id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-57118263
https://www.bbc.com/amharic/news-57118263
የአሜሪካው ልዩ ልዑክ በኢትዮጵያ ላይ ያደረባቸው ስጋት
በትግራይ እየተፈፀሙ ያሉ ጭካኔዎች እንዲሁም የሰብዓዊ ሁኔታዎች ደረጃ ተቀባይነት እንደሌለው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጄፍሪ ፌልትማን አስታውቀዋል።
የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጄፍሪ ፌልትማን የአፍሪካ ቀንድ አገራትን ጨምሮ በሱዳንና ግብፅ ጉብኝት ያደረጉት ልዩ ልዑኩ በትግራይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስና አሰቃቂ ብለው የጠሩት ግጭት እንዲቆም፤ የሚያስፈልገው አስቸኳይ ህይወት የማዳን ተግባር እንዲከናወን አገራቸው አሜሪካ ከተለያዩ አለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመሆን ትሰራለች ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የፈፀሙ አካላትም ተጠያቂ የሚሆኑበትንም መንገድ አገራቸው እንደምትተባበር ገልፀዋል። ልዩ ልዑኩ የአፍሪካ ቀንድ አገራትን ጨምሮ በግብፅና በሱዳን ከሚያዝያ 26፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያደረጉትን የመጀመሪያ ጉብኝት በትናንትናው ዕለት ግንቦት 5፣ 2013 ዓ.ም አጠናቀዋል። የመጀመሪያ ጉብኝታቸው መጠናቀቁን ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ ገፁ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በትግራይ የተከሰተው ቀውስ በመላው አገሪቷ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዳያመጡ የተደቀኑ ዘርፈ ችግርች ማሳያ ነው በማለትም ልዩ ልዑኩ መቃኘታቸውን አስፍሯል። ሉዓላዊነቷ የተከበረና አንድነቷ የፀና ኢትዮጵያን ማየት የአሜሪካ ፍላጎት መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን በአገሪቷ ውስጥ ያለው ጫፍና ጫፍ የደረሰው የብሄር ፅንፈኝነትና ፖለቲካዊ ውጥረት ስጋት እንዳሳደረባቸው መናገራቸውን መግለጫው አስፍሯል። በመግለጫው ልዩ ልዑኩ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውን ገልፆ አገሪቷ የተደቀኑባት ችግሮች ሁሉንም ባማከለ መልኩ ሊፈታ እንደሚችል ጠቁሟል። አገሪቷ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቶች ወደሚከበሩባት ብሄራዊ መግባባት መገንበት እንደሚቻል የጠቆመው መግለጫው ከዚህም ጋር ተያይዞ የኤርትራ ሰራዊት በኢትዮጵያ መቆየት ለነዚህ ግቦች መሳካት ተቃርኖ ነው ብሎታል። ይህንንም አስመልክቶ ልዩ ልዑኩ ፌልትማን ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ባደረጉት ቆይታ የኤርትራ ሰራዊት በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ መውጣት ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ጉዳይ መሆኑን መንገራቸውን መግለጫው አስምሯል። አገራቸው አሜሪካ ትስስር ያላቸውን ቀጣናዊ ቀውሶችን በመፍታት ረገድ እንዲሁም የህዝቦች ድምፅ የሚሰማበትና መንግሥታት ለህዝባቸው ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት እንዲዘረጋና በአጠቃላይ የበለፀገችና የተረጋጋች የአፍሪካ ቀንድ እንዲፈጠር ድጋፍ እንደምታደርግ አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በሱዳን ላለው የሽግግር መንግሥት አሜሪካ አጋርነቷን እንደምታሳይ የጠቆመው ይህ መግለጫ በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ያለው ግጭትና የህዳሴ ግድብ ውዝግብ ከአብዮቱ በኋላ የተፈጠረውን ሂደት እንዳያበላሸው ከአለም አቀፍ አጋሮች ጋር መፍትሄ ለመሻት እንሰራለን ብለዋል። ልዩ ልዑኩ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ከሚወዛገቡት ሶስቱ አገራት ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን መሪዎች ጋር መክረዋል። ግብፅና ሱዳን ከሚያነሷቸው የግድቡ ደህንነትና አጠቃላይ አሰራር እንዲሁም ከውሃ ደህንነት ጋር ተያይዞ ያላቸውን ስጋትና ኢትዮጵያ ያላት የልማት ጥያቄ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በሚደረገው ድርድር ይፈታል ብለዋል። ተቋርጦ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድሩም በአስቸኳይ እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል። በሶስቱ አገራት በአውሮፓውያኑ 2015 የተፈረመው የመርሆች መግለጫ ስምምነት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ባለፈው አመት ክረምት ላይ ያወጣው መግለጫ ለድርድሩ መስረት እንደሆነ የጠቆመው መግለጫው አሜሪካም ሽምግልናው ፍሬያማ እንዲሆን ፖለቲካዊም ሆነ ቴክኒካል ድጋፏን ትሰጣለች ብሏል። ልዩ ልዑኩ የአሜሪካን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከንን በመወከል የሚደረገውን ዲፕሎማሲያዊ ሂደት ለማሳለጥ ወደ ቀጠናው በቅርቡ እንደሚመለሱ ተመልክቷል።
news-47772442
https://www.bbc.com/amharic/news-47772442
አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የገጠመው ምንድን ነበር?
ከሦስት ሳምንታት በፊት አደጋ ስለደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች እየወጡ ነው።
በዚህም በቦይንግ 737 ማክስ ላይ ያለው አውሮፕላኑ ዝግ እንዳይል ወይም እንዳይቆም የሚያደርገው የአውሮፕላኑ ሥርዓት የ157 ሰዎችን ህይወት ለቀጠፈው አደጋ ምክንያት እንደሆነ እየተነገረ ነው። • ቦይንግ ተከሰሰ፤ ሰለአደጋው ተጨማሪ መረጃዎች እየወጡ ነው አደጋው ከመድረሱ በፊት በሁለቱ አብራሪዎች መካከል የተደረገን ምልልስ ጠቅሶ ዎል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው፤ የአውሮፕላኑ የሬዲዮ ግንኙነት ከመቋረጡ በፊት አንደኛው አብራሪ "ቀና አድርገው! ቀና አድርገው!" በማለት ለባልደረባው ሲናገር ተሰምቷል። • ቦይንግ ተከሰሰ፤ ሰለአደጋው ተጨማሪ መረጃዎች እየወጡ ነው በአውሮፕላኑ ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለውን ሥርዓት አብራሪዎቹ ቢጠቀሙም አደጋውን ለማስቀረት እንዳልተቻለ እየተደረገ ላለው ምርመራው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለጋዜጣው ተናግረዋል። አደጋ ከደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይን 737 ማክስ አውሮፕላን የበረራ መረጃ መሰብሰቢያ ሳጥን ውስጥ ከተገኘ የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ መሰረት አደጋው ከመድረሱ በፊት እያሽቆለቆለ ያለውን አውሮፕላን ሊታደግ ይችላል የተባለው የአውሮፕላኑ ሥርዓት እንዲሰራ ተደርጎ እንደነበር አመልክቷል። • "የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል የተባለው ጋዜጣ ስለአደጋው የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ስማቸው ያልተጠቀሱ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የአውሮፕላኑ ከፍታና ዝቅታ ለመቆጣጠር እንዲያስችል ተደርጎ የተሰራው የኮምፒውተር ሥርዓት ችግር እንዳለው አመልክቷል። በኢትዮጵያው አውሮፕላን ላይ ምን ተከሰተ? የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ302 መጋቢት 1/2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ጠዋት 2፡38 በመነሳት ሁለት ሰዓት ብቻ ለሚፈጀው በረራ ወደ ናይሮቢ ፊቱን ቢያዞርም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ችግር ገጥሞታል። አውሮፕላኑ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከስድስት ደቂቃዎች በኋላም 48 ኪሎሜትሮችን ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምሥራቅ ተጉዞ ከቢሾፍቱ አቅራቢያ ባለችው ቱሉ ፈራ መንደር ውስጥ ነበር ወድቆ የተከሰከሰው። • "በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል" እናት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ ያሬድ ጌታቸው ችሎታን በተመለከተ አብራሪው ከ8ሺህ ሰዓታት በላይ የማብረር ልምድ እንዳለው በመጥቀስ "የሚያስመሰግን ብቃት" አለው ብሏል። አደጋው በደረሰበት ዕለትም አብራሪው ያሬድ ጌታቸው ችግር እንደገጠመውና ተመልሶ ለማረፍ ለበረራ ተቆጣጣሪዎች መልዕክት አስተላልፎ ነበር። የቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላኖች ከበረራ ታግደዋል ጥያቄ ውስጥ የወደቀው ኤምካስ ምንድን ነው? ከዚህ አደጋ ጋር በተያያዘ የአውሮፕላኑ የደህንነት መጠበቂያ ሥርዓት ለሚደረገው ምርምራ ዋነኛው ጉዳይ ሆኗል። ኤምካስ የተባለውና አውሮፕላኑን በከፍተኛ ሁኔታ ወደላይ እንዳይወጣ ወይም ወደታች እንዳያሽቆለቁል ለመቆጣጠር እንዲቻል ተብሎ የተሰራ ሥርዓት ነው። በአውሮፕላኑ ዝግ ሲል በትክክለኛው አቅጣጫ እንዲበር ለማስቻል የሚፈለገውን ኃይል ለማግኘት ወደ ላይ ወይም ቁልቁል በመሄድ ወደሚፈለገው ከፍታ ይመለሳል። ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን በአውሮፕላኑ ክንፎች በኩል ያለውን የመቆጣጠሪያ አቅም በመቀነስ አውሮፕላኑ እንዲወድቅ ሊያደርገው ይችላል። • አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው? በተለመደው ሁኔታ አውሮፕላኑን ከዝግታ ለማውጣት አብራሪው የአውሮፕላኑ አፍንጫ ወደታች እንዲያዘቀዝቅ ያደርጋል። አደጋው በደረሰበት ቦይንግ 737 ማክስ አይነት አውሮፕላኖች ላይ ያለው የመቆጣጠሪያ ሥርዓት (ኤምካስ) ግን እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ሲከሰት አውሮፕላኑን እራሱ አስተካክሎ ወደ ትክክለኛው ቦታ ይመልሰዋል። አውሮፕላኑ ላይ ተመሳሳይ ነገር የሚከሰት ከሆነና ኮምፒውተሩ ይህንኑ ካወቀ የመቆጣጠሪያ ሥርዓቱ በተደጋጋሚ የማስተካከያ እርምጃን በእራሱ ይወስዳል። በኢትዮጵያው አየር መንገድ ላይ አደጋው ከመድረሱ አምስት ወራት ቀደም ብሎ ተመሳሳይ አደጋ የደረሰበት የኢንዶኔዢያው አውሮፕላንም የበረራውን ማዕዘን በሚያሰላው የአውሮፕላኑ መቆጣጠሪያ ላይ ተመሳሳይ አይነት እክል ገጥሞት እንደነበር ተገልጿል። በቦይንግ ምስለ በረራ ላይ በተደረገ ሙከራ እንደተረጋገጠው ኤምካስ የተባለው መቆጣጠሪያ ከሚጠበቀው በላይ ከበድ ያለ በመሆኑ በተደጋጋሚ የአውሮፕላኑ አፍንጫ ቁልቁል እንዲያዘቀዝቅ ያስገድዳል። • በእርግጥ የአብራሪዎቹ ስልጠና ከአደጋው ጋር ይያያዛል? በኢንዶኔዢያው አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ ለማወቅ በተደረገው የምስለ በረራ ሙከራ ላይ እንደተደረሰበት አውሮፕላኑ ቁልቁል በአፍንጫው ባህር ላይ ሊከሰከስ መሆኑን ያወቁት ከ40 ሰከንዶች ያነሰ ጊዜ ሲቀራቸው መሆኑን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። ይህንንም ተከትሎ ቦይንግ ኤምካስን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ለአብራሪዎች መመሪያ ቢያወጣም፤ ነገር ግን በአውሮፕላኑ ላይ ያለውን ሥርዓት የሚቆጣጠረው ሶፍትዌር ላይ ያስፈልግ የነበረው መሻሻያ ዘግይቶ ባለፈው ሳምንት ነው ይፋ የተደረገው። በተጨማሪም በበረራ ወቅት ችግር በሚያጋጥም ጊዜ አብራሪዎችን ሊያስጠነቅቅ ይችል የነበረው የማስጠንቀቂያ መብራትም አደጋው በደረሰባቸው ሁለቱ የኢትዮጵያ እና የኢንዶኔዢያ አውሮፕላኖች ላይ አልተገጠመም ነበር። ሁለቱን አደጋዎች ምን ያመሳስላቸዋል? ከሁለቱ አደጋው ከደረሰባቸው አውሮፕላኖች የተገኙ የበረራ መረጃዎች ተመሳሳይነት እንዳላቸው መርማሪዎች አመልክተዋል። የአውሮፕላኖቹን ወደ ላይ የመውጣትና የመውረድ ፍጥነት ንባብ እንደሚያመለክተው ሁለቱም አውሮፕላኖች ከፍና ዝቅ እያሉ እንደነበሩና አብራሪዎቹም ይህንን በመቆጣጠር አውሮፕላኖቹ ከፍ ብለው እንዲበሩ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። • አደጋው በአውሮፕላን አብራሪዎች ላይ ምን ስሜት ፈጠረ? ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ ጋር በመሆን ምርመራውን እያካሄደ የሚገኘው የአሜሪካ የአየር ትራንስፖርት ባለስልጣን እንዳለው ከአደጋው ስፍራና ከሳተላይት የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሁለቱ አውሮፕላኖች ላይ በጣም የሚመሳሰሉ ነገሮች እንደታዩ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ መረጃ መመዝገቢያውና የአብራሪዎቹ ክፍል ድምጽ መቅጃው ወደ ፈረንሳይ ተወስዶ ምርመራ ተደርጎበታል።
news-56380692
https://www.bbc.com/amharic/news-56380692
የኢትዮጵያ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ማኅበርን ማቋቋም ለምን አስፈለገ?
ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ ከስድስት መቶ በላይ አባላት ያሉት እና ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን የያዘ ማኅበር መመስረቱን መሥራች አባላቱ ለቢቢሲ ተናገሩ።
በኢትዮጵያ የሥራ ፈጣሪዎች ማኅበር መስራችና ፕሬዝዳንት የሆነችው ሳሚያ አብዱል ቃድር ማኅበሩ በኢትዮጵያ ደረጃ የመጀመሪያው መሆኑን ገልጻለች። ሳሚያ ኤም ቪው አጠቃላይ የትምህርት አማካሪ እና የባለሙያ ድጋፍ ሰጪ መስራችና ፕሬዝዳንት ስትሆን ተቋሙ የኢትዮጵያን ትምህርት በአዎንታዊ አስተሳሰብ ለማዘመን እንደሚሰራ ለቢቢሲ ተናግራለች። ከመስራች አባላቱ መካከል አንዱ የሆነው ቀረመንዝ ካሳዬም በበኩሉ ከስድስት በላይ በስሙ የተመዘገቡ የፈጠራ ሥራዎች ያሉት መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። ቀረመንዝ የሥራ ፈጣሪዎች በተለያዩ ስፍራዎች በየግላቸው እየሮጡ እንደሚገኙ አስታውሶ፣ ለየብቻ መሮጣቸው ያስገኘው ይህ ነው የሚባል ውጤት አለመኖሩን በማንሳት ማኅበር ማቋቋሙ ጠቃሚ እንደሆነ ይናገራል። ይህ ከስድስት መቶ በላይ የተመዘገቡ አባላት መያዙ የተገለፀው ማኅበርን መመስረት የፈለጉበትን ምከንያት ሲያስረዱም አስፈላጊው ክትትል እና እገዛ ቢደረግላቸው ጥቅማቸው ለሌሎች የሚተርፉ የሥራ ሃሳብ ፈጣሪ ወጣቶችን መደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ይላል። "ዓለም አሁን ለደረሰችበት ደረጃ የበቃቸው በሥራ ፈጣሪዎቿ ነው" የሚሉት ሳሚያ እና ቀረመንዝ፣ ሕይወትን የሚያቀሉና የሚያቀላጥፉ ፈጠራዎች ባለቤት የሆኑ ወጣቶች ተገቢው ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የዓለም ተሞክሮን በመጥቀስ ይናገራሉ። በኢትዮጵያ የሥራ ፈጣሪዎች ላይ ተግዳሮቶች እንደሚበዙ የምትናገረው የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ሳሚያ፣ ከአሁን በኋላ የሚመጡ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ተመሳሳይ ችግር እንዳይገጥማቸው በማሰብ ማኅበሩ መቋቋሙን ገልጻለች። በትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ በግብርና እና በሌሎች ኢትዮጵያን ዕድገት በሚያሳልጡ ዘርፎች ሁሉ የኢትዮጵያ ወጣቶች በሥራ ፈጠራ እና በሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ የሚያመለክቱት ወጣቶቹ፤ ነገር ግን ያላቸውን ርዕይ ወደ ተግባር ላይ ለመለወጥ በርካታ ተግዳሮቶች እንደሚገጥማቸው ይናገራሉ። በመላ አገሪቱ የሚገኙ የሥራ ፈጣሪዎች በአገር ውስጥ እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ካሉ ባለሙያዎች ጋር ማስተሳሰር፣ ሃብቶችን ማሰባሰብ እና የክህሎት ሥልጠናን ለአባላቱ መሥጠት ከማኅበሩ አላማዎች መካከል ቀዳሚዎቹ መሆናቸውን ገልፀዋል። የሥራ ፈጣሪዎች ወደ ሥራ ፈጣራ ኮሚሽንም ሆነ ወደ ኢኖቬሽን ሚኒስቴር በተበታተነ መልኩ በመሄድ ድጋፍና እገዛ እንደሚጠይቁና ይህ ግን ለተቋማቱም ሆነ ለሥራ ፈጣሪዎቹ አስቸጋሪ መሆኑን ይናገራሉ። ስለዚህ ማኅበራቸው መመስረቱ በጋራ በመሆን የሚያስፈልጓቸውን ጉዳዮች ለመጠየቅ እንዲሁም የሥራ ፈጣሪዎችን በተገቢው መልኩ ለማገዝ ይረዳል ይላሉ። የማኅበሩ ፕሬዝዳንት የሆነችው ሳሚያ አብዱል ቃድር፣ ይህ ማኅበር መቋቋሙ የሥራ ፈጣሪዎችን ውጣ ውረድ በግማሽ እንደሚቀንሰው በመግለጽ፣ ከተለያየ የመንግሥት ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት እንደሚፈልጉ ትናግራለች። እነዚህ ወጣቶች እንቅፋት በገጠማቸው ቁጥር እነርሱም ሆነ አገር ተገቢውን ጥቅምና ግልጋሎት ከማግኘት እንደሚሰናከሉ የምታስረዳው ፕሬዝዳንቷ፣ ይህ ማኅበር ሥራ ፈጣሪዎች እርስ በእርሳቸው መደጋገፍ እንዲችሉ በማሰብ የተመሰረተ ነው ብላለች። በርካታ ወጣቶች በመደበኛው ትምህርት ውስጥ የሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ሳይሆን የተቀጣሪነትን አስተሳሰብ እንዲይዙ ተደርገው መሰልጠናቸውን በማስታወስም፣ ማህበሩ ለሥራ ፈጣሪ አባላቱ የክህሎት እና ራስን የማነጽ ሥልጠናዎችን እንደሚሰጥም ተናግራለች። ሳሚያ፣ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ትክክለኛ ቀጥተኛ እና ጠቃሚ የሆነ መረጃ በማግኘት ረገድ ክፍተት እንዳለባቸው ጠቅሳ፣ ማኅበራቸው በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ያለውን ክፍተት ለመድፈን እንደሚሰራም ገልጻለች። በተጨማሪም ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች፣ ስለ አዳዲስ ሕጎች፣ የሥራ ፈጠራቸውን የት ይዘው መሄድ እንዳለባቸው፣ ለተለያዩ ጉዳዮቻቸው ማሟላት ያለባቸውን መሥፈርቶችን በሚመለከት ማኅበራቸው እገዛ ለማድረግ እና መረጃ ለማቅረብ ይሰራል። በኢትዮጵያ ውስጥ በተመሳሳይ መስክ በርካታ የፈጠራ ባለሙያዎችን አሉ የሚሉት ሳሚያ እና ቀረመንዝ፣ ማኅበራቸው እነዚህን ባለሙያዎች በማስተሳሰር እርስ በእርስ የሚደጋገፉበት እና መረጃ የሚለዋወጡበትን መንገድ እንደሚያመቻች ይናገራሉ። የሥራ ፈጣሪዎችን ከባለሀብቶች፣ ከመንግሥት እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ማስተሳሰር ሌላ ዓላማቸው መሆኑንም ሳሚያ ገልጸለች። ወጣቶች ያላቸውን የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ዋነኛ እንቅፋት ከሆኑት መካከል ገንዘብ አንዱ መሆኑን ያነሳችው ሳሚያ፤ ለእነዚህ ወጣቶች የገንዘብ ምንጮችን ማፈላለግ እና ማገናኘት ከተመሰረቱባቸው እና ከሚሰሩባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። የሥራ ፈጣሪዎች በተለያዩ ፖሊሲዎች እንዲታገዙ እና እንዲበረታቱ ለማድረግ ፖሊሲዎችን እና ደንቦች አመቺ ለማድረግ እንደሚሰሩም ይናገራሉ። የኢትዮጵያ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ማኅበር በሁሉም ክልሎች ቢሮዎችን ለመክፈት እቅድ መያዙን የምትናገረው ሳሚያ፣ በተለያዩ ቋንቋዎችም በመገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን ለማድረስ መዘጋጀታቸውን ገልጻለች።
46023079
https://www.bbc.com/amharic/46023079
በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ
በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ቄለም በምትባል አነስተኛ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጅ እንደሚሉት ከሆነ በሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና በኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ታጣቂዎች መካከል ሰኞ ጠዋት ግጭት ነበር።
ነዋሪው እንደሚሉት የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን የያዙ ስድስት ኦራል መኪኖች ሰኞ ጠዋት ወደ ከተማዋ ገብተው ነበር። ''እንደ መትረየስ ያሉ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ድምጾች ሲተኮሱ ይሰማል። ትናንት ቤጊ ወረዳ ውስጥ ከፍተኛ ውጊያ እንደነበረ ሰምተናል። ዛሬ ጠዋት ቄለም ከተማ ግጭት ነበር።'' እኚህ የከተማው ነዋሪ እንደሚሉት ከሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭቱን በመሸሽ ተሽሽገው ይገኛሉ። • አቶ ዳውድ ኢብሳ ማናቸው? • መንግሥት ከኦነግ ጋር ካገር ውጭ ሊወያይ ነው • ኦነግ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማወጁን ገለፀ ጊዳሚ ወረዳ ግራኝ ሶንካ በምትባል መንደር ውስጥ የሚኖሩ ሌላኛው ነዋሪ እሁድ ጀምሮ የተኩስ ድምጽ ሲሰሙ እንደነበረ ይናገራሉ። ''ከዕሁድ ጠዋት ጀምሮ በቤጊ እና ቄለም ወረዳዎች መካከል ባሉ አካባቢዎች ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ነበረ። እንደሰማነው ከሆነ ግጭቱ በሃገር መከላከያ እና በኦነግ ሠራዊት አባላት መካከል ነው'' ይላሉ። ከእኚሁ ነዋሪ እንደሰማነው እሳቸውን ጨምሮ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ከነቤተሰባቸው ወደ ሌሎች ስፍራዎች ሽሽተዋል። የቄለም ወለጋ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ታመነ ኃይሉ በበኩላቸው በዞኑ ውስጥ በሃገር መከላከያ እና በኦነግ ሠራዊት አባላት መካከል የተደረገ ምንም አይነት ግጭት የለም ይላሉ። ''ኦነግ ትጥቅ መፍታት የለበትም የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በቅርቡ ተካሂደዋል። ሰልፎቹም በሰላማዊ መንገድ ተጠናቀዋል። ከዚህ ውጪ ምንም አይነት ግጭት የለም። በፌስቡክ ላይ የሚወራ ወሬ ነው'' ብለዋል። • “ትጥቅ መፍታት ለድርድር አይቀርብም”፡ መንግሥት • የማንነት ጥያቄዎች የጎሉበት የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ አቶ ታመነ የሃገር መከላከያ ሠራዊት በዞኑ ውስጥ ለምን በስፋት ተሰማራ ተብለው ለተጠየቁት ''ከዚህ ቀደምም የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በስፋት ተሰማርተው ይገኛሉ። ምንም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም። ጊዳሚ ወረዳ ለደቡብ ሱዳን ድንበር ቅርብ ናት ለዚህም ነው የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በቦታው የሚገኙት'' በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ታመነ ''ኦነግ ትጥቅ መፍታት የለበትም'' ተብሎ በተወጣው ሰልፍ ምክንያት እስከ ሰኞ ጠዋት ድረስ በዞኑ አንዳንድ ከተሞች መንገድ ዝግ ሆኖ ቆይቷል። መንገድ ለማስከፈት ኃይል ከመጠቀም ይልቅ በሃገር ሽማግሌዎች አማካኝነት መፍትሄ ለመፈለግ ጥረት እየተደረገ ነው'' ብለዋል። በሌላ በኩል የደምቢዶሎ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ክብረት ዋቅጋሪ ትናንት ምሽት ሦስት የፖሊስ አባላት በቦንብ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታላቸው እንደመጡ ይናገራሉ። ''ከለበሱት የደንብ ልብስ መረዳት እንደቻልኩት የፖሊስ አባላት ናቸው። ምናልባትም የደንቢ ዶሎ ከተማ ፖሊስ አባላት ሳይሆኑ አይቀሩም። ሦስቱም በቦንብ የተጎዱ ሲሆን፤ እግራቸው ላይ እና ጀርባቸው ላይ ክፉኛ ቆስለዋል። የቦንቡ ፍንጣሪ ሰውነታቸው ውስጥ ይገኛል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢቢሲ ይህንን ሁኔታ በተመለከተ ከኦሮሚያ ክልል ሃላፊዎች፣ ከሃገር መከላከያ ሠራዊትም ሆነ በቅርቡ ከተቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። የኦነግ ባለስልጣናትም በክስተቱ ላይ ለጊዜው አስተያየታቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
news-54278847
https://www.bbc.com/amharic/news-54278847
ኮሮናቫይረስ፡ አፍሪካ ቫይረሱን ለመቆጣጠር በወሰደችው እርምጃ ተመሰገነች
የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) ዋና ኃላፊ የአፍሪካ አገራት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የወሰዱትን እርምጃ በማመስገን አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
አፍሪካ እስካሁን ከ1.4 ሚሊዮን በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን ከ34 ሺ በላይ ደግሞ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ይህ ቁጥር ከአውሮፓ፣ እስያ እና አሜሪካ ከታየው የቫይረሱ ስርጭት አንጻር እጅግ ዝቅተኛ ነው ቀደም ብለው የተጀመሩ የምርመራና የመከላከል ስራዎች የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር እንደረዱ የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር ማዕከል ዋና ኃላፊ ጆን ኒኬንጋሶንግ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። የአፍሪካ ሲሰዲሲ 55 አባል አገራት ያሉት ማዕከል ነው። አፍሪካ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ዜጎች ያሏት ቢሆንም በዓለም ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሲሰላ ግን አፍሪካ ድርሻዋ 5 በመቶ ብቻ ነው። በመላው ዓለም በቫይረሱ ከሞቱት ሰዎች መካከል ደግሞ ደግሞ አፍሪካ 3.6 በመቶ ብቻ ነው ድርሻዋ። ዋና ኃላፊው እንደሚሉት ምንም እንኳን በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ ቢሆንም አገራት በትክክል መረጃዎችን አለመስጠታቸው በወቅቱ አሳሳቢ ነበር። '' ምናልባት በየቦታው የተከሰተውን የወረርሽኙን ስርጭት እንደሌላ የዓለማችን ክፍል አልተከታተልነው ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ቀደም ብሎ ሲባል እንደነበረውና እንደተፈራው በአፍሪካ በርካታ ሰዎች በየመንገዱ ሞተው አልተመለከትንም'' ብለዋል። የአፍሪካ አገራት የመጀመሪያው የቫይረሱ ኬዝ ሪፖርት ከተደረገበት ቀን አንስቶ የተለያዩ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን ሲወስዱ ነበርም ተብሏል። እንደ ደቡብ አፍሪካ ያሉ በርካታ አገራት ጠበቅ ያለ አገር አቀፍ የእንቅስቃሴ ገደብ ሲጥሉ እንደ ኢትዮጵያ ያሉት ደግሞ ቀለል ያሉ ገደቦችን በመጣል በሌላ ጎን የምርመራ አቅማቸውን ከፍ በማድረግ ሲንቀሳቀሱ ነበር። ዋና ኃላፊው አክለውም የአፍሪካ አገራት የቫይረሱን ስርጭት ከመቆጣጠር አንጻር ያሳዩት መተባበርና "ወንድማማቻዊ ስሜት" የሚደነቅ ነው ብለዋል። ''በተጨማሪም በበርካታ አገራት፤ እኔ የምኖርባት አዲስ አበባን ጨምሮ ሰዎች በየመንገዱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገው ሲንቀሳቀሱ ተመልክቻለው። በአዲስ አበባ 100 በመቶ ማስክ ይደረግ ነበር'' አፍሪካ ከአጠቃላይ ህዝቧ መካካል አብዛኛው በአማካይ ወጣት መሆኑ ደግሞ ለቫይረሱ ዝቅተኛ ስርጭት አስተዋኦ እንዳለውም ዋና ኃላፊው ጨምረው አስረድተዋል። እነዚህ ነገሮች በሙሉ እንዳሉ ሆነው እንደ ኢቦላ አይነት ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር በተሰሩ ስራዎች ምክንያት በአፍሪካ ከዚህ በፊት ልምድ ስለነበረ በኮሮረናቫይረስ የተያዙትን መለየትና ንክኪ ያላቸውን አድኖ ማግኘት ላይ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል'' በማለት የአፍሪካን ስኬት ገልጸዋል። በአሁኑ ሰአት በኮቪድ-19 ከሚያዙና ከተያዙ ሰዎች ውስጥ ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛውን ቁጥር የምትይዝ ሲሆን በአጠቃላይ ካለው ቁጥር ለግማሽ የቀረበው የተመዘገበውም በዚችው አገር ነው። ነገር ግን በደቡብ አፍሪካ ቁጥሩ እንዲህ ከፍ ሊል የቻለው አገሪቱ በየቀኑ የምትመረምረው ሰው ብዛት በጣም ብዙ ስለሆነ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ ደቡብ አፍሪካ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የመረመረች ሲሆን በአጠቃላይ 50 የሚሆኑ የአፍሪካ አገራት በጋራ ያደረጉት ምርመራ ግን በቅርቡ ነው ከ10 ሚሊየን የተሻገረው። ''በዓለም አቀፍ መመዘኛዎች መሰረት በአፍሪካ ያለው ቁጥር ዝቅተኛ ቢሆንም በበቂ ሁኔታ ምርመራ እየተደረገ አለመሆኑ ለዚህ በምክንያትነት ይቀርባል። በዚህም ምክንያት የአፍሪካ ስኬት በአግባቡ እየታየ አይደለም''
50535212
https://www.bbc.com/amharic/50535212
በየቤቱ እና በየጎዳናው የሚደፈሩ ሴት የአእምሮ ህሙማን
ወጣቷ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበረች ። በመጀመሪያዎቹ የትምህርት ዓመታት የዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ የአእምሮ መታወክ ይገጥማትና በአማኑኤል ሆስፒታል ህክምና ለመከታተል ወደ አዲስ አበባ ትመጣለች።
ህመሟ በረታ፣ ግን ነገሮችን ተከታትሎ ህክምናዋ ከዳር እንዲደርስ የሚያደረግ ሰው ከጎኗ ስላልነበረ ጎዳና ላይ ወደቀች። ከዓመታት በፊት ጎዳና ተዳዳሪነት ላይ ለሚደረግ ጥናት መረጃ እየሰበሰበች የነበረችው ዶ/ር ማጂ ኃይለማሪያም ያገኘቻት ይህች ወጣት በወቅቱ አስራ አምስት በሚሆኑ የተለያዩ ወንዶች መደፈሯን ገልፃላት ነበር። አጥኚዎቹ ወጣቷ አማኑኤል ሆስፒታል በቋሚነት ገብታ እንድትታከም አደረጉ። በተደጋጋሚ የሚደፈሩ የአእምሮ ህመምተኛ ሴቶች ኤች አይ ቪ የሚያዙ ቢሆንም ይቺ ወጣት ግን እንደ እድል ሆኖ ውጤቷ ኔጌቲቭ ሆነ። ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ ወጣቷ ከአማኑኤል ሆስፒታል አገግማ ወደ አንድ መጠለያ ተላከች። ቢሆንም ከዓመታት በኋላ ይቺን ወጣት ዳግም አዲስ አበባ ልደታ አካባቢ የምትወስደውን መድሃኒት አቁማና ተጎሳቁላ ጎዳና ላይ እንዳገኘቻት ዶ/ር ማጂ ታስታውሳለች። ስለ ደረሰባቸው ነገር፣ ስለ ማንነታቸው እንዲሁም ከየት እንደመጡ፤ እንዲህ እንዲያ ነው ብለው መናገር የማይችሉ የተደፈሩ የአእምሮ ህመምተኛ ሴቶች ሁሌም ለተደፈሩ ሴቶች ድጋፍ ወደ ሚሰጠው የሴቶች ማረፊያና ልማት ማህበር ይሄዳሉ። • "በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ሴቶች አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸው፣ አርግዘው ወይም ጨቅላ ህፃን ይዘው ወደ መጠለያው እንደሚሄዱ የሴቶች ማረፊያና ልማት ማህበር ኃላፊ ነርስ የሆነችው ስምረት ተስፋዬ ትናገራለች። ስምረት እንደምትለው ስለተፈጸመባቸው ጥቃት መናገር አለመቻላቸው ለእነሱ የሚደረገውን እርዳታ እጅግ ከባድ ያደርገዋል። እነዚህ ሴቶች ብዙ ጊዜ የሚደፈሩት ጎዳና ላይ ቢሆንም "በአባት፣ በወንድም፣ በጎረቤትና በአስተማሪም ተደፍረው የሚመጡም የአእምሮ ህመምተኛ ሴቶች አሉ" ትላለች ስምረት። እነዚህ ሴቶች የቅርብ በሚሏቸው ወንዶች መደፈራቸው የሚታወቀው ራሳቸው ተናግረው ሳይሆን ሌሎች የቅርብ ሰዎች ተከታትለው ነገሮች ላይ ሲደርሱ እንደሆነም ታስረዳለች። እነዚህን የተደፈሩ የአእምሮ ችግር ያለባቸው ሴቶችን ለመርዳት መጠለያው መጀመሪያ የሚያደርገው አካላዊና አእምሯዊ የህክምና ምርመራ እንዲያደርጉና ወደ ጤናቸው እንዲመለሱ ማገዝ ነው። ተደፍረው ወደ መጠለያው የሚሄዱት ብዙ ጊዜ እድሜአቸው ከ10 - 30 የሚሆን ነው። በኤች አይ ቪ መያዝም ሌላው አስከፊ ጥቃቱን ተከትሎ ሊያጋጥም የሚችል ችግር ነው። ሁሉንም ነገር 'ስለሚያማት ነው' በሚል ከማለፍ የአእምሮ ህመምተኛ ሴቶችን ከህመማቸው ባሻገር መመልከት እንደሚያስፈልግ "የአእምሮ ችግር አንድ ነገር ነው፤ ጥቃቱ ደግሞ ከሴትነት ጋር የተያያዘ ሌላ ችግር ነው። ስለዚህ ይህች ሴት ይህ ችግር ደርሶባት ሊሆን ይችላል የሚለው ነገር ወደ ሰዎች አእምሮ ቢመጣ ጥሩ ነው" በማለት ታስረዳለች ስምረት። የአእምሮ ህመምተኛ ሴቶች በህክምና ተቋማት ውስጥም እንደሚደፈሩ በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ዙሪያ ላሉ የአእምሮ ህምምተኞች ማገገሚያዎች ትኩረት ባልተሰጠበት ቀደም ባሉት ዓመታት መጠለያዎቹ የሚገኙባቸው አካባቢ ያሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ሴትም ሆነ ወንድ የአእምሮ ህመምተኞችን ያለ ክፍያ የጉልበት ሥራ ያሰሯቸው፣ እርሻ ያሳርሷቸው ጭምር እንደነበር ዶ/ር ማጂ ታስታውሳለች። ሴቶቹ ደግሞ በአካባቢው ኗሪ ወንዶች ይደፈሩ ሁሉ እንደነበርም ታስታውሳለች። • የህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያለ ዕድሜ ጋብቻን መደፈር ነው ብሎ ደነገገ በተደጋጋሚ መደፈር እንደ አማኑኤል ሆስፒታል ካሉ ተቋማት ተሽሏቸው እየወጡ ዳግም ጎዳና ወድቀው በተደጋጋሚ የሚደፈሩ የአእምሮ ህመምተኛ ሴቶች ጥቂት አይደሉም። አብዛኛውን ጊዜ በተለይም ቤተሰብ ወይም መጠጊያ የሌላቸው የአእምሮ ህመምተኛ ሴቶች የሚላኩት ወደ መጠለያዎች ሲሆን፤ ያለ ልምምድ በአንድ ጊዜ ቁጥጥር ያለበትን እንደዚህ አይነት ህይወትን መልመድ አቅቷቸው በተደጋጋሚ ጎዳና እንደሚወጡ ዶ/ር ማጂ ታስረዳለች። የኮሌጅ ትምህርቷን በአእምሮ ህመም አቋርጣ ጎዳና የወጣችው ወጣት የህይወት እውነታም ይኸው ነው። በአጠቃላይ በአገሪቱ ያለው የሴቶች ለጥቃት ተጋላጭነት ላይ የአእምሮ ህመምተኝነት ሲጨመርበት ነገሩ ምን ያህል እንደሚከፋ "ተከታትሎ የሚያሳክማት ሰው የሌላት፤ ለራሷ መናገርና መቆም የማትችል የአእምሮ ህመምተኛ ሴት ለመደፈር ተጋላጭነቷ ከሁለም የከፋ ይሆናል" በማለት ትገልፃለች። እሷ እንደምትለው ከጎዳና የሚነሱ ሰዎችን ወደ መጠለያ የመመለስ ሂደት፤ ማለትም ቁጥጥርና ሥርዓት ከሌለበት ነፃ የኑሮ ዜዬ ወደ መደበኛ ኑሮ የመመለስ ሂደት ሽግግር ቢያስፈልገውም በኢትዮጵያ ለዚህ ሽግግር የሚሆን መዋቅር አለመኖሩ ሴቶችን ይበልጥ ተጋላጭ አድርጓል። ወጣቷ የአእምሮ ህመምተኛ ከመጠለያ ለምን እንደወጣች ስትጠየቅ መልሷ "እዚህ ጋር ፀጉርሽን ማበጠር አትችይም፣ እዚህ ጋር መቀመጥ የለብሽም ፣ መብላት ያለብሽ በዚህ ሰዓት ነው" የሚሉ ነገሮችን መቋቋም እንዳቃታት ነበር የተናገረችው። • ህገወጡ የአረብ አገራት ጉዞ በአዲሱ አዋጅ ይገታል?
49603904
https://www.bbc.com/amharic/49603904
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አረፉ
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓመት በሞት ተለዩ።
ሮበርት ሙጋቤ ዚምባብዌ ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የመጀመሪያው መሪ የሆኑት ሙጋቤ፤ ባደረባቸው ህመም ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ሙጋቤ ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ሲንጋፖር በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተከታተሉ ነበር። • ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን ለቀቁ • የሮበርት ሙጋቤ ጥቅሶች እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2017 ላይ የዚምባብዌ መከላከያ ኃይል፤ ሮበርት ሙጋቤ ለሦስት አሥርት ዓመታት ይዘውት ከነበረው መንበረ ሥልጣን ማስነሳቱ ይታወሳል። በ1980 በዚምባብዌ የተካሄደውን የመጀመሪያ ምርጫ አሸንፈው ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የነበሩት ሙጋቤ፤ 1987 ላይ ፕሬዘዳንት ሆነዋል። የአገሪቱ የትምህርት ሚንስትር ጸኃፊ ፋዲዛይ ማሀሬ "ነፍስዎትን በገነት ያኑራት" ብለው በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። ሙጋቤ የተወለዱት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1924 ነበር። ከእንጨት ሠሪ ቤተሰብ የተገኙት ሙጋቤ፤ በካቶሊክ የሚሽነሪ ትምህርት ቤት ነበር ትምህርታቸውን የተከታተሉት።
news-53628660
https://www.bbc.com/amharic/news-53628660
ወታደራዊ ትዕይንት በትግራይ ክልል
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ በርካታ የክልሉ የልዩ ኃይል አባላትና ታጣቂ ሚሊሻዎች በዛሬው ዕለት ወታደራዊ ሰልፍ በማካሄድ ትዕይንት አድርገዋል።
በሰልፉ ላይ የተሳፉት የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላቱ ቀላልና ከባድ የጦር መሳርያዎችን ታጥቀው መታየታቸውን የቢበሲ ዘጋቢ ከመቀለ ገልጿል። ዛሬ ረፋድ ላይ በክልሉ ዋና ከተማ በመቀለ ጎዳናዎች ላይ በሰልፍ ሲጓዙ የታዩት ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱት የልዩ ኃይሉ አባላትና ሚሊሻዎች በከተማው ወደሚገኘው ስታድየም በመጓዝ ተሰብስበው ታይተዋል። በመቀለ ከተደረገው ከዚህ ወታደራዊ የሰልፍ ትዕይንት ባሻገር በሌሎችም የክልሉ ከተሞች ጭምር መደረጉ ለማወቅ ተችሏል። ቢሆንም ይህ ዛሬ የተካሄደው ወታደራዊ ሰልፍ ዓላማው ምን እንደሆነ የትግራይ ክልል መንግሥት የገለጸው ነገር የለም። ነገር ግን የትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮ ፌስቡክ ገጹ ላይ "ለሰላም ሲባል ለሚከፈል ዋጋ ሁሌም ዝግጁ ነን" የሚል መልዕክት አስፍሯል። ቢሮው አክሎም "የአንድ ሕዝብ የሰላሙ ዋስትና ውስጣዊ አቅሙ እንጂ የማንም የውጭ ኃይል ድጋፍና ጥበቃ ሆኖ አያውቅም" ሲል ገልጿል። የእዚህ ወታደራዊ ትዕይንት ዓላማ ባይገለጽም የትግራይ ክልል መንግሥት ከፌደራሉ መንግሥት በኩል ይደርስብኛል የሚለውን ጫና ለመመከት እየሰራ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። የቀድሞው ገዢ ፓርቲ ኢህአዴግ ከከሰመና የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት ከአዲሱ የብልጽግና ፓርቲ እራሱን ካገለለ በኋላ በፌደራሉ መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለመግባባት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረረ መጥቷል። ይህም ሁኔታ በሁለቱ ወገኖች መካከል የኃይል ግጭት ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት ከአንዳንድ ወገኖች በኩል ሲነሳ ቆይቷል። ባለፈው ሳምንት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር በተደረገ ውይይት ላይ የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ጋር ምንም አይነት ፍጥጫ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ተናግረዋል። በዚህም "ማን ነው ማንን የሚወጋው? ለምንድነው የፌደራል መንግሥት ትግራይን የሚወጋው? ይህ የእብደት ንግግር ነው። የፌደራሉ መንግሥት የራሱን ሕዝብ የመውጋት ሃሳብና ፍላጎት ፍጹም የለውም" ብለው ነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ነግ ግን የትግራይ ክልል መንግሥት ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተያየት እውነታውን አያንጸባርቅም ሲል አጣጥሎታል። የትግራይ ክልል መንግሥት ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫም "ስልጣን ላይ ያለው አሃዳዊ አምባገነን ቡድን የትግራይ ሕዝብና መንግሥት ምርጫ አካሂዳለሁ በማለቱ ብቻ 'ተዘጋጅቻለሁ፣ እናቶች ያለቅሳሉ፣ የወጣቶች ደም ይፈስሳል፣ መሰረተ ልማት ይወድማል' ሲል በአደባባይ ፎክሯል" ሲል የፌደራል መንግሥቱን ከሷል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ያለው አለመግባባት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው ለነሐሴ ወር የተያዘው አጠቃላይ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወርሽኝ ሰበብ መራዘሙን ተከትሎ ነው። የምርጫውን መራዘም የትግራይ ክልል የተቃወመው ሲሆን ከሌሎቹ የአገሪቱ ክልሎች ተለይቶ በተናጠል ምርጫውን ለማካሄድ ወስኖ አስፈላጊ የተባሉትን ሥራዎች እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም ሳቢያ ባለፈው ሳምንትም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በአፋጣኝ እንዲያቆም የሚጠይቅ ደብዳቤ ፅፏል። በደብዳቤው ላይ ክልሉ በዚህ ውሳኔው የሚገፋ ከሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት "በሕገ መንግሥቱና ሌሎች ሕጎች የተሰጠውን ስልጣን ለመተግበር እንደሚገደድ" ማስጠንቀቁ ይታወሳል።
news-52147721
https://www.bbc.com/amharic/news-52147721
ኮሮናቫይረስ፡ በፓኪስታን ቤት መቀመጥን ህግ ጥሰው ቤተሰባቸውን ሲቀብሩ የተገኙ ሃዘንተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ፓኪስታን ያወጀችውን ከቤት ያለመውጣት አስገዳጅ ሕግን ተላልፈው ቤተሰባቸውን ሲቀብሩ የተገኙ ሃዘንተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የዶክተር አንጁም ማህሙድ ቤተሰቦች ናቸው። ዶክተሩ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱትን እናቱን ሊቀብሩ በሄዱበት ወቅት ቀብር ላይ መላ ቤተሰቡ በቁጥጥር ስር ውለዋል። አንዳንድ ዘመዶቹም ከቤት ውጭ በር ተቆልፎባቸው በፖሊስ እየተጠበቁ እንደሚገኙ ዶክተሩ ለቢቢሲ አስረድቷል። የአካባቢው ባለስልጣናት ሃያ የሚሆኑ የቤተሰቡ አባላት በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙም ገልፀዋል። ቤተሰቦቹም ሆነ እሱ ነዋሪነታቸው በእንግሊዝ ሲሆን ወደ ፓኪስታን ያቀኑትም ለሠርጉ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለመሸመት በሚል ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባይከሰት የሠርጉ ቀን የተቆረጠው መጋቢት ወር ላይ ነበር። በፓኪስታንም ቆይታቸው እናቱ በቫይረሱ ሞቱ፤ በነገታው ለቀብር በወጡበት ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሟች ሻሂዳ ማህሙድ "የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ፀሎት እየተጠናቀቀ በነበረበት ወቅት በርካታ የፖሊስ መኪኖች መጥተው ሃያ አምስት የሚሆኑ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል" ብሏል ዶክተሩ። በኮሮናቫይረስ ተይዘው የነበሩት አባቱ ለኮሮናቫይረስ ህመምተኞች በተዘጋጀ የለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል። "አባቴ የ74 ዓመት እድሜ ባለፀጋ ነው፤ በሃዘን ልቡ ተሰብሮ ባለበት ወቅት እንዲህ የሚያስጨንቅ ቦታ ውስጥ ማስገባት ትክክል አይደለም" ብሏል። አክሎም "ከኮሮናቫይረስ ነፃ ነህ ቢባልም እስካሁንም ከለይቶ ማቆያው ሊለቁት አልቻሉም" "ዘመዶቼም ለባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ተቆልፋባቸው ያለ ምግብና ውሃ ይገኛሉ" ብሏል። የአካባቢው ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር ሰይፍ አንዋር ጃፓ በበኩላቸው በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ወቅት መመሪያዎቹ ተግባራዊ አልሆኑም ብለዋል። ነገር ግን ዶክተር አንጁም በኮሚሽነሩ ሃሳብ አይስማም በመመሪያው መሰረት አካላዊ ርቀትን እንደጠበቁና በቀብሩ ላይ የተገኙትም ሰዎች ቁጥር ጥቂት እንደሆነ ነው።
news-52228817
https://www.bbc.com/amharic/news-52228817
ቻይና ዉሃንን ከፍታ ስዊፌ ከተማን ለምን ዘጋች?
ቻይና የኮቪድ-19 መነሻ ናት የምትባለውን የ11 ሚሊዮን ሕዝቦች መኖርያ ውሃንን ትናንት ሙሉ በሙሉ ክፍት አድርጋለች፡፡ 7ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ከውሃን ከተማ ወጥተዋል ተብሏል፤ የትናንቱን ውሳኔ ተከትሎ፡፡
በምትኩ ግን አንዲት ከተማ ተቆልፋለች፡፡ ስዊፌ ትባላለች፡፡ 100ሺ ሰዎች የሚኖሩባት ትንሽዬ የድንበር ከተማ ነች፡፡ ከራሺያ የምትዋሰን ሩቅ ከተማ ናት፡፡ ከቤጂንግ 1ሺ ማይል ትርቃለች፡፡ በዚች ከተማ ነዋሪዎች በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ከቤት እንዳይወጡ ተነግሯቸዋል፡፡ 600 አልጋ ያለው ሆስፒታልም እየተገነባላቸው ነው፡፡ ሆስፒታሉ ሰኞ ተጀምሮ እሑድ ይመረቃል፡፡ አንድ የአከባቢው ነጋዴ ለቢቢሲ ‹‹በጣም ፈርቻለሁ›› ሲል ተናግሯል፡፡ ሌላ ነዋሪ ደግሞ በመንግሥቴ እተማመናለሁ ይላል፡፡ ረቡእ እለት ቻይና 59 ሰዎች በኮሮና መያዛቸውና እነዚህ በሙሉ ከውጭ የመጡ መሆናቸውን አሳውቃ ነበር፡፡ የአገሬው ሚዲያዎች ይፋ እንዳደረጉት ከሆነ ከነዚህ ከውጭ ገቡ ከተባሉት ውስጥ 25ቱ ከዚች ስዊፌ ከተባለች ድንበር ከተማ የመጡ ነበሩ፡፡ • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ድብደባ፣ ግድያ፣ ስለላ- ኮሮናቫይረስ በአፍሪካ • የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ምንድናቸው? መቼ ነው ሐኪም ቤት መሄድ ያለብኝ? አብዛኛዎቹ ታማሚዎች ከሞስኮ ወደ ቪላቮስኮት የተጓዙና ከዚያም በዚች ከተማ አድርገው ወደ ቻይና የገቡ ናቸው፡፡ ሌሎች ከዚህ ከተማ ወደ መሀል ቻይና የገቡ 86 ሰዎች የኮቪድ-19 ምልክት የማያሳዩ፤ ነገር ግን ቫይረሱ ያለባቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የቻይና መንግሥት ዕቃ የጫኑ ካርጎዎች ካልሆኑ በዚያ ድንበር በኩል መንገደኛ እንዳይተላለፍ መመሪያ አስተላልፏል፡፡ የድንበር ከተማዋ ነዋሪዎች ቤት እንዲቀመጡ የተነገራቸው ሲሆን ከየቤቱ አንድ ሰው በ3 ቀን አንድ ጊዜ አስቤዛ ለማድረግ ከቤት መውጣት ይቻላል፡፡ አዲስ የሚሰራው ሆስፒታል ታዲያ በመጪው እሁድ በሩን ለታማሚዎች ክፍት ያደርጋል ተብሏል፡፡ ቻይና የወረርሽኙ መነሻ ብትሆንም የደረሰባት ሰብአዊ ጉዳት ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነጻጸር የከፋ አይደለም፡፡ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙም ሆነ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ይገኛል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ እንዲያውም አንድም ታማሚ ያልተመዘገበበት እለት ሆኖ ውሏል፡፡ ሁኔታዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ለ11 ሳምንታት ተዘጋግታ የነበረችው ውሃን ከተማ የተከፈተችው በትናንትናው እለት ረቡእ ነበር፡፡ ይህ ከመሆኑ ታዲያ 221 ገቢና ወጪ በረራዎች በአንድ ቀን ተደርገዋል፡፡ 7ሺ ሰዎች ዉሃንን ለቀዋል፡፡ 4ሺ 500 ሰዎች ደግሞ ገብተዋል፡፡ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ የተለያዩ የሕዝብ ማመላለሻዎችን ተጠቅመዋል፡፡ ቤጂንግ አሁንም ከውሃንም ሆነ ከሌላ ቦታ የሚመጡ ቻይናዊያንን ሳትመረምር አታስገባም፡፡ ደህና ቢሆኑ እንኳ ከውሃን የመጡት ለ14 ቀናት ተገለው ይቀመጣሉ፤ ክትትልም ይደረግባቸዋል፡፡
50312840
https://www.bbc.com/amharic/50312840
የአውስትራሊያ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች በወር 2 ሚሊዮን ብር ሊከፈላቸው ነው
የአውስትራሊያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን 'ማቲላድስ' ከወንዶች እኩል ደሞዝ እና ጥቅማጥቅም ሊያስገኝላቸው የሚችል ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የአውስትራሊያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ በኋላ ሴቶች እና ወንዶች እኩል ነው የሚከፈላቸው ሲል ይፋ አድርጓል። ማቲላድስ በሚል ቅጥያ የሚታወቁት የአውስትራሊያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን አባላት በዓለም የሃገራት እግር ኳስ ሰንጠረዥ 8ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ወንዶቹ 44ኛ ናቸው። በወንዶችና እና ሴቶች መካከል ያለውን የክፍያ ክፍተት ከመሸፈን አኳያ ይህ ትልቅ እርምጃ ነው ያሉት የፊፋ ሥራ አስፈፃሚ ዴቪድ ጋሎፕ ናቸው። የአውስትራሊያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማሕበርም ውሳኔውን አድንቋል። በስምምነቱ መሠረት ወንዶቹም ሆኑ ሴቶች ከማስታወቂያ የሚገኘውን 40 በመቶ ገቢ እኩል ይካፈላሉ። አልፎም ወርሃዊ ደሞዛቸው እኩል ይሆናል። ዋና ዋና ተጫዋቾች በወር 69 ሺህ ዶላር [2 ሚሊዮን ብር ገደማ] እንደሚከፈላቸውም ተሰምቷል። አልፎም ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ከወንዶች እኩል ለሴቶች እንደሚደርሳቸው ታውቋል። ለምሳሌ ለወንዶች ብቻ ይፈቀድ የነበረው 'የቢዝነስ ክላስ' በረራ አሁን ለሴቶቹም ተፈቅዷል። ቢሆንም አሁንም ወንዶቹ ከሴቶቹ የተሻለ የሚያገኙበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል ተብሏል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ከውድድሮች በኋላ የሚከፈላቸው ገንዘብ ከሴቶቹ ላቅ ያለ መሆኑ ነው። አዘጋጆች ለወንዶች የሚከፍሉት ገንዘብ ከሴቶቹ ላቅ ያለ ነው። ባለፈው ሐሙስ የተካሄደው የሴቶች ዓለም ዋንጫ በሴቶች እና ወንዶች መካከል ያለው የፍክያ ልዩነት እንደ አዲስ መነጋገሪያ እንዲሆን አድርጓል። የዓለም ዋንጫ ባለድሎቹ የአሜሪካ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት የሃገራቸውን ፌዴሬሽን በዚሁ በክፍያ ጉዳይ መክሰሳቸው አይዘነጋም። አውስታራሊያ፤ ከኒውዚላንድ እና ኖርዌይ ቀጥላ ሶስተኛዋ የሴቶች እና ወንዶች ክፍያ እኩሌታ የተከበረባት ሃገር ሆናለች።
news-53039730
https://www.bbc.com/amharic/news-53039730
በቻይና አውስትራሊያዊው ዕጽ በማዘዋወር ወንጀል የሞት ፍርድ ተፈረደበት
በቻይና አውስትራሊያዊው ግለሰብ ዕጽ በማዘዋወር ወንጀል የሞት ፍርድ እንደተላለፈበት የአውስትራሊያ መንግሥት አስታወቀ።
የአውስትራሊያ መገናኛ ብዙኃን ካርም ወይም ካም ጊሌስፔ ብለው የሚጠሩት ይህ ግለሰብ 7.5 ኪሎ ግራም የሚመዝን 'ሜታምፌታሚን' ወይም 'አይስ' የሚባል ዕጽ በሻንጣው ውስጥ ይዞ በመገኘቱ አየር ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከ7 ዓመታት በፊት እንደነበር ሲድኒ ሞርኒንግ ሄራልድ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ካርም ጊሌስፔ ከጉዋንዡ ደቡባዊ ከተማ በሚገኝ ባዩን አየር ማረፊያ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተነግሯል፡፡ የቻይና መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት በጉዋንዡ በሚገኝ ፍርድ ቤት የሞት ብያኔው የተላለፈበትም ከአራት ቀናት በፊት ነው፡፡ የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይና ንግድ መሥሪያ ቤትም በግለሰቡ ላይ በተላለፈው የሞት ብይን የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡ "አውስትራሊያ በምንም ዓይነት ሁኔታ በማንኛውም ሰው ላይ የሚፈጸም የሞት ፍርድን ትቃወማለች፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሞት ቅጣት መሰረዙን እንደግፋለን፡፡ ይህም ከግብ እንዲደርስ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" ሲል ባወጣው መግለጫ ላይ አስፍሯል፡፡ ቻይና ምን ያህል የሞት ብያኔ ትሰጣለች? ቻይና ምን ያህል ሰዎችን በሞት እንደቀጣች መግለጽ አትፈልግም፡፡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ግን በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የሞት ብይኑ እንደሚፈጸም ያምናል፡፡ የሞት ፍርዱ ተፈጻሚ የሚደረገውም ገዳይ መድሃኒት በመውጋት አሊያም በጥይት ነው፡፡ በርካታ የውጭ አገር ዜጎችም ከዕጽ ዝውውር ወንጀል ጋር በተያያዘ የተገደሉ ሲሆን ሌሎች በርካቶችም የሞት ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ የሞት ቅጣቱ ከተፈጸመባቸው ግለሰቦች መካከልም ታዋቂው እንግሊዛዊ አክማለ ሻይክህ ይጠቀሳሉ፡፡ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ግለሰቡ የአዕምሮ ጤና ችግር እንዳለባቸው በመግለጽ ይግባኝ ቢሉም ከ11 ዓመታት በፊት በሞት ተቀጥተዋል፡፡ አውስትራሊያዊያን ላይ ከዕጽ ዝውውር ጋር ተያይዞ እንዲህ ዓይነት ውሳኔም ሲተላለፍ ካርም የመጀመሪያው አይደለም፡፡ከዚህ ቀደምም የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው አውስትራሊያዊያን አሉ፡፡ ከ5 ዓመታት በፊት ዕጽ ሲያዘዋውር በጉዋንዡ አየር ማረፊያ የተያዘው ጋዜጠኛ ቤንጋሊን ሸሪፍ አንዱ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ቤንጋሊ በሁለት ዓመታት የእስር ጊዜው መልካም ጠባይ በማሳየቱ የሞት ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተለውጦለታል፡፡ የአውስትራሊያናና የቻይና ግንኙነት ከኮሮና በኋላ የቻይናና አውስትራሊያ ግንኙነት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት በንግድ አለመግባባትና የእርስበርስ ወቀሳዎች ሻክሯል፡፡ አውስትራሊያ ባለፈው ዓመት በቻይና ውሃን የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መነሻ ገለልተኛ ወገን እንዲያጣራ ጥሪ ማቅረቧ ቻይናን አስቆጥቷታል፡፡ ቤጂንግም በተደጋጋሚ በእስያዊያን ላይ የሚደርስ ዘረኛ ጥቃቶች እየጨመሩ መሆናቸውን በመግለጽ ዜጎቿ ወደ አውስትራሊያ እንዳይጓዙ አስጠንቅቃለች፡፡ ቻይናዊያን ተማሪዎችም ይህንን የተጋረጠባቸውን አደጋ ከግምት እንዲያስገቡ አሳስባለች፡፡ ከዚህም ባሻገር ቻይና የአውስትራሊያን የበሬ ስጋ ወደ አገሯ እንዳይገባ ያገደች ሲሆን በገብስ ምርቷም ላይ ከፍተኛ ቀረጥ ጥላለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስተር ስኮት ሞሪሰን በበኩላቸው "አውስትራሊያ በቻይና ማስፈራሪያ ፈጽሞ ስጋት አይገባትም" ብለዋል።
44782738
https://www.bbc.com/amharic/44782738
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃቸው በ100 ቀናት
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ወደ መሪነት መምጣት ተከትሎ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ለውጦች እየተካሄዱ ነው። የኢህአዴግ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ኢኮኖሚውን ነፃ ለማድረግ በሚል በመንሥስት ይዞታ ስር የሆኑትን ቴሌ ኮሙኑኬሽንን፣ አየር መንገድን በከፊል ወደግል ለማዘዋወር ወስኗል።
ከእነዚህ ድርጅቶች በተጨማሪም የኢንደስትሪ መንደሮችን፣ የስኳር ፋብሪካዎችን፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች አምራች ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር ተወስኗል። ይህ ውሳኔ የተወሰነው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱንና የዋጋ ግሽበቱን ለመቋቋም፣ የገቢ ማመንጨት አቅምን ለማጠናከርና የወጪ ንግዱን ለማቀላጠፍ በሚል ነው። ለዚህ ውሳኔ ሌላኛው ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ የብድር መጠን ከፍ በማለቱም እንደሆነ ተነግሯል። ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? ‹‹እነ ቴሌን ለግል ባለሀብት?›› ታሪካዊ ስህተት ወይንስ መልካም አጋጣሚ ? ዶ/ር አብይ በግላቸው ለውጥ ያመጣሉ? በአሁኑ ሰዓት መንግስት ያጋጠመው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚኖሩ ዜጎችን እየጎዳ መሆኑ ይነገራል። አበበ መኮንን በአዋሽ መልካሳ የአንድ አነስተኛ መድሀኒት ቤት ሰራተኛ ነው። ባለፉት አራት ወራት ከፍተኛ የሆነ የመድሃኒት እጥረት እንዳለ ይናገራል። "በርካታ ሰዎች የወባ መድሀኒት ይጠይቁናል፤ ነገር ግን የለንም። በዚህች ከተማ ለአንዳንድ ሕመሞች የሚፈለግ ክንኒም ሆነ መርፌ ማግኘት ከባድ ነው" ይላል። ሰዎች ከሐኪም የታዘዘላቸውን መድሃኒት ሳይዙ ባዶ እጃቸውን ነው ወደ ቤታቸው የሚመለሱት የሚለው አቶ አበበ በዚህም የተነሳ ሕሙማን ፈውስ ርቋቸው ለመኖር ተገደዋል ይላል። "የጅምላ አከፋፋዮቹም በመጋዘናቸው ውስጥ ምንም የላቸውም። እነርሱ እያሉት ያለው ዶላር የለም ነው" በማለት ለቢቢሲ ገልጧል። "175 ብር እንሸጣቸው የነበሩ መድሃኒቶች 900 ብር ገብተዋል፤ ስለዚህም ሰዎች መግዛት አልቻሉም" ሲል ይጨምራል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚያካሄዳቸው ኢንቨስትመንቶች በሚል ትላልቅ ማሺነሪዎችንና ቁሳቁሶችን ከዓለምአቀፍ ገበያ ይገዛል፤ እንደ ባለሙያዎች አስተያየት ከሆነ ደግሞ ይህ ግዢ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ክምችት እያሟጠጠና ከፍ ያለብድር ውስጥ የከተተ ነው። የተከፋፈለ ኃሳብ በኪዊን ማሪ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ለንደን የምጣኔ ሐብት ምሁር የሆኑት አቶ ነመራ ገበየሁ (ዶ/ር) "መንግስት ገቢ ከማያመነጩ እና የዶላር እጥረቱን ከማይቀርፉ ከእንደዚህ አይነት ትልልቅ ግንባታዎች ራሱን መግታት አለበት" ይላሉ። መንግስት በቁጥጥሩ ስር ያሉትን ተቋማት ወደ ግል ይዞታ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ወደ ግል አዞራቸዋለሁ ካለ በኋላ በምሁራኑ መካከል አንድ ወጥ አቋም አይታይም ። የምጣኔ ሐብት ምሁሩ ደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) እነዚህ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታ መዛወራቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተጠቃሚዎች የተሻለ አገልግሎትና ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፤ እንዲሁም ይላሉ ምሁሩ የዋጋውን ግሽበት ለመቆጣጠር ይረዳቸዋል። እንደ ዶ/ር ነመራ ከሆነ ግን በአሁኑ ወቅት እነዚህን ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታ ማዘዋወር ሀገሪቱን ወደባሰ የኢኮኖሚ ቀውስ መግፋት ይሆናል። "የሀገሪቱ ሀብት በከፍተኛ ደረጃ በኪራይ ሰብሳቢዎችና በሙሰኞች እጅ ነው የሚገኝው፤ እነዛ ሰዎች ናቸው እነዚህን ድርጅቶች የሚገዙት፤ ይህ ደግሞ በግለሰቦችና ቡድኖች መካከል ያለውን የሀብት ልዩነት ክፍተት ከፍ ያደርገውና ወደ ቀውስ ያመራል። " በከፍተኛ ሁኔታ በአስመጪና ላኪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ኪራይ ሰብሳቢዎችን የሚቆጣጠር መስፈርት መዘርጋት እንዳለበትም ይመክራሉ። በአዋሽ መልካሳ የኢንተርኔት ካፌ ባለቤት የሆነው ተክለማርያም "ኢንተርኔት ቀርፋፋ ነው። በተደጋጋሚም ይቆራረጣል። አንዳንዴ ለሁለት ቀን ያህል ተቋርጦ ይከርማል" ሲል ያማርራል። የ 512 ሜጋ ባይት አቅም ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት ከቴሌ ቢገዛም ቀርፋፋ እንደሆነ ያስረዳል። አገልግሎቱን ከፍ ለማድረግ አቅሙ እንደማይፈቅድ የሚናገረው ተክለማርያም የውጭ ባለሀብቶች ድርጅቱን ቢገዙት አገልግሎቱ እንሚሻሻል ተስፋ ያደርጋል። ትላልቅ የማሻሻያ እርምጃዎች አሁን ያለውን የኢኮኖሚ ተግዳሮት ለማለፍ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ከማዞር ባሻገር ዋና ዋና የሚባሉ የኢኮኖሚ ማሻሻዮች ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ። አየለ ገላን በኢትዮጵያ የምጣኔ ኃብት ላይ ምርምር የሚያደርግ ባለሙያ ነው። እንደ አቶ አየለ ከሆነ የኢትዮጵያን የምጣኔ ኃብት ችግሮች ከመነሻቸው መመልከት ተገቢ ነው። "ወደ ውጪ የሚላኩ እንደ ቡና ሰሊጥና አበባ ያሉ የግብርና ምርቶችን በጥራትና በመጠን ለማሳደግ መስራት ያስፈልጋል" ይላል። ለነመራ የበለጠ አሳሳቢ የሆነው ኢኮኖሚው በፌደራል መንግስቱ የተማከለ አስተዳደር ስር መሆን፣ ሙስናና ሰዎች የሚያገኙት ያልተገባ ጥቅም ናቸው። "ፖለቲካውና ኢኮኖሚው በፌደራል መንግስቱ በከፍተኛ ደረጃ በማዕከል ተይዘዋል። በክልሎች ያልተማከለ ኢኮኖሚያዊ ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል።" እንደባለሙያው ከሆነ ክልሎች እና የአካባቢ አስተዳደሮች እንደ ውሃ እና መብራት ያሉ አገልግሎታቸውን ለማስተዳደር ጠንካራ መሆን ይገባቸዋል። ሙስናን ለመዋጋትም ጠንካራ እርምጃ ያስፈልጋል።
news-46041931
https://www.bbc.com/amharic/news-46041931
ጠ/ሚ ዐብይ ጀርመን ውስጥ ባደረጉት ንግግር በፍትህ ተቋማት ላይ ለውጥ እንደሚደረግ ተናገሩ
በኢትዮጵያ የፍትህ ተቋማት ላይ መሰረታዊ ለውጥን የሚያመጡ ተከታታይ የለውጥ እርምጃዎች በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ።
የፍትህ ዘርፉ በህዝቡ ዘንድ ገለልተኝነና ተአማኒነት እንዲኖረው የሚያስችሉት የማሻሻያ እርምጃዎች የፆታ ተዋጽኦንም ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ እንደሚከናወን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃገሪቱ የተጀመሩት የለውጥ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ውጤታማ እንደሚሆኑና ኢትዮጵያም ተለውጣ ለዜጎቿ የምትመች ታላቅ ሃገር እንደምትሆን ያላቸውን እምነትና ተስፋ "አምናለሁ! ተስፋም አደርጋለሁ!" ሲሉ በተደጋጋሚ በጎላ ድምፅ ሲናገሩ ተደምጠዋል። በጀርመን ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፍራንክፈርት ውስጥ በአውሮፓ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ንግግር ነው ይህንን የተናገሩት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በንግግራቸው ላይ አስፈላጊ የሆኑት "የዴሞክራሲና የፍትህ ተቋማት ባልተገነቡበት ሁኔታ የምንመኘውን ፍትህ ሳይሆን ሥርዓት አልበኝነት እንጂ ፍትህ አይገኝም" ብለዋል። • የኢትዮጵያ እና የጂ-20 ወዳጅነት • ሐረር በፈረቃ ውሃ ማግኘት ጀምራለች ለዚህም በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማድረግ አስፈላጊው ሥራ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። ለዚህም በአዲሱ የለውጥ እርምጃ ፍትህና ዲሞክራሲን ሊሸከሙና ሊያሰፍኑ የሚችሉ ተቋማት እየተገነቡ ከመሆናቸው ጎን ለጎን ብቁ ባለሙያዎችም እንደሚመደቡ ገልፀዋል። ከፍትህ ሥርዓቱ በተጨማሪም ምርጫ ቦርድ ነፃና ተአማኒ እንዲሆን አስፈላጊው ማሻሻያ እንደሚደረግበት፤ የደህንትና ፀጥታ ተቋማት ለውጥ እየተደረገባቸው መሆኑን ጠቁመው፤ የመከላከያ ሠራዊቱም ዘመናዊና ሃገሪቱን የሚመጥን እንዲሆን እየተሰራ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ተስፋ የሚያጭሩና የሚያሳስቡ ሁኔታዎች እየተከሰቱ መሆናቸውን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ቢሆንም ግን "ኢትዮጵያን ማንም ተነስቶ እንደፈለገው የሚያደርጋት የግል ዕርስቱ ሳትሆን ዘመናት ያስቆጠረች ታላቅ ህዝብ የመሰረታት ታላቅ ሀገር ናት" በማለት ጠንክራ እንደምትወጣ ተናግረዋል። • ኦብነግ የፖለቲካ አላማውን በሰላማዊ መንገድ ለማከናወን ተስማማ • በኢትዮጵያ አደገኛ ከሆኑት መንገዶች አንዱ የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈ ነው ሃገሪቱ ካለችበት ሁኔታ እንደትወጣ ሁሉም በኩሉን በጎ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበው፤ መንግሥታቸውም የህዝቡን ፍላጎት ለማርካት ተግቶ እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል። ለዚህም በውጪ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለሃገራቸው ያላቸውን ፍቅር በተግባር እንዲገልፁ ጠይቀዋል። ጨምረውም ከዚህ በፊት በአሜሪካ እንዳደረጉት ኢትዮጵያዊያኑ በቀን አንድ ዶላር እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ንግግር ባደረጉበት "በአንድነት እንነሳ፣ ነገንም እንገንባ" በሚል መሪ ሃሳብ በኮሜርዝ ባንክ አሬና ስታዲየም በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ከ20 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከጀርመንና ከተለያዩ አውሮፓ ሃገራት ታድመዋል።
49093787
https://www.bbc.com/amharic/49093787
በአውስትራሊያ አደንዛዥ ዕፅ የጫነ መኪና የፖሊስ መኪና ገጭቶ በቁጥጥር ሥር ዋለ
በአውስትራሊያ ሲድኒ በፖሊስ ጣቢያ ቆሞ የነበረ የፖሊስ መኪናን ገጭቶ ለማምለጥ የሞከረ መኪና በቁጥጥር ሥር ሲውል 200 ሚሊየን ዶላር የተገመተ አደንዛዥ ዕፅ ይዞ ተገኝቷል።
አሽከርካሪው 28 ዓመቱ ሲሆን የፖሊስ መኪና ገጭቶ በፍጥነት ለማምለጥ ሞክሯል። ፖሊስ ከአንድ ሰዓት በኋላ በከተማዋ ሰሜናዊ ክፍል ኢስትውድ በተባለ ስፍራ በቁጥጥር ሥር አውሎታል። • "አዲስ አበባ የምንወዛገብባት ሳትሆን በጋራ የምንኖርባት ከተማ ናት" ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ • አሜሪካ ስደተኞችን ፍርድ ቤት ሳታቀርብ ወደመጡበት አገር መመለስ ልትጀምር ነው • በመድፈር የተወነጀለው ሮናልዶ አይከሰስም ተባለ መኪናው ሲበረበርም 273 ኪሎ ግራም ሜት የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ተገኝቶበታል። ባለሥልጣናት በግጭቱ ማንም ሰው አለመጎዳቱን የተናገሩ ሲሆን፤ የፖሊስ መኪናው ግን "ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል" ብለዋል። በአውስትራሊያ ሜት የተሰኘው አደንዛዥ ዕፅ በበርካታ ተጠቃሚዎች ዘንድ የተለመደ ነው። ይህ አደንዛዥ ዕፅ ዋጋው እጅግ ውድ ሲሆን፤ በአገሪቱ በዚህ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለሚፈፅሙት የተደራጀ ወንጀል ምክንያትም ነው ተብሏል። በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ስሙ ያልተጠቀሰ ሲሆን፤ ፍርድ ቤት ቀርቦ ዕፅ በማቅረብ እና በግዴለሽነት በማሽከርከር እንደሚከሰስ ተነግሯል።
54229710
https://www.bbc.com/amharic/54229710
ጃዋር መሐመድ፡ "ክስ የተመሠረተብን በምርጫ እንዳንሳተፍ ነው"
የሽብር ክስን ጨምሮ ማታቸው ተደራራቢ ክሶች ከቀረበባቸው ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ጃዋር መሐመድ ለሁለተኛ ጊዜ በሽብር መከሰሳቸው በቀጣዩ ምርጫ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ታስቦ መሆኑን ለፍርድ ቤት ተናገሩ።
ጃዋር መሐመድ፣ ብርሃነመስቀል አበበ፣ በቀለ ገርባ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ጃዋር መሐመድ በዛሬው ችሎት "ለሁለተኛ ጊዜ በሽብር በመከሰሴ ኩራት ይሰማኛል" ሲሉ ለፍርድ ቤት ተናግረዋል። አቶ ጃዋር ከዚህ ቀደም ከአገር ውጭ እያሉ ተመሳሳይ ክስ ቀርቦባቸው የነበረ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ሲመጡ ክሳቸው ከተነሳላቸው ሰዎች መካከል አንዱ እንደነበሩ ይታወሳል። አቶ ጃዋር ጨምረውም ክሱ የተመሰረተባቸው በአገራዊ ምርጫው እንዳይሳተፉ ለማድረግ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፤ ገዢው ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል እሸነፋለሁ ብሎ በመስጋቱ የሽብር ክስ እንዲመሰረትብኝ ተደርጓል ሲሉ በችሎቱ ተናግረዋል። ክሱ እሳቸውን ብቻ ሳይሆን "አቶ እስክንድር ነጋም በአዲስ አበባ ምርጫው ያሸንፋል ተብሎ ተፈርቶ እንጂ፤ ወንጀል ሰርቶ አይመስለኝም" ሲሉም አቶ ጃዋር ሌሎችም ላይ የቀረበው ክስን ጠይቀዋል። በተጨማሪም አቶ ልደቱ አያሌውን ጠቅሰው ለእስር የተዳረጉት የሽግግር መንግሥት ይቋቋም የሚለው ሃሳባቸው ተሰሚነት እያገኘ ስለነበረ ነው ሲሉ አቶ ጃዋር ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። ክሱ የተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች ዛሬ ዝርዝሩ በጽሑፍ የተሰጣቸው ሲሆን ችሎቱ ክሱን ለመስማት ለፊታችን ሐሙስ መስከረም 14/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። በዛሬው ችሎት ተጠርጣሪዎቹ የፍርድ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት ለሃጫሉ ሁንዴሳና የሃጫሉ ግድያን ተከትሎ የተገደሉትን "በሺህዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ጀግኖችን" በህሊና ጸሎት እንድናስብ በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ሳምንት ክስ እንደመሰረተባቸው ከገለጻቸው 23 ሰዎችና ኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ መካከል 18ቱ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ በማረሚያ ቤት የሚገኙት አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ መስተዋርድ ጀማል ሳይቀርቡ ቀርተዋል። በተጨማሪም በውጭ አገራት የሚገኙት አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ብርሀነ መስቀል አበበ፣ ፀጋዬ አራርሳ እና የኦኤምኤን ቴሌቪዥን በሌሉበት ጉዳያቸው መሰማት ጀምሯል። ዐቃቤ ሕግ ባሳለፈው ቅዳሜ አቶ ጃዋርን ጨምሮ በ24 ግለሰቦች እንዲሁም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) ላይ የሽብር ክስን ጨምሮ በአስር ተደራራቢ ወንጀሎች እንደከሰሳቸው ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ክሱ ከተመሰረተባቸውና በእስር ላይ ከሚገኙት ሰዎች መካከል የተወሰኑት ዛሬም [ሰኞ] በተገኙበት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸዋል። በአስር ላይ የሚገኙትን አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሀምዛ አዳነ፣ የኦሮሚያ ሜዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን)፣ ዐቃቤ ሕግ ጨምሮ ግለሰቦቹ እና ድርጅቱ ላይ የቀረበው ክስ ዛሬ በንባብ እንደሚቀርብ ጠቁሞ ነበር። በዚህም መሠረት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው በጽሑፍ ከተሰጣቸው መካከል አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሃምዛ አዳነ ይገኙበታል። የኦፌኮ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ በሌላ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው እየታየ ስለሆነ ሳይቀርቡ ቀርተዋል። የኦኤምኤን ኃላፊ አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ የኢትዮጵያ ቆንስላ ዲፕሎማት የነበሩት ብርሃነመስቀል አበበ (ዶ/ር)፣ ነዋሪነታቸው አውስትራሊያ የሆነው አቶ ፀጋዬ ረጋሳን ጨምሮ በአጠቃላይ 24 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባሳለፈው ቅዳሜ ማስታወቁ ይታወሳል። በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ የቀረበባቸው ተቋምና ግለሰቦች "እንደየተሳትፏቸው በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርንና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ፣ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድግ" የሚሉ ክሶች የቀረቡባቸው መሆኑን አመልክቷል። በተጨማሪም ተከሳሾቹ የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 761/2004 እና የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በመተላለፍ በፈፀሙት ወንጀልም ክስ መስርቷል። የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስከረም 6/2013 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 260215፤ በአጠቃላይ አስር ተደራራቢ ክሶች የከፈተባቸውና ዛሬ ሰኞ መስከረም 11/2013 ዓ.ም የክሳቸው ዝርዝር የደረሳቸው ተከሳሾችን ዝርዝር ቢቢሲ አግኝቷል። 1. ጃዋር መሐመድ 2. በቀለ ገርባ 3. ሃምዛ አዳነ 4. ጉቱ ሙሊሳ 5. ደጀኔ ጣፋ 6. አረፋት አቡበከር ከድር 7. አማን ቃሉ ባቲ 8. አለማየሁ ገለታ 9. ደጀኔ ጉተማ 10. መለሰ ዲሪብሳ 11. ሸምሰዲን ጣሃ 12. ቦና ባቢሌ 13. ብርሃነስቀል አበበ (ዶ/ር) 14. ጸጋዬ አራርሳ 15. የሃምሳ አለቃ ያዓለምወርቅ አሰፋ 16. ሳጅን ኦላና ጌቱ ተረፈ 17. የ10 አለቃ ታምራት ሁሴን 18. ሳጅን ኦላና በሽር ሁሴን 19. የሃምሳ አለቃ ሰቦቃ ቃቆ 20. የሃምሳ አለቃ ኬኔ ዱሜቻ 21. የሃምሳ አለቃ ዳዊት አብደታ 22. ቦጋለ ዲሪብሳ 23. ማስታዋርድ ተማም እና 24. ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) ናቸው። ታዋቂው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሠኔ 22/2012 ዓ.ም መገደልን ተከትሎ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ160 በላይ ሰዎች መገደላቸው እና ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረትም መውደሙ ይታወሳል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን ጨምሮ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
news-50709909
https://www.bbc.com/amharic/news-50709909
የቀድሞ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ መደፈሯን እንዳትናገር አባቷ እንደተጫኗት አሳወቀች
የቀድሞ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦብ ሃውኬ ልጅ እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1980ዎቹ ላይ ብትደፈርም የፖለቲካ ህይወታቸውን እንዳትጎዳ በሚል በምስጢርነት እንድትይዘው መገደዷን ከሰሞኑ ይፋ አድርጋለች።
ሮዝሊን ዲለን ውንጀላዋን ያቀረበችው ፍርድ ቤት መሆኑን የአውስትራሊያ ሚዲያ ዘ ኒው ደይሊ ዘግቧል። • ታዳጊዋ አንድን ግለሰብ ከጎርፍ ለማዳን ስትጥር ህይወቷ አለፈ • አምስቱ ተስፋ የተጣለባቸው አፍሪካውያን ሙዚቀኞች ደፋሪዋ ሌበር ፓርቲን ወክሎ የፓርላማ አባል የነበረው ቢል ላንደርዩ መሆኑንም ተናግራለች። አባቷም ሆነ ፖለቲከኛው ቢል ላንደርዩ በህይወት የሉም። የ59 አመቷ ሮዝሊን በአባቷ ንብረት ላይ የአራት ሚሊዮን ዶላር ይገባኛል ጥያቄም አንስታለች። በሰጠችው ምስክርነት ፖለቲከኛው የደፈራት ቢሮው ውስጥ ትሰራ በነበረበት ወቅት ነው። ሌሎች ሚዲያዎች እንደዘገቡት በተለያዩ ሶስት ጊዜያት መደፈሯን ነው። በሶስተኛው ጊዜ መደፈሯን ለአባቷ የተናገረች ሲሆን ለፖሊስ ልትከስ መሆኗን ብታሳውቀውም በወቅቱ የአባቷ ምላሽ " ወደ ፖሊስ መሄድ አትችይም። በአሁኑ ሰዓት ውዝግብ ውስጥ መግባት አልችልም። የሌበር ፓርቲን አመራር ለመቆጣጠር የስልጣን ፍትጊያዎች አሉ" እንዳላት የፍርድ ቤት መረጃዎች ያሳያሉ። እህቷም ሱ ፒተርስ ሃውክ ለኒውደይሊ እንደተናገረችው መደፈሯን ታውቅ እንደነበር ነው። • ለዓመቱ ምርጥ የታጨችው ኢትዮጵያዊት "በወቅቱ ለተለያዩ ሰዎች ተናግራ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ድጋፍ ሰጥተዋታል፤ ነገር ግን የትኛውንም የፍትህ ስርዓት ያሳተፈ አልነበረም" በማለት ቃሏን ሰጥታለች። ሌሎች የቤተሰቡ አካላት ምንም ከማለት ተቆጥበዋል። ቢል ላንደርዩ በፓርላማ አባልነት እንደ ጎርጎሳውያኑ ከ 1976-1992 አገልግሏል። ከአባቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦብ ሃውኬም ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበራቸው ተብሏል። በአውስትራሊያ ፖለቲካ ትልቅ ስፍራ የነበራቸውም ቦብ ሃውኬም አራት ጊዜ ምርጫዎችን ማሸነፍ ችለዋል ። በሃገሪቱም የኢኮኖሚ እንዲሁም የማህበረሰቡ ለውጦች ላይ ትልቅ ስፍራ ተጫውቷል ይባላል።
55767353
https://www.bbc.com/amharic/55767353
ተመድ በትግራይ ክልል የሚፈፀም ወሲባዊ ጥቃት እንዳሳሰበው ገለጸ
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በግጭት ወቅት የሚከሰት ወሲባዊ ጥቃት ላይ አተኩሮ የሚሠራው ቡድን በትግራይ ክልል እየደረሰ ያለው ወሲባዊ ጥቃት እንዲገታ አሳሰበ።
የቡድኑ ልዩ ተወካይ ፕራምሊያ ፓተን ሁሉም አካላት ወሲባዊ ጥቃት እንዲገታ እንዲሁም ውጥረት እንዲረግብ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። ትላንት በወጣው ይህ መግለጫ ልዩ ተወካይዋ "በመቀለ ከተማ በርካታ ቁጥር ያለው ሰው የመደፈሩ ክስና በአጠቃላይ ከትግራይ ክልል የተሰሙት የወሲባዊ ጥቃት ክሶች እጅግ አሳስበውኛል" ብለዋል። ጨምረውም "ሰዎች የገዛ ቤተሰባቸውን እንዲደፍሩ እየተገደዱና ይህን ካላደረጉ ጥቃት እንደሚደርስባቸው የሚጠቁሙ በጣም የሚረብሹ ሪፖርቶች ተሰምተዋል" ብለዋል። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ መንግሥትን ለመጠየቅ ወደ ሚመለከታቸው አካላት ቢሮ ቢደውልም ምላሽ ማግኝት አልቻለም። የቡድኑ ልዩ ተወካይ ፕራምሊያ ፓተን፤ አንዳንድ ሴቶች መሠረታዊ መገልገያ ለማግኘት ከወታደሮች ጋር ወሲብ ለመፈጸም እንደሚገደዱ ሪፖርት እንደተደረገም በመግለጫቸው ጠቁመዋል። የሕክምና ተቋሞችን ጠቅሰው ፕራምሊን እንደተናገሩት፤ የእርግዝና መከላከያ እንክብል የሚገዙና በወሲብ የሚተላለፍ በሽታ የሚመረመሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። "ይህም በግጭት ወቅት ወሲባዊ ጥቃት እየደረሰ ስለመሆኑ ማሳያ ነው" ብለዋል። በስደተኞች ማቆያ የሚኖሩ ሴቶች ስለመደፈራቸው የሚጠቁሙ ሪፓርቶች እየተበራከቱ እንደመጡ በመግለጫው ተመልክቷል። በትግራይ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ፣ የተለያዩ የክልሉ አካባቢዎችን ለመድረስ እንዳልተቻለና በተለይም በስደተኞች ማቆያ ያሉ ሰዎች ጉዳይ አስከፊ እንደሆነ ተናግረዋል። "ሰብአዊ እንርዳታ ሰጪዎችና ገለልተኛ የመብት ተሟጋቾች ባፋጣኝ ሙሉ ክልሉን እንዲቃኙ መፈቀድ አለበት" ሲሉም አሳስበዋል። በክልሉ ውስጥ የተፈናቀሉና ስደተኞችም ጭምር ወሲባዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ሪፖርት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። በአፋጣኝ የሕክምናና የሥነ ልቦና ድጋፍ እንዲደረግ እንዲሁም ከለላ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል። በወታደራዊ ግጭቱ ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች በካምፖች ውስጥ ወሲባዊ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ አያይዘው በመግለጫቸው ተናግረዋል። ሽሬ አካባቢ ከ5,000 በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች ወለል ላይ እንደሚተኙ፣ ምግብና ውሃ እንደሌላቸው ተናግረዋል። በተጨማሪም ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን የተሰደዱ 59,000 ገደማ ኢትዮጵያውን ስለሚገኙበት ሁኔታም ፕራምሊያ ፓተን አንስተዋል። ለሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት አለመቻላቸውና በቂ ሕክምና መስጫ መሣሪያ አለመኖሩን ጠቅሰው "ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ተገቢው እርዳታ አልደረሰም" ብለዋል። ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ከኤችአይቪና ሌሎችም በግብረ ስጋ የሚተላለፉ በሽታዎች የሚከላከል ሕክምና፣ የሥነ ልቦና ሕክምናና ሌሎችም መሣሪያዎች ተደራሽ እንዳልሆኑ አስረድተዋል። "በሰብአዊና ዓለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት ወሲባዊ ጥቃት የሚያደርሱ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለሁሉም አካል አሳስባለሁ" ብለዋል። መንግሥት ንጹሀን ዜጎችን ከወሲባዊ ጥቃት እንዲሁም ከሌሎች ጉዳቶች እንዲከላከል ሲሉም በመግለጫቸው ተናግረዋል። መንግሥት ብሔር ሳይለይ ንጹሀን ዜጎችን ከጥቃት እንዲታደግ፣ ወሲባዊ ጥቃቶች በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ እንዲፈቅድና ጥፋተኞችን ተጠያቂ እንዲያደርግ የቡድኑ ልዩ ተወካይ ፕራምሊያ ፓተን አሳስበዋል።
news-44679026
https://www.bbc.com/amharic/news-44679026
"የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ የህዝቡን ውይይት መጠየቁ አይቀሬ ነው" - አቶ ንጉሡ ጥላሁን
ዕለተ እሁድ ሰኔ 24/2010፤ የባህርዳር እና አከባቢዋ እንዲሁም ከሌሎች ሥፍራዎች የመጡ ኢትዮጰያዊያን "ለውጥን እንደግፍ፤ ዲሞክራሲን እናበርታ" በሚል መሪ ቃል ከተማዋን አድምቀዋት ውለዋል።
ወደ መቶ ሺህ እንደሚጠጉ የተነገራለቸው እኚህ የሰልፉ ተሳታፊዎች በዋነኛነት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለማሻሻያ እርምጃዎቻቸው ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ ነው አደባባይ የወጡት። ይህንን ተከትሎም አማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ንጉሥ ጥላሁን ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ቢቢሲ- የትናትንትናውን ሰልፍ አጠቃላይ ሁኔታ ምን ይመስል ነበር? ምን ያህል ሰዎች ተገኙ? ሰልፉስ እንዴት አለፈ? አቶ ንጉሱ፦ ከሰኔ 16 ጀምሮ እስከ ትናትናውን ዕለት ድረስ በክልላችን ከ43 በላይ ከተሞች ነው የድጋፍ ሰልፍ የተደረገው። ሰሞኑን የሚያደርጉም አሉ። በሁሉም ከተሞች ባለቤት ሆኖ፣ አቅዶ የፈፀመው የየከተሞቹ ህብረተሰብ ነው። ወጣቶቹ ራሳቸው አስተባባሪ ኮሚቴ መስርተው፣ መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብርላቸው ጥያቄ አቅርበው ነው የሄዱት። እናም በአስካሁኑ በሁሉም ሥፈራዎች የተካሄዱ የድጋፍ ሰልፎች በሰላም ተጠናቅቋል። የባህር ዳሩ ክልላዊ ነው፤ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተገኘበትም ነው። በባህር ዳር ስቴዲየም ለመጀመሪያ ጊዜ ይሄን ያህል ሰው፣ በሜዳውም በመቀመጫውም ሞልቶ የተገኘበት ነበር። ሜዳውን የሚያስተዳድሩ ባለሞያዎች እንደሚያስረዱት ሕዝቡ ከመቶ ሺህ በላይ ይገመታል። እንግዲህ በሰልፉ ላይ ህብረተሰቡ መልዕክት አስተላልፏል። ከዚያ ባሻገር እጅግ ሰላማዊ እና በተፈለገው መልኩ የተጠናቀቀ ሰልፍ ነው። ቢቢሲ- በሰልፉ ላይ በተለየ ሁኔታ ጎልተው ከተስተዋሉት ጉዳዮች አንዱ ከሰንደቅ ዓላማ አጠቃቀም ጋር የተያያዘው ነው። አርማ የሌለበት አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በስፋት ታይቷል። ይህ ምን ዓይነት መልዕክት ወይንም አንድምታ ይዟል ብላችሁ ታስባላችሁ? አቶ ንጉሱ፦ [ይህ ባንዲራ] በእኛ ክልል፤ በተለያዩ ጊዜያት፤ በተለይም በኃይማኖት በዓላት፣ በጥምቀት፣ በደመራና በመሳሰሉት በዓላት ላይ ህብረተሰቡ በአገልግሎት ላይ ይውላል። በሃዘንም፣ በደስታም፣ በለቅሶ ላይ ሁሉ ተይዞ ይወጣል። በተለይ በአማራ ክልል፣ በተለይም ቀደም ሲል በነበሩት ጊዜያት፣ ህብረተሰቡ በሰፊው ጥቅም ላይ ያውለዋል። ህገ መንግስታዊው፤ አርማ ያለው ሰንደቅ ዓላማ በመንግስት መድረኮች እና መንግስታዊ በሆኑ ተቋማት የሚውለበለብ እና አገልግሎት ላይ የሚውል ነው። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ይሄ ሰንደቅ ዓላማ አንዳንድ ጊዜ በርከት ብሎ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አነስ ብሎ በአደባባዮች ጭምር የሚታይ ነው። በኃይማኖት ተቋማት የሚታይ ነው። ለእኛ ብቻ ሳይሆን፣ ለማንም ይሄን ላየ ሕብረተሰቡ ይሄንን ሰንደቅ ዓላማ ፈልጎ ይዞ መውጣቱና ህገ መንግስታዊውን ሰንደቅ ዓላማ በተመለከተ ከክልላችን ህዝብ ጋር ብዙም ያልተግባባን መሆኑን ያስረዳን ነው። ምናልባትም በመመሪያዎች በደንቦች ያስቀመጥናትቸው ህግጋት ስላሉ፤ ለህግ ተገዥነቱን ለማሳየት፤ ግን ደግሞ ልዩነቱን በእንደዚህ ዓይነት መልኩ በስፋት እንዲገልፅ ዕድል በተፈጠረበት ጊዜ መግለፅ መቻሉን ነው ያስረዳን። ለምንድን ነው እስካሁን እንደዚህ በስፋት አጥለቅልቆ ይዞ ያልወጣው? ብለን ብንጠይቅ መልሱ እኛ ህብረተሰቡ ማንኛውንም ነገር እንዲያደርግ አልፈቀድንለትም፤ ተፅዕኖ አሳድረንበታል ነው። ስለዚህ ህገ መንግስታዊ በሆነው ሰንደቅ ዓላማ ላይ አልተግባባንም፣ አልተቀበለንም ማለት ነው። ስለዚህ ቀጣይ፤ ለበለጠ መግባባት ህብረተሰቡን በዚህ ጉዳይ ላይ ማወያየት፤ ውሳኔውን አይቶ እንዲወስን፤ ያመነበትን እንዲያደርግ ስራ እንዳለብን ነው ያስተማረን። ቢቢሲ - በዚህ ረገድ በእናንተ በኩል የክልሉን ህዝብ ውሳኔ እና ምርጫ ተግባራዊ ለማድረግ የመስራት ተነሳሽነት አለ? አቶ ንጉሱ፦ ህገ መንግስቱ የአማራ ክልል ሕዝብ ብቻ አይደለም። ህገ መንግስታችን ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝቦች፥፣ ብሄር እና ብሄረሰቦች ህገ መንግስት ነው። ሰንደቅ ዓላማውም ህገ መንግስታዊ ሰንደቅ ዓላማ ነው። ስለዚህ የአማራ ክልል ለብቻው ከህገ መንግስቱ ያፈነገጠ ውሳኔ አይወስንም። በመንግስትም በሕዝብም። ነገር ግን ህብረተሰቡ ኃሳቡን ገልጿል፤ ምልክት አሳይቷል። ስለሆነም ምን እናድርግ ብለን ከሕዝባችን ጋር ነው የምንመካከረው። የአማራ ህዝብ ከሌሎች ብሄሮች እና ብሄረሰቦች ጋር በእኩልነት፣ ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ እንኑር ነው ያለው። ዴሞክራሲያዊ ማለት በሁሉም ጉዳዮች ላይ መክሮ ዘክሮ አብዛኛው ይሁን ያለውን መቀበል ነው። ስለዚህም በተናጠል አንድ ክልል የሚወስነው ሳይሆን፤ ሁሉም ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚወስኑት ነው ማለት ነው። ነገር ግን በአማራ ህዝቦች ዘንድ ያለው መልዕክቱ ህገ መንግስታዊው ሰንደቅ ዓላማን በተናጠልም ይሁን በጋራ ይዞ መውጣት አልፈለገም ማለት ነው። ለምን ብለን መመርመር አለብን። ሃያ ሰባት ዓመት ሙሉ ይሄንን እንዲቀበለው፤ በልቡ ላይ እንዲፃፍ አልሰራንም፤ መመሪያ እና ደንብ በአዋጅ አውጥተናል። እነዚህ መመሪያ እና ደንቦች በልቡ እንዲቀበላቸው አላደረግንም። ስለዚህ እነዚህን ጉዳዮች በደንብ አግባብተን እና ተግባበተን፤ መነሻውን እና መድረሻውን፤ አንድምታውን ለይተን በደንብ መነጋገር እና መግባባት የምንችልበት ሁኔታ ይፈጠራል። ወይንም ሌሎች ጉዳዮች ካሉ የሚታይ ነው የሚሆነው። ዞሮ ዞሮ የህዝብ ውይይት፤ የህዝብ ኃሳብ የሚፈልግ አጅንዳ እንደሆነ አይተናል። ችግሩ የሚመስለኝ የህዝቦችን ነፃነት፣ አብሮነት እና ህገ መንግስቱን በሰንደቅ ዓላማ አጀንዳ ማሳነስ፤ የሰንደቅ ዓላማ ንትርክ ውስጥ መግባት ነው። የክልላችንም ህዝብ ይሄንን ይገነዘባል። እኔ ያልኩት ካልሆነም አይልም። ነገር ግን የህዝቡን ውይይት መጠየቁ አይቀሬ ነው። ቢቢሲ- በተለያዩ የክልሉ ክፍሎች ውስጥ በተከናወኑ ሰልፎች ላይም የክልሉ ሰንደቅ ዓላማ እንዲሁ በብዛት አልታየም። ይሄስ ምንን ያመለካታል ይላሉ? አቶ ንጉሱ፦ በዚህ ጉዳይ ላይ የግል አስተያየቴን ነው የምሰጠው። እንደክልል መንግስት ለውይይት የቀረበ እና አቋም የተወሰደበት ጉዳይ አይደለም። ለምን የአማራ ክልል ሰንደቅ ዓላማ አልታየም ብለን ብንወስድ ይሄ የራሱ ምክንያት ይኖረዋል። አሁን እየተነጋገርን ያለነው፤ ህብረሰተቡ ይሄንን ሰንደቅ ዓላማ ይዟል፤ በህገ መንግስት የተደነገገውን ሰንደቅ ዓላማ አልያዘም፤ በክልሉ ህገ መንግስትም የተደነገገውን ሰንደቅ ዓላማ አልያዘም የሚል ነው። ይሄ ኅብረ ብሄራዊ ክልል ነው። በርካታ ብሄር ብሄርሰቦች በጊዜያዊነትም፤ በቋሚነትም የሚኖሩበት ክልል ነው። ስለዚህ ይህ ጉዳይ የአማራ ህዝብ አጀንዳ ብቻ ሳይሆን በመላ አገሪቱ ህገ መንግስት ላይ በተቀመጡት ጉዳዮች በተለይም ሰንደቅ ዓላማን በሚመለከቱት ላይ መነጋገር እና እንደገና በደንብ መወያየት እና የጋራ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይጠይቃል። በአዲስ አበባው ሰልፍ እንዳየነው በርካታ ሰንደቅ ዓላማዎች ነው የታዩት፤ በባህር ዳር ደግሞ አንድ ዓይነት ነው። ስለዚህም እነዚህን ፍላጎቶች እንዴት ነው ማጣጣም የሚቻለው? የሚለው መመለስ ያለበት በህዝብ ስምምነት እና ከህዝብ ጋር በሚደረግ ውይይት ነው። ስለዚህ የክልሉ እና የፌዴራሉ ሳንል በአጠቃላይ በሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ የቤት ስራ አለብን ብለን ነው መደምደም የምንችለው።
48559839
https://www.bbc.com/amharic/48559839
ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ "ሄሜቲ"፦ የሱዳንን መፃዒ ዕድል የሚወስኑት የጦር አበጋዝ
ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ "ሄሜቲ" የሱዳን አስተዳዳሪ ለሆነው የመከላከያ ኃይል ምክትል ፕሬዝዳንትና እጅጉን ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰው ናቸው።
በቀውስ ላይ ያለችውን ሱዳን የመጠገን አቅም አላቸው። ነገር ግን ኮማንደሩ ዳርፉር ላይ በተከሰተው የሚሊሻዎች ጭፍጨፋ ይከሰሳሉ። አሁን ላይም ካርቱም ውስጥ በተካሄዱት ግድያዎች እጃቸው አለበት የሚሉ ወገኖች በርካቶች ናቸው። ሄሜቲ የዳርፉሩን ጭፍጨፋ በተመለከተ "እርምጃው ንዑሃንን ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊ ነበር" ሲሉ የካርቱሙን ጉዳይ ደግሞ ገለልተኛ ወገን ገብቶ ያጠናዋል፤ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ተፈናቃዮች አይንና ጆሮ እንደተነፈጋቸው ተገለፀ "ማንኛውም ሰው ድንበሩን ካለፈም መቀጣት አለበት" ብለዋል። የተቃዋሚዎችን መብት አፍናችኋል የተባሉት ኮማንደሩ ሰልፈኞቹ በአጭበርባሪዎችና በአደንዛዥ እፅ ነጋዴዎች የተደለሉ ሰዎች ናቸውም ሲሉ ተደምጠዋል። "ቀውስ እንዲፈጠር አንፈልግም ወደ ቀደመ እምነታችንም አንመለስም" የሚሉት ሄሜቲ "ወደኋላ የምንመለስበት ምክንያት የለም። የሃገሪቱን ክብር በሕግ እናስከብራለን" ብለዋል። አሜሪካ፡ የመድኃኒት ዋጋ ሰማይ የደረሰባት ሃገር ሄሜቲና የሱዳን ተቃውሞ ሄሜቲ የቀድሞው የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር የቅርብ ሰው ነበሩ። ነገር ግን ተቃውሞዎች በታህሳስ ሲጀምሩ ወዳጅነታቸውን ቀንሰዋል። የተቃውሞ ሰልፎች ሲጀመሩ ከከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች መካካል ድጋፍ በመስጠት ሄሜቲ የመጀመሪያው ናቸው። መንግሥትንም "ለዜጎች ተገቢ አገልግሎት በመስጠት ኑሯቸውን ሊያሻሽል ይገባል" ብለዋል። ሚያዝያ 11 ኮማንደሩ ፕሬዝዳንት አል በሽር ሥልጣን እንዲለቁ ካስገደዱ ከ2 ቀናት በኋላ የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው መጡ። "ደላላው ወደ ቤቱ ወሰደኝ፤ በዚያው ቀን አስገድዶ ደፈረኝ" ሄሜቲ ለምን ጠንካራ ሥልጣን አገኙ? ምንም እንኳ የወታደራዊ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ቢሆኑም ከምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ጋር ሲደራደሩ የሚታዩት ግን ሄሜቲ ናቸው። የዐረብ ቡድን የሆነውና በምዕራብ ሱዳን የሚገኘው የጃንጃዊድ ወታደር ፖለቲከኞች እንደሚደግፏቸውም ይነገራል። የቢቢሲ አፍሪካ አርታኢው ፈርጋል ኪን እንደሚለው "ተቃውሞውን መቀልበስ የሚችሉ መሪና ከወታደሩም የተለየ አመለካከት ያላቸው" ይላቸዋል። የ 'ምን ልታዘዝ' ድራማ ሰምና ወርቅ ከግብፅ፣ ሳዑዲ ዐረቢያና የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚሰጣቸው ድጋፍም ሌላኛው የሄሜቲ የኃይል ምንጭ ነው ይባላል። እነዚህ የዐረብ ሃገራት፤ የሱዳንን መረጋጋት ስለሚፈልጉት ምንም ዓይነት ማዕቀብ በወታደራዊ አስተዳደሩ ዙሪያ መጣል አይፈልጉም። በእርግጥ ሳዑዲ ዐረቢያ የቀጠናው አለመረጋጋት እንደሚያሳስባትና ሁለቱ አካላት መደራደር እንዳለባቸው ጥሪ ማቅረቧ ይታወሳል። የምሥራቅ ሸዋ ፖሊስ የተዘረፈውን ቡና እየፈለገ ነው የአልጀዚራ ሪፖርት እንደሚያሳየው ሄሜቲ በግንቦት ወር መጀመሪያ አካባቢ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በመሄድ ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማንን አግኝተዋቸዋል። በዚህም ከሁሉም ጥቃትና ስጋት ሃገሪቱን ለመከላከል፣ ከኢራንና ከሁቱ ሚሊሻዎች የሚሰነዘረውን ጥቃት ለመመከት እንዲሁም ሳዑዲ በየመን ለምታካሂደው የቅንጅት ጦርነት ሱዳን ወታደር እንደምትልክም ቃል ገብተው ተመልሰዋል። ምናልባትም የሳዑዲው ልዑል በአፀፋው ከሄሜቲ ጋር ጠንካራ ወዳጅነትን መርጠው ሊሆን ይችላል። ከግመል ነጋዴነት ወደ ጦር መስፍንነት ሄሜቲ ከቻዳዊ የዐረብ ጎሣ ነው የተወለዱት። ጦርነትን በመሸሽ በ1980ዎቹ በዳርፉር መኖር ጀመሩ። እ.አ.አ 2003 ላይ በዳርፉር ጦርነት ተቀሰቀሰ። መብታችን ተረግጧል የሚሉ ጥቁር ነዋሪዎች አማፂ ቡድንን ፈጠሩ። የመንግሥት ወታደርም ጃንጃዊድ ከሚባለው ቡድን ጋር በመሆን ጥቃት ፈፀመ። በዚህም ግመል የሚያረቡ ሰዎች ተገደሉ፣ ሴቶች ተደፈሩ፣ ማንኛውንም ያገኙትንም ንብረት ዘረፉ። ''ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም'' ከ2005 ጀምሮም ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የዘር ፍጅት እና በንፁሃን ላይ በተከፈተ የጦር ወንጀል ጥናት አድርጓል። በዚህም በርካታ የሱዳን ባለሥልጣናት፣ የጃንጂዊድ እና የአማፂ ቡድኑ ጥፋተኛ ተብለዋል። በሱዳንና ቻድ ድንበር ያለውን አካባቢ ከተቆጣጠሩት የዐረብ ጎሣዎች መካከል የሄሜቲ አጎት ጁማ ዶንጎሎ ዋናው ናቸው። ሄሜቲ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አቋርጠው የግመል ንግድ ይሠሩ የነበር ሲሆን በዳርፉር ጦርነት ወቅትም ለተዋጊዎች ግመል ያከራዩ ነበር። በዚህ ሥራቸው የንግድ ሰው እና ባለፀጋ መሆንም ችለዋል። ወደ ለንደን የሚሄደው አስደናቂው የትራምፕ ጓዝ በ2003 የዳርፉር አማፂያን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ሄሜቲ ዘላኖችን በማደራጀት መንግሥትን እንዲያግዙ አድርገዋል። ከዓመት በኋላ ደግሞ ይህ ቡድን መደበኛ ወታደር መሆኑን መንግሥት ይፋ አደረገ። በዚህም ሄሜቲ በፕሬዝዳንት አል በሽር ድጋፍ አገኙ። ወዲያውም ዳርፉር አካባቢ ለሚገኘው የድንበር ጠባቂ ጦር መሪ ሆነው ተመረጡ። በ2013 መደበኛ ሠራዊቱን ለማገዝ "ፈጥኖ ደራሽ ኃይል" ተቋቋመ። ከዓመት በኋላ ደግሞ ቡድኑ መደበኛ ሠራዊት እንዲሆን በመንግሥት እውቅና ተሰጠው። ተንታኞች እንደሚሉት ግን ጃንጂዊድን እንደገና ማቋቋም ነው። አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዳርፉር ላይ በተፈጠረው የዘር ፍጅት፣ የጦር ወንጀለኝነትና በሰብዓዊ ቀውስ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ይፈለጋሉ። በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ስማቸው ባይጠቀስም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን በግርፋት እና ሴቶች በብዛት እንዲደፈሩ በማድረግ ሄሜቲን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ስለአልኮል ማስታወቂያ ክልከላ የሚዲያ ባለሙያዎች ምን ይላሉ? የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት በ2014/15 በተካሄደ አመፀኞችን የማፅዳት ዘመቻ መድፈር፣ ቤቶችን ማቃጠል፣ ነዋሪዎችን በጅምላ መግደል በሱዳን ወታደርና በጃንጃዊድ ሚሊሻዎች ተፈፅሟል። ግንቦት 19፣ 2014 እርምጃው የዳርፉር ንፁሃንን ለመጠበቅ የተወሰደ መሆኑን ሄሜቲ ገልፀው ነበር። ጦሩ ማንኛውንም የፀጥታ ስጋት የሚፈጥር አካል ላይ እርምጃ እንዲወስድም አስጠንቅቀዋል። በካርቱም በሚካሄደው ተቃውሞም ዳርፉር ጎልቶ ስሟ ተነስቷል። ሁላችንም ዳርፉር ነን፣ ዳርፉር ቤታችን ነው የሚሉ ድምፆች ተሰምተዋል። የታኮ ጫማ ውዝግብ በጃፓን ሄሜቲ በዳርፉርም በካርቱምም ጨካኝነታቸው በተግባር ቢታይም ሰላማዊ ተቃዋሚዎቹ ግን መብታችንን ለማስጠበቅ እጅ አንሰጥም እያሉ ነው።
news-49167652
https://www.bbc.com/amharic/news-49167652
የታዋቂዋ ወጣት አስክሬን ሻንጣ ውስጥ ተገኘ
ተጽእኖ ፈጣሪዋ እና ኢንስታግራም ላይ ብዙ ተከታዮች ያሏት ሩሲያዊት፤ ሞስኮ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ አስክሬኗ ሻንጣ ውስጥ ተገኝቷል።
ኤካቴሪና ከሞስኮ የህክምና ትምህርት ቤት በቆዳ ህክምና የዶክትሬት ዲግሪዋን ተቀብላ ነበር። ፖሊስ እንዳለው የ24 ዓመቷ ወጣት ኤካቴሪና ካራግላኖቫ በስለት ተወግታ ስለመሞቷ በአስክሬኑ ላይ ምልክቶች ታይተዋል። በኢንስታግራም ላይ ከ85ሺህ በላይ ተከታዮች የነበሯት ኤካቴሪና በቅርቡ በህክምና ዘርፍ የዶክትሬት ድግሪዋንም ተቀብላ ነበር። • ጠብ አጫሪና ጥቃት አድራሽ የፌስቡክ ፖስቶችን እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል? ኤካቴሪና ከቤተሰቧቿ ጋር ግንኙነት አለማድረጓን ተከትሎ በቤተሰብ አባላት ላይ ጥርጣሬ ካደረ በኋላ ነው አስክሬኗ ሊገኝ የቻለው። የገዳዩ ማንነት እስካሁን ባይታወቅም የተገደለችው ግን በቅናት መንፈስ በተነሳሳ ሰው ሳይሆን አይቀርም ሲል ፖሊስ ቅድመ ግምቱን አስቀምጧል። ሞስኮበስኪይ ኮመሶሞሌትስ የተሰኘ የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው ከሆነ ኤካቴሪና ከዚህ ቀደም የነበራትን የፍቅር ግንኙነት በማቋረጥ አዲስ ፍቅር መጀመሯን እና ልደቷን ለማክበር ወደ ሆላንድ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ ነበረች። ኤካቴሪናን ለቀናት ያላገኙት ወላጆች ተከራይታ ወደ ምትኖርበት የጋራ መኖሪያ ቤት ያቀናሉ። ተከራይታ ከምትኖርበት ቤት ከደረሱም በኋላ ከአከራይዋ ቁልፍ በመቀበል ወደ ውስጥ ሲዘልቁ አስክሬኗን ሻንጣ ውስጥ ተከቶ አግኝተዋል። • ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች ድንጋጤ ውስጥ የነበሩት ወላጆች የአምቡላንስ እርዳታን ቢጠይቁም የልጃቸው ህይወት ቀድሞ ማለፉ ከጤና ባለሙያዎች ተነግሯቸዋል ሲል የሩሲያው መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ኤካቴሪና አንገቷ ላይ በስለት ስለመቆረጧ ምልክት መኖሩም ተዘግቧል። ከጥቂት ወራት በፊት ከዚህ በታች የተመለከተው በኢንስታግራም ገጿ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት፤ መኖሪያ ቤቷን እንዴት እንደምታስጌጥ እና ስላሰበቻቸው የውጪ አገር የጉዞ እቅዶች ብዙ ብላ ነበር። ፖሊስ ወንጀሉ የተፈጸመበት መሳሪያ በቦታው አለማግኘቱን የተናገረ ሲሆን፤ የቀድሞ እጮኛዋ በጠፋችበት ቀን ወደ ቤቷ ሲገባ በሲሲቲቪ ካሜራ መታየቱን ፖሊስ አሳውቋል። • "የአደገኛ ግለሰቦች" የፌስቡክ ገጽ መዘጋት ጀመረ ፖሊስ ይህን ይበል እንጂ የቀድሞ ፍቅረኛዋ ከግድያው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ስለመዋሉ ያለው ነገር የለም። ኤካቴሪና በኢንስታግራም ገጿ ላይ የምትለጥፋቸው ፎቶግራፎች ከትውልድ ሃገሯ ሩሲያ ተነስታ ወደ በርካታ የዓለማችን ከፍሎች መጓዟን ያሳያሉ። ለመጨረሻ ግዜ የለጠፈችው በግሪክ ሃገር ኮርፉ በተሰኘ ደሴት ላይ የተነሳችው ፎቶግራፍ ሲሆን "ጉዞ ማድረግ እወዳለሁ። በየትኛው ሃገር ግን ከ3-5 ቀናት በላይ መቆየት አያስደስተኝም" የሚል ጽሁፍን አብራ አያይዛለች። ከኢንስታግራም ተከታዮቿ በተጨማሪ ኤካቴሪና በሺዎች የሚቆጠሩ የሚጎበኙት ስኬታማ የሆነ የጉዞ ማስታወሻ መጣጥፎቿን የምታስነብብበት ድረ-ገጽም ነበራት። ከዚህ በተጨማሪም ኤካቴሪና ከሞስኮ የህክምና ትምህርት ቤት በቆዳ ህክምና የዶክትሬት ዲግሪዋን ተቀብላ ነበር።
news-57313049
https://www.bbc.com/amharic/news-57313049
በቤልጂየም አንዲት ታዳጊን ደፍረው ለሞት የዳረጉ አምስት ወንዶች ተያዙ
በቤልጂየም የ14 አመቷን ታዳጊ በቡድን ደፍረው ለሞት ዳርገዋል የተባሉ አምስት ታዳጊ ወንዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ታዳጊዋ ከአራት ቀናት በኋላ ራሷን አጥፍታለች። የቤልጂየም ሚዲያዎች ሪፖርት እንዳደረጉት ጥቃቱ ሲደርስባት የሚያሳዩ ምስሎች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተጋሩ ነበር ብለዋል። የአገሪቱ አቃቤ ህግ እንዳሳወቀው ሶስቱ ተጠርጣሪዎች ከ18 አመት በታች ሲሆኑ ሁለቱ ግን 18ና 19 መሆናቸውን አስታውቆ በዛሬውም እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ብሏል። ታዳጊዋ መሞቷን ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት ታዳጊዎች ምርመራ እንደተከፈተባቸውም ተዘግቧል። የቤልጂየም ሚዲያ ሪፖርት እንዳደረገው ታዳጊዋ አንድ ጓደኛዋን መቃብር ስፍራ አካባቢ ሊገናኙ ቀጠሮ ይዘው የነበረ ቢሆንም አራት ጓደኞቹን ይዞ መጥቶ በቡድን ደፍረዋታል። ጥቃት ሲደርስባት የሚያሳዩ ምስሎችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ተጋርተዋል። "በእነዚህ ምስሎች ናቸው አለም ሁሉ ያያት፤ ሙሉ አለሟ ተገለባበጠ" በማለት አባትዋ ሄት ኒውስባልድ ለተባለ የቤልጂየም ሚዲያ ተናግሯል። ጉዳዩ የቤልጂየም ባለስልጣናትን አስቆጥቷል የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ሺልትዝ ወሲባዊ ጥቃቶችን የሚያሳዩ ምስሎች በበይነ መረብ እንዳይጋሩ ለማድረግ ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገብተዋል። "እንዲህ አይነት ጥቃቶችን የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያ መጋራት የሚረብሽ ብቻ ሳይሆን ህገ ወይም ነው። በጭራሽ መደረግ የሌለበት ነገር ነው" ያሉት ሚኒስትሯ ቡድንም አዋቅረው ከተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ተወካዮች ጋር ለመነጋጋርና ቁጥጥር የሚደረግበትን ፖሊሲም አንደሚገመግሙ አስታውቀዋል። "በጭራሽ ቃላት የለኝም። አፀያፊ ነው" በማለት የቤልጂየም ፍትህ ሚኒስትር ቪንሰንት ቫን ኩይኬንቦርን በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። "ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባችሁ እባካችሁ ሪፖርት አድርጉ። ፍትህ ከናንተ ጎን ናት። ጥቃት ያደረሱባችሁን ለመቅጣት ሁሉንም ነገር እናደርጋለን። እንዲሁም እንዲህ አይነት ምስል የሚያጋሩትንም ጭምር" ብለዋል። ሊዝቤት ስቲቨንስ የተባሉ የስርዓተ ፆታ ባለሙያ ለቪአርቲ ሚዲያ እንደተናገሩት ይህ ጥቃት ብቸኛ እንዳልሆነና በቤልጂየም በየአመቱ 200 የቡድን ደፈራዎች ሪፖርት ይደረጋሉ ብለዋል።
news-49068096
https://www.bbc.com/amharic/news-49068096
እስራኤል በፍልስጤም ይዞታ ሥር የሚገኙ ቤቶችን እያፈረሰች ነው
እስራኤል በፍልስጤም ይዞታ ስር የሚገኙ እና ''በሕገ-ወጥ መንገድ'' ተገነቡ ያለቻቸውን ቤቶች ማፍረስ ጀመረች።
እስራኤል በፍልስጤም ይዞታ ስር የሚገኙ 'በሕገ-ወጥ መንገድ ተገነቡ' ያለቻቸውን ቤቶች እያፈረሰች ነው እስራኤል ''በሕገ-ወጥ" ተገነቡ የምትላቸው ቤቶች እአአ 1967 በተካሄደው የስድስት ቀን ጦርነት ከተቆጣጠረቻቸው ግዛቶች አንዱ በሆነው ዌስት ባንክ አጥር አቅራቢያ የተገነቡ ቤቶችን ነው። በፖሊስ እና በእስራኤል ጦር የታጀቡ ቡልዶዘሮች እነዚህን መኖሪያ ቤቶች ሲያፈራርሱ ታይተዋል። ነዋሪዎች ቤቶቹን ለመገንባት ከፍልስጤም ግዛት አስተዳደር ኃላፊዎች ፍቃድ ማግኘታቸውን እና እስራኤል ቤቶቹን የምታፍርሰው የዌስት ባንክ መሬትን ለመውረር ነው ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። • እየሩሳሌም፡ የትራምፕን ውሳኔ ዓለም እያወገዘው ነው • አሜሪካ ለእየሩሳሌም የእሥራኤል መዲናነት እውቅና ልትሰጥ ነው የእስራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግን ቤቶቹ የተገነቡበት ቦታ ግንባታ ላለማካሄድ ስምምነት የተደረሰበት ሥፍራ ነው በማለት ቤቶቹ እንዲፈርሱ ድጋፉን ሰጥቷል። ቤቶቹ የተገነቡት በፍልስጤም አስተዳደር ሥር በሚገኝ የዌስት ባንክ ግዛት ውስጥ እና እስራኤል በገነባችው ሁለቱን አካላት ከሚለየው አጥር መካከል ነው። እስራኤል በዌስት ባንክ እና አቅራቢያው አጥር የገነባችው ሁለተኛ የፍልስጤማውያን ተቃውሞ ከተቀጣጠለ በኋላ ነበር። እስራኤል ግንቡ ከፍልስጤም አቅጣጫ ሊቃጣብኝ የሚችለውን የሽብር ጥቃት እና የደህንነት ስጋትን ለማስቀረት የገነባሁት ነው ትላለች። ፍልስጤማውያን ግን የፍልስጤም ምድርን ለመውረር እና የዘር መድልዎ ለማድረግ ነው በማለት ግንቡን 'የአፓርታይድ ግንብ' ሲሉ ይጠሩታል።
news-49224756
https://www.bbc.com/amharic/news-49224756
ቴክሳስ የሚገኝ መገበያያ ውስጥ በተከሰተ ጅምላ ጥቃት 20 ሰዎች ሞተዋል
በአሜሪካዋ ቴክሳስ ክፍለ-ግዛት ውስጥ በምትገኝ አል-ፓሶ በተባለች ሥፍራ በደረሰ ጅምላ ግድያ 20 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ 26 ደግሞ በፅኑ መጎዳታቸው ታውቋል።
የቴክሳስ ሃገረ-ገዥ ግሬግ አቦት ግድያው በግዛቲቱ ታሪክ አሰቃቂው ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ዎልማርት የተባለ መገበያያ ሥፍራ ውስጥ ሃገር ሰላም ብለው ሲገበያዩ የነበሩ ሰዎች ናቸው የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት። • በካሊፎርኒያ ከተገደሉት መካከል የስድስት ዓመት ታዳጊ ይገኝበታል ከግድያው ጋር በተያያዘ ፓትሪክ ክሩሲየስ የተባለ አንድ የ21 ዓመት ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አሳውቋል። ግለሰቡ ጥቃቱ ከደረሰበት አንድ ሺህ ኪሎሜትር ርቃ የምትገኘው የዳላስ ግዛት ነዋሪ ነው ተብሏል። የሲሲቲቪ ካሜራው እንደሚያሳየው ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ጥቁር ቲሸርት አድርገው፤ በድምፅ መከላከያ መሰል ነገር ጆሯቸው ጀቡነው ነው ወደ መገበያያው የገቡት። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥቃቱን 'የአረመኔነት መገለጫ' ሲሉ ገልፀውታል። በትዊተር ገፃቸው መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዝደንቱ ጥቃት አድራሾቹን ያደረጉት ድርጊት ምንም ዓይነት ፍትሃዊ አመክንዮ የሌለው ነው ሲሉ ተደምጠዋል። • 'የተሳመው ከንፈር' ጥቃት ደረሰበት አሜሪካን ከሜክሲኮ ከሚያዋስነው ድንበር አካባቢ በደረሰው በዚህ ጥቃት የሞቱ ግለሰቦች ስም እስካሁን ይፋ አልሆነም። የሜክሲኮው ፕሬዝደንት ማኑዌል ሎፔዝ ኦብራዶር ግን ሶስት የሃገሬ ሰዎች ሞተዋል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ጥቃቱ በሃገሪቱ አቆጣጠር ከረፋዱ 4 ሰዓት ሲሆን የደረሰው በርካቶች በድንጋጤ ሕንፃውን እየለቀቁ ሰወጡ ታይተዋል። ካሊፎርኒያ ውስጥ በነበረ የምግብ ፌስቲቫል ላይ አንድ በአሥራዎቹ የሚገኝ አፍላ ሶስት ሰዎች ከገደለ ሳምንት እንኳን ሳይሞላው ነው ይህኛው የጅምላ ጥቃት የደረሰው። • በደብረማርቆስ 'ባለስልጣኑ አርፈውበታል' የተባለው ሆቴል ጥቃት ደረሰበት
48973391
https://www.bbc.com/amharic/48973391
በሶማሊያ ኪስማዮ ግዛት በአንድ ሆቴል ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 26 ሰዎች ሞቱ
በደቡባዊ ሶማሊያ በአንድ ሆቴል ላይ በደረሰ ጥቃት ሐያ ስድስት ሰዎች መሞታቸው እየተነገረ ነው። ከሟቾቹ መካከል ትውልደ ሶማሊያዊት የሆነችው ካናዳዊት የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሆዳን ናላህ እንደምትገኝበት ዘገባዎች ያሳያሉ።
ባለስልጣናት ከአደጋው የተረፉት ሰዎች ነገሩን በማለት እንደሚያስረዱት፤ ጥቃቱን ያደረሰው ቦንብ የጫነ የአጥፍቶ ጠፊ መኪና ወደ አሳሴይ ሆቴሉ ጥሶ ከገባ በኋላ በመፈንዳቱ ነው። ከፍንዳታው በኋላ መሣሪያ የታጠቀ ግለሰብ ወደ ሆቴሉ በመግባት ያገኛችው ሰዎች ላይ መተኮስ መጀመሩ ተገልጿል። • በቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ባለሙያ በታጣቂዎች ተገደሉ • ኢህአዴግ ከአባል ፓርቲዎቹ መግለጫ በኋላ ወዴት ያመራል? • የጣልያን ፍርድ ቤት በተሳሳተ ማንነት የታሰረው ኤርትራዊ ነፃ መሆኑን ወሰነ አልሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ገልጿል። የአካባቢው ፖለቲከኞችና የጎሳ መሪዎች ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት በሆቴሉ ውስጥ በቅርቡ ስለሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ ውይይት እያደረጉ እንደነበር ማወቅ ተችሏል። የአይን እማኞች እንደሚሉት፤ ከቦንብ ፍንዳታው በኋላ ወዲያውኑ የተኩስ እሩምታ ሰምተዋል። ከጥቃቱ በኋላ ምናልባት ጥቃት አድራሾቹ ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ወደ አካባቢው አንድም ብቅ ያለ አካል እንዳልነበር ለማወቅ ተችሏል። የደህንነት አባል የሆነው አብዲ ዱሁል ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደተናገረው፤ ከሞቱት መካከል የቀድሞው የአካባቢ አስተዳዳሪ ሚኒስትር እና የሕግ አውጪው ይገኙበታል። በተጨማሪም ከሟቾቹ መካከል ሶስት ኬኒያውያን፣ ሶስት ታንዛኒያውያን፣ ሁለት አሜሪካውያን እና አንድ የብሪቴይን ዜጎች እንደሚገኙበት ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። የአካባቢው መገናኛ ብዙኀን እና የሶማሊያ ጋዜጠኞች ማኅበር የ43 ዓመቷ ናላይህ እና ባለቤቷ ከሞቱት መካከል መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
53987815
https://www.bbc.com/amharic/53987815
ሱዳን፡ በጎርፍ የተነሳ ቢያንስ 90 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ
በሱዳን በጎርፍ ምክንያት 90ያህል ሰዎች ሲሞቱ 400 ሺዎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ።
የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ እና ከ100 ዓመታት ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ሁናቴ የናይል ወንዝ ሞልቶ 17.5 ከፍ በማለቱ ጎርፉ ሊከሰት ችሏል። ድርጅቱ አክሎም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ንፁህ የመጠጥ ውሃ ማግኘት ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ በጎርፉ የተነሳ ይህም ተስተጓጉሏል ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያደረገው ዳሰሳ እንደሚያሳየው በጎርፉ ምክንያት ወደ 2 ሺህ የውሃ መገኛ ስፍራዎች ተበክለዋል ወይንም ተሰብረዋል። በጎርፉ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ክልሎች ምስራቅ ሱዳን፣ ነጭ ናይል፣ ዳርፉር፣ እና ካርቱም ሲሆኑ የተፈናቀሉ ሰዎች በአፋጣኝ የመጠለያና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል። " እሁድ እለት በካርቱም ብቻ፣ ከ21,000 ሰዎች በላይ በጎርፍ ተጎድተዋል። መንግሥትም በካርቱም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል። በመላ አገሪቱ ከነሐሴ ወር መጨረሻ ጀምሮ 380 ሺህ ሰዎች በጎርፍ ምክንያት ሲጎዱ 90 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።" ያሉት የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ቃል አቀባይ ዤንስ ላይርኬ ናቸው። በጎርፉ የተነሳ መንገዶች በመበላሸታቸው አስቸኳይ የሰብዓዊ ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ተጎጂዎች ማድረስ አልተቻለም።
54826547
https://www.bbc.com/amharic/54826547
በምዕራብ ትግራይ በኩል ውጊያ መቀጠሉን ደብረፅዮን (ዶ/ር) ተናገሩ
የአማራን ክልል በሚያዋስነው የምዕራብ ትግራይ ድንበር በኩል ግጭቶች እንዳሉ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ገለፁ።
ለሁለት ቀናት ያህል በቀጠለው የትግራይና የፌደራል መንግሥት ግጭትን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን ያሳወቁት። ደብረፅዮን (ዶ/ር) ውጊያው የአማራ ክልል በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ቀጥሏል ከማለታቸው ውጭ የትኛው ግዛት (ግዛቶች) እንደሆኑ አልጠቀሱም። የአማራ ልዩ ኃይልና የፌደራል ሰራዊቱ በጥምረት በመሆን የትግራይ ኃይል ጋር በትናንትናው ዕለት ጥቅምት 25/ 2013 ዓ.ም መዋጋታቸውን ተናግረዋል። የትግራይ ኃይል በክልሉ የሚገኙትን የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ጦር መሳሪያም ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል ብለዋል። "ትግራይ በሚገኙ የጦር መሳሪያዎች የትግራይ ህዝብ ጥቃት ሊፈፀምበት አይገባም። አሁን በሙሉ ታጥቀናል። በጦር መሳሪያ ከነሱ ያነስን አይደለንም፤ ምናልባት የተሻልን ነን" ብለዋል በመግለጫቸው በተጨማሪም ድንበር አካባቢ ሰፍረው የነበሩ የተወሰኑ መከላከያ ሰራዊት አባላት በአዲያቦ በኩል አድርገው ወደ ኤርትራ ድንበር ተሻግረዋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ ይህም "ያላቸውን ግንኙነት ያሳየ ነው" በማለት አስረድተዋል። የሰራዊት አባላቱ ትግራይ ክልል ከሚቆዩ ወደ ኤርትራ እንዲሻገሩም ትዕዛዝ ተሰጥቷቸውም ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትናንትናው ዕለት ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም ማምሻቸውን በሰጡት መግለጫ በሁመራ፣ በዳንሻ እና በቅርቃር አካባቢዎች የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻ "ሕወሓት ያሻውን ሳያደርግ የሞከራቸው ሙከራዎች ከሽፈዋል" ብለዋል። የአገር መከላከያ ሠራዊትም "የተቃጣበትን ጥቃት በመመከት እንዲሁም በማክሸፍ የሕዝቦችን ደህንነት እና የአገሪቱን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ኃላፊነቱን እየተወጣ" እንደሆነ ገልፀዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ የመጣው የፌደራልና የትግራይ ክልል መንግሥት ግንኙነት የማይታረቅ ደረጃ ደርሶ በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ህወሃት በትግራይ የሚገኘው የመከላካያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ገልፀው ጦርነት መከፈቱን አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው የመከላከያ ሠራዊት በኮማንድ ፖስት እየተመራ "ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል" ብለዋል። በትግራይና በፌደራል መንግሥት ያለውን ግጭት ተከትሎ በትግራይ ክልል የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው። የመብራት አገልግሎትም አለመኖሩን መቀሌ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። በከተማዋ ውስጥ ያሉ ባንኮችም ዝግ ሲሆኑ ነዋሪው ከትናንት በተሻለ ሁኔታ ከተማዋ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ታዝቧል። ከዚህም በተጨማሪ መቀሌ የሚገኙ የንግድ ተቋማትና የገበያ ማዕከላትም አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ብሏል።
51789011
https://www.bbc.com/amharic/51789011
'ፌክ' ፓስፖርት ይዞ ተገኝቷል የተባለው ሮናልዲንሆ ፍርድ ቤት ቀረበ
ብራዚላዊ የእግር ኳስ ጠቢብ ሮናልዲንሆና ወንድሙ ፓራጓይ ለመግባት ሃሰተኛ ፓስፖርት ተጠቅመዋል ተብለው በመጠርጠራቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ።
አቃቤ ሕግ፤ ወንድማማቾቹ ባለፈው ረቡዕ የፓራጓይ ዋና ከተማ አሱንሲዮን ሲደርሱ ሃሰተኛ ሰንዶች ተሰጥቷቸዋል ሲል ይከሳል። አቃቤ ሕግ ወንድማማቾቹ ቀለል ያለ ቅጣት ይቀጡ የሚል ሃሳብ ቢያቀርብም ዳኛው ግን የኋሊት ጠፍራችሁ አምጡልኝ ሲሉ አዘዋል። ሮናልዲንሆና ወንድሙ አርብ ዕለት ነው የካቴና ሲሳይ የሆኑት። አቃቤ ሕግ ሮናልዲንሆና ወንድሙ በቀጣፊዎች ተታለዋል ይላል። ወንድማማቾቹም 'እኛ የምናውቀው ነገር የለም' ይላሉ። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ያረፉበትን ሆቴል ከበረበረ በኋላ ምርመራ አድርጎባቸዋል። ሮናልዲሆንና ወንድሙ 'ፖስፖርቱ ሲሰጠን የክብር መገለጫ መስሎን ነበር' ይላሉ። ፓርጓዊው ዳኛ ሮናልዲንሆም ሆነ ወንድሙ ፍርድ እስኪሰጣቸው ድረስ ማቆያ እንዲሰነብቱ አዘዋል። ዓለም ካየቻቸው ድንቅ እግር ኳሰኞች አንዱ የሚባለው ሮናልዲንሆ ባለፈው ሐምሌ ግብር አልከፈለም ተብሎ የብራዚልና የስፔን ፓስፖርቱን መነጠቁ አይዘነጋም። አልፎም ብራዚል ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈጥሮ ሃብት መጠበቂያ ሥፍራ ገንብቷል ተብሎ ክስ ቀርቦበት ነበር። «ቃዋቂ እግር ኳሰኛ ነው። አከብረዋለሁ። ነገር ግን ሕግ ሕግ ነው» ሲሉ የፓራጓይ ሃገር ውስጥ ሚኒስቴር ለሃገራቸው ጋዜጠኞች ተናግረዋል። የ39 ዓመቱ ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ያቀናው አዲስ የታተመ መፅሐፉን ለማስተዋወቅና እርዳታ ለሚሹ ሕፃናት ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው። ሁለት ጊዜ የዓለም ኮከብ ተብሎ የተሸለመው ሮናልዶ የ2002 ዓለም ዋንጫ አሸናፊ ነው። አልፎም ከባርሴሎና ጋር ስኬታማ ጊዜ አሳልፏል። ብራዚላዊው የኳስ ቀማሪ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የተጣራ ሃብት እንዳለው ይገመታል።
news-56427911
https://www.bbc.com/amharic/news-56427911
የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት "በምንም ዓይነት መልኩ" እንደማይራዘም ተገለፀ
ኢትዮጵያ ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት እንደማታራዝም ገለፀች።
የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር በቀጣዩ ክረምት ቀጠሮ የተያዘለት ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በምንም ዓይነት መልኩ እንደማይራዘምና ለዚያ የሚያበቃ አሰራርና ምክንያትም እንደሌለ ገልጿል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይህንን የገለፀው የህዳሴ ግድብን 10ኛ ዓመትን በማስመልከት በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኝ የግድቡን አጠቃላይ ሁኔታ፣ የሦስትዮሽ ድርድሩ የደረሰበት ደረጃ ለመግለፅ እና ግብዓት ለመሰብሰብ ባለመ የምክክር መድረክ ላይ ነው። በሲምፖዚየሙ ላይ የተገኙት የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ዶ/ር ስለሺ በቀለ፣ የህዳሴው ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 79 በመቶ እንደደረሰ ገልፀዋል። ሱዳንና ግብጽ ባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው አማካይነት በተደረጉ ጉብኝቶች ላይ ኢትዮጵያ ቀጣዩን ዙር የግድቡን ውሃ ሙሌት ከማከናወኗ በፊት በሦስቱ አገራት መካከል ከስምምነት መደረስ አለበት ማለታቸው ይታወሳል። ለዚህም በአገራቱ መካከል በግድቡ ውሃ አሞላልና ቀጣይ ሥራ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ላይ ተጨማሪ አደራዳሪዎች እንዲሳተፉ የሚጠይቅ ደብዳቤ ሱዳን መጻፏን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሱዳን ዜና ወኪል የሆነው ሱና ዘግቧል። ሱና እንዳለው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ፣ የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ለሆኑት ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት፣ ለአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳዮችና ደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ፣ ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሕዳሴን ግድብ ድርድር በሚመለከት ደብዳቤ ልከዋል። ይህንን የሱዳንን ጥያቄ በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ማክሰኞ በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በሰጡት ምላሽ "በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የሚያደርጉት የሦስትዮሽ ድርድር የሚቋጨው በሦስቱ አገራት እንጂ በአደራዳሪዎች አይደለም" ብለዋል። "የአደራዳሪ ሚና ማስተባበር እንጂ ማጉረስ አይደለም" ያሉት አምባሳደር ዲና፤ ነገር ግን ሱዳንና ግብጽ አራት አደራዳሪ ወገኖች ይግቡ በሚል ያቀረቡት ሃሳብ ለኢትዮጵያ በይፋ እንዳልቀረበ ገልጸዋል። አክለውም አደራዳሪነት ማስተባበር እንጂ ውይይቱ የሚቋጨው በሦስቱ ተደራዳሪዎች እንደሆነ በስምምነት ሰነዱ መቀመጡን ገልጸዋል። "ለአፍሪካ ሕብረት ትልቅ ክብር አለን፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካን ችግር በአፍሪካ የመፍታት ፅኑ አቋም አላት" በማለትም ተናግረዋል። ሃምዶክ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ሱዳን "ኢትዮጵያ ሦስቱ አገራት [ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ] ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ሁለተኛውን ሙሌት በሰኔ ወር ለማካሄድ መወሰኗ አሳስቦናል" ብለዋል። አምባሳደር ዲና በበኩላቸው "ኢትዮጵያ ለድርድር ሁሌም ዝግጁ ናት። ሙሌቱ ይቀጥላል። ድርድሩ ግን ከሙሌቱ በፊትም ቢሆን ቢቋጭ ኢትዮጵያ ችግር የለባትም" ብለዋል። ሐምዶክ አራተኛ አደራዳሪ መግባቱ "ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ድጋፍ ያስገኛል እንዲሁም በድርድሩ ላይ መተማመንን ያረጋግጣል" ብለዋል። የመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ሱዳንና ግብጽ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የግድብ ሙሌት ሥምምነት ከመደረሱ በፊት እንዳታካሂድ ጠይቀዋል። ሱዳን በበኩሏ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ ሦስቱ አገራት ከሥምምነት ላይ ሳይደርሱ የግድቡ ሁለተኛ ዙር ሙሌት እንዳይካሄድ መግለጫ አውጥታ ነበር። ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታው እየተካሄደ ያለውና አስረኛ ዓመቱን የያዘው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከአፍሪካ ትልቁ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን፣ ከአምስት ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል አቅም ያለው ግዙፍ ግድብ ነው። የግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ባለፈው ዓመት ክረምት ላይ የተከናወነ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ደግሞ ከጥቂት ወራት በኋላ እንደሚከናወን ኢትዮጵያ ያስታወቀች ሲሆን፤ በሚጥለው ዓመት በተወሰነ ደረጃ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር ይጠበቃል። የታላቂ ሕዳሴ ግድብ "የኤሌትሪክ ብርሃን ላላገኙ 65 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ተስፋ ነው" ሲሉ የውሃ ሚኒስትሩ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ አስፍረዋል።
news-52358688
https://www.bbc.com/amharic/news-52358688
ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች
አና ሆይኒትዝካ ለ4 ዓመታት ኢትዮጵያ ከኖረች በኋላ ወደ ትውልድ አገሯ እንግሊዝ የተመለሰችው ከጥቂት ወራት በፊት ነበረ።
አና ሆይኒትዝካ እርሷ ከወራት በፊት ከኢትዮጵያ ትውጣ እንጂ "ኢትዮጵያ ከውስጤ አልወጣችም" የምትለው አና ትንሽ ከባህሉም ትንሽ ትንሽ ደግሞ ከቋንቋው በውስጧ እንዲቀር አሁንም ጥረት እያደረገች ነው። አልፎ አልፎ ስታወራ 'እሺ' እና 'እንዴ' የሚሉት ቃላት ከአፏ እንደማምለጥ እያሉ በእንግሊዝኛ ንግግሯ መሃል አግራሞቷን የምትገልፅባቸው ጊዜያትም ብዙ ናቸው። በተለይ በሐበሾች በምትከበብባቸው ጊዜያት ላለመርሳት ይመስል በንግግሯ መካከል የምታውቀውን አማርኛ ጣል ጣል ከማድረግ ወደ ኋላ አትልም። አና ባለፈው እሁድ የተከበረውን የፋሲካ በዓል ባታከብረውም እንኳ 'ጣፋጭ' የምትላቸውን ጊዜያት አብሬያቸው አሳልፌያለው የምትላቸውን ጓድኞቿን በማሰብ፤ በግሏ ማኅበራዊ ድረ ግፅ ላይ መልካም ምኞቷን ገልጻላቸዋልች፤ ለዚያውም ባልተለመደ ሁኔታ በሙዝ ላይ የመስቀል ስዕል ሰርታ በአማርኛ 'መልካም ፋሲካ' በማለት። ፋሲካ አና በሙዝ ላይ ስዕል መሳል የጀመረችው ግን ሙዝ መመገብ አስጠልቷት ወይንም በጥበብ ጎዳና ተመርታ ልዩ ሥራ በማቅረብ ፍላጎት ተነሳስታ አልነበረም። አና ከወር በፊት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይተውባት ለ10 ቀናት በመኝታ ቤቷ እራሷን አግልላ በቆየችበት ወቅት ነው። "ወላጆቼ ዕድሜያችው ከፍ ያለ ስለሆነ እንዳይታመሙ በጣም እሰጋ ነብር። ለ10 ቀናት ሳላገኛቸው በክፍሌ ውስጥ እራሴን ሰወርኩኝ። ህመሙ ሻል እያለኝ ሲመጥጣ ግን ላብድ ትንሽ የቀረኝ መሰለኝ" የምትለው አና ከቤተስቦቿ ጋር የምትኖረው ገና ከኢትዮጵያ መመለሷ ስለነበረ እንደሆነ ታስረዳለች። ለንደን ሕይወትን እንዳዲስ እስክትጀምር ወላጆቿ ጋር የተቀመጠችው አና በዕድሜ የገፉት እናትና አባቷ በኮሮናቫይረስ እንዳይታመሙ በጣም ትሰጋ እንደነበር ትናገራለች። ብቻዋናም መኝታ ቤቷን ዘግታ የተቀመጠችው አና፤ ወላጆቿ የማይጋሩትን መታጠቢያ ቤት ለመጠቀም ካልሆነ በስተቀር ከክፍሏ አትወጣም። አና እራሷን ለይታ በቆየችባቸው የመጀመሪያዎቹን ቀናት ተኝታ ብታሳልፍም ቀኑ እየጨመረ ሲሄድና የህመሙ ምልክት ሻል ሲላት ቁጭ ብላ መመገብ ጀምራ ነበር። ታዲያ በአንዱ ዕለት ለምሣ ቀርቦላት የነበረው የሙዝ ሽፋን ላይ እንደ ቀልድ መሞነጫጨር ጀመረች። የጠረጠረችው የኮሮናቫይረስ በሽታ ምልክቶች ለይተው ወይ ነጻ እስክትሆን ካልሆነም የህክምና ድጋፍ እንድታገኝ እስኪደረግ ምንም ሳትሠራ በአንድ ክፍል ውስጥ ተቆልፎ መቀመጡ ከበሽታው በላይ ህመም የሆነባት አና ይህን አዲስ ግኝት በየዕለቱ ሥራዬ ብላ ተያያዘችው። ከዚያ ጊዜ ወዲህ ታዲያ እንደ ኤሚ ዋይንሃውስ እና ዘ ቢትልስ የተሰኙትን ታዋቂ ሙዚቀኞች፣ በልጅነት የተጫወተቻቸውን ጨዋታዎች፣ የምትወዳቸውን እንስሶችና ከኢትዮጵያ የሚናፍቋትንም ነገሮች በሙዝ ላይ ሙንጭር ሙንጭር አርጋ በመሳል ማኅበራዊ ሚዲያ ገጿ ላይ ለዘመድ ወዳጆቿ ማጋራት ጀመረች። ኤሚ አና ከህመሙ በደንብ እንደተሻላት ስታውቅ ለቀናት እራሷን ለይታ ከቆየችበት መኝታ ቤቷ ወጥታ በሽታው እንዳይዛቸው ከተጠነቀቀችላቸው አዛውንት ከወላጆቿ ጋር ተቀላቀለች። ነገር ግን አና ካጋጠማት ህመም ብታገግምም የብሪታኒያ መንግሥት የበሽታውን መዛመት ለመቆጣጠር ሲል ባወጣው ሕግ መሠረት ከቤት በመውጣት ሌላ ቦታ መሄድ አልቻለችም። በዚህም ምክንያት የምታያቸውንና በምናቧ የሚከሰቱ ነገሮችን በሙዝ ላይ መሳሏን ቀጠለች። አናም "ሙዝ ላይ ሥዕል አሰፍራለሁ ብዬ መቼም አስቤ አላውቅም ነበር። ልጅ እያልሁ እስል እንደነበረ ትዝ ይለኛል። ግን ዕድሜ እየገፋ ሲመጣ እንደሚረሱ ልማዶች ሁሉ፤ በሚያሳዝን ሁኔታ የሥዕል ዝንባሌዬ ትቼው እንደነበረ በዚህ ጊዜ ታወሰኝ። ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ስላልተረሳኝ ብዙዎችን ያስደሰቱ ሥዕሎችን ቢያንስ በማህበራዊ ገፆች ለዕይታ ማቅረብ ችያለሁ" ትላለች። ቡና ከሙዝ ሌላ ምንም ዓይነት ፍራፍሬም ሆነ አትክልት ላይ ስዕሎችን የማትሞክረው አና "ለሙዝ የተለየ ፍቅር ወይም ጥላቻ ኖሮኝ አይደለም። በአጋጣሚ እጄ ላይ ሙዝ ስለተገኘ ብቻ ነው አሁን ርዕስ ለመሆን የበቃው" ትላለች።አክላም "ብዙ ሰዎች ሙዞቹ ላይ በብዕር የምስልባቸው ይመስላቸዋል ነገር ግን እየሳልኩባችው ሳይሆን ስጫንና ስቧጭራችው መጀምሪያ ምንም ምልክት ባይኖርባቸውም ብዙም ሳይቆዩ ግን የተጫሩበት ቦታ ላይ መበለዝ ይጅምራሉ። "እኔ ባውጣሁላቸው መስመሮች መሠረት ቀስ በቀስ እየበለዙ ቅርፁን ተከትለው የሣልኩባቸውን ነገሮች አጉልተው ያወጣሉ" በማለት በቅርብ ያካበተችውን ችሎታ እንዴት እንደምታቀናብር ታስረዳለች። ሙዞቹ ሽፋን ላይ አና በምታሳርፍባቸው የመጫን ኃይል መሠረት ሲበልዙ፤ ወይ ጠቆር ወይም ደግሞ ፈዝዝ እያሉ ማሳት የምትፈልገውን ምስል ያወጡላታል። በዚህም መሰረት በየቀኑ አልያም አለፍ አለፍ እያለች የተለያዩ ለዓይን ደስ የሚሉና ሙዞቹን ለመብላት የሚያሳሱ ሥዕሎችን ታሰፍርባቸዋለች። "ሙዞቹ ከቧጨርኳቸው በኋላና አንዴ መበለዝ ከጀመሩ ጊዜ አንስቶ ብዙም አይቆዩም። እንደውም ሥዕሎቹ እንደዛ በውበት እንዳልደመቁት ጭራሽ ምንነታቸው እስኪጠፋ ሙሉው የሙዞቹ ሽፋን መበለዝ ይጀምራል። ዘ ቢትልስ "አንዳንዶቹ ብቻ አንድ ሁለት ቀናት ሊቆዩ ይችላሉ" የምትለው አና ሆን ብላ ሙዞቹን ታበልዛቸው እንጂ ምንም ቢብልዙ ከመብላት እንደማትቆጠብ ትናገራለች። "ሲጀመር ይህን ማድረግ የጀመርኩት ሥዕሎቹ ለዕይታ እንዲቅርቡ ወይንም ሙዞቹ እንዲቀመጡ አይደለም። ለእዕምሮዬ ሰላም ስል ብቻ ነበር። መሞነጫጭሩ ሃሳቤን ስብስብ አድርጎ እጆቼ ከሚሰሩት ሥራ ውጪ ሌላ ነገር እንዳላስብ ስለሚያግዝኝ ብቻ ነው። በተለይ በአሁን ሰዓት" ትላለች። እነዚህ በሙዝ ቆዳ ላይ በአና የሚሰሩት ሥዕሎች እድሜያቸው ከጥቂት ቀናት የዘለለ ባይሆንም ፎቶ በማንሳት ለጓደኞቿ ታጋራቸዋለች። ከሁሉ በላይ ግን በኮሮናቫይረስ ምክንያት እራሷን ለይታ በአንድ ክፍል ውስጥ በቆየችባቸው ጊዜያት ብቸኝነቷን እንድትቋቋም ከማድረግ ባሻገር በውስጧ ተዳፍኖ የነበረውን የሥዕል ዝንባሌ እንድታወጣ ረድቷታል።
news-55019588
https://www.bbc.com/amharic/news-55019588
ትግራይ፡ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኃላፊነታቸው ተነሱ
የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሁሴይን ሮብሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ የሶማሊያ አቋም ውዝግብ ማስነሳቱን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን አህመድ ኢሴ አዋድን ከኃላፊነታቸው አንስተዋቸዋል።
ከኃላፊነታቸው የተነሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አህመድ ኢሴ አዋድ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን አንድነት እንደግፋለን የሚል መልዕክት በመስሪያ ቤቱ ይፋዊ ትዊተር ገፁ ወጥቷል። "የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የአገሪቷን ግዛት ለማስከበር በሚያደርጉት እርምጃ ሶማሊያ ያላትን ድጋፍ እንደገና ታረጋግጣለች" የሚል መግለጫ በመስሪያ ቤቱ ትዊተር ገፅ ቢወጣም ከሰዓታት በኋላ መልዕክቱ ተነስቷል። በትናንትናው ዕለትም አህመድ ኢሴ አዋድ በግላቸው የትዊተር ገፅ "ሶማሊያ በኢትዮጵያ ስለተፈጠረው ግጭት ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ አልሰጠችም" በማለትም አስተባብለዋል። ይህንንም ውዝግብ ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን በሳቸውም ቦታ መሃመድ አብዲሪዛክ መሃመድ አብዱቃድር እንደተተኩም ከሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ከኃላፊነታቸው የተነሱት ሚኒስትርም አምባሳደር ተደርገው እንደተሾሙም የአገሪቷ የመንግሥት ሬድዮ ድረገፅ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቢሮ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ሆኖም አህመድ ኢሴ አዋድ በአሁኑ ወቅት "በአምባሳደርነትም ሆነ በየትኛውም ቦታ ለመሾም ዝግጁ እንዳልሆኑ" በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ይፋዊ የትዊተር ገፅም ሚኒስትሩ ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ቢገልፅም ምክንያቱ አልተጠቀሰም። ከሁለት ሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የትግራይ ልዩ ኃይል በክልሉ የሚገኘውን የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ገልፀው ወታደራዊ ግጭት መቀስቀሱን አስታውቀዋል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጦርነቱ ውስንና በተወሰኑ የህወሓት አባላት ላይ ያነጣጠረና ሕገ መንግሥትን ለማስከበር እየተወሰደ እርምጃ መሆኑን ገልፀው በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ መግለፃቸው ይታወሳል። የትግራይ ክልል በበኩሉ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጦርነት እንደተከፈተበትና ሕዝቡም ላይ ያነጣጠረ ነው ይላል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል (አሚሶም) ስር ወታደሮቿን በሶማሊያ አሰማርታለች። በባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ከሶማሊያ 3 ሺህ ወታደሮቿንም እንዳስወጣች የሶማሊያው ዳልሳን ሬድዮ ዘግቦ ነበር።
53074875
https://www.bbc.com/amharic/53074875
ቻይና 20 የሕንድ ወታደሮችን ድንበር ላይ ገደለች
ሕንድና ቻይና በሥርዓት ባልተማከለው አወዛጋቢ ድንበራቸው አካባቢ ተጋጭተዋል፡፡
ሁለቱ በዓለም በሕዝብ ብዛት 1ኛ እና 2ኛ የሆኑት አገራት በዓለም ረዥም የሚባሉ ድንበሮችን ይጋራሉ፡፡ አሁን የተጋጩበት ድንበር 3500 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው ነው፡፡ በዚህ በሂማሊያ ሰንሰለት ድንበር አቅራቢያ የሁለቱ የኒክሌየር ጦር መሣሪያ ታጣቂ አገራት ግጭት የተከሰተው ከእሑድ ጀምሮ ነበር፡፡ ሁለቱ ኃያል አገራት በዚህ መልኩ ሲጋጩ ከ45 ዓመታት ወዲህ የመጀመርያቸው ነው፡፡ ክስተቱ ወደለየለት ጦርነት የሚያስገባቸው ይሆናል ተብሎ ባይጠበቅም በአካባቢው ውጥረት ነግሷል፡፡ የሕንድ የውጭ ጉዳዮች ሚኒስትር በጋልዋን ሸለቆ አካባቢ ከዚህ በፊት የተስማማንባቸውን የቁጥጥር መስመሮች ቻይና ጥሳቸዋለች ሲሉ ከሰዋል፡፡ የቢቢሲ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዘጋቢ ጀምስ ሮቢንስ እንደሚለው ይህ በሂማሊያ ሰንሰለታማ ድንበር የተፈጠረው ነገር በዋዛ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም፡፡ ጣጣው ለአካባቢው አገራትም ሊተርፍ የሚችል ነው፡፡ ከዚህ በፊት ተጋጭተው ያውቃሉ? ትናንት ማክሰኞ ጠዋት የሕንድ መከላከያ ሚኒስቴር በካሽሚር ግዛት ላዳካህ በሚባል አካባቢ ሦስት ወታደሮቹ ከቆሰሉበት በኋላ እንደሞቱ ገልጾ ነበር፡፡ ከሰዓት ላይ ሚኒስቴሩ ባወጣው ሌላ መግለጫ ከቻይና ጋር መጠነኛ ግጭት ድንበር አካባቢ መፈጠሩን አመነ፡፡ በዚህ መግለጫው በግጭቱ ቆስለው የነበሩ 17 ወታደሮች መሞታቸውን ይፋ አደረገ፡፡ ቻይና እስካሁን ቆሰለብኝ ወይም ሞተብኝ ያለችው ወታደር ባይኖርም ሕንድ ድንበሬን ጥሳ ገብታለች ስትል ከሳታለች፡፡ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አፈ ቀላጤ ዣዎ ሊዢያን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሰኞ ለታ የሕንድ ወታደሮች ከአንድም ሁለት ጊዜ ድንበር አልፈው ገብተው ነበር፡፡ ይህ ድርጊት የቻይና ወታደሮችን ያስቆጣ ስለነበር በወታደሮቹ መካከል የለየለት ድብድብ ተደርጓል፡፡ ድብድቡ ወደ መሣሪያ ጸብ በመዞሩ ጉዳት ሊደርስ ችሏል፡፡ ሕንድ በበኩሏ በዚህ ግጭት ተኩስ አልነበረም ስትል ክዳለች፡፡ ሆኖም እንዴት መሣሪያ መታኮስ በሌለበት ሁኔታ 20 ወታደሮች በድብድብ ብቻ ሊሞቱ እንደቻሉ ለብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡ አንዳንድ ምንጮች በዚህ ግጭት ወታደሮቹ በድንጋይ ተፈነካክተው ነው የሞቱት እያሉ ነው፡፡ የሕንድ መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው የሕንድ የድንበር ወታደሮች የሞቱት በተኩስ ሳይሆን በቻይና ወታደሮች በድንጋይ ተደብድበው ነው፡፡ ግጭቱ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? ይህ በዓለም ረዥም ከሚባሉ ድንበሮች አንዱ የሆነው የሁለት ኃያላን አገራት ድንበር መልከአ ምድሩ በተራራ፣ በሀይቆችና በጠመዝማዛ ኮረብታዎች የተሞላ ስለሆነ ለቁጥጥር አመቺ ያልሆነ ቀጠና ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የሁለቱ አገራት ወታደሮች በብዙ አጋጣሚ አንዱ የአንዱን መስመር ተላልፎ ይገኛል፡፡ ሕንድ የቻይና መንግስት ወደ ላዳካህ ጋልዋን ሸለቆ በርካታ ወታደሮችን እያሰፈረ ነው ስትል ትከሳለች፡፡ ‹‹ቻይና የኔ የሆነ 38ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታን ይዛብኛለች›› ስትልም ቅሬታ ታቀርባለች፤ ሕንድ፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት ይህን የድንበር ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅረፍ ተሞክሮ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ሁለቱ አገራት እስከዛሬ የለየለት ጦርነት ያደረጉት አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን ይህም በአውሮጳዊያን አቆጣጠር በ1962 ነበር፡፡ በዚህ ጦርነት ሕንድ በቻይና እንዳይሆኑ ሆና ተሸንፋለች፡፡ ባለፈው ግንቦት የሁለቱ አገራት ወታደሮች በሰሜን ምሥራቅ ሲኪም ግዛት ጸብ ፈጥረው መደባደባቸው ተዘግቦ ነበር፡፡ ከዚያ በፊት በ2017 ቻይና አንድ ድንበር ላይ የሚገኘውን መንገድ አስፋፍታ ለመገንባት ስትሞክር ሕንድ ድንበሬን ነክተሸል በሚል ተጣልታት ነበር፡፡ ሕንድ በበኩሏ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደዚህ ሩቅ የድንበር ግዛት የሚወስድ መንገድ መገንባት በመጀመሯ ቤጂንግ ደስተኛ ሳትሆን ቀርታለች፡፡ ይህ የሕንድ መንገድ ግንባታ እና የጦር አየር ማረፊያ ጥርጊያ ግንባታ ወደፊት ግጭት ቢፈጠር ለሕንድ የሎጂስቲክ ጥቅም ይሰጣል ስትል ነው ቻይና የሕንድ ልማትና ብልጽግና ቀልቧ ሊወደው ያልቻለው፡፡ ሕንድ ከቻይና ሌላ በሂማሊያ ክልል በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩበትና 140ሺህ ስኬዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ካሽሚርን ይገባኛል ስትል ከፓኪስታን ጋር ትፋጠጣለች፡፡ ፕሬዝዳንት ሞዲ የወታደሮቻቸውን ሞት ተከትሎ ወደ ወዳጃቸው ዶናልድ ትራምፕ ስልክ እንደሚደውሉ እየተጠበቀ ነው፡፡ ሕንድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅነቷን እያጠበቀች ትገኛለች፡፡
57019409
https://www.bbc.com/amharic/57019409
የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር ተወያዩ
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተነጋገሩ።
የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር በቅርቡ በፕሬዝደንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ፌልትማን፤ በቀጠናው ወደሚገኙ አገራት ጉዞ ማድረግ መጀመራቸው ይታወሳል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሁለት ቀናት የሱዳን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ከተመለሱ በኋላ ከአምባሳደር ፌልትማን ጋር ረዘም ላለ ሰዓት መወያየታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል። አራት ሰዓት በቆየው ውይይት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ኤርትራ ከአሜሪካ ጋር አብራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል ሲሉ የማስታወቂያ ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው በበኩላቸው በአፍሪካ ቀንድ ስላሉ ችግሮች የአሜሪካ አስተዳደር መልዕከትን አብራርተዋል ብለዋል። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ልዩ መልዕከተኛው ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 5/2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ወደ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ያቀናሉ ብሎ ነበር። አምባሳደሩ የኤርትራውን ፕሬዝደንት ከማግኘታቸው በፊት ወደ ግብጽ አምርተው ከፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ፣ ከውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ሳሚህ ሽኩሪ እና ከአገሪቱ የውሃ ሚንስትር ጋር ስለመገናኘታቸው ተዘግቧል። ፌልትማን በመጀመሪያው መዳረሻቸው ግብጽ ከፕሬዝደንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ጋር ተገናኝተዋል። በውይይታቸው ወቅት አል-ሲሲ ግብጽ ከአባይ ውሃ የምታገኘው ድርሻ መቀነስን አትታገስም በማለት ስለመናገራቸው ዋሽግተን ፖስት ዘግቧል። አምባሳደር ፌልትማን ከግብጽ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ የጆ ባይደን አስተዳደር በቀጠናው ላሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች መፍትሄ ለመስጠት ትኩረት ያደርጋል ሰለማለታቸው ዋሽንግተን ፖስት ምንጮቹን ጠቅሶ ጨምሮ ዘግቧል። ጄፍሪ ፌልትማን ፌልትማን ማን ናቸው? ጄፍሪ ፌልትማን በሹመታቸው ወቅት በተለይ በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ስላሉ ሁኔታዎች የተለየ ትኩረት እንደሚሰጡ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አስታውቆ ነበር። ፌልትማን በድርድርና የሽምግልና ጉዳዮች ላይ ጥናትን በማካሄድና በአደራዳሪነትም ከፍ ያለ ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። ፌልትማን በፖለቲካዊና በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞውንና የአሁኑን ዋና ጸሐፊዎች ባን ኪሙን እና አንቶኒዮ ጉቱሬዝን ያማከሩ ሲሆን፤ ለጸጥታው ምክር ቤት በሠላምና በደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያዎችን በመስጠት ይታወቃሉ። በተባበሩት መንግሥታት ቆይታቸው ወቅትም በልዩ መልዕክተኝነት አገልግለዋል፤ በተጨማሪም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ለ26 ዓመታት ያገለገሉት ፌልትማን በሊባኖስ፣ በኢራቅ፣ በእስራኤል፣ በቱኒዚያ፣ በሃንጋሪና በሄይቲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል። የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ላይ እየገነባች ያለችው ግዙፍ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ኃይል በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል ውጥረት ፈጥሯል። ሦስቱ አገራት በግደቡ ውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ ከስምምነት ለመድረስ ለበርካታ ዓመታት ሲያደርጉት የነበረው ድርድር እዚህ ግባ የሚባል ውጤት አላስገኘም። የቅርብ ጊዜያት ድርድሮችም ያለስምምነት መበተናቸው ይታወሳል። ግብጽ እና ሱዳን የኢትዮጵያ ግድብ የውሃ ድርሻችንን ይቀንሳል ሲሉ ኢትዮጵያ በበኩሏ ከግድቡ የምታገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል በጭለማ ለሚኖሩ 60 ሚሊዮን ዜጎቼ ብርሃን ነው ትላለች። ባሳለፍነው ዓመት ውሃ መያዝ የጀመረው ግድብ በዚህ ዓመት የክረምት ወራትም ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ መንግሥት ቀድሞ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
56554165
https://www.bbc.com/amharic/56554165
ኮሮናቫይረስ፡ በጥብቅ ተግባራዊ የሚሆነው የኮቪድ-19 መመሪያ ምን ይዟል?
ባለፈው መስከረም ወር ላይ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እየጨመረ የመጣውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና የሚያስከትለው ጉዳት ለመቀነስ በሚል የተለያዩ ክልከላዎች እና ግዴታዎች የያዘ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።
ነገር ግን ተግባራዊነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ችላ ተብሎ ቆይቶ ከመረሳት ደረጃ ላይ ደርሷል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን ወረርሽኙ በአሳሳቢ ደረጃ እየተስፋፋ በመምጣቱ መመሪያውን በተገቢው መንገድ በጥብቅ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት በጤና ሚኒስቴር፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና በፌደራል ፖሊስ ተወስኗል። ይህ "የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የወጣ መመሪያ ቁጥር 30/2013" የሚባል ሲሆን ከመጋቢት 20/2013 ዓ.ም ጀምሮ በጥበቅ መተግበር እንደሚጀምርና ተላልፈው የሚገኙ ሰዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል። ለመሆኑ በዚህ መመሪያ ውስጥ የተከለከሉ ተግባራት ምንድናቸው? የተጣሉ ግዴታዎች በቤት ውስጥ ማቆያ እንክብካቤ ወቅት መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ መመሪያው ማንኛውም ቀላል ወይም ምንም አይነት የኮቪድ-19 ምልክት የሌለበት ታማሚ በቤት ውስጥ የኮቪድ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል ይላል። የኮቪድ 19 ታማሚ ወይም በኮቪድ-19 በሽታ ተይዟል ተብሎ የተጠረጠረ ሰው ተለይቶ በተዘጋጀ በቂ የአየር ዝውውር ባለው ክፍል ውስጥ ለ14 ተከታታይ ቀናት መቆየት አለበት። በቤት ውስጥ ራሱን ለይቶ ያለ ሰው የኮቪድ-19 በሽታ ምልክቶቹ ከተባባሱ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ተቋም በስልክ ሪፖርት ማድረግ ይኖርበታል። የውሸባ እና የድንበር ላይ ጤና ቁጥጥርን በተመለከተ ከትራንዚት መንገደኛ በስተቀር በአየር ማረፊያ በኩል የሚገባ ከ 10 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ተጓዥ ከመጣበት አገር ከ120 ሰዓት በላይ ያልሆነው የተረጋገጠ ምርመራ ነጻ መሀኑን የሚያሳይ ማስረጃ ይዞ መምጣት አለበት ይላል። ወደ አገር የሚመጡ ከስደት ተመላሾች ከ120 ሰዓት በላይ ያልሆነው የተረጋገጠ ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ይዘው ካልመጡ፣ ለምርመራ ናሙና ተወስዶ በአድራሻቸው ተመዝግቦ ውጤቱ እስኪመጣ ድረስ በቤታቸው ራሳቸውን ለይተው የማቆየት ግዴታ አለባቸው። የቀብር ሥነ ሥርዓት፣ የአስከሬንማጓጓዝ እና የሀዘን ሥነ ሥርዓት በተመለከተ የሟች ቤተሰብ አስከሬን ከጤና ተቋም ወይንም ከውጭ አገር በሚረከቡበት ጊዜ ከአስከሬኑም ሆነ ከሳጥኑ ጋር ማንኛውም አይነት ንክኪ ያለማድረግ ኃላፊነት አለባቸው። ከጤና ተቋም ውጪ ሞት ሲከሰት በአስከሬን ግነዛ ሂደት የሚደረግ እንቅስቃሴ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት። አስከሬን የሚያስተካክሉና የሚገንዙ ሰዎች የእጅ ጓንት፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ከፕላስቲክ የተሠራ ጋዋን እና እንደ አስፈላጊነቱም የአይን መከላከያ ወይም መነጽር መልበስ አለባቸው። የሟች ቤተሰብ ሟች በታመመበት ወቅት ተኝቶ የነበረበት አልጋ፣ ሲገለገልባቸው ወይም በዙሪያ የነበሩ እቃዎች፣ የቤቱን ወለልና ሌሎች ከሟች ጋር ንክኪ የነበራቸውን ቁሳቁሶች በጸረ ተህዋሲያን ውህድ እንዲፀዳ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። በለቅሶ ቦታ የተገኘ ማንኛውም ሰው፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች የመተግበር ግዴታ አለበት። በቀብር ላይ ከ50 ያልበለጠ ሰው ብቻ መገኘት ይኖርበታል። ቀብርን በተመለከተ ቤተሰብ አስከሬን ከተገነዘ በኋላ ሟች በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲቀበር የማድረግ ኃላፊነት አለበት። በጤና ተቋማት ሞት ከተከሰተ ወይም አስከሬን ከውጭ አገር የሚገባ ከሆነ የሟች ቤተሰቦች አስክሬን ከተቀበሉ በኋላ ወደ ቤት ሳይወስዱ በቀጥታ ወደ ቀብር ቦታ የመውሰድ ግዴታም አለባቸው። ማንኛውም ለቅሶ ሊደርስ የሚመጣ ሰው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ የማድረግ፣ ለቅሶ ቤት ከመግባቱ በፊትና ሲወጣ እጅን በውሃና በሳሙና የመታጠብ ወይም በሳኒታይዘር የማፅዳት ግዴታ አለበት። በሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት እና የአደባባይ በዓላት አከባበርን በተመለከተ በሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ላይ የሚሳተፉ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ማንኛውም ሐይማኖታዊ ሥርዓት ከሁለት የአዋቂ እርምጃዎች በታች ተጠጋግቶ መፈጸም የለበትም። ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት ከአንድ አራተኛው በማይበልጥ ሰው ሥርዓቱን መካሄድ ይኖርበታል። መመሪያው ሕዝብን በብዛት የሚያሳትፉ የአደባባይ ላይ በዓላት ባይደረጉ ይመከራል ይላል። በዓሉን ማክበር ግድ ከሆነ በዓላቱ የሚታደምም ሆነ አከባበሩን የሚያስተባበር ሰው፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የማድረግ እና በአከባበርም ወቅት ሁለት ሜትር ርቀትን ጠብቆ የመቆምና መቀመጥ ግዴታ አለበት። በዓላት የሚከበሩባቸው አደባባዮች የሚሸፍኑትን ጠቅላላ ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት ከአንድ አራተኛውን የማይበልጥ ሰው በመያዝ ሥርዓቱን መካሄዱን ማረጋገጥ ይገባል። በስብሰባ ወቅት መወሰድ ስላለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች የጤና መመሪያውን በተከተለ መልኩ ያለተጨማሪ ፈቃድ እስከ 50 ሰው ሆኖ መሰብሰብ ይቻላል። ከ50 ሰው በላይ መሰብሰብ ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ስብሰባው ሊደረግበት የታሰበው አዳራሽን ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት ከአንድ አራተኛው በማይበልጥ ሰው ልዩ ፈቃድ ከሰላም ሚኒስቴር እና በተዋረድ ካሉ የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች አስቀድሞ ማግኘት አስፈላጊ ነው። ስብሰባውን የጠራው አካል እና ተሳታፊዎች የጤና መመሪያውን የመከተል ግዴታ አለባቸው። በመዝናኛ እና በመስተንግዶ ስፍራዎች የሚደረጉ የጥንቃቄ እርምጃዎች ካፌዎች፣ ባርና ሬስቶራንቶች እንዲሁም መጠጥ ቤቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሦስት ሰው በላይ ማስተናገድ የተከለከለ ሲሆን በእያንዳንዱ ጠረጴዛ መካከል የሁለት ሜትር ርቀት ሊጠበቅ ይገባል። በእነዚህ ስፍራዎች ተገልጋዮች ከሚመገቡበት እና ከሚጠጡበት ወቅት ውጪ እንዲሁም አገልግሎትን የሚሰጡ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ተቋማቱ ተገልጋዮቻቸው የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶችን ከእያንዳንዱ አገልግሎት በኋላ በጸረ ተህዋሲያን ውህድ የማጽዳት ኃላፊነት አለባቸው። ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በሚገኙባቸው ተቋማት የአረጋዊያን መጦሪያዎች እና የማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በአካል መጠየቅ የተከለከለ ነው። በማረሚያ ቤቶች ላይ የሚደረግ የታራሚን በአካል የመጎብኘት ሂደት በታራሚው እና በጠያቂው መካከል ሁለት የአዋቂ እርምጃ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ አለባቸው። ታራሚውም ሆነ ጠያቂው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በማስደረግ፣ ጠያቂው ወደ ማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ከመግባቱም በፊት እና ሲወጣ እጁን በውሃ እና ሳሙና እንዲታጠብ ወይንም በሳኒታይዘር እንዲያጸዳ መደረግ አለበት። በዚህ መመሪያ የተደነገጉ ክልከላዎችን እና ግዴታዎችን የተላለፈ ማንኛውም ሰው አግባብነት ባለው የወንጀል ሕግ መሰረት ተጠያቂ ይሆናል።
news-49792739
https://www.bbc.com/amharic/news-49792739
ጣልያናዊው በአደን ወቅት በስህተት አባቱን ተኩሶ ገደለ
ጣልያን ውስጥ የዱር አሳማ ለማደን በወጡበት አባቱን ተኩሶ የገደለው ልጅ ክስ እንደተመሰረተበት ፖሊስ አስታወቀ።
የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በደቡባዊ ሳሌርኖ ግዛት በምትገኘው ፖሰቲግዮን ከተማ ክስተቱ ያጋጠመው አባትና ልጅ የዱር አሳማ ለማደን ጥቅጥቅ ባሉ ተክሎች መካከል በመጓዝ ላይ ሳሉ ነበር። • ጣልያን በተሸነፈችበት አድዋ ቆንስላዋን ለምን ከፈተች? • ጀብድ የፈጸመው ተማሪ ጣልያናዊ ዜግነት ሊሰጠው ነው የ34 ዓመቱ ጣልያናዊ ለአደን በተጠንቀቅ ተዘጋጅቶ በነበረበት ወቅት ድንገት የሆነ ነገር ጥላ ሲመለከት ሳያቅማማ ተኩስ እንደከፈተ አምኗል። ተኩሶ የመታው ግን የገዛ አባቱን መሆኑን ሲገነዘብ ወዲያው ጉዳዩን ለፖሊስ በማሳወቅ አባቱ ቶሎ ህክምና እንዲያገኙ ጥረት አድርጓል። ሟች የ55 ዓመቱ ማርቲኖ ጋዲዮሶ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸውን ማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል። አባትና ልጅ የዱር አሳማ ለማደን ሲንቀሳቀሱበት የነበረው አካባቢ በብሔራዊ ፓርክነት ታጥሮ የነበረና አደን በፍጹም የተከለከለበት ነበር ተብሏል። ፖሊስም የሁለቱንም ግለሰቦች መሳሪያ በቁጥጥር ማዋሉን አስታውቋል። ከአደጋው በኋላ በጣልያን የእንስሳትና አካባቢ መከላከያ ሊግ ፕሬዝዳንት ''ጣልያን ህግ አልባ እየሆነች ነው'' ሲሉ ተደምጠዋል። • ሳባ አንግላና፡ "ኢትዮጵያዊትም፣ ጣሊያናዊትም ሶማሊያዊትም ነኝ" ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ አንድ 18 ዓመት ወጣጥ በአደን ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ ከተገደለ በኋላ የጣልያኑ የአካባቢ ሚኒስትር ሰርጂዮ ኮስታ ዘወትር እሁድ የሚደረጉ አደኖች መታገድ እንዳለባቸው አሳስበው ነበር። በዛው ወር መጨረሻ ደግሞ አንድ 50 ዓመት ጎልማሳ እና የ20 ዓመት ወጣት አደን ላይ እያሉ በስህተት በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል።
news-50120931
https://www.bbc.com/amharic/news-50120931
ካንታስ፡ ያለእረፍት ከአስራ ዘጠኝ ሰዓት በላይ የበረሩ መንገደኞች ምርመራ ተደረገላቸው
የአውስትራሊያ የአየር መንገድ ካንታስ ያለምንም እረፍት ያለማቋረጥ ረዥም ሰዓት ያደረገው በረራ ተጠናቋል።
የምርምር አካል የሆነው ይህ በረራ ረዥም በረራዎች በመንገደኞች፣ በፓይለቶችና በአውሮፕላን አስተናጋጆች ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖን በጥልቀት የሚያይ ይሆናል። ቦይንግ 787-9 አውሮፕላን አርባ ዘጠኝ መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን አስራ ዘጠኝ ሰዓታት ከአስራ ስድስት ደቂቃ በሯል። •"አደጋውን ስሰማ ክው ነበር ያልኩት..." አቶ ተወልደ ገ/ማርያም •"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ መነሻውን ኒውዮርክ አድርጎ የአውስትራሊያ መዲና ሲድኒ ለመድረስም የ16 ሺህ ሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ርቀትን በሯል። አየር መንገዱ በሚቀጥለው ከለንደን ወደ ሲድኒም የሚደረግ በረራንም አቅዷል። እነዚህ በረራዎች ካንታስ በተያዘው የአውሮፓያውያን ዓመት የሚጀምረውን የበረራ መስመር የሚወስን ይሆናል። •ቦይንግ ተከሰሰ፤ ሰለአደጋው ተጨማሪ መረጃዎች እየወጡ ነው •"አደጋውን ስሰማ ክው ነበር ያልኩት..." አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በረራዎቹም ከተሳኩ በሚቀጥሉት አራትና አምስት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ በረራ የሚጀመር ይሆናል። እስካሁን ባለው መረጃ መንገደኞችንና እቃ ጭኖ ያለምንም እረፍት ይህን ያህል ሰዓት መብረር የቻለ አውሮፕላን እንደሌለ ሮይተርስ ዘግቧል። ለዚህም በረራ ቅድመ ዝግጅቶች የተደረጉ ሲሆን፤ አውሮፕላኑ የነዳጅ እጥረት እንዳያጋጥመውና፤ ነዳጅ ለመሙላትም እንዳይቆም ሙሉ በሙሉ ነዳጅ ከመሞላት በተጨማሪ፤ የተወሰኑ የመንገደኛ ሻንጣዎችን ብቻ ጭኖ ሌላ ምንም አይነት እቃ እንዳይጭን እንደተደረገ ተገልጿል። መንገደኞቹ ከተሳፈሩበት እስኪወርዱበት ባሉት ሰዓታት ውስጥ በጥብቅ ቁጥጥር ስር የነበሩ ሲሆን፤ አውሮፕላኑ ላይ እንደተሳፈሩም ወዲያው እንዳይተኙም ተደርጓል። ከስድስት ሰዓት በኋላም ከፍተኛ የካርቦሃይድሬት መጠን ያለው ምግብ እንዲመገቡ የተደረገ ሲሆን፤ በአውሮፕላኑ ውስጥ ያለው የብርሃን መጠን ተቀንሶ እንዲተኙ ተበረታትተዋል። •የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? በአውሮፕላኑ ውስጥም የፓይለቶችን የአዕምሮ እንቅስቃሴ፤ የእንቅልፍን ሁኔታ የሚቆጣጠረውን የሜላቶንን ሆርሞን መጠን እንዲሁም ካላቸው የንቃት ሁኔታም ጋር ተያይዞ ክትትሎች ነበሩ ተብሏል። መንገደኞቹ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን በተለይም የተለያየ መልክአ ምድርን በሚያልፉበት ጊዜ ሰውነታቸው ላይ የሚመጣውንም ለውጥ ለማየት ተሞክሯል። በቅርቡ ረዥም ሰዓትን የሚበሩ አየር መንገዶች ቁጥራቸው እየጨመሩ ሲሆን ለምሳሌም የሲንጋፖር አየር መንገድ ከሲንጋፖር ወደ ኒውዮርክ የአስራ ዘጠኝ ሰዓታት በረራ ባለፈው ዓመት ጀምሯል። በአሁኑም ሰዓት ረዥሙ በረራ የሚባለው ይኸው ነው። ባለፈው ዓመትም እንዲሁ ኳንታስ የ17 ሰዓታት በረራ ከፐርዝ ወደ ለንደን የጀመረ ሲሆን፤ የኳታር አየር መንገድም በተመሳሳይ ከኦክላንድ ወደ ዶሃ የ17.5 ሰዓታት ጉዞ ጀምሯል።
news-41654154
https://www.bbc.com/amharic/news-41654154
ካይሮ ለሴቶች በጣም አደገኛ ከሆኑች ከተሞች አንዷ ናት - ጥናት
የግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ለሴቶች "በጣም አደገኛ" ከሆኑ ትልልቅ ከተሞች አንዷ መሆኗ ተገልጸ።
ከተማው ለሴቶች አስቸጋሪ ነው ከ10 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ባሏቸው ከተሞች፤ የሴቶችን ሁኔታ በሚመለከት የተካሄደው የመጀመሪያው ዓለም አቀፋዊ የሕዝብ አስተያየት ጥናት ነው ይህንን የገለጸው። ጥናቱ በህዝብ ብዛታቸው ትልልቅ በሆኑ 19 ከተሞች ሴቶች ምን ያህል ከወሲብ ጥቃቶች እንደተጠበቁ በሚያመለክቱ ጉዳዮች ላይ የሥነ-ጾታ ባለሙያዎችን በመጠየቅ የተካሄደው ነው። በምርጫው ለንደን ቀዳሚውን ቦታ ስትይዝ ቶክዮ እና ፓሪስ ተከታዮች ሆነዋል። ሴቶች ሥነ-ጥበብ፣ ንግድ እና ፖለቲካን ጨምሮ በሁሉም የማህበራዊ ክፍሎች ቀዳሚ በመሆን እየመሩ ናቸው ሲሉ የለንደን ከተማ ከንቲባ ሳዲቅ ካን ገልጸዋል። በካይሮ የሚገኙ የሴቶች መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ለመቶ ዓመታት የቆዩ ልምዶች፤ መድልዎ እንዲኖር ከማድረጋቸውም በላይ ሴቶችን ለመርዳት የሚወሰዱ እርምጃዎችን አዝጋሚ አድርገውታል። በተጨማሪም በቂ የጤና እንክብካቤ፣ የገንዘብ እና የትምህርት ተደራሽነት አያገኙም። ግብጻዊቷ ጋዜጠኛ ሻሂራ አሚን ከተማዋ ለሴቶች አስቸጋሪ ናት ትላለች። በመንገድ ላይ እንደ መራመድ ያሉ ቀላል ነገሮችም ሴቶችን ለውክቢያ እና መንገላታት ሊያጋልጡ ይችላል ብላለች። በቶማስ ሮይተርስ ፋውንዴሽን የተደረገው ጥናት የፓኪስታኗ ካራቺ፣ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክዋ ኪንሻሳ እና የሕንዷ ዴልሂ ያገኙት ውጤት ከካይሮ ኋላ አስቀምጧቸዋል። ዴልሂ እና የብራዚሏ ሳኦ ፓውሎ ሴቶች ወሲባዊ ትንኮሳ፣ ወሲባዊ ጥቃት እና አስገድዶ የመድፈር ስጋት ከፍተኛ ከሆነባቸው ከተሞች ቀዳሚ ሆነዋል። እ.አ.አ በ2012 በአውቶብስ ውስጥ የተደፈረችን ሴት ምክንያት በማድረግ ከነበረው ከፍተኛ ተቃውሞ በኋላ ጠንካራ ህግ ቢወጣም ዴልሂ በዝርዝር ውስጥ ገብታለች። በብራዚል 16 ዓመትና ከዚያ በላይ ከሆናቸው ሦስት ሴቶች ውስጥ አንዷ አካላዊ፣ የንግግር ወይንም የሥነ-ልቦና ጥቃት እንደሚደርስባት የብራዚል ፎረም ኦፍ ፐብሊክ ሴክዩሪቲ ያካሄደው የህዝብ አስተያየት ጥናት ይፋ አድርጓል።
54347638
https://www.bbc.com/amharic/54347638
የአሜሪካ ምርጫ ፡ በመጀመሪያው የዶናልድ ትራምፕ እና የጆ ባይደን ክርክር ማን የበላይ ሆነ?
ትራምፕና ባይደን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ለ90 ደቂቃ ተናንቀዋል። በክሊቭላንድ፣ ኦሃዮ።
ክርክሩ እንደተፈራው ነበር የሆነው። ትራምፕ ባይደንን ብቻ ሳይሆን የክርክሩን አጋፋሪ እያቋረጡ መናገር፣ እኔን ብቻ ስሙኝ ማለት አብዝተው ነበር። እምብዛምም የይዘት ከፍታ አልነበረውም። መዝናኛነቱ ያይላል ቢባል ይቀላል። ትራምፕና ባይደን የተከራከሩባቸው አበይት ነጥቦች በጤና መድኅን፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሹመት፣ በኮሮና ተህዋሲ፣ የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት፣ ዘረኝነትና የምርጫ ሂደትና የምርጫ ገለልተኝነት ነበሩ። ትራምፕ ባይደንን የክፍልህ ሰነፉ ተማሪ ነበርክ፣ አሳፋሪ ነህ ሲሉ፤ ባይደን በበኩላቸው አሜሪካ እንዳንተ የከንቱ ከንቱ መሪ አይታ አታውቅም ሲሉ መልሰዋል። ባይደን ትራምፕን ‹ቀጣፊ› ብለዋቸዋል። ወደ ካሜራው በቀጥታ በመዞርም ‹ይህ ሰውዬ የሚላችሁን ታምኑታላችሁን?› ሲሉ የአሜሪካን ሕዝብ ጠይቀዋል። ይህ ክርክር ከመካሄዱ በፊት ብዙዎች ትራምፕ ጆ ባይደንን በነገር እየሸነቆጡ ንግግር ይነሷቸው ይሆናል ሲሉ ሰግተው ነበር። ባይደን ትንሽ ዘገም የማለት ሁኔታ ስላለባቸውና ትራምፕ ግልብ ቃላትን፣ ግልብ ሀሳብን፣ መደዴ የክርክር ነጥቦችን አዘውትረው ስለሚጠቀሙ ሰውየውን አያናግሯቸው ይሆናል ሲባል ነበር። ባይደን ግን እንደተፈራው ያን ያህል ችግር ውስጥ አልገቡም። አልፎ አልፎ ቃላት አልታዘዝ ሲሏቸው ቢታይም በርካታ ቁምነገር አንስተዋል። በኮሮናቫይረስ ዙርያ ባደረጉት ክርክር ሁለቱም አንዱ ሌላውን ሲከስ ተስተውሏል። ትራምፕ ‹‹እንኳንም እኔ ፕሬዝዳንት ሆንኩኝ እንጂ ባይደን በዚህ ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢሆን ኖሮ አሜሪካዊያን ሞተው ያልቁ ነበር፣ ሚሊዮኖች ይሞቱ ነበር›› የሚል ይዘት ያለው ሐሳብ ሲያሰሙ፣ ባይደን ወደ ካሜራው በቀጥታ በማየት በበሽታው የሞቱባቸውን አሜሪካዊያንን ልብ ለማሸነፍ ‹‹ስንቶቻችሁ በዚህ ሰዓት ሐዘን ላይ እንዳላችሁ ይገባኛል፣ ስንቶቻችሁ አባታችሁን፣ እናታችሁን፣ እህታችሁን…እንዳጣችሁ ይሰማኛል›› እያሉ የብዙ አሜሪካዊያንን አንጀት ለመብላት ሞክረዋል። የክርክሩ መሪ የፎክስ ኒውሱ ክሪስ ዋለስ ክርክሩ ገና ከመጀመሩ ትራምፕ ባይደንን ‹‹ፈዛዛ ነህ›› ሲሏቸው ባይደን ትራምፕን ‹‹አሻንጉሊት ነህ፣ መሳቅያ መሳለቅያ ነህ›› ብለዋቸዋል። ጆ ባይደን የትራምፕ ጣልቃ ገብነት ከመጠን በላይ በሆነባቸው ቅጽበትም፣ ‹‹አንተ ሰውዬ፣ እባክህን አፍህን ዝጋ›› ብለዋቸው ነበር። የክርክሩ አጋፋሪ የፎክስ ኒውሱ ክሪስ ዋለስ ትራምፕን ለመግራት የተቻለውን ሞክሯል። ሆኖም ትራምፕ በጄ አላሉም። እንኳን ባይደን ሲናገር ይቅርና የአከራካሪውን ክሪስ ዋለስንም ሐሳብ የሚያስጨርሱ አልሆኑም። ማይክራፎኑን ሊያሳርፉት አልቻሉም። ኮሮናቫይረስ አንድ ቦታ ላይ እንዲያውም የክርክሩ አጋፋሪ ክሪስ ዋለስ እንዲህ አለ፤ ‹‹ለሚቀጥሉት ሁለት ተኩል ደቂቃዎች ሁለታችሁም የምታወሩት ስለ ኮሮና ብቻ ይሆናል። ማንም ማንንም ማቋረጥ አይችልም›› ባይደን በዚህ ጊዜ ወደ ክሪስ ዋላስ ዞረው እንዲህ ሲሉ ቀለዱ። ‹‹ይቅናህ ወንድሜ!›› እንደቀደለዱትም ትራምፕ ገና ከመጀመሩ ክርክሩን ማቋረጥ ቀጠሉ። ይህም ሳቅን ያጫረ ክስተት ነበር። ትራምፕ '200ሺህ አሜሪካዊያ መሞታቸው እኔ በመሆኔ ነው ባይደን ፕሬዝዳንት ቢሆን አሜሪካዊያን ያልቁ ነበር። ይሄ ቻይና የላከችብን በሽታ ነው። እኔ ግን ቶሎ ብዬ ድንበር በመዝጋቴ ሟቾቹ ትንሽ ሊሆኑ ችለዋል። ዶ/ር ፋውቺ አድንቆኛል። መስክሮልኛል። በጊዜ ድንበር በመዝጋቴ ነው አሜሪካዊያንን የታደኩት' የሚል ሁልጊዜም በጋዜጣዊ መግለጫ የሚሉትን በክርክሩም አንስተዋል። በዚህ ጊዜ ነበር ባይደን ወደ ትራምፕ ወይም ወደ ዋላስ መዞር ትተው በቀጥታ ወደ ካሜራ በማየት ‹ይህን ሰውዬ የሚለውን ታምኑታላችሁ ብለው የጠየቁት። ይህን የምሽቱ የባይደን ስኬታማ ደቂቃ ተደርጎ ተወስዷል። ትራምፕ የነጭ አክራሪዎችን፣ የጥቁር ጠሎችን እንዲያወግዙ በክርክር መሪው ዋለስም ሆነ በባይደን ቢጠየቁም ይህን ሊያደርጉ አልደፈሩም። ትራምፕ ባይደንን ከፍና ዝቅ ባደረጉበት በዚህ የክርክር ጊዜ ይህንን ብለዋል። ‹‹ለ47 ዓመት በአሜሪካ ፖለቲካና አስተዳደር ቆይተሃል፣ ምንም ያሳካሀው ነገር የለም። አንተ በ47 ዓመት ያላሳከሀውን እኔ በ47 ወራት ሰርቼዋለሁ›› ብለዋል። ባይደን ለዚህ ምላሽ የሰጡት ዘግየት ብለው ነው። ‹‹ባንተ ጊዜ አሜሪካ ድሀ፣ ደካማ፣ የተከፋፈለችና የታመመች ሆናለች›› ብለዋል። ባይደን ስለ ገቢ ግብር ከሰሞኑ ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ስለ ትራምፕ ያጋለጠው ምስጢር አስደንጋጭ ነበር። ትራምፕ ለዐሥር ዓመታት ግብር አለመክፈላቸው ዓለምን አነጋግሯል። ይህንን ጉዳይ ባይደን በማንሳት ተቀናቃኛቸውም በአሜሪካዊያን ዘንድ ያዋርዷቸዋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ርእሰ ጉዳዩ በክርክር አጋፋሪው ዋላስ ሲነሳ ትራምፕ ቶሎ ብለው የገቢ ግብር እንደሚከፍሉና ትንሽ ገንዘብ የመክፈላቸው ምስጢር ግን የግብር ሕጉ የሚሰጣቸውን እድል በብልሀት በመጠቀማቸው እንደሆነ ይህም ወንጀል እንዳልሆነ አብራርተዋል። ባይደን እድሉ ሲሰጣቸው ትራምፕን በቀጥታ ከመቀጥቀጥ ይልቅ የሪፐብሊካን የታክስ ማሻሻያ ሐሳብ ላይ ተንከባለዋል። ትራምፕ ከአንድ አስተማሪ በታች ነው ግብር የከፈሉት የሚል አረፍተ ነገር ከመናገራቸው ባሻገር ተቀናቃኛቸውን ብዙ ነጥብ ሊያስቆጥሩ የሚችሉበትን እድል አምክነዋል። ክርክሩ የነገ ሳምንት በምክትሎቹ ማይክ ፔንስና ካመላ ሐሪስ መካከል ይቀጥላል። የምርጫውን ውጤት በጸጋ መቀበል በመጨረሻ ዋላስ ለሁለቱ እጩዎች ያቀረበላቸው ጥያቄ ምርጫው ከተካሄደ በኋላ ደጋፊዎቻችሁ የምርጫውን ውጤት በጸጋ እንዲቀበሉ ትማጸናላችሁ ወይ? የሚል ነበር። ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው አካሄድ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው፣ ሊጭበረበር ስለሚችል ደጋፊዎቻቸው ነቅተው እንዲጠብቁ፣ በየምርጫ ጣቢያው የሚሆነውን በቅርብ እንዲከታተሉ አደርጋለሁ ብለዋል። ባይደን ቀበል አድርገው ‹‹ይሄ ሰውዬ የሚናገረውን አያውቅም›› ሲሉ ትራምፕን ተችተዋል። ባይደን የምርጫውን ውጤት በጸጋ እንደሚቀበሉ አረጋግጠዋል። ካሸነፍኩ ፕሬዝዳንት የምሆነው ለዲሞክራቶች ብቻ አይደለም፣ ለአሜሪካውንያ በሙሉ እንጂ ሲሉም አክለዋል።
52576830
https://www.bbc.com/amharic/52576830
የሩሲያው ወታደራዊ ቡድን ''በሊቢያ እየተዋጋ ነው''
በመቶዎች የሚቆጠሩ የሩሲያ ስውር የወታደራዊ ኃይሎች በሊቢያ አማፂያንን በደገፍ እየተዋጉ መሆኑን ሾልኮ የወጣ የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ገለፀ።
ወታደራዊ ኃይሉ አማፂው ጄነራል ካሊፋ ሃፍታርን በመደገፍ መቀመጫውን ትሪፖሊ ያደረገውን መንግሥት ይወጋል። እ.ኤ.አ. ከ2014 ጀምሮ ሊቢያ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ተከፋፍላ ትገኛለች። • ከጋዳፊ በኋላ ሰላም በራቃት ሊቢያ የሌሎች ሃገራት ፍላጎት ምንድነው? • ከባድ ጎርፍ በምስራቅ አፍሪካ 260 ሰዎች ገደለ ይሄው የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል 'ዋግነር' ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን በዩክሬን፣ ሶሪያ እና ሌሎች አካባቢዎች ባሉ ግጭቶች ውስጥ ተሳትፎ እንዳለው ይታመናል። የሩሲያ መንግሥት በሁለቱ ተዋጊዎች መካከል ምንም ዓይነት ወታደራዊ ተሳትፎ እንደሌለው በመግለፅ አስተባብሏል። ዋግነር የሚባሉት ወታደራዊ ኃይሎች በቀድሞው የሩሲያ ልዩ ኃይል ባልደረባ ዲሚትሪ ኡትኪን መመስረቱ ይነገርለታል። የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ምን ይላል? ሪፖርቱ የተጠናቀረው የተባበሩት መንግሥታት በሊቢያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ በሚመለከተው ገለልተኛ ቡድን ነው። ሪፖርቱ ይፋ ባይሆንም በዜና ተቋማት እጅ ውስጥ ግን ገብቷል። የተባበሩት መንግሥታት በሊቢያ ዋግነር ስለላው ተሳትፎ በይፋ ሲናገር የመጀመሪያ ጊዜው ነው። የመንግሥታቱ ድርጅት እንደሚለው ወታደሮቹ ከ 800 እስከ 1000 ያህል ይሆናሉ። ይህ ባለ 57 ገፅ ሪፖርት እንደሚለው ዋግነር የተሰኘው የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል እ.አ.አ. ከጥቅምት 2018 ጀምሮ በሊቢያ ነበር። "ለወታደራዊ መኪኖች እና በጦርነቱ ላይ ለሚሳተፉ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል" አባላቱ የጦር መሳሪያ እንዲሁም የአየር ቅኝት በማድረግ የሚሳተፉ ሲሆን በተጨማሪም " ከተቃራኒ ወገን የሚመጡ የኤሌክትሮኒክ ሞገዶችን ምላሽ ለመስጠት ሙያዊ ድጋፍ ማድረግና አልሞ ተኳሽ በመሆን ይሰማራሉ" ተብሏል። ወታደሮቹ አብዛኞቹ ሩሲያውያን ሲሆኑ ነገር ግን የቤላሩስ፣ ሞልዶቫ፣ ሰርቢያ እና ዩክሬን ዜጎችም እንዳሉበት በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንት ፑቲን በሊቢያ የሚገኝ ማንኛውም ሩሲያዊ አገራቸውን እንደማይወክል እንዲሁም በመንግሥታቸው ተከፋይ አለመሆኑን ገልፀው ነበር። • አል ሲሲን ተችቶ ለእስር የተዳረገው የፊልም ባለሙያ 'ሳኒታይዘር ጠጥቶ ህይወቱ አለፈ' የመንግሥታቱ ድርጅት ሪፖርት እንደሚለው ከሆነ የሶሪያ ቅጥረኞች ከጄነራል ሃፍታር ጎን ሆነው እየተዋጉ ነው። ሊቢያ ሙዓመር ጋዳፊ እ.አ.አ. በ 2011 በሕዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን ከወረዱና ከተገደሉ በኋላ ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች ነው። በሊቢያ ዓለም አቀፋዊ እውቅና ያለው መንግሥት ያለ ሲሆን በኳታር፣ እና በቱርክ ይደገፋል። በዚህ መቀመጫውን በትሪፖሊ ባደረገው መንግሥት ላይ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የጄነራል ሃፍታር አማፂ ኃይል ጥቃት መሰንዘሩን አጠናክሮ ቀጥሏል።
news-57111323
https://www.bbc.com/amharic/news-57111323
እስራኤል በጋዛ የምትወስደውን እርምጃ አጠናክራ ቀጠለች
አምስተኛ ቀኑን በያዘው የፍልስጤምና እስራኤል ፍጥጫ ፍልስጤም ታጣቂዎች ሮኬቶችን መተኮስ መቀጠላቸውን ተከትሎ የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረዋል።
የእስራኤል ጦር ታንኮችን ጭምር ወደ ጋዛ ድንበር አስጠግቷል የእስራኤል መከላከያ ኃይል እንደሚለው ጥቃቱ አሁንም ድረስ እየተካሄደ ሲሆን ወታደሮች በአየርና በእግረኞች በመታገዝ ጥቃቱን እየፈጸሙ ነው። ነገር ግን ወታደሮች ወደ ጋዛ አለመግባታቸው ተለግልጿል። በጋዛ ሮኬቶች፣ ተዋጊ ጀቶችና ሄሊኮፕተሮች ጥቅም ላይ ሲውሉ እንደነበር የቢቢሲ ዘጋቢ ተመልክቷል። እስራኤል እና ፍልስጤማውያን ሰኞ ዕለት ወደለየለት ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ እስካሁን ከ100 በላይ ሰዎች ጋዛ ውስጥ የተገደሉ ሲሆን እስራኤል ውስጥ ደግሞ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። በሌላ በኩል እስራኤል ውስጥ የሚገኙ አይሁዶችና አረቦችም ግጭት ውስጥ ገብተዋል። የእስራኤል ባለስልጣናት ነገሮች በዚህ መልኩ ከቀጠሉ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳያመራ ስጋታቸውን ገልጸዋል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ቤኒ ጋንትዝ በበኩላቸው በአገሪቱ የተቀሰቀሰውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር እየተሰማራ እንደሆነና እስካሁንም ከ400 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ደግሞ መከላከያ ኃይሉ በጋዛ ታጣቂዎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ አስፈላጊ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ እንዲቀጥል በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በመግለጫውም ጋዛን የሚመራው ኢስላማዊው ቡድን ሃማስ ላደረሰው ጉዳት ከባድ ዋጋ ይከፍላል ብለዋል። የእስራኤል ጦር ጋዛ ድንበር አቅራቢያ ሐሙስ ዕለት የሃማስ ቃል አቀባይ የሆኑት ግለሰብ በበኩላቸው ቡድኑ የምድር ጥቃት ለመፈጸም የሚወስን ከሆነ የእስራኤልን ወታደሮች መራር ትምህርት እንሰጣቸዋለን ሲሉ ተደምጠዋል። የእስራኤል መንግሥት በእስራኤላዊያን እና አረቦች መካከል ከፍተኛ አመፅ መነሳቱን ተከትሎ በሎድ ከተማ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል። በሎድ ከተማ በተነሳው አመፅ መኪኖች ጋይተዋል እንዲሁም 12 ሰዎች ተጎድተዋል። የከተማው ከንቲባም ስማቸው ከእርስ በእርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ እየተነሳ ይገኛል። ማክሰኞ ምሽት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በሎድ ከተማ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጁን ይፋ አድርገዋል። የእስራኤል የድንበር ጠባቂ ፖሊሶችም ከዌስት ባንክ እንዲመጡ ተደርጓል። በቴል አቪቭ አቅራቢያ ባለችው የሎድ ከተማ የሚኖሩ እስራኤላዊያን አረቦች የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ ወደ ረብሻ ተቀይሮ ፖሊስ ላይ ድንጋይ በመወርወሩ ፖሊስ ከፍተኛ ድምፅ በሚያሰሙ ፍንዳታዎች ምላሽ ሰጥቷል። የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በሎድ ከተማ በርካታ የንግድ ሱቆች እና ምኩራቦች በእሳት ተያይዘዋል። ሮይተርስ እንደዘገበው አንድ አረብ እየነዳ በነበረበት ወቅት አይሁዶች መኪናውን በድንጋይ አጥቅተዋል። የፍልስጤም ተዋጊዎች በበኩላቸው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ባካሄደችው የአየር ጥቃት አንድ ህንፃ ሙሉ ለሙሉ መውደሙን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን ወደ ቴል አቪቭ ተኩሰናል ብለዋል። የዚህ ሳምንቱ ግጭቱ ከአውሮፓውያኑ 2014 በኋላ ከባዱ የተባለ ሲሆን በርካታ ንጹሀን ዜጎችና መሰረተ ልማቶች ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ ይገኛሉ። የእስራኤል መከላከያ እስከ 7 ሺ የሚደርሱ ተጠባባቂ ወታደሮችን የጠራ ሲሆን ወደ ጋዛ ድንበር ደግሞ ወታደሮችን እና ታንኮችን ማስጠጋት ጀምሯል። ግጭቱ አምስተኛ ቀኑን መያዙን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሁለቱም አካላት ግጭቱን ለማበረድ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
46340475
https://www.bbc.com/amharic/46340475
በደብረ ማርቆስ ከተማ አንድ ግለሰብ ዛፍ ላይ ወጥቶ አልወርድም ካለ ከ24 ሰዓት በኋላ መውረዱ ታወቀ
በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 03፣ ሰፈር አንድ፣ ድብዛ አካባቢ ከህዳሴ ጤና ጣቢያ ዝቅ ብሎ በሚገኝ ዛፍ ላይ የወጣ አንድ ግለሰብ አልወርድም ብሎ ከቆየ ከ24 ሰዓት በኋላ በራሱ ፈቃድ መውረዱን የቀበሌው ስራ አስኪያጅ አቶ አወቀ አዛዥ ለቢቢሲ ተናገሩ፡፡
በትናንትናው ዕለት የአካባቢው ሰዎች ስንት ሰዓት ላይ ዛፉ ላይ እንደወጣ ባያዩትም ከ4 ሰአት ጀምሮ ግን ዛፉ ላይ ወጥቶ መመልከታቸውን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ጨምረው አስረድተዋል። ዛሬ ምሳ ሰአት አካባቢ ያለምንም ረዳት ከዛፉ ላይ እንደወረደ የሚናገሩት ስራ አስኪያጁ ለምን ዛፉ ላይ እንደወጣ ለመናገር ፈቃደኛ አልሆነም ብለዋል። ከዛፉ ላይ እንደወረደ የአካባቢው ሰዎች የሚጠጣው ውሃና ያላቸውን ገንዘብ አዋጥተው እንደሰጡት ጨምረው ነግረውናል። ግለሰቡ በአሁኑ ሰአት በከተማው ፖሊስ እጅ እንደሚገኝም ጨምረው አስረድተዋል። የቀበሌው ስራ አስኪያጅ እንደሚሉት ግለሰቡ የወጣበት ዛፍ የሚገኝበት አካባቢ ገደላማ ሲሆን በተለምዶ የግምጭ ወንዝ የሚባለው የሚገኝበት ነው። ይህም ግለሰቡን ለማውረድ የሚደረገውን ጥረት ፍሬ አልባ አድርጎት ቆይቶ ነበር ብለውናል። ዛፍ ላይ ወጥቶ አልወርድም ያለው ግለሰብ ዕድሜው ከ35 እስከ 45 የሚገመት ሲሆን የቆሸሸ ልብስ መልበሱን ክራንችም ከዛፉ ስር ወድቆ መገኘቱን ጨምረው ነግረውናል። እርሳቸውም አንድ እግሩና እጁ ላይ ጉዳት እንዳለበት መመልከታቸውን እና የአካል ጉዳተኛ እንደሆነ ተናግረዋል። • "ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ • ወሎ በነዳጅ 'ልትባረክ' ይሆን? • «በሸካ ዞን የመንግሥት ቢሮዎች ለወራት ሥራ ፈተዋል. . .» የደብረማርቆስ ከተማ ኮሚዩኑኬሽን የዜናና ሕትመት ባለሙያ ወ/ሮ ሐረጓ አበበ የወጣበት ዛፍ ትልቅ መሆኑን ተናግረው ለማውረድ በተሞከረ ቁጥር እርሱ ወደ ላይ ስለሚወጣ ተቸግረው ነበር። የከተማው ኮሙዩኑኬሽን ባልደረቦች ዛሬ ማለዳ ሄደው እንዳዩት የሚናገሩት ወ/ሮ ሐረጓ ለማነጋገር ቢሞከርም ምላሽ እንደማይሰጥ ያስረዳሉ። የወጣበት ባህር ዛፍ ትልቅ ቢሆንም እርሱ ግን ጫፍ ላይ የሚገኝ ቅርንጫፍ ላይ መውጣቱን ማየታቸውን ጨምረው አስረድተዋል። ፖሊስ በአካባቢው ተገኝቶ እንደነበር የሚናገሩት የኮሙዩኑኬሽን ባለሙያ እንዲወርድ ለማድረግ የተለያዩ ሙከራቸውን ማድረጋቸውንም ተናግረዋል። ግለሰቡ ደብረማርቆስ ቦሌ ኮንዶሚኒየም አካባቢ በጫማ ማሳመር ስራ ላይ ተሰማርቶ እንደነበር መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
news-46983377
https://www.bbc.com/amharic/news-46983377
ኦነግና ኦዴፓ የእርቀ ሰላም ውይይት አካሂደዋል
በኦሮሞ ነፃነት ግንባርና በመንግስት መካከል የተከሰተውን አለመግባበበት ለማስታረቅ የተቋቋመው የእርቅና የሰላም ኮሚቴ ዛሬ ሁለተኛ ስብሰባውን በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ አካሂዷል።
የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳዉድ ኢብሳ፣ የኦዴፓ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎችና ምሁራን በተሳተፉበት ስብሰባ፤ ኮሚቴው ሁለቱም ወገኖች ለሰላም በቁርጠኝነት እንዲሠሩና ሰላም በዘላቂነት እንዲወርድ ውሳኔ አስተላልፏል። • "በረከትና ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ • የጂግጂጋ ነዋሪ ጥንዶች ስጋት ላይ ነን እያሉ ነው በእርቀ-ሰላም ጉባዔው ከተላለፉት ዋና ዋና ውሳኔዎች መካከል፦ • ማንኛውም ዓይነት ፕሮፓጋንዳ በሁለቱም በኩል እንዲቆምና ቅሬታ ቢኖራቸው እንኳን ለኮሚቴው ማቅረብ እንጂ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት እንደማይችሉ፤ • ኦነግ ወታደሮቹን በ20 ቀናት ውስጥ ወደ ካምፕ ጠቅልሎ እንዲያስገባና ወታደሮቹ የጀግና አቀባበል እንዲደረግላቸው፤ • ወታደሮቹ ወደ ካምፕ በሚገቡቡት ወቅት ምንም ዓይነት ችግር እንዳይፈጠር የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጥበቃ እንዲያደርጉ፤ • ወታደሮቹ የሚሠፍሩባቸው ካምፖች ከዚህ በፊት ችግር ተነስቶባቸው ከነበሩ ቦታዎች የራቁ እንዲሆኑና ኮሚቴው በማንኛውም ሰዓት ሄዶ መጎብኘት እንዲችል፤ • ወታደሮቹ በካምፕ ውስጥ ከሁለት ወራት በላይ እንዳይቆዩ፤ በተካሄደው የእርቅ ውይይትም በኦሮሞ ባህል መሰረት ኮርማ በሬ ታርዶ ሰላም እንዲወርድ ሁሉም መስማማታቸውን በቦታው የተገኘው ባልደረባችን ነግሮናል። የኦሮሞ አባገዳዎች ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ አቶ በየነ ሰንበቶ ''የመጨረሻው እርቅ ተካሂዷል፤ ሰላምም ወርዷል'' ብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኮሚቴው አባል አቶ ሃይሌ ገብሬ ደግሞ ''ከዛሬ በኋላ ለነጻነት በሚል የሚተኮስ አንድም ጥይት አይኖርም" ሲሉ ተደምጠዋል። • በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል? • ኦዲፒ፡ ኦነግ እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው የኦሮሞ ፌዴራል ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ በቀለ ገርባ በበኩላቸው ይህ ውሳኔ የመጨረሻ ስለሆነ ውሳኔውን የማይቀበል አካል ኦሮሚያ ውስጥ መኖር አይችልም ብለዋል። ኮሚቴው ያሳለፈውን ውሳኔ መንግሥት ሙሉ በሙሉ የሚቀበለው መሆኑን የተናገሩት ደግሞ መንግሥትን ወክለው የኮሚቴው አባል የሆኑት አቶ ሞገስ ኢደኤ ናቸው። አክለውም በአጭር ጊዜ ውስጥ የኦነግን ሰራዊት ብንቀበል ደስውታውን አንችለውም ብለዋል። የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታደሰ ቀነአ፤ ሁሌም ችግር ሲፈጠር የሚጎዳው ህዝቡ ስለሆነ ለህዝቡ ሰላም ሲባል ሁለቱም ወገኖች ሁሉንም ነገር ትተው እጅ ለእጅ ተያይዘው መስራት እንዳለባቸው አሳስዋል።
46530699
https://www.bbc.com/amharic/46530699
በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃና ግፍ ለተፈጸመባቸው ካሳ ሊጠየቅ ነው
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ ለስቃይ እና ለእንግልት የተዳረጉ የቀድሞ እስረኞች መንግሥትን ካሳ እንጠይቃለን አሉ።
የ32 ዓመቱ ሰይፈ ግርማ በሽብር ወንጀል ተከሶ ለሦስት ዓመታትን በእስር አሳልፏል። በቆይታውም ከፍተኛ የማሰቃየትና የማስፈራራት ተግባራት ይፈፀምበት እንደነበረ የሚናገረው ሰይፈ እግሩ ላይ የሚገኘውን ትልቅ ጠባሳና በግራ ትከሻው ላይ ያለው ጉዳት ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ በነበረበት ወቅት የደረሰበት እንደሆነ ያስረዳል። •"ከሞቱት አንለይም" የሶማሌ ክልል እስረኞች • ''አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግራቸውን በተግባር ሊያሳዩ ይገባል'' የተመድ ኮሚሽነር • ". . . ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል" ጠ/ሚ ዐብይ ''ጨለማ ቤት ውስጥ ታስሬያለሁ። ምርመራዎች የሚካሄዱት በጉልበት ሲሆን፤ ደድብደባ፣ ውስጥ እግር ገልብጦ መግረፍ እና አጸያፊ የሆኑ ስድቦችን እንሰደብ ነበር። ምርመራዎች የሚካሄዱት ሌሊት ላይ ሲሆን መርማሪዎች መጠጥ ጠጥተው የሚመጡበት ጊዜ አለ" ይላል ሰይፈ። ይህ የሰይፈ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በቁጥጥር ስር ውለው ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመባቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ። አብዛኛዎቹ ደግሞ መንግሥትን በመቃወምና ዴሞክራሲያዊ የሆኑ ለውጦች ይምጣ በማለት ሰልፍ የወጡ ናቸው። ከእነዚህም መካከል ሌላኛው ዮናስ ጋሻው ይገኝበታል። የሽብር ክስ ተመስርቶበት የነበረው ዮናስ፤ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ሱሪውን በማውለቅ የደረሰበትን ድበደባ ለማሳየት በመሞከሩ ብዙዎች ያስታውሱታል። • ልዩ ፖሊስን ማን መሰረተው? • ሜጀር ጄኔራል ክንፈ: ‘‘ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም፤ ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው’’ በእስር ላይ በነበረበት ወቅት የደረሰበትን ጉዳት ሲያስረዳ ''በደረሰብኝ ድብደባ ምክንያት ዛሬ በክራንች ነው የምሄደው፣ በጀርባዬ መተኛት አልችልም። ሽንት ቤት እንኳ በሰው ድጋፍ ነው የምሄደው'' የሚለው ዮናስ ''በቁሜ የሞትኩ ያህል ቢሰማኝም ይህንን ለውጥ በማየቴ ደስተኛ ነኝ'' ይላል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በወርሃ ሰኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ቀርበው በእስረኞች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጽም እንደነበረ አምነው ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል። ወደ ስልጣን ከመጡ ሰባት ወራትን ያስቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፤ እየወሰዷቸው ያሉት የለውጥ እርምጃዎች በበርካቶች ዘንድ ተስፋን ያጫሩ ከመሆኑ በተጨማሪ ከሰብአዊ መብት ጥሰትና ሙስና ጋር በተያያዘ ወደ 70 የሚጠጉ ከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊዎችን በጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋል። የሰብአዊ መብት ተከራካሪ እና የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ አምሃ መኮንን በመቶዎች ለሚቆጠሩ በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ቤት ለነበሩ ዜጎች ጠበቃ በመሆን አገልግለዋል። አቶ አምሃ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት እየተከናወኑ ያሉ ጥፋተኛ ናቸው የተባሉ አመራሮችን ለህግ የማቅረቡ ሥራ ገና የመጀመሪያ እርምጃ ነው ይላሉ። ''በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቂም ተፈጥሯል። መንግሥት በአፋጣኝ መልስ ሊሰጥባቸው የሚገቡ ቅሬታዎች አሉ። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የመጀመሪያው እርምጃ መሆን ያለበት ደግሞ ግልጽ ውይይት መጀመር ነው። ሃገራዊ እርቅ ያስፈልገናል'' የይላሉ የሕግ ባለሙያው። ''በተጨማሪም ተጎጂዎች ካሳ የሚያገኙበትን መንገድን ለማመቻቸት እየሰራን ነው። ጉዳያችን በሃገር ውስጥ ፍርድ ቤቶች መልስ የማያገኝ ከሆነ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ድረስ ለመሄድም ተዘጋጅተናል። እስከመጨረሻው እንታገላለን። መታገላችንን አናቆምም'' በማለት አቶ አምሃ አቋማቸወን ገልፀዋል።
news-49041902
https://www.bbc.com/amharic/news-49041902
ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላን መታ መጣሏን ተናገሩ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ባህር ኃይል የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላንን በስትራይት ሆርሙዝ አካባቢ መታ መጣሏን ተናገሩ።
ሐሙስ ዕለት የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን የአሜሪካ የጦር መርከብን በ914 ሜትር ርቀት ቀርቦ እንደነበር የተናገሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የጦር መርከቡም "ራሱን የመከላከል እርምጃ" ወስዷል ብለዋል። ኢራን በበኩሏ ሰው አልባ አውሮፕላን ስለመጥፋቱ መረጃ የለኝም ስትል ተናግራለች። ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ኢራን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላንን መታ መጣሏ ይታወሳል። • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው? ኢራን እሁድ ዕለት የሌላ አገር "የነዳጅ ጫኝ መርከብና" 12 ሠራተኞቹን በገልፍ በኩል ነዳጅ በሕገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ በቁጥጥር ስር ማዋሏን ተናግራ ነበር። ኢራን ከግንቦት ወር ጀምሮ በአሜሪካ የዓለም እቃ ጫኝ መርከቦች በከፍተኛ ሁኔታ በሚንቀሳቀሱበት የባህር ክልል የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት በማድረስ ስትከሰስ ነበር። ክሱን ግን ቴህራን አስተባብላለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁለቱ አገራት መካከል የሚፈጠሩ ምልልሶችና እሰጥ አገባዎች በክልሉ ጦርነት ይቀሰቅሳል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ፈጥሯል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ ላይ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን መተው ጥለዋል የተባሉትን የአሜሪካ ጦር መርከብ ባልደረቦችን አደናንቀዋል። • የአዲስ አበባ መስተዳደርና የባላደራው ምክር ቤት • በአዲስ አበባ ቢያንስ 3.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ትራንስፎርመሮች ተሰረቁ "በግምት 914 ሜትር ተጠግታ የነበረች የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን ላይ የወሰዱት እርምጃ ራስን መከላከል ነው፤ አውሮፕላኗ በተደጋጋሚ ከአካባቢው እንድትርቅ ቢነገራትም ትዕዛዙን በመተላለፍና የመርከቡንና የሠራተኞቹን ደህንነት አደጋ ላይ በመጣሏ የማያዳግም እርምጃ ተወስዷል" ብለዋል። ዋሺንግተን ከዚህ አስቀድሞ ኢራን በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸውን ነዳጅ ጫኝ መርከብና ሠራተኞቹን እንድትለቅ ጥሪ አቅርቦ ነበር። የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኀን የኢራን ሪቮሊውሽነሪ ጋርድን ጠቅሶ፤ ነዳጅ ጫኝ መርከቡ አንድ ሚሊየን ሊትር ነዳጅ በድብቅ እያጓጓዘ ነበር ብሏል። በኋላም መገናኛ ብዙኀኑ ባወጣው ተንቀሳቃሽ ምስል የኢራን ፈጣን ጀልባ የፓናማ ባንዲራ የምታውለበልብ ሪሀ የተሰኘች ነዳጅ ጫኝ መርከብን ሲከብና ሲያስቆም አሳይቷል።
50093605
https://www.bbc.com/amharic/50093605
የግብጽዊው አርቲስት ድርጊት አውሮፕላን አብራሪው እስከወዲያኛው ከሥራቸው እንዲባረሩ አደረገ
ግብጻዊው ተዋናይና ድምጻዊ ከሥራ አጋሮቹ ጋር በመሆን ወደ ሳዑዲ አረቢያ እየበረረ በነበረበት ወቅት ድንገት ብድግ ብሎ ወደ አብራሪዎቹ ክፍል ያመራል።
ይህ ዝነኛ ተዋናይ በረዳት አብራሪው ቦታ ተቀምጦ አውሮፕላኑን ሲያበር የተቀረፀ ሲሆን ይህ እንዲሆን የፈቀዱት የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ እስከ ህይወታቸው ፍፃሜ አውሮፕላን እንዳያበሩ በግብጽ መንግሥት ታግደዋል። ስመ ጥሩ ተዋናይ መሐመድ ረመዳን የተባለ ሲሆን በግል አውሮፕላን ወደ ሳዑዲ አረቢያ እየሄደ ባለበት ወቅት ነው አብራሪው ከጎናቸው አስቀምጠውት የታየው። • የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን? • የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ከየት ወደ የት? • ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ ድምጻዊውን የኡጋንዳ ጠላት ሲሉ ተናገሩ ዝነኛው ተዋናይና ድምጻዊም በረዳት አብራሪው ወንበር ላይ ተቀምጦ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስልን በሞባይል ቀርጾ በቲውተር ገፁ ላይ የለጠፈ ሲሆን መቆጣጠሪያውን ሲይዝም ይታያል። ረዳት አብራሪውም በዚሁ የተነሳ ለዓመት ያህል አውሮፕላን በደረሰበት እንዳትደርስ በማለት ታግዷል። የመሐመድ ድርጊት መዘዙ በረራውን ያካሄደው የስማርት አቪየሽን ባለሰልጣናትንም ጋር ደርሷል፤ ከስልጣናቸው እንዲለቁ መደረጉ ተገልጿል። የግብጽ ሲቪል አቪየሽን ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ "የግብጽን ሲቪል አቪየሽን ህግ መጣሳቸው እንደተረጋገጠ አብራሪው ለግዴለሽነቱና ኃላፊነት ለጎደለው ድርጊቱ እንዲሁም ሌሎች አካላት ላይ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስደናል" ብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም የአቪየሽን ደህንነት ለግብፅ አየር መንገዶች በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው ብሏል። መሐመድ ረመዳን ከ7 ሚሊዮን በላይ የዩቲዩብ ተከታዮች ያሉት ሲሆን ይህንን ምስል በቲውተር ገፁ ላይ የለጠፈው የዛሬ ሳምንት ገደማ ነበር። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይም "ለመጀመሪያ ጊዜ አውሮፕላን ላበር ነው" ሲል ይደመጣል። በምስሉ ላይ ወደ አብራሪዎቹ ክፍል ሲገባ ያለው ክፍል ተቆረጦ ያጠረ ሲሆን የረዳት አብራሪው መቀመጫ ላይ ሲቀመጥና መቆጣጠሪያውን ሲይዝ ግን ይታያል። ማንነቱ ያልታወቀ ሌላ ሰው "ፈጣሪ ምስክሬ ነው መሐመድ ረመዳን በአሁን ሰዓት አውሮፕላን እያበረረ ነው" ሲል ይደመጣል። የግብጽ አቪየሽን ባለስልጣን መንገደኞች አውሮፕላኑ በበረራ ላይ እያለ ወደ አብራሪው ክፍል እንዳይገቡ የሚከለክል ህግ አለው። አንዳንዶች በተዋናዩ የተበሳጩ ሲሆን የእርሱን ሥራዎች ማየት ማቆም አለብን ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡም አሉ። ረመዳን በግብጽ ሲኒማዎችና ድራማዎች ላይ በብዛት የሰራ ሲሆን ወደ ሳዑዲ የሄደውም የባንድ አባላቱን ይዞ በአንድ ፌስቲቫል ላይ ለመዝፈን እንደሆነ ገልጿል። የ31 ዓመቱ ተዋናይ በዩቲዩብ ላይ 158 ሚሊዮን ጊዜ የታየለት ሙዚቃ አለው። ይህ ተዋናይና ድምፃዊ ዝናው ጣሪያ የነካ ቢሆንም አከራካሪ ጉዳዮችም አያጡትም። ከዚህ ቀደም በአንድ የሙዚቃ ድግስ ላይ አካሉን የሚያጋልጥ አለባበስ ለብሶ ሲደንስ ታይቶ በአድናቂዎቹ መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቶ ነበር። ከሦስት ዓመታት በፊት ደግሞ ስለገዛቸው ሁለት ቅንጡ መኪኖች ጉራውን በመቸርቸሩ 'ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አድናቂዎቹ ስሜት አይጨነቅም' በሚል ወቀሳ ቀርቦበት ነበር።
news-51894638
https://www.bbc.com/amharic/news-51894638
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌና ላልይበላ በረራዎችን ሰረዘ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መቀሌና ላልይበላ ጨምሮ በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍሎች ዛሬ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎችን ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት መሰረዙን አስታወቀ።
አየር መንገዱ ጨምሮም በተመሳሳይ ወደ ጎንደር፣ አክሱምና ሽሬ ሊያደርጋቸው የነበሩ በረራዎችም ዛሬ ጠዋት በነበረው አመቺ ያልሆነ የአየር ሁኔታ ሳቢያ መስተጓጎሉን አመልክቷል። በዛሬው ዕለት የተሰረዙትን በረራዎች ያለው የአየር ሁኔታ መሻሻሉን በተመለከተ ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት የሚገኝን መረጃ መሰረት በማድረግ እንዲቀጥል የሚደረግ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን አሁን ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በረራዎችን ያስተጓጎለው የአየር ሁኔታ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ውስጥም ሊቀጥል እንደሚችል አመልክቷል። በተያያዘ ዜና ከአርብ ከሰዓት ጀምሮ ቅዳሜ ዕለትም የባህር ዳር ከተማ ሰማይ በአቧራ ጭጋግ ተሸፍኖ እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ይህንን ክስተት በተመለከተ የምዕራብ አማራ የሜቲዮሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የትንተናና ትንበያ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጥላሁን ውቡ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት "ጠንካራ የአቧራ ጭጋግ ተከስቷል።" ይህ የአቧራ ጭጋግ የሚከሰተው በደረቅ አካባቢዎች የሚከሰትን አውሎ ነፋስ ተከትሎ ነው የሚሉት ባለሙያው፤ በባህር ዳር ላይ የታየው የአቧራ አውሎ ነፋስ ሱዳን ላይ በተከሰተ ዝቅተኛ የአየር ግፊት ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። ይህ የአቧራ ጭጋግ የተከሰተው በባህር ዳር ከተማ ብቻ አለመሆኑን የሚናገሩት ባለሙያው ጎንደር ላይም መታየቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ክስተቱ ብዙ ጊዜ ለረዥም ሰዓት አይቆይም የሚሉት አቶ ጥላሁን ቶሎ ሊጠፋ እንደሚችል ያስረዳሉ። ነገር ግን በእንዲህ ዓይነት የአየር ሁኔታ አውሮፕላኖች ለመነሳትም ሆነ ለማረፍ እይታን ስለሚጋርድ ለበረራ አስቸጋሪ እንደሚሆን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ግን በረራዎች ከተስተጓጎሉባቸው ከተሞች ውስጥ የአቧራ ጭጋጉ የተከሰተባት የባህር ዳር ከተማ የለችበትም። ባለሙያው ጨምረውም እንዲህ አይነት አቧራ ጭጋግ የመተንፈሻ አካል ችግር በተለይ አስም ላለባቸው ሰዎች አስቸጋሪ እንደሚሆን አስታውሰው፤ እንዲሁም ክስተቱ የማጅራት ገትር በሽታ መንስዔም ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ባህር ዳር የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳረጋገጠው የአቧራ ጭጋጉ ዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም የተወሰኑ ምልክቶች ግን እንዳሉ አመልክቷል።
news-52240990
https://www.bbc.com/amharic/news-52240990
ሦስት ሰዎች በምዕራብ ወለጋ በታጣቂዎች ተገደሉ
የታላቁ ተልዕኮ በኢትዮጵያ (ግሬት ኮሚሽን) አገልጋዮች የሆኑ ሁለት ግለሰቦችና አንድ ተማሪ በምዕራብ ወለጋ ገንጂ ከተማ አቅራቢያ በታጣቂዎች በጥይት መገደላቸውን የድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ ግርማ አልታዬ ለቢቢሲ ገለፁ።
የአካባቢው ባለስልጣናት ግድያው የተፈፀመው በአካባቢው ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ነው ማለታቸውን የሚናገሩት አቶ ግርማ ግለሰቦቹ በበርካታ ጥይት ተመትተው መሞታቸውን አስረድተዋል። አቶ ግርማ የድርጅታቸው ሠራተኞች የተገደሉብትን ሁኔታ ሲያስረዱ "አቶ ምስጋን ሥራ በመዘጋቱና ወደ ቤተሰቦቹ ለመሄድ በመፈለጉ እንዲሁም በነቀምት የትራንስፖርት እጥረት ስለነበር አቶ አሰፋ መኮንን በድርጅቱ መኪና እንዲሸኙት" መደረጉን ይገልፃሉ። አቶ አሰፋ የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነውን ልጃቸውን ሳሙኤል አሰፋን ጭነው ወደ ጊምቢ ግለሰቡን ለመሸኘት እንደሄዱ ያስረዳሉ። "ከጊምቢ በኋላ ወደ ውስጥ ወደ ገንጂ መግባታቸውን በወቅቱ አላወቅንም ነበር" የሚሉት አቶ ግርማ ወደ ከተማ ሲቃረቡ የተኩስ ርምታ እንደተከፈተባቸው ተናግረዋል። "ምናልባት ከጊምቢ በኋላ ትራንስፖርት በማጣታቸው ምክንያት ወደ ውስጥ ለመዝለቅ ወስነው ይሆናል" ሲሉ ሁኔታው የተቀየረበትን አጋጣሚ ያስረዳሉ። ከሟቾቹ መካከል የሆኑት አቶ አሰፋም ሆኑ አቶ ምስጋኑ "በአካባቢው ማኅበረሰቡ ድረስ በመዝለቅ የሚያገለግሉ ነበሩ" ያሉት አቶ ግርማ፤ የአቶ ምስጋኑ የትውልድ አካባቢያቸው ጭምር መሆኑን ገልፀዋል። ታላቁ ተልዕኮ በኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ መንቀሳቀስ ከጀመረ አርባ ዓመት ሆኖታል የሚሉት ዳይሬክተሩ፤ "ድርጅታችን ከማንኛውም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የራቀ ነው" በማለት ሠራተኞቻቸው ትኩረት ተደርጎባቸው መጠቃታቸውን እንደማያምኑ ይገልጻሉ። ምዕራብ ወለጋ ከ20 ዓመት በላይ ተንቀሳቅሰናል በማለትም ጥቃት ይደርስብናል የሚል ስጋት በሠራተኞቻቸውም ላይ እንደሌለ ያስረዳሉ። ግለሰቦቹ ተሳፍረውበት የነበረው መኪና በበርካታ ጥይት መመታቱን የሚናገሩት ዳይሬክተሩ ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰበት በአካባቢው ያለው የኮማንድ ፖስት ካምፕ ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል። አቶ ምስጋኑ ከትናንት በስቲያ በትውልድ መንደራቸው፣ አቶ አሠፋና ልጃቸው ደግሞ በትናንትናው ዕለት በጉደር ከተማ ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል ብለዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጨምሮ በተለያዩ ሰዎች ላይ ጥቃትና ግድያ ተፈጽሟል። አካባቢውም ከክልሉና ከፌደራል መንግሥቱ በተወጣጣ ኮማንድ ፖስት ስር ከሆነ ረጅም ጊዜ እንደሆነው ይታወቃል።
news-53473464
https://www.bbc.com/amharic/news-53473464
ፋና ብሮድካስቲንግ የመቀሌ ኤፍ ኤም ስርጭቱን አቋረጠ
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ከትግራይ ክልል መቀለ ከተማ በኤፍኤም አማካይነት ሲያደርገው የነበረውን ስርጭቱን ማቋረጡን የቢቢሲ ሪፖርተር አረጋገጠ።
የቢቢሲ ሪፖርተር የብሮድካስት ባለስልጣን ለጣብያው የጻፈውን ደብዳቤ ከድርጅቱ ጋዜጠኞች በማየት ማረጋገጥ እንደቻለው ስርጭቱ ከትናንት ጀምሮ እንደተቋረጠ የተገለፀ ሲሆን ቢሮውም መዘጋቱን ለማወቅ ተችሏል። ቢቢሲ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የመቀለ ቅርንጫፍ ጋዜጠኛ ከሆነው ዮናታን ገዛኸኝን ባገኘው መረጃ መሰረት አራት የድርጅቱ ሠራተኞች ከአርብ እለት ጀምሮ ከደሞዝ እና ከሥራ መታገዳቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሷቸዋል። መገናኛ ብዙሃኑ የመቀለ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ከዚህ ቀደም በተከሰተ አለመግባባት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል። ቢቢሲ ከፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ቅርጫፎች ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ገመዳ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ለማግኘት በስልክ ባደረገው ጥረት ከድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ምላሽ እንደሚሰጡንና ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ እንድንደውል ቢነግሩንም በተደጋጋሚ ያደረግነው የስልክ ጥሪ ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል። የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የመቀለ ቅርንጫፍ 32 ሠራተኞች የነበሩት ሲሆን የሠራተኞቹ መብትና ሌሎች የሚነሱ ጥያቄዎች በሂደት እንደሚመለሱ መግለፁን ከጣቢያ ባልደረቦች ለማወቅ ችለናል። ለቅርንጫፍ የሬዲዮ ጣቢያው በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በኩል የተጻፈውን ደብዳቤ በተመለከተም በስልክ መረጃ ለማግኘት ባለስልጣኑ ጋር ያደረግነውም ሙከራ ስልካችን ባለመነሳቱ አልተሳካም። ቢቢሲ በማንኛውም ሰዓት ከሁለቱም ወገኖች ምላሽ ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት የሚቀጥል ሲሆን ጉዳዩን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት የምናገኘውን ተጨማሪ መረጃ እናቀርባልን።
news-55155503
https://www.bbc.com/amharic/news-55155503
ትግራይ ፡ በትግራይ ያሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች የምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ተባለ
ከሦሰት ሳምንታት በላይ ወታደራዊ ግጭት በተካሄደባት ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ የስደተኛ ማቆያዎች ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ስደተኞች የምግብ እጥረት እያጋጠማቸው እንደሆነ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ዩኤንኤችሲአር አስታወቀ።
ኤርትራውያን ስደተኞች ተቋሙ ለስደተኞቹ አስፈላጊውን አቅርቦት ለማድረስ የሚያስችለው የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አቅርቦት መንገድ እንዲከፈት ጠይቋል። በትግራይ ክልል ኃይል እና በፌዴራል መንግሥት ሠራዊት መካከል ወታደራዊ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ በክልሉ የመገናኛ መስመሮችና እርዳታ የሚገባባቸው መንገዶች ተዘግተዋል። እንደ ድርጅቱ መረጃ በትግራይ ክልል ውስጥ 100 ሺህ የሚሆኑ ኤርትራውያን በአገራቸው ያለውን ፖለቲካዊ እስርና አስገዳጅ የግዳጅ የውትድርና ሥልጠና በመሸሽ ተሰደው ይገኛሉ። ከኤርትራውያኑ ስደተኞች የምግብ እጥረት ጉዳይ በተጨማሪ ከተቀሰቀሰ አንድ ወር ሞላውን ወታደራዊ ግጭትን በመሸሽ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ነዋሪዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ተሰደዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች መሥሪያ ቤት አክሎም "ኤርትራውያን ስደተኞች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፤ ታፍነው እየተወሰዱ ነው" የሚሉ ያልተጣሩ ዘገባዎችን ተከትሎ ስጋት ላይ ነኝ ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ የመቀለ ከተማ በፌደራል ሠራዊቱ ቁጥጥር ሥር መዋሏን ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ሕግን የማስከበር ዘመቻ ተጠናቋል ማለታቸው ይታወሳል። ነገር ግን የህወሓት ሊቀ መንበር የሆኑት ደብረፂዮን ገብረሚካዔል አሁንም ጦርነት እንዳለና ኃይላቸው ድል እያገኘ እንደሆነ ተናግረዋል። ቢቢሲ ይህንን በእራሱም ሆነ ከሦስተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም። ረሃብ ጄኔቫ ከሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት መግለጫ የሰጠው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም (ዩኤንኤችሲአር) ጊዜው እየገፋ በሄደ ቁጥር ትግራይ ክልል ያሉ የኤርትራውያን ስደተኞች ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እየወደቀ ነው ብሏል። "መጠለያ ካምፖች የምግብ እጥረት እየገጠማቸው ነው። ረሃብና ያልተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት እያንዣበበ ነው። ትግራይ ክልል ግጭት ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ ስለዚህ ጉዳይ ማስጠንቀቂያ ስንሰጥ ነበር" ይላል መግለጫው። አክሎም "በጣም የሚያስጨንቀን ጉዳይ በካምፖች አካባቢ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑና ጥቃቶች መሰማታቸው ነው። ስተደኞች በግድ ታፍነው እየተወሰዱ እንደሆነም ሰምተናል። ስለዚህ ወደዚያ ሄደን ሁኔታውን ራሳችን እንድናጣራ መንገድ ሊከፈትልን ይገባል" ሲል መግለጫው ያትታል። ድርጅቱ አክሎም ሰላማዊ ዜጎች ጥበቃ እንዲደርግላቸው ጥሪ አቅርቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባለፈው ሰኞ ለአገሪቱ የሕዝብ እንደራሴዎች ስለወቅታዊ ጉዳዮች በሰጡት ማብራሪያ ላይ በግጭቱ መንግሥት አንድም ንፁህ ዜጋ እንዳልገደለ ተናግረዋል። መንግሥት ለሰብዓዊ እርዳታ የሚሆን በር እንደሚከፍትም አስታውቋል። በፌደራል መንግሥቱ የሠሜን ዕዝ ላይ በትግራይ ክልል ኃይሎች አማካይነት የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ከሦሰት ሳምንታት በኋላ የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ ባለፈው ቅዳሜ በመንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ስር መዋሏ ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ መንግሥት ክልሉን መልሶ በመገንባትና የተፈናቀሉትን ወደቀያቸው በመመለስ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
47314978
https://www.bbc.com/amharic/47314978
ከቴፒ ግጭት ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች እየታሰሩ ነው
ማሻና አንድራቻ 12፣ ቴፒና የኪ ላይ ደግሞ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ። እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉት በአካባቢው ለተፈጠረው አለመረጋጋት የተለያየ አስተዋፅኦ አድርገዋል በሚል መሆኑን የዞኑ የኮሙኑኬሽን ባለሙያ ለቢቢሲ አስረድተዋል።
ካለፈው ዓመት ነሐሴ 7 ጀምሮ በሸካ ዞን ውስጥ የሚገኙት ወረዳዎች ማሻ፣ አንድራቻ፣ ቴፒና የኪ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የአካባቢው አስተዳደሮችም ሆኑ ነዋሪዎች የሚናገሩት ነው። በዚህም የተነሳ ከፌደራልና ከክልል መንግሥት የተውጣጡ አካላት ከዞን አስተዳደር ጋር በመሆን ኮማንድ ፖስት ተቋቋሙ አካባቢውን ለማረጋጋት እየሠሩ እንደሆነ የዞኑ ኮሙኑኬሽን ባለሞያ አቶ አስማማው ኃይሉ ይናገራሉ። በነበረው ብሔር ተኮር ግጭትና አለመረጋጋት 'ከስድስት ሺህ በላይ የተፈናቀሉ ሰዎች በቴፒ ከተማ አዳራሽ ይገኛሉ' የሚሉት ደግሞ በአካባቢው ሰላም ለማምጣት ታስቦ የተቋቋመው ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መንገሻ አዲስ ናቸው። • ግዙፍ የሽብር ጥቃት ሊያደርስ የነበረው አሜሪካዊ ወታደር • ሳምሰንግ እንደ መጽሐፍ የሚገለጥ ስልክ አመረተ የእነዚህን ተፈናቃዮች ጉዳይና ሌሎች የሕግ ጥሰቶችን ለከፍተኛ የመንግሥት አካላት እንዲሁም ለፌደራልና ለክልል መንግሥታት ቢሮዎች አቤት በማለታችን ማዘዣ ወጥቶብን እየታደንን ነው ይላሉ አቶ መንገሻ። "የዞኑን ሸፍጥ የሚያጋልጡ ሰዎች ፍትኃዊ ባልሆነ መልኩ እየታሰሩ ነው" በማለትም ደረሰ ያለውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ የሆነውና የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ወዳጆ ለስራ ጠዋት ከሚኖሩበት አካባቢ ወጥተው በሞተራቸው ሲንቀሳቀሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሸካ ዞን ከመጡና ማዘዣ ከያዙ የፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸውም ባለቤታቸው ከድጃ ሰይድ ነግረውናል። ባለቤታቸው እንደሚናገሩት አቶ ስንታየሁ ኑሯቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ ስምንት ዓመት ተቆጥሯል። ነገር ግን በሸካ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩትን የሕግ ጥሰቶች ለተለያዩ የፌደራል መንግሥት ቢሮዎች አቤቱታ በማስገባት የክልሉን ሰዎች ይረዱ እንደነበር አልሸሸጉም። "ለቀይ መስቀል ስለተፈናቀሉ ሰዎች ጉዳይ መረጃ በመስጠት፣ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚመለከታቸው አካላት በማድረስ የአካባቢውን ተወላጆች ይረዳ ነበር" ሲሉም ተናግረዋል። • ከ300 በላይ የሚዛን ቴፒ ተማሪዎች ታመው እንደነበር ተሰማ •"በግጭቱ 'ጀምበሬ' የሚባለው ሰፈር ሙሉ በሙሉ ወድሟል" ነዋሪዎች አቶ ስንታየሁ የታሰሩት ወንጀሉ ተፈፀመ ከተባለበት ሥፍራ ከ90 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ ነው የሚሉት ወ/ሮ ከድጃ የታሰሩበት ስፍራ ከአዲስ አበባ ደግሞ 900 ኪሎ ሜትር ያህል ርቆ እንደሚገኝና ቤተሰብም ሊጠይቃቸው የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ ባለቤታቸው ለቢቢሲ አስረድተዋል። አቶ መንገሻ አዲስ እንደነገሩን ከሆነ የሰላም ኮሚቴው ፀሐፊ የሆኑት አቶ ሸዋ ቱቻም ለተለያዩ የመንግሥት አካላት የቴፒን ጉዳይና ያለውን ኢፍትሀዊነት ስለሚያሰሙ በዞኑና በወረዳው የሚፈጠረውን ኢ- ፍትሃዊነት ስለሚቃወሙ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። የሸካ ዞን ኮሙኑኬሽን የሆኑት አቶ አስማማው ኃይሉ እነዚህ ግለሰቦች በዞኑ ውስጥ ችግር በመፍጠር የተያዙ መሆኑን ጠቅሰው የተያዙት መረጃ ተሰባስቦባቸው ጥፋት መሥራታቸው ተረጋግጦ ነው ይላሉ። በዞኑ የተነሳው የመዋቅር ጥያቄ መሆኑን ያሰታወሱት አቶ አስማማው "የመዋቅር ጥያቄ የሚፈታው የመንግሥትን መዋቀር ተከትሎ ነው" በማለት፣ ንብረት እየወደመ፤ ብሔር ተኮር ጥቃት እያደረሱ፤ የሰው ሕይወት እየጠፋ የመዋቅር ጥያቄ የለም የሚለው የኮማንድ ፖስቱ ግምገማ እንደሆነ አብራርተዋል። "እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ማስረጃ ተገኝቶባቸው፤ ምስክር ተቆጥሮባቸው ነው" የሚሉት አቶ አስማማው እስካሁን ድረስ 29 ሰዎች በሕግ ጥላ ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በቴፒ ከተማ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ ግጭት ሰባት ሰዎች መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ የሽዋስ አለሙ ለቢቢሲ መግለፃቸው ይታወሳል። በወቅቱ በግጭቱ 100 የሚጠጉ ቤቶች ሲቃጠሉ፤ 1500 ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለው ነበር። በአጠቃላይ በዞኑ ለሚገኙ ተፈናቃዮቹ እየተደረገ ስላለው ድጋፍ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት በጉዳዮ ላይ ምላሽ የሚሰጠን አካል ባለማግኘታችን አልተሳካም።
news-48606864
https://www.bbc.com/amharic/news-48606864
የእንቅልፍ ሰዓትዎን እንዴት ማስተካከል እንደሚችሉ ያውቃሉ?
ሰዎች የተለያየ የእንቅልፍ ሰዓት አላቸው፤ አንዳንዶች በጊዜ ተኝተው በማለዳ መንቃትን ያዘወትራሉ። ሌሎች ደግሞ ሌሊቱን ገፍተው ሲነጋ እንቅልፍ የሚጥላቸው አሉ። እርስዎ የትኛው ልምድ ነው ያለዎት? የማለዳ ወፍ ወይስ የሌሊት ወፍ?
የእንግሊዝና የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች የእንቅልፍ ሰዓትን በማስተካከል የአካልና የአዕምሮ ጤንነትን መጠበቅ እንደሚቻል እንደደረሱበት ይፋ አድርገዋል። አጥኚዎቹ ትኩረት ያደረጉት ሳይተኙ እኩለ ሌሊቱን የሚገፉ 'የምሽት ሰዎች' (የሌሊት ወፎች) ላይ ነው። • ስለ እንቅልፍ የተሳሳቱ አመለካከቶች • የኢትዮጵያን አደራዳሪነት የሱዳን ህዝብ እንዴት ይመለከተዋል? • በንቅለ ተከላ ዕይታው የተመለሰለት ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ባለሙያዎቹ እንደሚሉት ጥናቱን ለማካሄድ ውስን የእንቅልፍ ሰዓት መስጠትን፣ አነቃቂ መጠጦችን ማስወገድና የጠዋት ፀሐይ መኮምኮም የተጠቀሟቸው ዘዴዎች ናቸው። ዘዴዎቹ የተለመዱ ቢሆንም በሰዎች ሕይወት ላይ ግን ከፍተኛ ልዩነት ማየት የተቻለበት ነበር ብለዋል። እያንዳንዱ ሰው የፀሐይን መውጣትና መግባት ተከትሎ የራሱ የእንቅልፍ ሰዓት አቆጣጠር አለው። ለዚህም ነው ሲመሽ እየተኛን፤ ሲነጋ የምንነቃው። ይሁን እንጂ ይህ ለሁሉም ሰው ላይሰራ ይችላል፤ ምክንያቱም የአንዳንድ ሰዎች ሰዓት ከሌሎቹ ዘግይቶ ይዘውራልና። • እንቅልፍ እንዲህ ጠቃሚ ነገር ኖሯል? በማለዳ ዝማሬያቸውን እንደሚያሰሙት 'የማለዳ ወፎች' ሁሉ የጠዋት ሰዎች በማለዳ ነው የሚነቁት ግን ማታ ለማምሸት ይቸገራሉ፤ በተቃራኒው የማታ ሰዎች (የሌሊት ወፎች) ምሽቱን ንቁ ሆነው ይገፉና ጠዋት ላይ ግን እንቅልፍ ያሸንፋቸዋል። ለምሽት ሰዎች (የሌሊት ወፎች) በጣም አስቸጋሪው ነገር ከምሽቱ 3፡00 እስከ ማለዳ 11፡00 ባሉት ሰዓታት ራሳቸውን ማስማማት ነው። የጠዋቱ የማንቂያ ደወል ሰውነትዎ ከመዘጋጀቱ አንድ ሰዓት ቀድሞ ያነቃዎታል። ይህም ከከፍተኛ የጤና ችግር ጋር ይያያዛል። ተመራማሪዎች ጥናት ባደረጉባቸውና በአማካይ ወደ መኝታቸው ለመሄድ እስከ ሌሊቱ 8፡30 የሚቆዩና እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ከእንቅልፋቸው የማይነቁ 21 የማታ ሰዎች (የሌሊት ወፎች) ላይ ጥናት አድርገዋል። በጥናቱ የተመረጡት ሰዎችም የሚከተሉትን እንዲፈፅሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር። • ሁል ጊዜ ከእንቅልፋቸው ከሚነቁበት ሰዓት ሁለት ወይም ሦስት ሰዓት ቀድመው እንዲነሱና የጠዋት ፀሐይ እንዲሞቁ ማድረግ • በተቻላቸው መጠን ቁርሳቸውን እንዲመገቡ • የጠዋት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ • በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት ምሳቸውን እንዲመገቡና ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት በኋላ ምንም ዓይነት ምግብ እንዳይመገቡ • የሚያነቃቁ መጠጦችን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በኋላ እንዳይጠቀሙ • ከቀኑ 10 ሰዓት በኋላ ምንም ዓይነት 'ሸለብታ' (ናፕ) እንዳያደርጉ • የብርሃን መጠኑ በተወሰነበት ክፍል ከተለመደው የእንቅልፍ ሰዓት ሁለት ወይም ሦስት ሰዓት ቀድመው እንዲተኙ እና • የሚተኙበትንና የሚነቁበትን ሰዓት ተመሳሳይ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር። ከሦስት ሳምንታት በኋላ፤ ሰዎቹ የመኝታ ሰዓታቸውን ከተለመደው በሁለት ሰዓት ማስተካከል ችለው እንደነበር የበርሚንግሃም፣ ሱሬይ እና ሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ውጤት አመልክቷል። • ደስታና እንቅልፍ- የፀሃይ ብርሃን ለህይወት አስፈላጊ የሆነባቸው ምክንያቶች የጥናት ውጤቱ እንዳሳየው ሰዎቹ ዐይናቸውን የሚከድኑበት ሰዓት ተመሳሳይ ነበር፤ ነገር ግን ዝቅተኛ በሆነ ደረጃም ቢሆን እንቅልፍ ማጣት፣ ጭንቀትና ድብርት አጋጥሟቸዋል። የሚነቁበት ሰዓት ግን መሻሻል አሳይቷል። "ተራና የተለመዱ የሆኑ ሥራዎችን መልክ ማስያዝ፤ የሚያመሹ ሰዎች (የሌሊት ወፎች) የእንቅልፍ ሰዓታቸውን እንዲያስተካክሉ ረድቷቸዋል፤ የአካልና የአዕምሮ ጤንነታቸውም ተሻሽሏል" ይላሉ በሰሬይ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ደብራ ኬኔ። እርሳቸው እንደሚሉት በቂ ያልሆነ እንቅልፍ እና የእንቅልፍ ሰዓት መዛነፍ የሰውነትን ጤናማ ተግባር ያውካል፤ ለልብ በሽታ፣ ለካንሰርና ለስኳር በሽታም ያጋልጣል። ሰውነታችን ለተለመደው ጤናማ ተግባሩ የሚያስፈልገውን የፀሐይ ሙቀት ማግኘት አለበት። በመሆኑም ሰውነትን ለማታ ፀሐይ ከማጋለጥ ይልቅ ለጠዋት ፀሐይ ማጋለጥ ይመከራል። ጥናቱ እንደሚያስረዳው የተዛባ የመተኛና የመንቂያ ሰዓት ካለን የሰውነታችንን ውስጣዊ ሰዓት (ሰርካዲያን ሪትም) የመተኛና የመንቂያ ሰዓታችን እንዲዛባ ያደርገዋል። በመሆኑም ይህን ተፈጠዕሯዊ ሰዓት ለማስተካከል የተጠቀምናቸው ዘዴዎች የተለመዱ ሊመስለዎት ቢችልም ሰውነታችን ሰዓቱን እንዲለማማድ ስለሚያስችለው የእንቅልፍ ሰዓታችንንም ለማስተካካል ይረዳል ። "አንፃራዊ በሆነ መልኩ እነዚህን ልምምዶች ማድረግ በጣም ቀላሉና ለውጥ የሚያስገኝ ነው፤ ይህ ለእኔም በጣም አስደንቆኛል" ብለዋል የበርሚንግሃም ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር አንድሪው ባግሻው።
news-51202584
https://www.bbc.com/amharic/news-51202584
ኢሳቤል ዶስ ሳንቶስ፡ ዩሮቢክ ባንክ ከአንጎላዋ ቢሊየን ጋር ያለውን ግንኙነት አቋረጠ
የፖርቹጋል ባንክ ዩሮቢክ ከአፍሪካዋ ቱጃር ሴት ኢሳቤል ዶስ ሳንቶስ ጋር ያለውን የንግድ ግንኙነት እንደሚያቋርጥ አስታወቀ።
የቀድሞው የአንጎላ ፕሬዝዳንት ልጅ ኢሳቤል ዶስ ሳንቶስ በመሬት፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ ዘይት ዘርፍ በመሰማራት የመንግሥትን እጅ በመጠምዘዝ ከድሃ አንጎላዊያን ጉሮሮ እየነጠቀች ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንዳካበተች ይነገራል። በተለይ አባቷ በመንግሥት ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የኢንቨስትመንት አማራጮች ለእርሷ ብቻ ተብለው የሚከፈቱና የሚዘጉ ነበሩም ይባላል። ሰሞኑን ይፋ እንደሆነ በሚነገረው መረጃ በእነዚህ ሥራዎች እንዴት ለእርሷና ባለቤቷ ሁኔታዎች ይመቻቹላቸው እንደነበሩና ለመንግሥት መክፈል የነበረባቸውን ገንዘብ እንዴት እንዳልከፈሉ ያሳያል። • 'የአፍሪካ ሃብታሟ ሴት' ንብረት በቁጥጥር ሥር እንዲውል ታዘዘ • አገሯን 'በሙስና ያራቆተችው' የአፍሪካ ሃብታሟ ሴት ታዲያ ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በቢሊየነሯ የተከናወኑ በርካታ አጠያያቂ የሆኑ ጉዳዮች በቢቢሲ እና አጋር ድርጅቶች በተሠራ ምርመራ ከተጋለጠ በኋላ ነው። ባሳለፍነው ሰኞ የባንኩ የቦርድ አባላት ባደረጉት ስብሰባ ከአክሲዮን ባለድርሻዋ ኢሳቤል ድርጅቶች እና ከዚህ ጋር በቅርበት ግንኙነት ካላቸው ሰዎች ጋር ያላቸውን የንግድ ግንኙነት ለማቋረጥ መወሰኑን አስታውቋል። ኢሳቤላ ያስተላለፈቻቸው በአስር ሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች ላይ ምርመራ እንደሚካሄድም ባንኩ አክሏል። ቱጃሯ ግን የቀረበባትን ክስ ሙሉ በሙሉ ሀሰት ነው ብላለች። የግለሰቧ የቢዝነስ ትስስር ከአንጎላ የመንግሥት ነዳጅ ዘይት ካምፓኒ ሶናንጎል እስከ ግዙፉ የሞባይል ስልክ አቅራቢ ድርጅት የሚደርስ ነው። ኢሳቤል፤ በሁለት ድርጅቶቿ ስም በባንኩ 42.5 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ያላት ሲሆን፤ ይህም የባንኩ ከፍተኛ የአክሲዮን ባለድርሻ እንድትሆን አድርጓታል። ኢሳቤላ በአውሮፓዊያኑ 2017 አባቷ ጡረታ ሲወጡ በአንጎላ የመንግሥት ነዳጅ ዘይት ካምፓኒ ኃላፊ ሆና ለሁለት ወራት ከሠራች በኋላ ተባርራለች። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አፈትልከው የወጡት መረጃዎች እንዳመለከቱትም ኢሳቤል በሶናንጎል የነዳጅ ዘይት ድርጅትን ስትለቅ 58 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ክፍያ ፈቅዳ ነበር። የተላለፈው ገንዘብም በዩሮቢክ ያለውን የሶናንጎል የገንዘብ ማጠራቀሚያ አካውንት አራቁቶት እንደነበር ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል። • ማሽተት አለመቻል ምን ይመስላል? ባለፈው እሁድ አፈትልከው በወጡ መረጃዎች፤ አባቷ በሥልጣን በነበሩበት ጊዜ በመሬት፣ በአልማዝ፣ ነዳጅ ዘይት እና በቴሌኮም ዘርፎች ለመሳተፍ እድሉን እንዴት እንዳገኘች ሊገለጥ ችሏል። መረጃው የአፍሪካ ቱጃሯ ሴት የገዛ አገሯን በመመዝበርና በሙስና 2 ቢሊየን የሚጠጋ ሀብቷን እንዴት እንዳከማቸች ለማሳየት ሞክሯል። የአንጎላ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ባለሃብቷ ወደ አንጎላ ተመልሳ ለቀረበባት ክስ መልስ እንድትሰጥ እንደሚፈልጉ ገልፀው፤ እርሷን ወደ አገሯ ለመመለስም የሚቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። ኢሳቤል ግን የቀረበባት ክስ በሙሉ ሀሰት አንደሆነና በፖለቲካ ምከንያት በአንጎላ መንግሥት እየተፈለገች እንደሆነ ትናግራለች። ቢሆንም በሙስና ቅሌት በአንጎላ ባለሥልጣናት የወንጀል ምርመራ ሥር ስትሆን ያላት ሃብቷም እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል። ኢሳቤል ከዚህ ቀደም ለደህንነቷ ስለምትሰጋ ወደ አንጎላ ተመልሳ እንደማትሄድ አስታውቃ ነበር። ኢሳቤል ዶስ ሳንቶስ ማን ናት?
news-47143088
https://www.bbc.com/amharic/news-47143088
በአማራ ክልል 5685 የጋብቻ ጥያቄዎች በዕድሜ ምክንያት ዉድቅ ተደርገዋል
በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የ 14 አመት ታዳጊ ልጅ የባህል ልብስ ለብሳ በዕድሜ ትልቅ ከሆነ ሰው ጋር በተክሊል የጋብቻን ስነ ስርዓት የፈፀመች መሆኗን የሚያሳይ ፎቶ መታየቱ ከፍተኛ ውዝግብን ፈጥሯል።
ብዙዎችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ህፃንን መዳር ወንጀል መሆኑን በምሬት ተናግረዋል። ይህንንም እሮሮ ተከትሎ የትግራይ ክልል የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ፣ የወረዳ አስተዳደርና በክልሉ የሚገኙ የፍትህ አካላት በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ገብተው እሁድ ሊደረግ የነበረውን ሰርግ እንዲቀር አድርገውታል። •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የዚህ ፎቶ መሰራጨት ያለ እድሜ ጋብቻ አሁንም ቢሆን በሀገሪቱ ላይ የሚፈፀም መሆኑን ፍንጭ ሰጥቷል። የአንድ ህፃን ታሪክ ብቻ ሳይሆን ብዙ ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ሳይደርስ እንደሚዳሩ መረጃዎች ያሳያሉ። ለዚህም እንደማሳያነት የሚሆነው በ2009 እና 2010 ዓ.ም በአማራ ክልል ብቻ 5685 የጋብቻ ጥያቄዎች በዕድሜ ምክንያት ዉድቅ ተደርገዋል። •የተነጠቀ ልጅነት በአማራ ክልል ሁሉም ወረዳዎች የህፃናት ጋብቻን ለማስቀረት ከጋብቻ በፊት የህክምና ምርመራ ይደረጋል። በዚህ ሂደት ሁሉም ለጋብቻ የተዘጋጁ ጥንዶች ጋብቻቸውን ለመፈጸም የባለሞያ ማረጋጋጫ ሊኖራቸው ይገባል። ምርመራውን ሳያልፋ ጋብቻ ከፈጸሙ ግን በአካባቢው ፍትህ ጽ/ት ቤት ተከስሰው ለፍርድ የሚቀርቡበት የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ ውሎ በመተግበር ላይ ነው።ቢሆንም ግን እንዲህ አይነት የህግ ማዕቀፍ ቢኖርም አሁንም ቢሆን ያለ እድሜ ጋብቻ በክልሉ ይፈፀማል። ችግሩ ከሚስተዋልባቸው አካባቢዎች መካከል የፋርጣ ወረዳ አንዱ ነው።በዚህ አመት በቤተሰቦቻቸው የተዘጋጀላቸውን ጋብቻ ሸሽተው ስድስት ህጻናት ከወረዳው ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ፅ/ት ቤት በመጠለል ከትዳር ወጥመድ አምልጠዋል። •"ከሞቱት አንለይም" የሶማሌ ክልል እስረኞች የ14 አመቷ እና የ5ኛ ክፍል ተማሪዋ ህጻን መሰረት በላይ ከስድስቱ ህጻናት መካከል አንዷ ናት። በእናቷ ወ/ሮ ይመኝ በላቸዉ አማካኝነት ቢቢሲ አግኝቷት 'ኩታራዉ ነዉ እንዳላገባ ያደረገኝ' ብላለች። ነገሩን ስታብራራ በእድሜ ከሷ የሚያንሰዉ የ4ኛ ክፍል ተማሪ የሚዳሩ ልጆችን ስም ዝርዝር ለትምህርት ቤት ያመለክታል። ከዛም ተማሪዎች እንዲያዉቁ ተደረገ። ወዲያዉ ለሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጽ/ት ቤት አመልክተዉ ሰርጉ እነዲያልፋቸዉ ተደርጓል። እናቷንም ቢቢሲ ያናገረ ሲሆን 'መጀመሪያማ ያዉ ታስቦ ነበር እንግዲህ ያዉ የድንቁርና ሁኔታ ነዉ። ሁሉን ነገር መጥቼ አይቼ ስለተማርኩ አሁንማ እየደባኝ(እየጸጸተኝ)ነዉ።አሁን ግን ትምህርቷን ነዉ የማስተምራት' ብለዋል። የፋርጣ ወረዳ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ፅ/ት ቤት ሃላፊ አምሳል ተስፋ በበኩላቸው እንደሚናገሩት በ2009 ዓ.ም 210 ፤ በ2010 ዓ.ም ደግሞ 124 የሚጋቡ ሰዎች ጥቆማ አቅርበዋል። በ2010ዓ.ም ሌሎቹን የጋብቻ ጥያቄዎች ማቋረጥ ሲቻል አምስት የህጻናት ጋብቻዎች ግን ተፈፅመዋል። ይህንንም ተከትሎ የሶስቱ ሴት ልጅ አባቶችና ባሎቻቸው የአንድና የሁለት አመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። የሁለቱን ህጻናት ጉዳይ ግን መረጃ በመጥፋቱ ክሱ መቋረጠን ወ/ሮ አምሳል ገልጸዋል። በክልሉ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የሴቶች ንቅናቄና ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ስማቸው ዳኘው ችግሩ ቢቀንስም አሁንም መኖሩን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተለይ ምርመራውን ማለፍ ያልቻሉ ህጻናትን መደበኛ ሰርግ ደግሶ ከመዳር ይልቅ በማህበርና ሰንበቴ እያሳበቡ ህጻናትን መዳር እየተለመደ መምጣቱን ተናግረዋል። ከሌሎች የክልሉ አካባቢዎችበተለየ መልኩ ምስ/ጎጃም፣ደ/ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ እና በኦሮሚያ ክልል ችግሩ በብዛት የሚታይባቸው አካባቢዎች መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። ከክልሉ ፍትህ ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተውበአማራ ክልል በ2009 እና 2010 ዓ.ም 24,259 የጋብቻ ጥያቄዎች ቀርበዋል። ከነዚህ መካከል 17,667 አመልካቾች ብቻ ጋብቻ እንዲፈጽሙ ከፍትህ ጽ/ቤቶች ይሁንታ አግኝተዋል። በነዚሁ ሁለት አመታት ብቻ 5685 የሚሆኑት የጋብቻ ማመልከቻዎች ደግሞ በምክር እንዲቋረጡ ተደርጓል። ነገር ግን የጋብቻ ጥያቄያቸዉ ዉድቅ ከተደረገባቸዉ አመልካቾች መካከል 79 የሚሆኑት ህጉን በመተላለፍ ጋብቻ ፈጽመው ክስ ተመስርቶባቸዉ በፍርድ ሂደት ላይ ይገኛል።
41071651
https://www.bbc.com/amharic/41071651
ከግብር የሚሰወረው የዓለም ሃብት የት ነው?
የግብር ወይም ታክስ ኩባንያዎች የገንዘብን ፍሰትን በተለመለከተ ዋነኛ ስራቸው ነገሮችን ማጠላለፍ እና በተቻለ መጠን እውነታው እንዳይታወቅ ማድረግ ነው።
ጭንቅላታችንን እስኪያመን ድረስ ጥልፍልፍ ሂሳብ ውስጥ የሚከቱን የሂሳብ ቀማሪ ኩባንያዎች ጉግል፥ ኢቤይ እና አይኪያ የመሳሰሉ በጣም ሀብታም ድርጅቶች እጅግ አነስተኛ ግብር በህጋዊ መንገድ እንዲከፍሉ ያደርጋሉ። ሰዎች ለምን ስለ ግብር ሲወራ እንደሚናደዱ ወይም ደስተኛ እንደማይሆኑ ግልፅ ነው። ግብር ልክ ለአንድ ማህበር እንደሚከፈል ክፍያ ነው። ክፍያውን አለመክፈል ብንፈለግም ማህበሩ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለመጠቀም ሲባል መክፈል ግድ ነው። የጦር ሀይል፥ ፖሊስ፥ መንገድ፥ ትምህርት እና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች ለማግኘት ሲባል። የግብር ማስወገድ እና ግብር ወረራ የግብር ኩባንያዎች ለእነዚህ ሁለት አበይት ጉዳዮች ማለትም ግብር ማስወገድ እና ግብር ወረራ እጀጉን ይወቀሳሉ። ግብር ማስወገድ ህጋዊ ሲሆን ግብር ወረራ ግን ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ ከመንግስት እና ከሕዝብ ገንዘብ መሰወር እንደማለት ነው። ምስጢራዊ ባንክ እ.አ.አ. በ1920ዎቹ በስዊዘርላንድ እንደተጀመረ ይነገራል። በአንድ በኩል አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ሀገራት በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የነበረባቸውን ዕዳ ለመክፈል በማሰብ ግብር ያጭበረብሩ የነበረ ሲሆን በሌላ በኩል ሀብታም አውሮፓውያን ያላቸውን ገንዘብ ለመደበቂያ መንገድ ይጠቀሙበት ነበር። ምስጢራዊ ባንክ የሚለው ኃሳብ ብዙ ደንበኛ እንዳፈራላቸው የተረዱት ስዊዞች እ.አ.አ. በ1934 ዓ.ም. ያለባለቤቱ ፍቃድ የባንክ ሂሳብ ይፋ ማድረግ ወንጀል እንዲሆን ደነገጉ። ቀስ በቀስ የግብር ኩባንያዎች እንደ ማልታ እና ካሬቢያን ባሉ ደሴቶች ላይ ግዛታቸውን ማስፋፋት ጀመሩ። ይሀንን የሚያደርጉበት ምክንያት መሰል ትናንሽ ደሴቶች ለግብርናም ሆነ የተለያዩ ዕቃዎችን ለማምረት ምቹ ስላልሆኑ የባንኩ ዘርፍ በጣም የተሻለ አማራጭ ሆኖ በመገኘቱ ነው። ልዩነቱ ሲሰፋ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጋብርኤል ዙክማን በባህር ዳርቻዎች ወይም በደሴቶች ላይ ምን ያህል ገንዘብ ተሰውሮ እንዳለ የሚመረምር መላ መታ። በህጉ መሰረት ዓለም ላይ ትላልቅ የገንዘብ ተቋማት ይፋ ከሚያደርጉት መረጃ በመነሳት ተቀማጭ እና ተንቀሳቃሹ ቢሰላ የመጨረሻው ሂሳብ የተጣጣ መሆን አለበት። ማለትም ወጭና ገቢ ሂሳብ ተጣርቶ ትርፉ እና ኪሳራው መለየት አለበት። ነገር ግን የተደረገው ጥናት ያሳየው ነገር ቢኖር እያንዳንዱ ግለሰብ ከትርፍ ይልቅ በስምንት በመቶ የበዛ ኪሳራ በሂሳብ መዝገቡ ላይ መመዝገቡን ነው። ዙክማን ጥናቱን ሲጨርስ ስምንት በመቶ ያህል የዓለም ሃብት የት እንደገባ እንደማይታወቅ ወይንም የግብር ወረራ ሰለባ መሆኑን ተረዳ። ከዛም አልፎ ችግሩ አዳጊ ተብለው በሚጠሩ ሀገራት ላይ የበለጠ ጎልቶ እንደሚታይ ተገነዘበ። ከአፍሪቃ ሰላሳ በመቶ የሚሆነው ሃብት 'በባህር ዳርቻ' የተደበቀ ነው። በግብር ስብሰባ ወቅት በአንድ ዓመት ብቻ ወደ አስራ አራት ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ ተሰልቧል። የግብር ወረራ ከምናስበው በላይ በጣም ጥልፍልፍ ኃሳብ ነው። እስቲ እርስዎ ቤልጂየም ውስጥ የዳቦ ፋብሪካ እንዳሎት እናስብ፥ የወትተ ተዋፅኦ ምርቶች ፋብሪካ ደግሞ በዴንማርክ እንዲሁም የሳንድዊች ሱቅ በስሎቬንያ። ከእያንዳንዱ ሳንድዊች ሽያጭ ላይ አንድ ዩሮ ያተርፋሉ። እናም ከዛ ከሚያተርፉት ትርፍ ምን ያህሉ በስሎቬንያ ግብር ይከፍላሉ? ምን ያህሉስ ቺዝ በሚያመርቱበት ዴንማርክ? ምን ያህሉስ ዳቦ በሚያመርቱበት ቤልጂም? እርግጥ የሆነ ምላሽ የለም። የሂሳብ ማታለያ መንገዶች በዚህ ዘርፍ እንደ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ የሚቆጠረው 'አፖክሪፋል' እየተባለ የሚጠራው ምሳሌ ነው። በትሪኒዳድ የሚገኝ አንደ ኩባንያ እስክርቢቶ አምርቶ በሌላ ሀገር ለሚገኝ እህት ኩባንያው አንዱን አስክርቢቶ በ8500 ዶላር ዋጋ ይሸጣል። ይህም ዝቅ ያለ ግብር በምታስገብረው ትሪኒዳድ ትርፍ እንዲያስመዘግብ በሌሎች ላቅ ያለ የግብር ምጣኔ ባላቸው ሀገራት ደግሞ ዝቅ ያለ ትርፍ እንዲያመጣ አደረገው። እኒህን የመሳሰሉ ማታለያ መንገዶች በጣም የሚታወቁ ሲሆኑ ምን ያህል ገንዘብ እንደተጭበረበረ ለማወቅም እጀግ አዳጋች ናቸው። ዙክማን እንደሚያምነው ከሆነ በአሜሪካ ግብር ከፋዮች እስከ 130 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ በየዓመቱ ይታለላሉ። ከዛም አልፎ በእርዳታ መልክ ወደ አዳጊ ሀገራት የሚሄደው ገንዘብ የትየለሌ ነው። ለነዚህ የሂሳብ ማታለያ መንገዶች መፍትሄ ማበጀቱ ከባድ ባይሆንም ፖለቲካዊ ቀርጠኝነት ወሳኝ ነው ይላል ዙክማን። መቼም የዓለም መሪዎች ይህ ጠፍቷቸው አይደለም ነገር ግን በዚህ ቀዳዳ የሚጠቀሙ ሰዎች ይህንን ለማድረግ ፈቃደኝነታቸው እጅግ ዝቅ ያለ ነው። በጣም አነስ ያሉ ደሴቶች ምጣኔ ሀብታቸውን ለማሳደግ ሲባል በሂሳብ እና የባንክ አገልግሎት ሕጋቸው ላይ ላላ ይላሉ። ነገር ግን ከዛም የላቀው አደጋ የግብር ኩባንያዎች የዓለማችንን ሃብታሞች፥ ፖለቲከኞች እንዲሁም ለአዳጊ ሀገራት እርዳታ የሚሰጡ ዲታዎችን ለመደገፍ ሲሉ የግብር ስርዓቱን እንዳሻቸው ያሾሩታል።
news-52000940
https://www.bbc.com/amharic/news-52000940
ኮሮናቫይረስ፡ ኡጋንዳ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዙትን እያደነች ነውው
ባለፈው ቅዳሜ አንድ ግለሰብ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጉዞ ኡጋንዳ ከደረሰ በኋላ የኮሮናቫይረስ ተጠቂ መሆኑ መረጋገጡን ተከትሎ የኡጋንዳ ባለስልጣናት ከግለሰቡ ጋር ንክኪ ነበራቸው ያሏቸውን 84 ሰዎች በማደን ላይ ናቸው።
ኢንቴቤ አውሮፕላን ማረፊያ ከግለሰቡ ጋር አብረው የነበሩት ተጓዦች እንዲመረመሩ ከያሉበት እየተጠሩ ነው። ምንም እንኳ ባለፈው ቅዳሜ የኡጋንዳ ጤና ሚንስትር ሁሉም ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ናቸው ብለው ነበር። ይሁን እንጂ ሁሉም ተጓዦች ወደየመዳረሻው እንዲሄዱና በእራሳቸው ፍቃድ እራሳቸውን ለይተው እንዲያቆዩ ነበር የተነገራቸው። ቢቢሲ ከባለስልጣናት ባገኘው ምለሽ መሰረት በጤና ሚንስቴር በኩል የተሰጠው መግለጫ ሁሉም በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዙ መንገደኞች በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሆኑ በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል። አሁን እነዚያን ተጓዦች ለማግኘት ባለስልጣናት ጥረት እያደረጉ ነው። ይህ በእንዲህ አንዳለ በኡጋንዳ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ሕዝባዊ ስብሰባ ተከልክሏል። ከክልከላው በኋላ ሕዝብን ሰብስበዋል የተባሉ ሁለት ቀሳውስት ታስረዋል። በመዲናዋ ካምፓላ ከታሰሩት አንዱ የሆኑት የካቶሊክ ቄስ ለምዕመኔ የሚተላለፍ ስብከት ለመቅረጽ ከቀረጻ ሙያተኞች ጋር ነው የነበርኩት፤ ሰው አልሰበሰብኩም ቢሉም የአካባቢው የአይን እማኞች ግን በርካታ ሰው ሰብስበው እንደነበር መስክረውባቸዋል። ኡጋንዳ የመጀመሪያውን የኮሮናቫይረስ ታማሚ ያገኘችው ቅዳሜ ዕለት ነበር። ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ታንዛንያና ናይጄሪያን ጨምሮ ብዛት ያላቸው የአፍሪካ አገራት የቫይረሱ ታማሚ ዜጎቻቸው ቁጥር እየጨመረ ነው።
news-55255842
https://www.bbc.com/amharic/news-55255842
ፈረንሳይ እስላማዊ ጽንፈኝነትን ለመግታት አዲስ ሕግ አረቀቀች
የፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ካቢኔ በፈረንሳይ ጽንፈኛ እስላማዊነትን ይገታል ያሉትን አዲስ ሕግ አረቀቁ።
የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በቅርቡ ፈረንሳይ በጽንፈኞች ተደጋጋሚ ጥቃትን ስታስተናግድ ቆይታለች። ረቂቅ ሕጉ ሰዎች በሃይማኖት ጉዳይ የተሰማቸውን እንዲገልጹ የሚፈቅድ ከመሆኑም በላይ ታዳጊዎችን በቤት ማስተማር ላይ ጥብቅ ክልከላዎችን ይጥላል ተብሏል። የፈረንሳይ መንግሥት ሃይማኖትን ለማጥቃት ያወጣው ሕግ ነው በማለት በርካቶች ረቂቅ ሕጉን ተችተዋል። የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንሰትር ጄን ካስቴክ ግን ሕጉ ሙስሊሞችን ከጽንፈኞች ነጻ የሚያደርግ ሕግ ነው ብለዋል። "የሪፐብሊካን መርሆችን" ይደግፋል የተባለው ረቂቅ ሕግ፤ በኢንተርኔት የሚፈጸሙ የጥላቻ ንግግሮች በጥብቅ እንዲመረመሩ ያዛል እንዲሁም በኢንተርኔት አማካይነት የሰዎችን ግላዊ መረጃ ማጋለጥን ይከለክላል። ከሳምንታት በፊት የነብዩ መሐመድን የካርቱን ምስል ለተማሪዎቹ ማሳየቱን ተከትሎ የተገደለው ሳሙኤል ፓቲ፤ በኢንተርኔት አማካኝነት ዘመቻ ተፍቶበት ነበር ተብሏል። ረቂቅ ሕጉ በኢንተርኔት አማካይነት የሰዎችን ግላዊ መረጃ ማጋለጥ የከለከለው ለዚሁ ምላሽ እንዲሆን ነው ተብሏል። ሕጉ "ሚስጥራዊ" በሆነ መልኩ እስላማዊ አስተምሮ የሚሰጡ ትምህርት ቤቶችን ያግዳል። ይህም ብቻ አይደለም ከአንድ ሰው በላይ ጋር ትዳር መመስረት ሕጉ አይፈቅድም። ከአንድ ሰው በላይ የትዳር አጋር ላላቸው አመልካቾች ፈረንሳይ የመኖሪያ ፍቃድ እንደማትሰጥ በረቂቅ ሕጉ ተጠቅሷል። በሴቶች ላይ የድንግልና ምርመራ የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች ቅጣት ይጣልባቸዋል። ከፍ ሲልም የሥራ ፍቃዳቸውን ሊነጠቁ ይችላሉ ተብሏል። ሙስሊም ማህበራት የፋይናንስ ምንጫቸው እና ወጪያቸው ግልጽነት የተሞላበት እንዲሆን ግዴታ ጥሏል ሕጉ። ፈረንሳይ ይህን መሰል ሕግ ለማውጣት ስታጤነው የቆየችው ጉዳይ ቢሆንም በቅርቡ በፈረንሳይ የደረሱ ጥቃቶች ሕጉ በፍጥነት እንዲወጣ አስገድደዋል። በቅርቡ በፓሪስ እና በመዲናዋ አቅራቢያ በጽንፈኛ ሙስሊሞች የተፈጸሙት ጥቃቶች የአገሪቱን ዜጎች አስቆጥተዋል። ፈረንሳይ ወደ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች የሚኖሩባት አገር ናት።
news-51615017
https://www.bbc.com/amharic/news-51615017
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሶማሊያዊያንን ለማቀራረብ የሚያደርጉት ጥረት እንቅፋት ገጥሞታል
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በሶማሊያው ፕሬዝዳናንትና እራሷን ነጻ አገር አድርጋ ካወጀችው ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት መካከል መቀራረብን ለመፍጠር እያደረጉት ያለው ጥረት እንቅፋት እንደገጠመው ኢስት አፍሪካን የተባለው ጋዜጣ ዘገበ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር ሆነው የሶማሊላንድ ዋና ከተማ የሆችውን ሐርጌሳን ለመጎብኘት የነበራቸው ዕቅድ ተቃውሞ ገጥሞታል። ጋዜጣው እንደዘገበው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የቀረበው የጉብኝት ሃሳብ በሶማሊያና በሶማሌላንድ አስተዳዳሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ዓላማ ያደረገ ነው። በሶማሊያ ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰና ማዕከላዊው መንግሥት ከወደቀ በኋላ ሶማሌላንድ በሌሎች አገራት ወይም ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ይፋዊ እውቅና ባታገኝም የእራሷን ነጻ መንግሥትነት በማወጅ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ መንግሥትን አቋቁማ ትገኛለች። በዚህ ወር መጀመሪያ አዲስ አበባ ውስጥ የተካሄደውን የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ሞሐመድ "ፋርማጆ" እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲን በጽህፈት ቤታቸው ጋብዘው አገናኝተዋቸዋል። በዚህ ጊዜም የሶማሊያው ፕሬዝዳንት እንደ አውሮፓዊያኑ በ1980ዎቹ ሶማሌላንድ ውስጥ ስለተፈጸመው ጭፍጨፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። የሶማሌላንዱ ፕሬዝዳንትም የቀረበውን የይቅርታ ጥያቄ የተቀበሉት ቢሆንም፤ ለአገራቸው የምክር ቤት አባላት እንደተናገሩት ግን የፋራማጆ ጉብኝት ጥያቄ "ግራ አጋቢ ነው" ብለዋል። የሶማሌላንድ ምክትል ሚኒስትር ሊባን ዩሱፍ ኦስማን በዚህ ጉዳይ ላይ ሰጡ በተባለው ምላሽ ላይም ጉብኝቱ የማይሆን ነገር እንደሆነ አመልክተዋል። "ፋራማጆ በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ የሚያደርጉት ጉብኝት ፈጽሞ የማይሆን ህልም ከመሆኑ በተጨማሪ የማይሳካ ዕቅድ ነው" ብለዋል ሚኒስትሩ።
news-48363232
https://www.bbc.com/amharic/news-48363232
በጉጂ አስር ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
በደቡብ ኦሮሚያ ጉጂ ዞን ግንቦት 12/2011 ዓ. ም. አስር ሰዎች በአንድ ቦታ መገደላቸው ተገለጸ። ግድያው ጎሮ ዶላ ወረዳ ውስጥ እንደተፈጸመ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ኦልኮዮ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ታጣቂዎች ተደብቀው የሽምቅ ውጊያ ሲያደርጉ እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን፤ አንድ የመከላከያ ኃይል አባል መግደላቸውንም አቶ ዮሃንስ አረጋግጠዋል። በዚህ ምክንያት የመከላከያ ኃይሉ ራሱን ለመከላከል በወሰደው እርምጃ 10 ታጣቂዎች ስለመገደላቸው ከአካባቢው መረጃ እንደደረሳቸው ኃላፊው አክለዋል። • የስኳር ፋብሪካዎችን ለግል ባለሃብቶች የመስጠት ፋይዳና ፈተናዎቹ • ጋዜጠኞች ስለ ለውጡ ማግስት ሚዲያ ምን ይላሉ? • የመስጠም አደጋ የተጋረጠባት ዋና ከተማ ልትቀየር ነው የታጣቂዎቹን ማንንት በተመለከተ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ዮሃንስ ሲመልሱ፤ '' ከሕዝቡ እንደሰማሁት ከሆነ የኦነግ ታጣቂዎች ናቸው'' ብለዋል። እነዚህ የኦነግ ታጣቂዎች የሲቪል ልብስ በመልበስ በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበረ ሲሆን፤ በአካባቢው ሰላም ለማስጠበቅ የተመደበው የመከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽመዋል ብለዋል። ኃላፊው እንዳሉት፤ ከሰሞኑ ሲወራ እንደነበረው የተገደሉት ሰላማዊ ዜጎች ሳይሆኑ እርምጃ የተወሰደባቸው ታጣቂዎቹ ናቸው። አክለውም መከላከያ በቂም በቀል ሕዝቡ ላይ ተኩስ ከፍቶ ሕይወት አጥፍቷል የሚባለው ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል። በተኩስ ልውውጡ መሃል ሕይወቱ ያለፈ ሰላማዊ ዜጋ ሊኖር እንደሚችችል ግን አልሸሸጉም። እሱም ማጣራት ያስፈልገዋል ብለዋል።
news-56372134
https://www.bbc.com/amharic/news-56372134
ከስልጣን በኃይል የተወገዱት የሚየንማር አመራሮች 'አብዮት' ለማስነሳት ቃል ገቡ
ከስልጣናቸው በኃይል የተወገዱት የሚየንማር አመራሮች በወታደራዊው አመራር ላይ አብዮት ለማስነሳት ከሰሞኑ ቃል ገብተዋል።
እነዚህ አመራሮች ተደብቀው ነው የሚገኙት ተብሏል። በአገሪቱ ላይ መፈንቅለ መንግሥት መነሳቱን ተከትሎ በዝምታ ላይ የነበሩት የቀድሞ የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ማህን ዊን ክሃይንግ ታን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ የሆነ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። "በአገራችን ታሪክ ውስጥ እንዲህ አይነት የጨለመ ወቅት አጋጥሞን አያውቅም። በቅርቡ ግን መንጋቱ አይቀርም" ብለዋል። ማህን መልዕክታቸውን ያስተላለፉት በፌስቡክ ሲሆን "ሁሉንም ብሄሮች ያካተተ ፌደራላዊ ዲሞክራሲ ለመመስረትና ለዘመናትም ያህል በአምባገነንነት የጨቆነን ስርዓት ለመገርሰስ ወቅቱ አሁን ነው። ሁላችንም ተባብረን አብዮት ልናስነሳ ይገባል" ብለዋል። አክለውም "ምንም እንኳን ልዩነቶች ቢኖሩንም እነሱን አቻችለን፤ ይህንን አምባገነናዊ ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቃ ልንለው ይገባል። አብዮት እናስነሳለን" በማለት ተናግረዋል። የቀድሞው ሚኒስትር ከተደበቁበት ሆነው ስልጣን በኃይል የጨበጠውን ወታደራዊ አገዛዝ የተቃወሙ የፓርላማ አባላት ቡድንን ይመራሉ። መፈንቅለ መንግሥት ከተነሳ ጀምሮ በተቃውሞ እየተናጠች ባለችው ሚየንማር በትናንትናውም ዕለት 12 ሰዎች ተገድለውባታል። በቀድሞ ስሟ በርማ ተብላ የምትጠራው ሚየንማር ከወር በፊት በተነሳ መፈንቅለ መንግሥት የሲቪል አመራር የነበሩትን አንግ ሳን ሱ ቺን ከስልጣን ከማስወገድ በተጨማሪ ለእስር ዳርጓቸዋል። አንግ ሳን ሱ ቺ ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ (ኤንኤልዲ) የተባለው የገዢው ፓርቲ መሪ ናቸው። ሚየንማር ባደረገችው ምርጫ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ኤንኤልዲ ስልጣን መቆጣጠር ቢችልም ወታደራዊው አገዛዝ ምርጫው ተጭበርብሯል ይላል። ወታደራዊው አገዛዝ የተወሰኑ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ቢያውልም ማምለጥ የቻሉ የፓርላማ አባላት አዲስ የአመራር ቡድን አቋቁመዋል። የዚህ ቡድን መሪ ማህን ዊን ክሃይግ ታህን ሲሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃም የሚየንማር ትክክለኛ መንግሥት ነን በማለት እውቅና ለማግኘት እየጣሩ ነው።
news-54456860
https://www.bbc.com/amharic/news-54456860
የአንበጣ መንጋ ፡ በአማራ ክልል የአርሶ አደሮችን ልፋት መና እያስቀረ ያለው አንበጣ መንጋ
አቶ ይማም መሐመድ በራያ ቆቦ ወረዳ የ024 ያያ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው።
በአካባቢው ጤፍ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ አተርና ሽንብራ የሚመረት መሆኑን ጠቅሰው አብዛኛው ማሳ የተሸፈነው በማሽላ እንደሆነ ይናገራሉ። ቀደም ሲል በአፋር ክልል የአንበጣ መንጋ መከሰቱን እንደሰሙ እና ወደ አካባቢያቸው ሳይመጣ ለመከላከል እንዳልተቻለ ጠቁመዋል። መስከረም 6 ጀምሮ ወደ አካባቢው መግባት የጀመረው የበረሃ አንበጣ መንጋን ለመከላከል ጥረት ቢያደርጉም መከላከል አልቻልንም ብለዋል። "አንዱን ንዑስ ቀበሌ ሲያጠናቅቅ [እኛም] እያፈገፈግን ስንከላከል አሸነፈን። አሁን ሙሉ በሙሉ [ሰብሉን] አጠናቀቀ" ሲሉ የለፉበት ሰብል መውደሙን ይናገራሉ። ''[አሁን] ዝም ብለን ቆመን እያየን ነው። ተዓምር ነገር ነው የምናየው።" "ከመስከረም 6 እስከ አሁን አርሶ አደሩ ቤቱ ሳይገባ ታገለ። ምንም ማድረግ አልተቻለም. . . የሚበላብንን ነገር ጨርሷል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ተስፋ የለንም" ብለዋል። በቀበሌው ያለውን ሰብል ሙሉ ለሙሉ ከመጨረስ ባለፈ ወደ አጎራባች ቀበሌዎች እየገባ መሆኑንም ለቢቢሲ ተናግረዋል። የዘንድሮ አዝመራ 'ጥሩ እና ቆንጆ' የሚባል እንደነበር የሚናገሩት አቶ ይማም፤ ሆኖም የአንበጣው መንጋ እንዳወደመውና መንግሥት ኬሚካል አቅርቦ፣ አርሶ አደሩ ደግሞ ጅራፍ እና ቆርቆሮ በመጠቀም በዘመናዊ እና ባህላዊ መንገድ ለመከላከል የተደረገው ጥረት አልተሳካም ብለዋል። እህል ከኅዳር አጋማሽ ጀምሮ ነበር መሰብሰብ የነበረበት ያሉት አርሶ አደሩ ለመሰብሰብ ያልደረሰ በመሆኑ በአንበጣ መንጋው መበላጡን ጠቁመዋል። የአንበጣ መንጋው ባደረሰው ጉዳት ግራ የተጋቡት አርሶ አደሩ ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ ይናገራሉ። "ዝም ብለን ቁጭ ብለናል። ከባድ ነው በጣም። ዝናብ ከጣለ ለበልግ እናርሳለን ብለን ቁጭ ብለናል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። አርሶ አደር ሙስጠፋ አሸብርም የራያ ቆቦ ነዋሪ ናቸው። ከመስከረም መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ አንበጣውን በኬሚካልም ሆነ በባህላዊ መንገድ ለመከላከል ባለመቻላቸው አካባቢውን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮታል ብለዋል። "ቀደም ብሎ ሁለት ቀበሌዎች ገባ። ቀዳሚዎቹ ንዑስ ቀበሌ 2 እና 3 ናቸው። አዚያ አሁን ሰብሉ አልቋል። አሁን ወደ ንዑስ ቀበሌ አንድ አቀንቷል። አዚያ አዳርሶ ወደ ቀበሌ 023 ሊገባ ነው" ሲሉ አስረድተዋል። "ጥይት ቢተኮስ፣ እሪ ቢባል እና መርዝ ቢረጭ አንዴ ከገባ አይነሳም" ሲሉ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል እንደተቸገሩ ይናገራሉ። አንበጣው ባለባቸው አካባቢዎች ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱንም ጠቀሙዋል። "ተስፋችን ምናልባት የበልግ ዝናብ ከጣለ በልግ እንዘራለን ነው እንጂ ምን ተስፋ አለን?" ሲሉ ማሳ ላይ የነበረው ሰብል መውደሙን አመልክተዋል። መንግሥት ዝናብ አግኝተው ለበልግ እስኪዘሩ ድረስ ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ የአንበጣው መንጋ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ጉዳት ማድረሱን አረጋግጠዋል። ጉዳቱ በምሥራቅ አማራ ሦስት ዞኖች መከሰቱን ጠቁመው መጠኑ ግን በባለሙያዎች ተጠንቶ ይፋ ይደረጋል ብለዋል። የአንበጣ መንጋው በደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች መከሰቱን ገልጸው፤ በተጨማሪም ጉዳቱ የከፋ ባይሆንም በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ በቅርቡ የአንበጣ መንጋው መከሰቱንም ያብራራሉ። በእነዚህ አካባቢዎች ከ151 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ አሰሳ ተደርጎ በ78 ሺህ 800 ሄክታር ላይ የአንበጣ መንጋው መከሰቱ መረጋገጡን ምክትል ቢሮ ኃላፊው ገልፀዋል። የአንበጣ መንጋውን ለመከላከልም በሰው ኃይል እና በአውሮፕላን በመታገዝ ቢያንስ ከ51 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነውን መሬት ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። ነገር ግን አሁን አንበጣው መብረር ስለጀመረ ከእስካሁኑ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ይገመታል ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። እንድ ምክትል ኃላፊው ከሆነ ችግሩን ለመቅረፍ ኅብረተሰቡን በማሳተፍ እና በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት በማካሄድ እየተሠራ ነው። በአንዳንድ ቦታዎች ያለውን የአንበጣ መንጋ በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ካልሆነ መቆጣጠር የማይቻል ነው ሲሉ የችግሩን ጥልቀት ያስረዳሉ። የመከላከል ሥራው ካልተጠናከረ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በንፋስ ኃይል እየተገፋ ሊሠፋ ይችላል ያሉት አቶ ተስፋሁን ለዚህም እየተሠራ ነው ነው ብለዋል። ከወራት በፊት ጀምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመከሰት በእጸዋት ላይ ጉዳት እያደረሰ ያለው የአንበጣ መንጋ፤ በአሁኑ ጊዜ በሰሜና፣ በሰሜን ምሥራቅና በመካከለኛው የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። በአንበጣ መንጋው ሳቢያ በሰብል ላይ በደረሰ ጉዳት በብዙ ቦታዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ለችግር ሊጋለጡ እንደሚችሉ እየተነገረ ነው።
news-43383040
https://www.bbc.com/amharic/news-43383040
ካለሁበት 24፡ ሃገርና ወገን ውበት ነው
ስሜ ኦብሴ ሉቦ ይባላል። በካሊፎረንያ ክፍለ ግዛት በብሬያ ከተማ ከባለቤቴና ከአንድ ልጄ ጋር ነው የምኖረው።
ወደ አሜሪካ የመጣሁት ከአስራ ስምንት ዓመት በፊት ሲሆን፤ አቋርጬ የመጣሁትን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እዚህ በመቀጠልና ከፍተኛ ዉጤት በማምጣቴ ሙሉ ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝቼ የጤና ባለሙያ መሆን ችያለሁ። ትምህርቴንም እንዳጠናቀቅኩኝ ከሚኒሶታ ወደ ካሊፎርኒያ ጥሩ ሥራ አግኝቼ ሄድኩ። እስከ አውሮፓውያኑ 2009 (እ.አ.አ) እዚህ ሥራ ላይ ከቆየሁ በኋላ በዚህ ሃገርና በሃገራችን መካከል ያለውን የጤና አገልግሎት ልዩነት እያሰብኩ እንዴት ወደ ሃገሬ ተመልሼ የአቅሜን ማበርከት እንደምችል ማውጠንጠን ጀመርኩኝ። በተለይም እዚህ ሃገር የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱና በአዳዲስ የተተኩትን የህክምና መሣሪያዎች ወደ ሃገር ቤት ቢሄዱ ምን ያህል አገልግሎት ሊሰጡ እንደሚችሉ ብዙ ጊዜ አስባለሁ። ከዚያም የነፃ አገልግሎት ለመስጠት ወደ ተወለድኩበት ምዕራብ ወለጋ አካባቢ ወደ ነጆ ሆስፒታል ሄድኩኝ። በአጭር ጊዜ ቆይታ በሕፃናት፣ በሴቶችና በአዋቂዎች ጤና አገልግሎት መጓደል የተነሳ የሚደርሰውን ስቃይና ሞትን በማየቴ በእጅጉ አዘንኩኝ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በዙሪያዬ ያሉትን የተለያዩ ሰዎች በማስተባበር በገንዘብ፣ በቁሳቁስና በልዩ ልዩ የሕክምና ሙያቸው ማገልገል የሚችሉትንም ጭምር በመጋበዝ ወደ ሃገር ቤት ይዤ ሄጄ የቻልኩትን መሥራት ጀመርኩኝ። ከተሠሩት ሥራዎች መካከል በልብ ሕመም የሚሰቃዩ ሕፃናትን በማከም እንዲሁም በሃገር ውስጥ ሊታከሙ የማይችሉትን ደግሞ ወደ ዉጪ ሃገር ወስዶ ማሳከም ጭምር ይገኝበታል። በተጨማሪም ደግሞ በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት ለማየት የተቸገሩ ሰዎች የቀዶ ሕክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ያስቻሉ የተለያዩ ዘመቻዎችን አድርገናል። አሜሪካንን ልዩ የሚያደርጋት ትልቁ ነገር ነፃነትና ለሰብዓዊ መብት ያለው ክብር ነው። በተለይም የመናገር ነፃነት በመኖሩ ማንኛውም ሰው እራሱን ሲገልጽ የሚነካውም ሆነ የሚያሰጋው ምንም ነገር የለም። ይህን ነፃነት ደግሞ በጣም እወደዋለሁ። በዚህ ሃገር ከሚገኙ ምግቦች ከባሕር የሚወጡ የዓሣ ዓይነቶችን በጣም እወዳለሁ። የሃገሬ ሰውንም ሆነ ምድሯ እንዲሁም ብዙ ነገሮች በጣም ይናፍቁኛል። በተለይም እናትና አባቴን ከሁሉ በላይ ይናፍቁኛል። ሃገርና ወገን ውበት ነው። የአንድ ሃገር ሃብት እነዚህ ናቸው። ስለዚህም የሰዉና የእንስሳው ጤንነት መጠበቅ አለበት። ለመሬቱም ደህንነትና እንክብካቤ መደረግ አለበት ብዬ አምናለሁ። በምኖርባት የብሬያ ከተማ አካባቢ ብዙ የሚያማምሩ የባሕር ዳርቻዎችና የመናፈሻ ሥፍራዎች አሉ። እኔ የምኖርበት አካባቢ ያለው ስቲንሰን ቢች የሚባለው ሲሆን አንዳንዴ ለመቆዘምም ሆነ ለመዝናናት እሄዳለሁ። ሁሌም 'ጎልደን ጌት' የተሰኘውን ድልድይ እወደዋለሁም እደነቅበታለሁም። ይህ ድልድይ በጣም ትልቅ ሲሆን በጣም ታዋቂም ነው። የዚህ ሃገርም ሆነ ከሌላ ሃገር የሚመጡ ሰዎች የሚጎበኙት ነው። ባለፍኩ ባገደምኩ ቁጥር አሠራሩን፣ ትልቅነቱን፣ የፈጀውን የሰው ኃይል ጨምሮ ሳስብ እግዚያብሔር ለሰው የሰጠውን ጥበብን ስለሚያሳየኝ እደነቃለሁ። እዚህ ከመጣሁ አንስቶ ካጋጠሙኝ ነገሮች ከሁሉም በላይ የሚያስደስተኝ ትምህርቴን ጥራት ባለው መልኩ በመጨረሴና በተማርኩትና ባካበትኩት ልምድ ደግሞ ሃገሬን መርዳት መቻሌ ነው። እንዲሁም ከተለያዩ ሃገራት ከተወጣጡ ሰዎችም ጋር በመተዋወቄ በሃገር ቤት የምሠራቸው ሥራዎችም ላይ ማሳተፍ በመቻሌ በጣም እደሰታለሁ። ከምመኛቸው ነገሮች መካከል ደግሞ ለየት ያለ ኃይል ወይንም ሥልጣን ቢኖረኝ፤ የጤና ዘርፍ መርሃ ግብር መቀየር እፈልጋለሁ። እዚህም እንደኛው ሃገር ችግር አለ። በምኖርበት ከተማ ብዙ ሰዎች የጤና ችግር እያለባቸው መታከም የማይችሉበት ሁኔታ አለ። ይህም የጤና አገልግሎቱ ወድ ከመሆኑ የተነሳ በሰዎቹ የኑሮ አቅም ላይ መሠረት ያደረገ ነው። ስለዚህ በማንኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች፤ ደሃም ሆነ ሃብታም፣ የመኖሪያ ፈቃድ ያለውም ሆነ የሌለው ሁሉ እኩል የሆነ የጤና አገልግሎት እንዲኖረው እመኛለሁ። በተለይም ለሕፃናት፣ ለሴቶችና ለአረጋዊያን ይህንን ማዳረስ ብችል ደስ ይለኛል። በምኖርበት በብሬያ አካባቢ ብዙ ደኖች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ የተለያዩ ዛፎች ይገኙባቸዋል። በተለይ ሃገሬን እንድናፍቅ ያደረገኝ አንድ ቀን ነጭ የባሕር ዛፍ ማየቴ ነበር። ወላጆቼ ልጅ እያለን ጉንፋን ሲይዘን ነጭ ባህር ዛፍ ያጥኑን ነበር። ባየሁት ቁጥር ደግሞ በሃሳብ ወደ ሃገሬ ይወስደኛል። በተለይ ከነጆ ወደ ጃርሶ ያለውን መንገድ ያስታውሰኛል። እዚህ ሃገር ስመጣ ቋንቋ በደንብ አለመቻሌና ቤተሰቤን መናፈቄ ቶሎ መልመድ እንዳልችል አድርጎኝ ነበር። እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ እንግሊዝኛን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንማራለን ነገር ግን መናገር ችግር ነው። ስለዚህ ለተወሰነ ጊዜ የቋንቋ እጥረት እንቅፋት ሆኖብኝ ነበር። ካለሁበት በቅፅበት ሃገሬ ወስዶ የሚጥለኝ ነገር ቢኖር እራሴን በተወለድኩበት ከተማ በቤተሰቦቼ ግቢ ውስጥ ማግኘት እፈልጋለሁ። ለጫሊ ነጋሳ እንደነገረችው የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ፦ ካለሁበት 25 ፡''የሰፈሬን አየር ድጋሚ ማጣጣም እፈልጋለሁ'' ካለሁበት 26 ፡ 'እዚህ አራስ፣ መታረስና ማረስ ብሎ ነገር አያውቁም'
news-52329161
https://www.bbc.com/amharic/news-52329161
ፌስቡክ ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዙ ሐሰተኛ መረጃዎችን ሊጠቁም ነው
ስለኮሮናቫይረስ ሐሰተኛ መረጃ ያነበቡ፣ የተመለከቱ እንዲሁም መረጃውን ለሌላ ሰው ያጋሩ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ሊላክላቸው መሆኑን ፌስቡክ አስታውቋል።
ፌስቡክ ኮሮናቫይረስን በተመለከተ በርካታ ሐሰተኛ መረጃዎች ይተላለፉበታል የዓለም ጤና ድርጅት ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ የተሳሳቱ መረጃዎችን "infodemic" የሚል መጠሪያ ሰጥቷቸዋል። ፌስቡክም የእነዚህን ሐሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን ለመግታት ሲል አዲሱን አሠራር ተግባራዊ እንደሚያደርግ ጠቁሟል። አንድ ገለልተኛ ጥናት እንደሚጠቁመው፤ ከወረርሽኙ ጋር የተያያዙ ሐሰተኛ መረጃዎች በዋናነት የሚሰራጩት በፌስቡክ ነው። በተለይ በስፓኒሽ ቋንቋ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ። ፌስቡክ በበኩሉ ጥናቱ ድርጅቱ አሁን የሚገኝበትን ደረጃ አያሳይም ይላል። መቀመጫውን ካሊፎርንያ ያደረገው ድርጅት፤ በሚቀጥሉት ሳምንታት ማስጠንቀቂያውን በዜና ገፆች ላይ ማስተላለፍ ይጀምራል። ማስጠንቀቂያው ተጠቃሚዎች ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ ወደ ዓለም የጤና ድርጅት ገፅ ይመራል። ሐሰተኛ መረጃን መለየት የፌስቡክ ቃል አቀባይ እንደሚሉት፤ ስለ ቫይረሱ ሐሰተኛ መረጃ ደርሷቸው፣ ከዚያም ትክክለኛ አለመሆኑን የደረሱበት ሰዎች መረጃውን ከፌስቡክ ውጪ ቢያገኙት እርስ በእርስ መረጃ የሚለዋወጡበት መንገድ ተዘርግቷል። ፌስቡክ አዲሱን አሠራር የዘረጋው ከሐሰተኛ መረጃ ጋር ተያይዞ በስድት ቋንቋዎች የተሠራ ጥናትን ተከትሎ ነው። ጥናቱን የሠራው ‘አቫዝ’ በተባለ የመብት ተሟጋች ቡድን ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ከወረርሽኙ ጋር ለተያያዙ ሐሰተኛ መረጃዎች እየተጋለጡ መሆኑን አጥኚዎች ይናገራሉ። አጥኚዎቹ ከደረሱባቸው ሐሰተኛ መረጃዎች መካከል፤ ኮሮናቫይረስ ጥቁሮችን አይዝም የሚለው እና ክሎሪን ዳይኢክሳይድ ቫይረሱን ይገድለዋል የሚሉት ይገኙበታል። እነዚህ የተሳሳቱ መረጃዎች በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ደርሰዋል። ‘አቫዝ’ የተባለው ቡድን በእንግሊዘኛ፣ በስፓኒሽ፣ በፖርቹጋልኛ፣ በአረብኛ እና በፈረንሳይኛ ከተሰራጩ 100 መረጃዎች ናሙና ወስዷል። እነዚህን ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ፈትሾም ቀጣዩን ውጤት አግኝቷል። 1. የፌስቡክ አጋር ድርጅቶች ወይም ሌላ አካል አንድ መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ለፌስቡክ ከጠቆመ በኋላ፤ ፌስቡክ ስለመረጃው ሐሰተኛን ማስጠንቀቂያ ለመጻፍ እስከ 22 ቀን ድረስ ሊወስድ ይችላል። 2. በእንግሊዘኛ ከተጻፉ ሐሰተኛ መረጃዎች 29 በመቶ የሚሆኑት፤ የተሳሳቱ ስለመሆናቸው የሚጠቁም ማስጠነቀቂያ አልነበራቸውም። 3. 70 በመቶ የሚሆኑት የስፓኒሽ ሐሰተኛ መረጃዎች፣ 68 በመቶ የሚሆኑት የጣልያንኛ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲሁም 50 በመቶ የሚሆኑት የፖርቹጋልኛ ሐሰተኛ መረጃዎች፤ የተሰሳቱ ስለመሆናቸው የሚጠቁም ማስጠንቀቂያ አልነበራቸውም። 4. በአረብኛ ከተጻፉት ሐሰተኛ መረጃዎች ማስጠንቀቂያ ያልነበራቻው 22 በመቶው ናቸው። ፌስቡክ እንደሚለው፤ በተለያየ ቋንቋ የሚሠሩ እውነተኛ መረጃን ከሐሰተኛው የሚለዩ ባለሙያዎች መቅጠሩን ገፍቶበታል። ከታማኝ ድርጅቶች ጋር በመጣመርና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በ50 ቋንቋዎች የሚሠሩ ባለሙያዎች መቅጠሩንም ድርጅቱ ያክላል። የ‘አቫዝ’ ንቅናቄ ዳይሬክተር ፋዲ ቁርዓን ግን “ስለ ወረርሽኙ ሐሰተኛ መረጃ በዋነኛነት የሚሰራጨው በፌስቡክ ነው” ይላሉ። ድርጅቱ ሐሰተኛ መረጃን ለተጠቃሚዎች ለመጠቆም መወሰኑን እንደ ትልቅ እርምጃ ያዩታል። “ፌስቡክ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለማጽዳት ሁነኛ ውሳኔ ላይ ደርሷል። ተጠቃሚዎችን የሐሰተኛ መረጃ ጥቆማ በመስጠትና ሕይወታቸውን ወደሚታደግ ትክክለኛ መረጃ በመጠቆም ግንባር ቀደቡ ማኅበራዊ ሚዲያ ይሆናል።” ስለኮሮናቫይረስ የሚወጡ ሐሰተኛ መረጃዎች በስፋት ይሰራጫሉ ሐሰተኛ መረጃን በመግታት ሕይወት ማዳን ከተሰራጩት ሐሰተኛ መረጃዎች አንዱ፤ ሰዎች ብዙ ውሃ በመጠጣት፣ በጨውና በዝንጅብል በመጉሞጥሞጥ ራሳቸውን ከቫይረሱ መከላከል ይችላሉ የሚለው ነው። ይህንን መረጃ ተጠቃሚዎች ከ 31 ሺህ ጊዜ በላይ ተጋርተውታል። አቫዝ ይህንን ሐሰተኛ መረጃ ለፌስቡክ ከጠቆመ በኋላ ድርጅቱ መረጃውን ከገፁ አውርዶታል። ሆኖም ግን አሁንም 2,600 የሚሆኑ የመረጃው ግልባጮች ድረ ገፅ ላይ ይገኛሉ። መረጃው ያለ ፌስቡክ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ወደ 100 ሺህ ጊዜ ተሰራጭቷል። የፌስቡክ መስራችና ዋና ኃላፊ ማርክ ዙከርበርግ፤ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ላይ ሁለት ቢሊዮን ተጠቃሚዎችን ወደ ትክክለኛ መረጃ መርተናል ሲል ድርጅቱን ተከላክሏል። 350 ሚሊዮን ሰዎች ስለ ቫይረሱ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት እንደተጠቀሙበትም ይናገራል። “አካላዊ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ሐሰተኛ መረጃን እናስቆማለን፤ ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ ከበሽታው አይከላከልም የሚሉና ሌሎችም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ከገፃችን አውርደናል” ሲልም ያስረዳል። ማርክ እንደሚለው፤ 95 በመቶ የሚሆኑት የፌስቡክ ተጠቃሚዎች፤ የሐሰተኛ መረጃ ጥቆማ ሲደርሳቸው፤ መረጃውን ከማንበብ ወይም ከመመልከት ይቆጠባሉ። በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያጠኑት ባለሙያ ኤምሊ ቴይለር፤ ፌስቡክ ጥሩ እርምጃ ወስዷል ይላሉ። በተለይም በቀደመው የአሜሪካ ምርጫ ወቅት ከተወሰደው እርምጃ ጋር እንዲህ ያነጻጽሩታል። “ጉልህ ለውጥ ያምጣ አያምጣ አናውቅም፤ ነገር ግን መሞከር አለበት። በምርጫ ወቅት የሚሰራጭ ሐሰተኛ መረጃ እና ከጤና ጋር የተያያዘ ሐሰተኛ መረጃ መካከል ልዩነት አለ። ጤና ነክ ሐሰተኛ መረጃ የሰዎችን ሕይወት ይቀጥፋል።”
news-53805866
https://www.bbc.com/amharic/news-53805866
የአሜሪካ ምርጫ፡ ጆ ባይደን ፕሬዝዳንት ከሆኑ የሚለወጡ 8 ጉዳዮች
ጆ ባይደን በ2020 ለፕሬዝዳንትነት እወዳደራለሁ ሲሉ ሁለት ነገር ለማሳካት እንደሆነ ተናግረው ነበር፡፡
አገሪቱን መልሶ ለመገንባት እና በትራምፕ የተነሳ የተበታተነውን "ብሔራዊ መንፈስ" ወደ አንድ ለማማጣት፡፡ ከዚህ ባሻገር የሚከተሉት 8 ነጥቦች ባይደን ከተመረጡ የሚቀየሩ ጉዳዮች ይሆናሉ፡፡ 1. ኮቪድ-19 ላይ ታላቅ ዘመቻ ይከፈታል በአሜሪካ ከኮሮናቫይረስ የባሰ ወቅታዊ ጠላት የለም፡፡ ባይደን ለሁሉም ዜጎች ነጻ ምርመራ በፍጥነት እንዲደረግ ያደርጋሉ፡፡ መቶ ሺህ ሰዎች ደግሞ ይቀጠራሉ፡፡ የእነዚህ 100ሺህ ሰዎች ሥራ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን እግር በእግር አድኖ ንክኪ ቀጠናቸውን መለየት ይሆናል፡፡ ‹መርምር-አድን› በሚለው ስልት የቫይረሱን ግስጋሴ ለማቆም ይሞከራል፡፡ በየግዛቱ 10 የምርመራ ማዕከላት ይከፈታሉ፡፡ ሁሉም የግዛት ገዢዎች ጭምብል ማድረግን ያስገድዳሉ፡፡ አሜሪካ በኅብረተሰብ ጤና ባለሙያዎቿ ሳይንሳዊ አካሄድ ቫይረሱን ድል ታደርጋለች ይላሉ፣ ባይደን፡፡ 2. በሰዓት ዜጎች የሚከፈላቸው ትንሹ ምንዳ ከፍ ይላል በኮሮና ምክንያት የተጎዱ ቢዝነሶች ዘለግ ባለ ጊዜ የሚመልሱት ብድር ይሰጣቸዋል፡፡ ለተቸገሩ ቤተሰቦች ወርሃዊ ክፍያ በቀጥታ ያገኛሉ፡፡ አሁን ከሚከፈለው በተጨማሪ 200 ዶላር ይሰጣል፡፡ የፌዴራል ትንሹ የሥራ ምንዳም በሰዓት ወደ 15 ዶላር ከፍ ይደረጋል፡፡ 3. የፍትሕ ሥርዓቱ ማሻሻያዎች ይደረጉበታል የጆርጅ ፍሎይድ በነጭ ፖሊስ መገደሉን ተከትሎ ጥቁሮች ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡ ጆ ባይደን ቁጣችሁ ይገባኛል ብለዋቸዋል፡፡ ጆ በአሜሪካ ዘረኝነት እንደተንሰራፋ ያምናሉ፡፡ ይህን ማሻሻል የሚቻለው ግን የፍትህ ሥርዓቱን በማዘመን፣ የኅብረተሰብ አቀፍ ልማቶችን በማካሄድ ነው፡፡ ስለዚህ ‹ቢዩልድ-ባክ› እየተባለ በሚጠራው መርሐግብራቸው ጥቁር ድሃ ማኅበረሰብን መደገፍ፣ የተገለሉ አሜሪካዊያንን እድል መስጠት፣ ሥራ እንዲፈጥሩ፣ ቢዝነስ እንዲኖራቸው ለማድረግ ያስባሉ፣ ባይደን፡፡ ለዚህ የሚሆን 30 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ አዘጋጃለሁ ብለዋል፡፡ የሞት ፍርድን ከማስቀረት ጀምሮ ፍርደኞችን ማንገላታት አስቆማለሁ፣ መብት አጎናጽፋቸዋለሁ፤ ፖሊስ የሚወስደውን ያልተመጣጠነ ኃይል ለማስቀረት ቃል እገባለሁ ብለዋል፣ ባይደን፡፡ 4. ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ትብብር መድረክ ይመለሳሉ ባይደን የአየር ንብረት ለውጥ ትልቁ የምድራችን ፈተና ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ትራምፕ ግን አሜሪካንን ለመጎተት ነው የአየር ንብረት ለውጥ ብሎ ነገር የለም፣ ‹‹ውሸት ነው›› ይላሉ፡፡ ዓለም ካልተባበረች ምድር ጭንቅ ውስጥ ትገባለች ብለው የሚያምኑት ጆ ባይደን በካይ ልቀትን ለመቀነስ እሰራለሁ ብለዋል፡፡ የፓሪስ ስምምነት አሜሪካ በ2025 የግሪንሀውስ ጋዝን በ28 ከመቶ እንድትቀንስ ይጠይቃል፡፡ የዚህ ስምምነት ፈራሚ የነበረችው አሜሪካ፣ በትራምፕ ውሳኔ ከስምምነቱ ወጥታለች፡፡ ባይደን እመለሳለሁ ብለዋል፡፡ለአረንጓዴና ታዳሽ ቴክኖሎጂዎች፣ ምርምሮችና ተያያዥ ሥራዎች 1.7 ትሪሊዮን ዶላር ለ10 ዓመት እመድባለሁ ይላሉ፣ ጆ፡፡ 5. ከኔቶና ከቻይና ጋር ግንኙነት ያሻሽላሉ ባይደን ቅድሚያ ለአገር ውስጥ ችግሮች እሰጣለሁ ቢሉም የውጭ ፖሊሲያቸው ምን እንደሚመስል ከመናገር አልተቆጠቡም፡፡ ከኔቶ ጋር በትራምፕ ምክንያት የሻከረውን ግንኙነት እጠግናለሁ ብለዋል፡፡ ከቻይናም ጋር ቢሆን የንግድ ጦርነት ውስጥ ከመግባትና የአንድ ወገን የታሪፍ ጭማሪ ከማድረግ ቻይና ችላ ከማትላቸው ከሌሎች አገሮች ጋር የጎንዮሽ ጥምረት በመፍጠር ቻይናን ወደ መስመር አስገባታለሁ ብለዋል፣ ጆ፡፡ እነዚህ ቻይና ችላ የማትላቸው አገራት እነማን እንደሆኑ ግን በስም አልጠቀሱም፡፡ 6. ኦባማኬር ይቀጥላል ባይደን ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሉ አለቃቸው ኦባማ ያስጀመሩት የጤና ኢንሹራንስ መድን መርሀግብር እንዲቀጥል ይፈልጋሉ፡፡ በዚህ የኢንሹራንስ ማዕቀፍ 97 ከመቶ አሜሪካዊያን ይታቀፋሉ ተብሎ ነበር የሚጠበቀው፡፡ ከኦባማኬር በተጨማሪ ሌሎች የጤና መድኅኖችን ለማካተትም ባይደን ይፈልጋሉ፡፡ 7. የትራምፕን ፖሊሶዎች ይከልሳሉ በመጀመርያዎቹ መቶ ቀናት እፈጽመዋለሁ ካሏቸው ነገሮች አንዱ ትረምፕ በሜክሲኮና በአሜሪካ ድንበር ጥገኝነት ጠየቂ ቤተሰቦችን የሚነጣጥለውን ፖሊሲ ቀዳድጄ እጥለዋለሁ ብለዋል፡፡ ይህ ፖሊሲ እናትና ልጅን ያለያየ ነበር ተብሎ ይተቻል፡፡ ከሙስሊም አገራት ወደ አሜሪካ የሚመጡ ሰዎችን የሚገድበውን ሕግ ለማንሳት ይፈልጋሉ ባይደን፡፡ በልጅነታቸው በሕግ ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ የመጡ ልጆችን (ድሪመርስ) ኦባማ ልዩ የመብት ጥበቃ እንዲደረግላቸው አድርገው ነበር፡፡ ትራምፕ ግን ያን ሽረውት ቆይተዋል፡፡ ይህንን በአገሬው አጠራር ድሪመርስ የሚባሉትን የሕለመኛ ልጆችን ሕልም ማስቀጠል ይፈልጋሉ ባይደን፡፡ ይህም ለ‹‹ህልመኞቹ›› ትምህርት የመማር፣ ሥራ የማግኘት መብቶቻቸውን ማስጠበቅን ይጨምራል፡፡ 8. የተማሪዎች የኮሌጅ ውዝፍ ብድር ይነሳል ግራ ዘመም ናቸው ካስባላቸው የጆ ባይደን ሐሳቦች አንዱ ትምህር ፖሊሲ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ባይደን ለአመታት የተከማቸ የተማሪዎችን ውዝፍ ብድር መሰረዝ ይፈልጋሉ፡፡ የነጻ ትምህርት የሚሰጡ ኮሌጆችን ማስፋፋት ይሻሉ፡፡ ከመዋእለ ሕጻናት በፊት ባሉ የትምህርት ደረጃዎች ሁሉም ሕጻን ተቀራራቢና ወጥ ትምህርትን በነጻ የማዳረሱን ሐሳብ (Universal preschool) እንዲስፋፋ ይፈልጋሉ፡፡ ጆ ለዚህ የሚሆን ገንዘብ ከየት ያመጣሉ ብሎ መጠየቅ አግባብ ነው፡፡ ይህን ሁሉ ገንዘብ ከየት ያመጡታል ሲባል ዶናልድ ትራምፕ የታክስ ምሕረት ካደረጉላቸው ባለጸጎች ግብር ሰብስቤ ለዚህ ተግባር አውለዋለሁ ብለዋል፤ ጆ፡፡ ይህ ሁሉ የሚሳካው ግን ኅዳር 3 የዕድል ቀናቸው ከሆነች ብቻ ነው፡፡ ያ ካልሆነ ግን ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካዊያንን ለሌላ አራት ዓመት ይሾፍራሉ፡፡
54546138
https://www.bbc.com/amharic/54546138
የፌደራል ፖሊስ 14 የውጪ አገራት ዜጎች የአደንዛዥ ዕፅ ሲያዘዋውሩ መያዙን ገለፀ
የፌደራል ፖሊስ 13 ናይጄሪያውያንና አንድ ብራዚላዊት አደንዛዥ ዕጽ ሲያዘዋውሩ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።
ግለሰቦቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉት በቦሌ ኣለም አቀፍ አውሮፕላን መሆኑ የኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል። የፌደራል ፖሊስ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ 24 የአደገኛ ዕጽ አዘዋዋሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገለፀ ሲሆን 39 ኪሎ ግራም ኮኬይንና 36 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካናቢስ (ዕፀ-ፋርስ) መያዙ ተገልጿል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት በትናንትናው እለት (ጥቅምት 9፣ 2013 ዓ.ም) በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ መነሻቸውን ላቲን አሜሪካ፣ ሳኦፖሎ ከተማ፣ መዳረሻቸውን ደግሞ የተለያዩ ሀገራት ለማድረግ በአውሮፕላን ሲጓዙ የነበሩት ተጠርጣሪዎችን እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ኮሚሽኑ ባሰራጨው ዜና አስታውቋል። የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ የያዝዋቸውን ዕጾች በውስጣዊና ውጫዊ የሻንጣ አካል ተደብቀው እንደነበር ተገልጿል። በተጨማሪም በሆዳቸው በመዋጥ እንዲሁም የጡት መያዣና የተለያዩ የማዘዋወሪያ ዘዴዎችን ተጠቅመው ለማሳለፍ ሙከራ ማድረጋቸው በመረጃው ላይ ተመልክቷል። ተጠርጣሪዎቹ ከ14 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ኮኬይን ይዘው ተገኝተዋል።
news-46464054
https://www.bbc.com/amharic/news-46464054
የሃምዛ ሃሚድ ፈጠራ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነቱ ሊጠበቅለት ነው
ገና የ3ኛ እና የ4ኛ ክፍል ተማሪ በነበረበት ጊዜ በፈጠራ ሥራዎች ቀልቡ መሳብ እንደጀመረና ከኤሌክትሪክ የተገናኙ ነገሮችን መስራት ያስደስተው እንደነበር ያስታውሳል - የ18 ዓመት ወጣቱ ሃምዛ ሃሚድ።
ሃምዛ በፈጠራ ሥራው ብቻ ሳይሆን በቀለም ትምህርቱም ጥሩ ውጤት ከሚያስመዘግቡ ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው፤ ፊዚክስና ሒሳብም አብዝቶ የሚወዳቸው የትምህርት ዓይነቶች ናቸው። • ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ተፈለሰፈ • ኮሌራን የሚቆጣጠር ኮምፕዩተር ተሰራ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ አስተማሪያቸው 'የፈጠራ ሥራ የሠራ ይበረታታል' ሲሉ ማስታወቂያ ያስተላልፋሉ። ሥራውን ለማሳየት ዕድሉን ለመጠቀም የፈለገው ሃምዛ የትራፊክ መቆጣጠሪያ መብራት ሠራ፤ ነገር ግን ሥራው የመጀመሪያው በመሆኑ በራስ መተማመን አልሰጠውም። እየፈራ እየተባ ፈጠራውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በተገኙበት አቀረበ። ያኔ ታዲያ ፊቱን በደስታ ብርሃን ያፈካ ያልጠበቀውን ምላሽ አገኘ። በሥራው ከመደነቃቸው የተነሳም ተማሪዎች በተሰበሰቡበት የአንድ 'ቢክ' እስክርቢቶ ሽልማት ተበረከተለት። ደስታው ወደር አልነበረውም፤ የልጅነት ልቡ ዳንኪራ ረገጠች። የትራፊክ መብራቱ (ፈጠራው) ሰዎች የተሽከርካሪ አደጋ እንዳይገጥማቸው የሚያስተምር ቅርፅ (ሞዴል) ነበር። እርሱ እንደሚለው ከዚያ በኋላ ድፍረትንም ድልንም ደጋግሞ መቀዳጀት ጀመረ። የ4ኛ ክፍል ተማሪ እያለ በአስተማሪው ድጋፍ ራዲዮ ላይ የሚገጠም ድምጽ ማጉያ (ስፒከር) ሰርቶ በመወዳደር የሁለተኛነት ደረጃን አግኝቷል። ሃምዛ 20 የሚሆኑ የፈጠራ ሥራዎችን በተለያየ ጊዜ አቅርቧል። የሻይ ማሽን፣ ጤፍን በመስመር ለመዝራት የሚያስችል መሣሪያ እንዲሁም ሻማ ከቀለጠ በኋላ እንደገና ተመልሶ አገልግሎት የሚያስገኝ መሣሪያ ሰርቶ ለዕይታ አቅርቧል። የሚማርበትን ትምህርት ቤት ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችልና አርፋጅ ተማሪን በዘመናዊ አሠራር የሚቆጣጠር ማሽን እና ዘመናዊ የአስተያየት መስጫ ሳጥን እንደሰራም ይናገራል። ኔት ወርክና ገንዘብ የማያስፈልገው ስልክ የፈጠረ ሲሆን የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ካሉበት ሆነው ስብሰባ ማካሄድ የሚያስችል ነው። እነዚህ የፈጠራ ሥራዎቹ ከብዙው በጥቂቱ ያውም በጥቅሉ የተገለጹ መሆናቸውን ግን አስምሮበታል - ሃምዛ። ገመድ አልባው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ (Wi-power) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካልና ኮምፒዩተር ምህንድስና የአንደኛ ዓመት ትምህርቱን በመከታተል ላይ የሚገኘው ሃምዛ የአልበርት አንስታይንና የቶማስ ኤድሰንን የሕይወት ታሪኮችና ሥራዎች ማንበብ ያዘወትራል። በኢትዮጵያ የሚታዩ ችግሮችን በፈጠራ ሥራዎቹ የመፍታት ህልም አንግቧል። እርሱ እንደሚለው ለዚህ የፈጠራ ሥራው ተወልዶ ባደገበት ጃን አሞራ ያለው የኃይል መቆራረጥ እንዳነሳሳው ይገልፃል። • ቶዮታ ያለአሽከርካሪ የሚንቀሳቀሱ መኪናዎችን ሊያሰማራ ነው • የሁዋዌ ባለቤት ልጅ ካናዳ ውስጥ ታሠረች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አቶ ሰለሞን መስፍን፤ ሃምዛ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ሳለ ሥራዎቹን ይከታተሉ እንደነበር ይናገራሉ። አመርቂ ውጤት በማስመዝገብም ዩኒቨርሲቲውን ሊቀላቀል ችሏል። አቶ ሰለሞን የእርሱ ፈጠራዎች አካል የሆኑት ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያና ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎት በዩኒቨርሲቲው እንደተሞከሩ ይገልጻሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የሳይንስ ቀን አስመልክቶ ለሦስተኛ ጊዜ በተከበረው የሳይንስና ቴክኖሎጂ አገር አቀፍ ውድድር ላይ ገመድ አልባው የኢንተርኔት አገልግሎት (Signal Wi Fi) ፈጠራው ሁለተኛ ደረጃን አግኝቶ ሽልማት ተበርክቶለታል። ይሁን እንጂ ገመድ አልባው የኤሌክትሪክ ኃይል (Wi power) ከሥራዎቹ ሁሉ አዲስና ተሰምቶ የማይታወቅ በመሆኑ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ስለ ሥራው በዝርዝር መግለፅ እንደማይፈልጉ አቶ ሰለሞን ጨምረው ተናግረዋል። "የኤሌክትሪክን ኃይል ያለ ገመድ ማስተላለፍ የማይታመን ነገር ነው" የሚሉት አቶ ሰለሞን በዩኒቨርሲቲው 60 ሜትር ርቀት ላይ እንደተሞከረና ያለምንም የገመድ ማስተላለፊያ አምፖል ማብራት እንደተቻለ በዐይናቸው መታዘባቸውን ግን አልሸሸጉንም። ከዚህ ቀደም በግሉ ባደረገው ሙከራ ኃይሉ በሚተላለፍበት አቅጣጫ ሰዎች ሲሻገሩ ንዝረት ይፈጥር እንደነበርና ያ ችግር ግን አሁን መስተካከሉን ከራሱ ከሃምዛ መስማታቸውን ገልፀውልናል። "የፈጠራ ሥራውን በአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ለማስመዝገብ እየተሠራ ነው" ወጣቱ የፈጠራ ባለሙያ ከዚህ ቀደም ዣንጥላዎችን እንዲሁም በኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን በመጠገን ከሚያገኘው ገንዘብ ለፈጠራ ሥራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ያሟላ ነበር። አንዳንዴም በኤሌክትሮኒክስ ንግድ የተሰማሩ የአካባቢው ነጋዴዎች የሚያስወግዷቸውን ቁርጥራጮችና ሌሎች ቁሳቁሶችን ይለግሱታል። አንዳንዴም በርካሽ ይሸጡለታል። ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላ ግን ይህ የቀረለት ይመስላል። በዩኒቨርሲቲው የፈጠራ ሥራ ማዕከልና ቤተ ሙከራዎች እንዲጠቀም፣ መምህራንም በቅርብ እንዲያግዙትና የሚያስፈልገው ነገር እንዲሟላለት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አቶ ሰለሞን ነግረውናል። • የአንስታይን ደብዳቤ በ84 ሚሊዮን ብር • በሕይወት ከሌለች እናት የተወለደችው ሕፃን ዩኒቨርሲቲውም ተጓዳኝ የሆኑ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት፣ እያንዳንዱን የፈጠራ ሥራዎች እንደ አንድ ፕሮጀክት በመውሰድ በጥናት እንዲሠሩ እያደረጉ መሆናቸውንም ገልጸውልናል። ዩኒቨርሲቲው ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመሆን እንደ ሃምዛ ያሉ በፈጠራ ሥራ የተሠማሩ ወጣቶችን በማገዝ እየሠራ ይገኛል። ተማሪው የጊዜም ሆነ የሌላ ጫና እንዳይገጥመው የፈጠራ ሥራ ውጤቶቹን ቀስ በቀስ ተግባራዊ እንዲደረጉና በጥናት ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ እየሠሩ ነው። በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲው የፈጠራ ሥራው በአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት እንዲመዘገብ ማድረግ ቅድሚያ የሰጠው ጉዳይ ሆኗል። ፈጠራውን ለማስመዝገብም በሂደት ላይ እንደሚገኙ አቶ ሰለሞን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
news-43985862
https://www.bbc.com/amharic/news-43985862
አዲስ ቋንቋ ለመማር አስበዋል? ለመሆኑ እድሜዎ ስንት ነው?
ቋንቋ መማርና እድሜ መሀከል ትስስር አይኖርም ብለው ለሚያስቡ፣ ቋንቋ ለመማር እድሜ መጠየቁ አስፈላጊ ላይመስላቸው ይችላል።
በቅርቡ ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው ግን ከ10 ዓመት በኋላ አዲስ ቋንቋ መማር ከባድ ነው። 'ኮግኒሽን' የተሰኘው እውቁ የሳይንስ መፅሄት ላይ የተተየበ አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው ሰዎች ከ17 ወይም ከ18 አመታቸው በኋላ አዲስ ቋንቋ የመማር ችሎታቸው እያሽቆለቆለ ይሄዳል። ጥናቱ የተሰራው በተለያየ እድሜና ሃገር የሚኖሩ 670 ሺህ ሰዎችን መሠረት አድርጎ ሲሆን፣ ተመራማሪዎቹ ማሳያ አድርገው የወሰዱት እንግሊዝኛ ቋንቋን ነበር። ጥናቱ የተሰራው የእንግሊዝኛ ሰዋሰው ጥያቄዎች በፌስቡክ ተለጥፈው በተገኙ ምላሾቹን ሲሆን፣ የተጠያቂዎቹ እድሜና እንግሊዘኛ ቋንቋ በሚነገርበት ሃገር የቆዩበት ግዜ መጠን ከግምት ገብቷል። አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ከ20 እስከ 30 ባለው የዕድሜ ክልል ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ የ10 አመትና የ70 አመት ሰዎችም የጥናቱ አካል ነበሩ። በጥናቱ ከተሳተፉት ወደ 246 ሺህ ሚሆኑ እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች ሲሆኑ፣ የተቀሩት ሁለትና ከዛም በላይ ቋንቋ ይችላሉ። ከነዚህ መካከል አፍ መፍቻቸው ጀርመንኛ፣ ሩስኪ፣ ቱርክኛና ሃንጋሪኛ የሆኑ ይገኙበታል። አዲስ ቋንቋ የመማር ፈተና ለጥናቱ በዋሉት የሰዋሰው ጥያቄዎች፣ ያለፈ ወቅትና ነባራዊ ሁኔታን የሚጠቁሙ አገላለፆች ተዋህደው፣ ምን ያህሉ ሰዎች ስህተቱን መለየት እንደሚችሉ ተፈትሿል። ተመራማሪዎቹ ከጥናቱ ያገኙትን ውጤት ሲተነትኑ የተገነዘቡት ቋንቋ የመማር ችሎታ በልጅነት የላቀ ሲሆን፣ በወጣትነት ባለበት ደረጃ ቀጥሎ፣ እድሜ ሲገፋ ይቀዛቀዛል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት፣ ዕድሜ እየጨመረ ሲሔድ አእምሮ አዳዲስ ነገር የመማር ብቃቱ እየተዳከመ ይመጣል። ምናልባትም ከ18 ዓመት በላይ ያሉ ሰዎች አዲስ ቋንቋ ለመማር የሚከብዳቸው በዚህ ምክንያት ይሆናል። ሰዎች ከልጅነት ወደ ወጣትነት ከዛም ወደ ጉልምስና ሲያመሩ፣ ቋንቋ የመማር ብቃታቸው እየከዳቸው ይሄዳል። የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ተቋም የአእምሮና ኮግኒቲቭ ሳይንስ ምሁሩ ጆሽ ቴንባውም "የቋንቋ ትምህርት ከአካላዊ ለውጥ በተጨማሪ በማሕበራዊና ባህላዊ ተፅእኖ ስር ጭምርም ነው" ሲሉ ያብራራሉ። መምህሩ እንደሚሉት፣ ሰዎች 18 ዓመት ከሞላቸው በኋላ የትምህርትና የስራ ጫና ስር መሆናቸው በቋንቋ ትምህርት ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል። ተስፋ አይቁረጡ. . . የጥናቱ ውጤት ሙሉ በሙሉ ተስፋ አስቆራጭ አይደለም። በጎልማሳነት አዲስ ቋንቋ ለመማር መሞከር የራሱ ጠቀሜታዎች አሉት። ለምሳሌ አዲስ ቋንቋ መማር የአዕምሮ መዋዠቅ (ዳይሜንሽያ) የመሰሉ ህመሞችን እንደሚከላከል ጥናቶች ያሳያሉ። ለዮርክ ዩኒቨርስቲ የቋንቋ መምህሩ ፕሮፌሰር ማርሊን ቪላሚን፣ አዲስ ቋንቋ ለመማር የግድ በልጅነት መጀመር ያሻል የሚለው መላ ምት ውሃ አይቋጥርም። "በ20 ዎቹ ዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች አዲስ ቋንቋ ተምረው ለስለላ የተላኩባቸው ሁኔታዎች አሉ። አዲስ ቋንቋ ለመማር የዕድሜ ገደብ አለ ብዬ አላስብም። ችሎታው ከሰው ሰው የተለያየም ነው" ይላሉ። ሌላው የቋንቋ ምሁር ዶ/ር ዳንጂላ ጣሪክ፣ ጥናቱ በሰዋሰው ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑ ክፍተት እንደሚፈጥር ገልፀው፣ የሰዋሰው ችሎታቸው ደካማ ሆኖ፣ ጥሩ ተናጋሪዎች እንዳሉ ይናገራሉ።
news-50065725
https://www.bbc.com/amharic/news-50065725
ቱርክ የአሜሪካን የተኩስ አቁም ጥሪ ውድቅ አደረገች
ቱርክ የአሜሪካንን አስቸኳይ የተኩስ አቁም ጥሪ ውድቅ አደረገች። ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ጦሩ ማጥቃቱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የጣይብ ኤርዶጋን አስተያየት የተሰማው ከአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ማይክ ፔንስና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ ወደ ቱርክ ለመብረር በተዘጋጁበት ወቅት ነው። ሁለቱ የአሜሪካ ሹማምንት በቱርክና በኩርዶች መካከል ሰላም እንዲወርድ ይጥራሉ ተብሏል። • አሜሪካ ቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች • የአምስት ቤተሰብ አባላትን ሕይወት የቀጠፈው የመሬት ናዳ " የተኩስ አቁም አውጁ ይሉናል በጭራሽ አናደርገውም" ያሉት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን፣ አክለውም " ጫና እያሳደሩብን ያሉት እርምጃችንን እንድናቆም ነው። ማዕቀብም ጥለዋል። ዓላማችን ግልፅ ነው። ስለማዕቀቡ አንጨነቅም" ብለዋል። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት " ቱርክ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ለማድረግ ካልተስማማችና ካልተገበረች" እንዲሁም በድንበሩ አካባቢ ስደተኞችን ለማስፈር ለመደራደር ፈቃደኛ ካልሆነች ማዕቀቡ ይበልጥ እንደሚጠብቅ አስጠንቅቀዋል። ቱርክ ኩርዶችን ከድንበር አካባቢ ማራቅ የዚህ ጥቃቷ ግብ እንደሆነ በፕሬዝዳንቷ በኩል ደጋግማ ተናግራለች። በኩርዶች የሚመራው የሶሪያ ዲሞክራቲክ ግንባር በቱርክ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ነው። አንካራ ከዚህ ቀደም በድንበሩ አቅራቢያ 30 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን "ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና" መመስረት እንደምትፈልግ አስታውቃለች። በዚህ ስፍራም ቱርክ የሚገኙ 2 ሚሊየን ሶሪያውያን ስደተኞችን የማስፈር ዕቅድ አላት። በሳምንቱ መጨረሻ አካባቢ በሩሲያ የሚደገፉ የሶሪያ ወታደሮች ከኩርዶች ጋር በመደራደር በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ላይ በመግፋት የቱርክ ወታደሮችንና አፍቃሪ ቱርክ አማፂያንን ርምጃ ለመግታት ሞክረዋል። • ለአንዲት ታካሚ ብቻ የተሠራው መድሃኒት ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ጦር ከቀጠናው መውጣቱ በተገለፀበት ቅፅበት ቱርክ ጦሯን በሶሪያ የድንበር ከተሞች በማዝመት መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፍታለች። ይህንን የአሜሪካ መንግሥትን እርምጃ የሚተቹ አካላት የአሜሪካ ድርጊት ለቱርክ ጥቃት ይኹንታን የሰጠ ነው ይላሉ። አሜሪካ ግን ይህንን በማስተባበል ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች። እስካሁን ድረስ በርካታ ተዋጊዎች ሲሞቱ ከ160 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ያሳያል።
52293115
https://www.bbc.com/amharic/52293115
ኮሮናቫይረስ፡ በወራቤ "ርቀታችሁን ጠብቁ" ያለው ወጣት ሕይወቱ አለፈ
በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በተለምዶ ዋሽንግተን በሚባለው አካባቢ ከትናንት በስቲያ አንድ ግለሰብ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ከሚመከሩት ጥንቃቄዎች መካከል አንዱ የሆነው ርቀት መጠበቅን መምከሩ ለሕይወቱ ማለፍ ምክንያት ሆኗል።
በአንድ ሻይ ቤት ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረው ሟች አራት ደንበኞች ተጠጋግተው መቀመጣቸውን ተመልከቶ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ መንገሩን ተከትሎ በተፈጠረ ግብግብ ሕይወቱ ልታልፍ እንደቻለች የስልጤ ዞን የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ኃለፊ የሆኑት አቶ ሙዲን ሙኒር ለቢቢሲ ገልፀዋል። • ከሳኡዲ አረቢያ የሚመለሱት ስደተኞች በኮሮናቫይረስ ምክንያት አይደለም • የኮሮናቫይረስን በመቆጣጠር በኩል እየተሳካላት ያለችው አገር ''የሚሰራበት ሻይ ቤት በር ላይ ሰዎች ሰብሰብ ብለው መቀመጣቸውን ሲያይ ለምን ተራርቃችሁ አትቀመጡም ብሎ ሀሳብ ያቀርባል። ሰዎቹም ሃሳቡን ካላመረዳት ሊሆን ይችላል፤ በመካከል በተፈጠረ ግብግብ ደብድበው ገድለውታል።'' አቶ ሙዲን አክለውም ''በቦክስ ነበር ድብደባውን የፈጸሙበት፤ ሕይወቱ በቦታው አላላፈችም ነበር። ፖሊስ በቦታው ከደረሰ በኋላ ሰዎች ተረባርበው ወደ ወራቤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢወስዱትም ሕይወቱን ግን ማትረፍ አልተቻለም'' ብለውናል። የሟች ሬሳም በወራቤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ለቤተሰቦቹ ተመልሶ የቀብር ስነስርአቱ ተፈጽሟል። ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የነገሩን ደግሞ የስልጤ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ካሚል ሀሚድ ናቸው። ''አራት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውለናል። በአሁኑ ሰአት መረጃ የማጠናከር ስራ እያከናወንን ነው። ቃላቸውን ተቀብለን፤ ከዛ በኋላ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አድርገናል። ለእኛ የሰጡንን ቃል ለፍርድ ቤት አረጋግጠዋል። አሁን ፍርድ ቤቱ የሰጠን ቀጠሮ እስኪደርስ እኛ ጋር ይቆያሉ።'' ብለዋል። ከኮሮናቫይረስ ስርጭት ጋር ተያይዞ በወራቤ ዞን ሰዎች ራሳቸውን ከበሽታው እንዲጠብቁና የተላለፉ ውሳኔዎችን ከማስከበር አንጻር ምን እየሰራችሁ ነው የሚል ጥያቄ ለኢንስፔክተር ካሚል አቅርበንላቸው ነበር። እሳቸውም '' ተሽከርካሪዎች መጫን በሚፈቀድላቸው ልክ ተሳፋሪዎችን እንዲጭኑ እየተቆጣጠርን ነው። በቁጥጥር ስር ያዋልናቸውም ግለሰቦች አሉ፤ ነገር ግን እያስተማርን እየለቀቅናቸው ነው። በአሁኑ ሰአት ማህበረሰቡ በሽታውን በደንብ እንዲገነዘብ ማድረጉ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው'' ብለዋል። አክለውም '' ግለሰቦችን ሰብስቦ ማሰሩ በራሱ ሌላ ችግር ይዞ ሊመጣ ይችላል። በዋናነት በመግባባትና በማሳመን ሰዎች ከበሽታው ራሳቸውን እንዲጠብቁ እየሰራን ነው'' ብለዋል። • ፋሲካና ረመዳን በኮሮናቫይረስ ጊዜ እንዴት ሊከበሩ ይሆን? የዞኑ የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ኃለፊ አቶ ሙዲን በበኩላቸው ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ኮሮና ማድረጋቸውን ይናገራሉ። ''በአካባቢው ቋንቋ ስልጥኛና አማርኛን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ እያደረስን ነው። ሶስት ዋና ዋና ነገሮች ላይ ትኩረት አድርገናል፤ የቫይረሱ መተላለፊያ፣ መከላከያ እና ከተያዙ ደግሞ ምን መደረግ አለበት በሚለው ላይ ታች ድረስ ወርደን ለማስተማር እየሞከርን ነው።'' መጨባበጥና ተቀራርቦ መንቀሳቀስን በተመለከተ ሕዝቡ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እየተገበረው እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ሙዲን እንደ ገበያና ወፍጮ ቤት የመሳሰሉ ቦታዎች ላይ ግን አሁንም ችግር አለ ብለዋል። ለማህበረሰቡ ተጨማሪ ግንዛቤ ለመፍጠርም እንደነ መሀመድ ሲርጋጋና አሊ ኑርን ያሉ ታዋቂ የአካባቢው ተወላጆችን በመጠቀም መልእክቶች እየተላለፉ መሆኑንም አቶ ሙዲን ገልጸዋል።
news-57099027
https://www.bbc.com/amharic/news-57099027
የሎተሪ አሸናፊዋ የ26 ሚሊዮን ዶላር ቲኬቷን በልብስ አጠባ እንዳጣችው አስታወቀች
የካሊፎርኒያ ነዋሪ የሆነች አንዲት ግለሰብ የ26 ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ ያደረጋትን የሎተሪ ቲኬት ሱሪዋ ኪስ ውስጥ ረስታው በመታጠቡ ከጥቅም ውጭ መሆኑንን ለአሜሪካ ሚዲያዎች ተናግራለች።
ግለሰቡ ይህንን ያህል መጠን አሸናፊ ያደረጋትን ቲኬት የገዛችው ሎስ አንጀለስ በሚገኝ አንድ የገበያ መደብር ውስጥ ህዳር ወር ላይ ነበር። ስሟ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ቲኬቱን በወቅቱ ከመደብሩ ስትገዛ በካሜራ የተቀረፀች ሲሆን አሸናፊ የሚያደርጋት ቁጥር መያዟም ታውቋል። የዕጣው አሸናፊ ገንዘብ የሚወስድበት የመጨረሻ ቀን በያዝነው ሳምንት ሃሙስ ነበር። አሸናፊው እንደታወቀ ቲኬቱን በገዙበት በ180 ቀናት ሊወስዱ ይገባል። ኤስፐራንዛ ሄርናንዴዝ የተባለው የገበያ መደብር ሰራተኛ የሆኑ ግለሰብ ካሊፎርኑያ ዊቲየር ደይሊ ኒውስ እንደተናገሩት በያዝነው ሳምንት ረቡዕ ሎተሪ ያሸነፈችው ግለሰብ መጥታ በአጋጣሚ ቲኬቷ ሱሪዋ ውስጥ ተረስቶ እንደታጠበ ተናግራለች። የካሊፎርኒያ ሎተሪ ቃለ አቀባይ ካቲ ጆንሰን በበኩላቸው ለጋዜጣው እንደተናገሩት ግለሰቧ ቲኬቱን ስትገዛ የሚያሳየው የመደብሩ ቪዲዮ ገንዘቡን ለመጠየቅ በቂ እንዳልሆነና ቲኬቱን በእጇ መያዝ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ሆኖም ቪዲዮው ለሎተሪው አዘጋጅ አካል እንደደረሰና ቀጣይ ምርመራም እየተደረገበት እንደሆነ ካቲ ተናግረዋል። የሎተሪው አሸናፊ ከሌለ ገንዘቡ ለካሊፎርኒያ የህዝብ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፋፈል አዘጋጆቹ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። መግለጫው አክሎም አሸናፊ የሆነውን ቲኬት የሸጠው መደብር በአሰራሩ መሰረት 130 ሺህ ዶላር እንደተከፈላቸው መግለጫው አክሏል። በካሊፎርኒያ ትልቅ ስፍራ ያለው ይህ ሎተሪ አሸናፊው ብሩን ሳይወስድ ሲቀር የተለመደ እንዳልሆነና አሸናፊም ነኝ ብሎ ቲኬት አለማሳየትም እንዲሁ የመጀመሪያ ነው ተብሏል። በአውሮፖውያኑ 2016ም እንዲሁ አንዲት እንግሊዛዊት ሴት አሸናፊ የሆነችበትን የሎተሪ ቲኬት ቆሻሻ ጅንሷ ውስጥ ረስታው በልብስ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ ገብቶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
news-51895007
https://www.bbc.com/amharic/news-51895007
በኮሮናቫይረስ ተጠርጥሮ ከአምቡላንስ ያመለጠው ወጣት ያደረገው ምንድን ነው?
አንድ ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሰ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶበት ተጠርጥሮ ወደ ለይቶ ማቆያ በአምቡላንስ በሚወሰድበት ጊዜ አምልጦ ወደ ትውልድ መንደሩ በመመለስ ላይ ሳለ በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።
ዛሬ ከሰዓት (ሰኞ) የኢትዮጵያ ሕብረሰተብ ጤና ኢንስቲትዩት ግለሰቡ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ በላቦራቶሪ ምርመራ ተረጋግጧል ብሏል። ቢቢሲ ስለግለሰቡ ከአካባቢው ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ነዋሪነቱ እዚያው ለጋምቦ ወረዳ ተወልዶ ያደገ ወጣት ሲሆን በሕገ ወጥ መንገድ ከአንድ ወር በፊት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለሥራ ተጉዞ የነበረ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል። ነገር ግን በስደት ለአንድ ወር ከቆየ በኋላ በሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ ተይዞ ወደ ኢትዮጵያ መላኩን የወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት አበባው ተናግረዋል። በመሆኑም ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በተደረገለት ምርመራ የኮሮናቫይረስ ምልክትቶች ስለታዩበት በአምቡላንስ ወደ ለይቶ ማቆያ ቦታ ሲወሰድ አምቡላንሱን ሰብሮ በማምለጥ እዚያው አዲስ አበባ ወደሚገኘው የእህቱ ቤት አምርቶ እንደነበረ ኃላፊው ይናገራሉ። ይህ መቼ እንደሆነ ቀኑን ለማወቅ እንዳልቻሉ አቶ ጌትነት ገልጸው፤ ትናንት (ቅዳሜ) ከፌደራል ጤና ጥበቃ ተደውሎ የአካባቢው ተወላጅ የሆነው ግለሰብ በኮሮናቫይረስ ተጠርጥሮ እንደነበርና ለይቶ ማቆያ ከመግባቱ በፊት እንደጠፋ እንደተነገራቸውና ክትትል እንዲያደርጉ መረጃ እንደደረሳቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከዚህ በኋላም የአካባቢው ባለስልጣናት ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ወደ አካባቢው የሚመጡ መኪኖች ላይ ፍተሻ በማድረግ ግለሰቡን ለማግኘት ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል። አቶ ጌትነት እንዳሉት የግለሰቡን ወንድም አብሯቸው እንዲሆን በማድረግ በመኪና ከሚጓዙ መንገደኞች መካከል ተፈላጊውን ለመለየት ጥረት ማድረጋቸውን አመልክተው ትናንት [ዕሁድ] ጠዋት 5 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ከፈተሹ በኋላ ስድስተኛው ላይ ተጠርጣሪው መገኘቱን ገልጸዋል። ከተፈላጊው ግለሰብ ጋርም ከአዲስ አበባ ጀምሮ ወደ ትውልድ መንደሩ ለማድረስ የተጓዘው የእህቱ ባልም አብሮት መገኘቱን ተነግሯል። ክስተቱን የበለጠ ውስብስብ ለማድረግም ከአዲስ አበባ ቀጥታ ወደ ሚፈልገው ቦታ የሚያደርሰው ትራንስፖርት ከመያዝ ይልቅ በተለያዩ ከተሞች ላይ እየወረደ መጓጓዣውን ሲቀይር እንደነበር ተገልጿል። በዚህም መሰረት ከክትትሉ ለማምለጥ በሚልም ኮምቦልቻ፣ ደሴና ጉጉፍቱ የሚባሉ ከተሞች ላይ ወርዶ መኪና መቀየሩንና መጨረሻ ላይም ጉጉፍቱ ላይ በሳይንት መኪና ሲጓዝ ለጋምቦ ላይ መያዙን ኃላፊው አረጋግጠዋል። ግለሰቡና አብሮት የነበረው የእህቱ ባለቤት በትራንስፖርት አብረዋቸው ከተጓዙት ሰዎች ባሻገር ከሌሎች ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ በለይቶ ማቆያ ውስጥ በመሆን ምርመራና ክትትል ወደሚያገኙበት ወደ አዲስ አበባ ክትትሉ ሲያደርጉ በነበሩት የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ታጅበው እንዲሄዱ ተደርጓል። ግለሰቡ ተሳፍሮበት በነበረው ውስጥ የነበሩት ወደ 60 የሚደርሱ ሰዎች ምርመራ ተደርጎ ውጤት እስኪታወቅ ድረስ ድንኳን ተዘጋጅቶ ለብቻቸው እንዲቆዩ እንደሚደረግም አቶ ጌትነት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ ባሻገር ግን በተለያዩ ከተሞች ውስጥ ከተሳፈረባቸው መኪኖች ላይ አብረውት የተጓዙትን መንገደኞች ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸው፤ የግለሰቡ የምርመራ ውጤት ቀጣይ መወሰድ ያለበትን እርምጃ የሚወስን መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት አመልክተዋል።
46484697
https://www.bbc.com/amharic/46484697
አፍሪካ የተሰጣትን ጨለምተኛ እይታ ለመቀየር ያለመው አዲስ ፎቶ ፌስት
በአፍሪካ ውስጥ ስመጥር ከሆኑት የፎቶ ፌስቲቫሎች ከፍተኛ ቦታ ያለው አዲስ ፎቶ ፌስት በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል ተከፍቷል።
ለአምስተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከ61 ሃገራት የተውጣጡ 152 የፎቶ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። ይህ አውደ ርዕይ በየአመቱ አሳታፊነቱ እየጨመረ የመጣ እንደሆነ የምትናገረው የአዲስ ፎቶ ፌስት ዋና አዘጋጅና የፎቶ ባለሙያ አይዳ ሙሉነህ ዋና ትኩረቱም የውክልና ጉዳይ ነው ትላለች። አፍሪካ በተለያዩ ምስሎችም ሆነ በውጭው ዓለማት የምትታወቀው ሁሌም ከችግር፣ ድርቅና ረሀብ ጋር ብቻ ከመሆኑ አንፃር ይህ ፎቶ ፌስትም በጎ ጎኗንም ለማሳየት እንዳለመ አይዳ ታስረዳለች። •ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች •በርካቶችን ግራ ያጋባው ፎቶ •ወጣቱ እራሱን 'ሰልፊ' ሲያነሳ ህይወቱ አለፈ "ይህንን የፎቶ አውደ ርዕይ የምናየው እንደ አቅም ግንባታ ነው። እነዚህን ሁሉ ወጣት የፎቶ ባለሙያዎች ስናሰባስብ ወይም ስልጠና ስንሰጥ የኢትዮጵያን ዕውነታ በምን መንገድ ሊያሳዩ ይችላሉ የሚለውን ለማሳየት" እንደሆነ ትናገራለች። በተለይም አፍሪካ እንደ ጨለምተኛ ብቻ አህጉር ተደርጋ መታየቷ ትክክለኛ እይታ እንዳልሆነ የምትናገረው አይዳ "ሁሉም ነገር በጎ አይደለም ነገር ግን ሁሉም ነገር ደግሞ መጥፎ አይደለም። በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ጎልተው ገኖ የሚታየው መጥፎ ነገር ነው" ይህንንም ለመቀየር ኢትዮጵያዊ ወይም አፍሪካዊ ፎቶ ባለሙያዎችን ማፍራትና እይታዎችንም መፍጠር እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ትሰጣለች። በዚህ ዓመት ዓውደ ርዕይ 1200 ፎቶዎች የሚቀርቡ ሲሆን ከአመት ወደ አመት የተሳታፊዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ተናገራለች። በባለፈው አመት ለመሳተፍ የጠየቁ የፎቶ ባለሙያዎች ቁጥር 500 የነበረ ሲሆን በዚህ አመት ወደ 832 ደርሷል። ከነሱም ውስጥ 152 ባለሙያዎች ተመርጠው ተሳታፊ ሆነዋል። ለአይዳ ሙሉነህ የተሳታፊዎች ቁጥር መብዛት የሚያሳየው አዲስ ፎቶ ፌስት በአለም ላይ ያለው ስፍራ እየጨመረ መሆኑን ነው። በተጀመረበት ወቅት አምስት የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ከኢትዮጵያ ያሳተፉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም 35 እንደደረሱ አይዳ ትናገራለች። ምንም እንኳን በፈተናዎች የተሞላ መሆኑን አይዳ ባትክድም "ይሄን ሁሉ ስራ የምንሰራው ሃገሪቷን ለማሳወቅ ነው" ትላለች።
news-51764786
https://www.bbc.com/amharic/news-51764786
የኮሮናቫይረስ በአዲስ አበባ ሆቴሎች ላይ ያጠላው ስጋት
የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ስጋት ምክንያት በአዲስ አበባ ሊካሄዱ ታቅደው የነበሩ ስብሰባዎች በመሰረዛቸው በአዲስ አበባ በሚገኙ ሆቴሎች ገቢ ላይ ተጽእኖ እንደሚያስከትል ተነገረ።
የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ብስራት ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ባይከሰትም በሌሎች አገራት ውስጥ ባለው ሁኔታ ሳቢያ ተጓዦች ቀደም ሲል የያዙትን እቅድ እየሰረዙ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ባይኖራቸውም የሚሰረዙት ከፍተኛ የቋማትና የግለሰብ መረሃግብሮች በአገሪቱና በሆቴሎች ገቢ ላይ የእራሳቸው የሆነ ተጽእኖ እንደሚኖራቸው አመለክተዋል። አቶ ቢኒያም እንደ አብነትም አዲስ አባባ ውስጥ ሚያዚያ ወር ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውና አንድ ሺህ ሰው እንደሚሳተፍበት የሚጠበቀው የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ዓመታዊ ጉባኤ ተሰርዟል። በዚህም እያንዳንዱ ተሳታፊ አራት ምሽቶችን አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚያሰልፍ ይጠበቅ የነበረ ሲሆን አንድ ሰው በአማካይ በአንድ ምሽት 100 ዶላር የሚከፍል ቢሆን የ400 ሺህ ዶላር ገቢ ሳይገኝ እንደሚቀር ተናግረዋል። ከእነዚህ መካከል በተባበሩት መንግሥታት ድርጀት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አማካይነት ከመጋቢት 9 እስከ 15 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ በከፍተኛ ሚኒስትሮች ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ጉባኤ አንዱ ነው። ይህም በገንዘብ፣ በዕቅድና በምጣኔ ሃብታዊ ልማት ሚኒስትሮች አማካይነት የሚደረግና የ53ኛው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጉባኤ አካል ነበር። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንን ጨምሮም በኮሮናቫይረስ መስፋፋት ሳቢያ እየጨመረ በመጣው ስጋት ከአጋሮቹ ጋር በመመካከር ለጥንቃቄ ሲባል ተጨማሪያ ማስታወቂያ እስኪያወጣ ድረስ "ሁሉም ሕዝባዊ ስብሰባዎች ለሌላ ጊዜ መተላላፋቸውን" ገልጿል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ አገራት ውስጥ በመስፋፋቱ ለሥራም ሆነ ለእረፍት ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎች በሽታው ባስከተለው ስጋት ሳቢያ ዕቅዳቸውን ለመሰረዝ ተገደዋል። በዚህም የሆቴል ዘርፉ ላይ የገቢ መቀነስ እንደሚያስከትል አቶ ቢያኒያም አመልክተዋል። የበሽታው መስፋፋትና ስጋት በዚሁ ከቀጠለ ግንቦትና ሠኔ አካባቢ ፊፋ የሚያዘጋጀው ትልቅ መሰናዶ እንዲሁም የዓለም ኢኮኖሚ መድረክ ለመስከረም ወር የያዟቸው ትልልቅ ስብሰባዎችንም የመካሄድ ጉዳይን ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባው እንደሚችል ጠቅሰዋል። እስካሁን በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ባይከሰትም ከሚያሳጣው ገቢ በላይ አሳሳቢው ነገር የጤና ጉዳይ በመሆኑ ማኅበሩ በሆቴሎች የሚገኙ ሠራተኞች ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄ ስልጠናዎችንና የጥንቃቄ መመሪያዎችን እየሰጡ ነው ብለዋል። ይህ በዓለም ዙሪያ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በገደለው የኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት የታላላቅ ጉባኤዎች መሰረዝ እያጋጠመ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የአፍረካ አገራት ውስጥ ጭምር ነው። ከእነዚህም መካከል በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በመጪው ሳምንት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው 'ዘ ኔክስት አይንስታይን ፎረም' የተባለው ስብሰባ ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ተነግሯል። መድረኩ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ለአምስት ቀናት ከ79 አገራት በላይ በመጡና ከሁለት ሺህ የሚበልጡ ተሳታፊዎች የሚታደሙበት እንደነበር ተገልጿል። ሌላው ደግሞ የአፍሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ፎረም የተባለውና በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን ውስጥ በሚቀጥለው ሳምንት ለሁለት ቀናት ሊካሄድ የነበረው ስብሰባም እንደዚሁ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዘዋወር ተደርጓል።
55547001
https://www.bbc.com/amharic/55547001
ኮሮናቫይረስ ፡ ዱባይ ውስጥ ሥራ አጥተው የተቸገሩ ወገኖቿን የምትመግበው ኬንያዊት
ኬንያዊቷ በዩናይትድ አረብ ኤምሬተስ በኮሮናቫይረስ ምከንያት ሥራ ፈትተው ለተቀመጡ ኬንያውያን ምግብ እየሰራች በነጻ እንደምትመግብ ተሰምቷል።
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት ዋንጌቺ ዋሩይሬ ለዱባይ ታክሲ ሹፌር ነበረች። ዋሩይሬ "የተወሰነ ወራት በዝቅተኛ ክፍያ ከሰራሁ በኋላ በዋናው አየር መንገድ የሚገኘው አንደኛው ተርሚናል በወረርሽኙ ምክንያት በመዘጋቱ የተነሳ በጥቅምት ወር ላይ ሥራ ፈታሁ" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። የሶስት ልጆች እናት የሆነችው ዋሩይሬ፣ በርካቶች በወረርሽኙ ምክንያት ስራ አጥተው መቸገራቸው ስትመለከት፣ ቢያንስ የሚበሉትን በነጻ በመስጠት ጭንቀታቸውን ለማቃለል ማሰቧን ገልጻለች። የዋሩይሬ ባለቤት ሥራ አለመፍታቱን ገልጻ እርሱ በሚገዛላት አስቤዛ፣ ሥራ ፈትተው ቤታቸው ለተቀመጡ የአገሯ ልጆች ምግብ በማዘጋጀት በፌስ ቡክ ገጿ ላይ በማጋራት አቅራቢያዋ የሚኖሩ መጥተው እንዲወስዱ መጠየቅ ጀመረች። ዋረያሬ በሳምንት ሁለቴ ከ 20 እስከ 25 ሰው እንደምትመግብ ትገልጻለች። ከዚህ ቀደም በመንግሥት ብርቱ አሽከርካሪነቷ ታይቶ 'ምርጥ የዱባይ ታክሲ አሽከርካሪ' ተብላ ተሸልማ ነበር።
news-53775705
https://www.bbc.com/amharic/news-53775705
ምርጫ ፡ የትግራይ ምርጫና የተቃዋሚ ፓርቲዎች የበጀት ጥያቄ
በትግራይ ክልል ሊያካሂደው ያቀደው ስድስተኛው ዙር ክልላዊ ምርጫ ጳጉሜ 4/2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።
ምርጫውን ለማካሄድ ከአራት ሳምንታት ያነሰ ጊዜ የቀረ ሲሆን በዚህም መሰረት የመራጮች ምዝገባ ቀን ከነሐሴ 15 አስከ 22/2012 ዓ.ም እንደሚከናወንና ሁለት ተጨማሪ የመጨረሻ የምዝገባ ቀናትም እንዳሉ የክልሉ የምርጫ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ፀሐየ መረሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫው የሚያካሂዱት ቅስቀሳ ነሐሴ 29 ተጠናቆ ከአራት ቀናት በኋላ ረቡዕ ጻጉሜ 4 ድምጽ የመስጫ ቀን እንደሚሆን ተገልጿል። በተያያዘ ዜና ሊካሄድ አራት ሳምንታት ያህል በቀረው ምርጫ ላይ የሚሳተፉ ተቃዋሚ ድርጅቶች ለምርጫው እንቅስቃሴ የሚያስፈልጋቸው የገንዘብ ድጋፍ እንዳላገኙ አመለከቱ። በምርጫው የሚሳተፉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቀደም ሲል በምርጫው ሥርዓት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ካነሷቸው ጥያቄዎች በተጨማሪ በበጀት ጉዳይም እንዳልተስማሙ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ገልጸዋል። የትግራይ ክልል የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ ከዚህ ቀደም ለቢቢሲ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ ክልሉ የሚያካሂደውን ምርጫ እንደማያስፈጽም መግለጹን ተከትሎ የክልሉ መንግሥት የምርጫውን ወጪ እንደሚሸፍን ገልጸው ነበር። ነገር ግን ለመካሄድ ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ ለቀረው ምርጫ ማስፈጸምያ የክልሉ መንግሥት የመደበው ባጀት ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎች መንቀሳቀሻ ገንዘብ አጥተው እንደተቸገሩ ገልጸዋል። የሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) የውጭ ግንኙነትና የፓርቲው የምርጫ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኃይሉ ከበደ የክልሉ መንግሥት ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች የሚመድበው በጀትን በአስቸኳይ እንዲለቅ ጠይቀዋል። እስካሁን ስለበጀት ጉዳይ የተባለ ነገር የለም የሚሉት አቶ ኃይሉ፤ ነገር ግን ኮሚሽኑ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ዝርዝርና መጠን እንዲሁም ምን ላይ እንደሚያውሉት በጽሑፍ እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ገልጸዋል። "እኛ በበኩላችን ኮሚሽኑ ያቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ በመግለጽ በጀት ጸድቆ በመመሪያው መሰረት ማከፋፈልና ለተባለለት አላማ መዋሉ ኦዲት ማድረግ እንዳለባቸው ነግረናቸዋል" በማለት ከኮሚሽኑ ጋር ሳይስማሙ መለያታቸውን ተናግረዋል። የባይቶና ሊቀ መንበር አቶ ኪዳነ አመነ በበኩላቸው "ፖለቲካ ፓርቲዎች በዓመት ውስጥ መሰራት ያለባቸውን ሥራ በአንድ ወር ጨርሱ ነው የተባለው። ይህንን ለመፈጸም ደግሞ ልዩ በጀትና የሚድያ ሽፋን ያስፈልገናል" ሲል ገልጸዋል። የትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ግን "የፖለቲካ ፓርቲዎቹን ለምርጫ ቅስቀሳ የሚያስፈልጋቸውን የገንዘብ መጠን ጠይቁ ብለናቸዋል፥ አሁንም እንዲያቀርቡ እየጠበቅናቸው ነው" ብለዋል። ኮሚሽነሩ ጨምረውም የበጀት ችግር አለ የሚል ነገር እንደሌለና ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ የሚጠበቀው የወጪዎቻቸውን መጠንና ዝርዝር አቅርቡ መባላቸውን ተናግረዋል። "ነገር ግን ከህወሓት ውጪ እስካሁን በጀቱን የጠየቀ የለም" ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ለምርጫ ቅስቀሳ በተመደላቸው የአየር ሰዓት በክልሉ ባሉ የመገናኛ ብዙሃን ላይ የምረጡን ዘመቻ እተጠናቀቀ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ማካሄድ ጀምረዋል። ነገር ግን በተሻሻለው የምርጫ ሥርዓትና የምርጫ ኮሚሽን አመራሮች ላይ ያቀረቧቸው ሀሳቦች ተቀባይነት አለማግኘታቸውን በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል። ይህንንም በተመለከተ "በፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ ህወሓት ቢሸነፍም በምክር ቤቱ ያለውን ቦታ ተጠቅሞ የፈለገው ሕግ አውጥቷል" የሚሉት የሳልሳይ ወያነው አቶ ኃይሉ ከበድ ናቸው። በተጨማሪ በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም፣ በምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ታዛቢዎች እንዲሁም በድምጽ ቆጠራ ላይ ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል የሚናገሩት አቶ ኃይሉ "የጣቢያ አመራሮች በቤተ ክርስትያን ሳይቀር ህወሓትን ምረጡ እያሉ እያዘዙ ነው" ሲሉ ይከሳሉ። ቀደም ሲል የምርጫው ደንብ ውይይት ወቅት መገለል እንዳጋጠማቸው ገልጸው የነበሩት የዐሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ዶሪ አስገዶም በበኩላቸው በሚካሄዱት መድረኮች እንደማይጠሩና አንዳንድ አመራሮች በስልክ ጭምር ወደሚንቀሳቀሱበት የኢሮብ ወረዳ በመደወል ስማቸውን እንደሚያጠፉ ተናግረዋል። ህወሓት ከተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚቀርቡበትን ክሶች እንደማይቀበል በተለያየ መንገድ የገለጸ ሲሆን ቢቢሲ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ግን አልተሳካም። የክልሉ ምክር ቤት አዲስ የምርጫ ሕግ እና የሥነ ምግባር ደንብን ቀደም ሲል ያጸደቀ ሲሆን የክልሉ የምርጫ ኮሚሽንም የፓርቲና የግል ተወዳዳሪዎችን መዝግቦ ወደ እንስቃሴ ገብቷል። የትግራይ ክልል ከሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ተለይቶ ምርጫ ለማካሄድ የወሰነው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በመላው ኢትዮጵያ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ምርጫ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ከተወሰነ በኋላ ነው። ክልሉ ምርጫውን ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ እንዲያካሂድለት ቢጠይቅም ቦርዱ ቀደም ሲል በአገሪቱ ምክርቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመጥቀስ ሂደቱን ማስፈጸም እንደማይችል ካሳወቀ በኋላ ምንም እንኳን የሕጋዊነት ጥያቄ ቢነሳበትም ክልሉ የራሱን የምርጫ ቦርድ አዋቅሮ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው።
news-50501072
https://www.bbc.com/amharic/news-50501072
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡጁምቡራ በአሸባሪነት በተጠረጠረ ግለሰብ ችግር ገጠመው
ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቡጁምቡራ ውስጥ ካረፈ በኋላ በሽብር ድርጊት የተጠረጠረ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የቡሩንዲ ባለስልጣናት አረጋገጡ።
በቡጁምቡራ ያረፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን አንድ ተሳፋሪ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት በሰነዘረው ማስፈራሪያ አውሮፕላኑ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ወደሚያርፉበት የቡጁምቡራ አየር ማረፊያ እንዲቆም መደረጉም ተነግሯል። አውሮፕላኑ ዛሬ በቀጥታ በረራ ከአዲስ አበባ ወደ ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ እየበረረ ሳለ ነበር ችግሩ የተከሰተው ተብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ የበረራ ቁጥር ኢቲ817 ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ቡጁምቡራ እና ኪጋሊ ሲበር በነበረው አውሮፕላን ውስጥ የነበረ ተሳፋሪ አውሮፕላኑ ቡጁምቡራ ላይ ሊያርፍ ሲል በውሸት ቦምብ ይዣለሁ ብሎ ማስፈራራቱን ተከትሎ አለመረጋጋት ተፈጥሮ ነበር ብሏል። አውሮፕላኑ በሰላም ያረፈ ሲሆን ተሳፋሪዎችም ቢሆኑ በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ መውረድ ችለዋል ይላል መግለጫው። ፖሊስም ግለሰቡን በዓለማቀፍ የአየር በረራ ረብሻ መሰረት በቁጥጥር ስር አውሎታል። አውሮላኑ እና የበረራ ሰራተኞቹ ወደታቀደላቸው ቀጣይ በረራ መቀጠላቸውንም አየር መንገዱ ያወጣው መግለጫ ይገልጻል። በበራው ላይ የነበሩ ሰራተኞች እንዲሁም የቡጁምቡራ እና የቡሩንዲ የደህንነት ቡድኖች ላሳዩት የተቀናጀ የደህንነት ተግባርም ሊመሰገኑ ይገባል ብሏል የኢትዮጵያ አየር መንገድ። በመጨረሻም በበረራ ቁጥር ኢቲ817 ተሳፍረው ለነበሩ ደንበⶉች ላጋጠማቸው ማንኛውም አይነት መጉላላት አየር መንገዱ ይቅርታ ጠይቋል። • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፊቱን ወደ ቻይና እያዞረ ይሆን? • ቦይንግ ለተጎጂ ቤተሰቦች 100ሚ. ዶላር ሊሰጥ ነው ቢቢሲ ስማቸው እንዳይጠቀስ ከጠየቁ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ለማረጋገጥ እንደቻለው የተባለው ችግር እንዳጋጠመና ምንም ጉዳት ሳይደርስ ቡጁምቡራ አርፏል። ነገር ግን መረጃ የተጠየቁት የአየር ባልደረባ ስለክስተቱ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበው ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ ለመስጠት አልፈቀዱም። ክስተቱን በተመለከተ ለቢቢሲ ያረጋገጡት የአየር መንገዱ ባልደረባ እንደሚሉት ከሆነ "አውሮፕላኑ በአየር ማረፊያው ወታደራዊ ክፍል ውስጥ እንዲያርፍ ተደርጎ ችግሩን የፈጠረው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል።" ነገር ግን በአውሮፕላኑ ውስጥ ያጋጠመውን ችግር የፈጠረው ግለሰብ ፍላጎቱ ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ግለሰቡ ፈንጂ መያዙን በመግለጽ አውሮፕላኑን እንደሚያፈነዳው ባስፈራራበት ወቅት ከፍተኛ ፍርሃት በተሳፋሪዎቹ ዘንድ መፈጠሩን ቢቢሲ ያነጋገራቸው መንገደኞች ገልጸዋል። የቡሩንዲ የደህንት ሚኒስቴር በትዊተር ገጹ ላይ ክስተቱን አረጋግጦ "በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ተሳፍሮ የነበረ ተጠርጣሪ ሽብርተኛ ቡጁምቡራ አየር ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል" ብሏል። ክስተቱን በተመለከተ ቢቢሲ ያገኘውና እስካሁን በሁለተኛ ወገን ያልተረጋገጠው መረጃ እንደሚያመለክተው ግለሰቡ በአውሮፕላኑ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት አውሮፕላኑን እንደሚያፈነዳው በመግለጽ በማስፈራራቱ ችግሩ መከሰቱ አመልክቷል። ከዚህ አንጻር ለቢቢሲ የተናገሩት የአየር መንገዱ ባልደረባ ክስተቱ በሰላም መጠናቀቁንና በተሳፋሪዎችም ሆነ በአውሮፕላኑ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋል። በእርግጥ ግለሰቡ እንዳለው የሚፈነዳ ነገር ይዞ እንደነበረ የሚያመለክት ነገር ያልተገኘ ሲሆን፤ ለፈጸመው ድርጊትም ምክንያቱ ምን እንደሆነ እስካሁን ምንም የታወቀ ነገር የለም። አውሮፕላኑ ምን ያህል ተጓዦችን አሳፍሮ እንደነበረና ችግሩ የተከሰተው ለማረፍ በተቃረበበት ይሁን ወይም በጉዞ ላይ እንዳለ አልታወቀም። ክስተቱን ተከትሎ አውሮፕላኑ በአየር ማረፊያው ውስጥ በሚገኝ የወታደራዊ አውሮፕላኖች ማቆሚያ ክፍል እንዲቆይ እንደተደረገ ምንጮች ከቡጁምቡራ አመልክተዋል።
news-57188527
https://www.bbc.com/amharic/news-57188527
ሴቶች ከአንድ ባል በላይ ለምን አያገቡም?
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት የአገሪቱን የጋብቻ ህግ ለማሻሻል አቅዷል። በያዝነው ወርም መሻሻል አለባቸው ያላቸውን ሃሳቦች አቅርቧል።
ከነዚህም መካከል ሴቶች ሁለትና ከዚያ በላይ ባል የማግባትን እውቅናን መስጠት ነው። በእንግሊዝኛው ፖሊአንድሪ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሴቶች ከአንድ በላይ ባል ማግባት መቻልንም የሚያንፀባርቅ ሃሳብ ነው። የዚህ ህግ መሻሻል እንደ ሃሳብ የመቅረብ ሁኔታ በደቡብ አፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያን ፈጥሯል። አንድ ሚስት፣ በርካታ ባሎች ፤ ምን ችግር አለው? በሚልም የደገፉት አልታጡም። "ከዚህ ርዕስ ጋር በተገናኘ በከፍተኛ ሁኔታ የደቡብ አፍሪካ ትዊተር በከፍተኛ ሁኔታ መወያያ ሆኗል" በማለት ላታሺያ ናይዶ የተባለች ጋዜጠኛ ከኬፕታውን ተናግራለች። በአሁኑ ወቅት ይህ ማሻሻያ ህዝቡ ውይይት እንዲያደርግበትም ተመርቷል። ነገር ግን እነዚህ ማሻሻያዎች ተግባራዊ የሚሆኑ ከሆነ በተለይም ሴቶች በርካታ ባሎች ማግባት ይችላሉ የሚለው ከተፈቀደ ለአፍሪካ የመጀመሪያው ይሆናል። ምንም እንኳን ዜናውን እሰዬው ብለው የተቀበሉ ቢሆንም የተቃወሙት መኖራቸው ብዙ የሚያስደንቅ አይደለም። "ወንዶች ሴቶቻቸውን ወይም ሚስቶቻቸውን ከሌሎች ወንዶች ጋር መጋራት አይፈልጉም" በማለት የተናገሩት የአፍሪካ ክርስቲያኖች ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ የሆኑት ቄስ ኬኔት መሾ ናቸው ቄሱ አክለውም "መንግሥት በውሳኔው ላይ የሰዎችን ሃሳብ ሊሰማ ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት እኔን ጨምሮ በርካቶቻችን መጥፎ ሃሳብ ነው ብለን እናስባለን" ብለዋል። ለማንኛውም ውሳኔውን በቅርቡ የምናየው ይሆናል። የሚያመጣውንም ለውጥ እንዲሁ
news-47208149
https://www.bbc.com/amharic/news-47208149
ሩሲያ ኢንተርኔትን ለማቋረጥ እያሰበች ነው
ሩሲያ እራሷን በኢንተርኔት አማካይነት ከሚፈጸም ጥቃት ለመከላከል በምታደርገው ዝግጅት ለአጭር ጊዜ እራሷን ከዓለም አቀፉ የኢንትርኔት ትስስር የማቋረጥ አማራጭን እያጤነች ነው።
ይህም ማለት የኢንትርኔት ግነኙነት በሃገር ውስጥ ብቻ የተገደበ ይሆናል። በዚህም ሩሲያዊያን የሚልኩት እና የሚቀበሉት መረጃ እርስ በርሳው እንጂ ከተቀረው ዓለም ጋር አይሆንም። ለሙከራው የተቆረጠ ቀን ባይኖርም በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚከናወን ይጠበቃል። የተቀሩት የዓለም ሃገራት ሩሲያን ከዓለም አቀፉ የኢንተርኔት አገልግሎት ቢያገሏት በእራሷ መቋቋም የሚያስችላት ረቂቅ አሰራር እየተገበረች ነው። • ፑቲን፡ አሜሪካ ስምምነቱን ጥላ ከወጣች ሩሲያ ሚሳዬል ትገነባለች • "እንግሊዝ በእሳት እየተጫወተች ነው"ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ከዚህ ቀደም ሩሲያ የሳይበር ጥቃቶችን ታደርሳለች በማለት ማዕቀብ እንደሚጣልባት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ሩሲያ እንዴት ከተቀረው ዓለም የኢንተርኔት ትስስር እራሷን በማግለል በሃገሪቱ ውስጥ ብቻ የኢንተርኔት አገልግሎትን ማኖር ትችላለች? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው። የዘርፉ በለሙያዎች ሲያስረዱ፤ "ኢንተርኔት የሚሰራበትን መንገድ መረዳት ይገባናል" ይላሉ። "በሺህዎች የሚቆጠሩ መረጃዎች የሚተላለፉባቸው ዲጂታል ኔትዎርኮች አሉ። እንዚህ ኔትወርኮች 'ራውተር' በሚባሉ መዳረሻዎች ይገናኛሉ። ሩሲያ ያቀደችው በራውተሮች በኩል ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ እና የሚወጡ ዳታዎችን መቆጣጠር ነው።" ይህን አካሄድ በመጠቀም ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ መረጃዎችን በመቆጣጠር ረገድ ቻይና ውጤታማ ስለመሆኗ ይነገራል። • ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መፈፀም የሌለባቸው ስህተቶች • በሞባይል ኢንተርኔት መቋረጥ የተገደቡ እንቅስቃሴዎች ሆን ተብሎም ባይሆን ሃገራት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከተቀረው ዓለም ጋር የሚኖራቸው የኢንተርኔት አገልግሎት ከዚህ ቀደም ተቋርጧል። ባህር ውስጥ ያለ የኢንተርኔት ገመድ በመቋረጡ ከዚህ ቀደም አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሪታኒያ ለሁለት ቀናት ከተቀረው ዓለም ተነጥላ ነበር።
news-50683335
https://www.bbc.com/amharic/news-50683335
በኩፍኝ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
በዓለም ዙሪያ በኩፍኝ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ከ140 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸውን አንድ ይፋዊ ግምት አመለከተ።
ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት መሆናቸውም ተነግሯል። የጤና ባለሙያዎች ስለዚህ ክስተት ሲገልጹ በቀላሉ በክትባት መከላከል የሚቻል በሽታ የሰዎችን ህይወት መቅጠፍ መጀመሩ በጣም አስደንጋጭና አሳሳቢ ነው ብለውታል። • ኢትዮጵያ አሁንም 'ኩፍኝ አልወጣላትም' • ኢትዮጵያዊያን ለክትባቶች ከፍተኛ የሆነ አውንታዊ አመለካከት አላቸው ባለፉት አስራ ዘጠኝ ዓመታት በሽታውን በመከላከል በኩል ትልቅ ውጤት የተመዘገበ ቢሆንም፤ የኩፍኝ በሽታ ክስተት በተለያዩ ቦታዎች እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ሆኗል። ባለፈው ዓመት ዩናይትድ ኪንግደም፣ አልባኒያ፣ ቼክ ሪፐብሊክና ግሪክ ኩፍኝን ከአገራቸው አስወግደዋል ተብለው የተሰጣቸውን እውቅና አጥተዋል። በዚህ ባለንበት ዓመትም የኩፍኝ በሽታ ክስተት የበለጠ የከፋ ሊሆን ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። ከ25 ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ የተባለ የኩፍኝ ክስተት በአገሯ መኖሩን አሜሪካ ይፋ ያደረገች ሲሆን፤ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በማዳጋስካርና በዩክሬን ከፍተኛ ወረርሽኝ መከሰቱም ተነግሯል። በፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘው ሳሞአ የተባለችው አገር ደግሞ በኩፍኝ ወረርሽኝ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገች ሲሆን የበሽታውን መከላከያ ክትባት ያልወሰዱ ቤተሰቦች የህክምና ባለሙያዎች በቀላሉ እንዲያገኟቸው ቤታቸው ላይ ቀይ ባንዲራ እንዲሰቅሉ አዛለች። ለበሽታው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች መገርሸት እንደ ዋና ምክንያት የሚጠቀሰው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህጻናት መከላከያ ክትባቱን ባለመውሰዳቸው ነው። ኩፍኝ መስፋፋትን ለማስቆም 95 በመቶ የሚሆኑ ህጻናት ሁለት ጊዜ የሚሰጠውን ክትባት መውሰድ ይኖርባቸዋል። • ዓለማችን የኩፍኝ ወረርሽኝ ያሰጋታል • ክትባት ከየት ተነስቶ የት ደረሰ? ነገር ግን አሃዞች እንደሚያሳዩት ላላፉት በርካታ ዓመታት 86 በመቶ ህጻናት ብቻ የመጀመሪያውን ክትባት ሲወስዱ ሁለተኛውን ክትባት ደግሞ 69 በመቶዎቹ ብቻ ወስደዋል። ለምን በርካታ ህጻናት ክትባቱን እንዳላገኙ የሚቀርቡት ምክንያቶች የተወሳሰቡ ሲሆኑ፤ ይህም ከአገር አገር የተለያየ ነው። በተለይ በደሃ አገራት ውስጥ እንደ ዋነኛ ችግር ተደርጎ የሚጠቀሰው የክትባቱ አቅርቦት አለመኖር ነው። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በበሽታው ክፉኛ የተመቱት አምስት አገራት ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ላይቤሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ሶማሊያና ዩክሬን ናቸው። ሌላኛው አሳሳቢ ችግር ደግሞ ክትባቱን ማግኘት እየቻሉ ልጆቻቸው እንዳይከተቡ የሚያደርጉ ወላጆች ጉዳይም ክትባቱ የሚፈለገው ቁጥር ላይ እንዳይደርስ ማድረጉ ተነግሯል።
news-46504964
https://www.bbc.com/amharic/news-46504964
በትራፊክ አደጋ የበርካታ ወጣቶች ሕይወት እየተቀጠፈ ነው
የትራፊክ አደጋ በዓለም ዙሪያ ሕፃናትንና ወጣቶችን ለሞት በመዳረግ በአሁኑ ጊዜ ቀዳሚ ሆኖ እንደተመዘገበ የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።
ድርጅቱ ያወጣው አሃዝ እንደሚያመለክተው ከሆነ በአፍሪካ ከሌሎች አህጉራት በከፋ ሁኔታ በትራፊክ አደጋ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። የወጣው ሪፖርት እንደሚለው በርካታ የአፍሪካ ሃገራት ለተሽከርካሪዎች አስፈላጊው የፍጥነት ገደብ የላቸውም። • በዩቲዩብ 22 ሚሊዮን ዶላር የሚያገኘው የሰባት ዓመቱ ህፃን የመኪና አደጋዎች ዕድሜያቸው ከአምስት አስከ 29 ያሉ ሰዎችን ለሞት በመዳረግ ረገድ በዓለም ዙሪያ ቀዳሚው ምክንያት መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል። ይህም በትራፊክ አደጋና በተያያዥ ምክንያቶች ለሞት የሚዳረጉት ሰዎች ቁጥር በኤችአይቪ/ኤድስ፣ በሳንባ በሽታ ወይም በተቅማጥ ከሚሞቱት ሰዎች የበለጠ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳሉት "በትራፊክ አደጋ ሳቢያ የሚመዘገቡት ሞቶች ተገቢ ያልሆነና ልናስቀረው የሚገባ ነው" ብለዋል። • እንግሊዝ አጭበርባሪ ባለሀብቶችን ቪዛ ልትከለክል ነው የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከ100 ሺህ ሰዎች 26.6ቱ በትራፊክ አደጋ ለሞት ይዳረጋሉ። በአፍሪካ የሚያጋጥመው የመንገድ ላይ አደጋ በአውሮፓ ከሚያጋጥመው ወደ ሦስት እጥፍ በሚጠጋ መጠን ከፍ ያለ ነው ተብሏል። አዲስ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 1.35 ሚሊዮን ሰዎች በዓለም ዙሪያ በትራፊክ አደጋ ምክንያት ለሞት ተዳርገዋል። ይህ አሃዝም ከባለፈው ዓመት በተወሰነ መጠን ጭማሪ አሳይቷል። • ስለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚነገሩ 8 የተሳሳቱ አመለካከቶች በማደግ ላይ ባሉ ሃገራት ውስጥ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ የመሞት ዕድል ከሌሎች አንፃር ሲታይ በሦስት እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑም ተመልክቷል። በአውሮፓ፣ በአህጉረ አሜሪካና በምዕራብ ፓሲፊክ ሃገራት ውስጥ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ የሚመዘገበው የሞት መጠን መቀነሱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
50654746
https://www.bbc.com/amharic/50654746
ግሬታ ተንበርግ፡ ሰዎች 'የተቆጡ ሕጻናትን' ዝቅ አድርገው ይመለከታሉ
የአየር ጠባይ ለውጥ ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግ፣ አዋቂ ሰዎች ታዳጊዎችን በዓለም ሙቀት መጨመር ምከንያት "ማስቆጣታቸውን" ቢያቆሙ ይሻላል ስትል ተናገረች።
ተንበርግ ፖርቹጋል፣ ሊዝበን፣ ከመሄዷ በፊት በሰጠችው ቃለምልልስ ወቅት ላይ ነው እንዲህ ማለቷ የተሰማው። ግሬታ ተንበርግ ከፖርቹጋል በኋላ ወደ አሜሪካ ቨርጂኒያ እንደምታቀና ይጠበቃል። " ሰዎች የተቆጡ ሕጻናትን አቅም ዝቅ አድርገው ይመለከታሉ" ብላለች ለጋዜጠኞች። • የአየር ጸባይ ለውጥ ላይ የሚመክረው ስብሰባ ምን ይዞ ይሆን? ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል? የ16 ዓመቷ ማድሪድ ወደሚካሄደው COP25 የአየር ጠባይ ጉባዔ እያቀናች ትገኛለች። በዚህ ጉዞዋ በካይ ከሆኑ መጓጓዣዎች ራሷን ለመጠበቅ በአውሮፕላን ወይንም በመኪና ላለመጠቀም ወስናለች። ለአየር ንብረት መበከል ዝቅተኛ አስተዋጽኦ አላቸው በተባሉ መርከቦች ወደ ጉባዔው እንደምታመራ ታውቋል። ከጋዜጠኞች አዋቂዎች የተቆጣች አድርገው እንደሚመለከቷት ለቀረበላት ጥያቄ ስትመልስ " ተቆጥተናል፣ የተበሳጨነው ግን ለበጎ ምክንያት ነው" ብላለች። "እንዳንቆጣ ከፈለጉ፣ የሚያስቆጣንን ነገር ከማድረግ መቆጠብ ነው ያለባቸው" ስትልም አክላለች። ግሬታ የመጀመሪያ እቅዷ የነበረው በደቡብ አሜሪካ ቺሊ የሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነበር። ነገር ግን በደቡብ አሜሪካ ሊካሄድ የታቀደው ጉባዔ በሀገሪቱ አለመረጋጋት ምክንያት ተሰርዟል። በዚህ ምክንያት የስብሰባው ስፍራ ወደ ስፔን ሲቀየር በመርከብ ለመሄድ መወሰኗ ተሰምቷል። ግሬታ በዚህ ጉዞዋ ላይ ከአውስትራሊያዊ ዩቲዩበርና ከእንግሊዛዊቷ የመርከብ ቀዛፊ ጋር የምትጓዝ ይሆናል። መርከባቸው የፀሐይ ብርሃንና ከውሃ የሚመነጭን ኃይል እንደሚጠቀም ታውቋል። ግሬታ ተንበርግ በዘንድሮው የኖቤል ሽልማት ላይ እጩ እንደነበረች ይታወቃል።
news-55501254
https://www.bbc.com/amharic/news-55501254
ኮሮናቫይረስ፡ ቻይና የኮቪድ-19 ክትባት ለሕዝብ እንዲሰጥ ፈቀደች
የቻይና ባለሥልጣናት ቻይናዊው መድሃኒት አምራች ሲኖፋርም ያበለፀገውን የኮቪድ-19 ክትባት ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ ፈቃድ ሰጡ።
ባለሥልጣናቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ድርጅቱ በሶስተኛ ደረጃ ሙከራው ክትባቱ 79 በመቶ ውጤታማ መሆኑን አረጋግጫለሁ ካለ በኋላ ነው። በቻይና በርካታ በሙከራ ላይ ያሉ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ለአስቸኳይ ጊዜ በሚል ፈቃድ ከተሰጣቸው በኋላ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባለፈው ዓመት ሕዳር ወር መጨረሻ ላይ ከቻይናዋ ዉሃን ከተማ መነሳቱ ይታመናል። ከዚያ በኋላ በመላው ዓለም የተዛመተው የተህዋሲው ወረርሽኝ ሚሊዮኖችን ለሞት ዳርጓል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መነሻ ለማወቅ የሚደረገው ጥረት ቻይናን ከምዕራባውያን ጋር ፍጥጫ ውስጥ ጥሏትቆይቷል። አሜሪካ እና ሌሎች በርካታ አገራት ቻይና ተህዋሲው በመጀመሪያ እዚያ ሲገኝ በነበሩ መረጃዎች ላይ ሙሉ በሙሉ ግልጽነበረች ወይ ሲሉ ይጠይቃሉ። ቻይና ስለመዳህኒቱ ምን አለች? ሐሙስ እለት የቻይና መድሃኒት አምራች ኩባንያ ሲኖፋርም ያበለፀገውን ክትባት በዓለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያለውሕዝብ ለመከተብ አንድ እርምጃ ወደፊት ነው ብለው ነበር። በሐምሌ ወር ቻይና ሶስት የተለያዩ ክትባቶችን ለቁልፍ ሰራተኞች እንዲሁም ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ሰዎች ለአስቸኳይ ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በሚል ፈቃድ ሰጥታ ነበር። ይህ ክትባት እስካሁን ድረስም 4.5 ሚሊዮን ክትባት ጥቅም ላይ ውሏል። ቻይና እስከ የካቲት ወር አጋማሽ ድረስ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝቧን ለመከተብ እቅድ ይዛ እየሰራች ነው። ሲኖፋርም እንዲሁ ሌላ ሁለተኛ ክትባት እያበለፀገ ሲሆን፣ ሌሎች በርካታ ክትባቶችም እየተመረቱ ነው። አንዳንድ ባለሙያዎች ግን ለሲኖፋርም የተሰጠውን ፈቃድ በጥርጣሬ እያዩት ነው። ለዚህም አንዱ ምክንያታቸው በሙከራው ወቅት የተገኙ መረጃዎች ለሕዝብ ይፋ አለመሆናቸው ነው። በቻይና ወይንም ደግሞ በሩሲያ የተሰሩ ክትባቶች ላይ አስተያየት ለመስጠት፣ ስለጥናትና ምርመሩ በዓለም ደረጃበሚታወቁ ሕክምና ጆርናሎች ላይ የተጻፈ አልያም በመንግሥት የቀረበ እና ሂደቱን የሚያሳይ መረጃ በሌለበት፣ ከባድመሆኑን እየተናገሩ ነው። እነዚሁ ባለሙያዎች አንድን መድሃኒት በአምራቹ ኩባንያ አስተየየት ላይ ብቻ ተመስርቶ መመዘን ጦስ እንደሚኖረውምያሰምሩበታል። የኮሮናቫይረስን ባለበት ለማቆም ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ መከተብ ይኖርበታል ሲሉ ባለሙያዎችይመክራሉ። ምዕራባውያን ፋይዘር ፣ባዮንቴክ እና ሞደርና ውጤታማነቱ 95 በመቶ እና 94 በመቶ የሆኑ ክትባቶችን አምርተውበመጠቀም ላይ ናቸው። በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የተመረተው አስትራዜንካ ደግሞ በትናንትናው ዕለት በዩናይትድ ኪንግደም ጥቅም ላይ መዋልእንደሚችል የተፈቀደ ሲሆን፣ ይህም ክትባት 70 በመቶ ሰዎች የኮቪድ-19 ምልክት እንዳያሳዩ ማድረግ ይችላል ተብሏል። ቻይና ያመረተችውን መድሃኒት ለድሃ አገራት ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ለመስጠት ቃል ገብታለች። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይም፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ሲኖፋርም ያመረተውን እና ውጤታማነቱ 68 በመቶ ነው የተባለውን ክትባት መጠቀም ጀምራለች። ባሕሬን አዋቂ ዜጎቿ ኦንላየን ተመዝግበው ይህንኑ ክትባት በነጻ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርባለች። ፓኪስታን፣ ሐሙስ እለት የሲኖፋርም ክትባት በቻይና መንግሥት ፈቃድ ባገኘ በሰዓታት ውስጥ 1.2 ሚሊዮን ክትባትለመግዛት ሥምምነት ላይ ደርሳለች።
51016652
https://www.bbc.com/amharic/51016652
ኢትዮጵያና ኤርትራን ጨምሮ ሌሎች ሃገራት ገናን ለምን ታኅሣሥ 29 ያከብራሉ?
አውሮጳና አሜሪካ ገና ያከበሩት ታኅሣሥ 15 ዕለተ ረቡዕ ነበር። ኢትዮጵያና ኤርትራ እንዲሁም የተወሰኑ ሌሎች ሃገራት ግን ገናን ዛሬ [ታኅሣሥ 28] እያከበሩ ይገኛሉ።
እነዚህን ሃገራት የሚያመሳስላቸው አንድ ጉዳይ የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ነው። ሌላኛው ደግሞ የቀን አቆጣጠር። ከአፍሪካ፤ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ግብፅ [በተለይ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ እምነት ተከታዮች] ያሉ ክርስትያኖች ገናን በየዓመቱ ታኅሣሥ 29 [በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ደግሞ ታኅሣሥ 28] ያከብራሉ። አብዛኛዎቹ ምዕራባውያን ሃገራት የግሪጎሪን የቀን አቆጣጠር ነው የሚከተሉት። የቀን አቆጣጠሩን የተፈጠረው በ1582 በሊቀ-ጳጳስ ግሪጎሪ ነበር። አብዛኛዎቹ የቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረትና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ደግሞ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ45 በጁሊየስ ቄሳር የተፈጠረውን የጁሊያን ቀን አቆጣጠር የሚከተሉ ናቸው። አሁንም ቢሆን በርካታ አገራት ኦፌሴላዊ የቀን አቆጣጠራቸውን በግሪጎሪ አድርገው ለአገር አቀፍ በዓላት ጁሊያንን የሚጠቀሙ አሉ። ከላይ የተጠቀሱትን ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ግብፅን ጨምሮ፡ ግሪክ፣ ቆጵሮስና ሮማኒያ የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ግን ገናን ያከበሩት በግሪጎሪ አቆጣጠር፤ ማለትም ታኅሣሥ 15 ነው። ከላይ ካሉት 14 ሃገራት በተጨማሪ አርሜኒያ በራሷ የቀን አቆጣጠር ነው ገናን የምታከብረው። አርሜኒያ ገናን ታኅሣሥ 28 [በአራት ዓመት አንዴ 27] ታከብራለች። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የራሷ ቀን አቆጣጠር ያላት አገር ናት። የቀን አቆጣጠሩ ከኮፕቲክ ኦርቶዶክስ እምነት ቀን አቆጣጠር ጋር ተመሳሳይነት አለው። ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ገናን ከምዕራቡ ዓለም በ13 ቀናት ዘግይተው ያከብራሉ። ጥምቀትና የፋሲካ በዓልን የሚያከብሩበት ቀንም ከምዕራቡ በቀናት ልዩነት ያለው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ኢቫንጀሊካል፣ እንዲሁም ጴንጤኮስታል እምነት ተከታዮች እና ሌሎች የክርስትና እምነት ተከታዮች ገናን የሚያከብሩት ዛሬ ነው። ኤርትራ በበኩሏ ኦፌሴላዊ የቀን አቆጣጠሯን በግሪጎሪ ብታደርግም የክርስትና እምነት ተከታዮች ግን የኦርቶዶክስ ቀን አቆጣጠርን ይከተላሉ። የሩስያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የዘንድሮውን ገና ሴይንት ፒተርስበርግ የሚገኝ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ውስጥ ተገኝተው አክብረዋል በዓለማችን ያሉ የኦርቶዶክስ እምነትም ሆነ የሌሎች ክርስትና ኃይማኖቶች ተከታዮች ገና ከመድረሱ በፊት ያሉትን ቀናት በፆም እንዲሁም በፀሎት ያስቧቸዋል። የገና አከባበር ከአገር አገር የተለያየ ቅርፅ አለው። ለምሳሌ ሩስያ ውስጥ ያሉ ክርስትያኖች ከአዲስ ዓመት መባቻ እስከ ገና ያሉትን 7 ቀናት፣ በቀን 12 የተለያዩ ዓይነት ምግቦችን በመብላት ያሳልፋሉ። ዓላማው ደግሞ 12ቱን ሐዋሪያት ማሰብ ነው። ዩክሬን ውስጥ ደግሞ የበዓሉ አክባሪዎች ከቤት ቤት በመዘዋወር ዝማሬ በማሰማት ነው ቀኑን የሚያሳልፉት። ቤላሩሲያውያን ለዕለቱ ቂጣና ዓሣ ያዘጋጃሉ። ሞንቴንግሮ ደግሞ ውስጡ ሳንቲም ያለበት ድፎ ዳቦ ይደፋሉ፤ ዳቦው ሲቆረስ መልካም ዕድል ይዞ እንደሚመጣ በማመን። ሰርቢያ ውስጥ ገና የሚዘከረው ልክ እንደ ቡሄ ከጫካ ዛፍ ተቆርጦ ከተሰበሰበ በኋላ እሱን በማቃጠል በዙሪያው ተሰብስቦ እራት በመብላት ነው። ጆርጂያውያን ደግሞ ወደ አውራ ጎዳናዎች በመውጣት የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ይዘክራሉ። ኢትዮጵያም ቢሆን የበዓሉ መሠረት አንድ ቢሆንም አከባበሩ ከቦታ ቦታ ይለያያል። ነገር ግን አብዛኛው ምዕመን በዓሉን ወደ ቤተ እምነቶች በመሄድ፤ ከዚያ መልስም በጋራ ማዕድ በመቁረስ ያከብረዋል።
49706315
https://www.bbc.com/amharic/49706315
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሄዱ
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
ደሴ፣ ጎንደር እና ደብረ ታቦር ከተሞች በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታዮች ሰልፍ ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል ተጠቃሾቹ ናቸው። የሰልፉ ተሳታፊዎች በቤተክርስቲያኗ፣ በኃይማኖት አባቶች እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ይቁም የሚል መልዕክት ይዘው ወጥተዋል። • ሁለት መልክ ያለው የጅግጅጋ የአንድ ዓመት ክራሞት • "የክልሎች ልዩ ኃይልን በተመለከተ ውይይት ያስፈልጋል" የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዝደንት ቢቢሲ ያነጋገራቸውና በደሴ ከተማ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያስተባብሩ የነበሩት አቶ ሙሉጌታ አሰፋ እንደነገሩን ሰልፉ መነሻውን ከደሴ ፒያሳ በማድረግ ከሁሉም አጥቢያ ቤተክርስቲያን የተወጣጡ ምዕመናን የተለያዩ መፈክሮች እያሰሙ ወደ ደሴ መስቀል አደባባይ ጉዞ አድርገዋል። ''በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ቤተ-ክርስቲያን ያቀጠሉ እና ምዕመናንን የገደሉ ለፍርድ ይቅረቡ፣ መንግሥት ቤተ-ክርስቲያንን ሊያከብር ይገባል'' የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ሲሰሙ እንደነበር አቶ ሙሉጌታ ነግረውናል። የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ ጠዋት 12 ሰዓት አካባቢ የተጀመረ ሲሆን ቀትር 6 ሰአት ላይ ተጠናቋል። አስተባባሪው እንደሚሉት በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በግምት እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ከ150 ሺ እስከ 200 ሺ የሚደርሱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የተሳተፉ ሲሆን ''ያለምንም የጸጥታ ችግር መጠናቀቁን ማረጋጋጥ እፈልጋለው ብለዋል'' አቶ ሙሉጌታ። ''በሃገር አቀፍ ደረጃ በእምነቱ ተከታዮች ላይ እና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ከሚፈጸመው በደል ባለፈ በከተማችንም ብዙ ጥያቄዎች አሉን'' ብለዋል። ''በደሴ ከተማ ህጋዊ የሆነ ካርታና ሌሎች እንደ ግንባታ ፍቃድን የመሳሰሉ ሰነዶች ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት ግንባታቸው ተከልክሏል። ህጋዊ እስከሆንን ድረስ መከልከል የለብንም። መንግስትም አፋጣኝ ምላሽና የህግ ከለላ ያድርግላቸው'' የሚሉ መፈክሮች መሰማታቸውን አስተባባሪው ይናገራሉ። ምዕመኑ ጥያቄውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ስላቀረበ መንግስት ቢቻል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ መጠየቃቸውንም አቶ ሙሉጌታ ነግረውናል። • "ህዝብ ከህዝብ ሊጋጭ አይችልም" አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሌላኛው ያነጋገርናቸው የደብረታቦር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደሳለኝ አባተ በበኩላቸው ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ቅዳሴ ከጨረሱ በኋላ ምዕመኑ ከየአቅጣጫው ወደ መስቀል አደባባይ ማምራቱን ነግረውናል። '' የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለሃገሪቱ ያበረከተችውን ከግምት ውስጥ በማስገባትና አስተዋጾዎችዋ ተጠብቀው እንዲቀጥሉ በቤተክርስቲያኗ እና በእምነቱ ተከታዮች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መንገስት በአስቸኳይ ያስቁም'' የሚል መልዕክት በአስተባባሪ ኮሚቴው በኩል መቅረቡን አቶ ደሳለኝ ይናገራሉ። አቶ ብርሃኑ አየሌው ደግሞ የጎንደር ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ሕብረት ጸሃፊ እና የሰልፉ አስተባባሪ ሲሆኑ፤ ዛሬ በጎንደር ስለተከናወነው ሰልፍ ለቢቢሲ ሲናገሩ "ቤተክርስቲያንን ማቀጠል ኢትዮጵያን ማቃጠል ነው!፣ ቤተ-ክርስቲያን ላይ የሚደርሰው ትንኮሳ በአስቸኳይ ይቁም፣ መንግሥት የቤተክርስቲያንን ደህንነት ማረጋገጥ አለበት፣ የተቃጠሉ አብያተ-ቤተክርስቲያናትን መልሶ መገንባት ይኖርበታል። ለተጎዱም ካሳ መክፈል አለበት" የሚሉ መከክሮች ተሰምተዋል።አቶ ብርሃኑ ዛሬ ረፋድ በጎንደር በተካሄደው ሰልፍ ላይ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ምዕመናን ተሳታፊ ነበሩ ያሉ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓትም "ምዕመኑ በዝማሬ፣ በእልልታ እና በሽብሻቦ ወደየመጣበት አቅጣጫ እየተመለሰ ነው" በማለት በጎንደር እየተካሄደ የነበረው ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን ነግረውናል።
news-46573822
https://www.bbc.com/amharic/news-46573822
ሞ ሳላሕ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች በመሆን ለ2ኛ ጊዜ ተመረጠ
የግብጽ ብሔራዊ ቡድን እና የሊቨርፑል አጥቂ የሆነው ሞሐመድ ሳላህ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የቢቢሲ የዓመቱ የአፍሪካ ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል።
የ26 ዓመቱ አጥቂ ሜዲ ቤናቲያ፣ ካሊዱ ኩሊባሊ፣ ሳዲዮ ማኔ እና ቶማስ ፓርቴይን አሸንፎ ነው ሽልማቱን ያገኘው። "ታላቅ ስሜት ነው፤በሚቀጥለው ዓመትም ለማሸነፍ እፈልጋለሁ። " ሲል ሳላህ ሐሳቡን ለቢቢሲ ገልጿል። • የዘንድሮ የቢቢሲ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ዕጩዎች የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋቾች ባለፈው ዓመት ለሊቨርፑል 52 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 44 ጎሎችን ከማስቆጠርም ባለፈ ቡድኑ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ እንዲደርስ አግዟል። "በእያንዳንዱን ጊዜ ጎሎችን በማስቆጠር ቡድኑ ነጥብ እንዲያገኝ በማድረግ ቡድኑ በሊጉ አናት እንዲቀመጥ እንዳገዝኩ ይሰማኛል. . . ይህ ደግሞ ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት ይሰጣል።" ይላል ሳላህ። ሩሲያው የዓለም ዋንጫ ሁለት ጎሎችን ለግብጽ ብሔራዊ ቡድን አስቆጥሯል። ቢቢሲ ዘንድሮ በሽልማቱ ታሪክ ክብረወሰን የሆነ ከ650,000 በላይ ድምፆችን ተቀብሏል። ሳላህ ከናይጄሪያዊው ጄይ-ጄይ ኦኮቻ ቀጥሎ በተከታታይ ዓመት ሽልማቱን ያሸነፈ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። የቀድሞው የቼልሲተጫዋች በቨውሮፓዊያኑ 2017 ከሮማ ወደ ሊቨርፑል ያቀናው። በሮም ቆይታው 15 ጎሎችን አስቆጥሮ 11 ደግሞ ለጎል አመቻችቶ አቀብሏል። በዚህም ቡድኑ ከሰባት ዓመት በኋላ በሴሪአው ሁለተኛው ሆኖ አጠናቋል። ሳላህ የሊቨርፑል ሕይወቱ በድንቅ ሁኔታ ነው የጀመረው። በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው 24 ጨዋታዎች19 ግቦችን አስቆጥሯል። ሉዊስ ሱዋሬዝ (2013 -14)፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ (2007-08) እና አለን ሺረር (1979-1996) በአንድ ውድድር ዓመት ካስቆጠሯቸው 38 ጎሎች ጋር እኩል በማስቆጠር ክብረወሰኑን ተጋርቷል። ሞሐመድ ባራክት (2005) እና ሞሃመድ አቡታሪካ (2008) ሽልማቶችን ያገኙ ሌሎች ግብፃውያን ናቸው።
54270104
https://www.bbc.com/amharic/54270104
ትምህርት ፡ ፌስቡክ ላይ በተሰራጨ ምስል ምክንያት ታሪኩ የተቀየረው ቦረና የሚገኘው ትምህርት ቤት
በቦረና ዞን በዱቡሉቅ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጎዳና ጨርፊ ከጥቂት ዓመታት በፊት በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት ባለመኖሩ የተነሳ የአካባቢያቸውን ነዋሪዎች በማስተባበር ትምህርት ቤት በአቅራቢያቸው ገንብተው ነበር።
ትምህርት ቤቱ እንደሚጠበቀው በአግባቡ የተገነቡ ክፍሎች እና አስፈላጊው ነገር የተሟላለት አልነበረም። ከዚያ ይልቅ ግድግዳው ከእንጨት፣ ጣሪያው ደግሞ በላስቲክ የተሸፈና ሲሆን ጥሩ የሆነ በር እንኳን እንዳልነበረው ያስታውሳሉ። ከዚህም የተነሳ ጣሪያው ስለሚያፈስ በየዓመቱ መስከረም ሲመጣ ታድሶ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ ይደረግ ነበር። አቶ ጎዳና እንደሚሉት ትምህርት ቤቱ መቀመጫ ስላልነበረው ተማሪዎች ይቀመጡ የነበረው በዱካ በተገኘው ነገር ላይ ነበር። ነገር ግን ባለፈው ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተማሪዎቹ የደንብ ልብስና የምገባ ፕሮግራም መጀመሩን በፌስቡክ ላይ በማየታቸው በአካባቢኣቸው ያለውን ትምህርት ቤት የማሳደስ የማሳሻል ሃሳብ እንደመጣላቸው አቶ ጉዳና ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚያን ጊዜ አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር በቦረና ዞን ዱቡሉቅ ወረዳ የሚገኘውን ይህን ትምህርት ቤት የሚያሳይ ምሰልን ከአዲስ አበባ አስተዳደር ተግባር ጋር በማነጻጸር በፌስቡክ ላይ መለጠፉን ያስታውሳሉ። የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ምስሉን ተቀባበሉት። ከዚያ በኋላ በአገር ውስጥና በባሕር ማዶ የሚገኙ ሰዎች ትምህርት ቤቱን ለማደስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው መጠየቅና መወያየት መጀመራቸውን ይጠቅሳሉ። ይህንን የተመለከቱ ግለሰቦች በመሰባሰብ ኮሚቴ አንድ ኮሚቴ አዋቅረው ሃሳብ መለዋወጥ እንደጀመሩ የኮሚቴው አባል የሆኑት አቶ ዳበሶ ዋሪዮ ስለሁኔታው ለቢቢሲ ሲናገሩ "ቀልድ የሚመስለው ነገር ነው ወደ ቁም ነገር የተለወጠው" ይላሉ። "መጀመሪያ ላይ አንድ የያቤሎ ነዋሪ 30 ሺህ ብር እለግሳለሁ አሉ። ከዚያ በኋላ አሜሪካ የሚኖሩ ሰዎችም ማገዝ እንደሚፈልጉ ጻፉልኝ። እኛም በፍጥነት ኮሚቴ አዋቅረን የባንክ ሒሳብ ከፍተን አሳወቅናቸው፤ በአጭር ጊዜ አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ ብር ሰበሰብን" ሲሉ ይናገራሉ። በተሰበሰበው ገንዘብም ፈራርሶ የነበረውን ትምህረት ቤት በብሎኬት ገንብተው ለመማር ማስተማሩ ዝግጁ ማድረጋቸውን አቶ ዳበሶ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ትምህርት ቤቱን አስገንብተን የጨረስነው ሦስት ወር በሚሆን ጊዜ ውስጥ ነው። ለግንባታውም አንድ ሚሊዮን የሚሆን ብር ወጪ ተደርጎበታል፤ ገንዘቡም በፌስቡክ በኩል ባደረግነው ጥሪ የተሰበሰበ ነው።" አቶ ዳበሶ አክለውም በፌስቡክ ተጠቅመው እንዲህ አይነት የኅብረተሰቡን ችግር የመቀርፍና በቋሚነት የሚያገለግል ሥራ በመስራታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ይገልጻሉ። "ከፌስቡክ ተነስተን እንደዚህ አይነት ቁምነገር በመስራታችን ደስተኛ ነኝ፤ የኮሚቴው አባል በመሆኔም በጣም ደስተኛ ነኝ። አሁን ሁለተኛ ፕሮጀክት ጀምረናል፤ . . ." ይላሉ። የወረዳው ነዋሪ የሆኑት አቶ ጎዳና በበጭራሮ ግድግዳ በላስቲክ ጣሪያ ተማሪዎችን እውቀት ለመስጠት ሲጥር የነበረው ትምህርት ቤት በበጎ ፈቃደኞች ጥረትና ድጋፍ ገጽታው ተለውጦ በማየታቸው ደስታቸው ወደር እንደሌለው ይናገራሉ። "መጀመሪያ ልጆች የሚቀመጡበት ቦታ አልነበራቸውም፤ ደብተር የሚያስቀምጡበትም አልነበረም፤ ትልቅ ችግር ነበር። አሁን ሁሉም ስለተሟላላቸው በጣም ደስተኛ ነኝ" ሲሉ የመማሪያ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን መቀመጫ መሟላቱ የፈጠረባቸውን ስሜት ለቢቢሲ አጋርተዋል።
news-52018997
https://www.bbc.com/amharic/news-52018997
64 ኢትዮጵያዊያን ሞዛምቢክ ውስጥ በጭነት መኮና ውስጥ ሞተው ተገኙ
ከማላዊ ወደ ሞዘምቢክ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ውስጥ ቢያንስ 64 ኢትዮጵያዊያን በመተፋፈን ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን ባለስልጣናት አስታወቁ።
ዛሬ ጠዋት በሞዛምቢክ ምዕራባዊ ግዛት በምትገኘው ቴቴ በተባለችው ክፍለሃገር ውስጥ በተገኘው ተሽከርካሪ ውስጥ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 14 ሰዎች በህይወት ተገኝተዋል። "የሞዛምቢክ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ሰራተኞች የጭነት መኪናውን ሞአትዜ በተባለችው የግዛቲቱ ከተማ ውስጥ አስቁመው ሲፈትሹ ነው ሟቾቹን ያገኙት" ሲሉ የቴቴ ክፍለ ሃገር የጤና ባለስልጣን የሆኑት ካርላ ሞሴ ተናግረዋል። ባለስልጣኗ እንዳሉት በጭነት መኪናው ላይ የተሳፈሩት ሰዎች ህይወታቸው በምን ምክንያት ሊያልፍ እንደቻለ ምርመራ እየተደረገ ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያዊያኑ ህይወት ያለፈው በአየር ማጣት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል። በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምበሳደር የሆኑት አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ኢትዮጵያኑ "ከማላዊ ወደ ሞዛምቢክ ጉዞ እያደረጉ ሳለ ነው ይህ አሳዛኝ ነገር የተፈጠው ብለዋል"። አምባሳደሩ እስካሁን ባላቸው መረጃ መሠረት ኢትዮጵያውያኑ ሕይወታቸው ሊያልፍ የቻለው በኮንቴነር ውስጥ ታፍነው ነው። ከ78 ተጓዞች የ64ቱ ሕይወት ማለፉን አምባሳደሩ አረጋግጠዋል። የሞዛምቢክ ብሔራዊ ኢሚግሬሽን አገልግሎት ቃል አቀባይ የሆኑት አሜሊያ ደሪዬሮ እንደተናገሩት ሟቾቹን ያሳፈረው የጭነት መኪና ሾፌር እንዲቆም ሲጠየቅ ፍላጎት አልነበረውም ብለዋል። ጨምረውም የኢሚግሬሽን ሰራተኞቹ ከመኪናው ውስጥ ድምጽ በመስማታቸው ስደተኞች በውስጡ ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ እንዳረባቸውና እንዲቆም እንዳረጉ ገልጸዋል። ይህ የሞዛምቢክ ክፍለ ግዛት ወደ ደቡብ አፍሪካ በሕገ ወጥ መንገድ ስደተኞች በስፋት የሚዘዋወሩበት አንዱ ቦታ መሆኑ ይታወቃል። በህይወት የተረፉት 14ቱ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንደተደረገላቸው ቃል አቀባይዋ ጨምረው ተናግረዋል።
44087449
https://www.bbc.com/amharic/44087449
በፀሐይ የሚሰራው የሕዝብ ማመላለሻ ጀልባ
አካባቢን ሳይበክሉ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዴት መስጠት ይቻላል? ኢኳዶር ውስጥ ተገልለው የሚኖሩት የአኩአር ነባር ሕዝቦች ሃገር በቀል መፍትሄ አላቸው።
ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ከሚያዝያ 2017 በጀምሮ በፀሃይ ብርሃን ብቻ የምትንቀሳቀሰው አነስተኛ ጀልባ ከካፓሁኣሪ አስከ 67 ኪሎሜትር የሚረዝመው ፓስታዛ ወንዝ ድረስ በመመላለስ ራሳቸውን አግልለው የሚኖሩትን 9 የአካባዊው ሰፈራዎች ከሌሎች ሰዎች ጋር ታገናኛለች። በአካባቢው በአፈ ታሪክ በሚታወቀው ኤሌክትሪክ አመንጪ ዓሳ ስም በመነሳት ታፒያትፒያ ተብላ የተሰየመችው ጀልባ ለአማዞን ጫካ የመጀመሪያዋ በፀሃይ የምትሰራ የትራንስፖርት አማራጭ ሆናለች። የአካባቢው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት በናፍጣ የሚሰሩ ጀልባዎችን ይጠቀሙ የነበረ ሲሆን፤ ናፍጣ በጣም ውድ ስለሆነ ጀልባዎቹ ያሏቸው ቤተሰቦች ቁጥር ትንሽ ነበር። የአዲሷን ጀልባ ግልጋሎት ለማግኘት 1 ዶላር ያስከፍላል። በናፍጣ የሚሰሩት ጀልባዎች ግን ከ 5 እስከ 10 ዶላር ነበር የሚያስከፍሉት። ዋጋው አምስት እጥፍ የሆነበት ምክንያት በአካባቢው የመኪና መንገድ ባለመኖሩ ናፍጣው በትንንሽ አውሮፕላኖች ተጭኖ ስለሚመጣ ነው። የዚህች ጀልባ አገልግሎት መጀመር በዓለማችን በብዝሃ ህይወት ሃብት ትልቁን ቦታ ለሚይዘው የአማዞን ጫካ ትልቅ ፋይዳ አለው። 32 የፀሃይ ብርሃን ኃይል መቀበያዎች በጣራዋ ላይ የያዘችው ጀልባ በአንድ ጊዜ እስከ 18 ተሳፋሪዎችን መሸከም ትችላለች። የአካባቢው ሽማግሌ እና የጀልባዋ ተቆጣጣሪ ሂላሪዮ ሳንት ይህች አዲስ ግኝት የአካባቢውን ሰዎች ህይወት እየቀየረች ነው ይላል። የታመሙ ህጻናት ሲኖሩ በቀላሉ ወደ ህክምና መውሰድ ችለናል፤ ህጻናቱን ወደ ትምህርት ቤት ማመላስም ሌላው የጀልባዋ ዋነኛ ሥራ ነው ሲል ያክላል ሂላሪዮ። በሌላ በኩል ጀልባዋ ምንም አይነት ድምጽ ስለማታወጣ በአካባቢው ያሉ እንሰሳት ያለ ምንም መረበሽ ይንቀሳቀሳሉ። በተለይ ደግሞ የአካባቢው ብርቅዬ እንስሳ የሆኑት ባለ ሮዝ ቀለሞቹ የወንዝ ውስጥ ዶልፊኖችን እንደልብ ማየት ይቻላል። ሁሊያን ኢሌንስ በኢኳዶር የአኩዋር ህዝቦች ግዛት መሪ ነው፤ እሱም ቢሆን የጀልባዋ ጥቅም ቀላል እንዳልሆነ ይናገራል። እነዚህ ህዝቦች በጎረቤት ሃገር ፔሩ ድንበር ላይ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ለዘመናት የቆየ የድንበር ይገባኛል ግጭት አላቸው። የዚህች ጀልባ መምጣት ደግሞ የነዚህን ተቀናቃኝ ህዝቦች ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት ወደ ንግድ እና ትብብር ትቀይረዋለች ተብሎ ይታሰባል። ጀልባዋን በመጠቀም ከእኛ አካባቢ ሙዝ፣ ዶሮ እና ጥራጥሬዎች ይዘንላቸው መሄድ እንችላለን። እነሱ ደግሞ የተለያዩ አልባሳት እና የጎማ ተክል ይሸጡልናል ይላል ሁሊያን። ጀልባዋ በወንዝ ዳር ቆማ የአኩዋር ህዝቦች እነማን ናቸው? በአማዞን ጫካ ውስጥ በኢኳዶር እና ፔሩ ድንበር መካከል የሚኖሩ፤ 19ሺህ አባላት ያሉዋቸው ሕዝቦች ናቸው። ባህላቸው በህልሞች እና ራዕዮች ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ የሚኖሩበት ጫካ ደግሞ የራሱ መንፈስ አለው ብለው ያምናሉ። ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ህይወታቸውን ይመሩ የነበሩ ሲሆን በ1940ዎቹ ከክርስትና መምጣት በኋላ ግን ተሰባስበው በመንደር መኖር ጀምረዋል። በአሁኑ ሰዓት በአደን፣ ዓሳ በማጥመድ እና በቀላል ግብርና ሥራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። እነዚህ ነዋሪዎች ከሰለጠነው ዓለም በጣም ርቀው ስለሚኖሩ የድሮውን የኑሮ ዘይቤ እስካሁን ማስቀጠል የቻሉ ሕዝቦች ናቸው። በኢኳዶር እና ፔሩ ከመንገዶች መገንባት ጋር ተያይዞ ስልጣኔ እየገባ ሲሆን፤ የነዳጅ ዘይት ፍለጋውም አብሮ መጥቷል። ይህ ደግሞ ጫካውን ለጭፍጨፋ እያጋለጠው ነው። የኢኳዶር መንግሥት ግን የመንገዱ ግንባታ ለአኩዋር ህዝቦች የተሻለ የጤና አገልግሎት እና ትምህርት ለማቅረብ ይረዳል ሲል ይከራከራል። በሌላ በኩል በፀሃይ የምትሰራዋ ጀልባ ደግሞ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አካባቢው ተፈጥሮውን ሳይለቅ ማከናወን እንደሚቻል እያሳየች ነው።
news-56136266
https://www.bbc.com/amharic/news-56136266
ደቡብ አፍሪካ ፡ ነፍሰ ጡር ፍቅረኛው እንድትገደል ያደረገው ግለሰብ ተፈረደበት
በደቡብ አፍሪካ ነፍሰ ጡር ፍቅረኛው እንድትገደል ቅጥር ነፍሰ ገዳይ የገዛው ግለሰብ ዛሬ በጆሃንስበርግ ከተማ ተፈረደበት።
ባለፈው ሳምንት ነፍሰጡሯን የገደለው ግለሰብ 20 ዓመት እስር እንደተፈረደበት ይታወሳል። የነፍሰጡሯ ሞት የአገሪቱን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳን ጨምሮ በበርካታ ደቡብ አፍሪካውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሶ ነበር። ንቱቱኮ ንቶኮዞ ሾቦ ነፍሰጡር እጮኛው ትሼጎፋትሶ ፑሌ እንድትገደል ቅጥር ነፍሰ ገዳይ በመግዛት ተከስሶ ነበር። ሾባ ለጥፋተኝነቱ የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርብ አልተጠየቀም ተብሏል። ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር የ28 ዓመቷ ትሼጎፋትሶ ፑሌ አስከሬን አንድ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሲገኝ የተለያዩ ቦታዎች ላይ በስለት መወጋቷን የሚያሳዩ ምልክቶች አካሏ ላይ ነበሩ። ቅጥር ነፍሰ ገዳዩ የ31 ዓመቱ ምዚካይሴ ማሌፋኔ በጆሃንስበርግ በሚገኝ ችሎት ቀርቦ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የ20 ዓመት አስር ተፈርዶበታል። ወንጀሉን የፈፀመው የልጅቷ የቀድሞ ፍቅረኛ ከፍሎት መሆኑን የተናገረው ማሌፋኔ በአሁኑ ጊዜ ግለሰቡ በእስር ቤት ይገኛል ሲል ፖሊሰ ተናግሯል። ገዳይ በጠበቃው አማካኝነት ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው የክስ ማቅለያ ላይ፣ 7,000 ራንድ [የደቡብ አፍሪካ ገንዘብ] በሟች የቀድሞ ፍቅረኛ ሊከፈለው ቢጠየቅም መጀመሪያ እምቢ ማለቱን ገልጿል። ነገር ግን ክፍያው ወደ 70,000 ራንድ ከፍ ማለቱን እና መቀበሉን አስረድቷል። ማሌፋኔ ለፍርድ ቤቱ ሾባ "ባለቤቱ ስለተረገዘው ልጅ እንድታውቅ አይፈልግም ነበር" ሲል አስረድቶ ነበር። ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ሳምንት በቁጥጥር ስር የዋለውን ሾባን በነፍስ ግድያ ወንጀል፣ ለግድያ በማሴር እና ከፍትህ ለማምለጥ በመሞከር ክስ መስርቶበታል። ትሼጎፋትሶ ፑሌ በተገደለችበት ወቅት የስምንት ወር ነፍሰ ጡር ነበረች። የፑሌ አጎት የሆኑት ቱሚሳንግ ካታኬ፣ ሾባን በችሎት ፊት ቀርቦ ሲያዩት "የቆየው ቁስሌ ጠገግ ማለት ጀመረ" ብለዋል። አጎትየው ሾባ ከፑሌ ጋር ይወጡ ይገቡ እንደነበር ገልፀው ቅርርባቸው "ምን ዓይነት እንደነበር" እንደማያውቁ ተናግረዋል። እንደቤተሰቧ ከሆነ ሾባ ላልተለወደው ልጅ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለመገዛዛት ወደ ቤቱ እንድትመጣ ከጋበዛት በኋላ ፑሌ ወደ ቤቱ ሄዳ ነበር። ከዚህ በኋላ ባለመግባባታቸው ታክሲ ጠርቶ እንደሸኛት ታውቋል። በኋላ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የታክሲ ሹፌሯ የገደላት ግለሰብ ማሌፌኔ ሆኖ ተገኝቷል። አስከሬኗ በዛፍ ላይ ተሰቅሎ በጆሃንስበርግ የምንዱባን ሰፈር ነዋሪዎች ከአራት ቀን ፍለጋ በኋላ የተገኘ ሲሆን ሁለት ቦታዎች ላይ በስለት መወጋቷም ይታይ ነበር። ፖሊስ በግድያው ጠርጥረነዋል ያሉትን የ32 ዓመት ወጣት በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ወዲያው ይፋ ያደረጉ ቢሆንም ስሙን ግን ከመግለጽ ተቆጥበው ነበር። በደቡብ አፍሪካ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ በትሼጎፋትሶ ፑሌ ግድያ የተነሳ ከፍተኛ ተቃውሞ የተቀሰቀሰ ሲሆን በትዊተር ላይም #JusticeForTshego ዘመቻ ተጀምሯል። ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳም ከዚያ በኋላ ባደረጉት ንግግር የጾታዊ ጥቃትን አውግዘው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሴቶችን ሕይወት ፈተና ውስጥ ጥሎታል በማለት "ነውጠኛ ወንዶች ይህንን የተቀመጠ ገደብ እየተጠቀሙ ሴቶችን እና ሕጻናትን እያጠቁ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። በደቡብ አፍሪካ 51 በመቶ ሴቶች በሚቀርቧቸው ወንዶች የተነሳ የተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶች ያጋጥማቸዋል። ፕሬዝዳንት ራማፎሳ በአገሪቱ ከተካሄዱ በርካታ ፀረ ጾታዊ እንቅስቃሴዎች በኋላ አገራቸው "በዓለማችን ላይ ለሴቶች ምቹ ያልሆነች አገር" ሲሉ ተናግረዋል።
news-55169358
https://www.bbc.com/amharic/news-55169358
ኢራን ከተፈቀደላት በላይ ዩራኒየም ማብላላት ልትጀምር ነው
ኢራን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሰላማዊ ተግባር ነው የምትለውን የኒኩሊየር ግንባታ ማዕከሎችን የሚመረምረውን ቡድንን ላለመቀበል ወስናለች።
ይህ ብቻም ሳይሆን ዩራኒየም ማበልጸግ የምትችልበትን ጣሪያ አልፋ ለመሄድ እንደራሴዎቿ ወስነዋል። ኢራን ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ የምታደርገው በአሜሪካ የተጣለባት ማዕቅብ በ2 ወራት ውስጥ ካልተነሳላት ነው። ኢራን ዩራኒየም እንድታበለጽግ የተፈቀደላት ምጣኔ 3.67 በመቶ ብቻ ሲሆን አሁን ወደ 20 በመቶ ለማሳደግ ነው የወሰነችው። የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሩሐኒ ይህንን የምክር ቤቱን ውሳኔ እንደተቃወሙት ተናግረዋል። ይህ የሸንጎው ያልተጠበቀ ውሳኔ የመጣው የጎምቱው የኒኩሊየር ሳይንቲስቷን የሞሐሰን ፋክሪዘድን ግድያ ተከትሎ ነው። ሳይንቲስቱ ሞሐሰን የተገደሉት ባለፈው ሳምንት ሲሆን ከቴህራን ወጣ ብሎ በሚገኝ አካባቢ ከርቀት መቆጣጠርያ በተበጀለት ፍንዳታ መገደላቸውን የኢራን ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ኢራን ሳይንቲስቷን የገደለችባት እስራኤል እንደሆነች ታምናለች። እስራኤል ስለ ግድያው ለጊዜው ያለችው ነገር የለም። ጎምቱው ሳይንቲስት ሞሐሰን በኒኩሊየር ግንባታው የመሪነት ሚና የነበራቸው ሳይንቲስት እንደሆኑ ይነገራል። የኢራን መንግሥት ይህ የኒኩሊየር ግንባታ ለሰላማዊ ተግባር የሚውል ነው ይላል። የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ናታንያሁ ከዚህ ቀደም በኢራን ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ የኚህን ሟቹን ሳይንቲስት ስም አንስተው ነበር። ኢራን ከአምስቱ ኃያላን ጋር በ2015 ከተስማማችበት መጠን በላይ ዩራኒየም አብላላለሁ ወደሚለው ውሳኔ የደረሰችው አሜሪካ ከዚህ ስምምነት ወጥታ በጫነችባት ከባድ ማእቀብ የተነሳ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቷ ነው። በዚህ አዲስ በጸደቀው ሕግ ቴህራን ለአውሮጳ የስምምነቱ ፈራሚ አገራት 2 ወራት የማስጠንቀቂያ ጊዜን ትሰጣለች። በዚህ ጊዜ ውስጥ ፈራሚዎቹ የአውሮጳ አገራት አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን ማእቀብ ሊያላላ የሚችል ሁኔታን መፍጠር ካልቻሉ ሁለት እርምጃዎችን ትወስዳለች። አንዱ ዩራኒየም ለማብላላት የተፈቀደላትን መጠን አልፎ መሄድ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የተባበሩት መንግሥታትን የኑክሊየር ተቆጣጣሪ ቡድን በናታናዝና ፎርዶው የኒኩሊየር መብሊያ ጣቢያ ጉብኝትና ቁጥጥር እንዳያደርግ ማገድ ነው። የኢራን ፋርስ ዜና አገልግሎት ይህ የሸንጎው ውሳኔ ፕሬዝዳንቱ እንዲያስፈጽሙ በደብዳቤ በይፋ እንደጠየቀ ዘግቧል። ሮሐኒ የሸንጎውን ውሳኔ የዲፕሎማሲ ቀውስ የሚፈጥር ነው ሲሉ ያላቸውን ልዩነት አስቀምጠዋል። ዶናልድ ትራምፕ ከአምስትዮሹ የ2015 የኑኩሊየር ስምምነት የወጡት በግንቦት 2018 ነበር። ከዚህ በኋላ የኢራንን ምጣኔ ሀብት ክፉኛ የሚጎዳ በፋይናንስ ተቋማትና በነዳጅ ሽያጭ ላይ ያተኮረ ከባድ ማዕቀብ ጥለውባታል። አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ሰላም ስምምነቱ ለመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው ይነገራል። ይህንንም በይፋ ተናግረዋል።
news-56702735
https://www.bbc.com/amharic/news-56702735
የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፉ
የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው ከመራጩ ሕዝብ 98 ከመቶ ድምጽ በማግኘት አሸነፉ።
ብቸኛው ተፎካካሪያቸው የነበሩት ዛካሪያ ኢስማኢል ፋራህ 1.59 በመቶ ብቻ የመራጮችን ድምጽ ሊያገኙ መቻላቸው ተነግሯል። የዋነኛው ተቃዋሚ መሪው ዕጩ ባለፈው አርብ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድኔ በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ እንግልት ደርሶበታል በሚል ድምጽ ሳይሰጡ ራሳቸው ከውድድሩ አግልለው ነበር። ምርጫውን በበላይነት የመሩት የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሙሚን አሕመድ ሼክ አርብ ዕለት 177 ሺህ መራጮች ድምጽ መስጠታቸውን ተናግረዋል። በመጀመሪያ ላይ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡት ሰዎች ድምር 200 ሺህ እንደነበር ተዘግቧል። ኤስማኤል ጊሌ አሁን የ73 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ እንደ አውሮፓውያን ከ1999 ጀምሮ በጂቡቲ የፕሬዝዳንተንት የሥልጣን መንበር ላይ ቆይተዋል። የዘንድሮውን ምርጫም በከፍተኛ የበላይነት በማሸነፋቸው ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት ጂቡቲን እንዲመሩ ያስችላቸዋል ተብሏል። በቆዳ ስፋት አነስተኛ ሆና ነገር ግን በአፍሪካ ቀንድ ቁልፍ አካባቢያዊና ወታደራዊ ቦታ የያዘችው ጂቡቲ ጠቅላላ የሕዝብ ብዛቷ ከአንድ ሚሊዮን ያነሰ ነው። አሜሪካ፣ ቻይናና ፈረንሳይ በጂቡቲ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ገንብተዋል። የዓለም ባንክ በቅርብ ያወጣው አንድ መረጃ ከ14 ከመቶ በላይ የሚሆኑ ጂቡቲያዊያን በከፍተኛ የድህነት ውስጥ ነው የሚኖሩት ይላል።
news-45545756
https://www.bbc.com/amharic/news-45545756
ኢትዮጵያና ኤርትራ የመጨረሻውን የሠላም ስምምነት ፈረሙ
የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች እሁድ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር ነው የተባለ የሰላም ስምምነት ጅዳ ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ተፈራረሙ።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ ንጉሥ ሳልማንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ስለተፈረመው ስለዚህ ስምምነት ዝርዝር ይዘት ይፋ የተደረገ ነገር እስካሁን ባይኖርም፤ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ስምምነቱን "ባለሰባት ነጥብ ስምምነት" ብቻ ሲል ገልጾታል። "የጅዳው ስምምነት" ተብሎ ስለሚጠራው ስምምነት የሳኡዲ ባወጣው መግለጫ "ሁለቱ ሃገራት ሕዝብ መካከል ባለው የመልካምድር፣ የታሪክና የባህል የቅርብ ትስስር የሰላም ስምምነቱ በመንግስታቱ መካከል መደበኛ ግንኙነት እንዲፈጠር ያደርጋል" ብሏል። • ሞትና መፈናቀል በአዲስ አበባ ዙሪያ • 'መቐለ' በምፅዋ • ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ አዲስ ዓመትን በቡሬና በዛላምበሳ ሁለቱ መሪዎች ስምምነቱን በቀይ ባሕሯ የወደብ ከተማ ጅዳ ላይ በተፈራረሙበት ወቅት የሳኡዲው ንጉሥ ሳልማን፣ አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሰልማን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ተገኝተዋል። "በአፍሪካ ቀንድ ተስፋ የሚሰጥ ንፋስ እየነፈሰ ነው" ሲሉ ጉቴሬስ ከፊርማው ሥነ-ሥርዓት በኋላ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። "የሰላም ስምምነቱ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ብቻ የሚቆም ሳይሆን በኤርትራና በጂቡቲ መካከልም የሚፈፀም ይሆናል" ብለዋል። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ንጉሥ ሳልማን ለኢትዮጵያና ለኤርትራ መሪዎች አብዱልአዚዝ አል ሳኡድ የተባለውን የሃገሪቱን ከፍተኛ ሜዳሊያ አበርክተውላቸዋል። መሪዎቹ ቀደም ሲልም ተመሳሳይ የክብር ሽልማት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ተሰጥቷቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሐምሌ ወር አሥመራ ላይ በተገናኙበት ወቅት ባለአምስት ነጥብ የሰላምና የወዳጅነት ባለአምስት ነጥብ ስምምነትን በመፈራረም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ጠላትነታቸው እንዲያበቃ አድርገዋል።
news-50969790
https://www.bbc.com/amharic/news-50969790
ጊኒ ቢሳው ምርጫ፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምባሎ ፕሬዚደንት በመሆን ተመረጡ
የቀድሞው የጊኒ ቢሳው ጠቅላይ ሚኒስትር ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ ተፎካካሪያቸውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በማሸነፍ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።
ኢምባሎ በጊኒ ቢሳው ያለውን የፖለቲካ ውጥረት ለመፍታት እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል የ47 ዓመቱ ኢምባሎ ተቀናቃኛቸውን ዶሚንጎስ ሳይሞስ ፔሬራን 54 ለ46 በሆነ ድምፅ ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ፔሬራ ግን የምርጫውን ውጤት "የተጭበረበረ ነው" ብለውታል። • የኢትዮጵያዊው ጉዞ፡ ከኬኒያ የስደተኞች ካምፕ እስከ ሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ • በሙስሊሞች የሚጠበቀው የአይሁዶች ቤተ መቅደስ ኢምባሎ ከአውሮፓዊያኑ 1974 ጀምሮ በተደጋጋሚ ዘጠኝ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች በታዩበት የምዕራብ አፍሪካ አገራት ያለውን የፖለቲካ ውጥረት እልባት መስጠት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። የቀድሞው ፕሬዚደንት ጆሴ ማሪዎ ቫዝ ባሳለፍነው በፈረንጆቹ ህዳር ወር በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ነበር ከውድድር ውጭ የሆኑት። ጆሴ ሳይባረሩም ሆነ መፈንቅለ መንግሥት ሳይካሄድባቸው የሥልጣን ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የመጀመሪያ የአገሪቷ መሪ ይሁኑ እንጅ፤ ፖለቲካዊ ቀውሶችን ችላ በማለትና እንደተስፋፋ የሚነገረው ሙስና ስማቸውን አጥልቶታል። የምርጫ ዘመቻ ቡድኑ ተቀናቃኛቸውን በምርጫ መጭበርበር ከስሰዋል። ነገር ግን የምዕራብ አፍሪካ ኢኮዋስ ክሱን አለመቀበሉን ገልፆ፤ የአገሪቷ የጦር ኃይል ሥርዓት ለማስከበር በተጠንቀቅ ላይ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የምርጫ ታዛቢዎች በበኩላቸው ባለፈው እሁድ የተጠናቀቀው ምርጫ ላይ የድምፅ ማጭበርበርን የሚያመላክት ምንም ማስረጃ አለማግኘታቸውን ገልፀዋል። ይሁን እንጅ ገዥ ፓርቲ የነበረው ፔ ኤ አይ ጂ ሲ መሪ የነበሩት ፔሬይራ፤ የምርጫው ውጤት፤ "ያልተመጣጠነ፣ ጥሰት የታየበት ነው" ብለውታል። ጉዳዩንም ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚያደርሱት ዝተዋል። • ስለ ሀብት ማውራት ነውር የሆነባት አገር በቅፅል ስማቸው 'ጀኔራሉ' በመባል የሚታወቁት የተቃዋሚ ተመራጭ እና የቀድሞ የአገሪቷ የጦር አዛዥ የነበሩት ኢምባሎ ከአውሮፓዊያኑ 2016 አስከ 2018 ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል። ፕሬዚደንቱ የአገሪቷን አንድነት ለማስጠበቅ፣ የ1.6 ሚሊየን ሕዝቦች መኖሪያ የሆነችውንና ከዓለም አገራት በድህነት የምትታወቀውን አገራቸውን ለማዘመን እና ድህነትን ለመቀነስ እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል። ነገር ግን የአደንዛዥ እፅ ዝውውር፣ ድህነትና ያልተረጋጋው የአገሪቷ ፖለቲካዊ ሁኔታ ፈተና ሊሆንባቸው ይችላል ተብሏል።
news-56569258
https://www.bbc.com/amharic/news-56569258
በምዕራብ ወለጋ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 28 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 28 ሰዎች መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ገለጸ።
ማክሰኞ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በዞኑ ውስጥ በሚገኘው ባቦ ገንቤል ወረዳ በቦኔ ቀበሌ የተፈጸመውን ጥቃት ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን እንደፈጸመው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ አመልክተዋል። ቡድኑ በጥቃቱ ዕለት ከምሽቱ ሦሰት ሰዓት ላይ ከ50 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን ሰብስቦ "ጭፍጨፋ ፈፅሟል" ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። በጥቃቱ ከተገደሉት 28 ሰዎች መካከል 16ቱ ወንዶች ሲሆኑ 12ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን የተናገሩት በተጨማሪ 12 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። ጥቃቱን በተመለከተ መግለጫ ያወጣው የኦሮሚያ ክልል መንግሥትም "አሰቃቂና ዘግናኝ" ያለውን ጥቃት የፈጸመው ኦነግ-ሸኔ እንደሆነ አመልክቷል። የፖሊስ ኮሚሽነሩ አራርሳ መርዳሳም ከጥቃቱ በኋላ የክልሉ ፖሊስ በአካባቢው በወሰደው እርምጃ የታጣቂው ቡድን አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት መግለጫ በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉና የጸጥታ አካላት በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ ስለደረሰ ጉዳት ያለው ነገር የለም። ጨምሮም ቡድኑን የህወሓት ተላላኪ በመሆን በአካባቢው የመንግሥት መዋቅርን በማፍረስ በገጠርና በከተማ በመንግሥት አመራሮችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከዚህ በፊት "ዘግናኝ የሽብር ጥቃቶችን ሲፈፅም ቆይቷል" ብሏል። ቡድኑ በሚፈጽመው ጥቃት የቀበሌና የክልል አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን ያመለከተው የክልሉ መንግሥት መግለጫ፤ በጥቃቶቹ የግልና የመንግሥት ንብረቶች መውደማቸውንም ገልጿል። መንግሥት "የኦነግ ሸኔ እኩይ ተግባር ለማስወገድ በወሰደው የሕግ የበላይነትን የማስከበር እርምጃ" ቡድኑ እየተዳከመ መሆኑን በመጥቀስ ነገር ግን "በሞትና በህይወት መካከል ሆኖ የጥፋት ሴራውንና እርምጃውን ቀጥሏል" ብሏል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተለይቶ የወጣውና መንግሥት ኦነግ-ሸኔ የሚለው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። በዚህ አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሠላማዊ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ሲዘገብ ቆይቷል። በተጨማሪም በአካባቢው ባሉ የመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችና፣ የጸጥታ አካላትና አመራሮች በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች ሰለባ ሆነዋል። ለእነዚህ ጥቃቶችም መንግሥት በኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ይመራል የሚባለው ኦነግ-ሸኔን ተጠያቂ ሲያደርግ ቡድኑ ግን ግድያዎቹን አለመፈጸሙን ሲያስተባብል ቆይቷል። መንግሥት ታጣቂ ቡድኑን ከአካባቢው ለማስወገድ በተለያዩ ጊዜያት በወሰዳቸው እርምጃዎች በርካታ አባላቱን መግደሉንና መማረኩን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሉት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የጸጥታ አካላት በኦነግ-ሸኔ ላይ በተወሰዱት እርምጃ 1947 አባላቱ ሲገደሉ 489ቱ ደግሞ መማረካቸውን ተናግረዋል። በዚህም ከጥቂት ወራት በፊትም የቡድኑ መሪ የሆነው ኩምሳ ድሪባ በጸጥታ ኃይሎች መገደሉ የተነገረ ቢሆንም ከቀናት በፊት በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ላይ መታየቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
news-46806097
https://www.bbc.com/amharic/news-46806097
ሃዩንዳይ የሚራመድ መኪና አምርቷል
ሃዩንዳይ የተባለው የመኪና አምራች ድርጅት ከባድ ተፈጥሮአዊ መልክአምድር ሲያጋጥመው እግሮቹን ዘርግቶ መራመድ የሚችል 'ኤሌቬት' የተሰኘ መኪና አምርቶ ለሙከራ አቅርቧል።
መኪናው በተገጠሙለት አራት እግሮች በሰአት አምስት ኪሎሜትር መጓዝ የሚችል ሲሆን 1.5 ሜትር ከፍታ መውጣትና 1.5 ሜትር ደግሞ ወደላይ መዝለል እንደሚችል ተገልጿል። መኪናው የተፈጥሮ አደጋዎች ሲያጋጥሙ የእርዳታ ስራ ለመስራት እጅግ ጠቃሚ እንደሚሆን አምናለሁ ብሏል አምራቹ ሃዩንዳይ። • በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? • ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች የመኪናውን ጽንሰ ሃሳብ ማሳደግና የግንባታ ስራውን ማጠናቀቅ ሶስት ዓመታትን የፈጀ ሲሆን በአሜሪካዋ ላስ ቬጋስ ከተማ ለእይታ ቀርቧል። ''ከባድ አውሎ ነፋስ አልያም የመሬት መንቀጥቀጥ ሲያጋጥም፤ ለሙከራ የተሰራው አዲስ መኪና እጅግ ከፍተኛ ግልጋሎት ይሰጣል። ከፈራረሱ ህንጻዎች ስር የተጎዱ ሰዎችን ለማውጣትም ወሳኝ ነው'' ብለዋል የሃዩንዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ጆን ሱህ። 'ኤሌቬት' ማንኛውም አይነት መልክአምድርና የአደጋ ቦታዎች በቀላሉ መውጣት ስለሚችል ጎርፍና መሰል አደጋዎች ሲከሰቱም ጥቅም ላይ መዋል ይችላል ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ። • የዓለምን ትራንስፖርት የቀየረው ዲዚል ሞተር መኪናው ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ መራመድ የማይችሉና በዊልቼር ለሚንቀሳቀሱ አካል ጉዳተኞችም እርዳታ መስጠት የሚችል ሲሆን ያሉበት ድረስ በመሄድ ወደ መኪናው እንዲገቡ ማድረግ ይችላል ተብሏል።
news-52423905
https://www.bbc.com/amharic/news-52423905
ከኮሮናቫይረስ ለማገገም ምን ያክል ጊዜ ሊወስድብዎ ይችላል?
ኮቪድ-19 ባለፈው ታህሳስ የተከሰተ ወረርሽኝ ነው። ነገር ግን ለአንዳንድ በሽተኞች ከቫይረሱ ለማገገም ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድባቸው ይችላል።
የአንድ ሰው የማገገም ሂደት በበሽታው ምን ያህል ተጠቅቷል የሚለው ላይ የተመረኮዘ ነው። አንዳንድ ሰዎች ከሽታው ወዲያውኑ ሊድኑ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ የበሽታው ስቃይ አብሯቸው ሊዘልቅ ይችላል። ዕድሜ፣ ፆታ እንዲሁም ሌሎች ነገሮች ሰዎች በበሽታዎች የመጠቃት ዕድላቸወን ሊወስኑ ይችላሉ። መካከለኛ የህመም ስሜት ብቻ ከሆነ ያለኝስ? ኮቪድ-19 የያዛቸው በርካታ ሰዎች መካከለኛ የህመም ስሜት ያዳብራሉ - እነዚህ ምልክቶች ሳልና ትኩሳት ናቸው። አልፎም ሰውነት ማሳከክ፣ ድካም፣ ጉሮሮ ማሳከክ እና የራስ ምታት ሊያጋጥማቸው ይችላል። ሳል መጀመሪያ ሲጀመር ደረቅ ያለ ነው። ትንሽ ቆይቶ ደግሞ አክታ የተቀላቀለበት ይሆናል። አክታው ቫይረሱ የገደላቸው የሳንባ ሴሎችን ይዞ ይወጣል። እነዚህ ምልክቶች በቂ እረፍት በማድረግ፣ ፈሳሽ በመጠጣትና በፓራሲታሞል ክኒን ማከም ይቻላል። መካከለኛ የህመም ስሜት ያላቸው ሰዎች በቀላሉ ሊያገግሙ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ትኩሳቱ ቶሎ ሊለቅ ይችላል፤ ሳሉ ግን ትንሽ ሊቆይ ይችላል፤ በአጠቃላይ ግን በሁለት ሳምንት ውስጥ ሊያገግሙ ይችላሉ ይላል። ከበድ ያለ የህመም ምልክት ካለብኝስ? አንዳንድ ሰዎች ከበድ ያለ ሕመም ሊያጋጥማቸው ይችላል። ቫይረሱ ከያዛቸው በ10 ቀናት ውስጥ ከበድ ያሉ ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላሉ። ለውጡ ድንገተኛ ሊሆን ይችላል። መተንፈስ አዳጋች ይሆናል። ይህ የሚሆነው የሰውነት መከላከል አቅም ከቫይረሱ ጋር በሚያደርገው ትግል ምክንያት ነው። አንዳንድ ሰዎች ሆስፒታል ገብተው ኦክስጂን ሊያስፈልጋቸው ይችላል። አጠቃላይ ሐኪሟ ሳራህ ጃርቪስ «የትንፋሽ እጥረት እስኪስተካከል ጊዜ ሊወስድ ይችላል» ይላሉ። ሐኪሟ ቢያንስ ስምንት ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ይጠቁማሉ። የፅኑ ህሙማን ክፍል መግባት ቢኖርብኝስ? የዓለም የጤና ድርጅት ከ20 ሰዎች አንድ ሰው ወደ ፅኑ ሕሙማን ክፍል ገብቶ በማደንዘዣና ቬንቲሌተር መታከም ሊኖርበት ይችላል ይላል። ከፅኑ ሕሙማን ክፍል ከወጡ በኋላ ወደ መደበኛ መታከሚያ ይወሰዳሉ። ከፅኑ ሕሙማን ክፍል የሚወጡ ሰዎች እስከ 18 ወራት የማገገሚያ ጊዜ ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ነገር ግን ከዚህም ባነሰ ወቅት ሊያገግሙ የሚችሉ ሰዎች ይኖራሉ። ቫይረሱ የዘለቄታ ጤና ላይ ያለው ጉዳትስ? ኮሮናቫይረስ በዘለቄታዊ ጤና ላይ ያለው ጉዳት አልተለየም። ነገር ግን አንዳንድ ጠቋሚ ክስተቶች የሚያሳዩትን ተመርኩዞ መገመት ይቻላል ይላሉ ባለሙያዎቹ። 'አርድስ' የተሰኘ የመትንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ በሽታን ተከትሎ ሳንባ ሊጎዳ ይችላል። ሌላኛው የጤና ባለሙያዎች የሚመክሩት ነገር በሽተኞች የአእምሮ ጤናቸውንም እንዲታዩ ነው። ምክንያቱም ሆስፒታል ውስጥ አእምሮ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉና። ሌላኛው ደግሞ ድካም ነው። መካከለኛ ምልክት ያሳዩ ሰዎች እንኳ ረዘም ላለ ጊዜ የድካም ስሜት ላይለቃቸው ይችላል። የጆንስ ሆፕኪስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ እንደሚያሳየው እስከዛሬ [ሚያዝያ 17/2012] ድረስ ከ2.8 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች መካከል 795 ሺህ ያህል ሰዎች አገግመዋል። ይህ ይፋዊ መረጃ ይሁን እንጂ ቁጥሩ ከዚህም ሊልቅ እንደሚችል ይነገራል። ኮቪድ-19 ድጋሚ ሊይዘኝ ይችላል? ኮቪድ-19 ድጋሚ ሊይዝ እንደሚችል በሰፊው ቢነገርም ምንም ማረጋገጫ አልተገኘም። በሽተኞች ቫይረሱን ተዋግተው ካሸነፉ ከዚያ በኋላ የመከላከል አቅማቸው ሊዳብር እንደሚችል ይታመናል። ድጋሚ ተይዘዋል ተብለው የታሰቡ ሰዎች ምናልባትም የምርመራ ስህተት አጋጥሞ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
news-54067731
https://www.bbc.com/amharic/news-54067731
ቻይና የሕንድ ወታደሮች "ተኩሰውብኛል" ስትል ከሰሰች
ቻይና የሕንድ ወታደሮች በህገወጥ መልኩ ድንበሯን አቋርጠው በጥበቃ ላይ የነበሩ ወታደሮች ላይ "ጠብ አጫሪ" የማስጠንቀቂያ ተኩስ መተኮሳቸውን በመግለጽ ከሰሰች።
የቻይና ወታደሮች "አፀፋውን ለመመለስ" ተገድደው ነበር ያሉት የጦር ኃይሉ ቃል አቀባይ በትክክል ስለወሰዱት እርምጃ አልገለፁም። ሕንድና ቻይና በአጨቃጫቂው ድንበር አቅራብያ መሳሪያ ላለመተኮስ የገቡትን ስምምነት በጣሰ መልኩ መሳሪያ ሲተኮስ ከ45 ዓመት ወዲህ የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም ተብሏል። ከቅርብ ወራት ወዲህ የሁለቱ አገራት ግንኙነት እያሽቆለቆለ መጥቷል። የቻይና መገናኛ ብዙኀን እንደዘገበው ከሆነ፣ " የሕንድ ወታደሮች በሺንፓኦ ተራራ አካባቢ በሕገወጥ መልኩ ድንበር አቋርጠዋል" ሲል የዜጎች ነፃነት ጦር ቃል አቀባይ የሆኑትን ኮሎኔል ዛንግ ሹኢሊን በመጥቀስ ዘግቧል። የሕንድን እርምጃ " ሁለቱ አገራት የገቡትን ስምምነት ፍፁም የሚጥስ፣ ውጥረትን የሚያነግስ. . . እና በባህሪው ጠብ አጫሪ የሆነ" ብለውታል ቃል አቀባዩ። የሕንድ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ምንም ኣይነት ምላሽ አልሰጡም። እንደ አውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ1996 ሁለቱ አገራት፣ ምንም እንኳ ወታደሮቻቸው ተጋጭተው የሚያውቁ ቢሆንም፣ የጦር መሳሪያ በድንበር አካባቢ ላለመጠቀም ተስማምተው ነበር። የጦር ኃይሉ ቃል አቀባይ በሕንድ ወገን " በአስቸኳይ አደገኛ የሆነ እንቅስቃሴያቸውን እንዲያቆሙ፣ ድንበርን ተሻግረው መሳሪያ የተኮሱትን ወታደሮች ከስፍራው እንዲያስወጡ. . . እና ጠብ አጫሪ የሆነ ተኩስ የከፈቱት ላይ ተገቢው ቅጣት እንዲጣልባቸው" ሲሉ ጠይቀዋል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ውጥረት መታየት የጀመረው፣ ሕንድ የቻይና ባለስልጣናትን በአጨቃጫቂው ድንበር አካባቢ አምስት ንፁኃን ዜጎች በወታደሮቻቸው ታግተው መወሰዳቸውን ካስታወቁ በኋላ ነው። በሰኔ ወር 20 የሕንድ ወታደሮች ከቻይና ወታደሮች ጋር ተጋጭተው ሕይወታቸውን ካጡ በኋላ በአካባቢው ውጥረት ተባብሷል። የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ወታደሮቹ "ክፉኛ ተደብድበዋል።" በነሐሴ ወር ሕንድ ቻይናን በድንበር አካባቢ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወታደራዊ ውጥረት እንዲፈጠር እያደረገች ነው ስትል ከስሳ ነበር። ሁለቱንም ክሶች ቻይና ያጣጣለች ሲሆን በድንበር አካባቢ የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ የሕንድ ጥፋት ነው ብላለች። በቻይናና በሕንድ መካከል ያለው አጨቃጫቂ ድንበር በአግባቡ የተሰመረ እንዳልሆነ ይጠቀሳል። በአካባቢው ወንዞች፣ ሐይቆችና በረዶ መኖሩ ድንበሩ መስመር እንዲተጣጠፍ ያደርጋል። በሁለቱም ወገን የሚገኙ ወታደሮች፣ በዓለም ላይ የሚገኙ ሁለት ትልልቅ የጦር ኃይሎችን የሚወክሉ ሲሆን፣ በርካታ ጊዜያት ተፋጥጠው ያውቃሉ። ሕንድ ቻይናን በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ድንበር በማስጠጋት ደጋግማ ከስሳለች። በሁለቱ መንግሥታት መካከል ላለፉት ሶስት አስርታት ንግግር ቢደረግም የድንበር ይገባኛል ጥያቄውን መፍታት አልተቻለም። ሁለቱ አገራት በ1962 አንዴ ብቻ ውጊያ ያደረጉ ሲሆን ሕንድ ሽንፈትን ተጎናጽፋለች።
news-51232623
https://www.bbc.com/amharic/news-51232623
የዶስ ሳንቶስ ኢሳቤላ የሒሳብ ባለሙያ ሞቶ ተገኘ
አገሯን በሙስና አራቁታለች ተብላ ክስ የተመሰረተባት የአፍሪካ ሃብታሟ ሴት የሒሳብ ባለሙያ በፖርቹጋል ሞቶ ተገኘ።
ይህ የሂሳብ ባለሙያ በኢሳቤላ ዶስ ሳንቶስ የክስ መዝገብ ላይ ተጠርጣሪ ተብሎ ስሙ ተጠቅሶ ነበር። የ45 ዓመቱ ኑኖ ሪቤኢሮ ዳ ኩሃን የተባለው የሒሳብ ባለሙያ በኢሳቤላ ዶስ ሳንቶስ ሊቀመንበርነት ይመራ የነበረው ሶናንጎል የተባለው በአንጎላ የነዳጅ ዘይት አምራች ኩባንያ ገቢ ወጪዎችን ይቆጣጠር ነበር። የአፍሪካ ባለጸጋዋ ሴት አገሯን በሙስና እንዴት እንዳራቆተቻት የሚያመላክቱ መረጃዎች ሲወጡ ነበር። ኢሳቤል ዶስ ሳንቶስ የቀድሞው የአንጎላ ፕሬዝዳንት ልጅ ስትሆነ የአንጎላ መንግሥት የሙስና እና ማጭበርበር ክሶች መስርቶባታል። የሒሳብ ባሙያው ሞት የተሰማውም የአንጎላ ጠቅላይ አቃቤ ሕጎች ሁለቱን ግለሰቦች በወንጀሎቹ ተጠርጣሪ መሆናቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው። የፖርቹጋል ፖሊስ እንዳለው የሂሳብ ባለሙያው ሞቶ የተገኘው በመዲናዋ ሊስበን ከሚገኙ መኖሪያ ቤቶች በአንዱ ሲሆን፤ "ሁሉም ነገር የሚጠቁመው ሕይወቱን በራሱ እጅ ስለማጥፋቱ ነው" ብለዋል። የፖርቹጋል መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ የሂሳብ ባለሙያው ከአንድ ወር በፊትም እራሱን ለማጥፋት መሞከሩን ዘግበዋል። ኢሳቤላ ዶስ ሳንቶስ የቀረቡባትን ክስ "ፈጽሞ አሳሳች እና ሃሰተኛ" ስትል ታጣጥላለች። ኢዛቤል ዶስ ሳንቶስ በመሬት፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ ዘይት ዘርፍ በመሰማራት የመንግሥትን እጅ በመጠምዘዝ ከድሃ አንጎላዊያን ጉሮሮ እየነጠቀች ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንዳካበተች ይነገራል። በተለይ አባቷ በመንግሥት ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የኢንቨስትመንት አማራጮች ለእርሷ ብቻ ተብለው የሚከፈቱና የሚዘጉ ነበሩ። ከነዳጅ ጋር በተያያዘ አንድ የለንደን የነዳጅ አውጭ ኩባንያ በአገሯ እንዲሰራ በተጭበረበረ መንገድ ሲገባ ወይዘሮ ዶስ ሳንቶስ የትወናው አካል ነበረች። በኋላ አባቷ ከሥልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ ኩባንያው ሲታገድ 58 ሚሊዮን ዶላር የከፈለችበት ደረሰኝ ተገኝቷል። ይህ ለምን እንደተፈጸመና ድርሻዋስ ምን ነበር የሚለው ያልተመለሰ ጥያቄ ነው። የወይዘሮ ኢሳቤላ ዶስ ሳንቶስ ጉዳይ በዚህ አያበቃም። አንድ ዱባይ ከሚገኝ ኩባንያ ጋርም በተመሳሳይ ተመሳጥራ ሁለት የክፍያ ሰነዶች እንደተላኩላት ማግኘት ተችሏል። ይህ ሕጋዊነት ይጎድለዋል የተባለው የክፍያ ሰነድም ለምን ክፍያው እንደሚፈጸም የሚያትተው ነገር የለም። በዚህ የሂሳብ መጠየቂያም በአንደኛው 472,196 ዩሮ ሁለተኛው ደግሞ 928,517 የአሜሪካን ዶላር ተጠይቆበታል። ይህም ሰነድ ሕጋዊነቱ ያልተረጋገጠ ቢሆንም ወይዘሮዋ ግን ሕጋዊ መንገድን ተከትየ የፈጸምኩት ነው ብላለች። ለኢሳቤላ የተላከ ሰነድ ሌላኛው ከነዳጅና ኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ለኢሳቤላ የቀረበው ክስ በ2006 የአንጎላ የኃይል አቅርቦት ለመሥራት ስትስማማ በወቅቱ 15% ብቻ ከፍላ ቀሪው ዝቅተኛ ወለድ ተደርጎላት በተራዘመ ጊዜ እንድትከፍል ነበር። ላለፉት 11 ዓመታት ግን መክፈል የነበረባትን 70 ሚሊዮን ዶላር አልከፈለችም። አሁን ኢሳቤላ በባለድርሻነት የምትመራው ኩባንያ አጠቃላይ ዋጋው 750 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። ተቋሟ እዳውን በ2017 ለመክፈል ተስማምቶ ነበር፤ ነገር ግን ቢያንስ ወለድ ተብሎ የታሰበውን 9 በመቶ ማካተት ስላልቻለ ክፍያው እንዳይፈጸም ተደርጓል። ከአልማዝ ጋር በተያያዘ በሙስና ሥራው ኢዛቤል ብቻዋን አትሳተፍም። ባሏም አጋሯ ነው። በ2012 ባለቤቷ ሲንዲካ ዶኮሎ መንግሥት ከሚቆጣጠረው ሶዳየም ከሚባለው የአልማዝ ኩባንያ ጋር የአንድ ወገን ፊርማ ፈርሟል። በፊርማው መሰረት ሁለቱ ፈራሚዎች የፕሮጀክቱን ወጪ ግማሽ ግማሽ መቻል ነበረባቸው። ነገር ግን ሙሉ ወጭው የተሸፈነው በመንግሥት ነው። ሰሞኑን የሚዲያዎች እጅ ላይ የገባው መረጃ እንደሚያሳየው ከ18 ወራት በኋላ ዶኮሎ 79 ሚሊዮን ዶላር መክፈል ሲገባው የከፈለው የገንዘብ መጠን ግን 4 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ይባስ ብሎ ደግሞ ጉዳዩን ስለደለልኩ ሽልማት ይገባኛል ብሎ ከዚሁ ፕሮጀክት ውስጥ የኢሳቤል ባለቤት ዶኮሎ ተጨማሪ 5 ሚሊዮን ዶላር ራሱን ሸልሟል። ከዚህ ስምምነት የአንጎላ ሕዝብ የሚያገኘው ጥቅም ምንም ሲሆን በአንጻሩ ለኩባንያው መሥሪያ ተብሎ ከግል ባንክ ለተበደሩት 200 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ይከፍላሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የአንጎላ መንግሥት አልማዝ በዝቅተኛ ዋጋ መሽጡን ቢያምንም ምንጮች እንደሚሉት ግን እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ከስሯል። ከዚህ ጀርባ ማን ሊኖር ይችላል ሲባል ደግሞ የብዙዎቹ ግምት ኢሳቤላ ዶስ ሳንቶስና ባለቤቷ መሆናቸውን አብዛኛው የአገሬው ሰው ይረዳዋል። ኢሳቤላ እና ባለቤቷ ከመሬት ጋር በተያያዘ ወይዘሮ ዶስ ሳንቶስ መሬት ላይም ሁነኛ ተሳታፊ ናቸው። መረጃው እንደሚያሳየው ወይዘሮ ዶስ ሳንቶስ በ2017 በዝቅተኛ ዋጋ መሬት እንድትገዛ መንግሥት አመቻችቶላታል። ይህንን በመዲናዋ ሉዋንዳ የባህር ዳርቻ የሚገኘውን ጋሻ መሬት የገዛችውም በአባቷ ረጅም እጅ በመታገዝ ነበር። ኮንትራቱ የሚለው መሬቱ 96 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ነው። ወይዘሮ ዶስ ሳንቶስ ያወጣችው ግን 5 በመቶ ብቻ ነው። ምስኪን ቦታው ላይ የነበሩ አንጎላዊያን ግን ይዞታቸው ለወይዘሮ ዶስ ሳንቶስ በመሰጠቱ ከነበሩበት ዋና ከተማዋ ሉዋንዳ 50 ኪሎ ሜትር ርቀው ተጥለዋል። ከመሬት ጋር በተያያዘ በሌላ የኢሳቤላ ዶስ ሳንቶስ ፕሮጀክት ከ500 በላይ ቤተሰብ በእርሷ ምክንያት ተፈናቅሏል። ከቴሌኮም ዘርፍ ጋር በተያያዘ ቢሊየነሯ ከቴሌኮም ዘርፍም አንጎላ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ አግበስብሳለች። በአገሪቱ ከፍተኛው የሞባይል ስልክ አቅራቢ ኩባንያ ውስጥ 25 በመቶ ድርሻ አላት። ዩኒቴል የተባለው ይህ ኩባንያ በቅርቡ ለኢሳቤላ 1 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ የሰጣት ሲሆን ቀሪ ሀብቷም ሌላ 1 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ተብሏል። ይሁንና ሴትዮዋ ከዘርፉ ገንዘብ የምታገኝበት ይህ ብቸኛ መንገድ አይደለም።
news-51296036
https://www.bbc.com/amharic/news-51296036
40 ዓመት በስደት የቆዩትን ጨምሮ ከ2ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሊመለሱ ነው
ለበርካታ ዓመታት በስደት ኬንያ ውስጥ የቆዩ ከሁለት ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን በፍቃዳቸው ወደ አገራቸው ሊመለሱ መሆኑን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገለጸ።
በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም ለቢቢሲ እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊያኑ በራሳቸው ፍላጎት ለበርካታ ዓመታት ከቆዩባቸው የዳዳብና የካኩማ ስደተኛ ካምፖች ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚያስችላቸው ድጋፍና ዝግጅት እየተደረገ ነው። አምባሳደሩ እንዳሉት በተለያዩ ምክንያቶች የተሰደዱት እነዚህ ኢትዮጵያዊያን ለረጅም ጊዜ በስደተኛ ካምፖቹ ውስጥ የቆዩ ሲሆኑ ከመካከላቸውም ከ40 ዓመት በላይ ከአገራቸው ወጥተው በስደት የኖሩ ይገኙባቸዋል ብለዋል። የኢትዮጵያዊያኑን ጉዳይ ለመከታተልና አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ በቅርቡ ወደ ዳዳብና ካኩማ የስደተኞች ካማፕ አቅንተው እንደነበረ ለቢቢሲ የተናገሩት አምባሳደር መለስ፤ "ስደተኞቹን የመመለሱ ሥራ ሙሉ በሙሉ ያለምንም ጫና በራሳቸው ፍላጎት የሚከናወን ነው" ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ካኩማና ዳዳብ በተባሉት የስደተኛ ካምፖች ውስጥ ባለፉት ዓመታት በፖለቲካዊና ሰብዓዊ ተግዳሮቶች ምክንያት አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ይገኙባቸዋል። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽንና ከኬንያ መንግሥት ጋር በመተባበር ወደ አገራቸው የመመለስ ፍላጎት ያላቸውን ስደተኞች ለመርዳት የሚያስፈልጉ ተግባራትን በማከናወን የመጀመሪያ ዙር ተመላሾችን በዚህ ሳምንት ማብቂያ ላይ ለመመለስ አቅዷል። አምባሳደር መለስ እንደጠቀሱት በመጀመሪያው ዙር 85 በሁለተኛው ዙር ደግሞ ከ2ሺህ በላይ ስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ዝግጅት ተደርጓል። ከእነዚህ መካከል ከሰባት ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው 400 ህጻናት ይገኙበታል ተብሏል። አምባሳደሩ አክለውም የኢትዮጵያ መንግሥትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወደ አገራቸው ለሚመለሱት ኢትዮጵያዊያን አስፈላጊ የሆነ ድጋፍ በማድረግ ወደ ቀድሞ አካባቢያቸውና ኑሯቸው እንዲመለሱ ያደርጋሉ። በኬንያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲም ወደ አገራቸው ለመመለስ ፍላጎት ላላቸው ኢትዮጵያዊያን አስፈላጊ የሆኑ የጉዞ ሰነዶችን እንዳዘጋጀና ለዜጎቹ ጥያቄ ምላሽ እየሰጠ መሆኑ ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ጋር ኬንያን ጨምሮ በሌሎች የአካባቢው አገራት ውስጥ የሚገኙ ስደተኞችን በፈቃዳቸው ለመመለስ የሚያስችል የመግባባያ ሰነድ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ተፈራርመው ነበር። ይህ በአሁኑ ጊዜ የሚከናወነው ፍቃደኛ ኢትዮጵያዊያንን ወደአገራቸው የመመለሱ ሥራ የተጀመረው ስምምነቱን ተከትሎ በኬንያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በስደተኛ ካማፖቹ ውስጥ ያሉትን ኢትዮጵያዊያን ፍላጎት በመረዳትና አስፈላጊውን ነገር በማዘጋጀቱ መሆኑ ተገልጿል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ እየወሰደችው ባለው ፖለቲካዊ የለውጥ እርምጃና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስደት የሚገኙ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ባቀረቡት ተከታታይ ጥሪ በርካቶች እየተመለሱ መሆኑ ይነገራል።
news-51277957
https://www.bbc.com/amharic/news-51277957
አንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ ኬንያ ውስጥ ተገኘ
ከአንድ መቶ በላይ ሰዎችን የገደለውና ወደ ተለያዩ የዓለም አገራት እየተዛመተ ባለው ቫይረስ የተጠረጠረ አንድ ኬንያዊ ተለይቶ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ተገለጸ።
ከኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ጋር የሚመሳሰል ምልክቶች የታዩበት ይህ ኬንያዊ ተማሪ ለትምህር ቻይና ቆይቶ እንደተመለሰ ተነግሯል። ተማሪው ከቻይና እንደተመለሰ የገዳዩ በሽታ የሚመስሉ ምልክቶች እንደታዩበት እንደታወቀ ዋና ከተማዋ ናይሮቢ ውስጥ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስዶ ከሌሎች ህሙማን ተለይቶ ክትትልና ህክምና እየተደረገለት ይገኛል። • የኮሮናቫይረስ እየተዛመተ ነው፤ የሟቾች ቁጥርም ጨምሯ • ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች • ቻይና በ 6 ቀናት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ልትገነባ ነው የሆስፒታሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ህዝቅኤል ጊካማቢ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው ተማሪ ከቻይናዋ ጓንግዡ ግዛት በኬንያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተሳፍሮ ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ጆሞ ኬንያታ አየር ማረፊያ መግባቱን ገልጸዋል። በአየር ማረፊያው ውስጥም በበሽታው የሚያስጠረጥሩ ምልክቶች እንደታዩበት በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ መደረጉን አመልክተዋል። ይህ ከአደገኛው ኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አፍሪካ ውስጥ የተገኘ የበሽታው ሁለተኛው ተጠርጣሪ ሲሆን በኬንያ ውስጥ ግን የመጀመሪያው ነው ተብሏል። በጉዳዩ ላይ የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እስካሁን ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።
news-51993760
https://www.bbc.com/amharic/news-51993760
በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች
የኮሮናቫይረስ ወርሽኝ በዓለም ሕዝብ ላይ ፈተናን በደቀነበት በዚህ ጊዜ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ እየሞቱም ነው፤ ከተሞችና አገራትም እንቅስቃሴዎችን በሙሉ አግደው ተቆልፈዋል።
ብዙዎችም ራሳቸውን ለይተው ተቀምጠዋል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በረራዎች በስፋት እየተሰረዙ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩም ሠራተኞች ከቤታቸው እየሰሩ ነው። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ጭንቅ ውስጥ ተስፋ የሚሰጡ ነገሮች አልታጡም። 1.የአየር ብክለት መቀነስ አገራት እንቅስቃሴዎችን ሲገቱ የአየር ብክለ በከፍተኛ መጠን መቀነሱ እየተገለፀ ነው። በቻይናም ሆነ በሰሜናዊ ጣልያን አየርን በከፍተኛ ደረጃ የሚበክለው ናይትሮጅን ዳይኦክሳይድ በጣም ቀንሷል። ይህ የሆነው የኢንዱስትሪዎች እንቅስቃሴ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በመገታቱ ነው። ኒውዮርክ የሚገኙ አጥኚዎች ለቢቢሲ እንደገለፁት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በተለይም ከመኪናዎች ሚወጣው ካርቦን ሞኖክሳይድ በ50 በመቶ ቀንሰሷል። 2.የመተላለፊያዎች ከሰዎች ጭንቅንቅ ነፃ መሆን የባህር ላይ ጉዞዎች በመቀነሳቸውም ውሃዎች ንፁህ እየሆኑ መምጣታቸው ሲነገር በጣልያኗ ቬኒስ ከተማ የሚያቋርጠው ውሃም ይህው ለውጥ እንደታየበት ነዋሪዎች ገልፀዋል። ይህ የሆነው ለወትሮው በቱሪስቶች በሚጨናነቁት የሰሜናዊ ጣልያን ጎዳናዎች ኦና በመሆናቸው ዝቃጮች በመቀነሳቸው ነው። የወሃው አካላት ንጹህ እየሆኑ መምጣት ውሃ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አሳዎችን በግልፅ ማየት ማስቻሉም እየተገለፀ ነው። 3.የደግነት ተግባራት ምንም እንኳ የቫይረሱ ስርጭትን እየጨመረ መሆኑን ተከትሎ የጥድፊያና የድንጋጤ ግብይቶች ብዙዎችን ላላስፈላጊ ንግግርና ብሎም ድብድብ ቢጋብዝም ኮሮናቫይረስ ዓለም ላይ ደግነትን በስፋት ቀስቅሷል ማለት ይቻላል። ሁለት የኒውዮርክ ነዋሪዎች በ72 ሰዓታት ውስጥ ብቻ አስፈላጊ የፍጆታ እቃዎችን እንዲሁም መድሃኒቶችን ለአዛውንቶችና ለሌሎች ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በፍቃደኝነት የሚያደርሱ 1300 በጎ ፍቃደኞችን ማሰባሰብ ችለዋል። ፌስቡክ እንዳለው በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በእንግሊዝ ውስጥ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ በሚደረገው የበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ በፈቃደኝነት ለማገልገል ዝግጁ ሆነዋል። ተመሳሳይም በጎ ፍቃደኞች ካናዳ ውስጥ ሌሎችን ለመርዳት የሚኣስችላቸውን ቡድን መመስረታቸው ተገልጿል። የአውስትራሊያ ሱፐርማርኬቶች "የአዛውነቶች ሰዓት" በማለት አዛውነቶችና አካል ጉዳተኞች ያለምንም ግፊያና ግርግር የሚፈልጉትን መሸመት የሚችሉበትን ሁኔታ አመቻችተዋል። በሌላ መልኩ ደግሞ ብዙ ሰዎች ገንዘብ እየለገሱ ነው፤ በተጨማሪም ራሳቸውን አግልለው ለሚገኙ ሰዎች የሞራል ድጋፍ እያደረጉና ሃሳብ እየሰጡ ነው። የተጠቀሱት አይነት የበጎ አድራጎት ሥራዎችና ድጋፎች ኢትዮጵያ ውስጥም በስፋት እየተስተዋሉ ነው። 4.በአንድነት መቆም በሥራና በሌሎች ኃላፊነቶች ምክንያት በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር መራራቅ የዘመኑ ኑሮ ሁነኛ መገለጫ ነው። አሁን ግን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ይህ መራራቅ አስቀርቶ ይልቁንም የዓለም ህዝብ ምንም እንኳ ርቀት ቢኖር በአንድ ላይ እንዲቆም አድርጓል። በጣልያን በእንቅስቃሴ እገዳ ከቤት የማይወጡ የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች በየመስኮታቸው ወጥተው አንድ ላይ በመዘመርና ለጤና ባለሙያዎች የምስጋና ጭብጨባ በማድረግ በጎነትን ማወደሳቸው የዚህ አንድ ማሳያ ነው። ብዙዎች ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ከወዳጅ ከጓደኛ ጋር ባሉበት ሆነው በስልክና በማኅበራዊ ሚዲያ ለመገናኘት እንደ እድል እየተጠቀሙበት ነው። 5.የፈጠራ ችሎታ ማበብ ብዙዎች በቫይረሱ ከቤት መዋላቸውን ተከትሎ አጋጣሚውን የፈጠራ ችሎታቸውን ለማውጣት እየተጠቀሙበት ነው። የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች አዳዲስ ልማዶችን እያመጡ መሆኑ እየታየ ነው። አንዳንዶች ማብሰልን ሌሎች ደግሞ ስዕል መሳልን አዲስ ልማድ አድርገዋል። ማንበብ ላይ ያተኮሩም እንዲሁ አሉ።