Unnamed: 0
int64
0
51.5k
headline
stringlengths
2
861
⌀
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
6
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
1
34.3k
⌀
link
stringlengths
28
722
word_len
int64
0
6.74k
48,475
ኢትዮጵያ ለሁለቱ ሱዳኖች መረጋጋት እየሰራች ነው
ፖለቲካ
August 1, 2013
Unknown
ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ችግራቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችውን ድጋፍ እንደሚያደንቅ በአውሮፓ ህብረት የሱዳንና ደቡብ ሱዳን ልዩ ልኡክ ሚስስ ሮዛሊንድ ገለፁልዩ ልኡኳ ይህን ያስታወቁት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ አድሀኖም ጋር የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልቶ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ነውየሰላም ሂደቱን ለማገዝ የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ጦር በአብዬ ግዛት መሰማራቱንም ህብረቱ እንደሚያደንቅ ሚስስ ሮዛሊንድ ተናግረዋልሁለቱ ሀገራት አሁን ካሉበት ውጥረት በመውጣት ችግራቸውን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ ከኢትዮጵያና ከአፍሪካ ህብረት ጋር እንደሚሰሩም ልዩ ልኡኳ ገልፀዋልየኢሬቴድ
https://waltainfo.com/am/27952/
74
39,398
የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኤርትራን ከሰሱ
ዓለም አቀፍ ዜና
October 02, 2015
Unknown
የጅቡቲ ፐሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ኤርትራን ባልተገባ ባህርይና በነገረኛነት ከስሰዋልለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር ፕሬዚዳንቱ ይህንን ክሳቸውን ያሰሙት ፕሬዚዳንት ጌሌ ኤርትራ ለአካባቢውና በአጠቃላይም ለአለምአቀፉ ማሀበረሰብ አደጋ ነች ብለዋልበአውሮፓ አቆጣጠር ከ2008 አም አንስቶ የኤርትራ ወታደሮች የሰሜናዊ ግዛቶቻቸውን አንዳንድ አካባቢዎች ያለአግባብ ከተቆጣጠሩ በኋላ በዚህም አመት ውጥረትና ውዝግቡ መቀጠሉን የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ተናግረዋልየመንግስታቸው ባለስልጣናትና እራሳቸውም በተደጋጌሚ ጉዳዩን ለማስረዳት ወደ ኒው ዮርክ መመላለሳቸውን አመልክተዋልሀገራቸው በሰላም በሽምግልናና በድርድር እንደምታምን የተናገሩት ፕሬዚዳንት ጌሌ የተክለ ግዛታችን የማይደፈር መሆን ግን ለድርድር የሚቀርብ አይደለም ብለዋልየኤርትራ መንግስት ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ የአካባቢው ብቸኛና ዋነኛ ያለመረጋጋት ምክንያት የኤርትራን ሏላዊ ግዛቶች በሀይል ይዛ ያለችው ኢትዮጵያ ናት ብሏልከጅቡቲ ጋር የገቡበት የድንበር ውዝግብ ጉዳይ በጋራ ለተስማሙባቸው ሶስተኛ ወገን አካላት የቀረበ መሆኑን የኤርትራ መንግስት ባለፈው የካቲት መጀመሪያ አውጥቶት በነበረ መግለጫ ተናግሮ የነበረ ሲሆን ንግግሩ በጥሩ ሁኔታ ተይዞ እያለ ብስለት የሌለውና በጎ መንፈስ የራቀው የጅቡቲ አቋም ለማስረዳት አስቸጋሪ ነው ብሏልለተጨማሪ ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡየጅቡቲ ፕሬዚዳንት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባኤ ያደረጉትን ንግግር ለመስማት ከዚህ ስር ያለውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ
https://amharic.voanews.com//a/djibouti-presiend-ismail-omar-guelleh-slammed-erritrea-10-01-15/2987889.html
157
44,695
ዙምባብዌ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ወደ አገሯ እንዳይገባ እገዳ ጣለች
ቢዝነስ
October 19, 2017
Unknown
ዙምባብዌ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ወደ አገሯ እንዳይገባ  እገዳ መጣሏን  አስታወቀች    ዙምባብዌ  የበቆሎ ምርት ወደ ሀገሯ እንዳይገባ በሰኔ ወር ላይ እገዳ ጥላ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ  ወደ ሀገሪቱ በምታስገባቸው  የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ላይ ሌላ እገዳ ጥላለች ዙምባብዌ ባላፈው አመት ከሰማንያ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ወደ ሀገር ውስጥ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን አስገብታለችእነዚህ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ድንች ካሮት ማንጎ ብርቱካን እና ሌሎችን እንደሚያጠቃልል ነው የሀገሪቱ የስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ  ያመላከተውየሀገሪቱ የግብርና ሚኒስትር ጆሴፍ ሜድ  ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚጠይቁ መሆናቸውን ገልፀው ሀገሪቱ አሁን ባጋጠማት የውጭ ምንዛሪ እጥረትም  የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከውጭ የሚገቡ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች እንዲቆሙ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን አስታውቀዋልእገዳው የተጣለው የሀገሪቱ አርሶ አደሮች ምርታቸውን በማሳደግ የውጭ ምንዛሬን መታደግ እንዲችሉ ነው ተብሏልየሀገሪቱ የግብርና ሚኒስትር የእገዳው መጣል ዚምባብዌ የሀገር ውስጥ ምርቶቿን እንድታሳድግ አስተዋፆኦ ይኖረዋል ብለዋልበተለይም የሀገሪቱ አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን በማሳደግ የውጭ ምንዛሪውን እንዲታደጉ ያስችላቸዋልም ነው የተባለው በተቃራኒውም ምርቶቿን የምታቀርበው ደቡብ አፍሪካ ላይ የሚፈጥረው ተፅእኖም ቀላል አለመሆኑን አስረድተዋልእገዳው በአስቸኳይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ገልፀው የሚመለከታቸው አካላትም ለገበያ የማይቅረቡ ከውጭ የሚገቡ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ዝርዝር በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ ሮይተርስ ዘግቧል
https://waltainfo.com/am/32854/
171
21,587
የተሻሻለው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ረቂቅ ለውይይት ቀረበ
ፖለቲካ
7 July 2019
Unknown
የተቀላጠፈና ፈጣን የወደብ አገልግሎት ማግኘት ለኢትዮጵያ ወሳኝ በመሆኑ የወደብ ጉዳይ የአገሪቱ ውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ቁልፍ ጉዳይ እንደሆነ ከባለወደብ አገሮች ጋር ዘላቂ የወደብ አገልግሎትና የባህር በር መዳረሻ የማግኘት መብቷን በሚያረጋግጡ አለም አቀፍና ቀጣናዊ ትብብሮች ላይ በትኩረት እንደምትሰራ የሚያትተው ረቂቅ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ለውይይት ቀረበጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዶር ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በተለያዩ ህጎችና ፖሊሲዎች ላይ ማሻሻያዎች ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ የሚገለፅ ሲሆን የዚህ ሂደት አካል የሆነውና በ1994 አም የወጣውን የውጭ ጉዳይና የአገራዊ ደሀንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ የሚተካ አዲስ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት የተዘጋጀ ነውየኢትዮጵያን አገራዊ ህልውናና ደሀንነትን ማስጠበቅ ዋነኛ ማጠንጠኛው እንደሆነ የሚገልፀው ረቂቅ ሰነዱ የውጭ ግንኙነትና አገራዊ ደሀንነት ፖሊሲ በ1994 አም ከወጣ ጊዜ ጀምሮ የተከሰቱ አዳዲስ አዝማሚያዎችንና በቋሚነት የቆዩ ጉዳዮችን  ከግምት ውስጥ በማስገባት አምስት ዋና ዋና ጉዳዮችንና አዝማሚያዎችን በመነሻነት መውሰዱ በረቂቅ ፖሊሲው ተመላክቷልበረቂቅ ፖሊሲው እንደ መነሻነት የተወሰዱት አምስት ዋና ዋና አዝማሚያዎችና ጉዳዮች ደግሞ አገራዊ ግንባታ አገራዊ ክብር የዜጎች መብትና ድንነት ማስጠበቅ ቀጣናዊ የጂኦፖለቲካ ሁኔታ ቀጣናዊ ውህደትና አለም አቀፋዊ ሁኔታና አዝማሚያዎች የሚሉ ናቸው አገራዊ ግንባታን በተመለከተ ረቂቅ ፖሊሲው በኢፌዴሪ ህገ መንግስት የተቀመጠው የጋራ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማሀበረሰብ የመገንባት ራእይ ገና ያልተጠናቀቀ ስራ በመሆኑ ይህንን ራእይ ለማሳከት የሚያስችሉ ሰላምና ደሀንነትን ማስጠበቅ የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ተግባራት ያለመታከት ማከናወን ፈጣንና ዘላቂነት ያለው ልማት ማረጋገጥና ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማስፈን ይህ ፖሊሲ እንደ መነሻ የሚወስደው ቀዳሚ ጉዳይ ሆኖ ይቀጥላል በማለት ከዋነኛ ማጠንጠኛዎች መካከል አገራዊ ግንባታ በግንባር ቀደምትነት እንደሚቀመጥ በማተት የአገር ውስጥ ጥንካሬና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረና በዋናነት ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲን እንደሚያራምድ ያስረዳልአገራዊ ክብርን በተመለከተ ደግሞ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛና የቀደምት ስልጣኔዎች ባለቤት መሆኗ በቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ አፍሪካዊ አገር ሆና መቆየቷ የተለያዩ የእምነት ተከታዮች በመከባበር የሚኖሩባት አገር መሆኗ የአገሪቱ የስኬት ምንጭ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል እንደሆኑ በመጥቀስ እስካሁን የተሳኩ ውጤቶችን እንደ መነሻና ማስፈንጠሪያ በመጠቀምና ያሉትን ክፍተቶች በማረም ወደ ላቀ የእድገትና የስልጣኔ ደረጃ መሻጋገር የፖሊሲው መነሻ ሆኖ እንደሚቀጥል ረቂቅ ሰነዱ ያመለክታልየዜጎች መብትና ደሀንነትን ማስጠበቅ በሚመለከት ዜጋ ተኮር የውጭ ግንኙነት ፖሊሲና የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ማካሄድ እንደ መነሻነት መወሰዱ የተገለፀ ሲሆን ዜጎች በአገራቸው ጉዳይ ላይ ባለድርሻ እንዲሆኑና በየሚኖሩበት አገር የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ሆነው እንዲያገለግሉ ማበረታታት ኢትዮጵያዊነትን ማእከል ያደረገ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማሀበረሰብን መገንባትና ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣት የሚያስችል ውስጣዊና ውጫዊ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት አገር መብታቸውና ጥቅማቸው እንዲከበር መስራት የረቂቅ ፖሊሲው መነሻ ሆኖ መወሰዱን ያትታልቀጣናዊ የጂኦፖለቲካ ሁኔታና ቀጣናዊ ውህደትን በሚመለከት ደግሞ በቀጣናው ዙሪያ የሚታየው ለውጥ የአገራችን ደሀንነትና ብሄራዊ ጥቅም ስጋት እንዳይሆን የሚያደርግ ዘላቂነት ያለው ፈጣን የወደብ አገልግሎት የማግኘት መብታችንን ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ መስራት ያስፈልጋል በማለት ረቂቅ ሰነዱ ይገልፃል  ከዚህ በተጨማሪም በቀጣናው በአሀጉርና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያጋጥሙንን ተግዳሮች ለመፍታት የሰላምና ደሀንነት ማስጠበቅ ተልእኮዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፖሊሲው በአገሮች የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ያለመግባት መርህ የተከተለ ዲፕሎማሲ የሚያራምድ ይሆናል ሲልም ያትታል በዚህም መሰረት ረቂቅ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲው የሰላም ዲፕሎማሲ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ወቅታዊ አለም አቀፍ ጉዳዮችና ቀጣናዊ አሀጉራዊና አለም አቀፋዊ ጉዳዮችን እንደ ስትራቴጂ መውሰዱን ያትታልበ1994 አም የወጣው ፖሊሲ ኤርትራን በተመለከተ በዝርዝር የሚያትትና የኤርትራ መንግስትንም ጀብደኛ በማለት ይገልፀው የነበረ ሲሆን ለውይይት በቀረበው ረቂቅ ፖሊሲ ግን ጎረቤት አገሮች ከሚል ጥቅል ማብራሪያ በዘለለ በእያንዳንዱ የጎረቤት አገር ስም ስለተዘጋጀው ዝርዝር የግንኙነት ማእቀፍ የሚገልፀው የለም የውጭ ግንኙነት ፖሊሲው ለጎረቤት አገሮች ልዩ ትኩረት ይሰጣል በማለት ከጎረቤት አገሮች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት በግርድፉ ይገልፃል ረቂቅ ፖሊሲው አዳዲስ አለም አቀፍ ክስተቶችንና ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ሲሆን በረቂቁ ውስጥም የአየር ንብረት ለውጥን ፍልሰትንና ስደተኛነትን የሳይበር ጉዳይንና የጠፈር ሳይንስ ጉዳይን በተመለከተ አገሪቱ የምትከተላቸውን አቅጣጫዎችን ያመላክታል   
https://www.ethiopianreporter.com/article/16108
513
36,468
የደቡብ ክልሉን ቀጣይ አከላለልና ዕጣ ፈንታ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 25, 2019
Unknown
ደቡብ ክልል አንድ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ የመጀመሪያና የተሻለ አማራጭ ተብሎ በጥናቱ ቀርቧልበጥናቱ በሁለተኛ አማራጭነት የቀረበው ደግሞ በምትኩ ከሁለት እስከ አምስት የሚደርሱ አዳዲስ ክልሎችን መፍጠር ነውእስክንድር ፍሬው በዛሬው ውይይት ላይ ተሳታፊ የነበሩ ምሁራን አስተያየት የያዘ ዘገባ ይዟል
https://amharic.voanews.com//a/snnpr-research-reaction-7-25-2019/5015315.html
36
18,971
ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲያካሂድ የቆየው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ እክል ገጠመው
ዓለም አቀፍ ዜና
Sep 9, 2020
940
አዲስ አበባ ጳጉሜን 4 2012 ኤፍቢሲ  ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲያካሂድ የቆየው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ እክል እንደገጠመው አስታወቀዩኒቨርሲቲው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ሙከራዎቹን በስኬት ማጠናቀቁ የሚታወስ ነውይህንንም ተከትሎ ኦክስፎርድ ከአስትራዜኒካ ጋር በመሆን ወደ ሶስተኛውና መጨረሻ የሙከራ ደረጃ ተሸጋሯልሆኖም በሶስተኛ ደረጃ ሙከራው እንዳረጋገጠው ፍቃደኛ ተሳታፊዎች ህመም እንደገጠማቸው ነው የገለፀውበዚህ ምንነቱን እስከ አሁን ባልገለፁት ህመም ምክንያት ሙከራውን ማዘግየታቸውን ነው ያሳወቁትየክትባቱ ሙከራ እክል ሲገጥመው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተነግሯልእስከ አሁን ድረስ ከአሜሪካ ብሪታንያ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ 30 ሺህ ሰዎች ተሳትፈዋልየዩኒቨርሲቲው ቃል አቀባይ እንደዚህ አይነት ሰፊ ሙከራዎች ሲካሄዱ ህመም ሊያጋጥም እንደሚችል ገልፀው ነገር ግን በጥንቃቄ አካሄዶ መመርመር ይገባል ሲሉ ነው የተናገሩትቃልአቀባዩ ሙከራው ዳግም በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚጀመርም ተስፋ ሰጥተዋልይህ በአለም ዙሪያ ተስፋ ከተጣለባቸው የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች መካከል ዋነኛው እንደነበር ይነገራልየአለም ጤና ድርጅት በአለም ዙሪያ 180 የሚደርሱ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች ሙከራ ላይ መሆናቸውን ገልጿል ምንጭ ቢቢሲ
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a6%e1%8a%ad%e1%88%b5%e1%8d%8e%e1%88%ad%e1%8b%b5-%e1%8b%a9%e1%8a%92%e1%89%a8%e1%88%ad%e1%88%b2%e1%89%b2-%e1%88%b2%e1%8b%ab%e1%8a%ab%e1%88%82%e1%8b%b5-%e1%8b%a8%e1%89%86%e1%8b%a8%e1%8b%8d/
131
15,630
የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ የሚዲያ ዘርፉን ለማሳደግና አቅምን ለመገንባት አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
Aug 27, 2020
179
አዲስ አበባ ነሀሴ 21 2012 ኤፍቢሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በስራ ላይ እንዲውል የተወሰነው የመገናኛ ብዙሀን ፖሊሲ የሚዲያ ዘርፉን ለማስፋፋት ለማሳደግ ለመደገፍና አቅምን ለመገንባት አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር ነው ተባለየብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ የወንድወሰን አንዷለም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ የመገናኛ ብዙሀን ፖሊሲው ሚዲያው ለሀገር ማበርከት ያለበትን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት የጎላ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋልእንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ወንድወሰን አንዷለም ገለፃ የሚዲያ ዘርፉ በፖሊሲ ማእቀፍ ያለመመራት በበዙ ችግሮች እንዲተበተብ አድርጎት ቆይቷልማንም እንደፈለገ አፍራሽ እና ልክ ያልሆኑ እሳቤዎች የሚዲያ ዘርፉን መርህ ባልተከተለ መልኩ ሲያንሸራሽርበት መቆየቱንም ይናገራሉእንደ አቶ የወንዶሰን አንዷለም ገለፃ አዲሱ የሚዲያ ፖሊስ  በአጠቃላይ የሚዲያ ዘርፉን ለማስፋፋት ለማሳደግ ለመደገፍና አቅምን ለመገንባት አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር ነው ብለዋልትውልደ ኢትዮጵያዊያንም የመገናኛ ብዙሀን ባለቤት የሚሆኑበትን እድልን የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል22 ዋና ዋና ሀሳቦች የተካተቱበት ፖሊሲው የመገናኛ ብዙሀን ነፃነትን የሚጠብቅ ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያደርግ እንዲሁም የኢኮኖሚ አቅማቸው እንዲጎለብት የሚያስችል ነው ሲሉም ገልፀዋልየመገናኛ ብዙሀን ባለቤትነት የመገናኛ ብዙሀን መሰረተ ልማት ብዝሀነት ስብጥርና አመራርንም በተመለከተ ፖሊሲው ሊተገበሩ የሚገባቸውን አካሄዶችን መፈተሹን አመልክተዋልበተጨማሪም ሀይማኖታዊ መገናኛ ብዙሀንም ለመጀመሪያ ጊዜ በፖሊሲው የተካተቱና ተመዝግበው ፈቃድ የሚያገኙ ሲሆን እስካሁን የነበሩት ህጎች እውቅና የሚሰጧቸው ስላልነበሩ ህግና ስርአትን ጠብቀው እንዲሰሩ ይደረጋል ነው ያሉትፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል በንግድና በህዝብ መገናኛ ብዙሀን መካከል እንዲኖር ለማድረግ የመንግስት ማስታወቂያዎችም በእኩል ደረጃ መሰራጨት እንዲችሉ አቅጣጫ ማስቀመጡንም ገልፀዋልመገናኛ ብዙሀን የኢኮኖሚ ጫና እንዳይደርስባቸው በፖሊሲው የተቀመጡ ነጥቦች መኖራቸውን የህትመት ዋጋ የሚቀንስበትና ተሳትፏቸው የሚጎለብትበት ሁኔታ መኖሩንም አመልክተዋልበቀጣይነትም የሚወጡ ዝርዝር መመሪያና ህጎች እንደሚኖሩም ምክትል ዳይሬክተር አቶ የወንድወሰን አንዷለም ተናግረዋልበአፈወርቅ አለሙFBCየዜና ሰአት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልእክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ 
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8c%88%e1%8a%93%e1%8a%9b-%e1%89%a5%e1%8b%99%e1%88%83%e1%8a%95-%e1%8d%96%e1%88%8a%e1%88%b2-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%b2%e1%8b%ab-%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%8d%89%e1%8a%95-%e1%88%88/
239
50,931
በሳዑዲ ነዳጅ ማጣሪያ ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ኢራንን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ገለጹ
ፖለቲካ
September 26, 2019
Unknown
በቅርቡ በሳኡዲ አረቢያ ሁለት የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት ላይ ለተፈፀመው ጥቃት ኢራንን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ገለፁፕሬዝዳንቱ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረውን ውጥረት አስመልክተው ከፎክስ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ በቅርቡ በሳኡዲ አረቢያ የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት ላይ የተፈፀመው ጥቃት በኢራን የተወሰደ እርምጃ መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አለመቅረቡን አንስተዋልበመሆኑም ተጨባጭና ተአማኒ መረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ኢራንን ብቻ ለጥቃቱ ተጠያቂ ማድረግ ውጤቱ የከፋ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመዋልበአንፃሩ ጥቃቱ የተፈፀመው ከተለያዩ የየመን አካባቢዎች በመጡ የሁቲ አማፅያን አማካኝነት መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች መኖራቸውን ተናግረው ቡድኑ ለጥቃቱ ሀላፊነት የወሰደ መሆኑ መረጃውን ይበልጥ ተአማኒ ያደርገዋል ብለዋል ፕሬዚዳንቱሳኡዲ አረቢያ አሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት ያለምንም ተጨባጭ መረጃ በድርጊቱ ኢራንን የሚወነጅሉበት ሁኔታ ተቀባይነት የሌለውና የቀጠናውን ሰላም ይበልጥ የሚያባብስ መሆኑንም ገልፀዋልበተያዘው ወር መጀመሪያ አካባቢ በሳኡዲ ሁለት የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት ላይ በድሮን የታገዘ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ሳኡዲ አረቢያ አሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት ለጥቃቱ ኢራንን ተጠያቂ ማድረጋቸው ይታወሳልበሌላ በኩል በየመን በስፋት የሚንቀሳቀሱትና በኢራን መንግስት የሚደገፉት የሁቲ አማፅያን ለጥቃቱ ሀላፊነት ወስዷልኢራን በበኩሏ በጥቃቱ እጇ የሌለበት መሆኑን በመግለፅ ጉዳዩን አስመልክቶ ሊፈፀምባት የሚችልን ማንኛውም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆኗን ማስታወቋ የኒታወስ ነው ሲል ሬውተርስ ዘግቧል
https://waltainfo.com/am/34006/
167
7,238
የአንስታይን ደብዳቤዎች ከ1ሚ ዶላር በላይ እንደሚሸጡ ይጠበቃል
ዓለም አቀፍ ዜና
Saturday, 13 June 2015 15:19
3296
  አንድ ደብዳቤው ከ3 አመታት በፊት 3ሚ ዶላር ተሽጧል ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ አልበርት አንስታይን በተለያዩ ጊዜያት የፃፋቸው ደብዳቤዎች በቀጣዩ ሳምንት ሎሳንጀለስ ውስጥ ለጨረታ እንደሚቀርቡና ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ይሸጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘ ቴሌግራፍ ዘገበለጨረታ የሚቀርቡት ደብዳቤዎች በአንስታይን የእጅ ፅሁፍ የተፃፉና በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ እንደሆኑ የጠቆመው ዘገባው ከደብዳቤዎቹ መካከልም አንስታይን ለልጆቹና ሀንስ እና ኤድዋርድ እንዲሁም ለቀድሞ የትዳር አጋሩ ሜሊቫ ማሪክ የፃፋቸው ይገኙበታል ብሏል አልበርት አንስታይን በደብዳቤዎቹ ፈጣሪን ፖለቲካን ታሪክን ሳይንስንና ሌሎች ጉዳዮቹን የተመለከቱ ሀሳቦቹን እንዳንፀባረቀና የሳይንቲስቱን የአመለካከት ጥልቀት የሚያሳዩ አስገራሚ ሰነዶች እንደሆኑ ጨረታውን ያዘጋጀው የሎሳንጀለስ አጫራች ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆሴፍ ማዳሌና ተናግረዋልአንስታይን ሀይማኖትን በተመለከተ የፃፈውና ጎድ ሌተር በመባል የሚታወቀው ደብዳቤ እኤአ በ2012 ለጨረታ ቀርቦ በ3 ሚሊዮን ዶላር መሸጡንም ዘገባው አስታውሷል
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=16342:%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%88%B5%E1%89%B3%E1%8B%AD%E1%8A%95-%E1%8B%B0%E1%89%A5%E1%8B%B3%E1%89%A4%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%8A%A81%E1%88%9A-%E1%8B%B6%E1%88%8B%E1%88%AD-%E1%89%A0%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B0%E1%88%9A%E1%88%B8%E1%8C%A1-%E1%8B%AD%E1%8C%A0%E1%89%A0%E1%89%83%E1%88%8D&Itemid=212
112
42,226
እሥራኤል ባደረሰችው ጥቃት ፍልስጤማዊ አርሶ አደር ህይወቱ አለፈ
ዓለም አቀፍ ዜና
March 30, 2018
Unknown
የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ የእስራኤል ታንክ ከሀነ ከተማ አቅራቢያ ባካሄደው ጥቃት አንድ ፍልስጤማዊ አርሶ አደር ሲሞት ሌላ አንድ መቁሰሉን አስታወቁየፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የአይን ምስክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበው አርሶ አደሩ የተገደለው እርሻ ማሳው ላይ እንዳለ ነውአንድ የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ እንዳመለከተው ሁለት ተጠርጣሪዎች ደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ወደሚገኘው የደሀንነት ጥበቃ አጥር ቀርበው የሚያስጠረጥር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በመታየታቸው የእስራኤል ታንክ በአፀፋው ተኩሶባቸዋልሟቹ ኡመር ሳሞረ የተባለ የሀያ ሰባት አመት ሰው መሆኑም ተገልጧልዛሬ ባጋጠመ ሌላ አደጋ ደግሞ ሀያ ሰዎች መቁሰላቸውን እየሩሳሌ ፖስት የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል
https://amharic.voanews.com//a/isreal-palestinians-3-30-2018/4324197.html
82
9,720
“ሰው የምንስበውም፤ የምንገፋውም እኛው ነን…” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 7, 2020
18
ባህር ዳር መስከረም 272013አም አብመድ ባህር ዳር ከተማን የበለጠ የኢንዱስትሪና የቱሪዝም ከተማ ማድረግ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዶክተር አስታወቁጠቅላይ ሚኒስትሩ የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክን በመረቁበት ስነ ስርአት ላይ ባህር ዳር በተፈጥሮ ውብ መሆኗ ለበለጠ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ምቹ እንደሚያደርጋት ገልፀዋል በተፈጥሮ ያልታደሉ ቦታዎችን ውብ አድርገው የሚስደምሙ በርካታ ሀገራት መኖራቸው በመጥቀስም ባህር ዳርን ትንሽ በመስራት ብዙዎችን የምትስብ ህይወትን የምታሻሽል የስራ እድል የምትፈጥር ማድረግ እንደሚቻል አስገንዝበዋልእንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ የኢፌዴሪ መንግስት በጎርጎራ ቀጣይ የሚጀመረው የቱሪዝም ልማት ስራ ጎብኝዎች ወደ ባህር ዳር አቅንተው በውበቷ እንዲደነቁ የህዝቡን ሰላም እና ስራ ወደዳድነት አይተው ሀብት እና እውቀታቸውን ፈሰስ እንዲያደርጉ የሚያነሳሳ ነውባህር ዳር ላይ የሚከናወኑ የቱሪዝም የኢንዱስትሪ እና የግብርና ስራዎች የነዋሪዎቿን ህይወት ከማሻሻል አልፈው ሌሎችን እንዲስቡ ማድረግም ይገባል ሰው የምንስበውም የምንገፋውም እኛው ነን በአንድ ቀን የግልፍተኝነት እና የስሜት ጥፋት የከተማዋ ስም ሊበላሽ ይችላል በትእግስት በጥበብ እና በማስተዋል ደግሞ በርካታ ጥበብ እና ሀብት ልንስብ እንችላለን በማለት የከተማዋ ማሀበረሰብ ስራ ወዳድ እና ሰላም ፈላጊ መሆናቸውን ሊያሳዩ እንደሚገባ መክረዋል በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኩ ተቀጥረው የሚሰሩ ወጣቶች ስራ መልመድ በጨዋ ደንብ መንቀሳቀስ እና አሰሪዎችን ማክበር እንደሚገባቸው አሳስበዋልዛሬ በተመረቀው ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ሳይታጠር ለቱሪዝም አማራጭ እንዲሆን በሚያስችል መልኩ መስራት እንደሚያስፈልግም መክረዋል ለመዝናኛ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምርምር ቦታ እና ለቱሪዝም ምቹ በሚሆን መልኩ ከተማ አስተዳደሩ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የኢንዱስትሪ ፓርክ ተቋሙ በሀላፊነት ቢሰሩት ጥሩ እንደሚሆን መክረዋልጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በባህር ዳር ያለ እምቅ አቅምን ለቱሪዝም ለኢንዱስትሪ እና ለውጪ ገበያ የሚመች ዘመናዊ ከተማ ለማድረግ ተፈጥሮ የሰጣትን ፀጋ በጭንቅላት ስራዎች ማልማት ይገባል ይህም ከምስራቅ አፍሪካ ተመራጭ እንደሚያደርጋት ነው የገለፁትዘጋቢ ደጀኔ በቀለ
https://www.amharaweb.com/%e1%88%b0%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%8a%95%e1%88%b5%e1%89%a0%e1%8b%8d%e1%88%9d%e1%8d%a4-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%8d%8b%e1%8b%8d%e1%88%9d-%e1%8a%a5%e1%8a%9b%e1%8b%8d/
234
46,092
በትግራይ ክልል በ100 ሺ ሄክታር የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ተጀመረ
ቢዝነስ
February 8, 2017
Unknown
በትግራይ ክልል ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ህዝብ የሚሳተፍበት የአፈርና ውሀ ጥበቃ ዘመቻ ስራ መጀመሩን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ የቢሮው የተፈጥሮ ሀብት ትግበራ አስተባባሪ አቶ አረፈ ኪሮስ ለዋልታ እንደገለፁት ከዛሬ ጀምሮ በክልሉ በተፋሰሶች ላይ ለ20 ቀናት በሚካሄደው የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ በየቀኑ 1 ሚሊየን 434 ሺህ 587 ህዝብ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል በክልሉ በ100 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ እንደሚካሄድ ገልፀዋልበክልሉ በካርታ ተደግፎ በተለዩት 2ሺ 594 ተፋሰሶች በጥራት ለማካሄድ ልዩ ክተትል እንደሚደረግ ነው ያስረዱት በክልሉ ለዘመቻው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በማዘጋጀት  ከ84 ሺ 258 በላይ የልማት ቡድኖች መደራጀታቸውን አቶ አረፈ አስታውቀዋልየአፈርና ጥበቃ ስራው ሰብል ጨርሶ ባልተሰበሰበባቸው ከሰሜን ምእራብና ምእራብ ዞኖች በስተቀር በሁሉም የክልሉ ገጠር ወረዳዎች እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋልየክልሉ እርሻና ገጠር ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር አትንኩት መዝገቡ በደቡባዊ ዞን ዛሬ ስራውን በይፋ ማስጀመራቸውን ለመወቅ ተችሏል
https://waltainfo.com/am/22983/
127
3,607
የፈጠራ ሳምንቱ በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማምጣት ያግዛል
ሀገር አቀፍ ዜና
October 30, 2019
29
አዲስ አበባ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከመላው አፍሪካ የተመረጡ 200 ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎች በመዲናዋ እየተሳተፉበት የሚገኘው የአፍሪካ የፈጠራ ሳምንት አካታች የሆነ ዘላቂ ልማትን በአፍሪካ ለማምጣት እንደሚያግዝ ተገለፀየአፍሪካ የፈጠራ ሳምንት ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ በተጀመረበት ወቅት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሀመት በተወካያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልእክት እንደገለፁት የፈጠራ ሳምንቱ አፍሪካውያን የፈጠራ ባለሙያዎችን ከኢንቨስተሮች ጋር ማገናኘትን ዋና አላማው አድርጓል መድረኩ የአፍሪካዊያንን የፖሊሲ አቅጣጫዎች ተመራማሪዎች ምሁራን የግል ዘርፍ ባለሀብቶች እና አለም አቀፍ ተዋንያንን አንድ ላይ የሚያገናኝ ከመሆኑም በላይ ፈጠራን የሚያሳድግና አካታች ዘላቂ ልማትን በአፍሪካ ለማምጣት የሚያግዝ ነውዝግጅቱ ከህብረቱ አጀንዳ 2063 ፕሮጀክት ጋር ተጣጥሞ እንደሚሄድ ሊቀመንበሩ ጠቁመው የፈጠራ ሳምንቱ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ እድልን የያዘ አዳዲስ የገበያ አማራጮችን የሚከፍት እና ተጨማሪ ባለሀብቶች ዘርፉን እንዲቀላቀሉ የሚያደርግ እንደሆነም ተናግረዋልበመድረኩ የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች ትኩረታቸውን በሴቶች እና ስራ ፈጠራ በግብርና በጤና በቱሪዝም በመስተንግዶ እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ያደረጉ መሆናቸውንም ጠቁመዋልየአይ ቢ ኤ ኢትዮጵያ የበላይ ጠባቂ እና የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በመድረኩ በላኩት የምስል መልእክት እንደገለፁት ይህ መድረክ መዘጋጀቱ ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎችን እና ውጤታማ ባለሀብቶችን በአንድ መድረክ በማገናኘት በሚፈጠሩ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ስራዎች አማካኝነት አህጉሪቱን በዘርፉ ከተቀረው አለም ጋር እንድትራመድ ያግዛታል ብለዋልየኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው መሰል የፈጠራ ስራዎች አዳዲስ የስራ እድሎችን በመፍጠር ረገድ ሚናቸው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው መንግስት በተለይ በአገልግሎት እና ማምረቻ ዘርፎች ላይ ወጣቶች የፈጠራ ስራዎችን እንዲሰሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋልየአፍሪካ የፈጠራ ሳምንት አጋር በመሆን በቅርቡ የተቀላቀለው የቮዳፎን የአፍሪካ የመካከለኛው ምስራቅና የኤዠያ ፓሲፊክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቪቬክ ባድሪናትየፈጠራ ሳምንቱን የምንደግፈው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለሁሉም የሚያስገኘውን ጥቅም ስለሚያሳይ ነው ብለዋል ኢትዮጵያ ያላትን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም በመጠቀም የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማሳደግ እየሰራች መሆኑን ጠቅሰው በመድረኩ በአዲስ አበባ መዘጋጀቱ ተገቢ መሆኑን አስታውቀዋል የፈጠራ ሳምንቱ የተዘጋጀው አይ ቢ ኤ ኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ኢኖቬሽን ከኢፌዴሪ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና ከኦስሎ ኢንተርናሽናል ሀብ ጋር በመተባበር መሆኑ ታውቋልአዲስ ዘመን ጥቅምት 192012  ሶሎሞን በየነ
https://www.press.et/Ama/?p=21704
286
38,563
በካርቱ የሥልጣን ክፍፍል ሥምምነት የፈረሙ የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች
ዓለም አቀፍ ዜና
August 08, 2018
Unknown
ካርቱም ላይ የስልጣን ክፍፍል ስምምነት ላይ ከደረሱት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አንዳንዶቹ በስምምነቱ በተካተቱት በአንዳንዶቹ አንቀፆች ባንስማም የፈረምነው ለሰላም እድል ስንል ነው ይላሉሆኖም ኢጋድ ማለት የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ የተጠናከረ የሰላም ውል እስኪደረስ ፕሬዚዳንት ኦመር ሀሰን አል በሺር ከሚገኙበት ከሱዳን ሸምጋዮች ቡድን ጋር ሆኖ ድርድሮቹን ማስተባበሩን እንደሚቀጥል አስታውቋልበኢጋድ መግለጫ መሰረት የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለካርቱሙ የሰላም ሂደት ቀጣይነት ድጋፍ የሚሰጥ የኤክስፐርቶች ቡድን ይልካሉ የድርድሩ ስፍራ ይለወጣል የሚሉ ሪፖርቶች ስናፈሱ ቆይተዋል
https://amharic.voanews.com//a/south-sudan-deal-reservation-8-8-2018/4518956.html
78
20,538
ኦነግ የሊቀመንበሩ መግለጫ በፀጥታ ኃይሎች እንዲቋረጥ መደረጉን አስታወቀ
ፖለቲካ
14 October 2020
Unknown
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በመኖሪያ ቤታቸው የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2013 አም ሲሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በታጠቁ ሀይሎች መቋረጡን የፓርቲው ጊዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ ለሪፖርተር አስታወቁ ከዚህ ቀደም ባሉት ሳምንታት በአገሪቱ አጠቃላይ የሽግግር መንግስት ይመስረት የሚል ጥያቄ ፓርቲው ማቅርቡን ያስታወሱት አቶ በቴ የሰኞ እለት ጋዜጣዊ መግለጫ አላማም ይህን አቋም ለማብራራት ያለመ እንደነበር አስታውቀዋል ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2013 አም 830 ሰአት ገደማ መግለጫው ተጀምሮ እንደነበር ያስታወሱት አቶ በቴ ነገር ግን መግለጫው ለ30 ደቂቃዎች ያህል እንደተከናወነ የፀጥታ ሀይሎች ወደ አቶ ዳውድ መኖሪያ ቤት በመግባት መግለጫው እንዲስተጓጎል ማድረጋቸውን አስረድተዋል ከመግለጫው መስተጓጎል በኋላ ከ20 እስከ 30 የሚደርሱ የመግለጫው ታዳሚዎችን ለመውሰድ መሞከሩን የገለፁት አቶ በቴ ነገር ግን አቶ ዳውድ የታጠቀ ሀይል ያለ ፈቃድ ወደ መኖሪያ ቤቴ አይገባም ችግር ካለም እኔን ጠይቁኝ ካስፈለጋችሁ እኔን እሰሩኝ እንጂ እንግዶቼን አታስሩም በማለታቸው በርካቶች በእሳቸው መኖሪያ ቤት እንደሚገኙ አቶ በቴ ገልፀዋል ሆኖም ስድስት ያህል የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ለጥያቄ እንፈልጋችኋለን ተብለው ወደ ጣቢያ መውሰዳቸውን ገልፀዋል በመግለጫው ላይ የነበሩ ከ20 እስከ 30 የሚሆኑ ግለሰቦች እዚያው ማደራቸውንና ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስም እዚያው እንደሚገኙ የገለፁት አቶ በቴ ይሁን እንጂ ማክሰኞ እለት ከአቶ ዳውድ መኖሪያ ቤት የወጡ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አክለዋል በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት መግለጫ ወይም ማብራሪያ አለማግኘታቸውን የሚገልፁት አቶ በቴ ከመግለጫው መስተጓጎል ጀምሮ አቶ ዳውድ ቤት ውስጥ ናቸው ከቤት የሚወጡ እንግዶች በር ላይ ተጠብቀው የሚታሰሩ ከሆነ የእሳቸው ሁኔታም አሳሳቢ ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል ኦነግ ከቅርብ ወራት ወዲህ በመሪዎቹ መከፋፈል ምክንያት የመገናኛ ብዙሀን የፊት ገፅ ማሟሻ የነበረ ሲሆን በሊቀመንበሩ አቶ ዳውድና በምክትል ሊቀመንበሩ አቶ አራርሶ ቢቂላ መካከል የተከሰተው የማገድና የመልሶ ማገድ ኩነት ፓርቲውን ለሁለት ከፍሎታል በሀምሌ ወር 2012 አም የተደረገው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ያለ እኔ እውቅና የተካሄደ ነው በሚሉት ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድና ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ አራርሶ በሚመሩት ቡድን መካከል በተፈጠረ ውዝግብ በፓርቲው ስብሰባ ላይ ውሳኔ መተላለፉን በመጥቀስ አቶ ዳውድ መታገዳቸው የተገለፀ ሲሆን አቶ ዳውድ በበኩላቸው ደግሞ የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ ከቤት እንዳይወጡ ተደርገው እያለ የተካሄደው ስብሰባ ህገወጥ ነው በማለት ስድስት የሚሆኑ የፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማገዳቸው የሚታወስ ነው በዚህ ውዝግብ መካከል ከሊቀመንበሩ ቡድን ተከፍሎ የወጣው በምክትል ሊቀመንበሩ የሚመራውና የፓርቲውን የህዝብ ግንኙነት አቶ ቀጄላ መርዳሳና አቶ ቶሌራ አዶባን በአባልነት የያዘው ቡድን በአቶ ዳውድ ምክንያት በፓርቲው ውስጥ የጋራ አመራር ጠፍቶ ወደ ግለሰባዊ አመራር ማዘንበል ተይዟል በማለት ሊቀመንበሩን ከሷል ከዚህ በተቃራኒው አቶ ዳውድ ውሳኔው ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እውቅና ውጪ በሆነ መንገድ መተዳደርያ ደንቡን የጣሰ ምልአተ ጉባኤው በሁለት ሶስተኛ ተሳታፊዎች ሳይሟላ የተደረገ ስብሰባ በመሆኑ እንዲሁም ውሳኔውን ያስተላለፉት አባላት የታገዱ በመሆናቸው ውሳኔው ተቀባይነት የለውም በማለት ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አቤት ብለዋል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኦነግ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት የሚያስረዱትን አቤቱታዎችና ደብዳቤዎች መስከረም 28 ቀን 2013 አም መመርመሩን ያስታወቀ ሲሆን ከሁለቱም ወገኖች አንድ አንድ ተወካይ የሚካተትበት ጊዜያዊ ጉባኤ እንዲቋቋም ወስኗል በዚህም መሰረት በሁለቱ አካላትና በቦርዱ የተመረጡ ባለሙያዎች ጉዳዩን አጣርተው በሚያቀርቡት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተመርኩዞ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥም መስከረም 29 ቀን 2013 ማስታወቁ ይታወሳል
https://www.ethiopianreporter.com/article/20132
451
37,876
የዓሣ ገበያ በባህር ዳር
ሀገር አቀፍ ዜና
June 16, 2020
Unknown
በቀውስ ጊዜ የሚሰጡ መረጃዎች ያለ ምንም አሻሚ ትርጉም ወደ ማሀበረሰቡ መድረሳቸውን ለማረጋገጥ ተደጋጋሚ ጥናት ማድረግ እንደሚገባ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች አሳሰቡበዚሁ በመረጃ አሰጣጥ ችግር ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የአሳ ገበያ መሻሻል ማሳየቱን ደግሞ በባህርዳር ከተማ የሚገኙ አስጋሪዎችና ነጋዴዎች ተናግረዋል
https://amharic.voanews.com//a/business-bahir-dar-fishery-6-16-2020/5465330.html
36
51,437
በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 353,633,660 ችግኞች ተተከሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 30, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 353633660 ችግኞች ተተከሉበኢትዮጵያ ሀምሌ 222011 በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን በመላ ሀገሪቱ 353 ሚሊየን 633 ሺህ 660 ችግኞች መተከላቸው ተረጋግጧል  በአገሪቷ በአረንጓዴ አሻራ ቀን 200ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ በተደረገው ዘመቻ በአንድ ጀምበር በመላ ሀገሪቱ 353 ሚሊየን 633 ሺህ 660 ችግኞች ተተክሏል ይህም በህንድ ከዚህ ቀደም ተይዞ ከነበረው የ66 ሚሊየን ችግኝ በእጅጉ የላቀ መሆኑ ተረጋግጧልበችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የክልሎች ርእሳነ መስተዳድርና ከንቲባዎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተለያዩ ቦታዎች በመገኘት ችግኝ ተክለዋል በዘመቻው መላው የአገሪቱ ህዝብ አንድ ሆኖ ሲሳተፍ ተስተውሏል
https://waltainfo.com/am/32602/
97
44,377
በድሬዳዋ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ 27 ሚሊዮን ብር ብድር መለቀቁ ተገለጸ
ቢዝነስ
January 9, 2018
Unknown
በድሬዳዋ  ከተማ  በወጣቶች  ተንቀሳቃሽ ፈንድ አማካኝነት ለወጣቶች  የስራ እድል  ፈጠራ የሚውል  27  ሚሊዮን ብድር መለቀቁን የድሬ ብድርና ቁጠባ  ተቋም አስታወቀ የተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው ይመር ለዋልታ እንደገለፁት በድሬዳዋ ከተማ  በወጣቶች  ተንቀሳቃሽ ፈንድ መርሀ ግብር  በአጠቃላይ 55  ሚሊዮን ብር  ብድር የተፈቀደ  ሲሆን ከግንቦት  2009 ጀምሮ እስካሁን 27  ሚሊዮን  ብር  የሚሆን  ብድር በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለተደራጁ ወጣቶች ተለቋል እንደ አቶ ጌታቸው ገለፃ በድሬዷ ወጣቶች በፈንዱ አማካኝነት የሚቀርብላቸውን ብድር  በአግባቡ ተጠቅመው  ወደ የተለያዩ  ስራ እንዲገቡም  አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው  ይገኛል የድሬዷ ነዋሪ  የሆነችው ወጣት  ጥሩዬ በዛብህ ለዋልታ እንደገለፀችው መንግስት በወጣቶች ተንቀሳቃሽ ፈንድ ለወጣቶች  የስራ እድል ፈጠራ  መንግስት  ብድር በማመቻቸቱ ደስተኛ መሆኗን ተናግራለች እምባቆም አለም በበኩሉ በምህንድስና ዘርፍ  አብረው  ከተመረቁት ጓደኞቹ  ጋር  ተደራጅቶ  በብሎኬት ምርት ስራ ላይ  በመሰማራቱ እሱና ጓደኞቹ  ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ተናግሯል    በድሬዷ  ከተማ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በመደራጀት 300 ሺህ ብር  ብድር ያገኘው ሌላው የድሬዷ  ወጣት  ብርሀኑ  ብሩ እንደሚናገረው  በማኑፋክቸሪንግ  ዘርፍ ስራ  ጀምሮ ለሌሎች ወጣቶችም ጭምር የስራ እድል መፍጠሩ እርካታ እንደሚሰማው ገልጿል  ዋልታ  ያነጋገራቸው የድሬዷ ወጣቶች በተለያዩ  የምርትና አገልግሎት  ስራ  ቢሰማሩም  የማምረቻና የመሸጫ  አጥረትና ጥበት እንዳለባቸው  አንስተዋል   በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር  የምግብ ዋስትናና ስራ እድል ፈጠራ ዳይሬክተር አቶ ወጋየሁ በጋሻው ወጣቶቹ ያነሱትን ችግሮች  በማስመልከት  በሰጡት ምላሽ  የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ችግሮችን  ለመፍታት ሼዶችን ተገንብተው  ለወጣቶች  ለማስተላለፍ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አስረድተዋል      
https://waltainfo.com/am/23388/
199
7,376
የ2013 የአለማችን ሃያላን ጥቁር ሴቶች ከአስራ አንዱ ሃያላን ሴቶች ሶስቱ አፍሪካውያን ናቸው
ዓለም አቀፍ ዜና
Monday, 23 December 2013 09:22
6841
በተሰማሩበት መስክ ጉልህ ስራ ሰርተዋል የላቀ ውጤት አስመዝግበዋል ብዙዎችን ተጠቃሚ አድርገዋል ሀያልነታቸውንም አስመስክረዋል ያላቸውን የአለማችን ሴቶች በየአመቱ የሚመርጠው ታዋቂው ፎርብስ መፅሄት ዘንድሮም የ2013ን የአለማችን 100 ሀያላን ሴቶች ዝርዝር ይፋ አድርጓልፎርብስ በመላ አለም ከሚገኙ የተለያዩ አገራት ከመረጣቸው 100 የአመቱ ሀያላን ሴቶች መካከል የቀለም ልዩነት ሳይበግራቸው ጉልህ ስራ ሰርተዋል የጥቁር ሴቶች የስኬታማነት ተምሳሌት ሆነዋል ብሎ በዝርዝሩ ውስጥ ያካተታቸው ጥቁር ሴቶች አስራ አንድ ብቻ ናቸው ከአስራ አንዱ ጥቁር ሀያላን ሴቶች መካከልም ከአፍሪካ አህጉር የተመረጡት ሶስት ብቻ ናቸው ፖለቲከኞችን የኩባንያ ስራ አስኪያጆችን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሀላፊዎችን የመንግስት ባለስልጣናትንና በሌሎች መስኮች የተሰማሩ ሴቶችን የያዘው የፎርብስ የአመቱ ምርጥ ሀያላን ሴቶች ዝርዝር ከጥቁር ሴቶች መካከል በቀዳሚነት ያስቀመጠው ቀዳማዊ እመቤት ሚሼል ኦባማን ነውፎርብስ ሚሼል ኦባማን የመረጠው በቀዳማዊ እመቤትነቷ በመጠቀም ህፃናትን ከመጠን በላይ ከሆነ ክብደት ለመታደግና ጤናማ አኗኗርና አመጋገብን ለማስፋፋት በምታደርገው ጥረት ነው ሚሼል ከባራክ ኦባማ ጋር ሲነፃፀር በአሜሪካውያን ዘንድ የበለጠ ተወዳጅነት እንዳላቸው የገለፀው የፎርብስ መረጃ ከአጠቃላዩ የአሜሪካ ህዝብ 67 በመቶ የሚሆነው ከባራክ ኦባማ ይልቅ ለሚሼል ጥሩ አመለካከት እንዳለው ያሳያልበሀያላኑ ጥቁር ሴቶች ዝርዝር ውስጥ የተካተተችው ሌላዋ አፍሪካ አሜሪካዊት ደግሞ ኦፕራ ዊንፍሬይ ናት ለ25 አመታት ስትመራው በነበረው ኦፕራ ሾው የተባለ ፕሮግራም አለማቀፍ ዝናን ያተረፈችው ኦፕራ በሀብት መጠን ቀዳሚዋ አፍሪካ አሜሪካዊት መሆኗንም ፎርብስ ጠቅሷል አዲስ ያቀዋቀዋመችው ዘ ኦፕራ ዊንፍሬይ ኔትዎርክ የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፈው አመት ብቻ 83 ሚሊዮን ተመዝጋቢ ተመልካች ቤተሰቦችን ለማግኘት በቅቷል ኦፕራ በበጎ አድራጎት ስራ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠራ የአለማችን ለጋስ ሴቶች አንዷ ስትሆን እስከ አሁን ድረስ ከ400 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገንዘብ ለበጎ አድራጎት ስራ አበርክታለችየዜሮክስ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆነችው አሜሪካዊቷ ኡርሱላ በርንስ ኩባንያውን ከማተሚያ መሳሪያ አምራችነት ጠቅላላ አገልግሎቶችን ወደሚሰጥ ግዙፍ ኩባንያነት አሳድጋለች በሚል ነው በሀያላኑ ዝርዝር ውስጥ የተካተተችው እኤአ በ1980 በተለማማጅ ሰራተኛነት ዜሮክስ ኩባንያን የተቀላቀለችው ኡርሱላ በርንስ በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪዋን መመረቋን ተከትሎ በቀጣዩ አመት የኩባንያው መደበኛ ሰራተኛ ሆና ተቀጥራለች በስራዋ ውጤታማ በመሆኗ እኤአ በ2000 የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ተደርጋ ተሹማለች ይህቺው ታታሪ ሰራተኛ እኤአ በ2009 የዜሮክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ከሆነች በኋላም የበለጠ ውጤታማ ስራ በማከናወኗና ኩባንያውን ወደተሻለ ትርፋማነት በማሸጋገሯ ነው ፎርብስ ከሀያላኑ ጎራ የቀላቀላትሌላዋ የፎርብስ የአመቱ ሀያል ሴት አሜሪካዊቷ ድምፃዊት ቢዮንሴ ኖውልስ ናት ፎርብስ እንዳለው ቢዮንሴ በሙዚቃ ስራዎቿ ከምታገኘው በሚሊዮን የሚቆጠር ገቢ በተጨማሪ ሀውስ ኦፍ ዴሪዮን በሚል ስያሜ ባቋቋመችው የአልባሳት አምራች ኩባንያዋም ከፍተኛ ትርፍ ማካበቷን ቀጥላለች ከፔፕሲ ጋር የፈፀመችው የማስታወቂያና የኮንሰርት ስምምነት 50 ሚሊዮን ዶላር ያሳፈሳት ቢዮንሴ የምንጊዜም ምርጥ ሽያጭ ካስመዘገቡ የአለማችን ታዋቂ ድምፃውያን ተርታ የምትመደብ ሲሆን 17 የግራሚ ሽልማቶችንም ተቀብላለች ከወራት በፊት በተዘጋጀ የሱፐር ቦውል የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ያቀረበችው የ15 ደቂቃ ሙዚቃዋን በአለም ዙሪያ የሚገኙ ከ104 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች እንደተመለከቱት የሚጠቅሰው የፎርብስ መረጃ ድምፃዊቷ በአለም ዙሪያ ያላትን ተቀባይነት የበለጠ እያሳደገች መምጣቷ በሀያልነት እንዳስመረጣት ይናገራልየታዋቂው ዎልማርት ኩባንያና ከአሜሪካ ታላላቅ የንግድ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው የሳምስ ክለብ ፕሬዚዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን የሰራችው ሮዛሊንድ ብሪዌርም ሌላዋ የፎርብስ የአመቱ ሀያል ጥቁር ሴት ናት ባለፈው አመት ጥር ወር ላይ የሳምስ መሪ ሆና የተመረጠችው ብሪዌር ለኩባንያው ትርፋማነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቷ ይነገራል እኤአ በ2006 ዎልማርትን በመቀላቀል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆና ያከናወነቻቸው ስራዎቿ ኩባንያውን ማሳደግ የእሷን ጥንካሬም ማስመስከር የቻሉ በመሆናቸው በሀያላኑ ዝርዝር ውስጥ መካተቷን ፎርብስ ተናግሯልአፍሪካን የጥቁር ሀያላን ሴቶች እናት አድርገው ካስጠቀሷት ሶስት የአመቱ የፎርብስ ሀያላን ሴቶች መካከል የማላዊ ፕሬዚዳንት ጆይስ ባንዳ አንዷ ናት የአገሪቱ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት በመሆን ወደ መሪነት የመጣችው ጆይስ ባንዳ የመጀመሪያዎቹን የስልጣን አመታት ከአለማቀፉ ማህበረሰብ እርዳታ በማሰባሰብና አገሪቱን ከሚፈታተናት የዋጋ ግሽበት ጋር በመታገል ነበር ያሳለፈቻቸው ጆይስ ባንዳ ከአጠቃላይ አመታዊ ገቢዋ 40 በመቶ ያህሉን ከውጭ እርዳታ የምታገኘውን ይህቺን ድሀ አፍሪካዊት ሀገር ከገንዘብ እጦት ለመታደግ በአለም ዙሪያ እየተንቀሳቀሰች የገንዘብ ተቋማትን በማሳመን ስራ ተጠምዳ እንደኖረች ፎርብስ ተናግሯል ባንዳ ያለፉት መንግስታት አያደርጉ አድርገዋት የሄዷትን ማላዊ እንድታገግምና ራሷን ችላ እንድትቆም ለማስቻል እያደረገችው የምትገኘው ተጠቃሽ ጥረት የፎርብስን ሚዛን በመድፋቱ ከሀያላኑ ጎራ ተቀላቅላለችየአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንትና እኤአ የ2011 የኖቬል የሰላም ተሸላሚዋ ሊይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የአፍሪካን ሴቶች ሀያልነት ያስመሰከረች ሌላኛዋ የፎርብስ ምርጥ ናት በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርቷን የተከታተለችው ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የላይቤሪያን የእርስ በርስ ግጭት በሰላማዊ ድርድርና መግባባት ለመቋጨት ከመቻሏ በተጨማሪ አለማቀፍ አበዳሪዎች የእዳ ስረዛ እንዲያደርጉ በማግባባት ረገድ የሰራቻቸው ስራዎችም ጠንካራና ስኬታማ ሴትነቷን ያስመሰክራሉ ብሏል ፎርብስፎርብስ የአመቱ ሀያል ሴት ብሎ የጠቀሳት ሌላዋ አፍሪካዊት የናይጀሪያ የፋይናንስ ሚንስትርና የኢኮኖሚ አስተባባሪ ሚንስትር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ ናት ኢዌላ በአለም ባንክ የነበራትን የማኔጂንግ ዳይሬክተርነት ስራ ለቅቃ እኤአ ከ2011 በሚንስትርነት ከተሸመች በኋላ ተጠቃሽ ስራ መስራቷን የጠቀሰው የፎርብስ መረጃ በቀጣዩ አመት የአገሪቱ ኢኮኖሚ 65 በመቶ እድገት እንዲያሳይ የእሷ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል እኤአ ከ2003 እስከ 2006 በአገሯ ናይጀሪያ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆና ትሰራ የነበረው ኢዌላ አበዳሪዎች የናይጀሪያን 18 ቢሊዮን ዶላር እዳ እንዲሰርዙ በማስቻል ረገድ ተጠቃሽ ስራ መስራቷ ይነገራልከፎርብስ የአመቱ ሀያላን ጥቁር ሴቶች ዝርዝር ውስጥ የተካተተችዋ ሌላኛዋ ትጉህ ደግሞ እኤአ በ2012 የአለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሆና የተመረጠችው አሜሪካዊቷ ኤርታሪን ኮሲን ናትድርጅቱ በአለም ዙሪያ በሚገኙ 78 የተለያዩ አገራት ከርሀብ የምግብ ዋስትናና የምግብ እጥረት ጋር  በተያያዘ የሚሰራውን ሰፊ ስራ በአግባቡ የመምራትና በስሯ የሚገኙ ከ15ሺህ በላይ ሰራተኞችን በወጉ የማስተዳደር ታላቅ ሀላፊነት የተጣለባት ኮሲን ውጤታማ ስራ ማከናወኗን ፎርብስ ይመሰክራል የመጀመሪያውን አመት በምእራብ አፍሪካ በድርቅ በሶሪያ ደግሞ በእርስበርስ ጦርነት ሳቢያ የተከሰተውን ርሀብ ለማሰወገድ ትኩረት ሰጥታ በመስራት ያሳለፈችው ኮሲን በቀጣይም ከምግብ እርዳታ ወደ ራስን ማስቻል የሚደረገውን ሽግግር በመምራት ተጠቃሽ ስራ ማከናወኗን ፎርብስ ዘግቧልበሀያላኑ ዝርዝር ውስጥ ለመቀላቀል የቻለችው ሌላዋ አሜሪካዊት የኬር ዩኤስኤ ፕሬዚደንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ሄለን ጋይሌ ናት እኤአ በ2006  የኬር ዩኤስኤ ፕሬዚደንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆና የተሸመችው ሄለን በ87 የአለም አገራት ድህነትን ለመዋጋት የሚከናወኑ ስራዎችን በአግባቡ መምራቷ ይነገርላታል በቻድ ኒጀር ማላዊና ሌሎች የአፍሪካ አገራት ከ750 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የምግብና የንፁህ የውሀ መጠጥ አቅርቦት ስራዎችን አከናውናለችእኤአ በ2003 ሮበርት ውድ ጆንሰን ፋውንዴሽን የተባለው የአሜሪካ ትልቁ የጤና ክብካቤ ተቋም ፕሬዚደንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆና የተመረጠችው ሪዛ ላቪዞ ሙርኒ ሌላኛዋ የፎርብስ የአመቱ ሀያል ጥቁር ሴት ናት ፋውንዴሽኑን ለአመታት በስኬታማነት መምራቷ የሚነገርላት ሙርኒ ተቋሙን በመምራት የመጀመሪያዋ ሴት እንዲሁም የመጀመሪያዋ አፍሪካ አሜሪካዊ ናት
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=13448:%E1%8B%A82013-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%88%9B%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%88%83%E1%8B%AB%E1%88%8B%E1%8A%95-%E1%8C%A5%E1%89%81%E1%88%AD-%E1%88%B4%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8A%A8%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%88%AB-%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B1-%E1%88%83%E1%8B%AB%E1%88%8B%E1%8A%95-%E1%88%B4%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%88%B6%E1%88%B5%E1%89%B1-%E1%8A%A0%E1%8D%8D%E1%88%AA%E1%8A%AB%E1%8B%8D%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8A%93%E1%89%B8%E1%8B%8D&Itemid=212
875
13,932
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጸረ ሰላም ሃይሎችን አጀንዳ ተቀብለው ወደ ጫካ የገቡ ወጣቶች ፍላጎቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲገልጹ ጥሪ ቀረበ
ሀገር አቀፍ ዜና
Nov 25, 2020
459
አዲስ አበባ ህዳር 16 2013 ኤፍ ቢ ሲ የፀረ ሰላም ሀይሎችን አጀንዳ ተቀብለው ወደ ጫካ የገቡ ወጣቶች ከድርጊታቸው ተቆጥበው ፍላጎታቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመንግስት እንዲያቀርቡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጥሪ አቀረቡ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በቀጠናው ላለው የሰላም እጦት መፍትሄ ለማበጀት ከማንዱራ ወረዳ ከጉሙዝ ብሄረሰብ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር መክረዋልበቀጠናው በተወሰኑ ቡድኖች በተፈጠረው አለመረጋጋት በርካታ የብሄረሰቡ እናቶች ህፃናት እንዲሁም ሴቶች በከፍተኛ የማህበራዊ ችግር ውስጥ ወድቀዋል ተብሏልሀገሪቱን በመበታተን ሰላም እንዳይኖር እየተንቀሳቀሰ ያለውን የጁንታውን አጀንዳ ተቀብለው ለጥፋት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ሀይሎች በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ካልቻሉ ችግሩ የከፋ እንደሚሆን ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ገልፀዋልየአካባቢውን የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀም የልማት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን እየተቻለ አግባብነት በሌለው አጀንዳ ወጣቱ ሰለባ መሆን እንደሌለበት በመግለፅ አሁንም ከድርጊታቸው ተቆጥበው ወደ ሰላም እንዲመጡ የሀገር ሽማግሌዎች ከመቸውም በላይ አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለባቸው ተናግረዋልየክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ይስሀቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው በዞኑ ውስጥ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብት ተጠብቆ ባለበት ሰአት በጠላት በኩል የሚነዛውን አጀንዳ በመቀበል የዜጎችን ህይወት መቅጠፍና ማፈናቀል ዋጋ እንደሚያስከፍል በመረዳት በአጭር ጊዜ ውስጥ እልባት ሊሰጠው ይገባል ብለዋልበቀጠናው ለረጅም ጊዜ እየተስተዋለ ያለውን የሰላም እጦት በአሁኑ ሰአት መልኩን እየቀየረ ወደ የእርስ በእርስ ግጭት እየተቀየረ በመሆኑ መፍትሄ ለማበጀት ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት በውይይቱ ወቅት ተገልጿልየሀገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው ሁሉም የብሄረሰቡ የሀገር ሽማግሌዎች ለእኩይ አላማ ተልእኮ አስፈፃሚ የሆነውን ወጣት ለመመለስ እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታልበወረዳው ህዝብን መታደግ በማይችልና ተራማጅ ባልሆነ መልኩ ለጥፋት ተልእኮ ወደ ጫካ የገቡ ወጣቶችን በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲመለሱ ለማድረግ አቅጣጫ ተቀምጧል
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%89%a4%e1%8a%95%e1%88%bb%e1%8a%95%e1%8c%89%e1%88%8d-%e1%8c%89%e1%88%99%e1%8b%9d-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%8c%bd%e1%88%a8-%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%83%e1%8b%ad/
238
5,214
የጋራ ኮሚሽኑ ስብሰባ ዋና ትኩረት የዜጎች መብትና ደህንነት እንደነበር  ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
February 2, 2019
37
የቀዳማዊ አፄ ሀይለስላሴ መታሰቢያ ሀውልት የካቲት 3 ይመረቃልአዲስ አበባ 15ኛው የኢትዮጅቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ለዜጎች መብትና ደህንነት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መምከሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ትናንት በሰጡት መግለጫ ከጥር 21 እስከ 23 ቀን 2011 አም በጅቡቲ የተካሄደው 15ኛው የኢትዮጅቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በጅቡቲ የሚኖሩ እንዲሁም ለስራ ጉዳይ ወደ ጅቡቲ የሚመላለሱ ኢትዮጵያውያን   ደህንነትና መብት ላይ በሰፊው መምከሩን ገልፀዋልእንደቃል አቀባዩ ገለፃ  የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የጅቡቲ መንግስት በአገሪቱ የሚኖሩ የውጭ አገራት ዜጎች የመኖሪያና የስራ ፈቃድን በተመለከተ በቅርቡ ያወጣው ህግ ለኢትዮጵያውያን አስቸጋሪ እንደሚሆን በመግለፃቸው የኢትዮጵያውያን ጉዳይ በልዩ ሁኔታ እንደሚታይ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኡመር ጊሌ ቃል ገብተዋልበወጪና ገቢ ንግድ መስመር የሚታየውን እንግልት ለመቀነስ በጅቡቲ በኩል ብልሽት የደረሰበት መንገድ እንዲጠገን ከስምምነት ላይ ተደርሷል ኢትዮጵያውያን በጅቡቲ በኩል ሲሻገሩ የሚያጋጥማቸውን  አደጋ ለማስቀረት ከጅቡቲ ጋር በቅንጅት ለመስራትና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል ውይይትም ተደርጓልከውጭ ጉዳይ ከትራንስፖርት ከገቢዎች እንዲሁም ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሮች በተጨማሪ የሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉበት በመሆኑ  በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ የቴክኒክ ኮሚቴዎች በመቋቋማቸው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ምክክር ማድረግ ተችሏል በየጊዜው የሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል ስርአት መፈጠሩንም  ቃል አቀባዩ አስረድተዋል32ኛው የአፍሪካ ሀብረት ስብሰባ ከጥር 30 ቀን 2011 አም ጀምሮ እንደሚካሄድ የጠቆሙት አቶ ነቢያት በሀብረቱ ተቋማዊ ሪፎርም በአህጉራዊ ነፃ ንግድና በሌሎች የአፍሪካ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክርም ጠቁመዋል ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ አፄ ሀይለስላሴ ለአፍሪካ ነፃነትና አንድነት ላበረከቱት አስተዋፅኦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ ፈለገ ሰላም የስነጥበብ ትምህርት ቤት ባለሙያዎች የተሰራው የመታሰቢያ ሀውልት የሀብረቱ የመሪዎች ስብሰባ በሚጀመርበት ቀን የካቲት 3 ቀን 2011 አም እንደሚመረቅም ተናግረዋልበተጨማሪም የአውሮፓ ሀብረት የውጭ ጉዳይና የፀጥታ ፖሊሲ ከፍተኛ ሀላፊ ፌደሪካ ሞጌሬኒ የካቲት 2 ቀን 2011 አምየኢስቶኒያ ፕሬዚዳንት ክሪስቲ ካልጁሌይድ ደግሞ የካቲት 3 ቀን 2011 አም ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡም አቶ ነቢያት ጠቁመዋልአዲስ ዘመን ጥር 252011አንተነህ ቸሬ
https://www.press.et/Ama/?p=3917
276
49,392
ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በጽዳት ለተሳተፉ ዜጎች ምስጋናቸውን አቀረቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
April 14, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ በፅዳት ለተሳተፉ ዜጎች ምስጋናቸውን አቀረቡየሰፈርና የአእምሮአችንን ቆሻሻ እያፀዳን በንፁህ ልቡና እና አእምሮ ሀገራችንን እናድስ ሀገራችንን እንገንባ ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋልበሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው የፅዳት ዘመቻ ጥሪ መሰረት በመላዉ ኢትዮጵያ ጠዋት ፅዳት ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋልይህ መልካም ጅምር እንደ ባህል በየጊዜዉ እንዲቀጥል ሁሉም የሀብረተሰብ ክፍል እንዲቀጥልበት ጠይቀዋልአብዛኛዉ ቦታ ላይ የነበረው እንቅስቃሴ የሰመረ እንደነበርም ከጠቅላይ ሚኒስተር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
https://waltainfo.com/am/32357/
66
16,026
ተቋማቱ ግምታዊ ዋጋቸው 34 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለተፈናቃዮች አደረጉ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jul 27, 2020
302
አዲስ አበባ ሀምሌ 20 2012 ኤፍ ቢ ሲ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ግምታዊ ዋጋቸው 34 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቃዮች አደረጉድጋፉ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው የፀጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ለሚያሰባስበው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ አማካይነት የተደረገ ነውበስነ ስርአቱ ወቅት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌውና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ ተገኝተዋልድጋፉ የምግብ ዘይት ስኳር ምስር ፓስታና አልባሳት መሆኑንን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታልአፈ ጉባኤ ታገሰ ተቋማቱ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ሀብረተሰቡ ከኢትዮጵያዊ እሴት ውጭ የተፈፀመውን አስነዋሪ ተግባር በማውገዝ ተጎጂዎችን ለማፅናናትና ለማቋቋም በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፍ ጠይቀዋልከዚህ ጎን ለጎንም የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋልአቶ ላቀ በበኩላቸው በሀገሪቱ የተከሰተውን ችግር ለማለፍ መደጋገፍና በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል
https://www.fanabc.com/%e1%89%b0%e1%89%8b%e1%88%9b%e1%89%b1-%e1%8c%8d%e1%88%9d%e1%89%b3%e1%8b%8a-%e1%8b%8b%e1%8c%8b%e1%89%b8%e1%8b%8d-34-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab/
118
44,282
የሩሲያ ዋነኛ የተቃዋሚ መሪ አሌክስ ናቫሊ ከእስር ተለቀዋል
ፖለቲካ
January 30, 2018
Unknown
የሩሲያ ዋነኛ ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫሊ በሀገሪቱ መጋቢት ወር ላይ የሚካሄደውን ፕሬዚደንታዊ  ምርጫ  በመቃወም በሞስኮ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ተሳትፈዋል በሚል በፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ከዋሉ ከቀናት በኋላ መፈታታቸው ተነግሯልዜጎችን ለአመፅ በማነሳሳት ክስ ተጠርጥረው ዘብጥያ ወርደው የነበሩት ናቫሊ ከእስር ውጭ ሆነው ጉዳያቸውን መከታተል እንደሚችሉም ነው የተዘገበውየናቫሊ ጠበቃ ኦልጋ ማኪኤሎቫ ለሮይተርስ እንደተናገረችው ደንበኛዋ ያለምንም ክስ በነፃ የተለቀቁ ቢሆንም በቀጣይ ቀናት ግን ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለባቸው ተነግሮአቸዋል ብላለችፍርድ ቤቱ ሰልፎችን በማነሳሳት ወንጀል ከሷዋቸው ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እስከ 30 ቀናት የሚዘልቅ የእስር ቅጣት እንደሚጠብቃቸውም ነው የተነገረውበተጨማሪም ናቫሊም በቲውተር ገፃቸው ላይ እንደፃፉት ፍርድ ቤቱ ክሱን እስከሚያሰማበት ቀን ድረስ ከእስር ቤት መለቀቃቸውን ቢያረጋግጡም በክሱ ዙሪያ ላይ ተጨማሪ ዝርዝር ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል ነው የተባለውበሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያን የሀገራቸውን ዜጎች የመጋቢቱን የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተቃውመው ወደ ጎዳና እንዲወጡ ጥሪ ሲያቀርቡ ታይተዋልተቃውሞዎችን ሲያስተባብሩ የነበሩት ናቫሊ ተቃውሞው ሲካሄድበት በነበረበት ባንዱ ቦታ በተገኙበት ወቅት የአድማ በታኝ ፖሊሶች በቀረፃ ላይ የነበሩ የቴሌቪዥን ካሜራዎች ፊት ለፊት በመግባት ከከበቧቸው በኋላ ወደ አንድ የጭነት መኪና ውስጥ አስረው ሲያስገቧቸውት መታየታቸው የአደባባይ ሚስጥር ስለመሆኑም ተነግሯልየናቫሊ መታሰር ግን ደጋፊዎቻቸውን ተቃውሞአቸውን ከማሰማት  አልበገራቸውም ይልቁንም በሞስኮ ጎዳናዎች ላይ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን የሚያጣጥሉ መጣጥፎችን ይዘው መፈክር ሲያሰሙ እንደነበር ተመልክቷልበሀገሪቱ ውስጥ አመፅ አካሂዷል ተብለው የተጠረጠሩ ከ 240  በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ስለመዋላቸው ገለልተኛ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋልየፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዋነኛ ተቀናቃኝ የሆኑት ናቫሊ በመጋቢት 18 በሚካሄደው የፕሬዝዳንትነት ምርጫ ላይ በማጭበርበር ወንጀል በመከሰሳቸው እንዳይሳተፉ ታግዷልም ነው የተባለው ይሁንና የናቫሊ ደጋፊዎች  ክሱ ሆን ተብሎ እጩ ተወዳዳሪ  እንዳይሆኑ ለማስቻል ፖለቲካዊ ሴራን ያነገበ ነው ሲሉ ይሞግታሉበሌላ በኩል  የክሬምሊን ቤተመንግስት ተቃውሞውን ህገወጥ በሚል  ፈርጆ ናቫሊ ከምርጫው በፊት አለመረጋጋት ለመፍጠር ሙከራ እያደረጉ ነው ሲል ይከሳልሩሲያን እያስተዳደሯት የሚገኙት  ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምርጫ ውድድሩ እንዲሳተፉ ከተፈቀደላቸው እጩ ተወዳዳሪዎች በላቀ መልኩ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ድምፅ እንደሚያገኙና ለ4ኛ ጊዜ ሊመረጡ እንደሚችሉ ብዙዎች ግምታቸውን ያስቀምጣሉየፕሬዝዳንት ፑቲን ዋነኛ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው የላቀ ግምት አግኝተው የነበሩት ናቫሊ በፈረንጆቹ 201112 የክረምት ወቅት የጎዳና ላይ ተቃውሞዎችን ሲያነሳሱ እንደነበር የተነገረ ሲሆን በፈረንጆቹ 2017 አመት ብቻ እውቅና ያልተሰጠውን ፀረ ፑቲን አመፅ አነሳስተዋል በሚል 3 ጊዜ ለእስር ተዳርገዋልቢቢሲና ሲጂቲኤን ዘግበውታል
https://waltainfo.com/am/33781/
312
46,103
የክልል ተሳታፊዎች ባዛሮች የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደረዷቸው ገለጹ
ቢዝነስ
February 3, 2017
Unknown
የሀገር አቀፉ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቢሽንና ባዛር የገበያ ተስስር ለመፍጠር ምቹ አጋጣሚ እንደሆኑላቸው ከተለያዩ ክልሎች የመጡ የባዛሩ ተሳታፊዎች ገለፁከተሳታፊዎቹ መካከል ከአርባምንጭ እንደመጣ የገለፀልን ወጣት አስራት ካሳ በህዳሴ የሞሪንጋ ማቀነባበሪያ እንደሚሰራና በተለይም ተመሳሳይ የኤግዚቢሽንና ባዛር መድረኮች መዘጋጀታቸው የገበያ ትስትስ ለመፍጠር ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና በስፋት ለመሸጥ እድል የሚሰጥ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል ብሏልመድረኩ በተለይም ለክልል ኢንዱስትሪዎች ወደ መሀል ከተማ መጥተው እንዲሰሩ የሚፈጥረው እድል ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነም አስራት ጠቁሟልኤልሳቤጥና ታደለ የቆዳ ውጤቶች የህብረት ሽርክና ማህበር ባለድርሻ ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ፍቅሬ በበኩሏ ቀደም ሲል በ2ሺህ ብር የተመሰረተው ማህበራቸው አሁን ላይ ካፒታሉን ወደ 15 ሚሊየን ብር በማሳደግ ወደ መካከለኛ ኢንትርፕራይዝነት ከመሸጋገሩም ባሻገር ምርት ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ለመላክም ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተናግራለች ማህበሩ ለ22 ሰራተኞችም የስራ እድል መፍጠር እንደቻለም ተመልክቷልየማምረቻ ቦታ እጥረት ግን በስፋት ለማምረት እክል እንደሆባቸው ወይዘሮ ኤልሳቤጥ አክላ ገልፃለችኤግዚቢሽንና ባዛሩ በተለይም የገበያ ትስስር በመፍጠርና የሚሰራበት ፋብሪካ አዲስ እንደመሆኑ ምርቱን ለማስተዋወቅ መልካም እድል እንደፈጠረለት የነገረን ደግሞ የባህርዳሩ የዩኒክ የማካሮኒ ፋብሪካ የሽያጭ ባለሙያ እዮብ አዱኛ ነውየባህል ልብሶችን በተለይም በትግራይ ክልል የሚለበሱ የፈትል ልብሶችን ይዛ ኤግዚቢሽንና ባዛሩን የተቀላቀለቸው የአድዋዋ ወይዘሮ አብረኸት በርሄ በበኩሏ ኤግዚቢሽኑና ባዛሩ የክልሉን ባህላዊ አልባሳት ለማስተዋወቅና ከአከፋፋዮች ጋር በቀጣይ በጋራ ለመስራት እንደስቻላት ገልፃለችየፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ልማት ኤጀንሲ የሀገር ውስጥ ገበያ ልማት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ መልካም ጌታሁን የሀገር አቀፉ ኤግዚቢሽንና ባዛር በጥርና ግንቦት ወራት እንደሚካሄድና በዚህም በተለይ ከክልል የሚመጡ ኢንተርፕራይዞች ተሳትፏቸው እየጎላ መምጣቱን ገልፀዋል ኤጀንሲው ለኢንዱስትሪዎች ልማት በሰጠው ትኩረትም አስከ 5 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ወጪ በማድረግ በተለይም የወጣቶችን ተጠቃሚነትና የስራ እድል ፈጠራ ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነውበኤግዚቢሽንና ባዛሩ 109 ኢንትርፕራይዞችና 21 ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ እንደሆነ ታውቋልበኤግዚቢሽንና ባዛሩ ላይ ከአፋርና ሶማሌ ክልሎች በስተቀር በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እየተሳተፉ እንደሆነ አቶ መልካም አያይዘው ገልፀዋልጥር 22 በድምቀት የተከፈተው ኤግዚቢሽንና ባዛር አስከ ጥር 28 2009 ድረስ እንደሚቆይ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል ዘግቧል
https://waltainfo.com/am/22979/
279
43,954
ምክር ቤቱ ባጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ስኬቶች ላይ ውይይት እያደረገ ነው
ፖለቲካ
April 10, 2018
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባለፉት የ9 ወራት ውስጥ ባጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ስኬቶች ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለስምንት ቀናት የሚቆይ የከተማውን የተለያዩ ቢሮዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን እየገመገመ ነውምክር ቤቱ የከተማ መሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ የ2010 አም የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያዳመጠ ሲሆን በሪፖርቱም በተግባር ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ስኬቶች ተዳስሰዋልየአስተዳደሩ የማዘጋጃ ቤታዊ ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የተለያዩ ክፍለ ከተማ የስራ ሀላፊዎች በአሰራር ላይ አሉ ያሏቸውን ችግሮች አንስተዋልበዚሁም የመልካም አስተዳደር የመልሶ ማልማት የፕላን ጥሰትያለአግባብ ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ጉዳይ ኪራይሰብሳቢነት ህገወጥ ግንባታዎች እና የመሬት ወረራ በስፋት ተነስተዋልየከተማ የመሬት ባንክ እና ማስተላለፍ ፅህፈት ቤት የይዞታ አስተዳደር ፅህፈት ቤት እና የከተማ ማደስ ኤጄንሲ ሀላፊዎችም ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥቷልበምላሻቸውም የማስፈፀም አቅም ውስንነትተቀናጅቶ ያለመስራትመመሪያና አዋጆችን በአግባቡ አለመተግበር በዘርፉ ታቅደው ላልተከናወኑ ስራዎች ዋነኛ ተግዳሮት እንደበሩ አንስተዋልበቀጣይ ያሉት ችግሮችን በመፍታት የነበሩ ድክመቶችን ለማካካስ ዝግጅት መደረጉንም ጠቁመዋል
https://waltainfo.com/am/29773/
137
18,240
ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ ዓመቱ ከ22 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jan 15, 2020
715
አዲስ አበባ ጥር 6 2012 ኤፍ ቢ ሲ ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ አመቱ 22 ቢሊየን 40 ሚሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገበስድስት ወር አፈፃፀሙ የእቅዱን 104 በመቶ ማሳካቱንም አስታውቋል ካለፈው አመት አንፃር የ32 በመቶ እድገት አሳይቷልተቋሙ የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶችም 73 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማግኘቱን ጠቁሟልየተገኘው ገቢ ከሞባይል ድምፅ 50 ነጥብ 4 በመቶ ከዳታና ኢንተርኔት 27 ነጥብ 3 በመቶ ከአለም አቀፍ ንግድ ገቢ 9 ነጥብ 8 በመቶ እሴት ከሚጨምሩ አገልግሎቶች 8 ነጥብ 5 በመቶ እንዲሁም ከሌሎች አገልግሎቶች 3 በመቶ መሆኑም ተገልጿልየደንበኞቹ ብዛት 45 ነጥብ 6 ሚሊየን መድረሱን የጠቀሰው ሪፖርቱ ይህም ከእቅዱ የ99 በመቶ አፈፃፀም ያለው እና ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ10 ነጥብ 9 በመቶ እድገት አሳይቷል ብሏልበአገልግሎት አይነት ደግሞ የሞባይል ድምፅ ተጠቃሚዎች ብዛት ከ44 ሚሊየን በላይ የዳታ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚ 22 ነጥብ 74 ሚሊየን የመደበኛ ስልክ ከ1 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ሲሆኑ አጠቃላይ የቴሌኮም ስርፀት መጠን ደግሞ 45 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ተነግሯልተቋሙ በሪፖርቱ የደንበኞችን ሁለንተናዊ ተሞክሮ ለማሻሻልና በተለይም እያደገ የመጣውን የዳታ አገልግሎት ተጠቃሚነት ፍላጎት ማስተናገድ የሚያስችል የኔትወርክ አቅም የማሳደግ ስራዎች በአዲስ አበባና በክልሎች እየተከናወነ መሆኑንም ገልጿልከዚህ ባለፈም የደንበኞችን የቴሌኮም አጠቃቀም ለማሳደግና ተሞክሯቸውን ለማሻሻል የሚያስችሉ የኔትወርክ ማስፋፊያና የአገልግሎት ጥራትን ለመጨመር የሚያስችሉ ማሻሻያዎችን ማከናወኑንም ነው የገለፀውእንዲሁም ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎቶች በተጨማሪ ሌሎች እሴት የሚጨምሩ 6 አዳዲስ እና 16 የተሻሻሉ የሀገር ውስጥና የአለም አቀፍ ምርትና አገልግሎቶችን ለገበያ ማቅረቡንም አስታውቋልበዚህም ባሳለፍነው ስድስት ወራት ከተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች 759 ሺህ 741 ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል የሶስተኛ ትውልድ 3ጂ እና 170 ሺህ 737 የሁለተኛ ትውልድ 2ጂ ሞባይል ኔትወርክ አቅም መፍጠር መቻሉን ጠቅሷልበሌላ በኩል በፍጥነት እያደገ ያለውን የዳታ አጠቃቀም ለማስተናገድ የሚያስችል የአለም አቀፍ ጌትዌይ አቅምን በግማሽ አመቱ ከ71 በመቶ በላይ ማሳደግ ችያለሁም ነው ያለውከዚህ በተጨማሪም በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የአራተኛ ትውልድ 4ጂ ኔትዎርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው መባሉን ከኢትዮ ቴሌኮም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae-%e1%89%b4%e1%88%8c%e1%8a%ae%e1%88%9d-%e1%89%a0%e1%8c%8d%e1%88%9b%e1%88%bd-%e1%8b%93%e1%88%98%e1%89%b1-%e1%8a%a822-%e1%89%a2%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%ad/
280
18,862
አርመንያ እና አዘርባጃን የደረሱትን የተኩስ አቁም እንዲያከብሩ ተመድ ጥሪ አቀረበ
ዓለም አቀፍ ዜና
Oct 19, 2020
223
አዲስ አበባ ጥቅምት 9 2013ኤፍ ቢ ሲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አርመንያ እና አዘርባጃን የደረሱትን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቀረቧና ፀሀፊው በናጎሮኖ ካራባህ ግጭት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አውግዘዋልእስካሁን ድረስ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከደረሰው ጥቃት አንዱ የሆነውንና ቅዳሜ በተፈፀመ ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ የ13 ሰዎች ህይወት ያለፈበትን ክስተት አንስተዋልአርመንያ እና አዘርባጃን የናጎሮኖ ካራባህ ግዛት የይገባኛል ግጭት ውስጥ ከገቡ የሰነባበቱ ሲሆን በዚህ የተነሳ በሁለቱም ወገኖች ሰላማዊ ዜጎች ህይወት እያለፈ ይገኛልየናጎርኖካራባህ ክልል መከላከያ ሚኒስቴር በተደረገው ውጊያ 710 የሚደርሱ ወታደሮች ህይወት ማለፉን አስታውቋልከፈረንጆቹ 1990ዎቹ ጀምሮ በአካባቢው በተነሳው ግጭት ሳቢያ ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይነገራልምንጭ አልጀዚራ
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a0%e1%88%ad%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8b%ab-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8a%a0%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%89%a3%e1%8c%83%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%8b%b0%e1%88%a8%e1%88%b1%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%89%b0/
99
7,602
ነብዩ ስሑል ሚካኤል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ  ኃላፊ ሆነው ተሾሙ
ሀገር አቀፍ ዜና
2021-01-04
860
ነብዩ ስሁል ሚካኤል ከመጋቢት 012012 ጀምሮ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅኀፈት ቤት ሀላፊ ሆነው መሾማቸው ተገለፀፓርቲው ለህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ በፃፈው ደብዳቤ ነብዩ የተጣለባቸውን ሀላፊነት በትጋት እንዲፈፅሙም አሳስቧልጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከዚህ ቀደም ከትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ጋር መክራቸውም ይታወሳል
https://addismaleda.com/archives/10508
40
16,707
ባለፉት 24 ሰአታት ለ3 ሺህ 645 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው
ሀገር አቀፍ ዜና
May 22, 2020
5,086
አዲስ አበባ ግንቦት 14 2012 ኤፍ ቢ ሲ ባለፉት 24 ሰአታት ለ3 ሺህ 645 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 26 ወንድ እና 4 ሴቶች ናቸውሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች ሲሆኑ ከ15 እስከ 60 አመት የሚገኙ ናቸው ተብሏልቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 18 አዲስ አበባ 3 አፋር ክልል 4 ኦሮሚያ ክልል 3 ትግራይ ክልል እንዲሁም 2 የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ናቸውከእነዚህ ውስጥ 9ኙ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ 17 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆኑ ተገልጿልአራቱ ደግሞ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ግንኙነት የሌላቸው ናቸው5 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አዲስ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 128 ደርሷልFBCየዜና ሰአት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልእክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ
https://www.fanabc.com/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-24-%e1%88%b0%e1%8a%a0%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%88%883-%e1%88%ba%e1%88%85-645-%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%88%8b%e1%89%a6%e1%88%ab%e1%89%b6%e1%88%aa/
139
19,533
ከቻይና ውጪ የመጀመሪያው ሰው በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ አለፈ
ዓለም አቀፍ ዜና
Feb 2, 2020
713
አዲስ አበባ ጥር 24 2012 ኤፍ ቢ ሲ በፊሊፒንስ ከቻይና ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ተሰምቷልበኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈው የ44 አመቱ ቻይናዊ ወደ ፊሊፒንስ ከመጓዛቸው በፊት ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በተቀሰቀሰበት ውሀን ከተማ ነዋሪ እንደነበሩ ተገልጿልግለሰቡ ፊሊፒንስ ከመድረሱ በፊት በቫይረሱ ተይዞ የነበረ መሆኑን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስታውቋልከግለሰቡ ህልፈት በኋለም ፊሊፒንስ ወደ ቻይና እንዲሁም ከቻይና ወደ ፊሊፒንስ የሚደረግን ማንኛውንም የአውሮፕላን በረራ ሙሉ በሙሉ ሰርዛለችአሁን ላይ የአለም ስጋት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ300 በላይ ደርሷልበአጠቃላይ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም ከ14 ሺህ 300 በላይ ማሻቀቡ ነው የተነገረውበቅርቡ በቻይና ውሀን ከተማ የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ በአሁኑ ወቅት አድማሱን በማስፋት ወደ ተለያዩ ሀገራት እየተዛመተ ይገኛልይህን ተከትሎም አሜሪካ አውስትራሊያ እና ሌሎች በርካታ ሀገራት ከቻይና ወደ ሀገራቱ የሚደረጉ የአውሮፕላን በረራዎችን አግዷል
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a8%e1%89%bb%e1%8b%ad%e1%8a%93-%e1%8b%8d%e1%8c%aa-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%aa%e1%8b%ab%e1%8b%8d-%e1%88%b0%e1%8b%8d-%e1%89%a0%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93-%e1%89%ab%e1%8b%ad/
120
23,441
አርትስ ሚዲያ ፕሮዳክሽን የቀድሞ የምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚን ሾመ
ቢዝነስ
1 December 2017
Unknown
አርትስ ሚዲያ ፕሮዳክሽን አክሲዮን ማሀበር የቀድሞ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩትን አቶ ኤርሚያስ እሸቱን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ ሾመ አቶ ኤርሚያስ የምርት ገበያውን ለሶስት አመታት ካገለገሉ በኋላ የስራ መልቀቂያቸውን በቅርቡ ማስገባታቸው ይታወሳልአቶ ኤርሚያስ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከማንቸስተር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ሲያገኙ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በአለም አቀፍ ንግድ ከማንቸስተር ማኔጅመንት ትምህርት ቤት ወስዷል አቶ ኤርሚያስ የምርት ገበያን ከመቀላቀላቸው በፊት የዘመን ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩ ሲሆን ከ20 አመታት በላይ በአለም አቀፍ ደረጃ በሚታወቁት በአይቢኤም በአልካቴል በኦሬንጅና በማክሮ ስትራቴጂ ኩባንያዎች ውስጥ በተለያዩ የሀላፊነት ደረጃ ላይ ሰርተዋል አቶ ኤርሚያስ ግዙፍ አለም አቀፍ ኩባንያዎችን ሲመሩ የነበሩ የ44 አመት ጎልማሳ ናቸው አክሲዮን ማሀበሩ እኤአ በ2018 የመጀመርያው ሩብ አመት ስራውን በይፋ ለመጀመር ያቀደ ሲሆን አቶ ኤርሚያስ ያላቸው አለም አቀፍ ልምድ አዲስ ለተቋቋመው የሚዲያ ተቋም ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጿልአርትስ ሚዲያ ፕሮዳክሽን አክሲዮን ማሀበር በኦሊምፒክ መድረክ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቶ የኢትዮጵያ ስም ካስጠራው ታዋቂ አትሌት ጀምሮ በህክምና በትምህርት በፋይናንስ በህግ በሚዲያና በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ የሆኑ ግለሰቦች የተቋቋመ የሚዲያ ድርጅት ነው የሚዲያ ተቋሙ ዘመናዊና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን በቢዝነስ በፖሊሲና በባህል ላይ ያተኮሩ ይዘቶችን በመላው አፍሪካ ላሉ ተመልካቾቹ ለማቅረብ አቅዷልአርትስ ሚዲያ አክሲዮን ማሀበር መቀመጫውን ኢትዮጵያ ያደረገ ሲሆን የዜናና የመዝናኛ ፕሮግራሞች በአፍሪካዊ እይታ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል አርትስ በተለይ ለአፍሪካውያን ወጣቶችና አፍሪካዊ ዝርያ ላላቸው አለም አቀፍ ተመልካቾች የሚሆኑ ፕሮግራሞች እንደሚስተናገዱበት ይጠበቃል
https://www.ethiopianreporter.com/article/4156
199
14,474
ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበላቸው
ሀገር አቀፍ ዜና
Nov 5, 2020
1,822
አዲስ አበባ ጥቅምት 26 2013 ኤፍቢሲ በዛሬው እለት ጥቅምት 26 ቀን 2013 ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ ወደ መከላከያ ሰራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል በትናትናው እለትም ከዚህ በፊት ከመከላከያ ሰራዊት ተቀንሰው የነበሩ ሶስት መኮንኖች ጥሪ እንደቀረበላቸው የሚታወስ ነው ጥሪ የቀረበላቸው መኮንኖችም ሌጄኔራል ባጫ ደበሌ ሌጄኔራል ዬሀንስ ገመስቀል እና ሌጄኔራል አበባው ታደሰ መሆናቸው ይታወቃል
https://www.fanabc.com/%e1%88%9c%e1%8c%80%e1%88%ad-%e1%8c%80%e1%8a%90%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%88%9d%e1%8a%a5%e1%88%b8%e1%89%b5-%e1%8b%b0%e1%8c%8d%e1%8d%8c-%e1%8b%88%e1%8b%b0-%e1%88%98%e1%8a%a8%e1%88%8b/
53
26,257
ሕገወጦችን ሕጋዊ ለማድረግ ከፍተኛ የሊዝ ክፍያ ተጠየቀ
ቢዝነስ
5 April 2015
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህገወጥ ባለይዞታዎችን ህጋዊ ለማድረግ የሊዝ ዋጋ ስሌት መመርያ ከወጣ ከ75 ካሬ ሜትር በላይ መሬት የያዘ አካል ተጨማሪውን ቦታ ለመጠቅለል የሚጠየቀው ከፍተኛ የሊዝ ዋጋ እንደሚሆን ምንጮች ገለፁአግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ የተያዙ ቦታዎችን ለማስተካከልና ለመከላከል የወጣው መመርያ እንደሚለው ለመኖሪያም ሆነ ለድርጅት አገልግሎት አግባብ ያለው አካል ሳይፈቅድ የተያዘ ቦታ እስከ 75 ካሬ ሜትር ድረስ በሊዝ መነሻ ዋጋ ይስተናገዳል ነገር ግን ከዚህ የቦታ ስፋት በላይ የያዙና መመርያው የሚፈቅድላቸው ባለይዞታዎች በወቅታዊ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንደሚስተናገዱ በመመርያው ተደንግጓልበዚህ መሰረት ዋጋውን ለመተመን የሚያስችል መመርያ በሚዘጋጅበት ከፍተኛ የጨረታ ገንዘብ ማለት በአንድ ውስን ቦታ የተጫረቱ ሰዎች ያቀረቡት ገንዘብ አማካይ ነውበአሁኑ ወቅት በሁሉም የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሊዝ ጨረታ ዋጋ እየናረ በመምጣቱ ህገወጥ የተባሉትን ህጋዊ ለማድረግ ከፍተኛ ዋጋ እንዲጠየቅ መደረጉን መረጃዎች አመልክተዋልየአዲስ አበባ ከተማ የሊዝ መነሻ ዋጋ የተጋነነ ነው ባይባልም በጨረታ ለሚቀርቡ ቦታዎች እየቀረበ የሚገኘው የመጫረቻ ዋጋ ግን ከፍተኛ መሆኑን ባለሙያዎች ይገልፃሉ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጀመንት ቢሮ ባለሙያዎች ያዘጋጁት የሊዝ ዋጋ ስሌት መመርያ አንድ ካሬ ሜትር ቦታ ከ8000 ብር እስከ 30000 ብር እንዲከፈልበት ሆኖ ተሰልቷል ይህ ገንዘብ ሊሰላ የቻለው መመርያው ከ75 ካሬ ሜትር መሬት ብቻ በሊዝ መነሻ ዋጋ የሚሰጥ ሲሆን ቀሪውን ቦታ በአካባቢው ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን በመደንገኑ ነውበዚህ መሰረት በአሁኑ ወቀት ከሰሜን አዲስ አበባ ውጪ ያሉ ቦታዎች በጨረታ ወቅት እየቀረበላቸው ያለው ገንዘብ ከፍተኛ ነው አብዛኞዎቹ ቦታዎች ከ20000 እስከ 30000 ብር በካሬ ሜትር ሲሆኑ ዝቅተኛው ስምንት ሺህ ብር ከፍተኛው ደግሞ 33000 ብር ሆኖ በክብረ ወሰን ተመዝግቧልህገወጥ የሚባሉት ግንባታዎች በአስሩም ክፍላተ ከተሞች እንደሚገኙ በከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ስልጣን ዘመን የመሬት አስተዳደር ስራዎችን ስርአት ለማስያዝ የተዋቀረው ኮሚቴ ያቀረበው ሪፖርት ያሳያል በዚህ ሪፖርት በአስሩም ክፍላተ ከተሞች 102402 ይዞታዎች ሰነድ አልባ ናቸውበአሁኑ ወቅት ለማስተናገድ የታሰበው ከመጋቢት 1988 አም እስከ ሚያዝያ 1997 አም ድረስ ያሉ ይዞታዎችን ነው በዚህ መመርያ ለመስተናገድ 46042 ባለይዞታዎች ተመዝገብው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉከንቲባ ድሪባ ኩማ በቅርቡ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በቀረቡት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በመመርያው መሰረት እየተጣራ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲያገኙ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስረድተው ነበርበዚህ መሰረት ከቅድመ ዝግጅት ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የሊዝ ዋጋ ትመና ተጠናቋል ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ለተጠቀሚዎች በይፋ ተገልፆ ህገወጦችን ህጋዊ የማድረግ ስራው ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿልነገር ግን ህገወጥ ባለይዞታዎች የተባሉት የያዟቸው ቦታዎች ከ75 ካሬ የሚበልጡ እንደሆኑ የሚናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምንጮች ለቀሪው ይዞታ የሚጠየቀው ገንዘብ ከፍተኛ በመሆኑ በስራው ላይ ተፅእኖ ሊፈጥር እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል
https://www.ethiopianreporter.com/article/3356
356
47,973
ለ8ኛው የብሔርና ብሔረሰቦች በዓል ስኬት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ በጅጅጋ ከተማ የሚገኙ ባለሃብቶች ገለፁ
ፖለቲካ
November 27, 2013
Unknown
በመጪው ህዳር 29 በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አስተናጋጅነት ለሚከበረው 8ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል ስኬት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ በጅጅጋ ከተማ በተለያዩ የንግድ ስራዎች የተሰማሩ ባለሀብቶች አስታወቁ 8ኛው የብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦች በአል ህገመንግስታችን ለህዳሴያችን በሚል መሪ ቃል ህዳር29 በጅጅጋ ከተማ ይከበራልበጅጅጋ ከተማ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ባለሀብቶች መንግስት በአሉን ለማዘጋጀት የሚያደርገውን ዝግጅት በገንዘብ በጉልበት ሰላምና ፀጥታን በማረጋገጥ የራሳቸውን ድርሻ ለመወጣት በሚችሉበት ሁኔታ ለመሳተፍ  ትላንት ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ጋር ውይይት አካሂዷልበክልሉ አስተናጋጅንት የሚከበረውን 8ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል በተሳካ ሁኔታ ለማክበር በገንዘብ በጉልበትና የአካባቢያቸውን ሰላም ነቅተው በመጠበቅ ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ ባለሀብቶቹ በውይይቱ ወቅት አረጋግጠዋልአቶ አብዱልቃድር አብዱላሂ ፋራህ የተባሉ ባለሀብት በተለይ ለዋልታ እንደገለፁት በአገር አቀፍ ደረጃ በመንገድ በህንፃ ግንባታዎችና በውሀ ጉድጓድ ቀፋሮ ስራዎች በመሳተፍ ወደ ከፍተኛ ባለሀብትነት ለመሸጋገር የቻሉት ህገመንግስቱ በፈጠረላቸው በየትኛውም አካባቢ ተንቀሳቅሶ የመስራት መብታቸውን ተጠቅመው ነውበተወለዱበት የጅጅጋ ከተማን ጨምሮ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በተለያዩ ከተሞች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እየተነቀሳቀሱ መሆኑን ባለሀብቱ ጠቁመው ህዳር 29 የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል የአንድነትና የእኩልነት መሰረት የሆነው የአገሪቱ ህገመንግስት የፀደቀበት እለት በመሆኑ በአሉ ለእሳቸው ትልቅ ፍራ እንዳለው ተናግረዋል በመሆኑም ለበአሉ መሳካት በገንዘብ በጉልበትና የአካባቢያቸውን ሰላም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን እንደሚጠብቁ አረጋግጠዋል ወደ ጅጅጋ ከተማ የሚመጡ እንግዶች በበአሉ ተደስተው እንደሚመለሱ ያላቸውን ተስፋ አቶ የገለፁት አብዱልቃድር ባለሀብቶችም በዚህ አጋጣሚ የክልሉን አዋጭ የኢንቨስትመንት አማራጮች አይተው በክልሉ እንዲሳተፉ እድል ይፈጥርላቸዋል ብለዋልበጅጅጋ ከተማ የኖጎቭ ሆቴል ባለቤት አቶ ከድር ጅግሬ በበኩላቸው በአሉ የተሳካ እንዲሆን በከተማዋ የሚገኙ ባለሀብቶችና በመካከለኛ ንግድ ስራ የተሰማሩ ነጋዴዎች በሙሉ  በተቻላቸው ለመደገፍ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋልየብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል በክልሉ መከበሩ የህዘቦችን አንድነትና ብዝሀነት ከማጠናከሩም በላይ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው በተለይም በክልሉ የመሰረተ ልማት እንዲስፋፋና የህዝቦች ትስስር እንድጠናከር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል እንግዶች በአሉን በሰላም አክብረው እንዲመለሱም የተለያዩ ዝግጅቶች መደረጋቸውን በመጥቀስ ያለምንም ስጋት ወደ ጅጅጋ እንዲመጡ መልክታቸውን አስተላልፈዋልባለሀብቶቹን ያወያዩት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በበኩላቸው ባለሀብቶቹ በአሉን በተሳካ ሁኔታ ለማክበር በሚደረገው ጥረት በረሳቸው ተነሳሽነት እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ የሚመሰገን መሆኑን ተናግረዋል በተለይም ሀብታቸውን በኢንቨስትመንት ላይ በማዋል በክልሉ እየፈጠሩት ላለው የልማት አጋርነት መንግሰት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አቶ አብዲ መናገራቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል ዘግቧል
https://waltainfo.com/am/28334/
321
44,859
“ካለፈው እየተማርን በአዲሱ ዓመት ለተሻለ ውጤት በአዲስ መንፈስ እንነሳ!”-መንግስት
ፖለቲካ
September 1, 2017
Unknown
2010 2010 52009 10 2010 10 10       10
https://waltainfo.com/am/29338/
20
7,826
የቻይናው ስቴት ግሪድ ኩባንያ በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
2021-01-04
473
በአለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም በሀይል ዘርፍ ግንባር ቀደም ተጠቃሹ የቻይናው ኩባንያ ስቴት ግሪድ ኮርፖሬሽን በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ተገለፀ ኩባንያው ከገራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በቴክኖሎጂ እንዲሁም በእውቀት ሽግግር ዘርፍ አብሮ ለመስራትም መግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን መለሰ ይመር ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋልበመግባቢያ ሰነዱም ላይ ቻይናዊያን አስተማሪዎች ወደ ኮሌጁ በመምጣት ያካበቱትን እውቀት ለተማዎች በማካፈል ጠቃሚ ልምዶችን እንደሚያጋሩም ተጠቁሟል መለሰ በዚህ ጉዳይ ላይ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት የሚደረገው ድጋፍ ቻይናዊያን አስተማሪዎችን ከማስመጣት ባሻገር ተማሪዎች እዛው ቻይና አገር ድረስ በመሄድ የሚሰለጥኑበትንም መንገድ እንደሚመቻች ጠቁመዋል አያይዘውም ድጋፉ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የትምህርት እድል ለሚሰጣቸው ከሌሎች አፍሪካ አገራት ለተወጣጡ ተማሪዎችም ጭምር እንደሆነ ተገልጿልስቴት ግሪድ ኩባንያ በኢትዮጵያ ከሀይል ጋር በተያያዘ ግንባታዎችን እያካሄደ እና ግንብቶም ያስረከበ ኩባንያ ሲሆን ከዚህም መካከል በሆለታ የሚገኘው እና በትልቅነቱ በአፍሪካ ብሎም በአለም ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነውን የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ሰብ ስቴሽን መገንባቱን ለማወቅ ተችሏል በቻይናው ስቴት ግሪድ ኩባንያ የተገነባው እና በአፍሪካ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ በትልቅነቱ እና በቴክኖሎጂ ስብጥሩ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው የሆለታ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ጣቢያ ሰብ ስቴሽን በቴክኖሎጂ ሽግግር እና ስልጠና ዘርፍ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሆነም መለሰ ተናግረዋል በሰብ ስቴሽኑም በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር ሄደው የሚጎበኙበት እድልም እንደተመቻቸ አዲስ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል 
https://addismaleda.com/archives/6837
196
13,279
በወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልኡክ በጂማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ጉብኝት እያደረገ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
Dec 20, 2020
143
አዲስ አበባታህሳስ 11 2013ኤፍ ቢ ሲ በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳር እና የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ በወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልኡክ በጂማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ጉብኝት እያደረገ ነውልኡኩ በዞኑ ቀርሳ ወረዳ በእንስሳት ማደለብ እና አሳ ማርባት ተግባር ተሰማርተው የስራ እድል የተፈጠረላቸውን ወጣቶች የጎበኙ ሲሆን በቀጣይነት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ምክትል ርእሰ መስተዳሯ ገልፀዋል በአፈወርቅ አለሙከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘትየፋና ድረ ገፅ ይጎብኙተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%8b%88-%e1%88%ae-%e1%8c%ab%e1%88%8d%e1%89%b1-%e1%88%b3%e1%8a%92-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%98%e1%88%ab-%e1%88%8d%e1%8a%a1%e1%8a%ad-%e1%89%a0%e1%8c%82%e1%88%9b-%e1%8b%9e%e1%8a%95-%e1%8b%a8/
89
7,349
ማየትና መስማት የተሳናት ትውልደ ኢትዮጵያዊት ታዋቂውን የአሜሪካ ኩባንያ ከሰሰች
ዓለም አቀፍ ዜና
Saturday, 30 August 2014 10:31
2803
  ከሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በህግ ሙያ የተመረቀችውና በአሜሪካ በአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋችነት በመስራት ላይ የምትገኘው ማየትና መስማት የተሳናት ትውልደ ኢትዮጵያዊት የህግ ጠበቃ ሀቤን ግርማ በአካል ጉዳተኞች ላይ መድልኦ ይፈፅማል ስትል ስክሪፕድ የተባለውን ታዋቂ የአሜሪካ የድረገፅ ኩባንያ መክሰሷ ተዘገበ ቢዝነስ ኢንሳይደር ድረገፅ ባለፈው ሳምንት እንደዘገበው ዲጂታል መረጃዎችን ለአንባብያን በስፋት በማቅረብ የሚታወቀው ስክሪፕድ የተባለው ኩባንያ የሚከተለው አሰራር ማየት የተሳናቸው አንባቢዎችን ፍላጎት ያላሟላና መድልኦ የሚፈጥር ነው በማለት ነው ሀቤን በኩባንያው ላይ ክስ የመሰረተችው የ26 አመቷ ጠበቃ ሀቤን ግርማ ናሽናል ፌደሬሽን ኦፍ ዘ ብላይንድ እና ብላይንድ ቬርሞንት ማዘር ሄዲ ቪነስ የተባሉትን የአሜሪካ የአይነስውራን መብቶች ተሟጋች ተቋማት በመወከል በስክሪፕድ ላይ በመሰረተችው ክስ ኩባንያው የድረገፅ አገልግሎቶቹ ሆን ብሎ ለአይነስውራን አንባብያን ተደራሽ እንዳይሆኑ በማድረግ የአገሪቱን የአካል ጉዳተኞች ህግ በሚጥስ መልኩ ያልተገባ ድርጊት ፈፅሟል ብላለችስክሪፕድ ከ40 ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያጠናከራቸውን መረጃዎች በድረገፁና በአፕሊኪሽኖቹ አማካይነት ለደንበኞቹ 8 ነጥብ 99 የአሜሪካ ዶላር ወርሀዊ ክፍያ በማስከፈል የሚያሰራጭ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የሚፅፉ ደንበኞቹን ስራዎች በድረገፅ አማካይነት ታትመው ለንባብ እንዲበቁ በማድረግ በአለማቀፍ ዙሪያ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኝ ኩባንያ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ገልጧልስትወለድ ጀምሮ ማየትና መስማት የተሳናት ሀቤን ትምህርቷን የተከታተለችው በአሜሪካ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከሊዊስ ኤንድ ክላርክ ኮሌጅ ተቀብላለች ከሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲም በህግ የሁለተኛ ዲግሪ ይዛለች በአሁኑ ወቅትም በበርክሌይ የአካል ጉዳተኝነት መብት ተሟጋች ጠበቃ በመሆን እያገለገለች ትገኛለችየቢዝነስ ኢንሳይደር ድረገፅ የ2013 እጅግ አስደማሚ 20 ምርጥ የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሚል ባለፈው አመት ከመረጣቸው ተጠቃሽ ተማሪዎች መካከል ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሀቤን ግርማ አንዷ እንደነበረች ዘገባው አስታውሷል
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=14785:%E1%88%9B%E1%8B%A8%E1%89%B5%E1%8A%93-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%88%9B%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%88%B3%E1%8A%93%E1%89%B5-%E1%89%B5%E1%8B%8D%E1%88%8D%E1%8B%B0-%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8B%8A%E1%89%B5-%E1%89%B3%E1%8B%8B%E1%89%82%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9C%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%8A%A9%E1%89%A3%E1%8A%95%E1%8B%AB-%E1%8A%A8%E1%88%B0%E1%88%B0%E1%89%BD&Itemid=212
221
17,919
ጠ/ሚ ዐቢይ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጉብኝታቸው የኢትዮጵያውያንን መብትና ጥቅም በሚያስከብሩ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ – አቶ ንጉሱ
ሀገር አቀፍ ዜና
Feb 12, 2020
724
አዲስ አበባ የካቲት 4 2012 ኤፍቢሲ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በሚያደርጉት ጉብኝት በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መብት እና ጥቅም የሚያስከብሩ ውይይቶችን እንደሚያደርጉ ተገለፀ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የሚያደርጉትን የሶስት ቀናት ጉብኝት አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን መግለጫ ሰጥተዋል በመግለጫቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከ15 ሺህ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ ብለዋል ዜጎች ክብራቸው ተጠብቆ መብታቸው ተከብሮ ጥቅማቸው ተረጋግጦ እና በማንነታቸው ኮርተው እንዲኖሩ የሚያስችሉ ውይይቶችን ከዜጎች እና ከመሪዎች ጋር ያደርጋሉም ነው ያሉት አቶ ንጉሱ ዜጎች ህጋዊነትን በተላበሰ ሁኔታ እንዲሰማሩ ከማድረግ ባሻገር የህግ ስምምነቶችን ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር መከናወኑን በመግለጫቸው አንስተዋል በዚህም እስካሁን ድረስ ከዮርዳኖስ ኳታር ሳኡዲ አረቢያ እና ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጋር ስምምነት መደረሱን አስረድተዋል ስምምነቶቹ ዜጎች ያሉባቸውን ችግሮች መቅረፍ እንሚያስችሉ እና አፈፃፀማቸው ላይ ውይይት እንደሚካሄድም ነው የተናገሩት መንግስት በአሁኑ ወቅት በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ትኩረት በማድረጉ እስካሁን ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አብራርተዋል
https://www.fanabc.com/%e1%8c%a0-%e1%88%9a-%e1%8b%90%e1%89%a2%e1%8b%ad-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%89%a3%e1%89%a0%e1%88%a9%e1%89%b5-%e1%8b%93%e1%88%a8%e1%89%a5-%e1%8a%a2%e1%88%9a%e1%88%ac%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%8c%89%e1%89%a5/
141
40,448
የካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት ዛሬም ቀጥሏል
ዓለም አቀፍ ዜና
August 22, 2020
Unknown
የምእራብ ዩናይትድ ስቴትስዋ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የተዛመተው የደን ሰደድ እሳት ዛሬም ቀጥሏልአገረ ገዥው ጋቪን ኒውሰም ቃጠሎውን ለመቆጣጠር አለም አቀፍ እገዛ ተማፅነዋልወደ አምስት መቶ ስድሳ በሚጠጉ ስፍራዎች በክፍለ ግዛቷ ዙሪያ የተቀሰቀሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት አስራ ሁለት ሺህ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እይተረባረቡ ናቸውበሰደድ እሳቱ እስካሁን ቢያንስ አምስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ጨምሮ አርባ ሶስት ሰዎች ተጎድተዋል ያሁኑ የአየር ሁኒታ ቃጠሎውን ያባብሰዋል የሚል ስጋት አለፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ አድርጉ ያልኳቸውን ስላልሰሙ ነው ብለው ለቃጠሎው የክፍለ ግዛትዋ አስተዳዳሪዎች ወቅሰዋል ጫካው ውስጥ ለአመታት የተከመረውን ቅጠሉን እና የወደቀ ዛፍ ጥረጉ ብያቸው ነበር ብለዋል
https://amharic.voanews.com//a/california-fire/5554042.html
87
10,343
አልቃይዳ እና አይ ኤስ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት መግባታቸው ተገለጸ፡፡
ዓለም አቀፍ ዜና
May 15, 2020
124
ባህር ዳር ግንቦት 072012 አም አብመድ ለአመታት ጥምረት መስርተው በማሸበር የሚታወቁት አልቃይዳ እና አይ ኤስ አይ ኤስ በሳሀል ቀጣና ጦር መማዘዛቸው ተሰምቷል በቅርቡ ሁለቱ ቡድኖች በመካከላቸው ስንጥቅ ተፈጥሮ እርስ በእርስ መታኮስ እንደጀመሩ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነውበመጀመሪያ በሶሪያ አካባቢ ይንቀሳቀሱ የነበሩት የሽብር ቡድኖቹ ወደ አፍሪካም ተስፋፍተው በሳሀል ቀጣና አካባቢ የተደራጀ ጥቃት ሲያደርሱ መቆየታውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧልእአአ በ2012 በማሊ መንቀሳቀስ የጀመረው አልቃይዳ የሽብር ቡድን ይዞታውን እያስፋፋ በቡርኪናፋሶ እና ኒጀር ጭምር ጥቃት ሲፈፅም ነበር በዚህ የተነሳም በሽዎች የሚቀጠሩ ወታደሮች ተገድለዋል በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ደግሞ ከቀያቸው ተሰድዷልበቅርቡ ደግሞ በአሸባሪ ቡድኖቹ በመካከላቸው አልፎ አልፎ ይነሳ የነበረው ግጭት በተያዘው የአውሮፓውያን አመት መግቢያ አንስቶ እያደገ ሄዶ ወደ ለየለት ግጭት መግባታቸው ነው የተገለፀውለአካባቢዎቹ ቅርበት ያላቸው የዘርፉ ልሂቃንና የአካባቢው መንግስታት እንደገለፁት በማእከላዊ ማሊ እና ቡርኪናፋሶ አካባቢ አልቃይዳ እና አይ ኤስ አይ ኤስ ወደለየለት ጦርነት ገብተዋል የግጭታቸው ምክንያት ደግሞ የግዛት ማስፋፋት እና ሰብል ማምረቻ ለም አካባቢዎች ላይ የተፈጠረ ይገባኛል መሆኑ ነው የተመላከተውበተባሩት መንግስታት ድርጅት የማሊ ልዩ ተወካይ ማሀማት ሳልህ አናዲፍ የሁለቱ ነውጠኛ ቡድኖች ወደ ግጭት መግባት ድብቅ አይደለም የማናውቀው የግጭታቸውን መቋጫ ነው ሁለቱም የበላይነቱን መውሰድ ይፈልጋሉና ለዚህም እየተፋለሙ ነው ብለዋልአልቃደይዳ በሰሜናዊ ማሊ እግሩን የተከለው በ2012 እአአ ነው በኋላም ከሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ጋር ሀብረት ፈጥሮ በማእከላዊ ማሊ በ2015 እአአ የራሱን ይዞታ መስርቷልየአይ ኤስ የቀጣናው ታሪክ ግን ከአልቃይዳ አንፃር አጭር የሚባል ነው እንደ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘገባ አቡ ዋድ አልሳህሩይ ከተባለ ሰው ጋር በመጣመር ነው በ2015 አልቃይዳ የተመሰረተው በዚህ ወቅትም በማሊ ቡርኪናፋሶና ኒጀር ድንበር አካባቢ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል
https://www.amharaweb.com/%e1%8a%a0%e1%88%8d%e1%89%83%e1%8b%ad%e1%8b%b3-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8a%a0%e1%8b%ad-%e1%8a%a4%e1%88%b5-%e1%8b%88%e1%8b%b0-%e1%8a%a5%e1%88%ad%e1%88%b5-%e1%89%a0%e1%8a%a5%e1%88%ad%e1%88%b5-%e1%8c%a6/
229
20,835
እስር ቤት ሳይሆን ኳራንታይን ነው የገቡት የተባሉት የፌዴራሊስት ኃይሎች አባላት መለቀቃቸውን ተናገሩ
ፖለቲካ
3 June 2020
Unknown
በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ግንቦት 10 ቀን 2012 አም በሚደረገው የፌዴራሊስት ሀይሎች ስብሰባ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች በረራ ማስተናገጃ ህንፃ አንድ ተገኝተው ለመብረር በመዘጋጀት ላይ እያሉ በፀጥታ ሰዎች ተይዘው መታሰራቸው የተገለፀው የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች የተጠረጠራችሁት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ነው ተብለው መለቀቃቸውን ተናገሩሪፖርተር ያነጋገራቸው የነፃነትና ሰላም ለኢትዮጵያ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ተሻገር አረጋና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ንቅናቄ ፕሬዚዳንት አቶ መሳፍንት ሽፈራው እንደገለፁት ምንም እንኳን እስር አይደለም ቢባሉም በ16ኛ ቀናቸው ተፈትተዋል በወቅቱ ወደ መቀሌ ለመሄድ በዝግጅት ላይ እያሉ ስማቸው ተጠርቶ ወደ ምድር ቤት እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ ውስጥ ለውስጥ በእግራቸው በአየር መንገዱ አውቶቡስ ተሳፍረው ወደ አለም አቀፍ በረራ መግቢያ በር እንደተወሰዱ ገልፀዋልከውጭ የገቡ እንግዶች በሚገቡበት በር ሲገቡ በር ላይ ፎርም እንዲሞሉ ሲጠየቁ እኛ ወደ መቀሌ ለመብረር ከአዲስ አበባ ነው የመጣነው ስለዚህ ፎርም መሙላት አያስፈልገንም የሚል ምላሽ ሲሰጡ በፎርም አስሞዪዎቹና በፀጥታ ሰዎች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር ተናግረዋል የፀጥታ ሀይሎች ለሀኪሞቹ ያስረዱት ግለሰቦቹ ከውጭ አገር ዜጎች ጋር ግንኙነት ስለነበራቸው መመርመር አለባቸው ቢሉም ሊስማሙ ባለመቻላቸው የፀጥታ ሀይሎች የጠሯቸው ሌሎች ሀኪሞች ጋወን የለበሱ መጥተው ፎርሙን እንዲሞሉ ካስደረጓቸው በኋላ ሙቀታቸው ተለክቶ እንዲቀመጡ መደረጉን ገልፀዋልትንሽ ቆይቶ የሲቪል ሰርቪስ አውቶብስ መጥቶ ለ16 ቀናት ወደ ቆዩበት ልዳታ አካባቢ በሚገኘው ህንፃ ኮሌጅ ወስደው እንደስገቧቸው ተናግረዋል ህንፃ ኮሌጅ እንደ ደረሱ እዚያ ያሉ ሀኪሞች አንቀበልም ያሉ ቢሆንም ለብቻቸው ወስደው ካነጋገሯቸው በኋላ በአደራ ተቀብለናችኋል በማለት ለየብቻቸው እንዲቀመጡ መደረጉንም አስረድተዋልከ16 ቀናት ቆይታ በኋላ የምርመራ ናሙና ተወስዶ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸውና ወደ ቤታቸው መሄድ እንደሚችሉ ተነግሯቸው ከቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸውንም ተናግረዋልከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ለአቶ መስፍን ሽፈራው ለአቶ ተሻገር አረዳ ለኢሰዴፓ ተወካይ ወሪት መዲና ኢማም ኢዴአን የተሰረዘ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጉኡሽ ገብረ ስላሴ የኢድህ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ገብሩ በርሄ ናቸው አቶ ገብሩ በርሄ ግን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሌሎቹ ሲወጡ እሳቸው እንዳልተለቀቁ ከፓርቲ አመራሮች ገለፃ ለመረዳት ተችሏል
https://www.ethiopianreporter.com/article/19020
276
8,576
ፕሬዝዳንት ኮንዴ የሀገሪቱን ሕገ-መንግሥት በማሻሻል ለሦስተኛ ጊዜ እየተወዳደሩ ነው
ፖለቲካ
2021/1/22 20:39 GMT
Unknown
የ 82 አመቱ ለሶስተኛ ጊዜ በሚወዳደሩበት የጊኒ አወዛጋቢ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራጮች ድምፃቸውን እየሰጡ ነው ቀድሞውንም በፖለቲካ ቀውስ የተከፋፈለችው የምእራብ አፍሪካዊቷ ሀገር አርብ እለት ታጣቂዎች በአንድ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ አንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ከገደሉ በኋላ የባሰ ውጥረት ውስጥ ገብታለች ፕሬዝዳንት ኮንዴ በርካታ ትችቶችን ጆሮ ዳባ ልብስ ብለው በመተው የህገመንግስት ለውጥ በማድረግ ነው ለሶስተኛ ጊዜ በእጩነት የቀረቡት ዋነኛ ተፎካካሪያቸው ሁለት ጊዜ ተወዳድረው በእሳቸው የተሸነፉት ሴሉ ዳሌን ዲያሎ ናቸው በምርጨጫ ቅስቀሳ ወቅት የተከሰቱ የጎሳ ግጭቶች የምርጫ ውጤቱ አከራካሪ ከሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ብጥብጥ እንዳይፈጠር ከወዲሁ ስጋት እንዲፈጠር አመላካች መሆናቸው ተዘግቧል የሀገሪቱ መንግስት የፀጥታ ምክንያቶችን በመጥቀስ ከአንዳንድ የጎረቤት ሀገራት ጋር ከወዲሁ ድንበሮችን ዘግቷል ወደ 54 ሚሊዮን መራጮች ድምፅ እንደሚሰጡ የሚጠበቅ ሲሆን ውጤቱ ለብዙ ቀናት ሳይገለፅ ሊቆይ ይችላል እንደ ቢቢሲ ዘገባ እጩዎች በቀጥታ ለማሸነፍ ከ 50 በመቶ በላይ ድምፅ ማግኘት ያስፈልጋቸዋል ይህ ካልሆነ ደግሞ በአውሮፓውያኑህዳር 24 ቀን ሁለተኛ ዙር ምርጫ ይደረጋል ጊኒ ከነፃነት በኋላ በአምባገነናዊ እና በወታደራዊ አገዛዝ ስር እንደቆየች ይገለፃል ሰራዊቱ ዳግም ፖለቲካ ውስጥ ሊገባ ይችላል የሚል ስጋትም አለ የመከላከያ ሚኒስትሩ አርብ እለት በሰጡት መግለጫ የተወሰኑ ወታደሮች ከዋና ከተማዋ ኮናክሪ በስተሰሜን አቅጣጫ በ 130 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ኪንዲያ ውስጥ ወደሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ በመግባት የካምፑን ኮማንደር ኮል ማማዲ ኮንዴን መግደላቸውን ገልፀዋል አንዳንድ ዘገባዎች ኮማንደሩን አንድ ወታደር እንደገደለ ቢያመለክቱም በኋላ ላይ ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫ ድርጊቱን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ እና ወንጀሉን የፈፀሙ ወታደሮችን ለመያዝ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል
https://am.al-ain.com/article/voters-in-guinea-are-casting-their-ballots
215
23,765
የሰፋፊ እርሻ ባለቤቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘርፉን ከአደጋ እንዲታደጉ ጠየቁ
ቢዝነስ
23 August 2017
Unknown
ሶስት መቶ ሀምሳ ያህል የሰፋፊ እርሻ ልማት ባለሀብቶችን እንወክላለን ያሉ አራት ማሀበራት እያጋጠሙ ባሉ ተግዳሮቶች ምክንያት ዘርፉ አደጋ ላይ እየወደቀ ስለሆነ መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለ ማርያም ደሳለኝን ጠየቁባለፈው ሳምንት በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተፃፈው ደብዳቤ ማሀበራቱ በስራቸው ያሉት ባለሀብቶች የመንግስትን ራእይና እቅድ አይተው ዘርፉ ውስጥ ቢገቡም ዘርፉን እንዲደግፉ በመንግስት የተቀመጡ አንዳንድ ሀላፊዎች የሰነቁትን አብሮ የማደግ ራእይ ለማኮላሸት ከጫፍ እንደደረሱ ገልፀዋል ስለዚህ ሀላፊነት የተሰጣቸው ባለድርሻ አካላት በመንግስት ቢሮክራሲ ውስጥ ጭምብል ለብሰው ለኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ ኢኮኖሚ ልእልና ተግተው የሚሰሩና በፀረ ልማት መስመር የተኮለኮሉ አንዳንድ ሀይሎችና አሰራሮች ላይ ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ በእርስዎ በኩል ይውሰዱልን ሲሉ ተማፅነዋልአያይዘውም ባለሀብቶች በአሁኑ ወቅት ዘርፉ እየገጠሙት ነው ያሏቸውን አምስት ዋና ዋና ችግሮች ጠቅሰዋል ወደ ስራ ከተገባ በሀላ አጋጠሙ ያሏቸውን የፖሊሲና የመመርያ መለዋወጥ የመሰረተ ልማት እጥረት የመልካም አስተዳደር መጓደል የፀጥታ ችግሮችና እንዲሁም የግብአት አቅርቦት ችግሮችን በዝርዝር እንደ አብነት ጠቁመዋልከዚህ ቀደም ለዘርፉ ሲደረጉ የነበሩ ብድርን የመሳሰሉት ድጋፎች አንድ አመት ለሚጠጋ ጊዜ ተቋርጠው እንደነበር ይታወሳልበተጨማሪም ከዚህ ቀደም በጋምቤላ ክልል በሚገኙ ሰፋፊ የእርሻ ልማቶች ላይ በተደረገው ጥናትና በቀረቡ ግኝቶች ምክንያት በባለሀብቶቹና በዋናነት ለዘርፉ ብድሮች ሲያቀርብ በነበረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መካከል ውዝግቦች ተነስተው ነበርበጥናቱ ለዘርፉ ሲሰጡ የነበሩ ብድሮች ለሌሎች ያልተገቡ ጉዳዮች ጥቅም ላይ እንዷሉ ቢገለፅም ባለሀብቶቹ ይኼን አጥብቀው ተቃውመዋልበቅርቡም መሬታቸውን ተነጥቀው የነበሩ 186 ባለሀብቶች መሬታቸው በክልሉ እንዲመለስላቸው ተደርጓል ነገር ግን ባለሀብቶቹ በፃፉት ደብዳቤ በዘርፉ አሁንም ድረስ የተወሳሰቡ ችግሮች ስላሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋልለምሳሌ ልማት ባንክ በሰፋፊ እርሻዎች ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ብድር በመስጠት የግብር ኢንቨስትመንትን ለመደገፍ የሚሰራ የፖሊሲ ባንክ ሆኖ ሳለ አሁን ግን ሀላፊነቱን እየተወጣ አይደለም ብለዋልካስቀመጡት ፀረ ልማት አቅጣጫዎች በመነሳት የባንኩ አመራሮች በየጊዜው የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታትና ለማለፍ ፍላጎት ቅንነትና ቁርጠኝነት የተላበሱ አይደሉም ሲሉ ገልፀዋልከመሰረተ ልማት ጋር በተያያዘ ኢንቨስትመንቶቹ የሚከናወኑባቸው ቦታዎች ላይ ያለው የመሰረተ ልማት አለማሟላት ባለሀብቱን ለተጨማሪ ወጪና ልፋት እንዳጋለጠውና የተመረተውን ወደ ገበያ ለማውጣት መቸገራቸውን ጠቁመዋልበመጨረሻም ባለሀብቶቹ አሉ ያሏቸውን ችግሮች ለመፍታት ሁሉም የዘርፉ ተዋናዮች ያሉበት የጋራ ኮሚቴ እንዲቋቋም ጠይቀዋል       
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%8B%A8%E1%88%B0%E1%8D%8B%E1%8D%8A-%E1%8A%A5%E1%88%AD%E1%88%BB-%E1%89%A3%E1%88%88%E1%89%A4%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8C%A0%E1%89%85%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%A9-%E1%8B%98%E1%88%AD%E1%8D%89%E1%8A%95-%E1%8A%A8%E1%8A%A0%E1%8B%B0%E1%8C%8B-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B2%E1%89%B3%E1%8B%B0%E1%8C%89-%E1%8C%A0%E1%8B%A8%E1%89%81
288
45,811
ሩሲያ የአሜሪካንን የሚሳኤል ጥቃት አወገዘች
ፖለቲካ
April 8, 2017
Unknown
ዩናይትድ ስቴትስ በሶሪያ ላይ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ ሩሲያ የአሜሪካንን ድርጊት ክፉኛ አወገዘችአሜሪካ በሶሪያ መንግስት ላይ ያካሄደችው የሚሳኤል ጥቃት የመጀመሪያው ቀጥታ ወታደራዊ ጣልቃ መግባቷን ያሳያል ነው የተባለው የፕሬዚዳንት ባሽር አል አሳድ መንግስትን የምትደግፈው ሩሲያ የአሜሪካንን ድርጊት ከመኮነን ባለፈ በሶሪያ አየር ክልል ውስጥ የሁለቱ ሀገራት የጦር ጄቶች የአየር ላይ ግጭትን እንዳያካሂዱ ገቡትን ስምምነት ሩሲያ መሰረዟን አስታውቃለችአሜሪካ የተጠቀመችው ተወንጫፊ ክሩዝ ሚሳኤል ዝቅ ብሎ የሚጓዝ ሲሆን በአየር መቃወሚያ ለማምከን አስቸጋሪ ነውሩሲያ የሶሪያን ከምድር ወደ አየር ተምዘግዛጊ ሚሳኤል ስርአት በማሻሻል የሶሪያን የመከላከል አቅም ለማሳደግ ውጥን እንደላት እየተነገረ ነውሶሪያ በሶቬት ዘመን የነበራት ብሄራዊ አየር ሀይል ስርአት ጠንካራ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ጦርነት በአየር ላይ መከላከል አቅሟን እንዳዳከመው ይነገራልሩሲያ የተወሰኑ ዘመናዊ ከምድር ወደ አየር ተወንጫፊ የሚሳኤል የጦር መሳሪያዎች በሶሪያ አየር ሀይል ምድብ ይገኛሉየሩሲያ ወታደራዊ ቃለ አቀባይ ሜጀር ጀነራል ኢጎር ኮንሼንኮቭ በሰጡት መግለጫ የአሜሪካ አየር ላይ ጥቃቶች እጅግ ዝቅተኛ ያውም ከ59 የሚሳኤል ጥቃቶች 23 ብቻ ናቸው ኢላማቸውን የሚመቱት ነው ያሉትየአሜሪካ ባካሄደችው የሚሳኤ ጥቃት የእቃ ማከማቻ መጋዝን የማሰልጠኛ ህንፃ እና ለጥገና የቆሙ ሚግ23 ጄቶች ማውደሟን የሩሲያ ጦርን ጠቅሶ ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል የሶሪያ መንግስት በጥቃቱ ስድስት ወታደሮች መገዳለቸውን አስታውቋል ኤፍ ቢ ሲ
https://waltainfo.com/am/33601/
178
35,233
ሁለቱ አስቻለዎች ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ…
ስፖርት
July 17, 2015
Unknown
የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ውዱስ ጊዮርጊስ በዝውውር ላይ ዝምታን መርጦ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ወሳኝ ተጫዋቾችን ለማዘዋወር ከጫፍ መድረሱን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ የደደቢቱ ተከላካይ አስቻለው ታመነ እና የኢትዮጵያ ቡናው የመስመር አጥቂ አስቻለው ግርማ ፈረሰኞቹን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል በቃል ደረጃም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአስቻለው ታመነ ጋር መስማማቱ ተነግሯል አስቻለው ታመነ ውሉን ለማደስ ከደደቢት ጋር ተስማምቷል ተብሎ መዘገቡም አይረሳም አስቻለው ታመነ በደደቢት እና በዋሊያዎቹ መለያ ያሳየው ድንቅ ብቃት ወደ 12 ግዜ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊዎቹ እይታ ውስጥ ከቶታል ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአስቻለው ታመነ ዝውውር ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ አልተገለፀም የመስመር አጥቂው አስቻለው ግርማ ሌላኛው ቅዱስ ጊዮርጊስን ይቀላቀላል ተብሎ የሚጠበቅ ተጫዋች ነው የኢትዮጵያ ቡናው ተጫዋች በአሁን ሰአት ለእረፍት ባሌ ይገኛል ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ውሉን ለማደስ ድርድር ላይ ነው የተባለው አስቻለው ለቡና ባላንጣ ወደ ሆነው ጊዮርጊስ ለማምራት ከጫፍ መድረሱን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉቅዱስ ጊዮርጊስ በተያያዘ የደደቢቱን የመስመር ተጨዋች ታደለ መንገሻን ለማስፈረም ፍላጎት አለው በቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ በ2001 የተጫወተው ታደለ ወደ ቀድሞ ክለቡ የመመለስ እድሉ ሰፊ ነው ተብሏል ቅዱስ ጊዮርጊስ የተከላካዩን ሳላዲን በርጌቾ እና የመሀል ሜዳ ተጫዋቹን ምንያህል ተሾመ ውል ለማደስ ከጫፍ ደርሷል አምና ከኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው ፋሲካ አስፋው ክለቡን የመልቀቅ እድሉ በጣም የሰፋ ነውየዋሊያዎቹ አጥቂ ባዬ ገዛኸኝ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ድርድር ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ለመከላከያ በመፈረሙ ዝውውሩ እውን መሆን ሳይችል ቀርቷልየአስቻለው ታመነ መምጣት ዩጋንዳዊውን አይዛክ ኢዜንዴ በፈረሰኞቹ የሚኖረው ቆይታ አጠራጣሪ ያደርገዋል በተያያዘም ጊዮርጊስ አንድ ጋናዊ ተጨዋች ለማምጣት ድርድር ላይ መሆኑ ታውቋል
https://soccerethiopia.net/football/3094
217
22,624
የግል ባንኮች ትርፍ ከ10.5 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሰ
ቢዝነስ
18 July 2018
Unknown
የአገሪቱ የግል ባንኮች በ2010 ሂሳብ አመት ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ105 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፋቸው ታወቀ የ16 የግል ባንኮች የ2010 ሂሳብ አመት ግርድፍ የሂሳብ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት ያገኙት የትርፍ መጠን ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው በአገሪቱ ላለፉት ሶስት አመታት ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በ2010 አም የራሱ የሆነ ተፅእኖ አሳድሯል ቢባልም የግል ባንኮች የትርፍ ምጣኔ እድገት ግን እየጨመረ ነው ሪፖርተር ያገኘው ግርድፍ የሂሳብ ሪፖርት እንደሚያመለክተው አዋሽ ባንክን ጨምሮ አራት ባንኮች በ2010 አም ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት ከፍተኛ ትርፍ አግኝተዋል የመጀመርያውን ደረጃ ከያዙት ሁለቱ ማለትም አዋሽ ባንክ 196 ቢሊዮን ብር ዳሸን ባንክ ደግሞ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በማትረፍ ይጠቀሳሉ ሁለት ባንኮች ደግሞ ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ አትርፈዋል ከግርድፉ የሂሳብ ሪፖርቱ መረዳት እንደሚቻለው በ2010 ሂሳብ አመት የሁሉም የግል ባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 2673 ቢሊዮን ብር መድረሱን ነው  ሪፖርተር ያገኘው ግርድፍ የሂሳብ ሪፖርት የባንኮቹ ትርፍ ላይ ያተኮረ ክፍል ሲሆን ባንኮቹ ምን ያህል ገንዘብ በሂሳብ አመቱ እንዳበደሩና ለትርፋቸው ያደረገውን አስተዋፅኦ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ይጠበቃል  
https://www.ethiopianreporter.com/article/11929
159
14,827
በመተከል ዞን ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ውይይት እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
Oct 21, 2020
369
አዲስ አበባ ጥቅምት 11 2013 ኤፍቢሲ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ውይይቶች እየተካሄደ ነውበውይይቱ ላይ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የፌደራል የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከግልገል በለስ ከተማ እና ከማንዱራ ወረዳ ሁሉም ቀበሌዎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቶችና ሴቶች ተገኝተዋልርእሰ መስተዳድሩ በመተከል ዞን ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የህብረተሰቡን የአብሮነት እሴቶች የበለጠ የማጠናከር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን በውይይቱ ላይ ተናግረዋልበቀጠናው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለውን የሰዎች ሞት እና ንብረት መውደም በዘላቂነት መፍትሄ ለማበጀት በዞኑ ስር ባሉ ሁሉም ወረዳዎች የህዝብ ለህዝብ ውይይቶችን በማካሄድ የማህበረሰቡን አብሮነት መልሶ ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8d-%e1%8b%9e%e1%8a%95-%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%b5%e1%89%b6-%e1%8b%a8%e1%8a%90%e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%8c%b8%e1%8c%a5%e1%89%b3/
102
42,257
የጂና ሃስፐል ሹመት ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ድምፅ ሊቀርብ ነው
ዓለም አቀፍ ዜና
May 16, 2018
Unknown
ዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ተቋም ሲአይኤ ዋና ዳይሬክተር እንዲሆኑ በፕሬዚዳንት ትረምፕ የታጩት ጂና ሀስፐል ሹመት ለህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ድምፅ ሊቀርብ ነውየሀስፐልን ሹመትና ታሪካቸውን እየመረመረ የቆየው የምክር ቤቱ ቡድን 10 ለ 5 በሆነ ድምፅ የሹመቱን ሀሳብ ዛሬ ተቀብሎ አሳልፏቸዋልአሀሁን የሲአይኤ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሆነው እያገለገሉ ያሉትን ጂና ሀስፐልን ሹመት በምክር ቤቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይደግፋሉ ከተባሉት ሪፐብሊካን እንደራሴዎች ጋር ቢያንስ አምስት ዴሞክራቶች ሳይቀላቀሉ እንደማይቀር ተሰምቷል
https://amharic.voanews.com//a/senate-panel-backs-haspel-to-lead-cia-5-16-2018/4396967.html
64
34,653
ፕሪሚየር ሊግ ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ መሪነቱ ሲመለስ ዳሽን ቢራ በወራጅ ቀጠናው ለመቆየት ተገዷል
ስፖርት
April 6, 2016
Unknown
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ አስተናግዶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዳሽን ቢራን 21 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ከደደቢት ተረክቧልግብ በማስቆጠሩ ረገድ ቀዳሚ የሆኑት ዳሽን ቢራዎች ሲሆኑ በ6ኛው ደቂቃ ከመልሶ ማጥቃት የተገኘውን ኳስ የተሻ ግዛው በግሩም ሁኔታ አስቆጥሮ የጎንደሩን ክለብ ቀዳሚ አድርጓልከግቡ መቆጠር በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ጫና ፈጥረው ቢንቀሳቀሱም በተደራጀ ሁኔታ ሲከላከሉ የነበሩት የዳሽን ተከላካዮችን ሰብረው ግብ ማስቆጠር አልቻሉም  የመጀመርያው አጋማሽ የተጠናቀቀውም በዳሽን 10 መሪነት ነበር በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረው የተጫወቱት ፈረሰኞቹ የፈጠሩት ጫና  ውጤት አስገኝቶ በ59 እና 61ኛው ደቂቃ በአዳነ ግርማ እና ምንተስኖት አዳነ አማካኝነት ግብ አስቆጥረው መሪነቱን ቀልብሰውታልድሉ ቅዱስ ጊዮርጊስን በ26 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ሲያስቀምጠው በመጪው ሰኞ በሌላ ተስተካካይ ጨዋታ መከላከያን ካሸነፈ ከተከታዩ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 4 አሳድጎ የመጀመርያውን ዙር ያጠናቅቃልየደረጃ ሰንጠረዥየከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ 
https://soccerethiopia.net/football/8484
120
14,165
በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን በሩዋንዳ ጉብኝት አደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
Nov 17, 2020
470
አዲስ አበባ ህዳር 8 2013 ኤፍ ቢ ሲ በኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በሯንዳ ጉብኝት አድርጓልየልኡካን ቡድኑ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ለሯንዳው የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ክቡር ለዶክተር ቪንሰንት ቢሩታ ገለፃ አድርጓልአቶ ደመቀ ባለፉት ሁለት አመታት ተኩል በኢትዮጵያ ሲካሄድ የነበረው ለውጥ ባስገኛቸው ሁለገብ ጠቀሜታዎች ላይ ገለፃ አድርገዋል በተለይም የህውሀት ጁንታ ቡድን ይህን ለውጥ ተፃሮ መቆሙን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አክራሪ ቡድኖችን ሲያደራጅ በገንዘብ ሲደግፍና ሲያሰማራ መቆየቱን የሀገሪቱን ህገ መንግስት በመፃረር ህገ ወጥ ምርጫ ማካሄዱንና ይህም በሀገሪቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መወገዙን አብራርተዋልበተጨማሪም ይህ ቡድን የፌደራል መንግስትን ህጋዊነት መፃረሩን በቅርቡ ደግሞ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ከሀያ አመታት በላይ በቆየው የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈፀሙን አንስተዋልየህወሀት ጁንታ ቡድን በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ ሰላማዊ ህዝባችን ላይ ጥቃት ፈፅሞ የንፁሀንን ህይወት ማጥፋቱን በዚህም ከብዙ ጊዜ ትእግስት በኋላ የፌደራል መንግስት የህግ ማስከበር ስራ መጀመሩንም ገልፀዋልየዚህ ዘመቻ ዋና ዋና አላማዎች የህግ የበላይነትን ማስከበር አጥፊዎችን ለህግ ማቅረብና የአካባቢውን ህዝብ ነፃ ማውጣት መሆኑን ለዚህም ወዳጁ የሆነው የሯንዳ ህዝብ ጉዳዩን በደንብ እንዲረዳው መልእክት አስተላልፈዋልየሯንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቪንሰንት ቢሩታ በበኩላቸው ሯንዳ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር መሆኗን እና የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት አጥብቃ እንደምትመኝም ገልፀዋልሁልጊዜም ከኢትዮጵያ ጋር በፅናት እንደምትቆም ስራው በአጭር ጊዜ የሰብአዊ መብትን ባከበረ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ፅኑ ፍላጎት እንዳላት እና በማንኛውም ረገድ ከኢትዮጵያ ጋር እንደሚቆሙ ዶክተር ቪንሰንት ቢሩታ አረጋግጠዋልበዚህ ውይይት ላይ የሯንዳው የደህንነት ሀላፊ ሜጀር ጄኔራል ጆሴፍ ዛባይታ ተገኝተው ይህንኑ በሚኒስትሩ የተሰጠውን አስተያየት ደግፈዋል አቶ ደመቀ የሚመራው ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ትናንት በኡጋንዳ እና በኬንያ ተመሳሳይ ውይይት ማድረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%89%b6-%e1%8b%b0%e1%88%98%e1%89%80-%e1%88%98%e1%8a%ae%e1%8a%95%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%98%e1%88%ab-%e1%8b%a8%e1%88%8d%e1%8b%91%e1%8a%ab%e1%8a%95-%e1%89%a1%e1%8b%b5-3/
251
43,689
የግንቦት 20 የድል በዓል ሲከበር የለውጥ እንቅስቃሴውን ከዳር በማድረስ ህዝቡ ሊረባረብ ይገባል- መንግስት
ፖለቲካ
May 17, 2018
Unknown
https://waltainfo.com/am/29914/
0
46,778
የእንግሊዝ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ እየተገነቡ ባሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሚገቡ ተገለፀ
ቢዝነስ
August 2, 2016
Unknown
የእንግሊዝ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያሳድጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ጥሪ አቀረቡሚኒስትሩ ከእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልእክተኛ ልኡክ ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋልኢትዮጵያ በሁለተኛው የእቅድ ዘመን በልዩ ትኩረት በምትሰራባቸው በኢንዱስትሪ ልማትና በአቅም ግንባታ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው እድሎች ዙሪያም መክረዋልዶክተር ቴድሮስ በውይይቱ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ወደተጠናከረ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር መሸጋገር እንዳለበት ተናግረዋልየእንግሊዝ ባለሀብቶች በቅርቡ ለስራ ክፍት የሆነውን የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች እየተገነቡ በሚገኙ ፓርኮች መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋልአገሪቱ የጤናውን ዘርፍ ለማጠናከር በትኩረት እየሰራችበት ባለው የፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ ማስፋፋት ላይም የእንግሊዝ ባለሀብቶች ተሳትፎ ይፈለጋል ብለዋልልኡኩን የመሩት በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሯ የንግድ ልዩ መልእክተኛ ሚስተር ሪቻርድ ቤንዮን በበኩላቸው ኢትዮጵያ የጀመረችው የለወጥ ራእይ እውን እንዲሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋልቀደም ሲል በኢትዮጵያ የነበሩትን የአገሪቱ ኩባንያዎች ከማበረታታት ባሻገር ሌሎችም እንዲመጡ ለማድረግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋልየአገራቸው ባለሀብቶች በሰው ሀይል ስልጠናም ሆነ በንግዱ ዘርፍ በቀጥታ በመሳተፍ በኢትዮጵያ እየተስፋፉ በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋልየመሰረተ ልማት ዝርጋታና የሀይል ምንጮች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ሌላው የትኩረት መስካቸው መሆኑንም አስታውቀዋልየበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመረው የተማረና የተሻለ ገቢ ያለው ህብረተሰብ የመፍጠር ጥረት እንዲሳካ አገራቸው የተለያዩ ድጋፎችን እንደምታደርግ መናገራቸውንም ተዘግቧል ኢዜአ የእንግሊዝ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያሳድጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ጥሪ አቀረቡሚኒስትሩ ከእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልእክተኛ ልኡክ ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋልኢትዮጵያ በሁለተኛው የእቅድ ዘመን በልዩ ትኩረት በምትሰራባቸው በኢንዱስትሪ ልማትና በአቅም ግንባታ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው እድሎች ዙሪያም መክረዋልዶክተር ቴድሮስ በውይይቱ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ወደተጠናከረ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር መሸጋገር እንዳለበት ተናግረዋልየእንግሊዝ ባለሀብቶች በቅርቡ ለስራ ክፍት የሆነውን የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች እየተገነቡ በሚገኙ ፓርኮች መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋልአገሪቱ የጤናውን ዘርፍ ለማጠናከር በትኩረት እየሰራችበት ባለው የፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ ማስፋፋት ላይም የእንግሊዝ ባለሀብቶች ተሳትፎ ይፈለጋል ብለዋልልኡኩን የመሩት በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሯ የንግድ ልዩ መልእክተኛ ሚስተር ሪቻርድ ቤንዮን በበኩላቸው ኢትዮጵያ የጀመረችው የለወጥ ራእይ እውን እንዲሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋልቀደም ሲል በኢትዮጵያ የነበሩትን የአገሪቱ ኩባንያዎች ከማበረታታት ባሻገር ሌሎችም እንዲመጡ ለማድረግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋልየአገራቸው ባለሀብቶች በሰው ሀይል ስልጠናም ሆነ በንግዱ ዘርፍ በቀጥታ በመሳተፍ በኢትዮጵያ እየተስፋፉ በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋልየመሰረተ ልማት ዝርጋታና የሀይል ምንጮች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ሌላው የትኩረት መስካቸው መሆኑንም አስታውቀዋልየበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመረው የተማረና የተሻለ ገቢ ያለው ህብረተሰብ የመፍጠር ጥረት እንዲሳካ አገራቸው የተለያዩ ድጋፎችን እንደምታደርግ መናገራቸውንም ተዘግቧል ኢዜአ
https://waltainfo.com/am/22818/
342
23,928
ፓርላማው በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አመራሮች ላይ የብቃት ጥያቄ አነሳ
ፖለቲካ
2 July 2017
Unknown
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ዝቅተኛ የስራ አፈፃፀምና ከሌሎች ተቋማት ጋር ባለው ጤናማ ያልሆነ ተቋማዊ ግንኙነት ጋር በተያያዘ በኮርፖሬሽኑ አመራሮች ላይ የብቃት ጥያቄ አነሳቋሚ ኮሚቴው የኮርፖሬሽኑን የ2009 አም አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ረቡእ ሰኔ 21 ቀን 2009 አም ካደመጠ በኋላ ነው በአመራሮቹ ላይ ጥያቄ ያነሳውቋሚ ኮሚቴው ባነሳው ጥያቄ ኮርፖሬሽኑ የያዛቸው ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆናቸውንና ከማጠናቀቂያ ጊዜያቸው በላይ ለአመታት መጓተት የኮንትራት አስተዳደር ችግሮች የእቅድ መጣረስ የኮርፖሬት ፋይናንስ ስርአት ተግባራዊ አለመሆንና ሌሎች በርካታ ችግሮች መኖራቸው በአብዛኛው የአመራር ብቃት ጥያቄ የሚያስነሱ ናቸው ብሏል ችግሮቹ እንዲቀረፉ ቋሚ ኮሚቴው በተደጋጋሚ ቢያነሳም በተቋሙ በኩል ተጨባጭ መልስ እየተሰጠ አይደለም ብሏል መንግስት አጠቃላይ የአሰራር ስርአቱን ለማዘመን በመንግስት ተቋማት የሚገብራቸውን ሳይንሳዊ የለውጥ መሳሪያዎች ኮርፖሬሽኑ ሊተገብር ይቅርና ከአመለካከት ጀምሮ እንደማይቀበለው የጠቀሰው ቋሚ ኮሚቴው ተቋሙ አሰራሮቹን ተግባራዊ ማድረግ ጀምሮ እንደሆነ ጠይቋልኮርፖሬሽኑ የያዛቸው ፕሮጀክቶች ከመጓተታቸው ባለፈ የፕሮጀክቶቹ ባለቤቶች ከሆኑ የመንግስት ተቋማት ጋር ተግባብቶ በቅንጅት እንደማይሰራ በተደጋጋሚ እንዲያስተካክል ቢመከርም ለውጥ አለመምጣቱን ጠቁሟልለዚህ ማሳያም በኮርፖሬሽኑና የፕሮጀክቶቹ ባለቤቶች በሆኑ የመንግስት ተቋማት የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀም አስመልክቶ የሚወጡ ሪፖርቶች የሚጣረሱ መሆናቸውን በማስረጃ አስረድቷልኮርፖሬሽኑ ከያዛቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል የስኳር ፋብሪካዎችና አንድ የማዳበሪያ ፋብሪካ ይገኝበታል ኮርፖሬሽኑ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ጣና በለስ ቁጥር አንድ የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት አፈፃፀም 91 በመቶ ሲሆን የፕሮጀክቱ ባለቤት የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ለቋሚ ኮሚቴው ያቀረበው ሪፖርት ግን 77 በመቶ መሆኑን ጠቅሷል የጣና በለስ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት አፈፃፀም በኮርፖሬሽኑ ሪፖርት መሰረት 572 በመቶ መሆኑ ቢገለፅም የፕሮጀክቱ ባለቤት ሪፖርት ግን 25 በመቶ ብቻ መሆኑን እንደሚጠቁም ቋሚ ኮሚቴው አብራርቷል ኦሞ ኩራዝ አንድ ስኳር ፋብሪካን ኮርፖሬሽኑ እንዳጠናቀቀ ሲገልፅ ባለቤቱ ግን 935 በመቶ ነው ይላልበተመሳሳይ የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት አፈፃፀም 465 በመቶ መድረሱን ኮርፖሬሽኑ ቢልም የፕሮጀክቱ ባለቤት ግን 423 በመቶ መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴው እንደገለፀ በመጥቀስ የችግሩ መንስኤ እንዲብራራለት ቋሚ ኮሚቴው ጠይቋልበያዩ የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት ግንባታ ከመጓተቱ በዘለለ በፋብሪካው ግንባታ ላይ ችግሮች መከሰታቸውን የቋሚ ኮሚቴው አባላት በአካል ተገኝተው መታዘባቸውን ቋሚ ኮሚቴው ገልጿልበማስረጃነትም ሪቴይኒንግ ዎል የድጋፍ ግንብ ስድስት መቶ ሜትር ያህል መሰንጠቁን የኩሊንግ ታወሩ እየሰመጠ መሆኑን ግንባታው የተመረጠበት አካባቢ ረዥም የመሬት መሰንጠቅ መኖሩን በማውሳት መንስኤውንና ዘላቂ መፍትሄውን ጠይቋል በማከልም ለማዳበሪያ ፋብሪካው ኮርፖሬሽኑ 60 በመቶ ክፍያ ተከፍሎት የፈፀመው 423 በመቶ ሆኖ ሳለ ተጨማሪ ክፍያ መጠየቁ ተገቢ ነው ወይ ሲል ቋሚ ኮሚቴው ጥያቄ አቅርቧልየስኳርና የማዳበሪያ ፋብሪካዎቹ በተገባው ውልም ሆነ ተሻሽለው በቀረቡ መረሀ ግብሮች መፈፀም አለመቻላቸውና ይህም በፕሮጀክቶቹ ባለቤት ተቋማት ላይ እንዲሁም በመንግስትና በህዝብ ሀብት ላይ ለደረሰው መባከን ተጠያቂው ማን እንደሆነ ቋሚ ኮሚቴው የኮርፖሬሽኑን አመራሮች ጠይቋልለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ኮርፖሬሽኑ ላይ ለሚመጣ ተጠያቂነት እርሳቸው ብቻ ተጠያቂ መሆን እንደሚፈልጉ ተናግረዋልበግሌ የማምነው ለዚህ አገር ልማት እየወደቅንና እየተሰዋን እንደምንሰራ ነው መጠየቅ ካለብኝ እኔ ልጠየቅ ከእኔ ውጪ ማንም እንዲጠየቅ አልፈልግም እኔ የሚፀፅተኝ ነገር የለም መታወቅ የተፈለገው ይህ ከሆነ ለዚህ ዝግጁ ነኝ ብለዋልበ2009 አም ደካማ የስራ አፈፃፀም እንደነበር ያመኑት ዋና ዳይሬክተሩ የውጭ ምንዛሪ እጥረት የሀይል መቆራረጥ የራሱ የውስጥ ችግር እንዲሁም በሌሎች ውጫዊ ምክንያቶች ችግሩ የመጣ መሆኑን አስረድተዋልበሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ በ2009 አም በአመዛኙ በፀጥታ ስራ ላይ ሲሳተፍ በመቆየቱ የልማት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ዝቅ ማለቱን ተናግረዋል ከዚህ ውጪ የፕሮጀክት አፈፃፀሞችን አስመልክቶ የቀረቡ ሪፖርቶች መጣረስ ስለተባለው መሬት ላይ የሚታይ በመሆኑ ማረጋገጥ ይቻላል ብለዋል ኦሞ ኩራዝ አንድ ስኳር ፋብሪካ የሙከራ አገዳ መፍጨት ጀምሯል ብለዋልኮርፖሬሽኑ የመንግስትን የአሰራር ስርአት የመቀበል ችግር አለበት ተብሎ የቀረበው ጥያቄ በራሱ ስህተት ያለበት ነው በማለት መልስ አልሰጡበትም በያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት ተሰንጥቋል የተባለውም ስህተት እንደሆነ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ የተፈረጠው ችግር የአፈር መንሸራተት ነው ብለዋልዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ይበሉ እንጂ በስፍራው ጉብኝት ያደረጉ የፓርላማ አባላት ፕሮጀክቱ ለመሰንጠቁ የፎቶ ማስረጃ አቅርበዋል ዋና ዳይሬክተሩ በሪቴይኒንግ ዎል ላይ መሰንጠቅ የሚታይ ቢሆንም ከዋናው ፋብሪካ ጋር ግንኙነት እንደሌለው ተናግረዋል አክለውም ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ አለመጠየቁን የተጠየቀ ቢኖርም የዋጋ ልዩነት ክፍያ መሆኑን ጠቁመዋልቋሚ ኮሚቴው በሰጠው አስተያየት አሁንም ቢሆን ፕሮጀክቶች መጓተታቸውንና ከዚህ በላይ የሚታየውን ችግር ኮርፖሬሽኑ እንዲፈታ አዟል ኮርፖሬሽኑም ያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካን በ2010 አም መጨረሻ ላይ እንደሚያጠናቅቅ ገልጿል 
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%88%8B%E1%88%9B%E1%8B%8D-%E1%89%A0%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%89%B3-%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%89%B5%E1%8A%93-%E1%8A%A2%E1%8A%95%E1%8C%82%E1%8A%90%E1%88%AA%E1%8A%95%E1%8C%8D-%E1%8A%AE%E1%88%AD%E1%8D%96%E1%88%AC%E1%88%BD%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%98%E1%88%AB%E1%88%AE%E1%89%BD-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8B%A8%E1%89%A5%E1%89%83%E1%89%B5-%E1%8C%A5%E1%8B%AB%E1%89%84-%E1%8A%A0%E1%8A%90%E1%88%B3
586
32,340
​ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ወልዲያ ከ መከላከያ
ስፖርት
March 1, 2018
Unknown
የ13ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሀ ግብር የነበረው የወልዲያ እና የመከላከያ ጨዋታ በተስተካካይነት ተይዞ ቆይቶ ዛሬ 9 ሰአት ላይ እንደሚደረግ ይጠበቃል ጨዋታውን አስመልክተንም በቅድመ ዳሰሳችን ተከታዮቹን ነጥቦች  አንስተናል ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ከቻን መልስ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሀል ዳኝነት የሚመራው ይህ ጨዋታ ለመከላከያ የመጀመሪያ ዙር  የመጨረሻው ጨዋታ ሲሆን ወልዲያም ተስተካካይ ጨዋታዎቹን የሚያጋምስበት ይሆናል አሁንም በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኙት ወልዲያዎች ከአንድ ወር  በላይ ከሆነ ቆይታ በሀላ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ሜዳቸው አቻ ሲለያዩ ከ5 ጨዋታዎች በሀላ በ9ኛው ሳምንት ወደ ተገኘው የአርባምንጩ ድል መመለስ ሳይችሉ ቀርተዋል ስማቸው ከአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ጋር በስፋት እየተነሳ የሚገኘው ሰመያዊ እና ነጭ ለባሾቹ አርባምንጩ ድል በሀላ ባደረጓቸው 5 ጨዋታዎች ማሳካት የቻሉት ሁለት ነጥቦችን ብቻ መሆኑ ደግሞ የወቅታዊ አቋማቸው ጥሩ አለመሆንን ያሳያል በተመሳሳይ ከአሸናፊነት ርቆ የሰነበተው መከላከያ በበኩሉ በሌላኛው ተስተካካይ ጨዋታው መቐለ ከተማን 10 በመርታት መጠነኛ መነቃቃት አሳይቷል እስካሁን በአንድ ጨዋታ ከአንድ በላይ ግብ ማስቆጠር የተሳነው መከላከያ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ወደ 9ኛ ደረጃ ከፍ ማለት የሚችል ሲሆን ወልዲያ ድል ከቀናው ደግሞ የመጨረሻ ደረጃውን ለአርባምንጭ ከተማ አስረክቦ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት ሙሉ ለሙሉ ከወራጅ ቀጠናው የሚወጣበትን እድል ይፈጥራል  ወልዲያ ተስፋሁን ሸጋውን ጨምሮ አሁንም በጉዳት ላይ የሚገኙትን  አዳሙ መሀመድ እና ሰለሞን ገመድህንን በዚህ ጨዋታ የማይጠቀም ሲሆን ትናንት ቀለል ያለ ልምምድ የሰራው ተስፋዬ አለባቸው የመግባት እና ያለመግባቱ ጉዳይም አለየለትም በመከላከያ በኩል ደግሞ አዲሱ ተስፋዬ እና ቴውድሮስ በቀለ ከጉዳት ያላገገሙ ሲሆም ምንይሉ ወንድሙ እና ተመስገን ገፃዲቅም በጉዳት ዝርዝሩ ውስጥ ተቀላቅለዋቸዋል  ሊንኩን ተጭነው ይወራረዱበወልድያ በኩል የአማረ በቀለ ከቅጣት መመለስ እንዳለ ቢሆንም በቡድኑ የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ በተደጋጋሚ ይካተቱ የነበሩ ተጨዋቾች አለመኖር ለአሰልጣኝ ዘማርያም ወጊዮርጊስ ፈተና የሚሆን ይመስላል በተለይም  ከወገብ በላይ ባለው የቡድኑ መዋቅር ውስጥ በማጥቃት ሂደት ላይ ወሳኝ የሆነው የተጨዋቾች ውህደት በድግግሞች የማይዳብር ከሆነ በሀከላቸው የሚኖረውን ጥምረት ውጤታማነት ይቀንሰዋል በተመሳሳይ በመከላከያ በኩልም ቡድኑ እስካሁን ካስቆጠራቸው ስድስት ግቦች መሀከል የአምስቱ ባለቤት የሆነው ምንይሉ ወንድሙ አለመኖር የሚፈጥረው ክፍተት ቀላል የሚባል አይሆንም ሌሎች የአማካይ ክፍል እና የፊት መስመር ተጨዋቾች በቋሚነት ወደ ግብ አስቆጣሪነት ካልተመለሱም መከላከያ ከግብ ፊት ያለው ደካማ ሪከርድ ውጤት እንዳያሳጣው ያሰጋል እጅግ ወደ መሀል አጥቦ በመጫወት የሚታወቀው የመከላከያ የአማካይ ክፍል እንደ መቐለው አይነት በጥቂቱ የተሻሻለባቸው ጨዋታዎች ቢኖሩም አሁንም ብዙ መስተካከል ይጠበቅበታል በዛሬውም ጨዋታ የግብ እድሎችን በብዛት ለመፍጠር በመስመር አማካዮቹ በኩል የሜዳውን ስፋት በአግባቡ የሚጠቀም ቡድንን ይዞ እንዲቀርብ ይጠበቅበታል ወልድያዎችም በብሩክ ቃልቦሬ እና ምንያህል ተሾመ መሀከል በሚገኘው ቦታ ላይ መበራከታቸው የማይቀሩትን የተጋጣሚያቸው ተጨዋቾችን አልፈው ወደ አንዷለም ንጉሴ የመጨረሻ ኳሶችን ለማድረስ ሊቸገሩ የሚችሉ በመሆኑ በሁለቱ ክንፎች የምደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ቢያተኩሩ የሚሻል ይመስላል በመሆኑም ጨዋታው መሀል ሜዳ ላይ ብዙ የቅብብል መቆራረጦች የሚገጥሙት እና የመስመር እንቅስቃሴዎች የተሻለ ክፍተትን የሚፈጥሩለት እንደሚሆን ይገመታል ተገናኙ 4ወልዲያ አሸነፈ 1 1 ጎልመከላከያ አሸነፈ 3 5 ጎሎችአቻ 0
https://soccerethiopia.net/football/34461
407
46,766
“የአፋር ሕዝብ ፓርቲ” በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ መስማማቱን ገለጸ
ፖለቲካ
July 21, 2016
Unknown
ስምምነቱ ትናንት በሰመራ ከተማ በተደረገበት ወቅት እንደተገለፀው ፓርቲው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከክልሉ መንግስት ጋር ላለፉት ሁለት አመታት ተደጋጋሚ ውይይት ካደረገ በኋላ መሆኑን ተመልክቷል በስምምነቱ ላይ የተገኙት በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የፕሬዚዳንቱ የህዝብ ግንኙነት አማካሪና የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አብዴፓ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ናቸውአምባሳደር ሀሰን ስምምነቱ ሲደረግ እንደገለፁት የክልሉ መንግስት የአርብቶ አደሩን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ነው በተለይም በውጭ የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች ያላቸውን እውቀትና ሀብት ለክልሉና ለሀገሪቱ እንዲያውሉ የተለያዩ ጥረቶች መጀመራቸውን አስታውቀዋልየአፋር ህዝብ ፓርቲ በሰላማዊ መንገድ በመታገል ለክልሉ አርብቶ አደር ህብረተሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የበኩሉን እንዲወጣ የጋራ ስምምነት ላይ የተደረሰውም የእዚህ ጥረት ውጤት አንድ ማሳያ ነው ብለዋልየክልሉን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ መንግስት እያደረገ ባለው ትግል ዲያስፖራውን ጨምሮ ሁሉም የክልሉ ተወላጆች ያለምንም ልዩነት ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋልየአፋር ህዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አሎ አይዳሂስ መሀመድ በበኩላቸው በክልሉ የነበረው የመልካም አስተዳደርና ኪራይ ሰብሳቢነት ችግር እንዲሁም ጎሰኝነትን ለመታገል ፓርቲው ከ2001 አመተ ምህረት ጀምሮ በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ጠቁመዋልበተለይ በክልሉ ከሚካሄደው የስኳር ልማት ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ የአፋር ህዝብ ከመሬቱ አላግባብ እንደተነሳ ተደርጎ ይናፈሱ የነበሩ መረጃዎችን ፓርቲው በቅጡ ሳይረዳ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በትጥቅ ትግሉ መቆየቱን አስታውቀዋልላለፉት ሁለት አመታት ከክልሉ መንግስትና መሪ ፓርቲ ጋር በተደረጉት ተደጋጋሚ ውይይቶች ከሀምሌ 13 ቀን 2008 ጀምሮ ፓርቲያቸው ሙሉ ለሙሉ በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ መስማማቱን ገልፀዋልየሀገሪቱንና የክልሉን ህገ መንግስት አክብሮ በሰላማዊ መንገድ በመታገል የክልሉን ህብረተሰብ የበለጠ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ለማድረግ ፓርቲው እንደሚሰራም አረጋግጠዋልበክልሉ ብሎም በሀገሪቱ እየተመዘገብ ያለውና ህብረተሰቡን ፍትሀዊ ተጠቃሚ ያደረገው ሁለንተናዊ እድገት በአለም መገናኛ ብዙሀን ሳይቀር በተደጋጋሚ መዘገቡ ለፓርቲው አቋም መቀየር አንዱ ምክንያት መሆኑን አመልክተዋልከሁለት አመት በፊት ከክልሉ መንግስት ጋር በተደረገ ድርድር በትጥቅ ትግሉ የነበሩ 400 የፓርቲው አባላት ወደሰላማዊ እንቅስቃሴ መግባታቸውን አስታውሰዋልአቶ አሎ እንዳሉት አባላቱ በአሁኑ ወቅትም በግብርና በጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም በክልሉ ፖሊስና ሌሎች ተቋማት ስር ተሰማርተው ሰላማዊ ህይወታቸውን እየመሩ ይገኛሉበትጥቅ ትግሉ ተሳታፊ ከነበሩና ወደሰላማዊ እንቅስቃሴ ከገቡ ወጣቶች መካከል አብዱ ዳውድ የተባለው በሰጠው አስተያየት የአፋር ህዝብ ከመሬቱ አላግባብ እንደተፈናቀለ ተደርጎ በተናፈሰው አሉባልታ ወሬ ከጓደኞቹ ጋር በስሜት ተነሳስተው ወደኤርትራ ገብተው ለአላስፈላጊ ስቃይና እንግልት መዳረጋቸውን አስታውሷልወደ ሰላማዊ ትግል ለመግባት ፓርቲው በወሰነው ትክክለኛ ውሳኔ በአሁኑ ወቅት የተረጋጋ ኑሮ እየመራ መሆኑን የገለፀው ወጣቱ ባለፈው አንድ አመት በሰመራ ከተማ በማህበር ተደራጅቶ በድንጋይ ንጣፍ ስራ ላይ በመሰማራቱ ከ40 ሺህ ብር በላይ በባንክ መቆጠቡን አረጋግጧልሌላው የፓርቲው አባል አቶ ሱለይማን ሁሴን በበኩላቸው ወደ ትጥቅ ትግሉ ከገቡ በኋላ ፓርቲያቸው የኤርትራ መንግስትና የአንዳንድ ፀረ ሰላም ሀይሎች ድብቅ አላማን በመረዳት ወደሰላማዊ ትግል ለመምጣት መወሰኑ ተገቢ ነው ሲሉ ገልፀዋልበዚህም እርሳቸውም በተመቻቸላቸው የስራ እድል ፈጠራ ሻይ ቤት ከፍተው እየሰሩና የቤተሰባቸውን ህይወት እየቀየሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል ኢዜአ
https://waltainfo.com/am/25757/
387
23,451
ዘንድሮ የአዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ አይኖርም
ቢዝነስ
29 November 2017
Unknown
ኢትዮጵያ ከ2007 አም ጀምሮ ከአዋሽወልዲያመቀሌ የባቡር መስመር ዝርጋታ እያካሄደች ቢሆንም ዘንድሮ አዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ እንደማይጀመር ታውቋልየኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ ለሪፖርተር እንደተናገሩት አገሪቱ ሁለት የባቡር መስመር ፕሮጀክቶችን እያከናወነች ቢሆንም ዘንድሮ የሚጀመር ፕሮጀክት የለም ከመቼ ጀምሮ የአዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ እንደሚጀመር አይታወቅም ብለዋልየአዋሽወልዲያ ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክት በጥቅምት 2007 አም  እንደተጀመረ ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው የባቡር መስመር ዝርጋታ 60 በመቶ መድረሱን አቶ ደረጀ ተናግረዋል 398 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የአዋሽ ወልዲያ የባቡር ፕሮጀክት 17 ቢሊዮን ዶላር በጀት ተይዞለት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል የአዋሽወልዲያ ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኮምቦልቻ እስከ ወልዲያ የሚከናወነው የባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክትም የመሬት ማስለቀቅ ስራው በቅርብ ቀን እንደሚጀምር አስረድተዋልከወልዲያ እስከ ኮምቦልቻ ያለው የባቡር መስመር 120 ኪሎ ሜትሮችን ብቻ የሚያካትት እንደሆነ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚታሰብም ገልፀዋልበጥቅምት ወር 2007 አም የመሰረት ድንጋይ የተጣለለት ሌላው ፕሮጀክት የመቀሌወልዲያ የባቡር መስመር ዝርጋታ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን አጠቃላይ አፈፃፀሙ 48 በመቶ እንደደረሰ ዳይሬክተሩ አስረድተዋልፕሮጀክቱ 216 ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን እንደሆነና 154 ቢሊዮን ዶላር እንደተመደበለት ገልፀዋል በመሬቱ ወጣ ገባነት የተነሳ በፕሮጀክቱ ላይ ችግር እየተፈጠረ እንደሆነም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል የተማረ የሰው ሀይል ውስንነት የመሬቱ ወጣ ገባነትና የመሬት ባለቤት አርሶ አደሮች ካሳ ጉዳይ ለፕሮጀክቶች መጓተት ምክንያቶች እንደሆኑ ጠቁመዋልየመቀሌወልዲያና የአዋሽወልዲያ የባቡር መስመር ፕሮጀክቶችን ለማከናወን አገሪቱ ከ120 ቢሊዮን ብር በላይ ከአበዳሪዎች እንዳገኘች መረጃዎች ያመለክታሉ ከቻይና የተበደረችውን ብር በጊዜው መመለስ ባለመቻሏም በባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቶች ላይ መስተጓጎል እየተፈጠረ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል አቶ ደረጀም የገንዘብ እጥረት ትልቁ የፕሮጀክቶች ፈተና ነው ብለዋልባለፈው አመት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባቡር መስመር ፕሮጀክቶች በፐብሊክ ፕራይቬት ፓርትነርሽፐ አማካይነት በራሳቸው ወጪ ወይም ከመንግስት ጋር በጥምረት እንዲከናወኑ መወሰኑ ይታወሳልበአዲሱ በፐብሊክ ፕራይቬት ፓርትነርሽፕ አማካይነት ይከናወናሉ ተብሎ በእቅድ ከተያዙት የባቡር መስመሮች መካከልም የሞጆሞያሌ የባቡር መስመር ይገኝበታልአቶ ደረጀ ወደፊት ይሰራሉ ተብለው የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠላቸው አዳዲስ የባቡር መስመሮች መካከል ከአምቦጂማበደሌ ከሞጆሻሸመኔሀዋሳና ከወልዲያወረታባህር ዳርሱዳን እንደሚገኙበት ተናግረዋል የእነዚህ የባቡር መስመሮች ፕሮጀክቶች የመስመር ዝርጋታ መቼ እንደሚጀመር ግልፅ ያለ ጊዜ አለመቀመጡንም ዳይሬክተሩ አክለዋል
https://www.ethiopianreporter.com/article/3947
299
30,866
ከፍተኛ ሊግ ሀ | ለገጣፎ በምርጥ አጀማመሩ ሲቀጥል ሰበታ እና ፌዴራል ፖሊስም አሸንፈዋል
ስፖርት
December 30, 2018
Unknown
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ሁሉም የአምሰተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ተከናውነው ለገጣፎ ለገዳዲ ሰበታ ከተማ እና ፌደራል ፖሊስ ድል ማስመዝገብ ችለዋልለገጣፎ ላይ በሰንጠረዡ አናት የሚገኙት ለገጣፎ ለገዳዲ እና ወልዲያን ያገናኘው ጨዋታ በለገጣፎ 10 አሸናፊነት ተጠናቋል  ጨዋታው መጀመር ካለበት ሰአት የፀጥታ ሀይል በስፍራው በሰአቱ ባለመገኘቱ ምክንያት ለ17 ያህል ደቂቃዎች ዘግይቶ የተጀመረ ሲሆን  በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በሁለቱም ቡድን በኩል የነበረው አላስፈላጊ የአካል ንክኪ የጨዋታውን ውበት ቀንሶት ታይቷል በሁለቱም በኩል ኳስን በረጅሙ ወደፊት ከማሻገር ያለፈ እንቅስቃሴ ሳይታይ ቆይቶ በ18ኛው ደቂቃ ወልድያዎች የመጀመሪያ የግብ አጋጣሚን አቢይ ቡልቲ ከርቀት አክርሮ መትቶ ወደ ውጪ በወጣበት ሙከራ መፍጠር ችለዋል ከዚች ሙከራ በኋላ ሁለቱም ቡድን ኳስን ይዘው ለመጫወት የሚደርጉት ጥረት ባልተገባ አጫዋወት ቶሎ ቶሎ ሲቆራረጥ ነበርበለገጣፎ በኩል የአጭር ኳስ ቅብብሉን በመተው  በቀኝ መስመር በማድላት ሀብታሙ ፍቃደ ከመስመር በሚሻግረው እና ይዞት በሚገባው ኳሶች ወልድያን ለመፈትን ሞከረዋል በዚህም አጨዋወት በ35ኛው ደቂቃ ሳዲቅ ተማም በረጅሙ የተሻገረለትን ኳስ የግብ ጠባቂው ስህተት ታክሎበት ያገኘው ኳስ በግንባሩ ገጭቶት የግቡ ግራ አግዳሚ ለትሙ ወጥቶበታል ተጋጣሚው ወልድያ በተደጋጋሚ ወደፊት ቢጠጉም ፍሬው ብርሀን እንዲሁም ይግርማቸው ተስፋዬ ካደረጉት የግብ ሙከራ ሌላ ምንም አይነት ሙከራ ሳያደርጉ ቀርተዋል ለገጣፎ ከተማዋች በ41ኛው ደቂቃ አንዋር አብዱልጀባል በግምት 25 ሜትር አክርሮ የመታው ኳስ በእጅ በመነካቱ የተሰጠውን ቅጣት ምት በሱፍቃድ ነገሽ በግሩም ሁኔታ መትቶ ግብ ጠባቂው ከላበት ሳይንቀሳቀስ ኳስን ከመረብ አገናኝቶ የመጀመርያው አጋማሽ በለገጣፎ መሪነት ተጠናቋልሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ብርቱ የመሸናነፍ ፉክክር እና በርካታ የግብ ሙከራ ተስተውሉበታል በነፋሻነቱ የሚታወቀው የለገጣፎ ሜዳ ለተጋጣሚው ወልዲያ ማስቸገሩ በግልፅ የሚታይም ነበር ኳስን ከግብ በመመስረት ወደ ሁለቱም የመስመር ተጫዋቾች በመበተን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት ለገጣፎዎች በ48ኛው ደቂቃ ሳዲቅ ተማም ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ግብ ጠባቂው ከፍያለው ሀይሉ ያዳነበት ሙከራ ጥሩ የግብ እድል ነበር ወልዲያዎች ውጤቱን ለመቀልበስ ከእረፍት መልስ ተጭነው ለመጫወት ሲሞከሩ በተለይም ተቀይሮ የገባው እንድሪስ ሰይድ ኳስን በማደራጀትም ሆነ የግብ ሙከራን በማድረግ ልቆ ወጥቶ ነበር በ51ኛው ደቂቃ ከርቀት መትቶ በግቡ አናት የሄድችበት እንዲሁም በ60ኛው ደቂቃ ሳጥን ውስጥ ያገኘውን ኳስ መትቶ የለገጣፎ ግብ ጠባቂ አንተነህ ሀብቱ በጥሩ ሁኔታ ያዳነበት የሚጠቀሱ ናቸው ወደ ኋላ አፈግፍጎ መጫወትን ምርጫቸው ያደረጉት ለገጣፎዎች አልፎ አልፎ ወደፊት በሚጣል ኳስ የግብ እድሎች ቢፈጥሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል በተለይም በ77ኛው ደቂቃ ሀብታሙ ፍቃደ በረጅሙ የተሻገረትን ኳስ ሮጦ ቢደርስም ተረጋግቶ ባለመምታቱ ኳሷ በግቡ አናት ላይ ወጥታበታለች ጨዋታውም ተጨማሪ ግብ ሳይሰተናግድበት በለገጣፎ መሪነት ተጠናቋል በቀድሞ ምክትል አሰልጣኝ ዳዊት የሚሰለጥነው ለገጣፎ በአምስት ጨዋታ 13 ነጥቦች በመሰብሰብ ምድቡን መምራት ላይ ይገኛልበሌሎች ጨዋታዎች ሰበታ ላይ ሰበታ ከተማ አውስኮድን በ7ኛው ደቂቃ አቤል ታሪኩ በ21ኛው ደቂቃ ኢብራሂም ከድር ባስቆጠሯቸው ጎሎች 20 አሸንፏል ወደ ዱከም ያመራው ፌዴራል ፖሊስ ገላን ከተማን 20 በማሸነፍ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል ሰይፉ ዘኪር በ27ኛው ደቂቃ ፖሊስን ቀዳሚ ሲያደርግ በሁለተኛው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ ሰይፈ መገርሳ ሁለተኛውን አክሏልኒያላ ሜዳ ላይ አቃቂ ቃሊቲ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቡራዩ ላይ ቡራዩ ከተማ ከአክሱም ከተማ እንዲሁም ደሴ ላይ ደሴ ከተማ ከወሎ ኮምቦልቻ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በተመሳሳይ ያለ ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል
https://soccerethiopia.net/football/42938
431
38,022
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የታጠቁ ኃይሎች በነዋሪዎች ላይ ጥቃት አደረሱ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 09, 2020
Unknown
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለንና ወንበራ ወረዳዎች የታጠቁ ሀይሎች በነዋሪዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ የቡለን ወረዳ አስተዳደር የሰላም ስጋት እንጂ ጥቃት እንደደረሰ መረጃ አልደረሰንም ብሏል ጥቂት ሰዎችም ታግተው እንደተወሰዱ የወንበራ ወረዳ አስታውቋልየቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጥቃቱን የፈፀሙት የቤኒሻንጉል ህዝብ ነፃነት ንቅናቄ ጉህነንሀይሎች መሆናቸውን ገልፀዋል
https://amharic.voanews.com//a/metekel-attack-09-9-2020/5577189.html
48
49,067
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከኩባ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ሳልቫዶር ቫልዴስ ሜሳን ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
May 29, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኩባን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር ቫልዴስ ሜሳን ተቀብለው አነጋገሩበውይይታቸው ኩባ የኢትዮጵያ ልዩ ወዳጅ ናት ያሉት ፕሬዝዳንቷ ግንኙነቱን የበለጠ ማዳበር በሚያስችሉ ተግባራት ላይ መስራት እንደሚገባም ገልፀዋል ሁለቱ ሀገራት ተባብረው ሊሰሩ የሚችሉባቸው እድሎች ሰፊ መሆናቸውንም ጠቅሰዋልየኩባው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ሳልቫዶር ቫልዴስ ሜሳን በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ወዳጅነት በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ከፍተኛ ፍላጎት አላት ብለዋል መረጃው የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ነው
https://waltainfo.com/am/31172/
62
4,616
አዲሱ የቱሪዝም ኢትዮጵያ መለዮ ወደ ህብረተሰቡ ዘልቆ አልገባም
ሀገር አቀፍ ዜና
May 12, 2019
53
አዲስ አበባ የቱሪዝም ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት የሚለው አዲሱ መለዮ በተፈለገው መጠን በህብረተሰቡ ዘንድ እንዳልሰረፀ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት አስታወቀ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሌንሳ መኮንን ትናንት በካፒታል ሆቴል በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ እንዳስታወቁት የሀገሪቱ የቱሪዝም መለዮ ስያሜ የ13 ወር ፀጋ የሚለው ከዛሬ ሶስት አመት በፊት ወደ ምድረ ቀደምት መቀየሩ ይፋ ቢደረገም አዲሱን ስያሜ ህብረተሰቡም ሆነ ቱሪስቶች እንዲያውቁት በሚያስችል ደረጃ አልተሰራም ይህም በመሆኑ የቀደመው ስያሜው የሰራውንና መለዮ የሆነውን ያህል አዲሱ መለዮ በእዛ ልክ ተፅእኖ አለመፍጠሩን ገልፀዋል ኢትዮጵያን በሚገባ ይገልፃታል የተባለው አዲሱ የቱሪዝም መለዮ ኢትዮጵያ የሁሉ ነገር መነሾ እንደሆነች የማስተዋወቅ አቅም እንዳለው ጠቁመው ድርጅቱ የማስተዋወቁን ስራ በሚገባ ባለመስራቱ መለዮው በሚጠበቀው ልክ እንዳይታወቅ አድርጎታል ብለዋል ይህንን ችግር ለመቅረፍ አንዱ መንገድ አገራዊ የምክክር መድረክ ማዘጋጀት ሲሆን በቀጣይም ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በመዞር እስከ ታችኛው የአገሪቱ መዋቅር ድረስ በመውረድ የማሳወቅ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል የቱሪዝም ኢትዮጵያ የገበያ ልማት ቡድን መሪ አቶ ወልደገብርኤል በርሄ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም ሀብት በሚገባ ያልተጠቀመች አገር መሆኗን ገልፀዋል አፍሪካ የአለም አቀፍ ቱሪዝም ድርሻዋ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም ካላት እምቅ የቱሪዝም አማራጮች አንፃር ዝቅተኛ መሆኑን በአለም አቀፉ ቱሪዝም ድርጅት የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክት ጠቅሰው ኢትዮጵያም ያላትን የቱሪዝም ሀብት በአግባቡ ባለመጠቀም የአንበሳውን ድርሻ እንደምትይዝ አንስተዋል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለትምህርት ለስራ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች ከአገር አገር ሲዘዋወር መለዮን ጨምሮ አገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን ማስተዋወቅ እንደሚገባም ተናግረዋል ድርጅቱም የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ መለዮ ምልክቱን ለማስተዋወቅ ይሰራል ብለዋል እአአ በ2000 የአፍሪካ ጎብኚ ቱሪስቶች ቁጥር 26 ሚሊዮን ገደማ እንደነበር አስታውሰው ይሄ ቁጥር በአሁኑ ወቅት ወደ 53 ሚሊዮን ቢያድግም ከአለም አቀፍ ያለው ድርሻ ከአምስት በመቶ ያልበለጠ ነው የእድገት መጠኑ ፈጣን የተባለለት የአፍሪካ ቱሪዝም እኤአ እስከ 2030 የቱሪስቶች ቁጥር ከእጥፍ በላይ በማደግ ከ134 ሚሊዮን እንደሚደርስ የአለም አቀፍ ቱሪዝም ድርጅት ትንበያ ይጠቁማልአዲስ ዘመን ግንቦት 42011 አብርሀም ተወልደ
https://www.press.et/Ama/?p=10627
269
12,560
የሀገሪቱን ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ዕድገት ለማምጣት የሴቶች ሚና ከፍተኛ ነው ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jan 15, 2021
82
አዲስ አበባ ጥር 7 2013 ኤፍ ቢ ሲ የሰላም ሚኒስቴር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ለተጠሪ ተቋማት ሴት አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነውስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስቴር የማኔጅመንት ድጋፍ ስራ አመራር ዳይሬክተር ጀነራል አቶ መብራቱ ካሳ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱንና የተጠሪ ተቋማትን የጋራ ራእይ እና ተልእኮ ለማሳካት የሴት አመራሮችንና ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ወሳኝነት አለው ብለዋልመንግስት የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎችና አዋጆች የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ያካተተ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋልም ነው ያሉትአያይዘውም የሀገሪቱን ዘላቂ ሰላም እና ሁለንተናዊ እድገት ለማፋጠን ሴት አመራሮችንና ባለሙያዎችን በተሰማሩበት የስራ መስኮች ሀላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ እገዛ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ገልፀዋልበስልጠናው ላይ የሰላም ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የሴቶች የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ደንብ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታልከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘትየፋና ድረ ገፅ httpswwwfanabccom ይጎብኙ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል httpswwwyoutubecomcfanabroadcastingcorporate ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል httpstmefanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን httpstwittercomfanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%aa%e1%89%b1%e1%8a%95-%e1%8b%98%e1%88%8b%e1%89%82-%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d%e1%8a%93-%e1%88%81%e1%88%88%e1%8a%95%e1%89%b0%e1%8a%93%e1%8b%8a-%e1%8b%95%e1%8b%b5/
150
24,340
በፋይናንስ ፍሰት መስተጓጎል የኮንዶሚንየም ቤቶች ግንባታ ችግር እንደገጠመው ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
5 February 2017
Unknown
የመኖሪያ ቤቶችን ችግር ለመፍታት በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመሩ የ2080 እና የ4060 ቤቶች ግንባታ በፋይናንስ ፍሰት በኩል መስተጓጎል በመፈጠሩ የቤቶቹ ግንባታ ችግር እንደገጠመው ተጠቆመየቤቶች ግንባታ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑት በሺህ የሚቆጠሩ ኮንትራክተሮች አማካሪዎች ጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ድርጅቶች የግንባታ እቃ አቅራቢዎችና የትራንስፖርት ባለንብረቶች ለሰሩት ስራ ክፍያ በወቅቱ እየተከፈላቸው ባለመሆኑ ችግር ውስጥ እንደሚገኙና ስራቸውንም ማከናወን የማይችሉበት ደረጃ ላይ እየደረሱ መሆኑን ይናገራሉየከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር በበኩሉ በ2080ም ሆነ በ4060 ቤቶች ግንባታ ዝቅተኛ የስራ አፈፃፀም እንደተመዘገበ አምኖ የችግሩ መንስኤ በፋይናንስ ክፍያ አፈፃፀም ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አሰራር በመጀመሩ መሆኑን ገልጿል ሚኒስቴሩ አዲሱ አሰራር ወደ መስመር እስኪገባ ድረስ የተፈጠረ የስራ መጓተት ነው ብሏልበተያዘው በበጀት አመት መጀመሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚገነባቸው ቤቶች  የሚውል የቦንድ ብድርና የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ተሰልቷል በስሌቱ መሰረት አጠቃላይ ፍላጎቱ 3103 ቢሊዮን ብር ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከዚህ ከሚያስፈልገው ገንዘብ ውስጥ 15 ቢሊዮን ብር የቦንድ ብድር ፈቅዷልከዚህ ውስጥ 85 ቢሊዮን ብር ለአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት 2080 65 ቢሊዮን ብር ደግሞ ለአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ 4060 ተደልድሏልነገር ግን የክፍያ አፈፃፀም ላይ ለውጥ ተደርጓል የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚጠቁመው ሀብትን በተገቢው መንገድ ስራ ላይ ማዋል በሚለው መርህ መሰረት ክፍያዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል እንዲፈፀሙ ተደርጓል ባንኩ በቅርብ ክትትልና ቁጥጥር ተግባራዊ እንዲያደርግ በመወሰኑ ምክንያት የክፍያ አፈፃፀም ሂደቱ የተጠበቀውን ያህል ቀልጣፋ ሊሆን አለመቻሉ ተገልጿልባለፉት ስድስት ወራት የቦንድ ብድር አጠቃቀም በአጠቃላይ ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ከፍ ሊል አልቻለም ይኸውም ለ2080 ቤቶች ፕሮግራም 14 ቢሊዮን ብር ለ4060 ቤቶች ፕሮግራም 105 ቢሊዮን ብር ብቻ ወጪ ተደርጓል ሲል የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፖርት ያስረዳልከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ክፍያ የጠየቀ የቤቶች ግንባታ ተዋናይ ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ቼክና ክፍያው እንዲፈፀም የሚገልፅ ደብዳቤ ይሰጠዋል ይህንን ይዞ ወደ ባንክ ሲሄድ ክፍያው ይፈፀም ነበርአሁን ባለው አሰራር የግንባታ ተዋናዩ ክፍያ እንዲከፈለው ለፕሮጀክት ፅህፈት ቤቱ ደረሰኝ ይቆርጣል የፕሮጀክት ፅህፈት ቤቱ ክፍያ እንዲፈፅም ለባንኩ ይገልፃል ባንኩ ክፍያ ይፈፅማል ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ባንኩ ክፍያ እየፈፀመ ባለመሆኑ ድርጅቶቹ ለሰራተኞቻቸው ደመወዝ መክፈል እንኳ እያቃታቸው መምጣቱን እየገለፁ ነውይህ ችግር አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ 18 የፕሮጀክት ፅህፈት ቤቶችን ያጨናነቀ መሆኑም ተመልክቷልበ2006 አም የተጀመሩ 20931 የ4060 ቤቶች ግንባታ በስምንት ሳይቶች እየተካሄደ ነው በግማሽ አመቱ ግንባታውን 97 በመቶ ለማከናወን ቢታቀድም ውጤቱ ግን 48 በመቶ ብቻ ነው በ20072008 አም የተጀመሩ የ17005 ቤቶች ግንባታ በአራት ሳይቶች እየተካሄደ ነው በግማሽ አመቱ በአማካይ 142 በመቶ ለማከናወን ቢታቀድም ውጤቱ ግን 79 በመቶ ብቻ ነውበ4060 የቁጠባ ቤቶች ፕሮግራም ከተጀመሩት መካከል 1292 ቤቶች 972 መኖርያ 320 የንግድ ቤቶች ግንባታቸው በአብዛኛው ተጠናቋልቤቶቹ ስለሚተላለፉበት ሁኔታ የተለያዩ መድረኮች በማዘጋጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን የሚተላለፉበት ዋጋና ሌሎች ተያያዥ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ተለይተው ለውሳኔ ሰጪ አካላት ተላልፏል ሲል የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፖርት ያመለክታልበአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት ሲካሄዱ የቆዩ የቤቶች ግንባታዎች ተቀዛቅዘዋል አንዳንድ ቦታ ላይ ጭራሽ የቆሙ ግንባታዎችን ማየት የተለመደ ክስተት ሆኗል
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%89%A0%E1%8D%8B%E1%8B%AD%E1%8A%93%E1%8A%95%E1%88%B5-%E1%8D%8D%E1%88%B0%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8C%93%E1%8C%8E%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%AE%E1%8A%95%E1%8B%B6%E1%88%9A%E1%8A%95%E1%8B%A8%E1%88%9D-%E1%89%A4%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8C%8D%E1%8A%95%E1%89%A3%E1%89%B3-%E1%89%BD%E1%8C%8D%E1%88%AD-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B0%E1%8C%88%E1%8C%A0%E1%88%98%E1%8B%8D-%E1%89%B0%E1%8C%A0%E1%89%86%E1%88%98
431
33,008
ከናጅራን የተለያየው ዋሊድ ለአል ካሊጅ ለመጫወት ተስማምቷል
ስፖርት
September 13, 2017
Unknown
ኢትዮጵያዊው የመሀል ተከላካይ ዋሊድ አታ ከሳውዲ አረቢያው ናጅራን ስፖርት ክለብ ጋር የነበረውን ውል በስምምነት አፍርሶ ወደ ሌላኛው የሳውዲ ክለብ አል ካሊጅ ማምራቱ ተረጋግጧል ዋሊድ በኖርዌይ ሊግ ለሚወዳደረው ሶግንዳል በውሰት ያለፉትን አራት ወራት ካሳለፈ በሀላ ከናጅራን ጋር የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ላይ ይገኝ የነበረ ቢሆንም ከክለቡ መለያየትን ምርጫው አድርጓልየቀድሞው የኤአይኬ ቢኬ ሀከን እና ዳይናሞ ዛግሬብ ተጫዋች በናጅራን መጫወት ሳይችል ከክለቡ መለያየቱ አስገራሚ ሆኗል ዋሊድ አል ካሊጅን ከወዲሁ የተቀላቀለ ሲሆን ከናጅራን የለቀቀበትን ምክንያት ለሶከር ኢትዮጵያ በተለይ ገልጿል ከናጅራን ጋር የነበረኝ ውል በስምምነት ፈርሷል ክለብ የቀየርኩት በናጅራን ባለው ከፍተኛ የውስጥ ችግር ነው ሲል ዋሊድ አስረድቷል አል ካሊጅ ለዋሊድ የምን ያህል ግዜ ውል እንዳስፈረመው ባይጠቆምም ተጫዋቹ ቢያንስ የአንድ አመት ውል ሳይፈርም እንዳልቀረ ተገምቷል አል ካሊጅ በ201617 ከአብዱላቲፍ ጃሜል ሳውዲ ፕሮፌሽናል ሊግ በ23 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቁ ሊወርድ ችሏል አል ካሊጅ በቀጣይ አመት በሳውዲ አንደኛ ዲቪዚዮን የሚወዳደር ሲሆን ዳግም ወደ ዋናው ሊግ በፍጥነት ለመመለስ አልሟልከ2007 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጀምሮ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የተወሰኑ ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለው የቀድሞ ስዊድን ከ21 አመት በታች ኢንተርናሽናል ባለፉት ሶስት አመታት ብቻ ለስድስት ክለቦች ተጫውቷል ዋሊድ በአንድ ክለብ ሰፋ ያለ ግዜ ለመቆየት እየተቸገረ ሲገኝ ከቢኬ ሀከን ቆይታው በሀላ በኦስተርሰንድስ መልካም የሚባል ግዜን አሳልፏል
https://soccerethiopia.net/football/30262
182
47,297
በአዲስ አበባ በተያዘው ዓመት 73 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ይጠናቀቃሉ
ፖለቲካ
January 5, 2015
Unknown
በአዲስ አበባ ከተማ በተያዘው አመት የ73 ሺህ ቤቶች ግንባታ እንደሚጠናቀቅ የከተማዋ የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ገለፀበከተማዋ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የማህበረሰብ አባላት የቤት ባለቤት ለመሆን እየቆጠቡ ይገኛሉየፅህፈት ቤቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት መሪ አቶ ካሳ ወልደሰንበት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት በከተማዋ በሶስት ምእራፎች  ከተከፋፈሉ ቤቶች የተወሰኑት ዘንድሮ ለአገልግሎት ይበቃሉእየተገነቡ ካሉት ቤቶች ከ2004 እስከ 2006 ባለው ጊዜ የተጀመሩ ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ሁለት አመታት ላይ የተጀመሩት ቤቶች በያዝነው አመት ይጠናቀቃሉበ2004ና 2005 አም ግንባታቸው ከተጀመሩ መኖሪያ ቤቶች መካከል አምስት ሺህ ያህሉ ተጠናቀዋልበ2006 የተጀመሩ ቤቶች 50 ሺህ ቤቶች ሲሆኑ በኩየ ፈጬ እየተገነቡ ይገኛሉ ያሉት አቶ ካሳ በቀጣይ አመት እንዲጠናቀቁ እቅድ መያዙንም ተናግረዋልየፕሮጀክቶቹ ግንባታ ከተያዘላቸው ጊዜ አንፃር ሲታይ መጓተት እንደታየባቸው አምነው  ለዚህም በአገሪቱ ያለው የመሰረተ ልማት አቅርቦት ማነስ መሆኑን አቶ ካሳ አስረድተዋልበአገሪቱ ያለው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ እድገትየግብአት አቅርቦትየሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት ግንባታው በሚፈለገው ፍጥነት እንዳይሄድ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን ነው ያብራሩትየመሰረተ ልማት ችግሩን ለማቃለል ከሚመለከታቸው የመሰረተ ልማት መስሪያ ቤት አካላት በሙሉ በተደራጀ መልኩ እየሰሩ መሆናቸውንም ተናግረዋልሆኖም አጠቃላይ የቤቶቹ ግንባታ አፈፃፀም በአገሪቱ ብቻ ሳይሆን በአለም ደረጃ ሲታይ ጥሩ የሚባል አፈፃፀም መሆኑን አመልክተዋልይሁን እንጂ ብዛት ያለው ህዝብ እየቆጠበ የቤት ባለቤት ለመሆን የቤቶቹ ግንባታ መጠናቀቅ እየተጠባበቀ ባለበት ሁኔታ በሚሆኑ ከፍተኛ ስራ እንደሚጠብቅ ተናግረዋልየንግድ ባንክ የኮሚኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በበኩላቸው ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ደንበኞች ለጋራ መኖሪያ ቤት እየቆጠቡ እንደሚገኙ ተናግረዋልደንበኞቹ በየወሩ በደንቡ መሰረት በጥሩ ሁኔታ እየቆጠቡ እንደሆነም ነው ያረጋገጡትየሚጠናቀቁት ቤቶች በ2004 እና 2005 በጀት አመት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች መሆናቸው ታውቋልእስካሁን ድረስ በ9 ዙሮች ከ108 ሺህ በላይ ቤቶች ተጠናቅቀው ለተጠቃሚ መተላለፋቸው ከፅህፈት ቤቱ የተገኘ መረጃ ያመላክታልኢዜአ
https://waltainfo.com/am/25231/
235
47,900
95 ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ሰኔ ግንባታቸው ተጠናቆ ለተጠቃሚ ይተላለፋሉ
ፖለቲካ
December 18, 2013
Unknown
በ2006 የበጀት አመት በአዲስ አበባ በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ 95ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ግንባታው ተጠናቆ ለተጠቃሚው ህብረተሰብ እንደሚተላለፍ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታወቀግንባታቸው በተጠናቀቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የመሰረተ ልማት ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለፀው የከተማ አስተዳደሩ ሪፖርት በ2080 ፕሮግራም አዲስ የሚጀመሩ የ50 ሺ ቤቶች ግንባታን አስመልክቶ የዲዛይን ስራ የመሬት ዝግጅትና የግንባታ ግብአት በማሟላት ግንባታው በበጀት አመቱ መጨረሻ 40 በመቶ እንዲጠናቀቅ ይደረጋል በ4060 ቁጠባ ቤቶች በቃሊቲ ክራውን ሆቴል አካባቢና በሰንጋተራ የተጀመሩ 1ሺ 290 ቤቶች ግንባታ እንዲፋጠን የሚደረግ ሲሆን በተጨማሪም አስፈላጊውን የግብአት ቅድመ ዝግጅት በአመቱ መጨረሻ ግንባታው 40 በመቶ እንደሚጠናቀቅና የ2ሺ 500 የማህበር ቤቶች ግንባታ ለመጀመር አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል
https://waltainfo.com/am/28387/
109
47,359
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም የ600 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጠ
ፖለቲካ
November 1, 2014
Unknown
የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የአራተኛው ምእራፍ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም የ600 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብድር ሰጠየገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ እና በአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሚስተር ጓንግ ዚ ቺን የብድር ስምምነቱን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተፈራርመዋልሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን በዚሁ ወቅት እንደገለፁት በኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ከተደረገ አስር አመታትን ያስቆጠረ ይህ ፕሮግራም ውጤታማና በርካታ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደረገ ነውበፕሮግራሙ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ኢትዮጵያን የእለት ተእለት ድጋፍ የሚያደርግ  ሲሆን ከድህነት እንዲወጡና ጥሪት እንዲቋጥሩም በማስቻል ረገድ ስኬታማ  ሰራዎችን መስራቱን  ጠቁመዋልበሁሉም ክልሎች ተግባራዊ የተደረገው ይህው ፕሮግራም ከ6 ሚሊዮን በላይ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ደረጃ በደረጃ ከድህነት እንዲወጡ ያስቻለ ነው ያሉት አቶ ሱፊያን በአፍሪካ ትልቁና የምግብ ዋስትናን ያረጋገጠ እንደሆነም አስረድተዋልፕሮግራሙ በኢትዮጵያና በልማት ተባባሪዎች የሚካሄድ ሲሆን በዛሬው እለት ከአለም ባንክ ጋር  በብድር የተገኝው ገንዘብም  በአራተኛው ምእራፍ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ስራ እንደሚውል ተናግረዋልከዚህ በፊት የነበረው የፕሮግራሙ ሶስት ምእራፍ  አፈፃፀም ተገምግሞ ውጤታማነቱ ተፈትሾዋል ያሉት  አቶ ሶፍያን በርካታ አርሶ አደሮች ራሳቸውን በመቻላቸው ከፕሮግራሙ ተመርቀው መውጣታቸውን አብራርተዋልበአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሚስተር ጓንግ ዚ ቺን በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአለም ባንክ የማህበራዊ ምግብ ዋስትና ዘርፍ በሚሰጠው ድጋፍ ተጠቃሚ እየሆነች ነው ብለዋልበዛሬው እለት የተፈረሙ የብድር ገንዘብ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክትን ለማስፋፋትየአደጋ ተጋላጭነት ለማስወገድለምግብ ፕሮግራም እንዲሁም በገጠራማው ኢትዮጵያ የሚኖሩ ቤተሰቦችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ይውላል ብለዋልፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጎን ለጎን አገሪቱ በተለያዩ መስኮች የምእተ አመቱን የልማት ግብ እንድታሳካ እገዛ እንዳደረገላትም አመልክተዋልይህው አራተኛው ምእራፍ የሴፍትኔት ፕሮግራም በኢትዮጵያ ውስጥ 411 ዲስትሪክቶች ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በየአመቱ 10 ሚሊዮን ሰዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እንደሚረዳም ገልፀዋል ኢዜአ
https://waltainfo.com/am/25163/
228
28,534
ቤዛዊት ታደሰ ወደ እግር ኳስ ለመመለስ ድጋፍ ትሻለች
ስፖርት
January 17, 2020
Unknown
ወጣቷ አጥቂ ቤዛዊት ታደሰ በጉልበቷ ላይ በደረሰ ጉዳት ከሜዳ ከራቀች ሶስት ወራት ያለፋት ሲሆን ወደ ሜዳ ለመመለስ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፃለችበኢትዮጵያ እግር ኳስ ተስፋ ከተጣለባቸው ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል አንዷ የሆነችው ፈጣኗ የአጥቂ እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ቤዛዊት ታደሰ በ2009 ክረምት ደቡብ ክልልን ወክላ በመላው ኢትዮጵያ ውድድር ስትጫወት ባሳየችው እንቅሴቃሴ በዛኑ አመት በደደቢት የመጫወት እድልን አግኝታ እስከ 2010 መቆየት ችላለች በ2011 የውድድር ዘመን አዲስ አበባ ከተማ በመጫወት ያሳለፈችው ተጫዋቿ የመዲናይቱን ክለብ በክረምቱ የዝውውር ወቅት ወደ ጌዲኦ ዲላ ማምራት ብትችልም በዝግጅት ወቅት ከክለቧ ጋር በልምምድ ላይ ሳለች ከጉልበቷ በታች ACL ጉዳት ገጥሟት ከሜዳ ከራቀች ወራቶችን አስቆጥራለች ተጫዋቿ ህክምና ለማድረግ ያሰበች ቢሆንም የህክምና ወጪው ከአቅሜ በላይ ነው ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ወደምወደው እግር ኳስ እንድመለስ ከጎኔ ይቁምልኝ ስትል ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግራለችየተጎዳውት በዝግጅት ላይ እያለው ነው ከጉልበቴ በታች አሸማቀቀኝ በሂደት ግን ልምምድ እየሰራሁ እየዳንኩ መስሎኝ ነበር ሆኖም እየባሰብኝ መጣ ለህክምና ወደ ካዲስኮ ሆስፒታል አምርቼ ሰርጀሪ መሰራት አለብሽ ተብያለሁ ከ160 ሺህ ብር በላይ ተጠይቄያለሁ አሁን ቀጠሮ ተይዞልኛል ለመታከም ደግሞ እኔ ከአቅሜ በላይ ስለሆነ ሁሉም ከጎኔ ሆኖ ወደ እግር ኳስ እንዲመልሰኝ እና እንዲረዳኝ በፈጣሪ ስም እማፀናለሁ ብላለች ተጫዋቿ የጌዲኦ ዲላ አዲስ ፈራሚ ብትሆንም ክለቡ እስካሁን ከጎኔ አይደለም ስትልም ቅሬታዋን ገልፃለችቤዛዊት ታደሰን ለመርዳትኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤዛዊት ታደሰ ዳኜ 1000181220426
https://soccerethiopia.net/football/54453
196
41,917
የፕሬዚዳንታዊ የምረጡኝ ዘመቻ የመጨረሻ ሰዓታት
ዓለም አቀፍ ዜና
November 06, 2016
Unknown
ገር አቀፍ የምርጫ ድጋፍ ግምገማዎች የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደልባቸው ተናጋሪውን ቱጃር በጠባብ ድምፅ ብልጫ መምራታቸው ቀጥለዋልአብዛኞቹ የህዝብ አስተያየት ተንታኞች ሚስስ ክሊንተን እንደሚያሸነፉ እየተነበዩ ናቸውይሁን እንጂ በእነዚህ የምረጡኝ ዘመቻ የመጨረሻ ሰአታት በተቀራረበ ድጋፍ ድምፅ እየታፋለሙ ባሉባቸውና ለወትሮ ዲሞክራቶችን በሚመርጡ አካባቢዎች ትራምፕ ከነጠቋቸው አሸንፈዋቸው ዋይት ሀውስ ሊገቡ እድል አላቸውየሰሞኑ ሀገር አቀፍ ግምገማ ጥንቅር ሁለት ወይም ሶስት ከመቶ የሚመሩት ክሊንተን የመጀመሪያ የዩናይትድ ስቴትስ ሴት ፕሬዚዳንት ሆነው ታሪክ ሊሰሩ ይመስላልዋሽንግተን ፖስትና አቢስ ኒውስ ያካሄዱት የኋለኛው አብይ የድምፅ ግምገማ ደግሞ አርባ ስምንት ለአርባ ሶስት እየመሩ እንደሆነ ያሳያል ዛሬ የየክሊቭላንድ ካቫሊየርስ የቅርጫት ኳስ ቡድን ኮከብ ተጫዋች ለብሮን ጄምስ ክሊቭላንድ ኦሀዮ ከሚሲስ ክሊንተን ጋር በምረጡኝ ዘመቻቸው ላይ ይቀሰቅሱላቸዋልዲሞክራትዋ እጩ በአሁኑ ጊዜ ትራምፕ እየመሩ ያሉበትን የከባድ ፍልሚያ ክፍለ ሀገር ነጥቀው ማሸነፍ አለባቸውይሄ ምርጫ ምን ያህል ክብደት እንዳለው ሁሉም ሰው እንደሚገነዘበው ተስፋ እለኝ ብለዋልሂላሪ ክሊንተንን እንደሚደግፍ በቅርቡ በአደባባይ ያስታወቀው የብሄራዊ ቅርጫት ኳሱ ኮከብ ከወዲሁ ድምፁን መስጠቱን ገልጿል ዛረኢ ሚሲ ክሊንተን ወደ ኒውሀምሻየር ክፍለ ግዛትም ይጓዛሉ ትራምፕ ደግሞ ዛሬ በርከት ያሉ ስፍራዎች ይደርሳሉበታሪክ ዲሞክራት እጩ በሚመርጡ በርከት ያሉ አካባቢዎች አይዋ ሚኔሶታ ሚሺጋን ፔንሲልቬንያ እና ቨርጂኒያ ይዘዋወራሉ ተቀናቃኜ የተመረጡ እንደሆን ሀገሪቱ እንዴት እንደምትሆን ትራምፕ አጨልመው እየሳሉ ሲያሳዩ ክሊንተን በበኩላቸውህብረታችን ጥንካሬችን ነው በማለት መራጩን መቀስቀሳቸውን ቀጥለዋልዶናልድ ትራምፕ ትናንት ቅዳሜ ኔቫዳ ክፍለ ግዛት ሪኖ ከተማ የምረጡኝ ዘመቻ ላይ እያሉመሳሪያ የያዘ ሰው አለ ተብሎ በተፈጠረ በኋላ ግን ሀሰት ሆኖ በተገኘ ግርግር ምክንያት የደህንነት ጠባቆዎች ተሯሩጠው ከመድረኩ አፍሰው ወደ መድረኩ ጀርባ ወስዷቸው ነበር አንድ ሰው ከአዳራሹ ታጅቦ ሲወሰድ የታየ ሲሆን ትረምፕ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደመድረኩ ተመልሰው ንግግራቸውን ቀጥለዋል ተጠርጣሪው ላይ ሽጉጥ እንዳልተገኘበት የደህንነት አገልግሎት ሰዎች መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል
https://amharic.voanews.com//a/us-campaign-11-6-2016/3583736.html
244
22,354
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ያቀረቡት የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሕግ ተጠያቂነት እንደሚኖርባቸው ተገለጸ
ፖለቲካ
14 October 2018
Unknown
ረቡእ መስከረም 30 ቀን 2011 አም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዶር ጋር ካልተወያየን በማለት ቤተ መንግስት የገቡት የመከላከያ ሰራዊት ኮማንዶዎች በፈፀሙት ድርጊት ምክንያት የህግ ተጠያቂነት እንደሚኖርባቸው ተገለፀ ወታደሮቹ ቡራዩ አካባቢ የተሰጣቸውን ፀጥታ የማስከበር ግዳጅ ከፈፀሙ በኋላ ነበር ወደ ቤተ መንግስት ያቀኑትየመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ሪፖርተር በስልክ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ወታደሮቹ ከግዳጃችን ከተመለስን ሁለተኛ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የማግኘት እድል ስለሌለን አጋጣሚውን ተጠቅመን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት አለብን በማለት ነው ተያይዘው የሄዱት ሲሉ አስረድተው አንደኛውና ትልቁ ነገር በዚህ ድርጊት ላይ ከተሳተፉት አካላት ጋር ህገ መንግስት እንደተጣሰ አካሄዳቸው ስህተት እንደሆነና በዚህም ምክያት እንደተፀፀቱ መግባባት ላይ ደርሰናል ድርጊቱ ስህተት ነው በዚህ አግባብ መሄድ ለአገርም ሆነ ለተመልካችና ለሀብረተሰቡ ተገቢ አይደለም በዚያ መንገድ መሄድ አልነበረብንም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል ሆኖም ለወደፊት በዝርዝር እየታየ ለምንድነው እዚህ ደረጃ ላይ የተደረሰው በወቅቱ እዚህ ደረጃ ላይ ከመደረሱ በፊት በቅርበት ያለው አመራር እንዴት አላየም ለሌላውስ እንዴት አላሳወቀም የሚሉት ነገሮች ደግሞ በቀጣይ ይታያሉ ብለዋልበአዲስ አበባ ዙሪያና በቡራዩ አካባቢ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ከጦላይ ከሶማሌ ክልልና ከተለያዩ ስፍራዎች እንደመጡ የተነገረላቸው ኮማንዶዎቹ ግዳጃቸውን ፈፅመው ወደ ጦር ሰፈራቸው እየተመለሱ እንደነበር ተጠቁሟል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማግኘት ወደ ቤተ መንግስት ከማቅናታቸው በፊት ከግዳጅ ስፍራቸው ሳይንቀሳቀሱ ሀሙስ መስከረም 29 ቀን 2011 አም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ሲያነሱ እንደነበር ሚኒስትሩ አስረድተዋልወታደሮቹ ከቤተ መንግስት ከተሸኙ በኋላ ከሚኒስትሩና ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሰአረ መኰንን ጋር ለሁለት ቀናት ስብሰባ ማድረጋቸውን በድርጊታቸው ተፀፅተው ይቅርታ መጠየቃቸውንና ይኼንንም የሚያመለክት የአቋም መግለጫ ማውጣታቸው ተገልጿልየእነሱን ጥያቄዎች በዝርዝር ሰምተናል በአብዛኛው በተቋሙ የሚታወቁ ጥያቄዎች ናቸው የአቅርቦቶች በጊዜ አለመቅረብ የኑሮ አለመመቸት የድጎማ ማነስና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ናቸው በተቋም ደረጃ መታየት ስለሚችሉ ወደዚያ መሄድ እንደሌለባቸውና ይህ ደግሞ ስህተት እንደሆነ ተማምነናል ያሉት አቶ ሞቱማ ወደ ቤተ መንግስት የሄዱት ለጥያቄ ነው እንጂ በማሀበራዊ ሚዲያ እንደተወራው መንግስት ለመገልበጥ ወይም ለሌላ ነገር አልነበረም ነገር ግን አካሄዳቸው ስህተት ነው ብለዋልይሁንና ይህ ክስተት ሲፈጠር አራት ኪሎ አካባቢ የነበሩ የአይን እማኞች ለሪፖርተር እንደተናገሩት ወታደሮቹ በስፍራው እንደተበተኑ መንገድ መዘጋቱንና ተሽከርካሪዎች ወደ ኋላ መመለስም ሆነ ወደ ፊት መሄድ እንዳይችሉ ሆነው መቆማቸውን ከወታደሮቹ መሀል የተሽከርካሪዎችን ኮፈን እየመቱ እግረኞችን ሲገፈትሩ ነበር የአይን እማኞች ወታደሮቹ በወቅቱ አላማቸው ግልፅ ስላልነበር አስደንጋጭ እንደነበር አክለዋልመንግስትም ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ ከሆነ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ አፋጣኝ ጥንቃቄ ማድረጉን ምንጮች ለሪፖርተር ገልፀዋል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ቢሮና የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች ጥብቅ ጥበቃ እንዲደረግላቸው መደረጉን ምንጮች አክለዋል ምንም እንኳን የትኞቹ ስፍራዎች የጥንቃቄ ትኩረት እንደነበሩ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ ባይገልፁም የታጠቀ ሀይል በእንዲህ አይነት ሁኔታ ሲገባ አስፈላጊው ክትትል ሲደረግ ነበር ችግር እንኳን ቢፈጠር ቶሎ ማስቀረት በሚቻልበት ደረጃ ዝግጅቶች በየቦታው ሲደረጉ ነበር ይህም የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ የተደረገ ነው ሁልጊዜ ዝግጁነት አስፈላጊ ነው ሰዎቹ ጥያቄ ነው ያቀረቡት እነሱ በሚፈልጉት መንገድ ካልተኬደና የሚፈልጉት ነገር ካልተገኘ ምንድነው የሚከተለው የሚለውን ማሰብ አስፈላጊ ነበር የሚሆነው ሲሉ የተደረገውን ጥንቃቄ አረጋግጠዋልየሰራዊቱ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዶር ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ዶር ከጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሀኑ ፀጋዬና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸው አይዘነጋም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከውይይቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ ወታደሮቹ አላማቸው ከእሳቸው ጋር መገናኘት ብቻ እንደነበርና አግኝተው ማወያየታቸውን አስታውቀዋልአቶ ደመቀ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የፌስቡክ ገፃቸው ላይ የሰራዊቱ አባላት እንደ ማንኛውም ዜጋ የመደመጥ መብት እንዳላቸው በመጠቆም ጥያቄያቸውን ማዳመጣቸውን አስፍረዋልይሁን እንጂ ይህ ክስተት በመከላከያ ሰራዊት የእዝ ሰንሰለት መላላቱን ወይም መበጠሱን የሚያመላክት ላለመሆኑ ምንም ማስተማመኛ አለ ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ አሉ ይህ ጉዳይ ቀድሞ አለመታወቁና ወዲያው ደግሞ አስፈላጊው እርምጃ አለመወሰዱ የደሀንነት ስጋት ይፈጥራል ሲሉም የሚተቹ አሏቶ ሞቱማ ይኼንን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት እኛ ዘንድ ከዚያ በፊት የታወቀ ነገር አልነበረም በዚያ ደረጃ ወደዚያ ይሄዳሉ በማለት የቅርብ አመራሮችም በያሉበት የተገነዘቡበት ሁኔታ አልነበረም ይህ የሚገመገም ነው ለምን እስከዚያ ድረስ ተሄደ ለምን ቀድሞ ባለበት ማረም አልተቻለም ለሚለው ጉዳይ ወደፊት የሚታይ ይሆናል ብለዋል የቅርብ አዛዦችም ከወታደሮቹ ጋር አብረው እንደነበሩ አክለዋልወታደሮቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ሲገቡ የምንወደውን ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ለማናገር ስለመጣን ትጥቅ መፍታት የለብንም በማለት ትጥቅ ላለመፍታት አንገራግረው እንደነበረ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል አቶ ዘይኑ ጀማል በእለቱ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ አስታውቀው ነበር ይሁንና የቤተ መንግስቱ አሰራር በመሆኑ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ መግባባት ላይ መደረሱንና ከዚያም ወደ ውይይት መገባቱን አስታውቀዋልወታደሮቹ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዶር ጋር ከነበራቸው ቆይታ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት ፑሽ አፕ መስራታቸው በምስል ተደግፎ ተዘግቧል የእራት ግብዣ ተደርጎላቸው መሸኘታቸውም መገለፁ አይዘነጋም
https://www.ethiopianreporter.com/article/13359
624
18,007
የሰላም ሚኒስቴር 12 የእርሻ ትራክተሮችን ለክልሎች አስረከበ
ሀገር አቀፍ ዜና
Feb 5, 2020
530
አዲስ አበባ ጥር 27 2012 ኤፍቢሲ የሰላም ሚኒስቴር በ28 ሚሊየን ብር የገዛቸውን የእርሻ ትራክተሮች ለጋምቤላና ለቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አስረከበበሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና የልዩ ድጋፍ ጀኔራል ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ደገፋ ቶሎሳ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎችና የአርብቶ አደር አካባቢዎች ልዩ ድጋፍ መስጠትና ሌሎች የፌደራል መስሪያ ቤቶች የሚሰጡትን ልዩ ድጋፍ ማስተባበር ከተሰጡት ተልእኮወች አንደኛው መሆኑን አንስተዋልየዚህ የልዩ ድጋፍ ማእቀፍ ለሆኑት አፋር ቤኒሻንጉል ጉምዝና ለጋምቤላ በየአመቱ 450 ሚሊየን ብር መድቦ በሰላም ሚኒስቴር በኩል የልማት ስራዎች እንዲከናወኑ እያደረገ ይገኛልም ነው ያሉትበዚህም 12 የእርሻ ትራክተሮች ለጋምቤላና ለቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የተረከቡ ሲሆን ግብርናን በማዘመን አርሶ አደሮቹን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲላመዱ በማድረግ እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማስረፅ ረገድ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ አንስተዋልከጋምቤላና ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የተወከሉ የስራ ሀላፊዎች በበኩላቸው በሁለቱ ክልሎች ሰፊና ሊለማ የሚችል መሬት እንዳለ ገልፀዋልትራክተሮቹ በክልላቸው የሚገኙ ወጣቶችን በማደራጀት ወደ እርሻ ስራ እንዲሰማሩና የልማት ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ከፍ ያለ ሚና እንዳላቸው መናገራቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታልትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ httpstmefanatelevision
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b4%e1%88%ad-12-%e1%8b%a8%e1%8a%a5%e1%88%ad%e1%88%bb-%e1%89%b5%e1%88%ab%e1%8a%ad%e1%89%b0%e1%88%ae%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%88%88/
148
35,656
መከላከያ በሊዮፓርድስ ተሸነፈ
ስፖርት
March 4, 2014
Unknown
የአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ወደ ናይሮቢ የቀናው መከላከያ በሊዮፓርድስ 20 ተሸንፏል እንግዳው መከላከያ በ30ኛው ሰከንድ በሙሏለም ጥላሁን አማካኝነት የመጀመርያ ሙከራውን ሲያደርግ የመጀመርያው ግብ እስኪቆጠርበት ድረስ ተመጣጣኝ ፉክክር አሳይቷልመከላከያ ግብ ያስተናገደው ጨዋው በተጀመረ በ23ኛው ደቂቃ ሲሆን ማርቲን ኢምባላምባላ በግንባሩ በመግጨት ግቡን አስቆጥሯል ከግቡ መቆጠር በሀላ ጫና የፈጠረው መከላከያ በ34ኛው ደቂቃ በሙሏለም ጥላሁን አማካኝነት ለግብ የቀረበ ሙከራ አድርጎ በግብ ጠባቂው ዋይክሊፍ ካሳያ ግብ ከመሆን ድኗልበ43ኛው ደቂቃ ፖል ዌር ከመስመር ያሻገረውን ኳስ የኬንያ ፕሪሚየርሊግ ኮከብ ተጨዋቹ ጃኮብ ኬሊ አስቆጥሮ ሊዮፓርድስን በ20 መሪነት እረፍት እንዲወጡ አግዟልበሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ሙከራዎች ቢያደርጉም በግብ ጠባቂዎቹ ጥረት ግብ ሳይሆኑ ጨዋው በሊዮፓርድስ 20 አሸናፊነት ተጠናቋል በጨዋው መከላከያ እንደተለመደው በኳስ ቁጥጥር የበላይ ቢሆንም የሊዮፓርድስን የመስመር አጨዋወት መቆጣጠር ሳይችል ወጥቷልሁለቱ ቡድኖች ቀጣይ እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም 10 ሰአት ላይ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉjcomments on
https://soccerethiopia.net/football/158
126
13,215
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በኢትዮጵያ የተሾሙ የሰባት ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
Dec 22, 2020
186
አዲስ አበባ ታህሳስ 13 2013 ኤፍ ቢ ሲ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የተሾሙ የሰባት ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ መቀበላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀየሹመት ደብዳቤዎችን ያቀረቡ አምባሳደሮች በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሮበርት ሼትኪንቶንግ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢሂዩዋን በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሾዛብ አባስ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ካንግ ሴኦሄ በኢትዮጵያ የቱኒዚያ አምባሳደር አብዱልሀሚድ ግሀርቢ እና በኢትዮጵያ የዚምባብዌ አምባሳደር ታኦንጋ ሙሰሀያቫንሁ ናቸውፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙት አጠናክራ ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋልየሹመት ደብዳቤውን ካቀረቡት ከተወሰኑት ሀገራት ጋር በተፈጠረ ስትራቴጂካዊ ትብብር የተገኘውን ጥቅም በማብራራት ሌሎች ሀገራትም ይህንኑ መንገድ እንደሚከተሉ ተስፋቸውን ገልፀዋልፕሬዚዳንቷ ለአምባሳደሮቹ መንግስት በትግራይ ክልል ያካሄደውን ህግን የማስከበር ዘመቻ ካጠናቀቀ በኋላ እያከናወነ ስላለው መልሶ የማቋቋም ስራ ማብራሪያ ሰጥተዋልአምባሳደሮቹ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ያከናወነችውን ዘመቻ በስኬት በማጠናቀቋ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋልእንዲሁም በኢትዮጵያና በወከሏቸው ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ያላቸው ቁርጠኝነት ገልፀዋልከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘትየፋና ድረ ገፅ ይጎብኙተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
https://www.fanabc.com/%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%9a%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%b3%e1%88%85%e1%88%88%e1%8b%88%e1%88%ad%e1%89%85-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%be/
173
43,917
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በቦታ እጥረት ምክንያት ተፈላጊውን አገልግሎት እየሠጠ አይደለም
ሀገር አቀፍ ዜና
April 16, 2018
Unknown
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ባለበት የቦታ እጥረት ምክንያት ተፈላጊውን አገልግሎት መስጠት እንዳልቻለ  ለዋልታ አስተያየታቸውን የሰጡት የሆስፒታሉ ተገልጋዮች ገለፁ          የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የህክም እና አገልግሎት አሰጣጥ እየተሻሻለ መምጣቱን ተገልጋዩች እና የሆስፒታሉ ሰራተኞች የተናገሩ ቢሆንም  ሆስፒታሉ ባለበት የህክምና ክፍሎች እጥረትና የሰራተኛ እጥረት ምክንያት የሚጠበቀውን ያህል አገልግሎት እንዳይሰጥ ማድረጉንም ተናግረዋልሆስፒታሉ ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ ታካሚዎችን በመቀበል አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ያለበት የቦታ ጥበት ግን አገልግሎቱን ይበልጥ እንዳይሻሻል እንቅፋት ሆኖበታል  ብለዋል አስተያየት ሰጪዎች የሆስፒታሉ የህክምና ክፍሎች ጥበት የተገዙ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች  የራሳቸውን ቦታ አግኝተው ተገቢውን አገልግሎት ለተገልጋዮች  እንዳይሰጡም  ማድረጉን  የሆስፒታሉ  ተገልጋዮች  ተናግረዋል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ተባባሪ ፕሮፌሰርና የአካዳሚና ምርምር ምክትል ፕሮቮስት የሆኑት ዶክተር ባልካቸው ንጋቱ ሆስፒታሉ በአሁኑ ወቅት ያለበትን የቦታ ችግር ለመፍታት እና ሆስፒታሉ ከመንግስት ባገኘው ድጋፍ ህንፃዎችን እያስገነባ መሆኑን ገልፀዋል የእናቶች እና የህፃናት የህክምና አግልግሎት መስጫ ህንፃ ወደ መጨረሻ ምእራፍ መድረሱን እና ሌሎች ህንፃዎችም በ3 አመት ውስጥ እንደሚጠናቀቁ ዶክተር ባልካቸው ተናግረዋል  
https://waltainfo.com/am/31931/
139
44,401
አሜሪካ እየሩሳሌምን የእስራኤል መዲና የማድረግ ውሳኔዋን መቀየር እንዳለባት የመንግሥታቱ ድርጅት ጥሪ አቀረበ
ፖለቲካ
December 20, 2017
Unknown
የተባበሩት መንግስታትም ሀገሪቱ ውሳኔዋን በመቀየር ለመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ሰላምና መረጋጋት መስራት እንዳለባት ጥሪ አቅርቧልአሜሪካ ኢየሩሳሌም የኢስራኤል መዲና ናት የሚለውን ውሳኔ ተከትሎ ትችት እና ወቀሳዎች ቀጥሏልየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየሩሳሌም የእስራኤል መዲና ናት የሚለውን ዉሳኔ ማስተላለፋቸውን ተከትለዉ በቀጠናዉ ግጭት እና አለመረጋጋት በየቀኑ እየተስተዋለ ይገኛልየቀጠናውን አለመረጋጋትም ተከትሎ የሰብአዊ መብቶች ሀላፊዉ ዜይድ ራአድ ሁሴን በዊልቼር ሰላማዊ ሰልፍ የወጣዉን የፍልስጤማውያን አሟሟትን በተመለከተ ነፃ እና ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡምንም ይሁን ምንም በኢብራሂም አቡ ቱራያህ ላይ የተወሰደ የግድያ ውሳኔ አሰቃቂ እና ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ ብሏል ዜይድሰሞኑን የዋሽንግተን ውሳኔን ተከትሎ የተሰበሰበዉ የተባበሩት መንግስታት ምክር ቤት የትራምፕን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳልበተባበሩት መንግስታት የፀጥታ ምክር ቤት በራማላህ ተሰብስቦ ውሳኔውን ሲያስተላልፍም ካሁን በኋላ ዋሽንግተን በገባችበት የትኛውም ድርድር ስምምነት ለማድረግ አልቀመጥም ያለው የፍልስጤም ነፃ አዉጪ ድርጅት የተባበሩት መንግስታት በኩል አባል ለመሆንም ጥያቄ አቅርቧል  ፍልስጤም በተባበሩት መንግስታት ሙሉ እውቅና ያልተቸራት ሀገር እንደመሆኗ ግን ካሁን በፊትም እኤአ በ2011 ጥያቄ ውድቅ እንደተደረገባት ይታወቃልየተባበሩት መንግስታት የፀጥታ ምክር ቤት ዋሽንግተን በቅድስት ከተማ እየሩሳሌም ላይ ያስተላለፈችዉ ዉሳኔ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለዉ እና ባዶ ስትል ውሳኔውን ባስተላለፈበት ስብሰባውም ከአሜሪካ በተቃራኒ መቆሙንም አሳይቷል ምክር ቤቱ በዚህ የአሜሪካ ውሳኔዉን መቀየር እንዳለባት አስጠንቅቋልባሳለፍነዉ ሳምንት በርካታ የሙስሊም ሀገራትን በኢስታምቡል ጠርተዉ ያወያዩ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን አሜሪካ ጉዳዩን እንደገና ማጤን አለባት አሉ ይህ  የማይሆን ከሆነ እንኳ ጉዳዩን ወደ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ መዉሰድ እንዳለባቸዉ በመግለፅ ላይ ናቸዉኢራን በበኩሏ አሜሪካን የህዝብን ሀሳብ ለመቀልበስ ያደረገችዉ ሴራ በሚል ወቀሳዋን አቅርባለች የአዉሮፓ ህብረት በበኩሉ እስራኤል በምስራቅ ኢየሩሳሌም እና ዌስት ባንክ እያደረገች ያለችውን ግንባታ እና የማስፋፊያ ስራዎች ተችቷል የአዉሮፓ ህብረት ካዉንስል ሀሙስ አድርጎ በነበረዉ ስብሰባም በምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ታስክ በኩል የዋሽንግተን ዉሳኔን ዉድቅ በማድረግ አቋሙ እንደማይቀየር ማሳወቁ የሚታወስ ነዉእስራኤል በስፍራዉ የገነባችዉ ትልቅ መንገድ እንኳ የዌስት ባንክ ሰፋሪዎችን በቀላሉ ወደ እየሩሳሌም ከማስገባቱም በተጨማሪ ፍልስጤማዉያን እየሩሳሌምን ሳይረግጡ ቤቴሊሄም እንዲገቡ የሚያደርግም ነዉ ተብሏልባሁኑ ጊዜ ከ208 ሺህ የሚበልጡ እስራኤላዉያን በምስራቅ እየሩሳሌም እንደሚኖሩም መረጃዎች ያመላክታሉ   
https://waltainfo.com/am/33766/
286
50,160
በህገ-ወጥ መንገድ ታጥረው የቆዩና ወደ መንግስት መሬት ባንክ ገቢ የተደረጉ ቦታዎች ለህዝብ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ
ፖለቲካ
December 18, 2018
Unknown
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ታጥረው የቆዩ እና ወደ መንግስት መሬት ባንክ ገቢ የተደረጉ መሬቶች ለህዝብ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የከንቲባው ፅህፈት ቤት አስታወቀከተማ አስተዳደሩ በዛሬው እለትም የከተማ አስተዳደሩ ህንፃ ፊት ለፊት ያለውን ቦታ በከፊል ጊዜያዊ የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ አገልግሎት ማዋሉ ተገልጿልየጊዜያዊ ፓርኪንጉ መጀመርም በአካባቢው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ የሚቀርፍ ሲሆን ቦታም በቋሚነት ለህዝብ መዝናኛ አገልግሎት እንደሚውል የከተማ አስተዳደሩ ቀደም ብሎ መግለፁ ይታወቃል ምንጭየከንቲባ ፅህፈት ቤት
https://waltainfo.com/am/30708/
65
14,341
ሰራዊቱ በአሁኑ ሰዓት ከሁመራ እስከ ሽራሮ ያለውን ቦታ በማጥቃት የተለያዩ ስፍራዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ ነው- ሜ/ጄ መሐመድ
ሀገር አቀፍ ዜና
Nov 11, 2020
1,976
አዲስ አበባ ህዳር 2 2013 ኤፍ ቢ ሲ ሁመራና አካባቢው ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ አስታወቁሰራዊቱ በአሁኑ ሰአት ከሁመራ እስከ ሽራሮ ያለውን ቦታ በማጥቃት የተለያዩ ስፍራዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝም አመልክተዋልሰራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ የእርዳታ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተነጋግረው ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ጠቁመዋልየህወሀት ጁንታ በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በማዘጋጀት ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ ኤርትራ እንደወረረች በመግለፅ ህዝብን እያደናገረ እንደሆነም  መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧልበዚህ የተቀናበረ ድራማ ህዝቡ ሳይታለል ለመከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል
https://www.fanabc.com/%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%8b%8a%e1%89%b1-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%88%81%e1%8a%91-%e1%88%b0%e1%8b%93%e1%89%b5-%e1%8a%a8%e1%88%81%e1%88%98%e1%88%ab-%e1%8a%a5%e1%88%b5%e1%8a%a8-%e1%88%bd%e1%88%ab%e1%88%ae/
97
45,458
የገቢ ግብርና የታክስ አስተዳደር ረቂቅ ደንቦች ውይይት ሊደረግባቸው ነው
ቢዝነስ
May 24, 2017
Unknown
የፌዴራል የገቢ ግብርና የታክስ አስተዳደር ረቂቅ ደንቦች ከመፅደቃቸው በፊት  ውይይት ሊደረግባቸው ነውከአገሪቷ የኢኮኖሚ እድገት ደረጃ ጋር የተጣጣመ የግብር ስርአት ለመዘርጋትና በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችሉ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 9792008 እና የታክስ አስተዳድር አዋጅ ቁጥር 9832008 አዋጆችን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው አመት ማፅደቁ ይታወቃልአዋጆቹ ከሀምሌ 1 ቀን 2008 አም ጀምሮ በተገኘ ገቢ ተፈፃሚ እንዲሆኑ በተወሰነው መሰረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንቦች ተዘጋጅተዋልየገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር የተዘጋጁትን ረቂቅ ደንቦች አስመልክቶ ትናንት ለመገናኛ ብዙኋን መግለጫ ሰጥቷልየሚኒስቴሩ የህግ ዳይሬክተር አቶ ዋሲሁን አባተ እንዳሉት ረቂቅ ደንቦቹ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከመፅደቃቸው በፊት በህዝብ አስተያየት እንዲዳብሩ ይደረጋልበመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ህብረተሰቡን ሊወክሉ ከሚችሉ አካላት ጋር በሶስት ዘርፎች ተከፍሎ ውይይት ይካሄዳልውይይቱ የንግዱን ማህበረሰብ ከሚወክሉ የንግድ ማህበራት ከትራንስፖርት ዘርፍ ከተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከሙያ ማህበራትና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለሙያዎች ጋር እንደሚካሄድ ነው ያብራሩትየረቂቅ ደንቦቹ አላማ በግብር ስርአቱ ፍትሀዊነት እንዲኖርና የመንግስትን ገቢ መጨመር ማስቻል እንደሆነ አቶ ዋሲሁን ገልፀዋልበአዲሱ የገቢ ግብር ረቂቅ ደንብ ከተጠቀሱት ጉዳዮች መካከል ከዚህ በፊት በመንግስት ተቋማት ግብር የማይከፈልበት በአይነት የሚገኝ  ጥቅምን ግብር እንዲከፈልበት ያስገድዳልስለሆነም የቤት የተሽከርካሪ የመብራት የስልክና መሰል ጥቅማጥቅሞች የሚያገኙ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች እንደሚያገኙት ጥቅማጥቅም ታይቶ እስከ አስር በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ተደንግጓልበሌላ በኩል በአመላካች መሰረት ግብር ሲጣልበት የነበረው የትራንስፖርት ዘርፍ ከገቢው ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ማስተካከያ ተደርጎበታልለአብነትም ባለ 5 ወንበር ተሽከርካሪ ባለቤት ከዚህ በፊት በአመት 120 ብር ይከፍል የነበረ ሲሆን በተስካከለው የግብር ረቂቅ ደንብ 1 ሺህ 171 ብር ይከፍላልምንም እንኳን ጭማሪው ቀድሞ ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ ቢሆንም ከሚያገኙት ገቢና ሌሎች ከሚከፍሉት ግብር መጠን አንፃር ግን አሁንም ዝቅተኛ መሆኑ ተጠቁሟልበተሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገው ጭማሪ በህብረተሰቡ የትራንስፖርት ሂደት ላይ ተእፅኖ አይፈጥርም ወይ ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ አቶ ዋሲሁን ባለ አምስት ወንበር ተሽከርካሪን ለአብነት በመውሰድ ምላሽ ሰጥተዋልየካፒታል እቃዎች እርጅና ቅናሽ በቤት ኪራይ ገቢ በንግድ ስራ ገቢና ኪሳራ ማሸጋገር በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በዋናነት የተጠቀሱ ሌሎች ነጥቦች እንደሆኑም በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተመልክቷልከ30 ቀናት ለማይበልጥ ጊዜ የተቀጠሩ የቀን ሰራተኞችና ለሰራተኞቻቸው በነፃ የሚያቀርቡ የምግብ አግልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ መደረጉም ተገልጿልሪቂቅ ደንቦቹ ከውይይት መድረኮች የሚገኙ ጠቃሚ አስተያየቶች ታክለውበት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተቀባይነት ካገኙ የሚፀድቁ ይሆናሉኢዜአ
https://waltainfo.com/am/23165/
313
42,558
"ኮቪድ-19 በፍጥነት እየተዛመተ ነው" የዓለም የጤና ድርጅት
ዓለም አቀፍ ዜና
June 20, 2020
Unknown
የፊት ጭምብል መጠቀም ወይስ አለመጠቀም ዛሬ አሚሪካውያንን የከፋፈፈለ ጉዳይ ሆኗል ፊታቸውን አፍና አፍንጫቸውን በጭንብል ሳይሸፈኑ ደጅ ዝር የማይሉ አሉ ሳይሸፈኑ የሚዘዋወሩም አሉጉዳዩ አብዝቶ ያሳሰባቸው የቴክሳስ ክፍለ ግዛት ዘጠኝ ከተሞች ከንቲባዎች ለነዋሪዎቻቸው በፃፉት ደብዳቤ እባካችሁ ያለጭንብል አትውጡ ብለው አጥበቀው መማፀናቸውን ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘግቧልቫይረሱ መዛመቱን ቀጥሏል የህመምተኛው ብዛት ከሆስፒታሎች አቅም በላይ እየሆነ ነው ሀቁን ልንነግራችሁ እንጂ ልናስፈራራችሁ ፈልገን አይደለም ቫይረሱ እኛ ቸል ስላልነው አይወገድም ሲሉ ከንቲባዎቹ መማፀናቸውን ፖስት ዘግቧልበሌላ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ዜና አለም አቀፉ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን የአለም የጤና ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም አስገንዝበዋልከትናንት በስቲያ ሀሙስ ብቻ በአለም ዙሪያ የተመዘገበው የአዲስ የቫይረሱ ተያዦች አሀዝ ከአንድ መቶ ሀምሳ ሽህ በላይ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ቴድሮስ ይህም ኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከጀመረበት ከታህሳስ ወር ወዲህ በአንድ ቀን ከተገኙት ሁሉ ትልቁ መሆኑን አሳስበዋል
https://amharic.voanews.com//a/covid-world/5470721.html
123
21,747
ቆዳ ፋብሪካዎች ለውጭ ኩባንያዎች የተሰጠውን ዓይነት ማበረታቻና ድጋፍ ባለማግኘታቸው ከአምራችነት እየወጡ እንደሚገኙ ገለጹ
ቢዝነስ
5 May 2019
Unknown
በከፊል የተዘጋጀ ቆዳ ወደ ውጭ እንዳይላክ ተጥሎ የቆየው እገዳ ለከፋ ጉዳት አጋልጦናል አሏገር በቀል የቆዳ ፋብሪካዎች ከመንግስት ተገቢውን ድጋፍና ማበረታቻ ሊያገኙ ካለመቻላቸውም በላይ የውጭ ባለሀብቶችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርግ አሰራር በመስፈኑ ህልውናቸው አደጋ ላይ መውደቁንና በርካቶችም ከኢንዱስትሪው ለመውጣት መገደዳቸውን አስታወቁ ከ12 ያላነሱ ቆዳ ፋብሪካዎች በአቅም እጦትና በእዳ መዘጋታቸው ተነግሯል አርብ ሚያዝያ 25 ቀን 2011 አም የቆዳ ኢንዱስትሪውን የሚመለከት ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን በማስመልከት የፍኖታ ካርታው ጥቅል ሰነድ ለውውይት በቀረበበት ወቅት የቆዳ ኢንዱስትሪው ተዋናዮች አበክረው እንደተቹት መንግስት ለውጭ ኩባንያዎች ትኩረት ከመስጠት አልፎ የአገር ውስጥ ፋብሪካዎችን ህልውና የሚፈታተን ፖሊሲ ተግባራዊ ሲያደርግ በመቆየቱ ሳቢያ ዘርፉ ቁልቁል ለመውረድ ተገዷል  መንግስት ተግባራዊ ሲያደርገው የቆየው ፖሊሲ ከስድስት አመታት በላይ የሆነውና እሴት የተጨመረበት ብሎም ያለቀለት ቆዳ ወደ ውጭ እንዲላክ የሚያስገድድ ነው ይህ ፖሊሲ በከፊል ያለቀለትና ከጥሬ ቆዳ ደረጃ ጥቂት ማሻሻያ የተደረገበት ምርት ወደ ውጭ እንዳይላክ ለማገድ የ150 በመቶ የወጪ ንግድ ታክስ ማወጁ ኢንዱስትሪውን በተለይም የአገር ውስጥ ፋብሪካዎችን ለአደጋ እንዳጋለጣቸው ሲገልፁ ተደምጠዋል በውይይቱ ወቅት ጎልተው ከተደመጡ ትችቶች መካከል የአገር ውስጥ ባለሀብት ድጋፍም ሆነ ማበረታቻ ከመንግስት ማግኘት አልቻለም የሚለው ይገኝበታል የዋልያ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ አለማየሁና የህንድ ፋሪድ ቆዳ ፋብሪካ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ኢዝራር አህመድ ለአገር ውስጥ ባለሀብቱ ቅድሚያ አለመስጠት ኢንዱስትሪውን ይበልጥ እንደጎዳው ገልፀዋል አቶ ያሬድ እንደሚሉት የአገር ውስጥ ባለሀብት ያገለገለ ማሽን ወደ አገር ውስጥ ማስገባት እየተከለከለ የውጭ ፋብሪካዎች ግን ይህ እየተፈቀደላቸው የስራ ማስኬጃ 30 በመቶ ያህል የገንዘብ ድጎማ እየተሰጣቸውና ወደ ውጭ እንዳይላክ የተከለከለ ከፊል ጥሬ ቆዳ ሲልኩ እጅ ከፍንጅ የተያዙ በመንግስት ጣልቃ ገብነት እየተለቀቁ የአገር ውስጥ ባለሀብቱ ግን ተገፍቶ እንዲወጣ እየተደረገ ነው ሚስተር ኢዝራር አህመድ በበኩላቸው የአገር ውስጥ ባለሀብቱ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ያሳሰቡት የአገራቸውን ተሞክሮ በማውሳት ነው የህንድ ባለሀብቶች በአገራቸው የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ ለሚያከናውኑት ኢንቨስትመንት በመንግስት ድጎማ ይደረግላቸዋል ብለው ለስራ ማስኬጃና ለዘመናዊ አሰራር በሚል እስከ 30 በመቶ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ በመንግስት እንደሚደረግላቸው ገልፀዋል ይህ ሁሉ በሆነበት አግባብ መንግስት በከፊል ያለቀለትና የተለፋ ጥሬ ቆዳ ወደ ውጭ እንዳይላክ ያወጣው የታክስ ክልከላ ቆዳ ፋብሪካዎችንና ቆዳና ሌጦ ነጋዴዎችን ክፉኛ መጉዳቱም በስፋት ተወስቷል ይህ ክልከላ የወጣው ያለቀለት ቆዳ ወደ ውጭ እንዲላክ ብሎም ቆዳ ፋብሪካዎች እሴት የታከለበት ምርት ወደ ውጭ መላክ ስራ ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ ቢሆንም ይህ ፖሊሲ ግን ያለጊዜው ተግባራዊ የተደረገና የኢትዮጵያ ፋብሪካዎችን ደረጃና አቅም ያላገናዘበ በመሆኑ በርካቶችን ከጨዋታ ውጪ በማድረጉ ወቀሳ ቀርቦበታል ፖሊሲው ከመውጣቱ ከስድስት አመታት በፊት የቆዳ ኢንዱስትሪው ከ200 እስከ 300 ሚሊዮን ዶላር ያስገኝ እንደነበር እያጣቀሱ ትችት ያቀረቡት የቆዳ ኢንዱስትሪው ተዋናዮች በአሁኑ ወቅት ከ70 ሚሊዮን ዶላር በታች እያስገኘ እንደሚገኝና ለዚህም የተዳከመ ውጤት ዋናው ተጠያቂ መንግስት ነው ተብሏል በፍኖተ ካርታው ጥቅል ሰነድ ውስጥ የሰፈሩ አሀዞች እንደሚያሳዩትም በአሁኑ ወቅት ከ26 በላይ የቆዳ ፋብሪካዎች ቢኖሩም 10 የውጭ ናቸው እየተገኘ ያለው የውጭ ምንዛሪ ግን ከ696 ሚሊዮን ዶላር ያልበለጠ ነው እነዚህ የቆዳ ፋብሪካዎች ከ120 ሚሊዮን እስከ 135 ሚሊዮን ካሬ ጫማ ቆዳ የማምረት አቅም ቢኖራቸውም ለውጭ ገበያ እየቀረበ የሚገኘው ግን ከ60 ሚሊዮን ካሬ ጫማ ያልበለጠ ያለቀለት ቆዳ ብቻ ነው ተብሏል በሌላ በኩል 16 የአገር ውስጥና ሶስት የውጭ ጫማ አምራቾች ሲኖሩ አጠቃላይ የማምረት አቅማቸው ከ33 ሚሊዮን ጥንድ ጫማ በላይ ሲሆን የሚያስገኙት ገቢም ከ386 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ የቻይናው ኋጂዬን ፋብሪካ ከ60 በመቶ በላይ ድርሻውን ይይዛል ገቢ እንደሆነ ይነገራል በተጨማሪም 15 ሚሊዮን ጥንድ የእጅ ጓንት ማምረት የሚችሉ ሶስት የውጭ ፋብሪካዎች አምስት ሚሊዮን ዶላር ማስገኘት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው ታውቋል የቆዳ ውጤቶችና አልባሳትን የሚያመርቱ 30 ፋብሪካዎች ሲኖሩ 19 ያህሉ ወደ ውጭ ምርት የሚልኩ ናቸው  ተብሏል እነዚህ ሁሉ ባሉበት የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ ለአመታት ለውጭ ኩባንያዎች ያደላ ፖሊሲና የኢንቨስትመንት ድጋፍ መደረጉ አድሏዊ ነው በማለት ቅሬታቸውን ያሰሙት ፋብሪካዎች በሌላ ጎኑ በአካባቢ ብክለትና በጥሬ ቆዳ ዋጋ ላይ በሚከተሉት አሰራር ወቀሳ ሲቀርብባቸው ቆይተዋል በአሁኑ ወቅት ሰባት የቆዳ ፋብሪካዎች የመጀመርያ ደረጃ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ መትከል ባለመቻላቸው ከተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ በኋላ መታሸጋቸው ይታወሳል ከዚህ በተጨማሪ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ነጋዴዎችም ለቆዳ ፋብሪካዎች የሚያቀርቡት ጥሬ ቆዳ ተቀባይነት እያጣ ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆነው ምርት እየተጣለ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ቆዳና ሌጦ ነጋዴዎች ማሀበር ፕሬዚዳንት አቶ ብርሀኑ አባተ አስታውቀዋል ፋብሪካዎቹ አቅም ከማጣቸው በተጨማሪ ለቀረበላቸው ቆዳ በወቅቱ ክፍያ እንደማይፈፅሙ በዱቤ ወስደውም ለወራት ሳይከፍሉ እንደሚያቆዩና ከገበያ በእጅጉ በወረደ ዋጋ እንዲቀርብላቸው እየጠየቁ አብዛኛውን ነጋዴ ለኪሳራ በመዳረግ ከስራ እንዲወጣ ሰበብ እንደሆኑት ገልፀዋል የኢትዮጵያ ቆዳና ሌጦ በውጭ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ ነው ቢባልም በአገር ውስጥ ግን ገዥ ማጣቱ እርስ በርሱ ይጋጫል ያሉት አቶ ብርሀኑ ክልከላ የተደረገበት ቆዳው ዋጋ ስለሌለው ነው ወይ የሚል ጥያቄም አቅርበዋል ይሁንና ከሰሞኑ በከፊል የዘተጋጀ ወይም ክረስት የተሰኘው ቆዳና ሌጦ በአገር ውስጥ ባለሀብቶች ብቻ ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መፈቀዱን መዘገባችን ይታወሳል አቶ ብርሀኑ ግን ያልተቀለመ ወይም ከጥሬ ቆዳ በመጠኑ የተዘጋጀና የተለፋ ቆዳ ዌትብሉና ፒክል የተሰኙት የቆዳና ሌጦ ምርቶች ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መፈቀድ እንዳለበት ይሞግታሉ ይህ የቆዳ ምርትም በየፈርጁ የ150 በመቶ ታክስ ተጥሎበታል    ሆኖም እንደ አቶ አምዴ አካለ ወርቅ ያሉና በዘርፉ ከ50 አመታት በላይ የካበተ ልምድ ያላቸው ባለሀብቶችና የዘርፉ ተዋንያን ግን በአቶ ብርሀኑ ሀሳብ አይስማሙም ዌትብሉና ፒክል የተሰኙት የቆዳና ሌጦ ምርቶች ለአገር ውስጥ ፍጆታ ብቻ መዋል እንደሚገባቸው ይሞግታሉ
https://www.ethiopianreporter.com/article/15535
732
13,250
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ
ሀገር አቀፍ ዜና
Dec 21, 2020
190
አዲስ አበባ ታህሳስ 12 2013 ኤፍ ቢ ሲ የማእድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመስምምነቱን የተፈራረሙት የማእድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ናቸውስምምነቱ ከኢትዮጵያ ማእድን ሀብትና ከዘርፉ ጋር የተጣጣሙ እንዲሁም በማእድን ዘርፍ በከፍተኛነት የተለዩ የእውቀት ዘርፎችን በመለየት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኩል ስርአተ ትምህርት እንዲዘጋጅላቸው እና ለባለሙያዎች እንዲሰጡ የሚያስችል ነው ተብሏልበማእድንና ነዳጅ ዘርፍ ዙሪያ በቀጣይነትም ፍላጎትን መሰረት ባደረገ መልኩ ተጨማሪ አዳዲስ የትምህርት ዘርፎችን በማዘጋጀት መደበኛ ትምህርት እና አጫጭር ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ነው የተገለፀውየማእድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የታደለች ብትሆንም በሀብት ላይ መቀመጥ ለብቻው ሀብታም አያደርግም ብለዋልሚኒስትሩ ከምድር በታች ያሉ ሀብቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ እና የባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት ያለውን ሀብት በአግባቡ መጠቀም መጀመር ይገባልም ነው ያሉትባለሙያዎች የትምህርት እድል ማግኘት በሚችሉበት መንገድ ዙሪያ የተደረገው ስምምነትም የዚሁ አንድ አካል መሆኑን ኢንጂነር ታከለ በመድረኩ መናገራቸውን ከማእድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታልከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘትየፋና ድረ ገፅ httpswwwfanabccom ይጎብኙተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል httpswwwyoutubecomcfanabroadcastingcorporate ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል httpstmefanatelevision ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን httpstwittercomfanatelevision ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%8b%95%e1%8b%b5%e1%8a%95%e1%8a%93-%e1%8a%90%e1%8b%b3%e1%8c%85-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b4%e1%88%ad-%e1%8a%a8%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3/
179
50,482
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሪ በድጋሚ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 30, 2020
Unknown
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሪ በድጋሚ መጀመሩን የብሄራዊ ባንክ አስታወቀየብር ቅያሪው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2013 አም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንደሚከናወን ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%89%b0%e1%89%8b%e1%88%ad%e1%8c%a6-%e1%8b%a8%e1%8a%90%e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%ae%e1%8c%8c/
32
8,249
የምንይሹ ክፍሌ ‹ዳዴ› አልበም ዓለም ዐቀፍ ስኬት
መዝናኛ
2021-01-04
557
በአገር ውስጥ አድማጮች ዘንድ ወሰንኩ እና ቡና በሚሉ ሙዚቃዎቿ ትታወቃለች በቀደመው ጊዜም በብሄራዊ ትያትር ተወዛዋዥነቷ ከእነ ኩሪባቸው ወልደማሪያም ኩሪ እና እንዬ ታከለ ጋር በነበራት ጥምረት ብዙዎች ያስታውሷታል ተወዛዥ ተዋናይት እና ድምፃዊት ምንይሹ ክፍሌ ግን አለም አቀፍ እውቅናዋ ከዚህ በእጅጉ ላቅ ይላል በቅርቡ ለአለም አቀፍ አድማጮቿ ያደረሰችው የተሰኘ አልበሟ ትራንስ ግሎባል በተሰኘ አለም አቀፍ የሙዚቃ ደረጃ ሰንጠረዥ የሀዳር ወር ደረጃ ከታዋቂዋ ደቡብ አፍሪካዊት አርቲስት አንጀሊክ ኪጆ በመብለጥ ስደስተኛ ደረጃን አግኝቷል ምንይሹ የተወለደችው በድሬዳዋ ከተማ ቢሆንም እድገቷ ግን በመዲናይቱ አዲስ አበባ ነበር በ17 አመቷ ብሄራዊ ትያትርን የተቀላቀለችው ምንይሹ 35 አገራትን ባዳራሰው እና አራት ወር በፈጀው የህዝብ ለህዝብ አለም አቀፍ የሙዚቃ ጉዞ ውስጥ ከተካተቱ አርቲስቶች መካከል ነበረች በዚህም ከእነ ሙላቱ አስታጥቄ መሀሙድ አህመድ ጥላሁን ገሰሰ እና ብዙነሽ በቀለ ጋር የመስራት እድል ገጥሟታል አገር ውስጥ እያለች ሰናይት በተሰኘ ፊልም ላይ መሪ ተዋናይ ሆና ተውና የምታውቀው ምንይሹ እአአ በ1996 ወደ አውሮፓ ተጉዛለች በአውሮፓ ቆይታዋ ሳን ግራትስማ ከተባለ የሙዚቃ ማነጀር እና አዘጋጅ ጋር ሞዛይክ ቪቫንት በተባለ የሙዚቃ አቅራቢ ጋር መስራት ችላለች እአአ 19971999 ከሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አርቲስቶች ጋር በመሆን አፍሪካ ዩናይት የተሰኘ ተካታታይ የሙዚቃ ድግሶችን ያቀረበች ሲሆን የመድረክ ሙዚቃዎቹ በሲዲ ተለቀው ነበር ምንይሹ እአአ 2002 መባ የተሰኘ አልበም የሰራች ሲሆን ይህም አልበም በኔዘርላንድ ቤልጂየም እና ጀርመን ከፍተኛ ተቀባይነትን አስገኝቶላታል ድሬ ዳዋ የተሰኘውን ሁለተኛ አልበሟን ሚ ኤንድ ማይ ሪከርድስ ከተሰኘ የሙዚቃ አቅራቢ ጋር የሰራች ሲሆን ይህም በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የሙዚቃ ዝግጅቶን እንድታቀርብ በሮችን ከፍቶላታል በአፍሪካ ውስጥም በሁለተኛው የፓን አፍሪካን ፌስቲቫል እና አለም አቀፉ የጥቁር ጥበብ ፌስቲቫል ላይ ሳሊፍ ኬታን ጨምሮ አንጀሊክ ኪጆ ዮሱ ዱር እና ባባ ማል ከተሰኙ ታዋቂ የአፍሪካ አርቲቶች ጋር ከውናለች ከዚህም ባለፈ አንጋፋ ከሆኑ አውሮፓዊ ባንዶች እና አርቲስቶች ጋር ተጣምራ የሙዚቃ ዝግጅቶችን አቅርባለች ጥቁር ቀለም የተሰኘው ሶስተኛ አልበሟን በ2013 መልቀቋ ይታወሳል መድረክ ላይ በምታሳያቸው እንቅስቃሴዎች ማራኪነት የምትታወቀው ምንይሹ ለዚህ ችሎታዋ በብሄራዊ ትያትር በምትሰራበት ወቅት ከእነ ታደሰ ወርቁ ጌታቸው አብዲ አለምፀሀይ ወዳጆ እና ከሌሎችም ያገኘችው ልምድ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳደረገላት ትናገራለች ነዋሪነቷን ባደረገችበት በኔዘርላንድስ ውስጥም የኢትዮጵያን ባህላዊ ጭፈራዎች ለዜጎቹ የምታስተምር ሲሆን በኬሪዮግራፈርነትም ጥቂት የማይባሉ መድረኮችን አሰናድታለች እአአ ጥቅምት 26 2018 የለቀቀችው ዳዴ የተሰኘ አራተኛ አልበሟን አርክ ሚውዚክ ከተባለ ድርጅት ጋር የሰራች ሲሆን በውስጡም 13 ዘፈኖች ተካተውበታል አልበሙ ዳልቶን በተባለ ስቱዲዮ ኤንዶቨን ኔዘርላንድስ ውስጥ የተቀረፀ ሲሆን በትዝታ ስልት የተዜመው የአልበሙ መጠሪያ የሆነው ዳዴ ጨምሮ ይቅርታ የታል አንተነህ ሀይሎጋ ወላይታ እና ገለቱማ የተሰኙ የኢትዮጵያን ቅኝቶ ከዘመናዊ ስልቶችና መሳሪያዎች ጋር በማዋሀድ የተሰሩ ሙዚቃዎችም ተካተዋል አልበሙ በተለቀቀበት የመጀመሪያ ወር በትራንስ ግሎባል የሙዚቃ ሰንጠረዥ ሰባተኛ ደረጃን ያገኘ ሲሆን በሀዳር ወር ደግሞ ስድስተኛ ደረጃን ተቀዳጅቶ ቆይቷል ትራንስ ግሎባ ባወጣው የ2018 ምርጥ መቶ አልበሞች ዝርዝር ውስጥም የምንይሹ ዳዴ አልበም 40ኛ ደረጃን አግኝቷል ቅፅ 1 ቁጥር 5 ታሀሳስ 6 ቀን 2011
https://addismaleda.com/archives/2365
407
38,215
አማራ ክልል ውስጥ በተከሰተው የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ድጋፍ ተጠየቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 11, 2021
Unknown
አማራ ክልል ውስጥ በተከሰተው የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ከሶስት ሚልየን በላይ ሰው የእለት ምግብ እንደሚያስፈልገው የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ የዋስትና ማስተባበሪያ ፕሮግራምና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽን አስታውቋልድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በተካሄዱባቸው የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ከቤንሻንጉል እና ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ችግር ላይ የወደቁ ዜጎች መሆናቸውን ኮሚሽኑ ገልጿልበእርዳታ አሰጣጡ ላይ አሉ የተባሉ ችግሮችን ለማስወገድ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማእከል ቻግኒ ላይ መቋቋሙን ኮሚሽኑ አስታውቆ በመሆኑም እርዳታ ማድረስ የሚፈልጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ወደ ማእከሉ ገቢ እንዲያደርጉ አሳስቧል
https://amharic.voanews.com//a/Amhara-emergency-1-11-2020/5733184.html
79
23,707
በሰሜን ጎንደር ዞን በዓመት ውስጥ 597 ታጣቂዎች መገደላቸው ተገለጸ
ፖለቲካ
10 September 2017
Unknown
በአማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ዞን በ2009 አም ጫካ ገብተው ከነበሩ የታጠቁ ሀይሎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 597 ሰዎች መገደላቸው ተገለፀየዞኑ አስተዳደርና ፀጥታ መምርያ ሀላፊ አቶ ዳኘው በለጠ ለሪፖርተር እንደተናገሩት ኤርትራ በመሄድ ከግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር ጋር ተቀላቅለው በመሰልጠን በዞኑ ህዝብ ላይ ከፍተኛ እንግልት ሲያደርሱና ግፍ ሲፈፅሙ የነበሩ በአጠቃላይ 708 ታጣቂዎች ናቸው ከእነዚህ መካከልም 111 በህይወት መያዛቸውን ተናግረዋልበአሁኑ ወቅት የዞኑ ፀጥታ በአንፃራዊነት ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የገለፁት የመምርያው ሀላፊ የሻእቢያ መንግስት እነዚህን ሀይሎች በገንዘብና በሎጂስቲክስ እገዛ ያደርግላቸው እንደነበር ተናግረዋል እነዚህ የታጠቁ ሀይሎች በህዝቡ ውስጥ ሰፊ የሆነ ግፍ ሲፈፅሙ የነበሩና ህፃናትንና ከብቶችን በመዝረፍ ሰቆቃ ሲያደርሱ የነበሩ ናቸው ብለዋልአሁንም ቢሆን ከኤርትራ ሰልጥነው የመጡና በየቦታው እየተንቀሳቀሱ በህዝቡና በመንግስት ንብረት ላይ ጉዳት ለማድረስ ያለሙ ሰባት ግለሰቦች እንዳሉ ጠቁመዋል በቀላል ወንጀል የታሰሩና ሰው ገድለው የሸሹ 23 ያህል ሽፍቶች በዞኑ ውስጥ ባሉ ጫካዎችና በሱዳን ድንበር አካባቢ እንዳሉም አስረድተዋል የዞኑ የፀጥታ ሀይልና አስተዳደር በ2010 አም መስከረም ወር እነዚህን ሀይሎች ለማጥፋት አቅዶ እየሰራ እንደሆነም አቶ ዳኘው ተናግረዋል እስካሁን በተደረገው ዘመቻም ከ500 በላይ የጦር መሳሪያዎች መማረክ ተችሏል ብለዋልበሰሜን ዞን የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቅማንት ህዝብ አንስቶት የነበረውን የማንነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል በ12 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወሳል ከዚህ ጋር በተያያዘ በጭልጋ ወረዳ ያሉ አራት ቀበሌዎች በህዝበ ውሳኔው ላይ ቅሬታ ማንሳታቸውን አቶ ዳኘው ገልፀዋል እንደ አቶ ዳኘው ገለፃ ጭልጋ ወረዳ ህዝበ ውሳኔው ከሚካሄድባቸው 12 ቀበሌዎች መካከል ስድስቱ የሚገኙበት ሲሆን ከእነዚህ መካከል አራቱ ማለትም ገለድባ አንከራደዛ ሹምየና አውርደርዳ ቀበሌዎች ውስጥ ከነዋሪዎች ቅሬታ ቀርቧልበእነዚህ ቀበሌዎች የሚኖረው ህዝብ ዋነኛ ጥያቄም ቅማንቶች ከ20 በመቶ በታች ሆነውና በቁጥር ደረጃ እኛ አማራዎች በልጠን ሳለ ህዝበ ውሳኔው ለምን አስፈለገ የሚል ነው ብለዋልመንግስት ለቅሬታው በሰጠው ምላሽ እንደተባለው የአማራዎች ቁጥር የሚበልጥ ከሆነ በድምፅ መስጠት ሂደት የሚረጋገጥ እንደሚሆን መጭበርበር እንዳይኖር ተብሎም ታዛቢዎች የሚመጡት ከሌላ ክልል እንደሆነም እንደተገለፀ ጠቅሰዋል እንደ አቶ ዳኘው ማብራርያ ህዝበ ውሳኔ ከሚካሄድባቸው 12 ቀበሌዎች መካከል ሁለቱ ጎንደር ከተማ ውስጥ ሲገኙ አራቱ ደግሞ መተማ ውስጥ የሚገኙ ቀበሌዎች ናቸውየቅማንትና የአማራ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ከተነሳባቸው መካከል በ12 ቀበሌዎች ላይ ህዝበ ውሳኔውን መስከረም 7 ቀን 2009 አም ለማድረግ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መወሰኑ ይታወሳል
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%89%A0%E1%88%B0%E1%88%9C%E1%8A%95-%E1%8C%8E%E1%8A%95%E1%8B%B0%E1%88%AD-%E1%8B%9E%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%8B%93%E1%88%98%E1%89%B5-%E1%8B%8D%E1%88%B5%E1%8C%A5-597-%E1%89%B3%E1%8C%A3%E1%89%82%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%88%98%E1%8C%88%E1%8B%B0%E1%88%8B%E1%89%B8%E1%8B%8D-%E1%89%B0%E1%8C%88%E1%88%88%E1%8C%B8
312
9,858
በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የፖለቲካ አቋም የያዙባቸውን ጉዳዮች ገለጹ፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
September 23, 2020
168
በአማራና ኦሮሚያ ክልል በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ ፖለቲካዊ አቋሞቻቸውን ገለፁ ፓርቲዎቹ የጋራ የፖለቲካ አቋሞች ስምምነት መግለጫ በጋራ ሰጥተዋልመግለጫውን የሰጡት የፖለቲካ ፓርቲዎችም የመላ አማራ ህዝብ ፓርቲ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርየአማራ ህልዉና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት የኦሮሞ ብሄራዊ ፓርቲ መላዉ አማራ ህዝብ ድርጅት ብልፅግና ፓርቲ የተባበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ነፀብራቅ አማራ ድርጅት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ ናቸውየጋራ የፖለቲካ አቋሞቹም1 የሀገሪቱ የጋራ ችግሮችን ለመፍታት ቀጣይ ዉይይቶች አስፈላጊ መሆናው2 ከጥርጣሬ ከመቃረን ከመገፋፋት ስም ከመጠፋፋት ህዝብ ለህዝብ ከሚያቃርኑ ድርጊቶች መቆጠብ3 የሁሉም የሀገሪቱ ብሄር ብሀረሰቦች የህዝብ ብዛት በትክክል እንዲቆጠር4 በሀገሪቱ ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ እንዲደረግ
https://www.amharaweb.com/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%88%9b%e1%88%ab%e1%8a%93-%e1%8a%a6%e1%88%ae%e1%88%9a%e1%8b%ab-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8a%95%e1%89%80%e1%88%b3%e1%89%80%e1%88%b1-%e1%8b%a8%e1%8d%96/
95
25,650
የቀድሞ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት በማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ተከሰሱ
ሀገር አቀፍ ዜና
4 November 2015
Unknown
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማሀበር ፕሬዚዳንት የነበሩት ሊቀ ትጉሀን አስታጥቄ አባተ በማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሰረተባቸውክሱ ቀደም ብሎ በ1998 አም ተመስርቶባቸው የነበረ ቢሆንም እንዲቋረጥ ተደርጎ ከቆየ በኋላ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በነበሩት አቶ ልኡል ወልዱ አሁን የትግራይ  ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል ትእዛዝ ተቋርጦ የነበረው ክሱ እንዲቀጥል ተደርጓልተከሳሹ የተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል አርበኛ ሳይሆኑ አርበኛ ነኝ በማለት የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የተሳሳተ መረጃና ማስረጃ አቅርበዋል የሚል መሆኑን የአቃቤ ህግ ክስ ይገልፃልተከሳሹ በ1938 አም ቢወለዱም በ1922 አም እንደተወለዱ ጣሊያን ከ1928 አም እስከ 1933 አም ድረስ ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ መሳተፋቸውንና አርበኛ ነኝ ማለታቸውን ክሱ ይገልፃልሊቀ ትጉሀን አስታጥቄ አርበኛ ሳይሆኑ እንደሆኑ በመግለፅና አሳሳች ነገሮችን በመናገር የራሳቸውን ማንነት መደበቃቸውን የሚገልፀው የአቃቤ ህግ ክስ በ1937 አም በወጣው አዋጅ ቁጥር 41937 አንቀፅ 33 ላይ በተደነገገው መሰረት አርበኝነታቸውን እንዳስመሰከሩ መናገራቸውንም ክሱ ያስረዳል በመሆኑም ከግንቦት 25 ቀን 1993 አም እስከ 1994 አም ድረስ የኢትዮጵያ አርበኞች ማሀበር ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን የአንድ ሺህ ብር ደመወዝተኛ ሆነው መስራታቸውን ክሱ ይጠቁማል ከ1998 አም ጀምሮ ደግሞ ፕሬዚዳንት በመሆን 4000 ብር ደመወዝና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን እያገኙ በመሆኑ በፈፀሙት የማታለል ወንጀል መከሰሳቸውን የአቃቤ ህግ ክስ ያስረዳል ሀዳር 2 ቀን 2008 አም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መጥሪያ እንደተላከላቸውም ለማወቅ ተችሏል
https://www.ethiopianreporter.com/article/9286
182
43,231
ዶክተር ወርቅነህ ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
August 15, 2018
Unknown
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር ተወያዩዶክተር  ወርቅነህ በጂቡቲ ከፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያና ጂቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት በሁኔታዎችና በአጋጣሚ የማይለወጥ መሆኑን አስምረውበታልየሁለቱ አገሮች ወዳጅነት ስትራቴጂካዊ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋልበጂቡቲ የሚኖሩ የተወሰኑ ኢትዮጵያዊያን በፀጥታ ስጋት ምክንያት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ያነሱት ዶክተር ወርቅነህ  ኢትዮጵያዊያን ጂቡቲን ሁለተኛ አገራቸው አድርገው የሚቆጥሩ በመሆኑ ያለ ስጋት እንዲኖሩ የጂቡቲ መንግስት አስፈላጊውን እንዲያደርግ ጠይቀዋልፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ በበኩላቸው ኢትዮጵያዊያን በጂቡቲ ውስጥ ያለ ምንም ችግር መኖር እንደሚችሉና መንግስታቸውም ይህን ለማድረግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋልአገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ሁለንተናዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር ፍላጎት እንዳላት ለዚህም እውን መሆን እንደወትሮው ሁሉ አሁንም እንደምትሰራ ተናግረዋልሁለቱ ህዝቦች በደምና በታሪክ ተሳስረው አብረው የሚኖሩ በመሆናቸው ይህ አይነት ክስተት ግንኙነታቸውን እንደማይገልፅና እንደማያበላሽ አረጋግጠዋልየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ቀደም ሲል ከጂቡቲ አቻቸው መሀመድ አሊ ዩሱፍ ጋር በሁለትዮሽና አካባቢ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም ከፅህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ኢዜአ 
https://waltainfo.com/am/30242/
144
8,833
ለአንድ አመት ያህል የቆየው የፍርድ ቤት ሂደት በፈረንጆቹ የሚመጣው ሃምሌ 19 ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶበታል
ፖለቲካ
2021/1/22 20:40 GMT
Unknown
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ስልጣንን አላግባብ በመጠቀምና ከባለሀብቶች ስጦታዎችን በመቀበል በሚሉ ክሶች ከተከሰሱ ቆይተዋል ይሁንና ረጅም ጊዜ የወሰደው የፍርድ ሂደት አሁንም አልተቋጨም ረጅም አመታትን እስራኤልን የመሩት ቢኒያሚን ኔታንያሁ ቢቢ በሀገራቸው ዜጎች እንደ ጀግና ሲወደሱ በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ሙሰኛ ይተቻሏወዛጋቢዋ የእየሩሳሌም ከተማ የእስራኤል መዲና እንድትሆን የእስራኤል ተፅእኖም ጎልቶ እንዲታይ አድርገዋል የሚሉ በአንድ ወገን የለም ሙስና ይሰራሉ ቅንጡ የሚባሉ ስጦታዎችን ሳይቀር ከባለሀብቶች ይቀበላ የሚሉ ደግሞ በሌላ ጎን ቢቢ እየተባሉ የሚቆላመጡትን የሊኩይድ ፓርቲ መሪን ይተቻሉ የማይካድ ሀቅ ግን አለ የሚሉት ተንታኞች አሜሪካ ኢምባሲዋን ከቴላቪቭ ወደ እየሩሳአሌም የቀየረችውም በቢቢ ዘመን አንደሆነም ይነሳል ያም ሆነ ይህ የእስራኤል ዳኞች ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያን ኔታንያን መጥሪያ ልከው ፍርድ ቤት አቁመዋል በርካቶች በጎዳና ላይ ሲደግፏቸውም ሲነቅፏቸውም ታተዋል ደጋፊዎቻቸው ቢቢ የእስራኤል ንጉስ ብቻዎትን አይጓዙም ሲሏቸው ነቃፊዎቻቸው ደግሞ የወንጀል ሚኒስትር እያሉ ተቃውመዋቸዋል ትናንት ፍርድ ቤት ሄደው ቃላቸውን የሰጡት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ በሀላፊነት ላይ ያሉ ፍርድ ቤት የቀረቡ የመጀመሪያው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው  አሜሪካዊው የህግ ባለሙያ አላን ደርሾዊትዝ በእየሩሳሌም ፖስት ላይ ባሰፈረው ፁሁፍ እስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትሯን ፍርድ ቤት በማቆሟ ልታፍር ይገባል ሲል አስፍሯል እርሱ እንዳለው ይህ ነገር የተደረገው ለተለየ የሚዲያ ሽፋን ሲባል እደሆነም ነው በፃፈው ፁሁፍ ላይ የገለፀው በሀገራቸው ዳኞች ፊት ቀርበውም ቃላቸውን ሰጥተዋል እርሳቸውም ምንም በወንጀል የሚያስጠይቅ ስራ አልሰራሁም ነፃ ነኝ ሲሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል ባጠለቋት ጭምብል ውስጥ ሆነው ምላሽ ሰጥተዋል ለሚቀጥሉት 18 ወራት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን የሚያገለግሉት ቢቢ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ከተቀናቃኛቸው ጋንዝ ጋር ስምምነት ካደረጉ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚቀጥሉ ቢያረጋግጡም የፍርድ ቤት ጉዳያቸው ግን አሁንም አልለቀቃቸውም ለአንድ አመት ያህል የቆየው የፍርድ ቤት ውሎ በፈረንጆቹ ለፊታችን ሀምሌ 19 ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶታል የእስራኤል የህግ ተንታኞች ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍርድ ቤት ጉዳይ ወራትን አሊያም አመታትን ሊወስድ እንደሚችል ገምተዋል ችሎቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መከላከያ ጭምብል እንዲያወልቁና በቴሌቪዥን ሁኔታውን እንዲያብራሩ ጠይቀው ነበር ከዚህ በተጨማሪም የፍርድ ቤቱ ውሎ በጣም ጠበቅ ያለ እንደነበር ገልፀው እዚህ ፍርድ ቤት የቆምኩት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኘ ነው ማታቸውም ተዘግቧል ኔታንያሁ ከ18 ወራት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ለተቀናቃኛቸው ጋንዝ ለማስረከብ የተስማሙ ሲሆን ሀገራቸው ከ10 አመታት በላይ መርተዋል
https://am.al-ain.com/article/pm-netanyahu-of-israel-appears-before-court-after-he-was-indicted-of-corruption
318
8,288
“ወቶ አደር” የሚለው ፈልም ለዕይታ ቀረበ
መዝናኛ
2021-01-04
1998
የአንተነህ ሀይሌ ፊልም የሆነው ወቶ አደር የተሰኘው ፊልም ከየካቲት 8 እስከ 10 ድረስ በሁለም ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል አንድ ሰአት ከአርባ ሁለት ደቂቃ የሚረዝመው ይህ ፊልም ወቅታዊ እና ሀገራዊ ሀሳቦችን በቀልድ እያዋዛ የሚነግረን ፊልም ሲሆን ፊልሙን አጠናቆ ለመጨረሰ 3 ወር ግዜ ወስዶበታልፊልም አጠናቆ ለእታ ለማቅረብ የወጣው ገንዘብ ባት በቶ ሀምሳ ሺህ ብር ሲሆን ከ ሀምሳ በላ አንጋፋና ወጣት ተዋንያንን አሳትፏልከነዚ መካከል ታሪኩ ብርሀኑ ማሀሌት ሰለሞን እና ሰላም አሻግሬ ተሳትፈውበታልየአንተነህ ሀይሌ አምስተኛ ፊልም የሆነው ወቶአደር በ16 ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በተስፋሁን ታደሰ የቀረበ ኮሜዲ ድራማ ፊልም ነውቅፅ 1 ቁጥር 14 የካቲት 9 ቀን 2011
https://addismaleda.com/archives/3402
91
1,917
የ‹‹ኢፍሚስ›› ሥርዓት ችግር እንደታየበት የፌዴራል ዋና ኦዲተር አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
May 31, 2020
83
አዲስ አበባ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርአት ኢፍሚስ በራሱ ስርአቱ ችግር ያለበት እና ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግም የብቁ ባለሙያዎች ባለመኖራቸው በአሰራር ላይ ችግር እንደታየበት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አስታወቀ ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት መስሪያ ቤታቸው የ2011 አም የፌዴራል ተቋማት የኦዲት ስራ ከባለፉት 11 አመታት በተለየ መልኩ ተንጠባጥቦ ተጠናቋል ለዚህም ዋናው ምክንያት በፌዴራል ተቋማት ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የኢፍሚስ ስርአት አንዱ መሆኑን አንስተዋል ዋና ኦዲተሩ እንደተናገሩት ተቋማቱ ወደ ኢፍሚስ ስርአት የገቡት በአመቱ መጀመሪያ ላይ ስላልሆነ በፊት የነበረውንና አዲስ ተግባራዊ የሚደረገውን ስርአት ለማጣጣም ተቸግረዋል ተግባራዊ ለሚደረገው ስርአትም ባለሙያዎች በቂ እውቀት ሳያዳብሩ ወደ ትግበራ ስለገቡ ስራውን ለመስራት ተቸግረዋልባለሙያዎቹ በትክክል የመዘገቡትንና ያልመዘገቡትን መለየትና ለችግሩም ማስተካከያ ማድረግ አልቻሉምችግሩን የሚያስተካክሉት የገንዘብ ሚኒስቴር ባለሙያዎች ሲሆን ሚኒስቴሩ ለፌዴራል ተቋማት ሁሉ በአንድ ጊዜ ድጋፍ የሚሰጥ የሰው ሀይል አልፈጠረም ይህም በአሰራር ላይ ክፍተት ፈጥሯል ዋና ኦዲተር መስራት የሚገባውን የኦዲት ስራ ቢያከናውንም የፌዴራል አንዳንድ ተቋማት ከኢፍሚስ ጋር በተያያዘ ማቅረብ የሚገባቸውን የሂሳብ ሰነዶች ማውጣት አልቻሉም በዚህም ምክንያት ስራዎች በመጓተታቸው የ15 ተቋማት የመውጫ ስብሰባ አልተደረገም ከዚህም በላይ ኦዲታቸውን ያልዘጉ ተቋማት መኖራቸ ውንና በአስተያየት መውጣታቸውንም ተናግረዋል የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርአት በራሱ ችግሮች እንዳሉበት ያነሱቱ አቶ ገመቹ ከገንዘብ ሚኒስቴር በማእከል የሚሰጡ ስያሜዎች ከተቋማቱ ስያሜ ጋር ያለመጣጣም ሚኒስቴሩ የገንዘብ ዝውውር መፈፀሙን ሳያውቅ በተቋማት ሊከናወን እንደሚችል ማየታቸውን አስታውቀዋል ይህም ትክክል አለመሆኑን ገልፀዋልየኢፍሚስ ስርአት ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት በዋና ኦዲተር ተገምግሞ ውጤታማ መሆኑን ሲረጋገጥና ተግባራዊ እንዲሆን ሲፈቀድ ወደ ተግባር መግባት ነበረበት ያሉት አቶ ገመቹ አሁን ግን ወደ ተግባር የተገባው ይሄን ሂደት ሳይከተል መሆኑን አስታውቀዋል ዋና ኦዲተሩ በስራ ሂደት ያገኟቸውን ችግሮች ነቅሰው በማውጣት ተቋማት ወደ ስርአቱ በበጀት አመት መጀመሪያ እንዲገቡ የተቋማት የሂሳብ ባለሙያዎች በቂ ስልጠና በመስጠት የሚኒስቴሩ ድጋፍ እንዲጠናከር በስርአቱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች እንዲታረሙ በማድረግ ማሻሻያ እንዲያደርጉ ለሚኒስቴሩ ምክር ቢሰጡም ተግባራዊ አለመደረጉን ገልፀዋል ይህ ካልተስተካከለ እስከወዲያኛው የማይፈታ ችግር እንደሚሆንም አስጠንቅቀዋል ሌላው ለኦዲት መጓተት በምክንያትነት ያነሱት የከፍተኛ አመራሮች የ17 ቀናት ስልጠና ሲሆን ሀላፊዎቹ ሳይገኙ የመውጫ ስብሰባ ማድረግ ባለመቻሉ መጓተት መፍጠሩን ተናግረው በመጋቢት ወር አብዛኞቹ ተቋማት ኦዲት ቢጠናቀቅም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የመውጫ ስብሰባ ለማድረግ አልቻሉም ሌሎች ተቋማትም ማስረጃ ማቅረብ አለመቻላቸውን አመልክተዋል መስሪያ ቤቱ የ2011 በጀት አመት ኦዲት ከያዘው አቅድ አንፃር ቢዘገይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 25 ቀን 2012 አም የኦዲት ሪፖርቱን ለማቅረብ ለምክር ቤት ተልኳልበዋና ኦዲተር አስተያየት ላይ ምላሽና አስተያየት እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የገንዘብ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ ዋና ኦዲተር ሪፖርት ካቀረበ በኋላ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተናግረዋልአዲስ ዘመን ግንቦት 232012 አጎናፍር ገዛኸኝ
https://www.press.et/Ama/?p=33419
378
9,478
የትህነግ ዘራፊ ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
November 24, 2020
161
የትህነግ ዘራፊ ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ዋለባህር ዳር ሀዳር 152013 አም አብመድ የትህነግ ዘራፊ ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ በተሽከርካሪ ተጭኖ ከሁመራ ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ሊገባ ሲል መያዙን የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ቴዎድሮስ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮማንደር ዘለቀ ምትኩ ተናግረዋል የተገኘው አደንዛዥ እፅ ካናቢስ የተሰኘ ነው
https://www.amharaweb.com/%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%88%85%e1%8a%90%e1%8c%8d-%e1%8b%98%e1%88%ab%e1%8d%8a-%e1%89%a1%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%88%b2%e1%8c%a0%e1%89%80%e1%88%9d%e1%89%a0%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8a%90%e1%89%a0%e1%88%a8-32/
53
37,570
ኢትዮጵያውያን ችግኞችን በመትከል የዓለም ክብረ-ወሰን ሰበሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
ዛሬ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይን ጥሪ መነሻ ያደረገ የችግኝ ተከላ ሲካሄድ ውሏል በርካቶች የተሳተፉበት ዘመቻ ከችግኝ ተከላም የበለጠ ትርጉም ያለው መሆኑን ቪኦኤ ያነጋገራቸውው ተሳታፊዎች ተናግረዋልዘመቻው አንድነትን ሊያጠናክር እንደሚችልም ገልፀዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በወላይታ ሶዶና በአርባ ምንጭ መሳተፋቸውም ታውቋል
https://amharic.voanews.com//a/ethiopia-tree-planting-record-/5019711.html
40
38,269
በኪሊማንጃሮ ተራራ የተነሳው እሳት
ዓለም አቀፍ ዜና
October 15, 2020
Unknown
ከአፍሪካ በከፍታው ወደር በሌለው በኪሊማንጃሮ ተራራ ላይ የተነሳውን ቃጠሎ ለማጥፋት የታንዛኒያ የእሳት አደጋ ሰራተኞ እየተረባረቡ ነውየታንዛኒያ የቱሪዝም እና የተፈጥሮ ሀብቶች ሚኒስትሩ እንዳሉት እሳቱ አእዋፍና ሌሎችም እንስሳት የሚኖርበትን የተጠበቀ የተፈጥሮ አካባቢ ሊያወድመው ስጋት ፈጥሯልየእሳት አደጋ ሰራተኞች በተከታታይ ለአምስት ቀናት የያዙትን ጥረት ቃጠሎው ያለበት ስፍራ የአየሩ ሁኔታ ደረቅ መሆኑና ሀይለኛ ንፋስ አዳጋች አድርጎባቸዋል በቃጠሎው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አልተዘገበምቃጠሎው የተነሳው ለተራራ ወጪዎች ምግብ ለማብሰል እሳት ባቀጣጠሉ ሰራተኞች እንደሆነ ተዘግቦ የነበረ ሲሆን ይሁንና ምርመራው ቀጥሏል
https://amharic.voanews.com//a/firefighters-continue-battling-mount-Kilimanjaro-fire-10-15-2020/5622723.html
72
27,150
ኢትዮጵያ 1-3 ዛምቢያ | የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ አስተያየት
ስፖርት
October 25, 2020
Unknown
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሶስት ቀን ቆይታ በኋላ ከዛምቢያ አቻው ጋር ያደረገውን ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታ 31 በሆነ ውጤት ተሽንፏል የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተም ከጨዋታው በኋላ ተከታዮቹን አስተያየቶች ሰጥተዋል አጠቃላይ ስለጨዋታው ምን አሰተያየት አለዎት እቅዳችን የነበረው ሁሉንም ለጨዋታው ብቁ የሆኑ ተጫዋቾችን መጠቀም ነበር ለሀሙሱ ጨዋታ መድረስ ያልቻሉ ተጫዋቾችንም ጭምር ተጠቅመናል በመሆኑም ጨዋታውን ቡድናችን ያለበትን ደረጃ ለመገምገም ተጠቅምንበታልቡድኑ የተጋጣሚን ጫና መቋቀም ተስኖት ነበር በሁለት ተከላካይ አማካዮች የመጠቀም እቅድ ይኗራችኋል በተደጋጋሚ ስለሚታዩ ቀላል ስህተቶችስ ምን ይላሉ የጨዋታው ዋና አላማ ውጤት ማግኘት ሳይሆን አቋማችንን መገምገሙ ላይ ነው በመሆኑም በጨዋታው ብዙ ተምረንበታል እንጂ ተነሳሽነታችንን አይቀንሰውምየተጠቀምናቸው የጨዋታ ዘዴዎች ተመሳሳይ ነበሩ በተለይም በሁለተኛው አጋማሽ ትልቁ ድክመታችን የነበረው ኳሱን ለማቀበል ወይም ለማንቀሳቀስ ሌሎች አማራጮች እያሉን በተመሳሳይ መንገድ መቀጠላችን ላይ ነው ሌሎች የቅብብል አማራጮችን መፍጠር እየቻልን በቀላሉ ወዳዘጋጁልን ወጥመድ እንገባ ነበርሁለት ተከላካይ አማካዮችን መጠቀም የተለየ ልዩነት አይፈጥርም ዋናው ነገር ኳስን የምንቆጣጠርበት እና ቅብብሎችን የምንከውንበት መንገድ ነው በዚህ ረገድ በጣም ደካማ ነበርን ዛምቢያዎችም ይህን ደካማ ጎናችንን በደንብ ተጠቅመውበታልስለመከላከል ስህተቶችስ ምን ይላሉ የመከላከል ስራ እንደሙዚቃ ኦርኬስትራ በቡድን የሚከወን ነው ኳስ ስንነጠቅ በቶሎ ወደ መከላከል ቅርፃችን መመለስ ይኖርብናል ክፍተቶቹ የሚጠበቁ ናቸው ክለብ ቢሆን በዚህ ፍጥነት መጫወታችን የማይጠበቅ ሊሆን ይችላል በተናጠልም ሆነ በቡድን ችግሮች አሉብንየዛምቢያ ቡድን አቀራረብ የወዳጅነት ጨዋታ አይነት አልነበረም በእርሶ ቡድን ውስጥ ይህን ስሜት መመልከት ይፈልጋሉ እንደማስበው ከሆነ ከጨዋታው በፊትም ሆነ በኋላ የተጫዋቾቻችን ተነሳሽነት ጥሩ ነበር ተጫዋቾቼ ለጨዋታው ሙሉ ትኩረት እንደሰጠ አምናለሁ ሜዳ ላይ ግን ያ ነገር ሙሉ በሙሉ አልታየም በእረፍት ሰአትም ጠይቂያቸው የተረዳሁት ይህንኑ ነውየወዳጅነት ጨዋታዎቹ የመጨረሻዎቹን ተጫዋቾች ለመለየት ምን ያህል ይረዳሉ ጨዋታዎቹ እንደጠቀሙን አስባለሁ ዋናው አላማችንም ወደ ማጣሪያ ጨዋታዎቹ የምንወስዳቸውን ተጫዋቾች መለየቱ ላይ ነው እያንዳንዱን ተጫዋች ሙሉ 90 ደቂቃ ማየት ብንችል ጥሩ ነበር ሽመልስን ጨምሮ 27 ተጫዋቾችን በመያዝ ለቀጣዩ ጨዋታ ዝግጁ እንሆናለን ጉዳት ወይም ኮቪድ ሊገጥመንም ይችላል ሆኖም ወደ ኒጀር ከማቅናታችን በፊት የመጨረሻዎቹን 23 ተጫዋቾች እንለያለን
https://soccerethiopia.net/football/61174
282
29,684
” ቡድናችን የቻምፒዮንነት እና የማሸነፍ መንፈስ ላይ ነው ያለው” ሚካኤል ደስታ
ስፖርት
August 9, 2019
Unknown
መቐለ 70 እንደርታ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የሚያደርገውን የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ነገ 1200 ላይ ከኢኳቶርያል ጊኒው ካኖ ስፖርት አካዳሚ ጋር ያከናውናል ቡድኑን በአምበልነት እየመራ ወደ ጨዋታው ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው አማካዩ ሚካኤል ደስታም ስለ ዝግጅታቸው እና ተያያዥ ጉዳዮች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓልለውድድሩ እያደረጋችሁት ቅድመ ዝግጅት ምን ይመስላልለውድድሩ ያደረግነው ዝግጅት መልካም ነው በውድድሩ ልምድ ያለው አሰልጣኝ ነው ያለን በነበሩብን ክፍተቶችም አዳዲስ ተጫዋቾች ጨምረናል ይሄንን ጨዋታ አሸንፈን ወደ ቀጣይ ዙር ለማለፍ እና በመጀመርያው ተሳትፏችን ጥሩ ጉዞ ለማድረግ ነው እቅዳችንበአፍሪካ በውድድሮች ያለህ አንፃራዊ ልምድ ለቡድኑ ምን ጥቅም ይኖረዋል ብለህ ታስባለህበግሌ ያለኝ ልምድ እንዳለ ሆኖ አዲስ ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉት እና አንዳንድ ነባሮችም በውድድሩ ጥሩ ልምድ ነው ያላቸው ሁላችንም በህብረት በመሆን ይህንን ዙር አልፈን በውድድሩ ላይ ጥሩ ጉዞ ለማድረግ ያግዘናልበዚህ ሰአት ያለው የቡድናችሁ ስሜት ምን ይመስላልየኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን ነን ውድድሩ ካለቀም ብዙ ግዜ አልሆነውም አሁንም በቡድናችን ያለው ያንን የሻምፕዮንነት እና ጥሩ የማሸነፍ መንፈስ ነው ይህንን ጨዋታ አሸንፎ ጥሩ ውጤት ይዞ መመለስ ነው እቅዳችን ደስ የሚለው ነገር ደግሞ የመጀመርያ ጨዋታችን ከሜዳችን ውጭ መሆኑ ነው በሁለተኛው ጨዋታ በሀገራችን በሜዳችን እና በደጋፍያችን ፊት ስለምንጫወት እንደምናልፍ እርግጠኛ ነኝየቡድኑ አምበል እንደመሆንህ በዚህ ጨዋታ በውጤት ደረጃ ምንድነው እቅዳችሁኳስ ላይ ቀድመህ ውጤቱ እንዲህ ነው ማለት አትችልም ተጋጣሚህን በደንብ ሳታይ እንዲህ ነው እንዲያ ነው ብለህ መናገር ከባድ ነው ግን አሸንፈን ወይም አቻ ወጥተን ጥሩ እድል ይዘን ወደ ሁለተኛው ጨዋታ እንገባለን ብዬ በእርግጠኝነት እናገራለው በሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ የተሻለ የመዘጋጃ ጊዜም ስላለን የተሻለ ቡድን ይዘን ነው በሜዳችን የምንጫወተውከጨዋታው በፊት ስለ ተጋጣሚያችሁ ምን መረጃ አግኝታችኋልአዎ አግኝተናል ግብ ጠባቂያን ፍሊፕ ኦቮኖ ኢኳቶሪያል ጊኒያዊ ስለሆነ በሱ በኩል ጥሩ መረጃዎች አግኝተናል መረጃዎቹም የተሻለ ዝግጅት እንድናደርግ ረድተውናል
https://soccerethiopia.net/football/49816
248
1,239
“የኢትዮ – ሱዳን ድንበር ግጭት የሱዳን መንግሥትና ህዝብ ፍላጎት አይደለም”አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
ሀገር አቀፍ ዜና
January 3, 2021
56
ዋቅሹም ፍቃዱ አዲስ አበባየኢትዮ ሱዳን ድንበር ግጭት ሱዳን መንግስትና ሰፊው የሱዳን ህዝብ ፍላጎት እንዳልሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ ግጭቱ ለማንም እንደማይበጅ የኢትዮጵያ አቋም መሆኑንም አመለከተዋልአምባሳደር ዲና ሙፍቲ በግጭቱ ዙሪያ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር 100 አመት ያስቆጠረ ቢሆንም በሌሎችም የአፍሪካ አገራት እንደሚታየው ከቅኝ ገዥዎች የተወረሱ ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል ኢትዮጵያ በቅኝ ገዥዎች ባትገዛም ሱዳን በቅኝ ግዥዎች ስር ስለነበረች ድንበሩ ምንም እንኳ ምልክቶች ቢኖሩትም በዘመናዊ ዘዴ በትክክል ባለመካለሉ አንዳንዴ በሁለቱም አገሮች የድንበር አካባቢዎች መገፋፋቶች ይፈጠራሉ ብለዋል አሁን ያለው ድንበር ባህላዊ መሆኑን ጠቁመው ሰሞኑን የሱዳን ሀይሎች ሀላፊነት በጎደለው መልኩ የኢትዮጵያን መሬት መያዛቸው ስህተት መሆኑ እንዳለ ሆኖ አንዳንድ የሱዳን ሚዲዎችና ባለስልጣናት መሬታቸውን እንዳስመለሱ አድረገው በመግለጫ የሚያሰራጩት መረጃ ተቀባይነት የሌለውና ህገ ወጥ መሆኑ አስታውቀዋልአንዳንድ የሱዳን ባለስልጣናት ከኋላ ሆነዉ ጉዳዩን ለሚያቀጣጥሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች መጠቀሚያ ሆነው ቢያገለግሉም የኢትዮጵያ መንግስት ግን ግጭቱ የሱዳን ህዝብና መንግስት ፍላጎት ነው የሚል መደምደሚያ ላይ እንዳልደረሰ ገልፀዋል ይልቁንስ መጠቀሚያ እየሆኑ ያሉ የሱዳን ባለስልጣናት ድርጊታቸው ሱዳንንም ሆነ ኢትዮጵያን በፍፁም ስለማይጠቅም ያሉትን ችግሮች በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግስት እያሳሰበ መሆኑን ገልፀዋል ድንበሩም በድንበር ኮሚሽን መርሆዎች ብቻ እንዲፈታም የኢትዮጵያ አቋም እንደሆነም አስታውቀዋል ግጭቱ የሱዳን መንግስትና የሱዳን ህዝብ ፍላጎት እንዳልሆነ የሚገልፁ እኛ ከኢትዮጵያ ጋር ፈፅሞ ወደ ግጭት አንገባም የሚሉ ድምፆች እየጨሩ መምጣታቸውን የጠቆሙት አምባሳደር ዲና ከበስተጀረባው ግን የተለያዩ ሀይሎች እንዳሉ ጠቁመዋል እነዚህ ሀይሎች ለዘመናት ያልጠቀሟትን ሱዳን ወዳጅ በማስመሰል የጥፋት አጀንዳቸውን ለማሳካት እየታተሩ እንደሚገኙ ጠቁመው የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ወዳዱ የሱዳን ህዝብ እና ባለስልጣናት እንዲሁም ለሰላም ወዳዱ የአረቡ ማህበረሰብ ግጭቱ ለማንም እንደማይበጅ በተጨባጭ እያሳወቀች መሆኑን አመልክተዋል አንዳንድ የሱዳን ወታደሮችና ሚሊሻዎች ሰሞኑን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በመግባት የሰው ህይወት ማጥፋታቸውና ንብረት ማውደማቸውን አመልክተው መንግስትም ፀጥታን ከማስከበር ጎን ለጎን ችግሩ በድርድር እንዲፈታ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋልአዲስ ዘመን ታህሳስ 252013
https://www.press.et/Ama/?p=38737
268
2,547
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አርሶ አደሩ የግብርና ሥራውን በቤተሰብ ደረጃ ወስኖ እንዲሰራ ጥሪ ቀረበ
ሀገር አቀፍ ዜና
April 8, 2020
6
አዲስ አበባ አርሶ አደሩ ቫይረሱን የመግታት ስራው ውጤታማ እንዲሆን ከዚህ ቀደም ይጠቀም የነበረውን የደቦ ስራ በመተው የግብርና ስራውን በቤተሰብ ደረጃ እንዲያከናውን የግብርና ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን ትናንት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት አርሶ አደሩ ከዚህ በፊት ይጠቀምበት የነበረውን የደቦ አሰራር በመተው የግብርና ስራውን በቤተሰብ ደረጃ በመስራት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የበኩሉን መወጣት አለበት እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ አርሶ አደሩ በፊት ለስራው የሚጠቀመውን የደቦ ስራ እንዲያቆምና ስራውንም በቤተሰብ ደረጃ እንዲሰራ ለማድረግ የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ወደ ቤተሰብ በተመለሱ ወጣት ተማሪዎችና በሌሎች በጎ ፍቃደኞች አማካይነት ለማከናወን ከክልሎች ጋር እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል በዚህ መልኩ የአርሶ አደሩን ግንዛቤ ማሳደግ ከተቻለ ተሰባስቦ የሚሰራውን ስራ በመግታት ግን ደግሞ የማምረት ተግባሩን ድርድር ውስጥ ሳያስገባ በቤተሰብ ደረጃ እንዲሰራ ለማድረግ ይቻላል ብለዋል በሌላ በኩልም የፌዴራልና የክልሎችን ድርሻ በመለየት ቀድሞ እስከ ወረዳ ድረስ ስልጠና በመስጠት በማስተሳሰር ይሰራ የነበረውን አሰራር በመቀየር ፌዴራል መስሪያ ቤቱ ሀብትን የማፈላለግ ምቹ የስራ ሁኔታን የመፍጠር ከውጭ አገር የሚገቡ ግብአቶችን የማሰባሰብ ትልቁ ድርሻ እንዲሆን ከታች ያለው ሀይል ደግሞ ከሀብረተሰቡ ጋር እየተገናኘ ወደ ስራ ማስገባት እንዳለበት ተስማምተናል ያሉት ሚኒስትሩ ለዚህም ቁጥራቸው 69 ሺ የሚጠጉ የልማት ጣቢያ ሰራተኞቸ ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት በሽታውን የመከላከል እንዲሁም ምርት አመራረቱም ላይ የመደገፍ ስራ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል ሚኒስትሩ በሽታው አርሶ አደሩ በለመደው አካሄድ አምርቶ ማቅረብ እንዳይችል የሚያደርግና የሚፈታተን ነው የስነ ልቦና ጫናው ከባድ በመሆኑ ሁሉም ወደራሱ ተመልሶ በነበረው መንገድ ለመሄድ ያስቸግራል በመሆኑም ትንሽ መፈተኑ አይቀርም ይህም ቢሆን ግን የምግብ ምርት ላይ ትኩረት በማድረግና በመጠንም ሆነ በአይነት ጨምረን ማምረት ይኖርብናል ብለዋል ይህንን ለማድረግ ከፊታችን እድሎች አሉ ያሉት ሚኒስትሩ ከነዚህም መካከል በበጋ ወቅት ከአነስተኛ መስኖ አሁን እየገባንበት ያለ የበልግ ስራ እንዲሁም ቀጥሎ የሚመጣው የመኸር ወቅት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ አንዱን በመስራት ለሌሎቹ ደግሞ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ሚኒስትሩ አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ የሚፈልገውን ግብአት ካገኘ እንዲሁም የአየር ሁኔታው ተስማሚ ከሆነ አሁን የገባንበትን ችግር ሊታደገን የሚችል ስራን መስራት ይችላል እስከ አሁን ያለውም ጥረት ተስፋ ሰጪ ነው መንግስት አምና በዚህን ወቅት እያቀረብን የነበረውን ያህል ማዳበሪያም እያቀረበ ነው በተመሳሳይ ኬሚካልና የሜካናይዜሽን አገልግሎቱም ይሟላል ይህ ደግሞ በተለይም በመኸር ወቅት ያለውን እድል እንዳናጣ ያደርግልናል ብለዋል ከ20 በመቶ የሚሆነው የሀብረተሰብ ክፍል ከድህነት ወለል በታች ያለና እንደዚህ አይነት ከባድ በሽታ ሲመጣም የመቋቋም አቅምም የለውም ያሉት ሚኒስትሩ አሁን ላይ ቆመን ምን ያህል የሀብረተሰብ ክፍል ወደዚህ ችግር ሊገባ ይችላል የሚለውን የመገመትና በዚያ መሰረትም ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል አዲስ ዘመን መጋቢት 302012 እፀገነት አክሊሉ
https://www.press.et/Ama/?p=29969
369
28,408
ያሬድ ዘውድነህ የሙከራ ዕድል አግኝቷል
ስፖርት
January 30, 2020
Unknown
የድሬዳዋ ከተማው ተከላካይ ያሬድ ዘውድነህ የውጭ ሀገር የሙከራ እድል አግኝቶ ወደ መቆዶንያ በቅርቡ ያቀናልከቅርብ አመታት ወዲህ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች በውጭ ሀገራት በሚገኙ ክለቦች የሙከራ እድል ማግኘታቸው እየተሰማ ባለበት በአሁኑ ወቅት የድሬዳዋ ከተማ ተከላካይ ያሬድ ዘውድነህ በመቄዶንያ ሀገር የሚገኘው ሲሌክስ የሙከራ እድል አግኝቶ በቅርቡ እንደሚጓዝ ተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯልኢትዮጵያ የሚገኘው ኤጀንቱ ይህን እድል እንዳመቻቸለት እና ወደ መቆዶንያ ለመጓዝ ህጋዊ ክለቡ ድሬዳዋ ከተማ ፍቃድ እየተጠባበቀ እንደሆነ የገለፀው ያሬድ ክለቡ የሙከራ እድሉን እንዲጠቀም ፍቃድ እንደሰጠውና በቅርቡ ወደ ስፍራው እንደሚያቀና ተናግሯልየአሁኑን ጨምሮ በተለያዩ ወቅቶች ለድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ለአዳማ ከተማ ለዳሽን ቢራ ወልዲያ እና ጅማ አባ ጅፋር የተጫወተው ያሬድ ዘውድነህ በቀጣይ ከጉዞው ጋር የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎች እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል
https://soccerethiopia.net/football/55125
103