርሲቲው አስተዳዳር ጋር ባለመስማማታቸው ግቢውን ለቀው እንደወጡ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው እጩ ሐኪሞች በትናንትናው እለት ግቢውን ለቅቀው የወጡት 250 እንደሚሆኑ ተናግረዋል። እጩ ሐኪሞቹ ለሰባት ወራት ያህል ይመለሳሉ እየተባሉ ያልተመለሱ ጥያቄዎች በመኖራቸው ግቢውን ለቀው ለመውጣት መወሰናቸውን ተናግረዋል። • "ሀኪሙ ትግሉን አቀጣጠለው እንጂ የሚታገለው ለታካሚው ነው" እጩ ሐኪም ታሪኩ ወርቁ ከጥያቄዎቻቸው መካከል የሕክምና ግብዓት አለመኖርና ለመስራት ምቹ አለመሆኑ ማኅበረሰቡ ለሐኪም ያለው አመለካከት የተዛባ እንዲሆን ምክንያት ሆኗል የሚል ነው። "ለቀዶ ሕክምና እንኳን ጓንት የምንገዛው ከመድሃኒት ቤቶች ነው" የሚለው እጩ ሐኪሙ ሕክምና የራሱ የሆነ ሥርዓተ ትምህርት ቢኖረውም ከሥርዓተ ትምህርቱ ውጭ እየሰሩ መሆናቸው ሌላኛው ቅሬታቸው እንደሆነ ይገልፃል። ሥርዓተ ትምህርቱ ላይ የተቀመጠውን ለመተግበር የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩም ብቃታቸው እየወረደ መምጣቱንም ያክላል። "ሥርዓተ ትምህርቱ ብዙ ያልተባባሱና ለሞት የማይዳርጉ ቀዶ ሕክምናዎችን እንድናደርግ የሚያዝ ቢሆንም ያንን ለመስራት ዕድሉን እያገኘን አይደለም፤ በሙያ የእኛ ያልሆኑ ሥራዎች እየሰራን ነው" በማለት ምሳሌ ያጣቅሳል። ይህንንም 'ዘመናዊ ባርነት' የሚል ስያሜ እንደሰጡት ይናገራል። • «በስልክዎ ታካሚና አካሚ እናገናኛለን» ሥራ ፈጣሪው ወጣት ሙሉ ሕይወታቸውን ለትምህርት የሰጡት ማንኛውም ያልተማረ ሰው ሊሰራ የሚችለውን ለመስራት አለመሆኑንም ይናገራል። ለ36 ሰዓታት እንደሚሰሩ የሚናገረው ሐኪሙ አብዛኛዎቹ የመንግሥት ሆስፒታሎች ማረፊያ ክፍል ስለሌላቸው ላለፉት ሰባት ወራት በዚህ ሁኔታ ሲሰሩ እንደነበር ያስታውሳል። ይሁን እንጂ ዩኒቨርሲቲው ቀላል ሥራዎችን የሚሰሩ ሰዎችን በመቅጠር፣ ማረፊያ ቤቶችን በማዘጋጀት፣ እንዲሁም የተወሰኑ ግብዓቶችን በማሟላት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የሥራ ማቆም አድማ ተገቢ እንዳልሆነ በደብዳቤ እንደገለፀላቸው ይናገራል። ነገር ግን ሌሎች ከክፍያ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎቻቸው ሊመለሱላቸው ባለመቻሉ ግቢውን ለቀው ለመውጣት እንደወሰኑ ለቢቢሲ ተናግሯል። የታሪኩን ሃሳብ የምትጋራው ሌላኛዋ እጩ ሐኪም ፍሬሕይወት አለሙ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ መልስ እንደሚሰጧቸው ቢነገራቸውም መልስ አለማግኘታቸውን ትናገራለች። በዚህም ምክንያት የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል። የሚመለከተው አካል ጥያቄዎችን ለመመለስ ድርድር የጀመረ ቢሆንም ባለመሳካቱ እንዲወጡ የሚያዝ ደብዳቤ እንደተለጠፈ ገልፃለች። • የ'ሰከረ' አዋላጅ ሐኪም እናትና ልጅን ገደለ ስለ ጉዳዩ የጠየቅናቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ ይዳኙ ማንደፍሮ ሃገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ሐኪሞቹ አስር የሚሆኑ የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ያቀረቡ መሆናቸውን ያስታውሳሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ዩኒቨርሲቲው በፌደራል መመለስ የሚገባውን ለሚመለከተው ያስተላለፈ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው መመለስ በሚገባው ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል። በጊዜው ጥያቄያቸውን ተቀብለው የሥራና ትምህርት ማቆም አድማ ማድረግ እንደሌለባቸው ተነጋግረው የነበረ ቢሆንም ሐኪሞቹ ወደ ሥራ ማቆም አድማ ገብተዋል። በመሆኑም የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች በተገኙበት በድጋሚ ውይይት ተደርጎ እንዲመለሱ የሚያሳስብ ማስታወቂያ ሦስት ጊዜ አውጥተው ሐኪሞቹ ባለመመለሳቸው ዩኒቨርሲቲው አስተዳዳደራዊ እርምጃ ሊወስድ ችሏል ብለዋል- ወ/ሮ ይዳኙ። ከዚህም በኋላ የዩኒቨርሲቲው ምክር ቤት በድጋሚ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ጥሪ በማቅረብ ይህንን የማያደርግ ተማሪ ለአንድ ዓመት ያህል እንደሚታገድ የሚገልፅ ማስታወቂያ አውጥቷል ብለዋል። ወ/ሮ ይዳኙ አክለውም ትምህርታቸውንና ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ዘዴዎችን ቢጠቀምም ሐኪሞቹ ወደ ሥራ አለመግባታቸውን ይናገራሉ። በዚህ ምክንያትም ዩኒቨርሲቲው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደወሰደባቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
news-49157023
https://www.bbc.com/amharic/news-49157023
አምባሳደር ሬድዋን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለምን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አላቀረቡም?
በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት የአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የሹመት ደብዳቤ እስካሁን በኤርትራ መንግሥት ተቀባይነት አላገኝም በሚል ወጣው መረጃ ትክክል አይደለም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባብሏል።
አምባሳደር ሬድዋን ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከአንድ ዓመት በፊት በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ሬድዋን ሁሴን የሹመት ደብዳቤያቸው በኤርትራ መንግሥት ተቀባይነትን አላገኝም የሚለው ዜና በስፋት መነጋገሪያ ነበር። የኢፌድሪ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው "የአንድ አምባሳደር የሹመት ደብዳቤ በተቀባዩ ሃገር ተቀባይነትን አላገኘም የሚባለው፤ አምባሳደሩ በተቀባዩ ሃገር እንዲሰራ ሳይፈቀድለት ሲቀር ነው። አምባሳደር ሬድዋን የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ በሶስተኛው ቀን ለኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አቅርበዋል። በዚህም መሰረት ስራቸውን እየሰሩ ይገኛል። አንድ አምባሳደር በተቀባዩ ሃገር ተቀባይነትን ሳያገኝ ሥራ መጀመር አይችልም" ሲሉ ያስረዳሉ። ነገር ግን ዋናውን የሹመት ደብዳቤያቸውን እስከ አሁንም ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር አለማቅረባቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። • ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ • ''የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር'' አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ ''ዋናው ቅጂ (የሹመት ደብዳቤ) የሚቀርበው ለርዕሰ ብሔሩ ነው። ተቀባዩ ሃገር በሚያዘጋጀው መረሃግብር ላይ ደብዳቤው ለርዕሰ ብሔሩ ይቀርባል። እስከዛው ግን ለውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የሹመት ደብዳቤውን እስካቀረበ ድረስ አምባሳደሩ ስራውን ይሰራል። የአምባሳደር ሬድዋንም ከዚህ የተለየ ነገር አይደለም" በማለት አቶ ነብያት ያብራራሉ። አምባሳደር አብደላ አደም በሱዳን የኤርትራ አምባሳደር ነበሩ። አንድ አምባሳደር ወደ ተሾመበት ሃገር ከመሄዱ ከሶስት ወራት በፊት የሹመት ደብዳቤው ወደ ተቀባዩ ሃገር የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቢሮ ይላካል ይላሉ። እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ አንድ አምባሳደር በተቀባዩ ሃገር ቀድሞውኑ ተቀባይነትን ሳያገኝ በምንም አይነት መልኩ ሹመቱ ወደ ተሰጠበት ሃገር ሊሄድና ሊሰራ አይችልም። ይሁን እንጂ ይላሉ አምባሳደር አብደላ፤ "አንድ አምባሳደር የሹመት ደብዳቤውን ርዕሰ ብሔሩ ጋር ቀርቦ ካላጸደቀ፤ በተሾመበት ሃገር ከሚገኙ ሌሎች አምባሳደሮች ጋር የሚኖረው ግንኙነት ላይ ትንሸም ቢሆን አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል'' ይላሉ። አቶ ነብያት ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ የሌሎች ሃገራት አምባሳደርን እንደ ምሳሌ ሲያስረዱ፤ በኢትዮጵያ የበርካታ ሃገራት ኤምባሲዎች መኖራቸውን አስታውሰው፤ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ጽ/ቤት በሚያዘጋጃቸው ሥነ-ስርዓቶች የሹመት ደብዳቤዎችን እንደሚያቀርቡ ተናግረው፤ እስከዚያው ግን ለውጪ ጉዳይ ደብዳቤያቸውን እስካስገቡ ድረስ ሥራ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል። አቶ ነብያት በአሥመራ ይህን መሰል አይነት ፕሮግራም በቅርብ አለመካሄዱን በመጥቀስ፤ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ከሾመቻቸው አምባሳደሮች መካከል የሹመት ደብዳቤያቸውን ለየሃገራቱ ርዕሰ ብሄሮች ያላቀረቡ ሌሎች አምባሳደሮች መኖራቸውንም ጠቁመዋል። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት የዛሬ ዓመት ገደማ ነበር። ቀደም ሲል በአየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፤ አምባሳደር ሆነው ከመሾማቸው በፊት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ ሚንስትር እንዲሁም የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር በመሆን አገልግለዋል።
news-55183656
https://www.bbc.com/amharic/news-55183656
ቴክኖሎጂ ፡ ፌስቡክ ለስደተኞች ሥራ ሰጥቷል ስትል አሜሪካ ከሰሰች
የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ፌስቡክ ለስደተኞች ቅድሚያ በመስጠት አሜሪካውያንን በድሏል ሲል ከሷል።
ክሱ እንደሚያመለክተው ማሕበራዊ ድር አምባው 2600 የሚሆኑ ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አሜሪካውያን መቅጠር ሲገባው አልቀጠረም። በምትኩ ጊዜያዊ ቪዛ ላላቸው የውጭ ሃገራት ዜጋዎች ሥራው ተሰጥቷል ሲል የክስ መዝገቡ አስነብቧል። ፌስቡክ የቀረበበትን ክስ ቢያጣጥልም ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሠራ እንደሆነ ግን ተናግሯል። ፌስቡክና ሌሎች ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ኤች-1ቢ የተሰኘውን ቪዛ በመጠቀም ከሌሎች ሃገራት ምጡቅ አእምሮ ያላቸውን ሰዎች ያስመጣሉ። ሐሙስ ዕለት ፍትህ ሚኒስቴር ያቀረበው ክስ ፌስቡክ ሆን ብሎ የሥራ ቅጥር ሲያወጣ ኤች-1ቢ ቪዛ ላላቸው ሰዎች እንዲሆን አድርጎ ነው ይላል። ሚኒስቴሩ ለሁለት ዓመት ምርመራ ካደረግኩ በኋላ ነው ክሱን የመሠረትኩት ብሏል። ክሱ ተሰሚነት የሚያገኝ ከሆነ ፌስቡክ "ሥራ ለነፈጋቸው አሜሪካዊያን" መክፈል የነበረበትን ያክል ገንዘብ ሊቀጣ ይችላል። የሚኒስቴሩ ሠራተኞ የሆኑት ጠበቃ ኤሪክ ድራይባንድ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መሰል ሕገ ወጥ የሆነ ተግባር ከመከወን እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። የባይደን የቤት ሥራ እስካሁን ሽንፈታቸውን በፀጋ ያልተቀበሉት ዶናልድ ትራምፕ ለመጪው የባይደን አስተዳደር የተዝረከረከ ሥራ ትተው ለማለፍ የፈለጉ ይመስላል ትላለች የቢቢሲዋ ተንታኝ ሳሚራ ሁሴን። ትራምፕ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አዳዲስ ሕግጋትና ፖሊሲዎች እያወጡ ይገኛሉ። ባለፉት አራት ዓመታት ኤች-1ቢ ቪዛ ያላቸው ሰዎችን ኩባንያዎች እንዳይቀጥሩ ትራምፕ ያልቆፈሩት ድንጋይ የለም። ምንም እንኳ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በመሰል የቪዛ ዓይነት ሰዎችን በመቅጠር የታወቁ ቢሆኑም ትራምፕ ግን ቅድሚያ ለአሜሪካዊያን በሚለው አጀንዳቸው አላፈናፍንም ብለዋቸዋል። ፌስቡክ ላይ የቀፈበውም ክስ ይህን የተንተራሰ ነው። ትራምፕ ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ያላቸወ ግንኙነት የሻከረ ነው። ፌስቡክን የመሰሉ ግዙፍ ማሕበራዊ ድር አምባዎች ሃሰተኛ መረጃ በአምባቸው እንዲሰራጭ ፈቅደዋል እየተባሉ ይተቻሉ። ይህን ትችት የሚያሰሙት ዴሞክራቶች ብቻ ሳይሆኑ ሪፐብሊካንም ጭምር ናቸው። ፌስቡክ ግን ይህን ክስ ያጣጥላል። ተጠቃሚዎች እንደፈቀዳቸው እንዲጠቀሙ ልንፈቅድ ይገባል ይላል።
51670264
https://www.bbc.com/amharic/51670264
በናይጄሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ተገኘ
ናይጄሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያውን ሰው ሪፖርት አደረገች።
ታማሚው ጣሊያናዊ ዜግነት ያለው ሲሆን ናይጄሪያ ውስጥ እንደሚሰራና ከሶስት ቀን በፊት( ፌብሪዋሪ 25) ከሚላን ወደ ሌጎስ መምጣቱ ተነግሯል። የናይጄሪያ ጤና ጥበቃ ባለሰልጣናት ግለሰቡ ጤንነቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረው፣ ሌጎስ በሚገኝ የሕክምና ተቋም ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። • በኮሮናቫይረስ ምክንያት የግል አውሮፕላን ተፈላጊነት ጨመረ • ሳዑዲ አረቢያ ወደ አገሯ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ጉዞዎችን አገደች • "ቻይና፣ ዉሃን በመሆኔ ደህንነቴ የተጠበቀ ነው" ኢትዮጵያዊው ተማሪ የናይጄሪያ መንግሥት የብሄራዊ ድንገተኛ ጊዜ እቅድ አውጥቶ አሁን ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራው በመግባት የመከላከል ሥራውን መስራት መጀመሩን ተናግረዋል። ከታማሚው ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉት በአጠቃላይ መለየት መጀመራቸውን ባለሰልጣናቱ ፀጨምረው አስረድተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወሳኝ ነጥብ ላይ መድረሱን በመግለጽ አገራት አስፈላጊውን የመከላከል እርምጃ ሁሉ እንዲወስዱ አሳስቧል። ከቻይና ውጪ በአሁን ወቅት ኢራንና ጣሊያን የወረርሽኙ መገኛ ማዕከል ሆነዋል። በኢራን ከፍተኛ ባለሰልጣናት ሳይቀር በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰውም ሞቷል። በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ በሚገኙ ከ50 በላይ ሀገራት 80 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ይታወቃል። እስካሁን ድረስ ከቻይና ውጪ 60 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በቻይና በቫይረሱ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል። በአፍሪካ ከናይጄሪያ ውጪ በአልጄሪያ እንዲሁም ግብጽ በቫይረሱ የተያዘ ሰው መገኘቱ ይታወሳል።
news-56198760
https://www.bbc.com/amharic/news-56198760
ኪነ ጥበብ፡ በ40 ተከታታይ ክፍል የተጠናቀቀው የእግር እሳት ድራማ
የእግር እሳት ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በ40 ተከታታይ ክፍል ሲተላለፍ ቆይቶ ባሳለፍነው ሳምንት ተጠናቋል።
የእግር እሳት በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ፍትህን ፍለጋ በሚኳትኑ ገጸ ባህርያት ልብ አንጠልጣይ ድርጊቶች የተሞላ ነበር። በዚህም የበርካቶችን ዐይንና ልብ መያዝ እንደቻለ ይነገራል። የድራማው ደራሲና ዳሬክተር አብርሃም ገዛኸኝ በአንድ ወቅት ለሥራ ወደ ለንደን አቅንቶ በነበረበት ወቅት ያነበበው መጽሐፍ ለድራማው መነሻ እንደሆነው ይናገራል። መጽሐፉ ኒኮላስ ቤሌክ በሚለው የብዕር ስሙ የሚታወቀው ጸሐፊ የሴሲል ደይ ልዊስ 'ዘ ቢስት መስት ዳይ' ነው። "መፅሐፉን ሳነበው በመጀመሪያዎቹ አራት ገጾች ውስጥ የድራማው ተዋንያኖቹ ምን እንደሚሆኑ፤ ምን እንደሚፈልጉ አወቅኩኝ" ይላል አብርሃም። የድራማው አፅመ ታሪክም በሚገባ ተዋቅሮ፤ አጓጊ እና ኢ-ተገማች በሆኑ የታሪክ ፍሰቶችና ሁነቶች ተሰናስሎ ነበር ለተመልካች የቀረበው። አብርሃም እንዳለው ድራማው ከታሪኩ ጥንስስ ጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ አራት ዓመታትን ፈጅቷል። አራት ሚሊየን ብር ገደማም ወጥቶበታል ብሏል። የእግር እሳት በታሪኩ፣ በዳሬክቲንጉ፣ በቀረጻውም ሆነ በተዋንያኑ ብቃት በርካቶች አወድሰውታል። ይህ ግን በቀላሉ የመጣ አልነበረም። አብርሃም ወትሮም ቢሆን ተከታታይ ድራማዎችን ሲመለከት "ቢሻሻል" ሲል የሚያወጣቸውና የሚያወርዳቸው ሃሳቦች ነበሩት። አሁንም ግን "በውስጤ ያሰብኩት ከዚህ የተሻለ ነበር። ያንን ማውጣት አልቻልኩም " ይላል፤ የገንዘብ እና የአቅም እጥረት ባሰበው ልክ እንዳይሰራ ተግዳሮት እንደነበሩበት በመግለፅ። ሆኖም ድራማው "በአቀራረቡና በአተራረኩ የተለየ ነበር" ብሏል። የእግር እሳት ድራማ ታዋቂና አዳዲስ ተዋንያንን ያሳተፈ ነው። የተዋንያንን መረጣ በተመለከተም ዋናው ገጸ ባሕርይ [አንተነህ] ከተመረጠ በኋላ ታሪካዊ ዝምድና ያላቸውን በመልክ እና በፊት አገላለጻቸው መመሳሰል እንደመረጣቸው አብረሃም ይናገራል። መረጣው ዋናው ገጸ ባሕርይ ከሌሎች ገጸባህርያት ጋር ባለው ታሪካዊ ትስስር መመሳሰል ላይ የተመሰረተ ነው። ብርሃኑ ድጋፌ እና መስከረም አበራ 'የእግር እሳት' መሪ ተዋንያን ምን ይላሉ? በድራማው ላይ ዋና ገጸ ባህርይውን አንተነህን ወክሎ የተጫወተው ብርሃኑ ድጋፌ፤ "የእግር እሳት ሲጀመር አልቆ ነው የተሰራው" ይላል። እርሱ እንደሚለው ማን ምን እንደሚሰራ እስከመጨረሻው ታውቆና በቂ ዝግጅት ተደርጎበት የተሰራ ነው። ታሪኩም ቀድሞውኑ በወረቀት ላይ ጥንቅቅ ብሎ በማለቁ ድራማውን የተለየ እንደሚያደርገው ገልጿል። ብርሃኑ በድራማው የተሳተፉ ባለሙያዎችም ሥራቸውን ጠንቅቀው መሥራታቸው ድራማው በተገባው ጊዜና ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አድርጎታል ይላል። ብርሃኑ ድጋፌ በአብርሃም ገዛኸኝ ድርሰት ላይ ሲሰራ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። "ትውልድን የሚያስተምሩ ታሪኮች ላይ መስራት ፍላጎቴ ነው" የሚለው ብርሃኑ፤ ከእዚህ ቀደም 'የነገን አልወልድም' በተሰኘው የአብርሃም ድርሰት በሆነው ፊልም ላይም ተውኗል። በድራማው የልዕልናን ገጸባህርይ ወክላ የተወነችው ተዋናይት መስከረም አበራ በበኩሏ፤ የእግር እሳትን "ምዕራፉ አጭር የሆነ፣ ሴራው በአቀራረፅና በታሪኩ ለየት ባለ በድርጊት የተሞላ ድራማ ነው" ስትል ትገልጸዋለች። ገጸ ባህሪዋ ልዕልና የተለያዩ ገጸባህርያትን ወክላ የምትጫወት በመሆኗም ፈታኝ እንደነበር ትናገራለች። "የታሪኩ አካሄድ ያልተጠበቀ ነበር። መልዕክቱም ጥሩ ነበር" ትላለች። መስከረም የእግር እሳት ድራማ የተለያዩ የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎችን ለመስራትም እድል ፈጥሮልኛል ብላለች። ደራሲና ዳሬክተር አብርሃም፤ ከዚህ በፊት የውጭ የባህል ተፅእኖ ያለባቸው ተከታታይ ድራማዎች በአንድ ማኅበረሰብ ባሕል ላይ የሚፈጥረው ለውጥ ላይ ያተኮረ የሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ጽሁፍ ሰርቷል። በዚህ ጥናቱም ማኅበረሰቡ ከተከታታይ ድራማዎች የወደዳቸውንና የጠላቸውን ነገሮች መለየት መቻሉን አስረድቷል። የጥናቱ ተደራሾች፤ ልዩ ገፀ ባህሪያትን፣ የተጎዱ ሰዎች ታግለው ሲያሸንፉ፣ ፍትህ ሲከበር ማየት እንደሚሹ ከመመረቂያ ጽሁፉ መረዳት ችሏል። ይህም በተወሰነ መልኩ ለድራማው ግብዓት እንደሆነው ጠቅሷል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መገኘቱ የተረጋገጠው ድራማው በእረፍት ላይ በነበረበት ጊዜ በመሆኑና በርካታ ክፍሎች ቀድመው በመዘጋጀታቸው ወረርሽኙ በድራማው ላይ እምብዛም ተፅዕኖ አላደረሰበትም። በእርግጥ ሁለት ተዋንያን በወረርሽኙ ተይዘው ከበሽታው አገግመዋል። 'የአስከሬን ሰብሳቢው' ታሪክ በ1969 ዓ.ም [እአአ1977] በኢትዮጵያ የሆነ ነው። ወጣቶች በአደባባይ በየቦታው በግፍ በሚገደሉበት የቀይ ሽብር ዘመን። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት በዚህ ዘመን የሰው አስከሬን በየቦታው እንደዘበት ተጥሎ እየተለቀመ ይነሳ ነበር። ታሪኩም አስከሬን የሚያነሱ የአምቡላንስ ሹፌር የሆኑ አባት ታሪክ ነው። የሌሎችን አስከሬን ሲያነሱ የልጃቸው ሬሳ አግኝተው ማንሳት ያቃታቸው የእኝህ ሹፌር ታሪክ ቀጣዩ የአብርሃም ገዛኸኝ "መሃል ሰፋሪ" የተሰኘው ፊልም ማጠንጠኛ ነው። አብርሃም እንደገለፀልን ይህን ሥራውን፤ ፊልሞች ታሽተውና አድገው የሚወጡበት አፍሪካዊና ዓለም አቀፋዊ የፊልም ቤተሙከራዎች ተቀብለው አሳድገውታል። ፕሮዲዩሰሮችም ፍላጎት እያሳዩ ነው ብሏል። የዚህ ሥራው ፕሮዲዩሰሮች ካናዳዊያን እንደሆኑም ፍንጭ ሰጥቷል። ከዚህም ባሻገር ከወራት በኋላ አስቂኝ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ [ሲትኮም] በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ለዕይታ ለማብቃት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።
51867054
https://www.bbc.com/amharic/51867054
ኬኒያ ወደ ሶማሊያ ሕገወጥ ደም የሚያዘዋውሩ ላይ ምርመራ ጀመረች
የኬኒያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ኬኒያውያን የለገሱት ደም በሕገወጥ መልኩ ወደ ሶማሊያ ይወሰዳል በሚል የቀረበውን ቅሬታ እየመረመርኩ ነው አለ።
የኬኒያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ መግለጫ በርካታ ኬኒያውያንን አስደንግጧል ምርመራው መንግሥታዊ ተቋም በሕገወጥ መልኩ የለጋሾችን ደም መሸጡን ጭምር ያካትታል ተብሏል። በኬኒያ ብሔራዊ የደም ለጋሾች አገልግሎት መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ኃላፊዎችንም ጭምር ያካትታል። • የደም ሻጮችና ለጋሾች ሠልፍ • በደም እጥረት እየተፈተነች ያለቸው ኬንያ • “የአባይ ውሃ ፀበሌ ነው፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ፀበል ነው” ኪሮስ አስፋው የኬኒያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር የሆኑት ሙታኢ ካግዌ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ሊውሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ኬኒያ ለረዥም ዓመታት ከለጋሾች የምትሰበስበው በቂ ባለመሆኑ በደም እጥረት ተቸግራ መቆየቷ ተጠቅሷል። የኬኒያ ደም ለጋሾች አገልግሎት ለ15 ዓመታት ሙሉ በሙሉ በአሜሪካ መንግሥት ሲደገፍ ቢቆይም ድጋፉ ግን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተቋርጧል። ኬኒያ በቂ የደም ክምችት እንዲኖራት ብትጥርም ሳይሳካላት የቆየ ሲሆን ለዚህም እንደምክንያት የተጠቀሰው የአሜሪካ ድጋፍ መቋረጥ እንዲሁም የኬኒያውያን ደም የመለገስ ባህል ዝቅተኛ መሆን ነው። ባለፈው ዓመት ኬኒያ 500ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅዳ ብትንቀሳቀስም ሩብ ያህሉን እንኳ መሰብሰብ ሳትችል መቅረቷ ተገልጿል።
news-48619205
https://www.bbc.com/amharic/news-48619205
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አውሮፕላናቸውን ሸጠው ሕገ-ወጥ ስደትን ሊቀንሱ አስበዋል
የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት አንድሬ ማኑዌል ሎፔዝ ኦብራዶር አውሮፕላናቸውን ሸጠው የሚያገኙትን ትርፍ ሕገ-ወጥ ስደትን ሊከላከሉበት እንደሆነ አሳውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ ሃሳቡን ያመጡት ሃገራቸው ሜክሲኮ ከአሜሪካ ጋር በደረሱት ስምምነት መሠረት ሲሆን ስምምነቱ ሜክሲኮ ከማዕከላዊ ወደ አሜሪካ የሚደረገውን ጉዞ መግታት የምትችል ከሆነ የዶናልድ ትራምፕ መንግሥት ሜክሲኮ ላይ የጫነውን ቀረጥ እንደሚቀንስ ያትታል። ፕሬዝዳንቱ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው ወቅት የፕሬዝዳንቱን አውሮፕላን ሸጬ ደሃ ሜክሲኳዊያንን ሕዝብ እረዳለሁ ሲሉ ቃል ገብተው ነበር። • ከፍተኛ መጠን ያለው ዕፅ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር ተያዘ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር የተሰኘው የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን 150 ሚሊዮን ዶላር [ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ገደማ] ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ስማቸው የረዘመባቸው የሃገሪቱ ሰዎች 'አምሎ' ብለው የሚጠሯቸው ፕሬዝዳንት ሎፔዝ አውሮፕላኑን ሸጨ እኔ ከሕዝብ ጋር ተጋፍቼ እሄዳለሁ ሲሉ ነበር ቃል የገቡት። አውሮፕላኑ ላለፉት ጥቂት ወራት ካሊፎርኒያ የሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ለሻጮች ክፍት ሆኖ ቆይቷል። ሜክሲኮ የፕሬዝዳንቱን አውሮፕላን አክሎ ሌሎች 60 የመንግሥት አውሮፕላኖችንና 70 ሄሊኮፕተሮችን ለመሸጥ ቆርጣ ተነስታለች። • "አቶ ጌታቸው አሰፋን ሜክሲኮ አግኝቻቸው ነበር" ነጋ ዘርዑ ሜክሲኮ ሶስተኛዋ ሃያል የአሜሪካ የንግድ አጋር ስትሆን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበራት እሰጥ-አገባ ምክንያት ከሜክሲኮ የሚመጡ ምርቶች ላይ ቀረጥ ተጭኖ ነበር። ሜክሲኮ አውሮፕላኗን ከመሸጥ አልፋ 6 ሺህ ገደማ ፖሊሶችን ወደ ጓቲማላ ልካ ሕገ-ወጥ ስድትን ለመግታት ቃል ገብታለች። የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን መሸጥ ለበርካታ ሜክሲኳውያን የተዋጠ አይመስልም፤ በሕዝብ ገንዘብ የተገዛ ንብረትን እንዴት ተደርጎ? እያሉም ይገኛሉ። • አሜሪካና ሜክሲኮን የሚለየው ግንብ መገንባት ተጀመረ
news-52724496
https://www.bbc.com/amharic/news-52724496
የትዋይላይት ፊልም ተዋናይ ግሪጎሪ ታይሪና የሴት ጓደኛው ሞተው ተገኙ
በታዋቂው 'ትዋይላት' ፊልም ላይ የተወነው ግሪጎሪ ታይሪ ቦይስና የሴት ጓደኛው ላስ ቬጋስ ውስጥ ሞተው ተገኙ።
ተዋናዩ በጎርጎሳውያኑ 2008 በተሰራው በመጀመሪያው ክፍል ትዋይላይት ላይ በመተወን ዝናን አትርፎ ነበር። ግሪጎሪ 30 ዓመቱ ሲሆን የሴት ጓደኛው ናታሊ አዴፖጁ ደግሞ 27 ዓመቷ ነው። ፖሊስ ምንም እንኳን ምርመራውን ባያጠናቅቅም ያሉትን ሁኔታዎች በመገምገም ወንጀል እንዳልተፈፀመባቸው አስታውቋል። ግሪጎሪ ቦይስ በቫምፓየር (የሰውን ደም እየመጠጡ በሚኖሩ) ህይወት ላይ በሚያጠነጥነው የትዋይላይት ፊልም ላይ ታይለር የሚባልን ገፀ ባሕሪይ ወክሎ ተጫውቷል። በአንደኛው በማይረሳ ትዕይንት ላይ መኪናውን እያበረረ ቤላ የምትባለውን ገፀ ባሕሪይ ሊገጫት ሲል ዋነኛው ተዋናይ ኤድዋርድ የተባለው ቫምፓየር በባዶ እጁ መኪናውን ሲያቆመው ያሳያል። ሞቱ ከተሰማ በኋላ በርካቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሃዘናቸውን የገለፁ ሲሆን ወንድሙ ክሪስ ዌይንም "ወንድሜ አብረኸኝ ብትሆን እንዴት ደስ ይለኝ ነበር። ዓለም ድንቅ የሚባል ሰው አጣች" በማለት ልቡ መሰበሩን በፌስ ቡክ ገፁ ላይ አስፍሯል። እናቱም ሊዛ ዌይን "ያላንተ ህመም ላይ ነኝ። ተበጣጥሻለሁ፤ ሁሉ ነገር ጠፍቶብኛል። ከፍተኛ የልብ ስብራት ላይ ነኝ" በማለት ሃዘኗን የገለፀች ሲሆን አክላም "በሆነ ምክንያት ሲጨንቀኝም ሆነ ስረበሽ መልዕክት እልክልሃለሁ ወይም እደውልሃለሁ። አንተም በምላሹ 'እማ ሁሌም ከጎንሽ ነኝ፤ ችግሩን አብረን እንጋፈጠዋለን' ትለኛለህ። ልጄ ለምን ትተኸኝ ሄድክ?" ብላለች። "ከዚህ በኋላ መቼም ቢሆን እቅፍ አድርህ አትስመኝም። እነዚህንም ቃላቶች ደግሜም አልሰማቸውም። ልጄ እወድሃለሁ። ስብርብር ብያለሁ። በጣም እወድሃለሁ ግሬጊ፤ የኔ ማር" በማለት እናቱ አንጀት የሚበላ ሃዘኗን ገልጻለች። ግሪጎሪና ናታሊ የዶሮ ጥብስ የሚሸጥበት ትልቅ ሬስቶራንት የመክፈት እቅድ እንደነበራቸውና፤ ለማጠናቀቅም ጥቂት እንደቀራቸው እናቱ ተናግራለች። "በአጭሩ የተቀጨው" ግሪጎሪ የአስር ዓመት ሴት ልጅ ያለችው ሲሆን፤ የሴት ጓደኛው ናታሊ ደግሞ ህፃን ወንድ ልጅ አላት። የናታሊን ቀብር የሚያስፈፅሙት በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ "ናታሊ ብዙ ዕቅድ የነበራትና ህይወትንም ገና እየጀመረች ነበር። እንዲህ በአጭሩ ህይወቷ በመቀጨቷ አዝነናል" ብለዋል። የላስ ቬጋስ ባለስልጣናት ዩኤስ ኤ ቱዴይን ጨምሮ ለተለያዩ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የአሟሟታቸው ምክንያትን በተመለከተ ገና የላብራቶሪ ውጤት እየተጠበቀ ነው በማለት አስረድተዋል። የፖሊስ ቃለ አቀባይ ላሪ ሃድፊልድ ለላስ ቬጋስ ሪቪው ጆርናል እንደተናገሩት "አሟሟታቸው ወንጀልን አያመላክትም" ብለዋል።
53864757
https://www.bbc.com/amharic/53864757
የአንበጣ መንጋ በ2011 ክረምት ወራት 3.5 ሚሊዮን ኩንታል እህል ላይ ጉዳት አድርሷል
ሰኔ 2011 አጋማሽ ላይ ከየመን በሶማሌ ላንድ አድርጎ ወደ አፋር እና ሶማሌ ክልል የገባው የአንበጣ መንጋ ሊገኝ ከታቀደው ምርት 2 በመቶውን ወይንም 3.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማውደሙ ተገለጸ።
መንጋው ከ70 እሰከ 100 ፐርሰንት ምርት ሊያጠፋ ይችል ነበር ያሉት በግብርና ሚንስቴር የዕጽዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ከበደ በተደረገው ርብርበብ የደረሰው ጉዳት አነስተኛ ሊሆን ችሏል ብለዋል። የአንበጣ መንጋው ሶማሌ እና አፋር ክልል ላይ የመከላከል ሥራ ሲሠራ ቢቆይም ከአፋር የተረፈው ወደ ወሎ እና ደቡብ ትግራይ ወጥቶ ማሳ ላይ ጉዳት አድርሷል። ከሶማሌ ክልል በመነሳት ደግሞ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ላይ ጉዳት አድርሶ ነበር ብለዋል። ባለፉት ወራት በተሠራው የመከላከል ሥራ ዓመቱን ሙሉ በግጦሽ እና ቁጥቋጦ እንጂ በሰብል ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ሲሉ ገልጸዋል። ሆኖም በግጦሽ እና ቁጥቋጦ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ቦታዎቹ ስለማያመቹ ማጥናት እንዳልተቻለ አስታውቀዋል። ሰኔ 2011 ጀምሮ በአፋር እና በሶማሌ ክልል የመከላከል ሥራ ቢሠራም፣ ለመድረስ አስቸጋሪ ከሆኑ አካባቢዎች ላይ አንበጣው በመነሳት በምስራቅ ኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ እንዲሁም በምዕራብ አማራ ወሎ፣ ቃሉና አርጎባ አካባቢዎች መጠነኛ የሆነ የምርት መቀነስ አድርሶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል። በሁለተኛ ዙር ደግሞ ህዳር እና ታህሳስ ላይ በምስራቁ የሃገሪቱ ክፍል የተከሰተ ቢሆንም ሰብል በመሰብሰቡ ጉዳት አላደረሰም። በበልግ ምርት ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ በዳሰነች፣ ኛንጋቶም፣ ኦሞ እና የኬንያ አቅራቢያ አካባቢዎች ቢከሰትም በበልግ ሰብል ላይ ጉዳት ሳያደርስ መከላከል መቻሉን አቶ ታምሩ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በ2012 የክረምት ወራት በአፋር እና በሶማሌ ላይ በሚገኙ ሰፊ አካባቢዎች፣ በአውሮፕላን የተጋዘ የአሰሳ እና መከላከል በሰው ሃይል እና በመኪና እየተሠራ ነው። "አምና በጣም ጥሩ የመከላከል ሥራ ተሰርቷል። ሁሉንም የሚያስመሰግን ሥራ ነው። ከአምና የሄሊኮፕተር እና ተሽከርካሪ ቁጥር ጨምረናል። የክልሎችም ተሳትፎ የተሻለ ነው ዘንድሮ" ብለዋል። የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ሰዎችን ከማሰማራት ጎን ለጎን በእጅ የሚያዙ መሣሪያዎች፣ በርካታ መኪናዎች፣ 4 ለኬሚካል ርጭት የሚሆኑ እና ሁለት የአሰሳ ሄሊኮፕተሮች ዝግጁ ሆነዋል። "አሁን በድሬዳዋ የመከላከል ቤዝ አንድ አውሮፕላን አለ። በሰሜን ምስራቅ ኮምቦልቻም አንድ አውሮፕላን አለ። በጅቡቲ እና ከኤርትራም የሚገባም ስለሚኖር ሰመራም አለ። ሰፊ የመከላከል ሥራው አለ፤ አሁንም ይቀጥላል" ብለዋል። አሁን በዋናነት አንበጣው ያለው በሃገሪቱ ምስራቅ እና ሰሜን ምስራቅ በሶማሌ እና አፋር ክልሎች ነው። ከሶማሌ የሚነሳው አንበጣ ባሌ እና ሐረርጌ አካቢዎችን የሚወር ሲሆን ከአፋር የሚነሳው ደግሞ ወሎ እና ደቡብ ትግራይ ነው የሚወረው። የመከላከል ስራውም በሁለት ሄሊኮፕተር እና በአንድ የአሰሳ አውሮፕላን ሶማሌ እና አፋር ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው ያለው" ሲሉ አስረድተዋል። አንድ አቶ ታምሩ ከሆነ በቅርብ ጊዜም በኬንያ በኩል ከቱርካና ሐይቅ ተነስቶ ደቡብ ኦሞ በኩል የሚገባ አምበጣ ስላለ እሱን ለመጠባበቅ አርባምንጭም ላይ ሄሊኮፕተር ተዘጋጅቷል። መረጃ ለመለዋወጥ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በቅርበት እየተሠራ ሲሆን በተለይ በአፋር ክልል ዳጉ የሚባለው የመረጃ መለዋወጫ ባህላዊ ዘዴን፣ እንዲሁም በሶማሌ እና በኦሮሚያ ደግሞ ስካውቶችን በመጠቀም መረጃዎችን እያገኘን የሚወሰደው እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ገልጸዋል። የመከላከል ሥራው 'ጥሩ' የሚባል ቢሆንም ከሌሎች ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ እና ከኢትዮጵያም ወደ ጎረቤት ሃገራት የሚንቀሰቀስ አንበጣ መንጋ መኖሩን ገልጸዋል። ሆኖም ከሚወጣው ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው ይበልጣል ብለዋል። "በጣም ጥሩ ስራ ቢሰራም ወደ ኤርትራ እና ወደ ሌላም የሚያመልጥ ይጠፋል አይባልም። ከኬንያ፣ ከሶማሌ ላንድ እና ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ነው። በንፋስም ወደ ኤርትራ፣ ሰሜንና እና ወደ ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል የመውጣት ዕድል አለው" ብለዋል። ችግሩን ለመቆጣጠር እንዲሁም ወደ ሌሎች አገራት እንዳይዛመት እና ጉዳት እንዳያደርስ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚሰራው ጠንካራ የመከላከል ሥራ ጎን ለጎን ከጎረቤት አገራት ጋር የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ዓለም አቀፉን የምግብና ግብርና ድርጅት /ፋኦ/ ያካተተ የጋራ ማዕከል ተቋቁሟል። በማዕከሉ በኩል የቅድመ ትንበያ መረጃዎች ለአካባቢው አገራት አበየጊዜው እየተሰራጨ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።
news-52873332
https://www.bbc.com/amharic/news-52873332
የፌስቡክ ሠራተኞች በመሥሪያ ቤታቸው ድርጊት ተበሳጩ
የፌስቡክ ሠራተኞች ድርጅታቸው የዶናልድ ትራምፕን ‹‹ያልተገባ›› የፌስቡክ 'ፖስት' አለመሰረዙ ወይም ማስጠንቀቂያ አለመጻፉ እንዳበሳጨቸው በይፋ ተናገሩ፡፡
ባለፈው ሳምንት ዶናልድ ትራምፕ በሜኔሶታ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ሕዝብን ከሕዝብ ሊያጋጭ የሚችል የተባለ መልእክት በትዊተር ገጻቸው ለጥፈው ነበር፡፡ ትዊተር መልእክቱ ላይ ‹‹ህውከት ቀስቃሽ›› እንደሆነ የሚያመላክት ምልክት በማድረጉ ፕሬዝዳንቱን ማስቆጣቱ ይታወሳል፡፡ ያው የፕሬዝዳንቱ የማኅበራዊ መዲያ መልእክት ግን ትራምፕ ፌስቡክ ገጻቸው ላይ ጽፈውት ሳለ ድርጅቱ ምንም እርምጃ አለመወሰዱ የገዛ ሰራተኞችን ቅር አሰኝቷል፡፡ ትዊተር በወቅቱ የፕሬዝዳንቱ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ የጻፉት ነገር ተገቢ አለመሆኑን ለማሳየት ከመልእክቱ ጎን ‹‹ሁከትን የሚያበረታታ›› የሚል የማስጠንቀቂያ ምልክት አድርጎበት ነበር፡፡ ፌስቡክ ግን ይህንኑ ሁከት ቀስቃሽ የተባለ የፕሬዝዳንቱን መልእክት የማንሳትም ሆነ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ሙከራ አለማድረጉ ሲያስተቸው ቆይቷል፡፡ አንዳንድ የፌስቡክ ኩባንያ ሠራተኞች "በድርጅታችን አፍረናል" ሲሉ በይፋ ተናግረዋል፡፡ የፕሬዝዳንቱ ሁከት ቀስቃሽ የተባለው የማኅበራዊ ሚዲያ መልእክት ‹‹ዝርፍያ ሲጀመር ተኩሱ ይንጣጣል›› የሚል ይዘት ነበረው፡፡ ይህ አባባል በታሪክ ጥቁሮች ላይ ከተደገ ጭቆናና ግድያ የሚተሳሰር "ውስጠ ወይራ መልእክት" እንዳለው ይነገራል፡፡ የፌስቡክ መሥራች ማርክ ዙክርበርግ ይህ የፕሬዝዳንቱ መልእክት ፖሊሲያችንን አይቃረንም ሲል የዶናልድ ትራምፕን መልእክት መርዘኝነት ለማርከስ ሞክሯል፡፡ የማርክ ዙከርበርግ ሠራተኞች ግን ተቃውሟቸውን ለመግለጽ የመሥሪያ ቤታቸውን "በምናብ ለቆ የመውጣት ተቃውሞ" አድርገዋል፡፡ ይህም የሆነው በየኮምፒውተር ገጾቻቻቸው የጋራ መልእክት መለዋወጫ መድረክ ላይ "በተቃውሞ ምክንያት ከቢሮ ለቅቄ ወጥቻለሁ" የሚል መልእክት በመጻፍ የተደረገ ተቃውሞ ነበር፡፡ ላውረን ታን የተባለች የድርጅቱ ሰራተኛ "በመሥሪያ ቤቴ ድርጊት እጅግ አፍሪያለሁ፤ ምንጊዜም ዝምታ የወንጀል ተባባሪነት ነው፡፡ ዝም አልልም" ስትል ጽፋለች፡፡ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ ተቃውሟቸውን በድርጅቱ የውስጥ መገናኛ ዘዴ ለመግለጽ ተገደዋል፡፡ የፌስቡክ ኩባንያ ቃል አቀባይ በበኩሉ "የሰራተኞች ሕመምና ቅሬታ ይገባናል፤ ዋናው እንዲህ በግልጽ መነጋገራችን ነው፡፡ ሰራተኞቻችንን ቅሬታቸውንም ሆነ ተቃውሟቸውን እንዲህ በግልጽ እንዲናገሩ ነው የምንፈልገው፤ ገና ብዙ አጨቃጫቂ ነገሮች ከፊታችን ይጠብቁን የለ?" ብሏል፡፡ ይህን የፕሬዝዳንቱን አወዛጋቢ ንግግር ተከትሎ ባለፈው ዓርብ ዶናልድ ትራምፕና ማርክ ዙከርበርግ በጉዳዩ ላይ በስልክ የተወያዩ ሲሆን ዝርዝር የንግግራቸው ይዘት ግን ይፋ አልተደረገም፡፡ ሁለቱም ውይይታችን ፍሬያማ ነበር ቢሉም ፍሬያማ ያሰኘው ምኑ እንደሆነ ግን ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡ ይህን አተካራ ተከትሎ ፌስቡክ ከውስጥም ከውጭም የተነሳበትን ቅሬታ ለማለዘብ ይመስላል 10 ሚሊዮን ዶላር በፍትህ ሂደት ለሚፈጠር ዘረኝነትን ለመዋጋት ይሆን ዘንድ እርዳታ አድርጊያለሁ ሲል ይፋ አድርጓል፡፡ "እንሰማለን፣ እናያለን ከናንተው ጋር ነን" ሲል የጸረ ዘረኝነት ተቃውሞውን እንደሚደግፍ አሳውቋል፡፡ "የጥቁሮችን ድምጽ እናስተጋባለን፤ ዘረኝነትን እንጸየፋለን ከጎናችሁ እንቆማለን" ያለው ፌስቡክ 10 ሚሊዮን ዶላሩን ለምን እንዴትና ለማን እንደሚሰጥ በግልጽ ያስቀመጠው ነገር የለም፡፡
news-46190740
https://www.bbc.com/amharic/news-46190740
አምነስቲ የማይናማሯን መሪ ሳን ሱ ኪን ከፍተኛ የተባለውን ሽልማት ነጠቀ
አምነስቲ የማይናማሯን መሪ ሳን ሱ ኪ ከፍተኛ የሚባለውን "የህሊና አምባሳደር" ሽልማት ነጥቋቸዋል።
የሰላም የኖቤል ሽልማት አሸናፊዋ ፓለቲከኛ ይህንን ሽልማት የተቀበሉት በአውሮፓውያኑ 2009 ሲሆን በወቅቱም በቤት እስር ላይ ነበሩ። የመብት ተሟጋቹ ድርጅት እንዳስታወቀው ይህንን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደው በአገሪቱ ውስጥ የሮሂንጃን ጥቃት መከላከል ባለመቻላቸው እንደሆነ አስታውቋል። ከነዚህ ውስጥ 700 ሺ ህዝብ በላይ ወታደራዊ ጥቃትን በመፍራት ሸሽተዋል። •የካናዳ ፓርላማ የሳን ሱ ኪን የክብር ዜግነት ገፈፈ •የበርማ ሙስሊሞች ጩኸት! •ሙገሳ እና ወቀሳ የተፈራረቀባቸው ሳን ሱ ኪ የ73 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋዋ አን ሳን ሱ ኪ ይህ ሽልማት በቅርብ ጊዜ ካጧቸው ሽልማቶች አንዱ እንደሆነም ተገልጿል። "የሰላም፣ የፅናትና የግለሰቦችን ሰብዓዊ መብት በመከላከል ረገድ የነበረሽ ተምሳሌነት አሁን የለም። ያንንም ስለማትወክይ እናዝናለን" በማለት የአምነስቲ ዋና ፀሐፊ ኩሚ ናይዱ ለማይናማሯ መሪ በፃፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል። ጨምረውም "በሮሂንጃ ላይ የደረሰውን ጭካኔያዊ ተግባርና የግፉን መጠን መካዷ ሁኔታውን ለማስተካከል ምንም ፍላጎት እንደሌለ አሳይ ነው" ብለዋል። ምንም እንኳን የተባበሩት መንግሥታት ባደረገው ምርመራ መሪዋ ቀጥታ በባለፈው ዓመት የሮሂንጃ የዘር ጭፍጨፋ ቀጥታ ተሳታፊ አለመሆናቸውን ቢያረጋግጥም፤ ስልጣናቸውን በመጠቀም በሰራዊቱ የደረሱ ግድያዎችንና መደፈሮችን ማስቆም እንደተሳናቸው ገልጿል። በአንድ ወቅት አምነስቲ የዲሞክራሲ ቁንጮ ብሏቸው የነበረ ሲሆን፤ ይህንንም ውሳኔ ያስተላለፈው የአን ሳን ሱ ኪ የቤት ውስጥ እስር ስምንተኛ አመት ክብረ በዓል ላይ ነው። ለዲሞክራሲ ያደርጉት በነበረው ትግል የማይናማር አምባገነን መንግሥት ለ15 ዓመታት ያህል በቤት ውስጥ እስር አቆይቷቸዋል። በዚህም ምክንያት የተለያዩ መንግሥታት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ክብራቸውን ለግሰዋቸው ነበር።
news-44479065
https://www.bbc.com/amharic/news-44479065
አንስታይን ቻይኖችን "ቆሻሾች" ሲል ተሳድቧል
አልበርት አንስታይን ቻይናዎችን "ቆሻሾች" ብሏቸዋል፤ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ስመጥር ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ዘረኛና መጤ-ጠል እንደነበረ እየተዘገበ ነው።
ይህ የታወቀው በቅርቡ በታተመው የሳይንቲስቱ የገዛ የጉዞ ማስታወሻዎች ላይ ነው። ይህ አቻ ያልተገኘለት ሳይንቲስት በዚህ ደረጃ ዘረኛና መጤ-ጠል (xenophobic) እንደነበር የሚያሳብቁ በርከት ያሉ አንቀጾች በማስታወሻው ላይ ሰፍረው መገኘታቸው ዓለምን ማነጋገር ይዟል። እንደ ጎርጎሮሲያዊያን አቆጣጠር ከጥቅምት 1922 እስከ መጋቢት 1923 የተጻፉት የግል ማስታወሻዎቹ ኤንስታይን በኢስያ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ቆይታው ያስተዋላቸውን ነገሮች የከተበበት ነበር። ጥቅልና ጅምላ ኮናኝ የሆኑት እነዚህ ማስታወሻዎቹ እሱ በተጓዘባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦችን ዘረኛ በሆነ መንገድ ይመለከታቸው እንደነበር አሳብቀዋል። ለምሳሌ ቻይናዎችን "የማይደክማቸው ሠራተኞች፣ ቆሻሾችና ደነዝ ሕዝቦች" ሲል በማስታወሻው ገልጧቸዋል። አንስታይን በመጨረሻ ሕይወቱ አሜሪካ ውስጥ ለሰብአዊ መብት ተሟጋች እንደነበር ሲታሰብ ከእነዚህ አስተያየቶቹ ጋር እሱን ለማስታረቅ ከባድ ሆኗል። እንዴትስ በዚህ ደረጃ ዘረኛ ሊሆን ቻለ የሚለው ጥያቄ የብዙዎች ሆኗል። ዘረኝነትን አንስታይን "የነጮች በሽታ" ሲል ነበር የሚጠራው። የኤንስታይን ማስታወሻዎች ራሳቸውን ችለው በመድበል መልክ በእንግሊዝኛ ሲታተሙ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። ኤንስታይን በዚያ ዘመን ከስፔን ተነስቶ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከዚያም በሲሪላንካ ወደ ቻይናና ጃፓን ተጉዞ ነበር። በግል ማስታወሻው ስለ ግብጾች እና የሲሪላንካ ሕዝቦችም በተመሳሳይ ሁኔታ መልካም ያልሆኑና ከርሱ የማይጠበቁ አስተያየቶችን መስጠቱን ከመጽሐፉ መደራት ይቻላል። በሌላ አንቀጽ ስለ ቻይና ሕጻናት ያልተገባ አስተያየት ሲሰጥ "ድንዙዝና ምንም የልጅነት ፈንጠዚያ እንኳ ያልፈጠረባቸው፣ እንዲሁም ፈዛዞች" ብሏቸዋል። ይህም ሳያንሰው ቻይኖች "እንደ በግ በጅምላ የሚነዱ፣ ሰው ሰው የማይሸቱ ሮቦቶች" ብሏቸዋል። "ሴቱን ከወንዱ እንኳ ለመለየት የሚያስቸገር ሕዝብ" ሲልም ተሳልቋል። እጅግ ሲከበር የኖረው ይህ ጎምቱ ሳይንቲስት በናዚዎች ላይ ከሚደርሰው ጭቆና በመሸሽ ወደ አሜሪካ ምድር የገባው በ1933 ነበር። በወቅቱ በጥቁሮችና በነጮች መሐል የነበረውን መከፋፈል ሲመለከት እጅግ መደንገጡ ይነገራል። ጥቁሮችና ነጮች የተለያየ ትምህርት ቤትና የተለያየ ሲኒማ ቤት እንደሚሄዱ ባየ ጊዜም ሐዘን ተሰምቶት ነበር። ይህን ያልተገባና ኋላቀር ዘረኝነት ለመቃወምም በወቅቱ የነበረውን ከጥቁርና ከነጭ የተወለዱ ዜጎች ያቋቋሙት የብሔራዊ ባለቀለም ዜጎች ማኅበርን ተቀላቅሎ ነበር። እንዲያውም በንግግሮቹ ውስጥ አሜሪካ በጥቁሮች ላይ የምታደርሰውን መገለል ጀርመን በነበረበት ወቅት በአይሁዶች ላይ ከሚደርሰው ጭቆና ተመሳሳይ ነው ሲል ይናገር ነበር። ስለ አንጻራዊ ለውጥ Relativity theory አብዝቶ የተጨነቀውና ለዓለም አዲስ እሳቤን ያበረከተው ይህ ጉምቱ ሳይንቲስት አንጻራዊ ዘረኝነቱን በሂደት አራግፎት ይሆን?
news-56954697
https://www.bbc.com/amharic/news-56954697
በአፍጋኒስታን በደረሰ የቦምብ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ተገደሉ
በአፍጋኒስታን የእንግዳ ማረፊያ ቤት አቅራቢያ መኪና ላይ ተጠምዶ የነበረ ቦምብ ፈንድቶ ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ።
ከተገደሉት መካከል የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንደሚገኙበት የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል። የቦምቡ ፍንዳታ የደረሰው በምስራቅ አቅጣጫ በምትገኘው ሎጋር ግዛት ሲሆን ተማሪዎቹ ያረፉበት የእንግዳ ማረፊያ አቅራቢያ ነው ተብሏል። በጥቃቱ ከሞቱት በተጨማሪ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ቆስለዋል። ጣራዎች መደርመሳቸውን እና ተጎጂዎች በፍርስራሽ ስር መያዛቸውን እማኞች ገልፀዋል። ወደ 90 የሚጠጉ ሰዎች ቆስለዋል ያሉት ደግሞ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ታሪቅ አሪያን ናቸው። የረመዳን ጾም ማፍጠሪያ ሰዓት አካባቢ ለደረሰው ፍንዳታ ኃላፊነት የወሰደ ቡድን የለም። የእንግዳ ማረፊያ ቤቱን ጨምሮ በርካታ ሕንፃዎች በፍንዳታው ተጎድተዋል። ፍንዳታው ሆስፒታሎችን እና መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በአካባቢው ሰፊ ጉዳት ማድረሱን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። "የቤቶች ጣራ ፈርሶ ሰዎች በክምሩ ስር ተይዘዋል" ብለዋል። የፀጥታ ኃይሎች እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ህይወት የማዳን ጥረት እያካሄዱ ነው ተብሏል። በበይነ መረብ በተዘዋወሩ ምስሎች ተጎጂዎችን ከፍርስራሹ ስር ሲወጡ ያሳያሉ። በካቡል የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ጥቃቱን ያወገዘ ሲሆን "ይህ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጸም ትርጉም የለሽ ጥቃት መቆም አለበት" ብሏል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ጦር እስከ መስከረም 11 ቀን ድረስ ሃገሪቱን እንደሚለቅ ከገለጹ ወዲህ አፍጋኒስታን ሁከትና ብጥብጥ ተመላልሶ ጎብኝቷታል። ፍንዳታው የደረሰው የአሜሪካ ጦር ቀሪ የመጀመሪያ ዙር ወታደሮቹን ከአፍጋኒስታን በይፋ ማስወጣት ከመጀመሩ ከአንድ ቀን በፊት ነው። ሀገሪቱ ከቅርብ ወራቶች ወዲህ በሠላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ጨምሮ የሽምቅ ተዋጊዎች አመጽ እየጨመረ መጥቷል።
51723917
https://www.bbc.com/amharic/51723917
"በጫናም ሆነ በተፅእኖ የሚሆን ነገር የለም" አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
የህዳሴው ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ድርድር ስምምነት እንዲፈረም በከፍተኛ ሁኔታ ጫና እያደረገች ያለችው አሜሪካም ሆነ የዓለም ባንክ ሚና ሊፈታ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን መንግሥት አስታውቋል።
የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እና የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይህ የተገለፀው የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በዛሬው ዕለት በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው። የአሜሪካና የዓለም ባንክ ሚና ከታዛቢነት ያለፈ ነው ያሉት አቶ ገዱ "እነዚህ ወገኖች ከታዛቢነት አልፎ ሕግ አርቅቆ የማቅረብ ፍላጎት አላቸው" ብለዋል። • የህዳሴው ግድብ ድርድር ትኩረቱን ስቶ የውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ ሆኗል ተባለ • ኢትዮጵያ በዋሽንግተኑ የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ አሳወቀች ከሰሞኑ የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በውሃ የመሙላትና የሙከራ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በአገራቱ መካከል ስምምነት መፈረም እንዳለበት ማስታወቁ የሚታወስ ነው። ይህንንም አስመልክቶ አቶ ገዱ መግለጫው የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ችላ ያለና ስህተት ነው ብለውታል። የአሜሪካ መንግሥት ያወጣውን መግለጫ ያስተካክለዋል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ የተናገሩት አቶ ገዱ "በፍፁም ተቀባይነት የለውም" ብለዋል። በተለይም ሦስቱ አገራት እያደረጉት ያሉት ድርድር ጥሩ እመርታ እያሳየ ባለበት ወቅት በታዛቢነት ገብታ ሚናዋ የተቀየረው አሜሪካንም አውግዘዋል። በአሜሪካ ሲደረጉ በነበሩ ድርድሮች ላይ አገራቱ ልዩነታቸውን እያጠበቡና በርካታ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ቢደረስም ከቴክኒክም ሆነ ከሕግ አኳያ ገና ያልተግባባንባቸው ጉዳዮች አሉ ብለዋል። ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ አገራት ጥቅምን በማይነካ መልኩ ከዲዛይን ጀምሮ ግድቡን እየገነባች መሆኑን አፅንኦት የሰጡት አቶ ገዱ ከግብፅም ሆነ ከሱዳን ጋር የምታደርጋቸውን ድርድሮች እንደምትቀጥልና በዚህም መልኩ እንደሚፈታም ተናግረዋል። አሜሪካም ይህንን ታሳቢ በማድረግ አገራቱ በራሳቸው ወደ ስምምነት እንዲደርሱ የድርሻዋን ብቻ እንድትወጣ እና በግፊትም ሆነ በጫና ማንንም እንደማይጠቀም እና በሌላ ተፅዕኖ የሚሆን ነገር እንደሌለ አረጋግጠዋል። አቶ ገዱ በግብፅም ሆነ በአሜሪካውያኑ በኩል ስምምነቱ ቶሎ እንዲፈረም ያላቸውን ፍላጎት ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ግን በበኩሏ ጊዜ ወስዳ ሕዝቡ ተሳትፎበት የሚወሰንና በድርድሩም ላይ በዋነኝነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የሚገባ መሆኑንም አሳውቀዋል። የህዳሴው ግድብ የውሀ አያያዝና አለቃቀቅ ድርድር ውጥረትና ውዝግብ በርትቶበታል ቢባልም ኢትዮጵያ ያላት ፅኑ አቋም በድርድር መፍታት ነው ብለዋል አቶ ገዱ በዛሬው መግለጫ። በተለይም ከሰሞኑ ከግብፅ በኩል የሚሰማው ማስፈራሪያና ዛቻ "ጥቅም የለሽ፣ ለማንም የማይጠቅም እና ግንኙነትን ከማሻከር ያለፈ ፋይዳ እንደሌለው ልትገነዘብ እንደሚገባ" አሳስበው ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የመገንባት ሙሉ መብት እንዳላት ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ ማንኛውንም አይነት ሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበልም ተገልጿል። • ኢትዮጵያ፤ የአሜሪካንን መግለጫ ተከትሎ ብሔራዊ ጥቅሜን አሳልፌ አልሰጥም አለች የውሃ፣ መስኖ ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው ከዘጠኝ አመት በፊት የተጀመረው የግድቡ ግንባታ ከብረት ሥራ፣ ከተርባይን ተከላ እና ከተቋራጮች አቅም ውስንነት ጋር ተያይዞ ከነበሩበት ችግሮች ወጥቶ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተው 71 በመቶው ተጠናቋል ብለዋል። በመጪው ሐምሌም ግድቡን ውሃ የመሙላት ሥራ እንደሚጀምር እቅድ እንዳለ ገልፀው፤ 4.9 ኪዩቢክ ሚሊሜትር የማመንጨት አቅምም አለው ብለዋል። በዚህም እቅድ መሰረት በየካቲት እና መጋቢት ወር አካባቢ የሙከራ እንዲሁም ኃይል የማመንጨት ሥራ እንደሚጀምር ተናግረዋል። በሱዳን በግብጽና በኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የቆየው የህዳሴ ግድብ ድርድር ትኩረቱን ስቶ ወደ ውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ መሄዱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ለቢቢሲ መናገራቸው የሚታወስ ነው። እኚህ ምንጫችን ሱዳን የአቋም ለውጥ አድርጋ ከግብጽ ጋር መወገኗን እንዲሁም አሜሪካ እና የዓለም ባንክ ለግብጽ መወገናቸውን በመጠቆም አሁን ላይ ጉዳዩ "4 ለ 1" ሆኗል በማለት ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። አሜሪካ እና ዓለም ባንክ በግድቡ ዙሪያ እጃቸውን እንዲያስገቡ መፈቀዱ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ እንድትከፍል እያደረጋት እንደሆነ እኚህ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ውስጥ አዋቂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከሰሞኑ የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ማንኛውም ነገር የኢትዮጵያን ፍላጎትና ጥቅም በሚጠብቅ መልኩ ብቻ እንደሚከናወንና ብሔራዊ ጥቅሟን የሚነካ ድርድር የኢትዮጵያ መንግሥት እንደማያደርግ ማሳወቁ የሚታወስ ነው። የታላቁን የህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ ሲደረግ ከነበረው ድርድር አንጻር ያወጣውን የአሜሪካ መንግሥት ያወጣው መግለጫ ተከትሎ ከፍተኛ ቅሬታ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል መፈጠሩን ተገልጿል። በአሜሪካ ዋሽንግትን ዲሲ ለሁለት ቀናት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ በሚደረገው ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንደማትካፈል የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። ሚኒስቴሩ የአሜሪካ መንግሥትና የአለም ባንክ በታዛቢነት በሚገኙበት የካቲት 19 እና 20/2012 ዓ. ም. ከሱዳን እና ግብጽ ጋር ሊካሂድ በታቀደው ቀጣይ የሦስትዮሽ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንደማትገኝ ያስታወቀው፣ ተደራዳሪ ቡድኑ በአገር ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ባለማጠናቀቁ መሆኑን በመግለጽ ነበር። ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙርያ የሚያደርጉትን ድርድር የአሜሪካ መንግሥት ቀደሞ በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት መግባቱን በመቃወም በአሜሪካ፣ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወቃል።
news-47227757
https://www.bbc.com/amharic/news-47227757
ታንዛኒያ ውስጥ በ8 እስር ቤቶች 1ሺህ 900 ኢትዮጵያዊያን ይገኛሉ
ከታንዛኒያ በቅርቡ 554 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ ዝግጅት መጠናቀቁን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ ለቢቢሲ ገለፁ።።
ከእነዚህ እስረኞች መካከል ከ300 በላይ የሚሆኑት የሚገኙት ከዋና ከተማው ዳሬሰላም 354 ኪሎ ሜትር ርቀው ታንጋ የሚባል አካባቢ ነው። 250ዎቹ ደግሞ ታንዛኒያ ዋና ከተማ አቅራቢያ ስለሚገኙ ለሁሉም የጉዞ ሰነድና ወጪያቸውን አሰናድቶ ለመሸኘት ከሦስት ሳምንት ያላነሰ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አምባሳደሩ ለቢቢሲ አስረድተዋል። • ኢትዮጵያዊያን ዛምቢያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ • የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ኑሮ በደዳብ ታንዛኒያ ውስጥ በስምንት እስር ቤቶች ውስጥ ከ1 ሺህ 900 በላይ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገኙ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ስደተኞቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚሻገሩ መሆናቸውን ገልፀው፤ ሁሉም የተሟላ የጉዞ ሰነድ እንደሌላቸው ተናግረዋል። አምባሳደር ዮናስ ጨምረው ኤምባሲው ከታንዛኒያው ፕሬዝዳንትና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ማድረጉንና ቀሪዎቹን እስረኞችንም ለመልቀቅ ፈቃደኞች መሆናቸውንም አሳውቀዋል። • ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ነገር ግን በእስረኞቹ አፈታት ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ጋር መነጋገር ይፈልጋሉ ሲሉ ገልፀዋል። አምባሳደር ዮናስ እንደሚናገሩት በዚህ ዓመት በህዳር ወር መጨረሻ ላይ ከ230 በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። ጨምረውም ከሚለቀቁት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል አንዳንዶቹ የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ሲሆኑ አብዛኞቹ ደግሞ ከታንዛኒያ መንግሥት ጋር በመነጋገር በምህረት ከእስር የሚወጡ ናቸው። ስደተኞቹ በእድሜ አፍላ ወጣቶችና ወንዶች መሆናቸውንም አማባሳደር ዮናስ ዮሴፍ ጨምረው ገልፀዋል።
48146416
https://www.bbc.com/amharic/48146416
ጋዜጠኞች ስለ ለውጡ ማግስት ሚዲያ ምን ይላሉ?
የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ዛሬ በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው። የዘንድሮው የዓለም የሚዲያ ነጻነት ቀን ሚዲያ በምርጫና በዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ያለውን አስተዋጽኦ በማጉላት እነደሚከበር ተገልጿል።
ከዚሁ የሚዲያ ነጻነት ጋር በተያያዘ በለውጡ ማግስት የኢትዮጵያ የሚዲያ ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የወደፊት አቅጣጫውስ? የሚል ጥያቄ ለተለያዩ ጋዜጠኞችና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዳይሬክተር አቅርበን ነበር። ጋዜጠኞቹ በኢትዮጵያ ስላለው የሚዲያ ነጻነት ሲያነሱ በተለይ ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ወደስልጣን መምጣት ጋር በተያያዘ ብዙ ነገሮች መቀየራቸውን ያነሳሉ። • የሚዲያ ነፃነቱ ወደ ሚዲያ ስርዓት አልበኝነት እያመራ ይሆን? • 'ሃሰተኛ ዜና '፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት? በሪፖርተር ፣ በሰንደቅና በሌሎችም ጋዜጦች ለረዥም ዓመታት የሰራው ፍሬው አበበ እንደሚለው ከውጪ የሚተላለፉ ስርጭቶችን ማፈን መቆሙና በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ላይ የነበሩ ብዙ ጋዜጠኞች መፈታታቸው ጥሩ የሚባል እርምጃ ቢሆንም ሚዲያውን ወደፊት ለማስኬድ ግን በቂ ስራ እየተሰራ አይደለም ይላል። ''በመረጃ ነጻነት አዋጁ መሰረት መረጃ የማግነት መብት ልክ እንደ ቀድሞው የተገደበ ሆኖ እንደቀጠለ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ብዙ የመንግስት ተቋማት በራቸው ለሚዲያው ክፍት አይደለም''ይላል። ሚዲያዎች የሆነ ነገር እንዲዘግቡ ሲፈለጉ ብቻ እንጂ ተገቢውን ስራ እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ አልተፈጠረላቸውም የሚለው ፍሬው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በአንድ አመት ውስጥ ጋዜጠኞችን ሁለት ጊዜ ብቻ ማግኘታቸውን በማስረጃነት ይጠቅሳል። የአዲስ ዘመን መፅሄት ዋና አዘጋጅ የነበረችው ጋዜጠኛ ስመኝ ይግዛው በበኩሏ ሚዲያው አሁን የሚታየውን አንጻራዊ ነጻነት በአግባብ እየተጠቀመበት ስመለሆኑ እጠራጠራለው ትላለች። ''አሁን ያለውን ሚዲያ ስንመለከተው በአብዛኛው ቀድሞ ወደነበረበት የጎራ ሁኔታ እየተመለሰ ይመስላል። በጣም ትንንሽና የማይመጥኑ ሃሳቦችን ይዘው የሚያትሙና የሚያሰራጩ ተቋማት በዝተዋል።''ትላለች። ሃላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡ፣ ለመንግስት አቅጣጫ የሚያሳዩና ፖሊሲዎችን የሚተቹ የሚዲያ ተቋማት እምብዛም እንደሆኑ ትገልፃለች። ሃገሪቱ በዴሞክራሲውም ሆነ ከነጻነት አንጻር ወደፊት ሊያራምድ በሚችል አይነት ደረጃ ላይ ናቸው ብላ እንደማታስብም ትናገራለች። በትግራይ ክልል እንደ ሚድያ ተቋም መረጃ ማግኘት እጅግ አዳጋች እንደሆነ የሚናገረው በትግርኛ የምትታመው ውራይና መጽሄት አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው አረጋዊ በተለይም ከክልሉ መንግስት ፣ ከሌሎች ተቋማት ወይም ከባለሃብቶች ድጋፍ ካላገኙ በስተቀር ወጪውን መሸፈን የሚችል የግል ሚዲያ እንደሌለ ይናገራል። ''ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሆነው በተሾሙበት ወቅት ሁሉም አካላት ሚድያዎችን እኩል የሚያስተናግዱ እና በነጻነት የሚሰሩ እንዲሆኑ እናደርጋለን ብለው የነበረ ቢሆንም አሁንም የመንግስት ሚድያዎች በነጻነት ሳይሆን በኮሚቴዎች እንዲመሩ እየተደረገ ነው'' ይላል። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዳይሬክተር ጌታቸው ድንቁ በበኩላቸው ሃገሪቱ የሚዲያውን ዘርፍ ለማሳደግና ነጻ ለማድረግ ባለፈው ዓመት በሰራችው ስራ በሃገራት ደረጃ ጠቋሚ መረጃ መሰረት 40 ደረጃዎችን በማሻሻል ከ150 ወደ 110 ከፍ ብላለች ብለዋል። ይህ ደግሞ እውነትም ለውጥ ስለመለኖሩ እንደማሳያ ሊወሰድ ፤ በአንድ ዓመት ውስጥ የተሰሩት ስራዎች እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል ይላሉ ዳይሬክተሩ። ዳይሬክተሩ በሃገሪቱ ከመጣው ለውጥ ጋር ተያይዞ ሚዲያዎች እያሳዩት ያለው ባህሪ እንደ ስጋት ሊወሰድ የሚችል እንደሆነ በመጠቆም ነገር ግን ችግሩ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገራት እንደሚያጋጥም ያስረዳሉ። ''አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ባለው ስሜታዊነትና ወገንተኝነት የሚያጠቃው አዘጋገብ በሙያዊ መነጽር በሚታዩበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ የጋዜጠኝነትን መርህና ስነምግባርና የጣሱ ናቸው።'' • የኤምሬትስና የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ፖለቲካ? • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሌላው ያነጋገርነው ጋዜጠኛ አስረኛ እትሙን ለአንባብያን ያበቃው የቦሌ ታይምስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ስዩም በለውጡ ማግስት ሚዲያው ነፃ እንዲሆን መደረጉ፤ ያሉት እንዲነቃቁ አዲሶችም እንዲፈጠሩ በር እንደከፈተ ያምናል።ሚዲያው ነፃና ክፍት ሲደረግ ግን አብሮ ስርዓት ተዘርግቶለት አለመሆኑ ጋዜጠኝነቱ ፣ አክቲቪዝሙና ፖለቲከኝነቱ አንድ ላይ ተደበላልቀው እየሄዱ መሆኑ የሚያስከትለው አደጋ እንዳለ ይሰማዋል። የሚዲያ ተቋማቱ በነጻነት እንዲሰሩና ዘርፉ እንዲጎለብት መንግስትም ሆነ ሚዲያው የየራሳቸውን ሃላፊነት መወጣት አለባቸው የሚለው ሃሳብ ሁሉንም የሚያስማማ። አሁን በሚዲያውና በመንግስት መካካል ያለው መተማመን በሚፈለገው ደረጃ አለ ብሎ የማያምነው ጋዜጠኛ ፍሬው መንግስት ከአንገት በላይ ነው ሚዲያውን እደግፋለው እያለ ያለው ይላል። ''እንደዚህ አይነት ንግግሮች ድሮም ቢሆን ነበሩ፤ መሬት ላይ ወርዶ መንግስት እውነትም ከሚዲያው ጋር መስራት አለበት። የድሮው አይነት ስርአት ተመልሶ እንዳይመጣ ስጋት አለኝ''ይላል። ስመኝም ብትሆን የሚዲያው ሙያዊ ነጻነት ከሃላፊነት ጋር አብሮ መሄድ ካልቻለ አሁን የመጣው ነጻነት ሌላ አይነት ችግር ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ስጋቷን ታስቀምጣለች። ''አሁን ያለውን የዘር ፖለቲካና ግጭት የበለጠ እያባባሱ ሃገሪቱን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይወስት ስጋት አለኝ።'' ሙያዊ ስነምግባርን ተከትሎ ካለመስራት ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እስካሁን የወሰደው እርምጃ አለ ወይ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ዋና ዳይሬክተሩ ሲመልሱ '' ከእርምጃ ይልቅ ወደ ድጋፍ ያተኮረ ስራ ነው እየሰራን ያለነው።'' ብለዋል። የሚዲያ ተቋማቱ አሁን እያሳዩት ያለውን ባህሪ ያመጡት በቀድሞ ስርአት በቂ በሆነ መልኩ ስራቸውን እንዲሰሩ ስላልተፈቀደላቸውና አቅማቸውን በተገቢው ሁኔታ ማጎልበት ስላልቻሉ ነው ሲሉ ያብራራሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘም መንግስት ሁለት ሃላፊነቶች አሉበት ብለው ያምናሉ። አንደኛው ሆደ ሰፊ ሆኖ ነገሮችን ማሳለፍ መቻል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ተቋማት አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ ድጋፍማድረግ፣ ስልጠና ማመቻቸት ናቸው።
news-55157339
https://www.bbc.com/amharic/news-55157339
ኮሮናቫይረስ ፡ ዩናይትድ ኪንግደም የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች
ዩናይትድ ኪንግደም ፋይዘርና በባዮንቴክ የተሰራው የኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል በመፍቀድ ከዓለማችን ቀዳሚዋ አገር ሆናለች።
የብሪታኒያ መድኃኒት ቁጥጥር መሥሪያ ቤት 95 በመቶ የኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ይህንን ክትባት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ጥቅም ላይ መዋል ይችላል ብሏል። ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ የሚባሉ ሰዎች ክትባቱን በወሰዱ በቀናት ውስጥ ሰውነታቸው መከላከያ ያዳብራል ተብሏል። ዩናይትድ ኪንግደም ፋይዘርና ባይንቴክ የተባሉት አምራቾች ከሚያመርቱት ክትባት ውስጥ 40 ሚሊዮን ይድረሰኝ ስትል አዛለች። በሽታውን ለመከላከል አንድ ሰው ክትባቱን ሁለት ጊዜ መወጋት አለበት። ይህ ማለት 40 ሚሊዮን ክትባት ለ20 ሚሊዮን ሰው ይበቃል ማለት ነው። አምራቹ 10 ሚሊዮን ክትባት ለዩናይትድ ኪንግደም በቅርብ ቀናት ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። ፋይዘር በ10 ወራት ጊዜ ውስጥ ክትባት ማምረት የቻለ የመጀመሪያ አምራች ነው። ክትባት አዘጋጅቶ በማምረት ጥቅም ላይ ለማዋል ብዙ ጊዜ ዓመታትን የሚፈጅ ሂደት የነበረ ሲሆን ለኮሮናቫይረስ ግን በአጭር ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል። የዩናይትድ ኪንግደም የጤና ሚኒስትሩ ማት ሃንኮክ በትዊተር ገፃቸው "እርዳታ እየመጣ ነው። ሰዎች በሚቀጥለው ሳምንት ክትባቱን ማግኘት ይጀምራሉ" የሚል መልዕክት አስተላፈዋል። ባለሙያዎች ክትባቱ ጥቅም ላይ መዋል ቢጀምር እንኳ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሕግጋትን አሁንም ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው ብለዋል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፤ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀምና ተመርምረው ኮሮናቫይረስ ያለባቸውን ሰዎች በማግለያ ጣብያዎች ማቆየት አሁንም ይቀጥላሉ ተብሏል። ክትባቱ ምን አይነት ነው? ኤምአርኤንኤ የተሰኘ ስያሜ ያለው አዲስ ክትባት ሲሆን ከኮሮናቫይረስ ቅንጣት ተወስዶ የተሰራ ነው። ክትባቱ የሰው ልጅ ሰውነት ቫይረሱን እንዲላመደውና የመከላከል ኃይሉን እንዲያደራጅ ያደርገዋል። ክትባቱ ከዜር በታች 70 ዲግሪ ሴልሲዬር በሆነ ቅዝቃዜ ውስጥ መቀመጥ ይኖርበታል። ከቦታ ቦታ ሲዘዋወር ለክትባቱ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በደረቅ በረዶ ታሽጎ መሆን አለበት። ባለሙያዎች ይህን ክትባት ቀድመው ማግኘት ያለባቸው ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ናቸው ይላሉ። በአረጋውያን ማቆያ ውስጥ ያሉ፤ በተለይ ደግሞ ዕድሜያቸው ከ80 በላይ የሆኑ ሰዎችና የጤናና ማኅበራዊ አገልግሎት ሠራተኞች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። በቅዳሚያ ከላይ ለተጠቀሱት የሕብረተሰቡ አባላት ከተዳረሰ በኋላ ከ50 ዓመት በላይ ላሉ ሰዎችን ጨምሮ ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው ወጣቶች ክትባቱ እንደሚሰጥ ተነግሯል። ክትባቱ ሁለት ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን የመጀመሪያው ከተሰጠ ከ21 ቀናት በኋላ ሁለተኛው ይሰጣል። ከፋይዘር በተጨማሪ ሌሎች ተስፋ የተጣለባቸው ክትባቶች ፈቃድ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ሞደርና የተባለ አንድ ክትባት ከዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ፈቃድ ለማግኘት ጠይቋል። ዩናይትድ ኪንግደም ከዚህ አምራች 7 ሚሊዮን ክትባት ለመግዛት ቅድመ ትዕዛዝ አስገብታለች። ሌላኛው ክትባት ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲና አስትራዜኔካ የሚያመርቱት ነው። ሩሲያ የራሷን ስፑትኒክ 5 የተሰኘ ክትባት አምርታ ጥቅም ላይ እያዋለች እንደሆነ ካሳወቀች ሰንበትበት ብላለች። የቻይና ጦር ሠራዊትም ክትባት አምርቶ እየተጠቀመ እንደሆነም አሳውቋል።
news-53634411
https://www.bbc.com/amharic/news-53634411
ኢራን በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥርን ማሳነሷን አንድ ሾልኮ የወጣ መረጃ አጋለጠ
በኢራን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር መንግሥት በይፋ ከገለጸው በሶስት እጥፋ እንደሚበልጥ የቢቢሲ ፐርሺያ ምርመራ አረጋገጠ።
ለህዝብ ይፋ ያልሆነ የኢራን መንግሥት አሃዝ የሚያሳየው በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 42ሺህ የሚጠጋ ነው። ይሁን እንጂ የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር እስካሁን በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 14ሺህ 405 ነው ይላል። ይህም ብቻ ሳይሆን ከኢራን መንግሥት የተገኘው መረጃ በቫይረሱ ስለመያዛቸው በይፋ የተነገረው ቁጥር በግማሽ እንዲቀንስ መደረጉን አመልክቷል። ጤና ሚንስቴር እስካሁን በቫይረሱ ተይዘዋል ያላቸው ሰዎች ቁጥር 278 ሺህ 827 ነው። ይሁን እንጂ የአገሪቱ መንግሥት 451ሺህ 024 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጧል። የኢራን መንግሥት በቫይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥርን ከማሳነሱም በተጨማሪ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታ ማለፍ ከጀመረ ከአንድ ወር በኋላ ነበር የአገሪቱ የጤና ሚንስቴር በቫይረሱ ሳቢያ የሰው ህይወት ማለፉን ሪፖርት ያደረገው። ይህ መረጃ እንዳረጋገጠው፤ መንግሥት የመጀመሪያውን ሟች ይፋ በሚያደርግበት ወቅት 52 ሰዎች ቀድመው በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። ማንነቱ ይፋ ያልሆነው ምንጭ ለቢቢሲ የላከው መረጃ በመላው ኢራን በየዕለቱ በኮቪድ-19 ተይዘው ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎችን ዝርዝር መረጃ የያዘ ነበር። ሥም፣ እድሜ፣ ጾታ፣ ታማሚው የሚታይበት ምልክት፣ ቀን እና ተጠቂው የተጓዳኝ በሽታ ታማሚ ስለመሆኑ እና ሌሎች መረጃዎች ተካተውበታል። መረጃውን ለቢቢሲ የላከው ምንጭ “እውነቱ መታወቅ ስላለበት” እና “በወረርሽኙ የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት የሚደረገው ጥረት መቆም አለበት” በሚሉ ምክንያቶች መረጃውን ለቢቢሲ ለማጋራት መወሰኑ ተመልክቷል። ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡ የኢራን የጤና ባለሙያዎች እንዳሉት የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር በኢራን መንግሥት የደህንነት አገልግሎት ጫና ይደረግበታል። የኢራን መንግሥት የቫይረሱን ስርጭት መደበቅ ለምን አስፈለገው? የቫይረሱ ስርጭት የተቀሰቀበት ወቅት የኢራኑ ኢስላሚክ አብዮት ጥበቃ ዘብ ክብረ በዓል ከሚከመርበት ወቅት ጋር ተጋጭቷል። ይህም ብቻ ሳይሆን የፓርላሜንታዊ ምርጫን ለማካሄድ ኢራን ደፋ ቀና የምትልበት ወቅት ነበር። ኢስላሚክ አብዮት ጥበቃ ዘብ ድጋፉን የሚያጠናክርበት ምርጫውም ስኬታማ የሚሆንብት እድል ሰፊ እንደሆነ በመገመቱ አጋጣሚውን በወረርሽኙ ሳቢያ አሳልፎ መስጠት አልተፈለገም ተብሏል።
50149249
https://www.bbc.com/amharic/50149249
ሩስያ አፍሪካ የጋራ ፎረም፡ ፑቲን ከአፍሪካ የሚፈልጉት ምንድን ነው?
ትናንት ጥቅምት 11፣ 2012 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በሩሲያ አፍሪካ የጋራ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ሩስያ ሶቺ አቅንተዋል። በሩስያ ሶቺ ከተማ በሚካሄደው በዚህ ጉባዔ ላይ ከ35 የአፍሪካ አገራት መሪዎች በላይ ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ በቆይታቸውም የሩስያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጨምሮ ከአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል። ሶቪየት ሕብረት ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት በፊት በአፍሪካ የተለያዩ አገራት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተሰማርታ የነበረች ቢሆንም ከዚያ በኋላ ግን በአፍሪካ ውስጥ በምጣኔ ኃብትና በፖለቲካ ያላት ተጽዕኖ እየቀነሰ መጥቷል። • "ኢትዮጵያ የኢህአዴግ አባት እንጂ፤ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ አባት አይደለም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሩሲያ ከአፍሪካ ይልቅ ከአውሮጳና ከኢሲያ ጋር የተሻለ የንግድ ግንኙነት አላት። እኤአ ከ2017 ወዲህም አፍሪካ ጠንካራ የንግድ ግንኙነት ያላት ከሕንድ፣ ቻይናና አሜሪካ እንጂ ከሩሲያ ጋር አይደለም። ለአፍሪካ ሩሲያ ከምታደርገው ሰብዓዊ እርዳታም በላቀ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ጃፓንና አውሮጳ ሕብረት ያደርጋሉ። "ሩሲያ በአንድ ወቅት የሶቪየት ሕብረት በአፍሪካ ላይ የነበራትን ተጽዕኖ ይኖራታል ማለት ከባድ ነው" የሚሉት ባለሙያዎች "የሩሲያ ተጽዕኖ ውስን ከሆኑ የአፍሪካ አገራት ጋር በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ብቻ በሚኖር ትብብር ይመሰረታል" ይላሉ። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ቀዳሚ አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል። ለመሆኑ ሩሲያ ከአፍሪካ የምትፈልገው ምንድን ነው? የሩሲያ ፍላጎት ሞስኮ በአፍሪካ ያላትን ሥፍራ ለማስፋት እንዲሁም ግንኙነቷን ማጠናከር እንደምትፈልግ ከሶቪየት ሕብረት ወቅት ጀምሮ የታወቀ ነው። ፑቲን ከዚህ ጉባዔ ቀደም ብሎ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንዳስታወቁት " የሩሲያ አፍሪካ ግንኙነት እያደገ ነው" በማለት ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፎችን፣ የመከላከያና ደህንነት ርዳታዎችን፣ የምጣኔ ኃብት ድጋፍ፣ ሕክምና፣ ሰብዓዊ ርዳታ እንዲሁም የሙያ ትምህርት ስልጠና ላይ ድጋፍ ለማድረግ እንደተዘጋጁ ዘርዝረዋል። • የዋግ ኽምራ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው ሩሲያ ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ፖለቲካዊ ግንኙነት ከ12 አፍሪካ መሪዎች ጋር እኤአ ከ2015 ጀምሮ የጀመረች ሲሆን ከእነዚህ መካከል ስድስቶቹ በ2018 የተቀላቀሉ ናቸው። ባለፈው ዓመት የቀድሞው የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን አሜሪካ ለአፍሪካ አዲስ አጋርነት ስልት እንዳዘጋጀች ጠቅሰው የዚህ ስልት ከፊሉ የቻይናና ሩሲያን ተጽዕኖ መቀነስ ያለመ ነው ብለው ነበር። ነገር ግን በቅርቡ በዋሺንግተን ፖስት ላይ የወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው ሩሲያ "በደህንነት ጉዳዮች ላይ ግንኙነቶችን ማጠናከርና ስምምነቶች ላይ መድረስ" በከፍተኛ ሁኔታ ትፈልጋለች። ወታደራዊ ግንኙነት ሩሲያ ለአፍሪካ ዋነኛ የመከላከያ አጋር ስትሆን የጦር መሳሪያም አቅራቢ ናት። ነገር ግን የመከላከያ ገበያዋ ዋነኛ መዳረሻ አፍሪካ ሳትሆን ኢሲያ ነው። እንደ ስቶክሆልም ዓለም ዓቀፍ የሰላም ጥናት ተቋም ከሆነ ከ2014 እስከ 2018 በአፍሪካ ግብፅን ሳይጨምር ከሩሲያ 17 በመቶ መሳሪያ ገዝተዋል። ከዚህ 17 በመቶው ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የምትይዘው አልጄሪያ ስትሆን ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ድርሻቸው በጣም ያነሰ ነው። • አዲስ አበባ ውስጥ ሲካሄዱ የነበሩ ስብሰባዎች በወጣቶች መስተጓጎላቸው ተነገሯል ለሩሲያ የመሳሪያ ዋና ገበያ ኢሲያ ስትሆን ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት ድርሻ በጣም አናሳ ነው። ይህ ቢሆንም ግን ሩሲያ ከ2014 ጀምሮ ከ19 የአፍሪካ አገራት ጋር ወታደራዊ ስምምነት ከፈፀመች ወዲህ እያደገ ነው። እኤአ በ2017/ 18 ሩሲያ ከአንጎላ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን፣ ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ጋር የመሳሪያ አቅርቦት ስምምነት ፈርማለች። ይህ የተዋጊ ጀቶችን፣ የጦርና የመጓጓዣ ሂሊኮፕተሮችን፣ ፀረ ታንክ ሚሳዔል እና ለተዋጊ አውሮፕላኖች የሚሆን ሞተሮችን ማቅረብን ያጠቃልላል። የግል ጠባቂ ቡድኖች የሩሲያ ወታደራዊና ደህንነት ስምምነት የጦር መሳሪያ ሽያጭ ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን፣ አንዳንዴ የግል ጠባቂ ቡድኖችን እስከማቅረብ የደረሰ ስምምነት ያላቸው የአፍሪካ አገራት አሉ። ለምሳሌ ሩሲያ በማዕከላዊ አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈውን መንግሥት ከአማጺያን ጥቃት ለመከላከል ተሰማርታለች። ነገር ግን በዚያ ያለው የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ለመንግሥት እና ወሳኝ ለሆኑ የኢኮኖሚ ሀብቶች ጥበቃ ያደርጋል። የሩሲያ የግል ጠባቂ ወታደራዊ ኃይል፣ ከክሬምሊን ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገረው የግል ጠባቂ ኃይል፣ ዋግነር፣ በሱዳንና በሊቢያ እንዲሁም በሌሎች የአፍሪካ አገራት ጥበቃ እንደሚያደርግ ይታወቃል። የሩሲያ ባለሥልጣናት ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ከማለት ተቆጥበዋል። የምጣኔ ኃብት ፍላጎቶች ሩሲያ በአፍሪካ በግልጽ የምጣኔ ኃብት ፍላጎቶች አሏት። እንደ ማንጋኒዝ፣ ቦክሳይት እና ክሮሚየም ያሉና ለኢንዱስትሪ ወሳኝ ግብዓት የሆኑ ማዕድኖችን ትፈልጋለች። የሩሲያ የመንግሥት ኩባንያዎች በጊኒ ቦክሳይት ማዕድን የሚያወጡ ሲሆን በአንጎላ ደግሞ ዳይመንድ ለማውጣት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ከሞዛምቢክ ጋርም እንዲሁ ጋዝ በማውጣት ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል። • "አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው" አቦይ ስብሃት ትልቁ የሩሲያ ኢነርጂ ኩባንያ በካሜሮን፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ፕሮጀክቶች ያሉት ሲሆን በኮንጎ ደግሞ ስምምነት ላይ ለመድረስ እየሰራ እንደሆን ለማወቅ ተችሏል። ሩሲያ ለበርካታ የአፍሪካ አገራት የኒውክለር ኃይል ቴክኖሎጂን የምታቀርብ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በሚቀጥለው ዓመት በግብፅ በ25 ቢሊየን ዶላር ብድር የሚገነባው የመጀመሪያው የኒውክለር ኃይል ይገኝበታል።
51131135
https://www.bbc.com/amharic/51131135
ታላቁ ሕዳሴ ግድብ፡ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸው ተነገረ
በዩናይትድ ስቴትስ አደራዳሪነት ዋሽንግተን ላይ ሲካሄድ የቆው የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሦስትዮሽ ውይይት ፍሬያማ እንደነበር ተነግሯል።
ሦስቱ ሃገራት እንዲሁም አሜሪካ እና የዓለም ባንክ በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት በሕዳሴው ግድብ ሙሊት እና ሌሎች መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት በሚያደርሱ ነጥቦች ላይ ተግባብተዋል። የአሜሪካው ገንዘብ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በድረ-ገፁ ባወጣው መግለጫ ላይ የሃገራቱ ውሃ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት እንዲሁም ቀደም ብሎ በተደረጉ ውይይቶች ላይ ተመሥርቶ ከስምምነት ተደርሷል። ሃገራቱ አደራዳሪዎች በተገኙበት በሚከተሉት ነጥቦች ላይ 'ለመስማማት' ለቅድመ ስምምነት ደርሰዋል። ሚኒስትሮቹ፤ ሦስቱም ሃገራት ለአጭር ጊዜ ወይም ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ድርቅን በመቋቋም ረገድ የጋራ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተስማምተዋል። ሚኒስትሮቹ ከጥር 19-20 ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ተገናኝተው በአባይ ግድብ ሙሊት ዙሪያ የተጠናከረ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስማምተዋል። እስከዚያ ባለው ጊዜ ቴክኒካዊና ሕጋዊ ውይይቶች እንደሚከናወኑም ታውቋል። የሦስቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በድንበር ዘለል ትብብር አስፈላጊነት ዙሪያ ጠንከር ያለ አቋም አንፀባርቀው ስምምነቱ እንዲፀና የበኩላቸውን እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል ይላል- የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስቴር ድረ-ገፅ ላይ የወጣው መግለጫ። የዋሽንግተኑ ስምምነት የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል ያለውን ውጥረት ያረግበዋል ተብሎ ይጠበቃል። 5 ቢሊዮን ዶላር ያወጣል የተባለለት የሕዳሴ ግድብ 'ፕሮጀክት' ሲጠናቀቅ በአፍሪቃ ትልቁ እንደሚሆን ይጠበቃል። 6 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትም ከግድቡ የሚጠበቅ ተግባር ነው። የሦስቱ አገራት የውሃ ሚንስትሮች በህዳሴው ግድብ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ጉዳይ ውይይት ሲያደርጉ ሕዳር ላይ በዋሽንግተን ካደረጉት ድርድር አንስቶ ይህ ለአምስተኛ ጊዜ ነው። በኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የውሃ ሚንስትሮች በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ትናንት ታህሳስ 29 ቀን 2012 ዓ. ም በአዲስ አበባ ያካሄዱት የሦስትዮሽ ቴክኒካዊ ስብሰባ ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወቃል።
news-49534054
https://www.bbc.com/amharic/news-49534054
የእንግሊዝ ወላጆች በትምህርት ቤት ስልክ እንዲታገድ ለምን ይፈልጋሉ?
በእንግሊዝ የሚኖሩ ግማሽ ያህሉ ወላጆች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሞባይል ስልክ እንዲታገድ ይፈልጋሉ ሲል 'ፕራይስ ኮምፓሪዝን ሳይት ዩስዊች' የተባለ ተቋም የዳሰሳ ጥናት አመለከተ።
የሞባይል ስልክ ክልክል ከሆነባቸው ትምህርት ቤቶች በስተቀር ዘመናዊ ስልኮችን የመጠቀም ልማዱ ጨምሯል ጥናቱ እንደሚያስረዳው ልጃቸው የሚማርበት ትምህርት ቤት ስልክ እንዳይጠቀሙ እንደሚከለክል የተናገሩት ከስምንቱ ወላጆች አንዳቸው ብቻ ነበሩ። • 'መኝታ ቤት ስልክ ይዘን አንገባም' • የኩላሊት በሽታን የሚመረምረው መተግበሪያ በዳሰሳ ጥናቱ የተሳተፉ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች፤ አንድ ተማሪ ወደ ትምህርት ቤት ይዞት የሚሄደው ዘመናዊ ስልክ በአማካይ 301 ፓውንድ የሚያወጣ መሆን እንደሚገባው አስተያታቸውን ሰጥተዋል። ባለፈው ዓመት 'ዜን ካልቸር' ፀሐፊ ማት ሃንኮክ፤ ተማሪዎች የሞባይል ስልክ በትምህርት ቤት ውስጥ የሚያግዱ ትምህርት ቤቶችን እንደሚያደንቁ ተናግረው ነበር። ይሁን እንጂ እገዳው ተማሪዎች ዘመናዊ ስልኮችን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው እንዳያውቁ ያደርጋቸዋል ሲሉ አንዳንዶች ተቃውመውታል። የዳሰሳ ጥናቱ እንደሚያስረዳው ዘመናዊ ስልክ ወደ ትምህርት ቤት ይዘውት የሚሄዱት ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። በእንግሊዝ በዚህ ዓመት ወደ ትምህርት ቤቶች የተወሰዱ ዘመናዊ ስልኮች በጠቅላላ 2.3 ቢሊየን ፓውንድ እንደሚያወጡ ተቋሙ ግምቱን አስቀምጧል። ከዚህም በተጨማሪ 43 በመቶ የሚሆኑት ሕፃናት የሚይዙት ስልክ ወላጆቻቸው ከሚይዙት እጅግ የዘመነ ሲሆን በየዓመቱ 13 ቢሊየን ፓውንድ የስልክ ወጭ ክፍያ ይከፈልባቸዋል። "በየቀኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ይዘዋቸው የሚሄዱት ስልኮች ቁጥርም ከአዕምሮ በላይ ነው " ሲሉ በድርጅቱ ውስጥ የሞባይል ስልክ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አርነስት ዶኩ ይናገራሉ። • ተማሪዎች ሞባይሎቻቸውን ሊነጠቁ ነው • ትውስታ- የዛሬ 20 ዓመት ኢትዮጵያ ሞባይል ስልክን ስትተዋወቅ ሞባይል ልጆቻቸውን ከትምህርት ሊያስተጓጉል እንደሚችል ማንኛውም ወላጅ ሊረዳው የሚችል ነው፤ በመሆኑም ስልኮችን በትምህርት ቤት እንዳይጠቀሙ ማገድ ትክክለኛ መፍትሔ አይደለም ሲሉ ባለሙያው ያክላሉ። ተማሪዎች ወደ ሥራ ዓለም ሲቀላቀሉ፤ ማንኛውንም ስልክ መጠቀማቸው አይቀርም በመሆኑም ደህንነታቸው ተጠብቆ ይህንን ክህሎት የሚያዳብሩበት አንዱ ሥፍራ ትምህርት ቤት መሆኑን ባለሙያው ያስረዳሉ። "ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ወላጆች የልጆቻቸውን ደህንነት በማረጋገጥ የአዕምሮ እረፍት ያገኛሉ፤ በስልካቸው ላይ ባለው መተግበሪያ አሊያም በቀጥታ በመደወል የት እንዳሉ ማወቅ ያስችላቸዋል" በማለት ከጉዳቱ ጥቅሙ እንደሚያይል በምሳሌ ያብራራሉ። ባለፈው ዓመት የኤተን አስተዳዳሪ፤ ትምህርት ቤቶችና ወላጆች ከተማሪዎች ስልክ መቀማትን መፍራት የለባቸውም ብለዋል። ነገር ግን በርካቶች በንግግራቸው አልተስማመሙም። አንዳንዶች እንዲያውም በዚህ ቴክኖሎጂ በተንሰራፋበት ዓለም ህፃናት ቴክኖሎጂ ከመጠቀም ሊከለከሉ አይገባም ሲሉ ይሟገታሉ። በብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ የአዕምሮ እና የትምህርት ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ፖል ሆዋርድ በበኩላቸው ባለፈው ዓመት ለቢቢሲ "ትምህርት ቤቶችና ትምህርት ለዚህ ዓለም ሕይወት እንድንዘጋጅ የሚረዱን ከሆነ፤ ስልክን መቼ መጠቀም እንዳለብንና እንደሌለብን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው" ብለው ነበር። "ህፃናት ራሳቸውን እንዴት እንደሚያስተዳድሩ መማር ይፈልጋሉ፤ ገና በማለዳው ስልካቸውን የሚነጠቁ ከሆነ ግን ይህንን እድል ማግኘት አይችሉም" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
news-54915697
https://www.bbc.com/amharic/news-54915697
ቲክቶክ የትራምፕ አስተዳደር ላይ የክስ ሂደት ጀመረ
የቻይናው የቪዲዮ ማህበራዊ መተግበሪያ ቲክቶክ ከህዳር 3/ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዳይውል ለማድረግ የታሰበውን እቅድ በመቃወም ቲክቶክ በትራምፕ አስተዳደር ላይ የክስ ሂደት ጀምሯል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክቶክን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ባይትዳንስ እስከ ህዳር 3/ 2013 ዓ.ም ድረስ በአሜሪካ ድርጅት የማይገዛ ከሆነ ጥቅም ላይ እንዳይውል ትእዛዝ አስተላልፈው ነበር። በአሁኑ ወቅት ቲክቶክ በአሜሪካ የሚኖረው የወደፊት እጣ ፈንታ ግልጽ አይደለም። በቻይናው ኩባንያ ባይቴንዳንስ ባለቤትነት የሚተዳደረው ቲክቶክ ለአሜሪካ ብሔራዊ ስጋት ነው የሚል ክስ ይቀርብበታል። የፕሬዝደንት ትራምፕ አስተዳደር ባይቴንዳንስ የአሜሪካውያንን ግላዊ መረጃ እየሰበሰበ ለቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ ያቀርባል ይላል። ባይቴንዳንስ በበኩሉ የመተግበሪያው ተጠቃሚ ሰዎች መረጃ በአሜሪካ እና በሲንጋፖር የሚከማች መሆኑን እና ለቻይና ሕጎች ተገዢ አለመሆኑን ይጠቅሳል። ቲክቶክ በአሜሪካ ብቻ 100 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን ለአሜሪካ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ድርሻውን ለመሸጥ ጫፍ ደርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን ባለቀ ሰዓት ሽያጩ ከሽፏል፡፡ ማይክሮሶፍት ቲክቶክን ለመግዛት ጣጣውን እየጨረሰ ነበር፡፡ ባለቀ ሰዓት ትናንት በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም ሽያጩ ተፋርሷል፡፡ ''እስካሁን ድረስ በአሜሪካ ሕግ መሰረት ማድረግ የሚገባውን እና ግልጽ መሆን ያለባቸውን ጉዳዮች በሙሉ በፈቃደኝነት ሲያካሂድ ነበር። ላለፉት ሁለት ወራትም ነገሮች እንደሚስተካከሉ በተስፋ ስንጠባበቅ ነበር'' ብሏል ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ። '' ፕሬዝዳንቱ ከተጠቃሚዎች ጋር በተያያዘ የገለጹት ስጋት ተገቢ እንዳልሆነ እና ምንም ነገር እንደሌለ ለማሳየት የተቻለንን በሙሉ ስናደርግ ነበር። ከግላዊነትና ደህንነት ጋር የተያያዙ የአገሪቱ ፖሊሲዎች ጋር ተጣጣጣመ አሰራርም ተከትለናል'' ይላል የድርጅቱ መግለጫ። ድርጅቱ አክሎም 'መብታችንን ለማስከበርና በአሜሪካ የሚገኙ ከ15 ሺ በላይ ሰራተኞቻችንን ጥቅም ለማስከበር' በፍርድ ቤት በኩል ክስ መስርተናል ሲል አስታውቋል።
49671694
https://www.bbc.com/amharic/49671694
ኦክስፎርድ ከዓለማችን ቀዳሚው ዩኒቨርስቲ ተባለ
ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በዓለማችን ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሁሉ ለተከታታይ አራትኛ ዓመት ቀዳሚ መሆኑ ተገለፀ።
የዓለማችን ግዙፍና ስመጥር የትምህርት ተቋማትን ደረጃ የሚያወጣው ተቋም ካምብሪጅን ሶስተኛ ኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደንን አስረኛ አድርጎ በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ አስቀምጧል። ነገር ግን ደረጃውን የሚያወጡ አካላት ሌሎች የዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሌላ ሀገር ተቋማት ጋር ባለባቸው ፉክክር የተነሳ "ደረጃቸውን ይዘው ለመቆየት እየታገሉ ነው" ብለዋል። በአውሮጳ ስመጥር ከሆኑ ዩኒቨርስቲዎች መካከል የጀርመን ዩኒቨርስቲዎች የዩናይትድ ኪንግደም አቻዎቻቸውን በመቀናቀን የበላይነቱን ይይዛሉ ሲሉ ግምታቸው በማስቀመጥ አስጠንቅቀዋል። • ከነፍስ የተጠለሉ የዘሪቱ ከበደ ዜማዎች • የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ ኦክስፎርድ ዳግመኛ የዓለማችን ምርጡ ዩኒቨርስቲ በመሆን አንደኛነቱን የተቆናጠጠ ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ሆኗል። የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ከምርጥ አስሮቹ መካከል ሰባቱን በመያዝ የደረጃ ሰንጠረዡን በበላይነት የተቆጣጠሩት ሲሆን ከ200 ዩኒቨርስቲዎች መካከል ደግሞ 60ዎቹ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ናቸው። የእሲያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ቢሆኑ የዋዛ አለመሆናቸው ነው የሚነገረው። ቻይናና ጃፓን ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ብቅ እያሉ መጥተዋል። በዚህ ዓመት ሳትጠበቅ ምርጥ የአለማችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እግሯን ያስገባች ጠንካራ ተፎካካሪ አገር ኢራን ናት። የዓለማችን ምርጥ 10 ዩኒቨርስቲዎች • መምህራንን ተክቶ ያስተማረው ወታደር እየተወደሰ ነው የዓለማችን ምርጥ ዩኒቨርስቲ ዝርዝር ከ92 ሀገራት የተገኙ 1300 ዩኒቨርስቲዎች የተካተቱበት ሲሆን ለደረጃ መመዘኛ መስፈርት ሆኖ ያገለገለው የማስተማር ብቃት፣ የምርምርና ስርፀት ስራዎች፣ ለማጣቀሻነት የዋሉ የምርምር ስራዎች እንዲሁም የኢንደስትሪው ገቢና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ናቸው። የጀርመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳጎስ ያለ ገንዘብ በማውጣት ዩኒቨርስቲዎቻቸው ላይ ኢንቨስት እያደረጉ መሆኑን ከደረጃው ጋር ተያይዞ የወጣው ዳሰሳ ያስረዳል። የእንግሊዝ ዩኒቨርስቲዎች የሆኑት ሶስቱ ተቋማት ኦክስፎርድ፣ ካምብሪጅና ሎንዶን ዩኒቨርስቲዎች ደግሞ ዛሬም እርስ በእርስ ባላቸው ትብብር ጥንካሬያቸው አብሯቸው አለ ተብሏል።
news-54744136
https://www.bbc.com/amharic/news-54744136
በፈረንሳይ ጥቃት ያደረሰው ከሰሜን አፍሪካ በስደተኞች ጀልባ አውሮፓ የገባ ነው ተባለ
ትናንት በፈረንሳይ ኒስ ከተማ ሦስት ግለሰቦች በስለት ወግቶ የገደለው ቱኒዚያዊ ወጣት አውሮፓ የደረሰው ከጥቂት ቀናት በፊት ነው ተባለ።
የ21 ዓመቱ ተጠርጣሪ ከሰሜን አፍሪካ በስደተኞች ጀልባ ጣሊያን ከደረሰ በኋላ የጣሊያን ቀይ መስቀል ሲደርስ የስደተኛ ወረቀት ተሰጥቶታል ተብሏል። ፖሊስ ተጠርጣሪው ብራሂም አውሳውሲ ጥቃቱ በተፈጸመበት ስፍራ ከፖሊስ በተተኮስበት ጥይት ተመትቶ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ብሏል። በጥቃቱ ሦስት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ሁለቱ የተገደሉት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። ፖሊስ በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል አንዷ የ60 ዓመት ሴት አንገቷ በስለት ተቀልታ ነው የተገደለችው ብሏል። ሌላኛው ሟች የ55 ዓመት ሰው ደግሞ ጉሮሯቸው በስለት ተወግቶ ተገድለዋል። ሌላኛው በጥታቱ የተገደለችው የ44 ዓመት ሴት ጥቃት አድራሹ በተደጋጋሚ በስልት ቢወጋትም ከስፍራው አምልጣ በአንድ ካፍቴሪያ ውስጥ ተሸሽጋ ነበር። ይሁን እንጂ በደረሰባት ጉዳት ሕይወቷ አልፏል። የኒስ ከተማ ከንቲባ ክርስችን ኤስቶርሲ ጥቃት አድራሹ ጥቃቱን ሲጸም በተደጋጋሚ 'አላሁ አክበር' ይል ነበር ብለዋል። ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ጥቃቱን "እላማዊ የሽብር ጥቃት" ሲሉ ገልጸውታል። ፕሬዝደንት ማክሮን በትምህርት ቤት እና በቤተ ክርስቲያን አቅራቢያዎች የሚሰማራ የፖሊስ ቁጥርን ከ3ሺህ ወደ 7ሺህ ከፍ እንደሚል አስታውቀዋል። ፈረንሳይም ብሔራዊ ደህንነት ስጋቷን "ከፍተኛ ደረጃ" ወደሚለው ደረጃ ከፍ አድርጋለች። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከተማዋ ውስጥ ጥቃቶች በተደጋጋሚ እየተሰነዘሩ ነው። ከአራት ዓመታት በፊት የ31 ዓመት ቱኒዝያዊ በዓል ለማክበር የተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በጭነት መኪና ጥቃት አድርሶ 86 ሰዎች ሞተዋል። ከቀናት በኋላ ጃክዊስ ሀሜል የተባሉ ቄስ ጸሎት እየመሩ ሳለ አንገታቸውን ተቀልተዋል። በዚህ ወር መባቻ ላይ በሰሜን ምዕራብ ፓሪስ ሳሙኤል ፓቲ የተባለ የታሪክ መምህር በተመሳሳይ አንገቱን ተቀልቶ መገደሉ ይታወሳል። መምህሩ ከመገደሉ በፊት የነብዩ መሐመድን አወዛጋቢ የካርቱን ሥዕል ለተማሪዎቹ አሳይቶ ነበር። ጥቃቱን ተከትሎ ፕሬዝደንት ማክሮን በፈረንሳይ እክራሪነትን ለመታገል ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ከቱርክ እና ከሌሎች አገሮች መንግሥታት ጋር አለመግባባት ውስጥ ከቷቸዋል። የቱርኩ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ኢማኑኤል ማክሮን "የጤና ሕክምና ያስፈልጋቸዋል" ማለታቸው ይታወሳል። ኤርዶዋን የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣልም ጠይቀዋል። ይህንንም ተከትሎ በበርካታ የአረብ አገራት የፈረንሳይ ምርቶች ከመደብሮች መደርደሪያ ላይ ተነስተዋል።
news-49706004
https://www.bbc.com/amharic/news-49706004
አል-ቃይዳ ከቢን ላደን ልጅ መገደል በኋላ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሃምዛ ቢን ላደን፣ የቀድሞ የአል-ቃይዳ መሪ የኦሳማ ቢን ላድን ልጅ አሜሪካ ባካሄደችው ኦፕሬሽን መገደሉን ይፋ አደረጉ።
ሃምዛ ቢን ላደን ከአንድ ወር በፊት በርካታ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን በስም ያልተጠቀሱ የአሜሪካ የደህንነት ቢሮ ባልደረባን ዋቢ እያደረጉ የሃምዛን መገደል ዘግበው ነበር። ሃምዛ ከሁለት ዓመት በፊት በአሜሪካ መንግሥት ''አሸባሪ'' ተብሎ ተፈርጆ ነበር። • አልቃይዳ ከወዴት አለ? • የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ 'በአየር ጥቃት መገደሉ' ተነገረ የ30 ዓመት ወጣት የነበረው ሃምዛ አባቱን በመተካት የአል-ቃይዳ መሪ እንደነበረ ይታመናል። ሃምዛ በተደጋጋሚ በአሜሪካ እና በሌሎች ሃገራት ላይ ጥቃቶች እንዲሰነዘሩ መልዕክቶችን ያስተላልፍ ነበር። ሃምዛ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት የአባቱን ገዳዮች ለመበቀል በምስልና በድምጽ የተቀረጸ መልዕክት ለተከታዮቹ አስተላልፎ ነበር። ዋይት ሃውስ ባወጣው መግለጫ ላይ ፕሬዝደንት ትራምፕ "የአል-ቃይዳ ከፍተኛ አመራር የነበረው እና የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ ሃምዛ ቢን ላደን የአሜሪካ ጸረ-ሽብር ግብረ ኃይል በአፍጋኒስታንና ፓኪስታን ድንበር ባካሄደው ኦፕሬሽን ተገድሏል" ብለዋል። መግለጫው ሃምዛ የተገደለበት ኦፕሬሽን መቼ እንደተካሄደ አልጠቀሰም። ከጥቂት ወራት በፊት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ ያለበትን ለጠቆመኝ ወደ 1 ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ ብሎ ነበር። መስከረም 11፣ 2001 አሜሪካ፣ ኒው ዮርክ ውስጥ የአውሮፕላን ግጭት በመፍጠር ወደ 3000 የሚጠጉ ሰዎች በመግደል ተጠያቂ የሆነው ቢን ላደን፣ ከአደጋው ከአስር ዓመት በኋላ በ2011 ፓኪስታን ውስጥ በአሜሪካ ልዩ ሃይል መገደሉ ይታወሳል። አል-ቃይዳ ወዴት አለ? የአልቃይዳ ቡድን መስራች ኦሳማ ቢላደን ፓኪስታን ውስጥ በአሜሪካ ኃይሎች ከተገደለ ዓመታት ተቆጠርዋል። ቡድኑ በዓለማችን ላይ አደገኛ የሚባሉ የጂሃድ ጥቃቶችን ይፈፅም የነበረ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎችንም ያዝዝ ነበር። ቡድኑ ጥቃቶችን ለመፈፀም የማይነጥፍ የገንዘብ ምንጭ እንደነበረውም ይታመናል። ነገር ግን የቡድኑ መሪ ቢን ላደን ከተገደለ በኋላ የአል-ቃይዳ ስም እየደበዘዘና ጉልበቱም እየሟሸሸ መጥቷል። አል-ቃይዳን ይመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የሃምዛ ቢን ላደን መገደል የአል-ቃይዳን አቅም እጅጉን ሊያዳክም ይችላል ተብሏል። • በሳዑዲ 'አንድ ወንድ እኩል ይሆናል ሁለት ሴት' የአሜሪካ ደህንነት ኃይል የቢንላደን መገደልና የአይኤስ ቡድን መጠናከር አል-ቃይዳ አዳዲስ ዘዴዎችን እንዲጠቀም አስገድደውታል ይላል። አል-ቃይዳም ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር በአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅና ደቡብ እስያ ቅርንጫፎች አሉት። እ.ኤ.አ. በ2015 የአል-ቃይዳ መሪ የሆኑት አይማን አል ዛዋሃሪ ለቡድኑ መሪነት "የመንጋው መሪ አንበሳ" ብለው አንድ ወጣት አስተውቀዋል። ወጣቱ የኦሳማ ቢላደን ልጅ ሃምዛ ቢን ላዲን ሲሆን በብዙዎች የወደፊቱ የአልቃይዳ መሪ ተደርጎ ይወሰድ ነበር። ጥቂት ስለ አል-ቃይዳ ኦሳማ ቢን ላደን እ.አ.አ. 2001 ዓ.ም. ካቡል አፍጋኒስታን
news-51957856
https://www.bbc.com/amharic/news-51957856
ለሦስት ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው 61 ዓመት የኖሩት ዶክተር ካትሪን ሃምሊን ማን ናቸው?
ሥራቸው እንጅ ሌላኛው የሕይወታቸው ገጽታ ብዙም የማይወራላቸው ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን በ96 ዓመታቸው በትናንትናው ዕለት አርፈዋል።
ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን፤ በፈረንጆቹ ጥር 24፡ 1924 ነበር የተወለዱት። አውስትራሊያ የተወለዱት ዶ/ር ካትሪን የማሕጸን ሃኪም ናቸው። ኒውዚላንድ የተወለዱት ባለቤታቸው ዶ/ር ሬጊናልድ ሃምሊንም ተመሳሳይ ሙያ ያላቸው ነበሩ። ካትሪን ሃምሊን ከሲድኒ ወጣ ባለች አነስተኛ ከተማ ያደጉ ሲሆን በፈረንጆቹ 1946 ከሲዲኒ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ሳይንስ ተመርቀዋል። • ፊደል ያልቆጠሩት ኢትዮጵያዊት የቀዶ ህክምና ባለሙያ በ1958(እ.አ.አ) የኢትዮጵያ መንግሥት አዋላጅ ሃኪሞችን በአዲስ አበባ ልዕልተ ፀሐይ ሆስፒታል ለመቅጠር ያወጣውን ማስታወቂያ ሰምተው ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ወሰኑ። በዓመቱ በ1959 የስድስት ዓመት ልጃቸውን ሪቻርድን ይዘው ሃኪሞቹ ባልና ሚስቶች ውቅያኖስ አቋርጠው አዲስ አበባ ገቡ። ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን ካትሪን ሃምሊንና ባለቤታቸው ሬግ ሃምሊን ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት እነሆ 60 ዓመታት ተቆጠሩ። በዚያን ወቅት ታዲያ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ እቅዳቸው ለሦስት ሳምንታት ብቻ ቆይተው ወደሃገራቸው በመመለስ የቀድሞ ሥራቸውን ማሳለጥ ነበር። በዚያች ገና የኢትዮጵያን መሬት በረገጡባት ምሽት ግን አንድ የማሕጸን ሃኪም "ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፊስቱላ ሁኔታ ልባችሁን ይሰብረዋል" ሲል ነገራቸው። በዚያን ወቅት ታዲያ እነ ሃምሊን የፊስቱላን በሽታ አይተው አያውቁም ነበር። ምክንያቱ ደግሞ የማሕጸን ፊስቱላ በአብዛኛው የዓለም ክፍል ጠፍቶ ለዚሁ ተግባር ተብለው የተሰሩ ሆስፒታሎችም ተዘግተው ነበርና ነው። ኒዮርክን የመሳሰሉት ትልልቅ ከተሞችም በሽታውን አጥፍተው ገና በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ ነበር የፊስቱላ ሆስፒታሎቻቸውን የዘጋጉት። በዚህ ነበራዊ ሁኔታ ውስጥ የኖሩት እነ ካትሪን ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ በሽታ ምንም አይነት ህክምና እንደሌለውና በርካቶችን እያሰቃየ እንደሆነ እውቀቱ አልነበራቸውም። ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነባራዊ ሁኔታውን ማየት ሲችሉ ግን ተገረሙ። በእርግጥም ያ የማሕጸን ሃኪም እንደነገራቸውም ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያጋጥመው ፈውስ አልባ የሴቶች የፊስቱላ በሽታ የነካትሪን ልብ ተሰበረ። ለሦስት ሳምንታት የተባለው የኢትዮጵያ ቆይታ ተሰርዞ ተጨማሪ ወራትን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማሳለፍ ወሰኑ። ምክንያታቸው ደግሞ በፊስቱላ የሚሰቃዩ የኢትዮጵያዊያን እንስቶችን እንባ ማበስና ከስቃያቸው መገላገል ነበር። እነዚህ ሁለት የቀዶ ሕክምና ሙያተኞች ታዲያ ለሦስት ሳምንታት የመጡበትን የኢትዮጵያ ቆይታ በማራዘም በፊስቱላ ምክንያት የሚገለሉትን ኢትዮጵያዊያን ለሦስት ዓመታት ለማከም ወስነው ወደ ሥራ ገቡ። ሥራቸው ፈጣን ለውጥ አስመዘገበ። በተለይ በወሊድ ጊዜ የሚከሰተው የማሕጸን ፊስቱላ ታማሚዎችን ከማሰቃየቱ በላይ በማሕበረሰቡ ዘንድ በጥርጣሬ እንዲታዩ የሚያደርግና መገለልን የሚያስከትል ነበር። ሶስት ዓመት ሲሞላቸው ግን አዳዲስ የበሽታው ተጠቂዎች በመገኘታቸው ወደ አውስትራሊያ ከመመለስ ይልቅ በዚሁ ሥራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ መቀጠል እንዳለባቸው ባልና ሚስቱ ወሰኑ። ለሥራቸው እንዲያግዛቸው አንድ የሕክምና ተቋም ማቋቋም ደግሞ ተከታዩ እቅዳቸው ነበር። እናም ወደ ኢትዮጵያ በመጡ በአስራ አምስተኛው ዓመታቸው አዲስ አበባ ውስጥ በ1974 (እ.አ.አ) የፊስቱላ ማዕከል የሆነ ሆስፒታል ሠሩ። ይህ ሆስፒታልም ከ45 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ሴቶችን ከህመም ፈውሶ መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲመሩ አድርጓል። ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን ዛሬ የኢትዮጵያ ሃምሊን ፊስቱላ ማዕከል የማሕጸን ፊስቱላን ለማጥፋት በሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በአርአያነት የሚታይ ተቋም ነው። በሁሉም ዘርፎች ውጤታማ ሙከራዎችን አድርጎ ሴቶችን ከሕመማቸው ፈውሶ፤ ወደ ትክክለኛ የሕይወት መስመራቸው የሚያስገባና በቤተሰባቸውና በማሕበረሰባቸው ያላቸውን ሚና እንዲያስቀጥሉ የሚያስችል ተቋም ሆኗል። የእርሳቸው [ዶ/ር ካትሪን] ፋውንዴሽን፤ 'ካትሪን ሃምሊን ፋውንዴሽን' አንድ ዓላማ ብቻ ሰንቋል፤ ብቸኛ ዓላማውም ፊስቱላን ከምድረገጽ ማጥፋት ነው። ይህ የእርሳቸው ተቋም አቅም የሌላቸው የፊስቱላ ታማሚ ሴቶችን በነጻ የሚያክም ተቋም ነው። ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን ላደረጉት መተኪያ የሌለው አስተዋጽኦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ሰጥቷቸዋል። ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን ከታካሚዎቻቸው ጋር ለሦስት ሳምንታት ሥራ ከአውስትራሊያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን፤ የፊስቱላ ታማሚ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ስቃይ ቀሪ የግል ሕይወታቸውን አስረስቶ የበጎ አድራጎት ሥራቸውን ብቻ ለ60 ዓመታት እንዲሰሩ አድርጓቸዋል። በዚህ ምክንያትም ኢትዮጵያን አገራቸው አድርገው ላለፉት 60 ዓመታት ከሞት ጋር የሚታገሉ የፊስቱላ ታካሚዎችን ወደ ሕይዎት እየመለሱ የሙያና የሞራል ግዴታቸውን ማድረግ ከሚችሉት በላይ ሲከፍሉ ከቆዩ በኋላ፤ ዶክተር ካትሪን ሃምሊን አዲስ አበባ ውስጥ በአስገነቡት የፊስቱላ የሕክምና ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ በ96 ዓመታቸው ሕይወታቸው አልፏል።
news-52891113
https://www.bbc.com/amharic/news-52891113
በምዕራብ ትግራይ በመሬት ካሳ ጉዳይ ለተቃውሞ የወጡ '45 ሰዎች ታሰሩ'
በትግራይ ክልል ምዕራብ ዞን ቆራሪት በምትባል ከተማ በተቀሰቀሰ አዲስ ተቃውሞ ላለፉት ሁለት ቀናት መንገድ ዝግ ሆኖ መቆየቱ ተነግሯል።
የከተማዋ ነዋሪዎቹ በተቃውሞው ላይ "የመሬት ካሳ ይከፈለን፣ ለከብቶች መዋያ ቦታ ይሰጠን፣ የመሬት ይዞታ ባለቤትነት ይረጋገጥልን፣ በከተማዋ የመሬት ጉዳይ ጽ/ቤት ይዋቀርልን" የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች አቶ ደስታ ሃጎስ እና መምህር ገብረዋህድ፤ "የመሬት ካሳው ጥያቄው ስለቆየብን ተቸግረናል፤ የምንበላው አጥተናል። መንግሥት ከገጠር ወደ ከተማ ሲያስገባን ቃሉን ይጠብቃል ብለን አምነን ነበረ፤ ነገር ግን እስካሁን ካሳው አልተሰጠንም፤ ካሳው ይሰጠን" ሲሉ ጥያቄያቸው ይህ እንደሆነ አስረድተዋል። ይህም ጥያቄም በሰላማዊ ሰልፍ ተጀምሮ፤ ሰው እየተሰባሰበ ድንጋይ በመወራወር፣ መንገዶችን ወደ መዝጋት ማምራቱ የተነገረ ሲሆን፤ ከትናንት በስቲያ የተዘጋው መንገድም የተከፈተውም ትናንት ነው። የከተማው መስተዳደር እና ምክር ቤት እንደ አዲስ እየተዋቀረ ባለባት ቆራሪት ከተማ ከአመራሮቹ አንዱ አቶ ኪዳነማሪያም አባይ፤ ከሕዝቡ የቀረበላቸውን ጥያቄ ትክክል መሆኑን አምነው፤ "አንዳንድ ሰዎች ግን የሕዝቡን ጥያቄ ተገን በማድረግ ድንጋይ እንዲወረወር፤ መንገድ እንዲዘጋና ሥራዎች እንዲስተጓጎሉ አድርገዋል" ብለዋል። "የሕዝቡን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ እየመለስን ነው" ያሉት አቶ ኪዳነማሪያም፤ አሁንም ጥያቄዎቻቸው ተገቢ ስለሆኑ እንደሚመልሱ እና ጥያቄዎቹን ለበላይ አካልም እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል። አቶ ኪዳነማሪያም አክለውም "ያልተፈለገ አመጽና አድማ የፈጠሩ ሰዎችን ሥርዓት ማስያዝ ስላለብን የተወሰኑ ሰዎችን ወስደን ልንገስጽ እንፈልጋለን። የታሰሩ ሰዎችም አሉ። እነሱን መክረን እንመልሳቸዋልን" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ 45 ሰዎች እንደታሰሩ ቢነገርም፤ አመራሩ ግን ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ እርግጠኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋ። ስለቆራሪት ከተማ ቆራሪት ከተማ የኢትዮጵያ መንግሥት በአካባቢው ከሚሰራቸው አንዱ የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክትን ተከትሎ በ2005 ዓ.ም ተዋቀረች። በተለይ ለስኳር የሸንኮራ አገዳ ምርት በጣም ሰፊ መሬት ያስፈልግ ስለነበር ለዚህ አገልግሎት ሲባል ከእርሻ መሬታቸው የተነሱ አርሶ አደሮች ነበሩ። እነዚህን አርሶ አደሮችን አሁን ከተማዋ ወደምትገኝበት ቦታ ተወስደው ቆራሪት የሚባል ከተማ ተመሰረተች። አርሶ አደሮችም ኑሯቸውን እዚያው አደረጉ። ነገር ግን አርሶ አደሮቹ ለነበራቸው የእርሻ መሬት እንዲሁም የከብቶች መዋያ ላለፉት 7 ዓመታት የመሬት ካሳ ሲጠይቁ ቆይተዋል። አንዳንዶቹ ጥያቄያቸው የተመለሰላቸው ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ እስካሁን ድረስ የመሬት ካሳ እንዳልተከፈላቸው ይናገራሉ። ከሰሞኑ ሲያነሱት የነበረው ጥያቄም የመሬት ካሳ ይሰጠን የሚል ሲሆን፤ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄያቸው እንዲመለስ፤ መሬታቸው ወደ ልጆቻቸው በውርስ መልክ በማስተላለፍ የባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
news-45019065
https://www.bbc.com/amharic/news-45019065
ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ
የሰላሳ ዓመቷ ሩሚያ ሱሌ መስከረም 01 ቀን 2010 ዓ.ም ከጂግጂጋ ተፈናቅላ የመጣች ሲሆን "ራበን ዳቦ ስጡን" የሚል ጥያቄ በማንሳቷ በመከላከያ ሰራዊት አባላት በጥይት ተመትታ ህይወቷ ማለፉን የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ዛሬ ያወጣው ሪፖርት ያትታል።
ከሞያሌ ከተማ ቻሙክ ቀበሌ የተፈናቀሉ ሰዎች የሰሩት የላስቲክ ቤቶች ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን ከጥር 29 2009 ዓ.ም እስከ ጥር 2010 ዓ.ም ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። በኢትዮጵያ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች በባለፉት ሁለት ዓመታት የብዙዎችን ህይወት ቀጥፏል፣ ንብረት ወድሟል እንዲሁም የሀገሪቷን ህልውናም አደጋ ላይ ጥለውታል። በተለይም በኦሮሞና በኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔር ተወላጆች መካከል ያለው ግጭት እጅጉን ተባብሶ እና መልኩን ቀይሮ ወደ ጥቃት በመቀየር አስከፊና አስፈሪ ደረጃ ላይ ደርሷል። •በርካታ ሰዎች ከሞያሌ በመሸሽ ወደ ኬንያ ገብተዋል •በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ድንበር ግጭት የገዳ ስርዓት መፍትሔ ለምን አላመጣም? ከግጭቱም ጋር በተያያዘ ሰላምን ሊያስከብሩ የተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት፣ በልዩ ፖሊስና የፀጥታ አካላት በሰብዓዊ መብት ጥሰት በቀጥታ ተሳታፊ እንደሆኑም ሪፖርቱ ያትታል። ብዙዎችን በመግደል፣ አስገድዶ በመድፈር፣ በዝርፊያና በማሰቃያት ተሳታፊ ናቸው በማለትም ይወነጅላቸዋል። ደብዛ የማጥፋት ወንጀሎች በሁለቱም ክልሎች መፈፀማቸውን ጠቁሟል በሁለቱ ክልሎች በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶችም እንደተደፈሩ ሪፖርቱ አስቀምጧል። ከነዚሀም ውስጥ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ አመት ተማሪ የነበረች አንዲት ሴት በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ለሶስት ከመደፈር በተጨማሪ፣ በዱላ እንደተደበደበችና በጩቤ እንደተወጋች ሪፖርቱ ጨምሮ ያትታል። የደረሱት የሰብዓዊ መብት ጥቃቶች ለመስማት የሚዘገንኑ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በአምስት ወታደሮች የተደፈረችና ለ28 ቀናትም በፊቅ ተራራ ላይ የታሰሩ ሴት ይገኙበታል። በስለት ታርደው የተገደሉ፣ በእሳት ተቃጥለው የሞቱና ከዚሀም በተጨማሪ የሶስት ዓመት ህፃን ልጅም እንደተገደለም ሪፖርቱ ጠቅሷል። ተቋሙ በልዩ መግለጫው ላይ ወደ 30 በሚጠጉ የሁለቱ ክልል አጎራባች ወረዳዎች በተደረገ ማጣራት ከ500 በላይ ዜጎች መገደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ለአካል ጉዳት እንደተዳረጉ አስታውቋል። በዚሀም ምክንያት በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት ላይ ያሉ ሲሆን የሰመጉ ባለሙያዎች በሚያነጋግሯቸው ወቅት በተደጋጋሚ ራሳቸውን እየሳቱ ይወድቁ ነበርም ይላል። ከማንነት፣ ከአስተዳደርና ከድንበር ይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል በሚገኙ በተነሱ ግጭቶች ምክንያት ከሁለቱም ክልሎች የተፈናቀሉት ዜጎች ቁጥር ከአንድ ሚሊየን በላይ እንደሚበልጥም ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እና OCHA3 በጋራ ያወጡት ሪፖርት ያሳያል። የችግሩን አሳሳቢነትም የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ቢንያም አባተ ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ቃሎች የተገቡ ቢሆኑም ወደ ተግባር ሊቀየሩ እንደሚገባም ዳይሬክተሩ ይናገራሉ። በጥቃቱና በግጭቱ እጃቸው ያለበት አካላትን ተጠያቂ ከማድረግ ጀምሮ በቂ ትኩረትና ዘለቄታዊ መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባ አቶ ቢንያም እንደ መፍትሔ የሚያስቀምጡት ነው። ሰመጉ የተጎጂዎች ቁጥርና ጉዳት መጠኖችን በዘረዘረበት ባለ 55 ገፅ ልዩ ሪፖርቱ ፤ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ፣ለወደፊቱም እንዳይደገሙ የመከላከል ርምጃ እንዲወሰድ ፣ጉዳት የደረሰባቸው ካሳ እንዲከፈላቸውና ተጠያቂዎችም ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
news-54886515
https://www.bbc.com/amharic/news-54886515
ኦነግ-ሸኔ፡ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በታጣቂዎች ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው አለ
የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተነጥሎ እንደወጣ በሚነገርለትና ኦነግ-ሸኔ ተብሎ በሚታወቀው ታጣቂ ቡድን ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ተነገረ።
የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ እንዳስታወቀው የክልሉ ልዩ ኃይል ከሰሞኑ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ባካሄደው ዘመቻ በታጠቂው ቡድን አባላት ላይ "ድል" ተመዝግቧል ብሏል። በዚህም በደቡብ ኦሮሚያ በሚገኘው የጉጂ ዞን 14 የኦነግ-ሸኔ አባላት መገደላቸውን የዞኑን አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኡዶን ጠቅሶ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በምዕራብ ኦሮሚያ አንዳንድ ስፍራዎች የቴሌኮም አገልግሎቶች ከተቋረጡ አራት ቀናት ማለፋቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቴሌኮም አገልግሎቶቹ እንዲቋረጡ ተደረገው የክልሉ መንግሥት በተለያዩ ስፍራዎች በታጣቂዎች ላይ እየወሰደ ካለው እርምጃ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም። በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች በሚገኙ እንደ ደምቢ ዶሎ፣ ቤጊ እና ጊዳሚ ከተሞች ስልክ እንደማይሰራ ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች አረጋግጠዋል። መቀመጫቸውን ነቀምቴ ከተማ ያደረጉት የኢትዮቴሌኮም ምዕራብ ሪጅን ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙላቱ ጋዲሳ ከላይ በተጠቀሱት ስፍራዎች የቴሌኮም አገልግሎት መቋረጣቸው የተሰማው ከጥቅምት 25 ጀምሮ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነገር ግን በአካባቢዎቹ የቴሌኮም አገልግሎቱ ለምን እንደተቋረጡ እንደማያውቁ አቶ ሙላቱ ገልጸዋል። "አገልግሎቱን ለማቋረጥ እና ለማስጀመር ስልጣኑ አልተሰጠንም። የእኛ ኃላፊነት ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት ነው" ብለዋል። የሞባይል ስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ለኢትዮቴሎኮም የበላይ አስተዳደር አስታውቀው ምላሽ እየጠበቁ እንደሆነ ጨምረው ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በምዕራብ ኦሮሚያ ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ላይ መንግሥት እርምጃ በወሰደበት ጊዜ የቴሌኮም አገልግሎት ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ እንዲቆይ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የጦር ክንፍ ነው የሚለው የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች በምዕራብ ኦሮሚያ እና በጉጂ ዞኖች እንደሚንቀሳቀሱ የሚነገር ሲሆን በስፍራዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ለሚፈጸሙ ጥቃቶች የክልሉ መንግሥት ቡድኑን ተጠያቂ ያደርጋል። ቡድን በክልሉ በንጹሃን ዜጎች እና በአካባቢ ባለስልጣናት ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶችና ግድያዎች ጋር በተደጋጋሚ ስሙ ሲነሳ ቆይቷል። በቅርቡም በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ በተበላው አካባቢ ለተገደሉት 36 ሰዎች የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ተጠያቂ መሆናቸው ተነግሯል።
news-51764735
https://www.bbc.com/amharic/news-51764735
አሜሪካ በቂ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ እንደሌላት ገለፀች
በመሃል አሜሪካ እንዲሁም ዳርቻዎች የኮሮናቫይስ ስርጭት እየጨመረ ቢሆንም አገሪቱ በቂ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያ እንደሌላት ዋይት ሃውስ አምኗል።
ምክትል ፕሬዘዳንቱ ማይክ ፔንስ የትራምፕ አስተዳደር በዚህ ሳምንት ውስጥ ያስፈልጋል የተባለውን አንድ ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያ ማሟላት እንደማይችል በግልፅ ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ኮንግረስ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው እንቅስቃሴ የድንገተኛ እርዳታ በጀት ለማፅደቅ ባልተለመደ ሁኔታ እየተጣደፈ መሆኑ ተሰምቷል። በትናንትናው እለት በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 12 መድረሱም ታውቋል። በአሁኑ ወቅትም በመላ አገሪቱ 200 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በ20 ግዛቶች ውስጥ ተመዝግበዋል። እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ 92 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 80 ሺህ የሚሆኑት የበሽታው ክስተቶች የተመዘገቡት ቻይና ውስጥ ነው። ሦስት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የሞቱ ሲሆን በተመሳሳይ አብዛኛው ሞት የተመዘገቡት ደግምኦ በቻይና ውስጥ ነው። በዋሽንግተን የሲያትል ባለስልጣናት 20 የሚሆኑ በበሽታው የተያዙ ሰዎች መመዝገባቸውን፤ ይህ ደግሞ በአካባቢው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 70 እንዳደረሰው ገልፀዋል። ከሟቾቹ መካከል ዘጠኝ የሚሆኑት ሞቶች የተመዘገቡት በአንድ የአዛውንቶች መንከባከቢያ ማዕከል ውስጥ ነው። ማዕከሉ ትክክለኛውን የኮሮናቫይረስ መከላከያ መርህ እየተከተለ ለመሆኑ ምርመራ ተጀምሮበታል። እንደ ማክሮሶፍትና አማዞን ያሉ የሲያትል አካባቢ ትልልቅ የቢዝነስ ተቋማት ቢሯቸውን በመዝጋት ሠራተኞች ከቤት እንዲሰሩ አድርገዋል። በኒውዮርክ የተመዘገበው የኮሮናቫይረስ ቁጥር በአንድ ጀምበር ሁለት እጥፍ አድጎ 22 መድረሱም ተነግሯል። የከተማዋ ከንቲባም በአፋጣኝ በርካታ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎች እንዲቀርቡላቸው ጠይቀዋል። 200 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በጥርጣሬ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ ይገኛሉ። በትናንትናው እለት ሳንፍራንሲስኮም የመጀመሪያውን በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው አግኝታለች።
47480287
https://www.bbc.com/amharic/47480287
በመሰለል የምትከሰሰው ሩሲያ 600 የሚጠጉ የውጪ ሀገራት 'የስለላ' ሰራተኞችን ቀነሰች
ፕሬዝዳንት ፑቲን የውጭ ሃገራት የስለላ ስራ በሩሲያ ላይ እየተጠናከረ በመምጣቱ ምክንያት በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2018 ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ የውጭ ሃገራት የስለላ ሰራተኞች መታገዳቸውን አስታውቀዋል።
ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት ፕሬዝዳንቱ 129 ቋሚ ሰራተኞችና 465 ተወካይ የውጭ ልዩ የስለላ አገልግሎት ሰራተኞች ታግደዋል ብለዋል። ሩሲያ የሌሎች ሃገራትን የስለላ ሰራተኞች ብታግድም የራሷ የስለላ ሰራተኞች ራሳቸው የተለያዩ ሴራዎችን በመጠንሰስ ይከሰሳሉ። ለምሳሌ የቀድሞውን የስለላ ወኪል ሰርጊ ስክሪፓል ለመመረዝ ማሴራቸው ይነገራል። • አረጋውያንን በነጻ የሚያሳፍረው ባለታክሲ • አሜሪካዊቷ ሴናተር በአየር ኃይል ባለስልጣን መደፈራቸውን ተናገሩ የአውሮፓ ህብረትና እንግሊዝ ባለፈው አመት የስከሪፓል ጥቃትን ያቀነባበረቸው ሩሲያ ናት ማለታቸውን ተከትሎ 25 ሃገራት የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ከሃገራቸው አስወጥተው ነበር። አሁን ሩሲያ በወሰደችው ርምጃ ሆላንድ ፣ ቼክ ሪፖብሊክና ስዊድን የስለላ ሰራተኞቻቸው የታገዱባቸው ሃገራት ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ሩሲያ በምርጫ ጣልቃ በመግባትም በምዕራባዊያን ዘንድ ትከሰሳለች። በስም ሩሲያ ብለው ባይጠቅሱም የአውሮፓ ህብረት ካውንስል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ተስክ ባለፈው ማክሰኞ "ጸረ የአውሮፓ ህብረት" የሆኑ አካላት ግንቦት ላይ በሚካሄደው የህብረቱ የምክር ቤት ምርጫ ጣልቃ ለመግባት እየሰሩ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን በመግለጫቸው "የወጭ የስለላ አገልግሎቶች በሩሲያ ላይ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ የሳይንስና የቴክኖሎጅ ፍላጎታቸው እየጨመረ ነው በመሆኑ ለሩሲያ ይበጃል ያልነውን የመፍትሔ ርምጃ ወስደናል'' ብለዋል። • የእኩልነት ዓለም ብለው የሚገልጿት የአውራምባውያኑ አምባ እንደዚህ አይነት ተግባራት በሩሲያ እየተለመደ መጥቷል። በየአመቱ ፕሬዝዳንቱ የፌደራሉን የደህንነት ተቋም ይጎበኛሉ። በዚህ ጉብኝታቸውም ሩሲያ ምን ያክል የውጭ የደህንነት ሰራተኞችን እየተከታተለች እንደሆነ ከአመት አመት ያለውን ንጽጽር ይገልጻሉ። ከአራት አመት በፊት 52 ቋሚ ሰራተኞችንና 290 የውጭ ወኪል የስለላ ሰራተኞችን እንደሚቀንሱ ቢናገሩም አሁን ላይ የተመዘገበው ቁጥር ግን ከተባለው ጋር ሲነጻጸር የተጋነነ ነው። 129 ቋሚና 465 የውጪ ወኪል ሰራተኞች ተቀንሰዋል።
news-52103778
https://www.bbc.com/amharic/news-52103778
ኮሮናቫይረስ ቤላሩስ፡ በኮቪድ-19 ያልተሸበረችው ብቸኛዋ አውሮፓዊት አገር
አሁን አውሮፓ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማዕከል ነች። ነገር ግን አውሮፓ ውስጥ ሆና ባላስልጣናቷ በአሁኑ ጊዜ ዓለምን እኣስጨነቀ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ ምንም አይነት የተለየ ማስጠንቀቂያም ሆነ ትዕዛዝ የማይሰጡባት አገር አለች።
ቅዳሜ ዕለት ጨዋታ ለማየት ስታዲየም ከነበሩ ተመልካቾች በከፊል የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ ቤላሩስ ከሌሎች የአውሮፓ አገራትም ሆነ ከጎረቤቶቿ ሩሲያና ዩክሬን የተለየ መንገድ እየተከተለች ነው። ጎረቤት ዩክሬን በመዲናዋ ኪየቭና በሌሎች ግዛቶቿ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች። ሩሲያም ትምህርት ቤቶችን ዘግታለች፣ ብዙ ሰው የሚያሰባስቡ ዝግጅቶችን ሰርዛለች። በተጨማሪም ሁሉንም በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚደረጉ በረራዎችን አቁማለች። በቤላሩስ ግን በብዙ መንገድ ሕይወት በትናንቱ መንገድ እየቀጠለ ነው። ቤላሮስ ምንም እንኳ 94 ዜጎቿ በቫይረሱ ቢያዙም [ሞት አልተመዘገበም እስከ ትናንት ድረስ] ድንበሮቿ ክፍት ናቸው፣ ሰዎች ወደ ሥራ ይሄዳሉ፣ እንዲያውም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ 6 ታላላቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ቤላሩስ ውስጥ ተደርገዋል። 'አትሸበሩ' የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ አገራቸው የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመግታት ምንም አይነት ቅድመ ጥንቃቄ እንደማያስፈልጋት ገልጸዋል። "የሚያጋጥም ነገር ነው። ዋናው ነገር ግን አለመደንገጥ ነው " ብለዋል ባለፈው ማክሰኞ ሚኒስክ ውስጥ ከቻይናው አምባሳደር ጋር በተገናኙበት ወቅት። ቤላሮስ ቲያትርን፣ ሲኒማን ወይም ሌሎች ሕዝባዊ መሰባሰቦችን አልከለከለችም። ቤላሩስ በዓለም ላይ ካሉ አገራት መካከል የእግር ኳስ ውድድሯን ያላቋረጠች ብቸኛዋ አገርም ናት። የቤላሩስ እግር ኳስ የውስጥ ሊግ እንደቀጠለ ሲሆን ተመልካቾችን ሰብስቦ ከማዝናናት በተጨማሪ ለጎረቤት ሩሲያዊያን ኳስ አፍቃሪዎችም በቴሌቪዥን በማስተላለፍ በዚህ የጭንቀት ጊዜ የመዝናኛ አማራጭ እየፈጠረላቸው ነው። ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ 'ኮሮናቫይረስን ትራክተር ያድነዋል' የፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ 'ኮሮናቫይረስን ትራክተር ያድነዋል' ንግግር ብዙ ሰዎችን ያወዛገበ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ በማሕበራዊ ሚዲያ እያሽሟጠጡት ይገኛል። ፕሬዝዳንቱ ማለት የፈለጉት 'እርሻ ቦታ ላይ ጠንከረን እንስራ' ነው። ምንም እንኳ እራሳቸው ፕሬዝዳንቱ አልኮል የማይጠጡ ቢሆኑም ለዜጎቻቸው ግን ከቻላችሁ የተወሰነ ቮድካ ብትጎነጩበት የኮሮናቫይረስን ስርጭት መግታት ትችላላችሁ በማለትም መክረዋል። ነገር ግን ከቤላሩስ ውጭ ባሉ የዓለም አገራት ላይ ቫይረሱ እያስከተለ ያለውን ቀውስ ስለሚያዩ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የአገሬው ሰዎች ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል። በሚኒስክ ተማሪዎች ሰው ከተሰበሰበበት ቦታ ላለመገኘት ሲሉ ሆን ብለው ታምሜያለሁ በማለት እቤታቸው እየቀሩ ይገኛሉ። ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የተወሰኑ ሰዓታትን ብቻ ማስተማር ጀምረዋል። በሚኒስክ በጣም ውስን ሰዎች ብቻ ወደ ጎዳና ይወጣሉ። በእድሜ የገፉ ሰዎችም የወረርሽኙ ቀዳሚ ተጠቂ መሆናቸው ግንዛቤው አለ። የሚገርመው ግን ይህ አይነቱ የግንዛቤ ፈጠራ ከባለስልጣናት ዘንድ የሚመጣው በጣም ውስኑ ነው። ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ሁሉም በዓለም አቀፍ በረራዎች በኩል ወደ ቤላሩስ የሚመጡ ሰዎች ስለሚመረመሩ ምንም መጨነቅ አያስፈልግም ብለዋል። "በየቀኑ ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ፖዚቲቭ ሆነው ይገኛሉ፤ ነገር ግን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለአንድ ወይም ሁለት ሳምንት ይቆዩና ይለቃቃሉ" በማለት ፕሬዝዳንቱ ለቫይረሱ መጨነቅ እንደማያስፈልግ በመግለጽ ዜጎቻቸውን አበረታትተዋል። ባለፈው ሳምንት የተደረገ የእግር ኳስ ግጥሚያ 'በፍርሃት የሚያሸብሩትን ፈልጓቸው' ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ በፍርሃት መራድ ከቫይረሱ በላይ አደገኛ ነው ይላሉ። በዚህም ምክንያት ለአገሪቱን የደኅንነት መስሪያ ቤት [የቤላሩስ ኬጂቢ] እነዚህን "በፍርሃት የሚያሸብሩትን ፈልጓቸው" የሚል ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። በአሁኑ ወቅት ምንም እንኳ በይፋ ባይነገርም በቫይረሱ ሳይሆን እንዳልቀረ የተነገረላቸው ሁለት ሰዎች ሞተዋል። የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት አካል የነበረችው ቤላሩስ በብዙ ነገር የተለየች አገር ነች። በአውሮፓ የሞት ቅጣትን ተግባራዊ የምታደርግ ብቸኛዋ አገር ነች። ባለስልጣናቷ በኮሮናቫይረስ ላይ ዘና ያለ አተያይ በመያዝም ከአውሮፓ በእጅጉ የተለዩ ናቸው። ባልተለመደ መልኩ ለወትሮው ሁሉንም ነገር ካልተቃወምኩ ሲል የነበረው የቤላሩስ የተቃዋሚ አክቲቪስት አንድሬይ ኪም "ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ልክ ናቸው። ምክንያቱም ቤላሩስ ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴዋ ቢዘጋ ምጣኔ ሃብቷ ይሞታል" በማለት ከፕሬዝዳንቱ ጋር መስማማቱን ገልጿል። "አሁን ነገሮች ላይ፣ ታች እየተዘበራረቁ ነው። በዚህ ወቅት ደግሞ መሪዎቿ በሕዝበኝነት የማይነዱ ነገር ግን ለዜጎቻቸው በጎ ነገር የሚመኙባት ብቸኛዋ የዓለም አገር ቤላሩስ ነች" በማለት አክሏል። "ይህን በማለቴ ክፉኛ እንደምብጠለጠል አውቃለሁ፤ ነገር ግን በዚህ እብደት በነገሰበት ሁኔታ ውስጥ ዝም ብዬ መቀጠል አልፈልግም" በማለት ቀሪው ዓለም ስለኮሮናቫይረስ የሚያወራው "እብደት" መሆኑን ኪም አመላክቷል። እርሱ እንደሚለው ቤላሩስ ከቫይረሱ ነጻ የምትሆነው የመመሪያ ጋጋታ በማውጣት ወይም ሌላ ነገረ በማድረግ ሳይሆን 'ምንም ባለማድረግ' ነው።
43254385
https://www.bbc.com/amharic/43254385
''ከ122 ዓመት በፊት የተጣለ መሰረት ዛሬ እየተናደ እንዳይሆን'' ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ
የታሪክ ምሁርና የግጭቶች ተመራማሪው ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ፤ የዛሬ 122 ዓመት ዓድዋ ላይ የተጣለ መሰረት ዛሬ እየተናደ እንዳይሆን ስጋት አላቸው።
ዛሬም የሃገሪቷን አንድነት የሚያሰጋ ሁኔታ ላይ ያለንበት ምክንያት "ያልሰራነው የቤት ሥራ ምን ይሆን?" ሲሉም ይጠይቃሉ። "ዛሬ ስለ ኢትያጵያዊነት እና ስለ ብሔረ-መንግሥት መነጋገራችን አሳዛኝ ነው" ይላሉ። "ገዢው ፓርቲ ዲሞክራሲንና ነፃነትን ጨምድዶ ይዞ ቦታውን ለፅንፈኞች ስላመቻቸ ሃገሪቱን አደጋ ላይ ጥሏታል" የሚሉት ፕሮፌሰር ገብሩ ከውስጥም ከውጭም "ጠንቀኛ ፖለቲካ የሚያራምዱ" እንዳሉም ጠቅሰዋል። ያልተተገበረ ህገ- መንግሥት ፕሮፌሰር ገብሩ ሦስት መንግሥታትና ሦስት ህገ-መንግሥታትን ያሳለፉ ናቸው። በመርህ ደረጃ አሁን ሥራ ላይ ያለው ህገ-መንግሥትና ፌደራላዊ ሥርዓት የተሻለ መሆኑን ይናገራሉ:: ይሁን እንጂ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አቀረቡት ባሉት መሰረት መሻሻል እንዳለበትም ያምናሉ። እሳቸው እንደሚሉት የኢፌዴሪ ህገ-መንግሥት በመሰረቱ ጥሩ ይሁን እንጂ ተግባራዊነቱ ጥያቄ ውስጥ ይገባል። ለምሳሌ ህገ- መንግሥቱ ለክልሎችና ለፌደራል መንግሥት ያስቀመጠው የስልጣንና የሃብት ክፍፍል ተጥሶ እንደቆየ በዋናነንት ያነሳሉ። በተለይ የ1993 ዓ.ም የህወሓት ክፍፍልን ተከትሎ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስልጣንን ለብቻቸው ጠቅልለው ስለያዙት፤ የክልሎች መብትና ስልጣን ተቀንሶና ተንዶ ቆይቷል ይላሉ። በ2008 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው አመፅ በአንድ ግዜ የተከሰተ እንዳልሆነ የሚጠቅሱት ፕሮፌሰር ገብሩ፤ የህገ- መንግሥቱ አለመተግበር፣ የአንድ ፓርቲ ጠቅላይነት፣ ህዝቡ መብቶቹን ለማስጠበቅ መንገዱ እየጠበበ መምጣት እንዲሁም ብሶቱን በአደባባይ የሚያሰማበት መንገድ መዘጋቱ እንደ መነሻ ይጠቅሳሉ። ፕሮፌሰር ገብሩ በትምህርቱ ጥራት ላይ ጥያቄ ቢያነሱም፤ ባለፉት 27 ዓመታት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መስፋፋታቸውን ያደንቃሉ። ይሁን እንጂ "በየዓመቱ በሺዎች ቢመረቁም ኢኮኖሚው ግን ይህን የሚሸከመው አልቻለም። ስለዚህም ሥራ አጥነት በዚሁ ልክ ጨምሯል" ይላሉ። እነዚህ ሁኔታዎች የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ራሱን እንዲመረምር ገፋፍቶታል የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ እነለማ መገርሳ 'ፖፕሊስት' (የህዝቡን የልብ ትርታ የተረዱ) መሪዎች ይሉዋቸዋል። የህዝቡንም ችግር ለመፍታት ሞክረዋል ይላሉ። ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ የፍርሃት እርምጃ ኣራቱ የኢህአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶችንም "ራሳችንን ፈትሽናል ወቅታዊና ጊዜያዊ መፍትሄ እንሰጣለን" ብለው ደጋግመው ቢማፀኑም "ህዝቡ በዚህ አልረካም" ይላሉ። በግንባሩ እርምጃዎች ህዝቡ አለመርካቱን አመላካች ያሉት፤ አሁን በድጋሚ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ ምክንያት መፈጠሩን ነው። "አዋጁ አስገራሚ ነው፤ ከፍርሃት የመነጨ ይምስለኛል" የሚሉት ፕሮፌሰር ገብሩ፤ ለችግሩ መሰረታዊ መፍትሄ እንደማይሆን ይሞግታሉ። በቀጥታ ከህዝቡ፣ ከተቃዋሚዎች፣ ከምሁራን እና ከፖለቲካ ጠበብት ጋር መመካከርንም በመፍትሄነት ያስቀምጣሉ። "መፍትሄው ሁሉን አቀፍ መሆን አለበት። ህዝቡ በአገሩ ጉዳይ ላይ ሊነጋገር ይገባል። ህግም ቢወጣ የሚተገብረው ህዝቡ ነው። ታንክና የጦር መሳርያ ማሰለፍ ሁኔታውን አይቀይረውም" ይላሉ ለጊዜው ፋታ ይሰጥ እንደሆነ በመገመት። "አሁን የደረስንበት የሃገርን አንድነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ችግርን ኢህአዴግ ብቻውን የሚወጣው አይደለም" ይላሉ ጨምረው። ፓርላማው በኢህአዴግ 'ካድሬዎች' ብቻ መሞላቱና የፍትህ አካሉ የለም በሚባልበት ደረጃ መድረሱን የሚናገሩት ፕሮፌሰር ገብሩ፤ "ተወቃሹ ሥራ አስፈፃሚው ብቻ ሳይሆን ግንባሩ በአጠቃላይ ነው" ይላሉ። በገዢው ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚው ጉድለት ነው ተብሎ የሚቀርበውን በመቃወም። ያለተጠያቂነትና ያለግልፅነት ሃገሪቱን ለ27 ዓመታት የመራ ድርጅት በማለት ግንባሩን ነቅፈው፤ "በድርጅቶች መካከል ያለው አለመተማመን አንድ ገዢ ፓርቲ ያመጣው አበሳ ነው" ይላሉ።
52891112
https://www.bbc.com/amharic/52891112
የጥቁር አሜሪካዊያን ተቃውሞ ወደ ፈረንሳይ ተዛመተ
በሺ የሚቆጠሩ ፓሪሳዊያን የተጣለባቸውን እቀባ ቸል በመላት አደባባይ ወጥተዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ በአሜሪካ የተቀሰቀሰው የጥቁሮች የመብት ጥያቄ ነው፡፡
የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ፈረንሳዊያንን የእነርሱንም ቁስል ነካክቶባቸዋል፡፡ በ2016 በግፍ ተገድሏል የሚሉትን የ24 ዓመቱን ጥቁር ፈረንሳያዊ አዳማ ትራኦሬን ለማስታወስም ጭምር ነው አደባባይ የወጡት፡፡ ወጣቱ ትራኦሬ ሦስት ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ሲያውሉት መላ ሰውነታቸው ስለተጫነው መተንፈስ አቅቶት ነበር ለሞት የተዳረገው፡፡ ፖሊሶች በበኩላቸው "እኛ ለሞት በሚያበቃ ሁኔታ አልተጫንነውም፤ እሱን በቁጥጥር ለማስቻል የሚያበቃ ጉልበት ነው የተጠቀምነው" ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ በኋላ በተደረገ ምርመራ ወጣቱ የልብ ድካም ሕመም እንደነበረበት ተረጋግጧል፡፡ ከርሱ ግድያ ጋር ምርመራ ላይ የነበረው ፖሊስም ነጻ ተደርጓል፡፡ ትናንት ማክሰኞ በፓሪስ አቅራቢያ ባሉ ከተሞች ፖሊስና አድመኞች የተጋጩትም የትኻውኼን ሞት ከጆርጅ ፍሎይድ ጋር አስታከው ዘረኝነትን ለመቃወም ሰልፍ በመውጣታቸው ነበር፡፡ የፓሪስ የፖሊስ አለቃ አባሎቻቸው በዘረኝነት መወቀሳቸውን አጣጥለውታል፡፡ በአንድ መሰብሰብ የሚከለክለውን እቀባ ጥሰው አደባባይ የወጡ ሰልፎች ብዛት ከ20ሺ ይልቃል ተብሏል፡፡ ተቃውሞው መጀመርያ አካባቢ ሰላማዊ የነበረ ቢመስልም ኋላ ላይ ግን ግጭትን አስተናግዷል፡፡ ሰልፈኞች ፖሊስ ላይ ድንጋይ የወረወሩ ሲሆን ፖሊስ በበኩሉ አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሟል፡፡ ተቃውሞው ከዋና ከተማዋ ፓሪስ አልፎ በማርሴይና በሌዮን አንዲሁም በሌሎች የፈረንሳይ ከተሞች ጭምር ተስፋፍቷል፡፡ ተቃዋሚዎቹ ‹‹ የጥቁር ሕይወት ዋጋው ስንት ነው›› (ብላክ ላይቭስ ማተር) የሚለውን መፈክር ይዘው ታይተዋል፡፡ ይህ የጥቁሮች የመብት እንቅስቃሴ በአሜሪካ ይጀመር እንጂ አድማሱን እያሰፋ የብዙ አገራት ጉዳይ ሆኗል፡፡ በጎርጎሳውያኑ 2016 የአዳማ ትራኦሬን ሞት ተከትሎ ለተከታታይ ቀናት በመላው ፈረንሳይ ተቃውሞ ተቀጣጥሎ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኮሮናቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ በፈረንሳይ ከ10 ሰዎች በላይ በተመሳሳይ ቦታ መሰብሰብ ክልክል ተደርጓል፡፡ ኾኖም ለዚህ ክልከላ ተቃዋሚዎቹ ቁብ የሰጡት አይመስሉም። የአዳማ ትራኦሬ እህት ለፈረንሳይ የዜና ወኪል እንደተናገረችው ‹‹ ዛሬ ተቃውሞ የወጣነው ለወንድሜ አዳማ ብቻ አይደለም፡፡ ለጆርጅ ፈሎይድ የግፍ ግድያ ብቻም አይደለም፡፡ ተጋድሎው ለሁሉም ተጨቋኞች ነው›› ብላለች፡፡
news-42476837
https://www.bbc.com/amharic/news-42476837
የሮማው ጳጳስ አለም የስደተኞችን ጉዳይ ቸል እንዳይል ተማጸኑ
የሮማው ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በፈረንጆቹ ገና ዋዜማ መላው አለም በስቃይ ላይ ያሉ ስደተኞችን ጉዳይ ትኩረት እንዳይነፍገው ጥሪ አስተላለፉ።
ጳጳሱ የዛሬውን የስደተኞች ሁኔታ ኢየሱስና እናቱ ማርያም ከናዝሬት ወደ ቤተልሄም ከመሰደዳቸውና የሚያስጠጋቸው ከማጣታቸው ጋር አመሳስለውታል። "የንፁሃንን ደም ማፍሰስ ምንም ከማይመስላቸው መሪዎች ለማምለጠ ብዙዎች ለመሰደድ እየተገደዱ ነው" ብለዋል ጳጳሱ ። ጳጳሱ የተለመደውን የገና ንግግራቸውን የሚያደረጉት ዛሬ ነው። የ81 ዓመቱ ፖፕ ፍራንሲስ ራሳቸው ቅድመ አያታቸው ጣልያናዊ ስደተኛ እንደነበሩ በገና ዋዜማ በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ ቤተክርስትያን ተሰብስቦ ለነበረው ምእመን ተናግረዋል። "የብዙ ሚሊዮኖችን ግለ ታሪክ ስንመለከት መሰደድን የመረጡ ሳይሆኑ የሚወዷቸውን ትተው መሰደድ ግዴታ የሆነባቸው ናቸው።"ብለዋል። በመላው ዓለም 1.2 ቢሊዮን የካቶሊክ እምነት ተከታዮችን የሚመሩት ፖፕ ፍራንሲስ ለእንግዶች በየትኛውም አገር ጥሩ አቀባበል ለማድረግ እምነት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። ጳጳሱ ለስደተኞች መከላከል የጵጵስና ዘመናቸው ዋንኛ ጉዳይ መሆኑን ቀደም ሲልም ግልፅ አድርገዋል። ጳጳሱ ስለ ስደተኞች ይህን እያሉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት አለም ላይ የስደተኞች ቁጥር 22 ሚሊዩን ደርሷል። የማይናማር ግጭትን የሚሸሹ በርካቶች ደግሞ ይህ ቁጥር በፍጥነት እንዲያሻቅብ እያደረጉ ነው። የገና ዋዜማ በተለያየ የአለም ክፍል በክርስትያኖች ተከብሯል። በቤተልሄምም ክርስትያኖች በተመሳሳይ መልኩ ተሰባስበው ነበር። ቢሆንም ግን በዌስት ባንኳ ከተማ የታየው የምእመናን ቁጥር አነስተኛ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ የዶናልድ ትራመፕ ለእየሩሳሌም በእስራኤል ዋና ከተማነት እውቅና መስጠትን ተከትሎ አካባቢው ላይ ውጥረት መንገሱ ነው።
news-50937648
https://www.bbc.com/amharic/news-50937648
'ልጃችንን እንደ ክርስቲያንም እንደ ሙስሊምም ነው የምናሳድጋት'
የእስልምና እምነት ተከታዩች በሚበዙባት ቡርኪናፋሶ በቅርብ ዓመታት ወዲህ በአክራሪ ጂሃዲስቶች ጥቃት ሰለባ መሆን ጀምራለች። በፈረንጆቹ ገና ዋዜማ እንኳን 30 ሰዎች በታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ ደግሞ ሴቶች ነበሩ።
ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ጀርባ በሀገሪቱ ያለው ምስል ለየት ያለ ነው። በቡርኪናፋሶ 23 በመቶ የሚሆኑት ክርስቲያኖች ከሙስሊሞች ጋር ትዳር መስርተው መኖር የተለመደና በብዛት የሚታይ ነው። እስቲ በዋና ከተማዋ ኡጋዱጉ የሚገኝ አንድ ቤተሰብን እንመልከት። • በቡርኪናፋሶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች ሞቱ • በቡርኪና ፋሶ መስጅድ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ የአምስት ዓመቷ አይሪስ ኦስኒያ ኡታራ ከአባቷ በወረሰችው የካቶሊክ እምነት እና በእናቷ የሙስሊም አስተምሮ መሰረት ነው የምታድገው። የፈረንጆቹን ገና ከአባቷ ጋር በደማቅ ሁኔታ የምታከብር ሲሆን በእስልምናው ደግሞ ኢድን ታከብራለች። ''አይሪስ ሁሌም ቢሆን ወደ መስጂድ ስሄድ አብራኝ እንድትሄድ አደርጋለሁ፤ እሁድ እሁድ ደግሞ ከአባቷ ጋር ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳ ትምህርት ትከታተላለች'' በማለት ስልጃቸው አስተዳደግ እናትየው ትናገራለች። የአይሪስ እናት አፎሳቱ በቀን አምስት ጊዜ በቤት ውስጥ የምትሰግድ ሲሆን አርብ ሲደርስ ደግሞ ልጇን ይዛ ወደ መስጂድ ትሄዳለች። አይሪስም ብትሆን የመጀመሪያውን ጸሎት ለማድረስ ከእናቷ ጋር በጠዋት ትነሳለች። '' እስልምና ሁሌም ቢሆን መቻቻልና ሌሎችን መቀበል ላይ የተመሰረት ነው፤ የሌሎችን ችግር መረዳት ነው እስልምና'' ትላለች አፎሳቱ። በእነ አይሪስ ቤት እስልምና ማስተማሪያ መጽሀፍት ቁርአን እንዲሁም የክርስትናው መጽሀፍ ቅዱስ ጎን ለጎን ተቀምጠው ይታያሉ። የአይሪስ አባት ዴኒስ እና እናቷ አፎሳቱ በቡርኪናፋሶ ቶዉሲያና ከተማ ከተዋወቁበት ጊዜ ጀምሮ ለስድስት ዓመታት አብረው ኖረዋል። በሚቀጥለው ዓመት ትዳር የመመስረት እቅድ ያላቸው ሲሆን ሰርጋቸው በሁለቱም እምነቶች ስነስርአት መሰረት እንዲካሄድ ይፈልጋሉ። • ቻይና ሙስሊም ልጆችን ከቤተሰቦቻቸው እየነጠለች ነው • ኬንያ ውስጥ ታየ የተባለው "ኢየሱስ" ማን ነው? ዴኒስ ለጊዜውም ቢሆን ሀይማኖቱን ወደ እስልምና ለመቀየር ያስባል። በቡርኪና ፋሶ ክርስቲያን ወንዶች የሚስቶቻቸው ቤተሰቦችን ለማስደሰት ወደ እስልምና መቀየር የተለመደ ነገር ነው። ነገር ግን ከሰርጉ በኋላ ወደ ቀድሞ ሀይማኖታቸው ይመለሳሉ። '' ለመጋባት መወሰናችንን ይፋ ስናደርግ ብዙ ተቃውሞ አጋጥሞናል'' ይላል ዴኒስ። '' መጀመሪያ አካባቢ ትንሽ የተወሳሰበ ነበር። አባቴ ምንም ችግር የለውም ሲለኝ እናቴ ግን አልተስማማችም። ባልና ሚስት የተለያየ ሀይማኖት የሚከተሉ ከሆነ ሁሌም እናቶች ደስ አይላቸውም።'' አሁንም ቢሆን የአፎሳቱን እናት ለማሳመን በጥረት ላይ ይገኛሉ ጥንዶቹ። በቡርኪና ፋሶ በርካታ ቤተሰቦች ከክርስቲያን እና ሙስሊሞች የተውጣጡ ናቸው። አንዱ በአንዱ ቤተ እምነት ውስጥም መግባት ይችላሉ። በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ የሀይማኖት መቻቻል ተምሳሌት ተደርጋ ትቆጠራለች። አፎሳቱ በምትኖርበት አካባቢ ብዙ ክርስቲያን ጓደኞች ያሏት ሲሆን በአላት ሲደርሱ ደግሞ ወደ ቤታቸው በመሄድ አብራቸው ታከብራለች። ከዴኒስ ቤተሰቦችም ጋር ቢሆን ጥሩ ግንኙነት መመስረት ችላለች። '' ክሪስማስም (የገና በዓል) ሆነ ኢድ አል አድሃ ሁሉንም በአላት አከብራለሁ። እድለኛ ነኝ ብዬ ነው የማስበው'' ትላለች አፎሳቱ። • ለልመና ታግቶ የነበረው ታዳጊ ከዓመታት በኋላ ተገኘ ዴኒስ በበኩሉ '' ሀይማኖቴ ሌሎችን እንድወድና በማንነታቸው እንድቀበላቸው አስተምሮኛል። ለሁሉም ነገር ፈራጁ ፈጣሪ ነው፤ እኛ አይደለንም'' ብሏል። ዴኒስና አፎሳቱ ልጃቸው አይሪስ እድሜዋ ከፍ ሲል የፈለገችውን ሀይማኖት እንድትከተል እንደሚያስመርጧት ይናገራሉ። ለአሁኑ ግን በመስጂድም ሆነ በቤተ በቤተክርስቲያን መመላለሷን ትቀጥላለች። የትኛውንም ሀይማኖት ብትመርጥ ለእኛ ግድ አይሰጠንም የሚሉት እናትና አባት ''ፍቅር ከሀይማኖት በላይ ነው'' መልእክታቸው ነው።
news-55423749
https://www.bbc.com/amharic/news-55423749
እውን የፈረንጆቹ 2020 መጥፎ ዓመት ነበር?
ለብዙዎቻችን 2020 ማብቂያ የሌለው አሰስ ገሰሱን መከራ ይዞ የመጣ ነበር። አንዳንዶች ይህን ዓመት በጣም 'የተረገመ' ሲሉ ይጠሩታል።
ነገር ግን ወደ ኋላ ዞር ብለን ታሪክ ስንቃኝ 'የተረገመ' ባይባሉ እንኳ ብዙ መከራ ይዘው የመጡ ዓመቶች ነበሩ። መጀመሪያ እስቲ ስላሳለፍነው የፈረንጆቹ 2020 ትንሽ እንበል። ከዚያ ከታሪካዊ 'የተረገሙ' ዓመታት ጋር እናነፃፅረው። ማን ያውቃል ይህም ነበር እንዴ ያስብል ይሆናል። በ2020 ኮቪድ 19 በርካታ ሰዎችን ገድሏል እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ መሠረት 74.5 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሞተዋል። ይህን መረጃ ያቀናበረው ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ነው። ነገር ግን ከዚህ ቀደም ከነበሩ ወረርሽኞች ጋር ሲነፃፀር ይህ ቁጥር ትንሽ ነው። ለምሳሌ በ1346 የተቀሰቀሰው ጥቁሩ ሞት እየተባለ የሚጠራው ወረርሽኝ አውሮፓ ውስጥ ብቻ 25 ሚሊዮን ሰዎች ሲገድል በዓለም አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ሰዎች እንደሞቱ ይነገራል። በ1520 ደግሞ የፈንጣጣ ወረርሽኝ ከ60 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑ የደቡብ አሜሪካ ሰዎችን እንዳጠፋ ይገመታል። ሌላኛው የ100 ዓመት ታሪክ ያለው ወረርሽኝ ስፓኒሽ ፍሉ ነው። ከአንደኛው ዓለም ጦርነት በኋላ በወታደሮች አማካይነት የተስፋፋው ይህ በሽታ 50 ሚሊዮን ሰዎችን ገድሏል። ይህ በወቅቱ ከነበረው የዓለም ሕዝብ ጋር ሲነፃፀር እስከ አምስት በመቶ የሚደርስ ነው። በ1980ዎቹ የተቀሰቀሰው ኤችአይቪ/ኤድስ ደግሞ 32 ሚሊዮን ሰዎችን ገድሏል። በ2020 በርካቶች ሥር አጥ ሆነዋል ወረርሽኙ ያስከተለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ እጅግ ከባድ ነው። የበርካቶችን በር አንኳኩቷል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ብዙ ሰዎች የዕለት ጉርስ ከሚያገኙበት ሥራቸው ተፈናቅለዋል። ነገር ግን ዘንድሮ የታየው የሥራ አጥ ሰዎች ቁጥር በ1929-33 ከተሰተው 'ግሬት ዲፕሬሽን' ተብሎ ከሚጠራው ቀውስ አይበልጥም። 1933 እጅግ 'የተረገመ' ዓመት እንደነበር ታሪክ ይናገራል። ጀርመን ውስጥ ከሶስት ሰዎች አንድ ሰው ሥራ አልነበረውም። የወቅቱን መሪ ደግሞ ብዙዎች ያውቁታል። አዶልፍ ሂትለር። በ2020 ጓደኞቼን ማግኘት አልቻልኩም እርግጥ ነው በወረርሽኙ ምክንያት በርካቶች ቤታቸው ተከርችመው ከርመዋል። ዘመድ አዝማድ ማግኘት ተስኗቸው ቆይቷል። ነገር ግን በ536 በርካታ የዓለም ዜጎች ሰማይን እንኳ ማየት አልቻሉም ነበር። ከየት እንደመጣ ያልታወቀ ጉም አውሮፓን፣ መካከለኛው ምስራቅንና አንዳንድ የእስያ ሃገራትን ሸፍኖ ነበር። ይህ የሆነው ለ18 ወራት ነበር። ይህ ዓመት በሰው ልጅ ታሪክ እጅግ የተረገመው ሳይሆን አይቀርም የሚሉ በርካቶች ናቸው። ባለፉት 2300 ዓመታት በጣም ከባድ ብርድ የታየውም በዚህ ዘመን ነበር። ሰብሎች ወድመዋል። በርካቶች ተርበዋል። በ2020 ለበዓል መጓዝ አልቻልኩም እየተገባደደ ያለው የፈረንጆቹ ዓመት ለቱሪዝም ዘርፍ ዱብእዳ ይዞ የመጣ ነው። በርካቶች ከሃገር ሃገር፤ ከከተማ ወደ ገጠር መጓዝ አልቻሉም። ነገር ግን ከ195 ዓመት በፊት የነበሩ ቀደምት የሰው ልጅ ዝርያዎች [ሆሞ ሳፒየንስ] በተመሳሳይ ከቦታ ቦታ መዘዋወር አልቻሉም ነበር። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የአየር ንብረት ነው። ወቅቱ እጅግ ቀዝቃዛ ሲያልፍ ደግሞ እጅግ ሞቃት ነበር። ቀደምት ሰው በዚህ ሁኔታ ለብዙ ሺህ ዘመናት ኖሯል። አንዳንድ ሳይንቲስቶች በወቅቱ የነበረው ድርቅ የሰውን ልጅ ከምድረ ገፅ ሊያጠፋ ተቃርቦ ነበር ይላሉ። አጥኚዎች እንደሚሉት የሰው ልክ ከዚህ ጥፋት የዳነው በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው [የኤደን ለምለም ሥፍራ] ተጠልሎ ከውቅያኖስ የሚያገኘውን እየተመገበ ነበር። በ2020 የፖሊስ ጭካኔ የበረታበት ነበር ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ ከተገደለ በኋላ አሜሪካን ጨምሮ በመላው ዓለም የፖሊስ ጭካኔን የሚቃወሙ ድምፆች ከሌላው ጊዜ በላይ ጎልተው ተሰምተዋል። ተቃውሞው ናይጄሪያ ደርሷል፣ ኮለምቢያ ገብቷል፣ ፈረንሳይን አጥለቅልቋል፣ ሆንግ ኮንግን አንቀጥቅጧል። ነገር ግን ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በ1992 አራት የሎስ አንጀለስ ከተማ ፖሊሶች ሮድኒ ኪንግ የተሰኘውን ጥቁር አሜሪካዊ በጭካኔ ሲቀጠቅጡ የሚታዩበት ምስል ከወጣ በኋላ ከባድ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ነበር። በዚህ ተቃውሞ ሳቢያ 54 ሰዎች ሞተዋል፤ ግምቱ 1 ቢሊዮን ዶላር የሆነ ንብረት ወድሟል። ይህን ተከትሎ ከተማዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃ ነበር። የተረገመው 2020 በአጠቃላይ 2020 በርካታ መከራ ያሳየን ዓመት ሆኖ ሊያልፍ ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ቢሆንም ግን የሰው ልጅ ከዚህ የበለጡ ብዙ መከራና ቸነፈር አልፎ እዚህ ደርሷል። ዓመቱ የበርካታ ሰዎችን ኑሮ ቢያመሰቃቅልም መልካም የሚባሉ ክስተቶችንም አስተናግዷል። የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ከየትኛው ጊዜ በላይ የሆነበት ነው 2020። ሰዎች የዘር መድልዎን በመቃወም አደባባይ ወጥተው ለውጥ ለማምጣት የጣሩበት ዓመትም ሆኖ ተመዝግቧል። 'ዕድሜ' ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተፈጥሮም ውበቷን በዚህ ዓመት መልሳለች። የሰው ልጅ ከመቼውም ጊዜ በላይ እጁን አብዝቶ የታጠበበት ዘመን ነው 2020። በቀጣዩ ዓመት ቸር ወሬ ያሰማን።
news-55421938
https://www.bbc.com/amharic/news-55421938
ምርጫ 2013 ፡ መጪው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 ሊካሄድ ነው
በዚህ ዓመት የሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ አጠቃላይ ምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ የትግራይ ክልልን ሳያካትት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ይፋ ተደረገ።
በዚህም መሠረት ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28/2013 ዓ.ም ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር የድምጽ መስጫ ቀን ደግሞ ከሳምንት በኋላ ሰኔ 5/2013 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። ይህ ረቂቅ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ የትግራይ ክልልን የማይጨምር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በክልሉ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምርጫ በሚስማማ መልኩ ሲመቻች ለክልሉ የምርጫ ሰሌዳ እንደሚዘጋጅ ቦርዱ አስታውቋል። ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ውጪ ድምጽ በሚሰጥበት ዕለት በተደራቢነት "የደቡብ ምዕራብ ሕዝበ ውሳኔ" የሚሰጥ መሆኑን ቦርዱ በጊዜ ሰሌዳው ላይ አመልክቷል። ይህ ሕዝበ ውሳኔ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በአዲስ መልክ ከማዋቀር ጋር ተያያዞ የሚካሄድ ነው። ቦርዱ አጠቃላዩ ምርጫ ሂደቱን በተመለከተ ባወጣው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቀደም ብለው ከሚካሄዱ የምርጫ ዝግጅቶች በተጨማሪ የእጩዎች ምዝገባ በየካቲት ወር ከ8 2013 እስከ 21 2013 ድረስ እንደሚካሄድ ተጠቅሷል። በምርጫው የሚወዳደሩ እጩዎች የምረጡኝ ዘመቻቸውን ከየካቲት 08 2013 እስከ 23 2013 ቀን ድረስ የሚያደርጉበት ጊዜ ይሆንና ከዚያ በኋላ እስከ ምርጫው ቀን ድረስ ቅስቀሳ የማይደረግበት ጊዜ ይሆናል። ምርጫዎቹ በተያዘላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሰረት ከተካሄዱ በኋላ ውጤት በምርጫ ጣቢያና በክልል ደረጃ በተለያዩ ቀናት የሚገልጽ ሲሆን የመጨረሻው ውጤት በብሔራዊ ምረጫ ቦርድ ግንቦት 29 እና ሰኔ 21/2013 ዓ.ም ይፋ ይደረጋል። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ እንዲካሄድ የጊዜ ሠሌዳ ወጥቶለት የነበረው ስድስተኛው ዙር አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ሳቢያ ማካሄድ እንደማይችል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁ ይታወሳል። ቦርዱ ባዘጋጀው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ምርጫውን ወረርሽኙ በደቀናቸው ስጋቶች ሳቢያ ለማካሄድ እንደሚቸገር አመልክቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሃሳብ መሰረት ምርጫው በቀጣይ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንዲካሄድ ወስኖ ነበር። እዚህ ውሳኔ ላይ ሲደረስም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያና በዓለም ደረጃ የሚኖረው ሁኔታ በአገሪቱና በዓለም የጤና ተቋማት የሚሰጡ መረጃዎች በየጊዜው እየተገመገሙ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ታይተው እንደሚወሰኑ ተገልጾ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ከወራት በኋላ በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ምክር ቤቱ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የዓለም ጤና ድርጅትና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባስቀመጡት ምክረ ሃሳብ መሰረት ቫይረሱን ለመካላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን በመውሰድ በ2013 ምርጫው እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወሳል።
news-51299516
https://www.bbc.com/amharic/news-51299516
ስለታገቱት ተማሪዎች መንግሥት ዝምታውን የሰበረበት መግለጫ
የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ የሚያጣራ ቡደን መቋቋሙን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ በተሰጠ መግለጫ ተነግሯል።
መግለጫውን የሰጡት የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን፣ የሳይንስ እና ከፍትኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጀኔራል ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ናቸው። በመግለጫው ምን ተባለ የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክቴሪያት አቶ ንጉሱ ጥላሁን በአገሪቱ በሚገኙ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንደተከሰተው ሁሉ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲም ተመሳሳይ የጸጥታ ችግር እንደተከሰተ አስታውሰዋል። በዚህም ለደህንነታቸው የሰጉ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው ሲወጡ እንደነበረ በማስታወስ፤ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጥለው እንዳይሄዱ ፌደራል ፖሊስ ከአካባቢው ማህብረሰብ ጋር የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ በአከባቢው ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ጥለው ከወጡ ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል ሲያስጠነቅቅ እና መረጃ ሲሰጥ ነበረ ብለዋል። "ተማሪዎች ግን በማይጠበቅ መንገድ በጋምቤላ በኩል ጉዟቸውን ቀጠሉ።" ብለዋል አቶ ንጉሱ። ቸአንፊሎ ወረዳ ሱዲ በምትባል ቦታ ላይ ተማሪዎች፣ ሌሎች ወጣቶች እና አንድ የአካባቢው አመራር ጭምር ህዳር 25፣ 2012 ላይ መያዛቸው መረጋገጡን አቶ ንጉሡ ተናግረዋል። "ሰዎች መያዛቸው ሲሰማ መከላከያ ሠራዊት አሰሳ አካሂዶ 21 ተማሪዎችና ሌሎች ተጨማሪ ሰዎችን ማስለቀቁን ጠቅሰው፤ 21ዱ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲው እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። "በቀን ጥር 2 ይህኑን መረጃ ለሕዝብ ማቅረባችን ይታወሳል፤ በእጃችን ላይ ያለን መረጃ ጥር 2 ላይ የሰጠነው መረጃ ትክክለኛነትን ያረጋግጣል" ብለዋል፤ አቶ ንጉሡ። ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ የአካባቢው የ2ኛ ደረጃ ተማሪና ሌሎች አምስት ሰዎች እየተጓዙ እያሉ 6 ሰዎች መያዛቸውን አቶ ንጉሡ ተናግረዋል። ከአምስቱ ተያዙ ከተባሉ ወጣቾች መሀል የአንዱ ወላጅ አባት ታጋቾቹ ተማሪዎች እንደሆኑ የገለጹ ቢሆንም እኛ ግን እያጣራነው ነው ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል አቶ ንጉሡ። አቶ ንጉሡ ጨምረወ እንዳብራሩት "አንድ መጥራት ያለበት ጉዳይ መገናኛ ብዙሃንም ሆኑ በማህብራዊ ሚዲያ ላይ የሚነገረው የታገቱት ተማሪዎች ቁጥር 17 ስለመሆናቸው ነው። ይህ ቁጥር ሲጣራ ግን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ የሚያሳያው 12 ብቻ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ናቸው። 5 ግን የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ስለመሆናቸው መረጃ የለም" ብለዋል። በአሁኑ ወቅት 800 የሚሆኑ ተማሪዎች የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጊቢ ለቀው መውጣታቸውን አስታውቀዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጀኔራል ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊሰ ኮሚሽነር ጀነራል በበኩላቸው "በስፍራው አላንቀሳቅስ አላላውስ ብለው ሕዝብ የሚያስቸግሩ አካላት አሉ" ሲሉ ተናግረዋል። "በደምቢ ዶሎ አካባቢ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል ተደምስሷል። ተደምስሶ ግን አልቀረም። የተረፈው አሁን እራሱን አደራጅቶ በሽፍታ መልክ እየተንቀሳቀስ ነው። መንግሥት ዝም አላለም። እርምጃ እየወሰደ ነው።"ብለዋል። እገታው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችንና የአካባቢው ነዋሪዎችን እንዲሁም ነጋዴዎችን ይጨምራል ሲሉ ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲማሩ ዝግጅት እየተደረገ ነውም ብለዋል። ልጆቹ የት ነው ያሉት ተብሎ ለሚነሳው ጥያቄ "በእጃችን በቂ መረጃ አለ። እነዚህ መረጃዎች ተገቢ ክትትል እየተደረገባቸው ነው የሚገኙት። መረጃዎች ልጆቹ ላይ ከቀላል እስከ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል እየተባለ በሚወራው ጉዳይ እስካሁን በፖሊስ የተረጋገጠ አይደለም። በጉዳዩ ላይ ምረመራ እየተካሄደ ስለሆነ ዝርዝር መረጃ መስጠት አልፈለግንም። ሦስት ቡደን አደራጅትን ምርመራዎችን እያካሄድ ነው" ብለዋል። የሳይንስ እና ከፍትኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ዶ/ር ሳሙኤል "ከተማሪዎቹ እገታ ጋር በተያያዘ የሰማነው ቁጥር 17 ነው። ይህን ቁጥር በመጀመሪያ የሰጠችው አስምራ ሹምዬ የምትባል ተማሪ ነች። በዚህ ጉዳይ መረጃ መስጠት ያለብኝ ስለመሰለኝ ነው ይህን ማብራሪያ የምሰጠው ብለዋል" ተማሪ አስምራ ለአካባቢው ኮማንድ ፖስት ሰጠች ያሉትን መረጃ ዶ/ር ሳሙኤል እንደሚከተለው አስቀምጠዋል። "በአካባቢው ላለ የኮማንድ ፖስት በ26-03-2012 የሰጠችው መረጃ፤ 'ህዳር 25 ላይ ከደምቢ ዶሎ ወጥተን በጋምቤላ አድርገን ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ሱዲ በሚባል ቦታ ላይ ወጣቶች ወሰዱን፤ እኔ አምልጬ አንድ ሽማግሌ አሳፍረው ወሰዱኝ' በማለት በንጋታው (ህዳር 26 ) ለኮማንድ ፖስት ተናግራለች" ብለዋል። "የታገቱት ተማሪዎች ከእርሷ ጋር 7 ሰው መታገቱን ተናግራ ነበር። እዚህ ከመጣች በኋላ 17 ብላላች። እገታው ከተካሄደ ከአራት ቀናት በኋላ የአገር መከላከያ 21 የሚደርሱ ሰዎችን አግኝቶ 19ኙ ተማሪዎች ናቸው ተብሎ ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሰዋል" ያሉት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዲኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ነገር ግን መንግሥት ተለቀዋል ያላቸው ተማሪዎች በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገኙ ጥቆማ ሰጥተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው አጭር መዘርዝር ጠፍተዋል ብለው ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ያቀረቡ ወላጆች ቁጥር 11 መሆኑን ጠቅሶ በተለያየ መልኩ ጠፍተዋል ተብለው ከተገለጹት ተማሪዎች ውስጥ 9ኙ ወላጆቻቸው ሪፖርት አላደረጉም ወይም የወላጆቻቸው አድራሻ ማግኘት አልተቻለም ይላል። በመንግሥት በኩል መረጃው ከደረሰ ጀምሮ ተማሪዎችናን ዜጎችን የማፈላለግ ሥራ በመሠራት ላይ እንደሆነ የሚጠቅሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፌት ቤት መግለጫ ጠቃሚ መረጃና ማስረጃዎች ተገኝተዋል፤ ጠንካራ የምርመራ ሥራ እየተሠራ ነው ሲል ያትታል።
news-53422738
https://www.bbc.com/amharic/news-53422738
ፍርድ ቤት ለፖሊስ በአቶ እስክንድር ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰጠ
ከሁለት ሳምንት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ሰር የዋሉት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋን በተመለከተ ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናቀቅ የጠየቀው ተጨማሪ ቀን ፍርድ ቤት ተፈቅዶለታል።
ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ እስክንድር ነጋ የብሔርና የሐይማኖት ግጭት እንዲፈጠር ወጣቶችን በማደራጀት ገንዘብና የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ጠበቃቸው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በዚህም ከፍተኛ መጠን ያለው ውድመት በንብረት ላይ እንዲሁም በሰዎች ህይወትና በአካል ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል የሚል ክስ በፖሊስ መቅረቡን ጠበቃው ጠቅሰዋል። ጉዳያቸው በፌደራል የመጀመሪያ አራዳ ምድብ ችሎት የሚታይ ቢሆንም ለደህንነት ሲባል ችሎቱ ልደታ በሚገኘው ፍርድ ቤት እንደተሰየመ የተናገሩት አቶ ሄኖክ፤ ፖሊስ ሃያ ምስክሮችን ማድመጡን እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃዎችን እየተመረመረ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ ፖሊስ እስካሁን ያከናወናቸውን መረጃ የማሰባሰብና ምርመራ የማካሄድ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አመልክቶ ቀሩኝ የሚላቸው ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ከዚህ ሌላ አቶ እስክንድር ለፍርድ ቤቱ ተፈጽሞብኛል ያሉትን በደል ያቀረቡ ሲሆን፤ ይህም በቁጥጥር ሰር በዋሉበት ዕለት በፌደራል ፖሊስ አባላት ድብደባ እንደተፈጻመባቸው እራሳቸውና ጠበቃቸው ለችሎቱ አቤት ብለዋል። ፍርድ ቤቱም በቀረበው አቤቱታ መሰረት በአቶ አስክንድር ላይ ድብደባ የፈጸሙት የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ምርመራ እንዲካሄድና እንዲጣራ ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናቀቅ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄን በተመለከተ የአቶ አስክንድር ጠበቆች ፖሊስ ማስረጃ እንዳለው ለችሎቱ መግለጹንና ጠቅላይ አቃቤ ህግም ተከሳሹን ወንጀለኛ የሚያስብላቸው ማስረጃ ማግኘቱን ማመልከታቸው አስረድተዋል። ስለዚህም እነዚህ ማስረጃዎች ደግሞ በፖሊስ እጅ መኖራቸውን በመጥቀስ ተጨማሪ የጊዜ ገደብ መጠየቅ ተገቢ አይደለም ብለው ለፍርድ ቤቱ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ፍርድ ቤቱ በቀረበው ተቃውሞ ላይ በሰጠው ምላሽ ምንም እንኳን ፖሊስ ማስረጃ አግኝቻለሁ ቢልም ምርመራው አልቋል ብሎ ስለማያምን ተጨማሪ 13 የምርመራ ቀናት መስጠቱ አስፈላጊ ነው በማለት ለሐምሌ 22 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ጠበቆች ግን መረጃዎች በፖሊስ እጅ ያሉ በመሆናቸው ምርመራውን በራሱ ለማካሄድ የሚችል በመሆኑ ተጨማሪ ቀን መስጠት ተገቢ አይደለም ብለው ቢከራከሩም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል ሲሉ አቶ ሄኖክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአቶ እስክንድር ነጋ ጠበቃ ጨምረው እንደተናገሩት ደንበኛቸው ቀደም ሲል ታስረውበት ከነበረው የማረፊያ ቦታ ከሁለት ቀናት በፊት ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወራቸውንም ለቢቢሲ ገልጸዋል።
news-51797888
https://www.bbc.com/amharic/news-51797888
የአባይ ግድብ፡ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በመግለጫ ምልልስ እየተወዛገቡ ነው
ኢትዮጵያ ጥቅሜን ይጎዳዋል ባለችውና በአሜሪካ እንደቀረበ በሚነገርለት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የስምምነት ሰነድ ላይ እንደማትፈርም ካሳወቀች በኋላ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በመግለጫ እየተወዛገቡ ነው።
የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ በአባይ ጉዳይ የሚድረገውን ውይይት ከፊት መስመር ሆነው ይመራሉ በተለይ የአረብ ሊግ ግብጽን የሚደግፍ የውሳኔ ሐሳብ ማውጣቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የውሳኔ ሐሳቡን ውድቅ የሚያደርግ መግለጫ አውጥታለች፤ ሱዳንም በዚሁ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሚሰጥና ጥሪ የሚያቀርብ መግለጫ አውጥታለች ግብጽም ምላሽ ሰጥታለች። ሱዳን፤ ኢትዮጵያና ግብጽ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ወደ ሚደረገው ድርድር በመመለስ ከስምምነት እንዲደርሱ ጥሪ አቅርባለች። ሱዳን የአረብ ሊግ ያቀረበውን ግብጽን የሚደግፍ የውሳኔ ሐሳብ እንደማትቀበለው ካሳወቀች በኋላ ነው ይህንን መግለጫ በማውጣት ለሁለቱ አገራት ጥሪ ያቀረበችው። በሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በወጣው መግለጫ ላይ አገራቱ ወደ ድርድሩ በመመለስ "የድርድሩን ሂደት በአሉታዊ መልኩ ከሚጎዳ ማንኛው ሁኔታ" እንዲቆጠቡ ሱዳን ጠይቃለች። መግለጫው አክሎም ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው ንግግር የሦስቱንም አገራት ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ እንዲሳካ ጥልቅ ፍላጎት አላት ብሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መግለጫው ባለፈው ሳምንት በአረብ ሊግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ሱዳን ያላትን ጥያቄም አብራርቷል። "በግብጽ የቀረበውና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ሱዳን ጥያቄ ያቀረበችው የሱዳን ሐሳብ ያልተጠየቀበት በመሆኑ እና እየተካሄደ ያለውን ውይይትና ድርድርን መንፍስ የሚጠቅም ባለመሆኑ ነው" ብሏል መግለጫው። የኢትዮጵያ መንግሥትም 'የአረብ ሊግ ግብጽን በመደገፍ ያወጣው ነው' ያለውን የውሳኔ ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ እንደማይቀበለው ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ገልጾ ነበር። ሱዳን የአረብ ሊግ የውሳኔ ሐሳብን በተመለከተና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ስለሚደረገው ድርድር ትናንት ዕሁድ ያወጣችውን መግለጫ ተከትሎ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አገራቸውን ደስተኛ አለመሆኗን መግለጻቸውን ኢጂፕት ቱዴይ ዘግቧል። ቃል አቀባዩ አህመድ ሐፊዝ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት ግብጽ የአረብ ሊግ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብን በተመለከተ ለሱዳን ተወካዮች ከቀናት በፊት ጀምሮ እንዲያውቁት ማድረጓንና እንደሚቀበሉት ቢገልጹም ምንም አይነት አስተያየት ለግብጽ ባለስልጣናት እንዳልሰጡ ጠቅሰዋል። ሐፊዝ እንዳሉት ሱዳን በኋላ ላይ የውሳኔ ሐሳቡን ደካማ እንዲሆን የሚያደርግ ማስተካካያ ማቅረቧንም ተናግረዋል። ጨምረውም በሱዳን ባለስልጣናት ጥያቄ መሰረት ስሟ ከውሳኔ ሃሳቡ ሰነድ ላይ እንዲወጣ ተደርጓል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ የአረብ ሊግ በግድቡ ዙሪያ እየተደረገ ያለውን ድርድር ቁልፍ እውነታዎችን ሳያገናዝብ በውሳኔ ሃሳቡ የሰጠው ጭፍን ድጋፍ እንዳሳዘነው አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት በመግለጫው የውሳኔ ሃሳቡን እንደማትቀበል አሳውቃለች የተባለችውን የሱዳንን አቋም ያደነቀ ሲሆን፤ ከግድቡ አንጻር በተቀነባበረው የአረብ ሊግ አቋም ላይ "ሱዳን በድጋሚ ለምክንያታዊነትና ለፍትህ ያላትን አቋም አሳይታለች" ሲል አወድሷታል። የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን መግለጫ ተከትሎ በሰጠው ምላሽ እንዳለው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫን "አግባብነት የጎደለው፣ ዲፕሎማቲክ ያልሆነ እንዲሁም በአረብ ሊግንና በአባላቱ ላይ የተሰነዘረ ተቀባይነት የሌለው ጉንተላ ነው" ሲል ተቃውሞታል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ አሞላልና የውሃ አለቃቀቅን በተመለከተ በዋሽንግተን፣ በአዲስ አበባ፣ ካርቱምና ካይሮ ሲካሄድ የቆየው ድርድር በፈረንጆቹ የካቲት ወር ማብቂያ ላይ ይፈረማል ተብሎ ቢጠበቅም ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣት መጠየቋን ተከትሎ የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ከኢትዮጵያ በኩል ተቃውሞ ገጥሞት ውዝግብን አስከትሏል። ግብጽ የተዘጋጀውን የስምምነት ሰነድ ብትፈርምም አገራቱ ስምምነቱ ከመፈረማቸው በፊት ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ያለችው ግድብ የውሃ ሙሌት እንዳይጀመር የሚለው የአሜሪካን መግለጫን ጉዳዩን ውስብስብ አድርጎታል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናትም የቀረበው ሰነድ መብታችንን የሚጋፋ ነው በማለት በይፋ ተቃውመውታል። 4.7 ቢሊዮን ዶላር ወጪን ይጠይቃል የተባለውና ከዘጠኝ ዓመት በፊት ግንባታው የተጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ባለስልጣንት እንደሚሉት ከሆነ በመጪው ዓመት በከፊል የኃይል ማመንጨት የሚጀምር ሲሆን ግንባታው በሦስት ዓመት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠናቅ ተነግሮለታል።
41679049
https://www.bbc.com/amharic/41679049
ሮቦቶችን ሥነ-ምግባር ማስተማር
ሮቦቶች ወይም ሰው-ሠራሽ ማሽኖች በራሳቸው ውሳኔ ሲወስኑ ማየት የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ይህን ህልም የሚመስል ነገር እውን የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ይላሉ ተመራማሪዎች። ግን እንዴት ሆኖ ማሽን አመዛዝኖ ውሳኔ መስጠት ይቻለዋል?
የቢቢሲው ዴቪድ ኤድሞንድስ ከዶ/ር ኤሚ ሪመር ጋር በመኪና ጉዞ ላይ ነው። ደንገት ዶ/ር ኤሚ መኪናው ላይ ያለን 'ስክሪን' ተጫነች። ከዛም መኪናው ያለማንም መሪነት በራሱ መጓዝ ጀመረ። የትራፊክ መብራት ላይ ቆም ካለ በኋላ አደባባዩን ዞሮ ቦታ ፈልጎ በእርጋታ ቆመ። መሪ የጨበጠ ሰው በሌለበት መኪና መጓዝ ለመጀመሪያዎቹ አምስት ደቂቃዎች እጅግ አስፈሪ ነበር ይላል ዴቪድ። ነገር ግም መኪናው ሁሉን ነገር በሥርዓቱ ሲከውን በማየቴ ተረጋጋሁ ሲል ያክላል። የ29 ዓመቷ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ዶ/ር ኤሚ፤ ጃጉዋር ላንድ ሮቨር የተሰኘው መኪና አምራች ኩባንያ ያለ አሽከርካሪ የሚንቀሳቃስ መኪና ለመሥራት በሚያደርገው ምርምር ላይ ዋና ኢንጂነር በመሆን እየሠራች ትገኛለች። እንደዶክተሯ ከሆነ መሰል አሽከርካሪ-አልባ መኪናን የዛሬ አስር ዓመት ገደማ መንገድ ላይ ማየት ብርቅ አይሆንም። እርግጥ ነው ለዚህ ህልም መሳካት በርካታ መካኒካዊ ጉዳዮች መፈታት አለባቸው። ከዛ በላይ አሳሳቢው ነገር ግን ማሽኖቹን ሥነ-ምግባር ማስተማር ነው። ወደፊት አሽከርካሪ-አልባ መኪኖች ጥቅም ላይ መዋል ሲጀምሩ ወዴት መዞር እንዳለባቸው፣ አደጋን እንዴት መቀነስ እንዳለባቸው፣ ወይም ማስወገድ እንዳለባቸው አመዛዝነው ውሳኔ መስጠት ይኖርባቸዋል። መንገድ ላይ እክል ቢያጋጥም መኪናው ውስጥ ካለው ሰው እና ውጭ ካለው ሰው የቱን ማዳን አለባቸው? ከተሳፋሪው ይልቅ ለመንገደኛ ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጥ መኪና ይግዙ ቢባሉስ ይገዛሉ? ይህንን ውሳኔስ የሚወስነው ማነው? መንግሥት? አምራቾች? እርስዎ ተጠቃሚው? ብዙ መሰል ጥያቄዎች መመለስ ይኖርባቸዋል ባይ ናቸው ተመራማሪዎቹ። እኒህንና ሌሎች ጉዳዮች በጥልቀት ለመመርመር የሚረዳው ዘዴ 'ማሽን ለርኒንግ' ወይም ማሽኖችን ማስተማር የተሰኘው ፅንሰ-ሃሳብ ነው። ሱዛን አንደርሰን የፍልስፍና ባለሙያ ስትሆን ባለቤቷ ማይክል አንደርሰን ደግሞ የኮምፒዩተር ሳይንቲስት ነው። እነሱ እንደሚያምኑት ማሽኖችን ሥነ-ምግባር ለማስተማር ዋነኛው መላ ሮቦቶቹ የተጫነላቸውን ፕሮግራም ሁኔታዎች ላይ እንዲተገብሩት ማስቻል ነው። 'ኬርቦትስ' የተሰኙት ሮቦቶች ለምሣሌ ሕመም ላይ ያሉና እርጅና የተጫጫናቸውን ሠዎች ለማገዝ የተሠሩ ናቸው። እኚህ ሮቦቶች ወደፊት አመዛዝነው ውሳኔ መወሰን ደረጃ ላይ መድረሳቸው አይቀሬ ነው። ቲቪ ከማብራት እና ምግብ ከማቅረብ የዘለለ ሥራ መሥራት መጀመራቸውም የማይቀር ነው። ሱዛንና ማይክል እንደሚሉት ሮቦቶች ሁኔታን ተመርኩዘው ውሳኔ እንዴት መስጠት እንዳለባቸው በተዳጋጋሚ ከተማሩ ከሰው ልጅ የበለጠ ውሳኔ የመስጠት ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ። "እጅጉን ሥነ-ምግባራዊ የሆነ ውሳኔ የመስጠት ደረጃ ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ አምናለሁ" ትላለች ሱዛን። ይህም ቢሆን ግን ማሽኖችን ማስተማር የተሰኘው ፅንሰ-ሃሳብ የራሱ ችግሮች ይዞ መምጣቱ አይቀርም። አንደኛው ነገር ማሽኖች የተሳሳተ ነገር ሊማሩ መቻላቸው ነው። ለጥቆም የከፋ ችግር የሚሆነው ወደፊት ማሽኖች እንዴት ያለ ባህሪ ሊያመጡ እንደሚችሉ መገመት አለመቻሉ ነው። ዋናው ነገር ግን እንደተመራማሪዎቹ አባባል ሮቦቶች መሰል ባህሪዎችን ማሳየት ከጀመሩ መቆጣጠር የሚያስችለን ቁልፍ በእጃችን መኖሩ ነው። ሮቦቶች ላጠፉት ጥፋት ወንጀለኛ ብለን ልንከሳቸው አለመቻላችን ለሚጠፋው ጥፋት እኛው ተጠያቂ መሆናችን ማሳያ ነው። ደጉ ነገር ግን አሽከርካሪ አልባ መኪኖች አይሰክሩም ወይም አይደክማቸውም፤ ተሳፋሪ ላይ ለመጮህም አይዳዳቸውም። በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ያጣሉ፤ በአብዛኛው በአሽከርካሪ ወይንም በመንገደኛ ጥፋት ነው። በአሽከርካሪ አልባ መኪናዎች በመታገዝ ይህንን አደጋ መቀነስ በራሱ ትልቅ ድል ነው። ሮቦቶች ዳኛ ሆነው ያልተጓደለ ፍርድ ሊሰጡም ይችላሉ በማለት ሃሳባቸውን ይሰንዝራሉ ተመራማሪዎች። በሰው ልጅ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያፈርስ ከንቱ ሃሳብ በማለት የሮቦቶችን ማመዛዘን ጉዳይ ውድቅ የሚያደርጉት ደግሞ የለንደኑ ኪንግስ ኮሌጅ ፕሮፌሰር ጆን ናቸው። "የሰው ልጅ ሁኔታዎችን አገናዝቦ ትክክለኛውን ፍርድ መበየን ሲችል በማሽን የታገዘ የፍርድ ሥርዓት ማለት ምን የሚሉት ነው?" ሲሉ ይከራከራሉ። ዶ/ር ኤሚ ስለ ተሽካርካሪ-አልባ መኪና ዕድገት እጅግ ተደስታለች። ሕይወት መታደጉ ብቻ ሳይሆን መጨናነቅና የበካይ ጋዝ ልቀትንም ለመከላከል ፍቱን መፍትሄ ነው ትላለች። ሮቦቶች ወጣም ወረደ ወደፊት የሰው ልጅ ሥራ እየተረከቡ መምጣታቸው ስለማይቀር ሥነ-ምግባር ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል የሚለው ሃሳብ ግን ሚዛን እየደፋ ነው።
news-56356820
https://www.bbc.com/amharic/news-56356820
አሜሪካ ከእስር ቤት በስህተት የተለቀቀውን የግድያ ወንጀል ተጠርጣሪ እያደነች ነው
የአሜሪካ ፓሊሶች ከኒውዮርክ እስር ቤት በድንገት በስህተት የተለቀቀውን ታራሚ እያደኑ መሆኑ ተነግሯል።
ግለሰቡ በግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ ይገኝ የነበረ ሲሆን በስህተት የተለቀቀውም በያዝነው ሳምንት ሰኞ ነው። የ26 አመቱ ክርስቶፈር በግስ በአውሮፓውያኑ 2018 በሽጉጥ ሰው ገድሏል በሚል ነው ለእስር የተዳረገው። ለሶስት አመታት ያህል በራይከርስ አይላንድ እስር ቤትም ቆይቷል። ከሰሞኑ ግን በማረሚያ ቤት ሰራተኞች ዘንድ በተሰራ ስህተት በነፃ ወጥቷል። በአሁኑ ወቅት ጥምር ግብረ ኃይል ተዋቅሮ ታራሚውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሞከረ ነው። ባለስልጣናቱ የታራሚውን ግለሰብ ፎቶ በየቦታው ከመበተን በተጨማሪ የአካባቢው ማህበረሰብ እንዳይቀርበው ማስጠንቀቂያ ተላልፏል። "ክስተቱ እንደተፈጠረ ተረድተናል። በምን መንገድ ግለሰቡ ሊለቀቅ ቻለ የሚለው ላይ ምርመራ ከፍተናል" በማለት የማረሚያ ቤቶች የህዝብ ግንኙነት ምክትል ኮሚሽነር ፒተር ቶርን መናገራቸውን ሲቢኤስ መግለጫቸውን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ቢል ደ ብላሲዮ በበኩላቸው ስህተቱ የተፈፀመው ግለሰቡ ተደራራቢ ክሶች መኖሩ በመዘንጋቱ ነው ብለዋል። በአንደኛው ክስ የተመሰረተበት ብያኔ ሰላሳ ቀናት ሲሆን ነገር ግን የግድያ ወንጀሉ የፍርድ ሂደቱ አልተጠናቀቀም። ይህንን ያላወቀቱት የማረሚያ ቤት ሰራተኞች በነፃ አሰናብተውታል በማለት ከንቲባው ማብራሪያ ሰጥተዋል። "ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነት ድጋሜ ስህተት እንዳይፈጠር ጠንካራ ቁጥጥሮችንና መመሪያዎችን እናወጣለን። የተፈጠረው ክስተት የሚያበሳጭ" ነው በማለት ከንቲና ቢል ደ ብላሲዮ በያዝነው ሳምንት ረቡዕ ተናግረዋል። ባለስልጣናቱ ታራሚውን በአጭር ወቅት በቁጥጥር ስር እንደሚያውሉት በሙሉ መተማመን ላይ ናቸው በማለት ከንቲባው አክለው ተናግረዋል። ክርስቶፈር በግስ በአውሮፓውያኑ 2016 በብሩክሊን፣ ኒውዮርክ አንድ ግለሰብን በሽጉጥ ገድሏል በሚል ወንጀል ነው በእስር ላይ ያለው።
news-47038370
https://www.bbc.com/amharic/news-47038370
ታንዛኒያ ውስጥ ለአካል ክፍላቸው ሲባል ስድስት ህጻናት ተገድለው ተገኙ
በደቡብ ምዕራብ ታንዛኒያ ውስጥ ስድስት ህጻናት ተገድለው ጆሯቸውና ጥርሳቸው ከአካላቸው ላይ ተወስዶ መገኘቱን ባለስልጣናት ተናገሩ።
"ወላጆችና አሳዳጊዎች ነገሮችን በንቃት መከታተል አለባቸው" የተገደሉት ህጻናት ዕድሜያቸው በሁለትና ዘጠኝ ዓመት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከአካላቸው ላይ እጅና እግራቸው ተቆርጦ እንደተወሰደም ተነግሯል። "ይህ ድርጊት በሙሉ ከባዕድ አምልኮት ጋር የተያያዘና በጥንቆላ አንዳች ድጋፍ ለማግኘት የተደረገ መሆኑን በርካቶች ያምናሉ" ሲሉ የአካባቢው አስተዳዳሪ ሩት ምሳፊሪ ተናግረዋል። • በረከት ስምኦን ከየት ተነስተው እዚህ ደረሱ • በታንዛንያ አርግዘው የተገኙ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ታሰሩ ፖሊስ ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑና ከተገደሉት መካከል ለሦስቱ ህጻናት የቅርብ ዝምድና አለው የተባለን አንድ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አውሏል። ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ጆምቤ በተባለው አካባቢ አስር ልጆች መጥፋታቸው የተነገረ ሲሆን ከመካከላቸውም አራቱ በህይወት ተገኝተዋል። የጠፉት ህጻናት ወላጆቻቸው በምሽት ምግብ ለመሸጥ ወደ ገበያ በሄዱበት ጊዜ ከቤታቸው እንደተወሰዱም ተነግሯል። • መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች • ዋትስአፕ በተደጋጋሚ መልዕክት ማጋራትን አገደ ዘጋቢዎች እንደሚሉት በአካባቢው የሚገኙ ጠንቋዮች የሰው ልጅ የአካል ክፍሎች ሃብትና መልካም ዕድልን የሚያስገኝ ለየት ያለ ኃይል እንዳላቸው እንደሚናገሩ ገልጸዋል። ይህንን ተከትሎም የአካባቢው አስተዳዳሪ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "ወላጆችና አሳዳጊዎች ነገሮችን በንቃት እንዲከታተሉና ለልጆቻቸውም በዙሪያቸው ካሉ እንዲህ አይነት ወንጀል ፈጻሚዎች እራሳቸውን እንዴት እንደሚጠብቁ ማስተማር አለባቸው" ሲሉ መክረዋል።
news-56006573
https://www.bbc.com/amharic/news-56006573
በትግራይ ለሕጻናት የሚደረገው ድጋፍ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተባለ
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ እርዳታ ተቋማት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ አስቸጋሪ ሁኔታ በመኖሩ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ረሃብና የምግብ እጥረት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል መግለጻቸው ይታወሳል።
የኖርወጂያን ረፊዩጂ ካውንስል ዋና ጸሐፊ በሳለፍነው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታና ጥበቃ በማያገኙበት ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ ብሎ ነበር። ይህን ተከትሎ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች፤ ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ወደ ክልሉ የሚገቡበትና አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የሚደርሱበት መንገድ እንዲመቻችላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል። ከትናንት በስቲያ የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስለይ በትዊተር ገጻቸው የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ከኢትዮጵያ መንግሥት ከስምምነት መድረሳቸውን በመግለጽ "ሦስት ሚሊየን የሚጠጉ የእኛን እርዳታ የሚሹ ሰዎች አሉ፤ የምናጠፋው ጊዜ የለም" ብለዋል። መንግሥት በበኩሉ፤ እስከ አሁን ለ1.8 ሚሊዮን ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ቁሳቁሶች ማድረሱን በመግለጽ 2.5 ሚሊየን ህዝብ ለመርዳት የሚያስችለው ዝግጁነት እንዳለው ይገልጻል። ይሁን እንጂ፤ ጦርነቱ ለዜጎች መፈናቀል፣ ለጾታዊ ጥቃትና ሌሎች ውድመቶችን ምክንያት እንደሆነ ሲገለጽ፤ በዚህ ውስጥ ሕጻናት ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸውን ይነገራል። በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ሚኪኤል ሰርቫዲ ለቢቢሲ በሰጡት ማብራሪያ፤ በክልሉ ባለው ሁኔታ ከፍተኛ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት መኖሩን፣ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ዝግ መሆናቸውንና ከፍተኛ የስነ ልቦና ችግር እንዳለ ገልጸዋል። "በክልሉ 1.3 ሚሊየን ሕጻናት ትምህርታቸውን አቋርጠዋል። በርካታ ትምህርት ቤቶች የወደሙ ሲሆን በመቀለ አስር ሺ የሚጠጉ ተፈናቃዮች የተጠለሉባቸው ትምህርት ቤቶች አሉ። በግጭቱ ምክንያት ያጋጠመውን ስነ ልቦናዊ ችግር ለማከምም እርዳታ ያስፈልጋል" ይላሉ። በክልሉ ያለው የትምህርትና የሕጻናት ጉዳይ ድሮም አሳሳቢ እንደነበረ የሚናገሩት ሚኪኤል፤ ሁኔታው በምግብ እጥረት የተጠቁ ሕጻናት ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። "ድሮም በትግራይ ከባድ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ችግር ነበር። ከግጭቱ በፊት በ2020 በርካታ እርዳታ ፈላጊዎች ነበሩ። ከኮሮናቫይረስ ስርጭት እና ከየአንበጣ መንጋ ወረራ ጋር በተያያዘ 34 በመቶ ከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የነበረባቸው ሕጻናት ነበሩ፤ አሁን ባገኘነው ሪፖርት መሰረት ደግሞ ቁጥሩ ከ4 እስከ 4.5 በመቶ ሊሆን እንደሚችል ነው። ይህም ከግጭቱ በፊት ከነበረው የላቀ ነው" ብለዋል። ከመቀለ ሆስፒታል መረጃ የሰጠን አንድ የጤና ባለሙያ፤ በምግብ እጥረት የተጠቁ ሕጻናት ወደ ህክምና እንደሚመጡና ለዚህ የሚሰጡ መድሃኒቶች የማግኘት ችግር መኖሩን ይናገራል። "ምግብ መብላት አስቸግሯቸው ሆዳቸው አብጦ፣ ቆስለው የመጡ ህጻናት አሉ። በዚህ ምክንያት ተቅማጥና የሳምባ ምች እያጠቃቸው ነው። ይህ ከምግብ እጥረት የሚመነጭ ነው። ስንጠይቃቸው 'ቤተ-ክርስቲያ ተጠልለን ነው የቆየነው፣ በረሃ ላይ የሚበላና የሚጠጣ ውሃ ሳናገኝ ነው የቆየነው' ስለሚሉ ችግራቸው የምግብ እጥረት እንደሆነ ያሳያል" ይላል። በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ወደ ክልሉ ለሕጻናት አልሚ ምግብ መላኩን ቢገልጽም ይህ ግን ከፍላጎት አንጻር ሲታይ በቂ አይደለም ይላል። እንደ ሚኪኤል ገለጻ በክልሉ ያለው ሁኔታ ወደ ሁሉም አካባቢዎች ለመድረስ የሚያስችል አለመሆኑ እና አብዛኛዎቹ በገጠር አካባቢዎች የነበሩ መዋቅሮች አሁን ባለመኖራቸው አልሚ ምግብ ወደ ክልሉ መላክ ካልተቻሉባቸው ምክንያቶች ተጠቃሽ ናቸው። "ከ600 በላይ የጤና ባለሙያዎች ወደ መቀለ ተፈናቅለዋል። ከ40 ሆስፒታሎች 14ቱ ተዘርፈዋል፤ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ሆስፒታሎች 4 ብቻ እንደሆኑ መረጃው አለን" ብለዋል። የስነ ልቦናዊ ቀውስ ስጋቶች በትግራይ ክልል በተከሰተው ግጭት ከባድ ጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። ግጭቱ በሰዎች ላይ ስነ ልቦናዊ ቀውስ ሊፈጥርም ይችላል። የመቀለ ከተማ ነዋሪ እና የሦስት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ ለተብርሃን ግደይ፤ በትንሽ ንግድ ልጆችዋን ታሳድግ እንደነበረ ትናገራለች። ከግጭቱ በፊትም በድህነት እንደምትኖር ገልጻ፤ ዛሬ ላይ ግን ግጭቱን ተከትሎ በልጆቿ ላይ የደረሰው ስነ ልቦናዊ ጫና እንዳሳሰባት ትገልጻለች። "በተለይ ትንሹ የአምስት አመት ሕጻን ስለ ጦርነት የሚያውቀው ነገር የለም። መቀለን ለመቆጣጠር በነበረው የአየርና የከባድ መሳሪያ ድብደባ ደንግጦ፤ አሁንም ድንጋጤው አልለቀቀውም። ጮክ ያለ ድምጽ ሲሰማ ያለቅስብኛል፤ ከእቅፌ መውጣት አይፈልግም" ትላለች። በምስራቃዊ ዞን ተንቤን አካባቢ በከፍተኛ ጦር መሳሪያዎች ከባድ ጦርነት እንደነበረ የምትናገረው ትርሐስ፤ ለሳምንታት በእግሯ ተጉዛ መቀለ እንደደረሰች ትናገራለች። "እስከ ዛሬ የሚሰማኝን ድንጋጤ መግለጹን ትቼ፤ ስለ ልጄ ልናገር። እዚህ የአየር ድምጽ ስትሰማ 'መጣችብኝ' እያለች ትደነግጥብኛለች። አይዞሽ . . . የእኛ ናት እያለኩ ማባበል ስራዬ ሆኗል" ትላለች። ሞትና የአካል ጉዳት እንዲሁም መፈናቀል፤ ጦርነትን ወይም ግጭትን ተከትለው የሚመጡ ችግሮች ሲሆኑ፤ በኢትዮጵያ የሕጻናት አድን ድርጅት ተወካይ ሚኪኤል ሰርቫዲ በግጭቱ ምክንያት በርካታ ሕጻናት ስነ ልቦናዊ ጫና ደርሶባቸዋል ብለዋል። "በትግራይ በርካቶች ተፈናቅለዋል። እኛ ማረጋገጥ ባንችልም ጾታዊ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ነው የሚሉ ሪፖርቶች ያሳስቡናል። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ሕጻናት ለስነ ልቦናዊ ችግር ተጋላጭ ሆነዋል" ይላሉ። "በምኖርባት መቀለ ከተማ እንኳን ብዙ የሚታይ ነገር ነው ያለው" የሚለው በመቀለ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ፕሮፌሰር ቢነጋ ሃይለስላሴ፤ ቀውሱ በአንድ ማህበረሰብ ሊያደርሰው የሚችለው ሁለንተናዊ ጉዳት ብዙ ነው ይላል። "አሁን ባለንበት ሁኔታ የአየር ወይም የመኪና ድምጽ ሰምቶ የሚደሰት ሕጻን የለም፤ ሁሉም ደንግጠዋል" የሚለው ተባባሪ ፕሮፌሰር ቢነጋ፤ በተለያዩ አካባቢዎች የነበሩ የጦርነት መሳርያ ድምጾች በልጆች ስነ ልቦና ትተውት ያለፉት ጠባሳ አለ ይላል። እንደዚህ አይነት ችግሮች የገጠሟቸው የባለሙያ ድጋፍ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ ወደ አእምሮ ጤና ችግር ሊያድግ እንደሚችልና ችግሩ ተባብሶ የሚጥል በሽታን የመሰሉ ህመሞች የመስፋፋት እድል እንዳላቸው ስጋቱን ይገልጻል። "ከአጸደ ሕጻናት ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው፤ መደበኛ ትምህርት የለም። የአንድ ሕጻን አእምሮአዊ እድገት የሚወሰንበት እድሜ እስከ ሰባት አመት ነው። ስለዚህ አጸደ ሕጻናቶቹ ከተዘጉ፣ መደበኛ ትምህርት ከተቋረጠ፤ የሕጻናቱ አእምሮ መሰረታዊ ቅርጽ የሚይዝበት ጊዜ ያልፋል ማለት ነው" በማለት እነዚህ ህጻናት ወደ ትምህርታቸው ለመመለስ ሰላም መስፈን አለበት ሲል ያብራራል። መሬት ላይ ብዙ ፍላጎቶች እንዳሉ የሚገልጹት ሚኪኤል በበኩላቸው፤ ለተለያዩ ጥቃቶች ተጋላጭ የሆኑ ሕጻናት በመኖራቸው ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች ሕጻናትና ንጹሀን ዜጎችን ከጥቃት እንዲከላከሉ ጠይቀዋል። በተጨማሪም መረጋጋት በሚታይባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ እና ተጠቂ የሆኑ ሕጻናት እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል። ለዚህም የተሻለ መንገድ እንዲከፈት ፍላጎታቸው እንደሆነ በመግለጽ ከመንግሥት ጋር እየሰራን ነው ብለዋል።
news-54351591
https://www.bbc.com/amharic/news-54351591
ሩሲያ ፡ ጋዜጠኛዋ በአደባባይ እሳት ለኩሳ በአሰቃቂ ሁኔታ እራሷን አጠፋች
ሩሲያዊቷ ጋዜጠኛ ወደ ሞስኮ ወደሚገኘው ሩሲያ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ደጅ ከሄደች በኋላ አደባባይ ላይ ራሷን በእሳት አጋይታ ለህልፈት ተዳረገች።
ኢሪና ስላቪና ኢሪና ስላቪና ይህን አሰቃቂ እርምጃ በራሷ ላይ ከመውሰዷ ቀደም ብሎ ፌስቡክ ሰሌዳዋ ላይ የሚከተለውን ጽፋ ነበር። "ለእኔ ሞት የሩሲያ መንግሥትን ተጠያቂ እንድታደርጉ እለምናችኋለው።" የአገሪቱ ባለሥልጣናት ድርጊቱን መፈጸሟን ያመኑ ሲሆን አስከሬኗ በእሳቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ብለዋል። ስላቪና ሐሙስ ዕለት ፖሊስ የምትኖርበት ቤት መጥቶ ፍተሻ እንዳደረገ ገልጻ ነበር። መኖርያ ቤቷ ውስጥ ብርበራው የተካሄደው ምናልባት በሩሲያ ዲሞክራሲ እንዲያብብ ከሚሰራው የ'ኦፕን ሩሲያ' ቡድን ጋር ግንኙነት ካላት በሚል ነው። ከብርበራው በኋላ ኮምፒውተሯን፣ ቤት ውስጥ የነበሩ ላፕቶፖችንና ፍላሽ ዲስኮችን እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች ተወስደውባት ነበር። ጋዜጠኛዋ ራሷን በእሳት ለኩሳ ስታቃጥል የሚያሳየው ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት በመጋራት ላይ ይገኛል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ አንድ ሰው የለኮሰችው እሳት ሊያጠፋላት ወደ እርሷ ሲሮጥ፤ እርሷ በተቃራኒው ነፍሷን ሊያድን የሚሞክረውን ሰው ገፍትራ ስትጥለውና ስትከላከለው ይታያል። በመጨረሻም እሳቱ እየበላት ተዝለፍልፋ ትወድቃለች። ይህም የሆነው ጎርኪ ተብሎ በሚጠራው የሞስኮ ጎዳና ላይ ነው። የሩሲያ ምርመራ ኮሚቴ ኢሪና ስላቪና በተባለው መንገድ መሞቷን አረጋግጦ ነገር ግን ቤቷን አልበረበርንም ሲል ክዷል። ኢሪና 'ኮዛ ፕሬስ' የተሰኘ የአንድ የዜና ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ነበረች። የድረ ገጹ መሪ ቃል "እውነትን ሳንሱር አናደርግም" የሚል ነበር። ኢሪና ስላቪና ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ እናት ነበረች።
news-52839415
https://www.bbc.com/amharic/news-52839415
አሜሪካ፡ "እኔ ብሆንስ?" የፍሎይድ ሞት የቀሰቀሰው የአፍሪካ አሜሪካዊያን ምሬት
"ትንፋሽ እያጠረኝ ነው። እባክህ ከአንገቴ ላይ ተነስ። መተንፈስ አልቻልኩም" ጆርጅ ፍሎይድ የተሰኘው ጥቁር አሜሪካዊ ያሰማቸው የመጨረሻ ቃላት።
ሟች ጆርጅ ፍሎይድ ከዚህ ክስተት በኋላ ሚኒያፖሊስ በተሰኘችው ከተማ ተቃውሞ ደርቶባታል። 'የጥቁር ሕዝቦች ሕይወት ዋጋ አለው'፤ 'መተንፈስ አልቻልኩም'፤ 'ዘረኝነት ይብቃ' እና መሰል መፈክሮችን ያነገቡ አሜሪካውያን ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። ለምን? የ46 ዓመቱ ጆርጅ ፍሎይድ ዕለተ ሰኞ ነው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዳለ ሕይወቱ ያለፈው። ግለሰቡ የጦር መሳሪያ አልያዘም። ጩቤም ሆነ ዱላ እጁ ላይ አይታይም። ነገር ግን በነጭ አሜሪካውያን ፖሊሶች ተከቧል። አንደኛው ፖሊስ ፍሎይድን አስተኝቶ በጉልበቱ አንገቱ ላይ ቆሟል። ይሄኔ ነው ፍሎይድ "ትንፋሽ እያጠረኝ ነው። እባክህ ከአንገቴ ላይ ተነስ። መተንፈስ አልቻልኩም" ሲል መማጸን የጀመረው። ጩኸቱ ግን ሰሚ አላገኘም። ይህ ሁሉ ሲሆን ታድያ የዓይን እማኞች ሁኔታውን በስልካቸው ካሜራ ይቀርፁ ነበር። በሥፍራው የነበሩ ሰዎች በስልካቸው ያስቀሯቸው ቪድዮች በስፋት ከተሰራጩ በኋላ በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉ አራት ፖሊሶች ከሥራቸው እንዲታገዱ ተደርገዋል። የሚኒያፖሊስ ከንቲባም አደባባይ ወጥተው 'ጥቁር መሆን የሞት ቅጣት መሆን የለበትም' ሲሉ ተደምጠዋል። አራቱ ፖሊሶች ወደ ሥፍራው የመጡት የሐሰተኛ ገንዘብ እንቅስቃሴ ተስተውሏል የሚል ጥቆማ ከደረሳቸው በኋላ ነው። ፖሊስ እንደሚለው ፍሎይድ ከፖሊስ መኪና ገሸሽ እንዲል ቢጠየቅም እምቢኝ ብሏል፤ ይሄኔ ነው በቁጥጥር ሥር ልናውለው የተገደድነው ብለዋል። ምንም እንኳ በዓይን እማኞች የተቀረፁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ፖሊስ ግለሰቡን እንዴት አድርጎ በቁጥጥር ሥር እንዳዋለው ባያሳዩም፤ ፍሎይድ ከመሬት ተጣብቆ ሕይወቱን ለማዳን ፖሊስን ሲማፀን ግን ያሳያሉ። መንገደኞች ፖሊስ ከጥቁር አሜሪካዊው አንገት ላይ እንዲነሳ ሲማፀኑም ይሰማል። ፍሎይድ ግን "ትንፋሽ እያጠረኝ ነው"፤ "እባክህ አትግደለኝ" ከማለት ውጪ ምንም ማድረግ አልቻለም። የፍሎይድ ልመና ያልበገረው ፖሊስ የግለሰቡ አንገት ላይ ቆሞ መንገደኞችን ሥፍራውን ለቀው እንዲሄዱ ያዛል። በመሃል ፍሎይድ መንፈራገጥ አቆመ፤ አምቡላንስም ተጠራ። ነገር ግን ፍሎይድ እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ። የፖሊስ ጭካኔ የተሞላበት ተግባር ሰለባም ሆነ። የአሜሪካ ወንጀል መርማሪ ተቋም ኤፍቢአይ ጉዳዩን እየመረመርኩ ነው ብሏል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው 'እኔ ነኝ ገዳዮቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ ያዘዝኩት' ይላሉ። ነገር ግን አገራቸው ጥቁር ሰው በሰቀቀን የሚኖርባት ሆናለች። አሜሪካ ምድረ ገነት አይደለችም፤ አሜሪካ የእኩልነት መገለጫ አይደለችም፤ አሜሪካ ነፃነት የሚታፈስባት አይደለችም፤ በተለይ ደግሞ ቆዳው ለጠቆረ ሰው ይላሉ ይህ መሰል ድርጊት ደጋግሞ የገጠማቸው አፍሪካ አሜሪካዊያን። እርግጥ ነው በርካቶች ሕይወታቸውን የቀየሩባት ናት፤ ልዕለ ኃይልነቷም የሚካድ አይደለም። አሜሪካ ስታስነጥስ የተቀረው ዓለም 'ይማርሽ' የሚለው ወዶ አይደለም። ነገር ግን አሜሪካ ቆዳ ትለያለች። ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተከሰቱት የጥቁር አሜሪካውያን ግድያዎች ለዚህ ምስክር ናቸውም ይላሉ። ጥቁር አሜሪካውያን የፖሊስ ጭካኔ ሰለባ ሲሆኑ ፍሎይድ የመጀመሪያው አይደለም፤ የመጨረሻው ነው ብሎ ማሰብም የዋህነት ነው። ከዊል ስሚዝ እስከ ጄሚ ፎክስ፣ ቢዮንሴ፣ ጀስቲን ቢበር፣ ከካርዲ ቢ እስከ ወጣቱ ጥቁር እንግሊዛዊ ተዋናይ ጆን ቦዬጋ ምሬታቸውን አሰምተዋል። ግድያው የቀሰቀሰው ተቃውሞና ውድመት ጥቁሮች ላይ የሚደርሰው ዘረኝነት ይብቃ ብለዋል። ዊል ስሚዝ በአንድ ወቅት ያለውን ልብ ይሏል፡ 'ዘረኝነት አሜሪካ ውስጥ ተፋፍሟል ብላችሁ እንዳትታለሉ፤ በተንቃሳቀሽ ስልክ ምክንያት የአደባባይ ምስጢር ሆነ እንጂ ሁሌም ነበር።' የፍሎይድ መገደል ያስቆጣቸው አሜሪካውያን ሚኒያፖሊስን በእሳት አጋይተዋታል። ሱቆች ተዘርፈዋል፤ ሕንፃዎች ተቃጥለዋል። ፍትህ ለፍሎይድ የሚል መፈክር የያዙ ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፤ የአስለቃሽ ጭስ ሲሳይ ሆነዋል። ተቃውሞውን የሚያስተባብሩ ሰዎች፤ በሺህ የሚቆጠሩት ሰልፈኞች ሰላማዊ እንዲሆኑና በኮሮናቫይረስ ምክንያት ርቀታቸው እንዲጠብቁ ቢመክሩም ሰሚ አላገኙም። ሲቢኤስ የተሰኘው ቴሌቪዥን ጣብያ ላይ የቀረበ አንድ ሰልፈኛ "በጣም አስቀያሚ ነው። ፖሊሶች ኑሯችንን ምንኛ እያከበዱት እንዳለ ሊያውቁት ይገባል" ሲል ተደምጧል። ሚኒያፖሊስ በርካታ ጥቁሮች የሚኖሩባት ከተማ ናት። በኢትዮጵያዊያንም ዘንድ ታዋቂ ናት። ለዚህም ይመስላል ነዋሪነታቸውን አሜረካ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በማኅበራዊ ድር-አምባዎች ድምፃቸው እያሰሙ የሚገኙት። ከሁሉም በላይ ጎልቶ የሚሰማው ድምፅ ግን "እኔ ብሆንስ?" የሚለው ነው። ለጥቁር አሜሪካውያን እኒህ ሁለቱ ቃላት ትልቅ ትርጉም አላቸው። አሜሪካ፤ ከዘመነ ማልኮም ኤክስ፤ ተቃውሞን በእንብርክክ እያሰማ እስካለው ካፐርኒክ ለጥቁሮች ጆሮ ለመስጠት ዳድታለች። የቆዳዎ ቀለም እንደኔ ከሆነ ነገ የፖሊስ ጭካኔ ሰለባ ላለመሆንም ምንም ማስረገጫ የለም። "እኔ ብሆንስ?" ማለት ይሄኔ አይደል?
news-50211097
https://www.bbc.com/amharic/news-50211097
አሜሪካ፡ የካንሰር ታማሚው ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ በሎተሪ አሸነፉ
በአሜሪካዋ ሰሜን ካሮላይና አንድ ግለሰብ ለካንሰር ኬሞቴራፒ ህክምና ለማድረግ እግረ መንገዳቸውን የገዙት የሎተሪ ቲኬት የ200 ሺ ዶላር (5.9 ሚሊየን ብር) አሸናፊ አድርጓቸዋል።
ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ግለሰቡ የመጨረሻ የኬሞቴራፒ ህክምናቸውን ለማድረግ በሚሄዱበት ወቅት ነበር ቲኬቱን የገዙት። ሮኒ ፎስተር ለረጅም ዓመታት በአንጀት ካንሰር በሽታ ሲሰቃዩ የነበረ ሲሆን መጀመሪያ በገዙት የሎተሪ ቲኬት አምስት ዶላር ካሸነፉ በኋላ በአምስት ዶላሩ ተጨማሪ ሁለት ቲኬቶችን ገዝተዋል። • የወላጆች ራስ ምታት እየሆነ የመጣው የልጆች የጌም ሱስ • ወንዶች፤ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒና ለመዋጥ ዝግጁ ናችሁ? ከሁለቱ ቲኬቶች መካከል አንደኛው ምንም አልነበረውም፤ ሁለተኛው ግን ያልጠበቁትን እድል ይዞ ነበር። '' ሁለተኛውን ትኬት ስፍቀው በጣም ብዙ ዜሮዎችን ተመለከትኩ፤ ማማን አቅቶኝ ቆሜ ቀረሁ'' ብለዋል። ሮኒ ፎስተር አክለውም ከሎተሪው ካገኙት ገንዘብ መካከል ጥቂቱን የህክምና ወጪያቸውን ለመሸፈን እንደሚጠቀሙበት ገልጸዋል። ለሰሜናዊ ካሮላይና ትምህርታዊ ሎተሪ ድርጅት አስተያየታቸውን የሰጡት የሎተሪው አሸናፊ '' ሎተሪው ከመድረሱ በፊት እራሱ የመጨረሻ ዙር የኬሞቴራፒ ህክምናዬን ላደርግ ስለነበር በጣም ደስተኛ ነበርኩ'' ብለዋል። '' ሎተሪ ማሸነፌ ደግሞ ይበልጥ ቀኔን አሳመረው።'' ብለዋል። ሮኒ ፎስተር ከግብር በኋላ 141 ሺ ዶላር ወይም 4.2 ሚሊየን ዶላር የሚያገኙ ይሆናል።በትራንስፖርት ቢሮ ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩት ግለሰቡ በአሁኑ ሰአት ጡረታ ወጥተው ነው የሚገኙት። • "ሥራዬን ለቅቄ ልጆቼን ያጠባሁት እድለኛ ሆኘ ነው" ሮዝ መስቲካ ምንም እንኳን የጤና መድህን ሽፋን ቢኖረኝም የካንሰር ህክምና ተጨማሪ ብዙ ወጪዎች ስላሉት ካገኘሁት ገንዘብ መካካል ጥቂቱን ለህክምናዬ ለማዋል ወስኛለው ሲሉ በደስታ ተውጠው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
news-51016938
https://www.bbc.com/amharic/news-51016938
አሜሪካ ወታደሮቿን ከኢራቅ ታስወጣለች የተባለው 'ስህተት ነው' አለች
የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ማርክ እስፔር አሜሪካ ወታደሮቿን ከኢራቅ ታስወጣለች መባሉ ሐሰት ነው አሉ።
በኢራቅ ከ5000 በላይ አሜሪካውያን ወታሮች ይገኛሉ። መከላከያ ሚንስትሩ ይህን ያሉት በኢራቅ የአሜሪካ ወታደሮች አመራር የሆኑት የጦር ጀነራል፤ ለኢራቅ መከላከያ ሚንስትር አሜሪካ በኢራቅ የሚገኙ ወታደሯቿን ታስወጣለች የሚል ደብዳቤ ከጻፉ በኋላ ነው። መከላከያ ሚንስትሩ ማርክ ስፔንሰር "በምንም ዓይነት ሁኔታ ኢራቅን ለቅቆ የመውጣት ውሳኔ የለም" ብለዋል። አሜሪካ ጀነራል ቃሲም ሱሌማኒን በኢራቅ ከገደለች በኋላ የኢራቅ ፓርላማ በአገራቸው የሚገኙ የውጪ ሃገራት ወታደሮች እንዲወጡ በአብላጫ ድምጽ ወስኖ ነበር። የጀነራሉን ግድያ ተከትሎ በመካከለኛ ምስራቅ አሜሪካ ጠል እንቀስቃሴዎች እና ዛቻዎች ተበራክተዋል። አሜሪካም በቀጠናው የሚገኙ ዲፕሎማቶቿን እና የአጋሮቿን ደህንነት ለማጠናከር ተጨማሪ 3000 ወታደሮች እንደምትልክ ማስታወቋ ይታወሳል። የደብዳቤው ይዘት ምን ነበር? ደብዳቤው የተላከው ለአብዱል አሚር፤ በኢራቅ የጥምር ጦር ኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ሲሆን፣ በኢራቅ የአሜሪካ ጦር አዛዥ የሆኑት የብርጋዴር ጀነራል ዊሊያም ኤች ሴለይ ስም አርፎበታል። ደብዳቤው አሜሪካ የኢራቅ የሕዝብ እንደራሴዎች ውሳኔን እና የኢራቅ ጠቅላይ ሚንስትር ጥሪን ተከትሎ፤ ጦሯን በሚመጡት ጥቂት ቀናት ውስጥ ማንቀሳቀስ እንደምትጀምር አሳውቀዋል። ብ/ጀነራሉ ጦራቸውን ሲያንቀሳቅሱ የባግዳድ ከተማን ነዋሪዎችን ላለመረበሽ እንቅስቃሴያቸውበምሽት እንደሚሆኑ ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎችን በደብዳቤያቸው ላይ አስፈረዋል። ዋሽንግተን የሚገኙት የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትሩ ግን፤ "ኢራቅን ለቅቆ ለመውጣት ምንም አይነት ውሳኔ የለም። ስለተባለው ደብዳቤ የማውቀው ነገር የለም . . . ይህ ደብዳቤ ከየት እንደመጣና ለምን እንዳስፈለገ እያጣራን ነው" ብለዋል። የመከላከያ ሚንስትሩ ይህን ካሉ በኋላ ሌላው የጦሩ ከፍተኛ አዛዥ ማርክ ማይሊ ለጋዜጠኞች ደብዳቤው 'ስህተት ነው' ብለውታል። ይህ የጦር አዛዥ "ደብዳቤው ገና በረቂቅ ላይ የነበረና በአሳሳች ቃላት የተሞላ ነው። ወጪ መደረግ አልነበረበትም። ቁልፍ የሆኑ የኢራቅ ጦር አባላት አስተያየታቸውን እንዲሰጡበት ነበር ወጪ የተደረገው" ብለዋል። ማርክ ማይሊ፤ "በስፍራው በከፍተኛ ወጪ የገነባነው የተራቀቀ የጦር ካምፕ አለን። በብሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወጪ ተደርጎበታል። ይህን መልሰው ካልከፍሉን ጥለን አንወጣም" ሲሉም ተደምጠዋል። በአሁኑ ሰዓት በኢራቅ አይኤስን ለመዋጋት ወደ ኢራቅ የተሰማሩ ከ5000 በላይ የአሜሪካ ወታደሮች ይገኛሉ። ከአሜሪካውያኑ በተጨማሪ የሌሎች የምዕራባውያን ሃገራት ወታደሮች በኢራቅ ይገኛሉ። ይህ የጥምር ኃይል አይኤስ ላይ ድል ከተቀናጀ በኋላ የምዕራባውያኑ ጦር ዋና ዓላማ ለኢራቅ ጦር ስልጠና እና የቁስ ድጋፍ ማድረግ ነበር።
news-54903836
https://www.bbc.com/amharic/news-54903836
ሴኔጋል፡በስደት ሰምጦ የሞተው ታዳጊ አባት በቁጥጥር ስር ዋለ
በሴኔጋል ወደ አውሮፓ በማቅናት ላይ እያለ ባህር ውስጥ ሰምጦ የሞተው ታዳጊ አባት በቁጥጥር ስር ውሏል።
ታዳጊው የ15 አመት ሲሆን ባለፈው ወርም ነው ወደ አውሮፓ ያቀናው። አባትየው ልጁን ወደ ስፔን እንዲወስዱት ለህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች 450 ዶላር ከፍሏልም ተብሏል። ከስፔንም በመቀጠል ወደ ጣልያን ተወስዶ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከልም እንዲገባ እቅድ ተይዞ ነበር። በቅፅል ስሙ ዱዱ ተብሎ የሚጠራው ታዳጊ አውሮፓ ሳይደርስ የሞተ ሲሆን አስከሬኑም ወደ ባህሩ እንደተጣለ ተነግሯል። የታዳጊው ሞት በሴኔጋል ኃዘን የፈጠረ ሲሆን፤ በቅርቡም ከምዕራባዊቷ አገር ተነስተው ወደ አውሮፓ ለመድረስ የሚሞክሩ ሴኔጋላውያን ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው ተብሏል። በርካቶችም ፈታኝ የሆነውን ባህርና ውቅያኖስ እንደሚሻገሩም ተገልጿል። የሴኔጋል ፖሊስ እንዳለው በቅርቡ ብቻ ከ1 ሺህ 500 በላይ ስደተኞችን መመለስ እንደቻለም አሳውቋል።
news-54446509
https://www.bbc.com/amharic/news-54446509
ትግራይ፡ ለ10 ማረሚያ ቤቶች 10 ሺህ መጻሕፍት
በመቀለ ከተማ እየተካሄደ ባለው "መጽሐፎች የማሰባሰብ ዘመቻ" በትግራይ ክልል ለሚገኙ 10 ማረሚያ ቤቶች የሚውሉ 10 ሺህ መጽሐፎች ለመሰብሰብ መታቀዱ አስተባባሪዎቹ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ሃሳቡን ያመነጨው ወጣት ሳሙኤል ደስታ እንደሚለው ከሆነ ዘመቻው ከመስከረም 20፣ 2013 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን እስከ ጥቅምት 30 ድረስ ይቀጥላል። መጽሐፎቹን ከተለያዩ ለጋሾች ለማግኘት ማቀዳቸውን የገለጸው ሳሙዔል፣ ሃሳባቸው በበርካታ ሰዎች ተቀባይነት እንዳገኘ ተናግሯል። ዘመቻው መስከረም 20 ላይ ከተጀመረ ጀምሮ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 700 ያህል መጽሐፎች መሰብሰብ ችለዋል። "ብዙም ትኩረት የማይሰጠዉ ጉዳይ ስለሆነ 'ለመሆኑ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ቤተ መጻህፍት አለን እንዴ?' ያሉን ሰዎች አሉ። ሰምተውና አስበውት ስለማያውቁ በጣም ነው ደስተኛ የሆኑት። ብዙ ሰዎች መጽሐፎች ሊለግሱልን እና ለስራችን አጋዥ የሆኑ መረጃዎች መስጠት ጀምረዋል" ይላል። ሳሙኤል ሐሳቡን ወደ ተግባር ለማሸጋገር ቆርጦ በሚነሳበት ጊዜ፣ በተለይም ሰዎች መጽሐፎች እንዲለግሱ በማነሳሳትና የሚለገሱትን በማሰባሰብ ሊረዱት የሚችሉ ወጣት ሴቶችን ለማነጋገር እንደወሰነ ይገልጻል። ለዚህም በተለያዩ የቁንጅናና ሞዴሊንግ መድረኮች ተሳትፎ ያላቸውን ሴቶች እንደመረጠ ያስረዳል። "የቁንጅና ወይም ሞዴሊንግ ውድድር አላማው፣ አርኣያ በመሆን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ላይ ለውጥ ማምጣት ነው። ሆኖም ግን በእነዚህ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ ሴቶች ከውድድሩ በኋላ ይህንን ሊያደርጉ የሚችሉበት ዕድል አያገኙም። ስለዚህ ይህን ከግምት በማስገባት ነው እንዲረዱኝ ያነጋገርኳቸው" ብሏል። በዚህም መሰረት በተለያዩ የቁንጅናና ሞዴሊንግ ውድድሮች ላይ የተሳተፉ አራት ሴቶች በመምረጥ ወደስራው ገባ። አዱኛ ዳኘው፣ ቢዚ መብራህቱ፣ ማክዳ ፍሰሃና ሮዳስ ሚዛንን የሚባሉት እነዚህ ወጣት ሴቶች "ኮኾባት ትግራይ" [የትግራይ ኮኮቦች] በሚል ስያሜ መጽሐፍ የማሰባሰብ ዘመቻውን እያስተባበሩ ይገኛሉ። "ሳሙኤል ሐሳቡን ሲያቀርብልን በጣም ደስተኞች ነበርን። ምክንያቱም ሞዴሎች ወይም የቁንጅና ውድድር አሸናፊዎች ከሙዚቃ ክሊፖችና ፊልሞች ውጪ በዚህ ዓይነት ተሳትፎ ላይ ብዙም አይታዩም" ትላለች ከወጣቶቹ መካከል አንዷ የሆነችው አዱኛ ዳኘው። መጻሕፍቶቹ፡ ታራሚዎች በእስር ቆይታቸው እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ ከማድረግ በተጨማሪ በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚያሳልፉት ጊዜ በጥሩ ሁኔታ እንዲያልፍ የሚያደርጉ መሆናቸውን ታምናለች። ስለሆነም እሷና ጓደኞቿ በዚህ ዘመቻ ላይ መሳተፍ መቻላቸው እንደ መልካም ዕድል ትቆጥረዋለች። መነሻ ሐሳቡ ምን ነበረ? ወጣት ሳሙኤል በፕሮሞሽን እና ኪነጥበብ ዘርፍ የተሰማራ ባለሙያ ነው። ለታራሚዎች የሚሆኑ መጽሐፎች ለማሰባሰብ ሲነሳሳ የታሰረ የቤተሰቡ አባል፣ ጓደኛው ወይም የቅርብ ሰው ኖሮት እንዳልሆነ ይናገራል። ከ ዘጠኝ ዓመታት በፊት የ ስምንተኛ ክፍል ተማሪ በነበረበት ወቅት በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ያሉትን ቤተ መጻህፍቶች የመጎብኝት ዕድል አጋጥሞት ነበር። ታዲያ ለዛሬው ሐሳቡ መነሻ የሆነው ይኼው አጋጣሚ እንደሆነ ያስረዳል። "ያኔ ተማሪ ሆኜ የተማሪዎች ፓርላማ አባል ስለነበርኩ፣ በትግራይ ወደሚገኙ ማረሚያ ቤቶች በመሄድ በማረሚያ ቤቶቹ ውስጥ ያሉትን ቤተንባቦች ጎብኝተን ነበር። የያኔው ሁኔታ በውስጤ ስለቆየ ዛሬ ጊዜው ሲደርስ በተግባር ለመንቀሳቀስ ውሳኔ ላይ ደረስኩ" ይላል። ታራሚዎች የፈለጉትን መጽሐፍ በቀላሉ የሚያገኙበት ዕድል አለመኖሩን በመታዘቡ ከዓመታት በኋላ ዛሬ የድርሻውን ለመወጣት እንደወሰነ ለቢቢሲ ተናግሯል። "በትግራይ 10 ማረሚያ ቤቶች አሉ። በቂ መጻሕፍት ባይኖራቸውም ላይብራሪዎች [ቤተ መጻህፍት] ግን አሏቸው። ታራሚዎቹ ነገ ወደ ኅብረተሰቡ ስለሚቀላቀሉ የእነርሱ ሙሉ መለወጥ ደሞ በቤተ መጻሕፍት ውስጥም ልናገኘው እንችላለን። ስለዚህ እውቀታቸውን እና ስነልቦናቸውን ገንብተው ቢወጡ በሚል ነው ወደ ስራው የገባነው" ሲል ይገልጻል። ከማራሚያ ቤቶቹ መካከል አንዱ ለሆነው መቀለ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ስለጀመሩት እንቅስቃሴ በሚመለከት ባነጋገሩበት ሰዓት 'ቤተ መጻሕፍት ቢኖረንም ታራሚዎች ግን የሚፈልጓቸውን ለማግኘት ይቸገራሉ። ስለዚ የጀመራችሁት ዘመቻ መልካም ነውና ለእኛም እንድትረዱን እንፈልጋለን' የሚል ጥያቄ እንደቀረበላቸው ሳሙኤል ያስታውሳል። የለጋሾች ተሳትፎ ከ 'መጻሕፍት ለትግራይ ማረሚያ ቤቶች ዘመቻ' አስተባባሪዎች አንድ የሆነችው ወጣት አዱኛ ከህዝቡ የተሰጠ ምላሽና ተሳትፎ እጅግ የሚያኮራ እንደሆነ ትገልጻለች። "ሰዎች ሐሳቡን ተቀብለውታል። በማህበራዊ ገጾችም እየተነጋገሩበት ነው። አንድም ይሁን ከዚያ በላይ መጽሐፍ ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች እንድንቀበላቸው ደውለው ያሳውቁናል። እኛም ወዳሉበት ቦታ በመሄድ እንቀበላቸዋለን" በማለትም ታስረዳለች። ከመቀለ ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ስልኮች እየተደወሉ "መጽሐፍ ተቀበሉን' የሚል ጥሪ ስለሚደርሳቸው ለጊዜው በመቀለ ብቻ ለሚቀርቡ ልገሳዎች አራቱም በመመካከርና በመተጋገዝ ይቀበላሉ። ከሌሎች አካባቢዎች የሚቀርቡ ስጦታዎች እንዴት መቀበል እንደሚችሉም ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ ናቸው። መጽሐፎቹን ለመቀበል በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የመጓጓዣ ወጪ ስለሚኖር ከኪሳቸው ይሸፍኑታል። ይህንን ከግምት ውስጥ ያስገቡ አንዳንድ ሰዎች ደሞ ለዚህ ዓላማ በማሰብ ለትራንስፖርት የሚሆን የተወሰነ ጥሬ ገንዘብ እንደሚሰጧቸው አዱኛ ትናገራለች። ሳሙኤል በበኩሉ "እኛ ስንጀምረው ለ10 ማረሚያ ቤቶች የሚከፋፈሉ 10 ሺ መጻሕፍት ለማሰባሰብ በማቀድ ነው። አሁን ባለው የሰዎች ተፋትፎ ግን ከዚያም በላይ ማሰባሰብ እንደምንችል አሳይቶናል" ይላል። ስለሆነም ለአንድ ማረሚያ ቤት ከ 1 ሺ መጽሐፎች በላይ እንደሚደርስ ያምናል። የመጻሕፍቶቹ ይዘቶች? ሳሙኤልና አዱኛ እንደሚሉት ከሆነ ሰዎች ምን ዓይነት መጽሐፍ መለገስ እንደሚችሉ የወጣ መለኪያና የተነገረ መመሪያ የለም። ይህም ሆኖ ግን ሰዎች "ለታራሚዎች" የሚለውን ሃሳብ ከግምት በማስገባት እስካሁን የሚያስረክቧቸው መጻሕፍት በማረሚያ ቤተቹ ውስጥ ለሚገኙ ቤተ መጻሕፍት ሊቀመጡ የሚችሉ ናቸው። "በርግጥ ወደ ዘመቻው ከመግባታችን በፊት በክልሉ ጸጥታ ቢሮ ጉዳዩ ከሚመለከትው አካል ጋር በመነጋገር ዳሰሳ ለማድረግ ሞክረናል" የሚለው ሳሙኤል ለታራሚዎቹ ምን ዓይነት መጻሕፍት እንደሚያስፈልጉ መረዳታቸውን ይገልጻል። "በንግድ፣ ባህላዊ አልባሳት ዝግጅት፣ የብረታ ብረትና እንጨት ስራዎች እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ በርካታ ታራሚ ወጣቶች ስላሉ ለዚህ ሊረዳቸው የሚችል የኢንዳስትሪና ፈጠራ መጽሐፍ በብዛት ይፈለጋል። በታራሚዎቹ ስነልቦናና እውቀት ግንባታ ላይ አስተዋጽኦ ሊኖራቸው የሚችሉ ሌሎች መጻሕፍቶችም እየተቀበልን ነው" በማለት ያስረዳል። እስካሁን 'ይህ አስፈላጊ አይደለም' በሚል የመለሱት መጽሐፍ እንደሌለ በማስታወስም የስነጽሑፍ ውጤቶች የሆኑ መጻሕፍቶችም በብዛት እየተቀበሉ መሆናቸውን ገልጿል። አዱኛ በበኩሏ "ብዙ ዓይነት መጽሐፍት ነው እየተቀበልን ያለነው። ሁሉም ጥሩ የሆነ ይዘት አላቸው" በማለት ከታራሚዎች መካከል ምሁራንም ስለሚገኙ 'ኣካዳሚያዊ' እንዲሁም ሌሎች እውቀቶችን ሊያዳብሩ የሚችሉ በእንግሊዝኛ ጭምር የተጻፉ እንደሚቀበሉ አስታውሳለች።
57053673
https://www.bbc.com/amharic/57053673
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሙስሊም ማህብረሰብን ይቅርታ ጠየቁ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ፣ አዳነች አቤቤ ትናንት እሁድ "ለተፈጠረው ነገር በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ" አሉ።
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምክትል ከንቲባዋ ትናንት በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የአፍጥር ስነ ስርአት መስተጓጎሉን አስታውሰው፤ ይህ የሆነው "ወቅታዊ የደህንነት እና የጸጥታ ሁኔታን ከግምት በማስገባት የቦታው ስፋት እና ርዝመት ውስን እንዲሆን ባቀረብነው ሀሳብ አዘጋጅ ኮሚቴው ባለማመኑ ብቻ መሆኑ ግልጽ እንዲሆን እንፈልጋለን" ብለዋል። ምክትል ከንቲባዋ የትናንት እሁድ፣ ምሽት ሁኔታ የሁላችንም ሰላም እና ደህንነት እንዲጠበቅ አስፈላጊ ጥንቃቄ ለማድረግ የጸጥታ አካላት ጥበቃ ለማድረግ ብቻ የተንቀሳቀሱት እንጂ "በፍፁም የአፍጥር ክልከላ አይደለም" ሲሉ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። ትናንት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ለማድረግ ያሰቡ ሙስሊሞች ፍቃድ አልተሰጠም በሚል ምክንያት ወደ መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ተከልክለው ነበር። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተጋሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ላይ እንደታየው ፖሊስ የተሰበሰበውን ሕዝብ ለመበተን አስለቃሽ ጪስ ተጠቅሟል። ምክትል ከንቲባዋ ክስተቱን "አንዳንድ ሃላፊነት የማይሰማቸው አካላት ይህን ጉዳይ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ለመውሰድ በማህበራዊ ሚዲያ ሊያራግቡት ሞክረዋል። በዚህ ሁኔታ ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የተሰማውን ቅሬታ የገለጸበት መንገድ ጨዋነት የተሞላበት እና ሰላማዊ መሆኑ ሊደነቅ ይገባል።" ብለዋል። ትናንት የጎዳና ላይ ኢፍጣር ለማድረግ አደባባይ የወጣ የሙስሊሙ ማህብረሰብ ስለጉዳዩ እስካሁን የምናውቀው ትናንት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሙስሊሙ ማህብረሰብ በመስቀል አደባባይ ሊያደርገው የነበረው የአፍጥር ስነ-ስርዓት በመከልከሉ ተቃውሞውን ሲገልጽ ተስምቷል። በወቅቱ ከተሰሙት መፈክሮች መካከል "በአገራችን ሁለተኛ ዜጋ መሆን የለብንም"፣ "አደባባዩ የእኛም ነው" እና "ለጿሚ አስለቃሽ ጪስ ኢ-ፍትሃዊ ነው" የሚሉ የተቃውሞ ድምጾች ተስተጋብተዋል። ባለፉት ቀናት በመስቀል አደባባይ ኢፍጣር የማድረግ እቅድ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ዋነኛ መነጋጋሪያ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል። ሃላል ፕሮሞሽን የተባለ ድርጅት፤ "ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ" በሚል ከአምስት ሺህ በላይ ሕዝብ የሚታደምበት የኢፍጣር ዝግጅት በመስቀል አደባባይ ለማካሄድ ጥያቄ ማቅረቡን ገልጾ ነበር። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በበኩሏ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢፍጣር ስነ-ስርዓቱ በመስቀል አደባባይ ሳይሆን በአዲስ አበባ ስታዲየም መከበር አለበት የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ ግንቦት 28 2013 ዓ.ም ጽፋለች። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የመስቀል አደባባይ ከመመረቁ በፊት ለሌላ አገልግሎት እንዳይውል የተገለጸ ስለሆነ ፈቃድ ጠያቂዎቹ በሚያቀርቡት ተለዋጭ ቦታ ብቻ እንዲካሄድ ይፈቀድላቸው ብሎ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ግንቦት 28 2013 ዓ.ም ደብዳቤ ጽፏል። የኢፍጣር ስነ-ስርዓቱን ሲያዘጋጅ የነበረው ድርጅት እንደሚለው ከሆነ የመንግሥት አካል የዝግጅት ቦታውን እንዲቀየር ጠይቋል። ድርጅቱ ግን የዝግጅት ቦታ መቀየሩ አግባብ አይደለም በሚል የኢፍጣር ፕሮግራሙን ለመሰረዝ ተገድጃለሁ ሲል በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል። በሌላ በኩል ትናንት ምሽት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሃ ግብሩ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ ብሏል። የከተማ አስተዳደሩ፤ የአገሪቱን አጠቃላይ ሁኔታ ከግምት በማስገባት፣ የአደባባዩ የመጨረሻ የግንባታ ሥራዎች አለመጠናቀቃቸው እንዲሁም የቦታው ስፋት እና ርዝመት ከታሰበው ታዳሚ አንጻር እንቅፋት እንዳይፈጥር በውስን አካባቢ እንዲካሄድ እንደ መፍትሔ ተውስዶ ነበር ብሏል። አስተዳደሩ አዘጋጆቹ ፕሮግራሙን የመሰረዝ አማራጭን ወስደዋል ብሏል የከተማ አስተዳደሩ። የከተማ አስተዳደሩ ጨምሮም ይህን ለሌላ አላማቸው ለማዋል በማህበራዊ ሚዲያ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንዲራገብ ያደረጉ አካላት እንዳሉ አስተውለናል ብሏል። በዘንድሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች በጎዳና ላይ የሚደረጉ የኢፍጣር ስነ-ስርዓቶች በተለያዩ ቦታዎች ተካሂደዋል። በአዲስ አበባ፣ ደሴ፣ ባህር ዳር፣ ከሚሴ መስል መርሃ ግብሮች ከተካሄዱባቸው ስፍራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
news-47937558
https://www.bbc.com/amharic/news-47937558
ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን?
ሱዳን በህዳሴው ግድብ ግንባታ ጉዳይ ከጅማሮ አንስቶ በነበራት አቋም የኢትዮጵያ አጋር ነች። በአጠቃላይ የተፋሰሱ ሃገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሶስትዮሽ ድርድር ሱዳን የቆመችው ከኢትዮጵያ ጋር ነው።
በአንፃሩ ግብፅ የግድቡ ሃሳብን በመቃወም ገና ከጠዋቱ ይሆናል ያለችውን ዕድል ሁሉ ስትሞክር ነበር። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ዛሬም ያን ጥረቷን አላቋረጠችም። ከቀናት በፊት አንቀጥቅጠው የገዟትን ኦማር ሃሰን አል-ባሽርን በቃኝ ብላ ከሥልጣን ያስወገደችው ሱዳን ያልለየለት የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ ነች። ይህን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ የአቋም ለውጥ ልታደርግ ትችላለች ወይ? በኢትዮጵያ በኩል የህዳሴው ግድብ ግንባር ቀደም ተደራዳሪ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የምስራቅ ናይል የቴክኒክ አህጉራዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ሱዳን የህዳሴው ግድብን በሚመለከት በአቋሟ ትቀጥላለች ብለው ያምናሉ። ግብፅ ግን ዳር ላይ ቆማ እንዲሁ ነገሮችን ልትመለከት አትችልም። በቀዳሚነት የሚያነሱት ነጥብ የግድቡን ግንባታ መደገፍ ለሱዳን የፖለቲካ ውሳኔ ሳይሆን የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ መሆኑን ነው። "ትልቅ ጥቅም ነው የሚያገኙት ያለምንም ኢንቨስትመንት" ይላሉ። ለአል-ባሽር ከሥልጣን መውረድ ምክንያት የሆነው ተቃውሞ በዳቦ ውድነት ፤ በኑሮ ውድነት የተቀሰቀሰ ነው። ግድቡ ደግሞ ለዚህ ጥያቄ በአጠቃላይ ለሃገሪቱ የልማት ጥያቄ መልስ እንደሚሆን አቶ ፈቅአህመድ ያስረዳሉ። አቶ ፈቅአህመድ እንደሚያስረዱት ግድቡ ለሱዳን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አለው፣ ያለ ምንም ወጪ እስከ ሶስት ሺህ ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ከኢትዮጵያ በርካሽ ሊገዙ ይችላሉ። በዚህ ደግሞ ኢንዱስትሪዎቻቸውን ሊያነቃቁ፣ ግብርናና ዓሣ እርባታቸውን ሊያስፋፉ ይችላሉ። • ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? ይህ ደግሞ ደቡብ ሱዳን ትልቁን የነዳጅ ሃብቷን ይዛ በመገንጠሏ 'አግኝቶ ማጣት' እንደሚሉት ለሆነችው ሱዳን ከሰማይ እንደሚወርድ መና ሊቆጠር ይችላል። ግድቡ ሱዳንን የማትወደው እንግዳ ከሆነባትና በየዓመቱ ከሚጎበኛት ጎርፍም ይታደጋታል። ጎርፉ የሚያመጣውን ደለል ከግድቦችና ቦዮች ለመጥረግ በየዓመቱ እስከ ሰባ ሚሊየን ዶላር ከመክሰርም ያድናታል። ስለዚህም ምንም ዓይነት መንግሥት ቢመጣ ከዚህ ከፍተኛ ጥቅም የሚበልጥበትና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ይኖራል ብለው እንደማያምኑ አቶ ፈቅአህመድ ያስረግጣሉ። በተመሳሳይ በአባይ ጉዳይ በርካታ ጥናቶችን ያደረጉት ዶ/ር ያዕቆብ አርሳኖም ግድቡን መደገፍ የብሔራዊ ጥቅም እንጂ የፖለቲካ ውሳኔ ባለመሆኑ ሱዳን በአቋሟ ፀንታ ከኢትዮጵያ ጎን መሰለፏን እንደምትቀጥል ያምናሉ። ነገር ግን ለመጭው የሱዳን መንግሥት የህዳሴው ግድብ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ይሆናል አይሆንም የሚለው በሂደት የሚታይ እንደሆነ ይገልፃሉ ዶ/ር ያዕቆብ። • ግብፅ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አዲስ ሃሳብ አቀረበች "ለዚህ ብሔራዊ ጥቅም ሲሉ ነው አቋማቸውን የማይቀይሩት" ሲሉም ያስረግጣሉ። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ያለችው ሱዳን ገና መንግሥት እስክታቋቁም የሚወስደው ጊዜ በተለይም በሂደት ላይ ያለው የሦስትዮሽ ድርድር ላይ የተወሰነ የማዘግየት ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ይናገራሉ። እርሳቸው በጠቀሷቸው ምክንያቶች ሱዳን ለእራሷ ስትል የአቋም ለውጥ አታደርግም ተብሎ ቢታመንም ግብፅ የአሁኑን የሱዳን ፖለቲካዊ ለውጥ እንደሚያመቻት ለመጠቀም የምታደርገው ጥረት ምን ድረስ ሊሄድ ይችላል? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። ግድቡ ከተጀመረ ጀምሮ ግብፅ ሱዳን ላይ በተለያየ መንገድ ከፍተኛ ጫና ስታሳድር እንደነበር የሚናገሩት አቶ ፈቅአህመድ የግብፅ ጫና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይናገራሉ። "ግብፆች አሁን ተጠናክረው ነው የሚንቀሳቀሱት። ጫናቸውም ሱዳን ላይ ይበረታል" ይላሉ። ነገር ግን እስከ ዛሬም ሱዳን ለህዳሴው ግድብ ድጋፏን ስትሰጥ የቆየችው የግብፅን ጫና ተቋቁማ ስለሆነ ከአሁን በኋላም በዚሁ ትቀጥላለች ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። ግብፅ ከጅምሩ ሱዳንም ኢትዮጵያም ላይ ጫና ለመፍጠር ከመሞከር ወደ ኋላ ብላ እንደማታውቅ የሚያነሱት ዶ/ር ያዕቆብ በቀጣይ የግብፅ ተፅዕኖ ስኬት የሚወሰነው ከምንም በላይ በኢትዮጵያ ጥንካሬ እንደሆነ ያስረዳሉ። በዚህ ረገድም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ቁርጠኝነታቸውን ማሳየታቸውን ይጠቅሳሉ። "ዋናው ነገር ኢትዮጵያ ግድቡን ለመሥራት ያላት አቅምና ቁርጠኝነት ነው" የሚሉት ዶ/ር ያዕቆብ ግብፅ በሱዳንም በኩል ሆነ በቀጥታ ኢትዮጵያ ላይ የምታደርገው ተፅዕኖ እንደ ከዚህ በፊቱ እንደሚቀጥል ያመለክታሉ። ሌሎቹስ የተፋሰሱ ሃገራት በአቋማቸው እንደፀኑ ናቸው? ለአቶ ፈቅአህመድ ያነሳነው ጥያቄ ነበር። እርሳቸው በግልፅ የአቋም ለውጥ ያሳየ ሃገር እንደሌለ ይገልፃሉ። ነገር ግን እንደ አውሮፓውያኑ በ2010 ኡጋንዳ ላይ የተፈረመውን የአባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ከአስራ አንዱ የተፋሰሱ ሃገራት የተወሰኑት በሦስት ወራት ውስጥ በፓርላማቸው ሲያፀድቁት ቀሪዎቹ እስከ አሁንም ሳያፀድቁት ዘጠኝ ዓመታት ተቆጥረዋል። ይህ መዘግየት ደግሞ እንዴት ነው ነገሩ የሚያስብል ነገር ነው። አቶ ፈቅአህመድ ደግሞ ይህን ስምምነት ብቻ በመመልከት የማፅደቁ ሂደት ዘግይቷል ሊባል ቢችልም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን ተመሳሳይ ስምምነቶች እንዲህ ያለ ጊዜ እንደሚወስዱ ይናገራሉ። የዚህ ዓይነቱ ድርድር እስከ 40 እና 50 ዓመት የፈጀባቸው ሃገራት መኖራቸውንም ይናገራሉ። ኬንያ ስምምነቱን ለማፀደቅ ሶስት ጊዜ ፓርላማ አድርሳ መመለሷ በደቡብ ሱዳንም በሃገሪቱ የፖለቲካ በተመሳሳይ ሰነዱ ፓርላማ ደርሶ በተደጋጋሚ መመለሱ የሚታወስ ነው። • ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ የተፋሰሱ ሃገራት የውሃ ሚኒስትሮች በየዓመቱ እየተገናኙ የሚወያዩ ሲሆን ያለፈው ስብሰባ እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 አስረኛው ወር በቡጁምቡራ ነበር የተካሄደው። የትብብር ማዕቀፉን ሱዳን ፣ ግብፅና ኮንጎ ጨርሶ አልፈረሙም። ከፈረሙት ሃገራት መካከል ደግሞ ሦስቱ ማለትም ኢትዮጵያ፣ታንዛኒያና ኡጋንዳ በፓርላማቸው ያፀደቁት ሲሆን ተጨማሪ ሦስት ሃገራት ቢያፀድቁት ለአፍሪካ ሕብረት በማቅረብ ከፍተኛ ትብብር ማድረግ የሚረዳቸውን ኮሚሽኑን ማቋቋም ይችላሉ። የትብብር ማዕቀፉን ፈርመው እስካሁን ያላፀደቁ ሃገራት ኬንያ ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ብሩንዲና ሩዋንዳ ናቸው።
news-53488247
https://www.bbc.com/amharic/news-53488247
በሁከቱ ከ1ሺህ በላይ መኖሪያና ንግድ ቤቶች፣ ከ240 በላይ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል
ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ከተሰማ በኋላ በኦሮሚያ ክልል ከ1 ሺህ በላይ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱ ተነገረ።
ከሃጫሉ ግድያ በኋላ በተከሰተ ሁከት ከፍተኛ የንብረት ውድመት ከተከሰተባቸው ስፍራዎች መካከል ሻሸመኔ ከተማ አንዷ ነች የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ አንደተናገሩት፤ መንግሥት በመኖሪያ ቤቶች፣ በንግድ ቤቶች እና በመንግሥት ተቋማት ላይ የደረሱትን ጉዳቶች፤ "የተቃጠሉ፣ የተሰባበሩ እና የተዘረፉ" በሚሉ ጎራዎች ከፋፍለው የደረሰውን የጉዳት እያጠኑ መሆኑን አስረድተዋል። ቃል አቀባዩ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋገት በቤቶች ላይ የደረሰው ጉዳት የሚከተለው ነው። በመኖሪያ እና በንግድ ቤቶች ላይ የደረሰ ጉዳት የአርቲስቱ ግድያ ከተሰማ በኋላ በአሮሚያ ክልል፤ 523 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። 499 መኖሪያ ቤቶች ደግሞ እንደተሰባበሩ የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው በንግድ ቤቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት በአሃዝ ሲያስቀምጡ፤ 195 ሆቴሎች መቃጠላቸውን እና ሌሎች 32 ሆቴሎች ደግሞ በንብረት ላይ የመሰባበር ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም 104 የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቃጠሎ ውድመት እንደደረሰባቸው አመልክተዋል። ስድስት አነስተኛ እና ግዙፍ ፋብሪካዎች በሁከቱ መቃጠላቸውን የተናገሩት አቶ ጌታቸው፤ የተቃጠሉ አነስተኛ ንግድ ቤቶች ቁጥር ድግሞ 232 እንዲሁም የተሰባበሩት አስተኛ ንግድ ቤቶች አሃዝ 219 መሆኑን አስረድተዋል። ከሃጫሉ ግድያ በኋላ በተከሰተ ሁከት ከፍተኛ የንብረት ውድመት ከተከሰተባቸው ስፍራዎች መካከል ሻሸመኔ ከተማ አንዷ ነች በተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የክልሉ ቃል አቀባይ እንደሚሉት ከሆነ 232 የግል እንዲሁም 12 የመንግሥት ተሸከርካሪዎች በእሳት እንዲጋዩ ተደርገዋል። በአጠቃላይ በግል እና በመንግሥት ቤቶች እንዲሁም ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል። ዘረፋን በተመለከተ ግን የተሰባሰቡ ማስረጃዎች ተጠናቅረው ስላላለቁ ዝርፊያ የተፈጸመበትን የንብረት መጠን ማወቅ ለጊዜው አዳጋች እንደሆነ ተናግረዋል። 'ጉዳቱ የደረሰው በሁሉም ላይ ነው' በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰው በምዕራብ አርሲ ሦስት ወራዳዎች ውስጥ መሆኑን የተናገሩት አቶ ጌታቸው፤ በተለይ በሻሸመኔ እና ባቱ ከተሞች እንዲሁም በባሌ ዞን ሮቤ እና አጋርፋ ከተሞች የደረሰው ገዳት ከሌሎች አካባቢዎች አንጻር ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል። አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ ህይወታቸውን ያጡት፣ ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው ሰዎች የአንድ ብሔር ወይም ሐይማኖት ተከታይ አይደሉም ብለዋል። "በአንደ ብሔር እና ሐይማኖት ላይ ብቻ ያነጣጠረ አልነበረም። ሁሉም ብሔር እና የሐይማኖት ተከታዮች ጉዳት ደርሶባቸዋል" ሲሉ አቶ ጌታቸው ተናግረዋል። መልሶ ማቋቋም ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎባቸው ባዶ እጃቸውን ቀርተው የእምነት ተቋማትን ጨምሮ በተለያዩ ስፍራዎች ተጠልለው የሚገኙ ዜጎች ቁጥር በርካታ መሆኑን አቶ ጌታቸው ገልጸው፤ በተፈጸመው ውድመት ንብረታቸው ወድሞባቸው የመንግሥት እርዳታን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሺህ በላይ እንደሚሆን አመልክተዋል። ንብረታቸው የወደመባቸው ሰዎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። "የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ በያሉበት እንዲደርሳቸው እየተደረገ ነው" ሲሉ አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ቁጥር ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በተፈጠረው አለመረጋጋት በኦሮሚያ ክልል በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች ቁጥር 7123 መድረሱን አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክልሉ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ጨምረውም በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሰዎች ጋር በተያያዘ ፖሊስ አና አቃቢ ሕግ ከ5 ሺህ በላይ በሚሆኑ መዝገቦች ተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ መመስረታቸውንም አመልክተዋል። አቶ ጌታቸው "መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ጠንክሮ እየሰራ ነው" ካሉ በኋላ፤ "በጸጥታ ኃይሎች የተያዙ ሰዎችም በቁጥጥር ከዋሉበት በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የማቅረብ ሥራ እየተሰራ" መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚህ ባሻገር ከሁከቱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙና በተባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፍርድ ቤት አልቀረቡም ስለሚባሉ ሰዎች በተመለከተ "እስካሁን ተይዘው ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ሰዎች ስለመኖራቸው መረጃው የለኝም" ብለዋል።
news-50172417
https://www.bbc.com/amharic/news-50172417
አረቄ ከእንቁላል እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር ቀላቅሎ በመጠጣት ታዋቂ የሆነው ቻይናዊ
ቢራ፣ ፔፕሲ፣ እሳት የሚነድበት ስፕራይት እና ጥሬ እንቁላል ቀላቅለው ቢጠጡ ምን ይሆናሉ?
ሊዩ ሺቻዎ ከላይ የተጠቀሰውን ቅይጥ ጭልጥ አድርጎ ሲጠጣ ራሱን ይቀርፅና ተንቀሳቃሽ ምስሉን ማሕበራዊ ድር-አምባ ላይ ያሠራጨዋል። ይህን ቪዲዮ ትዊተር ላይ ብቻ 12 ሚሊዮን ሰዎች ተመልክተውታል። ታድያ ሊዩ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ሌላ ጊዜ ደግሞ እንዲሁ በከንፈሮቹ መሃል አንድ ትንባሆ እንደያዘ ስድስት መለኪያ ኮረንቲ የሚያስንቅ መጠጥ ሲጨልጥ የሚታይበትን ቪዲዮ 800 ሺህ ሰዎች አይተውለታል። ደግሞ በሌላ ቪድዮ ቮድካ፣ ዊስኪ፣ ቀይ ወይን እና ቢራ እንዲሁም መገለጫው የሆነውን ጥሬ እንቁላል ቀላቅሎ እንደ ቀዝቃዛ በጉሩሮው ሲያወርድ ይታያል። ይህን ምስል ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች አይተውታል። ለመሆኑ ሊዩ ሺቻዎ ማነው? ሰውነቱስ እንዴት ነው ይህን ሁሉ አረቄያዊ መጠጥ እየዋጠ ዝም የሚለው? የሊዩን ጠባይ ተመልክቶ ቻይናውያን የአረቄ ሱሰኞች ናቸው ማለት ይቻላል? እንዴት ሲል ጀመረው? ሊዩ የመጀመሪያ ሙከራው ሰባት ጠርሙስ ቢራ በ50 ሰከንድ መጨለጥ ነበር። አደረገው። የዛሬ ሶስት ዓመት። «የሆነ ቀን ሰዎች ቢራ ሲጠጡ አየሁና እኔስ ምን ይሳነኛል ብዬ ተነሳሁ» ይላል ለቢቢሲ ቻይና ክፍል ቃሉን ሲሰጥ። ከዚያም እራሱን በራሱ እየቀረፀ ቻይናውያን ቪድዮ የሚጋሩበት አምባ ላይ ይለጥፈዋል። ኩዋይሹ የተሰኘው ማሕበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚዎች ከአንድ ደቂቃ በላይ የሆነ ቪዲዮ እንዲለቁ አይፈቅድም። ይህ ለሊዩ ፈተናም ዕድልም ነበር። ሰባት መለኪያም ጠጣ ሰባት ቡትሌ ከአንድ ደቂቃ በታች ማጠናቀቅ አለበት። ሊዩ፤ ኩዋይሹ ላይ 470 ሺህ ተከታዮች ነበሩት። በወርም 10 ሺህ ዩዋን [1400 ዶላር] ያገኝ ነበር። ኋላ ላይ ግን ድርጅቱ ሊዩ የሚለጥፋቸው ቪዲዮች ጤናን ከግምት ውስጥ ያስገቡ አይደሉም በማለት ገፁን ዘጋበት። ነገር ግን የሊዩ ቪዲዮ ሾልኮ ወጥቶ ትዊተር ላይ ደረሰ። ሊዩም ከቻይና ውጭ ታዋቀቂነት አገኘ። «ሰዎች ትዊተር ላይ እኮ ታዋቂ ሆነሃል እያሉ ይነግሩኛል፤ እኔ ግን ትዊተር ምንድነው? ስል እጠይቃቸዋለሁ።» «ሚስቴ ትናደዳለች» ቤይጂንግ አቅራቢያ ካለች መንደር የሚኖረው የ33 ዓመቱ ሊዩ ስለ ማሕበራዊ ድር አምባዎች የሚያውቀው ነገር አልነበረም። «እኔ የገጠር ሰው ነኝ። እንዴት አድርጌስ ላውቅ እችላለሁ» ይላል። ትዊተር እና መሰል ድር አምባዎች ቻይና ውስጥ የተከለከሉ ናቸው። ቪዲዮቹ የሚጫኑለት ውጭ ሃገር ባለ ሰው ነው። በስድስት ወራት ብቻ 60 ሺህ ተከታዮች ማፍራት ችሏል። «ውጭ ሃገር ያሉ አድናቂዎቹ በጣም ደጋግ ናቸው። ባለፈው አንኳ አንድ ቱርካዊ አድራሻዬን ፈልገ የቱርክ ቢራ ላከልኝ።» ሊዩ አሁንም በቪዲዮዎቹ አማካይነት ገንዘብ ያገኛል። የትዊተር ገፁ 'ፔይ ፓል' ከተሰኘ የበይነ መረብ ገንዘብ መላላኪያ ጋር የተገናኘ ነው። ነገር ግን ሕይወቱን የሚመራው ከትዊተር በሚያገኘው ገቢ ብቻ አይደለም፤ ስጋ በመሸጥ እንጂ። «ብዙዎቹ አድናቂዎቼ ወንዶች ናቸው። ምናልባት እነሱም መጠጣት ይወዱ ይሆናል። ይቀኑበኝም ይሆናል። ሚስቴ ግን ትናደዳለች። ለጤናዬ በመስጋት ነው። አንዳንዴ እንጨቃጨቃለን።» ሊዩ እኔ የአልኮል ሱሰኛ አይደለሁም ይላል። «እንደ ሰሜና ቻይናውያን ብቻዬን ቁጭ ብዬ ኮረንቲ ስጎነጭ አልገኝም።» ሊዩ ጤናው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰበት ይናገራል። ቪዲዮዎቹን ሲለጥፍም ከማስጠንቀቂያ ጋር ነው። በተለይ ታዳጊዎች እንዳይሞክሩት ይመክራል። የሎንዶኗ ዶክተር ሳራ ካያት ግን ምን ቢሆን አልኮል አልኮል ነው ይላሉ። አሁን ምን ዓይነት ጉዳት ላይመጣ ይችላል። ቆይቶ ግን መዘዝ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። አልፎም አልኮል ሲበዛ የአእምሮ መቃወስ ሊያመጣ እንደሚችል ያሰስባሉ። • የሰከረው ጃፓናዊ አብራሪ የ10 ወራት እስር ተበየነበት የዓለም ጤና ድርጅት ቻይናውያን ወንዶች በጣም ጠጪዎች ናቸው ሲል በመረጃ አስደግፎ የሁኔታውን አሳሳቢነት ይፋ አድርጓል። 36 በመቶ ወንድ ቻይናውያን አንድ ጊዜ የብርሌ አንገት ካነቁ አይነሱም ይላል መረጃው። ለጊዜው ሊዩ የሚለጥፋቸው አዳዲስ ቪዲዮዎች ሳይሆኑ የቀደሙትን ነው። ለመጨረሻ ጊዜ በለጠፈው ምስል ላይ እንዲህ ሲል ለአድናቂዎቹ መልዕክት አስተላልፏል። «እኔ አንድ የገጠር መንደር የምኖር ቻይናዊ ነኝ። ስለተዋወቅን ደስ ብሎኛል። እወዳችኋለሁ» ወረድ ብሎ ያለውን ቪዲዮ ሲጫኑት ሊዩ ቢራ፣ የሩዝ ወይን፣ ስፕራይት፣ ሬድ ቡል እና የማትለየውን ጥሬ እንቁላል ቀላቅሎ ሲጨልጥ ይታያል። በስምንት ሰከንድ ውስጥ።
54701702
https://www.bbc.com/amharic/54701702
የቤልጂየም ሀኪሞች በኮሮናቫይረስ ቢያዙም ሥራ እንዲቀጥሉ ተነገራቸው
የቤልጂየም ሀኪሞች በኮሮናቫይረስ ቢያዙም ሥራ እንዲቀጥሉ ተነገራቸው። በወረርሽኙ ተይዘው ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ ነው ይህ ውሳኔ የተላለፈው።
ሊዮግ በተባለ ከተማ አንድ አራተኛው የህክምና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል። 10 ሆስፒታሎች ሀኪሞች በቫይረሱ ቢያዙም የበሽታው ምልክት ካልታየባቸው ሥራ እንዳያቋርጡ ወስነዋል። የቤልጂየም ሀኪሞች ማኅበር ኃላፊ ዶ/ር ፊሊፔ ዴቮስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሆስፒታሎች በቀናት ውስጥ አገልግሎት መስጠት ሊያቆሙ ስለሚችሉ የህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ ቢያዙም ሥራ ከመቀጠል ውጪ አማራጭ የላቸውም። ሀኪሞች በሽታውን ወደ ታካሚዎች የሚያስተላልፉበት እድል ሊኖር እንደሚችል ግን ሳይጠቅሱ አላለፉም። በምሥራቅ ቤልጂየም በሚገኘው ከተማ ከሦስት ሰዎች አንድ ሰው ላይ ቫይረሱ ይገኛል። ታማሚዎች ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች እየተዘዋወሩ ሲሆን፤ አጣዳፊ ያልሆነ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ደግሞ ቀጠሯቸው ወደ ሌላ ጊዜ ተዘዋውሯል። የጤና ሚንስትሩ ፍራንክ ቫንደንብሮክ አገሪቱ በወረርሽኙ ክፉኛ ልትጎዳ እንደምትችል እና ከዚህ በኋላ ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። የዓለም ጤና ድርጅት አመራሮች እንዳሉት፤ በአህጉሪቱ የጉዞና ከቤት ያለመውጣት ገደብ ሊያስፈልግ ይችላል። የድርጅቱ የድንገተኛ ጊዜ ኃላፊ ዶ/ር ማይክ ራየን "አሁን ላይ አውሮፓ ውስጥ ቫይረሱን ለመቆጣጠር እርምጃዎችን ማጥበቅ ያስፈልጋል" ብለዋል። መጋቢት ላይ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጎዳችው ጣልያን ቴአትር ቤቶች፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያ እና መዋኛ ስፍራዎችን ዘግታለች። ሬስቶራንቶች እና ካፌዎች ከ12 ሰዓት በኋላ የመስተንግዶ አገልግሎት መስጠት አይችሉም። እስከ ጥቅምት 24 በሚቆየው መመሪያ መሠረት፤ 75% የሁለተኛ ደረጃ እና ዩኒቨርስቲ ትምህርቶች በድረ ገጽ ይሰጣሉ። በተጨማሪም ዜጎች እጅግ አስፈላጊ ካልሆነ ከከተማ ከተማ እንዳይዘዋወሩ ተነግሯቸዋል። በእርግጥ ይህን አዲስ መመርያ በመቃወም በኔፓልስ፣ ቱሪን እና ሮም ከተሞች ሰልፍ ተካሂዷል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያ የተዘጋው በጣልያን ብቻ ሳይሆን በቤልጄም መዲና ብራሰልስ ጭምርም ነው። መደብሮች ከምሽቱ 2 ሰዓት እንዲዘጉ መመሪያ ተላልፏል። ሰው በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ ነው። ዩኬ ውስጥ በወረርሽኙ ሳቢያ ከ16 እስከ 25 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች ሥራቸውን የማጣት እድላቸው ከጎልማሶች በእጥፍ የበለጠ ሆኗል። በሌላ በኩል ፈረንሳይ ውስጥ በየቀኑ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ደ100,000 ደርሰዋል። ይህም የበሽታውን ምልክት የማያሳዩና ህክምና ያልተሰጣቸውን ሰዎች እንደሚያካትት የአገሪቱ የሳይንስ ካውንስል ኃላፊ ፕ/ር ጀን ፍራንኮስ ደልፍረሲ ተናግረዋል። ሌላዋ የአውሮፓ አገር ቼክ ሪፐብሊክ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥላለች። ለህክምና ወይም ለሌላ አንገብጋቢ ጉዳይ ካልሆነ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 11 ሰዓት ድረስ ከቤት መውጣት አይቻልም። መደብሮች ከ2 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት የሚያቆሙ ሲሆን፤ ዘወትር እሑድ ይዘጋሉ። ሌላ በኩል ስፔን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጋለች። የሰዓት እላፊ ገደብም ተጥሏል። ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እንዳሉት ሰዓት እላፊው ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋት ይቆያል። የተለያዩ ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ጉዞ የማገድ ሥልጣንም ተሰጥቷቸዋል። ሩስያ ውስጥ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር 17,347 መድረሱ ተገልጿል። አጠቃላይ በሽታው የተገኘባቸው ሰዎች 1.5 ሚሊዮን ደርሰዋል።
news-56192194
https://www.bbc.com/amharic/news-56192194
የቻይና የኤሌክትሪክ መኪኖች ከቴስላ በሽያጭ መብለጣቸው ተነገረ
የቻይና በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ መኪኖች በገበያው ላይ ተፈላጊ የሆኑትን የቴስላ መኪናዎችን ሽያጭ መብለጣቸው ተነገረ።
መኪኖቹ ረከስ ያሉ ሲሆን ዋጋቸውም 4 ሺህ 500 ዶላር ወይም በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ወደ 180 ሺህ ይሆናል። የሆንግ ሁዋንግ ሚኒ ኢቪ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው እነዚህ መኪኖች ሽያጭ መመንደግ፤ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ላለውና ከፍተኛ የመኪና አምራች ኩባንያው ሳይክ ሞተር ስኬት አስመዝግቦለታል። መኪኖቹ እየተመረቱ ያሉት ከሳይክ ሞተርስ በተጨማሪ ሌላኛው አጋር ድርጅትና የአሜሪካው ትልቁ የመኪና አምራች ጄኔራል ሞተርስ ጋር በጥምረት ነው። በባለፈው ወር እነዚህ የኤሌክትሪክ መኪኖች የቴስላን ሽያጭ እጥፍ ያስመዘገቡ ሲሆን በደህንነታቸው ጉዳይ ላይም አንዳንድ ጥያቄዎች መነሳታቸው አልቀረም። ሆንግ ጉዋንግ ሚኒ የሚል ስያሜ የተሰጠው የሳይክ የኤሌክትሪክ መኪና ታዋቂውና በዋጋው ረከስ ያለው ሞዴል ሲሆን በቅርቡም ኩባንያው ኤይር ኮንዲሽነር በመግጠም 5 ሺህ ዶላር የሚሸጡ መኪኖችን አስተዋውቋል። መኪኖቹም ማንኛውም ነዋሪ ለትራንስፖርት በየቀኑ ሊገለገልባቸውና ምቹ የሆኑ በሚል ነው እየተዋወቁ ያሉት። የመኪና ባለሙያዎች እነዚህ ምርቶች ከቴስላ ጋር ሲነፃፀሩ በባትሪያቸው፣ በአቅማቸው ደከም ያሉ ቢሆኑም ዋጋቸው ርካሽ በመሆኑና ምቹ በመሆናቸው በሽያጭ ደረጃ የቁንጮነቱን ስፍራ መቆናጠጥ ችለዋል። በባለፈው አመት ለገበያ የበቁት እነዚህ መኪኖች በአማካኝ 100 ኪሎ ሜትር በሰዓት ፍጥነት ያላቸው ሲሆኑ መያዝ የሚችሉትም ተጠጋግቶ አራት ሰው ብቻ ነው። "የቻይና መንግሥት የአየር ብክለትን ለመቀነስ ቁርጠኝነት ያለው ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በአለም ላይ የሳይንስና ፈጠራን በመጠቀም የተሰሩ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በማስተዋወቅ የቀዳሚነቱን ስፍራ መያዝ ይፈልጋል" በማለት የቻይና የገበያዎች የምርምር ቡድን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሻውን ሬይን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሆንግ ሁዋንግ ሚኒ ኢቪን ለማስተዋወቅ የቻይና መንግሥት የመኪና ሰሌዳ ቁጥር በነፃ እየሰጠ ሲሆን ዋስትና አለውም ብሏል። በተለያዩ ከተሞች በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን የሰሌዳ ቁጥር ለማግኘት ወራት እንዲሁም አመታት ይፈጃል ተብሏል።
news-52217128
https://www.bbc.com/amharic/news-52217128
የቢል ክሊንተንና የሞኒካ ሊዊንስኪን ቅሌት ያጋለጠችው ሴት ሞተች
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተንን በስልጣን ላይ እያሉ ከተከሰሱ ጥቂት የአገሪቱ መሪዎች መካከል እንዲገቡ ያደረገቻቸው ግለሰብ አረፈች።
ሊንዳ ትሪፕ በ90ዎቹ መጨረሻ የፕሬዝዳንት ክሊንተን ከትዳራቸው ውጭ ከዋይት ሐውስ አንዲት ሠራተኛ ጋር የድብቅ ፍቅር መጀመራቸውንና አንሶላ መጋፈፋቸውን ከጓደኛዋ ሞኒካ ሰምታ ክሊንተን እንዲከሰሱ መረጃ ያቀበለችው ሴት በ70 ዓመቷ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው። ሴትየዋን ለሞት ያበቃት ኮሮናቫይረስ ሳይሆን የጣፊያ ካንሰር ነው ተብሏል። ሊንዳ ትሪፕ ከሞኒካ ሊዊኒስኪ ጋር የእድሜ አቻ ባትሆንም የቅርብ ወዳጇ ነበረች። ያን ጊዜ እሷ በፔንታገን የመንግሥት ሠራተኛ የነበረች ሲሆን ሞኒካ ከክሊንተን ጋር ግንኙነት መጀመሯን ከነገረቻት በኋላ አብዛኛውን ንግግሯን በድብቅ በድምጽ ስትቀዳ ቆይታለች። የቀዳቻቸውን ድምጾች ለመርማሪዎች አሳልፋ በመስጠቷ ክሊንተር ፕሬዝዳንትነታቸው ሊያጡ የደረሱበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር። ሚስ ሊንዳ ትሪፕ የቢል ክሊንተር የወንድ ፈሳሽ በሞኒካ ሊዊንስኪ ሰማያዊ ቀሚስ ላይ መታየቱን ሁሉ በመጥቀስ ቢል ክሊንተን ከትዳራቸው ውጭ ስለመማገጣቸው በማያሻማ ሁኔታ መረጃ ይዛ ነበር። ሊንዳ የያኔዋን ጓደኛዋን የሞኒካ ሊዊንስኪን ምስጢር አሳልፋ በመስጠቷ አንዳንዶች ቢያወግዟትም እሷ ግን በአርበኝነት ለአገሬ ያደረኩት ነገር ነው ስትል ቆይታለች። ክሊንተር ክሳቸውን ሴኔት ካቋረጠው በኋላ ሊንዳ ከፔንታገን ተባረረች፤ ከዚያም በቨርጂኒያ ከባሏ ጋር አንዲት ሱቅ ከፍታ ትኖር ነበር። ሊንዳ ከመሞቷ በፊት ሞኒካ ሊዊንስኪ በትዊተር ሰሌዳዋ፤ "ምንም እንኳ ያለፈው ታሪካችን መልካም ባይሆንም ለወ/ሮ ሊንዳ ጤንነት እመኛለሁ" ብላ ነበር። በ1998 በሴኔት ፊት ቀርባ ምስክርነት የሰጠችው ሞኒካ ሊዊንስኪ የምስክርነት ቃሏን ስታሳርግ "ስለሆነው ነገር አዝናለሁ፤ ጓደኛዬ የነበረችው ሊንዳ ግን እጅግ እስጠሊታ ሴት ናት" ብላ ነበር።
news-47731663
https://www.bbc.com/amharic/news-47731663
ፌስቡክ የነጭ ብሔረተኝነትናና የተገንጣይ አመለካከት አራማጆችን ሊያግድ ነው
ፌስቡክ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ "የነጮችን ብሔርተኝነትና መለየትን የሚያሞግሱና የሚደግፉ" ፅሁፎችን ከፌስቡክና ከኢንስተገራም ገፆች ላይ እንደሚያግድ አሳወቀ።
የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ ትልቁ የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ የሽብርተኝነት ይዘት ያላቸውን ይዘቶች ከድህረገፁ ላይ ለመለየትና ለማስወገድ እንደሚሰራም ቃል ገብቷል። ቁጣን የሚቀሰቅሱ አባባሎችን የሚፈልጉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ወደ የሚከላከሉ የበጎ አድራጎት ገጾች በመምራት ድግፍ እንዲያገኙ ያደርጋል። • ፌስቡክ የምንጠቀምበት ሰዓት ሊገደብ ነው በኒውዚላንድ የሁለት መስኪዶች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች በቀጥታ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከተላለፈ በኋላ የማህበራዊ ሚዲያዎች ጫና በዝቶባቸዋል። ፌስቡክ ከዚህ በፊት የነጮችን ብሔርተኝነት የሚያሳዩ ይዘቶችን እንደ ዘረኝነት ስለማይቆጥራቸው በገፁ ላይ እንዲገኙ ፈቅዶ ነበር። "የአሜሪካ አክራሪ የነጮች ቡድንና በስፔን ያለው የባስክ ተገጣይ ቡድኖች አስፈላጊ የሰዎች ማንነት ክፍል እንደመሆኑት ሁሉ" የነጭ ብሔርተኝነትም ተቀባይነት ያለው እንደሆነ ይቀበል ነበር። ነገር ግን ረቡዕ እለት ገፁ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ ፌስቡክ ለሦስት ወራት "ከህብረተሰብ አካላትና ምሁራን" ጋር ምክክር ካደረገ በኋላ የነጮችን ብሔርተኝነት ከነጮች የበላይነትና ከሌሎች የተደራጁ የጥላቻ ቡድኖች "መለየት" አይቻልም ብሏል። 'የለቀቀው ሰው ብቻ አይደለም ተጠያቂ' በኒውዚላንድ የተደረገውን ጥቃት ተከትሎ ብዙ መሪዎች የማህበራዊ ሚዲያዎች በገፆቻቸው ላይ ለሚለጠፏቸው ፅንፈኛ ይዘቶችን ሃላፊነት እንዲወስዱ አስጠንቅቀዋል። የኒውዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ስለማህበራዊ ሚዲያዎች ስትናገር "መልዕክቱን የለቀቀው ሰው ብቻ ሳይሆን አሳታሚዎቹም" እንደዚህ አይነት ይዘቶች ሲለቀቁ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል። • የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የይለፍ ቃል ደህንነት አስተማማኝ አይደለም ተባለ 50 ሰዎችን የገደለው የኒውዚላንዱ ጥቃት ምስል ከማህበራዊ መድረኩ ላይ ከመውረዱ በፊት ከ4 ሺህ ጊዜ በላይ እንደታየ ፌስቡክ አስታውቋል። ድርጅቱ በ24 ሰዓት ውስጥ የምስሉ 1.2 ሚሊዮን ቅጂዎችን ከመለቀቅ የከለከለ ሲሆን 300 ሺህ የሚሆኑትን ደግሞ ከድረ ገፁ ላይ አጥፍቷል። የፈረንሳይ ሙስሊሞችን የሚወክል አንድ ቡድን ፌስቡክና ዩትዩብ ምስሉን በገፃቸው ስላስተላለፉ ከሷቸዋል። ፌስቡክ ላይ ያለን ግላዊ መረጃን እንዴት መጠበቅ ይቻላል?
news-53590831
https://www.bbc.com/amharic/news-53590831
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትርፉ መጨመሩን ሳምሰንግ አስታወቀ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት የወጡት መመሪያዎችን ተከትሎ ሚሊዮኖች ከቤት ሆነው ስራቸውን ማከናወን እንዲሁም በርቀት ለመማር ተገደዋል።
ይህም ሁኔታ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች አምራች ለሆነው ሳምሰንግ ትርፉ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል። በአለም ግዙፉ ዘመናዊ የተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች የሆነው ሳምሰንግ ከባለፈው አመት ጋር ሲወዳዳር 23 በመቶ የትርፍ ጭማሬ ማግኘቱን አስታውቋል። በተለይም የኮምፒውተር መቀያየሪያ ምርቶች በተለይም የኮምፒውተር መረጃዎች የማስቀመጫ ቋት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር በአለም አቀፉ ገበያም ዘንድ ዋጋውን አንሮታል። የደቡበ ኮሪያ ኩባንያ ሳምሰንግ እንዳሳወቀው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተማሪዎችና ሰራተኞች ከቤት በመስራታቸው የሚሰሩባቸውን መረጃዎችን የሚያስቀምጡበት የኮምፒውተር መተግበሪያዎች ፍላጎት አሻቅቧል። በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ ያለው ፍላጎት ይህን ያህል አልጨመረም ተብሏል። ሌሎች ኩባንያዎች እንዲሁ የኮምፒውተር መረጃ ቋት (ሜሞሪ ቺፕ) የሚያመርቱ የኮሪያው ኤስኬ ሂኒክስና የአሜሪካው ማይክሮን ቴክኖሎጂም ሰዎች በቤታቸው በመገደባቸውና ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚያደርጓቸው ስብሰባዎችና ፊልሞች መመልከት እንደተጠቀሙና ትርፋቸው እንደጨመረ ከሰሞኑ አስታውቀዋል። አዳዲስ የጋላክሲ ኖትና ታጣፊ የጋላክሲ ዚ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ለማስተዋወቅ በዝግጅት ላይ ያለው ሳምሰንግ በመጪው ወራት የስልክ ሽያጮች እንደሚያንሰራራም ግምቱን አስቀምጧል። ምንም እንኳን በገበያው ያለው ውድድር የጠነከረ ቢሆንም ሳምሰንግ ይህንን ሰብሮ መውጣት እንደሚችል ያምናል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት አዳዲስ የቴክኖሎጂ ተንቀሳቃሽ ስልክ ፍላጎት ቢቀንስም ኩባንያዎች አዳዳዲስ ምርቶቻቸውን እያስተዋወቁ ነው። በሚያዝያ ወር አፕል አይፎን ኤስ ኢ የተባለ አዲስ ምርት ሲያስተዋውቅ ከሳምነት በፊትም የቻይናው ኩባንያ ዋን ፐላስ አዲስ ምርት አውጥቷል። ሁዋዌ ፒ40 አዲስ ስልኩን ወደ ገበያ አውጥቷል። በዚህ አመትም አይፎን 12ና ጉግል ፒክስል 5ና 4ኤ አዳዲስ ምርቶች ለገበያ እንዲወጡ እቅድ ተይዟል።
news-54098154
https://www.bbc.com/amharic/news-54098154
ኮሮናቫይረስ፡ በካናዳ አንዲት ጨቅላ ሕጻን ጭምብል ባለማጥለቋ በረራ ተሰረዘ
ነገሩ አስገራሚ ነው፡፡ በካናዳ አንዲት ጨቅላ ሕጻን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረጓ ብቻ ፖሊስ ተጠርቷል፣ በረራውም ተሰርዟል፡፡
ሕጻኗ ከተወለደች ገና 19 ወሯ ነው፡፡ ዌስት ጄት ደግሞ ሁሉም ተሳፋሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማጥለቅ እንዳለባቸው ያሳስባል፡፡ ጨቅላዋ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሲደረግላት እሪታዋን ታቀልጠዋለች፡፡ ብትባል ብትሰራ እምቢኝ ትላለች፡፡ እናትና አባት ያልሞከሩት ነገር የለም፡፡ ሕጻኗ ሞቼ እገኛለሁ አለች፡፡ የአየር መንገዱ አስተናጋጆችና ቤተሰብ አንድ ሁለት ሲባባሉ ነገሩ ተካሮ በረራ እስከመሰረዝ ደርሷል፡፡ አየር መንገዱ ግን ታሪኩ ሌላ ነው ይላል፡፡ የ19 ወር ጨቅላዋ አይደለችም ችግር የፈጠረችብኝ ብሏል ዌስትጄት፡፡ እንዲያውም በሷ ደረጃ ያሉ ሕጻናት ጭምብል እንዲያጠልቁም አይገደዱም ብሏል፡፡ ታዲያ ለምን በረራውን ሰረዛችሁ ሲባል ሌላ የጨቅላዋ ታላቅ እህት አለች፤ 3 ዓመቷ ነው፡፡ እሷ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አጥልቂ ስትባል እምቢ በማለቷ ነው በረራውን እንድንሰርዝ የተገደድነው ብሏል፣ ዌስትጄት፡፡ የሕጻናቱ እናትና አባት፣ እንዲሁም ተሳፋሪዎች ግን" ዌስትጄት ቀጣፊ ነው፣ ዋሽቷል፤ የ3 ዓመቷ ልጅ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነበር ሲሉ "ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ግርግር በሞባይል የተቀረጸ ቪዲዮም የ3 ዓመቷ ልጅ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነው የምትታየው፡፡ ፖሊስም በበኩሉ እኔ ስደርስ ታላቅየው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነበር ብሏል፡፡ ይህ የሆነው ማክሰኞ ነው፤ ከትናንት በስቲያ፡፡ በረራው ከካልጋሪ ተነስቶ ቶሮንቶ የሚደርስ ነበር፡፡ በረራ 652 ግን ከመነሻው ሳይሳካ ቀርቶ ሁሉም ተሳፋሪዎች ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደርገዋል፡፡ የልጆቹ አባት አቶ ኮድሀሪ እንዲህ ዓይነት ጉድ በፍጹም ያጋጥመኛል ብዬ በሕልሜም በእውኔም አስቤም ጠብቄም አላውቅም ብሏል ለቢቢሲ፡፡ ‹‹እኔና ባለቤቴ ከሁለቱ ሴት ልጆቻችን ጋር ነበርን፤ አውሮፕላኑ ሊነሳ ሲል የሦስት ዓመቷ ልጄ ቁርስ ቢጤ እየበላች ነበር፡፡ የበረራ አስተናጋጇ መጥታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንድታጠልቅ ነገረቻት፡፡ እኔና እናቷ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገናል፤ የ3 ዓመቷ ልጃችን ደግሞ እየበላች ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹የበረራ አስተናጋጇ ዌስትጄት በአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጉዳይ ጥብቅ ፖሊሲ እንደሚከተልና ልጃቸው ቁርሱ መብላቷን ትታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ካላጠለቀች በረራው እንደማይደረግ ነገረችን›› ይላል አባት፡፡ ‹‹ልጆች ደግሞ በአንድ ጊዜ መታዘዝ እሺ ስለማይሉ ማባበል ጀመርኩ፡፡ የ3 ዓመቷ ልጄ ትንሽ ካስቸገረችን በኋላ እሺ ብላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዋን አጠለቀች፡፡›› ‹‹ታናሽየው ግን እምቢኝ አለች፤ እንዲያውም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛውን ስናደርግላት ወደላይ አላት›› ይላል አባት፡፡ ‹‹ዌስትጄት ትእግስት አልፈጠረባቸውም፡፡ ትንሽዋ ልጄ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ስላላጠለቀች አውሮፕላኑ እንደማይበር ነገሩን፡፡›› እንዲያውም ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ እንደታዘዙና አንወርድም ካሉ ግን እንደሚታሰሩ እንደተነገራቸው ለቢቢሲ አስታውቋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከአውሮፕላኑ ለመውረድ ተስማማን ብሏል አባት ለቢቢሲ፡፡ አባት በረራው ከተሰረዘ በኋላ ተረዳሁ እንደሚለው ከሆነ ‹‹በካናዳ ትራንስፖርት ፖሊሲ መሰረት የ19 ወሯ ጨቅላ ልጃቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማጥለቅ አትገደድም ነበር፡፡›› ዌስትጄት ባወጣው መግለጫ ግን በረራው የተሰረዘው የ19 ወሯ ጨቅላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ስላላጠለቀች ሳይሆን የሷ ታላቅ የ3 ዓመቷ ህጻን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ነው ብሏል፡፡
news-55156386
https://www.bbc.com/amharic/news-55156386
ቅርጫት ኳስ ፡ የኦባማ እና የጆርዳን የቅርጫት ኳስ መለያዎች በከፍተኛ ገንዘብ በጨረታ ተሸጡ
በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማና በታዋቂው የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ኮከብ ማይክል ጆርዳን የተለበሱ ሁለት የቅርጫት ኳስ መለያዎች አርብ ዕለት ሎስ አንጀለስ ከተማ ውስጥ በተካሄደ ጨረታ ክብረ ወሰን ነው በተባለ ከፍተኛ ገንዘብ ተሸጡ።
በከፍተኛ ገንዘብ የተሸጡት የማይክል ጆርዳንና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ መለያዎች ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ማይክል ጆርዳን በ1984 (እአአ) ለቺካጎ ቡልስ ቡድን ለመጫወት በፈረመበት ጊዜ የለበሰው ባለ 23 ቁጥር መለያ ለጨረታ ቀርቦ 320 ሺህ ዶላር ተሽጧል። ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ለትምህርት ቤታቸው ፑናሁ ቡድን በተጫወቱበት ጊዜ ለብሰውት የነበረው መለያ ደግሞ በ192 ሺህ ዶላር ሲሸጥ፤ ይህም በጨረታ ከተሸጡ የተማሪዎች መለያ ከፍተኛውን ዋጋ አውጥቷል። ባለፈው ዓመት በተካሄደ ጨረታ ኦባማ ተማሪ ሳሉ ለብሰውት የነበረ ሌላ የቅርጫት ኳስ መለያ በ120 ሺህ ዶላር ተሽጦ ነበር። በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠው የኦባማ መለያ የትምህርት ቤታቸው ቡድን በ1979 (እአአ) የሃዋይ የቅርጫት ኳስ ውድድርን ባሸነፈበት ጊዜ ለብሰውት የነበረው ባለ 23 ቁጥር መለያ ነው። የቀድሞው ፕሬዝደንት ለቅርጫት ኳስ ስፖርት ከፍተኛ ፍቅር ያላቸው ሲሆን፤ በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፋቸው ላይ የተፎካካሪ ቡድን አባላት ወላጆች ተገቢ ያልሆነ የበላይነትን እንዲያገኙ አድርገዋል በሚል ቅሬታ በማሰማታቸው ልጃቸው ሳሻ የምትጫወትበትን የቅርጫት ኳስ ቡድን ማሰልጠን እንደተዉ ጽፈዋል። የመጀመሪያው ቢሊየነር ስፖርተኛ የሆነው ኮከቡ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ጆርዳን ቡድኑ ቺካጎ ቡልስ በአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ውድድር የበላይ ሆኖ ስድስት ጊዜ አሸናፊ ለመሆን አስችሎታል። የጆርዳን መለያዎች በተለያዩ ጊዜያት በጨረታ የተሸጡ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ከተሸጡ 23 ቁጥር መለያዎች ከፍተኛው 288,000 ዶላር ነበር።
news-41480358
https://www.bbc.com/amharic/news-41480358
ፖሊስ የላስ ቬጋሱ ታጣቂ ጥቃቱን ለመፈፀም ምን እንዳነሳሳው እያጣራ ነው
ፖሊስ 59 ሰዎችን ለሞት፣ ከ500 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ለጉዳት የዳረገው ሰቴፈን ፓዶክ ጥቃቱን ለመፈፀም ምን እንዳነሳሳው እያጣራ ነው ።
ጥቃቱ እንዴት እንደተፈፀመ? የ64 ዓመት ታጣቂ ማንዳላይ ቤይ ከተሰኘ ሆቴል 32ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ በአቅራቢያው ይካሄድ በነበረና 22 ሺህ ሰዎች በታደሙበት የሙዚቃ ፌስቲቫል ተሳታፊዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ነው ጉዳቱን ያደረሰው። በነበረበት የሆቴል ክፍል ውስጥ ፖሊስ 23 የጦር መሳሪያዎችን ያገኘ ሲሆን ከ19 በላይ ደግሞ በመኖሪያ ቤቱ ተገኝቷል። ፖሊስ እንዳለው እሳካሁን ለጥቃቱ ግልፅ የሆነ ምክንያት አልተገኘም። ምንም እንኳ አይኤስ አይኤስ (ISIS) እያለ ራሱን የሚጠራው የሽብር ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ቢልም መርማሪዎች እሳካሁን ባለን መረጃ ጥቃቱ ከዓለም አቀፍ የሽብር ቡድን ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ብለዋል። ጥቂት መርማሪዎች ስቴፈን ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ውስጥ ነበር ይላሉ። ዶናልድ ትራምፕ ድርጊቱን ''እኩይ'' ሲሉ ኮንነውታል።
news-47480292
https://www.bbc.com/amharic/news-47480292
የሰው ፊት ማስታወስ የማትችለው ሴት
በአንድ ወቅት የከተማ አውቶብስ ውስጥ የማላውቃት ሴት እጇን አውለብልባ ሰላም አለችኝ። የማላውቃት ሴት እንዴት እነደዚህ ሰላም ልትለኝ ቻለች ብዬ አስቤ ነበር በወቅቱ ትላለች ቡ ጄምስ።
የኋላ ኋላ ግን ያቺ አውቶብስ ውስጥ ሰላም ያለቻት ሴት እናቷ ነበረች። እሷ እንደምትለው የሰዎችን የፊት ገጽታ ማስታወስ እንዳትችል የሚያደርጋት የጤና እክል አለባት። የቤተሰቦቿን፣ የጓደኞቿን፣ ይባስ ብሎ የእራሷንም መልክ ማስታወስ አትችልም። ሁሌም ቢሆን በመስታው አጠገብ ሆና ስትመለከት የምታየው ፊት ለእሷ አዲስ ነው። • አረጋውያንን በነጻ የሚያሳፍረው ባለታክሲ • የሴቶችና ወንዶች የኢኮኖሚ እኩልነት እንዴት ይስፈን? በዚህ የጤና እክል ምክንያት ከሌላ ዓለም የመጣችና ከሰዎች የተለየች እንደሆነች ታስብ እንደነበረ ቡ ትናገራለች። '' ማንም ሰው ሊያስበው ከሚችለው በላይ አስጨናቂና የስሜት መዋዠቅ የሚያስከትል ህመም ነው። በተቻለኝ መጠን ትክረት ላለመስጠት እሞክራለሁ፤ ግን ቀላል አይደለም።'' ''ቀኑን ሙሉ ከባድ ጊዜ ነው የማሳልፈው። በመንገድ ላይ የምመለከታቸው ሰዎች ሁሉ የሚያውቁኝ ይሆን፤ ሰላም ማለት ይኖርብኝ ይሆን እያልኩ እጨነቃለሁ። '' ብሏል። ምንም እንኳን ይህ የጤና እክል 'ፕሮሶፓግኖዚያ' የሚል ሳይንሳዊ ስያሜ ቢኖረውም እሷ ግን አብዛኛውን የእድሜዋን ክፍል እራሷን በመውቀስና የመርሳት ችግር እንዳለባት በማሰብ አሳልፋለች። "ብዙ ሰዎች ከእኔ ግዴለሽነትና ስንፍና የተነሳ መልካቸውን እንደምረሳ ያስባሉ። እኔም ቢሆን የራሴ ጥፋት እንደሆነ ነበር የማስበው።'' ትላለች። በእድሜዋ አርባዎቹ ውስጥ ከገባች በኋላ ነበር ቡ ስለ በሽታው የተዘጋጀ ጥንቅር በቴሌቪዥን የተመለከተችው። '' ልክ ዜናውን ስመለከት የተረዳሁት ነገር የሰዎችን መልክ የምረሳው ከእኔ ግዴለሽነት በመነጨ ሳይሆን አእምሮዬ ይህንን የማድረግ አቅም እንደሌለው ነው።'' ስል ልጅነቷ ስታስታውስ በጣም አስጋሪ እንደነበረ ትገልጻለች። ፊታቸውን የማታስታውሳቸው ህጻናት ጋር አንድ ክፍል ውስጥ መማርና ጓደኝነት መመስረት ምን ያክል ከባድ ሊሆን እንደሚችል ማንም ሊረዳው እንደማይችል ታስባለች። አስተማሪዎቿንም ቢሆን አታውቃቸውም ነበር። በአሁኑ ሰአት የ51 ዓመት ዕድሜ ላይ ሲሆን የምትገኘው ድንገት ካገኘቻቸው ሰዎች ጋር ውይይት ማካሄድ ይከብዳታል። ምክንያቱም ያንን ግለሰብ ትወቀው አትወቀው እርግጠኛ አይደለችም። '' በአንድ ወቅት ከእናቴ ጋር ሆነን የድሮ ፍቶዎች ስንመለከት እናቴ በተደጋጋሚ በምስሉ ላይ ስላለች ሴት ታወራልኝ ነበር። ግራ ስለገባኝ ይህች ሴት ማን ነች? ብዬ ጠየቅኳት። አንቺ እኮ ነሽ ስትለኝ በጣም ደነገጥኩኝ።'' ቡ እንደምትለው የሰዎችን አፍንጫ፣ አይን፣ ጆሮ የመሳሰሉ ክፍሎችን ልታስተውል ትችላለች፤ ነገር ግን ሁሉንም አንድ ላይ አድርጋ እንደ አንድ ፊት መመልከት አትችልም። • ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው? • "ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች ምንም እንኳን ይህ የጤና እክል ብዙ ውስንነቶች ቢፈጥሩባትም የራሷ የሆኑ መንገዶችን እንፈጠረች ትናገራለች። ሰዎች ደጋግመው የሚለብሱት የልብስ አይነት፣ ድምጻቸውን፣ ጌጣ ጌጦች፣ የጸጉር አይነትና የሰውነት ቅርጽ የመሳሰሉ ነገሮችን ለማስታወስ እንደምትሞክር ትናገራለች። የዚህ በሽታ ሌላኛው ተጠቂ የሆነው ሪቻርድ ዋር ደግሞ ማስታወስ የማይለው እምብዛም የማይግባባቸውን ሰዎች ፊት እንደሆነ ይናገራል። ከዚህ ባለፈ ግን ልክ እንደ ቡ የቤተሰቦቹንና የጓደኞቹን መልክ መለየት እንደማይቸገርና አዲስ ሰዎችን ሲተዋወቅ ጉዳዩን ቶሎ እንደሚያስረዳቸው ይናገራል። • መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት 'ፕሮሶፓግኖዚያ' የተባለው የሰዎችን የፊት ገጽታ ማስታወስ ያለመቻል ችግር በዋነኛነት በሁለት ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። የመጀመሪያው በአደጋ አልያም በተለያዩ ምክንያቶች ጭንቅላታችን ሲጎዳ የሚፈጠረው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተፈጥሮ ስንወለድ ጀምሮ አንዳንድ የአእምሯችን ክፍሎች በአግባቡ መልእክት መለዋወጥ ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰት ነው።
48429821
https://www.bbc.com/amharic/48429821
በጃፓን በተፈጸመ ጥቃት ከሞቱት ሦስት ሰዎች መካከል አንዲት ህጻን ትገኝበታለች
ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አውቶቡስ እየጠበቁ የነበሩ ሕፃናት በስለት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነገረ።
ጥቃቱ የተፈፀመው በደቡባዊ ቶኪዮ ሲሆን 18 ሰዎች ጉዳት ሳይደርስባቸው እንዳልቀረ ተገልጿል። አንዲት የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ እና አንድ የ39 አመት ጎልማሳ በጥቃቱ መገደላቸው ታውቋል። ጥቃቱን አድርሷል የተባለ እድሜዎቹ በ50ዎቹ የሚገመት ግለሰብ ራሱን በያዘው ስለት አንገቱ አካባቢ የወጋ ሲሆን በፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ እንደሞተ ተነግሯል። ጥቃቱ የደረሰባቸው 16 ሕፃናት ሴት ተማሪዎች መሆናቸው የታወቀ ሲሆን ወንጀሉ የተፈፀመበትን ሁለት ቢላ ፖሊስ በእግዚቢትነት ይዟል። • ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ለሚካሄደው ምርጫ 3.7 ቢሊዮን ብር ጠየቀ • የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ • ጋዜጠኛ ታምራት አበራ በመታወቂያ ዋስ ተለቀቀ ተማሪዎቹን ወደ ትምህርት ቤታቸው ለመውሰድ በስፍራው ተገኝቶ የነበረው አሽከርካሪ እንደተናገረው ጥቃት አድራሹ ወደ መኪናው ለመግባት ተራ ይዘው የነበሩ ተማሪዎችን በስለት መውጋት እንደጀመረ እና በኋላም ወደ መኪናው በመግባት ውስጥ ያሉትንም እንደወጋቸው አስረድቷል። አንድ የአይን ምስክር "በአውቶቡስ ማቆሚያው አካባቢ አንድ ሰው ወድቆ ደም ሲፈስሰው አይቻለሁ" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል። ''ተማሪዎችም ወድቀው ተመልክቻለሁ... ሰላማዊ አካባቢ ነበር። እንዲህ አይነት ነገር ማየት ያስፈራል'' ሲል የተሰማውን ለጋዜጠኞች ተናግሯል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በስፍራው ደርሰው የተጎዱትን እርዳታ እያደረጉ ሲሆን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አሜሪካ የሚገኙት ዶናልድ ትራምፕም የተሰማቸውን ሐዘን ገልጠዋል። ጃፓን እንዲህ አይነት ጥቃቶች በስፋት ከማይስተዋልባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በስለት የሚደርሱ ጥቃቶች ቁጥር እየጨመረ መጥተዋል።
news-53996732
https://www.bbc.com/amharic/news-53996732
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የፕላስቲክ ብክለትን ጨምሮታል ተባለ
የባህር ዳርቻዎችን የሚያጸዳ አንድ ምግባረ ሰናይ ድርጅት እንዳስታወቀው ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽን በኋላ የፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለት እንደ አዲስ በእጅጉ እየጨመረ መጥቷል።
'ሰርፈርስ አጌኒስት ሲዌጅ' የተሰኘው ድርጅት እንደገለጸው ከወረርሽኙ በኋላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችና ሌሎች የፕላስቲክ ምርቶች በባህር ዳርቻዎች አካባቢ በብዛት ተገኝተዋል። ድርጅቱ አክሎም ሰዎች ወረርሽኙን እንደ ምክንያት በመጠቀም ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የተለያዩ የፕላስቲክ ምርቶችን መጠቀም የጀመሩ ሲሆን አወጋገድ ላይም ቢሆን ቸልተኝነት ተስተውሏል ብሏል። ከፊታችን መስከረም ወር ጀምሮም እንዲህ አይነት ተግባር ሲፈጽሙ የሚገኙ ሰዎችንና ድርጅቶችን የመውቀስና የማሳፈር ቅስቀሳ በማህበራዊ ሚዲያ ለመጀመር ታስቧል። ከባህር ዳርቻዎች በተጨማሪም በሀይቆችና ወንዞችም የፕላስቲክ ብክለት በስፋት እየታየ ነው። ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እንዲሁም ሌሎች የግል ንጽህና መጠበቂያዎችን ከተጠቀሙ በኋላ እንዴትና የት እንደሚያስወግዱ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ ተጠቁሟል። ''የፕላስቲክ ጠርሙሶችና እቃ መያዣዎችን በውሃ አካባቢዎች ከዚህ በፊትም የተለመደ ነገር ቢሆንም ባለፉት ሶስትና አራት ወራት የተያው ግን ከምን ጊዜውም ቢሆን ከፍ ያለ ነው'' ብሏል ምግባረ ሰናይ ድርጅቱ። በዚህ ምክንያትም ሰዎች በድጋሚ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስኮችን እንዲሁም ሌሎች መገልገያዎችን መጠቀም እንዲያዘወትሩ ምክር እየተሰጠ ነው። ከአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎች በተጨማሪ በውሀ አካባቢዎች ከተገኙት የፕላስቲክ ምርቶች መካከል የውሃ መጠጫዎች፣ ጓንቶች፣ የፕላስቲክ ማንኪያና ሹካዎች እንዲሁም ኮዳዎች ይገኙበታል። በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙ ባህር ዳርቻዎች በተደረገ ዳሰሳ እነዚህ የፕላስቲክ ምርቶች በብዛት ተስተውለዋል። ምግባረ ሰናይ ድርጅቱም ይህንን ችግር ለመቅረፍ በማሰብ 600 የሚደርሱ የባህር ባርቻና የወንዝ ዳር አጽጂዎችንለማሳተፍ ያሰበ ሲሆን የፕላስቲክ ምርቶቻቸው በብዛት የሚገኙ ድርጅቶችንም የማጋለጥና የማስተማር ዘመቻ ለማካሄድ አቅዷል።
news-46608417
https://www.bbc.com/amharic/news-46608417
በጾታ እኩልነት የሚያምኑ ወንዶች የትኞቹ ናቸው. . .?
ተመራማሪዎች ደረስንበት ያሉት ድምዳሜ ሴት ልጅ ያላቸው ወጣት አባቶች በጾታ እኩልነት ያምናሉ፤ ያረጁና ያፈጁ አመለካከቶችንም ይቃወማሉ ብለዋል።
የሎንዶን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ባካሄደው በዚህ ጥናት መሠረት በጾታ እኩልነት ዙርያ የተንሸዋረረ አመለካከት የነበራቸው ወጣት አባቶች ሴት ልጅ ከወለዱ በኋላ የባሕሪ ለውጥ አምጥተዋል። • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ የባሕሪ ለውጡ ሴት ልጃቸው የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ስትጀምር በ8 በመቶ፣ 2ኛ ደረጃ ስትገባ ደግሞ በአማካይ በ11 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ተብሏል። ጥናቱ እንዴት ተሠራ? በዚህ ጥናት ውስጥ የተካተቱት አባቶች ከ21 ዓመት በታች ሴት ልጅ ያላቸው ብቻ ናቸው። በጥናቱ 5 ሺህ የሚሆኑ አባቶች ተካፍለዋል። ሌሎች 6 ሺህ የሚሆኑ እናቶችም የጥናቱ አካል ነበሩ። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ወላጆቹ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎችን የተጠየቁ ሲሆን "የሴትና የወንድ ሚና በቤት ውስጥ ምን መሆን አለበት?" በሚለው አመለካከት ላይ አስተያየታቸውን ተጠይቀዋል። ለምሳሌ "ባል ሥራ ሠርቶ ገንዘብ ማምጣት፣ ሚስት ደግሞ ልጆችን መንከባከብና ምግብ ማብሰል" አለባቸው በሚለው ላይ ይስማሙ እንደሆን ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። በዚህና ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎች ዙርያ አባቶች የሰጡት መልስ በጊዜ ሂደት እየተቀየረ እንደመጣ ተነግሯል። "የሚስት ሚና በቤት ውስጥ መታጠር አለበት" የሚለው አመለካከት ሴት ልጆች በወለዱ ወንዶች ዙርያ ቀስ በቀስ እየተቀየረ መጥቷል። • ለልጃቸው "ሂትለር" የሚል ስም የሰጡ እናትና አባት ተፈረደባቸው የምርምሩ ውጤት ተመራማሪዎች በጥናታቸው ማሳረጊያ ላይ ተረዳን እንዳሉት ከሆነ ጾታዊ አመለካከት በጊዜ ሂደት እየተለወጠ የሚመጣ መሆኑና በተለይም ወንዶች ሴት ልጅ ከወለዱ በኋላ በጾታ እኩልነት ዙርያ ያላቸው አመለካከት እየተሻሻለ እንደመጣ ተመላክቷል። የጥናቱ ተባባሪ ደራሲ ጁሊያ ፍሊፕ "የባሕሪ ለውጥ በጊዜ ሂደት መኖሩ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ነው" ብላለች።
45308859
https://www.bbc.com/amharic/45308859
በሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ወቅት ጥቅም ላይ ከዋለው ቦምብ ጋር የሚመሳሰል ቦምብ በተጠርጣሪ ቤት ተገኘ- ፖሊስ
በሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ወቅት ጥቅም ላይ ከዋለው ቦምብ ጋር የሚመሳሰል ቦምብ በተጠርጣሪ ቤት አገኘው ሲል መርማሪ ፖሊስ አስታውቋል።
መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ በስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ የደረሰበትን የምርመራ ደረጃ ለፍርድ ቤት ባስረዳበት ወቅት ነበር በተጠርጣሪ ቤት ተመሳሳይ ቦምብ ማግኘቱን ያስታወቀው። በተመሳሳይ ሁኔታ ከሁለተ ቀናት በፊት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጥረው በምርመራ ላይ የሚገኙት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ቦምብና የጦር መሳሪያ እንደተገኘባቸው መርማሪ ፖሊስ ማስታወቁ ይታወሳል። በወቅቱ ሌሎች በቁጥጥር ስር ያልዋሉ የጦር መሳሪያዎችን ለመያዝም ጥረት እያደረገ መሆኑን መርማሪው ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቶ ነበር። • በሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ የተጠረጠሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ የጦር መሳሪያ ተገኘባቸው- ፖሊስ • በሰልፉ ላይ የታየው ክፍተት ምን ነበር? • አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታገዱ • አቶ ጌታቸው አሰፋ የት ናቸው? የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል? መርማሪ ፖሊስ ዛሬ የምርመራ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁሞ የኤፍ ቢ አይ የቴክኒክ ምርመራ ውጤቶቸን ለመቀበል ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለት 14 ቀን ጠይቋል። የተጠርጣሪ ጠበቃ ግን ምረመራው ይህን ያህል ረዥም ጊዜ የሚወስድ ባለመሆኑ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ጊዜ አያስፈልግም ሲሉ አስተባብሏል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ተጠርጣሪዎቹ የተጠረጠሩበት ድርጊት በማስረጃ መረጋገጡን ፖሊስ እንዲያሰረዳ በጠየቀው መሰረት፤ ፖሊስ ጌቱ ግርማ መኖሪያ ቤት ውስጥ በሰኔ 16 የቦምብ ጥቃት ላይ የዋለው ቦምብ አይነት ጋር ተመሳሳይ ቦምብ ማግኘቱን ገልጿል። አብዲሳ ቀነኔ የተባለው ተጠርጣሪም ሌላኛውን ተጠርጣሪ ከአቤት ሆስፒታል ለማስመለጥ ነርሶችን ሲያግባባ ነበር፤ ለዚህም መረጃ አለኝ ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ ቦምቡ ከመፈንዳቱ በፊት እና ከፈነዳ በኋላ የተለዋወጡት መረጃ አለኝ ብሏል። ፍርድ ቤቱም የምርመራው ሂደት የተወሳሰበ መሆኑን በመጥቀስ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። ከሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ ጋር በተገናኘ ተጠርጥራ በአማኑኤል ሆስፒታል ህክምና ላይ የምትገኘውን የህይወት ገዳን ምርመራን ማቋረጡንም ፖሊስ ለችሎቱ አሳውቋል።
news-47797189
https://www.bbc.com/amharic/news-47797189
የልጇን ልጅ የወለደችው አያት
የ61 ዓመቷ አሜሪካዊቷ አያት፣ ወ/ሮ ሲሲሊ፣ ልጇ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ቢሆንም ከትዳር አጋሩ ጋር የራሳቸውን ቤተሰብ ለመመስረት ያላቸውን ፍላጎትና ወልደው ለመሳም ያላቸውን ጉጉት ትሰማለች።
ይኼኔ ለሁለቱ ጥንዶች ሀሳብ የነበረውን ማህፀን የማግኘት ሀሳብ እርሷ ማህፀኗን ለመስጠት ፈቃደኛ በመሆኗ ተቃለለ። ከዚያም ልጇን ሴት ልጅ ወልዳ አስታቅፋዋለች። ነገሩ ትንሽ ግራ ገብ ይመስላል። • የወንድ የእርግዝና መከላከያ፤ ለምን እስካሁን ዘገየ? • 100 ሺህ ብር፤ ብልትን ለማወፈር • የኒፕሲ ሐስል ግድያ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ ወ/ሮ ሲሲሊ ኤሌጅ ወንድ ልጇ ከተመሳሳይ ፆታ የትዳር አጋሩ ጋር ትዳር የመሰረተ ሲሆን ልጅ የማግኘት ተስፋው የመነመነ በነበረበት ጊዜ ነበር ማህፀኗን ሰጥታ ሴት ልጅ የወለደችላቸው። መጀመሪያ ወ/ሮ ሲሲሊ ይህን ሃሳብ ያነሳችው ልጇና ባለቤቱ ቤተሰብ ለመመስረት ያላቸውን ጥልቅ ፍላጎት ሲነግሯት ነበር። ሃሳብዋንም ስታጋራቸው ሁለቱም እንደሳቁባት ታስታውሳለች። "እስከ ረጅም ጊዜ ሃሳቡ ቀልድ ተደርጎ እንጂ እውን ይሆናል ብለን በውል አንነጋገርበትም ነበር" ትላለች ወ/ሮ ሲሲሊ። ነገር ግን በጊዜ ሂደት ልጇ ማቲው ኤሌጅና ባለቤቱ ልጅ ሊያገኙ የሚችሉበትን መንገድ በህክምና ባለሙያዎች ድጋፍ ሲፈልጉ ስለነበር የእናቱ ማህፀን ምቹ መፍትሄ እንደሆነ ተረዱ። በዚህም መሰረት ወ/ሮ ሲሲሊ ቃለመጠይቅና ብዙ የጤና ምርመራ ያደረገች ሲሆን ውጤቶቹም ህልማቸውን የሚያሳካ ሆኑ። ወ/ሮ ሲሲሊ ስለ ምርመራው ስትናገር "በጤናዬ ዙሪያ በጣም ጠንቃቃ ነኝ፤ ፅንስ መሸከም እችላለሁ ብዬ አልተጠራጠርኩም ነበር" ትላለች። እናቱ ማህፀን መስጠት እንደምትችል ከተረጋገጠ በኋላ የልጇ ዘር ተወስዶ የሴቴ እንቁላል ደግሞ ከባለቤቱ አቶ ዶፈርቲ እህት በመውሰድ ልጅ የማግኘት ህልማቸው ተጀመረ። የማቲው አባት "ሁልጊዜም ከተለመደው አስተሳሰብ ወጥተን መፍትሄዎችን መፈለግ እንዳለብን እናውቅ ነበር" ይላሉ። ወ/ሮ ሲሲሊ እርግዝናው ሙሉ በሙሉ ጤናማ በሆነ መንገድ እንዳለፈ ስትናገር "ከበፊቶቹ እርግዝናዬ ግን ትንሽ ከበድ ይላል" ብላለች። የልጇ ባለቤት ዶፈርቲ ድርጊቷን " በጣም በፍቅር የተሞላ" ብሎ ሲገልፀው አያትየውንም "ለራሷ የማትል ሴት ናት" ብሏል። እርግዝናዋ ለሌሎቹ ሁለት ልጆችዋ በመጀመሪያ "አስደንጋጭ" ቢሆንም ከተነገራቸው በኋላ ሁለቱም በሁኔታው ደስተኛ ነበሩ። ወ/ሮ ሲሲሊ በእርግዝናዋ ወቅት ከመድን ዋስትና ድርጅቷ ጋር ችግር እንደገጠማት ትናገራለች። የመድን ድርጅቱ የራስዋ ልጅ ቢሆን የሚሸፍናቸውን ወጪዎች የራሷ አይደለም በማለት ድጋፍ ከማድረግ ተቆጥቧል። የማቲው አባት በባለቤታቸው ድርጊት ላይ "እነዚህ ዓይነት ጥቃቅን ነገሮች በመንገዳችን እንቅፋት ሆነውብናል" ይላሉ። በመቀጠልም " የሚገጥሙንን ተቃውሞዎች የግል ጉዳይ አድርጎ መውሰድ ትቻለሁ፤ዋናው ነገር ቤተሰብ፣ ጓደኞችና የሚደግፉን ብዙ ሰዎች አሉ" ሲሉ ይናገራሉ። ልጅቱ ከተወለደች አንድ ሳምንት በኋላ ሁለቱም አያትና የልጅ ልጅ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ። "ይች ሕፃን በፍቅርና በሚደግፋት ቤተሰብ ውስጥ ነው የምታድገው" ብለዋል አራሷ ወ/ሮ ሲሲሊ።
news-51830172
https://www.bbc.com/amharic/news-51830172
የማንችስተር ሲቲና የአርሰናል ግጥሚያ በኮሮናቫይረስ ስጋት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ
ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ዛሬ እሮብ፤ ሊያደርግ የነበረው የፕሮሪሚየር ሊግ ጨዋታ "ቅድመ ጥንቃቄ" በሚልና በርካታ የአርሰናል ተጫዋቾች ራሳቸውን ለይተው በመቀመጣቸው የተነሳ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ።
የመድፈኞቹ ተጫዋቾች ራሳቸውን አግልለው በር ዘግተው የተቀመጡት የኦሎምፒያኮስ ባለቤት የሆኑት ኢቫንጀሎስ ማሪናኪስ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው። አርሰናል እንዳለው ከሆነ ማሪናኪስ ከሁለት ሳምንት በፊት በነበረው አውሮፓ ሊግ ጨዋታ ወቅት በርካታ ተጫዋቾችን አግኝተው ነበር። የ52 ዓመቱ ማሪናኪስ በኮቪድ 19 [ኮሮናቫይረስ] መያዛቸውን የተናገሩት ማክሰኞ ዕለት ነበር። ኦሎምፒያኮስ በአውሮፓ ሊግ ዎልቭስን ሐሙስ ዕለት የሚያስተናግድ ሲሆን፤ ዎልቭስ ግን አስቀድሞ ጨዋታው እንዲራዘምለት ጠይቆ የነበረ ቢሆንም ተከልክሏል። የፕሪሚየር ሊግ የበላይ ኃላፊዎች ግን ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ዓይነት ጨዋታ የማራዘም ሃሳብ እንደሌላቸው ገልፀው "አስፈላጊው ጥንቃቄ ሁሉ ተወስዷል" ሲሉ ተናግረዋል። ብራይተን በበኩሉ ከአርሰናል ጋር ያላቸው ግጥሚያ ቅዳሜ እለት በተያዘለት ሰዓት እንደሚካሄድ አስታውቋል። "ተጫዋቾቹ ራሳቸውን ነጥለው የሚያቆዩበት ጊዜ የሚያበቃው ሐሙስ በመሆኑ አደጋው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው" ብለዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን ድረስ 382 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ስድስት ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። የኮሮናቫይረስ የስፖርት ውድድሮችን በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳ ሲሆን የጣሊያን ሴሪ አ ሲቋረጥ የፈረንሳይና የስፔን ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም እንዲካሄዱ ተወስኗል። ማንችስተር ዩናይትድን፣ ሬንጀርስንና ቼልሲን የሚያሳትፈው የአውሮፓ ዋንጫም በሚቀጥሉት ቀናት በኦስትሪያ እና በጀርመን በዝግ ስታዲየሞች ይካሄዳሉ። በዩናይትድ ኪንግደም ግን ስፖርት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሲስተጓጎል ይህ የመጀመሪያው ጨዋታ ነው።
news-54821200
https://www.bbc.com/amharic/news-54821200
የአሜሪካ ምርጫ፡ አሸናፊውን እስካሁን ያላወቅነው ለምንድነው?
አሜሪካውያን እንዲህ ባለ መልኩ በንቃትና በከፍተኛ ቁጥር ሲሳተፉበት በቅርብ ዓመታት አልታየም በተባለው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕና ጆ ባይደን አስስከመጨረሻዋ ሰዓት አንገት ላንገት ተናንቀዋል።
ለመሆኑ በምርጫው አሸንፎ ፕሬዝደንት የሚሆነው ማነው? ይህ ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አላገኘም። ጆ ባይደንም ሆነ ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው የማሸነፍ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። እንደውም በኮሮረናቫይረስ ምክንያት በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ የተባለ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በፖስታ በኩል ድምጻቸውን መላካቸውን ተከትሎ የምርጫ ቆጠራውና ይፋዊ ውጤቱ ከዚህ በኋላ ቀናት ሊፈጅ እንደሚችል ይገመታል። . የአሜሪካን ምርጫ በቀላሉ መረዳት የሚያስችሉ ነጥቦች . ስለ አሜሪካ ምርጫ ምን ዜና ልንሰማ እንችላለን? . የዶናልድ ትራምፕ ሕይወት፡ ከሆቴል እስከ ቤተ መንግሥት እንደ አሪዞና፣ ጆርጂያ እና ፔንሲልቬኒያ ያሉ ወሳኝ ግዛቶች ዛሬ ውጤት ይፋ እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ነው። የእነዚህ ግዛቶች አጠቃላይ ውጤትና በቀላሉ ተፎካካሪዎቹ ያሸንፉባቸዋል ተብሎ የሚገመቱ ግዛቶችን ውጤት ከግምት ውስጥ አስገብቶ እንኳን ማን ያሸንፋል? የሚለውን ለማወቅ ምናልባት እስከ አርብ ድረስ መጠበቅ ግድ ሊል ይችላል። ነገር ግን ይሄ ብቻ አይደለም አሳሳቢው ጉዳይ። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በውጤቱ ደስተኛ እንዳልሆኑና 'ምርጫው ሊጭበረበር' እንደሚችል በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል። ምናልባት ፕሬዝዳንቱ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የሚወስዱት ከሆነ ደግሞ የ2020 አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊን ሳናውቅ ሳምንታት ልንቆይ እንችላለን። ወሳኞቹ ግዛቶች በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማሸነፍ የበርካቶችን ድምጽ ማግኘት ብቻ በቂ አይደለም። በኢሌክቶራል ኮሌጅ የምርጫ ሥርዓት መሠረት ሁለቱም ተፎካካሪዎች ካሉት 538 ድምጾች ቢያንስ 270 ማግኘት አለባቸው። በዚህ የምርጫ ስርአት መሰረት እያንዳንዱ ግዛት ባለው የህዝብ ብዛት መሰረት ድምጽ ያገኛል። በርካታ ነዋሪዎች ያሏቸው ግዛቶች ከፍተኛ ድምጽ ያላቸው ሲሆን፤ ለምሳሌ ፔንሲልቬንያን ያሸነፈ ተፎካካሪ 20 ድምጾችን ያገኛል ማለት ነው። ዝቅተኛ የሚባል ድምጽ ካላቸው ግዛቶች ማካከል ደግሞ እነ ሞንታና፣ ኖርዝ ዳኮታ እና ሳውዝ ዳኮታ ይጠቀሳሉ። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ድምጽ የሚገኝባቸው ግዛቶች ወሳኞቹ የፍልሚያ ቦታዎች ተብለው ይጠራሉ። የአሜሪካ ምርጫ በቅድመ ትንበያ የተሞላ ነው። የግል ድርጅቶችና መገናኛ ብዙሃን ሕዝቡን 'እንደው ማንን ለመምረጥ አስባችኋል?' ብለው ይጠይቁና ውጤት ይተንብያሉ። በዚህ ቅድመ ትንበያ መሠረት ደግሞ ባይደን የአሜሪካውን ምርጫ ተደላድለው እንደሚያሸንፉ ተገምቶ ነበር። ነገር ግን ባለፈው የ2016 ምርጫ እንዲሁ ትንበያ ተሰርቶ ሂላሪ ክሊንተን ያሸንፋሉ ቢባልም ውጤት ሲመጣ ግን ብዙዎች ያልጠበቁት ሆኖ ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንት መሆን ችለዋል።
news-45958853
https://www.bbc.com/amharic/news-45958853
የአማራ ክልል በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች እንዲፈቱ መንግሥት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠየቀ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች በአስቸኳይ እንዲፈቱ መንግሥት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠየቀ።
ይህንን የተናገሩት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ሲሆን ከሰሞኑ አላማጣ ውስጥ የተከሰተው ክስተት ፍትህ የሚሻ ነው ብሏል። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የግጭቱ መነሻ የራያ አካባቢ ህዝብ የማንነት ጥያቄ እንደሆነ ጠቅሶ ከህዝቡ ጋር በመነጋገር ህገ-መንግስታዊ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥቷል። መፍትሄው ጥያቄውን ከሚያነሳው የአካባቢው ህዝብ ጋር የሰከነ ውይይት በማድረግ የሃይል እርምጃ መውሰድ አለመሆኑ ሊሰመርበት እንደሚገባ መግለጫው አትቷል። •በአላማጣ ግጭት ቢያንስ 5 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ •ሃምሳ በመቶ የሚኒስትሮች ሹመት ለሴቶች •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በአንድ ክልል የሚፈጠር የሰላም መደፍረስ ለአጐራባች አካባቢዎች መትረፉ አይቀርምና የሰሞኑ የትግራይ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ችግር ለክልላችንም ትልቅ የፀጥታ ስጋት ነው በማለት መግለጫው ጨምሮ አስታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ በአንዳንድ አካላት ዘንድ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ለሚፈጠረው ችግር የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን መክሰሳቸው መሠረት ቢስ ውንጀላ ነው ያለው መግለጫው ክሱንም እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። የትግራይ ክልል ችግሩን ለመፍታት በሚያደርገው ህጋዊና ሰላማዊ ጥረት ሁሉ የአማራ ክልል ድጋፍ እንደሚያደርግም መግለጫው ጠቅሷል። የትግራይ ክልል በበኩሉ የትግራይ ክልል መንግስትና ህዝብ ሰላሙን አስጠብቆ የክልሉን ውስጣዊ ችግሮች ለመፍታት ሌትና ቀን በሚረባረብበት ወቅት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ የትግራይ ክልል በአማራ ክልል ለሰላም ችግር ፈጣሪ መባሏ አሳዛኝና ከትንኮሳ የማይተናነስ ጠብ አጫሪ አቋም ነው ብሏል። መግለጫው አክሎም "የትግራይ ክልል መንግስትና ህዝብ ለአማራ ህዝቦች ማረጋገጥ የምንፈልገው ለሰላማቸው መረጋገጥ እንጂ በማንኛውም ጊዜ ለፀጥታቸው መደፍረስ ምክንያት ሊሆኑ እንደማይችሉ ነው" ሲል ያትታል። መግለጫው በመቀጠልም "የተከሰተው ግጭት መነሻው የራያ አካባቢ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ሲሆን ይህንን ጥያቄ ከህዝቡ ጋር በመነጋገር ሕገ መንግስታዊ ምላሽ መስጠት እንደሚገባ በአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርትም ሆነ በኢህአዴግ ጉባኤዎች አቅጣጫ መቀመጡን ይታወሳል" ብሏል። ኾኖም ግን "ሕገ መንግስቱ በማንነት ጉዳይ ላይ ያስቀመጠውን ስርዓት በመጣስ በሌላ ክልል የውስጥ ጉዳይ ጠልቃ መግባቱ የሚያረጋግጥ መግለጫ ነው።" ሲል የአማራ ክልል መግለጫን ኮንኗል። አያይዞም በራያም ሆነ በወልቃይት አካባቢዎች ለተፈጠሩ ችግሮችንም የአማራ ክልል መንግስት ኃላፊነቱን መውሰድ ይኖርበታል ብሏል። መግለጫውን ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም ለትግራይ ህዝብ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠይቋል።
news-55950981
https://www.bbc.com/amharic/news-55950981
የዘር ቅንጣት የሚያክል እስስት ተገኘ
ተመራማሪዎች በምድራችን ላይ ትንሽ ነው የተባለ እስስት በማዳጋስካር ማግኘታቸውን ተናገሩ።
እስስቱ ከማነሱ የተነሳ የዘር ቅንጣት ያክላል ተብሏል። የማዳጋስካር እና ጀርመን ተመራማሪዎች በተጨማሪም ሁለት ትንንሽ እንሽላሊቶች ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል። ወንዱ እስስት፣ ብረኬዢያ ናና የሚባል ሲሆን አካሉ 13.5 ሚሊሜትር እንደሆነ ተገልጿል። በሙኒክ እንደሚገኘው ባቫሪያን የእንስሳት ሙዚየም ከሆነ ይህ እስስት በዓለም ላይ ከታወቁት 11 ሺህ 500 ተሳቢ እንስሳት መካከል በጣም ትንሹ ነው። ይህ በዓለማችን ላይ ትንሽ ነው የተባለው እስስት፣ ከጭራው ጫፍ እስከ አፍንጫው ድረስ ርዝመቱ 22 ሚሜትር ርዝመት አለው። ሴቷ ግን ከወንዱ በጥቂት ሚሊ ሜትሮች ረዘም ትላለች ያሉት ተመራማሪዎች 29 ሚሜትር እንደምትረዝም አሳውቀዋል። ተመራማሪዎቹ ሌላ ዝርያ ይገኛል በሚል ተስፋ ጥረታቸውን ቀጥለዋል። አዲሱ እስስት የተገኘው በሰሜን ማዳጋስካር ሞንታኔ በሚባል ጫካ ውስጥ ሲሆን የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተብሏል። በሃምቡርግ በሚገኘው የተፈጥሮ ታሪክ ማዕከል ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ኦሊቨር ሃውልቲሼክ ይህ የፍሬ ያክል ትንሽ የሆነ እስስት በደን ጭፍጨፋ ምክንያት ለመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል። ነገር ግን አካባቢው በቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥበቃ እየተደረገለት ሲሆን ይህም ዝርያው ሊተርፍ ይችላል የሚል ተስፋ አሳድሯል። ተመራማሪዎች ይህንን የእስስት ዝርያ ምስጥ አድኖ እንደሚበላ እና በምሽት በሳሮች መካከል እንደሚደበቅ ደርሰውበታል። ተመራማሪዎች ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ይህ የእስስት ዝርያ በዓለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ ሕብረት ዘንድ ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል እጅግ በጣም ለአደጋ የተጋለጡ ዝርያዎች ዝርዝር ውስጥ እንዲመዘገብ ጠይቀዋል።
news-55962060
https://www.bbc.com/amharic/news-55962060
ዩኬ በጋዜጠኝነት ሽፋን ‘ለቻይና ሲሰልሉ’ ነበሩ ያለቻቸውን አባረረች
በጋዜጠኝነት ሽፋን ለቻይና ሲሰልሉ ነበር የተባሉ ሦስት ጋዜጠኞች ከወራት በፊት ከዩናይትድ ኪንግደም እንዲወጡ ተደርገው እንደነበረ ተገለጸ።
የቻይና እና ዩኬ ሰንደቅ ዓላማዎች ጋዜጠኛ መስለው ለቻይና መንግሥት ሲሰልሉ ነበሩ የተባሉት ሰዎች ከዩኬ ተገደው እንዲወጡ መደረጋቸው ሳይሰማ የቀረው ግለሰቦቹ በጋዜጠኝነት ቪዛ ወደ ዩኬ በመግባታቸው ነው ተብሏል። ግለሰቦቹ በጋዜጠኝነት ሽፋን ለቻይና ብሔራዊ ደህንነት ሚንስትር መረጃ ሲሰበስቡ ነበር ተብሏል። ግለሰቦቹ ጋዜጠኛ መስለው በየትኛው መገናኛ ብዙሃን ሲሰሩ እንደቆዩ ግልጽ አልሆነም። የዩናይትድ ኪንግደም የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። በለንደን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲም በተመሳሳይ በጉዳዩ ላይ ምንም ሳይል አልፏል። ይህ መረጃ የተሰማው የዩናይትድ ኪንግደም የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ ድርጅት የቻይናው ብሔራዊ ጣቢያ ሲጂቲኤን በዩኬ የነበረውን የሥራ ፍቃድ መሰረዙን ተከትሎ ነው። የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ ድርጅቱን ውሳኔ አጥብቆ እንደሚቃወም አስታውቋል። “ሴጣናዊ ተግባራት” በተያያዘ ዜና የቢቢሲን ዘገባ ተከትሎ የአሜሪካ መንግሥት በቻይና የሙስሊሞች አያያዝ እጅጉን እንዳሳሰባት አስታውቃለች። ቢቢሲ በዘገባው የኡጉሩ ሙስሊም ሴቶች በማጎሪያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚደርስባቸውን ወሲባዊ ጥቃቶች አጋልጧል። “እነዚህ ጥቃቶች አስደንጋጭ ናቸው። ጠንከር ያለ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል” ሲሉ የመንግሥት ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የዩኬ መንግሥት ሚንሰትር የሆኑት ኒጌል አደምስ የቢቢሲ ሪፖርት “ሴጣናዊ ተግባራት” መፈጸማቸውን አጋልጧል ሲሉ ለአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። በመላ ቻይና በሚገኙ ማጎሪያዎች ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኡጉሩ ሙስሊሞች እንደሚገኙ ይገመታል። ቢቢሲ ትናንት ባቀረበው ዘገባ በማጎሪያ ጣቢያዎች ውስጥ በሚገኙ ሙስሊሞች ጾታዊ ጥቃቶች እና ስቃይ እንደሚደርስባቸው አጋልጧል።
news-53713050
https://www.bbc.com/amharic/news-53713050
ህንድ፡ የማህተመ ጋንዲ መነፅር 700 ሺህ ብር እንደሚያወጣ ተገምቷል
የህንዳዊው ነፃነት ታጋይ ማህተመጋንዲ መነፅር በእንግሊዝ ለጨረታ ሊቀርብ መሆኑ ተሰምቷል።
የማህተመ ጋንዲ መነፅር በምስራቅ ብሪስቶል ግዛትም በሚገኝ የጨረታ ቦታም እንዲሸጥ በፖስታ ተልኳል። የጨረታው አስተባባሪ አንድሪው ስቶው መነፅሩ 700 ሺህ ብር (15 ሺህ ፓውንድ) እንደሚያወጣ የገመተ ሲሆን ለኩባንያውም ታሪክ ነው ተብሏል። የመነፅሩ ባለቤት ዋጋው ሲነገራቸው በድንጋጤ "ልባቸው ሸተት" ሊል ነበርም ተብሏል። "መነፅሩን በፖስታ ሳጥናችን ውስጥ አንድ ሰው እንዳስገባውና ከዚያም ጋር ተያይዞ የማህተመ ጋንዲ መነፅር ሊሆን ይችላልም የሚል ማስታወሻም እንደሰፈረ አንድ ሰራተኛ ነገረኝ። እኔም በመጀመሪያ ብዙም ትርጉም አልሰጠሁትም ነበር እናም ዝም ብዬ ወደስራዬ ቀጠልኩ"ብለዋል። ነገር ግን አንድሪው ስቶው እንደሚሉት መነፅሩን ሲመረምሩት ህንዳዊው የነፃነት ታጋዩ መሆኑም ተረጋገጠ። "የማህተመ ጋንዲ መነፅር መሆኑን ሳውቅ ከወንበሬ ልወድቅ ነበር። ባለቤቴንም ደውዬ ስነግረው እሱም በድንጋጤ ልቡ ሸተት ልትል ነበር" ብለዋል። አስተባባሪው እንደሚሉት ባለቤቱ መነፅሩን ያገኙት ከትውልድ ወደ ትውልድ በመወራረሱ እንደሆነ ነግረዋቸዋል። የቤተሰብ አባላቸውም በጎርጎሳውያኑ 1920 ማህተመ ጋንዲን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አግኝተዋቸው ከሳቸው እንደተቀበሉም ለአቶ አንድሪው አጫውተዋቸዋል። "የነገሩንን ታሪክም ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጠናል፤ ማህተመ ጋንዲ መነፅር ማድረግ ከጀመሩበት ጋር ጊዜው ተገጣጥሟል" የሚሉት አቶ አንድሪው የመጀመሪያ መነፅራቸው ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል። ይኼንንም ግምት እንዲያስቀምጡ ያደረጋቸው የመነፅሩ ቁጥር ደከም ያለ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ነው። "የግል ንብረታቸውን ብዙ ጊዜም ስለሚሰጡ ይኸም መገኘቱ አይገርምም" ብለዋል። መነፅሩን መግዛት የሚፈልጉ በርካታ ሰዎች ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን በተለይም ከህንድ ጥያቄዎች እየጎረፉ እንደሆነም ተናግረዋል።
news-56206664
https://www.bbc.com/amharic/news-56206664
ቢል ጌትስ ቢትኮይን ላይ ገንዘቤን አላፈስም አሉ
የማይክሮሶፍት ፈጣሪ ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ ቢትኮይን ላይ ገንዘባቸውን እንዳላፈሰሱ ተናገሩ።
ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ ባላሃብቱ ይህን ያሉት ክለብሃውስ የተሰኘው ማሕበራዊ ድር-አምባ ላይ ቀርበው ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው። ጌትስ፤ ቢትኮይን ላይ ገንዘባቸውን ከሚያፈሱ ይልቅ "ምርት ባላቸው" ኩባንያዎች ላይ ፈሰስ ቢያደርጉ እንደሚመርጡ አስታውቀዋል። ለምሳሌ የወባና ኩፍኝ በሽታዎች ክትባት ላይ ገንዘባቸውን ቢያውሉ እንደሚመርጡ ተናግረዋል። ጌትስ ከዚህ በፊት በአሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች አምራች የሆነው ቴስላ ባለቤት ኢላን መስክ ገንዘቡን ቢትኮይን ላይ ማዋሉን አስመልክቶ በቅርቡ ሐሳባቸውን ሰጥተው ነበር። "በቢትኮይን ላይ ያለኝ አጠቃላይ ትንተና ምንድነው ከኢላን መስክ ያነሰ ገንዘብ ካላችሁ ተጠንቀቁ ማለት ነው የምሻው" ሲሉ ለብሉምበርግ ተናግረው ነበር። "ኢላን በርካታ ገንዘብ አለው። ደግሞም እሱ በጣም ውስብስብ ሰው ነው። እኔም የሱ ቢትኮይን መጠን ድንገት ተነስቶ ይቀንሳል ወይም ይጨምራል የሚል ግምት የለኝም።" ቴስላ 1.5 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን መግዛቱን ካሳወቀ በኋላ የቢትኮይን ዋጋ 50 በመቶ ጨምሯል። ቴስላ አክሎም ቢትኮይንን እንደመገበያያ ገንዘብ እንደሚቀበል ይፋ አድርጓል። ነገር ግን የቢትኮይን ዋጋ ኋላ ላይ በ20 በመቶ ዝቅ ብሏል። የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የሌን መገበያያውን "በጣም ብቁ ያልሆነ ነው" ሲለ ገልፀውት ነበር። ቢል ጌትስ ለረዥም ጊዜ በቢትኮይን ላይ ያላቸው እምነት ዝቅ ያለ መሆኑን ሲናገሩ ነበር። ቢትኮይን ምንድነው? ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታልገንዘብ+መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን 'ኦንላይን' የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች ቁጥጥር ይደረግበታል። ቢትኮይንን የፈጠረው ግለሰብ/ቡድን በዓለም ላይ 21 ሚሊዮን ቢትኮይኖች ብቻ እንዲፈጠሩ ገደብ እንዳስቀመጡ ይታመናል። የብሎክቼይን መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስካሁን 17 ሚሊዮን ያህል ቢትኮይኖች ማይን ተደርገዋል።
news-55513635
https://www.bbc.com/amharic/news-55513635
የሞት ቅጣት የምትጠባበቀው የብቸኛዋ አሜሪካዊት ፍርድ እንዲጸና ታዘዘ
በፌዴራል ደረጃ የሞት ቅጣት በምትጠባበቀው ብቸኛዋ ሴት ላይ የቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ የአሜሪካ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።
ይህች ሊሳ ሞንትጎመሪ የተባለችው ሴት ሞት የተፈረደባት ከ15 ዓመት በፊት ሚዙሪ ውስጥ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴትን አንቃ በመግደልና ሆዷን በመቅደድ አሰቃቂ ድርጊት በመፈጸሟ ነው። የሞት ፍርዱ ከጸና በ70 ዓመታት ውስጥ የተገደለች የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ፌደራል መንግሥት እስረኛ ትሆናለች። የሊሳ የሞት ቅጣት የሚፈጸምበት ቀን ከአንድ ወር በፊት እንዲሆን ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ጠበቆቿ ኮቪድ -19 ስለያዛቸው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ተደርጓል። ይህን ተከትሎም የፍትህ መምሪያው ፍርዱ ጥር 12 እንዲፈጸም ወስኗል። ነገር ግን የሊሳ ጠበቆች ቀኑ ሊወሰን እንደማይችል ተከራክረዋል። ፍርድ ቤት የጠበቆቿን ሐሳብ ተቀብሎ የእስር ቤቱ ዳይሬክተር የሞት ፍርዱ የሚከናወንበትን ቀን መቁረጡን ውድቅ አድርጎት ነበር። ሆኖም ግን አርብ ዕለት የዳኞች ቡድን ዳይሬክተሩ የሞት ፍርዱ እንዲፈፀም የወሰነውን በሕጉ መሠረት ጠቅሶ ይተግበር የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። የሊሳ ጠበቆች ዳኞቹ የሰጡትን ውሳኔ እንደገና እንዲያጤኑት አቤቱታ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። በሞት ፍርድ መረጃ ማዕከል መሠረት፤ ሚዙሪ ግዛት ውስጥ በ1953 (እአአ) የሞት ፍርድ የተፈጸመባት ቦኒ ሄዲ ለመጨረሻ ጊዜ በአሜሪካ መንግሥት ውሳኔው የተፈጸመባት ሴት ናት። ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ዓመት መጀመሪያ ቅጣቱ እንዲጀመር ትዕዛዝ ከመሰጠታቸው በፊት የፌዴራል የሞት ፍርድ ለ17 ዓመታት ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቶ ነበር። የሊሳ የሞት ፍርድ የሚከናወነው ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ከመረከባቸው ጥቂት ቀናት በፊት ይሆናል። የደላዌር ሴናተር ሆነው ለአስርት ዓመታት የሞት ቅጣትን ሲደግፉ የነበሩት ባይደን ስልጣናቸውን ከያዙ በኋላ ግን የሞት ፍርድን ለማስቆም እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ሊሳ ሞንትጎመሪ ማን ናት? በታኅሣስ 2004 (እአአ) ሊሳ ከካንሰስ ወደ ሚዙሪ ያቀናቸው ቦቢ ጆ ስቲንኔት ቤት ያሳደገውን ቡችላ ለመግዛት እንደነበር የፍትህ መምሪያው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቋል። "ሊሳ ወደ መኖሪያው ከገባች በኋላ የስምንት ወር ነፍሰ ጡር የነበረችው ስቲኔት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ራሷን እንድትስት አድርጋለች" ይላል መግለጫው። "ቢላ በመጠቀም የስቲኔትን ሆድ ስትቀድ ግለሰቧ በዚህ ወቅት ነበር። ሲታገሉ ሊሳ ባደረሰችባት ጥቃት ስቲንኔት ለሞት በቅታለች። ከዚያም ሊሳ ህፃኑን ከሆዷ በመውሰድ አገተቻች" ብሏል። በ2007 (እአአ) በፌደራል እገታ እና ግድያ ጥፋተኛ ሆና ስለተገኘች የሞት ፍርድ ተላልፎባታል። የሊሳ ጠበቆች ግን በልጅነቷ በደረሰባት ድብደባ የአንጎል ጉዳት የደረሰባት ሲሆን የአዕምሮ ህምተኛ ስለሆነችም የሞት ቅጣት ሊተላለፍባት አይገባም ብለው ተከራክረዋል። የፌዴራል እና የግዛቶች የሞት ፍርዶች ልዩነት ምንድነው? በአሜሪካ የፍትህ ሥርዓት መሠረት ወንጀሎች በአገር አቀፍ ደረጃ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ወይም በግዛት ደረጃ ደግሞ በግዛቶቹ ፍርድ ቤቶች ሊታዩ ይችላሉ። እንደ ሐሰተኛ ገንዘብ ማዘዋወር ወይም የመልዕክት ስርቆት ያሉ ወንጀሎች በፌደራል ደረጃ ይታያሉ። የሞት ፍርድ መረጃ ማዕከል በተሰበሰበው መረጃ መሠረት በ1988 እና 2018 (እአአ) መካከል በፌዴራል ደረጃ 78 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው ሲሆን የተገደሉት ግን ሦስት ሰዎች ብቻ ናቸው።
news-54368871
https://www.bbc.com/amharic/news-54368871
ኢትዮጵያ፡ ተንከባካቢ ለሌላቸው እናቶች መጠጊያ የሆነችው የመቀሌዋ ነዋሪ
በመቀለ ከተማ ተወልዳ ያደገችው አስቴር ገብረታትዮስ መጠለያ የሌላቸውን እናቶች ትንከባከባለች፤ በዚህ የእርጅና እድሜያቸውም መጠጊያ "እሆናችኋለሁ" ብላቸዋለች።
ለዚህ መነሻ የሆናትም በየቀኑ በየጎዳናው ተኝተው የሚለምኑ እናቶችን ያለ መጠለያና ተንከባካቢ ማየት አለመቻሏ ነበር። በቤተሰብ የእንጨት ስራና ለአመታት የሰራችው አስቴር በካሜራ ሙያ ሰልጥና የራሷንም ፎቶ ቤት ከፍታ ትሰራም ነበር። የእናቶቹ ሁኔታ አንጀቷን ያላስቻለው አስቴር ሙያዋን እርግፍ አድርጋ በመተው እነሱን ለመርዳት ቆርጣም ተነሳች። በመቀለ ከተማ ውስጥ በተለምዶ 11 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢም ቅዱስ ሚካኤል የአረጋውያን ማደራጃ ማዕከልን ከአራት አመት በፊት አቋቋመች ። ስትጀምርም በ13 እናቶች ሲሆን ማዕከሉም በአሟቿ ወይዘሮ ጥሩወርቅና ግራዝማች በቀለ ግቢ ውስጥ ይገኛል። ወይዘሮ ጥሩ ወርቅ በህይወት እያሉም መጠለያ ላጡ እናቶች እንክባቤ በመስጠትም ይታወቁ ነበር። አስቴርም ያንኑ ተግባርም ተቀብላ ለአረጋውያኑ የመጨረሻ አመታት ድጋፍ ሆናላቸዋል። በማዕከሉም ውስጥ ከ70- 110 የእድሜ ባለፀጋ እናቶች ይገኛሉ። በመጀመሪያ አካባቢ ግቢው ውስጥ የገቡ እናቶች በቅጡ እንኳን መጠለያ ያልነበራቸው ሲሆን ከጊዜ በኋላ ግን የአካባቢው ወጣቶች ተሰባስበው ለሁሉም እናቶች መጠለያ የሚሆን ክፍሎችን አስገነቡላቸው። "እኔ ከቆርቆሮ በተሰራ መጠለያ ውስጥ ነበር እናቶቹን መንከባከብ የጀመርኩት:: ነገር ግን ሳልገልፀው ማለፍ የማልፈልገው በርካታ ሰዎች እንደረዱኝ ነው" ትላለች። በርካታ ሰዎች ለዚህ በጎ ተግባር የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዳደረጉ የምትናገረው አስቴር ምዕራፍ ካሳ የተባለ ግለሰብ ወጣቶችን በማስተባበርና ገንዘብ በማሰባሰብ፣ የእናት ህክምና ማዕከል ባለቤት ዶ/ር ሳምሶን ሙሉጌታ ለእናቶቹ በሙሉ አልጋና ፍራሽ በመለገስ እንዲሁም ሌሎች ወጣቶች አንሶላ እና ብርድ ልብስ በመለገስ ማዕከሉ እውን እንዲሆን የራሳቸውን አስተዋፅኦ አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ማህሌት አረጋዊና ቤተልሔም አባይ የተባሉ ነዋሪዎችም ነፃ አገልግሎት በመስጠት ከጎኗ አልተለዩም። የከተማዋ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ባለቤቷም አቶ አማኑኤል በቀለ ከጎኗ አልተለየም። "በርካቶችም በየጊዜው ወደ ማእከሉ በመምጣት የእናቶቹን ልብስ ያጥባሉ፣ ፀጉራቸውን ይሰራሉ፣ ጥፍራቸውን ይቆርጣሉ። ከዚያም አልፎ እናቶች በሚታመሙበት ወቅት በመርዳት ያግዙኛል" ስትልም እናቶቹን ለመርዳት እየተደረገ ያለውን የሕብረተሰቡ ትብብር ትገልፃለች። አስቴር እናቶቹ እንደ ቤተሰብ የሆኗት ሲሆን ሲታመሙም ሆነ በህይወት ሲለዩ ከፍተኛ ኃዘን ውስጥ ትወድቃለች። ማዕከሉን ባቋቋመችበት አራት አመታት ውስጥም አራት እናቶች በሞት መለያታቸውን በጥልቅ ኃዘን ተውጣ ትናገራለች። በማዕከሉ ከሚኖሩት መካከል ወይዘሮ ሮዚና አፈወርቅ አንዷ ናቸው። ወይዘሮ ሮዚና ተወልደው ያደጉት አስመራ ነው። አስመራ በነበሩበት ወቅት አነስተኛ ምግብ ቤት ከፍተውም ጥረው ግረው ልጆቻቸውን አሳድገዋል። ያለ መታደል ሆኖ ልጆቻቸውን በሞት ተነጠቁ። በአሁኑ ጊዜ የመቀለ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ሮዚና ከሶስት ግለሰቦችም ጋር እየተዘዋወሩ ምግብ በማዘጋጀት ተቀጥረው ሲሰሩ ነበር። በአንድ መጥፎ ቀንም ወድቀው እግራቸው ተሰበረ፤ ስራ መስራትም አልቻሉም። ደጋፊ፣ ተንከባካቢ በሌላቸውም ወቅት ማዕከሉ አለንልዎት ብሏቸዋል። "እኔ አስቴርን ደግፏት እንጂ እኔ ደህና ነኝ። እሷን አግዙዋት፤ አይዞሽ በሉዋት: እኛ ከሷ ነው የምንጠብቀው፤ እናንተ ደግሞ እሷን አግዙዋት" ብለዋል ለቢቢሲ አስቴር ከሰባት ወራት በፊት ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ባደረገችው ቆይታ እናቶቹን ለመንከባከብ ምግብ እንዳጠራትና የሚያግዛት አጥታም ከባድ ችግር ላይ መውደቋን በመጥቀስ ህዝብ እንዲረዳት ተማፅና ነበር። እናቶቹን መርዳት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ከግማሽ ሚልዮን በላይ (560,000) ብር ለማሰባሰብ ችለዋል። አስቴር በተሰበሰው ገንዘብ አነስተኛ የንግድ ስራ በመስራት ማእከሉ በራሱ እንዲቆምና ያሉትንም ወጪዎች መሸፈን እንዲያስችል እቅድ ይዛለች።
news-44920804
https://www.bbc.com/amharic/news-44920804
ሶማሊያዊ አባት የአስር ዓመት ልጁን በግርዛት ሳቢያ በሞት ቢነጠቅም ግርዛትን ከማሞገስ አላገደውም
የአስር ዓመት ልጁ በግርዛት ሳቢያ የሞተችበት ሶማሊያዊ አባት "ባህላችን ነው" ሲል ግርዛትን አወድሷል።
ግርዛትን በመቃወም የተደረገ ሰልፍ ዳሂር ኑር የተባለው ግለሰብ ልጅ የሶማሊያ ባህላዊ ገራዦች ዘንድ ለግርዛት ከተወሰደች በኃላ ለሁለት ቀናት ደሟ ያለማቋረጥ ፈሶ በስተመጨረሻ ህይወቷ አልፏል። አባትየው በበኩሉ ልጁን የነጠቀውን የግርዛት ባህል ሳይኮንን "የአካባቢው ነዋሪዎች ባህል ነው" በማለት ለቪኦኤ ተናግሯል። የታዳጊዋን ህይወት ለማትረፍ ከተረባረቡ የህክምና ባለሙያዎች አንዱ ዶ/ር አብዱራህማንኦማር ሀሰን "በዚህ ሁኔታ የተገረዘ ሰው በህይወቴ ገጥሞኝ አያውቅም" ብለዋል። ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች ''ኤርትራ የእምነት ነፃነት የምታከብር ሃገር ነች'' አቶ የማነ ገብረ-መስቀል የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? በዱሳማረብ ከተማ የሚገነው ሀናኖ ሆስፒታል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አብዱራህማን ታዳጊዋን ለመግረዝ ጥቅም ላይ የዋሉ ስለቶች ንጹህ እንዳልነበሩ አክለዋል። የታዳጊዋ አባት ግን ለልጃቸው ሞት ማንንም ተጠያቂ እንደማያደርጉ ተናግረዋል። ጋሌኮ ኤዱኬሽን ሴንተር ፎር ፒስ ኤንድ ዴቨሎፕመንት የተሰኘው የመብት ተከራካሪ ቡድን ዳይሬክተር ሀዋ አደን መሀመድ አባትየው ክስ ቢከፍትም ትርጉም አልባ መሆኑን ይናገራሉ። "ልጅቷን የገረዟት ሴት በቁጥጥር ስር አልዋሉም። ቢታሰሩም የሚቀጣቸው ህግ የለም" ብለዋል። ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች ጉዳዩ ዘወትር ሶማልያ ውስጥ ከሚስተዋሉ የግርዛት ጉዳዮች እንደማይለይም ተናግረዋል። በሀገሪቱ በግርዛት ሳቢያ የሴት መራቢያ አካል ውጫዊ ክፍል ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ይወገዳል። ሴቶች አስከፊ የጤና እክልም ይገጥማቸዋል። በሶማሊያ ህገ መንግስት ግርዛት ክልክል ቢሆንም 98 በመቶ የሀገሪቱ ሴቶች እንደሚገረዙ የዩኒሴፍ መረጃ ያሳያል። ሶማልያ ውስጥ ግርዛትን እንደ ሀይማኖታዊ ግዴታ የሚያዩ በርካቶች ናቸው። ፖለቲከኞች እነዚህን የማህበረሰቡ አካላት ላለማስቀየም ግርዛትን ለማስቀረት መመሞከርን አይደፍሩም።
news-55200359
https://www.bbc.com/amharic/news-55200359
ኮሮናቫይረስ ፡ አርጀንቲና በኮቪድ-19 ሰበብ ባለሀብቶች ላይ አዲስ ግብር ጣለች
አርጀንቲና ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ሕክምና የሚያስፈልጉ የሕክምና አቅርቦቶችን ለማሟላትና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላትን ወጪ ለመሸፈን ሀብታም ዜጓቿ ላይ አዲስ ግብር ጣለች።
አገሪቱ ምክር ቤት በአዲሱ ግብር ላይ ሲወያይ ሰልፈኞች በምክር ቤቱ ዙሪያ ተሰብስበው ነበር ይህ አንድ ጊዜ የሚከፈለውና "የሚሊየነሮች ግብር" የተባለውን ታክስ ለመጣል የወጣው ረቂቅ ለአርጀንቲና ምክር ቤት አባላት ቀርቦ 26 እንደራሴዎች ቢቃወሙትም የ42ቱን ድጋፍ በማግኘቱ ጸድቋል። ይህ ግብር ይመለከታቸዋል የተባሉት የአርጀንቲና ባለጸጋዎች ሀብታቸው ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን ብዛታቸውም 12 ሺህ እንደሚሆኑ ታውቋል። አርጀንቲና እስካሁን 1.5 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያረጋገጠች ሲሆን 40 ሺህ የሚደርሱት ደግሞ በበሽታው ሳቢያ ለሞት ተዳርገውባታል። አርጀንቲና በወረርሽኙ ክፉኛ ከተመቱ የዓለም አገራት መካከል አንዷ ስትሆን ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህሙማን በማስመዝገብ አምስተኛዋ አገር ሆናለች። አገሪቱ ያላት አጠቃላይ ሕዝብ 45 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን ከቁጥር አንጻር በበሽታው የተያዙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከተገኙባቸው አገራት መካከል ትንሽ የሕዝብ ቁጥር ያላት አገር ሆናለች። ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ የምትገኘው አርጀንቲና የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት በሚል የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ በሥራ አጥነት፣ በድህነትና በመንግሥት ዕዳ ላይ ተጨማሪ ጫናን ፈጥሯል።. በአገሪቱ ባለሀብቶች ላይ የተጣለው አዲሱ ግብር ከአጠቃላዩ ግብር ከፋይ 0.8 በመቶውን ብቻ የሚመለከት መሆኑን የግብሩን ደንብ ካረቀቁት ሰዎች መካከል አንዱ ተናግረዋል። ግብሩን ይከፍላሉ ተብለው የሚጠበቁት ሚሊየነሮች በአገር ውስጥ ካላቸው ሀብት እየጨመረ በሚሄድ ሁኔታ አስከ 3.5 በመቶ እንዲሁም በውጪ አገር ካላቸው ሀብት ደግሞ 5.25 በመቶ እንደሚሆን ተገልጿል። የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደዘገበው፤ በአዲሱ ግብር አማካይነት ከሚሰበሰበው ገንዘብ ውስጥ 20 በመቶው ለሕክምና አቅርቦቶች፣ 20 በመቶው ለአነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት ድጋፍ፣ 20 በመቶው ለተማሪዎች የነጻ ትምርት ዕድል ድጋፍ፣ 15 በመቶው ለማኅበራዊ ልማትና ቀሪው 25 በመቶው ደግሞ ለተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ሥራ ይውላል። በአዲሱ ታክስ አማካይነት በፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ የሚመራው የአርጀንቲና መንግሥት 300 የአርጀንቲና ፔሶ ወይም ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን ተቃዋሚዎች አዲሱ ግብር እንደተባለው የአንድ ጊዜ ብቻ ላይሆን እንደሚችልና የውጭ መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾችን ሊያሸሽ ይችላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። አንደኛው ተቃዋሚ ፓርቲ አዲሱን ሕግ ሀብት "የመውረስ" ድርጊት ሲል ተቃውሞታል።
news-51576545
https://www.bbc.com/amharic/news-51576545
የሌሴቶው ጠቅላይ ሚኒስትር በሚስታቸው ግድያ ተከሰሱ
የሰማኒያ ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት የሌሴቶው ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ የቀድሞ ሚስታቸውን በመግደል ወንጀል መከሰሳቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ በመጪው ሐምሌ ወር ላይ በእድሜ መግፋት የተነሳ ከስልጣናቸው እንደሚለቁ ጠቁመዋል። ቢሆንም ግን ስለግድያው ክስ ያሉት ነገር የለም። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሁኗ ባለቤት ሜሲያህ ታባኔ ቀደም ሲል ከግድያው ጋር በተያያዘ ክስ ተምስርቶባታል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የቀረበው ክስ በደቡብ አፍሪካ ተከባ የምትገኘውን የተራራማዋን የሌሴቶን ሕዝብ ያስደነገጠ ሲሆን፤ ክሱ በደቡባዊ አፍሪካ በስልጣን ላይ እያሉ በግድያ ወንጀል የተከሰሱ የመጀመሪያው መሪ ሆነዋል። ከሦስት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ከመረከባቸው ከሁለት ቀናት በፊት ነበር ግድያው የተፈጸመው ተብሏል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ ግድያውን "ጭካኔ" ሲሉ ገልጸውት የነበረ ሲሆን አሁን ግን በግድያው ውስጥ እጃቸው አለበለት በማለት ፖሊሰ ከሷቸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ነገ አርብ ክስ እንደሚመሰረትባቸውም ተገልጿል። ሟቿ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ሊፖሌሎ ታባኔ በዋና ከተማዋ ማሴሮ ዳርቻ ላይ ወደሚገኝ ቤታቸው ሲያቀኑ ነበር በቅርብ እርቀት በጥይት ተመትተው ተገድለው የተገኙት። በግድያው ወቅትም ግለሰቧ ከቀድሞ ባለቤታቸው ጋር ከበድ ባለ የፍቺ ውዝግብ ውስጥ እንደነበሩም ተገልጿል። በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከ42 ዓመቷ ሜሲያህ ጋር እንደሚስት አብረው እየኖሩ ነበር። ለአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የተመረጡት ታባኔ ሚስት ነኝ በማለት ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ሟች የአገሪቱ ቀዳማዊ እመቤት መሆናቸው ተወስኖላቸው ነበር። ነገር ግን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመተ በዓል ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ ባልታወቀ ሁኔታ ተገድለው ተገኝተዋል። ይህንንም ተከትሎ ሁለተኛዋ ሴት በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደሚስት ተገኝታ ነበር። ከሁለት ወራት በኋላ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሜሲያህ ዋና ከተማዋ ውስጥ በሚገኝ ስታዲየም ተዘጋጅቶ በርካታ ሕዝብ በታደመበት ድግስ በካቶሊክ ቤተክረስቲያን ሥርዓት ጋብቻቸውን ፈጽመዋል። ሜሲያህ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚስት ግድያ ክስ ቀርቦባት በዋስ ተለቃለች፤ እስካሁንም የቀረበባትን የወንጀል ክስ መፈጸም አለመፈጸሟን በሚመለከት ቃሏን አልሰጠችም።
news-49737849
https://www.bbc.com/amharic/news-49737849
"ሰውነቴ ወሲብ እንድፈጽም አይፈቅድልኝም'' የብዙ ሴቶች የጤና እክል
"ሰውነቴ ወሲብ እንድፈጽም አይፈቅድልኝም። ለማድረግ ስሞክር በስለት የመወጋት አይነት ህመም ነው የሚሰማኝ" የምትለው ሃና ቫን ዲ ፒር ''ቬጂኒስመስ'' የተባለ የጤና እክል አለባት።
ሃና ቫን ዲ ፒር ይህ የጤና እክል ሃናን ብቻ ያጋጠመ ሳይሆን፤ በመላው ዓለም የሚገኙ በርካታ ሴቶች የጤና ችግር ነው። ብዙ ያልተነገረለት ''ቬጂኒስመስ'' በሴቶች ላይ የሚከሰት የጤና እክል ሲሆን፤ ማንኛውም ነገር ወደ ብልት ሊገባ ሲል በፍርሃት ምክንያት ብልት አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች በድንጋጤ ሲኮማተሩ የሚፈጠር ነው። • ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል? • እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ''ደካማ ነው'' ተባለ ይህ የጤና እክል ያለባት ሴት ወሲብ ለመፈጸም ስትሞክር፤ የሰውነት አካሏ ከቁጥጥሯ ውጪ በመሆን የወንድ ብልት ውስጧ እንዳይገባ በመኮማተር ይከለክላል። ይህ ብቻ ሳይሆን በማህጸን ምርመራ ጊዜ፣ አነስተኛ ቁሶች ወደ ብልት እንዳይገቡ ሊከላከልም ይችላል። "ተመሳሳይ የጤና ችግር ካለባቸውን ሴቶች ጋር ተገናኝቼ ተወያይቼያለሁ። ሁላችንም አንድ አይነት ስሜት ነው የምንጋራው" ስትል ሃና ትናገራለች። የጤና እክሉ ተጠቂ የሆኑ አንዳንድ ሴቶች ወሲብ መፈጸም ይቅርና በወር አበባ ወቅት ጥቅም ላይ የሚውል ከጥጥ የተሠራ ሹል የንጽህና መጠበቂያ ለማስገባት እንደሚቸገሩ የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። አሁን የ21 ዓመት ወጣት የሆነችው ሃና፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ለመፈጸም ስትሞክር የተሰማትን ሰሜት ታስታወሳለች። "ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ሲፈጸም ህመም እንዳለው አስብ ነበር። በዚያ ወቅት የተሰማኝ ስሜት ግን በቢላዋ የመወጋት አይነት ህመም ነው'' በማለት ታስዳለች። ተመሳሳይ የጤና እክል ያለባቸው ሴቶች "በስለታማ ነገር የመቆረጥ ወይም በመርፌ የመወጋት አይነት ሰሜት አለው" በማለት ወሲብ ለመፈጸም ሲሞክሩ የሚሰማቸውን ህመም ያጋራሉ። ይህ የጤና አክል ያለባቸው ሴቶች ይህን መሰል ንጽህና መጠበቂያ መሳሪያ ወደ ብልት ውስጥ ለማስገባት ይቸገራሉ። የማህጸን ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ለይላ ፍሮድሻም፤ ስለዚህ የጤና እክል ሰዎች በግልጽ እንደማይወያዩ ያስረዳሉ። "ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ መፈጸም ሊያስፈራ ይችላል። ሁላችንም ያለፍንበት ጭንቀት ነው። "ቬጂኒስመስ" ያለባቸው ሴቶች ግን ሁሌም ጭንቀቱ አለባቸው" ይላሉ ዶ/ር ለይላ። • ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል? በ20ዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኘው አሚና ይህ የጤና እክል ሕይወቷን ባላሰበችው አቅጣጫ እንደቀየረው ትናገራለች። "ቬጂኒስመስ ትዳሬን ነጥቆኛል። ልጅ መቼ ልውልድ? የሚለውን ምርጫዬን ወስዶብኛል" ''ቬጂኒስመስ'' መቼ እና እንዴት ሊከሰት ይችላል? "ቬጂኒስመስ" በማንኛው የዕድሜ ክልል ያለችን ሴት ሊያጋጥም ይችላል። አንዲት ሴት ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ለመፈጸም ሞክራ ሳይሳካ ሲቀር ይህ የጤና እክል ሊያጋጥም ይችላል። ከወሊድ በኋላ ሊከሰት ይችላል። አንዲት ሴት ማርገዝ የምትችልበትን እድሜ ስታልፍ ሊያጋጥምም ይችላል። • ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን? ዶ/ር ለይላ ይህም ብቻ ሳይሆን የአስተዳደግ ሁኔታ ለዚህ የጤና እክል ሊያጋልጥ ይችላል ይላሉ። " 'የሰርግሽ ዕለት ወሲብ ስትፈጽሚ ህመም ይኖራል' ወይም 'ድንግልናን ለማረጋገጥ ደም መታየት አለበት' የሚሉ አመለካከቶች ለዚህ የጤና እክል ይዳርጋሉ" ይላሉ። ባለሙያዎች ለዚህ የጤና እክል ስልጠናዎችን እና የወሲብ የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣሉ "የተማርኩት በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ወሲብ መፈጸም ብዙ ደም መፍሰስ፣ እርግዝና ወይም በሽታ እንደሚያስከትል ነው የተነገረኝ" የምትለው ሃና ቫን ድ ፒር ነች። ሌላዋ የዚህ የጤና እክል ተጠቂ ኢስለይ ሊን፤ "ቬጂኒስመስ" ለአእምሮ ጭንቀት ዳርጓታል። "የሕይወት አጋሬ ከእሱ ጋር ወሲብ መፈጸም እንደማያስደስተኝ ያስብ ይሆን? እያልኩ እጨነቃለሁ። እሱን እንደማልወደው እና ከእሱ ጋር ወሲብ መፈጸም እንደማልፈልግ ነው የሚያስበው" ትላለች። ሃና እና አሚና ካጋጠማቸው የጤና እክል ለመዳን ስልጠናዎችን እና የወሲብ የምክር አገልግሎቶችን እየወሰዱ ይገኛሉ። አሚና "የወሲብ የምክር አገልግሎት እና ስልጠናዎችን መውሰድ ከጀመርኩ በኋላ በራሴ ላይ ለውጥ እየተመለከትኩ ነው" ትላለች። ሃና በበኩሏ የህክምና ድጋፉ ለውጥ ቢያመጣላትም የምትፈልገውን አይነት ለውጥ ግን እስካሁን እንዳላየች ትናገራለች። "በወሲብ እርካታን ማግኘት እሻለሁ። እዚያ ደረጃ እስክደርስ ድረስ ንጽህና መጠበቂያውን ወደ ውስጥ ለማስገባት በመሞከር እቆያለሁ" ትላለች።
news-47717659
https://www.bbc.com/amharic/news-47717659
አሥመራ፡ ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ
ጦርነትና ከዓለም መድረክ መነጠልን ጨምሮ በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች ታስቦባቸው ባይሆንም ኤርትራን ለብስክሌትና ለብስክሌተኞች ምቹ ስፍራ እንድትሆን አድርጓታል።
• አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ • ጉዞ ከአዲስ አበባ ወደ አሥመራ በፎቶ አሥመራ 500 ሺህ ብቻ ነዋሪዎች ሲኖሯት ዝቅተኛ ደሞዝ፣ ከፍተኛ ቀረጥና የነዳጅ እጥረት ከተማዋ ትንሽ ተሽከርካሪ እንዲኖራት ምክንያት ናቸው። ብዙ ጊዜ የሚታዩት ሰዎችም በተለየ የእድሜ ክልል ውስጥ ናቸው። የአሥመራ መንገዶች በአንፃራዊነት ከመኪና ብቻ አይደለም ነፃ የሆኑት። ሃገሪቱ ዜጎች እንደሚሉት ኤርትራዊያን ባለፉት 20 ዓመታት አካባቢያዊ ግጭት በፈጠረው ጫናና የግዳጅ ብሔራዊ አገልግሎትን ሸሽተው በርካታ ወጣቶች ሃገራቸውን ጥለው ተሰደዋል። አሥመራ በተለያዩ ምክንያቶች በመኪና ከተጨናነቁ ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች የተለየ መልክ አላት። ይህ አስገራሚ ከሆነው የከተማዋ አየር ንብረት ጋር ተጨምሮ ብስክሌተኞች በከተማዋ እንዲያንዣብቡ ድንቅ ስፍራ ሆናለች። የ25 ዓመቱ ወጣትም "ብስክሌት መጋለብ አንዱ ባህላችን ሆኗል" በማለት ይገልፃል። የአሥመራ የኪነ ሕንፃ ስብስብም በቅርብ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን እ.አ.አ. ከ1897 እስከ 1943 የቆየው የጣልያን ቅኝ ግዛት ትሩፋቶች ነው። የብስክሌት መጠገኛ ሱቆች አሥመራ ውስጥ በስፋት ይገኛሉ። ከ30 ዓመታት ጦርነት በኋላ ከኢትዮጵያ ተነጥላ ሉዓላዊት ሃገር የሆነችው ኤርትራ ከነጻነት በኋላ በገጠማት ከዓለም አቀፍ ግንኙነት መገለል ምክንያት ብስክሌትም ሆነ የመለዋወጫ አካላትን ወደ ሃገሪቷ ማስገባት እጅግ በጣም ውድ እንዲሆን አድርጎታል። ኤርትራዊያን በቀለምም ሆነ በዓይነታቸው የተለያዩ ዓይነት ብስክሌቶችን ይነዳሉ። የተራራ ብስክሌቶች፣ የከተማ ብስክሌቶችና የውድድር ብስክሌቶች ይጠቀሳሉ። ኤርትራዊያን ከህፃን እስከ አዋቂ፣ ሴቶችና ወንዶች፣ አትሌቶችና የቤት እመቤቶች ሁሉም ብስክሌትን ተላምደዋል። የህዝብ አውቶብስ የሚጠቀሙ ነዋሪዎች ከመጠን በላይ የተጨናነቀው አውቶብስ ላይ ከመግባታቸው በፊት ለረጅም ሰዓታት ቆመው መጠበቅ አለባቸው። "አውቶብሶች በጣም ጥቂትና ያገጁ ናቸው። በአስመራ ብስክሌት ህይወትን ነው የሚያድነው" ትላለች የ30 ዓመቷ ሰላም። መንግሥት የአካባቢ ጥበቃን ለረጅም ጊዜ ሲቀሰቅስ ቆይቷል። የፕላስቲክ ምርትንና አጠቃቀምን መቀነስ፣ ደንን ማልማት፣ የሃገሪቷን አረንጓዴ ቦታዎች መንከባከብና የቻይናና የዱባይ ብስክሌቶችን መጠቀም ከወሰዳቸው አንዳንድ እርምጃዎች መካከል ናቸው። ለብዙ ኤርትራዊያን መኪኖች ቢኖሩ እንኳን እንደ ብስክሌት ዋጋ ተመጣጣኝ አይደሉም። ከኢትዮጵያ ጋር በቅርብ በተደረገው የሰላም ስምምነት አማካኝነት ድንበሩ በ20 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከፍቷል። አሁን ርካሽ የኢትዮጵያ ሸቀጣ ሸቀጦች በሃገሪቷ ሙሉ ይሸጣሉ፤ ይህም የኑሮ ውድነቱን እያቀለለ ነው። የግጭት፣ ከዓለም መገለልና የተባበሩት መንግሥታት ማዕቀብ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ባለፈው ህዳር ቢያበቁም፤ በኤርትራ አሁንም የብዙ ምርቶች እጥረት አለ። የነዳጅ እጥረት መኪኖች ለረጅም ሰዓታት እንዲቆሙ በማድረግ ሰዎች በእግራቸው ከመሄድና ብስክሌት ከመንዳት ሌላ ብዙ ምርጫ እንዳይኖራቸው አድርጓል። ብስክሌት መንዳት በኤርትራዊያን ዘንድ በጣም የታወቀ ስፖርት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በጣልያዊያን የተዋወቀው የብስክሌት ውድድር ለኤርትራ ህዝብ የኩራት ምንጭ ነው። ሞሳና ድበሳይን ያካተተው የሃገሪቱ ብሔራዊ ቡድን በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች በጣም ስኬታማ ነው። በቅርብ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገው ግንኙነት ብዙ ኤርትራዊያን የሃገራቸው ኢኮኖሚ በፍጥነት እንደሚያድግና የዕለት ከዕለት ኑሯቸውን እንደሚያቀልላቸው ተስፋ ያደርጋሉ። በአንትሮፖሎጂስት ሚሊና ቤሎኒ እና በጋዜጠኛ ጄምስ ጄፍሪ
54032416
https://www.bbc.com/amharic/54032416
"የኤምባሲ ሠራተኞችን ደህንነት አደጋ ላይ መጣል ወንጀል ነው" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ 'የኤምባሲ ሠራተኞችን ደህንነት አደጋ ላይ መጣል 'ተራ ወንጀል ነው' ብለዋል።
ከሰሞኑ ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለተቃውሞ በተሰበሰቡ ሰልፈኞች የአገሪቱ ባንዲራ እንዲወርድ መደረጉና በኤምባሲው ሠራተኛ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል። «በቪዬና ኮንቬንሽን መሠረት የኤምባሲዎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት በዋናነት የአስተናጋጁ ሃገር ነው» ብለዋል ቃል አቀባዩ። «ችግር ተፈጥሮባቸዋል ከተባሉ ኤምባሲዎች አምባሳደሮች ጋር ተግባብተናል፤ አስፈላጊውን ነገር እንደሚያደርጉም ቃል ገብተውልናል» ሲሉ ከዲፕሎማቶች ጋር ውይይት እንዳደረጉ ቃል አቀባዩ አሳውቀዋል። አምባሳደር ዲና፤ ዜጎች በየትኛውም ሃገር ሆነው ተቃውሞ የማድረግ መብት አላቸው ይላሉ። «ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፤ በፅሑፍ ሐሳብን ማቅረብ ወዘተ. . . ነገር ግን ከዚያ ባለፈ የኤምባሲዎችንና ዲፕሎቶችን ደህንነት 'ትሬትን' [አደጋ ላይ መጣል] ተራ ወንጀል ነው። የዲሞክራሲ መብት መገለጫ አይደለም።» ቃል አቀባዩ ከለውጡ ጋር ተያይዞ «በሠለጠነ መንገድ ተቃውሞ መግለፅ ይቻላል፤ ይህ የመንግሥት ፅኑ አቋም ነው» ሲሉ ተደምጠዋል። የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለንደን ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባጋጠመው ክስተት አዲስ አበባ ውስጥ ላሉ የብሪታኒያ ኤምባሲ ከፍተኛ ባለስልጣን በይፋ ቅሬታቸውን ማቅረባቸው ይታወሳል። አምባሳደር ሬድዋን ኤምባሲው ላይ ስለተከሰተው ነገር በኢትዮጵያ የታላቋ ብሪታኒያና የዩናይትድ ኪንግደም ቻርጅ ዲ አፌር ለሆኑት አሌክስ ካሜሩን ነው ቅሬታቸውን ያቀረቡት። በአረብ ሃገራት ያሉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ጉዳይ አምባሳደር ዲና በአረብ ሃገራት በስደት ላይ ያሉ ኢትዮጵያንን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ትላንት [ሐሙስ] ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው ያወጣውን መግለጫ ዋቢ በማድረግ መንግሥት ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ባለፉት ወራት 3500 ዜጎች ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ መደረጉንም ቃል አቀባዩ አውስተዋል። ቃል አቀባዩ በተደጋጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከውጭ ሃገር ሲመለሱ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን በቻርተር አውሮፕላን ሁላ ወደ ሃገር ቤት እየመለሱ መሆኑ የመንግሥትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከሰሞኑ የተለያዩ የመብት ተሟጋቾች ቡድኖች ሳዑዲ አራቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያ ሰቆቃ በተሞላበት መንገድ ነው በስደተኛ ካምፖች ውስጥ የሚኖሩት የሚል ዘገባ አውጥተው የኢትዮጵያ መንግሥት ተገቢውን እርምጃ አልወሰደም ሲሉ ወቅሰዋል። ቃል አቀባዩ ግን መንግሥት ስደተኞቹን ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ የተቻለውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
41684080
https://www.bbc.com/amharic/41684080
ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ተመለስዉ በመሄድ ላይ ናቸው
ወጣት አባዲ ባደገበት መንደር 'እነ እገሌ ሣኡዲ አረቢያ ሄደው አለፈላቸው' የሚለውን ተደጋጋሚ ወሬ ሲሰማ ነው ያደገው። እናም እሱም እንደ ሌሎቹ 'አልፎለታል' ተብሎ እንዲወራለት የየመን በረሃን አቋርጦ ሳዑዲ አረቢያን የረገጠው የስምንተኛ ከፍል ተማሪ ሳለ ነበር።
የ18 ዓመት ወጣት ሆኖ በብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ዘንድ ጥሩ ገንዘብ የሚገኝባት ሃገር ተደርጋ ወደምትታሰበው ሳዑዲ አረቢያ የተጓዘው አባዲ፤ ነገሮች እንዳሰባቸው ሳይሆኑ የረገጣት ጅዳ ወህኒ ቤት አዘጋጅታ ጠበቀችው። ጅዳ ወህኒ ቤት ውስጥ ለሦስት ዓመታት በታሰረበት ወቅትም ብዙ ስቃይ እና መከራ እንዳሳለፈ የሚናገረው ወጣቱ አብዲ፤ የሌሎች ሃገር ዜጎች በኤምባሲዎቻቸው አማካኝነት የጤና ሁኔታቸው እና የፍርድ ቤት ጉዳያቸው ክትትል ሲደረግላቸው ኢትዮጵያውያን ግን አንድም ጠያቂ እንዳልነበራቸው ያወሳል። ከዚህ የተነሳም በወህኒ ቤቱ ታስረው የነበሩት ኢትዮጵያውያን 'ለመሆኑ ሃገር አለን ወይ?' እስከ ማለት ደርሰው እንደነበር ይገልጻል። አባዲ 'ምንም እንኳ ህገወጥ ስደተኞች ብንሆንም እንደ ዜጎች ግን ከኤምባሲያችን አስፈላጊው ክትትል ሊደረግልን ይገባ ነበር' ባይ ነው። ቢቢሲ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ማብራርያ ለመጠየቅ ሳዑዲ አረቢያ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደጋጋሚ ቢደውልም ሳይሳካ ቀርተዋል። 'በቴሌቭዥን የሚወራ ውሸት ነው' ተክሊት ብርሃነም ሌላኛው በለጋ እድሜው ሣኡዲ አረቢያን የረገጠ ኢትዮጵያዊ ነው። በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት አዋጅ መሰረትም ሀገሪቱን ለቆ ኢትዮጵያ ከተመለሱት መሃከል ነው። ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ መንግሥት በመገናኛ ብዙሃን አመካኝነት ለተመላሾቹ የተለያዩ የሥራ እድል እና የብድር አገልግሎት እንደሚሰጥ የተነገረውን ተስፋ አድርጎ ሀገሩ መግባቱን ይናገራል። ወደ ትውልድ ስፍራው ተጉዞ ያገኘውን ግን ተስፋ አስቆራጭ እንደነበር ለቢቢሲ በሰጠው ቃለመጠይቅ ገልጿል። አንድም የመንግሥት አካል ያነጋገረው እንደሌለ እና በቴሌቭዥን የሰማቸው የመንግሥት ሃሳቦችን መሬት ላይ አላገኛቸውም። ምንም እንኳ ተመልሶ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ቢገባ ህይወቱ አጣብቂኝ ውስጥ እንደምትወድቅ ቢረዳም፤ ከዚህ በፊት ያለፋቸውን አደገኛ የጉዞ ውጣ ውረዶች አልፎ ተመልሶ ሳዑዲ አረቢያ መግባቱን ይናገራል። ከዚህ የተነሳም ተክሊት 'ቴሌቭዥን ላይ የሚወሩት ወሸት ናቸው' ይላል። በአዋጁ ምክንያት ወደ ሃገሩ ያልተመለሰው እና ተክሊት ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንዲገባ ለደላሎች 13 ሺህ ብር መክፈሉን የሚናገረው ታላቅ ወንድሙ ፍስሃ፤ ሌሎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰው የነበሩት ሁለት እህቶቹ ተመልሰው ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት በየመን በረሃ እንደሚገኙ ይናገራል። በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንደሚባለው፤ ፍስሃ የመን ላይ በደላሎች ተይዘው የሚገኙ እህቶቹን ለማስለቀቅ በአማካይ እስከ 50 ሺህ ብር መክፈል እንደሚጠበቅበት በመግለጽ ሁኔታው አጅግ እንዳስጨነቀው በምሬት ይገልጻል። ተመላሾቹ ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ተጨማሪ እድሜያቸው 18 ያልደረሱ ልጆችን ሳይቀር ይዘው በመንገድ ላይ ናቸው። በዚህም ሳቢያ ደግሞ የኢትዮጵያውያን ህይወት በየመን እና በሳዑዲ አረቢያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ስደተኞቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሃገር ቤት ስላለው ሁኔታ እየደወሉ እነደሚጠይቁ እና ተስፋ የሚሰጥ ነገር በማጣታቸው፤ ላለመመለስ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን እነዚህ ወጣት ስደተኞች የይገልፃሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ በሀገር ደረጃ ያለውን አንድምታ ለመጠየቅ ጉዳዩ ወደሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ብንደውልም ሳይሳካ ቀርቷል። የእኛ ይብሳል! በሳዑዲ ጂዛን አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ መጨረሻቸውን የማያውቁ ኢትዮጵያውያን እስረኞች እንደሚገኙ የሚናገረው ወጣት አባዲ፤ ስደተኞች በየቀኑ ግርፋት እና ግድያ እንደሚደርሳቸው ለቢቢሲ ተናግሯል። 'አሁን በስልክ ሳናግርህ ራሱ ሀዘን ላይ ተቀምጠን ነው' የሚለው አብዲ በቅርቡ አንድ ኢትዮጵያዊ በሳዑዲ አረቢያ ታጣቂዎች ተገድሎ አስከሬኑን ወደ ሀገር ቤት ለመላክ ብር በማዋጣት ላይ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ተስፋ ስላጡ እንጂ የስደት ኑሮን ወደዉት እንዳልሆነ የሚናገሩት ወጣቶቹ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወት በየበረሃው እየተቀጨ መሆኑን በጥልቅ ሀዘን ይናገራሉ። ይህ ጉዳይ ፈጣን ምላሽ የሚያሻው ነው፤ በማለት የሁኔታው አሳሳቢነት የሚገልጹት ወጣቶቹ 'የሀገራችን መገናኛ ብዙሃን ስለ የኤርትራውያን ስደት ያወራሉ እንጂ፤ ችግሩ እኛ ላይ ይብሳል' ብለዋል። ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በርካታ ወጣቶች ሥራ ወደ ሳዑዲ አረቢያ እና ሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት በአደገኛ መንገድ ተጉዘው ለችግር ይዳረጋሉ። በህገወጥነት ተመልሰው የመጡት ሳይቀር ተመልሰው ወደ መጡበት እየተጓዙ ነው።
news-54437954
https://www.bbc.com/amharic/news-54437954
ለሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን ኢትዮጵያዊነትና ኦሮሞነት ምንና ምን ናቸው?
ግጥም፣ ተውኔት ሲጽፍ የልቡን ቀለም እየቀባ ያቀርባል። ስለ ሕዝብ፣ ስለ አገር፣ ስለ ወንዝ፣ ስለ ስልጣኔ፣ በአጠቃላይ ያመነበትን እውነት በቅኔ ወደ ብርሃን ያወጣል።
በጥልቁ ያሰላስላል፤ ምናቡም ሩቅ ነው። ሎሬቱን ራሱ በጥበብ ተጠቅልሎ ለትውልድ የተላለፈ ቅርስ ነው እያሉ የሚያሞጋግሱት በቅርብ የሚያውቁት ብቻ ሳይሆን በሥራዎቹ በፍቅር የወደቁ እና በፍቅር ያጣጣሙት ጭምር ናቸው። . . .የማይድን በሽታ ሳክም የማያድግ ችግኝ ሳርም የሰው ሕይወት ስከረክም እኔ ለእኔ ኖሬ አላውቅም. . . በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፉ ከ30 በላይ ተውኔቶችን ጽፏል።'እሳት ወይ አበባ' የግጥም መድብሉ ሲሆን፣ 'ሀሁ በስደት ወር'፣ 'እናት ዓለም ጠኑ'፣ 'የከርሞ ሰው'፣ 'መልዕክተ ወዛደር'፣ 'ሀሁ ወይንም ፐፑ'፣ 'የመቅደላ ስንብት' የተሰኙ ደግሞ ከተውኔቶች መካከል የተወሰኑት ናቸው። ሐምሌትና ማክቤዝ፣ ደግሞ ከእውቁ ዊሊያም ሼክስፒር ወደ አማርኛ ከመለሳቸው ስራዎቹ መካከል ናቸው። እነዚህ የጥበብ ሥራዎች ፀጋዬ በአገር፣ በብሔርተኝነትና በማንነት ላይ ያለውን አቋም ያሳዩ ይሆን? ለዚህ ጥበበኛ ኢትዮጵያዊነትና ኦሮሞነት ምንና ምን ናቸው? አቶ ሚካኤል ሽፈራው በሙያው ሥነ ሕንጻ ባለሙያ ሲሆን፣ የፀጋዬን በክብር እንደሚወደውና እንደሚያነበው ይናገራል። ከስራዎቹ አንዱንም በመተንተን መጽሐፍ አሳትሟል። መጽሐፉ 'ምስጢረኛው ባለቅኔ' ይሰኛል። ፀጋዬ በቅኔ እና በምሳሌ ስለሚጽፍ ያኔ ሰው አይረዳም ነበር ይላል። አቶ ሚካኤል፣ ፀጋዬ በመጨረሻዎቹ ዘመናት የጻፈውን 'ሀሁ በስድስት ወር'፣ ምዕራፍ በምዕራፍ ትርጉም ለመስጠት ሞክሯል። ከዚህም በተጨማሪ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ለሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን ማስታወሻነት እየተገነባ ያለውን ማዕከል ዲዛይን በማድረግ በነጻ እያገለገለ ነው። "ማንም የፍፁም እውነት ባለቤት አይደለም" ሎሬት ፀጋዬ ስለ አንድ ነገር በጭራሽ በእርግጠኝነት አይናገርም። በቡድንም አያስብም። ከኢትዮጵያዊነትም ከኦሮሞነት የሚበልጠውን እውነት ሊያሳየን ይሞክራል ይላል አቶ ሚካኤል። በዚህ በተነተነው የፀጋዬ ተውኔት ውስጥ፣ ሁለት ሰዎች እግራቸውና እጃቸው አንድ ላይ ተጠፍሮ ነው የሚጀምረው። ይህም የአንድ እናት ልጆች መሆናቸውን ለማሳየት የተጠቀመው ምሰላ (ሲምቦሊዝም) መሆኑን ያስረዳል። ይኹን እንጂ እነዚህ ሰዎች ወዲያው መጣላት ይጀምራሉ። አትተያዩም፤ አትደማመጡም እንጂ እውነት አንድ ቦታ የለችም እያለ ያን ዘመን በፖለቲካ አቋማቸው ለሚጣሉ ፖለቲከኞች ይናገራል። ይሁን እንጂ ፀጋዬ "ይህ ተጎድቷል፤ ያ ጎድቷል በሚል መፍትሄ አይሰጥም" እንደውም ፀጋዬ ለዚህ ሕዝብ መፍትሔ ነው ብሎ የሚያስበው፣ መንቃት፣ አይንን መክፈት እና ማወቅ ነው ይላል አቶ ሚካኤል። አንዱ ቡድን ስለሌላው ቡድን ማወቅ፣ መመራመር ከቻለ ሁለቱ ብርሃኑ ውስጥ ይገናኛሉ ይላል። ለእርሱ መንቃት ማለት ታሪካችንን ማወቅ፣ ያወቅነው እውቀት ጎዶሎ መሆኑን መረዳትን ይጨምራል። ፀጋዬ ገብረ መድህን ማን ነው? ፀጋዬ አምቦ ቦዳ የሚባል አካባቢ ተወለደ። እናቱ በጣሊያን ጊዜ ሸሽተው ነው ከአባታቸው ጋር ጎረምቲ የምትባል አካባቢ የሄደው። አባቱ የሜጫ ኦሮሞ ሲሆኑ፣ እናቱ ደግሞ የአንኮበር አካባቢ አማራ ነው። እናቱ ወ/ሮ በለጠች ታዬ አምቦ ከማህበረሰቡ ጋር በፍቅር ነበር የሚኖሩት፣ ከባላቸው እህት፣ ወ/ሮ አርገቱ ጋር ደግሞ የጠበቀ ወዳጅነት ነበራቸው። እናቱ ወንድ ልጅ ለማግኘት ለአቦ ቤተክርስትያን ስለት አስገብተው ፀሎት ሲያደርጉ፣ በእምነታቸው ዋቄፈቱ የነበሩት ወ/ሮ አርገቱም ለወዳጅነት ሲሉ አብረው ይፀልዩ ነበር ይላል አቶ ሚካኤል። ሎሬት ፀጋዬ በኦሮምኛ ነው አፉን የፈታው። በኋላም የጣልያን ወረራ ጊዜ ከአንኮበር ሸሽተው የመጡት የእናታቸው ወንድሞች ግዕዝን አስተማሩት። አባቱ ደግሞ ዘመናዊ ትምህርት አስገቧቸው። በኋላ ላይ ነው ጄነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት የዊሊያም ሼክስፒርን ጠነን ያለ እንግሊዝኛን ነበር የተማረው። አባቱ ሹመት እናቱ ደግሞ ክህነት ይመኙለት ነበር። ስለዚህ የዚህ ሰው ማንነት በራሱ ውስጥ አንዴ ሲዋደድ አንዴ ሲጣላ በአገር ደረጃ አይተነዋል። የእናቱን ፍላጎት ለመሙላት፣ ከካህናት ጋር ይውል ነበር። እነርሱን ደግሞ ይተውና ከሹማምንት ጋር ይሄዳል። በዚያው ቀርቶ አይቀርም ተመልሶ ሲጽፍ ይታሰራል። ስራዎቹም አንዳንዴ ይታገዱበት ነበር ይላል አቶ ሚካኤል ሽፈራው። ስለ አገር ማወቅ የሚፈልገውን እውነት ፀጋዬ፣ ከውጪ ሳይሆን ከውስጡ ለማግኘት ይለፋ ነበር። ኢትዮጵያን መከፋፈል ደሜን ማፍሰስ ነው ብሎ ያምን ነበር። ይህ ሰው በኢትዮጵያዊነቱ ልቆ ይሂድ እንጂ የዓለም ዜጋ ነው። የእውቁን ፀሀፊ ዊሊያም ሼክስፒርን፣ ጠነን ያለ እንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ቢተረጉምም፣ ብዙ ጊዜውን ያዋለው ግን ኢትዮጵያዊ የሆኑ ሥራዎቹ ላይ ነው። ለእርሱ ኦሮሞነትና አማራነት ፍፁም ተጋጭተውበት አያውቁም። እንዲያውም ወደ ጥናትና ጥበብ ይቀይራቸዋል። ይኹን እንጂ ፍትህ ሲጎድል ደግሞ ዝም ብሎ የሚመለከት አይደለም። ለምሳሌ 'ይድረስ ለወንድሜ ለምታውቀኝ ለማላቅህ' የሚለው ስራ የብሔር ብሔረሰቦች ጭቆና የሚያትት ነበር። ሎሬቱ ብሔርተኛ ነበሩ? በሚኒሶታ ኖርዝ ዌስተርን ዩኒቨርስቲ የሥነጽሑፍ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ተፈሪ ንጉሤ፣ ፀጋዬ ገብረ መድህን የፓን አፍሪካ ብሔርተኝነት ያቀነቅን ነበር ይላሉ። እይታውና ፍልስፍናው ከጥቁር ሕዝቦች ማንነት ይመነጫል። ኦሮሞነቱንም ካየነው ኦሮሞ ከኩሽ ሕዝቦች አንዱ ነው ብሎ ስለሚያምን እነርሱ ደግሞ የስልጣኔ ጀማሪዎች ናቸው ይላል። እርሱ የሚዘምርለት ኢትዮጵያዊነት፣ ኦሮሞ የሚፈልገው አይነት ነው ይላሉ ዶ/ር ተፈሪ። ይሄንን ደግሞ በጽሑፎቹ ውስጥ በግልጽ ታይቷል። እሳት ወይ አበባ በሚለው የግጥም መድብል ውስጥ፣ አቴቴ ዱብራ ኦሮሞ በኔና በአንቺ መሃል አጉል ስልጣኔ ቆሞ የሚሉት መስመሮች ተምረናል የሚሉ ሰዎች እንዴት ራሳቸውን እንደሚክዱና ሕዝብን እንደሚበድሉ ይናገራል። በትያትር በኩልም አርሶ አደሩን ባላባቱ (ባለመሬቱ)፣ እንዴት አድርጎ እንደሚበድል በጥልቀት አሳይቷል። በብዛት በኦሮምኛ አልጻፈም ማለት ብሔርተኛ አይደለም ወይንም በማንነቱ አይኮራም ማለት አይደለም። ምክንያቱም እርሱ ኦሮሞ ለዓለም እንዴት መተዋወቅ አለበት ብሎ የሚያስበው ነው በማንነቱ የሚኮራ የሚያደርገው። ለምሳሌ በእንግሊዘኛ የተጻፈው 'ኦዳ ኦፍ ኦራክል' የሚለው ስራው፣ የኦሮሞ ምልክት የሆነውን ኦዳን መጠቀሙ በራሱ በማንነቱ እንደሚኮራ የሚያሳይ ነው። እርሱ በኖረበት ዘመን የነበሩ መንግሥታት ማነነታቸውን ከሰለሞን ግንድ ቢመዙም እርሱ ግን ሁሌም በጥቁርነቱ እንደ ኮራ ነው። አድዋና ቴዎድሮስ የሚሉ ሥራዎቹም ሲታዩ በጥቁር ማንነት የተቃኙ ናቸው። ስለዚህ ፀጋዬ ጥበብን ለጥበብነቱ ብቻ ሳይሆን ለማህበራዊ ለውጥና ባህልን ለማስተዋወቅ ተጠቅሞበታል። ፀጋዬ ገብረመድህን እኤአ በ1998 ኢትዮጵያ ሪቪው በተባለው መጽሔት ላይ በታተመ ቃለምልልሱ ላይ ኢትዮጵያዊነት ለአንተ ምንድን ነው ተብሎ ተጠይቆ ነበር። ለሎሬቱ ኢትዮጵያዊነት የአፍሪካን ታሪክ፣ ስልጣኔና ባህል የሚረዳ፤ እንዲሁም የዓለምን ስልጣኔ፣ ባህል እኩልነትና ወንድማማችነት ጠንቅቆ የሚገነዘብ ነው። ሎሬቱ አክሎም፣ "ስለዚህ እኛ ለትምህርት አሜሪካ እንደምንሔደው፣ እነርሱም [አሜሪካውያን] ግብዝነታቸውን ትተውና ዝቅ ብለው ከቀደምት የሰው ዘሮች ምድር ለመማር መምጣት አለባቸው። ለኔ ኢትዮጵያዊነት ያ ነው" ብሎ ነበር።
news-54790568
https://www.bbc.com/amharic/news-54790568
የአሜሪካ ምርጫ፡ ምን ዜና ልንሰማ እንችላለን?
በስተመጨረሻም እንዳይደርሱት የለ ጊዜው ደርሷል። የመጨረሻው መጨረሻ። በጉጉት የተጠበቀው የአሜሪካ ምርጫ ቁርጡ ሊለይለት ነው።
የዘንድሮው ምርጫ እንደሌሎቹ ጊዜዎች አይደለም። ግራ አጋቢ ዜናዎች የተሰሙበት፣ የሚጠብቁት ቀርቶ የማይጠብቁት የሚሆንበት ነው የዘንድሮው። የአሜሪካ ምርጫ ልክ እንደ ሃብታም ድግስ አንድ ቀን የሚበቃው አይደለም። መራጮች ድምፅ መስጠት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ከ90 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ድምፃቸውን እኮሮጆው አስገብተዋል። . ጆ ባይደን ማን ናቸው? . በአሜሪካ ፕሬዘዳንት የሚመረጠው እንዴት ነው? . ከነገ በስትያ አሸናፊው በሚለየው የአሜሪካ ምርጫ በሕዝብ አስተያየት ማን እየመራ ነው? ታድያ ስለ አሜሪካ ምርጫ ምን ዓይነት ዜና ይጠብቀን ይሆን? ሶስት ተጠባቂ ዜናዎች አሉ። አንደኛ፡ ባይደን በቀላሉ አሸነፉ የአሜሪካ ምርጫ በቅድመ ትንበያ የተሞላ ነው። የግል ድርጅቶችና መገናኛ ብዙሃን ሕዝቡን 'እንደው ማንን ለመምረጥ አስባችኋል?' ብለው ይጠይቁና ውጤት ይተንብያሉ። በዚህ ቅድመ ትንበያ መሠረት ባይደን የአሜሪካውን ምርጫ ተደላድለው ማሸነፍ አለባቸው። ነገር ግን ባለፈው ምርጫ እንዲሁ ትንበያ ወጥቶ ሂላሪ ክሊንተን ያሸንፋሉ ቢባልም ውጤት ሲመጣ ግን ብዙዎች ያልጠበቁት ሆኗል። ቢሆንም የዘንድሮው ትንበያ ከባለፈው ጊዜ በተለየ ፍፁም ነው የሚሉ አልጠፉም። ትንበያው ባይደንን በሃገር አቀፍ ደረጃ አናት ላይ አስቀምጧቸዋል። እንግዲህ ይህን መሠረት አድርገን ልንሰማቸው ከምንችላቸው ዜናዎች አንዱ ይህ ነው ብንል ማበል አይሆንም። ሁለተኛ፡ ትራምፕ በአስደንጋጭ ሁኔታ አሸነፉ ለምን በአስደንጋጭ መልኩ ካሉ ምክንያቱም ትንበያው የሚለው ሌላ ስለሆነ እንሎታለን። የአሜሪካ ዜና አውታሮች ትራምፕ ምርጫውን ከረቱ 'ቅድመ ትንበያው አሁንም ተሳስቷል' ከማለት የሚቆጠቡ አይመስሉም። ትራምፕ በፍሎሪዳና ፔኒሲልቬኒያ ግዛቶች ማሸነፍ ከቻሉ ሁኔታውን ለጆ ባይደን ሊያከብዱባቸው ይችላሉ። ትራምፕ፤ እንደውም ከባለፈው ምርጫ በተሻለ በላቲን አሜሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት አላቸው እየተባለ ነው። ይህ ደግሞ ፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ ትልቅ ሃብት ነው። በሌላ በኩል ፔኒሲልቬኒያ ግዛት በርካታ ነጭ ሠራተኛ መደብ ሰዎች የሚኖሩባት ስለሆነች ለትራምፕ አደጋ ልትሆን ትችላለች። ሶስተኛ፡ ጆ ባይደን በሰፊ ልዩነት አሸነፉ እርግጥ ነው ቅድመ ትንበያው ጆ ባይደን ያሸንፋሉ ይላል። ነገር ግን በጠባብ ውጤት እንደሆነ ነው የሚጠቁመው። ሶስተኛው ዜና ግን ምናልባት ጆ ባይደን ቅድመ ትንበያውን ጥሰው በሰፊ ውጤት ማሸነፋቸውን የሚናገር ሊሆን ይችላል። ይህ ከሆነ ፕሬዝደንት ትራምፕን ጉድ የሰራቸው ኮሮናቫይረስ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ባለፈው ምርጫ ትራምፕ ግልፅ መልዕክት ነበር ይዘው የቀረቡት። የግንብ አጥር እገነባለሁ ብለዋል፤ ሙስሊሞችን ወደ ሃገሬ አላስገባም ከማለት አልቦዘኑም፤ ስለ ንግድም ቁልጭ ያለ ዕቅድ ነው ይዘው የቀረቡት። በዘንድሮው ግን እዚህ ግባ የሚባል ዕቅድ የሌላቸው ሰው ሆነው ታይተዋል። ይህ ለጆ ባይደን ያላሰቡት ፍርቱና ሊሆናቸው እንደሚችል ፖለቲካ የሚበልቱ ሰዎች ይናገራሉ።