Unnamed: 0
int64
0
51.5k
headline
stringlengths
2
861
⌀
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
6
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
1
34.3k
⌀
link
stringlengths
28
722
word_len
int64
0
6.74k
50,090
ፕሬዚደንት አልበሽር በሱዳን ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ በኋላ የመጀመሪያ መልዕክታቸውን አስተላለፉ
ፖለቲካ
December 26, 2018
Unknown
በሱዳን ኑሮ ተወደደብን በሚል የተነሳው ተቃውሞ  የቀጠለ ሲሆን ፕሬዝደንት ኦማር ሀሰን አልበሽርም ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ ወዲህ የመጀመሪያ መልእክታቸውን አስተላልፈዋልበሱዳን ላለፉት ስድስት ቀናት በኑሮ ተወደደብን በሚል በተለይም በዳቦ እና ነዳጅ እጥረት ምክንያት የተቀሰቀሰው አሁንም አለመብረዱ ነው የተነገረውበሺዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች በአደባባይ ወጥተው ተቃውሟቸውን እየገለፁ ነውተቃውሞ በተለያዩ አካባቢዎች መቀጠሉን ተከትሎ ፖሊስ ተቃውሞውን ለመበተን ባደረገው ሙከራም ግጭት ተፈጥሮ በህይወትና በአካል ላይ ጉዳት መድረሱ ነው የሚነገረውተቃዋሚዎች በግጭቱ ምክንያት 22 ዜጎች ተገድለዋል ሲሉ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽል በበኩሉ 37 ዜጎች በግጭቱ መሞታቸውን ገልጿልየሀገሪቱ መንግስት ግን ሰልፈኞቹ ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው 8 ሰዎች ተጎድተዋል ከማለት ውጭ የሞቱትን ይፋ አላደረገምአሁን የሰልፈኞቹ መፈክር የዳቦና የነዳጅ ዋጋ እና እጥረቱ ይቀረፍ ኑሮ ተወደደብን የሚለው የተቀየረ ይመስላል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በቤተ መንገስቱ አቅራቢያ አልቃሳር በተባለው መንገድ አካባቢ ተሰባስበው ነፃነት እንፈልጋለንፍትህ እንፈልጋለን ፕሬዝደንቱ ከስልጣን ይውረዱ የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል ነው የተባለውፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተንም አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙንና በርካታ ሰልፈኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ምንጮችን ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧልፕሬዝደንት ኦማረ ሀሰን አልበሽር በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አስመልክቶ ለመጀመሪ ጊዜ ባስተላለፉት መልእክትም የተቃውሞ ሰልፉ በውጭ ሀገራት ጫና ምክንያት የተቀሰቀሰ መሆኑን አንስተዋልየሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ ለማሻሻልና የኑሮ ውድነቱን ለማረገብም መንግስት እየሰራ መሆኑን አስተላልፈዋልአሜሪካና አንግሊዝን ጨምሮ ሌሎች የምእራባውያን ሀገራት ከሰብአዊ ጥሰትና ሙስና ጋር ተያይዞ በሱዳን ላይ የኢኮኖሚ ማእቀብ መጣላቸው ይታወሳልምንም እንኳ ፕሬዝደንት አልበሽር  ይህን ቢሉም የሀገሪቱ ተቃዋሚዎች ግን የተቃውሞ ሰልፍና የሀገሪቱን ችግር  ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ መሆኑን እየገለፁ ነውየሱዳን ኮምኒስት ፓራቲው ሳዲቅ ካቢሎ እንደሚሉት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ችግር የሀገሪቱ ፖለቲካ መቀላቀል ያስከተለው ችግር መሆኑን ነው የሚናገሩትየ74 አመቱ ፕሬዝደንት አልበሽር ላለፉት 3 አስርት አመታት አካባቢ ሱዳንን በፕሬዝደንት እየመሩ ሲሆን በመንግስታቸው ሰብአዊ ጥሰትና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ተፈፅመዋል በሚል በአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ እንደቆረጠባቸው ይታወቃል
https://waltainfo.com/am/33231/
254
49,789
የኢትዮ-ጊኒ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰበ ተጀመረ
ፖለቲካ
February 7, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የጊኒ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማማዲ ቱሬ በተገኙበት በዛሬው እለት የሁለቱ አገሮች የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ በይፋ ተጀመሯልውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ የሁለቱን አገሮች የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን መመስረቻ ስምምነት ፈርመዋልከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተገኙበት የከፍተኛ ኤክስፐርቶች ቃለ ጉባኤ ስምምነት ተፈርሟልየከፍተኛ ኤክስፐርቶች ስብሰባ በአራት ቡድኖች ተከፍሎ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጓልሁለቱ አገሮች በቀጣይ በጋራና በትብብር ሊሰሩ በሚገባቸው የሁለትዮሽና አለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ በሚኒስትሮች የሚፈረሙ በርካታ ሰነዶችን የመመርመርና የመከለስ ሰራዎችን አከናውኗልምንጭየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ፅቤት
https://waltainfo.com/am/30920/
85
44,589
በኢትዮጵያ የተሽከርካሪዎች ቁጥር 831ሺህ መድረሱ ተገለጸ
ቢዝነስ
November 10, 2017
Unknown
በኢትዮጵያ የተሽከርካሪዎች ቁጥር 831 ሺህ መድረሱን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው ለዋሚኮ እንደገለፁት ከአገሪቱ  የምጣኔ ሀብት እድገት ጋር  በተያያዘ የዜጎች የገቢ መጠን በማደጉ ምክንያት ወደ  አገሪቱ  የሚገቡ  የተሽከርካሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እያደገ  መጥቷል ብለዋል በ2008 አም የአገሪቱ የተሸርካሪዎች ቁጥር 708ሺህ 410 እንደነበር ያስታወሱት አቶ ይግዛው  እስከ ሰኔ 30  2009 ድረስ የአገሪቱ  የተሽከርካሪዎች ቁጥር  831ሺህ 265  መድረሱን  ተናግረዋል በአጠቃላይ  በአገሪቱ ሁሉም  ክልሎች  የተሽከርካሪዎች ቁጥር  እያደገ መምጣቱን የጠቆሙት አቶ ይግዛው በአገሪቱ  ከሚገኙት   ተሽከርካሪዎች 62 በመቶ የሚሆኑት በአዲስ አበባ ከተማ  ይገኛሉ ብለዋል በአገሪቱ ውስጥ  በአገልግሎት ላይ የሚገኙ ያረጁ ተሽከርካሪዎች  አገልግሎት  እንዳይሰጡ ለማድረግ  ባለስልጣኑ በየአመቱ የተጠናከረ የቴክኒክ ፍተሻ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አቶ ይግዛው አመልክተዋል በተጨማሪም  ረጅም  አመት  ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች  ወደ አገር ውስጥ  እንዳይገቡ  የሚደረግበትን ሁኔታ  በማጥናትም    ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ማቀረቡን አቶ ይግዛው ተናግረዋል 
https://waltainfo.com/am/23340/
128
46,622
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀጣዩ ዓመት ተጨማሪ ተማሪዎችን ይቀበላል
ሀገር አቀፍ ዜና
September 9, 2016
Unknown
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ እንዲረዳው በሚከፍታቸው ሁለት አዳዲስ ካምፓሶች ተጨማሪ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ለዋልታ ገለፀሁለቱ አዳዲስ ካምፓሶች ሰላምና ሜዲካል እንደሚባሉ በዩኒቨርሲቲው በስትራቴጂክ ማኔጅመንትና ኮሙኒኬሽን ክፍል የድረ ገፅና የማህበራዊ ሚዲያ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ሙሉ ለዋልታ ተናግረዋልበሰላም ካምፓስ የጨርቃ ጨርቅ ትምህርትበሜዲካል ካምፓስ ደግሞ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገንብቶ የህክምና ትምህርት እንደሚሰጥ ስራ አስኪያጁ አስረድተዋልበአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ በማታበርቀትና በድህረ ምረቃ መርሀ ግብር 52 ሺ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ እንደሚገኝ አቶ ሰለሞን ገልፀዋልዩኒቨርሲቲው በአዲሱ አመት በመደበኛ መርሀ ግብር አንድ ሺ ተጨማሪ ተማሪዎችን በመቀበል የቅበላ አቅሙን 14ሺ እንደሚያደርስ ነው በገለፃው የተመለከተውዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ መርሀ ግብር 68 የተለያዩ የትምህርት ዘርፎችን እየሰጠ ይገኛል በድህረ ምረቃ መርህ ግብርና ለማህበረሰብ አገልግሎት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚንቀሳቀስም ለማወቅ ተችሏልየድህረ ምረቃ መርህ ግብር ዘርፍን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ከውጭ አገር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅትና በአጋርነት እየሰራን ነው ብለዋልአቶ ሰለሞንዩኒቨርሲቲው እያካሄደ ባለው የማስፋፊያ ስራ መምህራን ጥቅማቸው ተከብሮላቸው ሙሉ አቅማቸውን ለማማር ማስተማሩ ሂደት ያውሉ ዘንድ የመኖሪያ ቤት እየተገነባ መሆኑንም አቶ ሰለሞን አስገንዝበዋልዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የማህበረሰብ ልማቶችን እያካሄደ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሰለሞን አብዛኛውን ማህበረሰብ ያቀፈ ስራ ለማከናወን ትኩረት መስጠቱን ተናግረዋል ከህዝቡ ጋርም 200 የማህበረሰብ ልማቶችን ለማከናወን ስምምነቶችን ተፈራርሟል ብለዋልባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ1993 አም ባህር ዳር ፖሊቴክኒክና ባህር ዳር የመምህራን ኮሌጅን በማጣመር ነው የተቋቋመው በአገሪቱ ውስጥ ካሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ ነውየተሻሻሉ የቲማቲም ዝርያዎችን ማስተዋወቅ የባዮ ጋዝ ልማትየህግ አገልግሎትና የአማርኛ ቋንቋን የማበልፀግ ስራዎች ዩኒቨርሲቲው ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ ከሚሰራባቸው ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ጥቂቶቹ ናቸው 
https://waltainfo.com/am/31460/
216
2,912
የእብድ ውሻ በሽታን ለማስወገድ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሠራ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
February 11, 2020
36
አዲስ አበባ የእብድ ውሻ በሽታን በ2022 አም ከኢትዮጵያ ለማስወገድ ስልታዊ እቅድ በማውጣትና ብሄራዊ የጤና የጋራ ግብረ ሀይል በማቋቋም እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሊያ ታደሰ ገለፁየእብድ ውሻ በሽታ አመታዊ በአልን አስመልክቶ ትናንት በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስልጠና ማእከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ሊያ ታደሰ እንደገለፁትለ60 በመቶው የሰው በሽታ መነሻው ከአንስሳት ነውየእብድ ውሻ በሽታ 90 በመቶው በውሻ መነከስ የሚመጣ እና በድመት መቧጨር ወደ ሰው የሚተላለፍ መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ሊያአብዛኞቹ ተጠቂዎችም ህፃናትና ሴቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል በሽታውን በ2022 አም ከኢትዮጵያ ለማስወገድ ስልታዊ እቅድ መዘጋጀቱን ጠቅሰውብሄራዊ የጤና የጋራ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑንም አብራርተዋል በሽታውን ለመከላከል ትምህርታዊ ግንዛቤዎች መሰጠት እንዲሁም የህክምና ማእከል እንደሚያስፈልግ ጠቁመው በአዲስ አበባም ጉለሌ አካባቢ ለዚህ የሚረዳ የህክምና ማእከል መሰራቱን ተናግረዋል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ዶክተር ጥላሁን አየለየበሽታው ተጠቂዎች በአብዛኛው የእስያና የአፍሪካ አገራት መሆናቸውን ገልፀዋል በኢትየጵያም በሽታው በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች እንዳለ ጠቅሰውመፍትሄ አለማግኘቱን ጠቁመዋል ችግሩን ለማቃለል በቁጭትና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋልበግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ህክምና ጤና ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት በቀለ በመድረኩ ላይ ባቀረቡት ጥናት በእብድ ውሻ በሽታ በአለም ላይ በአመት ከ70 ሺ በላይ ሰዎች በኢትዮጵያ ደግሞ 2 ሺ 700 እንደሚሞቱ አስታውቀዋል ይህም ህክምና ሳይሄዱ በየቤቱ የሞቱትን እንደማያካትት አመላክተዋል በመድረኩ በሽታውን ለመቆጣጠር የግብአት እንዲሁም ባለሙያዎች አቅርቦት ማጎልበትና የህዝቡን ግንዛቤ ማሻሻል እንደሚገባ መንግስት ለዚህ ትኩረት መስጠት እንዳለበት ተጠይቋል ከዚህ ባለፈ በየመንገዱ ያሉ ውሾች የሚወገዱበትን ሁኔታ መፍጠርዘላቂ ክትባት ለውሾች መስጠትበውሻ የተነከሱትም በፍጥነት ህክምና እንዲሄዱ ማድረግና የተነከሱትንም ለ15 ደቂቃ በውሀና ሳሙና ማጠብ እንደሚገባም ተመላክቷልአዲስ ዘመን የካቲት 32012ሀይለማርያም ወንድሙ
https://www.press.et/Ama/?p=27042
234
12,874
ታላቁ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ ሳትቀበለው ቀርታለች
ሀገር አቀፍ ዜና
Jan 3, 2021
4,054
አዲስ አበባ ታህሳስ 25 2013ኤፍቢሲ ታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡትን ረቂቅ ሰነድ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ ሰነዱን ሳትቀበለው ቀርታለች በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዛሬ የተካሄደውን የሶስትዮሽ ውይይት አስመልክቶ የውሀ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧልአዲስ አበባ ታህሳስ 25 ቀን 2013 የኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሀ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው እለት በበይነ መረብ ስብሰባ አካሂዷልስብሰባው በደቡብ አፍሪካ የአለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈፃሚ ምከር ቤት ሊቀመንበር ሰብሳቢነት ነው የተካሄደውሚኒስትሮቹ የህዳሴው ግድብ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ምክከር ያደረጉ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድ ላይ በማተኮር ምክክር ተደርጓልበዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ባለሙያዎቹ የቀረፁትን ሰነድ በበጎ እንደምትመለከተው እና በቀጣይ በሚካሄደው ድርድር ሰነዱን እንደግብአት ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆኗን ገልፃለችየሱዳን ወገን በበኩሉ ሰነዱን ለሂደቱ ጠቃሚ አድርጎ እንደሚመለከተው እና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ተጨማሪ ሚና ላይ ቢጋር በማፅደቅ ድርድሩን መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጿልየግብፅ ወገን ደግሞ ሰነዱን ጨርሶ እንደማይቀበለው አስታውቋልየህዳሴው ግድብ ሙሌት እና አመታዊ አስተዳደርን የሚመለከተው ሰነድ ላይ የሚደረገው ድርድር በአመዛኙ መግባባት የተደረሰበት ቢሆንም ወደፊት በአባይ ተፋሰስ ላይ በሚገነቡ የውሀ ልማት ስራዎች ጋር በተያያዘ የሚኖረው ቁርኝት ዋነኛ የልዩነት ሀሳብ ነውየታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሀ ፍጆታ የሌለው የሀይል ማመንጫ ግድብ እንደመሆኑ በግድቡ ላይ የሚደረሰው ስምምነት ይህንኑ ከግምት ያስገባ እና የተሟላ የውሀ ስምምነት በሌለበት እና ኢፍትሀዊ አጠቃቀም በሰፈነበት ተፋሰስ የኢትዮጵያን የመጠቀም መብት የሚያቅብ እንዲሆን ኢትዮጵያ አትፈቅድምይህን መሰረት በማድረግም ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ እሞላል እና አመታዊ አስተደዳር የሚመለከተውን ደንብ በጋራ ስምምነት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ ናትበዚህ መሰረት የስምምነት አማራጮችን ለግብፅ እና ሱዳን ወገን ያቀረበች ሲሆን የሀገራቱ ምላሽ ቀና እንደሚሆን ተስፋ ይደረጋልበቀጣይ የሀገራቱ ባለሙያዎች በውሀ ሚኒስትሮች አመራር ስር ስብሰባቸውን በመቀጠል ስምምነት የተደረሰባቸውን እና የልዩነት ሀሳቦችን በመለየት በቀጣይ እሁድ ጥር 1 ቀን 2013 አም ለሚካሄደውየስድስት ሚኒስትሮች ስብሰባ ውጤቱን ያቀርባሉከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘትየፋና ድረ ገፅ httpswwwfanabccom ይጎብኙ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል httpswwwyoutubecomcfanabroadcastingcorporate ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል httpstmefanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን httpstwittercomfanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
https://www.fanabc.com/%e1%89%b3%e1%88%8b%e1%89%81-%e1%8b%a8%e1%88%95%e1%8b%b3%e1%88%b4-%e1%8c%8d%e1%8b%b5%e1%89%a5%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%88%98%e1%88%8d%e1%8a%ad%e1%89%b6-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8d%8d%e1%88%aa/
313
25,188
በማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት የዲአፍሪክ ሆቴል ባለቤት በነፃ ተሰናበቱ
ፖለቲካ
17 April 2016
Unknown
ወላጅ አባታቸው ሳይናዘዙላቸው እንደተናዘዙ በማስመሰል ለሀሰተኛ የኑዛዜ ማረጋገጫ ሰነድ በማቅረብ 821 ሚሊዮን ብር ወስዷል በመባል ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀምና በማታለል ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የዲአፍሪክ ሆቴል ባለቤት በነፃ ተሰናበቱየአባታቸው የኑዛዜ ቃል ሳይሆን እንደሆነ በመግለፅ ለፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍትሀ ብሄር ችሎት በማቅረብ የማታለል ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የፌዴራል አቃቤ ህግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ክስ መስርቶባቸው የነበሩት የሆቴሉ ባለቤት አቶ ብስራት ሰይፉ ናቸውአቶ ብስራት አቃቤ ህግ ተበዳዮች ናቸው ያላቸውን የዲአፍሪክ ሆቴል መስራችና ባለቤት የነበሩትን የአቶ ሰይፉ ገብረ ዮሀንስ ወራሾችን አሳምነውና በሟች አባታቸው ያልተፈረመን የኑዛዜ ሰነድ ለፍርድ ቤት በማቅረብና ፍርድ ቤቱ ኑዛዜውን እንዲያፀድቅላቸው በማድረግ ሌሎች ወራሾችን የሚጎዳ 82160000 ብር ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን በክሱ አካቶ አቅርቦ ነበርፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ከተገቢው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ የክስ መዝገቡን መመርመሩን ጠቁሞ ተከሳሹ ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉት ከ15 አመታት በፊት በ1992 አም ከመሆኑ አንፃር በይርጋ የሚታገድ ወይም ቀሪ የሚሆን እንደሆነ መገንዘቡን በውሳኔው አስታውቋልተከሳሹ ለስር ፍርድ ቤት አቀረቡት የተባለው ሀሰተኛ ኑዛዜ የተደረገው መስከረም 18 ቀን 1991 አም መሆኑን የጠቆመው ፍርድ ቤቱ ኑዛዜ በሶስት መንገድ ሊቀርብ እንደሚችል የፍትሀ ብሄር ህግ አንቀፆችን ጠቅሶ አስቀምጧል በፍትሀ ብሄር ህግ ቁጥር 881 መሰረት በግልፅ በሚደረግ ኑዛዜ በፍሀብሄህቁ 884 መሰረት ተናዛዡ በፅሁፍ በሚያደርገው ኑዛዜና በፍሀብሄህቁ 892 በቃል የሚደረግ ኑዛዜ መሆኑን ጠቁሟል በተጠቀሰው የህግ አካሄድ መሰረት ኑዛዜ ከመደረጉ ውጪ በፍርድ ቤት ቀርቦ ሊፀድቅ ወይም የፍርድ ቤቱን ይሁንታ ሊያገኝ ስለሚችለበት ሁኔታ በፍትሀ ብሄር ህግ ውስጥ አንድም ቦታ ተደንግጎ እንደማይገኝ ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አሳውቋልበመሆኑም አቶ ሰይፉ ሳይናዘዙ በሀሰት የተዘጋጀ ነው የተባለው ኑዛዜ ወደ መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሄዶ ፀድቋል መባሉን ማየት አስፈላጊ ባለመሆኑ ተቀባይነት እንደሌለው ፍርድ ቤቱ በዝርዝር አስቀምጧል ፍርድ ቤቱ የተመሰረተው ክስ ሊያከራክር ይችላል ቢል እንኳን ጊዜውን መመልከት ግድ እንደሚለው ጠቁሞ ክርክሩ በወንጀል ህግ አንቀፅ 217 1ሀ እና በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርአት ህግ አንቀፅ 226 መ መሰረት በይርጋ ቀሪ መሆኑን በመግለፅ ክርክሩ መዘጋቱን አስታውቋል
https://www.ethiopianreporter.com/article/12170
284
25,654
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለምስክርነት እንዲቀርቡ የተላለፈው ትዕዛዝ ታገደ
ፖለቲካ
1 November 2015
Unknown
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በሽብር ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው ለተከሰሱት ለእነ ዘመኑ ካሴ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ያስተላለፈውን ትእዛዝ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አገደውየፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ሀምሌ 6 ቀን 2007 አም የሰጠውን ብይን ያገደው የፌዴራል ማእከል አቃቤ ህግ ያቀረበውን ይግባኝ ሲመረምር የሚያስቀርብ ሆኖ በማግኘቱ መሆኑን ባስተላለፈው ትእዛዝ አስታውቋልአቶ አንዳርጋቸው በመከላከያ ምስክርነት በቆጠሯቸው በእነ ዘመኑ ካሴ የክስ መዝገብ አስር ሰዎች የተካተቱት አቶ አሸናፊ አካሉ አቶ ደህናሁን ቤዛ አቶ ምንዳዬ ጥላሁንና አቶ አንሙት የኔዋስ ሲሆኑ እንዲመሰክሩላቸው የፈለጉትም ተከሳሾቹ ኤርትራ ሄደው ከአቶ አንዳርጋቸው ትእዛዝና መመርያ እንደተቀበሉ አቃቤ ህግ የጠቀሰባቸውን ክስ እንዲያስረዱላቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳልበወቅቱ ከሳሸ አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው በተለያዩ ጊዜያት በተመሰረቱባቸው የወንጀል ክሶች በአንዱ እድሜ ልክ ሲፈረድባቸው በሌላኛው ሞት ተፈርዶባቸዋል በመሆኑም ለምስክርነት ስለማይበቁና ህግም ስለሚከለክላቸው ቀርበው ሊመሰክሩ አይገባም ብሎ ተቃውሞ ነበር ፍርድ ቤቱ ግን የአቃቤ ህግን ክርክር ውድቅ በማድረግ አቶ አንዳርጋቸው ቀርበው እንዲመሰክሩ ሶስት ጊዜያት ትእዛዝ የሰጠ ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት ሳያቀርባቸው ቀርቷል በአራተኛው ቀጠሮ አቶ አንዳርጋቸው ማረሚያ ቤት የሉም ብሎ ጥቅምት 12 ቀን 2008 አም በደብዳቤ ገልጿልተከሳሾቹ በማረሚያ ቤቱ ምላሽ ተማረው የተወሰኑት ብይን ይሰጠን ሲሉ አቶ ደህናሁን ቤዛና አቶ ሞንዳዬ ጥላሁን ቀርበው መመስከር እንዳለባቸው በመግለፅ ፍርድ ቤቱ ከውጭ አገር የመን ሰንአ ይዞ ያመጣቸው ፀረ ሽብር ግብረ ሀይሉና ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲጠየቁ ትእዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀው ነበርጥቅምት 12 ቀን 2008 አም በችሎት ያመለከቱትን አቤቱታ በማጠናከር ጥቅምት 15 ቀን 2008 አም ጉዳያቸውን እያየው ለሚገኘው ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ፅፈዋል ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤቱ በፃፉት ደብዳቤ እንደገለፁት አቶ አንዳርጋቸው በትውልድ ኢትዮጵያዊ ቢሆኑም በዜግነት እንግሊዛዊ በመሆናቸው በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ጉዳያቸውን እንደሚከታተሉ ጠቁመዋል በመሆኑም የእንግሊዝ ኤምባሲ የፀረ ሽብር ግብረ ሀይሉና ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲጠየቁ ትእዛዝ እንዲሰጥላቸው አመልክተዋልየስር ፍርድ ቤት በተከሳሾቹ ደብዳቤ ላይ ብይን ከመስጠቱ በፊት አቃቤ ህግ ያቀረበውን ይግባኝ የመረመረው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዳይፈፀም በማገድ ያስቀርባል ባለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለሀዳር 8 ቀን 2008 አም ቀጠሮ ሰጥቷል
https://www.ethiopianreporter.com/article/9258
303
1,679
በሙያው ኮቪድን እየታገለ ያለው የመዲናዋ ኮሌጅ
ሀገር አቀፍ ዜና
June 19, 2020
9
ለአንድ አገር እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት ትምህርትና ስልጠና ማእከላት አንዱ ፖሊ ቴክኒክ መሆኑ ይታወቃል በየደረጃው ያሉት ሁሉ እንደየባህርይና አይነትይዘታቸው አስፈላጊዎች ሲሆኑ በተለይ ለታዳጊ አገራት የፖሊዎችን ያህል የቀዳሚ አስፈላጊነት የሚወዳደር የሌለ መሆኑን ያደጉት አገራት ተሞክሮና ስኬት ያስገነዝባል ጀርመን ደኮሪያ ቻይና ዩጎዝላቪያ ህንድና መሰል አገራትም ለዚህ ተምሳሌቶች ናቸው አገራችን የሌሎች በተለይም በእድገት ፈለጋቸው ውጤታማ የሆኑ አገራት ለዘርፉ የሰጡትን ትኩረት ልብ በማለት ለፖሊ ቴክኒክ ተቋማት ልዩ ትኩረትን በመስጠት አበረታች እንቅስቃሴ ላይ የምትገኝ ስትሆን ለዚህም በአገር አቀፍና ክልሎች ደረጃ ዘርፉን የሚያስተናግዱ ኤጀንሲዎች መኖራቸው በስራቸውም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችን አቋቁመው መስራታቸው የሰለጠኑ ወጣት ባለሙያዎችንም ማፍራታቸውና ለፈጠራ ስራዎችም ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆናቸው ተጠቃሽ ሲሆን ከዚሁ አኳያም በዚሁ ፅሁፍ የምንቃኘውና መነሻውን 1969 አም ባደረገው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ስር የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አንዱ ነው በአቃቂቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ይህ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ወጣት ባለሙያዎችን በማፍራት ላይ ይገኛል በመደበኛና ማታው ፕሮግራሞች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማትን ፍላጎት መሰረት በማድረግ አጫጭር ስልጠናዎችን በ12 ክፍለትምህርቶች እየሰጠ ይገኛል ደረጃቸውን በጠበቁ ማሺነሪዎች በመደራጀት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን በማከናወን የአገሪቱን የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎትና የአካባቢውን ማህበረሰብ የአኗኗር ዘይቤ ያገናዘቡ ምርቶችንና ግብአቶችን ተደራሽ በማድረግ ተቋማዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ላይ ሲሆን በተለይ ወቅታዊና አንገበጋቢ የሆኑ አገራዊ ችግሮች ሲያጋጥሙ ፈጥኖ በመለየትና በመረዳት ምርምርና ፈጠራን መሰረት ያደረጉ መፍትሄዎችን ማፈላለጉ ላይ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን የኮሌጁ ዲን አቶ ደመላሽ ተስፋዬ ይናገራሉ እንደ አቶ ተስፋዬ ገለፃ ኮሌጁ ከ2009 አም ወዲህ ስር ነቀል በሚባል ደረጃ ከፍተኛ ለውጥን በማሳየት ላይ ይገኛል በሙያው በሰለጠኑ ከፍተኛ ልምድና እውቀት ባላቸው ምሁራንና በዘመናዊ ማሽነሪዎች ተደራጅቷል በቂና ሰፋፊ ስፍራዎችሾፖችም አሉት ኮሌጁ የተለያዩ ክፍለትምህርቶችን እንደሚያካትት የሚናገሩት ዋና ዲኑ 10ኛ ክፍልን ካጠናቀቁ ተማሪዎች መካከል በማወዳደርና ከፍተኛ ውጤት ያላቸውን በመቀበል በተለያዩ ደረጃዎች በሌቭልስ የሚያሰለጥን መሆኑን በአካባቢው ህብተረሰብ የተለያዩ ተቋማትና በአነስተኛና ጥቃቅን ለተደራጁ ወጣቶች የካይዘን ድጋፍ ያደርጋል ስለስራ ፈጠራ ግንዛቤን ያስጨብጣል የስራ ላይ ሳይንሳዊ እውቀትን የሚያስጨብጡ የክሂሎች ማዳበሪያ ስልጠናዎችን ይሰጣል ዎርክሾፖችን በማዘጋጀት ሰርቶ ማሳያዎችን ይተገብራል በተለይ የአገሪቱን ፍላጎትና አቅጣጫ መሰረት በማድረግ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ በማተኮር የምርምርና ፈጠራ ስራዎችን ይሰራል በተለይም ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘትን ታሳቢ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ከመሆኑ አኳያ ኮሌጁ ጥራትንና ደረጃን ሳያማክል ምንም ነገር እንደማይሰራም ዲኑ ተናግረዋል በተለይ ጥራት ደረጃና ተወዳዳሪነት የማይደ ራደሩበት መሆኑን የሚናገሩት ዲኑ እቅዳቸው በአለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ በመሆን አገርንና ወገንን መጥቀም በየዘርፉ ብቁ ባለሙያ ወጣቶችን ማፍራት አካባቢው የአርሶ አደሮች እንደመሆኑ መጠን ለእነሱ ግብአት ማቅረብና ምርትና ምርትማነትን ማሳደግ በከተማው መስተዳድር ለከተማ ግብርና የተሰጠውን ትኩረት በመከተልና አንድም መሬት ፆም አያድርም የሚለው መርሁን ተግባራዊ በማድረግ በኩል ኮሌጃቸው ሳያሰልስ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል ኮሌጃችን ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት በኩል የተዋጣለት ነው ባለፈው በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የተሸለመው ወጣትም የዚሁ ኮሌጅ ምሩቅ ነው የሚሉት አቶ ተስፋዬ በኮሌጁ ስራዎች ይፈጠራሉ ይሰራሉ ይባዛሉ ይሸጋገራሉ ተደራሽ ይሆናሉ ስራ ላይ በመዋልም ለማህበረሰቡና ለአገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን ያደርጋሉ ሲሉም ይነገራሉ የኮቪድን ድንገተኛ ወረርሽኝ በተመለከተ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የተናገሩት ዲኑ ከ11ሺህ በላይ ማስኮችንና ለማቆያ የሚሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ 250 አልጋዎችን አምርተው ማሰራጨታቸውን 100 አልጋዎች ተዘጋጅትው ለስርጭት ዝግጁ መሆናቸውን የተለያዩ የእጅ መታጠቢያ ማሽኖችን መሰራታቸውንና አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውንም አብራ ርተዋል ዘመናዊ የእጅ መታጠቢያውን የሰሩትን ሁለት የኤሌክሮኒክስ ክፍለትምህርት የደረጃሌቨል አምስት 3ኛ አመት ተማሪዎች አግኝተን አነጋግርናቸዋል ተማሪ የአብስራ ስነወርቅ እንደነገረን ከሆነ ከሄኖክ ስንታየሁ ጋር ይህንን ፈጠራ ሊሰሩ የቻሉት የኮሌጁ መምህራን ያስጨበጧቸውን ተግባራዊ እውቀት በመጠቀም ነው የእጅ መታጠቢያ ማሽኑን ከሌሎች ልዩ የሚያደርገውን ገፅታ ሲያስረዳም እኛም ተመልክተነዋል ሰአት 20 ሰከንዱን የሚቆጥረው እራሱ መሆኑ ሰኮንዱ ሳይሞላ ውሀ አለመልቀቁና የሚታጠበው ሰው ለ20 ሰከንድ እጁን ፍትግ አድርጎ እንዲታጠብ ማድረጉ ይህም በተገጠመለት ሰአት አማካኝነት የሚታይነበብ መሆኑ ከማሽኑ ጋር ምንም አይነት ንክኪ የማይኖር መሆኑ ነው ይላል የወደፊት እቅዱና ምኞቱንም ከዚህ የበለጡ ሌሎች ለአገር ጠቃሚ የሚሆኑ ማሽኖችን የመስራት እቅድ አለኝ ለዚህም በቂ እውቀትን ከኮሌጁ አግኝቻለሁ በማለት ተናግሯል የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ መምህርና የስልጠና ክፍል ተጠሪ አቶ ወንድማገኝ ደርቤ እና የጋርመንት ዲፓርትመንት ተጠሪ ወሪት ራሄል ለማ በበኩላቸው በኮሌጁ በሁሉም ዘርፎች ጥራቱን የጠበቀና ተግባር ተኮር የሆነ ትምህርት ይሰጣል ሁሉም ተማሪ ፕሮጀክቶችን ሳይሰራ አይወጣም ለዚህ ደግሞ ኮሌጁ የተደራጀ መሆኑ በራሱ ትልቅ እድል ነውና ተማሪዎቻችንም እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ብለዋል አዲስ ዘመን ሰኔ 122012ግርማ መንግስቴ
https://www.press.et/Ama/?p=34630
604
1,331
“ስብሀት ነጋ በዚህ መልኩ በቁጥጥር ስር መዋል የኢትዮጵያን ህዝብ በድሎ በሰላም መተኛት እንደማይችል የሚያስተምር ነው “አቶ ሊላይ ኃይለማርያም የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራር
ሀገር አቀፍ ዜና
January 12, 2021
64
እፀገነት አክሊሉ አዲስ አበባ የጁንታው ቁንጮ ስብሀት ነጋ በዚህ መልክ በቁጥጥር ስር መዋሉ የኢትዮጵያን ህዝብ በድሎ በሰላም መተኛት እንደማይችል የሚያስተምር እንደሆነ አቶ ሊላይ ሀይለማርያም አስታወቁየትግራይ ጊዜያዊ መንግስት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ሊላይ ሀይለማርያም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለፁት የጁንታው ስብሀት ነጋ በዚህ መልኩ ተዋርዶ መያዝ ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ሰርቶ ማምለጥ የኢትዮጵያን ህዝብ በድሎ በሰላም መተኛት እንደማይችል ያሳየ ነውየህወሀት ጁንታ ቡድን ሲፈጠር ጀምሮ ከአንድ ቤተሰብ ከስብሀት ነጋ ቤተሰብና አካባቢ የወጣ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ሊላይ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚም ሆነ ፖለቲካ በዚህ የቤተሰብ ኔትዎርክ በመያዝ አገሪቷን ሲዘርፍ ኖሯል ብለዋልበቤተሰብና በአካባቢ ተደራጅቶ ለ27 አመታት የኢትዮጵያን ሀብት ሲዘርፍ የቆየው የህወሀት ጁንታ አዲስ አበባ ውስጥ ከ600 ሺ እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚከራይ ህንፃ ያላቸው ጄኔራሎችን መፍጠሩን አመልክተዋል የጁንታው አባላት እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን በትግራይ ህዝብ ላይ በፈፀሙት ክፋት እና በደል አደህይተው ለመግዛት ባደረጉት ጥረት በጣም የተጠሉ ሆነዋል ይህንን ደግሞ ልቦናቸው በሚገባ ያውቃል ያሉት አቶ ሊላይ የትግራይ ህዝብ እነሱን አጥቶ ለአንድ ሳምንት እንኳን መኖር እንደማይችል ሲያስወሩ ቢኖሩም ነገሩ ግን በፍፁም ከሚሉት ተቃራኒ ነው ብለዋል አሁንም በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑ ህዝቡን ከሚገባው በላይ እያስደሰተው መሆኑን አስታወቀዋልአሁን ላይ የህግ ማስከበር ዘመቻው ተጠናቅቆ እነዚህ አካላት በመከላከያ ሰራዊት እየተያዙ መሆኑ ለመላው ኢትዮጵያውያን ደስታን የሚፈጥር ቢሆንም ለትግራይ ህዝብ ደግሞ የድል ድል ሆኖ ነው ያገኘነው ያሉት አቶ ሊላይ ጁንታው ለትግራይ ህዝብ ታሪካዊ ጥላት ነው ላለፉት 46 አመታት የትግራይን ህዝብ ሲያርዱ ሲገድሉ በስሙ እየነገዱ እነሱ ሲበለፅጉ ኑሯቸውን በተቀናጣ ሁኔታ ሲመሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል እነዚህ ሰዎች ከዚህም አልፈው ኢትዮጵያውያንን በብሄር በቋንቋ ሲከፋፍሉ ሲያራርቁና ደም ሲያቃቡ የኖሩ ሴረኞች መሆናቸውን አመልክተው አሁን ላይ መንግስት ህግ በማስከበር ዘመቻው የወሰደው እርምጃ ከምንም በላይ ትግራይን ብሎም መላው ኢትዮጵያን ነፃ   ያወጣ መሆኑን አብራርተዋልየትግራይ ህዝብ በእነዚህ ፋሽስቶች መማረሩንና ከላዩ ላይም እንዲነቀሉለት መፈለጉ የሚታወቀው መከላከያ ሰራዊትን እየደገፈ መውጫ መግቢያቸውን እያሳየ ከተደበቁበት ጎሬ ተፈንቅለው እንዲወጡ የራሱን ሚና እየተጫወተ መሆኑ ነው ያሉት አቶ ሊላይ በዘመቻው መቶ በመቶ በሚባል ሁኔታ ተሳትፎውን አሳይቷል በማሳየት ላይም ነው ብለዋል የትግራይ ህዝብ ጁንታው በፍጥነት ከላዩ ላይ ተነቅለው ወደቀድሞ ሰላሙና ልማቱ የሚገባበትን ቀን እየናፈቀ መሆኑን ጠቅሰዋል አሁን ላይ መከላከያና ህዝቡ እንደ ውሀና ወተት ተግባብተው ግዳጃቸውን በአስደናቂ ጀግንነት እየተወጡ ስለመሆኑ የተናገሩት አቶ ሊላይ ይህ ሁኔታ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማድረግ ሌሎች ጁንታዎችንም በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራም ስለመሆኑ አብራርተዋል የእነዚህ ጁንታዎች መያዝ እንደ አገር ትልቅ እንደምታ ያለው ከመሆኑም በላይ ላለፉት 50 አመታት ከኢትዮጵያም አልፎ አጎራባች አገሮችን ሲያምሱ የነበሩ መሰሪ ወሮበላዎች መጥፋት ለመላው ምስራቅ አፍሪካ ጂኦፖለቲካዊ ሰላም ትልቅ ነገርን የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ህዝብ ዘንድ ያለመረጋጋትና ስጋት ይታያል የተገለሉም የሚመስላቸው አሉ በመሆኑም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ህዝቡን የማረጋጋት ስራውን በተፋጠነ ሁኔታ መስራት አለበት እስከ አሁን ያን ያህል የተሄደበት አይመስልም ከዚህ በኋላ ጠንከር አድርገን የምንሰራበት ይሆናል ብለዋል የፌዴራል መንግስቱ በክልል ያለውን ሁኔታ ይረዳል ከዚህ አንፃርም ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን ሊያደርግ ይገባል አሁን ላይ መላው የአገራችን ህዝቦች ከትግራይ እህት ወንድሞቻቸው ጎን ሊቆሙ ይገባል ያሉት አቶ ሊላይ ትግራይ ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ የመሰረተ ልማቶች በጁንታው መውደማቸውን ጠቁመዋልአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ገብቶ ማተሚያ አልያል ፎቶ ኮፒ ማሽን ማግኘት አይቻልም ስራዎች እየተሰሩ ያለው በየሆቴሉ ገንዘብ በመክፈል ነው ከዚህ አንፃር መላው ህዝብ የትግራይ እህት ወንድሞቹን ከሞራል ጀምሮ በቁሳቁስና በሚችለው ሁሉ ማገዝ እንደሚጠበቅበት አመልክተዋል ከዚህ በኋላ የሚያለዩን ከፋፋዮች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተወገዱ በመሆኑ በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችንም ባለማግለል ወዷንድነት መጥተን ታላቋን ኢትዮጵያ መስርተን አንድ ባንዲራ እንዲኖረን መስራት ያስፈልገናል ብለዋል
https://www.press.et/Ama/?p=39323
509
15,084
የሰላም ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከሚገኘው የዓለም ባንክ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ
ሀገር አቀፍ ዜና
Oct 6, 2020
486
አዲስ አበባ መስከረም 22 2013 ኤፍቢሲ የሰላም ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአለም ባንክ ፅህፈት ቤት አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደውይይቱ ያተኮረው ነባር የጋራ ፕሮግራሞችን በማጠናከር እና ተጨማሪ የትብብር ዘርፎችን በመዳሰስ ላይ ነበር ተብሏልየሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሀት ካሚል በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ ለሚደረጉ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ባንኩ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋልበኢትዮጵያ የባንኩ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን በበኩላቸው ከመንግስት ጋር ይበልጥ ውጤታማ የሆነ አጋርነት ለመመስረት እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b4%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%8a%a8%e1%88%9a%e1%8c%88%e1%8a%98%e1%8b%8d/
69
36,770
የጉዞ አድዋ የልዑካን ቡድን በወረኢሉ ከተማ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 18, 2019
Unknown
የጉዞ አድዋ ስድስት በጎ አድራጎት ማሀበር ዛሬ ወረኢሉ ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደረጎለታልአዳማ ላይ በኦሮሞ አባቶችና አባገዳዎች ተመርቆ ጥር 1 ከአዲስ አበባ የተነሳው የልኡካን ቡድን 15 አባላትን ይዞ ዛሬ ስምንት ሰአት ገደማ ወረኢሉ ከተማ ደርሷልየአካባቢው ኗሪዎች በባህላዊ አልባሳት ተውበው ጥንታዊ የጦር መሳሪያዎችን ይዘውና በፈረስ ታጅበው ከሶስት ኪሎ ሜትር በላይ በመጓዝ ነበር የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባባል ያደረገላቸውሰላም ፍቅር አንድነት በሚል መሪ ሀሳብ ጉዞውን ያሟሸው ልኡክ ካለፉት አምስት ተመሳሳይ መርሀ ግብሮች ለየት የሚያደርጉት ቁም ነገሮችን ይዞ ነው የተነሳው መስፍን አራጌ ከስፍራው ዘገባ ልኳል
https://amharic.voanews.com//a/adwa-youth-homage-1-18-2019/4749077.html
81
5,956
በደብረማርቆስ በ650 ሚ. ብር የዘይት ፋብሪካ ሊገነባ ነው
ቢዝነስ
Sunday, 04 June 2017 00:00
1649
 የሀገሪቱን 20 በመቶ የዘይት ፍጆታ ይሸፍናል ተብሏል   በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ በ650 ሚሊየን ብር WA የተባለ የዘይት ፋብሪካ ሊገነባ ነው ፋብሪካው ስራ ሲጀምር 20 በመቶ የሀገሪቱን የዘይት ፍጆታ በመሸፈን  ለዘይት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስቀር የWA የዘይት ፋብሪካ ሀላፊዎች ተናግረዋልፋብሪካው ዘይቱን ለማምረት ኑግሰሊጥ ሱፍና አኩሪ አተርን የሚጠቀም ሲሆን በቀን 250 ቶን የእህል ምርት  በመጠቀም 130 ቶን ንፁህ ዘይት የማምረት አቅም እንዳለው የገለፁት ሀላፊዎቹየፋብሪካውን ግንባታ የሚሰራው የቻይና ኩባንያ በ3 ወራት ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ ተፈራርሟል ብለዋል በ30 ሺ ካሜ መሬት ላይ ያርፋል የተባለው የዘይት ፋብሪካው ስራ ሲጀምር ለ650 ሰራተኞች የስራ እድል ከመፍጠሩም ባሻገር የምስራቅ ጎጃም ዞን 40 ያህል ሰሊጥ አምራች ባለ ሀብቶችና ገበሬዎች በተሻለ ዋጋ ለፋብሪካው ግብአት የሚሆን ጥሬ እቃ በማቅረብ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ታውቋል ወደፊት ፋብሪካው የራሱን ጥሬ እቃ ለመጠቀም የራሱ እርሻ እንደሚኖረውም ሀላፊዎቹ ገልፀዋልWA የዘይት ፋብሪካ ይህንን ፕሮጀክት አጠናቆ ስራ ጀመረ በኋላ የበቆሎ ዘይት ለማምረት እቅድ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=20230:%E1%89%A0%E1%8B%B0%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%89%86%E1%88%B5-%E1%89%A0650-%E1%88%9A-%E1%89%A5%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%8B%98%E1%8B%AD%E1%89%B5-%E1%8D%8B%E1%89%A5%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%88%8A%E1%8C%88%E1%8A%90%E1%89%A3-%E1%8A%90%E1%8B%8D&Itemid=240
138
46,224
ዩናይትስ ስቴትስ በአልሻባብ ላይ የአየር ጥቃት ፈጸመች
ፖለቲካ
December 30, 2016
Unknown
ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በሶማሊያ በሚገኘው  የአልሻባብ አሸባሪ ቡድን ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሟን  የፔንታጎን  ፕሬስ ሴክሬተሪ  አድሚራል  ጆን ኪርቤይ  አስታወቁ የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የጮር ጄቶች  ድብደባ  የፈፀሙት  በሶማሊያ ሳኮው በተባለ ስፍራ ላይ  ሲሆን  የእስልምና አክራሪ ታጣቂ ቡድኑ   ከፍተኛ አመራርን  ሊላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል  እስካሁን ድረስ  በአየር ድብደባው ምክንያት  ምን  ያህል  ጉዳት  እንደደረሰ ያልታወቀ መሆኑንና አስፈላጊ ከሆነ  በአየር ጥቃቱ የደረሰው ጉዳት እንደታወቀ   ተጨማሪ መረጃ ሊሰጥ እንደሚችል  አድሚራ ኬርባይ ተናግረዋል   በሶማሊያ አልሻባብ ቡድን ላይ የተፈፀመው  የአየር ጥቃት በሰው አልባ አውሮፕላኖች የተካሄደ  መሆኑን  የፔንታጎን ሀላፊው አመልክተዋል ባለፈው ቅዳሜ ሁለት የሶማሊያ የጦር አዛዦች የአልሻባብ ከፍተኛ አመራሮችንም  መያዛቸውን መናገራቸው የሚታወስ  ሲሆን  የአልሻባብ  የደህንነት ዋና አዛዥ  ዘካሪያ እስማኤል አህመድ ሀርሲ  በኢል ዋክ ከተማ አቅራቢያ በቁጥጥር ስር  መዋላቸው  ተገልጿል  የአልሻባብ  ታጣቂ ቡድን ባለፈው ሳምንት  ሞቃዲሾ በሚገኘው  የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስካባሪ ሀይል ወታደራዊ ይዞታ ላይ ጥቃት በመፈፀም የኡጋንዳ ወታደ ችና ሲቪሎች  እንዲገደሉ ካደረገ  በኋላ  የቡድኑ ወሳኝ  አመራሮች እየታደኑ ይገኛሉ አልሻባብ በበኩሉ  በሞቃዲሾ  የአፍሪካ  ህብረት ይዞታ ላይ  የፈፀመው ጥቃት  ዩናይትድ ስቴትስ  የቀድሞ የቡድኑ መሪ በሆነው ጎዳኔ ላይ   ለፈፀመችው  ግድያ  የበቀል ምላሽ  እንደሚሆን  ገልጿል የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ  የቀድሞ  የአልሻባብ መሪ ጎዳኔ ያለበት ቦታ ለጠቆመ ግለሰብ   የ7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሽልማት መስጠቱ ይታወሳል ምንጭ ሲኤን ኤን ትርጉም  በሰለሞን ተስፋዬ  
https://waltainfo.com/am/32924/
195
39,504
የመንግሥት እንቅስቃሴዎችን አንቆጣጠርም - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ዓለም አቀፍ ዜና
May 16, 2015
Unknown
የመንግስትን ሀብት ለምርጫ ቅስቀሳ መጠቀም ህገወጥ መሆኑን ያስታወሱት በሚኒስትር ማእረግ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና መንግስታዊ እንቅስቃሴዎችን መቆጣጠር ግን አንችልም ብለዋልቦርዱ የዘንድሮውን ምርጫ ለማስፈፀም በትክክለኛ መንገድ እየተጓዘ መሆኑን የገለፁት ፕሮፌሰር መርጋ ነገሮች ከኔ አቅም በላይ ከሆኑ ስራዬን በፈቃዴ የመልቀቅ መብት አለኝ ብለዋልፕሮፌሰር መርጋ ይህንን የተናገሩት ዛሬ ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነውለተጨማሪ በመግለጫው ላይ የተገኘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ
https://amharic.voanews.com//a/national-elections-board-ethiopia-chairman-merga-bekana-05-15-15/2771259.html
62
23,586
የሙስና ክስ በተመሠረተባቸው ባለሀብቶች ላይ የቀረበው ንብረት አስተዳዳሪ ይሾም አቤቱታ ተቀባይነት አጣ
ፖለቲካ
29 October 2017
Unknown
አቃቤ ህግና መርማሪ ቡድን በጋራ እንዲቆጣጠሩ ትእዛዝ ተሰጥቷልበተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙና በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ባለሀብቶች ንብረትና ተንቀሳቃሽ የባንክ ሂሳብ ታግዶ ንብረት አስተዳዳሪ እንዲሾም የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አጣ አቤቱታውን የመረመረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስረኛ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት የንብረት እግዱ እንዲሻሻል ትእዛዝ ሰጥቶ አስተዳዳሪ እንዲሾም የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን በሰጠው 14 ገፅ ውሳኔ አሳውቋልቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸው እንዲሁም የባንክ ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ እግድ እንዲጣልለትና ንብረት አስተዳዳሪ እንዲሾምለት መርማሪ ቡድኑ ጠይቆ የነበረው በገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በየማነ ግርማይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ በአሰር ኮንስትራክሽን ኩባንያ በዲኤምሲ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ስህን ጎበና መሰረት አለሙ አብዶ መሀመድ እውነቱ ታዬና ስንዱ ታደሰ በሚባሉ ባለሀብቶች ላይ ነበርእግድ የተጣለባቸው ባለሀብቶች ከሚያገኙት ገቢ በላይ በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ  ክምችት እንዳላቸው በመርማሪ ቡድኑ የተገለፁት የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ምንም አይነት የሂሳብ እንቅስቃሴ ማድረግ አለመቻላቸውን የሰራተኞች ደመወዝ መክፈል አለመቻላቸውን ቤተሰቦቻቸው የሚተዳደሩበት የቀለብ መሸመቻ እንደሌላቸው በመግለፅ በተለይ ተንቀሳቃሽ ሂሳባቸው ሊታገድ እንደማይገባ ጠቁመው መቃወሚያ አቅርበው ነበር በተለይ ድርጅቶቹ ተንቀሳቃሽ ንብረት ታግዶ የሚዘልቅ ከሆነ ሊተካ የማይችል ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችልና እየደረሰም እንደሚገኝም በማመልከት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በመቃወሚያቸው አመልክተው ነበር በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩት ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን የማነ ግርማይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ አሰር ኮንስትራክሽንና ዲኤምሲ ኮንስትራክሽን ከመንግስት ተቋማት ጋር ውል ፈፅመው የተረከቧቸውና በመገንባት ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ማስቀጠል ባለመቻላቸው ጉዳቱ የድርጅቶቹ ብቻ ሳይሆን የአገርም ጭምር መሆኑን በመጠቆም የባንክ ሂሳባቸው እንዲለቀቅላቸውም አመልክተው ነበር  ሌላው ድርጅቶቹ ያቀረቡት መቃወሚያ አስተዳዳሪ እንዲሾም መርማሪ ቡድኑ ያቀረበውን አቤቱታ ነው ንብረቶቹን ያፈሩት ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ማፍራት ወንጀል መሆኑን የሚገልፅ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በመሆኑና ህግ ወደኋላ ተመልሶ ሊሰራ እንደማይችል ሲሆን ቋሚ ንብረቶች እንዳይሸጡና እንዳይለወጡ እግድ መጣል የሚቻል መሆኑን በማስረዳት አስተዳዳሪ ሊሾም እንደማይገባም ተከራክረዋል የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ግን በሰጠው የመቃወሚያ መቃወሚ ሀሳብ እንዳስረዳው ድርጅቶቹ በመንግስትና በህዝብ ላይ ያደረሱት ጉዳት በድምሩ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በመሆኑ ለጉዳቱ ማካካሻ የሚሆን ንብረት አሳግዷል ንብረት አስተዳዳሪ ሲሾም የሰራተኛ ደመወዝ ክፍያና የፕሮጀክቶች ቀጣይነት እንደሚረጋገጥ በማስረዳት ድርጅቶቹ ያቀረቡት መቃወሚያ ውድቅ ተደርጎ አቤቱታው ላይ ውሳኔ እንዲሰጥለት ተከራክሮ ነበርድርጅቶቹም ሆኑ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን የገቢና ወጪ ዝርዝር እንዲሁም እግድ የተጣለባቸውን ንብረቶች ዝርዝር ያቀረቡና ቢሮውም ታገዱ ያላቸውን ንብረቶች ዝርዝርና ግምታቸውን ያቀረበ ቢሆንም በምን ሁኔታና አግባብ እንዳቀረበ የወንጀል ምርመራ ቢሮው ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው ማስረጃ እንደሌለ ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ገልጿልፍርድ ቤቱ በተጠርጣሪዎቹ ንብረቶችና የባንክ ሂሳቦች ላይ የተጣለው እግድ ሊነሳ ይገባል ወይስ አይገባም ባለቤቶቹ በንብረቶቹ የመጠቀም መብት ውስንና የባንክ ሂሳቦች ላይ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተከትሎ የሚነሱ የሶስተኛ ወገን መብቶችና የድርጅቶቹ ህልውናና አጠቃላይ እንቅስቃሴ በምን አግባብ ይመራ ንብረት ጠባቂስ ሊሾም ይገባል ወይስ አይገባም ሊሾም ይገባል ከተባለስ ለምንና እንዴት የሚሉ ጭብጦችን በመያዝ ክርክሩን መመርመሩን በውሳኔው አሳውቋልበተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ ስነ ስርአትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 43497 አንቀፅ 81 እና 91 መሰረት ተከሳሽ በሙስና ወንጀል ያገኘው የማይገባ ጥቅም ወይም የደረሰ ጉዳት ለመድረሱ በመሀላ የተደገፈ አቤቱታ ከቀረበ ተጣርቶ ሊታገድ እንደሚችል በመደንገጉ እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 88207 አንቀፅ 91 መሰረት በተጠርጣሪው የትዳር ጓደኛና 18 አመት በሆኑ ልጆች ስም የተመዘገበ ንብረትና የተቀመጠ ገንዘብ ካለ እግድ እንደሚጣልበት ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አስታውሷል በመሆኑም መርማሪ ቡድኑ ያቀረበውን ንብረትና የባንክ ሂሳብ ይታገድልኝ አቤቱታ ተቀብሎ እግድ መጣሉን ፍርድ ቤቱ ገልጿልንብረቶቹና የባንክ ሂሳቦች እንዲታገዱ የተደረገው ተጠርጣሪዎቹ በተመሰረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ በፈፀሙት ወንጀል ምክንያት ያገኙት ጥቅምና ያደረሱት ጉዳትን ለማካካስ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ገልፆ ህጉ ማስረጃ ማቅረብ ሳያስፈልግ የእግድ ትእዛዝ መስጠት እንደሚቻል የደነገገ ቢሆንም ምርመራ ከተጀመረበት የወንጀል ድርጊት ጋር ግንኙነት አለ ወይስ የለም የሚለው ማስረጃ የሚመዝነው በመደበኛ ችሎት በሚደረግ ምርመራ መሆኑን ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ በውሳኔው ገልጿል የተሰጠው እግድም ሊነሳም ሆነ ሊሻሻል የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 43497 አንቀፅ 163 መሰረት መሆኑን ጠቁሞ በተመሰረተው ክስ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ ባልታወቀበት ሁኔታ እግዱን ማንሳት የህጉ አላማን የሚያሳካ ነው ተብሎ ስለማይታመን እግዱ ይነሳልን የሚለውን ጥያቄ እንዳልተቀበለው ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ገልጿል እግድ የሚሰጥበት ንብረት በወንጀል ተገኘ ከተባለው የማይገባ ጥቅም ወይም ደረሰ ከተባለው ጉዳት ጋር ተመጣጣኝ መሆን እንዳለበት በአዋጅ ቁጥር 43497 አንቀፅ 9 እና አዋጅ ቁጥር 88207 አንቀፅ 9 ስር መደንገጉን ፍርድ ቤቱ ጠቁሞ ተጠርጣሪ ወገኖችና የወንጀል ምርመራ ቡድኑ የየራሳቸውን መከራከሪያ ሀሳብ ያስረዱ ቢሆንም ንብረቶቹ የወንጀል ፍሬ መሆን አለመሆናቸውን ወይም ተጠርጣሪዎቹ ጥቅም ብቻ ነው ያገኙት ወይስ ጉዳትም አድርሰዋል የሚለውን እልባት መስጠት ያለበት መደበኛ ችሎት መሆኑን የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ በውሳኔው አስረድቷል በባንክ ሂሳቦቹ ላይ የተሰጠውን እግድ ተከትሎ በሶስተኛ ወገን መብቶች ድርጅቶች ህልውናና የሰራተኛ ደመወዝ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳለው የጠቆመው ፍርድ ቤቱ የባንክ ሂሳብ እንዳይንቀሳቀስ ማገድ ክፍያዎች እንዳይሰበሰቡና እንዳይከፈሉ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል በመሆኑም የእግዱ ዋነኛ አላማ ገንዘቡ ከውሳኔ በፊት እንዳይጠፋ ለማድረግ እንጂ የንግድ ድርጅቶች ስራቸውን እንዳይሰሩ ለማድረግ ባለመሆኑ ሂሳቦቹን ሙሉ በሙሉ ማገድ ምክንያታዊ አለመሆኑን አብራርቷል በአዋጅ ቁጥር 43497 አንቀፅ 92 እና አዋጅ ቁጥር 88207 አንቀፅ 92 እና 3 መሰረት ተጠርጣሪ በታገደ ንብረቱ የመጠቀም መብቱ እንደማይነካ እንዲሁም የመጠቀም መብት እንደሌለው የተደነገገ ቢሆንም አስገዳጅ ሁኔታ ሲያጋጥም ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪው ሊጠቀምበት የሚገባን መጠን ወስኖ ሊፈቅድለት እንደሚችልም ችሎቱ በውሳኔው ገልጿል በመሆኑም የድርጅቶቹ የሂሳብ እንቅስቃሴ እንዲታገድ ማድረግ ከህግም ሆነ ከፍሬ ነገር አኳያ ተገቢ አለመሆኑንና በድርጅቶቹ ላይ የተጣለው እግድ ሊሻሻልና እንቅስቃሴያቸው አስፈላጊው ቁጥጥር እየተደረገበት ህልውናቸው ሊቀጥል ይገባል ብሏል ንብረት አስተዳዳሪ መሾምን በሚመለከት ፍርድ ቤቱ እንዳብራራው የተጠርጣሪዎች ወኪሎች በችሎት ቀርበው የስራ መሪነት ሚናቸውን እንደሚወጡና ሙሉ ሀላፊነት እንደሚወስዱ አረጋግጠዋል ንብረቶቹ በእነሱ እጅ ቢቆዩ ጉዳት ይደርስባቸዋል ቢባልም ተጠርጣሪዎቹ የንብረቶቹ ባለቤትነታቸው በህግ እስካልተወሰደ ድረስ የማስተዳደር ስልጣን ያላቸው በመሆኑ ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ውሳኔ ከመስጠት በፊት ነፃ ሆነው የመገመት መብት ያላቸው በመሆኑ ንብረቶቹ በእጃቸው ቢቆዩ ጉዳት ይደርስባቸዋል ተብሎ እንደማይታሰብ ገልጿል በአዋጅ ቁጥር 43497 አንቀፅ 13 እና 17 እስከ 21 ያሉት ድንጋጌዎች መሰረት ጥናትና ማጣራት ሳይደረግ አዲስ ንብረት ጠባቂ መሾም ተገቢ አለመሆኑን አስረድቷል ድርጅቶቹና የሚያንቀሳቅሷቸው ሰራተኞች ብዛት ያላቸው ከመሆናቸው አንፃር አዲስ አስተዳዳሪ ከመሾም ይልቅ ባሉበት ቢቀጥሉና ድርጅቶቹ አመራሮች ሀላፊነት እንዲወስዱ ማድረጉ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ የሚረዳ መሆኑን ፍርድ ቤቱ እንዳመነበትም በውሳኔው ገልጿል የድርጅቶቹ የስራ እንቅስቃሴ እየታየ በሂደት ትእዛዝ የሚሰጥበት በመሆኑ መርማሪ ቡድኑ ወይም አቃቤ ህጉ ንብረቱን ከጉዳት ለመከላከል አስተዳዳሪ ይሾምልን በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ እንዳልተቀበለው ገልፆ መርማሪ ቡድኑ ወይም አቃቤ ህግ በጋራ በድርጅቶቹ የሚከናወኑ ገቢና ወጪዎችን ንብረቱን ከጉዳት ለመከላከል በሚጠቅም መንገድ እንዲቆጣጠሩ ትእዛዝ ሰጥቷል          
https://www.ethiopianreporter.com/article/2163
903
2,971
አላግባብ የተከፈለ ሁለት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር እንዳልተመለሰ ዋና ኦዲተር ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
February 2, 2020
50
ገንዘቡን ለማስመለስ የሚያስችል ውሳኔ መተላለፉንና ክስ እንደሚመሰረትም ተጠቆመአዲስ አበባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ኮሚቴ አቋቁሞ አላግባብ የተከፈለ ሁለት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ለማስመለስ ቢሰራም ማስመለስ አለመቻሉን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ገለፀ ገንዘቡን ለማስመለስ የሚያስችል ውሳኔ መተላለፉንና ክስ እንደሚመሰረትም ተጠቆመ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የውጭና አለም አቀፍ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አወቀ ጤናው ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት ዋና ኦዲተር ከ2002 እስከ 2009 አም ባደረገው ኦዲት  አላግባብ ሁለት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ተከፍሏል ድርጊቱ የተፈፀመው በሁሉም 190 የፌዴራል ተቋማት ሲሆን በተለይም ከፍተኛ ክፍያ የፈፀሙ 35 ተቋማት ናቸው ዋና ኦዲተር የኦዲት ግኝቱን በየጊዜው ማስተ ካከያ እንዲያደርጉ ለምክር ቤቱ ቢያሳውቅም በምክር ቤቱ መደበኛ አሰራር ሳይስተካከል በየአመቱ ሲንከባለል መጥቷል ያሉት ዳይሬክተሩ በ2011 አም በምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤው አቶ ታገሰ ጫፎ አማካኝነት ከምክር ቤቱ የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና ከሌሎች ቋሚ ኮሚቴዎችና  የሚመለከታቸውን አካላት ያቀፈ ልዩ ኮሚቴ በማቋቋም ተቋማቱን በመደገፍ አላግባብ የተከፈለውን ገንዘብ በስድስት ወራት ለማስመለስ ጥረት ቢደረግም 27 ተቋማት የሚያስመልሱበትን የጊዜ መርሀ ግብር ከማቅረብና እጅግ በጣም ጥቂት ገንዘብ ከማስመለስ ያለፈ ገንዘቡን እስካሁን ማስመለስ አለመቻሉን ገልፀዋል እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ልዩ ኮሚቴው ድጋፍ በማድረግ ለአሰራር እንቅፋት የሆኑ ህጎችን ከማውጣት ያለፈ አላግባብ የተከፈለውን ገንዘብ ለማስመለስ በሚፈለገው ደረጃ ውጤት አላመጣም ኮሚቴው የደረሰበትን የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርቦ አላግባብ የህዝብ ገንዘብን የከፈሉ ሀላፊዎች ሰራተኞችና ተባባሪዎቻቸው በጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዲጠየቁ ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ ውሳኔ አሳልፏል ዋና ኦዲተር የኦዲት ሪፖርቱን በወቅቱ ለጠቅላይ አቃቤ ህግ ማቅረቡን ያስታወሱት አቶ አወቀ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶ ገንዘቡ አለመመለሱንም አንስተዋል ዋና ኦዲተር ከሀላፊነቱ በላይ በመለጠጥ ግፊት ቢያደርግም ገንዘቡ አልተመለሰም ተጠያቂነትም አልተረጋገጠም አላግባብ የተከፈለው ገንዘብ ካለመመለሱም በላይ አሁንም በተቋማት ተመሳሳይ ችግሮች እየተከሰቱ ነው በመሆኑም ተጠያቂነት መረጋገጥ እንዳለበት ተናግረዋል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበኩሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዲያስመልስ ውሳኔ አሳልፌያለሁ ሲል የገለፀ ሲሆን ጠቅላይ አቃቤ ህግም አላግባብ የከፈሉ አስራ አራት ተቋማት ሀላፊዎች ሰራተኞችና ተባባሪዎቻቸው ላይ በቅርብ ቀን ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋልበህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክዋኔ ኦዲት ዘርፍ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢና የወቅቱ የልዩ ኮሚቴው ሰብሳቢ የነበሩት ወይዘሮ ወይንሸት ገለሶ ልዩ ኮሚቴው አላግባብ የተከፈለውን ገንዘብ ለተቋማት ድጋፍ በማድረግ ገንዘቡን እንዲመልሱና ለአሰራር አስቸጋሪ የሆኑ ህጎችን ለማሻሻል ተቋቁሟል ልዩ ኮሚቴው የሚመለከታቸውን ተቋማት በማቀናጀት ለአሰራርና ለሀብት ብክነት ምክንያት የሆኑ አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎችን ማሻሻሉንም ተናግረዋል ድጋፍ በማድረግ አላግባብ የተከፈለውን ገንዘብ ለማስመለስ ጥረት ተደርጓል ሆኖም ያልተመለሰ ገንዘብ በመኖሩ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ በመመስረት ገንዘቡን እንዲያስመልስ ዋና ኦዲተርም የኦዲት ሪፖርት በማቅረብ እንዲያግዝ ምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳብ አሳልፏል አቃቤ ህግ የከሰሳቸውና ለመክሰስም በሂደት ላይ እንዳለና ምክር ቤቱም ክትትል እያደረገ መሆኑንም ገልፀዋል የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱሉ የዋና ኦዲተር ያለአግባብ የተከፈለ ገንዘብ መመለስ ያለባቸው ተቋማት የኦዲት ሪፖርት ደርሷል ከተሰጡት ተቋማት መካከል የ14 ተቋማት አላግባብ ክፍያ የፈፀሙ ሀላፊዎች ሰራተኞችና ተባባሪዎቻቸውን ክስ ለመመስረት ዝግጅት አጠናቀናል የክስ መዝገብም ከፍተናል በቅርብ ጊዜ ውስጥም ክስ መስርተን ተጠያቂ እናደርጋለን ብለዋል ከዚህም በተጨማሪ ችግሩ በአስተዳደራዊ እርምጃ ሊስተካከሉ የሚችሉ እርምጃ እንዲወሰድና ማስተካከያ እንዲያደርጉ ለተቋማቱ አስተያየት ሰጥተናል ያሉት አቶ ዝናቡ በቀጣይም ክትትልና ምርምራ በማድረግ በሌሎች ተቋማት ላይም እርምጃ እንወስዳለንየህዝብን ሀብት የመዘበሩ አካላት ቅጣታቸውን እንዲያገኙና የመዘበሩትም ገንዘብ እንዲመልሱ እናደርጋለን ብለዋልአዲስ ዘመን ጥር 242012አጎናፍር ገዛኸኝ
https://www.press.et/Ama/?p=26524
473
8,872
ምዕራባዊ ቴክሳስ የአሜሪካ ግዛትም በ24 ነጥብ 56 ዶላር በመሸጥ ላይ ነው
ቢዝነስ
2021/1/22 20:40 GMT
Unknown
በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የከፋ የገበያ ችግር እና የዋጋ ቀውስ ውስጥ ገብቶ የነበረው የነዳጅ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማንሰራራት ጀምሯል ተብሏል እጅግ አሽቆልቁሎ ከአንድ ዶላር በታች ወርዶ የነበረው የነዳጅ ዋጋ መሻሻል ማሳየቱንም ነው አረብ ኒውስ የዘገበው አንድ በርሜል ድፍድፍ ዘይት ትናንት በመካከለኛው ምስራቅ ከ30 ዶላር በሚበልጥ ዋጋ ሲሸጥ ነበርም ተብሏል ይህ ችግር ውስጥ ገብቶ ከነበረበት ከያዝነው ወር አጋማሽ ወዲህ የመጀመሪያው እንደሆነም ነው ዘገባው የሚያትተው የ13 ነጥብ 9 በመቶ ወይም የ3 ነጥብ 77 ዶላር የዋጋ ጭማሪ ስለማሳየቱም ነው የተነገረው ከዜሮ በታች በኔጋቲቭ የዶላር ዋጋ ይሸጥ በነበረበት ምእራባዊ ቴክሳስ የአሜሪካ ግዛት ደግሞ የ20 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ በ24 ነጥብ 56 ዶላር በመሸጥ ላይ ነው በወረርሽኙ ምክንያት ነዳጅ አምራቾች የምርት ምጣኔያቸውን ቢቀንሱም አሁን አሁን ግን ፍላጎቱ እየተነቃቃ መጥቷል ይህ ደግሞ የዋጋው መወደድን ሊያስከትል እንደሚችል የፋይናንስ ተቋማት ከወዲሁ እያሳሰቡ ይገኛሉ የሳኡዲ የድፍድፍ ነዳጅ የውጭ ግብይት ኤክስፖርት በወርሀ ግንቦት በቀን ወደ ስድስት ሚሊዬን በርሜል ዝቅ እንደሚል ይጠበቃል ይህ በኦፔክ ፕላስ አባል ሀገራት ስምምነት የሚሆን ነው ጉዳዩን ተንተን አድርገው ለሮይተርስ እንዳስረዱ ባለሙያዎች ገለፃ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተጥለው የነበሩ ገደቦች መነሳት መጀመራቸው የአቅርቦትና ፍላጎትን ለማመጣጠን እንደሚያስችልም የስዊዘርላንዱ ዩኤስቢ ባንክ አስታውቋል ሆኖም የፍላጎቱ ማደግና የአቅርቦቱ ማነስ ዋጋን ሊያነቃቃ ይችላል መባሉ ተስፋ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር መስጋታቸውን የዘርፉ የገበያ ተዋናዮች አልሸሸጉም
https://am.al-ain.com/article/price-surge-on-oil-is-reviving
189
4,750
ቤተክርስቲያኗ ለማህበራዊ አገልግሎቶች 2 ነጥብ 3ቢሊዮን ብር መደበች
ሀገር አቀፍ ዜና
April 18, 2019
23
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተጀመረው የፈረንጆች በጀት አመት የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማከናወን ሁለት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በመመደብ ወደ ስራ መግባቷን ገለፀች የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የማህበራዊና ልማት ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ በቀለ ሞገስ ትናንት በፅህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቤተክርስቲያኗ በተያዘው በጀት አመት አራት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሁለት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር መድባ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነች መሆኗን አስታውቀዋል በተያዘው በጀት አመት የልማት ኮሚሽኑ በሁሉም ቅርንጫፍና ፕሮጀክት ፅህፈት ቤቶች 199 ፕሮጀክቶችን እንደሚተገብር የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ በጥሬ ገንዘብ እና በአይነት በድምሩ ሁለት ቢሊዮን 381 ሚሊዮን 792 ሺ 670 ብር መመደቡን ገልፀዋል የተመደበው ብር ለጤና አገልግሎት ለምግብ ዋስትና ለሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ለተፈናቃዮችና ለጉዳት ተጋላ ጮች ለትምህርት ለመጠጥ ውሀ ግንባታና ንፅህና ለአየር ንብረት ጥበቃ ለስደተኛና ከስደት ተመላሾች ወዘተ ድጋፍ ለመስጠት ጥቅም ላይ እንደሚውል ዋና ዳይሬክተሩ አብ ራርተዋል ቤተክርስቲያኗ ባለፈው በጀት አመት አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለአምስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ልዩ ልዩ የልማት ድጋፎችን ማበርከቷን ዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰው ከዚህም ውስጥ በኦሮሚያ በሶማሌና በደቡብ ክልል ለተፈናቀሉ ሰዎች የተደረገው ድጋፍ ከፍ ያለውን ቁጥር እንደሚወስድ ከተያዘው በጀትም 32 በመቶ ለዚህ ተግባር መዋሉን ጠቁመዋል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስር የተቋቋመው የማህበራዊና ልማት ኮሚሽን ቤተክርስቲያኒቱ ካቋቋመቻቸው የበጎ አድራጎት ተቋማት አንዱ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ 13 ቅር ንጫፍና 58 ፕሮጀክት ፅህፈት ቤቶች እንዲሁም ከአራት ሺ በላይ ሰራተኞች እንዳሉት ይታወቃልአዲስ ዘመን ሚያዝያ 102011በ
https://www.press.et/Ama/?p=9111
207
49,913
የአጋሮ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ ግንባታን ለማፋጠን የከተማው አስተዳደር እየሠራ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
January 21, 2019
Unknown
የአጋሮ ከተማን የ10ነጥብ1 የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ ግንባታን በተያዘለት የጊዜ  ገደብ ለማጠናቀቅ  የአጋሮ ከተማ  አስተዳደር ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን  አስታወቀ የአጋሮ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሚፍታህ አብደላ ለዋልታ እንደገለፁት የአጋሮ ከተማ አስተዳደር ከኦሮሚያ  ክልል  መንግስት  ጋር በመተባባር በ420 ሚሊዮን ብር ግንባታው እየተከናወነ ያለውን የከተማውን የውስጥ ለውስጥ መንገድ  ግንባታ ለማፋጠንም እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል የከተማውን የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታን ለማፋጠን  ችግር የሆኑትን  የወሰን ማስከበር የካሳ ክፍያና የዲዛይን ስራዎችን  ቀድሞ ለማጠናቀቅም ከክልሉ መንግስት ጋር  በመናበብ እየተሰራ መሆኑን  አቶ ሚፍታህ ተናግረዋል የአጋሮ ከተማ  ነዋሪ የሆኑት መምህር ያደታ አያና ለዋልታ እንደገለፁት የአጋሮ ከተማ  ቀደም ብሎ ከተቆረቆሩት ከተሞች አንዷ ብትሆንም የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ስራ ላይ ወደ  ኋላ  በመቅረቷ አሁን የተጀመረው ግንባታ ትልቅ  ጥቅም እንዳለው ገልፀዋል የከተማው ነባር  ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ነዝሬ አባፎጊ በበኩላቸው የአጋሮ ከተማ  የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ አዲስ  ተስፋን  ሰንቆ የመጣ መሆኑንና  ህብረተሰቡ   ከ20 አመት በላይ ሲያነሳው የነበረው  የመንገድ ይገንባልን ጥያቄው ምላሽ በማግኘቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል
https://waltainfo.com/am/32219/
149
3,612
በሩስያ የተካሄዱ የተናጠልና የጋራ መድረኮች ስኬታማ እንደነበሩ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 28, 2019
18
አዲስ አበባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡክ ለሁለት ቀናት በሩስያ ሶቺ ከተማ በተካሄደው የአፍሪካና ሩስያ የኢኮኖሚክ ጉባኤ ላይ በሁሉም መስክ የነበረው ተሳትፎ ውጤታማ እንደነበር ተገለፀ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው የተሳተፉባቸው መድረኮችና ያደረጓቸው ውይይቶች ስኬታማ ነበሩ በዚህም በሁሉም ዘርፎች የሩስያና የኢትዮጵያ የሩስያና አፍሪካ እንዲሁም ከህዳሴው የውሀ ሙሌት አኳያ የኢትዮጵያና የግብፅ ግንኙነት የተዳሰሱባቸው ውጤታማ መድረኮች ተከናውነዋል እንደ አቶ ንጉሱ ገለፃ በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልእክታቸውም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሪፎርም በተለይም ከኢኮኖሚ አኳያ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት የሚያግዝ ኢትዮጵያም ለዚህ ከፍተኛ ፍላጎት ኖሯት ወደ ስራ የገባች መሆኑን አብራርተዋል ይህ መልእክት ደግሞ የሩስያን ኢንቨስተሮች እንዲሁም ጉባኤውን በተለያየ መልኩ ሲከታተሉ የነበሩ አካላትን ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን እንዲገነዘቡ ያደረገ ሲሆን ኢንቨስትመንቱን ለመሳብም ምቹ  ሁኔታን የሚፈጥር ነው በተመሳሳይ የሩስያ ኢንቨስተሮች ወደ ኢትዮጵያ ቢገቡ ምን ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩ ሲሆን በተለይም በአበባና አትክልት በባቡር በመንገድ በማዳበሪያና በስኳር ፋብሪካዎች እና ሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች ቢሰማሩ ኢትዮጵያም በስፋት የምትሄድባቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ከመሆናቸው አኳያ ያለውን እምቅ ሀብት እንዲገነዘቡ አድርገዋል የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንም ይህ ጥሩ እድል እንደሆነ ይሄንንም እንደሚያበረታቱ የገለፁ ሲሆን በጋራ ለመስራትም ቃል ገብተዋልበተመሳሳይ የሩስያ ኢንቨስተሮች ወደ ኢትዮጵያ ቢገቡ ምን ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያብራሩ ሲሆን በተለይም በአበባና አትክልት በባቡር በመንገድ በማዳበሪያና በስኳር ፋብሪካዎች እና ሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች ቢሰማሩ ኢትዮጵያም በስፋት የምትሄድባቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ከመሆናቸው አኳያ ያለውን እምቅ ሀብት እንዲገነዘቡ አድርገዋል የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንም ይህ ጥሩ እድል እንደሆነ ይሄንንም እንደሚያበረታቱ የገለፁ ሲሆን በጋራ ለመስራትም ቃል ገብተዋል ከዚህ በተጓዳኝ ኢትዮጵያና ሩስያ የኒውኩለር ሀይልን በማበልፀግና በመገንባት ለልማትና ለሰላማዊ ተግባራት ለማዋል ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን ይሄም በሁለቱ አገራት የሚመለከታቸው ሚኒስትሮች ተፈርሟል ቀደም ሲል በሩስያ ድጋፍ የተገነባው የመልካ ዋከና የሀይል ማመንጫ ግድብ እድሳትን ሩስያ ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላት ፕሬዚዳንት ፑቲን ገልፀዋል ኢትዮጵያ የነበረባትን የ163 ነጥብ5 ሚሊዮን ዶላር እዳ ተሰርዞ ወደልማት እንዲውል ከስምምነት ላይ ተደርሷል በመሆኑም የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር የተካሄዱ መድረኮች ስኬታማ እንደነበሩ አቶ ንጉሱ ገልፀዋል አቶ ንጉሱ እንዳሉት ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ ተወክላ ሌሎች የጎንዮሽ ውይይቶችን ያከናወነች ሲሆን በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብን አስመልክቶ ስኬታማ ውይይት አድርጋለች በዚህም የግድቡን የውሀ ሙሌት በተመለከተ እንዲሁም ከግብፅ ጋር ባለው ግንኙነት ዙሪያ ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር ተወያይተዋል በዚህም ከፖለቲካ አኳያ ማንኛውም ሶስተኛ ወገን አስተያየት ቢሰጥም ሁለቱ አገራት ጉዳዩን በስምምነት ይዘው እንዲጨርሱት ፍላጎት ከማሳየትና ድጋፍ ከማድረግ አኳያ መታየት እንደሚገባው አንስተዋል የተቋረጡት የውይይት መድረኮችም በተጠናከረ መልኩ እንደገና እንዲጀምሩ እና ኢትዮጵያም የግድቡን ሙሌት ባስቀመጠችው መልኩ እንዲጠናቀቅና ይህ ሲሆን ግን የግብፅን ስጋት በመጋራት የኢትዮጵያ ተጠቃሚነት ግብፅን በመጉዳት ላይ ያልተመሰረተ መሆኑን ግንዛቤ እንዲጨበጥበት ማድረግ ተችሏል በጥቅሉ በውይይቱ ሁለቱም መሪዎች በጥሩ መግባባት ውይይታቸውን አጠናቅቀዋል ከዚህ ባሻገር የተለያዩ የተናጠል ፎረሞች ተደርገዋል ከእነዚህ መካከል አንዱ የአፍሪካና ሩስያ ግንኙነትን ለማሳለጥ የመገናኛ ብዙሀን ሚና ምን መሆን አለበት የሚለው ሲሆን በዚህ ረገድ የአፍሪካ ሚዲያዎችና የሩስያ ሚዲያዎች ይሄን ግንኙነት በማሳካት ረገድ ያላቸውን ሁነኛ አቅም መጠቀም እንደሚገባ ተመላክቷል በአጠቃላይ የጉባኤው ተሳትፎ በሁሉም ዘርፍ የሩስያና የኢትዮጵያ የሩስያና አፍሪካ እንዲሁም ከህዳሴው የውሀ ሙሌት አኳያ የኢትዮጵያና ግብፅ ግንኙነት የተዳሰሱበት ስለነበር መድረኩ ስኬታማ እንደነበር አቶ ንጉሱ ገልፀዋልአዲስ ዘመን ጥቅምት 172012ወንድወሰን ሽመልስ
https://www.press.et/Ama/?p=21551
470
18,048
ባለፉት አራት ዓመታት በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የድርቅ አደጋ ስጋትን መቀነስ መቻሉ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
Feb 2, 2020
91
በአዲስ አበባ ጥር 24 2012 ኤፍ ቢ ሲ በኢትዮጵያ ባለፉት አራት አመታት የተሰራው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የድርቅ አደጋ ስጋትን በመቀነስ በግብርና ምርትና ምርታማነት ላይ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀበእነዚህ አመታት ከ58 ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ በህብረተሰብ ተሳትፎ ተከናውኗል ባለፉት አራት አመታት የተጀመረው ህብረተሰቡን ያሳተፈ የበጋ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ካስገኘው ውጤት ባሻገር ለኢትዮጵያ አለም አቀፍ እውቅናን አትርፏል በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚሰራው ስራ የተፈጥሮ ሀብትን ከመጠበቅ የህብረተሰብ ኑሮን ከመደገፍና አብሮ የመስራት ባህልን ከማጎልበት አንፃር በርካታ ጥቅሞች ማስገኘቱን ተጠቁሟል በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ታደሰ እንደገለፁት በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚካሄደው የአፈርና ውሀ ጥበቃ የውሀ አማራጮችን በማሳደግና በማበልፀግ ለመስኖ ልማት መስፋፋት ጉልህ ሚና አበርክቷል ከዛሬ 20 አመት በፊት ምንም አይነት የእፅዋት ሽፋን የማይታይባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች የተሻለ የእፅዋት ሽፋን ተስተውሎባቸዋል ያሉት ዳይሬክተሩ የሰብል ምርትና የግጦሽ ሳር እንዲጨምር ማድረጉን ገልፀዋል ቀደም ሲል በአንድ ሄክታር መሬት ላይ ይገኝ ከነበረው ምርት በትንሹ አንድ ኩንታል ጭማሪ ማግኘት መቻሉን በየሁለት አመቱ በሚደረገው የተፅእኖ ግምገማ ሪፖርት ላይ መታየቱን ገልፀዋል ባለፉት አራት አመታት በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች 58 ቢሊየን ብር የሚያወጣ ዘጠኝ ሚሊዮን ሄክታር ላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ መካሄዱን ኢዜአ ዘግቧል በዘንድሮው የበጋ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት ስራ መጀመሩን ተጠቁሟል
https://www.fanabc.com/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%8b%93%e1%88%98%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%8a%93%e1%8b%88%e1%8a%90%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8d%88/
191
7,035
በአንድ ሳምንት 1 ሺህ የሜዲትራኒያን ባህር ስደተኞች ሞተዋል
ዓለም አቀፍ ዜና
Saturday, 04 June 2016 12:56
2127
ከጥር ወዲህ ከ2 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋልአለማቀፉ የስደተኞች ተቋም በዚህ ሳምንት በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ስደተኞችን አሳፍረውሲጓዙ በነበሩ ጀልባዎች ላይ በደረሱ አደጋዎች  አለማቀፉ የስደተኞች ተቋም በዚህ ሳምንት በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ስደተኞችን አሳፍረው ሲጓዙ በነበሩ ጀልባዎች ላይ በደረሱ አደጋዎች ለሞት የተዳረጉ የተለያዩ አገራት ዜጎች ቁጥር 1 ሺህ ያህል እንደደረሰ ማስታወቁን ዘ ጋርዲያን ዘገበካለፈው ጥር አንስቶ በሜዲትራኒያን ባህር በደረሱ የጀልባ አደጋዎች ከ2 ሺህ 500 በላይ ስደተኞች ህይወታቸው እንዳለፈ የገለፀው ተቋሙ በአካባቢው በሚከሰቱ አደጋዎች ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መሆኑን ጠቁሞ በ2014 ተመሳሳይ ወቅት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 57 ብቻ እንደነበር አስታውሷል በተለይም ከሊቢያ ወደ ጣሊያን የሚዘልቀው የባህር ላይ የጉዞ መስመር እጅግ አስቸጋሪና አደገኛ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው አንድ ጀልባ ከመያዝ አቅሙ በላይ እስከ 600 ስደተኞችን በማሳፈር ረጅሙን የባህር ላይ ጉዞ ለማድረግ እንደሚሞክር ገልፆ በተያዘው የፈረንጆች አመት 2016 ብቻ በአካባቢው 2 ሺህ 119 ሰዎች ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸውን አስረድቷልወደ አውሮፓ የሚደረገው ስደት እየተባባባሰ መምጣቱን የጠቆመው ዘገባው ካለፈው ጥር ወዲህ 204 ሺህ ስደተኞች ሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጠው በሰላም ወደ አውሮፓ መግባታቸውን በመግለፅ ባለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ አውሮፓ የገቡ ስደተኞች ቁጥር 92 ሺህ ብቻ እንደነበር አስታውሷል
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=18305:%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5-%E1%88%B3%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%89%B5-1-%E1%88%BA%E1%88%85-%E1%8B%A8%E1%88%9C%E1%8B%B2%E1%89%B5%E1%88%AB%E1%8A%92%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%89%A3%E1%88%85%E1%88%AD-%E1%88%B5%E1%8B%B0%E1%89%B0%E1%8A%9E%E1%89%BD-%E1%88%9E%E1%89%B0%E1%8B%8B%E1%88%8D&Itemid=212
170
1,483
ስኳር ኮርፖሬሽን እና ሜቴክን ያሽመደመደው የቀድሞው መንግሥት ደካማ አሠራር ታክሎበት ስለመሆኑ ተነገረ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
97
 ክፍለዮሀንስ አንበርብርአዲስ አበባ ስኳር ኮርፖሬሽን እና ሜቴክን ያሽመደመደው የቀድሞው መንግስት ደካማ አሰራር ጭምር መሆኑን በሜቴክ እና በስኳር ኮርፖሬሽን ቦርድ አባልነትና አማካሪነት ሲሰሩ የነበሩ ምሁር አስታወቁ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ስኳር ለማምረት እያደረገችው ያለው ጥረት ከኋላቀርነት ያልተላቀቀ መሆኑም ተገልጿል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ምህንድስና መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር በላይ ወልደየስ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት በኢትዮጵያ ስኳር ለማምረት የሚያስችላት ሰፊ አቅም እንዲሁም ከ80 በመቶ በላይ አርሷደር የሚፈልገውን ማዳበሪያን ለማምረት የምትችልበት አቅም ያላት ቢሆንም የስኳር ምርቱ ኋላ ቀር ማዳበሪያ ለማምረት ያደረገችው ጥረትም በግንባታ ደረጃ መክኖ የቀረ ሆኗል በመሆኑም የስኳር ምርቱም ሆነ የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ለኪሳራ የተዳረገው ተገቢውን አሰራር መከተል ባለመቻሉ ነውእንደ ፕሮፌሰር በላይ ገለፃ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሸንኮራ ተክልን ለማልማት የሚያስችል የአየር ፀባይና ሰፋፊ ተፋሰሶች ያሉባት ሀገር ናት ይሁንና ካላት ምቹ ሁኔታ በጣም ባነሰ ከ50 አመት ጀምሮ ስኳርን ከሸንኮራ ተክል እያመረተች ትገኛለች ኢትዮጵያ እያመረተች ያለው በዋናነት ስኳር ሲሆን በሁለት ፋብሪካዎች በጣም በጥቂቱ ለተሽከርካሪ ነዳጅ የሚሆነው ኤታኖል ይመረታል ሆኖም ይህ አሰራር ወደ ኋላ የቀረ ነውየስኳር ኢንዱስትሪዎችን ወደ ዘመናዊነት በመቀየር የተለያዩ ምርቶችን ለማምረት በእኔ የሚመሩ ታዋቂ መሀንዲሶች እና ሳይንቲስቶች በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በፖሊሲ ጥናት ምርምር ኢንስቲትዩትና በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን አስጠኚነት ወደ አራት አመት የሚጠጋ ጥናት አጥንተናል በዚህም ከስኳር በተጨማሪ በአገራችን በከፍተኛ ደረጃ ተፈላጊ የሆኑ እንደ ኤታኖል ወረቀት ቅንጣጢት ቦርድ ማዳበሪያ የእንስሳት መኖ እና የኤሌክትሪክ ሀይል በስኳር ኢንዱስትሪዎች መመረት እንደሚችሉ አሳይተን ነበር የሚሉት ፕሮፌሰር በላይ ጥናቱም ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከነካቢኔያቸው ለትግራይ እና ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ፕሬዚዳንቶችና ካቢኔዎቻቸው ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች ለስኳር ኢንዱስትሪዎች ሀላፊዎች ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት እንዳላገኘ አብራርተዋል አሁን ባለው ሁኔታም አሰራሮችን መፈተሸ ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል ከስኳር ምርት በተጨማሪም ያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ለኪሳራ የተዳረገው ተገቢውን አሰራር ባለመከተል መሆኑን የገለፁት ፕሮፌሰር በላይ ከአገሪቱ በግብርና ከሚተዳደረው 80 ከመቶ ህዝብ በላይ ከአመት ወደ አመት ማዳበሪያ ፍጆታው እየጨመረ መሆኑን አመልክተዋል በመሆኑም ማዳበሪያን በቢሊዮን ዶላር በላይ እየተከፈለ ከውጭ የሚገባ ሲሆን ይህንን ችግር ለማቃለል ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ለማምረት ካለፉት 25 አመታት ጀምሮ ጥረት መደረጉን አውስተዋልይሁንና በቅርቡ ሜቴክ ጀምሮ ትርጉም አልባ ያደረገውን ያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካን ጨምሮ ስኬታማ መሆን አለመቻሉን በመግለፅ ይህ ሊሆን የቻለው በመንግስት ደካማ አሰራር መሆኑን አስረድተዋል የያዩ ማዳበሪ ፋብሪካ ግንባታም አሻጥር እንደነበረበትና ለዚህም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጭምር አስደንጋጭ ውሳኔ ይወስኑ እንደነበር አብራርተዋል አሁን ባለው ሁኔታም ለጥናቱ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት ያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ሁኔታ አሳሳቢ ነው ያሉት ፕሮፌሰር በላይ መንግስት የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ፕሮጀክቱ ወደ ተግባር የሚቀየርበት እድል ላይ ማማተር እንዳለበት አስገንዝበዋል በተመሳሳይ ሁኔታ የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ አሁናዊ አሰራርና ምርቶች አለም ከደረሰበት ቴክሎጂና እውቀት አኳያ መቃኘት እንደሚገባቸውና የዘርፉን ባለሙያዎች ማማከር አስፈላጊ እንደሆነም አስገንዝበዋልአዲስ ዘመን ታህሳስ 172013
https://www.press.et/Ama/?p=38171
397
6,187
ፍላይ ዱባይ ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቁን አስታወቀ
ቢዝነስ
Saturday, 20 February 2016 09:55
1301
የተባበሩት የአረብ መንግስታት ንብረት የሆነው ፍላይ ዱባይ አየር መንገዱ ከወር በፊት በተጠናቀቀው የፈረንጆች አመት ባደረገው እንቅስቃሴ ስኬታማ እንደነበር አስታወቀ  አየር መንገዱ በአመቱ ውስጥ 81530 በረራዎችን በማድረግና 904 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን በማጓጓዝ 274 ሚሊዮን ዶላር ያገኘ ሲሆን የተጓዞቹ ብዛት ከ2014 ጋር ሲነፃፀር በ18 ሚሊዮን ሰዎች ብልጫ 25 በመቶ መጨመሩን እንዳለውና ለ4ኛ አመት ትርፋማ መሆኑን ገልጿል አጠቃላይ ገቢው 133 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከ2014 ጋር ሲነፃፀር የ11 በመቶ እድገት አሳይቷል በአንዳንድ መዳረሻ መስመሮች በሚፈጠሩ እገዳዎች ብዙ መስተጓጎሎች መፈጠራቸውንና ከአዳዲስ የበረራ መስመሮች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ግፊትና ጫና እንደነበረበትም አመልክቷል የፍላይ ዱባይ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚር ጋኢዝ አል ጋኢዝ አጠቃላይ የንግድ ሁኔታው ፈታኝ ቢሆንም የእድገት ታሪካችንን በመጠበቅ አመቱን በስኬት አጠናቀናል ብለዋል 
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=17728:%E1%8D%8D%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8B%B1%E1%89%A3%E1%8B%AD-%E1%8B%93%E1%88%98%E1%89%B1%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%88%B5%E1%8A%AC%E1%89%B5-%E1%88%9B%E1%8C%A0%E1%8A%93%E1%89%80%E1%89%81%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B3%E1%8B%88%E1%89%80&Itemid=240
105
46,012
ትግራይ ክልል ለ960 አዳዲሰ የኢንቨስትመንት ፕሮጄክቶች ፈቃድ ሰጠ
ቢዝነስ
February 25, 2017
Unknown
በተያዘው በጀት አመት የመጀመሪያ አጋማሽ ለ960 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጄክቶች ፈቃድ መስጠቱን የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀየቢሮው ኢንቨስመንት ማስፋፋት የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ጎይቶም ገብረኪዳን ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት በግማሽ አመቱ ለ1ሺህ 300 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ 960ዎቹን ወይም 95 በመቶ ያህሉን ማሳካት ተችሏልበገንዘብ ረገድም 10 ነጥብ 8 ቢሊየን ያህል የታቀደ ቢሆንም ባለሀብቶች በግዙግፍ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች በመሰማራታቸው 12 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ያህል ኢንቨስት ማድርግ ችለዋል ይህ አሀዝ ከባለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ4 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው አቶ ጎቶም አክለው ገልፀዋልማኑፋክቸሪንግ ግብርና ሆቴልና ቱሪዝም የግንባታ ስራዎችና የማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ከተሰማሩባቸው ዘርፎች ውስጥ ይጠቀሳሉፈቃዱ ከተሰጣቸው የውጭ ባለሀብቶች ከአራት እንደማይበልጡና ቀሪዎቹ ሁሉም ኢትጵያውያን ባለሀብቶች ናቸውእነዚህ አዳዲስ ባለሀብቶች ለ53ሺህ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠር እነደቻሉም ተገልጿልአዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በፍጥነት ወደ ስራ መግባት ላይ መጓተት ተስተውሏል በተመሳሳይ ሁኔታም ወደ ስራ የገቡት ላይም ለኢንቨስትመንት የመረጡት ዘርፍ ላይ በቂ ጥናት ሳያደረጉ ስራ መጀመር የአመራር ድግፍ አናሳ መሆንና የኤሌክትሪክ ሀይል እጥረትና መቆራረጥ ተጠቃሽ ችሮች ናቸውክልሉ የተጠቀሱትን ችግሮች በመቅረፍ በተለይ ክልሉ ለማኑፋክቸሪንግና አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፎች ያለውን ምቹነት ተጠቅመው ባለሀብቶች ኢንቨሰት ቢያደርጉ ይበልጥ ውጤታማ የሚሆኑበትን ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ አቶ ጎይቶም ጠቁመዋልበተያዘው በጀት አመት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የመቀሌ ኢንደስትሪ ፓርክ ወደ ስራ ሲገባ በሚኖሩት 15 ሼዶች ባለሀብቶችን በመሳብ በክልሉ የበለጠ የኢንቨስትመንት ስራ እንደሚከናወን ይጠበቃልበትግራይ ክልል የኢንቨስትመንት ቢሮ ከተቋቋመበት ከ1985 አም  ጀምሮ ከ6ሺህ በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጄክቶች እንደተመዘገቡና ከ60 ቢሊየን ብር በላይ ኢንቨስት በማድረግ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠር ችለዋልበቅርቡ ሰሊጥና ሌሎች የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የሆነውን የሁመራ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ በጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እንደተቀመጠ በማስታወስ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል ዘግቧል
https://waltainfo.com/am/23009/
262
41,737
አባ ፍራንሲዝ ለአሜሪካ እንደራሴዎች ንግግር አደረጉ
ዓለም አቀፍ ዜና
September 24, 2015
Unknown
በዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤቱ ተገኝተው ለጥምር ጉባኤው ንግግር አድርገዋልአባ ፍራንሲስ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ አባላት ያሳለፉት መልእክት በመካከለኛው ምስራቅ ስደተኞች የአየር ንብረት ለውጥና የካፒታሊዝም ስርአት ቅጥ ባጣ መልኩ መግዘፍን አስመልክቶ ነበር በአንተ ላይ እንዲደረግብህ የማትፈልገውን በሌሎች ላይ አታድርግ የሚለውን ወርቃማው ህግ ተብሎ የሚጠራውን የቅዱስ መፅሀፍን ጥቅስ አንስተው ሰፊ ንግግር አድርገዋልበፖለቲካ ልዩነት የተከፈለው ኮንግረስ ዛሬ በአቡኑ መገኘት ለአፍታም ቢሆን አንድነት አሳይቷልበዚህ ሁኔታ በእጅጉ ከተደሰቱት መካከል አፈ ጉባኤው ጆን ቤነር ይገኛሉ ቤነር እራሳቸው የካቶሊክ እምነት ተከታይ ናቸው አባ ፍራንሲስን በክብር ተቀብለው አስተዋውቀዋቸዋልየዛሬው የአቡነ ፍራንሲዝ ንግግር ለዩናይትድ ስቴትስ ህዝብ በቀጥታ የተላለፈ ሲሆን ለእንደራሴዎቹ ለአሜሪካዊያንና ለአለም ያስተላለፏቸው መልእክቶች የገቢ አለመመጣጠን የድህነት መስፋፋትና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትሏቸው ችግሮች የስደት ጉዳይ ሰላምና አለምአቀፍ ትብብር ፍቅርና መከባበር ላይ ያተኮሩ ናቸውዘጋቢዎቻችን ከየስፍራው ያጠናቀሯቸውን ዘገባ የያዘውን ቅንብር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
https://amharic.voanews.com//a/pope-francis-addresses-congress-on-capitol-hill-in-washington-dc/2976878.html
136
41,840
ዩናይትድ ስቴትስ የመን ውስጥ የአል-ቃይዳ ማሠልጠኛ ካምፕ ላይ ባካሄደችው የአየር ድብደባ፥ ብዙ አሸባሪዎች መገደላቸውን አስታወቀች
ዓለም አቀፍ ዜና
March 24, 2016
Unknown
ዩናይትድ ስቴትስ የመን ውስጥ በሚገኝ አንድ የአልቃይዳ ማሰልጠኛ ካምፕ ላይ ባካሄደችው የአየር ድብደባ ብዛት ያላቸው አሸባሪዎች ተገድለዋል ሲል ፔንተገን ማለትም የመከላከያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቷ ትላንት አስታውቋል ጥቃቱ በአረቡሰላጤ የአልቃይዳ እንቅስቃሴ ላይ ከባድ በትር በማሳረፍ የመንን እንደ መጠለያ በመጠቀም በዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ስጋት ያስወግዳል ሲልም አስረድቷል የፔንታገን ቃል አቀባይ ቲተር ኩክ Petyer Cook አክለውም የተወሰደው እርምጃ የሚያሳየው አልቃይዳን ለማሸነፍና ቡድኑ በየትም ስፍራ መጠለያ እንዳያገኝ ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል ብለዋል ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት ከ 70 በላይ አሸባሪዎች ካምፑ ውስጥ በስልጠና ላይ እንደነበሩና ያየር ጥቃቱ በትክክል ምን ያህል ጉዳት እንዳደረሰ ለማወቅ ባለሞያዎች አሁንም እአመረመሩ መሆናቸውን ቃል አቀባዩ ጨምረው አስረድተዋል ከወዲሁ የተገኙ ውጤቶች ግን በደርዘኖች የሚቆጠሩ የአልቃይዳ አባላት መገደላቸውን ያሳያሉ ሲሉም አብራርተዋልየዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ካላቸው አሸባሪ ቡድኖች ውስጥ በአረቡ ሰላጤ የየመኑ ቅርንጫፍ ከሁሉም አደገኛው ነው ይላሉ ይህ ቡድን በዚያች ሀገር የሚካሄደውን ውጊያ ትርምስና የፖለቲካ ቀውስ በመጠቀም መሬት ሲመቀራመትና የሽብር ጥቃት ሲያደርስ ይታያል
https://amharic.voanews.com//a/us-airstrike-on-al-qaida-training-camp-in-yemen-killed-dozens-of-terrorists-/3251689.html
144
15,994
የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አባላት ችግኝ ተከሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jul 29, 2020
349
አዲስ አበባ ሀምሌ 22 2012 ኤፍቢሲ የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የችግኝ ተከላ አካሂዷልምክትል ርእሰ መስተዳድሩ የሀገር አቀፍ አረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም አካል አንድ የሆነው በክልሉ በአንድ ጀንበር ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ ሲካሄድ ቆይቷል ብለዋልበሀገር አቀፍ ደረጃ 5 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ንቅናቄ ውስጥ ክልሉ 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ድርሻ ወስዶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል ያሉት አቶ ሙስጠፌ እስከ ዛሬ 2 ሚሊየን 358 ሺህ ችግኞች መተከላቸውን ገልፀዋልለመትከል የተቀመጠው እቅድ ለማሳካት የቀሩትን 1 ሺህ 441 ሺህ ችግኞችን በተቀመጠው ግዜ ሰሌዳ ዉሰጥ እንደሚተከሉ አሳውቀዋልለዚህ ስኬት ከፍተኛ ርብርብ ያደረጉ የክልሉ አመራሮችና ህዝብ ሊመሰገኑ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል የአረንጓዴ ልማት የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ቀጣይነትና ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ተናግረዋልበክልሉ በየጊዜው የሚፈጠሩ የተፈጥሮ አደጋዎችን የሚቀንስ በመሆኑም ህብረተሰቡ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ጥሪ በማቅረብ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ለኮሮና ቫይረስ በሚያጋልጥ መልኩ መሆን እንደሌለበት ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታልበተመሳሳይ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተሳተፉ የጉባኤ አባላት የችግኝ ተከላ አካሂዷልየክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የአረንጓዴ ልማት ስራ የህልውና ጉዳይ ስለሆነ መትከል ብቻ ሳይሆን ማሳደግና መንከባከብ ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንደሚኖርበት አስታውቀዋልከህዝብና ከመንግስት የተሰጣቸውን አደራ ለመወጣት በማሰብ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ማከናወናቸውን አመልክተዋልበጋምቤላ ክልል የሚካሄደው ችግኝ ተከላ የክልሉን ደን ሽፋን የማሳደግ ጉልህ ሚና እንዲወጣ የጉባኤ አባላት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ላክዴር ላክባክ አሳስበዋል
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%b6%e1%88%9b%e1%88%8a-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8a%a8%e1%8d%8d%e1%89%b0%e1%8a%9b-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%88%ab%e1%88%ae%e1%89%bd-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8c%8b%e1%88%9d/
213
16,032
የፌደራል መንግስት፣ ብልጽግና ፓርቲና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ከትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jul 26, 2020
2,994
አዲስ አበባ ሀምሌ 19 2012 ኤፍቢሲ የፌደራል መንግስት የብልፅግና ፓርቲና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሀላፊዎች ከትግራይ ተወላጅ ባለሀብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷልበውይይቱ ላይም የፌደራል መንግስት ጦርነት ሊከፍትብን ነው መንግስት የትግራይ ክልልንና ተወላጆችን እያገለለ ነው ወዘተ የሚሉ የፕሮፖጋንዳ ትርክቶች ለፖለቲካ ፍጆታ ከመዋላቸው ባለፈ መሬት ላይ የሌሉ መሆናቸውን በመተማመን ላይ መደረሱን የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመልታልከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም በህጋዊ መንገድ ልማት ላይ የሀገር እድገት ላይ መዋእለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ የትግራይ ባለሀብቶች መንግስት ከጎናቸው እንደሚቆምም ቃል እንደተገባላቸውም ተገልጿልይህን ጉዳይ እየተከታተለ የሚያስፈፅም ተወካዮች መሰየማቸውም ነው የተገለፀውአገር ሊፈርስ ነው ጓዝህን ጠቅልለህ ወደ ክልልህ ግባ የሚለውን ውዥንብር ፕሮፖጋንዳ ሳይታለሉ ራሳቸውን አረጋግተው ሊሰሩ እንደሚገባም ተወያይቷልይህ በንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ የሁሉም አገር ናት ሁላችንም ሰርተን የምንለወጥባት ሀገር እንጂ የምንሸማቐቅባት ሀገር አለመሆንዋንም ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል ተብሏል በውይይት መድረኩ ላይFBCየዜና ሰአት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልእክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%8d%8c%e1%8b%b0%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%8d%a3-%e1%89%a5%e1%88%8d%e1%8c%bd%e1%8c%8d%e1%8a%93-%e1%8d%93%e1%88%ad%e1%89%b2%e1%8a%93-%e1%8b%a8/
146
3,922
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለኩራት ከተናገሩት
ሀገር አቀፍ ዜና
September 8, 2019
108
  ትላንት አባቶቻችን በመተማ በአድዋ በማይጨውና በካራ ማራ አጥንታቸውን ከስክሰው የከበረ ደማቸውን አፍስሰው በክብርና በአንድነት ያቆይዋት አገር አለችን እኛ እድለኞች ነን ውብ አገር አኩሪ ታሪክ አለን እኛ መነሻችንን እናውቃለን በርካታ ዘመናትን የሚሻገር ታሪክ ያለው ታላቅ ህዝብ ነን ህብረታችን ለአለም ምሳሌ መሆን ይችላል ጠላቶቻችንን አንበርክኳል ሏላዊነታችንን ጠብቆ ዛሬ ላይ ከማድረሱም በላይ ለሌሎች ህዝቦችም የነፃነት ትግል አርአያ ሆኗል ማንነታችን እንዳይለያይ ሆኖ የተሰናሰለ እንዳይነጣጠል ሆኖ የተገመደ የተዋደደ እና የተዋሀደ ነው አማራው በካራ ማራ ለሀገሩ ሏላዊነት ተሰውቶ የካራ ማራ አፈር ሆኖ ቀርቷል ትግራዋይ በመተማ ከሀገሬ በፊት አንገቴን ውሰዱ ብሎ የመተማ አፈር ሆኗል ኦሮሞው በአድዋ ተራሮች ላይ ስለሀገሩ ደረቱን ሰጥቶ የሀገሩን ሏላዊነት ለማስጠበቅ ከአድዋ አፈር ተቀላቅሏል ሱማሌው ሲዳማው ቤንሻንጉሉ ወላይታው ጋምቤላው ጉራጌው አፋሩ ስልጤው ከምባታው ሀዲያው እና ሌሎቹም  የኢትዮጵያ ህዝቦች ሁሉ በባድመ ከሀገሬ በፊት እኔን ብለው እንደወደቁ ከባድመ አፈር ጋር ተዋህዷል  አዲስ ዘመን ጳጉሜ 32011
https://www.press.et/Ama/?p=17478
130
50,826
እነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ
ፖለቲካ
October 14, 2019
Unknown
ከሰኔ 15 ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በማረፊያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ኮሎኔል አለበል አማረ እና ኮሎኔል ባምላኩ አባይ እያንዳንዳቸው በአስር ሺህ ብር ዋስ ዛሬ ከሰአት በኋላ ተለቀቁበሰኔ 15 ጥቃት ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየተጣራ በእስር የቆዩት ተጠርጣሪዎቹ ባለፈው ሀሙስ ዋስትና ጠይቀው ነበር መዝገቡን ተመልከቶ ውሳኔ ለመስጠትም ለዛሬ ተቀጥሮ ነበርበዋስትናው ዙሪያ መዝቡን ተመልክቶ አስተያዬት ለመስጠትም ለዛሬ ቀጠሮ ተሰጥቶ ነበር በቀጠሮው መሰረትም አቃቤ ህግ አስተያዬት ሰጥቷልከምርመራ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የተጣሩ መሆናቸውንና ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም የሚለው ጭብጥ ዋስትና የሚያስከለክል አለመሆኑን አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ መግለፁን የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የክልል አቃቤ ህግ ኢዮብ ጌታቸው ለአብመድ ተናግረዋልጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲወጡ አዝዟልበዚህ መሰረትም ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና አቅርበው ከሰአት በኋላ መውጣታቸውን አቶ ኢዮብ ለአብመድ አረጋግጠዋል ሲል የአማራ ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ ዘግቧል
https://waltainfo.com/am/31404/
131
28,544
ቅድመ ዳሰሳ | ስሑል ሽረ ከ ፋሲል ከነማ
ስፖርት
January 16, 2020
Unknown
ስሁል ሽረ በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ስር ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻለ መጥቷል በተለይም የቡድኑ የመልሶ ማጥቃት አጨዋወቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥሩ መሻሻሎች በማሳየት በዚ ሰአት በሊጉ አስፈሪ የመልሶ ማጥቃት ካላቸው ቡድኖች አንዱ ሆኗልሽረዎች በሊጉ የመጀመርያ ጨዋታዎች እጅግ ደካማ የሚባል የተከላካይ ክፍል የነበራቸው ሲሆን ባለፉት ጨዋታዎች የአማካይ ክፍሉን ለተከላካይ ጥምረቱ ሽፋን እንዲሰጥ ካደረጉ በሀላ ችግራቸው በተወሰነ መልኩ ቀርፈው ጥሩ የመከላከል አደረጃጀት ሰርተዋል የነገው ተጋጣሚያቸው ባለፉት ጨዋታዎች በርካታ ጎሎች ያስቆጠረውና የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሲነት የሚመራ አጥቂ ባለቤት የሆነው ፋሲል ከነማ እንደመሆኑም የተከላካይ ክፍላቸው ይፈተናል ተብሎ ይጠበቃልየተለጠጡ የመስመር አማካዮች እና ከሳጥን ውጭ እምብዛም ተሳትፎ በሌላቸው አጥቂዎች የተዋቀረው ስሁል ሽረ ባለፉት ጨዋታዎች በመልሶ ማጥቃት እና ፈጣን የማጥቃት ሽግግር ላይ በርካታ ጥሩ ለውጦች ቢያሳይም እድሎች ወደ ግብ መቀየር ግን የቡድኑ ዋነኛ ደካማ ጎን ነውበሁሉም ረገድ ለውጦች ያደርጋሉ ተብለው የማይጠበቁት ስሁል ሽረዎች በነገው ጨዋታ በጉዳት የሚያጡት ተጫዋች የለም ልምምድ የጀመረው አዳም ማሳላቺ ወደ መጀመርያ አሰላለፍ የሚመለስበት እድል እንዳለም ይገመታልከሜዳቸው ውጪ ማሸነፍ የከበዳቸው አፄዎቹ በዚህ ወቅት በጥሩ መነቃቃት የሚገኘው እና በሀላ ክፍሉ በቀላሉ ክፍተት የማይሰጥ ቡድን ጋር መገናኘታቸው ፈተናውን ከፍ ያደርግባቸዋልበአመዛኙ በኳስ ቁጥጥር ተመስርተው መሀል ለመሀል በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለማጥቃት ጥረት የሚያደርጉት 0ፄዎቹ የመከላከል ባህሪ ባላቸው አማካዮች የተሞላውን የስሁል ሽረ ቡድን ላይ በርካታ የግብ እድሎች ለመፍጠር ይቸገራሉ ተብሎ ስለሚጠበቅ የማጥቃት አጨዋወታቸው መስመር ላይ የተመረኮዘ ይሆናል ተብሎ ይገመታልከዚህ በተጨማሪ ባለፉት ጨዋታዎች ጎል ለማስተናገድ ያስገደዳቸው የመከላከል ቅርፅ የነበራቸው አፄዎቹ በነገው እለት የስሁል ሽረን መልሶ ማጥቃት ለመመከት የተለየ አቀራረብ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል በተለይም የኳስ ቁጥጥርን በመቀነስና ሽረዎች ኳስ እንዲይዙ በማድረግ ክፍተቶችን ማግኘት የመጀመርያ ኢላማቸው እንደሚሆን ይጠበቃልአፄዎቹ ያሬድ ባዬ አብዱራህማን ሙባረክ እንየው ካሳሁን እና ሰለሞን ሀብቴ ከጉዳት ቢመለሱላቸውም ለጨዋታ ብቁ ባለመሆናቸው ወደ መቐለ አልተጓዙምምንተስኖት አሎክብሮም ብርሀነ ዮናስ ግርማይ አዳም ማሳላቺ ረመዳን የሱፍሀብታሙ ሽዋለም ነፃነት ገብረመድሀንዲድዬ ለብሪ ያስር ሙገርዋ አብዱለጢፍ መሀመድሚኬል ሳማኬአለምብርሀን ይግዛው ሰኢድ ሀሰን ከድር ኩሊባሊ አምሳሉ ጥላሁንጋብርኤል አህመድ ሀብታሙ ተከስተሽመክት ጉግሳ ሱራፌል ዳኛቸው ኦሴይ ማውሊሙጂብ ቃሲም
https://soccerethiopia.net/football/54406
295
18,164
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የወረዳና የቀበሌ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jan 22, 2020
282
አዲስ አበባ ጥር 13 2012አዲስ አበባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ አመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ አፅድቋልምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የምክር ቤት አባላት ቁጥር መወሰኛ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አፅድቋልበተጨማሪም የክልሉ መንግስት የአስፈፃሚ አካላት የ6 ወር የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለጉባኤው አባላት ቀርቧልርእሰ መስተዳደሩ በሪፖርታቸው ባለፈው ግማሽ አመት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ተከስተው የነበሩ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች በተሰራው ስራ ተቀርፈው አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት መስፈኑን አመላክተዋልከአጎራባች ክልል ህዝቦች ጋር የነበረውን የቆየ ግንኙነት ለማጠናከር አልፎ አልፎ የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በእርቅና በይቅርታ በመፍታት አበረታች ለውጦች መመዝገባቸውንም ተናግረዋልበክልሉ መተከል ዞን አካባቢ የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው መመለስና በዘላቂነት ለማቋቋም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ርእሰ መስተዳድሩ በእርሻ ዝግጅት ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር እና አርሶ አደሩ እና ባለሀብቶች ወደ ስራ ባለመግባታቸው ምክንያት አፈፃፀሙ ዝቅ ማለቱን አስረድተዋልበትምህርት ዘርፉም በክልሉ 312 ሺህ 396 ተማሪዎች ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ባሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙም ተጠቅሷልመከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና ፖሊሲ ተቀርፆ ወደ ትግበራ ከተገባ በኋላም የእናቶችንና የህፃናት ሞትን ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራና መልካም ውጤት እየተመዘገበ መሆኑም ተመላክቷልበከተማና በገጠር ለ15 ሺህ 814 ወጣቶች ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል ለመፍጠር መቻሉንም ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታልበክልሉ የተለያዩ ቀበሌወች ወረዳ እንዲሆኑ እና የስም ለውጥ በማድረግ እና በክልሉ 474 ቀበሌ የነበሩት አዳዲስ ቀበሌዎች ተጨምረው 518 ቀበሌ በመሆን እንዲፀድቅ መወሰኑ ተነግሯል
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%89%a4%e1%8a%92%e1%88%bb%e1%8a%95%e1%8c%89%e1%88%8d-%e1%8c%89%e1%88%99%e1%8b%9d-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%88%ad-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%88%a8/
223
5,130
የግብር ፍትሃዊነት ትብብር ፕሮጀክት ጽ/ቤት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሄደ
ሀገር አቀፍ ዜና
February 20, 2019
65
የአገራዊ የታክስ ንቅናቄው አንድ አካል የሆነዉ የግብር ፍትሀዊነት ትብብር ፕሮጀክት ፅቤት የመክፈቻ ስነስርአት በአዲስ አበባ ተካሂዷልበስነስርአቱ ላይ ከ200 በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በገቢዎች ሚኒኒስቴር ስልጠና ተሰጥቷቸዉ በፕሮጀክት ፅቤቱ ታቅፈዉ የማህበረሰቡን የግብር ግንዛቤ ለማሳደግ እንደሚሰሩ ተጠቁሟልእንደ ኢቢሲ ዘገባ የግብር ፍትሀዊነት ትብብር ፕሮጀክት ፅቤቱ በአዲስ አበባ መርካቶ ሾላ ገበያ እና ኮልፌ ላይ በቅርቡ ስራ ይጀምራሉበቀጣይም ፕሮጀክት ፅቤቱን ድሬዳዋ ባህርዳር አዳማ አዋሳ እና ሌሎች ከተሞች ላይ ስራ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታዉቋልበንግዱ ውስጥ ሆነው ገቢ እያገኙ ግብር የማይከፍሉ የንግድ ማህበረሰብ በመኖራቸው እየተሰበሰበ ያለዉ ግብር ዝቅተኛ መሆኑ በመክፈቻ ስነስርአቱ ላይ ተገልፆአል
https://www.press.et/Ama/?p=5112
89
4,114
በግል ትምህርት ቤቶች እየተደረገ ያለው የክፍያ ጭማሪ ወላጆችን እያማረረ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 12, 2019
66
 አዲስ አበባ አዲስ አበባ በሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች እየተደረገ ያለው የክፍያ ጭማሪ በወላጆችና ትምህርት ቤቶች አስተዳደር መካከል ውዝግብ እየፈጠረ ይገኛል አዲስ ዘመን ያነጋገራቸው ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እንደተናገሩት የግል ትምህርት ቤቶቹ የአገሪቱን የኢኮኖሚም ሆነ የወላጆችን የመክፈል አቅም ያላገናዘበና የተጋነነ ክፍያ በመጠየቃቸው ምክንያት በመጪው 2012 አም ወላጆች ልጆቻቸውን ለማስተማር መቸገራቸውን ገልፀዋል የሳፋሪ አካዳሚ የወላጅ ኮሚቴ ፀሀፊ አቶ መንግስቱ ታደሰ እንደተናገሩት የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ከወላጅ ኮሚቴ ጋር ስምምነት ላይ ሳይደርስ የተጋነነ የክፍያ ጭማሪ አድርጓል ጭማሪው የተጋነነ መሆኑን በተመለከተ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ባቀረበው ጥናት ፕሮፖዛል ላይ ተደጋጋሚ ውይይት ቢደረግም የወላጆች አስተያየት በአስተዳደሩ በኩል ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም አቶ መንግስቱ እንደተናገሩት የተደረገው ጭማሪ ተገቢነት የሌለው የተጋነነ ከሁሉም በላይ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሀምሌ 302007 አም ያወጣውን መመሪያ በተለይም የተከለከሉ የክፍያ አይነቶች አንቀፅ 8 በሚለው ስር ምንም አይነት ክፍያ ለአጋዥ መፃህፍት ለኮምፒዩተርና ለሌሎች አገልግሎቶች ተጨማሪ ክፍያ አይፈፅሙም የሚለውን የጣሰ ነው ይህንኑ በተመለከተም እንደ ወላጅ ኮሚቴም ሆነ ወላጅ ከግንቦት ወር ጀምሮ እንዲስተካከል ሲጠይቅ ቆይቷል በትምህርት ቤቱ ሶስት ቅርንጫፍ ያሉ ወላጆችም የጋራ ውይይት አድርገው 850 ወላጆች ፊርማቸውን በማኖር ጭማሪውን መቶ በመቶ ቢቃወሙትም አስተዳደሩ ምንም አይነት ማስተካከያ ሊያደርግ አልቻለም የወላጅ ኮሚቴው የትምህርት ቤቱ አስተዳደር መጨመር እንደሚችል ነገር ግን ጭማሪው የተጋነነ መሆን እንደሌለበት ሀሳብ ቢያቀርብም በትምህርት ቤቱ አስተዳደር በኩል ግን ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም ያሉት አቶ መንግስቱ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የተለያዩ አካላት ቢያቀርቡም ምላሽ ሊሰጧቸው እንዳልቻሉ ተናግረዋል ምን ያህል እንደተጨመረ የጠየቅናቸው አቶ መንግስቱ ከ14ኛ ክፍል 1ሺህ 260 የነበረው ክፍያ 59 በመቶ በመጨመር 2ሺህ ብር ከ58ኛ 1ሺህ 252 በነበረው ላይ 60 በመቶ በመጨመር ብር 2ሺህ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ትምህርት ቤቱ ያለ ምንም አይነት ደረሰኝ ለተማሪዎች ምረቃ የአጋዥ መፃህፍት ግዥ እና የመሳሰሉትን እንደሚሰበስብም ተናግረዋል በመንግስት የተሰጠውን ከሀምሌ አንድ እስከ ነሀሴ 30 የተማሪ ምዝገባ የምዝገባ ጊዜ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር አልቀበልም በማለት የራሱን የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት ከሀምሌ 1 እስከ 15 አድርጎ እንደነበር የነገሩን ፀሀፊው ለወረዳው ትምህርት ፅህፈት ቤት አመልክተው ወረዳው በወሰደው እርምጃ መሰረት የምዝገባው ጊዜ ወደ ነበረበት እንደተመለሰም ተናግረዋል በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን ያነጋገርናቸው በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትና ሬጉላቶሪ ማረጋገጫ ባለስልጣን ምክትል ሀላፊ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ መንግስት ከሚከተለው የነፃ ገበያ ፖሊሲ አኳያ በግል ትምህርት ቤቶች አሰራር ላይ ገብቶ ክፍያ ጨምሩም ሆነ ቀንሱ ማለት አይችልም ወሳኞቹ ባለ ሀብቱና ወላጆች ናቸው በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ነው መቀነስም ሆነ መጨመር የሚቻለው በድርድር እንዲፈቱም ነው የሚጠበቀው እንጂ እኛ እንደ ከተማ አስተዳደር ገብተን ዋጋ መወሰን አንችልም በማለት መልሰዋል በመመሪያው መሰረት በኛ በኩል ቀደም ብለን ለሁለቱም ወገኖች የጋራ መድረክ ፈጥረን እንዲወያዩ አድርገናል ይህንን ያደረግነውም ካልተስማሙ ከወዲሁ ሌሎች አማራጮችን እንዲፈልጉ በማሰብ ነው የሚሉት ወይዘሮ ፍቅርተ የእሳቸው ቢሮ ሀላፊነት የትምህርት ጥራትን መከታተልና ደረጃውን እንዲጠብቅ ማድረግ ሲሆን የክፍያ ጉዳይ የሁለቱ ወገኖች የድርድር ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል በከተማዋ ሁለት ሺህ የግል ትምህርት ቤቶች ሲገኙ 958ቱ ጭማሪ ማድረጋቸውን ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏልአዲስ ዘመን ነሀሴ 62011
https://www.press.et/Ama/?p=15923
417
24,398
በበርሃሌ በ331 ሚሊዮን ብር የጨው ፋብሪካ ሊገነባ ነው
ቢዝነስ
15 January 2017
Unknown
ደናክል ኢንዱስትሪያል የተሰኘ አገር በቀል ኩባንያ በ331 ሚሊዮን ብር ወጪ የጨው ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በአፋር ብሄራዊ ክልል በርሀሌ ከተማ ለመገንባት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀደናክል ኢንዱስትሪያልን ያቋቋመው ቲቲኬ ኢንዱስትሪያል የተባለ በገላን ኢንዱስትሪያል ዞን የዲተርጀንት ፋብሪካ ባለቤት ነው የደናክል ኢንዱስትሪያልና ቲቲኬ ኩባንያ ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ካሳ ለሪፖርተር እንደተናገሩት ደናክል ኢንዱስትሪያል በበርሀሌ ከተማ የሚገነባው የጨው ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የኢንዱስትሪ ግብአት የከብቶች መኖ ለገበታ የሚሆን ጨው ያመርታል በበርሀሌ ወረዳ ከፍተኛ የአሞሌ ጨው ክምችት የሚገኝ ሲሆን የአካባቢው ሀብረተሰብ በባህላዊ መንገድ ለዘመናት ሲያመርት ኖሯልአቶ ሳሙኤል እንደተናገሩት ፋብሪካው የአካባቢው ማሀበረሰብ ሀመዴላ በተባለ አካባቢ የሚያመርተውን ጥሬ የአሞሌ ጨው በማነቀባበር ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ያቀርባል ፋብሪካው በወር 500000 ኩንታል ጨው የማምረት አቅም እንደሚኖረው ከዚህ ውስጥ 30 በመቶ የኢንዱስትሪ ግብአት 20 በመቶ የእንስሳት መኖ 50 በመቶ የገበታ ጨው ነውፋብሪካው የሚገነባው ከአዲስ አበባ 890 ኪሎ ሜትር ሰሜን ምስራቅ ርቃ በምትገኘው በርሀሌ ከተማ ሲሆን ደናክል ኢንዱስትሪያል ከከተማዋ መስተዳድር 20000 ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቧል የፋብሪካው የተለያዩ ዘመናዊ የጨው ማቀነባበሪያ ማሽኖች ከህንድና ከስፔን ለመግዛት ከአቅራቢዎቹ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን አቶ ሳሙኤል ተናግረዋልየፋብሪካው ግንባታ በአገር በቀል ኮንስትራክሽን ኩባንያ እንደሚካሄድና የማሽን ተከላው ስራ በማሽን አቅራቢዎቹ እንደሚከናወን ገልፀዋል የመሬት ማስተካከል ስራ ከሁለት ሳምንት በኋላ ተጀምሮ ግንባታው በስድስት ወራት ውስጥ ተጠናቆ ምርት እንደሚጀምር ተናግረዋልደናክል ኢንዱስትሪያል ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚውል ጨው ለአገር ውስጥ ቆዳ ኢንዱስትሪ ለዲተርጀንትና ለኬሚካል ፋብሪካዎች እንደሚያቀርብ ተገልጿል በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማራን በመሆኑ በአገር ውስጥ የኢንዱስትሪያል ጨው እጥረት እንዳለ እናውቃለን በገላን ኢንዱስትሪያል ዞን የዲተርጀንት ማምረቻ አለን ለፋብሪካችን የኢንዱስትሪ ጨው በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት ያለውን ችግር ስለምናውቅ ለምን ራሳችን አናመርትም ብለን ነው የተነሳነው ብለዋል አቶ ሳሙኤልደናክል ኢንዱስትሪያል ለእንስሳት መኖ የሚሆነውን ጨው በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ለማቅረብ አቅዷል አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የገበታ ጨው በማምረት ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ከወዲሁ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ አቶ ሳሙኤል ተናግረዋልመጀመሪያ የአገር ውስጥ ገበያ ፍላጎት ካሟላን በኋላ ወደ ውጭ መላክ እንጀምራለን ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚውል ጨው በተመሳሳይ የአገር ውስጥ ፍላጎት ካማሏን በኋላ ለውጭ ገበያ እናቀርባለን ያሉት አቶ ሳሙኤል የፋብሪካውን ምርቶች ተረክቦ ለውጭ ገበያ እንዲያከፋፍል ሊጎ ኢንተርናሽናል ከተባለ የዱባይ ኩባንያ ጋር መስማማታቸውን አስረድተዋልበማእድን ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ኬሚካል ሶሳይቲ የተሰራ ጥናት በደናክል ዝቅተኛ ቦታ 1200 ካሬ ሜትር መሬት በጨው የተሸፈነ እንደሆነ ያሳያል የአሞሌ ጨው ክምችቱ አንድ ቢሊዮን ቶን እንደሚገመት ይህም ከአለም ትልቁ የጨው ክምችት እንደሆነ ጥናቱ ይጠቁማል ጥናቱ የአሞሌው ጨው ጥራት ያለው መሆኑን ገልፆ ለምግብነት ለማዋል ግን በፋብሪካ ሊቀነባበር እንደሚገባ ይጠቁማልየጨው ክምችቱ በዝርዝር ተጠንቶ ባለሀብቶች በዘመናዊ የጨው ማምረት ዘርፍ እንዲሰማሩ አስፈላጊው የማስተዋወቅ ስራ ሊከናወን እንደሚገባ ጥናቱ ያሳስባል ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው የጨው ክምችት በአገር ውስጥ እያለ አገሪቱ አሁንም ጨው በውጭ ምንዛሪ የምታስገባ በመሆኑ ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ ሊበረታቱ እንደሚገባ ይጠቁማልአቶ ሳሙኤል የአካባቢው ማሀበረሰብ ከፍተኛ ሙቀት ባለው በረሀ የእጅ መሳሪያዎችን በመጠቀም አነስተኛ መጠን ያለው አሞሌ ጨው እንደሚያመርት የሚያገኘውም ገንዘብ አነስተኛ እንደሆነ ተናግረዋል ሙቀቱ እስከ 50 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚደርስ በመሆኑ በአመት የተወሰኑ ወራት ነው ማምረት የሚችሉት በገንዘብ ብዙ ተጠቃሚ አይደሉም በከፍተኛ ስቃይ ያመረቱትን አሞሌ ጨው በግመል ጭነው በዚያ ከፍተኛ ሙቀት ከሀመዴላ በርሀሌ ድረስ 60 ኪሎ ሜትር በእግራቸው ይጓዛሉ ያሉት አቶ ሳሙኤል ደናክል ኢንዱስትሪያል በዘመናዊ የአመራረት ዘዴ ስልጠና እንደሚሰጥ ማሽነሪዎችንና የትራንስፖርት አገልግሎትን ለአካባቢው ሀብረተሰብ በማቅረብ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋልደናክል ኢንዱስትሪያል የሚገነባው የጨው ፋብሪካ ለ250 ዜጎች ቋሚ የስራ እድል እንደሚፈጥር ከዚህ በላይ ግን ለአካባቢው ጨው አምራቾች ሰፊ ገበያ እንደሚፈጥር አስረድተዋል ከአካባቢው ሀብረተሰብና ሽማግሌዎች ጋር ለረጅም ጊዜ መወያየታቸውንና ሀብረተሰቡም ኢንቨስትመንቱን መቀበሉን ሶስት የጨው አምራች ማሀበራት ለፋብሪካው አሞሌ ጨው ለማቅረብ መስማማታቸውን ተናግረዋል ፋብሪካችን በጣም በተሻለ ዋጋ አሞሌ ጨውን ከአምራች ማሀበራት ይገዛል በማሽነሪና በትራንስፖርትም እገዛ እናደርግላቸዋለን ብለዋል አቶ ሳሙኤልየአፋር ክልል መንግስት ለኩባንያቸው ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው የጨው ማቀነባበሪያ ፋብሪካው ምርት ከጀመረ በቀጣይ የጨው ከረጢት ፋብሪካ ለመገንባት እቅድ መያዙን ገልፀዋል ማዳበሪያው ለራሱ ለደናክል ፋብሪካና በክልሉ ለሚገኙ ሌሎች ጨው አምራቾች እንደሚቀርብ አስረድተዋልየደናክል ኢንዱስትሪያል እህት ኩባንያ የሆነው ቲቲኬ ከስድስት አመት በፊት በ35 ሚሊዮን ብር ካፒታል ተቋቁሞ በገላን ኢንዱስትሪ ዞን ሳሙና ሻምፑና ሌሎች የፅዳት ኬሚካሎች በማምረት ላይ ይገኛል ኩባንያው ካፒታሉን ወደ 120 ሚሊዮን ብር በማሳደግ በቅርቡ ለሳሙናና ሻምፑ ማሸጊያ የሚውል ፕላስቲክ ማምረቻ ገንብቶ የሙከራ ምርት ጀምሯልቀጣዩ የመንግስት የልማት አቅጣጫ በማኑፋክቸሪንግ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እኛም ኢንቨስት ማድረግ የምንፈልገው በዚሁ ዘርፍ ነው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርም ጥረታችንን ተመልክቶ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገልን ነው ብለዋል 
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%89%A0%E1%89%A0%E1%88%AD%E1%88%83%E1%88%8C-%E1%89%A0331-%E1%88%9A%E1%88%8A%E1%8B%AE%E1%8A%95-%E1%89%A5%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%8C%A8%E1%8B%8D-%E1%8D%8B%E1%89%A5%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%88%8A%E1%8C%88%E1%8A%90%E1%89%A3-%E1%8A%90%E1%8B%8D
618
25,552
የጤና መድን ዋስትና ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ ተግባራዊ ሊሆን ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
6 December 2015
Unknown
የኢትዮጵያ የጤና መድን ኤጀንሲ ከመጪው ጥር ወር 2008 አም መጨረሻ ጀምሮ ማሀበራዊ የጤና መድን ዋስትና አገልግሎት እንደሚጀምር አስታወቀከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ ከአሰሪና ከሰራተኞች ደመወዝ መሰብሰብ ይጀመራል ከየካቲት ወር መጀመርያ ጀምሮ ደግሞ አባላት አገልግሎት የሚያገኙበትን አሰራር ከጤና ተቋማት ጋር ውል በመግባት አገልግሎቱ ይጀመራል በማለት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ አብርሀ ለሪፖርተር ገልፀዋልምንም እንኳ የጤና መድን ዋስትና አገልግሎት ለመስጠት የወጣው አዋጅ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ጡረተኞችና ከአስር በላይ ሰራተኛ ባላቸው የግል ተቋማት ተግባራዊ እንደሚደረግ ቢደነግግም ኤጀንሲው አገልግሎቱን የሚጀምረው ግን በመንግስት ሰራተኞች በጡረተኞችና በተወሰኑ የግል ተቋማት እንደሆነ ዳይሬክተሩ አስታውቀዋልአሁን የምንጀምረው በመንግስት ሰራተኞችና በጡረተኞች ላይ ነው አዋጁ አስርና ከዚያ በላይ ቢልም እነዚህን ድርጅቶች የማግኘት የማደራጀት የገንዘብ ፍሰቱና አሰባሰቡ እንዴት መሆን አለበት የሚለው ከአቅም አንፃር ትንሽ ጊዜ ይፈልጋል እንደየክልሉ 50 እና ከዚያ በላይ ወይም 100 እና ከዚያ በላይ ያሏቸው ሰራተኞችን ካዳረስን በኋላ ለተቀሩት ደግሞ በቀጣይ እየሰራን እንሄዳለን ብለዋልከሁለት አመት በፊት የጤና መድን አገልግሎትን ተግባራዊ ለማድረግ የነበረው እቅድ እስከ አሁን  ሳይተገበር ስለቆየበት ምክንያት ሪፖርተር ላቀረበው ጥያቄ ተግባራዊ ለማድረግ የነበረው እቅድ ሁለት ጊዜ ተላልፏል ይኼም የሆነበት ምክንያት አንደኛ ኤጀንሲው ይኼን ለማስፈፀም ተቋማዊ ዝግጅቱ የነበረበትን ሁኔታ በማየት ነው አስፈላጊ መዋቅሮች ተቀርፀውና አስፈላጊ ቅጥሮች ተከናውነው አቅሙ ጠንካራ ነው ወይ ገንዘብ መሰብሰብ ቢጀምር የህዝብ ገንዘብን ማስተዳደር ይችላል ወይ የሚሉት ተገምግመው አንዳንድ መሟላት የሚገባቸው ነገሮች ስለነበሩ ነው በማለት መልሰዋልአገልግሎቱ እንዳይጀመር ያደረገው ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ከአገልግሎት ሰጪ ጤና ተቋማት ዝግጁነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ አስገንዝበዋል ህዝቡ በፕሮግራሙ ጠቃሚነት ተስማምቶ በዋናነት ይጠይቀው የነበረው ጥያቄ ክፍያ ከፈፀምን በኋላ የጤና ተቋማቱ ሙሉ አገልግሎት ሊሰጡን ዝግጁና ብቁ ናቸው ወይ የሚለውን ነበር ከዚህ አንፃርም ተቋማቱን ፈትሸን መስፈርትና ደረጃ አውጥተን አጠናቀናል በመሆኑም አሁን ኤጀንሲው ከማንኛውም ጊዜ በላይ በሰው ሀይል በእውቀትና በልምድ የውስጥ አሰራሩን በተሻለ ሁኔታ ዘርግቷል ሲሉም አክለዋልየገንዘብ አሰባሰብን በተመለከተም ለጊዜው ያለውን የመንግስት የገንዘብ አሰባሰብ ስርአትን ተጠቅመን ነው የምንሰበስበው ብለዋል ሁለት ሚሊዮን አባላት እንደሚኖሩት የሚገመተው ይህ አገልግሎት አንድ ቤተሰብ አምስት አባላት እንደሚኖሩ ታሳቢ አድርጎ አጠቃላይ የተጠቃሚውን ቁጥር አስር ሚሊዮን እንደሚሆን ተገምቷልየጤና መድን አስቀድሞ በሚደረግ አነስተኛ መዋጮ ወይም ክፍያ ግለሰቦች ወይም ቤተሰቦች የጤና መታወክ ባጋጠማቸው ጊዜ ካልታሰበ ከፍተኛ የህክምና ወጪ የሚጠበቁበት ስልት እንደሆነ ኤጀንሲው በተለያዩ ወቅቶች ገልጿል የኢትዮጵያ የጤና መድን ኤጀንሲ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤት ሆኖ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 1912003 የተቋቋመ ነው
https://www.ethiopianreporter.com/article/9741
333
21,683
ጫማ አምራቹ ሁጂያን ግሩፕ የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ለመጠቅለል ተስማማ
ቢዝነስ
30 May 2019
Unknown
በጂማ የቡና ማቀነባበሪያ ይገነባልየቻይና ጫማ አምራች ሁጂያን ግሩፕ የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ሙሉ በሙሉ ከመንግስት በመረከብ ለማስተዳደርና የምርት ስራዎችን ለማካሄድ የመግባቢያ ስምምነት ፈረመ ስምምነቱን የኋጂያን ተጠሪ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወሪት ሌሊሴ ነሜ ጋር በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አዳራሽ ስምምነቱን ሀሙስ ግንቦት 22 ቀን 2011 አም ፈርመዋልጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዶር ከቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አል በሽርና ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኦማር ጊሌ ጋር በመሆን ከወራት በፊት ያስመረቁት የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአራት ወራት ውስጥ ስራ እንደሚጀምር ይጠበቃልበምክትል ፕሬዚዳንት ማእረግ የኦሮሚያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ግርማ አመንቴ ዶር በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት የኩባንያው ወደ ጂማ ኡንዱስትሪ ፓርክ መግባት በተለይ በአካባቢው ለሚገኘው የቡና ሀብት ትልቅ ፋይዳ አለው የቡና ማቀነባበሪያው እቅድ በሁለተኛው የሁጂያን የኢንቨስትመንት ምእራፍ ተግባራዊ እንሚሆን የገለፁት የኩባንያው ፕሬዚዳንት ዣንግ ኋሮግ በስምምነቱ ወቅት እንዳስታወቁት በመጀመሪያው አመት ከቻይናና ከሌሎችም አገሮች ኢንቨስተሮችን በማምጣት ከ30 ሄክታር በላይ በሆነ ይዞታ ላይ በተገነባው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ እንዲያመርቱና ለአገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ ይደረጋል  በሁለተኛው ምእራፍም የቡና ማቀነባበሪያ በመገንባት ለቻይና ገበያ ምርቶቹን እንደሚያቀርብ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማእከልም እንደሚገነባ አስታውቆ ለጂማና ለአካባቢዋ ወጣቶች ስልጠና እንደሚሰጥም ገልፀዋል ከ60 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጫማን ጨምሮ ልዩ ልዩ መገልገያዎች እንደሚመረቱበትና ከዘጠኝ ሺህ እስከ 12 ሺህ ለሚደርሱ ወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጠር ወሪት ሌሊሴ ተናግረዋልየኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ በበኩላቸው ኩባንያው ከሰባት አመታት በላይ በኢትዮጵያ ልምድ ያለው በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፓርኩን ወደ ስራ እንደሚያስገባው እምነታቸውን ገልፀዋል
https://www.ethiopianreporter.com/article/15785
219
13,838
መንግሥት በጥንቃቄና በፍጥነት እየወሰደ የሚገኘው ህግ የማስከበር እርምጃ በስኬት ታጅቦ ወሳኝ የድል ምዕራፍ ተቀዳጅቷል- አቶ ደመቀ መኮንን
ሀገር አቀፍ ዜና
Nov 28, 2020
540
አዲስ አበባ ህዳር 19 2013 ኤፍቢሲ መንግስት በጥንቃቄና በፍጥነት እየወሰደ የሚገኘው ህግ የማስከበር እርምጃ በስኬት ታጅቦ ወሳኝ የድል ምእራፍ መቀዳጀቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መልእክት ውድ የሀገራችን ህዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን ብለዋልእነሆ ዛሬ በሀገር መከላከያ ሰራዊታችን በሳል የውጊያ ጥበብ እና የትግል ወኔ የህውሀት ጁንታ ቡድን የከተመባትን የመቀሌ ከተማ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል ብለዋልመንግስት በክልሉ በጥንቃቄ እና በፍጥነት እየወሰደ የሚገኘው ህግ የማስከበር እርምጃ በስኬት ታጅቦ ወሳኝ የድል ምእራፍ መቀዳጀቱንም ገልፀዋልለዚህ ዘመን ተሻጋሪ ድል ላበቁን ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ለአማራ ክልል ልዩ ሀይል እና ሚሊሻዎች ታላቅ ምስጋና እና ክብር ይገባቸዋል ብለዋል አቶ ደመቀበዚህ ህግ የማስከበር እርምጃ በኢትዮጵያዊነት ለአፍታ ለማይደራደረው የትግራይ ክልል ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊታችን ብርቱ ደጀን በመሆን ለተጫወተው ታሪካዊ ሚና ልዩ ክብር እና ምስጋና ይገባዋል ብለዋል በመልእክታቸውበመቀጠል የጁንታውን ቡድን አድኖ ለህግ የማቅረብ ተልእኮ በተቀጣጠለው የድል ስሜት እስከመጨረሻዋ ሰአት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋልመንግስት በደረሰበት ወሳኝ የድል ምእራፍ ዜጎችን ከጥቃት የመጠበቅ እና የመከላከል ተግባሩን በጥንቃቄ በንቃት እና በሀላፊነት ስሜት የሚወጣ መሆኑንም ገልፀዋልበቀጣይ በትግራይ ክልል እና በአከባቢው ፍፁም ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን አስፈላጊውን ሁሉ በመንግስት በኩል ተፈፃሚ ይደረጋል ብለዋልበአጭር ሂደት በትግራይ ክልል በጁንታው ቡድን ሴራ የፈራረሱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት እና የማቋቋም እንዲሁም በሂደት በክልሉ ዘላቂ ሰላም እና ልማት የማረጋገጥ ስራዎች በትኩረት እንደሚከናወኑም አስታውቀዋልበጠንካራ የአመራር ጥበብ የተመራው ህግ የማስከበር እርምጃችን መሪ አላማ የጁንታውን ቡድን ካለበት ለቅሞ ለህግ ማቅረብ ተልእኮ በመሆኑ አሁንም እስከመጨረሻው ድረስ ለአላማው የተሟላ ተፈፃሚነት የትግራይ ክልል ህዝብ ወንጀለኞችን ከተደበቁበት ፈልፍሎ የማጋለጥ ታሪካዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል
https://www.fanabc.com/%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%a5%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%83%e1%89%84%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%8d%8d%e1%8c%a5%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%88%b0%e1%8b%b0/
241
31,850
“ቻምፒዮን መሆናችን ይገባናል ” የጥረት አሰልጣኝ ሰርካዲስ እውነቱ 
ስፖርት
June 6, 2018
Unknown
ጥረት ኮርፖሬት በዛሬው እለት አዲስ አበባ ከተማን አስተናግዶ 20 በማሸነፍ የ2010 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ዲቪዝዮን ቻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል ከጨዋታው በኋላ የቡድኑ አሰልጣኝ የሆነችው ሰርካዲስ እውነቱ ለሶከር ኢትዮጵያ የሰጠችውን አስተያየት እንደሚከተለው አቅርበነዋልስለ ውድድር አመቷመቱ በጣም ጥሩ ነበር ጥሩ እና ደስ የሚል ጊዜያትን አሳልፈናል በተለይ ደግሞ እንደ ዋነኛ እቅድ የያዝነውን ነገር በማሳካታችን ደስተኞች ነንቡድኔ በጣም ጥሩ ስብስብ ያለው ቡድን ነውጥሩ ጥሩ ወጣት እና ታዳጊ ተጨዋቾችን ይዣለው ይህ ደግሞ የምፈልገውን የጨዋታ እቅድ በቀላሉ ነግሬያቸው እንዲተገብሩት እና ጥሩ ውጤት እናድናመጣ አድርጎናልሁልጊዜ ስላለብን ጨዋታ እና ተጋሚያችን ስናስብ ምንም አንረበሽም እንደውም እኛ እንደ መመሪያ አድርገን የምንቀሳቀሰው ተጋጣሚ አንንቅም በተጋነነ ሁኔታም አናከብርም ብለን ነውይህ ደግሞ ምንም ሳንፈራ ለሁሉም ቡድኖች እኩል ዝግጅት እያደረግን ለጨዋታ እንድንቀርብ አድርጎናልስለ ቻምፒዮንነታቸው አሸናፊ መሆናችን ይገባናል ምክንያቱም በጣም ለፍተን ነበር እኛ በምንወዳደርበት ሊግ ላይ ካሉ ክለቦች የተሻለ የመጫወቻ ከባቢ ያለው የኛ ክለብ ነው ተጫዋቾችን ለመጥቀም በሚከፈል ክፍያም ሆነ የተስማማ የመጫወቻ ሜዳ በማዘጋጀት የተሻለ ስራዎችን ቀድመን ሰርተን ነበር ስለዚህ ቻምፒዮን መሆናችን ያንስብናል እንጂ አይበዛብንምየድል ምስጢርእዚህ ደረጃ እንድንደርስ ያደረገን ጠንክረን በህብረት መስራታችን ነው ከላይ እንደጠቀስኩት ታዳጊ ተጨዋቾች ስለሆኑ ቡድኔ ውስጥ ያሉት የምፈልገውን ነገር በቀላሉ እንድናደርግ ረድቶናል ውድድሩን ከመጀመራችን በፊት አመታዊ የክለቡን እቅድ ስናወጣ ያለምንም ጥርጥር ቻምፒዮን ለመሆን ነበር ያንን ደግሞ ለማሳካት ተጨዋቾችን ከማስፈረም ጀምር የተለያዩ ስራዎችን ሰርተናል ይሄ ደግሞ እንድናሸንፍ ረድቶናልፈታኝ ጉዳዮችውድድሩ ብዙ ፈታኝ ነገሮች ነበሩበት ሁለተኛ ዲቪዝዮን ይባል እንጂ ከስሙ በላይ አድካሚ ነገሮች ነበሩበት በክለቦች የቁጥር ብልጫም ሆነ ፉክክር አስቸጋሪ ነገሮች ነበሩበት በተደጋጋሚ ጨዋታዎችን ማድረግ አድካሚ ጉዞዎችን ማድረግ እና የመሳሰሉት እኛን እንደ ቡድን ፈትኖን ነበር ከምንም በላይ ግን ለሴቶች እግር ኳስ አሁንም የሚሰጠው ትኩረት አሁንም ዝቅተኛ ነው ይህ ደግሞ ብዙዎቻችንን ያስከፋናል የሴቶች እግር ኳስ አሁን አሁን መነቃቃቶች እያየንበት እንገኛለን ነገር ግን ይህንን እድገት በሚገባ ማስቀጠል እያልቻልን እንደሆነ እየተሰማኝቀጣይ እቅድበሚቀጥለው አመት እንደ ክለብ የምናቅደው ተፎካካሪ ለመሆን እንጂ ተሳታፊ ቡድን ላለመሆን ነው ቡድኔ ብዙ ክፍተቶች አሉበት ብዙ ልናሻሽላቸው የምንፈልጋቸው ነገሮች አሉን ያንን ደግሞ በሚገባ እናውቃለን ስለዚህ በቀጣይ አመት በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ሳይሆን ለዋንጫ ተፎካካሪ ቡድን ይዞ ለመቅረብ እንጥራለን
https://soccerethiopia.net/football/36934
307
49,175
ትራምፕ ደቡብ ኮሪያን ሊጎበኙ ነው
ፖለቲካ
May 16, 2019
Unknown
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ  በቀጣዩ ሰኔ ደቡብ ኮሪያን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለፀየጉብኝታቸው አላማም ከደቡብ ኮሪያው መሪ ሙን ጃ ኢን ጋር በሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር መርሀ ግብር ዙሪያ ለመወያየት እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧልከኋይት ሀውስ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ትራምፕ ከፕሬዚዳት ሙን ጋር ከመከሩ በኋላ በግሩፕ 20 አገራት ውይይት ለመሳተፍ ወደ ጃፓን ኦሳካ ያቀናሉትራምፕና ሙን በውይይታቸው በሰሜን ኮሪያ ኒውክሌር ዙሪያ ቁርጥ ያለ አቋም ለመያዝ ያቀዱ ሲሆን ለጉዳዩ የመጨረሻ እልባት ለማበጀትም ቆርጠዋልበትራምፕና በሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን መካከል ባለፈው የካቲት ወር በሀኖይ  ሊካሄድ የነበረው ውይይት ከተሰረዘ በኋላ ትራምፕና ሙን ሲገናኙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነውፕሬዚዳንት ሙን የኒውክሌር ታጣቂዋ ሀገር መሪ ኪም እና ትራምፕ ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲወያዩ ሁኔታዎችን ሲያመቻቹ የቆዩ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች በሲንጋፖር ተገናኝተው እንዲወያዩም ጉልህ ድርሻ ነበራቸውበሲንጋፖር በተደረገው ውይይትም ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር መርሀ ግብሯን በሂደት ለማቋረጥ ከስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ስምምነቱ በሁለቱ መሪዎች ፊርማ ተቋጭቶም ነበርይሁን እንጂ ፒዮንግ ያንግ አሜሪካ በደቡብ ኮሪያ የጀመረችውን የኒውክሌር መርሀ ግብር እንደምታቋርጥ እና በቀጣናው ያሰፈረችውን 28 ሺህ 500 ወታደሮቿን እንደምታስወጣ በስምምነቱ መካተት ሲገባው አልተካተተም በማለቷ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዳግም ሊደፈርስ ችሏልይህም በትራምፕና ኪም መካከል በሀኖይ ሊካሄድ የነበረው ውይይት እንዳይካሄድ እንደ አንድ ምክንያት ይጠቀሳልአሁን ግን ትራምፕ ከደቡብ ኮሪያው መሪ ጋር በመወያየት ለጉዳዩ የመጨረሻ እልባት ለመስጠት በቀጣይ ወር ቀጠሮ ይዘዋል
https://waltainfo.com/am/33933/
190
26,889
ስለ ሳዳት ጀማል ሊያውቋቸው የሚገቡ ዕውነታዎች
ስፖርት
December 16, 2020
Unknown
በጠንካራ ግብጠባቂነቱ የሚታወቀው በሀገሪቱ ትልልቅ ክለቦች እስከ ብሄራዊ ቡድን ድረስ ለረጅም አመት ማገልገል የቻለው የቀድሞ ድንቅ ግብጠባቂ ሳዳት ጀማል ማነውበኢትዮጵያ የግብጠባቂዎች አብዮት በተነሳበት ዘመን ከተገኙ ኮከብ ግብጠባቂዎች መካከል አንዱ ነው በስልጤ ዞን ተወልዶ እስከ አምስት አመቱ ድረስ ይደግ እንጂ የእድሜውን አብዛኛውን ዘመን የኖረው በአዲስ አበባ ተክለሀይማኖት ጡረታ ሰፈር በምትባል አካባቢ ነው አባቱ ለእግርኳስ ካላቸው ከፍተኛ ፍቅር የተነሳ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ አለ ከተባለ የማይቀሩ ቀንደኛ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ ናቸው ሁሌም ታዲያ በአንድ እጃቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ አርማ በሌላ እጃቸው አንድ ልጃቸውን ይዘው ወደ ስታዲየም ይመጡ ነበር ሁሌም ስታዲየም መጥቶ በሚመለከተው ጨዋታ ደሳለኝ ገብረጊዮርጊስ በለጠ ወዳጆ አብዱ ሳላህ ፈቱሼ ፀጋዘአብ አስገዶም እና ሌሎችንም እየተመለከተ ግብጠባቂ የመሆን ፍላጎቱ እየጨመረ መጥቷልየአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በሚማርበት ትምህርት ቤት ውስጥ ቁመና እና ቅልጥፍናውን አይተው የስፖርት መምህሩ አንተ ግብጠባቂ መሆን አለብህ በማለት በእርሳቸው ምርጫ ግብጠባቂነትን በትምህርት ቤት ውድድር ጀምሯል የሳዳት ጀማል አቅም አጀማመሩን እና የነበረውን እድገት የተመለከቱ ሁሉ በክለብ ታቅፎ ራሱን እያሳየ ማደግ አለበት በሚል በወቅቱ በአሰልጣኝ ቢረጋ ወደሚሰለጥነው መብራት ሀይል ሲ ቡድን ከብዙ ታዳጊዎች መሀል አልፎ በ1985 መቀላቀል ቻለ ወደ ዋናው ቡድን እስካደገበት 1989 ድረስ ለአራት አመታት በመብራት ሀይል ቆይታ ቢያደርግም በለጠ ወዳጆ እና ፀጋዘአብ አስገዶምን ሰብሮ በመጀመርያ አሰላለፍ መግባት የማይታሰብ መሆኑን በመረዳት በ1990 ለወራት ያህል ሊጫወት ወደ ደብረ ብርሀን ብርድ ልብስ አምርቶ ቆይታ አድርጓል በመቀጠል ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ በመመለስ ጥሩ ቆይታ አድርጓል በአንድ ወቅት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከቀድሞ የፊፋ ፕሬዝደንት ሴፕ ብላተር ጋር በጃን ሜዳ ጉብኝት እያደረጉ ሳዳት ጀማል ሲጫወት ተመልክተውት በጊዜው ሌሎች በትልልቅ ክለቦች የሚጫወቱ ግብጠባቂዎች ቢኖሩም መብራት ሀይል ነኝ ጊዮርጊስ ነኝ አይሰራም ዋናው ብቃት ነው በማለት ከታችኛው የዲቪዚዮን ውድድር ለታዳጊ ብሄራዊ ቡድን ለመረጥ ችሏልለታዳጊ ብሄራዊ ቡድን መመረጡ የበለጠ ራሱን ለማሳየት ረድቶት እንዲሁም በየጊዜው እድገቱ እና አቅሙ እየጨመረ በመምጣቱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ቀጥሎ ወደ ኒያላ በማቅናት ኒያላ ከታችኛው ዲቪዚዮን አንስቶ ፕሪምየር ሊግ እስከገባበት ጊዜ ድረስ በነበረው ሂደት ከሌሎቹ ተጫዋቾች ጋር በመሆን የእርሱ አስተዋፆኦ ከፍተኛ ነበር ለዚህም ይመስላል ወደ አርጀንቲና የወጣቶች አለም ዋንጫ አይሂድ እንጂ ቡድኑ በኢትዮጵያ በተስተናገደው የአፍሪካ ወጣቶች ዋንጫ ደቡብ አፍሪካን አሸንፎ የአለም ዋንጫ እስከገባበበት ጊዜ ድረስ የወጣት ቡድኑ ቋሚ ግብጠባቂ በመሆን ማገልገል ችሎ የነበረው በመጨረሻ ከአሰልጣኝ ዲዬጎ ጋርዚያቶ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ከብሄራዊ ቡድኑ ውጭ ቢሆንምበክለብም በብሄራዊ ቡድንም አብሮት የተጫወተው የቀድሞ ድንቅ አጥቂ ማሞአለም ሻንቆ አስፕሬላ ስለ ሳዳት ሲናገር ሳዳት ከታዳጊ ብሄራዊ ቡድን ጀምሮ አብሮኝ የተጫወተ ጓደኛዬ ነው በጣም የማደንቀው ግብጠባቂ ነው በፀባዩም ምንም ነገር የማይመስለው ዴንታ የሌለው የማይጨነቅ ግብጠባቂ ነው በጣም ቀልደኛ የሆነ የሚያስቅ ጓደኛዬ ነው እኔ ስለ እርሱ መናገር ይከብደኛል በጣም ጎበዝ የማደንቀው የማከብረው ግብጠባቂ በተለይ ከእኔ ጋር ብዙ ነገሮችን አብሮ ያሳለፈ ጥሩ ወንድሜ ነው ብሎታልየአራት አመት ስኬታማ ቆይታውን በኒያላ አጠናቆ በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ወደሚሰለጥነው ኢትዮጵያ ቡና በማምራት አይረሴ አጋጣሚዎችን በማሳለፍ ጥሩ ቆይታ አድርጓል ሳዳት በቡና ቤት በቆየባቸው ሁለት አመታት በጣም ጥሩ ብቃቱ እንዳለ ሆኖ ፈገግ የሚያሰኙ ከስፖርት ቤተሰቡ አእምሮ የማይጠፉ ብዙ ገጠመኞችን አሳልፏል ምንም እንኳን በተጫወተባቸው ክለቦች አጫጭር ቆይታ ቢኖረው በአመዛኙ በመጀመርያ አሰላለፍ ውስጥ ይገባ እንደነበረ መመልከቱ በወቅቱ የነበረውን ብቃት ማሳያ ነው ከቡና በመቀጠል መከላከያ ሙገር እና ሀዋሳ ከተማ ከተጫወተ በሀላ በ2002 ጓንቱን ለመስቀል ችሏልበኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ1990 ለታዳጊ ቡድን ከተመረጠበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም የእድሜ እርከን ሀገሩን ያገለገለው ሳዳት በ1997 በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በተካሄደውና ብሄራዊ ቡድኑ ዋንጫውን ባስቀረው የሴካፋ ዋንጫ ድል ውስጥ የቡድኑ አባል ነበርበኢትዮጵያ ቡና አብሮት የተጫወተው የቀድሞ ድንቅ ተከላካይ አንዳርጋቸው ሰለሞን ስለ ሳዳት ጀማል ሲናገር አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ለራሱ ለሚከተለው አጨዋወት ይመቸኛል ብሎት ነው ቡና ያመጣው በዚህ ዘመን ግብጠባቂዎች ኳስን መጫወት አለበት ከመባሉ በፊት በዛን ዘመን ኳስን መስርቶ በእግሩ ይጫወት የነበረ ግብጠባቂ ነው ለእኛ ለተከላካዮች ምቾት እንዲሰማን የሚያደርግ ቀለል አድርጎ የሚጫወት በረኛ ነው ግብጠባቂ ብቻ ነው የማትለው ሁሉን ነገር አቅፎ የያዘ ድንቅ ግብጠባቂ ነበር ስለ እርሱ ብዙ መናገር ይቻል ነበር ሆኖም መጫወት እየቻለ በጊዜ ነው ያቆመው በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ከታዩ ድንቅ ግብጠባቂዎች አንዱ ነበር በማለት ምስክርነቱን ይሰጣልጓንቱን ከሰቀለ በኋላ ወደ ግብጠባቂ አሰልጣኝነቱ በመግባት ሀዋሳ ከተማ ሲዳማ ቡና ሀድያ ሆሳእና አዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ቡድንን በማሰልጠን በረጅም አመት ያገኘውን ከፍተኛ ልምድ ሲያካፍል ቆይቶ በአሁኑ ወቅት በትውልድ ስፍራው ወራቤ ከተማ ከአንጋፋው አሰልጣኝ ጋሽ ከማል ጋር በመሆን የታዳጊዎች ፕሮጀክት በመክፈት ትኩረቱን ታዳጊዎች ላይ በማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ ይገኛል ከ25 አመት በላይ በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ በተጫዋችነት እና በአሰልጣኝነት ያሳለፈው ይህ የቀድሞ የዘጠናዎቹ ድንቅ በግብጠባቂ ሳዳት የዛሬው እንግዳችን በመሆን የእግርኳስ ህይወቱን እንዲህ አጫውቶናል መልካም ንባብከምንም በላይ ለኔ ስኬቴ የምለው እና የማልረሳው ወደ አርጄንቲና በሄደው ወጣት ቡድን ውስጥ ባልካተትም መላ ኢትዮጵያን ባነቃነቀው የአፍሪካ የወጣቶች ዋንጫን ደቡብ አፍሪካን አራት ለአንድ ያሸነፍንበት ድል በታሪክ እስካሁን ድረስ እንዲህ ያለው ውጤት ድልም እንደ ሀገር አልታየም የነበረው ደስታ የህዝቡ ስሜት እስከ ህይወቴ መጨረሻ ድረስ የምረሳው አይደለም ፈጣሪ አስክቶልኛል የምለው ለሀገሬ አንድ ነገር ሰርቻለው የምለው ትልቁ ድል እና ስኬቴ የምለው ይሄ ነው በመቀጠል አዲስ አበባ በተዘጋጀው የሴካፋ አላሙዲን ሲንየር ቻሌንጅ ዋንጫ ያነሳንበት ለኔ ሌላው ስኬት ነበር እንዲሁም ቡና መጫወቴ ለኔ ከምንም በላይ የምደሰትበት በቡና በነበረኝ ቆይታ አንድም ቀን ተጠባባቂ ሳልሆን ሙሉውን እስከወጣሁበት ጊዜ ድረስ የተጫወትኩበት እና ትልቅ ስም ያገኘሁበት በመሆኑ ለኔ ትልቅ ስኬት ነው በመጨረሻም አባቴ ከልጅነቴ ጀምሮ ስታዲየም ይዞኝ ይሄድ ነበር እኔ ደግሞ ስጫወት ቁጭ ብሎ ለማየት መታደሉ ሌላው ትልቁ ስኬቴ ነው በአጠቃላይ ያገኘኋቸው ስኬቶች ሀገሬን እንድወድ ያገኘሁኝ ያህል እንዲሰማኝ ያደረገኝ ትልቁ ስኬቴ እግርኳሱ ነው በአጠቃላይ በጣም በሁሉም ነገር ደስተኛ ነበርኩበህይወቴ የምቆጭበት ነገር የለም በኳስ ጨዋታ ጠግቤያለሁ በሁሉም በተጫወትኩበት ክለብ ተቀምጬ አላውቅም በሆነ ክለብ ባልጫወት ቁጭ ብል ኖሮ ይቆጨኝ ነበር በሄድኩበት ክለብ ሁሉ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ አላንሳ እንጂ በሁሉም ክለብ ከሀዋሳ ከተማ ውጭ በዋንጫ የታጀበ ጊዜን ነው ያሳለፍኩት በዚህም ስኬታማ ነኝ ሆኖም በ1996 ኢትዮጵያ ቡና በምጫወትበት ዘመን ከጊዮርጊስ ጋር ስንጫወት የተሳሳትኳት ኳስ እና ኢትዮጵያ ቡና ሻምፒዮን መሆን የሚችልበትን እድል እኔም ኮከብ ተጫዋች የምሆንበትን እድል ያጣሁበት አጋጣሚ ሁሌም የምቆጨበት ጊዜ ነውበ1996 የተፈጠረው ከጊዮርጊስ ጋር ስንጫወት ያንን ጨዋታ ብናሸንፍ ኖሮ ሻምፒዮን መሆናችንን የምናረጋግጠበት ነበር በወቅቱ ሁለት ለአንድ እየመራን ባለንበት ሁኔታ ኳስ ይዤ ባጋጣሚ ተፈንክቼ ደሜ እየፈሰሰ ጭንቅላቴን ተጠቅልዬ ነበር የያዝኩትን ኳስ ለእኛ ልጅ እሰጣለው ብዬ ኳሱ ተጠቅልሎ መሀል ላይ ያለው ሙሏለም ረጋሳ አገኘው መሰለኝ ከጎልም ውጭ ነበርኩ ያ ኳስ ጎል ገብቶ ቡና ዋንጫ ያጣበት እኔም አመቱን ሙሉ የለፋሁት ኮከብ ተጫዋች የመሆን እድሌን ያሳጣኝ መጥፎ አጋጣሚ ነውኒያላ እውነት ለመናገር አንድን ቡድን የሚገነባውም የሚያፈርሰውም የክለቡ አስተዳደሮች ናቸው በወቅቱ የነበሩ የኒያላ አስተዳደር እነ አቶ ምናሴ አቶ በቀለ አቶ ጌታቸው የሚባሉ እግርኳሱን የሚረዱ ስፖርት አዋቂ ሰዎች ነበሩ በሀላ ነው የማይሆኑ አመራሮች ከመጡ በሀላ ነው ቡድኑ እየተበላሸ የመጣው በእውነት የአስተዳደር ችግር እንጂ መፍረስ የሌለበት ቡድን ነው በኢትዮጵያ እግርኳስ ትልቅ ውለታ ያበረከተ እኛን በጥሩ ፍቅር ትልቅ ተጫዋች ያደረገን አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱን ያበቃ እስከ አሁኑ ታፈሰ ሰለሞን ድረስ ብዙ ታዳጊዎችን በሻንበል መላኩ አማካኝነት መፍጠር የቻለ ብዙ ደጋፊዎች የነበሩት ይህ ቡድን በአንድ ሰው ምክንያት ኒያላ እንዲህ በመሆኑ በጣም ነው የምናዝነውበታላቁ ክለብ ቡና የነበረኝ ቆይታ በጣም አስደሳች ነበር በጣም በማከብረው አሰልጣኝ ካሳዬ ተፈልጌ ቡና እንድገባ ስጠየቅ ያለምንም የገንዘብ ድርድር ቡና ለመጫወት ከነበረኝ ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ በሙሉ ደስታ ልፈርም ችያለው ምክንያቱም ቡና ትልቅ ቡድን ነው ይህን ማልያ መልበስ ስለምፈልግ እና ወደፊት ሁሌም በታሪክ የሚቀር ስለሆነ ለቡና ለመጫወት ወዲያውኑ ነው የፈረምኩት በሁለት አመት ቆይታዬም ሽንፈት ያየሁት ከአራት ጨዋታ አይበልጥም ትልቅ ስም ያገኘሁበት እና ትልቁን ብቃቴን ያሳየሁበት ቡድን ነው ለኢትዮጵያ ቡና በመጫወቴም ትልቅ ክብር አለኝ በቡና ቆይታዬ የዙሩን ዋንጫ ባናገኝም ሁለት የጥሎ ማለፍ ዋንጫን ማንሳት ችያለውያው እኔ ስጫወት ፉገራዎች ቀልዶች አሉ ብዙ ገጠመኞች አሉ በነገራችን ላይ ስጫወት ጎል ሲገባ አይገርመኝም ብናሸንፍም አይገርመኝም ለኔ ምንም የሚያስደንቀኝ ነገር የለም ዋናው ስራዬን በተግባር ይዤ መውጣት ላይ ነው የማተኩረው አንዳንዴ ጎል ሲገባ ሲናገሩህ የምትመልሰው መልስ አስቋቸው የሚሄዱ አሉ አንዴ ምን ሆነ መሰለህ ጋሽ ፀጋዬ ደስታ የሚባሉ አሰልጣኝ አሉ ሜዳ ላይ አንድ ጎል ገባብኝና ተቀየር ይሉኛል እኔ ባላየ ባልፍም ውጣ ብለው ጨቀጨቁኝ ዳኛው ውጣ ተቀየር እያሉህ ነው ሲለኝ አልወጣም ተዋቸው አንተ ብቻ ጨዋታውን አጫውት አልኩት እኔ በጎሉ መቆጠር ሂደት ላይ ምንም ያጠፋሁት ነገር የለም የተሳሳተውን ተከላካዩን ትተው ያላጠፋሁትን ውጣ ሲሉኝ አልወጣም አልኳቸው እረፍት ወጥተን መልበሻ ክፍል ስነገባ ጋሽ ፀጋዬ እንዴት ይህ ጎል ይገባል ሲለኝ እንዴ ጎል የተሰራው ሊገባበት አይደለም አልኩት በዚህ ሰአት እንዳለ የሳቁ በት ገጠመኝ አለ ሌላው ከአስፕሪላ ጋር በጣም እንፎጋገር ነበር እኔ እና እርሱ ካለን ሰርቪሱ በሳቅ ነው የሚሞላው አንድ ጊዜ ከሱሉልታ ስንመጣ መኪና ውስጥ የሆነ ጥያቄ እና መልስ ሬዲዮ ላይ ይጠየቅ ነበር በአለም ላይ ትልቁ ጎሬላ የት ሀገር ነው የሚገኘው ሲል አሰፕሪላ ከፊቴ ቁጭ ብሎ ስለነበር ይሄው ፊለፊት ተቀምጦ ነው ያለው ብዬ ስናገር ሰርቪሱ ውስጥ የነበሩት የሳቁት ሳቅ የማልረሳው ገጠመኝ ነው የመጨረሻ ቡና እያለሁ ከትራንስ ጋር ስንጫወት በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ትራንሶች የቅጣት ምት ያገኛሉ አጋጣሚ ሆኖ ከዛ ርቀት ቦታ ወደ ጎል ይመታዋል ብዬ ስላላሰብኩ ጎሉን ለቅቄያለሁ ተመልካቹ ግባ እያለኝ ነው እኔ ምንም አልሰማም ልጁ ኳሱን በቀጥታ ወደ ጎል መቶት ባለቀ ሰአት ጎል ይቆጠራል የቡና ደጋፊ ከፍተኛ ተቃውሞ ያቀርባሉ ወደ መልበሻ ክፍል ስገባ እኔ እየሳቅኩ ነው የምገባው ምንም አይመስለኝም በሀላ ካሳዬ ሰርቪሱን የጭነት መኪና ነው የምታደርገው ልብስህን ለብሰህ ኮፍያ አድርገህ በጊዮርጊስ በር አድርገህ ውጣ አለኝ እኔም በዛ አድርጌ ተሸፋፍኜ በጥቁር አንበሳ ዳገቱን በእግሬ እየወጣሁ ማንም ሰው ሳያየኝ ሄድኩ መንገድ ላይ ሰው ይሳደባል እኔን መሆኔን ግን አያውቅም እየሰማሁ ቤት የደረስኩበት አጋጣሚ ትዝ ይለኛል ይገርማል በሳምንቱ አዳማ ላይ ቡድኑን ይዤ ወጥቼ አንድ ለባዶ አሸንፈን ስንወጣ ደጋፊው እኔን ተሸክሞ ሲጨፍር ካሳዬ በል ውረድ ነገ ደግሞ የሚሆነው አይታወቅም ያለኝ ጊዜ አረሳውምአርጀንቲና የአለም ዋንጫ እዚህ ሀገራችን በነበረው የአፍሪካ ወጣቶች ውድድር በሁሉም ጨዋታ ላይ ተሰልፌ ነበር በኋላ ከአሰልጣኝ ጋርዚያቶ ጋር በነበረው አለመግባባት ወደ አርጀንቲና ሳልሄድ ቀርቻለሁ ምክንያቱ በልምምድ ወቅት በሚሰጡ ስልጠናዎች ዙርያ ግምገማዎች ነበሩ በዛን ሰአት እኔ አሰልጣኝ ጋርዝያቶን የሚተች ነገር ተናገርኩ ስልጠናዎቹ ከበድ የሚሉ ናቸው ለምሳሌ ግብጠባቂ ሆነን ያን ያህል ተራራ መዞሩ ለምን ያስፈልጋል የሚል አንዳንድ ጥያቄዎች አንስቼለት ነበር ከዚህ ጋር ተያይዞ የአስተርጓሚ ችግር እንደሆነ አላውቅም በዚህ ንግግሬ ጠመደኝና ወደ አርጀንቲና በመሄድ እንዳልጫወት ተደረግኩ እንግዲህ የተናገርኩትን መልእክት በሚገባ ሳያደርሱት በመቅረታቸው ጠመደኝ እንጂ በዛን ወቅት በነበረኝ አቅም እና ችሎታ የሚደሰት ሰው ነበር እዚህ ሀገር መጫወት የለብህም በማለት ሁሌም ይነግረኝ ነበርየኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከተመረጥኩበት ጊዜ ጀምሮ ግብጠባቂነትን እስካቆምኩበት ጊዜ ድረስ አንድም ቀን ሳላርፍ ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ብሄራዊ ቡድን ተመርጬ መጫወት ችያለው ከአሰልጣኝ አስራት ሀይሌ ገዛኸኝ ማንያዘዋል ጋሽ ከማል አህመድ ፀጋዬ ደስታ አብርሀም ተክለሀይማኖት ጋሽ ሰውነት ቢሻው ወንድማገኝ ከበደ ስዩም አባተ በአጠቃላይ ከሁሉም አሰልጣኞች ጋር ከውጭዎቹ አሰልጣኞች ከጋርዚያቶ ኤፊ ኦኔራ ጋር ሳይቀር አብሬ ሰርቻለሁ በዚህም በጣም ደሰረተኛ እና እድለኛ ነኝበአሰልጣኝነቱ አጀማመሬ ሀዋሳ እያለሁ ነው የጀመርኩት በመቀጠል ሲዳማ ቡና ሰርቻለሁ በ2008 ደግሞ ሀዲያ ሆሳእናን ማሰልጠን ችዬ ነበር በተለያዩ ስራዎች ምክንያት እስካቆምኩበት ጊዜ ድረስ በአሰልጣኝ መሰረት ማኒ ይመራ የነበረው አዲስ አበባ የሴቶች ቡድን መስራት ችዬ ነበር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰጡ የአሰልጣኝ ኮርሶችን ከ A ላይሰንስ በቀር ሁሉንም ስልጠናዎችን ወስጃለሁ የግብጠባቂ አሰልጣኝነት ኮርስ ሳይቀር ወስጃለሁ ብቃቱ አለኝ ልምዱም ኖሮኝ እየሰራሁ ነበር አሁን በወራቤ የታዳጊዎች ፕሮጀክት ላይ እየሰራሁ ነውአባቴ የቀለጠ የጊዮርጊስ ደጋፊ ነው ከድሮም ጀምሮ በጊዮርጊስ የማይደራደር ክብር የሚሰጥ የታወቀ ደጋፊ ነው ከእኛ ከቤተሰቡ በላይ ቤት ውስጥ ገጠር የሚሄድ ሬሳ ተቀምጦ አቆዩት ብሎ ስታዲየም ገብቶ አስራ ሁለት ሰአት ጨዋታ ጨርሶ በማታ አስከሬን ይዞ የሄደበትን ሁኔታ አስታውሳለሁ ይሄን ያህል ለጊዮርጊስ ትልቅ ዋጋ የሚከፍል አባት ነው ያለኝ በዚህ አጋጣሚ ለአባቴ የተለየ ክብር እንዳለኝ መግለፅ እፈልጋለሁ እኔ የተሻለ ደረጃ እንድደርስ በመምከር ሜዳ ውስጥ የማጠፋቸው ነገሮች ካሉ እንዳስተካክል እየነገረኝ ከአሰልጣኝ እኩል ብዙ ዋጋ የከፈለልኝ የተለያዩ ስኬቶችን እንዳሳካ ትልቅ ውለታ የወሰለልኝ ሰው ነው በዚህ አጋጣሚ አባቴን በጣም አመሰግነዋለኋባቴ የጊዮርጊስ ደጋፊ የነበረ በመሆኑ የ1996 የሰራሁትን ስህተት በማገናኘት የተለያዩ የተሳሳቱ በመላ ምት የሚወሩ ወሬዎች ይነገራሉ ለአባቱ እንዲህ አድርጎ የሚባሉ ነገሮች ከሌላ ከጥቅማጥቅም ጋር አያይዘው የሚያወሩ አሉ ለኔ ግን ከዛ ጥቅም በላይ ከየትኛውም ሀብት በላይ የቡና ገብያ ክብር ነው ለእኔ የሚቀድመው ከደጋፊው በፊት የምደሰተው እኔ ነኝ ኮከብ ተጫዋች ክብርን ለማግኘት ስለፋ ስጥር ነበር አመቱን ሙሉ ቡድኑን ስጠቅም ከርሜያለሁ በወቅቱ የተባለው ነገር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም አባቴ እንዲያውም ደስ የሚለው እኔ ኮከብ ተጫዋች ሆኜ ብሸለም ነው እንጂ የጊዮርጊስ ማሸነፍ መሸነፍ አይደለም በርግጥ በጊዮርጊስ አይደራደረደም ይታወቃል ነገር ግን የኔን ኮከብነትን ያስቀድማል የሚል እምነት አለኝ ከዚህ አንግል ደጋፊዎችን ለማሳሳት የራሳቸውን ፍላጎት ለማሳካት በወቅቱ የኔ ስም ሲገን የማይወድ ሰው አሁን ስሙን መጥራት የማልፈልገው ሰው ነው ይሄን የሚያስወራው የሚገርምህ አንተነህ አላምረው በዚሁ አመት ተባረረ አንተነህ ቢኖር ኖሮ ዋንጫ እንወስድ ነበር ሆኖም የራሱ ስም ብቻ እዛ ክለብ ውስጥ እንዲገን የሚፈልግ ሰው ነበር ያው ይታወቃል ስሙን መጥራት ስለማልፈልግ ነው ዋንጫውን ያጣነው አንተነህ አላምረው የወጣ ጊዜ ነው ስለዚህ ከኔ ጋር አይያዝም ሌላው በተከታታይ አምስት ጨዋታ ነጥብ እየጣልን ነው ከጊዮርጊስ ጋር መጨረሻ የተጫወትነው ስለዚህ ከአምስቱ ጨዋታ አንዱን ለምን አላሸነፍንም ከወንጂ መተሀራ አርባምንጭ እና ሙገር ሌሎች ተራ ተራ ቡድኖች ማሸነፍ አቅቶን ነው ዋንጫ ያጣነው ከጊዮርጊስ ጋር ይሄ የተነሳው እኔ ከቡና ክብር በላይ የማስቀድመው ሌላ ጥቅም የለም እኔ በዚሁ አጋጣሚ የቡና ደጋፊ በዚህ ልክ የተረዱ ካሉ ቢያስተካክሉ ጥሩ ነው ለኔ ቡና ማለት ከየትኛውም ክለብ በላይ ትልቅ ክብር የሰጠኝ ደጋፊ በምንም ነገር የማገኘውን የኮከብነት ክብር የማበላሽ ሰው አይደለውም እንደዚህ ያለ ወሬ ባወሩ ሰዎች አዝናለው እንጂ ሌላ የምለው ነገር የለምወደ አሰልጣኝነት ለመመለስ ፍላጎቱ አለኝ ያው እንደሚታወቀው ቦታው በጉሩፕ ተይዟል ሰዎች ክለብ የሚይዙት በአቅማቸው አይደለም እኛን ወደ አሰልጣኝነቱ እንድንመጣ የሚጋብዙ ነገሮች የሉም እኔ በጣም የማዝነው እኛ ለሀገር ካገለገልነው ከለፋነው አንፃር በክለብም በብሄራዊ ቡድንም ማሰልጠን ነበረብን ይህ በመሆኑ አዝናለሁ ወጣት ብሄራዊ ቡድን እኛ ለማሰልጠን መጠራት ሲገባን ሌላ ከየት እንደሚመጣ አናውቅም አሁን ነው ደሳለኝ ገብረ ጊዮርጊስ ሲጠራ ደስ ያለኝ የኮራሁት ዝም አልኩኝ እንጂ በተደጋጋሚ የሚጠራው የሚሄደው ሰው አንድ ነው ስለዚህ ለሀገር የለፋነውን ከግምት አስገብተው ወጣት ቡድን የምንሰራበት መንገድ መመቻቸት አለበት ፌዴሬሽኑን ስንጠይቅ የአሰልጣኙ ምርጫ ነው ይሉናል አሰልጣኙ ከመንገድ ላይ የግብጠባቂ አሰልጠኝ ቢመርጥ ሊቀበሉ ነው ስለዚህ ይህ መስተካከል አለበት የግብጠባቂ ችግር አለ ይባላል ለምን አይኑር አሰልጣኙ ማነው ይህ መመለስ አለበት እኛ ሀገራችንን ማገልገል አለብን እኔ ብቻ አደለሁም ብዙ ለሀገራቸው የሰሩ እንደ ሰብስቤ ሸገሬ እድሉ ደረጄ ሌሎችም አሉ ለሀገራቸው ለፍተው ሰርተፍኬት ይዘው ቤታቸው የተቀመጡ አሉ ለምን ለእነርሱ አይሰጥም ይህ ውለታ አይደለም ባለን አቅም እንስራ ነው ሁሉ ነገር በጉሩፕ መሆኑ መቅረት አለበትወራቤ ላይ እየሰራነው ያለው ፕሮጀክት ወደ መቶ ሰማንያ የሚጠጉ ታዳጊዎች አሉን ከስምንት አመት ጀምሮ እስከ አስራ ሰባት አመት ድረስ ያሉትን ነው የያዝነው በእድሜ እና በብቃታቸው እየለየን ወደ ብቃት ያልመጡትን እያሰራን ሀያ አምስት ሀያ አምስት እያደረግን የወዳጅነት ጨዋታ ጀምረናል በቀጣይ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የተለያዩ ጨዋታዎች በማድረግ የተሻሉ ልጆችን ወደ ተለያዩ ክለቦች እንዲሄዱ ለማድረግ እየሰራን ነው መብራት ሀይል በዚህ ረገድ መጥቶ ልጆችን ለማየት ፍቃደኛ ሆኗል በዚህ አጋጣሚ እናመሰግናለን እንግዲህ ከጋሽ ከማል ጋር በመሆን ወርደን ወራቤ ታዳጊዎች ላይ እየሰራን ነው ጋሽ ከማል ብዙ አቅም ያላቸው ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ናቸው እርሳቸውም ወርደው እየሰሩ ነው እስካሁን ባለው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው የሚገኘው ለዚህም የስልጤ ህዝብ የሰልጣኝ ወላጆች ወራቤ አስተዳደር ወራቤ ትምህርት መምርያ ወራቤ ዩኒቨርስቲ ወራቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ወራቤ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እነዚህ ሁሉ ደግፈውን ለሀገር የሚጠቅሙ መልካም ልጆችን እያፈራን እንገኛለን በዚህ አጋጣሚ ከላይ የጠቀስኳቸውን አካላት በሙሉ አመሰግናለሁየቤተሰብ ህይወቴ ያገባሁ ነኝ ስሟ ኢክማ ሀሰን ትባላለች ከእርሷም አንድ ልጅ አለኝ አብዱልከሪም ሳዳት ይባላል ስድስት አመቱ ነው የምኖረው ሀዋሳ ነው ልጄም የኔን ፈለግ በመከተል እየሰራ ነው አሁን ካለው ፕሮጀክት ጋር ቀላቅየው በማሰራት ጥሩ ግብጠባቂ አደርገዋለው ብዬ አስባለውበመጨረሻም ለአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው አስራት ሀይሌ አብርሀም መብራቱ አብርሀም ተክለሀይማኖት እና ሌሎች አሰልጣኞች ትልቅ ክብር አለኝ ለፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ ምስጋና አቀርባለሁ የሀገራችንን እግርኳስ ለማሳደግ ሁሉም የሚመለከተው አካላት በጋራ በመሆን መረባረብ አለበት እላለሁላለፉት ስምንት ወራት በተለያዩ አምዶች ስር ስናቀርብላችሁ የቆየው መደበኛ ፕሮግራሞች የመጀመርያ ምእራፍ ተጠናቋል ወደፊት በሁለተኛ ምእራፍ በተሻለ ይዘት እና ቅርፅ ወደ እንደምንመለስ እንገልፃለን
https://soccerethiopia.net/football/62307
2,300
17,967
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱርዶ ከኢትዮጵያ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
Feb 9, 2020
415
አዲስ አበባ የካቲት 1 2012 ኤፍቢሲ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱርዶ ከኢትዮጵያዊያን ሴት ስራ ፈጣሪዎች ጋር ተወያዩካለፈው አርብ ጀምሮ ለስራ ጉብኝት በአዲስ አበባ የሚገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ቱርዶ በዛሬው እለት ነው ከኢትዮጵያዊያን ሴት ስራ ፈጣሪዎች ጋር የተወያዩትበውይይታቸውም ሴት ስራ ፈጣሪዎች በስራ ሂደታቸው በሚያጋጥሟቸው ችግሮች እና በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሴት ስራ ፈጣሪዎችን ተግባር መደገፍ በሚያስፈልጉባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋልኢትዮጵያ ከዜጎቿ ውስጥ 70 በመቶ ወጣት እንደመሆኑ መጠን ስራ ፈጣሪዎችን መደገፍና ማብዛት በርካታ ወጣቶች የስራ እድል እንዲያገኙ የራሱን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግም በውይይታቸው ላይ ተነስቷልየካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ባለፈው አርብ ነበር ይፋዊ የስራ ጉበኝት ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ የመጡትትናንትናም ከፕሬዚዳንት ሳህለወረቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳልበመታገስ አየልኝ
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%8a%ab%e1%8a%93%e1%8b%b3%e1%8b%8d-%e1%8c%a0%e1%89%85%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%8c%80%e1%88%b5%e1%89%b2%e1%8a%95-%e1%89%b1%e1%88%ad%e1%8b%b6/
110
15,547
በ500 ሚሊየን ብር በአዳማ ከተማ የተገነባው ሀይሌ ሪዞርት ዛሬ ተመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
Sep 3, 2020
1,540
አዲስ አበባ ነሀሴ 28 2012 ኤፍቢሲ የሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ድርጅት በ500 ሚሊየን ብር በአዳማ ከተማ ያስገነባው 7ኛው የሀይሌ ሪዞርት ዛሬ ተመርቋልበሪዞርቱ የምርቃት ስነስርአት ላይ ሻለቃ ሀይሌን ጨምሮ የሪዞርቱ የስራ ሀላፊዎች መግለጫ ሰጥተዋልዛሬ የተመረቀው ሪዞርት ሰፋፊና ምቹ የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች ጨምሮ 106 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎች የመዋኛ ገንዳዎች እና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿልበአዳማ የተገነባው ሰባተኛው ሪዞርት በ 500 ሚሊየን ወይም በግማሽ ቢሊየን ብር ወጪ ተገነባ መሆኑን ሀይሌ በመግለጫው ገልጿልከዚያም ባለፈ 300 ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል መፍጠሩን ተናግሯልሪዞርቱ በግንባታም ሆነ በአገልግሎቱ ከሌሎች ሪዞርቶች ለየት ባለ መልኩ መቅረቡን የተናገረው ሻለቃ ሀይሌ ከባለ 4 እና 5 ኮኮብ ደረጃን የሚያሟሉ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ገልጿልግንባታውንም ለማጠናቀቅ ሁለት አመታትን የፈጀ ሲሆን በአዲሱ አመት እየተገነቡ ያሉ ሶስት ሪዞርቶችእንደሚጠናቀቁ ገልጿልበፍሬህይወት ሰፊው የዜና ሰአት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልእክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0500-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8b%b3%e1%88%9b-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8c%88%e1%8a%90%e1%89%a3%e1%8b%8d-%e1%88%80/
140
51,142
የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ሊወያዩ ነው
ፖለቲካ
September 9, 2019
Unknown
የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ሊወያዩ ነውማቻር ከሳልቫ ኪር ጋር ለሚያደርጉት ውይይት ዛሬ ጁባ የገቡ ሲሆን ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታም ሳልቫ ኪርን ጨምሮ ከሌሎች ተቀናቃኝ ሀይሎች ጋር በተደረሰው የሰላም ስምምነት ተፈፃሚነት ዙሪያ እንደሚወያዩ ተገልጿልየአሁኑ የማቻር ጉብኝት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት ተስፋን ሰጪ ነው የሚል እምነት ተጥሎበታልበፈረንጆቹ 2011 ከሱዳን ተነጥላ ሏላዊ ሀገር የሆነችው ደቡብ ሱዳን ሁለት አመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ እርስ በርስ ግጭት ገብታ ሰላም ከራቃት ሰንብታለችበወቅቱ ለተፈጠረው ግጭት ሳልቫ ኪር ሪክ ማቻርን ከስልጣን ማንሳታቸው መሆኑም ይነገራልይህን ተከትሎ የተፈጠረውን ቀውስ እልባት ለመስጠት ከአንድ አመት በፊት የሰላም ስምምነት ቢደረስም እስካሁን ተፈፃሚ ሳይሆን ቆይቷልለዚህ ደግሞ ሳልቫ ኪር ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታትና ሂደቱን ተፈፃሚ ለማድረግ የገንዘብ አቅም የለኝም የሚል ምክንያት ያቀርባሉ ነው የተባለው ምንጭሬውተርስ
https://waltainfo.com/am/33335/
119
38,842
ሳምንታዊ የስፖርት ፕሮግራም
ዓለም አቀፍ ዜና
February 06, 2017
Unknown
በአሜሪካ ፉትቦል የኒው ኢንግላንድ ፔትሪየትስ በሱፐርቦል ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደ የጭማሪ ሰአት አሽንፈው ዋንጫ አነሱ ዋና አከፋፋዩ ቶም ብሬዲ ከቻርልስ ሄሊ ቀጥሎ 5 የሱፐርቦል ቀለበት በማግኘት ሁለተኛው ተጫዋች ሆኗልየኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግና የአትሌቲክስ ስፖርት ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
https://amharic.voanews.com//a/sport-weekly-2-6-2017/3708260.html
38
14,796
በቀላል ባቡር መንገድ መሸጋገሪያዎች ላይ የሚታየውን የትራፊክ ፍሰትና የደህንነት ችግር ለመቅረፍ ያለመ ውይይት ተካሄደ
ሀገር አቀፍ ዜና
Oct 22, 2020
270
አዲስ አበባ ጥቅምት 12 2013 ኤፍቢሲ በአዲስ አበባ ከተማ የቀላል ባቡር መንገድ መሸጋገሪያዎች ላይ የሚታየውን የትራፊክ ፍሰትና የደህንነት ችግር መቅረፍ ላይ ያተኮረ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሂዷልውይይቱን የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ሰላማዊና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን እንዲሁም በቀላል ባቡር መንገድ ላይ ማሻሻያዎችን ለማካሄድ በማለም ነው ያካሄደውበውይይቱ ላይ የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት እና ትኩረቱን በተፈጥሮ ሀብቶች ላይ አድርጎ የሚሰራው አለም አቀፍ ተቋም ባለሙያዎች ተሳትፈዋልውይይቱ የከተማዋ ቀላል ባቡር በሚያልፍባቸው መስመሮች ላይ ህብረተሰቡ በተሽከርካሪ እና በእግር መንገዱን ለማቋረጥ አስቸጋሪ መሆኑ ባቡሩ የሚያልፋባቸው መንገዶች ሙሉ በሙሉ በአጥር የተዘጉ በመሆናቸው እና ሌሎች መሰል ችግሮች መፍትሄ የሚያገኙበት ላይ ያተኮረ ነውበኤጀንሲው እንደ መነሻ ሀሳብ የቀረበው የማሻሻያ ስራ በሰባተኛ እና አደይ አበባ አካባቢ ለሚስተዋሉ የእግረኛ እና የተሽከርካሪ ፍሰት እና ደህንነት ችግር የባቡር እንቅስቃሴውን በማያስተጓጉል መልኩ ለመተግበር የሚያስችል ነው ተብሏልውይይቱ የህብረተሰቡን በተለይ በቀላል ባቡር መንገዶች እና መሸጋገሪያዎች ላይ የሚስተዋለውን የትራፊክ ፍሰት እና የደህንነት ችግሮችን በጋራ ለመቅረፍ ያለመ በመሆኑ እስከ ትግበራው ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልከአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%89%80%e1%88%8b%e1%88%8d-%e1%89%a3%e1%89%a1%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%8b%b5-%e1%88%98%e1%88%b8%e1%8c%8b%e1%8c%88%e1%88%aa%e1%8b%ab%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%88%8b%e1%8b%ad/
168
49,031
የሃጅና ኡምራ ተጓዦች ያለእንግልት ደርሰው እንዲመለሱ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
June 5, 2019
Unknown
ለሀጅና ኡምራ የሚጓዙ ዜጎች ያለምንም ችግር ደርሰው እንዲመለሱ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ገለፀህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ በፊት ለሀጅና ኡምራ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲሄድ የሚደርሰውን እንግልት ለመቀነስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኮሚቴ በማቋቋም ችግሩን እንዲቀል እያደረገ እንደሚገኝ ነው የተገለፀውበዚህም የአውሮፕላን ወጪን ጨምሮ እያንዳንዱ ተጓዥ 78 ሺህ 150 ብር መክፈል የሚጠበቅበት ሲሆን ገንዘቡን የሚከፍለው በባንክ ብቻ እንደሆነ አስታውቋልክፍያውም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እንዲሁም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በተከፈቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች የሚፈፀም እንደሆነ ተገልጿልጉዞ የሚያደርግ ሰው ከሰኔ 12011 አም ጀምሮ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኩል ምዝገባ ማድረግ እንደሚችሉና ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ዝግጅቶች ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ተጠቁሟልትኬቱን በግል ገዝተው መሄድ የሚፈልጉ ተጓዦችንም ምክር ቤቱ እንደሚያስተናግድና የተጓዦቹ ትኬት መሄጃ ከአዲስ አበባ እስከ መዲና መመለሻው ደግሞ ከጅዳ እስከ አዲስ አበባ መሆን አለበት ተብሏል 
https://waltainfo.com/am/32488/
127
44,622
ኢትዮጵያዊነት በቀላሉ የሚጠፋም ሆነ የሚደበዝዝ ማንነት አይደለም….የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት
ፖለቲካ
November 6, 2017
Unknown
ኢትዮጵያዊነት በብሄር ብሄረሰቦች ትስስር የተገነባ በመሆኑ በቀላሉ የሚጠፋም ሆነ የሚደበዝዝ ማንነት አለመሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ገለፁፕሬዚዳንቱ አቶ ለማ መገርሳ በባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች የጋራ ምክክር መድረክ ላይ እንደገለፁት ኢትዮጵያ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝብች የዘመናት ጥረት ትስስር የተገነባች ሀገር ናትእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአገሩ ጉዳይ በማንነቱ በአንድነቱና በህብረቱ የማይደራደርና በጠንካራ ገመድ የተሳሰረ የፀና ፍቅር ያለው ህዝብ መሆኑን ገልፀዋልኢትዮጵያዊነት በሀገሪቱ ህዝቦች የልብ ማህተም የታተመ በመሆኑ በቀላሉ የሚጠፋም ሆነ የሚጨልም ማንነት አለመሆኑን ተናግረዋልከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትናንሽ ጉዳዮች በሚፈጠሩ አለመግባባቶች የአንድነታችንን ጥንካሬ እየተፈታተኑት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ  አንዳንዴ የሚፈጠሩ ችግሮች ክስተቶች ናቸው በማለት ከችግሩ ጋር የመላመድ አዝማሚያ እየታየ መሆኑን ገልፀዋልልዩነቶችን በማጥበብ አንድነትን ማጠናከር የሚቻለው ለዘመናት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የህዝቦችን የእርስ በርስ ግንኙነት አጠናከሮ ማስቀጠል ሲቻል ብቻ እንደሆነም አስረድተዋልበሀገሪቱ ተዋደው ተፋቅረውና ተሳስበው በሚኖሩ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ግንኙነት መካከል ምንም አይነት የሚከለክል አጥር ሊበጅ አይገባውም ሲሉም አቶ ለማ ተናግረዋልበመሆኑም ለእዚህች አገር አንድነትና ቀጣይነት የነገ አገር ተረካቢ የሆነውን ወጣት በስነ ምግባር በማነፅ በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎውን ማጠናከር የግድ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አቶ ለማ አመልክተዋልየሀገሪቱ ምሁራንም ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለችግሮች መፍትሄ በመጠቆም ሙሁራዊ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋልእንደ አቶ ለማ ገለፃ የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች የዘመናት ግንኙነት ለአፍታም ቢሆን ሳይቋረጥ ተጠናከሮ የሚቀጥል ነውበሁለቱ ክልሎች የተጀመረው የህዝብ ለህዝብ ትስስር ከሌሎች ክልሎች ህዝቦች ጋርም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋልከኦሮሚያ ክልል የመጡት አባ ገዳ ቱፋ ደራርሶ በበኩላቸው የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች ለዘመናት በጉርብትና በዝምድና ተሳስረው የኖሩ ናቸውየሁለቱ ክልል ህዝቦች ከአያት ቅድመ አያት የወረሱትን ጀግንነት ተላብሰውና መስዋእትነት ከፍለው የአገራቸውን ዳር ድንበር በጋራ አስከብረው የኖሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋልበኦሮሞና አማራ ህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩ አካላት ጥቅማቸው የተነካባቸው እንጂ ችግር መፍጠር የኦሮሞም ሆነ የአማራ ህዝብ መገለጫ ባህሪ ሆኖ አይደለም ያሉት ደግሞ አባ ገዳ ፈቃዱ ባልቻ ናቸው አብሮነታችን ለሰላማችን ሰላማችን ለአብሮነታችን በሚል መሪ ቃል የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች የጋራ ምክክር መድረክ ትናንት ማምሻውን የተጠናቀቀ ሲሆን የመድረኩ ተሳታፊዎችም በዛሬ እለት የጣና ገዳማትን ቤዛዊት ቤተ መንግስትና የአማራ ሰማእታት ሀውልትን በመጎብኘት ላይ ናቸውኤዜአ 
https://waltainfo.com/am/29438/
290
12,841
የተሰነደው 23 ነጥብ 8 ቢሊየን ወደ ገንዘብ እንዲቀየር ኮሚቴው አሳሰበ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jan 4, 2021
1,115
አዲስ አበባ ታሀሳስ 26 2013ኤፍ ቢ ሲ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በሰነድ ብቻ ያስቀመጠው 23 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ወደ ገንዘብ እንዲቀየር የገቢ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበቋሚ ኮሚቴው የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱን የስራ እንቅስቃሴ በአካል ከጎበኘ በኋላ ግብረመልስ ሰጥቷልየቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ ቡድን አስተባባሪ አቶ መስፍን መሸሻ ግብረመልሱን ባቀረቡበት ወቅት የሚሰሩ እና የማይሰሩ የግዢ እና የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖች ተለይተው ጥገና እድሳት እና ክትትል እንዲደረግላቸው ጠቁመዋልየታክስ ማጭበርበርን እና ስወራን በሚመለከትም ክትትል እና ቁጥጥር እንዲደረግ እና ግብር የማያሳውቁ እና የሚያሳንሱ ግብር ከፋዮችን መቆጣጠሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋልበሰነድ የተቀመጠው 23 ነጥብ 8 ቢሊየን ብርም ወደ ገንዘብ እንዲቀየር ከፍተኛ ክትትል እንዲደረግም በቋሚ ኮሚቴው ስም መልእክታቸውን አስተላልፈዋልበሌላ በኩልም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ማሳወቅ ጋር በተያያዘ 52 ድርጅቶች ያላሳወቁ መሆናቸው 496 የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖች በስራ ላይ አለመሆናቸው እና 199ኙ ወደ ስራ የማይመለሱ መሆናቸውን በቅርንጫፉ የአሰራር ክፍተትነት ተነስተዋልየሽያጭ እና የግዢ መረጃዎችን በመረጃ መረብ የመላክ ስልጠና እና መረጃን ወደ ኮምፒውተር ስርአት የመቀየር ተግባር እንዲሁም ለህፃናት ማቆያ ዝግጅት ትኩረት አለመሰጠቱ በእጥረት ተጠቅሰዋልኮሚቴው 87 ነጥብ 5 በመቶ ግብር ከፋይ በኢታክስ ማወቁ እና የውዝፍ እዳ አሰባሰብ ከእቅድ አኳያ የተበሻለ መሆኑ ተነስቷልየታክስ ኦዲትን በሚመለከትም የተሻለ አፈፃፀም መኖሩ እንዲሁም የግዢ ተግባር በእቅድ መመራቱ አዋጆች እና ህጎች ተደራሽ እንዲሆኑ መደረጋቸውን አበረታቷልከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘትየፋና ድረ ገፅ httpswwwfanabccom ይጎብኙ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል httpswwwyoutubecomcfanabroadcastingcorporate ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል httpstmefanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን httpstwittercomfanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b0%e1%8a%90%e1%8b%b0%e1%8b%8d-23-%e1%8a%90%e1%8c%a5%e1%89%a5-8-%e1%89%a2%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%b0-%e1%8c%88%e1%8a%95%e1%8b%98%e1%89%a5-%e1%8a%a5%e1%8a%95/
231
25,184
አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ
ቢዝነስ
20 April 2016
Unknown
የሚያዙበት ገንዘብ ሳይኖራቸው ቼክ በማውጣት በመፃፍ ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው የአክሰስ ሪል ስቴት አክሲዮን ማሀበር መስራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሚያዝያ 10 ቀን 2008 አም ለፍርድ ቤት ሰጧቶ ኤርሚያስ አመልጋ የተመሰረተባቸውን ክስ እየመረመረው የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት የተከሰሱበትን የወንጀል ድርጊት መፈፀም አለመፈፀማቸውን በሚመለከት እንዲናገሩ ጠይቋቸው ድርጊቱን አልፈፀምኩም ወንጀለኛም አይደለሁም በማለት ምላሽ ሰጥተዋልተጠርጣሪው የተመሰረተባቸውን ክስ ክደው በመከራከራቸው ከሳሽ የፌዴራል አቃቤ ህግ እንደ ክሱ እንደሚያስረዱለት የቆጠራቸውን ምስክሮች አቅርቦ እንዲያሰማ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷልበመሆኑም አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ግንቦት 5 ቀን 2008 አም አቅርቦ ለማሰማት ተቀጥሯልየአቶ ኤርሚያስ ጠበቆች ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ ማለትም ፍርድ ቤቱ መጋቢት 23 ቀን 2008 አም ጠቅሰው አቶ ኤርሚያስ የተመሰረተባቸው ክስ ዋስትና እንደማያስከለክል በ600 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የፈቀደ ቢሆንም አለመለቀቃቸውን በመጠቆም በእስር እንዲቆዩ ያደረጋቸው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መመርመር ዳይሬክቶሬት እንዲጠየቅላቸው አመልክተዋል ፍርድ ቤቱም ፖሊስ አቶ ኤርሚያስን ለምን እንዳለቀቃቸው ማብራሪያ እንዲሰጠው ትእዛዝ እንደሚሰጥ አሳውቋልአቶ ኤርሚያስ ለተለያዩ ስድስት ግለሰቦች የሚያዙበት ገንዘብ ሳይኖራቸው በድምሩ 49 ሚሊዮን ብር ደረቅ ቼክ ፅፈው ሰጥተዋል ተብለው የተመሰረተባቸውን ስድስት ክሶች ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል  በዋስትና ጉዳይ ላይ ከሳሽ አቃቤ ህግ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቦ ከተከሳሹ ጋር ክርክር ማድረጉንና ለብይን ለሚያዝያ 18 ቀን 2008 አም መቀጠሩም መዘገቡ አይዘነጋም
https://www.ethiopianreporter.com/article/12223
190
17,911
በጅማ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ
ሀገር አቀፍ ዜና
Feb 13, 2020
776
አዲስ አበባ የካቲት 5 2012 ኤፍቢሲ የጅማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች በዛሬው እለት በጅማ ከተማ ስታዲየም የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱሰልፉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይን መላውን የለውጥ አመራር እና ብልፅግናን ለማበረታታት ያለመም ነውበሰልፉ ላይ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰዎች ባላቸው ፖለቲካዊ አመለካከትና አስተሳሰብ ሊሰደቡ አይገባም ብለዋልየኦሮሞ ህዝብ አቃፊና ከብሄር ብሄረሰቦች ጋር በሰላም በፍቅርና በመከባበር ለዘመናት የኖረ ነው ሲሉም ሰልፈኞቹ ገልፀዋልነዋሪዎቹ በማከልም ከመንግስት ጎን በመቆም ሰላማችንን አስጠብቀን ብልፅግናችንን እናረጋግጣለን ነው ያሉትበድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ መኪዩ መሀመድ ባስተላለፉት መልእክት ህብረተሰቡ ሰላሙን ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ተሳትፎ አድንቀዋልበዚህ ረገድ የጀመረውን ስራ ወደፊትም አጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክት አስተላልፈዋልበተመሳሳይ የአጋሮ ከተማ እና ዙሪያዋ ነዋሪዎችን ያሳተፈ የድጋፍ ሰልፍ በዛሬው እለት በአጋሮ ከተማ ተካሂዷልበሙክታር ጠሀ
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%8c%85%e1%88%9b-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b-%e1%8b%a8%e1%8b%b5%e1%8c%8b%e1%8d%8d-%e1%88%b0%e1%88%8d%e1%8d%8d-%e1%89%b0%e1%8a%ab%e1%88%84%e1%8b%b0/
106
14,608
ኢትዮጵያውያን የፕሬዚዳንት ትራምፕን አስተያየት በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲና በለንደን ሰልፍ አካሄዱ
ሀገር አቀፍ ዜና
Oct 30, 2020
1,153
አዲስ አበባ ጥቅምት 20 2013 ኤፍቢሲ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን አስተያየት በመቃወም ኢትዮጵያውያን በለንደን እና በዋሽንግተን ዲሲ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱበአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሰጡትን አስተያየት በመቃወም ከፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ስፍራ ኋይት ሀውስ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋልየፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተያየት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት የሚያሻክር እና ተገቢነት የሌለው ነው ሲሉም ተችተዋልበለንደን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የፕሬዚዳንት ትራምፕን አስተያየት በመቃወም ለንደን በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ አካሄዷልበፕሬዚዳንቱ አስተያየት የተበሳጩ ኢትዮጵያውያን ትናንት የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኔ ነው አሜሪካ ገለልተኛ አይደለችም የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ሰልፍ ወጥተዋልሰልፈኞቹ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለግዴለሽ አስተያየታቸው ይቅርታ መጠየቅ ይኖርባቸዋልም ብለዋልበህዳሴ ግድብ ዙሪያ በቅርቡ የሰጡትን አስተያየት እንዲያስተባብሉ እና ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ ለማቋረጥ የወሰኑትን ውሳኔ ዳግም እንዲያጤኑት እንጠይቃለንም ይላል በብሪታንያ የኢትዮጵያውን ማህበር ያወጣው መግለጫምንጭ ቪኦኤ እና ቢቢሲ
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8b%8d%e1%8b%ab%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%9a%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%89%b5%e1%88%ab%e1%88%9d%e1%8d%95%e1%8a%95-%e1%8a%a0/
128
32,087
ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድኑ ለመልሱ ጨዋታ ዝግጅት ጀምሯል
ስፖርት
April 14, 2018
Unknown
በ2019 በኒጀር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የቶታል የአፍሪካ ከ20 አመት በታች ዋንጫ የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታውን ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ስታድየም ያደረገው የኢትዮዽያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በቡሩንዲ 2 0 በሆነ ውጤት በመሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሉን አጣብቂኝ ውስጥ መክተቱ ይታወሳል  ቡድኑ ከጨዋታው በኋላ ለአንድ ሳሞንት እረፍት ተበትኖ የነበረ ሲሆን አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ ለመልሱ ጨዋታ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን በማድረግ 18 ተጨዋቾችን ብቻ ይዘው በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሜዳ ከትላንት በስትያ ጀምሮ ዝግጅታቸውን እያደረጉ ይገኛል ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር አብረው ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል ግብጠባቂው ፅዮን መርእድ ተከላካዮቹ ዮናታን ፍስሀ እና ሰለሞን ወዴሳ አማካዮቹ ሚካኤል ሀሲሶ እና ሶፎንያስ መኮንን እንዲሁም አጥቂው ቃልኪዳን ዘላለም ከብሄራዊ ቡድኑ ውጭ ሲሆኑ ግብጠባቂው በረከት አማረ ከጉዳት መልስ ተከላካዩ ይትባረክ ሀብታሙ ከቡራዮ ከተማ እና አጥቂው እስራኤል እሸቱ ከሀዋሳ ከተማ ጥሪ ተደርጎላቸው ቡደሰኑን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸውዛሬ ረፋድ ላይ ብሄራዊ ቡድኑ በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሜዳ ከአይቮሪኮስት ከመጣ የፕሮጀክት ቡድን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አድርገዋል አሰልጣኙ አጥናፉ አለሙም ዝግጅታቸውን በቀጣይ ቀናትም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል የመጀመርያ ጨዋታ ላይ የነበሩብንን ድክመቶች በሚገባ አይተናል በቀጣይ ድክመቶቻችንን አሻሽለን በመልሱ ጨዋታ ውጤቱን ለመቀልበስ በቂ ዝግጅት እናደርጋለን በተወሰኑ ቦታዎች ላይ በነበሩን ክፍተቶች ላይ ተጫዋቾችን ቀንሰን በምትካቸው ሁለት ተጫዋቾችን ጨምረናል ብለዋል
https://soccerethiopia.net/football/35651
193
47,124
ኢሕአዴግ ከህዝብ ጋር የሚያደርገውን ውይይት አጠናክሮ ይቀጥላል-ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም
ፖለቲካ
May 21, 2015
Unknown
የመልካም አስተዳደር ችግሮች የልማት እንቅፋት ከመሆናቸው በፊት ኢህአዴግ ከህዝብ ጋር በሚያደርገው ውይይት አስቀድሞ ለመፍታት የተከተለውን አቅጣጫ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁጅማ ከተማን ጨምሮ ከጅማ ዞን ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች በልማትና መልካም አስተዳደር አፈፃፀም ችግሮችና ጠንካራ ጎኖች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝከኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከድርና ከከተማው አስተዳደር ጋር ዛሬ ተወያይተዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በተለይ ከኤሌክትሪክ መቆራረጥና መንገድ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ችግር በጅማ ዞን ብቻ ሳይሆን በሁሉም የአገሪቱ አካባቢ ጎልቶ የሚነሳ ችግር ነው ብለዋልበሁሉም አካባቢ የሚታየው ችግር ከመንግስት ጉድለት የመነጨ ሳይሆን የህብረተሰቡ የአገልግሎት ተጠቃሚነት ፍላጎት እየሰፋ ከመምጣት ጋር ተያይዞ የመጣ መሆኑንም ገልፀዋል መንግስት በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ 75 በመቶ የገጠሩን አካባቢ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ በያዘው ሰፊ እቅድ አበረታች ውጤት ቢመዘገብም የትራንስፎርመርና ቆጣሪ አቅርቦት እጥረት በማጋጠሙ የአቅም ውስንነት ለችግሩ ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ትራንስፎርመርና ቆጣሪ በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመሩን ተናግረዋል በመንገድ መሰረተ ልማት በኩል መንግስት በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋፋት በሰራው መጠነ ሰፊ ስራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን አገልግሎቱ ባልተዳረሰባቸው አካባቢ እንደችግሩ ስፋትና እንደ አካባቢዎቹ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የመንገድ ግንባታ ለማካሄድ አቅጣጫ መያዙን አስታውቀዋል ከመልካም አስተዳደርና አፈፃፀም ጋር ተያይዞ የሚታየው ችግር ሙሉ በሙሉ አለመቀረፉን ገልፀው ችግሩ እንደስርአት ሳይሆን በግለሰቦች ደረጃ የሚፈፀም በመሆኑ መንግስት የድርጊቱ ሰለባ በሆኑ አመራሮች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን በአፅኖት ተናግረዋል በሀገሪቱ የሚታየው የሰዎች ህገወጥ ስደት የችግሩ መንስኤ ከፖለቲካ ጋር ምንም አይነት ተያያዥነት የሌለው መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከግንዛቤ እጥረትና ከድህነት ጋር የተያያዘ መሆኑን አስታውቀዋል የህብረተሰቡን አመለካከት በመለወጥና ልማትን በማፋጠን ችግሩን በዘላቂነት መፍታት የሚቻለው በመንግስት ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡም ከፍተኛ የሀላፊነት ድርሻ ያለበት በመሆኑ በቀጣይ የተቀናጀ ስራ ለመስራት ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል መንግስት በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራ ለሚያከናውናቸው ስራዎች በዋናነት ህዝቡን ያሳተፉ እንዲሆኑ አቅጣጫ መያዙን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም በልማትና መልካም አስተዳደር ላይ ከህዝቡ ጋር የሚደረጉ ውይይቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከድር ድርጅታቸው ኦህዴድኢህአዴግ ከህዝብ ጋር የሚያደርገው ውይይት ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ድክመቶቹን እያረመ ለመጓዝ ትልቅ የአቅም ምንጭ ሆኖታል ብለዋል ድርጅቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ወደ ልማት እንቅፋትነት ከመቀየራቸው በፊት አስቀድሞ የመፍታትና የማስወገድ አቅጣጫን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል በተለይም በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከህብረተሰቡ የተነሱ ቅሬታዎችን በማጥናት የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል መንግስት ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ሙክታር በተለይ በጅማ ዞን በገጠር መንገድ ተደራሽነት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በክልሉ በአርያነት ተጠቃሽ በመሆኑ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል እንደ ኢዜአ ዘገባ ነዋሪዎቹ በውይይቱ ላይ ካነሷቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች መካከል የመብራት አገልግሎት መቆራረጥ በከተማው ከመሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ የሚታይ ህገወጥ የመሬት ይዞታና ካርታ አሰጣጥ የከተማ ንፅህና መጓደል ለከተማው ውበት የነበረው የአወይቱ መናፈሻ መፍረስና ያለ አገልገሎት መቀመጥየጊቤ አዳራሽና ቤተመንግስት ክብካቤ ማጣትና ለጉዳት መዳረግ የሊሙ ገነት ከተማ የውስጥ ለውስጥና ከኦሞናዳ ተርጫ መንገድ ብልሽትና የአስፓልት ጥያቄ  ይገኙባቸዋልበአገሪቱ ጎልቶ በሚታየው ህገወጥ የሰዎች ስደት የጅማ ዞን ትልቁን ድርሻ መያዝአካባቢው ለግብርና ልማት አመቺ ቢሆንም በተለይ የጓሮ አትክልት ምርት በገበያ ላይ ባለው እጥረት ከሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች መቅረብጅማ ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ የጎበተ ልምድ ቢኖረውም ችግሩን መቅረፍ የሚያስችል ምርምር በማድረግ ተግባራዊ አለማድረጉ ነዋሪዎቹ ካነሷቸው ችግሮች ተጠቃሽ ናቸው ለረዥም ጊዜ ችግር ሆኖ የቆየው የጅማ ከተማ አስፓልት መንገድ ግንባታን ጨምሮ የነዋሪውን ማህበራዊና ኢኮኖሚ ችግር ለመፍታት እየተካሄደ ያለው የመሰረተ ልማት ግንባታ አበረታች መሆኑን በጠንካራ ጎኑ የገለፁት ነዋሪዎቹ በከተማው ግዙፍ የማምረቻ መንደር ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ መቀመጡ የከተማውን ህብረተሰብ የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍና የህዝቡን የረዥም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል የጅማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሰለሞን አበበ በከተማው ከመሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ የሚታየው የአፈፃፀም ክፍተት እየተሻሻለ የመጣበት ሁኔታ በመፈጠሩ ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች በአስተዳደርና በህግ አግባብ እልባት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል በከተማው የአወይቱ መናፈሻ በአካባቢው ከመሰረተ ልማት ግንባታና ውስጣዊ ችግር ጋር ተያይዞ የተፈለገውን አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ለልማታዊ ባለሀብት በመስጠት ጥቅም ላይ ማዋል የሚቻልበት አቅጣጫ መያዙን ገልፀዋል
https://waltainfo.com/am/25407/
581
3,487
በህዝበ ውሳኔው ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ
ሀገር አቀፍ ዜና
November 15, 2019
58
ከሁለት ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋልአለታ ወንዶ ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች ገለፁየኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ እስከ ህዳር 3 ቀን 2012 አም ከሁለት ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምፅ ለመስጠት መመዝገባቸውን አስታውቋል በአለታ ወንዶ ከተማ ጨፌ ቀበሌ ፅህፈት ቤት ምርጫ ጣቢያ የተመዘገበው ወጣት እንዳሻው አበበ እንደተናገረው እስካሁን በአገራዊ ምርጫም ሆነ በህዝበ ውሳኔ ላይ ድምፅ ሰጥቶ አያውቅምየምርጫ ካርድ ለመውሰድ በጉጉት ሲጠባበቅ የነበረ ቢሆንም በስራ ምክንያት ከከተማዋ ወጥቶ ካርድ ሳይወስድ ቆይቷል አሁን ግን ከሄደበት በመመለስ ታሪካዊ ለሆነው ህዝበ ውሳኔ ካርድ ወስዷልድምፁን ለመስጠትም ህዳር 102012ን በጉጉት እየጠበቀ መሆኑን ገልፆ ህዝበ ውሳኔው ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ለመወጣት ዝግጁ እንደሆነ ተናግሯል በአለታ ወንዶ ከተማ የዴላ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ገብረመድህን ወልዱ በበኩላቸው ምዝገባው እንደተጀመረ ከነቤተሰባቸው የድምፅ መስጫ ካርድ መውሰዳቸውንና ህዳር 10ን በጉጉት እየተጠባበቁ መሆኑን ተናግረዋልየድምፅ አሰጣጡ ያለችግር እንዲጠናቀቅ ህዝቡ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ያሉት አቶ ገብረ መድህን በተለይም ወጣቶች ለጠብ ከሚጋብዙ ነገሮች ራሳቸውን በማራቅ ህዝበ ውሳኔው በሰላም እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው  ተናግረዋልየህዝበ ውሳኔውን አፈፃፀም ለማስተባበር ከአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ክልል ከሰበታ ከተማ የሄዱት አቶ ጫጮ ሲኖ በአለታ ወንዶ ከተማ የሸይቻ 02 የምርጫ ጣቢያ አስተባባሪ ናቸው በጣቢያው 850 መራጮችን ለመመዝገብ ታቅዶ እስከአሁን አስፈላጊ መስፈርቶችን ያሟሉ 872 ሰዎች መመዝገባቸውን ተናግረዋልይህም ህዝቡ ፍላጎቱን ለመግለፅ በከፍተኛ ጉጉት ላይ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ብለዋልየድምፅ ሰጪዎች ምዝገባ በጥሩ ሁኔታ ሲካሄድ መቆየቱን የተናገሩት አቶ ጫጮ የከተማዋ ህዝብና የፀጥታ ሀይሉ ያደረጉት ትብብር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበረው ብለዋልህዝበ ውሳኔው እስኪጠናቀቅም ይህ በጎ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋልየአለታ ወንዶ ከተማ ከንቲባ ተወካይ አቶ ፍሬው አለሙ እንደተናገሩት የድምፅ ሰጪዎች ምዝገባ ሂደት ያለችግር ሲከናወን ስምንተኛ ቀኑን መያዙንና በህዝበ ውሳኔው ድምፅ ለመስጠት 21 ሺህ 676 ሰዎች ይመዘገባሉ ተብሎ ታቅዶ እስከአሁን 22 ሺህ 92 ሰዎች መመዝገባቸውን ገልፀዋልበከተማዋ በ18 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ፍሬው በመጀመሪያው ቀን ከመራጮቹ ከ50 በመቶ በላይ መመዝገባቸውንና በአሁኑ ወቅት አብዛኛዎቹ መራጮች ካርድ ወስደው የድምፅ መስጫውን ቀን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋልበተለያዩ ምክንያቶች ከከተማዋ ራቅ ብለው የሄዱ ነዋሪዎች መጥተው ካርድ እየወሰዱ  መሆናቸውንም አክለዋልየኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ እንደተናገሩት እስካሁን ከሁለት ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምፅ ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን ቁጥሩ እስከሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሊደርስ ይችላል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች በመጀመሪያዎቹ ቀናት የመራጮቹ ቁጥር ከተጠበቀው በላይ በመሆኑና ካርድ በፍጥነት ባለመድረሱ እጥረት አጋጥሞ የነበረ ቢሆንም በአካባቢው ከሚገኙ ማስተባበሪያ ጣቢያዎች በአፋጣኝ እንዲቀርብ ተደርጎ ችግሩ መቀረፉን ተናግረዋል እንዷማካሪዋ ማብራሪያ በአሁኑ ወቅት የድምፅ መስጫ ኮሮጆዎች ወደየምርጫ ጣቢያ ዎች እየተጓጓዙ መሆኑንም አስረድተዋልአዲስ ዘመን ህዳር 52012መላኩ አሮሴ
https://www.press.et/Ama/?p=22555
370
28,656
ሪፖርት | ቡናማዎቹ ሆሳዕና ላይ የግብ ናዳ አዘነቡ
ስፖርት
January 4, 2020
Unknown
በ6ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ የጨዋታ ቀን አዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና ሀዲያ ሆሳእናን 50 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃውን በእጅጉ ከፍ አድርጓልኢትዮጵያ ቡናዎች ድሬዳዋ ላይ አቻ ከተለያየው ቡድናቸው ላይ ሁለት ቅያሬዎችን ሲያደርጉ በዚህም ግብጠባቂው በረከት አማረ እንዲሁም የመስመር ተከላካዩ ሀይሌ ገተንሳይን ወደ መጀመሪያ ተሰላፊነት በማስገባት ጀምረዋል በአንፃሩ ሀዲያ ሆሳእናዎች ደግሞ በሜዳቸው ከባህርዳር ከተማ አቻ ከተለያየው ቡድን ውስጥ ተከላካዩቹን ትእግስቱ አበራና ሱራፌል ዳንኤልን እንዲሁም አማካዩ አብዱልሰመድ አሊን ዳግም ወደ መጀመሪያ ተመራጭነት በማካተት ለጨዋታው ቀርበዋልአማኑኤል ዮሀንስ ባደረጋት ሙከራ የጀመረው ጨዋታው የመጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃዎች ኢትዮጵያ ቡና ከወትሮው በተለየ በቀደመውን ጨዋታዎች ያሳዩት የነበረውን የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ለማሳየት የተቸገሩበት ብሎም በቅብብሎች ወቅት በርከት ያሉ ስህተቶችን ሲሰሩ የታየበት ነበር ነገርግን በዚህ ሂደት ሀዲያዎች የሚያገኟቸውን ኳሶች በመጠቀም በኩል ሰፊ ክፍተቶች ነበሩባቸው በጥቅሉ ኢትዮጵያ ቡናዎች ደካማ በነበሩበት የመጀመሪያ አጋማሽ ሀዲያዎች በተለይ ሳይጠበቁ በሚያደርጓቸው አስደንጋጭ ሙከራዎች ጨዋታውን ሳቢነት አላብሰውታልበሂደት ቀስ በቀስ ወደ ቡና የግብ ክልል መድረስ የጀመሩት ሀዲያዎች በ17ኛው ደቂቃ ሄኖክ አርፌጮ ከግራ መስመር ያሻማውን ኳስ በበረከት አማረ የጊዜ አጠባበቅ ስህተት የተገኘውን ኳስ አዩብ በቀታ ተቀልብሶ የሞከራትና የግቡ አግዳሚ የመለሰበት ኳስ አስቆጭ አጋጣሚ ነበር ጫናቸውን አጠናክረው የቀጠሉት ሀዲያዎች በ28ኛውና 29ኛው ደቂቄ አፈወርቅ ሀይሉ አክታትሎ በግንባር በመግጨት እንዲሁም አክርሮ በመምታት ያደረጋቸው ሙከራዎችን በበረከት አማረ ሊያድን ችሏልእስከ 30ኛው ደቂቃ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ማድረግ ያልቻሉት ቡናዎች በ30ኛው ደቂቃ ከመስመር የተሻማን ኳስ ገጭቶ ለማውጣት ግቡን ለቆ የወጣው አቤር ኦቮኖን ክፍተት ተመልክቶ አማኑኤል ዮሀንስ የተመለሰውን ኳስ ከግብጠባቂውና ተከላካዮች አናት በላይ በመምታት ቡድኑን መሪ ያደረገች ማራኪ ግብ ማስቆጠር ችሏልከግቧ መቆጠር ሰከንዶች ልዩነት አቡበከር ናስር በአስደናቂ ፍጥነት የሆሳእና ተከላካዮችን አታሎ የቡድኑን መሪነት ከፍ ያደረገች ግብ ማስቆጠር ችሏልየመጀመሪያ አጋማሽ መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ ሆሳእናዎች በሄኖክ አርፊጮ አማካኝነት ከማእዘን ያሻገሩት ኳስ ተጨራርፎ ሲመለስ ያገኘው ቢስማርክ አፒያ ወደ ግብ የላከው ኳስ ለጥቂት የግቡን አግዳሚ ለትሞበት ሊወጣ ችሏልበሁለተኛው አጋማሽ ጅማሮ በሶስት የመሀል ተከላካዮች ጨዋታውን ጀምረው የነበሩት ሆሳእናዎች አንድ የመሀል ተከላካይ በመቀነስ የመስመር ተጫዋቹ መስቀሉ ለቴቦን በማስገባት ወደ ጨዋታው መመለስን የተለመ ቅያሬ በማድረግ ነበር የጀመሩት ነገርግን በሁለተኛው አጋማሽ ኢትዮጵያ ቡናዎች ፍፁም ተሻሽለው ነበር የቀረቡት በኳስ ቅብብሎች በፍጥነት ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በተደጋጋሚ ለመድረስ ያልተቸገሩት ቡናማዎቹ የሀዲያን የግብ ክልል እየተፈራረቁ ሲያስጨንቁ ውለዋልበ53ኛው ደቂቃ ከተከላካይ ጀርባ የተጣለለትን ኳስ ተጠቅሞ እንዳለ ደባልቄ የሞከረውን አቤር ኦቮኖ ሲያድንበት በደቂቃዎች ልዩነት እንዲሁ አቤል ከበደ ከእንዳለ ከበደ የተቀበለውን ያለቀለት ኳስ በድጋሚ አቢር ሊያድንበት ችሏል በሁለተኛው አጋማሽ ሆሳእናዎች በ57ኛው ደቂቃ መስቀሉ ሌቴቦ ከረጅም ርቀት የሞከረውና በረከት አማረ በአስደናቂ ሁኔታ ካዳነበት ኳስ ውጭ ወደ ግብ ለመድረስ ተቸግረው ተስተውሏልእንደመጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ ኢትዮጵያ ቡናዎች በ62ኛና 64ኛ ደቂቃ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ግቦች ልዩነታቸውን ማስፋት ችለዋል በቅድሚያ በ62ኛው ደቂቃ ፍቅረየሱስ ተብርሀን ላይ ሱራፌል ዳንኤል በሰራው ጥፋት የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት አቡበከር ናስር ሲያስቆጥር በ64ኛው ደግሞ አቤል ከበደ በግሩም አጨራረስ በማስቆጠር ልዩነቱን አራት ማድረስ ችሏልከሁለቱ ተከታታይ ግቦች መቆጠር በኋላ ኢትዮጵያ ቡና ጫናቸውን አጠናክረው ቢቀጥሉም በ3 አጋጣሚዎች ከሆሳእናው ግብጠባቂ ጋር 1ለ1 ተገናኝተው እንዲሁም በርከት ባሉ አጋጣሚዎች ግብ መሆን የሚችሉ አጋጣሚዎችን አግኝተው በሚያስቆጭ ሁኔታ መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል በመጨረሻም በጭማሪው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው ሀብታሙ ታደሰ በጥሩ የማጥቃች ሽግግር የመጣውን ኳስ አስራት ቱንጆ ከግራ የሳጥን ጠርዝ አመቻችቶለት ማስቆጠር ችሏልኢትዮጵያ ቡና በሁለተኛው አጋማሽ ከነበራቸው የበላይነት አንፃር የተገኙት አጋጣሚዎች ተቆጥረው ቢሆን ለሆሳእናዎች ቀኑ ከዚህ በላይ አስከፊ በሆነ ነበርጨዋታው 5ለ0 መጠናቀቁን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በሁለት ተከታታይ የሜዳ ላይ ጨዋታዎቹ 9 ግቦችን በማስቆጠር የደጋፊዎቹ የግብ ጥማት በማራስ ሲቀጥል ደረጃውንም ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል በአንፃሩ ሆሳእናዎች እስካሁን በሊጉ ማሸነፍ አልቻሉም በሊጉ ግርጌ ላይም በሁለት ነጥቦች ለመቀም ተገዷልየጨዋታውን ጎሎች በዩቲዩብ ቻነላችን ይመልከቱ
https://soccerethiopia.net/football/53779
519
32,523
​ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ | መሪዎቹ ቡድኖች ነጥብ ጥለዋል
ስፖርት
January 29, 2018
Unknown
የከፍተኛ ሊጉ 11ኛ ሳምንት የምድብ ለ ጨዋታዎች እሁድ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ሲካሄዱ በሰንጠረዡ አናት የሚገኙ ክለቦች ነጥብ ጥለዋል ናሽናል ሴሜንት 11 ዲላ ከተማበዳንኤል መስፍን1000 ላይ በተካሄደውና የምድብ ለ መሪ ዲላ ከተማን ናሽናል ሴሜንት ያገናኘው ጨዋታ ጠንካራ እንቅስቃሴ ተደርጎበታል ለጎል የቀረበ ሙከራ በማድረግ ዲላዎች ቀዳሚ ሲሆኑ ሙና በቀለ ከቀኝ መስመር ሰብሮ በመግባት አክሮ የመታው ኳስ ግብ ጠባቂው ያዳነበት አጋጣሚ መልካም አጋጣሚ ነበር ጨዋታው በጥሩ ፉክክር እየቀጠለ ባለበት ወቅት በሁለቱም ቡድኖች መካከል በተፈጠረ ግጭት ጨዋታው ለተወሰነ ደቂቃ ሲቋረጥ ጨዋታውን የመራችው ኢዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ወንደሰን ቃይሌን ከዲላ መሀሙድ መሀመድን ከናሽናል ሴሜንት በቀይ ካርድ ከሜዳ አስወግዳቸዋለች ጨዋታው ቀጥሎ ምንም ጎል ሳይቆጠርበትም ወደ መልበሻ ክፍል ለእረፍት አምርተዋል እልህ የተቀላቀለበት ጠንካራ ፉክክር በሁለተኛው አጋማሽ ቀጥሎ 61ኛው ደቂቃ ላይ ኤሊያስ እንድርያስ በጥሩ ሁኔታ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ተቀይሮ የገባው ማስረሻ ደረጄ ወደ ጎልነት ቀይሮ ዲላ ከተማዎችን መምራት አስችሎ የነበረ ቢሆንም በ71ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው መሀመድ አብዱላሂ በግንባሩ ገጭቶ ያስቆጠራት ጎል ናሽናልን ወደ አቻነት አሸጋግሮታልበቀሪው ደቂቃ እጅግ አስገራሚ ፉክክር እንድናይ አስችሎናል በተለይ ናሽናል ሴሚንቶች ተመልካቹን ቁጭ ብድግ የሚያደርግ የጎል ሙከራዎች ቢያደርጉም በዲላዎች ግብ ጠባቂ ተካልኝ ሀይሌ ጥረት ከሽፈው ጨዋታው 11 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋልጅማ አባ ቡና 11 መቂ ከተማበቴዎድሮስ ታደሰበጅማ ስቴድየም በተደረገው ጨዋታ ባለሜዳዎቹ የጎል ሙከራ ማድረግ የጀመሩት ገና በመጀመሪያው ደቂቃ ሲሆን በተለይ ኳስን ተቆጣረው በመጫወት የተቃራኒ ተከላካዮችን በመረበሽ ተደጋጋሚ ኢላማቸውን ያልጠበቁ የጎል ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል በመቂ ከተማ በኩል መከላከልን መሰረት ባደረገ የመልሶ ማጥቃት ስኬታማ ያልነበረ ሲሆን በመጀመርያው አጋማሽ የተከላካይ ክፍሉ ጫና በዝቶበት ታይቷልበ9ኛው ደቂቃ በድሉ መርድ ያሻማውን ቅጣት ምት አብዱረዛቅ ናስር በግንባሩ በመግጨት ባለሜዳዎቹን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል ከጎሉ መቆጠር በሀላ በ26ኛው ደቂቃ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል የገቡት አባቡናዎች አብዱረዛቅ ናስር ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ያመከነው እና በ 34ኛው እና 42ኛው ደቂቃዎች ቴዎድሮስ ታደሰ በብዙ ንክኪ የተገኙትን አጋሚዎች አመጠቀሙ በሚያስቆጩ አጋጣሚዎች ነበሩከእረፍት መልስ ባልተለመደ መልኩ ሁለቱም ቡድኖች ተቀዛቅዘው የታዩ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ ከተገኙት አጋሚዎች መካከል በ75ኛው ደቂቃ ብዟየሁ እንደሻው በመቂ ከተማ ግብ ጠባቂ ስህተት የተገኘውን ክፍት ጎል መጠቀም አለመቻሉ የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበርበ80ኛው ደቂቃ የአባቡናው ግብ ጠባቂ ስህተትን በመጠቀም ድንቁ በዳኔ አስቆጥሮ በጨዋታው እምብዛም ወደ ጅማ አባ ቡና የግብ ክልል ሲደርሱ ያልታዩት መቂ ከተማዎችን አቻ አድርጓል መቂዎች ግብ ካስቆጠሩ በሀላ የአባቡና ደጋፊዎች በክለቡ አመራሮች ላይ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን ተቃውሞው ተባብሶ በሜዳ ተገኝተው የነበሩ የክለቡ አመራሮች ላይ ቁሳቁስ በመወርወር ሜዳውን ለቀው ወጥተዋል ጨዋታው ከተጠናቀቀ በሀላም የክለቡን ተጫዋቾች ከሜዳ አናስወጣም በማለታቸው በእለቱ የነበሩ የፀጥታ ሀይሎች ታጅበው ከሜዳ ሊወጡ ችለዋል ይህ በተደጋጋሚ የሚፈጠሩት ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆኑ ድርጊቶች የክለቡ አመራሮች ቆም ብለው ሊያስቡበት እንደሚገባ ለማሳሰብ እንወዳለንድሬዳዋ ፖሊስ 11 ሻሸመኔ ከተማበዳንኤል መስፍን0800 ላይ የተጀመረው ጨዋታ የመጀመርያ አጋማሽ ማራኪ እንቅሰስቃሴ የተመለከትንበት ሲሆን በአሰልጣኝ ያሬድ አበጀ የሚመሩት ሻሸመኔ ከተማዎች በኳስ ቁጥጥሩም ሆነ በፍጥነት ወደ ጎል በመድረስ በሚደረግ ሽግግር የተሻሉ ቢሆንም ጎል በማስቆጠር ቀዳሚ የነበሩት ባለሜዳዎቹ ፖሊሶች ነበሩ በ22ኛው ደቂቃ ዘርአይ ገሶላሴ ባለሜዳዎቹን ቀዳሚ አድርጓልሻሸመኔዎች ጎሉ ከተስተናገደባቸው በኋላም በነበራቸው የመጫወት ፍላጎት እና ጥሩ እንቅስቃሴ ተጠቅመው በ37ኛው ደቂቃ ላይ ከሳጥን ውጭ ይድነቃቸው ብርሀኑ በግሩም ሁኔታ ባስቆጠራት ጎል አቻ መሆን ችለዋል በ44ኛው ደቂቃ ላይ እራሱ ይድነቃቸው ብርሀኑ ነፃ የማግባት አጋጣሚን ከቡድን አጋሮቹ ጋር አብሮ ተጫውቶ ጎል ሊሆን የሚችለውን ኳስ በግሉ ለመጠቀም በማሰብ ያመከናት ኳስ ሻሸመኔዎችን ቀዳሚ ማድረግ የምትችል መልካም አጋጣሚ ነበርከእረፍት መልስ ሻሸመኔዎች የአቻ ውጤቱን ለመጠበቅ በሚመስል መልኩ ወደፊት አጥቅቶ ከመጫወት ይልቅ ማፈግፈጋቸው ለድሬዳዋ ፖሊሶች የማጥቃት እድል ቢሰጣቸውም የአማካይ ክፍሉ ደካማ መሆኑ ለአጥቂዎች በተገቢው መልኩ የጎል እድል ሳይፈጠርላቸው ቀርቷል በመስመር አጥቂዎቻቸው የሚፈጥሩት የማጥቃት እንቅስቃሴ ከአንድ የጎል የማግባት እድል ከመፍጠር የዘለለ ጉዞ አልነበረውም 81ኛው ደቂቃ ላይ እዩኤል ተስፋዬ ከመስመር የተሻገረለትን በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት የወጣው ኳስ የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር ሻሸመኔዎች በመልሶ ማጥቃት አልፎ አልፎ ወደ ድሬዷ ፖሊስ የግብ ክልል ቢደርሱም ይህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ የተሳካ የጎል ሙከራ ማድረግ ሳይችሉ ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል ጨዋታውም በስፍራው የተገኘው የድሬዳዋ ስፖርት አፍቃሪን ያዝናና ነበርሌሎች መርሀ ግብሮችበአምሀ ተስፋዬወደ ቤንጅ ማጂ ያመራው ደቡብ ፖሊስ የ10 ሽንፈት አስተናግዶ ከመሪው ዲላ ጋር የነበረውን የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል በ17ኛው ደቂቃ ላይ የተገኘውን ቅጣት ምት መሰለ ወልደሰማያት ወደ ግብነት ለውጦ ቤንችማጂ ቡናን ድል አስጨብጧልካፋ ቡና ነገሌ ከተማን አስተናግዶ ወደ 30 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ካለፈው ሳምንት ሽንፈቱ አገግሟል ኦኔ ኦጅሎ ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር ትእዛዙ ወንድሙ ቀሪዋን ጎል አስቆጥሯልወደ ወራቤ ያመራው ሀምበሪቾ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው ስልጤ ወራቤን 10 አሸንፏል ከእረፍት መልስ በ65ኛው ደቂቃ ላይ የስልጤ ወራቤ ተጨዋች በፈጠረው ስህተት በራሱ ላይ ባስቆጠረው ግብ ነው ሀምበሪቾ 3 ነጥብ መሰብሰብ የቻለው ከጨዋታው በሀላ የእለቱ 2ኛ ዳኛ በነበሩት ፌደራል ዳኛ ቢቄላ ሁንዴሳ ላይ ጉዳት ደርሶ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መሄዳቸው ሶከር ኢትዮጵያ ከስፍራው ያገኘችው መረጃ ያመለክታልሀላባ ላይ ሊደረግ የነበረው የሀላበ ከተማ እና ቡታጅራ ከተማ ጨዋታ በሀላባ ሴራ በአል ምክንያት ወደ ማክሰኞ ሲሸጋገር በወልቂጤ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳእና መካከል ሊደረግ የነበረው ጨዋታ በፀጥታ ችግር ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግሯል
https://soccerethiopia.net/football/33525
720
51,175
የሲቪል ማህበራት ተቋማት በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚኖረው ምርጫ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቁ
ፖለቲካ
September 4, 2019
Unknown
የሲቪል ማህበራት ተቋማት በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚኖረው ምርጫ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቁየኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ የፀደቀውን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ውይይት እየተደረገ ሲሆን በዚሁ መድረክ የሲቪል ማህበራት ተቋማቱ በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚኖረው ምርጫ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠይቋልየኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች መድረክ ዋና ዳይሬክተር ወሮ ብሌን አስራት ቦርዱ ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት በአገሪቱ በተካሄዱት ምርጫዎች የሲቪል ማህህበራት ተቋማት ሚና አናሳ እንደነበር አስታውሰዋልባለፉት አመታት የሲቪል ማህበራት በአገሪቱ በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የሚጠበቅባቸውን እንዳይወጡ በማህበራቱ ላይ የነበሩት አሳራሪ አሰራሮች የማህበራቱን እንቅስቃሴ ውስን እንዲሆን አድርጎት ቆይቷል ብለዋልየሲቪል ማህበራቱ በቀጣይ በሚኖረው አገራዊ ምርጫ ህብረተሰቡን በምርጫ ስነ ምግባርና ደንቦች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖረው የተለያዩ ስልጠናዎች በመስጠት መስራት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋልየሲቪል ማህበራቱ በቀጣዩ ምርጫ ሂደትም ገለልተኛ ታዛቢዎችን በማሰማራት በሂደቱም ከምርጫ በኋላም በሚኖረው የምርጫው ተአማኒነት ሚናቸውን እንዲወጡ ዋና ዳይሬክተሯ ጠይቀዋልየኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አባል ወይዘሪት ብዙወርቅ ከተተ በበኩላቸው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ ምንም እንኳ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀ ቢሆንም መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በቦርዱ ለሚወጡ መመሪያዎች ግብአት የሚገኝበት ይሆናል ብለዋል
https://waltainfo.com/am/31329/
155
32,467
ሪፖርት | መከላከያ እና ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል
ስፖርት
February 4, 2018
Unknown
የአዲስ አበባ ስታድየም ባስተናገደው የእለቱ የ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ መከላከያ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደ ሲሆን በውጤቱም 00 ተለያይተዋልከአስራአምስት ቀናት በፊት ከጅማ አባ ጅፋር ጋር 11 ከተለያየው ስብስባቸው የአምስት ተጨዋቾች ለውጥ ያደረጉት መከላከያዎች ቴውድሮስ በቀለን አማኑኤል ተሾመን ቴውድሮስ ታፈሰን አቤል ከበደን እና ማራኪ ወርቁን በሙሉቀን ደሳለኝ ሳሙኤል ታዬ መስፍን ኪዳኔ ሳሙኤል ሳሊሶ እና አቅሌሲያስ ግርማ ተክተዋል በሲዳማ ቡና በኩል ደግሞ ከመቐለው ሽንፈት በተደረገው ብቸኛ ቅያሪ ወንድሜነህ አይናለም ወደ ተጠባቂነት ወርዶ በምትኩ አምሀ በለጠ የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ገብቷልበመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ተመጣጣኝ ፉፉክር በተመለከትንበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ መከላከያዎች ወደ ግብ በመድረስ የተሻሉ ሆነው ታይተዋል ጨዋታው አስረኛው ደቂቃ ላይ እስኪደርስም ምንይሉ ወንድሙ ከቅጣት ምት እንዲሁም የመስመር ተከላካዮቹ ሽመልስ ተገኝ እና ታፈሰ ሰረካ ከሳጥን ውጪ የሞከሯቸው ኳሶች ተጠቃሽ ነበሩ 10ኛው ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ሳሊሶ ከመስፍን ኪዳኔ በተሰነጠቀለት ኳስ ከ አበበ ጋር እየታገለ መሳይ አያኖ ጋር ደርሶ የሳተው ኳስ ግን ከሁሉም በላይ ቡድኑ ለጎል የቀረበበት ነበር ይህ የመከላከያዎች ተደጋጋሚ ጥቃት ግን በቀሪዎቹ የመጀመሪያ አጋማሽ ደቂቃዎች ሊታይ አልቻለም ቡድኑ ቀጣዩን ሙከራ እንኳን ያደረገው 41ኛው ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ሳሊሶ ከረዥም ርቀት ወደጎል በላከው እና በግቡ ቋሚ በተመለሰው የቅጣት ምት ኳስ ነበር ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው መግባት የቻሉት ሲዳማዎች መሀል ሜዳ ላይ ተጋጣሚያቸው ሊቀባበል የሚሞክረውን ኳስ ጫና ፈጥሮ በመንጠቁ በኩል የተዋጣላቸው ሆነዋል በዚህ አኳሀን ከሚያገኟቸው ኳሶች ወደ ግብ ለመድረስም አልተቸገሩም በተለይ ተጋጣሚያቸው መሀል ሜዳውን ካለፈ በሀላ የሚነጠቁትን ኳሶች በአግባቡ በማሰራጨቱ በኩል የዮሴፍ ዮሀንስ ሚና በግልፅ ተደጋግሞ ታይቷል ተጨዋቹ በመከላከያዎች የመስመር እና የመሀል ተከላካዮች መሀል መሬት ለመሬት ይልካቸው ከነበሩ ኳሶች መነሻነትም ሲዳማዎች በክፍሉ ኬአ ሀብታሙ ገዛሀን እና ትርታዬ ደመቀ አማካይነት አደጋ ያላቸውን ኳሶች ወደ ውስጥ መጣል ችለው ነበር ከዚህ ውጪ ቡድኑ 15ኛው ደቂቃ ላይ በሀብታሙ ገዛሀኝ ከርቀት እንዲሁም በ30ኛው ደቂቃ ላይ በአዲስ ግደይ ቅጣት ምት ጥሩ ሙከራዎችን ቢያደርግም በእጅጉ ለጎል የቀተበበት አጋጣሚ የተፈጠረው ግን በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ነበር በዚህም ከግራ መስመር የተጣለውን ኳስ አቤል ማሞ ማራቅ ሳይችል ቀርቶ አዲስ ግደይ ከግቡ አፋፍ ላይ ግልፅ የማግባት እድል ቢያገኝም ሙከራው ለማመን በሚከብድ መልኩ ኢላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷልከእረፍት መልስ በነበሩት የመጀመሪያ ደቂቃዎችም የሲዳማ ቡናዎች የሙከራ የበላይነት ቀጥሎ ታይቷል 48ኛው ደቂቃ ላይ ትርታዬ ደመቀ ከቀኝ መስመር ከላከው ኳስ አዲስ ግደይ እና ባዬ ገዛሀኝ ግልፅ የማግባት አጋጣሚ ቢያገኙም በአቤል ማሞ ጥረት ግብ ሳያስቆጥሩ ቀርተዋል አቤል የ55ኛው ደቂቃ የባዬ ገዛሀኝን ድንቅ ቅጣት ምትም ማዳን ችሏል ከሁለት ደቂቃዎች በሀላ ደግሞ ከአዲስ ግደይ እና አምሀ በለጠ ጥምረት የተገኘውን ኳስ ሀብታሙ ገዛሀኝ ወደ ግብነት መቀየር ሳይችል ቀርቷል ሲዳማዎች በሚያጠቁበት ወቅት የቀኝ መስመር አጥቂነቱን ቦታ ለትርታዬ በመተው ሶስቱን አጥቂዎቻቸውን አዲስ ባዬ እና ሀብታሙን በሳጥን ውስጥ እንዲጠብቁ የሚያደርጉበት ሁኔታ ተደጋግሞ ይታይ ነበር ይህ እቅድ መሀል ሜዳ ላይ አምሀ በለጠን እና ዮሴፍ ዮሀንስን የሚያጋልጥ የነበረ እና ለመከላከያዎች የኳስ ፍሰት የተመቸ ቢሆንም የጦሩ የአማካይ ክፍል ከበሀይሉ ግርማ ፊት በነበረው የሳሙኤል ሳሊሶ ሳሙኤል ታዬ እና መስፍን ኪዳኔ ሶስት የመስመር አማካዮች ጥምረት ተመሳሳይ የአጨዋወት ባህሪ ምክንያት የተጋጣሚያቸውን ደካማ ጎን መጠቀም አልቻሉም ሆኖም 57ኛው ደቂቃ ላይ ቴዎድሮስ ታፈሰ ተቀይሮ ወደ ሜዳ ከገባ በሀላ ከበሀይሉ ጎን በመሆን የተሻለ ጥቃትን የማስጀመር ሀላፊነትን ለመወጣት ሞክሯል ከቅያሪው በሀላ የሲዳማዎች ሙከራ ጋብ ያለ ሲሆን እንግዶቹ በቀሪዎቹ ደቂቃዎች በአዲስ እና ሀብታሙ አማካይነት ሁለት ተጨማሪ ሙከራዎችን ብቻ ነበር ያደረጉት በአንፃሩ እየተሻሻሉ የመጡት መከላከያዎች ደግሞ ጨዋታውን ጨርሰው መውጣት የሚችሉባቸውን አጋጣሚዎች መፍጠር ችለዋል በተለይ 74ኛው ደቂቃ ላይ ከበሀይሉ እና መስፍን ኪዳኔ ቅንጅት ሳጥን ውስጥ ሳሙኤል ሳሊሶ ያገኘው እድል ወደ ግብ ሙከራነት ሳይቀየር መቅረቱ ለቡድኑ በጣሙን የሚያስቆጭ ነበር ከዚህ ውጪ 80ኛው ደቂቃ ላይ ምንይሉ ወንድሙ ከግብ ጠባቂ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ያመከነው እንዲሁም ተቀይሮ የገባው የተሻ ግዛው በጭማሪ ደቂቃዎች ሁለት ጊዜ የሞከራቸው ኳሶች ለጦሩ የመጨረሻ ደቂቃ የበላይነት ማሳያ ነበሩ ሆኖም ጥሩ ፉክክር የተደረገበት ጨዋታው ያለግብ ከመጠናቀቅ አልዳነም ውጤቱን ተከትሎም መከላከያ ወደ 12ኛ ደረጃ ከፍ ሲል ሲዳማ ቡና በነበረበት የ8ኛ ደረጃ ላይ ረግቷልየአሰልጣኞች አስተያየትአሰልጣኝ ምንያምር ፀጋዬ መከላከያከነበረብን እንቅስቃሴ አንፃር አንድ ነጥብ ያንሳል አሸንፈን መውጣት ነበረብን ከእረፍት በፊት እና በሀላ ያገኘናቸው አራት እና አምስት የሚሆኑ አጋጣሚዎች ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ነበሩ ኳስ የሚጫወት ቡድን ነው ሳጥን ውስጥ እንገባለን ግን የመጨረስ ችግር አለብን ሰው ላይ የሚሰራ ነገር በአንዴ የሚሰራ አይደለም ጊዜ ይፈልጋል ድግግሞሽንም ይጠይቃል እንደየአቀባበሉ ማለት ነው ዋናው ነገር ግን ጎል ላይ ከደረስን በሀላ እርጋታ የሚያስፈልገን መሆኑ ነው ጊዜ ቢፈጅም ይህን ችግራችንን እናሻሽላለንአሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህ ሲዳማ ቡናበመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ጥንቃቄ ላይ ያመዘነ ጨዋታ ነበር ብዙም ውበት አልነበረውም እኛም ተጋጣሚ ሲጫወት ብዙ የማየት እድል ስላልነበረን ጥንቃቄን መርጠን አጨዋወቱን ለማየት በማሰብ በመልሶ ማጥቃት ተጫውተናል  በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመሪያ 25 ደቂቃዎች ጥሩ ተንቀሳቅሰናል ወደ መጨረሻው ላይ ጫና ፈጥረውብን ነበር በዛም ሰአት ተጠንቅቀን ተጫውተናል ከዛ ውጪ የመስመር ዳኛው ከጨዋታ ውጪ የነበሩ ኳሶችን በመፍቀድ ጫና አሳድሮብን ነበር
https://soccerethiopia.net/football/33769
703
5,058
በአቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ጉዳይ ላይ የ14 ቀን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ
ሀገር አቀፍ ዜና
February 25, 2019
26
ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎች በማረሚያ ቤት ስልክና ኮምፒዩተር ይሟላልን አቤቱታም ውድቅ አድርጓልየባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ጉዳይ ላይ የ14 ቀን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ አቃቤ ህግ ከዚህ በፊት በተሰጡት የጊዜ ቀጠሮዎች ምርመራውን ማጠናቀቅ አለመቻሉንና የአቃቤ ህግ ምስክሮች በውጭ ሀገር ለህክምና እንደሄዱ አለመመለሳቸው ገልፆ ነበር በተጨማሪ የኦዲት ስራዎች አለመጠናቀቃቸው እና የባለሙያ ክትትል የሚያስፈልጋቸው መሆኑን በመጠቆም የ14 ቀን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ነበርአቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ በበኩላቸው የምርመራ ሂደቱ በይፋ እንደተጠናቀቀ መገለፁን የማረፊያ ቤት ቆይታቸውም እየተራዘመ መሆኑን እና ሌሎች ምክንያቶችን በመዘርዘር የክርክር ሂደቱ እንዲጀመር እና ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁ አላስፈላጊ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አቅርበው ነበርበማረሚያ ቤት ቆይታቸው ጉዳያቸውን ለመከታተል እና መረጃ ለመሰብሰብ የግል የስልክ ኮምፒውተር እና ኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሟላላቸውም ጠይቀው ነበርፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ያቀረባቸውን የምርመራ አለመጠናቀቅ እና የምስክሮች አለመሟላት ከግምት ውስጥ በማስገባት የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል በዚህ መሰረት መጋቢት 2 ቀን 2011 አም ምርመራ ተጠናቅቆ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ቀን ተቆርጧልአብመድ እንደዘገበው ፍርድ ቤቱ የአቶ በረከት ስምኦንና የአቶ ታደሰ ካሳን በማረሚያ ቤት ስልክና ኮምፒዩተር ይሟላልን አቤቱታም ውድቅ አድርጓልእንደማንኛውም በህግ ጥላ ስር ያለ ሰው በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ያሉ ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች እና መደበኛ ስልኮችን እንዲጠቀሙ አዝዟል ማረሚያ ቤቱ ከከተማ የወጣ በመሆኑ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደሌለው የማረሚያ ቤት ተጠሪው ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡትን ሪፖርት ችሎቱ ለአቤቱታ አቅራቢዎች ገልጿልአቶ በረከት እና አቶ ታደሰ የመገናኛ ብዙሀን በፍረድ ቤት ጉዳያቸው ላይ ቁንፅል መረጃ እየለቀቁ መሆኑንም ለችሎቱ በአቤቱታ መልኩ አቅርበዋል ሙሉ መረጃዎችን ብዙሀን መገናኛዎች ለህዝቡ እንዲያደርሱም ጠይቀዋል ለአብነትም የአማራ ብዙሀን መገናኛ ደርጅት አንዱ መሆኑን አቶ ታደሰ በግልፅ ጠቅሰዋልፍርድ ቤቱ በተጠቀሰው መገናኛ ብዙሀን የተነሱ ጉዳዮች በችሎቱ የተነሱ መሆናቸውን አስታውሶ የተዛባ መረጃ የሚያደርሱ የመገናኛ ብዙሀን ካሉም ድርጊቱ ህገወጥ መሆኑን አስታውቋል ለህዝቡ ቁንፅል ያልሆነና ያልተዛባ መረጃ እንዲያደርሱም አሳስቧል
https://www.press.et/Ama/?p=5620
267
45,718
3ኛው የምግብናመጠጥ አውደ ርዕይ በትናንትናው ዕለት ተከፈተ
ቢዝነስ
April 22, 2017
Unknown
ለአምስት ቀናት የሚቆየው 3ኛው የምግብናመጠጥ አውደ ርእይ በትናንትናው እለት ተከፈተየምግብና የመጠጥ ፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከኤስ ፒ ጀነራል ቢዝነስ ጋር በመሆን ነው 3ኛው የምግብና መጠጥ አውደ ርእይ ተዘጋጅቶ በትናንትናው እለት የተከፈተው አውደ ርእዩ ጥራት  ለአለም አቀፍ ተወዳዳሪነት   በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን የአገር ውስጥ  የምግብና የመጠጥ ምርቶች ላይ የተሰማሩ አካላትን በመደገፍ አገሪቱ የምታወጣውን  የውጭ ምንዛሪን ለማስቀረት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል የአገር ውስጥ አምራቾች ሆነው ከውጭ አገር የሚገቡ የምግብና መጠጥ ምርቶችን ለመተካት  የሚሰሩ  ድርጅቶችን  በዋነኝነት በአውደ ርእዩ እንዲሳተፉ በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ እገዛ እንደሚኖረው ታምኖበታል  በተጨማሪም አውደ ርእዩ የሀገር ውስጥ አምራች ተቋማት ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበትና እርስ በራሳቸዉ ግንኙነት የጋራ ህብረት የሚፈጥሩበትም ይሆናል ተብሏልበ3ኛው የምግብና መጠጥ አውደ ርእይ ከ70 በላይ የሚሆኑ አምራች  ድርጅቶች  እየተሳተፉ ይገኛል      
https://waltainfo.com/am/23097/
115
51,317
ጳጉሜ ‘ጳጉሜን በመደመር’ በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይታሰባል
ፖለቲካ
August 21, 2019
Unknown
ጳጉሜን በመደመር በሚል መሪ ሀሳብ ሀገራዊ የመርሀ ግብር ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል የመደመር ስድስት ምሰሶዎችን ባማከለ መልኩ  ጳጉሜን በመደመር ሀገር አቀፍ መርሀ ግብር መዘጋጀቱን ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው የተለያዩ የመንግስት አካላት የየእለት እንቅስቃሴዎቹን ለማቀድ ለመምራት ለማስተባበርና ለማስፈፀም ሀላፊነት ወስደው እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል እየፈፀሙ በዚህም መሰረት  የጳጉሜን ስድስቱ ቀናት ስያሜ እና አስተባባሪዎች ይፋ የሆኑ ሲሆን ጳጉሜን 1 ብልፅግናን የወከለ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስተባባሪነት ጳጉሜን 2 ደግሞ የሰላም ቀን ሲሰኝ በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፊሪያት ካሚል እንደሚመራ ነው የተገለፀው ጳጉሜን 3 ሀገራዊ ኩራት የሚል ስያሜን ሲሰጠው በማስተባበር በኩል የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ሀላፊነቱን ወስዷል ጳጉሜን 4 ዲሞክራሲ የሚል ስያሜን በትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተሰጠ ሲሆን እለቱን በአስተባባሪነት የሚመሩት ይሆናል ጳጉሜን 5 የፍትህ ቀን ሆኖ እንዲታሰብና  የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሀኑ ፀጋዬ እንደሚያስተባብሩት ተመልክቷል የመጨረሻው እና የአዲስ አመት ዋዜማው ጳጉሜን 6 ደግሞ የሀገራዊ አንድነት ቀን ሆኖ ታስቦ እንዲውል ውሳኔ ተላልፏል ህብረተሰቡም በእነዚህ ቀናት ሰፊ ተሳትፎ በማድረግ ወደ መጪው አዲስ አመት ተስፋን ሰንቆ ለመሻገር እንዲሰናዳ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል  
https://waltainfo.com/am/31302/
171
12,101
ኢትዮጵያ፡ የ2013 የትምህርት ዘመንን ለማስጀመር ምን እየተሰራ ነው?
ሀገር አቀፍ ዜና
26 ነሐሴ 2020
Unknown
በ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮቪድ19 እንዳይጋለጡ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀየትምህርት ሚኒስቴር ኮሙኑኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሀረግ ማሞ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ትምህርት ከመጀመሩ በፊት እንዴት ይጀመር ተብሎ ሲታሰብ ከግምት ውስጥ ከገቡ ጉዳዩች አንዱ ለተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማቅረብ የክፍል ውስጥ ጥግግትን ለማስቀረት ትምህርት በፈረቃ ይሁን አይሁን የሚሉት ናቸውየሚኒስቴሩ የኮሙኑኬሽን ዳይሬክተር ለቢቢሲ እንደገለፁት አንድ ትምህርት ቤት የኮሮናቫይረስን ከመከላከል አንፃር ምን ማድረግ አለበት የሚለውን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ሲያስብ የተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ያላቸው ቁጥር አንዱ ነው ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በፈረቃ ይሁን አይሁን ተማሪዎችን እንዴት አድርገን አራርቀን እናስቀምጥ የሚሉና የተማሪዎች ጤንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችን በተመለከተ ምን መደረግ እንዳለባቸው የት መቀመጥ እንዳለባቸውና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋልትምህርት ሚኒስቴር መጪው አመት የትምህርት ዘመን ሲጀምር ምን መደረግ አለበት የሚለውን ከጤና ሚኒስቴርና ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመሆን እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋልከኮሮናቫይረስ መከላከያ መንገዶች አንዱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ በመሆኑ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን ትምህርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ሀላፊዋ ገልፀዋልትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለትምህርት ማህበረሰቡ አጠቃላይ መረጃ እንደሚሰጥ የገለፁት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሯ ይህንን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ እንደሚያሳውቁ ገልፀዋልየትምህርት ሚኒስቴሩ በትናንትናው እለት ከአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ጋር በነበራቸው ቆይታ ወደ መማር ማስተማር ተግባር በሚገባበት ወቅት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልፀው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የእጅ ማፅጃ እና መሰል አቅርቦቶችን ከባላድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረው ነበርየሚኒስቴሩ ኮሙኑኬሽን ዳይሬክተር በበኩላቸው ለቢቢሲ እንደገለፁት ይህንን ታሳቢ በማድረግ ውይይት እና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋልሀላፊዋ ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ድረስ የ2013 የትምህርት ዘመን መቼ እንደሚጀመር አለመወሰኑን በመግለፅ ትምህርት የሚጀመርበትን ወቅት ለማሳወቅ የስርጭቱ መጠንና የመንግስት ውሳኔ ይወስነዋል ሲሉ ገልፀዋልትምህርት ቤቶች ምዝገባ በሚያካሄዱበት ወቅት የኮሮናቫይረስ ስርጭት እንዳይከሰት ተማሪዎች መምህራንና ወላጆች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እና እጅን በመታጠብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ወሮ ሀረግ ማሞ ጨምረው ገልፀዋል የተማሪዎች ምዝገባው እስከ መቼ ድረስ ይካሄዳል ለሚለው የቢቢሲ ጥያቄ ሀላፊዋ ሲመልሱ እንደ ትምህርት ቤቶቹ ተጨባጭ ሁናቴ የሚወሰን መሆኑን ገልፀዋልበትምህርት ቤቶች ውስጥ ከምዝገባ ጀምሮ የኮቪድ19 በመከላከል ረገድ ሀላፊነቱ የሁሉም ነው ያሉት ወሮ ሀረግ ተማሪዎች ወላጆች የትምህርት ማህበረሰቡ ሀላፊነት አለበት በማለት በተለይ ደግሞ በትልቁ መምህራን ሀላፊነት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋልእንዲሁም መምህራንን ተማሪዎች እንደ ወላጅ ስለሚመለከቷቸው መምህራን ተማሪዎቻቸውን ከኮሮና ራቸውን እንዲከላከሉ በማድረግ ረገድ እጥፍ ድርብ ሀላፊነት አለባቸው ብለዋልበተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ በለይቶ ማቆያነት ያገለገሉ እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ በተከሰቱ አለመረጋጋቶች የተለያዩ አገልግሎት የሰጡ ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ከመጀመራቸው በፊት በሚገባ መፅዳት እንዳለባቸውና ትምህርት ቤቶችም ይህንን ማረጋገጥ እንዳለባቸው በመግለፅ የምዝገባ ጊዜው ሰፋ የተደረገው ይህንን ታሳቢ በማድረግ መሆንም ለቢቢሲ ጨምረው አስረድተዋል ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች በ2012 የትምህርት ዘመን በ2ኛ ሴሚስተር ያለፋቸውን ትምህርቶች ማካካሻ ለመስጠት መታሰቡንም ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትናንት ከአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት መግለፃቸው ይታወሳል በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱ ከታወቀ ወዲህ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚል ከመጋቢት ሰባት 2012 አም ጀምሮ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ይታወሳል ትምህርት ሚኒስቴር ከስምንተኛ ክፍል እና የ12 ክፈል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ወሳጆች ውጪ ቀሪዎቹ ተማሪዎች በግማሽ አመት ውጤታቸው ወደ ቀጣዩ ክፍል እንዲዛወሩ መወሰኑ ይታወቃልእስካሁን ድረስ የስምንተኛም ሆነ የ12 ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና መቼ እንደሚካሄድ አልታወቀም
https://www.bbc.com/amharic/53917951
460
32,805
​ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና መከላከያ በአቻ ውጤት አመቱን ጀምረዋል
ስፖርት
November 7, 2017
Unknown
የሊጉን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና መከላከያ ጥሩ ፉክክር ባሳዩበት ምሽት በተቆጠሩ ሁለት ማራኪ  ጎሎች 11 ተለያይተዋል የመሀል ሜዳ ላይ ፉክክር በርክቶበት የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የመጀመሪያ ሙከራ ለማስተናገድ ዘጠኝ ደቂቃዎችን ጠብቋል የኤሌክትሪኩ የፊት አጥቂ ዲዲዬ ለብሪ በመከላከያ የግብ ክልል ውስጥ ከሞከረው እና ይድነቃቸው ካዳነበት ከዚህ አጋጣሚ በሀላ ግን ጨዋታው በሙከራዎች የታጀበ ሆኖ ቀጥሏል የቡድኑ ጠንካራ ጎን ሆኖ ይታይ የነበረው የመስመር ተከላካዮች እና አማካዮች እንቅስቃሴ እንደወትሮው ሆኖ ያልታየበት መከላከያ በመጀመሪያው አጋማሽ የፈጠራቸው የግብ እድሎች በሙሉ ከሳጥኑ ውጪ የተገኙ ነበሩ  ሳሙኤል ታዬ 17ኛው ደቂቃ ላይ እንዲሁም ምንይሉ ወንድሙ በ26ኛው ደቂቃ ላይ ከረጅም ርቀት ኢላማቸውን የጠበቁ ሁለት ሙከራዎች ሲያደርጉ ምንይሉ 28ኛው ደቂቃ ላይ የሞከራት ሌላ ኳስ ደግሞ ወደላይ ተነስታ ወጥታለች የተሻለ የመሀል ሜዳ ብልጫ የነበራቸው ኤሌክትሪኮች በበኩላቸው ወደቀኝ ባደላ የማጥቃት እንቅስቃሴ በሁለቱ አዲስ ፈራሚዎቻቸው ዲዲዬ ለብሪ እና ካሉሺያ አልሀሰን ጥምረት በመጠቀም የጦሩን የተከላካይ ክፍል ፈትነዋል33ኛው ደቂቃ ላይ ኤሌክትሪክ መሪ ሲሆን ካሉሺያ በድንቅ አጨራረስ ላስቆጠረው ጎል ኳሷን አመቻችቶ ያቀበለው ዲዲዮ ለብሪ ነበር በጨዋታው ጥሩ የተንቀሳቀሰው ግብ አስቆጣሪው ካሉሺያ በ14ኛው ደቂቃ ከሳጥን ውጪ ላይ ካደረገው ሙከራ በሀላ 19ኛው ደቂቃ ላይም የመታው ድንቅ ቅጣት ምት ይድነቃቸው ካዳነው በሀላ መስመር ማለፍ አለማለፉ አጨቃጫቂ ሆኖ የተመልካቹን ቀልብ የሳበ ነበር ሁለተኛው አጋማሽ ጅማሮ ላይ መከላከያዎች በግምት 25 ሜትር ርቀት ላይ ያገኙትን  ቅጣት ምት ቴዎድሮስ ታፈሰ በአስደናቂ ሁኔታ በሱሊማን አቡ መረብ ላይ በማሳረፍ ቡድኑን አቻ አድርጓል ከዚህ በሀላም የመከላከያዎች ጫና ከመጀመሪያው አጋማሽ በተለየ ጨምሮ ታይቷል በዚህም መሰረት 55ኛው ደቂቃ ላይ በግራ መስመር ሽመልስ ተገኝ የሻማው እና ሳሙኤል ታዬ ወደግብ ለመምታት አስቦ የጨረፈውን ኳስ ምንይሉ አግኝቶ ሲሞክር የግቡ አግዳሚ መልሶበታል ከሶስት ደቂቃዎች በሀላም ሽመልስ በግንባሩ ሞክሮት ወደውጪ የወጣበት ኳስም ተጠቃሽ ነበር ቀስ በቀስ የጨዋታ የበላይነቱ ወደ ቀያዮቹ አድልቶም ኤሌክትሪኮች በተደጋጋሚ በግራ መስመር እየሰበሩ በመግባት ሙከራዎችን ሲያደርጉ ተስተውሏል በተለይም 67ኛው ደቂቃ ላይ ዲዲዬ ከጎሉ አፋፍ ላይ ያመከነው ኳሱ ቡድኑ ሶስት ነጥብ ለማግኘት እጅግ የቀረበበት አጋጣሚ ሲሆን  በሀይሉ ተሻገር እና አዲስ ነጋሽ ከሳጥን ውጪ የሞከሯቸው ኳሶችም ተጠቃሽ ነበሩ88ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው ምንያህል ይመር እና ጥላሁን ወልዴ ከይድነቃቸው ፊት የያገኙት ሌላውእድል እንዲሁ በሚያስቆጭ መልኩ ተስቷል በሱሊማን አቡ ጉዳት ምክንያት ሰባት ደቂቃዎች የተጨመሩበት የእለቱ ብቸኛ ጨዋታ በዚህ መልኩ  እስከ መጨረሻው ብርቱ ፉክክር ታይቶበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል በሁለተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ቅዳሜ 11 30 ላይ መከላከያ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ወላይታ ድቻን ሲያስተናግድ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ሊያደርግ የነበረው ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ተራዝሟልየአሰልጣኞች አስተያየትአሰልጣኝ ብርሀኑ ባዩ ሁለተችንም አሸንፈን ለመውጣት ነው የገባነው የጎል እድሎችም በሁለተችንም በኩል ተፈጥረዋል በሁለተኛው አጋማሽ የአጥቂ አማካይ ቀይረን በማስገባት ተጫውተናል ኳሱን ብዙ አልሰጠናቸውም ስለዚህ ጥሩ ተንቀሳቅሰናል አሰልጣኝ ምንያምር ፀጋዬ የአመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ እንደመሆኑ ሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ ነበር የተጫወቱት እኛም ያገኘናቸውን እድሎች አልተጠቀምንም እነሱም እንደዛው ከዚህ አንፃር አቻው ፍትሀዊ ይመስላል
https://soccerethiopia.net/football/31164
421
15,663
የደቡብ ክልል የገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን ለመደገፍ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
Aug 25, 2020
421
አዲስ አበባ ነሀሴ 19 2012 ኤፍቢሲ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን በገንዘብም ሆነ በመንፈስ ለመደገፍ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ገለፁጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሰሞኑን የኮይሻ የጎርጎራና የወንጪ ሀይቅ አካባቢን በህብረተሰብ ተሳትፎ በማልማት አካባቢዎቹን ተመራጭ የቱሪስት መድረሻ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል ይህንን ተከትሎም በየደረጃው ያሉ የደቡብ ክልል ማእከል አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን መለገሳቸው ተጠቁሟልየደቡብ ክልል ማእከል አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክት ዙሪያ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ አቶ እርስቱ ይርዳ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን በገንዘብም ሆነ በመንፈስ ለመደገፍ የክልሉ ህዝብና መንግስት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል በገበታ ለሸገር የታየው አዲስ አስተሳሰብና እይታ ድንቅ ውጤት ወደ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፕሮጀክት ገበታ ለሀገር መሸጋገሩ ሁሉንም የሚያስደስት ነው ሲሉም አክለዋልየኮይሻ ፕሮጀክት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሁሉንም የክልሉ ህዝብ በሁለንተናዊ መልኩ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ያሉት አቶ ርስቱ ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊመሰገኑ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል የኮይሻ ፕሮጀክት የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክንየግቤ 3 እና ኮይሻ ግድቦችና የአካባቢው ተፈጥሯዊ መስህቦችን የሚያስተሳስር በመሆኑ ፋይዳው ከፍተኛ እንደሆነ ተነግሯልበዚህም ፕሮጀክቱ የሀገር ገቢን ከማሳደግ ባለፈ ለአካባቢው ህዝብ በተለየ ሁኔታ ደግሞ የቱሪዝም ፍሰትን በመጨመርና ትርጉም ያለው የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል ህዝቡም የበኩሉን አሻራ እንዲያሳርፍም ጥሪ አቅርበዋል የደቡብ ክልል ባህልቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል የኮይሻ ፕሮጀክትን ስኬታማ ለማድረግ ህዝቡን በማስተባበር 1 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ እቅድ መያዙን ተናግረዋልለዚህም በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር የሚመራ አብይ ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራዎችን የሚያስተባብር ይሆናል ነው የተባለውየሚዋቀሩት ኮሚቴዎችም ህዝብ የራሱን ድርሻ እንዲያበረክት የማድረግ የአካባቢውን የቱሪዝም እምቅ የማስተዋወቅና በአካባቢው አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ የማስፈን ግቦችን ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ አቶ ስንታየሁ መናገራቸውን ከደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል የዜና ሰአት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልእክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%8b%b0%e1%89%a1%e1%89%a5-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%8c%88%e1%89%a0%e1%89%b3-%e1%88%88%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%8d%95%e1%88%ae%e1%8c%80%e1%8a%ad%e1%89%b5%e1%8a%95/
275
39,396
ኢትዮጵያ ሳተላይት በቅርቡ ሳታመጥቅ አትቀርም
ዓለም አቀፍ ዜና
September 02, 2015
Unknown
ኢትዮጵያ በመጭዎቹ ከሶስት እስከ አምስት አመታት ጠፈር ላይ የራሷ ሳተላይቶች ሊኖሯት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የሀዋ ሳይንስ ማሀበር የበላይ ጠባቂ አቶ ተፈራ ዋልዋ አስታውቀዋልየማሀበሩ መስራች ሊቀመንበር የነበሩትና አሁን የበላይ ጠባቂው እንዲሁም የእንጦጦ የሀዋ ምርምርና ልዩ ማሰልጠኛ ማእከል የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ተፈራ ዋልዋ ሰሞኑን ለቪኦኤ በተለይ በሰጡት ቃለምልልስ ኢትዮጵያ በአንዳንድ መስኮች በጠፈር ላይ አገልግሎት እራሷን እንድትችል የሚያርግ የራሷ የሰው ሀይልና ተቋም ሊኖራት ይገባል ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋልበድሀነት ውስጥ ያለችና የበዙ ችግሮች ያሉባት ኢትዮጵያ ስለጠፈር ማሰቧን በጥርጣሬና በቅሬታ የሚያዩ ወገኖች መኖቸውን አስመልክቶ የተጠየቁት አቶ ተፈራ የሀዋ ልማት ከድሀነት መውጫ የምጣኔ ሀብት ዘርፍ እንጂ በድሀነት ምክንያት ወደኋላ የሚቀርበት ባለመሆኑ የአስተሳሰብ ድሀነትን አስወግዶ ከተሰራ የታሰበውን ወደ ተግባር መተርጎምና የመስኩ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል ብለዋልበሀዋ ልማት ኢትዮጵያ አሁን ለተለያዩ አገልግሎቶች የምታወጣውን የኪራይ ክፍያ ለማስቀረትና እንዲያውም አገልግሎቱን ወደመሸጥ ልትገባ እንደምትችልም ሀሳቡ ወደ ተጨባጭ ዝርዝር እቅድ መቀየር እንደሚቀረው የጠቆሙት አቶ ተፈራ ጠቁመዋልየኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ማኀበር በ1996 አም በ47 ሰዎች የተቋቋመ የበጎ ፍቃደኞች ማሀበር መሆኑንና አሁን ከእንጦጦ የሀዋ ምርምር ማእከል ጋር በመሆን ከበርካታ የሀገር ውስጥና የውጭም ምሁራን ጋር እየሰራ ያለ መሆኑን ገልፀዋልየኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የገነባውን የእንጦጦውን ማእከል ለሀገሪቱ የመንግስትና የግሉ ዩኒቨርሲቲዎች ባለቤትነት ማስረከቡንና ማሀበሩ በቦርድ አባልነት እንደሚሳተፍ የጠቆሙት አቶ ተፈራ በማእከሉ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ 18 የፒኤችዲ አጥኝዎች እንደሚገኙ አመልክተዋልሰሞኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ማሀበር የወቅቱ ሊቀመንበር ከሆኑት ከዶር ከላሊ አድሀና ጋር ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የስራ ጉዞ ላይ የሰነበቱት አቶ ተፈራ ዋልዋ ከአሜሪካው የኤሮኖቲክስና የጠፈር አስተዳደር ናሳ ባለልስጣናትና ከዋና ዳይሬክተሩ ከቻርለስ ቦልደን ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋልውይይቶቻቸው ስላተኮሩባቸው ሶስት ዋና ዋና ነጥቦች አቶ ተፈራ ሲያስረዱ የመስኩን ተማሪዎችና ሰልጣኞች ኢትዮጵያ ሄደው የሚያስተምሩ ሳይንቲስቶች እና የሳተላይት ግንባታን ጨምሮ ስራውን እየሰሩ የሚያሰለጥኑ መሀንዲሶች ከአሜሪካ የሚገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት አንዱ መሆኑን ገልፀዋልበተጨማሪም የጋራ ምርምር ለማከናወን የአሜሪካዊያኑን በህዋም ያሉ ያሰቧሰቧቸውንም መረጃዎች ኢትዮጵያዊያኑ ሊያገኟቸው የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች መፍጠር እንዲሁም በመካከለኛና በረዥም ጊዜ በትብብር መስራት የሚቻልባቸው አካባቢዎች ካሉ ስምምነት ላይ መድረስ ይቻል እንደሆነ መነጋገር ከውይይቶቸው መካከል እንደሚገኙ ተናግረዋልከናሳ በኩል ያገኘው አዎንታዊ ምላሽ ጠንካራና ከጠበቅነው በላይ ነው ሊደግፉን ከልባቸው ጥረት እንደሚያደርጉ ብለዋል አቶ ተፈራበእንጦጦ የሀዋ ምርምር ማእከል እነርሱ በምስራቅ አፍሪካ መስራት ያልቻሉትን ኢትዮጵያ ልትሰራ እንደምትችልና የጋራ ምርምር ማድረግ እንደሚገባ መንገድ ሲያሳዩን ነበር ብለዋል አቶ ተፈራ አክለውየእርሳቸው ቡድን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመጣው የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን የኬንያና የኢትዮጵያን ጉብኝት ተከትሎ በመሆኑ ምናልባት ተልእኳቸው ከሰፈሩ የፀጥታ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ አንዳንድ ጭምጭምታዎችን አስመልክቶ ኢትዮጵያና አሜሪካ ከሚተባበሩባቸው ሰፊ መስኮች መካከል አንዱ ፀረሽብር እንቅስቃሴ መሆኑ ግልፅ መሆኑን ከመጥቀስ በስተቀር የእርሳቸው ጉዞ ከእንዲህ አይነቱ ትብብር ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው አላብራሩም ስለዚህ ጉዳይ የሚመለከተውን ቢሮ መጠየቅ የሚሻል ይመስለኛል በሚል አልፈውታል ኢትዮጵያ በመስኩ ከዩናይትድ ስቴትስ ሌላም ከሩሲያ ከደቡብ ኮሪያ ከአውሮፓ ሀብረት ከጃፓን ከቻይና ከህንድና ከደቡብ አፍሪካ ጋርም እየሰራች መሆኗን የገለፁት አቶ ተፈራ በእንጦጦው የሀዋ ምርምር ማእከል ውስጥ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ከሚያሰለጥኑት መካከል የሩሲያ ፕሮፌሰሮች እንደሚገኙ የደቡብ ኮሪያ የጠፈር ልማት ጀማሪ የነበሩ ሳይንቲስትና መሀንዲስ ኢትዮጵያ ሄደው መስራታቸውን የአውሮፓ ሀብረት የሀዋ ኤጀንሲ ሰዎች አንዳንዴ ብቅ እያሉ እንደሚያግዟቸው አስረድተዋልኢትዮጵያ አጠቃላይ ዋጋቸው በዛሬ ምንዛሪ ከስድስት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ከፍተኛ አቅም ያላቸውን ሁለት ቴሌስኮፖች እንጦጦ የጠፈር ቅኝት ጣቢያ ላይ ተክላለችየኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ማሀበርና የእንጦጦው የሀዋ ምርምርና ልዩ ስልጠና ማእከል የተቋቋሙትና የሚንቀሳቀሱት ከሀገር ውስጥ በሚገኙ ድጋፎች መሆኑን አቶ ተፈራ ጠቁመው የግል ባንኮች የመንግስት የልማት ድርጅቶች የማሀበሩ አባል የሆኑና ያልሆኑም ግለሰቦች በሚሰጧቸው ልገሳዎች መሆኑን ገልፀዋልበተለይ ከማሀበሩ ምስረታ አንስቶ ለአስር አመታት የቦርድ አባል ሆነው የቆዩት ሼኽ መሀመድ አል አሙዲ ግዙፍ ድጋፍ ማድረጋቸውን አቶ ተፈራ ተናግረዋልማሀበሩ ከእንግዲህ በልመና መቀጠል አይኖርበትም እንደሀገርና እንደመንግስት መታሰብ አለበት ያሉት አቶ ተፈራ በሁለተኛው የሀገሪቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ተገቢውን ቦታ ሊያገኝ እንደሚገባ ያመለክታል ብለዋልአቶ ተፈራ ዋልዋ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
https://amharic.voanews.com//a/ethiopia-may-soon-launch-a-satellite-to-space-09-01-15/2941846.html
544
10,449
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከኔዘርላንድስ የውጭ ንግድ እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
April 30, 2020
45
ባህር ዳር ሚያዝያ 222012 አም አብመድ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ከኔዘርላንድስ የውጭ ንግድ እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ሲግሪድ አግነስ ማርያ ካግ ጋር በስልክ ተወያይተዋል
https://www.amharaweb.com/%e1%8a%a0%e1%89%b6-%e1%8c%88%e1%8b%b1-%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8b%b3%e1%88%ad%e1%8c%8b%e1%89%b8%e1%8b%8d-%e1%8a%a8%e1%8a%94%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%88%8b%e1%8a%95%e1%8b%b5%e1%88%b5-%e1%8b%a8%e1%8b%8d/
26
34,661
ደደቢት ከሱር ኮንስትራክሽን የአውቶብስ ስጦታ ተበረከተለት
ስፖርት
April 2, 2016
Unknown
የደደቢት እግርኳስ ክለብ ዛሬ በጦር ሀይሎች መኮንኖች ክበብ ከሱር ኮንስትራክሽን የተበረከተለትን የተጫዋቾች ማጓጓዣ አውቶብስ አስተዋውቋልከሱር ኮንስትራክሽን የተበረከተው አውቶብስ 45 ሰዎችን መያዝ የሚችል ሲሆን 23 ሚልዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል በአውቶብሱ ላይም የሱር ኮንስትራክሽን አርማ በጉልህ ተደርጓልበርክክብ ስነስርአቱ ላይ ሱር ኮንስትራክሽንን በመወከል አቶ ታደሰ የተገኙ ሲሆን ባደረጉት ንግግርም ደደቢት ወደ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ክለብነት ለመሸጋገር የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ይህ የአውቶብስ ስጦታ አንድ አካል መሆኑን ተናግረዋል በቀጣይ አመታትም ከክለቡ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ገልፃዋልበደደቢት በኩል የቴክኒክ ዳይሬክተሩ አቶ ሚካኤል አምደመስቀል ከሱር ኮንስትራክሽን ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ከኩባንያው ጋር ያላቸው ግንኙነት በቀጣይ አመት ወደ አጋርነት እንደሚሸጋገር ገልፀዋል ከሱር ጋር በአሁኑ ሰአት ያላቸው ግንኙነት ከክለቡ ባሻገር ድርጅቱን ተጠቃሚ እንደማያደርግ አምነው ለሱር እንደ ትልቅ ስኬት የሚታየው ማህበራዊ ሀላፊነቱን መወጣቱ እንደሆነ አብራርተዋልበርክክብ ፕሮግራሙ የወንዶቹ ቡድን አምበል ብርሀኑ ቦጋለ እና የሴቶቹ ቡድን አምበል ኤደን ሽፈራው ተጫዋቾችን በመወከል ሱር ኮንስትራክሽንን አመስግነዋልበፕሮግራሙ መጨረሻ የክለቡ እና የሱር ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት የወንድ እና ሴቶች ቡድን አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች በጋራ በመሆን የፎቶ ፕሮግራም አካሂዷል
https://soccerethiopia.net/football/8269
150
13,353
ስሁል ሽረ አጠቃላይ ሆስፒታል መድኃኒቶችንና የሕክምና ቁሶችን ከጤና ሚኒስቴር ተረከበ
ሀገር አቀፍ ዜና
Dec 17, 2020
170
አዲስ አበባ ታህሳስ 8 2013ኤፍ ቢ ሲ ስሁል ሽረ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጤና ሚኒስቴር የተላከለትን የስኳርና ሌሎች ህሙማንን ለማከም የሚያስችሉ መድሀኒቶችንና የህክምና ቁሳቁሶችን ተረከበ
https://www.fanabc.com/%e1%88%b5%e1%88%81%e1%88%8d-%e1%88%bd%e1%88%a8-%e1%8a%a0%e1%8c%a0%e1%89%83%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%88%86%e1%88%b5%e1%8d%92%e1%89%b3%e1%88%8d-%e1%88%98%e1%8b%b5%e1%8a%83%e1%8a%92%e1%89%b6%e1%89%bd/
23
10,836
ሰባተኛው የመላው አማራ ጨዋታዎች በወልድያ ከተማ ተጀምሯል፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
March 4, 2020
106
ሰባተኛው የመላው አማራ ጨዋታዎች በወልድያ ከተማ አስተዳደር ትናንት ተጀምሯል ከ15 ዞኖች እና ሶስት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ3 ሺህ በላይ ስፖርተኞች በ20 የስፖርት አይነቶችም ተሳታፊ ሆነዋልየአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አብዮት መኩሪያው ለአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት ሰባተኛው የመላ አማራ ጨዋታዎች ትናንት በወልዲያ ከተማ ሼህ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም ከሁሉም ዞኖች እና ከሶስቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ3 ሺህ በላይ ስፖርተኞች ተሳታፊ ሆነዋልበሰባተኛው የመላው አማራ ጨዋታዎች ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ውሹ እና ዳርት ለመጀመሪያ ጊዜ ለውድድር ቀርበዋል ውድድር ከሚካሄድባቸው 20 የስፖርት አይነቶች ውስጥ 18ቱ በወልድያ ከተማ ሼህ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን እና በመልካ ቆሌ ሰታዲየሞች ይካሄዳሉ ውሀ ዋና በኮምቦልቻ እና ባድሜንተን በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ይካሄዳሉበየሁለት አመቱ አንድ ጊዜ የሚካሄደው የመላው አማራ ጨዋታዎች ስድስተኛው የመላው አማራ ጨዋታዎች በባህር ዳር ከተማ አስተናጋጅነት መካሄዱ ይታወሳልዘጋቢ ታዘብ አራጋውፎቶ ከአብክመ ስፖርት ኮሚሽን
https://www.amharaweb.com/%e1%88%b0%e1%89%a3%e1%89%b0%e1%8a%9b%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%88%8b%e1%8b%8d-%e1%8a%a0%e1%88%9b%e1%88%ab-%e1%8c%a8%e1%8b%8b%e1%89%b3%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%89%a0%e1%8b%88%e1%88%8d%e1%8b%b5/
127
43,330
በአገሪቷ አንዳንድ ማረሚያ ቤቶች መለቀቅ አለብን በሚል ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ተቀባይነት የለውም- መንግስት
ፖለቲካ
July 26, 2018
Unknown
በአገሪቷ አንዳንድ ማረሚያ ቤቶች መለቀቅ አለብን በሚል ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ታራሚው ህግና ስርአትን አክብሮ መንቀሳቀስ እንዳለበት መንግስት አሳሰበየመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋልአቶ ካሳሁን እንደገለፁት መንግስት በማረሚያ ቤት ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ ለማሻሻል በጥናት የተደገፈ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷልበቅርቡም የይቅርታ አዋጁን መነሻ በማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎች መለቀቃቸውን አስታውሰው የምህረት አዋጁን ስራ ላይ ለማዋልም ከጫፍ ተደርሷል ብለዋልይሁን እንጂ የይቅርታና የምህረት አዋጁን ተከትሎ በአንዳንድ ቦታዎችና ታራሚዎች ዘንድ መለቀቅ አለብን በሚል ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት እየተስተዋሉ መሆኑን ገልፀዋልለአብነትም በቂሊንጦና ቃሊቲ በጩሄት ማረሚያ ቤቱን ማወክ በአርባ ምንጭ ማረሚያ ክሊንክ ላይ ጉዳት ማድረስ በደብረ ማርቆስ ወልድያና ፍኖተሰላምም በተመሳሳይ ህግን ያልተከተሉ ተግባራት ታይተዋል ነው ያሉትመሰል እንቅስቃሴዎች መንግስት በጊዜ የለኝም ቅኝትና ስሜት እየፈፀማቸው ያሉትን የለውጥ ስራዎችን ጭምር ወደ ኋላ የሚጎትቱ ናቸው ያሉት አቶ ካሳሁን ያልተፈቀደ የይቅርታና የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ ለመሆን የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋልበማረሚያ ቤቶች የታራሚዎች አያያዝ ላይ ከዚህ በፊት የነበሩ ክፍተቶች እንዳይደገሙ መንግስት አበክሮ እንደሚሰራ የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው ከማረሚያ ቤት በጉልበትና ህግን በመጣስ ለመውጣት መሞከር ተገቢ እንዳልሆነና በዚህ ድርጊት የሚሳተፉ ታራሚዎች ህጉን ሊያከብሩ ይገባል ሲሉ አሳስበዋልእንደ አቶ ካሳሁን ገለፃ በአንዳንድ ማረሚያ ቤቶች የተስተዋሉ አለመረጋጋቶች በመንግስት እልባት እያገኙ ነው ኢዜአ
https://waltainfo.com/am/30173/
186
48,676
ኢትዮጵያና ግብጽ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሰላማዊ መፍትሄ ማግኘት እንደሚችሉ ተመለከተ
ፖለቲካ
July 5, 2013
Unknown
በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ኢትዮጵያና ግበፅ ሰላማዊ መፍትሄ ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር በኢትዮጵያ ተናገሯምባሳደር ዴቪድ ሺን ከኢራኑ የቴሌቪዠን ጣቢያ ፕሬስ ቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት በአገራቱ መካከል ያለው አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ሊፈታ የሚችል ነውእስከማውቀው ድረስ በውሀ ምክንያት ብቻ የተነሳ ጦርነት የለም በሁለቱ አገራት መካከል ያለው አለመግባባትም የመጀመሪያን ጦርነት ይፈጥራል ብዬ አልገምትም ሲሉ አምባሳደር ሺን አስተያየታቸውን ሰጥተዋልሁለቱ አገራት ልዮነታቸውን በምክክር በውይይትና በግልፅነት ሊፈቱት እንደሚገባ ያስገነዘቡት አምባሳደሩ በዚህ ላይ የአሜሪካ ሚና የማማከር እንጂ አለመግባባቱን የመዳኘት መሆን የለበትም ብለዋል በተለይ በግበፅ በኩል ሰፊ የተሳሳተ ግንዛቤ በመኖሩ ምክንያት በተለይ ባለፈው ወር ስሜታዊነት የተንፀባረቀበት አስተያየቶች መሰማታቸውን ያስታወሱት አምባሳደር ሺን ግድቡ ለሀይል ማመንጫ አስከዋለ ድረስ የውሀው ፍሰት መጠን ሳይቀንስ ከዚህ ቀደም በነበረው መንገድ ለታችኛው ተፋሰስ አገራት እንደሚደርስ መረዳት ይገባል ብለዋልግድቡ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅእኖ ለመመርመር በኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን የተቐቐመው የአለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን ጥናት ውጥት መሰረት ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ የሚያደርሰው ጉልህ ጉዳት የለም
https://waltainfo.com/am/24643/
142
9,895
ተጎጂዎችን ማቋቋምና በወንጀሉ የተሳተፉትን በቁጥጥር ሥር ማዋል የቀጣይ ዐበይት ተግባራት መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
September 19, 2020
91
ሀላፊነታቸውን ያልተወጡና በቸልተኝነት ጥቃቱ እንዲፈፀም ያደረጉ የስራ ሀላፊዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋልባህር ዳር መስከረም 092013አም አብመድ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የኢፌዴሪ መከላከለያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው እና የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ጥቃት የተፈፀመባቸውን ተጎጂዎች አፅናንተዋል ውይይትም አድርገበጥቃቱ ተጎጂ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ከአካባቢው እንዲፈናቀሉ የሚፈልጉ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቤተሰቦቻቸውን አጥተዋል ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል መኖሪያ ቤቶቻቸው ፈርሶባቸዋል ንብረታቸው መዘረፉንና መውደሙንም ለስራ ሀላፊዎቹ ገልፀዋልከህይወት መጥፋት መሰደድ የስነ ልቦና መጎዳት በተጨማሪ ነገን ለመኖር ስጋት ላይ በመሆናቸው መንግስት አስተማማኝ ሰላም እንዲፈጥርላቸው ከመንግስት ለልዩ ልዩ ተግባራት የተበደሩት ብድር አሁን ላይ መመለስ እንደማይችሉና አስቸኳይና ዘላቂ መቋቋሚያ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል ነዋሪዎቹ በህይወት ያሉና በሞት የተለዩ ቤተሰቦቻቸውን ከየተሰወሩበት ለመሰብሰብ የፀጥታ ሀይሉ አብሯቸው እንዲሆንም ጠይቀዋልበቡለን ወረዳ የኤጳር ቀበሌ አስተዳዳሪ ጋዋ መኔ ክፉዎች ከነምግባራቸው ጨለማና ጫካን ነው ማደሪያ የሚያርጉት በዚህ ክፍለ ዘመን ሽፍታ ጥቃት ማድረሱ አሳዛኝ ነው ብለዋል የክልል እና የፌዴራል መንግስታት በቀጣናው ለሚታዩ ተመሳሳይ ድርጊቶች ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጡም ጠይቀዋልየቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጥቃቱ ልብ የሚሰብር መደገም የሌለበት ኢሰብአዊ ክስተት ነው ብለዋል ክልሉ ከጥቃቱ በፊት በደረሰው መረጃ በቡለን ወረዳ ኤጳር ቀበሌ ጥቂት የፖሊስ ሀይሎችን የመደበ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ሲመጡ ሸሽተው መጥፋታቸው እንዳሳዘናቸው እና ሙያዊ መገለጫ አለመሆኑንም አቶ አሻድሊ ተናግረዋል በቀጣይ ህግ በማስከበር ተጎጂዎችን የመካስ እና የማቋቋም ስራ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል
https://www.amharaweb.com/%e1%89%b0%e1%8c%8e%e1%8c%82%e1%8b%8e%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%88%9b%e1%89%8b%e1%89%8b%e1%88%9d%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%8b%88%e1%8a%95%e1%8c%80%e1%88%89-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b3%e1%89%b0%e1%8d%89/
220
27,301
ምዓም አናብስት ወደ ልምምድ ሊመለሱ ነው
ስፖርት
September 28, 2020
Unknown
መቐለ 70 እንደርታዎች ለካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋልበካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ኤንዲሳተፉ ከሰሞኑ የተወሰነላቸው የ2011 የፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮኖቹ መቐለዎች የኮቪድ 19 የመከላከያ ፕሮቶኮልን በተከተለ መንገድ ወደ ልምምድ እንደሚመለሱ ከክለቡ ለማወቅ ተችሏል በመስከረም 23 እና 24 ሙሉ የህክምና ምርመራዎች አድርገው መስከረም 25 ልምምድ የሚጀምሩ ይሆናልመቐለዎች ከዚህ ቀደም ከነበረው የካምፕ ህይወት በተለየ መንገድ ዝግጅታቸው ለመጀመር እንዳቀዱም ለማወቅ ተችሏል በዚህ መሰረትም የወረርሺኙ ስጋትን ለመቀነስ ተጫዋቾችን በሆቴል በማሳረፍ ለቻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታ ዝግጅት የሚጀምሩ ይሆናልበዝውውር መስኮቱ የወሳኝ ተጫዋቾች ውል አድሰው በረከት አማረ ምንተስኖት ከበደ ሰለሞን ሀብቴ ነፃነት ገብረመድሀን እና ምንይሉ ወንድሙን ለማስፈረም የተስማሙት 70 እንደርታዎቹ በቀጣይ ቀናት የአንድ ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል ለማደስ በብርቱ ጥረት ላይ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል
https://soccerethiopia.net/football/60384
108
27,505
ሀዋሳ ከተማ የወሳኙን አጥቂ ውል አራዝሟል
ስፖርት
August 11, 2020
Unknown
ብሩክ በየነ በሀዋሳ ከተማ ውሉን ለማራዘም ከስምምነት ደርሷልከሀዋሳ አመታዊው የቄራ ሻምፒዮና ከተገኘ በሀላ በ2009 በቀጥታ ለወልቂጤ ከተማ ለከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪ በነበረበት ወቅቶ በመፈረም ሁለት ድንቅ የውድድር አመታትን በክለቡ በመጫወት አሳልፏል የአጥቂ ስፍራ እና የመስመር አጥቂው ብሩክ በየነ በ2011 መስከረም ወር ላይ ለሀዋሳ ከተማ ፈርሞ ሁለት ድንቅ አመታትንም በክለቡ ቆይታው ማሳየት ችሏል በተለይ ዘንድሮ በተሰረዘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ዝርዝር ውስጥ ሲፎካካር የነበረ ሲሆን ውሉም መጠናቀቁን ተከትሎ በተለያዩ የፕሪምየር ክለቦች ሲፈለግ ቢሰነብትም በመጨረሻም በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረቱ ሀዋሳ ለሁለት ተጨማሪ ሁለት አመት ለመቆየት ከስምምነት ደርሷልበዝውውር ገበያው ዘግየት ያለው ሀዋሳ ከነማ ከሰሞኑ እንቅስቃሴ እንደሚጀምር የሚጠበቅ ሲሆን እስከ አሁንም ክለቡ ውላቸውን ያራዘመላቸውን ተጫዋቾች ቁጥር ስምንት አድርሷል
https://soccerethiopia.net/football/59285
104
27,071
አዳማ ከተማ ቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በዚህ ሳምንት ይጀምራል
ስፖርት
November 10, 2020
Unknown
አዳማ ከተማዎች 2013 የውድድር አመት ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋልካለፉት አመታት በተለየ መልኩ ከከፍተኛ ሊጉ እንዲሁም ጥቂት ተጫዋቾችን ከፕሪምየር ሊጉ ያስፈረመው አዳማ ከተማ ከፈረሙ ተጫዋቾች ባሻገር አብዛኛዎቹን በሙከራ ከተመለከተ በሀላ የመጨረሻ ፈራሚዎቹን ከሰሞኑ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል በአሰልጣኝ አስቻለው ሀይለሚካኤል እና ረዳቶቹ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች ለ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በዛሬው እለት ለተጫዋቾቹ ጥሪ አቅርቦ ሁሉም ወደ ካምፕ ገብተዋልነገ ረቡእ ለሁሉም አሰልጣኞች ተጫዋቾች እና ለክለቡ አባለት የኮቪድ 19 ምርመራን ካደረጉ በሀላ ውጤቱን መሰረት በማድረግ የፊታችን አርብ ወደ ዝግጅት እንደሚገቡ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል ዝግጅታቸውን በሌላ ከተማ ለማድረግ አቅደው የነበረ ቢሆንም ከወቅታዊ ሁኔታ አኳያ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እየሰሩ ይቀጥላሉ
https://soccerethiopia.net/football/61492
98
17,922
በግዕዝ ቋንቋ ሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
Feb 12, 2020
458
አዲስ አበባ የካቲት 4 2012 ኤፍቢሲ የግእዝ ቋንቋ ትምህርትን ወጥ በሆነ መልኩ መስጠት የሚያስችል የስርአተ ትምህርት ቀረፃ ውይይት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነውውይይቱ የግእዝ ቋንቋን ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያደርጉትን ጥረት ወጥ በሆነ መልኩ ለማስቀጠል ያለመ ነው ተብሏልበሀገር አቀፍ ደረጃ በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ወጥ የሆነ የግእዝ ቋንቋ የትምህርት አሰጣጥ እንዲኖር ለማድረግም በመሰረታዊው የቋንቋው ይዘት ዙሪያ ውይይት እየተደረገበት ይገኛልውይይቱ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከተለያዩ ጥናትና ምርምር ተቋማት የተውጣጡ ምሁራን እየተሳተፉ መሆኑን የአማራ መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ዘገባ ያመላክታልየቋንቋ ትምህርቱ ከዚህ ቀደም በተወሰኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሰጠት ቢጀምርም ተቋማቱ የራሳቸውን መለስተኛ ጥናት ብቻ መሰረት አድርገው መስራታቸው ክፍተት መፍጠሩ በውይይቱ ወቅት ተገልጿልትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ httpstmefanatelevision
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%8c%8d%e1%8b%95%e1%8b%9d-%e1%89%8b%e1%8a%95%e1%89%8b-%e1%88%a5%e1%88%ad%e1%8b%93%e1%89%b0-%e1%89%b5%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%89%80%e1%88%a8%e1%8d%83-%e1%88%8b%e1%8b%ad/
115
47,138
በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች አይ ኤስ አሸባሪውን ድርጊት በሰላማዊ ሰልፍ አወገዙ
ፖለቲካ
April 25, 2015
Unknown
አይ ኤስ የተባለው የሽብር ቡድን ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመው አስቃቂ የግድያ ወንጀል እንደሚያወግዙ  የመቐለ የባህርዳርና የጎንደር ከተሞች ነዋሪዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ገለፁበክልሎቹ ዛሬ በተካሄዱ ሰለማዊ ሰልፎች የከተማ ነዋሪዎችየመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትየሀይማኖት መሪዎችና ወጣቶ ተሳታፊ ሆነዋል የከተሞቹ ነዋሪዎቹ ህገወጥ ስደት ይወቁምበየትኛውም አለም ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች በአስቸካይ ይቁሙ የውጭና የውስጥ ፀረ ሰላም ሀይሎች በዜጎቻችን ጉዳት የፖለቲካ ትርፍ አያገኙም አክራሪነትየከሰረ ፖለቲከኞች ሽንፈት ነው  በሚሉና በሌሎችም መፈክሮች ታጅበው ተቋወሞአቸውን ገልፀዋል አሸባሪነትን ጥቃት ከመከላከል ጎን መንግስት ከህዝብ ጋር በመሆን ህገ ወጥ ደላሎችን ወደ ህግ እንዲቀርቡና የፀረ ሽብር ህጉ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ በሰላማዊ ሰልፉ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ከዚህ በፊት መንግስት አሸባሪነትን  እየታገለ እንደመጣና ኢትዮጵያ አሸባሪነትን በመቆጣጠር ረገድ ለአለም አርአያ እንደሆነች አስገንዝበዋልይሁንና  አሁን በሊብያ ራሱን አይ ኤስ ብሎ የሚጠራው ፅንፈኛ አሸባሪ የፈፀመው ግፍ በመኮነን መንግስት ከህዝብ ጋር በመሆን የሚያደርገው ትግል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ሀብረተሰቡም ህገወጥ ደላሎች ወጣቶችን እያማለሉ ለሞት እየዳረጓቸው በመሆናቸው ህብረተሰቡ በሀገራቸው ሰርተው የተሻለ ኑሮ መኖር እንደሚችሉ ሊመክሯቸው ይገባል ብለዋል የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ላቀ አያሌው በበኩላቸው በሚሊንየም ስታድዮም ተገኝተው ባሰተላለፉት መልእክት  በተፈፀመው ሰይጣናዊ ድርጊትም የተሰማቸው  መራርና ጥልቅ  ሀዘን ገልፀው አሸባሪዎቸ በኢትዮጵያወያን የፈፀሙት ግፍ ኮንነዋል የሽብር ቡድኑ የእስልምና ሀይማኖትን የማይወክል ይልቁንም የእስልምና ሀይማኖትን በማርከስ በመላው አለም በሀይማኖቶች መካከል ግጭትና ጦርነት በማፋፋም የሰውን ዘር ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ገልፀዋል ጎንደር ከተማ ከተንቲባ አቶ ጌትነት አማረ የአሸባሪዎች ድርጊት ልማታችን ፈፅሞ ወደ ኋላ አይመልሰውም ካሉ በኋላ በውጭ የሚገኙ ስደተኞችም ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በማልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አሳስበዋል  ሽብርተኝነት ዘር ቀለም ሀይማኖትና ዜግነት የማይለይና በተለይም በወጣቱ ላይ ያነጣጠረ እኩይ ተግባር በመሆኑ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ከመንግስት ጎን እንደሚሰለፉ አሳስበዋል በተመሳሳይም  በሀዋሳ በሰመራ ና በሌሎችም በርካታ ከተሞች የአየ ኤስ አይ ኤስ ደርጊት በማውገዝ የሀይኖታቸው ዋስትና ህገ መንግስታችን ነው የአንድነትና የመከባበር እና የሰላም እሴቶቻችንን በአክራሪዎችና ፀረ ሰላም ሀይሎች አይደናቀፍም የሚሉ መልልእከቶችን አስተላልፈዋል ማለታቸውን ዋልታ ዘግቧል
https://waltainfo.com/am/25384/
278
806
የሊጉ የዋንጫ ትንቅንቅ ምዕራፍ ተገልጧል
ስፖርት
May 14, 2019
49
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2011 አም ዋንጫ መቋጫውን ሊያገኝ በጣት የሚቆጠሩ ጨዋታዎች ቀርተዋል ይሁንና እንደወትሮው ሻምፒዮን የሚሆነው ክለብ ከወዲሁ ለመጠቆም አልተቻለውም ተፋላሚ ክለቦችም የሊጉ ሻምፒየን ለመሆን ብርቱ ትንቅንቅ እያደረጉ ይገኛሉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት መርሀ ግብርም ካሳለፈነው አርብ ጀምሮ በሳምንቱ የእረፍት ቀናት በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ተካሂዷል በዚህም ከአንድ እስከ ሶስት የተቀመጡት ክለቦች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2011 አም የሊግ ዋንጫ ዋነኛ ተፋላሚ ስለመሆናቸው አስመስክረዋል የዚህ ሳምንት መርሀግብር ባሳልፈነው አርብ ሲጀመርም ወደ ትግራይ በማቅናት ስሁል ሽረን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና ያልተጠበቀ ሽንፈት ገጥሞታል ቡናዎች ባለፉት አምስት ጨዋታዎች በወላይታ ድቻ በአዳማ ከተማና በስሁል ሽሬ ሲሸነፉ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነጥብ ተጋርተው አዲስ አበባ ላይ ባህር ዳር ከተማን አስተናግደው አምስት ግቦችን በማስቆጠር ማሸነፋቸው ይታወሳል ሊጉ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ያልሆነለት የ2003ቱ የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ቡና ምንም እንኳን በሁለተኛው ዙር አሰልጣኝ በመቀየር ለሊጉ ሻምፒዮንነት ብርቱ ትንቅንቅን ቢያደርግም ባለፉት አምስት ጨዋታዎች የጣላቸው ነጥቦች የዋንጫ ጉዞውን አጨናግፍውበታል አሁን ላይ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ33 ነጥብ ስምንተኛ ላይ የተቀመጠው ኢትዮጰያ ቡና ከመሪው መቀሌ ያለው የነጥብ ልዩነት 15 መሆኑም የሻምፒዮንነት ጉዞው የተጨናገፈ ሰለመሆኑ ምስክርን ሰጥቷል በሊጉ ሁለተኛ ምእራፍ ተሽለው የታዩትና በተለይ በ20ኛው ሳምንት አዳማ ከተማ 2ለ1 እንዲሁም በ22ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ሀዋሳ ከተማን ሳይጠበቅ አራት ለዜሮ ያሸነፉት ስሁል ሽሮች በዚህ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡናን አንድ ለዜሮ ማሸነፋቸውን ተከትሎ በተለይ በሊጉ ሰንጠረዥ ከግርጌ ለመውጣት በሚያደርጉት ትንቅንቅ ከፍተኛ መነቃቃትን አግኝተዋል ደረጃቸውን በማሻሻል በሊጉ ለመቆየት አንድ እርምጃን የሚያራምዳቸው ሆኗል መርሀ ግብሩ ባሳለፈነው ቅዳሜ ሲቀጥል ወላይታ ዲቻን ከደደቢት ለማገናኛት ቀጠሮ ቢይዝም በእንግዳው አለመገኘት ጨዋታው ሳይካሄድ ቀርቷል በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ የሚገኘው ደደቢት ከፋይናንስ ችግር ጋር በተገናኘ ከ24ኛ ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር አንስቶ በሊጉ እንደማይቀጥል ለኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤን ማስግባቱን ተከትሎ ወላይታ ዲቻዎች ጨዋታውን አሸንፈው ከሶስት ነጥብ ተቀዳጅተዋል ከዚህ ባሻገር ከጨዋታው ውጤት 3 ንፁህ ጎል ማግኘታቸው ያልታሰበ ሲሳይ ሆኖላቸዋል ነጥባቸውን 27 ከፍ በማድረግ በደረጃ ሰንጠረዡ 12 ላይ ተቀምጠዋል የ24ኛው ሳምንት መርሀ ግብር ተጠባቂ ፍልሚያ አዋሳ ላይ የሲዳማ ቡና ከመቀሌ 70 እንደርታ አፋልሟል ሁለቱ ክለቦች እርስ በእርስ ከመገናኘታቸው ቀድሞ በሀያኛው ሳምንት ከጣና ሞገዶቹ ሽንፈት በኋላ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 በመርታት ወደ አሸናፊነት የተመለሱት መቀሌዎች በ22ኛ ሳምንት በፈረሰኞቹ የአንድ ለዜሮ ሽንፈት ሲያስትናግዱ ባሳልፈነው ሳምንት መርሀ ግብርደግሞ በትግራይ ደርቢ ስሁልን በመፋለም የጨዋታው አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል ሲዳማዎች በአንፃሩ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር አስደናቂ ብቃትና ውጤት በማስመዝገብ የሊጉ መሪ እስከመሆን በቅተው የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች ምንም እንኳን በሁለተኛ ዙር ላይ መዳከም ቢያሳዩም አሁን ላይ ይህን ድክመታቸውን እያረሙ የመጡ መስለዋል በተለይ በሀያኛ ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ለደረሰበት ሁለት ለዜሮ ሽንፈት መቀሌዎችን በቅርብ ርቀት የሚከተልበትን እድል ቢያመክንባቸውም በ21ኛ ሳምንት ስሁል ሽረን 3ለ2 በማሸነፉ ወደ ሊጉ ፉክክር ተመልሰዋል ይሁንና በቀጣዩ መርሀ ግብር በአምናው የሊጉ ሻምፒዮን ሽንፈት ማስተናግድ ግድ ብሏቸዋል ሆኖም ግን ባሳልፈነው ሳምንት መርሀ ግብር ሀዋሳን ያስተናገዱት ሲዳማዎች ድል ከእነርሱ ጋር ሆናለች ጨዋታውንም አንድ ለዜሮ ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን ይህም ነጥባቸው 40 በማድረስ ደረጃቸውንም ወደ ሶስተኛ ከፍ እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል የዚህ ሳምንት የሊጉ መርሀግብር እነዚህ ሁለት ክለቦች ሲያገናኝም ሁለቱ ከለቦች በአንደኛና በሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸውም ጨዋታውን ይበልጥ ተጠባቂ አድርጎታል በሊጉ የሻምፒዮና ጉዞ ላይ የሞት ሸረት ትግል እያደረጉ የሚገኙት ሁለቱ ክለቦች መካከል የተካሄደው ፍልሚያም ባለሜዳዎቹ ሲዳማዎች 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል ግቡን ሀብታሙ ገዛህኝና አዲስ ግደይ ለሲዳማ አማኑኤል ገብረሚካኤል ደግሞ ለመቀሌ አስቆጥረዋል ከሜዳው ወጪ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ለማሸነፍ የሚቸግረው መቀሌ ከሀያኛው ሳምንት ጨዋታዎች በኋላ ያለውን ስንመለከት እንኳን በባህር ዳር በቅዱስ ጊዮርጊስና በሲዳማ ቡና ተሸንፏል በተለይ ከወልዋሎ ጋር በሜዳው ነጥብ መጣሉ ከተከታዮቹ ጋር የነበረውን የነጥብ ልዩነት አስጠብቆ እንዳይጓዝ አድርጎቷል ከተከታዩ ፋሲል ከነማ የነበረው የአምስት ነጥብ ልዩነትም አሁን ላይ ወደ ሁለት ዝቅ ሲል ሲዳማዎችም በአምስት ነጥብ ዝቅ ብለው ይከተሉታል የዚህ ሳምንት መርሀ ግብር በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሁለተኛ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አገናኝቷል በሀያኛው ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ከደቡብ ፖሊስ ጋር ነጥብ በመጋራት የሊጉን መሪ በቅርብ ርቀት የመከታላቸውን ሩጫ ያቀዘቀዙት ፋሲሎች በቀጣዩ አዲስ አበባ ላይ መከላከያ አራት ለዜሮ በ22ኛው ሳምንት በሜዳቸው ድሬዳዋ ከተማን አስተናግደው 2 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል ባሳለፍነው ሳምንት የሊጉ ፍልሚያም ደደቢትን አስተናግደው በሰፊ የግብ ልዩነት ባለድል መሆናቸው ይታወሳል ቢጫ ሰርጓጆቹ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በአንፃሩ በአዲሱ አስልጣኝ እየተመሩ በሊጉ ሁለተኛ ዙር ድንቅ አቋም ውጤት በማሳየት ላይ ይገኛሉ ያለፉት አራት ጨዋታዎቻቸውን ስንመለከትም በሀያኛው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ መከላከያን አንድ ለዜሮ አሸንፈዋል በ21ኛው ሳምንት በድሬዳዋ ሁለት ለአንድ ሲሸነፉ በቀጣዩ መርሀ ግብር ደደቢትን ሁለት ለዜሮ ድል አድርገዋል ባሳልፈነው ሳምንት ጨዋታም ከአምናው ሻምፒዮን ጅማ አባጅፋር ጋር ተፋልመው ነጥብ ተጋርተዋል የዚህ ሳምንት መርሀ ግብር ሁለቱ ክለቦች ሲያገናኝም በሊጉ የሻምፒዮና ጉዞ ላይ የሞት ሸረት ትግል እያደረጉ የሚገኙት አፄዎቹ ባለድል ሆነዋል በበዛብህ መለዩ ግብ ባለድል የሆኑት አፄዎቹ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከመሪው መቀሌ በሁለት ነጥብ ዝቅ ብለው በ46 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል በዚህ ሳምንት መርሀ ግብር የመቀሌዎች መሸነፍ ፋሲልና ሲዳማ ደግሞ ማሸነፍ በሶስቱ ክለቦች መካከል የሊጉን የዋንጫ ትንቅንቅ ምእራፍ በይፋ ከፍቶታልሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሀ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስን ከደቡብ ፖሊስ አገናኝቷል ባሳልፈነው የሊጉ መርሀ ግብርም በሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግደው ነጥብ የተጋሩት ፈረሰኞቹ በዚህ ሳምንቱ ጨዋታም ነጥብ መጋራታቸውን ተከትሎ በሊጉ የሻምፒዮንነት ትንቅንቅ ጉዟቸው ላይ ቀዝቃዛ ውሀን ቸልሶባቸዋል ፈረሰኞቹ በጨዋታው ያሳዩት ደካማ አቋም በበርካቶች ዘንድ አስተችቷቸዋል ባሳልፈነው ሳምንትም አዳማን በሜዳውና በደጋፊያቸው ፊት ሁለት ለዜሮ በማሸነፍ ወደ አሸናፊነታችው የተመለሱት ደቡብ ፖሊሲች ከሊጉ የምንጊዜም ሻምፒዮን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ነጥብ ተጋርተው መውጣታቸው ከሊጉ ግርጌ ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረት አሳምሮላቸዋል ፈረሰኞቹ በሊጉ ሰንጠረዥ በ39 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ደቡብ ለፖሊሶች በ24 ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል የአምናው የሊጉ ሻምፒዮን ጅማ አባጅፋርን ከሀዋሳ ከተማ ያገናኘውም ሌላኛው የዚህ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ነበር የአምናው የሊጉ ሻምፒዮን ጅማ አባጅፋሮች በሊጉ የሁለተኛ ዙር ድንቅ አቋም በማሳየት ላይ ይገኛሉ ከሀዋሳው ጨዋታ ቀድሞ ካለፉት አራት ጨዋታዎች ሶስቱን ሲያሸንፍ በአንዱ ነጥብ ተጋርቷል በሀያኛው የሊጉ መርሀ ግብር ላለመውረድ የሚታገለው ስሁል ሽሬ ሁለት ለዜሮ እንዲሁም በ21ኛ ሳምንት ደደቢትን እንዲሁም በ22ኛ ሳምንት ሲዳማን በማሸነፍ ወደ ሻምፒዮናው ፉክክር መጠጋት ችለዋል ይሁንና ባሳለፍነው ሳምንት ወልዋሎን አስተናግደው ነጥብ መጋራታቸው በዋንጫው ፍልሚያ ሩጫቸው ላይ መቀዛቀዝን ፈጥሮባቸዋል ጅማዎች በዚህ ጨዋታ ከሊጉ የዋንጫው ትንቅንቅ ላለመራቅ የሚያስቸላቸውን ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉ ቢገመትም አሽንፈው ሶስት ነጥብ ማግኘት አልሆነላቸውም ጨዋታውም አንድ አቻ ተጠናቋል ግቦቹን ለባለሜዳዎቹ ኦኪኪ አፎላቢ ለሀዋሳዎች ደግሞ ዳንኤል ደርቤ አስቆጥረዋል የአምናው የሊጉ ሻምፒዮን በሜዳው ያገኘው ውጤትም ነጥቡን ከፍ በማድረግ ወደ መሪዎቹ ክለቦች የሚጠጋበትን እድል አሳጥቶታል ሌላኛው መርሀ ግብር ባህርዳር ከተማ ከድሬዳዋ አገናኘቷል በሁለተኛው የሊጉ መርሀ ግብር የጣና ሞገዶቹ አቋም ተዳክሞ እየታየ ይገኛል በተለይ በኢትዮጰያ ቡና የደረሰባቸው የ5 ለ0 አስደንጋጭ ሽንፈትና በሜዳና በደጋፊያቸው ፊት ከደቡብ ፖሊስ ጋር ሶስት አቻ የተለያዩበት ጨዋታ በርካታ ደጋፊዎቻቸውን አስከፍቷል በተለይ የተከላካይ ክፍሉ ደካማ ሆኖ መታየት ክለቡን ዋጋ እያስከፈለው መሆኑ ተስተውሏል ክለቡ ባሳልፈነው ሳምንት ከወራጅ ቀጣና ለመራቅ በሚታገለው መከላከያ መሸነፉም ደግሞ በሊጉ የዋንጫ ፍልሚያ ላይ ያደርግ የነበረውን ግስጋሴ ይበልጡን አደናቅፎበታል ክለቡ በተለይ ያለፉት ሶስትና አራት ጨዋታዎች ያስመዘገበው ውጤት ተከትሎም በሊጉ የሻምፒዮንነት ትንቅንቅ ከመሪዎቸ ተርታ እየራቀ እንዲሄድ አስገድዶታል በሀያኛው መርሀ ግብር ደደቢትን ሶስት ለሁለት በማሸነፍ በቀጣዩ መርሀ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2ለ1 በመርታት ተከታታይ ድል ማስመዝገብ የቻሉት ድሬዳዋዎች ምንም እንኳን በ22ኛው ሳምንት በአፄዎቹ የሁለት ለባዶ ሽንፈት ቢቀምሱም ባሳልፈነው ሳምንት ወላይታ ድቻን አስተናግደው ሁለት ለዜሮ በማሸነፍ ወደ ድል መመለሳቸው ይታወሳል የጣና ሞገዶች በውጤት ቀውስ ውስጥ ሆነው የድል ጉዞን በማድረግ ላይ የሚገኘውን ድሬዳዋን የገጠሙ ሲሆን ጨዋታውም በባለሜዳዎቹ የሁለት ለአንድ አሸናፊነት ተጠናቋል የጣና ሞገዶቹ ከሽንፈታቸው አገግመው ወደ አሸናፊነታቸው የሚመልሳቸውን ውጤት ሲያስመዘግቡም ወሰኑ አሊና ዳግማዊ ሙሉጌታ የግቦቹ ባለቤት ሆነዋል ድሬዳዋን ከመሸነፍ ያላዳነችውን ግብ ኤርምያስ ሀይሉ አስቆጥሯል ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሀ ግብር አዳማን ከመከላከያ አገናኝቷል በሊጉ የዋንጫ ፍልሚያ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ከሚሳናቸው ቡድኖች አንዱ የሆነው አዳማ ከመቐለ 70 እንደርታ ከደረሰበት የ2 ለ 1 ሽንፈት በኋላ በ22ኛ ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር ኢትዮጵያ ቡናን በማስተናገድ አንድ ለዜሮ ማሸነፍ ቢችሉም በቀጣዩ ጨዋታ ሽንፈትን ማስተናገዳቸው ይታወሳል መከላከያ በአንፃሩ በሁለተኛው የሊጉ ምእራፍ ወጥ አቋም ማሳየት ተስኖት አሰልጣኙን እስከማሰናበት ተሻግሯል በሀያኛው ሳምንት ወደ መቐለ ተጉዞ በወልዋሎ እንዲሁም በ21ኛው ሳምንት በፋሲል ተሸንፏል ክለቡ ወቅታዊ አቋም እያደር መዋዠቅና በውጤት ቀውስ ላይ መሆኑን ተከትሎም የመውረድ አደጋ እንደተጋረጠበት ሲነገር ቆይቷል ይሁንና ክለቡ ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች ላይ ያሳየው አቋምና ድል ግን ምናልባትም ስጋቶቹን ሁሉ ከንቱ ሊሆኑ እንደሚችል አስመስክሯል በውጤት ቀውስ ወደ ሊጉ ግርጌ የሚንደረደረው አዳማ ከሊጉ ግርጌ ለመውጣት ከሚጣጣረው መከላከያ ጋር ያገናኘው የዚህ ሳምንት ጨዋታም በአቻ ውጤት ተጠናቋል በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ መቐሌ ሰባ እንደርታ አርባ ስምንት ነጥቦች በመሰብሰብ በቀዳሚነት ይመራል ፋሲል ከነማ በአርባ ስድስት በሁለተኛነት ሲከተል ሲዳማ ቡና በአርባ አምስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል የሊጉን ወራጅ ቀጣና ስንመለከት ደቡብ ፖሊስ በ24 ነጥብ አስራ አራተኛ ስሁል ሸረ በ22 ነጥብ አስራ አምስተኛ እንዲሁም ደደቢት በ10 ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘዋል የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ፉክክር የመቐሌው አማኑኤል ገብረሚካኤል በአስራ አምስት ግቦች የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በአስራ ሶስት እንዲሁም የመከላከያው ምን ይሉህ ወንድሙ በአስራ አንድ ግቦች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋልአዲስ ዘመን ግንቦት 62011 በ
https://www.press.et/Ama/?p=10772
1,306
41,092
ትንታኔ:- የሦሥቱ የመንግሥት ዋልታዎች፤ ሕገ መንግሥትና ፖለቲካ
ዓለም አቀፍ ዜና
February 17, 2017
Unknown
መንግስት አወቃቀር የስልጣን ክፍፍል ቁጥጥር እና ሚዛንሶስቱ የመንግስት ቅርንጫፎች በየበኩላቸው አንዳንዳቸው ከሌላቸው ፈፅሞ የተለየ ስልጣንና ሀላፊነቶች ያላቸው መሆኑ አንዱ ከሌላው ስልጣንና ሀላፊነት ጋር እንዳይጋጭ ያደርገዋልየዩናይትድ ስቴትስን በመሰሉ ዲሞክራሲያዊ ስርአቶች ውስጥ የሶስቱ የመንግስት አስተዳደር ቅርንጫፎች ምንነትና ሚና ላይ ያተኮረ ልዩ የትንታኔ ቅንብር ነው
https://amharic.voanews.com//a/separation-power-three-branches-of-power-check-and-balance-voa-with-dr-brook-hailu-alula-kebede-jan-and-feb-2017/3727951.html
42
12,146
ወላይታ ፡ በወላይታ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደው የኃይል እርምጃ "ተመጣጣኝነት አጠያያቂ ነው" ኢሰማኮ
ሀገር አቀፍ ዜና
11 ነሐሴ 2020
Unknown
በወላይታ ዞን አንዳንድ ከተሞች በነበሩ ተቃውሞዎች የፀጥታ ሀይሎች እርምጃ ተመጣጣኝነት አጠያያቂ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀኮሚሽኑ በወላይታ ዞን የተለያዩ ከተሞች ነሀሴ 42012 አም ሰኞ እለት ተቃውሞ መካሄዱን ጠቅሶ የፀጥታ ሀይሎች ሰላማዊ ሰልፈኞችን በሚቆጣጠሩበት ወቅት የሞት አደጋን የሚያስከትል የሀይል እርምጃ ከመውሰድ ሊቆጠቡ ይገባል ብሏልእንዲህ አይነት እርምጃዎች ቀድሞውንም የነበሩ ውጥረቶችን እንደሚያባብሱ የገለፀው ኮሚሽኑ በግጭቱ ወቅት የተከሰተው የስድስት ሰልፈኞች አሟሟትን እና የፀጥታ ሀይሎች የሀይል አጠቃቀምን አስመልክቶ ፈጣን ምርመራ እንደሚያስፈልግ ገልጿልበወላይታ የተቃውሞ ሰልፉ የተቀሰቀሰው እሁድ እለት ከፍተኛ የዞኑ ባለስልጣናት አክቲቪስቶች ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የአገር ሽማግሌዎች መታሰራቸውን ተከትሎ ነው ግለሰቦቹና ባለስልጣናቱ የታሰሩት ዞኑን በክልልነት ለማደራጀት የተቋቋመው ሴክሬተርያት የህግ ኮሚቴ ባዘጋጀው የህገመንግስት ረቂቅ ላይ ለመወያየት ተሰብስበው ሳሉ ነውእንደ ኮሚሽኑ መግለጫ ከሆነ እስካሁን ድረስ 178 ሰዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከእነዚህ መካከል 28 የዞኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸውግለሰቦቹ ታስረው የሚገኙት በወላይታ ሶዶ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ ውስጥ መሆኑን መግለጫው አክሎ ገልጿልባለፈው እሁድ ከወላይታ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በፀጥታ ሀይሎች በተያዙ ሰዎች ሰበብ በተከሰተ አለመረጋጋት ቢያንስ የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ ዞኑን በክልልነት ለማደራጀት ከተቋቋመው ሴክሬታሪያት ስብሰባ ተሳታፊ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች የህግ ባለሙያዎችና የአገር ሽማግሌዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነው ችግሩ የተከሰተውበተለይ አለመረጋጋቱ ከፍተኛ ነበር በተባለባትና ከሶዶ ከተማ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቦዲቲ ከተማ የሟቾች ቁጥር ከሰባት በላይ እንደሆነና በሶዶም ሰዎች መገደላቸውን ከሆስፒታሎችና ከአካባቢው ነዋሪዎች አገኘሁት ያሉት መረጃን ጠቅሰው የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ማቴዎስ ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋልበሶዶ ሶስት ሰዎች እንደሞቱና በቦዲቲም ሌሎቹ እንደተገደሉ አቶ ማቴዎስ አስረድተዋል ከሰበሰቧቸው መረጃዎች ተረዳሁት ያሉት አቶ ማቴዎስ ብዙዎቹ በእድሜ ታዳጊ እንደሆኑና መንግስት ያለ አግባብ ሀይል ተጠቅሟል ሲሉም ወንጅለዋልየሚያሳዝነው እነዚህ ልጆች ጠንከር ያለ አርጩሜ ይበቃቸው ነበር አስለቃሽ ጋዝም መርጨት ይቻል ነበር አንዳንዶቹ እየሮጡ አሳዶ መተኮስ በጣም የሚያሳዝን ነው ብለዋልየክልሉ ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር የግለሰቦቹ ህይወት የጠፋው መሳሪያ ለመንጠቅ ባደረጉት ትንቅንቅ ነው ማለታቸውን ጠቅሰው ይሄ ትክክል እንዳልሆነ ለቢቢሲ አስረድተዋል ስለግለሰቦቹ ሞት ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት በሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ውስጥ ከትናንት በስቲያ በጥይት ተመትቶ የመጣ አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፏል ግለሰቡ የ30 አመት እድሜ እንደሆነ የሚናገሩት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያ ሶስት ግለሰቦችም በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋልየ22 አመት እድሜ ያለው አንደኛው ግለሰብ በጥይት አንገቱ ላይ ተመትቶ በፅኑ ህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን በከፋ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም እኚሁ የጤና ባለሙያ ለቢቢሲ አስረድተዋል ሌላኛው የ25 አመት ጎልማሳ ሲሆን እግሩ ላይ በጥይት ተመትቶ ደም ስሩም በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል በተጨማሪም ሌላኛው ህመምተኛ በጥይት ሳይሆን በዱላ ከፍተኛ ድብደባም ደርሶበታል ብለዋልከፅኑ ማቆያ ህሙማን ክፍል በተጨማሪም ሶስት ግለሰቦችም በጥይት ተመትተው የአጥንት ህክምና ክፍል ውስጥ ተኝተው እየታከሙ ነውም ብለዋል ከዚህም በተጨማሪ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና አድርገው የተመለሱ ወደ አምስት ሰዎች መኖራቸውንም እኚሁ ባለሙያ ገልፀዋል ምንም እንኳን ሆስፒታል ውስጥ መጥቶ ህይወቱ ያለፈ ባይኖርም በቦዲቲ አምስት ሰዎች መሞታቸውን መረጃ ማግኘታቸውን እንዲሁም በሶዶ ከተማም ውስጥ ሆስፒታል ሳይመጡ በጥይት የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውንም ተናግረዋልበአሁኑ ሰአት የንግድ እንቅስቃሴዎችም ሆነ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች መቆማቸውን ገልፀው ሶዶ ብትረጋጋም በቦዲቲ መጠነኛ ውጥረት እንዳለ አስረድተዋልየሶዶ ከተማ ፀጥ ረጭ እንዳለችና ከመከላከያና የፀጥታ ሀይሎች ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በስተቀር ምንም እንደሌለ ስሜ አይጠቀስ ያሉ ነዋሪ አስረድተዋልምንም እንኳን ከትናንትናው ጋር ሲነፃፀር አንፃራዊ ሰላም ቢኖርም ስጋቶች እንደነገሱ ይኸው ነዋሪ ይናገራሉ እሳቸው ሰማሁ ባሉት መረጃ በቦዲት ሰባት ሰዎች መገደላቸውን በሶዶ ደግሞ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል ብለዋል በዛሬው እለት በሶዶ እንዲሁም በቦዲት ከተሞች የቀብር ስነ ስርአቶች እየተካሄዱና ነዋሪው ለሀዘን ተቀምጠዋልም ብለዋል ባለው የመንገድ መዘጋት የተነሳ ከአዲስ አበባ ወደ ቦዲቲ ለመሄድ ያልቻለው ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የቦዲቲ ከተማ ነዋሪም አንድ አክሊሉ የተባለ ጓደኛው በጥይት መገደሉን ተናግሯል አክሊሉ በሀያዎቹ እድሜ ላይ የሚገኝ እንደሆነም ለቢቢሲ አስረድቷል ከትናንት ጀምሮ ለደቡብ ክልል ፖሊስና ለሰላም ፀጥታ ቢሮ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን ደጋግመን በመደወል ቀጠሮ ቢሰጡንም ምላሻቸውን ማግኘት አልቻልንም የደቡብ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ በወላይታ ዞን የተከሰተውን አለመረጋጋት በተመለከተ በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች 10 መሆናቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ትናንት ገልፀው እነሱም የክልል እንሁን ጥያቄ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እንዳይፈታ ለማድረግ ሲጥሩ የነበሩ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን ተናግረዋል የፀጥታ ሀይል እነዚህን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ መንገድ የመዝጋትና ግርግር የመፍጠር አዝማሚያ መታየቱን ገልፀው ከዚህ ጋር ተያይዞም የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ሌሎች ደግሞ መቁሰላቸውንም ሀላፊው አቶ አለማየሁ ትናንት ተናግረው ነበር ለግጭቱ መነሻ ምክንያት የሆነው በዞኑ የተቋቋመው የክልል ምስረታ ሴክሬታሪያት ካውንስል አማካሪ ቦርድ አባላት በህግ ኮሚቴው የተዘጋጀውን የህገ መንግስት ረቂቅ ላይ እንዲወያዩ ስብሰባ ላይ የተጠሩ ሰዎች መታሰራቸውን ተከትሎ ነውከታሰሩትም ውስጥ የዞኑ አስተዳዳሪ ዳጋቶ ኩምቤ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ጥበቡ ዮሀንስ የዞኑ ከፍተኛ አመራር ወሮ እቴነሽ ኤልያስ የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ ስራ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጎበዜ አበራ የወላይታ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶር አስራት ኤልያስ ይገኙበታልከዚህም በተጨማሪ ከአገር ሽማግሌዎች አቶ ሰይፉ ለታና አቶ ዳንኤል ደሳለኝ የንግድ ምክር ቤት ዋናና ምክትሉ አቶ በተላ ቦረናና አቶ አክሊሉ ደስታ የመብት ተሟጋቾችና ከህግ ባለሙያዎች መካከል አቶ አሸናፊ ከበደ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ አቶ ተከተል ለቤና በአጠቃላይ 26 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላችውን አቶ ማቴዎስ ተናግረዋልእሳቸውም አባል የሆኑበት የዚህ ሴክሬታሪያት አባላት መታሰር እንዳሳዘናቸው ጠቅሰው ግለሰቦቹን ከመፍታት በተጨማሪ የሞቱ ግለሰቦችንም አሟሟት ነፃና ገልልተኛ የሆነ አካል ሊያጣራ ይገባል ብለዋል የወላይታ ዞን ምክር ቤት ሰኔ 152012 አም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የወላይታ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እንዲቋቋም ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳልየክልሉን መንግስት ለማደራጀት የሚያስችል ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤትም እንዲቋቋም እና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንዲከናወኑም በዚሁ ወቅት ወስኖ ነበር
https://www.bbc.com/amharic/news-53733422
781
1,774
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አመራሮች የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የጥንቃቄ የቅስቀሳ መልዕክት አስተላለፉ
ሀገር አቀፍ ዜና
June 11, 2020
18
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የስራ ሀላፊዎች የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን አገራዊ ጥረት ለመደገፍ ትናንት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር የቅስቀሳ መልእክት አስተላለፉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በዚሁ ቅስቀሳ ላይ ባስተላለፉት የጥንቃቄ መልእክት ዛሬ በመካከላችሁ የተገኘነው በሚዲያ ከምንነግራችሁ የጥንቃቄና መከላከያ መንገዶች በተጨማሪ ከመዘናጋት ወጥተን በጤና ባለሞያዎች የሚሰጡትን መመሪያዎችን በትክክልና በአግባቡ መተግበር ከቻልን ቫይረሱን መከላከል እንደምንችል ለማሳሰብ ነው ብለዋል ኮሮናን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሀላፊነታችሁን በአግባቡ እየተወጣችሁ ያላችሁ የከተማችን ነዋሪዎችን ላመሰግን እፈቅዳለሁ ያሉት አቶ ጌትነት የጤና ባለሞያዎች የሚያስተላልፏቸውን መልእክቶች ሰምቶ ተግባራዊ ማድረግ አንዱ የስልጣኔ ምልክት ነው እያንዳንዱ ሰው ሀላፊነቱ ሊወጣ ይገባል መንግስት የሚወስዳቸውን እርምጃዎችን ጠንከር ብሎ ማስፈፀም ያስፈልጋል የሚል መልእክት አስተላልፈዋል ከቅስቀሳው በኋላ ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየታቸውን የሰጡት ዋና ስራ አስፈፃሚው የሚዲያው አመራር ንቅናቄ ስራ ለአራት ቀናት ጋዜጠኞችን ጭምር አካቶ የሚደረግ መሆኑን አስታውቀዋል እንደ ሚዲያ በርካታ የግንዛቤ መፍጠሪያ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት አቶ ጌትነት ችግሩም ከተከሰተ በኋላም ሚዲያው በስፋት አጀንዳ አድርጎ ሲሰራበት መቆየቱን በህብረተሰቡ ዘንድ ግን መረጃውን ወስዶ ተግባር ላይ ማዋል ላይ ትልቅ ክፍተት መኖሩን ተናግረዋል ዛሬ ወደ ህብረተሰቡ የወረድንበት ዋናው ምክንያት ከጤና ባለሞያዎች የሚተላለፉ መልእክቶችን አድምጡ ያደመጣችሁትንም ተግባራዊ አድርጉ የሚለውን ሀሳብ ለማስተላለፍና ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን አገራዊ ጥረት ለማገዝ ነው ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚው ለቅስቀሳ በተዘዋወሩባቸው አከባቢዎች ጉራማይሌ ነገሮችን ማስተዋላቸውን የገለፁት አቶ ጌትነት ህብረተሰቡ ስለቫይረሱ ወረርሽኝና መከላከያ መንገዱ መረጃው ቢኖረውም በርካታ ሰው የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛውን በአግባቡ አላደረጉትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አድርገውም አካላዊ ርቀትን ያልጠበቁና ያልተራራቁ ሰዎችን በብዛት መመልከት ችለናል ይህም የሚያሳየው ከችግሩ ለመውጣት ገና ትልቅ ስራን የሚጠይቅ መሆኑን ነው ብለዋል ሀላፊዎቹ የቅስቀሳ ስራ ባከናወኑባቸው አካባቢዎች ያገኘናቸውና ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየትም የዚህ አይነቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ጥቅማቸው የጎላ በመሆኑ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል በድለላ ስራ ላይ የተሰማራው ወጣት ዮሀንስ አባተ የአዲሱ ገበያ አከባቢ ነዋሪ ሲሆን በአከባቢው የሚኖሩ አንድ አንድ የማህበረሰብ ክፍሎች የቫይረሱን መከላከያ መንገድ እንዲተገብሩ ሲነገራቸው ከመተባበር ይልቅ የማንጓጠጥና ምን አገባህ የሚል ምላሽ እንደሚሰጡ ጠቅሶ የዚህ አይነት የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ቅስቀሳ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መጨበጥ የጎላ ሚና አላቸው ብሏል ሌላው አስተያየት ሰጪ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ነዋሪ የሆኑት አቶ ተመስገን ወልደ ሰንበት ናቸው እንደ እርሳቸው ገለፃም ህብረተሰቡ ማድረግ ያለበት ጥንቃቄ ብዙም አልገባውም በተለይ በወጣቱ ዘንድ ትልቅ ቸልተኝነትና መዘናጋት ስላለ ብዙ መሰራት ይገባል ወጣቶች በአንድ አከባቢ ተሰባስበው ይቀመጣሉ እንደ እኔ በእድሜ ገፋ ገፋ ያሉት ሰዎች በተሻለ ሁኔታ ርቀትን ጠብቀው የመከላከያ መመሪያውን እየተገበሩ ናቸው በወጣቱ ዘንድ ግን ትኩረት ተደርጎ ሊሰራበት ያስፈልጋል ሚዲያውና አመራሩ እንደዚህ መልእክቶችን በማስተላለፍ ማስተማር ይጠበቅበታል ብለዋል አቶ ተመስገን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የስራ ሀላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ እና አራዳ ክፍለ ከተሞች ላይ በማተኮር በሚቀጥሉት አራት ቀናት ተመሳሳይ መልእክት እንደሚያስተላለፉ ታውቋል አዲስ ዘመን ሰኔ 42012 በወንድማገኝ አሸብር
https://www.press.et/Ama/?p=34145
398
47,803
አቶ ያረጋል አይሸሹምና ሌሎች ተከሳሾች ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተፈረደባቸው
ፖለቲካ
January 13, 2014
Unknown
አዲስ አበባ ጥር 52006 ዋኢማ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት በነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹምና አብረዋቸው ተከሰው የነበሩ አምስት ተከሳሾች ከስድስት እስከ 15 አመታት የሚደርስ ፅኑ እስራትና ከ20 ሺህ ብር እስከ 60 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ጥር 2 ቀን 2006 አም ተፈረደባቸውበመንግስት ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት በስልጣን ያላግባብ የመገልገል የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ ጥቅምት 20 ቀን 2004 አም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመስርቶባቸው ላለፉት ሁለት አመታት ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ ሀዳር 11 ቀን 2006 አም ጥፋተኛ መባላቸው ይታወሳል በመሆኑም የኮሚሽኑ አቃቤ ህግ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃና ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ ሀሳብ በመስማት አዲስ ከተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመርያ ቁጥር 22006 እና ከሌሎች የህግ ድንጋጌዎችን አንፃር ፍርድ ቤቱ በመመርመር አቶ ያረጋል አይሸሹም ሰባት አመት ፅኑ እስራትና 20 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል አቶ ያረጋል ጥፋተኛ የተባሉት በአንድ ክስ ሲሆን ከሌሎቹ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በዋና ወንጀል አድራጊነት ስልጣናቸውን ያላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል መስራታቸው በኮሚሽኑ አቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ መረጋገጡን  በመዘርዘር ነው አቶ ያረጋል ክሱ በተመሰረተባቸው ወቅት የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የፌዴራል ሀብረት ስራ ማሀበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ነበሩ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩትና የወንጀል ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ነበሩ የተባሉት አቶ ሀብታሙ ሂካ በሶስት ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውንና ካቀረቡት የቅጣት ማቅለያዎች አራቱ ተይዘውላቸው 15 አመታት ፅኑ እስራትና 45 ሺህ ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል ጥፋተኛ የተባሉትም በሶስት ተደራራቢ የሆኑ ስልጣንን ያላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል መፈፀማቸው በኮሚሽኑ አቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች እንደተረጋገጠባቸው ፍርድ ቤቱ በውሳኔው በዝርዝር አስረድቷል አቶ አሰፋ ገበየሁ የተባሉት ግለሰብ ደግሞ 15 አመታት ፅኑ እስራትና 60 ሺህ ብር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው ሲሆን ለቅጣቱ መነሻ የሆነው የወንጀል ድርጊት ከሌሎቹ ተከሳሾች ጋር ግብረ አበር በመሆን በልዩ ወንጀል ተካፋይ በመሆናቸው በሶስት ተደራራቢ ስልጣን ያላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል መፈፀማቸው ከሳሽ አቃቤ ህግ በሰውና በሰነድ ሊያስረዳ በመቻሉ መሆኑን የቅጣት ውሳኔው ያብራራልአቶ አሰፋ የኮንስትራክሽንና ዲዛይን አክሲዮን ማሀበር የዲዛይን ስቱዲዮ ክፍል ሀላፊና የጌዲዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት ወኪል ሆነው በሚሰሩበት ወቅት የወንጀል ድርጊቱን ሊፈፅሙ መቻላቸውን ውሳኔው ይጠቁማልየፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት አቶ ጌዲዮን ደመቀ የተባሉት ተከሳሽ 14 አመታት ፅኑ እስራትና 60 ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል በሶስት ክሶች ጥፋተኛ መባላቸውንም በዝርዝር አስረድቷል የጌዲዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅም ናቸው የጋድ ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ አድገህና የኮለን ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መክብብ ሞገስ ደግሞ በአንድ ክስ ጥፋተኛ የተባሉ መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ አስታውሶ በልዩ ወንጀል ተካፋይ በመሆንና በዋና ወንጀል አድራጊነት ስልጣንን ያላግባብ የመገልገል ሙስና ወንጀል መፈፀማቸው በኮሚሽኑ አቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ እያንዳንዳቸው ስድስት አመት ፅኑ እስራትና 25 ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ተሰጥቷል በአቶ ገዛኸኝ አድገህ ላይ የተወሰነው ቅጣት በልዩነት በአብላጫ ድምፅ ማለትም አንድ ዳኛ የጥፋተኛነት ፍርድ በሚሰጥበት ወቅት በነፃ ሊሰናበቱ ይገባል በማለት ሲለዩ ሁለት ዳኞች ጥፋተኛ ናቸው በማለታቸው የቅጣት ውሳኔው መሰጠቱን መዝገቡ ያብራራል የፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ አቶ ያረጋል አይሸሹምን ጨምሮ በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ የመሰረተ ቢሆንም በሰባተኛነት ተካተው ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የአቶ ሀብታሙ ሂካ ወንድም አቶ ሀይለ ገብርኤል ሂካ በብይን በነፃ ተሰናብተዋል ፍርደኞቹን ለቅጣት ያበቃቸው የወንጀል ድርጊት ተፈፀመ የተባለው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሰሩ በክልሉና በፌዴራል መንግስት በጀት ተይዞላቸው እንደነበር ከተገለፁት የግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ የጣና በለስ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤትና የአሶሳ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ጋር በተገናኘ ተፈፅሟል በተባለ የሙስና ወንጀል መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል ፍርደኞቹ ክልሉ በመስከረም ወር 1992 አም ያወጣውን የግዥ መመርያ ቁጥር 192 አንቀፅ 91 እና 2 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ እንዲሁም ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚፈፀም የአገር ውስጥ ግዥ በክልሉ የፋይናንስ ቢሮ መፅደቅ እንደሚኖርበት በመመርያው አንቀፅ 223ሀ እና 231 1ኛ ሰንጠረዥና 232 ስር የተደነገገውን ግልፅ መርህ መተላለፋቸውን የኮሚሽኑ አቃቤ ህግ የመሰረተውን ክስ መዘገቡ አይዘነጋም ለፕሮጀክቶቹ የተመደበው ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን አቶ ያረጋልና አቶ ሀብታሙ እያወቁ በግልፅ ጨረታ የተሻሉ ተወዳዳሪዎችን በመጋበዝ ማጫረትና ማሰራት ሲገባቸው የሶስቱንም ፕሮጀክቶች ጨረታ በህገወጥ መንገድ ለጌዲዮን አማካሪ ድርጅት መስጠታቸውን የግዥ ዘዴ ቅድመ ሁኔታዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ ስራው አስቸኳይ ነው በማለት በውስን ጨረታ እንዲፈቀድ ማድረጋቸውን ከመመርያ ውጪ የጨረታ ሰነድ ለኮንስትራክሽንና ዲዛይን አክሲዮን ማሀበርና ለጋድ ኮንስትራክሽን ድርጅት እንዲላክ ማድረጋቸውን ስራው በማጓተቱ 2832450 ብር ተጨማሪ ክፍያ መውጣቱንና ሁሉም ተከሳሾች በመንግስት ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሳቸውና በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት በስልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል ሪፖርተር
https://waltainfo.com/am/24851/
656
47,989
ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት የ5ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ድጋፍ አገኘች
ፖለቲካ
November 25, 2013
Unknown
የአውሮፓ ህብረትና የኢትዮጵያ መንግስት የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር እርዳታ ስምምነት ዛሬ ተፈራረሙየእርዳታ ስምምነቱን ተፈራረሙት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር ዴኤታ አቶ አህመድ ሺዴና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የልማት ኮሚሽነር አንድሪስ ፒይበልግስ ናቸውየእርዳታ ገንዘቡ ለእናቶችና ጤና ለመሰረታዊ አገልግሎትለመንገድና ድርቅን ለመከላከል የሚውል ነውበስምምነቱ ወቅት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር ዴኤታ አቶ አህመድ ሺዴ እንዳሉት የእርዳታ ስምምነቱ የእድገትና ትራስፎርሜሽን እቅድ እንዲሁም የሚሊኒየሙን የልማት ግቦች ለማሳካት ያግዛልየአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የልማት ኮሚሽነር አንድሪስ ፒበልግስ በበኩላቸው ስምምነቱ የህብረቱና የኢትዮጵያ የልማት አጋርነት እየጎለበተ መመጣቱን ያሳያል ብለዋልህብረቱ ለሀገሪቱ ባደረጋቸው ድጋፎች ውጤታማ ለውጥ በመመዝገቡም የልማት ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋልበእርዳታ ስምምነቱ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮነን ገንዘቡ ለታለመለት ግብ ለማዋል መንግስት ቁርጠኛ ነው ብለዋል
https://waltainfo.com/am/24798/
105
4,102
ኢንተርፕራይዙ ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ሰበሰበ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 14, 2019
41
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2011 በጀት አመት 275 ሚሊዮን 583 ሺ 602 ብር መሰብሰቡን አስታወቀየኢንተርፕራይዙ የማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ ወይዘሮ ዘሀራ መሀመድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ተቋማቸው ስምንት ሚሊዮን 487 ሺ 743 የትራፊክ ፍሰትን በማስተናገድ 264 ሚሊዮን 307 ሺ134 ብር ከማስታወቂያ ቦታዎች ኪራይ ከተሽከርካሪ ማንሻና መጎተቻ እንዲሁም ከሌሎች አግልግሎቶች 11 ሚሊዮን 276 ሺ 468 ብር ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል የመንገዱን ደህንነት ከማስጠበቅ አኳያም የግንዛቤ መፍጠሪያ መርሀ ግብሮችን መካሄዳቸውን እንዲሁም የ24 ሰአት የመንገድ ላይ የትራፊክ ቁጥጥር እንደሚደረግ የተናገሩት ቡድን መሪዋ በአገልግሎት እድሜ ማብቃትና በአደጋ ምክንያት በንብረቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመወያየት መንገዶችን በመስራትና በመጠገን ምቾት እንዳይጓደል መደረጉን አብራርተዋል እንደ ቡድን መሪዋ ገለፃ ኢንተርፕራይዙ የአገልግሎት አሰጣጡን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ ሄዷል በዚህም የመንገድ ላይ መብራት ማስፋፊያና ዝርጋታ የአገልግሎት መስጫ ጣቢያና የደንበኞች የጥሪ ማእከል ግንባታ እንዲሁም የስራ ቦታን ምቹ የማድረግ ተግባራት ታቅደው በመከናወን ላይ ናቸውአገልግሎት መስጠት ከጀመረ አምስት አመት ያስቆጠረው የአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ የ24 ሰአት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ከ31 ሚሊዮን በላይ ተሽከርካሪዎችን በማስተናግድ ከ965 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል ኢንተርፕራይዙ በ2011 በጀት አመትም የድሬዳዋ ደወሌ የክፍያ መንገድንም ስራ አስጀምሯልአዲስ  ዘመን ነሀሴ 82011 አጎናፍር ገዛኸኝ
https://www.press.et/Ama/?p=16022
185
47,341
በዓሉ ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን ህዳሴ ለማረጋገጥ እንዲተጉ አስችሏል
ፖለቲካ
November 21, 2014
Unknown
አዲስ አበባ ህዳር 112007 ዋኢማ የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል መከበር ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን በማጠናከር የአገሪቱን ህዳሴ ዳር ለማድረስ የጎላ ሚና እንዲወጡ ማስቻሉን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለፀበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚከበረው 9ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል ዝግጅት መጠናቀቅ  በማስመልከት  የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተክለብርሀን  እንደገለፁት ለተከታታይ 8 አመታት የተከበረው በአል በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል መተማመንና መከባበርን  እንዲጨምር አድርጓልታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሰረት በተጣለበት ክልል     መሆኑ የመጀመሪያው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ማጠናቀቂያ አመትና ሁለተኛው የሚጀምርበት አመት መሆኑና ክልላዊና ሀገራዊ ምርጫ የሚካሄድበት አመት መሆኑ የዘንድሮውን የብሄሮች ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል ለየት እንደሚል አፈ ጉባኤ ካሳ ተናግረዋል በአሉ የኢትዮጵያ ህዝቦች ህገ መንግስታችን ኢትዮጵያዊነት በልዩነት ውስጥ አንድነትንና መቻቻልን በአንድነት ውስጥ ጥንካሬን የሚያጎለብቱ እሴቶችን በመፍጠር ሀገራችን በህዳሴ ጉዞ ላይ እንድትገኝ ያስቻለ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የቃል ኪዳን ሰነድ  መሆኑን በመረዳት አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ አስችሏል ብለዋልአፈ ጉባኤው አያይዘውም በአሉ በህዝቦች ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት የተቀመጠውን ህገ መንግስታዊ ግብ በማሳካት የኢትዮጵያን ህዳሴ ለማረጋገጥ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን ለመቀጠል ዳግም     ቃል     የምንገባበት     ቀን ይሆናል ብለዋልየብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች  በአል ከ1999 አም ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች  በደማቅ ሁኔታ     እየተከበረ     እንደመጣ ገልፀው  ለ9ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በደማቅ ሁኔታ ለሚከበረው በአልም ዝግጅቱ  መጠናቀቁን  አቶ ካሳ ተናግረዋል በአሉ     ሲከበር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጉብኝትና የኪነጥበብ ምሽት     ያሉት አፈ ጉባኤው በአሶሳ ከተማ አገር አቀፍ ሲምፖዚየም የባህል ትርኢት የንግድ ትርኢት  ባዛርና  ኤግዚብሽን በማካተት ከዋዜማው ጀምሮ     በአሉ     በደማቅ     ሁኔታ ይከበራል ብለዋል በህገመንግስታችን የደመቀ ኢትዮጵያነታችን ለህዳሴያችን በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የዘንድሮው የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል ከ2 ሺህ 5አአ በላይ የአገር ውስጥና የውጭ አገራት እንግዶች እንደሚገኙ ይጠበቃል
https://waltainfo.com/am/25181/
243
40,984
የሮሒንግያ የተኩስ አቁም ስምምነት የሚያንማር መንግሥት ተቃወመ
ዓለም አቀፍ ዜና
September 25, 2017
Unknown
የሮሂንግያ አማፅያን ያቀረቡትን የተኩስ አቁም ስምምነት የሚያንማር መንግስት እንደማይቀበል አስታወቀከበስተጀርባ የሆኑትና በመሪነት የሚታወቁት የአንግ ሳን ሱቺ ቃል አቀባይ ዛዊ ሀትያበሰጡት አፋጣኘኝ መልስከሽብርተኛ ጋር የመደራደር ባህል የለንም ነው ያሉትበምህፃረ ቃሉ ARSA የሚባለው የሽምቅ ቡድኑ እአአ ባለፈው ነሀሴ 25 ቀን በፖሊስና በጦር ሀይሎች ካምፕ ላይ ጥቃት ከአካሄደ ወዲህ ነው የሚያንማር መንግስት በአሸባሪነት የመደበውአንዳንድ ታዛቢዎችና የራሱ የቡድኑ አባላትም እንደሚናገሩት የሚያንማር ከሌሎች በአካባቢው ከሚዋጉ አነስተኛ ቡድኖች ጋር ሲደራደር ቆይቷልእናም ይህ የአሁኑ የአንደራደርም መልስ እንዴትና ከየት እንደመጣ ይጠይቃሉ
https://amharic.voanews.com//a/rohingya-myanmars-government-9-25-2017/4043297.html
73
12,819
ከ3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች በጎንደር ከተማ ለማልማት ጥያቄ አቀረቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jan 5, 2021
108
አዲስ አበባ ታህሳስ 27 2013 ኤፍ ቢ ሲ በጎንደር ከተማ ከ3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ጥያቄ ማቅረባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ገለፀየከተማዋ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ ባዩ አቡሀይ በአካባቢው ከአመታት በፊት የነበረው አለመረጋጋት በኢንቨስትመንት ፍሰቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሮ እንደነበረ አስታውሰዋልይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የከተማ አስተዳደሩ ከሀብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ ችግሩን ለመፍታት በሰራው ስራ ሰላም በመረጋገጡ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ መጨመሩን ተናግረዋልበአካባቢው ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃ የሚሆን ግብአት መገኘቱና በቂ የሰለጠነ የሰው ሀይል አቅርቦት መኖሩ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋልበከተማ አስተዳደሩ 33 ኢንዱስትሪዎች ማምረት መጀመራቸውንና 60 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ግንባታቸውን በማጠናቀቅ ማሽነሪ በማስገባት ሂደት ላይ እንደሚገኙ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧልበከተማዋ በተያዘው በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ከ3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 75 ባለሀብቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለመሰማራት ጥያቄ ማቅረባቸውንም ጠቅሰዋል ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘትየፋና ድረ ገፅ httpswwwfanabccom ይጎብኙተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል httpswwwyoutubecomcfanabroadcastingcorporate ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል httpstmefanatelevision ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን httpstwittercomfanatelevision ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን 
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a83-%e1%8a%90%e1%8c%a5%e1%89%a5-8-%e1%89%a2%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8a%ab%e1%8d%92%e1%89%b3%e1%88%8d-%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%88%98%e1%8b%98/
161
18,846
ስፔን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሰዓት እላፊ ገደብ ጣለች
ዓለም አቀፍ ዜና
Oct 25, 2020
269
አዲስ አበባ ጥቅምት 15 2013 ኤፍቢሲ ስፔን በሀገሪቱ ዳግም እያገረሸ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት በመላ ሀገሪቱ የሰአት እላፊ ገደብ መጣሏ ተነግሯልበተጨማሪም ሀገሪቱ ብሄራዊ የጤና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇንም የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋልጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እንዳስታወቁት የምሽት የሰአት እላፊ ገደቡ ከምሽቱ 5 ሰአት ጀምሮ እስከ ንጋት 12 ሰአት ተፈፃሚ ይሆናልየሰአት እላፊ ገደቡም ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ተፈፃሚ እንደሚደረግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋልእንዲሁም በጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአየካባቢው የሚገኙ ባለስልጣናት በክልሎች መካከል የሚደረግ ጉዞን የመከልክል እርምጃን መውሰድ እንደሚችሉም አስታውቀዋልበተጨማሪም በአንድ ስፍራ የሚሰበሰቡ ሰዎች ቁጥር ከ6 እንዳይበልጥ ክልከላ ሊጣል እንደሚችልም ተነግሯልአዲሱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና መመሪያው ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ የሀገሪቱ ምክር ቤት ክልከላው ለ6 ወራት እንዲያራዝመው እንደሚጠይቁም አስታውቀዋልስፔን ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰውችም ሁለተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በሀገሪቱ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን ተከትሎ ነውጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ይህንን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫም አሁን ላይ ያለው የቫይረሱ ስርጭት አስጊ መሆኑን አስታውቅዋልስፔን በመጀመሪያው ዙር የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ ጉዳት ከረሰባቸው ሀገራት ተርታ ተሰልፋ እንደነበረ አይዘነጋምአሁንም ልክ አንደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በሀገሪቱ በርካቶችን እያጠቃ እንደሚገኝ ተነግሯልበስፔን እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን የተሻገረ ሲሆን 35 ሺህ ሰዎችንም በቫይረሱ ምክንያት አጥታለችምንጭ ቢቢሲ
https://www.fanabc.com/%e1%88%b5%e1%8d%94%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93-%e1%89%ab%e1%8b%ad%e1%88%a8%e1%88%b5-%e1%88%b5%e1%88%ad%e1%8c%ad%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%88%88%e1%88%98%e1%89%86%e1%8c%a3%e1%8c%a0/
184
4,324
ከእጃችን ሊያመልጥ ጥቂት የቀረው የአባጅፋር ቤተ መንግሥት
ሀገር አቀፍ ዜና
July 10, 2019
54
ከጅማ አናት ላይ በኩራት ተቀምጧል የጅማን ጓዳና ጎድጓዳዋን ወጭና ወራጁን ቁልቁል በትዝብት ይመለከታል የጅማን እድገትና ውድቀት ለ141 አመታት ታዝቧል ጅማን ከአፈጣጠሯ ጀምሮ ያውቃታል ስለጅማ ቃል አውጥቶ ቢናገር ከሱ በላይ የሚመሰክር አይኖርም የጅማ ከተማና የስልጣኔዋም መገለጫ ነው የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግስት ይህ ቤተ መንግስት 29 ክፍሎች 65 በሮችና 54 መስኮቶች አሉት የቀደመው ዘመን ስልጣኔ ፈስሶበታል ድንቅ የእጅ ጥበብና የአእምሮ እሳቤም አርፎበታል የእንጨት ጣውላ ጥበቡ ህሊናን ይገዛል በድንጋይ የተሰራውም ድንቅ የኪነ ህንፃ ስራን የሚናገር ጥበብ ይታይበታል የቤቱ ጣሪያ ቅርፅና ኪነ ህንፃ ስራ ያስደምማል ግድግዳው የተለሰነበት ጭቃና ቀለም ልስላሴና ውበቱ ለሚያየው አይንና ለሚዳስሰው እጅ ልዩ ስሜት ይፈጥራል በአጠቃላይ ቤተ መንግስቱ ልዩ የኢትዮጵያ የኪነ ህንፃ ውጤት ነው ለማለት የሚያስደፍር ነው ነገር ግን ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል እንደሚባለው ቤቱ ቢቆምም ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦበታል ቤተ መንግስቱ በተንከባካቢ እጦት ምክንያት ለጉስቁልና ተጋልጧል ከውጭ ያለው ግርማ ሞገስ ወደ ውስጥ ሲገባ የለም በቤቱ ውስጥ የንጉስ አባጅፋር እቃዎች የሉም ውስጡ ኦና ኦና መሽተት ጀምሯል ግድግዳውም አልፎ አልፎ ተሰንጥቋል የእንጨት ጥበቦቹም በተንከባካቢ እጦት ምክንያት መበስበስ ጀምረዋል ግድግዳው ላይ ስሜት የሚሰጠው ልስን ተፋፍቋል በአጠቃላይ የጅማው መለያ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ምሳሌ የአባጅፋር ቤተ መንግስት በጠና ታሟል በቶሎ መድሀኒት ካላገኘ ህመሙ ወደ መፍረስ እንደሚያደርሰው ያስታውቃልቤተ መንግስቱን ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ መጥተው ያገኘናቸው አቶ ብሩ ኪሮስ የአገራችን ኪነ ህንፃ ልዩ ጥበብ እንደሆነ ይናገራሉ የዛን ዘመን ጥበብ እያሳደግነው ብንመጣ ዛሬ ላይ የትበደረስን ሲሉ ይቆጫሉ ይህን የኪነ ህንፃ ጥበብ ዛሬ ላይ ተግባራዊ ማድረግ ባንችል እንኳ አለመንከባከብ ግን አሳፋሪ መሆኑን ይጠቁማሉ በቁጭት ተነስተን ቅርሶቻችንን መጠገንና መንከባከብ አለብንም ሲሉ ይናገራሉ ከደቡብ ክልል ጋሞጎፋ መጥቶ ሲጎበኝ ያገኘው አቶ ማርቆስ ማኖቴ የአቶ ብሩን ሀሳብ ይጋራል ቅርሶቻችንንና ታሪካችን ለዛሬ ማንነታችን መሰረት ናቸው በዝርዝር አውቀን እየተጠቀምንባቸው ግን አይደለም መንከባከብ አልቻልንም የአባጅፋር ቤተ መንግስትም ህንፃው ብቻ ነው በቦታው ላይ የሚገኘው በውስጡ ያሉ ቁሳቁሶች የሉም ህንፃውም ቢሆን አደጋ ላይ ነው ስለዚህ መጠገን መንከባከብና መጠቀም ይገባናል ሲልም ያሳስባል ሌላው የአዲስ አበባ ጎብኝ ወይዘሪት ሉባ መሀመድም ቤተ መንግስቱን አዲስ አበባ ሆና ያሰበችውና በአካል ያገኘችው የተለያየ እንደሆነ ትናገራለች በመሆኑም በተጎሳቆለው ቤተ መንግስት ማዘኗንና መከፋቷንም ትናገራለች መንግስት ለዚህ ትልቅ ቅርስ ትኩረት አለመስጠቱ ሚዛን የማይደፋ ነው አሁን በቶሎ ካልተጠገነ ለልጆቻችን ማውረስ አንችልምና አፋጣኝ ምላሽ ያስፈልጋል ትላለች የቤተ መንግስቱ አስጎብኝና ጊዜያዊ ተጠሪ አቶ ክብሩ ተስፋዬ ለቤተ መንግስቱ ችግር ላይ መውድቅ ጥናት ላይ ሳይመሰረት በየጊዜው የተደረገው ጥገና እንደሆነ ያመላክታሉ እሳቸው እንደሚሉት ቤተ መንግስቱ በ1984 አም ያለጥናት በጣራው ላይ በተደረገው እድሳት ረጅም የነበረውን የህንፃው ጣሪያ ጌጡ እየታየ አይደለም ይህ ደግሞ በግድግዳው ላይ ፀሀይና ዝናብ እንዲፈራረቅበት አደረገ በተለይም ዝናቡ ግድግዳውን ሲያረጥበው ምስጥ በመፍጠሩ የተሰራበት እንጨት በምስጥ እንዲበላ ምክንያት ሆነ በ1994 እና በ2002 አም የተደረገው ጥገናም ጎርፍ ወደ ቤተ መንግስቱ እንዲገባ በማድረጉ መሰረቱና ህንፃው እንዲሰነጠቅ ምክንያት ሆኗል የአሜሪካ ኤምባሲ ቤተ መንግስቱ አደጋ ላይ መሆኑን ተገንዝቦ የክልሉ መንግስትና የፌዴራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በወርልድ ሞንመንት ከተባለ ድርጅት ጋር ስምምነት ተደርጎ ወደ ስራ ተገብቶ ነበር የውጭ አገር ባለሙያዎችም መጥተው ጥናት አድርገዋል እስከ ሰኔ 2011 አም ስራው እንደሚጀመርም ለህዝብ ይፋ ተደርጎ ነበር እስካሁን ግን ስራው አልተጀመረም ቅርሱ ግን እየፈረሰ ነው ከሁለትና ሶስት ወራት በፊት ጎብኚዎች ፎቅ ላይ ወጥተው ይጎበኙ ነበር አሁን ላይ ግን አይቻልም በዚህ ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ ከቆየ መፍረሱ አይቀርም ሲሉ ያላቸውን ፍራቻ ይገልፃሉ ቤተ መንግስቱ ቀደም ሲል ያረፈው 40 ሄክታር መሬት ላይ ነበር በአሁኑ ወቅት ግን 1ነጥብ5 ሄክታር ብቻ ነው ያለው ይህም ሌላው ቤተ መንግስቱን ለጎብኚዎች ምቹ ያላደረገ ነው ከዚህም በተጨማሪ በመንግስት ለውጥ ወቅት ግርግር ስለነበረ ቤተ መንግስቱን የመዝረፍ ሙከራ ሲደረግበት የአባጅፋር የመጨረሻ ልጅ በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያለውን እቃ ለመንግስት አስረክበዋል ቅርሶቹ ወደዚህ ሳይመለሱ በጅማ ሙዚየም ይገኛሉ ቤተ መንግስቱ ከተጠገነ ቅርሶቹን ወደዚህ የመመለስ እቅድ ቢኖርም ጥገናው ባለመከናወኑ ቤቱ ባዶ ነው የቅርስና ጥናት ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብ እና አለም አቅፍ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ፋንታ በየነ በአሜሪካ መንግስት ድጋፍ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣንና ከወርልድ ሞንመንት ጋር በመተባበር ጥገና ለማድረግ ስምምነት ተደርጎ ባለፈው አመት ጥቅምት ወር ስራው በይፋ መጀመሩን ይናገራሉ ሆኖም ወርልድ ሞንመንት ወደ ጥገና ከመገባቱ በፊት ተጨማሪ ጥናት ያስፈልጋል በማለቱ ጥናት ተደርጓል በዚህም መሰረት አሁን ላይ ጥገና ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እየተገዙ ነው በቅርብ ጊዜ ጥገናው ይጀመራል በተገባው ውልና ቃል መሰረት ወደ ጥገና ያልተገባው ጥገናውን የሚያካሂደውን ድርጅት እኛም ማስገደድ ስላልቻልን ነው በውሉ ላይ ጥገናውን ለማጠናቀቅ አንድ አመት ከ6 ወራት የሚፈጅ በመሆኑ ድርጅቱ በውሉ መሰረት እንደሚያጠናቅቅ እምነት አለን ይላሉ አሁን ላይ የሚደረገው ጥገና ከዚህ ቀደም እንደተ ደረገው ችግር አያመጣም ወይ ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄም ችግር አለማምጣቱን መቶ በመቶ ማወቅ አይቻልም ጥገናውን የሚያከናውነው አለም አቀፍና ልምድ ያለው ድርጅት በመሆኑ በጥሩ ሁኔታ እንደሚጠግነው እምነት አለን ብለዋል በአለም አቀፍ ደረጃም ከሱ የተሻለ ድርጅት አለ ለማለት እንደሚቸገሩም ተናግረዋልአዲስ ዘመን ሀምሌ 32011አጎናፍር ገዛኸኝ
https://www.press.et/Ama/?p=13802
689
27,440
ወልቂጤ ከተማ አጥቂ ለማስፈረም ተስማማ
ስፖርት
August 28, 2020
Unknown
ወልቂጤ ከተማ የአጥቂ መስመር ተሰላፊው አሜ መሀመድን ለማስፈረም ተስማምቷልየቀድሞው የጅማ አባ ቡና እና ኢትዮጵያ ወጣት ቡድን አጥቂ አባ ቡናን ወደ ፕሪምየር ሊግ በማሳደጉ ወሳኝ ሚና የተጫወተ ሲሆን በሊጉ ያሳየውን ጥሩ እንቅስቃሴ ተከትሎ በ2009 ክረምት ነበር ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያመራው በፈረሰኞቹ የተጠበቀውን ያህል የተሰላፊነት እድል ያላገኘው አሜ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከቡድኑ ጋር በመለያየት ወልቂጤን ለመቀላቀል ተስማምቷል ጫላ ተሺታን በማጣታቸው የተፈጠረውን ክፍተት ይሸፍናል ተብሎም ይጠበቃልባለፈው የውድድር አመት ክስተት የነበረው ረመዳን የሱፍ ጨምሮ ስድስት ተጫዋቾች ለማስፈረም የተስማሙት ወልቂጤዎች ቀደም ብለው የበርካታ ነባር ተጫዋቾች ውልም ማራዘማቸው ይታወሳል
https://soccerethiopia.net/football/59710
83
35,139
Ramkel Lok joins Kidus Giorgis
ስፖርት
August 28, 2015
Unknown
agreed to sign striker Ramkel Lok for an undicloseed fee Ramkel will pen a 2 years contract Nonetheless the player told the Radio that he is no longer pursuing the dream to go to Portugal instead he wants to show his worth in Ethiopia firstRamkel at first rumored to join Giorgiss arch rival Ethiopia Bunna Although the proposed move was off Ramkel is now at Adama for preseason preparation with GiorgisIt is expected that he will sign a contract in the coming days Ramkel previously played for Electric He is the cousin of Ethiopian international and Ethiopia Bunna midfielder Gatoch Panom 
https://soccerethiopia.net/football/3751
101
18,035
 በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
ሀገር አቀፍ ዜና
Feb 4, 2020
499
አዲስ አበባ ጥር 26 2012 ኤፍ ቢ ሲ በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሰጎ እና የሲሌ ወንዝ በመሙላቱ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ የንብረት ጉዳት ደረሰበአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ትላንት ለሊት የጣለውን ዝናብ  ተከትሎ የሰጎ እና ሲሌ ወንዝ በመሙላቱ ቆላ ሸሌ ቤሌ ንኡስ ሸሌ ሜላ እና ኤልጎ ቀበሌዎች ላይ   የጎርፍ አደጋ  ተከስቷልበዚህም  በቀበሌው የሚገኙ አብዛኛው ቤቶች በውሀ ተውጠዋል የቤት ንብረት ወድሟል በማሳ ላይ ያለ ቋሚ ሰብል እና ንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል ነው የተባለውበቀበሌዎቹ ሰብአዊ እርዳታ በፍጥነት ለማድረስ እንቅስቃሴ መጀመሩን ከጋሞ ዞን አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታልበተያያዘ ዜና በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ እየጣለ ባለው ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ በተከሰተ የመሬት ናዳ የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿልበአደጋው የሰው ህይወት ከመጥፋቱ ባሻገር 170 ቤተሰቦች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋልተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ነው የተባለውወቅቱን ያልጠበቀው ዝናብ በመቀጠሉ ምክንያት ተመሳሳይ አደጋ ሊደርስ ይችላል ተብሎ በተገመቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖችን የማንሳት ስራ መሰራቱ ተገልጿልእንዲሁም በዞኑ ከፍታማ ቦታዎች እና ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ዞኑ አሳስቧል
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%88%ad%e1%89%a3%e1%88%9d%e1%8a%95%e1%8c%ad-%e1%8b%99%e1%88%aa%e1%8b%ab-%e1%8b%88%e1%88%a8%e1%8b%b3-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%b0%e1%89%b0-%e1%8b%a8%e1%8c%8e%e1%88%ad/
161
42,174
በኢሚግሬሽን ጉዳይ ዋይት ኃውስ ለምክር ቤት አስታራቂ ሀሳብ አቀረበ
ዓለም አቀፍ ዜና
January 26, 2018
Unknown
ኢሚግሬሽንን በተመለከተ ዋይት ሀውስ ትናንት አንድ አስታራቂ ሀሳብ ለምክር ቤት አባላት ማቅረቡ ተገለፀለምክር ቤቱ አባላት የቀረበው ይህ አስታራቂ ሀሳብ ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መጥተው በጥገኛነት ለሚኖሩና ድሪመርስ በመባል ለሚታወቁ 18 ሚሊዮን ህፃናት ከአንዳንድ ቅድመ ሁኔታ ጋር ዜግነት የማግኘት እድል እንዳለውም ታውቋልበዳካ ፕሮግራም አማካኝነት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንዲኖሩ የተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎችና እንደ ስራ ትምህርትና ጥሩ ስነምግባር የመሳሰሉትን መስፈርቶች ጨምሮ ከ10 12 አመት ባለው ጊዜ የዜግነት ጥያቄ ማቅረብ እንደሚቻልም ተመልክቷልፕሬዚዳንት ትራምፕ ይህን ያቀረቡትን ሀሳብ በተመለከተ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በሰጡት ፍንጭ እነዚህ 18 ሚሊዮን ህፃናት ሊጨነቁ እንደማይገባቸው ገልፀዋል
https://amharic.voanews.com//a/white-house-proposes-high-price-tag-on-border-wall-long-road-to-dreamers-citizenshiop-1-26-2018/4226397.html
85
49,651
መሪዎቹ የሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክን እየጎበኙ ነው
ቢዝነስ
March 1, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት እያደረጉ ነውየሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ጉብኝቱ የሚካሄደው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር በማሰብ ነውባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተመሳሳይ በኬንያ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳልበዚህም መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድ ትስስራቸውን በተለይም በሀገራቱ አየር መንገዶች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋልከጉብኝቱ በተጨማሪም በኬንያ ታስረው የነበሩ ኢትዮጵያውያን እንዲፈቱ መደረጉም የሚታወስ ነው
https://waltainfo.com/am/23737/
79
15,210
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 73 ሺህ አለፈ
ሀገር አቀፍ ዜና
Sep 28, 2020
473
አዲስ አበባ መስከረም 17 2013 ኤፍቢሲበኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 73 ሺህ ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋልባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 631 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 632 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሚኒስቴሩ  አስታውቋልበአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 73  ሺህ 332 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመላክታልከዚያም ባለፈ ባለፉት 24  ሰአታት ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ 5 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 170 መድረሱንም ተመላክቷልበ24 ሰአታት ውስጥ 330 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 30 ሺህ 363ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል41  ሺህ 797 ሰዎች በአሁን ወቅት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሲሆን 249 ፅኑ ህሙማን ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏልበኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 256 ሺህ 182 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%89%a0%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93-%e1%89%ab%e1%8b%ad%e1%88%a8%e1%88%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8b%ab%e1%8b%99-%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd-6/
122
12,400
በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ለመለየት ክትትል እየተደረገ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
31 መጋቢት 2020
Unknown
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በትናንትናው እለት ባደረገው 66 ተጨማሪ ምርመራ ሁለቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ግለሰቦች በአማራ ክልል ነዋሪ መሆናቸውን አስታውቋልይህንንም ተከትሎ ከታማሚዎቹ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲሁም ንክኪ ይኖራቸዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎችን የመለየትና የክትትል ሂደት እየተከናወነ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶር ፋንታ ማንደፍሮ ገልፀዋልበቫይረሱ የተያዙት ግለሰቦች በአማራ ክልል ባህር ዳር ነዋሪ የሆኑ የ37 አመት ሴትና በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የአዲስ ቅዳም ነዋሪ የሆኑ የ32 አመት ወንድ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውም ተገልጿል ግለሰቦቹ መንግስት ያዘዘው የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ እለት አስቀድሞ ከዱባይ እና ከአሜሪካ የገቡ ሲሆን የበሽታውን ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ ምርመራ ተደርጎላቸዋል በምርመራው መሰረትም መያዛቸው ተረጋግጧል ብሏልበተለይም ከአሜሪካ የመጣው ግለሰብ እንኳን ደህና መጣህ በሚሉ በርካታ ሰዎች መጎብኘቱን ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲጋሩት ነበር የሚለውን ቢቢሲ ጠቅሶ ለዶር ፋንታ ጥያቄ ሰንዝሮላቸዋል በምላሻቸውም ግለሰቡ መጋቢት 12 ከአሜሪካ መጥቶ ወደ አዊ ዞን ደግሞ መጋቢት 15 መሄዱን ማረጋገጣቸውን ገልፀው አቀባበል ነበር የሚለውን የዞኑ አስተዳደር ሀላፊነት ወስዶ ከጤና ባለሙያዎች ጋር እያጣራን ነው ብለዋል አቀባበል ከነበረ የሚደበቅ ነገር የለውም በሽታው በንክኪ የሚተላለፍ ስለሆነ በሽተኛውም ቤተሰቦቹን የሚደብቅ አይመስለኝም ጉዳዩ ሌሎችን የመርዳት ነው የተጠቁ ካሉ ጥንቃቄ አድርገው ራሳቸውን ረድተው የሚሸጋገሩበትን ለማመቻቸት ስለሆነ እንደሚስጥር ይታፈናል ብዬ አላምንም ተደርጎ ከሆነ እነዚህ ሰዎች መረዳት አለባቸው ሌላውን ወገናቸውን እና ቤተሰባቸውን እንዳይበክሉ የመለየት ስራ እየሰራን ነው ብለዋል ሁለቱም ታማሚዎች በአማራ ክልል የለይቶ ህክምና መስጫ ማእከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኝ ሲሆን እስከ ትላንት ምሽት ድረስ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ በተጫማሪ አስረድተዋልበክልሉም እስከ ትላንት ድረስ 27 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በምርመራው መሰረት ሁለቱ ቫይረሱ እንዳለባቸው ሲረጋገጥ ሌሎቹ ነፃ መሆናቸው መረጋገጡን ዶር ፋንታ አስረድተዋል የአለም ጤና ድርጅትም ሆነ የተለያዩ የጤና ሚኒስትሮችም ሆነ ባለሙያዎች አበክረው እንደሚናገሩት ዶር ፋንታም ግለሰቦች አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንዲሁም ንክኪን ማስወገድ መፍትሄ እንደሆነና በተለይም ምልክቱ ስለማይታይ ከቫይረሱ ነፃ የመሆን ማረጋገጫ አይደለም ብለዋል ከቫይረሱ ነፃ ነን ለማለት በምርመራ ብቻ የምናረጋግጠው ነው በማለት አስረድተዋልበተለይም 27 ሰዎች ተጠርጥረው ምርመራ መደረጉና 25 ነፃ መሆናቸውና ሁለት ሰዎች መገኘታቸው ቫይረሱ ተዛምቷል ወይም አልተዛመተም የሚለውን ሳይሆን የሚያሳየው ዶር ፋንታ እንደሚሉት ቁጥሩ ተጠርጥረው ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤታቸው የታወቁትን ብቻ የሚያሳይ መሆኑን አስታውቀዋል ከማህበረሰብ ስንቱ ተጠቅቷል ስንቱ አልተጠቃም የሚለውን እንዲሁም በክልሉ ያለው ሁለት ብቻ ነው ለማለት የክልሉን ህዝብ መመርምረን ነው ያንን መናገር የምንችለው ብለዋልበቀጣዪም በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማካሄድ እየተሰራ መሆኑንም ዶር ፋንታ ገልዋል ከክልሉ ወደ ፌደራል ማእከል ከመላክ እዚሁ ለመጀመር የሚያስችል አንድ ማሽን አግኝተን ሶፍት ዌር ኮንፊገሬሽን እየተሰራ ነው እሱ እንዳለቀ ክልሉ እዚሁ ናሙና እየተወሰደ ውጤቱን በአጭር ከዚሁ የምንሰማበት ቀን በቅርብ ይኖራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን በማለት አስረድተዋልበቅርቡ ከውጭ ሀገራት የመጡ ግለሰቦች ሪፖርት እንዲያደርጉ ክልሉ ትላንት ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ምን ያህል ሰዎች ሪፖርት እንዳደረጉ ተጠይቀው እስካሁን ሪፖርቱ እንዳልደረሳቸው አስታውቀዋል
https://www.bbc.com/amharic/52106873
401
14,563
የኢንዱስትሪ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ውህደት ፈጸሙ
ሀገር አቀፍ ዜና
Nov 2, 2020
141
አዲስ አበባ ጥቅምት 23 2013 ኤፍ ቢ ሲ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን በይፋ ውህደት ፈፀሙ
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%8b%b1%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%aa-%e1%8a%a0%e1%88%b0%e1%88%aa%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8a%ae%e1%8a%95%e1%8d%8c%e1%8b%b4%e1%88%ac%e1%88%bd%e1%8a%95%e1%8a%93-%e1%8b%a8/
20