id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
45493636
https://www.bbc.com/amharic/45493636
ኢትዮጵያ በውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ብዛት ቀዳሚ ሆነች
ባለፉት ስድስት ወራት ኢትዮጵያ በሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ብዛት ከዓለም ቁጥር አንድ መሆኗ ተነገረ።
በምግባረ ሰናይ ድርጅቶች የሚከፋፈሉ የዕርዳታ ቁሶችን ለማገኘት ተፈናቃዮች እሰከ 50 ኪ.ሜ ድረስ በእግር መጓዝ ሊጠበቅባቸው ይችላል። ዓለም አቀፉ የሃገር ውስጥ ተፈናቀዮች ተቆጣጣሪ ማዕከል (ኢንተርናሽናል ዲስፕለስመንት ሞኒተሪንግ ሴንተር) እንደሚለው ከሆነ የ2018 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለደህንነታቸው በመስጋት የመኖሪያ ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል። ''1.4 ሚሊዮን ህዝብ ግጭት በመሸሽ የመኖሪያ ቀዬውን ጥሎ ሲሰደድ በቂ ትኩረት አልተሰጠውም። የተቀረው ዓለም የኢትዮጵያን ችግር ማየት አልፈቀደም'' በማለት የኖርዌ የስደተኞች ካውንስል የቀጠናው ዳይሬክተር ኒገለ ትሪክስ ተናግረዋል። • በጉጂ እና ጌዲዮ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ • "የጌዲዮና ጉጂ ተፈናቃዮች ቸል ተብለዋል" የዓለም ቀይ መስቀል ማኀበር • በችግር ላይ የሚገኙት ተፈናቃዮች በጌዲዮ እና ምዕራብ ጉጂ የተከሰቱት ግጭቶች እንዲሁም በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር ላይ የተከሰቱት ተደጋጋሚ ግጭቶች በሃገር ውስጥ የተፈናቀሉትን ሰዎች ቁጥር 1.4 ሚሊዮን እንዳደረሱት ሪፖርቱ ይጠቁማል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለተፈናቀዮች ምላሽ ለመስጠት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ፤ ይሁን እንጂ ከተፈናቀዮች ከፍተኛ ቁጥር አንጻር ያለው ፍላጎትና ዝናባማው የአየር ሁኔታ ችግሩን ከመንግሥት እና ከበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ አቅም ባላይ እንዳደረገው ሪፖርቱ ጠቁሟል። የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ እየሰራ ነው። መንግሥት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ መኖሪያቸው ለመመለስ ቅድሚያ ሰጥተው እየሰሩ ነው። በዚህም ተፈናቀዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው። ይሁን እንጂ አሁንም በርካቶች ቤታቸው እንደወደመ ነው፤ ይላል ሪፖርቱ። ''ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ ቢፈልጉም ከመኖሪያቸው ሲሰደዱ ባዶ እጃቸውን ነው ይወጡት። ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚደረግበት መንገድም በራሳቸው ፍቃድ እና ደህንነታቸው ተረጋግጦ አንዲሁም አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው ሊሆን ይገባል'' ሲሉ ትሪክስ ይናገራሉ።
news-55614497
https://www.bbc.com/amharic/news-55614497
በኢንዶኔዢያ መሬት መንሸራተት ነፍስ ለማዳን የተሰማሩ ሠራተኞች ሞቱ
በኢንዶኔዢያ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት የተጎዱትን በመፈለግ ላይ የነበሩ የነፍስ አድን ሠራተኞች ሁለተኛ ዙር በተከሰተ የመሬት ናዳ ተጭኗቸው መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።
መጀመሪያው በዌስት ጃቫ ቺያንጁዋንግ መንደር በጣለ ከባድ ዝናብ ሳቢያ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከስቶ ነበር። ሌላኛው አደጋ ደግሞ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች አካባቢውን ለቅቀው እየወጡ ባለበት ሰዓት የተከሰተ ነው። በአደጋውም ቢያንስ 12 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም። በኢንዶኔዢያ በዝናብ ወቅት የመሬት መንሸራተት አደጋ የተለመደ ሲሆን፤ የደን መጨፍጨፍ ለዚህ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። በቅርብ የተከሰተው አደጋ ከዋና ከተማዋ ጃካርታ 150 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሰሜዳንግ የሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል። የአደጋ ኤጀንሲ ቃል አቀባይ ራዲይታ ጃቲ በመግለጫቸው እንደተናገሩት አደጋዎቹ ያጋጠሙት በ3፡30 ሰዓት ልዩነት ነው። ቃል አቀባዩ የመጀመሪያው አደጋ የተከሰተው በከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የአፈር መሸርሸር ሳቢያ ሲሆን፤ ቀጣዩ ደግሞ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በመጀመሪያው አደጋ የተጎዱትን ለማውጣት እየሰሩ ባለበት ወቅት ያጋጠመ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ አደጋም የነፍስ አድን ሠራተኞቹ ከሞቱት መሃል እንደሚገኙበት ቃል አቀባዩ አክለዋል። የ6 ዓመት ሕጻንም ከሟቾቹ መካከል እንደሚገኝበት ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። እሁድ ዕለት 27 ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ እና 46 የሚሆኑት ከአደጋው መትረፋቸውን የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። በአካባቢው ያለው ከባድ የአየር ሁኔታም የነፍስ አድን ሥራውን እንዳስተጓጎለው የተገለፀ ሲሆን ፍለጋው ዛሬ ይቀጥላል ተብሏል።
news-54887931
https://www.bbc.com/amharic/news-54887931
ትራምፕ ሥልጣን አለቅም ቢሉ በአሜሪካ ምን ይከሰታል?
በአሜሪካ 244 ዓመት የፖለቲካ ታሪክ ሥልጣን አለቅም ብሎ ያለ አንድም ፕሬዝዳንት አልተወለደም። ትራምፕ ግን እያስፈራሩ ናቸው። ነገሩን ሁሉ ወደ ፍርድ ቤት እየወሰዱት ነው።
ቆጠራው ይደገም፣ ተጭበርብሯል፣ ታዛቢዎች ሲጭበረበር እንዳያዩ ተደርገዋል፣ እከሳለሁ፣ ባይደን አላሸነፈኝም፤ የአሜሪካ ሚዲያ ነው ያሸነፈኝ እያሉ ናቸው። በየዕለቱ ገና ምን አይታችሁ እያሉ ይዝታሉ። ታዲያ ምን ተሻለ?ባይደን አሸነፉ ተብሎ አገር ጉድ ሲል ትራምፕ ቨርጂኒያ ነበሩ። ጎልፍ ይጫወቱ ነበር። ወዲያውኑ የፕሬዝዳንቱ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን “ባይደን አሸነፈ ያለው ማነው? ገና እንተያያለን”የሚል መግለጫ አወጣ። አሜሪካዊያን ግራ ተጋቡ። እንዲህ ዓይነት ነገር ገጥሟቸው አያውቅማ። ታዲያ አሁን ምን ተሻለ? ከዋይት ሐውስ ነቅነቅ አልልም ቢሉስ፣ ትራምፕ? እዚሁ ቅበሩኝ ቢሉስ ትራምፕ?የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው። የአሜሪካ ሕገ መንግሥት አንድ ቁልጭ አድርጎ የሚያስቀምጠው ነገር አለ፤ በጥር (ጃንዋሪ) ወር በዕለት 20፣ ዕኩለ ቀን ላይ የተሸናፊው ፕሬዝዳንት ሥልጣን ይለቃል፣ ከነጩ ቤተ መንግሥትም ማቄን ጨርቄን ሳይል ይወጣል። ጆሴፍ ባይደን ከዋና ዋና ግዛቶች ለፕሬዝዳንትነት የሚያበቃቸውን የውክልና ድምጽ አግኝተዋል። ከ270 የአሸናፊነት መስመርም አልፈዋል። እንዲያውም በአሜሪካ ታሪክ እንዲህ በርካታ የሕዝብ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ የለም። ባራክ ኦባማ ራሱ ተበልጠዋል። ችግሩ ወዲህ ነው። ትራምፕ የሽንፈትን ጽዋ ግጥም አድርጎ መጠጣት አይችሉም። በቃ አይችሉም። ስለዚህ በአሜሪካ የምርጫ ታሪክ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙትን ሰው ድል ለመቀበል አልቻሉም። ስለዚህ ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ተሸጋገሩ። ምርጫው ተጭበርብሯል ወደሚለው ምዕራፍ። ይህን ደግሞ መፋለም የሚችሉት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በሳቸው ወዳጆች፣ በወግ አጥባቂ ዳኞች የተሞላ ነው። ነገሩን እዚያ ካደረሱት ያልተጠበቀ ነገር ሊከሰት ይችላል።ትራምፕ አሁን ከፍተኛ ሚሊዮን ዶላር መድበው፣ እሳት የላሱ ጠበቆቻቸውን አሰልፈው 'ዳይ' ፍርድ ቤት ክስ መዝገብ ክፈት እያሉ ነው። ሩዲ ጁሉያኒ የጠበቆቻቸው አለቃ ናቸው። ትራምፕ አሁን ላይ የሕግ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፣ ምርጫው ላይ ከሕግ ያፈነገጡ ነገሮች ከነበሩና ይህን በማስረጃ ማስደገፍ ከቻሉ ነገሮች እንዳልነበሩ ሊሆን ይችላሉ። ገና ከአሁኑ ዳግማዊ ቆጠራ የታዘዘላቸው ግዛቶች አሉ።የሚገርመው ትራምፕ ምርጫው ተጭበረበረ ማለት የጀመሩት ግን ምርጫው ገና ከመጀመሩ፣ ድምጽም ከመሰጠቱ በፊት ነው። “እኔ ልሸነፍ የምችለው ምርጫው ከተጭበረበረ ብቻ ነው” ያሉት ገና የባይደን ድል ከመሰማቱ ቀደም ብሎ ነበር።አሁን የአሜሪካ ሚዲያ “ሰውየው ከዋይት ሐውስ የምርም አልወጣ ቢሉስ?” በሚል እየቃዠ ነው። ይህ ነገር በሌላ ጊዜ ቢሆን በአሜሪካ ለፌዝ እንጂ ለቁምነገር የሚነሳ ጉዳይ አልነበረም።የፖለቲካ ኮማኪዎች እንጂ የፖለቲካ ጋዜጠኞች እንዲህ ቧልት የሚመስል ነገር አያነሱም ነበር። የትራምፕ ዘመን ግን ግራ የሚያጋባ ነው። ስለዚህ ይሄ ነገር ገና ቀደም ብሎ ነው አሳሳቢ የሆነው።ለምሳሌ በሰኔ ወር ላይ ጨዋታ አዋቂው ትሬቨር ኖዋ ለባይደን “በምርጫ ቢያሸንፉና ሆኖም ግን ባላንጣዎ ትራምፕ ከቤተ መንግሥት አልወጣ ቢልዎትስ?” በሚል በወቅቱ አስቂኝ የነበረ ጥያቄ ጠይቋቸው ነበር። “ለመሆኑ እጩ ፕሬዝዳንት ባይደን በዚህ ጉዳይ ላይ አስበውበታል??” አላቸው። ትሬቨር ኖዋ ለባይደን። “እውነት ለመናገር አስቤበታለሁ። በዚህ ዓይነት ሁኔታ መከላከያው ጣልቃ ገብቶ ነገሮችን ሊያስተካክል ይችል ይሆናል”ብለውት ነበር። ባይደን ያኔ ሰኔ ላይ ይህንን ሲሉ ዛሬ የሆነው ነገር ይሆናል ብለው አስበዋል ለማለት ይከብዳል። ባይደን ደግመው ደጋግመው እንደሚሉት ድምጽ ሰጪው ሕዝብ ነው እንጂ እጩዎች አይደሉም የምርጫ ውጤት ምን መሆን እንዳለበት የሚወስኑት። ምናልባት ትራምፕ ከቤተ መንግሥት አልወጣም ካሉ የአሜሪካ ሲክሬት ሰርቪስ (የደህንነት አገልግሎት) ነገሩን ይቆጣጠራል። ሲክሬት ሰርቪስ (የደህንነት አገልግሎት) የሚባለው ከወታደራዊ ተቋም ያልሆነ፣ ሁነኛ ሥራው የፕሬዝዳንቱን ደህንነት የሚጠብቅ አካል ነው። ይህ ልዩ የደህንነት አካል ታዲያ ፕሬዝዳንቱ ፕሬዝዳንት ሳሉ ብቻም ሳይሆን ከዋይት ሐውስ ከለቀቁ በኃላም ለፕሬዝዳንቱ ጥበቃ እንዲያደርግ በሕግ ይገደዳል። ለዚህም ነው አሁን ተመራጭ ፕሬዝዳንት ለሆኑት ባይደን ምንም እንኳ ዋይት ሐውስ መግቢያቸው ገና ቢሆንም የሲክሬት ሰርቪስ ጥበቃ አገልግሎትን እየሰጣቸው የሚገኘው። ቢቢሲ ነገሮች እንዳው የከፉ ቢሆኑ ምን ሊከሰት ይችላል በሚል በጉዳዩ ዙርያ አዋቂዎችን አነጋግሮ ነበር። ፕሮፌሰር ዳኮታ ሩደሲል በአገር ደህንነት ፖሊሲ ኦሐዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ ናቸው። “ትራምፕ እምቢ ቢሉ አሜሪካ ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል። የዲሞክራሲ ተምሳሌት በምትባል አገር ይህ ከሆነ መቼስ የሚደንቅ ነው? ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ይህ የመሆኑ ዕድል ግን እጅግ ጠባብ ነው ባይ ናቸው። “ወታደሩ ትራምፕን ሊደግፋቸው አይችልም። ወታደሩ ታማኝነቱ ለሕገ መንግሥቱ ነው። ለፕሬዝዳንቱ አይደለም። ስለዚህ ትራምፕ ብቻቸውን ይቀራሉ” ብለውም ያስባሉ፣ ፕሮፌሰሩ። ከርሳቸው ጋ የሚስማሙት የፒትስበርግ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ኬይሸ በሌይን ናቸው።“ትራምፕ አያረጉትም ባይባልም ይህ ነገር የመሆን እድሉ የጠበበ ነው” ይላሉ ፕሮፌሰር ኬይሸ። “ትራምፕ በቅርብ ጊዜ በተነሱ ተቃውሞዎች ወታደር ማሰማራታቸው አይዘነጋም። አሁንም ከቤተ መንግሥት አልወጣም ብለው ወታደሩን ሊያሰማሩ ቢችሉስ የሚለው በጣም የራቀ ሀሳብ ነው” ፕሮፌሰር ሩድሲል የሚያሳስባቸው ፕሬዝዳንቱ ከቤተ መንግሥት አልወጣም ይላሉ ብለው ሳይሆን የሕዝብ ለሕዘብ ግጭቶች እንዲከሰቱ ፕሬዝዳንቱ ምክንያት እንዳይሆኑ ነው። “በአንድ ጽሑፌ ላይ ገልጨዋለሁ። ትራምፕ ፍጹማዊ ሥልጣናቸው ሳያበቃ በፊት የመንግሥት መዋቅሩን ወይም ደግሞ የፍትሕ ዲፓርትመንቱን የሚያዝ ልዩ መመርያ ሊያወጡ ይችላሉ። ለምሳሌ ምርጫው አሸናፊው እኔ ነኝ ስለዚህ የምትታዘዙት ለኔ ነው የሚል”ይህንን ካደረጉ ወታደሩ ከአስፈጻሚው ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መግባቱ አይቀርም። አሁን ከፕሬዝዳንቱ ሽንፈትን አለመቀበል በላይ አሳሳቢ የሆነው ለደጋፊዎቻቸው፣ አይናቸውን ጨፍነው ትራምፕ ወይም ሞት ለሚሉት ደጋፊዎቻቸው ለአመጽ የሚገፋፋ ጥሪ እንዳያቀርቡ ነው። ዶናልድ ትራምፕ ይህን ካደረጉ የአሜሪካ ከተሞች ታይቶ በማይታወቅ ግጭት ሊታመሱ ይችላሉ። ትራምፕ ደግሞ አያደርጉትም አይባልም።
news-57146300
https://www.bbc.com/amharic/news-57146300
ኮሮናቫይረስ፡ ሁለት የተለያዩ የኮቪድ-19 ክትባቶችን ብንወስድ ምን እንሆናለን?
የዓለም አገራት የክትባት ሽሚያ ላይ ናቸው። የሃብታም አገራት መሪዎች "ከሕዝባችሁ ሕዝቤ ይቀድማል" እያሉ ከሚያስፈልጋቸው ክትባትም በላይ ገዝተው መጋዘን እየቆለፉ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ የሃብታም አገራት መስገብገብን ክፉኛ ተችተዋል፤ በተደጋጋሚ። አሁን በዓለም ቅቡልነት ያገኙት ክትባቶች የሩሲያው ስፑትኒክ፣ የቻይናው ሲኖፋርም፣ የእንግሊዙ አስትራዜኔካ፣ የአሜሪካኖቹ ፋይዘር፣ ሞደርና እንዲሁም ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ይገኙበታል። እነዚህ የኮቪድ-19 ክትባቶች በአውሮፓና በአሜሪካ በስፋት እየተሰጡ የሚገኙ ናቸው። በደቡብ አሜሪካ፣ በአፍሪካና በእሲያም አንዳንዶቹ እየተዳረሱ ናቸው። ክትባቱን ለዜጎቿ በከፍተኛ ትጋት እያቀረበች የምትገኘው አሜሪካ በመጪው ሐምሌ ወር 70 ሚሊዮን ዜጎች ክትባት አግኝተው በነጻነት መንቀሳቀስ ይጀምራሉ ስትል ዕቅድ ይዛ እየሠራች ነው። ባይደን በክትባቱ ዘመቻ ላሳዩት ትጋትም እየተሞካሹ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ታዲያ ሳይንቲስቶች አዲስ ምርምር ይዘዋል። ሰዎች አንድ ክትባት ተከትበው ሲያበቁ በ2ኛው ዙር ሌላ ዓይነት ክትባት ቢወስዱ ይሞታሉ? ይጎዳሉ? ወይስ ይጠቀማሉ? የሚል ነው ምርምሩ። ምርምሩ ገና መቋጫ ባያገኝም ለጊዜው ያገኙት ውጤት አንድ ሰው አንድ ክትባት ወስዶ ሌላ ቢቀላቅል የጎንዮሽ ጉዳቱ መጠነኛ የሚባል ብቻ ነው የሚኾነው። ክትባት የቀላቀሉ ሰዎች ክትትል ተደርጎላቸው ያሳዩት ብቸኛ ምልክት ብርድ ብርድ ማለት፣ ራስ ምታትና የጡንቻ ህመም ብቻ ነው። ይህ መካከለኛ የጎንዮሽ ጉዳት አንድ ዓይነት ክትባት የወሰዱት ሰዎች ከሚያሳዩት ህመም ባስ ያለ ነው። ክትባት የቀላቀሉ ሰዎች ይህ ነው የሚባል ለሕይወት አስጊ የሆነ ምልክት አላሳዩም። "ምርምሩን ስንጀምረው ይህን ውጤት አልጠበቅንም ነበር" ብለዋል የኦክስፎርድ የክትባት ቡድን ባልደረባ ፕሮፌሰር ማቲው ስኔፕ። ይህ ካም-ኮቭ የተባለ ስም የተሰጠው ጥናት የተጀመረው ባለፈው የካቲት ወር ነበር። ዓላማ ያደረገውም በአንደኛና በሁለተኛ ምዕራፍ አንድ ሰው ሁለት የተለያዩ የክትባት ጠብታዎችን ቢቀላቅል የመከላከል አቅሙ ይበልጥ ያድጋል ወይስ በተቃራኒው ይሆናል? የሚል ነበር። መላምቱ የነበረው የክትባት ጠብታ ቀላቅለው የወሰዱ ሰዎች የመከላከል አቅማቸው ይጎለብት ይሆናል የሚል ነበር። አንዳንድ አገሮች አንዱን የክትባት ዓይነት ቢጨርሱ በምዕራፍ ሁለት ጠብታ ለሚወስዱ ሰዎች ሌላኛውን ዓይነት ክትባት ቢሰጧቸው ምን ሊፈጠር ይችላል የሚል ነበር። ጥናቱ የተመራው በኦክስፎርድ ዩነቨርስቲ ነበር። ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ 830 በጎ ፈቃደኞች በዚህ ጥናት ውስጥ ተሳትፈዋል። በመጪው ሰኔ የዚህ ምርምር የተሟላ ውጤት ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። አሁን የጥናቱ ቅድመ ውጤት የታተመው በዝነኛው 'ላንሴት' የጤና አካዳሚ መጽሔት ላይ ነው። የካናዳ ግዛቶች የሆኑት ኦንታሪዮና ኩቤክ ይህን የመቀላቀል ሙከራ ተግባራዊ ለማድረግ እያሰቡበት እንደሆነ ተነግሯል። ሙከራው ከተደረገባቸው 10 ሰዎች በአንዱ አነስተኛ የሚባል የጎንዮሽ ጉዳት ያሳያል። እነዚህ 10 ሰዎች በአራት ሳምንት ልዩነት አስትራዜኒካ ክትባትን ብቻ የወሰዱ ናቸው። ይህም ማለት ሌላ የክትባት ዓይነት አልቀላቀሉም። ይህ አነስተኛ የጎንዮሽ ጉዳት የተባለውም ትኩሳታቸው ከፍ በማለቱ ነው። አስትራዜኒካንና ፋይዘርን በ4 ሳምንት ልዩነት ቀላቅለው የወሰዱ (ማለትም መጀመርያ አስትራዜኒካን ከ4 ሳምንታት በኋላ ደግሞ ፋይዘርን የወሰዱ) የሚያሳዩት የጎንዮሽ ምልክቶች በ34 ከመቶ ከፍ ብሎ ታይቷል። ከፍ ካሉ ምልክቶች መካከልም ድካም፣ የጡንቻ ህመም፣ ራስ ምታት ይገኙበታል። "ምርምሩ ያመለከተው ነገር ቢኖር ክትባቱን ቀላቅለን ለነርሶች ብንሰጣቸው በነገታው ወደ ሥራ የሚመጡት ነርሶች ቁጥር እንደሚቀንስ ነው" ብለዋል ፕሮፌሰሩ። ይህም አባባላቸው ክትባቶችን መቀላቀል ለጊዜው የጎንዮሽ ጉዳቱን (ምንም እንኳ ለጤና አስጊ የሚባል ባይሆንም) እንደሚጨምር ነው። ለጊዜው ሙከራው የተደረገው አስትራዜኒካን ከፋይዘር ጋር በመቀላቀል ነው። በመጋቢት ወር የበጎ ፍቃደኞችን ቁጥር ወደ 1ሺህ 50 አድጎ ሌላ ሙከራ ተደርጓል። እነዚህ በጎ ፈቃደኞች ደግሞ እንዲወስዱ የተደረገው የሞደርና እና የኖቫቫክስት ክትባቶችን ነው። የዚህ ውጤት ገና ለኅትመት አልበቃም።
news-54857571
https://www.bbc.com/amharic/news-54857571
የአሜሪካ ምርጫ፡ ባይደን አሸንፈዋል፤ ቀጥሎ ምን ይሆናል?
ዲሞክራቱ ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት በመሆን ተመርጠዋል።
132 ክፍሎች እና 35 መጸዳጃ ቤት ወዳለው ዋይት ሃውስ የሚያደርጉት ጉዞም ተረጋግጧል። በቀጣይ ምን ይሆናል? ትራምፕ ስልጣናቸውን አሳልፈው መቼ ይሰጣሉ? ባይደን መንበረ ስልጣናቸውን የሚቀበሉት መቼ ነው? በአሜሪካ ሕገ-መንግሥት መሠረት አዲሱ የፈረንጅ ዓመት በገባ በ20ኛ ቀኑ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝነዳንት ስልጣኑን ይረከባል። ይህም በዋሽንግተን ዲሲ በሚካሄድ ስነ-ስርዓት ይከናወናል። ፕሬዝደንቱ እና ምክትል ፕሬዝደንቷ ቃለ መሃል ይፈጽማሉ። የምርጫ ውጤቱን ይፋ ከተደረገ በኋላ ተመራጩ ፕሬዝደንት ስልጣን እስከሚረከቡት ጊዜ ድረስ የሽግግር ቡድን ያቋቁማሉ። ይህም ፕሬዝደንቱ ስልጣናቸውን በይፋ ከተረከቡ በኋላ ስራቸውን በፍጥነት እንዲጀምሩ ነገሮችን ቀላል ያደርጋል። ከሰሞኑ በመገናኛ ብዙሃን የምንሰማቸው ቃላት ባይደን ምርጫውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ በመገናኛ ብዙሃን በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው ቃላት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። 'ተመራጩ ፕሬዝዳት' (President-elect): ይህ ማለት እጩዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫውን አሸንፈዋል። ስልጣን ግን አልተረከቡም ማለት ነው። ጄነዋሪ 20 ላይ 'በዓለ ሲመት' ተብሎ በሚጠራው ስነ-ስርዓት ላይ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ ፕሬዝደንት ተብለው ይጠራሉ። ካቢኔ: ባይደን በቅርቡ የካቢኔ አባላቶቻቸውን ያሳውቃሉ። ይህም ከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣናት እና ኤጀንሲ መሪዎችን ያካተተ ይሆናል። ሴልቲክ፡ ተመራጩ ፕሬዝደንት በአሜሪካው ሴክሬት ሰርቪስ (የደህንነት ጥበቃ የሚሰጠው አካል) ጥበቃ ይደረግላቸዋል። ጥበቃ ለሚያደረገው ቡድን ደግሞ ስያሜ ይሰጣል። ስያሜውን የሚሰጠው ተመራጩ ፕሬዝደንት ነው። ባይደን ለሴክሬት ሰርቪስ ቡድኑ "ሴልቲክ" የሚል ስያሜ ሰጥተዋል። ካማላ ሃሪስ በበኩኣለቸው 'ፓዮኒር' የሚል ስያሜን መርጠዋል። ትራምፕ በቀጣይ ምን እንዲያደርጉ ይጠበቃሉ? በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ተሸናፊው አሸናፊው ጋር ደውሎ እንኳን ደስ ያለህ/ያለሽ ማለቱ የተለመደ ነው። ትራምፕ ይህን ማደረግ ግዴታቸው አይደለም። ይሁን እንጂ ትራምፕ የተመራጩ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቡድን ወደ ስልጣን ለመምጣት በሚያደርገው ዝግጅት የሎጂስቲክ አቅርቦት እንዲደረግላቸው የመፍቀድ ግዴታ አለባቸው።
news-42029612
https://www.bbc.com/amharic/news-42029612
የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታ የማን ነው?
'ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገረሰስ በህይወት የመኖር፤ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አለው' ይህ የሰፈረው በኢፌድሪ ህገ-መንግሥት አንቀፅ 14 ላይ ነው።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል በተነሱ ተቃውሞዎች የብዙዎች ሕይወት ጠፍቷል፤ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ክልሎች መካከል ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችም ተነስተው በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀል፤ ንብረት መውደም እንዲሁም ሕይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል። ከነዚህም ውስጥ ከደቡብ ክልልና ከቤኒንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ብሔር ተወላጆች፤ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች እንዲሁም ከጎንደር የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆችን መጥቀስ ይቻላል። በተለያዩ ክልሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በተነሱ መሰል ግጭቶች የመማር ማስተማር ሂደት እስከመስተጓጎል ደርሷል። በሃገሪቱ ውስጥ በሚፈጠሩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች የተነሳ ብዙዎች ስጋታቸውን ለቢቢሲ ሲገልፁ ቆይተዋል። የበርካቶች ቅሬታ የመንግሥት ተቋማት የዜጎችን መብት በማስጠበቅ ፋንታ "እየጣሱ" መሆኑ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በፌስቡክ ገፆቻችን ከሰበሰብናቸው አስተያየቶች መካከል "ሕገ መንግሥቱ በግልፅ ተጥሷል፤ ሃገሪቱን እየመራ ያለው ኢህአዴግ ደህንነት እንዳይሰማን እያደረገው ነው ያለው" የሚሉ ይገኙበታል። በሌላ በኩል በክልሎች እየታየ ያለው የፀጥታ ስጋት የፌደራል መንግሥት ችግሩን ለክልሎች ብቻ መተዉና ኃላፊነቱ በአግባቡ ያለመወጣቱ ውጤት ነው የሚልም ቅሬታና ትችትም ይደመጣል። "የፀጥታ ጉዳይ ለክልሎች የሚተው ነገር አይደለም። የፌደራል መንግሥት በክልሎች ያለውን ስርዓት አልበኝነት መቆጣጠር አለበት" በማለት። ህገ-መንግሥቱና የዜጎች መብት? በኤፌድሪ ህገመንግስቱ አንቀፅ 32 (1) "ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነፃነት አለው" ይላል። አንቀፅ40 (1) ደግሞ "ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ውስጥ በማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራት፤ ለመተዳደሪያው የመረጠውን ስራ የመስራት መብት አለው" ይላል። በተጨማሪም በህገ መንግሥቱ አንቀፅ 30 ላይ ዜጎች ከሀገሪቱ የመንግሥት አካላት ማግኘት ስላለባቸው መሰረታዊ መብቶች ይዘረዝራል። የመኖር መብት፣ የአካል ደህንነት መብቶች፣ የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶች እንዲሁም ንብረት የማፍራትና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ይጠቀሳሉ። በአንቀፅ 13 ንኡስ አንቀፅ አንድ ላይም በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌደራል መንግሥትና የክልል ህግ አውጪ፣ ህግ አስፈፃሚና የህግ ተርጓሚ አካላት እነዚህን መብቶች እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ ኃላፊነትና ግዴታ ተጥሎባቸዋል። እነዚህ መብትና ግዴታዎች በክልል ሕገ-መንግሥቶች ላይም በድጋሜ ተረጋግጠዋል፡፡ በሀገር ውስጥ ለመዘዋወር ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻውን በቂ እንደሆነ ህገ-መንግሥቱ ያረጋግጣል። እነዚህ መብቶች በሌሎች እንዳይጣሱ የማስከበር ግዴታ ያለበት መንግሥት መሆኑን የህግ ሙሁርና በፌዴራሊዝም ስርዓት ምርምር ያደረጉት አቶ ውብሸት ሙላት ለቢቢሲ ይናገራሉ። "የዜጎች የመንቀሳቀስ መብት ሲጣስ ወይንም እክል ሲፈጠር፣ በተጨማሪም ከተሰማሩበት ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት የሆኑ ሰዎችን ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ በፍርድ ቤት ማስወሰን ይቻላል" ይላሉ። "ዜጎች የፍትሕ ተቋማትን እንዲጠቀሙ ድጋፍ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ያለው የፍትሕ ተቋማት አወቃቀር ለዜጎች መተማመኛ ይሆናል ማለት የሚቻል አይመስልም፡፡" ይላሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶችና ድንጋጌዎች መርሆች ጋር በተጣጣመ መንገድ እንደሚተረጎሙም ይናገራሉ። የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ በህገ-መንግስቱ መሰረት መንግስት የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች የማክበርን እና የማስከበር ግዴታ ተጥሎበታል። አቶ ውብሸት እንደሚሉት በተለይ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች በሚነሱበት ወቅት የግለሰቦችን ሰብዓዊ መብት የማስከበር ግዴታ የሁለቱም መንግስት መዋቅሮች ግዴታ ነው። ''ነገር ግን ህገ-መንግሥቱን በማስፈፀም ደረጃ የተቋማት ችግር አለ። ምክንያቱም አንዳንድ ግጭቶች የብሔር መልክ ሲኖራቸው የግለሰቦች መብትና ደህንነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል'' ይላሉ። "በአንድ ክልል ውስጥ የሚኖር አንድ ብሔረሰብ በክልሉ መንግስትና ተቋማዊ አስተዳደር በደል ተፈፅሞብኛል ቢል አቤቱታውን የሚያቀርበው ለማን ነው?" በማለትም ይጠይቃሉ። እንደ ምሳሌም ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የተፈናቀሉ አማሮች፤ ጎንደር ላይ የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች፤ በሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች በደል ተፈፅሞብናል ብለው ክሳቸውን የሚያቀርቡት የት እንደሆነም መታወቅ አለበት ሲሉ ይሞግታሉ። "የአንድ ክልል መንግሥት ወይም የክልል ተቋማዊ አስተዳደር ክስ ቀርቦበት የዚያው ክልል መንግሥት አጣሪ እና ፈራጅ ከሆነ የሕገ-መንግሥት ክፍተት እንዳለው የሚያሳይ ነው" በማለት አቶ ውብሸት ይናገራሉ። በእኔ እምነት ይህ ክፍተት ሊፈታ ይችል የነበረው በፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው። "ሆኖም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የብሔር አወቃቀር ገለልተኛ አቋም እንዲይዝ አያስችለውም። ምክንያቱም ከተለያየ ብሔር የተውጣጡ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ አንድ ብሔር ተከሶ በሚመጣበት ወቅት የሚከሰሰው ብሔር ተወካዮች ለዳኝነት መቀመጣቸው ገለልተኛ ውሳኔ እንዳይሰጡ እክል ይፈጥራል" ብለዋል። መፍትሄ? "ችግር ፈጣሪዎቹ ባለሥልጣናት ከሆኑ፣ ዞሮ ዞሮ በመንግሥት ተቋም ውስጥ ስላሉ መንግሥት የዜጎችን መብት ማክበር ግዴታው ነው፡፡ ሌሎች ሰዎች የእነዚህን ዜጎች መብት ሲጥሱ የማስከበር አሁንም ግዴታ አለበት፡፡" የሚሉት ኣቶ ውብሸት፥ "እንደነዚህ ዓይነቶቹን የመብት ጥሰቶች የፖለቲካ አንድምታቸው ላይ ከማተኮር ይልቅ ግለሰባዊ ማድረግ፣ መፍትሔያቸውንም በፍርድ ቤት በኩል እንዲሰጥ ማድረግ መቻል አለብን፡፡" ይላሉ። "መንግሥትም ይሄንን አካሄድ ማበረታታት ሲገባው ፖለቲካዊ መፍትሔ በመስጠት ተጠምዶ ኖሯል'' የሚሉት አቶ ውብሸት መፍትሄው ግን የፍትሕ ተቋማትን ገለልተኛ እንዲሆኑ በማደረግ ሕጋዊነትን እና የሕግ የበላይነትን ማስፈን እንደሆነ ይናገራሉ። በተለይ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች በሚነሱበት ወቅት የፌዴራል መንግሥት ልዩ ትኩረት በመሥጠት በበላይነት ሊቆጣጠርና ሊያያቸው እንደሚገባ አቶ ውብሸት ይናገራሉ። "በተቻለ መጠን ከሳሾቹ ከአጣሪው አካል እንዲሁም ዳኝነቱን ከሚሰጡት አካላት በብሔር ሊለያዩ ይገባል። " የሚሉት አቶ ውብሸት ከዚህ በተጨማሪም "የየትኛውም ብሔር አካል ሆነ ግለሰብ ግለሰባዊ መብቱ መጠበቅ አለበት" ይላሉ። ህገ መንግስት ጥናት ያደረገው የህግ ባለሞያው አቶ ኤፍሬም ታምራት ግን ከዚህ የተለየ አስተያት ኣለው። በፌዴሬሽን ምክር ቤት ፍትሃዊ የሆነ ውክልና እንዳለና የህገ መንግስት አተረጓጎም ስህተት ሲኖር ብቻ ወደ ምክር ቤቱ እንደሚኬድ ይናገራል። "ለአብነትም ከዓመታት በፊት፥ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተከስቶ የነበረው የብሄር ግጭት ምክር ቤቱ ፍትሃዊ የሆነ ውሳኔ መስጠቱ አመላካች ነው" ይላል። እንደ አቶ ኤፍሬም ገለፃ ከሆነ፥ ማናቸውም የግለሰብም ይሁን የቡድን የመብት ጥሰቶች ከክልል እስከ ፌዴራል በተዘረጉ የህግ መዋቅሮች በወንጀል ህግ መዳኘት ይኖርባቸዋል።
news-41989509
https://www.bbc.com/amharic/news-41989509
ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በመበደል ከዓለም ቀዳሚ ሃገራት አንዷ ነች ተባለ
ኢትዮጵያ ከቻይና በመቀጠል ከሶሪያ እኩል የኢንተርኔት እና የሞባይል ተጠቃሚዎች ላይ ገደቦችን በመጣል በዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች ሲል ፍሪደም ሃውስ በሪፖርቱ ገልጿል።
ኢትዮቴሌኮም በበኩሉ ''የኢንተርኔትም ሆነ የሞባይል አገልግሎት በኢትዮጵያ ተዘግቶ አያውቅም'' ይላል። የቻይና እና የሩሲያ መንግሥታት የረቀቁ መንገዶችን በመጠቀም የኢንተርኔት ላይ ውይይቶችን እና ተጠቃሚዎችን በመግታት የጀመሩት ተግባር አሁን በመላው ዓለም ተንሰራፍቷል ሲል ፍሪደም ሃውስ በሪፖርቱ ይገልጻል። ኢትዮጵያ በፍሪደም ኦፍ ዘ ኔት (Freedom of the Net) ሪፖርት ''0=የኢንተርኔት ነጻነት ያለበት እንዲሁም 100=የኢንተርኔት ነጻነት የሌለበት'' በሚል መስፈርት ተመዝና 86 ነጥቦችን በማምጣት ከሶሪያ እኩል ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ከቻይና ቀጥላ ተቀምጣለች። ሪፖርቱም ኢስቶኒያ እና አይስላንድ 6 ነጥብ በመያዝ በኢንተርኔት ነፃነት ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል። ሪፖርቱ የተከናወነው በ65 ሃገራት ሲሆን ሰሜን ኮሪያ እና ኤርትራ በጥናቱ ውስጥ አልተካተቱም። ''የኢንተርኔትም ሆነ የሞባይል አገልግሎት በኢትዮጵያ ተዘግቶ አያውቅም። ከዚህ በፊት የ ኦቨር ዘ ቶፕ (Over The Top) የሚባለውን ፌስቡክ እና የመሳሰሉ የማሕበራዊ ሚዲያዎች መጠቀም የሚያስችለውን አገልግሎት ብሔራዊ ፈተና ሲኖር ለተወሰነ ጊዜ እናግዳለን እንጂ በሃገራችን ኢንተርኔት ተዘግቶ አያውቅም'' በማለት የኢትዮ-ቴሌኮም የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አብዱራሂም ጨምረው እንደተናገሩት ፍሪደም ሃውስ የተሰኘው ድርጅት ከራሱ ፍላጎት ተነስቶ ያወጣው ሪፖርት ነው እንጂ እውነታውን የሚያሳይ አይደለም ብለዋል። ''ዓለም አቀፉ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ህብረት (ITU) እና አይሲቲ አፍሪካ (ICT Africa) የመሳሰሉ ተቋማት ናቸው የኛን መሰረተ ልማት የሚያውቁት እና ሊመዝኑን የሚችሉት እንጂ ይህ ሪፖርት ተዓማኒነት የለውም'' ሲሉ ተናግረዋል። ፍሪደም ሃውስ ዓመታዊ ሪፖርቱን ''ማህበራዊ ሚዲያን በማዛባት ዲሞክራሲ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር'' በሚል ርዕስ ያወጣ ሲሆን በዋናነት ኢትዮጵያን በሚመለከት ካነሳቸው ነጥቦች መካከል፡ ለአስር ወራት ያህል በስራ ላይ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማኅበራዊ ሚዲያ ተቃውሞ መደገፍን ጨምሮ ሌሎችንም መሰረታዊ የዜጎች መብቶች አፍኗል የሚለው ሪፖርቱ ራስን ሳንሱር የማድረግ እና ኃሳብን ከመግለፅ የመቆጠብ አዝማሚያዎች በአዋጁ ጊዜ ተጠናክረው ታይተዋል ሲል ይገልፃል፤ በርካቶች ኃሳባቸውን በኢንተርኔት መድረኮች ላይ በመግለፃቸው ታስረዋል፤ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ተከስሰው ተፈርዶባቸዋል በማለትም መንግስትን ይወነጅላል። ሪፖርቱ ጨምሮም በ2008 ዓ.ም የወጣው የኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ የመንግስትን በዜጎች ግንኙነት ጣልቃ የመግባት እና መረጃ የመሰብሰብ ስልጣን ማስፋቱን የኢንተርኔት ነፃነትን ከሚያዳክሙ ምክንያቶች አንዱ ነው ይላል። በተጨማሪ በሃገሪቱ ውስጥ ደካማ የቴሌኮም መሰረተልማት መኖሩ፣ የቴሌኮም አገልግሎት በመንግሥት ቁጥጥር ስር ብቻ መሆኑ እና የቴሌኮም ፖሊሲዎች ተጠቃሚዎችን የሚገደቡ ሌሎች ምክንያቶች ናቸው ሲል በዝርዝር ሪፖርቱ ያስቀምጣል። በኢትዮጵያ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት እና የመረጃ ነጻነት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራ ለነበረው አርቲክል 19 (ARTICLE 19) ተቀጣሪ የነበረው እና በኢትዮጵያ መንግሥት ከሃገር እንዲወጣ የተደረገው ፓትሪክ ሙታሂ በሪፖርቱ ላይ ይህን አስተያየት ሰጥቷል ''በኔ ግምገማ የፍሪደም ሃውስ ሪፖርት በኢትዮጵያ ያለውን ትክክለኛ ገጽታ ያሳያል።'' "ሰዎች ኢንተርኔትን እና የሞባይል ግንኙነትን ለመደራጀት፣ ሃሳባቸውን ለመግለጽ እና ለመቀስቀስ ይጠቀማሉ ይህም የኢትዮጵያን መንግሥት ስለሚያሳስበው የማይፈልጋቸውን ድረ-ገጾች፣ የኢንተርኔት እና የሞባይል አገልግሎቶችን ማቋረጥ የተለመደ ነገር አድርጎታል" በማለት ፓትሪክ ያብራራል። የሰሞኑ የኢትዮ-ቴሌኮም ምዝገባ ነፃነትን ይገድብ ይሆን? ኢትዮ-ቴሌኮም፡ አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ? ፍሪደም ሃውስ እአአ1941 በዩናይትድ ስቴትስ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በሰብዓዊ መብቶች፣ በዲሞክራሲ እና በፖለቲካ ነጻነቶች ዙሪያ የመብት ስራዎችን እና ጥናቶችን ያከናውናል። እ.ኤ.አ በ2011 ከ1 በመቶ ትንሽ ብቻ ከፍ ብሎ ይገኝ የነበረው የኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስርገት መጠን በ2016 ወደ 15 በመቶ ከፍ ቢልም እንዲሁም በተመሳሳዩ ጊዜ የተንቀሳቃሽ ስልኮች ስርጭት ከ16 በመቶ ወደ 51 በመቶ ቢያድግም አገሪቷ አሁንም ከዓለማችን እጅግ በአነስተኛ ደረጃ በኢንተርኔት የተያያዙ አገራት መካከል መገኘቷ አልቀረም። ሪፖርቱ የተለያዩ ጥናቶችን በማጣቀስ ኢንተርኔት በጣም ውድ ከሆኑባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ያወሳል። አንድ ጥናት እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያዊያን በተንቀሳቃሽ ስልክም ሆነ በኮምፒውተር ላይ ኢንተርኔትን ለማግኘት በአማካይ በወር 85 የአሜሪካ ዶላር ያወጣሉ፤ የተሻለ የኢንተርኔት ስርጭት አለባቸው በሚባሉት ኬንያና ኡጋንዳ ግን ይህ ወጭ በአማካይ ከ30 የአሜሪካ ዶላር የማይበልጥ ነው።
news-50724414
https://www.bbc.com/amharic/news-50724414
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኖቤል ሽልማትን በመቃወም ኤርትራውያን በኦስሎ ሰልፍ ወጡ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን የሰላም የኖቤል ሽልማት በመቃመወም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ሰልፈኞች በኖርዌይ መዲና ኦስሎ መፈክራቸውን አንግበው ወጥተዋል።
በትናንትናው ዕለት በኖርዌይ የሚኖሩ ኤርትራውያን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሽልማት ለሰጠው የኖቤል ኮሚቴ "የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰላም በሚገባ አልተረጋገጠም፤ የኖቤል ሽልማት ሊሰጣቸው አይገባም" በሚልም ተቃውሟቸውን ገልፀዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ከተለያዩ የኖርዌይና የስዊድን ከተሞች የመጡ 250 የሚጠጉ ኤርትራውያን "በሰላም ስም ሳይታሰብበት ሽልማት ሊሰጥ አይገባም፤ በተግባር እንጂ የወሬ ሰላም አንቀበልም" የሚሉ የታቃውሞ ድምፆችን በማሰማት ወደ መንግሥታዊ ተቋማትም አምርተዋል። የኤርትራ መንግሥትን በተመለከተ የተለያዩ ስር ነቀል ለውጦች ሊመጡ ይገባል በሚል የሚንቀሳቀሰው በኖርዌይና አካባቢው የሚገኝ የ 'ይበቃል' (ይአክል) ኮሚቴ ለሦስት የመንግሥት ተቋማት ደብዳቤ እንደፃፈ የኮሚቴው ሊቀ መንበር ቲቲ ኃይለ ለቢቢሲ ገልፃለች። ቲቲ እንደምትለው፤ ለኖርዌይ መንግሥት በአካል፣ ለኖቤል ኮሚቴ በአድራሻቸው እንዲሁም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ደግሞ በኢሜይል ያላቸውን ተቃውሞ አድርሰዋል። የይበቃል ኮሚቴ ፀሐፊ ይብራህ ዘውደ፤ ምንም እንኳ ኤርትራና ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ቢፈራረሙም "መሬት ላይ ያለውን እውነታ ስናይ ወደ ተግባር የተሸጋገረ ነገር እንደሌለ" ይናገራል። የኤርትራ ሕዝብ የጠበቀውና የተመኘው ለውጥ እንዳልመጣ በመግለፅ፤ በሁለቱም አገራት የሰላም ስምምነት አማካኝነት የተሰጠው የኖቤል ሽልማት ፍትሃዊ እንዳልሆነም አክሎ ገልጿል። • የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ክፍፍልና ጠብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ለሁለት አስርት አመታት ተቋርጦ የነበረው የስልክ፣ የበረራ መስመሮች ተጀምረዋል። ለአጭር ጊዜ ቢሆንም የተዘጉ ድንበሮች ተከፍተው የተለያዩና የተነፋፈቁ ሕዝቦች መገናኘታቸውን ብዙዎች በበጎነት የሚያዩት ተግባር ነው። ይሁን እንጂ እነዚህ መልካም ጅምሮች እንዳሉ ሆነው፤ በሁለቱ አገራት መካከል በተጨባጭ የመጣ ሰላም አለመኖሩን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊገነዘብ እንደሚገባው ተቃዋሚዎቹ ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንም እንኳን ጅምሮቻቸው መበረታት ቢገባቸውም፤ ሽልማቱ የሁለቱን አገራት መሬት ላይ ያለ እውነታ የሚያንፀባርቅ እንዳልሆነ ከተቃዋሚዎቹ መካከል ለይላ ካሊድ ታስረዳለች። • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . • ፊንላንድ በዓለም በእድሜ ትንሿን ጠቅላይ ሚኒስትር መረጠች "በሌላ በኩል የኤርትራ ሁኔታ እየባሰ እንጂ እየተሻሻለ የመጣ ነገር የለም፤ የተከፈቱ ድንበሮች ተዘግተዋል፤ ሕገ መንግሥቱ አሁንም ቢሆን ሥራ ላይ አልዋለም፤ ለተወሰነ ጊዜ መሆን የነበረበት ብሔራዊ አገልግሎት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ለማስገንዘብ ጭምር" የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ትናገራለች። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ኖርዌይን ጨምሮ የተለያዩ የአውሮፓ አገራት ለኤርትራ እያደረጉት ካለው ድጋፍ ባሻገር በአገሪቷ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በደል እንዲወገድ ከሕዝቡ ጎን ሊቆሙ እንደሚገባ ለይላ አበክራ ትናገራለች። "የኤርትራ ሕዝብ ሰላምና ፍቅርን ይፈልጋል ይሁን እንጂ የናፈቀውንና ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለበትን ሰላም ሊያገኝ አልቻለም" ያለው ይብራህ፤ "በተግባር የሚጨበጥ ሰላም እንጂ የወሬ ሰላም አንቀበልም" በማለት መረር ባለ ቃል መልእክቱን አስተላልፏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከጋዜጠኞች ጋር ሊያደርጉት የነበረው ቃለ መጠይቅ አልሳተፍም ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኖ ሰንብቷል።
news-46687573
https://www.bbc.com/amharic/news-46687573
ኦዲፒ፡ ኦነግ በተለያዩ ዞኖች እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ለሰላማዊ ትግል ወደ ሃገር ውስጥ ከገባ በኋላም በተለያዩ የክልሉ ዞኖች ውስጥ እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው ብለዋል የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊው አቶ አዲሱ አረጋ።
አቶ አዲሱ ዛሬ ጋዜጠኞች ሰብሰበው በሰጡት መግለጫ፤ በኦነግ እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል አሥመራ ላይ የተደረሰው ስምምነት ሆን ተብሎ ዝርዝሩ ከህዝብ ተደብቋል የተባለው ከእውነት የራቀ ነው ያሉ ሲሆን፤ የስምምነቱ ተፈጻሚነትም እንደፈለጉት በፍጥነት እየሄደ እንዳልሆነ አስረድተዋል። ከጥቂት ወራት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የሚመራ ልዑክ ወደ ኤርትራ ተጉዞ ከኦነግ ጋር ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል። በርካቶች መንግሥት ከኦነግ ጋር አሥመራ ላይ የደረሰውን ዝርዝር ስምምነት ለህዝብ ይፋ አለደረገም በማለት መንግሥትን ይወቅሳሉ። የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳም በቅርቡ ለሃገር ቤት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፤ በሁለቱ ወገን የተደረሰው ስምምነት ለህዝብ ግልጽ እንዳይሆን እያደረገ ያለው መንግሥት ነው ብለዋል። • የኦነግ እና የመንግሥት እሰጣገባ በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን እና ከኤርትራ የገቡ የኦነግ ሰራዊቶችን በማሰልጠን እንደየ አስፈላጊነቱ የጸጥታ ኃይሉን እንዲቀላቀሉ ወይም በሌሎች መስኮች እንዲሰማሩ ለማድረግ ከኦነግ ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን ያስታወሱት አቶ አዲሱ፤ በሃገር ውስጥ የሚገኙ የኦነግ ወታደሮችን ከኤርትራ ከተመለሱት ጋር በአንድ ላይ ሰልጠና ለማስጀመር ብንሞክርም በሃገር ውስጥ ያሉት ሳይገኙ ቀርተዋል ይላሉ። በሃገር ውስጥ የሚገኙ የኦነግ ወታደሮች ስልጠና እንዲጀምሩ ለ15 ቀናት ቢጠበቁም ሳይገኙ በመቅረታቸው ከኤርትራ ለመጡት ብቻ ሰልጠና መስጠት መጀመሩን አስታውቀዋል። በመንግሥት እና በኦነግ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ለማስፈጻም ከሁለቱም ወገን ተወካዮች በተዋቀረው ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በሚደረጉ ውይይቶች ከስምምነት ይደረሳል፤ ተፈጻሚ ግን አይሆኑም ይላሉ አቶ አዲሱ። • በምዕራብ ኦሮሚያ በታጠቁ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱ ተገለፀ የኦነግ አመራር በጠቅላለው ሰላማዊ ትግልን እንደ አማራጭ አድርጎ መቀበሉ አጠራጥሮናል የሚሉት አቶ አዲሱ፤ የኦነግ አመራር እና በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ የጦር አመራሮች የሚሰጡት መግለጫዎች የተለያዩ ናቸው ይላሉ። ''ኦነግ በጉጂ፣ ቄለም፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ኢሉ አባቦራ ዞኖች ውስጥ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው ይህም እጅጉን ያሳስበናል'' ብለዋል አቶ አዲሱ። አቶ አዲሱ ጨምረውም ሕገ-ወጥነት እየተስፋፋ ነው፤ አመራሮቻችንም እየተገደሉ ነው ብለዋል። ትናንት በነቀምቴ ከተማ ውስጥ የጉቶ ጊዳ ወረዳ ምክትል አስተዳደሪ የነበሩት ግለሰብ መገደላቸውን ያስታወቁ ሲሆን፤ የመንግሥት ባለስልጣናትን መግደል፣ የአስተዳደር ስርዓቱን ማፈራረስ፣ ዘረፋ እና ሚሊሻዎችን ጦር ማስፈታት የመሳሰሉ ወንጀሎች በኦነግ ሥራዊቶች እየተፈጸሙ ነው ብለዋል። • ኦነግ ከመንግሥት ጋር ያደረኩት ስምምነት አልተከበረም አለ በሌላ በኩል ከቀናት በፊት የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ድርጅታቸው ከመንግሥት ጋር ከስምምነት ላይ የደረሰባቸው ጉዳዮች በመንግሥት እየተጣሱ ነው ማለታቸው ይታወሳል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ መከበር፣ የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አስከባሪ እና ደህንነት አካል ገለልተኛ እንዲሆን ማድረግ፣ የኦነግ ሠራዊት ወደ መንግሥት ኃይል እንዲካተት ማድረግ ከኦነግ ሠራዊት አንፃር ከመንግሥት ጋር የተስማሙባቸው እንደሆኑ አመልክተው እነዚህ ስምምነቶች ግን በመንግሥት እየተጣሱ ነው ብለው ነበር።
news-55205082
https://www.bbc.com/amharic/news-55205082
ትራምፕ የአንድ ግዛት አስተዳዳሪ የምርጫ ውጤት እንዲቀይሩ እየወተወቱ ነው
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሪፐብሊካኑ የጆርጂያ ግዛት አስተዳዳሪ የጆ ባይደንን ድል እንዲቀለብሱላቸው ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ።
ፕሬዝደንቱ አከታትለው የትዊተር ግድግዳቸው ላይ በለጠፏቸው መልዕክቶች የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ብራያን ኬምፕ ውጤቱን እንዲቀለብሱ ወትውተዋል። ትራምፕ ጆርጂያ ተገኝተው በቅርቡ ለሚካሄደው የላይኛው ምክር ቤት እንደራሴዎች ምርጫ ቅስቀሳ አካሂደዋል። የአሜሪካ ምርጫ ውጤት ይፋ ከሆነ ቢቆይም ትራምፕ ግን ውጤቱን አምነው አልተቀበሉም። አልፎም ምርጫው ተጭበርብሯል የሚል ማስረጃ የሌለው ዜና እያወጁ ይገኛሉ። ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ውጤቱን ለመቀልበስ ክስ ቢመሰርቱም አልተሳካላቸውም። ጆርጂያ በዘንድሮው ምርጫ እጅግ ወሳኝ ሚና ከተጫወቱ ግዛቶች መካከል ናት። ጆ ባይደን በጠባብ ውጤት ነው ትራምፕን በጆርጂያ የረቱት። በፈረንጆቹ ከ1992 በኋላ በዚህች ግዛት ያሸነፉ የመጀመሪያው የዴሞክራት ፓርቲ ዕጩም ሆነዋል። በቅርቡ ደግሞ የላይኛው ምክር ቤት እንደራሴዎች ምርጫ ይከናወንባታል። በዚህች ግዛት የዴሞክራት ፓርቲ ዕጩዎች ምርጫውን ማሸነፍ ከቻሉ ሪፐብሊካኖች በምክር ቤቱ ያላቸውን የበላይነት ያጣሉ። እንደ ዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ከሆነ ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት ሃገረ ገዠ ኬምፕ ጋር ደውለው የምርጫው ውጤት ድጋሚ እንዲጣራ ጠይቅ ሲሉ ወትውተዋል። ይህን የማድረግ ሥልጣን ያላቸው ሃገረ ግዥ ኬምፕ ግን ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ይላል የጋዜጣው ዘገባ። ትራምፕ በዘንድሮው ምርጫ ሰዎች በፖስታ መምረጣቸው ምርጫው እንዲጭበረበር አስተዋፅዖ አድርጓል ይላሉ። ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ምንም ዓይነት ማስረጃ አልተገኘም። ትራምፕ በጆርጂያ ሁለት ሰዓት የፈጀ ንግግር አድርገዋል። ምንም እንኳ ግዛቲቱ የሄዱት ለምክር ቤት አባላት ዕጩዎች ለመቀስቀስ ቢሆንም ምርጫው ባይጭረበረበር እሳቸው በቀላሉ እንደሚረቱ ያልተረጋገጠ ወሬ ሲነዙ አምሽተዋል። ደጋፊዎቻቸውም የሳቸውን ወቀሳ ተከትሎ 'ማጭበርበሩ ይብቃ' የሚል ጩኸት ሲያሰሙ አምሽተዋል። ዴሞክራቱ ጆ ባይደን የአሜሪካን ምርጫ ማሸነፋቸው ታውጇል። በቀጣይ ጥር ምክትላቸው ከማላ ሃሪስን ይዘው ወደ ዋይት ኃውስ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
48591302
https://www.bbc.com/amharic/48591302
የበርካታ ዕፅዋት ከምድረ-ገፅ መጥፋት ለፍጡራን ሁላ አሳሳቢ ነው ተብሏል
ባለፉት 250 ዓመታት 600 ገደማ ዕፅዋት ከምድረ-ገፅ መጥፋታቸውን አንድ አዲስ ጥናት ይፋ አድርጓል።
ጥናቱ 600 ያክል ዕፅዋት ከምድረ ገፅ መጥፋታቸው ለፍጡራን እጅግ አሳሳቢ ነገር ነው ሲል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ያስተላልፋል። ቁጥሩ በተመሳሳይ ጊዜ ከምድረ-ገፅ ከጠፉ አእዋፍ፣ አጥቢ እንስሳት እና ውሃ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳት እጥፍ እንደሆነ ነው ጥናቱ የሚያሳየው። • ስለ ጠልሰም ወይም የአስማት ጥበብ ተብሎ ስለሚጠራው ምን ያህል ያውቃሉ? ሳይንቲስቶች ዕፅዋቱ እየጠፉ ያሉት በተፈጥሯዊ ሂደት መጥፋት ከነበረባቸው በ500 እጥፍ ፍጥነት መሆኑ አሳሳቢ ያደርገዋል ይላሉ። ባፈለው ግንቦት የተባበሩት መንግሥታት አንድ ሚሊዮን ዕፅዋት እና እንስሳት ከምድረ-ገፅ ሊጠፉ ነውና እናስበበት ሲል መደመጡ አይዘነጋም። ዶክተር አሊስ ሃምፍሬይስ «የእንስሳት ከዚህች ምድር መጥፋት ብዙም ላያስገርም ይችላል፤ የዕፅዋት ግን እጅጉን ሊያስጨንቀን የሚገባ ጉዳይ ነው» ይላሉ። • የቦረናን የዘመን አቆጣጠር ከሌሎች አቆጣጠሮች ምን ይለየዋል? «ጥናታችን የትኞቹ ዕፅዋት የውሃ ሽታ ሆነው እንደቀሩ፤ እንዲሁም የጠፉበት ፍጥነት እንዴት አስደንጋጭ እንደሆነ ያሳያል» ይላሉ ዶክተሯ አክለው። ከጠፉት ዕፅዋት መካከል ለወይራ ዘይት ምርት ጥቅም ላይ የሚውሉ የተወሰኑ እንደሚገኙበት ጥናቱ ይጠቁማል። ባለፉት ሁለት ከግማሽ ምዕት ዓመታት ምድራችንን የተሰናበቱ ዕፅዋት ቁጥር 571 ሲሆን፤ 217 ደግሞ የአእዋፍ፣ የአጥቢ እና ውሃ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳት ቁጥር ነው። ምድር ላይ የሚኖሩ ፍጡራን [የሰው ልጅን ጨምሮ] የሚተነፍሱት ኦክስጅን ከዕፅዋት መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ እንደሆን አድርጎታል። ከዓለማችን ላይ ሊጠፉ የተቃረቡ 5ቱ እንስሳት የትኛዎቹ ናቸው?
news-54409380
https://www.bbc.com/amharic/news-54409380
ለንደን ማራቶን፡ ያልተጠበቀው ኢትዮጵያዊ ሹራ ቂጣታ በለንደን ማራቶን ማሸነፍ ዓለምን አስደመመ
የአለም የማራቶን ሬኮርድ ባለቤት ኢሉይድ ኪፕቾጌን በማሸነፍ ኢትዮጵያዊው ሹራ ቂጣታ በዛሬው የለንደን ማራቶን ያልተጠበቀ ድልን ተጎናፅፏል።
ሹራ ኪታታ መጨረሻው ዙር ላይ የለንደን ማራቶን አራት ጊዜ አሸናፊው ኪፕቾጌ እንደሚያሸንፍ ብዙዎች ባይጠራጠሩም ባልተጠበቀ ሁኔታ ሁለት ዙር ሲቀረው ወደኋላ ቀርቶም በዚህ ውድድር ስምንተኛ ሆኗል። ኢትዮጵያዊው ሹራና ኬንያዊው ቪንስንት ኪፕቹምባ ተከታትለው አንደኛና ሁለተኛ የሆኑ ሲሆን፣ ሹራ ያሸነፈበትም ሰዓት 2፡05፡41 ነው። በሴቶችም የማራቶን ውድድር የክብረ ወሰኑ ባለቤት ብሪጅድ ኮሴጊ አሸንፋለች። "በጣም ነው ያዘንኩት፣ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም" በማለትም ኪፕቾጌ ከውድድሩ በኋላ ተናግሯል። "በመጨረሻዎቹ 15 ኪሎሜትሮች የቀኝ ጆሮዬ ተደፍኖ ነበር። በጭኔና ጉልበቴም የቁርጥማት ህምም እየተሰማኝ ነበር" ያለው ኪፕቾጌ አክሎም "ድንገት በውድድሩ ላይ ያጋጠመኝ ነው። ውድድሩን በመልካም ሁኔታ ነበር የጀመርኩት። አየሩ በጣም ቀዝቃዛ ነበር ግን እሱን ምክንያት አላደርግም" ብሏል። ባቱ ላይ ባጋጠመው አደጋ ምክንያት ቀነኒሳ በቀለ ውድድሩን ማቋረጡን ተከትሎም ኪፕቾጌ በቀላሉ ያሸንፋልም የሚል ግምት ተቀምጦ ነበር። በ2፡01፡39 የኦለምን ሬኮርድ የተቆናጠጠው የ35 አመቱ ኪፕቾጌ ስምንተኛም ቢሆን ውድድሩን ሳያቋርጥ ጨርሷል። በተለይም ውድድሩ አስራ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ሹራ ሩጫውን ያፋጠነው ሲሆን ኪፕቾጌም ምቾት ተነስቶ ታይቷል። በርካቶች ውድድሩን ያቋረጡ ሲሆን ሹራ በአንደኛነት፣ በሁለተኛነት ኬንያዊው ኪፕቹምባና በሦስተኛነት ሲሳይ ለማ ተከታትለው ገብተዋል። የ24 ዓመቱ ሹራ ኪፕቹምባን በአንድ ሰኮንድ የቀደመው ሲሆን ሲሳይን ደግሞ በሶስት ሰኮንዶች ብቻ ነው። "ለዚህ ውድድር በደንብ ተዘጋጅቼ ነበር። ቀነኒሳ በቀለም በጣም ነው የረዳኝ፤ በማሸነፌ ደስተኛ ነኝ" ብሏል። ኢትዮጵያውያኖቹ ሞስነት ገረመው፣ ሙሌ ዋሲሁንና ታምራት ቶላም ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ያለውን ቦታ ይዘዋል።
news-53394388
https://www.bbc.com/amharic/news-53394388
አውሮፕላኑ መታጠቢያ ቤት ውስጥ 'ቦምብ አለ' የሚል ማስታወሻ በማግኘቱ የተነሳ በረራውን አቋረጠ
ከክራኮው ደብሊን እየበረረ የነበረው ራይናኤር በአውሮፕላኑ ውስጥ ቦምብ መኖሩን የሚገልጽ ማስታወሻ በንጽህና ቤት ውስጥ በመገኘቱ የተነሳ በረራውን አቋርጦ ለማረፍ ተገደደ።
አውሮፕላኑ መንገደኞቹን ከማውረዱ በፊት ራቅ ወዳለ ጥቅ ተወስዶ እንዲቆም ተደርጓል ራይናኤር በረራውን አቋርጦ ያረፈው ኤሴክስ ስታንስቴድ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ሲሆን ፖሊሶችም አውሮፕላኑን በሚገባ መፈተሻቸው ተገልጿል። አውሮፕላኑ ሲያርፍ ሁለት የጦር ጄቶች አጅበውት እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል። የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ " አውሮፕላኑ በሰላም ነው ያረፈው፥ ነገር ግን መንገደኞች ከመውረዳቸው በፊት ራቅ ያለና ደህንነቱ የተጠበቀ ስፍራ እንዲቆም ተደርጓል" ሲሉ ተናግረዋል። በትዊተር ላይ አውሮፕላኑ በጦር ጄቶች ታጅቦ ሲያርፍ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተጋርተዋል። አውሮፕላኑ ሲያርፍ የተመለከተው ኪርቢ ከኤሲክስ እንዳለው "የአውሮፓ ተዋጊዎች ስታንስቴድ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ እያንዣበቡ ነበር የሚመስለው" የራይናኤር ቃል አቀባይ በበኩላቸው "አውሮፕላኑና መንገደኞቹ ተፈትሸዋል፤ የዩናይትድ ኪንግደም ፖሊስ ወደ ደብሊን መቼ መብረር እንደሚችሉ ይወስናል" ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል። "ደብሊን ወደ ክራኮው ለመሄድ እየጠበቁ የነበሩ መንገደኞች እንዳይዘገዩ በማሰብ ወደ ሌላ አውሮፕላን እንዲሸጋገሩ ተደርጓል" የኤሴክስ ፖሊስ "ሁሉም መንገደኞች ከአውሮፕላኑ ላይ በሰላም ወርደዋል። አውሮፕላኑም በስታንስቴድ ነጠል ባለ ስፍራ ይቆያል፤ እኛም ምርመራችንን እንቀጥላለን" ብሏል።
news-51780955
https://www.bbc.com/amharic/news-51780955
ዓይነ ስውሩ የተሰጠውን ጽሁፍ ባለማንበቡ የአሜሪካ ዜግነት ተከለከለ
አንድ ዓይነስውር የአሜሪካ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት በብሬል በተጻፈ የእንግሊዝኛ ንባብ ፈተና ምትክ ለአይናማዎች የተዘጋጀን ጽሁፍ ሰጥተውት ፈተናውን ባለማለፉ የአሜሪካ ዜግነት ተከለከለ።
ሉሲዮ ዴልጋዶ የተባለው የ23 ዓመት ወጣት ሲወለድ ጀምሮ ዓይነ ስውር የነበረ ሲሆን ከስድስት ዓመታት በፊት ነበረ አሜሪካ የገባው። ዴልጋዶ እንዳለው ምንም እንኳን ሙሉ ለሙሉ ዓይነ ስውር ቢሆንም የኢሚግሬሽን ሰራተኞቹ በወረቀት ላይ የሰፈረ ጽሁፍ እንዲያነብ ሰጥተውት ለማንበብ አልቻለም። በአሜሪካዋ ኢሊኖይ ግዛት ሕግ መሠረት ዴልጋዶ ዓይነ ስውርነቱ የተረጋገጠ ቢሆንም፤ ከዶክተር ይህንኑ የሚገልጽ ማስረጃ እንዲያቀርብ ተነግሮታል። የዕይታ ምርመራውን ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ከወሰደ በኋላ ከአሜሪካ የዜግነትና ስደተኝነት አገልግሎት መስሪያ ቤት በቅርቡ የደረሰው ደብዳቤ ዜግነት ለማንኘት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉን የሚያመለክት ነው። "በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፈን ዓረፍተ ነገር ማነበብ አልቻልክም" ይላል የደረሰው ደብዳቤ። "ዜግነት ለማግኘት በተሰጠህ ፈተና ላይ ያለውን የንባብ ክፍል ለማለፍ የሚያስችል ነጥብ ማግኘት አልቻልክም" በማለት ጥያቄው ውድቅ መሆኑን አመልክቷል። ዓይነ ስውሩ ዴልጋዱ ለእሱ በሚያመች ሁኔታ ፈተናው አለመቅረቡ እንዳስደነገጠውና በውጤቱም ማዘኑን ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ገልጿል። በፈተናው ወቅት ዓይነ ስውር መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ከሐኪም ዘንድ እንዲያመጣ የተነገረው ቢሆንም የጤና ኢንሹራንስ ስለሌለው ለምርመራው መክፈል አልቻለም። የአሜሪካ የዜግነትና ስደተኝነት አገልግሎት ቃል አቀባይ ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ዴልጋዶ ፈተናውን ከወሰደ ከወራት በኋላ ለዓይነ ስውራን ተፈታኞች የንብብ ፈተናውን በብሬል መስጠት እንደጀመሩ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት የዓይነ ስውሩ ዴልጋዶ ጉዳይ ከተዘገበ በኋላ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤቱ ዴልጋዶ ሌላ ፈተና እንዲወስድ ቀጠሮ እንደተያዘለት ለጠበቃ ነግሮታል።
54663985
https://www.bbc.com/amharic/54663985
ሰሜን ኮሪያ ከቻይና ይመጣል ባለችው "ቢጫ አቧራ ምክንያት" ማስጠንቀቂያ አስተላለፈች
ሰሜን ኮሪያ ከቻይና የሚመጣ ቢጫ አቧራ ምክንያት ዜጎቿን ከቤት አትውጡ ስትል አስጠንቅቃለች። ይህ የሰሜን ኮርያ መንግሥትን ያሰጋው "ቢጫ አቧራ" ከቻይና ስለሚነፍስ ኮሮናቫይረስ ሊያመጣብን ይችላል በሚል ነው።
ቢጫ አቧራ ከሞንጎሊያና ቻይና በረሃማ አካባቢዎች የሚነሳ አሸዋ ያዘለ አቧራ ሲሆን በሰሜን እና ደቡቡ ኮሪያ ይነፍሳል። የፒዮንግ ያንገግ ዋና አውራ ጎዳናዎች፣ ከሐሙስ እለት ጀምሮ ጭር ማለታቸው ተዘግቧል። ሰሜን ኮሪያ ከኮሮናቫይረስ ነጻ መሆኗን ብትናገርም ከታሕሳስ ወር ጀምሮ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላ ድንበሮቿን ዘጋግታ በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ ትገኛለች። እስካሁን ድረስ በወቅታዊ አሸዋ አዘል አቧራ እና በኮቪድ-19 መካከል ስላለ ግንኙነት ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ሰሜን ኮሪያ ብቻ አይደለችም ይህንን ጥቅጥቅ አቧራ ከኮሮናቫይረስ ጋር በማያያዝ ስትናገር የተደመጠችው። ከዚህ ቀደም ቱርኬሚስታን ዜጎቿን የአፍና አፍንጫ ጭምብል እንዲያደርጉ ያዘዘችው ይህንን ጥቅጥቅ አቧራማ ደመና ኮሮናቫይረስ ያስከትላል ስትል በመናገር ነበር። በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኘው የኮሪያ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣብያ፣ ኬሲቲቪ ረቡዕ እለት የአየር ትንበያ መረጃ የያዘ ልዩ ፕሮግራም አስተላልፎ ነበር። በዚህ ፕሮግራሙ ላይ በሚቀጥሉት ቀናት ቢጫ የአቧራ ደመና እንደሚመጣ በመግለጽ አስጠንቋቋል። በተጨማሪም ከቤት ውጪ የሚደረጉ ግንባታዎች በሙሉ ታግደዋል። ይህ አቧራ የሁለቱ አገራት ዜጎችን መርዛማ አቧራ ነው በሚል የጤና ስጋት ሲጥል የቆየ ነው፥። ሐሙስ እለት ለመንግሥት ወገንተኛ የሆነው ሮዶንግ ሺንሙን የተሰኘው ጋዜጣ " ሁሉም ሰራተኞች. . . ቫይረሱን አደገኛነት ሊገነዘቡ ይገባል" ብሏል። በሰሜን ኮሪያ የሚገኙ ኤምባሲዎችም የፒዮንግያንግ አቧራ ስጋት በሚመለከት መረጃ ደርሷቸዋል። በፒዮንግያንግ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በፌስቡክ ገጹ ላይ ከሰሜን ኮሪያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በአገሪቱ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖችን እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ስለ አቧራው ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው እና በቤት ውስጥ እንዲቆዩ፣ መስኮታቸውን አጥብቀው እንዲዘጉ ማስጠንቀቁን አስፍሯል። የሰሜን ኮሪያ መገናኛ ብዙኃን ኮሮናቫይረስ ላይ የሚደረጉ ምርምሮች ቫይረሱ አየር ወለድ መሆኑን በመግለጻቸው "የሚመጣው የቢጫ አቧራ ስርጭቱን እንዳያስፋፋ በጥብቅ ክትትል እናደርጋለን" ሲል ገልጿል። የአሜሪካው በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት ኮሮናቫይረስ በአየር ላይ "ለሰዓታት ይቆያል" ቢልም ሰዎች በዚህ መንገድ በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው በጣም አነስተኛ ነው ሲል አስታውቋል። የደቡብ ኮሪያ መገናኛ ብዙኃን ከቻይና የሚነሳው ቢጫ አቧራ ኮሮናቫይረስ ሊያስከትል ይችላል የሚለውን ስጋት መሰረተ ቢስ ሲል አጣጥሎታል።
news-49774493
https://www.bbc.com/amharic/news-49774493
ሞቷል ተብሎ የነበረው የአል ሸባብ መሪ በህይወት እንዳለ ተነገረ
ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በካንሰር ህመም መሞቱ የተነገረው የሶማሊያው ታጣቂ እስላማዊ ቡድን አል ሸባብ መሪ አህመድ ዲሪዬ በህይወት እንዳለ ተነገረ።
ግለሰቡ መሞቱ ከተነገረ ከዓመት በኋላ የተለቀቀው የድምጽ መልዕክት ዲሪዬ በህይወት እንዳለ አመላካች መሆኑ ተገልጿል። በአል ሸባብ ቡድን የመገናኛ ብዙኀን ክንፍ በኩል ይፋ በተደረገው የ20 ደቂቃ የድምጽ ቅጂ ላይ በተደረገ ትንተና ድምጹ ከነሐሴ 16/2011 እስከ መስከረም 6/2012 ባለው ጊዜ ውስጥ የተቀረጸ መሆኑ ተነግሯል። • አል ሻባብ የጎሳ መሪዎችን አስጠነቀቀ • የጋዜጠኛዋ መገደል ለምን የዓለም መነጋገሪያ ሆነ? ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያለው የአል ሸባብ ቡድን መሪ የነበረው አህመድ አብዲ ጎዳኔ ከአምስት ዓመት በፊት በአሜሪካ በተፈጸመ የአየር ጥቃት መገደሉን ተከትሎ የመሪነት ቦታውን የተረከበው አህመድ ዲሪዬ ባስተላለፈው የድምጽ መልዕክት በተለያዩ ርዕሶች ላይ ሲናገር ተደምጧል። ጠንከር ያለ ድምጸት ያለው የዚህ የድምጽ መልዕክት ዋነኛ ዓላማ ግለሰቡ በህይወት እንዳለ ታልሞ የተደረገ ንግግሩ መሆኑ ተገልጿል። የእስላማዊው ቡድን መሪው አህመድ ዲሪዬ እድሜው በአርባዎቹ ክልል ውስጥ እንደሚሆን የሚገመት ሲሆን፤ ባስተላላፈው በዚህ የድምጽ መልዕክት ላይ አል ሸባብ በሞቃዲሾ ከንቲባ ላይ ስለፈጸመው ግድያ፣ በቅርቡ ስለተካሄደውና አወዛጋቢ ስለነበረው የደቡብ ጁባላንድ ምርጫም አንስቷል። • የሶማሊያ ባለስልጣናት ከአልሸባብ ጋር በተያያዘ የጎሳ መሪዎችን አስጠነቀቁ • ብዙ ባሎችን አግብታለች የተባለች ሴት በአልሻባብ ተገደለች በተጨማሪም የቡድኑ መሪ በቅርቡ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደሚሰማ ስለሚጠበቀውና በሶማሊያና በኬንያ መካከል ስላለው የባሕር ጠረፍ ውዝግብም በማንሳት፤ አል ሻባብ ጉዳዩን በተመለከተ የሚሰጥን የውጭ ፍርድ ቤት ውሳኔን እንደማይቀበል ገልጿል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ታጣቂው ቡድን በአፍሪካ ኅብረትና በሶማሊያ መንግሥት ወታደሮች ከዋና ዋና የሐገሪቱ ከተሞች ተገፍቶ የወጣ ቢሆንም ዋና ከተማዋን ጨምሮ በሌሎችም ስፍራዎች ከፍተኛ ጥቃቶችን ከማድረስ ግን አልተገታም። በብዛት በአሜሪካ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖች የሚደገፈው የሶማሊያ ሠራዊት በታጣቂው ቡድን ስር በሚገኙት የደቡባዊና ማዕከላዊ የሐገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የሚባል ወታደራዊ ዘመቻን በቅርቡ ማካሄድ ጀምሯል።
news-54752157
https://www.bbc.com/amharic/news-54752157
እንስሳት፡ውሾች የሰው ልጅ እድሜ ጠገብ ወዳጆች መሆናቸውን አንድ ጥናት አመለከተ
ውሾች በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ለረጅም ዓመታት ወዳጅ ሆነው የቆዩ የቤት እንስሳት እንደሆኑና የሚስተካከላቸው ሌላ እንስሳ አለመኖሩን አንድ በቅርቡ የተሰራ ጥናት ጠቁሟል።
በጥናቱ መሰረትም የሰው ልጅ ውሾችን ጓደኛ ማድረግና በቤቱ ማሳደግ የጀመረው ከ11 ሺ ዓመታት በፊት እንደሆነ ተገልጿል። ይሀም ማለት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እንደ ውሻ ከሰዎች ጋር አብሮ ለረጅም ዓመታት የኖረ እንስሳ የለም መላት ነው። ከዛሬ 11 ሺ ዓመታት በፊት ውሾች በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ በኩል በብዛት ይገኙ የነበረ ሲሆን ከዚያም ወደ አምስት አይነት ዝርያዎች ተከፋፍሏል። ምንም እንኳን በቅኝ ግዛት ዘመን አውሮፓውያን የሚያሳድጓቸው ውሾች ከጊዜ በኋላ ዓለምን ቢወሩም የቀድሞዎቹ አገር በቀል ውሾች ግን አሁንም ድረስ በላቲን አሜሪካ፣ እስያ፣ አፍሪካ እና ኦሽኒያ እንደሚገኙ ጥናቱ ጠቁሟል። ''ውሾች ከሰው ልጅ ጋር እንዴት ወዳጅነት ሊመሰርቱ ቻሉ የሚለው ጥያቄ በጣም አስገራሚ ነው። የሰው ልጅ አደኛና የሜዳ ፍሬዎችን ለቃሚ በነበረበት ጊዜ እንኳን ውሻዎችን አላምዶ ነበር። በበርካታ የዓለማችን ክፍሎች የውሻ ቤተሰብ የሆነው ተኩላ በጣም አስፈሪና አዳኝ የዱር እንስሳ ነበር'' ይላሉ በጥናቱ ላይ ተባባሪ የሆኑት ዶክተር ፖንተስ ስኮግሉንድ። ''ትልቁ ጥያቄ ሰዎች ለምን ውሻን መረጡ? እንዴትስ ሊሳካላቸው ቻለ? የሚሉትን ጥያቄዎች ነው ለመመለስ የፈለግነው'' በማለት የጥናቱን ዓለማ ያስረዳሉ። የሆነ ያክል ደረጃ ድረስ የሰው ልጆች ዘረመል እና የውሻዎች ዘረመል አወቃቀር ተቀራራቢ ነው። ምክንያቱም የሰው ልጅ ለመኖር የሄደበት ቦታ በሙሉ አብረው በመሄድ መኖር ስለሚችሉ ነው። ነገር ግን ወሳኝ የሆኑ ልዩነቶችም አሉ። ለምሳሌ ቀደምት አውሮፓውያን ውሾች የተለያዩ የዘር ሀረጎች ያሏቸው ሲሆን ዋነኛ የዘር ግንዳቸው ግን በሁለት የሚከፈል ነው። የመጀመሪያው ቀረብ ያሉት ምስራቅ አካባቢ ውሻ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሳይቤሪያ ውሾች ናቸው። ነገር ግን የሆነ ቦታ ላይ አንድ የውሻ ዘር በመላው አውሮፓ የሚገኙ የውሻ ዝርያዎችን በመዋጥ መስፋፋት ችሏል። ጥናት አድራጊዎቹ ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ይኖሩ የነበሩ 27 የውሻ አይነቶችን ቅሪተ አካል በመመርመር ከአሁኖቹ የውሻ ዝርያዎች ጋር ለማመሳከር ጥረት አድርገዋል። በዚህም መሰረት ለምሳሌ 'ሮዴዢያን ሪጅባክ' የሚባለው በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው እና በሜክሲኮ የሚገኙት 'ቺዋዋ' እና 'ዞሎይትኩንቲ' የውሻ ዝርያዎች ከብዙ ሺ ዓመታት በፊት በአካባቢው ይኖሩ ከነበሩት ቀደምት ውሾች ጋር ዝምድና እንዳላቸው ማወቅ ተችሏል። ነገር ግን በምስራቅ እስያ የሚገኘው የውሻ ዝርያ እጅግ የተወሳሰበ እንደሆን ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ። በቻይና የሚገኙት የውሻ ዝርያዎች ከዚህ በፊት በአውስትራሊያ እና ኒው ጊኒ አካባቢ ከሚገት ውሾች ጋር ተመሳሳይነት አላቸው። በጥናቱ ላይ የተሳተፉት ሌላኛው ተመራማሪ ግሬገር ላርሰን እንደሚሉት ውሾች ከሰው ልጅ ጋር ለብዙ ዓመታት አብረው የቆዩ እንስሳት መሆናቸው የተረጋጋጠ ሲሆን ይህንንም ማድረግ የተቻለው በዘረመል ላይ በተደረገ ጥናት ነው። ውሾች ከተለያዩ የተኩላ ዝርያዎች የመጡ እንደሆነና የሰው ልጅ አደን በሚያካሂድበት ወቅት ጭምር እገዛ እንደሚያደርጉ ከዚህ በፊትም የሚገመት ነገር ነበር። በአዲሱ ጥናት መሰረት ደግሞ ሁሉም ውሾች የመጡት ከአንድ በአሁኑ ሰአት ከጠፋ የተኩላ ዝርያ ነው። ነገር ግን ውሾችን ማላመድ መቼና የት ተጀመረ የሚለው እስካሁንም እርግጠኛ ምላሽ ያላገኘ ጥያቄ ነው። እንደ ድመት ያሉት የቤት እንስሳት ደግሞ የሰው ልጅ ከዛሬ 6 ሺ ዓመታት በፊት በአንድ ቦታ ላይ ተረጋግቶ መኖር ሲጀምር የመጡ ናቸው ተብሏል። ምክንያቱም የሰው ልጅ በአንድ ቦታ ሰፈረ ማለት የሚጥለው ቆሻሻ በሚኖርበት አካባቢ ይጠራቀማል ማለት ነው። ይህንን ቆሻሻ ተከትለው ደግሞ አይጦች ወደ ሰው ልጅ ሕይወት ገቡ። እነዚህን አይጦች ለማባረርና ለማጥፋት ደግሞ ከድመቶች የተሻለ የቤት እንስሳ የሰው ልጅ አላገኘም።
news-46684378
https://www.bbc.com/amharic/news-46684378
የእርቀ-ሰላም እና ይቅርታ ኮሚሽን ከደቡብ አፍሪካ እስከ ኢትዮጵያ
የእርቀ ሰላም እና ይቅርታ ጉዳይ የአትዮጵያን በር ካንኳኳ ወራት ተቆጠሩ፤ ሕዝብን በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ በኩል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የመሪነቱን ሥፍራ ይወስዳሉ።
ምንም እንኳ የተወሰኑ የምክር ቤቱ አባላት ሕዝብ ከሕዝብ ስላልተጣላ የኮሚሽኑ መቋቋምም አስፈላጊ አይደለም በማለት ቢከራከሩም፤ ታኅሳስ 16 ቀን 2011 ዓ.ም የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የብሔራዊ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ያቋቋመው። በተለያዩ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ በደሎች ሕዝብ ተከፍቷልና፤ እውነተኛ ይቅርታ በመጠያየቅና የተበደሉ ወገኖችን ሕመም በመጋራትና በማከም የቁርሾ ታሪክን ተዘግቶ ወደፊት ለመራመድ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ሲሉ ለኮሚሽኑ መመስረት አስፈላጊነት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ ይከራከራሉ። ኮሚሽኑ በደል የደረሰባቸው ሰዎች በሚያቀርቧቸው ቅሬታዎች ላይ በመነሳት ሥራውን እንደሚያከናውን ተሰምቷል። ወጣም ወረደ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገራት ተሞክሮ መማር እንዳለበት እሙን ነው። እርቀ-ሰላሙ እና ይቅርታው ለይስሙላ አለመሁኑን ማስጠበቅ ደግሞ ፈተናዋ ይሆናል። ይህን መሰሉን የእርቅና የይቅርታ ኮሚሽን በማቋቋም ሌሎች የአፍሪካ ሃገራትም በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙ በደሎች እልባት እንዲያገኙ አድርገዋል። ደቡብ አፍሪካ የዛሬ 32 ዓመት ገደማ ነበር ደቡብ አፍሪካ የሃቅ እና የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ያቋቋመችው። በጊዜው ሃገሪቱ ከአፓርታይድ አገዛዝ ገና መላቀቋ ነበርና ያለፈውን ለመርሳት እና ወደፊት ለመጓዝ በሚል ነበር የኔልሰን ማንዴላ መንግሥት ኮሚሽኑ እንዲቋቋም የወሰነው። ለዓመታት ከዘለቀ ዘርን መሠረት ካደረግ የግፍ አገዛዝ በኋላ እንዴት ተኩኖ ነው በጋራ በሰላም ወደመኖር የሚመጣው? ደቡብ አፍሪካ የተጋፈጠችው ትልቅ ፈተና ነበር። የደቡብ አፍሪካ የሃቅ እና እርቀ ሰላም ኮሚሽን ሥራው ቀላል አልነበረም፤ ሥራው የዘር ፖለቲካ ክፉኛ የተጎዳችን ሃገር ማከም ነበርና። • አርበኞች ግንቦት 7 ፈርሶ አዲስ ፓርቲ ሊመሰረት ነው ዳኛ ሲሲ ካምፔፔ የእርቀ ሰላም ኮሚሽኑ አባል ነበሩ። ዳኛዋ የይቅርታ ኮሚቴ ተብሎ የተቋቋመው ብሔራዊ ጥምረት አባልም እንደነበሩ ያዋሳሉ። የእርቀ ሰላም አባላት ኮሚቴው በአፓርታይድ ዘመን ደቡብ አፍሪካዊያን ላይ ግፍ ፈፅመዋል የተባሉ ሰዎችን የመመርመር ግዴታ አለባቸው። ነገር ግን ጥፋት ፈፅሟል የተባለው ሰው ጥፋቱን በውዴታ ካላመነ በቀር ፍርድ አይበየንበትም። ለደቡብ አፍሪካዊያን ትልቁ ፈተና የነበረው የይቅርታ ጉዳይ እንደነበር ዳኛ ሲሲ ይናገራሉ። «እንዴት የሰው ልጅ ላይ አሰቃቂ ግፍ የፈፀመ ግለሰብ ይቅርታ ይደርግለታል? የሚለው ትልቁ ፈተና ነበር» ይላሉ። በደቡብ አፍሪካው የእርቀ ሰላም ሂደት ውስጥ ትልቅ ሚና እንደተጫወቱ የሚነገርላቸው አርክቢሾፕ ዴዝሞን ቱቱ ናቸው። በእርሳቸው መሪነት ግቡን ከሞላ ጎደል እንደመታ የሚነገርለት የሃቅ እና እርቀ ሰላም ኮሚሽን ዋነኛ ተግባሩ በሕዝቦች መካከል ሰላም ማውረድ ነበር። ኡጋንዳ በኢትዮጵያ ግርጌ ከኬንያ ጋር የምትዋሰነው ኡጋንዳም የተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ተቋዳሽ ነበረች። ለዓመታት የዘለቀው በመንግሥት እና 'ሎርድስ ሬዚዝስታንስ አርሚ' በተሰኘው የሽምቅ ተዋጊ ቡድን መካከል የነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ሃገሪቱን በሰላም እጦት እንድትቆረቁዝ አድርጓት ነበር። ጭካኔ በተሞላበት ድርጊቱ የሚታወቀው የሎርድስ ሬዚዝስታንስ አርሚ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን አቾሊ የተባሉትን ሰሜናዊ ኡጋንዳዊያን ነፃ ለማውጣት የሚታገል ነበር። • የሪፐብሊኩ ጠባቂ ሃይል መቋቋም ምን ያመለክታል? ከዓመታት ትግል እና ያልተሳካ የሰላም ድርድር በኋላ ሽምቅ ተዋጊ ቡድኑ በመግንሥት ኃይል ተሸንፎ ሃገር ጥሎ መውጣቱ ተነገረ። ኋላ ላይ ግን መንግሥት ያቋቋመውን እርቀ ሰላም ከሚቴ ተከትሎ የቡድኑ ተዋጊዎች ወደ ሃገራቸው መመለስ ያዙ፤ 32 ሺህ ገደማ ወታደሮች ከተሰደዱበት ሃገር ተመልሰው ከማሕበረሰቡ ጋር መዋሃድ ያዙ። 'ማቶ ኦፑት' የተሰኘ ባሕላዊ የይቅርታ እና እርቀ ሰላም ኮሚቴ ተቋዉሞ ማሕበረሰቡ ለተዋጊዎቹ ይቅርታ ቢያደርግም በጊዜው ተቀባይነት ግን አልነበራቸውም። ጋምቢያ ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሃገር ጋምቢያም ተመሳሳይ ታሪክ መዝገቧ ላይ የሰፈረባት ሃገር ናት። የቀድሞው የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ያህያ ጃሜህ ሃገር ጥለው ቢጠፉም ለሁለት አሥርት ዓመታት ጥለውት ያለፉት አሻራ ግን በቀላሉ የሚፋቅ አይመስልም። አዲሱ ፕሬዝደንት አዳማ ባሮው የሃቅ፣ የእርቀ-ሰላም እና መልሶ መቋቋም ኮሚሽን ያሻናል ብለው ያቋቋሙት በያዝነው ዓመት ነው፤ "ብሔራዊ ቁስላችን እንዲሽር" በማለት። ኮሚሽኑ በቀድሞው ፕሬዝደንት ዘመን ተፈፅመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መመርመር እና ተገቢውን ብይን የመስጠት ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ጋምቢያዊው የቢቢሲ ጋዜጠኛ በቀድሞው ፕሬዝደንት አገዛዝ ዘመን 'ፍሪደም' ከተሰኘው እና መንግሥት በጥላቻ ከሚያየው ጋዜጣ ጋር ስሙ ተያይዞ ለእሥር እና ስቃይ ተዳርጓል፤ ሃገሩን ጥሎ ተሰዷል። «እስከዛሬ ድረስ በብሔራዊ የምርመራ ኤጀንሲ መሥሪያ ቤት በኩል ማላፍ አልችልም» ይላል፤ ስቃይ የቀመሰበት ሥፍራ ነውና። አሁን ሁሉም ያለፈ ይመስላል፤ የአዳማ ባሮው መንግሥትም የቀድሞውን መሪ ሃጥያት ለማሰረይ ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ከላይ የተጠቀሱት ሃገራት ብቻ ሳይሆኑ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት የእርቀ-ሰላም እና ይቅርታ ኮሚሽን ማቋቋም ግድ ብሏቸዋል። ሩዋንዳ ስለእርስ በርስ ጦርነት ሲነሳ እንደምሳሌ የምትጠቀሰው ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር ሩዋንዳ 800 ሺህ ዜጎቿን ያጣችው የዛሬ 35 ዓመት ገደማ ነው። 'ጋቻቻ' የተሰኘው እና በሩዋንዳው ዘር እልቂት ወቅት ጥፋት ፈፅመዋል በተባሉ ሰዎች ላይ ፍርድ እንዲበይን የሚተጋው አካል ሁለት ሚሊየን ያክል ሰዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ አድርጓል። • "ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ነገር ግን የሩዋንዳ መንግሥት እርቀ ሰላም እና ይቅርታን በሕዝቡ ዘንድ ከማስረፅ አንፃር ተገቢውን ሥራ አልሠራም ተብሎ በተደጋጋሚ ይተቻል። ሩዋንዳ ውስጥ አሁንም ድረስ ስለዘር ማውራት ያስነውራል፤ ስለ እልቂቱ ማውሳት ያስወቅሳል። ሬድዮ ጣብያዎች የእርስ በርስ ጦርነቱን አንስተው እንዲነጋገሩበት አይበረታቱም፤ ቴሌቪዥኖች ስለጉዳዩ አያወጉም። የሩዋንዳ ጎረቤት ሃገር የሆነችው ቡሩንዲ ግን በእርቀ ሰላም ጉዳይ መልካም ምሳሌ ሆና ትነሳለች፤ ምንም እንኳ በእርስ በርስ ጦርነት 300 ሺህ ያህል ዜጎቿን ካጣች ዘመናት ቢቆጠሩም።
news-56427912
https://www.bbc.com/amharic/news-56427912
በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ወልዳ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀችው
ፎዚያ ጀማል በ 2010 ዓ.ም ኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ ተመድባ ስትሄድ ገና አዲስ ሙሽራ ነበርች።
የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ፎዚያ በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከወሰደቻቸው 38 ኮርሶች 31 A+ በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቃለች በዩኒቨርስቲው የኢኮኖሚክስት ትምህርት ክፍል እንድትማር ስትመደብ ነፍሰጡር መሆኗን አወቀች። በዚህ ምክንያት ግን ምህርቷን ማቋረጥ አልፈለገችም። በእርግዝናዋ ወራት በዙሪያዋ ምን አማረሽ? ምን ይምጣልሽ? የሚል ወላጅ እና ባል ባይኖርም፤ እንደ ሌሎች የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በካፌም በቤተመጻህፍት በትምህርት ክፍልም እኩል እየተገኘች ትምህርቷን ተከታትላለች። ፎዚያ የመጀመሪያ ዓመት ትምህርቷን ስታጠናቅቅ የወሰደቻቸውን ኮርሶች በአጠቃላይ ኤ ያመጣች ስትሆን ሴት ልጅ ወልዳ ለመሳምም በቅታለች። ፎዚያ ከዚያ በኋላ በአንድ እጇ ልጇን አቅፋ በሌላ እጇ መጽሐፍ ዘርግታ ትምህርቷን በትጋተት ተከታትላለች። ትጋቷም ፍሬ አልባ አልነበረም። የሶስቱን ዓመት ትምህርት አጠናቅቃ ስትመረቅ ከወሰደቻቸው 38 ኮርሶች መካከል 31 A+ ሰባቱን ደግሞ A አምጥታለች። ፎዚያ ጀማል ከኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ በ2012 ተመራዊ የነበረች ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በ2013 ጥር ወር መጀመሪያ ላይ ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪዋን በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቅቃ ተመርቃለች። የኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ ከእርሷ ጋር አንድ ላይ 929 ተማሪዎችን አስመርቋል። ምዕራብ ሐረርጌ ቦኬ ወረዳ የተወለደችው ፎዚያ የ11ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ትዳር መመስረቷን ለቢቢሲ ትናገራለች። በሶስት ዓመት የዩኒቨርስቲ ቆይታዋ አንድ ዓመት ነፍሰጡር ሆና ሌላኛውን ዓመት ደግሞ ጨቅላ ልጇን እያሳደገች ስትማር የተለያዩ ፈተናዎች የነበሩ ቢሆንም ዓላማዋና ትኩረቷን በአንድ ጉዳይ ላይ በማድረግ በድል ማጠናቀቋን ትናገራለች። "ሥራዬ ነው ብለህ ራስህን አሳምነህ ከጀመርክ የማይቻል ነገር የለም። እኔም ነፍሰጡር መሆኔ በውጤቴ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር የለበትም በማለት በርትቼ ሳጠና ነበር፤ ነፍሰጡር ሆኖ በትምህርት ፈተና ውስጥ ማሳለፍ በዚያ ላይ ልጅን እያሳደጉ ፈታኝ ቢሆንም ያሰብኩትን አሳክቻለሁ። የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ሳለች እርግዝና ተጨማሪ ኃላፊነት ይዞባት ስላመጣ በእርግዝናና ልጅ ማሳደግ ነጥቧ እንዳይቀንስ ከበፊቱ በበለጠ ስታነብ እንደቆየች ታስታውሳለች። ከዚህ ስኬቷ ጀርባም የባለቤቷ ድጋፍ ብዙ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጻለች። ለዚህ ሁሉ ስኬቴ የባለቤቴ ሚና ትልቅ ነው የምትለው ፎዚያ "ባለቤቴ እውነቱን ለመናገር የተለየ ሰው ነው፤ እርሱ ለትምህርቴ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ልክ ለእርሱ እንደምማር ነው የሚወስደው፤ ከእኔ በላይ እርሱ ነው የሚጨነቀው። በሁሉም በኩል በጣም ያግዘኛል። እርሱ የስኬቴ ምስጢር ነው።" ፎዚያ ሶስት ዓመት ኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ በቆየችበት ወቅት ላስመዘገበችው ከፍተኛ ነጥብ ሁለት ዋንጫ እና አንድ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልማለች። እቅዴን ፈጣሪ ረድቶኝ ስለተሳካልኝ፣ ያሰብኩትን ስላሸነፍኩ በማለት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ እያለች የወለደችውን ልጅ ሞኔት [ Mooneet] ብለው እንደሰየሟት ትናገራለች። ሞኔት የሚለው ወደ አማርኛ ሲመለስ አሸነፍን ማለት እንደሆነ ትናገራለች። ሴቶች ስኬታማ ለመሆን ቆራጥ መሆና ያስፈልገናል የምትለው ፎዚያ፣ ኋላ ቀር የሆኑትን አስተሳሰቦች በመተው የስኬት መንገዶችን ማየት አለብን በማለት ሴቶችን ትመክራለች። "ምንም አንችልም ብለን ራሳችንን ማሳመን የለብንም። አንችልም ብለን ራሳችንን ካሳመንን እውነትም አንችልም። እችላለሁ ብሎ ያመነ አእምሮ ይችላል። በሥራዬ ከግብ እደርሳለሁ ብላ የምትሰራ እደርሳለሁ ያለችው ቦታ ለመድረስ የሚከለክላት የለም " ትላለች። ፎዚያ በአሁኑ ጊዜ በኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል በመምህርነት ተቀጥራለች። ለወደፊት ደግሞ ትምህርቷን ማሳደግ እና ባገኘችውና እውቀት ኅብረተሰቡን የማገልገል ፍላጎት እነዳላት ትናገራለች።ፎዚያ ጀማል በ 2010 ዓ.ም ኦዳ ቡልቶም ዩኒቨርስቲ ተመድባ ስትሄድ ገና አዲስ ሙሽራ ነበርች።
news-53852366
https://www.bbc.com/amharic/news-53852366
አሜሪካ፡ የትራምፕ የቀድሞ አማካሪ ስፒቭ ባነን በማጭበርበር ወንጀል ተከሰሱ
የቀድሞው የትራምፕ አማካሪ ስቲቭ ባነን አሜሪካ ራሷን ከሜክሲኮ ለመነጠል ለምትገነባው ግንብ ከተዋጣው ላይ በመቆንጠር ወደ ግል ኪሳቸው አስገብተዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ስቲቭ ባነን በአንድ ወቅት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ታማኝ አማካሪ ነበሩ ባነን እና ሌሎች ሶስት ሰዎች "እንገነባዋለን" በተሰኘው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ለጋሾችን አጭበርብረዋል በሚልም ተከስሰዋል። በወቅቱ በዘመቻው 25 ሚሊዮን ዶላር ማሰባሰብ ተችሎ እንደነበር የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል። ባነን ግን ለግል ኑሯቸው መደጎሚያ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ መቀበላቸውና ማጥፋታቸው ተገልጿል። ስቲቭ ባነንና ሌሎቹ ተከሳሶች ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ እየተገለፀ ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ2016 የምረጡኝ ቅስቃሳቸው ወቅት አሜሪካንና ሜክሲኮን በሚያዋስነው ድንበር ላይ ግንብ ለመገንባት ቃል የገቡ ሲሆን "እንገነባዋለን" የተሰኘው ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻም ብራያን በሚባሉ ግለሰብ ነበር የተጀመረው። እንደ ኒውዩርክ ግዛት አቃቤ ህግ ኦድሪ ስትራውስ ከሆነ፤ ባነንና ሌሎች ሶስት ግለሰቦች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ለጋሾችን ግድቡን ለመገንባት በሚሊዮን ዶላሮች እንዲያዋጡ ቢያደርጉም፣ የግል ፍላጎታቸውን በማስቀደም እና፤ "የሚሰበሰበው ገንዘብ ሁሉ ለግንባታው ይውላል በሚል በመዋሸት አጭበርብረዋል።" ስቲቭ ባነን በሚቆጣጠሩት አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በኩል ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀብለዋል፤ ቢያንስ ደግሞ "በመቶ ሺዎች የሚቇጠር ዶላር ለግል ጥቅማቸው ወጪ አድርገዋል" ሲል የፍትህ ቢሮው አስታውቋል። የ 'እንገነባዋለን' ዘመቻ መስራች ሆኑት ብራያን ኮልፋግ በበኩላቸው 350,000 ዶላር ለግልጥ ቅማቸው ማዋላቸውን መግለጫው ያመለክታል። በዘመቻው ግለሰቦችን "ጡብ ይግዙ" በማለት ይቀሰቀስ ነበር አቃቤ ህግ ስትራውስ "የእንገነባዋለን ዘመቻ መስራችና ግንባር ቀደም ተዋናይ የሆኑት ብራያን ኮልፋግ ሰባራ ሳንቲም እንዳልተከፈላቸው ቢናገሩም፣ በምስጢር በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ለተቀናጣ ኑሯቸው መደጎሚያ እንዲውል አድርገዋል" ሲሉ ተናግረዋል። አራቱ ተከሳሶች ወንጀላቸውንም ለመደበቅ "ለህግና ለእውነት ደንታ ቢስ ሆነው ከለጋሾች የሚሰበሰበውን ገንዘብ በተጭበረበረ ሰነድ ይሰበስቡ ነበር" ያሉት ደግሞ ጉዳዩን በመመርመር ላይ የተሳተፉት ፍሊፕ አር ባርትሌት ናቸው። "ይህ ለሌሎች አጭበርባሪዎች ማንም ሰው ከህግ በላይ እንደማይሆን ትምህርት ሊሆን ይገባል፣ . . . ሚሊየነር የፖለቲካ ስልት ነዳፊ ቢሆንም" ብለዋል። አራቱም ተከሳሾች የተከሰሱበት ወንጀል እስከ 20 ኣመት ድረስ በእስራት የሚያስቀጣ ነው። የ66 ዓመቱ ስቲቭ ባነን ኒውዮርክ ሌሎቹ ደግሞ ፍሎሪዳ በሚገኙ ፍርድ ቤቶች የሚቀርቡ ይሆናል።
48419946
https://www.bbc.com/amharic/48419946
በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀሰ ረብሻ የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ግጭት አንድ ተማሪ መሞቱን ተማሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ። ሟች ሰዓረ አብርሃ እንደሚባልና የሶስተኛ ዓመት የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተማሪ እንደነበረ ለማወቅ ችለናል።
በዩኒቨርስቲው ከዓርብ ጀምሮ የተቀሰቀሰው ግጭት እስከዛሬ ድረስ አለመረጋጋቱን ተማሪዎቹ ገልጸዋል። በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ደሳለው ጌትነትም በተቋሙ ከባለፈው አርብ 11 ሰዓት ጀምሮ ግጭቶች መኖራቸውን አረጋግጠዋል። በዚህም አርብ ግንቦት 16 ላይ 3 ልጆች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረው ልጆቹ አሁን ሆስፒታል ይገኛሉ ብለዋል። የተጎዱት ተማሪዎች በባህርዳር እና አዲስ አበባ ሪፈራል ተጽፎላቸው ወደዚያው መወሰዳቸውንም ጨምረው ያስረዳሉ። • የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ • የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ኃላፊ ተይዞ ለኢትዮጵያ ተሰጠ • አይስላንድ አንድ ተማሪ ብቻ የቀረውን ትምህርት ቤት ልትዘጋ ነው በግጭቱ ሁለት ተማሪዎች በድንጋይና በዱላ ጉዳት እንደደረሰባቸው የዓይን እማኞቹ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተፈጸመበት ጥቃት ምክንያት አንደኛው ተማሪ ወድያውኑ ህይወቱ ማለፉንና ሌላኛው ተማሪ ደግሞ ለህክምና እርዳታ ወደ ባህርዳር መወሰዱን ከተማሪዎቹ መረዳት ችለናል። የረብሻውን ምክንያት እስካሁን ማረጋገጥ አልቻልንም ያሉት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አርብ ዕለት ተሳትፎ የነበራቸውን የተወሰኑ ልጆች ፖሊስ ተከታትሎ ከግቢ ውጭ ይዟቸው ፖሊስ ጣቢያ ስለሚገኙ ጉዳያቸው እየተጣራ ነው በማለት የግጭቱ መንስኤ ከዚያ በኋላ ተጣርቶ የሚታወቅ ይሆናል ብለዋል። በአሁኑ ሰዓት በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ የተጠለሉ ተማሪዎች እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን ትላንት የሟችን አስክሬን ለመሸኘት የተሰበሰቡ ተማሪዎችም "ትምህርቱ ይቅርብን ወደ መጣንበት መልሱን" በማለት ለዩኒቨርሲቱው ፕሬዚዳንት ጥያቄ ማቅረባቸውን ነግረውናል። የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው በፖሊስና የፌደራል ጸጥታ ሃይሎች እገዛ ደህንነታችሁ ለማስጠበቅ እንሰራለን በማለት ምላሽ መስጠታቸውን ተማሪዎቹ ይናገራሉ። አሁን ረብሻ የለም፤ ተማሪዎች ግን ወደ ትምህርትም ሆነ ወደ ጥናት የሚያመሩበት ሁኔታ የለም። ችግሩ ስለማይታወቅ ከፖሊስ ጋር ችግሩን በመለየትና መፍትሔ ለመስጠት እየሠራን ነው ያሉት ደግሞ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ናቸው። ግጭቱ በብሔር መካከል የተነሳ አይደለም የሚሉት ኃላፊው ትምህርት አለመጀመሩን አረጋግጠው የመማር ማስተማሩ ስራ ግን ማክሰኞ ይቀጥላል ብለዋል። ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ የተላከው የሟች ተማሪ አስከሬን ዛሬ ከሰአት ወደ ትውልድ ስፍራው ትግራይ ሽረ እንዳስላሴ ከተማ እንደሚላክ አንድ ስሟ እንዲገለጽ ያልፈለገች ተማሪ ለቢቢሲ ተናገራለች። አቶ ደሳለው በበኩላቸው አስከሬኑ ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ እንዳልተላከና ወደ ቤተሰቦቹ እንደተሰኘ ገልፀዋል።
news-52909590
https://www.bbc.com/amharic/news-52909590
ኮሮናቫይረስና የወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ፈተና
ዘመኑ አካላዊ ርቀት መጠበቅን ግድ ይላል። የሰዎች ንክኪ የሚበዛባቸው ሱቆችና አገልግሎት ሰጪዎች ተዘግተዋል። በተለይ ደግሞ አስፈላጊነታቸው ይህን ያህል አይደለም የተባሉ ሱቆች መስኮታቸውን ጥርቅም አድርገው ከዘጉ ወራት ሆኗቸዋል።
ኮሮናቫይረስ ዓለምን ሰቅዞ ከያዘ ወዲህ የራቁት ዳንስ ቤት፣ መጠጥ ቤቶችና በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ የሚገኙባቸው ሥፍራዎች በራቸው ከተከረቸመ ውሎ አድሯል። በወሲብ ንግድ ላይ ያሉ ሰዎች ደንበኞቻችን በአንድ ምሽት ቀለጡ ይላሉ። ኢስቴል ሉቃስ ሜልበርን ውስጥ ላለፉት 10 ዓመታት ኑሮዋን የገፋችው በወሲብ ንግድ ነው። ነገር ግን ኮቪደ-19 መጥቶ ምድርን ሲያገለባብጣት የእሷ ሥራ አፈር በላ። ለዓመታት የተንከባከበቻቸው ደንበኞቿም ረሷት። "ለስድስት ወራት ሥራ ሳልሰራ ቆየሁ ማለት ደንበኞቼን አጣሁ ማለት ነው" ትላለች። ኢስቴል አትዋሽም። ከኮሮናቫይረስ በፊት ገቢዬ ከአማካይ በላይ ነበር ትላለች። ሜልበርን መሃል እሚገኝ አንድ ሠፈር ውስጥ ቤት ሰርታለች። አሁን ግን የገቢዋ ባልቦላ ተቆርጧል። ሥራዋን በኢንተርኔት አማካይነት ለማስቀጠል ብትሞክርም እንደከዚህ በፊቱ ሊሆንላት አልቻለም። "ደንበኞቼን በኢንተርኔት ላገኛቸው ሞክሬ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ሰው ቴክኖሎጂ የገባው ነው ማለት አይቻልም። አንዳንድ ደንበኞቼ ስልካቸውን እንኳን በሥርዓት መጠቀም አይችሉም።'' ምንም እንኳ ምግብ ቤቶችና ካፌዎች መከፈት ቢጀምሩም የወሲብ ንግዱ ግን ገና ፀሐይ አልወጣለትም። አልፎም ሰዎች አካላቸውን ለማነካካት ያላቸው አለመተማመን ደግሞ ሌላው በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ሰዎች ፈተና ሆኗል። "እኔ የተሰማራሁበት ሥራ ከጥቅም ውጪ ሆኖ ልክ መጀመሪያ ስጀምር እንደሆንኩት እንዳልሆን ነው የምፈራው። ሥራው ቢመለስ እንኳ ደንበኞቼ ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም። ብቻ ሁሉም ነገር ያስፈራል።" የአውስትራሊያ መንግሥት በኮቪድ-19 አማካይነት የገቢ ምንጫቸው ለተጓደለባቸው የገንዘብ እርዳታ እያደረገ ነው። ነገር ግን ድጎማው እንዲደርስዎ ከፈገሉ ታክስ የከፈሉበትን ደረሰኝ ማቅረብ ግዴታ ነው። ይህ ደግሞ ሕጋዊ መዝገብ ላይ ስማቸው ላልሰፈረ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩና ስደተኞች ደንቃራ ነው። አውስትራሊያ ያሉ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ብቻ ሳይሆኑ በርካታ አገራት የሚኖሩ የመስኩ ሰዎች ተቸግረዋል። የሌይስተር ዩኒቨርሲቲዋ ቲላ ሳንደርስ፤ መንግሥት ሕጋዊ ወረቀት ላላቸው እንጂ ኢ-መደበኛ ሥራ ለሚሠሩ ድጎማ ሊያደርግ አልፈቀደም ስትል ትሞግታለች። ችጋር ያንገበገባቸው በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ፤ እንዲሁም የመብት ተሟጋቾች መንግሥታት ኢ-መደበኛ ሥራ ላላቸው ዜጎቻቸው እንዲያስቡ እየሞገቱ ይገኛሉ። ላስ ቬጋስ ውስጥ የሚገኙ በወሲብ ንግድ ላይ ተሰማሩ ሰዎች 19,300 ዶላር መሰብሰብ ችለዋል። ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ማለት ነው። ጣልያን ውስጥ ደግሞ በወሲብ ንግድ ለሚተዳደሩ የተሰበሰበው ዩሮ 21,700 ደርሷል [820 ሺህ ብር እንደማለት ነው]። አንዳንዶች ግን ጤናቸውን አደጋ ላይ ጥለው እየሠሩ ነው። አልፎም ከቤታቸው ውጪ ከተያዙ የገንዘብ ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል። እንግሊዝ ውስጥ ያሉ በርካታ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ሴቶች የልጅ እናት ናቸው ትላለች የመብት ተሟጋቿ ኒኪ አዳምስ። ይህ የአውሮፓና አሜሪካ እውነታ ነው። እያደጉ ያሉ በሚባሉ አገራት ብዙዎች ኑሯቸውን በወሲብ ንግድ ይገፋሉ። አልፎም ቤተሰብ ያስተዳድራሉ። ዱዋላቲዳ የተሰኘው ባንግላዴሽ ውስጥ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ በብዛት የሚኖሩበት መንደር በፖሊስ እየተጠበቁ ነው። መውጣትም ሆነ መግባት ከባድ ሆኗል። መንደሩ በዓለም በወሲብ ንግድ ከሚደራባቸው ሥፍራዎች ትልቁ ተደርጎ ይቆጠራል። በውስጡ ቢያንስ 1300 ሴተኛ አዳሪዎችና 400 ሕፃናት እንደሚኖሩበት ይነገራል። መንግሥት ይህን መንደር ሲዘጋ የወሲብ ንግድን ገቢ እንደዘጋ አላስተዋለም የሚሉ በርካቶች ናቸው። በርካቶች ከዚያም ከዚህም በሚያገኙት እርዳታ ነው ኑሯቸውን እየገፉ ያሉት። ትክክለኛ ስሟን ማሳወቅ ያልፈለግችው የሦስት ልጆች እናቷ ናዝማ የምንበላው የለንም፤ ሥራም የለንም ምን እንደሚውጠን አላውቅም ትላለች። ''ምንም እንኳ መሥራት ብፈልግም ቫይረሱ ቢይዘኝስ የሚለው ጭንቀት ሊገለኝ ነው።'' በዓለም ደረጃ የወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ትልቁ ፈተና የጤና ኢንሹራንስ አለመኖር ነው። በተለይ ደግሞ ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች የጤና ኢንሹራንስ ከሌላቸው ፈተናው ይልቃል። የዘመኑ ፈተና በወሲብ ንግድ ላይ በተሰማሩት ሰዎች ላይ ይበልጥ እንዲከብድ የሚያደርገው ንግዱ ለማንሰራራት ገና ብዙ ይቀረዋል መባሉ ነው። ወረርሽኙ ተረጋግቶ ሰዎች ወደ ቀድሞ ኑሯቸው ቢመለሱ እንኳ እምነት ላይኖራቸው ስለሚችል ሴተኛ አዳሪዎችን ላይጎበኙ ይችላሉ።
44464599
https://www.bbc.com/amharic/44464599
የአቢሲኒያ ባንክ የዝርፊያ ድራማ
ለአቶ አንተነህ ረዳኢ ትናንት አመሻሽ ልክ እንደወትሮው ሁሉ የተለመደ ምሸት ነበር። ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ ሻይ ቡና ለማለት ቦሌ መድሀኒያለም ጀርባ በሚገኘው አቢሲኒያ ኮፊ ፊት ለፊት የያዙትን መኪና አቁመው የሚጠጡትን ይዘው መጫወት ጀመሩ።
ይህን ጊዜ አንድ ቪትዝ መኪና መጥታ ከእነርሱ መኪና ጋር በኃይል ተላተመች። ግጭቱን ያደረሰው መኪና ለማምለጥ ሲሞክር ተሯሩጠው ለማስቆም ይሞክራሉ። በአቅራቢያውም ፓርኪን የሚሰራ ልጅ ስለነበር እንዲያስቆምላቸው እንደነገሩት አቶ አንተነህ ያስታውሳል። "መኪናዋ መሄድ ከነበረባት በተቃራኒው አቅጣጫ ነበር የመጣችው" የሚለው አቶ አንተነህ በግጭቱ ምክንያት በአግባቡ መሄድ ስላልቻለች ከሃምሳ ሜትር በኋላ እንደቆመች ይናገራል። ቀጥሎም ሾፌሩም በፍጥነት በመውረድ ወደፊት መሮጥ ይጀምራል፤ ጋቢና ከሾፌሩ ጋር የነበረው ሌላኛው ተሳፋሪም ሾፌሩ ወደ ሄደበት አቅጣጫ ተከትሎ ይሮጣል። " በወቅቱ በሾፌሩ እና በእኔ መካከል የነበረው ክፍተት በግምት አምስት ሜትር ያህል ብቻ ነበር" ይላል አቶ አንተነህ ስለ ሁኔታው ሲያስረዳ። "የአካባቢው ማህበረሰብ 'ያዘው ያዘው' እያለ መጮህ ጀመረ" የሚለው አቶ አንተነህ ይህን ጊዜ ከመኪናዋ የኋላ በር ጥቁር ሌዘር የለበሰ ግለሰብ በእጁ ጩቤ ይዞ ወጣ ይላል። "የአካባቢው ማህበረሰብ ሰውየው በያዘው ጩቤ ሳይደናገጥ ግለሰቡን በመጣል መደብደብ ጀመረ" የሚለው አቶ አንተነህ ይህ ሁሉ ሲሆን መኪና ገጭተው ለማምለጥ የሚሞክሩ እንጂ ባንክ የዘረፉ እንደሆነ ማንም አላወቀም ነበር ይላል። እነ አንተነህ ዘግይተው ነው ግጭቱን ያደረሰችው መኪና ውስጥ በማዳበሪያ የተዘረፈ ብር እንዳለ ያወቁት። በአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ትናንት ማታ 12፡30 ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሦስት ቦሌ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ከሚገኘው የአቢሲኒያ ባንክ ቴሌ መድሃኒያለም ቅርንጫፍ 5 ሚሊየን ስድስት መቶ ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ስድስት ብር ከ 73 ሳንቲም ተዘርፎ በፖሊስ እና በአካባቢው ማህበረሰብ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ዘረፋው የተፈፀመው የድርጅቱ የጥበቃ ሰራተኛ ከነበሩት ግለሰብ ጋር ሌሎች ሁለት ግለሰቦች አብረው እንደሆነ ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል። በአሁን ሰዓት ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው አጠቃላይ የተወሰደው ገንዘብ ተመልሷል ያሉ ሲሆን በቀጣይ ሌላ የጠፋ ንብረት ካለ እና ሌሎች ተሳታፊዎች ካሉ በምርመራ የሚታወቅ ይሆናል ብለዋል። የአቢሲኒያ ባንክ የማርኬቲንግ፣ የኮሙኑኬሽንና ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አስቻለው ታምሩ በበኩላቸው የዘረፋ ሙከራው የተፈፀመው መኪና ይዘው በመደራጀት መሆኑን እና የተወሰደው ብር ሙሉ በሙሉ መመለሱን ለቢቢሲ ገልፀዋል። እንዲሁም ዛሬ ማለዳ በወንጀሉ ላይ ተሳትፎ ነበራቸው በሚል የተጠረጠሩ ሌሎች ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነግረውናል። በአሁኑ ሰዓት ቅርንጫፉ ሙሉ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሆንም አክለው ተናግረዋል።
news-53900408
https://www.bbc.com/amharic/news-53900408
ኮሮናቫይረስ ፡ ደቡብ ኮሪያ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው እንዲዘጉ አዘዘች
ደቡብ ኮሪያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በዋና ከተማ ሴኡል የሚገኙ መዋዕለ ሕጻናትን ጨምሮ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በአስቸኳይ እንዲዘጉ አዘዘች።
በቅርብ ቀናት ውስጥ በዋና ከተማዋ እና በከተማዋ ዙርያ የኮሮናቫይረስ ማገርሸቱን ተከትሎ ነው ባለሥልጣናቱ እዚህ አስቸኳይ ውሳኔ ላይ የደረሱት። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ 200 የሚሆኑ መምህራንና ተማሪዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘው ተገኝተዋል። በዚህም የተነሳ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እስከ መስከረም 11 ድረስ ትምህርት የመስጠቱ ሂደት በርቀት እንዲቀጥል የደቡብ ኮሪያ የትምህርት ሚኒስቴር ቁርጥ ውሳኔ ላይ ደርሷል። የጤና ጥበቃ ባለሥልጣናት በመላው አገሪቱ ወረርሽኙ መልሶ እንዳያገረሽ ስጋት አላቸው። ዋና ከተማዋ ሴኡል 25 ሚሊዮን ሕዝብ ይኖርባታል። በርካታ ትምህርት ቤቶች በከተማዋ የሚገኙ ሲሆን ሁሉ ተማሪዎች ታዲያ ከቤት ሆነው በበይነ መረብ ትምህርታቸውን ይከታተሉ ተብለዋል። ይህ መዋዕለ ሕጻናት ያሉትንም ይጨምራል ተብሏል። በዚህ ግዴታ ውስጥ ያልተካተቱት በታኅሣሥ ወር የዩኒቨርስቲ የመግቢያ ፈተና የሚወስዱት ብቻ ናቸው። ከእነዚህ በተጨማሪ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ተከታታዮችና በአንድ ትምህርት ቤት ከ60 ተማሪዎች በታች ያሏቸው፤ ይህንን መመርያ እንዲከተሉ አይገደዱም። አብዛኛዎቹ የደቡብ ኮሪያ ትምህርት ቤቶች በድጋሚ የተከፈቱት ባለፉት የግንቦትና የሰኔ ወራት ሲሆን ይህም በሽታውን በተገቢው ሁኔታ መቆጣጠር በመቻሉ የሆነ ነበር።. ደቡብ ኮሪያ እስካሁን በኮቪድ-19 ከ20ሺህ የሚያንሱ ሰዎች ነው የተያዙባት። በሞት ያጣቻቸው ዜጎቿ ደግሞ 310 ብቻ ናቸው። አገሪቱ ቫይረሱን በመቆጣጠር ረገድ ያሳየችው ስኬታማነት ተምሳሌት ሆኖ ሲነገርላት ቆይቷል። ሆኖም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በሽታው ማገርሸቱ አዲስ ስጋት ደቅኖባታል። ባለፈው ማክሰኞ ዕለት ብቻ 280 ሰዎች ተህዋሲው እንዳለባቸው ተረጋግጧል። ለብዙ ጊዜያት በአገሪቱ በተህዋሲው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሳይበልጥ ቆይቶ ነበር። ብዙዎቹ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ፍተሻ ሲደረግላቸው ለበሽታው የተጋለጡት ከተሳተፉባቸው የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ እንደሆነ ተደርሶበታል። ከሳምንት በፊት በሴኡል ከተማ ውስጥ የአንድ የጴንጤ ቆስጤ ቤተክርስቲያን አባላት ተሰባስበው ከተበተኑ በኋላ በዚያ መንፈሳዊ ጸሎት ላይ የታደሙ በርካቶች በበሽታው መያዛቸው ተነግሯል።
news-48687916
https://www.bbc.com/amharic/news-48687916
በኢትዮጵያ የኮሌራ ወረርሽኝ አሳሳቢ በመሆኑ ክትባት መሰጠት ተጀመረ
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ600 በላይ መድረሱን ተከትሎ የኮሌራ ክትባት መሰጠት ተጀምሯል።
ክትባቱ የሚሰጠው ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው ተብለው ለሚታሰቡ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ አረጋውያን፣ የህፃናትና ወጣቶች ማገገሚያ ማዕከላት የሚኖሩ ሰዎች መሰጠት እንደተጀመረ የጤና ጥበቃና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጿል። ኮሌራ ምንድን ነው? የኮሌራበሽታ የሚተላለፈው ኮሌራ ቪብሮ ኮሌሬ በተባለ ባክቴሪያ ሲሆን የተበከሉ ምግቦችንና መጠጦች በመመገብና በመጠጣት የሚከሰት ነው። በባክቴሪያው በተበከሉ ምግቦችና መጠጦች በቀላሉ በሽታው ይተላለፋል። በተለይ በባክቴሪያው የተጠቃ ሰው አይነ ምድር፣ ምግብንና ውሃን በቀላሉ ይበክላል። • ፈር ቀዳጅ የታይፎይድ ክትባት ተገኘ • ክትባት ከየት ተነስቶ የት ደረሰ? ባክቴሪያው ወደ ሰውነት ከገባ በኋላ አስፈላጊው ሕክምና በአስቸኳይ ካልተደረገ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከትን በማስከተል፤ ከፍተኛ ፈሳሽን ከሰውነታችን እንዲወጣ በማድረግ እስከሞት የሚያደርስ በሽታ ነው። ምልክቶቹ አብዛኞቹ በኮሌራ ባክቴሪያ የተጠቁ ሰዎች የበሽታው ምልክቶች ላይታይባቸው ይችላል። ሌሎቹ ግን አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ያጋጥማቸዋል። በዚህም ሳቢያ ከፍተኛ መጠን ያለው የሰውነት ፈሳሽ ስለሚያወጡ ክፉኛ ይዳከማሉ። በተጨማሪም ክንድና እግሮች ላይ ሕመም እንዲሁም የሆድ ቁርጠት ያጋጥማል። • ሰዎች በክትባት ላይ ያላቸው እምነት ቀንሷል በሽታውን ለመከላከል ንጽህንው የተጠበቀ ውሃ መጠቀም ለማንኛው አገልግሎት በተቻለ መጠን ንጽህናው የተጠበቀ ውሃ መጠቀም ዋነኛው የበሽታው መከላከያ መንገድ ነው። የታሸገ፣ ፈልቶ የቀዘቀዘና አስተማማኝ የውሃ ማከሚያ መድሃኒቶችን መጠቀም ተገቢ ነው። እጅን አዘውትሮ መታጠብ ምግብ በማዘጋጀት ጊዜ፣ ምግብ ከመመገብ በፊት፣ ሕጻናትን ከመመገብ በፊት፣ መጸዳጃ ቤት መልስ፣ የሕጻን ልጅዎን ካጸዳዱ በኋላና በተቅማጥ የተጠቃ ሰውን እርዳታ ካደረጉ በኋላ እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል። በተገቢ ቦታዎች መጸዳዳት ዘወትር መጸዳቻ ቤት መጠቀም፤ የመጸዳጃ ቤት በሌለባቸው ቦታዎች ከወንዞችና ከመሰል የውሀ አካላት በመራቅ ለመጸዳጃነት በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ መጸዳዳት። ምግቦች ላይ መጠንቀቅ ወረርሽኝ ባለባቸው አካባቢዎች ምግቦችን አብስሎ ሳይቀዘቅዙ መመገብ የሚመከር ሲሆን እንዲሁም ምግቦችን ከተመገቡ በኋላም ሆነ ከመመገብዎ በፊት ሸፍኖ ማስቀጥ ይመከራል። በተጨማሪም አትክልትና ፍራፍሬዎችን በሚገባ አጥቦና ልጦ በመመገብ ራስን ከኮሌራ መከላከል ይቻላል። በጥሬው የሚበሉ ምግቦችን አለመመገብ ሁል ጊዜም የሚመከር ጉዳይ ነው። ንጽሕናን መጠበቅ በቤት ውስጥ የምግብ ማብሰያና የመታጠቢያ ቤቶችን ንጽህና በአግባቡ መጠበቅ፣ የመጠጥ ውሃ የሚቀመጥባቸውና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ንጽህና መቆጣጠር፣ ቆሻሻን በአግባቡ መያዝና የአካባቢን ንጽህና መጠበቅ በባለሙያዎች ዘወትር የሚመከር አንዱ መከላከያ መንገድ ነው። ክትባት መውሰድ የኮሌራ ክትባት በአፍ በጠብታ መልክ የሚሰጥ ሲሆን አንድ ዓመት ከሆናቸው ህጻናት ጀምሮ መከተብ ይችላሉ። ክትባቱ ለአምስት ዓመታት በሽታውን ለመከላከል ያስችላል።
49037287
https://www.bbc.com/amharic/49037287
በሐዋሳ ለግርግሩ ተጠያቂ የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸው ተገለፀ
ዛሬ ረፋድ ላይ በሐዋሳ ከተማ አለመረጋጋቶች ቢኖሩም አሁን አንፃራዊ መረጋጋት እንዳለ የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ተጠባባቂ ቢሮ ሃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
በሁሉም ከተማይቱ አካባቢ የተፈጥረውን ግጭትና ሁከት ለመቆጣጠር እንደተቻለ ገልፀው ለግርግሩ ተጠያቂ የተባሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጠናከሩንም ጨምረው ተናግረዋል። ግጭቱ የተነሳው ሐምሌ 11፣2011 ዓ.ም የሲዳማ ክልልነት መታወጅና በዞኑ ምክር ቤት ተወስኖ ይፋ መሆን አለበት በማለት በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰንደቅ አላማና ታፔላዎችን መትከል አለብን በሚል ኃሳብ የተነሱ ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመጋጨታቸው እንደሆነ ኃላፊው ይናገራሉ። •ለሲዳማ ክልልነት 'ይሁንታ ተሰጠ' በሚል በርካቶች ደስታቸውን እየገለጹ ነው •በሐዋሳ ውጥረት ነግሷል ተባለ •ስጋት ያጠላበት የሲዳማ የክልልነት ጥያቄና የሀዋሳ ክራሞት በርከት ያሉ ከከተማም ሆነ ከገጠር የመጡ ወጣቶች ወደ ባህላዊ ስፍራ መሰብሰቢያና ሌሎች አካባቢዎች በጥዋት ሲንቀሳቀሱ እንደነበርና በኋላም ስብስቡ እንደጨመረ ይናገራሉ። በተለይም በተለምዶ አቶቴ፣ ዲያስፖራ፣ አዲሱ ገበያና ዶሮ እርባታና በሚባሉ አካባቢዎች ላይ ሰፋ ያለ ግጭት ነበር ይላሉ። የፌደራል ፖሊስ፣ መከላከያ፣ የክልሉ ኃይልና እንዲሁም መደበኛ ፖሊስ በጋራ በመቀናጀት እነዚህ አካባቢዎች ላይ እንደተረባረበ ገልፀው በተለይም የመንገድ መዝጋት ስራዎች በስፋት እንዳይቀጥሉ እንደተሰራም ኃላፊው አስረድተዋል። በዚህም ውስጥ ለውስጥ ባሉ መንገዶች ላይ ጎማ የማቃጠል መንገድ የመዝጋት ስራዎችም ቢኖሩም አሁን መንገዱን የመክፈት ስራም እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል። አንዳንድ የአይን እማኞች የተኩስ ልውውጥ ነበረ ቢሉም ኃላፊው በበኩላቸው "ከተኩስ በመለስ በትዕግስት ሰራዊቱ ይሄንን ግርግርና ግጭት ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ ነው እስካሁን የቆየው፤ በዚህ ቦታ ላይ የተፈጠረ ተኩስ አለ የሚል ሪፖርት የለንም። " ብለዋል። ዝርዝሩ በቀጣይ ቀናት የሚታወቅ ይሆናል በማለት "በተጨባጭ ግን በአብዛኛው ሊባል በሚችል ሁኔታ ወደ ከፋ እርምጃ ሳይሄዱ የተሰበሰቡና ግርግር የሚፈጥሩ ኃይሎችን ለመበተን ጥንቃቄ በተሞላ ሁኔታ ተሰርቷል" ብለዋል። የተገደለ ሰው እንዲሁም በአካባቢው የቆሰሉ ሰዎች አሉ ቢባልም ኃላፊው እስካሁን ባለው ምርመራ የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ ገልፀው ነገር ግን "በርካታ ግጭቶች ስለነበሩ መቁሰል ሊኖር ይችላል" ብለዋል። ዝርዝሩ በቀጣይ ምርምር እንደሚገለፅ ተናግረዋል።
news-52629906
https://www.bbc.com/amharic/news-52629906
ከኮሮናቫይረስ የትኞቹ ድርጅቶች አተረፉ? እነማንስ ከሰሩ?
ኮሮናቫይረስ በርካታ የንግድ ዘርፎችን አሽመድምዷል። በተቃራኒው ቀን የወጣላቸው የቴክኖሎጂ ዘርፎችም አሉ። ለመሆኑ የበሽታውን ሥርጭት ተከትሎ የትኞቹ ድርጅቶች አተረፉ? እነማንስ ከሰሩ?
ትርፋማ ድርጅቶች 1. ዙም ኮቪድ-19 ብዙዎች ከቤታቸው እንዲሠሩ ምክንያት ሆኗል። እርስ በእርስ በቪድዮ የሚያገናኘው ዙም ታድያ ገበያ ደርቶለታል። በአንድ ቀን ተጠቃሚዎቹ ከ10 ሚሊዮን ወደ 200 ሚሊዮን ከፍ ብለዋል። • አቅመ ደካሞችን እያማለለ የሚገኘው የማፊያዎች ገንዘብ • "የቱሪዝም እንቅስቃሴው ልክ መብራትን የማጥፋት ያህል በቅጽበት ቆሟል" በተመሳሳይ ሁኔታ የማይክሮሶፍት ተጠቃሚዎችም ጨምረዋል። ካለፈው ወር ወዲህ 44 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያገኘ ሲሆን፤ ይህም ቀድሞ ከነበረው 40 በመቶ እድገት አሳይቷል። ‘ቲምቪወር’ የተባለው መተጋበሪያም እንደ ዙም እና ማይክሮሶፍት ትርፋማ ሆኗል። 2. ‘ጌም’ እንቅስቃሴ መገደቡን ተከትሎ የድረ ገፅ ጨዋታ (ኦንላየን ጌሚንግ) የብዙዎች ጊዜ ማሳለፊያ ከሆነ ሰነባብቷል። ለምሳሌ ከድሮውም ተወዳጅ የነበረውን ‘ኮል ኦፍ ዲውቲ’ ወደ አስር ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ይጫወቱታል። ተንታኞች እንደሚሉት የ ‘ጌም’ ዓመታዊ ሽያጭ 35 በመቶ አድጓል። ሆኖም ግን አዳዲስ ጨዋታዎች እየተመረቱ አይደለም። ተቋማቱ ሥራ ማቆማቸው በቀጣዩ ዓመት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራልም ተብሏል። 3. ኔትፍሊክስ ሲኒማ ቤቶች ዝግ ስለሆኑ፤ ብዙ ፊልሞች በድረ ገፅ እየታዩ ነው። ስለዚህም ፊልም የሚያሰራጩ ድረ ገፆች ካለፉት ዓመታት በላቀ በርካታ ተከታዮች ያፈሩት በዘመነ ኮሮናቫይረስ ነው። ለምሳሌ ኔትፍሊክስ 16 ሚሊዮን አዳዲስ ተከታዮች አግኝቷል። ኔትፍሊክስን በዋነኛነት የሚፎካከረው 'ዲዝኒ ፕላስም' ትርፉ ጨምሯል። ሌላው አትራፊ 'ስፖቲፋይ' ተከታዮቹ 130 ሚሊዮን ደርሰዋል። 4. ክላስፓስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከናወኛ (ጂም) መዘጋቱ፤ ሰዎች ፊታቸውን ወደ ድረ ገፅ እንዲያዞሩም አስገድዷል። እንደ 'ክላስፓስ' ያሉ በድረ ገፅ ስፖርት የሚያሠሩ በከፍተኛ ደረጃ ተፈላጊ ሆነዋል። 'ፔሎቶን' የተባለው ገፅ የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ከሚያሳዩ አንዱ ነው። ምንም እንኳን ስቱድዮው በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ቢዘጋም፤ ትርፉ ከ60 በመቶ ዘሏል። • የቻይናና የአፍሪካ ግንኙነት በኮሮና ዘመን ምን ድረስ ይዘልቃል? • በኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነታቸው የጨመረ 6 ምርቶች በድረ ገፅ በሚተላለፉ ስፓርቶች ተጠቃሚ የሆኑት ትልልቅ ተቋሞች ብቻ አይደሉም። ዩ ቲዩብ ላይ ቤት ውስጥ የሚሠሩ ስፖርቶች የሚያስተምሩ ግለሰቦችም ስኬታማ እየሆኑ ነው። ከነዚህ አንዱ ጆ ዊክስ ሲሆን፤ በዩ ቲውብ የቀጥታ ሥርጭት ተከታዮች ብዛት የዓለምን ክብረ ወሰን ሰብሯል። 5. አማዞን የድረ ገፅ መገበያያው አማዞን ከፍተኛ ገቢ እያካበተ ነው። ሆኖም ግን ተቀጣሪዎቹን ከኮቪድ-19 ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረገ ባለመሆኑ ይተቻል። ከሠራተኞች ደህንነት ጋር በተያያዘ የቀረቡ ቅሬታዎች እስኪጣሩ ፈረንሳይ መሠረታዊ ያልሆኑ የአማዞን ግዢዎችን አግዳለች። የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ ገቢውን በ24 ቢሊዮን አሳድጓል። የከሰሩ ተቋሞች 1. የመጓጓዣ ዘርፍ የበረራ ዘርፍ እንዲሁም የመኪና ሽያጭም በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁሏል። ዩናይትድ ኪንግደምን እንደ ምሳሌ ብንወስድ የመኪና ሽያጭ ከ1946 ወዲህ ሲቀንስ የመጀመሪያው ነው። በሌላ በኩል 'ኡበር' የተሰኘው የታክሲ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቹን አሰናብቷል። 2. የቴክኖሎጂ ውጤቶች አሻሻጮች ባያመርቱም ሻጭና ገዢን የሚያገናኙ አካላት በዚህ ወቅት ሥራ ፈተዋል። በተለይም በቴክኖሎጂ ውጤቶች ለሸማቾች አገልግሎት ያቀርቡ የነበሩ ተቋሞች በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ንግዳቸው ተቀዛቅዟል። ትርፍ የመኝታ ክፍል ያላቸው ሰዎች በድረ ገፅ ለኪራይ የሚያቀርቡበት 'ኤርቢኤንቢ' ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ይጠቀሳል። 1,900 ሠራተኞቹንም አሰናብቷል። አሁን ላይ ምግብ ቤቶች እንዲሁም መሥሪያ ቤቶችም እንደ ቀድሞው እየሠሩ አይደለም። ስለ ምግብ ቤቶችና ሌሎችም አገልግሎት ሰጪዎች አስተያየት እየሰበሰቡ ለተጠቃሚዎች ከሚያቀርቡ ድረ ገፆች አንዱ የሆነው 'የልፕ' አንድ ሦስተኛ የሚሆኑ ሠራተኞቹን አጥቷል። 'ዊወርክ' የሚባለው ቢሮ ተከራይና አከራይ አገናኝም ኪሳራ ውስጥ ገብቷል።
44105462
https://www.bbc.com/amharic/44105462
አንድ በሞቴ!
ባሳለፈነው ቅዳሜ በጊዮን ሆቴል ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ተሰባስበው በሙዚቃ ድግስ ላይ ተጎራርሰዋል።
አዘጋጆቹ ክስተቱ ቋሚ የጉርሻ ቀን ሆኖ እንዲሰየም ይፋልጋሉ። በኢትዮጰያ የማይቋረጥ ዓመታዊ የመጎራረስ ፌስቲቫል እንዲኖር ያልማሉ። ከፍ ሲልም ጉርሻን በማይዳሰስ ቅርስነት የማስመዝገብ የረዥም ጊዜ ትልምን ሰንቀዋል። 5 ሺህ ጉርሻዎች! በቅዳሜው ኩነት ላይ 5ሺ ሰዎችን በማሳተፍ በጊነስ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በተለያየ ምክንያቶች ሳይሳካ ቀርቷል። በፕሮግራሙ ላይ ወደ 1700 የሚጠጉ ሰዎች ተገኘተው እንደነበር አስተናጋጆቹ ተናግረዋል። ከአዘጋጆቹ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ አብረሃም "እንደ ጉርሻ ግን የሚያግባባን የለም. . . ጉርሻ እኮ አንዱ ለሌላው የማጉረስ ተግባር ብቻ አይደለም፤ በተጠቀለለው እንጀራ ውስጥ ፍቅር አለ፣ መተሳሰብ አለ፣ አክብሮት አለ።" ሲል ከዝግጅቱ በፊት ተናግሮ ነበር። 5 ሺህ ጉርሻዎች!
news-49310396
https://www.bbc.com/amharic/news-49310396
የጣልያኑ ምክትል ጠ/ሚ እና የሆሊውዱ ተዋናይ በስደተኞች ጉዳዩ ተጋጭተዋል
የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሆሊውዱ ተዋናይ ሪቻርድ ጊር በስደተኞች ምክንያት ግጭት ውስጥ ገብተዋል።
ሪቻርድ ጊር፤ የጣልያኑ ጠቅላይ ምክትል ሚኒስትር ማቴዎ ሳልቪኒን ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር አመሳስሎ ሲታቸቸው ተሰምቷል ተዋናዩ ሪቻርድ ጊር የጣልያን መንግሥት ሜድትራኒያን ባሕር ላይ አንዲት መርከብ ውስጥ ታሽገው የሚገኙ ስደተኞችን ጉዳይ አንድ እንዲለው አሳስቧል። 160 ስደተኞች፤ አንዲት የስፔን የእርዳታ መርከብ ውስጥ እንዳሉ ሜድትራኒያን ባሕር ላይ ከአንድ ሳምንት በላይ እንዳስቆጠሩ መነገር ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል። • በቱኒዚያ የ48 ስደተኞች ሕይወት አለፈ የጣልያን መንግሥት 'ሰዎችን ከሰው በታች ማየት ማቆም አለበት' ሲል ነው ተዋናዩ ወቀሳውን ያሰማው። ተዋናዩ በጣልያን መንግሥት መልሕቅ መጣያ የተከለከለችውን መርከብ ሄዶ መጎብኘት ችሏል። የጣልያኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማቴዎ ሳልቪኒ፤ ተዋናዩ ካሻው ስደተኞቹን ወደ ሆሊውድ ይዟቸው ሊሄድ ይችላል ሲል ምላሽ ሰጥተዋል። ሪቻርድ ጊር፤ ስደተኞች ወደሃገራቸው እንዳይገቡ ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩት የጣልያኑ ጠቅላይ ምክትል ሚኒስትር ማቴዎ ሳልቪኒን ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር አመሳስሎ ሲተቻቸው ተሰምቷል። • በሊቢያ የባህር ዳርቻ ስደተኞች ሰጠሙ የጣልያኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማቴዎ ሳልቪኒ «ይህ ስደተኞችን ከሰው በታች አድርጎ የማየት ጉዳይ መቆም አለበት። ደሞ ይቁም የምንል ከሆነ መቆሙ አይቀርም» ሲል ነው የሆሊውዱ ሰው ድጋፉን ለስደተኞች የሰጠው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ለመስጠት ብዙም አልዘገዩም። «ይህ ለጋስ ሚሊዬነር ለስደተኞች ድጋፍ ማድረጉ እንዳው የሚያስመሰግነው ነው። ቢቻለው 160ዎቹን ስደተኞች በግል አውሮፕላኑ ወደ ሆሊውድ ወስዶ በልጥጥ መኖሪያ ቤቱ ቢያኖራቸው ደግሞ እጅግ መልካም ነው። እናመሰግንሃለን ሪቻርድ!» ሳልቪኒ ስደተኞችን ይዘው ወደ ጣልያን ወደብ የሚመጡ የእርዳታ መርከቦች ላይ እገዳ እንዲጣል ከጊዜ ጊዜ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። • ቬኔዝዌላውያን ወደ ፔሩ ድንበር እየተመሙ ነው
53509807
https://www.bbc.com/amharic/53509807
ጆርጅ ፍሎይድን በመግደል የተጠረጠረው ዴሪክ ሾቪን በታክስ ወንጀል ተከሰሰ
ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድን በመግደል የተጠረጠረው የቀድሞው የሚኒያፖሊስ የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ሾቪን በታክስ ወረራ ወንጀል ተከሰሰ።
የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ሾቪን በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ተወንጅሎ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ነው የሚገኘው ዴሪክ ሾቪን እና ባለቤቱ 38 ሺህ ዶላር ለሚኒሶታ ግዛት መገበር ሲገባቸው ይህን አላደረጉም ተብለው ነው የተከሰሱት። ሾቪን ከሥራው የተባረረው ጆርጅ ፍሎይድ ላይ በፈፀመው ድርጊት ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ግድያ ወንጀል ተከሷል። በድርጊቱ ተባባሪ ነበሩ የተባሉ ሌሎች ሶስት መኮንኖችም ክስ ተከፍቶባቸዋል። ሾቪን እና አብራው የማትኖረው ሚስቱ ኬሊ በስድስት የተለያየ ወንጀሎች ተጠርጥረው ነው የተከሰሱት። ሁሉም ክሶች ከታክስ ማጭበርበር ጋር የተያያዙ ናቸው። ጠንዶቹ፤ በአውሮፓውያኑ ከ2014 እስከ 2019 ባለው ካስገቡት 464 ሺህ 433 ዶላር የሚገባውን ግብር አልከፈሉም ተብለዋል። ተጠርጣሪው ከመደበኛ ሥራው ውጪ ቅዳሜና እሁድ በጥበቃ ሥራ ተሠማርቶ ካስገባው ገቢ ላይ ጭምር ለመንግሥት አልገበረም ተብሏል። አቃቤ ሕግ ኢምራን አሊ ለአሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል እንዳስታወቁት ተጠርጣሪዎቹ ያልከፈሉት ግብር መጠን ምርመራው ሲጠናከር ሊጨምር ይችላል። ዴሪክ ሾቪን በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ነው የሚገኘው። ነገር ግን ባለቤቱ ኬሊ እስካሁን በቁጥጥር ሥር እንዳልዋለች ታውቋል። የቀድሞው የሚኒሶታ የቁንጅና ውድድር አሸናፊ የነበረችው ሚስት ወ/ሮ ኬሊ፤ ባለቤቷ ጆርጅ ፍሎይድን በመግደል ከተወነጀለ በኋላ ፍቺ ጠይቃለች። የዋሽንግተን ክፍለ ግዛት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፒት ኦርፑት ባወጡት መግለጫ «ግብር አለመክፈል ማለት ከሚኒሶታ ነዋሪዎች ኪስ ገንዘብ መመንተፍ ማለት ነው» ሲሉ ተደምጠዋል። «አቃቤ ሕግ ብትሆኑ፣ ፖሊስ አሊያም ዶክተር ወይም መኖሪያ ቤት አሻሻጭ፤ ከሕግ በላይ አይደላችሁም» የሚል ማስጠንቀቂያም ሰጥተዋል። የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ አንገት ላይ ለዘጠኝ ደቂቃዎች በጉልበቱ ቆሞ የሚያሳይ ምስል ከወጣ በኋላ በአሜሪካና በሌሎች ክፍለ ዓለማት ፀረ-ዘረኝነት ተቃውሞ ተቀስቅሷል።
45937027
https://www.bbc.com/amharic/45937027
በአላማጣ የማንነት ጥያቄ ባነሱ ወጣቶችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰዎች ህይወት ጠፋ
ትናንት በአላማጣ ከተማ በታጠቀ የልዩ ኃይልና በወጣቶች መካከል በተፈጠረው ግጭት አምስት ግለሰቦች በጥይት ተመትተው መሞታቸው የዓይን እማኞች ተናገሩ።
ከጥቂት ወራት በፊት ጀምሮ የአላማጣ ከተማ ወጣቶች የማንነት ጥያቄዎችን እንደሚያነሱ የከተማው ነዋሪዎች ይናገራሉ። አቶ ዝናቡ ማርፌ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ትናንት በከተማዋ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ተሳታፊ ነበሩ። በስልፉ ወቅት ድብደባ ተፈጽሞብኛል የሚሉት አቶ ዝናቡ ''ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ የከተማዋ ወጣቶች ወረቀት በመበተን ሰላማዊ ሰልፎችን ለማካሄድ ጥረቶችን ያደርጉ ነበር። ለውጡን እንደግፋለን የሚሉ ከነቴራዎችን ያደርጋሉ በእነዚህ ተግባሮቻቸውም ይታሰራሉ ከዚያም ይፈታሉ። የትናንቱ ግን አስከፊ ነበር'' በማለት የትናንቱን ክስተት ያብራራሉ። • በመጨረሻም ጀማል ኻሾጂ መገደሉን ሳዑዲ አመነች • በዝምታ የምትጠማ ከተማ -ሐረር • አርፋጁ ተማሪ መምህሩ ላይ ሽጉጥ ደቀነ ትናንት የእጅ ኳስ ሜዳ ላይ በተጀመረ የተቃውሞ ሰልፍ ለበርካቶች የህይወት መጥፍት እና የአካል ጉዳት ምክንያት ሆኗል። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ መሰብሰብ አትችሉም የተባሉት የከተማዋ ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ተጋጭተዋል። ሌላው ለደህንነቱ ሲል ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የከተማዋ ነዋሪ በትናንቱ ግጭት በጥይት ታፋው ላይ ተመትቷል። ''በጥይት የተመታን ልጅ ለማንሳት ስሄድ እኔም ተመታሁኝ'' ይላል። ''በጥይት መመታቴን እንኳ አልታወቀኝም ነበር። አጠገቤ ያሉ ሰዎች ናቸው ስሜን እየጠሩ በጥይት መመታቴን የነገሩኝ። አንገቴ ላይ ደም ስመለከት አንገቴን የተመታሁ መስሎኝ ነበር። አንገቴ ላይ የነበረው ደም ግን የሟቹ ልጅ ነበር'' በማለት ሁኔታውን ያስረዳል። ይህ ወጣት ትናንት ወደ የእጅ ኳስ ሜዳው ተሰባሰበው በሄዱበት ወቅት እንዲበተኑ በመደረጉ በተፈጠረ ግጭት ጉዳቱ መድረሱን ያስረዳል። ''የሆነ ነገር ያደርጉኛል ብዬ ስለሰጋሁ ወደ የግል ሕክምና እንጂ ሆስፒታል አልሄድኩም። አሁንም የምገኘው በመኖሪያ ቤቴ ነው'' ይላል። የአላማጣ ከተማ ነዋሪው አቶ ዝናቡ እንደሚሉት የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በቦታው ቢደርሱም የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ግን ተስኗቸዋል ይላሉ። ''የልዩ ኃይሉ የሚፈጽመውን ጥቃት እንዲያስቆሙ ስንጠይቃቸው 'የተዘጋውን መንገድ ብቻ ነው የምናስከፍተው' አሉን'' ይላሉ። የተጎጂዎች ቁጥር ከአቶ ዝናቡ ማርፌ እና ከሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሰማነው ከሆነ 5 ሰዎች ተገድለዋል 15 የሚሆኑ ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። እንዲሁም ከ50 ባለይ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል። የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አግዜ ህዳሩ በበኩላቸው የሟቾችን ቁጥር 9 የተጎጂዎችን ደግሞ 16 ያደርሱታል። የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ደግሞ በፌስቡክ ገጹ ላይ በአላማጣ ከተማ በማንነት ስም በሚንቀሳቀሱ አካላት እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተከሰተ ግጭት የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል ብሏል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአላማጣ ሆስፒታል ባልደረባ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከሆነ በትናንቱ ግጭት ጉዳት የደረሰባቸው 25 ሰዎች በሆስፒታሉ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ እና አንድ ሰው ደግሞ ባጋጠመው ከፍተኛ ጉዳት ለተጨማሪ ህክምና ወደ መቀሌ መላኩን ነግረውናል። አላማጣ ዛሬ ረፋድ አቶ ዝናቡ እና ሌላ የከተማዋ ነዋሪ እንደሚሉት ከሆነ ዛሬ እስከ ረፋድ ድረስ አላማጣ ውስጥ መንገድ ዝግ ነው። የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት መንገድ ለማስከፍት ጥረት እያድጉ ነው። ትናንት ከተገደሉት 5 ሰዎች የሁለቱ ሰኞ ጠዋት አላማጣ እየሱስ ቤተ ክርስቲያን የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ተፈጽሟል። ''የሟቾች ሰውነት በከፍተኛ ሁኔታ የተበጣጠሰ ስለሆነ በጠዋት ነው የተቀበሩት'' ሲሉ አቶ ዝናቡ ነግረውናል። ከሟቾቹ መካከል የሦስቱ ግለሰቦች አስክሬን ከአላማጣ ውጪ ወደ ሆኑ ቦታዎች የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ሊፈጸም አስክሬናቸው ወደ ትውልድ ስፍራቸው መላኩን ከከተማዋ ነዋሪዎች ሰምተናል። • ''ይህን ስላደረገ ነው የተገደለው' ብሎ የሚነግረን እንኳ አላገኘንም'' • ወልዲያ ትናንትም በውጥረት ውስጥ ውላለች የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አግዜ ህዳሩ በበኩላቸው የአካባቢው ህዝብ ላለፉት ሦስት እና አራት ወራት የማንነት ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ያሉ ሲሆን፤ ''የትግራይ ክልል መንግሥት ግን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ልዩ ኃይል ወደ አካባቢው በማስገባት የማንነት ጥያቄውን ለማዳፈን ወጣቶችን በማሸማቀቅ ከፍተኛ የሆነ የሥነ-ልቦና ጫና እያደረገ ነው'' ይላሉ። አቶ አግዜ ጨምረውም ራያ አዘቦ፣ ራያ አላማጣ እና ኦፍላ የማንነት ጥያቄ የሚነሳባቸው ወረዳዎች ናቸው ብለዋል። የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ኮሚኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በበኩሉ በፌስቡክ ገጹ ላይ ''የህዝብን የማንነት ጥያቄ በማስመሰል ሌላ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተደረገ ያለው ሩጫ በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።'' በማለት ተግባሩ ኮንኗል። ''ይህ ሳያንስ የዜጎች ሰላም፣ ፀጥታና ደህንነት ለመጠበቅ ከተሰማራው የፀጥታ መዋቅር ጋር መጋጨትና አነሳስቶ እርምጃ እንዲውስድ መግፋት ደግሞ በፍፁም መደገም የሌለበት ተግባር ነው'' በማለት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ በመግለጫው አትቷል። መግለጫው በዚህ ተግባር ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፉትን አካላት በቸልታ አላልፋቸውም ብሏል። አላማጣ ወረዳን ወክለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ረዳኢ ዝናቡ በበኩላቸው የወረዳው ነዋሪ በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አለበት ካሉ በኋላ "በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት እኛ ማንነታችን ራያ ነው፤ ስለዚህም በራሳችን ሰዎች መተዳደርና መዳኘት አለብን ማለት የጀመረ የህብረተሰብ ክፍል አለ" ብለዋል። በትግራይ ምክር ቤት ውስጥ የወረዳው ህዝብ ተወካይ የሆኑት ወይዘሮ ጃኖ ንጉሰ ደግሞ "እኛ ትግራዋይም አማራም አይደለንም፤ እኛ ራያ ነን የሚሉም አሉ። ይህ ተግባር የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ያለበትን የህብረተሰብ ክፍል ለማጋጨት እየተደረገ ያለ ነገር ነው። እንደዚህ አይነት ጥያቄ በህጋዊ መንገድ መጠየቅ አለበት።" ብለዋል።
news-53291844
https://www.bbc.com/amharic/news-53291844
በጥቁር አሜሪካዊው ሞት ያሾፉ ሦስት ፖሊሶች ከሥራቸው ተባረሩ
በአሜሪካዋ ኮሎራዶ ግዛት አንድ ጥቁር አሜሪካዊ አንገቱ በክንድ ተይዞ ትንፋሽ አጥሮት የሞተበትን አያያዝ በማስመሰል እተሳለቁ ፎቶ የተነሱ ሦስት የፖሊስ አባላት ከሥራቸው መባረራቸው ተገለጸ።
ፖሊሶቹ ለመሳለቅ የተነሱት ፎቶ ሌላ ተጨማሪ የፖሊስ አባል ደግሞ ከጉዳዩ ጋር በተያኣዘ በገዛ ፈቃዱ ከሥራው መልቀቁ የተገለጸ ሲሆን አንድ የአካባቢው ፖሊስ ፎቶ የመነሳት ድርጊቱን ለማሰብ የሚከብድ ነው ብሎታል። ኤላእጃህ ማክሌይን ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ በፖሊስ እንዲቆም ተደርጎ አንገቱ ክፉና በክንድ ታንቆ ከተያዘ በኋላ ነበር ሕይወቱ ያለፈችው። የኤላይጃህ ጉዳይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለ ሕይወቱ ካለፈችው ከጆርጅ ፍሎይድ በኋላ በድጋሚ መነሳት ጀምሯል። ተግባሩን በመጸማቸው ከሥራቸው የተባረሩት የፖሊስ አባላት ጄሰን ሮዘንብላት፣ ኤሪካ ማሬሮ እና ካይል ዲትሪች የሚባሉ የፖሊስ ኃይል አባላት መሆናቸው ታውቋል። አራተኛው የፖሊስ አባል ጃሮን ጆንስ ደግሞ ባሳለፍነው ማክሰኞ ሥራውን ለቋል። የዴንቨር አካባቢ ፖሊስ ጊዜያዊ ኃላፊዋ ቫኔሳ ዊልሰን ምስሎቹን ሰብአዊነትና ሞራል ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው ብለዋል። "በተፈጠረው ነገር በእጅጉ አዝነናል፣ ተቆጭተናል እንዲሁም ተበሳጭተናል" ሲሉም ተደምጠዋል። "ምንም እንኳን ጉዳዩ በወንጀል የማያስቀጣ ቢሆንም ሰብአዊነትን ግን በእጅጉ የጣሰ ነው። አንዲህ አይነቱን ነገር አይደለም ማድረግ ማሰብ በራሱ ከባድ ነው" ብለዋል። የፖሊስ አባላቱ ከተነሷቸው ፎቶዎች መካከል በአንደኛው ላይ አንገቱ የታነቀ ሰው በመምሰል የቆሙ ሲሆን ሦስተኛዋ ፖሊስ ደግሞ ከኋላ ሆና ፈገግ ብላ ትታያለች። በመቀጠል ጄሰን የተባለው የፖሊስ አባል ፎቶውን ከጽሁፍ መልዕክት ጋር የላከው ሲሆን በሳቅ ቃላት ምላሽ ሰጥቷል። ኤላይጃህ ማክሌይን እንዴት ሞተ? ኤላይጃህ ማክሌይን የ24 ዓመት ወጣት የነበረ ሲሆን፤ ከዓመት በፊት አውሮራ ከተማ ውስጥ በእግሩ በመጓዝ ላይ ሳለ ነበር በድንገት ሦስት የፖሊስ አባላት ያስቆሙት። የአካባቢው ዐቃቤ ሕግ እንዳለው ከሆነ የፖሊስ አባላቱ የኤላይጃህ አይነት አካላዊ ቅርጽ ያለው ተጠርጣሪ እየፈለጉ እንደሆነ አስታውቀው ነበር። በሁኔታው የተደናገጠው ኤላይጃህ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር ሊያውሉት ሲሉ ታግሏቸው ነበር። ከዚያም ፖሊሶቹ የጦር መሳሪያ መያዝ አለመያዙን ለመፈተሽ ሲሞክሩ ግብግብ ተፈጠረ። ከፖሊሶቹ ደረት ላይ ያለው ካሜራ ቀርጾ ባስቀረው ምስል ላይ ኤላይጃህ 'ጭንቀት አልችልም በጣም እየተጠጋችሁኝ ነው' ሲል ተደምጧል። በመቀጠል አንደኛው ፖሊስ ሽጉጥ ሊያወጣ ነው በማለት ወደ መሬት ወርውረው፤ አንገቱን ተጭነው ያዙት። ሪፖርቱ እንደሚለው በወቅቱ ኤላይጃህ እራሱን ስቶ ነበር። ከሰመመኑ ሲነቃ በድጋሚ ትግል ያደርጋል፤ ነገር ግን አልተሳካለትም። በወቅቱ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር አልውልም ያለ ሰው አለ በማለት እርዳታ ይጠይቃሉ። ወዲያውም አምቡላንስ መጥቶ ‘ኬታሚን’ የተባለ ማደንዘዣ መድኃኒት ወጉት። በመቀጠል ኤላይጃህ በቃሬዛ ላይ ተደርጎ ወደ አምቡላንሱ እንዲገባ ተደረገ። ወዲያው ግን በቦታው የነበረው የህክምና ባለሙያ ደረቱ አካባቢ ምንም እንቅስቃሴ አለመኖሩን አስተዋለ። እዚያው አምቡላንስ ውስጥም እያለ ሕይወቱ አለፈች። ቤተሰቦቹ እንደሚሉት ፖሊሶች ለ15 ደቂቃዎች ያክል አላስፈላጊ ኃይል በመጠቀም ለሞት አብቅተውታል። በወቅቱም በተደጋጋሚ መተንፈስ እንዳልቻለ ይጮህ ነበር። ሲያስመልሰውም ነበር። ቤተሰቦቹ አክለውም አርፎ ካልተቀመጠ በውሾች እንደሚያስነክሱት ሲዝቱበት ነበር ብለዋል። በአስክሬኑ ላይ በተደረገ ምርመራም የሞቱ መንስኤ ያልታወቀ ተብሎ ተመዝግቧል።
news-52164476
https://www.bbc.com/amharic/news-52164476
በአዲስ አበባ ወታደራዊና የፖሊስ የደንብ ልብሶችን በግለሰብ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው ተያዙ
የተለያዩ ወታደራዊና የፖሊስ የደንብ ልብሶችን ጨምሮ የጦር መሳሪያዎችን በአንድ መጋዘን ውስጥ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ፖሊስ እንዳለው የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ የተለያዩ ክልል ፖሊሶችን የደንብ ልብስ እንዲሁም የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በመጋዘን ውስጥ ተከማችተው ማግኘቱን ገልጿል። በተጨማሪም አንድ ቦንብ፣ አንድ ሽጉጥና ከ250 በላይ ጥይቶች አብሮ መያዙን አመልክቶ እነዚህን ወታደራዊ አልባሳትና መሳሪያዎች "አከማችተው" አገኘኋቸው ያለቸውን አምስት ተጠርጣሪዎችንም ይዞ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ኮሚሽኑ አመልክቷል። • አሜሪካ የጀርመንን የፊት ጭምብል (ማስክ) ‘በመውሰድ’ ተከሰሰች • ወሲብና ኮሮናቫይረስን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች • "ምርጫ ቦርድ የሄደበት መንገድ ትክክል አይደለም" ኦነግ እና ኦፌኮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ከበደ አስፋ እንዳብራሩት እፎይታ የገበያ ማዕከል አካባቢ የሚገኝን መጋዘንን የተከራዩ አንዲት ግለሰብ ከወታደራዊና የፖሊስ አልባሳቱ አርማዎች፣ ቀበቶዎች፣ መለዮችን፣ ጫማዎችን፣ ካቴናዎች እንዲሁም ወታደራዊ የውሃ መያዥ ኮዳዎችን አከማችተው መገኘቱን ገልጸዋል። ኃላፊው በተጨማሪም መጋዘኑን የተከራዩት ግለሰብ ቦታውን ለጫማ ማስቀመጫነት በሚል መሆኑን በምርመራ መረጋገጡን አመልከተው እንዲህ አይነቱን ድርጊት ለመቆጣጠር የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። የወታደርና ፖሊስ የደንብ አላባሳትን እንዲሁም ቁሳቁሶችን ከተፈቀደላቸው አካላት ውጪ ይዞ መገኘት፣ ማከፋፈልና መሸጥ በሕግ የተከለከለ መሆኑን በመጥቀስ በወንጀሉ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የሚደረገው ምርመራ መቀጠሉን ተናግረዋል።
news-46646920
https://www.bbc.com/amharic/news-46646920
'የእሳተ ገሞራ ቱሪዝም'፡ አፍቃሬ እሳተ ገሞራዎች
በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ እየፈነዳ ያለ እሳተ ገሞራን ቀረብ ብለው የመመልከት፣ የፍንዳታ ድምፆቹን የመስማት ከዚህም አልፎ አካባቢው ላይ ተገኝተው ሙቀቱ እንዲሰማቸው የሚፈልጉ አፍቃሬ እሳተ ገሞራ ጎብኚዎች እየበዙ መሆኑ እየተነገረ ነው።
ቢያስደነግጥም እሳተ ገሞራ ያለባቸውን አካባቢዎች በማዘውተር የሚደሰቱት እነዚህ ቱሪስቶች ራሳቸውንም አደጋ ላይ እየጣሉ ፤ የድንገተኛ ህክምና እርዳታ አገልግሎት ላይም ችግር እያስከተሉ ነው እየተባለ ነው። የሚፈነዳ እሳተ ገሞራ ለማየት ጎብኚዎች የሚገሰግሱባት አይስላንድ በነገሩ በጣም ከተቸገሩ አገራት የምትጠቀስ ናት። በአገሪቱ በመፈንዳት ላይ ያሉ እሳተ ገሞራዎችን በቅርበት የመመልከት ፍላጎት በጎብኚዎች ዘንድ ከፍተኛ ነው። ጎብኚዎቹ በዚህ ምን ያህል ራሳቸውን ለአደጋ እያጋለጡ እንዳሉ እንደማይረዱም ተገልጿል። በካምብሪጅ የመልክአ ምድር ማህበረሰብ የታተመ አንድ ጥናት የዚህ አይነቱ ቱሪዝም የአገራት የነፍስ አድን ስራ ላይ ትልቅ ጫና እንደሚፈጥር ያሳያል። • "በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው" የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉት ዶ/ር ዶኖቫን እንደሚሉት እንደዚያ ያለ አስጨናቂ ቦታ ላይ በመገኘት የሚደሰቱ ሰዎች በሌሎች መሰል ነገሮችም ይሳባሉ። "ጋዙን መተንፈስና ምድር የምታወጣውን ድምፅ መስማት ያሻቸዋል፤ የመሬትን ድምፅ በደንብ ለመስማት መቅረብ ይፈልጋሉ" ይላሉ። የዚህ ዓይነቱ ፍላጎታቸው አይሎ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ፈንድተው ያልጨረሱ እሳተ ገሞራዎችን እያደኑ የሚጎበኙ አፍቃሬ እሳተ ጎመራዎችም (ቮልካኖፋይል) እንዳሉ ዶ/ር ዶኖቫን ይናገራሉ። እነዚህ አፍቃሬ እሳተ ገሞራዎች ስሜታቸው አሸንፏቸው ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ችግር የዘነጉ መሆናቸውን ዶክተሯ ያስረዳሉ። • «ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር» አዲስ ዓለማየሁ በፍንቃይ አለቶች ወይም በእሳት ውርዋሪ መመታት እንዲሁም መርዛማ ጋዞችም ሊኖሩ ይችላሉ። እሳቸው እንደሚሉት ጎብኚዎቹ ይበልጥ የማይረዱት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች በፍጥነት ተቀይረው እንደ ጎርፍ ያለ አደጋ ሊመጣም ይችላል። በእንዲህ ያለው አጋጣሚ ጎብኚዎችን መታደግ የድንገተኛ አደጋ ተቋማት ላይ ከባድ ጫና ሲፈጥር የጎብኚዎች ደህንነትም አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በአይስላንድ በአንድ ወቅት የደህንነት ቁጥጥርን ለማምለጥ ቱሪስቶች በሄሊኮፕተር ምሽት ላይ እሳተ ገሞራ ሳይት ላይ አርፈዋል። እአአ 2010 ላይም የቮልካኖ ግግር አቋርጠው ወደ ፍንዳታው የሄዱ ሁለት ጎብኚዎች ሞተዋል። የእሳተ ገሞራ ቱሪዝም ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ ትልቅ እርምጃ ቢሆንም አደገኛ ጎንም እንዳለው ተገጿል። • 1550 ተማሪዎች ለኩረጃ ሲሉ ስማቸውን ለውጠዋል
news-48174147
https://www.bbc.com/amharic/news-48174147
ቢን ላዲን ከሞተ በኋላ አልቃይዳ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
የአልቃይዳ ቡድን መስራች ኦሳማ ቢላዲን ፓኪስታን ውስጥ በአሜሪካ ኃይሎች ከተገደለ ስምንት ዓመት አስቆጠረ። ቡድኑ በዓለማችን ላይ አደገኛ የሚባሉ የጂሃድ ጥቃቶችን ይፈፅም የነበረ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎችንም ያዝ ነበር።
የኦሳማ ቢን ላደንን መገደል ተከትልሎ እአአ 2015 በፓኪስታን አሜሪካን የመቃወም ሰልፍ። ቡድኑ ጥቃቶችን ለመፈፀም እና የማይነጥፍ የገንዘብ ምንጭ እንደነበረውም ይታመናል። ነገር ግን የቡድኑ መሪ ቢን ላዲን ከተገደለ በኋላና አይኤስ የተባለው እስላማዊ ቡድን እየተጠናከረ ሲመጣ የአልቃይዳ ስም እየደበዘዘ ጉልበቱም እየሟሸሸ መጣ። ታዲያ አልቃይዳ አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ምን ያህል ተፅዕኖ ፈጣሪ ነው? ምን ያህልስ ለዓለም ደህንነት ያሰጋል? በዝምታ ማንሰራራት አይኤስ የእስላማዊ ቡድን በቅርቡ የሚዲያ ገፆችን የተቆጣጠረ ሲሆን አልቃይዳ በበኩሉ ከዓለም እይታ ራሱን ሸሽጎ እያንሰራራ ይገኛል። • መሸፈን የተከለከለባቸውን የዓለም አገራት ያውቃሉ? • ከንቲባ ለመሆን ፈተናዎችን የሰበረች ከዚህም በተጨማሪ ቡድኑ ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ትብብርን በመፍጠር ራሱን እያሳደገ ይገኛል። የአሜሪካ የደህንነት መስሪያቤት ባወጣው ወቅታዊ መረጃ የአልቃይዳ መሪዎች "የቡድኑን ዓለም አቀፍ አደረጃጀት እያጎለበተና በምዕራቡ ዓለም ላይ ጥቃት እንዲፈፅሙ እያበረታታ ነው" ብሏል። የተባበሩት መንግስታት በያዝነው ዓመት መግቢያ ላይ ያወጣው የሽብርተኝነት መረጃ "አልቃይዳ በውስጥ ለውስጥ ራሱን እያደራጀ ከምንግዜውም በላይ ጠንካራ እየሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃም እያዳገ መጥቷል" ይላል። በሶማሊያ በተደጋጋሚ የአልቃይዳ አጋር በሆነው አልሻባብ የቦንብ ጥቃት ይደርሳል ዓለም አቀፍ ግንኙት የአሜሪካ ደህንነት ኃይል ተከታታይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት፣ የቢንላደን መገደልና የአይኤስ ቡድን መጠናከር አልቃይዳ አዳዲስ ዘዴዎችን እንዲጠቀም አስገድደውታል። አልቃይዳም አሁን ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር በአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅና ደቡብ እስያ ቅርንጫፎች አለው። ለአልቃይዳ መሪነት ራሳቸውን ያስገበሩት አማፂ ቡድኖች በተለያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ በስውር የሚንቀሳቀሱ ናቸው። • በሳዑዲ 'አንድ ወንድ እኩል ይሆናል ሁለት ሴት' • የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ወደ ሱዳን አቀኑ ከአይኤስ በተቃራኒው አልቃይዳ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከማግለል ተቆጥቧል። በዚህም ስልቱ ከማህበረሰቡ ጋር በመግባባት የአካባቢ ልማት ፕሮጀክቶች ጋር መሳተፍ ጀምሯል። በአዲሱ የአደረጃጀት ስልቱም አልቃይዳ ማህበረሰብ ተኮር መንገድን እየተጠቀመ ሲሆን፣ ወታደሮቹን "የብዙሃኑን ተቃውሞ" ከሚያነሳሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ በመተዳደሪያ ህጉ ላይ አስፍሯል። "ይህንም ተከትሎም ረዳት የሌላቸውን የሚታደግ እና 'የጂሃድ መልካም ሰዎች' በማለት ራሱን አረመኔ ከሆኑት አይኤስ ነጥሎ አስቀምጧል" የምትለው ዶ/ር ኤልሳቤት ካንዳል የፔምብሮክ ኮሌጅ አማካሪ ናት። አልቃይዳ በ2018 እ.ኤ.አ፣ 316 ጥቃቶችን እንደፈፀመም አርምድ ኮንፍሊክት ሎኬሽን ኤንድ ኤቨንት ዳታ ፕሮጀክት (ACLED) አሳውቋል። የወደፊቱ የአልቃይዳ መሪ እ.ኤ.አ በ2015 የአልቃይዳ መሪ የሆኑት አይማን አል ዛዋሃሪ ለቡድኑ መሪነት "የመንጋው መሪ አንበሳ" ብለው አንድ ወጣት አስተውቀዋል። ወጣቱ የኦሳማ ቢላደን ልጅ ሃምዛ ቢን ላዲን ሲሆን በብዙዎች የወደፊቱ የአልቃይዳ መሪ ተደርጎ ይወሰዳል። • ቻይና ሙስሊም ዜጎቿን እየሰለለች ነው ተባለ አሜሪካ ሃምዛ ቢን ላዲንን ሽብርተኛ ብላ ሰይማ፣ መገኛውን ለጠቆመ የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደምታበረክት ገልፃለች። በቅርብ ዓመታት ሃምዛ የአባቱን በቀል ለመመለስ ሲል አሜሪካን ለማጥቃት ትብብር የሚጠይቅ ምስልና የድምፅ መልእክት ለቅቋል።
news-55690051
https://www.bbc.com/amharic/news-55690051
ትግራይ ፡ 'በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሊሞቱ ይችላሉ'
በትግራይ ክልል ውስጥ "በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ" አንድ የመንግሥት ባለስልጣን መናገራቸውን ከእርዳታ ሠራተኞች ጋር ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ የሰፈረ ጽሁፍ አመለከተ።
በመንግሥት የሚመራው የትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል በክልሉ የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በተመለከተ ጥናት ያካሄደ ነው። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁ መገለጹ ይታወሳል። ነገር ግን አልፎ አልፎ ውጊያ እንደሚካሄድ የተነገረ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ "የከፋ" ሲል ገልጾታል። ጨምሮም "ምግብ አለመኖር ወይም በገበያዎች ላይ ያለው አቅርቦት ውስን መሆን እየባሰ የሚሄድ የምግብ እጥረት አደጋን እየፈጠረ መሆኑን ሪፖርቶች እያመለከቱ ነው" ብሏል። በተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰውና የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል እንደሚለው በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል። ታኅሣስ 30/2013 ዓ.ም በትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል አማካይነት በተካሄደው ስብሰባ ላይ በአንድ ተሳታፊ አማካይነት የተነሱ ነጥቦች የሰፈሩበትና ሾልኮ የወጣው ማስታወሻ እንደሚያሳየው፤ የማዕከላዊ ትግራይ ክፍል የጊዜያዊ አስተዳደሪ አንድ ባለሥልጣን እንዳለው "በስፍራው ያለው ሁኔታ በጣም የከፋ ነው" ብሏል። "ምግብና ምግብ ያልሆኑ ነገሮች ወይም ሌሎች ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ተዘርፈዋል ወይም ወድመዋል። ጨምሮም አስቸኳይ እርዳታ ካልቀረበ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ሊሞቱ ይችላሉ።" ጥር 01/2013 ዓ.ም በተካሄደ ስብሰባ ላይ ሌላ ባለሥልጣን የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎትን በተመለከተ ተናገረ ተብሎ በማስታወሻው ላይ እንደሰፈረው "የተለያዩ ቦታዎችን ለመጎብኘት በተጓዝንበት ጊዜ አብረውን የነበሩ አጃቢዎቻችንን ብስኩት ይጠይቋቸው ነበር" ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው አሁን ድረስ ወደ ተወሰኑ የትግራይ አካባቢዎች ለመግባት ውስንነት ቢኖርም የተወሰነ የእርዳታ ድጋፍ ግን እየገባ ነው። የስልክና የኢንትርኔት አገልግሎቶች በአብዛኛው የትግራይ ክፍል የተቋረጡ በመሆናቸው የሚወጡ ሪፖርቶችን ትክክለኝነት ለማረጋገጥ አዳጋች አድርጎታል። አርብ ዕለት ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ላይ የአገሪቱ ባለሥልጣናት እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለመርዳት እንደሚፈልጉ ገልጿል። "የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰብአዊ እርዳታና የልማት አጋራሮች ጋር በመተባበር በችግር ላይ ላሉ ሰዎች የሚቀርበው እርዳታ ደኅንነቱ ተጠብቆ በውጤታማና በተገቢው ሁኔታ እንዲደርስ ለማድረግ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ቁርጠኛ ነው" ብሏል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል በሚገኘው ሠራዊቱ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ ነበር ወታደራዊ ዘመቻ የከፈተው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሠራዊታቸው በክልሉ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበርና "ወንጀለኛውን ቡድን" ለሕግ ለማቅረብ የተወሰደው እርምጃ ተመጣጣኝ እንደሆነ ገልጸዋል። የፌደራሉ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ ከተቆጣጠረ በኋላ ውጊያውን እንደሚቀጥሉ ያሳወቁትን የህወሓት አመራሮችን ለመያዝ አሰሳ እያካሄደ ይገኛል። እስካሁንም በርካቶች መያዛቸውንና መገደላቸው የአገሪቱ ሠራዊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
news-54752421
https://www.bbc.com/amharic/news-54752421
ኢትዮጵያ በትራምፕ የህዳሴ ግድብ አስተያየት ላይ ያለመ የተቃውሞ ፊርማ ልታሰባስብ ነው
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳዋለች" የሚልና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አሉታዊ አስተያየቶችን መስጠታቸውን በመቃወም ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ልትጀምር ነው።
ስነ ስርአቱ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 21፣ 2013 ዓ.ም በግዮን ሆቴል 10 ሰዓት ላይ እንደሚጀመርም በዋነኝነት ይህንን ፊርማ የማሰባሰብ ስራ የሚመራው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታውቋል። የፅህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኃይሉ አብርሃም ፊርማው በበይነ መረብ (ኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳዋለች ለሚለው አፀፋዊ የተቃውሞ ምላሽ መሆኑንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከዛሬ ጥቅምት 21፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ባሉትም አራት ቀናት ኢትዮጵያውያን የፕሬዚዳንቱን ንግግር ፊርማቸውን በማኖር እንዲቃወሙ ጥሪ የቀረበላቸው ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለሚመለከታቸው አገራት ደግሞ ትኩረት እንዲሰጡትም ያለመ መሆኑንም አቶ ኃይሉ ያስረዳሉ። በነዚህ አራት ቀናትም ውስጥ እስከ 150 ሺህ ፊርማ የማሰባሰብ እቅድም ተይዟል። በተለያዩ አገራትም በርካታ ሰዎችም በቡድን ሆነ በተናጠል የተቃውሞ ፊርማዎችን ማሰባብ መጀመሩን የሚናገሩት ዳይሬክተሩ የህዝብ ጥያቄ አይሎ በመምጣቱና ፅህፈት ቤቱም ህዝባዊ ተሳትፎ በቀጥታ የሚመለከተው በመሆኑ አንድ ወጥ በሆነና የበለጠ በተጠናከረ መልኩም ለማገዝም እንዳለመ ይናገራሉ። የዶናልድ ትራምፕ ንግግር "ፀብ የሚጭር ነው" ያሉት አቶ ኃይሉ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ የአለም ሰላም ወዳድ ህዝቦችም በዚህ ሊሳተፉ እንደሚችሉም ጠቆም አድርገዋል። "ኃላፊነት የጎደለውና ግልፅ የሆነ ለአንድ ወገን ያዘነበለና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚነካና የሚሸረሽር ተናግረዋል። ይህም ንግግር በአገር ውስጥም ሆነ በተለያየ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ዳር እስከ ዳር አስቆጥቷል።" ብለዋል። "ንግግራቸው በአፍሪካም ሆነ በቀጠናው ያለውን ሰላም የሚያናጋ ነው" በማለትም አክለዋል። ግብጽ በጎርጎሳውያኑ 1959 የተፈረመውና፣ የአብዛኛውን የውሃውን ድርሻ የሚሰጣትን የቅኝ ግዛት ስምምነት አጥብቃ በመያዝ ታሪካዊ ተጠቃሚነት በሚል መርህ የወንዙን ውሃ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ለብቻዋ የመጠቀም ፍላጎት አላት የምትለው ኢትዮጵያ ግድቡን የምትገነባውም ለፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነትም መሆኑንም ትናገራለች። ባልነበረችበት የተፈረመ ስምምነት ለናይል ወንዝ 77 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ለምታመነጨው ኢትዮጵያ ምንም ድርሻ የማይሰጥና ተፈጥሯዊም ሆነ ሕጋዊ መብቴን የሚነጥቅ ነው በማለትም ኢትዮጵያ ትከራከራለች። አቶ ኃይሉ እንደሚሉት የግድቡ ግንባታ ከዚያ ባለፈ የቀጠናው የሰላም ምንጭ ነው ይላሉ ለዚህም እንደ አባሪነት የሚያነሱት ከአፍሪካ ህብረትም ርቃ የነበረችው ግብፅ በህብረቱ አደራዳሪነት የሶስትዮሽ ድርድር እያካሄደች መገኘቷን በመጥቀስ ነው። በብዙ ነጥቡም የሶስትዮሽ ድርድሩ ላይ መግባባት ላይ መደረሱንም አክለው ይገልፃሉ። በዋናነት ይህንን ፊርማ በማሰባሰብ ከሚያስተባብረው ፅህፈት ቤት በተጨማሪ ሊፍት ኢትዮጵያ፣ ጀስቲስ ፎር ሂውማኒቲ የሚባሉ ድርጅቶችም ፊርማውን በማሰባሰብ አብረው ይሰራሉ። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥቅምት 13፣ 2013 ዓ.ም ሱዳን እና እስራኤል ግንኙነታቸውን ለማደስ የደረሱበትን ስምምነት አስመልክቶ ከሱዳን ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ እና ከእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ በተነጋገሩበት ወቅትም ነው የህዳሴ ግድብን ጉዳይን ያነሱት። "ግብፅ በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማትችል ሁኔታው አደገኛ ነው። ግብፅ የህዳሴ ግድብን ታፈነዳለች፤ አሁንም በግልፅ እናገረዋለሁ ግብፅ በድጋሚ ታፈነዳዋለች" በማለት በተደጋጋሚ የተናገሩት ትራምፕ "ስምምነት ለአገራቱ ባቀርብም ኢትዮጵያ ስምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። አንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም ይህ ትልቅ ስህተት ነው። በዚህም ምክንያት የምንሰጣቸውን ብድር አቁመናል። ስምምነቱን ካልተቀበለች በስተቀር ኢትዮጵያ ያንን ገንዘብ አታየውም " ማለታቸው የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች እንዲሁም የሕግ እና የውሃ ጉዳይ የቴክኒክ ባለሞያዎች በዋሽንግተን ዲሲ ሲደራደሩ በነበረበት ወቅት በዓመታት የተራዘመ ድርቅ እንዲሁም በተራዘመ ዓመታት አነስተኛ የውሃ ፍሰት ላይም መሰረታዊ መግባባት ተደርሷል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ያለምንም ውጤት መቋረጡ ይታወሳል። በወቅቱም ግብጽ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቴን ይቀንሰዋል እንዲሁም ለእርሻ የሚያስፈልገኝ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በየዓመቱ ይገባኛል ስትል የቆየች ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በበኩሏ 31 ቢሊዮን ኪዩቡክ ውሃ በዓመት ለመልቀቅ ሃሳብ አቅርባ ነበር። ነገር ግን አሜሪካ በበኩሏ 37 ቢሊዮን ኪዩብክ ሜትር እንዲለቀቅ መጠየቋ ተነግሮ ነበር። ኢትዮጵያ ወንዙ በግድቡ ስፍራ እንደሚኖረው ዓመታዊ የፍሰት መጠን ከ4 -7 ዓመታትን በሚወስድ የሙሌት ደረጃ ግድቡን የመሙላት እቅድን ብታቀርብም ግብፅጽ በበኩሏ ጥቅሜን የሚጋፋ ነው በማለት ከ12 እስከ 21 ዓመታት መውሰድ አለበት ትላለች። ኢትዮጵያ ዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረውንም ድርድር ያቋረጠችበት ምክንያት በግብጽ ፍላጎት ታዛቢ እንዲሆኑ የገቡት አሜሪካና የዓለም ባንክ ለግብጽ ከመወገን አልፈው የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ላይ ጫና ለማሳደር ሞክረዋል በማለት ኢትዮጵያ መውቀሷ የሚታወስ ነው። አሜሪካ፣ የዓለም ባንክ ከግብጽ ጎን ቆመው ነበር በተባለው በዚህ ድርድር ላይ ከመጀመሪያው ሙሌት በኋላ ኢትዮጵያ ለምትጠቀመው ውሃ ለግብጽ የተጠራቀመ የውሃ ጉድለት ማካካሻ እንድትሰጥ የሚያስገድድ እንደሆነም ተገልጾ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ የግብጽ ሃሳብ በአባይ ወንዝ ላይ ተፈጥሯዊ መብት እንዳይኖራት ወይም ምንም ዓይነት የውሃ ልማት ያልተገነባበት ፍሰት እንዲኖር የሚጠብቅ ነው በማለትም ትተቻለች። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ይህንን ማለታቸውን ተከትሎም በግድቡ ዙሪያ የሚሰጡ ማስፈራሪያዎች ከመረጃ ክፍተት የሚነሱ፣ ውጤታማ ያልሆኑ እና የዓለም አቀፍ ሕግን የጣሱ እንደሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ ሰጥቷል። ከዚህም በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ተቀማጭ የሆኑትን የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሬይኖርን ጠርተው ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቀዋቸዋል። በርካቶችም ቁጣቸውን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በመግለፅ ላይ ሲሆኑ ፤ የተቃውሞ ሰልፎችም ተካሂደዋል። በዩናትድ ኪንግደም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የትራምፕን አስተያየት በመቃውም ለንደን በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ነው ሰልፍ በትናንትናው ዕለት አካሂደዋል። በተለያዩ አገራትም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለማምጣትም እየሰሩ መሆናቸውንም አቶ ኃይሉ ይናገራሉ።
news-53747873
https://www.bbc.com/amharic/news-53747873
ኮሮናቫይረስ፡ በስፔን አንድ ግዛት ሕዝብ በሚሰበሰብበት ስፍራ ሲጃራ ማጤስ ታገደ
ጋሊሲያ የተሰኘችው የስፔን አንድ ክልል ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ ሲጃራ ማጤስን የኮቪድ-19 ስርጭትን ያስፋፋል በሚል አገደች።
በክልሉ በጎዳናዎች ላይም ሆነ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ እገዳው የተጣለ ሲሆን በዚህም የተነሳ አካላዊ ርቀት መጠበቅ በማይቻልባቸው እንደ በምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች ባሉ ስፍራዎች ክልከላው ተቀምጧል። በስፔን በምዕራብ ሰሜን የምትገኘው ይህቺ ክልል ምንም እንኳ ሌሎች ይከተሏታል ተብሎ ቢታሰብም እንዲህ አይነት ገደብን ስታስቀምጥ ግን የመጀመሪያዋ ናት። ውሳኔው የመጣው ስፔን በምዕራብ አውሮጳ ከሚገኙ አገራት መካከል ወርሽኙ በፍጥነት ዳግም እየተስፋፋባት ባለበት ሰዓት ነው። በሰኔ ወር በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በቀን 150 የነበረ ሲሆን በነሐሴ ግን ወደ 1500 ከፍ ብሏል። ረብዑ እለት በአንድ ቀን 1690 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህም በመላው አገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 330,000 አድርሶታል። የጋሊሲያ የማጤስ ክልከላ ይፋ የሆነው ባለሙያዎች ለክልላዊ መንግሥት እንደ መከላከያ መንገድ ሃሳባቸውን ካቀረቡ በኋላ ነው። ውሳኔው በጤና ሚኒስተር የምርምር ቡድን ድጋፍ ያገኘ ሲሆን በማጤስና በኮሮናቫይረስ ስርጭት መስፋፋት መካከል ያለውን ግንኙነት አብራርተዋል። ባለሙያዎቹ እንዳሉት አጢያሾች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አለማድረጋቸው የበለጠ ለቫይረሱ እያጋለጣቸው ነው። እንዲሁም ሰዎች በሚያጤሱበት ወቅት ከአፍንጫቸው የሚወጣ ነጠብጣብ መኖሩን ከዚያም ሲጋራውን ወደ አፋቸው ከመውሰዳቸው በፊት በእጃቸው የሚነኩት መሆኑንም ገልፀዋል። " በየትኛውም አካባቢ ሲጋራ ማጤስ. . .ሰዎች በአቅራቢያ ካሉ እንዲሁም የአካላዊ ርቀት በሌለበት ከፍተኛ አደጋ ይደቅናል" ያሉት የክልሉ ፕሬዝዳንት አልቤርቶ ኑዋኔዝ ፌይጆ ናቸው። መንግሥትን የሚያማክረው ቡድን አባል የሆኑት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ ቪላር "ይህ በአጢያሶች ዘንድ ድጋፍ የማያገኝ ውሳኔ መሆኑን እናውቃለን" ሲሉ አክለዋል። እንዲሁም " እንደማነምነው በተለየ ሁናቴ ውስጥ ነው ያለነው" ሲሉ የውሳኔውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተውታል። በደቡብ አፍሪካ ከኮሮናቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ አልኮል መጠጥና ሲጋራ መሸጥ መታገዱ ይታወሳል። ክልከላው ከጤና ደህንነት ጋር በተያያዘ የቀረበ ሲሆን በባለሙያዎችና በዓለም ጤና ድርጅት ምክር መፈፀሙን አገራቱ ተናግረዋል። በዩናይትድ ኪንግደም የተሰራ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች በላይ ማጤስ በቃኝ ብለዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አጢያሾች ከሌሎች በበለጠ ለኮቪድ-19 ምልክቶች ተጋላጭ መሆናቸውን በማንሳት ዜጎቹን ይመክራል።
news-54920173
https://www.bbc.com/amharic/news-54920173
ትግራይ፡ ኢሰመኮ ወደ ማይካድራ የምርመራ ቡድን መላኩን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በማይካድራ የተፈጸመውን ሰብአዊ ቀውስ በአፋጣኝ ለማጣራት የምርመራ ቡድን ወደ ቦታው ማሰማራቱን ገለፀ።
ጥቃቱ ተፈጸመ የተባለበት ማይካድራ ከሁመራ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ ትገኛለች ኮሚሽኑ ባወጠው በትናንትናው ዕለት በትግራይ ክልል እተካሄደ ስላለው ጦርነት እና የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫው እንዳለው በግጭቱ በተሳተፉ ማንኛውም ወገኖች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በመመርመር እና ማስረጃ በማሰባሰብ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጿል። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ የትግራይ ክልልን በተመለከተ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ ኃይል በአፋጣኝ፣ የሰብአዊ ዕርዳታ ጉዳይ ዴስክ እንዲያቋቁም እና ከሰብአዊ ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ጋር ምክክር እንዲጀመርም ጥሪ አቅርቧል። ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀረበው በትግራይ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው ውጊያ የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አደጋን በሚመለከት በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን በገለፀበት በዚሁ መግለጫው ላይ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ እና የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ካትሪን ሶርዚ (ዶ/ር) ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ፤ ድርጅቱ በግጭት ቀጠና የቴሌኮም አገልግሎቶች መቋረጣቸው እና መንገዶች ዝግ መሆናቸው የሰብዓዊ እርዳታ ለማደረግ በሚያደርገው ጥረት ላይ እንቅፋት እንደሆነበት ገልፀው ነበር። "ቀድሞውንም ቢሆን በትግራይ ከ600ሺህ በላይ የሚሆኑ በቋሚነት የምግብ እርዳታ የሚሹ ሰዎች ይገኙ ነበር" ያሉት ካትሪን (ዶ/ር)፤ በአራት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከ96ሺህ በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች መኖራቸውን ጠቀሰው የሰብዓዊ እርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል። ለስደተኞቹ የዕርዳታ ድጋፍ የሚሰጠው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካል ያለው የመሠረታዊ ፍጆታዎች ክምችት በቅርቡ ሊሟጠጥ እንደሚችል አስጠንቅቋል። ኢሰመኮ በመግለጫው በተጨማሪም ቀይ መስቀል ማህበር ሰብአዊ አገልግሎቶችን ማከናወን እንዲችል በውጊያው ተሳታፊ የሆኑ አካላት ተፈፃሚነት ባላቸው ዓለም አቀፍ ሕጎች መሰረት የቀይ መስቀል አርማ እንዲያከብሩና ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ከሁመራ ዳንሻ ባለው መስመር ሶስት አምቡላንሶች በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶባቸው ጉዳት እንደደረሰባቸው ለቢቢሲ መግለፁ ይታወሳል። በተጨማሪም ኮሚሽኑ በአሁኑ ሰዓት በልዩ ልዩ የአገሪቱ ክፍሎች መንግሥት እየወሰደ ባለው እርምጃ የታሰሩ ሰዎችን በሚመለከት ከደረሱት ጥቆማዎችና መረጃዎች በመነሳት በብሄራቸው ማንነት በመለየት ለጥርጣሬ እና መድልዎ እንዲጋለጡ የሚያደርግ "ምክንያታዊ ስጋት" መፈጠሩን መረዳቱን በመግለጽ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል። ኢሰመኮ ከዚህ ጋር በተያያዘም በቅርቡ የጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈጻሚነቱ ወሰን በትግራይ ክልል ውስጥ መሆኑን በመጥቀስ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የሚደረግ የሕግ ማስከበር ሂደት መደበኛውን የሕግ ማስከበር ሥነ ሥርዓት ደንቦች ተከትሎ የሚፈጸም መሆን እንዳለበት በመግለጫው ላይ አመልክቷል። በተመሳሳይ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂውመን ራይትስ ዋች በበኩሉ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥትና በጦርነቱ የንፁኀን ዜጎችን ሕይትና ንብረት መጠበቅና መከላከል እንዳለበት አሳስቧል። ተቋሙ አክሎም የሰብዓዊ እርዳታ እና አገልግሎቶች አቅራቢዎች ተደራሽ እንዲሆኑ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች ማቋረጥ እንዲቆምና በክልሉ የስልክ ግንኙነት እንዲከፈት ጥሪ አቀርቧል። የድርጅቱ የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላይቲታ ባደር በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እና አገልግሎቶችን መገደብ ማለት በጦርነቱ እየተጎዳ ያለው በሚሊየን የሚቆጠር የትግራይ ሕዝብን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ ያደርገዋል ሲሉ ገልፀዋል። አክለውም "የፌደራልና የትግራይ ክልል መንግሥታት የመኖር መብትን እንዲያከብሩና ሕዝቡን ለመደገፍና ለመከላከል አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ" አሳስበዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይም በትግራይ ክልል ማይካድራ ከተማ በርካታ ዜጎች ተገድለዋል የሚል ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ በትናንትናው እለት (አርብ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት "ግድያዎቹ መረጋገጥ ከቻሉ እንደ ጦር ወንጀል ይቆጠራል" ሲል አሳስቧል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በትግራይ ክልል ውስጥ ሰኞ ምሽት በርካታ ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት መፈጸሙን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች እንዳገኘም ገልጾ ነበር። አምንስቲ እንዳለው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በምትገኘው ማይካድራ ከተማ ውስጥ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ቁጥራቸው በመቶዎች ሊቆጠሩ የሚችሉ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተገድለዋል። የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪው ድርጅት ግን በትግራይ ክልል ደቡብ ምዕራብ ዞን በምትገኘው ማይካድራ ግድያውን ማን እንደፈጸመው ለማረጋገጥ አለመቻሉን አመልክቷል። ነገር ግን ድርጅቱ ያነጋገራቸው የአይን እማኞች ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር የሚዋጉትን የህወሓት ታማኝ ኃይሎች ጥቃቱን እንደፈጸሙ ይከስሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጭፍጨፋውን የፈፀሙት የህወሓት ታጣቂዎች ናቸው ቢሉም የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው በግድያዎቹ እጃችን የለበትም በማለት ውድቅ አድርገውታል። የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ውንጀላዎቹ "መሰረት" የሌላቸው ናቸው ማለታቸውንም አጃንሰ ፍራንስ ፕሬስ እርሳቸውን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በበኩላቸው የፌደራል መንግሥት የምዕራብ ትግራይን "ነፃ ካወጣ" በኋላ የህወሓት ታጣቂዎች በማይካድራ ከተማ በርካታ ንፁሃን ዜጎችን "በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል" ብለዋል። የፌደራል መንግስት በኮሮናቫይረስ ምክንያት አገራዊ ምርጫ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ መወሰኑን ተከትሎ ባለፈው ዓመት በትግራይ ምርጫ መካሄዱ በሁለቱ መንግሥታት መካከል ያለው ውጥረት እንዲባባስ መባባስ መንስኤ ሆኗል። የትግራይ ክልልና የፌደራል መንግሥት ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ከገቡ በኋላ የተለያዩ ወገኖች ግችቱ እንዲቆና ውይይት እንዲደረግ ጥሪ እያቀረቡ ቢሆንም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት በትግራይ ክልል የሚያደርገውን ወታደራዊ እርምጃ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች እስኪፈፀሙ ድረስ እንደሚቀጥል ማስታወቁ ይታወሳል።
news-55447033
https://www.bbc.com/amharic/news-55447033
ምርጫ 2013 ፡ ኦፌኮ እና ባልደራስ በመጪው ምርጫ የመሳተፋቸው ነገር እንደሚያሳስባቸው ገለጹ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ወደ ምርጫ መግባት ያሳስበናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ሁለቱ ፓርቲዎች ይህንን ያሉት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ዓመት ለሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ማስፈጸሚያ የሚሆን ረቂቅ የጊዜ ሠሌዳን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው። የኦፌኮ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ፤ "ከከፍተኛ እስከ መካከለኛ የፓርቲያችን አመራሮች መታሰር እና የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ለምርጫ የምናደርገውን ዝግጅት አስቸጋሪ ያደርገዋል" ሲሉ ተናግረዋል። በተመሳሳይ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ፤ የባልደራስ አመራሮች በተራዘመ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ እንዳሉ በመጥቀስ "የምንገባበት ምርጫ እጅግ አሳስቦናል" ብለዋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቃል አቀባይ ሶሊያና ሽመልስ ከቀናት በፊት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ "ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው መካሄድ አለበት ነው ያሉት። ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ስጋት ይሆናል ያሉት ሁለት ነገር ነው። አንዱ የአገሪቱ የጸጥታ ችግር ነው። አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ቢሯቸው እንደሚዘጋ እና አባሎቻቸው ችግር እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል" ብለዋል። ፓርቲዎች ለሚያነሷቸው መሰል ችግሮች መፍትሄ መስጠት የሚችለው የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካል እንጂ ምርጫ ቦርድ አለመሆኑንም ተናግረዋል። የምርጫ ቦርድ ረቂቅ የምርጫ የጊዜ ሠሌዳውን አርብ እለት ይፋ ባደረገበት መድረክ ላይ የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የተሳተፉት አቶ ዛዲግ አብረሃ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እየደረሰብን ነው ያሉት ጫናን በተመለከተ ምላሽ ሰጥተው ነበር። በዚህም መሰረት የቀረቡ ቅሬታዎች ላይ ማጣራት እንደተደረገና አንዳንዶቹ የተጋነኑ መሆናቸውን ገልጸው፤ የቀረቡትን አቤቱታዎችን ፓርቲያቸው እንደማያጣጥላቸውና ለማረም አስፈላጊውን ነገሮች ሁሉ እንደማያደርግ እንዲሁም ቀጣዩ ምርጫ ትክክለኛ ፉክክር የሚደረግበት እንዲሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በዚህ ዓመት ለሚካሄደው ስድስተኛው ዙር አገራዊና ክልላዊ አጠቃላይ ምርጫ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ በተደረገው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የድምጽ መስጫው ቀን ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 መሆኑ ገልጿል። አቶ ጥሩነህ በርካታ አባሎቻቸው መታሰራቸውን፣ የቀሩትም ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን እና በዞንና በወረዳ ደረጃ ያሉ ጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋታቸውን በመጥቀስ፤ "በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት ቢኖረንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን" ብለዋል። ይህንንም ስጋታቸውን ከዚህ ቀደም መግለጫ በማውጣት ማስታወቃቸውን አስታውሰዋል። ትናንት ምርጫ ቦርድ ባካሄደው ስብሰባ ላይም ተገኝተው ይህንኑ ስጋታቸውን ማስረዳታቸውን የተናገሩት አቶ ጥሩነህ፤ "ችግሮችን ለማስተካከል ጥረት እናደርጋለን" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። "ነገር ግን አንዳንድ ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ነገሮች መኖራቸውንም ተገንዝበናል" ብለዋል አቶ ጥሩነህ። እንደ ኦፌኮ እስካሁን በምርጫው አንሳተፍም የሚል ውሳኔ ላይ ባይደርሱም፤ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በሚያስችል አቅም ላይ አለመሆናቸውን ግን አስረግጠው ተናግረዋል። ለዚህም የጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋት፣ የአባላቶቻቸው እስር፣ ስደትና ማስፈራሪያ እንዲሁም በአገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ችግሮችን እንደ ምክንያት ጠቅሰዋል። "በዚህ ሁኔታስ መንግሥትና ምርጫ ቦርድ ምርጫ ማካሄድ ይችላሉ ወይ?" ሲሉም ጠይቀዋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቤ ሕግ ምስክር እንዲያሰማ ለመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። በትናንቱ የፍርድ ቤት ውሎ ማዘናቸውን የገለፁት የፓርቲው ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው፤ "በእነአቶ እስክንድር ነጋ ላይ የተሰጠው ቀጠሮ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች በውድድሩ ውስጥ ሳይገቡ መንግሥት ብቻውን ሮጦ 'አሸናፊ ነኝ' ለማለት የተደረገ ይመስላል" ሲሉ ኮንነዋል። አቶ ገለታው "ምርጫው በህወሓት ዘመን የተለመደ የምርጫ ዓይነት ሊሆን ነው" በማለትም በእነርሱ በኩል ተስፋ እየታያቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል። "አባላቶቻችን ወከባ አለባቸው። መንግሥት በየጊዜው ምህዳሩን እያጠበበ ነው፤ ባልሰፋ ምህዳር ውስጥ ታሪካዊ ምርጫ ሊደረግ እንደማይችል እያረጋገጠ ነው" ሲሉም ወቅሰዋል። ይህ እንደ ፓርቲ ብቻም ሳይሆን እንደ አንድ ግለሰብ እንደሚያሳስባቸውም አልሸሸጉም። አቶ ገለታው "ይህ ምርጫ እንደ በፊቱ ተጭበርብሮ እንራመድ ቢባል የማያራምድ ሕዝብ የተነሳበት ወቅት ስለሆነ፤ ድህረ ምርጫ አገሪቷን ወደ ብጥብጥ እንዳይወስዳት ያሳስባል" ብለዋል። መንግሥት ሁኔታዎችን በፍጥነት ማስተካከል ካልቻለም ምርጫው ታሪካዊ መሆኑ ቀርቶ፤ አደጋዎችን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቃል አቀባይ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ "ፓርቲዎች ችግር ገጥሞናል ባሉት ጉዳይ ላይ ለክልል አስተዳደር፣ ለፖሊስ ኮሚሽን ወይም ሌላ ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ቦርዱ ያሳውቃል" በማለት የመሥሪያ ቤታቸው የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት አስረድተዋል። በዚህም መሰረት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ካላቸው ለቦርዱ በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ተጠይቆ፤ 11 ፓርቲዎች የሚገጥማቸውን ችግር ለቦርዱ ማሳወቃቸውን የጠቀሱት ሶሊያና፤ ቦርዱም ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ያስፈልጋል ብሎ ለመንግሥት ማሳወቁን ገልጸዋል። በየክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የሚገጥማቸውን ችግር በተመለከተ ከገዢው ፓርቲ፣ መንግሥትና ምርጫ ቦርድ ጋር የሦስትዮሽ ውይይት የሚካሄድበት አሠራር መዘርጋቱንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። የኦፌኮ እና ባልደራስ ፓርቲዎች አመራር እና አባላት የሆኑት ጀዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እንዲሁም እስክንድር ነጋ፣ አስቴር ስዩምና ስንታሁ ቸኮል በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር እንደሚገኙ ይታወቃል። ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ከየካቲት 8 ጀምሮ የእጩዎች ምዝገባ እንደሚያከናውኑ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ በትናንትናው ዕለት ገልጿል። ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21 ድረስ ደግሞ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወን ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የድምጽ መስጫ ቀን በአንድ ሳምንት ዘግይቶ ሰኔ 5/2013 ዓ.ም እንደሚከናወን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን የሚደርሱ መራጮች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠብቅ ማስታወቁ ይታወሳል።
42056829
https://www.bbc.com/amharic/42056829
ዘመናዊውን የመፀዳጃ መቀመጫ የፈጠረው ሰዓት ሠሪ
ለዘመናዊው የመፀዳጃ መቀመጫ ፈጠራ ሊመሰገን የሚገባው በለንደን የነበረ ሰዓት ሠሪ ነው።
በ18ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጠረው ይህ ቀላል የሆነ የታጠፈ ቱቦ ለዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች ችግር ምላሽ ያስገኘና አስፈላጊው ክፍል ነው። ከግኝቱ ከሁለት መቶ ዓመታት በኋላም እስካሁን መደበኛ የሆነው የዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች የሌሏቸው ሰዎች ቁጥር ከሁለት ቢልዮን በላይ ይሆናሉ። ሰዓት ሠሪው ቴክኖሎጂውን ቢያመጣውም ለሁሉም ማዳረስ ግን እስካሁን ችግር ሆኖ ቀጥሏል። እንዴት መጣ አሌክሳንደር ካሚንግ የመፀዳጃ ቤት መሃንዲስ ብቻ አልነበረም። ብዙ የፈጠራ ሥራዎቹ የተለዩ ነበሩ። የአየር ጫናን ሊመዘግብ የሚችል የተራቀቀ መሣሪያ ለመሥራት በእንግሊዙ ንጉስ ጆርጅ 3ኛ ተቀጥሮ ነበር። ጥናታዊ ምርምሮችን ለማካሄድ የሚጠቅመውን ማይክሮቶም የተሰኘ እንጨት በስሱ የሚቆርጥ መሣሪያ በመስራትም የመጀመሪያው ነበር። ዓለምን የቀየረው የአሌክሳንደር ፈጠራ ግን ከምህንድስና ሙያው ጋር አይገናኝም ነበር። ለውጡን ያመጣው እጥፋት የነበረበት ቱቦ ነው። እ.አ.አ በ1775 አሌክሳንደር የ 'S' ን ቅርጽ ለያዘው ቧንቧ የፈጠራ ባለቤትነት ሆኖ ተመዘገበ። ይህም በዘመናዊ መንገድ ዉሃ የሚለቀውን የመፀዳጃ መቀመጫ ለመፍጠር መንገድ ከፈተ። ከዚህም ጋር አብሮ የሕዝብ ንጽህና ተከተለ። ቀላል ዘዴ ከዚህ ቀደም የዉሃ መልቀቂያው ዘዴ ሽታ ያስከትል ነበር። ጠበቅ ያለ የማፈኛ ዘዴ ካልተፈጠረለት በስተቀር ዉሃ ከተለቀቀ በኋላ በቧንቧው በኩል ወደ ጉድጓድ የዉሃ ሽንትና ሰገራ ቢያስወግድም የጉድጓዱን ሽታ ግን ወደ ላይ ይመልስ ነበር። የአሌክሳንደር መፍትሔ ደግሞ ቀላል ነበር እሱም ቧንቧውን ማጠፍ ነበር። ዉሃ እጥፋቱ ላይ ስለሚከማች ወደ ላይ የሚመለሰውን ሽታ ይገድብ ነበር። ዉሃው በተለቀቀ ቁጥር ደግሞ ይታደሳል። አሁን ያለው ቧንቧ እንደፈረንጆቹን ፊደል ቀድም ተከተል ቅርጹ ከ 'S' ወደ 'U' ቢዘዋወርም በመፀዳጃ ቤት ዉሃ የመልቀቅ ግንዛቤው ግን አልተቀየረም። ግኝቱ ቢኖርም በሥራ ላይ ለማዋል ግን ረዥም ዓመታትን ፈጅቷል። እ.አ.አ በ1851 በለንደን ታላቅ ኤግዚብሽን ከዓለም አቀፍ ግኝቶች ጋር ለሕዝብ ቀረበ። በመፀዳጃ ቤት ዉሃ መልቀቅ በለንደን አዲስ ከመሆኑ የተነሳም ለሕዝቡ ታላቅ የደስታ ምንጭ ምክንያት ሆኖ ነበር ። በዚህ መልኩ የተሠሩ መፀዳጃ ቤቶችን ለመጠቀም በእንግሊዝ ሀገር አንድ ሳንቲም ያስከፍል ነበር። እስከ ዛሬ ለዉሃ ሽንት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄድ ሲፈለግ 'አንድ ሳንቲም ልከፍል ነው' ይባላል። ዘመናዊው የቧንቧ ሥራ ባሰገኘላቸው አዲስ ፈጠራ ለመደነቅና ለመተንፈስ ብለው በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የለንደን ነዋሪዎች ተሰልፈው ነበር። ከዓለም የጤና ድርጅት በተገኘው መረጃ መሠረት እ.አ.አ በ1980 አንድ አራተኛ የሚሆነው የዓለም ህዝብ ብቻ የዘመናዊ የመጸዳጃ ቤት ተጠቃሚ የነበረ ሲሆን ከ170 ዓመታት በኋላሁለት ሶስተኛ የሚሆነው ሕዝብ ተጠቃሚ መሆን ችሏል። ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለው ወጪ ይህ ማለት ከሁለት ቢልዮን ሕዝብ በላይ የሚሆኑ ሰዎች የዘመናዊ መፀዳጃ ቤት አገልግሎት የላቸውም። ይህ ዘዴ ጤናማ በሆነ መልኩ ''የሰውን ቆሻሻ ከሰው ግንኙነት ያርቃል'' እንጂ የቧንቧውንና የቱቦውን ችግር አያስወግድም። እንደዚህ አይነት የቆሻሻ ማስወገጃ አገልግሎት ያላቸው የዓለም ሕዝቦች ግማሽ እንኳን አይሞሉም።
news-55321486
https://www.bbc.com/amharic/news-55321486
የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤት 4 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጠች
ማኬንዚ ስኮት ለምግብና አስቸኳይ ጊዜ የሚሆን 4 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጠች። ገንዘቡ ከአንድ ግለሰብ በአራት ወራት ውስጥ ብቻ የተሰጠ ከፍተኛ እርዳታ ሆኖ ተመዝግቧል።
ማኬንዚ ስኮት በጦማሯ ላይ እንዳለችው ገንዘቡ በወረርሽኙ ምክንያት ኑሮ ዳገት የሆነባቸው አሜሪካዊያንን የሚያግዝ ነው። ማኬንዚ ስኮት በዓለም 18ኛዋ ሀብታም ናት። በቅርቡም የሀብት መጠኗ በዚህ ዓመት ብቻ በ23 ቢሊዮን ዶላር ጨምሮ አሁን በድምሩ ወደ 60 ቢሊየን ዶላር ተመንድጎላታል። አብዛኛው የሀብቷ ምንጭ ታዲያ ከቀድሞ ባለቤቷ ፍቺ በኋላ በፍርድ ቤት የተወሰነላት ገንዘብ ነው። ግለሰቧ የዓለም ቁጥር አንድ ሀብታም የአማዞኑ ጌታ ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤቱ መሆኗ ይታወቃል። "ይህ ወረርሽኝ የብዙ አሜሪካዊያንን ሕይወት አመሳቅሏል" ያለለችው ስኮት ከ6500 የእርዳታ ድርጅቶች ውስጥ 380 የሚሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ነቅሳ በማውጣት ገንዘቡን እንደሰጠች ገልጻለች። "የምጣኔ ሀብት መቀዛቀዙ በተለይ በሴቶችና በጥቁር አሜሪካውያን ላይ ፈተናን ደቅኗል። ቢሊዮኖች ግን ሀብታቸው ይበልጥ እያበጠ ነው" ያለችው ስኮት ባለፈው ሐምሌም በተመሳሳይ ወደ 2 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ መለገሷ የሚታወስ ነው። ስኮት በዚህ ዓመት ብቻ በድምሩ 6 ቢሊዮን ዶላር በመስጠት ለጋስነቷን አስመስክራለች። ባለፈው ዓመት ደግሞ አብዛኛውን ሀብቷን ለበጎ አድራጎት ለማዋል "ጊቪንግ ፕሌጅ" የተሰኘውን የቃልኪዳን ሰነድ ፈርማለች። "ጊቪንግ ፕሌጅ" የዓለም ቢሊዮነሮችና ቤተሰቦቻቸው ሀብታቸውን ለበጎ አድራጎት ለማዋል መስማማታቸውን የሚገልጡበት ሰነድ ነው። ስኮት ይህን ልግስናዋን ተከትሎ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አድናቆታቸውን እየገለጡላት ነው። የገንዘቡ ትልቅ መሆን ብቻም ሳይሆን ስኮት ጊዜ ወስዳ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን መርጣ በተጠና ሁኔታ ገንዘቡን መለገሷን ወደውላታል። በዚህ ዓመት የቀድሞ ባሏ ጄፍ ቤዞስም ለአየር ንብረት ለውጥ ጥናትና ምርምር 10 ቢሊዮን ዶላር መለገሱን ይፋ አድርጎ ነበር። ባለፈው ህዳር ወር የዚህን ገንዘብ የመጀመርያ ዙር እርዳታ ለ16 ድርጅቶች አከፋፍሏል። 10 ቢሊዮኑ በብዙ ዓመታት የሚቸር የገንዘብ መጠን ሲሆን ባለፈው ወር 800 ሚሊየኑ ወጪ ተደርጓል። ቤዞስ የሀብት መጠኑ በዚህ ዓመት ብቻ በ70 ቢሊዮን ዶላር ጨምሮ አሁን በጥቅላላው 185 ቢሊዮን ዘሏል። ብሉምበርግ እንደሚለው ጄፍ ቤዞስን የመሰለ ሀብታም በምድር ላይ የለም። ይህ ከፍተኛ የሀብት ጭማሪ ወረርሽኙ ያመጣለት አዱኛ እንደሆነ ተዘግቧል። ይህም ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቤት በመቀመጣቸው የኦንላይን ግብይቱ እየደራ መምጣቱ ነው።
news-51993425
https://www.bbc.com/amharic/news-51993425
ኮሮናቫይረስ፡ ኢራን ከአሜሪካ ቀረበላትን የህክምና እርዳታ አልቀበልም አለች
የኢራን ሐይማኖታዊ የበላይ መሪ አገራቸው የኮሮናቫይረስን ለመዋጋት ለምታደርገው ጥረት ከአሜሪካ የቀረበላትን እርዳታ የመስጠት ጥያቄ እንደማይቀበሉት አሳወቁ።
አያቶላህ አሊ ሃሚኒ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር ላይ እንዳሉት አሜሪካ የኢራን "ከሁሉ የባሰች ጠላት" ናት በማለት ቀደም ሲል አሜሪካ ለወረርሽኙ መከሰት ተጠያቂ ናት ሲሉ አንዳንድ የቻይና ባለስልጣናት ያቀረቡትን የሴራ ትንተና ክስ ጠቀስ አድርገዋል። "ይህ ክስ ምን ያህል እውነተኛ መሆኑን አላውቅም ነገር ግን እየተነገረ ነው፤ ታዲያ አእምሮው በትክክል የሚሰራ ሰው መድሃኒት ይሰጡኛል ብሎ እምነት ይጥልባቸዋል?" ሲሉ የጠየቁት ሃሚኒ "ስለዚህም የምትሰጡን መድሃኒት ቫይረሱን የበለጠ ለማስፋፋት የምትጠቀበት መንገድ ነው" ሲሉ አሜሪካንን ከሰዋል። መሪው ጨምረውም ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ "የኮሮናቫይረስ የኢራናዊያንን የዘረመል መረጃ በተለያዩ መንገዶች በመውሰድ በተለየ ሁኔታ ለኢራን የተሰራ ነው" ሲሉ ጣታቸውን አሜሪካ ላይ ቀስረዋል። ሌሎች የኢራን ባለስልጣናትም አሜሪካ በአገራቸው ላይ የተጣሉትን ከባድ ማዕቀቦች ለማንሳት ፈቃደኛ ሳትሆን በዚህ ጊዜ እርዳታ ልስጥ ማለቷን አስመሳይነት ሲሉ ወርፈዋታል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ኢራን ክፉኛ በበሽታው ከተጠቁት አገራት መካከል አንዷ ስትሆን፤ በመካከለኛው ምሥራቅ ካሉ አገራት መካከል 21,600 ሰዎች በበሽታው የተያዙባት ቀዳሚ አገር ሆናለች። እስካሁንም በበሽታው ምክንያት የሞተዋል ተብለው በይፋ የተነገረ ኢራናዊያን አሃዝም 1,685 ደርሷል። ነገር ግን በበሽታው የተያዙና የሞቱ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር ከተጠቀሰው ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል። በሽታውን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የፈረንሳይ ድንበር የለሽ ሐኪሞች የበጎ አድራጎት ቡድን ዛሬ ኢስፍሃን በምትባለው የኢራን ግዛት ውስጥ ባለ 50 አልጋ የድንገተኛ ህክምና ማዕከል አቋቁሟል። ኢራን ከምዕራባዊያን ጋር እየተካረረ ባለ ፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ባለችበት ሁኔታ ከብሪታኒያና ከጀርመን በተጨማሪ ፈረንሳይ የህክምና እርዳታ ድጋፍ እያበረከቱ ይገኛሉ።
48211263
https://www.bbc.com/amharic/48211263
አማዞን ነፍሰ ጡር ሠራተኞቹን ከሥራ በማሰናበት ተከሰሰ
አሜሪካዊቷ ትሠራበት የነበረው አማዞን ነፍሰ ጡር ነሽ ብሎ በማባረሩ ፍርድ ቤት ልትገትረው መሆኑ ተሰማ። አማዞን ባለፉት ስምንት ዓመታት ብቻ ተመሳሳይ ክሶች ሲቀርቡበት ነበር።
ባለፉት ስምንት ዓመታት ተመሳሳይ ክስ ሲያቀርቡ የነበሩ ሴቶች እንደሚሉት፤ ይሠሩበት የነበረው ድርጅት ፍላጎታቸውን ሊያሟሟላቸው ፈቃደኛ አልነበረም። አማዞን በበኩሉ ምን ሲደረግ ነፍሰ ጡር የሆኑ ሠራተኞቼን አባርራለሁ ሲል ክሱን አስተባብሏል። • ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት "አማዞን ሠራተኞቹን በማርገዛቸው ብቻ አባረረ የሚለው ክስ ፍፁም ውሸት ነው" ሲል ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል። አክሎም "ድርጅታችን ሁሉንም በእኩል የሚያይ ነው" ብለዋል። "ሠራተኞቻችን የሚያስፈልጋቸውን የሕክምና እገዛ የምናደርግ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ነፍሰ ጡር ለሆኑ እናቶችም ይሠራል።" በማለት ልጅ ለወለዱ እናቶችም ሆነ አባቶች የወሊድ ፈቃድ እንደሚሰጥም ያስረዳሉ። ባለፉት ዓመታት ለቀረቡባቸውና ከሕግ ውጪ ስለፈቷቸው ጉዳዮች ግን አስተያየታቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል። • "ዳቪንቺ ሞናሊዛን ያልጨረሰው ስለታመመ ነው" በቅርቡ የደረሰባትን በደል ወደ ፍርድ ቤት የወሰደችው ቤቨርሊ ሮዜልስ፤ በሰኔ ወር በካሊፎርኒያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳይዋ ይታያል ተብሏል። አማዞን ከ613ሺህ በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን በገና ሰሞን ብቻ እስከ 100 ሺህ ጊዚያዊ ሠራተኞችን ይቀጥራል። • ማይክሮሶፍት ጽሁፍን የሚያቀል አሠራር ፈጠረ የአማዞን ሠራተኞች ድርጅታቸው ላይ ተመሳሳይ ቅሬታ ሲያቀርቡ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራትና ስሟ እንዳይገለፅ የጠየቀች እናት እንደተናገረችው፤ ነፍሰ ጡር በነበረች ወቅት ለአለቃዋ እርጉዝ መሆኗን ተናግራ ወደ ሌላ ክፍል እንድትዘዋወር ብትጠይቅም ሳይፈቀድለት ቀርቷል። ሥራዋ ከባድ ጋሪ መግፋት፣ ከባድ እቃ ማንሳትና ጎንበስ ቀና ማለት ስለሚበዛው ጤናዋ ላይ ችግር ገጥሟት እንደነበር አትረሳም። አማዞን ግን ማንነታቸውን በግልፅ ስላልተናገሩ ሠራተኞቹ አስተያየት ከመስጠት እንደሚቆጠብ ገልጾ፤ ነፍሰ ጡር መሆናቸውን ካሳወቁ ሠራተኞቹ ጋር በቅርበት እንደሚሠራ ተናግሯል። በእንግሊዝ የሚገኘው ጂኤምቢ የሠራተኞች ማኅበር ቃል አቀባይ የሆኑት ግለሰብ እንደሚሉት "በአማዞን የሚሠሩ ነፍሰ ጡር እናቶች የሚነግሩን ለ10 ሰዓት ያህል ቆመው እንደሚሰሩ ነው። እንደ አማዞን ያሉ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን በአግባቡ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፤ እንደ ሮቦት ሊያሠሯቸው አይገባም" ብለዋል።
56534022
https://www.bbc.com/amharic/56534022
ወደ ስልክ መተግበሪያ የተሻገረው ዕቁብ
ተንቀሳቃሽ ስልክ መደዋወያ ብቻ የነበረበት ዘመን አልፏል። ስልካችን ገንዘብ መላኪያ፣ ምግብ ማዘዣ፣ ዜና መመልከቻ ወዘተ. . . ሆኗል።
ዮሐና ኤርምያስ ስልክ ምስጋና ይግባውና፤ በአካል መገናኘት ይጠይቁ የነበሩ ክንውኖች ወደ ስክሪን ከተሻገሩ ሰነባብተዋል። መተግበሪያ ሠሪዎች በተለምዶ 'ባህላዊ' የምንላቸውን ነገሮች ለማዘመን የኮምፒውተር ቀመር ያወጣሉ። በዚህ መልኩ ወደ መተግበሪያ ከተሻገሩ አንዱ ዕቁብ ነው። እድሜ ጠገቡ ማኅበራዊ መረዳጃ አሁን በስልክ መከናወን ጀምሯል። በሰፈር ወዳጅነት፣ በዘመድ አዝማድ ትስስር ወይም በሥራ ባልደረባነት ዕቁብ የሚገቡ ሰዎች ሙሉ ሂደቱን በስልክ የሚያከናውኑበት መተግበሪያ ነው። ስሙ ዕቁብ ይባላል። እንደ ፕሌይ ስቶር ባሉ መተግበሪያ መጫኛዎች ላይ eQUB ተብሎ ተመዝግቧል። ባለፉት ሳምንታት ከ1000 በላይ ሰዎች መተግበሪያውን ጭነዋል። "ሰውን ሰው ያደረገው ዕቁብ ነው" ዮሐና ኤርምያስ የዕቁብ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ አጋር መስራች እና ዋና የቴክኒክ ኃላፊ ናት። ዕቁብ መተግበሪያን እውን ለማድረግ አንድ ዓመት እንደወሰደ ትናገራለች። "ሁሉንም ነገር በስልካችን እየተጠቀምን ነው። የባንክ አገልግሎት፣ የንግድ ልውውጥና አብዛኛው ነገር በስልክ ሆኗል። እኛም ባህላዊውን ዕቁብ ወደ ስልክ መተግበሪያ አመጣነው" ትላለች። ብር ለመቆጠብ እንዲሁም ጠቀም ያለ ገንዘብ በአንድ ጊዜ ለማግኘት የሚረዳው ዕቁብ በመተግበሪያ ሲከወን ቀላል እንደሚሆን ታምናለች። በእርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት ውስንነት፣ ስማርት ስልክ የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ማነስና ሌሎችም መሰናክሎች ከግምት መግባት አለባቸው። ዮሐናም በዚህ ትስማማለች። "ረዥም ጊዜ እንደሚወስድ እንጠብቃለን። ያለው የቴክኒክ እውቀት ውስንነትም መታሰብ አለበት። ሆኖም ግን በጊዜ ሂደት ብዙ ሰው እንዲጠቀምበት ነው የምንፈልገው" ትላለች። ዮሐና እንደ ዕቁብ ያሉ ዓመታት ያስቆጠሩ ማኅበራዊ እሴቶችን ወደ ዲጂታሉ ዓለም በማሻገር ታምናለች። ላለንበት ዘመን ምቹና ቀላሉ መንገድ ዲጂታል አሠራር ነው። "ዲጂታል አሠራር የሚሰጠውን ቅለት ወደ ዕቁብም አምጥተናል። ሰውን ሰው ያደረገው ዕቁብ ነውና የአሁኑ ትውልድም ዕቁብን እንዳይረሳ መተግበሪያው ይረዳል" ስትል ታስረዳለች። ዲጂታል ዕቁብ እንዴት ይሠራል? መተግበሪያው ሲጠነሰስ ቀድሞውንም ዕቁብ የነበራቸውን ሰዎች ወደ ዲጂታሉ ለማምጣት ነው። በተጨማሪም ዕቁብ ያልነበራቸውን ወጣቶች ለመሳብ ታቅዷል። ዕቁብ በቤተሰብ ወይም በሥራ በሚተዋወቁ ሰዎች ሲገደብ፤ ዲጂታል ዕቁብ ግን በየትኛውም ቦታ ያሉ ሰዎች ገንዘብ እንዲጥሉ ያደርጋል። መተግበሪያውን በስልኩ የሚጭን ሰው ስም፣ የትውልድ ቀን፣ መታወቂያ ጽፎ ይመዘገባል። መተግበሪያው ሁለት አማራጮች አሉት። ዕቁብ መፍጠር እና ዕቁብ መሳተፍ። ዕቁብ መፍጠር ማለት የዕቁብ ሰብሳቢ ሆኖ፣ ሰዎችን አስገብቶ ሂደቱን መምራት ነው። መሳተፍ ደግሞ የዕቁብ ቡድኑ አባል መሆን። ዕቁቡ የግል (ፕራይቬት) ወይም የሕዝብ (ፐብሊክ) ሊሆን ይችላል። የግል ዕቁብ እርስ በእርስ የሚተዋወቁ ሰዎች ተገባብዘው ዕቁብ የሚጥሉበት ነው። አሁን ላይ አገልግሎት የሚሰጠውም ይህኛው የመተግበሪያው ክፍል ነው። ዕቁብ ሰብሳቢ ምን ያህል ሰው መሰብሰብ እንደሚፈለግ፣ በምን ያህል ጊዜ ዕቁብ እንደሚጣል እና የገንዘብ መጠኑን ይወስናል። ዕቁብ በቀን፣ በሳምንት ወይም በወር መጣል ይቻላል። ትንሹ የገንዘብ መጠን 10 ብር ሆኖ 50፣ 100 ወይም ከዛ በላይም መጣል ይቻላል። ሰብሳቢው ዕቁብ ፈጥሮ ሰው ይጋብዛል። ከዚያም አባላቱ መለያ ቁጥር ይሰጣቸዋል። እያንዳንዱ የዕቁብ ቡድን የራሱ መለያ ቁጥር አለው። ዕቁቡ ከመጀመሩ በፊት ሰዎች እንዲገቡ ሦስት ቀን ይሰጣል። የተጋበዙት ሰዎች መስፈርት አሟልተው ከተመዘገቡ በኋላ ለዕቁቡ በተቀመጠው ቀን የተስማሙትን የገንዘብ መጠን ይከፍላሉ። ሰብሳቢው ገንዘብ የሚገባበትን የባንክ ቁጥር ይፋ ያደርግና፤ አባላቱ ባንክ ሄደው የሚጠበቅባቸውን ገንዘብ ያስተላልፋሉ። ከዚያም ብር ያስገቡበትን ደረሰኝ መተግበሪያው ላይ ይጭናሉ። ሲጭኑ የዕቁብ ሰብሳቢው መልዕክት ይደርሰዋል። ትክክለኛ መሆኑንም ያረጋግጣል። የዕቁቡ ቀነ ገደብ ሲያልቅ ሰብሳቢው ለአሸናፊው ሰው ገንዘብ ያስተላልፋል። ዕቁብ ጣዮች እንዴት ይተማመናሉ? ዕቁብ የሚጥሉ ሰዎች በትክክል ገንዘብ ስለማስገባታቸው፣ የሚያስገቡት ገንዘብ ሰብሳቢው ጋር ስለመድረሱ ወይም አሸናፊው ሰው ገንዘቡን ስለማግኘቱ መተማመኛ ያስፈልጋቸዋል። ሂደቱ ዲጂታል መሆኑ ደግሞ ነገሮችን ሊያወሳስብ ይችላል። ዮሐና እንደምትለው፤ የሚተዋወቁ ሰዎች የግል ዕቁብ እንዲመሠርቱ የወሰኑት መተማመን ለመፍጠር ነው። ተቋሙ የገንዘብ አቅም ኖሮት እዳ (ላየቢሊቲ) ውስጥ መግባት ሲችል ደግሞ የሕዝብ (ፐብሊክ) ዕቁብ መጀመር ይቻላል። "ለአሁን ዕቁብ የሚገቡት የሚተዋወቁ ሰዎች ናቸው። የዕቁቡ እዳ ሰብሳቢው ላይ ወድቆ፣ የዕቁቡ ተሳታፊዎችም አውቀው ነው የሚገቡት" ትላለች። ተቋሙ አቅሙን አሳድጎ እዳውን መካፈል እስኪችል ሰዎች የግል ዕቁብ ብቻ እንዲገቡ ቢፈቅድም፤ ለወደፊት ከባንኮች ጋር ተጣምሮ የመሥራት እቅድ እንዳላቸውም ትናገራለች። እንደ ምሳሌ የምትጠቅሰው ከባንኮች ጋር አጋር ሆኖ ለዕቁብ የሚሆን የተለየ የሒሳብ ቁጥር መፍጠርን ነው። ከባንኮች ጋር በጥምረት መሥራት ሲጀምሩ፤ አንድ ሰው መተግበሪያውን ተጠቅሞ ከፈለገበት ቦታ ገንዘብ እንዲያስገባ ማድረግም ይቻላል። አሁን ባለው አሠራር የዕቁብ ሰብሳቢ አካውንት ሲፈጥር፣ ተሳታፊዎቹ ገንዘብ ሲያስገቡና ሰብሳቢው ለአሸናፊው ገንዘብ ሲያስገባም መተግበሪያው እንዲያሳውቅ ተደርጓል። "ገንዘብ ሲገባ የዕቁብ ሰብሳቢው ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል። ማን ከፈለ ወይም አልከፈለም የሚለው ይታያል። ዕቁብ ሰብሳቢው ያሸነፈው ሰው አካውንት ተሰጥቶት ገንዘቡን ያስገባል። አሸናፊው ደግሞ ገንዘቡ መግባቱን ያረጋግጣል" ስትል ታብራራለች። ግልጽ አሠራር ለመፍጠር ሲባል መተግበሪያው ከክፍያ ሥርዓት ጋር የተያያዘ ነጥብ አሰጣጥ አለው። ለምሳሌ ዕቁብ አሸናፊው ብር ካልገባለት ከዕቁብ ሰብሳቢው ነጥብ ይቀነሳል። ዮሐና እንደምትለው፤ ቀጣይ እቅዳቸው፤ ማንኛውም ሰው የሚገባበት (ፐብሊክ) ዕቁብን መተግበር ነው። ይህም የተቋሙን የገንዘብ አቅም ማጠንከርና ከባንኮች ጋር መጣመር ይጠይቃል።
news-56914183
https://www.bbc.com/amharic/news-56914183
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የሥልጣን ዘመናቸውን የሚያራዝመውን ውሳኔ ቀለበሱ
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋራማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን በሁለት ዓመት ለማራዘም እያደረጉት የነበረውን ሙከራ መተዋቸውን ተነገረ።
ፕሬዝዳንቱ ምርጫ ሳይደረግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ውሳኔ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ጎሳን መሠረት ባደረጉ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል። ውጊያውፕ ሬዝዳንት ፋርማጆን በሚደግፉና በሚቃወሙ የሠራዊት አካላት አልያም በታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ነው። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ለአገሪቱ ሕዝብ በተላለፈ ንግግር አዲስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አድርገዋል። ጨምረውም የሥልጣን ጊዜያቸው ካበቃበት ከየካቲት ወር ጀምሮ ሲቃወሟቸው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትራቸው ውዝግቡ ከተጀመረ በኋላ ላደረጉት አወንታዊ ጥረት አመስግነዋቸዋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ በመጪው ቅዳሜ በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ሊካሄድ ታቅዶ በነበረው ምርጫ ዙሪያ ባለፈው መስከረም የተደረሰውን ስምምነት ወደነበረበት እንዲመለስ ያደርጋሉ ተብሏል። በዚህም ከሳምንታት በፊት የምክር ቤት አባላት የፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ዘመን ለሁለት ዓመት እንዲራዘም ያስተላለፈው ውሳኔ የሚሻር ይሆናል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በተደረሰው ስምምነት የአገሪቱ ጎሳ መሪዎች ተወካዮቻቸውን ከመረጡ በኋላ እነሱም በበኩላቸው የአገሪቱን ፕሬዝዳንት የሚመርጡ የፌደራሉ የምክር ቤት አባላትን ይሰይማሉ። "ከዚህ በፊት እንዳደረኩት አሁንም በሶማሊያ ውስጥ በወቅቱና ሠላማዊ በሆነ መንገድ ምርጫ እንዲደረግ ያለኝን ፍላጎት በድጋሚ ላረጋግጥ እወዳለሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። ጨምረውም የአገሪቱ የጸጥታ ተቋማት የሠላማዊ ሰዎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ "የአገሪቱን መረጋጋት ከሚያውክ ድርጊቶች" እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል። የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ዘመን መራዘም ተከትሎ በሞቃዲሾ ውስጥ ባሉ ታጣቂዎች መካከል በለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ የተፈጠረውን ግጭት በመሸሽ ነዋሪዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየሄዱ ነው። በተጨማሪም የተከሰተው አለመረጋጋት ታጣቂው እስላማዊ ቡድን አል ሻባብ ሊጠቀምበት ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል።
47931821
https://www.bbc.com/amharic/47931821
ከሸዋ ሮቢት እስከ ሃርቡ ከፀጥታ ኃይሎች ውጭ መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ
ከሸዋ ሮቢት እስከ ሃርቡ ከተማ ድረስ ባለው ዋናው መንገድ ግራ እና ቀኝ 5 ኪሎ ሜትር ድረስ ከፀጥታ አስከባሪ ኃይላት ውጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ።
ይህ የተነገረው በሰሜን ሽዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የተከሰተውን የፀጥታ መደፍረስ ለመፍታት ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከፌደራል ልዩ ኃይል እና ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል የተውጣጣ ጥምር የፀጥታ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ከገባ በኋላ መሆኑን የአማራ ክልል መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል። በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የ11ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ሰኢድ ትኩየ በትናንትናው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጥምር የፀጥታ ኃይሉ፣ በሁለቱም ዞኖች በሚገኙ እና የፀጥታ ስጋት ባለባቸው 10 ወረዳዎች ከሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አድርጎ ወደ ሥራ መግባታቸውን አስታውቀዋል። አክለውም ‹‹ችግሩ ከተከሰተ በኋላ የተለያዩ የፀጥታ ኃይሎች በመግባታቸው በአካባቢው አንፃራዊ ሰላም ቢኖርም አሁንም ድረስ ግን ሕዝቡ ስጋቶች አሉበት›› ብለዋል። ጥምር የፀጥታ ኃይሉ የፀጥታ ዕቅድ አውጥቶ የሕዝቡን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ፣ ተጎጅዎችን ለማቋቋም፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር እና አጥፊዎችን በመለየት ለሕግ ማቅረብ እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። • "የአማራ ልዩ ኃይል ሕዝብን የሚጎዳበት ምክንያት የለውም" አቶ ገደቤ • በአዲስ አበባ ሊፈጸም የነበረ የሽብር ጥቃት መክሸፉ ተነገረ ጥምር የፀጥታ ኃይሉ በመግለጫው ላይ እንዳስታወቀው በሁለቱም ዞኖች ለፀጥታ ስጋት ይሆናሉ ያላቸውን 12 የሚደርሱ ቦታዎች ለይቷል፡፡ በነዚህ ቦታዎች ላይም ጊዜያዊ እና ቋሚ ፍተሻ ይደረጋል ሲል ተናግሯል። በመጨረሻም ከክልል እና የፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ውጭ በየትኛውም አካባቢ በግልም ሆነ በቡድን የሚደረግ ፍተሻ የተከለከለ መሆኑን ገልጿል። የተከሰተው ምን ነበር? በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደዌ ሃረዋ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎችና በአካባቢው ነዋሪ መካከል ለመጀመሪያ ግጭት የተቀስቅሰው መጋቢት 26 2010 ዓ.ም ነበር። ግጭቱ በተፈጠረበት እለት ያነጋገርናቸው የአማራ ክልል የሠላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ፣ ቢያንስ የሁለት የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ማለፉን ለቢቢሲ አረጋግጠው ነበር። ምክትል ኃላፊው በወቅቱ ግጭቱን በማድረስ የወነጀሉት "አካባቢውን ለማተራመስ አጀንዳ የያዘ፣ በዋናነት ከኦነግ አባላት ጋር ትስስር ያለው ኃይል" ያሉትን ነው። • የአማራ ክልል፣ መንግሥት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠየቀ ይህንን ተከትሎም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) "የራስን ጥፋት ለመደበቅ የኦነግን ስም ማጠልሸት ከተጠያቂነት አያስመልጥም፤ አሁንም ቢሆን ሰላማዊ ትግል ላይ ነው ያለነው፤ የአማራ ልዩ ኃይሉ ተግባር የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደርን በማፍረስ ወደ ሌላ ዞን ለመቀላቀል የሚደረግ የድንበር ማስፋፋት ነው ብለን እናምናለን" ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ መግለጫ አውጥቷል። ለተፈጠረው ችግር መጠየቅ ያለበትም ቡድኑን የሚቆጣጠረው የክልሉ መንግሥት እንጂ ኦነግ አለመሆኑንም በመግለጫው ጠቅሷል። ይህ በከሚሴ የተጀመረው ግጭት ወደ አጣዬ፣ ካራቆሬ፣ ማጀቴና በዙሪያቸው ባሉ አካባቢዎች ተሸጋግሮ የበርካታ ንፁኀን ሕይወት አልፏል፤ ንብረትም ወድሟል። • አወዛጋቢው ግጭት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በወቅቱ የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸው በቀለ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት በግጭቱ የታጠቁ ኃይሎች መሳተፋቸውንና የዘረፋ ድርጊትም ተከስቶ እንደነበር ተናግረው ክስተቱ ከክልሉ ልዩ ኃይል አቅም በላይ በመሆኑ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እንዲገባ መደረጉንም አመልክተዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) ግጭቱ በተከሰተበት ወቅት መግለጫ የሰጡ ሲሆን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠሙ ግጭቶች በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም የግጭቱን ምክንያት እና ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን በተመለከተ በማጣራት ለሕዝቡ ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል። ከዚህ በኋላ ነው በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሜ/ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ "በክልሉ የጸጥታ መዋቅር የሚመራው የጸጥታ ኃይል ነው በዋናነት ችግር ያደረሰው" ሲሉ የተናገሩት። የአማራ ክልል የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ምክትል ኅላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ በበኩላቸው "ልዩ ኃይሉም ሆነ የጸጥታ መዋቅሩ ተልዕኮውን በሚገባ የሚያውቅና የአማራ ክልል ህዝብን ደህንነት የሚጠብቅ እንጂ መልሶ የአማራን ህዝብ የሚጎዳበት ምክንያት የለውም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ገደቤ እንዲህ አይነቱ ሃሳብ በጣም የተሳሳተና የአማራን ህዝብ መብትም ታሳቢ ያላደረገ ነው በማለት "እዚያ አካባቢ የሚንቀሳቀስ ኃይል መኖሩ ይታወቃል ማስረጃዎችም አሉን። የተፈጸመው ጥቃትም በአማራው ህዝብ ላይ እና በንጹሃን ላይ ነው። ይህን የፈጸመው ልዩ ኃይል ነው ማለት ምን ማለት ነው?" ሲሉ ይጠይቃሉ። የአማራና የኦሮሞ ክልል የፀጥታ አካላት በሁለቱ ክልሎች የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት አብረው ለመስራት በባህር ዳር ከተማ በተሰበሰቡበት ወቅት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል።
news-45318953
https://www.bbc.com/amharic/news-45318953
አብዲ ሞሃመድ ዑመር ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ
የሶማሌ ክልልን ለአስር ዓመታት ገደማ ያስተዳደሩት አብዲ ሙሃመድ ዑመር ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ።
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው መደበኛ ያልሆነ ጉባዔ ነው አብዲ ሙሃመድ ዑመርን ጨምሮ የሰባት አባላቱ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ የወሰነው። ምክር ቤቱ የግለሰቦቹን መብት ያነሳበት ምክንያት በቅርቡ በክልሉ ከተነሳው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ እንደሆነም አስታውቋል። • በሶማሌ ክልል በተከሰተ ቀውስ ህይወት ሲጠፋ አብያተ-ክርስትያናት ተቃጠሉ የአባላቱን ያመለከሰስ መብት የማንሳት ውሳኔውንም ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ እንዳፀደቀው ነው የተገለፀው። ከዚህ በፊት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ሙስጠፋ ሙሀመድን ዑመርን የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዝደንት አድርጎ መሾሙ አይዘነጋም። ክልሉን ለበርካታ ዓመታት የመሩትን አቶ አብዲ ሙሐመድ ኡመርን በመተካት ለሁለት ሳምንታት ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ አህመድ አብዲ ሞሐመድ፤ አቶ ሙስጠፋ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲቀጥሉ የፓርቲው ሕገ-ደንብ እንደሚፈቅድላቸው ገልጸው ነበር። • ሙስጠፋ ኡመር የሶማሌ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ • አብዲ ሞሃመድ ኡመር ከስልጣናቸው ወረዱ • አቶ አብዲ ስለተናገሩት ጉዳይ እንደማያውቅ ኢህአዴግ ገለፀ
news-49605277
https://www.bbc.com/amharic/news-49605277
ለጉብኝት ክፍት የተደረገው የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት በፎቶ
የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት ዛሬ ለጉብኝት ክፍት ተደርጓል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2011 ዓ. ም. እሥር ቤቱ ለሕዝብ እይታ ክፍት እንደሚሆን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታውቋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እሥር ቤቱን ጎብኝተዋል • የእስረኞች መፈታትና የማዕከላዊ መዘጋት ውሳኔ አንድምታዎች • ''የፍርድ ቤቶች ተዓማኒነት እና ገለልተኛነት ይመለሳል'' ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈጸምበት ነበር የሚባለው ማዕከላዊ እሥር ቤት፤ ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ. ም. የሚከበረውን የፍትህ ቀን ምክንያት በማድረግ ለሕዝብ እይታ ክፍት መደረጉንም የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታውቋል። የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እሥር ቤቱን ጎብኝተዋል። በቦታው የሚገኘው ባልደረባችን ካነሳቸው ፎቶግራፎች ጥቂቱን እናካፍላችሁ፦ የማዕከላዊ እስር ቤት ውጫዊ ገፅታ በከፊል ለጉብኝት ክፍት የተደረገው የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እሥር ቤቱን ጎብኝተዋል የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት የቀድሞው እሥር ቤት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2011 ዓ. ም. ድረስ ለሕዝብ እይታ ክፍት ይሆናል ጳጉሜ 5 ቀን 2011 ዓ. ም. የሚከበረውን የፍትህ ቀን ምክንያት በማድረግ ለሕዝብ እይታ ክፍት መደረጉንም የጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታውቋል
news-46510556
https://www.bbc.com/amharic/news-46510556
ግብጽ 'የፒራሚድ የእርቃን ምሰል' ላይ ምርመራ ጀመረች
ዴንማርካዊ ጥንዶች የግብጽ ፒራሚድ ላይ እርቃናቸውን ሆነው የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ቁጣን ከቀሰቀሰ በኋላ ግብጽ የተንቀሳቃሽ ምስሉን በሚመለከት ምርመራ ለመጀመር ተገድዳለች።
ተንቀሳቃሽ ምስሉ ወግ አጥባቂ በሆነችው ሃገረ ግብጽ ከፍተና ቁጣን ቀስቅሷል። አቃቤ ሕግ የተንቀሳቃሽ ምስሉን ትክክለኛነት የማረጋገጥ ኃላፊነት እንደተሰጠው የተዘገበ ሲሆን ቪዲዮ እውነት ሆኖ ከተገኘ ጥንዶቹ 140 ሜትር የሚረዝመውን ፒራሚድ እንዴት አድረገው መውጣት ቻሉ የሚለውም ሌላው ጥያቄ ነው። • የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ከኢትዮጵያና ኤርትራ ጋር ባላቸው ግንኙነት ጥያቄ ቀረበባቸው • አባቱ ላይ 5000 ዓመት ያስፈረደው ልጅ • ቢዮንሴ በህንድ ለቱጃር ልጅ ሰርግ ዘፈነች በግብፅ ጊዛ ከተማ የሚገኘው ፒራሚድ ከ7ቱ የዓለማችን ድንቃ ድንቅ ስፍራዎች መካከል እንዱ ነው። ተንቀሳቃሽ ምስሉን የቀረጸው ፎቶግራፈር እንደሚለው ከሆነ እሱ እና ጓደኛው ለሰዓታት ተደብቀው ከቆዩ በኋላ የፒራሚዱ አናት ላይ መውጣት ችለዋል። የግብጽ ባለስልጣናት ፒራሚዶች ላይ መውጣት ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን አስታውሰው በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚታዩት ትዕይንቶች የግብጽ ሕዝብን ሞራል የሚጥሱም ናቸው ይላሉ። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከግብጽ ውጪም ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። በርካቶች ድርጊቱን ''አሳፋሪ የሌላ ሕዝብን ባህል፣ ሃይማኖት እና እሴት መናቅ ነው'' ሲሉ ገልጸውታል። ቪዲዮውን የቀረጸው ፎቶግራፈር ለረዥም ዓመታት ፒራሚዱን መሰል ግዙፍ መዋቅር የመውጣት ፍላጎት እንደነበረው በመጥቀስ፤ ''በድርጊታችን በርካቶች ቢበሳጩም አድናቆታቸውን የገለጹልን በርካታ ግብጻውያን መኖራቸውንም መዘንጋት የለብንም'' ብሏል። ፎቶግራፈሩ ጥንዶቹ በፒራሚዱ አናት ላይ ወሲብ ፈጽመዋል የተባለው ውንጀላ ግን ከእውነት የራቀ እንደሆነ ተናግሯል። ከዚህ ቀደም በርካታ ጎብኚዎች የግብጽ ፒራሚዶች አናት ላይ ለመውጣ በሚያደርጉት ሙከራ ህይታቸውን ያጡ ነበር። እአአ 1980 ላይ ግን የግብጽ መንግሥት ፒራሚዶች ላይ መውጣትን ከለከለ። ክልከላው ግን አንዳንድ ሕግ ጣሽ ጎብኚዎችን ከፒራሚዱ አናት ላይ ከመውጣት አልገደበም። ከሁለት ዓመታት በፊት በአስራዎቹ የሚገኝ ጀርመናዊ ታዳጊ ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስል በካሜራው ለማስቀረት ከፒራሚድ አናት ላይ ወጥቶ ነበር። ጥፋቱ ታዳጊው ላይ እስከ ሶስት ዓመት ሊያስፈርድበት ይችል የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ በጀርመን መንግሥት ጣልቃ ገብነት ታዳጊው ከመከሰስ ተርፏል። ከአንድ ዓመት በፊትም የቱርክ ዜግነት ያለው ጎብኚ ፒራሚድ ላይ በመውጣቱ ለአጭር ጊዜ ለእስር ተዳርጎ ነበረ።
news-56021561
https://www.bbc.com/amharic/news-56021561
በትግራይ ክልል አጣሪዎችና ሚዲያዎች እንዲገቡ በመንግሥት ላይ ጫና እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ
የኢትዮጵያ የውጭ አጋሮች የመብት መርማሪዎችና ሚዲያዎች ያለ ምንም እክል በመላው ትግራይ ክልል እንዲንቀሳቀሱ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
በተለያዩ የዓለማችን አገራት ውስጥ ግጭቶችን የሚከታተለው አለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ ነው ይኼንን ጥሪ ያቀረበው። ቡድኑ "Finding a Path to Peace in Ethiopia's Tigray Region" በሚል ርዕስ ባወጣው የ19 ገፅ ሪፖርት አገሪቷ ወደ ሰላም በዘላቂነት የምትመለስበትን፣ ከትግራይ ክልል ጋር ያለው ግጭት በቋሚነት የሚፈታበትን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን አካቷል። ቡድኑ ለአሜሪካ መንግሥት፣ ለአውሮፓ ህብረትና ለአፍሪካ ህብረት እንዲሁም ሌሎች አጋሮች የመብት ተመራማሪዎችና ሚዲያዎች ያለምንም እክል ገብተው ስራቸውን እንዲያከናውኑ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንዲፈቅዱ ጫና እንዲያደርጉ ጠይቋል። ተፈፀሙ የሚባሉ ጥሰቶች በሙሉ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ እነዚሁ አካላት ጫና ሊያደርጉ ይገባል ብሏል። የተረጋጋ ፖለቲካ ለመፍጠር ባለስልጣናቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ጨምሮ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሚጠይቀው የህይወት አድን እርዳታ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ መንግሥት በሩን ሊከፍት እንደሚገባም በሪፖርቱ አካቷል። በክልሉ ውስጥ በፌደራል መንግሥት የተቋቋመው የአዲሱን ጊዜያዊ አስተዳደር ባለስልጣናት ጨምሮ፣ የተለያዩ የረድዔት ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ ከዚህ እንዳይከፋ እንዲሁም በርካቶችን ከሞት ለመታደግ የተለያዩ የረድዔት ድርጅቶች ያለ ምንም እክል ሊንቀሳቀሱና እርዳታቸውን ሊለግሱ እንደሚገባም አስምሯል። ለሳምንታት ያህል የዘለቀውን ውጊያ ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ የክልሉን አስተዳዳሪ ህወሃት ከስልጣን በማስወገድ የክልሉን መዲና እንደተቆጣጠረና ድል እንደተቀናጀ አሳውቋል። ምንም እንኳን የፌደራል መንግሥቱ ጦርነት እንዳለቀ ቢያውጅም የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ ሌሎች ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ውጊያው መቀጠሉን ነው። በዚህ ውጊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዳለቁ፣ በትግራይ 1/3ኛ የሚሆነውን ነዋሪ አፈናቅሏል፣ በርካታ ጥሰቶችም በሁሉም ወገኖች ተፈፅመዋል ያለው ሪፖርቱ እንዲሁም 4.5 ሚሊዮን የሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች አስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። የፌደራል መንግሥቱ፣ ከስልጣን የተወገዱት የትግራይ አመራሮች፣ ሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና አቀንቃኞች መሬት ላይ ስላለው ነገር የተለያየ እውነታን መናገራቸውን ተከትሎ ልዩነቶች እየሰፉ ነው፤ ለሚያስፈልገው እርዳታም እንቅፋት ሆኗል ይላል ሪፖርቱ። ይህንንም ለማስተካከል መደረግ ያለበት ብሎ ሪፖርቱ ያሰፈረው የፌደራል መንግሥቱ ጋዜጠኞች ሪፖርት እንዲያደርጉ እንዲሁም ሪፖርት የተደረጉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተጨማሪ ምርመራ እንዲያደርግ መሆን አለበት። ከዚህም በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር እንዲሁ የራሱን ምርመራ እንዲያከናውን መፈቀድ እንዳለበትና መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤን ጨምሮ በአገሪቷ ላሉት የሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ሂውማን ራይትስ ዋች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ለመሳሰሉ አለም አቀፍ ድርጅቶች በሩን ሊከፍት ይገባል ብሏል። በተለያዩ ሪፖርቶች የኤርትራ ወታደሮች መሳተፋቸው የተጠቀሰ ሲሆን በቅርቡ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል በአስቸኳይ እንዲወጡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) የአውሮፓ ህብረት መጠየቃቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በተደጋጋሚ ይህ ህግ የማስከበር ዘመቻ እንደሆነና በትግራዩ ግጭት የኤርትራ ጦር አለመሳተፉን ማሳወቁ የሚታወስ ነው። የአውሮፓ ህብረትን ተከትሎ አሜሪካም ሆነ ሌሎች ተባብረው የሰብዓዊ ረድዔት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ እርዳታ እንዲደርስ እንዲያደርጉም ካስፈለገም ከትግራይ ኃይሎች ጋር እንዲደራደሩ መሆን እንዳለበት ሪፖርቱ አቅጣጫ ያስቀምጣል። የፌደራል መንግሥቱ "የኢትዮጵያን ለውጥ ለመቀልበስና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚሞክሩ ኃይሎች ናቸው ብሎ የሚጠራቸው የህወሃት ኃይሎች" ጋር ምንም አይነት ድርድር አይኖርም ይላል። በአንፃሩ "የወንጀለኞች ቡድን" የጠራቸውን ግለሰቦች ወደ ፍትህ መቅረብ አለባቸው ማለቱ ይታወሳል። የህወሃት ኃይል ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በአገሪቷ ላይ ለደረሱ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በባለፉት አመታት ለተነሱ የብሔር ግጭቶችና አለመረጋጋቶች የፌደራል መንግሥቱ ተጠያቂ አድርጓቸዋል። የህወሃት ከስልጣን መወገድ ለክልሉ ዘለቄታዊ ሰላም ያመጣል ብሎ የሚያምነው የፌደራል መንግሥት የትግራይ ክልል መሰረተ ልማት ለመገንባትና በግጭቱ ወቅት የወደሙ ልማቶችን እንደገና ለመቀጠል ጥረት እያደረግኩ ነው በማለት በተደጋጋሚ በመግለጫዎቹ አስታውቋል። ሪፖርቱ በበኩሉ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ "የፌደራል መንግሥቱ የትግራይ ተወላጆችን ከአዲሱ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ትግራይን እንደገና እንዲገነቡ ሊያሳምናቸው ይገባል" ብሏል። አሁን ባለው ሁኔታ በፌደራል መንግሥቱ በተሾመው አዲሱ አስተዳደር ላይ በክልሉ የተነሳው ተቃውሞን ለመቀልበስ መንግሥት ማድረግ አለበት ያላቸውንም ሪፖርቱ አስቀምጧል። የአካባቢውን ትብብር ለማሳደግ የፌደራል መንግሥቱ የኤርትራን ወታደሮች እንዲያስወጣ እንዲሁም ለበርካታ የትግራይ ተወላጆች አልዋጥ ያለውን የአማራ የግዛት መቆጣጠር እንዲያስመልስ ማድረግ አለበት የሚል ነጥብ አስቀምጧል። በአማራ በኩል የይገባኛል ጥያቄዎች የሚነሳባቸውን የደቡብና ምዕራብ ግዛቶች በፌደራል የድንበር አጣሪ ኮሚሽን ተገምግሞ በፖለቲካዊ ድርድር መፍትሄ እንዲያገኝ መደረግ እንዳለበትም አቅጣጫ አስቀምጧል። በተለይም በተለያዩ ሪፖርቶች ላይ በግጭቱ ተሳታፊ መሆኑ የተጠቀሰው የኤርትራ ሰራዊት ከአካባቢው እንዲወጣ ለማድረግ በኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ የእርዳታ መቋረጥን ጨምሮ ሌሎች ጫናዎችን እንዲያደርጉ ቡድኑ ለአውሮፓ ህብረትና ለአለም አቀፍ አካላት ጥሪውን አቅርቧል። ከዚህም በተጨማሪ የባይደን አስተደዳደር እንዲሁ የኤርትራ ሰራዊት እንዲወጣ ያደረገውን ጥሪ እንዲደግምና በአስመራ ላይ ተፅእኖ ማድረስ የሚችሉትን አጋሮቹ የሆኑትን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ሳዑዲ አረቢያ በኩል መልዕክት እንዲደርስ ማድረግ አለበት ይላል። በአጠቃላይም "በዋናነት የኢትዮጵያ ተፎካካሪ ልሂቃን በዋናነት የትግራይን በራስ የማስተዳደር መብት እንዲሁ ሰፋ ባለ መልኩ ሲታይ ደግሞ በማዕከላዊ መንግሥትና በክልሎች መካከል ሊኖር የሚገባውን የስልጣን ክፍፍል፣ በፌደራል ስርዓቱ ላይ የብሔር ሚና ምን ሊሆን ይገባዋል የሚለው ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እየተካሄደ ያለው ሽግግር ወደ ከፋ ቀውስ ከማምራቱ በፊት፤ የኢትዮጵያን ስር የሰደደና መሰረታዊ ፖለቲካዊ ክፍፍልን ለመፍታት ሁሉን ያካተተ ውይይት አስፈላጊነትን" አስምሯል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው መቃቃርና አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል።
news-56276139
https://www.bbc.com/amharic/news-56276139
ትግራይ፡ የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ ግጭት ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል አለ
በትግራይ ግጭት የተሳተፉ አካላት "የጦር እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ፈጽመው ሊሆን እንደሚችል" የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባሽሌት ገለጹ።
ኮሚሽነሯ ዛሬ [ሐሙስ] ከትግራይ የሚወጡ ተያያዢነት ያላቸውና ተአማኒ ሪፖርቶች በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ የተለያዩ ወገኖች የተፈፀሙ ከባድ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊ እርዳታ ሕጎች ጥሰት ማመልከታቸውን ተናግረዋል። በዚህም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ተፈጸሙ የተባሉትንና እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ ሪፖርት የተደረጉ የጅምላ ግድያዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ወሲባዊ ጥቃቶችን ለመመርመር እንዲችል ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል። ሚሸል ባሽሌት የተፈፀሙት የመብት ጥሰቶች እንደ ጦር እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ሊቆጠሩ እንደሚችሉ ገልፀው በዚህም ውስጥ የተለያዩ አካላት ተሳታፊ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ጠቁመዋል። በተጠቀሱት ድርጊቶች ውስጥ ተሳትፎ ሊኖራቸው ይችላል ያሏቸውን አካላት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ህወሓት፣ የኤርትራ ወታደሮች፣ የአማራ ክልል ኃይሎችና ግንኙነት ያላቸው ታጣቂ ሚሊሻዎች ናቸው ብለዋል። "በግጭቱ ላይ በርካታ አካላት መሳተፋቸውን ጨምሮ፤ ጥሰቶቹን መካድ እንዲሁም ጣት መጠቆም ይታያል። የጥሰቶቹን ሪፖርት በተመለከተ ግልፅ፣ ነፃ የሆነ ግምገማና ምርመራ ያስፈልጋል። የጥቃቱ ሰለባና ተራፊዎች የእውነትና የፍትህ ጥያቄያቸው ሊካድ አይገባም" ብለዋል ኮሚሽነሯ። አክለውም "የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ቢሮና ሌሎች ነፃ መርማሪዎች ወደ ትግራይ ገብተው ያለውን ሁኔታ እንዲገመግሙና እንዲመረምሩ ፍቃድ እንዲሰጠን እንጠይቃለን። የትኛውም አካል ይፈፅመው እውነታው መታወቅ አለበት፤ ፈጻሚዎቹም ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል" በማለት ጥሪ አቅርበዋል። ኮሚሽነሯ ሚሸል ባሽሌት በአሁኑ ወቅት "የሚረብሹ" ያሏቸው የመደፈር፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ መጠነ ሰፊ የንብረት ውድመትና ዘረፋ መፈጸሙን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች እየደረሳቸው መሆኑን አስታውቀዋል። "በክልሉ ተዓማኒ የሚባሉ ዓለም አቀፉን የሰብዓዊ መብት የሚጥሱ ሪፖርቶች በግጭቱ ተሳታፊ በሆኑ አካላት በሙሉ መፈፀማቸውን የሚገልጽ መረጃ ደርሶናል" ብለዋል። አክለውም "ግልጽና ነፃ ምርመራ ካልተካሄደና ጥሰቱን የፈፀሙትን አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ካልተቻለ እነዚህ ጥቃቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ እፈራለሁ። ሁኔታውም ባልተረጋጋ መልኩ ለዓመታት ሊቀጥል ይችላል" ብለዋል። ኮሚሽነሯ ከአስተማማኝ ምንጭ ነው ያገኘሁት ባሉት መረጃ መሰረት በአዲግራት፣ በመቀለ፣ በሽረና በውቅሮ በተነሳው ተቃውሞ ስምንት ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል ብለዋል። በተጨማሪም በትግራይ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙት በመቀለ፣ በአይደር፣ በአዲግራትና በውቅሮ በአንድ ወር ብቻ 136 ወሲባዊ ጥቃቶች ሪፖርት መደረጋቸውን ገልፀው፣ ይህም ከዚህ በላይ በርካታ ጥቃቶች መድረሳቸውን ማሳያ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ እነዚህ ጥቃቶች መድረሳቸውን አረጋግጦ ምርመራ ከፍቻለሁ ማለቱ የሚታወስ ነው። በተጨማሪም በቅርቡ ሂውማን ራይትስ ዋች፣ በትግራይ ከተሞች በኅዳር ወር በዘፈቀደ የከባድ መሣሪያ ድብደባ ደርሷል ያለውን መረጃ እንዳገኙና ማረጋገጥ መቻላቸውን ጠቁመዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአክሱም፣ ደንገላትና በማዕከላዊ ትግራይ በኤርትራ ጦር የተፈፀሙ ግድያዎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም እንዲሁ ማረጋገጣቸውን አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በቅርቡ ታስረው የተፈቱትን የቢቢሲ ጋዜጠኛን ጨምሮ ሌሎች ዘጋቢዎችና ተርጓሚዎችን በተመለከተ ያላቸውን ስጋትም ገልጸዋል። ምንም እንኳን ጋዜጠኞቹ በአሁኑ ሰዓት ያለ ክስ ቢለቀቁም አንድ የመንግሥት ባለስልጣን "ዓለም አቀፉን ሚዲያ የሚያሳስቱ ግለሰቦችን ተጠያቂ ይሆናሉ" ማለታቸው እንዳሳሰባቸውም ገልፀዋል። "የሰብዓዊ መብት ጥቃት ሰለባዎችና የዓይን እማኞች ጉዳት ሊደርስብን ይችላል በሚል ፍራቻ ሊገደቡ አይገባም" ብለዋል ከፍተኛ ኮሚሽነሯ። ባሽሌት በዛሬው መግለጫቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊ ረድዔት ድርጅቶች የሰጠውን ፈቃድ እንዲሁም አንዳንድ እርምጃዎቹን በመልካም ጎን አነንስተዋል። በተጨማሪም ባለስልጣናቱ የገቡትን ቃል ወደ ተግባር እንዲለወጡ ጠይቀዋል። የእራሳቸው ቢሮም በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚደረጉ ምርመራዎችን ይደግፋል ብለዋል። በትናንትናው ዕለትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከትግራይ ክልል ግጭት ጋር በተያያዘ የተነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ግድያዎችን በተመለከተም መንግሥት ከፌደራል ፖሊስ፣ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመጣመር ይመረምራል ብለዋል። ጨምረውም የእነዚህን አካላት ምርመራ መሰረት በማድረግም መንግሥታቸው በድረጊቱ ውስጥ እጃቸው ያለበትን አካላት ወደ ፍትህ እንደሚያቀርብ አፅንኦት ሰጥተው፤ በምርመራው ላይ ተጨማሪ እርዳታ ካስፈለገ መንግሥት የውጭ አካል ሊጋብዝ እንደሚችል ጠቆም አድርገዋል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናትና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሚያደርጉት ምርመራ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም ሕዝብ በወቅቱ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ቃለ አቀባዩ ገልፀዋል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት በመፈፀሙ መንግሥት "ሕግ የማስከበር" ወታደራዊ ዘመቻን ማካሄዱን ገልጿል። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን ቢገልጽም በአንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች እንዳሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከፍተኛ ኮሚሽነሯም በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ትግራይ ጦርነቱ መቀጠሉንም መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።
news-55082614
https://www.bbc.com/amharic/news-55082614
የዲያጎ ማራዶናን ሞት ተከትሎ በአርጀንቲና የሶስት ቀን ሐዘን ታወጀ
የዲያጎ ማራዶናን ሞት ተከትሎ በአርጀንቲና የሶስት ቀን ሐዘን ታወጀ።
ዲያጎ ማራዶናን በአገሩ የእግር ኳስ ንጉስ እየተባለ የሚንቆለጳጰሰው ማራዶና በ60 ዓመቱ ትናንት ረቡዕ ምሽት ሕይወቱ ማለፏን ተከትሎ በአርጀንቲና የሶስት ቀናት ሐዘን ተጀምሯል። የማራዶና አስክሬንም በመጪዎቹ ሶስት ቀናት የአርጀንቲና መንግሥት መቀመጫ በሆነቸው ካሳ ሮዛዳ እንደሚቆይ ተገልጿል። የማራዶና ሞትን ተከትሎ በርካቶች ሐዘናቸውንም እየገለጹ ይገኛሉ ነው። ''ማራዶና እግጅ አስገራሚ ፍጥረት ነው፤ ነገር ግን እሱን መሆን በጣም ከባድ ነበር። ገና በለጋ እድሜው በታዋቂነቱ ምክንያት የመገናኛ ብዙሃን ትኩረትን ማግኘት ችሏል። እንደ ሌሎቻችን አይነት ሕይወት አላሳለፈም።'' ብሏል የማራዶና ቡድን አባል የነበረው ኦሲ አርዲለስ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ። የቀድሞው የአርጀንቲና ኮከብ ተጫዋች እና በኋላም የአገሩ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ያረፈው ቤቱ ውስጥ ሳለ በልብ ሕመም እንደሆነ ተገልጿል። ማራዶና በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን በተከታይነትም ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ ሕክምና ይደረግለታል ተብሎ ነበር። ትናንት ምሽት በተደረጉ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች መጀመሪያ ላይ ለማራዶና የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት የተደረገ ሲሆን በዚህ ሳምንት በሚደረጉ ሁሉም የአውሮፓ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ማራዶና ይታሰባል። ሜሲ እና ሮናልዶን ጨምሮ ብራዚላዊው የእግር ኳስ ጥበበኛ ፔሌ እንዲሁም በርካታ የእግር ኳስ ፈርጦች በማራዶና ሕልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። ''አንድ ቀን በሰማይ ቤት ከማራዶና ጋር እግር ኳስ እንደምንጫወት ተስፋ አደርጋለሁ'' ብሏል ፔሌ። የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በበኩሉ ''የዓለምን እግር ኳስ ያሻሻል ሰው ነበር'' ብሏል። የቀድሞ የቶተንሀም አሰልጣኝና የአርጀንቲናዊው ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ''በሀዘን ልቤ ተሰብሯል። ማራዶና የእኔ ጀግና እና ጓደኛዬ ነበርክ። ከአንተ ጋር እግር ኳስና ሕይወትን በማየቴ በጣም ዕድለኛ ነኝ'' ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል። የማራዶና ሕይወት የዓለማችን የምንጊዜም ታላላቅ ተጫዋቾች ከሚባሉት አንዱ የሆነው ማራዶና አርጀንቲና እአአ በ1986 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ስትሆን የቡድኑ አምበል የነበረ ሲሆን ድንቅ ችሎታውንና የታወቀባቸውን የኳስ ጥበቡን በማሳየት ዓለምን አስደምሞ ነበር። በተለይ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ባደረገችው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ እሱ "የእግዜር እጅ" ያላትና ዳኞች ሳያዩ በእጁ ያስቆጠራት ግብ ዘወትር ትታወሳለች። በተጨማሪም ለስፔኑ ባርሴሎናና ለጣሊያኑ ናፖሊ ቡድኖች በአውሮፓ ውስጥ የተጫወተ ሲሆን፤ በጣሊያን ሴሪ አ ውስጥም ሁለት ጊዜ ዋንጫ ማንሳት ችሏል። የአርጀንቲና እግር ኳስ ማኅበር የማራዶና ሞት በተሰማ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ "በጀግናችን ሞት በጣሙን አዝነናል" በማለት "ሁልጊዜም በልባችን ውስጥ ትኖራለህ" ብሏል። ማራዶና ለአገሩ አርጀንቲና በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ በተደረጉ 91 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 34 ግቦችን አስቆጥሯል። ማራዶና የተከለከሉ አበረታች መድኃኒቶችንና ዕጽ በመጠቀም ስሙ በተደጋጋሚ ሲነሳ የቆየ ሲሆን ከስፖርትም እገዳ ተጥሎበት ነበር። ማራዶና ፕሮፌሽናል እግር ኳስን ከዛሬ 23 ዓመት በፊት በ37 ዓመት ዕድሜው ያቆመ ሲሆን፤ በአርጀንቲና ውስጥ ያሉ ቡድኖችን በአሰልጣኝነት ከመራ በኋላ የአገሩን ብሔራዊ ቡድንንም በማሰልጠን ለዓለም ዋንጫ አብቅቷል። ከዚያም በኋላ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና በሜክሲኮ ውስጥ የሚገኙ ቡድኖችን በተለያዩ ጊዜያት አሰልጥኖ ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ደግሞ የአገሩን አንድ ቡድን በማሰልጠን ላይ ነበር።
news-53685716
https://www.bbc.com/amharic/news-53685716
ምርጫ፡ የትግራይ ክልል የምርጫ ሥርዓት ለውጥና አንድምታው
የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ በማድረግ የምርጫ ሥርዓት ለውጥና እንዳደረገና በክልሉ ምክር ቤት ውስጥ ያለው የመቀመጫ ብዛት ላይ 38 በመጨመር ወደ 190 ከፍ እንዲል አድርጓል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው በክልሉ ከዚህ በፊት የነበረውን የአብላጫ ድምጽ የምርጫ ሥርዓት በመቀየር በ"ቅይጥ ትይዩ የምርጫ ሥርዓት" እንዲተካ በማድረግ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። በዚህም በምክር ቤቱ ውስጥ ካሉ መቀመጫዎች ውስጥ 80 በመቶዎቹ የአብላጫ ድምጽ ባገኘው የፖለቲካ ድርጅት የሚያዝ ሲሆን፤ 20 በመቶው ደግሞ በተመጣጣኝ ውክልና ለተወዳዳሪ ድርጅቶች እንደሚከፋፈል ተገልጿል። በክልሉ ያሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምን ይላሉ? በክልሉ ከሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክንፈ ሃዱሽ ከመጀመሪያ ጀምሮ የምርጫ ሥርዓቱ መቀየር አለበት የሚል አቋም እንደነበራቸውና "ተመጣጣኝ ውክልና" እንዲኖር ሃሳብ አቅርበው እንደነበር ያስታውሳሉ። "ይሁን እንጂ ዛሬ ምክር ቤቱ ያፀደቀው በገዢው ፓርቲ የቀረበውን 'ቅይጥ ትይዩ የምርጫ ሥርዓት' ነው" ይላሉ። እንደ ተፎካካሪ ፓርቲ ያቀረቡት ሃሳብም በአዋጁ እንዳልተካተተ ይናገራሉ። ይህ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ ምክር ቤት የሚገቡበትን እድል የሚያጠብና የገዢው ፓርቲ እድል የሚያሰፋ ነው ብለው እንደሚያምኑ ያስረዳሉ። አቶ ክንፈ 38 ወንበር ለሚኖረው 20 በመቶ ውክልናም ገዥው ፓርቲ ስለሚወዳደር በምክር ቤቱ የፀደቀው ቅይጥ የምርጫ ሥርዓት አካታች እንዳልሆነ እንደሚያስቡ ይናገራሉ። "በዚህ የምርጫ ሥርዓትም ተጠቃሚ የሚሆነው ገዢው ፓርቲ ነው። እኛ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እንደ ገዥው ፓርቲ የተደራጀ መዋቅር የለንም። የመንግሥት ሃብት የምንጠቀምበት እድል የለም" ሲሉ ምክር ቤቱ በገዥው ፓርቲ በኩል የሚቀርቡ ሃሳቦችን እንደሚያፀድቀው የሚጠበቅ ነው ብለዋል። ክልሉ አካሂደዋለሁ ያለው ምርጫውም ፍትሃዊ፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ የምርጫ ሕጉ አካታች መሆንና ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በመሰረታዊ ጉዳይ የተስማሙበት መሆን ቢኖርበትም የምርጫ ሕጉ ግን ይህንን ባካተተ መልኩ አይደለም የተዘጋጀው ይላሉ። ከዚህም ባሻገር "ገለልተኛ የሆነ የፍትህ ተቋማት መኖር አለባቸው" የሚሉት አቶ ክንፈ፤ እስካሁን ባለው ሂደት እነዚህ አካላት ነፃ ናቸው ማለት እንደማይቻል ይናገራሉ። የአሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶሪ አስገዶም ግን ከዚህ የተለየ ሃሳብ ነው ያላቸው። እርሳቸው እንደሚሉት በክልሉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ ሕጉ መለወጡና ቁጥሩ ከፍ ማለቱ እነርሱን ለማካተት ይጠቅማል ብለዋል። ከዚህ በፊት የትግራይን ምክር ቤት ወንበር ሙሉ በሙሉ የያዘው ገዥው ፓርቲ መሆኑን የገለፁት አቶ ዶሪ፤ አሁን ግን በምርጫው ያሸነፈው ፓርቲ አብላጫ መቀመጫ እንዲኖረው ያስችላል ብለዋል። ወደፊት ይህ ቁጥር መሻሻል እንዳለበት አቶ ዶሪ ሃሳብ ሰጥተዋል። የክልሉ እርምጃ በሕገ መንግሥት ባለሙያ ዕይታ በሕገ መንግሥት ላይ ጥናት የሰሩት አደም ካሴ (ዶ/ር) በክልሉ በተሻሻለው የምርጫ ሥርዓትና የምክር ቤት መቀመጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የተወሰነ ቦታ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ይላሉ። ነገር ግን የሚያሸንፈው ፓርቲ ከ20 በመቶውም መቀመጫ ስለሚወስድ ለተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ብዙም ለውጥ እንደማያመጣ ይናገራሉ። የምርጫ ሕግን የማውጣት ሥልጣን የፌደራል መንግሥት ነው የሚሉት አደም (ዶ/ር) ያለ ፌደራል መንግሥቱ እውቅና ይህንን መቀየር ሥልጣን አላቸው ወይ የሚለው ወሳኝ ጥያቄ መሆኑን ያነሳሉ። "ሕገ መንግሥቱ የምርጫ ሥርዓቱ በአብላጫ ድምፅ የተመሰረተ የሚያደርገው የፌደራል ፓርላማውን ብቻ ነው፤ የክልሎቹን በምርጫው ሕግ እንዲወጣ ነው የሚለው፤ በመሆኑም እንደ ክልል ይህንን ሕግ ማውጣት ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይፃረራል" ይላሉ። ይሁን እንጂ ክልሎች ይህ ሥልጣን ቢሰጣቸው እንደ ራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ምርጫ እንዲያካሂዱና በምክር ቤቱም የተለያዩ አካላትን ማካተት እንደሚያስችል ሃሳብ ይሰጣሉ። ምክንያታቸውን ሲያስቀምጡም "ለፌደራል ያለው የምርጫ ሥርዓትና ግብዓቶች በክልል ካሉት ጋር አንድ አይነት አይደለም" ይላሉ። በቅርቡ ምርጫውን ለማራዘም የወጣው የሕገ መንግሥት ትርጓሜም የምርጫ ሕግን የማውጣት ሥልጣን የፌደራል መሆኑን ይጠቅሳል ያሉት አደም (ዶ/ር)፤ በመሆኑም ክልሎች ይህን የማድረግ ሥልጣን ቢኖራቸው ክልሉ ያደረገው ጥሩ ጅማሮ ይሆን ነበር ብለዋል። "በ2007 አገራዊ ምርጫ ገዢው ፓርቲ መቶ በመቶ መቀመጫ አግኝቷል። ይህ ማለት ግን መቶ በመቶ የሕዝብ ድምፅ አግኝቷል ማለት አይደለም። ከ30 በመቶ በላይ ያለውን ድምፅ የተለያዩ ተቃዋሚዎች ናቸው ያገኙት፤ ነገር ግን አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ መቀመጫ አላገኘም" በማለት የሚያስታውሱት አደም (ዶ/ር)፤ የምርጫ ሥርዓት ለውጥ መኖሩ አንድ ፓርቲ በምክር ቤት ያለው መቀመጫና በሕዝቡ ውስጥ ያለው ድጋፍ የማይመጣጠን እንዳይሆን ያደርጋል ብለዋል። በመሆኑም ከዚህ ቀደምም ወደዚህ ዓይነት የምርጫ ሥርዓት ጥያቄዎች እንደነበሩ አቶ አደም (ዶ/ር) አስታውሰዋል።
news-46190682
https://www.bbc.com/amharic/news-46190682
የጀማል ኻሾግጂ ግድያ፡ የካናዳ የደህንነት መስሪያ ቤት የግድያውን የድምፅ ቅጂ ሰምቶታል
የካናዳ የደህንነት መስሪያ ቤት የሳዑዲ አረቢያውን ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ግድያን የተመለከተ የድምፅ ቅጂ መስማቱን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ ገለፁ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በሳዑዲ አረቢያ ቆንስላ የተገኘውን የጋዜጠኛውን ግድያ የተመለከተውን የድምፅ ቅጂ መስማታቸውን ይፋ ያደረጉ የመጀመሪያ ምዕራባዊ መሪ ናቸው ተብሏል። • የጀማል ኻሾግጂን ግድያ ለመሸፈን 'ባለሙያዎች ተልከዋል' • ልዑሉ የኻሾግጂን ገዳዮች ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ዛቱ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጠይብ ኤርዶዋን ባለፈው ቅዳሜ በሰጡት መግለጫ የድምፅ ቅጂውን ለእንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ሳዑዲ አረቢያ መስጠታቸውን ገልፀው ነበር። ፕሬዚዳንቱ ለአንደኛው የዓለም ጦርነት 100ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ወደ ፈረንሳይ ከመብረራቸው አስቀድሞ "የሰጠናቸው የድምፅ ቅጂውን ነው " ብለዋል። በፈረንሳይ በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ትሩዶ የአገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት የጋዜጠኛውን ግድያ ለመመርመር ከቱርክ ጋር በቅርበት እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። "ከሳምንታት በፊት ኤርዶጋን ጋር በስልክ ተነጋግረን ነበር፤ አሁንም ተወያይተናል፤ በእውነቱ ቱርክ የጋዜጠኛውን ግድያ ጉዳይ ለማጣራት ያላትን ቁርጠኝነት አደንቃለሁ" ብለዋል። የድምፅ ቅጂውን እርሳቸው ባያዳምጡትም የካናዳ የደህንነት መስሪያ ቤትና የስለላ ድርጅት ወደ ቱርክ ተጉዘው ግድያውን በተመለከተ የወጣውን የድምፅ ቅጂ እንደሰሙ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከዚያም ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ ለሌሎች የአገሪቱ ባለስልጣናት ገለፃ እንዳደረጉ ጨምረው አስረድተዋል። ማስረጃው ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሊያሻክረው ይችላል ስለመባሉም ዝርዝር መልስ ከመስጠት ቢቆጠቡም ከሳዑዲ አረቢያ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ዙሪያ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል። • ጠቅላይ አቃቤ ሕግ 63 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል አለ • "ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ በሌላ በኩል የፈረንሳዩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጀን ይቬስ ሊ ድሪያን የደረሳቸውን የድምፅ ቅጂ በማስመልከት " የቱርክ መሪ የፖለቲካ ጨዋታ" ማለታቸውን ተከትሎ ቱርክ ተቆጥታለች። "እውነታው አልወጣም፤ ሀቁን እንፈልጋለን፤ ከዚያም አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን" ብለዋል ሚንስትሩ ለአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ምላሽ። ይህን ተከትሎ "የቱርኩ ፕሬዚደንት 'ዋሽተዋል ማለት ነው?" ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም መንግሥት እየተጫወተ ያለው ፖለቲካዊ ጨዋታ እንደሆነ ለማስረዳት ዙሪያ ጥምጥም ሄደዋል። የቱርኩ ፕሬዚዳንት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ በበኩላቸው "ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ የሚንስትሩን ንግግር አጣጥለው የፈረንሳይ የደህንነት መስሪያ ቤት ተወካይ የድምፅ ቅጂውን እንዲሰሙ መደረጉን ገልፀዋል። ኃላፊው "በፈረንሳይ መንግሥት የሚገኙ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተግባቦት ችግር ካለባቸው ይህ የቱርክ ጉዳይ አይደለም" ሲሉ የአፀፋ መልስ ሰጥተዋል። አሜሪካ የድምፅ ቅጂው ይድረሳት አይድረሳት ያለችው ነገር የለም ።
news-48672687
https://www.bbc.com/amharic/news-48672687
ግብፅ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሞርሲ ሞት ውርጅብኝ እያሰተናገደች ነው
የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሞርሲ በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ተዝለፍልፈው ወድቀው ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የግብፅ ባለስልጣናት ከፍተኛ ትችት እየደረሰባቸው ነው።
በአውሮፓውያኑ 2013 ከስልጣን የተወገዱት የ67 አመቱ ሞሀመድ ሞርሲ እስከ እለተ ህልፈታቸው ድረስ በግብፅ ባለስልጣናት ቁጥጥር ስር ነበሩ። የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ አሟሟታቸው በገለልተኛ ቡድን እንዲጣራ የጠየቀ ሲሆን የግብፅ ባለስልጣናት በበኩላቸው በልብ ህመም ነው የሞቱት ብለዋል። • ሞሐመድ ሙርሲ ፍርድ ቤት ውስጥ ሞቱ •አምነስቲ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለውጥ እንዲደረግበት ጠየቀ •በኬንያ ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰሉ ምልክቶች ያለባት ታማሚ ተገኘች የቀሞው ፕሬዚዳንት ቤተሰቦችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በበኩላቸው ለብቻቸው ተገልለው በታሰሩበት ወቅት በአያያዛቸው ምክንያት የጤና ሁኔታቸው አሽቆልቁሎ ነበር በማለትም እየተናገሩ ነው። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ሞሀመድ ሙርሲ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጥዋት ከቤተሰቦቻቸው ጋር አንድ ላይ ታይተዋል ተብሏል። ልጃቸው አብዱላህ ሞሀመድ ሞርሲ ለሮይተርስ እንደተናገረው የአባቱን አስከሬን ወስደው ለህዝብ ክፍት በሆነ የቀብር ስርአትን ማከናወን ቢፈልጉም የግብፅ ባለስልጣናት እንደከለከሏቸው ነው። በሙስሊም ብራዘር ሁድ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው ሞሀመድ ሙርሲ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠው ያሸነፉ የመጀመሪያው መሪ ናቸው። ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞን ተከትሎ በመፈንቅለ መንግሥት ከስልጣን የተወገዱት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከአመት በኋላም በወታደሩ ቁጥጥር ስር ውለዋል። በወቅቱ የጦሩ መሪ የነበሩት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ከጎርጎሳውያኑ 2014 ጀምሮ በስልጣን ላይ ነበሩ። የፕሬዚዳንቱን ከስልጣን መወገድ ተከትሎ ባለስልጣናቱ በደጋፊዎቻቸው ላይና ሌሎችም ሰላማዊ ዜጎችን ማንገላታትየቀጠሉ ሲሆን ከአስር ሺዎችም በላይ ለእስር ተዳርገዋል። ሙስሊም ብራዘርሁድና የቱርኩ ፕሬዚዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ለቀድሞው ፕሬዚዳንት ሞት የግብፅ አመራሮችን ወንጅለዋል። በስለላና ከፓለስታይን እስላማዊ ቡድን ሀማስ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። ባለስልጣናቱ እንደገለፁት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከተከለሉበት ቦታ ሆነው ዳኞቹን ለአምስት ደቂቃ ያህል አዋርተዋል። የፍርድ ሂደቱ እረፍት ላይ እራሳቸውን ስተው ተዝለፍልፈው እንደወቀዱ ተገልጿል። ሆስፒታል አፋፍሰው ቢወስዷቸውም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እንደሞቱ የግብፅ አቃቤ ህግ ገልጿል። በአሟሟታቸው ዙሪያ ምርመራዎች የቀጠሉ ሲሆን ሰውነታቸውም ላይ የሚታይ ጉዳት እንደሌለ ተገልጿል። የኃገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው የሞታቸው ምክንያት የልብ ህመም ነው ብሏል። ሞሀመድ ሞርሲ ከዚህ በፊት በነበረው ፍርድ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሲሆን በኋላም ውሳኔው ተቀይሯል።
55706109
https://www.bbc.com/amharic/55706109
ሰዎችን ለማሰቃየት የተቀጠሩት የናዚ ዘመን ሴት ጥበቃዎች
እአአ በ1944 በጀርመን ጋዜጣ የወጣ ማስታወቂያ እንዲህ ይነበባል. . .
ውሾቻቸውን ይዘው ደን ውስጥ ሲንሸራሸሩ ይታያል "በወታደራዊ ማዕከሉ የሚቀጠሩ ከ20 እስከ 40 እድሜ ክልል ያሉ ጤናማ ሴት ሠራተኞች እንፈልጋለን። ጥሩ ደመወዝ እንከፍላለን። በነጻ ማረፊያና ልብስ እናቀርባለን።" ማስታወቂያው በግልጽ ያላስቀመጣቸው ሁለት ነጥቦች አሉ። አንደኛው ሠራተኞቹ የሚለብሱት የአዶልፍ ሒትለር የናዚ ፓርቲ የደንብ ልብስ መሆኑን ነው። ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ 'ወታደራዊ ማዕከል' የተባለው ሴቶች የታገቱበት የግዳጅ ማቆያ እንደሆነ ነው። እነዚህ በሰሜን በርሊን የሚገኙ እስር ቤቶች ከተዘጉ ዓመታት ተቆጥረዋል። በአቅራቢያቸው የሚገኙ ስምንት ቅንጡ ቤቶች ግን አሁንም ድረስ አሉ። እነዚህ ቤቶች የሴት ጥበቃዎች መኖሪያ ነበሩ። አንዳንዶቹ ጥበቃዎች ከልጆቻቸው ጋር ይኖሩ ነበር። በዛ ዘመን ጥበቃ ከነበሩት አንዷ ከቤቱ ማዶ ያለውን ደን በማስታወስ "በሕይወቴ ጥሩ ጊዜ ያሳለፍኩበት ወቅት ነበር" ይላሉ። በእርግጥ ከመኝታ ቤታቸው አሻግረው ሲመለከቱ እስረኞችን እና በጭስ ታፍነው የሚገደሉበትን የሰቆቃ ክፍል ይመለከታሉ። ራቨንስበርክ የሚባለው ይህ ቦታ አሁን መታሰቢያ ሙዝየም ሆኗል። የሙዝየሙ ዳይሬክተር ዶ/ር አንድራ ገንሰት እንደሚሉትም፤ አብዛኞቹ ጎብኚዎች የሚጠይቁት ከወንዶች ይልቅ ስለ ሴት ሠራተኞች ነው። "በርካታ ሰዎች ሴቶች ጨካኝ ሊሆኑ እንደሚችሉ አያስቡም" ይላሉ ዳይሬክተሯ። አብዛኞቹ የተቀጠሩት ሴቶች ከድሀ ቤተሰብ የተገኙ፣ በልጅነታቸው ትምህርት ያቋረጡና ሌላ ሥራ መያዝ የማይችሉ ናቸው። በግዳጅ ማቆያው ጥሩ ገንዘብ ይከፈላቸዋል። ማረፊያም ያገኛሉ። ዶ/ር አንድራ እንደሚያስረዱት በዘመኑ በዚህ እስር ቤት መቀጠር የፋብሪካ ሠራተኛ ከመሆን የተሻለ ነበር። አብዛኞቹ ሴቶች በናዚ የወጣት ሊግ የተመለመሉና በሒትለር ሐሳብ የሚያምኑ ናቸው። "ማኅበረሰቡን ከጠላቶቹ በመከላከል በጎ ተግባር እንደፈጸሙ ያምኑ ነበር" ይላሉ ዳይሬክተሯ። "እርጉም ሰዎች ናቸው" አሁን ሙዝየም በሆነው ክፍል የሚታዩ ፎቶዎች የያኔ ወጣት ሴቶች በዘመነኛ ልብስና የጸጉር አሠራር ተውበው ያሳያሉ። ብዙዎቹ በ20ዎቹ እድሜ ክልል ሲሆኑ፤ ቤታቸው ውስጥ እየሳቁና ተቃቅፈው ቡና ሲጠጡ፣ ኬክ ሲበሉ እንዲሁም ውሾቻቸውን ይዘው ደን ውስጥ ሲንሸራሸሩ ይታያል። እነዚህ ሴቶች የናዚ ፓርቲ መለያ ልብስ ማድረጋቸውን ሲያስተውሉ የያዟቸው ውሾች ሰዎችን ለማሰቃየት ይውሉ እንደነበር ያስታውሳሉ። በናዚ እስር ቤቶች ወደ 3,500 የሚጠጉ ሴት ጥበቃዎች ነበሩ። ሥራቸውን በራቨንስበርክ ጀምረው ኋላ ላይ ግድያ ይፈጸምባቸው ወደነበሩት ካምፖች የተዘዋወሩ አሉ። ጀርመናዊት የአይሁድ እምነት ተከታይ ሰልማ ቫን ደ ፔሬ 98 ዓመታቸው ነው። በናዚ እስር ቤት ታስረው ከነበሩ አንዷ ናቸው። አሁን ለንደን የሚኖሩት አዛውንት ያንን ዘመንና የናዚ ሰዎችን ሲገልጹ "እርጉም ሰዎች ናቸው" ይላሉ። "ሥራቸውን ይወዱት የነበረው ምናልባትም ኃያል እንደሆኑ ስለተሰማቸው ይሆናል። እስረኞቹ ላይ ጉልበታቸውን ያሳዩ ነበር። የተንገላቱ፣ የተደበደቡ እስረኞች ነበሩ" ሲሉ ሰቆቃውን ያስታውሳሉ። ሰልማ ያኔ በናዚ ተይዞ በነበረው ኔዘርላንድስ ስውር እንቅስቃሴ በማድረግ አይሁዳውያን ቤተሰቦችን ነጻ ለማውጣት ይለፉ ነበር። በያዝነው ዓመት መባቻ ላይ ስለ ሕይወት ተሞክሯቸው የሚያትት "ማይ ኔም ኢዝ ሰልማ" የተባለ መጽሐፍ አሳትመዋል። የሰልማ ወላጆችና እህታቸው የተገደሉት የናዚ ካምፕ ውስጥ ነው። በየዓመቱ ወደ ካምፑ እየሄዱ ቤተሰቦቻቸውን ይዘክራሉ። የተፈጸመው ግፍ እንደማይዘነጋም ያስባሉ። ራቨንስበርክ የሴቶች ብቻ ከሆኑ የናዚ ካምፓች ትልቁ ነው። ከመላው አውሮፓ ወደ 120,000 ሴቶች ታስረውበታል። አብዛኞቹ ናዚን የሚቃወሙ የንቅናቄ መሪዎች ነበሩ። አይሁዳውያን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችና በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩም ይገኙበታል። ቢያንስ 30,000 ሴቶች በካምፑ ተገድለዋል። በረሀብ የተቀጡ፣ በበሽታ የሞቱ፣ በሥራ እንግልት ሕይወታቸው ያለፈም ብዙ ናቸው። እስረኞቹ በሴት ጥበቃዎች ስቃይ ይደርስባቸው፣ ይገደሉም ነበር። ጥበቃዎቹ ታሳሪዎቹን በሚያንቋሽሹ ቅጽል ስሞች ይጠሯቸዋልም። "ምንም ስህተት አልሠራሁም" እአአ በ1945 የናዚ የጦር ወንጀል ለፍርድ ቀርቦ ሳለ ኢርማ ግሬስ የተባለች ሴት በሰው ግድያ ተፈርዶባት በስቅላት ተቀጥታለች። እንደሷ አይነት ሴቶች ጭካኔያቸውን በሚያጎላ ሁኔታ የፊልም ገጸ ባህሪ ሲሆኑ ተስተውሏል። በሺዎች ከሚቆጠሩ የናዚ ጥበቃ ሴቶች በአግባቡ ለፍርድ የቀረቡት 77 ብቻ ነው። የተፈረደባቸው ደግሞ ጥቂቶች። አንዳንዶቹ ስማቸውን ቀይረው፣ ከአካባቢው ርቀው፣ ትዳር መስርተው ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለዋል። ሀርታ ቦቴ የተባለች ሰዎችን በማሰቃየት ተከስሳ ታስራ የነበረች ሴት በአደባባይ ንግግር አድርጋ በእንግሊዞች ይቅርታ ተደርጎላት ተለቅቃለች። የታሰረችው ለውስን ጊዜ ነው። ከመሞቷ በፊት በተደረገላት ቃለ ምልልስ አንዳችም ጸጸት አላሳየችም ነበር። "ምንም ስህተት አልሠራሁም። ችግሩ ቦታው የግዳጅ ማቆያ መሆኑ ነው። ባልቀጠርበት ኖሮ እኔ ራሴ እገባበት ነበር። ያ ደግሞ የኔ ስህተት አይደለም" ብላለች። ቀድሞ የናዚ ካምፖች ጥበቃ የነበሩ ሰዎች ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው። ሆኖም ግን አማራጭ ስለሌላቸው የካምፑ ጥበቃ እንደሆኑ መናገራቸው ትክክለኛ መረጃ አይደለም። በካምፑ ሊቀጡ ካመለከቱ በኋላ ሥራው ምን እንደሆነ ሲነገራቸው ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ሌላ ሥራ ለመፈለግ የወሰኑ አሉ። ሥራውን አንቀጠርም ያሉ ሰዎች አንዳችም ቅጣት እንዳልተጣለባቸውም ታሪካዊ ሰነዶች ይጠቁማሉ። ሰልማ ስለ ጥበቃዎቹ ሲጠየቁ "ክፉ ድርጊት የሚፈጽሙ ነገር ግን እንደማንኛውም ሰው ተራ ናቸው፤ እዚህ እንግሊዝ ውስጥ ወይም ሌላ ቦታም እንዲያ ያለ ድርጊት ቢፈቀድ ብዙ ሰዎች ሊሳተፉ ይችላሉ" ይላሉ። ያኔ የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት አሁን ላለንበት ዘመን ትምህርት እንደሚሆን ተስፋ ያደርጋሉ። አንዳንድ ፊልሞች የናዚ የግዳጅ ማቆያ ጥበቃ ሴቶችን እንደ አውሬ ሲስሉ፤ ሌሎች ደግሞ እንደ ተጠቂ ያቀርቧቸዋል። እውነታው ግን እንደማንኛውም ሰው ያሉና የጭካኔ ተግባር የፈጸሙ ሴቶች መሆናቸው ነው።
53075790
https://www.bbc.com/amharic/53075790
ኬንያ ከ‹‹አሊባባው ጃክ ማ የተላከልኝን እርዳታ›› ተሰርቄያለሁ አለች
የኬንያ የወንጀል ምርመራ ፖሊሶች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከቻይናው ቢሊየነርና የአሊባባ ኩባንያ ባለቤት ጃክ ማ ተልከው የነበሩ ቁሳቁሶችን ማን እንደሰረቃቸው እየፈለግን ነው ብለዋል፡፡
የኬንያ ፖሊስ እንደሚለው የኬንያ መንግሥት የተሰረቀው ለኮሮናቫይረስ የተላኩ በርካታ ቁሳቁሶች ብቻ ሳይሆኑ በሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብም ጭምር ነው፡፡ የጤና መጠበቂያ ቁሳቁሶቹ የቀዶ ጥገና ጓንቶች፣ የአፍ አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች፣ የሙቀት መለኪያ መሣሪያዎችና በሐኪሞችና ነርሶች የሚለበሱ ጋውኖችን ያካተተ ነው፡፡ የኬንያ ፖሊስ ይህን መግለጫ የሰጠው ኬቲኤን የተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ ከቻይና መንግሥት በእርዳታ የተሰጠ ግምቱ 2 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የሕክምና ቁሳቁስ እንዴት እንደተሰወረ ካጋለጠ በኋላ ነው፡፡ ቴሌቪዥን ጣቢያው ባሰራጨው የምርመራ ዘገባ አንድ ከመንግሥት ባለሥልጣናትና ከቻይና ባለሀብቶች ጋር እጅና ጓንት ሆኖ የሚሰራ የግል ኩባንያ እነዚህ እርዳታዎች ኬንያ አየር መንገድ ሲደርሱ ይህ ኩባንያ የቁሳቁሶቹ ተረካቢ ሆኖ እንደቀረበ ያጋልጣል፡፡ ኬንያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከቻይናው ቢሊየነር ጃክ ማ በተጨማሪ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ እና ከአውሮጳ አገራት እርዳታ ተለግሷታል፡፡ ሆኖም የኅብረተሰብ ጤና ባለሞያዎች የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ገጥሟቸዋል፡፡ ይህ እጥረት በልገሳ የተገኙ ቁሳቁሶች የት ገቡ የሚል ጥያቄ አስነስቶ ቆይቷል፡፡ በኬንያ እስከ ዛሬ 3 ሺህ 727 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 104 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የኬንያ የጤና ባለሞያዎች እንደሚሉት ይህ በሽታ በማኅበረሰብ ደረጃ መሰራጨቱ የተረጋገጠ ሲሆን በመስከረም ወር የሟቾች ቁጥር በብዙ እጥፍ እንደሚጨምር እየተጠበቀ ነው፡፡ የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሙታይ ካግዌ ሌቦቹን የገቡበትን ገብተን እንይዛቸዋለን ሲሉ ዝተዋል፡፡ ኬንያዊያን ፌስቡክን በመሰሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ያለውን ሙስናና መንግሥታቸው ሙሰኞችን ለመያዝ የሚያሳየው ዳተኝነት እንዳስቆጣቸው እየገለጹ ነው፡፡
news-55445728
https://www.bbc.com/amharic/news-55445728
ወደፊት እግር ኳስ ተጫዋቾች 'ቴስታ' መምታት ይከለከሉ ይሆን?
ቴስታ ወይም የጭንቅላት ኳስ ወደፊት ከእግር ኳሱ ዓለም ሊወገድ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መነጋገሪያ ሆኗል።
ዴቪድ ሉዊዝ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ጤና ነው። ተመራማሪዎች ኳሰን በጭንቅላት መግጨት ጣጣ አለው እያሉ ነው። እንግሊዝ ይህን በማስመልከት ሕፃናት እግር ኳስ ሲጫወቱ ቴስታ እንዳይመቱ የሚከለክል ሕግ እያወጣች ነው። አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው የቀድሞ ተጫዎቾች ከሌሎች በተለየ በጭንቅላት ሕመም የመሞት ዕድላቸው በሦስት እጥፍ የጨመረ ነው። በዚህ ሃሳብ እግር ኳስ ተጫዎቾችም ይስማማሉ። የቀድሞው የቶተንሃምና የሃል ሲቲ ተጫዋች ራያን ሜሰን ቴስታ በሚቀጥሉት ከ10 አስከ 15 ዓመታት ባለው ጊዜ ሊቀር ይችላል ይላል። ሜሰን በ2017 ጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት በጊዜ ከእግር ኳስ ሕይወት ራሱን አሰናብቷል። የ29 ዓመቱ ሜሰን "በሚቀጥሉት ዓመታት ቴስታ ከእግር ኳስ ዓለም መወገድ አለበት ቢባል አልደነቀም" ሲል ለቢቢሲ ይናገራል። ሜሰን እንደሚለው ቴስታን በተመለከተ የሚሠሩ ጥናቶች ከዚህም በላይ በጣም አስደንጋጭ ውጤቶች ይዘው ሊመጡ ይችላሉ። "እኔ እግር ኳስ ተጫዋቾች ቴስታ የሚያመጣውን ተፅዕኖ በቅጡ ያወቁት አይመስለኝም። ለዚህ ነው ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ የምለው።" "በጣም አስጨናቂ ጉዳይ ነው" ይላል ሜሰን ስለጭንቅላት ኳስ ሲያወራ። "ችግሩ የቴስታን ጉዳት አሁን አናየውም። ጉዳቱ የሚመጣው ከዓመታት በኋላ ነው።" ቴስታ በእግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ የሚያመጣው ጉዳት ምንድነው የሚለውን ያጠኑት ዶ/ር ዊሊ ስቴዋርት ቴስታ የጭንቅላት ሕመምና የመርሳት በሽታ ሊያስከትል ይችላል ይላሉ። በፈረንጆቹ 1966 ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫ ያነሳው ኖቢ ስታይልስ ባለፈው ጥቅምት ከመሞቱ በፊት በተደጋጋሚ ኳስን በጭንቅላቱ በመምታቱ ለመርሳት በሽታ እንደተጋለጠ ተናግሮ ነበር። ከቴስታ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ጉዳይ የአየር ላይ ኳስ በጭንቅላት ለመግጨት በሚደረግ ፍልሚያ የሚከሰተው አደጋ ነው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት አርሰናልና ዎልቭስ በነበራቸው ጨዋታ የአርሴናሉ ዴቪድ ሉዊዝና የዎልቭሱ ራዉል ሂሜኔዝ ለጭንቅላት ኳስ ሲሻሙ ተጋጭተው ሂሜኔዝ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። በወቅቱ ሂሜኔዝ በቃሬዝ ነበር ከጨዋታው የወጣው። ሉዊዝ ደግሞ ጭንቅላቱን በፋሻ አስሮ ጨዋታውን ቀጥሎ ነበር። እንግሊዛዊው የቀድሞ የፕሪሚዬር ሊግ ኮከብ አለን ሺረር አርሴናል ሉዊዝን ከሜዳ ማስወጣት ነበረበት ብሎ ትችት መሰንዘሩ አይዘነጋም። የቀድሞው የቶተንሃም ተጫዋች ያን ቬርቶንገን ከሁለት የውድድር ዘመን በፊት በቻይምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የጭንቃላት አደጋ አጋጥሞት ነበር። ተጫዋቾ የዚህ አደጋ ሕመም ለዘጠኝ ወራት ያህል ይሰማው እንደነበር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ተናግሮ ነበር። ሜሰን ከቼልሲው ተከላካይ ጋሪ ካሂል ጋር ተጋጭቶ ባጋጠመው አደጋ ነው ጉዳት የደረሰበት። "በሕይወቴ መቆየቴ በራሱ ዕድለኛነት ነው" ይላል። ከሚቀጥለው ጥር ወር ጀምሮ ክለቦች የጭንቅላት አደጋ ሲያጋጥም ከመደበኛው ቅያሪ በተጨማሪ ሁሉት ተጫዋቾችን መቀየር እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል። አሁን የቶተንሃም አካዳሚ አሠልጣኝ ሆኖ የሚያገለግለው ሜሰን ግን ይህ ከሚሆን የጭንቅላት ኳስ ሕግ ሙሉ በሙሉ መቀየር አለበት ብሎ ያምናል። ቴስታ ወደፊት ከእግር ኳስ ዓለም ይወገድ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ግን አከራካሪነቱ እንደቀጠለ ነው።
news-50470343
https://www.bbc.com/amharic/news-50470343
የዓለም መፀዳጃ ቤት ቀን፡ መፀደጃ ቤት ተጠቅሞ መታጠብ ወይስ መጥረግ?
መፀዳጃ ቤት ተጠቅሞ መጥረግ ወይስ መታጠብ የሚለው ጉዳይ ከባህልና ከታሪክ አንፃር አሁንም አለምን በሁለት ጎራ እንደከፈለ ነው።
በምእራቡ ዓለም መፀዳጃ ቤት ተጠቅሞ ከመታጠብ ይልቅ መጥረግ የተለመደ ነው። በተቃራኒው በአረቡና በሙስሊሙ አለም መታጠብ የሚመረጥ ነው። የመፀዳጃ ቤት ባለ እጀታ መታጠቢያዎች በተለይም በአንዳንድ አገሮች የተለመዱ ናቸው። ይህም በእነዚህ አገራት ወሃ ይዞ ወደ መፀዳጃ ቤት የመሄድን የብዙ ዘመን ልምድ ታሪክ እያደረገ ያለ ይመስላል። ምንም እንኳ ዘመናዊ ሶፍቶች እጅግ ለስላሳ ቢሆኑም ከውሃ የበለጠ ለስላሳ አለመሆናቸው ግን አያከራክርም። ቢሆንም ግን አሁንም እንግሊዝና አሜሪካን ጨምሮ አብዛኛው የምእራቡ አለም ሶፍት መጠቀምን ይመርጣል። የእነዚህ ሁለት አገራት የመፀዳጃ ቤት አሰራር በአለም አቀፍ ደረጃ ሰፊ ተፅእኖ እንዳለው ይነገራል። • በግጭት አዙሪት ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች መፀዳጃ ቤት ተጠቅሞ ሶፍት መጠቀም ወይስ መታጠብ? የሚለው እንደ አውስትራሊያው ዙል ኦስማንን የመሰሉ ሰዎችን የሚስብ ክርክር ነው። ባህላዊና ታሪካዊ ሁነቶች የመፀዳጃ ቤት አጠቃቀም ላይ ያላቸውን ተፅኖ አጥንተዋል። የሳቸው ጥናት እንደሚያሳየው የተወሰኑ የእስልምና እምነት ተከታይ አውስትራሊያዊያን ሁለቱንም ይጠቀማሉ። ህንዳዊቷ አስታ ጋርግ እንደምትለው ምንም እንኳ የተወሰኑ ህንዳዊያን ሶፍት መጠቀም ቢለምዱም አብዛኞቹ ግን ውሃ ይመርጣሉ። ሁሌም ወደ አሜሪካ ስታቀና የጓደኞቿ ወይም የዘመዶቿ ቤት መፀዳጃ ቤት ባለ እጀታ መታጠቢያ እንደሚኖረው ካልሆነም ልትጠቀምበት የምትችል ትንሽ ፕላስቲክ ጠርሙስ እንደሚኖር ትጠብቃለች። ውሃ ይበልጥ ያፀዳል፣ ሶፍት ተጨማሪ ወጪ ያስወጣል እንዲሁም የመፀዳጃ ቤት ቱቦ ሊዘጋ ይችላል የሚሉ ምክንያቶችን በማስቀመጥ ወሃ መጠቀም የተሻለ ነው የሚል አስተያየት የሚሰነዝሩም ብዙዎች ናቸው። ተቀምጦ ወይስ ቁጢጥ ብሎ መፀዳዳት ጤናማ ነው? የሚለውም ሌላው ጉዳይ ነው ስለ መፀዳጃ ቤት አጠቃቀም ሲነሳ። በዚህ ረገድም ልዩነቶች አሉ። ዛሬም ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የአለም ህዝብ የሚፀዳዳው ቁጢጥ በማለት ነው። ከአካላዊ አቀማመጥ አንፃር ቁጢጥ ማለት በቀላሉ ለመፀዳዳት ትክክለኛው መንገድ ነው የሚሉም አሉ። • ዘመናዊውን የመፀዳጃ መቀመጫ የፈጠረው ሰዓት ሠሪ እነዚህ አስተያየት ሰጭዎች ምንም እንኳ ጤናማው የመፀዳዳት አቀማመጥ ቁጢጥ ማለት ቢሆንም ይህ አዎንታዊ ጎን ብዙም ትኩረት አይሰጠውም ይላሉ። በሌላ በኩል አሜሪካዊያን ተቀምጦ መፀዳዳትን ተመቻችቶ የመቀመጥ ብቻም ሳይሆን እያነበቡ የሚዝናኑበት እንዲሆን በማድረግም አዘምነውታል። ቁጢጥ ብሎ መፀዳዳት የብዙዎች ምርጫ በሆነበት ቻይና እናቶች "መፀዳጃ ቤት ሆናችሁ አታንብቡ ኪንታሮት ይይዛችኋል" ሲሉ ልጆቻቸውን ይመክራሉ። የ7 ዓመቷ ህፃን መፀዳጃ ቤት አልሰራልኝም ስትል አባቷን ከሰሰች
news-45194493
https://www.bbc.com/amharic/news-45194493
ኦብነግና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያለው ለውጥ
አልቃይዳና አልሸባብን ጨምሮ በ2003 ዓ.ም ኦነግን፣ ኦብነግንና ግንቦት 7ን አሸባሪ ድርጅቶች ብሎ የፈረጀዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ በዚህ ዓመት ሦስቱን ከመዝገቡ ላይ ሰርዟል።
በተለያዩ አገራት ሆነው የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩት ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈተዉ ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ፤ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ነሐሴ 6/2010 ዓ.ም ልኡኩን ወደ አዲስ አበባ ልኳል። የኢትዮጵያ አዲሱን የፖለቲካ ሁኔታና ወደፊት የሚፈጠረውን ጉዳይ በመወያየት ለሕህዝብ ሰላምና መረጋጋት የበኩላችንን ለማበርከት ወስነናል የሚለው ኦብነግ፤ የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ ላይ በመድረስ ወደ አገር ቤት መግባቱን ይገልጻል። • አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ኦብነግ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተደራደረ ነው • አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ኦብነግ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተደራደረ ነው • የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ጦስ በሶማሊያ? የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር ሥራ አስፈጻሚ አባልና የኮሚዩኒኬሽን ሃላፊ አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "ጊዜው የጠመንጃ አይደለም።" "በሕዝባችን ላይ ይደርስ የነበረው በደልና ጭቆና አሰቃቂ ነበር። እኛም ሕዝባችን ፍትህና እኩልነት እንዲያገኝ ነበር ጠመንጃ ያነሳነዉ። አሁን ደግሞ ጊዜው አይደለም። ሁሉም ነገር በሰላማዊ ድርድር መፍትሄ ይገኝበታል ብለን እናምናለን" ይላሉ። የኦብነግ ፍላጎት የሶማሌ ክልል ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ከቀጠናው አገራት ሕዝቦች ጋር የሚያስተሳስረው ማህበረናዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር ሰፊ እንደሆነ የሚያነሱት አቶ ሀሰን አብዱላሂ "የያዝናቸውን እቅዶች ሁኔታዎችን አይተን የምንተገብራቸው ሲሆን፤ ለወደፊቱ በጠረጴዛ ዙርያ በሰላማዊ መንግድ ችግሮች ይፈታሉ ብለን እናምናለን" ይላሉ። በግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ አዳኒ አብዱልቃድር ጌርሞጌ የተመራው እና ሦስት አባላት ያው የድርጅቱ ልኡክ አዲስ አበባ ሲገባ፤ በቀጠናው ምንም አይነት የተኩስ ድምጽ እንዳይሰማና ክልሉን ለማረጋጋት እንደሆነ ገልጸዋል። የዋርዴር ኒውስ ዶት ኮም መስራች፣ ጸሃፊና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ቋሚ ተንታኝ ፈይሰል ሮቤል የኦብነግ ተኩስ የማቆም ውሳኔ መስዋዕትነት ሲከፍል ለነበረው የሶማሌ ክልል ሕዝብ እረፍት የሚሰጥና ሕዝብ ሲጠብቀው የነበረ ጉዳይ ነው ይላል። ይህ በቀጣይነት ለሚደረጉ የውይይትና አብሮ የመስራት እንቅስቃሴዎች ትልቅ ሚና ቢኖረውም ቀላል ይሆናል ብሎ እንደማያስብ ስጋቱን ፈይሰል ይገልጻል። "በኢትዮጵያ መንግሥትና ኦብነግ መካከል የሚደረጉ ውይይቶች በፈተና የተሞሉ ናቸው። በመጪው የክልሉ እጣ ላይ የሚያካሂዱት ውይይቶች እንዴት ይሆናሉ? በተለይ ደግሞ የራስ እድል በራስ የመወሰን መብትን በተመለከተ ጥያቄዎች ሊኖሩ ይችላሉ" ይላል ፈይሰል። ከዚህ ባሻገር ደግሞ "ማዕከላዊው መንግሥት ክልሉ ውስጥ የሚኖረው ሚና ምን፣ በክልሉ ያለው የነዳጅ ሃብት፣ የሚሉና ሌሎች ጉዳዮች ትኩረት የሚሹ ናቸው" ሲል ያስቀምጣል። ኦብነግ በሶማሌ ክልል ሕዝብ ውስጥ ትልቅ መሰረትና ተቀባይነት አለው የሚለው ተንታኙ፤ ህጋዊ ፓርቲ ሆኖ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መምጣቱን ሕዝቡ በደስታ እንደሚቀበለው ገልጿል። የኦብነግ ኮሚዩኒኬሽን ሃላፊ አቶ ሀሰን አብዱላሂ እንደሚሉትም "ድርጅቱ ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት አገር በመገንባት ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን እራሱ እንዲወስን ማድረግ ነው። ሆኖም ግን ሕዝቡ ፍትህ፣ ዲሞክራሲና ነፃነትን ካገኘ ኢትዮጵያዊነቱን ሊመርጥ ይችላል" ይላሉ። • ማይግሬን መድሃኒት ሊገኝለት ነው • የ"ይቻላል" መንፈስ የሰፈነበት የአዲስ አበባው ቴድኤክስ የንግግር መድረክ በሶማሌ ክልል ስላለው ለውጥ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ የሚፈጠረው ሰላምና መረጋጋት እንደ አገር ካለው ጥቅም ባለፈ ለቀጠናው መሰረታዊ መፍትሄን በማምጣት የአፍሪካ ቀንድ አገራትም እንዲቀራረቡና እንዲረጋጉ እንደሚያደርግ ሁለቱም ይስማማሉ። ከሳምንት በፊት በሶማሌ ክልል በተከሰተው ሁከት ህይወት ጠፍቷል፣ ንብረት ወድሟል፣ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ይሄንን ተከትሎ የክልሉ ፕሬዚደንት የነበሩት አቶ አብዲ ሞሃመድ ኡመር ስልጣናቸው እንዲያስረክቡ ተደርጓል። "ሰላማዊ ነው" ከተባለው የስልጣን ሽግግር በኋላ አቶ አሕመድ አብዲ መሀመድ የክልሉ ፕሬዝደንት ሲሆኑ፤ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሸዴ የክልሉ ፓርቲ ሊቀ-መንበር በመሆን ተሹመዋል። ይህ በብጥብጥ የታመሰውን ክልል በማረጋጋት የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ቢረዳም "የፌደራል መንግሥት ሰፊ እጅ ያለበት በመሆኑ ክልሉ ያረጋጋል አልልም" ይላል ፈይሰል። "በአብዲ መሀመድ ሲመራ የነበረው ጨካኝ አስተዳደር ቢነሳም ለውጡ ክርክር እያስነሳ ነው። በአመራር ለውጡ ላይ የፌደራል መንግሥት እጅ አለ የሚሉ ስላሉ፤ ይህ ደግሞ የራሱ ችግር ይዞ ሊመጣ ይችላል።" ሕዝብ ይህ አካሄድ ላለፉት 27 ዓመታት መንግሥት ሲተገብረው የነበረው ነው በሚል የሚፈጠረው ስጋት አንደኛው ሲሆን፤ ክልሉ ውስጥ ያለው አለመረጋጋት ሌሎች ችግሮችን በመፍጠር ሌላ አደጋን እንዳያስከትል የሚል ስጋትም እንዳለ ይናገራል። "አዲሱ አመራርም ካለው ችግር ለመውጣት ለሕዝቡ አዲስ ቀን መሆኑ፣ ነገሮች በፌደራል መንግሥት የሚወሰኑ አለመሆናቸውንና አስተዳደሩ ከሕዝቡ የወጣ ነው የሚል አስተሳሰብ መፍጠር አለበት።" ቀጣይ የአገሪቷ ስጋቶች አሁን እየታዩ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገቡትን ቃል ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸውና ጊዜ ሳይወስዱ የመፍትሄ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ሁለቱም ይመክራሉ። "በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ እየታየ ያለዉ ችግር መፍትሄ ካልተበጀለት አገሪቷን ወደ መጥፎ ሁኔታ ሊመራት ስለሚችል በሰከነ መንፈስ ሊፈታ ይገባል" ይላኩ የኦብነግ ኮሚዩኒኬሽን ሃላፊ አቶ ሀሰን አብዱላሂ። በቀጣይ ለአገሪቷ ትልቅ ፈተና ሊሆን የሚችለው፡ አሁን እየቀጠሉ ያሉ ግጭቶች ናቸው የሚለው ፈይሰል ሮቤልም በበኩሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ እየታዩ ባሉት ግጭቶች ዙሪያ ቀዝቀዝ ማለታቸው ተገቢ አይደለም ይላል። "ቀጠናውን ለማረጋጋት ሲታሰብ አገሪቷ ውስጥ ያሉ ግጭቶችና አለመግባባቶች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለእነዚህ ችግሮች መፍትሄ ለማበጀት አለመፍጠናቸው መልካም አይደለም። ውይይቶችን ለመጀመርም ዘግይተዋል" ባይ ነው። ስለሆነም እነዚህን ግጭቶች የሚከታተልና የሚፈታ አደረጃጀት በመፈጠር ዘላቂ መፍትሄ ወደ ሚሰጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መግባት ወቅቱ የሚጠይቀው እርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል።
news-49479732
https://www.bbc.com/amharic/news-49479732
ኢትዮጵያ፡ ፖሊስ አንድን ወጣት ሲደበድብ በተንቃሳቃሽ ምስል ያስቀረው የዐይን እማኝ
ትናንት ነሐሴ 20 ቀን 2011 ዓ.ም ፖሊስ እጁ በእጀ ሙቅ [ካቴና] የታሰረን ወጣት ሲደበድብ፤ አብሮት የነበረው ሌላኛው ፖሊስ ወደላይ ሲተኩስ፤ አንዲት እናት ለመገላገል ሲሉ ሲገፈተሩ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል መነጋጋሪያ ሆኗል።
ሕግ በሚያስከብሩ የፖሊስ አባላት ድብደባው መፈፀሙ ደግሞ ብዙዎችን አስቆጥቷል። • የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታ የማን ነው? • “በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ አዲስ አበባ ቄራ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ ተቀረፀ የተባለው ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል እንዲሁም ከዚህ ቀደም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የወጡ ተመሳሳይ ድርጊቶች ፖሊስ ዜጎች ላይ እየፈፀመ ስላለው የጭካኔ ድርጊት ምስክር ነው ሲሉ በርካቶች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ይህንን ተንቀሳቃሽ ምስል የቀረፀውንና አቤል በሚል ስም በትዊተር ገፁ ያጋራውን ወጣት ቢቢሲ አነጋግሮት ነበር። አቤል እንደሚለው በወቅቱ ከጎፋ ገብርዔል ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ አካባቢ ሲደርስ ሰው መበታተን እና መሮጥ ጀመረ። ጉዳዩን በቅርበት መከታተሉን የቀጠለው አቤል "ሲደበደብ የነበረው ልጅ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ከሚታዩት እናት ኋላ ሲሄድ ነበር" ይላል። እየሄዱ ሳሉም ወጣቱና ፖሊሱ መገፋፋት ጀመሩ። ከዚያም ሲደበድበው የነበረው ፖሊስ ጠመንጃውን አብሮት ለነበረው ፖሊስ ይሰጠዋል። ፖሊሱ ጠመንጃውን አቀባብሎ መተኮስ ጀመረ [የመጀመሪያውን ተኩስ በቪዲዮው አላስቀረውም]። ከዚያም ወጣቱ እጁን ሰጠ። አሰሩት። ልክ እንዳሰሩት መምታት ጀመሩት። በአካባቢው በርካታ ሰው ቢኖርም ማንም ሰው ሊገላግል የደፈረ አልነበረም። ሁሉም ሰው ፈርቶ እየሸሸ ነበር። በዚህ መሃል መሳሪያ የያዘው ፖሊስ "ዞር በሉ" እያለ ሁለተኛ ጥይት ይተኩስ ነበር። 'እናቱ ናቸው መሰል' ያላቸው ሴትም በተደጋጋሚ ሊገላግሉ ሞከሩ። ይሁን እንጂ በደብዳቢው ፖሊስ ያለምንም ርህራሄ ሲገፈተሩና በአካባቢው ያለ ሰው እንዳይጠጉ ሲይዛቸው አቤል አስተውሏል። አቤል እንደሚለው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ምንም ማድረግ አልቻሉም ነበር። መሳሪያ የያዘው አንደኛው ፖሊስ እየተኮሰ "እንዳትጠጉ" እያለ እያስፈራራ ስለነበር ማንም ደፍሮ ሊገላግል የሞከረ አልነበረም። "በወቅቱ ማንም የተጠጋው ሰው አልነበረም፤ በፍርሃት ይመስለኛል የተኮሰው። እጁ ላይ መገናኛ ራዲዮ ይዞ ነበር፤ ደውሎ እርዳታ መጥራት ይችል ነበር ከአቅሙ በላይ ከሆነም" ሲል ፖሊሱ ለምን መተኮስ እንዳስፈለገው እንዳልገባው ይናገራል። • "በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ከዚያ በኋላ መኪናው መንቀሳቀስ ስለ ጀመረ አቤል ቪዲዮውን መቅረፅ አልቻለም። ተንቀሳቃሽ ምስሉ አጭር የሆነውም ለዚያ ነው ይላል። የዐይን እማኙ እንደሚለው እንደዚህ ዓይነት አጋጣሚዎችን በቪዲዮ እየቀረፀ በማህበራዊ ሚዲያ ሲያጋራ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። አዲስ አበባ ውስጥ ብዙ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ነገሮች ያጋጥማሉ የሚለው አቤል "ፖሊሶችን ለምንድን ነው የምትማቱት? ስንላቸው 'ምን አገባችሁ እናንተንም እነርሱ ጋር እንዳንቀላቅላችሁ' ይሉን ነበር" ሲል የማን አለብኝነት ምላሽ እንደሰጡት ያስታውሳል። የህግ ባለሙያዋ ብሌን ሳህሉ በአንድ ወቅት 'ሃሽታግ ነግበኔ' ብላ ትዊት አደረገች። ከዚያም የእርሷን ተቀብሎ የራሱን ጽሁፍ መፃፍ እንደጀመረ ይናገራል። "ፖሊስ ያልተገባ ኃይል ሲጠቀም ማንም የሚናገራቸው ሰው የለም፤ ሲቀጡ አናያቸውም፤ አንሰማም፤ በመሆኑም መረጃው ሰዎች ጋር እንዲደርስ ነው የቀረፅኩት" ሲሉ ምክንያቱን ያስረዳል። በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡን የጠየቅናችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር "ስብሰባ ላይ ነኝ" በማለታቸው ሃሳባቸውን ማካተት አልቻልንም። ለኮሚሽነሩና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ጋር ያደረግነው የስልክ ጥሪም ምላሽ አላገኘም። ይሁንና ዛሬ ጠዋት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ላይ የፖሊስ አባላቱ የፈፀሙትን ድርጊት እያጣራ መሆኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ትናንት ከረፋዱ 5 ሰዓት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ስሙ ቄራ ጎፋ ማዞሪያ በድለላ የተሰማሩ ሁለት ቡድኖች መካከል የተፈጠረን አለመግባባት ለማብረድ ፖሊሶቹ ጣልቃ እንደገቡ ያስረዳል። ፖሊሶቹ ግለሰቦቹን ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄዱ በሚያደርጉበት ጊዜም አለመግባባቱ በመካረሩ የፖሊስ አባላቱ ድብደባ እንደፈፀሙና እንደተኮሱ ኮሚሽኑ ይገልፃል። የፖሊስ አባላቱ አዲስና በቅርቡ የተቀላቀሉ መሆናቸውን የገለፀው ኮሚሽኑ የፈፀሙት ድርጊት ግን ያልተገባ በመሆኑ ጉዳያቸው በወንጀልና በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት እየተጣራ መሆኑን አስታውቋል።
news-52284127
https://www.bbc.com/amharic/news-52284127
ኮሮናቫይረስ፡ የናይሮቢው ገዢ ለችግረኞች አልኮል ጭምር አቀርባለሁ አሉ
የኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የዕለት ጉርሳቸውን ለመሸፈን ላልቻሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ከሚያቀርበው የምግብ እርዳታ ጋር አብሮ መጠጥ ሊያቀርብ እንደሆነ የከተማው ገዢ መናገራቸው መነጋገሪያ አድርጓቸዋል።
አገረ ገዢው ማይክ ሶንኮ ይህንን የተናገሩት ማክሰኞ ዕለት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነበር። ሶንኮ "አነስተኛ ጠርሙስ ሄኒሴ [የኮኛክ መጠጥ ዓይነት ነው] በምግብ እድላው ላይ ጨምረን ለሕዝባችን እናቀርባለን" ማለታቸው ተሰምቷል። የከተማዋ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በዚህ የአገረ ገዢው ንግግር ሲሳለቁ ተስተውሏል። አገረ ገዢው አክለውም "በዓለም ጤና ድርጅትም ሆነ በሌሎች የጤና ተቋማት የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አልኮል ኮሮናቫይረስንም ሆነ ሌሎች ቫይረሱችን ይገላል" ብለዋል። በአገሪቱ በሚሰራጨው ሲትዝን ቲቪ የአገረ ገዢው አስተያየት ተደምጧል። የመዲናዋ ናይሮቢ ገዢ በተናገሩት ነገር ላይ በርካታ ኬንያዊያን በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ እየተሳለቁበት ነው። በሚያደርጉት ንግግርና በድርጊታቸው ውዝግብ ውስጥ በመግባት አዲስ ያልሆኑት ገዢው፤ ቀደም ሲል እሳቸው ቢያስተባብሉትም በዕፅ ማዘዋወርና ሕገ ወጥ ገንዘብ ወደ ሕጋዊነት በማስገባት ክስ ቀርቦባቸው ነበር። በተጨማሪም የአገሪቱ እስር ቤት ባለስልጣናት የአሁኑ የናይሮቢ ገዢ ከ20 ዓመታት በፊት ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግለት እስር ቤት አምልጠዋል ብለው ይከሷቸዋል። ባለፈው ታኅሳስ ወር ፍርድ ቤት የከተማዋ ገዢ 3.3 ሚሊዮን ዶላር አባክነዋል በሚል ወደ ጽህፈት ቤታቸው እንዳይገቡ መከልከሉን ተከትሎ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በየካቲት ወር የከተማዋን ቁልፍ ኃላፊነቶች የአገሪቱ መንግሥት ወስዶ እንዲያስተዳድር አድርገዋል። ነገር ግን ይህም ቢሆን ማይክ ሶንኮ ምንም አይነት መጥፎ ተግባር አልፈጸምኩም ብለው ይከራከራሉ። የኬንያ ማዕከላዊ መንግሥት በአሁኑ ጊዜ የናይሮቢ ከተማን የጤና፣ የትራንስፖርትና ሌሎች የሕዝብ አገልግሎቶችን ሥራ ተረክቦ እያከናወነ ይገኛል።
50754155
https://www.bbc.com/amharic/50754155
የዩኒቨርስቲ መምህርቷ ሞዴል ገነት ጸጋይ፡ "ውበት ባመኑበት ነገር ጠንክሮ መሥራት ነው"
ገነት ለቤተሰቧ አስራ አንደኛ ልጅ ናት። አስራ ሁለት ልጆች ወልዶ ባሳደገው ቤተሰብ ውስጥ ታላላቆቿን አርዓያ እያደረገች ነው ያደገችው።
የኪነ ሕንጻ ባለሙያዋ ገነት ጸጋይ የመጀመሪያውን የቁንጅና ውድድር ያሸነፈችው የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳለች ነበር ስለቤተሰቧ ስትናገርም "ሁሉም ቆንጆ እንድሆን ይፈልግ ነበር" ብላለች ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር በነበራት ቆይታ። የመቀለ ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸር ትምህርት ክፍል ተማሪ እያለች ነበር ወደ ቁንጅና ውድድር የተቀላቀለችው። ውድድሩን ግን ለመሳተፍ ብቻ ሳይሆን ለማሸነፍ አልማ የተካፈለችበት ነበር። ያሰበችው አልቀረም በ2003 'ወይዘሪት ትግራይ' ሆና ዘውድ ደፍታለች። • እሷ ማናት?: ለነፃነትም ለጥበብም ያልታከቱ እጆች "ወይዘሪት ትግራይን ሳሸንፍ፤ ገና ከቤት የወጣሁበት ጊዜ ነበር። ውጪ ስላሉ ነገሮችና የህይወት ፈተናዎች የማውቀው ነገር አልነበረም" በማለት የምታስታውሰው ገነት፣ በቀጣዩ ዓመትም [2004] በአገር አቀፍ የቁንጅና ውድድር አሸንፋ 'ወይዘሪት ኢትዮጵያ' ተብላለች። ከዚያ በኋላም ወደ ዓለም አቀፍ መድረኮች ተቀላቀለች። "ለእኔ እነዚህ መድረኮች እጅግ ደስ የሚሉ ግን ከባድ ነበሩ። የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ስለነበርኩ፣ በመሃል ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እየተንቀሳቀሱ መስራት ቀላል አልነበረም።" ገነት ጸጋይ በ'ሚስ ዎርልድ' የተካፈለችው ገና ተማሪ እያለች ነበር። በዚህ ምክንያትም በአሜሪካ በትልልቅ የፋሽን መድረኮች የመስራት እድል አግኝታለች። ዓለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር መድረኮች፤ ዳጎስ ያለ ልምድና ችሎታ፣ የዳበረ አቅምና ልምድ ያላቸው ተወዳዳሪዎችና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ነው። በዚህም የተነሳ ለተወዳዳሪውም ሆነ ለተሳታፊው የሚፈጥሩት ተጨማሪ እድል በርካታ የመሆኑን ያክል፣ ፈተናውም በዚያው ልክ የበዛ መሆኑን ትናገራለች። "ከዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ነጥብ ስመረቅ፤ ሁሉም ሰው የትምህርት ውጤቴን ለማመን ይቸገር ነበር። ብዙ ጊዜ የቁንጅና ሥራዎች ላይ ነሽ፤ እንዴት ውጤትሽ እንዲህ ሊሆን ቻለ? ይሉኝ ነበር" የምትለው ሞዴል ገነት፤ "የምፈልገውን ለመሆን ቀን ከሌት እተጋ ስለነበር ስኬታማ መሆን ችያለሁ" ትላለች። • "የተመረጥኩት በኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ነው" ቤቲ ጂ በአንዲት ወጣት ሴት ሕይወት ውስጥ፤ ከሕይወት ግብ የሚያሰናክሉ በርካታ አጋጣሚዎች ሊከሰቱ ቢችሉም፤ ተግዳሮቶቹን ወደ መልካም አጋጣሚ ቀይሮ ማለፍ መቻልን ደግሞ ትልቁ ነገር እንደሆነ ትናገራለች። "መሬት ላይ ያለው ሃቅ ለሴት ልጅ ቀላል ባይሆንም፤ ማንኛውንም ነገር ለመስራት ስነሳ መሰናክል ይሆንብኛል ብዬ የማስቀምጠው ነገር የለም።" ቁንጅና ምኑ ላይ? በ2018 የዩክሬይን ወይዘሪት በመሆን ዘውዱን ያነሳችው ቬሮኒካ ዲዱሴንዶ፤ ልጅ እንዳላት ሲታወቅ ከአራት ቀን በፊት የተሰጣትን የቁንጅና ዘውድ ተነጥቃለች። በዚህ ምክንያት የዓለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ሕጎችን እንዲቀየሩ ሕጋዊ እርምጃ እንደምትወስድ በዚህ ሳምንት ገልጻ ነበር። የ'ሚስ ወርልድ' ውድድር እናት ወይም ባለትዳር የሆነች ሴት በቁንጅና ውድድሮች እንዳትሳተፍ የሚከለክል ሕግ አለው። ትዳር ወይም ወሊድ የሴት ልጅ ውበትና ቅርጽ ስለሚቀይሩ፣ የቤተሰብ ኃላፊነትን ስለሚጨምሩ፤ መድረኩ የሚፈጥራቸውን የበጎ ፈቃድ ሥራዎች፣ ፋሽንና ሌሎችን በቂ ጊዜና ትኩረት ሰጥተው ለመስራት ይገድባቸዋል ተብሎ እንደሚታመን፤ በኢንዳስትሪው የሚገኙ ቆነጃጅት ያነሳሉ። • ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑ ተገለፀ "እንደዚህ አይነት አመለካከቶች የሴትን ልጅ ጥንካሬና ብርታት ጥያቄ ውስጥ ከሚያስገቡ ሰዎች የሚመነጩ ናቸው" የምትለዋ ሞዴል ገነት፤ ለሴት ልጅ "ኃላፊነትና ትዳርን ሳይሆን ማንኛውም ነገር ስንጀምር ፈልገነውና ልባችን ፈቅዶ ነው ወይ የምንጀምረው? የሚለውን ማወቁ ጠቃሚ ነው" ትላለች። "ከሁሉም ይልቅ እኛን የሚገነባን ትምህርት ነው" የምትለው አርክቴክት ገነት፤ "የሚያዳግታት ነገር ሁሉ አሸንፋ ለመውጣት ማንኛዋም ሴት መማር አለባት። በዚህ መልኩ አስተሳሰባችን ስለሚያድግ መድረስ የምንፈልገው ስፍራ ለመድረስና ዓላማችንን ለማሳካት አቅም እናገኛለን" ብላ ታምናለች። ሞዴልና አርክቴክት ገነት ጸጋይ፤ አሁን በተለያዩ የፋሽንና የቁንጅና መድረኮች ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ወጣት ሴቶች የምታሰለጥንበት ዓለም አቀፍ ተቋም አላት። ይህ 'ኢትዮጵያን ቢዩቲ ክሪምስ' የተሰኘ ኩባንያ፤ በየዓመቱ የወይዘሪት ኢትዮጵያ ውድድሮችን በማዘጋጀት፤ በወይዘሪት ዓለም፣ ወይዘሪት ኢንተርኮንትነንታል፣ በወይዘሪት ግራንድ ኢንተርናሽናል፣ በወይዘሪት ኢንተርናሽናል ላይ የሚወዳደሩና የሚሳተፉ አራት ሴቶችን ይልካል። እስከ አሁን፤ ወደ ፊሊፒንስ፣ ጃፓን፣ ኢንዶኔዥያና አሜሪካ ኩባንያው አወዳድሮ የመረጣቸውን ቆነጃጅቶች ልኳል። "በቁንጅናው ኢንዳስትሪ ይህን ፈጥሬያለሁ። ውበት ግን ውጫዊው ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመን ነው። ለእኔ፤ የራስ መተማመን ያላትና ራስዋን የምትችል ሴት ቆንጆ ናት። ትልቅ ውበት ብዬ የምወስደው ደግሞ ባመኑበት መስክ አብዝቶ መስራት ነው። ዓለም ላይ ከባዱ ነገር ፍላጎትን አለማወቅ ነው ብዬም አምናለሁ።" ገነት ጸጋይ ማን ናት? አርክቴክት ገነት፤ በአሁን ወቅት ባለትዳርና የልጆች እናት ናት። ባለፈው ዓመት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ'ላንድስኬፕ አርክቴክቸር' ሁለተኛ ዲግሪዋን ይዛለች። በዩኒቨርሲቲውም የአርክቴክቸር ትምህርት ክፍል መምህርት ናት። በሙያዋ ቤቶችን ማስዋብንና ዲዛይን ማድረግን ስትሰራ፤ ልብሶቿንም ራሷ ዲዛይን በማድረግ አዘጋጅታ ትለብሳለች። • የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ክፍፍልና ጠብ "ሥራ ለመስራት ግን ውስጤ እስካመነበት ድረስ ቦታ አልመርጥም። በማህበራዊ ኑሮዬ እና ተማሪዎቼን ለማስተማር ስሄድ የተለያየሁ ሰው ነኝ። ውጪ ላይ ፋሽን እከተላለሁ፤ ሳስተምር ግን እንደማንኛውም ሰው ስለምሆን ተማሪዎች ብዙም አያውቁኝም። 'ፋሽን ላይ ያለ ሰው ግን እንዲህ በትምህርትም ስኬታማ ይሆናል እንዴ?' የሚሉኝ ሰዎች አሉ። " በህይወታችን ውስጥ ልናገኘው የምንፈልገው ነገር በቀላሉ አይገኝም የምትለው ገነት "አላማዬን የሚያስተኝ ከሆነ ፈጽሞ ወደ ህይወቴ እንዲገባ አልፈቅድለትም" በማለት ህይወታቸውን በጥንቃቄ ከሚመሩ ሰዎች ጎራ መሆንዋን ትናገራለች። "እናትነት ልዩ ተፈጥሯዊ ምስጢር ነው። ከራስ በላይ የሚኖርበት ምክንያት የሚሰጥ ጸጋ ነው። ብዙ ሰው ትዳር ሲመሰርት ሁሉም ጫና ሴቷ ላይ ነው የሚወድቀው ብሎ ይሰጋል። ለእኔ ግን እንደዚህ አይደለም፤ ምርጫችንና ውሳኔያችንን ነው የምንኖረው። ሴት ልጅ ራሷን የምትችል ከሆነ፤ አስጠጊ አያስፈልጋትም።"
43903957
https://www.bbc.com/amharic/43903957
የፌስቡክ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ
ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ከተከሰሰ በኋላ ይፋ የሆነ ሪፖርት እንዳመለከተው የሩብ ዓመት ገቢው በ50 በመቶ ከፍ ብሏል።
ኩባንያው እንደገለፀው በአውሮፓውያኑ ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራት ገቢው 11.9 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አመልክቷል። ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ያገኘው ገቢ 8 ቢሊዮን ዶላር ነበር። የፌስቡክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ስለተገኘው ገቢ ሲናገር "ምንም እንኳን ከባድ ተግዳሮት የገጠመን ቢሆንም፤ ለዓመቱ ሥራችን መልካም ጅማሬ ነው።" ጨምሮም ተቋሙ ያለበትን ሃላፊነት በስፋት እየመረመረ መሆኑን አሳውቋል። ይህ ፌስቡክ በሦስት ወራት ውስጥ ያስመዘገበው ከፍተኛ ገቢ የባለፈው ዓመት ገቢውን እንዲያድግ አድርጎታል። ፌስቡክ በመጋቢት ወር ላይ የፖለቲካ አማካሪ ተቋም ከሆነው ኬምብሪጅ አናሊቲካ ከተባለው ድርጅት ጋር በተያያዘ የተጠቃሚዎችን መረጃ አሳልፎ ሰጥቷል በሚል ከፍ ያለ ውዝግብ ውስጥ ገብቶ ነበር ። በዚህም ፌስቡክ 87 ሚሊዮን የሚደርሱ ተጠቃሚዎቹን ግላዊ መረጃ ተገቢ ባልሆነ መንገድ አሳልፎ መስጠቱን አምኗል። የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ እንዳለውም "ያለብንን ሃላፊነት ሰፋ አድርገን እየተመለከትነው ሲሆን የምናቀርበው አገልግሎትም ለመልካም ነገር መዋሉን ለማረጋገጥ የሚያስፈልገውን እያደረግን ነው። "በተጨማሪም ሰዎችን ለማገናኘት፣ ማሕበረሰባችንን ለማጠናከርና ዓለምን ለማቀራረብ አዳዲስ ዘዴዎችን ማፈላላጋችንን እንቀጥላለን" ብሏል። ፌስቡክ እንደሚለው በመጋቢት ወር ላይ የየእለቱ አማካይ መደበኛ የተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 1.5 ቢሊዮን ደርሷል። ይህም ከባለፈው ዓመት በ13 በመቶ ጨምሯል። የመጋቢት ወር አማካይ ወርሃዊ መደበኛ ተጠቃሚዎች ቁጥር 2.2 ቢሊዮን ደርሶ በ13 በመቶ ከፍ ብሏል። የፌስቡክ ሰራተኞች ቁጥርም በ48 በመቶ አድጎ 27742 ደርሷል።
news-56186298
https://www.bbc.com/amharic/news-56186298
ባይደን ከኬንያው ፕሬዝደንት ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ ተነጋገሩ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰሜን ኢትዮጵያ ስለተከሰተው ቀውስ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር መወያየታቸውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ከዋይት ሐውስ በወጣው መግለጫ ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች በስልክ በነበራቸው ወይይት፤ "በትግራይ ክልል እየተባባሰ ስለመጣው የሰብዓዊ ቀውስና የሰብዓዊ መብት ጥሰት" ተነጋግረዋል ብሏል። መሪዎቹ በትግራይ "ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ መከላከልና የሰብዓዊ ድጋፍ መድረስ አስፈላጊነት ላይ" ተነጋግረዋል ሲል የዋይት ሐውስ መግለጫ አመልክቷል። ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች ትናንት በነበራቸው ውይይት ከኢትዮጵያ ጉዳይ በተጨማሪ በአሜሪካና ኬንያን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር አስፈላጊነት ላይ ተነጋግረዋል። ባይደን በቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት ላይ ከኬንያ ጋር አብሮ ለመስራት አሜሪካ ጽኑ ፍላጎት አላት ብለዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን የኬንያን የአፍሪካ ቀንድ መሪነትን፣ የኢኮኖሚ እድገት፣ የጸረ-ሽብር እንቅስቃሴዋን እና በአየር ጸባይ ለውጥ ላይ እያደረገች ያለችውን ጥረት አድንቀዋል። በተያያዘ ዜና የካናዳው ጠቅላይ ሚንሰትር ጀስቲን ትሩዶ ከጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ ጋር መወያየታቸውን የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት አስታውቋል። ሁለቱ መሪዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በኢትዮጵያና በካናዳ እየተደረጉ ስላሉ ጥረቶች እንዲሁም በወረርሽኙ መስፋፋት ለተጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች መደረግ ስላለበት ድጋፍ መወያየታቸው ተገልጿል። መሪዎች የኮቪድ-19 ክትባትን ለማዳረስ እየተደረጉ ያሉ ዓለም አቀፍ ትብብሮች አስፈላጊነት ላይ መነጋገራቸውም ተገልጿል። የጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ ጽ/ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ ጨምሮ እንደገለጸው፤ ሁለቱ መሪዎች በትግራይ ስለተከሰተው ጉዳይም ተወያይተዋል። መሪዎቹ በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትና የሰብዓዊ መብት መከበር አስፈላጊነት ላይ መክረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ትሩዶ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረትና ጋዜጠኞች ወደ ስፍራው እንዲጓዙ መፍቀዱን አበረታች ነው ያሉ ሲሆን፤ ካናዳ በኢትዮጵያ ሁሉን አካታች የሆነ ሰላምና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል።
news-54252050
https://www.bbc.com/amharic/news-54252050
በ2024 የመጀመሪያዋ ሴት ጠፈርተኛ ጨረቃን ትረግጣለች
ናሳ እአአ በ2024 ወደ ጨረቃ በድጋሚ ለመጓዝ 28 ቢሊዮን ዶላር መድቧል። ‘አርቴሚስ’ የሚል ስያሜ የተሰጠው ጉዞ አንድ ወንድና አንድ ሴትን ያሳትፋል።
ጉዞው ከ1972 ወዲህ ሁለተኛው ሲሆን፤ ናሳ ጉዞውን በታቀደለት ጊዜ የሚያካሂደው ምክር ቤት 3.2 ቢሊዮን ዶላር ለመልቀቅ ሲስማማ ነው። ጠፈርተኞቹ ጨረቃ ላይ የሚያርፉት እንደ አፖሎ ባለ ኦሪዮን በሚባል ሮኬት ነው። የናሳ አስተዳዳሪ ጂም ብሪድንስትን እንዳሉት 28 ቢሊዮን ዶላሩ ለሮኬትና ሌሎችም ጠፈርተኞች ጨረቃን እንዲረግጡ የሚረዱ ቁሳ ቁሶች ይውላል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 600 ሚሊዮን ዶላር የፈቀደ ሲሆን፤ ናሳ ግን ለጉዞው ተጨማሪ ገንዘብ ይፈልጋል። አርቴሚስ-1 የተባለው የጉዞው የመጀመሪያ ዙር በቀጣዩ ዓመት ይካሄዳል። ይህም የሙከራ በረራን ያካትታል። የናሳ የሰዎች መንኮራኩር ዘርፍ ኃላፊ ካቲ ሉደርስ እንዳሉት አርቴሚስ-1 ለወር የሚቆይ ሙከራ ነው። አርቴሚስ-2 ላይ ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮችንም ይቀንሳል። አርቴሚስ-3 ከ48 ዓመታት በኋላ የሰው ልጆች ጨረቃን የሚረግጡበት ፕሮጀክት ይሆናል። ናሳ 967 ሚሊዮን ዶላር መድቦ የተለያዩ ተቋሞች የመንኮራኩር ዲዛይን እንዲሠሩ አድርጓል። በምዕተ ዓመቱ ማገባደጃ ምርምር የሚደረግበትና ‘አርቴሚስ ካምፕ’ የተባለ ቋሚ መቆያ ይዘጋጃል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ሰዎች ዘለግ ላለ ጊዜ ስለ ጨረቃ እንዲመራመሩ ያግዛል። ከጨረቃ ደቡባዊ ጫፍ ውሃ በማውጣት ወደ ጨረቃ ለሚጓዝ መንኮራኩር ነዳጅ የማመንጨት እቅድ አለ። ከተሳካ ከምድር ወደ ጨረቃ ለሚደረገው ጉዞ የሚወጣውን የነዳጅ ገንዘብ ያተርፋል። ከዓመታት በፊት አፖሎ ወደ ጨረቃ ሲላክ 250 ቢሊዮን ዶላር ነበር የፈጀው።
51166803
https://www.bbc.com/amharic/51166803
ፌስቡክ የቻይናውን ፕሬዝደንት ስም ሲተረጉም በአፀያፊ መልኩ በማንሻፈፉ ይቅርታ ጠየቀ
ፌስቡክ የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጂንፒንግን ስም ከበርማ ቋንቋ ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጉም በማንሻፈፉ ይቅርታ ጠይቋል።
የቻይናው ፕሬዝደንት ወደ ምያንማር አቅንተው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነው ይህ የተከሰተው። በጉብኝታቸው መሠረትም ዢ ከምያንማር መሪ አንግ ሳን ሱ ኪ ጋር መክረዋል። የምያንማር ቋንቋ በሆነው በርሚዝ የሁለቱ መሪዎች መገናኘት ዜና ተፅፎ ወደ እንግሊኛ ሲተረጎም ነው የቻይናው ፕሬዝደንት ስም ተንሻፎ የተገኘው። የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጂንፒንግን ስም ወደ እንግሊዝኛ ሲገለበጥ 'ሺትሆል' ወይም 'ቆሻሻ ሥፍራ' ተብሎ ተነቧል። ይህን ደግሞ የለጠፉት የሳን ሱ ኪ ሰዎች ናቸው። ይህን ያስተዋለው ፌስቡክ እክሉን ካስወገደ በኋላ መንሻፈፉ የተከሰተው በቴክኒካዊ ብልሽት ነው ብሏል። ወደፊት መሰል ጥፋት እንዳይፈፀም እተጋለሁ ብሏል ፌስቡክ። በርሚዝ የምያንማር ኦፌሴላዊ ቋንቋ ሲሆን ሁለት ሶስተኛው የሃገሪቱ ሰው ይጠቀመዋል ተብሎ ይገመታል። የዢ ስም ቋቱ ውስጥ እንዳልገባ ያመነው ፌስቡክ፤ ትርጉም አመንጪው ቴክኖሎጂ በግምት የገጣጠማቸው ቃላት የፈጠሩት ስህተት ነው ብሏል። በምያንማር መንግሥት የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰዎች የተለጠፈው ሃተታ እንዲነሳ መደረጉም ታውቋል። ምንም እንኳ ቻይና ፌስቡክ ባይኖራትም የተንሻፈፈው ትርጉም ቻይና ውስጥ እንዳይሰራ መደረጉም እየተዘገበ ነው። የቻይና መንግሥት የመረጃ ፍሰትን በመገደብ ይታማል። የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ወደ ምያንማር ያቀኑት ስለ ሁለትዮሽ ግንኙነቶች ለመወያየት ነው ተብሏል። የምያንማሯ መሪ ሳን ሱ ኪ የኖቤል ሰላም ሽልማት አሸናፊ ሲሆኑ የሮሂንጃ ሙስሊሞች ላይ በደረሰ ጥፋት ተወንጅለው ባለፈው ወር ፍርድ ቤት መቆማቸው አይዘነጋም።
news-48361904
https://www.bbc.com/amharic/news-48361904
በሳዑዲ አረቢያ 3ሺህ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች መኖራቸው ተገለፀ
በሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ሰባት ክልልሎች ወደ 3ሺህ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ እስር ቤቶች በእስር ውስጥ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኮንሱላር ጀኔራል አቶ አብዱ ያሲን ለቢቢሲ ገለፁ።
ከ45 ሺህ በላይ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል በጂዛን እስር ቤት ብቻ ከ30 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች እንዳሉም አቶ አብዱ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው እስረኞች ከ40 ቀናት በላይ መታሰራቸው ገልፀው በእስርቤቱ ያለው አያያዝ ጥሩ እንዳልሆነ ተናግረዋል። እስረኞቹም ወደ ሃገሪቱ በሕጋዊ መንገድ እንደገቡ እና ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እንዳላቸው ገልጸዋል። • ያልተገታው የኢትዮጵያውያን ጉዞና መከራ በሳዑዲ አረቢያ በሽ ከተባለ አካባቢ ተወስዶ የታሰረው ካህሳይ ብርሃነ ''ያገሪቱ ፖሊሶች አፍሰው አሰሩን፤ እኛ ከስድስት ዓመታት በላይ የኖርን እና የመኖሪያ ፍቃድ ያለን ነን'' ብሏል። "'የመኖሪያ ፍቃዳችሁ ትክክለኛ አይደለም፤ እናጣራዋለን' ብለው እስርቤት ውስጥ አስገቡን። ከዚያም አሻራችሁን ስጡ አሉን፤ እኛ ዓረብኛ መጻፍና ማንበብ አንችልም፤ ምንድን ነው? ስንላቸው፤ ዝም ብላችሁ አድርጉ አሉን። አሻራ አንሰጥም ስንላቸው ደብድበው በኃይል አሻራ እንድንሰጥ አደረጉን'' ይላል ስለ ሁኔታው ሲያስረዳ። አክሎም "ለ 10 ቀናት ያለ ምግብ እና ውሃ፤ ሽንት ቤት ዘግተው እንድንታመም እና እንድንሰቃይ አድርገውናል፤ እያንዳዳንዳችን እያስወጡ በመግረፍ አሰቃይተውናል'' ሲል እስር ቤቱ ውስጥ የደረሰባቸው ግፍ ገልጿል። ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ድጋፍ ቢጠይቁም ኤምባሲው ችላ እንዳላቸው በመግለፅ ቅሬታቸው ተናግረዋል። • በኢትዮጵያ የሚጠለሉ ስደተኞች የመማርና የመሥራት መብት ሊኖራቸው ነው ሌላኛው ቢቢሲ ያነጋገረው እስረኛ ''ጂዛን ወዳለው ትልቅ እስር ቤት ወሰዱን፤ እነሱም አንቀበላቸውም ምን አድርገው ነው? ውሰዷቸው አሉ፤ እንደገና ተመልሰን ወደዛ ሄድን'' ይላል። ከዚያም ወደ ጂዛን እንደተመለሱ እና አሁንም እዚያው መሆናቸውን ተናግሯል። ከካህሳይ ጋር ታስሮ የሚገኘው ኪዳኔ ሺበሺ በበኩሉ ሕክምና ተከልክለው፤ እንዲሁም ያለ በቂ ልብስ ለተባይ እንደተጋለጡ ለቢቢሲ አስረድቷል። ኪዳኔ ለሰባት ዓመታት በሹፌርነት ሥራ ሕጋዊ ሆኖ ይሠራ እንደነበር ገልፆ የመኖሪያ ፈቃዱ ተመልሶለት ወደ ሥራው እንዲመለስ ይጠይቃል። ብዙ ንብረት እንዳፈሩ የሚናገሩት ኢትዮጵያዊያኑ አሠሪዎቻቸው ሊያሰሩዋቸው እንደሚፈልጉ ቢገልጹም ባለስልጣናቱ ለመፍታት ፍቃደኛ አለመሆናቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። የአስርኞቹን ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ አብዱ፤ በጂዛን የሚገኙት እስረኞች ለእስር የተዳረጉት የአገሪቷን ሕግ ባለማክበራቸው ነው ብለዋል። በጉዳዩ ላይ የተለያዩ አካላትን ያነጋገሩም ሲሆን 'በአገሪቷ በሚፈቅደው ሕግ መሠረት ሲሠሩ አላገኘናቸውም' የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ገልፀዋል። • ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እርሳቸው እንደሚሉት በአገሪቱ ሕግ መሠረት የመኖሪያ ፍቃድ መያዝ ብቻ ሕጋዊ አያደርግም። መኖሪያ ፈቃድ ኖሯቸውም በተመደቡበት የሥራ መደብ ሲሰሩ ካልተገኙ ሕጋዊ እንዳልሆኑ ነው የሚቆጠረው። "ጉዳዩ አጠቃላይ ከስደተኞች ጋር የሚያያዝ ነው፤ በአየር መንገድ ብቻ ተሳፍረው ስለመጡ ሕጋዊ የሆኑ ይመስላቸዋል" የሚሉት አቶ አብዱ በሕጋዊ መንገድ መጥተው ስለማይመለሱ ሕገ ወጥ ይሆናሉ ይላሉ። ሌላኛው ጉዳይ በተመደቡበት የሥራ መደብም አለመገኘት ነው። "የእኛ ዜጎች ስለ መብታቸው እንጂ፤ ስለ ግዴታቸው አያውቁም። ለዚያም ነው ችግር የሚያጋጥማቸው" ሲሉም ስደተኞቹ ለችግር የሚዳረጉበትን ዋና ምክንያት ያነሳሉ። ይሁን እንጂ የእስረኞቹን ጉዳይ የኤምባሲው ጉዳይ ፈፃሚ በቅርበት እየተከታተሉት ሲሆን በምህረት እንዲለቀቁም የተለያዩ ጫናዎችን እያሳድሩ መሆኑን ይገልፃሉ። "ምንም እንኳን በቦታው የተመደቡ ሰዎች ቢኖሩም፤ በጂዛን ቆንስላ ጽ/ቤት የለንም" የሚሉት ኮንሱላር ጀኔራሉ ቀይ ባህርን ተሻግረው የሚመጡ ስደተኞች የሚበዙበት አካባቢም በመሆኑ የሰው ኃይል እጥረት እንዳለባቸው ይገልፃሉ። ለዚህም ባለፉት ሰባት ወራት ቀይ ባህርን ተሻግረው የመጡት ስደተኞችም 70 ሺህ የሚጠጉ እንደሆኑ በመጥቀስ ባላቸው የሰው ኃይል እነዚህን ማስተናገድ ፈታኝ እንደሆነባቸው ይናገራሉ። • ስደተኞች በየዓመቱ 8 ቢሊዮን ዶላር ለቤተሰቦቻቸው ይልካሉ በሳዑዲ አረቢያ ሰባት ክልሎች እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ ብቻ 3 ሺህ የሚጠጉ እስረኞች ይገኙ እንደነበር ገልፀውልናል። እስረኞቹ ከቀላል እስከ ከባድ ወንጀሎች ሲፈፅሙ ተይዘው የታሰሩ ናቸው ብለዋል። እንደዚህ ዓይነት ችግሮችን ለመፍታት በሁለት መንገድ ሥራቸውን ያከናውናሉ። አንደኛው የኢኮኖሚ ስደተኞች በመሆናቸው ምህረት ተደርጎላቸው እንዲሰሩ እርዳታ መጠየቅ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በእስር ላይ የሚገኙትም መብታቸው እንዳይነካ ማድረግ ነው። ከዚህ አልፎ ወደ አገር ቤት የሚመልሷቸው ከሆነ እስከሚሄዱ በቆዩባቸው ጊዜያት መብታቸው እንዲከበርና ሲሄዱም የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ንብረታቸውን ይዘው እንዲሄዱ እንደሚሠሩ ነግረውናል።
news-45591143
https://www.bbc.com/amharic/news-45591143
ኤርትራ በምሽት በሰርሃና ዛላምበሳ ድንበርን ማቋረጥ ከለከለች
ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በሚያስገባው ሰርሃ አካባቢ በሚገኘው ጊዜያዊ ፍተሻ ከምሽቱ 12 ሰአት በኋላ መኪና መግባት እና መውጣት እንደማይችል የኤርትራ የፀጥታ ኃይሎች አስታወቁ።
ይህ ከትናንትና ጀምሮ የተተገበረ ሲሆን ሰንዓፈ ደርሶ ወደ አዲግራት ሲመለሱ ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነው ሙሉብርሃን ገብረዋህድ ከአስመራ ሲመጡ ከነበሩ ሰዎች ጋር ማለፍ እንደማይፈቀድለት ተነግሮት ሰርሃ ለማደር እንደተገደዱ ለቢቢሲ ገልጿል። • የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ሲታወስ • ድንበር ላይ የነበረው የድንጋይ አጥር ፈረሰ • ኢትዮጵያና ኤርትራ፦ ከእራት በኋላ ምን ተወራ? ለምን ማለፍ እንዳልቻሉ የኤርትራ የፀጥታ ኃይሎችን እንደጠየቁ የተናገረው ሙሉብርሃን "ማታ የሚያጋጥም የመኪና አደጋ እየበዛ ስለሆነ መግባት እና መውጣት እንድንከለክል ታዘናል" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸውም ጨምሮ ተናግሯል። በዚህም የተነሳ በርካታ መኪኖች መንገድ ላይ እንዳደሩ እሱም መኪና ውስጥ ማደሩን ይናገራል። የትግራይ ምስራቃዊ ዞን አስተዳደር ስለዚህ ጉዳይ መረጃ ይኖረው እንደሆን ጠይቀን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ፈረደ ተናግረዋል። ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠው የነበሩት ኤርትራና ኢትዮጵያ ጉዟቸው ምን ይመስላል?
news-50931786
https://www.bbc.com/amharic/news-50931786
ግብር አጭበርባሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ 'ፖስት' ሊታደኑ ነው
ፈረንሳይ የዜጎቿን የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ በመፈተሽ ግብር አጭበርባሪዎችን ልትለይ ነው።
የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በገጻቸው ላይ የሚለጥፉትን ፎቶግራፍና የግል መረጃ ዝርዝር (ፕሮፋይል) በማየት ግብር የከፈሉና ያልከፈሉ እንደሚለዩ ተገልጿል። ድንጋጌው ባለፈው ሳምንት ከግብር ክፍያ ጋር በተያያዘ የወጣው ሕግ አካል ነው። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የፈረንሳይ የመረጃ ደህንነት ክፍል ሕጉ እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል። ሕጉን ያፀደቀው ምክር ቤት፤ እርምጃው የዜጎች ራስን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ጫና ሊያሳድር ቢችልም፤ ድንጋጌው የሚተገበርበት ቅድመ ሁኔታዎች አሉ ብሏል። ከቅድመ ሁኔታዎቹ አንዱ በሚስጥራዊ ይለፍ ቃል (ፓስወርድ) የተቆለፉ ገጾችን ሰብሮ አለመግባት ሲሆን፤ የግብር ክፍያ ክፍሉ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለሕዝብ ይፋ የተደረጉ መረጃዎችን መጠቀም ግን ይችላል። የፈረንሳይ መንግሥት የዜጎቹን የድረ ገጽ እንቅስቃሴ የሚቃኝበት የሦስት ዓመት እቅድ ነድፏል። ግብር ያልከፈሉ ሰዎችን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚለጥፉት መረጃ ማግኘት የዚሁ እቅድ አካል ነው። የፈረንሳይ የመረጃ ደህንነት ክፍል የሦስት ዓመት እቅዱ ሕጋዊ አግባብነት ቢኖረውም፤ ግብርን በተመለከተ የወጣው ድንጋጌ የዜጎችን ነፃነት ይጋፋል ብሏል። የበጀት ሚንስትሩ ጄራልድ ዳርማኒን በበኩላቸው "አጭበርባሪዎችን የምንገታበት አንድ መንገድ ነው" ሲሉ ሕጉን ገልጸውታል። "በዚህ ዓመት ፈረንሳይ አልኖርኩም ብለሽ፤ ኢንስታግራም ላይ የፈረንሳይ ፎቶዎችን ብትለጥፊ ችግር አለ ማለት ነው" ሲሉ ለ 'ለ ፊጋሮ' ጋዜጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። • 17 ታካሚዎችን የመረዘው ዶክተር • ፈረንሳይ ኩሽና ውስጥ ተሰቅሎ የተገኘው ሥዕል ብሔራዊ ሐብት ነው አለች • ኩባንያው በደረሰበት ጫና ሂጃብ መሸጥ አቆመ
43068690
https://www.bbc.com/amharic/43068690
"በሰላማዊ ትግል እስከመጨረሻው በፅናት እንታገላለን" እስክንድር ነጋ
ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከሰባት ዓመታት እስር ቆይታ በኋላ ትናንትና ነፃ ወጥቷል።
ብዙዎች በከፍተኛ ደስታ ተሞልተው የተቀበሉት ሲሆን እርሱም የተሰማውን ደስታ ለቢቢሲ ገልጿል። "በመፈታቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ከሁሉ በፊት ኃያሉን እግዚአብሔር አመሰግናለሁ እንድፈታ እስከመጨረሻ ድረስ ለታገለልኝ የኢትዮጵያ ህዝብን ማመስገን እፈልጋለሁ።" ብሏል። በተደጋጋሚ ለእስር የተዳረገው እስክንድር ኢትዮጲስ የሚባል ጋዜጣም ባለቤት ነበር። የሰርካለም ማተሚያ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረ ሲሆን በስሩም አስኳል፣ ሳተናውና ሚኒልክ የተባሉ ጋዜጦችንም ያሳትም ነበር። የ1997 ምርጫ ቀውስንም ተከትሎ ጋዜጦቹ የተዘጉ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ በሀገር ክህደት ወንጀል ለእስር የበቃው እስክንድር በይቅርታ እንደተፈታ የሚታወስ ነው። ከዚያም ከሰባት ዓመታት በፊት በሽብር ተከሶ ለ18 ዓመታት የተፈረደበት እስክንድር የኢትዮጵያ መንግሥት 'አሸባሪ' ብሎ ከፈረጀው ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለህ በሚል ነው። የመጨረሻ ቀናት ስለነበረው የእስር ቤት ቆይታው የተናገረው እስክንድር መንግስት በይቅርታ ለመፍታት ካስቀመጠው የስልጠና እንዲሁም ከመፈረም ጋር የተያየዙ ናቸው። "ፈርሙ አትፈርሙ የሚሉ ጉዳዮች ነበሩ። ስንታሰር ጀምሮ ይቅርታ እንደማንፈርም ተማምነን ነበር፤ በዛው ቃላችንን ጠብቀናል።" ብሏል ባለመፈረማቸው ከእስር ቤት ላንለቀቅ እንችላለን የሚለው ፍራቻ እነደነበራቸው የሚናገረው እስክንድር ሆኖም አቶ በቀለ ገርባ በይቅርታ መውጣታቸውን ሲሰሙ "ያው እንደምንፈታ ገምተናል" ይላል። ትናንት ከዕስር ከወጣም በኋላ በትግሉ እንደሚቀጥልም ተናግሯል። "አሁንም በሰላማዊ ትግል ውስጥ እስከመጨረሻው ድረስ በፅናት እንታገላለን። በሰላማዊ መንገድ የዴሞክራሲውን ጥያቄ ባለን አቅም ሁሉ እናግዛለን። " ጨምሮም "የወጣነው ትግሉን ከዳር ለማድረስ ነው።የህዝቡ ጥያቄ የእስረኞች መፈታት አይደለም፤ የዴሞክራሲ ጥያቄ እንዲመለስለት ነው፤ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ነው፤ ይህንን ትግል ደግሞ ባለኝ አቅም ሁሉ ከዚህ በፊት ካበረከትኩት አስተዋፅኦ በላይ አበረክታለሁ" ብሏል። እስክንድር በእስር ላይ ሳለ እ.ኤ.አ የ2012ን የፔን/ባርባራ ጎልድስሚዝ የፅሁፍ ነፃነት እና እ.ኤ.አ የ2017 የዓለም አቀፍ የፕሬስ ተቋምን የዓለም የፕሬስ ነፃነት የጀግንነት ሽልማትን ተቀዳጅቷል።
news-54509752
https://www.bbc.com/amharic/news-54509752
ኮሮናቫይረስ፡ ማኅበራዊ ርቀት ጉንፋንን ከነጭራሹ ያጠፋው ይሆን?
በአውሮፓውያኑ 2014 በብራዚል አማዞን ጫካ ውስጥ ይኖሩ ለነበሩት ጎሳዎች የማይረሳ ዓመት ነው። ስማቸው ሳፓናዋ የሚባል ሲሆን ከጎረቤት አገር ፔሩ የመጡ ሌሎች ጎሳዎች መንደራቸውን ወርረውባቸው ነበር።
ይህን ወረራ የሸሹት የዚህ ጎሳ አባላት ከዚህ በፊት አይተውት ከማያውቁት ስልጣኔ ጋር ተዋወቁ። ሰዎቹ ከዚህ በፊት ከሌሎች ሰዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አድርገው የማያውቁ ሲሆን እኛ የምናውቀውን ዘመናዊ ዓለም ከነጭራሹ ስለመኖሩም አያውቁም ነበር። ከጥቅጥቁ ጫካ ሲወጡ ያገኟቸው ሰዎችም ከሚመለከተው የብራዚል መንግስት ያቋቋመው ድርጅት ጋር አገናኟቸው። እዛው ሆነውም ሶስት ሳምንታትን አሳለፉ። እነዚህ ሰዎች አብዛኛዎቻችንን የሚያሰቃዩን እንደ ጉንፋን የመሳሰሉ በሽታዎችን አያውቋቸውም ነበር። ነገር ግን በቀናት ውስጥ ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ አብዛኛዎቹ ጤናቸው ተቃወሰ። ጉንፋን እና ትኩሳት ያሰቃያቸው ጀመር። ደግነቱ በተደረገላቸው ህክምና አንዳቸውም ሕይወታቸው ሳያልፍ መዳን ቻሉ። በወቅቱ የያዛቸው በሽታ ተላላፊ ስለነበር እራሳቸውን ለይተው እንዲቀመጡና አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ ተደርገው ነበር። በዚህም ምክንያት በሳምንታት ውስጥ ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር ዋለ። የጉንፋን ወረርሽኙም ጉዳት ሳያስከትል ጠፋ። ስለዚህ ጉንፋንን የማያውቁ ማህበረሰቦች አሉ ማለት የተቀረው ዓለምም ጉንፋንን አይንህን ለአፈር ብሎ ማጥፋት ይችል ይሆን ወይ የሚለውን ጥያቄ እንዲነሳ ያስገድዳል። በሳለፍነው ጥር ወር ላይ አውስትራሊያ ውስጥ 6962 ሰዎች በድንገት በጉንፋን መያዛቸው ተሰምቶ የነበረ ሲሆን በወቅቱ ኮቪድ-19 ቻይና ውስጥ ብቻ የተወሰነ ከባድ ጉንፋን ተደርጎ ነበር የተወሰደው። ሚያዝያ ወር ላይ ደግሞ ወረርሽኙ መላው ዓለምን አዳርሶ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን አጥቅቶ ነበር። በዚህም ምክንያት በርካታ አገራት እንቅስቃሴዎችን ሙሉ በሙሉና በከፊል አገዱ፣ የአውሮፕላን በረራዎችን አቋረጡ፣ ሰዎች አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁም ማሳሰቢያ ማስተላለፍ ጀመሩ። የፈረንጆቹ በጋ ወቅት ሲመጣ ጉንፋን የተለመደ ነበር። ነገር ግን እንደ አውስትራሊያ እና ኒው ዚላንድ ባሉ አገራት የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ ሰዎች አካላዊ ርቀታቸውን በመጠበቃቸውና ሌሎች ጥንቃቄዎችን ማድረግ በመጀመራቸው በጉንፋን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል። የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ የተላላፊ በሽታዎች መቆጣጠሪያ ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው ከዚህ በፊት ከነበሩት የጉንፋን ወቅቶች አንጻር ዘንድሮ ከነጭራሹ የለም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ነገሮች ተቀይረዋል። ኒው ዚላንድም ቢሆን ዘንድሮ በጉንፋን የተጠቃ ምንም ዜጋ አላገኘሁም ያለች ሲሆን ባለፈው ዓመት ግን የጉንፋን ምርምራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል 57 በመቶ የሚሆኑት ጉንፋን መያዛቸው ተረጋግጦ ነበር። በርካቶችም ይህ የሆነው ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ሰዎች አካላዊ ርቀታቸውን በመጠበቃቸውና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ በመጀመራቸው ነው ይላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው በመላው ዓለም ይመዘገቡ የነበሩ የጉንፋን አይነቶች ጠፍተዋል። 'ፍሉማርት' በመባል የሚታወቀው የጉንፋን መከታተያ ስርአት በመስከረም ወር በመላው ዓለም መመዝገብ የቻለው 12 በላብራቶሪ የተረጋገጡ በጉንፋን የተያዙ ሰዎችን ብቻ ነው። ከቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ሳራ ኮቤይ እንደሚሉት ደግሞ ምናልባት በጉንፋን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የቀነሰው ሰዎች ወደ ሆስፒታል ለመምጣት ፍርሀት ስላለባቸውና ከኮሮናቫይረስ ጋር እንዳይመሳሰልባቸው ስለሚሰጉ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይህ ማለት በጉንፋን የሚያዙ ሰዎች ከዚህ በፊት ከነበረው አልቀነስም ማለት አይደለም ይላሉ። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ በጉንፋን ይያዙ ነበር፤ አሁን ግን ከነጭራሹ የሚያዙ ሰዎችን ማግኘት ከባድ ሆኗል። ስለዚህ ያለው ብቸኛ መልስ ሊሆን የሚችለው አካላዊ ርቀት በመጠበቃችንና ንጽህናችንን በአግባቡ እየተከታተልን ስለምንጠብቅ ነው ብለዋል የበሽታ ስርጭት ባለሙያዋ ሳራ። ጉንፋን ከነጭራሹ ከሰው ልጆች ሕይወት የመጥፋት ዕድል ይኖረው ይሆን? የሰው ልጅ እድሜ ልኩን ከጉንፋን ጋር አልኖረም። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የሰው ልጅ ጉንፋን ለመጀመሪያ ጊዜ የያዘው ምናልባትም ከ10 ሺ ዓመታት በፊት ከሚያረባቸው የወፍ ዝርያዎች እንደሆነ ይገመታል። ጉንፋንን ሁሌም አስቸጋሪ የሚያደርገው እራሱን ስለሚቀያይር እንደሆነ ባለሙያዎቹ ይነገራሉ። አንድ ሰው በአንድ የጉንፋን ቫይረስ ከተያዘ በኋላ በሽታ የመከላከል ስርአቱን ስለሚገነባ መልሶ አይዘውም። ነገር ግን ቫይረሱ እራሱን ትንሽ ቀይሮ ሲመጣ እንደ አዲስ ሰውነታችንን ያጠቃል። ለዚህም ነው በዓለማችን ላይ ከሚኖሩት 7 ቢሊየን በላይ ሰዎች መካከል በየዓመቱ 10 በመቶ የሚሆኑት ጉንፋን የሚጠቁት። ምናልባት የሰው ልጅ አሁን እየሄደበት ባለው አካሄድ ቀጥሎ ጉንፋንን ማጥፋት ቢችል እንኳን አንድ ሰው ከሆነ ጊዜ በኋላ በጉንፋን መያዙ አይቀርም። ይህ ደግሞ ቫይረሱ በቀላሉ ዓለምን እንዲያዳርስ ይረዳዋል። አሜሪካ ውስጥ የተነሳው ጉንፋን አፍሪካ ሲደርስ ሌላ አይነት ቫይረስ ይሆናል። ከአውስትራሊያ የመጣው ቫይረስ ቻይና ሲደርስ እራሱን ቀያይሮ አዲስ አይነት ባህሪ ይዞ ይመጣል። ለዚህም ነው ቫይረሱ በቀላሉ እራሱን መቀያየር የሚችለውና እንዳይጠፋ የሚሆነው። ምንም እንኳን ጉንፋን እንዲህ በቀላሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጠፋ ነገር ባይሆንም አሁን ያለው ወረርሽኝ የቫይረሱን እድገትና ስርጭት በእጅጉ እንደገታው ግን ማስተዋል ከባድ አይደለም።
news-49590170
https://www.bbc.com/amharic/news-49590170
የአሜሪካ መከላከያ ለትራምፕ አጥር የ3.4 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ
የአሜሪካ መከላከያ ኃይል ፔንታጎን በአሜሪካ እና በሜክሲኮ ድንበር ላይ ለሚገነባው አጥር 3.4 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ።
የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ማርክ እሰፔር 280 ኪሎ ሜትር ለሚረዝመው አጥር ግንባታ የ3.4 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደረጉት 127 የሚሆኑ የጦር ኃይሉ ፕሮጀክቶችን በማስቆም ነው። ዶናልድ ትራምፕ ለፕሬዝደንትነት ሲወዳደሩ ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል በሜክሲኮ እና በአሜሪካ መካከል የግንብ አጥር መገንባት አንዱና አጨቃጫቂው ነበር። ከዛም አልፎ ፕሬዝደንቱ የአጥሩን ግንባታ ወጪ ሜክሲኮ እንደምትሸፍን ሲናገሩም ከርመዋል። • የትራምፕ አማካሪ፡ የግንቡ ውጥን ውድቅ ከተደረገ ሰነባብቷል • አሜሪካና ሜክሲኮን የሚለየው ግንብ መገንባት ተጀመረ ሜክሲኮ ለአጥሩ ግንባታ ቤሳቤስቲን እንደማታወጣ ብትናገርም፤ ትራምፕ ግን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሜክሲኮ እንደምትከፍል ሲያሳውቁ ቆይተዋል። የአሜሪካ ኮንግረስ ለአጥሩ ግንባታ የሚሆን ገንዘብ እያፈላለገ ቢሆንም፤ አብዛኞቹ ሪፐብሊካኖች ግን እስከ 21.5 ቢሊዮን ዶላር ሊያወጣ በሚችለው ግንባታ ደስተኛ እንዳልሆኑ የአሜሪካ የአገር ውስጥ ጉዳዮች መምሪያ ዘገባ ያሳያል። ትራምፕ በበኩላቸው አጥሩ ከ12 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደማያወጣ ሲናገሩ ይደመጣል። የአሜሪካ መከላከያ የ3.4 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደረገው በ23 የአሜሪካ ግዛቶች እና በ20 ሌሎች አገራት ውስጥ እየተከናወኑ የነበሩ 127 የጦሩ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ለጊዜው እንዲቆሙ በማድረግ መሆኑ ተነግሯል። ዲሞክራቶች በአሜሪካ ጦር ውሳኔ ደስተኛ አይደሉም። የአሜሪካ ሲቪል ሊበሪቲስ ማኅበር በበኩሉ፤ ፕሬዝደንት ትራምፕ ለአጥር ግንባታው የሚያስፈልጋቸውን ፈንድ ለማግኘት የሚያዙበትን ሕግ በፍርድ ቤት ለማሳገድ ማዘዣ እንደሚያስወጣ ቃል ገብቷል።
50386844
https://www.bbc.com/amharic/50386844
"የኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊዎች ሕይወቱን ማዳን ይችሉ ነበር" የአቶ ገመቺስ ባለቤት ወ/ሮ መሰረት
'የኢትዮ ቴሌኮም የምዕራብ ዞን ኃላፊ የነበሩት አቶ ገመቺስ ታደሰ በተደጋጋሚ ለኢትዮ ቴሌኮም የዝውውር ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ባለቤታቸው ወ/ሮ መሰረት ሁንዴሳ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ወ/ሮ መሰረት እንዳሉት፤ አቶ ገመቺስ ከዓመት በፊት የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ነበር። ይህን ተከትሎም አቶ ገመቺስ ለኢትዮ ቴሌኮም የዝውውር ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ገልጸዋል። ወ/ሮ መሰረት ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ አቶ ገመቺስ የዝውውር ጥያቄያቸውን ለኢትዮ ቴሌኮም አቅርበው ከተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር እየተጻጻፉ ነበር። አቶ ገመቺስ ከኢትዮ ቴሌኮም ባገኙት ምላሽ ደስተኛ እንዳልነበሩ የተናገሩት ባለቤታቸው፤ "የኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊዎች ሕይወቱን ማዳን ይችሉ ነበር" ብለዋል። • "በኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊ ግድያ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም" የነቀምቴ ፖሊስ አዛዥ • "ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው" የአቶ ገመቺስን ግድያ እየመረመረ ያለው ቡድን አንድ ሰው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ለቢቢሲ ገልጿል። አቶ ገመቺስ ጥቅምት 16 ቀን 2012 ዓ. ም. በነቀምቴ ከተማ ውስጥ ጨለለቁ በተባለ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ መገደላቸው ይታወሳል። ወ/ሮ መሰረት እንደሚሉት፤ በእለቱ አቶ ገመቺስ ከጓደኞቻቸው ጋር ቤት ውስጥ ሳሉ ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ ስልክ ተደውሎላቸው ነበር። "የደወለለት የሚያምነው ጓደኛው" ነበር የሚሉት ወ/ሮ መሰረት፤ አቶ ገመቺስ ስልክ ለማውራት ከቤት ከወጡ በኋላ የተኩስ ድምጽ እንደሰሙ ይናገራሉ። "የተኩስ ድምጽ ሰምተን ስንወጣ ገሜን [ገመቺስን] መሬት ላይ ወድቆ አገኘሁት" ሲሉ የተከሰተውን ይገልጻሉ። ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋለው ግለሰብ ለአቶ ገመቺስ ደውሎ የነበረው ሰው እንደሆነም ያክላሉ። አቶ ገመቺስን ወደ ሆስፒታል እንደወሰዷቸው ተናግረው፤ "ሆስፒታል ከደረስን በኋላ በቂ አገልግሎት አልተደረገም" ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል። የነቀምቴ ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ዳምጠው ጋረደው፤ አቶ ገመቺስ ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ከአንድ ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ሕይወታቸው እንዳለፈ አስታውሰው፤ "በአጭር ጊዜ ተገቢው ህክምና ተደርጓል" ብለዋል። ሜዲካል ዳይሬክተሩ፤ አቶ ገመቺስ ቢያንስ አራት ጊዜ በጥይት መመታታቸውን እና አንድ ጊዜ ደግሞ በስለት መወጋታቸውን ተናግረዋል። "ግራ እጁ ላይ ሁለት ጊዜ በጥይት ተመቷል። ትከሻው ላይም በጥይት ተመቶ በብብቱ በስተግራ በኩል ጥይቱ ወጥቷል" ያሉ ሲሆን፤ ታፋቸው አካባቢ ሁለት ቦታ መመታታቸውን እና ጥይቶቹ የገቡበት እና የወጡበት ቦታ ይታይ እንደነበረም በወቅቱ ገልጸዋል። ዶ/ር ዳምጠው እንደሚሉት ከሆነ፤ የአቶ ገመቺስ ሕይወት በፍጥነት እንዲያልፍ ያደረገው ደረታቸው ላይ በስለት መወጋታቸው ነው። ወ/ሮ መሰረት እንደሚሉት፤ አቶ ገመቺስ ሕዳር 5 ቀን 2011 ዓ. ም. ነቀምቴ ከተማ ውስጥ፣ ምሽት ላይ 'አስክ' በሚባል ትምህርት ቤት መኪናቸውን አቁመው ሲወጡ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ነበር። "ያኔ ክስተቱን ለፖሊስ ሪፖርት ብናደርግም ያገኘነው መፍትሔ አልነበረም" ብለዋል። ከሁለት ሳምንት በፊት ከመገደላቸው አስቀድሞ ስጋት እንዳላቸው እንደገለጹም አክለዋል። • ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ጋር በተያያዘ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ • "ሴት ተማሪዎችን ባጠቃላይ ተመርመሩ ማለት መፈረጅ ነው" የሕግ ባለሙያ ከግድያ ሙከራው በኋላም ለኢትዮ ቴሌኮም የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸውን እንዲሁም ሌላ ሥራ እያፈላለጉ እንደነበረም ያስረዳሉ። "ለኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስኪያጅ ፍሬሕይወት ታምሩ እዚህ መኖር ስጋት ውስጥ እንደጣለው ተናገሮ ነበር" የሚሉት የአቶ ገመቺስ ባለቤት፤ ኢትዮ ቴሌኮም ቦታ እንፈልግልሀለን የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ገልጸዋል። "ቦታ እንፈልግልሀለን ቢሉም ከቃል ባለፈ ሊሳካ አልቻለም" ይላሉ። የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሪት ጨረር አክሊሉ፤ አቶ ገመቺስ ዝውውር ጠይቀው እንደነበር ለቢቢሲ አረጋግጠው፤ በምዕራብ ዞን ይሠሩበት ከነበረው አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው፣ አዲስ አበባ እንዲሠሩ እንደተነገራቸው እና አቶ ገመቺስ ግን እንዳልፈለጉ ተናግረዋል። "ጥያቄውን ከአንድ ዓመት በፊት አቅርበው ነበር። እሳቸው የጠየቁት ቦታ እስኪገኝ አዲስ አበባ በሌላ ቦታ እንዲሠሩ ሥራ አስኪያጇ ፈቅደው ነበር። ውሳኔውን ግን አልተቀበሉም" ይላሉ። አቶ ገመቺስ በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ለምን ነቀምቴ ውስጥ ቆዩ? ስንል ባለቤታቸውን ጠይቀን፤ "በሁኔታዎች ተገዶ እንጂ ወዶ አልቆየም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። • ሦስቱ ሃገራት በዋሽንግተን ምን ተስማሙ? • የኢትዮጵያዊቷ ህክምና መቋረጥ በደቡብ አፍሪካ አነጋጋሪ ሆነ የሁለት ልጆች አባት የነበሩት አቶ ገመቺስ፤ በኢትዮ ቴሌኮም ለአሥር ዓመታት ሠርተዋል። ወ/ሮ መሰርት "መንግሥት ችግሩን አይቶ ቢፈታ ኖሮ የገመቺስ ልጆች አባት አልባ አይሆኑም ነበር" ብለዋል።
news-53891753
https://www.bbc.com/amharic/news-53891753
ደቡብ ኮርያ፡ የዩቲዮብ ክብረ ወሰንን የሰባበሩት የኮርያ ድምጻውያን
የኮርያ የወንዶች ሙዚቃ ቡድን፣ ቢቲኤስ፣ በዩቲዩብ ታሪክ አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበ የሙዚቃ ቪዲዮ ለቋል። ሙዚቀኞቹ የዩናይትድ ኪንግደም የነጠላ ዜማ ሰንጠረዥንም ተቆጣጥረውታል።
ቢቲኤሶች የለቀቁት የሙዚቃ ቪዲዮ "ዳይናማይት" የሚሰኝ ሲሆን የዩቲዩብ ክብረወሰንን ብቻ ሳይሆን በዩናይትድ ኪንግደም ነጠላ ሙዚቃዎች ሰንጠረዥ ላይም አርብ ዕለት በአንደኝነት ተቀምጧል። የቡድኑ የሙዚቃ ቪዲዩ አርብ ዕለት ብቻ በ24 ሰዓት ውስጥ 101.1 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል። ከዚህ ቀደም 'ብላክ ፒንክ' የተሰኙ የኮሪያ የሙዚቃ ቡድን አባላት 'ሃው ዩ ላይክ ዛት' በሚለው የሙዚቃ ቪዲዮዋቸው 86.3 ሚሊዮን ተመልካቾችን በ24 ሰዓት ውስጥ በማግኘት የክብረወሰኑ ባለቤት ሆነው ነበር። ይህንን ክብረ ወሰን እንደ ቀልድ ያለፉት ቢቲኤሶች በአንድ ቀን 100 ሚሊዮን ተመልካቾችን ማግኘት ችለዋል። የሙዚቃ ክሊፑ በቀጥታ ሲሰራጭ ሦስት ሚሊዮን አድናቂዎቻቸው የተከታተሉት ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በብላክ ፒንኮች 'ሃው ዩ ላይክ ዛት' ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በእጥፍ በልጠዋል። ቢቲኤሶች እንግሊዘኛን ከኮርያኛ ቀላቅለው በመዝፈን ይታወቁ የነበረ ቢሆንም 'ዳይናማይት' ግን ሙሉ በሙሉ በእንግሊዘኛ ያቀነቀኑት የመጀመሪያ ሥራቸው ነው። ቡድኖቹ በጎ ሃሳብን፣ ተስፋን፣ ፍቅርን እና ንጹህ መንፈስን በሙዚቃቸው መስበክ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። ቡድኑ ይህንን የሙዚቃ ቪዲዮ መልቀቅ የፈለጉት አድናቂዎቻቸውን በፍጥነት መድረስ በመፈለጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት የዓለም ሕዝብ በበርካታ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አልፏል ያሉት ቡድኑ አባላት ከአድናቂዎቻቸው ጋር በጎ ኃሳብን መጋራት እቅዳቸው ነው። ሙዚቃው በ104 አገሮች አይቲዩንስ ላይ ከፍተኛ አድማጭ አግኝቷል። ቢቲኤሶች ተቀናቃኝ አላጣቸውም፤ በአገራቸው ልጆች የተመሰረተው 'ብላክ ፒንክ' የተሰኘው ሙዚቃ ቡድን አርብ እለት የያዙትን የዩቲዩብ ክብረወሰን ለመስበር በመዛት ከሴሌና ጎሜዝ ጋር ጥምረት ፈጥረው የሰሩትን 'አይስ ክሬም' የተሰኘ የሙዚቃ ክሊፕ እንደሚለቅቁ ተናግረዋል።
42947580
https://www.bbc.com/amharic/42947580
አሜሪካ ለላሊበላ ቤተክርስትያን ጥበቃ ፕሮጀክት 13.7 ሚሊዮን ብር ሰጠች
የአሜሪካ ኤምባሲ ለላሊባለው ቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ቤተክርስትያን ጥበቃ ይውል ዘንድ 13.7 ሚሊዮን ብር መስጠቱን ኤምባሲው በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ይህ ፕሮጀክት ይፋ የሆነው ቅዳሜ እለት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ወልደ ማርያምና በአሜሪካው አምባሳደር ማይክል ሬይኖር ነው። ከዚህ የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የአለም ቅርስ ፈንድ የሰጠው 119500 ዶላርም ለቤተክርስትያኑ ጥበቃ ስራ እንደሚውል ታውቋል። በቤተክርስትያኑ ላይ የሚደረጉ የጥበቃ ስራዎች ቀደም ሲል እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 ላሊበላ ላይ የተሞከሩ እንደሚሆኑም ተጠቁሟል። በፕሮጀክቱ የአካባቢው የግንባታ ባለሙያዎችም እንደሚሰለጥኑና የጥበቃ ስልቱን ለወደፊቱ እንዲተገብሩ እንደሚደረግም ተገልጿል። ፕሮጀክቱ ይፋ በተደረገበት ዝግጅት ላይ አምባሳደር ሬይኖር እነዚህ ቤተክርስትያኖች ከመቼውም በላይ አስፈላጊ እንደሆኑና፤ የሚደረግላቸው ጥበቃም እንዲሁ አስፈላጊ ሆነው እንዲቀጥሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። " እየሰራን ያለነው የኢትዮጵያን ያለፈ ታሪክ አካል ለመጠበቅ ብቻ አይደለም።ይልቁንም የዛሬ የኢትዮጵያ ባህልና ሃይማኖት አካልን ነው"በማለት የኢትዮጵያ ባህል ከብዙ ምክንያቶች መካከል በብዝሃነቱ ልዩ ቦታ እንዳለው ተናግረዋል። አምባሳደሩ እንደዚህ ካሉ የኢትዮጵያ እሴቶች ባሻገር በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካዊ አመለካከትን መግለፅንና የሃሳብ ልዩነትን ማቻቻል ላይም ማተኮር እንደሚገባ ተናግረዋል። እንደ አውሮፓውያኑ ከ2003 ጀምሮ የአሜሪካ ኤምባሲ ለዘጠኝ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ቅርሶች ጥበቃ ድጋፍ ማድረጉም በመግለጫው ተገልጿል።
news-52541183
https://www.bbc.com/amharic/news-52541183
7 ፓርቲዎች አሁን ላይ ላለው ችግር ምላሽ የሚሆነው 'ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው' አሉ
7 ፖለቲካ ፓርቲዎች አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት "ከመስከረም 30 በኋላ አገርን ማስተዳደር የሚያስችል ሕጋዊ መሰረት ሊኖረው አይችልም" በማለት አሁን ላለው ችግር ምላሽ የሚሰጠው ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው ብለዋል።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በነሐሴ ወር ለማካሄድ ታቅዶ የነበረውን ምርጫ ማስፈጸም አስቸጋሪ በመሆኑ መንግሥት የምርጫ ጊዜን በማራዘም ምርጫውን ማካሄድ ያስችላሉ ያላቸውን አራት አማራጮች ማቅረቡ ይታወሳል። • ህወሐት ክልላዊ ምርጫ ለማከናወን ዝግጅት አደርጋለሁ አለ • እውን የትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ ማካሄድ ይችላል? እነዚህም አማራጮች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፣ ሕገ-መንግሥትን ማሻሻል እና የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ የሚሉ ናቸው። 7ቱ ፓርቲዎች፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፣ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ፣ የአገው ብሔራዊ ሸንጎ፣ የሞቻ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ አረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ እንዲሁም ከፋ አረንጓዴ ፓርቲ ''መንግሥት ያቀረባቸውን አማራጮች ገምግመን የራሳችንን አቋም ይዘናል" ብለዋል። 7ቱ ፓርቲዎች ምን አሉ? ከላይ የተጠቀሱት 7 ፖለቲካ ፓርቲዎች አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት "ከመስከረም 30 በኋላ አገርን ማስተዳደር የሚያስችል ሕጋዊ መሰረት ሊኖረው አይችልም" ብለዋል። መንግሥት ያቀረባቸው 4 አማራጮች "የመንግሥትን የሥራ ዘመን ለማራዘም የሚያስችል ሕገ-መንግሥታዊ መከራከሪያ ማቅረብም አይችሉም' ብለዋል። ፓርቲዎቹ ባወጡት መግለጫ፤ "መፍትሔው የኮሮናቫይረስ አልፎ (ተወግዶ) ምርጫ እስክናካሂድ ድረስ የሚፈጠረውን የመንግስት የስልጣን ክፍተት ለመሙላት የሚረዳው ሀገራዊ የፖለቲካ ስምምነት ላይ መድረስ ብቻ ነው" ብለዋል። • የጠቅላይ ሚንስትሩ አራት አማራጮች ፓርቲዎቹ ለዚህ ችግር ምላሽ የሚሆነው "የፖለቲካ መፍትሄ" እንደሆነ የጠቆሙ ሲሆን፤ መፍትሄ ያሉትን በዝርዝር የሚገልጽ ሰነድ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ለማቅረብም ዝግጅታችንን አጠናቀናል ብለዋል። "ከዚህ ውጪ የሚወሰድ ማንኛውም እርምጃ ፖለቲካዊ፣ ሕጋዊና እና ሕዝባዊ ተቀባይነት ስለሌለው አገሪቱን ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስና ብጥብጥ የሚወስድ ነው የሚል ስጋት አለን" በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ቅቡልነት ያለው ስምምነት ላይ ለመድረስ፤ ውይይቱ እና ድርድሩ በገለልተኛ አካል እየተመራ በ2012 ምርጫ ለመሳተፍ የተመዝገቡ ፓርቲዎች ብቻ መሳተፍ እንዳለባቸው እና በድርድሩ የሚደረሰው ስምምነት በሁሉም ወገን ተፈጻሚነት የሚኖረው መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
44530512
https://www.bbc.com/amharic/44530512
እስራኤል የቀድሞ ሚኒስትሯን በኢራን ሰላይነት ፍርድ ቤት አቆመች
የእስራኤል መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል የነበሩትን ጎነን ሰጌቭ ለኢራን ይሰልሉ ነበር በማለት ከሳቸዋለች።
በአውሮፓውያኑ 1990ዎቹ የኢነርጂ ሚኒስትር የነበሩትና የህክምና ዶክተር የሆኑት ጎነን ሰጌቭ ናይጀሪያ ይኖሩበት በነበረበት ወቅት በኢራን የደህንንት ሰዎች እንደተመለመሉ የእስራኤል የደህንነት መረጃ ድርጅት ሺን ቤት አስታውቋል። ግንቦት ወር ላይ ኢኳቶሪያል ጊንኒ በሚጎበኙበት ወቅት በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰብ በእስራኤል ፖሊስ ጥያቄ መሰረት ተላልፈው ተሰጥተዋል። የ62 ዓመቱ የቀድሞ ሚኒስትር በአውሮፓውያኑ 2005 አደንዛዥ ዕፅና ሀሰተኛ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት በመያዝ በቁጥጥር ስር ውለው ለአምስት ዓመታት እስር ተፈርዶባቸው ነበር። በዚህም ምክንያት የህክምና ፈቃዳቸው ታግዷል። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ በአውሮፓውያኑ 2007 በናይጀሪያ መኖሪያቸውን አድርገው በዶክተርነት ሙያቸውም ያገለግሉ ነበር። ሺን ቤት ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ የቀድሞው ሚኒስትር ባለፈው ወር እስራኤል እንደደረሱም በቁጥጥር ስር ውሏል። ከኢራን የደህንነት ወኪሎች ጋር ስላላቸው ግንኙነት እንዲሁም ኢራንን በፀረ-እስራኤል አቋሟ በመደገፍ ጥያቄ ውስጥ ገብተዋል። በምርመራውም ወቅት የቀድሞው ሚኒስትር ናይጀሪያ በሚገኘው የኢራን ኤምባሲ ባለስልጣናት እንደተገናኙና በአውሮፓውያኑ 2012ም ሁለት ጊዜ ወደ ኢራን ተጉዘው እንደነበር ሺን ቤት ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ በሌላም ሀገራት ከኢራን ስለላ ተቆጣጣሪያቸው ጋር ተገናኝተው ምስጢራዊ መረጃዎች የተላለፈላቸው ሲሆን በኮድም መልዕክቶችን እንደተቀያየሩ ሺን ቤት ያስረዳል። የቀድሞው ሚኒስትርን የእስራኤልን የኢነርጂ ዘርፍ፣ የፀጥታ ሁኔታ፣ በፖለቲካውና በፀጥታው ዘርፍ ስላሉ ባለስልጣናት ለተቆጣጣሪዎቻቸው መረጃ በማስተላለፍ ሺን ቤት ወንጅሏቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የኢራን ሰላዮችን በንግዱ የተሰማሩ ግለሰቦች በማለት ለእስራኤል ባለስልጣናት እንዳሰተዋወቁም ክሱ ይጨምራል። አርብ ዕለት እየሩሳሌም ፍርድ ቤት በዋለው ችሎትም " ጠላትን በጦርነት ጊዜ በማገዝ" እንዲሁም "በእስራኤል ግዛት ላይ በመሰለልና" በሌሎች ወንጀሎችም ክስ ቀርቦባቸዋል። መረጃው ለህዝብ እንዳይቀርብ ጥሎት የነበረውን እገዳ ፍርድ ቤቱ ሰኞ ዕለት ያነሳ ቢሆንም አሁንም ቢሆን አንዳንድ ዝርዝሮች ለህዝብ ግልፅ አይደሉም ተብሏል። የቀድሞው ሚኒስትር ጠበቃ በበኩላቸው ሙሉ ክሳቸው የሺን ቤት ካወጣው መግለጫ በተለየ መልኩ መሆኑን የእስራኤል ሚዲያ ዘግቧል። በአውሮፓውያኑ 1979 የእስልምና አብዮትን ተከትሎ የኢራን መሪዎች እስራኤል ህገ-ወጥ ወራሪ ናት በሚል እንደ ግዛት መታወቅ እንደሌለባት ሲናገሩ ነበር። እስራኤል በበኩሏ ኢራንን የኒውክሊየር መስፋፋት በመቃወም እንደ ጠላት የምታያት ሲሆን በመካከለኛው ምስራቅ ያላትም ተፅእኖ ያስፈራቸዋል።
news-53762399
https://www.bbc.com/amharic/news-53762399
ሂዩማን ራይትስ ዎች፡ የየመን ታጣቂዎች ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን አባረዋል፤ ገድለዋል
የሁቲ ታጣቂዎች ኮቪድ-19ኝን ምክንያት በማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከሰሜናዊ የመን አስወጥተዋል እንዲሁም ገድለዋል ሲል ሂዩማን ራይተስ ዎች የተሰኘው ተቋም አስታውቋል።
ድርጅቱ ያወጣው መግለጫ እንደሚያትተው ወደ ሳዑዲ ድንበር የተባረሩት ስደተኞች በድንበሩ ጠባቂዎች ሌላ ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ የተወሰኑ ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች የሚቆጠሩት ወደ ተራራማ አካባቢ ሸሽተዋል ይላል። ድምፃቸውን ለመብት ተሟጋቹ ድርጅት የሰጡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ለቀናት ያለምግብና ውሃ እንደቆዩ ተናግረው ከዚያ በኋላ ወደ ሳዑዲ መግባት ቢችሉም ንፅሕና በሌለው ሥፍራ ታጉረው እንደከረሙ ተናግረዋል። ሕፃናትን ጨምሮ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አሁንም በየመንና ሳዑዲ ተራራማ ድንበር አካባቢ ሊኖሩ እንደሚችሉ ድርጅቱ ይገምታል። የድርጅቱ ጥናት ቡድን አባላት ናዲያ ሃርድማና የሳዑዲና የየመን ኃይሎች ኢትዮጵያዊኑ ላይ የፈፀሙትን ግፍ ወቅሰው የተባበሩት መንግሥታት ለጉዳዩ መፍትሔ እንዲሰጠው አሳስበዋል። ድርጅቱ ሰኔና ሐምሌ ወር ላይ 19 ኢትዮጵያውያንን ማለትም 13 ወንዶች፣ 4 ሴቶችና ሁለት ታዳጊ ሴቶች አናግሯል። ከመስከረም 2014 ጀምሮ የየመን ዋና ከተማ ሰንዓን የተቆጣጠሩት የሁቲ አማፅያን በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን አል ጋር የሚባል አካባቢ ከበው ጥቃት እንዳደረሱባቸው ድርጅቱ ያናገራቸው ስደተኞች ያስረዳሉ። ይህ የሆነው ወርሃ ሚያዚያ ላይ ሲሆን ከዚያም ስደተኞቹን የጭነት መኪና ላይ አሳፍረው ወደ ሳዑዲ ድንበር እንደወሰዷቸውና ሊያመልጡ የሞከሩ ሰዎች ላይ እንደተኮሱ ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። የድርጅቱ ምንጮች እንደሚሉት ታጣቂዎቹ ስደተኞቹ ኮሮናቫይረስ ሊኖርባቸው ይችላል በሚል ከአል ጋር ያባረሯቸው። ተቋሙ ያናገራት አንዲት ሴት "ሁለት ሰዎች ሲሞቱ አይቻለሁ" ስትል ሌላ ሴት ደግሞ "ታጣቂዎቹ ሥፍራውን ለቀን እንድንወጣ ሲያዋክቡን ነበር በዚህም መካከል 40 ያክል ሰዎች እንደሞቱ ማየት ችያለሁ" ብላለች። ለድርጅቱ ቃላቸውን ከሰጡ 19 ሰዎች መካከል 12 ሰዎች፤ ስደተኞች ሲገደሉ የተመለከቱ ቢሆንም የሟቾች ቁጥር በይፋ ምን ያክል እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም ይላል መግለጫው። አል ጋር የተሰኘው ኢ-መደበኛ የስደተኞች ጣቢያ በርካቶች ተጠልለው የሚኖሩበት ነው። ሂዩማን ራይትስ ዎች ጥቃቱ ተፈፅሟል ከተባለት ወቅት በፊት እንዲሁም በኋላ ያሉ የሳተላይት ምስሎችን ተመልክቶ ቢያንስ 300 መጠለያ ሸራዎች ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን ተገንዝቧል። ስደተኞቹ፤ ከሳዑዲ አረቢያ ድንበር ጠባቂዎች አምልጠው በሥፍራው በሚገኝ አንድ ወንዝ አቅራቢያ ቢደበቁም በወታደሮቹ ተይዘው ወደ 'ወታደራዊ ካምፕ' መወሰዳቸውንና በካምፑ ለሰዓታት መቆየታቸውን ይናገራሉ። ስምንት ስደተኞች የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች ገንዘብና ሌሎች ንብረቶችን እንደወሰዱባቸውና በቀጣዮቹ ቀናት ደቡባዊ ሳዑዲ ወደ ሚገኝ አል-ጂዛን የተባለ የማጎሪያ ጣብያ እንደወሰዷቸው ተናግረዋል። የሳላይት ምስሎችን የተጠቀመው ሂዩማን ራይትስ ዎች ስደተኞቹ ታጉረን ነበር ባሏቸው ሥፍራዎች የሚገኙ ካምፖችን መመልከት ችሏል። ሂዩማን ራይትስ ዎች አሁን ጂዛን የሚገኙ 6 ኢትዮጵየዊያን ወንዶችና፤ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ በለይቶ ማቆያ ያሉ 6 ሴቶችን አናግሮ ሁሉም በጂዛን ጣብያ ታጉረው ለቀናት እንደቆዩ ተናግረዋል። ስደተኞቹ፤ ማጎሪያ ጣብያው በጣም የተጨናነቀ፣ በቂ መፀዳጃ ክፍሎች የሌሉት፣ አልጋና ብርድ ልብስ የማይገኝበት፣ የሕክምና አገልግሎት የሌለው እንደሆነና ብዙዎቹ ወለል ይተኙ እንደነበር ተናግረዋል። ድርጅቱ ከስደተኞቹ የፎቶና የተንቀሳቃሽ ምስሎች መረጃ እንዳገኘ መግለጫው ላይ አስፍሯል። ድርጅቱ፤ የሁቲ ኃላፊዎች ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ ግፍ የፈፀሙትን ታጣቂዎች መርምረው እንዲቀጡ ብሏል። አልፎም የሳዑዲ መንግሥት የድንበር ጠባቂዎቹን እንዲመረምርና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል። ስደተኞቹ የሚገኙባቸው ማጎሪያ ጣብያዎችን ሁኔታ እንዲያሻሽልም ድርጅቱ ለሳዑዲ መንግሥት ማሳሰቢያ አስተላልፏል። የሳተላይት ምስሎችና ከስደተኞች የተገኙ ምስሎችና ሌሎች ብርካታ መረጃዎች የተካተቱበት ዘርዘር ያለው የድርጅቱ መግለጫ በየመን በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት በርካታ ስደተኞች በሕይትና ሞት መካከል እንዳሉ ያስረዳል። 2019 ላይ የተገኘ አንድ መረጃ እንደሚያሳየው የመንን እንደ ሁለተኛ ሃገር ከሚጠቀሙ ስደተኞች መካከል 90 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ናቸው።
news-54263716
https://www.bbc.com/amharic/news-54263716
ሩሲያ ፡ በገዳይ መርዝ ተመርዞ የነበረው አሌክሴ ናቫልኒ ከሆስፒታል ወጣ
በገዳይ መርዝ ተመርዞ የነበረው እውቁ የሩሲያው ፕሬዝደንት ተቀናቃኝ አሌክሴ ናቫልኒ ከህመሙ አገግሞ ከበርሊን ሆስፒታል ወጣ።
አሌክሴ ናቫልኒ እውቁ የጀርመኑ ሻርሌት ሆስፒታል የአሌክሴ የጤና ሁኔታ በመሻሻሉ ከሆስፒታል ውጪ ሆኖ ህክምናውን መከታተል ይችላል ሲል አስታውቋል። አሌክሴ ለ24 ቀናት በጽኑ ሕሙማን ክፍል መቆየቱን እና አሁን ያለበትን ሁኔታ ከግምት በማስገባት ሙሉ ለሙሉ ሊያገግም እንደሚችል ሆስፒታሉ ገልጿል። አሌክሴ ያለ ምንም ድጋፍ ቆሞ የሚያሳየውን ምስሉን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ካወጣ በኋላ ሃኪሞች እንዲያገግም የተቻላቸውን ሁሉ እንዳደረጉት ጽፏል። አሌክሴ ጀርመን ከገባ በኋላ በተደረገለት ምርመራ የነርቭ ስርዓትን በሚያውክ ኖቪቾክ በተሰኘ መርዝ መመረዙን ውጤቶች አረጋግጠዋል። ፑቲን የሥልጣን ዘመናቸውን ማራዘማቸው ትክከል አይደለም፣ ሕገ መንግሥቱን ጥሰዋል፣ ሥልጣን ማራዘማቸው መፈንቅለ መንግሥት ከማድረግ አይተናነስም ሲል አሌክሴ በተደጋጋሚ በፕሬዝደንቱ ላይ የተቃውሞ ድምጽ በማሰማት ይታወቃል። ከአንድ ወር ገዳማ በፊት ከሩሲያዋ ቶምስክ ከተማ ወደ ሞስኮ እየበረረ ሳለ ከፍተኛ ሕመም ስለተሰማው አውሮፕላኑ በድንገት ኦምስክ፣ ሳይቤሪያ እንዲያርፍ ተገዶ ነበር። አሌክሴ አውሮፕላኑን ከመሳፈሩ በፊት በቶምስክ አውሮፕላን ጣቢያ ቁጭ ብሎ ሻይ ሲጠጣ የሚያሳይ ፎቶ ተለቆ ነበር። የአሌክሴ ደጋፊዎች እና ቡድን አባላት አሌክሴ ከሻይ ጋር ተቀላቅሎ በተሰጠው መርዝ መመረዙን ይናገራሉ። ለዚህም ፑቲንን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ክሬምሊን ግን ስለ ጉዳዩ የማውቀው ነገር የለም ይላል። አሌክሴ ወደ ጀርመን ለህክምና ከተወሰደ በኋላ የተደረጉለት መርመራዎች የነርቭ ስርዓትን በሚያውክ መርዝ መመረዙን አረጋግጠዋል። ለአሌክሴ ቀድመው ሕክምና ያደረጉት የሩሲያ ሃኪሞች አሌክሴ ስለመመረዙ ምንም አይነት ማረጋገጫ የለም ብለው ነበር።
news-54201152
https://www.bbc.com/amharic/news-54201152
የጀርመን እግር ኳስ ቡድን በኮሮና ፍርሃት 37 ለ 0 ተሸነፈ
የቅርጫት ኳስ ውጤት አይደለም፡፡ የእግር ኳስ ነው፡፡ አንድ የጀርመን እግር ኳስ ቡድን በባለጋራው 37 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
‹ለመሆኑ ተጫዋቾቹ ሜዳ ላይ ነበሩ ወይ?› ብሎ መጠየቅ የአባት ነው፡፡ አዎ ነበሩ፡፡ ነገር ግን በኮሮና ምክንያት 7 ተጫዋችችን ብቻ ነበር ለማሰለፍ የተገደዱት፡፡ 7ቱ ተጫዋቾችም ቢሆኑ የኮቪድን ማኅበራዊ መራራቅ ሕግን አጥብቀው ለማክበር ሲሉ አይጠጋጉም ነበር፡፡ ኳስ በርቀት እየመቱ መናበብ አቃታቸው፡፡ ይህ 37 ጎሎች የገቡበት ቡድን ሪፕዶርፍ ይባላል፡፡ ሪፕዶርፍ በእሁዱ ግጥሚያ ማሰለፍ የቻለው በእግር ኳስ ጨዋታ ማሰለፍ የሚቻለውን ትንሽ ቁጥር ነው፡፡ 7 ተጫዋቾች ብቻ፡፡ ይህን ያደረገው 4 ተጫዋቾች በጉዳት ቀርተው ወይም ቀይ ካርድ አይተው አይደለም፡፡ ኮሮናን ለመከላከል በሚል ነው 7 ተጫዋች ብቻ ያሰለፈው፡፡ ሪፕዶርፎች በዚህ ደረጃ ኮሮናን ለምን ፈሩ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ ቡድኑ የበዛ ጥንቃቄ ያደርግ የነበረው ተጋጣሚው ኤስ ቪ ሆልደንስቴድ ቀደም ባለ ጨዋታ፣ አንድ ተጫዋቹ በኮቪድ መያዙ ከተሰማ በኋላ ነው፡፡ በዚህ ግጥሚያ ግን ሁሉም ተጫዋቾች ኮሮና እንደሌለባቸው ቢረጋገጥም ተሸናፊው ቡድን ግን እርግጠኛ ስላልሆነ ነው ጎዶሎ ተጨዋቾችን በማሰለፍ ከቫይረሱ ለመጠበቅ የሞከረው፡፡ ከዚህ ይልቅ ጨዋታውን ለምን ፎርፌ አልሰጡም ሊባል ይችላል፡፡ ሪፕዶርፍ ያን ቀን በጨዋታው ባይገኝ 200 ፓውንድ ቅጣት ይጠብቀው ነበር፡፡ 200 ፓውንድ ከየት ይመጣል? ቡድኑ ይህን ዓይነት ታሪካዊ ሽንፈት ከመሸነፉ ቀደም ብሎ ጨዋታው እንዲሰረዝለት ቢጠይቅም ውድድሩን የሚያስተናብረው የአካባቢው የስፖርት ማኅበር ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎበት ነው ለዚህ ውድቀት የዳረገው፡፡ ሪፕዶርፍ የኳስ ቡድን አባላት እንደተናገሩት ባለፈው ጊዜ በኮቪድ ታመመ የተባለው የባለጋራው ቡድን ተጫዋች ፍርሃት ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ ምክንያቱም ከሱ ጋር ንክኪ የነበራቸው ልጆች በዚህ ጨዋታ ተሰልፈው ሊሆን ይችላል በሚል ተጠግቶ ኳስ ለመቀማት የሚሞክር አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሁሉም የባለጋራ ተጨዋቾች ተመርምረው ከቫይረሱ ነጻ ተብለው ነው የተሰለፉት፡፡ ‹ተመርምረው ነጻ ተብለው የለም ወይ? ለምን ፈራችሁ ሲባሉ›› ቢመረመሩም የነሱ ተጨዋች በኮሮና መያዙ ከተነገረ 14 ቀናት አላለፈውም ነበር፤ ስለዚህ ራሳችንን መጠበቅ ነበረብን ብለዋል፡፡ የአሸናፊው ቡድን ሆልደንስቴት አሰልጣኝ ፍሎሪያን ሺዋተር በበኩላቸው ይህንን ጨዋታ ባልተጨበጠ ፍርሃት ተመስርቶ መሰረዝ አግባብ አይደለም፤ ስለዚህ ባገኘነው ክፍተት ተጠቅመን በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችለናል ብለዋል፡፡ 39 ጎል የገባበት ቡድን 90 ደቂቃውን ሙሉ ይጫወት አይጫወት ዘገባው ያለው ነገር የለም፡፡
news-44315977
https://www.bbc.com/amharic/news-44315977
በተሰማሩበት ሙያ ስኬትዎን የሚወስኑ 6 የሰብዕና መገለጫዎች
ጉጉ፣ ጠንቃቃ እና ተፎካካሪ ነዎት? ከሁኔታዎች ጋር ቶሎ የመላመድ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም እና ግራ መጋባትን አምኖ መቀበልን የመሰሉ ምስጢራዊ ችሎታ አለዎት?
እንግዲያውስ እንኳን ደስ አለዎ! በሥነ-ልቦ ባለሙያዎች በተደረገ ጥናት መሰረት እነዚህ ስድስቱ መገለጫዎች በህይወትዎ እና በሚሰሩት ሥራ ስኬታማ እንዲሆኑ ያደርጋሉ። እውነታው ግን አንዳንድ ልዩነቶች አሉት። እነዚህ ባህሪያት ሲበዙ ደግሞ ውጤታማነትዎን ሊቀንሱ ይችላሉ። ስለዚህ የስኬት ሚስጥሩ በሁለቱ ፅንፎች መካከል ሚዛንን ጠብቆ መቆየት መቻል እና ጠንካራ እና ደካማ ጎንን ለይቶ ማወቅ ነው። ይህ አቀራረብ በሥራ ባህሪያችን ላይ ጫና የሚያሳድሩ የተወሳሰቡ የሥነ-ልቦና መገለጫዎችን ለመረዳት ይረዳል። ከዚህ በፊት የሥራ አካባቢ ባህሪያትን ለማወቅ የተደረገው ጥረት አከራካሪ ውጤቶች አስገኝቷል። በሥነ-ልቦናው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች በሥራ አካባቢ ውጤታማ ያደርጋሉ የሚለውን ግኝት ከግምት ውስጥ በማስገባት የለንደን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎቹ ኢየን መክሪ እና ኤድሪየን ፈርሃም በተሰማሩበት ሙያ ስኬታማ የሚያደርጉ ስድስት የስብዕና መገለጫዎችን አስቀምጠዋል። መክሪ እንደሚለው እያንዳንዱ መገለጫዎች የራሳቸው የሆነ ውስንነት እና ጠንካራ ጎን አላቸው። ስለዚህ የእያንዳንዱ መገለጫ ጥቅም የሚወሰነው ግለሰቦች በሚሰሩት ሥራ ላይ ስለሆነ መለኪያው ከእያንዳንዱ ሁኔታ ጋር ይቀያየራል። ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህ ስድስት የስብዕና መገለጫዎች እንዴት ወደ ስኬት እንደሚወስዱ እንመልከት 1. ጠንቃቃነት ጠንቃቃ ሰዎች ሁሌም እቅዳቸውን በትክክል ይተገብራሉ። የእያንዳንዱ ውሳኔያቸው የወደፊት ውጤት ተጽዕኖን ያውቃሉ። ስሜታቸውንም መቆጣጠር ይችላሉ። ከአእምሮ ብቃት ምዘና ፈተና በኋላ ይህ የጠንቃቃነት ባህሪ በህይወትዎ ስኬታማ ለመሆን ወሳኝ ነው። በሥራ አካባቢ ለትንሽ ነገሮች ትኩረት መስጠት ስልታዊ በሆነ መልኩ እያንዳንዱን ሥራ ለማቀድ ይጠቅማል። 2. ከነገሮች ቶሎ መላመድ ሁሉም ሰው የሚያስጨንቀው ነገር ያጋጥመዋል፤ ዋናው ጥያቄ ግን እንዴት ያልፈዋል የሚለው ነው። ይህ ማለት ሥራዎት እና ሌላ ህይወትዎ ላይ ጫና እንዳሳያሳድር ለመላመድ መሞከር ማለት ነው። ይህ ባህሪ የሌላቸው ሰዎች የሥራ አካባቢ አፈጻጸማቸው ደካማ ነው። ነገር ግን ተገቢውን የሥነ-ልቦና እርምጃ ከወሰዱ ውጤታማ መሆን ችላሉ። ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ውጤታማ ለመሆን ሲባል አስጨናቂ ጉዳዮች ላይ በደንብ ትኩረትን መስጠት ከተቻለ፤ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለ ሰው ያሰበውን ነገር ማሳካት ይችላል። 3. ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል የጥያቄዎን መልስ የሚያውቁበት አይነት ሥራ ነው የሚወዱት ወይስ ግራ የሚያጋባ እና አስጨናቂ የሥራ ቦታ? የማያውቁትን ነገር የማይፈሩ እና ግራ መጋባትን አምነው የሚቀበሉ ሰዎች የተሻለ ውሳኔ ለመወሰን ይችላሉ። ብዙ ነገሮችንም ከግምት ውስጥ ያስገባሉ። ይህ ባህሪ ትንሽ አምባገነናዊ ወደ ሆነ አስተሳሰብ ይመራል ይላል መክሪ። እንደዚህ አይነት ሰዎች ትንሽ የምትባለው ነገር ትርጉም እስከምትሰጣቸው ድረስ ስለሚጨነቁ የራሳቸውን ውሳኔ የመጨረሻ አድርገው ሊወስዱ ይችላሉ። ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል የሚችል ሰው ለማንኛውም አይነት ለውጥ ሁሌም ዝግጁ ነው። ግራ መጋባትን አምኖ አለመቀበል ግን ሁሌም መጥፎ ነው ማለት አይደለም። 4. ጉጉ መሆን ከሌሎች ባህሪያት ጋር ሲነጻጸር በሥነ-ልቦና አጥኚዎች ዘንድ ጉጉት ብዙ ትኩረት አልተሰጠውም። ነገር ግን በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የማናውቀውን ነገር ለማወቅ ያለን ጉጉት ሁሌም አዲስ ነገር ለመፍጠር ይረዳናል። ይህ ማለት ለአዳዲስ ነገሮች ክፍት የሆነ ጭንቅላት አለን ማለት ሲሆን፤ በምንሰራው ሥራ ደስተኞች እንድንሆን ይረዳናል። አንዳንዴ ግን የበዛ ጉጉት ወዳልተፈለገ የጊዜ ብክነት ሊወስደን ይችላል። 5. አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም ደስ የማይል ነገር ሲያጋጥምዎት ለጊዜው ስለቀለልዎት ብቻ ዝም ብለው ያልፋሉ ወይስ ምቾት ባይሰጦትም ጉዳዩን ተጋፍጠው ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ይሞክራሉ? ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች ጋር እራስን ማላመድ መቻል ወደፊት ወደ አመራር ቦታ እንድንመጣ እና ለብዙ ነገሮች ውሳኔ መስጠት እንድንችል ይረዳናል። 6. ተፎካካሪ መሆን ለስኬት ሲባል የሚደረግ ትንቅንቅ እና ጤናማ ያልሆነ ፉክክር ወይም ቅናት ትልቅ ልዩነት አላቸው። ፉክክር ሁሌም ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሳ ሲሆን፤ ተጨማሪ ጥረት እንድናሳይና እቅዳችንን እንድናሳካ ሊረዳን ይችላል። ሲበዛ ግን የቡድን ሥራዎችን ያስተጓጉላል። እነዚህ ስድስቱ ባህሪያት በአንድነት በሥራ ገበታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። በተለይ ደግሞ ወደ አመራር ቦታ መምጣት ለሚፈልጉ ሰዎች። ምንም እንኳን ጥናቱ ገና ባያልቅም ከላይ የተዘረዘሩት የሰዎች ባህሪያት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የሥራችንን ፍሬ እና ውጤታማነታችንን ለመለካት ይረዱናል። በመጨረሻም ተፎካካሪነት እና ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል ከሁሉም በተሻለ ተቀባይነትን ያገኙ ሲሆን፤ የተሻለ ገቢ እንደሚያስገኙም ተጠቁሟል።
news-47084584
https://www.bbc.com/amharic/news-47084584
በታሪክ ከፍተኛ መጠን ያለው አደገኛ ዕፅ በአሜሪካ-ሜክሲኮ ድንበር ተያዘ
የአሜሪካ ገቢዎች እና ደንበር ጥበቃ ባለስልጣን በታሪኩ ከፍተኛ መጠን ያለውን አደጋኛ ዕፅ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ሰራተኞች እንዳስታወቁት 114 ኪሎ ግራም የሚመዝን 'ፌንታኒል' እና 180 ኪሎ ግራም የሚመዝን 'ሜታአፌታሚን' የተሰኙ አደገኛ እፆችን በጭነት መኪና በሜክሲኮ-አሜሪካ ድንበር ላይ በቁጥጥር ሥር አውለናል ብለዋል። የአሪዞና ግዛትን እና ሜክሲኮን የሚያገናኘው የደንበር ጥበቃ ኃላፊ የሆኑት ማይክል ሃምፕሪስ እፆቹን የስንዴ ዱቄት በማስመሰል ድንበር ለማሻገር ተሞክሯል ብለዋል። • ኢትዮጵያዊቷ የዕፅ ነጋዴው ኤል ቻፖን ጉዳይ ለመዳኘት ተመረጠች ሜክሲካዊው የጭንት መኪና አሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን እና ክስ እንደተመሰረተበትም ተነግሯል። የደንበር ጥበቃ ኃላፊው እንደሚሉት ከሆነ በቁጥጥር ሥር የዋለው 114 ኪሎ ግራም የሚመዝነው 'ፌንታኒል' የተሰኘው ዕፅ ብቻ ወደ አሜሪካ መግባት ቢችል ኖሮ በጥቁር ገብያው ላይ 3.5 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያወጣ ነበር። • የትራምፕ አማካሪ፡ የግንቡ ውጥን ውድቅ ከተደረገ ሰነባብቷል ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ 'ፌንታኒል' የተሰኘው በጣም በትንሹ እንኳ ቢወሰድ ለሞት ሊዳርግ ይችላል። የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል አህዞች እንደሚያሳዩት እአአ 2016 ብቻ 18ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ይህን ዕፅ ከመጠን በላይ ወስደው ህይወታቸው አልፏል።
news-44449908
https://www.bbc.com/amharic/news-44449908
የባርሳ ሴቶች ከወገብ በላይ ራቁት ለመሆን ድምጽ ሰጡ
ባርሴሎና አቅራቢያ በምትገኝ መንደር የሚገኙ ሴቶች በሕዝብ የመዋኛ ሥፍራ ከወገብ በላይ ራቁታችንን መሆን ይፈቀድልን በሚል ያነሱት ጥያቄ መልስ አገኘ።
የባርሳ መንደር ሴቶች ከእንግዲህ ከወገብ በላይ ለምን የዋና ልብስ አለበሳችሁም የሚላቸው የለም የመንደሯ ነዋሪዎች ድምጽ እንዲሰጡበት ተደርጎ ከመቶ 61 እጅ ነዋሪዎች "መብታቸው ነው" ሲሉ ቀሪዎቹ 39 ከመቶ ነዋሪዎች "ድርጊቱ ያሳፍራል፤ በሕግ ይከልከል" ብለው ድምጽ ሰጥተዋል። የካታሎኒያ የአውራጃ አስተዳደር ባዘጋጀው በዚህ የድምጽ መስጠት ሂደት "ራቁታችንን እንሁን" የሚሉት በከፍተኛ ድምጽ በማሸነፋቸው ከዚህ በኋላ በዚያች አውራጃ ከወገብ በላይ መለመላቸውን መቅረት በሕግ ተፈቅዶላቸዋል። የመንደሪቷ ሴቶች ለዚህ ሰፊ የእርቃን መብት የተፋለሙት ባለፈው የፈረንጆች በጋ የጸጥታ ኃይሎች የመዋኛ ልብስ (ቢኪኒ) ያልለበሱ ሴቶችን እንዲለብሱ በማስገደዳቸው ነው ተብሏል። በመዋኛ ሥፍራው ተቀጥሮ ይሠራ የነበረ ሕይወት አድን ዋናተኛ በወቅቱ ለፖሊስ ደውሎ "አንዳንድ ሴቶች ከወገብ በታች መለመላቸውን ናቸው" በሚል ጥቆማ በመስጠቱ ነበር ፖሊስ ወደ ሥፍራው ደርሶ ሴቶቹን የዋና ልብስ እንዲሊብሱ ያስገደዳቸው። ይህ ክስተት በሴት መብት ተቆርቋሪዎች ዘንድ ቁጣን በመቀስቀሱ የፖሊስን ድርጊት ለመቃወም የአካባቢው ወንዶች ሳይቀሩ ደረታቸው ላይ የጡት ጫፍ በመሳል ወደ መዋኛው ሥፍራ በማቅናት የፖሊስን ክልከላ በማውገዝ ተቃውሞ አሰምተው ነበር። ከዚህ በኋላ ግን የዚህች የባርሴሎና መንደር ሴት ነዋሪዎች በሕዝብ የመዋኛ ሥፍራዎች ከወገብ በላይ ራቁታቸውን መዋኘት በሕግ ተፈቅዶላቸዋል። በሰሜን ባርሴሎና 35 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኘው ይህች መንደር 8ሺህ ነዋሪዎች አሏት።
news-54581080
https://www.bbc.com/amharic/news-54581080
ኮሮናቫይረስ፡ በፈረንሳይ ከተሞች የሰዓት እላፊ ታወጀ
የፈረንሳይ መዲና ፓሪስን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የሰዓት እላፊ ታወጀ።
የሰዓት እላፊ የታወጀው እየጨመረ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ነው። ፈረንሳይ ከአውሮፓ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ከሆኑባቸው አገራት መካከል አንዷ ናት። የሰዓት እላፊ በታወጀባቸው ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ከቤት መውጣት አይችሉም። የሰዓት እላፊው ከታወጀባቸው ከተሞች መካከል ፓሪስ፣ ማርሴል፣ ሊዮን እና ሊል ይገኙበታል። 20 ሚሊዮን ፈረንሳውያን የሰዓት እላፊው አዋጅ ይተገበርባቸዋል። የፈረንሳይ መንግሥት የሰዓት እላፊ አዋጁ መተግበሩን የሚያረጋግጡ 12ሺህ የፖሊስ አባላት እንደሚያሰማራ አስታውቋል። ከምሽቱ 3 ሰዓት በፊት ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ካፊቴሪያዎች እና ሲኒማ ቤቶች መዘጋት ይኖርባቸዋል። የሰዓት እላፊውን ተላልፎ የሚገኝ ሰው 135 ዩሮ የሚቀጣ ሲሆን፤ ዳግም ተላልፎ የተገኘ ደግሞ የስድስት ወራት እስር እና የ3ሺህ 700 ዩሮ ቅጣት ይጠብቀዋል። እንደ ሰርግ ያሉ ማህበራዊ ሰብስቦች ክልክል ናቸው። በፈረንሳይ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከ32ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ኮሮናቫይረስ በሌሎች የአውሮፓ አገራት የስፔን መንግሥት በማድሪድ እና አካባቢዋ ለ15 ቀናት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። 7ሺህ ፖሊስ አባላት አዋጁን ያስፈጽማሉ። መሠረታዊ ላልሆኑ ጉዳዮች ከማድሪድ መውጣትም ሆነ መግባት ክልክል ነው። ሆቴሎች እና ምግብ ቤቶች መያዝ ከሚችሉት አቅማቸው ግማሹን ብቻ ነው ማስተናገድ የሚችሉት። በኔዘርላንድስ የቫይረሱ ስርጭት ዳግም እያገረሸ ይገኛል። በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍልም በከፊል የእንቅስቃሴ ገደቦች እየተጣሉ ይገኛሉ። በአምስተርዳም መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች እየተዘጉ ነው። በጀርመንም በተመሳሳይ የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ ይገኛል። በቀን ከ7ሺህ በላይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየተመዘገቡ ይገኛል። ጀርመን አንዳንድ ጎረቤት አገራትን የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶባቸዋል ስትል አውጃለች። ከእነዚህም መካከል ፈረንሳይ እና ኔዘርላንድስ ተጠቃሽ ናቸው። ከእነዚህ አገራት ወደ ጀርመን የሚገባ ተጓዥ ራሱን ለይቶ የማቆየት ግዴታ ይኖርበታል። አየርላንድ በበኩሏ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የተለያዩ ገደቦችን ከጣለች አራት ሳምንታት አልፈዋታል። በመኖሪያ ቤት ሄዶ ወዳጅ ዘመድ መጠየቅ ከተከለከለ ሰነባብቷል።
47863331
https://www.bbc.com/amharic/47863331
ሱዳናውያን ፕሬዚዳንታቸውን ከስልጣን ይውረዱ እያሉ ነው
ሱዳናውያን ፕሬዝዳንታቸውን ኦማር አል በሽር ከስልጣን እንዲወርዱ በመጠየቃቸው ከደህንነት አካላት የተለያዩ እርምጃዎች ቢወሰድባቸውም አሁንም አደባባይ ከመውጣት አላቆሙም።
በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በመናገሻ ከተማዋ ካርቱም በፕሬዝዳንቱ መኖሪያ ቅጥር ግቢ ፊት ለፊት በመገኘት የይውረዱ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ሰኞ ዕለት ከመከላከያ ኃይሉ ጋር የሽግግር መንግሥት መመስረት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መነጋገር የሚፈልግ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ተቃውሞ አካሂዷል። እንደ ሀገሪቱ ባለስልጣናት ከሆነ ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ ሰባት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ለሀገሪቱ የህዝብ እንደራሴ ተወካዮች ሰኞ ዕለት እንዳሉት ስድስቱ ሰዎች በካርቱም አንዱ ደግሞ በዳርፉር ተገድለዋል። • የሩዋንዳ ዘር ጭፍጨፋ 25ኛ አመት እየታሰበ ነው • በሰሜን ሸዋ ዞኖች የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዘ • ሕዝብ ስለመሪው ምን እንደሚያስብ እንዴት እንወቅ? አክለውም 15 ተቃዋሚ ሰልፈኞች እና 42 የፀጥታ አካላት ጉዳት ሲደርስባቸው 2ሺህ አምስት መቶ ሰዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲሉ አስረድተዋል። ፕሬዝዳንት አል በሺር እ.ኤ.አ ከ 1989 ጀምሮ ሱዳንን ያስተዳደሩ ሲሆን 'ስልጣን ይብቃዎት፤ ይውረዱ' የሚል የሕዝብ ድምፅ በአደባባይ መሰማት ከጀመረ ወራት ተቆጥሯል። የተቃውሞ ሰልፉ መነሻ ሰበብ የኑሮ ውድነት የነበረ ሲሆን አሁን ግን ፕሬዝዳንቱን ይውረዱ ወደሚል ተቀይሯል። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚ ሰልፈኞች ካርቱም በሚገኘው የመከላከያ ኃይሉ እና የፕሬዝዳንቱ ዋና ቢሮ ፊት ለፊት በመሰባሰብ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ወታደሩ ለመንግሥት ያለውን ወገንተኝነት እንዲተው ጠይቀዋል። ሰኞ እለት ምሽት የተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ተወካዮች ከመከላከያ ኃይሉ ጋር የሽግግር መንግስት ስለሚመሰረትበት መነጋገር እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። ኦማር ኤል ዲጊር የሚባሉ ጎምቱ የተቃውሞ ፖለቲካ አስተባባሪ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል "የአብዮቱን ፍላጎት የሚወክል መንገድ" እየፈለግን ነው ብለዋል። ምንም እንኳ የፀጥታ ኃይሎች የተቃውሞ ሰልፉን ለመበተን የተለያዩ ነገሮች ቢያደርጉም ሰኞ ዕለት ግን የመቀመጥ አድማው ለሶስተኛ ጊዜ ተካሂዷል። መንግሥት ተገቢ ያልሆነ ኃይል ሰልፈኞቹ ላይ በመጠቀም በመብት ተሟጋጮች ስሙ እየተብጠለጠለ ይገኛል።
news-51388868
https://www.bbc.com/amharic/news-51388868
ካቲ ፓሲፊክ ኮሮኖቫይረስ ያሳደረውን ጫና ለመቋቋም ሠራተኞቹ እረፍ እንዲወጡ ጠየቀ
የሆንግ ኮንግ አየር መንገድ የሆነው ካቲ ፓሲፊክ ኮሮኖቫይረስ በሥራው ላይ ያሳደረበትን ጫና መቋቋም እንዲቻለው ሠራተኞቹ ሳይከፈላቸው ለሶስት ሳምንታት እረፍ እንዲወጡ ጠየቀ።
አየር መንገዱ ኮሮናቫይረስ ከተቀሰቀሰ ወዲህ የደንበኞቹ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተነግሯል። ካቲ ፓስፊክ የተሰኘው የሆንግ ኮንግ አየር መንገድ በሆንግ ኮንግ በነበረው ተቃውሞ ቀድሞም የፋይናንስ ጫና አጋጥሞት ነበር ተብሏል። አየር መንገዱ ሰራተኞቹ በፍቃዳቸው ለሶስት ሳምንታት የማይከፈልበት እረፍ እንዲወስዱ ጠይቋል። "የንግድ እንቅስቃሴዬን ለማስቀጠል ጥሬ ገንዘብ መቆጠብ አለብኝ" ብሏል አየር መንገዱ። ካቲ ፓስፊክ ባወጣው መግለጫ ከቻይና መዳረሻዎቹ መካከል 90 በመቶ በሚሆኑት በቀጣይ ሁለት ወራት መብረር እንደሚያቆም አስታውቋል። "ዛሬ ላይ ሰራተኞቻችን ከየካቲት 22 እስከ ሰኔ 23 ባሉት ቀናት ለሶሰት ሳምንታት የማይከፈልበት እረፍት እንዲወስዱ በትህትና እንጠይቃን" ሲሉ የካቲ ፓሲፊክ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኦገስታስ ታንግ የቪዲዮ መልዕክት ለሠራተኞች መላካቸውን ሬውተርስ ዘግቧል። አውሮፕላን አምራቹ ኤርባስ በቻይና የሚገኙ ሰራተኞቹ ከቤት ሆነው እንዲሰሩ የቻይና መንግሥት መመሪያዎችን እያጤነ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን በቲያንጂን የሚገኘውን መገጣጠሚያውን መዝጋቱን አስታውቋል። የእስፖርት ትጥቅ አምራቹ አዲዳስ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በቻይና የሚገኙ አብዛኞቹ መደብሮቹን ለመዝጋት መገደዱን አስታውቋል። የዴንማርኩ ቢራ አምራች ኩባንያ ካርስልበርግ በቻይና ያለው የንግድ እንቅስቃሴ ሊገታ እንደሚችል ለሠራተኞቹ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
47249336
https://www.bbc.com/amharic/47249336
ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች
አሌክሳንድራና ካልደር ይባላሉ። መንትያ እህትና ወንድም ሲሆኑ፣ ከተወለዱ 19 ወራት ተቆጥሯል።
ሳይመንና ግራይም በርኒ- ኤድዋርድስ ልጆቻቸው አሌክሳንድራና ካልደርን አቅፈው መንትዮቹን ለየት የሚያደርጋቸው ከአንድ እናት እና ከሁለት አባት መወለዳቸው ነው። አሌክሳንድራ የሳይመን ልጅ ናት። ወንድሟ ካልደር ደግሞ የግራይም። ለመሆኑ መንትዮች እንዴት ከተለያየ አባት ይወለዳሉ? • ልብ የረሳው አውሮፕላን • በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሦስት ሀገሮች፣ አራት የቤተሰብ አባላት፣ ሁለት ልጆች ሳይመንና ግራይም በርኒ- ኤድዋርድስ አይቪኤፍ ወይም ቪትሮ ፈርቲላይዜሽን በመጠቀም ልጅ ለመውለድ ከሚወስኑ ጥቂት እንግሊዛውያን ጥንዶች መካከል ናቸው። አይቪኤፍ በቤተ ሙከራ ውስጥ እንቁላል ከወንድ ዘር ፍሬ ጋር ተዋህዶ ጽንስ የሚፈጠርበት መንገድ ነው። ሳይመንና ግራይም ልጆች ያገኙበት ሂደት ቀላል አልነበረም። • በሕይወት ከሌለች እናት የተወለደችው ሕፃን በመጀመሪያ እንቁላል ማግኘት ነበረባቸው። ሀሳባቸው ከሁለት የኪራይ እናቶች (በእንግሊዘኛ ሰረጌት ማዘር የሚባለው) ሁለት ልጆች ለመውለድ ነበር። ሆኖም በሂደቱ የሚያግዛቸው ተቋም ከአንድ እንቁላል ለጋሽ በአንድ የኪራይ እናት ሁለት ልጆች በአንድ ጌዜ ማግኘት እንደሚቻል አሳወቃቸው። ቀጣዩ የሂደቱ ክፍል እንቁላል ማግኘት ነበር። ሳይመን "ማንነቷን ከማናውቅ አሜሪካዊት ለጋሽ እንቁላል አገኘን" ይላል። ስለዚህም ሁለቱም በአንድ ጊዜ የዘር ፍሬያቸውን ለአንዲት የኪራይ እናት ሰጡ። ሳይመንና ግራይም ልጆቹን ከወለደችው ሜግ ስቶን ጋር የለጋሿ እንቁላሎቹ ለሁለት ከተከፈሉ በኋላ ግማሹ ከሳይመን ዘር ሌላው ግማሽ ደግሞ በግራይም ዘር ጋር ተዋህዶ ጽንስ እንዲፈጠር ተደረገ። ከዛም ካናዳ ውስጥ ልጆቹን አርግዛ የምትወልድ የኪራይ እናት አገኙ። ካናዳዊት የቅጥር እናት ሜግ ስቶን ሁለቱን ልጆች የወለደችው ካናዳዊት የኪራይ እናት ናት። "ካናዳን የመረጥነው የሕግ ማዕቀፋቸውን ስለምንወደው ነው። ነገሩ የሚከናወነው እንደ ንግድ ሳይሆን ከልብ በመነጨ የመተባበር ስሜት ነው" ሲል ሳይመን ያስረዳል። ሁለቱ አባቶች ልጆች ማግኘት እንደሚችሉ የምስራች የሰሙት እንግሊዝ ሳሉ ነበር። ግራይም ቅጽበቱን ሲገልጽ "በጣም ስሜታዊ ሆነን ነበር። እጅግ በጣም ተደስተን ነበር" ይላል። ሳይመንና ግራይም የተረገዙት ልጆቻቸውን እድገት የሚከታተሉት ከእንግሊዝ ሆነው ነበር። ልጆቹ ሊወለዱ ስድስት ሳምንት ሲቀራቸው ደግሞ ወደ ካናዳ አቀኑ። አባቶቹ ከኪራይ እናቷ ሜግ ስቶን ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ። ሳይመንና ግራይም አሁን በተወለዱት ልጆች ደስተኛ ቢሆኑም፤ ለወደፊት ተጨማሪ ልጅ ሊወልዱ የሚችሉበት እድል እንዳለ ሳይመን ጠቁሟል።
news-57167683
https://www.bbc.com/amharic/news-57167683
እስራኤል-ጋዛ፡ ሐማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ ተባለ
አንድ የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት የጋዛ ታጣቂዎችና የእስራኤል ባለሥልጣናት የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈርሙ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ።
ምሥሉ በጋዛ ሁለት ፍልስጥኤማውያን እህታማቾች በእስራኤል የጦር አውሮፕላን በተተኮሰና ባልፈነዳ ሚሳይል ላይ ተቀምጠው ያሳያል። ከዚህ አስተያየት በተቃራኒ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ ትናንት ረቡዕ "ለእስራኤል ዜጎች ሰላምና ደኅንነት እስኪመለስ ድረስ ጥቃቱን እንቀጥልበታለን" ብለዋል። ሐሙስ ከቀትር በፊት ብቻ ከመቶ በላይ የእስራኤል የአየር ጥቃቶች በሐማስ ወታደራዊ መዋቅር ላይ እንደተተኮሱ ተዘግቧል። በምላሹ የፍልስጤም ታጣቂዎች ወደ እስራኤል ሮኬት ተኩሰዋል። የጋዛው ግጭት የተጀመረው በእስራኤልና ፍልስጤማዊያኑ መሀል እስራኤል በኃይል በያዘቻቸው የምሥራቅ ኢየሩሳሌም አካባቢ በረመዳን ወር ለቀናት ውጥረት ከነገሠ በኋላ ነው። ሙስሊሞችና አይሁዳዊያን ቅዱስ ቦታችን ነው በሚሉት አል አቅሳ የደማስቆ በር መግቢያ ላይ የእስራኤል ወታደሮች ክልከላ በማድረጋቸው ጋዛን የሚቆጣጠረው ሐማስ ቁጣውን ሲገልጽ ቆይቷል። ፍልስጤማዊያንም በእስራኤል ወታደሮች የሚደርስባቸው እንግልት እያየለ መምጣቱ ግጭቱን ወደከፋ ደረጃ እያደረሰው መምጣቱ ይታወሳል። ነገሮች እየተጋጋሉ መጥተው ሐማስ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን ማስወንጨፍ መጀመሩን ነው ለብዙዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግጭት የተጀመረው። እስከአሁን በነበረው መጠነኛ ጦርነት በትንሹ 227 ፍልስጤማዊያን በጋዛ ተገድለዋል። ከነዚህ ውስጥ 100 የሚሆኑት ሕጻናትና ሴቶች ናቸው። እስራኤል በበኩሏ 150 የሚሆኑት የጋዛ ሟቾች የሐማስ ታጣቂዎች ናቸው ትላለች። ሐማስ የሞቱበትን ተዋጊዎቹን ቁጥር ለጊዜው ይፋ አላደረገም። ሆኖም ቁልፍ ወታደራዊ መኮንኖቹ እንደሞቱበት ይገመታል። በእስራኤል በኩል የሟቾቹ ቁጥር 12 ብቻ ሲሆን ከነዚህ መሀል ሁለቱ ሕጻናት ናቸው። ሆኖም ወደ እስራኤል የተወነጨፉት የሮኬቶች ብዛት ከ4ሺህ ይልቃሉ። ከነዚህ ውስጥ 99 ከመቶ የሚሆኑት በእስራኤል ጸረ ሮኬት ሲስተም የመከኑ እንደሆኑ እስራኤል ትናገራለች። በቅርብ ሰዓታት ውስጥ የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሙሳ አቡ መርዙቅ ለሊባኖሱ ማያዲን ቲቪ በሰጡት ቃለምልልስ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ፈር እየያዘ እንደመጣ ጠቁመዋል። "ከሁለት ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ስምምነት የምናደርግ ይመስለኛል"› ብለዋል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ በጋራ መግባባት ላይ የሚመሠረት እንደሆነም አብራርተዋል። ይህ የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን አስተያየት የተሰማው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሁለቱ ተዋጊዎች የንጹሐንን እልቂት እንዲያቆሙ ጫና እየደረሰባቸው ባለበት ወቅት ነው። አንድ የግብጽ የደኅንነት ምንጭ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ድርድሩ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ትናንት ረቡዕ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለ4ኛ ጊዜ ወደ ናታንያሁ ስልክ መተው በጉዳዩ ላይ ተወያይተዋል። ሁለቱን ወገኖች የማደራደር ሂደቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ዛሬ ጠዋት እስራኤል የአየር ጥቃት ማድረጓ ተዘግቧል። በዚህ ጥቃት ሁለት ቤቶችን ሙሉ በሙሉ አውድማለች። በዚህ ጥቃት በካን ዩኒስ ከተማ አራት ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል የሕክምና ምንጮች። እስራኤል በበኩሏ ይህ የዛሬው ጥቃት ሐማስ ሮኬት የሚያከማችባቸውና የሚተኩስባቸው ግቢዎችን ያለመ ነበር ብላለች። በእስራኤል ከተማ ቢርሼባ አሁንም የማስጠንቀቂያ ደውሎች ተከታትለው እንደሚሰሙ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
news-51471719
https://www.bbc.com/amharic/news-51471719
"እናቴ 'አንቺ ለሽያጭ የምትቀርቢ አይደለሽም፤ ማንም ሊገዛሽ አይችልም' ትለኝ ነበር''
''ለሙሽሪት ቤተሰቦች የሚከፈል ገንዘብ እኔን ከፍሎ ለመውሰድ እንደሚደረግ ነገር አልቆጥረውም፤ እንደውም ጄፍሪ በገንዘብ ልግዛሽ ቢል በጣም ውድ እሆንበታለው'' ትላለች እንግሊዝ ውስጥ የተወለደችውና ትውልዷ ከጋና የሚመዘዘው አንጄላ።
ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ለሙሽሪት ቤተሰቦች ገንዘብ አልያም ስጦታ መስጠት፤ በእኛም ሀገር ጥሎሽ እንደሚባለው ማለት ነው የተለመደ ነገር ቢሆንም አይነቱ እና መጠኑ ግን እንደየባህሉ ይለያያል። አንጄላ ደግሞ ''እጮኛዬ እና ቤተሰቦቹ በገንዘብ እንደገዙኝ ሳይሆን ወደቤተሰባቸው የገባሁ ትልቅ ሀብት አድርገው እንዲቆጥሩኝ ነው የምፈልገው'' ትላለች። • ''ባልሽን በጥንቆላ አሳብደሸል አሉኝ፤ እኔ ግን እስካሁን ከጎኑ አልተለየሁም'' • ጓደኛዎት ጤናዎትን እያቃወሱት ይሆን? በጋናውያን ባህል መሰረት የሙሽራው ቤተሰቦች ገንዘብ፣ ስጦታ ወይም የሁለቱን ቅልቅል በአንድ ጊዜ አልያም ቀስ እያሉ ይከፍላሉ። ይህ ባህል በታይላንድ፣ ቻይና እና ፓፓው ኒው ጊኒም ይስተዋላል። አንጄላ ምንም እንኳን እንግሊዝ ውስጥ ተወልዳ ብታድግም ጉዳዩ ባህሏን የመቀበልና የማስቀጠል እንደሆነ ታስባለች። ''አፍሪካዊ መሆን በራሱ ትልቅ ጫና የሚያስከትልባቸው በርካታ ዘመናት አልፈዋል፤ አሁን ግን ነገሮች እየተቀየሩ ነው። አፍሪካዊ ባህሎቻችንን መግለጸዕና መተግበር ችለናል።'' የአንጄላ ባለቤት ጄፍሪ ከጋናውያን ቤተሰቦች የተገኘ ሲሆን እሱም እንግሊዝ ውስጥ ነው የተወለደው። ለሙሽሪት ቤተሰቦች የሚከፈለው ገንዘብም ሆነ ስጦታ 'ልጃችሁን ስለሰጣችሁን እናመሰግናለን' እንደማለት እንጂ ሌላ ምንም ትርጉም የለውም ይላል። ''መሆን ከሚገባው በላይ የተጋነነ ገንዘብ ከሆን ግን ትርጉሙን ያጣል። ሴቲቱን በገንዘብ ገዝቶ እንደ መውሰድ ነው የሚቆጠረው።'' ከዋናው ሠርግ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ጄፍሪና አንጄላ በጋና ባህላዊ ሥነ ሥርዓት መሰረት ተሞሽረዋል። በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይም ለሙሽሪት ቤተሰቦች ገንዘብና የተለያዩ ስጦታዎች ተበርክተዋል። ነገር ግን ባህሉን ትንሽ በማሻሻል ከጄፍሪ ቤተሰቦች የተገኘውን ገንዘብና ሌሎች ስጦታዎች መልሰው፤ ከቤተሰቦቿ ለመውሰድና ኑሯቸውን ለማቋቋም ተስማሙ። ''እናቴ ሁሌም ቢሆን ስለብዙ ነገሮች ታወራኝ ነበር። አስታውሳለው ወጣት እያለሁ 'አንቺ ለሽያጭ የምትቀርቢ አይደለሽም፤ ማንም ሊገዛሽ አይችልም' ትለኝ ነበር'' ብላለች አንጄላ። እንግሊዝ ውስጥ የሚኖሩት ሌላኞቹ ጥንዶች ብለሲንግና ቼልሲ ደግሞ ነገሮችን በተለየ መልኩ ነበር የተቀበሉት። ብለሲንግ ትውልዱ ከዚምባብዌ ሲሆን ለሙሽሪት ቤተሰቦች የሚከፈለውን ጥሎሽ ለማሟላት በማሰብ ሁለት ሥራዎችን በአንድ ጊዜ ይሰራ እንደነበር ያስታውሳል። ምንም እንኳን ኑሮ ከባድ ቢሆንም ባህሌ ስለሆነ ማድረግ ነበረብኝ ብሏል። ''ቼልሲ በባህላቸው መሰረት ገንዘብና ስጦታዎችን ለእሷ ቤተሰቦች በመስጠቱ ሀሳብ ብዙም አልተስማማችም ነበር። ምክንያቱም አባቷ በሕይወት ስለሌሉ ነው። እኔ ግን አሳምኛት ለቤተሰቦቿ ጥሎሹን ለመስጠት ተስማማን።'' ብለሲንግ ይህን ማድረጉ የባለቤቱን ቤተሰቦች በኩራት ለመጋፈጥ እንደሚያስችለው ያምናል። ''የጥሎሽ ገንዘቡን ለቤተሰቦቿ ባልከፍል ኖሮ ልንጠይቃቸው ስንሄድ ወይም በተለያዩ አጋጣሚዎች ስንገናኝ አንገቴን ሊያስደፋኝ የሚችል ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ስለዚህ ጥሎሹን በመክፈሌ ደስተኛ ነኝ።'' • መመሳሰላቸው እጅጉን የበዛ መንትዮች ኤቨሊን ሺለር ኡጋንዳ ውስጥ ለሙሽሮች የሚከፈል ገንዘብን የሚቃወም እንቅስቃሴ ትመራለች። እሷ እንደምትለው የማህበረሰቡ ትኩረት ከባህላዊ እሴቱ ወደ ጥሬ ገንዘብ ምንጭነት ዞሯል። ''አሁን አሁን የሚደረጉትን ስንለመከት አብዛኛዎቹ ጥሬ ገንዘብ ላይ ነው ትኩረታቸው። ስለዚህ ከጥሎሽነት አልፎ ሙሽሪትን ወደመግዛት ይጠጋል። ይሄ ባህላችንም አይደለም፤ ተቀባይነትም ሊኖረው አይገባም'' ትላለች። በኡጋንዳ ለሙሽሪት ቤተሰቦች የሚሰጥ ገንዘብ ወይም ሌላ አይነት ስጦታ ግዴታ እንዳልሆነ የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሰነ ሲሆን የጥንዶቹ ትዳር የሚፈርስ ከሆነ ግን የጥሎሹን ገንዘብ ይመለስልኝ ማለት አይቻልም።
news-53895409
https://www.bbc.com/amharic/news-53895409
የሩስያው የተቃዋሚ መሪ ሳይመረዝ እንዳልቀረ የጀርመን ሐኪሞች ገለፁ
የሩሲያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆነው አሌክሴ ናቫልኒን እያከመ የሚገኘው የበርሊን ሆስፒታል መመረዙን አረጋገጠ።
የሩሲያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አሌክሴ ናቫልኒ በጀርመን ቻሪቲ ሆስፒታል ሕክምና እያገኘ ነው ቻሪቴ ሆስፒታል ያወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው፤ በጽኑ ታምሞ በሕክምና ላይ የሚገኘው ናቫልኒ ላይ የተደረገው ምርመራ እንደሚያሳየው "በኮላይኔስትሬስ አጋጅ ኬሚካል ተመርዟል"። በተጨማሪም "ክፉኛ የታመመ ቢሆንም ለሕይወቱ አያሰጋውም" ብሏል መግለጫው። አሌክሴ አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ በሚገኝ አንድ ካፌ ውስጥ ያዘዘው ሻይ ላይ መርዝ ሳይሰጠው አልቀረም ተብሏል። አውሮፕላን ውስጥ እንደገባ ነው ተዝለፍልፎ የወደቀው። ናቫልኒ ከሰርብያዋ ቶምስክ ወደ ሞስኮ እየበረረ ሳለ ክፉኛ ታምሞ ሲያጣጥር የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቷል። ደጋፊዎቹ በጠጣው ሻይ እንደተመረዘ ይጠረጥራሉ። "በምን እንደተመረዘ እቅጩን መናገር አይቻልም" ያለው ሆስፒታሉ፤ "ሰፋ ኣለ ምርመራ ተጀምረወል። የመርዙ- ያም ማለት ኮላይኔስትሬስ አጋጅ ኬሚካል በኦርጋኒዝም ውስጥ ያለው ተጽዕኖ በበርካታ የግል ቤተ ሙከራዎች በተደጋጋሚ ተረገግጧል።" ናቫልኒ አትሮፓይን የተሰኘ አንቲዶት እየተሰጠው መሆኑ ተገልጿል። ሆስፒታሉ እንደገለፀው ምናልባት ግለሰቡ የተመረዘበት ኬሚካል ቀጣይ ያለው ተጽዕኖ በሚገባ ያልተለየ ሲሆን ምናልባት የነርቭ ስርአቱ ላይ ቋሚ ተጽዕኖ ሊያስከትል ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
45873106
https://www.bbc.com/amharic/45873106
አሜሪካዊው ራፐር ካንዬ ዌስትና ኪም ካርዳሽያን ዩጋንዳዊ ስም ተሰጣቸው
ታዋቂው የሂፕሆፕ አቀንቃኝ ካንዬ ዌስትና ባለቤቱ ኪም ካርዳሽያን በዩጋንዳ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ጋር ተገናኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በባለፈው ወር ስሙን የ በሚል ለቀየረው ካንዬ ዌስት ካንሲግየ የሚል መጠሪያ የሰጡት ሲሆን ትርጉም "አምናለሁ" ማለት ነው። ለባለቤቱ ኪም ካርዳሺያን ደግሞ ኬሚጊሻ የሚል ስም ሰጥተዋታል፤ ትርጉሙም "የአምላክ ስጦታ" ማለት እንደሆነ የፕሬዚዳንቱ ቢሮ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። ራፐሩና ባለቤቱ ፕሬዚዳንቱ አዲስ ስም ስለሰተጧቸውም መደሰታቸውንም ጭምር ተገልጿል። •የሰኔ 16ቱ ጥቃት ተጠርጣሪ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተሰጠ •"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" •የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ ፕሬዚዳንቱ ጨምረውም ዩጋንዳ የሁሉም አገር እንደሆነች ገልፀውላቸዋል። "ይህች መሬት የሰው ልጅ መገኛ ናት፤ ነጭ ህዝቦች ራሱ መነሻቸው ከዚህ ነው" በማለት ፕሬዚዳንቱ እንደተናገሩ በፌስቡክ የሰፈረው ፅሁፍ ያስረዳል። ራፐሩ በበኩሉ ዩጋንዳ በመምጣቱ ደስተኛነቱን ገልፆ ሁለተኛ ቤቴ ሲልም ተናግሯል። "ካንዬ ለፕሬዚዳንቱ ደረጃውን የጠበቀ የቱሪዝም ትምህርት ቤት እንደሚከፍት አስታውቋቸዋል። ይህ ለዩጋንዳ ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ ጠቃሚ ይሆናል" በማለት የፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት በመግለጫው ጨምሯል።
news-55241933
https://www.bbc.com/amharic/news-55241933
የአሜሪካ ወታደራዊ መኮንኖች ሴት ወታደሮች ላይ ወሲባዊ ጥቃት በማድረስ ተባረሩ
የአሜሪካ ጦር አስራ አራት ከፍተኛና ዝቅተኛ አመራር ያሉ ወታደራዊ መኮንኖች በሴት ወታደሮች ላይ ግድያን ጨምሮ ወሲባዊ ጥቃቶችና ትንኮሳን ፈፅመዋል በሚል አባሯቸዋል።
በቴክሳስ በሚገኘው የፎርት ሁድ የጦር ሰፈርም ነው እነዚህ ተደጋጋሚ ጥቃቶች የተፈፀሙት። ቫኔሳ ጉሊየን የተባለች ወታደር በባለፈው አመት መገደሏንም ተከትሎ ነው በጦር ሰፈሩ ላይ ምርመራ የተጀመረው። የ20 አመቷ ቫኔሳ ለሁለት ወር ያህል ጠፍታ የነበረ ሲሆን የአስከሬኗም የተወሰነ ክፍል የተገኘው በሰኔ ወር ነበር። በጦር ሰፈሩ ውስጥ በድብደባ እንደተገደለችም መርማሪዎች ገልፀዋል። በሞቷ ዋነኛው ተጠርጣሪ የጦር መኮንኑ አሮን ሮቢንሰን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲል ሃምሌ ወር ላይ ራሱን አጥፍቷል። የቫኔሳ ቤተሰቦች በአሮን ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባታል ቢሉም ባለስልጣናቱ በበኩላቸው ወሲባዊ ጥቃትና ትንኮሳ ሪፖርት አልደረሰንም በማለት ተናግረዋል። የቫኔሳ ግድያ የምርመራ ጉዳይ ገና አልተቋጨም። የጦሩ ዋና ፀሃፊ ራያን ማካርቲ እንዳሉት " በፎርት ሁድ ጦር ሰፈር የተፈፀሙት ጉዳዮች ቀጥታ አመራሩ ጉድለት ጋር የተያያዙ ናቸው" ከዚህም በተጨማሪ በጦር ሰፈሩ ጠፉ የተባሉ ወታደሮችንም በተመለከተ አዲስ ፖሊሲ እንዲወጣ ጦሩ ትእዛዝ አስተላልፏል። የተባረሩትና የታገዱት ወታደራዊ መኮንኖች ጉዳይ የተገለፀው በትናንትናው ዕለት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ሜጀር ጄኔራሎቹ ስኮት ኤፍላንድትና ጄፈሪ ብሮድዋተር ይገኙበታል። በተለይም የቫኔሳ ግድያ "ሁላችንም አስደንግጦናል። በአሜሪካ ጦርም ውስጥም ሆነ በፎርት ሁድ ጦር ውስጥ ስር የሰደደውን ችግር እንድንመለከተው አድርጎናል" ብለዋል ዋናው ፀሃፊው። አክለውም "በስርዓታችን፣ በፖሊሲዎቻችንና ራሳችንንም በጥልቀት እንድንመለከትና እንድንፈትሽም አስገድዶናልም" በማለት ለሪፖርተሮች ተናግረዋል። በፎርት ሁድ በሚገኘው የጦር ሰፈር በአንድ አመት ብቻ 25 ወታደሮች በተለያዩ ምክንያቶች ሞተዋል። አንዳንዶቹ ራሳቸውን አጥፍተዋል፣ ተገድለዋል ወይም አደጋ ደርሶባቸው ነው የሞቱት በማለት አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
news-45861918
https://www.bbc.com/amharic/news-45861918
በቀዶ ህክምና የሚወልዱ (ሲ-ሴክሽን) እናቶች ቁጥር መጨመሩን አንድ ጥናት አመለከተ
አሁን አሁን በተለይ በከተሞች አካባቢ 'ምጡን እርሽው ልጁን አንሽው' የሚባለው አባባል የተረሳ ይመስላል፤ እናቶችም በተፈጥሯዊ መንገድ በምጥ ለመውለድ ፍላጎት የማሳየታቸው ጉዳይ አጠያያቂ እየሆነ ነው።
በቀዶ ህክምና መውለድ የእናቶችንና ህፃናትን ከሞት ቢታደግም፤ ከፍተኛ የጤና ችግርም ያስከትላል ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢነሱም ምጥን ከመፍራትና ከዘመናዊነት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ይነገራል። የህክምና ተቋማትም ያለ አግባብ ገንዘብ ለመሰብሰብ ሲባል ብቻ የሚደረግ ውሳኔ እንደሆነም ይታሙበታል። • ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት በዓለማችን በቀዶ ህክምና የሚወልዱ እናቶች ቁጥር ባለፉት 15 ዓመታት በእጥፍ መጨመሩን ገልጿል። ይህ ደግሞ በአንዳንድ አገሮች አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጥናቱ አመልክቷል። ዘ ላሴንት የተባለ የህክምና የሪፖርት ላይ እንደሰፈረው ከ15 ዓመታት በፊት 16 ሚሊዮን ሕፃናት ወይም 12 በመቶ የሚሆኑት በቀዶ ህክምና ሲወለዱ ከሦስት ዓመታት በፊት ደግሞ አሃዙ በእጥፍ ከፍ ብሎ 29.7 ሚሊዮን ህፃናት ወይም 21 በመቶ ደርሷል። • ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ በቅርቡ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው በቀዶ ህክምና ታግዘው ልጃቸውን የሚገላገሉ እናቶች ቁጥር ከ15 በመቶ ከበለጠ በጣም ከፍተኛ አሃዝ እንደሆነ በመጥቀስ አስጠንቅቆ ነበር። በቀዶ ህክምና የሚወልዱ በርካታ እናቶች ካሉባቸው አገራት መካከልም የዶሚኒካን ሪፐብሊክ 58.1 በመቶ በመሆን በቀዳሚነት ተቀምጣለች። የህክምና ባለሙያዎቹ እንደተናገሩት ብዙ ጊዜ ሐኪሞች ይህንን ቀዶ ህክምና ለማድረግ በቂ ምክንያት የላቸውም። ጥናቱ 168 አገራትን ያሳተፈና ከሦስት ዓመታት ወዲህ ያለውን ናሙና የወሰደ ሲሆን፤ እናቶች ቀዶ ህክምና ማድረግ የሚጠበቅባቸው በህፃኑም ሆነ በእናትየዋ ላይ አደጋ የሚያስከትል የጤና ሁኔታ ላይ ሲገኙ ብቻ ቢሆንም ቀዶ ህክምናውን የሚያደርጉት ግን በርካቶች ከዚህ ችግር ውጪ እንደሆኑ አስታውቋል። በዚህም መሰረት ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ብራዚል፣ ግብፅና ቱርክ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውን ቁጥር ይዘው በዚህ የህክምና እገዛ በሚወልዱ እናቶች ቁጥር ቀዳሚ ሆነዋል። ይህም በአገራት ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ደረጃ በማደግ ያሉ አገራት ካዳጉት አገራት ጋር ሲነፃፀር አሃዙ የሚለያይ ሆኖ ተገኝቷል። ለምሳሌ ከሰሃራ በርሃ በታች ባሉ አገራት በቀዶ ህክና መውለድ አስፈላጊ ሆኖ ቢገኝም በቂ ቁሳቁስና የህክምና ተቋም ባለመኖሩ ይህንን እድል የማግኘት እድል የላቸውም። • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና በአንፃሩ ደግሞ ከሦስት ዓመት በፊት ያለው መረጃ እንደሚያሳየው በላቲን አሜሪካና ካረቢያን ያሉ እናቶች ከምዕራብና መካከለኛው አፍሪካ ከሚገኙ እናቶች ጋር ሲነፃፀር በተደጋጋሚ በዚህ የህክምና ዘዴ ይገላገላሉ። በዚህም የጤና ባለሙያዎች፣ እናቶችና ቤተሰቦች ይህንን ቀዶ ህክምና መምረጥ የሚኖርባቸው በህክምና ሁኔታ ሲገደዱ መሆን አለበት ሲል ጥናቱ አስረድቷል። ስልጠናዎችና ትምህርቶችም በስፋት መሰጠት እንዳለባቸው መክሯል። ምክንያቱ ደግሞ ምንም እንኳን ይህ ህክምና በእናትየው ጤና፣ በፅንሱ አቀማመጥና አመጣጥ ሁኔታ የሚወሰን ሆኖ የህፃኑን ህይወት የሚታደግበት አንዱ መንገድ ነው። በለንደን ኪንግስ ኮሌጂ የማህበራዊ ሳይንስና የሴቶች ጤና ፕሮፌሰር የሆኑት ጀን ሳንዳላ አደጋው ለእናትየውም ሆነ ለህፃኑ የአጭር ጊዜ አሊያም የረጅም ጊዜ ማገገሚያ ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል። • የአስር ደቂቃ እንቅስቃሴ የማስታወስ ችሎታን እንዴት ይጨምራል? ቀዶ ህክምናው ለእናትየው በጣም ውስብስብ የሆነ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፤ በማህፀናቸው አካባቢ ጠባሳም ስለሚፈጥር የደም መፍሰስ፣ የእንግዴ ልጅ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ማደግ፣ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ሊያጋጥማቸው ይችላል። እነዚህ ግን በጣም ጥቃቅን የሆኑ የጤና ችግሮች ሲሆኑ በተደጋጋሚ ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ በጣም አደገኛና ውስብስብ የጤኛ ችግሮች ሊገጥማቸው ይችላል ብለዋል ፕሮፌሰሩ። ቀዶ ሕክምናው የእናቶችንና የህፃናትን ጤና ለመጠበቅ የሚረዳ ቢሆንም አሳማኝ ምክንያት ሲኖር ብቻ መሆን አለበት ሲሉ ይመክራሉ። በቀዶ ህክምና መውለድ (Caesarean section) ምን ማለት ነው? ይህ ህክምና አንዲት እናት በተለያየ ምክንያት ተፈጥሯዊ በሆነው መንገድ በምጥ መውለድ ሳትችል ስትቀር ቀዶ ህክምና በማድረግ ህፃኑ ከማህፀን እንዲወጣ የሚደረግበት መንገድ ነው። ይህም በሦስት ምድቦች ሊከፈል ይችላል። አንደኛው ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሲሆን ያለምንም የህክምና ምክርና አስፈላጊነት አንዲት እናት በዚህ መንገድ መውለድ ስትፈልግ የሚደረግ ነው። ሌላኛው በታቀደ መልኩ በህክምና አስገዳጅነት የህፃኑ አቀማመጥና አመጣጥ አማካኝነት ሊደረግ ይችላል። በድንገተኛ ወይም በምጥ ጊዜ በሚከሰት ውስብስብ ችግሮች ሳቢያ ህክምናው ተመራጭ ይሆናል። ይህ በቀዶ ህክምና የመውለድ ሂደት በምጥ ከሚወልዱት እናቶች ጋር ሲነፃፀር ረጅም የማገገሚያ ጊዜን የሚጠይቅና በሰውነት ላይ ጠባሳም የሚፈጥር ነው።
news-53525197
https://www.bbc.com/amharic/news-53525197
በስተርጅና የኢንስታግራም ሞዴል የሆኑት ባልና ሚስት
በዚህ ዕድሜዬ ሰዎች የእኔን ፎቶ ማየት ይሻሉ ብዬ አስቤ አላውቅም ይላሉ የ84 ዓመቷ ሱ ሂሱ ሂ።
አዛውንቶቹ ጥንዶች ልክ እንደ ኮረዳ ሞዴሎች ሁሉ እማማ ሱ ሂሱም ፈገግ፣ ሞንደል፣ ወዝወዝ እያሉ ፎቶ ይነሳሉ። ለላውንደሪ ማስታወቂያ የሚሆኑ በደረቁ በታጠቡ ልብሶች አጊጠዋል። ላለፉት 70 ዓመታት እማማ ሱ እና የ83 ዓመቱ ባለቤታቸው አባባ ዋን ጂ በታይዋን ሀውሊ ክፍለ ከተማ ልብስ ሲያጥቡ ነው የኖሩት። ላውንደሪ ቤት አላቸው። ብዙ ሰዎች ይታጠብልን ብለው የሰጧቸውን ልብሶች ዘንግተውት ኖረዋል። በቅርቡ የልጅ ልጃቸው ሪፍ ቻንግ ታዲያ አንድ ሐሳብ አቀረበላቸው። ለምን ሰዎች የረሷቸውን ልብሶች እየለበሳችሁ ፎቶ አትነሱም ይላቸዋል። "ኧረ ምን በወጣን! አሉ አሮጊቷና ሽማግሌው ባልና ሚስት። ደሞ በስተርጅና እንቅበጥ እንዴ ሳይሉ አልቀሩም። የልጅ ልጃቸው ግን ወትውቶ፣ ወትውቶ በመጨረሻ አሳመናቸው። አሁን ከመላው ዓለም 130ሺህ ተከታዮችን አፍርተዋል። የኢኒስታግራም ከዋክብት ሆነዋል። የልጅ ልጃቸው በኋላ ላይ እንደተናገረው ሐሳቡን ሲያመነጭ ዓላማው አያቶቹን ዝነኛ ማድረግ አልነበረም፤ "እኔ ሐሳቡን ያቀረብኩላቸው ከድብታ እንዲያወጣቸው በሚል ነበር። አለ አይደል? እንዲሁ መደበርያ እንዲሆናቸው. . ." የልጅ ልጅ ይህን ሐሳብ ሲያመነጭ አያቶቹን ከድብርት ከማውጣትም ባሻገር ልብሶቻቸውን ከላውንደሪው ያልወሰዱ ሰዎች መጥተው እንዲወስዱም ያበረታታቸዋል ብሎም አስቦ ነበር። ሽማግሌዎቹ ባልና ሚስት ዝናቸው እየተመነደገ ሲሄድ የፋሽን መጽሔቶች እየመጡ ፎቶዎች መውሰድ ጀመሩ። አሮጊቷ በአጭር ቀሚስ ሽማግሌው ደግሞ በቁምጣ ሆነው ልክ ለሽርሽር የሚሄዱ ነው የሚመስሉት። እንደዚያ ስዘንጥ የ30 ዓመት ጎረምሳ የሆንኩ ያህል ነው የሚሰማኝ ይላሉ ሽማግሌው ዋን ጂ። አባባ ዋን ጂ የደረቅ እጥበት ላውንደሪ የጀመሩት በ14 ዓመታቸው ነው። ድሮ ሰው ልብሱን አሳጥቦ ላውንደሪ ውስጥ አይረሳም ነበር። አሁን አሁን ግን ልብስ ርካሽ እየሆነ ሲመጣ ሰው ልብሱን ላውንደሪ ይረሳ ጀምሯል ይላሉ። "አስታውሳለሁ. . . እኔ ሳገባ አንድ ፈረስ ጋሪ ሙሉ ኩንታል ሩዝ ሽጬ ነበር ሱፍ ልብስ የገዛሁት። ልብስ ድሮ ቀረ. . .።" አባባ ዋን ጂ እንደሚሉት ሰዎች ልብሶቻቸውን የሚረሱት አንድም ሀብታም ስለሆኑ ነው፤ አንዳንዴ ግን የልብሱ ባለቤት ስለሚሞት ነው። የዋን ጂ እና የባለቤታቸው የዕድሜ ጀምበር ወደ መጥለቂያዋ ተቃርባለች። ነገር ግን የዚህችን ዓለም ኮንትራት ጨርሰው እስኪሄዱ ድረስ እየዘነጡ በኢኒስታግራም ላይ ዓለማቸውን እየቀጩ ይቆያሉ።
news-52433110
https://www.bbc.com/amharic/news-52433110
ኮሮናቫይረስ፡ ቺሊ ከኮሮናቫይረስ ላገገሙ "ከቫይረሱ ነፃ" የሚል የምስክር ወረቀት ልትሰጥ ነው
የቺሊ መንግሥት ከኮሮና ቫይረስ ላገገሙ ዜጎች "ከቫይረሱ ነፃ" የሚል የምስክር ወረቀት እሰጣለሁ ማለቱ አወዛጋቢ ሆኗል።
ይህ የምስክር ወረቀትም ወደ ስራ እንዲመለሱ ማስረጃ እንደሚሆናቸውም የአገሪቷ ምክትል የጤና ሚኒስትር ፓውላ ዳዛ ገልፀዋል። ውሳኔውን የተቹት አካላት በበኩላቸው የምሰክር ወረቀቱ ባዶ ተስፋን ይሰጣል፤ ቫይረሱም የበለጠ እንዲስፋፋ በር ይከፍታልም እያሉ ነው። •ስለቫይረሱ ከሚናፈሱት በጥቂቱ፡ የአሪቲ መድኃኒትነት፣ የአለምን ህዝብ መቆጣጠሪያ መንገድ •"ሞትን ተሻገርኳት" ከኮሮናቫይረስ ያገገመች ሴት ለዚህም እንደ ማስረጃነት የሚጠቅሱት የአለም ጤና ድርጅት ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ ሰዎች እንደገና ላለመያዛቸውም ምንም አይነት ዋስትና የለም በማለትም ማስጠንቀቁን በማውሳት ነው። ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ በተገኘው መረጃ መሰረት በቺሊ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 13ሺ ሰዎች ሲሆን፣ 189ም ዜጎቿን በሞት ተነጥቃለች። "እስካሁን ባለው መረጃ ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ ሰዎች እንደገና የመጠቃት እድል የላቸውም የሚል ምንም አይነት መረጃ የለም። በሽታውን የመቋቋም አቅማቸው ይጨምራል የሚልም ማስረጃ የለም" በማለት አለም አቀፉ የጤና ድርጅት ባለፈው ሳምንት አሳውቋል። •በቺካጎ የኢትዮጵያውያን ማኅበር መስራች አቶ መንግሥቴ አስረሴ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አለፈ •በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? ድርጅቱ አክሎም ከበሽታው ነፃ ነው የሚል የምስክር ወረቀት መስጠቱ ህዝቡ በሽታውን ለመከላከል ከሚያደርገው ጥንቃቄ እንዲዘናጋና፤ ነፃ የተባሉትም ሰዎች በሽታውን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያስተላልፉ ይችላሉ ብሏል። የቺሊ ጤና ሚኒስቴር ግን በድርጅቱ ሃሳብ አይስማም፣ በተቃራኒው ፓውላ ዳዛ እንደሚሉት "በኮሮናቫይረስ ተይዞ ያገገመ ሰው ሁለተኛ የመያዝ እድሉ ዝቅተኛ እንደሆነ እናውቃለን" የሚሉት ሚኒስትሯ የምስክር ወረቀቱ ከበሽታው ማገገማቸውን የማሳወቂያ መንገድ እንጂ እንደገና አይያዙም የሚል አይደለም ብለዋል። የአለም ስጋት በሆነው ኮሮና ቫይረስ ከ200 ሺ ሰዎች በላይ ህይወትን ያጠፋ ሲሆን፤ መንግሥታትም የቫይረሱን ለመዛመት ጥለዋቸው የነበሩ አስገዳጅ መመሪያዎችን ለማላላት መንገዶችን እየቀየሱ ነው።
54546132
https://www.bbc.com/amharic/54546132
ልደቱ አያሌው፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አቶ ልደቱን እንዲፈታ ታዘዘ
አቶ ልደቱ አያሌውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከእስር እንዲፈታቸው ፍርድ ቤት ማዘዙን ጠበቃቸው አቶ አብዱልጀባር ሁሴን ለቢቢሲ ተናገሩ።
ጠበቃው አክለውም የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አላከበረም የተባለው የቢሾፍቱ መምሪያ ምክትል ኃላፊ እና የወንጀል ምርመራ ኃላፊዎች ችሎት ፊት ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ብለዋል። ለወራት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ልደቱ፤ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ፍርድ ቤት በ100 ሺህ ብር በዋስትና ወጥተው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ወስኖ ነበረ ቢሆንም የቢሾፍቱ መምሪያ ፖሊስ ግን ሳይለቃቸው ቆይቷል። በወቅቱም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አቶ ልደቱን በሚመለከት ባወጣው መግለጫ፤ አላስፈላጊ እስር ማስቀረትና የዋስትና መብት ማክብር ያስፈልጋል ሲል ጠይቋል። አቶ ልደቱ በአንድ መቶ ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ መስከረም 12/2013 ዓ. ም ትዕዛዝ ቢሰጥም እስካሁን አልተፈቱም። አቶ ልደቱ ዛሬ ረፋድ ላይ የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት ከዚህ በፊት በነበረ ቀጠሮ የተሰጡ ሁለት ትዕዛዞችን ለማየት እንደሆነ ጠበቃቸው አቶ አብዱልጀባር ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ልደቱ ማለዳ 4፡30 ላይ ችሎት ፊት መቅረባቸውን አስታውሰው፤ ችሎቱም ሁለቱን ጉዳዮች በማየት ትዕዛዝ አስተላልፏል ብለዋል። አንደኛው ሕገ ወጥ መሳሪያ በመያዝ የቀረበባቸውን ክስ ላይ አቃቤ ሕግ አሉኝ ያላቸውን ምስክሮች ለማሰማት የነበረ ሲሆን ሶስት ምስክሮችም ቀርበው መስክረዋል። ሌላኛው ደግሞ ከዚህ በፊት የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም መምሪያው የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አልቀበልም በማለቱ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መጥሪያውን አድርሶ፤ ስለማድረሱ ደግሞ ለፍርድ ቤቱ እንዲያሳውቅ መቀጠሩን ጠበቃው ይገልጻሉ። በዚህም መሰረት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የተላከውን መጥሪያ ተቀብሎ ያደረሰ ቢሆንም ነገር ግን ለቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ስለማድረሱ ደብዳቤ አልጻፈም ነበር ብለዋል። ኃላፊውም ችሎት ፊት ያልቀረቡ ሲሆን አቶ ልደቱንም ወደ ችሎት ይዘው የመጡት ፖሊስ ለመምሪያው አዲስ ኃላፊ መመደቡን እና እርሳቸው ይህንን ጉዳይ እንደማያውቁ አስረድተዋል። ፍርድ ቤቱ ይህንን ተከትሎም ሁለት ትዕዛዝ መስጠቱን ጠበቃ አብዱልጀባር ይናገራሉ። አንደኛው የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምክትል ኃላፊ እንዲሁም የወንጀል ምርመራ ኃላፊው መስከረም 13፣ 14 እንዲሁም በ26 እና በ27 ሲሰጡ የነበሩ ትዕዛዞች ፖሊስ ሳይቀበል በመቅረቱ እነዚህን የፍርድ ቤት ትዕዛዞች እስካሁን ለምን እንዳልተፈፀሙ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ አዝዟል። የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የፍርድ በቶች ትዕዛዝ ሊከበሩ ይገባል ያለው ችሎቱ፤ የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ትዕዛዙን አልቀበልም ካለ የበላይ አካሉ የፖሊስ ኮሚሽኑ ኃላፊነት ሊወስድ ስለሚገባ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሸን በአስቸኳይ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት አቶ ልደቱን እንዲፈታ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል። ዛሬ አቃቤ ሕግ ያሰማቸው ምስክሮች ቃላቸው የሰፈረው በትርጉም በመሆኑ ወደ ጽሑፍ ተገልብጦ ከመዝገብ ጋር እንዲያያዝ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ አስቀድሞ ተጽፎ የሚቀርብ በመመርመር ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ ምክትል ኃላፊ እና የወንጀል ምርመራ ኃላፊውን ደግሞ ጥቅምት 9፣ 2013 ዓ. ም እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
news-55541611
https://www.bbc.com/amharic/news-55541611
የሕዝብ እንደራሴዎች ትራምፕ በወንጀል እንዲከሰሱ ደብዳቤ ጻፉ
የጆርጂያ ግዛት የምርጫ አስፈጻሚ የሆኑት ብራድ ራፈንስበርገር ትራምፕ ስልክ ደውለው 'እንዳሸንፍ የሚያበቃኝን የመራጮች ድምጽ ከየትም ውለድ' ማለታቸው "አሳፋሪ ስህተት ነው' ሲሉ ተናገሩ።
ብራድ ይህን አስተያየት የሰጡት በእሳቸውና በፕሬዝዳንቱ መካከል የተደረገው የስልክ ልውውጥ ድምጽ በዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ መጋለጡን ተከትሎ ነው። ትራምፕ ግለሰቡን ስልክ ደውልው ቁም ስቅላቸውን ሲያሳይዋቸው የሚያስደምጠው የድምጽ ቅጂ ይፋ ከሆነ ወዲህ በተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ላይ ውግዘት በርትቷል። አንዳንዳንዶች እንዲያውም "የፕሬዝዳንቱ ድርጊት በወንጀል የሚያስጠይቅ ነው" እስከማለት ደርሰዋል። ሁለት ሕግ አዋቂ የታችኛው ምክር ቤት አባላትም ለአሜሪካ ወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ፕሬዝዳንቱ ላይ የወንጀል ዶሴ እንዲከፈትባቸው የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፈዋል። ዶናልድ ትራምፕ ከጆ ባይደን ጋር ለፕሬዝዳንትነት ሲፎካከሩ በጆርጂያ ግዛት በጠባብ ልዩነት ነበር የተሸነፉት። ይህን ለማስቀልበስ ነበር የምርጫ አስፈጻሚው ጋር ፕሬዝዳንቱ በግል ደውለው "ትንሽ ድምጽ ብትፈልጉልኝ ምናለበት" እያሉ ሲያባብሉ የነበረው። የትራምፕ ወዳጆች የሆኑት የሪፐብሊካን ፓርቲ ባለሥልጣናት የፕሬዝዳንቱ ቅሌት በዚህ ሰዓት ይፋ መደረጉ በጆርጂያ አሁን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት መቀመጫ ለማግኘት ለሚደረገው ወሳኝ ምርጫ የትራምፕ ድርጊት በሪፐብሊካኑ እጩ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊፈጥር ይችላል በሚል ስጋት ገብቷቸዋል። ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት እንደራሴነት ዛሬ በጆርጂያ በሚደረገው ምርጫ ዲሞክራቶች ካሸነፉ የላዕላይ ምክር ቤቱን በበላይነት ለመቆጣጠር ስለሚያስችላቸው ለጆ ባይደንና ለካምላ ሐሪስ ሠርግና ምላሽ ይሆንላቸዋል ተብሏል። ምክንያቱም ዲሞክራቶች ናንሲ ፒሎሲ የሚመሩትን የሕግ መምሪያውን ምክር ቤት የበላይነት የተቆጣጠሩ ሲሆን አሁን በጆርጂያ በለስ ከቀናቸው ደግሞ የላዕላይ ምክር ቤቱ በዲሞክራቶች ቁጥጥር ይወድቃል። ይህም ጆ ባይደን ያለምንም ፈተና ፖሊሲዎቻቸውን እንዲያስፈጽሙ ያግዛቸዋል። የጆርጂያ ምርጫ ላይ ዲሞክራቶች ቢያሸንፉ ከሪፐብሊካን ጋር በውክልና እኩል ቁጥር ያገኛሉ። ሆኖም የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የሚመራው በምክትል ፕሬዝዳንት ስለሆነ ካምላ ሐሪስ የሚኖራቸው ድምጽ ወሳኝ ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው። በትራምፕ ዘመን የላዕላይ ምክር ቤቱ በሪፐብሊካን አብላጫ መያዙ ለዲሞክራቶች ራስ ምታት ሆኖ እንደቆየባቸው ይታወቃል። የጆርጂያ ምርጫ አስፈጻሚ ብራድ ከኤቢሲ ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በወቅቱ ፕሬዝዳንቱ እየደወሉ ሲያባብሏቸው ብዙውን ጊዜ ፕሬዝዳንቱ ተናጋሪ እሳቸው ደግሞ አድማጭ ሆነው ለሰዓታት እንደሚቆይ ተናግረዋል። ሆኖም ግን "ፕሬዝዳንቱ እየተናገሩ ያሉት ነገር ስህተት እንደነበረ በተደጋጋሚ ነግሪያቸዋለሁ" ብለዋል ብራድ። ብራድ ራፈንስበርገር ዋሺንግተን ፖስት ይፋ ያደረገው የስልክ ቅጂ እሳቸውና ፕሬዝዳንቱ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል ሲነታረኩ የሚያስደምጥ ነው። የትራምፕ ጥያቄ በግዛቲቱ ውስጥ ምርጫው ተጨበርብሯል በሚል ለማሸነፍ የጎደሏቸውን ድምጾች ከየትም ብሎ ፈልገው እንዲሞሉ የሚወተውቱ ነበሩ። ብራድ ለኤቢሲ እንተናገሩት ይህ የስልክ ልውውጥ እየተቀዳ እንደሆነ በወቅቱ መረጃ አልነበራቸውም። "ዶናልድ ትራምፕ ይሉኝ የነበረው በሺዎች የሚቆጠሩ የሞቱ ሰዎች ድምጽ ሰጥተዋል (በፖስታ ድምጽ ሰጥተው ሕይወታቸው ያለፈ) ነው። እኔ ደግሞ ያገኘሁት ሁለት ሰዎችን ብቻ ነው። በዚህ ደረጃ ፕሬዝዳንቱ በስህተት ተነክረው ነበር" ብለዋል። ዶናልድ ትራምፕ በስልክ ልውውጡ ወቅት ብራድ የተወሰኑ ድምጾችን ከዚያም ከዚህም ብለው ቢያገኙላቸው እሳቸው ግዛቲቱን አሸንፈው ለሌላ 4 ዓመት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ ይናገራሉ። ዶናልድ ትራምፕ ሰውየውን አንዳንዴ በማባበል፣ ሌላ ጊዜ በማስፈራራት ሊያግባቧቸው ሲሞክሩ በቀጭኑ ሽቦ ይሰማል። የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት የምርጫ አስፈጻሚው ብራድ ግን በእርጋታ ፕሬዝዳንቱ የሚሉት አሐዝ የተሳሳተ እንደሆነ ሲነግሯቸው ይሰማል። "የእስርዎ ችግር ክቡር ፕሬዝዳንት! የተሳሳተ መረጃ ይዘው መውጣትዎ ነው" ሲሏቸውም ይደመጣል። የዚህን የስልክ የድምጽ ልውውጥ ሾልኮ መውጣትን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ በወንጀል መጠየቅ የለባቸውም ወይ የሚሉ አስተያየቶች ሚዲያውን ሞልተውታል። ሁለቱ የታችኛው ምክር ቤት አባላትን ለኤፍቢአይ ደብዳቤ የጻፉት ይህን ተከትሎ ነበር። ደብዳቤው ኤፍ ቢ አይ በትራምፕ ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጀምር የሚጠይቅ ነው። ጆርጂያ የሚገኙት ተመራጭ ምክትል ፕሬዝዳንት ካምላ ሐሪስ በበኩላቸው የትራምፕን ድርጊት በሥልጣን መባለግ ነው ሲሉ ገልጸውታል። የሴኔት ተጠሪ ዲክ ደርቢን በበኩላቸው የትራምፕን ድርጊት አደገኛ ብለውታል። የትራምፕ ድርጊት በጆርጂያ ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ወይ የሚለው የፖለቲካ አዋቂዎችን እያከራከረ ነው። ጆ ባይደንም ሆኑ ካምላ ሐሪስ ከትናንት ጀምሮ በጆርጂያ የዲሞክራቲክ እጩ እንዲያሸንፍላቸው ቅስቀሳ በማድረግ ተጠምደው ነው የዋሉት። ጆ ባይደን በአትላንታ ተገኝተው መራጮች ለዲሞክራቲክ እጩ ድምጽ እንዲሰጡና ታሪክ እንዲሰሩ ተማጽነዋል። ትራምፕ በበኩላቸው የጆርጂያ መራጮች በፍጹም ዲሞክራት እጩ እንዳይመርጡ አስጠንቅቀዋል። "ዲሞክራቶች የታችኛውንም የላይኛውንም ምክር ቤት ከተቆጣጠሩ አደገኛ ነው። ልንታገላቸው ይገባል" ብለዋል። አክለውም፤ ይህ የምትሰጡት ድምጽ በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ከምትሰጡት ድምጽ እጅግ ወሳኙ እንደሆነ ልነግራችሁ እወዳለሁ ብለዋል። ጆርጂያ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት እንደራሴ የነበሩት ሪፐብሊካኑ ሴናተር ዴቪድ ፐርዱ ውክልናቸውን ለማስጠበቅ ነው የሚታገሉት። የዲሞክራቱ እጩ ጆን ኦሶፍ የትራምፕን ድርጊት የዲሞክራሲ ጸር ሲሉ ኮንነውታል።
news-54384868
https://www.bbc.com/amharic/news-54384868
ምርጫ 2013፡ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ 50 ሚሊዮን መራጮች ይጠበቃሉ ተባለ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን የሚደርሱ መራጮች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታወቀ።
ምርጫ ማስፈጸሚያ ቁሳቁስ ቦርዱ ይህን ያለው ዛሬ 6ኛውን አገር አቀፍ ምርጫን አስመልክቶ እያደረጋቸው ያሉ ለምርጫው የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች ሥራን ባስታወቀበት ወቅት ነው። ቦርዱ እድሜያቸው ለመምረጥ ደርሶ በምርጫው ይሳተፋሉ ያላቸው ዜጎች ከአገሪቱ ሕብ ቁጥር ወደ ግማሽ የሚተጉ ሲሆኑ፤ በመላው አገሪቱ በምርጫው ድምጽ የሚሰጡባቸው 50 ሺህ 900 የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚኖሩም አስታውቋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር የቤት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የቀረበለትን በአገሪቱ ያለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ግምገማና ምክረ ሐሳብ ተመልክቶ ከባለፈው ዓመት የተሸጋገረውን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወሳል። በዚህም መሠረት ከድምጽ መስጫ ጣቢያዎች በተጨማሪ የመራጮች ምዝገባን የሚያከናውኑ 152 ሺህ 700 ሰዎችን እንዲሁም ለድምጽ መስጫ ቀን 254 ሺህ 500 ምርጫ አስፈጻሚዎችን እንደሚያሰማራም አስታውቋል። በዚህ ዓመት ሊካሄድ እንደሚችል ለተጠቆመው አገራዊ ምርጫ በአምስት ቋንቋዎች የተዘጋጁ የመራጮች መዝገቦች መዘጋጀታቸውም ተገልጿል አስታውቋል። የምርጫውን ተአማኒነት ለማረጋገጥም መራጮችም የሚወስዱት ለማባዛት እና አስመስሎ ለማተም የማይቻል የደኅንነት መጠበቂያ ያለው የመራጮች መታወቂያ ካርድ መዘጋጀቱንም አስታውቋል። ቦርዱ እንደ ድምጽ መስጫ ሳጥኖች፣ የሚስጥር ድምጽ መስጫ መከለያዎች፣ ማስፈጸሚያ ቁሳቁሶች የያዙ ቦርሳዎች፣ የጠረጴዛ ባትሪ የመሳሰሉ ለምርጫ ቀን የሚውሉ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል። አገራዊ ምርጫ መቼ እንደሚካሄድ የሚያመለክተው የጊዜ ሰሌዳ ያልወጣ ቢሆንም፤ ቦርዱ ከወዲሁ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል። ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ መርጫ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደዚህ ዓመት እንዲተላለፍ መወሰኑ ይታወሳል።