headline
stringlengths
2
1.42k
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
9
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
63
36.2k
link
stringlengths
28
740
word_len
int64
16
6.74k
label
class label
6 classes
የገለልተኛ የብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ተመሰረተ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 14, 2020
Unknown
የኢትዮጵያ ገለልተኛ የብሄራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት መመስረቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ።የመንግሥትን የማሻሻያ ፕሮግራም በስኬት ለማስፈጸምና በአጠቃላይ የኢኮኖሚውን እድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ የምሁራንና የባለሙያዎችን ምክር እንዲሁም ግብረመልስ መቀበል ጠቃሚ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።ገለልተኛ ከሆኑ ምሁራንና ባለሙያዎች ሃሳብ መቀበል የፖሊሲን አካታችነት ከመጨመር ባለፈ፤ ያልታዩ ጉዳዮችን ለማየት፣ ሃገሪቱ ያለችበትን ውስብስብ የሆነ የድህነትንና ሌሎች ማኅበራዊ ችግሮችን ለመረዳትና ዉጤታማ የፖሊሲ አማራጮችን ለመመርመር ያስችላል ነው የተባለው።ከዚህም በመነሳት በታህሳስ 21 ቀን 2012 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በወጣው ማስታወቂያ መሰረት የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት እጩ አባላትን በጥቆማና በስራ ማመልከቻ መቀበል መጀመሩን ይፋ አድርጎ እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጠቁሟል።ይህንንም ጥሪ ተከትሎ በጥቅሉ ወደ 290 እጩዎች የቀረቡ ሲሆን፣ በሶስት ደረጃ የተከፈለ የማጣራት ሂደት ከተከናወነ በኋላ 16 ምሁራን ፍቃደኝነትታቸው ተረጋግጦ የመጀመሪያው የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት አባላት ሆነው መመረጣቸው ተገልጿል።በዚህም2.ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8c%88%e1%88%88%e1%88%8d%e1%89%b0%e1%8a%9b-%e1%8b%a8%e1%89%a5%e1%88%94%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8a%ae%e1%8a%96%e1%88%9a-%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%88%ad-%e1%89%a4%e1%89%b5/
124
0ሀገር አቀፍ ዜና
አሜሪካ ሱዳንን ሽብርተኝነትን ከሚደግፉ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ ሰረዘች
ዓለም አቀፍ ዜና
December 14, 2020
Unknown
ሱዳን ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ ከሚባሉት ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ መውጣቷ ተገለጸ፡፡አሜሪካ ከ27 ዓመታት በፊት በሀገር ደረጃ ሱዳን ሽብርተኝነትን ትደግፋለች በሚል በጥቁር መዝገብ ዝርዝሯ ውስጥ ማስፈሯ ይታወሳል፡፡ይህንንም ተከትሎም ሱዳን ለረዥም ዓመታት ማዕቀብ ውስጥ ቆይታለች፡፡ባለፉት ወራትም ሁለቱ ሀገራት አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ ለመክፈት ውይይቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡ውይይቱን ተከትሎም ሱዳን ከአሜሪካ የጥቁር መዝገብ ለመውጣት ከዚህ ቀደም በኬንያና በታንዛኒያ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ ለተፈጸሙ ጥቃቶች 335 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል መስማማቷን ይፋ አድርጋለች፡፡የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክም ሃገራቸው አሜሪካ የጠየቀችው የካሳ ክፍያ መፈጸሟን ገልጸው ነበር፡፡ይህን ተከትሎም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ሱዳንን ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ ከሚባሉ ሃገራት ዝርዝር ለመሰረዝ አሜሪካ ሂደት መጀመሯን መግለጻቸውና ይህም በ45 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ማለታቸውም ይታወቃል፡፡አሁን ላይ የተሰጠው የ45 ቀናት ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ካርቱንም ከዝርዝር መሰረዝ የሚያስችለውን ፊርማ ማኖራቸውን በካርቱም የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡የአሁኑ የአሜሪካ እርምጃ ለሱዳን ኢኮኖሚ መነቃቃት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a0%e1%88%9c%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%88%b1%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%8a%95-%e1%88%bd%e1%89%a5%e1%88%ad%e1%89%b0%e1%8a%9d%e1%8a%90%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%8a%a8%e1%88%9a%e1%8b%b0%e1%8c%8d%e1%8d%89/
135
4ዓለም አቀፍ ዜና
በትግራይ ክልል ጭላ ወረዳ በአንድ አካባቢ ጁንታው ደብቋቸው የነበሩ ከ140 በላይ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች ከጦር መሳሪያ ጋር ተገኙ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 14, 2020
Unknown
በትግራይ ክልል ማእካላዊ ዞን የጭላ ወረዳ በአንድ አካባቢ ጁንታው ደብቋቸው የነበሩ ከ140 በላይ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችና የተለያዩ ፈንጅዎች ጨምሮ በርካታ የከባድ መሳሪያ ተተኳሾች ሰራዊቱ ባደረገው አሰሳ  አግኝቷል።በአካባቢው የተሰማራው የ11ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል ያሲን ኑርዬ እንደገለፁት፣ የህወሓት ጁንታ “ሰራዊቱ አይደርስበትም” ብሎ ባሰበው የጭላ ወረዳ ልዩ ስፍራው ሰረፍረፍ በተባለ አካባቢ ስንቅና ትጥቅ የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎችን ደብቋቸው  ተገኝተዋል።በአካባቢው የተሰማራው ሰራዊት ባደረገው ህግን የማስከበር ተግባር እና አሰሳ  የተደበቁት መኪኖች ፣ቀላል እና ከባድ  የጦር  መሳሪያዎች ጭምር መገኘታቸውን ኮሎኔል ያሲን ተናግረዋል።የ11ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል ያረጋል መኮንን በበኩላቸው ፣ አካባቢው ከጁንታው አባላት ሙሉ ሙሉ ነፃ በመውጣቱ ህብረተሰቡ ወደቀደመ የተረጋጋ ህይወቱ እየተመለሰ እንደሚገኝና ሰራዊቱ የህብረተሰቡን ሰላም ከማስጠበቅ አንፃር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከኢፌዴሪ  መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው  መረጃ  ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8c%ad%e1%88%8b-%e1%8b%88%e1%88%a8%e1%8b%b3-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8b%b5-%e1%8a%a0%e1%8a%ab%e1%89%a3%e1%89%a2/
116
0ሀገር አቀፍ ዜና
በማንነት ጥያቄያችን ብቻ ከእስርና መንገላታት ነጻ መውጣታችን አስደስቶናል- በከሃዲው ህወሓት ታስረው የነበሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 14, 2020
Unknown
ከብዙ እንግልትና መከራ በኋላ በሃገር መከላከያ ሰራዊት እገዛ ነጸ ወጥተው በሰላም ወደ ቤት መመለሳቸው ዳግም የተወለዱ ያህል እንደተሰማቸው የራያ አላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት መካከል አቶ ብርሃኑ በላይ “በህጋዊ መንገድ የራያ ማንነት ጥያቄ በማንሳታችን የትግራይን አንድነት አፍርሳችኋል፣ ሰልፍ አስተባብራችኋል በሚል ተልካሻ ምክንያት ላለፉት ሁለት አመታት በህወሓት ማጎርያ ቤቶች እንግልት እና ስቃይ ደርሶብኛል” ብለዋል።ከ2011 ዓ.ም በህገ ወጡ የህወሓት ቡድን እጅ ውስጥ ከገቡ ጀምሮ በእምባ አላጄ፣ እንዳመኾኒ፣ ማይጨው እና በመቀሌ ባዶ ስድስት እና ማረሚያ ቤቶች ሲንከራተቱ እንደነበርም ገልፀዋል።“በእስር ቤት በቆየሁባቸው ጊዜያት የጸሀይ ብርሃን አላገኝም ነበር ከፍተኛ ድብደባም ተፈፅሞብኛል” ብለዋል።በመቀሌ ማረሚያ ቤት በነበሩበት ወቅት የመከላከያ ሰራዊት ወደ መቀሌ እየተጠጋ ሲመጣ ሌሎች እስረኞች ሲፈቱ የራያ፣የወልቃይት እና የኤርትራ ሰላይ ብሎ ያሰራቸው ሰዎች ወደ ተምቤን ማረሚያ ቤት መወሰዳቸውንም ተናግረዋል።“መንግስት በህወሓት ላይ በወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ ሲሸነፍ የማንነት ጥያቄ ያነሳን 64 ሰዎች የሞት ፍርድ ቢፈረድብንም የአብይ አዲይ ማረሚያ ቤት ምክትል አስተዳዳሪ ኮማንደር ሐጎስ ውሳኔው እንዳይፀና በማድረጉ ባለቀ ሰአት መከላከያችን ደርሶ ህይወታችንን ታድጎናል” ብለዋል።“አሁን በህይወት ተርፈን ከቤተሰቦቻችን መገናኘታችን ዳግም የተወለድን ያህል ስሜት ተሰምቶኛል” ብለዋል አቶ ብርሃኑ።“የሞት ፍርድ ተፈርዶብን በመከላከያ ሰራዊት ጥረት ነፃ መውጣታችን በጣም አስደስቶኛል” ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ በራያ ማንነት ጥያቄ ምክንያት ብቻ ታስረው የቆዩት ወይዘሮ ትህንዋ አገዞም ናቸው።“በፅንፈኛው እጅ ወድቄ በህይወት ወደ ቤት እመለሳለሁ የሚል ተስፋ አልነበረኝም፤ አሁን ግን በሰላም ተመልሼ ከቤተሰቦቼ ጋር መገናኘት ችያለሁ” ብለዋል።እስረኞቹ ከሞት ፍርድ አውጥቶ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ላደረጋቸው የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና ወደ አላማጣ ሲገቡም ደማቅ አቀባበል ላደረገላቸው የከተማው ነዋሪ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸውና በፖለቲካ ልዩነታቸው ምክንያት በህወሓት ጁንታ ቡድን ታስረው የነበሩ 64 ሰዎች በመከላከያ ሰራዊት ጥረት ነፃ መውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%9b%e1%8a%95%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%8c%a5%e1%8b%ab%e1%89%84%e1%8b%ab%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%89%bb-%e1%8a%a8%e1%8a%a5%e1%88%b5%e1%88%ad%e1%8a%93-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88/
240
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አለፈ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 14, 2020
Unknown
 የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አምብሮሲ ድላሚኒ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ መንግስት አስታወቀ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአራት ሳምንታት በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ገልጸው በመልካም ጤንነት ላይ ይገኙ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ምንም እንኳን ለሞታቸው ምክንያት ምን እንደሆነ በይፋ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኮሮረናቫይረስ ከተያዙ በኋላ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ነበር ተብሏል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%88%b5%e1%8b%8b%e1%89%b2%e1%8a%92-%e1%8c%a0%e1%89%85%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93-%e1%89%ab%e1%8b%ad/
49
4ዓለም አቀፍ ዜና
ፕሬዳዝንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉብንት አቢጃን ገቡ
ፖለቲካ
December 14, 2020
Unknown
የኢፌዴሪ ፕሬዳዝንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለይፋዊ የስራ ጉብንት ኮቲዲቯር አቢጃን ገብተዋል፡፡ለፕሬዝዳንቷ በአቢጃን ከተማ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ በኮትዲቯሩ ፕሬዝዳንት አላሳኔ ኦታራ በአለ ሲመት ላይ ለመገኘት ወደ ስፍራው ማቅናታቸው ነው የተገለጸው፡፡ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ በኮትዲቯር ቆይታቸው ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በምዕራብ አፍሪካ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት እንደሚያርጉ ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::
https://waltainfo.com/am/%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%b3%e1%8b%9d%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%a3%e1%88%85%e1%88%88%e1%8b%88%e1%88%ad%e1%89%85-%e1%8b%98%e1%8b%8d%e1%8b%b4-%e1%88%88%e1%8b%ad%e1%8d%8b%e1%8b%8a-%e1%8b%a8%e1%88%b5/
50
5ፖለቲካ
ለከተሞች በ10 ዓመታት ውስጥ 15 ሚሊዮን ምርታማ የስራ ዕድልን የመፍጠር ግብ ተቀመጠ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 14, 2020
Unknown
የከተሞችን ድህነትና ስራ አጥነትን ለመቀነስ በአስር ዓመታት ውስጥ 15 ሚሊዮን ምርታማና ተስማሚ የስራ ዕድልን የመፍጠር ግብ መቀመጡ ተገለጸ፡፡የፌዴራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በከተማ ልማት ሴክተር የአስር ዓመትና የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ ላይ በሀዋሳ ውይይት አካሄዷል፡፡በሚኒስቴሩ የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ተስፋዬ ወ/ሚካኤል ለአስር ዓመት የተያዘው የዘርፉ ዕቅድ ዓላማው ከተሞችን የብልፅግና ማዕከላት ማድረግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡በገጠርና በከተማ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን ማስተሳሰር፣ የሀገራዊ ምርት ድርሻን በ73% ማሳደግ እንዲሁም ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢን በ2022 ዓ.ም 4 ሺህ 689 ዶላር ማድረስ የዕቅዱ ዋንኛ ግቦች መሆናቸውን አቶ ተስፋዬ አስረድተዋል፡፡በተጨማሪም የከተሞችን ድህነትና ስራ አጥነት ለመቀነስ በአስር ዓመት ውስጥ 15 ሚሊዮን ምርታማና ተስማሚ የስራ ዕድልን ለመፍጠር ግብ ተጥሏል ብለዋል፡፡ዕቅዱ የከተማ ነዋሪዎችን ኑሮ ከማሻሻል ረገድ ተስፋ ሰጪ መሆኑን የገለፁት የውይይቱ ተሳታፊዎች ለዕቅዱ ተግባራዊነት ከአደረጃጀት፣ ከግብዓት፣ ከክህሎትና ከቅንጅት አንፃር ተገቢውን ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/%e1%88%88%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9e%e1%89%bd-%e1%89%a010-%e1%8b%93%e1%88%98%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-15-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%ae%e1%8a%95-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%89%b3%e1%88%9b/
131
0ሀገር አቀፍ ዜና
የዋይት ሃውስ አባላት ኮሮናቫይረስ ክትባቱን ቀድመው ሊወስዱ ነው
ዓለም አቀፍ ዜና
December 14, 2020
Unknown
በትራምፕ አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሆኑ የዋይት ሃውስ አባላት የኮሮና ቫይረስ ክትባቱን ቀድመው ከሚወሰዱት አሜሪካውን መካከል እንደሚሆኑ ተገለጸ።አሜሪካ የፋይዘር/ባዮንቴክ ሰራሹን የኮቪድ-19 ክትባቶቹን “ወደ ሁሉም ግዛቶቿ” ማከፋፈል መጀመሯ ተገልጿል።አሜሪካ ዜጎቿን ዛሬ መከተብ የምትጀምር ሲሆን፣ እስከ መጋቢት ማገባደጃ ድርስ 100 ሚሊየን ሰዎችን ለመከተብ ታቅዷል ተብሏል።ክትባቱን ቅድሚያ የሚያገኙት ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ የሆኑት የጤና ባለሙያዎችና በእንክክብካቤ ማዕከላት የሚገኙ አረጋውያን መሆናቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ አሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የዋይት ሃውስ ባለስልጣናትን ጠቀሰው እንደዘገቡት የዋይት ሃውስ አባላት ክትባቱን ቀድመው ከሚወስዱ አሜሪካውያን ተርታ ተሰልፈዋል።አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት፤ የዋይት ሃውስ አባላት ክትባቱን ቀድመው ማግኘታቸው የመንግሥት ሥራዎች ሳይቋረጡ እንዲከናወኑ ይረዳል።በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን የማከፋፈል ሥራ ለ3 ሚሊየን ዜጎቿ የሚሆን ክትባቶች በመላው የአሜሪካ ግዛቶች እየደረሰ ነው። የክትባት ስርጭቱን በበላይነት የሚቆጣጠሩት የአሜሪካ ጦር ጀነራል ጉስታፍ ፔርና ዛሬ ክትባቱ በአሜሪካ 145 ቦታዎች ይላካል ብለዋል። ነገ እና ከነገ በስቲያ ደግሞ ክትባቱ ወደ ተጨማሪ 491 ቦታዎች እንደምላክ ገልጸዋል፡፡አሜሪካ ፋይዘር/ባዮንቴክ ያበለጸጉትን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት እንዲውል ፍቃድ መስጠቷ ይታወሳል።ይህ ክትባት የኮሮናቫይረስ በሽታን በመከላከል 95 በመቶ አስተማማኝ መሆኑ ተገልጿል። ይኸው ተመሳሳይ ክትባት በዩኬ ጥቅም ላይ መዋል የጀመረ ሲሆን በካናዳ፣ ባህሬንና ሳዑዲ አረቢያም ፈቃድ አግኝቷል ነው የተባለው።በኮሮናቫይረስ ክፉኛ እየተጠቃች በምትገኘው አሜሪካ ከትናንት በስቲያ ብቻ 3 ሺህ 309 ዜጎቿን አጥታለች።አኃዙን ሪፖርት ያደረገው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ድረገፅ የበለጠ እንደሚያስረዳው በአለም ላይ ከፍተኛ በቀን የተመዘገበ ሞትም አድርጎታል።የፋይዘር/ባዮንቴክ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለአስቸኳይ ጊዜ መጠቀም ፍቃድ እንዲያገኝ በከፍተኛ ሁኔታ በትራምፕ አስተዳደር ጫና የተደረገበት የምግብና መድኃኒት አስተዳደርም ውሳኔውን የወረርሽኙ “አዲስ ምዕራፍ” ብለውታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8b%8b%e1%8b%ad%e1%89%b5-%e1%88%83%e1%8b%8d%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a3%e1%88%8b%e1%89%b5-%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93%e1%89%ab%e1%8b%ad%e1%88%a8%e1%88%b5-%e1%8a%ad%e1%89%b5%e1%89%a3/
222
4ዓለም አቀፍ ዜና
የሀገሪቱን የእድገት ጉዞ የሚያጠናክር የአስር አመት ብሔራዊ እቅድ ጸደቀ-ጠ/ሚ ዐቢይ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 11, 2020
Unknown
ሀገሪቱ በከፍተኛ የእድገት መንገድ እንድትጓዝ እና አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያስችላት የ10 ዓመት እቅድ በካቢኔው መፅደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።የ10 ዓመት አቅድ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና መብራት ያደርጋታል ተብሏል።እቅዱ 10 ማዕዘኖች ያሉት ሲሆን የሰላም ግንባታ እና የተቋማት ሽግግርን የተመለከቱት ልዩ ትኩረቶችን ማካተቱም ተገልጿል፡፡በተጨማሪም፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኅትመት እና የብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን መተዳደሪያ ሆኖ የሚያገለግለውን እና ለማኅበራዊ ሚዲያ የሕግማሕቀፍ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚተገበረውን፣ ረቂቅ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት አዋጅ ጸድቋል።የዘርፉን ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች የሚተነትነው አዋጅ፣ የመረጃ እና የፕሬስ ነጻነት ተግባራዊነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚደግፍ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%aa%e1%89%b1%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%8a%a5%e1%8b%b5%e1%8c%88%e1%89%b5-%e1%8c%89%e1%8b%9e-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%8c%a0%e1%8a%93%e1%8a%ad%e1%88%ad-%e1%8b%a8/
85
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ ያሉ ሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ተወሰነ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 11, 2020
Unknown
መንግስት የሀገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል ከታህሳስ 02/2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/2013 ዓ.ም ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡የአውሮፕላን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር 25.37 በዓለም ወቅታዊ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ በተገኘው ልዩነት 10 ሳንቲም ጨምሮ በሊትር ብር 25.47 እንዲሸጥ የተወስኗል።በአለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግም እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ  ሊደረግ እንደሚችል ተገልጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a8%e1%8a%a0%e1%8b%8d%e1%88%ae%e1%8d%95%e1%88%8b%e1%8a%95-%e1%8a%90%e1%8b%b3%e1%8c%85-%e1%8b%8d%e1%8c%ad-%e1%8b%ab%e1%88%89-%e1%88%8c%e1%88%8e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%8a%90%e1%8b%b3%e1%8c%85/
74
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር ማጠናከር እንደምትፈልግ አስታወቀች
ሀገር አቀፍ ዜና
December 11, 2020
Unknown
ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ማጠናከር እንደምትሻ በኢትዮጵያ የአገሪቷ አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ገለጹ።አምባሳደሯ አገራቸው የኮቪድ-19 ወረርሽኝና የአንበጣ መንጋን ለመከላከል ድጋፍ እንደምታደርግም አስታውቀዋል።ኢትዮጵያና ጃፓን 90 ዓመታትን ያስቆጠረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤  በትምህርት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በግብርናና በማህበራዊ መስኮችም ትብብር ያደርጋሉ።ጃፓን በዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲዋ /ጃይካ/ አማካኝነት ለልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ እንደምታደርግ መረጃዎች ያመለክታሉ።አምባሳደር ታካኮ እንደተናገሩት ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች ግንኙነት ማጠናከር ትፈልጋለች።የጃፓን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያወጡ ድጋፍ እንደሚደረግም ገልጸዋል።ጃፓን በፖለቲካ፣ በደህንነትና በባህል ስፖርት ያላትን ትብብር ማጎልበት ትፈልጋለችም ብለዋል።አገራቸው ለኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በተለይም በቢዝነስ መስክ የምትሰጠውን ነጻ የትምህርት ዕድል እንደምታሳድግም ገልጸዋል።ጃፓን በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሸኝና የአንበጣ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደምታደርግም አምባሳደሯ ተናግረዋል።በጃፓን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ /ጃይካ/ በቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት ድጋፍ የሚያደርግባቸው የትብብር መስኮች ተለይተው በቅርቡ ይፋ እንድሚደረግ ለኢዜአ ገለጸዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8c%83%e1%8d%93%e1%8a%95-%e1%8a%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8c%8b%e1%88%ad-%e1%8b%ab%e1%88%8b%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%8b%b5-%e1%8a%a5%e1%8a%93/
129
0ሀገር አቀፍ ዜና
መንግሥት በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ እየሠራ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 11, 2020
Unknown
የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡የኢፌዴሪ መንግሥት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ እንዲደርስ ለማድረግ እየሠራ ነው ተብሏል፡፡ወደ ክልሉ የሚላከው የሰብአዊ ድጋፍ በአንዳንድ ከተሞች ባለው ጦርነት እንቅፋት ገጥሞታል ተብሎ የሚወራው እውነት እንዳልሆነ እና የመከላከያ ሠራዊት አካባቢውን ለማረጋጋት እየሠራ ላለው ሥራ እውቅና ካለ መስጠት የሚመነጭ መሆኑ ተገልጿል፡፡የሕወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንደተወሰደ በሰላም ሚኒስቴር የሚመራው እና የሚደረገው ሰብአዊ ድጋፍን የሚቆጣጠር ከፍተኛ ኮሚቴ መቋቋሙ ይታወሳል፡፡ኮሚቴው ባደረገው ቴክኒካዊ የዳሰሳ ጥናት መሠረት የሰብአዊ ድጋፉ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡ባለፈው ወር ውስጥ የመጀመሪያ ዙር ሰብአዊ ድጋፍ እና የሕክምና ቁሳቁሶች ወደ ዳንሻ፣ ወልቃይት፣ ቃፍታ/ሁመራ እና ደባርቅ አካባቢዎች እንደተላከ ተገልጿል፡፡ባለፈው ማክሰኞ ዕለት በ44 የጭነት መኪኖች የተጫኑ 18 ሺህ 200 ኩንታል ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ እህሎች ወደ ተለያዩ የትግራይ ከተሞች መላካቸውንም ጽ/ቤቱን ዋቢ አድርጎ ኢዜአ ዘገቧል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%a5%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%8b%b5%e1%8c%8b%e1%8d%8d-%e1%88%88%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%8d%88%e1%88%8d%e1%8c%8b%e1%89%b8/
130
0ሀገር አቀፍ ዜና
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የክለሳ ትምህርት በቴሌቪዥን ይሰጣል – ት/ሚ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 11, 2020
Unknown
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለመከለስ የሚያስችል የቴሌቪዥን ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሚሰራጭ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ፕሮግራሙ ሰባት የትምህርት ዓይነቶችን ማለትም እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስን እንደሚያካትት ተገልጿል፡፡ፕሮግራሙ ከሰኞ እስከ እሁድ በድግግሞሽ እንደሚተላለፍ የገለፀው ሚኒስቴሩ ወላጆች ለልጆቻቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡የስርጭት የጊዜ ሰሌዳውን ጨምሮ የተዘጋጀውን ፕሮግራም በአማራጭነት በሚከተሉት ማህበራዊ ሚዲያ ማግኘት እንደሚቻልም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡Portal – www.eict.edu.etYouTube -Educational Plasma Programs Grade 11-12Telegram – የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን (MOE-TV)  
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a812%e1%8a%9b-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d-%e1%89%a5%e1%88%94%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%8d%88%e1%89%b0%e1%8a%93-%e1%88%88%e1%88%9a%e1%8b%88%e1%88%b5%e1%8b%b1-%e1%89%b0%e1%88%9b%e1%88%aa%e1%8b%8e/
71
0ሀገር አቀፍ ዜና
ወጣቶች የሀገርን ልማት ለማረጋገጥ የሰላም አምባሳደር መሆን አለባቸው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 11, 2020
Unknown
ወጣቶች የሰላም አምባሳደር በመሆን የሀገርን ሰላምና ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ወጣቶች ሲቪክ ማህበራት አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ወጣቶች ሲቪክ ማህበራት በአራዳ ክፍለ ከተማ 200 የሚሆኑ ወጣቶችን በማሳተፍ የሰላም የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡ከአራዳ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው የሰላም ውይይት መድረክ ወጣቶች ጥያቄዎቻቸውን በሰከነ እና ማህበረሰቡን በማይጎዳ መልኩ የማቅረብ ክህሎት ማዳበር እንደሚገባቸውም ተገልጿል፡፡እኛ ኢትዮጵያውያን በውይይት የማይፈቱ ችግሮች የሉንም የሚሉት የማህበሩ መስራች አቶ ጫላ አሰፋ ወጣቱ ለሀገር መከታ መሆኑን በተግባር ማረጋገጥ አለበት ብለዋል፡፡በኢትዮጵያ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ወጣት መሆኑን የኢፌዴሪ የሥራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን መረጃ ያሳያል፡፡ወጣቱ በሰከነ መንገድ ለሀገርና ለወገኑ ደጀን የሚሆን ዜጋ መሆን እንዳለበት ተገልጿል፡፡ወጣቱ የወጣትነት ጊዜያቸውን በሀገር ሰላም ልማት እና አንድነት ግንባታ ላይ ሊያውሉ እንደሚገባ ተጠቁሞ፣ የሀገር ፍቅር ያለው ወጣት ለማፍራት በውይይት መታመን እንዳለበትም ተረጋግጧል፡፡(በሀኒ አበበ)
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%88%e1%8c%a3%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%ad%e1%8a%95-%e1%88%8d%e1%88%9b%e1%89%b5-%e1%88%88%e1%88%9b%e1%88%a8%e1%8c%8b%e1%8c%88%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b/
114
0ሀገር አቀፍ ዜና
መርማሪ ቦርዱ ባካሄደው የመጀመሪያ ዙር የመስክ ምልከታ መግለጫ ሰጠ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ባካሄደው የመጀመሪያ ዙር የመስክ ምልከታ በተመለከተ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መግለጫ ሰጥቷል፡፡መርማሪ ቦርዱ በመጀመሪያ ዙር የመስክ ምልከታው በባህርዳር እና በጎንደር በሲቪል አየር መንገዶች ላይ የሕወሓት ጁንታ ቡድን ያደረሰውን የሮኬት ጥቃት በቦታው በመገኘት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምልከታ ማድረጉን  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም  መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ  በመግለጫው ገልጸዋል ፡፡በሲቭል አየር መንገዶች ላይ ሮኬት ማስወንጨፍ በአለም አቀፍ ህግ እና ስምምነትቶች ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መሆኑን ስለሚያስቀምጡ ጁንታ በአለም አቀፍ የወንጀል ህግ ተጠያቂ የሚሆን መሆኑንም ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡በማይካድራ በተደረገው ጭፍጨፋ እጅግ ዘግናኝ መሆኑን በመግለጽ በአንድ መቃብር በርካታ አስክሬን መቀበራቸውንም ተጠቁሟል፡፡ባህርዳ ምዕራብ እዝ ሆስፒታል እና በጎንር ዩኒቨርሲቴ ሆሰፒታ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለምርከኞች እየተደረገ ያለውን ህክምና እና ሰብአዊ ድጋፍ የተመለከቱ ሲሆን አስፈላጊው እርዳታ እየተደረገ መሆኑንም ቦርዱ አስታውቋል፡፡ጽንፈኛው ቡድን በሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው የክህደት ወንጀል የተለያዩ ክፍለ ጦሮች የተፈናቀሉ የሰራዊቱ ቤተሰቦች ተጠልው በሚገኙበት በጎንደር ህዳር 11 ትምህርት ቤት እና በአዘዞ ኮንዶሚኒየም አከባቢ በመገኘት ያሉበትን ሁኔታ እንዲሁም መንግስት እና የአካባቢው ማህበረሰብ እያደረገ ያለውን ድጋፍ መመልከታቸውንም ገልጸዋል፡፡የጽንፈኛው ቡድን ያስታጠቃቸው ሀይሎች በሱዳን ተጠልለው ባሉ ወገኞች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱም አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ አስታውቋል፡፡ (በሜሮን መስፍን) 
https://waltainfo.com/am/%e1%88%98%e1%88%ad%e1%88%9b%e1%88%aa-%e1%89%a6%e1%88%ad%e1%8b%b1-%e1%89%a3%e1%8a%ab%e1%88%84%e1%8b%b0%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%aa%e1%8b%ab-%e1%8b%99%e1%88%ad-%e1%8b%a8/
180
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ተፈራረመች
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
 የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO) እና የጀርመን ተራድኦ ድርጅ(GIZ) የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍና ለማሳደግና የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡የሶስትዮሽ ስምምነቱን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአግሮ ፕሮሰሲንግ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረየሱስ፣ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይ እና የቀጠናው ዳይሬክተር ኦሬሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ አካሂደዋል፡፡ስምምነቱም በኢትዮጵያ የሚገኙ የቻይና ፋብሪካዎችንና የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎችን አቅም በመገንባት ማህበራዊና አካባቢያዊ ኃላፊነታቸውን የሚወጡና ዘላቂና ቀጣይነት ያለው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ መገንባት መሆኑ ተነግሯል፡፡የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ የሚካሄደው ሁለንተናዊ ድጋፍ ከቻይና መንግስት በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ በተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት አስተባባሪነት የሚከናወን መሆኑን ዳይሬክተሯ ኦሬሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ ገልፀዋል፡፡የቻይና መንግስትና የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ  ድጋፍ ያመሰገኑት ሚኒስቴር ዴኤታው ወደፊትም አብሮ ለመስራት የመንግስትን ዝግጁነት መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8c%a8%e1%88%ad%e1%89%83%e1%8c%a8%e1%88%ad%e1%89%85-%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%8b%b1%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%aa%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%88%88/
112
0ሀገር አቀፍ ዜና
በትግራይ ክልል የተቋረጠውን የቴሌኮም አገልግሎት መልሶ ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
በትግራይ ክልል ከጥቅምት 24 ጀምሮ የተቋረጠውን የቴሌኮም አገልግሎት መልሶ ለማስጀመር የኢቲዮ-ቴሌኮም ባለሞያዎች ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።በሰሜን ሪጅን በመቐለ እና በሽሬ ያሉ ዋና ጣቢያዎች ያላቸውን አማራጭ የመገናኛ መስመሮች በሙሉ በመቋረጥ እንዲሁም የኮሜርሻል የኃይል አቅርቦት በማቋረጥ የተከሰተ ነው ተብሏል።በተለይ በመቀሌ በሚገኘው የቴሌኮም ጣቢያ እና ከመቀሌ ከተማ ወደተለያዩ አካባቢዎች የተዘረጉ መስመሮች መቋረጣቸው ከተረጋገጠ በኋላ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል አፋጣኝ እርምጃ ስለመወሰዱም  ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ኣሳውቀዋል።አፋጣኝ እርምጃው ባይወሰድ ኖሮ በአገር አቀፍ ደረጃም ጭምር ጉዳት ሊደርስ ይችል እንደነበር ተገልጿል።በመቀሌ የቴሌኮም ጣቢያ ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩ አካላትም በደህንነት ካሜራ እይታ ውስጥ ለማየት ተችሏል፤ ጉዳዩ በፖሊስ የምርመራ ሂደት ላይ በመሆኑ ውጤቱ ሲታወቅ እንደሚገለፅም ተጠቁሟል።ከዚህ በተጨማሪም በቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ባለፈው አንድ ወር ውስጥ 39.8 ቢሊየን የሳይበር ጥቃቶች ተሞክረው መክሸፋቸውን ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።በወሩ ውስጥ የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት በመሰረተ ልማቶች ላይ መሞከራቸውን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በዚህም የተነሳ የከፋ አካላዊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ጥበቃ ሲደረግላቸው መቆዬቱን ተናግረዋል።በአሁኑ ወቅትም በአከባቢው የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር ሰፊ ጥረቶች እየተከናወኑ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በዚህም የተጎዱ መስመሮችን በመጠገን፣ መልሶ በማቋቋም እና አማራጭ ሃይል አቅርቦቶችን በመጠቀም በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሽራሮ፣ በማይፀብሪና፣ ማይካድራ፣ በኮረም በከፊል የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን አረጋግጠዋል፡፡ይሁን እንጅ ሪጅኑ የቴሌኮም አገልግትን ለማስጀመር አስቸጋሪ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የሃይል አቅርቦት መቋረጥ፣ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች መቆራረጥ፣ በአከባቢው የሰው ኃይል ለማሰማራት አዳጋች መሆን እና ሌሎች አገልግሎቱን ለማስጀመር የሚያስችሉ መሰረታዊ አቅርቦቶች አለመኖር መሆኑ ተገልጿል።በዘርፉ በደረሰው ጉዳት በዝርዝር ለማየትና በዋጋ ተምኖ ለማቅረብ፤ ጥፋቱ እንዴትና በማን እንደተፈጸመ የመለየት ስራ እየተሰራ ሲሆን ሲጠናቀቅ ከፖሊስ ጋር በጋራ የሚገለጽ ይሆናልም ተብሏል።(በሳራ ስዩም)
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%89%8b%e1%88%a8%e1%8c%a0%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%89%b4%e1%88%8c%e1%8a%ae%e1%88%9d-%e1%8a%a0/
233
0ሀገር አቀፍ ዜና
በፈተናዎች የባከነውን ጊዜ ለማካካስ ከፍተኛ ጥረት ከማድረግ ባሻገር ገፅታ የመቀየር ስራ ይሰራል – አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በፈተናዎች የባከነውን ጊዜ ለማካካስ ከፍተኛ ጥረት ከማድረግ ባሻገር ገፅታ የመቀየር ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡አምባሳደር ሬድዋን ሀገሪቱ ላይ የተጋረጡት የኮቪድ 19፣ የአንበጣ መንጋ፣ የጎርፍ፣ ስራ አጥነት እና ሌሎችም ችግሮች ለውጡን ባይቀለብሱም ፍጥነቱን ግን እንደቀነሱት አስረድተዋል፡፡ለዚህ ከፍተኛ ሃላፊነት መንግስት፣ ማህበረሰቡ እና መገናኛ ብዙሃን በቁርጠኝነት ሊዘጋጁ ያገባል ብለዋል፡፡በፅንፈኛው የህወሃት ቡድን ላይ እየተወሰደ ስላለው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ተያያዥ ጉዳዮች ገለፃ አድርገዋል፡፡የፅንፈኛው ቡድን አካሄድ ባለፈው ሁለት አመት ተኩል ከቀደመው ጊዜ አንፃር ተመሳሳይነትም ልዩነትም ባለው መንገድ የሚገለፅ ነው ያሉት አምባሳደር ሬድዋን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መመረጥ በኋላ ቡድኑ የማኩረፍ እና እራሱን የማግለሉን ነገር ማጠናከሩን ገልፀዋል፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህም መቀሌ የመሸገው ቡድን ከቃላት ዘለፋ አልፎ በግልፅ ህገ መንግስቱን የመጣስ እርምጃ ወስዷል ብለዋል፡፡እነዚህ ግልፅ ጥሰቶች ሲፈፀሙ መንግስት ዋጋ በመክፈል በትዕግስት አልፏል ያሉት አምባሳደሩ ሀገሪቱን ሌላ ምስቅልቅል ውስጥ ላለመክተት ወዲያውኑ እርምጃ ከመወሰድ በመቆጠብ ህገ ወጥ እንቅስቃሴውን ለመታገል ተሞክሯል ብለዋል፡፡(በሳሙኤል ሀጎስ)  
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8d%88%e1%89%b0%e1%8a%93%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%89%a3%e1%8a%a8%e1%8a%90%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8c%8a%e1%8b%9c-%e1%88%88%e1%88%9b%e1%8a%ab%e1%8a%ab%e1%88%b5-%e1%8a%a8%e1%8d%8d/
152
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማድረግ ተስማማች
ዓለም አቀፍ ዜና
December 11, 2020
Unknown
ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመጀመር ከተስማሙ የአረብ አገራት ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።በአሜሪካ አደራዳሪነት የተደረሰውን ስምምነት ፕሬዝደንት ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል።ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ከስምምነት መድረሷን ተከትሎ በዌስተርን ሳሃራ ግዛት ለምታነሳው የይገባኛል ጥያቄ አሜሪካ እውቅና ለመስጠት ተስማምታለች።ሞሮኮ ከነሐሴ ወር ወዲህ ከእስራሴል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማሻሻል ከስምምነት የደረሰች አራተኛዋ አገር ሆናለች።በቅርቡ የትራምፕ አስተዳደር ሱዳን፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ እና ባህሬን ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዲያወርዱ ማደራደሩ ይታወሳል።ከዚህ ቀደም ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት የፈረሙት ግብጽ እና ጆርዳን ሲደመሩ፤ ከአረብ ሊግ አባል አገራት ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት የደረሱት አገራት ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ ይላል ሲል ቢቢሲ በድረ ገፁ ዘግቧል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/%e1%88%9e%e1%88%ae%e1%8a%ae-%e1%8a%a8%e1%8a%a5%e1%88%b5%e1%88%ab%e1%8a%a4%e1%88%8d-%e1%8c%8b%e1%88%ad-%e1%8b%b2%e1%8d%95%e1%88%8e%e1%88%9b%e1%88%b2%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%8c%8d%e1%8a%95%e1%8a%99/
93
4ዓለም አቀፍ ዜና
ለዜጎች የሚደረገው ጥንቃቄና ሰብዓዊ ድጋፍ የሚደነቅ ነው – የትግራይ ተወላጆች
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
በአዳማ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በመንግስት እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር ሂደት እና በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡በውይይቱ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ እየተደረገ ያለው ጥንቃቄ እና የሰብዓዊ ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን ተወላጆቹ ተናግረዋል፡፡በከተማዋ ደህንነታቸው እና መብታቸው ተጠብቆ ለረዥም አመታት መኖራቸውን ያነሱት ተወላጆቹ አጥፊው የትህነግ ቡድን ላይ በመንግስት እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡በውይይቱ የትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ) ፅንፈኛ ቡድንን መንግስት ለህግ ለማቅረብ እየሠራ ነው ያሉት የአዳማ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አለማየሁ ቱሉ በህግ የማስከበር ተግባሩ የትግራይ ህዝብ እና ትህነግ አንድ እንዳልሆኑ በተግባር የታየበት ነው ብለዋል፡፡በዚህም በከተማዋ በርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ተዋደው እና ተከባብረው የሚኖሩባት እንደመሆኑ ይህ ሰላማዊ የሆነ አካሄድ ለማስቀጠል እንደሚሰራም ኃላፊዊው ተናግረዋል፡፡የትህነግ ቡድን አባላትን ለህግ ለማቅረብ የሚደረገው ሂደት በመደገፍ ለሀገር ሰላም መረጋገጥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድሻውን መወጣት እንደሚገባም ተገልጿል፡፡ (በብዙአየሁ ወንድሙ)  
https://waltainfo.com/am/%e1%88%88%e1%8b%9c%e1%8c%8e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%b0%e1%88%a8%e1%8c%88%e1%8b%8d-%e1%8c%a5%e1%8a%95%e1%89%83%e1%89%84%e1%8a%93-%e1%88%b0%e1%89%a5%e1%8b%93%e1%8b%8a-%e1%8b%b5%e1%8c%8b/
120
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኮቪድ 19 ክትባት ክፍፍል ፍትሀዊ አለመሆኑ ተገለጸ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
በሀብት የበለፀጉ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባቶችን በማከማቸት ታዳጊውን ዓለም ወደ ኋላ በመተው ላይ መሆናቸውን ዓለም አቀፉ የክትባቶች ህብረት አስታወቀ፡፡በሀብት የበለፀጉት ሀገራት ህዝቦቻቸውን በሶስት እጥፍ ለመከተብ የሚያስችል በቂ የኮቪድ 19 ክትባት መግዛታቸውንና ታዳጊ ሀገራት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ዓለም አቀፉ የክትባት ክትትል ቡድን አስታውቋል፡፡በዚህም ምክንያት በ67 ታዳጊ ሀገራት ውስጥ ከሚኖሩ 10 ሰዎች መካከል ቢያንስ አንዱ ብቻ ክትባቱን በሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ያገኛል ተብሎ ይታሰባል፡፡ታዳጊ ሀገራት አሁንም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለማስቆም በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ኋላ መቅረታቸውንም መረጃው ጠቁሟል፡፡ከዓለም ህዝብ ቁጥር 14 በመቶውን ብቻ የሚይዙ ያደጉት ሀገራት ተስፋ ሰጭ ክትባቶችን ከግማሽ በላይ ለመግዛት ቀድመው ማዘዛቸውም ተገልጿል፡፡ቡድኑ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ቴክኖሎጂአቸውንና አዕምሯዊ ንብረታቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት እንዲያካፍሉ ያሳሰበ ሲሆን መንግስታትም ከአደገኛው የኮቪድ-19 ተፅዕኖ ለመላቀቅ ክትባቶችን ወደ ታዳጊ ሀገራት ለመላክ ቁርጠኛ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ማንኛው ሰው ኪሱ ውስጥ ባለው ገንዘብና በሚኖርት ሀገር ምክንያት ብቻ ህይወት አድን የሆነውን የኮቪድ ክትባት ማጣት የለበትም ሲሉም ክትባቱ ለህዝብ እንዲደርስ ከሚሰሩ የበጎ አድራት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የኦክስፋም የጤና ፖሊሲ ሥራ አስኪያጅ ተናግረዋል፡፡አሁን ያለው አካሄድ ካልተቀየረ  በቢሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ደህንነቱ የተረጋገጠ የኮቪድ ክትባትን ለማግኘት ከባድ ይሆንባቸዋልም ተብሏል፡፡ካናዳ የዜጎቿን ሶስት እጥፍ ለመከተብ የሚያስችል ክትባት የገዛች ሲሆን ከ50 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ  ለ88 ከመቶው ህዝቧየሚሆን በቂ ክትባት መግዛት ችላለች፡፡ማረጋገጫ ከተሰጣቸው ክትባቶች 96 በመቶ በአደጉት ሀገራት መያዛቸውን የገለጸው ቡድኑ በዚህ ምክንያት 67 ሀገራት የኮቪድን ክትባት የማግኘት እድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን ማስታወቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡በትዕግስት ዘላለም 
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%89%aa%e1%8b%b5-19-%e1%8a%ad%e1%89%b5%e1%89%a3%e1%89%b5-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%8d%8d%e1%88%8d-%e1%8d%8d%e1%89%b5%e1%88%80%e1%8b%8a-%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%88%98%e1%88%86%e1%8a%91/
210
4ዓለም አቀፍ ዜና
የአማራ ባንክ አ.ማ የውክልና ግዜው ተራዘመ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
የአማራ ባንክ አ.ማ የውክልና ግዜው እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙ ተገለጸ፡፡የአክሲዮን ሽያጩን ህዳር 21 ቀን 2013 ሲያጠናቅቅ 8 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ቃል የተገባና 6 ቢሊዮን ብር ደግሞ የተከፈለ ካፒታል ማሰባሰብ መቻሉን የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ መላኩ ፈንታው ተናግረዋል፡፡ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት የባለአክሲዮኖች ቁጥር መብዛትና የኮሮና መመሪያ ጉባኤውን ማካሄድ የማይቻል በመሆኑ በውክልና ተሳታፊ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡በመሆኑም የውክልና ጊዜ ማራዘም እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል፡፡በተጨማሪም በኢንሹራንስ ዘርፍ ለመሰማራት ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑ ተገልፆ አለም አቀፍ ተደራሽ የሆነ ባንክ ለማድረግም ይሰራል ተብሏል፡፡አማራ ባንክ አ.ማ 185 ሺህ ባለአክሲዮኖች እንዳሉት ተገልጿል፡፡  
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%9b%e1%88%ab-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ad-%e1%8a%a0-%e1%88%9b-%e1%8b%a8%e1%8b%8d%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%8a%93-%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%8b%8d-%e1%89%b0%e1%88%ab%e1%8b%98%e1%88%98/
86
0ሀገር አቀፍ ዜና
የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ የ10 አመት እቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ የ10 አመት እቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት በሀዋሳ ከተማ ዛሬ ተጀምሯል፡፡በመድረኩ የኤጀንሲውን የሪፎርም ስራዎች እና የ10 አመት እቅዱን ገቢራዊ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እየተደረገ ነው።የክልሎች የህብረት ስራ የስራ ሀላፊዎች እየተሳተፉ በሚገኙበት በዚሁ መድረክ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት በ2012 በጀት አመት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመቋቋም አመርቂ ዉጤት ማስመዝገብ ተችሏል።የሴክተሩን የ10 አመት   መሪ አቅድ ተፈፃሚ ለማድረግም ዘመናዊ የአሰራር ስርአትን መተግበር ይገባል ብለዋል።የህብረት ስራ ሴክተር ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ ከቻለባቸው ስኬቶች መካከል የአባላትን ቁጥርና ካፒታል ማሳደግ   መቻሉን ለአብነት አንስተዋል።በዘርፉ ለተመዘገበው ውጤት የሴክተሩ አካላት በቅንጅት መስራታቸው መሆኑንም ለአብነት አንስተዋል።(በበሀይሉ ጌታቸው)
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8d%8c%e1%8b%b0%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%88%85%e1%89%a5%e1%88%a8%e1%89%b5-%e1%88%b5%e1%88%ab-%e1%8a%a4%e1%8c%80%e1%8a%95%e1%88%b2-%e1%8b%a810-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%89%85/
93
0ሀገር አቀፍ ዜና
የውጪ መገናኛ ብዙሀን በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተዛባ መረጃ እያሰራጩ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተዛባ መረጃ የሚያሰራጩ የውጪ መገናኛ ብዙሀን  ስራቸውን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ከመስራት ይልቅ በጥቅም የተሳሰሩ አካላት የሚሰጡዋቸውን መረጃ እውነትነት ሳያረጋግጡ እያቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ዋልታ ያነጋገራቸው ምሁራን የኢትዮጵያ መንግስት እየሰራው ባለው የዲፕሎማሲ ስራ  እውነታውን ለአለም እያሳወቀ በመሆኑ ለውጥ ማምጣቱን ጠቅሰው አሁንም ያለውን መረጃ በወቅቱ ማድረስ ላይ የተጠናከረ ስራ መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ጥቂቶቹ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ሚዛናዊ ና ትክክለኛ መረጃን ለማድረስ ሲሞክሩ በርካቶች ደግሞ ከእውነት የራቀና የራሳቸውን መላምት የሚመስሉ ዘገባዎችን እያሰራጩ ነው ተብሏል፡፡መንግስት በሰራው እውነታውን ለአለም የማሳወቅ ዲፕሎማሲያዊ ስራ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀኑ መጠነኛ ማሻሻያ ቢያሳዩም አሁንም አጀንዳዎችን እየቀረጹ ጉዳዩን የተለያየ ምልከታ እንዲሰጠው እያደረጉ ይገኛሉ፡፡የኢትዮጵያ መንግስት እውነታውን ለአለም የማሳወቅ ስራ መስራት በመቻሉ በጉዳዩ ላይ መጠነኛ ለውጥ መጥቷል ያሉት ምሁራኑ አሁንም የደረሰበትን ወቅታዊ ሁኔታ በወቅቱ እና በስፋት መረጃዎችን የመስጠት ስራ መስራት አለበት ብለዋል፡፡እንዲሁም አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀኑን  ህግ የማስከበር ዘመቻው የተካሄደበትን ቦታ ወስዶ ያለበትን ሁኔታ ሊያስመለክታቸው ይገባል ብለዋል፡፡በመስከረም ቸርነት  
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8b%8d%e1%8c%aa-%e1%88%98%e1%8c%88%e1%8a%93%e1%8a%9b-%e1%89%a5%e1%8b%99%e1%88%80%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%8b%88%e1%89%85%e1%89%b3%e1%8b%8a-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5/
142
0ሀገር አቀፍ ዜና
የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ ለ2ኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፉ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
የጋና ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ በድጋሚ ምርጫ በማሸነፋቸው ተጨማሪ የአራት ዓመት የስልጣን ጊዜ እንዳገኙ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡የ 76 ዓመቱ አኩፎ አዶ 51 ነጥብ 6 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ሃላፊ ጄን ሜንሳ ገልጸዋል።ተቀናቃኛቸው ናሽናል ዴሞክራቲክ ኮንግረስ መሪ ጆን ማሃማ 47 ነጥብ 4 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸውንም የኮሚሽኑ ሃላፊ አስታውቀዋል።በ 38 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች 17 ሚሊየን መራጮች መሳተፋቸው የተገለጸ ሲሆን ፣ መራጮች ለብሔራዊ ፓርላማ 275 የሕግ አርቃቂዎች መምረጣቸውም ሲጂቲኤን አስነብቧል፡፡አፍሪካ ህብረት፣ ኢኮዋስ እና የምዕራብ አፍሪካ የተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት በጋራ በሰጡት መግለጫ የጋና ህዝብ ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ በማከናወኑ አመስግነዋል። 
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8c%8b%e1%8a%93-%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%9a%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%8a%93%e1%8a%93-%e1%8a%a0%e1%8a%a9%e1%8d%8e-%e1%88%882%e1%8a%9b-%e1%8c%8a%e1%8b%9c-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab/
90
4ዓለም አቀፍ ዜና
ባለፈው አንድ ወር ውስጥ 370 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ የህወሃት ጁንታ ተላላኪ በሆነው ኦነግ ሸኔ ላይ ሲወስድ በነበረዉ እርምጃ 370 መደምሰሳቸው ተገልጿል ፣ 176 ደግሞ  በፖሊስቁጥጥር ስር መዋላቸው እና 154 ደግሞ በህዝቡ መያዛቸውም ተመልክቷል፡፡በዚሁ ወቅት ትጥቅና ስንቅ ለሽፍታዉ ሲያቀርቡ የነበሩ 183 የህወሃት  አባላትም በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል፡፡በሎጂስቲክ በኩል 4 ብሬኖችን ጨምሮ 1585 ጠመንጃዎች፣ 10,902 ጥይቶች፣ 605 ከብቶች፣ 353 ፍየሎች፣ 54 አህዮች፣ 48 ግመሎች፣ 682,680 ብር እና 204,000 የሀሰት ገንዘብ መያዙም መገለጹን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የኦሮሚያ ፖሊስን ጠቅሶ  አስታውቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%88%e1%8b%8d-%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8b%b5-%e1%8b%88%e1%88%ad-%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%8c%a5-370-%e1%8b%a8%e1%8a%a6%e1%8a%90%e1%8c%8d-%e1%88%b8%e1%8a%94-%e1%89%b3%e1%8c%a3%e1%89%82/
77
0ሀገር አቀፍ ዜና
የተባበሩት መንግስታት የዳርፉር ተልዕኮውን እንዲያራዝም አምነስቲ ጠየቀ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሱዳን መንግስት ለንጹኃን ዜጎች ጥበቃ ማድረግ ባለመቻሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሱዳን ዳርፉር ያለውን ተልዕኮ ለስድስት ወራት እንዲያራዝም ጠይቋል፡፡የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ መንግስት በተቆጣጠረባቸው አካባቢዎች የሱዳን ኃይሎች ለዜጎች ጥበቃ ማድረግ አለመቻላቸውን በመጥቀስ ነው ድርጅቱ ተልዕኮውን እንዲያራዝም ጥያቄ ያቀረበው፡፡የሱዳን መንግስት ኃይሎች ንጹሃን ዜጎችን ለመጠበቅ ያላቸው ዝግጁነት እንዳሳሰበውም  ገልጿል ፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ዜጎች በአማጺያን ከሚሰነዘሩባቸው ጥቃቶች ለሚያደርገው ጥበቃ አምነስቲ አመስግኗል::እ.ኤ.አ. ከ2003 ጀምሮ በሱዳን መንግሥት እና በአማጺያን በተደረገ ውጊያ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ከቄያያቸው ተፈናቅለዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%89%a3%e1%89%a0%e1%88%a9%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%b5%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8b%b3%e1%88%ad%e1%8d%89%e1%88%ad-%e1%89%b0%e1%88%8d%e1%8b%95%e1%8a%ae/
89
4ዓለም አቀፍ ዜና
በሚዲያ ተቋማት አካል ጉዳተኞችን አካቶ መስራት የሚያስችል የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
በሚዲያ ተቋማት አካል ጉዳተኞችን አካቶ መስራት የሚያስችል የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነየመንግስትና የግል ሚዲያ ተቋማት አካል ጉዳተኞችን አካቶ መስራትን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና የምክክር መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው፡፡በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አዘጋጅነት ለሶስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ የተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያ ባለሙያዎችና አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ሚኒስቴሩ አካል ጉዳተኞችን በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ውስጥ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡በተለይም የመንግስትና የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አካል ጉዳተኞችን አካታችና ተደራሽ በሆነ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚዲያ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ ነውም ተብሏል፡፡መድረኩ የፌደራልና የክልል ሚዲያ ተቋማት አካል ጉዳተኞችን አካተው የሚሰሩበትንና ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን የሚወጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ያለመ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ (በአድማሱ አራጋው)
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%9a%e1%8b%b2%e1%8b%ab-%e1%89%b0%e1%89%8b%e1%88%9b%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%8a%ab%e1%88%8d-%e1%8c%89%e1%8b%b3%e1%89%b0%e1%8a%9e%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%8a%ab%e1%89%b6-%e1%88%98/
98
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሕብረታችንን ለማጠናከር አል-ሸባብ እና ኦነግ-ሸኔን ከቀጠናው ማስወገድ አለብን- ጠ/ሚ ዐብይ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ኬንያ እና ኢትዮጵያ የአል-ሸባብ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር- ሸኔ ታጣቂዎችን ከቀጠናው ቢያስወግዱ የሁለቱ አገራት ሕብረት እንደሚጠናከር ተናገሩ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት በሞያሌ የተገነባውን የድንበር መተላለፊያ ከፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው።“አል-ሸባብ እና ኦነግን ከቀጠናው ብናስወግድ ሕብረታችን ይጠነክራል” ብለው ተናገሩ ሲሆን ኦነግ ሲሉ ኦነግ-ሸኔ የተባለውን ታጣቂ ቡድንን እንደሆነ የጠቅላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ገልጸዋል።ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከኦነግ ተገንጥሎ በመውጣት በምዕራብ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር በምትዋሰንበት ደቡባዊ ክፍል የትጥቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ ይነገራል።ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማምጣት የአካባቢው ደህንነት ማረጋገጥ ግድ መሆኑን ተናግረዋል።“የደኅንነት ችግር እያለብን ኢኮኖሚያዊ ድል ማስመዝገብ አይቻለንም” ያሉት ፕሬዝደንት ኡሁሩ፤ “እንደ ሁለት ጎረቤት አገራት በውስጣችን እየኖሩ የኢትዮጵያንም የኬንያንም ሰላም የሚያውኩት ላይ መስራት ይኖርብናል” ብለዋል።ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንሰትሩ “መሰረተ ልማቶች ላይ በጋራ እንደምንሰራው ሁሉ የአከባቢውን ደህንነት ለማረጋገጥ እንድንሰራ” ለፕሬዝደንት ኡሁሩ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ብለዋል።(ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/%e1%88%95%e1%89%a5%e1%88%a8%e1%89%b3%e1%89%bd%e1%8a%95%e1%8a%95-%e1%88%88%e1%88%9b%e1%8c%a0%e1%8a%93%e1%8a%a8%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%88%8d-%e1%88%b8%e1%89%a3%e1%89%a5-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8a%a6/
133
0ሀገር አቀፍ ዜና
በጃንሜዳ የሚገኙ የአትክልት ነጋዴዎች ወደ ኃይሌ ጋርመንት መገበያያ ስፍራ ይዛወራሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
Unknown
ከቀጣይ ሳምንት በኃላም በጃንሜዳ የሚገኙ የአትክልት ነጋዴዎች ወደ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ የተገነባው የአትክልት መገበያያ ስፍራ እንደሚዛወሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።ምክትል ከንቲባዋ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በግንባታ ላይ ያለውን የአትክልት መገበያያ ስፍራን ጎበኝተዋል።የአትክልት መገበያያ ስፍራውን የግንባታ ሂደት ተዘዋውረው የጎበኙት ምክትል ከንቲባዋ በመጀመሪያው ምዕራፍ እየተገነቡ ያሉ አብዛኛው የመገበያያ ሼዶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን የተመለከቱ ሲሆን ከቀጣይ ሳምንት በኃላም በጃንሜዳ የሚገኙ የአትክልት ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ የማንሳት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ 80 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እየተገነባ ያለው የአትክልት የገበያ ማዕከል በመጀመሪያው ምዕራፍ ከሚገነቡት አስራ አራት ሼዶች እያንዳንዳቸው ሼዶች ሰባ ሜትር በ6 ነጥብ 6 ሜትር ስፋት እንዲሁም 588 የመገበያያ ሱቆች እንደሚኖሩት ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። 
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8c%83%e1%8a%95%e1%88%9c%e1%8b%b3-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8c%88%e1%8a%99-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%89%b5%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%89%b5-%e1%8a%90%e1%8c%8b%e1%8b%b4%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8b%88/
124
0ሀገር አቀፍ ዜና
መዲናዋ የስነምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን እንደሌላት ተገለጸ የስነምግባር እና ጸረ-ሙሽና ኮሚሽን እንደሌላት ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ የማቋቋሚያ ቻርተር  የስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በከተማዋ ተቋቁሞ እንዲያስተዳድር በህግ ቢደነገግም ከተማዋ ግን እስካሁን የስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን እንደሌላት ተገለጸ፡፡የፌዴራል ስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ከከተማና ከክፍለ ከተማ ከተውጣጡ አመራሮች ጋር አዲስ በተዋቀረው የስነ ምግባር  መከታተያ አደረጃጀት ላይ ውይይት አድርጓል፡፡የፌዴራል ስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጸጋ አረጋ በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሶስት አመታት ምከንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በከተማ፣ በክፍለ ከተማና ወረዳ አደረጃጀት የነበሩ የስነምግባር መከታተያ መዋቅሮች ፈራርሰው ቆይተዋል ብለዋል፡፡የፌደራል ስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ከተሞች በራሳቸው ህግ ማእቀፍ አቋቁመው የስነምግባርና ጸረ-ሙስና ጉዳዮችን እንዲከታተሉ መወሰኑን የገለጹት ኮሚሽነር ጸጋ፣ ለጊዜው በየአደረጃጀቱ የተቋቋመው የስነምግባር መከታተያ ስርዓት በርካታ ስራዎችን እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡በከተማዋ የተደራጀ የስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን መከታተያ አደረጃጀት ባለመኖሩም በከተማዋ የህዝብ ሀብት ያለአግባብ እንዲመዘበር እና ብልሹ አሰራር እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአገልግሎት  ሰጪ  ተቋማት አስተባባሪ ዣንጥራር አባይ ሙስና ከጊዜያዊ ጥቅም ሊያልፍ እንደማይችል ገልጸው፣ በከተማዋ የተዋቀረው የስነምግባር መከታተያ አደረጃጀት ስራውን በተገቢው መልኩ እንዲያከናውን የሁሉም የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ሚና ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡ይህንን መዋቅር በድጋሚ ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑም በአዲስ መልክ የስነምግባር መከታተያ አደረጃጀት መዋቀሩን ተናግረዋል፡፡የሀገሪቱ ከፍተኛ ሀብት በሚንቀሳቀስባት አዲስ አበባ ከተማ እስካሁን የስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን አለመኖሩን ተከትሎ ሙስና እንዲንሰራፋ እድል የሚሰጥ ነው ሲሉ ከከተማና ክፍለ ከተማ የተውጣጡ አመራሮች በውይይት መድረኩ ላይ አንስተዋል፡፡እስከ ታህሳስ 30 ሁሉም የመንግስት ሰራተኞችና የመንግስት የልማት ድርጅት ሰራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡም መመርያ ወጥቷል፡፡ (በመስከረም ቸርነት)
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b%e1%8b%8b-%e1%8b%a8%e1%88%b5%e1%8a%90%e1%88%9d%e1%8c%8d%e1%89%a3%e1%88%ad-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8c%b8%e1%88%a8-%e1%88%99%e1%88%bd%e1%8a%93-%e1%8a%ae%e1%88%9a%e1%88%bd/
201
0ሀገር አቀፍ ዜና
“የሲንቄ/ሲቆ ባህላዊ ስነስርአት ምንነት እና በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ያላት ሚና” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መጽሐፍ ተመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
“የሲንቄ/ሲቆ ባህላዊ ስነስርአት ምንነት እና በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ያላት ሚና” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመረቀ፡፡የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የግጭት መፍትሔ የሆነችውን የስንቄን ባህላዊ ስነስርአት ምንነት ለማህበረሰቡ ለማስተዋወቅ ብሎም ለትውልድ ለማስተላለፍ በጥናት ተደግፎ ለህትመት የበቃ መጽሐፍ ስለመሆኑ ታውቋል።በምረቃ ስነስርአት ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው የሀደ ስንቄ ባህላዊ ስነስርአት ለሰላም የቆመ በመሆኑ ከአማረኛ ቋንቋ በዘለለ ባህላችንን ለአለም ለማሳወቅ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እየተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡የሰላም ምልክት የሆነችውን የሀደ ስንቄ በትር ከያዝን ጦርነቱ ወደ እርቅ ይቀየራል፤ ሰላም ምልክታችንም ይሆናል ሲሉ ዶ/ር ሂሩት ተናግረዋል።በመጽሐፍ ምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ከበደ ደሲባ በበኩላቸው፣ ሴቶች እናትም፣ እህትም፣ ሚስትም ልጅም ናቸው፤ ለሀገራችን ሰላም ሀደ ስንቄ መፍትሄ ናት ብለዋል።(በቁምነገር አህመድ)
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%b2%e1%8a%95%e1%89%84-%e1%88%b2%e1%89%86-%e1%89%a3%e1%88%85%e1%88%8b%e1%8b%8a-%e1%88%b5%e1%8a%90%e1%88%b5%e1%88%ad%e1%8a%a0%e1%89%b5-%e1%88%9d%e1%8a%95%e1%8a%90%e1%89%b5/
121
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያስተሳስረውን የመንገድ ፕሮጀክት መረቁ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሐዋሳ-ቡሌ ሆራ-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ መንገድ እና የጋራ ፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክትን ዛሬ በይፋ መርቀዋል።500 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውና የሞምባሳ-ናይሮቢ-አዲስ አበባ ኮሪደር አካል የሆነው መንገዱ ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያስተሳስር መሆኑ ተገልጿል።በመንገዱ ምረቃ መርሐ ግብር ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ባለሥልጣናት ታድመዋል።ይኸው የሐዋሳ-ቡሌ ሆራ-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል።የሐዋሳ-ቡሌ ሆራ መንገድ የመጀመሪያው ኮሪደር 199 ነጥብ 6 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን፣ ግንባታው ከ3 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በሦስት ተቋራጮች ግንባታው ተከናውኗል።ቡሌ ሆራ-ያቤሎ ያለው ሁለተኛው ኮሪደር 192 ነጥብ 3 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው እና ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ነው።በአጠቃላይ የአዲስ አበባ-ሐዋሳ-ቡሌ ሆራ-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ መንገድ ግንባታ አዲስ አበባን ከካይሮ፣ ጋቦሮኒ፣ ኬፕ ታውን እና ኬንያ-ሞምባሳ የሚያገናኝ ከመሆኑም ባሻገር ደቡብ ሱዳንን-ከኬንያ ላሙ ወደብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል መሆኑ ታውቋል።በሌላ በኩል ሦስተኛው እና የኢትዮጵያን መሬት አቋርጦ የሚያልፈው የትራንስ-አፍሪካ አውራ ጎዳና የመጨረሻው ኮሪደር የሆነው 109 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የሜጋ-ሞያሌ መንገድ ግንባታ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተጠናቅቆ በይፋ ተመርቋል።በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቦረና ዞን ከምትገኘው ከሜጋ ከተማ ጀምሮ እስከ ሞያሌ የሚዘልቀው ይኸው የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል የወጪ እና ገቢ ንግድን የሚያጠናክር ነው ተብሏል።በአጠቃላይ ከሐዋሳ-ሞያሌ የሚዘልቀው 500 ኪ.ሜ መንገድ እና የጋራ ፍተሻ ኬላ የጉምሩክ፣ የኢሚግሬሽን፣ የጤና እና የደረጃ ድርብርብ ፍተሻ በማስቀረት የጉምሩክ ሥርዓቱን ግልጽ፣ ቀላል እና ቀልጣፋ እንደሚያደርግ ታውቋል።ከዚህ ባለፈ በድርብርብ የፍተሻ አሠራር የሚባክነውን ጊዜ እና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስቀር ነው ተብሏል።መንገዱ የኢትዮጵያ እና ኬንያን የወጪ እና ገቢ ንግድ በማቀላጠፍ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ ቀደም ሲል የተጎዳ ይዞታ እንደነበረው ተጠቁሟል።ዘገባው የኢቢሲ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8c%a0%e1%89%85%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%8b%90%e1%89%a2%e1%8b%ad-%e1%8a%a0%e1%88%95%e1%88%98%e1%8b%b5-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab/
243
0ሀገር አቀፍ ዜና
ዳያስፖራው ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ስለ ሕግ ማስከበር ዘመቻው በማስረዳት ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል – የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
ዳያስፖራው ሐሰተኛ መረጃዎችን በማጋለጥ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የሕግ ማስከበር ዘመቻውን በትክክል እንዲገነዘብ ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረጉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።ኤጀንሲው ዳያስፖራው ለሠብዓዊ ድጋፍ 80 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ማበርከቱንም ገልጿል።ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ በህወሓት ቡድን ላይ የተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተጠናቆ ተልዕኮው ወደ ‘ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ’ መሸጋገሩ ይታወቃል።የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ሠራዊቱ ላይ በተፈፀመው ጥቃት የዳያስፖራው ስሜት የነበረው የመደናገጥ፣ የመጨነቅና ስለ ጉዳዩ ማብሪሪያ የመጠየቅ እንደነበር ለኢዜአ ገልጸዋል።ኤጀንሲው ሚሲዮኖችን፣ በውጭ አገሮች የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበራት፣ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ሌሎች የዳያስፖራ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የተፈፀመውን ጥቃትና የሕግ ማስከበር ዘመቻውን አስመልክቶ ትክክለኛ መረጃ የማድረስ ስራ መከወኑን ተናግረዋል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%b3%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%8d%96%e1%88%ab%e1%8b%8d-%e1%88%88%e1%8b%93%e1%88%88%e1%88%9d%e1%8a%a0%e1%89%80%e1%8d%89-%e1%88%9b%e1%8a%85%e1%89%a0%e1%88%a8%e1%88%b0%e1%89%a5-%e1%88%b5%e1%88%88/
107
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ ከሚኖሩ የሞያሌ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ    
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሁለቱ አገራት የጋራ ድንበር ላይ በኬንያ ከሚኖሩ የሞያሌ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኬንያ ይገኛሉ።ሁለቱ መሪዎች አዲሱ ድንበር ተሻጋሪ መሠረተ ልማት ቀጠናዊ ትስስር ያጠናክራል፤ የሰዎች ለሰዎች ግንኙነትን በመጨመር ንግድን ያሳድጋል ብለዋል።                                                                                                                                                                                        መሪዎቹ ነዋሪዎች በቀጠናው አካባቢ የግለሰብ ግጭቶችን እንዲያስወግዱ አሳስበው፣ የኬንያ እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በሁለቱ አገራት ድንበር ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት አበክረው እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን የኬንያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ አመልክቷል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8c%a0%e1%89%85%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%8b%90%e1%89%a2%e1%8b%ad-%e1%8a%a0%e1%88%95%e1%88%98%e1%8b%b5-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%9a/
71
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያውያን በታሪካችን መተሳሰብ እንጂ እርስ በእርስ መጠፋፋት አይመጥነንም –  ፕሬዝዳንት ሳለወርቅ ዘውዴ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
በትላንትናው እለት 15 ኛው የብሄር ብሔረሰቦች ቀን በዓል በደማቅ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን የማጠቃለያ እና የመዝጊያ ስነ-ስዓቱም ማምሻውን በወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል ፡፡በመዝጊያ ስነ- ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ  ኢትዮጵያውያን በታሪካችን መተሳሰብ እንጂ እርስ በእርስ መጠፋፋት አይመጥነንም ያሉ ሲሆን ታሪካችንን አናበላሽ ብለዋል፡፡ፕሬዝዳንቷ አክለውም ታሪክ ራሱን ይደግማል ይባላል ፤ ነገር ግን መለወጥ ያቃተን እና ክፉ ታሪክን እየደገምን ያለነው እኛ ነን ብለዋል ፡፡ከግለሰብ ጀምሮ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን መብት እና ግዴታ ማወቅ አለበት ያሉት ፕሬዝዳንቷ የሀገር ሉአላዊነት ጥያቄ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ጥንቃቄ ይደረግ ብለዋል ፡፡ሁሉም ሰው ለራሱ ሊያሰምር የሚገባው ቀይ መስመር አለ ያሉት ፕሬዝዳንቷ ይህንን ቀይ መስመር ጥሶ ማንም ሰው የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ሊያደርግ አይገባውም ሲሉም ተናግረዋል ፡፡ሁላችንም ኢትዮጵያ የምትባል መርከብ ላይ ተሳፍረናል፣ ለዚህም የምናደርጋቸው እና የምንወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ እስከወዲያኛው ዋጋ እንዳያሥከፍሉን እንጠንቀቅ ብለዋል ፡፡እያንደንዱ የህብረተሰብ ክፍል ከራሱ ጀምሮ እስከ ሀገር ደረጃ የሚሰራቸው፣ የሚያስባቸው እና የሚያከናውናቸው ነገሮች በሀገር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደማያመጡ ሊያውቅ እና ሊያረጋግጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ልዩነታችን ውበታችን እንደሆነው ሁሉ የሃሳብ እና የፖለቲካ ልዩነታችንንም እንደ  ጸጋ ልንቆጥረው ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቷ የፖለቲካ፣ የዘር፣ የቋንቋ እና የአስተሳሰብ ልዩነቶቻችንን ጸጋ አድርገን ልንቆጥረው እንጂ እንደ መርገም ልናየው አይገባም ብለዋል ፡፡ብሄር ብሄረሰቦች በቀጣይ የኢትዮጵያን ትንሳኤ በማረጋገጥ የራሳቸውን አሻራ በማኖር ለለውጥ እና ለብልጽግና የምናደርገውን እርምጃ እናፋጥን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡ (በሜሮን መስፍን) 
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8b%8d%e1%8b%ab%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%89%b3%e1%88%aa%e1%8a%ab%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%88%98%e1%89%b0%e1%88%b3%e1%88%b0%e1%89%a5-%e1%8a%a5%e1%8a%95/
197
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑዌላ ዴል ሬ ጋር በስልክ ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
የሰላም ሚኒስትር  ሙፈሪሃት ካሚል ከጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑዌላ ዴል ሬ ጋር የስልክ ውይይት አካሂደዋል።ሚኒስትሯ በህወሓት ጁንታ ላይ ሲካሄድ የነበረው ህግ የማስከበር ተግባር መጠናቀቁን እና በሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ ስላለው ትብብር ገለፃ አድርገዋል፡፡የሕግ ማስከበር ሥራው ሲቪሎችንና መሠረተ ልማቶችን ከጉዳት ለመጠበቅ እጅግ በጣም ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መከናወኑንም ገልፀዋል።ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በበኩላቸው፣ በሕግ ማስከበር ሂደት ወቅት ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ የተደረገውን ጥረት ያደነቁ ሲሆን የጣሊያን መንግስት በኢጣሊያ የቀይ መስቀል ማህበር አማካይነት በተለይ የህክምና ግብዓቶችን በማቅረብ የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ ፍላጎቶችን ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል።በሁለቱ ሀገራት መካከል ለረጅም ጊዜ የዘለቀው የወዳጅነት ግንኙነትም የበለጠ እንደሚጠናከር አረጋግጠዋል ፡፡የሰላም ሚኒስትሯ የጣሊያን መንግስት ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%88%99%e1%8d%88%e1%88%aa%e1%88%83%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%88%9a%e1%88%8d-%e1%8a%a8%e1%8c%a3%e1%88%8a%e1%8b%ab/
104
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጆ ባይደን በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት 100 ሚሊየን ሰዎችን ለመከተብ ማቀዳቸውን ገለጹ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
አዲሱ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ስልጣን በመጡ በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት 100 ሚሊየን ሰዎች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት እንዲያገኙ ለማድረግ ግብ አስቀምጠው እየሰሩ መሆናቸው ገልጸዋል።ባይደን አክለውም ምንም እንኳን በመጀመሪያዎቹ የስልጣናቸው ወራት ወረርሽኙን ማጥፋት ከባድ እንደሚሆን ባይክዱም ክትባቱ እንዴት እንደሚከፋፈልና ጉዳቱ እንዴት መቀነስ እንደሚቻል እቅድ አዘጋጅተናል ብለዋል።ተመራጭ ፕሬዝዳንቱ ጥር ወር ላይ ስራ የሚጀምረው የጤና ቡድናቸውን በሚያስተዋውቁበት ሰአትም አሜሪካውያን ለመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።ትናንት ማክሰኞ ዕለት ደግሞ ፋይዘር/ባዮንቴክ የሚያመርተው ክትባት ለአሜሪካውያን መከፋፈል እንዲጀመር የሚረዳ አንድ ሪፖርት መውጣቱ ደግሞ በበርካቶች ዘንድ ተስፋን አጭሯል።በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮቪድ ክትባት ፕሮግራማቸውን በተመለከተ ዋይት ሀውስ ውስጥ ስብሰባ ያካሄዱ ሲሆን፣ በቅርቡ ፈቃድ ይሰጠዋል የተባለውን ክትባት ፍጥነት አድንቀዋል ተብሏል።በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ መሰረት አሜሪካ እስካሁን ድረስ 15 ሚሊየን ሰዎች በኮሮረና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ 285 ሺህ ሰዎች ደግሞ በዚሁ ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። ይህ ቁጥር በአለማችን ከፍተኛው ነውም ተብሏል።በአሁኑ ሰአት በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች እንደ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም ወደ ሆስፒታሎች እየገቡ ስለመሆናቸው ቢቢሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8c%86-%e1%89%a3%e1%8b%ad%e1%8b%b0%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%aa%e1%8b%ab%e1%8b%8e%e1%89%b9-100-%e1%89%80%e1%8a%93%e1%89%b5-100-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95/
158
4ዓለም አቀፍ ዜና
በህግ ማስከበር ሂደቱ ጉዳት ያጋጠማቸው ወገኖች ያሉባቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
በአላማጣ፣ መኾኒ፣ ጨረጨር፣ ዳንሻ፣ ማይካድራ እና ሌሎች በህግ ማስከበር ሂደቱ ጉዳት ያጋጠማቸው ወገኖች ያሉባቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ተቋማት ከሰላም ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋሙ ብሔራዊ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ጋር በትብብር በርካታ የምግብና ቁሳቁስ ጭነት በዛሬው ዕለት ሽሬ ከተማ ማድረሳቸው ተገልጿል።ስርጭቱ እንደየ ጉዳት መጠን ቅድሚያ እየተሰጠ በተደራጀ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተገልጿል።ድጋፉ ማህበረሰቡን መልሶ እስከማቋቋም የሚዘልቅ ሲሆን የተደራሽነት ክትትል በሚመለከታቸው አካላት በአትኩሮት እየተካሄደ እንደሚገኝ ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። 
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%85%e1%8c%8d-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%88%82%e1%8b%b0%e1%89%b1-%e1%8c%89%e1%8b%b3%e1%89%b5-%e1%8b%ab%e1%8c%8b%e1%8c%a0%e1%88%9b%e1%89%b8%e1%8b%8d-%e1%8b%88/
74
0ሀገር አቀፍ ዜና
የህግ ማስከበር በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንደሚፈጸም ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
መንግስት በትግራይ ክልል በማከናወን ላይ ስለሚገኘው ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብና የህግ ማስከበር በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንደሚፈጸም ተገለጸ፡፡መንግስት በትግራይ ክልል በማከናወን ላይ ስለሚገኘው ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብ እና መልሶ ግንባታ ስራዎችን አስመልክቶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት እና የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን  በጋራ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንደገለጹት፣ መንግስት በትግራይ ክልል በማከናወን ላይ ስለሚገኘው ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብ እና የመሰረተ ልማት መልሶ ግባታዎችን ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡የተለያዩ ሚዲያ አካላትና የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅቶችና ኤጀንሲዎች በክልል መንቀሳቀስ አትችሉም ተብለናል የሚሉ ቅሬታዎችን እያቀረቡ እንደሚገኙ የጠቀሱት አምሳደር ሬድዋን፤ ይህም  መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እንደሚፈጸም አብራርተዋል፡፡ የህግ ማስከበር በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከማክበር ጎን ለጎን ለራሳቸውም ደህንነት ሲባል እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በበኩላቸው እየተከናወነ ያለው የሰብዓዊ ድጋፍና አቅርቦት በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ቅንጅታዊ አሰራሩም የሚፈለገውን ድጋፉ በትክክክለ ለማድረስ እንዲያስችል በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ የእርዳት ድርጅቶችጋር በጥምረት እየተሰራም ነው ብለዋል፡፡ኮሚሽንሩ የሰብዓዊ ድጋፉ የሚያደርጉ የእርዳታ ድርጅቶችም ከመንግስት ጎን በመሆን መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንደሚፈጸም አስታውሰው ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ያላት ልምድ በመጠቀም በአጭር ጊዜ የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ይከናወናሉ ማለታቸውን  
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8c%8d-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%9a%e1%8a%ab%e1%88%84%e1%8b%b5%e1%89%a3%e1%89%b8%e1%8b%8d-%e1%8a%a0%e1%8a%ab%e1%89%a3%e1%89%a2%e1%8b%8e/
177
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በህግ ማስከበር ዘመቻ ዘገባ ለተሳተፉ የሚዲያ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጠ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በህግ ማስከበር ዘመቻ በዘገባ ላይ ለተሳተፉ የሚዲያ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጠ።ድርጅቱ 80ኛ የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከሁሉም ሚዲያ ተቋማት በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ በዘገባ ለተሳተፉ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጥቷል።በእውቅና መርሃ ግበሩ ላይ ጋዜጠኞች፣ የሚዲያ ተቋማት ኃላፊዎችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንዳሉት ባለሙያዎች መረጃ በማድረስና ከወታደሩ እኩል ፈተናውን በመጋፈጥ የተሳፉበት ስራ ዕውቅናና ምስጋና መስጠት ያስፈልጋል።በፅንፈኛው ከሃዲ ቡድን ጥቃት የተሰነዘረበት ኢትዮጵያዊነትና የአገር ሉዓላዊነት እንደሆነ ገልፀው፤ የችግሩን መጠን ከማሳየት በተጨማሪ በቀጣይ ኢትዮጵያዊነትና አገራዊ አንድነት ዳግም በአዲስ ተስፋ እንዲያንሰራራ ሚዲያዎች ትልቅ ኃላፊነትና የቤት ስራ እንደተጣለባቸው ገልፀዋል ።ባለሙያዎቹ ለነበራቸው ሚና የዕውቅና እና የምስጋና ሰርተፊኬት በአምባሳደር ሬድዋንና በድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተበርክተዋል።ጋዜጠኞች በግንባር ለዘገባ በተሰማሩበት ወቅት ባጋጠማቸውና በተመለከቱት ትዝብት አጋርተዋል።ጋዜጠኞቹ ከዚህ በፊትም በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በኩል የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።ምንጭ- የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%88%b5-%e1%8b%b5%e1%88%ad%e1%8c%85%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%88%85%e1%8c%8d-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%89%a0%e1%88%ad/
135
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሀዋሳ ሞያሌ የ500 ኪሎ ሜትር መንገድ ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
Unknown
የሀዋሳ ሞያሌ የ500 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ እና የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክቶች በነገው እለት ይመረቃሉ።የሀዋሳ ሞያሌ 500 ኪሎ ሜትር መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የፈጀ ሲሆን፣ የግንባታው ወጪ የተሸፈነው ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ ብድር ነው።በተመሳሳይ በኬንያ በኩል ደግሞ ከኢሲኦሎ እስከ ሞያሌ የሚወስደው የ503 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታም በመጠናቀቁ በነገው እለት ይመረቃል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።መንገዶቹ ግንባታ የትራንስ አፍሪካ አውራ ጎዳ አንዱ አካል ናቸው።ግንባታዎቹ መጠናቀቃቸው ኢትዮጵያና ኬንያ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮቸ ላይ ያላቸውን የትብብር ግንኙነት ለማሳለጥ ያግዛል ተብሏል።መንገዶቹ ከናይሮቢ ሞምባሳ እስከ አዲስ አበባ ያሉትን መንገዶች የሚያገናኘው የአፍሪካ አህጉር አቋራጭ የፍጥነት መንገድ አካል ናቸው።በምረቃው ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሁለቱ አገሮች ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። 
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%80%e1%8b%8b%e1%88%b3-%e1%88%9e%e1%8b%ab%e1%88%8c-%e1%8b%a8500-%e1%8a%aa%e1%88%8e-%e1%88%9c%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%8b%b5-%e1%8d%95%e1%88%ae%e1%8c%80%e1%8a%ad/
104
0ሀገር አቀፍ ዜና
የህብረ ብሄራዊ አንድነታችን መገለጫ የሆነው ልዩነታችን ውበታችን ነው – ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አገር አቀፍ የሲምፖዚየም መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው።የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሲምፖዚየሙን በይፋ ሲከፍቱ የህብረ ብሄራዊ አንድነታችን መገለጫ የሆነው ልዩነታችን ውበታችን ነው፤ ይህ ከየቦታው መጥቶ በአንድ ላይ እንደሚፈስ ወንዝ ነው ብለዋል።የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሀገራዊ አንድነት ማጠናከር ይገባቸዋልም ብለዋል።የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ላለፉት አመታት ሀገሪቱን በእኩይ ተግባሩ ሲያምስና ሲንቀሳቀስ የነበረው የህወሓት ጁንታ ቡድን የተወገደበት በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው በመግለጽ ዋጋ ለከፈሉት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር ይገባል ብለዋል።የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ለሚከፋፍላቸው እድል ሳይሰጡ ሕብረ ብሔራዊነት አንድነታቸዉን ማጠናከር እንዳለባቸው አስታውሰዋል።ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በማክበርና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትትን በማረጋገጥ የጋራ እሴቶች ላይ መስራት እንደሚገባም አንስተዋል።በሲምፖዝየሙ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች ፣ የሀገር ሽማየግሌዋች እና የሐይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል “እኩልነትና ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መርህ አዲስ አበባ፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ተከብሯል። (በህይወት አክሊሉ)
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%89%a5%e1%88%a8-%e1%89%a5%e1%88%84%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8b%b5%e1%8a%90%e1%89%b3%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%88%98%e1%8c%88%e1%88%88%e1%8c%ab-%e1%8b%a8%e1%88%86/
163
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከ33.4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ33.4 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በገቢ እና ወጪ ኮንትሮባንድ 33 ሚሊየን 430 ሺህ 62 ብር የሚገመት ዕቃ ከህዳር 18 እስከ 24፣ 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ከዚህ ውስጥ 31 ሚሊየን 253 ሺህ 301 ብር የሚገመተው ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር የተያዘ ሲሆን፣ ወደ ውጭ ሲጓጓዙ የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ግምታዊ ዋጋቸው 2 ሚሊየን 176 ሺህ 760 ብር መሆኑ ተገልጿል፡፡የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት በፍተሻ፣ በብርበራ እና በተሽከርካሪ በመከታተል ነው ተብሏል፡፡የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የጉምሩክ ሰራተኞች እና አመራሮች ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር በቅንጅት በመስራት በተለያዩ የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች  በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a833-4-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8c%88%e1%88%98%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%8a%95%e1%89%b5%e1%88%ae%e1%89%a3/
103
0ሀገር አቀፍ ዜና
የትምህርት ሚኒስቴር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊየን ማቲዮስ የትምህርት መርሀግብሩን ለማስቀጠል የሀገር ሰላም ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ የመከላከያ ሰራዊቱ የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ ያደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።የትምህርት ሚኒስቴርም እንደ ተቋም መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን እና በቀጣይም ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን እንደሚቆም አስታውቀዋል።የገንዘብ ስጦታውን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሊዊጂ ትምህርት ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከዚህ ቀደም “ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ደም መለገሳቸው ይታወሳል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b4%e1%88%ad-%e1%88%88%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%8a%a8%e1%88%8b%e1%8a%a8%e1%8b%ab-%e1%88%b0/
81
0ሀገር አቀፍ ዜና
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት አምባሳደሮች በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ አደረጉ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት አምባሳደሮች በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ አድርገዋል።ሚኒስትሩ ገለጻውን ለጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡሩንዲ፣ ርዋንዳ፣ ኡጋንዳ እና ደቡብ አፍሪካ አምባሳደሮች ነው ያደረጉት።በገለፃቸው፣ የህወሓት ጁንታ በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ መንግስት በክልሉ የወሰደውን ህግ የማስከበር ዘመቻ አምባሳደሮቹና የየሃገራቱ መሪዎች ያሳዩትን ድጋፍ አድንቀዋል።ደቡብ አፍሪካ እንደ አፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበርነቷ በቀጠናው ሰላምን ለማምጣት የምትጫወተው ሚናም የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።ሚኒስትሩ በገለጻቸው ዘመቻው ንጹሃን ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ እና መንግስት በክልሉ ህግና ስርአትን ለማስፈን የያዘውን እቅድ ማከናወን በሚያስችለው አግባብ በፍጥነት መጠናቀቁንም ለአምባሳደሮቹ አስረድተዋል።አሁን ላይም መንግስት በክልሉ ቴሌኮምን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶችንና የሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ የሚያስችሉ አማራጮችን መዘርጋትና ማረጋገጥ እንዲሁም ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ እያከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።መንግስት በክልሉ ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል።አምባሳደሮቹም መንግስት ህግ የማስከበር እርምጃውን ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ሳይደርስ በፍጥነት በማጠናቀቁ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።አያይዘውም መንግስት ለተጎዱ ዜጎች ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ የሚያደርገውን ጥረት እንደግፋለን ብለዋል።ኢትዮጵያ የቀጠናው “የሰላም መልሕቅ” መሆኗን በመጥቀስም የየሃገራቱ መሪዎች ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን እንደሚቆሙ ተረጋግጧል፡፡(ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8b%8d%e1%8c%ad-%e1%8c%89%e1%8b%b3%e1%8b%ad-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%8b%b0%e1%88%98%e1%89%80-%e1%88%98%e1%8a%ae%e1%8a%95%e1%8a%95-%e1%88%88%e1%89%b0%e1%88%88/
166
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጆ  ባይደን ጥቁር አሜሪካዊውን ሎይድ ኦስቲንን እጩ የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው መረጡ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጥቁር አሜሪካዊውን የቀድሞ ጀነራል ሎይድ ኦስቲን እጩ የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው መረጡ።በኦባማ አስተዳደር ወቅት የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድን የመሩት ሎይድ ኦስቲን ጡረታ ከወጡ ሰባት አመት ያልሞላቸው በመሆኑ የኮንግረሱ ይሁንታ ያስፈልጋቸዋል ነው የተባለው።ጆ ባይደንም ሆነ ሎይድ ኦስቲን በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት ባይሰጡም የ67 ዓመቱ የቀድሞ ጄነራል በመከላከያ ሚኒስትርነት ፔንታገንን የመሩ የመጀመሪያው አፍሪካዊ- አሜሪካዊ ይሆናሉ።ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የብሔራዊ ደህንነት ቡድን ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ይፋ ካደረጉ  ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው የመከላከያ ሚኒስትር ምርጫ ያካሄዱት ተብሏል።የወቅቱን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በምርጫ ያሸነፉት ባይደን በስልጣን ዘመናቸው ብዝሃነትን የምታስተናግድ አሜሪካን ለመፍጠር እንደሚሰሩ ተናግረው ነበር።ለዚህም ከወዲሁ እያካሄዱት ለሚገኘው የተለያዩ ቦታዎች  ውስጥ ለሴቶች፤ለጥቁሮች ፤ላቲኖች እና ሌሎች በከፍተኛ የካቢኔ ቦታዎች ላይ  ሹመት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።በአወዛጋቢው የአሜሪካ ምርጫ ሽንፈትን ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑት ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል እንዳሉ  ቀጥለዋል።ሎይድ ኦስቲን ኢራቅ  የነበረው ሰራዊት የአሜሪካ ጦር ኃይሎች የመጨረሻው አዛዥ ጄኔራል ሆነውም አገልግለዋል፡፡በኢራቁ ተልጽኮ ወቅት የባራክ ኦባማ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ከነበሩት  ጆ  ባይደን ጋር በቅርበት ሰርተዋል ነው የተባለው፡፡የትራምፕ አስተዳደር የወቅቱ የመከላከያ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ሚለር ሲሆኑ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፉት አራት አመታት ውስጥ ስድስተኛ የመከላከያ ሚኒስትር ሹመት ሰጥተዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8c%86-%e1%89%a3%e1%8b%ad%e1%8b%b0%e1%8a%95-%e1%8c%a5%e1%89%81%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%88%9c%e1%88%aa%e1%8a%ab%e1%8b%8a%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%88%8e%e1%8b%ad%e1%8b%b5-%e1%8a%a6%e1%88%b5%e1%89%b2/
166
4ዓለም አቀፍ ዜና
የትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
ተጋሩ የኢትዮጵያዊያን ድርጅት በትግራይ ወቅታዊና መጻኢ ጉዳዮች ዙሪያ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖሊቲካ ፓርቲ አመራሮችና  የሲቪክ ማህበራት ጋር ውይይት አድርገዋል።የኢትዮጵያዊያን ተጋሩ ድርጅት የቦርድ ሰብሳብ አቶ ዩሐንስ ጎይቶም ውይይቱን ማድረግ የተፈለገው በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ግልፅ እና አሳታፊ ለማድረግ ነው ብለዋል።ለውጡን ተከትሎ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች እንዲፈቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ  አካላትና ማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ችግሮቹ እንዲፈቱ እና አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ መሆኑንም ገልጸዋል።ከሃማኖት አባቶች፣ ከአገር ሽማግሌዎች፣ ከፖሊቲካ ፓርቲዎች እና ዜጎችን ያካተተ የመማክርት ጉባኤ መቋቋም ስላለበት ለባለድሻ አካላት ለማስገንዘብ መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።የትግራይ ህዝብ በተጀመረው የለውጥ ጉዞ ፖሊቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፍትህ እንዲቀዳጅ ተባብረን መስራት አለብን ብለዋል አቶ ዮሐንስ።በውይይቱ ላይ የተገኙት የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ነብዩ ሰሁል ሚካኤል እንዳሉት በትግራይ በሚደረገው መልሶ የማቋቋም ተግባር በክልሉ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲ እና የሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን ለመወጣት እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው ።በትግራይ ክልል በሚደረግ ለውጥ ሁላችንም አብረን መጓዝ አለብን ያሉት አቶ ነብዩ ለውጡ ሁሉን አቃፊ መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል።በትግራይ ክልል ያለውን ችግር መፍታት የሚቻለው በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ ምሰሶ በሆኑት የሲቪከ ማህበራት መሆኑንም አብራርተዋለ።የሲቪክ ማህበራትም በቀጣይ በክልል በሚደረጉ የለውጥ ጎዞዎች የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀው፤ ፓርቲውም ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ በበኩላቸው የህወሐት ጁንታ በትግራይ ክልል ለሶስት አስርት አመታት ያደረሰውን ችግር መፍታት የሚያቻለው ተቀራርቦ በመነጋገር ነው ብለዋል።የትግራይን ህዝብ ችግር መፍታት የሚቻለው የፖሊቲካ ፓርቲ በማቋቋም ብቻ ሳይሆን የሲቪክ ማህበራትንም በማደራጀት መሆኑን ገልጸዋል።የሕወሐት የጥፋት ቡድን የትግራይን ህዝብ ለተለያዩ ችግሮች መዳረጉን አስታውሰው ችግሩን ለመፍታት ሁሉም መረባረብ አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘገቧል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d%e1%8a%95-%e1%88%98%e1%88%8d%e1%88%b6-%e1%88%88%e1%88%98%e1%8c%88%e1%8a%95%e1%89%a3%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%88%9a%e1%8b%b0/
222
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ አራት ግለሰቦች ተያዙ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
በወልዲያ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ከ3 ሺህ በላይ የተለያዩ አይነት ተተኳሽ ጥይቶችን ሲያጓጉዙ የነበሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ አስታወቀ፡፡በቅርንጫፉ የደንበኞች ትምህርት ቡድን አስተባባሪ አቶ አሳምነው አዳነ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በቅርንጫፍ ጉምሩክ ጣቢያው በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ጥይቶቹና ተጠርጣሪ ግለሰቦች ተይዘዋል።ተጠርጣሪዎቹ ኮድ 3 – 01470 አፋ በሆነ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ጭነው ከቆቦ መስመር ወደ አፋር ክልል ሲጓዙ ህዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊት በጣቢያው ተቆጣጣሪዎች መያዛቸውን ተናግረዋል።በተደረገው ፍተሻም 1 ሺህ 941 የብሬን፣ 1 ሺህ 132 የክላሽ፤ 5 የብሬን ሽንሽን ጥይቶችና 3 የክላሽ ካዝና መገኘቱን ገልጸዋል፡፡አሽከርካሪውን ጨምሮ በዚሁ ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ መታየት መጀመሩን አብራርተዋል።ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደበኛ ፖሊስ፣ ፌዴራል ፖሊስና የጉምሩክ ሰራተኞች ላደረጉት የተቀናጀ ጥረት አቶ አሳምነው ምስጋና አቅርበዋል፡፡በአካባቢው መሰል የህገ ወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውር እንዳይደረግ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ እንዳለ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a83-%e1%88%ba%e1%88%85-%e1%89%a0%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%89%b0%e1%89%b0%e1%8a%b3%e1%88%bd-%e1%8c%a5%e1%8b%ad%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%89%a0%e1%8b%88%e1%88%8d%e1%8b%b2%e1%8b%ab-%e1%8c%89%e1%88%9d/
134
0ሀገር አቀፍ ዜና
ለምርጫው የሚዘጋጀው የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል መተግበሪያ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል እያበለፀገ ያለውን መተግበሪያ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።የባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ አብዮት ለሚታ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ መተግበሪያው ተሻሽሎ እየበለጸገ ያለው ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል ከእጅ ንክኪ ነጻ ለማድረግ ነው።መተግበሪያውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ ምርጫ ቦርድና ብሮድካስት ባለስልጣን በጋራ እያዘጋጁት መሆኑንም ተናግረዋል።“የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ መገናኛ ብዙሃንና የተመደበውን የአየር ሠዓት ወደ ሲስተሙ በማስገባት መተግበሪያው ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ቀመር መሰረት ለእያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲና ሚዲያ የተዘጋጀውን ሠዓት ይደለድላል” ብለዋል።መተግበሪያው የሰው ጉልበት፣ ጊዜና ሀብት በመቆጠብ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎችና መገናኛ ብዙሀን በድልድሉ መሰረት መረጃቸውን በፍጥነት እንዲያገኙም ያስችላል።ቴክኖሎጂው መገናኛ ብዙሃን የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ለማንና በየትኛው ሠዓት መስጠት እንዳለባቸው ጊዜ ሳይፈጁ ለማወቅ እንደሚያስችላቸውም ተገልጿል።መተግበሪያ መተግበሪያው በ2007 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ጥቅም የዋለ ሲሆን አስፈላጊው ማሻሻያ ተደርጎ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ነው አቶ አብዮት የገለጹት።መተግበሪያው በ2007 ዓ.ም በአጭር ጊዜና በችኮላ በመዘጋጀቱ ያልተካተቱ ክልሎችና ቋንቋዎች እንደነበሩበት አቶ አብዮት አስታውሰዋል።
https://waltainfo.com/am/%e1%88%88%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%98%e1%8c%8b%e1%8c%80%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8b%a8%e1%88%ad-%e1%88%a0%e1%8b%93%e1%89%b5%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8c%8b/
144
0ሀገር አቀፍ ዜና
15ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በብሔራዊ ትያትር አዳራሽ ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ 15ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓልን በብሔራዊ ትያትር አዳራሽ “እኩልነትና ህብረ- ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል አከበሩ፡፡የበዓሉን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደገለጹት የዘንድሮው በዓል ከሌላው ለየት የሚያደርገው ህብረ ብሔራዊነታችንን የምናደምቅበት እና ከመቼውም በተለየ ሁላችንም ለጋራ ብልጽግና የምንጓዝበት መንገድ ላይ በመሆናችን ብለዋል፡፡ሚኒስትሯ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን አከባበር ሲታሰብ ልዩነት ብቻ ሳይሆን በውስጡ በአንድነት የሚታይ ውበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡በዓሉ የብሔራዊ ትያትር የባህል ቡድን የብሔር ብሔረሰብ ባህላዊ ሙዚቃ በማቅረብ ለበዓሉ ድምቀት መስጠቱ ተጠቅሷል፡፡ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሃብታሙ ሲሳይ በበኩላቸው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ ከህገ መንግስቱና ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር አዛምደው የስፖርት ዘርፍ የውይይት ሰነድ አቅርበው ውይይት እንደተካሄደበት ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/15%e1%8a%9b%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%89%a5%e1%88%94%e1%88%ad-%e1%89%a5%e1%88%94%e1%88%a8%e1%88%b0%e1%89%a6%e1%89%bd-%e1%89%80%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%89%a5%e1%88%94%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%89%b5%e1%8b%ab/
111
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሃገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
በሃገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነበሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ተጠርጣሪዎቹ መንግስት እና ህዝብ የጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል በማድረግ የህዋሓት ፀረ-ሠላም እና ፀረ-ህዝብ ከሆኑ ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ መቀበላቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ከዚህ ባለፈም በጽንፈኝነት አስተሳሰብ በመነሣት በሀይል ወደ ስልጣን የመምጣት ፍላጎትን ካነገቡ ፀረ-ሠላም ሀይሎች ተልዕኮ በመቀበል በሀገር ውስጥ ሌሎችን በማደራጀት ሀገር የመበተን፣ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር እና ህገ-መንግስታዊ ሥርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ መንገድ በመሳተፍ ህዝብ በመንግስት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው በማድረግ በሃገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ በተለያዩ የአመራር ደረጃ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል ነው ያለው፡፡የመያያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው ተጠርጣሪዎችበመሆኑም መላው ህዝብ በተለይም ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፣ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታው የህዋሓት የጥፋት ቡድን ተፈላጊዎች አባላትን አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ተግባር በያሉበት የድርሻቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡በቀጣይም የጁንታው ርዝራዥ ቡድን ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመግለጽ በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚያደርግ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%83%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%8a%ad%e1%88%85%e1%8b%b0%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%88%b0%e1%89%a5%e1%8a%a0%e1%8b%8a-%e1%88%98%e1%89%a5%e1%89%b5-%e1%8c%a5%e1%88%b0%e1%89%b5/
176
0ሀገር አቀፍ ዜና
ለሀገር ህልውና፣ ሰላምና ልማት በጋራ መቆም ያስፈልጋል – የመቐለ ሃገር ሽማግሌዎች
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
Unknown
ለሀገር ህልውና፣ ሰላምና ልማት በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ የመቐለ ከተማ የሃገር ሽማግሌዎች አስገነዘቡ።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ህዝብ በማወያየት ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ በመቐለ ከተማም ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።በመቐለ ከተማ ከጊዜያዊ አስተዳዳሩ ጋር ውይይት ያደረጉት የሀገር ሽማግሌዎች ለሃገር ህልውና፣ ሰላምና ልማት በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።“ያለችን አንዲት ሀገር ነች፣ ሰላማችንን እውን ማድረግ የምንችለውም እኛው ነን፤ በአንድ ሃገር ላይ ሁለት የተለያየ የታጠቀ አካል ካለ ደግሞ ችግር ያስከትላል” ብለዋል።በመሆኑም በህወሓት የጥፋት ቡድን በህገ ወጥ መንገድ የታጠቁ የመቐለ ወጣቶች መሳሪያቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመከላከያ ሠራዊት እንዲያስረክቡ የሃገር ሽመግሌዎች ጠይቀዋል።የህወሓት ቡድን በጫና በርካታ ወጣቶችን በማስታጠቅ በተለይ በክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር መስራቱ ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም ገልጸዋል።የሀገር ሽማግሌዎቹ የትግራይ ህዝብ የሚፈልገው ሰላም፣ ልማትና አብሮነትን እንደሆነ ገልጸው፤ የህወሓት ቡድን ወጣቶችን በማስታጠቅ ወደ ግጭትና አለመረጋጋት ማምራቱን አውግዘዋል።በህገ ወጥ አካል መሳሪያ የታጠቁ ወጣቶች መሳሪያውን በአፋጣኝ ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/%e1%88%88%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%88%85%e1%88%8d%e1%8b%8d%e1%8a%93%e1%8d%a3-%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d%e1%8a%93-%e1%88%8d%e1%88%9b%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%8c%8b%e1%88%ab-%e1%88%98%e1%89%86/
132
0ሀገር አቀፍ ዜና
በምዕራብ ሸዋ ዞን 95% የሰብል ምርት ተሰበሰበ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
Unknown
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመቋቋም ለመሰብሰብ ከታቀደው የሰብል ምርት 95 በመቶ ማሳካት መቻሉን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡በዞኑ 9ሺህ 150 አርሶአደሮችን በክላስተር በማደራጀትና ግብዓቶችን በማከፋፈል ምርትና ምርታማነትን ማስቀጠል መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡የምዕራብ ሸዋ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከበደ ደበሎ በዞን ደረጃ በጤፍ፣ ስንዴና በቆሎ ምርቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደተሰራ ገልጸው፣ ከታቀደው የሰብል ምርት 327 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን ገልጸዋል፡፡ከዚህ ቀደም የምርጥ ዘር አቅርቦት፣ የማዳበሪያና የኬሚካል እጥረት በዞኑ ይገጥም እንደነበር የተናገሩት ኃላፊው፣ አርሶአደሮችን በስልጠና በታገዘ መልኩ በክላስተር ማደራጀት በመቻሉ የግብዓት እጥረቶችን ማቃለል እንደተቻለ ጠቁመዋል፡፡በ2012 ዓ.ም መጋቢት ወር ወደ ኢትዮጵያ የገባው ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በግብርናው ዘርፍ ለአርሶአደሩ ስልጠና እና ክትትል ከማድረግ አንፃር የፈጠረው ተጽዕኖ ቢኖርም ቤት ለቤት ስልጠና በመስጠት እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም ጫናውን መቀነስ መቻሉ ተገልጿል፡፡በዘንድሮ ዓመት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ መከሰቱን ተከትሎ በሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ቀደም ብሎ አጨዳ መጀመሩንም የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ከበደ ገልጸዋል፡፡በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀርሳ ለፌ ወረዳ የጨለለቃ ቀበሌ ገበሬ ማህበር አርሷአደር አባ ሊቃ በበኩላቸው፣ በክላስተር ተጀራጅተው ሰብል በማምረታቸው ትርፋማ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ (በሀኒ አበበ)
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%9d%e1%8b%95%e1%88%ab%e1%89%a5-%e1%88%b8%e1%8b%8b-%e1%8b%9e%e1%8a%95-95-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%b6-%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%89%a5%e1%88%8d-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%88%b0/
166
0ሀገር አቀፍ ዜና
ባለፉት አራት ወራት ከማዕድን ዘርፍ 269.1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
Unknown
ባለፉት አራት ወራት ከማዕድን ዘርፍ 269 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የነዳጅና ማዕድን ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡የነዳጅና ማዕድን ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ በማዕድን ዘርፍ አፈፃፀምና ቀጣይ እቅዶች ዙሪያ ከክልል የማዕድን ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ባለፉት አራት ወራት 3 ሺህ 602.8 ኪሎግራም ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ 265.8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።ከጌጣጌጥ ማዕድናት ደግሞ 3.215 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱ ተነግሯል።በእቅድ የተያዘው የወርቅ ምርት የተከለሰ ሲሆን፣ በተሻለ መንገድ ኢኮኖሚውን መደገፍ በሚያስችል መልኩ ምርቱን ለመጨመር ከክልል አመራሮቹ ጋር መግባባት ላይ መደረሱን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።በቀጣይም ዘርፉን ዘመናዊ መልክ ለማስያዝ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተገለጸ ሲሆን፣ የማዕድን ፈቃድ ተሰጥቷቸው በአግባቡ እየተጠቀሙበት ያልሆኑ ተቋማት ላይ መወሰድ ስላለበት እርምጃ በተመለከተ ውይይት መደረጉን ከነዳጅና ማዕድን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%8b%88%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%8a%a8%e1%88%9b%e1%8b%95%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%8d%8d-269-1-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%a8/
122
0ሀገር አቀፍ ዜና
የፌደራል መንግስት ተግባር ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ፣ ህግና ስርዓት ማስከበርና መልሶ ማቋቋም ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
Unknown
የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል በአሁኑ ወቅት የሚያከናውናቸው ተግባራት ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ ህግና ስርዓት ማስከበርና መልሶ ማቋቋም መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።ጽሕፈት ቤቱ በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር እርምጃው ንጹሃን ዜጎች ሳይጎዱና ንብረቶች ሳይወድሙ የመቐለ ከተማን በመቆጣጠር እርምጃው መጠናቀቁን ገልጿል።በአሁኑ ወቅት የፌደራል መንግስት ተግባራት ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ፣ በአካባቢው ሕግና ስርዓት እንዲኖር እንዲሁም መልሶ ማቋቋም መሆኑም ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል።እንዲሁም ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲያገኙ፤ ከአካባቢያቸው ርቀው ድንበር አቋርጠው የተሰደዱ ዜጎችን መልሶ ማቋቋምና በወንጀለኛው ቡድን የፈረሱና አገልግሎት ያቋረጡ የትራንስፖርትና መገናኛ መሰረተ ልማቶችን መልሶ መገንባት እየተከናወኑ መሆኑንም ነው የገለጸው።የትግራይ ህዝብ የሚፈልገው ዕድገት፣ ሰላም፣ ነጻነትና ደህንነት ቢሆንም የህወሓት ጁንታ ቡድን በፍትሃዊና እኩልነት የተመሰረተች ኢትዮጵያን ለመመስረት አጋር መሆን የማይችል እንደሆነም አውስቷል፡፡ቡድኑ ከተጠያቂነት ለማምለጥ መንግስት የወሰደውን የህግ ማስከበር እርምጃ በተመለከተ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት ዓለም አቀፍ ተቋማት ጣልቃ ገብተው ድርድር እንዲደረግ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱም ተመልክቷል።የጁንታው ህወሓት ቡድን በሚገባ የተሸነፈ እና የደፈጣ ውጊያ ለማድረግ ምንም አቅም የሌለው መሆኑ እየታወቀ ቡድኑ ግን ከእነሙሉ አቅሙ እንዳለና ስልታዊ ማፈግፈግ አድርጎ የደፈጣ ውጊያ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የሚያትቱ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሲነዛ መቆየቱንም ጽሕፈት ቤቱ አስታውሷል።ቡድኑ ዓለም የተለያዩ የሐሰት ውንጀላዎችን በማቅረብና የሕግ ማስከበር ዘመቻው ዓለም አቀፍ መልክ እንዲይዝና ከተጠያቂነት ለመምለጥ ጉዳዩ ወደ ድርድር እንዲወሰድ ፍላጎት አሳይቶ እንደነበርም አስታውቋል።የህወሓት ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት ከመፈጸሙም ባሻገር በማይካድራ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ፣ እንዲሁም ወደ ባህርዳርና ጎንደር ጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያ መላኩ ለሰላማዊ ዜጎች ምንም ግድ የሌለው ቡድን መሆኑን ግልጽ ያደርጋል ብሏል ጽሕፈት ቤቱ።የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማብራሪያው መንግስት በማንኛውም ጊዜ ለዜጎች ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑንም አረጋግጧል።በትግራይ ክልል በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች እንዲሁም በክልሉ በስደተኞች ካምፕ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላልሆኑ ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ከሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማትና ከመንግስታቱ ድርጅት ኤጀንሲዎች ጋር በትብብር እየሰራ ነውም ብሏል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8d%8c%e1%8b%b0%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%b5%e1%89%b5-%e1%89%b0%e1%8c%8d%e1%89%a3%e1%88%ad-%e1%8b%88%e1%8a%95%e1%8c%80%e1%88%88%e1%8a%9e%e1%89%bd%e1%8a%95/
266
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሁሉም ዜጋ ለሀገር ሰላም እና መረጋጋት በኃላፊነት መስራት እንዳለበት ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
Unknown
በሻሸመኔ በተካሄደው የእርቅ እና የሰላም ኮንፍረንስ ላይ የነበሩ ተሳታፊዎች የሚዲያ ተቋማትን ጨምሮ ሁሉም ዜጋ ለሀገር ሰላም እና መረጋጋት መስራት እንዳለበት አሳሰቡ።የጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ አባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና የሻሸመኔ ከተማዋ ነዋሪዎች ካለፉት ስህተቶች በመማር እና ይቅር በመባባል የበለፀገች ሀገር መገንባት አለብን ብለዋል።መዝረፍ እና ሰዎችን መጉዳት የገዳ ስርዓት አይደለም ያሉት የጉባኤው ተሳተፊ አባገዳዎች በቄሮ ስም በከተማዋ እና አከባቢዋ ላይ ጉዳት ያደረሱ ሰዎች ከማንም ዘር እና ኃይማኖት አለመሆናቸውን አስረግጠዋል።ከዚህ በኋላ በአካባቢያቸው ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ኃላፊነት እንወስዳለን ያሉት አባገዳዎቹ፣ ከዚህ በፊትም ሆነ ከዚህ በኋላ በኃይማኖትና በዘር ሽፋን ጉዳት ያደረሱም ሆኑ የሚያደርሱትን በመከታተል ለህግ እንዲቀርቡ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።በከተማዋ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖችን በፍጥነት ወደ መደበኛ ህይወታቸው እንዲመለሱ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።ከተማዋ ወደ ቀድሞ ሰላሟ በመመለሷ ደስተኛ መሆናቸውን በመድረኩ የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች የዜጎች እና የሀገር ሰላም በዘላቂነት እንዲጠበቅ መንግስት የህግ የበላይነትን እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል።ከዚህም በተጨማሪ በመድረኩ ላይ ቃል የተገቡ የአብሮነት፣ አንድነት እንዲሁም ለሰላም ዘብ መቆም ተግባራዊ መሆን አለበትም ብለዋል።በመድረኩም ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ም/ስራ አስኪያጅ ቀሲስ በላይ ታደለ  እና የኢትዮጵያ ኃይማኖት ጉባኤ ም/ቦርድ ሰብሳቢ ሼህ መሀድ ሲራጅ ያለፈውን ይቅር በመባባል ስለሰላም እና አንድነት መሥራት እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ ጉታ ላቾሬ መንግስት የዜጎችን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ በቁርጠኝነት አየሰራ መሆኑን ገልፀው፣ ሻሸመኔ ልማቷ እንዲፋጠን የኢንቨስትመንት ከተማ በማድረግ ብልፅግናን እናረጋግጣለን ብለዋል።(በሚልኪያስ አዱኛ)
https://waltainfo.com/am/%e1%88%81%e1%88%89%e1%88%9d-%e1%8b%9c%e1%8c%8b-%e1%88%88%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%88%98%e1%88%a8%e1%8c%8b%e1%8c%8b%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%8a%83/
202
0ሀገር አቀፍ ዜና
በጎሎልቻ ወረዳ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
Unknown
በምስራቅ ባሌ ዞን ጎሎልቻ ወረዳ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሽመልስ ገበየሁ እንደገለጹት፤ በቁጥጥር ሥር የዋሉት አዳዲስ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ አልባሳት፣ ሽቶና ሌሎችም እቃዎች ናቸው።ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. እኩለ ቀን አካባቢ የተገኙት እነዚህ የኮንትሮባንድ እቃዎች የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 03214 አዲስ አበባ እና ኮድ 3 – 36058 አዲስ አበባ በሆኑ አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭነው መሆኑን ተናግረዋል።ተሽከርካሪዎቹ ከሶማሌ ክልል ከገይዳ ወደ ሃረርጌ ለመጓዝ ሲሰናዱ በጎሎልቻ ወረዳ ድሬ ሼህ ሁሴን ቀበሌ በቁጥጥር ስራ ማዋል መቻሉን አስረድተዋል።አሽከርካሪዎቹ ለጊዜው ቢሰወሩም ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል እያደረገባቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል።የአገር ኢኮኖሚንና የፀጥታ ሥራን እየተፈታተነ የሚገኘውን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታት ሁሉም የተቀናጀ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።የወረዳው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለውን የኮንትሮባንድ እቃ ዛሬ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ለሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስረክቧል።እቃዎቹን የተረከቡት የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የህግ ተገዢነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዴሳ ለማ በበኩላቸው ህገ ወጥ ንግድ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ የሚያሳጣ እና ህጋዊ ነጋዴዎችን ከውድድር በማስወጣት በንግድ ሥርዓቱ ላይ አሉታዊ ጫና እንደሚያሳድር አስገንዝበዋል።በመሆኑም ሁሉም ህገ ወጥ ድርጊቱን ለመከላከል እንዲሰራ ጠይቀዋል።(ምንጭ፡ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8c%8e%e1%88%8e%e1%88%8d%e1%89%bb-%e1%8b%88%e1%88%a8%e1%8b%b3-%e1%8a%a86-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8c%8d%e1%88%9d%e1%89%b5/
164
0ሀገር አቀፍ ዜና
የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ከምርጫው ድል በኋላ አዲሱ ካቢኔያቸውን ይፋ አደረጉ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 7, 2020
Unknown
የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ከባለፈው ሀገራዊ  ምርጫ ድል በኋላ  አዲሱ ካቢኔያቸውን ይፋ አድርገዋል።ፕሬዝዳንቱ በአዲሱ ካቢኔያቸው ውስጥ ሴቶችን ጨምሮ አዳዲስ ሚኒስትሮችን እና የቀድሞ ፖለቲከኞችን አካተዋል ተብሏል።ሲያወዛግብ የነበረውን የታንዛኒያ ምርጫ በማሸነፍ ለሁለተኛ  የስልጣን ዘመናቸው የበቁት ማጉፉሊ ቃለመሃላ ከፈፀሙ ከ 30 ቀናት በኋላ ነው አዲሱን ካቢኔያቸውን ይፋ ያደረጉት።በሀገሪቱ ባመጧቸው በርካታ የሪፎርም ስራዎች ተወዳጅነትን ያተረፉት ማጉፉሊ ምርጫውን 84 ከመቶ  ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸው ይታወሳል።ከቀድሞ ሚኒስትሮች መካከል  በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ በፕሬዝዳንቱ  የተካተቱት የፋይናንስ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይገኙበታል።ከመንግስት ምክር ቤት የተሰጠው መግለጫ እንደሚያሳየው የፋይናንስ ሚኒስትሩ ፊሊፕ ምፓንጎ ፖሊሲዎችን በማስቀጠል የኢኮኖሚ እድገት እንዲመዘገብ በማድረጋቸው በፕሬዝዳንቱ እምነት ተጥሎባቸዋል።እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፓላማጋምባ ካቡዲ ሀገሪቱ ከውጭ አጋሮች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራት አስተዋጽኦ አድርገዋል ተብሏል።አዲስ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙት መካከል ፎስቲን ጉጉሊን በአዲስ መልክ የተቋቋመውን የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተቋም ይመራሉ ነው የተባለው፡፡የፕሬዝዳንት ፖምፔ ማጉፉሊ አዲሱ ካቢኔ በአጠቃላይ ሁለት የፓርላማ አባላትን ጨምሮ 23 ሚኒስትሮችን የያዘ መሆኑን አናዶሉ ኤጀንሲን ዋቢ አድርጎ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b3%e1%8a%95%e1%8b%9b%e1%8a%92%e1%8b%ab%e1%8b%8d-%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%9a%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%8a%a8%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab%e1%8b%8d-%e1%8b%b5%e1%88%8d-%e1%89%a0/
141
4ዓለም አቀፍ ዜና
የትራምፕ ጠበቃ በኮቪድ-19 ተይዘው ሆስፒታል ገቡ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 7, 2020
Unknown
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የግል ጠበቃና የቀድሞው የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ሩዲ ጁሊያኒ በኮቪድ-19 ከተያዙ በኋላ ወደ ሆስፒታል መግባታቸው ተገለጸ።ፕሬዝዳንት ትራምፕ የጠበቃቸውን ሆስፒታል መግባት በማስመልከት ጠበቃው ቶሎ እንዲሻላቸው ምኞታቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።ጠበቃው ጁሊያኒ ከምርጫው በኋላ የትራምፕን የፍርድ ቤት ክርክር ሲመሩ የቆዩ ናቸው።የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የ76 ዓመቱ ጠበቃ ሕመም ጸንቶባቸው ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሜድስታር ጆርጅታዎን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል እንዲገቡ መደረጉን በስፋት ዘግበዋል።የቀድሞ የኒው ዮርክ ከተማ ከንቲባ የአሁኑ የፕሬዝዳንቱ ጠበቃ መልካም ምኞት የገለጹላቸውን አመስግነው ከሕመማቸው እያገገሙ እንደሆነ ገልጸዋል።በዋይት ሐውስ የሚሰራው የጠበቃው ልጅ አንድረው ጁሊያኒ ወላጅ አባቱ እረፍት እያደረጉ እና እየተሻላቸው መሆኑን ገልጿል። ጠበቃው ጁሊያኒ የትኞቹን የበሽታው ምልክቶች እያሳዩ እንደሆነ አልተገለጸም።እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አሃዝ ከሆነ በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 14.6 ሚሊየን የተቃረበ ሲሆን፣ ከ281 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሕመሞች ሕይወታቸው አልፏል። ይህም በዓለማችን ከፍተኛው ነው። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%88%ab%e1%88%9d%e1%8d%95-%e1%8c%a0%e1%89%a0%e1%89%83-%e1%89%a0%e1%8a%ae%e1%89%aa%e1%8b%b5-19-%e1%89%b0%e1%8b%ad%e1%8b%98%e1%8b%8d-%e1%88%86%e1%88%b5%e1%8d%92%e1%89%b3%e1%88%8d/
127
4ዓለም አቀፍ ዜና
የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር /አኖካ/ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአህጉሩን ከፍተኛ የስፖርት ሽልማት አበረከተ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
Unknown
የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር /አኖካ/ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአህጉሩን ከፍተኛ የስፖርት ሽልማት/ኦርደር ኦፍ ሜሪት/  አበረክቷል።በመድረኩ ላይ የተገኙት የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የስፖርትን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ መጠቀም የቻሉ መሪ ናቸው” ብለዋል።ሽልማቱ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ለኦሎምፒክ ስፖርት ማደግ ለሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ ነው።በርካታ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ይህንን ሽልማት ማግኘት ችለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ስፖርት ያሳዩት ድጋፍና ለኦሎምፒክ መንደር ግንባታ ያደረጉት የ3 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለሽልማት እንዳበቃቸው በሥነ ስርዓቱ ላይ ተጠቁሟል።ሽልማቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመወከል የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው ተቀብለዋል፡፡ሚኒስትሯ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ስፖርት ያለውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በሚገባ የሚጠቀሙ መሪ መሆናቸውን ተናግረዋል።ለአብነትም ስፖርትን በመጠቀም ላልተገባ ዓላማ ወደ ጽህፈት ቤታቸው ያመሩ የሠራዊት አባላትን ያረጋጉበትን ብልሃት አስታውሰዋል።ይህን በማድረግም ኢትዮጵያን ይገጥማት ከነበረው ብጥብጥ መታደግ ችለዋል ነው ያሉት።የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክት በሆነው የእንጦጦ ፓርክ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ሰፊውን ቦታ እንዲዙ መደረጉንም ጠቅሰዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ ወጣቶች ለስፖርትና ለበጎ አድራጎት ተግባራት ትኩረት እንዲሰጡ አርዓያ በመሆን ጭምር ትልቅ ስራ ማከናወናቸውንም ገልጸዋል።የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ ቤራፍ በበኩላቸው በቆይታቸው ኢትዮጵያ እንግዳ በማስተናገድ የተካኑ ሕዝቦችን ያቀፈች ታላቅ ሀገር መሆኗን መገንዘባቸውን ተናግረዋል።በኢትዮጵያ ቆይታቸው ለተደረገላቸው እንክብካቤም ምስጋና አቅርበዋል።በመድረኩ በአዲስ አበባ ለተካሄደው የአፍሪካ ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቅ አበርክቶ ለነበራቸው ግለሰቦችና ተቋማት እውቅና መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8d%8d%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%8a%a6%e1%88%8e%e1%88%9d%e1%8d%92%e1%8a%ad-%e1%8a%ae%e1%88%9a%e1%89%b4%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%88%9b%e1%8a%85%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%8a%96/
193
0ሀገር አቀፍ ዜና
የዋልታ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
Unknown
“ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን” በሚል መሪ ሐሳብ የዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም የመለገስ መርሃግብር አከናውነዋል፡፡የሕወሓት የጥፋት ቡድንን ለማስወገድ እና ሕግ ለማስከበር መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊቱ የደም ልገሳው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በመገንዘብ ነው የደም ልገሳውን ያከናወኑት፡፡በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ንጉሴ መሸሻ፣ ዋልታ ፈጣን፣ ተዓማኒ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በማሰራጨት፣ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፋችንን በማሳየት በሀገራችን የተረጋጋ ሰላም ለመፍጠር ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡የሀገር ሉአላዊነትን የሚነቅፍ ማንኛውንም ሃይል ለመመከት ለማህበረሰቡ አስተማማኝና ትክክለኛ መረጃን ተደራሽ በማደረግ ጠንከርን እየሰራን ነው ያሉት የተቋሙ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ አጋርነታቸውን በማሳየታቸው ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት ህገወጡ የጥፋት ቡድን ላይ እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር እርምጃን በተመከለተ ግንባር ድረስ በመገኘት በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶችን በመጠቀም መረጃዎችን ለማህበረሰቡ እያቀረበ ይገኛል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8b%8b%e1%88%8d%e1%89%b3-%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%89%b0%e1%8a%9e%e1%89%bd-%e1%88%88%e1%88%98%e1%8a%a8%e1%88%8b%e1%8a%a8%e1%8b%ab-%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%8b%8a%e1%89%b5-%e1%8b%b0%e1%88%9d/
119
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሐረሪ ክልል የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
Unknown
በሐረሪ ክልል የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በአገራዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው።በሐረር ከተማ  በሚካሄደው ውይይት ላይ ተወላጆቹ የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ከክልሉ መንግስት ጋር በትብብር በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ ተብሏል።ከጁንታው ሕወሓት ቡድን ራሳቸውን በመጠበቅ ለጥፋት የተሰማሩ አካላትን አጋልጠው በሚሰጡበት ሁኔታ ላይም ይወያያሉ።በመድረኩ ላይ የተለያዩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ኢዜአ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%90%e1%88%a8%e1%88%aa-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8c%88%e1%8a%99-%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%89%b0%e1%8b%88%e1%88%8b%e1%8c%86%e1%89%bd/
51
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያና ስዊድን ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ትስስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
Unknown
የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከስዊድኑ የአለም ዓቀፍ የልማት ትብብር ምክትል ሚኒስትር ፔር ኡልሰን ፍሪዝ ጋር ተወያይተዋል።በነበራቸው የስልክ ቆይታ በሃገራችን ሰሜናዊ ክፍል የህግ ማስከበር ሂደት ውስጥ ከመገባቱ አስቀድሞ ሰላምን በስልጡን ምክክር ለማስፈን የተሄደበትን ረጅም ርቀት በዝርዝር አስረድተዋል።በተጨማሪም በህግ ማስከበር ሂደቱ ወቅት ሰላማዊ ዜጎቻችን ጉዳት እንዳይደርስባቸው በከፍተኛ ጥንቃቄ መካሄዱን ተናግረዋል።የስዊድኑ ምክትል ሚኒስትርም በበኩላቸው በሁለቱ ሃገራት መካከል የቆየው የእህታማማችነት ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ባለው ሁኔታ የተጎዱ ዜጎችን መልሶ የማቋቋምና መሰረተ ልማትን መልሶ የመገንባት ርብርብን ለመደገፍ ከኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ጎን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8a%93-%e1%88%b5%e1%8b%8a%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%88%a8%e1%8c%85%e1%88%9d-%e1%8b%98%e1%88%98%e1%8a%93%e1%89%b5-%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%89%86%e1%8c%a0/
81
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሶማሊያ የሚገኘው የሀገሪቱ ጦር እንዲወጣ ትዕዛዝ ሰጡ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 5, 2020
Unknown
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሶማሊያ የሚገኘውን የአሜሪካ ጦር በአስቸኳይ እንዲወጣ ትእዛዝ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡ፕሬዚዳንቱ በሶማሊያ ያለው ጦር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ ጥር 15 ለቆ እንዲወጣ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን ከፔንታጎን የወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡ጦሩ ላለፉት በርካታ አመታት በሀገሪቱ አልሸባብ የሚፈፅመውን የሽብር ጥቃት ሲዋጋ መቆየቱ የተጠቀሰ ሲሆን አሁን ላይ ለቆ መውጣቱ በሀገሪቱ ያለውን ብቻ ሳይሆን ቀጣናውን ስጋት ላይ የሚጥል ነው ተብሏል፡፡ትዕዛዙ አሜሪካ በአለም አቀፍ ደረጃ እየወሰደች ያለውን ወታደራዊ ቅነሳ አካል ስለመሆኑም ነው የተነገረው፡፡በሶማሊያ የሚገኘው አፍሪኮም የሚል ስያሜ ያለው ይህ የሰላም አስከባሪው ሃይል ቁጥሩ  ከ650 እስከ 800 እንደሚሆን አልጀዚራ በዘገባው አመላክቷል፡፡የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካዩ እና ተሰናባቹ ፕሬዝደነት ዶናልድ ትራምፕ የስልጣን መንበራቸው ከማስረከባቸ በፊት የወሰኑት ውሳኔ እንደሆነ የተወሳ ሲሆን የወሰዱት ውስኔ ትክክል አይደለም በሚልም ትቸት ቀርቦባቸዋል፡፡የወታደራዊ ሃይሉ እንደሚወጣ ቢረጋገጥም አሜሪካ ለአፍሪካውያን ያላትን አጋርነት በቀጣይነት መንግስታትን በመደገፍ ትቀጥላለች መባሉን ቢቢሲ እና አልጀዚራ ዘግበዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%9c%e1%88%aa%e1%8a%ab%e1%8b%8d-%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%9d%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%8b%b6%e1%8a%93%e1%88%8d%e1%8b%b5-%e1%89%b5%e1%88%ab%e1%88%9d%e1%8d%95-%e1%89%a0/
123
4ዓለም አቀፍ ዜና
በሰላም ማስከበር ወቅት የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን የመማር ማስተማሩ ስራ በሁሉም ቦታ ይጀምራል- የትምህርት ሚኒስቴር
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
Unknown
በትግራይ በትግራይ ክልል የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን ትምህርት ለማስጀመር 50 ሚሊየን ብር በጀት መያዙን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊየን ማቲዎስ ገለጹ።በአማራ ክልል አጎራባች አካባቢዎች በህግ ማስከበር ሂደቱ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን በመጠገን ወደ ስራ ለማስገባትም እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።ለትግራይ ክልልም ከ700 ሺህ በላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መዘጋጀቱንም ጠቁመዋል።ሚኒስቴሩ ትምህርት በሁሉም አካባቢ እንዲጀመር ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ይታወሳል። መረጃውን ያገኘነው ከትምህርት ሚኒስቴር ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%8b%88%e1%89%85%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8c%8e%e1%8b%b1-%e1%88%98%e1%88%b0%e1%88%a8%e1%89%b0-%e1%88%8d/
62
0ሀገር አቀፍ ዜና
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዴንማርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
Unknown
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዴንማርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፒ ኮፎድ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።በውይይታቸውም አቶ ደመቀ በትግራይ ክልል ስለተካሄደው ሕግ የማስከበር ዘመቻ እና የሰብአዊ አገልግሎቶች ገለጻ አድርገዋል።በአሁኑ ወቅት መንግሥት የሕግ ማስከበር ዘመቻውን አጠናቅቅ ክልሉን መልሶ መገንባት እና ማረጋጋት ላይ እየሠራ መሆኑን ለዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚነኒስትር ገልጸውላቸዋል።ጄፔ ኮፎድ በበኩላቸው ሰብዓዊ ዕርዳታ በመስጠትና የዜጎችን መብት ለማስጠበቅ የኢትዮጵያን መንግሥት በሚቻለው ሁሉ ለመደገፍ አገራቸው ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡ሚኒስትሮቹ በተጨማሪ ስለ መጪው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ላይም ተወያይተዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%89%b5%e1%88%8d-%e1%8c%a0%e1%89%85%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8b%8d%e1%8c%ad-%e1%8c%89%e1%8b%b3%e1%8b%ad-2/
75
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሚቀጥሉት 5 አመታት ኢትዮጵያ 10 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ሃይል የማመንጨት አቅም ይኖራታል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
Unknown
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና የኮይሻ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች  ሲጠናቀቁ በሚቀጥሉት 5 አመታት  ኢትዮጵያ  ከ10 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ  የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም እንደሚኖራት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተናገሩ።በሚቀጥሉት 10 አመታት ደግሞ ኢትዮጵያ 20 ሺህ ሜጋዋት  የኤሌክትሪክ ሃይል ለማመንጨት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር አቅዳ እየሰራች መሆኑንም በዌቢናር በተካሄደው የዩይትድ ኪንግደምና የአፍሪካ የኢነርጂ ሚኒስተሮች ሲምፖሲየም ላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡በዚህ ሲምፖዚየም ላይ የኢትዮጵያ፣ የሞሮኮ፣ የግብጽ፣ የሞዛምቢክና የሞሪታኒያ ሃገራት የኢነርጂ ሚኒስትሮች እንዲሁም በረካታ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡በዚሁ መድረክ ኢትዮጵያ እስካሁን 6ዐ በመቶ  የሚሆኑት ዜጎቿ  የሃይል ተጠቃሚ እንዳልሆኑና ይኸው የሃይል አቅርት ችግር ሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን እያስከተለ እንደሆነ ሚንስትሩ አስረድተዋል።እ.ኤ.አ በ2025 ኢትዮጵያ በግሪድና በኦፍ ግሪድ ለዜጎች ሙሉ በሙሉ ሃይል ለማቅረብ ያለመች መሆኑን ጠቁመው፣ ይሁንና ግን ዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪና ቴክኖሎጂ የሚጠይቅ በመሆኑ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ሃገራት ባለሃብቶች በዘርፉ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅርባችውን ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%9a%e1%89%80%e1%8c%a5%e1%88%89%e1%89%b5-5-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-10-%e1%88%ba%e1%88%85-%e1%88%9c%e1%8c%8b-%e1%8b%8b%e1%89%b5/
137
0ሀገር አቀፍ ዜና
“የሕወሓት ቡድን የሚያሰራጫቸውን መረጃዎች ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በጥንቃቄ ማየት ይኖርበታል”- የፍራንስ24 ሚዲያ የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
Unknown
የሕወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ ዙሪያ የሚያሰራጫቸውን የተለያዩ መረጃዎች ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በጥንቃቄ ማየት እንደሚኖርበት የፍራንስ24 ሚዲያ የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ ሮበርት ፓርሰን ገለጹ።ሮበርት ፓርሰን ከፍራንስ24 ጋር ባደረጉት ቆይታ ጁንታው የሕወሓት ቡድን የሚያሰራጫቸው የድል አድራጊነት መረጃዎችን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውነት ስለመሆናቸው በጥንቃቄ ሊያይ ይገባል ብለዋል።ቡድኑ “የኤርትራ ሠራዊት ከመንግሥት ጎን ሆኖ በሕግ ማስከበር ዘመቻው ላይ ተሳትፏል፣ ተዋጊ ጀት ጥለናል እንዲሁም ከመቐለ ከተማ ወጣ ባሉ ቦታዎች ውጊያው ቀጥሏል” የሚላቸው መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን ነው የገለጹት።እንዲሁም ቡድኑ የመከላከያ ሠራዊት ላይ ከፍተኛ የሆነ ድል መጎናጸፉን እና የአክሱም ከተማን በድጋሚ ተቆጣጥሬያለሁ የሚለውን እንማይቀበሉት ጠቁመዋል።መንግሥት በትግራይ ክልል የጀመረውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቁም አስገራሚ ነው ብለዋል።ቡድኑ ዋነኛዋ ይዞታው የነበረችው መቐለን ለቅቆ የሸሸው ጥቃት ሲበረታበት አፈገፈገ እንጂ  ከዚህ በፊት እንደሚለው ለወታደራዊ ስትራቴጂ ነው በማለት የሚያሰራጨው መረጃ መሬት ላይ ያለውን እውነታ አያሳይም ሲሉም ተናግረዋል።የሕወሓት ቡድን በቀጣይ ከተደበቀበት ስፍራ ሆኖ ውጊያ የሚያስቀጥል አቅም ይኖረዋል የሚል እምነት እንደሌላቸው ሮበርት ፓርሰን ገልጸዋል።የሕወሓት ቡድን ወደነበረበት ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት ከ1970ዎቹ ጀምሮ ወደ ሥልጣን እስከመጣበት ጊዜ ድረስ ካካሄደው የትግል እንቅስቃሴ ጋር የአሁኑ ይለያያል ብለዋል።የሕወሓት ቡድን ከኤርትራን እየወነጀለ፣ የጎረቤት ሀገራት ድንበር ላይ ቁጥጥር እያለ እና በክልሉ በቂ ድጋፍ ሳይኖረው ያጣውን መልሶ ለማግኘት የሚችል አይመስለኝም ሲሉ ሐሳባቸውን ማካፈላቸውን ፍራንስ24ን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%95%e1%8b%88%e1%88%93%e1%89%b5-%e1%89%a1%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%8c%ab%e1%89%b8%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%88%98%e1%88%a8%e1%8c%83/
187
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
Unknown
የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር የበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።በውይይቱ በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት የሰብዓዊ ድጋፍ ዳይሬክተር ሚስስ ሬና ገላኒ እና በተባበሩት መንግስታት አስተባባሪና የሰብዓዊ ድጋፍ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ካትሪን ሶዚ ተካፍለዋል።ሚኒስትሯ በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበር ሂደት እንዲሁም ከወታደራዊ ህግ የማስከበር ሂደት ቀድሞ ሰላምን በሰለጠነ መልኩ በውይይት ለማምጣት ስለተሄደው ረጅም እርቀት ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።በሰላም ማስከበር ሂደቱም ንጹሃን እንዳይጎዱና መሰረተ ልማት እንዳይፈርስ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ የተሞላበት ኦፕሬሽን እንደተካሄደ አስረድተዋል።ሚስስ ሬና ገላኒ በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ መንግስት ንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ የተደረገውን ጥረት አድንቀዋል።በመጨረሻም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደ ሁልጊዜውም ሰብዓዊና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን ከመንግስት ጋር በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%88%99%e1%8d%88%e1%88%aa%e1%88%83%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%88%9a%e1%88%8d-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%89%a3%e1%89%a0/
116
0ሀገር አቀፍ ዜና
በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት የሚገልጽ ዝግጅት አካሄዱ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
Unknown
በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነትና ድጋፍ የሚገልጽ ዝግጅት አካሂደዋል።የመከላከያ ሰራዊት በከሃዲውና ጽንፈኛው ህወሓት ቡድን የተቃጣበትን ጥቃት መክቶ በፍጥነት ኢትዮጵያን ወደ ድል ብስራት በማሸጋገሩ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።ለመከላከያ ሃይል ድጋፍ ለማድረግና በጽንፈኛው ህወሓት ርጥባን ተከፋዮች የሚነዛውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ለማክሸፍ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።ዝግጅቱ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አስተባባሪነት የተካሄደ መሆኑን በዋሽንግተን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8b%8b%e1%88%bd%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%89%b0%e1%8a%95-%e1%8b%b2%e1%88%b2-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8a%a0%e1%8a%ab%e1%89%a3%e1%89%a2%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8a%96%e1%88%a9-%e1%8a%a2/
63
0ሀገር አቀፍ ዜና
የ15ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል አካል የሆነው የባህል አውደርዕይ የመክፈቻ ስነስርዓት ተካሄደ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የ15ኛው የብሔር ብረሰቦችና ህዝቦች በአል አካል የሆነው የባህል አውደርዕይ የመክፈቻ ስነስርአት በአዲስ አበባ ከተማ አበባ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄደ፡፡“እኩልነትና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው 15ኛው የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልክት “ኑ ኢትዮጵያን በአንድ መድረክ እንያት” በሚል  ከህዳር 24 እስከ 27 በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚካሄደው የባህል አውደርዕይ የመክፈቻ ስነ ስርአት ዛሬ ተጀምሯል፡፡በመክፈቻ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ የባህል አውደርዕይው የኢትዮጵያ ህዝቦችን ባህል፣ ታሪክና ቅርስ በአንድ መድረክ በማስተዋወቅ አንድነቱን የሚያጠናክር ነው ብለዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሳውን የህወሓት ፅንፈኛውን ቡድን የመከላከያ ሰራዊቱ ድል ባደረገበት ማግስት በአሉ በመከበሩ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡በአውደርዕዩ የመክፈቻ ስነስርአት ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የክልል የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም  ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የባህል ሉኡካን ቡድን አባላት ተገኝተዋል፡፡በሕይወት አክሊሉ
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a815%e1%8a%9b%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%89%a5%e1%88%94%e1%88%ad-%e1%89%a5%e1%88%94%e1%88%a8%e1%88%b0%e1%89%a6%e1%89%bd%e1%8a%93-%e1%88%85%e1%8b%9d%e1%89%a6%e1%89%bd-%e1%89%a0%e1%8b%93%e1%88%8d/
139
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኤጀንሲው በትግራይ ክልል በነበረው ህግ የማስከበር እርምጃ የምግብ ግብዓት እጥረት እንዳይከሰት እየተሰራ መሆኑ ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ የህወሓት ጁንታ ቡድን በሀገሪቱ የፈጠረውን የኢኮኖሚ እና የምግብ ግብዓት አቅርቦት ችግር ለመፍታት እና በትግራይ ክልል በነበረው ህግ የማስከበር እርምጃ በህብረተሰቡ ዘንድ የምግብ ግብዓት እጥረት እንዳይከሰት ቅድመ ዝግጅች እየተደረገ መሆኑን ገለጸ፡፡የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ሱሩር ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት ከአዲሱ የትግራይ ክልል አመራር ጋር በመቀናጀት እና በመነጋገር በክልሉ የሚያጋጥሙ የምግብ ግበዓት አቅርቦቶችን ለመፍታት እና ለህብረተሰቡ የማቅረብ ስራ ይሰራል፡፡የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ ሁሉም በአንድነት መስራት አለበት ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ሁሉም ህብረተሰብ ከመንግስት ጎን በመሆን አጋርነቱን ማሳየት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ያለፉት ጊዜያት በተለይም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና የምግብ ግበዓት አቅርቦትን በብርቱ የፈተኑትን ኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የአንበጣ መንጋ እና ጎርፍ መሆናቸውን ገልጸው፣ የተፈጠሩ ችግሮችን በመለየት በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንም ተናግረዋል፡፡ኤጀንሲው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ345 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በአስቸጋሪ መንገድ ሄደው ህዝባቸውን እና ሀገራቸውን ለማዳን ያደረጉትን ጥረት እንደሚያደንቁ የተናገሩት አቶ ኡስማን፣ ሀገር እና ህዝብን መውደድ በተግባር መገለጽ የሚችል መሆኑን በተግባር አሳይተዋል ብለዋል፡፡(በሜሮን መስፍን)
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a4%e1%8c%80%e1%8a%95%e1%88%b2%e1%8b%8d-%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%89%a0%e1%8a%90%e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8b%8d-%e1%88%85%e1%8c%8d-%e1%8b%a8/
145
0ሀገር አቀፍ ዜና
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራርና አባላት የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄዱ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
ከ600 በላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል፣ ጸጥታና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት አመራሮችና አባላት ለሀገር ህልውና ሲሉ መስዋትነት ለከፈሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላትና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብር በመግለጽ የደም ልገሳ መርኃግብር አካሄዱ፡፡የጸጥታና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬቱ የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንዲቀርቡ በሚደረገው ጥረት የፖሊሳዊ ግዴታቸውን ከመወጣት ጎን ለጎን ደም ከመለገስ ጀምሮ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8d%8c%e1%8b%b4%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%8d%96%e1%88%8a%e1%88%b5-%e1%8a%ae%e1%88%9a%e1%88%bd%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%88%ab%e1%88%ad%e1%8a%93-%e1%8a%a0%e1%89%a3%e1%88%8b%e1%89%b5/
63
0ሀገር አቀፍ ዜና
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ ይጠናቀቃል- የትምህርት ሚኒስቴር
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
Unknown
የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሁሉም ክልሎች እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ።ይህንንም ተከትሎ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየትና አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለመስጠት የራሳቸውን የጊዜ ሰሌዳ እያወጡ እንደሚገኙ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡በዚህም መሰረት የሀረሪ ክልል ከታህሳስ 7 እስከ 9፣ የአማራ ክልል ከታህሳስ 12 እስከ 14 ፈተናውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።ሌሎች ክልሎችም በቀጣይ ቀናት ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ይፋ እንደሚያደርጉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከትላንት ጀምሮ መሰጠት መጀመሩም የሚታወስ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a88%e1%8a%9b-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8b%e1%8b%8a-%e1%8d%88%e1%89%b0%e1%8a%93-%e1%8a%a5%e1%88%b5%e1%8a%a8-%e1%89%b3%e1%88%85%e1%88%b3%e1%88%b5-30-%e1%89%b0%e1%88%b0/
83
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሀይሌ ጋርመንት አካባቢ እየተገነባ ያለው የገበያ ማዕከል ግንባታ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ ወደ አንድ ቢሊየን ብር በሚጠጋ የኮንትራት ዋጋ እየሰራ የሚገኘውን ተለዋጭ የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል የግንባታ ሥራ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚያጠናቀቅ አስታውቋል፡፡የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሀቢቢ መስቀላ ኮርፖሬሽኑ የገበያ ማዕከሉን በሁለት ምዕራፍ ከፋፍሎ እየገነባ መሆኑን ገልጸው፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ 14 የገበያ ሸዶች፣ በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ የፓርኪንግና የአረንጓዴ ቦታዎች፣ መጋዘኖች፣ የአስተዳደር ህንጻዎች እና ሌሎች የግንባታ ስራዎች እንደሚያከናውን ተናግረዋል፡፡ኮርፖሬሽኑ የገበያ ማዕከሉን ከ999 ሚሊየን 886 ሺህ 603 ብር የኮንትራት ዋጋ ለመገንባት ከአዲስ አበባ የኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በመፈራረም የግንባታ ስራውን ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም መጀመሩን የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ፣ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ በመጀመሪያው ምዕራፍ የሚገነቡትን የመገበያያ ሼዶች ከ70 በመቶ በላይ ማጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡የገበያ ማዕከሉ 80 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ እንደሚሸፍን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ የሚገነቡት 14 ሼዶች ውስጥ በ588 የመገበያያ ሱቆች እንዳሉት፣ ሼዶቹ 70 ሜትር በ6  ነጥብ 6 ሜትር ስፋት በ14ቱ ሼዶች ውስጥ ያሉት 588 የመገበያያ ሱቆች ደግሞ ሶስት ሜትር በ ሶስት ሜትር ስፋት እንዳላቸው የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%80%e1%8b%ad%e1%88%8c-%e1%8c%8b%e1%88%ad%e1%88%98%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%8a%ab%e1%89%a3%e1%89%a2-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8c%88%e1%8a%90%e1%89%a3-%e1%8b%ab%e1%88%88/
164
0ሀገር አቀፍ ዜና
የ8ኛ ክፍል ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ መሰጠት ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡በዛሬው ዕለት በወጣው መርኃግብር መሠረት ተማሪዎች በየተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።በከተማ አስተዳደሩ 156 የፈተና ጣቢዎች እንዳሉና 73 ሺህ 45 ተማሪዎች ለፈተና እንደተቀመጡ ታውቋል፡፡  
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a88%e1%8a%9b-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d-%e1%8d%88%e1%89%b0%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b-%e1%88%98%e1%88%b0%e1%8c%a0/
36
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር በመስራት ሰላማችንን እናረጋግጣለን — የሽሬ ከተማ ነዋሪዎች
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጎን በመቆም የከተማቸውን ሰላም ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የሽሬ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። የህወሓት የጥፋት ቡድን በህዝቡ ላይ በተለያዩ መንገዶች ሲያደርሰው የነበረው ብዙዎቹ ግፍና ጫና በአማርሮ እንደነበር  ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። “ህልውናችሁ የህወሓት ቡድን ብቻ ነው፣ ህወሓት ከሌለ ትግራይና ህዝቧ አይኖርም” በማለት ጁንታው ሲያደናግር እንደነበር  ኢዜአ ያነጋገራቸው የሽሬ ከተማ ተናግረዋል። የህወሓት ታጣቂ ቡድን ይባስ ብሎ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የትግራይ ህዝብ መከታ እና የልማት አጋር የነበረውን የሰሜን ዕዝ በማጥቃት የጭካኔውን ጥግ ማሳየቱንም ነው ነዋሪዎቹ የጠቀሱት። ድርጊቱ በሃይማኖትም የተወገዘ ከሰብዓዊነትም የወጣ እኩይ ተግባር መሆኑን የሽሬ ከተማ ነዋሪው መልዕከ ሰላም ገብረዋህድ ገብረማርያም ገልጸውልናል። “የሰውን ልጅ ያውም ወገንን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ለአሞራና ጅብ የሰጠ የህወሓት ቡድን የትግራይ ህዝብ ወኪል ነኝ ቢል ማንም የሚሰማው የለም” ብለዋል። የትግራይ ህዝብ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር እጅ እና ጓንት ሆኖ አብሮ እየበላ፣ ተዛምዶና ተዋልዶ የኖረ ስለመሆኑም አንስተዋል። ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ ሃጂ ሙሃመድ ሙርሃን ሲራጅ፤ “የመከላከያ ሠራዊት የህዝብ ልጅ እንጂ ወራሪም ጠላትም አለመሆኑን የትግራይ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል” ብለዋል። ሠራዊቱ የአርሶ አደር አዝመራ ሲሰበስብ፣ አንበጣ ሲያባርር እና በብዙ አጋጣሚዎች አብሮነቱን በተግባር ያሳየ የትግራይ ህዝብ ቤተሰብ መሆኑንም ጠቅሰዋል። “ይህንን የህዝብ አጋር የሆነ ሠራዊት ላይ ጥቃት የፈጸመው የህወሓት የጥፋት ቡድን የትግራይ ህዝብ ጠላት መሆኑን በግልጽ አሳይቷል፤ በቁጥጥር ሥር ውሎ በህግ ተጠያቂ መሆን ይኖርበታልም” ብለዋል ሃጂ ሙሃመድ። በጥፋት ተግባር የተሰማራው የህወሓት ቡድን በፈፀመው ወንጀል በህግ ተጠያቂ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ህዝቡ በየአካባቢው ሰላሙን በማረጋገጥ ልማቱን እንዲያስቀጥል ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙ ተገቢ መሆኑንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ከጊዜያዊ አስተደደሩ ጋር በመሆን ለከተማው ሰላምና ልማት በጋራ እንደሚሰሩም ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል። በተለይ ወጣቶች ለከተማቸው ብሎም ለአገራቸው ሰላም የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል። በሽሬ ከተማ በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩን በስፈራው የተገኘው የኢዜአ ሪፖርተር አረጋግጧል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የተሾሙት ዶክተር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በህዝብ ምርጫ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ በማቋቋም ላይ ይገኛሉ።
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a8%e1%8c%8a%e1%8b%9c%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%89%b0%e1%8b%b3%e1%8b%b0%e1%88%a9-%e1%8c%8b%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%88%b5%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9b/
280
0ሀገር አቀፍ ዜና
“አዲስ አበባ በዓለም መጎብኘት ካለባቸው 21 ምርጥ ቦታዎች አንዷ ናት” – ኮንዴ ናስት ትራቭለር መጽሔት
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
አዲስ አበባ እንደ አውሮጳዊያኑ አቆጣጠር 2021 በዓለም ላይ መጎብኘት ካለባቸው ምርጥ ቦታዎች አንዷ መሆኗን ታዋቂው የአሜሪካ የጉዞ መጽሔት “ኮንዴ ናስት ትራቭለር” ገለፀ።መፅሄቱ “ከተማዋ እንደ ስሟ እየሆነች መጥታለች” ብሏል።መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው ታዋቂው የጉዞ መጽሔት እንደዘገበው በቀጣዩ የአውሮጳዊያን ዓመት በዓለማችን መጎብኘት አለባቸው ያላቸውን 21 ምርጥ ቦታዎች ይፋማደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተጣሉ ገደቦች ምክንያት እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮጳዊያኑ ዓመት ሰዎች እንደልባቸው መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ መጽሔቱ አስታውሷል።በዓመቱ ውስጥ ሰዎች ጉዞ ባያደርጉም ለጉዞ ያላቸው ፍላጎትና ጉጉት አሁንም እንዳልተገታና ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ የሚገባው አዲሱ ዓመት ዳግም ወደ ጉዞ  የሚገቡበት ይሆናል ብሏል።“ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ስምና ዝና እየጨመረ መጥቷል” ያለው መጽሔቱ፤ እንደ አውሮጳዊያን አቆጣጠር በ2017 መጨረሻ የተጀመረው የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ አገልግሎት አገሪቷን ለመጎብኘት ያለውን ሂደት እንዳቀለለውና የቱሪዝም ዘርፍ 48 ነጥብ 6 በመቶ ዕድገት እንዲመዘግበት ማድረጉን ገልጿል።መፅሄቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኖቤል የሠላም ሽልማት ማግኘታቸው የዓለምን ትኩረት መሳቡን አንስቷል።ጎብኚዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም /ዩኔስኮ/ ዘጠኝ የሚዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበላትን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ሲመጡም አዲስ አበባን መዳረሻቸው እንዲያደርጉም ጠቁሟል።ባለፈው ዓመት የተከፈተው ባለ ብዙ ገጽታው የአንድነት ፓርክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በተሰራው ቤተ መንግስት ቅጥር ግቢ 16 ነጥብ 2 ሄክታር ቦታ መያዙን ገልጿል።ጎብኚዎች በፓርኩ በሚገኙ በግድግዳ የስነ-ጥበብ ስራዎች፣ አገር በቀል እፅዋትና የተቀረጹ ምስሎች በያዙ የአትክልት ስፍራዎች መጓዝ ይችላሉ፤ የዘጠኙን ክልሎች ባህል የሚያሳዩ ድንኳኖችንም ይመለከታሉ ብሏል።“በጥላ ውስጥ ያሉ ፊቶች” የኢትዮጵያን ታሪክ በጥልቅ የሚዳስስና የንጉሳዊውን ስርዓት የገለበጠው የደርግ መንግስት፣ የቀይ ሽብር ጊዜና የደርግ የፖለቲካ እስረኞች የደረሰባቸውን ስቃይ እንደሚያሳይ ያትታል።መፅሄቱ በአዲስ አበባ በስተሰሜን በኩል 20 ደቂቃ ከተጓዙ በኋላ ለአየር ንብረት ተስማሚ፣ አዲስ ፈጠራ የታከለበት የመዝናኛና የማረፊያ ቦታ የእንጦጦ ፓርክ እንደሚገኝም ይገልጻል።በባህር ዘፎች በተከበበውና በ1 ሺህ 295 ሄክታር መሬት ላይ የተንጣለለው የእንጠጦ ፓርክ በውስጡ ረጅም ርቀት ጉዞ የሚደረግባቸው ቦታዎች፣ የብስክሌትና የፈረስ መጋለቢያ ስፍራዎች፣ ዒላማ መተኮሻ፣ የቡድን ተኩስ ስፖርት መጫወቻ /ፔይንትቦል/፣ የመወዳደሪያ መኪኖችና በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የገመድ ወይም ኬብል ላይ መጓጓዣ ስለመኖሩም ጠቅሷል።ጎብኚዎች በእንጦጦ ፓርክ ምሽቱን በኩሪፍቱ ሪዞርት በማሳለፍ  በኮከብ ከደመቀችው ሰማይ ስር ሆኖ በፓርኩ በተዘጋጁት አነስተኛ የድንኳን ማደሪያዎች ጊዜ ማሳለፍ እንደሚችሉ መጽሔቱ አመልክቷል።በተጨማሪም አዲስ አበባን መጎብኘት ማለት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሚገኘው “የዓለማችን የመጀመሪያው ከንኪኪ ነጻ የተጓዦች ተርሚናል” ማለፍ እንደሆነና የተርሚናሉ ግንባታ ለብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ትኩረት መስጠቱን ይገልጻል።ባለፈው ዓመት የተከፈተው የኢትዮጵያን እምቅ የእስልምና ሃይማኖት ቅርሶችን የያዘው ቢላሉል ሐበሺ ሙዚየምም በመዲናዋ ይገኛል ብሏል።የፓርኮች ግንቦታ መጀመሩ ከተማዋ በያዘችው ፍጥነት መጓዟን እንደምትቀጥል እንደሚያሳይ ጠቅሶ አዲስ አበባ ‘ከአስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ስሟ እየኖረች ነው ይላል መጽሔቱ በዳሰሳው።የአሜሪካው ታዋቂ የጉዞ መጽሔት ኮንዴ ናስት ትራቭለር አንጎላና ጋናን ከአፍሪካ መጎብኘት ያለባቸው በማለት የምርጥ ቦታዎች ዝርዝር ውስጥ አካቷቸዋል።ኒው ዮርክ ከተማ፣ ሂልድስበርግ,ካሊፎርኒያ፣ ቤርሙዳ፣ ቺያፓስ /ሜክሲኮ/፣ ኪዮቶ /ጃፓን/፣ ኖቫ ስኮቲያ /ካናዳ/፣ ኢጣሊያ፣ ኦስሎ /ኖርዌይ/፣ ጠረፋማ የእንግሊዝ አካባቢዎችና ሆኪያንጋ /ኒውዚላንድ/  መጎብኘት አለባቸው ከተባሉት 21 ምርጥ ቦታዎች ውስጥ ይገኙበታል።በኮንዴ ናስት ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ኩባንያ የሚተዳደረው የአሜሪካ ታዋቂ የጉዞ መጽሔት ከ33 ዓመታት በፊት መቋቋሙን መረጃዎች ያመላክታሉ።
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%89%a0%e1%8b%93%e1%88%88%e1%88%9d-%e1%88%98%e1%8c%8e%e1%89%a5%e1%8a%98%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%88%88%e1%89%a3%e1%89%b8%e1%8b%8d-21/
420
0ሀገር አቀፍ ዜና
የብሔራዊ መታወቂያ ዝግጅት ወደ ተግባር መግባት እንዳለበት ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሰላም ሚኒስቴርንና ተጠሪ ተቋማትን የ2013 በጀት አመት ዕቅድና የአንደኛ ሩብ አመት አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት የብሔራዊ መታወቂያ ዝግጅት ወደ ተግባር መግባት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡የሰላም ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ብርቱካን ሰብስቤ የብሔራዊ መታወቂያ ዝግጅትን በተመለከተ ከሂደት ባለፈ ወደ ተጨባጭ ተግባር አለመግባቱን ገልጸው፣ በሀገራዊ የጋራ ታሪክ፣ ትርክትና መገለጫዎቹ እንዲሁም በህገ መንግስቱ መሰረታዊ መርሆች ላይ ብሄራዊ መግባባት ለመጀመር እና አለመግባባቶች ግጭት አልባ በሆነ ግንኙነት እንዲፈቱ መከላከል የሚያስችል ስትራቴጂክ ሰነድ መዘጋጀቱን በጥንካሬ ጎን አንስተዋል፡፡ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠርና ለመከታተል የሚያስችል የሶፍትዌር ቴክኖሎጂ በሚኒስቴሩ እና በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን መሪነት ስራ መጀመሩም በጥንካሬ ተነስቷል፡፡የ2012 ዓ.ም በጀት አመት የኦዲት ግኝትን በተመለከተ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በኩል እንዲስተካከሉ የተባሉ የኦዲት ግኝቶች ላይ የተወሰደው እርምጃ ዝርዝር ሪፖርት አለመቅረቡን ሰብሳቢዋ በውስንነት ጠቅሰዋል፡፡ብሔራዊ መግባባትን አስመልክቶ በሩብ አመቱ የተፈጸመው ከታቀደው 42 በመቶ ብቻ መሆኑንም ወ/ሮ ብርቱካን በጉድለት አንስተዋል፡፡የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፣ የብሔራዊ መታወቂያ የሙከራ ትግበራ መደረጉን አንስተው፣ እስካሁን ያሉ እንቅስቃሴዎች ለ30 ሚሊየን ዜጎች መታወቂያ ማተም የሚያስችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ መሰረት በማድረግ ደንብና መመሪያ መዘጋጀቱን የገለጹት ወ/ሮ ሙፈሪሃት፣ ሁሉም መሳሪያዎች የመንግስትን ጨምሮ መመዝገብና በስርአት መመራት እንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ከ700 በላይ በወንጀል ተጠርጣሪዎች ከ500 በላይ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያዎች እንዲሁም ከ14 ሺህ በላይ ጥይቶች መያዛቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል አቶ መላኩ ፋንታ መግለፃቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%a5%e1%88%94%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%88%98%e1%89%b3%e1%8b%88%e1%89%82%e1%8b%ab-%e1%8b%9d%e1%8c%8d%e1%8c%85%e1%89%b5-%e1%8b%88%e1%8b%b0-%e1%89%b0%e1%8c%8d%e1%89%a3%e1%88%ad-%e1%88%98/
219
0ሀገር አቀፍ ዜና
ምክር ቤቱ የፌዴራልና የክልል መንግስታት የግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራልና የክልል መንግስታት የግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ።ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ ኒውክለርን አማራጭ የሃይል አቅርቦት ለማድረግ ከሩሲያ ጋር የተፈራረመችውን የስምምነት ረቂቅም በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።በዚህም የፌዴራልና የክልል መንግስታት የግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።ከሶስት ዓመታት በፊት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣው ረቂቅ አዋጅ በምክር ቤቱ የህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና በሚመለከታቸው አካላት በጥንቃቄ ሲታይ እንደነበር ተገልጿል።የፌዴራልና የክልል መንግስታት ያላቸውን አቅም በማቀናጀት ህጋዊ በሆነ መንገድ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ የግንኙነት ስርዓቱ ወሳኝ መሆኑ ተብራርቷል።ረቂቅ አዋጁ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ አልዘገየም ወይ? የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የክልል መንግስታት በረቂቅ አዋጁ ላይ የነበራቸው ተሳትፎ ምን ይመስላል? የሚሉና ሌሎችንም ጥያቄዎች በምክር ቤት አባላት ተነስተዋል።የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በኢትዮጵያ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት የፌዴራልና የክልል መንግስታት ግንኙነት ህጋዊ ዕውቅና ሊኖረው ይገባል ብለዋል።በተናጠልና በጋራ የተሰጣቸውን ስልጣንና ተግባር በግልጽ በማስቀመጥ አገራዊ የልማት ስራዎችን በተናበበ መልኩ መስራት እንደሚገባቸውም ነው ያነሱት።በኢትዮጵያ ቀደም ሲል የነበረው የአንድ ፓርቲ ስርዓት የመንግስት ስራ በህግ አግባብ ሳይሆን በመንግስታቱ በጎ ፍቃድ ብቻ እንዲመራ አድርጓል ብለዋል።ይህም በፌዴራልና በክልሎች መካከል የተናበበ ውጤታማ ስራ እንዳይሰራ እንቅፋት ሆኗል ነው ያሉት።ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ቀደም ሲል ሲያወጣቸው ከነበሩ ህጎች በተለየ ጊዜ ወስዶ በከፍተኛ ጥንቃቄ ማየቱንም አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ ኒውክለርን ለሰላማዊ ዓላማ ተጠቅማ አማራጭ የሃይል አቅርቦቷን ለማስፋት ከሩሲያ መንግስት ጋር የፈረመችው ስምምነት ረቂቅ አዋጅንም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።የኢትዮ-ሩሲያን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ አዲስ የሃይል አማራጭ ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል።በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ የኒውክለር ስምምነቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አብራርተዋል።የኢዜአ ዘገባ እንዳመለከተው የምክር ቤቱ የ6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤም በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።
https://waltainfo.com/am/%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%88%ad-%e1%89%a4%e1%89%b1-%e1%8b%a8%e1%8d%8c%e1%8b%b4%e1%88%ab%e1%88%8d%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%b5%e1%89%b3%e1%89%b5/
270
0ሀገር አቀፍ ዜና
የህወሓት ቡድን ከአገራዊ ለውጡ በፊትና በኋላ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ህገ-ወጥ ተግባራትን ፈፅሟል- አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የህወሓት ቡድን ከአገራዊ ለውጡ በፊትና በኋላም ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ክልላዊ ምርጫን ጨምሮ የተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባራት መፈፀሙን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ ገለጹ።አፈ ጉባኤው ዛሬ በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል የተደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ህገ-መንግስታዊ ስርዓትን ተከትሎ በብቃትና በውጤታማነት መፈጸሙን ገልጸዋል።ቡድኑ ህገ -ወጥ ድርጊቱን እንዲያቆም በምክር ቤቱ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግለትም ህገ-መንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን ከማድረግ ሊቆጠብ አልቻለም ነበር ብለዋል።ይህን ተከትሎ የህወሓት ምክር ቤት እንዲፈርስ ስራ አስፈጻሚው አካልም ዕውቅና እንዳይኖረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ማሳለፉን ያስታወሱት አቶ አደም፣ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ምክር ቤቱ መወሰኑና ውሳኔውም ህገ-መንግስቱን ለማስፈጸም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 359/95 መሰረት በማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።መንግስት ይህን ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የወሰደው እርምጃ የንጹሃን ዜጎችን ደህንነት በጠበቀ መልኩ መሆኑንም ገልጸዋል።የህግ ማስከበር ዘመቻው በህገ-መንግስቱ መሰረት በብቃትና በውጤታማነት መፈጸሙንም ምክር ቤቱ ገምግሟል ብለዋል።ምክር ቤቱ በቀጣይም በትግራይ ክልል የሚከናወኑ ተግባራት በህገ-መንግስቱ መሰረት መፈጸም አለመፈጸማቸውን የሚከታተል መሆኑን ተናግረዋል።በዚህ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በክልሉ ስላለው ሁኔታ በቀጣይ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባሉም ብለዋል።በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር የክልሉ ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል የነበሩት ስልጣንና ተግባር የሚኖሩት በመሆኑ የክልሉን እቅድና በጀት ያጸድቃል ነው ያሉት።ጊዜያዊ አስተዳደሩ በይፋ ስራውን መጀመሩን ተከትሎ በከተሞችና ወረዳዎች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በሚያሳትፍ መልኩ አመራሮችን መመደቡ ጥሩ ጅምር መሆኑንም አፈ ጉባኤ አቶ አደም መግለፃቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8b%88%e1%88%93%e1%89%b5-%e1%89%a1%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%8a%a8%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%88%88%e1%8b%8d%e1%8c%a1-%e1%89%a0%e1%8d%8a%e1%89%b5%e1%8a%93-%e1%89%a0/
195
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ከሀዲውን ኮሎኔል ማንቁርቱን ይዛ አስረከበች
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
20ኛ  ክ/ጦር ሰሜን ዕዝ ካሏት የጦር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ክ/ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄ የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ አጃቢ ነች ። ጁንታ መሆኑን ግን አታውቅም።የእብሪት ርምጃቸው ከመጀመሩ ከ3 ቀናት በፊት ሰራዊቱ የምግብና መጠጥ አገልግሎት የሚያገኝባቸውን መንገድ በመዝጋት ሰራዊቱን ለከፍተኛ ርሃብና ጥም ዳርጏል።ሁሉም የሰራዊት አባል የግል ትጥቁን በአንድ ክፍል በማስቀመጥ በህብረተሰብ የድጋፍ ስራዎች ላይ እንዲረባረብ ማድረጉን ትናገራለች ።በተለይም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ምሽት ላይ ሁሉንም የጥበቃ ቦታዎች በትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት እንዲሸፈኑ በማድረግ ፣ የከሃዲው ቡድን ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ምንም አይነት ዝግጅትና ትጥቅ ባልነበረው ሰራዊታችን ላይ ከፍተኛ ተኩስ እንዲከፍትም አድርጏል ብላለች ።ሆኖም ታላቅ ጀግንነትና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የወረሰው ጀግናው ሃይላችን የማይታሰቡ ጀብዶችን ጭምር በመፈፀም ፣ ወደ ኤርትራ ስልታዊ ማፈግፈግ በማድረግ ራሱን ማዳን ችሏል ብላለች ።በዚህ ሁሉ ግፍና በደል መሃል የሻለቃዋ ዋና አዛዥና ለዘመናት የመራቸውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የካደው ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ ራሱን መፀዳጃ ቤት ውስጥ በመደበቅ በጁንታው የተሰጠውን ተልዕኮ መፈፀም እንደጀመረ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆና አስታውሳለች ።ውትድርና በኢትዮጵያዊነት ፍቅር መታጠብና በጀግንነት ካባ መድመቅ ነው የምትለው እንስቷ ጀግና ፣ ራስህን ለሃገር አሳልፈህ ከሰጠህ ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻውን ጀግንነትን ይወልዳል ስትል የቀድሞ አለቃዋን እንዴት ከስሯ እንዲንበረከክ እንዳደረገችው እንዲህ ታጫውተናለች ።“… ሰራዊታችን በታፈነበት ጥቅምት 24 ምሽት 2 ሰዓት ላይ በከባድ መሳሪያ የታጀበ ተኩስ ወደ ካምፓችን ተተኮሰ፣ በዚህ ሰዓት ወደ መፀዳጃ ቤት ራሱን የደበቀው ከሃዲው አዛዥ ተብዬ ፣ እኔ በትግራይ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ጥይት ከምሞት አንተን ገድዬ ራሴን አጠፋለሁ አልኩት፣ ተኩሱ በርትቷል፣ ሁሉም ራሱን ለማዳን ወደህሊናው የመጣለትን አማራጭ እየተጠቀመ ይሯሯጣል…”“… በመጨረሻም ከተደበቀበት መፀዳጃ ቤት እንዲወጣና እኔ የምለውን ብቻ እንዲፈፅም እሽ የማይል ከሆነ ግን እንደምገድለው አስጠነቀቁት፥ እሱም በፍርሃት ውስጥ ሆኖ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ወደነገርኩት ቦታ መጣ፥ ሽጉጡንና ማዕረጉን እንዲሰጠኝ አደረኩ፣ ከዛም ጫማውን እንዲያወልቅ አድርጌ በየመንገዱ ከማገኛቸው የሰራዊት አባላት ጋር በመተባበርና ሙሉ ለሊት የእግር ጉዞ በማድረግ ኤርትራ ይዤው በመግባት ታማኝ እና ሙሉ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ አመራሮች አስረከብኩ ።”ሰራዊታችን በራሱ ወገኖች የደረሰበትን በቃላት የማይገለፅ ግፍና በደል ተሸክሞ ቂምን ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ፍቅር አስቀድሞ ለድል በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማትም ምክትል አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ ስሜቷን አጋርታናለች ።ኢትዮጵያችን ምንም እንኳን በራሱ ጉያ ተወሽቀው ሳቋን እየቀሙ ውርደቷን የሚያፋጥኑና መበተኗን ገሃድ ለማውጣት ሌት ተቀን የሚሯሯጡ ወጪት ሰባሪዎች ቅዠታቸውን ቢኖሩትም ፣ ክብሯን የሚያስጠብቁ ከራሳቸው ህይወት ይልቅ የሃገራችውን ክብር የሚያስቀድሙ ፣ የማይታመን ጀግንነት እየፈፀሙ ኢትዮጵያችንን ከፍ ያደረጉ የበርካታ የቁርጥ ቀን ልጆች ባለቤት ናት ኢትዮጵያ !ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄም ጀግና ማፍራት የማትሰለቸው ሃገራችን ከሰጠችን እንቁ ኢትዮጵያውያን አንዷ ናት ። እንዳንቺ አይነት ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሁሌም በኢትዮጵያዊ ክብር ደምቆ ይኖራል ።የከሃዲዎች መጨረሻ ፣ ሃገርን ለማዋረድ ባሴሩት ህልም ውስጥ ተጠልፎ መውደቅ ነው ።(ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ) 
https://waltainfo.com/am/%e1%8c%80%e1%8c%8d%e1%8a%93%e1%8b%8b-%e1%88%9d-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%89%83-%e1%8a%a8%e1%88%80%e1%8b%b2%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8a%ae%e1%88%8e%e1%8a%94%e1%88%8d-%e1%88%9b/
395
0ሀገር አቀፍ ዜና
በመቀሌ ከተማ የአገር መከላከያ ሰራዊት የማያውቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኘ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የልዩ ዘመቻ 2ኛ ብርጌድ 3ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሳድቅ አህመድ እንዳሉት መቀሌ ላይ መከላከያ የማያውቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፖ ተገኝቷል።የጁንታው ቡድን ውጊያውን መቋቋም ሲሳነው ትጥቁን እያራገፈ መሸሹን ተከትሎ ሰራዊቱ የማያውቀው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የተከማቹበት ዲፖ ተገኝቷል ብለዋል፡፡የሰሜን እዝ አመራሮችን ጠይቀን ስለዲፖው እንደማያውቁ ገልጸውልናል ያሉት ሌተናል ጀነራሉ፣ በቀጣይም ተመሳሳይ የመሳሪያ ማከማቻወችም ሊገኙ እንደሚችሉ ገልፀዋል።የኢዜአ ዘገባ እንዳመለከተው እነዚህ ከቀላል እስከ ቡድን መሳሪያዎች ወንጀል እዳይፈጸምባቸው የፍተሻ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%80%e1%88%8c-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%8a%a8%e1%88%8b%e1%8a%a8%e1%8b%ab-%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%8b%8a%e1%89%b5-%e1%8b%a8/
67
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው እያካሄደ የሚገኘው፡፡በስብሰባው የምክር ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ከዚህ ባለፈም በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክርም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%95%e1%8b%9d%e1%89%a5-%e1%89%b0%e1%8b%88%e1%8a%ab%e1%8b%ae%e1%89%bd-%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%88%ad-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%8b%b0%e1%89%a0%e1%8a%9b-%e1%88%b5%e1%89%a5%e1%88%b0/
53
0ሀገር አቀፍ ዜና
ቻይና በባይደን ቡድን ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እየጣረች ነው ተባለ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
ቻይና በቅርቡ ስልጣናቸውን በሚረከቡት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እየጣረች መሆኑን የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡በሀገሪቱ ብሔራዊ የደህንነት ተቋም ውስጥ ባልደረባ የሆኑት ዊሊያም ኢቫኒና ቻይና በባይደን ቡድን ውስጥ የሚሰሩ ግለሰቦችን ኢላማ ማድረጓን ገልጸዋል፡፡በባይደን ቡድን ላይ የተደረገው ተጽዕኖ የተጠናከረ ነበር ያሉት ኢቫኒና፣ በተጨማሪም ቻይና አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማግኘት በምታደርገው ጥረት እና በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ጣልቃ ለመግባት መሞከሯን ነው ያስረዱት፡፡ኢቫኒቫ ቀጣዩ አስተዳደር ይህንን የቻይና ተፅዕኖ መረዳት መቻል አለበትም ነው ያሉት፡፡2020 በተደረገው የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ትራምፕ ቻይና ባላቸው የባንክ ደብተር እንዲሁም ባይደን ልጃቸው ሃተር ከቻይና ጋር ባካሄደው የንግድ ስምምነት ዙሪያ ስማቸው ሲነሳ እንደነበር አስታውሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%89%bb%e1%8b%ad%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%89%a3%e1%8b%ad%e1%8b%b0%e1%8a%95-%e1%89%a1%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%89%b0%e1%8c%bd%e1%8b%95%e1%8a%96-%e1%88%88%e1%88%9b%e1%88%b3%e1%8b%b0/
96
4ዓለም አቀፍ ዜና
የሙሴቬኒ ተፎካካሪ ቦቢ ዋይን የምርጫ ቅስቀሳ አላደርግም አለ
ዓለም አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የኡጋንዳ ፕሬዝዳንትዊ ምርጫ ተፎካካሪ የሆነውና በጥበብ ስሙ ቦቢ ዋይን ተብሎ የሚጠራው ሮበርት ኪያጉላኒ የምረጡኝ ዘመቻን ለማቆም እንደተገደደ ተናገረ።ለዚህ ውሳኔ ያበቃው ደግሞ የቅስቀሳ ቡድን አባላቱ ላይ ጥቃት በመበራከቱ ነው።ቦቢ እንደሚለው መኪናው ተሳብሮበታል፣ የቅርብ ረዳቶቹም ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል።ፖሊስ ደጋፊዎቹን በመደብደብና በማሰቃየት ላይ ይገኛል።በምሥራቅ ካምፓላ ካዩንጋ የቦቢ ደጋፊዎች አደባባይ በመውጣታቸው ፖሊስ በቆመጥና በአስለቃሽ ጭስ በትኗቸዋል።አራት የቅስቀሳ ቡድን አባላቱም ክፉኛ ቆስለዋል ተብሏል።ከአራቱ አንዱ የሙዚቃ ፕሮዲዩሰር የሆነው ዳን ማጂክ ሲሆን ፊቱ ላይ ጉዳት ደርሶበታል።ቦቢ ዋይን ዛሬ ረቡዕ ወደ ምርጫ ኮሚሽን በመሄድ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ፈተና እንደሆነበት እንደሚያብራራ ለጋዜጠኞች ተናግሯል።ምንጭ ፡- ቢቢሲ 
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%99%e1%88%b4%e1%89%ac%e1%8a%92-%e1%89%b0%e1%8d%8e%e1%8a%ab%e1%8a%ab%e1%88%aa-%e1%89%a6%e1%89%a2-%e1%8b%8b%e1%8b%ad%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab-%e1%89%85%e1%88%b5/
86
4ዓለም አቀፍ ዜና
ተመድ በሱዳን የሚገኙ ስደተኞች ለመመለስ የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞን ለመመለስ የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ ገለጸ።የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፍሊፕ ግራንዲ ከሲኤንኤን ጋር በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ቆይታ አድርገዋል።ኮሚሽነሩ በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በመገኘት ያለውን እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።ከሲኤንኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ስደተኞችን በማስተናገድ ረገድ አዎንታዊና የሚደነቅ ታሪክ አለው።በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት በርካታ ኢትዮጵያውያን ድንበር አቋርጠው ሱዳን መግባታቸውን አስታውሰው፤ በጉዟቸው በየትኛውም ግጭት ወቅት እንደሚደረገው በየቦታው ኬላዎች እንደነበሩ ገልጸዋል።የነበረው ውጥረት በአሁኑ ወቅት በምዕራብ ኢትዮጵያ ወደመረጋጋት እየተመለሰ በመሆኑ ቀደም ሲል ከነበረው የስደተኛ ቁጥር አንጻር እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል።የኢትዮጵያ መንግስት ቀውሱን በመሸሽ የተሰደዱትን ዜጎቹን ለመመለስ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ተመድ የመመለስ ጥረቱን እንደሚደግፍ አስታውቀዋል።የተሰደዱት ሰዎች አብዛኛዎቹ አርሶ አደሮች በመሆናቸውና ወቅቱ የምርት መሰብሰቢያ መሆኑ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ሊወድቁ እንደሚችሉም ገልጸዋል።“ስደተኞቹ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግስት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያደርገውን ጥረት እናግዛለን” ብለዋል።ምንጭ- ኢዜአ
https://waltainfo.com/am/%e1%89%b0%e1%88%98%e1%8b%b5-%e1%89%a0%e1%88%b1%e1%8b%b3%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8c%88%e1%8a%99-%e1%88%b5%e1%8b%b0%e1%89%b0%e1%8a%9e%e1%89%bd-%e1%88%88%e1%88%98%e1%88%98%e1%88%88%e1%88%b5/
129
0ሀገር አቀፍ ዜና
“የአብሮነት እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ወደ ፊት ማራመድ ይገባል”- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 2, 2020
Unknown
በኢትዮጵያ የቆየውን የአብሮነትና የአንድነት እሴቶች ይበልጥ በማጠናከር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ወደ ፊት ማራመድ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ተናገሩ።የሕብረ ብሔራዊ አንድነት ችቦ ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ጋምቤላ ክልል ሲገባ አቀባበል ተደርጎለታል።ርዕሰ መስተዳድሩ በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት፣ የሕወሓት ጁንታ ሲያራምደው የነበረውን የከፋፋይ አስተሳሰብ በማስወገድ አንድነትንና አብሮነትን የመገንባቱ ተግባር ሊጠናከር ይገባል።የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አንድነታቸውንና አብሮነታቸውን በማጠናከር የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ እና የብልጽግና ጉዞ ወደ ፊት ማራመድ እንዳለለባቸውም ተናግረዋል።የሕብረ ብሔራዊ አንድነት ችቦ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በቅብብሎሽ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል እንዲከበር የተወሰነው በሕዝቦች መካከል ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን አንድነት እና ወንድማማችነት ለማጠናከር መሆኑን አቶ ኡሞድ አስረድተዋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ ወ/ሮ ዘርፈሸዋል ንጉሴ የሕብረ ብሔራዊ አንድነት ችቦውን ለጋምቤላ ክልል ሲያስረክቡ “ኢትዮጵያ ለሁሉም የምትበቃ ቤታችን፣ ከለላ እናታችን ናት” ብለዋል።በሀገሪቱ ሰላም፣ ዕድገት እና ብልጽግና  እንዲረጋገጥ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል።የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች  በዓል ጁንታው ሀገር ለማፍረስ የከፈተው ዘመቻ በተቀለበሰበት ማግስት እየተከበረ መሆኑ የተለየ እንደሚያደረግው ጠቅሰዋል።የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ -ጉባኤ አቶ ጁል ናጋል በበኩላቸው ባለፉት 27 ዓመታት ህዝቦችን ለመለያየት ሲሰበክ የነበረውን ከፋፋይ አስተሳሰብ በማስወገድና አንድነትን በማጠናከር የተጀመረው ልማት ለማስቀጠል በጋራ መረባረብ ይገባል ብለዋል።በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ጭምር ታጅቦ ትናንት ጋምቤላ ከተማ የደረሰው  የህብር ብሄራዊ አንድነት ችቦ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች  እና የአካባቢው ነዋሪዎች አቀባበል የተደረገ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%89%a5%e1%88%ae%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%88%b4%e1%89%b6%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8b%ad%e1%89%a0%e1%88%8d%e1%8c%a5-%e1%89%a0%e1%88%9b%e1%8c%a0%e1%8a%93%e1%8a%a8/
204
0ሀገር አቀፍ ዜና
የተሻሻለው አዋጅ የውጭ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ክፍት እንደሚያደርግ ተነገረ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 2, 2020
Unknown
የተሻሻለው የኢንቨስትመንት አዋጅ ለውጭ ኩባንያዎች ዝግ የነበሩ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ክፍት እንደሚያደርግ ተነገረ።የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተሻሻለውን የኢንቨስትመንት አዋጅ በሚመለከት ለባለድርሻ አካላት ገለፃ አድርጓል።ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ የተሻሻለው የኢንቨስትመንት አዋጅ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን እንደሚያበረታታ ተናግረው የሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ገልፀዋል።የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉ በበኩላቸው በውጭ ኢንቨስትመንት እንዲሁም በሽርክና በሚሰሩ ስራዎች ላይ ከኤምባሲዎችና ሚሲዬኖች ጋር በጥምረት እየሰራን ነው ብለዋል።በዘርፉ የመረጃ እጥረት መኖሩን ያነሱት ሚንስትር ዴኤታዋ ትክክለኛ መረጃን ለውጭ ኢንቨስተሮች መስጠት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ብለዋል።በዘርፉ ስኬታማ ለመሆንም ለኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑንም አንስተው እንደ ሙስና ያሉ ብልሹ አሰራሮችን ማፅዳት ያስፈልጋል ብለዋል።ቀጥተኛ  የውጭ ኢንቨስትመንት ለመሳብ በሚያስችሉ ሂደቶች ላይም ውይይት ተካሂዷል።(በትዕግስት ዘለላም)
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%bb%e1%88%bb%e1%88%88%e1%8b%8d-%e1%8a%a0%e1%8b%8b%e1%8c%85-%e1%8b%a8%e1%8b%8d%e1%8c%ad-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%89%a8%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%98%e1%8a%95%e1%89%b5/
100
0ሀገር አቀፍ ዜና
ግብጽ በ2 ወራት ብቻ 57 ሰዎችን በስቅላት ቀጣች
ዓለም አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
ግብጽ በሞት የምትቀጣቸው ፍርደኞች ብዛት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ።ግብጽ ባለፉት ጥቅምትና ኅዳር ወራት ብቻ 57 ሰዎችን በስቅላት እንደቀጣችና ይህም በፈረንጆች 2019 በስቅላት ከተቀጡ ጠቅላላ ሰዎች እጥፍ በ2 ወራት ብቻ መፈጸሙን እንደሚያሳይ ተጠቁሟል፡፡ ግብጽ በአምነስቲ ዘገባ ላይ ያለችው ነገር የለም።ባለፈው ወር አምነስቲ ባወጣው አንድ ሪፖርት በግብጽ የሰብአዊ መብት አያያዝ ማሽቆልቆል ላይ የሰላ ትችት ሰንዝሮ ነበር።የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ እንደሚለው በቁጥር በርከት ያሉ ተቃዋሚዎች እና የመብት ተቆርቋሪዎች በግብጽ ብዙ ውጣ ውረድ እየደረሰባቸው ነው።ግማሾቹ የታሰሩ ሲሆን ቀሪዎች ደግሞ ከአገር እንዳይወጡ መደረጉንና አንዳንዶቹ ደግሞ በአልሲሲ መንግሥት ሀብትና ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ተወስኖባቸዋል።አልሲሲ በ2013 ወደ ሥልጣን የመጡት በዲሞክራሲያዊ መንገድ ሥልጣን ላይ የወጡትን ሟቹን መሐመድ ሞርሲን በመፈንቅለ መንግሥት ከጣሉ በኋላ ነው።በአብላጭ ድምጽ ወደ ሥልጣን መጥተው የነበሩት ሙሐመድ ሙርሲ በእስር ቤት ሳሉ ታመው ብዙም ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ መሞታቸው ይታወሳል።አልሲሲ በአገሬ አንድም የፖለቲካ እስረኛ የለም የሚሉ ሲሆን፣ የአምነስቲ መረጃ እንደሚያስረዳው በግብጽ በስቅላት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር በአንድ ጊዜ ማሻቀብ የጀመረው በካይሮ እጅግ ጥብቅ እንደሆነ ከሚነገርለት ከቶራ እስር ቤት ፍርድኞች ለማምለጥ ከሞከሩ ወዲህ ነው።በእስር ቤት ለማምለጥ ሞክረው በርካታ የሞት ፍርደኞችና ፖሊሶች መሞታቸው አይዘነጋም።ግብጽ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በሰብአዊ መብት ድርጅቶች የሚሰሩ በርከት ያሉ ዜጎቿን በማሰሯ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ከመብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍ ያለ ወቀሳ ሲቀርብባት ከርሟል።እንደ ቢቢሲ ዘገባ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግን ሕግን የማስከበር እርምጃ ተወሰደ እንጂ ሌላ የሆነ ነገር የለም ይላሉ።
https://waltainfo.com/am/%e1%8c%8d%e1%89%a5%e1%8c%bd-%e1%89%a02-%e1%8b%88%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%89%a5%e1%89%bb-57-%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%88%b5%e1%89%85%e1%88%8b%e1%89%b5-%e1%89%80%e1%8c%a3%e1%89%bd/
205
4ዓለም አቀፍ ዜና
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከእስራኤል የኢሚግሬሽን ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የእስራኤልን የኢሚግሬሽን ሚኒስትር ፕኒና ቶማኖ ሻታን በቤተመንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ሚኒስትሯ ወደ ትውልድ አገራቸው ኢትዮጵያ በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ለማጠናክር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ፕኒና ቶማኖ ሻታ በእስራኤል ይህንን የስራ ኃላፊነት የያዙ የመጀመሪያዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊት መሆናቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%9d%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%a3%e1%88%85%e1%88%88%e1%8b%88%e1%88%ad%e1%89%85-%e1%8b%98%e1%8b%8d%e1%8b%b4/
46
0ሀገር አቀፍ ዜና
የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን መቐለ ከተማ ገባ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 3, 2020
Unknown
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም መቐለ ከተማ መግባቱን አስታውቋል።የፌዴራል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የጁንታውን ተፈላጊ ወንጀለኛ ቡድን ማደን መጀመሩ ተገልጿል።የኮማንዶ ቡድኑ በከተማዋ በሚያደርጋቸው አሰሳዎችና የተለያዩ ኦፕሬሽኖች እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ቡድኑ የሚገኙ ውጤቶችን በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8d%8c%e1%8b%b4%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%8d%96%e1%88%8a%e1%88%b5-%e1%88%8d%e1%8b%a9-%e1%8a%ae%e1%88%9b%e1%8a%95%e1%8b%b6%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%8a%95%e1%8c%80%e1%88%8d-%e1%88%9d/
51
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያ የምታካሂደው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ሉዓላዊ መብቷ ነው- አምባሳደር ነብያት ጌታቸው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 2, 2020
Unknown
በአልጀርስ የኢፌዴሪ  ኤምባሲ ባለሙሉ ሥልጣን  አምባሳደር ነብያት  ጌታቸው ትላንት ከሬዲዮ አልጄሪያ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ በግዛቷ የምታካሂደው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ሉዓላዊ መብቷ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ በአጭር ጊዜ በድል መጠናቀቁና ቀጣዩ ሥራ ተፈላጊ የሆኑትን የአጥፊውን የጁንታ አባላት በቁጥጥር ሥር አውሎ ለህግ የማቅረብ መሆኑንም ነው የገለጹት።በአጥፊው ቡድን የተከሰተውን ግጭት ቀጠናዊና ዓለም ዓቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው በኤርትራ ላይ ሮኬት በመተኮስ የተደረገው እኩይ እንቅስቃሴም የታለመለትን ዓላማ ሳያሳካ መክሸፉን አምባሳደሩ አብራርተዋል፡፡የአፍሪካ ኀብረትን ጨምሮ በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች በኩል የቀረቡ የውይይት ጥሪዎች ቢኖሩም መንግሥት በውስጥ ጉዳዩ ሕግንና ሥርዓትን የማስከበር ሙሉ አቅም ያለው መሆኑንና በዚህ ወቅት ከወንጀለኞች ጋር መደራደር ሳይሆን ለሕግ የማቅረብ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቱን እንደሚወጣም ገልፀዋል፡፡በክልሉ በቀጣይ የሚከናወኑ የመልሶ ማቋቋምና የሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳዮች ዙሪያ በክልሉ ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን  አምባሳደር ነብያት  መግለጻቸውን ። 
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%89%b3%e1%8a%ab%e1%88%82%e1%8b%b0%e1%8b%8d-%e1%88%95%e1%8c%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%8b%98/
124
0ሀገር አቀፍ ዜና
ባለፉት 14 አመታት የተከበረው ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ህገ መንግስቱን ከማስረጽ አኳያ ውስንነት ነበረበት ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 2, 2020
Unknown
ባለፉት 14 አመታት የተከበረው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል አከባበር  ህገ መንግስቱንና ፌደራል ስርአቱን ከማስረጽ አኳያ ውስንነት ነበረበት ሲሉ የፌደሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡ሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እራሳቸውን እንዲያስተዋውቁና እንዲተዋወቁ እድል ቢፈጥርም በህዝቦች መካከል ትስስር ፈጥሮ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በመፍጠር ረገድ ክፍተት አለበት ብለዋል፡፡የዘንድሮ 15ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል እኩልነትና ህብረብሄራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡በዓሉ ሲከበር ከባለፉት አመታት ሲከበር የነበሩት አውንታዊ ጎን በመያዝና ውስኝነቶቹን በመቅረፍ መሆኑን አፈ ጉባዔው አደም ፋራህ ተናግረዎል፡፡ኢትዮጵያ ካላት  ብዝሀነት አንጻር የፌደራሊዝም ስርአት ተመራጭ መሆኑ  ሁሉንም ያስማማል ይሁን እንጂ ጽንፈኛው የህውሀት ቡድን ይከተለው የነበረው የመከፋፈል ስርአት የፌደራሊዝም ስርአቱ በአግባቡ እንዳይተገበር አድርጓል ብለዋል፡፡15ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በዘንድሮ አመት የህዝቦችን ትስስር በሚያጠናክር መልኩ በተለየ ሁኔታ ይከበራል ተብሏል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-14-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8b%8d-%e1%89%a5%e1%88%84%e1%88%ad%e1%8d%a3-%e1%89%a5%e1%88%84%e1%88%a8/
113
0ሀገር አቀፍ ዜና
ምርጫ 2013 ቁልፍ የሽግግር ምዕራፍ በሚል በጠ/ሚ ፅህፈት ቤት ውይይት እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 2, 2020
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምርጫ 2013 ቁልፍ የሽግግር ምዕራፍ በሚል ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ከሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።ውይይቱ ዐበይት ባለ ድርሻ አካላት ያላቸውን ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም የምርጫ ስርዓትን በሚያስቃኝ ገለጻ እየተደረገ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የገኘነው መረጃ ያመላክታል።ዐበይት ዴሞክራሲያዊ ተቋማት መሠረታዊ ለውጥ ማካሄዳቸውን ተከትሎ የሚከናወነው ታሪካዊ ምርጫ፣ ከ2010 አንስቶ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጎዳና የምታደርገው ጉዞ ዓይነተኛ ማሳያ ይሆናልም ተብሏል።
https://waltainfo.com/am/%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab-2013-%e1%89%81%e1%88%8d%e1%8d%8d-%e1%8b%a8%e1%88%bd%e1%8c%8d%e1%8c%8d%e1%88%ad-%e1%88%9d%e1%8b%95%e1%88%ab%e1%8d%8d-%e1%89%a0%e1%88%9a%e1%88%8d-%e1%89%a0%e1%8c%a0-2/
63
0ሀገር አቀፍ ዜና
የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት በ83 ከተሞች ሊተገበር ነው፡- ኢ/ር አይሻ መሐመድ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 2, 2020
Unknown
 የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት በቀጣይ ተጨማሪ 72 ከተሞችን በማቀፍ በጠቅላላ በ83 ከተሞች እንደሚተገበር የኮንስትራክሽን ሚኒስትርና የፕሮጀክቱ ስትሪንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢ/ር አይሻ መሐመድ አስታወቁ።ኢ/ር አይሻ መሐመድ ባለፉት 5 ዓመታት ከ600 ሺህ በላይ ዜጎችን የዕለት ጉርስ ማሟላት እና ሕይወታቸውን ማስቀጠል መቻሉንም ገልፀዋል።የስትሪንግ ኮሚቴው በ2012 ሪፖርት እና በ2013 ዕቅድ ላይ እየተወያየ ነው።ፕሮጀክቱ በተተገበረባቸው ከተሞች ለከተሞች ፅዱነት እና አረንጓዴነት አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል ኢ/ር አይሻ።የደሴ ከተማ ደግሞ በአርዓያነት በተነሳበት ውይይቱ ፕሮጀክቱ በቀጣይ ተጨማሪ 72 ከተሞችን በማቀፍ በጠቅላላ በ83 ከተሞች ይተገበራል ተብሏል።በፕሮጀክቱ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማካተት እና የስደተኞች የሥራ ዕድል ፈጠራም ለመተግበር በዝግጅት ላይ ነውም ተብሏል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9e%e1%89%bd-%e1%88%8d%e1%88%9b%e1%89%b3%e1%8b%8a-%e1%88%b4%e1%8d%8d%e1%89%b2%e1%8a%94%e1%89%b5-%e1%8d%95%e1%88%ae%e1%8c%80%e1%8a%ad%e1%89%b5-%e1%89%a083-%e1%8a%a8/
90
0ሀገር አቀፍ ዜና
በትግራይ በሚገኙ ባንኮች ሒሳብ የከፈቱ እና ከትግራይ ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት አካባቢ ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ተፈቀደ – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 2, 2020
Unknown
በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በወንጀል ተጠርጥረው ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ ከተደረገው ደንበኞች በስተቀር በትግራይ ክልል በሚገኙ ባንኮች ሒሳብ የከፈቱ እና ከትግራይ ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት አካባቢ ሒሳባቸውን ከዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መፈቀዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወጣው መግለጫ አስታወቀ።በትግራይ ክልል እየተከናወነ ባለው የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የፀጥታው ሁኔታ ለባንኮች አመቺ በሆነባቸው ከተሞች ባንኮች ተከፍተው ሥራ እንዲጀምሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው ጋር እየሠራ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።የፀጥታው ሁኔታ አመቺ ባልሆነባቸው ከተሞች ደግሞ ባንኮች ተዘግተው የሚቆዩ መሆኑን ነው የገለጸው።በትግራይ እየተካሄደ ባለው የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ምክንያት የፀጥታው እና የኔትወርክ ሁኔታ እስኪሻሻል ባንኮች ተዘግተው እንዲቆዩ መወሰኑ ይታወሳል።
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%89%a0%e1%88%9a%e1%8c%88%e1%8a%99-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ae%e1%89%bd-%e1%88%92%e1%88%b3%e1%89%a5-%e1%8b%a8%e1%8a%a8%e1%8d%88%e1%89%b1-%e1%8a%a5/
95
0ሀገር አቀፍ ዜና
ባለፉት 5 ዓመታት በከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ከ600ሺ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል
ሀገር አቀፍ ዜና
December 2, 2020
Unknown
ባለፉት 5 ዓመታት በከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ከ600ሺ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ እንደሆኑ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ ገለጹ።የከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ተግባራት ላይና ሊሰሩ በታቀዱ አጀንዳዎች ላይ ምክክር እያካሔዱ ነው።ውይይቱ ከልማታዊ ሴፍቲኔት የመጀመሪያ ፕሮጀክት ተጠቃሚ በሆኑ 11 ከተሞች ላይ ያተኮረ ነው።በምክክር መድረኩ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፍዬ፤ የፌደራል ከተሞች የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገ/መስቀል ጫላን ጬምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ የከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት በከተሞች የሚታየውን የከፋ ድህነት ለመለወጥ የሚያስችል ነው ብለዋል።በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ከሐምሳ በመቶው በላይ ሴቶች መሆናቸውን ገልጸው፤ ሴቶች በሚያገኙት ተጠቃሚነትም አገር ተረካቢ ትውልድ ማፍራት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።በመቶሺዎች የሚቆጠሩ አቅመ ደካሞች በቀድሚያ ተጠቃሚ መደረጋቸውን ጠቁመው በአምስት አመት የፕሮጀክቱ ቆይታ ከ600ሺ በላይ ዜጎች በከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀዋል።በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ዙር ተጠቃሚ የሆኑት በአሁኑ ወቅት ከገቢያቸው ላይ ቀንሰው ባጠራቀሙት ቁጠባና ከፕሮጀክቱ ሲለቁ ባገኙት ድጋፍ ቋሚ ገቢ በሚያገኙበት ሥራ ላይ መሰማራታቸውንም ነው የገለጹት።በሌላ በኩል ፕሮጀክቱ ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ከተሞችን ጽዱና ውብ በማድረግ በከተማ ልማት ስራዎች ላይ አሻራውን እያኖረ እንደሚገኝ ሚኒስትሯ ተናግረዋል።በቀጣይ አምስት አመታት የሚተገበረው ሁለተኛ ዙር የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ከአንድ ወር በፊት በደሴ ከተማ የተጀመረ ሲሆን ተጨማሪ 72 ከተሞችን በማካተት በ83 ከተሞች እንደሚካሄድ ታውቋል።(ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-5-%e1%8b%93%e1%88%98%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9e%e1%89%bd-%e1%88%8d%e1%88%9b%e1%89%b3%e1%8b%8a-%e1%88%b4%e1%8d%8d%e1%89%b2%e1%8a%94/
208
0ሀገር አቀፍ ዜና
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ከፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
November 28, 2019
Unknown
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡በኪጋሊ ከተካሄደው የአለም አቀፉ የስርአተ ጾታ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው መሪዎቹ የተወያዩት፡፡መሪዎቹ ሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ የሀሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡በሌላ በኩል ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የተባበሩት መንግስታት የመጠለያ ጉዳዮች ድርጅት ሃላፊ የሆኑትን ማይሙና ሞድ አግኝተው አነጋግረዋል፡፡ድርጅቱ በኢትዮጵያ እየሰራ ስላለው ስራ በዝርዝር ተነጋግረዋል፡፡ፕሬዚዳንቷ በተጨማሪም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሶማሊያ ድጋፍ ሰጪ ቢሮ ሃላፊ የሆኑትን ሊዛ ፊሊፒቶን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%9d%e1%8b%b0%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%88%a3%e1%88%85%e1%88%88-%e1%8b%88%e1%88%ad%e1%89%85-%e1%8a%a8%e1%8d%95%e1%88%ac%e1%8b%9d%e1%8b%b0%e1%8a%95%e1%89%b5-%e1%8d%96%e1%88%8d/
79
0ሀገር አቀፍ ዜና