Unnamed: 0
int64
0
51.5k
headline
stringlengths
2
861
⌀
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
6
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
1
34.3k
⌀
link
stringlengths
28
722
word_len
int64
0
6.74k
42,073
ወታደሩ የማን ነው? የዋሽንግተን ዲሲው “የጀግኖች ቀን” ሥነሥርዓት እና ሌሎች ታሪኮች
ዓለም አቀፍ ዜና
September 30, 2017
Unknown
ላገሩ ህይወቱን እስከ መሰዋት የተሰለፈን ዜጋ ማንነትና ያገለገለበትን ስርአት ለይቶ ያሳየ እውቅና በሚሰጠው ስራቸው የሚታወሱ ለክብር የበቁበት የምስጋና ስነ ስርአት ነው የዋሽንግተን ዲሲው የጀግኖች ቀንከዘንድሮው የጀግኖች ቀን ተሸላሚዎች እና ሸላሚዎቻቸው ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡየስነ ስርአቱን የቪዲዮ ምስል ቀጥሎ ያለውን አያያዥ በመጠቆም ከዚህ ይመልከቱ
https://amharic.voanews.com//a/ethiopian-former-soliders-honored-washington-dc-sept-2017/4050418.html
45
30,950
ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት ውድድር በአስመራ ሊካሄድ ነው
ስፖርት
December 16, 2018
Unknown
የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወጣት ብሄራዊ ቡድኖችን የሚያገናኝ ውድድር በቅርቡ አስመራ ላይ ይደረጋልየሰላም እና ወዳጅነት ዋንጫ በሚል ስያሜ በየካቲት ወር መጀመሪያ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ውድድር የ10 ቀናት እድሜ የሚኖረው ሲሆን የኢትዮጵያ ኤርትራ ሶማሊያ እና ጅቡቲ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድኖችን ያሳትፋልየኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራን ጨምሮ የቀጠናው የእግርኳስ አመራሮች ከሳምንት በፊት በአስመራ በነበራቸው ስብሰባ ውድድሩ በሚደረግበት ሂደት ላይ ተነጋግረዋል የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ በበኩሉ 25000 ዶላር ለኤርትራው ፌዴሬሽን በመስጠት ዝግጅቱን ለማገዝ ተስማምቷልየኤርትራ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ለዚህ ውድድር ከወዲሁ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ዛሬ ኢትዮጵያዊ ዳኞች በሚመሩት የወዳጅነት ጨዋታ የሱዳን አቻውን ያስተናግዳልሁለቱ ሀገራት በቅርቡ ሰላማዊ ግንኙነት ከቀጠሉ በኋላ በብሄራዊ ቡድን እና በክለቦች ደረጃ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ቢታሰብም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ እንደቀረ ይታወሳል
https://soccerethiopia.net/football/42304
114
24,262
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን በስም ማጥፋት ከሰሰ
ሀገር አቀፍ ዜና
8 March 2017
Unknown
አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአመታት የኦዲት ሂሳብ አለማከናወኑን የሚያትቱ ዘገባዎች በ2007 እና 2009 አም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሁለት ጊዜ በመታተማቸው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትንና የጋዜጣውን አዘጋጅ በስም ማጥፋት ክስ መሰረተባቸው እንዲሁም የሀበሻ ወግ የተሰኘው የግል መፅሄት በራሱና አዲስ ዘመንን ዋቢ አድርጎ ለሀትመት ባበቃቸው ተመሳሳይ ዘገባዎች በስም ማጥፋት አሳታሚውና አዘጋጆቹ የሞራል ጉዳት ማድረሳቸውም በክሱ ተመልክቷልዩኒቨርሲቲው ጥር 15 ቀን 2009 አም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ፍትሀ ብሄር ችሎት በፅሁፍ የመሰረተው የክስ ሰነድ እንዳመለከተው ሁለቱ የሀትመት ተቋማትን ጨምሮ አምስት ተከሳሾች በሀሰት የሀትመት ስራ የተቋሙን ስምና ዝና እንዲሁም በህዝብ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ሆነን ብለው አስበው ያደረጉትን ድርጊት ለማሳረምና ከሳሽ ላይ ለደረሰው የሞራል ጉዳት ካሳ ለመጠየቅ አዋጅ ቁጥር 5902000 አንቀፅ 412 መሰረት ክስ መስርቷልበተጠቀሰው የአዋጁ አንቀፅ መሰረት ከአንደኛ እስከ አምስተኛ የዘረዘራቸው ተከሳሾች ጠቅላላ ድምሩ 200 ሺህ ብር የሆነ የሞራል ካሳ እንዲከፍሉት ፍርድ ቤቱን ጠይቋልክስ የተመሰረተባቸው አንደኛ ተከሳሽ ቴዲአብ መልቲ ሚዲያና ኢንተርቴይንመንት የሀበሻ ወግ መፅሄት ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሀበር ሁለተኛ ተከሳሽ ከፍተኛ አዘጋጅ አቶ ዮናስ ወልደሰንበት ሶስተኛ ተከሳሽ ዋና አዘጋጅ ወሮ ፅጌሬዳ ገብረ ማርያም አራተኛ ተከሳሽ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዲስ ዘመን ጋዜጣ አምስተኛ ተከሳሽ አቶ አጎናፍር ገዛኸኝ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አዘጋጅ የስም ማጥፋት ክስ ተመስርቶባቸዋል አዲስ ዘመን ጋዜጣ ነሀሴ 9 ቀን 2007 አም ዩኒቨርሲቲውን አስመልክቶ ለአምስት አመታት ኦዲት ያልተደረገ ተቋም እንዲሁም ሀዳር 7 ቀን 2009 አም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስድስት አመታት የኦዲት ሪፖርት አይታወቅም የሚሉ ዘገባዎችን ለሀትመት በማብቃቱ ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷልአምስተኛ ተከሳሽ በተጠቀሱት ሁለቱ ዘገባዎች ዩኒቨርሲቲው ኦዲት ለማስደረጉም ሆነ ስላለማስደረጉ ሳያረጋግጡና ምንም አይነት መረጃ ሳይኖራቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴና የፌዴራል ዋና ኦዲተር አመራሮችን የዘገባ ምንጭ በማድረግ ያልተጠቀሰ መረጃን በመያዝ ሆን ብሎ ተቋሙን በህዝብ ተቀባይነትና ተአማኒነት ለማሳጣት ከአሳታሚው ድርጅት ጋር በመተባበር ባወጡት የሀትመት ውጤት በከሳሽ ላይ ከፍተኛ የህሊና ጉዳት ማድረሳቸው በክሱ ጠቅሷልበተለይ አምስተኛ ተከሳሽ አቶ አጎናፍር የከሳሽን ስም ሆን ብለው በሀሰት የሀትመት ፅሁፍ ለመጉዳት ሲሰሩ እንደቆዩ የዩኒቨርሲቲው ክስ ያስረዳልእንዲሁም ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ተከሳሽን አስመልክቶ ይኸው ክስ ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ዮናስ ወልደሰንበትና ሶስተኛ ተከሳሽ የሀበሻ ወግ መፅሄት አዘጋጅ ወይዘሮ ፅጌረዳ ሀዳር 6 ቀን 2009 አም በሳምንታዊ መፅሄት እትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ ምርመራ ለአምስት አመታት አስደርጎ እንደማያውቅ ነሀሴ 9 ቀን 2007 አም እና ሀዳር 7 ቀን 2009 አም እንዲሁም ለፅሁፋቸው ቀኑ ባልተጠቀሰ ጊዜ ማለትም የካቲት 2007 አም ከ2700 አልጋዎች ውስጥ 750 አልጋዎች ለተማሪዎች ሳይተላለፉ በወር 400 ብር በአጠቃላይ ሲሰላ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በድብቅ ለተማሪዎች በማከራየት ግለሰቦች ኪስ ውስጥ እንደሚገባ በውሸት ባዘጋጁዋቸው ዘገባዎቻቸው በሀበሻ ወግ መፅሄት የፊት ገፅ ታትሞ እንዲወጣ አድርገዋል ይላልበተጨማሪም ሶስተኛ ተከሳሽ ወይዘሮ ፅጌረዳ በሁለተኛ ተከሳሽ ተቀነባብሮ የቀረበውን የውሸት ዘገባ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በዩኒቨርሲቲው በድብቅ አልጋ እየተከራየ የግለሰቦች ኪስ ገንዘብ እንደሚገባ የወጣ ዘገባ ስለመኖሩና አለመኖሩ ሳያረጋግጡ በአንደኛ ተከሳሽ መፅሄት ላይ እንዲወጣ ከመደረጉ በፊት ማረጋገጥ ሲገባቸው የአዘጋጅነት ሙያዊ ተግባራቸውን ባለመወጣታቸው በከሳሽ ላይ ከፍተኛ የሞራል ጉዳት እንዳደረሱ ተጠቅሷልየፍትሀ ብሄር ህግ ቁጥር 2044 እና ተከታዮቹ እንዲሁም በመገናኛ ብዙሀን የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 5902000 በመጥቀስ ከሳሽ መብቱን ለማስከበር ወደ ክስ ለመግባት መገደዱንም አመልክቷል በመሆኑም ሁለቱም የሚዲያ ተቋማት በየሀትመቶቻቸው ላይ ያወጧቸውን አርመው እንዲያሳዩ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታውን አቅርቧል የስም ማጥፋትና ማጉደፍ ደርሶብኛል ላላቸው በደሎች ሁሉም ተከሳሾች እንደድርጅቶቻቸው ቅደም ተከተል መሰረት በተናጠልና በጋራ ከሁለቱም ወገኖች የ100 ሺህ ብር በድምሩ 200 ሺህ ብር የሞራል ካሳ እንዲከፈለው በክሱ ጨምሮ ጠይቋልከአንደኛ እስከ አምስተኛ የተዘረዘሩት ሁሉም ተከሳሾች ለቀረበባቸው የፍትሀ ብሄር ክስ የካቲት 30 ቀን 2009 አም የፅሁፍ መልስ እንዲያቀርቡ መጋቢት 25 ቀን 2009 አም ደግሞ በአካል ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የፅሁፍ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል 
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3-%E1%8B%A9%E1%8A%92%E1%89%A8%E1%88%AD%E1%88%B2%E1%89%B2-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8D%95%E1%88%AC%E1%88%B5-%E1%8B%B5%E1%88%AD%E1%8C%85%E1%89%B5%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%88%B5%E1%88%9D-%E1%88%9B%E1%8C%A5%E1%8D%8B%E1%89%B5-%E1%8A%A8%E1%88%B0%E1%88%B0
523
11,918
የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ በተከሰተው አለመረጋጋት ለወደሙ ኢንቨስትመንቶች መንግሥት የሚከፍለው ካሳ እንደሌለ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
22 ጥቅምት 2020
Unknown
የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተ አለመረጋጋት ለወደሙ ኢንቨስትመንቶች የሚከፍለው ካሳ አለመኖሩን የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀየድምፃዊ ሀጫሉን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች 89 የኢንቨስትመንት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል መውደማቸው ኮሚሽኑ ለቢቢሲ ገልጿልከወራት በፊት በክልሉ በተስተዋለው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ከተሞች መካከል ሻሸመኔ ዝዋይ የሚገኙበት ሲሆን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ደርሷልየኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዋሲሁን ጎልጋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የአርቲስት ሀጫሉን ግድያን ተከትሎ በኢንቨስትመንት ድርጅቶች ላይ የደረሰው ጉዳት በገንዘብ ሲሰላ ከ3 ቢሊዮን በር በላይ እንደሚሆን ለቢቢሲ ተናግረዋልኮሚሽኑ ጉዳቱ ከደረሰ በኋላ የተለያዩ ድርጅቶችን ለማገዝ የተለያዩ እርምጃዎች መውሰዱንም ገልፀዋልየደረሰው ጉዳት ከተለየ በኋላ ከፌደራል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በመወያየት ከዚህ በፊት መኪና እና ማሽኖችን ከቀረጥ ነፃ ያስገቡ አሁንም በድጋሚ በነፃ እንዲያስገቡ የባንክ ብድር ያለባቸው ደግሞ የእፎይታ ጊዜ እንዲሰጣቸው ተወስኗል ብለዋልከዚህ በተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው እነዚህ የኢንቨስትመንት ድርጅቶች ከዚህ በፊት የመሬት ጥያቄ አቅርበው ከነበረ በፍጥነት ምላሽ እንዲያገኙ መወሰኑን ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋልእነዚህ ድርጅቶች ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ከማገዝ ውጪ ለደረሰው ጉዳት መንግስት የሚከፍለው ምንም አይነት ካሳ እንደሌለ እንዲሁም ለመክፈል ቃል የሚገባው ነገር አለመኖሩን አቶ ዋሲሁን ገልፀዋልበአሁኑ ሰአትም ጉዳት ከደረሰባቸው 89 ድርጅቶች መካከል ጥቂቶቹ ወደ ስራ እየተመለሱ መሆኑን ተናግረዋልበኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በሚፈጠረው አለመረጋጋት የተነሳ በኢንቨስትመንት ድርጅቶች ላይ በሚደርሰው ጉዳት ስራ ላይ ያሉ ኢንቨስትመንቶች በሙሉ አቅማቸው እንዳይሰሩ ጫና እያሳደረባቸው እንደሆነም ገልፀዋል ኢንቨስትመንት የተረጋጋ ሰላም ይፈልጋል የሰላም ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ኢንቨስተሮች በሙሉ አቅማቸው ለመስራት ስጋት ያድርባቸዋል ይህም አንድ ጫና ነው በቅርቡ የደረሰው አለመረጋጋትም እንደዚህ አይነት ጫና ፈጥሯል ብለዋልስራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙት ላይም ፍርሀት ቢታይም የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት መስህብ ጭማሬ እያሳየ መሆኑንና ያለው ፍላጎትም ጥሩ መሆኑን ተናግረዋልበኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከ12 ሺህ በላይ የኢንቨስትመሰንት ድርጅቶች ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ
https://www.bbc.com/amharic/54635974
254
32,931
​ኢትዮጵያ፣ ሞሮኮ እና ኤኳቶሪያል ጊኒ የቻን 2018ን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርበዋል
ስፖርት
October 2, 2017
Unknown
የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን ካፍ የ2018ቱን የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ ቻን ማስተናገድ ለሚፈልጉ ሀገራት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ ባቀረበው ጥሪ መሰረት እስከቅዳሜ ድረስ ሶስት ሀገራት በጥር ወር የሚደረገውን ውድድር ለማስተናገድ ፍላጎት አሳይተዋል ካፍ እሁድ ይፋ እንዳደረገው ኢትዮጵያ ሞሮኮ እና ኤኳቶሪያል ጊኒ ፍላጎት ያሳዩ ሀገራት ናቸውካፍ ኬንያን ከአስተናጋጅነት ካነሳ በኋላ ላለፈው አንድ ሳምንት ሞሮኮ ደቡብ አፍሪካ እና ዛምቢያ የውድድሩ አዘጋጅ ሊሆኑ እንደሚችሉ በርካታ መረጃዎች ቢወጡም ከሞሮኮ ኢትዮጵያ እና ኤኳቶሪያል ጊኒ በስተቀር ውድድሩን ለማስተናገድ ፍላጎት ያለው የአፍሪካ ሀገር ሊገኝ አልቻለም ሞሮኮ የፊፋ የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድርን ማስተናገድ የቻለች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ስትሆን በ2015 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅነት እድል ቢሰጣትም በወቅቱ በተሰወኑ የምእራብ አፍሪካ ሀገራት በተቀሰቀሰው የኢቦላ በሽታ ወረርሽኝ ምክንያት ውድድሩን ከማስተናገድ እሯሷን አግልላለችኤኳቶሪያል ጊኒ በበኩሏ በ2015 ሞሮኮን ተክታ የአፍሪካ ዋንጫን ማስተናገድ የቻለች ሲሆን በ2012 በጣምራ ከጋቦን ጋር የአፍሪካ ዋንጫውን ማስተናገዷ ይታወሳል ኢትዮጵያ በቅርብ አመታት የአህጉራዊ ውድድርን አስተናግዳ አታውቅም በ2015 የዲኤስቲቪ ሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ዋንጫ ያስተናገደችው ኢትዮጵያ እኤአ በ1976 የአፍሪካ ዋንጫ ካስተናገደች በሀላ በ2001 የአፍሪካ ከ20 አመት በታች ዋንጫ በቀደሞ አጠራሩ የአፍሪካ ወጣቶች ዋንጫ ያስተናገደችው ትልቁ ውድድር ነውቀጣይ አዘጋጅ ሀገርን በ15 ቀን ውስጥ ይፋ እንዲረግ በጋና ርእሰ መዲና አክራ በነበረው ስብሰባ የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መወሰኑ ይታበሳል
https://soccerethiopia.net/football/30594
179
30,396
የአሰልጣኞች አስተያየት | ድሬዳዋ ከተማ 1-0 ኢትዮጵያ ቡና
ስፖርት
March 17, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ስምአን አባይ ድሬዳዋ ከተማ ስለ ጨዋታው ከዚህ ቀደም በሜዳችን በምናደርገቸው ጨዋታዎች ዋጋ እየከፈልን እንወጣ ነበር ዛሬ ግን ውጤቱን እንደመፈለጋችን በተጫዋቾቼ እና ሜዳ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረጋችን በሶስት ነጥቡ ደስተኛ ነኝ እነርሱ ኳሱን ይዘው ለመጫወት ጥረት ቢያደርጉም እኛ የሜዳ ክፍል ሲደርሱ በተከላካዮቻችን ጥንካሬ መቆጣጠር ችለናል አሁንም ቢሆን ከዚህ ቀደም የነበረብንን ያገኘነውን አጋጣሚ ያለመጠቀም ክፍተት አሁንም ስራ ይጠብቀናልከእረፍት መልስ ብልጫ ስለመወሰዱ ጫና የፈጠረብን የፍፁም ቅጣት ምቱ ከሳትን በኋላ ነው ያ ደግሞ ስነ ልቦናቸውን አውርዶት ነበር ይህ ማለት በሜዳችን የነበረን አሸንፎ የመውጣት ችግር እና ውጤቱን አስጠብቀን ለመውጣት ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ የመረበሽ ነገር ታይቶባቸዋል ይሄም ቢሆን በኢትዮጵያ ቡና በኩል ከባድ ነው የምትለው የጎል ሙከራ ማየት አልተቻለምቡድኑን የተቀላቀሉ አዲስ ፈራሚዎች ከመጡ ገና አስራ አምስት ቀናቸው ነው ምንያህል ተሾመ ለእኔ በጣም አስገርሞኛል ሳመጣውም ይሄን አገልግሎት ከእርሱ ፈልጌ ነው ሜዳ ውስጥ ይሰራልኝ የነበረው አንደኛ ልምድ አለው ልምዱን ይጠቀማል ሁለተኛ ታክቲካሊ ዲሲፒሊንድ ነበር ሶስተኛ ሜዳ ውስጥ ቡድን ይመራል ያደራጃል የግል እንቅስቃሴውም የሚያስከፋ አልነበረም በቀጣይም ከዚህ የተሻለውን እንደሚያደርግ አስባለው ኤልያስ ማሞም ወደ ሪትም ሲገባ በጣም ጥሩ እንደሚሆን እና የበለጠ ቡድኑን ከዚህ በተሻለ እንደሚጠቅም እርግጠኛ ነኝገዛኸኝ ከተማ ኢትዮጵያ ቡና ስለ ጨዋታውጥሩ መንቀሳቀስ ችለናል ዛሬ ከትኩረት ማጣት እና ባሉብን ክፍተቶች ምክንያት ውጤቱ አልተሳካም በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ቡድን ይዘን እንመጣለንጉዳት እና የብሄራዊ ቡድን ጥሪ ቡድኑ ጥሪ የፈጠረው ተፅእኖአዎ ሁለት ተጫዋቾች ብሄራዊ ቡድን ናቸው ያሉት የተወሰኑ ተጫዋቾች በጉዳት ላይ ናቸው በዛ ላይ በዛሬው ጨዋታ ላይ ወጣቶችን ተጠቅመናል ሜዳ ላይ ውጤቱ ጥሩ አይሁን እንጂ ጥሩ ነገር ማሳየት ችለዋል ከዚህም በኋላ ወጣቶች ላይ እየሰራን እንሄዳለን
https://soccerethiopia.net/football/45772
254
6,376
ሳምሰንግ፤ ቴክኖሎጂውን ለቻይና የሸጡበት ሰራተኞቹን ከሰሰ
ዓለም አቀፍ ዜና
Sunday, 02 December 2018 00:00
806
 ግዙፉ የአለማችን የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ የደቡብ ኮርያው ሳምሰንግ የጋላክሲ ስማርት ሞባይል ስልኮቼን የማመርትበትን ቴክኖሎጂ በህገወጥ መንገድ መንትፈው ለቻይና ኩባንያዎች በመሸጥ 138 ሚሊዮን ዶላር ያህል ገንዘብ አግኝተዋል በሚል በ8 ሰራተኞቹና ፈጠራዎቹን ገዝተዋል በተባሉት ሁለት የቻይና ኩባንያዎች ላይ ክስ መስርቷልኩባንያው ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ ብሉምበርግ እንደዘገበው ሳምሰንግ በ8ቱ ሰራተኞቹ ላይ ክስ የመሰረተው የጋላክሲ የሞባይል ስልኮቹን ስክሪን የሚሰራበትንና 13335 ሚሊዮን ዶላር ያህል ወጪ ያደረገበትን ኦርጋኒክ ላይት ኢሚቲንግ ዳዮድ የተሰኘውን የቴክኖሎጂ ፈጠራውን መንትፈው ለሁለት የቻይና ኩባንያዎች ሸጠውብኛል በሚል ነውበአለማችን የስማርት ፎን ገበያ ቀዳሚነቱን የያዘው የደቡብ ኮርያው ሳምሰንግ የቻይና ኩባንያዎች በራሳቸው ፈጠራ በገበያ ላይ መወዳደር ሲያቅታቸውየቴክኖሎጂ ፈጠራዎቼን መዝረፍ ጀምረዋል በሚል በኩባንያዎቹ ላይም ክስ መመስረቱን ዘገባው አመልክቷልየቻይና ኩባንያዎች በአገሪቱ መንግስት የተደገፈ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ምንተፋ ላይ በስፋት ተሰማርተዋል በሚል አሜሪካም በተደጋጋሚ ቻይናን ስትወነጅል እንደቆየች ያስታወሰው ዘገባው የተለያዩ የአሜሪካ ኩባንያዎችም የፈጠራ መብቶች ጥሰት ፈፅመዋል በሚል በተለያዩ የቻይና ኩባንያዎችና በሀላፊዎቻቸው ላይ ክስ መመስረታቸውንም አክሎ ገልጧል
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=22748:%E1%88%B3%E1%88%9D%E1%88%B0%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%8D%A4-%E1%89%B4%E1%8A%AD%E1%8A%96%E1%88%8E%E1%8C%82%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%88%88%E1%89%BB%E1%8B%AD%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%88%B8%E1%8C%A1%E1%89%A0%E1%89%B5-%E1%88%B0%E1%88%AB%E1%89%B0%E1%8A%9E%E1%89%B9%E1%8A%95-%E1%8A%A8%E1%88%B0%E1%88%B0&Itemid=212
135
29,110
ከፍተኛ ሊግ | ነገሌ አርሲ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል
ስፖርት
November 3, 2019
Unknown
ባለፈው አመት በከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ በመጨረሻው ሳምንት በሊጉ መቆየታቸውን ያረጋገጡት አርሲ ነገሊ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በተሻለ መልኩ ለመቅረብ የአስራአንድ ተጫዋቾች ዝውውር ማጠናቀቅ ችለዋልበግብጠባቂ ስፍራ ሁለት ተጫዋቾች ፈርመዋል የቀድሞው ወልቂጤ ከተማ ኒያላ እና ሀረር ሲቲ ግብጠባቂ ብርሀኑ ወልደማርያም እንዲሁም ምንተስኖት ሀይሌ ከአንደኛ ሊግ ተሳታፊው ላስታ ላሊበላ ሌላኛው ቡድኑን የተቀላቀለ ግብጠባቂ ነውደካማ የነበረውን የተከላካይ መስመራቸውን ለማጠናከር የአራት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀዋል የቀኝ መስመር ተከላካዩ ያያ አሎ ከሀምበሪቾ ሲፈርም መሀል ተከላካዮቹ ታዬ ገሹ ከአዳማ ተስፋ ቡድን ማንያዘዋል በላቸው ከባሌ ሮቤ እንዲሁም በሀይሉ ተስፋዬን ከአራዳ ክፍለ ከተማ ማስፈረም ችለዋል ከአዳማ ተስፋ ቡድን ቡድኑን የተቀላቀለው ታዬ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት እንደነበረም ይታወሳልበተጨማሪም በአጥቂ ስፍራ ላይ ዱሬሳ ሹቢሳን ከአዳማ ተስፋ ቡድን ሙሉቀን ተሾመ ከሻሸመኔ ከተማ በደደቢት ተስፋ ቡድን መጫወት የቻለው አሸብር ኦቶራ ከነገሌ ቦረና በባሌ ሮቤና ሀሰን ሁሴንና በኢኮስኮ ተስፋ ሰጪ ቆይታ የነበረው ሚካኤል ወልደሩፋኤል ከሀምበሪቾ በአዲስ መልኩ እየዋቀረ የሚገኘውን የአርሲ ነገሌ በአጥቂ ስፍራ የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸውበተያያዘ ዜና የቀድሞ የቡድኑ ተጫዋች እና አንበል የነበረው ሀሰን በሽር በምክትል አሰልጣኝነት ቡድኑን እንዲያገለግል ተሹሟል
https://soccerethiopia.net/football/51473
163
29,472
ኢትዮጵያ ቡና አጥቂ አሰፈረመ
ስፖርት
September 9, 2019
Unknown
በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ እየተመራ በዝውውር ሂደቱ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና አጥቂው እንዳለ ደባልቄን አስፈርሟልየአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ እንዳለ በ2010 የውድድር ዘመን ደግሞ ከጅማ አባጅፋር ጋር የሊጉን ዋንጫ ያሸነፈ ሲሆን ከደደቢት ጋርም የሊጉን ዋንጫ በክለቡ ቆይታው አግኝቷል የተጠናቀቀውን የውድድር አመት ከጅማ አባ ጅፋር ለቆ ወደ ባህር ዳር በማምራት በጣና ሞገዶቹ ቤት የቆየው እንዳለ ከዚህ ቀደም በአሰልጣኝ ድራገን ፖፓዲች የአሰልጣኝነት ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ቡና ለማምራት ከጫፍ ደርሶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በመጨረሻም በሁለት አመት ውል ቡናማዎቹን መቀላቀል ችሏልእስከ አሁን በጥቅሉ 12 ተጫዋቾችን ያስፈረመው ኢትዮጵያ ቡና ከመስከረም 5 ጀምሮ ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚገባ ይሆናል
https://soccerethiopia.net/football/50524
91
34,418
” በመጀመርያ ጨዋታዬ ድል በማስመዝገቤ ደስታ ተሰምቶኛል ” አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ
ስፖርት
June 7, 2016
Unknown
እጅግ በጣም ደስ ይላል ኩራት ነው የሚሰማኝ ለኔ በመጀመርያ ጨዋታዬ  ጨዋታው ከሜዳ ውጪ በሆነበት እና ውጤት ባጣንበት ጊዜ የተመዘገበ በመሆኑ ደስታ ተሰምቶኛል መልካም ነበር በተለይ የመጀመርያ 45 ደቂቃ ላይ ይዘነው የገባነው እቅድ በማጥቃት ላይ መሰረት ያደረገ ስለነበር ብዙ የግብ እድሎችን ፈጥረናል ሆኖም ማግባት አልቻልንም ነበር በመጨረሻ እረፍት ልንወጣ ስንል ጎል ማስቆጠራችን ትልቅ ሞራል ሰጥቶናል በሁለተኛው አጋማሽ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ሁለተኛ ግብ አስቆጥረናል ከዛ በኋላ ያው ውጤት ለመጠበቅ ከነበረን ፍላጎት የተነሳ የተወሰነ ጫና ተፈጥሮብናል በመጀመርያ በምን መልኩ መጫወት እንዳለባቸው ማስረዳት ማነሳሳት እና  አንድነት እንዲፈጥሩ ማድረግ ታክቲኩ እንዳለ ሆኖ እነዚህ ነገሮች ተደምረው ነው በሙሉ ፍላጎት እንዲጫወቱ ያደረጋቸው እኔ ከመጀመርያው ምን አይነት ውጤት ሊመዘገብ እንደሚችል ከጨዋታ በፊት ነግሬያቹ ነበር የነበራቸው ተነሳሽነት የስራ  ፍላጎታቸው ለኔ የነበራቸው ስሜት ጥሩ ስለነበር ይቀበሉኝ ነበር በትክክል ውጤትም ይመዘገብ እንደነበር ያስታውቅ ነበር የማለፍ እድላችን በእኛ ላይ ብቻ የተመሰረተ አይደለም በሌሎች ምድቦች ውጤት ጭምር ስለሆነ ቀጣይ ያለው ነገር የሚታይ ነው የሚሆነው ዋናው እኛ ያለንን ቀሪ አንድ ጨዋታ አሸንፈን የቤት ስራችንን መጨረስ ነው በእውነት ከፍተኛ የሆነ ክብር አለኝ በጣም ብዙ ነበሩ ኢትዮዽያዊነት በጣም ደስ ይላል ሁልጊዜ ከጎንህ ይቆማሉ ማልያ ለብሰው ሜዳ በመምጣት ሆቴል ድረስ ያላቸውን ፍቅር ሲገልፁ ደስ ይላሉ
https://soccerethiopia.net/football/12018
190
50,575
ከ39 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖቶች የተገኘባቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 22, 2020
Unknown
በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በሰንበቴ ከተማ ከ39 ሺህ ብር በላይ ባለ 200  ሀሰተኛ የብር ኖቶች  የተገኘባቸው  ሁለት  ተጠርጣሪዎች  በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀየወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሀመድ አሊ  እንደገለፁት ተጠርጣሪዎቹ ትናንት ቀን  በከተማዋ ገበያ ቦታ ሁለት ሰንጋዎችን በ29 ሺህ 400 ብር በመግዛት ከፍለው ሊሄዱ ሲሉ ሻጮች ብሩን በመጠራጠራቸው ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠታቸው ሊደረስባቸው ችሏልፖሊስም ባደረገው የማጣራት ስራ ብሩ ሀሰተኛ መሆኑን በማረጋገጡ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ባደረገው ፍተሻ ተጨማሪ 10ሺህ ሀሰተኛ የብር ኖት ማገኘቱን ተናግረዋልበአሁኑ ወቅት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ዋና ኢንስፔክተሩ አስረድተዋልከአንድ ወር በፊትም 6 ሺህ ሀሰተኛ  ባለ 200 የብር ኖቶች  በመያዝ ህብረተሰቡን ለማጭበረበር የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉንም አስታውሰዋልህብረተሰቡ በብርም ሆነ ሌሎች አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥመው በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት እንዲጠቁምና ሀሰተኛ የብሩን ኖት ለመለየት ግብይት ከመፈፀሙ  በፊት  ለሚያውቅ ሰው  በማሳየት ከመጭበርበር መዳን እንደሚችል መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a839-%e1%88%ba%e1%88%85-%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%88%80%e1%88%b0%e1%89%b0%e1%8a%9b-%e1%8b%a8%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%8a%96%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8c%88/
133
17,243
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በኮቪድ-19 ሕይወታቸው ላለፈው ሁለት ኢትዮጵያውያን ሀዘናቸውን ገለጹ
ሀገር አቀፍ ዜና
Apr 5, 2020
4,730
አዲስ አበባመጋቢት 272012ኤፍቢሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኮቪድ19 ህይወጣቸው ላለፈው ሁለት ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ለሁለቱም በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያ ቤተሰቦች እና ወዳጆች ከልብ መፅናናትን ለነፍሳቸው ዘላለማዊ እረፍትን እንዲያገኙ ተመኝተዋልዜናውን የሰማችሁ ሁሉ እንድትረጋጉ እና የወጡትን መመሪያዎች በጥብቅ እንድትከተሉ አሳስባለሁም ነው ያሉትየሚገጥመንን ሁኔታ በጋራ ለማስተናገድ በምንዘጋጅበት በዚህ ጊዜ በእምነት ፀንተን ቫይረሱ በማሀበረሰባችን መካከል እንዳይሰራጭ በትጋት ልንሰራ ያስፈልጋልም ብለዋልጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አካላዊ ርቀታችሁን ጠብቁ እጆቻችሁን በሚገባ ታጠቡበምትችሉት መንገድ ሁሉ ለሌሎች ድጋፍ አድርጉ ሲሉም አሳስበዋል
https://www.fanabc.com/%e1%8c%a0-%e1%88%9a-%e1%8b%b6-%e1%88%ad-%e1%8b%90%e1%89%a2%e1%8b%ad-%e1%89%a0%e1%8a%ae%e1%89%aa%e1%8b%b5-19-%e1%88%95%e1%8b%ad%e1%8b%88%e1%89%b3%e1%89%b8%e1%8b%8d-%e1%88%8b%e1%88%88%e1%8d%88%e1%8b%8d/
81
36,091
የኅዳሴው ግድብ ሙሊት ከሁለት ሳምንታት በኋላ ይጀመራል
ሀገር አቀፍ ዜና
June 27, 2020
Unknown
ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የሀዳሴውን ግድብ መሙላት እንደምትጀመር የውሀ መስኖና ኤሌክትሪክ ሀይል ሚኒስትር ዶር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋልትናንት የአፍሪካ ሀብረት ሊቀመንበርና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በሆኑት ሲሪል ራማፎዛ ሰብሳቢነት የተካሄደው ውይይትም ሙሊትን የማዘግየት አቅጣጫ የተያዘበት አለመሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋልየውሀ ሙሊት መጀመር የግድቡ ግንባታ ሂደት የደረሰበት ደረጃ የግድ የሚለው እንጂ ስምምነት ላይ ከመድረስ ጋር የሚገናኝ አለመሆኑንም ዶር ስለሽ አስረድተዋልምንም ልታደርገው አትችልም ግድቡ እኮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል ሚኒስትሩቅድመ ሁኔታ ደግሞ ማንም በሌላ ሏላዊ ሀገር ላይ ማስቀመጥ አይችልም በማለትም አክለዋልበአፍሪካ ሀብረት በተመራው የትናንትናው የሀዳሴ ግድብ ውይይት ላይ ከጠሚ አቢይ አህመድ ጋር ሲሳተፉ የታዩት የኢትዮጵያ የውሀ መስኖና ኤሌክትሪክ ሀይል ሚኒስትር ዶር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ያደረጉትን የስልክ ቃለ መጠይቅ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ
https://amharic.voanews.com//a/Ethiopian-minister-on-au-led-gerd-meeting-6-27-2020/5479902.html
114
33,643
ፕሪምየር ሊግ | ከሜዳቸው ውጪ የተጫወቱ ክለቦች አስደሳች ሳምንት አሳልፈዋል
ስፖርት
February 26, 2017
Unknown
ወደ ጎንደር ያቀናው ሲዳማ ቡና ፋሲል ከተማን ከድንቅ እንቅስቃሴ ጋር 31 በመርታት ደረጃውን ወደ 3ኛ ከፍ አድርጓል ሄይቲያዊው ሳውሬል ኦልሪሽ በቅጣት ምት ባስቆጠረው ጎል ሲዳማ ቡናን ቀዳሚ ሲያደርግ ናትናኤል ጋንጂላ ፋሲልን አቻ አድርጎ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል ፈጣኑ አጥቂ አዲስ ግደይ በ71ኛው ደቂቃ የይርጋለሙን ክለብ በድጋሚ መሪ ሲያደርግ ወሰኑ ማዜ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት የሲዳማን መሪነት ወደ ድልነት ያሸጋገረች ግብ አስቆጥሮ በሲዳማ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል በጨዋታው ፋሲል ከተማዎች የፍፁም ቅጣት ምት ይገባን ነበር በሚል አርቢቴር በአምላክ ተሰማ ላይ ተቃውሟቸውን አሰምተዋልወደ አርባምንጭ ያመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል አስመዝግቦ መሪነቱን አጠናክሯል ፈረሰኞቹ በሀይሉ አሰፋ ባስቆጠረው ጎል ቀዳሚ ሆነው እረፍት ሲወጡ ከእረፍት መልስ አዳነ ግርማ አከታትሎ ያስቆጠራቸው ግቦች የቅዱስ ጊዮርጊስን መሪነት ወደ 30 አስፍቶታል ታደለ መንገሻ በ89ኛው ደቂቃ የጎል ልዩነቱን ያጠበበች ግብ ቢያስቆጥርም ተቀይሮ የገባው አይቮሪያዊው አዲስ ፈራሚ ብሩኖ ኮኔ የማሳረጊያዋን ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 41 አሸናፊነት ተጠናቋል ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ስታዲየሙ በከፍተኛ ሁከትና ግርግር ታምሶ በሰዎች ላይ ጉዳት ተከስቷልአዲስ አበባ ስታድየም እንደትላንቱ ሁሉ ዛሬም በጎል ድርቅ ተመትቶ ውሏል  ከሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታዎች አንዱ የነበረው የደደቢት እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ 0900 ላይ ተካሂዶ ያለ ግብ ተጠናቋል ኢትዮጵያ በግብ ሙከራዎች የታጀበ እንቅስቃሴ ቢያደርግም የደደቢትን ጠንካራ የተከላካይ መስመር መስበር ሳይችል ቀርቷል1130 ላይ መከላከያን የጎበኘው ወላይታ ድቻም ጨዋታውን ያለ ግብ በአቻ ውጤት አጠናቋል በዋነኝነት የመከላከል እቅድን ይዘው የገቡት ድቻዎች በጨዋታው አብዛኛው ክፍል ከኳስ በስተጀርባ ሆነው ሲያሳልፉ መከላከያዎችም የተጋጣሚያቸውን የመከላከል አጥር ለመስበር ያደረጓቸው ሙከራዎች የተሳኩ መሆን ባለመቻላቸው ጨዋታውን በስድስተኛ ተከታታይ የአቻ ውጤት ለመደምደም ተገዷልበዚህም ትላንት በንግድ ባንክ እና ወልድያ እንዲሁም በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ጅማ አባ ቡና መካከል የተደረጉትነ ንጨዋታዎች ጨምሮ በሳምንቱ በተደረጉ አራቱም ጨዋታዎች የአዲስ አበባ ስታድየም ግብ ሳይስተናገድበት ተጠናቋልወደ አዲስ አበባ ተጉዞ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ አዲስ አበባ ከተማን የገጠመው ሀዋሳ ከተማ ሌላው ከሜዳው ውጪ ድል ያስመዘገበ ክለብ ነው በመጀመርያው አጋማሽ የሀዋሳ በሁለተኛው ግማሽ ደግሞ የአአ ከተማ ብልጫ የታየበትን ጨዋታ ውጤት የወሰነች ብቸኛ ግብ የተገኘችው በ69ኛው ደቂቃ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ጊት ጋትኮች በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሮ ነው የትኬት ቆራጮች ዘግይተው በመምጣታቸው ጨዋታው ከተጀመረ በኋላ ሜዳ የገባውን ተመልካች ሁለት ጊዜ እንዲወጣ ማድረጋቸው የጨዋታው ክስተት ነበር ሁኔታው ተመልካቹ እንዲጉላላ እና ጨዋታውን የመመልከት ፍላጎት እንዲያጣ ያደረገ ነበርወደ ድሬዳዋ ያመራው አዳማ ከተማ ድል ለማስመዝገብ ተቃርቦ በመጨረሻ ነጥብ ጥሎ ወጥቷል የአምናው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ታፈሰ ተስፋዬ በ5ኛው ደቂቃ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ በግርግር መሀል አስቆጥሮ አዳማ ከተማን ቀዳሚ ቢያደርግም ውጤት ለማስጠበቅ በጥልቀት ማፈግፈጋቸው የኋላ ኋላ ዋጋ አስከፍሏቸዋል በረከት ይስሀቅ መደበኛው 90 ደቂቃ ተጠናቆ በተጨማሪ ደቂቃ ያሻማው የማእዘን ምት በቀጥታ ወደ ግብነት ተቀይሮ ድሬዳዋን አቻ ማድረግ ችሏልበአጠቃላይ በ16ኛው ሳምንት የኢተዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከሜዳቸው ውጪ የተጫወቱ ክለቦች አስደሳች ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል ሀዋሳ ከተማ ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ሲያስመዘግቡ አዳማ ከተማ ጅማ አባ ቡና ወልድያ እና ወላይታ ድቻ ደግሞ ነጥብ ተጋርተዋል
https://soccerethiopia.net/football/25983
423
341
የቶኪዮ ኦሊምፒክ የጎዳና ላይ ውድድሮች ስፍራ ተቀየረ
ስፖርት
December 6, 2019
26
በ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሮች የሚካሄድባቸው ስፍራዎች መቀየር ላይ ሲነሳ የቆየው አወዛጋቢ ሀሳብ መቋጫ አግኝቷል የኳታር አለም ቻምፒዮና የማራቶን ውድድር ላይ የታየውን ክስተት ተከትሎ አለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአለም አትሌቲክስ ጋር በመሆን ውድድሩ የሚካሄድበት ስፍራ እንዲቀየር ጥያቄ ማንሳታቸው የሚታወስ ነው የቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴው በበኩሉ የውድድር ስፍራውን ከቶኪዮ ወደ ሌላ ስፍራ የማዘዋወር አላማ እንደሌለውና በሀሳቡም እንደማይስማማ ማሳወቁ ይታወሳል ትናንት በወጣው ዜና መሰረትም በውድድሮቹ ላይ የመርሀ ግብር ቅየራ መደረጉ ታውቋል በዚህም መሰረት የማራቶን እና የእርምጃ ውድድሮቹ ከቶኪዮ በ800ኪሎ ሜትር ርቀት በሆካኢዶ ተራራማ አካባቢዎች በሚገኘውና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ባለው ሳፖሮ የተባለ ከተማ የሚካሄዱ ይሆናል የውድድር ስፍራውን መቀየር ተከትሎ መርሀ ግብሮቹም ላይ ለውጥ የተደረገ ሲሆን የሴቶች ማራቶን እና በሁለቱም ፆታ የእርምጃ ውድድሮች ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳሉ የወንዶች ማራቶን ደግሞ እንደተለመደው የኦሊምፒኩ የመዝጊያ ውድድር ይሆናል ሁለቱ አለም አቀፍ ተቋማት አትሌቶችን ከጉዳት ለመጠበቅ ሀሳቡን በቅድሚያ ያነሱት ሲሆን የውድድሩ አዘጋጆች ተቃውሟቸውን ሽረው ይሁንታቸውን ለመስጠት ምክንያት የሆነው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም የአትሌቶች ማህበር መሆኑን ስካይ ስፖርት አስነብቧል ከውሳኔው ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን የሰጡት በአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የአትሌቶች ኮሚሽነር ክርስቲ ኮቬንተሪ የአትሌቶች ጤና ከሁሉ አስቀድሞ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ጠቁመዋል አያይዘውም የማራቶን እና እርምጃ ውድድሮችን ከቶኪዮ ወደ ሳፖሮ መውሰዳችንም በአትሌቶች ጉዳይ ምን አይነት አቋም እንዳለን የሚያሳይ ነው ብለዋል ወራት ብቻ የቀሩት ኦሊምፒኩ በሚካሄድበት ወቅት በጃፓኖች ዘንድ በጋ ነው በጊዜው የቶኪዮ የሙቀት መጠን ደግሞ እስከ 30ዲግሪ ሴሊሽየስ በማሻቀብ ከፍተኛ ወበቅ የሚያስከትል ይሆናል ይህ ደግሞ ረጃጅም ርቀት ለሚሸፍኑት የውድድር አይነቶች የማይስማማ በመሆኑ በኳታር ያጋጠመው እንዳይደገም ያሰጋል የውድድሩ አዘጋጆችም ሙቀቱን ለመቋቋም መጠለያዎችን በማበራከት የውሀ ማቀዝቀዣና ከፍተኛ የውሀ አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ እንዲሁም አትሌቶች ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ሙያዊ እገዛ ለማድረግ ማሰባቸውን ነበር ያሳወቁትሆኖም በአለም አቀፎቹ ተቋማት በተደረገው ግፊት የውድድር ስፍራው እንዲለወጥ ተደርጓል የቶኪዮ ኦሊምፒክ ስራ አስኪያጅ ቶሺሮ ሙቶ በሳፖሮ የሚገኘው የኦዶሪ ፓርክ ለእነዚህ ውድድሮች የተመቸ ስፍራ ነው በመሆኑም ውሳኔውን ተከትለን በፍጥነት ቦታውን በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን ኦሊምፒኩ ስምንት ወራት ብቻ ቢቀሩትም በትብብር ዝግጁ የምናደርገው ይሆናል ሲሉም ማረጋገጫ ሰጥተዋልአዲስ ዘመን አርብ ህዳር 262012 ብርሀን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=23653
301
18,225
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጭዎች ምዝገባ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jan 17, 2020
1,166
አዲስ አበባ ጥር 8 2012 ኤፍቢሲ በመላ ሀገሪቱ ለአንድ አመት ያህል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ በጎ ፈቃደኛ የዩኒቨርሲቲ እና የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎች ምዝገባ መጀመሩን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀበበጎ ፈቃዱ አገልግሎት ላይ የሚሳተፉት እድሜያቸው ከ18 እስከ 35 የሆኑ ተመራቂዎች ሲሆኑ ፍላጎቱ ያላቸው በጎ ፈቃደኞችም በየወረዳው በሚገኙ የፀጥታ ተቋማት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿልበተጨማሪም በሰላም ሚኒስቴር ድረ ገፅ ላይ ቀጥታ በመግባት መመዝገብ እንደሚችሉም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀውበዚህ በመጀመሪያው ዙር በብሄራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 10 ሺህ በጎ ፈቃደኞችን እንደሚቀበልም በሚኒስቴሩ የስትራቴጂክ አጋርነትና ተጠሪ ተቋማት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር ወይዘሮ አስማ ረዲ ገልፀዋልበጎ ፈቃደኞቹ ለሶስት ወራት በአብሮ የመኖር እሴት ተግባቦት አቅም ግንባታ እንዲሁም የአካል ብቃት ስልጠና ከወሰዱ በኋላ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማህበረሰቡን ለማገልገል ይሰማራሉም ነው ያሉትአገልግሎቱ ሀገርን ከማወቅና ህዝቦቿን ከማገልገል ባለፈ ጥሩ የስራ ልምድና የስራ እድል የሚያገኙበትን ሁኔታ እንደሚያመቻች ጠቅሰው ለስራ እድል ፈጠራው የሰላም ሚኒስቴር ከባለስርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ ተናግረዋልተመራቂ ወጣቶቹ በግብርና ጤና ግንባታ እና መሰል ዘርፎችን ጨምሮ ህብረተሰቡ አገልግሎት በሚፈልግባቸው መስኮች እንደሚሰማሩም ነው የተገለፀውበጎ ፈቃደኞቹ ስራ የሌላቸው በመሆኑም የምግብ መኖሪያ እና ሌሎች መሰረታዊ ወጪዎችን መንግስት ይሸፍናል ያሉት ዳይሬክተሯ የጤና እና የትራንስፖርት አገልግሎትንም የመንግስት ተቋማት በነፃ እንዲሰጧቸው ይመቻቻል ብለዋልለአንድ አመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሚሰጡት ወጣቶች 900 ሚሊየን ብር በጀት እንደሚመደብም አስረድተዋልበጎ ፈቃደኞቹ ካደጉበት አካባቢ ወደ ሌሎች ስፍራዎች ሄደው አገልግሎት መስጠታቸው የኢትዮጵያን ባለ ብዙ ቀለም ባህል እና እሴት እንዲረዱ በማድረግና በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን በማገዝ አለኝታነታቸውን ለማሳየት እንደሚያግዛቸው ተገልጿልበጎ ፈቃደኞቹ የማህበረሰቡን ባህል ቋንቋ እሴት እና ስርአት እንዲጋሩ እና ጥብቅ ቁርኝት እንዲፈጥሩ የተለያዩ ፕሮግራሞች ይቀረፃሉ ተብሏልበፋሲካው ታደሰ
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%89%a0%e1%8c%8e-%e1%8d%88%e1%89%83%e1%8b%b5-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8e%e1%89%b5-%e1%88%b0%e1%8c%ad%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%88%9d%e1%8b%9d%e1%8c%88%e1%89%a3-%e1%89%b0/
228
26,454
የክልል ከተሞች የመኖሪያ ቤት ፍላጎታቸውን በምዝገባ እንዲያረጋግጡ መመርያ ተሰጠ
ሀገር አቀፍ ዜና
28 January 2015
Unknown
የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የክልል ክተሞች ትክክለኛ የመኖሪያ ቤቶች ፍላጎት መኖሩን በምዝገባ እንዲያረጋግጡ መመርያ ሰጠ ሚኒስቴሩ ይህንን መመርያ የሰጠው ትላልቅ የክልል ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው የመኖሪያ ቤቶች ለመገንባት ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል ከደቡብ ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል ከተሞች የቀረበለትን ጥያቄዎች ከመረመረ በኋላ ሚኒስቴሩ ሰሞኑን ይህንን መመርያ መስጠቱን ምንጮች ገልፀዋል ሚኒስቴሩ በሰጠው አዲስ አቅጣጫ በክልል ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ፍላጎትና የመቆጠብ አቅም በምዝገባ ይረጋገጣል ምዝገባው ከተካሄደ በኋላ በተመዝጋቢዎቹ ቁጥር ልክ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሊካሄድ እንደሚችል የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ካሳሁን ጎፌ ለሪፖርተር ገልፀዋል የመኖሪያ ቤቶች ፈላጊዎች ቁጥር በትክክል ካልታወቀ ግንባታ ማካሄድ አይቻልም የሚሉት አቶ ካሳሁን ከዚህ ቀደም በክልሎች የኮንዶሚኒየም ግንባታ ተካሂዶ ተጠቃሚ መጥፋቱን በማስታወስ ይህ አዲስ መመርያ መሰጠቱን አስረድተዋል በአሁኑ ወቅት አራቱም የመኖሪያ ቤቶች ፕሮግራም እየተካሄዱ ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ እንደሆነ ይታወቃል ነገር ግን በ1996 አም በአዲስ አበባ ከተማ የኮንዶሚየም ቤቶች ግንባታ መካሄድ ከጀመረ በኋላ የክልል መንግስታት በዋና ዋና ከተሞች የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንዲካሄድ አድርገዋል ነገር ግን ተጠቃሚ ባለመኖሩ ቤቶቹ ቆመው ቀርተዋል ነገር ግን ከቆይታ በኋላ የመኖሪያ ቤቶች ፍላጎት በድጋሚ በመቅረቡ የክልል ከተሞች የግንባታ ጥያቄ ለማቅረብ መገደዳቸው ታውቋል ከዚህ በተጨማሪም በክልሎች የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች በማሀበር ተደራጅተው የመኖሪያ ቤቶች እንዲገነቡ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑን አቶ ካሳሁን ገልፀዋል የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሀይሌ ባለፈው ሳምንት ለአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ባደረጉት ንግግር የከተማው አስተዳደር ለመንግስት ሰራተኞች የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ማካሄድ የሚቻልበትን መንገድ ማመቻቸት ይኖርበታል ብለዋል
https://www.ethiopianreporter.com/article/2529
224
10,396
ሰኔ ውስጥ በኢትዮጵያ የፀሐይ ግርዶሽ ይከሰታል፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
May 7, 2020
345
ባህር ዳር ሚያዝያ 292012 አም አብመድ በኢትዮጵያ ፓኪስታን ህንድ እና ማእከላዊ አፍሪካ ሰኔ 14 ቀን 2012 አም ቀለበታዊ የፀሀይ ግርዶሽ እንደሚከሰት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀበኢትዮጵያ የፀሀይ ግርዶሹ ከምእራብ እስከ ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በተለይም በላልይበላ አካባቢ ከጠዋቱ 1245 እስከ ቀኑ 633 እንደሚቆይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሰሎሞን በላይ ዶክተር ገልፀዋልእንደ ኢብኮ ዘገባ በእለቱም ከረፋዱ 340 አካባቢ ለተወሰኑ ሴኮንዶች ጨለማ እንደሚፈጠርም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል
https://www.amharaweb.com/%e1%88%b0%e1%8a%94-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8d%80%e1%88%90%e1%8b%ad-%e1%8c%8d%e1%88%ad%e1%8b%b6%e1%88%bd-%e1%8b%ad%e1%8a%a8/
64
44,818
የኬንያ ተቃዋሚ ፓርላማ አባላት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የጠሩትን ስብሰባ ተቃወሙ
ፖለቲካ
September 13, 2017
Unknown
የኬንያ የተቃዋሚ የፓርላማ አባላት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አዲሱን ፓርላማ መክፈታቸውን ተቃወሙፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የጠሩትን የፓርላማ አባላት  ስብሰባ ጥሪ  ተከትሎ አብዛኞቹ  የአደሱ ፓርላማ አባላት ስብሰባን አልታደሙም ተብሏልየኬንያ ጠቅላይ  ፍርድ ቤት ከወር በፊት በሀገሪቱ የተካሄደውን ምርጫ ውድቅ በማድረጉ ዳግም ምርጫ  በመጭው ጥቅምት ወር ላይ እንዲካሄድ ወሰኗልየፍርድ ቤቱ ውሳኔ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት ያልተለመደ እና ኬንያዊያን ያልጠበቁት ለአሸናፊው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታም ቢሆን እፎይታን ያልሰጠ ነበርእንዲያውም ፕሬዝዳንት ኡሁሩ እንዳሉት ዳግም በምርጫ ካሸነፉ የሀገሪቱን የፍርድ ቤት አደረጃጀት እንደሚያስተካክሉም ከውሳኔው በኋላ ተናግረዋልአሁን ደግሞ የኬንያ የተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ  የህዝብ ተወካይዮች  ምክር ቤት አባላትን መሰብሰባቸው ተገቢ አይደለም ብለዋልየተቃዋሚ አባላቱን ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸው  ነጥብ ደግሞ በሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት  ዳግም ምርጫ ሳይደረግ ፕሬዝዳቱ ፓርላማውን የመሰብሰብ ስልጣን ተገቢ አይደለም ብለዋልፕሬዚዳንቱ በጠሩት የፓርላማው ስብሰባ ላይ የተቃዋሚ የፓርላማ አባላት እንደማይገኙ አስታውቀዋልይልቁንም የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ተቀናቃኝ የሆኑትን የራይላ ኦዴንጋን የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ነውተቃዋሚ የፓርላማ አባላት ይህን ማለታቸውን ተከትሎ ግን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ እንዳሉት የትኛውም የተቃዋሚ አባል በፓርላማው መክፈቻ ላይ አለመገኘታቸው ስብሰባውን ከማካሄድ እንደማይቆጠቡ ገልፀዋልእሳቸው የሚመሩት የጁቢሊ ፓርቲ አብላጫ የፓርላማ መቀመጫ ስላለው ስበሰባውን ማድረግ እንደሚችሉም አንስተዋልኬንያታ አክለውም አሁንም ስልጣን ላይ ነኝ ስለሆነም በየትኛውም ጊዜ ፓርላማው እንዲሰበሰብ የማድረግ ስልጣኑ አለኝ ብለዋልፕሬዝዳንቱ አዲስ መንግስት በዚህች ሀገር ላይ እስካልተሰየመ ድረስ በህገ መንግስታዊ ስርአቱ መሰረት ፓርላማውን የመሰብሰብ ሀላፊነት አለኝም ነው ያሉትእሳቸው አሁን ያካሄዱት የፓርላማ ስብሰባ አንድ ብቻ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የተሳተፈበት እና አመዛኙ ተቃዋሚዎች ግን ያልታደሙበት ነው ተብሏልባሳለፍነው ነሀሴ ወር ፕሬዝዳንት ኬንያታ የሀገሪቱን ጠቅላላ ምርጫ ሀምሳ አራት በመቶ በማግኘት ማሸነፋቸው ተገልፆ ነበረ ይሁን እንጅ ምርጫው ትክክለኛ ሂደቱን አልጠበቀም መባሉን ተከትሎ የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲደገም ወስኗልየሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀጣይ ሳምንት መጨረሻ በፁሁፍ የተደገፈ ማስረጃ በማቅረብ የፕሬዝዳንት ኡሁሩን ማሸነፍ ውድቅ እንዳደረገ እንደሚያስታውቅ ገልጧልየፕሬዝዳት ኡሁሩ ተቀናቃኝ ራይላ ኦዲንጋ ይህ ምርጫ እንዲጭበረበር እጃቸውን ያስገቡ የመንግስት ባለስልጣናት ከስልጣናቸው እንዲወገዱ እስካልተደረገ ድረስ በሀገሪቱ የሚካሄደውን ዳግም ምርጫ ደጋፊዎቻቸው እንዲቃዎሙ መልእክት እያስተላለፉ ነው ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው
https://waltainfo.com/am/33038/
286
21,910
የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትብብርና ውጥረት ውስጥ ያለችው የኢትዮጵያ ሚና
ፖለቲካ
6 March 2019
Unknown
የአፍሪካ ሀብረት ከተቋቋመበት ጊዜ ቀደም ብለው በነበሩ አመታት ከቅኝ ግዛት ነፃ የወጡ የአፍሪካ አገሮች ዋነኛ ትኩረት የነበረው አሀጉራዊ ውህደትን ማምጣት ነበር ይሁን እንጂ በወቅቱ ከኢኮኖሚያዊ ውህደትና ከፖለቲካ ውህደት የትኛው ይቅደም በሚለው አታካራ ወደ አንድ መምጣት አቅቷቸው በጎራ በመከፋፈል ወደ ፉክክርና ክርክር ገብተው ነበርሆኖም በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የነበሩት ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ባመጡት አስታራቂ ሀሳብ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የዛሬው የአፍሪካ ሀብረት ሊመሰረት ችሏል ነገር ግን የዚህ አሀጉራዊ ድርጅት መቋቋምና ከ50 በላይ የአፍሪካ አገሮችን በአባልነት ማቀፍ ለ56 አመታት ቢዘልቅም ይኼ አላማ ከግብ አኳያ ጠብ ያለ ነገር አላመጣምይኼ የሀብረት ፕሮጀክት በግዝፈቱ ሊገፋ ባለመቻሉም ቀጣናዊ ውህደት ላይ ወደ ማተኮር የተዞረ ሲሆን ይኼም በሂደት አሀጉራዊ ውህደቱን እውን ለማድረግ ያግዛል የሚል እምነት ተጥሎበታል በዚህ ተነሳሽነትም የተለያዩ የአፍሪካ አገሮች በቀጣናቸው ኢኮኖሚያዊ ውህደት ላይ በማተኮር የተለያዩ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማሀበረሰብ መስርተዋል ከእነዚህም መካከል የምእራብ አፍሪካ አገሮች የኢኮኖሚ ማሀበረሰብ ኤኮዋስ የደቡባዊ አፍሪካ አገሮች የልማት ማሀበረሰብ ሳድክ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ አገሮች የጋራ ገበያ ኮሜሳ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት  ድርጅት ኢጋድ የአረብ ማግርብ ሀብረት የሳህል ሰሀራ አገሮች ማሀበረሰብና የምስራቅ አፍሪካ ማሀበረሰብ የሚጠቀሱ ሲሆን እነዚህም በትልቁ ለሚታሰበው አሀጉራዊ ውህደት ድምር ውጤት ግብአት ይሆናሉ ተብለው ይጠበቃሉይኼንን ቀጣናዊም ሆነ አሀጉራዊ ውህደት እንደ መርህና አስፈላጊ አቅጣጫ መቀበል ላይ በሁሉም የአፍሪካ አገሮች እምብዛም መለሳለስ የማይታይ ሲሆን እንዲያውም ውህደቱን ለማቀላጠፍ ያግዛል በሚል እሳቤ አንድ አፍሪካዊ ፓስፖርት እስከ ማዘጋጀት ተደርሷል በዚህ የውህደት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ቀጣናዊ ውህደቶችን ደግሞ በቀዳሚነት የሚያንቀሳቅሱ አገሮች ያሉ ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ለዚህ ህልም እውን መሆን ከፍተኛ ሚናና አስተዋፅኦ በማድረግ ረገድ ኢትዮጵያ ትጠቀሳለችኢትዮጵያ በአገር ውስጥ በምታደርጋቸው የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች የቀጣና ውህደትን የምታገናዝብ ሲሆን ካሁን ቀዳም የተደረጉ የኤሌክትሪክ ሀይልና የትራንስፖርት ኢንቨስትመንቶች ተጠቃሽ ናቸው ለዚህም በተለያዩ ጊዜያት የመጡ የአፍሪካ መሪዎች ጉልህ አስተዋፅኦ ማድረጋቸው ይወሳልየቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የአፍሪካ ሀብረትን አጀንዳ በመቅረፅ ረገድና ቀጣናዊ ውህደትን በማቀንቀን ረገድ ቀዳሚ እንደነበሩ የተለያዩ ሰነዶች ያስረዳሉ በተለይ የሀይል ዲፕሎማሲ በመባል የሚታወቀውና በርካታ የምስራቅ አፍሪካ አገሮች በኤክትሪክ ሀይል ከኢትዮጵያ ጋር ማስተሳሰር ዋነኛ ግባቸው እንደነበር እሳቸው በ2005 አም ሲያርፉ አልጄዚራ ያስነበበው ፅሁፍ ያወሳል ይሁንና በእሳቸው ማረፍ ምክንያት የዚህ ግብ ህልውና ጥያቄ ውስጥ ይገባል በማለት ይደመድማልሆኖም በእሳቸው ቦታ የተተኩት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለ ማርያም ደሳለኝ ተመሳሳይ ትልም የነበራቸው ሲሆን በእሳቸው ጊዜ ፍላጎቶች የተግባር ገፅታን የተላበሱበት ነበር በአቶ ሀይለ ማርያም የስልጣን ዘመን የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር መስመር መዘርጋትና የኢትዮ ኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል መስመር መጠናቀቅ የቀጣናዊ ውህደትን አንድ እርምጃ ወደፊት የወሰደ ነበር ተብሎ ይጠቀሳልኢትዮጵያን ከሱዳን ከጂቡቲ ከኬንያ ከደቡብ ሱዳንና ከሶማሊያ ጋር የሚያገናኙ መንገዶችም ተገንብተዋልይኼ በተከታታይ በሁለት መሪዎች ተቀባይነትን አግኝቶ ትኩረት ተሰጥቶት ተግባራዊ ሲሆን የቆየው የቀጣናዊ ውህደት ፌዴሬሽኑ ከተመሰረተ አንስቶ ሶስተኛ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት አብይ አህመድ ዶር ቀዳሚ አጀንዳ እንደሆነም ማስተዋል አያዳግትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ባደረጓቸው ንግግሮች ኢትዮጵያውያን እንኳን ለአገሪቱ ለአሀጉሪቱም የመብቃት ሀላፊነት በጫንቃቸው ላይ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ሲገልፁ ተደምጠዋል ከዚህ አልፎም የስልጣን ዘመናቸው የመጀመርያ የውጭ አገር ጉብኝት መዳረሻ ያደረጓቸውም የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ሲሆኑ በእነዚህ አገሮች ተደጋጋሚ ጉብኝቶችንም ሲያደርጉ ቆይተዋል በተጨማሪም የቀጣናዊ አገሮች መሪዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ በመጋበዝ የሱዳን የኬንያ የጂቡቲ የደቡብ ሱዳንና የሶማሊያ ፕሬዚዳንቶች አገሪቱን እንዲጎበኙ ተደርጓል ነገር ግን ካሁን ቀደም በየትኞቹም መሪዎች ከቃል ንግግር ያላለፈ የነበረውን የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላም ስምምነት እውን ማድረግ መቻላቸው ለቀጣናዊ ውህደቱ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ታላቅ እርምጃ እንዲሆን እየተጠቀሰ ይወደሳሉከኤርትራ ጋር ከተደረገው የሰላም ስምምነት በኋላ የሁለቱ አገሮች መሪዎች ተደጋጋሚ ጉበኝቶችን ያደረጉ ሲሆን በተገናኙባቸው አጋጣሚዎችም የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ይጎበኙም ነበር ከእነዚህ መከከል ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ዞንን መጎብኝታቸውና ከሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አል በሽር ጋር በመሆን የጂማን ኢንዱስትሪ ፓርክ ማስመረቃቸው የሚጠቀስ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም በኤርትራ ጉብኝታቸው የሎጎና የምሰላም ግድብ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋልበተመሳሳይ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2011 አም በኢትዮጵያ በነበራቸው የስራ ጉብኝት የሀዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክን ከመጎብኘት ባለፈ የደብረ ብርሀን የኢንዱስትሪ ፓርክን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በመሆን አስመርቀዋልከዚህ መልስም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመያያዝ በኤርትራ አስመራ ጉብኝት አድርገዋል ከጉብኝቱ በኋላም ሶስቱ አገሮች በቀጣናቸው ውህደትና በወቅታዊ አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር አስታውቋልከኬንያ ፕሬዚዳንት ኬንያታ ጋር አስመራ ከተለያዩ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፕሬዚዳንት ኢሳያስን ይዘው ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ በማቅናት በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ዙሪያና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትብብርን ከግብ ለማድረስ በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው በጋራ ባወጡት መግለጫ ተጠቅሷልበቀጣናዊ በተለይም ኢትዮጵያ ከሚያዋስኗት ኬንያ ሱዳን ኤርትራ ሶማሊያና ጂቡቲ ጋር የታቀደው ኢኮኖሚያዊ ውህደት ከተሳካ ለሁሉም ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር በአለም አቀፍ ገበያዎች ውስጥ የላቀ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ያስችላል የሚሉ በርካቶች ናቸው የስድስቱ ጎረቤት አገሮች ጠቅላላ አገራዊ ምርት እኤአ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ሲሆን ጠቅላላ የህዝብ ብዛታቸው ደግሞ 250 ሚሊዮን ገደማ እንደሚሆን የአለም ባንክ መረጃዎች ያሳያሉ ይኼም ትልቅ የገበያና የሰው ሀይል አቅርቦት እድል ሊሆን የሚችል ሀብት ነው ሲሉም ባለሙያዎች ይመለከታሏገሮቹ ያሉበት ቀጣናዊ አቀማመጥም ለአለም አቀፍ የንግድ ግንኙነትም ተመራጭ ያደርጋቸዋል ሲሉ ከውህደቱ ጋር ተያይዘው ስለሚመጡ እድሎች ያስረዳሉይኼ የኢኮኖሚ ውህደት በተደጋጋሚ ሲነሳ የቆየና በሁሉም የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና አገሮች ተቀባይነት ያለው ሀሳብ ቢሆንም ፈተናዎች የተደቀኑበት እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉየመጀመርያው ጉዳይ በሁሉም የቀጣናው አገሮች ያለው ከፍተኛ ድህነትና የመልካም አስተዳዳር እጦት እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጀት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ያስገነዝባል ይኼንንም ፈተና ለማሸነፍ በአገሮች መካከል ትብብር እንዲኖር ማድረግና የልማት ትብብሮችን ማስፋት አስፈላጊ እንደሆነ ያስረዳልበመቀጠልም ከመጀመርያው ጋር ተያያዥነት ያለው የብጥብጥና የደሀንነት ስጋት ፈተና ሲሆን በርካታ የቀጣናው አገሮች የፖለቲካ ግጭቶች ያሉባቸውና የደሀንነት ስጋቶች የተደቀኑባቸው ናቸው ሶማሊያ በአልሸባብ ሽብር ከሳምንት ሳምንት የምትናጥ ኬንያ የሽብር ጥቃቶች እየደጋገሙ የሚጎበኟት ሱዳን የፖለቲካ አለመረጋጋት የነገሰባት ኤርትራ አምባገነን የሆነ ስርአት አላት በሚል ሰበብ ከአለም አቀፉ ማሀበረሰብ የራቀች ደቡብ ሱዳን በእርስ በርስ ጦርነት የምትናጥ ናት በዚህም ምክንያት ፈተናው ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደቱን ህልም ሆኖ እንዲቀር ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚያስብል ነው ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ ከአንድ አመት በፊት ለተከታታይ ሶስት አመታት ሲያምሳት ከነበረው የተቃውሞ ፖለቲካ ትኩሳት ያልቀዘቀዘች መሆኗ እንዲሁም ጉልህ ውስጣዊ ችግሮችን አቅፋ ያለች አገር መሆኗ ለውህደት እንደ ካሁን ቀደሙ ፊታውራሪ እንዳትሆን አደናቃፊ ይሆንባታልም ይባላልእያደር የሚያገረሸው የተቃውሞ ፖለቲካ ብሎም በአገራዊ ማንነት ላይ እየተነሱ ላሉ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት አለመቻሉ በአንዳንዶች ዘንድ የራስን ጥሎ የሰው አንጠልጥሎ እያስባለ ይገኛል የአገር ውስጡን ማጥራት ለውጭው ጥረት ተጨማሪ ግብአት ይሆናልና ከቀጣናዊ ውህደቱ በፊት ይኼኛው ይቅደም ባዮችም አልጠፉም ይኼ ካልሆነ በአገር ውስጥ እያደገ የመጣው የብሄር ተኮር ፖለቲካና የጎጥ አስተሳሰብ እንኳን ለአገሪቱ ለቀጣናውም ስጋት ሊሆን ይችላል ሲሉም ያስጠነቅቃሉበተያያዘም የደሀንነት ስጋት ዋነኛው የቀጣናው የኢኮኖሚ ውህደት እንቅፋት እንደሆነ ኬንያንና ኢትዮጵያን በምሳሌነት በመውሰድ የኢኮኖሚ ውህደትን ያጠኑት አቶ ዳዊት አያሌው በፅሁፋቸው አስፍረዋል የኢትዮጵያም ሆነ የኬንያ የጋራ ስጋቶች ጦርነት አመፅና ግጭት ናቸው በማለት እነዚህን ለመቋቋም ኬንያና ኢትዮጵያ የተሻለ የውህደት ጥረቶችን ማድረጋቸውን ያወሳሉበፕሬዚዳንት ኬንያታ የኢትዮጵያ ጉብኝት ወቅት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በነበረ የጋራ የቢዝነስና የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሁለቱን አገሮች ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማቀላጠፍ እንዲረዳ በሞያሌ የጋራ ገበያና የድንበር ላይ ንግድ እንደሚኖር እንዲሁም የኬንያን የላሙ ወደብ በጋራ ማልማት እንደታሰበ ገልፀው ነበር ፕሬዚዳንት ኬንያታ ተመሳሳይ ልማቶች እንደሚኖሩ ተናግረዋልሆኖም የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ቀጣናዊ ውህደት ትልም የምእራብ አፍሪካ አገሮችን ያህል የጋራ መገበያያ ገንዘብን በመጠቀም ረገድ እንኳን አንድ እርምጃ አልተራመደመ ምንም እንኳ አሀጉራዊ የኢኮኖሚ ውህደቱ ብዙ የሚቀረው ቢሆንምያም ሆነ ይህ ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ ፖለቲካ ተወጥራ ሳለች አሀጉራዊና ቀጣናዊ ውህደቱን በብቃት ለመምራት ያዳግታታል ከማለት ባለፈ ለአገር ውስጥ ችግር ቅድሚያ መስጠት ካልተቻለ ከፈረሱ ጋሪውን ማስቀደም ይሆናል ሲሉም የሚተቹ አሉ
https://www.ethiopianreporter.com/article/14975
1,054
17,539
ጠ/ሚ ዐቢይ ከሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
Mar 11, 2020
1,062
አዲስ አበባ መጋቢት 2 2012 ኤፍቢሲ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሰአት ከሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋልየሀገር ሽማግሌዎቹ መንግስት የሚያካሂደውን የለውጥ ስራዎች በመደገፍ በፅናት ለመቆም ያላቸው አቋም የሚደነቅ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋልጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የበረከት ደጅ መክፈቻ ነው ሲሉም ጠቁመዋልጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ከህዝብ ተወካዮችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነውትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.fanabc.com/%e1%8c%a0-%e1%88%9a-%e1%8b%90%e1%89%a2%e1%8b%ad-%e1%8a%a8%e1%88%b2%e1%8b%b3%e1%88%9b-%e1%8b%a8%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%88%bd%e1%88%9b%e1%8c%8d%e1%88%8c%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8c%8b%e1%88%ad/
75
46,671
ኢትዮጵያ ለታንዛኒያ 400 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ልትሸጥ ነው
ቢዝነስ
August 27, 2016
Unknown
ኢትዮጵያ ለታንዛኒያ 400 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ልታደርግ ነውየኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አዜብ አስናቀ እንደገለፁት ሁለቱ አገሮች የሽያጭ ስምምነቱን በሚቀጥሉት ሳምንታት ያከናውናሉኢትዮጵያ ለታንዛኒያ የምታቀርበው የኤሌክትሪክ ሀይል በኬንያ በኩል የሚያልፍ በመሆኑ በኬንያና ታንዛንያ መካከል የሚደረግ ስምምነትም እንዳለ ተናግረዋልከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል ገዝተው መጠቀም የጀመሩት ሱዳን ጅቡቲና ኬንያም ተጨማሪ ሀይል መጠየቃቸውን ነው ኢንጅነር አዜብ የገለፁትአገራቱ ከውድና አካባቢን ከሚጎዳ የሀይል አጠቃቀም ይልቅ ኢትዮጵያ የምታመርተውን ታዳሽ ሀይል ለመጠቀም ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ መሆኑንም ጠቁመዋልበቀጣይ ሀገራቱ የጠየቁትን የሀይል ፍላጎት ለማቅረብ ተጨማሪ መስመሮችና የማከፋፈያ ጣቢያዎችን ለመስራት ጥናት እየተደረገ መሆኑንም ነው ያብራሩት200 ሜጋ ዋት ሀይል ፍላጎት ላላት ኬንያ ሀይል ለመስጠት የመስመርና የማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት ተፈርሞ ወደ ስራ ተገብቷልኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት እያቀረበች ያለችው የኤሌክትሪክ ሀይል የአገራቱን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በማጠናከርና የልማት ትስስሩን በማፋጠን ላይ ይገኛልግንባታው በቅርቡ የተጠናቀቀውና 1 ሺህ 870 ሜጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው ጊቤ ሶስት ሀይል ማመንጫ አሁን ላይ 900 ሜጋ ዋት እያመነጨ ነውበአሁኑ ወቅት ጊቤ ሶስትን ጨምሮ በአገሪቱ ያሉት ግድቦች የሚያመነጭቱን አቅም ለመጠቀም የሚያስችል የሀይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ጣበያዎችን አቅም የማሳደግና አዲስ የመዘርጋት ስራ በመከናወን ላይ ይገኛልታላቁን የህዳሴ ግድብ ጨምሮ በግንባታ ላይ ያሉ ሌሎች ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ኢትዮጵያ ለሌሎች አገራት የምታቀርበው ሀይል እንደሚጨምር ይጠበቃልኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ ባሻገር ሯንዳና ቡሩንዲ ለመሳሰሉ በጣም ውድና ታዳሽ ያልሆነ ሀይል ለሚጠቀሙ አገራት እንዲሁም ለሰሜን አፍሪካ መካከለኛው ምስራቅና አውሮፓ የማቅረቡ እቅድ አላትታንዛንያ ከጅቡቲ ሱዳንና ኬንያ በመቀጠል ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል የምታገኝ አራተኛዋ አገር ትሆናለችኢዜአ
https://waltainfo.com/am/22840/
214
206
አትሌቶች ፈታኙን ጊዜ እንዴትይወጡታል?
ስፖርት
April 13, 2020
38
በአትሌቲክስ ስፖርት ዝና እና ክብሯን የገነባችው ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችንም አግኝታበታለች ስፖርቱ አንድ የስራ ዘርፍ በመሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት አትሌቶችን ያቅፋል አትሌቶችም በአለም አቀፍ ውድድሮች ሲሳተፉ ከውጤት ባሻገር የውጭ ምንዛሪን በማስገኘት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ያግዛሉ በሚያፈሱት መዋእለ ነዋይም ለበርካቶች የስራ እድል ፈጥረዋል እንደሚታወቀው በዚህ ወቅት ይህ ዘርፍ እንደሌሎች ስፖርቶች ሁሉ ለውድድር ዝግ ሆኗል ማልዶ ለልምምድ ይወጣ የነበረውና በአመት ውስጥ ተደጋጋሚ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበረው እረፍት የለሽ አትሌትም ከተላላፊው ቫይረስ ጋር ተያይዞ ከቤት ውሏል በብሄራዊ ቡድን የተያዙ በተለያዩ ክለቦች የተካተቱ እንዲሁም የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ተቋማት ሰልጣኝ የሆኑ አትሌቶችም እንዲበተኑ ተደርጓል በግላቸው የሚሰለጥኑትም ቢሆን እንደ ቀድሞው ከመኖሪያቸው ርቀው የማይጓዙበት ሁኔታ ተጋርጦባቸዋል ለአንድ አመት የተራዘመውን ኦሊምፒክ ጨምሮ በሌሎች አለም አቀፍ ቻምፒዮናዎች ላይ ተሳታፊ ለመሆን በብሄራዊ ቡድን የተካተቱ አትሌቶች ደግሞ ከሌሎች በተለየ ሁለት አማራጮችን ያስተናግዳሉ የመጀመሪያው ለተላላፊው የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ላለመሆን በሚደረገው የቤት ውስጥ ቆይታ ከልምምድ በመራቃቸው የአቋም መውረድን ማስተናገድ ነው ሌላኛው ደግሞ የውድድሮችን መራዘም እንደ መልካም እድል በመጠቀም በተደጋጋሚ ውድድር ላይ ያሳለፉ አትሌቶች እንደ ማገገሚያ ጊዜ በመመልከት በተሻለ ብቃት ለመመለስ የራሳቸውን ጥረት ማድረግ ነው በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ስፖርተኞች ከስፖርቱ ላለመራቅ ምን ማድረግ አለባቸው ፌዴሬሽኑስ ሚናውን በምን መልኩ እየተወጣ ነው ለሚለው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ህክምና ከፍተኛ ባለሙያና እና የፀረ አበረታች ቅመሞች ተጠሪዋ ቅድስት ታደሰ ከአዲስ ዘመን ጋር ቆይታ አድርገዋል የመጀመሪያው ነገር ስነልቦና መሆኑን ባለሙያዋ ይገልፃሉበአለምና በሀገር በመጣው በዚህ ቫይረስ ምክንያት በቤታቸው እስኪቆዩ ድረስ ኦሊምፒክን ጨምሮ ለዚህ የውድድር ወቅት በዝግጅት ላይ የነበሩ አትሌቶች በጥሩ አቋም ላይ ነበሩ በዚህም ምክንያት አቋማቸው እንዳይወርድና ጂምናዚየሞችም በመዘጋታቸው በቤት ውስጥ የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ይገደዳሉ ከትንፋሽ ጋር በተያያዘ ያለውን ደግሞ የሰዎች ንክኪ በሌለበት በግላቸው ጫካ አካባቢ መስራት ይችላሉ ይህም ወቅታዊ ብቃታቸው እንዳይወርድ እንጂ ለውድድር በሚደረግ ልክ አይሆንም ይህ እንዲሆን ደግሞ አስቀድሞ እንደተገለፀው ዋናው ነገር በመልካም ስነልቦና ላይ መገኘት መሆኑን ይጠቁማሉ በማብራሪያቸውም የሰው ልጅ በተፈጥሮው በጭንቀት ወቅት ሰውነቱ በሚሰጠው ግብረመልስ የተለያዩ ቅመሞችን ስለሚያመነጭ ለውጥረትና ለመደበት ስሜት ይጋለጣል አትሌትሌቲክስ የሙሉ ጊዜ ስራው የሆነው አትሌትም ውድድሮች ከሌሉ በእንዲህ አይነቱ ሁኔታ ውስጥ ሊገባ ይችላል ይህ እንዳይከሰትም አትሌቶች ራሳቸውን በስነልቦና ማዘጋጀት ይገባቸዋል ሲሉ ያስረዳሉ ባለሙያዋ ሁኔታዎችን አእምሮ ሲቀበል ሌሎች አካላትን ማዘዝ ስለሚቻል ስነልቦና የመጀመሪያውና ዋነኛው ጉዳይ ነው ከዚህ ባሻገር በአትሌቲክስ ስፖርት የሚፈራው ነገር ክብደት መጨመር ነው በክብደት ተወስነው እንደሚካሄዱት የቦክስና የማርሻል አርት ስፖርቶች ሁሉ የረጅም ርቀት በአትሌቲክስም ክብደት መጨመር የራሱ አደጋ ይኖረዋል በመሆኑም የቡድን እና ጫና ያላቸውን ልምምዶችን በማስቀረት ሰውነትን ባለበት እንዲቆይና የብቃት መዋዠቅ እንዳይከተል የሚያደርግ መሆን እንዳለበት ባለሙያዋ ያስገነዝባሉ አመጋገብ ላይም አትሌቶች የራሳቸውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል አመጋገብ ከሚወጣው ሀይል ጋር ተመጣጣኝ መሆን ይኖርበታል በዚህ ወቅት ቀለል ያሉ ልምምዶችን እየሰሩ እንደ ወትሯቸው የሚመገቡ ከሆነ ግን ሰውነት ያንን ለማስተናገድ ስለሚከብደው የክብደት መጨመር ይከሰታል በመሆኑም ይህንን መከታተልና ከቻሉ በየእለቱ ያሉበትን ሁኔታ በመመዝገብ ማስታወሻ እንዲይዙ ይመከራል የአለም አትሌቲክስም በየወቅቱ የሚያወጣውን መረጃ መከታተልም አስፈላጊ ነው በዚህ ሂደት ሊዘነጋ የማይገባው ዋናው ነገር በቤት ውስጥ የሚሰሩ ማሳሳቢያዎችና ሌሎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ንፁህ አየር ባለበት ስፍራ መሆኑን ማረጋገጥ ነው ሰው የማይበዛበትና ነፋሻማ አየር ባለበት ስፍራ ቢንቀሳቀሱ ደግሞ የተሻለ ይሆናል እንደ አለም አትሌቲክስ መረጃ ከሆነ አትሌቶች በተለይም የረጅም ርቀት ሯጮች ትንፋሻቸው የዳበረ በመሆኑ ከሌላው በተለየ ተጋላጭነታቸው የሰፋ ይሆናል በመሆኑም ራሳቸውን ለየት ባለመልኩ መጠበቅ ይኖርባቸዋል ፈሳሽ በብዛት መውሰድና በሽታን ሊቋቋሙ የሚችሉ ምግቦችንም ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ሁኔታ ማዘውተርና በአለም የጤና ድርጅት እንዲሁም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ከመሳሰሉ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎችን መከታተል ለአትሌቱ ጠቃሚም ነው ምክንያቱም አብዛኛው የማህበራዊ ትስስር ገፆችን የሚጠቀም እንደመሆኑ መረጃዎችን የሚያገኙበት መንገድ በራሱ ጎጂ ሊሆን ይችላል ይህንንና መሰል ግንዛቤዎችን ከማስጨበጥ አንፃር ባለሙያዎች አትሌቱን በአካል ለማግኘት አዳጋች በመሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለያዩ ስራዎችን እንደጀመረም ባለሙያዋ ይጠቁማሉ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ባደረጉት ውይይት አትሌቱ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ክልሎችም የሚገኝ እንደመሆኑ ሁሉንም ተደራሽ ለማድረግ በቴሌቪዥንና በሬዲዮኖች መልእክቶችን ማስተላለፍ የተሻለ አማራጭ ሆኖ አግኝቶታል በመሆኑም ሰፊ ሽፋን ካላቸውና ከክልል የመገናኛ ብዙሀን ጋር በመተባበር አትሌቱ ልምምዱን እንዴትና በምን ሁኔታ መስራት እንዳለበት በባለሙያዎች ግንዛቤ የሚሰጥ ይሆናል ከዚህ ባሻገር ከወቅታዊው ሁኔታና ከቫይረሱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ስነ ምግብ ስፖርታዊ ስነልቦና የስፖርት ህክምና የመረጃ ክትትል ምን መምሰል አለበት የሚሉና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ነባራዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ ለአትሌቱ እንዲደርስ ይደረጋል በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ ግን መዘንጋት የሌለበት ዋነኛ ጉዳይ አበረታች ቅመም መሆኑን ያሳስባሉ ይህንን ግንዛቤ የሚሰጡትም በስፖርቱ ላይ ለረጅም ጊዜ ያሳለፉ ባለሙያዎች እና ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች ላይ ስኬታማ የሆኑ አንጋፋና ተምሳሌት አትሌቶች ሲሆኑ መልእክቶችን ምክሮችንና በተግባር የታገዙ እንቅስቃሴዎችንም ለአትሌቶች የሚያስተላልፉ ይሆናል ከፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ከስልጠና ጥናትና ምርምር ክፍል ጋር በመሆንም በተለያዩ የማህበራዊ ገፆች መልእክቶችን ለማስተላለፍም በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ባለሙያዋ ጨምረው ገልፀዋል አዲስ ዘመን ሚያዝያ 5 2012 ብርሀን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=30273
674
44,074
በሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቭላድሚር ፑቲን አሸነፉ
ፖለቲካ
March 19, 2018
Unknown
በሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቭላድሚር ፑቲን በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋልቀድሞውንም ቢሆን የአሸናፊነቱን ቅድመ ግምት ያገኙት  ፑቲን ሩሲያን ለቀጣዮቹ 6 አመታት ይመራሉ76 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ በማግኘት ዳግም መመረጥ የቻሉት ፑቲን ከአውሮፓዊያኑ 1999 ጀምሮ ሩሲያን በፕሬዚዳንትነት እና በጠቅላይ ሚኒስትርነት መርተዋልየፕሬዚዳንት ፑቲን ዋነኛ የምርጫ ተፎካካሪ የነበሩት አሌክሲ ናቫሊ ከምርጫ ውድድሩ መታገዳቸው ይታወሳልበምርጫ ቅስቀሳው ወቅት ፑቲን በሞስኮ ባደረጉት ንግግር መራጮች ሩሲያ ባለፉት ያስመዘገበችውን ስኬቶች ልብ እንዲሏቸው ጠይቀውም ነበርከውጤቱ ይፋ መደረግ በኋላ በቀጣዩ ምርጫ ይሳተፉ እንደሆን ተጠይቀው ሲመልሱ ለ100 አመታት በስልጣን መቆየትን የምፈልግ እንዳይመስላችሁ ብለዋልቢቢሲ
https://waltainfo.com/am/33807/
78
9,784
“ከመስከረም 30 በኋላ መንግሥት የለም እያሉ ለሚያወዛግቡ ኃይሎች የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ቦታ እንደማይሰጡ ርእሰ መሥተዳድሩ አስታወቁ።
ሀገር አቀፍ ዜና
October 1, 2020
102
ባህር ዳር መስከረም 212013አም አብመድ የክልሉ የፀጥታ መዋቅር ለህዝብ ሰላምና ደሀንነት ስጋት የሆኑ አካላትን ቀድሞ በመከላከል ህዝባዊ አደራቸውን ይበልጥ መወጣት አለባቸው ሲሉ ርእሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁየአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ለከፍተኛ ባለስልጣናትና ታዋቂ ሰዎች እጀባና ጥበቃ ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች ዛሬ አስመርቋልየአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ምክትል ኮሚሽነር አንማው አለሜ የህዝብ ሰላምና ደሀንነት እንዲጠበቅ ብቃት ያለው ፖሊስ መገንባት ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ በተለያዩ ዙሮች በአካል ብቃት የዳበረና ተልእኮን በቁርጠኝነት የሚተገብር ሀይል እያሰለጠነ መሆኑን ተናግረዋልየአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የአማራ ህዝብ ከድህነት ወጥቶ ሰላሙ እንዲረጋገጥና የሀገር አለኝታነቱ እንዲቀጥል ጠንካራ መንግስት ያስፈልገዋል ነው ያሉት
https://www.amharaweb.com/%e1%8a%a8%e1%88%98%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%88%a8%e1%88%9d-30-%e1%89%a0%e1%8a%8b%e1%88%8b-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%a5%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%88%88%e1%88%9d-%e1%8a%a5%e1%8b%ab%e1%88%89-%e1%88%88/
90
13,897
መንግስት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች በተቀላጠፈ መልኩ ድጋፍ እንደሚያቀርብ ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
Nov 26, 2020
5,561
አዲስ አበባ ህዳር 17 2013 ኤፍቢሲ መንግስት በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች በተቀላጠፈ መልኩ ድጋፍ እንደሚያቀርብ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ
https://www.fanabc.com/%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%b5%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%89%a5%e1%8b%93%e1%8b%8a-%e1%8b%b5%e1%8c%8b%e1%8d%8d/
21
14,779
ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ጥራታቸውን ያልጠበቁ የምግብ ምርቶች እና የሕክምና መሣሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ
ሀገር አቀፍ ዜና
Oct 23, 2020
487
አዲስ አበባ ጥቅምት 13 2013 ኤፍቢሲ ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ጥራታቸውን ያልጠበቁ የምግብ ምርቶች እና የህክምና መሳሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መታገዳቸውን የኢትዮጵያ የምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀጥራታቸውን ያልጠበቁ የምግብ ምርቶች እና የህክምና መሳሪያዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ የታገዱት በ2013 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት መሆኑ ተጠቁሟልከዚህ ባለፈም 14 የምግብ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ማገዱን ባለስልጣኑ ገልጿልበሩብ አመቱ እንዳይገቡ ከታገዱት የህክምና መሳሪያዎች ውስጥ የእጅ ጓንት የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች እና የሙቀት መሳሪያዎች ይገኙበታል ተብሏል
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a813-%e1%89%a2%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%8b%88%e1%8c%a1-%e1%8c%a5%e1%88%ab%e1%89%b3%e1%89%b8%e1%8b%8d%e1%8a%95/
77
5,798
የቻይና የንግድ ሳምንት እየተካሄደ ነው
ቢዝነስ
Monday, 07 May 2018 09:51
1846
 የቻይናው ኩባንያ MIE events DMCC እና አገር በቀሉ ፕራና ኢቨንትስ በጋራ ትብብር ያዘጋጁት ሁለተኛው የቻይና የንግድ ሳምንት ከትናንት በስቲያ በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተ ሲሆን የንግድ ሳምንቱ በዛሬው እለት ይጠናቀቃል በዘንድሮው የንግድ ትርኢቴ ላይ የኮንስትራክሽን ግብአቶችና ማሽነሪዎች የኤሌክትሪክ ቁሳቁስና ኤሌክትሮኒክሶች የመብራትና የኢነርጂ መሳሪያዎች የግብርና ማሽነሪዎች ለማእድን ስራ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች የምግብ ማቀነባበሪያ ማሽኖች የሆቴል እንጨት ስራዎች ለእለት ተእለት ፍላጎት የሚውሉ እቃዎች የእንስሳት መኖ ቴክኖሎጂና የጤና መጠበቂያዎችን ያካተተ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀዋል የኤምአይኢ ኢቬንትስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚር ዴቪድ ዋንግ የቻይና የተለያዩ ምርቶችን ለማስመጣት እንደዚሁም ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት የኢትዮጵያ አምራቾችና ነጋዴዎች ከቻይና ኩባንያዎች ጋር ጠንካራ የንግድ ግንኙነት እንዲኖራቸው ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረግ በመቻላችን የላቀ ደስታ ይሰማናል ብለዋል ከቻይና ጋር በጋራ በመስራቱ በኩል ከዚህ ቀደም ምንም አይነት እድሉ የሌላቸው እንደዚሁም ስራውን ከየት እንደሚጀምሩ ምንም አይነት ፍንጩ ለሌላቸው የኤግዚቢሽኑ ጎብኚዎች በምን መልኩ ከቻይና ጋር የንግድ ልውውጥ ማድረግ እንደሚችሉ መረጃ የሚሰጥ ሴሚናር በሶስቱ ቀናት ኤግዚቢሽን እንደሚካሄድ ታውቋል ኤም እይ ኢ አለም አቀፉ የሁነቶች Events ዳይሬክተር ሚስ ሚሸል ሜይሪክ በሰጡት ማብራሪያ የሴሚናሮቹ ዋነኛ አላማ የቻይና ምርቶች ዝቅተኛ የጥራት ደረጃ አላቸው የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት ለመለወጥ መሆኑን ጠቁመው እንደዚህ አይነቱ አመለካከት እንደ አጋጣሚ ሆኖ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በበርካታ ሀገራት ያለ በመሆኑ መሰል ሴሚናርም የኢትዮጵያ ኩባንያዎች በሚከፍሉት የተሻለ የክፍያ መጠን የተሻለ ጥራት ያለው ምርትን ከቻይና የሚያገኙ መሆኑን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይጠቅማል ብለዋል የቻይና የንግድ ሳምንት ማንም ሰው በነፃ ከኢንተርኔት ላይ አውርዶ ሊጠቀምበት የሚችል የራሱ የሆነ ኢንተርኔት መተግበሪያ ወይም አፕልኬሽን ያለው ሲሆን ጎብኚዎች ስለ ኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች ወቅታዊ መረጃን እንዲያገኙ እንደሚደረግና ከተሳታፊዎች ጋር በቀጥታ ኦንላይን የሀሳብ ልውውጥ ማድረግ በሴሚናሩ ንግግር አድራጊዎች ዙሪያ መረጃ ማግኘት ብሎም በቻይና የንግድ ሳምንት 80 ሺ ተሳታፊ ከሚደርሱ በቻይና የንግድ ሳምንት ተሳታፊ ኩባንያዎች ጋር የሚገናኙበት እድልም ይፈጠርላቸዋል ሲሉ አዘጋጆቹ አመልክተዋል   
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=21800:%E1%8B%A8%E1%89%BB%E1%8B%AD%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%8B%B5-%E1%88%B3%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%8A%A5%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%8A%AB%E1%88%84%E1%8B%B0-%E1%8A%90%E1%8B%8D&Itemid=240
259
49,185
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብት ልዩ መልዕክተኛ ኢሞን ግሊሞርን አነጋገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
May 13, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአውሮፓ ህብረት የሰብአዊ መብት ልዩ መልእክተኛ ኢሞን ግሊሞርን ዛሬ በብሄራዊ ቤተመንግስት ተቀብለው አነጋገሩየዛሬ ሶስት ወራት አካባቢ ሀላፊነታቸውን የተረከቡት ኢሞን ግሊሞር ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር የነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት በመሰረቱት ስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ያተኮረ እንደነበረ ከፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታልህብረቱ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ስራዎችን እንደሚያደንቅና በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ልዩ መልእክተኛው አረጋግጠዋል
https://waltainfo.com/am/32437/
58
28,286
የወልዋሎ አመራር ቦርድ አሰልጣኙን ለማሰናበት ወስኗል
ስፖርት
February 11, 2020
Unknown
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በዋና አሰልጣኙ ጉዳይ ላይ የተወያየው የወልዋሎ የስራ አመራር ቦርድ አሰልጣኙ እንዲሰናበቱ ወሰነበአሰልጣኙ ቆይታ ላይ ዛሬ ጠለቅ ያለ ስብሰባ ያደረገው የክለቡ የቦርድ አመራር አሰልጣኙ እንዲሰናበቱ ሲወስን ቡድኑ በጊዚያዊነት በአብርሀ ተአረ እና ኮማንደር ኪዳነ ሀፍተ እየተመራ ጨዋታዎች እንደሚያካሂድ ይጠበቃልበተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግደው ወደ ወራጅ ቀጠናው የተጠጉት ቢጫ ለባሾቹ ባለፈው አመትም በተመሳሳይ ሰአት ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም በስምምነት መለያየታቸው ሲታወስ አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌም በቦርዱ ውሳኔ መሰረት ከአንድ አመት የቡድኑ ቆይታ በኋላ የሚሰናበቱ ይሆናልአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች በቅጣት ምክንያት ቡድኑን አለመምራታቸው ይታወቃል
https://soccerethiopia.net/football/55429
83
1,446
የሦስት ሺ ዓመት ባለፀጋው የገና ጨዋታ
ስፖርት
January 8, 2021
6
ቦጋለ አበበ የባህል ስፖርት ከሰው ልጅ የአኗኗር ዘይቤ አንፃር በየአካባቢው የሚያከናውናቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አንዱ ነው ባህል የአንድ ህብረተሰብ ልዩ ልዩ ማህበራዊ መተዳደሪያ ስርአቶችን የሀዘንና የደስታ ስሜት መገለጫ የሆኑ ልዩ ልዩ ስነ ቃሎች ጭፈራዎች ዳንኪራና አልባሳትን ያካተተ ሲሆን ሲጠቃለል የህዝቦች ማህበራዊ ህይወት ማሳያና የማንነት መገለጫ ነው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ማሳተፍ የሚችሉና ብሄር ብሄረሰቦች የበለጠ እንዲቀራረቡ የመከባበርና የመቻቻል ባህላቸውንም እንዲያዳብሩ በማድረግ ጉልህ ሚና አለው የባህል ስፖርት የሰው ልጅ በተፈጥሮ በለገሰው ነገር ህልውናውን ለማኖር በሚያደርገው የእለት ተለት ውጣ ውረድና እንቅስቃሴ አማካኝነት የተፈጠረ ማህበራዊ ጨዋታና እንቅስቃሴ ነው የባህል ስፖርት በአዝጋሚ ለውጥ ከህብረተሰቡ እድገት ጋር እያደገና እየዳበረ የመጣ የህብረተሰብ ወጉና ማእረጉ የሱነቱ መገለጫ ከሆኑ ቅርሶቹ ውስጥም አንዱና ዋነኛው ነውከክርስቶስ ልደት በፊት በ6ኛው እና 7ኛው ክፍለ ዘመን በተለያዩ አካባቢዎች በመንደር በቤተሰብና በደብር የተመሰረተ የባህል ስፖርት ጨዋታ በኢትዮጵያ ይካሄድ እንደነበረ የባህል ስፖርቶች የውድድር ህግ በሚል ሰኔ 2oo6 አም በባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ተዘጋጅቶ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የባህል ማእከል ድጋፍ የታተመው መፅሀፍ ያስረዳል በአለም አቀፍ ደረጃ ሆኪ ተብሎ የሚታወቀውን የገና ጨዋታ ኢትዮጵያውያን ከሶስት ሺ አመት በፊት ይጫወቱት እንደነበር የአለም ሆኪ ፌዴሬሽን በድረገፁ ከአራት አመት በፊት ያሰፈረው ፅሁፍ ያስረዳል ያም ሆኖ ሆኪ አሁን ያለበት ደረጃና የእኛው የገና ጨዋታ ለንፅፅር እንኳን የማይበቃ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማንም መናገር ይችላል የሆኪ ስፖርት መነሻው ከገና ጨዋታ መሆኑን ከጨዋታዎቹ ፍፁም መመሳሰል ተነስቶ መገመት ከባድ አይሆንም ነገር ግን ይህን ተወዳጅ ስፖርት በኢትዮጵያ ማበልፀግና አለምአቀፋዊ ይዘቱን ማጎልበት ባለመቻሉ ምእራባውያኑ የግላቸው አድርገው አሁን ላይ መነሻ የሆነው የገና ጨዋታ በሆኪ ተውጦ እናገኘዋለንየገና ጨዋታ በኢትዮጵያ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ይዘት ያለው ከጥንት ጀምሮ የነበረ ጨዋታ እንደሆነ መዛግብት ያስረዳሉ መምህር ካህሳይ ገብረእግዚአብሄር የተባሉ የታሪክ ተመራማሪና ደራሲ ስለ ገና ጨዋታ ታሪካዊ አጀማመር ሁለት ትውፊቶች ተደጋግመው እንደሚነገሩ አስቀምጠዋል ክርስቶስ ሲወለድ እረኞች ከመላእክት ጋር አብረው እንደዘመሩና በወቅቱም የገና ጨዋታ መጫወት እንደጀመሩ አንደኛውን ትውፊት በመጥቀስ ያስረዳሉሁለተኛው ትውፊት ደግሞ ከሰብአ ሰገሎች ጋር የሚገናኝ ነው ንጉስ ሄሮድስ የሚባለው የዘመኑ ንጉስ አዲስ የሚወለደው ህፃን የበለጠ ዝናና ክብር እንደሚያገኝ የሰማው ትንቢት ስላስደነገጠው በዚያን ጊዜ የተወለዱ ወንድ ህፃናት በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጥቶ እያሳደደ ያስገድል እንደነበር ይወሳል ሄሮድስ ታዲያ ክርስቶስ ሊወለድ መሆኑ ተነግሮት ስለነበር የት እንደሚወለድና ስለ አጠቃላይ ሁኔታው በቅርበት ለማወቅ በመፈለጉ አንድ ሰላይ የሰብአ ሰገል አይነት ልብስ አስለብሶ ከእነሱ ጋር እንዲቀላቀል ይልካል ሰላዩ ከሰብአ ሰገል ጋር ተቀላቅሎ ጌታ ወደሚወለድበት ስፍራ ሲጓዙ ይመራቸው የነበረው ኮከብ ድንገት ቀጥ ይላል ይኼኔ ተጠራርተው መሀላቸውን ሲፈትሹ ሰላዩን እንዳገኙት ይኸው ትውፊት ያስረዳል ከዚያም ሰብአ ሰገል ሰላዩን ይገድሉና ራሱን ቆርጠው እንደ አሁኑ የገና ሩር እየተቀባበሉ ተጫወቱበት ይላል ሁለተኛው ትውፊት ከዚያም በመነሳት የገና ጨዋታ ተፈጠረ ይላሉ የታሪክ ተመራማሪው ከዚያን ጊዜ አንስቶ ትውልድ ከትውልድ እየተቀባበለ እስከ አሁን የቀጠለው የገና ጨዋታ በየአመቱ በታህሳስ ወር በተለይ በኢትዮጵያ የገጠሩ ክፍል እረኞች በድምቀት ይጫወቱታል ከክርስቶስ ልደት በኋላም በተለያዩ ጊዜያት በወቅቱ ነግሰው በነበሩ የኢትዮጵያ ነገስታት ጊዜ በመሳፍንት በሹማምንቱ በሎሌዎች በህዝቡ መካከል በሰንበትና በአውድ አመት የባህል ስፖርት ጨዋታዎች በከፍተኛ ሁኔታ ውድድርና ፉክክር በማድረግ ይዝናኑበት እንደነበር በተለያዩ ፅሁፎች ተገልጿልበአፄ ቴዎድሮስ እና በአፄ ሚኒልክ ዘመነ መንግስታት ወቅት በራሳቸው ንጉሶቹ አዘጋጅነትና ዳኝነት በከፍተኛ ሁኔታ የባህል ስፖርት ጨዋታዎች ይካሄዱ ነበር አፄ ቴዎድሮስ የኢትዮጵያኖችን ጥንካሬና ጀግንነት ለውጪ አገር ዜጎች ለማሳየት የኢትዮጵያ ጎበዝ ታጋዮችን ከውጪ አገር ከመጡ ዜጎች ጋር በራሳቸው ዳኝነት የትግል ውድድር በማወዳደር ላሸነፉ ኢትዮጵያኖች ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ይሸልሙ እንደነበርም የታሪክ ድርሳናት ይነግሩናል አፄ ሚኒሊክ ደግሞ የራሳቸው የገና ተጫዋቾች በማደራጀት ከእቴጌ ጣይቱ ቡድን ጋር የገና ጨዋታ ውድድር ያደርጉ ነበር እቴጌ ጣይቱም በስማቸው የከፈቱትን ሆቴል ለማስተዋወቅ የገበጣ ጨዋታ አዘጋጅተው ያጫውቱ ነበርበአሁኑ ወቅትም በገጠር የሚኖረው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ አካላዊ ብቃቱን ከሚያዳብርባቸውና መንፈሳዊ እርካታን ከሚጎናፀፍባቸው እሴቶች መካከል የሱነቱ መለያ ባህልና ልምዱን ወግና ማእረጉን ከሚገልፅባቸው መንገዶች አንዱ የባህል ስፖርት ነው በተለይም የተዳከመ አእምሮውንና የዛለ አካሉን የሚያነቃቃባቸውና የሚያፍታታባቸው በትርፍ ሰአቱና በበአላት ቀናት ማህበራዊ ግንኙነቱን የሚያጠናክርበት መሳሪያው የባህል ስፖርት ነው አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የባህል ስፖርቶች በተለይም በበጋው ወራት የገና በአልን ምክንያት በማድረግ ውድድሮች ይካሄዳሉ የክርስቶስ ልደት ወይንም የገና በአልን ምክንያት በማድረግ እረኞች የገና ጨዋታን ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ጥር ከዚያም እስከ ክረምቱ መግቢያ ይጫወቱ እንደነበርም የቀድሞ አባቶች ይናገራሉበተለይም የገና ጨዋታ በከፍተኛ ሁኔታ የሚካሄደው መኸር በተሰበሰበበት አካባቢ ለጥ ባለ ሜዳ ከሰአት በኋላ ሩሩ ለአይን መታያት እስከተቻለበት ጊዜ ድረስ ጨዋታው ይካሄድ ነበር ጨዋታው የሚካሄደው በሁለት የቡድን አባቶች አማካኝነት እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የተለየ ስም እያስመረጡ ወደ ቡድናቸው ይቀላቀላሉ ይህም የሚሆነው ሁለት ቡድኖች ከአንድ መንደር ወይም ቀበሌ ከሆነ ብቻ ነው ሌላው ከፍተኛ የውድድር አይነት ደግሞ የቡድን አባቶች የተመደበው ደብር ከደብር የላይ አምባ ከታች አምባ የአንዱ ቀበሌ ከሌላው ቀበሌ ከሆነ ብቻ ነው እንዲሁም ባገቡና ባላገቡ መካካል ተካፍለው የጨዋታውን አይነት በስምምነት የሚፈፀምም ነው በዚህ የጨዋታ አይነት ለመንደር ወይም ለደብር ገናን ለመጫወት የፈለጉ ሁሉ የሚሳተፉበትና ለቡድኑ መግባት የሚችሉት የተጫዋቾች ቁጥር ማእቀብ የሌለውና ሊበላለጥ የሚችል የትርምስ የገና ጨዋታ ሲሆን አንድ ተጫዋች ሲወጣና ሲገባም በቡድኑ አባላት የማይጠየቅበት ነው በቡድን አባቶች በምርጫ የሚጫወቱ ሌላው ገና ግን አንዱ በጨዋታው ተጎድቶ ቢወጣ ወይም አዲስ ለመግባት ቢፈልግ ለቡድኑ አባት ለጎበዝ አለቃ ወይም ለአጫዋቾች ተናግሮ ሲፈቀድለት የሚገባበት ነው የገና ጨዋታን ይጫወቱበት የነበረው ዱላ ከጫፉ ቀለስ ያለ የእንጨት ገና ሲሆን የመጫወቻ ሩር ጥንግ ከቆዳ ወይም ከዛፍ ስር ድቡልቡል አድርጎ በማዘጋጀት በመምታት በማንከባለልና በመለጋት ነበር የሚካሄደው አለባበሳቸውም ጉልበት ላይ የሚቀር ሱሪ እጀ ጠባብ ከወገቡ ላይ የሚጠመጠም ድግ ነበር ለብሰው የሚጫወቱት በአንዳንድ አካባቢ የገና ጨዋታ በሚደረግበት ጊዜ አንድ የጎበዝ አለቃ ከአማካሪዎቹ ጋር ከመሀል ሜዳ አቆራቋዥና ጨዋታውን የሚመሩ አራት የድንበር ጠባቂዎች ይደረግለት ነበር የጨዋታው ፍፃሜም በግብ ወይም በነጥብ የሚለይ ነውየገና ጨዋታ ብዙ አይነት ውድድር ይደረግበት ነበር ለምሳሌ ያህልም ቁርቁዝ ሙጭ ቀልቦ መለጋትና አፍሶ መለጋት ይጠቀሳሉ አፍሶ መለጋት ከባድ የአውዳመት ጨዋታ ሲሆን አፍሶ በመለጋት የሚጫወቱት ነው ህግና ሚና በሚከበርበት ጊዜ ደግሞ ቀልቦ መለጋት ጨዋታ ላይ ይውላል ሙጭ ጨዋታ በመጥረግ ብቻ እንጫወት ብለው በስምምነት ያገኙትን የሰውንም እግር ሆነ ጥንጉን በመጥረግ የሚጫወቱት ነው ቁርቁዝ የተባለው አጨዋወት ህግን በመከተል በሚናህ በማለት ጥንጓን በሀይል ሳይጫወቱ ወይም ሳይመቱ በማንከባለል ብቻ የሚጫወቱት ጨዋታ ነበርበቀድሞው የገና ጨዋታ ጊዜ ጨዋታው የሁሉም መሆኑን ለመግለፅ በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ እየተባለ በሚደርሰው አደጋ ምንም አይነት ቂም መያዝና አደጋ መፍጠር ወይም ጠብ በማያስከትል መንገድ ይካሄድ እንደነበርም ይወሳልአዲስ ዘመን ታህሳስ 292013
https://www.press.et/Ama/?p=39149
905
1,643
የአረንጓዴ አሻራ አርበኞች
ሀገር አቀፍ ዜና
June 22, 2020
22
ከግቢው አጥር ግራና ቀኝ ተፈጥሮአዊ መስህብ የተላበሱ አለፍ አለፍ ብለው የተተከሉ ችግኞች ይታያሉ ልምላሜያቸው መፅደቅ መጀመራቸው ያመለክታል አደራደራቸውም እንዲሁ ለአይን ይማርካል በግቢው ውስጥ ያሉ ዛፎች አትክልት ፍራፍሬዎችና አበባዎች መአዛ ያውዳል በስርአት ችምችም ብለው ያደጉት ብዙ አይነት ዛፎች በቦታው ለተገኘ ፍጡር ንፁህ አየር ይመግባሉ ከግቢው በስተግራ በተሰናዳው ስፍራ በፕላስቲክ ከረጢቶች ለመትከል የተዘጋጁ ብዙ አይነት ዝርያ ያላቸው ችግኞች ከጫፍ እስከ ጫፍ ተሰልፈው ይታያሉ የቤተሰቡ አባላት ችግኞቹን በመንከባከብ ስራ ተጠምዷል ይህ በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ነዋሪ የሆኑት የኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ ግቢ ነው ለአረንጓዴ አሻራ ማኖር በግለሰብ ደረጃ ከሚተጉ የአረንጓዴ ልማት አርበኞች መካከል ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ አንዱ ናቸው ኮማንደር ጥላሁን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የአረንጓዴ ልማት ቀድመው የጀመሩ የታታሪዎች ምሳሌ ናቸው በግል ተነሳሽነት ከ1984 አም ጀምሮ ችግኞች አፍልቶ በመትከል በግቢያቸው ውስጥ ፅድ ባህር ዛፍ ግራቪሊያ ግራር ዋንዛ ሸውሸዌ ቡና ፓፓያ አቮካዶና የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎች አልምተዋል የተከልኳቸው ዛፎች የአይኔ ማሳረፊያ ልጆቼ ናቸው ኮማንደር ጥላሁን ለተፈጥሮና ለዛፎቹ ያላቸው ጥልቅ ፍቅር የሚያሳዩት እንደ ልጆቻቸው ተንከባክበው ለመጪው ትውልድ የሚያስተላልፉት መተኪያ የሌለው ሀብት መሆኑን ይናገራሉ ከራሳቸው አልፈው ለማህበረሰቡና ለተለያዩ ድርጅቶች ለአመታት ችግኞችን አፍልተው በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርቡም ይገልፃሉ ተፈጥሮን መጠበቅ እና መንከባከብ ህይወትን ማስቀጠል ነው የሚሉት ኮማንደር ጥላሁን በዚህ አመት የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ለመትከል ማቀዳቸውንና ችግኞችን ለህብረተሰቡ ለማከፋፈል ማዘጋጀታቸውን ይገልፃሉ ዛፍ የሰው ህይወት ከሞት የሚታደግ በመሆኑ ሁሉም በግሉ አረንጓዴ ልማት ላይ የጎላ ተሳትፎ ማድረግ የሚገባው መሆኑንም ይጠቁማሉ ለ50 አመታት ችግኞችን በመትከልና በማልማት የተራቆተ አካባቢ መልሶ እንዲያገግም በማድረግና የእድሜያቸውን አብዛኛው ክፍል በአረንጓዴ ልማት ላይ በማዋል ትልቅ አበርክቶ ያተረፉ ሌላኛው የአረንጓዴ አሻራ አርበኛ ደግሞ አቶ ጌታሁን መብራቴ ናቸው ባፀደቋቸው ዛፎች ምክንያት አባ ዛፉ በማለት የሚጠሩት የ85 አመት እድሜ ባለፀጋ የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ አርሶ አደር ናቸው ከላሊበላ ከተማ 42 ኪሜ ርቀት ላይ ከሚገኘው አቡነ ዮሴፍ ቀበሌ ከአቡነ ዮሴፍ ዝጊት አቦሀይ ጋሪያ ማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ በቅርብ ርቀት ላይ ልዩ ቦታው እመቤት ዋሻ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነዋሪ ናቸው ከደርግ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በራሳቸው ተነሳሽት ጉልበታቸውንና ሀብታቸውን በማፍሰስ ለ50 አመታት አገር በቀል ዛፎችን በማልማት በመጠበቅ በመሆን በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዛፎች አልምተዋል በነዚህ አመታት ውስጥ በ30 ሄክታር በተጎዳና በተራቆተ አካባቢ ለሰብል ምርት የሚጠቀሙበትን የግል የእርሻ መሬት ጨምሮ ቁጥቋጦዎችንና የሳር ዝርያ አይነቶችን ሳይጨምር በርካታ የሀገር በቀል ዛፎችን አፅድቀዋል በተለይ አምጃ አስታ ቀለዋ የተባሉ አገር በቀል ዛፍ ማልማታቸውን ይገልፃሉ ለዛፍና ለተፈጥሮ ሀብት ልዩ ፍቅር አለኝ የእድሜን አብዛኛው ክፍል ስተክልና ስንከባከብ የኖርኩት ሊዚያ ነው በማለት የሚገልፁት አቶ ጌታሁን የደን ልማት ዋና ትኩረት ያደረጉት እየጠፉ በሚገኙ የአገር በቀል ዛፎች ላይ ነው ከነዚህም ውስጥ የአካባቢውን ስነ ምህዳር ያስጠበቁት አስታ አምጃ ቀለዋ ቀጋ ኮሶ ሲሆኑ ከዚህ ባለፈ የውጭ ዝርያ የሆኑ ዛፎችን አልምተዋል አዲስ ዘመን ሰኔ 152012 ተገኝ ብሩ
https://www.press.et/Ama/?p=34826
402
40,959
የሰዎችን የሕገወጥ ዝውውር የሚያሳይ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን
ዓለም አቀፍ ዜና
October 26, 2017
Unknown
በሀያ አንደኛው ምእተ አመት እውነት ይሄ ይሆናል ሊያሰኝ ይችላል በአለም ዙሪያ በሚያስገርም ቁጥር ሰው እንደጉድ ይሸጣል ይገዛልየዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው አሀዝ መሰረት በየአመቱ በአለምቀፍ ድንበሮች በህገወጥ አዘዋዋሪዎች የሚላከው ሰው ከስድስት መቶ እስከ ስምንት መቶ ሺህ ይደርሳልሌሎች ብዙ ሚሊዮኖችም በሀገሮች ብሄራዊ ድንበሮች ውስጥ በባርነት ተጠፍረው ይገኛሉየሰዎች ህገወጥ ዝውውርን ወንጀል አጉልቶ ለማሳየት የታለመ ማሀበረሰባዊ ጥረት እዚህ ዋሽንግተን አካባቢ ተጀምሯልArtwork For Freedom በኪነ ጥበብ ለነፃነት መሟገት የተባለ ድርጅት የጀመረው ዘመቻ ነው
https://amharic.voanews.com//a/photography-exhibit-highlights-human-trafiicking-10-26-2017/4087333.html
70
32,797
የእለቱ ዜናዎች፡ ሰኞ ህዳር 4 ቀን 2010 
ስፖርት
November 13, 2017
Unknown
አስመራጭ ኮሚቴ ከ42 ቀናት በኋላ የሚደረገው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምርጫን ለማካሄድ በሚሰየመው የአስመራጭ ኮሚቴ እና የምርጫ እንቅስቀቃሴን በሚመለከት በቅርቡ የፊፋ ተወካዮች አዲስ አበባ እንደሚገቡ ታውቋል ተወካዮቹ በምርጫው ዙርያ ከፌዴሬሽኑ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን እስከ ምርጫው ድረስ የሚደረገው እንቅስቃሴ ላይም ይሳተፋሉ ተብሏል አቶ ተክለወይኒ ይቅርታ ጠይቀዋልየኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር መነጋገርያ ሆነው መሰንበታቸው ይታወቃል አቶ ተክለወይኒ ዛሬ በመቀለ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም ላደረጉት ያልተገባ ንግግር ይቅርታ ጠይቀዋል ባለፉት ግዜያት በትግራይ እና በ ሀገር ደረጃ በነበሩት የስፖርት እንቅስቃሴዎች በተለይም በትግራይ ስቴድየም ፕሮጅክት እና በ የደረጃው ያሉ ክለቦችን ለማጠናከር በተሰሩት ስራዎች በግሌም ድርጅቴን ወክዬም ትልቅ አስተዋፅኦ አርግያለው በ4 አመት የፌደሬሽኑ ቆይታዬም በፌደሬሽኑ የነበሩትን ችግሮች ለመፍታት የበኩሌን ተወጥቻለው ዘመናዊ ያልነበረው የተጫዋቾች የዝውውር ስርአት ለማስተካከል እና በፋይናንሱ በኩልም እኔ በቆየሁባቸው 4 አመታት ፌደሬሽኑ 300 ሚልየን የሚጠጋ ብር እንዲያገኝ የበኩሌን አስተዋፅኦ አበርክቻለሁ  ሆኖም በ10ኛው የፌደሬሽኑ ጉባኤ መቀለ እንዲካሄድ ከነበረኝ ፍላጎት ተነስቼ የሰጠሁት አስተያየት ተሳታፊዎቹ መቀለ ና ወልዋሎ ወደ ፕሪምየር ሊግ በማለፋቸው በክልሉ ያለው የስፖርት መነቃቃት እንዲታዘቡና የትግራይ ስቴድዬም እንዲጎበኙ በማሰብ ነበር መቀለ የቆነጃጅት ሀገር መሆንዋን ለመግለፅ ፈልጌ በሌላ መልኩ ስለተተረጎመ እና እኔው ራሴ በፈጠርኩት አላስፈላጊ ነገር የትግራይ ክልል ሴቶች በተለይም የመቀለ ሴቶችን በይፋ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል ድቻ እና አርባምንጭ ወላይታ ድቻ እና አርባምንጭ ከተማ በክረምቱ ካስፈረሟቸው ሁለት የውጭ ተጫዋቾች ጋር  ተለያይተዋል ወላይታ ድቻ ክለቡ በክረምቱ ካስፈረማቸው 4 የውጭ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ናይጄሪያዊው አማካይ ሂላሪ ኢኬና ጋር ተለያይቷል ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፀው ተጫዋቹን የተጫዋቹን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቪድዮ ተመልክተው በአንድ አመት የውል ኮንትራት እና 4500 ዶላር ወርሀዊ ክፍያ ለማስፈረም ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም በልምምድ ወቅት አጥጋቢ እንቅስቃሴ ባለማሳየቱ እንደተለያየ ገልጿልበተመሳሳይ አርባምንጭ ከተማ ካስመጣቸው 3 ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ጋናዊው አጥቂ ሰይዱ ባንሴ ጋር ተለያይቷል አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ተጫዋቹ ወደ ሀገር ውስጥ የመጣ ቢሆንም አስቀድሞ የተጎተቱ የተጫዋቹ ጉዳዮች በክለቡ የዝግጅት እና የቅድመ ውድድር ወቅት አብሮ ያልነበረ ከመሆኑም ባለፈ ጉዳት እንዳለበት ከመግለፁ ጋር ተደማምሮ ለመለያየት እንዳበቃቸው ተገልጿልከውጪ የሚመጡ ተጫዋቾች አንድም ጨዋታ ሳያደርጉ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ መመልከት እየተለመደ መጥቷል አዳማ ከተማ ከደቡብ ሱዳናዊው ፒተር ዱስማን ጋር መለያየቱ ሲነገር ጅማ አባ ጅፋር አስመጥቶት የነበረው ናይጄርያዊ ግብ ጠባቂ በሀገሩ ኮንትራቱን ሳያጠናቅቅ መምጣቱ በመረጋገጡ ወደ ሀገሩ መመለሱ ይታወሳል ቅሬታእሁድ እለት የተደረገው የሲዳማ ቡና እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ላይ ሲዳማ ቡና በመጀመርያ 11 ላይ 4 የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን መጠቀሙን ተከትሎ አርባምንጭ የፌዴሬሽኑ ህግ በአንድ ጨዋታ ላይ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት 3 ተጫዋቾች ብቻ ናቸው በሚል ቅሬታ አቅርበው የነበረ ቢሆንም በተሻሻለው የፌዴሬሽኑ ደንብ መሰረት 5 የውጪ ተጫዋቾች በአንድ ጨዋታ መሰለፍ እንደሚችሉ በመግለፅ ቅሬታው ውድቅ ተደርጓል ከ17 አመት በታች ሴቾች የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከናይጄርያ ጋር ለሚያደርገው የአለም ዋንጫ ማጣርያ ነገ ዝግጅት እንደሚጀምር ታውቋል አሰልጣኝ ሰላም ዘርአይ በቅድሚያ ከጠሯቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾችን የጠሩ ሲሆን ነገ 0400 በአአ ስታድየም ልምምድ ይጀምራሉ ተብሏል አክሊሉ አያናው የአክሊሉ አያናው ጉዳይ እስካሁን እልባት አላገኘም ተጫዋቹ ለሁለት ክለብ ፈርሟል በሚል ለፋሲል ከተማ 600ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኖበት የነበረ ቢሆንም ባቀረበው ይግባኝ ቅጣቱ ወደ 20ሺህ ብር ቀሎለት ለኢትዮጵያ ቡና እንዲጫወት ተወስኖ ነበር ኋላ ላይ ደግሞ ጉዳዩ በስራ አስፈፃሚ ውሳኔ እንደገና እንዲታይ ተወስኖ እስካሁን እልባት ሳያገኝ ቀርቷል ተጫዋቹም በቀጣይ ሳምንሀት ጨዋታዎች የማድረጉ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል መሰረት ማኒ በ2008 ድሬዳዋ ከተማን በመምራት በታሪክ ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሴት አሰልጣኝ ለመሆን የበቃችው አሰልጣእ መሰረት ማኒ በግል ህይወቷ ዙርያ መፅሀፍ ልታሳትም ነው አሰልጣኝ መሰረት ግለ ታሪኳን ራሷ ያዘጋጀችው ሲሆን በቅርቡ ታትሞ ለገበያ እንደሚቀርብ ታውቋልየእግርኳስ ሰዎች ግለ ታሪክ በኢትዮጵያ እምብዛም ባይለመድም በቅርብ አመታት አሸናፊ ግርማ እና አሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው መፅሀፍ ማሳተማቸው የሚታወስ ነው ከፍተኛ ሊግ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አስቀድሞ ከወጣለት መርሀ ግብር በሁለት ሳምንት ተገፍቶ ህዳር 9 እንዲጀመር መወሰኑ ይታወሳል ሆኖም ክለቦች የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ከፍለው ባለማጠናቀቃቸው ውድድሩ በድጋሚ ሊራዘም እንደሚችል ተሰምቷል አሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ደግሞ በርካታ ክለቦች ገንዘብ ከፍለው ያላጠናቀቁ በመሆኑ ውድድሩ በከፈሉት መካከል ብቻ ሊደረግ እንደሚችል ታውቋል ሰናይ ተግባርየኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ደማችንን ለወገናችን በሚል መርህ ትላንት በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ተገኝተው የደም ልገሳ አከናውነዋል የክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እንዳስታወቀውም ከ850 በላይ ደጋፊዎች ደም በመለገስ የማህበሩን ሪኮርድ ሰብሯል ከዚህ ቀደም የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች የደም ልገሳ ላይ መሳተፋቸው የሚታወስ ነው ድጋፍ በሀገሪቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ተጫዋቾች ለቀድሞ ክለቦቻቸው ድጋፍ የማድረግ ልማድ እየተበራከተ መጥቷል በቅርቡ አስቻለው ታመነ ለዲላ ከተማ የወንድ እና የሴት ቡድኖች የትጥቅ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ሌሎች ተጫዋቾችም የትጥቅ ድጋፍ አድርገዋል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ የሆነው ለአለም ብርሀኑ ከቀድሞ የእግርኳስ ተጫዋች ግሩም ባሻዬ እና በጀርመን ዝቅተኛ ዲቪዝዮን እየተጫወተ የሚገኘው ወንድሙ አማኑኤል ባሻዬ ጋር በጋራ ለደቡብ ፖሊስ ስፖርት ክለብ ቡድኑ በውድድር አመቱ የሚጠቀምበት ማልያ እና የልምምድ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋልበዘንድሮው ክረምት አዲስ አበባ ከተማን የተቀላቀለው ግብ ጠባቂው ሀብቶም ቢሰጠኝ ሌላው ለቀድሞ ክለቡ ድጋፍ ያደረገ ተጫዋች ነው ሀብቶም ለቀድሞ ክለቡ ሽረ እንዳስላሴ የማልያ ድጋፍ አድርጓል የአማራ ዋንጫ የአማራ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሚያዘጋጀው የአማራ ዋንጫ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ፍፃሜውን አግኝቷል ከጥቅምት 5 ጀምሮ በደብረ ማርቆስ ከተማ ሲደረግ የነበረው ውድድር ለ11 ክለቦች ጥያቄ ቀርቦላቸው የነበረ ቢሆንም የጁ ፍሬ ወልድያ ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀን ዳሞት ከተማ መርሳ ከተማ እና ላስታ ላሊበላ ጥሪውን ባለመቀበላቸው  በውድድሩ ያልተሳተፉ ክለቦች ናቸው ጎጃም ደብረ ማርቆስ አዊ እምፒልታቅ አማራ ፖሊስ ደባርቅ ከተማ ዳባት ከተማ እና አምባ ጊዮርጊስ የተሳተፉበት ውድድር ቅዳሜ ፍፃሜውን ሲያገኝ አማራ ፖሊስ እና አምባ ጊዮርጊስ ያደረጉት ጨዋታ በአማራ ፖሊስ 30 አሸናፊነት ተጠናቋል አምባ ጊዮርጊስ ከመጨረሻው ጨዋታ በፊት ያሉትን አራት ጨዋታዎች በማሸነፉ በ12 ነጥብ የውድድሩ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል አዊ እምፒልታቅ ከደባርቅ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በአዊ 10 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን አዊዎች ሁለተኛ ደረጃን ያዘው ማጠናቀቃቸውንም አረጋግጠዋል ጎጃም ደብረ ማርቆስ ዳባት ከተማን 21 በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁንም ለማወቅ ተችሏል ቀጣይ መርሀ ግብርየኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ቅዳሜ ህዳር 9 ቀን 20100900 ወልዋሎ አዩ ከ ሲዳማ ቡና አዲግራት0900 ወልዲያ ከ ድሬዳዋ ከተማ ወልዲያ1130 ኢትዮጵያ ቡና ከ መከላከያ አአ እሁድ ህዳር 10 ቀን 20100900 አርባምንጭ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አርባምንጭ0900 ጅማ አባ ጅፋር ከ ፋሲል ከተማ ጅማ0900 ደደቢት ከ ሀዋሳ ከተማ አአ0900 ወላይታ ድቻ ከ አዳማ ከተማ ሶዶ1130 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቀለ ከተማ አአ
https://soccerethiopia.net/football/31234
919
17,373
ባለፉት 24 ሰአታት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው 106 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ ሆኑ
ሀገር አቀፍ ዜና
Mar 25, 2020
2,724
አዲስ አበባ መጋቢት 16 2012 ኤፍ ቢ ሲ ባለፉት 24 ሰአታት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው 106 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተገለፀየኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ በሰጠው መግለጫ በህብረተሰቡ ዘንድ ከሚስተዋለው የመዘናጋት ሁኔታ ጋር ተዳምሮ ቫይረሱ እንዳይስፋፋ የጋራ ስራ ይጠይቃል ብሏልእስካሁን በሁሉም መግቢያ በሮች 668 ሺህ ሰዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ተናግረዋልበዚህም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት 474 መንገደኞች የሁለት ሳምንት የለይቶ ማቆያ ክትትላቸውን ትናንት መጀመራቸውንም ገልፀዋልከቫይረሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመመርመር ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ሁለት ተጨማሪ የላቦራቶሪ ተቋማት በቅርብ ቀናት ውስጥ የምርመራ ውጤታቸውን ይፋ ያደርጋሉም ብለዋልከአሜሪካ የመጡ የመመርመሪያ ቁሳቁስ አምራች ኩባንያዎች ፈቃድ የተሰጣቸው በመሆኑ ለክልሎች የሚበቃ መመርመሪያ እንዲያመርቱ በማድረግ እየተስተዋለ ያለውን የመመርመሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለመቅረፍ ይሰራልም ነው ያሉትበአሁኑ ሰአት 20 ሰዎች የበሽታው ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉም ተብሏልከህክምና መስጫ ግብአቶች ጋር በተያያዘም ከዚህ በፊት ከተሰራጩት የህክምና መስጫ ግብአቶች በተጨማሪ ከ2 ሚሊየን በላይ የፊት ጭምብሎች ለሁሉም ክልሎች የተሰራጩ ሲሆን ለ112 የፌደራል መስሪያ ቤቶችም የፊት ጭምብልና የእጅ ጓንት እየተሰራጨ ይገኛልበሶዶ ለማትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ httpstmefanatelevision
https://www.fanabc.com/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-24-%e1%88%b0%e1%8a%a0%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93-%e1%89%ab%e1%8b%ad%e1%88%a8%e1%88%b5-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%88%98%e1%88%ab-%e1%8b%a8/
174
26,611
ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ድንቅ ጎል ያስቆጠረው ተስፈኛ ወጣት ይናገራል
ስፖርት
January 15, 2021
Unknown
የአዲሱ ትውልድ ተጫዋቾችን እየተመለከትን በምንገኝበት የዘንድሮ አመት ውድድር በዛሬው እለት ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ አስደናቂ ጎል ካስቆጠረው ተስፈኛ ወጣት ቤካም አብደላ ጋር ቆይታ አድርገናልጅማ ከተማ ቁጠባ በሚባል አካባቢ ተወልዶ አድጓል በአሰልጣኝ ጋሻው ፕሮጀክት እግርኳስን እየተጫወተ ለሶስት አመት ቆይታ አድርጓል በነገራችን ላይ አሰልጣኝ ጋሻው እንደ ሳላዲን ሰኢድ ያለ ታላቅ ተጫዋች ያፈራ በርካታ ትውልዶችን መፍጠር የቻለ ክብር ሊቸረው የሚገባ አሰልጣኝ ነው ቤካም አብደላ የአካዳሚ እድል አግኝቶ አሰላ ወደሚገኘው ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማእከል ለአራት አመታት ሰልጥኖ መጨረስ ችሏል በ2012 ጅማ አባ ጅፋርን በመቀላቀል ባህር ዳር ላይ በተደረገ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ብቻ ተቀይሮ በመግባት የመጫወት እድል አግኝቷል በዛሬው እለት ለሁለተኛ ጊዜ ተቀይሮ በመግባት በአስገራሚ ሁኔታ በ83ኛው ደቂቃ ተከላካዮች እና ግብ ጠባቂውን በተረጋጋ ሁኔታ አልፎ እጅግ ድንቅ ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ማስቆጠሩ እና የመጠርዬ ስሙን ለየት ማለት ተከትሎ ዛሬ የመነጋገርያ ርእስ ሆኖ ውሏልወደ ፊት በቂ የመጫወት እድል ካገኘ የተሻለ ነገር ማሳየት እንደሚችል ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያሳየው ቤካም ስለ መጠርያ ስሙ ስለ ዛሬው ጎል እና በቀጣይ ስለሚያስበው በተከታዩ መልኩ አጋርቶናልቤካም የሚለውን ስም ያወጣልኝ አባቴ ነው ያው እግርኳስን ስለሚወድ እና የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ በመሆኑ በእንግሊዛዊው ተጫዋች ቤካም ስም የኔን መጠሪያ አውጥቶልኛል አባቴ እግርኳስ ተጫዋች እንድሆን ትልቅ እገዛ ሲያደርግልኝ ቆይቷልሁሌም ለእንዲህ አይነት ቀን ራሴን እያዘጋጀሁ እጠብቅ ነበር አንድ ቀን የመሰለፍ እድል አገኛለሁ ወይም ተቀይሬ እገባለው የሚል እምነት በውስጤ ነበር ዛሬ አሰልጣኝ ጳውሎስ ተነስተህ አሟሙቅ ሲለኝ እጅግ ደስ ብሎኝ ነው የተነሳሁት ለኔ ተቀይሮ ገብቶ መጫወቱ በራሱ በቂ እድል ነው በጨዋታው ጎል አስቆጥራለሁ የሚል ፍፁም ግምት አልነበረኝም ኳሱ እግሬ ሲገባ ተረጋግቼ መወሰን ያለብኝን ወስኜ ጎል አስቆጥሬያለው እንጂ ጎል አገባለው ብዬ አላሰብኩም ይህች ጎል ለነገ የእግርኳስ ህይወቴ ትልቅ መነሳሻ ነው የሚሆነኝ የበለጠ ጠንክሬ እንይሰራ አስተዋፅኦ የሚያደርግ ነው ጎሉን በመልሶ ማሳያ ሆቴል ከገባው በሀላ ደጋግሜ ሳየው ማመን አቅቶኛል አስበው ቅዱስ ጊዮርጊስ ትልቅ ቡድን ነው ተከላካዮቹ ግብጠባቂው ልምድ ያላቸው ናቸው እነርሱን በዚህ መልኩ አልፌ ይህን ጎል ማስቆጠር በጣም አስደሳች ነው ምንም አላመንኩም ነበር ጎሉን አግብቼ ደስታዬን የገለፅኩበት መንገድ ራሱ ደግሜ ሳየው አስገርሞኛልአሰልጣኝ ጋሻው ለኔ ትልቅ ባለ ውለታዬ ነው ሁልጊዜም ጠንክሬ ጥሩ ተጫዋች እንድሆን ይመክረኛል ሳላዲን ሰኢድን እንደማሰልጠኑ ሁሌም እንደ እርሱ ዲሲፕሊንድ ሆኜ እንድወጣ ይነግረኛል ወደፊት ብዙ ነገር አስባለሁ በሀገሬ መጫወት እና የብሄራዊ ቡድን ማልያ ለብሶ መጫወት ትልቁ ህልሜ ነው አሁን ገና እየጀመርኩ ነው ከዚህ በሀላ ከእኔ ብዙ ነገር ይጠበቃል ሳላዲን እና ጌታነህ የደረሱበት ደረጃ እንደምደርስ ተስፋ አደርጋለሁ
https://soccerethiopia.net/football/63476
353
22,414
በአዲስ አበባ ከተማ ታግዶ የቆየው የመሬት መስተንግዶ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
26 September 2018
Unknown
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋርጦ የነበረው የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት መስተንግዶ በይፋ ተጀመረየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ኢንጂነር ስልጣን በተረከቡ ማግስት የመሬት ኦዲት እስኪካሄድ የመሬትና መሬት ነክ መስተንግዶ እንዳይሰጥ አግደው ነበርበዚህ መሰረት የኢንዱስትሪ አልሚዎች የመሬት ጥያቄ የሰነድ አልባና አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ በወረራ የተያዙ ቦታዎች መስተንግዶ መሬት ያልተረከቡ የመኖሪያ ቤት ሀብረት ስራ ማሀበራት መስተንግዶ እንዲሁም ምክትል ከንቲባው ስልጣን ከመረከባቸው በፊት ወጥቶ የነበረው 30ኛው የሊዝ ጨረታ ታግደው ቆይተዋል ምክትል ከንቲባው የመሬት ኦዲት በማእከልም ሆነ በክፍለ ከተማ ከተጠናቀቀ በኋላ ሰኞ መስከረም 14 ቀን 2011 አም አስሩም ክፍላተ ከተሞች መስተንግዶ እንዲጀምሩ መመርያ ሰጥተዋልየቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም ኢቲቻ ለሪፖርተር እንደገለፁት ቦሌ ክፍለ ከተማ በመመርያው መሰረት ከሰኞ ጀምሮ የመሬትና መሬት ነክ መስተንግዶ አገልግሎት ጀምሯል ነገር ግን ሀብረተሰቡ ባለመስማቱ ሊሆን ይችላል በሳምንቱ መጀመርያ አገልግሎት ለማግኘት እምብዛም አልመጣም ክፍለ ከተማው አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ሀብረተሰብ መስተናገድ ይችላል ሲሉ አቶ ፍፁም ጥሪ አቅርበዋል አቶ ፍፁም ጨምረው እንደገለፁት በማእከል ከተካሄደው የመሬት ኦዲት በተጨማሪ በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚካሄደው ኦዲትም ተጠናቋል የኦዲት ግኝቱን በቅርቡ ለሀብረተሰብ ይፋ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል  
https://www.ethiopianreporter.com/article/13109
167
12,654
የተገልጋይን እርካታ የሚጨምሩና ለኦዲት ምቹ የሆኑ የፋርማሲ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ጤና ተቋማት ተመረቁ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jan 12, 2021
144
አዲስ አበባ ጥር 4 2013 ኤፍቢሲ የተገልጋይን እርካታ የሚጨምሩና ለኦዲት ምቹ የሆኑ የፋርማሲ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ጤና ተቋማት ተመረቁበሲዳማ ክልል ለኦዲት ምቹ የሆነ የፋርማሲ አገልግሎት ለመስጠት ብቁ የሆኑ 12 ተቋማት ተመርቀው ስራ ጀምረዋልየጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ ተቋማቱን መርቀው ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የፋርማሲ አገልግሎትን የማሻሻል ኢንሺዬቲቭ በጤና ሴክተር የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ ከተጀመሩ ስራዎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋልይህም የግልፀኝነትና የተጠያቂነት ስርአትን እንደሚያጠናክር ገልፀው ቁርጠኝነት ካለ በሁሉም ተቋማት ለመተግበር ይቻላል ብለዋልየጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዮሀንስ ያታሞ በበኩላቸው በበጀት አመቱ ተጨማሪ 3 ተቋማት ወደ ስራ እንደሚገቡ የገለፁ ሲሆን ጤና ሚኒስቴር 190 የፋርማሲ ባለሙያዎችን በማሰልጠን ሙያዊና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላሳየው ድጋፍ አመስግነዋልለቀጣይ ውጤታማነም የመድሀኒት አቅርቦት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ጠቁመዋልጤና ሚኒስቴር በ2013 በጀት አመት በሀገር አቀፍ ደረጃ የ80 ጤና ተቋማትን የፋርማሲ አገልግሎትን ጥራት በማሻሻል የተገልጋዮችን እንግልት በመቀነስ እርካታ ለመጨመር እንዲሁም ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነ ለኦዲት ምቹ የፋርማሲ አገልግሎት ለማስጀመር እየሰራ መሆኑ ተመላክቷልበዚህም 54 ጤና ተቋማት የሚጠበቅባቸውን መስፈርት አሟልተው አገልግሎት መጀመራቸውን ከእነዚህም መካከል 12ቱ በሲዳማ ክልል እንደሚገኙ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታልከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘትየፋና ድረ ገፅ ይጎብኙተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8b%e1%8b%ad%e1%8a%95-%e1%8a%a5%e1%88%ad%e1%8a%ab%e1%89%b3-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8c%a8%e1%88%9d%e1%88%a9%e1%8a%93-%e1%88%88%e1%8a%a6%e1%8b%b2%e1%89%b5/
194
37,303
የኢትዮጵያ ሴቶች ሃገርአቀፍ የሰላም ጉባዔ
ሀገር አቀፍ ዜና
November 05, 2018
Unknown
በመንግስት ከፍተኛ ሀላፊነት ላይ ከተቀመጡት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ብርቱ ስራ እና ከፍ ያለ ውጤት እንደሚጠበቅ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አሳስበዋል ለዚህም ጊዜ እንደሌለና በፍጥነት ወደተጨባጭ ድርጊቶች መሸጋገር እንደሚያስፈልግ ፕሬዚዳንቷ አስገንዝበዋል
https://amharic.voanews.com//a/women-peace-confrence-in-addis-ababa-11-5-2018/4645648.html
28
12,852
የአዕምሮ ጤና ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
Jan 4, 2021
108
አዲስ አበባ ታህሳስ 26 2013 ኤፍ ቢ ሲ በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት በአእምሮ ጤና ዙሪያ የመጀመሪያ የሆነውን ሀገራዊ ውይይት አካሂዷልበውይይቱ የጤና ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ የአእምሮ ጤና በአገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ ችግር ሆኖ ሳለ በበቂ ደረጃ ትኩረት ሳይሰጠው ኖሯል ብለዋልበአእምሮ ጤና ህክምና አገልግሎት የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክረን እንሰራለን ያሉት ዶክተር ደረጄ በአምስት አመት የጤናው ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይም የአእምሮ ጤና ጉዳይ ተካቷል ብለዋልበመንግስት ደረጃም የአእምሮ ጤና የማህበረሰቡ ትልቅ ችግር እየሆነ በመምጣቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተናግረዋል የአእምሮ ጤና ህክምና አገልግሎት ላይ ተግዳሮቶች እንዳሉ የጠቆሙት የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ህይወት ሰለሞን ችግሩን ለመቅረፍ ጤና ሚኒስቴር ከባለድርሻዎች ጋር በመሆን የተጠናከረ ስረ መሰራት እንዳለበት ተናገረዋልከዚህ ጎን ለጎን የአእምሮ ጤና ህክምና አገልግሎት ተቋማት ቁጥርን ለመጨመር እና ተደራሽነቱን ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ወይዘሮ ህይወት ሰለሞን መጠቆማቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታልከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘትገፅ ይጎብኙተንቀሳየፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8b%95%e1%88%9d%e1%88%ae-%e1%8c%a4%e1%8a%93-%e1%89%b5%e1%8a%a9%e1%88%a8%e1%89%b5-%e1%88%8a%e1%88%b0%e1%8c%a0%e1%8b%8d-%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8b%b0%e1%88%9a%e1%8c%88%e1%89%a3/
165
40,883
ዩናይትድ ስቴትስ እአአ 2019 እሥራኤል የሚገኘውን ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም ታዞራለች
ዓለም አቀፍ ዜና
January 22, 2018
Unknown
የዩናይትድ ስቴትስ እስራኤል የሚገኘውን ኤምባሲዋን እአአ 2019 መጨረሻ ላይ ወደ ኢየሩሳሌም እንደምታዞር ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ዛሬ ሰኞ ተናገሩበመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ኤምባሲዋን በ2019 መጨረሻ በፊት በማዞር ረገድ ያለውን እቅድና ዝግጅት ይጀምራል ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ፕሬዚደንት ትራምፕ እንደተናገሩት ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ነችውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ኤምባሲያችንን ከቴልአቪቭ ወደ ኢየራሳሌም የማዘዋወሩን ዝግጅት በቶሎ ያጠናቅቃል ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስየውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሬክስ ቲሌርሰን ቀደም ባሉት ቀናት ሲናገሩ ኤምባሲውን የማዞሩ ስራ አመታት ሊወስድ ይችላል ማለታቸው አይዘነጋምኔታንያሁ በበኩላቸው ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዩናይትድስ ስቴትስን ኤምባሲ የእስራኤል ዋና ከተማ ወደሆነችው ኢየሩሳሌም ለማዛወር የወሰዱትን እርምጃ ታሪካዊ ብለው ማወደሳቸው አይዘነጋም
https://amharic.voanews.com//a/pence-us-embassy-will-move-to-jerusalem-in-2019-1-22-2018/4218597.html
93
46,061
ፌደሬሽኑ በሥራ አፈጻጻምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
February 16, 2017
Unknown
የኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽን ምክር ቤት ያለፉትን ሶስት አመታት  የስራ አፈፃፃም ሪፖርትን በመገምገም  የቀጣይ አምስት አመታት ስትራቴጂክ  አቅጣጫዎች ላይ  ውይይት አደረገ         ባለፉት ሶስት አመታት ፌደሬሽኑ የሴቶችን የትምህርት ተደራሽነት ለማሳደግ   የተለያዩ  ድጋፎችን  ሲያደርግ ከመቆየቱም በላይ  የሴቶችን  መብት በማስጠበቅና ጎጂ  ልማዳዊ ድርጊቶችን  በመከላከል ረገድ እንቅስቃሴ መደረጉን  የፌደሬሽኑ ፕሬዚደንት ወሮ አዜብ መስፍን ገልፀዋል         ፌዴሬሽኑ በሚቀጥሉት አምስት አመታት  የሴቶችን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ  ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የጠቆሙት ወሮ አዜብ ሁሉም  የፌዴሬሽኑ አባላት  በተመረጡባቸው አካባቢዎች  ይህንን እውን ለማድረግ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል        ሁሉም የክልል አመራሮች  ለሴቶች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ  ትብብራቸው  የላቀ እንደሚሆን እምነታቸውን የገለፁት ወሮ አዜብ  የፌዴሬሽኑን የገንዘብ ምንጭ በማጠናከር ለፌደሬሽኑ ግቦች ስኬት መታገል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋልየኢትዮጵያ  ሴቶች ፌደሬሽን  ምክር ቤት    በመላ አገሪቱ  ከ 8 ሚሊዮን  በላይ  አባላት እንዳሉት ይታወቃል  ትርጉም  በሰለሞን ተስፋዬ
https://waltainfo.com/am/31561/
117
5,574
‘‘ሚዲያው ለሀገሩ ቀናኢ የሆነነና ተግቶ የሚሰራ ማህበረሰብ ለመፍጠር መሥራት ይጠበቅበታል’’ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
ሀገር አቀፍ ዜና
November 24, 2018
31
የሰላም ሚኒስቴር ሚዲያ ለሰላም በሚል መሪ መልእክት ዛሬ በካፒታል ሆቴል ከጋዜጠኞች የሚዲያ አመራሮችና አክቲቪስቶች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል
https://www.press.et/Ama/?p=370
18
44,471
ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ 1ነጥብ1 ቢሊየን ብር ብድር ማቅረቡን አስታወቀ
ቢዝነስ
December 7, 2017
Unknown
በደቡብ ክልል የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለተሰማሩ የክልሉ ነዋሪዎች ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ማቅረቡን ገለፀየደቡብ ክልል ኦሞ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ የሺዋስ አለሙ እንዳሉት ባለፉት 5 ወራት በክልሉ በገጠር እና በከተማ በተለያዩ የስራ መስኮች ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን በላይ ብር ብድር ማሰራጨት ተችሏልየህብረተሰቡን የቁጠባ ባህል ለማጎልበት በተደረገ ዘርፈ ብዙ ጥረት ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን በላይ ብር ከቁጠባ መሰብሰብ መቻሉንም ጠቁመዋልየህብረተሰቡን የብድርና ቁጠባ አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ተቋሙ የነበሩበትን የአፈፃፀም ውስንነቶች በማረም የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ተቋማዊ የአሰራር ለውጥ በመዘርጋት እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋልተቋሙ ከተመሰረተ ጀምሮ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎች ከ13 ነጥብ 7 ቢሊዮን በላይ ብር መቆጠብ መቻላቸውን ጠቁመው የህብረተሰቡ የቁጠባ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንም አስረድተዋልከባለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት ወዲህ የህብረተሰቡ የቁጠባ አቅም እድገት ማሳየቱን የገለፁት አቶ የሺዋስ በቀጣይም በዘርፉ የሚካሄደው ሁሉን አቀፍ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋልከብድር ስርጭትና አመላለስ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፈተሽ የአገልግት አሰጣጡን በማዘመን ተደራሽነቱን ይበልጥ የማጠናከር ስራ ትኩረት እንደተሰጠው አቶ የሺዋስ አመልክተዋል
https://waltainfo.com/am/23360/
161
14,346
የመዲዋና ነዋሪዎች ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን የሚገልጹባቸው መርሃግብሮችን ለማስተባበር ዝግጅት ተጠናቋል
ሀገር አቀፍ ዜና
Nov 11, 2020
1,008
አዲስ አበባ ህዳር 2 2013 ኤፍ ቢ ሲ የከተማዋ ነዋሪዎች በተለያዩ መንገዶች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን የሚገልፁበትን የተለያዩ መርሀግብሮች ለማስተባበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀየከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ አንቺነሽ ተስፋዬ መርሀግብሮቹን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋልሀላፊዋ የመከላከያ ሰራዊቱ የፅንፈኛው የህወሀት ቡድንን ወደ ህግ ለማምጣት እያደረገ ባለው ጥረት ህብረተሰቡ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆኑን የሚገልፅበትን የድጋፍ ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ መቀበሉን ተናግረዋልበዚህም ከነገ ጀምሮ በሚካሄደው የደም ልገሳ መርሀግብር ደማችን ለወገናችን እና ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን በሚሉ እንደሚካሄድ ገልፀዋልበተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን መሆናቸውን ለመግለፅ ሰላማዊ ሰልፍ የሚደረግ ሲሆን በሰልፉም የፀጥታ ችግሮች እንዳይፈጠር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በተገቢው መንገድ ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም አመላክተዋልበተጨማሪም ህብረተሰቡ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆኑን ለማሳየት እንዲሁም ከሰራዊቱ ጎን ለተሰለፉ ሚሊሻዎች በገንዘብ እና ቁሳቁስ እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍ እንደሚደረግም ነው የተናገሩትየህወሀት የማፍያ ቡድን ስልጣን የለቀቀው በዴሞክራሲያዊ ትግል ተሸንፎ ነው ያሉት ሀላፊዋ ህብረተሰቡ እያሳየ ያለውን የአንድነት እና የሰላም እሴቶችን በማጠናከር ሀገሪቱን ወደ ተሟላ ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲ ለማሸጋገር መረባረብ ይኖርበታልም ብለዋልሰላማዊ ሰልፈኞቹም ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በመተባበር ሰልፎች በሰላም እንዲጠናቀቁ የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱና ራሳቸውንም ከኮቪድ 19 ስርጭት ለመከላከል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልእክት ማስተላለፋቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሰክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8b%b2%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%8a%90%e1%8b%8b%e1%88%aa%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8a%a8%e1%88%98%e1%8a%a8%e1%88%8b%e1%8a%a8%e1%8b%ab-%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%8b%8a%e1%89%b5-%e1%8c%8e/
190
44,116
ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን ተቀብለው አነጋገሩ
ፖለቲካ
March 9, 2018
Unknown
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ሬክስ ቲለርሰን ትናንት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀይለማርያም ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቴለርሰን  ጋር   በሁለቱ አገራት ግንኙነትና  በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋልበውይይቱ ላይ ኢትዮጵያና አሜሪካ  በልማት በፀጥታ በሰላምና በፀረ ሽብር ትግል የሚያደርጉትን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተስማምተዋልበአፍሪካ ቀንድ  ሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይም የተወያዩ ሲሆን  አካባቢው የሚከሰቱ  የፀጥታ ችግሮችን  በጋራ ለመፍታት እንደሚሰሩ  ነው ሀገራቱ የተስማሙትየውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ለሌሎች አገሮች መሪዎችም መልካም ተሞክሮ የሚሆን መሆኑን ገልፀው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል
https://waltainfo.com/am/29704/
86
4,283
በክልሉ 2 ቢሊዮን ችግኞች ይተከላሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 16, 2019
44
ሀምሌ 22 ቀን 100 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል በአማራ ክልል በዚህ ክረምት ወራት 2 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ተናገሩ ሀምሌ 22 ቀን 100 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከልም ዝግጅት ተደርጓል በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ከዞን እስከ ቀበሌ ያለው አመራር ሙያተኞች እና የቀበሌው አርሶ አደሮች በአሳግርት ወረዳ ጎላ ቀበሌ ውዱ ተፋሰስ ትናንት ችግኝ ተክለዋል በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ማርቆስ ወንዴ እንደተናገሩት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተያዘው 4 ቢሊዮን ችግኝ ውስጥ 2 ቢሊዮን በክልሉ ለመትከል ታቅዷል እስከ ሀምሌ 15 ድረስ ተከላውን ለመጨረስ ርብርብ እየተደረገ ነው እስከ ባለፈው ሳምንት በአዊና ደቡብ ወሎ ዞኖች 400 እስከ 500 ሚሊዮን የሚሆኑ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን የሌሎች አካባቢዎች ምን ያህል ችግኝ እንደተተከለ መረጃ የማሰባሰብ ስራው እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል የውሸት ሪፖርት እንዳይጨመር ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል አንድ ነጥብ 6 ቢሊዮን ገደማ ችግኞች በየችግኝ ጣቢያዎችና በግለሰብ አርሶ አደሮች ተዘጋጅተዋል ያሉት አቶ ማርቆስ በክልሉ የችግኝ ተከላ የንቅናቄ መድረኮችም እየተካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ቀን 200 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ከተያዘው ውስጥም 100 ሚሊዮኑን በክልሉ ለመትከልም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል እንደ አቶ ማርቆስ ማብራሪያ ለችግኝ ተከላው ምቹ የሆኑ አካባቢዎች ተመርጠዋል የመስኖ አውታር ያሉባቸው አካባቢዎች ከተመረጡት አካባቢዎች መካከል ናቸው ኢኮኖሚያዊ ጠቃሜታቸው ከፍ ያሉ ችግኞች በብዛት እንዲተከሉ እየተደረገ ነው በዋናነት ድርቅን የሚቋቋሙ እንዲሆኑ ጥንቃቄ ይደረጋል እያንዳንዱ ችግኝ ከተተከለ በኋላ እንዴት ይፀድቃል የሚለውን በጂፒኤስ ኮርድኔት ክትትል ይደረጋል ከሁለት አመት በኋላ እያንዳንዱ ችግኝ በምን ሁኔታ ይገኛል የሚለው ማረጋገጫ ይሰጣል ማረጋገጫው የሚሰጠው በተተከለው ልክ ሳይሆን በፀደቀው ልክ ይሆናልበደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አልማዝ አፈራ እንደሚሉት ችግኝ ከመትከል ባሻገር ለየትኛው አካባቢ ምን አይነት ችግኝ ተስማሚ ነው የሚለው ላይ ትኩረት መደረግ አለበት ይህንን ተግባር የምርምር ተቋማት ማከናወን አለባቸው ብለዋል ችግኞች ከተተከሉ በኋላም ከአርሶ አደሮቹ ባሻገር የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች እየተከታተሉ ችግኞቹን ለችግኞቹ ተገቢው እንክብካቤ እንዲደረግ ድጋፍና ክትትል ሊያደርጉ ይገባል ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ ሀገር በቀል ችግኞችን አፍልቶ በማቅረብ ለችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ስኬታማነት የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል በሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ወይዘሮ በለገ አማረ በበኩላቸው እንደተናገሩት አሁን የሚተከለው ችግኝ ለነገ የሚኖረውን ፋይዳ ስለሚያውቁ ያለማንም ጫና በችግኝ ተከላ ለመሳተፍ ወጥተዋል በመንግስት ከሚዘጋጁ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሮች ባሻገር ካለፉት 10 አመታት ወዲህ በግላቸውም ችግኞችን እየተከሉ መሆናቸውን የተናገሩት ወይዘሮ በለገ እስካሁን ድረስ ከ4 ሺህ እስከ 5 ሺክ የሚሆኑ መፅደቃቸውን አንስተዋል ከሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ችግኞቹን እንደሚንከባከቡም አንስተዋልአዲስ ዘመን ሀምሌ 92011
https://www.press.et/Ama/?p=14200
378
14,371
በህወሓት ውስጥ ያለ ቡድን ለውጊያ ያሰለፈን በግዳጅ ነው – በቁጥጥር ስር የዋሉ ታጣቂዎች
ሀገር አቀፍ ዜና
Nov 10, 2020
984
አዲስ አበባ ህዳር 1 2013 ኤፍቢሲ በህወሀት ውስጥ ያለ ቡድን ለውጊያ ካሰለፋቸው የክልሉ ልዩ ሀይልና ሚሊሻዎች መካከል በርካቶቹ በግዳጅ ወደ ጦርነት መግባታቸውን በሀገር መከላከያ ሀይል በቁጥጥር ስር የዋሉ ታጣቂዎች ተናገሩየህወሀት ጁንታ በትግራይ ክልል በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ሰራዊቱ ሀገር የማዳን ተልእኮ ተሰጥቶት በትግራይ ክልል ህግ የማስከበር ስራ ላይ ይገኛልየሀገር መከላከያ ሰራዊት በተሰጠው ተልእኮ መሰረት በምድርና በአየር የዘመቻ ስራውን እያከናወነ ሲሆን የተለያዩ ቦታዎችንና ለውጊያ የተሰለፉ ታጣቂዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ላይ መሆኑ ይታወቃልመከላከያ ሰራዊቱ በቁጥጥር ስር እያዋላቸው ካሉት ታጣቂዎች ውስጥ አብዛኞቹ እድሜያቸው ለጦርነት ያልደረሱ ታዳጊዎች ናቸውከታጣቂዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደገለፁት ህወሀት ውስጥ ያሉ አመራሮች ልጆቻቸውን በውጭ ሀገር እያስተማሩ የደሀ ልጆችን በግዳጅ ለውጊያ በማሰለፍ ህይወታቸውን እንዲያጡ እያደረጉ ነውለውጊያው እንዲሰለፉ ከተደረጉት የትግራይ ልዩ ሀይልና ሚሊሻዎች መካከል በርካቶቹ በህወሀት ተገደው ወደ ውጊያ የገቡ መሆኑንም ገልፀዋልየህወሀት ቡድን የሚያደርገውን የግዳጅ ዘመቻ ያልተቀበለ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ እስከሞት የሚደርስ ቅጣት የሚፈፀምበት መሆኑንም ተናግረዋልታጣቂዎቹ ህወሀት ህፃናትን ለጦርነት በማሰለፍ የሚፈፅመው ተግባር መቆም እንዳለበትም መልእክታቸውን አስተላልፈዋልበፅንፈኛው የህወሀት ቡድን ትእዛዝ በሰሜን እዝ የመከላከያ ሀይል ላይ የክልሉ ልዩ ሀይል ጥቃት እንዲፈፅም መደረጉም ስህተት መሆኑን ተናግረዋልበጦርነቱ በሀገር መከላከያ ሀይል በቁጥጥር ስር የዋሉት ታጣቂዎች እጃቸውን ከሰጡ በኋላ የደረሰባቸው ችግር እንደሌለና በጥሩ ሁኔታ መያዛቸውን አስረድተዋልጦርነቱን በሚመለከት በህወሀት አመራሮች የተነገራቸው ሁሉ የተሳሳተና ሀገርን የመካድ ድርጊት መሆኑን ገልፀው በርካቶች ባገኙት አጋጣሚ ህወሀትን እየከዱ መሆኑን መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%88%85%e1%8b%88%e1%88%93%e1%89%b5-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-%e1%8b%ab%e1%88%88-%e1%89%a1%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%88%88%e1%8b%8d%e1%8c%8a%e1%8b%ab-%e1%8b%ab%e1%88%b0%e1%88%88%e1%8d%88/
202
32,740
በሴካፋ የሚሳተፈው የብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ታውቋል
ስፖርት
November 29, 2017
Unknown
ከህዳር 24 ጀምሮ በኬንያ አስተናጋጅነት በ9 የክልሉ ሀገራት መካከል በሚደረገው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 27 ተጫዋቾችን በመያዝ ላለፉት 7 ቀናት ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለም ከስብስቡ ላይ 4 ተጫዋቾችን በመቀነስ ወደ ውድድሩ የሚያቀናውን የመጨረሻ ቡድናቸውን ይፋ አድርገዋልየድሬዳዋ ከተማው ተከላካይ አናጋው ባደግ የጅማ አባ ጅፋሩ ዮናስ ገረመው እና የኢትዮ ኤሌክትሪኩ ሀይሌ እሸቱ ከቡድኑ ጋር ወደ ኬንያ የማይጓዙ ተጫዋቾች ሲሆኑ የኢትዮጵያ ቡናው አማካይ መስኡድ መሀመድ ሀሙስ ክለቡ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው ጨዋታ ካጋጠመው ጉዳት ማገገም ባለመቻሉ ከቡድኑ ውጪ ሆኗልዝርዝርግብ ጠባቂዎች 3ታሪክ ጌትነት ደደቢት በረከት አማረ ወልዋሎ ተክለማርያም ሻንቆ ሀዋሳ ከተማተከላካዮች 7ቴዎድሮስ በቀለ መከላከያ አበበ ጥላሁን ሲዳማ ቡና አበባው ቡታቆ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግርማ በቀለ ኤሌክትሪክ አምሳሉ ጥላሁን ፋሲል ተመስገን ካስትሮ አርባምንጭ ከተማ ኄኖክ አዱኛ ጅማ አባ ጅፋርአማካዮች 6ሳምሶን ጥላሁን ኢትዮጵያ ቡና ተስፋዬ አለባቸው ወልዲያ ከነአን ማርክነህ አዳማ እንዳለ ከበደ አርባምንጭ ብሩክ ቃልቦሬ ወልዲያ ፍሬው ሰለሞን ሀዋሳ ከተማአጥቂዎች 7አቡበከር ሳኒ ቅዱስ ጊዮርጊስ አብዱራህማን ሙባረክ ፋሲል ከተማ አዲስ ግደይ ሲዳማ ቡና ዳዋ ሁቴሳ አዳማ ከተማ አማኑኤል ገብረሚካኤል መቐለ ከተማ አቤል ያለው ደደቢት ፀጋዬ ብርሀኑ ወላይታ ድቻዋልያዎቹ ነገ ጠዋት 2 ሰአት ላይ ወደ ናይሮቢ የሚያቀኑ ሲሆን በምእራብ ኬንያ ከዋና ከተማዋ 360 ኪሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው ካካሜጋ የሚጓዙ ይሆናል ውድድሩ እሁድ ተጋባዧ ሊብያ ከታንዛኒያ ጋር በሚታደርገው ጨዋታ ሲጀመር ሰኞ በ8 ሰአት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከብሩንዲ አቻው ጋር በካካሜጋው ቡክሁንጉ ስታዲየም የሚጫወት ይሆናልበተያያዘ ዜና በ2017ቱ የምስራቅ እና መካከለኛው ዋንጫ ተሳታፊ እንዲሆኑ ከተጋበዙ 2 ቡድኖች አንዱ የሆነው እና ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ ለ ተደልድሎ የነበረው የዚምባቡዌ ብሄራዊ ቡድን ራሱን ከውድድሩ እንዳገለለ አስታውቋል የዚምባቡዌ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ በኬንያ ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት የተነሳ ለተጫዋቾቹ ደህንነት አስተማማኝ ዋስትና ማጣቱን በውድድሩ ላለመሳተፉ በምክኒያትነት አስቀምጧል ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በምድብ ጨዋታዎች ከብሩንዲ ዩጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ጋር ብቻ የሚገናኝ ይሆናል
https://soccerethiopia.net/football/31544
281
47,939
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በካርቱም እየተወያዩ ነው
ፖለቲካ
December 9, 2013
Unknown
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ መካከል በሚኒስትሮች ደረጃ የሚደረገው ውይይት በካርቱም መካሄድ ጀመረሀገራቱ  በካርቱም የሚወያዩት የታላቁን የህዳሴ ግድብ መሰረት በማድረግ በአባይ ውሀ አጠቃቀም ላይ  ነውየመጀመሪያ ዙር ውይይት በሶስቱ ሀገራት የውሀ ኢነርጂና መስኖ ሚኒስትሮች ጥቅምት ወር ላይ የተደረገ ሲሆን ትናንት የተጀመረውም ሁለተኛው ዙር ከዚህ የቀጠለ ነውውይይቱ በዋናነት አለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን ግድቡን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት ላይ በቀጣይ ሊታዩ ይገባል ያላቸውን ነጥቦች የሚመለከት የጋራ ኮሚቴ ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኩራል ተብሏልበመጀመሪያው ዙር ውይይት ሶስቱ ሀገራት የተካተቱበት አለም አቀፍ የአጥኝዎች ቡድን ባቀረበው ሪፖርት ላይ ግብፅ  ባቀረበችው ሀሳብ ሳይስማሙ መለያየታቸው ይታወሳልከትናንቱ ስብሰባ አስቀድሞ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መንግስታቸው ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረው ነበር ኤፍቢሲ
https://waltainfo.com/am/28360/
109
22,949
በጃኖ የደመቀው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ክልል ጉብኝት
ፖለቲካ
22 April 2018
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዶር በጎንደር ከተማ ተገኝተው ከከተማዋና ከአጎራባች ወረዳዎች ከመጡ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አደረጓርብ ሚያዝያ 12 ቀን 2010 አም ከማለዳው የጀመረው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በመጀመርያ በአፄ ፋሲል ስታዲዮም ለተሰበሰቡ በሺዎች ለሚቆጠሩ የከተማዋና የአጎራባች ወረዳ ነዋሪዎች ንግግር አድርገዋል በባህላዊ ጃኖ ልብስ ደምቀው የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ይህ ህዝብና ይህ ምድር በገዥዎች ጭካኔ በትር ይሳደዱ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ለማትረፍ መስዋእትነት የከፈለ ኢህዲንን የመሰረቱት ያልተንበረከኩ ቆራጥ ታጋዮች ያፈራ ህዝብ ነው ሲሉ አሞካሽተዋል ባሳለፍናቸው ትግሎች በርካታ የአማራ ወጣቶች በአደባባይ ተረሽነው ሬሳቸው ሜዳ ተጥሏል ታስረዋል ተገርፈዋል አካላቸው ጎሏል ሲሉ ዘክረዋል ጎንደር ለማእከላዊ መንግስት ምስረታ ያደረገችውን አስተዋፅኦና ታሪካዊ አበርክቶዋን ዳሰዋልበተጨማሪም ህዝቡ ከጎናቸው እንዲቆምና እንዲያግዛቸው ጠይቀዋል ከጎናችን እስካላችሁ ድረስ በምንችለው ፍጥነትና መጠን ተረባርበን በመስራት በጥበብ የማናቋርጠው የህይወት እክል በፍፁም ሊኖር አይችልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንዲሁም ከሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ታጅበው ከህዝቡ ጋር ውይይት አድርገዋል በውይይታቸውም ከተለያዩ አካላትና ግለሰቦች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል በውይይቱ ወቅት ከወልቃይት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለተነሳላቸው ጥያቄ ጉዳዩ በህግ አግባብ ሊፈታ እንደሚችል ህገ መንግስቱም ይህን ጉዳይ ሊፈታ ይችላል ብለው መናገራቸው ተደምጧል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ ከወልቃይት ኮሚቴ አባላት ጋር ተገናኝተው በጉዳዩ ላይ እንደሚወያዩ መናገራቸውን የአማራ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ዘገባ ያመለክታል ከሁለቱ አመት በፊት የወልቃይት ኮሚቴ አባላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በተፈጠረ ችግር ጎንደር ከተማን ጨምሮ በክልሉ የህዝብ ተቃውሞና የፀጥታ ችግር ማጋጠሙ ይታወሳል  በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የወልቃይት ኮሚቴ አባላትም በቅርቡ ከእስር መፈታታቸው ይታወሳል በሱዳን ድንበር ላይ ከሚከሰቱ ግጭቶችና ከመሬት ጥያቄ ጋር በተያያዘም ባህር ዳር ለጣና ፎረም ጉባኤ ይመጣሉ ተብሎ ከሚጠበቁት የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አል በሽር ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ለጊዜው ድንበር ላይ የሰፈሩ የሁለቱም አገሮች ወታደሮች ገለል እንዲሉ ይደረጋሉ ብለዋል በተጨማሪም ከመሰረተ ልማት መጓደል ጋር በተያያዘ አዳዲስ መንገዶች ትምህርት ቤቶች በቂና በጥራት እንደሌላቸው ተጠይቀዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩም ያነሳችኋቸው የመሰረተ ልማት ግንባታ ጥያቄዎች ማለትም እዚሁ ወረዳን ከወረዳ ጋር ማገናኘት ዞን ከዞን ጋር ማገናኘት የፌዴራል መንግስትን አይመለከትም ይኼ የክልል መንግስት ሀላፊነት ነው ብለው የፌዴራል መንግስት ዋና ስራ ጎንደርን ወደ ትግራይ ወደ ሱዳን ከዚያም ሲያልፍ በወሎ በኩል ከጂቡቲ ጋር ማገኛነትና ከዚያም ባለፈ በክልል አቅም የማይሰሩ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት ነው በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎንደር ጉብኝታቸውን ጨርሰው ወደ ባህር ዳር አቅንተዋል በባህር ዳር ቆይታቸውም ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ውይይትና ምክክር እንደሚያደርጉና የጣና ፎረም ስብሰባን እንደሚሳተፉ የተያዘላቸው መርሀ ግብር ያስረዳል  
https://www.ethiopianreporter.com/article/10106
348
21,181
በአዲስ-ጂቡቲ የባቡር ፕሮጀክት ላይ የተካሄደ ጥናት የኃይልና የፋይናንስን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች አገልግሎቱን እንዳስተጓጎሉት ይፋ አደረገ
ቢዝነስ
29 December 2019
Unknown
የአዲስ አበባጂቡቲ የባቡር ፕሮጀክት በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዳይሆን የህግ ማእቀፍ ችግሮችን ጨምሮ የኤሌክትሪክ ሀይል የጥገና አገልግሎትና የመለዋወጫ ችግሮች እንዲሁም የፋይናንስ አቅርቦት እጦት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቱን እንዳስተጓጎሉት በአገር በቀል አማካሪ ድርጅት የተካሄደ ጥናት ይፋ አደረገ ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንስ ኢንተርናሽናል ኮንሰልት የተሰኘው አገር በቀል አማካሪ ድርጅት ይፋ ባደረገው ጥናት መሰረት በአዲስ አበባና በጂቡቲ የባቡር መስመር ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ48 ሺህ ሰአታት ያላነሰ ጊዜ ወይም በአንድ አመት ውስጥ ከ131 ቀናት በላይ የኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ሲያጋጥመው መቆየቱ በጥናቱ ታውቋል የአማካሪ ድርጅቱ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌዲዮን ገሞራ ጃለታ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት ይህንን ችግር ጨምሮ የህግ ማእቀፍ ክፍተቶችና ባቡሩ በሚጓዝባቸው መስመሮች የሚያጋጥሙ አደጋዎች የባቡር ትራንስፖርቱን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ እያወኩት ነው እስካለፈው ጥቅምት ወር የተመዘገቡ 573 አደጋዎች እንደተከሰቱ ጥናቱ አመላክቶ በሚያዝያ ወር 2012 አም በምስራቅ ሸዋ ዞን ያጋጠመው ከባድ አደጋ ዋናው ተጠቃሽ እንደነበር አስታውሷል 53 ተጎታች ፉርጎዎች የነበሩት ባቡር የደረሰበት አደጋ ከ200 እስከ 300 ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት እንደደረሰበት በዚህ ሳቢያም ለበርካታ ቀናት የባቡር መስመሩ ከእንቅስቃሴ ውጪ ሆኖ ለመቆየት መገደዱን ጠቅሷል በየጊዜው የእንስሳት ግጭት የሚደርስበት የባቡር መስመሩ በተደጋጋሚ በሚያጋጥመው የኤሌክሪክ ሀይል መቋረጥ ሳቢያም ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች እየተሰረቁ እንደሚወሰዱበት ይህም ተጨማሪ ወጪዎችንና መስተጓጎሎችን እያስከተለበት እንደሚገኝ ተገልጿል በጥቅምት ወር ብቻ ከ6742 ጊዜ በላይ የሀይል መቋረጥ እንዳጋጠመም ተመልክቷል የሀይል መቋረጥ በሚያጋጥመበት ወቅት ከ60 በመቶ በላይ ለሶስት ሰአታት እንደሚቆይ ሶስት በመቶ የሚገመቱና ቀላል የሚባሉት አብዛኛውን ጊዜ ከአንድ ቀን በላይ መልሰው ሳይስተካከሉ እንደሚቆዩ ጥናቱ አሳይቷል በጥገና ረገድም የባቡር ኦፕሬሽኑን ፈተና ውስጥ የጣሉ የጥገናና የመለዋወጫ ችግሮች በሰፊው እንደሚታዩ ተጠቁሞ በተለይም መሰረታዊ ችግሮች እያጋጠማቸው እንደሆኑ ተመልክቷል ስምንት በኤሌክትሪክ ከሚሰሩ 35 የሎኮሞቲቮች ክፍሎች ውስጥ 23 ክፍሎች መሰረታዊ ችግር እንደሚታይባቸው ስድስት ክፍሎች ካሏቸው ሁለት የናፍጣ ሎኮሞቲቮች 34 በመቶው ችግር እንዳጋጠሟቸው አራት የመንገደኞች ፉርጎዎች ካሏቸው 30 ክፍሎች ውስጥ 14 በመቶ ያህሉም ተመሳሳይ ችግር ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል ከ502 ያላነሱ የጭነት ባቡር ክፍሎች ውስጥ አብዛኞቹ እክል ሲታይባቸው የኩሽኔታ ዘይት ማንጠባጠብ በፍሬን አካባቢ የአየር ማስረግና የመሳሰሉት የቴክኒክ ችግሮች የባቡሩን የደሀንነት ደረጃ ጥያቄ ውስጥ እንደሚጥሉት ከጥናቱ ውጤቶች ለመረዳት ተችሏል እንዲህ ያሉትን ችግሮች ቀርፎ የባቡሩን ጤንነት የሚያረጋግጥ ዘላቄታዊነቱንና ቀጣይነቱን የሚያስጠብቅ የፋይናንስ አቅርቦት ለማግኘት አለመቻሉም የባቡሩን ዋስትና ጥያቄ ውስጥ ከጣሉት መካከል ተካቷል ከቻይና መንግስት በተገኘ ብድር ከአምስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት የአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር ፕሮጀክት በሁለቱ መንግስታት መካከል ብሎም በቻይናና በኢትዮጵያ መንግስታት በኩል ተጨማሪ ትብብሮችንና ስምምነቶችን በመፈፀም የባቡር መስመሩን ህልውና ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግ አቶ ጌዲዮን አሳስበዋል ከሁለት አመታት ባነሰ የአገልግሎት ቆይታው የአዲስጂቡቲ የባቡር መስመር ከ160 ሺህ ያላነሱ መንገደኞችንና ከ1240 ቶን በላይ ጭነቶችን በማመላለስ 60 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ
https://www.ethiopianreporter.com/article/17676
379
17,071
ኤጀንሲው በጃክ ማ የተበረከቱ የህክምና ቁሳቁሶች እያሰራጨ መሆኑን ገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
Apr 21, 2020
323
አዲስ አበባ ሚያዚያ 13 2012 ኤፍቢሲ የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በመጀመሪያ ዙር በጃክ ማ የተበረከቱትን የኮሮናቫይረስ ኮቪድ19 መመርመሪያ መሳሪያዎችና የህክምና መገልገያዎችን እያሰራጨ መሆኑን አስታወቀበጃክ ማ ሁለተኛ ዙር የተሰጠው ድጋፍም ለስርጭት ዝግጁ ሆኗል ተብሏልበመጀመሪያ ዙር በእርዳታ የተሰጠውን የኮቪድ19 መመርመሪያ ኪቶችና የህክምና መገልገያዎች እየተሰራጩ መሆኑን የኤጀንሲው መድሀኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች የመጋዘንና የክምችት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው መኮንን ገልፀዋልቫይረሱ መኖር አለመኖሩን ለመለየት የሚያስችሉ 20 ሺህ 89 የመመርመሪያ ኪቶች 47 ሺህ 950 N95 የፊት መሸፈኛ ጭምብል 1 ሺህ 100 መከላከያ ሙሉ ፕላስቲክ ልብሶች 52 ሺህ የፊት መሸፈኛ ጭምብል እና 1 ሺህ የፊት መከላከያ ፕላስቲክ በመሰራጨት ላይ ናቸውየህክምና ግብአቶቹ ስርጭት በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥያቄ መሰረት እየተካሄደ መሆኑም ታውቋልበጃክ ማ በሁለተኛ ዙር የተሰጠው ድጋፍም በኤጀንሲው መጋዘኖች ገብተው ለስርጭት ዝግጁ ሆነዋል ብለዋል ዳይሬክተሩኤጀንሲው ከዚህ ቀደም በቻይና መንግስት በእርዳታ የተሰጠውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ የሙቀት መጠን መለኪያ ኢንፍራሬድ ቴርሞሜትር ጨምሮ ሌሎች የህክምና ግብአቶችን ማሰራጨቱን አውስተዋልበጃክማ ፋውንዴሽን ለተደረገው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍም አቶ እንዳልካቸው ምስጋና ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a4%e1%8c%80%e1%8a%95%e1%88%b2%e1%8b%8d-%e1%89%a0%e1%8c%83%e1%8a%ad-%e1%88%9b-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8a%a8%e1%89%b1-%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8a%ad%e1%88%9d%e1%8a%93-%e1%89%81/
155
295
ከተሞች ለቅርጫት ኳስ ያላቸውን ግምት ትዝብት ላይ የጣሉበት ውድድር
ስፖርት
February 11, 2020
17
የቅርጫት ኳስ ስፖርት በአለማችን ላይ ተወዳጅ ከሆኑ ስፖርቶች መካከል በቀዳሚነት ይቀመጣል በአገራችንም ቢሆን የቅርጫት ኳስ ስፖርት ጥሩ እንቅስቃሴ የሚደረግበትና በተለይም በከተሞችና ትምህርት ቤቶች አካባቢ በወጣቶች እጅግ ተወዳጅ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ስፖርቱን ለማስፋፋትና ለማሳደግ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን የቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲካሄድ ማድረጉ አንዱ ትልቅ እርምጃ ነው ከዚህ ጎን ለጎን ስፖርቱ ሰፊ መሰረት ያለው በከተሞች አካባቢ እንደመሆኑ ከሰባት አመት በፊት የከተሞች የቅርጫት ኳስ ውድድርን በየአመቱ በማካሄድ አበረታች እርምጃ ወስዷል ፌዴሬሽኑ ዘንድሮም የከተሞችን የቅርጫት ኳስ ውድድር ከኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር በቢሾፍቱ ከተማ እንዲካሄድ አድርጓል ለአምስት ተከታታይ ቀናት ተካሂዶ ባለፈው አርብ በተጠናቀቀው የከተሞች የቅርጫት ኳስ ውድድር በወንዶች መካከል በሚደረገው ፉክክር አዘጋጁ ቢሾፍቱ ከተማን ጨምሮ አዳማድሬዳዋሀረሪቡታጅራ ከተሞች እንዲሁም የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ተሳታፊ ሆነውበታል በሴቶች መካከል በሚደረገው ፉክክር ግን ባልተጠበቀ መልኩ አሰላ ከተማና የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ብቻ ተሳታፊ ሆነዋል ከመሀል አገር ራቅ ያሉ ከተሞች በውድድሩ ለመሳተፍ ያሳዩትን ተነሳሽነት ያህል በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች በፉክክሩ ላይ መገኘት አለመቻላቸው ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ መሆኑ የአገራችን ከተሞች ለስፖርቱ እየሰጡት ያለውን ትኩረት ትዝብት ላይ የጣለ ነው አንዳንድ ከተሞች በውድድሩ መሳተፍ ያልቻሉት የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው የቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው ሲሆን ራቅ ያሉት ከተሞች በአገራችን ከሚታየው የፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ ምክኒያት እንደሆነ የፌዴሬሽኑ የስራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ ይመር ሀይሌ ለአዲስ ዘመን ገልፀዋልበዚህ ውድድር አግራሞትን ካጫሩት ሁነቶች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አፍንጫው ስር በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ በሚካሄድ ውድድር በወንዶችም በሴቶችም መሳተፍ አለመቻሉ ነው ከተማውን በሁለቱም ፆታ ወክለው ለመወዳደር ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩት ወጣቶች ከበጀት እጥረት ጋር በተያያዘ መጨረሻ ሰአት ላይ መሳተፍ እንዳልቻሉ ከተለያዩ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል አዲስ አበባ በየወረዳው እንኳ መሳተፍ የሚያስችል እምቅና ሀይል ያለው መሆኑ ይታወቃል በየትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ያለውን የአዲስ አበባ የወጣቶች ቅርጫት ኳስ ፍቅርና አቅምን አሰባስቦ አለመሳተፉ አሳፋሪ ነው በአገራችን ከሚገኙ ከተሞች ሁሉ በአፍሪካ ደረጃ ለሚካሄዱ ውድድሮች ጠንካራ ቡድን መገንባት የሚያስችል የቅርጫት ኳስ ፍቅር ጉልበት የፋይናንስና የተጫዋቾች አቅም ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ነገር ግን በዚህ የወጣቶችን ችሎታ አቅምና ጉልበት ለማወቅና ጠንካራ ቡድንን ለመገንባት የሚረዳ የከተሞች ውድድር ላይ አዲስ አበባ ለማሸነፍ ወይም ለመወዳደር ለምን እንዳልቻለ ወይም እንዳልፈለገ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶት ማስተካከል መቻል እንዳለበት የብዙዎች እምነት ነውአዲስ አበባ የአፍሪካና የኢትዮጵያ መዲና ናት ወጣቶች ታዳጊዎችና ህፃናት በስፖርት እንዲሳተፉ እድል በመስጠት በስነልቦናና በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ መገንባት በአገር ደረጃ ትውልድን ከሱስና አልባሌ ስፍራ ማራቅ ብቻም ሳይሆን ከተሞቻችንንና ትውልድን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል ግዴታ እንጂ ውዴታ አይደለም አዲስ አበባ በበጀት እጥረት በውድድሩ አለመሳተፉ የማይመስል ነገር ነው የከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን የቅርጫት ኳስ ውድድሩ ከተጠናቀቀ አንድ ቀን በኋላ እዚያው ቢሾፍቱ ላይ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ የስፖርት ማህበራት አመራሮችን ለሁለት ቀን ሰብስቦ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሲሰጥ ነበር በዚህ ስልጠና ላይ ሰላሳ አምስት ከሚጠጉ የስፖርት ማህበራት የተውጣጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል ለዚህም የሁለት ቀን ስልጠና ከተማ አስተዳደሩ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ማድረጉ አይቀሬ ነው ጥያቄው ከተማ አስተዳደሩ በስሩ የሚገኙ የስፖርት ማህበራት አመራሮችን አያሰልጥን ሳይሆን ቅድሚያ ለየትኛው መስጠት አለበት ይሆናል በቅርጫት ኳስ ውድድሩ በሁለቱም ፆታ ለመሳተፍ ቢበዛ ሀያ የሚሆን ተጫዋችና የልኡካን ቡድን ነው የሚያስፈልገው የበጀት እጥረት ቢኖር እንኳን ውድድሩ በቅርብ ርቀት እንደመካሄዱ ተጫዋቾች እየተመላለሱ እንዲሳተፉ ማድረግ ቀላሉ አማራጭ ነበር የከተማ አስተዳደሩ የስፖርት ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ በአመራሮቹ ስልጠና ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባን የስፖርት ማእከልነት መልሰን እንገነባለን ሲሉ ተደምጠዋል የከተማዋን የስፖርት ማእከልነትና ገፅታ መገንባት ከተማዋ በስፖርቱ ያላትን ትልቅ አቅም አውጥታ በማሳየት እንደ ቅርጫት ኳስ ውድድሩ ባሉ አገር አቀፍ መድረኮች ተሳታፊ በመሆንና ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ በመስጠት እንደሚጀምር ሌሎቹም ቢሆኑ ሊማሩበት ይገባል አዲስ ዘመን የካቲት 32012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=27070
550
28,384
ስሑል ሽረዎች የአማካያቸውን ውል ለማራዘም እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ
ስፖርት
February 1, 2020
Unknown
ባለፈው አመት አጋማሽ ፋሲል ከነማን ለቆ ወደ ስሁል ሽረ በማምራት ከቡድኑ ጋር የተሳካ አንድ አመት ያሳለፈው ዩጋንዳዊው ያስር ሙገርዋ ከስሁል ሽረ ጋር ያለውን ውሉን ለማራዘም ከጫፍ ደርሷልተጫዋቹ ባለፈው ሳምንት በግል የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ወደ ዩጋንዳ ፕሪምየር ሊግ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ የሚሰጥ ፅሁፍ መለጠፉን ተከትሎ ወደ ሀገሩ ይመለሳል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይህ አማካይ ውሉን ለማራዘም ወደ አዲስ አበባ አቅንቶ ሂደቶችን የጀመረ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ሂደቱ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ተጫዋቹ ምንም እንኳ ከአዲስ አበባ የቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ቡድኑ ቢቀላቀልም የአንድ አመት ውሉ በመጠናቀቁ ምክንያት ከነገው ጨዋታ ውጭ መሆኑ ተረጋግጧልበኢትዮጵያ ቆይታው ለቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ መጫወት የቻለው ያሳር ሙገርዋ ከዚህ በፊት ለኦርላንዶ ፓይሬትስ እና ለሀገሩ ብሄራዊ ቡድን መጫወቱ ይታወሳል ሶከር ኢትዮጵያ
https://soccerethiopia.net/football/55198
113
26,583
ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ድሬዳዋ ከተማ ሦስተኛ ተከታታይ ድሉን አሳካ
ስፖርት
January 17, 2021
Unknown
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት የእለቱ ሁለተኛ ጨዋታ በድሬዳዋ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ መካከል ተደርጎ በመጨረሻም በድሬዳዋ ከተማ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል1000 ሲል የሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሳር ላይ ሁለተኛውን የቀኑን ጨዋታ አስተናግዷል ድሬዳዋ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ደግሞ ተጋጣሚ ቡድኖቹ ናቸው በእንቅስቃሴ ረገድ ተዳክሞ በታየው እና ተመሳሳይ ይዘት በነበረው የመጀመሪያው አጋማሽ ድሬዳዋ ከተማ በጥልቀት ከመስመር በሚያገኙት አጋጣሚ እድሎችን ለመፍጠር ጥረት ያደረጉበት አርባምንጮች በአንፃሩ ወጥነት ባይታይባቸውም የድሬዳዋን የመከላከል ክፍተት ለመጠቀም ሞክረዋልበመሰረት ወርቅነህ ሙከራ አርባምንጮች ወደ ግብ መጠጋት ቢችሉም ለማጥቃት ያላቸው ጥንካሬ የተቀዛቀዘ በመሆኑ ከዚህች አጋጣሚ ውጪ የጠራ እድልን መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋልየአሰልጣኝ ብዟየው ጀምበሩው ድሬዳዋ የአርባምንጭን ክፍተት እየተጠቀሙ በፈጣን የመልሶ ማጥቃት በቀኝ በኩል ባዘነበለ አጨዋወት ወደ ፊት ሲሄዱ ተስተውሏል በተለይ ከቀኝ መስመር በመነሳት ፀጋነሽ ወራና ወደ ሳጥን ተጠግታ በመጫወት ስታደርግ የነበረው እንቅስቃሴ እና ቁምነገር ካሳ የአርባምንጭን የተከላካይ ክፍል በመረበሽ ስታደርግ የነበረበት መንገድ በተወሰነ መልኩ ለድሬዳዋ ብልጫ መውሰድ አስተዋፅኦ ነበረውፀጋነሽ ከቁምነገር ያገኘችሁን በቀጥታ መታ ግብ ጠባቂዋ ድንቡሽ አባ የያዘቻት ከቅጣት ምት ሀሳቤ ሙሶ አክርራ መታ በተመሳሳይ ድንቡሽ የመለሰችባት አጋጣሚ ድሬዳዋ ለመሻሉ ፍንጭ ሰጪ መልካም ሙከራዎች ነበሩ ማለት ይቻላልይህ ጥረታቸው ፍሬ አፍርቶ 36ኛው ደቂቃ ላይ የአርባምንጭ ተከላካዮች ባሳዩት ደካማ ቅብብል ጥበበኛዋ አማካይ ማእድን ሳህሉ የተቋረጠውን ኳስ አግኝታው ጣጣውን ጨርሳ ለቁምነገር ካሳ ሰጥታት አጥቂዋም ወደ ጎልነት ለውጣው ድሬዳዋን መሪ አድርጋለች በቀሪው ደቂቃም ምንም ለውጥ ሳይታይ በድሬዳዋ 1 ለ 0 ወደ መልበሻ አምርተዋልከእረፍት መልስ በነበረው እንቅስቃሴ አርባምንጮች ከመጀመሪያው አጋማሽ ፍፁም ተሻሽለው ወደ ሜዳ የገቡበት ቢሆንም ከፊት መስመሩ ላይ የነበራቸው ድክመት ግን እጅጉን ደካማ ነበረ ሆኖም በመልሶ ማጥቃት የግራ እና ቀኝ ኮሪደሩን በቀላሉ ሲጠቀሙበት የተስተዋሉት ድሬዳዋ ከተማዎች በዚህኛው አጋማሽ በቁምነገር ካሳ አማካኝነት ቶሎ ቶሎ ወደ ጎል ቀርበው ታይተዋል 65ኛው ደቂቃ ላይ የድሬዳዋ ግብ ጠባቂ ሂሩት ደሴ በአርባምንጯ አጥቂ መቅደስ ከበደ ላይ በሳጥን ውስጥ የሰራችሁን ጥፋት ተከትሎ የእለቱ ዋና ዳኛ ምስጋና ጥላሁን የሰጠችውን ፍፁም ቅጣት ምት መሰረት ወርቅነህ በሚገባ ተጠቅማ አስቆጥራ አርባምንጭን አቻ አድርጋለችበመጨረሻዎቹ አስራ አምስት ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች ቅርፅ ያለው እንቅስቃሴ ማሳየት ባይችሉም አሰልጣኝ ብዟየው ጀምበሩ ያደረገቻቸው ሁለት ቅያሬዎች ቡድኑ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ረድቶታል 81ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይራ የገባችሁ እና ከመቐለ ድሬዳዋን ከሰሞኑ የተቀላቀለችሁ ትንቢት ሳሙኤል ከቀኝ በኩል ከሀሳቤ ሙሶ የመጣችን ኳስ አቋቋሟ ጥሩ ለነበረው ፀጋነሽ ወራና አቀብላ የመስመር አጥቂዋም የቀድሞው ክለቧ ላይ ጎል አስቆጥራ ጨዋታው በድሬዳዋ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋልድሬዳዋ ከተማም ከሽንፈት መልስ ይሄ ተከታታይ ሶስተኛ ድልም ሆኖለታልከጨዋታው መጠናቀቅ በሀላ የድሬዳዋ ከተማዋ የተከላካይ አማካይ እታለም አመኑ የጨዋታው ምርጥ ተብላ በልሳን የሴቶች ስፖርት ሽልማት ተበርክቶለታል
https://soccerethiopia.net/football/63533
373
23,732
ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ስኳር ኤክስፖርት አደረገች
ቢዝነስ
30 August 2017
Unknown
በኬንያ አዲስ ገበያ ተፈጥሯል የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመ ከ2003 አም ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ስኳር ኤክስፖርት ተደረገ መንግስት ከኬንያ መንግስት የቀረበለትን ጥያቄ በመቀበል ለስኳር ኮርፖሬሽን በሰጠው መመርያ መሰረት 43 ሺህ ኩንታል ስኳር ወደ ኬንያ ተልኳልስኳር ኮርፖሬሽን በ2003 አም ከመቋቋሙ በፊት የአውሮፓ ሀብረት ለታዳጊ አገሮች ከጦር መሳሪያ በስተቀር የሚያመርቱትን ምርት ከቀረጥ ነፃ እንዲልኩ በሚሰጠው  እድል ኢትዮጵያ ያላለቀለት ስኳር ወደ አውሮፓ ትልክ እንደነበር ይታወሳልከዚያ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ ስኳር ወደ ውጭ መላከ ከማቋረጧም በላይ በአገር ውስጥም ከፍተኛ የስኳር እጥረት በመከሰቱ እስከ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ድረስ ከውጭ ስታስገባ ቆይታለችየስኳር ኮርፖሬሽን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጋሻው አይችሉም ለሪፖርተር እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከኬንያ መንግስት በቀረበላት ጥያቄ መሰረት 43 ሺህ ኩንታል ስኳር ወደ ውጭ ልካለችየኬንያ መንግስት ጥያቄ የመጣው ኮርፖሬሽኑ በጥሩ ዋጋ ኤክስፖርት ለማድረግ በአገር ውስጥ እጥረት ከተፈጠረም ኢምፖርት ለማድረግ ባቀደበት ጊዜ ነው በማለት አቶ ጋሻው ገልፀዋልበአሁኑ ወቅት ኬንያ ለኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ሁነኛ መዳረሻ መሆን ጀምራለች በተለይ በተጠናቀቀው በጀት አመት ኬንያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ አገሮች በድርቅ ከተመቱ በኋላ ኢትዮጵያ ለኬንያ ገበያ በቆሎ አቅርባለች የኬንያ ገበያ ከበቆሎ በተጨማሪ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን እንዲሁም የኢንዱስትሪ ምርት ለሆነው ስኳር ሁነኛ መዳረሻ መሆኑ እንደታመነበት አቶ ጋሻው ገልፀዋልበሚቀጥለው 2010 በጀት አመት ነባሮቹን ጨምሮ ስምንት የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ምርት ይገባሉ በበጀት አመቱ በአጠቃላይ 65 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ይመረታል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ጋሻው ተናግረዋልየአገሪቱ የስኳር ፍላጎትም ከዚሁ ምርት ጋር የሚቀራረብ በመሆኑ ስኳር ኮርፖሬሽን ጥሩ ዋጋ በሚገኝበት ወቅት ወደ ውጭ ለመላክ እጥረት በሚፈጠርበት ወቅት ደግሞ ከአራማጭ ገበያዎች ወደ አገር ለማስገባት አቅዷልከ43 ሺህ ኩንታል በተጨማሪ ስኳር ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የስኳርና የተለያዩ የስኳር ተረፈ ምርቶችን ለአለም ገበያ ለማቅረብ የጥራት ሰርተፊኬት  የምርት መለያ ብራንድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተመልክቷልበአሁኑ ወቅት ሁሉም ስኳር ፋብሪካዎች በእድሳት ላይ በመሆናቸው ስራ አቁመዋል ይሁንና እንደ አቶ ጋሻው ገለፃ በቂ አቅርቦት አለስኳር እየተከፈፈለ የሚገኘው ንግድ ሚኒስቴር በሚያወጣው ኮታ መሰረት በሸማች ማሀበራት በሀብረት ስራ ማሀበራት በኢትፍሩትና በቀድሞ ጅንአድ አማካይነት ነው
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%8A%A8%E1%8A%A0%E1%88%9D%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%8B%93%E1%88%98%E1%89%B5-%E1%8B%88%E1%8B%B2%E1%88%85-%E1%88%88%E1%88%98%E1%8C%80%E1%88%98%E1%88%AD%E1%8B%AB-%E1%8C%8A%E1%8B%9C-%E1%88%B5%E1%8A%B3%E1%88%AD-%E1%8A%A4%E1%8A%AD%E1%88%B5%E1%8D%96%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%8B%B0%E1%88%A8%E1%8C%88%E1%89%BD
281
33,641
ስዩም ከበደ ከአአ ከተማ አሰልጣኝነት ለቀቁ
ስፖርት
February 28, 2017
Unknown
ከየመኑ አልዋሂዳ ሰንአ ከተመለሱ በኋላ በ2008 የውድድር ዘመን መጀመርያ አዲስ አበባ ከተማን የተቀላቀሉት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በመጀመርያ አመት የክለቡ ቆይታቸው ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ያደረጉ ሲሆን ክለቡ በዘንድሮው አመት የፕሪምየር ሊግ ቆይታ የመጨረሻ ደረጃን ይዞ ይገኛል አሰልጣኝ ስዩምም በአመቱ መጀመርያ በሚፈልጉት መንገድ የዝግጅት ጊዜ እና ተጫዋቾች አለማግኘታቸው በውጤት ላይ ተፅእኖ እንደፈጠረ እና ነገሮችን ለማስተካከል መጣራቸውን ገልፀው  ክለቡ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲሸጋገር መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ክለቡን ለመልቀቅ እንደወሰኑ በደብዳቤ አስታውቀዋልበጉዳዩ ዙርያ ከክለቡ የተሰጠ ማብራርያ የሌለ ሲሆን በቀጣይ ክለቡን ስለሚረከበው አሰልጣኝ እና ዝርዝር ጉዳዮች ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል
https://soccerethiopia.net/football/26006
85
19,309
በቻይና ከውጭ ሃገራት የገቡ 108 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተገኙ
ዓለም አቀፍ ዜና
Apr 13, 2020
1,122
አዲስ አበባ ሚያዚያ 5 2012 ኤፍቢሲ በቻይና ከውጭ ሀገራት የገቡ አዳዲስ 108 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተገኙየሀገሪቱ የጤና ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ከሰሞኑ ከተለያዩ ሀገራት የገቡ ሰዎች ላይ በተደረገ ልየታና ክትትል 108 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧልይህ ቁጥር ቻይና የኮሮና ቫይረስን መቆጣጠሯን ከገለፀች በኋላ በሳምንት ውስጥ የተመዘገበ ከፍተኛው መሆኑም ነው የተነገረውበቻይና 83 ሺህ135 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 3 ሺህ 219ኙ ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል77 ሺህ 956 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ምንጭ ቢቢሲ
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%89%bb%e1%8b%ad%e1%8a%93-%e1%8a%a8%e1%8b%8d%e1%8c%ad-%e1%88%83%e1%8c%88%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8c%88%e1%89%a1-108-%e1%89%a0%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93-%e1%89%ab%e1%8b%ad%e1%88%a8/
68
617
የእግር ኳስን ‹‹መዝገብ›› ያደበዘዙ ገፆች
ስፖርት
July 28, 2019
36
 በአለማችን ላይ ተወዳጅ ከሆኑ ስፖርቶች መካከል እግር ኳስ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል ስፖርቱ ታዳሚዎችን ከማዝናናት ባለፈ በርካታ ክስተቶችንም ያስተናግዳል በዚህ ተወዳጅ ውድድር ላይ የሚታዩ ክስተቶች አወንታዊ እና አሉታዊ ጎን ያላቸው ናቸው በዛሬው ዝግጅታችን ላይ በእግር ካስ ላይ በአሉታዊ ጎን ጥቁር ነጥብ ጥለው ያለፉ ታሪካዊ ክስተቶችን እናነሳለን ስፖርቱ ላይ መጥፎ አሻራቸውን ያኖሩ አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው ከነዚህ መካከል ተጫዋቾች በአደገኛ ሁኔታ የመጎዳት እና ሞት የሜዳ ላይ ግጭቶች የደጋፊዎች ነውጥ ያልተጠበቀ የዳኝነት ስህተቶች የውጤት ማጭበርበር ወይም ማች ፊክሲንግ ይጠቀሳሉ ታሪክ ደግሞ እነዚህን ትዝታዎች ከማይዘነጉ ተመሳሳይ ክስተቶች መካከል ሰንዶ ያስቀምጣቸዋል ለዛሬ ወደ ኋላ መለስ ብለን ከላይ ካነሳናቸው እግር ኳስን ካደበዘዙ ታሪኮች መካከል የሚመደበውን ጉዳይ እናንሳ ትኩረታችንንም የስፖርቱ ሞገስ የሆኑት ደጋፊዎች እና ስታዲዮሞች ላይ አድርገን የደረሰውን የማይዘነጋ አሳዛኝ አጋጣሚ እናስቃኛለን የእግር ኳሱ ጨዋታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እጅግ በጣም በርካታ አሳዛኝ ክስተቶች በስቴዲዮሞች ተስተናግዷል ይህም ምናልባት ስፖርቱ በጣም በብዙ ሚሊዮን ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ በመሆኑ የሚፈጠር ሊሆን ይችላል ነገር ግን የደጋፊዎች እና ሌሎች አካላት የአጥፊነት እና ጠብ አጫሪነት ባህሪ Hooliganism ከአፍ እስከ ገደፋቸው ስታዲየሞች በመሙላታቸው ያረጁ እና ተገቢውን ጥገና ያላረጉ ስታዲዮሞች በመሆናቸው እንዲሁም በሁለት ባላንጣ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ጨዋታዎች ከቁጥጥር  ውጪ በመውጣታቸው የሚከሰቱ አሳዛኝ አደጋዎች ዋናውን ድርሻ ይወስዳሉ አሁን የምናነሳው ታሪክ የአርጀንቲና ከተማ ወደ ሆነችው ቦነስ አይረስ ይወስደናል አሳዛኙ አጋጣሚ የተከሰተው እአአ በ1968 ነው ቦታው ደግሞ ስታዲዮ ሞኑምንታል በአርጀንቲና ክለቦች መካከል ከሚደረጉ የእግር ኳስ ፍጥጫዎች መካከል አቻ የማይገኝለት የደርቢ ጨዋታ በሪቨር ፕሌት እና በቦካ ጁኒየርስ እየተካሄደ ነበር ሆኖም ግን ከጨዋታው በኋላ ያልተጠበቀ ክስተት ስታዲየሙን በድንገት አናወጠው ወትሮውንም እነዚህ ሁለት ክለቦች ሲገናኙ በደጋፊዎቻቸው መካከል ግጭት የተለመደ ነው እርስ በርስ ተሸናንፈው በከተማዋ ላይ መንገስን ከምንም ነገር በበለጠ የሚፈልጉት ነው ይህ ጉዳይ ሊጉን በበላይነት ከማጠናቀቅም የበለጠ ለሁለቱ ባላንጣዎች አስፈላጊ ነው በዛች ቀን ግን ከምን ጊዜውም በበለጠ የአርጀንቲናን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የአለምን ትኩረት የሳበ እና የእግር ኳስን አስቀያሚ ገፅታ ያሳየ አጋጣሚ ተፈጠረ ጨዋታው እንደተጠናቀቀ ተመልካቾች ወደ መውጫው በር እያቀኑ ነበር በድንገት ግርግር በመነሳቱ ሁሉም ወደ በሩ እግሬ አውጪኝ አሉ በዚህ ግርግር ውስጥ አቅም ያልነበራቸው እና ማምለጥ ያልቻሉት ለከፍተኛ ጉዳት እና ሞት ተጋለጡ በዚች የተረገመች ቀን ከ71 ሰዎች በላይ ለህልፈተ ህይወት ሲዳረጉ 150 ደጋፊዎች ደግሞ ክፉኛ ቆሰሉ እግር ኳስም አፍቃሪዋን በላች ለዚህ አሳዛኝ ክስተት መነሻ እርግጠኛ የሆነ ምክንያት ግን ሊገኝ አልቻለም አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን ግርግሩ የተነሳው የቦካ ጁኒየርስን ደጋፊዎች የሪቨር ፕሌትን ባንዲራ በእሳት አያይዘው በብዛት ህዝብ ወደ ነበረበት ስፍራ በመወርወራቸው ነው በማለት ሲዘግቡ ሌሎች ደግሞ የሪቨር ፕሌት ደጋፊዎች የተቀናቃኛቸው የመቀመጫ ስፍራ በመሄዳቸው በዚህ ምክንያት በተፈጠረ ግርግር አደጋው ተከስቷል የሚል መላ ምት ይሰነዝራሉ ፖሊስ ለሶስት አመት በጉዳዩ ላይ ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል ሆኖም ማንም ግለሰብም ሆነ ቡድን ወንጀለኛ እንዳልሆነ ይህ አሳዛኝ ክስተት የተፈጠረው በበሩ አካባቢ በተፈጠረ ፍፁም መጨናነቅ መሆኑን ሪፖርት አድርጓል የሆነው ሆኖ የሁለቱ ተቀናቃኝ ቡድኖች ጨዋታ አለም በመጥፎ ጎኑ እንዲያስታውሰው ሆኖ ተጠናቋል ሌላኛው እና በስታዲዮም ውስጥ ጥቁር ጠባሳውን ጥሎ ያለፈው ክስተት የ ፖርትሴይድ ስታዲዮም ዲዛዝተር ነው ወቅቱ እአአ በ2012 ሲሆን ሁነቱ ደግሞ ግብፅ ውስጥ ነበር በዚህ ስታዲዮም ውስጥ ይጫወቱ የነበሩት አልማስሪ እና አልአህሊ ነበሩ በወቅቱ አልማስሪ ተቀናቃኙን 3ለ1 ማሸነፍ ችሎ ነበር ነገር ግን ፍፃሜው ማንም እንደሚወደው አይነት ሆኖ ሊጠናቀቅ አልቻለም በግልባጩ ይህ ጥቁር ቀን ለ79 ደጋፊዎች ህይወት መጥፋት መንስኤ ሆነ እንጂ ለህይወት መጥፋት መነሻ የነበረው የአል ማስሪ ደጋፊዎች ባልተጠበቀ ሁኔታ በተቀናቃኛቸው የአልአህሊ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ነበር በሺ የሚቆጠሩት እነዚህ ደጋፊዎች ሜዳውን ስፖርታዊ ጨዋነት በጎደለው መልኩ በመውረር ተቀናቃኞቻቸውን አጠቁ ወትሮ ሰላም የሚሰበክበትን እግር ኳስን በማጠልሸት ጥቁር ታሪክ ፃፉ ክስተቱ ለ79 ሰዎች ህይወት መጥፋት እና በሺ ለሚቆጠሩት የመቁሰል አደጋን አደረሰ በጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር መጋቢት 12 ቀን 1988 ተመሳሳይ አሳዛኝ ክስተት ተስተናገደ ወትሮውኑ ቀለምና ዘርን የማይለየው እግር ካስ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለብዙሀን ሞትን ለሌሎች ደግሞ ሀዘንን ይዞ ከተፍ አለ አገሪቷ ኔፓል ስትሆን ቦታው ደግሞ ካትማንዱ ብሄራዊ ስታዲዮም ኔፓል እና ባንግላዲሽ በዚህ ቀን ጨዋታቸውን ያደርጉ ነበር ሆኖም ነገሮች እንደተጠበቀው ሊሄዱ አልቻሉም ነበር ከዚህ በተቃራኒው 30 ሺ ተመልካቾችን የሚይዘው የካትማንዱ ስታዲዮም ታሪክ የማይዘነጋው አጋጣሚን አስተናገደ ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን በሚያደርጉበት ወቅት በጣም ሀይለኛ ዝናብ መጣል ጀመረ በረዶ ከተቀላቀለበት ዶፍ ዝናብ ለማምለጥ የሞከሩ ሰላሳ ሺ ደጋፊዎች ወደ በሩ መውጫዎች ሩጫቸውን ተያያዙት ነገር ግን ከስምንቱ መውጫ በሮች አንዱ ብቻ ክፍት ነበር በዚህ ግርግር በርካታ ሰዎች ተረጋገጡ አቅም ያልነበራቸው ወጣቶች እና ህፃናት ለሞት ተዳረጉ 93 ሰዎች በዚህ አደጋ ሲሞቱ በርካቶች ደግሞ ክፉኛ ቆሰሉ ይሄኛው ጥቁር ጥላ ደግሞ ወደ ጋና ይዞን ይጓዛል እአአ ግንቦት 9 በ2001 በአክራ ስፖርት ስታዲዮም ወደ ተፈጠረ አሳዛኝ አጋጣሚ ጨዋታው የሚካሄደው በጋና የእግር ካስ ሊግ ከፍተኛ ተፎካካሪዎች በሆኑት በህርትስ ኦፍ ኦክ እና በአሳንቴ ኮቶኮ መካከል ነበር ከሁለቱም ክለቦች 70 ሺ የሚደርሱ ደጋፊዎች ይህን አጓጊ ጨዋታ ለመታደም በስታዲዮሙ ተገኝተዋል አጋጣሚው ከመፈጠሩ በፊት ህርትስ ኦፍ ኦክ 2 ለ1 እየመራ ነበር ነገር ግን ወደ ጨዋታው ማብቂያ ላይ ፖሊስ በደጋፊዎች መካከል ተፈጥሯል ያለውን ብጥብጥ ለመበተን የአስለቃሽ ጭስ ይጠቀማል ከዚህ አስለቃሽ ጭስ ለማምለጥ በሚደረግ ፍትጊያ ደግሞ በርካታ ሰዎች ለመረጋገጥ እና ለህልፈተ ህይወት ተዳረጉ የሞቱት የደጋፊዎች ቁጥር 126 ነበር አብዛኞቹ ፖሊስ በሰራው ስህተት ደጋፊዎች ለሞት እና ለቁስለት መዳረጋቸውን ይናገራሉ በወቅቱ አጋጣሚውን ሽፋን የሰጠው ቢቢሲም ይህንኑ ነበር በዘገባው ያነሳው በአለም እግር ኳስ ታሪክ ጥቁር ጥላቸውን ካሳረፉ አሳዛኝ አደጋዎች ውስጥ በአስከፊነቱ ወደር የማይገኝለት ተብሎ ተመዝግባል ወቅቱ እአአ ግንቦት 24 1964 ነበር በሊማ ብሄራዊ ስታዲዮም ጨዋታቸውን የሚደርጉት ደግሞ ፔሩ እና አርጀንቲና ነበሩ ለኦሎምፒክ ውድድር ለማለፍ በሚደረገው በዚህ የማጣሪያ ጨዋታ ላይ አርጀንቲና ቀዳሚውን ጎል በማስቆጠር መምራት ጀመረች በዚህ ጊዜ የፔሩ ደጋፊዎች ብስጭት ውስጥ በመግባታቸው ወደ ሜዳ ቁሳቁሶችን በመወርወር ተቃውማቸውን መግለፅ ጀመሩ ከደቂቃዎች በኋላ ግን ፔሩዎች አቻ የሚያደርጋቸውን ጎል በተመሳሳይ ማስቆጠር ቻሉ ሆኖም ግን ይህንን ግብ ዳኛው ሊያፀድቀው አልቻለም ነበር ይህ ደግሞ እነዚህን ደጋፊዎች ክፉኛ አበሳጨ ነገሩም ወደ ከፋ ብጥብጥ ተቀይሮ ለ318 ሰዎች ህልፈትና ከ500 ሰዎች በላይ ለሆኑት ደግሞ የመቁሰል ምክንያት ሆነ ይህ አጋጣሚም በጥቁር ቀለም ተከትቦ የእግር ኳስ ታሪክ ላይ ሰፈረ ከላይ ያነሳናቸው የእግር ኳስ መቅሰፍቶች በታሪክ ውስጥ ሰላማዊውን ስፖርት ወደ ጦር ሜዳነት የቀየሩ ክስተቶች ነበሩ ከነዚህ አጋጣሚዎች በተጓዳኝ ግን በተወዳጁ ስፖርት ፍቅር ይሰበካል ሰላማዊ ፉክክር ይደረጋል ሰብአዊነትን የሚያሳዩ ፍፁም አስደሳች ድርጊቶች ዘርን እና ቀለምን መሰረት ሳያደርጉ ይካሄዳሉ ባላንጣ ፖለቲከኞች በእግር ካስ ጨዋታ ይታረቃሉ ለአለም ህዝብ በጎው እንዲመጣና ጥላቻ እንዲጠፋ ሁለት ተቃራኒ ቡድኖች እጅ ለእጅ ተያይዘው ይፀልያሉ ሆኖም ግን ይሄ ሁል ጊዜ አይሳካም በተወዳጅነቱ ወደር የማይገኝለት የእግር ኳስ መዝገብ ላይ የደበዘዙ ታሪኮች የራሳቸው ገፅ ይኖራቸዋልአዲስ ዘመን  ሀምሌ 212011  ዳግም ከበደ
https://www.press.et/Ama/?p=14917
946
46,777
በሰሜን ጎንደር የተከሰተው ሁከት የሽብርተኞች ሴራ ነው- አቶ ጌታቸው ረዳ
ፖለቲካ
July 15, 2016
Unknown
ሚኒስቴሩ ዛሬ  ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ ተከስቶ የነበረው ችግር ምንጩ ኢትዮጵያን የማተራመስ አላማ ያላቸው በህቡእ የተደራጁ የሻቢያና ተላላኪዎቹ የሽብር ቡድኖች የፈፀሙት ተግባር መሆኑን ገልፀዋል ህውከቱን በማስነሳት በዋነኝነት የተጠረጠሩት ግለሰቦች  ስድስት መሆናቸውንና አራቱ  በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ሁለቱ  ከፀጥታ ሀይሉ ጋር  ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ  ህይወታቸው ማለፉን  አቶ  ጌታቸው አመልክተዋል በህውከት ወንጀሉ ላይ የተሰማሩት ግለሰቦች ከኤርትራና ከግንቦት ሰባት የጦር መሳሪያዎች የቀረበላቸው መሆኑንና ግለሰቦቹ ከዚህ ቀደም በበርካታ ወንጀሎችና የግርግር ተግባራት ተሳትፎ ሲያደርጉ መቆየታቸውን  አስረድተዋል የተከሰተውን ግርግር በመጠቀም የህቡእ ቡድኖቹ በተለይ ወጣቶችን ለማነሳሳት የተለያዩ ዘዴዎችን  ሲጠቀም  እንደነበር የጠቀሱት  አቶ ጌታቸው የአካባቢው ነዋሪ  ሰላምን የሚፈልግ በመሆኑ  ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል የተከሰተውን ችግር ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር የሚያያዙት የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ጠቁመው ይህ ሽፋን በማድረግ ለህውከት ሊጠቀሙበት የሚፈልጉ ሀይሎች እንዳሉም ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል እንደ አቶ  ጌታቸው  ማብራሪያ የሽብር ቡድኖቹ  በትጥቅ  በመታገዝ በትግራይና በአማራ አዋሳኝ ቦታዎች  ተሽከርካሪዎችን  በጥይት በመምታት  የተከሰተውን ግርግር ይበልጥ  ለማቀጣጣል ሙከራ  መደረጉን ጠቅሰዋልለዚህም ከድርጊቱ ጀርባ የሚገኙ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል መንግስት ህዝብና የፀጥታ ሀይሉ በትብብር ሲሰሩ መቆየታቸውን ነው ያረጋገጡት በአካባቢው የተከሰተውን ችግር በህብረተሰቡ መካከል መቃቃር እንዳይፈጠርና ሁከት  እንዳይስፋፋ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ጌታቸው አስታውቀዋል
https://waltainfo.com/am/25755/
185
45,896
ቢሮው ውጤት ተኮር አሠራረን የሚያጎለብት ሥልጠና መሥጠት ጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
March 29, 2017
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀይል ልማት  ቢሮ ውጤት  ተኮር አሰራሮችን  የሚያጎለብት የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት መጀመሩን  አስታወቀ የቢሮው የስልጠናና ጥናት ዳይሬክተር ወይዘሮ ዘበናይ ሸጋና ለዋሚኮ እንደገለፁት ቢሮው 600 ለሚሆኑ የሲቪል ሰርቪስ አመራሮች  ለአራት ቀን የሚቆይ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ተጀምሯል እንደ ወይዘሮ ዘበናይ ስልጠናው በአራት  ርእሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩርና ከ88 ተቋማት ለተውጣጡ አመራሮች  በሁለት  ቦታ  የተከፋፈለ ስለጠና  እየተሰጠ ይገኛል የስልጠናው ተሳታፊዎች በተለያዩ ተቋማት የክፍል  ሀላፊዎችና  ምክትል  ሀላፊዎች መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ ዘበናይ  በቀጣይ   ሀላፊዎቹ  በስልጠናው ያገኙትን  ተሞክሮ  በስራቸው ለሚገኙት  ሰራተኞች  ያካፍላሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል ስልጠናው በዋናነት በስራ ጊዜ አጠቃቀም ሀላፊነትን በመወጣት በካስኬዲንግ ተግባራዊነትና በስራ አፈፃፃም ግምገማ ርእሳነ ጉዳዮች ላይ  የሚያተኩር መሆኑን  አቶ ዘበናይ አብራርተዋል  እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና  አላማ  የሲቪል ሰርቪስ  ሰራተኛው የስራ  ጊዜውን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲያውል የተገልጋይ እርካታን እንዲያሳድግና የክህሎትና እውቀት  ክፍተቱን ለመሙላት እንዲችል መሆኑን  አቶ ዘበናይ አስረድተዋል በአዲስ አበባ ከተማ  የሲቪል ሰርቪስ አሰልጣኞች  ስልጠና  በሚቀጥለው ወር ይጠናቀቃል ተብሎ የሚገመት ሲሆን በአጠቃላይ   3ሺ አመራሮችን ለማሳተፍ ታቅዷል     
https://waltainfo.com/am/31596/
151
2,646
ኮሮናን በቤት ተወስኖ በመቆየት
ሀገር አቀፍ ዜና
March 31, 2020
12
እጆችን በንፁህ ውሀና ሳሙና መታጠብ በሳኒታይዘር ማፅዳት ከሰዎች ጋር አለመጨባበጥ ባልታጠበ እጅ አፍና አፍንጫን አለመንካትና ሳል ወይም ትኩሳት ካለበት ሰው ሁለት የአዋቂ እርምጃ መራቅ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በአብዛኛው በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮች ናቸው ከዚህ በተጨማሪ ራስን በቤት ወስኖ ማቆየት stay at home የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ስርጭቱንም ባለበት ለማቆም ዋነኛ መንገድ መሆኑን ባለሙያዎቹ ይስማሙበታል ኢትዮጵያም የቫይረሱን ስርጭት ባለበት ለመከላከልና ከዚህ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል በፌዴራልና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች በቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ውስናለች ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ያሉ ተማሪዎችም በቤታቸው ሆነው እንዲቆዩ ትእዛዝ አስተላልፋለች በአዳማ ከተማም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሶስት ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ ቫይረሱ ወደሌሎች አካባቢዎች ይበልጥ እንዳይስፋፋ የከተማዋ ነዋሪዎች በቤታቸው ተወስነው እንዲቆዩ ታዟል ሆኖም እስካሁን ባለው ሂደት መንግስት ከላይ የተጠቀሱት የህብረተሰብ ክፍሎች በቤታቸው ራሳቸውን ወስነው እንዲቆዩ ያሳተላለፈውን መመሪያ ወደጎን በመተው ከቤት ውጪ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ዜጎች አሁንም ይታያሉ ቻይና የቫይረሱን ስርጭት ሙሉ በሙሉ ለመግታት ያስቻላት ህዝቧ በቤቱ ተወስኖ እንዲቆይ ያስተላለፈቸውን መመሪያ በመፈፀሙ ነውመመሪያው የህዝቡ ቀና ትብብር ታክሎበት ቫይረሱን በመከላከል ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል ኢትዮጵያውያንም ከቻይናውያን ትምህርት በመውሰድ መንግስት ያወጣውን በቤት ተወስኖ የመቆየት መመሪያ በጥብቅ ዲስፕሊን ተግባራዊ ሊያደርጉት ይገባል አዲስ ዘመን መጋቢት 222012
https://www.press.et/Ama/?p=29440
175
30,089
ሪፖርት | ሸገር ደርቢ ያለ ጎል ተጠናቋል
ስፖርት
May 5, 2019
Unknown
በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ የነበረው የሸገር ደርቢ ያለ ጎል ተጠናቋልዩጋንዳዊው ግብጠባቂያቸው ኢስማኤል ዋቴንጋን በሁለተኛው ዙር ለመጀመሪያ ጊዜ በቡድን ስብስባቸው ውስጥ ያካተቱት ባለሜዳዎቹ ኢትዮጵያ ቡናዎች ባሳለፍነው ሳምንት በአዳማ ከተማ ከሜዳው ውጭ 1ለ0 ከተረታው የመጀመርያ ተሰላፊ ውስጥ አጥቂውን ፍፁም ጥላሁን በቃልኪዳን ዘላለም እንዲሁም አህመድ ረሺድን በሀይሌ ገተንሳይ ተክተው ወደ ጨዋታው ገብተዋል በአንፃሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሳምንቱ መጀመሪያ የሊጉን መሪ መቀለ 70 እንደርታን 1ለ0 ከረታው ስብስብ ውስጥ ናትናኤል ዘለቀን በታደለ መንገሻ በመተካት ጨዋታውን ጀምረዋልእንደወትሮው የሁለቱ ግንኙነት ሁሉ ብዙም ሳቢ ባልነበረው የመጀመሪያው አጋማሽ ኢትዮጵያ ቡና ምንም እንኳን በጠሩ የግብ እድሎች ባይታጀብም ከተጋጣሚያቸው በተሻለ የመሀል ሜዳ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው በአንፃሩ ጊዮርጊሶች በአመዛኙ ከተከላካዮች በቀጥታ ፊት መስመር ላይ ወደ ግራ መስመር አድልቶ ይንቀሳቀስ ወደነበረው አቤል ያለው በሚሻገሩ ረጃጅም ኳሶች ተወስነው ሲንቀሳቀሱ ተስተውሏልበኢትዮጵያ ቡናዎች በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ሀይሌ ገተንሳይ ከቅጣት ምት ከሞከራት ኳስ በተጨማሪ ቃልኪዳን ዘላለም ከቀኝ መስመር የተሻገረለትን ኳስ ተቆጣጥሮ አስቆጠረ ተብሎ ሲጠበቅ ያመከናት ኳስ ተጠቃሽ ሙከራ ነበረች በቅዱስ ጊዮርጊሶች በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ከፍሪምፓንግ ሚንሱ የቅጣት ምት ሙከራ በተጨማሪ ሪቻርድ አርተር ከሳጥን ውጪ በቀጥታ ሞክሮ ወደ ውጪ የወጣበት ኳስ ተጠቃሽ ነበሩበመጀመሪያው አጋማሽ በተለይ ኢትዮጵያ ቡናዎች ከወትሮው በተለይ ሀይልን የቀላቀለ የጨዋታ አቀራረብ መርጠው በመምጣታቸው በርከት ያሉ ጥፋቶችን ሲፈፅሙ ተስተውሏል በተለይም ፈጣኑን አቤል ያለውን ለማቆም ሆነኛ አማራጭ ሆኗቸው ታይቷልቅዱስ ጊዮርጊሶች ሪቻርድ አርተር ላይ በተፈፀመበት ጥፋት የፍፁም ቅጣት ምት ይገባኛል ጥያቄ የጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ሁለተኛ አጋማሽ በንፅፅር ከመጀመሪያው የተሻለ የመሸናነፍ ተነሳሽነት ተስተውሎበታል በ59ኛው ደቂቃ በጨዋታው በተገኘችው ብቸኛ የጠራ የግብ አጋጣሚ አስራት ቶንጆ በግሩም ሁኔታ ያሳለፈለትን ኳስ ሁሴን ሻባኒ ከቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብጠባቂ ማታሲ ጋር 1ለ1 ተገናኝቶ ያመከናት የጨዋታው የተሻለችው ሙከራ ነበረችኢትዮጵያ ቡናዎች በተሻለ የኳስ ቁጥጥርና በፍጥነት ወደ ተጋጣሚያቸው ሳጥን በተደጋጋሚ መድረስ ቢችሉም በተጫዋቾች ደካማ ውሳኔ አሰጣጥ የተነሳ ፍሬያማ አልነበሩም በአንፃሩ አሜ መሀመድ እና በሀይሉ አሰፋን በሁለተኛው አጋማሽ ቀይረው ካስገቡ በኋላ በተሻለ ከመስመር በሚጣሉ ኳሶች ለመጠቀም የሞከሩት ጊዮርጊሶች በርካታ የመልሶ ማጥቃት አጋጣሚ ቢያገኙም መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋልበጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ በሁለተኛው አጋማሽ ሰአት በማባከን የቢጫ ካርድ የተመለከተው የኢትዮጵያ ቡናው ግብጠባቂ ወንድወሰን አሸናፊ ከሳጥን ውጭ ኳስ በእጅ በመንካቱ በሁለት ቢጫ ከሜዳ ሊወጣ ችሏልጨዋታው 00 በሆነ የአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለዋንጫ የሚያደርገው ጉዞ እንቅፋት ሲገጥመው ደረጃውም ወደ አራተኛ ዝቅ ብሏል ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ወደ 6ኛ ደረጃ በአንድ ከፍ ማለት ችሏል
https://soccerethiopia.net/football/47326
340
4,872
ሙዚየሙ የአፄ ቴዎድሮስን ‹‹ቁንዳላ›› ተረከበ
ሀገር አቀፍ ዜና
March 24, 2019
30
አዲስ አበባ መንግስት ለአመታት ከእንግሊዝ መንግስት ጋር ባደረገው ዲፕሎማሲያዊ ድርድር ከ151 አመት በኋላ ወደ አገሩ የተመለሰው የአፄ ቴዎድሮስ ጉንጉን ፀጉር ቁንዳላ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየም በአደራተቀበለ የአንድነት ገመድ እንደሆነ በብዙሀን የሚታመንበት ታላቅ ቅርስ ወደ አገሩ ሲገባ ደማቅ የአቀባበል ስነስርአት ተካሂዶለታል ትናንት በቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን በተካሄደው የአቀባበል ስነ ስርአት ላይ ከአገረ እንግሊዝ በቀጥታ የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ይዘውየገቡት የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ቅርሱ ወደፊት በሚዘጋጅለት ትክክለኛ ቦታ እስኪያርፍ ድረስ በአደራ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየም አስረክበዋል በርክክብ ስነስርአቱ ላይ እንደተናገሩት የአፄ ቴዎድሮስ ፀጉር ከረጅም አመታት በኋላ መመለሱ ለኢትዮጵያውያን እና ለመንግስት ኩራት ነው መንግስት ለአገረ እንግሊዝ ካቀረበው በርካታ ጥያቄዎች ውስጥ የመጀመሪያው የሆነውን አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቅርሱን መልሷል ከዚህ በኋላም ምላሽ የሚያገኙ ጥያቄዎች እንዳሉ ገልፀው በታሪክ አጋጣሚ ከአገር የወጡ ቅርሶችን የዲፕሎማሲ ግንኙነቱን በማጠናከር ለማስመለስይሰራል ብለዋል እንደ ዶክተር ሂሩት ገለፃየአፄ ቴዎድሮስ የኢትዮጵያ አንድነት እንዲሁም ራእይ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ውስጥ አለ ይህ ቅርስ መመለሱ ራእዩ እንዲታደስ እና ብዝሀነትን የምታስተናግድ አንድ ጠንካራ ኢትዮጵያ እንድትገነባ የሚያግዝ ነው ታላቅ የመንፈስ ጥንካሬንም በአገሪቷ ላይ ያሰፍናል አፄ ቴዎድሮስ ኢትዮጵያዊ ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ ከዚህ ውጪ ሌላ ዘር የላቸውም ብለዋል  እንግሊዞች 151 አመት የአፄ ቴዎድሮስን ፀጉር ለምን ጠብቀው አቆዩት የሚል ጥያቄ በማንሳትም የታሪክ እና የቅርስ አያያዝ ስርአቱን በተመለከተ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እራሱን መጠየቅ እና መመርመር ይኖርበታል ብለዋል የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ በበኩላቸው የአፄ ቴዎድሮስ ጉንጉን ፀጉር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን አንድነት አስተሳስሮ የያዘ ታላቅ ቅርስ መሆኑን ገልፀዋል መጪው ትውልድም እንደ አይኑ ብሌን ሊጠብቀውና ሊንከባከበው ይገባል የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ በብሄራዊ ሙዚየም በአደራ ከሌሎች በጥብቅ ከተያዙ መሰል ቅርሶች ጋር በጊዜያዊነት እንደሚቀመጥ ታውቋል ትክክለኛው ማረፊያው ሲዘጋጅለት ወደዚያው ያመራል ንጉሱ በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ቦታ የነበራቸውና እስካሁንም በጀግንነታቸው የሚጠሩ ናቸው ከስማቸውና ከአልበገር ባይነት ስሜታቸው በተጨማሪ ደግሞ እስከዛሬ ብዙዎች የሚያነሷቸው በፀጉር አሰራራቸው ጭምር ነው ይህ ታላቅ ቅርስ ወደ አገሩ መመለሱ በአገረ ጀርመንፈረንሳይ ጣሊያን እንዲሁም ሌሎች አገራቶች የሚገኙትን መሰል ቅርሶች ለማስመለስ ትልቅ እድል እንደሚከፍት ተገልጿልመረጃዎች እንደሚያመለክቱት በእንግሊዝ ሙዚየሞች ውስጥ ብቻ 11 ታቦቶች እንዲሁም ከ300 በላይ የብራና መፅሀፍትን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች ይገኛሉ በአቀባበል ስነስርአቱ ላይ አምጡ ቆርጣችሁ ከሹሩባው ላይሚዛን እንሰር እንዳንለያይ በሚለው የአፄ ቴዎድሮስ ሙዚቃ እና በሌሎች ስራዎቹ የሚታወቀው ተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮን ጨምሮ በርካታ ታዋቂና ተፅእኖ ፈጣሪ እንግዶች ታዳሚ ሆነዋልአዲስ ዘመን መጋቢት 152011በዳግም ከበደ
https://www.press.et/Ama/?p=7427
342
13,544
ዶክተር አዲሳለም ባሌማ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
Dec 10, 2020
825
አዲስ አበባ ታህሳስ 1 2013 ኤፍቢሲ የህወሀት የጥፋት ቡድን ከፍተኛ አመራር የነበሩት ዶክተር አዲሳለም ባሌማ ፍርድ ቤት ቀረቡዶክተር አዲሳለም በፀረሰላም ቡድን ተደራጅተው በመስራት ተጠርጥረው ፍረድ ቤት ቀርበዋልተጠርጣሪው አምባሳደር በነበሩበት ዘመንም ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ለማበላሸት እና ለማስቆም ተፅእኖ ሲፈጥሩና ሲሰሩ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷልበተጨማሪም የመንግስት መረጃና ሚስጥሮችን አሳልፈው ሲሰጡ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷልከኦነግ ሸኔ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም መረጃ ሲለዋወጡ እና የመንግስትን ሚስጥር አሳልፈው በመስጠት ለተፈፀሙ ወንጀሎች በጋራ ሲሰሩ እንደነበር አስረድቷልመርማሪ ፖሊስ ዶክተር አዲሳለም የአፍሪካ ከፍተኛ አመራሮች የፌዴራል መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥሩ ተፅእኖ ሲያደርጉ እንደነበርና ህገ መንግስትንና ህገመንግስታዊ ስርአትን ለመናድ ከዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል እና ከቡድናቸው ጋር በመሆን ወንጀል የሚፈፀምበትን ሁኔታና እቅድ ሲያወጡ እንደነበር ጠቅሷልበተጨማሪም ወጣቶችን በመመልመል ሁከትና አመፅ እንዲፈጠር በየክልሉ ሲያስተባሩ እንደነበር የጠቀሰው መርማሪ ፖሊስ ዶክተር አዲሳለም ባሌማ ከቻይና አንድ አምባሳደር ጋር በመገናኘት የቻይና እና የህወሀት ኮሙኒስት ፓርቲ ለመፍጠር ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ሲሰሩ እንደነበረም ጠቅሷልካልተያዙ ግብረአበሮቻቸው ጋርም በህዳር 24 ቀን 2013 አም በማይካድራ የንፁሀን ዜጎች እንዲጨፈጨፍ የሰሜን እዝ ጦር ጥቃት እንዲፈፀምበትና ከባድ የጦር መሳያ እንዲዘረፍ ሁኔታዎችን ሲያመቻቹ እንደነበር ለችሎቱ አስረድቷልመርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት የጠየቀ ሲሆን ተጠርጣሪው ከዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጋር በሽምግልና ጉዳይ ሰኞ እለት ስነጋገር ቆይቼ ረቡእ በቁጥጥር ስር ውያለሁ ሌሎች አምባሳደሮችንና ሀላፊዎችንም በሽምግልና ጉዳይ ነው ያነጋገርኳቸው ብለዋልዶክተር አዲሳለም ወንጀሉን አልፈፀምኩም ያሉ ሲሆን መርማሪ ፖሊስ ወንጀሉን ስለመፈፀማቸው የሚያስረዱ በቂ መረጃዎች እንዳሉት ለችሎቱ አብራርቷልጉዳዩን የተከታተለው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም ለመርማሪ ፖሊስ 14 ተጨማሪ ቀናትን ፈቅዷልታሪክ አዱኛ የፋና ድረ ገፅ httpswwwfanabccom ይጎብኙተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል httpswwwyoutubecomcfanabroadcastingcorporate ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል httpstmefanatelevision ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን httpstwittercomfanatelevision ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
https://www.fanabc.com/%e1%8b%b6%e1%8a%ad%e1%89%b0%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b3%e1%88%88%e1%88%9d-%e1%89%a3%e1%88%8c%e1%88%9b-%e1%8d%8d%e1%88%ad%e1%8b%b5-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%89%80%e1%88%a8%e1%89%a1/
257
36,914
ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚያገናኙ የሑመራ - ኡምሓጀርና የራማ -ዓዲዃላ መስመር
ሀገር አቀፍ ዜና
November 20, 2018
Unknown
ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚያገናኙ የሁመራ ኡምሀጀርና የራማ አዲዃላ የመንገድ መስመሮች በቅርብ ግዜ ተከፍተው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ለማጠናከር ውይይት አመራሮች እያካሄድን ነው አሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልምክትል ርእሰ መስተዳድሩ በትናንትናው እለት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫበክልሉ ደቡባዊና ምእራባዊ ዞኖች ስላካሄዱት ጉብኝት ማብራርያ ሰጥተዋልበትግራይና አማራ ክልሎች ግንኙነት ለማጠናከር የህዝብ ለህዝብና የአመራሮች ግንኙነት መፍጠር ስራ በአዋሳኝ አከባቢዎች እየተፈፀመ ነው ብለዋል
https://amharic.voanews.com//a/tigray-presser-11-20-2018/4666452.html
61
39,547
የአንድነት ፅ/ቤት በፖሊስ ተያዘ
ዓለም አቀፍ ዜና
January 31, 2015
Unknown
አዲስ አበባ የሚገኘው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለምርጫ ቦርድ እውቅና የነሳቸው የፓርቲው አመራር አባላትም ወደ ፅህፈት ቤቱ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ይገልፃሉፖሊስ ከፅህፈት ቤቱ ሲያግዳቸው የፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዳላሳየም ተናግረዋልየየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ እርምጃውን የወሰደበትን ምክንያት ተጠይቆ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነምየአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና እንደራሴ አቶ ግርማ ሰይፉ ለቪኦኤ መግለጫ ሰጥተዋልለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
https://amharic.voanews.com//a/police-seized-udj-offce-in-addis-01-30-15/2622115.html
59
35,245
ኬንያዎች ውጤቱን መቀልበስ እንደሚችሉ እየተናገሩ ነው
ስፖርት
July 2, 2015
Unknown
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቻን ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ የኬንያ አቻውን 20 አሸንፎ ወደ ተከታዩ የማጣርያ ዙር ለማለፍ የሚያስችውን እድል አስፍቶ ወደ ናይሮቢ አምርቷል አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌም አጥቅተው በመጫወት ውጤታቸውን አስጠብቀው ለመውጣት እንደተዘጋጁ ትላት ናግረዋል በሌላ በኩል ደግሞ የሀራምቤ ከዋክብት ወደ ተከታዩ ዙር የማለፍ እድላቸው እንዳልተሟጠጠ እየተናገሩ ይገኛሉ የሊዮፓርድሱ ቤርናርድ ማንጎሊ ለሱፐር ስፖርት በሰጠው አስተያየት ጨዋታው ገና እንዳልተጠናቀቀ ተናግሯል ወደ ተከታዩ ዙር የሚያሳልፈንን ውጤት ማግኘት እንደምንችል እተማመናለሁ ሲል ሀሳቡን መስጠት የጀመረው ቤርናርድ ውጤቱን መቀበስ ከባድ ቢሆንም የማይቻል እንደሆነ ያምናል 20 መሸነፍ ከባድ ነበር ምክንያቱም ጨዋታው ተመጣጣኝ ነበር በጨዋታው የፈጠርናቸው የግብ እድሎችንም ወደ ግብ መቀየር አልቻልንም በናይሮቢ 90 ደቂቃ ይቀረናል እድላችንን ለመወሰን ሜዳ ላይ ያለንን ሁሉ መስጠት አለብን ጨዋታው እንዳልተጠናቀቀ በማሰብ መልካም አቋም አሳይተን የምንፈልገውን ውጤት ማሳካት እንችላለን ሲል በባህርዳሩ ጨዋታ ቋሚ ተሰላፊ የነበረው ቤርናርድ አስተያየቱን ሰጥቷልአሰልጣኙ ቦቢ ዊልያምሰን ለዴይሊ ኔሽን በሰጡት ቃል ደግሞ በደጋፊያቸው ፊት ውጤቱን ቀልብሰው ወደ ተከታዩ ዙር እንደሚያልፉ ተስፋ አድርገዋል በጨዋታው የሚያስፈልገን አንድ ግብ ብቻ አይደለም ሶስት ግቦች ማስቆጠር ይጠበቅብናል ይህን በደጋፊያችን ፊት እንደምናሳካም ተስፋ አለኝነገር ግን በ20 ሽንፈት የመልስ ጨዋታ ማድረግ ቀላል አይደለም ሲሉ ለማሳካት ከባድ ቢሆንም ወደ ተከታዩ ዙር የማለፍ ተስፋቸው እንዳልመነመነ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል 
https://soccerethiopia.net/football/2992
183
12,232
የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት አምቦ ውስጥ ተፈጸመ
ሀገር አቀፍ ዜና
2 ሀምሌ 2020
Unknown
የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ስነ ስርአት በአምቦ ከተማ በሚገኘው የገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተፈፀመ ይሁን እንጂ አሁንም ድምፃዊው መቀበር ያለበት በአዲስ አበባ ነው በሚል ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ በርካቶች ናቸው ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በመገኘት ሽኝት አድርገዋል በስታዲየሙ የተገኘው ሰው ቁጥር አነስተኛ እንዲሆን የተደረገው በደሀንነት ስጋት መሆኑ ተነግሯል ለቀብር ከአምቦ ዙሪያ የሚመጡ ሰዎች ወደ ከተማው እንዳይገቡም ተከልክለዋል የመንግስት የፀጥታ ሀይል መንገደኞች ወደ ከተማው እንዳይገቡ እና ወደ መጡበት እንዲመለሱ ለማድረግ አስለቃሽ ጭስ ሲተኩስ ነበር ተብሏልአንዳንድ ሰዎችም አስከሬኑ ወደሚቀበርበት ቦታ የሚወስዱ መንገዶችን የመዝጋት ሙከራዎች እንደነበሩና ቀብሩ ሊፈፀም የነበረበት ጉድጓድን መልሶ የመድፈን ሙከራዎችም መደረጋቸውንም የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋልትናንት በጥይት ተመትተው ህይወታቸው ያለፈው የሀጫሉ አጎት ቀብር በዛሬው እለት ቀደም ብሎ ተፈፅሟል ከአምቦ ከተማ ነዋሪዎች እንደሰማነው የክልሉ ፕሬዝድንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ በቀብር ስነ ስርአቱ ላይ ይገኛሉ ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም መገኘት አለመቻላቸውን ተነግሯል
https://www.bbc.com/amharic/news-53260523
144
40,426
ለፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕና ባለቤታቸው ሜላንያ የተላለፈ የመልካም ምኞት መልዕክት
ዓለም አቀፍ ዜና
October 02, 2020
Unknown
የፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕና ባለቤታቸው ሜላንያ ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ መያዝ ዜና ተከትሎ በአለም ዙሪያ የሚገኙ መሪዎችና ታዋቂ ገለሰቦች የመልካም ምኞት መገለጫዎች እያስተላለፉ ነው ምክትል ፕሬዚደንታቸው ማይክ ፔንስ በትዊተር ባወጡት የመልካም ምኞት መግለጫ ከኬረን ጋር ሆነን ለውዶቹ ጓደኞቻችን ለፕሬዚደንት ትረምፕ እና ለቀዳማዊት እመቤት ሚላንያ ፍቅራችንን እንገልፃለን እንፀልያላቸዋለን በመላዋ አሜሪካ ከሚሊዮኖች ጋር ሆነን በፍጥነት እንድታገግሙና ሙሉ ጤንነታችሁ እንዲመለስ እንፀልያለን እግዚአብሄር ፕሬዚደንቱንና ቀዳማዊት እመቤትን ከነቤተሰባችሁ ይባርክ ብለዋል የምክትል ፕሬዚደንቱ የፕሬስ ፀሀፊ ዴቪድ ኦማሊ በትዊተር ገፃቸው ባወጡት ቃልም ምክትል ፕሬዚደንቱና ባለቤታቸው ተመርምረው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው መረጋገጡን ተናግረዋል በክሮሽያ ጉዞ ላይ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ በበኩላቸው ተመርመረው ኮቪድ እስራ ዘጠኝ እንዳልተያዙ አብረዋቸው ለተጓዙ ጋዜጠኞች ያረጋገጡ ሲሆን እስከትለውም ፕሬዚደንቱና ባለቤታቸው ፈጥነው እንዲያገግሙ ፀሎቴ ነው ብለዋል በመጪው ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲው የፕሬዚደንቱ ተፎካካሪ የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ጆ ባይደንም በትዊተር ገፃቸው ለፕሬዝዳንቱና ለቀዳማዊት እመቤት ሚላንያ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል እኔና ጂል ፕሬዚደንት ትረምፕና ቀዳማዊት እመቤት ሚላንያ በቶሎ እንዲያገግሙ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን ለፕሬዚደንቱና ለቤተሰባቸው ጤናና ደህንነት እንፀልያለንም ብለዋል ባይደን የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶር ቴድሮስ አድሀኖምም እንዲሁ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የመልካም ምኞት መገለጫቸውን በትዊተር ገፃቸው አማካኝነት አስተላልፈዋል ዶክተር ቴድሮስ በመልክታቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ባለቤታቸው በፍጥነት ሙሉ ለሙሉ እንዲያገግሙ ተመኝተዋል ዶክተር ቴድሮስ የሚመሩት የአለም ጤና ድርጅት ኮቪድ 19 የአለም ወረርሽን መሆኑን ከመጋቢት ጀምሮ ያወጀ ሲሆን እስካሁንም ከ 34 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በአለም ዙሪያ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከአንድ ሚሊየን በላይ ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል ከነዚህ ውስጥ 71 ሚሊዮን የሚሆኑት አብዛኛው የቫይረሱ ተያዦች በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ሲሆን ከ 205 ሺህ ሰዎች በላይ ለሞት መዳረጋቸውን የጤና ድርጅቱ መረጃ ያሳያል ፕሬዝዳንት ትራምፕ አርብ እለት ጠዋት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በትዊተር ገፃቸው ሲያሳውቁ በመጀመሪያ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ከላኩ የመጀመሪያ መሪዎች መሀል ቀዳሚው የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲ ናቸው ሞዲ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ጓደኛዬ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላንያ ትራምፕ ቶሎ እንዲያገግሙና በመልካ ጤንነት ላይ እንዲሆኑ እመኛለሁ ብለዋል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በበኩላቸው ለፕሬዝዳንት ትራምፕና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ቶሎ እንዲያገግሙ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን አስተላልፈዋል በድህረገፃቸው አማካኝነት መልክታቸውን ያስተላለፉት ሌላው የአለም መሪ ደግሞ የራሺያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ናቸው ፑቲን ለፕሬዝዳንት ትራምፕ መልካም ጤና ተመኝተው ጥንካሬህ መልካም መንፈስህና ተስፈኝነትህ ከዚህ አደገኛ በሽታ ቶሎ እንድታገግም ይረዳሀል ብለዋል በመልክታቸው ከ291 ሺህ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች የሚገኙባት ጀርመን ቻንስለር አንጄላ ማርኬል በቃል አቀባያቸው አማካኝነት ባወጡት መግለጫም ለዶናልድ እና ሜላኒያ መልካም እመኝላቸዋለሁ ከኮሮና ቫይረስ ቶሎ አገግመው ወደ ሙሉ ጤንነትታቸው እንደሚመለሱም ተስፋ አለኝ ብለዋል መስከረም አጋማሽ ላይ ከባህሬንና ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር የሰላም ስምምነት ለመፈራረም ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ተገናኝተው የነበሩት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔትናሁም እንዲሁ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በፍጥነት እንዲያገግሙ የሚገልፅ መልክታቸውን አስተላልፈዋል ከአገር መሪዎች በተጨማሪ በቴክሳስ የዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው የኮንግረስ አባል የሆኑት ጃኩዊን ካስትሮ በበኩላቸው ፕሬዝዳንቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው አሳሳቢ ነው ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል ይሄ የፕሬዝዳንቱ የጤና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገሩቱ ደህነት ጉዳይ ነው ብለዋል ካስትሮ በአፍጋኒስታን የብሄራዊ መግባባት መማክርት ጉባኤ ሰብሳቢ የሆኑት አብዱላህ አብዱላህም የአሜሪካው ፕሬዝዳንትና ባለቤታቸው በፍጥነት እንዲሻላቸው በትዊተር ገፃቸው ላይ ያሰፈሩ ሲሆን የአሜሪካ ህዝብ ይህን ወረርሽኝ በአሸናፊነት እንዲያልፉት እመኛለሁ ሲሉ አክለዋል ፕሬዝዳንት ትራምፕን በተደጋጋሚ በመንቀፍ የሚታወቁት የሲቪል መብት አቀንቃኙ ጄሲ ጃክሰን ጨምሮ ሌሎች ተቺዎቻቸውም በትዊተር መልክቶቻቸውን አስተላልፈዋል ጄሲ ጃክሰን በመልክታቸው ፕሬዝዳንቱና ቀዳማዊት እመቤት የዚህ በሽታ አስከፊ ገፅታ እንዳይደርስባቸውና በቶሎ እንዲያገግሙ እንፀልያለን በየትኛውም ሀይማኖትም ሆነ የፖለቲካ አመለካከት ውስጥ ብንሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ በሽታ ተጠቅተዋልና ሁላችንም ልንፀልይ ይገባል ብለዋል
https://amharic.voanews.com//a/5606763.html
507
41,691
በዞን ዘጠኝ ሴት እሥረኞች አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤት መልስ ሰጠ
ዓለም አቀፍ ዜና
March 05, 2015
Unknown
የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የሴቶች ዘርፍ ጥበቃ በነሶሊያና የክስ መዝገብ በተከሰሱት ማሀሌት ፋንታሁንና ኤዶም ካሳዬ ላይ የተፈፀመ በደል የለም ሲል ለፍርድ ቤት መልስ ሰጥቷልአቃቤ ህግ ደግሞ የተከሳሾቹ ጠበቆች በማስረጃነት የተጠቀሰው ሲዲ እንዲሰጣቸው የጠቀዩትንም ፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዲያደርገው አመልክቷልበሌላ በኩል ደግሞ የዞን ዘጠኝ አባላት የተከሰሱበት ዶሴ በስሟ የተመዘገበውና በሌለችበት የተከሰሰው ሶሊያና ሺመልስ ከቪኦኤ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለችለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
https://amharic.voanews.com//a/addis-ababa-police-says-there-was-no-mistreatmet-against-female-prisoners-of-zone9-03-04-15/2667933.html
60
24,647
ለመንገድ ፈንድ ሁለት ቢሊዮን ብር በጀት ፀደቀ
ቢዝነስ
19 October 2016
Unknown
የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ፅህፈት ቤት ለ2009 በጀት አመት ለመንገድ ጥገና እንዲውል ያቀረበወ ሁለት ቢሊዮን ብር በጀት ፀደቀ ከነዳጅ ሽያጭ ከሚሰበሰበው ተጨማሪ እሴት ታክስ ግማሹ ለመንገድ ፈንድ እንዲገባ ተፈቀደ ከፅህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ለበጀት አመቱ ተጠይቆ የነበረው 19 ቢሊዮን ብር ነበር የመንገድ ፈንድ ቦርድ ባለፈው ሳምንት ባካሄደው ስብሰባ ለበጀት አመቱ ለመንገድ ፈንድ ጥገና የሚውለው በጀት ሁለት ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወስኗልለመንገድ ጥገናው የተፈቀደው ይህ በጀት ፅህፈት ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ ለመንገድ ጥገና እንዲውል የፀደቀ ከፍተኛው በጀት ነው ከተጠየቀው በጀት በላይ ሊፈቀድ የቻለው በበጀት አመቱ ለፅህፈት ቤቱ የሚገባ ተጨማሪ ገቢ በመገኘቱ ነው ተብሏልባለፈው በጀት አመት ለመንገድ ጥገና ተፈቅዶ የነበረው በጀት 15 ቢሊዮን ብር እንደነበር የሚታወስ ነው ከዚህ በጀት ውስጥ 65 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሚወስድ ሲሆን ቀሪውን ከተሞችና የክልል መንገድ ባለስልጣኖች የሚከፋፈሉት ነውየመንገድ ፈንድ ለመንገድ ጥገና የሚያውለውን ገንዘብ የሚያሰባስበው ከነዳጅ ላይ ከተጣለ ታሪፍ ከአመታዊ ተሽከርካሪዎች ፈቃድ ማሳደሻ ክፍያና የጎረቤት አገር ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ከሚከፈለው የኮቴ ክፍያ ነውይህ በእንዲህ እንዳለ ከእነዚህ የገቢ ምንጮች በተጨማሪ ፈንዱን ለማሳደግ የነዳጅ ሽያጭ የሚሰበሰበው የተጨማሪ እሴት ታክስ ወደ ፈንድ ፅህፈት ቤቱ እንዲገባ የተጠየቀው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱም ታውቋል ጥያቄው የነዳጅ ሽያጭ በሙሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢው ለፈንዱ እንዲገባ ቢሆንም መንግስት ግማሹን ሊፈቅድ መቻሉን ለማወቅ ተችሏል ይኽም የፅህፈት ቤቱን የገቢ ምንጭ ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ያደርሳል ተብሎ ይጠበቃል በፅህፈት ቤቱ በበጀት አመቱ በሚመደበው በጀት ከ25 እስከ 30 ሺህ ኪሎ ሜትር መንገድ ጥገና ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%88%88%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%88%E1%8B%B5-%E1%8D%88%E1%8A%95%E1%8B%B5-%E1%88%81%E1%88%88%E1%89%B5-%E1%89%A2%E1%88%8A%E1%8B%AE%E1%8A%95-%E1%89%A5%E1%88%AD-%E1%89%A0%E1%8C%80%E1%89%B5-%E1%8D%80%E1%8B%B0%E1%89%80
216
30,262
ኦሊምፒክ ሴቶች እግርኳስ ማጣርያ | ዩጋንዳ ከ ኢትዮጵያ – ቀጥታ የውጤት መግለጫ
ስፖርት
April 6, 2019
Unknown
https://soccerethiopia.net/football/46445
0
30,449
ሴቶች 1ኛ ዲቪዝዮን | አዳማ እና ንግድ ባንክ ከሜዳቸው ውጪ ሲያሸንፉ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሜዳው ድል አስመዝግቧል
ስፖርት
March 9, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዝዮን የ15ኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች በዛሬው እለት ተካሂዷል መሪው ንግድ ባንክ እና ተከታዩ አዳማ ከሜዳቸው ውጪ ሲያሸንፉ ቅዱስ ጊዮርጊስም በሰፊ ልዩነት ድል አስመዝግቧል0800 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚን ያስተናገዱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች 30 አሸንፈዋል አምበሏ ሶፋኒት ተፈራ ባስቆጠረችው ጎል ቅዱስ ጊዮርጊሶች 10 በመምራት ወደ መልበሻ ክፍል ሲያመሩ በሁለተኛው አጋማሽ ብርሀን ሀይለስላሴ ከቅጣት ምት እና ከክፍት ጨዋታ አከታትላ ባስቆጠረቻቸው ጎሎች 30 ተጠናቋል ባሳለፍነው ሳምንት በንግድ ባንክ 70 የተሸነፉት እንስቶቹ ፈረሰኞች ከከባዱ ሽንፈት ያገገሙበትን ድል ማስመዝገባቸውን ተከትሎ በ10 ነጥቦች ግርጌውን ለጥሩነሽ ዲባባ አስረክበው አንድ ደረጃ ማሻሻል ችለዋል1000 በቀጠለው የአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ አዳማ ከተማ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ባለሜዳው ኤሌክትሪክን 40 በሆነ ውጤት አሸንፏል ሎዛ አበራ በአዲሱ ቡድኗ መለያ ጎልታ ባለችበት በዚህ ጨዋታ እንግዶቹ አዳማዎች በፍጥነት ወደ ጎል በመድረስ በሴናፍ አማካኝነት ለጎል የቀረበ ሙከራ ቢያደርጉም ግብጠባቂዋ እስራኤል ከተማ አውጥታባታለች ከሲዳማ ቡና አዳማ ከነማን ዘንድሮ በመቀላቀል መጀመርያ አሰላለፍ መግባት ከጀመረች ጊዜ አንስቶ በአዳማ የግራ መስመር ላይ በመከላከል ሆነ በማጥቃት ሽግግር ውስጥ ልዩነት እየፈጠረች ያለችው የግራ ተከላካይዋ ነፃነት ፀጋዬ ቆርጣ በመግባት ተከላካላካዮችን በማለፍ ያሻገረችውን ሎዛ አበራ በግንባራ ገጭታ መትታ ግብጠባቂዋ እስራኤል የያዘችው ኳስ አዳማዎች ብልጫ ወስደው ለመጫወታቸው ማሳያ ነውበኢትዮ ኤሌክትሪክ በኩል ኳሱን ለመቆጣጠር ጥረት እና በይበልጥ የሜዳውን ሁለቱን መስመሮች ለመጠቀም ቢጥሩም ወርቅነሽ መልመላ ፍጥነቷን ተጠቅማ የፈጠረችው የግብ አጋጣሚ እንዲሁም 23ኛው ደቂቃ መሳይ ከቅጣት ምት የሞከረችው ኳስ ካልሆነ በቀር ሌላ የግብ እድል መመልከት አልቻልንምየአዳማ የበላይነት ይበልጡኑ ጎልቶ መታየት የጀመረው በ26ኛው እፀገነት ብዙነህ ከግራ መስመር ያሻገረችውን በቅርቡ አዳምን የተቀላቀለችው ሎዛ አበራ የውድድር አመቱን የመጀመርያ ጎሏን በግንባሯ ገጭታ ካስቆጠረች በኋላ ነበር ከዚህ ጎል መቆጠር በኋላ በተደጋጋሚ ወደ ጎል በመድረስ ጫና ፈጥረው ሲጫወቱ የቆዩት አዳማዎች 40ኛው ደቂቃ ላይ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ጎል በመድረስ ሎዛ አበራ አመቻችታ የሰጠቻትን ከጎል ርቃ የቆየችው የአምና የሊጉ ኮከብ ተጫዋች ሰናይት ቦጋለ ከሳጥን ውጭ ጥሩ ጎል አስቆጥራ የአዳማን ጎል ሁለት ማድረስ ችላለች እረፍት መውጫ መዳረሻ ላይ እፀገነት ብዙነህ ሶስተኛ ጎል መሆን የሚችል እድል አግኝታ የነበረ ቢሆንም ለጥቂት በግቡ ቋሚ ታኮ ሊወጣባት ችሏልከእረፍት መልስ ገና በ47ኛው ደቂቃ ሴናፍ ዋቁማ ጎል መሆን የሚችል አጋጣሚ ከግብ ጠባቂዋ እስራኤል ጋር ተገናኝታ ኳሱ ከፍ ብሎ በመርዘሙ የወጣባት ጠንካራ የግብ እድል ነበር የጨዋታው ሚዛን ሙሉ ለሙሉ ወደ አዳማ ባጋደለበት በዚህ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 52ኛው ደቂቃ ሴናፍ ከቀኝ መስመር ይዛ በመግባት ያሻገረችውን ሎዛ አበራ ሁለተኛ ጎሏን ለቡድኗ ሶስተኛ ጎል በግንባሯ በመምታት አስቆጥራለችበዛሬው ጨዋታ ጎል አታስቆጥር እንጂ ጥሩ በመንቀሳቀስ ለጎሎች መቆጠር ትልቁን አስተዋፆኦ ያደረገችው ሴናፍ ዋቁማ 56ኛው ደቂቃ በተመሳሳይ ሌላ የጎል እድል ለሎዛ አበራ አመቻችታ በመስጠት ሎዛ አበራ ሶስታ ሀትትሪክ የሰራችበትን ጎል አስቆጥራለች ከስድስት ወር ቆይታ በኋላ ዳግም ወደ ሜዳ የተመለሰችው ሎዛ አበራ በዛሬ አቋሟ በቀሩት የሊጉ ጨዋታዎች ጎል ማስቆጠሯን የምትቀጥል ከሆነ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ሆና ለመጨረስ ሰፊ እድል ያላት ይመስላልበተወሰደባቸው ብልጫ መረጋጋት ያቃታቸው ኢትዮ ኤሌትሪኮች በቆሙ ኳሶች እና በግል ጥረቷ መሳይ ተመስገን ከምታደርገው ጥረት በቀር ወደ ጨዋታ የሚመልሳቸውን የጎል እድሎች መፍጠር ተስኗቸው ውሏል ኳስን ተቆጣጥሮ ከመጫወት ባለፈ እንምብዛም ወደ ፊት መሄድ አቁመው የነበሩት አዳማዎች ከ72ኛው ደቂቃ በሀላ ሎዛ አበራ ከሳጥን ውጭ በጠንካራ ምቷ ወደ ጎል የላከችውን ግብጠባቂዋ በሚገርም ብቃት ወደ ውጭ ካወጣችባት በኋላ ሴናፍ ሶስት ጎል መሆን የሚችሉ እድሎችን አምክናለችበመጨረሻም ሌሎች በርከት ያሉ ጎል መሆን የሚችሉ ኳሶችን ሎዛ ተቀይረው የገቡት ሳራ ነብሶ ሰርካዲስ ጉታ እና ጤናዬ ወመሴ ሳይጠቀሙ ቀርተው ጨዋታው በአዳማ 40 አሸናፊነት ተጠናቋልወደ ድሬዳዋ ያመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10 በማሸነፍ መሪነቱን አስቀጥሏል ብዙነሽ ሲሳይ በመጀመርያው አጋማሽ የንግድ ባንክን ብቸኛ ጎል ያስቆጠረች ተጫዋች ናት
https://soccerethiopia.net/football/45485
519
21,547
ኢዜማ በሲዳማ ዞን የተፈጸመውን ጥቃት አሳፋሪና አሳዛኝ በማለት አወገዘ
ፖለቲካ
24 July 2019
Unknown
ከቀናት በፊት በደቡብ ክልል ከሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች በሚኖሩ የተለያዩ የሀብረተሰብ ክፍሎች ላይ እጅግ አሳዛኝ ጉዳት መድረሱ የዜጎች ህይወት መጥፋቱ በርካታ ንብረት መውደሙ የቤተ እምነቶች መቃጠል እንዲሁም ከጥያቄው ጋር ምንም ግንኙነት በሌላቸው ሰላማዊ የሀብረተሰብ ክፍሎች ላይ የደረሰው ጉዳት አሳዛኝና አሳፋሪ መሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሀበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ ገለፀኢዜማ ይህን አቋሙን ያስታወቀው ማክሰኞ ሀምሌ 16 ቀን 2011 አም በቀድሞው የኢትጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ ፅህፈት ቤት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነውከቀናት በፊት ከሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ክስተት አሳዛኝና አሳፋሪ ብሎ ከመግለፅ በተጨማሪ እንደ አገር የደረስንበትን አስከፊ ደረጃ የሚጠቁም ነው ሲል ፓርቲው አስታውቋልይህ ጉዳት ከመድረሱ በፊት አደጋ እንዳለ በቂ ምልክቶች የታዩ ቢሆንም ኢመደበኛ በሆኑ ቡድኖች በዜጎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ግፊት ያደረጉ የፖለቲካ ሀይሎች ለደረሰው መጠነ ሰፊ ጉዳት ሀላፊነት ሊወስዱ ይገባል ብሎ እንደሚያምን ኢዜማ አቋሙን አስታውቋል በአገሪቱ ውስጥ እየታዩ ላሉ የፖለቲካ ውጥንቅጦች ሁሉ መነሻ በተወሰነ ደረጃ አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ መንግስት መሆኑን የአገሪቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በዘላቂነት የሚፈቱት በዚህ ህገ መንግስት ውስጥ አሉ የሚባሉ ችግሮች ሲሻሻሉ እንደሆነ እምነቱን እንደሆነ ገልፆ ነገር ግን አሁን አገሪቱ ውስጥ ባለው ያለመረጋጋት ሁኔታና በእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የህዝብ ወኪሎች በሌሉበት በህገ መንግስቱ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን በሰከነና በሰለጠነ መንገድ ችግሮችን መፍታት ይቻላል ብለን አናምንም በማለት ከሁሉም በፊት ሰላምና መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪውን አስተላልፏልበመሆኑም መንግስት አሁን በሲዳማ ዞንም ሆነ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለተፈጠሩ ችግሮች አፋጣኝ ፖለቲካዊና ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ በዚህ ጥፋት እጃቸው ያለበትን አካላት ሁሉ የህግ አግባቡን በመከተል በተገቢው አካላት በማጣራት ለፍርድ እንዲያቀርብና ውጤቱንም ለህዝብ እንዲያሳውቅ ሲል ጥያቄውን አቅርቧል በቀጣይም በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ መንግስት የፀጥታ መዋቅሩን በማጠናከር ዜጎችን ከጥቃት የመከላከል ሀላፊነቱን ይወጣ በማለት ጥሪውን አስተላልፏል ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ የማንነትና የክልልነት ጥያቄዎችን የሚያቀርቡ የሀብረተሰብ ክፍሎች ጥያቄ የማቅረብ መብት እንዳላቸው የሚያምን መሆኑን የጠቆሙት ኢዜማ ይሁን እንጂ በክልል ከሚቀርቡ ጥያቄዎች ጋር ተዛማጅነት በሌለው ሁኔታ የሌሎች የሀብረተሰብ ክፍሎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዳይጣሱ ህዝቡ የማናቸውንም ቡድኖች ህገወጥ ድርጊቶች እንዲከላከልና አጥፊዎችን ለህግ አሳልፎ በመስጠት የዜግነት ድርሻውን ይወጣ ሲልም ጥሪውን አቅርቧልበአሁኑ ወቅት ከተለያዩ ፖለቲካዊ ክስተቶችና ግጭቶች ጋር ተያይዞ በወንጀል ተጠርጥረው የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ፓርቲው መታዘቡን በመግለፅ አልፎ አልፎ የኢዜማ አባላትም የእስሩ ሰለባ ሆነዋል ህግን ለማስከበር በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች ህግ ፊት መቅረባቸው ተገቢ መሆኑን ብናምንም ተጠርጣሪዎች ከመታሰራቸው በፊት ለእስር የሚያበቃ በቂ ምክንያት መኖሩ መረጋገጥ አለበት በማለት አሳስቧል ኢዜማ ከሁለት ወር ከግማሽ በፊት የተመሰረተ ፓርቲ ነው ራሳቸውን በማክሰም ፓርቲውን የመሰረቱት ደግሞ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መኢዴፓ አርበኞች ግንቦት ሰባት አግ 7 ሰማያዊ ፓርቲ ሰማያዊ አዲስ ትውልድ ፓርቲ አትፓ የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ አንድነት ፓርቲ ሲሆኑ ከሳምንት በፊት ደግሞ የኢትዮጵያ ራእይ ፓርቲ ኢራፓ ተቀላቅሎታል  
https://www.ethiopianreporter.com/article/16256
410
19,803
እናት ባንክ የብድር ወለድ ስረዛና የአገልግሎት ማሻሻያ አደረገ
ቢዝነስ
May 14, 2020
486
አዲስ አበባግንቦት62012 ኤፍቢሲ እናት ባንክ ለተለያዩ የብድር ዘርፎች የብድር ወለድ ስረዛና የአገልግሎት ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀባንኩ በሰጠው መግለጫ ኮረና ቫይረስ  በወረርሽኝነት በአለምአቀፍ ደረጃ መሰራጨት ከጀመረበት ወቅት አንስቶ በአለም ማህበረሰብ ላይ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውሶችን በማድረስ ላይ  እንደሚገኝ ጠቅሷልይህ አለም አቀፍ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ በተለይም በኢኮኖሚው ዘርፍ   የንግድ እንቅስቃሴና በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት በማድረስ ላይ መሆኑን ነው የገለፀውበመሆኑም ባንኩ ይህንን ጉዳይ በከፋተኛ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት  በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ተበዳሪዎቹ የብድር ወለድ ስረዛና የተለያዩ የአገልግሎት ማሻሻያዎችን  ማድረጉን ነው የተናገረውየማሻሻያው ዋና አላማም እየተከሰተ ያለውን ችግር በጋራ ለመወጣት  በደንበኞች የንግድ እንቅሳቃሴ  ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ የብድር አመላለስን የተሻለ ለማድረግና የአገራችን  ኢኮኖሚ ሚዛናዊነቱን ጠብቆ ማስኬድ በሚቻልበት አካሄድ ባንኩ የራሱን ድርሻ ለመወጣት ታሳቢ ያደረገ  ነው ብሏል በዚህም መሰረት የብድር ወለድና አገልግሎት ክፍያን አስመልክቶ በሆቴልና ቱሪዝም የስራ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ደንበኞች ከግንቦት እስከ ሀምሌ የብድር ወለድ እንዳይከፍሉ መሰረዙን ገልጿልከዚያም ባለፈ የብደር ማራዘሚያ ላይ የሚከፈለዉ የአገልግሎት ዋጋ የኦቨር ድራፍት እድሳት ላይ የሚከፈለዉ የአገልግሎት ዋጋ ብድራቸውን ከሚጠበቅባቸው የመክፈያ ጊዜ ቀድመው ለሚከፋሉ ደንበኞች ይጣል የነበረው ቅጣት እንዲሁም  ውዝፍ የብድር እዳን አዘግይቶ ሲከፈል የሚጣል ቅጣት ሙሉ ለሙሉ መነሳቱንም ነው ያብራራውበአለምአቀፍ ባንኪንግ ዙሪያም  ባንኩ የተለያዩ ማሻሻያዎች ማድረጉን ገልፆ በዚህም አስመጪዎች እቃ ወደ ሀገር ለማስገባት ለከፈቱት ሌተር ኦፍ ክሬዲት LC አሁን በአለም ላይ ከተፈጠረዉ ችግር አኳያ አስቀድመዉ  ለማራዘሚያ የሚጠየቁት የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ለሙሉ እንዲነሳ መደረጉን አንስቷልበተያያዘም  ከኮቪድ 19 ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን እቃዎች ለሚያሰመጡ  አስመጪዎች ባንኩ  ሀምሳ በመቶ 50 የአገልግሎትና የኮሚሽን  ክፍያ መቀነሱን ነው የገለፀውባንኩ ማህበራዊ ሀላፊነትን ለመወጣትና ኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ለብሄራዊ የኮቪድ 19 ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ  የብር 2 ሚሊዮን ብርድጋፍ ከማበርከቱም ባለፈ የባንኩ ሰራተኞችና የደንበኞች ደህንነት ከወረርሽኙ ለመጠበቅ  የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆኑን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል የዜና ሰአት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልእክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ 
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a5%e1%8a%93%e1%89%b5-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ad-%e1%8b%a8%e1%89%a5%e1%8b%b5%e1%88%ad-%e1%8b%88%e1%88%88%e1%8b%b5-%e1%88%b5%e1%88%a8%e1%8b%9b%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d/
287
2,107
የዛፍ ጥላ ስር ትውስታዬ
መዝናኛ
March 22, 2019
106
እ ናንተ የአሁን ዘመን ወጣቶች መቼም ይህን ርእስ ስታነቡ ምን ትዝ ሊላችሁ እንደሚችል አላውቅም ቢበዛ ቢበዛ ዛፍ ጥላ ስር ሆነን ስንጨዋወት የሚለውን የሙሀሙድ አህመድ ዘፈን ሊያስታውሳችሁ ይችላል ለዛውም ቆየት ያሉ ዘፈኖችን የማዳ መጥ ልምድ ካላችሁ ነው የድሮ ወጣቶች የዛፍ ጥላ ስር ትዝታችን ብዙ ነው ጋሽ ሙሀሙድም የድሮ ሰው በመሆኑ ነው የዛፍ ጥላ ትዝታን በዘፈን የገለፀው እውነት ነው የዛፍ ጥላ ስር ሲባል ሁላችንም እንደየ አጠቃቀማችን ትዝታዎቻችን ይለያያሉ አንዳንዶቻችን በዛፍ ጥላ ስር አረፍ ብለን ከፍቅረኛችን ጋር ተጨዋውተን ሊሆን ይችላል አንዳንዶቻችን ፊደል ቆጥረን ይሆናል ሌሎቻችንም ዛፍ ጥላስር ተቀምጠን በሀገር ሽማግሌዎች ተመክረን ወይም ተዳኝተን ሊሆን ይችላል ዝናብና ፀሀይን የተጠለልን ደግሞ ብዙዎች ነን ብዬ እገምታለሁ ዛሬም ድረስ በተለይም በገጠሩ የሀገራችን ክፍል የዛፍ ጥላ እንደ ትምህርት ቤት እንደ መኖሪያ ቤት እንደ ፍርድ ቤት እና እንደ መዝናኛ ቤት ወዘተ ያገለግላል በልጅነቴ በቄስ ትምህርት ቤት በየኔታ እግር ስር ቁጭ ብዬ ፊደል መቁጠር የጀመርኩት በዛፍ ጥላ ስር ነው የኔታ ከዛፉ ላይ ቅርንጫፉን እየዘነጠፉ ገርፈውኝ ስርአት ይዤ እንዳድግ አድርገውኛል መቼም አንዳንድ አሽሟጣጮች አንተን ብሎ ስርአት አዋቂ ልትሉኝ እንደምትችሉ እገምታለሁ በተለይ እነ እከሌ ይህን ጊዜ ስንት ብላችሁኛል አይዟችሁ ስማችሁን አልጠራም ለማንኛ ውም ለፀባዬ ማማር ውለታ የዋሉልኝን የኔታንና ዛፉን ሳላመሰግን አላልፍም አለንጋና ቀለም ጠግበን ስናበቃ መጨረሻ ወደ ቤት ልንሄድ ስንል ጠዋት በፀሎት የጀመርነውን ትምህርት ማታም በፀሎት እንዘጋለን ከፀሎት በኋላ መጨረሻ ላይ ድምፃችንን ከፍ አድርገን በየኔታ ጉሮሮ ጠጅ ይንቆርቆር በእኛ ጉሮሮ ቀለም ይንቆርቆር የምንለውን ምርቃት መሰል የፀሎት ማሳረጊያ አልረሳውም አንድ ቀን ታድያ የኔታ አጠገቤ መሆና ቸውን ሳላውቅ በእኛ ጉሮሮ ጠጅ ይንቆርቆር በየኔታ ጉሮሮ ቀለም ይንቆርቆር ብዬ አባባሉን ገልብጬ ለመቀለድ ስሞክር ሰምተውኝ ኖሮ ጎትተው ጭናቸው ስር አስገብተው በቁንጥጫ አድብነው አድብነው የጣሉኝ አይረሳኝም አይ የእኔ ነገር ትዝታዬን ለማውራት ብዬ ሙት ወቃሽ ሆንኩኝ ነፍስ ይማር የኔታ እንኳንም ቆነጠጡኝ እንኳንም ገረፉኝ የእርሶ ምክርና ቅጣት ነው ጥሩ ስብእና እንድይዝ ያደረገኝ ይሄው ዛሬ እኔም እንደእርሶዎ አስተማሪ ሆኜ ተማሪዎችን በጥሩ ስነምግባርና በእውቀት እየገነባዋቸው ነው ይህ ዘመናዊ ትምህርት ቤት በመሆኑ እርሶ ያደርጉ እንደነበረው ትምህርታችንን በፀሎት ጀምረን በፀሎት አንዘጋም ተማሪዎች ተነሱና አንዴ ፀሎት እናድርግ ብላቸው ጉሮሯቸው እስኪሰነጠቅ እንደሚስቁብኝ አልጠራጠርም ግብረገብነት ጠፍቷል መምህርን ከማወደስ ይልቅ ማንኳ ሰስ ይቀናቸዋል እንደ ተማሪና አስተማሪ ሳይሆን እንደሌባና ፖሊስ መተያየት ይዘናል ያኔ እርሶ አራት የትምህርት አይነቶችን በአንድ ግዜ ያስተምሩን ነበር እኛን ፊደል ያስቆጥራሉ እነተሻለን ዳዊት ያስደግማሉ እነግዛውን አቡጊዳ ሄውዞ ያስጠናሉ እነአብዩን ወንጌል ያስነብባሉ በዚህም ላይ ቁጭ ብለው ቆብዎን እየሰፉ ያለበለዚያም ነጠላዎን እየቋጩ ሁሉንም ተማሪዎች እየተቆጣጠሩ የሚሰጡት ማስተካከያ ያስገርመኛል የኔታ እኔ ዛሬ አንድ ትምህርት እያስተ ማርኩ ተማሪዎቼን በቅጡ መቆጣጠር አልቻ ልኩም የተማሪዎቼን የትምህርት ፍላጎት አይና ሀሞቴ ይፈሳል እነሱስ ልጅነትና የአእምሮ ያለመብሰል ችግር ስላለባቸው ነው እኔ ሀላፊነቴን ለምን መወጣት ያቅተኛል እያልኩ እበሳጫለሁ በእርግጥ እራሴን ከእርሶ አንፃር ስመለከት ጥፋተኛ ነኝ መታረም ይኖርብኛል ከእኔ የሚጠበቀውን ሁሉ በማድረግ እነዚህን እንቦቀቅላ ልጆች ለፍሬ እንዲበቁ የማድረግ ሀላፊነቴን መወጣት ይኖርብኛል ለነገሩ የኔታ እነዚህ ተማሪዎች የእርስዎ ተማሪዎች ቢሆኑ ኖሮ አለም በቃኝ ብለው ይመንናሉ ካልሆነም በዱላ አስተካክላቸዋለሁ ብለው ያንን ዛፍ ካለ ቅርንጫፍ መለመሉን ያስቀሩት ነበር ነገረ ስራቸው ሁሉ እንደሚያናድዶት አስባለሁ እርሶ እኮ ለምን ውሀ ቀጠነ ብለው ነበር የሚገርፉን ድሮ የተቀደደ ልብስ ለብሰን ስንመጣ ከቀዳዳ ይሻላል ጨምዳዳ እያሉ የሚተርቱብንና በማግስቱ ሰፍተን ካልመጣን የሚጨርሱብን ልምጭ ይታወሰኛል ዛሬ የኛ ተማሪዎች ሆነ ብለው ፀጉራቸውን ያንጨባርራሉ ጆሯቸው ላይ ሎቲ ያንጠለጥላሉ የተቀደደ ቦላሌ ይለብሳሉ እሱንም እጉልበታቸው ድረስ አውርደው ይተውታል በተለይማ የደንብ ልብስ በማይለበስ ቀን ጉድ ይታያል ሱሪ የሚለብሱ ሴቶች እንደ አሸን ፈልተዋል መልበሱን እንኳን ይልበሱ ግን ጭናቸውን የሚያሳይ ሱሪ ካልሆነ አይለብሱም ይህ የእኔን ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን የዘመኑን ወጣቶች በሙሉ የተፀናወታቸው በሽታ ነው እንዲህም ሆነው እነሱ ደስተኞች ናቸው በሆነው ባልሆነው መሳቅ ይወዳሉ እውነት ለማለት ሳቃቸው ያስቀናኛል ያኔ እዛ እዛፍ ስር ስንማር አንድ ቀን መሳቄ ትዝ ይለኛል ለዛውም ተሻለ ግንባር ላይ ወፎች ኩሳቸውን ጥለውበት አይቼ ነው ወዲያው ታድያ እርሶ ሳቃችንን እስቁመው ሂድ ጅረት ወርደህ ታጠብ ብለው ከእኔ ጋር ላኩት በዚህ ዘመን በተለይ በከተማ የቄስ ትምህርት ቤት ምን ማለት እንደሆነ አይታ ወቅም ህፃናት ትምህርት የሚጀምሩት በመዋእለ ህፃናት ነው ፊደል እንዲቆጥሩ የሚበረታቱትም በእንግሊዘኛ ነው ለምን ቢባል አለም ወደ አንድ መንደር እየመጣች ስለሆነ ወደፊት ከአለም ህዝብ ጋር በእንግሊዘኛ ቋንቋ ለመግባባት እንዲያመቸን ተብሎ ነዋ አንዳንድ አሽሟጣጮች ግን ኢትዮጵያ ራሷ መች አንድ ሆነችና ነው ከአለም ህዝብ ጋር አንድ ልትሆን ያሰበችው እያላችሁ እንደምታንሾካሽኩ አልጠራጠርም እናንተ ሰዎች ግን የህዝባችን በተለይም የወጣቱ ንቃተ ህሊና ያልገባችሁ ናችሁ መጀመሪያ ከአለም ህዝብ ጋር ከመቀላቀላችን በፊት ምናልባት ሁኔታው ሳይመቸን ቀርቶ እንለያይ ብንል እንዴት መለያየት እንዳለብን በተግባር የተደገፈ ስልጠና እንውሰድ በሚል ነው ወጣቱ ሙከራ እያደረገ ያለው ስለዚህ አሁን በየክልሉ አንዱ አንዱን የሚገፋው የስልጠናው አንድ አካል ስለሆነ ነው ከፈለጋችሁ የስልጣኔው አንድ አካል ነው ብላችሁ አስተካክሉት አይ የእኔ ነገር የተነሳሁት የዛፍ ስር ትውስታችንን መለስብለን እንድናይ ለማድረግ ነበር ሳላስበው ሌላ ጉዳይ ውስጥ ከተታችሁኝ የጀመርኩላችሁን ወግ ልጨርስላችሁ ዛሬ ዘመኑ ተለውጧል ሰውም ሰልጥኗል ከተሞች አድገዋል ትምህርት ተስፋፍቷል በሚባልበት በዚህ ወቅት ልቤን የሰበረኝ ነገር ያደግሁባት መንደር ምንም እድገት ያለማሳየቷ ነው በዚች የገጠር ቀበሌ አንድ የመለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኝ ሲሆን ስምንት የመማሪያ ክፍሎች አሉት ከእነዚህ ውስጥ ግድግዳና የቆርቆሮ ክዳን ያላቸው ሶስቱ ብቻ ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የመምህራን ቢሮና ማረፊያ ነው በተረፈ የተቀሩት አምስቱ ሶስቱ በዳስ ሁለቱ ደግሞ በዛፍ ጥላ ስር ትምህርት የሚሰጥባቸውና እንደ መማሪያ ክፍል የሚቆጠሩ ናቸው እናንተ የከተማ ልጆች በመንግስት ትምህርት ቤት ያውም በዚህ ዘመን ዛፍ ጥላ ስር የሚማሩ ተማሪዎች አሉ ስትባሉ ታምናላችሁ ብዬ አልገምትም ግን የምነግራችሁ እውነት ነው በአንድ የክረምት ወቅት ወደ ቤተሰቦቼ ሄጄ ያለስራ ከምቀመጥ አልኩና ፊደል በቆጠርኩበት ዛፍ ስር የሰፈሩን ልጆች ሰብስቤ ማስተማር ጀመርኩኝ ታድያ አንድ ቀን እያስተማርኩ እያለሁ በመሀል አንድ ሁለት ተማሪዎች እንቅልፍ ይዟቸው ጭልጥ አለ ላነቃቃቸው በማሰብ ቀልድ ብጤ ላወራላቸው ሞከርኩኝ ተማሪዎች መምህር በጀኔሬተር ተማሪ ደግሞ በአንፑል ይመሰላል ይህ ማለት መምህር ሞተር ሆኖ ለተማሪዎቹ ሀይል ሲሰጣቸው ተማሪዎቹ ደግሞ አንፑል ሆነው ያበራሉ ማለት ነው አልኳቸው በመሀል አንዱ ተማሪ መምህር ጄኔሬተርን እንኳ አውቃለሁ ውሀ ከወንዝ እየሳብን መስኖ እያለማንበት ነው አምፑል ማለት ግን ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም አለኝ እውነቱን ነው ሰፈራቸው መብራት ሳይገባ አንፑልን ማወቅ አይጠበቅበትም ስለዚህ አንፑል ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስረዳሁት እንዳሰብኩት እንደምንም ብዬ አሳቅኳቸውና ተነቃቅተው እንዲማሩ አደረግ ኳቸው አይ የልማቱ ተቋዳሽ ያልሆኑት የመንደሬ ልጆችአዲስ ዘመን መጋቢት 122011ኢያሱ መሰለ
https://www.press.et/Ama/?p=7313
901
42,449
ልዮ መርምሪ ሮበርት ሞለር የመጀመሪያ መግለጫ
ዓለም አቀፍ ዜና
May 29, 2019
Unknown
የሮበርት ሞለር ልዩ መስርያ ቤት ከሶስት አመታት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው የምርጫ ዘመቻ የሩስያ እጅ መግባትን አስመልክቶ ለ22 ወራት ያህል ምርመራ ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወቅ ነውሞለር የምርመራውን ሂደት ባለፈው መጋቢት ወር ሲያጠናቅቁ በዶናልድ ትረምፕ የምርጫ ዘመቻና በሞስኮ መካከል የመመሳጠር ተግባር መፈፀሙን የሚያረጋግጥ ማሰረጃ አልተገኘም ብለዋልፕሬዚዳንት ትረምፕ የምርመራውን ሂደት ለማሰናክል ሞክረው እንደሆነ ግን የክስ ምክረ ሀስብ ለማቅረብ ባይችሉም እንኳን ነፃ ናቸው እንደማይሉ ባወጡት ባለ 448 ገፅ የምርመር ውጤት ግልፅ አድርገዋልሞለር ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ፕሬዚዳንቱ ምንም አይነት ወንጀል አልፈፀሙም በሚለው ነጥብ ላይ ብንተማመን ኖሩ በግልፅ እናስቀምጠው ነበር ብለዋልየዩናይትድ ስቴትስ ዋና አቃቤ ህግ ዊልያም ባር የሞለርን ዘገባ ከሌሎች ከፍተኛ የፍርድ ሚኒስቴር ባለስልጣኖች ጋር ሆነን ከመረመርን በኋላ ትረምፕን የፍርዱን ስርአት ለማሰናክል በመሞከር ተግባር ለመክሰስ የምንችልበት በቂ ማስረጃ አልተገኝም ሲሉ ለሀገሪቱ ምክር ቤት አባላት ተናግረዋ ነበር
https://amharic.voanews.com//a/muller-explains-decision-not-to-charge-trump-5-29-2019/4937379.html
119
11,065
ወጣቱ የራሱን ታሪክ እንዲሠራ አባቶች አሳሰቡ፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
January 24, 2020
61
ባህር ዳር ጥር 152012አም አብመድ ወጣቱ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ከፍታ የማድረስ አደራውን እንዲወጣ የጋሞ አባቶች አሳስበዋልየዘመናችን ጀግኖችን ለማብሰር እና ለሌላ ጀብድ እንዲነሳሱ ለማድረግ ያለመ መርሀ ግብር ትናንት ምሽት በባህር ዳር ተካሂዷል በዝግጅቱ የጋሞ አባቶች የከተማ አስተዳድሩ የስራ ሀላፊዎችና ወጣቶች ታድመዋል አባቶቹም ወጣቱ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ከፍታ የማድረስ አደራውን እንዲወጣ አሳስበዋል በአባቶች ታሪክ ከመመካት ባለፈ የእራሱን ታሪክ በመስራት ለቀጣዩ ትልድ አርአያ መሆን እንዳለበትም ነው የጠየቁትየባህር ዳር ከተማ አስተዳድር ከንቲባ መሀሪ ታደሰ ዶክተር ደግሞ ወጣቱ ትውልድ በሀገራዊ አንድነት ግንባታ ላይ የአባቶቻችን ጀግንነት ሊደግም እንደሚገባ አሳስበዋል ጀግንነት በጦር ሜዳ ብቻ የሚገለፅ ባለመሆኑ በኪነጥበቡ በህክምናው በባህል እድገቱ በአጠቃላይ በየተሰማራበት የስራ ዘርፍ ሁሉ ውጤታማ ስራ በመስራት ጀግና መሆን እንደሚገባም ዶክተር መሀሪ አስገንዝበዋል ለሀገር መልካም ነገር እየሰሩ ለሚገኙት የጋሞ አባቶችም የሰላም እና የፍቅር ጀግኖች በመሆናቸው ምስጋና ቀርቦላቸዋል ወጣቱ ከጋሞ አባቶች ሰላምን ፍቅርን እና ይቅርባይነትን ተምሮ ለሀገር አንድነት መስራት እንደሚገባውም የመርሀ ግብሩ ታዳሚያን ጠይቀዋልየደግ ኢትዮጵያውያን የስልጠና ማእከል መስራች እና የፕሮግራሙ አዘጋጅ አቶ ቤንጃሚን ወንዴ የአብዛኛዎቹ ሀገራት የሀያልነታቸው እና የእድገታቸው ምስጢር አስተሳሰብ ላይ ተኩረት ሰጥተው መስራታቸው እንደሆነ አስገንዝበዋል አስተሳሰብ ላይ መስራት ሀገር ላይ መስራት ነውና ተቋማትም የሰው አእምሮ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ነው በመርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች የተነሳውየተሰራ አእምሮ የፈረሰን ከተማ ይሰራል ያልተሰራ አእምሮ የተሰራ ከተማን ያፈርሳል በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደውን መርሀ ግብር የደግ ኢትዮጵያውያን የስልጠና ማእከል ከባህር ዳር ከተማ አስተዳድር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁትዘጋቢዳግማዊ ተሰራ
https://www.amharaweb.com/%e1%8b%88%e1%8c%a3%e1%89%b1-%e1%8b%a8%e1%88%ab%e1%88%b1%e1%8a%95-%e1%89%b3%e1%88%aa%e1%8a%ad-%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8b%b2%e1%88%a0%e1%88%ab-%e1%8a%a0%e1%89%a3%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%8a%a0%e1%88%b3/
212
2,474
ሕግ ወዲህ ተግባር ወዲያ – በፋሲካ ገበያ
ሀገር አቀፍ ዜና
April 18, 2020
50
አዲስ አበባ ነጋዴውም የቁም እንስሳቱም ሸማቹም አንድ ላይ ተፋፍገዋል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ትንፋሽን በሚያፍነው ሽታ ባለበት የገበያ ቦታ ከወዲያ ወዲህ ይርመሰመሳሉ አንዱም ግን የእጅ ጓንት ሆነ የአፍ መሸፈኛ ሲጠቀም አልታየም ምናልባትም ከመቶ ሰዎች በአማካይ አንዱ ብቻ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጓል ቢባል ማጋነን አይሆንም እርሱም ቢሆን ለመሸመት ከመጡት ሰዎች መካከል እንጂ ነጋዴው ምንም የጥንቃቄ ነገር አይታይበትም ለግብይት የሚመጣው ሰው የሚገለገልበት የእጅ መታጠቢያ ሆነ ሳኒታይዘር በአካባቢው አይታይም መንግስት ያወጣውን ህግ የሚያስከብር የፀጥታ ሀይልም ሆነ የመስተዳድር አካል የለም የገበያው ቦታ ፍፁም ህገ ወጥነት የሰፈነበት ነው ስለበሽታው አደገኛነት ሆነ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ የተነገረው እና የተመከረው ሁሉ በርግጥም ሰሚ እንዳላገኘከበሽታው ጋር በተያያዘ የቱን ያህል እንደተዘናጋን ተጨባጭ ማሳያ ነውየገበያውን ሁኔታ ለሚመለከት ከአመት እና ከሁለት አመት በፊት የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት የተደረገ እንጂ አሁን ላይ ስለመሆኑ ሊጠራጠር ይችላል ይህ ሁሉ ሁነት ግን የሚታየው በሰፊው በአያት አደባባይ የመንገድ አካፋይ ላይ በተዘረጋው የበአል ገበያ ቦታ ነው ኮሮና ስለመጣ አትጠጋገጉ ንፅህናችሁንም ጠብቁ እየተባለ በመገናኛ ብዙሀን በሚነገርበት በዚህ ወቅት በገበያው ያለውን መተፋፈግ እና የሳሙናና እጅ መታጠቢያ አለመኖር ተመልክቶ አንድ የሚል አካል መጥፋቱ ብዙዎችን አሳዝኗል ወዴት እያመራን ነው ያሉም አልጠፉም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአዋጁ የተደነገጉ የአታድርግ አድርግ ህጎች አዋጁን እንዲያስፈፅም ስልጣን የተሰጠው አካል ሁሉም በገበያው ስፍራ የሚታሰቡ አይደሉም አካባቢው በልዩ ሁኔታ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ነፃ አካባቢ ነው የሚመስለው በገበያው የተገኙት አቶ ታደሰ ዳምጠው ሰባ የበአል በጎችን በተሽከርካሪ አስጭነው ወደ አያት አካባቢ ደርሰዋል ወደተዘጋጀው የገበያ ቦታ ሲገቡ ግን አንድም ሰው ጓንት አድርጎ አሊያም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጎ ባለማየታቸው ተገርመዋል በአካባቢው የበሽታው መከላከያ የጥንቃቄ እቃዎች አለመኖራቸው አስጨንቋቸዋል አልፎ አልፎም የሚመጡ ገበያተኞችን እያስተናገዱ በጎን ደግሞ ሌላው ቢዘናጋ ለእራሴ ማሰብ ይገባኛል በሚል ለአፍና አፍንጫቸው መከላከያ የሚሆናቸው ፎጣ ቢጤ እንዲገዙላቸው ጓደኞቻቸውን መላካቸውን ይናገራሉ የአያት አደባባዩ የበአል ገበያ በየመገናኛ ብዙሀን የሚገለፀውን የጥንቃቄ እርምጃ ወደጎን ያለ በመሆኑ እንዳሳሰባቸው አቶ ታደሰ አልሸሸጉም ይሁንና በገበያው መሀል በርካታ አስተናባሪዎችን እና የፀጥታ ሰዎችን በመመደብ ገበያተኛው አስፈላጊውን ርቀት ጠብቆ በጥንቀቄ እንዲገበያይ አለመደረጉ ነገ ላይ የከፋ ጉዳት ሊያመጣ ይችላልና እያንዳንዱ ዜጋ እራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ ይናገራሉ አቶ ሰኢድ የሱፍ ደግሞ ከአዲስ አበባ አጎራባች አካባቢዎች የቁም እንስሳትን አጓጉዘው በመምጣት በአያት አደባባዩ ገበያ የተገኙ ነጋዴ ናቸው በገበያው አካባቢ አንድም የእጅ መታጠቢያ እና ሳሙና አሊያም ሳኒታይዘር አቅርቦት አለመኖሩ አሳስቧቸዋል የገበያው ጭንቅንቅ እና የንፅህና እጦትም በሽታው ከሀገር የጠፋ ያህል እንደተዘነጋ ማሳያ እንደሚሆን ይናገራሉ ይሁንና ዋነኛ ገቢያቸው ከእንስሳት ሽያጭ የሚገኝ ትርፍ በመሆኑ ለበአል ገበያው ላይ መሳተፋቸውን ያስረዳሉ እያንዳንዱ ሸማች እንስሳቶችን ለመግዛት ሲመርጥ በእጁ በመነካካት መሆኑን የተናገሩት አቶ ሰኢድ ቆሻሻውን በነኩበት እጅ የቆጠሩትን ገንዘብ ለነጋዴው ሲሰጡ መዋላቸውን ይገልፃሉ አንዳንዱም ብሩን ሲቆጥር በልምድ ምክንያት ምራቁን ጢቅ እያለ መሆኑ ሲታሰብ በሽታው አይምጣ እንጂ አንድ ጊዜ ገበያው መሀል ላይ የታመመ ሰው ከተገኘ ችግሩ ሀገርን ለአደጋ የሚያጋልጥ እንደሆነ መገንዘባቸውን ይናገራሉ የእለት ጉርሱን ለመሸፈን የወጣውን ነጋዴ በየጊዜው ማንቃት እና የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድ ማስተማር የአካባቢው አስተዳደር ብሎም የህክምና ሰዎች እና የመገናኛ ብዙሀኑም ድርሻ መሆኑን ይናገራሉ በአዲስ አበባ ፈረንሳይ አካባቢ እና ሾላ አካባቢ የሚገኙ የበአል እርድ የእንስሳት መሸጫዎች ቦታዎች ላይ በንፅፅር የተሻለ መራራቅ መኖሩን መታዘብ ቢቻልም በሁሉም ገበያዎች ላይ ግን ነጋዴውም ሆነ ሸማቹ የእጅ ጓንት ሳያደርግ እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳይዝ ገንዘብ ሲለዋወጥ በስፋት ይታያል ወይዘሮ አልማዝ ታዬ ደግሞ በሾላ ገበያ የሚታየው ጥንቃቄ ከመራራቅ ባለፈ የእጅ ንፅህና ላይ ያተኮረ አለመሆኑን መታዘባቸውን ይናገራሉ ኮሮና ደግሞ ከመራራቅ ባለፈ ንፅህና የሚጠይቅ በመሆኑ አብዛኛው ሰው በሽታውን ይዞ ወደቤቱ እንዳይመለስ በገበያ አካባቢዎች አስፈላጊውን ስራ የሚመለከተው አካል ፈጥኖ ሊሰራ እንደሚገባ ይመክራሉ የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እና የተረጋጋ የበአል ገበያ ለማካሄድ ያስችላሉ የተባሉ የቁም እንስሳት መሸጫ ቦታዎች ይፋ ማድረጉ ይታወሳል በተለይ በገበያዎቹ እና ሰው በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ነጋዴው እና ሸማቹ ማህበረሰብ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እና የእጅ ጓንት የመጠቀም ግዴታ የተጣለ ቢሆንም የመንግስትን ትእዛዝ እንዳልተፈፀመ መታዘብ ተችሏል ኮሮናን አስመልክቶ መንግስት ያወጣቸው ህጎችም በመገናኛ ብዙሀን እና በየአውራ ጎዳናዎች ላይ ሲተላለፉ ቢውሉም የገበያ ቦታዎች ላይ ተግባር አልባ ሆነው ውለዋል ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ ፈጥኖ ካልተወሰደ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል መገመት የሚከብድ አይሆንም ለጉዳዩ መልስ ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ምላሽ ማግኘት አልተቻለምአዲስ ዘመን ሚያዝያ 102012 ጌትነት ተስፋማርያም
https://www.press.et/Ama/?p=30535
613
30,389
ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት የሚያደርጉት ጨዋታ ላይካሄድ ይችላል
ስፖርት
March 20, 2019
Unknown
በ17ኛ ሳምንት ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት ጨዋታ አስቀድሞ በወጣለት መርሀ ግብር መሰረት ላይካሄድ ይችላልመጋቢት 15 እሁድ 1000 ላይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው አጋማሽ የውድድር ዘመን 17ኛ ሳምንት ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት ጨዋታቸውን እንዲያደርጉ አስቀድሞ መርሀ ግብር ማውጣቱ ይታወሳል ሆኖም በኢትዮጵያ ቡና በኩል በአሁኑ ሰአት አማኑኤል ዮሀንስ እና አቡበከር ናስር ለ23 አመት በታች የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ብሄራዊ ቡድን ምክንያት ለኢትዮጵያ ቡና አገልግሎት እየሰጡ አይገኙም አሁን ደግሞ ብሩንዲያዊ አዲስ ፈራሚ አጥቂ ሀሰን ሻባኒ ለሀገሩ ብሄራዊ ቡድን ለመጫወት ጥሪ ቀርቦለት ወደ ሀገሩ ሲያቀና ሌላው ዩጋንዳዊው አማካይ ክሪዚስቶም ንታምቢ በተመሳሳይ ለሀገሩ ብሄራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለት ለመጫወት ወደ ሀገሩ አምርቷልየቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ  በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ደንብ መሰረት አንድ ቡድን ሶስት ወይም ከሶስት በላይ ለብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ካስመረጠ ውድድር እንደማያደርግ የተቀመጠ በመሆኑ አወዳዳሪው አካል በቅርቡ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚያሳውቀው ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ ቡና እና የደደቢት ጨዋታ ወደ ሌላ ቀን የመተላለፍ እድል ሰፊ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል
https://soccerethiopia.net/football/45897
158
15,413
በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያን ባሉበት ፖስፖርትና መታወቂያ ማሳደስና መረከብ የሚችሉበት ስርአት ተግባራዊ ሆነ
ሀገር አቀፍ ዜና
Sep 14, 2020
490
አዲስ አበባ መስከረም 4 2013 ኤፍቢሲ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን ወደ ኤምባሲ መምጣት ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው ፖስፖርት እና የትውልድ ኢትዮጵያን መታወቂያ Origin ID ማሳደስና መረከብ የሚችሉበት ስርአት በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ ተጀመረስርአቱን የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ቪዲቸር ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በመተባበር ነው ተግባራዊ ማድረግ የጀመረውበስርአቱ የሚጠቀሙ ተገልጋዮች የታደሰ ፓስፖርት ወይም ትውልድ መታወቂያ በ15 ቀን ማግኘት ይችላሉ ተብሏልበተጨማሪም ወደ ኤምባሲ በመመላለስ የሚያጠፉት ግዜና ወጪ አይኖርምየተዘረጋው ስርአት ለ6 ወር በሙከራ የሚቆይና ያመጣው ለውጥ የሚገመገም ሲሆን ውጤቱ ታይቶ በሌሎች ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ደረጃ በደረጃ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%88%9c%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8c%88%e1%8a%99-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8a%95%e1%8a%93-%e1%89%b5%e1%8b%8d%e1%88%8d%e1%8b%b0-%e1%8a%a2/
93
43,453
ሰበር ዜና;በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከተከሰተዉ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ 4 የስራ ሃላፊዎች ታገዱ
ፖለቲካ
July 3, 2018
Unknown
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈጠረዉን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር  በተደረገዉ ጥረት ሀላፊነታቸዉን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ 4 የስራ ሀላፊዎች ታገዱየታገዱትም የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ማስተባበሪያ ቢሮ ሀላፊ የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርየክልሉ ልዩ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ እና የክልሉ ልዩ ፖሊስ መምሪያ ምክትል ሀላፊ ሲሆኑ በችግሩ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 11 የፖሊስ አባላት ጭምር መታገዳቸዉ ታዉቋል
https://waltainfo.com/am/30083/
48
13,884
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ በሰላምና ደህንነት መስኮች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ
ሀገር አቀፍ ዜና
Nov 26, 2020
624
አዲስ አበባ ህዳር 17 2013 ኤፍ ቢ ሲየብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ በሰላምና ደህንነት መስኮች እንዲሁም ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%89%a5%e1%88%84%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%88%98%e1%88%a8%e1%8c%83%e1%8a%93-%e1%8b%b0%e1%88%85%e1%8a%95%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8e%e1%89%b5-%e1%8a%a5/
28
9,635
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሁለት ወረዳዎች የአንበጣ መንጋ ተከስቷል።
ሀገር አቀፍ ዜና
October 21, 2020
27
ባህር ዳር ጥቅምት 112013 አም አብመድ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ከሌሊቱ 600 ጀምሮ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የብሄረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ አስታውቋልበዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ አንድ ቀበሌ እና ፃግቭጂ ወረዳ አራት ቀበሌዎች የበረሀ አንበጣ መንጋ መከሰቱን የአስተዳደሩ ግብርና መምሪያ አስታውቋልየግብርና መምሪያው የሰብል ልማት ጥበቃ አስተባባሪ በዛብህ ጌታሁን የበረሀ አንበጣ መንጋው ከአጎራባች የትግራይ ክልል ወረዳዎች ተነስቶ ትናንት ከሰአት በኋላ 900 አካባቢ ወደ ብሄረሰብ አስተዳደሩ ፀግቭጂና ሰቆጣ ወረዳ ቀበሌዎች ገብቷል ብለዋልበፃግቭጂ ወረዳ 02 07 08 እና 09 ቀበሌዎች በሰቆጣ ወረዳ ደግሞ 07 ቀበሌ ላይ ተከስቷልየአንበጣ መንጋው በጊዚያዊነት በቀበሌዎቹ አረንጓዴ እፅዋት በሚገኙባቸው ተራራማና ደን ቦታዎች ሰፍሮ የእንስሳትን መኖ እያጠፋ መሆኑን አቶ በዛብህ ተናግረዋልየአንበጣ መንጋውን መንግስት ቀድሞ ባሰራጨው ኬሚካልና ባህላዊ የማባረሪያ መሳሪያዎችን በመጠቀም ከሌሊቱ 600 ጀምሮ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋልየበረሀ አንበጣ መንጋው ወደሰብል እንዳያርፍ የተደረገው ርብርብ ውጤታማ ቢሆንም አሁንም ተጨማሪ የአንበጣ መንጋ ሊመጣ ስለሚችል ኀብረተሰቡ ሊጠባበቅ እንደሚገባ አሳስበዋልተጨማሪ ኬሚካልና ግብአቶችን ክልሉ እየላከ ነው ያሉት አስተባባሪው የአካባቢው መልክአ ምድር አስቸጋሪ በመሆኑ ለመከላከሉ ስራ ውጤታማነት በተሽከርካሪና ድሮን የታገዘ ርጭት ማድረግ እንደሚገባ አስታውቀዋል
https://www.amharaweb.com/%e1%89%a0%e1%8b%8b%e1%8c%8d-%e1%8a%bd%e1%88%9d%e1%88%ab-%e1%89%a5%e1%88%94%e1%88%a8%e1%88%b0%e1%89%a5-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%89%b0%e1%8b%b3%e1%8b%b0%e1%88%ad-%e1%88%81%e1%88%88%e1%89%b5-%e1%8b%88/
157