id
int64
60k
84.2k
text
stringlengths
6
3.93k
date
stringlengths
19
19
hashtags
stringlengths
2
366
emojis
stringlengths
1
96
symbols
stringlengths
1
137
links
stringlengths
2
588
mentions
stringlengths
2
186
84,209
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ምንም ያህል ቢደረግ የህዳሴውን ግድብ እንዳሳካነው የባህር በሩም በተመሳሳይ ይሳካል አሉ። አምባሳደር ሬድዋን፤ የህዳሴውን ግድብ ያሳካነው ተጨብጭቦልን ሳይሆን ከቅርብም ከሩቅም እየተላጋን፣ የሥጋት ከበሮ እየተደለቀ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ በምድርም በአየርም ልምምድ እያስገመገመብን ፣ ሁሉንም ኣይነት ጫና ተቋቁመን ነበር ብለዋል። የባህር በሩም እንዲሁ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል።
2024-01-12T00:19:12
['#Ethiopia', '#ጫና']
null
""""
[]
['tikvahethiopia']
84,217
በምጥ የተያዘችን እናት ሊያመጣ ሲሄድ በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአምቡላንስ ሼፌሩ በተተኮሰበት ጥይት ። በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን ‘የእምባስነይቲ ቅርንጫፍ’ የአምቡላንስ ሹፌር አቶ ወልዱ አረጋዊ በርሀ የወላድ እናትን ህይዎት ለማዳን እያሽከረከረ ባለበት ሰኣት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል። አቶ ወልዱ በቀን 01/05/2016 ኣ/ም ከምሽቱ/ከሌሊቱ 5፡20 አካባቢ ከተመደበበት የስራ ቦታው ‘ከነበለት’ ለመውለድ በምጥ የተያዘችን እናት ሊያመጣ ወደ ‘ኣዲ ጉደም’ የተባለ ቀበሌ የሕክምና ባለሙያ ይዞ በመጓዝ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ጥይት ተተኩሶበት ክፉኛ ሊቆስል ችሏል። በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ደርሰዉለት ወደ ‘ነበለት ጤና ጣቢያ’ የተወሰደ ቢሆንም፣ ጉዳቱ ከጤና ጣብያው አቅም በላይ ስለነበር ወደ መቐለ ኣይደር ሆስፒታል ሪፈር ተብሎ እየሄደ ሳለ ሆስፒታል ሳይደርስ ህይወቱ አልፏል። አቶ ወልዱ አረጋዊ በኢቀመማ ትግራይ ክልል ማእከላይ ዞን ቅርንጫፍ በእምባስነይቲ ወረዳ ከ2008 ኣ/ም ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ድረስ የአምቡላንስ ሹፌር በመሆን በማገልገል ላይ ነበር። የቀይ መስቀል መርህ እና ህግን ተከትሎ በታማኝነት በማገልገል ላይ የነበረው አቶ ወልዱ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል። አቶ ወልዱ አረጋዊ ባለትዳርና የ6 ልጆች አባት ነበር። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በማህበሩ ሰራተኞችና አምቡላንሶች እንዲሁም ንብረቶች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን ገልፆ ይህ ተቀባይነት የሌለዉ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስት የፈረመዉን ኣለም አቀፍ የጄኔቫ ስምምነት የሚጥስ ነው ብሏል። ማንኛዉም አካል የማህበሩን ሰራተኞችና ንብረቶች የጥቃት ኢላማ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
2024-01-12T00:54:13
['#ተገደለ።']
null
""-
[]
['tikvahethiopia']