id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-50371706
https://www.bbc.com/amharic/news-50371706
ሰዎች 'ፖፒ' የተሰኘችውን ቀይ አበባ ለምን ደረታቸው ላይ ያደርጓታል?
"ፖፒ" የተሰኘውን ቀይ አበባ ብዙዎች ደረታቸው ላይ አድርገውት በቴሌቪዥን መስኮቶች ተመልክተው ይሆናል።
"ፖፒ" በመባል የምትታወቀው ቀይ አበባ ደረት ላይ የምትደረገው በተለያዩ የጦር ሜዳዎች ህይወታቸውን ለሃገራቸው መስዋዕት ያደረጉት ሰዎችን ለመዘከር ነው። ከዚህ በተጨማሪም በሽብር ጥቃት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ለማስታወስ እና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቤተሰቦች አስተዋጽኦን ለማጉላት በፈረንጆቹ ኖቬምበር ወር ላይ ደረት ላይ ይደረጋል። "ፖፒ" እ.አ.አ. ከ1921 ጀምሮ በጦር ሜዳ መስዕዋት የሆኑትን ለማሰብ በተለይ ደግሞ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ ሲደረግ ቆይቷል። በየዓመቱም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች "ፖፒ" ደረታቸው ላይ ያደርጋሉ። የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ጦርነቱን በተካሄደባቸው ሜዳዎች ላይ "ፖፒ" በቅሎ ነበር። ቀይዋ አበባ "ፖፒ" ለምን ተመረጠች? የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ጦርነቱን በተካሄደባቸው ሜዳዎች ላይ "ፖፒ" በቅሎ ነበር። ከዚያ በኋላ በጦርነቱ ለሃገራቸውን ህይወታቸውን የገበሩ ሰዎችን ለመዘከር ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። በዚህ በፈረንጆቹ ወር ከአበባው ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ በህይወት የሚገኙ እና ለሃገራቸው የተዋደቁ አርበኞችን ለመደገፍ ይውላል። እንግሊዝ ውስጥ የሚካሄዱ እግር ኳስ ጨዋታዎች እና መሰል ዝግጅቶች የአንድ ደቂቃ የኅሊና ፀሎት በማድረግ በጦርነት የወደቁትን ያስባሉ። አልፎም ቴሌቪዥን ላይ የሚታዩ አቅራቢዎችም ሆኑ እንግዶች ቀይዋን አበባ ደረታቸው ላይ ሰቅለው ማየት የተለመደ ነው። በስፋት ጥቅም ላይ ከምትውለው ቀይዋ 'ፖፒ' በተጨማሪ ነጭ፣ ሮዝ፣ ጥቁር እና የቀስተደመና ቀለማት ያሏቸው ፖፒዎች ለመዘከሪያነት ጥቅም ላይ ይውላሉ።
news-55422347
https://www.bbc.com/amharic/news-55422347
ትግራይ ፡ የተባበሩት መንግሥታት የመብት ጥሰቶችን ለማጣራት ወደ ትግራይ ለመግባት ጠየቀ
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው መሆኑን ገልጸው በክልሉ ሁሉም ሥፍራዎች ገደብ የለሽ የሰብዓዊ እርዳት እንዲሰራጭ ጥሪ አቅርበዋል።
ማክሰኞ ዕለት መግለጫ ያወጡት ኮሚሽነሯ ድርጅታቸው በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት በተሳተፉ ሁሉም ኃይሎች "የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞ ሊሆን እንደሚችል" የሚያሳዩ መረጃዎች በተደጋጋሚ እየደረሳቸው እንደሆነ አሳውቀዋል። "ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ሕግ እና የሰብዓዊ መብት ሕግን የተመለከቱ ሰላማዊ ሰዎች በሚኖሩባቸው ቦታዎች ላይ የከባድ መሣሪያ ጥቃት መፈፀም፣ ሰላማዊ ሰዎችን ሆን ብሎ ማጥቃት፣ ሕግ የጣሰ ግድያና ሰፊ ዝርፊያ እንዳለ የሚጠቁሙ መረጃዎች ደርሰውናል" ይላል መግለጫው። ኮሚሽነር ባሽሌት እንዳሉት ሁለት የሰብዓዊ እርዳታ ተልዕኮዎች ግጭት ወደተከሰተበት ክልል ታህሣሥ 12/2013 ዓ.ም መግባት መቻላቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን በክልሉ አሁንም በአንዳንድ ቦታዎች ያለው የመገናኛ መስመር መቋረጥ ገለልተኛ መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል። በትግራይ ክልል ኃይሎችና በፌዴራል መንግሥት መካከል ግጭት የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. ነበር። ከግጭቱ መቀስቀስ በኋላ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል። በርካቶች ድንበር አቋርጠው ጎረቤት አገር ሱዳን በስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። የመንግሥት ኃላፊነት የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡ ድርጅቶች መግባት እንዲችሉ ይመቻቻል ሲል ከተባበሩት መንግሥታት ጋር በኅዳር ወር ላይ ከስምምነት ደርሶ ነበር። ነገር ግን በትግራይ ክልል ያለው ግብረ ኃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ሬድዋን ሁሴን በክልሉ የሰብዓዊ መብት እርዳታ የማመቻቸትና ጥሰቶችን የመመርመር ብቸኛው ኃላፊነት ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት ነው ሲሉ ለጋዜጠኖች ተናግረዋል። የዓለም አቀፉ ሰብዓዊ መብት ድርጅት ቃል አቀባይ የሆኑት ሊዝ ቶርሴል ማክሰኞ ዕለት ከጄኔቭ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "እስካሁን ወደ ክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ የተደረገው ጥረት 'የሚበረታታ' ቢሆንም ድርጅታችን ወደ ትግራይ ክልል ለመግባት ያልተገደበ መንገድ ማግኘት ይሻል" ብለዋል። ቃል አባይዋ በክልሉ ያሉ ሰላማዊ ዜጎች በግጭቱ ምክንያት ተጎድተዋል፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም ሊጣሩ ይገባልም ብለዋል። ድርጅታችሁ ወደ ክልሉ ገብቶ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እስካሁን ማጣራት ችሏል ወይ ተብለው የጠየቁት ቃል አቀባይዋ፤ "እስካሁን ድረስ አልቻልንም። እኛም እያልን ያለነው እሱን ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። "አሁን ወደ ክልሉ ለመግባት ያለውን ክልከላ ከግምት ውስጥ በማስገባት እስካሁን ድረስ እያደረግን ያለነው የተለያዩ መረጃዎችን መሰብሰብ ነው። ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው ወደ ሱዳን የገቡ ስደተኞችን ቃለ መጠይቅ አድርገንላቸዋል፤ ከርቀት ሆነን ሁኔታዎችን ተከታትለናል፤ አዲስ አበባም ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሰዎችን አናግረናል። ይህን ያደረግነው በክልሉ የተፈጠረውን ነገር የሚያሳየን መሠረት ይዘን ወደፊት ለመጓዝ ነው" ብለዋል። ግጭቱ እንደቀጠለ የሚያመለክቱ ዘገባዎች ቃል አቀባይዋ አሁንም በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ግጭቱ እንደቀጠለ የሚያመለክቱ ዘገባዎች ደርሰውናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን በተደጋጋሚ በክልሉ ያለው ግጭት መቆሙን ተናግሯል። "ግጭቱ እንደቀጠለ ነው እየተባለ ነው። በተለይ ደግሞ በሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡባዊ ትግራይ ባሉ አንዳንድ ሥፍራዎች" ብለዋል ቃል አቀባይዋ። የመንግሥት ኃይሎች የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለን ከተቆጣጠሩ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ 'በክልሉ ያለው ሕግን የማስከበር ዘመቻ ተጠናቋል፤ የትግራይ ክልል ኃይሎች ተሸንፈዋል' ማለታቸው ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ማክሰኞ ዕለት ይህን የሚያጠናክር ሃሳብ ተናግረዋል። "ትግራይ ክልል ውስጥ አሁንም ጦርነት ቀጥሏል የሚባለው ፍፁም ሐሰት ነው። እርግጥ ነው በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ ጦርነት ተፋፍሟል" ብለዋል አምባሳደር ዲና። በፌዴራል መንግሥቱ የተሾው አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በአንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ሥራ መጀመሩ ተዘግቧል። በመቀለና በአንዳንድ የምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎትና የኤሌክትሪክ ኃይል ሥራ ጀምረዋል። ነገር ግን በሌሎች ሥፍራዎች አሁንም የመገናኛ መስመሮች እንደተቋረጡ ናቸው። ይህም በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ሁኔታ በገለልተኛ ወገን ለማጣራት ሁኔታዎችን አስቸጋሪ አድርጓቸዋል። የሰብዓዊ እርዳታ ጥሪ በግጭቱ ምክንያቱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው አሳሳቢ ሆኗል። ማክሰኞች ዕለት የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽንና አጋሮቹ በትግራይ ክልል ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል የ156 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ጠይቀዋል። የስደተኞች ኮሚሽን እንደሚለው ከ52 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሱዳን ተሰደዋል። ድርጅቱ 96 ሺህ የሚሆኑ ከግጭቱ በፊት በትግራይ ክልል ተጠልለው የነበሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች ጉዳይም እንዳሳሰበው አስታውቋል። ኮሚሽኑ ወደ ሱዳን የስደተኛ መጠለያዎች የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ቢቀንስም "የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የአስቸኳይ ጊዜ ሥራ ላይ ናቸው፤ ምክንያቱም አሁን ስደተኞቹ ያሉበት ቦታ ለዓመታት እንዲህ ዓይነት የስደተኞች ቁጥር አስተናግዶ አያውቅም" ብሏል።
news-46028214
https://www.bbc.com/amharic/news-46028214
በቱኒዝያ በደረሰ ጥቃት አንዲት ሴት ራሷን በቦምብ አፈነዳች
በቱኒዝያዋ መዲና ቱኒስ የ30 ዓመት ዕድሜ ያላት አንዲት ሴት በቦምብ ራሷን በማፈንዳቷ ዘጠኝ ሰዎች መጎዳታቸውን የቱኒዝያ የኃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።
ፍንዳታውን ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ቢገልፁም ሴትዮዋ ምንም ዓይነት ወታደራዊ ስልጠና እንደሌላት አስታውቀዋል። የከተማዋ ማዕከል በሆነው ሐቢብ ቦርጉይባ ተብሎ በሚጠራው ጎዳና በደረሰው ፍንዳታም የተጎዱት ስምንቱ ግለሰቦች ፖሊስ መሆናቸው ተገልጿል። እስካሁን ድረስ ሞት ያልተከሰተ ሲሆን፤ ለጥቃቱም ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን የለም። •መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት ወዴት ያመራል? •እንደወጡ የቀሩት ተመራማሪዎች •በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ ይህ ጥቃት የተፈፀመው ከሶስት ዓመት በፊት በደረሱ ክፉኛ የሽብር ጥቃቶች ተሽመድምዶ የነበረው የሃገሪቱ ኢንዱስትሪ እያንሰራራ በነበረበት ወቅት ነው ። በአውሮፓውያኑ 2015 ባርዶ ሙዝየም በደረሰ ጥቃት 22 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ በዛው ዓመት ከጥቂት ወራት በኋላ በአንድ መዝናኛ ቦታ 38 ሰዎች ተገድለዋል። የአሁኑ ጥቃት የደረሰው ከፈረንሳይ ኤምባሲ 200 ሜትር ርቀትና የኃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒሰቴር በሚገኝበት ጎዳና መሆኑን የሀገሪቱ ጋዜጠኛ ሱሐይል ክሚራ ለቢቢሲ ገልጿል። ፍንዳታው ከደረሰ ከ15 ደቂቃ በኋላ ሲሆን ቦታው የደረሰው ጋዜጠኛ ከፍተኛ የሆነ ጥቁር ጭስም አካባቢውን ሸፍኖት ነበር ብሏል። ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ ሱቆች የተዘጉ ሲሆን ፖሊስም መንገዱን ዘግቷል። በአውሮፓውያኑ 2015 አጥፍቶ ጠፊ 12 የፀጥታ ኃይሎችን ከገደለ በኋላ ቱኒዝያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ እንደነበረች የኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም እስከ ህዳር መጀመሪያ ላይ እንዲራዘም መወሰኑን የዜና ወኪሉ ኤኤፒ አስታውቋል።
news-46563265
https://www.bbc.com/amharic/news-46563265
ልብ የረሳው አውሮፕላን
አሜሪካ ውስጥ ከሲያትል ወደ ዳላስ ይጓዝ የነበረ አውሮፕላን ለህመምተኞች ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረስ የነበረበትን ልብ ረስቶ በመሄዱ ከሰአታት በኋላ እንዲመለስ ተገዷል።
የአውሮፕላኑ ባለቤት የሆነው 'ሳውዝዌስት' አየር መንገድ እንዳስታወቀው የልብ ንቅለ ተከላ ለሚደረግላቸው ሰዎች በሆስፒታል ማስተካከያ ሊሰራለት የነበረው የሰው ልብ መረሳቱ አስገርሞታል። ልቡን ሲጠባበቁ የነበሩ የህክምና ባለሙዎች ሁኔታው አላምር ሲላቸው አውሮፕላኑ ዳላስ ለመድረስ ግማሽ ያህል ርቀት ሲቀረው ወደኋላ እንዲመለስ አስገድደውታል። እስካሁን ልቡ ለማን ሊሰጥ እንደሆነ አልተወሰነም ተብሏል። • ልባችን ከእድሜያችን ቀድሞ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ? • የቀድሞ የአልሸባብ መሪ በኢትዮጵያ ሠራዊት በሶማሊያ በቁጥጥር ሥር ዋለ • የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ ደንበኞችም ዋና አብራሪው ሁኔታውን ሲያስረዳቸው በጣም መደንገጣቸውንና በጭንቀት ሲተባበሩ እንደነበረ አየር መንገዱ አስታውቋል። አንዳንዶቹ እንዳውም ስልኮቻቸውን በመጠቀም የሰው ልብ በማቀዝቀዣ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንደሚችል ሲያጣሩ ነበር ተብሏል። ባለሙያዎች እንደሚሉት የሰው ልጅ ልብ በማቆያ ውስጥ ከአራት እስከ ስድስት ሰአት መቆየት ይችላል። ከሶስት ሰአታት በረራ በኋላ ወደተነሳበት አየር ማረፊያ እንዲመለስ የተገደደው አውሮፕላን፤ ውስጥ ተሳፋሪ የነበረ የህክምና ባለሙያ ለጋዜጠኞች እንደተናገረው ክስተቱ ከባለሙያዎች የማይጠበቅ ቸልተኝነት ነው ብሏል። ምንም እንኳን አውሮፕላኑ በታሰበለት ሰአት ልቡን ማስረከብ ባይችልም፤ ከስድስት ሰአታት በኋላ ልቡ ሟቾች ከመሞታቸው በፊት የለገሷቸው የሰውነት አካላት ወደ ሚጠራቀምበት ሆስፒታል መወሰዱ ተገልጿል።
50003877
https://www.bbc.com/amharic/50003877
በበዴሳ ከተማ የ13 ዓመት ታዳጊን ህይወት ለማዳን የሞከሩ 4 ሰዎች የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ
ትናንት እኩለ ቀን ላይ በምዕራብ ሃረርጌ ዞን በዴሳ ከተማ ውሃ ለመቅዳት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ የቀረውን የ13 ዓመት ታደጊ ህይወት ለማትረፍ የሞከሩ 4 ሰዎችን ጨምሮ አምስት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።
የዓይን እማኞች እና የአከባቢው መስተዳደሮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቅድሚያ እስከ 22 ሜትር ጥልቀት ያለው እና ከኮንክሪት ወደ ተሰራው ጉድጓድ ውስጥ የ13 ዓመት ታዳጊው ከገባ በኋላ የእርሱን ህይወት ለማዳን በተደረጉ ጥረቶች ነው የተቀሩት የአራቱ ሰዎች ህይወት ያለፈው። • ግብጽ በአባይ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች • በቤተ መንግሥት ግቢ የተገነባው አንድነት ፓርክ በውስጡ ምን ይዟል? ጎረቤት እና አደጋው ሲከሰት በስፍራው የነበሩት የዓይን እማኝ ቱሬ ሃረር የተፈጠረውን እንዲህ ሲሉ ያስረዳሉ። "በመጀመሪያ የ13 ዓመቱ አራርሶ የሚባለው ልጅ ውሃ ለመቅዳት የውሃ ጉድዷ ውስጥ ገባ። ልጁ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ በመቅረቱ አጎቱ የሆነው ሌላ የ15 ዓመት ልጅ አራርሶን ለማውጣት ጉድጓድ ውስጥ ገባ። ሁለቱ ልጆች ገብተው ስለቀሩ ሌላ ሶስተኛ ሰው ልጆቹን አወጣለሁ ብሎ እሱም ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ እዛው ቀረ። ሰዎች ሲሞቱ ቆመን አናይም ብሎ ሌላ አራተኛው ሰው ገባ። እሱም ገብቶ ቀረ። እንደገና ሰዎቹን አድናለሁ ያለ አምስተኛ ሰው ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ የእርሱም ህይወት አለፈ።" አቶ ረመዳን ሃሩን የበዴሳ ከተማ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳይ ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሲሆኑ በቅድሚያ ከኮንክሪት ወደተሰራው ጉድጓዱ ውስጥ የወደቀው ታዳጊ ለመስገድ ውሃ መቅዳት ፈልጎ እንደነበር ይናገራሉ። አቶ ረመዳን በኤክስካቫተር በታገዘ ቁፋሮ የሟቾች አስክሬን ከስድስት ሰዓታት ጥረት በኋላ እንደወጣ ተናግረዋል። "ጉድጓዱ ሲቆፈር እንዳየነው፤ በጉድጓዱ ውስጥ አንድ በርሜል እንኳን የማይሞላ ውሃ ነው ያየነው" ይላሉ የዓይን እማኙ አቶ ቱሬ። አቶ ረመዳንም "ምናልባት ሰዎቹ ህይወታቸው ያለፈው በኦክስጅን እጥረት ሳይሆን አይቀርም" ሲሉ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። ከሟቾቹ መካከል አራቱ ግለሰቦች የሥጋ ዝምድና እንዳላቸው እና አምስተኛው ሰው ደግሞ የጋራዥ ሠራተኛ እንደሆነ አቶ ረመዳን ገልጸውልናል። በከተማው የውሃ እጥረት መኖሩን ተከትሎ ሰዎች ከከተማው መስተዳደር ፍቃድ ውጪ የውሃ ጉድጓዶችን እንደሚቆፈሩ የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊው ይናገራሉ። ከዚህ በኋላ መሰል አደጋዎች እንዳይደርሱ ምን ታስቧል ለሚለው ጥያቄ አቶ ረመዳን ሲመልሱ፤ "በከተማዋው መሰል 20 ጉድጓዶች እንዳሉ ይገመታል። ጉድጓዶቹ እንዲዘጉ ወይም ሰዎች የሚጠበቅባቸውን መስፈርት በሟሟላት ከውሃ ቢሮ ፍቃድ እንዲያገኙ ይደረጋል" ብለዋል። የሟቾች የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ ተፈጽሟል።
news-52259814
https://www.bbc.com/amharic/news-52259814
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጨረቃ ላይ ማዕድን ቁፋሮ እንዲጀመር ለምን ፈለጉ? መብቱስ አላቸው?
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሃገራቸው ጨረቃ ላይ ማዕድን ቁፋሮ እንድትጀምር አጥበቀው ይፈልጋሉ።
እሱ ብቻ አልበቃቸውም አሜሪካ ጨረቃም ሆነ ከፕላኔታችን መሬት ውጭ ያለ ሥፍራ ላይ ማዕድን እንድትቆፍር ሙሉ መብት የሚሰጣት ሙሉ ሥልጣን ያዘለ ወረቀት ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል። ወረቀቱ ላይ የሰፈረ አንድ አንቀፅ እንዲህ ይላል፡ «አሜሪካ በውጭው ዓለም [ከፕላኔታችን ምድር ውጭ ያለው መሆኑ ነው] ያለ ጥሬ ሃብት የጋር ነው ብላ አታስብም። ማዕድን ለማውጣትም ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጋር ስምምነት መድረስ አይጠበቅባትም።» ሰውዬው ጨረቃ ላይ ወጥተው ማዕድን ቁፋሮ ለመጀመር ለምን ፈለጉ? ብዙዎችን ሰቅዞ የያዘ ጥያቄ ሆኗል። ሕይወትን ማራዘም ሳራህ ክሩዳስ እንደሚሉት ጨረቃ ላይ ቁፋሮ መጀመር ሰዎች ወደ ሌሎች ፕላኔቶች ለመጓዝ ያላቸውን ተስፋ የሚያለመልም ነው - በተለይ ደግሞ ወደ ማርስ። ሳራህ የሕዋ ጥናት ጋዜጠኛ ናቸው። ጨረቃ ትንሽ ቆይቶ ሰዎች ነዳጅ የሚቀዱባት መሆኗ አይቀርም ሲሉ ይተንብያሉ። ነዳጅ ሲባል የመኪና ወይ የባጃጅ አይደለም፤ ለሮኬት ማስወንጨፊያ የሚረዳ እንጂ። ጨረቃ ሃይድሮጅንና ኦክስጅን የሞላባት ሥፋራ ናት። እኒህ ንጥረ ነገሮች ደግሞ ለሮኬት ግንባታ ትልቅ ግልጋሎት አላቸው። ሮኬቶች በቂ ነዳጅ አላቸው ማለት ደግሞ ወደ ሌሎች ፕላኔቶች ለመጓዝ አይገዳቸውም ማለት ነው። ጨረቃ ከዚህም በላይ ሃብት አላት ይላሉ በዘርፉ ጥርስ ነቅለናል የሚሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ፕሮፌሰር ቤንጃሚን ሳቫኮ፤ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ዓለም ወደ ታዳሽ ኃይል እያመራች ነውና የጨረቃ ጥሬ ሃብት ያስፈልገናል ባይ ናቸው። ሰሴክስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የኤነርጂ ፖሊሲ ፕሮፌሰሩ ቤንጃሚን ከጨረቃ ላይ በሚገኝ ሃብት በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ መኪናዎችን ማምረት ይቻላል ይላሉ። «ለምሳሌ ሊቲየም ወይም ኮባልትን እንውሰድ። እኒህን ማዕድናት የምታገኙት ቻይና፣ ሩስያ ወይም ኮንጎ ነው። በብዛት ማግኘት ደግሞ እግጅ አዳጋች ነው።» ቢሆንም ይላሉ ፕሮፌሰሩ . . . ቢሆንም ከጨረቃ ላይ የሚገኘው ጥሬ ሃብት የዓለምን ችግር በአንድ ጊዜ ይቀርፋል ማለት አይደለም። የአሜሪካ - ቻይና ውጥረት ፕሬዝደንት ትራምፕ ጨረቃን ካልቆፈርን ያሉት ምናልባት ሃገራቸው እንደ ቻይና ካሉ ጋር ስትነፃፀር ያላት ጥሬ ሃብት አነስ ያለ ስለሆነ ይሆናል የሚሉ መላ ምቶች አሉ። ቻይና የምታወጣቸውን ማዕድናት በየክፍለ ዓለማቱ ትቸበችባለች። ሩስያም ብትሆን አሜሪካን ጥላት ሄዳለች። ትራምፕ ቻይና ያልደረሰችበትን ሥፋራ ለመድረስ የሚጣጣሩት ለዚህ ይሆናል። ትራምፕ በትረ ሥልጣኑን ከጨበጡ ወዲህ ከቻይና ጋር ዓይንና ናጫ ሆነዋል። ቀላል የማይባል ውጥረት ይስተዋላል። ፕሮፌሰር ቤንጃሚን እንደሚሉት ትራምፕ ያላቸውን ጉልበት ማሳያው ጨረቃ ላይ ሄድ ማዕድን መቆፈር ነው። ሕጉ ምን ይላል? ትራምፕ ትዕዛዝ ያስተላለፉበት ወረቀት 'መሬታዊ ሕግ' አይገታንም ሲል በግልፅ አስቀምጧል። የሰው ልጅ ያወጣቸው ሕግጋት ከመሬት ውጭ ምን ያህል ተፈፃሚ ይሆናል የሚለውም ግልፅ አይደለም። ሳራህ እንደሚሉት ማንም ሃገር ጨረቃ የኔ ናት አላለም። ነገር ግን ወደ ጨረቃ ተጉዘ ማዕድን ያወጣ የኔ ነው የማለት መብት እንዳለው ይታሰባል። ባለሙያዎች የሰው ልጅ ምድርን እንዳልሆነች አድርጓታል። አሁን የቀረው ከመሬት ውጭ ያለው ነው ይላሉ። በእኛ ዕድሜ የሚሆን ይሆን? እንደ ሳራህ ከሆነ 'ቴክኖሎጂው አለ'። አልፎም የግል ድርጅቶች መሣተፍ ስለመጀመሩ ካሰብነው በላይ በፍጥነት ሊከናወን ይችላል። «በፊት በፊት መንግሥታት ብቻ ነበሩ ይህን ማድረግ የሚችሉት። አሁን ግን የግል ኩባንያዎችና ግለሰቦች ፍላጎት ማሳየት መጀመራቸው የተሻለ ቴክኖሎጂና የገንዘብ አቅም እንዲኖር ያደርጋል።» «ጨረቃና ውቅያኖስ ላይ የሚደረግ ማዕድን ቁፋሮ፣ እንዲሁም ማርስን መጎብኘት በእኛ ሕይወት ዘመን የምናያቸው ናቸው» የሚል እምነት አላቸው ጋዜጠኛዋ።
47454968
https://www.bbc.com/amharic/47454968
ሴቶችና ወንዶች በምጣኔ ኃብቱ እኩል መብት ያላቸው የት ነው?
በአለማችን ስድስት ሃገራት ብቻ ናቸው ለሴቶችና ለወንዶች እኩል ህጋዊ የምጣኔ ኃብት መብት የሰጡት። እነማን ናቸው?
የአለም ባንክ አዲስ ባወጣው "ሴቶች፣ ቢዝነስ እና ህግ" በተባለ መግለጫው ላይ የሴቶችና የወንዶችን የኢኮኖሚ እኩልነት ሙሉ ለሙሉ መፍጠር የቻሉት ከ187 ሃገራት ስድስት ብቻ ናቸው ብሏል። በዋሽንግተን መቀመጫውን ያደረገው ተቋም የ10 ዓመታት ገንዘብ ነክና ህጋዊ የሆኑ በሴቶችና ወንዶች መካከል እኩልነት እንዳይሰፍን የሚያደርጉ እንደ በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ እናትነት፣ የቤት ውስጥ ጥቃትና ንብረት አስተዳደርን የመሳሰሉ መረጃዎችን ተመልክቷል። • ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ? • ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ? በአለም ባንክ መስፈርት መሰረት በእነዚህ መስኮች ላይ የሁለቱን ፆታዎች እኩልነት ሙሉ በሙሉ ማስፈን የቻሉት ስድስት ሃገራት ቤልጂየም፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ላቲቪያ፣ ሉክዘምበርግና ስዊድን ናቸው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶች በአማካይ 75 በመቶ የሚሆነውን ለወንዶች የተሰጠ ተመሳሳይ መብት እንደሚጠቀሙ መረጃው ያሳያል። ከቦታ ቦታ ያለው ያለ ልዩነት አማካይ ውጤቱ እንደየቦታው ይለያያል። ለምሳሌ በአውሮፓና መካከለኛው እስያ 84 በመቶ ሲሆን በመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ ደግሞ ወደ 47̄ በመቶ ዝቅ ይላል። • በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ አሜሪካ 83.75 በመቶ የሚሆን ውጤት ቢኖራትም ከመጀመሪያዎቹ 50 ሀገራት ውስጥ መካተት አልቻለችም። ህጎቿ የሴቶችን መብት በጣም የሚገታው ሳዑዲ አረቢያ ደግሞ 25.6 በመቶ በሆነ ውጤት የዝርዝሩ መጨረሻ ደረጃን ይዛለች። የመጀመሪያ ስራዋን ከጀመረች አንዲት የ25 ዓመት ወጣት ወይም ስራዋን እየሰራች ልጆቿን ለማሳደግ ጥረት ከምታደርገው እናት እስከ ጡረታ መውጫዋ የደረሰባትን ሴትን ውሳኔ ታሳቢነት አድርጎ የተሰራው ጥናት ሴቶች የሚወስዷቸው ውሳኔዎች እንዴት በህግ ተፅዕኖ ስር እንደሆኑ ተመልክቷል። " በማለት ክሪሰታሊና ጂኦርጂቫ የአለም ባንክ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ተናግራለች። "ብዙ ህግና ደንቦች ሴቶች የስራ መስኩን እንዳይቀላቀሉ ወይም የራሳቸውን ቢዝነስ እንዳይጀምሩ ይከለክሏቸዋል። ይህ ሴቶችን በኢኮኖሚ የማግለል ሂደት በኢኮኖሚው ውስጥ የመሳተፍ እና የስራ ሃይሉን መቀላቀል ላይ ዘላቂ የሆነ ጠባሳ ያስከትላል።" መግለጫው በአንዳንድ ሃገራት የተወሰደውንም አበረታች ውሳኔ አካቷል። የአለም ባንክ ባለፉት 10 ዓመታት 131 ሃገራት 274 የፆታ እኩልነትን የሚያሰፍኑ ህግና ደንቦችን ማፅደቃቸውን ገልጿል። • ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት ሴቶችን በስራ ቦታ መጠበቅ እነዚህ ለውጦች በ35 ሀገራት የሚገኙ ሴቶችን በስራ ቦታ ከሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶች መከላከል ያስቻሉ ሲሆን የዛሬ አስር ዓመት ከነበረው 2 ቢሊዮን ተጨማሪ ሴቶችን መከላከል ተችሏል። ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት ባለፉት 10 ዓመታት ብዙ የፆታ እኩልነትን የሚያሰፍኑ የህግ ለውጦችን ያደረጉ ሃገራት ናቸው። የወርልድ ባንክ ዘገባ የሴቶችን ሙሉ የስራ ህይወት ያጠና ሲሆን ስራ ከመፈለግ ጀምሮ፤ ቢዝነስ ማቋቋምን እና ጡረታ የማግኘት እድላቸውን አካቷል። በአለም አቀፍ ደረጃ 33 ሃገራት አባቶች ልጅ ሲወልዱ የስራ ፈቃድ እንዲወስዱ የሚፈቅድ ህግ እና 47 የሚሆኑት ደግሞ በቤት ውስጥ ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት ላይ ጠበቅ ያለ ህግ አፅድቀዋል። • የሴት ልጅ ግርዛት ምንድነው? የት እና ለምን ይፈጸማል? "የፆታ እኩልነትን ለማስፈን ህግ እና ደንቦችን ብቻ ማፅደቅ እና መቀየር በቂ እንዳልሆነ እናውቃለን። ህጎቹ መተግበር አለባቸው። ይህ እንዲሆን ደግሞ የመሪዎች ድጋፍ፣ የሁለቱም ፆታዎች ንቁ ተሳትፎ እና ለረጅም ጊዜ ተይዘው የቆዩ ባህላዊ አመለካከቶችን መቀየር ያስፈልጋል።" ብላለች ክርስታሊና ጂኦርጂቫ። በመጨረሻም ''መረጃው እንደሚያሳየው ህጎች ሴቶችን የሚያጠናክሩ እንጂ ማሳካት ከምንችላቸው ነገሮች ወደ ኋላ የሚጎትቱን መሆን እንደሌለባቸው ነው።" ብላለች።
news-41226132
https://www.bbc.com/amharic/news-41226132
ካለሁበት 1፡ በርካታ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን የሚጋሩት አስደናቂ የኤርትራው ወጣት የስደት ጉዞ!
ሽሻይ ተስፋዓለም እባላለሁ፤ በርካቶች ነሽነሽ እያሉ ነው የሚጠሩኝ። ተወልጄ ያደኩት ኤርትራ ውስጥ ኳዕቲት በምትባል አካባቢ ነው። ለሙዚቃና ለኮሜዲ ልዩ ፍቅር አለኝ። ይሁን እንጂ በሳዋ ወታደራዊ ሥልጠና ከወሰድኩ በኋላ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ነበር የሆንኩት።
የሜዲትራንያን ባህርና የሳህራ በረሃን ኣቋርጦ ጀርመን የደረሰው ኤርትራዊ ስደተኛ፡ ሽሻይ ተስፋኣለም (ነሽነሽ) በዚህ ሥራዬ ደስተኛ አልነበርኩም፤ የማገኘውም ገቢ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ ወላጆቼን ገንዘብ ስጡኝ እያልኩ አስጨንቅ ነበር። በጊዜ ሂደት የኤርትራን ኑሮ ጠላሁት። በሃገሪቷ ውስጥ የነበረው ነባራዊ ሁኔታ ለምፈልገው አይነት ኑሮ ምቹ ስላልነበረ ከሃገር ለመውጣት ወስንኩኝ። ከሁለት ዓመታት በፊት ከኤርትራ ለመሰደድ ስነሳ በቤተሰቦቼና በራሴ ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ አውቅ ነበር። ለስደት ምን አይነት ዝግጅት ማድርግ እንዳለብኝ እርግጠኛ አልነበርኩም። ሆኖም ግን ለጉዞ የሚያስፈልገኝን ገንዘብ ለማግኘት የነበረኝን ንብረት በሙሉ በመሸጥ፤ አጭር በሚባል ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ የእግር ጉዞ ጀመርኩ። የኤርትራን ድንበር በእግር ለማቋረጥ መሞከር በራሱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባት ማለት ነው። ፈጣሪ ረድቶኝ ከረጅምና እጅግ አድካሚ የእግር ጉዞ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ገባሁ። ከዚያም በኢትዮጵያ ዓዲሓርሽ በሚባል የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ለሰባት ውራት ያክል ቆይቻለሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረኝ ቆይታ ከኤርትራ የተሻለ ነጻነት ነበረኝ። ከሞላ ጎደል ካምፑ ለኔ ጥሩ ነበር። በሽረ እንዳስላሴ ከተማ ከሚገኝ የባህል ቡድን ጋር የሙዚቃ ሥራዎችን የመስራት እድልም አግኝቼ ነበር። በኢትዮጵያ ቆይታዬ የሰራኋቸው ሙዚቃዎችም አሉኝ። ከዚህም በተጨማሪ በሙዚቃ ሥራችን ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ህዝቦች የሰላምና የአንድነት መልዕክቶችን እናስተላልፍ ነበር። ሺሻይ ከኤርትራ ጀርመን ለመድረስ የተጓዘበት መንገድ ጉዞ ወደ ሊቢያ ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ቆይታዬ መልካም የሚባል ቢሆንም አውሮፓ የመግባት ህልሜን ማሳካት እንዳለብኝ ሁሌም ይሰማኛል። ከዚያም ፍላጎቴን ለማሳካት ለሌላ የስደት ጉዞ እራሴን አዘጋጅ ጀመር። ኢትዮጵያ ውስጥ ከተዋወቅኳቸው ጓደኞቼ ጋር በመሆን ጉዞ ወደ ሱዳን ተጀመረ። ለቀናት በእግርና በመኪና ረጅም ጉዞ ካደረግን በኋላ ሱዳን ገባን። ሱዳን ከደረስን በኋላ አውሮፓ የመግባት ፈላጎቴ እጅጉን ጨመረ። በሱዳን በቂ እረፍት እንኳን ሳናደርግ እያንዳንዳችን ለደላሎች 1600 የአሜሪካን ዶላር በመክፈል ረጅሙን የሊቢያ ጉዞ ጀመርን። የሊቢያው ጉዞ እጅግ ፈታኝና አደገኛ ነበር። የዓለማችንን ትልቁንና እጅግ ሞቃታማ የሆነውን የሰሃራ በረሃን ማለፍ ይጠይቃል። ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው የፈጣሪ እገዛ ተጨምሮበት እንጂ ሰሃራ በረሃን ማቋረጥ በእኔ አቅም የማይታሰብ ነበር። በበረሃው የአውሬ ሲሳይ ሳልሆን ከብዙ ድካምና ስቃይ በኋላ ሊቢያ እንደደረስን ተነገረን። ሊቢያ መድረሴን ስስማ አውሮፓ የደረስኩ ያህል ነበር የተሰማኝ። ካሳለፍኳቸው ስቃዮች መካከል ትልቁን የተጋፈጥኩት ሊቢያ ውስጥ ነበር። ከሊቢያ ወደ አውሮፓ መሄድ የሚፈልግ የሜዲትራንያን ባህርን በጀልባ ማቋርጥ አለበት። በሊቢያ ደግሞ ስደተኞችን የሚያዘዋውሩ በርካታ አደገኛ ደላሎች አሉ። እነዚህ ደላሎች ስደተኞችን የማሰር እና የማሰቃየት ልምድ አላቸው። እኔም በወቅቱ ወደ አውሮፓ ለመሄድ የሚያስፈልገው ገንዘብ ስላልነበርኝ ለሦስት ወራት በደላሎችና በህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በተደጋጋሚ ድብደባ ደርሶብኛል። ከሦስት ወራት ስቃይ በኋላ ከቤተሰቦቼ የተላከልኝን 2000 ዶላር ከፈልኩኝ። ከዚያም የሜዲትራንያንን ባህር ለማቋረጥ እንድዘጋጅ ተነገረኝ። ከጥቂት ቀናት በኋላ በግምት 1500 የምንሆን ስደተኞችን ደላሎቹ በሶስት ቡድን ከፍለው በአነስተኛ ጀልባዎች የሜድትራንያን ባህርን አቋርጠን ወደ ጣሊያን ለመግባት ጉዞ ጀመርን። ከነበረው ሰው ብዛት የተነሳ የጀልባዋን አካል ማየት ሁሉ ይከብድ ነበር። ጥቂት እንደተጓዝን ማለቂያ የሌለው ባህር እንጂ የመሬት አካል አይታይም ነበር። በዚህ እጅግ አስፈሪ በሆነው ባህር ላይ በሰላም የተጓዝነው ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነበረ። ከአንዷ ጀልባ በቀር እኔ የተሳፈርኩባት ጀልባን ጨምሮ ሁለቱ ጀልባዎች ችግር ገጠማቸው። እኔ ያለሁባት ጀልባ ተበላሸታ ስትቆም ሌላኛዋ ጀልባ ከአቅሟ በላይ ሰው ስለጫነች በዓይኔ እያያኋት ቢያንስ 500 ስደተኞችን እንደጫነች ሰመጠች። እጅግ በጣም አሰፈሪና አሰቃቂ ሁኔታ ነበረ። ስደተኞች የሜዲትራንያንን ባህር በማቋረጥ ወደ ኣውሮፓ ይገባሉ። ከሰዓታት በኋላ የሊቢያ የባህር ድንበር ጠባቂዎች ደርሰው እኛንና ከመስመጥ አደጋ የተረፉትን ወደ ሊቢያ በመመለስ እስር ቤት ወረወሩን። እስር ቤት እያለሁ ሦስተኛዋ ጀልባ ጣሊያን እንደደረሰች ሰምቻለሁ። ሊቢያ እስር ቤት ውስጥ እያለሁ እጀጉን ተስፋ ቆርጬ ነበር። በምንም አይነት ሁኔታ ግን ሊቢያ መቆየት እንደማልችል አውቅ ነበር። ለሁለተኛ ጊዜ ገንዘብ እንድከፍል የፈለጉት ደላሎች ለሊቢያ ፖሊሶች ጉቦ በመስጥት ካስፈቱኝ በኋላ 800 የአሜሪካን ዶላር አስከፍለው ዳግመኛ የሜዲትራንያን ባህርን ለማቋረጥ ተሰናዳሁ። ሁለተኛው ጉዞ ግን እንደፈራሁት ሳይሆን ጣሊያን ደረስኩ። እዚያ ግን የተቀበለኝ ፖሊስ ነበር። ጣሊያን ሃገር በእስርና በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ለ11 ወራት ቆይቻለሁ። ጣሊያን ለወራት ከቆየሁ በኋላ በጀርመን መንግሥት ፈቃድ በህጋዊ መንገድ ወደ ጀርመን እንድገባ ተፈቀደልኝ። በመጨረሻ ያለምንም ስጋት ተመችቶኝ ከጣሊያን ወደ ጀርመን በአውሮፕላን ገባሁ። በሜዴትራንያን ባህር ላይ ከመስመጥ መትረፌ ግን ሁሌም ይደንቀኛል። የጀርመን ኑሮ ጀርመን ከገባሁ ሦስት ወራት ተቆጥረዋል። በምዕራባዊ ጀርመን ሙንስተር ከተማ ውስጥ ነው የምኖረው። ህይወትን በጀርመንና በኤርትራ ከቶ ማወዳደር አይቻልም። ጀርመን እጅግ በጣም ጥሩ ሃገር ናት። ከደጃፌ ጀምሮ ዓይንን የሚማርኩ ነገሮችን አያለሁ። በጣም ንፁህና አረንጓዴ አካባቢ ነው። በጣም ባማር ቤት ውስጥ ነው የምኖረው። አሁን ሥራ ከመጀመሬ በፊት የጀርመን ቋንቋ መማር ግዴታ ስለሆነ ለስድስት ወራት ጀርመንኛ ቋንቋን እየተማርኩኝ ነው። ኣረንጓዴ አከባቢ፡ ማፐን ዲ፡ ጀርመን ኤርትራ እያለሁ ሁል ጊዜ መብላት የምፈልገውን ዶሮ እዚህ እንደልቤ አገኛለሁ። እዚህ ሁኜ የሚናፍቀኝ ነገር ቢኖር ኤርትራ ውሰጥ ያሳለፍኩት ጥሩ ጊዜና የአብሮ አደግ ጓደኞቼ ፍቅር ነው። የወደፊት ዕቅድ በአጠቃላይ ለጥበብ ልዩ ፍቅርና ፈላጎት አለኝ። ወደፊት የሙዚቃ ሥራን መስራት እፍልጋለሁ። ከዚህም በተጨማሪ በአማርኛና በትግረኛ የተፃፉ የፊልም ድርስቶች አሉኝ። እንዚህን ድርሰቶች ወደ ፊልም የመቀየር እቅድ አለኝ። ኤርትራ እያለሁ የአማርኛ ፊልሞችን በብዛት ከማየቴ የተነሳ ተዋናይት ሠላም ተፋዬን እጅግ አፈቅራታለሁ። ወደፊትም ድርሰቶቼን ከሠላም ጋር ወደ ፊልም ለመቀየር እመኛለሁ። ለላይን ጽጋብ እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 2፡ ''ከምንም በላይ እናቴን ማየት እፈልጋለሁ'' ካለሁበት 3፡ "ኢትዮጵያ ውስጥ የማውቀው ሁሉም ነገር ይናፍቀኛል"
news-50321279
https://www.bbc.com/amharic/news-50321279
"የአንበጣ መንጋው ጉዳት ማድረሱን ባንክድም፤ ምን ያህል እንደሆነ ለጊዜው አልታወቀም" የግብርና ሚኒስቴር
ከየመንና ከሶማሌላንድ እንደመጣ የተነገረው የአንበጣ መንጋ በተለያዩ አገሪቷ ክፍሎች ውድመት እያስከተለ እንደሆነ እየተነገረ ነው። በአማራ ክልል፣ በአፋር፣ ደቡባዊ ትግራይ፣ ምስራቅ ኦሮሚያና ምስራቅ ሀረርጌ አንዳንድ አካባቢዎች መከሰቱ ይታወቃል። መንጋው ቀደም ሲል ያልገባባቸው ቦታዎች ላይ አሁንም እየዘመተ ነው።
• ከሶማሌላንድና የመን የመጣው አንበጣ በአምስት ክልሎች ተከስቷል የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል በቃሉ ወረዳ ከሁለት ቀናት በፊት የአውሮፕላን ርጭት ለማድረግ ተሞክሮ በአካባቢው የመልክዓ ምድር አቀማመጥ ምክንያት ሳይሳካ መቅረቱን የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አብዱ እንድሪስ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አቶ አብዱ አክለውም በሰው ኃይል ሰብሉን ለመሰብሰብ ጥረት ቢደረግም ያለጊዜው በመሰብሰቡ ከውድመት እንደማይድን ያክላሉ። በዚያው ወረዳ ያነጋገርናቸው አርሶ አደር አህመድ ሀሰን "የአንበጣ መንጋው በተለያዩ ፎቶዎች ላይ እንደሚታየው አይደለም፤ ረዥምና ሰፊ ነው" ይላሉ። ከአንዱ ሥፍራ ሲያባርሩት ወደ አንዱ የሚሰደደው የአንበጣ መንጋ ሦስተኛው ዙር ትናንት እነርሱ ጋር ውሎ አራተኛው ከሌላ ቦታ እንደሚመጣ ተነግሯቸው በስጋት እየጠበቁ እንደሆነ ይገልፃሉ። አቶ አህመድ እንደሚሉት በአካባቢው እርሳቸውን ጨምሮ በርካታ አርሶ አደሮች ሰብላቸው ወድሞባቸዋል። የአንበጣ መንጋው በዚያው ደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳም በተለያዩ ቀበሌዎች ተከስቶ ዛሬ ወደ ሰሜን ወሎ ዞን መግባቱን ቢሰሙም አሁንም ስጋቱ እንዳላበቃ እና እየመጣ ያለ መንጋ መኖሩን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ይገልፃሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ በባህላዊ መልኩ በጩኸትና በዛፍ ዝንጣፊ በማባረር ለመከላከል ቢሞከርም ተከታትሎ የሚመጣው መንጋ አሁንም ፈተና እንደሆነ ነው። • የአንበጣ መንጋው እስካሁን በሰብል ላይ ጉዳት አላደረሰም በአርጎባ ብሔረሰብ አስተዳደር ላይም በ6 ቀበሌዎች ተከስቷል። የመከላከል ሥራ ሲሠሩ ቢቆዩም አሁንም በሁለት ቀበሌዎች ላይ በስፋት ይገኛል ያሉት የወረዳው ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ አህመድ ጌታቸው ናቸው። "አርጎባ ተራራማ አካባቢ ነው፤ ዳገት ቆፍረው ነው ሰብል የሚያመርቱት ከዛም ብሶ አንበጣ በላው። ስጋት ላይ ነው ያለነው" ብለዋል። ከሳምንት በፊት ከወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ያገኙት መረጃን ጠቅሰው እስካሁን በወረዳው 275 ሄክታር ሰብል ላይ ጉዳት መድረሱን የገለፁት አቶ አህመድ በሚዲያዎች ላይ በሰብል ላይ ጉዳት አለመድረሱን የሚዘገበው ትክክል አይደለም ሲሉ ተችተዋል። በዚሁ ወረዳ አርሶ አደር ዙቤር ሸህ አዩብ ሰብላቸው ከወደመባቸው አንዱ ናቸው። "አወዳደሙ ከመውደምም በላይ ነው፤ ሰብሉን ለመሰብሰብ በገባንበት ሰዓት ድንገት ከደረሰ ፊትም ጆሮም ይመታል፤ እዚያው እህሉ ውስጥ ነው ቁጭ የምንለው፤ የምናደርገው የለም" ሲሉ እርሳቸው 2 ሄክታር ላይ ያለ ሰብል እንደወደመባቸው ገልፀዋል። እስካሁን በሰብል ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልቶ ጥያቄ የቀረበላቸው በግብርና ሚኒስቴር የዕፅዋት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ዘብዲዎስ ሰላቶ፤ በተባይ መከላከል ሥርዓት ውስጥ ጉዳት የሚታወቀው መከላከሉ ሲጠናቀቅ ነው ብለዋል። ከሥር ከሥር ጉዳቱን ለመግለፅ ጊዜ እንደሌላቸው የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ "ጉዳት ማድረሱ ባይካድም የጉዳቱን መጠን ግን ምን ያህል እንደሆነ አናውቀውም፤ ይሄ ነው ብለን አንገልፅም፤ የራሱ ሂደት ስላለው" ብለዋል። በአብዛኛው በመከላከል ሂደቱ ላይ ትኩረት እንዳደረጉ ገልፀዋል። ይሁን እንጅ በፀጥታ ችግር ምክንያት፣ በቦታዎች የመልክዓ ምድር አቀማመጥ እንዲሁም በአንዳንድ ቦታዎች ጫት ላይ ጉዳት ያደርስብናል በሚል ምክንያት የኬሚካል ርጭት ለማካሄድ ተግዳሮት እንደገጠማቸው ሳይጠቅሱ አላለፉም። ኬሚካሉ በተጠኑ ቦታዎች ላይ በጥንቃቄ እንደሚረጭም በመግለፅ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። አንበጣን በጭስ፣ በጥይት፣ በርችት፣ በጩኸት፣ በጅራፍ. . ? ማህበረሰቡ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ድምፅ የሚፈጥሩ ነገሮችን በማቃጨል፣ በጅራፍ፣ በጥይት፣ በጩኸት፣ በርችት፣ በዘፈን፣ በፉጨት፣ ጨርቅ በማውለብለብ ለመከላከል ሲሞክሩ ተስተውለዋል። ይህ ልማድ በሳይንስስ ይደገፍ ይሆን? አንበጣ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አዲስ አይደለም የሚሉት አቶ ዘብዲዎስ አንበጣን በባህላዊ መንገድ መከላከል በሳይንስም የሚደገፍ ነው ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ኢትዮጵያ የበረሃ አንበጣ መከላከል አባል የሆነችው በአውሮፓዊያኑ 1940/42 አካባቢ ነው። ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል በነበረችበት ጊዜ ቀይ ባህር አካባቢና ከሌሎች አረብ አገራት አንበጣ ይሻገር ስለነበር አንበጣን በባህላዊ መንገድ የመከላከል ልማድ ነበር። አንበጣው ሰብል ላይ እንዳያርፍ የማባረር ሥራም ይሠራ ነበር። ነገር ግን ከቦታ ቦታ የመረጃ ልውውጥ መኖሩ እጅግ አስፈላጊ ነው። ወደ ሄደበት አካባቢ ሪፖርት ማድረግ መዘንጋትም የለበትም ይላሉ። • የኢትዮጵያዊቷ ህክምና መቋረጥ በደቡብ አፍሪካ አነጋጋሪ ሆነ ይሁን እንጅ አሁን በተለያዩ አካባቢዎች አንበጣን በጥይት ለማባረር የሚደረገው ሙከራ ትክክል አይደለም ሲሉ ነቅፈዋል- በጥይት የማባረር ተግባር በአውሮፓዊያኑ 2016 ብዙ ዋጋ እንዳስከፈለ በማስታወስ። እንደ ዳይሬክተሩ ከሆነ በወቅቱ ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ ከምስራቅ ኢትዮጵያ መከላከል አምልጦ ወደ አዲስ አበባ የገባው በጥይት ምክንያት ነው። ከዚያም ወደ ሰሜን የአገሪቷ ክፍሎች አምርቶ በርካታ ቀበሌዎችን ማዳረሱ የቅርብ ጊዜ ትውስታቸው ነው። በመሆኑም "ብዙ ጭስ ማጨስ ሳያስፈልግ፤ በጭስ፣ በቆርቆሮ ድምፅ፣ በልጆች ጩኸት ድምፅ፣ በተለይ በጅራፍ ከሰብል ላይ መንጋውን ማባረር በቂ ነው" ሲሉ ይመክራሉ። ነገር ግን ከሰብል አቅራቢያ ያለ የግጦሽ መሬት ላይ፣ ደን አካባቢ እና ሌሎች አካባቢዎች ሄዶ ካረፈ ማደሪያውን ብቻ መከታተል እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ። በርካታ ሕዝብ የማይኖርበትና ለመጠጥና ለምግብነት የሚውሉ ሰብሎች ባሉበት ቦታ ካልሆነ ፀረ ተባይ ኬሚካል መርጨት እንደሚቻል በመግለፅ የመከላከሉን ሥራ ማቅለል እንደሚቻል አቶ ዘብዲዎስ አስገንዝበዋል። የአንበጣ መንጋው አሁንም በኢትዮጵያ እንደሚቀጥልና ወደ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኦማን፣ የመን፣ ሕንድ፣ ፓኪስታን፣ እንዲሁም በሰሜን አፍሪካ አገሮችን ጭምር ሊከሰት እንደሚችል ትንበያ መኖሩን አቶ ዘብዲዎስ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
news-55999126
https://www.bbc.com/amharic/news-55999126
ትግራይ፡ መንግሥት “20 ሺህ የኤርትራ ስደተኞች የገቡበት ጠፋ” የተባለው ሐሰት ነው አለ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከ20 ሺህ የኤርትራ ስደተኞች በላይ የገቡበት ጠፋ ተብሎ በማሕበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ የሐሰት ነው አለ።
ከአንድ ሳምንት በፊት በትግራይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ 20 ሺህ የኤርትራ ስደተኞች ከህጻጽ እና ሽመልባ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ጠፍተዋል የሚል ዜና በበርካታ መገናኛ ብዙሃን ተዘግቦ ነበር። በተጨማሪም በትግራይ ክልል የሚገኙ ሁለት የኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን በቅርቡ ልትዘጋ መሆኑን የስደት እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቋል። እንደ ኤጀንሲው ከሆነ የሚዘጉት መጠለያ ጣብያዎች ሽመልባ እና ህጻጽ የተሰኙት ሲሆኑ ለዚህም ምክንያት ነው ያሉትን ዘርዝረዋል። ሽመልባ የተመሰረተበት ቦታ ከኢትዮ-ኤርትራ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለመዘጋቱ በምክንያትነት ሲጠቀስ፣ በበረሃማ ቦታ የሚገኘው ህጻጽ፤ ለኑሮም ሆነ ለስደተኞች መጠለያነት አመቺ ባለመሆኑ በተመሳሳይ እንደሚዘጋ ኤጀንሲው ገልጿል። በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ከአገራት አዋሳኝ ድንበር ቢያንስ በ50 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ መገንባት እንዳለበት እንደሚያስቀምጥ ተገልጿል። የህወሓት ኃይሎች ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ በክልሉ ፌደራል መንግሥት "የሕግ ማስከበር ዘመቻ" እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ ግጭት መቀስቀስ በኋላ በርካታ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በክልሉ ስለተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ አሳሳቢነት እየተናገሩ ሲሆን ከህጻጽ እና ሽመልባ ስደተኛ ጣብያዎችም ጦርነቱን የሸሹ 20 ሺህ ኤርትራውያን የደረሱበት እንደማይታወቅ ተዘግቦ ነበር። የስደት እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ተስፋሁን ጎበዛይ ከሁለቱ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የጠፋ ስደተኛ የለም ሲሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ “19 ሺህ ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ እናውቃለን። በረሃብ እና በሕመም የተጎዱ ሊኖሩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ የጠፋ ሰው የለም” ብለዋል። በኢትዮጵያ ከ200 ሺህ በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች እንዳሉ ይገመታል። የስደት እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ተስፋሁን ጎበዛይ በትግራይ ክልል ደግሞ ከግጭቱ በፊት ከ92 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደነበሩ ተናግረዋል። ከእነዚህ መካከል 49 ሺህ የሚሆኑት በክልሉ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ይኖሩ ነበር። አቶ ተስፋሁን በትግራይ ክልል በሚገኙቱ ዓዲ ሃሩሽ፣ ማይ ዓይኒ፣ ሕጻጽ እና ሽመልባ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ግጭቱ ሲከሰት የእርዳታ አቅርቦት ተቋርጦ ነበረ ብለዋል። “በሕግ የማስከበር ስራው ወቅት ላይ በተለያዩ ምክንያቶች የእርዳታ ሥራ ተስተጓጉሏል። በተለይ በሕጻጽ እና ሽመልባ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በርካታ ኦፕሬሽን ይካሄድ ስለነበረ ሥራ መስራት አልተቻለም። በስፍራው የነበሩ ሰራተኞች አካባቢውን ጥለው ወጥተዋል። ሰብዓዊ ድጋፍ ያደርጉ የነበሩ ተቋማትም ሰራተኞቻቸውን ከስፍራው አስወጥተዋል። በእነዚህ ምክንያቶች በአራቱ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ሥራ ቆመ” ብለዋል። በዚህም ምክንያት በመጠለያ ጣቢያዎቹ የነበሩ ስደተኞች ለከፋ ችግር ተጋልጠው ነበር። በተለይ በሕጻጽ እና ሽመልባ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የነበሩ ስደተኞች፤ መጠለያ ጣቢያዎቹን ጥለው ወጥተው ነበር ሲሉ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። ከመጠለያ ጣቢያዎቹ የወጡ ስደተኞችን ወደ መጠለያ ጣቢያዎች ለመመለስ በተሰራው ሥራ ወደ 5ሺህ የሚጠጉ “ሠላም ወዳለበት” ዓዲ ሃሩሽ እና፣ ማይ ዓይኒ መጠለያዎች መመለስ እንደተቻለ የስደት እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ተስፋሁን ጎበዛይ ተናግረዋል። 3ሺህ ስደተኞች ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚገኙ እና የተቀሩት ስደተኞች ደግሞ በትግራይ እና አማራ ክልል ከተሞች ተበታትነው እንደሚገኙ አስረድተዋል። ተበታትነው የሚገኙ ስደተኞችን አገልግሎት ማግኘት ወደሚችሉበት አንድ ስፍራ የመሰብሰብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል። በሌላ በኩል ዳይሬክተሩ፤ አንዳንድ ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ኤርትራ እንደሄዱ መስማታቸውን ገልጸው፤ “በትክክልም ወደ ኤርትራ ስለመሄዳቸውን እና ቁጥራቸው ምን ያክል እንደሆነ የምናጣራው ይሆናል” ብለዋል። በክልሉ የተከሰተው ግጭት በርካቶች ቀያቸውን ጥለቀው እንዲሰደዱ አድርጓል። ከ2 ሚሊዮን በላይም በዚያው በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው ይገኛሉ። ከ50 ሺህ በላይ ደግሞ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ሸሽተዋል። የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢዎች ከትግራይ ክልል እየተሰደዱ ያሉ ዜጎችን ለመድረስ እንዲቻል ያለገደብ አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠር በተደጋጋሚ ጠይቀዋል። በክልሉ ያለው ሁኔታም ወደ ሰብዓዊ ቀውስ ሊሸጋገር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በትግራይ ክልል በተከሰተው ግጭት ምን ያህል ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም።
news-55287300
https://www.bbc.com/amharic/news-55287300
ትግራይ ፡ የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ የኤርትራውያን ስደተኞች ሁኔታ አሳስቦኛል አለ
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተቋም በትግራይ ወታደራዊ ግጭት ከተከሰተ በኋላ በክልሉ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለጸ።
ድርጅቱ እነዳለው ኤርትራውያን ስደተኞች መገደላቸውን እንዲሁም በግድ ታፍነው ወደ ኤርትራ እየተወሰዱ እንደሆ የሚያሳዩ ሪፖርቶች እጅግ እንዳሳሰበው አስታውቋል። የተመድ የስደተኞች ክንፍ ኃላፊ ፊሊፖ ግራንዲ እንዳሉት፤ ስደተኞቹን እንዳጋጠሙ የተጠቀሱት ድርጊዎች ተፈጽመው ከሆነ ከፍተኛ የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ነው ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ትግራይ ውስጥ ወደሚገኙ አራት የስደተኞች መጠለያዎች መግባት መቻል እንዳለበት አመልክተው፤ ስደተኞቹ ያለፍላጎታቸው በግድ ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ መደረጉ ተቀባይነት የለውም ሲሉም አክለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት መከላከያ ሠራዊቱ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው አብቅተወል ቢልም፤ የህወሓት ኃይሎች ውጊያው በተለያዩ ግንባሮች መቀጠሉን ተናግረዋል። አርብ ዕለት ኤርትራውያን ስደተኞችን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዳለው የተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ምንም አይነት ስጋትን የሚደቅን እንዳልሆነ አመልክቶ፤ ነገር ግን በተሳሳተ መረጃ ሳቢያ ከካምፖቻቸው ወጥተው ወደ አዲስ አበባ የሄዱ ስደተኞች እንዳሉ ገልጿል። ጨምሮም በትግራይ ክልል ከሚገኑ የስደተኞች መጠለያዎች ወደ አዲስ አበባ የሄዱ ስደተኞችን እየመለሰ እንደሆነም አስታውቋል። ትግራይ በሚገኙ የስደተኛ ማቆያዎች ካምፖች ውስጥ በአገራቸው ፖለቲካዊ እስርና አስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎትን የሸሹ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ኤርትራውያን ስደተኞች እንደሚገኙ ይነገራል። መንግሥት ባወጣው መግለጫ፤ “በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸውና ትክክለኛ መረጃ ያላገኙ ስደተኞች በሕገ ወጥ መንገድ ከማቆያ ካምፖቹ እየወጡ ነው። መንግሥት እነዚህን ስደተኞች ወደ የካምፖቻቸው እየመለሰ ነው” ብሏል። መንግሥት ለስደተኞቹ የሚሆን ምግብ አቅርቦት ወደ ካምፖቹ እየላከ መሆኑንም አመልክቷል። ይህንንም ተከትሎ ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ አዲስ አበባ ካሉ ኤርትራውያን ስደተኞች “በፍርሀት የተሞላ” የስልክ ጥሪ ደርሶኛል ብሏል። ለስደተኞቹ ስጋት ዋነኛው ምክንያት በአውቶብስ ወደ ትግራይ እንደሚወሰዱ ቢነገራቸውም ካለፍላጎታቸው ወደ ኤርትራ እንወሰዳለን ብለው እንደሚፈሩ ተናግረዋል። አንዲት ኤርትራዊት እንዳለችው፤ "ኤርትራ የኢትዮጵያን መከላከያ እንዲያግዙ ወታደሯቿን በመላኳ፤ የትግራይ ተወላጆች ኤርትራውያኑ ስደተኞች ላይ ተቆጥተዋል።" ስደተኛዋ ለሮይተርስ እንደተናገረችው፤ “አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ባለቤቴን ደብድበውታል። አገራችሁ መጥታ እየወጋችን ነው ይሉናል። እኛም እንገድላችኋለን ሲሉን ፈራን” ማለቷን የዜና ወኪሉ ዘግቧል። አሜሪካ፤ የኤርትራ ኃይሎች ትግራይ ገብተዋል የሚል መረጃ ብታወጣም፤ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሐሰት ነው ሲሉ አስተባብለውታል። ፊሊፖ ግራንዲ እንዳሉት፤ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) እና አጋሮቹ አራቱ በትግራይ የሚገኙ የስደተኞች ካምፖች ውስጥ መግባት አልቻሉም። “ይሄ የስደተኞቹን ደኅንነት እና ህልውና ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ይከታል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አያይዘውም “ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ኤርትራውያን ስደተኞች እየተገደሉ፣ በግድ ታፍነው ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ እየተደረጉም እንደሆነ የሚያሳዩ አሳሳቢ ሪፖርቶች ደርሰውናል። እነዚህ ሪፖርቶች ከተረጋገጡ ከፍተኛ የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ነው” ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ስደተኞችን የመጠበቅና ዓለም አቀፍ ሕግን የማክበር ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል። ከሁለት ዓመታት በላይ በህወሓት እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል የዘለቀው ፍጥጫ በትግራይ ክልል ምርጫ መደረጉን ተከትሎ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ. ም የህወሓት ኃይሎች በትግራይ ክልል በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸው ይታወሳል። ከሦስት ሳምንት ግጭት በኋላ የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በመንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ስር እንደገባችና ወታደራዊ ዘመቻው እንዳበቃ መገለጹ አይዘነጋም። የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎች የሰብአዊ እርዳታ አቅራቢ ተቋማት መንግሥት ለስደተኛ ካምፖችና የመሠረታዊ እርዳታ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች ለማድረስ ነጻ የእንቅስቃሴ ፈቃድ ሲተይቁ የቆዩ ሲሆን፤ ለዚህም ተባበሩት መንግሥታት ከመንግሥት ጋር ከስምምነት መድረሱ ይታወቃል።
news-48242592
https://www.bbc.com/amharic/news-48242592
የየመን ጦርነት፡ የሁቲ አማፂያን የሁዴይዳን ወደብ ለቀው እየወጡ ነው
ባለፈው ታህሳስ ወር ከተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ የየመን ሁቲ አማፂያን ቁልፍ የሆኑ ወደቦችን ለቀው መውጣት ጀምረዋል። ይህም ከስምምነቱ በኋላ በየመን ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት በሰላማዊ መልኩ ለመቋጨት ዋና እርምጃ እንደሆነ ተነግሯል።
• በስለላ ወንጀል የተጠረጠረው ጥንብ አንሳ የሁቲ አማፂያንና የመንግሥት ወታደራዊ ኃይሎች ከሁዴይዳ ወደብ ለቀው የወጡት በአካባቢው የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ለማስቻል ነው ተብሏል። ይሁን እንጂ የየመን መንግሥት አማፂያኑ ሁኔታውን ለመቀልበስ የተጠቀሙት ዘዴ ነው ሲል እምነት እንዳልጣሉባቸው ገልጿል። የቀድሞ የመንግሥት ባለሥልጣን የነበረው አል ሃሰን ታሄር አማፂያኑ በሌሎች የሁቲ ወታደሮችን ተክተዋል ሲሉ ወቅሰዋቸዋል። ቢቢሲ ያስቀረው ተንቀሳቃሽ ምስል የሁቱ አማፂያን ከአንድ መኪና ላይ ተሳፍረው ሲወጡ የሚያሳይ ሲሆን ወታደሮቹ በአራት ቀን ውስጥ በሌላ ቦታ ይመደባሉ ተብሎ ይጠበቃል። • 85 ሺ የየመን ህጻናት በምግብ እጥረት ሞተዋል ኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል የተባበሩት መንግሥታትን ቃል አቀባይ ፋርሃን ሃቅን ጠቅሶ እንደዘገበው አማፂያኑ ለቀው እየወጡ መሆናቸው ተዘግቧል። በየመን የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኛ እንዳሉት አሁን እየሆነ ያለው የመጀመሪያ እርምጃ ነው ። "በዚህ እርምጃ የየመን መንግሥት ደስተኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የቤት ሥራ ይጠብቀናል" ሲሉ ማርቲን ግሪፊት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሁለቱም ወገኖች ዘንድ አለመተማመን እንዳለም አክለዋል። • አብረሃም መብራቱ፡ የየመንን ብሔራዊ ቡድን ለትልቅ ውድድር ያበቃ ኢትዮጵያዊ በየመን ባለፉት አራት ዓመታት በነበረው የርስ በርስ ጦርነት በትንሹ 6,800 የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎች የተገደሉ ሲሆን ከ10,700 በላይ የሚሆኑት ለጉዳት ተዳርገዋል። እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈው ቀድሞ መከላከል በሚቻሉ በሽታዎች ፤ እንደ የተመጣጠነ ምግብ እጦት፣ በሽታዎች፣ ደካማ የጤና እንክብካቤ መኖር ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል።
news-42791349
https://www.bbc.com/amharic/news-42791349
ካለሁበት 19፡ እንጀራ ማግኘት የማይታሰብባት ከተማ - ሌጎስ
ቤቴልሔም ብርሃኔ እባላለሁ። ናይጄሪያ-ሌጎስ ነው የምኖረው። የምሰራበት መስሪያ ቤት ጄነራል ኤሌትሪክስ ይባላል። መስሪያ ቤቱ የሁለት ዓመት የድህረ ምረቃ ፕሮግራም አለው። በየስድስት ወሩ ከሃገር ሀገር እየተዘዋወርኩ ነው የምሰራው።
ይህ የናይጄሪያ ቆይታዬ አራተኛው ሀገር ነው። ባለፈው ነሐሴ ወር ስለሆነ ወደዚህ የመጣሁት በዚህ በጥር ወር መጨረሻ የስድስት ወር ቆይታዬ ይጠናቀቃል። ወደ ሌጎስ ከመምጣቴ በፊት ለስድስት ወር እየቆየሁ የሰራሁባቸው ከተሞች በ2016 ናይሮቢ - ኬንያ፣ ከዚያ ጆሃንስበርግ - ደቡብ አፍሪካ፣ ቀጥሎ ደግሞ ቡዳፔስት - ሐንጋሪ ነበር። ከዚህ ቀጥሎ አዲስ አበባ የምመለስ ይመስለኛል። ሌጎስ እና አዲስ አበባ በሌጎስ ብዙ ነገሮችን በኢንተርኔት መገበያየት ይቻላል። ለሀገሩ አዲስ ለሰዉ እንግዳ በሆንኩባቸው ሀገራት ውስጥ ምግብ ለማዘዝ እና ሌሎች ነገሮች ለመግዛት የኢንተርኔት ግብይት መኖሩ ሕይወቴን ቅልጥፍ አድርጎልኛል። በባንክ ካርዴ የምፈልገውን ማዘዝና መግዛት መቻሌ ሌጎስ ከአዲስ አበባ የተለየች እንደሆነች እንዲሰማኝ አድርጓል። ከተማዋም ብትሆን የምዕራባውያን ስሜት ይታይባታል። ምናልባት በቅኝ ግዛት ስር ስለነበሩ ሊሆን ይችላል። በእርግጥ የራሳቸው ባህል የሚንፀባረቅበት ቦታም አለ ግን ምዕራባዊነት ግን ገኖ ይታያል። ለእኔ በጣም አስፈላጊ ነው የምለው እንጀራ ነው። ከሄድኩባቸው በርካታ ቦታዎች በተለየ እንጀራ ማግኘት የማይታሰብ የሆነባት ከተማ ሌጎስ ናት። እንጀራ ሳልበላ ለረጅም ጊዜ የቆየሁበት ሀገር ይህ ነው። በዚህ የተነሳም የእነሱን ምግብ መልመድ ፈተና ሆኖብኝ ቆይቷል። በጣዕምም ሆነ በሽታው ከእኛ ፈፅሞ ይለያል። በሌጎስ ቆይታዬ ፍላጎቴ ተከፍቶልኝ የምበላቸው የባህል ምግባቸው ከሩዝ የሚሰራውን ጆሎፍ፣ ከሙዝ ዝርያ የሚሰራውን ፕላንቴይን እና ደረቅ ያለ ጥብስ ሆኖ እነሱ ሱያ የሚሉትን ነው። ትዝ አለኝ ሀገሬ ከኢትዮጵያ የሚናፍቀኝ ምግቡ ነው። እዚህ ባለሁበት ጊዜ ሁሉ ኢትዮጵያን ከሚያስታውሰኝ ነገራቸው መካከል የባህል ልብሳቸው ነው። አርብ አርብ የባህል ልብስ ይለብሳሉ፤ በሠርግ ወቅትም እንዲሁ። ምንም እንኳ የባህል ልብሱ የኢትዮጵያውያን ጋር ባይመሳሰልም ሀገሬን ግን ያስታውሰኛል። ከቤቴ መስኮት ወዲያ ማዶ አሻግሬ ስመለከት ደስ የሚለኝ በውቅያኖሱ ላይ የሚያልፈው በአፍሪካ ትልቁ የሆነው ድልድይ ይታየኛል። ይህ ማራኪ እይታ መንፈሴን ያድሰዋል። ወደ ሌጎስ ከተማ ከመምጣቴ በፊት ሰምቼ ጠንቃቃ እንድሆን ካደረጉኝ መረጃዎች መካከል በከተማዋ የዕገታ ወንጀል መኖሩን መስማቴ ነው። ከመምጣቴ በፊት ይህንን መስማቴ እዚህ እንደደረሰኩ ወጥቼ ከተማዋን እንዳላያት አድርጎኝ ነበር። ቀስ በቀስ ግን እየለመድኩት ስመጣ እንደሚወራው እንዳልሆነ አየሁ። በእርግጥ በቴሌቪዥን ሰዎችን በእንዲህ አይነት ተግባር ማስደንገጥ (ፕራንክ) ያደርጋሉ። ስለሌጎስ ሲወራ ወንጀል እና ዕገታ እንደሚበዛ ነው የሰማሁት። ነገር ግን ሁሉን ስለምደው የሚወራውን ያህል እንዳልሆነ ተረድቻለሁ። እኔም ላይ እስካሁን ምንም ነገር አልደረሰም። ሌጎስን መቀየር ቢቻል ከሌጎስ ጋር ሲነፃፀር አዲስ አበባ በጣም የተረጋጋች ከተማ ናት። ሌጎስ ግን ሁሉ ነገሯ ወከባ ነው። መኪና መንዳት ቀርቶ ጭራሽ ማሰቡ በጣም ይከብዳል። ብችል የኢትዮጵያዊያንን መረጋጋት ባጋባባቸው ደስ ይለኛል። ሌላው እኔ በራሴ ተንቀሳቅሼ የምፈልገውን ገበይቼ ወደ ቤቴ መመለስ እፈልግ ነበር። ወጣ ብዬም በእግሬ መንሸራሸርና አየር መቀበል የስደስተኝ ነበር። ነገር ግን የወንጀል ስጋቱ ከፍ ያለ በመሆኑ በመኪና የሚያደርሰኝን ሾፌር መጠበቅ የግድ ስለሆነ ይጨንቀኛል። አየሩም በጣም ስለሚሞቅ በእግሬ መንሸራሸር ባለመቻሌ ምቾት አይሰማኝም። አሁን ቢሆንልኝ የምመኘው ነገር ቢኖር፤ ድንገት ተነስቼ ቤተሰቦቼ መካከል በመገኘት አብሬያቸው ማዕድ ብቋደስ እና በተለይ የገና በዓልን ከቤተሰቦቼ ጋር ባሳልፍ ደስ ይለኝ ነበር። ለክሪስቲን ዮሐንስ እንደነገረቻት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ፦ ካለሁበት 20፡ አንዳንድ ቦታዎች ጀጎልን ያስታውሱኛል ካለሁበት 21፡በእንግሊዝ ሰው ወደየግል ጉዳዩ ነው የሚሯሯጠው
news-45662599
https://www.bbc.com/amharic/news-45662599
ከደሴ ወደ አሰብ የትራንስፖርት አገልግሎት ሊጀመር ነው
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተፈጠረውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሁለቱ አገራት ህዝቦች በተለያየ መልኩ የንግድና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ከአዲግራት ወደ ዛላምበሳ አስመራ የአውቶብስ ጉዞ መጀመሩም አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ከሰሞኑም ከመስከረም 14፣ 2011 ዓ.ም አንስቶ ከደሴ ከተማ ወደ አሰብ የትራንስፖርት ስምሪት መጀመሩን የሚገልፁ ማስታዋወቂያዎች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ ይገኛል፡፡ እውን ጉዞው ተጀምሯል? • ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች • የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ሲታወስ አቶ ተፈሪ ኃይሌ በደሴ ከተማ ጥምረት በተሰኘ የአገር አቋራጭ አውቶብሶች ባለንብረት ማህበር ሊቀመንበርና ባለ ሃብት ናቸው፡፡ "ጉዞው አልተጀመረም እያስተዋወቅን ነው፤ ታሪፍና አንዳንድ ሂደቶች ይቀራሉ" ብለዋል፡፡ ስምሪቱ ከደሴ ከተማ አይጀምር እንጂ ከሎጊያ አሰብ ትራንስፖርት መጀመሩንና በቀን እስከ 10 አውቶብሶች ሰዎችን ጭነው ወደ አሰብ እንደሚሄዱ መታዘባቸውን ነግረውናል፡፡ • የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ጦስ በሶማሊያ? ስምሪቱን የማውጣት ድርሻው የፌደራል መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን በመሆኑ ለመስሪያ ቤቱ ደብዳቤ ማስገባታቸውን የገለጹልን ሊቀመንበሩ በመጭው ቅዳሜ አሊያም እሁድ ስራ ለመጀመር ተስፋን ሰንቀዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክተን የጠየቅናቸው የደቡብ ወሎ ዞን መንገድ ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምሴ ተፈራ በበኩላቸው"የሁለቱ አገራት የትራንስፖርት ስምሪት አፈጻጸም መመሪያ በፌደራል ደረጃ ወጥቶ ለኛ የደረሰን ነገር የለም፤ የመንገዱ ታሪፍ ወጥቶ በዚህ መልኩ ስምሪት ስሩ የሚል በሌለበትና በእኛና በፌደራል መካከል የመንገዱ አፈጻጸም ምን ይሁን የሚለው ጉዳይ የጋራ ባለመደረጉ፤ መንገዱ ተፈቅዷል የሚለው ነገር በእኛ በኩል አናውቀውም" ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ምን አልባት በህገ ወጥ መንገድ የሚገቡና የሚወጡ ተሸከርካሪዎች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል ብለዋል፡፡ ወደፊት ወደ አሰብ የሚደረገውን የትራንስፖርት ስምሪት ለማዘጋጀት በዞን ደረጃ ምን እየተሰራ እንደሆነ የጠየቅናቸው ኃላፊው፤ የሰላም ስምምነቱ የቅርብ ጊዜ ክንውን በመሆኑ ዘግይተናል ብለው ባያስቡም፤ ተጠቃሚዎች ካሉ ለሚመለከተው የፌደራል መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ጥያቄውን ለማቅረብ ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸውልናል፡፡
news-56884634
https://www.bbc.com/amharic/news-56884634
አፕል የተጠቃሚዎችን መረጃ አሳልፌ አልሰጥም ማለቱን ፌስቡክ ተቃወመ
አይፎንና አይፓድ አምራቹ ግዙፉ አፕል ኩባንያ ከሰሞኑ ያመጣው አንድ ቴክኖሎጂ ፌስቡክን አስቀይሟል።
የአፕሉ ቲም ኩክ (በግራ) እና የፌስቡኩ ማርክ ዙከርበርግ አዲሱ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች መተግበሪያዎችን [አፕሊኬሽን] ስልካቸው ላይ ሲጭኑ መረጃቸው እንዳይሰበሰብ የሚያስችል ነው። ለምሳሌ የአይፎን 12 [ከተመኙ አይቀር] ባለቤት ኖት እንበል። ከዚያ ፌስቡክ ስልክዎ ላይ መጫን ፈለጉ። ፌስቡክን ካለበት አፈላልገው ወደ ስልክዎ ሲያወርዱ አንድ መልዕክት ይደርስዎታል። መልዕክቱ እንዲህ ይነበባል፡ 'ይህ መተግበሪያ ስለ እርስዎ መረጃ እንዲሰበስብ ይሻሉ? ካልሆነ ይህን ይጫኑ።' ይህ ጉዳይ ነው ፌስቡክን ያስቆጣው። ምክንያቱም የፌስቡክ ዋነኛ ገቢ ማስታወቂያ ነው። ማስታወቂያ ለተጠቃሚዎች የሚለቀው ደግሞ በድብቅ በሚሰበስበው መረጃ ነው። ምንም እንኳ ትርፋማው ድርጅት ፌስቡክ ይሁን እንጂ ሌሎችም ኩባንያዎች በአፕል ድርጊት ደስተኛ አይመስሉም። ያው ደስተኛው የአይፎንና አይፓድ ባለቤትና ተጠቃሚው ብቻ ነው። ፌስቡክ ስልክዎ አሊያም ኮምፒውተርዎ ላይ ካለ በይነ መረብ ላይ ምን እያደረጉ እንዳሉ ሊያውቅ ይችላል። ለምሳሌ አንድ በልክዎ የተሠራ ጫማ አይተው ወደዱት እንበል። ወደ በይነ መረብ ዓለም ገብተው ይህን ጫማ ጎልጉለው ቤቴ ድረስ ይምጣልኝ ብለው አዘዙ። በበነጋው ወደ ፌስቡክ መንደር ሲገቡ የሚያዩትና የሚሰሙት ሁሉ ጫማ ጫማ [አዲስ ጫማ] ቢልዎ አይግረምዎ። ይህ የሚሆነው ፌስቡክ ወደ ሄዱበት ከኋላ ኋላ እየተከተለ በቴክኖሎጂ አማካይነት ስለሚሰልል ነው። ታድያ አይኦኤስ 14.5 [የአይፎንና አይፓድ መንቀሳቀሻ ሶፍትዌር] ይህን ለመመከት ቆርጦ ተነስቷል። በፊት በፊት አንድ መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሲጭኑ መረጃዎን እንሰብስብ ወይ የሚል ምርጫ አይመጣልዎትም ነበር። አዲሱ አይኦኤስ 14.5 በግላጭ ይህን ይጠይቃል። መቼም 'አዎ መረጃዬ ይበርበር' እንደማይሉ ይታወቃል። አንድ ፌስቡክ የተስማማበት ጥናት ተሰርቶ 80 በመቶ ተጠቃሚዎች "ኧረ በፍፁም" እንደሚሉ አሳይቷል። የመረጃ ጥበቃን ለኔ ተዉት እያለ ሁሌም የሚፎክረው አፕል ትርፍ የሚያገኘው ቁሳቁስ በመሸጥ እንጂ ማስታወቂያ ለተጠቃሚዎች በመልቀቅ አይደለም። ሟቹ የአፕል መሥራች ስቲቭ ጆብስ፤ ሰዎች መረጃቸው መወሰዱ ባያስገርማቸው እንኳ እንዴት እንደተወሰደ ሊያውቁት ይገባል የሚል አቋም ነበረው። በቅርቡ ደግሞ የወቅቱ የአፕል ዋና ሥራ አስኪያጅ ቲም ኩክ ኩባንያዎች 'ኩባንያዎች መረጃ መዝብረው ሊበልፅጉ አይገባም' ሲሉ ፌስቡክን በነገር ሸንቆጥ አድርገው ነበር። ሳፋሪ ማለት አይፎን ላይ ወደ በይነ መረብ የሚያስገባ መስኮት ማለት ነው። ሰዎች ሳፋሪን ሲጠቀሙ መረጃቸው በፍፁም እንዳይበረበር አድርጓል አፕል። ይህም ፌስቡክን ካበሳጩ የአፕል ድርጊቶች አንዱ ነው። ፌስቡክ ይህ የአፕል ድርጊት ጥቃቅንና አነስተኛ 'ቢዝነሶችን' የሚገድል እንዲሁም 'ተጠቃሚዎች የተሻለ ነገር እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው' ሲል ይሞግታል። ፌስቡክ ይህን መልዕክቱን ለሰዎች ለማድረስ ባለፈው ታህሣሥ በጋዜጣ ሁሉ ዜና አስነብቧል። ነገር ግን አፕል ጆሮ ዳባ ልበስ እንዳለ ነው። ታድያ የሁለቱ ግዙፍ ኩባንያዎች እሰጥ አገባ ምን ይገደኛል? ሊሉ ይችላሉ። የአይፎን ተጠቃሚ ሆኑም አልሆኑም መረጃዎ ለሌሎች ኩባንያዎች ተላልፎ እየተሰጠ መሆኑን መርሳት የለብዎትም ይላሉ የቴክኖሎጂ ሰዎች። ይህ መረጃዎ መንግሥታትን ጨምሮ ለማንም ተላልፎ ሊሰጥ ይችላል። ፌስቡክና ቲክ ቶክ የተጠቃሚዎችን መረጃ ለቁሳቁስና አገልግሎት አቅራቢዎች በመሸጥ ነው ትርፍ የሚያገኙት። የዘርፉ ሰዎች እንደሚሉት አፕል ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቴክኖሎጂዎች ጠንከር ያለ እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ። ታድያ ፌስቡክ በምን ዓይነት አዲስ መላ ብቅ ይል ይሆን?
news-53160664
https://www.bbc.com/amharic/news-53160664
ኮሮናቫይረስ፡ የሜዳ ቴኒሱ ኮከብ ሰርቢያዊው ጆኮቪች በኮቪድ-19 ተያዘ
ሰርቢያዊው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ጆኮቪች 33 ዓመቱ ሲሆን በቤልግሬድ አንድ የቴኒስ ውድድር አሰናድቶ ነበር ሰሞኑን፡፡ ውድድሩ የተሰናዳው ሁለት ዓላማ አንግቦ ነበር፡፡
አንደኛው በደቡም ምሥራቅ አውሮጳ የሚገኙ ቴኒስ ተጫዋቾች ከውድድር ርቀው ስለነበር ለቀጣይ ውድድር እንዲዘጋጁ ለማድረግ ሲሆን ሁለተኛው የሚገኘው ገቢ ከኮሮና ጋር በተያያዘ የሚውል ለበጎ አድራጎት እንዲሰጥ ነበር፡፡ ይህ ውድድር ገና ከመጀመሩ ታዲያ አሳዛኝ ዜና አጋጥሞታል፡፡ ቢያንስ አራት የሚሆኑ ዕውቅ የቴኒስ ተጫዋቾች በኮሮና መያዛቸው ታውቋል፡፡ ከነዚህም መሐል ክሮሺያዊው ቦርና ኮሪክ እና ሰርቢያዊው ቪክተር ትሮይኪ እንዲሁም ቡልጋሪያዊው ግሪጎር ዲሚትሮቭ ይገኙበታል። • ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ተሞከረብኝ አለች • የናይጄሪያ ፖሊስ በሩዝ ፋብሪካ ተቆልፎባቸው እንዲሰሩ የተገደዱ 300 ሰራተኞችን ነፃ ማውጣቱን ገለፀ • በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ሊደረግ ነው ‹‹ይህንን የቴኒስ ውድድር ያሰናዳሁት ከቅን ልቦና ተነስቼ ነበር፡፡ ሁሉንም የጤና መመርያዎች ለመከተል ሞክረናል፡፡ ይህ አሳዛኝ ዜና በመምጣቱ ከልብ አዝናለሁ›› ብሏል ቾኮቪች፡፡ የእንግሊዙ እውቅ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች አንዲ ሙሬይ በበኩሉ ‹‹ይህ ለኛ ትልቅ ትምህርት ነው›› ሲል ትዊተር ሰሌዳው ጽፏል፡፡ ይህንን ውድድር በዚህ ወቅት ማሰናዳት አደጋ ሊኖረው ይችላል የሚል ሐሳብ ቀድሞውንም ሲንጸባረቅ ነበር፡፡ የቴኒስ ውድድሩ በጆኮቪች ሐሳብ አመንጪነት ሲሰናዳ እውቅ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾች ራሳቸውን ከውድድር በማራቃቸው እንደ ማነቃቂያ ሊሆናቸው ይችላል፤ በዚያውም የበጎ አድራጎት ሥራ ይሆናል በሚል ነበር፡፡ ጆኮቪች በድረገጹ እንደጻፈው መጀመርያ ቤልግሬድ እንደደረሰ በኮሮና መያዙ ይፋ የተደረገው ኖቫክና ቤተሰቡ ነበር፡፡ ሆኖም ምንም ምልክት አያሳይም ነበር፡፡ ይህ በሰርቢያ የተሰናዳው ውድድር 4ሺህ ሰዎች ታድመውታል፡፡ ሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾችም ከውድድር በኋላ መሸታ ቤት ሲደንሱ የሚያሳይ ፎቶ ወጥቷል፡፡ በመጀመርያው ቀን ውድድር የቡልጋሪያው ዲሚትሮቭ ከክሮሺያው ኮሪክ ጋር ቅዳሜ እለት ተጫውተው ነበር፡፡ ጆኮቪች ከዚህ ቀደም የኮሮናቫይረስ ክትባት ቢኖር እንኳ ክትባቱን ለመወጋት ፍቃደኛ እንደማይሆን በትዊተር ገጹ በመጻፉ የሴራ ንድፈሐሳብ አራማጆች ክትባቱ በቢልጌትስ የተቀነባበረ ስለመሆኑ እንደ አንድ ማስረጃ የርሱን ጽሑፍ ሲያጋሩ ነበር፡፡ ሚስቱ ጄሌና ከዚህ ቀደም ኮሮናቫይረስ የመጣው በ5ጂ ቴክኖሎጂ ነው የሚል ይዘት ያለው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራቷ ሲታይ ቤተሰቡ በወረርሽኙ ምንነት ላይ ጥርጣሬ እንደነበረው እንዲገመት በር ከፍቷል።
news-51513604
https://www.bbc.com/amharic/news-51513604
የወሲብ ሮቦቶች የሥነ ልቦና ጉዳትን ሊያስከትሉ ይችላል ተባለ
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የወሲብ ሮቦቶች በስፋት መገኘት በግለሰቦችና በማኅበረሰብ ሥነ ልቦናዊ እንዲሁም ሞራላዊ ደህንነት ላይ እየጨመረ የመጣ ስጋት እየቀኑ መሆናቸውን የአሜሪካ ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ።
ቁጥጥር የሚያደርጉት ተቋማት ክትትል ለማድረግ በጣም አሳፋሪ ስለሆነባቸው ቴክኖሎጂውን የሚያቀርቡት ድርጅቶች ከምርመራና ቁጥጥር ትኩረት ለማምለጥ ችለዋል። ተመራማሪዎቹ ግን ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ጥቅም ላይ የሚውሉትን ሮቦቶች ጉዳይ በተመለከተ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል። የዱክ ዩኒቨርስቲዋ ዶክትር ክርስቲን ሄንድረን ለቢቢሲ እንደተናገሩት "የሚያስከትለው አደጋ ከፍተኛ ነው" ብለዋል። "አንዳንዶቹ የወሲብ ሮቦቶች እምቢ እንዲሉና ለአስገድዶ መድፈር የሚገፋፉ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ ፕሮግራም ይደረጋሉ" ብለዋል ዶክተሯ። "አንዳንዶቹም ህጻናትን እንዲመስሉ ተደርገው ዲዛይን ይደረጋሉ። ጃፓን ውስጥ ይህንን ከሰሩት ሰዎች መካከል አንዱ ህጻናትን የሚያባልግ እንደሆነ አምኖ የነበረ ግለሰብ ነው" ይህንንም የፈጠረው ህጻናት ላይ ጉዳት ከማድረስ ራሱን ለመቆጠብ ሲል እንደሆነ ተናግሯል። በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው የበዛ ለወሲብ አገልግሎት የሚውሉ ሮቦቶች በበይነ መረብ ላይ ለሽያጭ ይተዋወቃሉ። አሜሪካ ውስጥ የሚገኝ አንድ ኩባንያ ለዚሁ ተግባር የምትውል 'ሐርመኒ' የተባለች ሮቦትን አምርቶ ከ8 ሺህ እስከ 10ሺህ በሚደርስ ዶላር ለሽያጭ አቅርቧል። 'ሐርመኒ' የተባለችው ሮቦት ሮቦቷ የአንድ ሰው አካላዊ ቁመና እንዲኖራት ተደርጋ የተሰራች ሲሆን ዓይኗ የሚንቀሳቀስ፣ የዓይን ሽፋሎቿ የሚርገበገቡና ስትናገር ከንፈሮቿ የሚንቀሳቀሱ ናቸው። ይህችን ሮቦት የሰራው ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማት ማክሙለን እንዳለው ሮቦቷ ከባለቤቷ ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖራት የሚያስችል አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አላት። "ሮቦቷ አብሯት ያለው ሰው ስለሚወደውና ስለሚጠላው ነገር እንዲሁም ከዚህ በፊት ስላጋጠመው ጉዳይ የተነገራትን ማስታወስ ትችላለች" ይላል ማክሙለን። ሌስተር ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሮቦቶችና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሥነ ምግባርና ባህል ፕሮፌሰር የሆኑት ካትሊን ሪቻርድሰን በዚህ ዘርፍ ያለው የግብይት ሥራ በሕግ እንዲከለከል ይፈልጋሉ። "ሮቦቶቹን የሚያመርቱት ድርጅቶች 'ጓደኛ የለህም? የህይወት አጋር የለህም? ስለዚህም አትጨነቅ የሮቦት የሴት ጓደኛ እንፈጥርልሃለን' እያሉ ነው" በማለት ይቃወሟቸዋል። "ከሴት ጓደኛ ጋር የሚኖር ግንኙነት መቀራረብ፣ የሚጎለብት ትስስርና ሰጥቶ መቀበልን መሰረት ያደረገ ነው። እነዚህን ነገሮች ደግሞ ማሽኖች ሊያደርጓቸው አይችሉም" ይላሉ ፕሮፌሰር ካትሊን። ፕሮፌሰሯ በእነዚህን ሮቦቶች ምርት መጀመር ዙሪያ ቁጥጥር ለማድረግ የተቋቋመው የተጽእኖ ቡድንን ያማክራሉ። ይህ የወሲብ ሮቦቶች ምርትን የሚቃወመው ቡድን ከፖሊሲ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ሮቦቶች ሰዎች ከሰዎች ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ሊተኩ ይችላሉ በሚል የሚደረገው ቅስቀሳ ለማገድ የሚያስችል ሕግ እንዲወጣ እየሰራ ነው። "ሴቶችን የወሲብ ቁስ እንደሆኑ አድርጎ የሚያቀርበውን ሐሳብ ችግር የሌለበት አድርገን ተቀብለን ወደ መጪው ዘመን ልንሸጋገር ነው" ሲሉ ፕሮፌሰሯ ይጠይቃሉ። ጨምረውም "አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ከሚኖረው ግንኙነት አንጻር ችግር ካለበት፣ ከሌሎች ጋር በመቀራረብ መፍትሄ ሊያገኝ እንደሚችል ከማበረታታት ይልቅ፤ ሮቦትን የሰውን ያህል ለህይወቱ መልካም አማራጭ እንደሆነ ማቅረብ ተገቢ አይደለም" ሲሉ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል። ሮቦት ገበሬዎች የሰዎችን ስራ ሊነጥቁ ነው።
news-56136265
https://www.bbc.com/amharic/news-56136265
ኪም ካርዳሺያን እና ባለቤቷ ካንዬ ዌስት ፊርማቸውን ሊቀዱ ነው
ኪም ካርዳሺያን ከባለቤቷ ካንዬ ዌስት ጋር ፊርማዋን ልትቀድ እንደሆነ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኀን እየዘገቡ ነው።
ራፐሩ ካንዬ ዌስትና ኪም ካርዳሺያንስ ላለፉት ሰባት ዓመታት በትዳር ተጣምረው የኖሩ ሲሆን አራት ልጆችንም አፍርተዋል። ሰማንያቸውን ሊቀዱ ነው፣ እህል ውሃቸው አብቅቷል የሚል ወሬ ለበርካታ ወራት ሲናፈስ ከቆየ በኋላ ቲኤምዚ የተሰኘው የታዋቂ ሰዎችን ጉዳይ የሚዘግበው ድረ ገጽ እውነት ነው ሲል ተናግሯል ። እንደ አሜሪካ መገናኛ ብዙኀን ከሆነ የ40 ዓመቷ ኪም ካርዳሺያን፣ በጋራ ያፈሯቸውን ልጆች በጋራ ለማሳደግ እንዲችሉ መጠየቋ የተዘገበ ሲሆን ጥንዶቹ ግን በጉዳዩ ላይ በይፋ አስተያየት አልሰጡም። ኪም ካርዳሺያንም ሆነች ካንዬ ዌስት በየግላቸው እጅግ በጣም ዝነኛ እና ስኬታማ ናቸው። ኪም ለመጀመሪያ ጊዜ ዝናን በእጇ ያስገባችው በ2007 በ E! ቴሌቪዥን ጣብያ ኪፒንግ አፕ ዊዝ ዘ ካርዳሺያንስ በተሰኘው የቤተሰቧን የእለት ተዕለት እንቅስቃሴን በሚያሳየው እውናዊ ተከታታይ የቴሌቪዥን ትርዒት ላይ ነው። ይህ እውናዊ የቴሌቪዥን ትርዒት ከተጀመረ ጀምሮ በተመልካች ዘንድ በጣም ዝነኛ ሲሆን 21ኛው እና የመጨረሻው ክፍል በሚቀጥለው ዓመት ይተላለፋል ተብሎ እቅድ ተይዞለታል። ኪም ካርዳሺያን ከቴሌቪዥን ትርዒቱ ባሻገር በሌሎች የንግድ መስኮችም እድል ፊቷን ያበራችላት ሴት ናት። ከሞባይል መተግበሪያ እስከ መዋቢያ ምርቶች ንግድ ውስጥ የተሰማራቸው ኪም ካርዳሺያንስ በፎርብስ የሃብታሞች ዝርዝር ውስጥ ሃብቷ 780 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተመዝግቧል። ካንዬም ቢሆን ላለፉት 15 ዓመታት በራፕ ሙዚቃ ውስጥ ስሙን የተከለ ድምጻዊ ነው። ይህ የግራሚ ሽልማት አሸናፊ የሆነው ራፐር፣ በፋሽኑም መስክ የስኬት ፀሀይ ወጥቶለታል። ጥንዶቹ ከመጋባታቸው በፊት ለረዥም ጊዜ ጓደኛሞች የነበሩ ሲሆን ካንዬ ዌስት ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተሰቡ እውናዊ የቴሌቪዥን ትርዒት ላይ በ2010 ቀርቧል። የጥንዶቹ የመጀመሪያ ልጅ ኖርዝ የምትባል ስትሆን እኤአ በ2013 ሰኔ ወር ላይ ነው የተወለደችው። ካንዬ ልጃቸው በተወለደችበት ዓመት ለኪም ካርዳሺያን የታገቢኛለሽ ጥያቄ ሲያቀርብ የሳን ፍራንሲስኮን ግዙፍ ስታዲያም ተከራይቶ፣ ኦርኬስትራ አደራጅቶ፣ ቤተሰቦቿ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ካሜራ ባለሙያዎች በተገኙበት ነበር። በ2014 በጣሊያን ጋብቻቸውን የፈፀሙት ጥንዶቹ ሲሳሳሙ የተነሱትን ምስል በኢንስታግራም ላይ አጋርተውት በማህበራዊ ድረ ገፁ ታሪክ እጅጉን የተወደደ ምስል ተብሎ ተመዝግቧል። ከዚህ በኋላ ኪምና እህቷ የማህበራዊ ሚዲያን ተከታዮቻቸውን ተጠቅመው ወደ ስኬታማ የንግድ ስራ አምርተዋል። በሚቀጥለው ዓመት ኪም ወንድ ልጅ፣ ሴይንት ዌስት፣ ወልዳለች። ከዚያ በመቀጠልም ቺካጎ እና ፕስላም የተሰኙ ልጆችን አፍርተዋል። በ2016 ኪም ካርዳሺያን በፈረንሳይ ባረፈችበት ሆቴል ውስጥ ክትትል ሲያደርጉባት በነበሩ ሰዎች ዘረፋ ተፈጽሞባታል። ከዚያም በኋላ ባለፈው ዓመት ካንዬ ዌስት በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እጩ ሆኖ ተሳትፏል። ለበርካታ ወራት የጥንዶቹ የፍቺ ወሬ ሲናፈስ ቆይቶ ኪም ካርዳሺያን በፍቺ ዙሪያ ጥርሷን የነቀለች ጠበቃ፣ ላውራ ዋሴር፣ መቅጠሯ ተሰምቷል።
news-52560732
https://www.bbc.com/amharic/news-52560732
ደቡብ ኮርያ ኪም የልብ ቀዶ ህክምና ስለማድረጋቸው 'ምንም ምልክት የለም' አለች
የደቡብ ኮርያ ደህንነት አጄንሲ የኪም ጆንግ-ኡን ጤና መቃወስን በማስመልክት ሲወጡ የነበሩ ዘገባዎች መሰረተ ቢስ ናቸው አለ።
ኤጀንሲው ጨምሮም ኪም የልብ ቀዶ ህክምና ስለማድረጋቸው የሚያሳይ ምንም አይነት ምልክት የለም ብሏል። የሰሜን ኮርያ መሪ በቅርቡ በአደባባይ ሳይታዩ ለ20 ቀናት ቆይተው ነበር። በአገሪቱ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የአያታቸው ልደት በዓል ላይ አለመገኘታቸው በርካቶች የጤና ሁኔታቸውን እንዲጠራጠሩ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል። አንዳንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ኪም በጠና መታመማቸውን የዘገቡ ሲሆን፤ ኪም ህይወታቸው አልፏል ያሉም በርካት መገናኛ ብዙሃን ነበሩ። በቅርቡ ግን ኪም የምርጥ ዘር ፋብሪክ ምርቃት ላይ ታይተዋል። ሙሉ ጤነኛም ይመስላሉ። የደቡብ ኮሪያ ደህንነት ኤጀንሲ ያለው ምንድነው? የደቡብ ኮርያ ደህንነት ኤጀንሲ አለቃ ሱን ሁን ለአገሪቱ የህዝብ እንደራሴዎች ኮሚቴ ሲናገሩ የኪም ጆንግ-ኡንን ጤና በማስመልከት ሲወጡ የነበሩ ዘገባዎች ስህተት ናቸው ብለዋል። ለፓርላማ አባለቱ የሰሜን ኮርያው መሪ በዚህ ዓመት ለ17 ጊዜ በአደባባይ እንደታዩ የተነገራቸው ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በነበሩ ዓመታት በተመሳሳይ ወቅት 50 ጊዜ በአደባባይ ታይተው ነበር። ምንም እንኳ ሰሜን ኮርያ በይፋ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ስለመኖሩ በይፋ ባታሳውቅም፤ ኪም በአደባባይ ያልታዩት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ሳይሆን አይቀርም ያሉ አልጠፉም። የኪም የጤና መቃወስ ዜና መናፈስ እንዴት ጀመረ? በሚያዚያ ወር የመጀመሪያ ሳምንት መጨረሻ አካከባቢ ኪም ጆንግ ኡን የአያታቸውን የልደት ዝግጅት ሳይታደሙ ቀርተዋል። ይህ በዓል የአገሪቱ መስራች እንደሆኑ የሚታሰቡ ግለሰብ ልደት እንደመሆኑ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ዝግጅት ነው። ኪም ጆንግ-ኡን ከዚህ ቀደም ሳይታደሙ ቀርተው አያውቅም - ብርቱ ጉዳይ ካልገጠማቸው በቀር አይቀሩም። ኪም በዝግጅቱ ሳይገኙ መቅረታቸው በበርካቶች ዘንድ እንዴት? ለምን? የሚሉ ጥያቄዎች እንዲነሱ አደረጉ። ኪም ለመጨረሻ ጊዜ በብሔራዊ ጣቢያው የታዩት ሚያዚያ 4 ላይ ነበር። በቴሌቪዥን ሲታዩ እንደተለመደው ዘና ብለው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ኪም በአደባባይ ሳይታዩ ቀሩ። ከዚያ በኋላም ሰሜን ኮርያ የሚሳኤል ሙከራ አድርጋ ነበር። የአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ በዘገበበት ወቅት የኪም ጆንግ-ኡንን ስም አልጠቀሰም። ምስላቸውንም አላሳየም። ከዚህ ቀደም ሰሜን ኮርያ መሰል ወታደራዊ ሙከራዎችን ስታካሂድ ኪም በቴሌቪዥን መስኮት ይታዩ ነበር።
news-45219221
https://www.bbc.com/amharic/news-45219221
ዓለማችንን ከረሃብ ሊታደግ የሚችለው የስንዴ ዘር
የትኛውንም አይነት የአየር ጸባይ መቋቋም የሚችሉ የስንዴ ዘር አይነቶችን ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች እየገለጹ ነው። አለማቀፉ የተመራማሪዎች ቡድን ለምርምሩ እንዲረዳው ከ100 ሺ በላይ የስንዴ ዘረ መል አይነቶች መለየታቸውን ገልጸዋል።
የዘረ መል ካርታው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለውን ከባድ ሙቀትም ሆነ ማንኛውም አይነት የአየር ጸባይ መቋቋም የሚችሉ አዳዲስ የስንዴ ዝርያዎችን በአጭር ጊዜ ለማስተዋወቅ ይረዳል ተብሎለታል። የምርምር ስራው ውጤት በአንድ ሳይንሳዊ ግኝቶች የሚቀርቡበት መጽሄት ላይ ታትሟል። በጆን ኢንስ የምርምር ማዕከል የሰብል ዘረመል ጥናት ክፍል መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ክሪስቶባል ኡዋይ አዲሱን ግኝት የስንዴ ምርትን በአስገራሚ ሁኔታ የሚቀይር ነው ብለውታል። • ምድር በአስፈሪ ሁኔታ እየሞቀች ነው • የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ በአየር ፀባይ ይመራ ነበር • የካርቦንዳይኦክሳይድ ከፍተኛ ክምችት አደጋዎችን ይጨምር ይሆን? አክለውም የሰው ልጅ ተለዋዋጭ የአየር ጸባይን ተቋቁሞ ለመኖር እንደዚህ አይነት የምርምር ውጤቶች ያስፈልጉታል ብለዋል። ''ሁላችንም ለብዙ ጊዜ ስንጠብቀው የነበረና በአለማችን ያለውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ ወሳኝ ግኝት ስለሆነ፤ ሁሉም የሰው ዘር ደስ ሊለው ይገባል'' ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል። ግኝቱ ምን ያክል ጠቃሚ ነው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና ግብርና መስሪያ ቤት (ኤፍ ኤ ኦ) እንደገመተው ከሆነ በ2050 የዓለማችን የህዝብ ቁጥር ወደ 9.6 ቢሊዮን ከፍ የሚል ሲሆን፤ የምግብ ፍላጎቱን ለማርካት ደግሞ የስንዴ ምርት ላይ 60 በመቶ ጭማሪ መደረግ አለበት። ይህንን ምርት ለመጨመርና የተሻሉ ዘሮችን የማግኘት ሃላፊነት ወስዶ እየሰራ የሚገኘው ደግሞ በሜክሲኮ ሲቲ መቀመጫውን ያደረገው አለማቀፉ የበቆሎና ስንዴ ምርት ማሻሻያ ማዕከል ነው። የማዕከሉ ዋና አላማ ደሃ በሚባሉ ሃገራት የሚገኙ ገበሬዎችን ህይወት ለማሻሻል ብዙ ምርት የሚሰጡ ዘሮችን በምርምር ማግኘት ነው። እስከዛሬ ሲያከናውኗቸው የነበሩት የምርምር ውጤቶች ተለዋዋጭ የአየር ጸባዮችን መቋቀወም የሚችሉ እንዳልነበሩና በተለይ ደግሞ ከፍተኛ ሙቀት አስቸጋሪ ሆኖ እንደቆየ የምርምር ማዕከሉ ዋና ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ራቪ ሲንግ ይናገራሉ። ይህንን የምርመር ውጤት ለማሳካት ከ73 የተለያዩ የምርምር ተቋማትና 20 ሃገራት የተውጣጡ 200 ተመራማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ 21 የስንዴ ዘረ መል አይነቶችን ከነቦታቸው ለይተዋል። •የቡና ምርትና ጣዕም አደጋ ላይ ነው • 2017: ያልተጠበቁ ቁጥሮች የተመዘገቡበት ዓመት የምርምር ውጤቱ የስንዴ ምርትን በብዙ እጥፍ የሚጨምር ሲሆን፤ ተለዋዋጭና አስቸጋሪ አየር ንብረት ላላቸው የሶስተኛው አለም ሃገራት ወሳኝ መፍትሄ ይዞ እንደሚቀርብ ይታሰባል። ነገር ግን የምርምር ውጤቱ ከተቺዎች አላመለጠም። ተቺዎቹም እንደ ዋና ነጥብ የሚያነሱት አሁንም ቢሆን በአለማችን የሚመረቱ ሰብሎች የአለምን ህዝብ ለመመገብ በቂ ናቸው። ዋናው ችግር ያለው ክፍፍሉ ላይ ነው በማለት ይከራከራሉ። ስለዚህ የዚህ የምርምር ውጤት ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም፤ በተገቢው መልኩ የማይከፋፈል ከሆነ ግን አሁንም ብዙ ቁጥር ያለው የአለማችን ህዝብ መራቡ አይቀርም እያሉ ነው።
45899031
https://www.bbc.com/amharic/45899031
"የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከተለው ዲፕሎማሲ ቀለም አልባ ነው" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዜጋ ተኮር እና ጎረቤት ተኮር ዲፕሎማሲ ላይ ትኩረት ሰጥቼ እየሰራሁ ነው አለ።
ሚኒስትሩ ዛሬ ሐሙስ ማለዳ በሰጠው መደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫው የኢፌድሪ መንግስት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት ላይ የማይተካ ሚና አላት ብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከኤርትራው አቻቸው ኦስማን ሳለህ ወደሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ያደረጉት ከጥቂት ቀናት ጉብኝት የጎረቤት ተኮር ዲፕሎማሲ አንድ ማሳያ ነው ያሉት የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ናቸው። •ሃምሳ በመቶ የሚኒስትሮች ሹመት ለሴቶች •ከጄኔራሎቹ ሹመት ጀርባ? •የአዲስ አበባ ወጣቶች በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚለቀቁ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ሚኒስትር ወርቅነህ በሶማሊያ ጉብኝታቸው ወቅት የአፍሪቃ ቀንድ ሰላም እና ደህንነት እውን እንዲሆን እንዲሁም ለቀጠናው ምጣኔ ኃብታዊ ትስስር በጋራ ለመስራት ከኤርትራ እና ሶማሊያ አቻዎቻቸው ጋር መወያየታቸውን ይህንንም የሚያስረግጥ የጋራ መግለጫ መስጣታቸውን አቶ መለስ አክለው ተናግረዋል። በሶስቱ አገራት መካከል በኤርትራ ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። "ጎረቤትን የሚያስቀድም ዲፕሎማሲ፣ የጎረቤቶቻችን እጣ ፈንታ ከእኛ ጋር የተሳሰረ ነው በሚል ፅኑ እምነት ላይ የተመሠረተ ነው" ብለዋል አቶ መለስ። የኢትዮጵያ መንግስት የሚከተለውን ዲፕሎማሲ "ቀለም አልባ ነው" ሲሉም ገልፀውታል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ በፈረንሳይ እና በጀርመን በሚያደርጓቸው ጉብኝቶች በአፍሪካ ቀንድ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቃል አቀባዩ ጨምረው ተናግረዋል። ጥቅምት 21 ቀን"አንድ ሆነን እንነሳ፤ ወደፊቱን እንገንባ" በሚል መሪ ቃል በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ቀን ይከበራል። በዕለቱም በአውሮፓ ያሉ ኢትዮጵያዊያን በጀርመኗ ፍራንክፈርት ይሰበሰባሉ ተብሏል። እንደአቶ መለስ ገለፃ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ ወይዘሮ ብርቱካን አያኖ የሚመራ እና በርካታ ታዋቂ ግለሰቦች የተካተቱበት ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራ ጀምሯል። "ሦስት ሚሊዮን የሚጠጉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የማይሳተፉበት የአገር ግንባታ ሒደት ስኬታማ አይሆንም" ሲሉ አቶ መለስ የዕለቱን አስፈላጊነት አብራርተዋል። "በቀድሞ በሬ በማረስ ለውጥ ማምጣት አይቻልም፤ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል። እነርሱም የአገራቸው ጉዳይ ያገባቸዋል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያዊያኑ ጋር ተገናኝተው፤ እየተካሄድ ስላለው ለውጥ ያስረዳሉ፤ ኢትዮጵያዊያኑ ሊኖራቸው የሚችለውን አስተዋፅዖ ይገልፃሉ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያዊያኑን ራዕይ እና ፍላጎት ያዳምጣሉ እንደቃል አቀባዩ ገለፃ። አውሮፓ ውስጥ በሚገኙ 13 ሚሲዮኖች እና የቆንስላ ፅህፈት ቤቶች ዝግጅቶች እየተከናወኑ ሲሆን ከ20 ሺህ እስከ 25 ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ዝርያ ያላቸው ዜጎች ይገኛሉ ተብሎም ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የመዋቅር ማሻሻያ እያደረገ ነው፤ ይህም በሚሲዮኖች እንዲሁም በዋናው መስሪያ ቤት ውስጥ ይከናወናል ብለዋል አቶ መለስ። "ይሄንን ተቋም የሃያ አንደኛውን ክፍለ ዘመን የሚመጥን ማድረግ ያስፈጋል፤ እንደዚያ ዓይነት ተቋም ለመፍጠር የሚያስችል የማሻሻያ ሥራ እየተካሄደ ነው።"
news-54437957
https://www.bbc.com/amharic/news-54437957
ትግራይ፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ 'ክልሉን ከፌዴሬሽኑ እንዲወጣ የሚገፋ ነው'፡ የትግራይ ምክትል ፕሬዝዳንት
የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገወጥ መንገድ የተቋቋመ ነው ላለው የትግራይ ክልል ም/ቤትና ካቢኔ የፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጎማ እንደማያደርግ መግለጹ ክልሉን ከፌዴሬሽኑ እንዲወጣ የሚገፋ ነው አሉ።
ይህ ውሳኔ እስካሁን ሲወሰድ የነበረው "ሕገወጥ እርምጃ" ቀጣይ አካል ነው ያሉት አብርሃም (ዶ/ር)፣ እርምጃው ኃላፊነት የጎደለው ከመሆኑ በተጨማሪ "የትግራይ ክልልን ከፌዴሬሽኑ እንዲወጣ የሚገፋ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀደም ብሎ የትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚው አካል በሕገመንግሥቱ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ምንም ዓይነት ሕጋዊ ግንኙነት እንዳያደርግ የወሰነ ሲሆን፤ በማስከተልም ከፌዴራል መንግሥቱ የሚደረግ የበጀት ድጎማን እንዳያገኝ መወሰኑን የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ለብሔራዊው ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ይህንን ውሳኔ በሚመለከት አብረሃም ተከስተ (ዶ/ር) ለቢቢሲ እንደተናገሩት ምክር ቤቱ የፌደራል መንግሥት ከክልሎች ከሚሰበስበው ገቢ ላይ ለትግራይ ክልል መንግሥት ድጎማ እንዳይሰጥ ውሳኔ ማሳለፉ "በሌላ አገላለጽ ትግራይ የፌዴሬሽኑ አካል አይደለችም እንደ ማለት ነው" ብለዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን ውሳኔ "በትግራይ ክልልና ሕዝብ ላይ ጦርነት እንደማወጅ" አድርገው እንደሚቆጥሩት የተናገሩት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ለዚህም ደግሞ ምክንያታቸውን ሲገልፁ ፌዴሬሽኑ እና የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት አንዱ የሚያገናኛቸው የበጀት ሥርዓቱ መሆኑን አመልክተዋል። የትግራይ ክልል የፌዴሬሽኑ አባል ናት ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንት አብረሃም (ዶ/ር)፤ እርምጃው ፌዴሬሽኑን የሚበትን ነው ብለዋል። የፌዴሬሽኑ አባላት አንዱ መሳሪያ የበጀት ግንኙነቱ ነው የሚሉት አብረሃም (ዶ/ር) ትግራይን ከበጀት ውጪ ማድረግ ማለት "ከፌዴሬሽኑ እንድትወጣ የሚገፋ ነው" ነው ሲሉ ተናግረዋል። እርምጃውን "በጣም አደገኛ" ያሉት አብረሃም (ዶ/ር)፣ አገሪቷን ወደ ቀውስ የሚያስገባ፣ የሚበትን በማለት "ኃላፊነት የጎደለው እርምጃ" ሲሉም ኮንነውታል። የፌደራል መንግሥት ገቢ የሚሰበስበው ትግራይን ጨምሮ ከክልሎች ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ይህንኑ መልሶ ለክልሎች እንደሚያከፋፍልም ተናግረዋል። ከትግራይ የሚሰበስበውን ገቢ ለትግራይ አላካፍልም ማለት "እብደት ነው" በማለት ውሳኔውን አጣጥለውታል። የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ እንዳለው ወደዚህ እርምጃ የሚገባ ከሆነ ክልሉ ለፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ የሚሰበስበው ገቢ ላይ እርምጃ እንደሚወስድም አመልክተዋል። እርምጃው ምን ዓይነት ነው ተብለው የተጠየቁት አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) የፌደራል መንግሥት ባለፈው ዓመት ብቻ ከትግራይ ክልል ወደ ሰባት ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን፣ በዚህ በተያዘው 2013 ዓ.ም ደግሞ ወደ ዘጠኝ ቢሊየን ብር እሰበስባለሁ ብሎ ማቀዱን ገልፀዋል። ስለዚህ ይህንን ሰብስቦ ሕጋዊ የፌዴሬሽኑ አካል ለሆነችው ትግራይ አላከፋፍልም የሚል መንግሥት "የእብደት ሥራ ነው" በማለት እንዲሁ ዝም ብለን አናይም ሲሉ ተናግረዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገወጥና ተፈጻሚነት የሌለው ነው ያለውና ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ ከሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በተለየ በትግራይ ክልል በተናጠል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ የተቋቋማው የክልሉ መንግሥት ላይ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚሁ መሰረትም ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ከትግራይ ክልል ከፍተኛ አስፈፃሚ አካላት ጋር እንደሕጋዊ አካላት በመቁጠር ደብዳቤ መፃፃፍ፣ መረጃ መላላክ፣ የፌዴራል ተቋማት ለክልል ተቋማት የሚሰጧቸውን ድጋፎች መስጠት፣ በፌዴራል ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች ላይ ማሳተፍ የመሳሰሉ ጉዳዮችን እንዳያከናውኑ ወስኗል። ከዚህም ጎን ለጎን የክልሉ ሕዝብ መሰረታዊ የልማትና የአገልግሎት ተጠቃሚነቱ እንዳይስተጓጎል እንደ ቀበሌ ፣ወረዳ ፣ ከተማ ካሉ ሕጋዊ መዋቅሮች ጋር ብቻ ግንኙነት እንደሚደረግና በዚህም ላይ ክትትል እንደሚደረግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ለኢቲቪ ተናግረዋል። የበጀት ድጎማን በተመለከተም "በሕገወጥ መንገድ የተቋቋመው የትግራይ ምክር ቤትና ካቢኔ ሕጋዊ ሰውነት ስለሌለው" ከፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጎማ እንደማያገኝ ተነግሯል። ነገር ግን የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል ካሉ የከተማ አስተዳደሮች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጋር በሚኖር ግንኙነት አማካይነት ሕዝቡ ማግኘት የሚገባውን መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኝ የሚደረግ መሆኑና ክትትልም እንሚደረግበት ተነግሯል።
news-56359821
https://www.bbc.com/amharic/news-56359821
ትግራይ፡ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከእስር በዋስ መለቀቃቸው ተነገረ
የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከእስር በዋስ መለቀቃቸውን ፖሊስ ዛሬ ለፍርድ ቤት ገለጸ።
ፖሊስ ዛሬ ለተሰየመው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት እንደተናገረው ቀዳሚ ምርመራ አስኪሰማ ድረስ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 28 መጀረት ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም በዋስ መፈታታቸውን ገልጿል። በተጨማሪም የቀድሞ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩት ወ/ሮ ህርይቲ ምህረተአብ እና የቀድሞው የትግራይ ክልል መስተዳደር አማካሪ የነበሩት አቶ ወልደጊዮርጊስ አሰፋ በዋስ ከእስር እንዲወጡ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተነግሯል። በእነአቶ ስብሐት ነጋ የክስ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታይ የነበሩት እነዚህ ግለሰቦች በዋስ እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው ዐቃቤ ሕግ እያካሄደ ባለው የምርመራ ሂደት ተጠርጣሪዎቹን በእስር ለማቆየት የሚያበቃ በቂ ማስረጃ አለማግኘቱን በመጥቀስ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን በመጠየቁ ነው። በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ ወ/ሮ ህርይቲ ምህረት እና አቶ ወልደጊዮርጊስ አሰፋ እያንዳንዳቸው በ30 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ወስኗል። በተጨማሪም ዛሬ ችሎቱ በተመለከተው የክስ መዝገብ ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙት አቶ ስብሐት ነጋ፣ አቶ ሰሎሞን ኪዳኔ፣ ቅዱሳን ነጋና የሌሎችም ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በቀዳሚ ምርመራ እንዲታይ ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱን ጠይቋል። በዋስ ከእስር መለቀቃቸው የተገለጸው የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ እጃቸውን መስጠታቸው የተነገረ ሲሆን ከሦስት ወራት በላይ በአስር ላይ ቆይተዋል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ በትግራይ ከተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ጋር በተያያዘ የፌደራል ፖሊስና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በበርካታ የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣታቸው ይታወሳል። ለእስር ማዘዣውም ዋነኛ ምክንያቶቹ ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል በመፈጸም፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ በማድረግና በሌሎች ከባድ ወንጀሎች ተጠርጥረው መሆኑ ተገልጿል።
51218245
https://www.bbc.com/amharic/51218245
የአፍ መሸፈኛ ጭምብል ማጥለቅ ከቫይረስ ይታደገን ይሆን?
በቫይረስ የሚተላለፉ የትንፋሽ በሽታዎች ጉዳይ በተነሳ ቁጥር የአፍ ጭምብል ያጠለቁ ሰዎችን ፎቶ ማየት የተለመደ ነው።
የአፍ ጭንብሎች በትንፋሽ የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል ሁነኛ አማራጭ ናቸው፤ ታዋቂም ናቸው። ቻይናውያን በተለይ በነጯ ጭምብል ይታወቃሉ። ለበሽታ ብቻ ሳይሆን ለአየር ብክለት መከላከያም ጥቅም ላይ ይውላል። የተላላፊ በሽታ ባለሙያዎች ግን የአፍ ጭንብሎቹ ይህን ያህል ጠቃሚ አይደሉም ይላሉ። ነገር ግን ጭምብሎቹ ከእጅ ወደ አፍ የሚተላለፍ በሽታን ለመከላከል ጠቃሚ እንደሆኑ የሚያስረዱ ጥናቶች አሉ። በህክምናው አጠራር 'ሰርጂካል ማስክ' የሚል ስያሜ ያላቸው እኒህ ጭምበሎች ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት በ18ኛው ክፍለ ዘመን ነው። የስፔን ጉንፋን የሚል ስያሜ የተሰጠው ወረረሽኝ በፈረንጆቹ 1919 ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ሲቀጥፍ ነው ጭንብሎቹ በስፋት ጥቅም ላይ መዋል የጀመሩት። የሎንዶን ዩኒቨርሲቲው ዶ/ር ዴቪድ ካሪንግተን የአፍ ጭንብሎች አየር ላይ ያሉ ቫይረሶችንም ሆነ ባክቴሪያዎች ለመከላከል ሁነኛ አማራጭ ናቸው ብዬ አላስብም ይላሉ። ምንም ጥቅም የላቸውም ማለት ግን አይደለም ይላሉ ዶክተሩ። ከእጅ ወደ አፍ የሚተላለፍ በሽታን ከማገድ አልፎ በማስነጠስ ወቅት ወይም በሳል የሚተላለፍ ቫይረስን ሊገቱ ይችላሉ ባይ ናቸው። ጥናቶቹ አፍን በጭንብል ከማፈን በላይ በቫይረስ የሚተላለፉ የትንፋሽ በሽታዎችን ለመግታት እጅን በተደጋጋሚ በሳሙና መታጠብ ሁነኛ መላ ነው ይላሉ። አልፎም ዓይንና አፍንጫን በእጅ አለመነካካት ይመከራል። የአፍ ጭንብሎች በትክክል መደረግ አለባቸው፣ ቶሎ ቶሎ ሊቀየሩ ይገባል፣ በጥንቃቄ ማስወገደም ግድ ነው ሲሉ ባለሙያዎቹ ያስጠነቅቃሉ። በቅርቡ በቻይና የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ሰዎች የአፍ ጭንብል እንዲያዘወትሩ ምክንያት ሆኗል።
news-54885168
https://www.bbc.com/amharic/news-54885168
የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ አዲስ አይነት የአእምሮ ጤና እክል ይዞ መጥቷል ተባለ
በኮሮናቫይረስ ከሚያዙ ሰዎች በእያንዳንዱ 17 ሰው አንድ ሰው ከባድ ጭንቀት፣ ድብርት እና እንቅልፍ ማጣት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያጋጥመው አንድ አሜሪካ ውስጥ የተሰራ ጥናት ጠቁሟል።
ይህ ቁጥር ታዲያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸው እንዲህ አይነት የጤና እክል ከሌሎች በሽታዎች ጋር ሲነጻጸር እጥፍ እንደሆነ ደርሰንበታል ይላሉ ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች። በጥናቱ መሰረት ባልተጠበቀ ሁኔታ የቀደም የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በኮሮናቫይረስ የመያዝ እድላቸው ከጤናማ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር 65 በመቶ ከፍ ያለ እንደሆነ ደርሰንበታል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያትነት የተቀመጠው የአእምሮ ጤና ችግር ኣላባቸው ታማሚዎች ሰውነታቸው የሚገኝበት አካላዊ ጥንካሬ፣ የሚወስዷቸው መድሀኒቶችና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ናቸው። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑትና የጥናቱ መሪው ፖል ሀሪሰን እንደሚሉት ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ ለከባድ የአእምሮ ጤና እክል የመጋለጣቸው እድል አብሮ ይጨምራል። ''ሌላው ቀርቶ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጦ ነገር ግን ሆስፒታል ሳይሄዱ በቤታቸው የዳኑት እንኳን ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው'' ይላሉ። ተመራማሪዎቹ 62 ሺህ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ፈቃደኛ ሰዎችን ለሶስት ወራት ያክል ሲከታተሉ የነበረ ሲሆን ከእነሱ የሚያገኙትን መረጃ እንደ ጉንፋን፣ የኩላሊት ህመም እንዲሁም የአጥንት ስብራት ካጋጠማቸው ሰዎች ጋር አወዳድረውታል፥። በዚህም መሰረት በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች ከፍተኛ የአእምሮ ጤና መቃወስ ታይቶባቸዋል ተብሏል። በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች በከባድ ጭንቀት፣ ድብርት እና እንቅልፍ ማጣት የመጠቃት ዕድላቸው ከሌሎቹ አንጻር 18 በመቶ ከፍ ብሎ ታይቷል። እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች መጠራጠርን እና ፍርሃትን መቋቋም አለመቻል የተለመደ የአእምሮ ህመም ባህሪ እንደሆነ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። "ብዙ ጊዜ የጭንቀት ህመም ገና ባልተፈጠረና ባልታወቀ ነገር ላይ ይሆናል ብሎ አብዝቶ በመጨነቅ የሚመጣ ነው። ከዚህ አንፃር ኮሮናቫይረስ ከባድ ነገር ነው" ፕሮፌሰር ፖል ሀሪሰን አዲስ ነገር በሚያጋጥመን ጊዜ አዕምሯችን ለተፈጠረው ነገር በተለያየ መንገዶች ምላሽ ይሰጣል። በአሁኑ ወቅት መላውን ዓለም እያስጨነቀ ያለው ኮሮናቫይረስም በኑሯችን፣ በሥራችናና በአጠቃላይ ህይወታችን ላይ ከዚህ በፊት ያልነበረ ሁኔታን ፈጥሯል። በዚህም ሳቢያ አዕምሯችን ወረርሽኙን በተመለከተና ተያያዥ ነገሮችን በተለየ ሁኔታ ለመገንዘብ ተገዷል። ይህም ክስተት ነው በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ለተለያዩ የአእምሮ ጤና ችግሮች እያጋለጣቻው የሚገኘው። ሰዎች አይደለም እንዲህ ነገሮች ከበድ ባሉበት ወቅት አይደለም በደህናው ዘመን እንኳን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በአካል ማግኘት አስቸጋሪ ሲሆንና ሃሳብ ጭንቀታቸውን አይን አይናቸውን እያዩ ማካፈል ሳይችሉ ሲቀሩ ቀላል የማይባል ሥነ ልቦናዊ ጫና ይደርስባቸዋል።
news-57097406
https://www.bbc.com/amharic/news-57097406
በአማኑዔል ወንድሙ ግድያ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምላሽ
በያዝነው ሳምንት ግንቦት 3፣ 2013 ዓ.ም በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ አማኑኤል ወንድሙ የተባለ ወጣት በአደባባይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መገደሉን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የአካባቢው የመንግሥት ኃላፊዎች ወጣቱ ባለስልጣናትን በመግደል የሚታወቀው 'አባ ቶርቤ' የተባለ ህቡዕ አባል ቡድን ነው በማለት መገደሉን ቢያረጋግጡም ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ሲሉ አስተባብለዋል። የደምቢ ዶሎ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት እንዲሁ ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በሆነው ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ ሲልም በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል። የአማኑኤል ወንድሙን ግድያ በተመለከተ ቢቢሲ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻን የጠየቀ ሲሆን ኃላፊው በክልሉ ህዝብን እያሸበሩ ነው የሚሏቸው አካላት ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ በአፅንኦት ተናግረዋል። "በከተሞች ሰውን እየገደሉ ህዝብን ማሸበር የነሱ የእለት ተእለት ተግባር ነው። እነሱ የሚያደርጉት መግደል ነው። ሰላምን ለማስከበር የሚሄደው ኃይል እነዚህ አካላትን አጋልጦ እርምጃ ወስዶ ሊቆጣጠር ይገባል የሚል እምነት አለኝ። ስለዚህ የተወሰደው እርምጃ የትኛውም አይነት ይሁን ህዝብን አሸብሮ፣ አስፈራርቶ እቆጣጠራለሁ የሚለው ኃይል ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።" ብለዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ይህንን በተመለከተም አቅጣጫ ሰጥቶ እየሰራበት መሆኑንም በተጨማሪ ገልፀዋል። "ሰው በቤቱ፣ በቀዬው ነው እየተገደለ ያለው፤ በማያውቀው ነገር ነው እየሞተ ያለው፤ እንዲህ አይነት ተግባር በሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ እነሱ በሚፈፅሙት ልክ ተመጣጣኝ መሆን አለበት።" በማለትም ይናገራሉ። ነገር ግን አማኑኤል በአደባባይ ነው የተገደለው ስለሚባለው ጉዳይ ""ወጣቱ የደምቢ ዶሎ ነዋሪ አደባባይ ላይ ነው የተገደለው ስለሚባለው ነገር ግን መረጃ የለኝም" ብለዋል። የቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ በበኩላቸው ወጣቱ ቆስሎ ከተያዘ በኋላ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ይላሉ። "ተጠርጣሪ አይደለም" የሚሉት አቶ ተሰማ፤ ይህ ወጣት ሁለት ሰዎች በጥይት መትቶ እያመለጠ ሳለ በፀጥታ ኃይሎች በጥይት ተመትቶ መያዙን ይናገራሉ። የደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑት እና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ ግለሰብ ወጣቱ በአደባባይ ሲገደል ማየታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አማኑኤል ሕዝብ የሚወደው ልጅ ነበር" ካሉ በኋላ፤ በጥይት ተመትቶ ከተያዘ በኋላ "ሲገደል በዓይናችን አይተናል" ብለዋል። እኚህ ነዋሪ እንደሚሉት ከሆነ የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ አካላት ወጣቱ ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ወጣቱ ከአንድ ሱቅ እቃ እየገዛ ነበር ይላሉ። የአማኑኤል ወንድሙ ግድያን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያና (extrajudicial killing) በአደባባይ ለህዝብ እንዲታይ የተደረገበት መንገድ እንዳሳሰበው ትናንትና ግንቦት 4/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኮሚሽኑ ማንኛውንም ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎችን የሚያወግዝ መሆኑን አስታውቆ ሁሉም የሕግ አስፈፃሚ አካላት ሕጋዊ መንገዶች ብቻ አንዲተገብሩ መልዕክቱን አስተላልፏል። የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ እናንተ ክልሉን እያስተዳደራችሁ እንዴት የወጣቱን የአደባባይ ግድያ አናውቅም ትላላችሁ? ተብለው ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ የ ክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ወንጅለዋል። "የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሁልጊዜ የክልሉን ስም ለማጥፋት ስለሚሰራ እነሱ ያላቸው መረጃ እኔ የለኝም። እነሱ ሄደው አይተው ነው ወይስ ከማህበራዊ ሚዲያ ያገኙትን ይዘው ነው ይህንን መግለጫ ያወጡት?" በማለት የሚጠይቁት አቶ ጌታቸው አክለውም "ይህ መጣራት አለበት። በማስረጃ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። ማን ምን አደረገ የሚለውን ነገር ሳይቀበሉ እንዲሁ ሆነ ብሎ ከአንድ ወገን ብቻ መረጃ ይዞ ማውራት ተቀባይነት የለውም። ለሰብዓዊ መብት ነው የምሰራው የሚል ተቋም ጉዳዩን መዘገብ ያለበት በአካል ተገኝቶ ነው። የሚጠየቅም አካል ካለ እርምጃ ሊወሰድ የሚችለው መረጃው ሙሉ ሲሆን ነው።" ይላሉ ኮሚሽኑ በበኩሉ "ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎች ህዝቦች በሕግ የበላይነት ላይ ዕምነት እንዲያጡ እና በዚህ ረገድ የተገኙ ስኬቶች እንዲቀለበሱ ያደርጋሉ" ከማለት በተጨማሪ ባለሥልጣናት ጉዳዩን በአፋጣኝ እንዲመረምሩ እና ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጠይቋል። ከዚህ ቀደምም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ያለው የእስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንዳሳሰበው መግለፁ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን በሕግ ከመዳኘት ይልቅ የፖለቲካ (የአስተዳደራዊ) ውሳኔዎች ሰለባ እንዲሆኑ ተድርጓል ብሎ ነበር። ከሰሞኑ የወጣው ቪዲዮ ምንን ያሳያል? በዚህ የፌስቡክ ገጽ ላይ ወጣቱ ከመገደሉ በፊት ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥ ይታያል። ቪዲዮን እየቀረጸ የሚገኘው ሰው የወጣቱን ስም እና የትውልድ ስፍራውን ይጠይቀዋል። እጁ ወደ ኋላ የታሰረው ወጣት አንገቱ ላይ ሽጉጥ ተንጠልጥሎ ይታያል። በወጣቱ እግር ላይ እና በዙሪያው ደም የሚታይ ሲሆን ልብሱም በጭቃ ተለውሷል። አደባባይ ፊትለፊት የቆመው ወጣት ስሙ አማኑኤል ወንድሙ ከበደ እንደሚባል እና ትውልዱ ደምቢ ዶሎ ከተማ 07 ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሆነ ይናገራል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎ ተከቦ ይታያል። ስለ ግድያው የአካባቢው ባለስልጣናት ምን አሉ? የከተማው ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት እንደሚለው ከሆነ ይህ ወጣት የመንግሥት ባለስልጣናትን በመግደል የሚታወቀው "አባ ቶርቤ' የተሰኘው ህቡዕ ቡድን አባል ነበር። ወጣቱ ትናንት በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊትም ንጋት ላይ ገመቹ መንገሻ የተባለ ግለሰብ በጥይት መትቶ ለማምለጥ ሲሞክር "በጸጥታ ኃይሎች ጠንካራ ትስስር እግሩን ተመትቶ ተይዟል" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከቀናት በፊት በደምቢዶሎ ከተማ የኦሮሚያ ብሮድካስቲን ኔትዎርክ ጋዜጠኛ የነበረውን ሲሳይ ፊዳ የገደለው የአባ ቶርቤ ቡድን ነው ሲል አክሏል። አቶ ተሰማ በደምቢዶሎ አካባቢ ከሰሞኑ በኦነግ ሸኔ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ተናግረው፤ ወጣቱ አንገት ላይ የተንጠለጠለው ሽጉጥ ንጹሃን ዜጎችን እና የመንግሥት ኃይሎችን ሲገድልበት የነበረ ነው ብለዋል። ቢቢሲ የዞኑ ፖሊስ ባልደረቦችን አነጋግሮ ያገኘው ምላሽ አቶ ተሰማ ከሰጡት አስተያየት ጋር ተመሳሳይ ነው።
55825418
https://www.bbc.com/amharic/55825418
ኖቫቫክስ የተሰኘ አዲስ የኮቪድ ክትባት ተገኘ
በብሪታኒያ በሙከራ ላይ የነበረው ኖቫቫክስ ክትባት ስኬታማነቱ ተረጋገጠ። ክትባቱ በሦስተኛ ደረጃ የሙከራ ሂደት ይበል የሚያሰኝ ውጤት ተገኝቶበታል።
ይህ ክትባት በበርካታ ሰዎች ላይ ተሞክሮ 89.3 በመቶ ፈዋሽነቱ በመረጋገጡ ትልቅ የምሥራች ሆኗል። ይበልጥ አስደሳች የሆነው ደግሞ ይህ ክትባት አዲስ ዝርያ ነው ለተባለው የኮቪድ ዓይነትም አይበገሬነቱን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ማረጋገጥ መቻሉ ነው። የታላቋ ብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የምሥራቹን በደስታ ተቀብለውታል። የአገሪቱ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣንም አሁን ክትባቱን ወስዶ በመመርመር የመጨረሻ ፍቃድ መስጠት ይችላል ብለዋል። ታላቋ ብሪታኒያ ይህን በሙከራ ላይ የነበረን ክትባት 60 ሚሊዮን ጠብታዎችን ቀደም ብላ አዝዛለች። አሁን በእንግሊዝ በሚገኘው ፋብሪካ ወደ ምርት ሥራ ለመግባት በመጨረሻ ዝግጅት ላይ ነው ይገኛል። 60 ሚሊዮን ጠብታዎች ምርት በዚህ የፈረንጆች ዓመት አጋማሽ ለሕዝብ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በኋላ የሚቀረው የመጨረሻ ሥራ የብሪታኒያ የመድኃኒትና የጤና ምርቶች ቁጥጥር ኤጀንሲ ክትባቱን በይፋ አገልግሎት ላይ እንዲውል ፈቃድ የመስጠት ሒደት ነው። ታላቋ ብሪታኒያ እስከ አሁን ሦስት የኮቪድ ክትባቶችን ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት እንዲውሉ ፈቅዳለች። እነዚህም የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲና አስትራዜኔካ ያመረቱትና በአጭሩ አስትራዜኔካ ተብሎ የሚጠራው አንዱ ሲሆን የፋይዘርና ባዮንቴክ ሁለተኛው እንዲሁም ሞደርና ሦስተኛው ነው። የኖቫቫክስ ክትባት በኤጀንሲው በይፋ ፍቃድ ሲያገኝ አራተኛው የኮቪድ ክትባት ሆኖ ይመዘገባል። ኖቫቫክስ በዚህ የመጨረሻ ምዕራፍ ሙከራው 15ሺ ሰዎችን ያሳተፈ ሲሆን ኮቪድን በመከላከል ረገድ 89.3% ውጤት አስመዝግቧል። ሙከራ የተደረገባቸው 15ሺ ሰዎች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 84 ነው። ከእነሱ ውስጥ ደግሞ 27 እጅ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ65 በላይ ነበር። የደቡብ አፍሪካ ዘርያ እየተባለ የሚጠራውና በገዳይነቱም በተዛማችነቱም የሚፈራው የኮቪድ ዝርያን በመከላከል ረገድ ኖቫቫክስ 60 እጅ ተከላካይ ሆኖ መገኘቱም ተነግሯል። ይህም ኤች አይ ቪ በሌለባቸው ሰዎች ላይ የተገኘ ውጤት ነው። የኖቫቫክስ ኃላፊ ስታን ኤሪክ ዜናው እንደጠበቅነው አስደሳች ነው፤ በደቡብ አፍሪካው ዝርያ የተገኘው ውጤት ደግሞ ብዙ ሰው ከጠበቀው በላይ ነው ብለዋል። ሚስተር ኤሪክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ይህን ክትባት የማምረቱ ሥራ በመጋቢትና ሚያዝያ ወር ይጀምራል ብለዋል። ምርቱን በመድኃኒትና በጤና ምርቶች ቁጥጥር ባለሥልጣን ክትባቱ መጽደቁን ተከትሎ ወዲያውኑ የሚጀመር ነው ብለዋል። የጤና ሚኒስትሩ ማት ሐንኩክ የአገሪቱ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት (ኤን ኤች ኤስ) ለዚህ ክትባት መጀመር በተጠንቀቅ ላይ ነው ብለዋል፤ ሐንኮክ 'ይህ መልካም ዜና ነው፤ ለክትባት ዘመቻው ትልቅ አቅም ይፈጥራል' ብለዋል። የጤና ሚኒስትሩ ኖቫቫክስን ላገኙ ሳይንቲስቶች ያላቸውን ክብር ገልጠውም አመስግነዋቸዋል። በክትባቱ ሙከራ በበጎ ፈቃድ ለተሳተፉትም ትልቅ ክብር አለኝ ብለዋል። ታላቋ ብሪታኒያ በተህዋሲው የሞቱባት ዜጎች ቁጥር ከመቶ ሺህ በላይ ነው። ሆኖም በከፍተኛ ፍጥነት ለዜጎቿ ክትባት በመስጠት ላይ ትገኛለች።
44800179
https://www.bbc.com/amharic/44800179
ለሀያ ዓመታት ያልተነጋገሩት ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ ቤተሰቦች
ሺሻይ ወረስ እባላለሁ። ብዙዎች ግን ወዲ ትሩንጒ እያሉ ነው የሚጠሩኝ።
እናቴ አምስት ልጆች ወልዳለች። ሶስት ሴትና ሁለት ወንዶች። ሁሉም ኤርትራ ውስጥ ናቸው። ሁለቱ ሲደውሉልኝ የተለየ ስሜት ወረረኝ። ለሃያ ዓመታት ያህል ተገናኝተን አናውቅም። ኤርትራ ውስጥ ያለ በኩር ወንድሜ ሶስት ልጆችን እናቴ አገር ልታሳያቸው ወደ ኢትዮጵያ ይዛቸው መጥታ ነበር። በዚያው ሶስቱ ልጆቹን ለሃያ ዓመታት ያህል ሳያያቸው ነው ያደጉት። የስልክ መስመር ክፍት የተደረገ እለት ማታ 2፡40 አከባቢ መፅሃፍ እያነበብኩ ነበር። የመጀምርያው ጥሪ ሳላነሳው ተዘጋ። የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? ድጋሚ ተደወለና አነሳሁት፡ "ሄሎ" አለችኝ "ማን ልበል" አልኳት። መጀመሪያ የጋዜጠኛድምፅ ነበር የመሰለኝ። "ፍርቱና ነኝ ከአስመራ" ስትለኝ ልቤ ቆመ። ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ። ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች ምን እንደ ምላት ጠፋኝ። መስመሩም ይቆራረጥ ነበር። በኋላ እየተሻሻለ መጣ፡ እኔም ተረጋግቼ ማነጋገር ቀጠልኩ። ወንድሜንም አቀረበችልኝ። በኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ስምምነት ሦስተኛ ወገን አልተሳተፈበትም ተባለ "በቀጥታ ከአስመራ ነው ምትደውይው ?" ስል ጠየቅኳት። "አዎ" "በአካል እስክንገናኝ ድረስ እንኳን በስልክ ድምፅህን ሰማሁ።" በዛች ቅፅበት ምን እንደተሰማኝ አላውቅም። በቃ የተለየ ስሜት ሰውነቴን ወረረኝ። ያኔ እድሜዋ 44 የነበረው እናቴ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ "ልጆቼን ሳላያቸው ልሞት ነው ትል"ነበር። የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? አሁን ግን ደስታዋ ከልክ በላይ ሆኗል።
news-54336116
https://www.bbc.com/amharic/news-54336116
ኮሮናቫይረስ፡ ዓለም አቀፉ የኮሮናቫይረስ ሟቾች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በለጠ
የዓለም ስጋት ሆኖ በቀጠለው ኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሆኗል። በተለያዩ አገራትም ወረርሽኙ እንደ አዲስ እያገረሸም ነው ተብሏል።
በሞት ቀዳሚ የሆኑት አሜሪካ፣ ብራዚልና ህንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የሞቱትን ግማሽ እንደሚይዙ ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም የላቀ እንደሆነ በዘርፉ ያሉ ልሂቃን ይናገራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቁጥሩን "አስደንጋጭ" ነው ያሉ ሲሆን "በቫይረሱ ህይወታቸውን የተነጠቁት አባቶች፣ እናቶች፣ ሚስቶች፣ ባሎች፣ እህቶች፣ ወንድሞችና የስራ ባልደረቦች ነበሩ። ሁልጊዜም ቢሆን ልናስታውሳቸው ይገባል" በማለትም በቪዲዮ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የኮሮናቫይረስ በቻይናዋ ግዛት ውሃን ከአስር ወራት በፊት ተነስቶ ዓለምን አጥለቅልቋል። በአሁኑ ወቅት በ188 አገራት የኮሮናቫይረስ ሪፖርት የተደረገ ሲሆን 32 ሚሊዮን ህዝብም ተይዟል። አገራት የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመግታት ያወጧቸው መመሪያዎችም በርካቶችን ሥራ አልባ አድርጓል፤ ምጣኔ ኃብቱን አሽመድምዷል። በዚህም ሁኔታ አገራትም ሆነ የምርምር ማዕከላት የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለማምረት እየተሽቀዳደሙና እየተሯሯጡ ቢሆንም ክትባቱ ከመገኘቱ በፊት የሟቾቹ ቁጥር 2 ሚሊዮን እንደሚደርስም የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ 240 የሚሆኑ ክትባቶች ምርምር እየተደረገባቸው ሲሆን 40 የሚሆኑትም በክሊኒካል ሙከራ አሉ። ዘጠኝ ያህል ክትባቶች ደግሞ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ሙከራ እየተደረገባቸውና መጨረሻ ደረጃ ላይ ናቸው። ክትባቶችን ለማምረትና ለሰዎችም ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲሰጥ ለማድረግ አመታት ቢፈጅም ባለው የወረርሽኙ ጊዜ የማይሰጥና አጣዳፊ መሆን ሳይንቲስቶች ቀን ተሌት ሳይሉ እየተጣደፉም ይገኛሉ። በዓለም ላይ አሜሪካ በቫይረሱ በተያዙም ሰዎች ቁጥርም ሆነ በሟቾች ቀዳሚ ስትሆን 205 ሺህ ዜጎቿንም ተነጥቃለች። በመቀጠልም ብራዚል 141 ሺህ 700 ሰዎች በቫይረሱ ሲሞቱ በህንድ ደግሞ 95 ሺህ 500 ሰዎች ህይወታቸው በቫይረሱ አልፏል።
news-53511867
https://www.bbc.com/amharic/news-53511867
ለሳምንታት የተቋረጠው ኢንተርኔት አገልግሎት ተመለሰ
በተወሰኑ የአገሪቱ አካባቢዎች የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ ከሦስት ሳምንታት በላይ ተዘግቶ የቆየው የሞባይል ኢንትርኔት አግልግሎት መመለሱ ተነገረ።
የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተከሰተው አለመረጋጋት ሳቢያ የኢትዮጵያ መንግሥት የመደበኛና የሞባይል ኢንትርኔት አገልግሎቶችን በመላዋ አገሪቱ እንዲቋረጥ አድርጎ መቆየቱ ይታወሳል። ቢቢሲ ዛሬ ረፋድ ከአዲስ አበባ ባሻገር ወደተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በመደወል ከነዋሪዎች ለማጣራት እንደሞከረው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ነገር ግን አገልግሎቱ በመላው አገሪቱ እንደተመለሰ ለማረጋገጥ አልቻለም። ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የዋይፋይ የኢንተርኔት አገልግሎት መመለሱ ይታወቃል። በርካታ ተጠቃሚ ያለው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ደግሞ ዛሬ ሐሙስ በበርካታ ስፍራዎች ላይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ እንደዋነኛ ምክንያት የጠቀሰው አንዳንድ ወገኖች ግጭትና አለመረጋጋትን የሚያባብሱ የጥላቻ መልዕክቶችን ለማሰራጨት እየተጠቀሙበት መሆኑን ነው። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የሆኑት ቢልለኔ ስዩም በወቅቱ ለቢቢሲ እንዳሉት የኢንተርኔት አገልግሎት የብሔር ጥላቻን ለማስፋፋት ጥቅም ላይ በመዋሉ መንግሥት አገሪቱንና ሕዝቡን የመጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት ለማቋረጥ መገደዱን ተናግረዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ዛዲግ አብረሃ በበኩላቸው ኢንተርኔት በአንዳንድ ወገኖች ለጥላቻ ንግግር ማሰራጫ መሳሪያ እንደተደረገ ጠቅሰዋል፤ በብሔሮችና በሐይማኖቶች መካከል ግጭቶች እንዲቀሰቀስ መሳሪያ በመሆኑ እንዲቋረጥ መደረጉን አመልክተዋል። ጨምረውም "መምረጥ የነበረብን ከመረጃ ነጻ ፍሰትንና የሕዝባችን ህይወት ከመካከል ነበር፤ በዚህም ለሰው ልጅ ሕይወት ቅድሚያ ሰጥተናል" ብለው የተወሰደው እርምጃ የዜጎችን ደኅንነት ከመጠበቅ አንጻር መሆኑን አመልክተዋል። የአገሪቱ ባለስልጣናት የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጣቸው ከተለያዩ ወገኖች ትችትና ወቀሳ ሲቀርብባቸው የሰነበተ ሲሆን፤ በምላሻቸው የነበረው አለመረጋጋት ወደነበረበት ሲመለስ የኢንተርኔት አገልግሎቱ እንደሚቀጥል ገልጸው ነበር። እነሆ ባለፈው ሳምንት የዋይፋይ አግልግሎት ዛሬ ደግሞ የሞባይል ዳታ የኢንርተኔት አገልግሎት በበርካታ ቦታዎች ላይ ወደ ሥራ መመለሱ ተነግሯል። የእለት ከዕለት ሥራቸው ኢንተርኔትን መሰረት ያደረጉ በርካታ ተቋማት ባለፉት ሦስት ሳምንታት ከፍተኛ መጠን ያለው ገቢ ማጣታቸውን እየገለጹ ነው። ከዚህ በፊት በአገሪቱ ተቋርጦ የነበረውን የኢንተርኔት አገልግሎት በማስመልከት 'ኔትብሎክስ' የተሰኘው የኢንተርኔት አገልግሎት ጥናት ቡድን ለቢቢሲ እንደተናገረው በኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት አገሪቱ በቀን በትንሹ 4.5 ሚሊየን ዶላር ታጣለች ይህ የገንዘብ መጠን ዝቅተኛው ግምት እንደሆነም ተገልጿል። ከዚህ አንጻር ባለፉት ሳምንታት ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ መጠን የሚታጣ ሲሆን ኢንተርኔትን መሰረት ያደረጉ በርካታ ሥራዎች መስተጓጎል እንደገጠማቸው ይገመታል። ባለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በመላው አገሪቱና በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ሰበብ ከ10 ጊዜ በላይ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ይታወሳል።
48041954
https://www.bbc.com/amharic/48041954
በ737 ማክስ አውሮፕላኖች ሳቢያ ቦይንግ ትርፋማነቱ እንደቀነሰ አስታወቀ
ቦይንግ በ2019 የመጀመሪያ ሶስት ወራት 737 ማክስ አውሮፕላኖቹን ማስረከብ ባለመቻሉ የትርፍ መጠኑ 20 በመቶ መቀነሱን ይፋ አደረገ።
የአሜሪካ አውሮፕላን አምራች ኩባንያው በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ያቀደውን ያክል የትርፍ መጠን ማሳካት እንደማይችልም ከወዲሁ ይፋ አስታውቋል። የቦይንግ ምርት የሆኑት 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዢያ ያደረሱትን አደጋ ተከትሎ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በረራ እንዳያደርጉ መታገዳቸው ይታወሳል። ቦይንግ ከአውሮፕላኖቹ ጋር በተያያዘ ጥርት ያለ ሙሉ መረጃ ሲኖረኝ የገበያ ድርሻዬን በተመለከተ መረጃዎችን ይፋ አደርጋለሁ ብሏል። ቦይንግ በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዥያ ለደረሱት አደጋዎች ምክንያት ነው የተባለውን የበረራ መቆጣጠሪያ ስርዓት አሻሽላለሁ ቢልም ማሻሻያው እስኪደረግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች አሁንም ከሰማይ እንዲርቁ ተደርገዋል። • ቦይንግ የአደጋውን የምርመራ ውጤት ተቀበለ • ቦይንግ "ችግሩ ተፈቷል" እያለ ነው • ቦይንግ ተከሰሰ፤ ሰለአደጋው ተጨማሪ መረጃዎች እየወጡ ነው በሁለቱ የአውሮፕላን አደጋዎች 346 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። የኢቲ 302 የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ የቦይንግ ከፍተኛ ኃላፊዎች የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን እንደሚቀበሉት መግለጻቸውም የሚታወስ ነው። የቦይንግ ኩባንያ ሊቀመንበር፣ ፕሬዚደንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዴኒስ ሚሌንበርግ '' . . . የኢቲ 302 የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንዳሳየው እንደ ከዚህ ቀደሙ [ላየን ኤየር] ኤምካስ የተሰኘው ሶፍትዌር በተሳሳተ መረጃ 'አክቲቬትድ' (ሥራውን እንዲጀምር) ሆኖ ነበር'' ማለታቸው ይታወሳል። ቦይንግ በ737 ማክስ አውሮፕላኖቹ ኪሳራ ቢገጥመውም፤ ለጦር አገልግሎት ከሚውሉ ምርቶቹ ግን ትርፍ ማግኘት መቀጠሉ ተነግሯል።
45089136
https://www.bbc.com/amharic/45089136
አብዲ ሞሃመድ ኡመር ከስልጣናቸው ወረዱ
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዲ ሞሃመድ ኡመር ከስልጣናቸው መነሳታቸውን የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ኢድሪስ ኢስማኤል ለቢቢሲ ሶማልኛ አረጋግጠዋል።
ከኢድሪስ ኢስማኤል መረዳት እንደተቻለው፤ አብዲ ሞሃመድ ኡመር ከክልሉ ፕሬዚዳንትነታቸው ይነሱ እንጂ የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪ ሆነው ይቆያሉ። ኢድሪስ ኢስማኤል ጨምረው እንደተናገሩት አህመድ አብዲ ሞሃመድ የቀድሞውን ፕሬዝደንት በመተካት ተሹመዋል። አቶ አብዲ ስለተናገሩት ጉዳይ እንደማያውቅ ኢህአዴግ ገለፀ በሶማሌ ክልል ከ10 የሚበልጡ አብያተ ክርስትያናት ጥቃት ደረሰባቸው አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት አህመድ አብዲ ሞሃመድ አዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አህመድ አብዲ ሞሃመድ የሶማሌ ክልል ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ በመሆን አገልግለዋል። አህመድ አብዲ ሞሃመድ አመሻሹን ከቢቢሲ ሶማልኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን አስረክበው በሰላም የስልጣን ሽግግር መካሄዱን ተናግረዋል። አህመድ አብዲ ሞሃመድ ''አብዲ ሞሃመድ ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የክልሉ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዲስ መሪ መርጧል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ጂግጂጋ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ'' ሲሉም ተደምጠዋል። ከቅዳሜ አንስቶ በጂግጂጋ እና በክልሉ ሌሎች ከተሞች የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደ ክልሉ ገብቶ ሰላም እንዲያስከብር መታዘዙ ከሰዓታት በፊት ይፋ ተደርጎ ነበር። መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ሶማሌ ክልል ገብቶ ሰላም እንዲያስከብር ታዘዘ በጅግጅጋ ግጭት ሸሽተው የተሸሸጉ ሰዎች በከፋ ችግር ላይ ናቸው ተባለ በሶማሌ ክልል በተከሰተ ቀውስ ህይወት ሲጠፋ አብያተ-ክርስትያናት ተቃጠሉ በስፋት ''አብዲ ኢሌ'' በመባል የሚታወቁት አብዲ ሞሃመድ ኡመር ስልጣን በፍቃዳቸው ወይም ተገደው ስለመልቀቃቸው የታወቀ ነገር የለም። ባለፉት ሶስት ቀናት በክልሉ በተከሰተው ሁከት የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረት መውደሙም ተነግሯል።
49625537
https://www.bbc.com/amharic/49625537
ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ድልድሉን ተቀላቀለች
በ2022 ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ተካሂደዋል።
ከቀናት በፊት በባህር ዳር ስታዲየም ከሌሴቶ አቻዋ ጋር ያለምንም ግብ የተለያየችው ኢትዮጵያ፤ የመልስ ጨዋታዋን በሌሴቶ አድርጋ አንድ አቻ ተለያይታለች። ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ህግ መሰረትም ወደቀጣዩ ዙር በማለፍ የምድብ ድልድል ውስጥ መግባቷን አረጋግጣለች። ሃያ ተጫዋቾችን ይዘው ወደ ሌሴቶ ያቀኑት አሰልጣኝ አብራሃም መብራቱ በተቻለ መጠን አጥቅቶ በመጫወት ከሜዳቸው ውጪ ግብ ለማስቆጠር እንደሚጥሩ ገልጸው ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተጠንቅቀው የተጫወቱ ሲሆን ዋልያዎቹ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ነበራቸው። ነገር ግን ብዙም የግብ ዕድሎችን መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። በአንጻሩ ሁለተኛው አጋማሽ ፈጣንና ብዙ የግብ ሙከራዎች የታዩበት ነበር። 50ኛው ደቂቃ ላይ በቀኝ መስመር የሚጫወተው ቢንያም በላይ ያሻማውን ኳስ የሌሴቶው ንካይ ኔትሮሊ ሲመልሰው ኳሷ አቅጣጫዋን ቀይራ በራሱ መረብ ላይ ግብ አስቆጥሮ ኢትዮጵያ መምራት ጀመረች። ነገር ግን ከአምስት ደቆቃዎች በኋላ ሌሴቶዎች አቻ የምታደርጋቸውን ግብ በሴፖ ሴትሩማንግ አማካይነት ማግኘት ችለዋል። ጨዋታው በዚሁ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ቢጠናቀቅም ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ አሥመራ ላይ ናሚቢያን አስተናግዳ በደጋፊዎቿ ፊት 2ለ1 የተሸነፈችው ኤርትራ ደግሞ የመልስ ጨዋታዋን የፊታችን ማክሰኞ ዊንድሆክ ላይ ታደርጋለች። • ሳሙኤል ኤቶ እግር ኳስ ሊያቆም ነው • 'አምብሮ' ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የአቅርቦት ውል ተፈራረመ ባለፈው ሐሙስ 1ለ0 በሆነ ጠባብ ውጤት ዚምባብዌን በማሸነፍ አስደናቂ ድል ያስመዘገቡት የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች፤ ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ የፊታችን ማክሰኞ ወደ ሃራሬ ያቀናሉ። በሌላ በኩል ከአርብ ጀምሮ የአውሮፓ ቻምፒየንሺፕ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተከሂደዋል። በዚህም መሰረት ሆላንድ ጀርመንን 4 ለ2 በማሸነፍ ጥሩ አጀማመር ያደረገች ሲሆን ቤልጂየም ሳን ማሪኖን 4 ለምንም አሸንፋለች። ክሮሺያም በተመሳሳይ ስሎቫኪያን 4 ለምንም ፤ አውስትራሊያ ደግሞ ላቲቪያን 6 ለባዶ ረምርማለች። ቅዳሜ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ እንግሊዝ ቡልጋሪያን 4 ለምንም፣ ፖርቹጋል ሰርቢያን 4 ለ2 እንዲሁም ፈረንሳይ አልባኒያን 4 ለ1 ማሸነፍ ችለዋል። ዕሁድ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ጣልያን ፊንላንድን 2 ለ1 ፣ ስፔን ፋሮ አይላንድስን 4 ለምንም ሲያሸንፉ ጆርጂያና ዴንማርክ 0 ለ0 እንዲሁም ስዊድን እና ኖርዌይ 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
43972246
https://www.bbc.com/amharic/43972246
ወደ ድብቁ የዋትስአፕ መንደር ስንዘልቅ
ጋዜጠኛ ጆሴፍ ዋሩንጉ ብዙ አባላት ያላቸው የዋትስአፕ ቡድኖች አስተዳዳሪዎች ትክክለኛ ማንነታቸው ምን እንደሚመስል ያስቃኘናል።
በቅርቡ ኬንያ ውስጥ በምትገኘው የትውልድ አካባቢዬ የልማት ሥራዎችን ለማስተባበር ተብሎ የተመሠረተ የዋትስአፕ ቡድን አስተዳዳሪ እንድሆን ተመረጥኩ ይላል ጆሴፍ። ወዲያው አባላትን ከቡደኑ ማስወጣትና ማስገባት ቀላል ሥራ ሆነልኝ የሚለው ጆሴፍ፤ የቡድኑን እንቅስቃሴ በመከታተልና በመቆጣጠር ብቻ ብዙ እንቅልፍ አልባ ምሽቶችን ማሳለፍ ጀመረ። "ስልጣን እንደዚህ እንደሚጣፍጥ አላውቅም ነበር፤ የመረጃ ሚኒስትር መሆን እንደዚህ ነው ማለት ነው?'' ይላል ጆሴፍ። ዋትስአፕ ተግባቦታችንን እና ማህበራዊ ግንኙነታችንን በአስገራሚ ሁኔታ ቀይሮታል። ጥሩ የዜና ምንጭ ነው። የመጥፎውም፣ የጥሩውም እንዲሁም የውሸቱ። የብዙ ሰዎችን ግንኙነትም አበላሽቷል። እኔ አባል በሆንኩበት አንድ የጋዜጠኞች የዋትስአፕ ቡድን ውስጥ የማንኛውንም ኬንያዊ ስልክ ማግኘት ሰከንዶችን ብቻ ነው የሚፈጀው። የተለያዩ የንግድ ፈጠራ ሃሳቦችን ከሚያንሸራሽሩት እስከ ፖለቲካ፤ ቀልድ እና ኃይማኖት የማይፈቀድባቸው ቡድኖች በናይሮቢ የሚስተዋሉ የዋትስአፕ እቅስቃሴዎች ናቸው። 'ዋትስአፕ ሕይወትን ለማዳን' በቅርቡ አንድ ኬንያዊ ጓደኛዬ ለአስቸኳይ ሕክምና ወደ ሕንድ ለመጓዝ በቂ ገንዘብ ስላልነበረው፤ በዋትስአፕ በተደረገለት ዘመቻ፤ በሁለት ቀን ውስጥ ብቻ 20ሺህ ዶላር ማሰባሰብ ችሎ ነበር። አንድ በጋና የሚገኝ ጓደኛዬ እንደነገረኝ ከሆነ፤ እሱ አባል የሆነበት ብዙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች የሚገኙበት የዋትስአፕ ቡድን ውስጥ አንዱ አባል እራሱን ሊያጠፋ እንደሆነ የሚገልጽ ረዥም መልዕክት ጽፎ ነበር። የቡድኑ አባላትም በፍጥነት በመሰባሰብ የእርዳታ እጃቸውን ለዚህ ወጣት ለመዘርጋት ይጣደፋሉ። በሚያሳዝን ሁኔታ እርዳታው ሳይደርስለት በፊት እራሱን አጠፋ። ይህ ቡድንም ለሞተው አባል ማስታወሻ እንዲሆን የቡድኑን ተልዕኮ ወደ ግንዘቤ ማስጨበጥ ለውጠው መንቀሳቀስ ጀመሩ። ከእራሴ እና ከሌሎች ልምድ በመነሳት ስድስት ዓይነት የተለያዩ የዋትስአፕ ቡድን አስተዳዳሪዎችን መለየት ችያለሁ ይላል ጆሴፍ። 1: አምባገነኖቹ እነዚህ ስልጣን የተጠሙ ናቸው። ማንም አልመረጣቸውም ግን ሁሉም አባል ይፈራቸዋል። ቡድኑን እንደራሳቸው የግል ንብረት ነው የሚቆጣጠሩት። ከእነሱ ፍላጎት ጋር የማይስማማ ማንኛውም ዓይነት ሃሳብ ከፍተኛ ትችትና ውግዘት ይደርስበታል። ማንም ሰው ቡድኑን እንዳይለቅ ያደርጋሉ። በእራሱ ቢለቅ እንኳን መልሰው ያስገቡታል። የቁም እስር እንደማለት ነው። 2: አስተጋቢዎቹ እነዚህ ደግሞ የእራሳቸውን ድምፅ ማስተጋባት የሚወዱት አስተዳዳሪዎች ናቸው። እንደዚህ ዓይነት አስተዳዳሪዎች ያለባቸው ቡደኖች ብዙ አባላት የሏቸውም። ሌላኛው እኔ አባል የሆንኩበት የዋትስአፕ ቡድን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ ነው። ብዙዎቹ አባላትም ቡድኑን ለቀው ወጥተዋል። ግን ሁሌም ቢሆን የቡድኑ አስተዳዳሪ እንደምን አደራቸችሁ አባላት እያለ መልዕክት ያስቀምጣል። ማንም አባል ግን መልስ አይሰጥም። 3: የማፍያ መሪዎች እነዚህን እንኳን እንደ አስተዳዳሪ ለመውሰድ ይከብዳል። ግን ከመሥራቾቹ በስተጀርባ ሆነው ብዙ ነገር ይቆጣጠራሉ። በቡድኑ ውስጥ ግንኙነቶች ምን መምሰል እንዳለባቸው ሕግ እና ደንብ ያወጣሉ። ማን አባል መሆን አለበት ማንስ መሆን የለበትም የሚለውን ውሳኔ ይሰጣሉ። የእነርሱ ፍላጎት ሲነካ ሁሌም ቢሆን ፈጣን ምላሽ ይሰጣሉ። 4: የአማፂያን መሪዎች እነዚህ መሪዎች አስተዳዳሪ መሆናቸውን የረሱ ዓይነት ናቸው። ሁሌም አስደንጋጭ እና አነጋገሪ ምስሎችን ለቡድኑ ለማጋራት የመጀመሪያዎቹ ናቸው። ብዙም ተሳትፎ የማያደርጉ አባላት ላይ ሁሌም አመፅ የሚያስነሱ እንዲሁም የቡድኑ ዋልታ እና ማገር መሆን የሚፈልጉ ናቸው። 5: ሁሉንም አስደሳቾች የአምባገነኖቹ ተቃራኒ ናቸው። ሁሉንም ያበረታታሉ። በቡድኑ አስተዳዳሪነት ኃላፊነታቸው ውስጥ ነገሮችን ችላ በማለት ማሳለፍ ይመርጣሉ። ስለዚህ ብዙ ጊዜ ቡድኑ የተረባበሸ እና ሕጎች የማይከበሩበት እንዲሁም ማንም ሕጎቹን ለማስከብር የማይንቀሳቀስበት ነው። 6: ሥነ-ጽሑፍ አስተማሪዎቹ እነዚህ ደግሞ ያለቦታቸው የተቀመጡ አስተማሪዎች ናቸው። ማንኛውንም የሥነ- ጽሑፍ ስህተት መለየት እና መሳለቅ ይወዳሉ። እንደዚህ ዓይነት የሥነ-ጽሑፍ ስህተት የሚሠሩ የቡድኑ አባላትን እንደ አዲስ ሊያስተምሯቸው ይሞክራሉ። ለቡድኑ አይመጥኑም ተብለው የሚታሰቡ ሃሳቦችም በእነዚህ አስተዳዳሪዎች ተሽቀንጥረው ይጣላሉ።
news-54703886
https://www.bbc.com/amharic/news-54703886
ኮሮናቫይረስ፡ በኤርትራ ቢራ በኩፖን መሸጥ ተጀመረ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎችና መጠጥ ቤቶቿን በዘጋችው ኤርትራ ቢራ በኩፖን (መሸመቻ ካርድ) መሸጥ መጀመሯ ተገልጿል።
ብቸኛው ሜሎቲ ቢራ በሱቆች በመሸመቻ ካርድ አማካኝነት እየተሸጠ እንደሚገኝም ቢቢሲ ትግርኛ ከምንጮች ያገኘው መረጃ አመላክቷል። ደንበኞች ቢራውን ማግኘት የሚችሉት በሱቆች ብቻ ሲሆን አንድ ቢራም በአስር ናቅፋ (ወደ 25 ብር በሚጠጋ) ዋጋ እንደሚሸጥ ተገልጿል። ኩፖኑን (የመሸመቻ ካርዱን) የያዙ ሰዎችም በአንድ ሳምንት መግዛት የሚፈቀድላቸው የቢራ ብዛት ስምንት ጠርሙስ ብቻ ነው። በኤርትራ ዳቦ፣ ዘይት፣ ስኳርና ማሽላ የመሳሰሉትን መሰረታዊ ሸቀጦች በስርጭት (በመሸመቻ) ካርድ በቀበሌዎች ሲሆን መግዛት የሚቻለው፤ መጠኑም በቤተሰብ ቁጥሩ ይወሰናል። በተለይም ዳቦ ለመግዛት በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ተመዝግበውም በየእለቱ ጧት የቤተሰባቸውን ቁጥር መሰረት ባደረገ መልኩም እንዲገዙ ይፈቅድላቸዋል። ሜሎቲ ቢራም በተመሳሳይ መልኩ እንደ ዳቦና ስኳር በሱቆች በመሸመቻ ካርድ መሸጡ አንዳንድ የመጠጥ ቤት ባለቤቶችን ቅር አሰኝቷል። በአስመራ የሚገኝ ስሜ አይጠቀስ ያለ አንድ የመጠጥ ቤት ባለቤት ነጋዴ "የንግድ ፍቃድ ያለን ሰዎች ንግድ ቤታችሁን ዝጉ ተብለን፤ ለሰራተኞች ደሞዝ ክፈሉ ተብለን ስናበቃ እኛ ልንሸጠው የሚገባ ቢራ በሱቆች እየተሸጠ ይገኛል" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል። ነጋዴው እንደሚለው መጠጥ ቤቶቹ የተዘጉት የሰዎችን መሰባሰብ ለመቀነስ መሆኑን ቢረዳም ቢራው በሱቆች መሸጥ ለመጀመሩ ምክንያቱ ግልፅ አልሆነለትም። መጠጥ ቤቶቹ ሱቆች አሁን እያደረጉት እንዳለው ቢራ መሸጥ ይችሉም እንደነበር ይናገራል። "ሰባት ወር ሙሉ ከስራ ውጪ ሆነናል። ለሰራተኞቻችን ደግሞ ምንም ሳንሰራ ደመወዝ እንድንከፍል እየተገደድን ነው። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ደንበኞች ቢራ በሱቆች ገዝተው እየሄዱ ነው፤ ገበያችንንም እያሳጡን ነው" ይላል። በአሁኑ ወቅት ቢራ በሱቆች መሸጥ ከመጀመሩም ጋር ተያይዞ ወጣቶች በሱቆች ገዝተው ተሰባስበው እየጠጡ እንደሚያመሹም ምንጫችን ትዝብቱን ይገልጻል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሳልፋ የነበረችው ኤርትራ አዋጇን ቀስ በቀስ እያላላች ትገኛለች። ሰዎችም ከቦታ ወደ ቦታ እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ። በተለይም በአገሪቷ ከጥቂት ከጎረቤት አገራት የመጡ ሰዎች በስተቀር ይህ ነው በማይባል ሁኔታ ወረረሽኙ አለመኖሩ እንዲሁም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ባለመኖራቸው አዋጁ ለምን በይፋ እንደማይነሳ በርካቶች ይጠይቃሉ። በኤርትራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ጊዜ ጀምሮ የንግድ እንቅስቃሴ የቆመ ሲሆን በተለይ ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን ህዝብ ከመንግሥት ምንም ዓይነት ድጋፍ ስለማይደረግለት ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ በሆነና በፈታኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ይናገራሉ። "ሜሎቲ" ወይም አሥመራ ቢራ በኤርትራ አንድ ብቻ የሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ። አንድ አይነት ቢራ፣ አንድ አውሮፕላን፣ አንድ ሥርዓት ያለው የባንክ አገልግሎት፣ እንድ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ፣ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ፣ አንድ የቴሌቪዝን ጣቢያ . . . ከ1939 ጀምሮ በኤርትራ ሲጠመቅ ቆይቷል። ይህ ለኤርትራ ብቸኛ የሆነው ቢራ በበርካቶች ዘንድ ትዝታ እና ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው። የቢራ ፈላጊውን እና የአቅርቦት መጠኑ ተመጣጣኝ ስላልነበረ ከቅርብ ዓመታት በፊት አንድ ሰው ሁለት ቢራ ብቻ ገዝቶ እንዲጠጣ ነበር የሚፈቀድለት። ከሁለት በላይ ደጋግሞ መጠጣት የፈለገ፤ ቢራ የማይጠጣ ሰው ወደ መጠጥ ቤት ይዞ በመሄድ የዚያን ሰው ኮታ ይጠጣ እንደነበር ሰምተናል። አሁን ላይ በቢራ ፋብሪካው በተካሄደ ለውጥ የቢራ አቅርቦቱን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስኑ የድንበር በሮች በተከፈቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ቢራ ምርቶች አሥመራን አጥለቅልቀዋት እንደነበረ በዚህም የአንድ ሜሎቲ ቢራ ዋጋ ከ25 ናቅፋ ከ11-15 እንደወረደ ነዋሪዎች ነግረውናል።
news-52163847
https://www.bbc.com/amharic/news-52163847
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19ን ለመከላከል የበኩላቸውን ያደረጉ አፍሪካዊ ጀግኖች
አፍሪካዊያን ዓለም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተጨነቀችበትን ይህን ጊዜ በማሰብ፤ ሌሎችን ለመርዳት አስገራሚ በጎ ተግባራት እያከናወኑ ነው። ከእነዚህ ጀግኖች መካከል ስድስቱን እናስተዋውቃችሁ። መኖሪያ ቤቷን ለለይቶ ማቆያነት የሰጠችው ኢትዮጵያዊት ድምጻዊት
አንጋፋዋ ድምጻዊት ሐመልማል አባተ መኖሪያ ቤቷን ለለይቶ ማቆያነት እንዲውል አበርክታለች። ባለፈው ወር መንግሥት ማንኛውም ወደ አገር ውስጥ የሚገባ ሰው በራሱ ወጪ ራሱን ለ14 ቀናት ያህል በሆቴል ውስጥ ለይቶ እንዲያቆይ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር። • ወሲብና ኮሮናቫይረስን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች ይህም ድምጻዊቷን ያሳሰበ ጉዳይ ነበር፤ ውሳኔው ገንዘብ ላላቸው የውጭ ዜጎች ይሁን፤ ገንዘብ ለሌላቸውስ በሚል ሀሳብ ገብቷት ነበር። በመሆኑም በአዲስ አበባ የሚገኘውን መኖሪያ ቤቷ ለለይቶ ማቆያ እንዲሆን አበረክታለች። ሐመልማል ቤታቸውንና የንግድ ቦታቸውን ለለይቶ ማቆያነት ከሰጡ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ ናት። ከፋሽን ዲዛነርነት የህክምና ገዋን ወደ መስፋት የተሻገሩት ሊቢያዊያን ሊቢያዊያኑ የፋሽን ዲዛይነር የፋሽን ልብስ ከመስራት ወደ የህክምና ገዋን ማምረት ተሸጋግረዋል። በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ በሚገኘው የፋሽን ልብስ ማምረቻ፤ ስድስቱ ሴቶች ለህክምና ባለሙያዎች የሚሆን ራስን መጠበቂያ አልባሳት መስፋቱን ተያይዘውታል። ሁሉም ሴቶች በጎ ፈቃደኞች ሲሆኑ አንዳንዴ በሥራ መብዛት ምክንያት እዚያው ፋብሪካው ውስጥ ይተኛሉ። በጎ ፈቃደኞቹ እስካሁን 50 የሚሆኑ የህክምና አልባሳት የሰሩ ሲሆን ሁለተኛ ዙር ተጨማሪ ለማምረት እየሰሩ ነው። የአረጋዊያን ቤትን በአበባ ያስጌጡት አበባ አምራቾች ወረርሽኙ በርካታ ሠርጎችና ሌሎች ክንውኖች እንዲሰረዙ ምክንያት ሆኗል። በዚህም ምክንያት የአበባ ምርቶች ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ በማድረግ መጥፎ አሻራ አሳርፏል። ይሁን እንጅ በደቡብ አፍሪካ ፓርል የሚገኙ አበባ ሻጮች በመሰባሰብ ይህንን ጨፍጋጋ ጊዜ ትንሽም ቢሆን ብርሃን ለመስጠት እየሰሩ ነው። ከአንድ የአበባ እርሻ የተበረከተላቸውን 600 አበቦች የአዛውንቶችን ቤት የውጪ ግድግዳ እያስጌጡበት ነው። የደቡብ አፍሪካ ነዋሪዎች ወረርሽኙን ለመከላከል በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ቤታቸው ከከተቱ ሁለት ሳምንታት አልፏቸዋል። የቤት ኪራይ ነጻ ያደረጉ ኬንያዊ ቤት አከራይ በኬንያ 34 ተከራዮች ያሉት የቤት ባለቤት ተከራዮች መጋቢትና ሚያዚያ ወርን ተከራዮች ኪራይ እንዳይከፍሉ ወስነዋል። ይህን ውሳኔ ያሳለፉት የኮሮናቫረስ ወረርሽኝ በርካቶችን ለገንዘብ ችግር ስለዳረጋቸው ነው ብለዋል። ማይክል ሙኔኔ የተባሉት እኝህ ባለሃብት በኬንያ ምዕራባዊ ግዛት እያንዳንዳቸው 3 ሺህ የኬንያ ሽልንግ [ከ250 ዶላር በላይ] የሚከፈልባቸው 28 አፓርትመንቶች አሏቸው። • የትኛው አገር ቢሄዱ ከኮሮናቫይረስ ያመልጣሉ? ከዚህም በተጨማሪ በወር 5 ሺህ ሽልንግ የሚከፈልባቸው ስድስት የንግድ ቤቶችም ባለቤት ናቸው። ተከራዮች ይህንን ካልከፈሉ በወር ከ2 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ ያጣሉ። ይህንን ነው በነጻ የሰጡት። "በዚህ ጊዜ ከእነርሱ ጋር መስራትና መረዳዳት ያስፈልጋል" ብለዋል። በኦንላይን የዳንስ ትርኢት የምታቀርበዋ ቱኒዚያዊት ቱኒዚያዊቷ ዳንሰኛ ኔርሚን ስፋር በእንቅስቃሴ ገደብ ቤት ውስጥ ተዘግተው ለሚገኙ የሰሜን አፍሪካ ሕዝቦች ዳንስ በማቅረብ ታዝናናቸዋለች። ከቤቷ ሆና የምታስተላልፈውን የዳንስ ትርኢትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በፌስቡክ ተከታትለውታል። • ባለስልጣኑ ወደ ለይቶ ማቆያ አልገባም በማለታቸው ታሰሩ ዳንሰኛዋ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "እናንተ ቤታችሁ ቆዩ፤ እኔ እደንስላችኋለሁ" የሚል ዘመቻ ከፍታ ነበር። ለአድናቂዎቹ የምግብ የከፈለው ናይጀሪያዊው እግር ኳስ ተጫዋች የናይጄሪያ ፕሪሚየር ዲቪዥን እግር ኳስ ተጨዋች ለአራት አድናቂዎቹ በወረርሽኙ ጊዜ ምግብ መመገብ የሚያስችላቸውን ገንዘብ ሰጥቷቸዋል። የፕላቶ ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ቺኔዱ አኖዜ፤ ለአራቱ አድናቂዎቹ ለእያንዳንዳቸው 5 ሺህ የናይጄሪያ ናይራ (14 ዶላር) ለግሷል። ይህም በጣም ትንሽ ልገሳ ነው ብሏል።
news-46644195
https://www.bbc.com/amharic/news-46644195
አሜሪካ ሁለት ቻይናዊያን 'ኢንተርኔት በርባሪዎችን' ከሰሰች
የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር የምዕራቡ አገራት ኮምፒተር ኔትወርኮችን በርብረዋል (ሃክ) አድርገዋል ያላቸውን ሁለት ቻይናዊያን ከሰሰ።
ግለሰቦቹ 'ሃክ' አድርገዋል የተባለው የግል ኩባንያዎችን እንዲሁም የመንግስት ኤጀንሲዎች ኮምፒውተሮችን ነው። አሜሪካና ካናዳ ከንግድ ጋር በተያያዘ ከነሱ ጋር ያደረገችውን ስምምነት በመጣስ ስለላ እያደረገች ነው ሲሉም ቻይናን ወንጅለዋል። • «ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር» አዲስ ዓለማየሁ የቀረበባቸው ክስ እንደሚያመለክተው ዙ ሁአ እና ዣንግ ሲሎንግ የተባሉት ግለሰቦች ህዋዌ ሄታይ ለተባለ ኩባንያ ሰርተዋል። ይህ ኩባንያ የሚንቀሰቀሰው ደግሞ ከቻይና የደህንነት ተቋም ጋር እንደነበርም በክሱ ተመልክቷል። የአሜሪካው የምርመራ ቢሮ ኤፍ ቢ አይ እንዳስታወቀው ግለሰቦቹ እአአ ከ2006 እስከ 2018 የኮምፒውተር ኔትዎርኮችን በመጥለፍ የአእምሮ መብት ጥበቃ ያላቸውን የፈጠራ ስራዎች፣ ምስጢራዊ የንግድና የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ሰርቀዋል። • የጭንቅላት ቀዶ ጥገና እየተደረገለት ጊታር የተጫወተው ግለሰብ ግለሰቦቹ የአሜሪካ ባህር ሃይል ኮምፒውተር ኔትወርክን በመጥለፍ በማድረግም ከመቶ ሺህ የሚበልጡ የባህር ሃይሉ አባላትን የግል መረጃም ሰርቀዋል ብሏል ኤፍ ቢ አይ። የኤፍ ቢ አይ ዳይሬክተር ክርስቶፈር ዋሪ ሁለቱ ግለሰቦች ከአሜሪካ ውጭ በመሆናቸው ለአሜሪካ ፍትህ ስርዓት ተደራሽ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።
news-51922473
https://www.bbc.com/amharic/news-51922473
በኮሮናቫይረስ የተያዙት ቶም ሃንክስና ሪታ ዊልሰን ከሆስፒታል ወጡ
አሜሪካዊው የሁለት ጊዜ የኦስካር አሸናፊ ተዋናይ ቶም ሃንክስና ባለቤቱ ሪታ ዊልሰን በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ በአውስትራሊያ ህክምና ሲከታተሉ ከነበረበት ሆስፒታል መውጣታቸው ተዘገበ።
ጥንዶቹ በአውስትራሊያዋ ጎልድ ኮስት የተገኙት የኤልቪስ ፕሪስሊ ሕይወት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን ፊልም ለመስራት ነበር። የ63 ዓመቱ ቶም ሃንክስ ባለፈው ሐሙስ እሱም ባለቤቱም በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያሳወቀው ከዚያው ነበር። • ቶም ሐንክስ እና ባለቤቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተናገሩ • ኮሮና ቫይረስ ከየት መጣ? • የአውስትራሊያ ሳይንቲስቶች ኮሮና ቫይረስን 'ሊያመርቱ' ነው ቶም ሃንክስና ባለቤቱ በሆስፒታል አስፈላጊው እርዳታ ተደርጎላቸው ቢወጡም አሁንም እዚያው አውስትራሊያ ክዊንስላንድ ውስጥ በተከራዩት ቤት ራሳቸውን ለይተው እንደሚቀመጡ ተገልጿል። የኦስካር ተሸላሚው ቶም ሃንክስ ብቻ ሳይሆን በኮሮናቫይረስ የተያዘው እንግሊዛዊ-ሴራሊዮናዊ ተዋናይ ኢድሪስ ኤልባም በቫይረሱ መያዙን በትናንትናው እለት በትዊተር ገፁ ላይ አስታውቋል። ኢድሪስ ኤልባ እንዳለው ምንም ዓይነት የህመም ስሜት ባይኖርበትም አግኝቶት የነበረ ሰው በቫይረሱ ስለተያዘ እንደተመረመረና በውጤቱም እሱም ኮሮናቫይረስ እንደያዘው መታወቁን ገልጿል። "ጥሩ ነኝ እስካሁን ምንም ምልክት የለኝም አትደናገጡ" ብሏል ኢድሪስ በትዊተር መልዕክቱ። ምንም እንኳ የሰው ዘር የተከፋፈለ ዓለም ላይ የሚኖር ቢሆንም በእንዲህ ያለው ጊዜ ግን አንዱ ለሌላው አጋርነቱን ማሳየት አለበት የሚል መልዕክቱንም አስተላልፏል። ኢድሪስ ካለፈው አርብ ጀምሮ ራሱን ለይቶ መቆየቱንም ተናግሯል።
news-53447242
https://www.bbc.com/amharic/news-53447242
የታሰሩ ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ መንግሥት እንዲያሳውቅ አምነስቲ ጠየቀ
በአገሪቱ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ እንዲያሳውቅ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግሥትን ጠየቀ።
በአዲስ አበባ ከተማና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ቢያንስ 5 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቀሰው አምነስቲ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የት እንዳሉ በማይታወቁበት ሁኔታ ተለይተው መያዛቸውን አመልክቷል። ጨምሮም በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ጃዋር መሐመድን ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፣ እሰክንድር ነጋ ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ዋነኛ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች እንደሚገኙበት ተገልጿል። ባለስልጣንት ታሳሪዎቹ ያሉበትን ቦታ ለቤተሰቦቻቸው ባለማሳወቃቸው ጭንቀትን እየፈጠሩ መሆናቸውን በመጥቀስ "በአስቸኳይ ያሉበትን ቦታ በማሳወቅ ክስ እንዲመሰርቱባቸው ካልሆነም በአስቸኳይ እንዲለቀቁ" ሲሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ኃላፊ ዲፕሮስ ሙቼና ጠይቀዋል። መግለጫው ጨምሮም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሳሳቢ በሆነበት በዚህ ወቅት ንጽህናቸው ባልተጠበቁና በተጨናነቁ ሁኔታዎች ውስጥ ሊታሰሩ ይችላሉ በሚል የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ጭንቀት ውስጥ ናቸው ብሏል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ዋነኛ ባለስልጣናት የት እንዳሉ ለማወቅ እንዳልቻሉ ጠበቆቻቸው እንደተናገሩ የጠቀሰው ሪፖርቱ የፌደራል፣ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖችን ጨምሮ ግለሰቦቹ በእነሱ ቁጥጥር ስር እንዳልሆኑ እንደገለጹላቸው አመልክተዋል። "ግለሰቦችን በእስር ለማቆየት የሚቻለው ፖሊስ በታሳሪዎቹ ላይ ጠንካራ ማስረጃ ካለው ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ፖሊስ ማስረጃ በሚያፈላልግበት ጊዜ ሰዎች የነጻነት መብታቸው ተገፎ ሊታሰሩ አይገባም" ብለዋል ዲፕሮስ ሙቼና። አምነስቲ በሪፖርቱ ላይ በእስር ላይ ይገኛሉ ያለቸውን ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን ጠቅሶ በማስረጃ ክስ እንዲመሰረትባቸው አሊያም እንዲለቀቁ ጠይቋል። አክሎም "የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወደተለመደው የጭቆና መንገድ መመለስ የለባቸውም። የመቃወምና የተለየ የፖለቲካ ሃሳብ ማራመድን መብት ማክበር ይጠበቅባቸዋል" ሲሉ የድርጅቱ የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ኃላፊ ማሳሰባቸውን ገልጿል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በተከሰተው አለመረጋጋት በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ወደ የማኅበረሰባዊ ጥቃት በተሸጋገሩ ተቃውሞዎችና በጸጥታ ኃይሎች ቢያንስ 177 ሰዎች መገደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸውን በሪፖርቱ አመልክቷል።
52482875
https://www.bbc.com/amharic/52482875
ኮሮናቫይረስ፡ ትራምፕ ቻይና በምርጫው እንድሸነፍ ትፈልጋለች አሉ
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ቻይና በቀጣዩ ምርጫ እንድሸነፍ የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም” አሉ።
ትራምፕ ባለፉት ሳምንታት ቻይና ለኮሮናቫይረስ ስርጭት ተጠያቂ እያደረጉ ነበር። አሁን ደግሞ በምርጫው እንድሸነፍ ትፈልጋለች ሲሉ ከስሰዋል። ዋይት ሁውስ ውስጥ ከሮይተርስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ቻይና በወረርሽኙ ሳቢያ ከአሜሪካ “ብዙ ነገር ደርሶባታል” ብለዋል። ቻይና ስለበሽታው ለዓለም ሕዝብ ቀደም ብላ ማስታወቅ ነበረባት ሲሉም ተችተዋል። በእርግጥ በርካቶች ፕሬዘዳንቱም በሽታውን ለመቆጣጠር የወሰዱት እርምጃ ዘግይቷል ሲሉ ይደመጣሉ። • በሊባኖስ ለሽያጭ የቀረበችው ናይጄሪያዊት ተረፈች • የኤርትራውያን ስደተኞች ስጋት በኢትዮጵያ • በርካታ ሰዎች ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየተሻገሩ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል ወረርሽኙ የአሜሪካን ምጣኔ ሀብት አላሽቆታል። ፕሬዘዳንቱ ለቀጣዩ ምርጫ ቅስቀሳ ሊጠቀሙ አስበው የነበረው ደግሞ አሜሪካን በምጣኔ ሀብት የበለጸገች አገር ማድረጋቸውን ነበር። ከቻይና ጋር የንግድ ጦርነት ያወጁት ትራምፕ፤ ጦርነቱ ምን እንደሚያካትት ያሉት ነገር የለም። ለሮይተርስ ግን በደፈናው “ብዙ ማድረግ የምችለው ነገር አለ” ብለዋል። ትራምፕ እንደሚሉት ከሆነ ቻይና ዴሞክራቱ ጆ ባይደን ትፈልጋለች። ጆ ባይደን ምርጫውን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ የሚጠቁም መረጃ እንደሌላቸውም አክለዋል። “የዚ አገር ሰዎች ብልህ ናቸው፤ አገር የመምራት ብቃት የሌለው ሰው ይመርጣሉ ብዬ አላስብም” ብለዋል። የመራጮችን ድምጽ በሚያሳየው አሃዝ (ፖሊንግ) እንደማያምኑ የሚናገሩት ትራምፕ፤ ባለፈው ሳምንት በዋነኛ ግዛቶች ነጥብ እያጡ መሆኑን ከሰሙ በኋላ አማካሪዎቻቸውን እንደተቆጡ ተዘግቧል። አማካሪዎቻቸው እንደ ፍሎሪዳ፣ ዊስኮንሰን፣ አሪዞና ባሉ ቁልፍ ግዛቶች ትራምፕ ያሸንፋሉ ብለው አያስቡም። “ጆ ባይደን አያሸንፈኝም” ሲሉ ለምርጫ ቅስቀሳ አማካሪዎቻቸው መናገራቸው ተሰምቷል። • ሞተዋል የተባሉት ሴት "አልሞትኩም እህቴ ጋር ደውሉልኝ" አሉ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ኃላፊያቸው ብራድ ፓርስኬልን “እከስሀለሁ” ብለውት እንደነበር ቢገለጽም፤ ዛቻውን ምን ድረስ እንደሚገፉበት አለመታወቁን ሲኤንኤን እና ዋሽንግተን ፖስት ዘግበዋል። በሌላ በኩል ትራምፕ ማኅበራዊ ርቀትን ለመጠበቅ የተላለፈው ውሳኔ ቀነ ገደቡ ካለፈ እንደማያራዝሙት ተናግረዋል። ከአንድ ወር በላይ ከዋይት ሀውስ ያልወጡት ትራምፕ በቀጣይ ሳምንት ወደ አሪዞና የመብረር እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል። ፕሬዘዳንቱ በቀጣይ ወራት ብዙ ሺህ ሰዎች የሚታደሙት የምርጫ ቅስቀሳ እንደሚያካሂዱም ጠቁመዋል። አሁን በዓለም ካለው የኮሮናቫይረስ ኬዝ አንድ ሦስተኛው በአሜሪካ ይገኛል። ከ60 ሺህ በላይ ሰዎችም ሞተዋል። በተጨማሪም 26 ሚሊዮን ነዋሪዎች ሥራ አጥ ሆነዋል።
news-54611167
https://www.bbc.com/amharic/news-54611167
ናይጄሪያ ልዩ የፖሊስ ኃይል ይወገድ በሚለው ተቃውሞ ትምህርት ቤቶቿን ዘጋች
በፖሊስ የበትር ጭካኔ የተማረሩ ናይጄሪያውያን ሳርስ ተብሎ የሚጠራው የፌደራል ፖሊስ ልዩ ኃይል ይበተን የሚለውን ተቃውሞ ተከትሎ በናይጄሪያዋ የንግድ መዲና ሌጎስ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ተወስኗል።
የትምህርት ሚኒስቴሩ ኮሚሽነር ፎልሳዴ አደፊሳዮ እንደተናገሩት የተማሪዎቹ፣ የመምህራኑ እንዲሁም አጠቃላይ የሰራተኞቹን ደህንነት ዋስትና መስጠት ስላልተቻለ ለመዘጋታቸው ምክንያት ሆኗል። ትምህርት ቤቶቹ ተመልሰው መቼ እንደሚከፈቱ በቅርቡ ይነገራል ተብሏል። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ትምህርት ቤቶቹ የርቀት ትምህርትን ጨምሮ ሌሎች አማራጮችን ሊጠቀሙ ይገባል ተብሏል። የፖሊስ ጭካኔን የሚቃወሙ ሰልፈኞች የከተማዋን አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የሚወስደውን መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎም ተቃውሞ ተጧጡፏል። በዚህ ሳምንት ሰኞም በተለያዩ የአገሪቷ ከተሞችም ተቃውሞው ተዛምቷል። ከዚህም በተጨማሪ በመዲናዋ አቡጃ፣ ቤኒንና ካኖ የነበሩት የተቃውሞ ሰልፎች ከፍተኛ ረብሻ እንደነበረባቸውም ተገልጿል። ፖሊሶች አንድን ሰው ሲገድል የሚያሳይ ቪዲዮ መውጣቱን ተከትሎም ነው ተቃውሞቹ የተቀጣጠሉት። እነዚህ ተቃውሞዎች በተለይም ዘረፋን ለማስቆም የተቋቋመውን ልዩ የፌደራል ፖሊስ ኃይል ወይም ሳርስ ተብሎ የሚታወቀው ላይ ያነጣጠሩ ሲሆኑ፤ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሰዎችን ማሰር፣ ማሰቃየትና ግድያም ይፈፅማል በሚልም ከፍተኛ ውግዘትም ቀርቦበታል። ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበበት ሳርስ እንዲበተን ቢደረግም የሳርስ አባላት በሌሎች የፖሊስ ክፍሎች እየተሰማሩና እየተመደቡ ነው የሚሉ ጉዳዮች መሰማታቸውን ተከትሎም እንደገና ተቃውሞቹ የቀጠሉት። ሰልፈኞቹ እነዚህ የሳርስ አባላት ለፈፀሙት ወንጀል ህግ ፊት መቅረብ አለባቸውም እያሉ ነው። ከሰሞኑ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት "ስር ነቀል" የፖሊስ ማሻሻያ እንደሚደረግና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል የተባሉትም የሳርስ አባላት ወደ ፍርድ ይቀርባሉ ብለው ነበር።
news-53761579
https://www.bbc.com/amharic/news-53761579
ኮሮናቫይረስ፡ ኒውዚላንድ 14 በከሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች አገኘች
የኒውዚላንዷ ትልቋ ከተማ ኦክላንድ በድጋሚ የእንቅስቃሴ ገደብ ከተጣለባት በኋላ አዲስ 14 በኮሮረናቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ።
በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ አራት አንድ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲሰማ መላው ኒውዚላንድ በድንጋጤ ተውጦ የነበረ ሲሆን የአሁኑ ደግሞ ነገሮችን አባብሷል። ከውጭ አገራት በቫይረሱ ተይዘው ከሚመጡ ሰዎች ውጪ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ አገሪቱ ላለፉት ሶስት ወራት ምንም በቫይረሱ የተያዘ ሰው አላገኘችም ነበር። ዛሬ ከተገኙት ተጨማሪ 14 ሰዎች መካከል 13ቱ ከዚሁ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን አንደኛው ግለሰብ ደግሞ ከሌላ አገር ወደ ኒውዚላንድ ገብቶ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ እንደሆነ ተገልጿል። ከትላንት ረቡዕ ጀምሮ ደግሞ በኦክላንድ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። '' ሁኔታው ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ማየት እንችላለን'' ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጃሲንዳ አርደርን። በሰጡት ጋዜታዊ መግለጫ ላይ አክለውም '' ጉዳዩ በተገቢው መንገድ ክትትል እየተደረገበት ነው፤ ፈጣንና ተገቢው እርምጃም ይወሰዳል'' ሲሉ ተደምጠዋል። ሁሉም ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን ኃላፊዎች ያስታወቁ ሲሆን ከነሱ ጋር በማንኛውም መንገድ ንክኪ የነበራቸው ሰዎችም ክትትል እንደሚደረግባቸው ገልጸዋል። ኒውዚላንድ እስካሁን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በወሰደቻቸው ፈጣንና ውጤታማ እርምጃዎች ከመላው ዓለም ምስጋናና ሙገሳ ሲጎርፍላት ነበር። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላም በመላው አገሪቱ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ግዴታ የተደረገ ሲሆን ቫይረሱ በተገኘባት ኦክላንድ ደግሞ ጠንከር ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። ከማክሰኞ በፊት በኒው ዚላንድ በአገር ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ሳታገኝ 102 ቀናት መቆየት የቻለች አገር ነበረች። የአገሪቱ የጤና ኃላፊዎችና ሰራተኞች ቫይረሱ ከየት እንደተነሳ ለማወቅ በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ተገልጿል። በኮቪድ-19 የተያዙት ሰዎች ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና የስራ ባልደረቦችም ተለይተው ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል። '' ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት ያለእረፍት እየሰራን ነው። ምንጩ ከየት እንደሆነም ለማወቅ የምንችለውን ነገር በሙሉ እያደረግን ነው'' ብለዋል ብሄራዊ የጤና ኃላፊው አሽሊ ብሉምፊልድ። ቫይረሱ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በድጋሚ ሲያገረሽ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም። በርካታ የአውሮፓ አገራት ሁኔታዎች መሻሻል ሲያሳዩ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ማንሳታቸውን ተከትሎ ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር መስፋፋት ጀምሯል። ቪየትናም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳታገኝ 99 ቀናት ሳታገኝ ከቆየች በኋላ ዳ ናንግ በተባለችው ከተማ ስርጭቱ በድጋሚ መጀመሩ የሚታወስ ነው። በኒውዚላንድ ወረርሽኙ በድጋሚ መቀስቀሱ ምናልባት በሌሎች ከተሞችም የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ሊያስገድድ እንደሚችል ተፈርቷል። አገሪቱ ደግሞ በሳምንታት ልዩነት ውስጥ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነበረች። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ምን አይነት ውሳኔዎች እንሚተላለፉ ነገ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
news-52147451
https://www.bbc.com/amharic/news-52147451
ኮሮና ቫይረስ፡ በዓለም ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሆነ
በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ መሆኑን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ወረርሽኙን ለመግታት ለሚደረገው ትንቅንቅም ጨለም ያለ ዜና ነው ተብሏል። እስካሁን ባለው መረጃ 53ሺ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል፤ 210 ሺ ሰዎች ደግሞ እንዳገገሙ የዩኒቨርስቲው መረጃ ጠቁሟል። •በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ለመለየት ክትትል እየተደረገ ነው •ኢትዮጵያ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ በሆነችው አሜሪካ በትናንትናው እለት መጋቢት 24፣ 2012 ዓ.ም አንድ ሺ 169 ሰዎች ሞተዋል። ለሰው ልጅ ጠንቅ የሆነው ኮቪድ- 19 የተከሰተው ከሶስት ወራት በፊት በቻይና፣ ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ ነው። የ34 አመቱ ዶክተር፣ ዶ/ር ሊ ዌንሊያንግ ቫይረሱን አስመልክቶ ለሌሎች የህክምና ባለሙያዎች ቢያስጠነቅቅም በምላሹ ግን የፖሊስ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲደርሰው ሆኗል። ዶክተሩም በውሃን ከተማ በቫይረሱ የታመሙ ሰዎችን ሲንከባከብ ህይወቱን ተነጥቋል። •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች •በአማራ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የትምህርት ተቋማት ለመጠለያነት ተዘጋጁ ምንም እንኳን ከዩኒቨርስቲው የተገኘው መረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ጥር ከአንድ ሚሊዮን ትንሽ ከፍ ያለ ቢሆንም ቁጥሩ ግን ከዚያ በላይ ነው ተብሏል። ምክንያቱም ከአመዘጋገብ ስርዓት ጋር ተያይዞ ክፍተቶች በመታየታቸው ነው፤ በባለፈው ወር በበሽታው የተያዙ መቶ ሺ ሰዎችን ለመመዝገብ ከአንድ ወር በላይ ጊዜን ወስዷል። ከዚህ ቁጥር ውስጥ ሩብ የሚሆነው በአሜሪካ የተከሰተ ሲሆን ግማሽ የሚሆነው ደግሞ በአውሮፓ ያለውን ቁጥር ያሳያል። በትናንትናው ዕለት በስፔን ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ብቻ 950 ሰዎች ሞተዋል። ከጣልያን በመቀጠል ብዙ ሰዎችን በኮሮናቫይረስ ባጣችው ስፔን፤ የምጣኔ ሃብት መዳሸቅ እያጋጠማት ሲሆን 900 ሺ የሚሆኑ ሰዎችም ስራቸውን አጥተዋል ተብሏል። በአሜሪካም በትናንትናው ዕለት 6.6 ሚሊዮን ሰዎች ስራቸውን በማጣታቸው የጥቅማጥቅሞች ይገባኛል ጥያቄዎች ቀርበዋል።
news-55883436
https://www.bbc.com/amharic/news-55883436
የዓለም ሂጃብ ቀን፡ የመገለል ስሜትን ለመታገል በማሰብ የሚከበረው ዓለማቀፉ የሂጃብ ቀን
ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሂጃብ ቀን እየተከበረ ነው። በዚህ ዕለት ሒጃብን ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶች ለአንድ ቀን ለብሰውት ይውላሉ፡፡ ይህ በተለይ በአሜሪካና በእንግሊዝ የተለመደ ነው፡፡
ለምሳሌ በታላቋ ብሪታኒያ ሊንክሻየር በርካታ ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶች ሂጃብን ለአንድ ቀን አድርጎ ለመዋል ተመዝግበው ይህንኑ አድርገዋል፡፡ በተለይ የ2ኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎች ቀኑን በዚህ መንገድ እንዲያሳልፉ ይበረታታሉ፡፡ ዋናው ምክንያት ሒጃብ የሚለብሱ ተማሪዎች የመገለል ስሜት እንዳይሰማቸው ለማድረግ ነው፡፡ የሒጃብ ቀን የሚከበርበት ዋንኛ ምክንያት ሙስሊም ሴቶች በሒጃብ ምክንያት የሚደርስባቸውን ሥነ ልቡናዊና ማኅበረሰባዊ መገለል ለመቃወም ነው፡፡ በሊንከንሻየር የሊንከን ሙስሊም ሲስተርስ ባልደረባና የመብት አቀንቃኝ የሆነችው ኻዳ መሐመድ እንዲህ ትላለች፡- ‹‹አንዳንድ ሴቶች ሒጃብ በማድረጋቸው ብቻ የዚህ ኅብረተሰብ ሙሉ አባል እንዳልሆኑ ይሰማቸዋል፤ የነሱን ስሜት ሌሎች እንዲጋሩትና ባለሒጃብ ሴትን እንዳያገሉ ለማድረግ ነው የሒጃብ ቀንን የምናከብረው፡፡" ይህ ተግባር ከዚህ ቀደምም በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ተሞክሮ መጠነኛ ማኅበረሳዊ የግንዛቤ ለውጥ እንዳመጣ ሲዘገብ ነበር፡፡ በተለይም ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶች ከአሜሪካ ባንዲራ ቀለማት ያጌጠ ሒጃብ በመልበስ ሒጃብን መልበስ ግማሽ አሜሪካዊ እንደማያሰኝና ብሔራዊ አገራዊ ስሜትን እንደማይቀንስ ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ነፍረቲቲ ብራውን ጥቁር አሜሪካዊት ናት፡፡ አጋርነቷን ለመግለጽ ሒጃብ ለብሳ ለቢቢሲ ሐሳቧን ባጋራችበት ቪዲዮ ላይ እንዲህ ስትል ትሰማለች፡ ‹‹የምወዳቸው ሙስሊም ጓደኞች አሉኝ፡፡ እኔ የማመልከውን አምላክ አይደለም የሚያመልኩት፡፡ ያ የእነርሱ ምርጫ ነው፡፡ ይህንን ሒጃብ (በእጇ እያመላከተች) ስለለበሱ ግን ከኔ ያነሱ አሜሪካዊ ተደርገው መወሰዳቸው ቅር ይለኛል›› ትላለች፡፡ የሒጃብ ቀን በኢትዮጵያ ሂጃብን ለሃይማኖታዊ ተግባሩ ብቻ ሳይሆን እንደባህልም ወስደው የሚለብሱ ማህበረሰቦች ባሉባት ኢትዮጵያም ‹የሒጃብ ቀን› ለሁለተኛ ጊዜ እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ይህንን ቀን የሚያዘጋጀው የሴቶች ጉዳይ ላይ የሚሠራው ድርጅት 'ውሜንስ አሊያንስ ፎር ፒስ ኤንድ ጀስቲስ' ይሰኛል።። የዚህ ድርጅት ኃላፊ የሆነችው ጀሚላ ሰዒድ፣ "በተለይ በምዕራባውያን አገራት ሂጃብ የለበሰች ሴት ስትታይ መጀመሪያ የሚመጣባቸው ምሥል ከአሸባሪነት ጋር የተያያዘ›› መሆኑን ትናገራለች። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሂጃብ የሚለብሱ ማኅበረሰቦችን የማግለል ስሜት ስለነበር ይህንን ለማስቀረት ተብሎ ነው ቀኑ መከበር የጀመረው ብላለች። " እኛ ሂጃብ ስለለበስን ብቻ የተለየ ሰዎች ተደርገን መታየት የለብንም። እስቲ እናንተም ልበሱትና የሚሰማችሁን ስሜት ንገሩን ብለን ሙስሊም ያልሆኑ ጓደኞቻችንን ሂጃብ እንዲለብሱ በማድረግ ነው ይህንን ቀን የምናከብረው" ትላለች ጀሚላ። የእስልምና እምነት እሴትና መገለጫ ከሆኑት መካከል አንዱ ሂጃብ ነው። ኢስላማዊ እሴት ከመሆኑም ባሻገር የሴቷ መብትና ክብር መገለጫ ነው ይላሉ በሂጃብ ዙሪያ ጥናት ያደረጉ ሴቶች። ሒጃብ የለበሰችን ሴት ሲያዩ አሉታዊ ስሜት የሚፈጠርባቸው ሰዎች ቀላል አይደለም፡፡ ይህን አስተሳሰብ ለማስቀረት በሚል እኤአ በ2013 የዓለም አቀፍ ሂጃብ ቀን በሚል መከበር ተጀመረ። ይህን ቀን ማክበር ያስጀመረችው ሴት በዜግነት አሜሪካዊት በትውልድ ደግሞ ባንግላዲሻዊት የሆነችው ናዝማ ካኻን ነች። ይህ ቀን ታስቦ በሚውልበት ወቅት የእስልምና እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆኑ የሌላ እምነት ተከታይ ጓደኞቻቸውም ሂጃብ መልበስ የሚፈጥረው ስሜት ምን ዓይነት እንደሆነ እንዲሰማቸው በማድረግ ነው የሚከበረው። ይህ የዓለም አቀፍ ሂጃብ ቀን እኤአ ፌበሪዋሪ 1 የሚከበር ሲሆን በኢትዮጵያም ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ እየተከበረ ነው። በሂጃብ ምክንያት የሚደርሰው ችግር ሲታይ የምዕራባውያን እና የእኛ ተመሳሳይ አይደለም የምትለው ጀሚላ በምዕራባውያኑ አገራት ሂጃብ የሚለብሱ ሙስሊሞች የተለያዩ ችግሮች ሲደረሰባቸው እንደሚታይ ታስረዳለች። " በምዕራባውያኑ አገራት ያሉ ሴቶች ከማህበረሰብም ሆነ በሥራ ዓለም የተለያየ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በእኛ አገር ግን ሕዝቡ በብዛት ሃይማኖተኛ ስለሆነ፣ ሂጃብ እና ቀሚስ ለብሶ መሄድ ይህን ያህል ችግር አይፈጥርም። ችግሩ ያለው በመንግሥት መሥሪያ ቤት፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና በንግዱ ዓለም ውስጥ ነው። የእኛ ዋና ዓላማ ይህንን ሐሳብ ማስቀየር ነው።" እርግጥ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ አንዲት ሴት ሂጃብ ስለለበሰች በማህበረሰብ ውስጥ የሚደርስባት ችግር ላይኖር ይችላል የምትለው ጀሚላ፣ በሥራ ዓለም ውስጥ ግን ይህ ችግር በብዛት እንደሚስተዋል ትናገራለች። አብዛኛው የሥራ ዘርፎች የመሥሪያ ቤታቸውን የልብስ ደንብ ሲያወጡ ሂጃብን ያማከለ የአለባባስ ደንብ ከነጭራሹ የለም ስትልም ታብራራለች። "በኢትዮጵያ እንደማኅበረሰብ ሂጃብ የሚለብሱ ማህበረሰቦች አሉ። ቁጥራቸውም ብዙ ነው። ስለዚህ የመሥሪያ ቤቶች ደንብ ልብስ ይህንን የሚያቅፍ መሆን እንዳለበት ለማሳየት ጭምር ነው የዚህ ቀን መከበር ያስፈለገው።" አክላም ሂጃብ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የዚያ ማኅበረሰብ መገለጫ ባሕል ሆኖ ሊለበስ ይችላል። ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ባህል ወስደው የሚለብሱም አሉ። ለምሳሌ ሶማሌ፣ አፋር፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ አካባቢዎች ሂጃብን የሚለብሱት ለሃይማኖት ብቻ ሳይሆን ባህላቸውም ስለሆነ ነው ትላለች ጀሚላ። ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ትርጉም ያለውን ልብስ ማግለል ትክክል እንዳልሆነ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ቀኑን ማክበር ያስፈለገው። አንዲት ሴት በአለባበሷ ምክንያት ከሥራ የምትገለል ከሆነ እንደ ማኅበረሰብም አንደ አገርም የሚደርሰው ኪሳራ ቀላል አይደለም የምትለው ጀሚላ፣ የመገለል ስሜቱ ለአገር ያለኝን ፍቅር ሊቀንስ እንደሚችልም በመግለጽ "ማንነቴን የማታስተናግድ አገር ከሆነች ሞራሌ ይነካል፤ ለአገሬም የማስበውን የበኩሌን ለማበርከት ሊቸግረኝ ይችላል።" ብላለች። ሂጃብ-መብትና የሴቶች መብትና ክብር የሂጃብ አለባበስ የአንዲት ሙስሊም ሴት የሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከሴቶች መብት ጋር የሚያያዝ ጽንሰ ሃሳብ ነው የምትለው ጀሚላ፣ "ይህ አለባበስ ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት በተወሰነ ሊቀንስ ይችላል ብላ ታምናለች፡፡ እንደ እስልምና ሃይማኖትም የሴቷን ለሥነ ሥርዓት ተገዢ መሆኗን ማሳያ ነው" ትላለች፡፡ በተጨማሪም የቁርዓን መርህም ሂጃብ አንዲት ሴት በምግባረ ብልሹ ሰዎች እንዳትጠቃ የሚከለክል ነው ስትል ትናገራለች። ለሴቶች መብት እንደ ከለላ ይታያል ስትልም ታክላለች። የሂጃቡ ዋና ጽንሰ ሃሳብ የሴቷ ክብር ነው። ሴቶች ሂጃብ ሲለብሱ በቀላሉ ለአካላዊ ጥቃት አይጋበዙም። የሂጃብ ትርጉም ከሃይማኖታዊም አልፎ የሴቷን መብት ለማስከበር የሚሆን ትርጉም አለው። የሂጃብ ቀን መከብር ከጀመረ ጀምሮ በርካታ ለውጦች ታይተዋል የምትለው ጀሚላ፣ ይህንኑም ስታስረዳ በአንዳንድ አገራት ለሂጃብ ያላቸው አመለካከት ተቀይሯል ትላለች። ለዚህም ማሳያ በዩኬ፣ ኒውዚላንድ፣ ደቡብ አፍሪካ ሙስሊም የፖሊስ አባላት ሂጃብ ለብሰው እንዲሠሩ መፍቀዳቸውን ትጠቅሳለች። እንደ ካናዳ ባሉ አገራት ደግሞ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሂጃብ ማድረግ ይፈቀዳል።
news-46107433
https://www.bbc.com/amharic/news-46107433
ትላልቅ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች ለታዳጊ ሃገራት "አዋጭ አይደሉም"
አዲስ ይፋ የተደረገ ጥናት እንዳመለከተው በአውሮፓ እና በአሜሪካ ያሉ በርካታ ትላልቅ የውሃ ኃይል ፕሮጀክቶች አካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ነበራቸው።
ካሊፎርኒያ በሚገኘው ኦሮቪል ግድብ ላይ በደረሰ ችግር 10 ሺህ ሰዎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል አደገኛ እና ኢኮኖሚያዊ እንዳልሆኑ ስለተገመተም ከእነዚህ ግድቦች ውስጥ ብዙዎቹ በየዓመቱ ሥራ እንዲያቆሙ ይደረጋል። ይሁን እንጂ በማደግ ላይ ባሉት ሀገራት ውስጥ እነዚህ ፕሮጀክቶች ዘላቂነት እንደሌላቸው አይታወቅም በሚል አጥኚዎች ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። • ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ በአሁኑ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ግድቦችን በአፍሪካ እና በኤስያ በሚገኙ ወንዞች ላይ ለመገንባት እየታቀደ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኘው የታዳሽ ኃይል 71 በመቶ የሚሆነው ከውሃ የሚገኝ ኃይል ሲሆን ለበርካታ ሀገሮች ዕድገትም ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ይሁን እንጂ በአውሮፓና በአሜሪካ ግድቦችን መገንባት በአውሮፓዊያኑ 1960ዎቹ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ቢደርስም፤ ከዚያን ጊዜ ወዲህ ግን በተቃራኒው እየቀነሰ ከመምጣቱም በላይ ከመገንባት ይልቅ ማፍረስ ላይ ትኩረት ተደርጓል ይላሉ አጥኚዎቹ። አሜሪካ ከውሃ ኃይል የምታገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል 6 በመቶ አካባቢ ነው። • አለመግባባት ለማንም አዋጭ አይደለም በአሁኑ ጊዜ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ሁለቱም ጫፎች በሳምንት ከአንድ ግድብ በላይ ከሥራ ውጭ እንዲሆን ይደረጋል። ከአካባቢ እና ከማህበራዊ ኪሣራው ይልቅ መንግሥታት በጭፍን በርካሽ በሚያገኙት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ላይ ብቻ አተኩረዋል ይላሉ የጥናቱ ጸሐፊዎች። በአውሮፓዊያኑ ከ1930ዎቹ ጀምሮ ከተገነቡት ግድቦች ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ከተጠበቀው በላይ ወጪ የጠየቁ ነበሩ። የወንዞችን ​​ሥነ-ምህዳር ያበላሹ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከቀያቸው ያፈናቀሉ እና በጎርፍ የሚጠረግ አፈር እና የተመነጠሩ ደኖች በግድቦቹ ውስጥ በሚፈጥሩት የግሪን ሃውስ ጋዞች ለአየር ሁኔታ ለውጥ አስተዋፅኦ ያደረጉ ነበሩ። የዋሽንግተኑ የኤልውሃ ወንዝ ግድብ በአውሮፓዊያኑ 2011 ሥራ እንዲያቆም ተደርጓል "የማይሳኩ ነገር ግን ጥቅሞቹን የሚያንቆለጳጵሱ መረጃዎች የሚያቀርቡ ሲሆን የተዘነጉ ነገር ግን በቀጣይ ለትውልድ የሚተላለፉ ወጪዎቹም ችላ ይባላሉ" ሲሉ የጥናቱ መሪ የሆኑት የሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ኤሚሊዮ ሞራን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሪፖርቱ በምሳሌነት ከአምስት ዓመታት በፊት አገልግሎት የጀመሩትን በብራዚል ማዴራ ወንዝ ላይ የተገነቡትን ሁለቱን ግድቦች ያነሳል። ግድቦቹ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከሚጠበቀው የኃይል መጠን የተወሰነውን ብቻ ነው እያመረቱ የሚገኙት። በአሁኑ ወቅት በማደግ ላይ በሚገኙ ሃገሮች ውስጥ የተለያየ መጠን ያላቸው 3,700 ግድቦች በተለያየ የግንባታ ደረጃዎች ላይ ይገኛሉ። • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ እንደአጥኚዎቹ ከሆነ አብዛኛዎቹ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በሚገነቡባቸው ወንዞች ላይ መልሶ የማይስተካከል ጉዳት ያደርሳሉ። በኮንጎ ወንዝ ላይ በሚገነባው የግራንድ ኢንጋ ፕሮጀክት ከአፍሪካ ጠቅላላ የኤሌክትሪክ ኃይል ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆን ኃይል ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል። አዲሱ ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ የ80 ቢሊዮን ዶላሩ ፕሮጀክት ዋና ግብ ለኢንዱስትሪዎች ኃይል ለማቅረብ ነው። "ከዚህ ፕሮጀክት ከሚገኘው ኃይል ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ለደቡብ አፍሪካ የሚሸጥ ሲሆን ይህም ለማዕድን ፍለጋ ይውላል። ስለዚህም የኮንጎ ህዝብ ብዙ ኃይል አያገኙም" ይላሉ ፕሮፌሰር ሞራን። "በብራዚል ጥናት ባደረኩባቸው ቦታዎች ያሉ ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ለእነሱ ሳይደርስ ከ4ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ በእነሱ በኩል ቢያልፍም ለአካባቢው ነዋሪዎች ግን ምንም ዓይነት ኃይል አልተሰጣቸውም።" በአሜሪካ የሚገኘው የሁቨር ግድብ ባለፉት ዓመታት የውሃ መጠኑ እየቀነሰ ነው "በገጠር ኤሌክትሪክን በማስፋፋት ውስጥ ያለው መልካም ግብ ይህንን ቴክኖሎጂ በሚደግፉ ትላልቅ ፍላጎቶች ተዳክሟል። መንግሥታትም ትክክለኛው አቅጣጫ እንደሆነ በማረጋገጥ በዚህ ሃሳብ ተስማምተዋል።" ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው ከሆነ በእነዚህ ታላላቅ ወንዞች ላይ የሚገነቡት ትላልቅ ኃይል ማመንጫዎች የምግብ ምንጮችን ያጠፋሉ። በሜኮንግ አካባቢ የሚኖሩ 60 ሚሊዮን ሰዎች ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የኑሮ መሠረታቸው የሆነውን የአሣ ምርት ሊያጡ ይችላሉ። በተጨማሪም የብዝሃ ሕይወት መገኛ የሆኑት እነዚህ ቦታዎች ውስጥ የሚገኙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዝርያዎችን ግድቦቹ ያጠፋሉ ብለው አጥኚዎቹ ያምናሉ። ከውሃ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ 67 በመቶውን የኤሌክትሪክ ኃይሏን በምታገኘው በብራዚል በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የውሃ መጠን በመቀነሱ ምላሽ እንዲሆን የተደረገው ተጨማሪ ግድቦችን መገንባት ነው። • አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች ጃየር ቦልሶናሮ በመመረጣቸው ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው አዲስ የሃይድሮ ኃይል ፕሮጄክት የመገንባት ሥራ ሊቀለበስ ይችላል። አዳዲስ 60 ግድቦች ለመሥራት ዕቅድ ተዘጋጅቷል። አጥኚዎቹ እንደገለፁት አገራት ታዳሽ ኃይልን እንዲያስፋፉ ካለባቸው ትልቅ ተጽዕኖ አንጻር ከውሃ የሚገኘውን ጨምሮ የተለያዩ የኃይል አማራጮችን መከተል ዘላቂነት ያለው አቀራረብ ነው ይላሉ። "ትላልቅ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች አዋጭነት የላቸውም የሚል ነው የእኛ መደምደሚያ" ይላሉ ፕሮፌሰር ሞራን። "በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሃይድሮኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ የተለያዩ የታዳሽ ኃይል ማመንጫዎች ማሰባጠር አለብን" ብለዋል ፕሮሰር ሞራን። "ወደ ከፍተኛ ደረጃ እስክንደርስ ድረስ ለፀሃይ፣ ለንፋስ እና ለባዮማስ እንዲሁም ወጪና ጥቅሙ ግልጽ እስከሆነ ድረስ ከውሃ ለሚገኝ የኃይል ማመንጫ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል።" ጥናቱ በፕሮሲዲንግ ኦፍ ዘ ናሽናል አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ ላይ ነው የታተመው።
49671797
https://www.bbc.com/amharic/49671797
ለመጀመሪያ ጊዜ በሌላ ፕላኔት ላይ ውሃ ተገኘ
የሥነ ህዋ ተመራማሪዎች በአንዲት ፕላኔት ላይ ውሃ ማግኘታቸውን ይፋ አድርጉ።
K2-18b ከመሬት ውጪ በፕላኔት ከባቢ አየር ላይ ውሃ ሲገኝ ይህ የመጀመሪያው መሆኑን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል። • ናሳ ህዋ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጀል ተፈጸመ አለ • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? • ጨረቃን የሚረግጠው የመጀመሪያው ጎብኚ ታወቀ ግኝቱን በበላይነት የመሩት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጂኦቫንያ ቲኔቲ፤ K2-18b የተባለችው ፕላኔት ላይ ውሃ የመታየቱን ዜና "እጅግ ድንቅ" ብለውታል። "በፕላኔት ላይ ውሃ ስናገኝ ይህ የመጀመሪያው ነው። ሙቀቱም የሰው ልጅ ሊኖርበት ከሚችለው የሙቀት መጠን ጋር የሚመጣጠን ነው" ብለዋል። K2-18b የተባለው ፕላኔት ከመሬት 650 ሚሊየን ማይል ይርቃል። ከመሬት ሥርዓተ ጸሐይ ውጪ ያሉ ፕላኔቶች ኤክሶፕላኔት ይባላሉ። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2020 ይሠራል ተብሎ በሚጠበቅ ቴሌስኮፕ፤ ፕላኔቷ ላይ ሕይወት ባላቸው ነገሮች የሚወጣ አየር ስለመኖሩ እንደሚፈተሽ ተመራማሪዎች ገልጸዋል። "በህዋ ውስጥ ያለነው የሰው ልጆች ብቻ ነን? የሚለው በሳይንስ ውስጥ ካሉ ጥያቄዎች ዋነኛው ነው" ሲሉ ፕሮፌሰር ጂኦቫንያ ተናግረዋል። የምርምር ቡድኑ ግኝቱ ላይ የደረሰው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2016 እስከ 2017 በሚገኙት ወራት በተደረገ ጥናት ነው። ከK2-18b ክፍል 50 በመቶው በውሀ የተሸፈነ እንደሆነ የሚታመን ሲሆን፤ ምናልባትም ለሰው ልጆች ምቹ መኖሪያ ልትሆን እንደምትችል መላ ምቶች አሉ። ፕላኔቷ ከመሬት ሁለት እጥፍ የምትበልጥም ናት።
news-53226337
https://www.bbc.com/amharic/news-53226337
በአሜሪካዋ የሉዊዚያና ግዛት ውርጃን የሚገድበው ሕግ ተሻረ
የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሉዊዚያና ግዛት ውርጃን የሚከለክለው ሕግ ኢ-ሕገመንግሥታዊ ነው በማለት ሽሮታል።
በተሻረው ሕግ መሰረት ዶክተሮች ጽንስ ለማቋረጥ የሚፈልጉ ሴቶችን አቅራቢያቸው ወደ ሚገኙ ሆስፒታል እንዲገቡ የሚያደርግ ሲሆን ይህ አሰራር ሴቶቹን ላልተፈለገ ችግር አጋልጧቸዋል ብለዋል ብይኑን ያስተላለፉት ዳኞች። ዋና ዳኛ ጆን ሮበርትስን ጨምሮ ሌሎች አራት ዳኞች ድምጻቸውን በመስጠት ሕጉ 5 ለ 4 በሆነ ድምጽ እንዲሻር ሆኗል። በአውሮፓውያኑ 2016 በተመሳሳይ ፍርድ ቤቱ በቴክሳስ ውርጃን የሚፈቅድ ሕግ አስተላልፏል። በትራምፕ አስተዳደር ዘመን እንዲህ አይነት ከፍተኛ የውርጃ ሕግ ሲሻር ይህ የመጀመሪያው እንደሆነ ተጠቁሟል። 2014 ላይ የወጣው ሕግ በሉዊዚያና የሚገኙ ዶክተሮች እስከ 48 ኪሎ ሜትር ድርስ ባሉ አካባቢዎች ጭምር ባሉ ሆስፒታሎች ስልጣን ያላቸው ሲሆን ግዛቲቱ ይህን ያደረግኩት የሴቶችን ጤና ለመጠበቅ ነው ብላ ነበር። ነገር ግን ተቺዎች እንደሚሉት ይህ አከራካሪው ሕግ ውርጃን የሚፈጽሙ ሆስፒታሎችን ቁጥር የቀነሰና የሴቶችን መብት የሚጥስ ነው። በቀደመው ሕግ መሰረት የጽንስ ማስወረድ መፈጸም የሚፈልጉ ሴቶች በአቅራቢያቸው እስከ 48 ኪሎሜትር ድረስ ባሉ ሆስፒታሎች ብቻ ውርጃውን መፈጸም አለባቸው። ምንም እንኳን ግዛቲቱ ሕጉን ጠበቅ ያደረግኩት የሴቶችን ጤና ለመጠበቅ ነው ብትልም ተሟጋቾች ግን በውርጃ ወቅት ሊያጋጥም የሚችለው የጤና እክል እምብዛም ነው ይላሉ። በተጨማሪም በዚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሆስፒታሎች ከሐይማኖት ጋር ግንኙነት ያላቸው አልያም ወግ አጥባቂ በመሆናቸው በሆስፒታሉ ውስጥ ውርጃ እንዲፈጸም አይፈቅዱም ብለዋል። ይህ ደግሞ ሴቶች የተሰጣቸውን ሕገ-መንግሥታዊ መብት እንዳይጠቀሙ አድርጓቸዋል በማለት ይከራከራሉ። የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ በአዲሱ ሕግ ምክንያት ማንኛውም ክሊኒክና ሆስፒታል አይዘጋም አልያም ላለመዘጋት ሲሉ ውርጃ እንዲፈጽሙ አይገደዱም ብሏል።
news-50626131
https://www.bbc.com/amharic/news-50626131
ቡርኪናፋሶ፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች ሞቱ
ትናንት በቡርኪናፋሶ ያልታወቁ ታጣቂዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ በከፈቱት ድንገተኛ ተኩስ በትንሹ 14 ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ።
ጥቃቱ የተፈጸመው በምስራቃዊ ቡርኪና ፋሶ ሃንቶኩራ በተባለው አካባቢ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች የዕለተ ዕሁድ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ለመካፈል በቤተክርስቲያኗ ተገኝተው ነበር። • በቡርኪናፋሶ ቤተ ክርስቲያን በደረሰ ጥቃት ምዕመናን ተገደሉ • በቡርኪና ፋሶ መስጅድ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ የጥቃት ፈጻሚዎቹ ማንነት እና ለምን ጥቃቱን እንደፈጸሙት እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ባለፉት ዓመታት በቡርኪናፋሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሰዎች በአክራሪ ኢስላማዊ ቡድኖች እንዲሁም ዘርና ሃይማኖትን መሰረት ባደረጉ ጥቃቶች ህይወታቸው አልፏል። የአካባቢው የመንግሥት ሀላፊዎች ሰጡት በተባለ መረጃ መሰረት ደግሞ በእሁዱ ጥቃት ከሟቾች በተጨማሪ በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል። አንድ የሀገሪቱ የደህንነት ምንጭን ጠቅሶ ኤኤፍፒ እንደዘገበው የጦር መሳሪያ የታጠቁት ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያኗ በመግባት የተኩስ እሩምታ የከፈቱ ሲሆን የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ ፓስተር እንዲሁም ህጻናትን ጨምሮ ብዙዎችን ገድለዋል። ባሳለፍነው ጥቅምት በቡርኪናፋሶ መስጂድ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት 15 ሰዎች ሲደገሉ ሁለት ደግሞ መቁሰላቸው የሚታወስ ነው።
news-55036272
https://www.bbc.com/amharic/news-55036272
ትግራይ፡ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገለፀ
የኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ፈተናው ባለው ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ምክንያት መራዘሙን ነው የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በዛሬው ዕለት [ኅዳር 15/ 2013 ዓ.ም] በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት። ባለፈው ዓመት በተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የ8ኛ ክልል ክልላዊ ፈተና ግን ከታኅሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ተገልጿል። የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት የሚወሰን እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴሩ ባስቀመጠው ወቅትም ይሰጣል ተብሏል። የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና መቼ እንደሚሆን ጊዜ ባይጠቀስም የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ባሉ የሕግና ፀጥታን የማስከበር ሂደቶች መቋጫ እንዳገኙ እንደሚሰጥ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት ተማሪዎች በሚኒስቴሩ የተሰጠውን ውሳኔ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለፈተና እየተዘጋጁ እንዲጠባበቁም ሚኒስቴር ዴኤታው አሳስበዋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ቤቶችን መዝጋትና ፈተናዎች እንዲራዘሙ ያደረገችው ኢትዮጵያ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኅዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ. ም ለመስጠት ማቀዷ ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከኅዳር 28 እስከ ታኅሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስቴር ገልፆ ነበር። በአገሪቱ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ዩኒቨርስቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲያራዝሙም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኗል። ሚኒስቴሩ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባስተላለፈው መልዕክት በተመደቡበት ያሉ ተማሪዎች በግቢያቸው እንዲቆዩ እና በየግቢያቸው የሚሰጧቸውን ማሳሰቢያዎችም እየተከታተሉ እንድትንቀሳቀሱ ብሏል። ከአካባቢያቸው ያልተነሱ ተማሪዎች በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ በያሉበት እንዲቆዩም ማሳሰቡ የሚታወስ ነው። ባለፈው ዓመት በመላው ዓለም የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የትምህርት ተቋማት መዘጋታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ግን በተለያዩ ደረጃዎች የመማር ማስተማሩ ሂደት ይጀምራል ተብሎ ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በትግራይ ውስጥ በተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወሳል።
news-55391889
https://www.bbc.com/amharic/news-55391889
ሰብዓዊ መብት፡ ፓኪስታናዊቷ የመብት ተሟጋች በካናዳ ሕይወቷ አልፎ መገኘቱ ተሰማ
ፓኪስታናዊቷ የመብት ተሟጋች ካሪማ ባሎች በካናዳ ቶሮንቶ ሕይወቷ አልፎ መገኘቱ ተሰማ።
ይህንንም ተከትሎ የመብት ተሟጋች ቡድኖች በአሟሟቷ ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። በምዕራብ ፓኪስታን ባሎቺስታን ግዛት ቅስቀሳ በማድረግ የምትታወቀው የ37 ዓመቷ ካሪማ፤ የፓኪስታን ጦርን እና መንግሥትን በመተቸት ትታወቃለች። ከአራት ዓመታት በፊትም በቢቢሲ 100 አነቃቂ ግለሰቦች ዝርዝር ውስጥ ተካትታ ነበር። የቶሮንቶ ፖሊስ እሁድ ዕለት ግለሰቧ መጥፋቷን አስታውቆ ነበር። የከተማዋ ፖሊስ ሰኞ ዕለት በትዊተር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ የመብት ተሟጋቿ ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው በከተማዋ ምዕራብ ክፍል ቤይ መንገድ ላይ እሁድ ዕለት መሆኑን ጠቅሷል። ከዚያም በድጋሜ በትዊተር ሰሌዳው ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ዝርዝር ሁኔታዎችን ሳይገልፅ ካሪማ 'መገኘቷን' ጽፏል። ይሁን እንጂ ጓደኞቿ እና አብረዋት የሚሰሩ የመብት ተሟጋቾች፤ ከዚያ በኋላ አስክሬኗ መገኘቱን ገልፀው፤ የሞቷ ምክንያት ግን ወዲያውኑ ግልፅ አለመደረጉን ተናግረዋል። የካሪማ እህት፣ ማህጋንጂ ባሎች ማክሰኞ ዕለት የእህቷ ሞት "ለቤተሰቡ ብቻ ሳይሆን ለካሪማ ብሔራዊ እንቅስቃሴ አሳዛኝ ነው" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። አክላም "ካሪማ ወደ ካናዳ የሄደችው ስለፈለገች ሳይሆን በፓኪስታን ግልፅ በሆነ መንገድ ስለ መብት መሟገት የሚቻል ስላልነበረ ነው" ብላለች። የባሎችስታን ግዛት ለረዥም ጊዜ የዘለቀ የተገንጣዮችን እንቅስቃሴ አስተናግዳለች። ካሪማም በፓኪስታን እንቅስቃሴ እንዳያደርግ የተከለከለው የመብት ተሟጋች ቡድን፤ 'የባሎች ተማሪዎች ድርጅት' የቀድሞ ኃላፊ ነበረች። በቡድኑ ውስጥም የመጀመሪያዋ ሴት መሪ ሆና አገልግላለች። ተቃውሞ ለማሰማት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አደባባይ የወጣችውም በአውሮፓዊያኑ 2005 መጀመሪያ አካባቢ ሲሆን ቦታውም ባሎቺስታን ቱርባት ነበር። ለተቃውሞ የወጣችውም ከጠፉት ዘመዶቿ የአንዱን ፎቶግራፍ ይዛ ነበር። ካሪማ ከአገሯ የተሰደደችው በዚህ እንቅስቃሴዋ በሽብር ከተከሰሰች በኋላ ነው። በአውሮፓዊያኑ 2015 ሕይወቷ አደጋ ላይ መሆኑን በመግለጽ ጥገኝነት ጠይቃ በካናዳ ኑሮዋን አድርጋ ነበር። ወደ ቶሮንቶ ከገባች በኋላም አብሯት የሚሰራውን የመብት ተሟጋች ሃማል ባሎች ጋር ትዳር መስርታ፤ እዚያም በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በካናዳና በአውሮፓ በሚካሄዱ የሰብዓዊ መብት እንቅስቃሴዎች ላይ በንቁ ስትሳተፍ ቆይታለች። በባሎቺስታን ያሉ የመብት ተሟጋቾች እንደሚሉት በቅርብ ዓመታት ውስጥ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች የደረሱበት አልታወቀም። ይሁን እንጅ የፓኪስታን ጦር የክልሉን ራስ ገዝ አስተዳደር እየጨቆነ ነው በሚል የቀረበውን ክስ ተቃውሟል። የካሪማን ሞት ተከትሎም የባሎቺስታን ብሔራዊ እንቅስቃሴ የ40 ቀናት የሐዘን ቀን አውጇል። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የደቡብ እስያ ቢሮ በትዊተር ገጹ ላይ "የካሪማ ሞት በጣም አስደንጋጭ ነው፤ በአፋጣኝና በሚገባ ምርመራ መካሄድ አለበት፤ ወንጀለኞችም በሕግ ፊት መቅረብ አለባቸው" ብሏል።
news-54920169
https://www.bbc.com/amharic/news-54920169
ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ኩባንያዎች ከቻይና ወታደራዊ ተቋማት ጋር እንዳይሰሩ አገዱ
ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ኩባንያዎች ከቻይና ወታደራዊ ተቋማት ጋር እንዳይሰሩ የሚያግድ አዲስ ትዕዛዝ አወጡ።
በዚህም መሰረት ማንኛውም የአሜሪካ ኩባንያ ከቻይና መከላከያ ጋር ያለውን የሥራ ግንኙነት እንዲያቋርጥ አዝዘዋል። ከዚህም በተጨማሪ በቻይና መከላከያ የሚደገፉ ኩባንያዎቸ ላይ የአሜሪካ ኩባንያዎች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዳያፈሱ ያግዳል። ትራምፕ ለዚህ ልዩ ትዕዛዝ መውጣት ዋንኛው ምክንያት ነው የሚሉት ቻይና የአሜሪካ ኩባንያዎችን እየተጠቀመችባቸው ነው የሚል ነው። እንዴት ለሚለው ሲያብራሩ ቻይና ከአሜሪካ ኩባያዎች ጋር የተለያዩ የሥራ ስምምነቶች በመፈራረም መከላከያዋን እየገነባችም ነው። የቻይና መከላከያን የሚያዘምኑት የኛው የአሜሪካዊያን ኩባንያዎች ናቸው ብለዋል። ይህ የትራምፕ እቀባ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው ከፈረንጆቹ የጃንዋሪ ወር በኋላ ነው። ይህ እቀባ የቻይና ሕዝብ ይደጉማዋል የሚባሉትን የቻይና ቴሌኮምን እንዲሁም ሂክቪሽን የቴክኖሎጂ ድርጅት ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ ያለፉትን አራት ዓመታት አገራቸው ከቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት ለመገደብ ብዙ ሲጥሩ ከርመዋል። ትራምፕ ከቻይና በሚመጡ ገቢ እቃዎች ላይ ጫን ያለው ግብር በመጣል በቢሊዯን ዶላር ለመሰብሰብ ሞክረዋል። እንደ ቲክቶክ ያሉ የቻይና ግዙፍ ቴክኖሎጂ ላይ በአሜሪካ ምድር አገልግሎት እንዳይሰጡ የደኅንነት ስጋትን በማንሳት እቀባን ጥለዋል። ቻይና በሆንግ ኮንግ ላይ እየወሰደችው ባለው ጥብቅ የቁጥጥር እርምጃ እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አነሳስና ሥርጭት የሁለቱ የዓለም ልዕለ ኃያላን ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲሻክር ካደረጉ ተጨማሪ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ። የትራምፕ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ይህ አዲስ ደንብ በዋይት ሐውስ ለወራት ሲብሰለሰል የነበረ ነው። በቻይና መከላከያ ይደገፋሉ፣ የተባሉ 31 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎችም በስም ከተለዩ ቆይተዋል። ዶናልድ ትራምፕ ይህ ያወጡት አዲስ እቀባ ተግባራዊ መሆን በጀመረ በ20 ቀናት ውስጥ ዋይት ሐውስን ይለቃሉ።
49055485
https://www.bbc.com/amharic/49055485
በወንዶ ገነት ከተማ በነበረ ተቃውሞ 3 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
ትናንት በወንዶ ገነት ከተማ በተነሳ ተቃውሞ ላይ በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የሦስት ወጣቶች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ገለጡ።
የወንዶ ገነት ከተማ ከንቲባ አቶ ዓለሙ ጉበሌ ተቃውሞው የጀመረው ትናንት ከሰዓት መሆንን ጠቅሰው፤ በተቃውሞው ላይ የተሳተፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣና ግርግሩ ያልተፈለገ አቅጣጫ ሊይዝ ሲል መከላከያ ሠራዊት ገብቷል ብለዋል። የወንዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ሌዳሞ በበኩላቸው ለግጭቱ መነሻ የሆነው በሐዋሳና በሌሎች አካባቢዎች የተነሱ ተቃውሞዎች መሆናቸውን ገልፀዋል። • የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ • በሐዋሳ ለግርግሩ ተጠያቂ የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸው ተገለፀ • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች በከተማዋ የተቃጠለ ንብረትም ሆነ የወደመ ሀብት አለመኖሩን የተናገሩት አቶ ዳዊት፤ አስር ግለሰቦች በተቃውሞው ላይ በደረሰ ግጭት ተጎድተው በሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆኑን ጠቅሰዋል። የተጎዱት ወጣቶች ህክምና እያገኙ ያሉት በሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታልና አዳሬ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ከንቲባው ናቸው። በተጨማሪም ወንዶ ገነት በንግድ እንቅስቃሴዋ የምትታወቅ ከተማ መሆኗን ጠቅሰው፤ ከተማዋን በማረጋጋት ወደነበረበት ለመመለስ ከአገር ሽማግሌዎችና ከሐይማኖት አባቶች ጋር እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል። ትናንት ተቃውሞ ከነበረባቸው የሲዳማ ዞን ወረዳዎች መካከል አንዷ የሆነችው የሀገረ ሰላም ከተማ የገቢዎች ባለሥልጣን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን፤ በከተማዋ በነበረው ተቃውሞ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ ቁጥራቸውን ይፋ ለማድረግ መረጃው በእጃቸው እንደሌለ ገልጠዋል። ትናንት ማታ 3 ሰዓት ላይ ወደ ከተማዋ የመከላከያ ሠራዊት መግባቱን ያረጋገጡት ኃላፊው፤ አሁን የተዘጉ ሱቆችን ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የማስከፈት ሥራ እየሠሩ እንደሆነና የአከባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ከአገር ሽማግሌዎች ጋር እየተወያዩ መሆኑን አረጋግጠዋል። ከሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ. ም ጀምሮ በሐዋሳ፣ አገረ ሰላም፣ አለታ ወንዶ፣ ይርጋለም፣ ለኩና ሌሎችም ከተሞች ግጭቶች ተቀስቅሰው እንደነበረ ይታወሳል። በግጭቶቹ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች መኖራቸው በተለያዩ ወገኖች ቢነገርም፤ እስካሁን ትክክለኛውን ቁጥር ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
news-55520507
https://www.bbc.com/amharic/news-55520507
በኒጀር ሁለት መንደሮች ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በርካቶች ተገደሉ
የእስላማዊ ቡድን አባላት ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ ታጣቂዎች በኒጀር ሁለት መንደሮች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሰዎችን መግደላቸው ተነገረ።
የኒጀር ወታደር በጥቃቱ ቾምባንጉ በተባለች መንደር 49 ሰዎች ሲገደሉ 17 የሚሆኑት ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸው ታውቋል። ዛሩምዳርየ በተባለችና በምዕራብ ኒጀር ከማሊ ጋር በምትዋሰነው ሌላኛዋ መንደር ደግሞ 30 ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። በታጠቁ ኃይሎች የሚፈጸሙ መሰል ጥቃቶች በአፍሪካ ሳህል አካባቢ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ ይገኛሉ። ፈረንሳይ ቅዳሜ ዕለት በማሊ ሁለት ወታደሮቿ መገደላቸውን አስታውቃለች። ከሰዓታት በፊት ደግሞ ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያለው እስላማዊ ቡድን፣ በማሊ ሰኞ ዕለት በተለያዩ ቦታዎች ሦስት የፈረንሳይ ወታደሮችን ገድያለሁ ብሎ ነበር። ፈረንሳይ የምዕራብ አፍሪካንና የአውሮፓን ጥምረት ኃይልን በመምራት ባሳህል አካባቢ እስላማዊ ታጣቂ ቡድኖችን እየተዋጋች ትገኛለች። ቢሆንም ግን አካባቢው የጎሳ ግጭት፣ ዝርፊያ፣ የሰው እና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር የተስፋፋበት ቀጠና መሆኑን ቀጥሏል። የትናንቱን ጥቃት ተከትሎ የአገር ውስጥ ሚንስትሩ አልካቼ አልሃዳ ወደ ስፍራው ወታደር መንቀሳቀሱን ገልጸዋል። ይሁንና ጥቃቱ እንዴት እንደተፈጸመ ያብራሩት ነገር የለም። የአካባቢው ባለስልጣናት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ሲገልጹ፣ አንድ የዚያው አካባቢ ጋዜጠኛ ደግሞ የሟቾች ቁጥር 50 መድረሱን ዘግቧል። ኒጀርን ከማሊና ቡርኪናፋሶ ጋር የሚያዋስነው ቲላበሪ ግዛት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የጂሃዲስት ኃይሎች በስፋት ጥቃት የሚፈጽሙበት አካባቢ ሆኗል። ከተሽከርካሪ ላይ በመሆን አክራሪ ኃይሎች የሚፈጽሙትን ጥቃት ለመከላከል ሲባል በሞተር ሳይክል መሽከርከር ከተከለከለ ከአንድ ዓመት በላይ አስቆጥሯል። ኒጀር በሌላ በኩል ከናይጀሪያ በሚነሳው የቦኮሃራም ቡድንም ጥቃት ይደርስባታል። ባለፈው ወር በኒጀር ደቡብ ምሥራቅ ዲፋ አካባቢ ይሄው የቦኮሃራም ቡድን በፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 27 ዜጎቿ ተገድለዋል። በቅርቡ ቲላቤሪ አካባቢ የደረሰው ጥቃት ብሔራዊ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅትና አገሪቱን ለሁለት አምስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት መሐማዱ ኢሱፉ በተሸነፉበት ዕለት ነበር። የአገሪቱ የምርጫ ባለስልጣናት ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቱን ቅዳሜ ያሳወቁ ሲሆን የቀድሞው ሚንስትርና የገዥው ፓርቲ አባል ሞሐመድ ባዙም እየመሩ መሆኑ ታውቋል። የአገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት የዚህኛውን ምርጫ ሐቀኝነት ካረጋገጠ በኋላ በሚቀጥለው የካቲት ወር በአገሪቱ ሁለተኛው ዙር ምርጫ ይካሄዳል ተብሏል።
news-52074718
https://www.bbc.com/amharic/news-52074718
ኮሮናቫይረስ፡ ፊታችንን በእጃችን መንካት ለምን ልምድ ሆነብን? እንዴትስ መተው እንችላለን?
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ የጤና ባለሙያዎችና ባለስልጣናት ደጋግመው እንደሚመክሩት የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝን ለመከላከል ቁልፍ ከሆኑ መንገዶች መካከል አንዱ ፊታችንን በእጃችን አለመንካት ነው።
ስናወራና የተለያዩ ነገሮችንን ስናከናውን ፊታችንን መነካካት የብዙዎቻችን ልምድ ነው። ነገር ግን በመጀመሪያ ደረጃ ለምንድን ነው ፊታችንን የምንነካው? አሁንስ ብድግ ብለን ለማቆም እንችላለን? የሥነ ልቦና ባለሙያዋ ናታሻ ቲዋሪ እንደሚሉት ይህንን ልማዳችንን በቀላሉ ለመተው አስቸጋሪ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ "ከአፈጣጠራችን ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው።" ባለሙያዋ እንደሚሉት በእጃችንን ፊታችንን መነካካት የተፈጥሯችን አካል ሆኗል። ለዚህም ምሳሌ ሲያስቀምጡ የሰው ልጅ በእናቱ ማህጸን ውስጥ እንኳን እያለ በደመ ነፍስ ፊቱን እንደሚነካካ ተናግረዋል። ለእራሳችን ፊታችንን በእጃችን መንካት እንደሌለብን፣ መንካት ማቆም እንዳለብን ደጋግመን ብንነግርም፤ ፊታችንን ከነካን ልንታመም እንደምንችል ብናስብም፤ የምንላቸውና የምናስባቸው ነገሮች በሙሉ ከተፈጥሯችን ውጪ የሆነ ነገር ይሆናሉ። ፊታችንን በምንነካካበት ጊዜ እያደረግን ያለነው እራሳችንን እያረጋጋን ወይም በአንድ ነገር ላይ ለማተኮር እየሞከርን ሊሆን ይችላል። የሥነ ልቦና ባለሙያዋ እንደሚሉት በተለይ ከፊታችን የተለዩ ክፍሎችን በእጃችን ስንነካ በሰውነታችን ውጥረትን የሚያስተናግዱ የተወሰኑ ክፍሎችን እያነቃቃን ይሆናል። በዚህም ፓራሲምፓተቲክ የሚባለውን የነርቭ ሥርዓታችንን እናነቃቃለን። ይህም እራሳችንን ለማረጋጋት የሚያስችለን አንድ መንገድ ነው። በውሾችና በድመቶች ላይም ተመሳሳይ ሁኔታ ማየት ይቻላል የሚሉት ባለሙያዋ፤ ህጻናትም ከወላጆቻቸው በመመልከት ተመሳሳይ ነገሮችን ያደርጋሉ ሲሉ ይገልጻሉ። እንደ ባለሙያዋ ከሆነ ቤተሰቦቻችን ሲደነግጡ፣ ሲበሳጩ ወይም ሲደነቁ ፊታቸውን በእጃቸው የሚይዙ ከሆነ፣ ልጆች ወላጆቻቸው የሚያደርጉትን የመድገም ሰፊ ዕድል አላቸው። ግራ የሚያጋባው ግን ፊታችንን አለመንካት እጅግ ጠቃሚ በሚሆንበት ጊዜ ሳናስበው አእምሯችን በመደበኛነት እጃችንን ለጤናችን አስፈላጊ ወደሆነው ቦታ እንዲሄድ ያደርገዋል። በእጃችን ፊታችንን እንዳንነካ ምን ማድረግ አለብን? ፊታችንን ፈጽሞ በእጃችን አለመንካት የማይቻል ነገር በመሆኑ ይህንን ልማዳችንን ለማስወገድ ቁልፍ ዘዴ የሚሆነው ያዳበርነውን ልማድ መሰረት አድርገን ፊታችንን ደጋግመን እንድንነካ የሚያደርጉንን ነገሮች መቀነስ ያስፈልጋል። በተጨማሪም እጃችንን ከፊታችን ጋር ያለውን መነካካት ለማስወገድ የሚያስችሉ ልማዶችን ማዳበርና እጃችንን የምናሳርፍበትን ቦታዎች መከታተልና መወሰን ጠቃሚ ነው። ለምሳሌም ሲያወሩ እጅዎ ለፊትዎ በቀረበ ሁኔታ እያንቀሳቀሱ የሚናገሩ ከሆነ እጅዎ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ፊትዎ ላይ እንዲያርፍ እድልን ስለሚሰጠው ከፊትዎ ማራቅ ይኖርብዎታል። ለዚህ ደግሞ ጣትዎትን በማቆላለፍ ጭንዎ ላይ እንዲያርፍ አድርገው እጅዎ ወደ ፊትዎ እንዳይቀርብ የሚያደርግ ልምድን ማዳበር ያስፈልጋል። ከዚያም እጅዎን አንስተው ፊትዎን የመንካት ስሜት ሲፈጠርብዎ በርቀት ያለውን የእጅዎን እንቅስቃሴ በቀላሉ በመረዳት ምን ማድረግ እንዳለብዎ ለመወሰን ስለሚችሉ በደመ ነፍስ የሚያደርጉትን ነገር ለመቆጣጠር ይችላሉ። ስለዚህም ፊታችንን የምንነካ ከሆነ ከሆነ እጃችን ንጹህ መሆን ይኖርበታል። በተለይ የኮሮናቫይረስ በፍጥነት እየተዛመተ ባለበት በዚህ ዘመን ደግሞ ከፍጥረታችን ጀምሮ አብሮን የቆየውን እንዲሁም ለዓመታት ያዳበርነውን ፊታችንን የመንካት ልማድ ከተቻለ ማስወገድ ካልሆነም መቆጣጠር ያስፈልጋል። ካልሆነ ደግሞ በተደጋጋሚ የእጃችንን ንጽህና በአግባቡ በመጠበቅ ከኮሮናቫይረስና ከሌሎች በሽታዎች እራሳችንን መጠበቅ እንዳለብን ባለሙያዎች ይመክራሉ።
news-52360204
https://www.bbc.com/amharic/news-52360204
ሰሜን ኮሪያ፡ የኪም ጆንግ-ኡን በጠና ታመዋል የሚለው ዜና የሐሰት ነው ተባለ
የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን በጠና ቃመዋል የሚለው ሪፖርት ሐሰት ነው አሉ።
ኪም ጆንግ ኡን ኪም ጆንግ-ኡን "በጠና ታመዋል"፣ "በሞት እና በህይወት መካከል ይገኛሉ" ወይም "ከቀዶ ህክምና በኋላ እያገገሙ ነው" የሚሉ ዜናዎች ትክክለኛነትን ማረጋገጥ ወትሮም ቢሆን እጅጉን ከባድ ናቸው። ይሁን እንጂ የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት የ36 ዓመቱ ኪም ጆንግ-ኡን በጠና ስለመታመማሳቸው ከሰሜን ኮሪያ ምንም አይነት ምልክቶች አልታዩም ብለዋል። የኪም ጆንግ-ኡን ጤናን በማስመልከትም የሚወጡ መሰል ዜናዎች በርካታ መሆናቸውን ተጠቅሷል። የኪም የጤና መቃወስ ዜና መናፈስ እንዴት ጀመረ? ከአንድ ሳምንት በፊት ሚያዚያ 7 ኪም ጆንግ ኡን የአያታቸውን የልደት ዝግጅት ሳይታደሙ ቀርተዋል። ይህ በዓል የአገሪቱ መስራች እንደሆኑ የሚታሰቡ ግለሰብ ልደት እንደመሆኑ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ዝግጅት ነው። ኪም ጆንግ-ኡን ከዚህ ቀደም ሳይታደሙ ቀርተው አያውቅም - ብርቱ ጉዳይ ካልገጠማቸው በቀር አይቀሩም። ኪም በዝግጅቱ ሳይገኙ መቅረታቸው በበርካቶች ዘንድ እንዴት? ለምን የሚሉ ጥያቄዎች እንዲነሱ አደረጉ። ኪም ለመጨረሻ ጊዜ በብሔራዊ ጣቢያው የታዩት ሚያዚያ 4 ላይ ነበር። በቴሌቪዥን ሲታዩ እንደተለመደው ዘና ብለው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ኪም በአደባባይ ሳይታዩ ቀሩ። ባሳለፍነው ሳምንት ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራ አድርጋ ነበር። የአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ በዘገበበት ወቅት የኪም ጆንግ-ኡንን ስም አልጠቀሰም። ምስላቸውንም አላሳየም። ከዚህ ቀደም ሰሜን ኮሪያ መሰል ወታደራዊ ሙከራዎችን ስታካሂድ ኪም በቴሌቪዥን መስኮት ይታዩ ነበር። በአያታቸው የልደት በኣል ላይ ባለመታየታቸው ነበር ወሬው መናፈስ የጀመረው የኪም በጽኑ የምታመም ዜና ኪም ጆንግ-ኡን በጽኑ የመታመማቸው ዜና ቅድሞ የተዘገበው ከሰሜን ኮሪያ ሸሽተው መኖሪያቸውን ደቡብ ኮሪያ ባደረጉ ሰዎች በሚመራ እንድ ድረ-ገጽ ላይ ነበር። 'ዴይሊ ኤንኬ' የተሰኘው ድረ-ገጽ አገኘሁት ባለው መረጃ መሠረት የሰሜን ኮሪያው መሪ በልብ ህመም እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም መገናኛ ብዙሃን ኪም ጆንግ ኡን አብዝተው ሲጋራ በማጨሳቸው፣ ከልክ ባለፈ ውፍረት እና ከሥራ ጫና ጋር ተያይዞ ለልብ ህመም ተጋልጠዋል እያሉ ነው። ይሁን እንጂ የደቡብ ኮሪያ መንግሥት መግለጫ እና በቻይና ደኅንነት ውስጥ ያሉ ምንጮች ለሬውተርስ እንደተናገሩት የኪም ጆንግ-ኡን ጤና እክል ገጥሞታል መባሉ ስህተት ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ እስካሁን ድረስ የትኛውም አካል ኪም ጆንግ-ኡን የልብ ቀዶ ህክምና አላደረጉም አላላም። የደቡብ ኮሪያ መንግሥትም ሆነ የቻይና ደኅንነት ምንጮች ያሉት የሰሜን ኮሪያው መሪ "በጽኑ ታመዋል" የሚለው ዜና ሐሰት ነው። ኪም ጆንግ-ኡን 'ሲሰወሩ' ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። እአአ 2014 ላይ ኪም ጆንግ-ኡን ለ40 ቀናት ሳይታዩ ቆይተው ነበር። ይህም በሕዝቡ ዘንድ ኪም ጆንግ-ኡን በተቀናቃኛቸው መፈንቅለ መንግሥት ተከናውኖባቸውዋል የሚል ወሬ በስፋት ተሰራጭቶ ነበር። ነገር ግን ከዚያ ብዙ ሳይቆዩ ከዘራ ይዘው የሚታዩበት ምስል ላይ ደህና መሆናቸው ለሕዝብ ቀረበ። ኪም ጆንግ-ኡንን ሊተካ የሚችለው ማነው? ሰሜን ኮሪያ ውስጥ አንዳች ነገር ቢከሰት ኪም ጆንግ-ኡንን ሊተካ የሚችለው ማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም። ኪም ጆንግ-ኡን ከአባታቸው ሞት በኋላ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት በአባታቸው ለበርካታ ዓመታት ለስልጣን ሲኮተኮቱ ቆየረተዋል። ምናልባት ኪም ጆንግ-ኡን አገር ማስተዳደር ባይችሉ፤ የኪም እህት ኪም ዮ-ዮንግ ወንድሟን ልትተካ ትችል ይሆናል። ኪም ዮ-ዮንግ ከወንድሟ ጎን ሆና በወሳኝ ስብሰባዎች ላይ ስትሳተፍ ትታያለች።
news-55082531
https://www.bbc.com/amharic/news-55082531
ትግራይ፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የዘመቻው የመጨረሻ ምዕራፍ መጀመሩን አስታወቁ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የአገር መከላከያ ሠራዊት የመጨረሻ እና ሦስተኛ ምዕራፍ የተባለውን ዘመቻ በህወሓት አመራሮችና በትግራይ ኃይሎች ላይ እንዲፈጽም ትዕዛዝ እንደተሰጠው አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ ለህወሓት አመራሮች እና ተዋጊ ኃይሎች እጃቸውን እንደሰጡ ባለፈው እሁድ አስቀምጠውት የነበረው የተሰጠው የ72 ሰዓታት ጊዜ ገደብ መጠናቀቁንም አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ መቀለ ከተማ መቃረቡን ተከትሎ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለማስቀረት በሚል ለሦስት ቀናት የቆየ የጊዜ ገደብ መስጠታቸው ይታወሳል። የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ የሰጡትን የሦስት ቀናት የጊዜ እንደማይቀበሉ አሳውቀው ነበር። "ሕግ የማስከበሩ ዘመቻችን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ መከላከያ ሠራዊት የመጨረሻውን እና ሦስተኛውን የዘመቻ ምዕራፍ እንዲፈጽም ትዕዛዝ ተሰጥቶታል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንሰትሩ ይህን ትዕዛዝ ያስተላለፉት የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ የተለያዩ አገራት መሪዎች ሰላም ወርዶ ልዩነቶች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ እየወተወቱ ባሉበት ወቅት ነው። የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀ-መንበር በደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የተላኩ ሦስት የቀድሞ የአፍሪካ አገራት ፕሬዝደንቶችም ዛሬ ጠዋት በጉዳዩ ላይ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጋር ለመወያየት አዲስ አበባ ገብተዋል። ከቀናት በፊት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጠቅላይ ሚንስትሩ ለአፍሪካ ኅብረት እና ለአፍሪካ መሪዎች ካለ አክብሮት የመነጨ ይህን ልዑክ ተቀብለው እንደሚያነጋግሩ አስታውሰው፤ "ከህወሓት ኃይሎች ጋር ግን እንደ ሕጋዊ አካል ቆጥሮ የሚደረግ ውይይት አይኖርም" ብለዋል። በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ዓለም አቀፉ ማኅብረሰብ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ ማሳሰባቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመግለጫቸው "የወዳጆቻችን ስጋት እና ምክረ ሃሳብ ከግምት እያስገባን፤ በውሳጣዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረግን ጥረትን አንቀበልም። ስለዚህም ዓለም አቀፉ ማኅብረሰብ ተቀባይነት ከሌላው እና ሕጋዊ ካልሆነ ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጣልቃ-አለመግባት መሠረታዊ ምርሆዎችን እንዲያከብር በአክብሮት እናሳስባለን" ብለው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሩ በዛሬው መግለጫቸው፤ "በዚህ ዘመቻችን ለንጹሐን ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ በሕዝባችን ላብ የተሠራችው የመቀለ ከተማ የከፋ ጉዳት እንዳያገኛት የሚቻለው ሁሉ ይደረጋል" ብለዋል። መንግሥት 72 ሰዓታት የጊዜ ገደብ የሰጠው ለሁለት ዓላማ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ "በአንድ በኩል ዋና ፍላጎቱ ሕግ ማስከበር እንጂ ጦርነት አለመሆኑን መግለጥ ነው። . . . ሁለተኛው ደግሞ የህወሓት የጥፋት ዓላማ ዘግይቶም ቢሆን የገባው አንድም ሰው ከተገኘ፤ ያንንነ ሰው ለማትረፍ እንዲቻል ነው" ያሉ ሲሆን፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ሚሊሻ እና ልዩ ኃይል አባላት እጃቸውን እየሰጡ ገብተዋል ብለዋል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን በሚመራው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባትና መካሰስ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል በተናጠል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ መባባሱ ይታወሳል። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በክልሉ ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ፍጥጫው ወደ ወታደራዊ ግጭት አምርቶ ከሦስት ሳማንት በላይ ሆኗል። ባለፉት ሳምንታት በተካሄዱት ወታደራዊ ዘመቻዎች የመንግሥት ኃይሎች የተለያዩ ከተሞችን መያዛቸው የተነገረ ሲሆን በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ አቅራቢያ መድረሳቸውም ተገልጿል። በመቀለ ከተማ ውስጥ ሊያጋጥም ይችላል የተባለውን ወታደራዊ ግጭት በማስመልከት ዓለም አቀፍ ተቋማትና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በከተማዋ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለ ከ500 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ያሉባት ከመተማ መሆኗ የሚነገር ሲሆን ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ በነበሩት ባለፉት ሦስት ሳምንታት የነዳጅና ሌሎች መሰረታዊ ነገሮች እጥረት በከተማዋ መከሰቱ ሲነገር ነበር። የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት ከመቀለ ከተማ ቀደም ብሎ የክልሉ ትላልቅ ከተሞች የሆኑትን ሽረ፣ አክሱም፣ አድዋና አዲግራትን መቆጣጠሩን ባለፈው ሳምንት ማሳወቁ ይታወሳል።
news-49956843
https://www.bbc.com/amharic/news-49956843
የካቶሊኩ ፖፕ ለቄሶች ማግባት ይፈቅዱ ይሆን?
በመላው አለም የሚገኙ የካቶሊክ ካህናት በቤተክርስቲያኗ ዕጣ ፈንታ ላይ ከሰሞኑ ይመክራሉ።
በሚቀጥሉትም ሦስት ሳምንታት 260 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ስለ አየር ንብረት ለውጥ፣ ስደትና ስለ ኢቫንጀላውያን እንቅስቃሴ የሚወያዩ ሲሆን ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የብዙዎችን ቀልብ የሳበው ቤተክርስቲያኗ ላገቡ ወንዶች የቅስና ማዕረግን ልትፈቅድ ትችል ይሆን ወይ የሚለው ነው። ስብሰባው በአማዞን የሚካሄድ ሲሆን ሸምገል ያሉና ያገቡ ወንዶች ቄስ እንዲሆኑ እንዲፈቀድላቸውም አንድ ረቂቅ ፅሁፍ መዘጋጀቱም ተጠቅሷል። •«የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ያሳስበኛል» ፖፕ ፍራንሲስ •የኤርትራ መንግሥት፡ 'የካቶሊክ ጤና ተቋማትን መውሰዴ ትክክል ነው' አለ በረቂቁ መሠረት ከዕድሜያቸው በተጨማሪ በማሕበረሰቡ ዘንድ አንቱታን ያገኙና የአገሬው ተወላጅና በአካባቢው ለመስራት ፈቃደኛ መሆን አለባቸው ተብሏል። በደቡብ አሜሪካ ያለውን የካህናት እጥረት ለመቅረፍም ስለሚያስችል የአካባቢው ጳጳሳት ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው። በቅዳሴ ሥነ ስርዓት ላይ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው የማቁረብ ተግባር (የኢየሱስን ስጋና ደም ለምዕመናን ማቀበል) የሚችሉት ቄሶች ብቻ ናቸው። በአማዞን መንደሮች ውስጥ ከሚገኙት ማህበረሰቦች ውስጥ 85 በመቶ የሚሆኑት በካህናት እጥረት ምክንያት መቁረብም ሆነ ቅዳሴውን መከታተል የሚችሉት በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው ተብሏል። ፖፕ ፍራንሲስ ትውልዳቸው ላቲን አሜሪካ ከመሆኑ አንፃር የቀጠናው ችግርን በበለጠ ሊረዱት እንዲሚችሉ በካቶሊክ ጥናት ማዕከል ፕሮፌሰር ግሪጎሪ ራያን ይናገራሉ። ለምን አወዛጋቢ ሆነ? በካቶሊክ እምነት ዘንድ ቄሶች ከወሲባዊ ግንኙነት መታቀባቸውና አለማግባታቸው ከፍተኛ ሥፍራ የሚሰጠው ነው። አለማዊ ሕይወታቸውን ቤተሰብም ሆነ ሚስትን ሳይሉ ሙሉ ሕይወታቸውን ለፈጣሪያቸው ሊሰጡ ይገባል በሚልም ነው ቤተክርስቲያኗ ጋብቻን የምትከለክለው። በሃይማኖቶች ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረገችው ፕሮፌሰር ሊንዳ ከጋብቻ ክልከላ በተጨማሪ የካቶሊክ ካህናትና መነኮሳት ቤትና የተወሰነ ገንዘብ ተሰጥቷቸው የምነና አይነት ሕይወት የሚኖሩበት ነው ትላለች። • ኤርትራ፡ ''እናቶች ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር ታስረዋል'' ለምዕመናኑም በሚፈለጉበት ወቅት ማንኛውንም አይነት አገልግሎት ለመስጠትም ራሳቸውን ዝግጁ ማድረግም እንዳለባቸው ቤተ ክርስቲያኗ እንደምታዝም ገልጻለች። ለወግ አጥባቂዎቹ ይህ ጉዳይ የሚዋጥ አልሆነም፤ የጀርመኑ ካርዲናል ዋልተር ብራንድሙለር እንዳሉት "ቤተ ክርስቲያኗ ለራሷ ጥፋት እየሰራች ነው" በማለት ጠንከር ያለ ትችት አቅርበዋል። በአማዞን ካህናት ማግባት ከተፈቀደላቸው ሌሎችም አካባቢዎችስ የማይፈቀድበት ምክንያት ምንድን ነው? በማለት የቤተክርስቲያኗ ሥር ነቀል ለውጥ ሊሆን እንደሚችልም እየተነገረ ነው። ለአንዳንዶች ቤተክርስቲያኗ እያለፈችበት ያለውን ተቋማዊ ለውጥ የሚያሳይ ነው ያሉ ሲሆን በተለይም ዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ትተችባቸው የነበሩ ነገሮችን እያሻሻለች ነው ተብሏል። •ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትን እንደማትቀበል አሳወቀች ያገቡ ካህናትን እናይ ይሆን? አሁንም ያገቡ ካህናት አሉ። የአንግሊካን እምነት ተከታይ የሆኑና ወደ ካቶሊክነት የተቀየሩ ያገቡ ቄሶች በማዕረጋቸው ቀጥለዋል። እነዚህ ቄሶች በአንግሊካን እምነት ውስጥ ያለውን የሴትን ቅስና መፍቀድ ተከትሎ ነው ወደ ካቶሊክነት የተቀየሩት። በአማዞን ጋብቻው ከተፈቀደ በሌሎችም አካባቢዎች ተመሳሳይ ሁኔታ ሊፈፀም እንደሚችል የሚናገሩ ቢኖሩም አንዳንዶች ግን ከችግሩ አንፃር ነጥሎ መፍቀድ ይቻላል ብለው ይከራከራሉ።
news-48518756
https://www.bbc.com/amharic/news-48518756
ፍርድ ቤት፡ ኤል ቻፖ ከእስር ክፍሉ ለአካላዊ እንቅስቃሴ መውጣት ተከለከለ
''ኤል ቻፖ'' በሳምንት ለሁለት ሰዓታት ከእስር ክፍሉ ውጪ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ የኒውዮርክ ዳኛ ውድቅ አደረጉ።
ዳኛው ኤል ቻፖ ይህን ምክንያት ያመጣው ከእስር ለማምለጥ አስቦ ነው ሲሉ ተከራክረዋል። ዮአኪን ጉዝማን ወይም ኤል ቻፖ ተብሎ የሚጠራው ሜክሲኳዊው የዕፅ ነጋዴ ከአንድም ሁለቴ ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የሜክሲኮ እስር ቤቶች በተለያዩ ጥበቦች ከእስር ማምለጥ ችሏል። ከወራት በፊት በዕፅ ዝውውር ወንጀለኛ የተባለ ሲሆን ከ20 ቀናት በኋላ ፍርድ ይተላለፍበታል። • ኢትዮጵያዊቷ የዕፅ ነጋዴው ኤል ቻፖን ጉዳይ ለመዳኘት ተመረጠች • በችሎት አደባባይ የወጣው የኤል ቻፖ ገመና የ61 ዓመቱ ኤል ቻፖ በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ባለቤትነት እና በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርም ክሶች ቀርበውበታል። የፍርድ ውሳኔውን የሚጠባበቀው ኤል ቻፖ የተቀረውን እድሜውን በእስር ሊያሳልፍ እንደሚችል ተገምቷል። ሲቢኤስ ኒውስ እንደዘገበው ኤል ቻፖ የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈበት ቀን ምንም አይነት የስሜት መለዋወጥ አላሳየም ነበር። ዮአኪን ጉዝማን ኒው ዮርክ ማንሃተን በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ያለ ሲሆን፤ ጠበቃዎቹ ኤል ቻፖ የተያዘበት ሁኔታ ''ተፈጥሯዊ ያልሆነ እና ሰብዓዊነት የጎደለው ነው'' ሲሉ ገልጸውታል። ጠበቆቹ እንደሚሉት ቻፖ አካላዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ የሚፈቀድለት በሳምንት አንድ ቀን ብቻ የእስር ቤት ክፍል ውስጥ ነው። የቻፖ ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበችው ጽሁፍ ደንበኛዋ ንጹህ አየር እና የጸሃይ ብርሃን ካየ ሁለት ዓመታት እንደተቆጠሩ አስረድታለች። ጠበቃዋ እንደምትለው ከሆነ ዮአኪን ጉዝማን ወደ አሜሪካ ተላልፎ ከተሰጠ ወዲህ ወደ ፍርድ ቤት ሲሄድ ብቻ ካልሆነ በቀር የጸሃይ ብርሃን አይቶ አያውቅም። አቃቤ ሕግ ግን በእስር ቤቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የሚቻለው የእስር ቤቱ ጣሪያ ላይ ብቻ ነው ብሏል። ''ፍርደኛው (ኤል ቻፖ) ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ሁለት እስር ቤቶች ማምለጥ ችሏል። መብራት የተገጠመለት፣ ንጹህ አየር የሚነፍስበት እና 1.6 ኪ.ሜ የሚረዝም ዋሻ አስቆፍሮ ያመለጠ ፍርደኛ፤ ከእስር ቤቱ አናት ላይ በሄሊኮፍተር ወይም በሌላ መንገድ ማምለጥ ለእርሱ ተራ ነገር ነው።'' በማለት ባለስልጣናት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ደግፈዋል። ጉዝማን ለእናቱ ከፍተኛ ፍቅር እንዳለው ይነገራል። በተያያዘም፤ የዮአኪን ጉዝማን እናት የሆኑት የ91 ዓመቷ ማሪያ ኮንሱኤሎ በአሜሪካ እስር ላይ የሚገኘውን ልጃቸውን ለመጎብኘት ከአሜሪካ መንግሥት ፍቃድ ማግኘታቸውን አስታቀዋል። ጉዝማን ለእናቱ ከፍተኛ ፍቅር እንዳለው ይነገራል። ኤል ቻፖ ጉዝማን ማነው? "ኤል ቻፖ'' ማለት ''አጭሩ'' እንደማለት ሲሆን በሰሜናዊ ሜክሲኮ ሲናሎአ የተሰኘ የዕፅ አዘዋዋሪ ቡድን መሪ ነበረ። ኤል ቻፖ የሚመራው ቡድን ወደ አሜሪካ ለሚላከው ዕፅ ትልቁን ድርሻ ይዞ ነበር። እ.አ.አ. 2009 ፎርብስ ኤል ቻፖ ጉዝማን የተጣራ 1ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገበ ከበርቴ ነው በማለት የዓለማችን 701ኛው ሃብታም ሲል የከበርቴዎች ዝርዝር ውስጥ አካቶታል። ጉዝማን ለቀድሞው የሜክሲኮ ርዕሰ ብሔር ኤንሪክ ፔና ኒቶ በ2012 ስልጣን ከያዙ በኋላ እርሱ ላይ የሚደረገው ክትትል እንዲቆም በመጠየቅ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር ጉቦ መክፈሉም የተሰማው ችሎት ላይ ነበር። ርዕሰ ብሔሩ ግን ይህ ውንጀላ እውነትነት የለውም ሲሉ አስተባብለዋል። ገድሎ ያቃጠላቸው የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴ ተፎካካሪዎች እንዳሉ ከዘመዶቹ መካከልም የገደላቸው እንዳሉ ተገምቷል። ችሎቱ ኤል ቻፖ በ2015 በሜክሲኮ እጅግ ጥብቅ ከሆነው እስር ቤት እንዴት እንዳመለጠም በዝርዝር አድምጧል። ልጁ በእስር ቤቱ አቅራቢያ የሚገኝ ቤት እንደተከራየና ጂፒኤስ ያለው ሰዓት ወደ እስር ቤቱ በድብቅ ማስገባቱ ተመስክሯል። በሚስቱ እና በቅምጦቹ ላይ ለመሰለል በስልኩ ላይ ሶፍትዌር ይጠቀም እንደነበርም ተመስክሮ፤ ኤፍ ቢ አይ የተለዋወጣቸውን የፅሑፍ መልዕክቶች እንዲያቀርብ ተደርጓል። በአንድ የፅሁፍ መልዕክቱ ላይም ከነበረበት ቤት አሜሪካዊያንና ሜክሲኳዊያን ከከፈቱበት ድንገተኛ ዘመቻ እንዴት እንዳመለጠ የሚገልጽና ልብስ፣ ጫማ እንዲሁም ጥቁር ሸሚዝ እንዲመጣለት የጠየቀበት መልዕክቱም ተነቧል። ጉዝማን በአሜሪካ የፍትህ አደባባይ ለፍርድ ከቀረቡ የሜክሲኮ የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴዎች መካከል ትልቁ ነው።
news-53666384
https://www.bbc.com/amharic/news-53666384
ጋዜጠኛ፡ ኬንያዊውንና የኦኤምኤን ጋዜጠኛን ጨምሮ 9 ሰዎች በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ
ኬንያዊው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ፣ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች በዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ወሰነ።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በጪብሳ አብዱልከሪም መዝገብ ውስጥ የተከሰሱ ሰዎች የዋስ መብታቸው ተከብሮ እንዲፈቱ በዛሬው ዕለት ትዕዛዝ አስተላልፏል። ተጠቀሰው መዝገብ ውስጥ አምስት ተከሳሾች የሚገኙ ሲሆን፣ እነዚህም የኦኤምኤን ጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ፣ ኬንያዊው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ፣ ሃሰን ጂማ እና ፈይሳ ባሳ ናቸው። ግለሰቦቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን በኃይል ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስና እንዲጉላላ በማድረግ እንዲሁም በተለያዩ ብሄሮችና ሃይማኖቶች መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መገደሉን ተከትሎ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች፣ ጋዜጠኞችና ነዋሪዎችን ጨምሮ ከ7ሺህ በላይ ሰዎች በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። ለቢቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡት የተከሳሾች ጠበቃ አቶ ከዲር ቡሎ፤ ደንበኞቻቸው ፈጽመውታል የተባለው ወንጀል በማስረጃ መቅረብ ባለመቻሉ በ3ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም በአቶ ጆምባ ሁሴን የክስ መዝገብ ላይ ኢብራሂም አብዱልጀሊል፣ ኪያር፣ መሐመድ፣ ኦብሳ እና አለማየሁ የሚባሉ ግለሰቦችም በ4ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ ማዘዙን ጠበቃው አቶ ከድር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፍርድ ቤት ተጠርጣሪዎቹን "የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ፣ ከእስር ይውጡ ብሎ እስካዘዘ ድረስ ፖሊስ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ሊለቃቸው ይገባል" ብለዋል አቶ ከድር። "የቤተሰብ አባላት ለዋስትና የተጠየቀውን ብሩን ለመክፈል እየተሯሯጡ ይገኛሉ። ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን አክብሮ ሊለቃቸው ይገባል" በማለትም በተጨማሪ ለቢቢሲ አስረድተዋል።
48933115
https://www.bbc.com/amharic/48933115
ኒኪ ሚናጅ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ አልዘፍንም አለች
ራፐሯ ኒኪ ሚናጅ በሚቀጥለው ሳምንት ቀጠሮ ተይዞለት የነበረውን የሳዑዲ አረቢያ የሙዚቃ ድግስ ዝግጅቷ መሰረዟ ተገለጸ። ለመሰረዟ ምክንያት ያደረገችው ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ የሴቶችንና የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን መብት አይከበርም በማለት ነው።
ኒኪ ሚናጅ በጅዳ የሙዚቃ ስራዎቿን እንደምታቀርብ ይፋ ከተደረገ ጀምሮ የተለያዩ የመብት ተሟጋቾች የሀገሪቱን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በማንሳት ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ነበር። ሌሎች ደግሞ የኒኪ ሚናጅን ግልጥልጥ ያለ አለባበስ እያነሱና የዘፈኖቿን ግጥሞች እየጠቀሱ በዚህ ወግ አጥባቂ ማህበረሰብ ውስጥ ይህ እንዴት ይሆናል ሲሉ ይሞግቱ ነበር። ሳዑዲ አረቢያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመዝናኛው ላይ ጥላ የነበረውን ገደብ ላላ በማድረግ ኪነጥበቡ እንዲያድግ እያበረታታች ትገኛለች። • ኻሾግጂ የዓመቱ ምርጥ ሰው ዝርዝር ውስጥ ተካተተ • «ኻሾግጂ አደገኛ ሰው ነበር» የሳዑዲው ልዑል • የሳኡዲው አልጋ ወራሽ የ20 ቢሊየን ዶላር የንግድ ስጦታ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የሳዑዲ ዜጋ የነበረው ጋዜጠኛ ኻሾግጂ ኢስታንቡል ውስጥ በሚገኘው የሳኡዲ ቆንፅላ ውስጥ ከተገደለ ወዲህ በሃገሪቱ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ በርካቶች አቃቂር ማውጣታቸውን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል። መጋቢት ወር ላይ ሳዑዲ 10 የሴቶች መብት ተሟጋች ሴቶችን ፍርድ ቤት መገተሯ ደግሞ የመንግሥት ተቺዎችን "ድሮም" አስብሏል። ኒኪ ሚናጅ "ግራ ቀኙን በሚገባ ከተመለከትኩ በኋላ ጅዳ ወርልድ ፌስት ላይ ይዤው የነበረውን ፕሮግራም ሰርዤዋለሁ" ብላለች በመግለጫዋ። "በሳዑዲ ለሚገኙ አድናቂዎቼ ስራዎቼን ማቅረብ ቢያስደስተኝም፣ በጉዳዩ ላይ ራሴን በሚገባ እውቀት እንዲኖረኝ ካደረግሁ በኋላ በሴቶች፣ በተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን መብትና የመናገር ነፃነት ላይ ድጋፌን ማሳየት እንዳለብኝ ወስኛለሁ" ብላለች። አርብ እለት መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ለሚናጅ በጅዳ የሚኖራትን የሙዚቃ ትርኢት እንድትሰርዝ ግልፅ ደብዳቤ ፅፎ ነበር። በደብዳቤው ላይ "የመንግሥትን ገንዘብ እምቢ" እንድትልና በእስር ቤት የሚገኙ የሴቶች መብት ተሟጋቾች ጎን ለመቆም ተፅእኖ ፈጣሪነቷን እንድትጠቀም ጥሪ አቅርቦ ነበር። ባለፈው ሳምንት የድምፃዊት ኒኪ ሚናጅ የጅዳ የሙዚቃ ድግስ እንደተሰማ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ በዓላት ላይ መገኘቷን በመጥቀስና የሳዑዲ መንግሥት በተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ላይ ያለውን አቋም በመጥቀስ አብጠልጥለዋታል። በሳዑዲ አረቢያ የሙዚቃ ድግስ ቀጠሮ ከተያዘለት በኋላ አልፈልግም ያለችው ኒኪ ሚናጅ ብቻ አይደለችም። ማሪያ ኬሪ እንዲሁም ራፐር ኔሊ እንዲሁ ስራዎቻቸውን ሳያቀርቡ ቀርተዋል። ለሁሉም ምክንያቱ ደግሞ ሀገሪቱ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የሚነሳባት ትችት ነው።
news-53317633
https://www.bbc.com/amharic/news-53317633
ጭምብል አለማድረግ "የማኅበረሰብ ጠንቅ" መሆን ነው ተባለ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሁሉም ሰው ከቤቱ ሲወጣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድግ እንዳለበት የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት መከሩ።
የሮያል ሶሳይቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሰር ቬንኪ ራማክሪሽናን (ፕሮፌሰር) ጭንብል ማድረግ የሚያደርገውን ሰውና በዙሪያው ያሉትን ሰዎች ከበሽታው እንደሚከላከል ማስረጃዎች አሉ ብለዋል። የጭንብል አጠቃቀምን በተመለከተ በመንግሥት የሳይንስ አማካሪዎች ዘንድ የተቀላቀሉ አስተያየቶች በተለያዩ ጊዜያት ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። አንዳንዶች በአንዳንድ የእስያ አገራት ውስጥ የጉንፋን መስፋፋትን ለመከላከል ጥቅም ላይ ቢውሉም ብዙም ያሳዩት ለውጥ የለም። ስለዚህም ጭምብል በመጠቀም ተገቢ ያልሆነ የደኅንነት ስሜት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። ነገር ግን ሁሉንም የሚያስማማው እውነታ ጭንብሎች ቫይረሱ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው የመታላለፍ እድሉን እንዲቀንስ ሊያደርገው ይችላል። ፕሮፌሰር ራማክሪሽናን የሮያል ሶሳይቲ በጭምብል ላይ ባቀረባቸው ሁለት ሪፖርቶች ዙሪያ እንደተናገሩት "የተላለፉት መልዕክቶች ግልጽና ወጥ ስላልነበሩ" ሕብረተሰቡ ውስጥ "ጥርጣሬ" ተፈጥሯል። በሚያዝያ ወር ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ጭምብል ያደርጉ የነበሩ ሰዎች 25 በመቶ ያህል ሲሆኑ በተመሳሳይ ወቅት ጣሊያን ውስጥ 83.4 በመቶ፣ በአሜሪካ 65.8 በመቶ እና በስፔን ደግሞ 63.8 በመቶ ሰዎች ጭምብል ይጠቀሙ ነበር። ከቤት ውጪ የአፍን የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አለመጠቀም ጠጥቶ እንደማሽከርከርና የመቀመጫ ቀበቶን እንዳለመጠቀም ሁሉ "ለኅብረተሰብ ጠንቅ" ድርጊት ተደርጎ መወሰድ አለበት ብለዋል ፕሮፌሰሩ። "ጭምብል አለማድረግ በእድሜ የገፉ ወላጆችንና የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ሁሉንም ሰው ለበሽታው ያጋልጣል" ብለዋል። የጭንብሎችን ሌሎች መሸፈኛዎች በሽታውን በመከላከል በኩል ስላላቸው ውጤታማነት በተመለከተ ፍተሻ ያደረገ ጽሁፍ ያቀረቡት የፔንሲልቫኒያ ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር ፖል ኤደል ስታይን፤ ሌሎችን በበሽታው ከማስያዝ እንደሚከላከል "እንደሁል ጊዜው ግልጽ " መሆኑን ጠቅሰው በተጨማሪም ተጠቃሚውንም ከበሽታው እንደሚከላከል " አንዳንድ መረጃዎች" አሉ ብለዋል። የበሽታው ምልክት የማይታይባቸው በርካታ ሰዎች የዕለት ከዕለት ሥራቸውን ለማከናወን በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ሳያውቁ ቫይረሱን የያዙ ጥቃቅን ፋሳሾችን ከትንፋሻቸው ጋር ስለሚያስወጡ በዙሪያቸው የሚገኙ ሰዎችን ለበሽታው ሊያጋልጡ ይችላሉ ይላሉ ፕሮፌሰር ፖል። "እነዚህ ሰዎች አፍና አፍንጫቸውን ከሸፈኑ ጥቃቅኖቹ ጠብታዎች ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳይሸጋገሩ ማድረግ ይችላሉ። ለዚህም ጭምብል ማድረግ ወረርሽኙን እንዳይተላለፍ በማድረግ የሰዎችን ህይወት መታደግ ይቻላል" ብለዋል።
news-48907446
https://www.bbc.com/amharic/news-48907446
ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አሥመራ ካቀኑ እነሆ አንድ ዓመት፤ ምን ተለወጠ?
ኢትዮጵያና ኤርትራ ደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነት ካደረጉ በኋላ ጉዳያቸውን ለግልግል ዳኝነት አቅርበው ውሳኔ ከተሰጠም በኋላ ፍጥጫቸው ለሁለት አስርት ዓመታት ዘልቆ ያለምንም ግንኙነት ቆይተው ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአሥመራ ኢትዮጵያን ለሦስት አስርት ዓመታት ሲያስተዳደር የቆየው ኢሕአዴግ ለዓመታት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ሲካሄድ የቆየውን ተቃውሞ ተከትሎ ባካሄደው የመሪ ለውጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ከወሰዷቸው ቀዳሚ እርምጃዎች መካከል ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት ማሻሻል ዋነኛው ነው። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከዛሬ ነገ ጦርነት ይቀሰቀሳል ተብሎ ሲሰጋበት የነበረውን ፍጥጫ በማርገብ በዓለም ዙሪያ አድናቆትን ያስገኘላቸውን ጉዞ ወደ አሥመራ ልክ የዛሬ ዓመት አደረጉ። • ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአዲስ አበባና ሃዋሳ ጉብኝት ያደርጋሉ • ሻምፓኝ እና ፅጌረዳ ያጀበው የአዲስ አበባ-አሥመራ በረራ • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ የመንግሥታቸውን ባለስልጣናት አስከትለው ባዳረጉት በዚህ ጉዞ ከሃያ ዓመታት በኋላ ኤርትራን ለመጎብኘት በመጓዝ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ መሪ ሆኑ። ይህ ጉዞ የተደረገው የዛሬ ዓመት ልክ በዛሬዋ ዕለት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጉዟቸው ተበላሽቶ የቀየውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የሚያሻሽሉ ስምምነቶችን ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መፈራረማቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ በኩል በተነሱ ጥያቄዎች ምክንያት ተግባራዊ ሳይሆን እንደቆየ ይነገር የነበረውን የአልጀርሱን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኗን ተከትሎ የተደረገው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሥመራ ጉዞ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነትን ለማሻሻል ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ይታመናል። ተከትሎም ከጦርነቱ መቀስቀስ ጀምሮ ተዘግቶ የቆየው የሁለቱ ሃገራት ድንበር ተከፍቶ ከሁለቱም ወገን እንቅስቃሴ ሲጀመር ለዓመታት ተለያይተው የቆዩ ቤተሰቦች እንዲገናኙ እንዲሁም የድንብር ላይ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። በብዙ መልኩ ከአካባቢያዊና አህጉራዊ ተቋማት ተገልላና እራሷን አግልላ የቆየችው ኤርትራ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ጉብኝት ተከትሎ ከሌሎች የአካባቢው ሃገራትና ተቋማት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ጥረት ማድረግ ጀምራለች። ኢትዮጵያም ባደረገችው ድጋፍ በኤርትራ ላይ ተጥለው የቆዩ ማዕቀቦች የተነሱ ሲሆን ከሌሎች ሃገራት ጋር ያላትም ግንኙነትን ለማሻሻል በር ከፍቷል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር በኤርትራ ያደረጉትን ጉብኝትና በሁለቱ መሪዎች መካከል የተፈረሙ ስምምነቶች ዝርዝር ይዘት ሳይታወቅ በተከፈቱት የድንበር መተላለፊያዎች በኩል የሚደረገው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በጣም ከፍተኛ እንደነበረ ተነግሯል። • በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል • ኤርትራ በምሽት ድንበር ማቋረጥን ከለከለች • ካለፈቃድ በዛላምበሳ ድንበር በኩል ማለፍ ተከለከለ ለዓመታት ተለያይተው የቆዩ ቤተሰቦች ለመገናኘት ጊዜ ሳያጠፉ ነበር ድንበር ማቋረጥ የጀመሩት። በተጨማሪም ነጋዴዎች በሁለቱም ወገን የሚፈለጉ የተለያዩ ምርቶችና የሸቀጦችን በማዘዋወር በድንበር አካባቢ ያለው የንግድ ልውውጥ እንዲጧጧፍ ምክንያት ሆነ። ከዚህ ባሻገርም ለኤርትራዊያን ወጣቶች ሽሽት ምክንያት የሆነውን የብሔራዊ አገልግሎት ለማምለጥ ይጠባበቁ የነበሩ በርካታ ወጣቶችም ነጻ በተለቀቁት የድንበር መተላለፊያዎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ መሻገራቸው ይነገራል። ይህ ነጻ የድንበር ላይ ዝውውር ግን ለወራት ነበር የቆየው። አንድ በአንድ ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚያገናኙት የድንበር መተላለፊያዎች የተዘጉ ሲሆን ለዚህም ከሁለቱ መንግሥታት ይፋዊ ምክንያት ባይሰጥም፤ ሃገራቱ የቪዛና የቀረጥ ጉዳዮችን መልክ ለማስያዝ የወሰዱት እርምጃ እንደሆነ ይነገራል። አንድ ዓመት ስለሞላው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የአሥመራ ጉዞና የሁለቱ ሃገራትን ግንኙነት ለማሻሻል ስለተወሰዱ እርምጃዎች ቢቢሲ ኒውስ ዴይ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጉዳይን በቅርበት የሚከታተሉትን የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትን ዶክተር ዮሐንስ ወልደማሪያምን አናግሯቸዋል። የሁለቱ ሃገራት የድንበር መተላለፊያዎች መዘጋታቸውን የሚያረጋግጡት ዶ/ር ዮሐንስ፤ አሁንም ድረስ ነገሮች አልጠሩም ይላሉ። ስምምነቱን ተከትሎ ድንበሮች በተከፈቱበት ወቅት "ሰዎች እንዳሻቸው መንቀሳስ መጀመራቸው ኢሳያስን ሳያስጨንቃቸው አልቀረም የድንበር በሮቹ የተዘጉት ከኤርትራ በኩል ነው" የሚል እምነት እንዳለቸው ዶ/ር ዮሐንስ ይናገራሉ። በሁለቱ ሃገራት መካከል ሰላም ሲወርድ ኤርትራ ህዝብ ቀዳሚው ነገር የድንበር ማካለል ሥራ ነው የሚሉት ዶ/ር ዮሐንስ፤ አሁንም ድረስ ድንበር የማካለሉ ሥራ አልተሰራም ለዚህም ምክንያቱ "ፕሬዝድንቱ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ አለመሆኑ ነው'' ይላሉ። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በደረሰችው ስምምነት ከሕዝቡ ይልቅ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ተጠቃሚ መሆናቸውን ይናገራሉ። "ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ ተነስቷል፣ ዓለም አቀፍ መገለሉ ቀርቷል። ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ቢሆን ከኤርትራ ጋር የተደረሰው ስምምነት ዓለም አቀፍ እውቅናን አስገኝቶላቸዋል" ይላሉ። ዶክተር ዮሐንስ እንደሚሉት ከሆነ "የኤርትራ መንግሥት ለህዝቡ ምን እየተከናወነ እንደሆነ የገለጸው ነገር የለም። ኤርትራዊያ ስለሁለቱ ሃገራት ስምምነት መረጃ የሚያገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃንን እየሰሙ ነው። የኤርትራ መንግሥት ምንም ያለው ነገር የለም" ይላሉ።
51830169
https://www.bbc.com/amharic/51830169
የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ ተያዙ
የዩኬ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር፣ ናዲን ዶሪስ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተሰማ።
ሚኒስትሯ በዩኬ በቫይረሱ የተያዙ የመጀመሪያዋ የሕዝብ እንደራሴ ሲሆኑ ቫይረሱ ከተገኘባቸው በኋላ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ አንደወሰዱና ራሳቸውንም ከሌሎች አግልለው መቀመጣቸውን ተናግረዋል። በዩኬ እስካሁን ድረስ በቫይረሱ ተይዘው የነበሩ ስድስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን 382 ደግሞ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተሰምቷል። • በኮሮናቫይረስ ተያዙ ከተባሉት ኢትዮጵያዊያን አንዱ ነጻ ሆነ • የኮሮናቫይረስ በአዲስ አበባ ሆቴሎች ላይ ያጠላው ስጋት • ከኮሮናቫይረስ ጋር የሚደረገውን ፍልሚያ የሚመሩት ሰው በቅርቡ በቫይረሱ ከተያዙና ከሞቱ ግለሰቦች መካከል የ80 ዓመት አዛውንት የሚገኙበት ሲሆን ግለሰቡ ሌሎች የጤና ችግሮች ነበሩባቸው ተብሏል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ፣ ናዲን ዶሪስ ያገኟቸው ሰዎች በአጠቃላይ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ ታውቋል። ሚኒስትሯ የቫይረሱን ምልክት ማሳየት የጀመሩት ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት እንደነበር የተነገረ ሲሆን በዚያው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ባዘጋጁት ስነስርዓት ላይ ተሳትፈው ነበር። ከአርብ ዕለት ጀምሮም ግን ራሳቸውን ከሰው አግልለው መቀመጣቸው ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ያድርጉ አያድርጉ የታወቀ ነገር የለም። ከሚኒስትሯ ጋር ግንኙነት የነበራቸው የጤና ሚኒስትር መስሪያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በአጠቃላይ ምርመራ እንደተደረገላቸው እንዳለ ተነግሯል።
49108189
https://www.bbc.com/amharic/49108189
የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት ቤጂ ኬይድ ኢሴብሲ፣ በ92 ዓመታቸው አረፉ
በነጻ ምርጫ የተመረጡት የመጀመሪያው የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት ቤጂ ኬይድ ኢሴብሲ በ92 ዓመታቸው ማረፋቸውን የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ኢሴብሲ የዓለማችን በእድሜ የገፉ በስልጣን ያሉ ፕሬዝዳንት ነበሩ። በምን ምክንያት እንደገቡ ባለስልጣናት ባይናገሩም ረቡዕ እለት ነበር ሆስፒታል የገቡት። በመካከለኛው ምሥራቅና በሰሜን አፍሪካ ሃገራት ውስጥ ተቀስቅሶ የነበረውን የአረብ አብዮትን ተከትሎ ቱኒዚያ ውስጥ እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 በተደረገው ነጻ ምርጫ ነበር ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት። • ደኢሕዴን የሐዋሳና የሲዳማ ዞን አመራሮችን አገደ • ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ማምረት ላቆም እችላለሁ ሲል አስጠነቀቀ • በባንግላዲሽ በሐሰተኛ ወሬ ሳቢያ ስምንት ሰው ተገደለ የዓለማችን ጎምቱ ፕሬዝዳንት ቱኒዚያዊው ቤጂ ኬይድ ኢሴብሲ ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ባጋጠማቸው ከባድ የጤና ቀውስ ምክንያት ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቶ ነበር። ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ በመጪው ሕዳር ወር በሚካሄደው ፕዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ዳግመኛ ለመመረጥ እንደማይወዳደሩ አስታወቀው ነበር። ቤጂ ኬይድ ኢሴብሲ ወደ ስልጣን የመጡት ኒዳ ቱውንስ (የቱኒዚያ ጥሪ) የተሰኘ እስላማዊ መንግሥትን የሚቃወም ፓርቲ መስርተው ነበር።
53696684
https://www.bbc.com/amharic/53696684
ሕንድ፡ 190 ሰዎች አሳፍሮ በማረፍ ላይ የነበረ አውሮፕላን ተከሰከሰ
ንብረትነቱ የኤር ኢንዲያ ኤክስፕረስ የሆነው የበረራ ቁጥሩ IX-1344 የነበረው አውሮፕላን በሕንድ ደቡባዊ ግዛት ኬራላ በሚገኝ አየር ማረፊያ 190 ሰዎችን አሳፍሮ ለማረፍ ሲንደረደር መከስከሱን ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ከዱባይ የተነሳው አውሮፕላኑ በካሊከት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ በመንደርደር ላይ ሳለ ተንሸራቶ ለሁለት መከፈሉን የሕንድ አቪየሽን ባለሥልጣን ገልጿል። በስፍራው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተው ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ። በአደጋው እስካሁን በትንሹ አብራሪውን ጨምሮ ሁለት ሰዎች መሞታቸውንና በርካታ መንገደኞች መጎዳታቸውን የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አውሮፕላኑ 10 ህፃናትን ጨምሮ 184 መንገደኞችን እንዲሁም ሁለት አብራሪዎችን ጨምሮ ስድስት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ነበር። የሲቪል አቪየሽን ዳይሬክቶሬት ጀነራል አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ሰዓት ተንደርድሮ መቆሚያ መስመሩን ጨርሶ ሸለቆ ውስጥ በመውደቁ ለሁለት መከፈሉን ተናግረዋል። የሕንድ መገናኛ ብዙኃን ያወጡት አደጋውን የሚያሳየው ምስልም አውሮፕላኑ ለሁለት መሰበሩን አሳይቷል። አደጋው ያጋጠመው ከቀኑ 8፡30 አካባቢ ሲሆን በአካባቢው ከባድ ዝናብ እየዘነበ ነበር ተብሏል። ሕንድ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት እያስከተለ መሆኑን ተናግራለች። በሕንድ መሰል አደጋ ሲያጋጥምም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከ10 ዓመታት በፊት ግንቦት ወር ላይ ኤር ኢንዲያ ኤክስፕረስ አውሮፕላን በማንጋሎር አየር ማረፊያ ተንሸራቶ ባጋጠመው አደጋ የ158 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።
news-52335991
https://www.bbc.com/amharic/news-52335991
ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካ ግዛቶች 'ጥብቅ' እርምጃ ወስደዋል ያሉት ትራምፕ የሕዝቡን ተቃውሞ ደግፈዋል
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአገሪቱ የተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችን የሚደግፍ ትዊት ጽፈዋል።
እንደ ሚኒሶታ፣ ሚቺጋን እና ቨርጂኒያ ያሉ ግዛቶች እየወሰዱ ያሉት እርምጃ 'በጣም ጥብቅ' በመሆኑ በትዊተር ገፃቸው ላይ ተቃውሞውን መደገፋቸውንም ተናግረዋል። 'ሚኒሶታ ነፃ ትውጣ'፣ 'ሚቺጋን ነፃ ትውጣ'፣ 'ቨርጂኒያ ነፃ ትውጣ' ሲሉም ትዊት አድርገዋል። የጤና ባለሙያዎች ዜጎች ከቤታች አለመውጣታቸው የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ይረዳል ይላሉ። ተቃዋሚ ሰልፈኞች በበኩላቸው፤ እንቅስቃሴ መግታት አላስፈላጊ ነው፤ ምጣኔ ሃብታዊ ጫናም እያስከተለ ነው ብለዋል። አሜሪካ ውስጥ ባለፈው ሐሙስ በ24 ሰዓት ውስጥ 4,591 ሰዎች ሞተዋል። ይህም እስካሁን በአንድ ቀን ከሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛው ነው። ቁጥሩ ከፍ ያለው ምናልባትም ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ፤ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የጤና እክል የሞቱ ሰዎችን መመዝግብ ስለጀመረም ሊሆን ይችላል። አሜሪካ ከመላው ዓለም በበለጠ በቫይረሱ ሰዎች የሞቱባት አገር ናት። በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ አሀዝ መሰረት እስካሁን ከ700 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል፤ 36 ሺህ ደግሞ ሞተዋል። ባለሥልጣናት እንቅስቃሴ ላይ የተጣለውን እገዳ እንዲያነሱ የሚጠይቁ ሰልፎች በሚቺጋን፣ ኦሀዮ፣ ኖርክ ካሮሊና፣ ሚኒሶታ፣ ዩታ፣ ቨርጂኒያ እና ኬንተኪ ተካሂደዋል። ትራምፕ ትላንት 'ነፃ ይውጡ' ብለው በትዊተር ገፃቸው የጠቀሷቸው ግዛቶች ዴሞክራት አገረ ገዢ ያላቸው ናቸው። ሪፐብሊካን አገረ ገዢ ስላላቸው ኦሀዮ እና ዩታ ግን ፕሬዘዳንቱ ያሉት ነገር የለም። በቨርጂኒያው ሰልፍ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገኙ ሲሆን፤ በሚቺጋን ደግሞ በሺህዎች የሚቆጠሩ አደባባይ ወጥተዋል። በቀጣይ የተቃውሞ ሰልፎች በዊስኮንሰን፣ ኦሬገን፣ ሜሪላንድ፣ አይዳሆ እና ቴክሳስ ይካሄዳሉ ተብሏል። ትራምፕ ለተቃዋሚዎቹ እንደሚያዝኑ ተናግረው፤ "እኔን የሚወዱኝ ሰዎች ይመስላሉ፤ ሀሳቤ ከሌሎቹ አገረ ገዢዎች ጋር ተመሳሳይ ነው" ብለዋል። 'ሚኒሶታ ነፃ ትውጣ' ሲሉ ተቃውሞ ያስተባበሩት፤ "የሚኒሶታ ዜጎችን እንቅስቃሴ አገረ ገዢው ሊገድቡ አይችሉም!" ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው ጽፈዋል። ገፁ 600 አባላት ያሉት ነው። የሚቺጋን አገረ ገዢ የእንቅስቃሴ ገደቡን ማራዘማቸውን ተከትሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች መንገድ ዘግተው ወደ ሥራ እንመለስ ሲሉ ነበር። በሌላ በኩል የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ሪፐብሊካን አገረ ገዢዎችን ጨምሮ ማኅበራዊ ርቀት እንዲጠበቅ ያሳሰቡ ባለሥልጣኖች አሉ። ባለፈው አርብ የቴክሳስ አገረ ገዢ 'ጥንቃቄ በተሞላው ሁኔታ ወደ ሥራ መመለስ' የሚል ሀሳብን የሚያራምድ ግብረ ኃይል መስርተዋል። አገረ ገዢው ከሳምንት በኋላ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ይፈልጋሉ። የህክምና ባለሙያዎችና የግሉ ዘርፍ ቀጣሪዎች ሀሳቡን ይገመግማሉም ተብሏል። የፍሎሪዳ ከንቲባ፤ የባህር ዳርቻ መዝናኛዎች ከቀጣይ አርብ ጀምሮ በሰዓት ገደብ አገልግሎት ይጀምራሉ ብለዋል።
news-51499610
https://www.bbc.com/amharic/news-51499610
እስካሁን ስለፕላኔቶች አፈጣጠር የምናውቀውን ይቀይራል የተባለው አዲስ ግኝት
የፀሐይ ሥርዓትና በዙሪያዋ ያሉ ፕላኔቶች እንዴት እንደተፈጠሩ የሚተነትነውና ከዚህ በፊት የነበረውን ንድፈ ሐሳብ "በማያወላዳ ሁኔታ" የሚቀይር ግኝት ላይ መድረሳቸውን ተመራማሪዎች ተናገሩ።
እስካሁን በፀሐይና በፀሐይ ዙሪያ ያለው ዓለም እንዲፈጠር ምክንያት ነው ተብሎ የተያዘው አመለካከት የግዙፍ ቁስ አካላት በከፍተኛ ሁኔታ ተመላትም ውጤት እንደሆነ ነው። አሁን አዲስ ተደረሰበት የተባለው ውጤት ግን ከዚህ የተለየና ቀላል ነው እንደሆነ ነው። እንዲያውም ከከባቱ ግጭት ይልቅ ቁስ አካላት ዝግ ባለ ሁኔታ በመጠጋጋት የተገኘ ውጤት ነው ይላሉ። ይህ አዲስ ግኝት አሜሪካ ሲያትል ውስጥ በተካሄደው የሳይንስ ባለሙያዎች ማህበር ጉባኤ ላይ የቀረበውና በሳይንሳዊ መጽሔት ላይ ታትሟል። ጥናቱን የመሩት ዶክትር አለን ስተርን ስለግኝቱ እንደተናገሩት "አጅግ የሚያስደንቅ ነበር" ብለዋል። "ከ1960ዎቹ ማብቂያ ጀምሮ በስፋት ተቀባይነት ያገኘው ከባድ ግጭት አሁን ደግሞ በዝግታ የተፈጠረ መሰባሰብ ለፕላኔቶች መፈጠር እንደምክንያት ቀርቧል። ይህም በፕላኔቶች ሳይንስ ውስጥ የሚታይ ነገር አይደለም፤ ታዲያ አሁን ለጉዳዩ መቋጫ አግኝተንለታል" ሲሉ ዶክትር አለን ለቢቢሰ ተናገረዋል። የፕላኔቶችን አፈጣጠር ለመረዳት ያገዘው ምሰል ይህ የአሁኑ ግኝት የተነሳው በፀሐይ ሥርዓት ውስጥ ያለን ቁስ አካል በጥልቀት ከማጥናት የተነሳ ነው። ይህ ቁስ አካል አሮኮት የሚል ስም የተሰጠው ሲሆን ከፀሐይ ስድስት ቢሊየን ኪሎሜትሮች እርቆ በሚገኘውና ኪዩፐር ቤልት ተብሎ በሚጠራው ክፍል ላይ ይገኛል። ይህም ፕላኔቶች በተፈጠሩበት ጊዜ የነበራቸው ይዘት ያለው ሲሆን ከስድስት ቢሊዮን ዓመታት በፊት ሁለት አካላት ወደ አንድ የመጡበትና የፀሐይ ሥርዓት የተፈጠረበት የተገኘ ነው። ከዓመት በፊት ናሳ "ኒው ሆራይዘን" የተባለችውን የህዋ መንኮራኩር ወደ አሮኮት ቀረብ ብላ በበረረችበት ጊዜ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ፎቶ ግራፎችን በማንሰቷ ለተመራማሪዎቹ ተጠቅመውበታል።ይህም ሳይንቲስቶቹ ላቀረቡት ቁስ አካላቱ ተላተሙ ወይስ በዝግታ ተቀራረቡ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስና የሁለቱን ተፎካካሪ ንደፈ ሐሳቦች ለመፈተን እድልን ፈጥሮላቸዋል። በዶክትር ስተርንና በጥናት ቡድናቸው በተሰራው ትንተና በዚህ ሂደት ውስጥ ከባድ ግጭት ስለመከሰቱ የሚያመለክት መረጃን ለማግኘት አልቻሉም። በግጭት ሳቢያ የሚከሰት መሰንጠቅም ሆነ የመደፍጠጥ ምልክት አላገኙም። ይህም ሁለቱ አካላት በዝግታ መያያዛቸውን አመላካች ነው። "ይህ ምንም የማያጠራጥር ነው" ይላሉ ዶክትር ስተርን። "በአሮኮት አቅራቢያ የተደረገው አሰሳ በአንድ ጊዜ በሁለቱ ንድፈ ሐሳቦች ዙሪያ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ አስችሏል።" ዶክትር ስተርን በተገኘው ውጤት እርግጠኛ ናቸው፤ ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቅሱት ኪዩፐር ቤልት የሚባለው አካል ከፀሐይ ሥርዓት መፈጠር አንስቶ እስካሁን ምንም ለውጥ ሳያሳይ ይህን ያህል ዘመን ባለበት መቆየቱ ነው። አዲሱ ንድፈ ሐሳብ ከ15 ዓማት በፊት ነበር የተጸነሰው ይህ አዲሱ በዝግታ የመያያዝ ንድፈ ሐሳብ ብቅ ያለው ከ15 ዓመት በፊት ስዊዲን ውስጥ በሚገኘው ሉንድ የምርምር ማዕከል ውስጥ በፕሮፌሰር አንድሬስ ዮሐንሰን ነበር። በወቅቱ ፐሮፌሰሩ ወጣት የዶክትሬት ተማሪ የነበሩ ሲሆን ሐሳቡም የፈለቀው በኮምፒውተር ላይ በተደረጉ ሙከራዎች ነው። ፕሮፌሰር ዮሐንሰን ከዓመታት በፊት የቀመሩት ንድፈ ሐሳብ በምርምር መረጋገጡ ሲነገራቸው ስሜታቸውን ለመግለጽ ቃላት አጥረዋቸው "በጣም ደስ ብሎኛል" ብቻ ነበር ያሉት ። አክለውም "የዶክትሬት ተማሪ ሆኜ እዚህ ውጤት ላይ ስደርስ በጣም ደንግጬ ነበር፤ ምክንያቱም ውጤቱ ቀደም ሲል ከተገኘው የተለየ ነበር። ምናልባትም ኮዶችን ስቀምር ወይም ስሌቶችን ስሰራ ስህተት ፈጽሜ ይሆን ብዬ ተጨንቄ ነበር።" "ታዲያ እነዚህ ውጤቶች በትክክለኛ ምልከታ ተረጋግጠው ስመለከት ትልቅ እፎይታን ነው የፈጠረልኝ" ብለዋል። ስለፕላኔቶች አፈጣጠር የምናውቀውን ይቀይራል የተባለው አዲስ ግኝት ፕሮፌሰር ዮሐንሰን ይህንን ውጤትም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በፒዛና በለስላሳ በኮካኮላ አስበውታል። በከዋክብት ዙሪያ የሚዘጋጀውን የቢቢሲን "ስካይ አት ናይት" ፕሮግራም ተባባሪ አቅራቢ የሆኑት ኢንጂነር ዶክተር ማጊ አድሪን-ፖኮክ እንደሚሉት ምንም እንኳን የተገኘው ውጤት "በብዙ መልኩ አሳማኝ ቢሆንም" በአንድ ቅኝት ብቻ ቀደም ሲል የነበረን ንድፈ ሐሳብ ውድቅ ማድረግ ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብለዋል። "ይህ ማስረጃ መገኘቱ ጥሩ ነገር ነው። ምንም እንኳን አንዳንድ ጥያቄዎች ቢቀርቡበትም የቁሶች መጋጨትን የሚጠቀመው ንድፈ ሐሳብ ድንቅ ነበረ። ከመለያየት ይልቅ ቁሶቹ ለምን ተያያዙ? የሚሉና ሌሎችም ምላሽ ያላገኙ ነገሮች አሉ" ብለዋል።
43665517
https://www.bbc.com/amharic/43665517
ልማትና የአርሶ አደሮች መፈናቀል በአዲስ አበባ
"መሬቱን ከኛ ሲወስዱ ጉዳዩን በጥልቀት አናውቅም ነበር። ተተኪ ስራ አልሰጡንም። የተሰጠችንም ገንዘብ ደግሞ እያለቀች ነው" በማለት አርሶ አደር ኃይሉ ከመሬቱ የተፈናቀለበትን አጋጣሚ ለቢቢሲ ያስረዳል።
ከስድስት ዓመት በፊት የአቶ ኃይሉ ደምሴ መሬት በአዲስ አበባ የመሬት አስተዳደር ልማትና ማኔጅመንት በልማት ስም ተወስዶባቸዋል። 22 ሺ ካሬሜትር ስፋት ያለው የእርሻና የመኖሪያ ቤት ቦታ ለአንድ ካሬ በ18 ብር ከ50 ሳንቲም ታስቦ ተከፍሎ እንደተወሰደባቸው አቶ ኃይሉ ይናገራሉ። የዚህ አርሶ አደር መሬት በከተማው የሚታዪት ትልልቅ የመሰረተ-ልማት ግንባታ ከዋሉት ፕሮጀክቶች መካከል በጋራ መኖሪያ ቤቶችና በረጃጅም ፎቆች ተሸፍኗል። በእንጨትና በጭቃ የተሰራችው የአቶ ኃይሉ ቤት ካሳ የተበላበት ቢሆንም አሁንም ከቤተሰቦቹ ጋር የክፉ ጊዜ መጠለያው ነች። ይህ መሬት የሚገኘው በከተማዋ አስተዳደር ስር ስለሆነ ቤቱንም ማሳደስ ሆነ ማስፋፋት አይችሉም። ይህ ታሪክ የአቶ ኃይሉ ብቻ ሳይሆን በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ አርሶ አደሮች በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸው ጉዳይ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ለልማት ተብሎ 12ሺ አባወራዎች ከቀያቸውና ማሳቸው ተፈናቅለዋል። የመፈናቀሉን አንድምታ በሁለት መልኩ ማየት የሚቻል ሲሆን አንዱ ለመንግሥት መሰረተ ልማት ማስፋፋት ሲሆን ለአርሶ አደሮች፣ ለሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችና በአገር ውስጥና በውጭ አገር ለሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች የባህልና ማንነታቸው ጋር መነቀል ነው። "መፈናቀልና ልማት" አዲስ አበባ ባሳለፈችበት የምዕተ-ዓመት ጉዞ በአካባቢው ይኖር በነበረው ኦሮሞ ማህበረሰብ መፈናቀልን አስከትሏል። ይህም የአዲስ አበባ ሰፈሮች የኦሮምኛ ቋንቋ መጠሪያ ስያሜ እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል። ከአዲስ አበባ መልሶ ልማትና ተኃድሶ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በያዝነው ዓመት በአዲስ አበባ 700 ሄክታር መሬት መልሶ ለማልማት እቅድ ተይዟል። ለዚህ የመሬት ልማት ስራ መሳካት ደግሞ ሁለት ሺ አባወራዎች እንደሚፈናቀሉ የኤጀንሲው ስራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ግርማ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ካሳ፣ቅሬታና ፍርኃት በቦሌ ተወልደው ያደጉት ሌላኛው አርሶ አደር ሲሳይ ነጋሳ ናቸው። የዛሬ 15 ዓመት ወደ አራት ሄክታር የሚጠጋ መሬት ከሳቸውና ካባታቸው ለልማት ተብሎ ተወስዶባቸዋል። ለመሬቱም ለአንድ ካሬ ሜትር በ3 ብር ከ50 ሳንቲም ተመን ካሳ ተከፍሏቸው ነበር። ይባስ ብሎም ከታሰባላቸውም ካሳ ግብር እንደከፈሉ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ከሳቸው የተወሰደ መሬት ላይ እስካሁን ካንድ አቋርጦ የሚያልፍ መንገድ ውጭ ምንም አይነት መሰረተ-ልማት አልተሰራበትም። አቶ ሲሳይ ነጋሳ ካሉበት የኢኮኖሚ ችግር በተጨማሪ አሁንም እፈናቀላለሁ የሚል ስጋት እንዳላቸው ለቢቢሲ ጨምረው ገልፀዋል። የተከፈላቸው ካሳ አናሳ መሆን፣ የመኖሪያ ቤት አለመሰጠት፣ የሚመጥናቸው የስራ አለመመቻቸት፣ ለአርሶ አደሮች የመኖሪያ ቤትና የስራ እድል አለመቻቸት እና አስፈላጊ የሆኑ የመሰረተ-ልማት አቅርቦት ለምሳሌ ውሃ ለአርሶ አደሮቹ አለመቅረቡ ከሚያነሷቸው ቅሬታዎች መካከል ናቸው። ካሳን ጨምሮ ሌሎች ቅሬታዎችን ተቀብሎ ሲያስተናግዱ እንደነበረ የኤጀንሲው ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ግርማ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ አስተዳደር በአርሶ አደሮች መፈናቀል የሚከሰቱ ችግሮችን ለማስቆም እየሰሩ እንዳለ ጨምረው ገልፀዋል። በዚህም መሰረት የአርሶ አደርን የአንድ ካሬ ሜትር ዋጋ ካሳ ወደ 62 ብር ያደገ ሲሆን የግል መኖሪያ ቤት ይዞታ ካሳ ደግሞ 552 ሺ ብር ማደጉን ተናግረዋል። በተጨማሪም ቤት መስሪያ ቦታ እንደሚሰጣቸው አክለው ገልፀዋል። በሌላ በኩል የከተማው አስተዳደር መሬትን ለተጠቃሚዎች በሁለት መልኩ የሚያስተላልፍ ሲሆን የልማት ድርጅቶች እንደ ፋብሪካዎች ላሉት በምደባ ለመኖሪያ ቤትና ለንግድ ቤቶች በሊዝ ይሰጣቸዋል። ለአርሶ አደሩ የሚከፈለው ካሳ ለሊዝ ከሚፈለው ካሳ ያንሳል ለሚለው ጥያቄ አቶ ሚሊዮን መልስ ሲሰጡ "ከአርሶ አደሩ የሚወሰደው መሬት ለመሰረተ-ልማት ግንባታ ለህዝቡ ጥቅም ስለሚውል በዛ መልኩ ይተላለፋል" አርሶ አደር ኃይሉ ደምሴ ድንበር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚዋሰኑበት የተከለለ ምልክት የላቸውም። ይህ ደግሞ አዲስ አበባ እየሰፋች የሚለውን ቅሬታና ተቃውሞ በማስነሳት ለብዙ ህይወቶች መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ የአዲስ አበባ ከተማ ስፋት 52ሺ ሄክታር እንደሆነ ይገመታል። ይህንን የድንበር ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከኦሮሚያ ክልልና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ባለሙያዎች ወሰኑን እየሰሩ ነው። ቢቢሲ እንዳገኘው መረጃ የወሰን ማካለል ስራ በአሁኑ ጊዜ ተጠናቆ የፖለቲካ ኃላፊዎችን ውሳኔ እየጠበቀ ነው። በዚህ የቴክኒክ ኮሚቴ ስራ አንዳንድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ ቦታዎች በኦሮሚያ ስር እንዲሁም በኦሮሚያ ስር ያሉት ደግሞ በአዲስ አበባ እንደተካለሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ለዚህ የማካለል ስራ መስፈርት እንደ ግብዓት ስራ ላይ ከዋሉት ውስጥ የ1987 የተካሄደው ምርጫ ነው። የልማት ዋጋ ምን ሊሆን ይገባዋል?
news-54977501
https://www.bbc.com/amharic/news-54977501
'በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተገኘ የተባለው ሐሰት ነው' - አ/አ ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአራዳ ክፍለ ከተማ በልመና በሚተዳደሩ አንዲት ግለሰብ ቤት ውስጥ ከ45 ሺህ በላይ ብር ማግኘቱን ሲያረጋግጥ፤ በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተገኘ የሚለውን ዘገባ ሐሰት ሲል አስተባብሏል።
በክፍል ከተማው በተለምዶ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በልመና የሚተዳደሩት ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው ገንዘቡ የተገኘው። ኮሚሽኑ ግለሰቧ ረዳትም ሆነ ልጅ በአጠገባቸው የሌላቸው የአእምሮ ህመም ያለባቸው ናቸው ያለ ሲሆን፤ ገንዘቡ የተገኘው በተለያዩ ፌስታሎች ነው ይላል ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገፁ ያሰፈረው ዜና። የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ስፍራው በማምራት ገንዘቡን እንዳገኘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል። "በቦታው ላይ በተደረገው የማረጋገጥ ሥራ በግለሰቧ መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የተቋጠሩ ፌስታሎች እና ሌሎች ቆሻሻ ዕቃዎች ተከማችተው የተቀመጡ ሲሆን ከተቋጠሩት ፌስታሎች መካከል ገንዘብ ያለባቸው" ይላል የኮሚሽኑ ገለፃ። በልብስ መዘፍዘፊያ ፕላስቲክ የተወሰነ ብር እንደተገኘ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከአካባቢው ነዋሪዎች ታዛቢዎችን በመጨመር ፖሊስ እና የወረዳው አስተዳደር ባደረጉት ቆጠራ የተገኘው ገንዘብ 45 ሺህ 858 ብር መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል። ፖሊስ ኮሚሽኑ ጨምሮ እንደገለጸው ከተገኘው ገንዘብ ውስጥ አንድ ሺህ ብር ግለሰቧ ለዕለት ወጪያቸው እንዲጠቀሙበት የተሰጣቸው ሲሆን፤ ቀሪው ብር ደግሞ በግለሰቧ ስም የባንክ የሂሳብ ተከፍቶ ገቢ ተደርጎላቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተከማችቶ ተገኘ በሚል በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች እየተላለፈ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታዉቋል። ማክሰኞ ረፋዱ ላይ አራዳ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ኢንፎኔት ኮሌጅ አካባቢ አንድ በርሜል ገንዘብ ወድቆ ተገኝቷል ሲሉ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር። የተገኘው ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር እና ዶላር እንደሆነና ገንዘቡን ማን እንደጣለው ያልተተረጋገጠ መሆኑን በመግለጽ የአካባቢው ፖሊስ በመኪና ጭኖ እንደወሰደውም ተዘግቦ ነበር። ኮሚሽኑ ግን ይህ ዘገባ የተሳሳተ ነው ሲል አስተባብሏል።
news-54063388
https://www.bbc.com/amharic/news-54063388
አስራት ሚዲያ ፡ ጋዜጠኞች በዋስትና እንዲፈቱ ቢወሰንም አለመለቀቃቸውን ጠበቃቸው ገለፁ
ዛሬ [ሰኞ] ጠዋት የአራዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀጠሯቸው መሰረት የቀረቡት የአሥራት ሚዲያ ጋዜጠኞች እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ ተላልፎ የነበረ ቢሆንም አለመለቀቃቸው ተነገረ።
የተጠጣሪዎቹ ጠበቃ የሆኑት አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አስፈላጊውን ነገር ሁሉ በሟሟላት በጥሬ ገንዘብ 40 ሺህ ብር ለአራቱም ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ ማስያዛቸው ገልፀዋል። ፍርድ ቤቱም የቀረበውን ዋስትና በመመልከት ፖሊስ እንዲፈታቸው የመፈቻ ትዕዛዝ መጻፉን ተናግረዋል። ጠበቃው እስረኞቹ ለሚገኙበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ትዕዛዙን ማድረሳቸውን ገልፀዋል። ነገር ግን ፖሊስ ተጠጣሪዎቹን "ይግባኝ ጠይቄባዋለሁ፣ የይግባኙ ሁኔታ የመጨረሻ እልባት እስኪያገኝ ድረስ አልፈታም" በማለት አለመልቀቁን ተናግረዋል። ይግባኙን በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት መከፈቱን ጠበቃው ጨምረው አስታውቀዋል። ዛሬ [ሰኞ] የአራዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለአምስተኛ ጊዜ የቀረቡት የአስራት ሚዲያ ጋዜጠኞችን በተመለከተ ፖሊስ "የምሰራው ሥራ አለኝ፤ ተጨማሪ 14 ቀን ያስፈልገኛል" ቢልም ፍርድ ቤቱ የፖሊስ ጥያቄን ውድቅ በማድረግ ለተጠርጣሪዎቹ ዋስትና ፈቅዶ እንደነበር ይታወሳል። አቶ ሄኖክ እንዳሉት በዛሬው የችሎት ውሎ ላይ የፖሊስን የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ፖሊስ በቂ ጊዜ ተሰጥቶታል፣ ከዚህ በሁዋላ ተጠርጣረዎቹ ቢወጡ የፖሊስ ምርመራ ሂደት ለይ ምንም የሚፈጥሩት ተጽዕኖ የለም በሚል መከራካቸውንና ዋስትና መጠየቃቸውን ገልፀዋል። የአስራት ሚዲያ ጋዜጠኞች "አመፅ ቀስቃሽ መልዕክት በጣቢያው ሲቀርብ ሠራተኞች ነበራችሁ" በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞቹ ሙሉጌታ አንበርብርና በላይ ማናዬ እንዲሁም የካሜራ ባለሙያው ምስጋናው ከፈለኝ ሲሆኑ ከዘጠኝ ወር በፊት የሚዲያ ተቋሙን የለቀቀው ዮናታን ሙሉጌታም ይገኝበታል። በጋዜጠኞቹ ላይ የቀረበው ክስም ከሕዳር 12 እስከ ሰኔ 12/2012 ዓ.ም ባለው ጊዜ "የአማራ ሕዝብ በተለየ ተበድሏል፤ መንግሥትም የአማራ ሕዝብ ሲበደል ሊከላከልለት አልቻለም ብሎ አስተላልፏል። "ይህ ሲተላለፍ እናንተ ሠራተኞች ነበራችሁ በማለት እንደሆነና በዚህም በኦሮሚያ ክልል ደንቢዶሎና ኦዳ ቡልቱ አካባቢ አመፅ መነሳቱን፤ ንብረት መውደሙንና የሰው ሕይወት በመጥፋቱ" መጠርጠራቸውን ፖሊስ መግለጹን ይታወሳል።
news-55785133
https://www.bbc.com/amharic/news-55785133
የእስያው አደንዛዥ ዕፅ ከበርቴ በአምስተርዳም በቁጥጥር ስር ዋለ
በአለም ትልቁ የአደንዛዥ ዕፅ ቡድን መሪ የሆነው እስያዊው የዕፅ ከበርቴ በአምስተርዳም በቁጥጥር ስር ውሏል።
የእስር ትዕዛዙ የወጣበት በአውስትራሊያ መንግሥት ነው ተብሏል። ትሲ ቺ ሎፕ የተባለው የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴ ትውልዱ ቻይና ቢሆንም ዜግነቱ ካናዳዊ ነው። በእስያ ውስጥ 70 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን የሚያካሂድ ኩባንያ አለው። በአለም ላይ ተፈላጊ ሰዎች ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴው በአምስተርዳሙ ሺፖል አየር ማረፊያ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው። አውስትራሊያ ግለሰቡ ተላልፎ እንዲሰጣትና የፍርድ ሂደቱም በአውስትራሊያ እንዲካሄድ ትፈልጋለች። የአውስትራሊያ ፌደራል ፖሊስ ሳም ጎር ሲንዲኬት ተብሎ የሚታወቀው የትሲ ቺ ኩባንያ በአውስትራሊያ ውስጥ ከሚገቡ ህገወጥ አደንዛዥ ዕፆች መካከል 70 በመቶውን እንደሚሸፍን አስታውቋል። የ56 አመቱ የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴ በዘረጋው የንግድ ስርአትና ሃብት ምክንያት ምክንያት ከሜክሲኳዊው "ኤል ቻፖ'' ጉዝማን ጋርም የሚያመሳስሉት አልታጡም። የአውስትራሊያ ፖሊስ ግለሰቡን ከአስር አመት በላይ ሲያድነው የነበረ ሲሆን ወደ ካናዳ ለመብረር ሲል ነው በዚህ ሳምንት አርብ በቁጥጥር ስር የዋለው። የፖሊስ መግለጫ እንደሚያሳው በኔዘርላንድስ የእስር ትዕዛዙ የወጣበት ከሁለት አመት በፊት በኢንተርፖል አማካኝነት ነው። "በአለም ላይ እየታደኑ ካሉ ቁንጮ ሰዎች መካከል አንደኛው ነው። በቁጥጥር ስር የዋለው ባገኘነው ጥቆማ መሰረት ነው" በማለት የኔዘርላንድስ ፖሊስ ቃለ አቀባይ ተናግረዋል። ሮይተርስ ከሁለት አመታት በፊት በሰራው ልዩ የምርምር ዘገባ "በእስያ አንደኛው ተፈላጊ ሰው" በሚል ትሲ ቺን የጠራው። በዚህ ዘገባ ላይ ግለሰቡ ሜታፌታሚን ተብሎ ከሚጠራው አደንዛዥ እፅ ሽያጭ ብቻ 17 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በአውሮፖውያኑ 2018 ማስገባት እንደቻለ የተባበሩትን መንግሥታት ግምት አስቀምጧል። የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴውን ለመያዝ በተለያዩ አህጉራት የሚገኙ 20 የደህንነት ኤጀንሲዎች የተሳተፉበት ኩንጉር የሚባል ዘመቻ መካሄዱን ሮይተርስ አስነብቧል። ግለሰቡ በቅርብ አመታት በማካው፣ ሆንግ ኮንግና ታይዋን እየኖረ ነበር ተብሏል። በአውሮፓውያኑ 1990ዎቹ በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ክስ በአሜሪካ ለዘጠኝ አመታት ታስሮ ነበር። የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴውን እስር ተከትሎ የአውስትራሊያ ሚዲያዎች የአገሪቱ ፌደራል ፖሊስ በሁለት አስርት አመታት ውስጥ የታየ ትልቁ ስኬት ሲሉ አሞካሽተውታል።
55561317
https://www.bbc.com/amharic/55561317
ትራምፕ ስምንት የቻይና መተግበሪያዎች ላይ እገዳ ጣሉ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስምንት የቻይና መተግበሪያዎች [አፕ] ጋር ግብይት እንዳይካሄድ የሚያግድ ትዕዛዝ ፈረሙ።
ከመተግበሪያዎቹ መካከል ታዋቂ የክፍያ ዘዴዎች የሆኑት አሊፔይ፣ ኪውኪው ዋሌት እና ዊቻት ፔይን ይገኙበታል። በ45 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ የሚሆነው ውሳኔ መተግበሪያዎቹ ለአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ስጋት በመሆናቸው ታግደዋል ተብሏል። መተግበሪያዎቹ የአሜሪካ ፌዴራል ሠራተኞች መረጃን ለመከታተል እያገለገሉ ሳይሆን አይቀርም የሚል ፍንጭ ሰጥቷል። ውሳኔው ቴንሴንት፣ ኪውኪው፣ ካምስካነር፣ ሼርኢት፣ ቨሜት እና ደብሊውፒኤስን የሚያካትት ሲሆን ትራምፕ ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ የሚተገበር ነው ተብሏል። የፕሬዝዳንቱ እርምጃ "ከቻይና ጋር ግንኙነት ያላቸውን የሶፍትዌር መተግበሪያዎች በሚያዘጋጁ ወይም በሚቆጣጠሩት ላይ አሜሪካ እርምጃ መውሰድ አለባት" ይላል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዚህ ውሳኔያቸው ላይ "ከቻይና ጋር የተገናኙ የሶፍትዌር መተግበሪያዎች እንደ ስማርት ስልኮች፣ ታብሌቶች እና ኮምፒውተሮች ያሉ የግል የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በማግኘት ግላዊ የሆኑትን ጨምሮ ሰፋ ያሉ መረጃዎችን ከተጠቃሚዎች ማግኘት እና መያዝ ይችላሉ" ብለዋል። የትራምፕ አስተዳደር ከመጨረሻዎቹ የስልጣን ወራቶቹ ጀምሮ የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ናቸው የሚሏቸውን ጨምሮ በቻይና ኩባንያዎች ላይ ጫናዎችን እያደረጉ ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቻይና መንግሥት መረጃዎችን ያጋራሉ በሚል በበርካታ የቻይና ኩባንያዎች ላይ እገዳዎችን ጥለዋል። የዋሽንግተን ቅጣት ከደረሰባቸው መካከል የቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያው ቲክቶክ እና ግዙፉ የቴሌኮም ተቋም ሁዋዌ ተጠቃሽ ናቸው። ቻይና እነዚህ ድርጅቶች መረጃዎቻቸውን ለቻይና መንግሥት ያካፍላሉ የሚሉ ቅሬታዎችን በተከታታይ ውድቅ ስታደርግ የቆች ሲሆን፤ የወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ውጭ መላክ የሚገድቡ የራሷን ሕጎች በማውጣት ምላሽ ሰጥታለች።
news-55097963
https://www.bbc.com/amharic/news-55097963
'ከሞት የተነሳው' ኬንያዊ ጉዳይ እያነጋገረ ነው
በኬንያዋ ኪሪቾ ግዛት አንድ ግለሰብ ድንገት ተዝለፍልፎ ከወደቀ በኋላ በጤና ባለሙያዎች ሕይወቱ አልፏል ከተባ በኋላ መተንፈስ መጀመሩ አነጋጋሪ ሆኗል።
ግለሰቡ በመኖሪያ ቤቱ ሳለ ነበር ድንገት ተዝለፍልፎ የወደቀው፤ ከዚያም ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን በሆስፒታሉ ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች ግለሰቡ ሕይወቱ ማለፉን ካስታወቁ በኋላ አስክሬኑ ሊገነዝ ሲዘገጃጅ ድንገት መተንፈስ ጀምሯል ተብሏል። የ32 ዓመቱ ፒተር ኪጀን በሆስፒታል ሠራተኞች ሕይወቱ አልፋለች ተብሎ ስለታመነ አስክሬኑ ወደ ሬሳ ማቆያ እንዲገባ መደረጉን መገናኛ ብዙሀን ጨምረው ዘግበዋል። ፒተርን ወደ ሆስፒታል ይዞት የመጣው ታናሽ ወንድሙ ለስታንዳርድ ጋዜጣ ሲናገር ''ነርሷ ወንድሜ ድንገተኛ ክፍል ውስጥ ከመድረሱ በፊት ሕይወቱ ማለፉን ነገረችኝ'' ብሏል። ነገር ግን እንደ ሆስፒታሉ ዋና ኃላፊ ከሆነ ቤተሰቦቹ የሞቱ ማረጋገጫ ወረቀት ሳይወስዱ አስክሬኑን በራሳቸው ፈቃድ ወደ ሬሳ ማቆያ ወስደውታል። ፒተር ኪጀን ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ከባድ የጤና እክል ገጥሞት የነበረ ሲሆን ከሞት ከተረፈ በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረገው ቆይታ ከዚህ በኃላ ሙሉ ሕይወቴን በሐይማኖታዊ ስራ ነው የማሳልፈው ብሏል። በወቅቱ የሬሳ ማቆያ ክፍል ሰራተኞች አስክሬኑን ለማዘገጃጀት በሚጣደፉበት ወቅት ድንገት መተንፈስ መጀመሩ በእጅጉ ነበር ያስደነገጣቸው። ''የአስክሬን ክፍሉ ሰራተኛ ስልክ ደወለችልኝና ስሄድ አንዳንድ የወንድሜ የሰውነት ክፍሎች ሲንቀሳቀሱ ተመለከትን። ሁላችንም በጣም ደነገጥን። ሞቷል ተብሎ ሬሳ ማቆያ ክፍል ውስጥ የገባ ሰው እንዴት ሊንቀሳቀስ ይችላል? ለማመን የሚከብድ ነበር'' ብሏል ታናሽ ወንድሙ። ፒተር በበኩሉ ሞቷል ተብሎ መወሰኑ እና ወደ አስክሬን ክፍል መወሰዱ አስደንግጦኛል ብሏል። ''ድንገት ስነቃ የት እንዳለሁ እንኳን አላውቅም ነበር። ነገር ግን ፈጣሪ ሕይወቴን ስላተረፈልኝ በጣም ደስተኛ ነኝ። ከዚህ በኋላ ሕይወቴን ሙሉ እሱን በማገልገል ነው የማሳልፈው'' ብሏል። ሞቷል የተባለው ፒተር ከአስክሬን ማቆያ ወደ ህክምና ክፍል ከተወሰደ በኋላ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል። በቅርብ ቀናት ውስጥ ከሆስፒታል እንደሚወጣም ይጠበቃል።
news-56547518
https://www.bbc.com/amharic/news-56547518
ፈረንሳይ የሩዋንዳን የዘር ጭፍጨፋ 'እንዳላየ' ማለፏን ሪፓርት ጠቆመ
ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት በሩዋንዳ ለተከሰተው የዘር ጭፍጨፋ ፈረንሳይ "እጅግ ከፍተኛ ተጠያቂነት" አለባት ሲል በፈረንሳይ የታሪክ ምሁራን የተዘጋጀ አንድ ሪፖርት አመለከተ።
ፈረንሳይ በተፈጠረው ነገር እጇ እንደነበረበት የሚጠቁም መረጃ ግን ምሁራኑ አላገኙም። ሪፖርቱ የቀረበው ለፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ነው። በሪፖርቱ መሠረትም ፈረንሳይ የዘር ጭፍጨፋውን "እንዳላየ" አልፋለች። በወቅቱ ሁቱዎች፤ ቱትሲዎችን እንዲሁም ለዘብተኛ የሚባሉ ሁቱዎችን ጨፍጭፈዋል። ቢያንስ 800,000 ሰዎች የተገደሉበት አሰቃቂ የዘር ጭፍጨፋ ነው። የታሪክ ምሁራኑ ጥናት ያደረጉት በፈረንሳይን ይፋዊ መዛግብት ላይ ነው። ሩዋንዳ በዘር ጭፍጨፋው ፈረንሳይ ተባባሪ ነበረች ስትል ትከሳለች። በታሪክ ምሁራኑ የወጣውንም ሪፖርት ተቀብላዋለች። የሩዋንዳ መንግሥት "በቱትሲዎች ላይ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ የፈረንሳይ ሚና ምን እንደነበር የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ ሪፓርቱ አንድ እርምጃ ነው" ሲል ገልጿል። እአአ ከግንቦት 1994 እስከ ሰኔ 1994 ድረስ ሩዋንዳ በሁቱ መሪ ሥር ነበረች። ከዚያም በቱስሲዎች የሚመራው አማጺው የሩዋንዳን ፓትርዮቲክ ፍሮት (አርፒኤፍ) አመራሩን ከሥልጣን አስወግዷል። አርፒኤፍ ያኔ ይመራ የነበረው በአሁኑ የሩዋንዳ ፕሬዘዳንት ፖል ካጋሜ ነው። ሪፖርቱ የያኔው የፈረንሳይ ፕሬዘዳንት ፍራንሷ ሚትራን ሩዋንዳን በተመለከተ ያራምዱት የነበረው ፖሊሲ "የከሸፈ" ነበር ይላል። ፈረንሳይ ሩዋንዳን ይመሩ ከነበሩት ሁቱዎች ጋር ስለነበራት ግንኙነት ለዓመታት ምንም ነገር በግልጽ ባይነገርም፤ አሁን ሪፖርቱ ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። ጥናቱ የተካሄደው 15 አባላት ባሉት ኮሚሽን ሲሆን፤ ኮሚሽኑን ከሁለት ዓመት በፊት ያዋቀሩት ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ናቸው። ኮሚሽኑ ፕሬዘዳንታዊ መረጃ፣ የዲፕሎማሲ ሰነዶች እንዲሁም ወታደራዊና የደኅንነት መዛግብትን እንዲፈትሽ ተፈቅዶለታል። የያኔው የፈረንሳይ ፕሬዘዳንት ሁቱ ከነበሩት ፕሬዘዳንት ዡቬናል ሀቢያሪማና ጋር ቅርብ ግንኙነት እንደነበራቸው መዛግብት ያሳያሉ። እአአ ግንቦት 6/1994 ሀቢያሪማና እና የብሩንዲውን ሲፒሪን ናታኒያሚራን የያዘ አውሮፕላን ተመቶ መውደቁን ተከትሎ ነበር የዘር ጭፍጨፋው የተቀሰቀሰው። ኤኤፍፒ እንደዘገው፤ ጥናቱን ባካሄደው ኮሚሽን ውስጥ ሚዛናዊነትን ለመጠበቅ ሲባል ሩዋንዳውያን ተመራማሪዎች አልተሳተፉም። ሆኖም ግን በአይሁዳውያን ላይ በናዚ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት [ሆሎካስት] ላይ ጥናት የሠሩ፣ በአንደኛው የዓለም ጦርነት የተጨፈጨፉ አርመናውያን ላይ ጥናት ያደረጉና ሌሎችም በዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግ የታወቁ ምሁራን ተካተዋል። ቪንሰንት ዱሴለርት በተባሉ የታሪክ ምሁር ነው ካውንስሉ የተመራው። እአአ በሰኔ 22/1994 የተባበሩት መንግሥታት የፈረንሳይ ኃይልን በሩዋንዳ ደቡብ ምዕራብ ግዛት አሰማርቶ ነበር። ይህ ተልዕኮ 'ቱርክዌስ' የተባለው ስምሪት አከራካሪ ነበር። የፈረንሳይ ሰብዓዊ አገልግሎት ክፍል ጥቂት ሰዎችን ከግድያ ታድጓል። ሆኖም ግን እነዚህ የፈረንሳይ ኃይሎች በቦታው የደረሱት እጅግ ዘግይተው እንደነበር እና ገዳዮቹ መጠለያው ውስጥ ተደብቀው እንደነበር ተነግሯል። 2015 ላይ የያኔው ፕሬዘዳንት ፍራሷ ሆላንዲን ሩዋንዳና በተመለከተ የተሰበሰቡ መረጃዎች ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረጉ ተናግረው ነበር። ሆኖም ግን አንድ አጥኚ ሰነዶቹን ከመረመሩ በኋላ የፈረንሳይ የሕገ መንግሥት ካውንስል መረጃው በምስጢር እንዲያዝ ውሳኔ አሳልፏል። የሩዋንዳ መንግሥት እንዳለው፤ ከፈረንሳይ የታሪክ ምሁራን ሪፖርት ጋር አብሮ የሚሄድ ሪፖርት በቅርቡ ይፋ ያደርጋል።
44249351
https://www.bbc.com/amharic/44249351
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግዕዝና ኦሮምኛ ቋንቋዎች ጥናት ፍላጎት ጨምሯል
የግዕዝና ኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠት የጀመረው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከጠበቀው የላቀ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ማግኘቱ ተገልጿል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ ለአስራ አራት ተማሪዎች መስጠት በጀመረው የግዕዝ ቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ ትምህርት፤ የኢትዮጵያን ጥንታዊና መካከለኛው ዘመን የተደበቀ የዕውቀት ጥሪት የመፈልቀቅ፤ የጥናት በርም የመክፈት ግብ እንዳለው ተመልክቷል። ፍላጎት ላላቸው የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ሠራተኞችና ተማሪዎች መሰጠት የጀመረው የኦሮምኛ ቋንቋ ስልጠናም በርካቶችን እንደሳበ ተገልጿል። ቋንቋው በመደበኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜ፤ በመጀመሪያ ዲግሪ በሚቀጥለው ዓመት መሰጠት ይጀምራል። የዩኒቨርሲቲው የሥነ-ሰብ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶክተር ዳዊት አሞኘ ለቢቢሲ እንደገለፁት የግዕዝ ቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ በሥርዓተ ትምህርት ተቀርጾ ተገቢውን ግምገማ ያለፈው ከወራት በፊት ሲሆን አሁን በተያዘው ሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ጸድቆ ወደተግባር ተገብቷል። እንደ ኃላፊው ገለጻ በልዩ ልዩ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የያዙና መሠረታዊ የግዕዝ ዕውቀት ያላቸው አርባ ዕጩ ተማሪዎች ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በቋንቋው ለመስራት ቢመዘገቡም፤ ከዩኒቨርሲቲው የአቅም ውስንነት አንጻር ሲሶውን ብቻ ተቀብሎ ማስተማር ጀምሯል። "የትምህርት ክፍሉ ዋነኛ ዓላማ በጥንታዊና በመካከለኛው የኢትዮጵያ የስልጣኔ ዘመን የነበሩ ብዙም የማይታወቁ የህክምና፣ የትምህርት፣ የፍልስፍና፣ የባህል፣ የሥነ-ልቦና፣ የእምነት እንዲህም የአስተዳደር ዕውቀቶችን መዳሰስና ለጥናት በር መክፈት ነው" ሲሉ ኃላፊው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በበቂ ሁኔታ የግዕዝ መምህራን አለማግኘት ቀዳሚው ፈተናቸው መሆኑን የሚያስረዱት ዶክተር ዳዊት "ችግሩን ለመቅረፍ እየሰራን ነው" ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው ኦሮምኛ ማስተማር የጀመረው በአጫጭር ስልጠና መልክ ሲሆን፤ የተማሪዎቹ የቋንቋ ብቃት ታይቶ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል ተብሏል። የመጀመሪያውን ስልጠና የሚወስዱ ተማሪዎች ቁጥር ሃምሳ ገደማ ሲሆን መማር የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር መብዛት ግን ተጨማሪና ተከታታይ ስልጠናዎች እንዲኖሩ እንደሚያስገድድ ዶክተር ዳዊት ይናገራሉ። ዩኒቨርሲቲው በሚቀጥለው ዓመት በኦሮምኛ ቋንቋ መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት መስጠት የሚጀምር ሲሆን አሁን የከፈተው ኢ-መደበኛ የስልጠና መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ላይ ያተኮረ ነው። "ለስልጠናው ጥሪ ስናቀርብ በርካታ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ አስተዳደሪዎች፣ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች ፍላጎት አሳይተው መማር ጀምረዋል" ይላሉ ኃላፊው። ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኦሮምኛ ቋንቋ በዲግሪ ደረጃ ሊያስተምር እንደተሰናዳ ከተዘገበበት ጊዜ አንስቶ፤ የቋንቋ ትምህርት በግዕዝ ሆሄያት ይሰጥ ዘንድ ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖች ነበሩ። ይህን መሰሉ እርምጃ ተማሪዎቹን ከጠቅላላ የቋንቋው ተናጋሪ ማህበረሰብ የሚነጥል መሆኑን በማውሳት እንደማይቀበሉት ዶክተር ዳዊት ይገልፃሉ። "ለውጥ የሚያስፈልግ ከሆነ የቋንቋው ባለቤቶች ከተናጋሪው ህብረተሰብ ጋር መክረው ካልለወጡት በስተቀር፤ በአንድ ቋንቋ ውስጥ ሁለት የተለያየ የአፃፃፍ ስርዓት የለም" ይላሉ።
sport-45704113
https://www.bbc.com/amharic/sport-45704113
ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች
ሁሉንም የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ያለ ማንም ትዕዛዝ የሚፈጽመውና ለአጠቃላይ ጤናችን ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው አንጀታችን በብዙዎች 'ሁለተኛው አንጎል' በመባል ይጠራል።
የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት አንጀታችን ምግብ ከመፍጨት የበለጠ ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያከናውናል። ዶክተሮች እንዲውም አንጀት የአእምሮ ህመምን ለማከምና የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ለመገንባት የሚያደርገውን አስተዋጽ በግልጽ ለመለየት ምርምር ጀምረዋል። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አውስትራሊያዊቷ ሜጋን ሮሲ በአንጀት ጤናና ህክምና ላይ በተለይ የሚሰሩ ዶክተር ናቸው። ስለምንበላቸው ምግቦችና በአንጀታችን ዙሪያ ማወቅ ስላሉብን ስድስት እውነታዎች ነግረውናል። • ልጆችዎ ጤናማ ምግብ እንዲመገቡ ማድረጊያ መላዎች • ልባችን ከእድሜያችን ቀድሞ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ? • የአስር ደቂቃ እንቅስቃሴ የማስታወስ ችሎታን እንዴት ይጨምራል? 1. ራስ ገዝ የነርቭ ሥርዓት ከሌሎቹ የሰውነት ክፍሎቻችን በተለየ መልኩ አንጀታችን በራሱ ጊዜ የሚያደርጋቸው ነገሮች ብዙ ናቸው። ማንኛውንም አይነት ትእዛዝ ከአንጎላችን እስኪመጣ አይጠብቅም። አንጀታችንን የሚያዘው አንጎላችን ሳይሆን ''ኢንትሪክ የነርቭ ሥርዓት'' የሚባለው ሲሆን፤ ይህም በዋነኛነት የሚቆጣጠረው ከሥርዓተ-ልመት (የምግብ መፈጨትና መዋሃድ) ጋር የተያያዙ ሂደቶችን ነው። ምንም እነኳን አንጀታችን ነገሮችን በራሱ ቢያናከውንም፤ ከማዕከላዊው የነርቭ ሥርዓት ጋር ግን መረጃዎችን ይለዋወጣል። 2. 70 በመቶ የሚሆኑት የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ሴሎች በአንጀታችን ውስጥ ይገኛሉ እንደ ዶክተር ሮሲ ከሆነ ይህ እውነታ አንጀታችን ከበሽታ መከላከልና ከአጠቃላይ ጤንነታችን ጋር በጥብቅ የተቆራኘ እንዲሆን ያደርገዋል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት የአንጀት ህምም ባጋጠመን ጊዜ እንደ ጉንፋን ላሉ በሽታዎች በቀላሉ ተጋላጭ እንሆናለን። • የመዋቢያ ምርቶች ውስጥ መርዛማ ንጥረ-ነገሮች ተገኙ 3. 50 በመቶ የሚሆነው የሰዎች አይነምድር ባክቴሪያ ነው ግማሽ ያህሉ ከሰውነታችን የሚወደው አይነ ምድር ባክቴሪያ ቢሆንም፤ አብዛኞቹ ባክቴሪያዎች ግን ጎጂ አይደሉም። ጎጂ ቢሆኑ እንኳን የአንጀታችን የመከላከል ብቃት ከፍተኛ ስለሆነ ብዙም የሚያሳስብ አይደለም። ነገር ግን ይላሉ ዶክተር ሮሲ አንጀታችንን ሥራ ካበዛንበትና ካልተንከባከብነው ውጤቱ አስከፊ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም ሰው በቀን ቢያንስ ሦስት ጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት ጎራ ቢል መልካም ነው ባይ ናቸው። • አዲሱ የማዋለጃ ቦርሳ የእናቶችን ህይወት እየታደገ ነው 4. የተለያዩ አይነት ምግቦች ስንመገብ አንጀታችን ደስ ይለዋል አንጀታችን ውስጥ በትሪሊዮኖች የሚቆዎጠሩና ብዙ ጥቅም ያላቸው "ማይክሮብስ" የሚባሉ ጥቃቅን ነገሮች ያሉ ሲሆን እነሱ ደግሞ የተለያየ አይነት ምግቦች ወደ አንጀታችን ሲገባ የሥራ ፍጥነታቸው ይጨምራል። • ኮሌራን የሚቆጣጠር ኮምፕዩተር ተሰራ እነዚህ ማይክሮብ የተባሉት ነገሮች የሥርዓተ ልመቱን ከማፋጠን አልፎ በምግቦች ውስጥ ያለውን ውሃ ለመምጠጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ''ማይክሮብስ'' በቤታችን እንደሚገኙ የቤት እንስሳት እንደማለት ናቸው። የእኛን እንክብካቤ ይፈልጋሉ በማለት ገልጸዋቸዋል ዶክተር ሮሲ። 5. የሆድ እቃችን ከጭንቀትና ስሜቶቻችን ጋር ግንኙነት አለው ከሆድና አንጀታችን ጋር የተገናኘ ማንኛውም አይነት ህመም ሲሰማን መጀመሪያ ልናስበው የሚገባው ነገር በሰዓቱ ጭንቀት ውስጥ መሆን አለመሆናችንን ነው። ለዚህም ነው በቅርቡ እየተሞከሩ ባሉ አዳዲስ የህክምና አይነቶች የአእምሮ በሽታና ቀላል ጭንቀቶችን ለማከም ጎጂ ያልሆኑ ባክቴሪያዎችን ወደ አንጀት ማስገባት የተጀመረው። የዘርፉ ባለሙያዎች እያደረጉት ባለው ጥናት ጤናማ የሆነ አንጀት ያላቸው ሰዎች ጤናማ ካልሆነ አንጀት ካላቸው ጋር ሲወዳደሩ ለጭንቀትና ሌሎች የአእምሮ በሽታዎች ያላቸው ተጋላጭነት የቀነሰ ነው። 6. የአንጀትዎትንና የሥርዓተ-ልመት ሂደቶችን ለማስተካከል የሚከተሉትን ያድርጉ
news-50130421
https://www.bbc.com/amharic/news-50130421
ድካምና የአቅም ማነስ ይሰማዎታል? እነሆ ምክንያቱና መፍትሄው
ከአምስት ሰዎች አንዱ ባልተለመደ መልኩ ለረዥም ሰዓታት የድካም ስሜት የሚያጋጥመው ሲሆን ከአስር ሰዎች አንዱ ደግሞ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ የሰውነት መዛልና ከፍተኛ ድካም እንደሚሰማቸው የእንግሊዙ ሮያል የሥነ ልቦና ኮሌጅ መረጃ ይጠቁማል።
ነገሮችን አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ድካምና የሰውነት መዛል ከሰው ልጆች ታሪክ ጋር አብረው የቆዩ ቢሆኑም ምክንያታቸው ምን እንደሆነ ለመረዳት ብዙም ጥረት አልተደረገም። • ለሰው ልጅ ምርጡ ምግብ እንቁላል ይሆን? አዲስ እየተሰሩ ያሉ ጥናቶች ደግሞ እነዚህ ስሜቶች ከምንበላው ምግብ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት እንዳላቸው ማሳየት ጀምረዋል። የአይረን (ብረት) እጥረት ጉዳቱ ምንድን ነው? የአይረን እጥረት በዓለማችን ሁሉም ክፍሎች የተለመደ የአመጋገብ ሥርዓት ችግር ነው። ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ የአይረን እጥረት እንዳለበት የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የእንግሊዝ ብሔራዊ የአመጋገብ እና ሥነ ምግብ ጥናት ማዕከል የሰራው ጥናት እንደሚያሳየው እድሜያቸው ከ11 እስከ 18 ከሆኑ ታዳጊ ሴቶች 48 በመቶ፣ ከ19 እስከ 64 ከሚሆኑ ሴቶች 27 በመቶ እንዲሁም እድሜያቸው ከ11 እስከ 18 ከሚሆኑ ታዳጊ ወንዶች ደግሞ ከአስሩ አንዱ ዝቅተኛ የሆነ የአይረን መጠን አካላቸው ያገኛል። ለመሆኑ የአይረን እጥረት እንዴት ከአቅም ማነስ ጋር ይገናኛል? ደማችን ከቀይ ደም ህዋሳት፣ ከነጭ ደም ህዋሳት፣ ከፕላዝማ እና ከፕላትሌትስ የተሰራ ነው። ቀይ የደም ህዋሳት ደግሞ በመላው ሰውነታችን ለሚገኙ ክፍሎች ኦክስጂን ማመላለስ ዋነኛ ተግባራቸው ነው። • ከልክ በላይ በወፈሩ ሰዎች ሳንባ ውስጥ ስብ እንደሚገኝ ያውቃሉ? እነዚህ ቀይ የደም ህዋሳት የሚመረቱት በአከርካሪ አጥንታችን ውስጥ ሲሆን በቀን በሚሊየኖች ይመረታሉ። ቀይ የደም ህዋሳት በደማችን ውስጥ የሚቆዩት እስከ 120 ቀናት ድረስ ብቻ ስለሆነ በየጊዜው መቀየር ያስፈልጋቸዋል። የአከርካሪ አጥንታችን ደግሞ እነዚህን ቀይ የደም ህዋሳት በየቀኑ በብዛት ለማምረት አይረን እንዲሁም እንደ ፎሊክ አሲድና ቢ12 ያሉ ቫይታሚኖችን በበቂ ሁኔታ ማግኘት አለበት። ስለዚህ የአይረን እጥረት ቀይ የደም ህዋሳት ቁጥር ትንሽ እንዲሆን ያደርጋል። ይህ ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ የኦክስጅን ስርጭትን በእጅጉ ስለሚቀንሰው አብዛኛዎቹ የሰውነታችን ክፍሎች ይዳከማሉ። ቀይ የደም ህዋስ እጥረት አኒሚያ የተባለ የጤና እክልን ያስከትላል። አኒሚያ አነስተኛ ቀይ የደም ህዋሳት ቁጥር ሲኖር አልያም በቀይ የደም ህዋሳት ውስጥ የሚገኘው ሄሞግሎቢን መጠን ዝቅ ሲል ይከሰታል። ሄሞግሎቢን ደግሞ በሰውነታችን ውስጥ የኦክስጂን ስርጭትን ይቆጣጠራል። • ልጆችዎ ጤናማ ምግብ እንዲመገቡ ማድረጊያ መላዎች ስለዚህ አኔሚያ ድካምንና የአቅም ማነስ፣ ማዞር፣ የትንፋሽ ማጠር እንዲሁም የልብ በፍጥነት መምታትን ያስከትላል። አንድ ሰው አኒሚያ ሲኖርበት ቀይ የደም ህዋሳት ከሌላ ጊዜው በተለየ የስፋት መጠናቸው ስለሚጨምር ከአከርካሪ አጥንት ወጥተው ወደ ሰውነታችን ለመሰራጨት ይቸገራሉ። ምናልባት አኒሚያ ከአመጋገብ ጋር ብቻ ላይገናኝ ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን በሰውነታችን ውስጥ የአይረን መጠንን ከፍ የሚያደርጉ ምግቦችን ማዘውተር ጠቃሚ ነው። ምግባችን ውስጥ የአይረን መጠንን ከፍ ማድረግ ለሰውነታችን ተጨማሪ ኃይልና ጉልበት እንደሚሆነው የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የእንግሊዝ የህክምና ጥናት ማዕከልና የእንግሊዝ የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት በጋራ እንደገለጹት፤ ይህ የድካምና አቅም ማነስ ችግር ከአይረን እጥረት ጋር እንደሚያያዝ ብዙዎች አይረዱም። በተለይ ደግሞ ልጅ የሚወልዱ እና ለመውለድ እድሜያቸው የደረሰ ሴቶች ለዚህ በእጅጉ የተጋለጡ ናቸው። ምንም እንኳን ዝቅተኛ የአይረን መጠን በብዛት ሴቶች ላይ የሚስተዋል ችግር ቢሆንም እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች ተጋላጭነት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው። • ሳናውቀው እያለቁብን ያሉ ስድስት ነገሮች • አፍሪካዊያን ተወዳጅ ምግባቸውን መተው ሊኖርባቸው ይሆን? ይህ ማለት ግን የአቅም ማነስና የድካም ስሜት የሚያጠቃው ማንኛውም ሰው አይረን መውሰድ አለበት ማለት ነው? መልሱ ሁሌም ላይሆን ይችላል ነው። ዋናውና የመጀመሪያው ጉዳይ መሆን ያለበት የህክምና ባለሙያን ማማከር ነው። ምክንያቱም ያለ ህክምና ባለሙያ ምክር አይረንን መውሰድ ሌላ የጎንዮሽ ችግር ሊያስከትል ይችላል። ስለዚህ የአይረን መጠናችንን ከፍ ለማድረግና የድካም ስሜትን ለመቀነስ ምን አይነት ምግቦች ማዘውተር አለብን? ቀይ ሥጋ፣ የዶሮ ሥጋ፣ ዓሳ፣ ጥራጥሬዎች፣ አፕል፣ ቦለቄ፣ የዱባ ፍሬ እና የመሳሰሉ ምግቦች ከፍተኛ የአይረን ክምችት ስላላቸው እነሱን አዘውትረን በአመጋገባችን ውስጥ ማካተት ጠቃሚ ነው። የቫይታሚን ዲ፣ የቫይታሚን ኤ እና የቫይታሚን ቢ12 እጥረት እንዲሁም የዚንክ እጥረት ድካምና የአቅም ማነስን ሊያስከትሉ የሚችሉ ችግሮች ናቸው።
news-46956179
https://www.bbc.com/amharic/news-46956179
ብቻቸውን ምግብ የሚመገቡ ሴቶች ለምን ትኩረት ይስባሉ
ስለሴቶች መብትና እኩልነት ብዙ ነገሮች በሚባሉበትና ተግባራዊ በሚደረጉበት ዘመን አንዲት ሴት ብቻዋን ሬስቶራንት ውስጥ መቀመጥ ብዙም የሚያስገርም ላይመስል ይችላል።
ነገር ግን በአብዛኛዎቹ የዓለማችን ክፍሎች ያደጉትንም ጨምሮ አንዲት ሴት ብቻዋን ምግብ አዝዛ ስትመገብ አልያም መጠጥ ስትጠጣ መመልከት ብዙዎችን ያስገርማል። አንዳንዴም የተለየ ትርጉም ሊሰጠው ይችላል። ታዋቂዋ ክለመንቲን ክሮውፎርድ በአሜሪካዋ ኒውዯርክ ከተማ ነዋሪ ነች። በጽሁፏ እንደገለጸችው በጣም በምትወደው የማንሃተን ሬስቶራንት ውስጥ ብቻዋን መቀመጥ እንደማትችል ተነግሯታል። በመጀመሪያ መልእክቱ ስላልገባኝ ግራ ገብቶኝ ነበር ትላለች። • ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ? • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ''ይባስ ብሎም ከእኔ በኋላ ለመጡ ወንድ ደንበኞች ወንበር ይመቻችላቸዋል፤ ትእዛዛቸውንም ወዲያው ይቀበላሉ።'' በሁኔታው ግራ የተጋባችው ክለመንቲን ምን አጥፍቼ ነው ብላ ስትጠይቅ የተሰጣት መልስ ያልጠበቀችው ነበር። እዚህ ሬስቶራንት ውስጥ ሴተኛ አዳሪዎችን እንዳናስተናግድ ትእዛዝ ተሰጥቶናል ነበር ያገኘችው መልስ። ''ብቻዬን በመሄዴና ዘንጬ ስለነበረ ሁሉም ሰው ያሰበው ሴተኛ አዳሪ እንደሆንኩ ነው።'' ምንም እንኳን ለብዙ ዓመታት ደንበኛ ብሆንም፤ ምንም እንኳን ጥሩ የሚባል ገቢ ያለኝ ሴት ብሆንም፤ ብቻዬን ከመጣሁ ትርጉሙ ሌላ መሆኑ እጅግ ያሳዝናል ትላለች። አንዲት ሴት ብቻዋን ወጥታ መዝናኛ ቤት ጊዜ ማሳለፍ አሁንም እጅግ ፈታኝ ነው። ነገር ብዙ ሴቶች ይህንን ፈተና ለመቋቋምና አካባቢያቸውን ለመርሳት መጽሃፍ ማንበብና ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ ጊዜ ማሳለፍ ያዘወትራሉ። ክለመንቲን ይህንን አጋጣሚዋን በጽሁፍ ካሰፈረችው ወዲህ ብዙ የኒውዮርክና ሌሎች ትልልቅ ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ሴቶች ተመሳሳይ ነገር እንዳጋጠማቸው ጽፈዋል። • ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ? በሬስቶራንቶችና በመዝናና ስፍራዎች የሚታየው የተሳሳተ አመለካከት ሴቶች ምን ያክል ፈተናዎችን እንደሚያልፉ ማሳያ ከመሆኑ ባለፈ በቤት ውስጥ ደግሞ ከዚህም የባሱ ነገሮችን እንደሚጋፈጡ መገንዘብ ይገባናል ትላለች ክለመንቲን። ''አንዲት ሴት ብቻዋን ምግብ አዝዛ መመገብ ከቻለች እንደ ጀግና ነው የምትቆጠረው። ይሄ እስከመቼ ነው የሚቀጥለው?'' ሌላናዋ በዚህ ጉዳይ ላይ ታሪኳን ያካፈለችው ለአምስት ዓመታት ዓለምን ስትዞር ነበረችው ግሎሪያ አታንሞ ናት። ''በሄድኩባቸው የዓለም ክፍሎች ሁሉ ብቻዬን ተቀምጬ ሰዎች አትኩረው ያልተመለከቱኝ አልያም ምን ፈልጌ እንደሆነ ያልተጠየቅኩበትን ጊዜ አላስታውስም።'' ትላለች። • በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ ሴቶች ብቻቸውን ሲሆኑ እንደ ሴተኛ አዳሪ የሚቆጠሩት በሬስቶራንቶች ወይም በመጠጥ ቤቶች ውስጥ ብቻ አይደለም። በተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያዎች ላይ እንኳን ብቻቸውን ቆሙ ሴቶች ከብዙ ወንዶች የተለያዩ ጥያቄዎች ይቀርቡላቸዋል። ለምሽቱ ስንት ልክፈልሽ ከሚሉት እስከ ብቻሽን ከምትሆኚ ከእኔ ጋር ብንሄድስ እስከሚሉት ድረስ እንዳጋጠሟት ሼሪ ኮሊንስ የተባለች ሴት ተናግራለች።
news-47214290
https://www.bbc.com/amharic/news-47214290
ናይጀሪያዊቷ ከመንግሥት ጋር በመተባበር ባለቤቴን ገድሏል በማለት ሼል ኩባንያን ከሰሰች
በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1995 ከተገደሉት ናይጀሪያዊያን ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች መካከል የአንዱ ባለቤት ግድያው የማይሽር ጠባሳን ትቶ እንዳለፈና በድህነት እንድትማቅቅ እንዳደረጋት ገልፃለች።
ኢሽተር ኪዮቤል የተባለችው ይህች ግለሰብ ሄግ በሚገኘው ፍርድ ቤት ለምስክርነት የቀረበች ሲሆን፤ ሼል ላጠፋው ጥፋት ካሳን እንዲሁም ይቅርታን እንደምትሻ ገልፃለች። በናይጀሪያ የነዳጅ ክምችት የተትረፈረፈ ኃብት አላት በምትባለው ኦጎኒ ግዛት ላይ ሼል እያደረሰ ያለውን ብክለትና የሰዎች ጉዳት በመቃወም ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመፅና እንዲሁም ተቃውሞዎች መነሳት ጀመሩ። •ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ ይህንንም ተከትሎ ተቃውሞውን ይመራሉ ያላቸውን ተሟጋቾች በአውሮፓውያኑ 1995 የናይጀሪያ መንግሥት አንቆ ገደላቸው። ምንም እንኳን ሼል ቢያስተባብልም በዚህም ግድያ ሼል ተባብሯል በማለት ይወነጀላል። •ጤፏን ለማስመለስ እየተውተረተረች ያለችው ኢትዮጵያ ተቃውሞዎቹ በዚያን ጊዜ ለነበረው ወታደራዊ አመራር ጄኔራል ሳኒ አባቻና ሼል እንደ ከፍተኛ ስጋት ታይተው ነበር። በወቅቱ እንቅስቃሴውን ይመሩ ከነበሩት ዘጠኙ አቀንቃኞች አንዱ የሆነው ኬን ሳሮ ዊዋ በወታደራዊ መንግሥቱ ታንቆ ከተገደሉት አንዱ ነው። ግድያቸው በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞን ያስነሳ ሲሆን ናይጀሪያንም ከኮመንዌልዝ አባልነቷ ለሶስት አመት አሳግዷታል። ባሎቻቸው ከተገደሉባቸው መካከል ሁለቱ በፍርድ ቤቱ የተገኙ ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ ቪዛ በመከልከላቸው ምክንያት አልተገኙም። ከሁለት አስርት አመታት በፊት ባሏ የተገደለባት ኢሽተር በእንባ እንደተጥለቀለቀች የቢቢሲዋ ዘጋቢ አና ሆሊጋን ከፍርድ ቤት ዘግባለች። እንባዋን እየጠረገች፣ በተቆራረጠና ሳግ በተሞላው ድምፅ ባለቤቷ ባሪኔም ኪዮቤል "ቀና ልብ " ያለው ሰው ነበር ብላለች። •በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? ከዚህ በተጨማሪም በተፃፈ መግለጫዋም "ጥሩ ባለቤቴን እንዲሁም ጓደኛየን አጣሁ" በማለት ተናግራለች። "በህይወቴ እንደ እንቁ የማየውን ነገር ሼል ቀማኝ፤ ሼል ባሏ የሞተባት ደሃ አደረገኝ። ሼል ስደተኛ እንድሆንና በከፍተኛ ድህነት ውስጥ እንድኖር አድርጎኛል። " ብለላች በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ጥገኝነት ጠይቃ ዜግነቷን ያገኘችው ይህች ግለሰብ ጨምራም "የናይጀሪያ መንግሥትና ሼል ተባብረው ባሌን እንዲሁም አጋሮቹን ኬኑሌ ቱዋ ሳሮ ዊዋ፣ ጆን ክፑይነን፣ ባሪበር ቤራ፣ ፖል ሌቩላ፣ ኖርድኡ ኢያዎና የሌሎቹንም ህይወት ነጥቆናል" ሼልንና የናይጀሪያ መንግሥትን በመሞገት የሚታወቀው ኬን ሳሮ ዊዋ "ባሌና ሌሎቹ የተገደሉትም አጋሮቹ ስቃይና እንግልት አሁንም ትናንት የተፈፀመ ይመስል ትዝ ይለኛል። አሁንም ቢሆን ህመሜን ቀለል ባያደርገውም ፍትህን እፈልጋለሁ" ብላለች።
news-45101715
https://www.bbc.com/amharic/news-45101715
አስራ አምስት ዓመታት በዋሻ ውስጥ የታገተችው ኢንዶኔዥያዊት ታዳጊ ነፃ ወጣች
የኢንዶኔዥያዋ ሱላወሲ ከተማ ፖሊስ እንደገለጸው ለ15 ዓመታት በዋሻ ውስጥ ታግታ የቆየች የ28 ዓመት ሴት ነጻ አውጥቷል።
አንድ የ83 ዓመት ሰው አፈናውን እንደፈጸመ የተጠረጠረ ሲሆን፤ ሴትየዋ ገና የ13 ዓመት ታዳጊ እያለች ነበር በግዳጅ ወደ ዋሻው ያመጣት። ሴትየዋ እንደገለጸችው በልጅነት እድሜዋ በመንፈስ የተሞላ እንደሆነ አሳምኗት ቆይቶ ነበር። ለብዙ ዓመታትም በምሽት ወደ ቤቱ እየወሰደ ጾታዊ ጥቃት ይፈጽምባት እንደነበርም ተናግራለች። በአካባቢው የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ሰውዬው ሃይማኖታዊ ፈውስ የሚሰጥና የባህላዊ ህክምና ባለሙያ መሆኑን እየዘገቡ ነው። •ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ •የተነጠቀ ልጅነት •"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" እ.አ.አ በ2003 ጥቃቱ የተፈጸመባት ሴት የ13 ዓመት ታዳጊ እያለች ለህክምና ተብሎ ወደ ተጠርጣሪው ቤት በቤተሰቦቿ መወሰዷንና በዛው መቅረቷን ፖሊስ ገልጿል። ሰውዬው በጾታዊ ጥቃትና የህጻናት መብት ጥሰት ክስ ቀርቦበታል። ለህክምና ወደ ሰውዬው ቤት በሄደችበት ያልተመለሰችውን ልጃቸው የት እንደሄደች ሲጠይቁት የተሻለ ስራ ፍለጋ ወደ ሃገሪቱ መዲና ጃካርታ መሄዷን እንደገለጸላቸው ታውቋል። ቤተሰቦቿና ሌሎች ዘመዶች ታዳጊዋን ለመፈለግ ጥረት ቢያደርጉም ሊሳካላቸው ስላልቻለ ለፖሊስ ጠፍታብናለች ብለው አስታውቀው ነበር። ፖሊስ እንደገለጸው ከሆነ ባለፈው እሁድ ሴትየዋን በአንዲት ትንሽ ዋሻ ውስጥ ተገኝታለች። በዋሻው ውስጥም አንዳንድ የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ማግኘቱንም ጨምሮ ገልጿል። ታዳጊዋ ለማምለጥ ብትሞክር እሱ የሚቆጣጠረው መንፈስ ጉዳት እንደሚያደርስባትና ቤተሰቦቿንም እንደሚከታተላቸው ስለነገራት በፍርሃት ለማምለጥም ሆነ ቤተሰቦቿን ለማግኘት አለመሞከሯን ተናግራለች። ተጠርጣሪው ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 15 ዓመት ድረስ የእስር ቅጣት ሊጠብቀው እንደሚችል ተገልጿል።
news-51904193
https://www.bbc.com/amharic/news-51904193
የአሊባባ ባለቤት ቻይናዊው ባለጸጋ ጃክ ማ አሜሪካንን ረዳ
ቻይናዊዉ ባለጸጋ የጭምብልና የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎቹን ወደ አሜሪካ ልኳል።
ጃክ ማ ባለሃብቱ የምርመራ መሳሪያዎቹና ጭምብሎች ሲጫኑ የሚያሳዩ ሁለት ምስሎችን በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል። በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ 5 መቶ ሺህ የመመርመሪያ መሳሪያዎችንና 1 ሚሊዮን ጭምብሎችን ወደ አሜሪካ እንደሚልክ ተናግሮ ነበር። ዓለም አቀፍ ትብብር ያስፈልገናል በማለት ቀደም ሲል ወደ አውሮፓም ተመሳሳይ የኮሮናቫይረስ የቅድመ መከላከያ መሳሪያዎችን ልኳል ጃክ ማ። የሚፈልጉት ይዘት የለም የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 አሁን ወደ አሜሪካ የተጫነው የእርዳታ መሳሪያም ባለፈው ሳምንት ጃክ ማ ፋውንዴሽንና አሊባባ ፋውንዴሽን 5 መቶ ሺህ የምርመራ መሳሪያዎችንና 1 ሚሊዮን ጭምብሎችን ወደ አሜሪካ ለመላክ ተዘጋጅተናል ማለታቱን ተከትሎ የተፈጸመ ነው። ከአሁን በፊትም ተመሳሳይ እርዳታ ለጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጣሊያን፣ ኢራንና ስፔን የረዳ ሲሆን በመላው አውሮፓ የሚሰራጩ 2 ሚሊዮን ጭንብሎችንም እንደሚያከፋፍል ቃል ገብቷል። ጃክ ማ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ሰዎችን በመቀላቀልም ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ተጨማሪ ምርምሮች እንዲከካሄዱ እየደገፈ ይገኛል። የማይክሮሶፍት መስራቹና የዓለማችን ሁለተኛው ሃብታም ሰው ቢል ጌትስ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በቢል እና ማሊንዳ ፋውንዴሽን በኩል 100 ሚሊዮን ዶላር መድበዋል። ከዚህም በተጨማሪ ቢል ጌትስ ከቦርድ ኃላፊነታቸው ወርደው በጤናና መሰል የበጎ አድራጎት ሥራዎች መቀጠል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። የቻይና ሌሎች በርካታ ባለሃብቶችም ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ገንዘባቸውን ፈሰስ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
49996605
https://www.bbc.com/amharic/49996605
በባንግላዴሽ ባለቤቱን አስገድዶ ፀጉሯን የላጨው በቁጥጥር ስር ዋለ
በባንግላዴሽ የቀረበለት ቁርስ ላይ ፀጉር በማግኘቱ ምክንያት የባለቤቱን ፀጉር በግድ የላጨው በቁጥጥር ስር ዋለ።
የ35 ዓመቱ ባብሉ ሞንዳል በቁጥጥር ስር የዋለው የሚኖርበት መንደር ነዋሪዎች ሚስቱ ላይ የፈፀመውን ለፖሊስ ካመለከቱ በኋላ ነው። በባንግላዴሽ በወግ አጥባቂ ሙስሊሞች ዘንድ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸውን የመብት ተሟጋቾች ይናገራሉ። • ግብጽ በአባይ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች • አሜሪካ ቱርክ ሶሪያ ላይ ጥቃት እንድትፈፅም ይኹንታዋን እንዳልሰጠች ገለፀች • "ትግላችን ከጨቋኝ ገዥዎች ጋር እንጂ ከሕዝቡ ጋር አልነበረም" ኦዴፓ " ቁርስ ላይ ባለቤቱ አብስላ ባቀረበችለት ሩዝና ወተት ላይ ፀጉር በማግኘቱ ነው ፀጉሯን ሙልጭ አድርጎ የላጨው" ብለዋል የአካባቢው ፖሊስ ኃላፊ ሻህሪር ካሃን ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል። አክለውም " ምግቡ ላይ ፀጉር በማግኘቱ በጣም በመቆጣት ምላጭ አንስቶ በግድ ፀጉሯን ሙልጭ አድርጎ ላጭቷታል" ብለዋል። •ፆታዊ ትንኮሳን ደርሶብኛል በማለቷ ተቃጥላ እንድትሞት የተደረገችው ወጣት የፖሊስ አዛዡ እንዳሉት ከሆነ የ35 ዓመቱ ባብሉ ሞንዳል የ23 ዓመቷ ሚስቱ ላይ "ሆን ብሎ ጉዳት በማድረስ" መከሰሱን የተናገሩ ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እስከ 14 ዓመት በሚደርስ እስር ሊቀጣ ይችላል ተብሏል። •"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" በአካባቢው ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚሰራ ቡድን እንዳለው ከሆነ በግማሽ ዓመቱ ብቻ በየቀኑ ቢያንስ ሦስት ሴቶች ተደፍረዋል። ድርጅቱ አክሎም ከታህሳስ እስከ ሐምሌ ባለው ጊዜ ውስጥ 630 ሴቶች ሲደፈሩ፣ 37 ተገድለዋል፣ ሰባቱ ደግሞ ከደረሰባቸው ጥቃት በኋላ ራሳቸውን አጥፍተዋል። 105 የመድፈር ሙከራዎችም በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ መፈፀሙን ተናግረዋል። በሚያዚያ ወር ላይ የ19 ዓመቷ ተማሪ መምህሯ ትንኮሳ እንዳደረሰባት ከተናገረች በኋላ በእሳት በመቃጠሏ ምክንያት ትልቅ ተቃውሞ ሠልፍ ተካሂዶ ነበር።
53813964
https://www.bbc.com/amharic/53813964
የሴቶች መብት፡ የገዛ ሴት ልጁን እየቀረጸ ወሲባዊ ጥቃት የፈጸመው ፍርድ ቤት ቀረበ
በጀርመን ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በኮሎን ከተማ የገዛ ሴት ልጁን በወሲባዊ ጥቃት ሲያሰቃይ የነበረው ሰው ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡
ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በልጆች ላይ የደረሰ ትልቅና ውስብስብ የወሲባዊ ጥቃት ፍርድ ሂደት ተደርጎ ተወስዷል፣ የዚህ ተጠርጣሪ ጉዳይ፡፡ ተጠርጣሪው ስሙ ለሴት ልጁ የወደፊት ጤና ሲባል አልተጠቀሰም፡፡ ሆኖም በሆቴል ቤት ምግብ አብሳይ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ይህ ሰው ሴት ልጁን ወሲባዊ ጥቃት እያደረሰባት በቪዲዮ ከቀረጸ በኋላ በህጻናት ወሲብ ሱስ ለተጠመዱ አስር ሺዎች አባል ለሆኑበት አንድ ሚስጥራዊ የኢንተርኔት ትስስር መድረክ ቪዲዮን ያጋራ ነበር ተብሏል፡፡ ቪዲዮን የሚያጋራው ትሪማ በተሰኘ ምስጢራዊ የትስስር መድረክ ላይ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ፖሊስ ኮሎን በሚገኘው የሰውየው ቤት ላይ ድንገቴ ብርበራ ባደረገበት ወቅት ሌሎች በተመሳሳይ አስነዋሪ ድርጊት የሚፈጽሙ የወንጀለኛ ሰንሰለቶችን እንዲደርስባቸው የረዱ ፍንጮችን ማግኘት ችሏል፡፡ የድንገቴ ብርበራው ለጊዜው በ16 የጀርመን ክልሎች ውስጥ 87 ተጠርጣሪዎች እንዲደርስባቸው መንገድ ጠርጓል፡፡ የሕጻናት ላይ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከ3 ወር እንቦቀቅሎች አንስቶ እስከ 15 ዓመት አዳጊዎች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ያደርሱ እንደነበረ የማያወላዳ የቪዲዮ መረጃ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ይህንን መረጃ ተከትሎ ፖሊስ 50 ሕጻናትን ከወላጆቻቸው በመውሰድ ታድጓቸዋል፡፡ የዚህ ተጠርጣሪ ጉዳይ አሁን በፍርድ ቤት ሂደት ላይ ሲሆን የገዛ ሚስቱ በሰውየው ላይ ምስክርነት ትሰጣለች ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ በዚህ እጅግ አሰቃቂና ፀያፍነቱ ወደር አልባ በተባለ የሕጻናት ወሲባዊ ጥቃት ዙርያ መርማሪ ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ሦስት ጀርመናዊያን ባዩት ነገር የአእምሮ መረበሽ ደርሶባቸው እረፍት እንዲወስዱና የሥነልቦና ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ይህ አባት በገዛ ሴት ልጁ ላይ በትንሹ 61 ጊዜ ጥቃት ፈጽሞባታል፡፡ የፍርድ ሂደቱ 11 ቀናትን እንደሚቆይ እና ተጠርጣሪውም እስከ 15 ዓመት እስር ሊፈረድበት እንደሚችል የጀርመን ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው፡፡ በዚህ የሕጻናት ወሲባዊ ጥቃት ይዘት ያላቸው ቪዲዮዎችን በሚጋሩበት ምስጢራዊ የትስስር መድረክ በትንሹ 30 ሺህ ጥቃት ፈጻሚዎች አባል እንደሆኑበት ተጠቅሷል፡፡ በዚህ ምስጢራዊ የበይነ መረብ ትስስር መድረክ ላይ ተጠርጣሪውና ሌላ አንድ ወንጀለኛ የገዛ ልጆቻቸው ላይ እየተቀያየሩ ወሲባዊ ጥቃት ሲያደርሱ ይታያሉ፡፡
news-53550416
https://www.bbc.com/amharic/news-53550416
ደቡብ ኮሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ ሸሽቶ የሄደው ግለሰብ ኮቪድ-19 አልተያዘም አለች
በኮሮናቫይረስ መያዙ የተጠረጠረው የመጀመሪያው ሰሜን ኮሪያዊ ነጻ መሆንኑን በምርመራ ማረጋገጧን ደቡብ ኮሪያ ገለፀች።
ግለሰቡ ከሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ ኮሪያ ከሦስት ዓመታት በፊት መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ግን ወደ ትውልድ አገሩ ተመልሶ ነበር። ግለሰቡ ከደቡብ ኮሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ የተሻገረው በደቡባዊ ደሴቲ አካባቢ በሚገኝ የቱቦ ማስተላለፊያ ውስጥ በመሹለከለክና በመዋኘት ነበር። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ሰሜን ኮሪያ በኮቪድ-19 የተጠረጠረ ሰው ማግኘቷን አሳውቃ ነበር። • በካንሰር ትሞታለህ ተብሎ ብዙ ያየው ታዳጊ ህይወትና ምኞት የአገሪቱ መንግሥት የዜና አገልግሎት እንደዘገበው በሽታው እንዳለበት የተጠረጠረው ግለሰብ ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ ከድቶ ሄዶ የነበረ ሲሆን በቅርቡ በድንበር በኩል ወደ ሰሜን ኮሪያ ከተመለሰ በኋላ የወረርሽኙ ምልክቶች ታይተውበታል። ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸውን ሰብስበው ከደቡብ ኮሪያ ጋር በምትዋሰነው የድንብር ከተማዋ ኬሶንግ ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ተደርጓል። ሰኞ ዕለት የደቡብ ኮሪያ ጦር የ24 ዓመቱ ወጣት ከሰሜን ኮሪያ ወደ ጋንጋህዋ ደሴት የደረሰው በድንበር አቅራቢያ መሆኑን ገልጿል። ግለሰቡ ወደ ሰሜን ኮሪያ በዋና ከማቋረጡ በፊት ወደ ቢጫ ባህር በሚወስደው የውሃ መውረጃ ቱቦ ውስጥ እየዳሃ መሄዱን አክለው አብራርተዋል። "በኬሶንግ ከተማ ድንገተኛ ነገር ተከስቷል፤ ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ ኮብልሎ የነበረ ግለሰብ በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር ተሻግሮ ወደ አገሪቱ ከገባ በኋላ ቫይረሱ እንዳለበት ተጠርጥሯል" ሲል የየአገሪቱ ዜና ወኪል ኬሲኤንኤ ዘግቧል። ቅዳሜ ዕለት በተካሄደው የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አስቸኳይ ስብሰባ መሪው ኪም ጆንግ-ኡን የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር "ከፍተኛ የአስቸኳይ ጊዜ ሥርዓት" እንዲዘረጋ አዝዘዋል። በተጨማሪም ዜና ወኪሉ እንደዘገበው መሪው ኪም ጆንግ-ኡን በበሽታው የተጠረጠረው ግለሰብ በከፍተኛ ጥበቃ ስር ባለው የድንበር አካባቢ ከደቡብ ወደ ሰሜን ኮሪያ እንዴት አልፎ ሊገባ እንደቻለ እንዲመረመር ያዘዙ ሲሆን፤ ተጠያቂ የሚሆኑ ሰዎች ላይ "ከባድ የቅጣት እርምጃ" እንዲወሰድባቸው አዘዋል። የደቡብ ኮርያ ከፍተኛ የጤና ባለስልጣን የግለሰቡን ጤንነት በተመለከተ ሲናገሩ "ግለሰቡ በኮቪድ-19 መያዙ፣ አልያም ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት እንዳለው አልተመዘገበም" ብለዋል ለዩንሃፕ ዜና ወኪል። ከእርሱ ጋር ቅርበት ያላቸው ሁለት ሰዎች ተመርምረው ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል ብለዋል። • የቀድሞውን የአል-በሽር መንግሥት ለመገልበጥ የሞከሩ ሰዎች የጅምላ መቃብር ተገኘ • በስፔን ወረርሽኙ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል ደቡብ ኮሪያ ከቻይና ቀጥሎ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተከሰተባት ብትሆንም በፍጥነት በቁጥጥር ስር አውላዋለች። ከ50 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ደቡብ ኮርያ በአማካኝ በቀን 50 አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን እያገኘች ሲሆን፤ ከእነርሱም መካከል አብዛኛዎቹ ከሌላ አገር የመጡ ግለሰቦች ናቸው ተብሏል። ሰሜን ኮርያ ግን እስካሁን ድረስ አንድም ሰው በኮቪድ-19 መያዙን አላሳወቀችም። ከደቡብ ኮሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ ሸሽተው የሚሄዱ ሰዎች በብዛት ባይኖሩም ከ2015 ወዲህ 11 ሰዎች መሄዳቸው ተመዝግቧል። አሁን ከደቡብ ኮርያ ወደ ሰሜን ኮሪያ የተሻገረው ግለሰብ ማንነት በሚገባ ከተጣራ በኋላ እውነት መሆኑ ከተረጋገጠ 12ኛ ይሆናል ማለት ነው። ከስድስት ወራት በፊት ቫይረሱ በዓለም ዙሪያ መስፋፋት በጀመረበት ጊዜ ሰሜን ኮሪያ ድንበሮቿን ዘግታ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ወደ ለይቶ ማቆያ ውስጥ አስገብታለች። በዚህ ወር መጀመሪያ ገደማ ላይ መሪው ኪም ጆንግ-ኡን አገራቸው በኮሮናቫይረስ ላይ "አንጸባራቂ ስኬት" እንደተቀዳጀች አሳውቀው ነበር።
news-56506560
https://www.bbc.com/amharic/news-56506560
ለነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት የሆነው የግብጹ መተላለፊያ መዘጋት
በሱዊዝ የመተላለፊያ መስመር ላይ ቆማ የባሕር ላይ ጉዞን ባስተጓጎለችው መርከብ ተነሳ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል።
በመተላለፊያው ዳርቻ ላይ በአሸዋ የተያዘው የመርከቧ ክፍል በመተላለፊያ መስመሩ መዘጋት ሰበብ የድፍድፍ ነዳጅ አቅርቦት ሊስተጓጎል ይችላል በሚል ስጋት ነው ረቡዕ ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የታየበት። በግብጹ የሱዊዝ የባሕር መተላለፊያ ቦይ ዳርቻ ላይ መንቀሳቀስ አቅቷት የዓለማችንን ወሳኝ የባሕር መስመርን የዘጋችውን የጭነት መርከብ ለማንቀሳቀስ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። የግብጽ ባለሥልጣናት እንዳሉት ኤቨር ጊቭን የተባለችው የጭነት መርከብ በመተላለፊያው መስመር ላይ መንቀሳቀስ አቅቷት የቆመችው ማክሰኞ ጠዋት በአካባቢው አሸዋ ያዘለ ከባድ አውሎ ነፋስ በተከሰተበት ጊዜ ነው። በዚህም ሳቢያ ከእስያ ወደ አውሮፓ አስፈላጊ ቁሶችን ጭነው በመተላለፊያው በኩል ለማቋረጥ የመጡ ከቦዩ ሰሜንና ደቡብ በኩል እጅግ በርካታ መርከቦች ማለፊያ አጥተው እንዲቆሙ ተገደዋል። በሰሜናዊ ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘውን ወሳኝ የባሕር ላይ መተላለፊያን ዘግታ የምትገኘው የጭነት መርከብ ባለቤት የሆነው ጃፓናዊ በመርከቧ ምክንያት በዓለም የንግድ ልውውጥ ላይ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ መጠየቁ ተነግሯል። በከባድ ንፋስ ምክንያት መስመሯን ስታ መተላለፊያውን የዘጋችውን መርከብ ለማንቀሳቀስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ የገለጸው የመርከቧ ባለቤት "ነገር ግን የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ" ላይ መሆናቸውን ገልጿል። አስካሁን ቢያንስ በመተላለፊያው በኩል ለማቋረጥ እየጠበቁ ያሉ ከ150 በላይ የጭነት መርከቦች ተሰልፈው እየተጠባበቁ መሆኑ ተነግሯል። ሜዲትራኒያንና ቀይ ባሕርን በሚያገናኘው በሱዊዝ መተላላፊያ ቦይ አውሮፓንና አስያን ለማገናኘት አጭሩ መስመር ሲሆን የዓለማችን 12 በመቶ የሚሆነው የንግድ ጭነት የሚያልፈው በዚሁ በኩል ነው። በአሁኑ ወቅት መርከቧን መንገድ እንድትለቅ ለማድረግ ስምንት ጎታች ጀልባዎች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ይህንን ሥራ እያከናወነ የሚገኘው ኩባንያ መተላለፊያውን ለማስከፈት ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ያስጠነቀቀ ሲሆን የመርከቧን ክብደት ለመቀነስ የጫነቻቸውን ኮንቴይነሮች መቀነስ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ተብሏል። መተላለፊያውን የዘጋችው ኮንቴይነር የጫነችው ኤቨርግሪን የጭነት መርከብ መተላለፊያውን የዘጋችው ኤቨርግሪን የጭነት መርከብ የሚያሳይ የሳተላይት ምሰል የሱዊዝ ቦይ ባለሥልጣናት ሁኔታውን በስፍራው ሆነው ሲከታተሉ ባለፈው ዓመት በየቀኑ መተላለፊያውን በአማካይ 52 የሚደርሱ መርከቦች አቋርጠውታል ሱዊዝ ቦይ 193 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ሦስት ተፈጥሯዊ ሐይቆች አሉት
news-57237157
https://www.bbc.com/amharic/news-57237157
ኮሮናቫይረስ፡ ሙሽሮቹ ኮቪድን ሽሽት ሰማይ ላይ ድል ያለ ሠርግ ደገሱ
ሕንዳዊያን ሙሽሮች ቻርተርድ አውሮፕላን ተጠቅመው በሰማይ ላይ ድል ያለ ሠርግ ደግሰው መነጋገርያ ሆነዋል፡፡
በዚህ የሰማይ ላይ የሠርግ ሥነ ሥርዓት 160 እንግዶች ተጠርተው በልተው፣ ጠጥተው ጨፍረው ተበትነዋል ተብሏል፡፡ ሙሽሮቹ ሠርጋቸውን በሰማይ ለማድረግ የተገደዱት በሕንድ ኮሮና ወረርሽኝ በመዛመቱ ይህን ተከትሎ የወጣው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደቡ ሊያፈናፍናቸው ባለመቻሉ ነው፡፡ በማኅበራዊ የትስስር ገጾች በአያሌው በተጋራው የሠርግ ድግስ ምሥል ላይ እንደታየው እንግዶች በቻርተርድ አውሮፕላን ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ ሲስተናገዱ ነበር፡፡ ሙሽሮቹ ከሕንድ የታሚል ናዱ ግዛት የመጡ ናቸው፡፡ ቻርተርድ አውሮፕላኑም የተነሳው ከዚያው ነው፡፡ ታሚል ናዱ ግዛት የእንቅስቃሴ ገደቦችን የጣለች ሲሆን ማንኛውም የሕዝብ ስብስብ ከ50 ሰው እንዳይበልጥ የሚያስገደድ ደንብ አውጥታለች፡፡ ይህን የሰማይ ላይ ሠርግ ተከትሎ የሕንድ አቪየሽን ባለሥልጣን አዲስ ምርመራ ጀምሯል፡፡ የሕንድ አቪየሽን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ለታይምስ ኢንዲያ ጋዜጣ እንደተናገሩት ሠርጉ የተደረገው በስፓይስጄት አውሮፕላን በረራ ውስጥ ነው፡፡ የስፓይስጄት ቃል አቀባይ ለኢንዲያ ኤክስፕረስ እንደተናገሩት ደግሞ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ተሳፋሪዎች በአንድ የጉዞ ወኪል የተመዘገቡ ሰዎች ኢሆኑ ከማዱራይ ወደ ባንግሎር እንደሚሄዱ ተደርጎ ነው ትኬት የተቆረጠላቸው፡፡ ቃል አቀባዩ ጨምረው እንዳሉት ተሳፋሪዎቹ በኮቪድ ጥንቃቄ ዙርያ መመርያዎች በግልጽ እንደተብራሩላቸውና ይህን የሚቃረን ተግባርም ሆነ ሠርግ አውሮፕላኑ ላይ እንዲደግሱ አልተፈቀደላቸውም ነበር፡፡ ሕንድ 2ኛ ዙር የኮቪድ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ እያናወጻት ሲሆን ትናንት በወጣ መረጃ በወረርሽኙ 300ሺህ ዜጎች መሞታቸው ተዘግቧል፡፡ የጤና ባለሙያዎች ግን በሕንድ በኮቪድና ተያያዥ የጤና ውስብስቦች ውስጥ የሞቱ ዜጎች አንድ ሚሊዮን ሊደርሱ ይችላሉ ይላሉ፡፡ ሆስፒታሎችና አስክሬን ማቃጠያዎች ከሚችሉት በላይ ተገልጋይ በመምጣቱ ከፍተኛ ቀውስ ገጥሟቸዋል፡፡ ሕንድ በኮቪድ ተህዋሲ የተያዙ ከ40 ሚሊዮን ዜጎች በላይ ተመዝግበውባታል፡፡ አስክሬኖች ከመብዛታቸው የተነሳ 24 ሰዓት አስክሬንን የማስወገድ ሥራ ሲደረግ ነበር፡፡ ይህም ሟቾችን በተገቢው ሥነ ሥርዓት ግብአተ መሬታቸውን ለመፈጸም ባለማስቻሉ ሬሳዎች በወንዝ ዳርቻ ተጥለው መታየታቸው ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ አስክሬንን የማቃጠል ሥነ ሥርዓትን ለማካሄድ ወጪው የናረባቸው ሕንዳዊያን የሟች ቤተሰብ ሬሳዎችን በየወዘንዙ ለመጣል እንደተገደዱም ተስተውሏል፡፡ ይህም የሟቾች ቁጥር በአግባቡ እንዳይቆጠር እንዳደረገና በሕንድ የሟቾች ቁጥር መንግሥት ይፋ ካደረገው አሐዝ በብዙ እጥፍ ሊሆን እንደሚችል ያረጋገጠ ነው፡፡ በሕንድ ለሳምንታት ያህል በቀን በተህዋሲው የሚሞቱ ሰዎች ዕለታዊ አሐዝ በሺዎች የሚቆጠር ሆኖ ቆይቷል፡፡
44312444
https://www.bbc.com/amharic/44312444
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብይ አህመድ በመብት ተቆርቋሪዎች ዐይን
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከወጡበት ጊዜ አንስቶ በሱዳን፣ኬንያ እንዲሁም በሳውዲ አረብያ በእስር ላይ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እንዲለቀቁ አድርገዋል።
የእርሳቸውን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በአገር ውስጥም በርካታ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ከእስር ተፈተዋል። የተለያዩ ተግባሮችንም ፈፅመዋል። ሚኒስትሩ በአገሪቱ የተለያዩ ለውጦችን እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል። በሽብርተኝነት የተፈረጀው ግንቦት 7 ዋና ፀሃፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መፈታት እንዲሁም ግጭት በማነሳሳት ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት እንደ ኢሳትና ኦ ኤም ኤን ያሉ ሚዲያዎች ክሳቸው መቋረጥ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እርምጃ ከፍ ያደረገው ይመስላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለት ወራት ውስጥ ያመጧቸውን ማሻሻያዎች በተመለከተ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትናንት በናይሮቢ ውይይት አካሂዶ ነበር፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልሳ ቀናት በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበረው ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ "እስካሁን ድረስ በርካታ ቃል ኪዳኖች ተገብተዋል፤ ነገርግን በተግባር የተፈጸመው እስረኞችን መፍታት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ አይደለም" ይላል፡፡ ግለሰቦቹ የታሰሩት የተለያዩ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን ስላነሱ እንደሆነ የጠቀሰው ጦማሪው እስካሁን ግን ለጥያቄዎቻቸው መልስ አላገኙም፤ መልስ መስጠትም አልተጀመረም ሲል ይገልጻል፡፡ እነዚያ ቃልኪዳኖች በህግ አግባብ ወይም በተቋማዊ ተሃድሶ ተግባራዊ መደረግ ካልጀመሩ ሊቀለበሱ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳለውም ጨምሮ ተናግሯል፡፡ በአምነስቲ የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት አጥኚ የሆኑት ፍሥሀ ተክሌ በበኩላቸው "ቢያንስ ለአስርና ለአስራ አምስት ዓመት ወደ ኋላ የሄደ የሰብዓዊ መብት ጉዞ ላላት አገር ሁሉን ነገር ለማስተካከል ሁለት ወር በጣም ትንሽ ነው፤ ነገር ግን ከተገባው ቃልና ህዝቡ ካለው ተነሳሽነት አንፃር ጅምሩ ጥሩ ነው" ሲሉ የጦማሪውን ሃሳብ ይጋራሉ፡፡ "ሁለት ወሯ የስራው ማስተዋወቂያ እንደመሆኑ ብዙ ባንጠብቅም መሰረት የምንጥልበት ጊዜ ነው" ይላሉ ቃልኪዳኑ የግል ወይስ የፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚገቡት ቃል ኪዳን አወንታዊና አሉታዊ በሆነ መልኩ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡ ጦማሪ በፍቃዱ 'አሁን ለጠቅላይ ሚንስተሩ የሚከብዳቸው የኢትዮጵያን ህዝብ መምራት ሳይሆን ፓርቲያቸውን ራሱ መምራት ነው' ሲሉ ዶክተር መራራ ጉዲና በአንድ ወቅት ያደረጉትን ንግግር በመጥቀስ የእርሳቸው ስጋት የእርሱም ስጋት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ቢሆንም ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህንን ፈተና የመወጣት ሃላፊነት አለባቸው፤ ይህ ደግሞ የሞራል ግዴታም ጭምር ነው ሲል ይገልጻል፡፡ የፓርቲያቸው ድጋፍ በሌለበትና ፓርቲያቸው ባላለው ነገር ላይ ይናገራሉ ብለው እንደማያስቡ የተናገሩት የሰብዓዊ መብት አጥኝው ፍሰሃ "ወክለው አይደለም የሚናገሩት የሚል ማስረጃ እስከሌለ ድረስ በመርህ ደረጃ ፓርቲያቸውን ወክለው ነው የሚናገሩት ብለን እናስባለን" ሲሉ ይገልጻሉ፡፡ የኢህአዴግ አዲሱ አረማመድ ኢህአዴግ ራሱ እንደ ፓርቲ ማሻሻል ላይ ነው ማለት ይከብዳል የሚለው ጦማሪ በፍቃዱ "ኢህአዴግ አራት ቡድኖች ናቸው ያሉት፤ አንዳንዶቹ ቡድኖች በተለይ ደግሞ ኦህዴድ ቀድሞ የነበረው አካሄድ ትክክል አይደለም የሚል አቋም አለው፤ እርሳቸውም የመጡት ከዚሁ ፓርቲ ነው:: ቢሆንም ግን ፓርቲዎች አንድ ዓይነት አቋም ይዘው ቢወጡም ግለሰቦች የተለየ ሃሳብ ሊኖራቸው ይችላል" የሚል እምነት እንዳለው ይናገራል፡፡ አሁን ባለው ርዕዬተ ዓለማዊ አካሄድ መሰረት አልተለወጠም፤ ነገር ግን ቃል የሚገባቸው ማሻሻያዎች በራሱ የርዕዬተ ዓለም ለውጥ ያመጣሉ ብሎ እንደሚገምት በፍቃዱ ይገምታል፡፡ የፖለቲካ እርቅ ስራዎች መሰራት አለበት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት አለበት ፣ አዋጆች መሻሻል አለባቸው፣ አንዳንድ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዳይሰፋ የሚያደርጉ ህገ መንግስታዊ ማዕቀፎችን ለማሻሻል ወደተግባር የሚገበቡበት ጊዜም ነው ሲልም ይጠቅሳል፡፡ "አሁንም ህዝባዊ ተቃውሞዎች የተቀዛቀዙት ጥያቄዎቻችን ይመለሳሉ በሚል ተስፋ እንጂ ጥያቄዎቻቸውን ረስተው አይደለም፤ ይህ ካልሆነ ህዝባዊ ተቃውሞዎች መልሰው ማገርሸታቸው አይቀርም" ሲልም ስጋቱን ገልጸል። በየጊዜው አንደዚህ ብለው ነበር የት አደረሱት እያለ የሚጠይቅ የተነቃቃ ፓርላ ቢኖር ስራቸውን ያግዛቸው ነበር የሚሉት ፍሰሃ ተክሌም ወደኋላ መመለስ እንዳይኖር የሚገቡ ቃል ኪዳኖችን ህጋዊና ተቋማዊ መልክ ማስያዙ ትልቁ መንገድ ነው፤ ይህም በቅርቡ ይጀመራል ብየ አስባለሁ ይላሉ፡፡ አክለውም የፓርላማ አባላት በሙሉ የኔ ናቸውና አንድ ድምጽ ይስጡ የሚለው አስተሳሰብ ከመሰረቱ መቀየር አለበት፤ አገሪቷን ለችግር ከዳረጋት አንዱ ምክንያት የሆነው ተቋማትን ጥቅም የለሽ ማድረግ ነው ይላሉ።
56993237
https://www.bbc.com/amharic/56993237
ቼልሲ ለፍጻሜ መድረሱን ተከትሎ የቻምፒንስ ሊግ ዋንጫ ከእንግሊዝ እንደማያልፍ እርግጥ ሆነ
ቼልሲ በስታንፎርድ ብሪጅ ሪያል ማድሪድን በአሳማኝ ሁኔታ በማሸነፍ ለኢስታንቡሉ የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል።
ቼልሲ በፍጻሜ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ይገጥማል። ይህም የእንግሊዝ ክለቦች ብቻ የሚሳቱፉበት የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ጨዋታ ይሆናል። ከአንድ ሳምንት በፊት ቼልሲ ወደ ሪያል ማድሪድ ተጉዞ ጨዋታው አንድ አቻ መጠናቀቁ አይዘነጋም። የቶማስ ቱሄል ቡድን ምስጋና ለግብ ጠባቂው ኤድዋርድ ሜንዲ ይሁንና ሁለት የካሪም ቤንዜማ ጥሩ አጋጣሚዎችን አድኗል። በጨዋታው ቲሞ ቨርነር በ28 እኛ ሜሰን ማውንት ደግሞ በጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ቼልሲ 2 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል። ቼልሲ በተለይም በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን በበላይነት አጠናቋል። ቼልሲ በአዲሱ አሰልጣኝ ቱማስ ቱሄል ስር እያንሰራራ ይገኛል። በሃቨርት እና በቨርነር ፈጣን እንቅስቃሴ ዕድሜ የተጫነው የሚመስለው ማድሪድ ላይ የበላይነት አሳይተዋል። ግብ ጠባቂው ሜንዲ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን ሲያድን አንቶንዮ ሩዲገርም በጨዋታው የኋላ ደጀንነቱን አስመስክሯል። ጉዞ ወደ ኢንስታንቡል ፍጻሜ ቼልሲዎች ከሲቲ ወቅታዊ አቋም አንጻር ዝቅተኛ ግምት ያገኘ ቡድን በመሆን ወደ ፍጻሜው ቢያቀኑም ዕድላቸውን ለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠቃል። ቼልሲዎች የኋላ መስመራቸው ጠንካራ ሲሆን መሐሉ ደግሞ ውጤተማ የሚባል ነው። አሰልጣኙ ቱሄል እና አምበሉ ቲያጎ ሲልቫ ባለፈው ዓመት ከፒኤስጂ ጋር ለፍጻሜ ደርሰው የነበረ ሲሆን ዘንድሮም በሌላ ቡድን ውስጥ ሆነው ለፍጻሜ ደርሰዋል። ቱሄል ባለፈው ዓመት በባየር ሙኒክ የደረሰባቸውን ሽንፈት ለማካካስ ወደ ቱርክ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዘንድሮ ዌምብሌይ ላይ በኤፍኤ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ቼልሲ 1 ለ 0 ማንችስተር ሲቲን በማሸን ለፍጻሜ ደርሷል። በፍጻሜው ሌስተር ሲቲን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል። አሰልጣኞቹ ምን አሉ? የቼልሲው ቶማስ ቱሄል ለቢቲ ስፖርት "[ተጫዋቾቹ] ማሸነፍ ይገባቸዋል። ሪያል ኳስ ብዙ በመያዙ አስቸጋሪ ቢሆንም የነበረው የመልሶ ማጥቃት ጥሩ ነበርን። የመከላከል ፍላጎት ነበራቸው" ብለዋል። "ሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ነበር። ከመከላከል በተጨማሪ ጎል ማስቆጠር ችለናል። ይህ አስደናቂ ስኬት በመሆኑ ለቡድኑ ትልቅ ደስታ ነው" ብለዋል። የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ለሞቪስታር "ድሉ ይገባቸዋል። በልጆቼ እኮራባቸዋለሁ። ሞክረናል፣ ከፍጻሜውም በአንድ ጨዋታ ብቻ ርቀናል። ቼልሲዎች ጥሩ ተጫውተው በማለፋቸው ውጤቱ ይገባቸዋል" ብለዋል።
news-41884678
https://www.bbc.com/amharic/news-41884678
የሩስያ አብዮት፡ አአአ ከ1917 ጀምሮ የነበሩ አስር የፕሮፖጋንዳ ፖስተሮች
የሩሲያ አብዮት ጣራ የነኩ ዓመፆችን ያስተናገደ ቢሆንም ከፍተኛ ፈጠራም የተስተዋለበት ወቅት ነው።
የአብዮቱን 100ኛ ዓመት ክብረ-በዓል በሚዘከርበት ወቅት፤ እአአ ከ1917 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ ማንቀሳቀስ የቻሉ አስር ፎቶዎች እነሆ፡ የነፃነት "ብድር" የሩሲያ በአንደኛው የዓለም ጦርነት መሳተፍ ከፍተኛ ገንዘብና ጉልበት በመፍሰሱ እአአ ከ1917 ዓ.ም ጀምሮ በነበረው የፊውዳል አገዛዝ ዛር ላይ ከፍተኛ የሆነ ዓመፅን አቀጣጥሏል። የቦሪስ ኩስቶዲየቭ ታዋቂ ስዕል የሆነው አንድ ጠመንጃ የተሸከመ የሩሲያ ወታደር ብዙዎችን ለጦርነቱ ገንዘብ እንዲለግሱ አነሳስቷል። ይህ ፖስተር በየካቲት ወር "የነፃነት ብድር"ን የሚለውን ሀሳብ ለማስተዋወቅ ሲሆን፤ ሁለተኛው የጥቅምት አመፅ እስከተነሳበትም ድረስ ይህ ወታደር በተለያዪ ፓስተሮች ታይቷል። አብዮታዊ ቀናት በአውሮፓውያን መጋቢት እአአ 1917 የሞስኮ ቮስክረሴንስካያ አደባባይና የከተማዋ የፓርላማ ህንፃ ለአብዮታዊ ሰልፎች ማዕከላዊ ቦታዎች ነበሩ። ይህ ፖስተርም የሚያሳየው አብዮቱን አዲስ ምዕራፍ ከፋችነቱን እንዲሁም ህዝቡ ምን ያህል የጠለቀ ስሜትና ጉጉት ለአብዮቱ እንደነበረው ነው። ይህ ሁሉ የተከናወነውም ከጦርነት ጀርባ በተቃራኒ ነው። መሪዎቹ ወንዶች ይህ በእውነቱ ፖስተር አይደለም። በበራሪ ወረቀት ላይ የተሳለው ይህ ስዕል በሩሲያ ውስጥ የነበረውን የስልጣን አደራደር ሰውኛ ምስል በመስጠት ነው። እነዚህ ወንዶችም በሽግግር መንግሰቱ መሪ የሆኑ ታላላቅ የፓለቲካ ሰዎች ናቸው። መሀል ላይ የሚታዩት የአገሪቷ ፓርላማ ሊቀ-መንበር ሚክሄይል ሮዲዚያንኮ ፤ የሀገሪቷ የመጀመሪያው ሶሻሊስት ፓርቲና ሊቀ-መንበር አሌክሳንደር ኬረንስኪ በግራ በኩል ተቀምጠዋል። ከላይ በኩል ያለው ደግሞ የሚያሳየው መሳሪያ የታጠቁ ወንዶች "መሬትና ነፃነት" እንዲሁም "በትግል ብቻ ነው መብት የሚከበረው" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው፤ እንዲሁም ለጊዜው ቦልሸቪካውያን የሉም የሚሉ ናቸው። የተቀየረው ንፋስ ይህ ግራ ዘመም ከሆነው ፓሩስ ከሚባለው ማተሚያ ቤት የተገኘ ሲሆን፤ የተቆረቆረውም ከፀሀፊው ማክሲም ጎርኪ አብዮት በፊት ነበር። የፓስተሮቹን ሀሳብ ያመነጩ የነበሩት እንደ ቭላድሚር ማያኮቭስኪና አሌክሲ ራዳኮቭ የመሳሰሉ ገጣሚያንና አርቲስቶች ናቸው። ከላይ ያለው ምስል አንድ ወታደር ንዑስ ከበርቴን ሲከላከል የሚያሳይ ሲሆን በምስሉ ላይ ያለው መግለጫም " ወታደሩ እነዚህን ነበር ከጥቃት የሚከላከለው" የሚል ነው። ሁለተኛው ምስል ከአብዮቱ በኋላ ሲሆን የምስል መግለጫውም "መሬትና ነፃነት!"፣ዲሞክራሲና ሪፐብሊክ"፣ "ነፃነት" የሚሉ ሲሆን ወታደሩም አሁን እነዚህን ነው የሚደግፈው የሚል የምስል መግለጫም ተሰጥቶታል። የምትወጣው ፀሀይ እአአ በመጋቢት በ1917 ዛር ኒኮላስ ሁለተኛ ተገርስሶ የሀገሪቷ የፓርላማ ተወካዮች የሽግግር መንግስትን መስርተዋል። የፓስተሩ ርዕስም "የህዝብ ድል ማስታወሻ" የሚል ነው። እንደሚያሳየውም በትህትና የተሞላው ዛር ለአብዮታዊ ሀይሎች ስልጣንን ሲያስረክብ ነው። የተመሰለውም በወታደርና በሰራተኛ ነው። ከጀርባ የሚታየው የታውሪድ ቤተ-መንግስት ሲሆን፤ የፓርላማ አባላቶቹም የተገናኙበት ነው። ከላይ የምትታየዉ በመውጣት ላይ ያለቸው ፀሀይም የነፃነት ምሳሌ ናት። በዛን ጊዜ በነበረውም ፖስተሮች የተወደደ ምልክት ነው። ማህበራዊው ፒራሚድ በፓሩስ ማተሚያ ቤት የማያኮቭስኪ ራዳኮቭ የተጣመሩበት ስራ ነው። በቀልድ መልኩ የተሰራው ይህ ፖስተር ዛሩ መጎናፀፊያውን እንደለበሰ ህዝቡን ከላይ ሆኖ ሲያይ የሚያሳይ ነው። ከላይ ወደታችም ፅሁፉ ሲነበብ " እንገዛለን፤ እንፀልይላችኋለን፤ እንዳኛችኋለን፤ እንጠብቃችኋለን፤ እንመግባችኋለን፤ እናንተም ትሰራላችሁ" የሚል ነው። እነዚህ ታዋቂ የሆኑ ምፀታዊ ታሪኮች ከክረምት 1917 በኋላ በዛሩ ኒኮላስ ሁለተኛና በሚስቱ ላይ ያተኮረ ሲሆን በተጨማሪም በፊውዳሉ ስርአትን ለመቃወም ያነጣጠረ ነው። የዘመቻው አካሄድ በ1917ቱ የበልግ ዘመን ሩሲያ የመጀመሪያውን የጠቅላላ ምርጫ ዘመቻ ማካሄድ ጀመረች። ፉክክሩ ጠንክራና የማይነቃነቅ ነበር። በርካታ ድርጅቶች ቢሳተፉበትም ከፍተኛ ቦታ የነበረው ግን የሶሻሊስት አብዮታዊ ፓርቲ ነበር። ፖስተሩ ላይ የሰፈሩት ቃላት ደግሞ '' ጓድ ዜጎች በተወካዮች ጉባኤ ቀን ራሳችሁን ለሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጁ'' የሚል ነበር። "አናርኪ በዴሞክራሲ ይደመሰሳል'' ይህ የእንስሳ እና የአፈታሪካዊ ምስሎች ስብጥር ፖስተር የሊበራል ካዴት ፓርቲ ነው፤ ግዙፉ ድራጎን አናርኪን(የመንግስትን አወቃቃር የሚቃወሙትን) ሲወክል ፈረሰኛው ደግሞ የዴሞክራሲ ተምሳሌት ነው። ሰንሰለቱን መሰባበር የሶሻሊስት አብዮታዊ ፓርቲ የምርጫ ፖሰተር ቀላልና ሰራተኞችና አርሶደሮችን ኢላማ ያደረገ ነበር። '' መብታችሁን የምታገኙት በትግል ብቻ ነው'' ይላል። ያካሄዱት ዘመቻም በጣም ተወዳዳሪ ሲሆን ድላቸውን የተጎነጸፉበት መሪ ቃል ደግሞ ''መሬትና ነጻነት' እንዲሁም " ሰንሰለቱን ሰባብሩ፤ያኔ መላው ዓለም ነጻ ይሆናል'' የሚሉ ነበሩ። ዘግይቶ የተቀላቀለው ፓርቲ የቦልሼቪክ ፓርቲ(አር ኤስ ዲ ኤል ፒ) የፖስተር ጫወታውን የተቀላቀለው ዘግይቶ ነው፤ ይህ የ1917 የምርጫ ዘመቻ ፖስተር '' የአር ኤስ ዲ ኤል ፒን ይምረጡ'' የሚል ብቻ ነው የሰፈረበት። አር .ኤስ .ዲ. ኤል. ፒ የሩሲያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ሌበር ፓርቲ ምህጻረ ቃል ነው። በሩሲያ ቋንቋ ግን አር.ኤስ.ዲ.አር.ፒ ነው። ህዳር 1917 የእርስ በእርስ ጦርነት ሲቀሰቀስ ቦልሼቪክም በፖስተር የሚመራውን የሶቪየት የፕሮፖጋንዳ ዘዴ ተቀላቀለ። ማያኮቪስኪ እና ራዳኮቭን የመሳሰሉ አርቲስቶችን ያቀፈ ቡድንም ዝነኛውን 'ሮስታ ዊንዶው' የተሰኘ መለያ ሥም ፈጠረ። ፖስተሮቹ ቀለል ያሉ፣ አጭር፣ ቀጥተኛና ግልጽ መልዕክት የሰፈረባቸው ነበሩ።በሂደትም የሶቪየት መገለጫና የዓለማቀፍ የፖስተር ዲዛይኖች ተመሳሌቶች ሆኑ። የሩሲያ ዘመናዊ ታሪክ ማዕከላዊ ሙዚየም ዳይሬክተር ቬራ ፓንፊሎቫ ነበረች ከቢቢሲ የሩሲያ አገልግሎት አሌክሳንድሪያ ሴምዮኖቭ ጋር የተነጋገረቸው።
news-53945831
https://www.bbc.com/amharic/news-53945831
የሊቢያ ጦርነት፡ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ሊቢያ ውስጥ ጥቃት መፈፀሟን ቢቢሲ አረጋገጠ
ቢቢሲ፤ ዩናይትድ አረብ ኤምቴትስ [ዩኤኢ] ሊቢያ ውስጥ በወሰደችው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት 26 ያልታጠቁ ወታደሮችን መግደሏን የሚያረጋግጥ መረጃ አግኝቷል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ባለፈው ጥር ሲሆን በሊቢያዋ መዲና ትሪፖሊ በሚገኝ አንድ የወታደር ማሠልጠና ካምፕ ላይ ነበር። በወቅቱ ትሪፖሊ እራሱን የሊቢያ ብሔራዊ ጦር ብሎ በሚጠራው ኀዓይል ከበባ ውስጥ ነበረች። ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ግን ጥቃቱን አልፈፀምኩም ስትል ታስተባብላለች። ኤምሬትስ ጥቃቱ የተሰነዘረው በአገሪቱ ወታደሮች ነው ብትልም ወታደራዊ ካምፑ ላይ የወረደው ሚሳኤል 'ብሉ አሮው' የተሰኘ ቻይና ሰራሽ መሣሪያ እንደሆና መረጃዎች ይጠቁማሉ። ቢቢሲ አፍሪካ አይ እና የቢቢሲ አረብኛ የዘገባ ክፍል ባልደረቦች ማረጋገጥ እንደቻሉት ዊንግ ሉንግ ሁለት [Wing Loong II] የተባለው ሰው አልባ አነስተኛ በራሪ [ድሮን] በወቅቱ ሊቢያ ውስጥ ጥቅም ላይ ይውል የነበረው አል ካዲም በተባለው ካምፕ ውስጥ ብቻ ነው። ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ ሊቢያ ውስጥ ምንም ዓይነት ወታደራዊ እርምጃ ወስጄ አላውቅም ስትል ታስተባብላለች። ነገር ግን ሊቢያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪዎችን እንደምትደግፍ ትናገራለች። ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ ለቢቢሲ ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥባለች። ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት 50 ያክል ታዳጊ ወታደሮች በደቡባዊ ትሪፖሊ በሚገኝ አንድ ካምፕ ውስጥ ልምምድ በማድረግ ላይ ነበሩ። ያለምንም ማስጠንቀቂያ ማሠልጠኛ ማዕከሉ ላይ የወረደው ሚሳዔል 26 ታዳጊ ሠልጣኞችን ሲገድል በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። በወቅቱ ወታደሮች ያልታጠቁ እንደነበሩ ተነግሯል። ከተረፉት መካከል የ20 ዓመቱ አብዱል ሞዊን አንዱ ነው። "የነበረውን ሁኔታ በቃላት ለመግለፅ ከባድ ነው" ሲል ለቢቢሲ የተፈጠረውን ያስረዳል። "ሁሉም በየቦታው ወድቆ ሲያቃስት ነበር። ሰውነታቸው የተበታተነ ጓደኞቼን አይቻለሁ፤ በጣም አሰቃቂ ነበር።" ጥቃቱ ከደረሰ ሰባት ወራት ቢያልፉትም ለደረሰው አደጋ ኃላፊነት የወሰደ ማንም አካል የለም። የሊቢያ ብሔራዊ ጦር ጄኔራል ካሊፋ ሃፍጣር በወቅቱ ስለጥቃቱ ምንም እንደማይውቁ ጥቅሰው፤ ምናልባት እዚያ ካምፑ ውስጥ በተነሳ ጠብ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው ነበር። ቢቢሲ ምን አገኘ? ቢቢሲ ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ጥቃቱ የተፈፀመው እጅግ በረቀቀ የጦር መሣሪያ ነው። ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ የተገኙ ምስሎችን የመረመረው ቢቢሲ፤ 'ብሉ አሮው 7' የተባለው ሚሳዔል ጥቅም ላይ እንደዋለ ማረጋገጥ ችሏል። አልፎም ዊንግ ሉንግ 2 የተባለው ድሮን ሚሳዔሉን ተሸክሞ ጥቃቱን እንዳደረሰ ማረጋገጥ ችለናል። በወቅቱ ይህ ድሮን ይንቀሳቀስበት የነበረው ብቸኛው ካምፕ አል ካዲም የተሰኘው ሲሆን ይህ ወታደራዊ ኃይል በጄኔራል ሃፍጣር ቁጥጥር ሥር ያለ ነው። ቢቢሲም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት ያገኙት ማስረጃ እንደሚጠቁመው እዚህ ካምፕ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ድሮኖች ንብረትነታቸው የዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ ነው። ባለፈው ዓመት ኤምሬትስ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉትን ሚሳዔሎችና ድሮኖች ወደ ሊቢያ ልካለች ሲል የተባበሩት መንግሥታት መውቀሱ አይዘነጋም። ሌላኛው ቢቢሲ ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ግብፅ ከሊቢያ ድንበር ጋር የሚያዋስናትን ስትራቴጂካዊ ቦታ ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ እንድትጠቀምበት ፈቃዳለች። አልፎም የግብፅ ንብረት ያልሆኑ የጦር ጄቶች በግብፅ አየር ሲንቀሳቀሱና ሲዲ ባራኒ በተሰኘው የግብፅ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ማረፋቸውን የሳተላይት ምስሎች አሳይተዋል። እኒህ የጦር ጄቶች የኤምሬትስ ንብረት መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። የግብፅ መንግሥትም ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም። በሊቢያ ጉዳይ እጃቸውን ጣልቃ ያስገቡት ግብፅና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ብቻ አይደሉም። ቱርክም ሊቢያ ውስጥ የተባበሩት መንግሥታትን ስምምነት የሚጥስ ተግባር መፈፀሟ ተረጋግጧል። በቱርክ መንግሥት ድጋፍ የሚያገኘውና በተባበሩት መንግሥታት እውቅና ያለው መንግሥት የጄኔራል ሃፍጣሪን ጦር ከትሪፖሊ ማስወጣት ችሏል።
news-46669931
https://www.bbc.com/amharic/news-46669931
ባልተወለዱ ልጆች ላይ የሚከናወን የአከርካሪ ቀዶ ጥገና የእንግሊዝ የብሔራዊ ጤና ሽፋን አካል ሊሆን ነው
ሰሞኑን ባልተወለዱ ልጆች ላይ የሚከናወን የአከርካሪ ቀዶ ጥገና የብሔራዊ ጤና ሽፋን አካል ሊሆን እንደሆነ የእንግሊዝ የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ቀዶ ጥገናው ልጆቹ በማህፀን ላይ እያሉ የአከርካሪን ህዋሳት መጠገን የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል። ይህም የመራመድ ችሎታቸውን ለማሻሻልና በህፃናት ላይ ከሚከሰቱ የአከርካሪ ችግሮች ጋር ተያይዘው የሚመጡ የጤና እክሎችን ለማሻሻል ያስችላል ተብሏል። ባልተወለዱ ህፃናት ላይ የሚደረገው የአከርካሪ ቀዶ ጥገና በብሔራዊ የጤና ሽፋን ካገኙት መካከል ሲሆን ከሚያዝያ ጀምሮም ተግባራዊ ይሆናል። •ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና •አርበኞች ግንቦት ሰባት ፈርሶ አዲስ ፓርቲ ሊመሰረት ነው በእንግሊዝ በየዓመቱ 200 የሚሆኑ ህፃናት ከአከርካሪ ችግሮች ጋር ተያይዞ የሚወለዱ ሲሆን፤ ይህም በቀሪው ህይወታቸው የእግር መሸማቀቅን እንዲሁም የመማር ችግሮችን እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከዚህ ቀደም ህክምናው የሚሰጠው ልጆቹ ከተወለዱ በኋላ የነበረ ሲሆን፤ በማህፀን ላይ እያሉ መሰጠቱ ለረዥም ጊዜ ጤናቸውን ከማሻሻሉ በተጨማሪ መንቀሳቀስ እንደሚያስችላቸው ተገልጿል። ባልተወለዱ ልጆች ላይ የሚደረገው የአከርካሪ ቀዶ ጥገና ለመጀመሪያ ጊዜ በእንግሊዝ ላይ የተከናወነው በዚህ ዓመት ሲሆን፤ በለንደን በሚገኝ የዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ውስጥ በማህፀን ላይ ባሉ ሁለት ልጆች ላይ ነው የተካሄደው። በቀደመው ጊዜም በማህፀን ላይ እያሉ ህክምናውን ለማግኘት ወደ ውጭ ሀገራት ይጓዙ ነበር ተብሏል። በህፃናት ላይ የሚከሰተው የአከርካሪ ችግር በምን እንደሚመጣ በግልፅ ባይታወቅም የፎሊክ አሲድ እጥረት ተጋላጭነቱን እንደሚጨምር ባለሙያዎች ይናገራሉ። "ምንም እንኳን በማህፀን እያሉ የሚደረገው ቀዶ ጥገና ለሁሉም አይነት እርግዝና የማይመከርና እንዲሁም የአከርካሪ የጤና እክልን ሙሉ በሙሉ ይፈውሳል ባይባልም የብዙ ህፃናት የጤና ሁኔታ ስለሚያሻሽል ዜናውን በይሁንታ ነው የተቀበልነው" በማለት ቻሪቲ ሻይን የተባለው ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ኬት ስቲል ይናገራሉ።
news-42233455
https://www.bbc.com/amharic/news-42233455
እውነታው ሲጋለጥ፡ እውን 90 በመቶ ዚምባብዌያውያን ሥራ አጥ ናቸው?
በእንግሊዝ ቤተ-ክርስትያን ሊቀ-ጳጳስ የሆኑት ጆን ሴንታሙ በዚምባብዌ 90 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ሥራ አጥ ናቸው ሲሉ በቅርቡ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።
የሃገሪቱ ስታትስቲክስ ቢሮ 2014 (እአአ) ላይ ባወጣው መረጃ መሠረት ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በላይ ከሆኑ ዚምባብዌያውያን መካከል 11.3 በመቶ የሚሆኑት ሥራ አጥ ናቸው ይላል። ይህ መረጃ ግን ከሚሰማው እጅግ ዝቅ ያለ ለመሆኑ ማስረጃ የሚሆነው ደግሞ በጎረቤት ሃገር ደቡብ አፍሪካ ከ15 ዓመት በላይ ከሆኑት ወጣቶች 24.9 በመቶ የሚሆኑት ሥራ አጥ መሆናቸው ነው። አዳዲስ ሕግጋት የስታትስቲክስ ቢሮው እንደሚገልፀው የ2014 አሃዝ ዝቅ ብሎ ሊታይ የቻለበት ምክንያት መረጃው በግብርና ሥራ ላይ የተሰማሩትን ዜጎች ሥራ ያላቸው አድርጎ ስለመዘገበ ነው። በአዲሱ የመረጃ አሰባሰብ ህግ መሠረት ግን በመሰል የሥራ መስክ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ሥራ አጥ ተብለው ነው የሚመዘገቡት ይላል ቢሮው። ቢሮው በዚህ ዓመት ተመሳሳይ የመረጃ ስብሰባ ማካሄድ ቢኖርበትም በአቅም እጥረት ሳቢያ ለሚቀጥለው ዓመት ማቆየቱንም አስታውቋል። የዓለም አቀፉ የሠራተኛ ድርጅት (ኤይኤልኦ) በበኩሉ በ2016 በሰበሰብኩት መረጃ በዚምባብዌ ከ15 ዓመታት በላይ ሥራ አጥ የሆኑት 5.2 በመቶ ብቻ ናቸው ይላል። ያልተመዘገበ ምጣኔ ሃብት ፎርብስ የተሰኘው የቢዝነስ ጋዜጣ በ2017 ወርሃ መጋቢት ባወጣው እትሙ "ሮበርት ሙጋቤ እንኳን ደስ ያሎት፡ ዚምባብዌ ውስጥ ሥራ አጥነት 95 በመቶ ደረሰ" ሲል መዘገቡ ይታወሳል። ዓምደኛው 95 በመቶ የሚሆኑ ለሥራ ብቁ የሆኑ የዚምባብዌ ዜጎች ሥራ የለሽ ሆነው ተቀምጠዋል ሲል ሃሳቡን ያሰፍራል። ነገር ግን መረጃው ከየት መጣ? ዓምደኛው መረጃውን ከዘ ኒው ዮርክ ታይምስ እንዳገኘው ይናገራል። ነገር ግን ኒው ዮርክ ታይምስ አሃዙ መደበኛ ባለሆነ ሥራ የተሰማሩ ሰዎችን ቁጥር የሚያሳይ እንጂ የሥራ አጥነት እንዳልሆነ ያስረግጣል። አሃዙም ከዚምባብዌ ስታስቲክስ ቢሮ እንደተገኘ ፅፏል። መደበኛ ባልሆነ ሥራ ላይ የተሰማሩ መደበኛ ክፍያ የሌላቸው፣ በቤተሰብ ሥራ ላይ የተሰማሩ፣ የዓመት እረፍት መጠየቅ የማይችሉ ግለሰቦች እንደሆኑ ነው ቢሮው የሚያትተው። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዋ ፕሮፌሰር ካትሪን ቡን ለአሃዞቹ መለያየት ዋነኛው ምንጭ መደበኛ ባልሆነ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች መብዛት ነው ይላሉ። "በመደበኛ ሥራ ላይ ተሰማርተው በየወሩ ደሞዝ የሚከፈላቸውና ግብር የሚቆረጥባቸው ሰዎችን ብቻ የምንቆጥር ከሆነ ከፍተኛ የሥራ አጥነት አሃዝ ማግኘታችን እርግጥ ነው" ይላሉ ፕሮፌሰሯ። መደበኛ ወዳልሆነው የሥራ መስክ ስንመጣ ግን በተቃራኒው ዝቅ ያለ አሃዝ ነው የምናገኘው ሲሉ ይሞግታሉ። ለምሳሌ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በአማካሪነት የሚሰራ ሰው ሥራ ያለው ሆኖ ላይመዘገብ ይችላል በማለት ካትሪን ያስረዳሉ። የመንገድ ላይ ንግድ የዚምባብዌ ሠራተኛ ማሕበራት ኮንግረስ የሥራ አጥነት አሃዙ 90 በመቶ ደርሷል ሲል ከተናገረ በኋላ፤ ተቃዋሚው ሞርጋን ሻንጋራይ "ሙጋቤ ሃገሪቱን ወደ መንግድ ላይ ንግድ ሥፍራነት ቀየሯት" ሲሉ መውረፋቸው ይታወሳል። በመንገድ ላይ ንግድ የተሰማሩ ሰዎች ሥራ አጥ ናቸው? 90 በመቶ ሥራ አጥ ተብሎ ከተመዘገበ በመንገድ ላይ ንግድ የተሰማሩ ሰዎች ሥራ አጥ ወደሚባለው ምድብ ውስጥ መግባታቸው እሙን ነው። የሥራ አጥነት መመዘኛን ለሃገራት የሚያወጣው የዓለም አቀፉ የሠራተኛ ድርጅት (ኤይኤልኦ) ዚምባብዌ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነው ነዋሪ፤ ሥራ አጥ የሚባለው ከሃቅ የራቀ እንደሆነ ይዘግባል። ነገር ግን በግብርና ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ከተካተተቡት በእርግጠኝነት ከ11.3 በላይ ነው ይላል። አብዛኛዎቹ ዜጎች መደበኛ ባልሆነ የሥራ መስክ ላይ መሰማራታቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ አይኤልኦ ዚምባብዌ የሥራ አጥ ቁጥርን ከመቀነስ በላይ የዜጎቿን ሕይወት ማሻሻል ላይ ብትሰራ የተሻለ ነው ሲል ይመክራል።
news-53711891
https://www.bbc.com/amharic/news-53711891
ኮሮናቫይረስ፡በሕንድ በኮቪድ ጊዜያዊ ሆስፒታል ባጋጠመ የእሳት አደጋ ቢያንስ አስር ህሙማን ሞቱ
በደቡብ ምስራቅ ሕንድ ቪጃያዋዳ በሚገኝ የኮቪድ-19 ጊዜያዊ ሆስፒታል በተነሳ እሳት ቢያንስ አስር ህሙማን መሞታቸው ተገለፀ።
እሳቱ ህሙማኑ ሕክምና በሚከታተሉበት 'ስዋርና ፓላስ' ጊዜያዊ የኮቪድ ማዕከል እሁድ ጠዋት መነሳቱ ተገልጿል። ባለሥልጣናት እንዳሉት እሳቱን በግማሽ ሰዓት ውስጥ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን፤ ከአደጋው የተረፉ ህሙማንም ወደ ሌላ ሆስፒታል ተዛውረዋል። የቪጃያዋዳ ፖሊስ ኮሚሽነር ቢ ስሪኒቫሱሉ፤ በሆስፒታሉ ውስጥ ከ30 በላይ ሰዎች እንደነበሩ ገልፀው የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ናርንድራ ሞዲም ተጎጂዎችን በፀሎታቸው እንደሚያስቧቸው እና አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው ከሚመለከታቸው ጋር መነጋገራቸውን በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። የአንድራ ፓራዲሽ ግዛት ሚኒስትር ጃጋን ሞሃን የተጎጂ ቤተሰቦች 66 ሺህ 670 ዶላር (5 ሚሊየን ሩፒስ) ካሳ እንደሚሰጣቸው አስታውቀዋል። የአደጋውን ምክንያት ለማጣራትም ምርመራ እየተካሄደ ነው ተብሏል። በቀናት ውስጥ በኮቪድ-19 የህክምና ማዕከል ውስጥ አደጋው ሲከሰት ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ሐሙስ እለት በአህሜዳባድ በሚገኝ የኮቪድ -19 ሆስፒታል ውስጥ በፅኑ ሕሙማን ክፍል በተነሳ የእሳት አደጋ ስምንት ህሙማን መሞታቸው ይታወሳል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ሕንድ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር በዓለማችን ካሉ አገራት በሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን እስካሁን ከ2.1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል። ከ43 ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። እሁድ ዕለት ብቻ 64 ሺህ ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህም በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው ተብሏል።
news-44050594
https://www.bbc.com/amharic/news-44050594
ኢቦላ ዳግም አገረሸ
በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኢቦላ ዳግም ማገርሸቱ የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቀ።
ለመጨረሻ ጊዜ የኢቦላ ወረርሽኝ በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተው በ2017 ሲሆን አራት ሰዎችን ገድሏል ኢቦላ መመለሱ የታወቀው በሰሜን ምዕራብ ኮንጎ የ17 ሰዎች ሞት ከተሰማና የሁለቱ ሞት በኢቦላ ቫይረስ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። ቦኮሮ በተባለችው ከተማ የተከሰተው ይህ ወረርሽኝ ዳግም የተከሰተው በአገሪቱ አራት ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ መሆኑ ነው። በአውሮፓውያኑ 2014 በተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ በጊኒ፣ በሴራሊዮን እና በላይቤሪያ ብቻ አስራ አንድ ሺህ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም የሚመሩት የዓለም የጤና ድርጅት እንዳስታወቀው የኢቦላ ዳግም ማገርሸት የተረጋገጠው ከአምስት ታማሚዎች በሁለቱ ላይ ናሙና ተወስዶ በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤት ነው። "ከአጋሮቻችን ጋር በቅልጥፍናና በተቀናጀ መልኩ በመሥራት በጊዜ የበሽታውን ሥርጭት መግታት ይኖርብናል" ብለዋል የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፒተር ሰላማ። ድርጅቱ አንድ ሚሊዮን ዶላር ከአስቸኳይ ጊዜ ፈንድ ወጪ በማድረግና 50 የጤና ባለሞያዎችን ወደ ሥፍራው በማሠማራት ምላሽ መስጠቱንም አሳውቋል። በኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ሲቀሰቀስ ይህ ለዘጠነኛ ጊዜ ነው። ቫይረሱ ለመጀመርያ ጊዜ በአገሪቱ የተገኘው እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ አቆጣጠር በ1976 ሲሆን ያን ጊዜ አገሪቱ ዛየር በሚል ስም ትጠራ ነበር።
news-56674362
https://www.bbc.com/amharic/news-56674362
ልዑል ፊሊፕ፡ የዓለም መሪዎች በልዑል ፊሊፕ ሞት ሐዘናቸውን እየገለጹ ነው
የልዑል ፊሊፕን ሞት ተከትሎ የዓለም መሪዎች የተሰማቸውን ሐዘን ለንጉሣዊው ቤተሰብ እየገለጹና ትውስታቸውን እያጋሩ ነው።
የባኪንግሃም ቤተመንግሥት ዛሬ እንዳስታወቀው የንግሥት ኤልዛቤት ባለቤት ልዑል ፊሊፕ በ99 ዓመታቸው አርፈዋል። ልዑሉ ንግሥቲቱን በዓለም ዙሪያ ባደረጓቸው በመቶዎቹ በሚቆጠሩ የባሕር ማዶ ጉብኝቶች ላይ አብረዋቸው ተገኝተዋል። "ዓለማችን ከዚህ በኋላ ፈጽማ የማታየው ትውልድ መገለጫ ነበሩ" በማለት የተሰማቸውን ሐዘን የገለጹት የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ናቸው። የቀድሞዋ የአውስትራሊያ መሪ ጁሊያ ጊላርድ ደግሞ ልዑሉ "የተግባር ሰው ከመሆናቸው ጎን ለጎን ተጫዋችም ነበሩ" ሲሉ አስታውሰዋቸዋል። የቤልጂየሙ ንጉሥ ፊሊፕ ደግሞ የሐዘን መግለጫቸውን ለንግሥቲቱ በግል የላኩ ሲሆን፤ ግርማዊነታቸው አመቺ ጊዜ ሲያገኙ ሊያናግሯቸው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። "ማልታን ቤታቸው አድርገው በተደጋጋሚ ሲመጡ በነበሩት በልዑል ፊሊፕ ሞት ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶናል። ሕዝባችንም ትተውት ያለፉትን ትዝታ ዘወትር ያስታውሳል" ሲሉ የማልታው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮቤርት አቤላ ጽፈዋል። "በዚህ ከባድ ሰዓት ውስጥ ሐሳቤና ጸሎቴ ከእርስዎና ከዩናይትድ ኪንግደም ሕዝብ ጋር ነው" ሲሉ ሊቱዋንያው ፕሬዝዳንት ጊታናስ ኑሴዳ ለንግሥቲቱ ጽፈዋል። የስዊዲኑ ንጉሥ ካርል ጉስታፍ "ልዑሉ ትልቅ ዋጋ የምንሰጠው ግንኙነት የነበረን ሲሆን፤ ለበርካታ ዓመታት የቤተሰባችን ታላቅ ወዳጅ ነበሩ" ብለዋል። የኔዘርላንድስ ንጉሣዊ ቤተሰብ ልዑል ፊሊፕን በታላቅ አክብሮት እንደሚያስታውሳቸው ገልጾ "ልዑሉ ሕይወታቸውን የብሪታኒያን ሕዝብና በርካታ ተግባራትና ኃላፊነቶችን ለመወጣት አውለውታል። ህያው ስብዕናቸው የማይረሳ ትውስታን ትቷል" ብለዋል። የኒው ዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርንም "በኒው ዚላንድ ሕዝብና መንግሥት ስም ልባዊ ሐዘኔን ለግርማዊነታቸውና ለመላው ንጉሣዊ ቤተሰብ መግለጽ እወዳለሁ" ሲሉ የሐዘን መግለጫቸውን አስተላልፈዋል። የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲም ሐዘናቸውን ኀብሪታኒያ ሕዝብና ለንጉሣዊው ቤተሰብ ገልጸው፤ ልዑሉ "የላቀ ወታደራዊ ሙያና በማኅበረሰብ አገልግሎትም ውስጥ ቀዳሚ ነበሩ" ሲሉ አስታውሰዋቸዋል። የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የኤደንብራውን መሥፍን "የቤተሰብ እሴቶች ከፍታ እንዲሁም የእንግሊዝ ሕዝብ እና የዓለም ሕዝብ አንድነት ተምሳሌት " ሲሉ ገልፀዋቸዋል። አክለውም " የሰው ልጅ በሰላም አብሮ እንዲኖር " አበክረው መስራታቸውን ገልፀዋል። ከአፍሪካ መሪዎች መካከል ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር ውጣ ውረድ የበዛበት ግንኙነት ያሳለፈችው ዚምባብዌ እንዲሁም በቅርቡ መሪዋን ያጣችው ታንዛንያ የሐዘን መግለጫ አስተላልፈዋል። አዲሷ የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚኣ ሱሉሁ ሐሳን "ጥልቅ የሆነ ሐዘናቸውን" ባለቤታቸውን ላጡት ለንግሥቲቱ፣ ለንጉሣዊው ቤተሰብና ለዩናይትድ ኪንግደም ሕዝብ ገልጸዋል። ጨምረውም "በዚህ አስቸጋሪ የሐዘን ጊዜ አብረናቸው እንቆማለን" ብለዋል። ታንዛኒያ ባለፈው መጋቢት ወር የ61 ዓመቱን ፕሬዝዳንቷን ጆን ፖምቤ ማጉፉሊን በሞት መነጠቋ ይታወሳል። የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ልዑሉ "ለአገራችንና ለዓለም ማኅበራዊ መስተጋብር በርካታ አስተዋጽኦን አብርክተዋል" በማለት ልዑሉ የታላቅ አላማና መርህ ሰው በመሆን "ለሌሎች መልካም ነገሮችን በማድረግ ኃላፊነታቸውን የሚወጡ ነበሩ። እኛም በንግሥታችን ህይወት ውስጥ አንድ ምሰሶ እንደሆኑ በክብር እንዘክራቸዋልን" ብለዋል። ልዑሉ "እንከን አልባ የሕዝብ አገልጋይ ነበሩ። እስራኤልም ሆነ ዓለም በእሳቸው ሞት በጣሙን ይጎዳሉ" ያሉት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ናቸው። በ1969 (እአአ) ያረፉት የልዑሉ እናት የባተንበርጓ ልዕልት አሊስ ቀብራቸው የተፈጸመው ኢየሩሳሌም ውስጥ በሚገኘው በማሪያም መቅደላዊት ቤተክርስቲያን ውስጥ ነበር።
news-55082524
https://www.bbc.com/amharic/news-55082524
የሳተላይት ምስል፡ አክሱም አየር ማረፊያ ከጥቃቱ በፊት እና በኋላ
ከመቀለ ከተማ በሰሜን አቅጣጫ የሚገኘው የአክሱም አየር ማረፊያ በትግራይ ውስጥ ቁልፍ ስፍራ መሆኑ ይታመናል።
ይህ የሳተላይት ምስል የአየር ማረፊያው መንደርደሪያ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ የተገኘ ነው መንግሥት አየር ማረፊያውን ከመቆጣጠሩ በፊት የትግራይ ኃይሎች የአየር ማረፊያው መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል። በትግራይ የቴሌኮም አገልግሎቶች ስለተቋረጡ በስፍራው ምን እየተከናወነ እንደሆነ ማረጋገጥ ከባድ ሆኖ ቆይቷል። የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ያስራጩትን ተንቀሳቃሽ ምስል፣ የሳተላይት ምስሎችን ጋር በማዛመድ በአክሱም አየር ማረፊያ መቼ ምን እንደተከሰተ ለማጣራት ጥረት ተደርጓል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አክሱም አየር ማረፊያን መቆጣጠሩን ከማስታወቁ በፊት አየር ማረፊያው በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ቆይቷል። በዚህም ሐሙስ ኅዳር 10 የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለሮይተርስ ዜና አገልግሎት አክሱም ከተማ በቁጥጥራቸው ሥር እንደምትገኝ ተናግረው ነበር። ይህ ግን የአክሱም አየር ማረፊያን እንደሚጨምር ገልጽ አይደለም። "አክሱም ከእኛ ጋር ነች- ግን አክሱምን ለመቆጣጠር የተላከ ጦር አለ- ጦርነት አለ" ብለው ነበር ደብረጽዮን። የፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት ከተሞችን ከህወሓት ኃይሎች ሲያስለቀቅ የህወሓት ኃይሎች በከተሞቹ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እያደረሱ እየሸሹ እንደሆነ አስታውቋል። እሑድ ኅዳር 13 የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን የአክሱም አየር ማረፊያ አውሮፕላን መንደርደሪያ ተቆፋፍሮ እና በድንጋይ ተሞልቶ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አሳይተዋል። መንግሥት "ለአክሱም ከተማ እና ለአከባቢዋ ከፍተኛ ጥቅም ያስገኝ የነበረውን አየር ማረፊያ እንዲወድም ተደርጓል" ሲልም ከሷል። የኢትዮጵያ መንግሥት "መረጃ ማጣሪያ" ገጽም ጉዳቱን የሚሳይ ቪዲዮ አውጥቷል ይህ ለማረጋገጥም ቢቢሲ የሳተላይት ምስሎችን ተመልክቷል። የሳተላይ ምስሎቹ የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት አክሱም አየር ማረፊያን ከመቆጣጠሩ በፊት እና ከተቆጣጠረ በኋላ ያለውን ልዩነት ያመለክታል። ከዚህ በተቻ ያለው ምስል የአክሱም አየር ማረፊያ ሐሙስ ኅዳር 10 ያሳያል። የሳተላይት ምስሉ ኅዳር 10 አክሱም አየር ማረፊያ ጉዳት እንዳልደረሰበት ያሳያል። የሳተላይት ምስሉ ኅዳር 10 አክሱም አየር ማረፊያ ጉዳት እንዳልደረሰበት ያሳያል። ሰኞ ኅዳር 14 የተነሳው የሳተላይ ምስል ግን በአየር ማረፊያው ላይ ጉዳት መድረሱን ያስመለክታል። ምስሉ የአየር መንገዱ አውሮፕላን መንደርደሪያ አስፋልት አውሮፕላን ማረፍ እንዳይችል ሦስት ቦታዎች ላይ ተቆፍሮ የሚታይ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም አውሮፕላን ማረፊያው መንደርደሪያ በድንጋይ ተሞልቶ ይታያል። ይህም ቀደም ባለው ቀን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ያሉትን የሚያረጋግጥ ሆኗል። ሰኞ ኅዳር 14 የተነሳው የሳተላይ ምስል በአየር ማረፊያው መንደርደሪያ ላይ ጉዳት መድረሱን ያስመለክታል። የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ግን ህወሓት በአየር ማረፊያው ላይ ጉዳት አለማድረሳቸውን አስተባብለዋል። ይሁን እንጂ የአገር መከላከያ ሠራዊት የወደፊት ጉዞን ፍጥነትን ለመግታት እክል ማድረጋቸውን አምነዋል። ከአየር ማረፊያው ጋር ተያይዘው የወጡ ሐሰተኛ ምስሎች በትግራይ የቴሌኮም አገልግሎቶች ተቋርጠው ስለሚገኙ በስፍራው እየተፈጠረ ያለውን በትክክል የሚያመለክቱ ምስሎችን ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። ይህም ሐሰተኛ ምስሎች በስፋት እንዲሰራጩ ምክንያት ሆኗል። መንግሥት አክሱም ከተማን እና አየር ማረፊያውን መቆጣጠሩን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የመንግሥት ደጋፊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች የቆዩ ወይም አክሱም አየር ማረፊያ ያልሆኑ ምስሎችን ሲያጋሩ ነበር። ከአሁኑ ግጭት ጋር ግነኙነት የሌላው የኢትዮጵያ ወታደር ምስል በአክሱም አየር ማረፊያ እንደተነሳ ተደርጎ በስፋት ተጋርቷል። ይህም ብቻ ሳይሆን የአየር ማረፊያው ተጓዞች መቆያ ቦታ (ተርሚናል) ጉዳት ደርሶበታል በሚል ከታች ያለው ምስል በስፋት ተጋርቷል። ይህ ከዚህ በታች ያለው ምስል የተወሰደው እአአ 2014 ላይ ጉዳት የደረሰበት የሊቢያ አየር ማረፊያ ነው። ምስል የተወሰደው እአአ 2014 ላይ ጉዳት የደረሰበት የሊቢያ አየር ማረፊያ ነው። የአክሱም አየር ማረፊያ ለምን ወሳኝ ሆነ? ኢትዮጵያ ሰፊ የሆነ የቆዳ ስፋት ያላት አገር በመሆኗ ጦር ሠራዊቱን እና ግብዓቶቹን ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ አየር ማረፊያዎች ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። በባልሲሌ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር አን ፊትዝ-ጄራል፤ "አክሱም አየር ማረፊያ ትልቅ ጥቅም አለው። አየር ማረፊያዎች ወታደሮችን ለማጓጓዝና የግንኙነት መስመርን ክፍት ለማድረግ አስፈላጊዎች ናቸው። ሌሎች በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙት የባሕር ዳር እና ጎንደር አየር ማረፊያዎች በደሰረባቸው ጥቃቶች ጉዳት አጋጥሟቸዋል። "የክልል ኃይሎች አየር ማረፊያውን መቆጣጠር ካልቻሉ ጥቅም ላይ እንዳይውል የማድረግ ዘዴን ሊጠቀሙ ይችላሉ። ይህም ስጋት ሲያይልባቸው እንደመጨረሻ አማራጭ የሚወሰድ ነው" ብለዋል።
43985856
https://www.bbc.com/amharic/43985856
መረጃ በርባሪው ድርጅት ሊዘጋ ነው
'ካምብሪጅ አናላቲካ' የተሰኘው የፖለቲካ ጉዳዮች አማካሪ ቡድን ከፌሰቡክ መረጃ በርብሯል ተብሎ ወቀሳ ሲበዛበት ሰንብቷል። ይህንን ተከትሎም ነው ድርጅቱ ሊዘጋ እንደሆነ ተገለጧል።
ፌስቡክ የተሰኘው የማሕበራዊ ትስስር ዘዴ የ87 ሚሊዮን ደንበኞቼ መረጃ ሕቡዕ በሆነ መልኩ ተመዝብሮኛል ሲል ከተደመጠ ወዲህ ነው አማካሪ ድርጅቱ ላይ ትችት ይበረታ የያዘው። ለመረጃው መሹለክ የኔም 'ዝርክርክነት' አለበት ሲል ያመነው ፌስቡክ ምርመራ ማካሄዴን እቀጠላለሁ ይላል። "መሰል ምዝበራ መልሶ እንዳያጋጥመን የማንፈነቅለው ድንጋይ የለም" የፌስቡክ አፈ ቀላጤ ቃል ነው። ካምበሪጅ አናሊቲካ በአውሮጳውያኑ 2016 ለተከናወነው የአሜሪካ ፕረዝደንታዊ ምርጫ ይሆን ዘንድ የበርካታ ሚሊዮን የፌስቡክ ተጠቃሚያንን መረጃ በርብሯል፤ ብሪታኒያ ከአውሮፓ ሕብረት በምትገነጠልበት ወቅት የበኩሉን ሚና ተጫውቷል፤ አልፎም በኬንያና ናይጄሪያ በተካሄዱ ምርጫዎችን ላይ እጁን አስገብቷል በሚል ነው ትችትና ክስ የወረደበት። ድርጅቱን መዝጋት ለምን አስፈለገ ብሎ ቢቢሲ ቃል አቀባዩን በጠየቀ ጊዜ "ምላሻችንን በድረ-ገፃችን ታገኙት ዘንድ ይሁን" ብለዋል። በተጠቆመው ድር ላይ የተለጠፈው መግለጫ "ድርጅቱ ተገቢነት በሌላቸው ውንጀላዎች ሲዋከብ የቆየ ቢሆንም ይህን ለማቅናት ያደረገው ጥረት ሊሳካ ባለመቻሉ፤ ደንበኞቻችንም በመገናኛ ብዙሃን ስማችን ሲጎድፍ በማድመጣቸው ምክንያት እምነት ስላጡብን ልንዘጋ ተገደናል" ሲል ይነበባል። ቢሆንም በርካታ ተንታኞች ይህ ጉዳይ የተዋጠላቸው አይመስልም። ድርጅቱ ስሙን ቀይሮ አሊያም ከሌላ ድርጅት ጋር በማበር ብቅ ማለቱ አይቀርም ይላሉ። በአንድ የቴለቪዥን ጣቢያ ላይ ስለሚሰሩት የመረጃ ምዝበራ ሲናገሩ የተያዙት የድርጅቱ የበላይ ሰው ከሥራቸው መታገዳቸው የሚታወስ ነው። ከድርጅቱ ባለሃብቶች መካከል አንዱ አሜሪካዊው ቱጃር ሮበርት መርሰር እንደሆነ ሲታወቅ 15 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ እንዳፈሰሱም ተዘግቧል። ድርጅቱ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን መረጃ የመበርበሩ ወሬ ከተሰማ ወዲህ ፌስቡክ 'በኔ ይሁንባችሁ፤ ከእንግዲህ ለመረጃችሁ ጥንቃቄ ማድረጉን ተክንነበታል' ሲል አትቷል። የፌስቡክ አለቃ ማርክ ዙከርበርግም በአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፊት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸው ከቶም የሚዘነጋ አይደለም።
news-57306932
https://www.bbc.com/amharic/news-57306932
ሽብርተኛ በተባሉት ቡድኖች አባላት ንብረትና ገንዘብ ላይ እገዳ ተጣለ
የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሪቱ ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብለው የተሰየሙ ቡድኖች አባላትና ደጋፊዎች ናቸው ባላቸው ላይ የንብረት እገዳ መጣሉን አስታወቀ።
ከተለያዩ የአገሪቱ የጸጥታ አካላት የተወጣጣው የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል እንደገለጸው 19 የህወሓት አመራር አባላት በአዲስ አበባ የሚገኙ ቋሚ ንብረት መታገዱን እንዲሁም መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው ቡድንን ይደግፋሉ የተባሉ 141 ግለሰቦች ገንዘብ እንዲታገድ መደረጉን አመልክቷል። ግብረ ኃይሉ በአሁኑ ጊዜ ከህወሓት ጋር ተሰልፈዋል ያላቸው እነዚህ ግለሰቦች፤ ቀደም ሲል ከፍተኛ ሃብት በመመዝበር በአዲስ አበባና በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ንብረቶችን እንዳሏቸው ጠቅሶ፤ በፈፀሙት የአገር ክህደት ወንጀል የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ገልጿል። ግለሰቦቹ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የገነቧቸውን የመኖሪያ ህንፃዎችና ያቋቋሟቸውን የንግድ ድርጅቶች በቤተሶቦቻቸውና በወኪሎቻቻው አማካኝነት በማከራየት የሚገኘውን ገቢ "የጦር መሣሪያዎችና ጥይቶች ግዢ እንደሚውል" አመልክቷል። ግብረ ኃይሉ ጨምሮም ንብረቶቹን በመሸጥም ሃብት ለማሸሽ ጥረት እንደተደረገ ጠቅሶ በዚህም ሳቢያ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል በማቅረብ እግዱ በፍርድ ቤት በኩል እንዲፈጸም መደረጉ ተገልጿል። ንብረታቸው ላይ እገታ ከተጣለባቸው 19 የህወሓት አመራርና አባላት መካከል ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ ሌተናል ጀነራል ፍስሐ ኪዳኑ፣ ሜጀር ጀነራል አበበ ተ/ሐይማኖት፣ ሜጀር ጀነራል ሀልፎም እጅጉ፣ ሜጀር ጀነራል ተስፋዬ ግደይ፣ ብርጋዴር ጀነራል ኃይለሥላሴ ግርማይ፣ ብርጋዴር ጀነራል ምግበ ኃይለ፣ ብርጋዴር ጀነራል ተኽላይ አሸብር ይገኙባቸዋል። በተጨማሪም በአንዳንድ የኦሮሚያ ክፍሎች ውስጥ እንደሚንቀሳቀስ የሚነገረውና መንግሥት ሸኔ የሚለውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራውን ቡድን በገንዘብ ሲደግፉ ነበሩ የተባሉ 141 ተጠርጣሪ ግለሰቦች የገንዘብ ዝውውራቸው እንዲታገደ መደረጉንም ግብረ ኃይሉ ገልጿል። በትግራይ ውስጥ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ ከክልሉ አስተዳዳሪነት የተወገደው ህወሓት እና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች ጀርባ ይገኛል የተባለው 'ሸኔ' ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ቡድኖች ተብለው መሰየማቸው ይታወሳል።
news-46451772
https://www.bbc.com/amharic/news-46451772
ጥቁር ለመሆን የሚጥሩት ነጭ እንስቶች
«ቀዶ ጥገና አልተደረግኩ፤ ከናፍሬን ላስወገዳቸው አልችል። በቀዶ ጥገና ያገኘሁትን መቀመጫም ፍቄ ልጥለው አልፈቅድም።»
በፈረንጅ አፍ 'ብላክፊሽ' ሲሉ ይጠሯታል፤ ጥቁር ለመሆን የማትፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ ያስተዋሉ። ቃሉ ማሕበራዊ ድር-አማባዎችን ተጠቅመው ባለጥቁር ወይንም ቅልቅል ደም ያለበት ቆዳ ለመላበስ የሚጥሩ ሰዎችን ለመግለፅ ጥቅም ላይ ይውላል። አጋ ብርዞስቶውስካ ግን ይህ ስያሜ አይዋጥላትም፤ እንዲያውም ነገሩ እንግዳ ሆኖባታል። • እውነተኛ ውበትን ፍለጋ የበርሚንግሃም ዩኒቨርሲቲ ተማሪና የ20 ዓመቷ ኮረዳ «ቆዳዬ በተፈጥሮ በጣም ነጣ ያለ አይደለም» ትላለች፤ ጠቆር ለማለት መሞከሯን ግን አትክድም። «ታኒንግ አለ አይደለ እንዴ?» ትላለች፤ ሰዎች ጠቆር ለማለት የሚጠቅሙበት የተለመደ ዘዴ በማጣቀስ። «እኔ ቆዳዬን ማጥቆሬን እርግፍ አድርጌ መተው አልፈልግም፤ ሳደርገው ደስ ይለኛል፤ ጥቅምም አገኝበታለሁ» ትላለች አጋ። አጋ ትቀጥልና «የነጭ የበላይነት የለም ብዬ የማምን ሰው አይደለሁም፤ ነገር ግን እኔን የሚተቹ ሰዎች መጥፎ ድርጊት እንደፈፀምኩ እንዲያስቡ አልፈቅድም» ስትል አቋሟን ታስረግጣለች። • የመጀመሪያው ጥቁር የኦክስፎርድ ተማሪ አጋ ቆዳቸው ጠቆር ብሎ እንዲታይ ከሚሹ እና ከሚያደርጉ የትየለሌ የማሕበራዊ ድር-አምባ ተጠቃሚዎች አንዷ ናት። ኢንስታግራም በተሰኘው የማህበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ ከሚገኙ 'ጥቋቁር ነጮች' መካከል 200 ሺህ ያክል ተከታይ ያላት ስዊዲናዊቷ ኤማ ሃልበርግ ትጠቀሳለች። በተፈጥሮ ቀለሟ የተነሳችው ልሙጥ ፎቶ ጠቁራ ከተነሳችው ጋር ተነፃፅሮ ማሕበራዊ ድር-አምባውን የሞላባት ኤማ «እኔ ራሴን እንደ ነጭ ሴት ነው የማየው ትላለች»፤ በእርግጥም ነጭ ናት። «ቆዳዬ ጠቁሮ ሊታይ የቻለው ከፀሐይ ብርሃን ከማገኘው ተፈጥሯዊ ኃይል ነው» ትላለች ኤማ። አጋ፤ ነገሩ እንደውም እኔ እና የሃገሬ ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለ በደል ነው ባይ ናት። በልጅነቷ ከነበራት ቀለም ጋር የማይገናኝ ቀለም እና የሰውነት ቅርፅ ነው ያላት ብለው ለሚተቿት ምላሽ ስትሰጥ «ሰውነቴ ጂም ገብቼ ጠብ እርግፍ ብዬ ያመጣሁት ነው» በማለት ሰዎች ለፖላንዳዊያን ያላቸው አመለካከት የተዛባ እንደሆነ ትጠቁማለች። ሰዎች ስለ ፖላንዳዊያን ሲያስቡ ነጭ እና ስስ ከናፍር ያላቸው አድረገው ማሰባቸው ዋናው ችግር እንደሆነ ታሰምራለች። ጉዳዩ ምን ያህል አሳሳቢ ይሆን? ጉዳዩን ወደሰው እዝነ ሕሊና ያመጣችው የትዊተር ተጠቃሚዋ ዋና ቶምፕሰን ናት፤ «ኧረ ሰዎች ይህ ነገር አሳስቦኛል» በማለት። አንዳንድ የትዊተር መንደር ሰዎች «ታድያ ምን ይጠበስ?» ቢሏትም በርካቶች ግን ነገሩ ዘልቆ የገባቸው ይመስላል። ዳራ ቱርሞንድ «እኔ የሚያንገበግበኝ እኒህ ነጭ ሴቶች እኛን መስለው መታየታቸው ሳይሆን፤ ጥቁር ሴቶች በተፈጥሯዊ መልካቸው ለመታየት የሚያደርጉትን ትግል አለመረዳታቸው ነው» ትላለች። • ጥቁር አሜሪካዊው ኮሊን ኬፐርኒክ የናይክ ኩባንያ መሪ አስተዋዋቂ ሆነ «እኛ ጥቁሮች እኮ በተፈጥሯዊ ፀጉራችን መታየት እየከበደን ነው፤ አፍሮ ወይም ቁጥርጥር መሰራት ንፅህና እንደሌለው እና ያፈነገጠ እንደሆነ እየተቆጠረብን ነው።» ኪም ካርዳሺያን የተሰኘችው አሜሪካዊት ታዋቂ ሴት 'ብላክፊሺንግ' ከተባለው ሃሳብ ጋር ስሟ በተደጋጋሚ ሲነሳ ይደመጣል። ምክንያቱ ደግሞ የኪም አድናቂዎች፤ በተለይ ወጣቶች፤ የሰውነት ንቅለ ተከላ በማድረግ ባህል 'መበከላቸው' ነው ተብሎ ሲነገር ይደመጣል። ዳራ ነገሩ ብዙም የሚደንቅ አይደለም ትላለች፤ «በርካታ ጥቁር ሴቶች በተፈጥሯዊ ውበታቸው ወደፊት ብቅ ብቅ ማለታቸው የፈጠረው ተፅዕኖ ነውና።» የአጋን ትክክለኛ ማንነት የተረዱ ሰዎች በማህበራዊ ገፆቿ ውስጥ መስመር በመግባት 'ራስሽን ብታጠፊ ይሻላል' በማለት በነገር እንደሚሸነቁጧት ሳትደብቅ ትናገራለች። «እውነት ለመናገር. . .» ትላለች አጋ፤ «እውነት ለመናገር አሁን አሁን ጉዳዩ እየገባኝ መጥቷል፤ ለጥቁር ሴቶች ጉዳዩ ምን ያህል ትርጉም እንዳለው ገብቶኛል።» ግን ፎቶሽን ትቀይሪ ይሆን? ለአጋ የቀረበላት ጥያቄ ነው። «እኔ ምኔን እንደምቀይር አላውቅም፤ ምክንያቱም ትክክለኛው እኔ ነኛ።»
news-53348436
https://www.bbc.com/amharic/news-53348436
ጃዋር መሐመድ እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ
አሁን ላይ በእስር ከሚገኙ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አንዱ የሆነው አቶ ጃዋር መሐመድ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ “ወደ ሕገ ወጥ መሪነት” እያመሩ ነው ማለቱ ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ የኖቤል ሽልማት ካገኙ ወዲህ ከታሰሩ እውቅ የተቃውሞ ፖለቲከኞች አንዱ ጃዋር፤ ፌስቡክ ላይ ወደ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ተከታዮች አሉት። የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተነሳው ግርግር በቁጥጥር ሥር ከዋሉ አንዱ ሲሆን፤ በግርግሩ ሳቢያ ከተገደለ ፖሊስ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶበታል። ደጋፊዎቹ ክሱን በማጣጣል፤ የታሰረው በጠቅላይ ሚንስትሩ ትዕዛዝ፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎውን ለማክሸፍ ነው ይላሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይና ፖለቲከኛው ጃዋር የወደፊቷን ኢትዮጵያን በተመለከተ ያላቸው ራዕይ የተለያየ ይመስላል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ሲይዙ በብሔር መስመሮች የተከፋፈለችውን ኢትዮጵያ ለማዋሃድና ዴሞክራሲ ለማስፈን ቃል መግባታቸው ይታወሳል። የመንግሥትን ሐሳብ የሚደግፉ አካላት፤ ጀዋር መታሰሩ ብሔርን ያማከለ ንቅናቄን ለማክሰም ያግዛል ይላሉ። ከጠቅላይ ሚንስትሩ የ “አንድነት” ራዕይ በተቃራኒው ብሔር ተኮር ግጭቶት ለመነሳታቸው ጀዋርን ተጠያቂ ስለሚያደርጉም መታሰሩን በበጎ ያዩታል። በተቃራኒው የጃዋር ደጋፊዎች እንደሚሉት መታሰሩ፤ ለ34 ዓመታት ሲቀነቀን የነበረው የኦሮሞ እንዲሁም የሌሎች ብሔሮች ራስን የአስተዳደር ሀሳብን ጠቅላይ ሚንስትሩ ማስተናገድ እንዳልቻሉ ያሳያል ይላሉ። “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ” ጃዋር የተወለደው እንደ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1986 ነው። አባቱ ሙስሊም እናቱ ደግሞ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ናቸው። ያኔ በስደት አሜሪካ የነበረው ጃዋር 2013 ላይ ከአልጀዚራ ጋር ባደረገው ቆይታ “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ” ብሎ፤ ኢትዮጵያዊ የሚለው ማንነት “እንደተጫነበት” ገልጾ ነበር። በኬል ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር የሆኑት አወል አሎ የዚያን ጊዜውን የጃዋር አስተያየት “ፖለቲካዊ ሱናሚ” አስነስቷል ብለው ነበር። ንግግሩ በኢትዮጵያና በውጪ አገራትም ጃዋርን በእጅጉ በሚደግፉና አጥብቀው በሚተቹ ሰዎች መካከል የጋለና የተካረረ ክርክርንም አጭሮ ነበር። “መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ” የኋላ ኋላ ወደ ፖለቲካዊ ንቅናቄ አድጓል። ጃዋር በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በመዘዋወር ዳያስፖራው የኢትዮጵያን አገዛዝ እንዲያወግዝ፣ ለነፃነቱ እንዲታገልም ቀስቅሷል። ንቅናቄው ይበልጥ የተቀጣጠለው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) 2013 ላይ የቴሌቭዥንን ጣቢያ በከፈተበት ወቅት ነው። ጣቢያው ሲመረቅ ጃዋር “አሁን የኦሮሚያን አየር ሞገድ ነፃ አውጥተናል” ማለቱ ይታወሳል። የኦኤምኤን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳለ፤ ጣቢያው የወጣቱን (ቄሮ) ድምጽ እንዲያስተጋባ አድርጓል። ቄሮ የሚለው መጠሪያ በስፋት የተዋወቀው በ1990ዎቹ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አማካይነት ነበር። ኦነግ ከሚንቀሳቀስባቸው ከተሞች በአንዱ ያደገው ጃዋር “የተወለድኩት በኦሮሞ ትግል ውስጥ ነው፤ በአምባገነኖች እና በአጼዎቹ ዘመን የኦሮሞ ሕዝብ መጨቆኑን አስተውያለሁ” ይላል። ጃዋር መሐመድ ከኢትዮጵያ የወጣው በወጣትነቱ ነው። 2003 ላይ ሲንጋፖር የነፃ ትምህርት እድል አግኝቶ ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ አሜሪካ ሄዶ ከስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ በፖለቲካ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ሁለተኛ ዲግሪውን ደግሞ 2013 ላይ ከኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በሰብዓዊ መብት ይዟል። ጃዋርና ጠቅላይ ሚንስትሩ ጃዋር የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳለ ራሱን ከኦነግ አርቆ ነበር። በአመራሩ መካከል ያለው መከፋፈል ግንባሩን “እንዳይጠገን አርጎ ሰብሮታል” ሲል በጦማሩ ላይ ጽፎ ነበር። ሆኖም ዳያስፖራ የኦሮሞ ተወላጆች የአገር ቤቱን ትግል እንዲደግፉ ከማነሳሳት ወደ ኋላ አላለም። በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመነሳቱ ምክንያት ከሆኑ እንቅስቃሴዎች አንዱም ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በዶ/ር ዐብይ ሲተኩ፤ ጀዋር “ስትራቴጂያዊ ስህተት” ብሎ ሥልጣኑን መያዝ ያለባቸው የአሁኑ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳ እንደሆኑ ተናግሮ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የመሪነት መንበሩን እንደያዙ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ ሲያደርጉና ጃዋርን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ውጪ የነበሩ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ከ ‘ሽብርተኛ’ መዝገብ ከሰረዙ በኋላ፤ ጃዋር ጠቅላይ ሚንስትሩን መደገፍ ጀምሮ ነበር። ወደ አገር ቤት ተመልሶም የኦኤምን ቅርንጫፍን በአዲስ አበባ ከፍቷል። ነገር ግን ጠቅላይ ሚንስትሩን በመደገፉ አልገፋበትም። የራስ አስተዳደር ለሁሉንም ብሔሮች የምጣኔ ሃብት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥና መረጋጋትን የሚፈጥር ነው ብሎ ስለሚያምን ከጠቅላይ ሚንስትሩ በተቃራኒው ቆሟል። የጃዋር መታሰር ደጋፊዎቹ በጠቅላይ ሚንስትሩ የነበራቸውን የተስፋ ጭላንጭል ያከሰመ ይመስላል። በተለይም በኮቪድ-19 ሳቢያ የተራዘመው ምርጫ ጉዳይ የሚነሱትን ጥያቄዎች አጉልቷቸዋል። ብልጽግና ፓርቲ እና ኦፌኮ ጠቅላይ ሚንስትሩ በብሔር ውክልና ላይ የተመሠረተውን የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባርን (ኢሕአዴግ) አክስመው ብልጽግና ፓርቲን ፈጥረዋል። ጃዋር ደግሞ ከኦኤምኤን ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለቆ፤ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) ተቀላቅሏል። ኦፌኮ እና በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ ጋር ከፍተኛ ፉክክር ሊኖር በሚችልባቸው አካባቢዎች በተቀናቃኝነት ሳይሆን በመደጋገፍ ለመሥራት ተስማምተዋል። ይህም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በኦሮሚያ የምርጫ ቀጠናዎች ሊያገኙ የሚችሉትን ድምጽ ሊያሳጣ ይችላል። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በወረርሽኙ ስጋት ሳቢያ ምርጫው እንደተራዘመ ማስታወቁን ተከትሎ፤ ጃዋር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከመስከረም 2013 ዓ. ም በኋላ “ሕገ ወጥ መሪ” ናቸው ብሏል። የኦፌኮ አመራሮች እንደሚሉት የጀዋር ጠበቃና ቤተሰቦቹን እስካሁን ሊያገኙት አልቻሉም። የረሃብ አድማ ላይ እንደሆነም የፓርቲው አመራሮች ገልጸዋል።