id
int64 60k
84.2k
| text
stringlengths 6
3.93k
⌀ | date
stringlengths 19
19
| hashtags
stringlengths 2
366
| emojis
nulllengths 1
96
⌀ | symbols
stringlengths 1
137
⌀ | links
stringlengths 2
588
| mentions
stringlengths 2
186
|
---|---|---|---|---|---|---|---|
60,002 | ኢትዮጵያ 381 ዜጎቿን ከሳኡዲ አረብያ መለሰች። ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባገኘነው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በዛሬው እለት 381 ዜጎቿን ከሳኡዲ አረብያ ፤ ጂዳ ከተማ በማስወጣት ወደ አገራቸው መልሳለች። ዜጎቻችን ከጄዳ ሹሜሲ የስደተኞች ማቆያ ጣቢያ ነው ወደሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገው። ኢትዮጵያ ሳኡዲ አረቢያ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎቿን በተጠናከረ ዘመቻ ወደ ሀገራቸው የመመለሱን ተግባር አሁንም ቀጥላለች። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ነው። | 2021-06-16T15:12:46 | [] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,003 | እናታችን ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) በኮቪድ 19 ተይዘው በጳውሎስ ሆስፒታል በፅኑ ሕሙማን ክፍል ሕክምና ማግኘት ከጀመሩ ሁለት (2) ሳምንት ሊሆናቸው ነው። እዳዬ አሁንም በሆስፒታሉ ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) በበጎ አድራጎት ስራቸው በሀገራችን ባሻገር በኣለምም በጣም የሚታወቁ የደግነት ምልክት ፤ የእናትነት ተምሳሌት ናቸው፡፡ | 2021-06-16T15:14:54 | ['#Update', '#AGOHELMA'] | null | - | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,004 | ምርጫ ቦርድ ለግል እጩ ተወዳዳሪዎች 50 ሺህ ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከግል እጩ ተወዳዳሪዎች ጋር በተለያየ ግዜ ባደረገው ምክክር መሰረት ቦርዱ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አምኖበት ለእያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ድጋፍ ለመስጠት መወሰኑን ዛሬ አሳውቋል። በምርጫ ቦርድ በግል እጩ ተወዳዳሪነት እውቅና አግኝተው ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚወዳደሩ በሙሉ ፦ ሙሉ ስማቸውን፣ አድራሻችሁን (ስልክ ቁጥራችሁን፣ ኢሜል) የባንክ አካውንታቸውን ለቦርዱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስራ ክፍል በአካል ወይም በ politicalpartiesorget ኢሜል አድራሻ ወይም በስልክ ቁጥሮች +251913551505/ +251929289444 የዋትስ አፕ እና ቴሌግራም እንዲልኩ መልእክት አስተላልፋል። | 2021-06-16T16:10:44 | ['#ምርጫ2013'] | null | --- | [] | ['nebe', 'tikvahethioia'] |
60,005 | ትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ጦርነት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑት የኤርትራ ወታደሮች በቅርቡ እንደሚወጡ በተባበሩት መንግሥታት (UN) የኢትዮጵያ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ተናገሩ። አምባሳደሩ በቅርቡ ይበሉ እንጂ ትክክለኛውን ቀን አልጠቀሱም። አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ግዛት ለመውጣት የቀራቸው አንዳንድ ቴክኒካዊና የአፈፃፀም ጉዳዮች ናቸው ብለዋል። የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ቁርጠኝነት እንዳለና በኤርትራውያኑ በኩልም ሁሉ ነገር ግልፅ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አምባሳደሩ ይህንን የገለፁት የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ በፀጥታው ምክር ቤት ቀርበው ግጭቱ እንዲቆም ተደርጎ የኤርትራ ወታደሮች ካልወጡ የ1977 አይነቱ የከፋ ረሃብ ተመልሶ ቢከሰት ማንም መደነቅ የለበትም ብለው ከተናገሩ በኋላ መሆኑን ሮይተርስን እና APን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በተጨማሪ አምባሳደር ታዬ ፦ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ሰብኣዊ ሁኔታ መሻሻል ያለውን ቁርጠኝነት፤ ስለሰብኣዊ ድጋፍ ሁኔታ፤ በትግራይ ተፈፅሟል ስለተባሉ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ እየተደረገ ስላለው ምርመራ ማብራሪያ ሰጥተዋል። Video Credit : United Nations | 2021-06-16T16:17:46 | ['#UN', '#ቢቢሲ'] | null | """"""""""--- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,006 | ጠ/ሚ አቢይ አህመድ : መላው ኣለም በምርጫ ቀን ይጋጫሉ ሲለን እኛ ደግሞ እናስተምራቸዋለን” የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ ዛሬ በምርጫ ቅስቀሳ የመጨረሻ ቀን በጅማ ከተማ በነበረ ዝግጅት ፥ መላው ኣለም በምርጫ ቀን ይጋጫሉ ሲለን እኛ ደግሞ እናስተምራቸዋለን” ሲሉ ተደምጠዋል። ጠ/ሚኒስትሩ በምርጫው እለት መራጮች ድምፅ ከመስጠት ጎን ለጎን ዛፍ በመትከል ለኣለም ትምህርት የሚሆን ተግባር እንዲያከናውኑ መልእክት አስተላልፈዋል። በጅማ ዩኒቨርስቲ ስቴድየም በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻችው ተገኝተው ነበር። ጠ/ሚኒስትሩ በሰኔ 14ቱ ምርጫ ከሚፎካከሩ ሃይሎች መካከል ኢትዮጵያን የሚወዱ፣ ኢትዮጵያን ማገልገል የሚፈልጉ፣ የኢትዮጵያ አንድነትን እና ነፃነትን የሚያከብሩ” ላሏቸው ተወዳዳሪዎች መልካም እድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል። ጠ/ሚር አብይ ዛሬ ባሰሙት ንግግር እምብዛም የምርጫን ጉዳይ አላነሱም። በተለያዩ ቦታዎች በሚካሄዱ መርሃ ግብሮች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲናገሩ የተደመጡትን የውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነትን” ጉዳይም አልጠቀሱም። እርሳቸው በንግግራቸው ጉዳዩን ባያነኩትም የጅማውን የስቴድየም መርሃ ግብር ይመሩ የነበሩ መድረክ መሪዎች እና ዘፋኞች ግን አሜሪካንን ጭምር በስም በመጥቀስ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መፈክር ቀመስ መልእክቶች ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል። በስቴድየም በተሰበሰበው ህዝብ ከፍተኛ ድጋፍ የተደመሙ የመሰሉት ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ ፤ የስቴድየሙን ግማሽ በሩጫ በመዞር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። መረጃው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው። Video Credit : ጋዜጠኛ ተስፋአለም ወልደየስ | 2021-06-16T16:24:43 | ['#ምርጫ2013'] | null | ""““ | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,007 | የደቡብ ምእራብ ህዝበ ውሳኔ ጳጉሜ 1 እንደሚካሄድ ቦርዱ ዳግም ገልጿል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ እየሰጠ በሚገኘው መግለጫ የደቡብ ምእራብ ህዝበ ውሳኔ ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ኣም እንደሚካሄድ ዳግም ገልጿል። የቦርዱ ኮሚኒኬሽን ሃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ቦርዱ ከዚህ ቀደም ከወሰነው ውሳኔ የተለየ ውሳኔ አለመኖሩን ነው የገለፁት። | 2021-06-16T17:39:37 | ['#Update', '#TikvahFamily'] | null | -- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,008 | ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ ድምፅ የሚሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ እጩዎች ዝርዝር በየክልሎቹ እና ከተማ መስተዳድሮቹ ከላይ ተያይዟል። PDF ፋይሉን ስትከፍቱን ቅደም ተከተሉ በዚህ መልኩ ያለ ነው ፦ አዲስ አበባ ከተማ : የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና ም/ቤት እጩዎች አፋር: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች አማራ: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች ቤንሻንጉል ጉሙዝ: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች ድሬዳዋ ከተማ: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና ም/ቤት እጩዎች ጋምቤላ: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች ኦሮሚያ : የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች ሲዳማ: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች ደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች: የተወካዮች ም/ቤት እጩዎችና የክልል ም/ቤት እጩዎች (ሁሉንም የተመዘገቡ እጩዎች የያዘው PDF ፋይል 94 MB ነው) | 2021-06-16T19:28:51 | ['#ምርጫ2013'] | null | --------- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,009 | የ24 ሰኣት የኮቪድ ሪፖርት : የላብራቶሪ ምርመራ 5,237 ቫይረሱ የተገኘባቸው 121 ህይወታቸው ያለፈ 3 ከበሽታው ያገገሙ 571 አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 274,601 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,260 ህይወታቸው ሲያልፍ 252,451 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,962,486 ደርሰዋል። | 2021-06-16T21:26:08 | [] | null | •-•-•-• | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,010 | ማስታወሻ ፦ ከነገ ሀሙስ ጀምሮ ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም። ሁሙስ አርብ ቅዳሜ እሁድ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይችሉም። ይህ ማለት፦ ፓርቲዎች ማንኛውም አይነት ስብሰባ ማድረግ አይችሉም ፣ ቤት ለቤት እየሄዱ ምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረግ አይችሉም፣ ወረቀት ፍላየር መበተን አይችሉም፣ የአደባባይና የአዳራሽ ስብሰባ ማድረግ አይችሉም፣ የኢንተርኔት (ኦንላይን) የማህበራዊ ሚዳያ የምረጡኝ ዘመቻ ማድረግ አይችሉም። | 2021-06-16T21:30:57 | ['#ምርጫ2013', '#SolianaShimeles', '#ሰኔ14እመርጣለሁ', '#ኢትዮጵያ'] | null | ---- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,013 | በምርጫ ወቅት ሊነሱ የሚችሉ ዋና ዋና የሚባሉ ክርክሮች ፦ የመራጮች እና የእጩዎች ምዝገባ ፣ የድምፅ አሰጣጥ ፣ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ የተመለከቱ ናቸው። እነዚህን ክርክሮች የሚዳኙ ፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና በቦርዱ የተቋቋሙ ውሳኔ ሰጪ አካላት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የኢፌዴሪ ህገመንግስት የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር ፲፩፻፷፪/፳፻፲፩ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፲፩፻፴፫/፳፻፲፩ አግባባ ያላቸው ሌሎች ሕጎች | 2021-06-17T11:27:16 | ['#ምርጫ2013', '#ተቋማት', '#ሕጎች', '#የኢትዮጵያ_የፌዴራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት'] | null | -------- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,015 | የፀጥት ችግር እና ግጭት አንበጣ መንጋ ጉዳት የኮሮና ቫይረስ ተፅእኖ የትግራይ ክልል ችግር ተደማምረው ኢትዮጵያ ውስጥ ከ125 ሚሊዮን በላይ ታዳጊዎች እና ህፃናት የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፈላጊዎች እንዳደረጋቸው ተገለፀ። ይህን የገለፁት UNICEF የኢትዮጵያ ቢሮ እና የስውዲን ኤምባሲ ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው። መግለጫው ትኩረቱን ያደረገው በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብኣዊ ድጋፍ ችግር ፣ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ላይ ነው። በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ችግር እስካሁን ከ700 ሺህ በላይ ህፃናት እና ታዳጊዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው በመግለጫው ላይ ተነግሯል። የUNICEF የኢትዮጵያ ቢሮ ተወካይ አደሌ ሆደር የረብሻ እና የፀጥታ ችግር፣ የኮቪድ 19 ተፅእኖ፣ የአንበጣ መንጋ፣ የትግራይ ክልል ችግር ተዳምረው በተያዘው የፈረንጆች ኣመት ሰብኣዊ እርዳታ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 235 ሚሊዮን አድርሶታል ብለዋል። ከዚህ ውስጥ 125 ህፃናት እና ታዳጊዎች መሆናቸው ችግሩን ይበልጥ አክፍቶታል ብለዋል። ሃላፊዋ ችግሩ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል እንዳለ የገለፁ ሲሆን በተለይ ግን በትግራይ ክልል ያለው ችግር ግን ይበልጥ የከፋ ነው ብለዋል። አክለውም ፥ በትግራይ ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ እና መገናኘት ያልቻሉ 6 ሺህ ህፃናት መረጃ በእጃችን አለ፤ ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ እና መገናኘት ያልቻሉ ህፃናት ጉዳይ ብዙ አደጋ ያለው ነው ። ለተለያየ ጥቃት ሊዳረጉ ይችላሉ፣ ማንኛውም ነገር ሊደርስባቸው ይችላል፤ ልጆቹ ሊሸጡ፣ ለሌላ ሰው ሊሰጡ ይችላሉ ስለዚህ ለእነዚህ ህፃናት ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። ያንብቡ : telegraph/Sheger FM 06 17 መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 1021 ሬድዮ ጣቢያ ነው። | 2021-06-17T11:28:29 | ['#Ethiopia'] | null | -----""--- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,017 | የኤርትራ ማስተባበያ ! ኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤትና የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ሃላፊ ተጨባጭ ያልሆኑ ተደጋጋሚ ክሶችን አቅርበውብኛል ስትል ተቃወመች። ኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) የኤርትራ ወኪል እንዳለው የፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ በሚወያይበት ጊዜ እንዲገኙ ወይም አስተያየት እንዲሰጡ እንዳልተጋበዙ አመልክቶ የኤርትራን ገፅታ ለማበላሸት ተገቢ ያልሆነና ግልፅነት የሌለው ያለውን ዘዴ ተቃውሞታል። ማክሰኞ በተደረገው የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የተመድ የሰብአዊ እርዳታ ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ሁኔታ ከታሰበው በላይ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረው ነበር። ማርክ ሎውኮክ ፥ ሴቶችን እና ታዳጊዎችን በተቀናጀ ሁኔታ በመድፈር ሽብርና ስቃይ እየተፈፀመ ነው። የኤርትራ ወታደሮች ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀሙበት ነው። የተፈናቀሉ የክልሉ ነዋሪዎች ይከበባሉ፣ ይደበደባሉ እንዲሁም ማስፈራሪያዎች ይደርሳቸዋል ይህንን ተከትሎ ኤርትራ የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣን ለምክር ቤቱ የኤርትራ ወታደሮች ይፈፅሙታል ያሉትን ድርጊት አስተባብላለች። በተመድ የኤርትራ ወኪል ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ፥ ኤርትራ በትግራይ ክልል ውስጥ ፈፅሞ የሰብአዊ እርዳታ እንዳይደረስ እገዳ አላደረገችም ብሏል። በተጨማሪ ኤርታራ ምግብን እንደ ጦር መሳሪያ ፈፅሞ አልተጠቀመችም፤ እንኳን አሁንና ከኢትዮጵያ ጋር የነፃነት ትግል በሚደረግበትና በድንበር ጦርነቱ ጊዜ እንኳን እንዲህ አይነት ነገር አልተፈፀመም ሲል አክሏል። ምንጭ፦ ቢቢሲ | 2021-06-17T11:45:15 | [] | null | """""""""" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,019 | በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና ከተማ ሚዛን አማን ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። ይህ የሚዛን አማን የአውሮፕላን ማረፊያ ጉዳይ የረጅም ጊዜ የህዝብ ጥያቄ መሆኑ ይታወቃል። በሌላ በኩል ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ ኢትዮጵያን እናልብሳት የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብርን እንዳስጀመሩ ተገልጿል። | 2021-06-17T12:23:22 | ['#MizanAman'] | null | "" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,022 | የአፍሪካ ሕብረት የሰብኣዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን ትግራይ ውስጥ ተፈፅመዋል ተባሉ የመብት ጥሰቶችን በይፋ መመርመር እንደሚጀምር ገልጿል። ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚያደርገውን ምርመራ ፥ የአፍሪካ የሰብኣዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን የምርመራ ሥራውን በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ እንደሚጀምር ነው ያስታወቀው። በዚህም መሰረት በትግራይ መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ እንደሚመረምር የገለፀ ሲሆን፤ አስፈላጊ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላም የጎረቤት ሀገራትን ሁኔታ ለማየት ይሞክራል። ኮሚሽኑ ለ3 ወራት ሁኔታውን እንደሚመረምር የገለፀ ሲሆን፤ የ3 ወራት ጊዜውም ሊታደስ እንደሚችልም ነው የተገለፀው። የአፍሪካ የሰብኣዊ እና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን የመብት ጥሰቶችን የመመርመር ሃላፊነት እንዳለው ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት ግን የአፍሪካ ሕብረት የሰብኣዊ እና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ የተናጠል ምርመራ አደርጋለሁ ማለቱን ተቃውሟል። መንግስት ተቃውሞውን የገለፀው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በተሰጠው መግለጫ ነው። ሚኒስቴሩ ፥ ኮሚሽኑ ብቻውን በትግራይ ክልል ተፈፅመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶችን እመረምራለሁ ማለቱ ተቀባይነት የለውም ብሏል፡፡ ነገር ግን ኮሚሽኑ ምርመራውን ማድረግ ከፈለገ ከኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ ማካሄድ ይችላል ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት፤ የአፍሪካ ሕብረት የሰብኣዊና የሕዝብ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ብቻዬን አካሂዳለሁ ያለውን የምርመራ ሂደት በአስቸኳይ ጠይቋል፡፡ | 2021-06-17T13:15:19 | ['#Tigray', '#እንዲያቋርጥ', '#አል_ዓይን_ኒውስ'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,023 | እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ። እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ዛሬ ለነበራቸው ቀጠሮ በፍርድ ቤት ትእዛዝ መሰረት ጉዳያቸውን ለመከታተል ችሎት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። ጉዳያቸውን የሚመለከተው ፍርድ ቤት እንዳለው ለተከሳሾች እና ለሰፊው ማህበረሰብ ደህንነት ሲባል ተከሳሾች ችሎት ፊት መቅረብ አይችሉም ሲል ትእዛዝ ሰጥቷል። በእነ አቶ ጃዋር መሀመድ የክስ መዝገብ ሥር የተዘረዘሩ ተከሳሾች ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀጠሮ ነበራቸው። የእነ አቶ ጃዋር መሀመድን ጉዳይ እየተመለከቱ ያሉት ዳኞች ባለፉት ጥቂት ቀናት ከፍተኛ የሆነ የምርጫ ቅስቀሳ ሲካሄድ መቆየቱን አስታውሰዋል። ለተከሳሾች ከፍተኛ ጥበቃ ነው የሚያስፈልገው በማለት በምርጫ ወቅት ተከሳሾችን ወደ ችሎት ማምጣቱ አስቸጋሪ ነው ብለዋል። በዚህም ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ 24ቱ ተከሳሾች ከምርጫው በኋላ ፍርድ ቤት ይቅረቡ ሲል ወስኗል። አቃቤ ሕግ ችሎቱ በዝግ ይከናወን እንዲሁም ምስክሮቼ ከመጋረጃ ጀርባ ቃላቸውን ይስጡ በሚል አሻሽሎ ባቀረበው አቤቱታ ላይ ተከሳሾች ምላሽ እንዲሰጡ ነበር የዛሬው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ የፀረ ሸብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ቀጠሮ ተይዞ የነበረው። ምንም እንኳ በችሎቱ ተከሳሾቹ ባይገኙም ስስት የተከሳሽ ጠበቆች ተገኝተዋል። ጠበቆቹም አቃቤ ሕግ አሻሽሎ ላቀረበው አቤቱታ ያዘጋጀነው ምላሽ በተከሳሾች እጅ ስለሚገኝ የምንሰጠው ምላሽ የለም ብለዋል። ምላሻቸውን በቀጣዩ ቀጠሮ ይዘው እንደሚቀርቡ አስረድተዋል። ፍርድ ቤቱም በአቶ ጃዋር መዝገብ ሥር የተከሰሱ ተከሳሾችን ጉዳይ ለመመልከት ለሰኔ 21/2013 ኣም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው። ፎቶ : ዘአፍሪካ ሪፖርት | 2021-06-17T13:42:30 | [] | null | """"--"" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,027 | ሼይኽ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ የአሳይታውን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ቃል መግባታቸው ተገልጿል። በአፋር ክልል በአሳይታ ከተማ በሼይኽ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ አማካኝነት ለአፋር ህዝብ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ታላቁን የሱልጣን አሊ ሚራህ ኢስላማዊ ማእከል እና ሌሎች የልማት ስራዎች አስገንብቶ ለማስረከብ ወደ ስራ ተገብቶ ነበር። የሀገራችን እውቅ ባለሃብት ሼይኽ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ ብዙ ገንዘባቸውን ውጪ ካደረጉ ቡሃላ በፖለቲካ አሻጥር ምክንያት በክልሉ እያካሄዱ ከነበሩት በርካታ የልማት ስራዎች ተገፍተው እንዲወጡ በማድረግ እና የዚህን ፕሮጀክት ፋይናንስ ማድረግ እንዲያቆሙ በመግፋት ግንባታው እና የልማት ስራዎች እንዲቆም ተደርጓል። ለሁለት አስርት አመታት ግንባታው የቆመው እና እሳቸው ያስጀመሩት ፕሮጀክት ዳግም ተጠናቆ ህዝቡን እና ሃገርን እንዲጠቅም ለማስቻል እንቅስቃሴ ሲደረግ ቆይቷል። ከጥቂት ቀናት በፊት አሳይታ ከተማ የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አወል አርባ ፥ ጨምሮ የተለያዩ ታላላቅ ኡለሞች፣ዱኣቶች እና የክልል መጅሊስ አመራሮች የተካፈሉበት የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሂዶ ነበር። በፕሮግራሙ ላይ አቶ አወል አርባ ፕሮጀክቱን ላስጀመሩት እና ከክልሉ በግፍ ተገፍተው እንዲወጡ ለተደረጉት ሼይኽ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ በይፋ ወደ ክልሉ ተመልሰው ለህዝባቸው ማድረግ የሚፈልጉትን የልማት ስራዎች ሁሉ ይሰሩ ዘንድ ሁኔታዎችን በሙሉ እንደሚያስተካክሉ ቃል በመግባት ጥሪ አድርገውላቸዋል። ሼይኽ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ፥ የቀረበላቸው ጥሪ በመቀበል ፕሮጀክቱን ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ ቃል መግባታቸውን ተወካያቸው ዛሬ አሳውቀዋል። ይህን መረጃ የተገኘው ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ካጋሩት ፅሁፍ ላይ ነው። | 2021-06-17T14:59:26 | ['#Update'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,029 | ዛሬ አ/አ መርካቶ ሚሊቴሪ ተራ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ ንብረት ወደመ። የአዲስ አበባ የእሳት አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እንዳሳወቀው ሚሊቴሪ ተራ አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ከ50,000 ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል። በእሳት አደጋው ምክንያት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። አደጋው በንግድ ሱቆች ላይ የደረሰ ሲሆን ቃጠሎ መንስኤ የኤሌክትሪክ ኮንታክት መሆኑ ተገልጿል። በተደረገው ርብርብ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ማትረፍ ተችሏል። እሳቱን ለመቆጣጠር 39 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መሳተፋቸውንና 30 ሺህ ሊትር ውሃ ጥቅም ላይ መዋሉን የአዲስ አበባ የእሳት አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢዜአ ገልጿል። | 2021-06-17T15:07:18 | [] | null | "" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,031 | ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በካፋ ዞን የውሽውሽ ሻይ ልማት የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል፣ የክልል እንዲሁም የዞን የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ና ሌሎች እንግዶች ወደ ሚዛን በሚሄዱበት ጊዜ የዞኑ ህዝብ ደማቅ አሸኛኘት እንዳደረገላቸው የካፋ ዞን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አሳውቆናል። | 2021-06-17T15:52:42 | [] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,034 | በመቐለ 400 ኩንታል የእርዳታ እህል ወደ ግለሰብ መጋዘን ሲራገፍ ተያዘ። የእርዳታ እህሉ መነሻውን ከጅቡቲ አድርጎ በቀጥታ መቐለ አዋሽ ተብሎ ከሚጠራው መጋዘን መራገፍ ሲኖርበት በ2 ግለሰብ መጋዘኖች ሲራገፍ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዟል፡፡ ከእርዳታ እህሉ ጋር የተሽከርካሪው ሹፌርና ረዳቱን ጨምሮ የመጋዘኑ ባለቤቶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል። በመቐለ ሰሜን ክፍለ ከተማ ላጨ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሁለት መጋዘኖች ሲራገፍ የተያዘው የእርዳታ እህል ትናንት ማምሻውን የገባ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ከሳምንት በፊት በወጣ አንድ ሪፖርት ባለፉት ጥቂት ወራት ከ4 ሺ 400 በላይ የእርዳታ ስንዴ ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ መገለፁን ኤፍ ቢ ሲ አስነብቧል። | 2021-06-17T15:53:08 | ['#Mekelle'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,035 | ቁጥራዊ መረጃ ፦ ከUNICEF እና ከስውዲን ኤምባሲ መግለጫ : 235 ሚሊዮን በተያዘው ዩፈረንጆች ኣመት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር (በረብሻ እና ግጭት፣ አንበጣ መንጋ፣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ የትግራይ ጦርነት ተዳምሮ) ከ235 ሚሊዮን መካከል 125 ታዳጊዎች እና ህፃናት እርዳታ ፈላጊ ናቸው። ከ700 ሺህ በላይ ህፃናት እና ታዳጊዎች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ። 6 ሺህ ህፃናት በትግራይ ጦርነት ምክንያት ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተለያዩ እና መገናኘት ያልቻሉ (እስካሁን ባለው ብቻ) 1927 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እስከ አመቱ መጨረሻ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን ችግር ለመደገፍ UNICEF የሚያስፈልገው ተጨማሪ ገንዘብ። 70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ፥ ከእአአ 2011 አንስቶ ስውዲን በUNICEF በኩል በኢትዮጵያ ለሚሰራው ስራ ያደረገችው ድጋፍ። 350 ሺህ ትግራይ ውስጥ ለረሃብ ፣ የከፋ ችግር ተጋልጠዋል የተባሉ ሰዎች ቁጥር። | 2021-06-17T15:54:57 | ['#ኢትዮጵያ', '#ሰብዓዊ_እርዳታ'] | null | -------- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,037 | ታላቁ የግብፅ ኢማም የታላቁ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት የሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያን ሀቅ ያልተመለከተ እና እውነት የጐደለው ነው ቀዳማዊ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ የግብፁ አለማቀፋዊ እስልምና ተቋም ታላቅ ኢማም የሆኑት ሼክ አልሃዛር አህመድ ጦይብ የህዳሴ ግድብን በሚመለከት ኢትዮጵያ ወንዙን በብቸኝነት በመጠቀም ሌሎች ሀገራት ላይ ጉዳት ለማድረስ እየሰራች መሆኑን መናገራቸው ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ ተናገሩ። ከሰሞኑን አልአዝሀር ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የህዳሴ ግድብ ትክክል አይደለም፤ ወንዙ የሁላችንም በመሆኑ ሁሉም ሰው ሊቃወመው ይገባል ፤ ግድቡ ግብፅ እና ሱዳን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ የሚጎዳ በመሆኑ አረቦች እና ሙስሊሞች ሁሉ እንዲቃወሙት ሲል ጥሪ አቅርቦ ነበር። ዛሬ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት መግለጫውን የኢትዮጵያን ሀቅ ያልተመለከተ ነው ሲሉ ውድቅ አድርገውታል። ኢትዮጵያ ሁሌም ቢሆን ውሃውን በፍትሃዊነት እንጠቀም የሚል አቋምን ስትገልፅ ከርማለች ያሉት የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዚዳንት፣ ግብፅ እና ሱዳንም ይሄንን እውነት ይዘው ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡም ጥሪ አቅርበዋል። የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዚዳንት ፥ የአባይ ውሃ ምንጩም ሆነ ተፈሳሱም አፍሪካ ምድር በመሆኑም መፍትሄውም እዚሁ ነው ሲሉ ተናግረዋል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አል ኣይን ነው። | 2021-06-17T15:56:15 | [] | null | ""--"" | [] | ['tikvagethiopia'] |
60,038 | ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በሃላ እለታዊ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላትም በቦታው ተገኝተዋል። ውድ አባላት በመግለጫው ላይ የሚነሱትን ዋና ዋና ጉዳዮችን የምንልክላችሁ ይሆናል። wwwtikvahethiopianet | 2021-06-17T17:00:00 | ['#ምርጫ2013'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,040 | የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ ለሚዲያዎች የሰጡት ቃለምልልስ ከምርጫ በፊት እንዳይሰራጭ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ። ቃለምልልሱ በዚህ በጥሞና ወቅት መተላለፍ የለበትም ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እድሪስ ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፥ ምንም እንኳን ቃለ መጠይቁ የመንግስት የስራ ክንውኖች ላይ ያተኮረና የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልሆነ ቢታወቅም በዚህ ጥሞና ወቅት ሊተላለፍ አይገባም ብለዋል። የቃለ መጠይቁ መተላለፍ ብዥታ እንዳይፈጥር ሲባል ከምርጫው በፊት መተላለፍ እንደሌለበት አቶ መሀመድ አስታውቀዋል። በተጨማሪም ቃለ መጠይቁ እንዳይተላለፍ የተፈለገው መንግስት በዚህ ኣመት የተሻለ ምርጫ እንዲካሄድና ፍትሀዊ እንዲሆን ፍላጎት ስላለው መሆኑን ተናግረዋል። ስለዚህ ቃለ መጠይቁን ለማስተላለፍ ማስታወቂያ እየሰሩ ያሉ መገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ለማስተላለፍ የተዘጋጁ ከወዲሁ አሳስበዋል። በተመሳሳይ የማሕበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የምርጫ ቅስቀሳ የሚመስሉ መልእክቶችን እያስተላለፉ ያሉ አካላትም ከድርጊታቸው መታቀብ አለባቸው ብለዋል። መገናኛ ብዙሃንም ቢሆኑ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በመጠናቀቁ ቅስቀሳ መሰል ዘገባዎችን ከማስተላለፍ ሊጠነቀቁ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ይገልፃል። | 2021-06-17T17:54:25 | ['#EMA', '#እንዲያቆሙ'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,041 | የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን መጪውን ምርጫ እንዳይታዘብ ተከልክሏል ? የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር የተፃፃፉትን ደብዳቤ መሰረት ተደረጎ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን መጪውን ምርጫ እንዳይታዘብ መከልከሉን የሚጠቅሱ ዘገባዎች ወጥተዋል። ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ይህ ጥያቄ የቀረበላቸው የቦርዱ የኮሚውኒኬሽን ሃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ሁለቱም በመንግስት ገለልተኛ ተቋም ናቸው ተብለው የተቋቋሙ ናቸው እኛ ባጅ የምንሰጣቸው የምንቆጣጠራቸውን ነው ሲሉ ገልፀዋል። በምርጫ ጣቢያዎች እንዲገቡ በቦርዱ የ ይለፍ ካርድ እንደሚሰጣቸው በአዋጅ 1162/2011 መጠቀሳቸውን ያነሱት ወ/ሪት ሶሊያና ኮሚሽኑ ከእነዚህ መካከል ባለመሆኑ በምርጫ ጣቢያዎች እንዲገቡ በቦርዱ የይለፍ ካርድ መስጠት እንደማይችል አንስተዋል። ባጅ ከመስጠትና የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ እንዲገቡ ፈቃድ የሚሰጣቸው በአዋጁ የተጠቀሱ እንዲሁም ቦርዱ ፈቃድ ሊሰጣቸው አስፈላጊ ሲሆንም ይህንን ፈቃዳቸውን ሊሰርዝ የሚችልባቸውን እንጂ ከቦርዱ ጋር ትይዩ ሥልጣን ላላቸው የመንግስት ተቋማት አይደለም ብለዋል። | 2021-06-17T18:42:32 | ['#ምርጫ2013', '#TikvahFamily'] | null | ''''''''"" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,042 | የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን ቦርዱ ከማእከል ማንቀሳቀስ መጀመሩን አስታወቀ። ዛሬ የ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው እለታዊ መግለጫ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች እሸጋና ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማንቀሳቀስ ሥራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። ዛሬ ቦርዱ በገለፀው መሰረት ፦ ለኦሮሚያ ክልል 118 (ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ) የምርጫ ክልሎች፤ የምርጫ ቁሳቁሶች ከማእከል ተልከዋል። ለአማራ ክልል በሬሾ 1/3 በሚሆን መልኩ፤ ለድሬደዋ ከተማ አስተዳደር 47 የምርጫ ክልሎች፤ ለአፋር ክልል 25 የምርጫ ክልሎች፤ ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 7 የምርጫ ክልሎች፤ ለጋምቤላ ክልል 14 የምርጫ ክልሎች የምርጫ ቁሳቁሶች ለምርጫ ክልሎች ተልከዋል። ለቀሪ ክልሎች በቀጣይ ቀናት የእሸጋና የስርጭት ሥራዎች የሚሰራ ሲሆን ከምርጫ ክልል ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የሚደረጉ ሥርጭቶች የክልል መንግሥታት እና የከተማ አስተዳድሮች አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርጉ በፁሁፍ ጭምር እንደገለፁ ተጠቅሷል። | 2021-06-17T19:17:15 | ['#ምርጫ2013', '#TikvahFamily'] | null | ------ | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,043 | የ24 ሰኣት የኮቪድ ሪፖርት : የላብራቶሪ ምርመራ 5,764 ቫይረሱ የተገኘባቸው 174 ህይወታቸው ያለፈ 2 ከበሽታው ያገገሙ 744 አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 274,775 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,262 ህይወታቸው ሲያልፍ 253,195 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,964,005 ደርሰዋል። | 2021-06-17T21:33:52 | [] | null | •-•-•-• | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,046 | በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ጉዳይ ፦ ኢትዮጵያ ሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ እና በችግር ላይ ያሉ ዜጎቿን በተለያየ ጊዜ ስትመልስ መቆየቷ ይታወቃል። ነገር ግን አሁንም በርካታ ዜጎች በሳኡዲ እርስ ቤቶች ውስጥ ታጉረው እንደሚገኙ፣ በርካቶችም በችግር ውስጥ ሆነው ወደሀገራችን መልሱን እያሉ ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች የተለያዩ የመገናኛ ዜዴዎች በመጠቅም ስላሉበት የከፋ ሁኔታ እየገለፁ ነው። ከሰሞኑን ደግሞ የሳኡዲ አረቢያ ፀጥታ ሃይል የሚሰራው ስራ በርካታ ዜጎቻችን የሰቀቅን ኑሮን እንዲገፉ ፣ በርካቶችንም ለስቃይ ፣ ለዘረፋ ፣ ለሰብኣዊ መብት ጥሰት እንዳጋለጣቸው ሰምተናል። አሁን አመሻሹን በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባሰራጨው መልእክት ፥ በሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ወደ አገር የመመለስ ጉዳይ መንግስትን ሲያሳስብ የነበረና መንግስት የዜጎች ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ ከሳኡዲ አረቢያ መንግስት ጋር በጉዳዩ ላይ ሲመክር መቆየቱን ገልጿል። ኤምባሲው የዜጎች ጥያቄ እልባት እንዲያገኝ ከሚመለከታቸው የሳኡዲ አረቢያ መንግስት እና የኢፌዲሪ መንግስት መስሪያ ቤቶች ጋር ጉዳዪ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሷል። በዚህም መሰረት ፦ (1) በእስር ቤት ያሉ እና (2) የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ወደ አገር መመለስ ፈልገው በተለያዩ ምክንያቶች ወደ አገር መመለስ ያልቻሉ ዜጎቻችን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ አገር የመመለስ ስራ ይጀመራል ብሏል። በሳኡዲያ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችንም ኤምባሲው ቃሉን አክብሮ ወደእናት ሀገራቸው እንዲመለሱ እንዲያደርጋቸው ባገኙት መገናኛ ዘዴ ጥሪ እያቀረቡ ነው። | 2021-06-17T21:38:05 | [] | null | ---- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,047 | ውድ የቲክቫህ አባላት የፊታችን ሰኞ ከሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች፣ ማብራሪያ የምትፈልጉበት ጉዳይ ይኖር ይሆን ? የምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ በቀጥታ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ። ወ/ሪት ሶሊያና ምላሽ የሚሰጡት በ Voice Chat ላይ ነው። ጥያቄዎቻችሁን ከታች በአስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡ ፤ አንድ አባል ለሚያቀርበው ጥያቄ ሌላ አባል መስጠት የማችል ሲሆን Reply የሚሰጣጡ አባላትን ከአስተያየት መስጫው ተሳትፏቸውን የምንገድበው ይሆናል። (ይህ ጥያቄ መቀበያ ነገ ጥዋት 3:00 ይዘጋል) | 2021-06-17T23:42:30 | ['#ምርጫ2013', '#በምርጫብቻ', '#በቀጥታ', '#Reply', '#TikvahFamily'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,050 | ውድ የቲክቫህ አባላት ከትላንት ለሊት 6 ሰኣት አንስቶ በምርጫ ዙሪያ ግልፅ ያልሆነላችሁ፣ ማብራሪያ የምትፈልጉበት ጉዳይ ካለ በሚል ጥያቄዎችን ሰብስበባል። እጅግ በርካታ ጥያቄዎች ከተለያየ የሀገሪቱ አቅጣጫ ከሚገኙ አባላቶቻችን ተሰብስቧል። ተመሳስይነት ያላቸውን ጥያቄዎች አንድ ላይ በማድረግ እና የኢትጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚመለከተውን ብቻ ለኮሚኒኬሽን ሃላፊዋ ወ/ሪት ሶሊያና አቅርበን ምላሽ እንዲሁም ማብራሪያ እንዲሰጥበት፤ እናተም ጋር ብዥታ ካለ የሚጠራበት መንገድን እናመቻቻለን። መቼ ነው ምላሽ የሚሰጠው ? ቀኑን ሰኣቱን እናሳውቃለን። ከዚህ ቀደም ምላሽ ያገኙ ጥያቄዎችን ደግሞ ከ ጋር የተያያዙ የተለዋወጥናቸውን መረጃዎችን መለስ ብላችሁ እንድትመለከቱት በትህትና እንጠይቃለን። ጠቃሚ የሚባሉ ወሳኝ መልእክቶችን በድጋሚ እንልክላችሃለን። | 2021-06-18T09:37:52 | ['#ምርጫ2013', '#በምርጫብቻ', '#ምርጫው'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,051 | የታጣቂዎች ጥቃት የ10 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ። 10 ሰዎች ተገድለዋል። የሟቾች አስክሬን ዛሬ አርብ ለቤተሰቦቻቸው ይሰጣል። ከቀናት በፊት በደቡብ አማሮ ልዩ ወረዳ አካባቢ ታጣቂዎች የሁለት ወጣት ኢንጂነሮችን ህይወት በግፍ ማጥፋታቸውን ከሰማን በሃላ ዛሬ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት በመንገድ ግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 10 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን ሰምተናል። ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ነው። ጥቃት ተፈፅም የሰዎች ህይወት መጥፋቱን የምእራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዲሪርሳ ዋቁማ ያረጋገጡ ሲሆን ጥቃቱ በዞኑ ሜታ ወልቂጤ ወረዳ ሎያ ጎዳኔ ቀበሌ ውስጥ ረቡእ ሰኔ 09/2013 ኣም አመሻሽ 12 ሰኣት አካባቢ መፈፁም ገልፀዋል። በታጣቂዎች የተገደሉት የፌደራል እና የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን ባለሙያ የሆኑ 9 ሰዎች እና የቀበሌው ነዋሪ የሆነች አንዲት ሴት ናቸው ብለዋል። ጥቃቱ በተፈፀመበት መኪና ውስጥ ከነበሩ 11 የመንገድ ሥራ ባለሙያዎች በሕይወት የተረፉ መኖራቸውንም አክለዋል። በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች አስከሬን አዲስ አበባ ወደሚገኘው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መላኩን እና ለቤተሰቦቻቸው መርዶ መነገሩን ጠቅሰው አስከሬናቸው ዛሬ አርብ እንደሚሰጥ ተናግረዋል። አቶ ዲሪርሳ ፥ ጥቃቱ ከተፈፀመባቸው አስራ አንድ የመንገድ ግንባታ ባለሙያዎች መካከል ከግድያው ያመለጡት ሁለቱ በአካላቸው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፤ ደህና ናቸው ብለዋል። በምእራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ ጥቃቱን የፈፀመው ኦነግ ሸኔ የተባለው ቡድን እንደሆነ ገልፀዋል። ያንብቡ : 06 18 | 2021-06-18T09:38:42 | [] | null | ••''"""""-"-- | ['https://telegra.ph/BBC'] | ['tikvahethiopia'] |
60,053 | የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጦር መሳሪያ እያጓጓዘ ነው ? ከሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የአፍሪካ ግዙፉ እና ግንባር ቀደሙ አየር መንገድ ወትግራይ እንዲሁም ወደሌሎች ቦታዎች መሳሪያ እያዘዋወረ ነው በሚል ስሙ ተነስቷል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (OLF) ይፋዊ የፌስቡክ ገፅም አየር መንገዱ ወደ መቐለ፣ ሃዋሳ፣ ኮምቦልቻ የጦር መሳሪያ እያዘዋወረ ነው ሲል በይፋ ፅፏል፤አየር መንገዱን ሎጅስቲክስ በማመላለስ የጦርነት ተሳታፊ እየሆነ ነው ሲል ከሷል። ትላንት ምሽት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ ምላሽ ሰጥቷል። ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጦር መሳሪያ እያጓጓዘ እንደሆነ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ መሆኑን አስረድቷል። በየትኛውም የሀገር ውስጥ ሆነ የውጪ በረራዎቹ ማንኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ እንዳላጓጓዘ ገልጿል። አየር መንገድ፥ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ወደ የትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል አላጓጓዝኩም፤ እንዳጓጉዝም አልተጠየኩም ብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገዱ አንጋፋና ፓን አፍሪካዊ አየር መንገድ መሆኑን ፣ ለአፍሪካውያን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት በግንባር ቀደምነት ላለፉት 75 ኣመታት አህጉሩን ሲያገለግል መቆየቱን በዚህም አየር መንገዱ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በተቀረው ኣለምም እጅግ የሚያኮራ ስም ማፍራቱን አንስቷል። በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በሰራው ስራም ከተለያዩ ሀገራት እና መሪዎች እውቅና ለማግኘት መብቃቱን አስታውሷል። ነገር ግን አንዳንድ ሀላፊነት የማይሰማቸው ግለስቦች ሀሰተኛ እና በፎቶ ሾፕ የተቀናበሩ ምስሎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በማሰራጨት የአየር መንገዱን ስም እና ዝና ለማጠልሸት የሚያደርጉት ጥረት መኖሩን ደምበኞቹ እንዲገነዘቡ አሳውቋል። | 2021-06-18T10:03:13 | [] | null | """" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,054 | በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሰንገን ኦባሳንጆ ሰኞ ለሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ ትላንት አዲስ አበባ መግባታቸውን የአፍሪካ ህብረት (AU) በይፋዊ የትዊተር ገፁ አሳውቋል። | 2021-06-18T11:42:59 | ['#ምርጫ2013'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,059 | በወገኖቻቸው ስቃይ የሚነግዱ አካላትን ታሪክ ይፋረዳቸዋል ብ/ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከዳንጉርና ማንዱራ ወረዳዎች ተፈናቅለው ቻግኒ መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ዜጎችን ወደቄያቸው የመመለስ ስራ መጀመሩ ተገለፀ። ተፈናቃዮቹ ሲመለሱ የሚጠቀሙባቸው መሰረታዊ ፍላጎቶችና መሰረተ ልማቶች ቀደም ሲል መዘጋጀቱ ተገልጿል። የም/እዝ ምክትል አዛዥና የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሃይል ኮማንድ ፖስት አባል ብ/ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ፥ የእነዚህን ወገኖች ደህንነት ለመጠበቅ ሰራዊቱ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል ብለዋል። ብርጋዴር ጄኔራል አለማየሁ ተፈናቅለው የነበሩት ወገኖች ወደቀዬአቸው ተመልሰው ሕይወታቸውን እንዲቀይሩ የማይፈልጉ አካላት መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን በወገኖቻቸው ስቃይ የሚነግዱ አካላትን ታሪክ ያፈረዳቸዋል ሲሉ ተናግረዋል። የአገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ አካላት ለደህንነታቸው ሙሉ ጥበቃ እንደሚያደርጉላቸው አረጋግጠዋል። መረጃው የኢዜአ ነው። | 2021-06-18T13:39:26 | [] | null | ""-"""""" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,062 | 2 የችሎት ጉዳዮች ! የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠ/ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰኣረ መኮንንና ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራን በመግደል በፍ/ቤት ጥፋተኛ የተባለው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በሞት እንዲቀጣ ጠይቋል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ አርብ ጥያቄውን ያቀረበው የአስር አለቃ መሳፍንትን የክስ ሂደት ለሚመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። አቃቤ ህግ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ባለ 3 ገፅ የቅጣት አስተያየት፤ በተከሳሹ ላይ ሶስት የቅጣት ማክበጃዎችን ጠቅሷል። የተከሳሽ ጠበቆች ፥ ተከሳሽ ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የለበትም ብለዋል። አቃቤ ህግ አንድም [የወንጀል] ሪከርድ ሳያቀርብ የሞት ፍርድ መጠየቁ ከህጉ ያፈነገጠ ነው” ሲሉ የአቃቤ ህግን የቅጣት አስተያየት ተቃውመዋል። ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሰኔ 21 /2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በዝርዝር ያንብቡ : telegraph/Ethiopia Insider 06 18 ዛሬ አርብ ማለዳ የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት የዋለው ችሎት በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ እጃቸው አለበት የተባሉ 55 ተከሳሾች ላይ ብይን ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ በሻምበል መማር ጌትነት የክስ መዝገብ ስማቸው የተዘረዘሩ 55 ተከሳሾች ውስጥ 6ቱ በሌሉበት፣ 49 በተገኙበት ፍርዳቸው ሲታይ የነበረ ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤቱ 20ዎቹን በነፀ አሰናብቷል። በነፃ እንዲሰናበቱ ከተበየነላቸው ተከሳሾች መካከል አቶ ዘመነ ካሴ ይገኙበታል። በዝርዝር ያንብቡ : telegraph/BBC 06 18 2 መረጃዎቹ ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር እና ከቢቢሲ የተውጣቱ ናቸው። | 2021-06-18T14:36:50 | ['#አዲስ_አበባ', '#ባህርዳር'] | null | *“------ | [] | ['tikvahethiopi'] |
60,064 | እስራኤል ለፍልሥጤም በቅርቡ ጊዜው የሚያበቃ አንድ ሚሊዮን ዶዝ ፋይዘር የኮቪድ 19 ክትባት ልትሰጥ ነው። ዛሬ ይፋ በሆነው ስምምነት እስራኤል 1 ሚሊዮን የኮቪድ 19 ክትባት ለፍልስጤም ትልካለች። ፍልስጤም በተመድ በሚደገፈው ፕሮግራም ክትባት ለሚያስፈልጋቸው ሀገራት ክትባት ሲላክላት አንድ ሚሊዮን ዶዝ ክትባቱን ለእስራኤል ትመልሳለች ተብሏል። እስራኤል 85% ጎልማሳ ዜጎቿን የኮቪድ 19 ክትባት የከተበች ሲሆን በዌስት ባንክ እና ጋዛ ለሚገኙ 45 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን ክትባት አላካፈለችም በሚል ስትተች ነበር። ዛሬ ይፋ የሆነው ክትባት የመላክ ስምምነት በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤንት በሚመራው መንግስት የተደረሰ እንደሆነ ተገልጿል ፤ እስካሁን ግን ከፍልስጤም ባለስልጣናት ምንም የተባለ ነገር የለም። በኣለማችን ካሉ ሀገራት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ስራ የሰራችው እስራኤል ዜጎቿን በመከተቡ ረገድም አመርቂ ስራን ሰርታለች ፤ በዚህ ሳምንት የሀገሪቱ ባለስልጣናት ቀሪ ነበር የተባለውን የመጨረሻ ገደብ በህዝብ መካከል ማስክ የማድረግ ገደብ እንዳነሱ ታውቋል። | 2021-06-18T15:13:17 | ['#Israel', '#Palestine'] | null | ---- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,065 | የኢትዮጵያን ያስቆጣው የሀርቪስቶ አስተያየት : ከ3 ቀን በፊት የፊንላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ለአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ሪፖርት አቅርበው ነበር። በዚህ ሪፖርታቸው ላይ ስለ ጉዳይ የተናገሩ ሲሆን በይበልጥ ግን የብዙሃን መነገሪያ የሆነው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በነበረኝ ቆይታ፥ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንደሚፈልጉ /ታጋሩዎችን ለ100 ኣመታት ማጥፋት እንደሚፈልጉ ነግረውኛል ብለው የተናገሩት ነው። የትኛው የኢትዮጵያ ባለስልጣን ይህን እንዳለ / ሲናገር እንደሰሙት ግን በስም ገልፀው ሲናገሩ አልታዩም። ሀርቪስቶ የአውሮፓ ህብረትን በመወከል ለጥቂት ቀን በኢትዮጵያ ቆይታ አድርገው እንደነበር አይረሳም። ፔካ ሀርቪስቶ ከቀናት በፊት ያቀረቡት አጠቃላይ ሪፖርት ኢትዮጵያን ክፉኛ አስቆጥቷል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሀርቪስቶ ያቀረቡት ሪፖርት ሃላፊነት የጎደለው፣ መሰረት የሌለው፣ ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን ያልተከተለና ከቅኝ ገዢነት የመነጨ ነው ብሎታል። ሚኒስቴሩ ፔካ ሃቪስቶ መንግስት እያከናወነ ያለውን ስራ የሚያጣጥል እና በሀሰተኛ መረጃዎች የተመሰረቱ ሪፖርቶችን፣ ውሸቶችን በማቅረብ ተገቢ ያልሆኑ ጣልቃ ገብነቶች እንዲኖሩ አድርጓል” ብሏል። በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ ፔካ ሃቪስቶ ከጠ/ሚር አቢይ አህመድ፣ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ከም/ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አውስቶ፤ የቀረበው ሪፖርት ግን ሃሰተኛና የተካሄዱ ሰፋፊ ውይይቶችን ያላካተተ መሆኑን ተገልጿል። የፔካ ሀርቪስቶ ሪፖርት ፥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ከላይ ተያይዟል። | 2021-06-18T17:07:48 | ['#ትግራይ', '#የትግራይ_ተወላጆችን_ለማጥፋት'] | null | ""“* | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,068 | (ሰኔ 11 ቀን 2013 ኣ/ም) ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በሃላ እለታዊ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላትም በቦታው ተገኝተዋል። ውድ አባላት በመግለጫው ላይ የሚነሱትን ዋና ዋና ጉዳዮችን የምንልክላችሁ ይሆናል። | 2021-06-18T17:10:27 | ['#ምርጫ2013'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,071 | የአዲስ አበባ ፖሊስ ላለፉት ኣመታት ሲጠቀምበት የነበረውን ፖሊሳዊ የደንብ ልብስ እና ኣርማ መቀየሩን ምክንያት በማድረግ የማብሰሪያ መርሀ ግብር ማዘጋጀቱን ዛሬ አስታውቋል። ይህ መርሀግብር ነገ ቅዳሜ ሰኔ 12/2013 ኣ/ም በመስቀል አደባባይ ነው ይካሄዳል የተባለው። በዚህ ምክንያት ከማለዳው 12 ሰኣት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6 ሰኣት ድረስ የተወሰኑ መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ ተብሏል። በዚህም መሰረት ፦ ከኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ ከ4ኛ ክፍለ ጦር/ጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ከሀራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ ከለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ ከብሄራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ እና በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ መጋቢ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ። አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል። መረጃውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ነው ያገኘነው። | 2021-06-18T17:38:24 | ['#አዲስ_አበባ'] | null | -•••••• | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,072 | የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በይፋዊ የትዊተር ገፁ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለሁለተኛ ጊዜ የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ በመሆን ዳግም እንደተመረጡ አሳውቋል። | 2021-06-18T17:44:53 | ['#UnitedNations'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,073 | የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ እየሰጠ በሚገኘው እለታዊ መግለጫ ላይ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች እሸጋ እና ከማእከል ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማንቀሳቀስ ሥራ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ መከናወኑን ገልጿል። ቦርዱ ይህን የሎጀስቲክ ሥራ ለማከናወን ከየብስ ትራንስፖርት በተጨማሪ የአየር ትራንስፖርትን መጠቀሙን የገለፀ ሲሆን በዚህም አስቸጋሪ በሚባሉ ቦታዎች ጭምር የምርጫ ቁሳቁስ ማድረስ መቻሉን ነው የገለፀው። ቀሪ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት የሚካሄድባቸው በደቡብ ክልል 4 የምርጫ ክልሎች እንዲሁም በአፋር ክልል አንድ የምርጫ ክልል የአየር ትራንስፖርት በመጠቀም የሚከናወን ይሆናል። በአጠቃላይ የምርጫ ቁሳቁስ እሸጋና ከማእከል ወደ ምርጫ ክልል የማድረስ ሥራዎች ከተወሰኑ የቅንጅትና ጥቂት የመዘግየት ችግሮች በስተቀር ከፍተኛ የሆነ ችግር ሳያጋጥም መጠናቀቁን የቦርዱ የኮሚውኒኬሽን ሃላፊ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል። ቦርዱ በዋናነት የድምፅ መስጫ ወረቀቶችንና ውጤት ማሳወቂያ ፎርሞችን ወደ ምርጫ ክልል በማድረሱ ሥራ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ አየር ሃይል ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው አንስቶ አመስግኗል። | 2021-06-18T17:55:44 | ['#UPDATE', '#ምርጫ2013', '#TikvahFamily'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,074 | የምርጫ ዝግጅት በወላይታ ዞን : 13 የምርጫ ክልሎች አሉ። ሰኞ በ7 የምርጫ ክልሎች ምርጫ ይደረጋል። ሰኞ በ6 የምርጫ ክልሎች ምርጫ ። በወላይታ ዞን በ13 የምርጫ ክልሎች 1 ሺህ 20 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን፥ 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይፎካከራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ካሉት 13 የምርጫ ክልሎች በሰባት የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን በ5 ምርጫ ክልሎች ላይ ደግሞ ምርጫ እንደማይካሄድ የዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አሳውቋል። ምርጫውን ማካሄድ የሚያስችል የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ምርጫ ወደሚካሄድባቸው 7 ወረዳዎች እየተሰራጨ የሚገኝ ሲሆን ወረዳዎችም ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የመጡ ቁሳቁሶቹን በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ። በምርጫው ከ1 ሚሊየን በላይ ህዝብ መመዝገብ አለበት ተብሎ ታቅዶ ከ 800 ሺህ በላይ ህዝብ በመራጭነት ተመዝግቧል። ሰኞ ምርጫ በሚካሄድባቸው በ7 ምርጫ ክልሎች ከ600 ሺህ በላይ ህዝብ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል ፤ ቀሪው መራጭ ህብረተሰብ በ2ኛው ዙር ድምፁን ይሰጣል ተብሏል። | 2021-06-18T18:48:49 | ['#ምርጫ2013', '#አይደረግም።', '#ኤፍቢሲ'] | null | ••• | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,075 | የኣለም ጤና ድርጅት ለወ/ሪት ሄራን ገርባ ሽልማት አበረከተ። በኣለም ጤና ድርጅት የ2013 ትምባሆ የማይጨስበት ቀን ጉልህ አስታዋፅፆ ላበረከቱት ለወ/ሪት ሄራን ገርባ ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡ የ2013 የኣለም ጤና ድርጅት ለኣመቱ ያዘጋጀውን የኣለም የማይጨስበት ቀን ሽልማት ከአፍሪካ አህጉር ተሸላሚ ከሆኑት ስድስት ግለሰቦች መካከል አንዷ ወ/ሪት ሄራን ገርባ ነበሩ። ወ/ሪት ሄራን ፥ ላበረከቱት አስተዋፆ የጤና ሚንስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በተገኙበት በኢትዮጵያ የኣለም ጤና ድርጅት ተጠሪ ዶ/ር ቡሬማ ሳምቦ ዛሬ ሰኔ11/2013 ኣም ሽልማቱን አበርክተውላቸዋል። | 2021-06-18T21:42:12 | ['#EFDA'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,076 | ኢትዮጵያ ከ21 ቀን በሃላ ከፍተኛ የኮቪድ 19 ሟቾችን ሪፖርት አደረገች። ባለፉት 21 ቀናት ሪፖርት ከተደረጉት ሁሉ ከፍተኛው የኮቪድ 19 ሟቾች ቁጥር ባለፉት 24 ሰኣታት ተመዝግቧል። ባለፉት 24 ሰኣት የ14 ዜጎች ህይወት በቫይረሱ አልፏል ፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,276 ደርሷል። | 2021-06-18T21:59:21 | ['#Ethiopia'] | null | -- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,077 | ዛሬ በአጣዬ ከተማ የእርቅ ፕሮግራም ተካሄደ። በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ጅሌ ጥሙጋ ወረደና በአጣዬ ከተማ አሰተዳደር ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በማክሰም የ ህዝብ ለህዝብ የእርቅ ፕሮግራም ተካሂዷል። በእርቀ ሰላም ሥነ ሥርኣቱ ላይ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ የወረዳ እና የዞን አመራሮች እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት አመራርና አባላቶች ተገኝተው ነበር። በተከታታይ ቀናት ግጭት በተፈጠረባቸው አካባቢዎች የህዝብ ለህዝብ የእርቅ ፕሮግራም እየተካሄደ መሆኑን ከጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የተገኘው መረጃ ያሳያል። ግጭት ሲፈጠር በሚዲያዎች የሚሰጠው ትኩረት ያህል እርቅና ሰላም ወረደ ሲባል እምብዛም ሽፋን ሲያገኝ አይታይም። | 2021-06-18T22:11:03 | [] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,079 | ኢትዮጵያውያን በስራ የራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመቀየር ብለው ሀገራቸውን ጥለው በስደት በሚኖሩባት ሀገረ ሳኡዲ አረቢያ እንግልት ፣ የሰብኣዊ መብት ጥሰት፣ ማሸማቀቅ፣ ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሆነ እየገለፁ መሆኑ ይታወቃል። በእስር ቤት ውስጥ ያሉ ዜጎቻችን ስፍር ቁጥር የላቸውም። በተለይ ደግሞ ከሰሞኑን የሳኡዲ አረቢያ ፀጥታ ሃይሎች መኖሪያ ፍቃድ ያላቸውም ሆነ የሌላቸውን እያፈሱ መሆኑ መገለፁ ይታወቃል። የሳአዲ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ ለምን ይህንን እያደረገ እንደሚገኝ ይፋዊ በሆነ መንገድ ስለመግለፁ ምንም አልተሰማም / መረጃም የለም። ዛሬ በሳአዲ አረቢያ ከሚገኙ ዜጎቻችን ጋር በተገናኘ በሰማነው መረጃ የኢትዮጵያ መንግስት ልኡካን ወደ ሳኡዲ አረብያ ሄደዋል። የልኡካን ቡድኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ሃላፊዎችን ያካተተ ሲሆን በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ይመክራል ተብሏል። የስደተኞች መብት አጠባበቅና ስደተኞች ወደ ሃገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ዙርያ ከሚመለከታቸው የሳኡዲ አረቢያ ባለስልጣናት ጋር መወያየት የልኡኩ ዋነኛው ተልኮ ነው። ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ችግር ለማቃለልና በክብር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የሳኡዲ አረብያ መንግስት ትብብር በጣም አስፈላጊ ነው ብሏል። በሳኡዲ አረቢያ ከሚደረገው ውይይት የሚገኘው ዉጤት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር አንዱ ማሳያ ይሆናል ሲል ገልጿል። | 2021-06-18T23:13:21 | ['#ሳዑዲ_አረቢያ'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,085 | የኦሮሚያ ፖሊስ አንድ የሸኔ ከፍተኛ አመራር ገደልኩኝ አለ። ከጥቂት ቀናት በፊት በደቡብ ኦሮሚያ በ4 ቀን ዘመቻ 95 የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላትን ደመሰስኩኝ ያለው ኦሮሚያ ፖሊስ ትላንት ምሽት ባወጣው መረጃ በምእራብ ኦሮሚያ ጃል ሮባ የተባለ የሸኔ ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ 295 የቡድኑን ታጣቂዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደወሰደ ገልጿል። ፖሊስ እንዳለው በ2 ወር ውስጥ ነው 295 የሸኔ ታጣቂዎች ደመስኩኝ ያለው። ከዚህ በተጨማሪ ቡድኑ ሲጠቀምበት የነበረ 126 የጦር መሳሪያ እና 1,995 የተለያዩ አይነት ጥይቶች ገቢ አድርጊያለሁ ብሏል። በዚህ ኦፕሬሽን ስራ በ ጅማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ራሱን ጃል ሮባ ብሎ የሚጠራ የሸኔ ከፍተኛ አመራር አብሮት ከነበሩ 22 የአሸባሪው ታጣቂዎች ጋር መገደሉን የክልሉ ፖሊስ በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ላይ ገልጿል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ፥ በኦፕሬሽኑ ብዛት ያለው የተማረከ እና እጅ የሰጠ ታጣቂ እንዳለ ገልፆ ለዘመናት ህዝቡን ሲያምሱ የነበሩ ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል የተለያዩ የሸኔ ታጣቂዎች ተደምስሰው ለህዝቡ እፎይታ ሆኗል ብሏል። | 2021-06-19T09:50:47 | [] | null | """""" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,090 | ሀረሪ ውስጥ ለህብረተሰቡ ሊከፋፈል የነበረ ደረጃውን ያልጠበቀ ሩዝ ተያዘ። በሀረሪ ክልል በ ሀኪም ወረዳ ደረጃውን ያልጠበቀ 120 ኩንታል የሩዝ ምርት ለህብረተሰቡ ሊከፋፈል ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን ከሀረሪ ክልል የጤና ቢሮ የተገኘው መረጀ ይጠቁማል። የሩዝ ምርቱ ከድሬዳዋ ተጭኖ በሀኪም ወረዳ የጅምላ ማከፋፈያ መደብር ለህብረተሰቡ ሊከፋፈል ሲል ነው በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር የዋለው። ለህብረተሰቡ ሊከፋፈል የነበረውን ደረጃውን ያልጠበቀ ሩዝ ምርት ከላይ በፎቶው ተመልከቱት። (የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ) | 2021-06-19T09:51:37 | [] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,092 | የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 አመት የ8ኛ ክፍል ፈተናዎችን በክልሉ ለሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ማከፋፈል ጀመረ። በሶማሌ ክልል የ2013 አመት የ8ኛ ክፍል ፈተናን ከሰኔ 21 እስከ ሰኔ 23 ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። በክልሉ በሚገኙ 735 ትምህርት ቤቶች 44,144 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ከትላንት ሰኔ 11 ጀምሮ ለዘንድሮ አመት የተዘጋጀውን የ8ኛ ክፍል ፈተናዎችን በክልሉ ለሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ፣ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ማከፋፈል ጀምሯል። ፈተናዎቹ ታትም በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ነበር የቆዩት። | 2021-06-19T09:59:03 | ['#Somali', '#SMMA'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,094 | የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ አደርገዋለሁ ያለውን አዲሱን የደንብ ልብስ እና አርማ ዛሬ በይፋ በመስቀል አደባባይ አስተዋውቋል። አዲሱ የደንብ ልብስ እና አርማ ከላይ በፎቶ ተያይዟል። አዲሱ የፖሊስ አርማ ምን አካቷል ? የሚሰጠው ትርጉም ምንድነው ? ጋሻ መከላከልን፣ ጥንካሬን፣ ድፍረትና ጀግንነትን ይወክላል ተብሏል። ቀጥ ያሉ እኩል ጨረሮች ጨረሮቹ የብሄር ብሄረሰቦችን፣ የህዝቦችን እና የሃይማኖት እኩልነትን የሚያሳዩ ናቸው። የተከበበ ክብ መስመር ጋሻነትን ለማመልከት የተቀመጠ ነው። የፍትህ ሚዛን የፍትህ ስርኣትን የሚወክል ነው። ሁሉንም ዜጎችን በእኩል አይን በማየት ፍትህን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ለማሳየት የተቀመጠ ነው። የዘንባባ ዝንጣፊ የሰላም ምልክት ሆኖ የቀረበ ሲሆን ፖሊስ የሰላም ዘብ መሆኑን ለማሳየት የተቀመጠ ነው ተብሏል። ባለ 5 ጎን ኮከብ የፖሊስን ማእረግ የሚወክል ነው። በተጨማሪ ኮከቡ የኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ስርኣትን፣ የብሄር ብሄረሰቦችን አንድነት እና እኩልነት ማሳያ ተደርጎ የቀረበ ነው ተብሏል። ቀለማት ፦ ሰማያዊ (ሰላምን የሚወክል ነው) ፣ ወርቃማ ቀለም (የክብር እንዲሁም የአሸናፊነት አስተሳሰብን የሚወክል ነው) ፣ ብራማ ቀለም (በአርማው ዙሪያውን ከቦት የሚገኝ ሲሆን የፖሊስን ጋሻነት እና መከታነት ለማሳየት ነው) ከአዲስ ቴቪ ያገኘነው መረጃ። | 2021-06-19T11:03:10 | ['#Update'] | null | •-•-•-•-•-•- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,095 | በሀረሪ የ2ተኛው ዙር የኮቪድ 19 ክትባት መሰጠት ተጀመረ። በሀረሪ ክልል የሁለተኛው ዙር የኮቪድ 19 ክትባት ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል። የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በጁገል ሆስፒታል በመገኘት የክትባት ዘመቻ በይፋ አስጀምረውታል። በክልሉ በመጀመሪያው ዙር 12 ሺህ 580 ዜጎችን ለመከተብ ታቅዶ 12,281 ዜጎች መከተባቸው የእቅዱን 98 በመቶ ማሳካት መቻሉን ከክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። | 2021-06-19T11:17:00 | [] | null | -- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,097 | ታዛቢ ቡድን ባለመላኬ አዝኛለሁ አውሮፓ ህብረት የአውሮፓ ህብረት ባወጣው መግለጫ ለምርጫ 2013 የታዛቢ ቡድን መላክ ባለመቻሉ ማዘኑን አስታውቋል፡፡ ከወር በፊት ህብረቱ ለመታዘብ ያስችሉኛል ባላቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረገው ውይይት አለመስማማቱን ገልፆ፣ የመታዘብ እቅዱን ማንሳቱን አስታውቆ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ህብረቱ ምርጫ 2013 ለታዘብ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሉኣላዊነት ስለሚጋፉ” ስለሆኑ ህብረቱ ምርጫ ለመታዘብ ያስቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታ እንደማይቀበል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት አቋሙን ካሳወቀ በኋላ ህብረቱ የምርጫው እለት ልኡክ እንደሚልክ አስታውቆ ነበር፡፡ ህብረቱ በዛሬ መግለጫ በድጋሚ ምርጫውን የሚታዘብ ልኡክ መላክ እንደማይችል እና በድርጊቱ ማዘኑን ገልጿል። ሰኞ ሰኔ 14 የሚካሄደው ምርጫ ለ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ለውጥ ሂደት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው የገለፀው ህብረቱ በቀጣይ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብሮ እንደሚሰራ አስታውቋል። አሁን ላይ በኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ጥሰት፤የፖለቲካ ውጥረቶች እና ሌሎች ውስብስብ ችግሮች አሉባት ያለው የህብረቱ መግለጫ በቀጣይ ሁሉን አቀፍ እና አሳታፊ ውየይቶች እንዲደረጉም አሳስቧል። በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፖለቲካ ሽግግር እረዳለሁ ያለው ህብረቱ የምርጫውን ሂደት እና የብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ስራ እንደሚደግፍ ገልጿል፡፡ የአውሮፓ ህብረት መግለጫ : releases/2021/06/18/ethiopia declaration by the high representative on behalf of the european union/ ምንጭ፦ አል ኣይን ኒውስ | 2021-06-19T11:39:54 | ['#ምርጫ2013'] | null | ""-“------------ | ['https://www.consilium.europa.eu/en/press/press'] | ['tikvahethiopia'] |
60,098 | በአማሮ ወረዳ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት 1 የልዩ ሃይል አመራርን እና አንድ ሲቪል ተገደሉ። የአማሮ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ዛሬ እንዳሳወቀው በወረዳው በተለያዩ አካባቢዎች በታጣቂዎች በተፈፀመው ጥቃት የንፁሃን ዜጎች ህይወት አልፏል ፤ የንብረት ዝርፊያም ተፈፅሟል። በታጣቂዎች ጥቃት ተፈፅሞ የሰዎች ህይወት ያለፈው እና ንብረት የተዘረፈው ባለፉት 2 ቀናት ነው። ከትላንት በስቲያ በቀን 10/ 2013 በጎልቤ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ስሆን በዚሁ መሰረት የአንድ ሰው ህይወት ሲጠፋ ሁለት አርሶ አደሮች ላይ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰ ሪፖርት ተደርጓል። ብዛት ያላቸው ከብቶች መዘረፋቸውም ተገልጿል። በትላንትናው እለት በቀን ሰኔ 11 ዳኖ ቀበሌ ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ተከታታይ ሙከራ መደረጉ ተነግሯል። የህዝቡን የድረሱልን ጥሪ በመስማት ሰላምና ፀጥታ አስከባሪ ሃይል ወደ ዳኖ ቀበሌ ገብተው የነበረ ሲሆን ታጣዊዎች በሰላምና ፀጥታ አስከባሪ ሃይል ጥቃት አድርሰው አንድ የልዩ ሃይል አመራር ገድለዋል። የአማሮ ወረዳ እንደሚለው ጥቃት የሚፈፅሙት በምእራብ ጉጂ ዞን በጋላናና ሱሮ ባርጉዳ ወረዳዎች በህገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ናቸው። በአማሮ ወረዳ የስጋት ቀጠና ውስጥ ያሉ የአይን እማኞች የታጠቁ ሃይሎች በተለያዩ ቡድን ሆነው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ፥ በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ጥፋቶችንም እየፈፀሙ ነው ሲሉ አመልክተዋል። ነዋሪዎቹ የፊታችን ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 የሚካሄደውን ምርጫ ለማበላሸት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ ሲሉም ጠቁመዋል። መንግሥት በአካባቢው ተጨማሪ የፀጥታ ሀይላትን ሊያሰማራ ይገባል ሲሉ አመልክተዋል። | 2021-06-19T12:52:08 | [] | null | "" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,101 | የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለ6ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ቀን የኢፌዴሪ መንግስት ሙሉ ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቁበት ለጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ የላኩት ደብዳቤ። | 2021-06-19T15:00:53 | ['#ምርጫ2013'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,102 | የምርጫ ዝግጅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል : በአጠቃላይ 22 የምርጫ ክልሎች አሉ። በአሶሳ ዞን ስር በሚገኙ 8 የምርጫ ክልሎች ምርጫ ይካሄዳል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰኔ 14 ምርጫ በሚካሄድባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫውን ለማከናወን በቂ ዝግጅት መደረጉን በኢትዮጲያ የምርጫ ቦርድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርጫፍ ፅ/ቤት አሳውቋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምርጫው በሁለት መርሀ ግብር ነው የሚካሄደው። በክልሉ በ8 የምርጫ ክልሎች በ302 የምርጫ ጣቢያዎች ሰኔ 14/2013 ኣም ምርጫው የሚካሄድ ሲሆን፣ የፀጥታ ችግር ተስተውሎባቸው የነበሩ የመተከል እና ካማሽ ዞኖች የምርጫ ጣቢያዎች ጳጉሜ 1/2013 ኣም ነው ምርጫ የሚደረገው። ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ 7 የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ይወዳደራሉ። ከ360 ሺ በላይ መራጮች ድምፅ መስጠት የሚያስችላቸውን ካርድ ወስደዋል ተብሏል። | 2021-06-19T15:01:00 | ['#ምርጫ2013', '#ሰኞ'] | null | •• | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,103 | ከሀሙስ ጀምሮ ፓርቲዎች በየትኛውም መንገድ የምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረግ እንደማይችሉ በጥብቅ መከልከሉ ይታወቃል። አሁን አሁን ከተጠቃሚው ብዛት ለቁጥጥር አዳጋች እየሆነ በመጣው ማህበራዊ ሚዲያ ጭምር ፓርቲዎች ቅስቀሳ እንዳያደርጉ ተከልክለዋል። የጥሞው ወቅት ነገ የሚያበቃ ሲሆን፤ ሰኞ ዜጎች ድምፅ ይሰጣሉ። ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት የጥሞና ውቅቱን የተላለፉ ፓርቲዎች ይኖሩ እንደሆነ (በማህበራዊ ሚዲያ ያደረጉት እንቅስቃሴ ካለ ብለን) የማህበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ገፆቻቸውን ለመከታተል የሞከርን ሲሆን ያየናቸው ፓርቲዎች ሁሉም በሚባል ደረጃ በማህበራዊ ሚዲያ እቅስቃሴያቸው አቁመዋል። በዋነኝነት ከተመልከትናቸው የፓርቲዎች ይፋዊ ገፆች መካከል የኢዜማ፣ አብን፣ ባልደራስ፣ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ፣ እናት ፓርቲ፣ ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ከጥሞና ወቅት ጋር በታያያዘ ከፍተኛ መነጋገሪያ የነበረው ትላንት አርብ ምሽት ለህዝብ ይሰራጫል የተባለው የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዜዳንትና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ለሚዲያ ሰጡት ቃለምልልስ ሲሆን ምንም እንኳን ለበርካታ ቀናት ማስታወቂያ እየተነገረ ቢቆይም ታግዶ በየትኛውም ሚዲያ ሳይተላለፍ ቀርቷል። ከብልፅግና ፓርቲ ፕሬዜዳንትና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣና ዋና ዳይሬክተር መሃመድ ኢድሪስ ቃለምልልሱን ሚዲያዎች እንዳያሰራጩ አሳስበው እንደነበር ይታወቃል። | 2021-06-19T15:03:17 | ['#ምርጫ2013'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,104 | ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከትላንት በስቲያ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ጥያቄ ይኖራችሁ እንደሆነ /ማብራሪያ የምትፈልጉበት ጉዳይ ካለ ጥያቄ እንድትልኩ ጥሪ አቅርበን ነበር። ለጥያቄዎቻችሁ ምላሽ የሚሰጡት የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ሃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ እንደሆኑም አሳውቀን ነበር። ዛሬ ከ10 11 ሰኣት ባለው ጊዜ በቀጥታ በ Voice Chat ለጥያቄዎቻችሁ ምላሽ የሚሰጡ ይሆናል። ቴሌግራም መተግበሪያ Update ካልተደረገ የማይሰራላችሁ ስለሆነ ከወዲሁ አረጋግጡ። | 2021-06-19T15:09:15 | ['#ምርጫ2013', '#Voice_Chat', '#በምርጫብቻ'] | null | - | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,108 | ውድ ቤተሰቦቻችን ከነገ በስታያ ከሚደረገው ምርጫ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ሃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ በቀጥታ በVoice Chat ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በቀጥታ ገብታችሁ ማዳመጥ ያልቻላችሁ፤ በድምፅ ቅጂው ማዳመጥ ትችላላችሁ። ከተዳሰሱት ጉዳዮች መካከል ፦ ምርጫው በሚካሄድበት እለት ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውጤት አገላለፅን በተመለከተ የምርጫ አስፈፃሚዎች ጉዳይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተመለከተ ምርጫ ካርዳቸው የጠፋባቸው ነገር ግን የተመዘገቡ ሰዎች ጉዳይ ከፀጥታ አንፃር እስካሁን ያለው ሁኔታ ይገኙበታል። የሁላችሁንም ጥያቄ ለመመለስ ግዜ ባይገኝም ፤ በተቻለ አቅም ግን ዋና ዋና ጥያቄዎቻችሁ እንዲመለሱ ተደርጓል። በዚሁ አጋጣሚ በቀጥታ ገብተው ለቤተሰቦቻችን ምላሽ ለሰጡት ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ምስጋና እናቀርባለን። | 2021-06-19T16:39:21 | ['#ምርጫ2013', '#TikvahFamily'] | null | ------ | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,109 | ምርጫ ካርድ የጠፋባቸው መምረጥ ይችላሉ ? የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ካርድ የጠፋባቸው ዜጎች ድምፅ የሚሰጡበት አሰራር እንዳለ ገልጿል። የቦርዱ የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ዛሬ ለቲክቫህ አባላት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ ተመዝግበው ምርጫ ካርድ ወስደው ነገር ግን ካርዱ የጠፋባቸው ዜጎች ምርጫ የሚመርጡበት መንገድ እንዳለ አስረድተዋል። ሂደቱም እንደሚከተለው ነው ፦ መራጮች የተመዘገቡበትን መታወቂያ ይዘው ይሄዳሉ፣ ካርዳቸው እንደጠፋባቸው ያሳውቃሉ፣ ስማቸው በመዝገብ ላይ ይፈለጋል በተመዘገቡበት መታወቂያ ላይ ባለው መሰረት በትክክል መዝገቡ ላይ ከተገኙ በቃለ ጉባኤ ካርድ ጠፍቶባቸዋል እና ድምፃቸውን ይስጡ ተብሎ ተይዞላቸው ድምፃቸውን ይሰጣሉ። በስራ ምክንያት ቀድሞ ከተመዘገቡበት ቦታ የተንቀሳቀሱ መራጮች ከተመዘገቡበት ምርጫ ጣቢያ ውጭ መምረጥ ይችላሉ ? ወ/ሪት ሶሊያና ለዚህ ጥያቄ የሰጡት የሚል አጭር ምላሽ ነው። ምርጫው የሚካሄደው መራጮች በተመዘገቡበት የምርጫ ጣቢያ ላይ ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል። መራጮች ድምፃቸውን ለመስጠት በተቻላቸው አቅም በእለቱ በተመዘገቡበት እና በሚኖሩበት አካባቢ ሊሆኑ ይገባል፤ ከዚህ ውጭ ግን ድምፃቸውን የሚሰጡበትም ምንም አይነት መንገድ እንደሌለ ገልፀዋል። ወ/ሪት ሶሊያና ፥ አንዱ ጣቢያ ተመዝግቦ ፤ ሌላ ጣቢያ ላይ ድምፅ መስጠት አይቻልም፤ ይህ ሁኔታ በሃላ ውጤት ለመደመር አስቸጋሪ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ አሰራሩ ዲጂታል ስላልሆነና የሚሰራው በወረቀት ስለሆነ ካርዱ ና መዝገቡ ተመሳክሮ ነው ድምፅ የሚሰጠው ስለዚህ ካርድ እና መዝገባቸው የተለያይ ሁለት ቦታ ስላሚሆን አይሆንም (ድምፅ መስጠት አይችሉም) ብለዋል። | 2021-06-19T18:29:29 | ['#ምርጫ2013', '#አይችሉም'] | null | •---""•"""" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,110 | አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሰርግ እና በተለያዩ ምክንያቶች ፍቃድ ሳይሰጥ ርችቶችን መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአ/አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ በተለያዩ አካባቢዎች ካለፍቃድ የሚተኩሱ ርችቶችን ሽፋን በማድረግ አንዳንድ ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ የገዙትን የጦር መሳሪያ እንደሚፈትሹ ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም በድርጊቶቹ ምክንያት የተለያዩ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ሁኔታዎች እያጋጠሙ መሆኑን አስታውቋል። ከዚህ ቀደም ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው ጥናቶችና አሰሳዎች አረጋግጦ ማንኛውም ግለሰብ ሆነ ማንኛውም ተቋም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ርችቶችን መተኮስ እንደማይችል ማሳሰቡ አስታውሷል፤ ነገር ግን አሁንም አንዳንድ ቦታዎች ላይ እንደሚታየው ግለሰቦችና ተቋማት በሰርግና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ርችቶችን ሲተኩሱ ተስተውሏል ብሏል። ሁኔታው የከተማው የፀጥታ ስጋት እንዳይሆን ህብረተሰቡ አካባቢውን በመጠበቅ ለፖሊስ አባላት መረጃዎችን እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል። ከሚመለከተው አካል ተገቢውን ፍቃድ ሳይሰጥበት ርችቶችን በሚተኩሱ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አስጠንቅቋል። | 2021-06-19T19:10:16 | ['#Attention'] | null | - | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,111 | ለደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ድጋሜ አይካሄድም ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ዛሬ እለታዊ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ ለደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ድጋሜ አይካሄድም ብለዋል። ለህዝበ ውሳኔው መራጮች በያዙት ካርድ እንደሚመርጡ ገልፀዋል። በሌላ በኩል ሰኞ ከሚደረገው ምርጫ ጋር በተያያዘ የፖለቲካ ፓርቲዎች እስከ ነገ ታዛቢዎቻቸውን ማስመዝገብ እንደሚችሉ አሳውቀዋል። የቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተም ፥ ከማእከል የሚከናወነው የቁሳቁስ ስርጭት መጠናቀቁን አስታውቀዋል። አዲስ አበባ ላይ ከዛሬ 9 ሰኣት ጀምሮ ስርጭት ተጀምሯል፡፡ ማምሻውንም ይከናወናል ተብሏል። በሌሎች አከባቢዎች ከማእከል ወደ ክልል የሚደረገው ስርጭት ተጠናቅቋል ብለዋል። ከምርጫ ታዛቢዎች ጋር በተገናኘም እስካሁን ከ120 በላይ ለሆኑ ኣለምአቀፍ ታዛቢዎች ባጅ እንደተሰጣቸው እና አሁንም ለመታዘብ እየገቡ ያሉ መኖራቸውን ወ/ሪት ሶሊያና ገልፀዋል። | 2021-06-19T19:24:15 | ['#Update', '#ኢፕድ'] | null | ""- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,112 | በአሁን ጊዜ የኮቪድ 19 ያለባቸው ዜጎች ስንት ናቸው ? ዛሬ ይፋ በሆነው የጤና ሚኒስቴር እለታዊ ሪፖርት እንደሚያሳያን በኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ያለባቸው አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 16,458 ነው። እስከዛሬ ከተደረገው 2,819,655 የኮቪድ 19 ላብራቶሪ ምርመራ 275,036 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 254,296 ሰዎች አገግመዋል። በአሁን ሰኣት ቫይረሱ ያለባቸው ዜጎች ቁጥር 16,458 ነው። | 2021-06-19T22:13:36 | [] | null | -- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,113 | የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድምፅ የሚሰጡት እንዴት ነው? የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የመራጮች ምዝገባ በኦላይን በዩኒቨርሲቲያቸው እያሉ ሲያካሂዱ ነበር። አሁን ላይ ተማሪዎች ወደቤታቸው ተመልሰዋል በምርጫው እንዴት መሳተፍ ይችላሉ ? ለሚለው ጥያቄ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚውኬሽን ሃላፊ ወዘሪት ሶልያና ሽመልስ ለቲክቫህ ቤተሰቦች ምላሽ ሰጥተዋል። ወ/ሪት ሶሊያና ፥ ተማሪዎች በኦንላይን ምዝገባ ተመዝግበው እንደጨረሱ የተሰጣቸው እንዳለ በመጠቆም ተማሪዎች ያንን ማረጋገጫ ይዘው አቅራቢያቸው የሚገኝ የምርጫ ጣቢያ መሄድ እንዳለባቸው አሳውቀዋል። በአካባባያቸው ያለው የምርጫ ጣቢያ በትክክል የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆነው መመዝገባቸውን ሲያረጋግጥ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ያደረጋል ሲሉ አስረድተዋል። ስለዚህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰኞ ድምፅ ለመስጠት ምን ማድረግ አለባችሁ ? በኦንላይን ላይ ምዝገባችሁን ያጠናቀቃሁበትን ማረጋገጫ ወረቀት መያዝ ይጠበቅባችኋል። በመኖሪያ አከባቢያችሁ አቅራቢያ ወደሚገኝ ምርጫ ጣቢያ በማቅናት የማረጋገጫ ወረቀቱን በማሳየት የምርጫ ወረቀት ማግኘት ትችላላችሁ። ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ እንድትይዙ ይመከራል። | 2021-06-19T22:14:01 | ['#ምርጫ2013', '#የማረጋገጫ_ወረቀት'] | null | --- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,116 | አንድ መራጭ ለክልል ምክር ቤት መቀመጫ ምን ያህል እጩዎችን መምረጥ ይችላል? ለክልል ወይም ለከተማ ም/ቤት መቀመጫ አንድ መራጭ መምረጥ የሚችለው የእጩዎች ብዛት እንደየምርጫ ክልሉ ይለያያል። አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 1 እጩ፣ እንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 3 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ደግሞ ላይ 9 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 14 እጩዎች ወይም ሌላ ቁጥር ያለው የመቀመጫ ብዛት ሊኖራቸው ይችላል። ብዛቱ የሚወሰነው የምርጫ ክልሉ በክልል ምክር ቤቱ ባለው የመቀመጫ ቁጥር ብዛት ነው። በመሆኑም አንድ መራጭ በክልል ምክር ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ መምረጥ የሚችለው የእጩዎች ብዛት በክልል ምክር ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ ከላይ ተፅፎ ይገኛል። በዚህም መሰረት አስፈፃሚዎች የድምፅ መስጫ ወረቀት ሲሰጡ ለመራጩ በምርጫ ጣቢያ ውስጥ እስከ ስንት እጩ መምረጥ እንደሚችል ያስረዳሉ። ሆኖም ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች አንድ እጩ ብቻ የሚመረጥ ይሆናል። ስለዚህም ከዚህ ቁጥር ገደብ በላይ ምልክት የተደረገባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ዋጋ አይኖራቸውም። ስለሆነም ድምፅዎን ሲሰጡ በወይን ጠጁ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወረቀት በክልል ምክር ቤት ወረቀት ደግሞ ወረቀቱ ላይ በተፃፈው እና ምርጫ አስፈፃሚው በሚነግርዎ ቁጥር መሰረት መሆኑን አይርሱ። ከተፈቀደው የእጬ ቁጥር በላይ ምልክት አያድርጉ። (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ) | 2021-06-20T11:00:25 | ['#ምርጫ2013', '#አንድ', '#ሼር', '#Share'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,117 | ኢሰመኮ ዛሬ በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ በምርጫው የሰብኣዊ መብት ሁኔታዎችን የሚከታተሉ ባለሙያዎችን እንዳሰማራ አሳውቋል። ኢሰመኮ ባለሙያዎቹን ያሰማራው በተሻሻለው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 6 በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት መሰረት ነው። በዚህም ምርጫ በሚካሄድባቸው በሁሉም ክልሎች የክትትል ቡድኖችን ማሰማራቱን አስታውቋል፡፡ ቡድኖቹ በሚሰማሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ በምርጫው እለት እና ከምርጫው በኋላ ባሉት ቀናት በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ምልከታ ያደርጋሉ ያለው ኮሚሽኑ መራጮችን፣ የምርጫ አስተባባሪዎችን፣ የፀጥታ አካላትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ እጩዎችን፣ ታዛቢዎችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር መረጃዎችን እንደሚሰባስቡ ገልጿል፡፡ በፖሊስ ጣቢያዎች እና በሕክምና ተቋማት በመገኘት አስፈላጊውን ክትትል እንደሚያደርጉም ነው ያስታወቀው። የኮሚሽኑን መለያ ካርድ (ባጅ) በመያዝ ለሚሰማሩት የክትትል ቡድኑ አባላት አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ | 2021-06-20T11:05:20 | ['#ምርጫ2013', '#አልዓይን'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,118 | ምን ያህል ታዛቢዎች ምርጫውን ይታዘባሉ ? እስካሁን ባለው መረጃ 6ኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ ከቦርዱ ፈቃድ የወሰዱ የሀገር ውስጥ ታዛቢ ድርጅቶች 42 ናቸው። በቁጥር ሲሰላ ወደ 46,000 በላይ የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫውን ለመታዘብ ከቦርዱ እውቅና አግኝተዋል። ለታዛቢነት ፍቃድ የመስጠቱ ሂደት ባለማብቃቱ ቁጥሩ ወደ 50 ሺህ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ኣለም አቀፍ ታዛቢዎችን በተመለከተ የትላንቱን ሳይጨምር እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ቁጥራቸው 120 የሚሆኑ ታዛቢዎች ባጅ ወስደዋል። ማስታወሻ፦ የምርጫ ታዛቢዎች ፍቃድ የመስጠቱ ስራ ባለመጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የታዛቢዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል። | 2021-06-20T11:11:45 | [] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,119 | በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፍቃድ ሳይኖር (የምርጫ ጣቢያ ኮድ ሳይሰጣቸው) የተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ ይሰጣል ? ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፍቃድ ሳይኖር (የምርጫ ጣቢያ ኮድ ሳይሰጣቸው) የተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች እንደነበሩ መግለፁ አይዘነጋም። አዲስ አበባ ላይ 2 እና ድሬዳዋ ላይ 6 የምርጫ ጣቢያ ኮድ ሳይሰጣቸው ተከፍተው ተገኝተዋል ፤ ከዚህም ጣቢያዎች ጋር በተያያዘም እንዴት ነው የሚሆነው የድምፅ መስጫ ቀን የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው። ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ የሰጡት ምላሽ ፦ በእለቱ እዛው ድጋሚ ህጋዊ ምዝገባ እያደረግን ዜጎች እንዲመርጡ እናደርጋለን። ምርጫ ጣቢያው ክፍት ነው የሚሆነው የተመዘገቡ ዜጎች የመራጮች ካርዳቸውን እና መታወቂያቸውን ይዘው ይመጣሉ በዛ መሰረት እዛ ጣቢያ ላይ መመዝገባቸው ካወቅን በሃላ የድጋሚ ምዝገባ እያደረግን ትክክለኛ ምዝገባ ከሆነ ትክክለኛነቱን እያረጋገጥን ችግር ያለበትን ደግሞ እዛው ድጋሚ ምዝገባ እየተደረገ አስፈፃሚዎች የዜጎችን ድምፅ መስጠት ያረጋግጣሉ። ሌላ ቦታ ላይ ምዝገቡን መንካት፣ መቀየር፣ ድጋሚ ምዝገባ ማከናወን ከዚህ በፊት የተመዘገበን ሰው እንዳይመዘገብ ማድረግ ወይም እንደአዲስ መመዝገብ አይቻልም በሌሎች ሁኔታዎች ላይ ለዚህ ግን በልዩ ሁኔታ እዛ ምርጫ ጣቢያ ላይ የተመዘገቡ ዜጎችን መብት ለማረጋገጥ ሲባል መራጮች ካርዳቸውን ይዘው ሲመጡ ህጋዊ ምዝገባ እየተደረገ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ይደረጋል። አዲስ አበባ ላይም ድሬዳዋ ላይም በዚህ ሂደት በምርጫ ጣቢያዎቹ ድምፅ መስጠት ይከናወናል | 2021-06-20T11:50:59 | ['#ምርጫ2013'] | null | "" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,120 | የኢትዮጵያ ኢ ቪዛ (E Visa) እና በመዳረሻ በሚሰጥ ቪዛ (Visa on Arrival) አገልግሎት ቆሟል ? የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትናንት ምሽት በይፋዊ ድረ ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ከኢሚግሬሽን ቢሮ በመጣ መመርያ መሰረት የE Visa እና Visa on Arrival አገልግሎቶች ከአርብ እኩለ ለሊት ጀምሮ ለግዜው አይሰጡም። ይህ ግን የትራንዚት መንገደኞችን እንደማይመለከት አክሎ ገልጿል። የኢሚግሬሽን ድረ ገፅ ደግሞ የ E Visa ድረ ገፁ እድሳት ላይ እንዳለ ገልፆ ተገልጋዮች ለቪዛ ጉዳዮች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ኤምባሲ ወይም ቆንፅላ ቢሮ እንዲያመሩ ይመክራል። በዚህ ዙርያ ኢሚግሬሽን ዛሬ ጥዋት ለኢትዮጵያ ቼክ በሰጠው ቃል አገልግሎቱ የተቋረጠው በድረ ገፁ ላይ የማሻሻያ ስራ እየተከናወነ በመሆኑ ነው። የማሻሻያ ስራው በቅርቡ ይጠናቀቃል ሲል ገልጿል። በዚህም መሰረት የ E Visa ያላቸው እንዲሁም Visa on Arrival የሚፈልጉ ተጓዦች ወደ ኢትዮጵያ የሚደረግ የአየር ጉዞን ማድረግ አይችሉም፣ አየር መንገዶችም አያሳፍሩም። ይህም ማለት ፦ ፓስፖርት፣ ቢጫ ካርድ (የትውልደ ኢትዮጵያዊ ካርድ) የተለጠፈ ቪዛ ያላቸው ብቻ መጓዝ ይችላሉ። ይህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ወደ ኢትዮጵያ በረራ የሚያደርጉ አየር መንገዶችን ይመለከታል። | 2021-06-20T12:27:36 | ['#Ethiopia', '#ኢትዮጵያቼክ'] | null | ------------- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,124 | የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ነገ ሰኔ 14/2013 ከሚካሄደው 6 ኛው ብሄራዊ ምርጫ በፊት ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ለመስጠት እንዲንቀሳቀሱ የተደረገውን የመጨረሻ ዝግጁነት ለመገምገም የብሄራዊ ምርጫ ደህንነት ስትራቴጂ ማዘዣ ዛሬ ጠዋት መምከሩን አሳውቀዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ ፥ የፀጥታ ዘርፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲሰማራ እና በቴክኖሎጂ ድጋፍ ለተለዩ እና ለሚከሰቱ አደጋዎች ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ሰፊ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ባሰራጩት መልእክት ፥ ሁሉም ዜጎች ነገ ድምፅ ለመስጠት ሲወጡ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲከታተሉ አበረታታለሁ ብለዋል። አክለውም መንግሥት ለሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ቀን በቂ ዝግጅት ማድረጉን አረጋግጣለሁ ሲሉ አሳውቀዋል። | 2021-06-20T12:45:06 | ['#Update'] | null | """" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,127 | ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች በዛሬው እለት የምርጫ ወቅት እና ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት ላይ ትኩረቱት ያደረገ አጭር ገለፃ በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat ይኖረናል። ገለፃው በዋነኝነት በዚህ ለሀገሪቱ ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ በሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት ሊፈጠር የሚችለውን ችግር በማስቀረቱ ረገድ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለን እንጠብቃለን። አቅራቢዎቹ : ከመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማእከል (CARD) በፍቃዱ ሃይሉ እና ከኢትዮጵያ ቼክ ኤልያስ መሰረት ናቸው። ሰኣት : ከቀኑ 9:30 ጀምሮ ለ30 ደቂቃ ቆይታ ያደርጋለን። ማስታወሻ፦ ቴሌግራም መተግበሪያችሁ Update ካልተደረገ ይህን የቀጥታ ስርጭት መከታተል ስለማትችሉ መተግበሪያችሁ Update መደረጉን አረጋግጡ። | 2021-06-20T14:48:19 | ['#ምርጫ2013'] | null | "" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,128 | ነገ በአዲስ አበባ ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች አገልግሎት ይሰጣሉ። ለነገው ምርጫ በአዲስ አበባ ሁሉም የትራንስፖርት አማራጮች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። በእለቱ የትራንስፖረት አገልገሎት አሰጣጡን የሚከታተል፣ የሚመራና ከየዘርፉ የተውጣጣ ግብረ ሃይል ተቋቁሟል ተብሏል። የታክሲ አሽከርካሪዎችና ማህበራት፤ የብዙሃን ትራንስፖርት አቅራቢ ድርጅቶች ማለትም አንበሳ፣ ሸገርና ሃይገር ባሶች፣ የላዳ ሾፌሮች እና ማህበራት ጋር ውይይት በማድረግ የስራ መመሪያ ተላልፏል። የአንበሳ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት በእለቱ 665 አውቶብሶችን ለትራንስፖርት ዝግጁ ማድረጉም ተረጋግጧል። የከተማው የትራንስፖርት ቢሮ ፥ የትራንሰፖርት እጥረት ይከሰትባቸዋል የተባሉ አካባቢዎችን በመለየት ተጨማሪ ስምሪቶች ይሰጣል ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል። | 2021-06-20T14:48:56 | [] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,136 | በሀላባ ቁሊቶ የሰኣት ገደብ ተጥሏል። የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ፅ/ቤት ነገ ከሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ከሰኔ 12/2013 ኣ/ም ጀምሮ ተግበራዊ የሚደረግ የሰኣት ገደብ መጣሉን አሳውቋል። እነዚህም መሰረት ፦ ምርጫው ተካሄዶ እስክጠናቀቅ ድረስ ባለ ሁለት እግር ሞተር ሰይክሎች ከ12:00 ሰኣት በሃለ ማንኛውንም እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ተከልክሏል። ማንኛውም የህዝብ ማመላላሻና የባለ ሶስት እግር በጀጅ ተሽከርከሪዎች ከ1:00 ሰኣት በሃለ መንቀሰቀስ አይችሉም። የግል የቤት መኪና ከ3:00 በሃለ እንዳይንቀሳቀስ ገደብ ተጥሏል። ማንኛውም ሰው እስከ ምርጫ ማብቂያ ማምሻ ከ3:00 ሰኣት በሃላ እንቅስቃሴ መካሄድ አይቻልም። መጠጥ ቤቶች ፣ የንግድ ሱቆች ፣ ሆቶሎች ፣ ቡና ቤቶችና ግሮሰሪዎች ከሰኔ 12 ጀምሮ 2:00 ሰኣት ላይ መዘጋት ይገባቿል። ይህን የሰአት ገደብ በሚተላለፍ አካል ላይ የፀጥታ አካላት እርምጃ እንደሚወስዱ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል። | 2021-06-20T16:18:33 | [] | null | ----- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,137 | ነገ ስራ ዝግ ሆኖ ይውላል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ነገ እንደማንኛውም የስራ ዝግ ቀን/እንደ በኣል ቀን ስራ ዝግ ሆኖ እንደሚውል በድጋሚ ተናግረዋል። ከትራንስፖርት ፣ ከመሰረታዊ እና ከድንገተኛ አገልግሎት (ዋና ዋና አገልግሎት) ከሚሰጡት ተቋማት በስተቀር ሌሎች ስራ ዝግ ሆነው ይውላሉ ብለዋል። የትራንስፖርት ፣ የመሰረታዊ ፣ ድንገተኛ እና አስቸኳይ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትና ሰራተኞች አሰራራቸውን ይዘው ይቀጥላሉ። ከዛ ውጭ ያሉት ግን ተዘግተው መራጮች ድምፅ የሚሰጡበት ነው ሲሉ አስገንዝበዋል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ነገ ስራ ካልገባችሁ ትቀጣላችሁ/ስራ ግዴታ መግባት አለባችሁ የሚሉ አካላትን አይትናል ያሉት ወይዘሪት ሶሊያና ይህ ህጋዊ አይደለም፤ የአዋጁን አንቀፅ 161 የመተባበር ግዴታን የሚጥስ ተግባር ነው ብለዋል። ስራ ግዴታ መግባት አለባችሁ የሚሉ አሰሪዎች ህግን ከሚጥስ የወንጀል ተግባር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። | 2021-06-20T16:40:50 | ['#ማሳሰቢያ', '#TikvahFamily'] | null | """""" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,138 | (ሰኔ 13 ቀን 2013 ኣ/ም) ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በሃላ እለታዊ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በቦታው ተገኝተዋል። ውድ አባላት በመግለጫው ላይ የሚነሱትን ዋና ዋና ጉዳዮችን የምንልክላችሁ ይሆናል። ከዚህ ባለፈ በቀጥታ መግለጫውን በ Voice Chat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን። | 2021-06-20T18:03:34 | ['#ምርጫ2013'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,140 | የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እለታዊ መግለጫን በቀጥታ በ Voice Chat ይከታተሉ : | 2021-06-20T18:14:08 | ['#LIVE'] | null | null | ['https://t.me/tikvahethiopia?voicechat=70755b28db3a6d96d7'] | ['tikvahethiopia'] |
60,142 | የቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ሰማያዊ ሳጥኖች ተከፍተው መገኘታቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ። ሳጥኖቹን ከፍተው የተገኙበት ምርጫ ክልሎች ላይ አንዳንዶቹ ወደወንጀል ምርመራ ሲላኩ አንዳንዶቹ ተወስኖባቸዋል። ደንቢያ የምርጫ ክልል ሰማያዊ ሳጥኖቹ ተከፍተው ፤ ውስጣቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የሚያሳየው የቡክሌት ተከፍቶ ውስጡ ያለውን ነገር አይተው ተገኝቷል፤ በዚህ ምክንያት 3 አስፈፃሚዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ለፌዴራል ፖሊስ ደብዳቤ ተፅፏል። ደምቢያ ምርጫ ክልል የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን መነካካት ፣ መክፈት በጥብቅ የተከለከለ የወንጀል ተግባር በመሆኑን አስፈፃሚዎች ምርመራ እንዲደረግባቸው ተልኳል። በደምቢያ ምርጫ ክልል ምርጫው ። ተውለደሬ 1 እና 2 ሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያሉእጩዎች እነማን እንደሆኑ ፣ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ ያሉትን እጩዎች የማየት (ፓርቲዎች ቅሬታ አለን ስላሉ ነው እዩ ተብለን ነው) በሚል ተክፍቶ ታይቷል። በዚህ ምክንያት ተውለደሬ 1 እና 2 ነገ ድምፅ አይሰጥም፤ ታግዷል። ግንደበረት (ኦሮሚያ) ነገ ድምፅ ፦ ድምፅ የማይሰጥበት ምክንያት የድምፅ መስጫ ወረቀት እና ቁሳቁስ ስለተከፈተ ሳይሆን የአስፈፃሚዎች እጥረት ነበር። ከዚህ ውጭ ግን ወረዳው አስፈፃሚዎችን አሰልጥኖ ለማስፈፀም ለማሰማራት ሲል በመገኘቱ ገንደበረት ላይ ድምፅ አይሰጥም። ነገሌ ምርጫ ክልል (ጉጂ ኦሮሚያ) ፦ በምርጫ ክልሉ የሚወዳደር የግል ተወዳዳሪ በምርጫ መስጫ ወረቀቱ ላይ ዝርዝሩ ባለመካተቱ ባቀረበው ቅሬታ መሰረት ቦርዱ ምርጫውን ወደ ጳጉሜ 1 አዛውሮታል። | 2021-06-20T18:36:29 | ['#ምርጫ2013', '#ምርጫ_እንዳይካሄድ', '#አይካሄድም።', '#አይሰጥም', '#TikvahEthiopia', '#SolianaShimeles'] | null | ----- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,143 | ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያለው የድምፅ መስጫ ወረቀት ማሸጊያው ባለመከፈቱ ምክንያት የምርጫ ሂደቱ እንዲቀጥል የተወሰነባቸው የምርጫ ክልሎች ስለመኖራቸው አሳውቋል። እነዚህም ፦ ስንቄ 1 እና 2 የምርጫ ቁሳቁስ ሳጥኑ (ሰማያዊ ሳጥን) ወድቆ በመሰበሩ የተወዳዳሪ ፖርቲዎች ወኪል ባሉበት ቃለጉባኤ ተይዞ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ የታሸገው ባለመከፈቱ ምርጫው እንዲካሄድ ተወስኗል። ይህ ምርጫ ጣቢያ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚወዳደሩበት ነው። መተማ ላይ የምርጫ ቁሳቁስ መያዣ ሳጥኑ (ሰማያዊ ሳጥኑ) ቢነካካም የድምፅ መስጫ ወረቀቶቹ ማሸጊያ ባለመከፈቱ ምርጫው እንዲቀጥል ቦርዱ ወስኗል። | 2021-06-20T19:04:04 | ['#Update', '#SolianShimeles', '#TikvahEthiopia', '#TikvahFamily'] | null | •• | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,145 | የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ታሽጎ የሚሄድበትን ሳጥን ፦ መክፈት ማንቀሳቀስ መቁረጥ ውስጡን ማየት ከፍተኛ የሆነ ነው። ምርጫ ቦርድ ለሁሉም ምርጫ አስፈፃሚዎች፣ ወረዳ ላይ ያሉ ዝቅተኛ እርከን ላይ የሚሰሩ የመንግስት አካላት (ይከፈት እንየው የሚሉ) በሙሉ ከፍተኛ ሰጥቷል። በማንኛውም ሁኔታ በምርጫ ክልሎች ላይ ችግር ተፈጥሮ ከተገኘ ወደድጋሚ ምርጫ እንደሚሄድ መታወቅ አለበት ብሏል ቦርዱ ፤ አክሎም የድጋሚ ምርጫ ለሀገር ሃብት ጠቃሚ ስላልሆነ፣ ቦርዱም ብዙ ገንዘብ ስለሚያባክን ከድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ጋር በተገናኘ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል። | 2021-06-20T19:15:37 | ['#ማስጠንቀቂያ', '#ወንጀል', '#ማስጠንቀቂያ', '#TikvahEthiopia', '#TikvahFamily'] | null | ---- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,146 | የምርጫ ወቅት ላይ ስለሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና እንዴት እነዚህን ሀሰተኛ መረጃዎችን መከላከል እንችላለን በሚለው ጉዳይ ዛሬ በቀጥታ Voice Chat ለቲክቫህ ቤተሰቦች ገለፃ ተደርጓል/ለጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል። ገለፃና ለጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ከCARD በፍቃዱ ሃይሉ ፤ ከኢትዮጵያ ቼክ ደግሞ ኤልያስ መሰረት ነበሩ። ምናልባት በቀጥታ በVoice Chat ገለፃውን ማዳመጥ ሳትችሉ የቀራችሁ ቤተሰቦቻችን ከላይ የድምፅ ቅጂው ተያይዟል፤ አዳምጡት። | 2021-06-20T21:21:21 | ['#ሀሰተኛ_መረጃ_እና_ምርጫ2013'] | null | "" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,147 | የነገ ምርጫ/የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ ያሉት ሂደቶች ፦ አንድ መራጭ የመራጮች ምዝገባ ካርዱና ለመራጮች ምዝገባ ያካሄደበትን መታወቂያ መያዝ አለበት። መራጩ ምርጫ ጣቢያ በደረሰበት ወቅት ሰልፍ ካለ መሰለፍ ይኖርበታል። በሰልፉ ላይ ምንም አይነት ቅደም ተከተል (በስም ፣ በፊደል ወይም በምርጫ ካርድ) የለም። የሰልፍ ርቀት የሚያስጠብቁ፣ ሰልፉን ሁኔታ የሚያስተካከሉ አካላት የሚሉትን ማዳመጥ ይኖርበታል። መራጩ ተሰልፎ ተራው ሲደርስ ወደውስጥ ገብቶ መዝገቡ ላይ ስሙ መኖሩ ተረጋግጦ የድምፅ መስጫ ወረቀት ይሰጠዋል። የድምፅ መስጫ ወረቀት ሲሰጠው እጁ ላይ የቀለም ምልክት ይደረግበታል። በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚመርጠውን እጩ የሚመርጥበት የተሸፈነ ወይም ደግሞ የተከለለ (የድምፅ አሰጣጥ መከለያ) አለ እዛ ገብቶ ድምፁን ይሰጣል፤ መራጩ ተመልሶ ሲወጣ ባሉት ሳጥኖች ወስጥ ድምፁን ይከታል። | 2021-06-20T21:23:37 | [] | null | ------- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,148 | በድምፅ መስጫ ቀን የተከለከሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው ? ማንኛውም ሰው ከምርጫ ጣቢያው 200 ሜትር ዙሪያ መለስ ርቀት ውስጥ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ፣ የጦር መሳሪያ ይዞ ወይም በሌላ በማናቸውም ፀጥታን በሚያደፈርስ ሁኔታ ውስጥ መገኘት የለበትም መራጭ ያልሆኑና ድምፅ የሰጡ ሰዎች በምርጫ ጣቢያው ውስጥ መገኘት የለባቸውም ማንኛውም ሰው ያለፈቃድ ወደምርጫ ጣቢያው በመግባት / በምርጫ ጣቢያው ግቢ ውስጥም ሆነ ውጭ የምርጫውን እንቅስቃሴ ማወክ ወይም ማደናቀፍ ወይም ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴ ማድረግ የለበትም ወደ ምርጫ ጣቢያ የማይገቡ ነገሮች ምንድናቸው? ማንኛውም ሰው እንደ በራሪ ወረቀት፣ ፖስተር እና በሌሎች አጭር ፅሁፍ መልክ የተዘጋጁ የምርጫ ቅስቀሳ ሰነዶችን ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያው መግባት አይችልም፡፡ ማንኛውም ሰው የጦር መሳሪያ ወይም እንደጩቤ እንደ ሴንጢ የመሳሰሉ ስለትነት ያላቸውን ወይም እንደየአካባቢው ሁኔታ ለሀይል መጠቀሚያነት የሚውሉ እንደዱላ ፣ አለንጋ ፣ ቁራጭ እንጨት ወይም ብረት ወይም ሌላ ማንኛውንም ተቀጣጣይ ወይም የሚፈነዳ ጠጣር ወይም ፈሳሽ ነገር ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያ መግባት የለበትም። ከላይ የተዘረዘሩትን የተከለከሉ ነገሮች ወደምርጫ ጣቢያ ይዞ የመጣ መራጭ የምርጫ ጣቢያው የሰልፍ አስከባሪ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት በአደራ አስቀምጦ መግባት አለበት። ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ | 2021-06-20T21:41:42 | ['#Attention'] | null | •••••• | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,149 | እጅግ የተከበራችሁ የTikvah Ethiopia ቤተሰብ አባላት በሙሉ ነገ ሀገራችን ከምታደርገው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጋር በተያያዘ መልእክታችሁን በእነዚህ አድራሻዎች አስቀምጡ ፦ በቴሌግራም Bot : በድረገፅ wwwtikvahethiopianet በትዊተር በመልእክት መቀበያ twittercom/tikvahethiopia?s=09 በኢሜል wtsegabcom SMS : +251919743630 ውድ አባላት በምርጫው ወቅት ምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸውን ደንቦች፣ ህጎች እና መመሪያዎች አክብራችሁ ሰላማዊ የሆነ ምርጫ ሂደት ይኖር ዘንድ ሀገራዊ ሃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ አደራ እንላለን። እያንዳንዱን የምርጫ ሂደት እንድትከታተሉ ይሁን። | 2021-06-20T23:32:37 | ['#ምርጫ2013', '#ኢትዮጵያ', '#በንቃት'] | null | ----- | [] | ['tikvahethiopiaBOT', 'gmail', 'tikvahethiopia'] |
60,152 | ኢትዮጵያ 6ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ ጀመረች። ዛሬ ምርጫ በሚካሄድባቸውን የምርጫ ጣቢያዎች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ጀምሯል። ከተለያዩ ከተሞች የወጡ ፎቶዎችን መመልከት እንደቻልነው ፥ ህዝቡ በለሊት ተነስቶ ድምፁን ለመስጠት ሰልፍ ይዟል። ወደ በሃላ ምርጫውን ተንቀሳቅሰው ለመመልከት ፍቃድ ያገኙ የቲክቫህ አባላት በየምርጫ ጣብያው በመገኘት ያለውን ሁኔታ በቀጥታ በVoice Chat በቀጥታ ያሳውቃሉ። Photo Credit : AAPS | 2021-06-21T07:09:52 | ['#ምርጫ2013'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,153 | ምርጫ 2013 በሚመልከት የTikvah Ethiopia አባላት በመልእክት መቀበያ አድራሻዎች መልእክታቸውን እያስቀመጡ ነው። ከለሊት 11:30 ጀምረው ተሰልፈው ምርጫ ጣቢያ ከጥዋት 1 ሰኣት በሃላ የተከፈተበት ቦታ እንዳለ፣ በአዲስ አበባ እና በክልል ባሉ አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ለምርጫው ቢገኙም ጣቢያዎች ዘግይተው መከፈታቸውን አሳውቀዋል። አባላቶቻችን እስካሁን ባለው የተመለከቱት ችግር ምርጫው ይጀመራል ተብሎ ይፋ በተደረገበት ሰኣት አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው መራጮችን አለማስተናገዳቸውን ነው። ከዚህ ባለፈ የኮቪድ 19 መከላከያ ፕሮቶኮል ያለማክበር ችግር እንዳለ አንስተዋል። በፀጥታ እና በሰላም በኩል ግን ሂደቱን በተረጋጋ መንፈስ እየሄደ እንዳለ አባላት እያሳወቁ ነው። የድምፅ መስጫ ሰኣቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ እየተከተልን እናሳውቃለን። Photo Credit : Tikvah Family | 2021-06-21T07:42:31 | ['#ምርጫ2013'] | null | -- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,160 | በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ፦ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ መዘግየት ፣ በድምፅ አሰጣጥ ላይ የሚታይ መደነጋገር፣ ሰኣት አለማክበር፣ የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል አለመጠበቅ፣ ረጃጅም ሰልፎች (በፍጥነት አለመሄድ) ፣ የሰልፍ ተራ አለመጠበቅ፣ የምርጫ ቁሳቁስ መቀያየር ቀልጥፍ ያለ መስተንግዶ ክፍተት መራጮች ምርጫ ካርዳቸውን የወሰዱበትን መታወቂያ ሳይዙ መሄድ እከሌን ምረጡ የሚል ቅስቀሳ ለማድረግ መሞከር የመሳሰሉት ችግሮች ከመስተዋላቸው በዘለለ የምርጫ ሂደቱ እየተካሄድ መሆኑን ከአዲስ አበባና ከክልል የምርጫ ጣቢያዎች የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል። የ Tikvah Ethiopia አባላት በተመለከቷቸው የምርጫ ጣቢያዎች እድሜያቸው የገፋ ዜጎች ፣ እናቶች አባቶች ድምፅ ለመስጠት ተሰልፈው ተመልከተዋል። ነፍሰ ጡሮች፣ ልጅ የታቀፉ እናቶች ተሰልፈው ድምፅ ሲሰጡ አስተውለዋል። በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ በፀጥታ እና በሰላም ረገድ ምንም ጥቆማ ከአባላቶቻችን አልተላከም፤ ሁሉም ሂደት ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ገልፀውልናል። Photo Credit : Tikvah Family (Addis Ababa) | 2021-06-21T09:08:33 | ['#ምርጫ2013', '#በሰላም', '#በተረጋጋ'] | null | -----------""- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,165 | ፎቶ : የኢትዮጵያ ስድስተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ መካሄድ ከጀመረ ሰኣታት ተቆጥረዋል፤ አሁንም የድምፅ መስጠት ሂደቱ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ቀጥሏል። | 2021-06-21T09:40:35 | ['#TikvahFamily'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,166 | ውድ ቤተሰቦቻችን ሁለት በቀጥታ የሚሰራጩ ጉዳዮች ፦ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል እስካሁን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውሮ የተመለከተው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት (ከ4:30 ጀምሮ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ከስካይ ላይት ሆቴል ከስፍራው እናሰማችሃለን (ሰኣቱ ሲደርስ እንነግራችሃለን) | 2021-06-21T10:24:14 | ['#LIVE'] | null | -- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,170 | በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ፦ ሰሚት 2 የምርጫ ጣቢያ፤ ወረዳ 5 ምርጫ ጣቢያ 1፤ ምሥራቅ በር ምርጫ ጣቢያ፤ ወረዳ 5 ምርጫ ጣቢያ 6 እና ምርጫ ጣቢያ 41 ተዘዋውረን የምርጫ ሂደቱን ተመልከትናል። በቀጥታ Voice Chat መከታተል ያልቻላችሁ የድምፅ ቅጂው ከላይ ተያይዟል። | 2021-06-21T10:50:32 | ['#ምርጫ2013'] | null | ---- | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,171 | የፖሊስ ሪፖርት : የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በአገር አቀፍ ደረጃ እስከአሁን ባሰባሰበው መረጃ መራጩ ህዝብ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላማዊና በተረጋጋ መንገድ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል። በቀጣይ ተመሳሳይ መረጃ ከፌዴራል ፣ ከክልልና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እያሰባሰበ ተአማኒነት ያለው መረጃ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል። | 2021-06-21T11:13:25 | [] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,174 | ፎቶ : ይህ አ/አ አያት ዞን ሁለት የሚገኝ ምርጫ ጣቢያ ነው። መራጩ ዜጋ ከጥዋት ጀምሮ ተሰልፏል፤ ሰልፉ ግን የሚጠበቀውን ያህል ንቅንቅ አላለም። ሌሎችም ጣቢያዎች ላይ ቀደም ብለን እንዳሳወቅነው ተመሳሳይ ሁኔታ ይታያል፤ ይህ ሁናቴ መራጩን ዜጋ እያሰላቸ ነው ይፈልጋል። (የቲክቫህ አባላት) | 2021-06-21T11:39:31 | ['#መፍትሄ'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,175 | (ሰኔ 14 ቀን 2013 ኣ/ም) ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በሃላ በዛሬው ቀን ስላለው የምርጫ እንቅስቃሴ የመጀመሪያ ዙር መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በቦታው ተገኝተዋል። ውድ አባላት በመግለጫው ላይ የሚነሱትን ዋና ዋና ጉዳዮችን የምንልክላችሁ ይሆናል። ከዚህ ባለፈ በቀጥታ መግለጫውን በ Voice Chat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን። | 2021-06-21T11:48:25 | ['#ምርጫ2013'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,177 | ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እየሰጡ የሚገኙትን መግለጫ በቀጥታ በ Voice Chat ያዳምጡ። | 2021-06-21T12:40:45 | ['#TikvahFamily'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,179 | ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከደቂቃዎች በፊት የሰጡትን መግለጫ በቀጥታ በVoice Chat ላይ ማዳመጥ ላልቻላችሁ እና ላመለጣችሁ የድምፅ ቅጂው ከላይ ተያይዟል። | 2021-06-21T13:09:38 | ['#መግለጫ1'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,180 | የሰማያዊ ሳጥን ስርቆት ደቡብ ክልል ኦባደብረፃሃይ የምርጫ ክልል አንድ ጣቢያ ላይ ሰማያዊ ሳጥን መሰረቁን የምርጫ ቦርድ ሰብሰባዊ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አሳውቀዋል። ይህንን ጉዳይ ፖሊስ እያጣራው መሆኑን በመግለፅ ምርጫ ቦርድ በፍጥነት ምን ማድረግ እንደሚችል በማወቅ እርምጃ ይውሳዳል ብለዋል። እስካሁን ድረስ ቦርዱ እርምጃ ያልወሰደ ሲሆን አንድ ጣቢያ ብቻ ስለሆነ ቦርዱ ፈጣን እርምጃ ይወስዳል ሲሉም ተናግረዋል። | 2021-06-21T13:17:21 | [] | null | "" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,181 | እስካሁን ያጋጠመ የፀጥታ ችግር የለም ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እስካሁን ባለው ሂደት አንድም ቦታ የፀጥታ ችግር እንዳልገጠመ አሳውቀዋል። በአምቦ አንድ የምርጫ ክልል አንድ ጣቢያ አስፈፃሚዎች በደረሳቸው መረጃ ተደናግጠው ከአካባቢው ገለል ማለታቸውን ነገር ግን ምን ችግር እንዳልነበር ገልፀዋል። ወ/ሪት ብርቱካን በጣቢያው የምርጫ ሂደቱ እናስቀጥላለልን ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል። ከዚህ ውጭ ምርጫው እየተደረገባቸው ባሉ ቦታዎች ሁሉ በሰላም መራጮች ድምፅ እየሰጡ እንደሆነ አሳውቀዋል። | 2021-06-21T13:22:20 | [] | null | ""-"" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,182 | በአማራና ደቡብ ክልል የታዩ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች በየምርጫ ጣቢያው ታዛቢ ወኪሎቻቸውን አስቀምጠው ጉዳዩን የመታዘብ እና የማየት ፣ችግር ካላቸው ያን አስመዝግበው ወደፍርድ ቤት የሚሄዱ ከሆነም ያን አስመዝግበው ሰነዶቻቸውም ይዘው ክርክራቸውን የመቀጠል መሰረታዊ መብት አላቸው። በዚህ ረገድ አብዛኛው ክልል ጥሩ የሚባል ሁኔታ አለ፤ ነገር ግን በሁለት ክልሎች (አማራ እና ደቡብ) በጣም አሳሰቢ በሆነ ደረጃ፣ በአንዱ (አፋር ክልል) በመለስተኛ ደረጀ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር ሁኔታ መመልከቱን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል። አማራ እና ደቡብ ክልሎች ላይ የፖለቲካ ፓርቲ እጩ ወኪሎች ከቦታ ቦታ በፈለጉበት አግባብ መንቀሳቀስ እየቻሉ እንዳልሆነ፣ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ፣ ባጅ እየተቀሙ እንደሆነ ፣ ወደ ጣቢያ ሊጠጉ የማይችሉበት ሁኔታ እየተፈጠረ እንደሆነ እጅግ በጣም ብዙ አቤቱታ ለቦርዱ ቀርቧል። አቤቱታው በስተቀር ከሁሉም ፓርቲዎች ነው ለቦርዱ የቀረበው። የክልሎቹ አስተዳዳሪዎች ይህን ችግር እንዲያስተካክሉ እና እንዲፈቱ ቦርዱ አሳስቧል። ቦርዱ፥ ችግሩ ካልተፈታ የምርጫ ሂደቱን እና የውጤቱን ታማኝነት ችግር ላይ እንደሚጥለው ሊታወቅ ይገባል ብሏል። ምርጫ ቦርድ ክልሎቹ በአፋጣኝ ማስተካከያ እንዲያደርጉ የታችኛው የአስተዳደር ክፍል በተጨማሪ አንዳንድ ጊዜ የህግ አስፈፃሚዎች በፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች ላይ ፣ በእጩ ወኪሎች ላይ የሚፈፅሙት ከህግ ውጪ የሆኑ ድርጊቶችን እንዲያቆሙ ሲል በጥብቅ አስገንዝቧል። | 2021-06-21T13:40:47 | ['#ከገዢው_ፓርቲ', '#አሁንኑ'] | null | '' | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,183 | አተዳዳሪዎች ዛሬ የስራ ቀን አይደለም ወደቤት ግቡ ከምርጫ ጣቢያዎች ውጪ በተለይም በፖለቲካ ፓርቲ እጩ ወኪሎች ላይ በስፋት የሚደረጉ ህገወጥ ተግባራት በውጤቱ ላይ ትልቅ ተፅእኖ አላቸው። ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ውጤት በሚመረምርበት ሁኔታ እና በሚያፀቅድበት ጊዜም ይህንን ታሳቢ አድርጎ ነው። ይሄን የመንግስት አካላት ማወቅ አለባቸው። የመንግሥት አካላት ሰራተኞቻቸውን ፣ አስተዳዳሪዎቻቸውን ወደቤቶቻቸው እንዲገቡ ማድረግ አለባቸው። ዛሬ የስራ ቀን አይደለም ከህግ አስፈፃሚዎች ውጪ፣ ከምርጫ ቦርድ ውጪ ፣ ከመሰረታዊ አገልግሎት ሰጪዎች ውጪ ደጅ ላይ የሚሰራ ማንኛውም አካል የለም። ለሎጅስቲክስ እገዛ በሚያስገልግበት ጊዜ መገኘት አለባቸው ነገር ግን ምርጫ ጣቢያ አካባቢ ተገኝተው ፣ ወይም የምርጫ ክልል ፅ/ቤት ተገኝተው /ሌላ ቦታ ተገኝተው የእጩዎችን ወይም የወኪሎቻቸውን ተግባር የሚያሰናክሉበት ምንም ምክንያት አይኖርም፤ ተቀባይነትም የለውም፤ ህገወጥ ነው። በአማራ እና በደቡብ ክልል በጣም አሳሳቢ በሚባል ደረጃ፣ በአፋር ክልል ደግሞ በመለስተኛ ደረጃ በፓርቲ እጩ ወኪሎች ላይ ህገወጥ ተግባር የመፈፀም ሁኔታ መታየቱን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል። ከምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን መግለጫ ላይ የወሰድነው። | 2021-06-21T14:18:28 | [] | null | '' | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,184 | በአዲስ አበባ ላይ ዘጠኝ የምርጫ ጣቢያዎች ስልጠና የተሰጣቸው የምርጫ አስፈፃሚዎች በጣቢያው ሳይገኙ በመቅረታቸው ምርጫው በጣቢያዎቹ ዘግይቶ መጀመሩን ቦርዱ ገልጿል። የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርትኳን ሚዴቅሳ እነዚህ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ አሰልጣኝ የነበሩ ብቁ 27 አስፈፃሚዎች መተካታቸውንና ምርጫው መጀመሩን ገልፀዋል። በተጨማሪም በአዲስ አበባ አንድ ምርጫ ጣቢያ የመራጮች መዝገብ መጥፋቱንም አሳውቀዋል። ጉዳዩ እንደሚጣራ በመጥቀስ አሁን ላይ መዝገብ እና ምርጫ አስፈፃሚ ተልኮ በጣቢያው የተመዘገቡ ካርዳቸው ከጣቢያው መወሰዱ የተረጋገጠ መራጮች እየተመዘገቡ የምርጫ ሂደታቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። የምርጫ ጣቢያዎችን አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርትኳን ሂደቱን ተመልክቶ ቦርዱ በተለየ ሁኔታ ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ እንደሚችል ገልፀዋል። | 2021-06-21T15:55:42 | ['#AddisAbaba', '#ዘግይተው_የተከፈቱ'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,185 | ድምፅ ለመስጠት ተሰልፌ 12 ሰኣት ቢሞላስ ? የድምፅ መስጫ ጊዜ ከንጋቱ 12:00 ሰኣት እስከ ምሽቱ 12:00 መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ሂደት መራጮች ለመምረጥ ሰልፍ ላይ እያሉ ምሽት 12 ሰኣት ቢሆን የተሰልፉት መራጮች መርጠው እስኪጨርሱ ምርጫው ይካሄዳል። በሰልፍ ላይ ያሉ መራጮችን 12:00 ሰኣት ሆኗል ወደቤታችሁ ሂዱ ወይም አትመርጡም የሚባልበት ሁኔታ የለም። : ከ12:00 ሰኣት በሃላ (የድምፅ መስጫ ጊዜ ከተጠናቀቀ በሃላ) አዲስ መራጮች ድምፅ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያ መሄድ አይችሉም። ከ12:00 በፊት ተሰልፈው የነበሩት እንጂ አዲስ የሚመጡት አይስተናገዱም። | 2021-06-21T15:55:51 | ['#ምርጫ2013', '#NB:'] | null | "" | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,186 | በአዳማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ። 1ኛ ስንታየሁ ኡርግዬ የተባለ ግለሰብ በአባገዳ ክ/ከተማ ኦዳ ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘቱ በአዋጅ ቁጥር 1177/2011 ኣም የተቀመጠን ክለከላ በመጣስ ወንጀል ተከሶ በአንድ ኣመት እስራትና በ5 ሺህ ብር ነው ተቀጥቷል። 2ኛ ከማል አብዶ የሚባል ገለሰብ በምርጫ ጣቢያ 6 ከጠዋቱ 2 ሰአት ከ40 ላይ ድምፅ ሰጪ መስሎ ድምፅ መስጫ ጣቢያው ድረስ በመግባት ሂደቱን ለማወክ ጥረት በማድረጉ በ8 ወር እስራት ተቀጥቷል። በምርጫ ወቅት ሊኖሩ የሚችሉ ወንጀሎችን ለመመልከት የተቋቋመው የአዳማ ወረዳ የወቅታዊ ጉዳይ ችሎት ነው ግለሰቦቹን በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ውሳኔ ያሳለፈው። መረጃው የኢዜአ ነው። | 2021-06-21T16:44:38 | ['#ምርጫ2013'] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
60,192 | የከሰኣቱ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት! የምርጫ 2013 ድምፅ መስጫ ሰኣት ወደመጠናቀቁ እየሄደ ነው። በጥዋቱ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በተለይ ረጃጅም ሰልፎች መኖራቸው፣ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ ወረቀት አልቋል በሚል መጉላላቶች ሲፈጠር ነበር። ከሰኣት በአ/አ ተዘዋውረን በተመለከትናቸው ጣቢያዎች አሁንም ረጃጅም ሰልፎች አሉ፣ ከክልል በመጡልን መልእክቶች አንዳድን ቦታዎች ላይ ወረቀት አልቋል በሚል መራጮች እንደተጉላሉ/ረጅም ሰልፎችም መኖራቸውን ገልፀዋል። በተለይ ሂደቱ ፍጥነት ያልተላበሰ በመሆኑ መራጮች እጅግ ረጅም ሰኣት ለመሰለፍ ተገደዋል። ያም ሆኖ ዝናብ፣ ፀሃዩን፣ ብርዱን ችሎ መራጩ ድምፁን እየሰጠ ነው። ምርጫ ቦርድ ምርጫው ዘግይቶ በጀመረባቸው፣ ረጃጅም ሰልፎች ባሉባቸው ቦታዎች የሰኣት ሁኔታውን እንዲያጤነው መልእክታቸውን የላኩ አባላት ጠይቀዋል። | 2021-06-21T17:15:12 | [] | null | null | [] | ['tikvahethiopia'] |
End of preview. Expand
in Dataset Viewer.
No dataset card yet
New: Create and edit this dataset card directly on the website!
Contribute a Dataset Card- Downloads last month
- 3