headline
stringlengths
2
1.42k
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
9
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
63
36.2k
link
stringlengths
28
740
word_len
int64
16
6.74k
label
class label
6 classes
የብልጽግና ፓርቲ ምሥረታ ሁሉንም ሕጋዊ መሠረት የያዘና ሕግን የተከተለ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ
ሀገር አቀፍ ዜና
November 28, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለብልጽግና ፓርቲ አባላት ዛሬ መልእክት አስተላለፉ።በዚሁ መልእክታቸው የብልጽግና ፓርቲን የመመሥረት ሂደት በምሁራን ሲጠና ቆይቶ በየደረጃው ሁሉም አመራሮች እንደተወያዩበት አስታውቀዋል።በዚህም መሠረት በትናትናው ዕለት ኦዲፒ እና አዴፓ ባካሔዱት አስቸኳይ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ ያጸደቁት ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ የደሕዴን አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል ብለዋል።የብልጽግና ፓርቲ ምሥረታ ሁሉንም ሕጋዊ መሠረት የያዘ እና ሕግን ተከትሎ የተፈጸመ መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ የገለጹት።በቀጣይም የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራሙን እያሻሻለ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ጎዳና የሚወስደውን እቅድ በመንደፍ ከሕዝቡ ጋር የሚወያይበት እና የሚያዳብረው ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና የመውሰድ ሕልማችን እውን የምናደርግበት ትክክለኛው መንገድ የተጀመረ መሆኑንም አብስረዋል።ከዚህ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ኃይሎች አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ አሐዳዊ ሥርዓትን የሚያመጣ፣ የፌዴራል ሥርዓትን የሚያጠፋ የሚል አሉባልታ ሲናገሩ ይደመጣል ብለዋል።ይሁንና በፕሮግራሙ ላይ በግልጽ እንዳስቀመጥነው የብልጽግና ፓርቲ ኅብረ ብሔራዊት፣ ፌዴራላዊት፣ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የሚያጠናክር እና የሚገነባ እንጅ የማያፈርስ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ አረጋግጠዋል፡፡በተመሳሳይ ሌሎች ፓርቲዎች ብልጽግና ፓርቲን በመክሰስ ሳይሆን አማራጭ ሐሳብ በማምጣት እንዲሞግቱ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ሐሳብ ይዘው እንዲቀርቡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%a5%e1%88%8d%e1%8c%bd%e1%8c%8d%e1%8a%93-%e1%8d%93%e1%88%ad%e1%89%b2-%e1%88%9d%e1%88%a5%e1%88%a8%e1%89%b3-%e1%88%81%e1%88%89%e1%8a%95%e1%88%9d-%e1%88%95%e1%8c%8b%e1%8b%8a-%e1%88%98/
159
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሩዋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ከ21 ሺህ ዶላር በላይ አበረከቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 2, 2020
Unknown
በሩዋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ በቦንድ ግዥና በድጋፍ 21 ሺህ 300 ዶላር አበረክተዋል፡፡በሩዋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሉሊት ዘውዴ በሩዋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡አምባሳደሯ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶቿን ለመጠቀም ያላትን ሕጋዊና ተፈጥሮአዊ መብቶችን በተመለከተ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መሰራት እንዳለበት መጠቆማቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%a9%e1%8b%8b%e1%8a%95%e1%8b%b3-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8a%96%e1%88%a9-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8b%8d%e1%8b%ab%e1%8a%95-%e1%88%88%e1%88%85%e1%8b%b3%e1%88%b4/
52
0ሀገር አቀፍ ዜና
ምርጫ 2013 ቁልፍ የሽግግር ምዕራፍ በሚል በጠ/ሚ ፅህፈት ቤት ውይይት እየተካሄደ ነው
ፖለቲካ
December 2, 2020
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምርጫ 2013 ቁልፍ የሽግግር ምዕራፍ በሚል ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ከሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።ውይይቱ ዐበይት ባለ ድርሻ አካላት ያላቸውን ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም የምርጫ ስርዓትን በሚያስቃኝ ገለጻ እየተደረገ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የገኘነው መረጃ ያመላክታል ።ዐበይት ዴሞክራሲያዊ ተቋማት መሠረታዊ ለውጥ ማካሄዳቸውን ተከትሎ የሚከናወነው ታሪካዊ ምርጫ፣ ከ2010 አንስቶ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጎዳና የምታደርገው ጉዞ ዓይነተኛ ማሳያ ይሆናልም ተብሏል።
https://waltainfo.com/am/%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab-2013-%e1%89%81%e1%88%8d%e1%8d%8d-%e1%8b%a8%e1%88%bd%e1%8c%8d%e1%8c%8d%e1%88%ad-%e1%88%9d%e1%8b%95%e1%88%ab%e1%8d%8d-%e1%89%a0%e1%88%9a%e1%88%8d-%e1%89%a0%e1%8c%a0-%e1%88%9a/
64
5ፖለቲካ
ዶክተር ሂሩት ካሳው የ2019 ‘የአፍሪካ ምርጥ ቱሪዝም መሪ’ ተባሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 2, 2020
Unknown
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የ2019 ‘ የአፍሪካ የቱሪዝም ምርጥ መሪ’ ተብለው ተመረጡ።አሸናፊ ሆነው መመረጣቸውን በጋና የሚገኘው ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዴሽን የተሰኘው ድርጅት አስታውቋል፡፡ሽልማቱ ከቀናት በኋላ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 12/2020 አዲስ አበባ በሚገኘው ስካይላይት ሆቴል የሚደረግ መሆኑን ከሽልማት ኮሚቴው የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል።‘እጅግ ምርጧ የአፍሪካ ቱሪዝም መሪ ተብለው የተመረጡት ዶክተር ሂሩት በበኩላቸው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንዳስነበቡት፤ “በቱሪዝም፣ በሆቴልና መስተንግዶ በአጠቃላይ በዘርፋችን ላይ ለተሰማራችሁ እና ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራር በሙሉ እውቅናው የእናንተው ነውና እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል።እጅ ለእጅ በመያያዝ ከተሰራ ሩቅ መጓዝ እንደሚቻልም አመልክተዋል።  
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%b6%e1%8a%ad%e1%89%b0%e1%88%ad-%e1%88%82%e1%88%a9%e1%89%b5-%e1%8a%ab%e1%88%b3%e1%8b%8d-%e1%8b%a82019-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8d%8d%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%a5-%e1%89%b1/
90
0ሀገር አቀፍ ዜና
እንግሊዝ ሩስያን ጦርነት ከገጠመች የጦር መሣሪያ ትጨርሳለች ሲል አንድ ቡድን አስጠነቀቀ
ዓለም አቀፍ ዜና
November 27, 2019
Unknown
እንግሊዝ በምዕራብ አውሮጳ ከሩስያ ጋር የምትላተም ከሆነ የብሪታኒያ እግረኛ ወታደሮች ከጦር መሣሪያ ውጭ ይሆናሉ ይላል አንድ ቡድን።ሮያል ዩናይትድ ሰርቪስስ የተሰኘው ተቋም ምንም እንኳ የብሪታኒያ ጦር የሰሜን አትላንቲክ ጦር የቃል-ኪዳን ድርጅት [ኔቶ] አባል ቢሆንም አሳሳቢ የጦር መሣሪያና ቀለሃ እጥረት አለበት።የዩናይትድ ኪንግደም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት በበኩሉ፤ ሃገራቸው ከኔቶ ጋር እየሠራች እንዳለችና በቂ የሆነ የጦር መሣሪያ እንዳላት ተናግረዋል።በሚቀጥለው ሳምንት የኔቶን 70ኛ ዓመት ለመዘከር አባላቱ ሎንዶን ከተማ ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸውን ተከትሎ ነው ጥናቱ የደረሰበትን ይፋ ያደረገው።እንግሊዝና ሌሎች የኔቶ አባላት ሩስያ በምዕራብ ሩስያ በኩል አደጋ እንዳትደቅን በማለት ጦረኞቻቸውን በተጠንቀቅ አቁመዋል።በኢስቶኒያ ግዛት ከሚገኙት ወታደሮች መካከል ከሁለት ዓመት በፊት ወደሥፍራው ያቀኑ 800 የእንግሊዝ ወታደሮች አሉ።በሥፍራው የቆመውን ወታደር የጦር መሣሪያ አቅም ከሩስያ ያነፃፀረው ይህ ጥናት ሃገሪቱ የሩስያ ጦር የመቋቋም አቅም የላትም ሲል ደምድሟል።የሩስያ ጦር ምን ያህል ጠንካራ መሆኑን ለመገመት በግሪጎሪ አቆጣጠር 2014 ላይ ሁለት የዩክሬን ባታሊዮኖችን በደቂቃዎች እንዴት እንደደመሰሰ ማሰብ ብቻ በቂ ነው ባይ ጥናቱ።ጥናቱ እንደ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ የሚያየው የጦር መሣሪያ እጥረትን ብቻ ሳይሆን የቀለሃንም ጭምር ነው።ለጥናቱ ምላሽ የሰጠው የዩናይትድ ኪንግደም መከላከያ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት እንግሊዝ ሩስያን ለመመከት ከአጋሮች ጋር እንጂ ብቻዋን አትደክምም ሲል ተደምጧል።ከሶስት ሳምንታት በፊት የረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማኽሮን ኔቶ ‘አእምሮው የበሰበሰ’ ሲሉ ቃል-ኪዳኑን ወርፈዋል።የእንግሊዝ ፖለቲከኞች መከላከያ ሠራዊቱ የበጀት ቀዳዳ አለበት ሲሉ ይወቅሳሉ።የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉዊቴሬዝ ‘ቀዝቃዛው ጦርነት’ ተመልሶ እየመጣ ነው በሃገራት መካከል ያለው ውጥረት ሊረግብ ይገባል ይላሉ።ምንጭ ፦ ቢቢሲ
https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%8a%e1%8b%9d-%e1%88%a9%e1%88%b5%e1%8b%ab%e1%8a%95-%e1%8c%a6%e1%88%ad%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%8a%a8%e1%8c%88%e1%8c%a0%e1%88%98%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%8c%a6%e1%88%ad/
209
4ዓለም አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያን በአፍሪካ ታላላቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እየተከናወኑ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
ፖለቲካ
October 20, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጅቡቲ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ዝግጅት ላይ በድንገት በመገኘት ባሰሙት ንግግር መንግስት በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ታላላቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት አንዷ እንድትሆን እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የ2019 ኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን አስመልክቶ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት የተሰናዳ የደስታ መግለጫ ፕሮግራም ላይ በድንገት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበዓሉ ታዳሚ ለሆኑት ኢትዮጵያውያን ንግግር አድርገዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ‹‹ይሄ የሚገርም ግጥምጥሞሽ ነው… ዳያስፖራው ዝግጅት አለው ሲባል ሰላምታ ለማቅረብ ነው የመጣሁት›› ብለዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹በጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚለዩበት አንድ መለያ በሰላም መኖር፣ የአገሪቱን ህግ ማክበር፣ ስራ መውደድ፣ እርስ በእርስ መግባባት፣ የተቸገረን መርዳት ሲሆን ሁሌ የምትመሰገኑበትን ይሄንን መልካም ስማችሁን እንድታቆዩ አደራ እላችኋለሁ›› ብለዋል፡፡ጅቡቲ ሁለተኛ ቤታችን ነው ያሉት ዶ/ር ዐቢይ መደመር በጅቡቲ እና በኢትዮጵያ በግልጽ መታዩት ጠቅሰዋል::ይሄንን በሁለቱ አገራት መካከል ያለ ጥብቅ ወዳጅነት የምታጠናክሩ ድልድዮች ጀግና ኢትዮጵያውያን ስለሆናችሁ በታማኝነት፣ በጨዋነትና በፍቅር እዚህ ካለው ህዝብ ጋር በመኖር የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር እያንዳንዱ ዜጋ እንደ አምባሳደር እንዲሰራም አደራ ብለዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማቱ በአንድ ሰው ስም መነገር ስላለበት እንጂ ሽልማቱ የሁላችሁም ነው ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና የጅቡቲ፣ የሶማሊያ፣ የሱዳን፣ የኤርትራ ብልጽግና መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡በውስጣችንም በአጎራባች አገራት ሰላም እንዲኖር እንሰራለን ብለዋል፡፡በሚቀጥለው ምርጫ ከተመረጥን እንሰራለን ካልተመረጥን አቅፈን በማስረከብ አርዓያ የሆነ ስራ እንሰራለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ተሸንፎ ስልጣንን በስርዓት ማስረከብ ከዚህ ኖቤል የሚበልጥ እንጂ የሚተናነስ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ስደት እንዲያበቃ ለትውልዶች የምትበጅ ኢትዮጵያን ሰርቶ ማቆየት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡በጅቡቲ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር አብዱልአዚዝ መሐመድ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለዚህ ታላቅ ዓለም-አቀፋዊ ሽልማት በመብቃታቸው በጅቡቲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል::ሽልማቱ መላው ኢትዮጵያውያንን ያኮራ ከመሆኑም ባሻገር አገሪቱን በዓለም-አቀፍ መድረኮች ላይ እየተጫወተች ያለውን ሚና የሚያጎላና እውቅናንም የሚሰጥ እንደሆነም ተናግረዋል::(ምንጭ:- በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ)
https://waltainfo.com/am/31427/
254
5ፖለቲካ
በመደመር ፍልስፍና ላይ የሚያተኩር አዲስ ወግ – አንድ ጉዳይ ውይይት ዛሬ ይካሄዳል
ፖለቲካ
October 21, 2019
Unknown
በመደመር ፍልስፍና ላይ የሚያተኩር አዲስ ወግ – አንድ ጉዳይ ውይይት በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይካሄዳል፡፡ውይይቱ ቅዳሜ ዕለት በመጽሃፍ መልክ ታትሞ በተሰራጨው የመደመር ፍልስፍና ላይ እንደሚያተኩር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡አዲስ ወግ – አንድ ጉዳይ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31428/
53
5ፖለቲካ
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ  አህመድ የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ
ፖለቲካ
October 21, 2019
Unknown
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊነት አስመልክቶ “ሰላም መቶ በመቶ ያሸልማል” በሚል የተዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር በሚሊኒየም አደራሽ ተካሂዷል።ዶክተር አቢይ አህመድ የአለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው እና ለሰላም ላበረከቱት አስተዋጽኦ መነሻነት ነው ሀገር አቀፍ የእውቅና ፕሮግራሙ የተዘጋጀው፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌደሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሸን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት፣ አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች፣ ከፍተኛ የመግስት ስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ተሳታፊ ሆነዋል።በስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኖቤል ሽልማቱ እንደ ሀገር እንድንኮራ ብሎም ለበለጠ እውቅና እንድንዘጋጅ የሚጋብዘን ነው ብለዋል።ለሰላማዊ መፍትሄ ሁልጊዜ ቀዳዳ እንዳለ የተናገሩት ፕሬዚዳንቷ፥ውይይታችን ከግለሰብና ከቡድን ፍላጎት ባለፈ ብቸኛ ሀገራችን ላይ ያተኮረ መሆን አለበት ብለዋልጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በበኩላቸው  የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን፣ እናታቸውን እና ባለቤታቸውን አመስግነዋል።ሁላችንም በውስጣችን ሰላም ሊኖረን ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በውስጥ ሰላም ከሌለ ወደ ውጭ የሚወጣ ሰላም አይኖርም ነው ያሉት፡፡የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በበኩላቸው ሽልማቱ ለአፍሪካዊ የግጭት አፈታት ሂደት እውቅና የሰጠ ነው ብለዋል፡፡ሽልማቱ የሁሉም ኢትዮጵያው ነው ያሉት ደግሞ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ናቸው።ወ/ሮ ሙፈሪያት ኢትዮጵያ ወደ ከፍታ ማማ እንድትደርስ ኢትዮጵያውያን ሰውነትን አስቀድመን እንዋደድ ፤ ይህን ማድረግ ከቻልን ሀገሪቱ ከልጆቿ አልፋ ከዓለም ሁሉ ለሚመጡ የተትረፈረፈ ሀብት አላት ነው ያሉት።በዚሁ መርሃግብር ላይ ስለ ዶክተር አቢይ አህመድ ስብዕና ና እሳቤን የሚያሳይ “አቢይ እንደ ሰው “የሚል ዶክመንተሪም ቀርቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/31429/
213
5ፖለቲካ
ታክስ በመሰወር እና ህገ-ወጥ ደረሰኞችን ሲጠቀሙ የተገኙ 166 ድርጅቶች ይፋ ተደረጉ
ቢዝነስ
October 29, 2019
Unknown
በዛሬው እለት በገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና በህግ ተገዢነት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ በተሰጠው መግለጫ በነፍስ ወከፍ ከ51 ሚሊየን ብር በላይ ግብይት የነበራቸው ነገር ግን ባዶ፣ ኪሳራና ተመላሽ ከሚጠይቁ ደርጅቶች መካከል 16 ድርጅቶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል፡፡ከ166 ድርጅቶች መካከል 136 ያህሉ ከ6 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ማድርጋቸውን በመረጃ ቋት ውስጥ መገኘቱን ተነግሯል፡፡የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጉዳዩን አስመልክተዉ በሰጡት መግለጫ፤ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የንቅናቄና አጠቃላይ የለዉጥ እንቅስቃሴ የመጣዉን አዎንታዊ ዉጤት አጠናክረን በማስቀጠል በህገ ወጥ ድርጊት ላይ ተሳትፈዉ እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካላት ላይ የሚወሰደዉ የህግ ማስከበር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ሚኒስትሯ አክለዉም እነዚህ ህገወጥ ድርጅቶች በዋናነት ሃሰተኛ ደረሰኝን የሚያቀርቡ በመሆኑ ግብር ከፋዩ ማንነታቸዉን አዉቆ ምንም አይነት ደረሰኝ ከነሱ እንዳይቀበልና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም እንዳያቀርብ አሳስበዋል፡፡ድርጅቶቹ ያለደረሰኝ ግብይት ማከናወን፣ ከተጠቃሚ የሚሰበሰበውን ታክስ ለራስ ጥቅም ማዋልና ግብይትን በመደበቅ መንግስት ሊያገኝ የሚገባውን ታክስ አሳጥተዋል ብለዋል፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውድድር ሜዳውን ለማስተካከል የህግ ተገዢነት ስትራቴጂን አጠናክሮ በመፈጸምና ህጋዊ እውቅና ለታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ለታማኝ ግብር ከፋዮች በመስጠት ከማስተማር፤ ህጋዊ እርምጃ እስከ መውሰድ የሚችልበት አቋም ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡ (ምንጭ፡-የገቢዎች ሚኒስቴር)
https://waltainfo.com/am/24019/
171
3ቢዝነስ
ዛምቢያዊው ፓይለት ‘በመብረቅ’እና ውሽንፍር የተመታውን አውሮፕላን በሰላም አሳረፈ
ዓለም አቀፍ ዜና
November 27, 2019
Unknown
ንብረትነቱ ፕሮፍላይት የተሰኘ የግል አየር መንገድ የሆነ ዳሽ 8-300 አውሮፕላን 41 መንገደኞችን አሳፍሮ የቱሪስት ከተማ ከሆነችው ሊቪንግስተን የዛምቢያ መዲና ወደ ሆነችው ሉሳካ በመቃረብ ላይ ሳለ በከባድ ውሽንፍርና መብረቅ መመታቱ ነው የተነገረው።በ19 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረውና በመብረቅ የተመታው አውሮፕላን አፍንጫው ላይ ጉዳት ቢደርስበትም ፓይለቱ በሰላም መሬት እንዲያርፍ ማድረግ በመቻሉ ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ እያወደሱት ነው።የፕሮፍላይት የበበራ ማናጀር የሆኑት ፊል ሊምባ 41 መንገደኞቻቸው በሰላም በመድረሳቸው ደስታቸውን ገልፅዋል።ዳሽ 8-300 የሆነው ይህ አውሮፕላን በሥሪቱ ምክንያት በመብረቁ አፍንጫው ከመጎዳቱ ባሻገር ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበት ማናጀሩ ቢገልፁም አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ ግን አውሮፕላኑ ላይ ጉልህ የሚባል ጉዳት ደርሷል ብሏል።የአየር መንገዱ መግለጫ እንደሚለው እርግጥም አውሮፕላኑ በከባድ ውሽንፍር ተመትቷል። እርግጠኛ ሆኖ በመብረቅም ተመትቷል ለማለት ግን ምርመራ መደረግ አለበት። (ምንጭ ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/%e1%8b%9b%e1%88%9d%e1%89%a2%e1%8b%ab%e1%8b%8a%e1%8b%8d-%e1%8d%93%e1%8b%ad%e1%88%88%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%a5%e1%88%a8%e1%89%85%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8b%8d%e1%88%bd%e1%8a%95%e1%8d%8d/
112
4ዓለም አቀፍ ዜና
“መደመር”መፅሃፍ ተመረቀ
ፖለቲካ
October 19, 2019
Unknown
በጠ/ሚዶ/ር ዐብይ አህመድ የተፃፈው መደመር”መፅሃፍ በዛሬው ዕለት ተመረቀ፡፡መፅሃፉ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በ30 የክልል ከተሞች ተመርቋል፡፡በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት፣ ነዋሪዎችና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የምረቃ ስነ ስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም ከ8 ሺህ በላይ የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡በ300 ብር በሶስት ቋንቋዎች ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚዎች የቀረበው መፅሃፉ 287 ገፆችን የያዘ ሲሆን በ16 ምዕራፎችና በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ መጽሃፉ በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ የታተመ ነው፡፡የሰው ተፈጥሮና ፍላጎት፣ፐለቲካዊ ጉዳዮች፣ የውጭ ግንኙነት እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችም በመፅሃፉ በስፋት ተዳስሰዋል፡፡ከመፅሃፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ትምህርትቤቶችን ለመገንባት እንደሚውል በመፅሃፉ ሽፋን ተመልክቷል፡፡መፅሃፉ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ አንድነትን የሚያበረታታ መሆኑም ተገልጿል፡፡የምረቃ ስነስርዓቱ የየአካባቢውን ባህል ባገናዘበ ሆኔታ እንደሚካሄድም ነው የተገፀው፡፡በተጨማሪም መፅሃፉ በውጭ ሀገራት የሚመረቅ ሲሆን በዋናነትም በአሜሪካ እና ኬንያ በተለይም በዋኝንግተን ዲሲ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ሚኒሶታ እና ናይሮቢ የሚመረቅ ይሆናል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31424/
151
5ፖለቲካ
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ተሻሻለ
ፖለቲካ
October 18, 2019
Unknown
የክልሉ መንግሥት ዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳተፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የክልሉ ምክር ቤት በ5ኛ ዙር 4ተኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ጉባዔ የክሉሉን አስፈጽሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 178/2011ን ማጽደቁ ይታወሳል፡፡ይሁን እንጂ አዋጅ የመለሳቸው በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም በተለይም በስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና አደረጃጀት፣ በአርበቶ አደር ጉደዮች፣ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን ስራዎች፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በመገናኛ ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂና የአካባቢ ጥበቃ፣ ደንና የአየር ነበረት ለውጥ ቁጥጥር ስራዎች ትግባራት ሂደት ላይ የአፈጻጸም ክፍተቶች ታይተዋል፡፡በተሻሻለው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ህገመንግስት አንቀጽ 51 ንዑስ አንቀጽ 3 (ሀ) መሰረት የሚከተለው ታውጇል።1 . የሠላምና ፀጥታ ቢሮ2. የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ3. ጠቅላይ አቃቤ ሕግ4. የእርሻና ተፈጥሮ ኃብት ልማት ቢሮ5. የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ6. የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ7. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ8. የውሃ፣ ማዕድንና ኢንርጂ ልማት ቢሮ9. የትምህርት ቢሮ10. የጤና ቢሮ11. የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ12. የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ13. የኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ14. የገቢዎች ባለሥልጣን15. የባሕል ቱሪዝም ስፖርት ቢሮ16. ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ17. የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ18. የእንስሳትና አሳ ኃብት ልማት ቢሮ19. የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ20. የአርብቶ አደር ጉዳዮችና ልዩ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ21. የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ22. የፕላን ኮሚሽን*የይዘት ለውጥ የሚደረግባቸው ቢሮዎች፡የኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ*የስያሜ ማስተካከያ ተደርጎ የተደራጀየመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ*ተዋህደው በአዲስ መልክ የተደራጁሳይንስና የኢንፎርሚሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ*የስያሜና የይዘት ለውጥ የተደረገለትየአርብቶአደር ጉዳዮችና ልዩ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ*የይዘት ለውጥ የተደረገበትየኢንተርፕራይዞችና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ*የፈረሱ አስፈጻሚ አካላትየአርብቶ አደር ኮሚሽን የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኮሚሽንየሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ኢንስቲትዩትመገናኛና ኢንፎርሤሽን ቴክኖሎጂ ኤጀንሲየፕሬስ ሴክሬተሪያት ጽ/ቤትየገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ኤጀንሲየከተማ ስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ባለሥልጣን ናቸው፡፡ምክር ቤቱ ከላይ በቀረበው የተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 180/2012 በሙሉ ድምጽ መፅደቁን ከደኢህዴን ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31422/
260
5ፖለቲካ
ከግድቡ ግንባታ ጋር ተያይዞ ለሚኒስትሮች ማብራሪያ ተሰጠ
ቢዝነስ
October 18, 2019
Unknown
ከግድቡ ግንባታ ጋር ተያይዞ ለሚኒስትሮች ማብራሪያ ተሰጠከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ የግድቡን አሁናዊ ገፅታ በተመለከተና በግብፅ ወቅታዊ አቋም ዙሪያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ለካቢኔ አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው የታላቁ የኢትዮጳያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በትኩረትና በተገቢው ፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ግድቡ የኢትዮጵያ የሃይል ፍላጎትን ከመሙላት ባሻገር ለዓሳ ሀብት ልማትና ቱሪዝም እድገትም ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡የተርባይን ቅነሳን በተመለከተም ማብራሪያ የሰጡት ሚኒስትሩ፤ የግድቡን የሃይል ማመንጨት አቅም እንደማይቀንሰው የገለጹ ሲሆን፤ የተርባይን ቅነሳው የሃብት ብክነትን የሚያስቀርና ከ100ሚሊዮን ዶላር በላይ መቆጠብ እንደሚያስችል ገልጸዋል።የተርባይን ቅነሳ ተግባር በዋናነት ቴኪኒካዊ ስራ መሆኑን የገለፁጽ ሚኒስትሩ የግድቡን ሃይል የማመንጨት አቅም የማይጎዳ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ሚኒስትሩ በተጨማሪ በግድቡ የውሃ አሞላልን በተመለከተም ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ፤ገለጻ የተደረገላቸው ሚኒስትሮች በተርባይን ቅነሳ ፣ በግድቡ ዙሪያ እየተከናወኑ ባሉ የዲፕሎማሲ ስራዎች እንዲሁም በግድቡ ግንባታ ላይ ግብፅ የያዘችውን አቋም በተመለከተ ላነሷቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/24015/
130
3ቢዝነስ
ህወሃት በተደጋጋሚ የሚሰጣቸው መግለጫዎች ስህተት መሆናቸውን የኢህአዴግ ምክርቤት ገለጸ
ፖለቲካ
October 18, 2019
Unknown
ህወሃት በተደጋጋሚ የሚሰጣቸው መግለጫዎች ስህተት መሆናቸውን የኢህአዴግ ምክርቤት ገለጸህወሃት እንደ ድርጅትም ሆነ በአንዳንድ አመራሮቹ በተደጋጋሚ የሚሰጣቸው መግለጫዎች በሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች ስህተት መሆናቸውን የኢህአዴግ ምክር ቤት አስታወቀ።የኢህአዴግ ምክርቤት ዛሬ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ ህወሃት ከድርጅት አሰራርና ዲስፒሊን የተጣረሰ እና  በይዘቱ ስህተት የሆነ መግለጫዎችን በተደጋጋሚ እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል። ምክርቤቱ በመግለጫው ህወሃት በተለያዩ መግለጫዎቹ ደጋግሞ የሚያነሳው ውህደቱ አሃዳዊ መንግስት ለመመስረት የታቀደ አስመስሎ ማቅረብ መሆኑን ጠቁሞ፤ ፓርቲው ወደ አንድ ወጥ ፓርቲ በሚቀየርበት ወቅት ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብታቸው እንደሚገፈፍና ፌዴራላዊ ስርዓቱ ፈርሶ አሃዳዊ ስርዓት እንደሚመስረት አድርጎ የሚያቀርበው ሃሳብ ለማደናገሪያ ካልሆነ በስተቀር ለመከራከሪያ የሚሆን ተጨባጭ ነገር የለውም ብሏል።ሌላኛው የህወሃት  መግለጫው ችግር የውህደት አጀንዳውን አሁን ያለው የለውጥ አመራር በድንገት ያመጣው በሚያስመስል መልኩ ማቅረቡ መሆኑን ጠቁሟል። የመግለጫው ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል።ኢህአዴግን ከግንባርነት ወደ አንድ ህብረ ብሄራዊ ውህድ ፓርቲ የማሸጋገር ጉዳይ በ1996 ዓ.ም ከተካሄደው 5ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ጀምሮ በተከታታይ በተካሄዱት የድርጅቱ ጉባዔዎችና የተለያዩ ድርጅታዊ መድረኮች ሲነሳ የቆየ ጥያቄ እንደሆነ ይታወቃል። በሁሉም የኢህአዴግ መድረኮች በውህደቱ አስፈላጊነት ላይ ስምምነት እየተያዘበት የሄደ ሲሆን በየጉባዔዎቹ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ውህደቱን በጥናት ላይ ተመስርቶ ለመፈፀም የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ቆይተዋል። ይልቁንም በቅርብ ጊዜያት በተካሄዱ ጉባዔዎች ይነሳ የነበረው ቁልፍ ችግር በአፈፃፀሙ ላይ የታየው ከፍተኛ መጓተት ነበር። በተለይ ባለፈው አመት በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የጥናት ስራው በቶሎ ተጠናቆ የኢሕአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች ውህደት ፈጥረው አንድ ጠንካራ ሀገራዊ ፓርቲ እንዲፈጠር ውሳኔ ተላልፏል። በሂደቱ የአጋር ድርጅቶችም ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል።ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የውህደቱ አቀንቃኝ ሆኖ ውህደቱን ሲመራ የነበረው ህወሃት በአሁኑ ወቅት ውህደቱን በተመለከተ አሉታዊ ገፅታ ያላቸው ተደጋጋሚ መግለጫዎችን በማውጣት ላይ ይገኛል። ምንም እንኳን ጉዳዩ በሂደት ላይ ያለና ያልተቋጨ በመሆኑ በዚህ ወቅት መግለጫ መስጠትም ሆነ በሚወጡ የተሳሳቱ መግለጫዎች ላይ መልስ መስጠት አስፈላጊ አይደለም በሚል እምነት ጉዳዩን በዝምታ ለማለፍ የተሞከረ ቢሆንም የተሳሳቱ መረጃዎች ተደጋግመው ሲወጡ  ችላ ማለት ደግሞ ህዝቡ ውስጥ መደናገርን ሊፈጥር የሚችል መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ለህዝቡ ጠቅለል ያለ መረጃ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።ህወሃት እንደ ድርጅትም ሆነ በአንዳንድ አመራሮቹ በተደጋጋሚ የሚሰጣቸው መግለጫዎች በሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች ስህተት ሆነው እናገኛቸዋለን። የመጀመሪያው ስህተት ከድርጅት አሰራርና ዲስፒሊን ጋር የተያያዘ ነው። በድርጅቱ አሰራርና ህገ ደንብ መሰረት የግንባሩ አባል ድርጅቶች በማንኛውም አጀንዳ ላይ ውይይትና ክርክር ካደረጉ በኋላ የመሰላቸውን አቋም መያዝና በአቋማቸውም ላይ ተመስርተው ክርክራቸውን መቀጠል የተለመደ ነው።በ2011 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ህወሃትን ጨምሮ ሌሎች አጋርና አባል ድርጅቶች ጥናቱ በአፋጣኝ ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዲገባ ያለልዩነት ወስነዋል። በውሳኔው መሰረት ተጠንቶ በቀረበው ሃሳብ ላይ ደግሞ ሁሉም ድርጅቶች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፤ ጥናቱ እንዲዳብርም የበኩላቸውን ተሳትፎ አድርገዋል። በአሁኑ ሰዓት እየተካሄዱ ያሉ ውይይቶችም ከውሳኔ በፊት ጥናቱን የሚያዳብሩ ሃሳቦችን የማሰባሰብ ሲሆኑ በዚህ ደረጃ በተካሄዱ የአመራር ውይይቶች ህወሃትም ሆነ ሌሎች አባልና አጋር ድርጅቶች ተሳትፈዋል፤ አስተያየታቸውንም ሰጥተዋል። የተሰጡት አስተያየቶች ጥናቱን ለማዳበር ወይም ያልታዩ ጉዳዮች በአግባቡ እንዲዳሰሱ ለማድረግ እንጂ የውሳኔ ወይም የአቋም ጉዳይ ሆነው የሚቀርቡ አልነበሩም። በመሆኑም ይህ አጀንዳ ገና በጥናት ውጤቱ ላይ ውሳኔ ያገኘበት ደረጃ ላይ አልደረሰም። የመጨረሻ የውህደት ውሳኔም አሰራሩን ጠብቆ ወደፊት የሚታይ ይሆናል። ጉዳዩ በዚህ ደረጃ ባለበትና የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጥቶ የሁሉም ድርጅቶች አቋም ባልተገለፀበት ሁኔታ ህወሃት አስቀድሞ ለብቻው በተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቱ የድርጅት አሰራርና ዲሲፒሊንን የጣሰ እንዲሁም ወቅቱን ያልጠበቀ በመሆኑ መታረም ያለበት ነው።የመግለጫው ሁለተኛው ስህተት ደግሞ ይዘቱ ነው። ህወሃት በተለያዩ መግለጫዎቹ ደጋግሞ የሚያነሳው ውህደቱ አሃዳዊ መንግስት ለመመስረት የታቀደ አስመስሎ ማቅረብ ነው። ፓርቲው ወደ አንድ ወጥ ፓርቲ በሚቀየርበት ወቅት ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብታቸው እንደሚገፈፍና ፌዴራላዊ ስርዓቱ ፈርሶ አሃዳዊ ስርዓት እንደሚመስረት አድርጎ የሚያቀርበው ሃሳብ ለማደናገሪያ ካልሆነ በስተቀር ለመከራከሪያ የሚሆን ተጨባጭ ነገር የለውም። በመሰረቱ የአንድ ሀገር የመንግስት አወቃቀር የሚወሰነው በሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎና በኢትዮጵያ ህዝብ ውሳኔ እንጂ በአንድ ፓርቲ ፍላጎት ብቻ ሊሆን አይገባውም። ስለዚህ የኢህአዴግ ውህደት ለብቻው የአገሪቱን የፌዴራል ስርዓት የሚያፈርስ አድርጎ ማቅረብ ውሃ የሚቋጥር መከራከሪያ አይደለም።ኢህአዴግ ወደ ውህደት መጥቶ ጠንካራ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ ቢሆን ሀቀኛ ፌዴራሊዝምን እውን በማድረግ እኩልነትና ፍትህ የነገሰባት፣ አንድነቷ የተጠናከረና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ይታገላል እንጂ የብሄር ብሄረሰቦችንንና ህዝቦችን መብት የሚሸራርፍበት ምንም ምክንያት የለውም።ጥናቱን ያስጠኑት ህወሃትን ጨምሮ ሁሉም የኢሕአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች ሲሆኑ የውህደቱ መነሻ ሃሳብም ሆነ የጥናቱ ውጤት ከአሃዳዊ ስርዓት ጋር ፈፅሞ ግንኙነት እንደሌለው ሁሉም ድርጅቶች በግልፅ የሚያውቁት ጉዳይ ነው። ስለሆነም ጉዳዩን ሁሉም የግንባሩ አባልና እህት ድርጅቶች በግልፅ የሚያውቁትና ወደፊት ውህደቱ ቢፈፀም ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች በግልፅ የሚገነዘቡት ሆኖ ሳለ እንዲህ አይነት የተዛባ መረጃ መስጠት መሰረታዊ ስህተት ነው።ሌላኛው የመግለጫው ችግር የውህደት አጀንዳውን አሁን ያለው የለውጥ አመራር በድንገት ያመጣው በሚያስመስል መልኩ ማቅረቡ ነው። ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው የውህደት አጀንዳው መነሳት የጀመረው ረዘም ካሉ አመታት በፊት እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ደግሞ በድርጅቱ ጉባዔዎች፣ ምክር ቤትና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባዎች ቃለ ጉባዔዎች ላይ ተመዝግቦ የሚገኝ እውነታ ነው። ሌላው ቀርቶ በአሁኑ ሰዓት ተጠናቆ ለውይይት የቀረበው ጥናት የተጀመረው አሁን ያለው አመራር ወደ ሃላፊነት ከመምጣቱ በፊት እንደሆነ በግልፅ የሚታወቅ ነው። አሁን ያለው የለውጥ አመራር የሰራው ነገር ቢኖር ለረጅም አመታት በልዩ ልዩ ምክንያት ሲጓተት የቆየውን ጥናት እንዲጠናቀቅ በማድረግ ለውሳኔ የሚቀርብበት ደረጃ ላይ ማድረስ ብቻ ነው። ስለሆነም በድርጅቱ ስም በሚወጡ መግለጫዎችም ሆኑ አንዳንድ አመራሮች በሚሰጧቸው ማብራሪያዎች የውህደቱን ሃሳብ አዲሱ የለውጥ አመራር በስልጣን ላይ ለመቆየት ሲል እንዳመጣው አስመስሎ ለህዝብ ማቅረብ የተሳሳተ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።በአጠቃላይ ኢሕአዴግን ወደ አንድ ህብረ ብሄራዊ ውህድ ፓርቲ የመቀየሩ ሃሳብ ዋነኛ ምክንያቶች አሁን ያለው የግንባሩ አደረጃጀት አባል ድርጅቶች የጋራ አሰራርን በሚጥሱ ጊዜ የድርጅቱ የውስጥ ጥንካሬ አደጋ ላይ የሚወድቅ መሆኑ፣ የግንባሩ የተጠናከረ ሀገራዊ አንድነት በመፍጠር አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመፍጠር ግቡን በተሟላ ሁኔታ ማሳካት አለመቻሉ፣ አጋር ተብለው የሚጠሩ ድርጅቶችን ከውሳኔ ሰጪነት ያገለለና የሚመሯቸውን ክልሎችና ህዝቦች አቃፊ ባለመሆኑ፣ ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ በቀጥታ የድርጅቱ አባል ሆኖ መታገል የሚችልበትን እድል የሚሰጥ ያለመሆኑን እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል አደረጃጀት እንዲኖር ታሳቢ በማድረግ እንጂ ህወሃት በመግለጫዎቹ ባስቀመጣቸው ምክንያቶች እንዳልሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች እንደሚገነዘቡት እንተማመናለን።በተጨማሪም ከዚህ አጀንዳ በተያያዘ በቀጣዮቹ ጊዜያት በየደረጃው የሚገኙ የድርጅቱ መዋቅሮች (መድረኮች) የሚወስኗቸውን ውሳኔዎች የድርጅቱ አሰራር በሚፈቅደው ዲሲፒሊን መሰረት ለመላው የድርጅታችን መዋቅርና ለሀገራችን ህዝቦች መረጃዎችን የምንሰጥና ግልፅ እያደረግን የምንሄድ መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን።
https://waltainfo.com/am/31423/
873
5ፖለቲካ
“መደመር”መፅሃፍ በተለያዩ ከተሞች ተመረቀ
ፖለቲካ
October 19, 2019
Unknown
መፅሃፉ በተመሳሳይ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በ30 የክልል ከተሞች በዛሬው ዕለት ለምረቃ በቅቷል፡፡ምረቃው ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል አዳማ፣ ጅማ፣ ባሌ፣ቦረና፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራ እና ሀረር ከተሞች ይገኙበታል፡፡በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ባለው የመጽሃፍ ምርቃ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።በተመሳሳይ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይም የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ጨምሮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳተፊ ሆነዋል፡፡በተመሳሳይ “መደመር” መፅሃፍ በሀዋሳ ሚሊኒየም አዳራሽ ተመርቋል፡፡ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው መፅሃፉ የተመረቀው፡፡በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የተፃፈው "መደመር" መፅሀፍ በጎንደር ከተማም ተመርቋል፡፡በምረቃ ስርአቱ ላይ የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የኢህአዴግ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ተፈራ ደርበው መፅሐፉ ስለሀገራዊ ለውጡ በቂ ግልፅነትና መግባባት የሚፈጥር እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት፣ ነዋሪዎችና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።በተጨማሪም መፅሃፉ በጅግጅጋ፣ ጋምቤላ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞችም በዛሬው ዕለት ለምረቃ በቅቷል፡፡
https://waltainfo.com/am/31425/
156
5ፖለቲካ
የመደመር መነሻውም፣ መድረሻውም የሰው ልጅ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ፖለቲካ
October 19, 2019
Unknown
የመደመር መነሻውም፣ መድረሻውም የሰው ልጅ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፉት መደመር መጽሐፍ ምረቃ ላይ ተገኝጠው ባደረጉት ንግግር “መደመር ከኛ ከሰዎች ማንነት የሚነሳ ነው፤ መደመር በኢትዮጵያ ለዘመናት የኖረ ሃሳብ ነው፤ መደመር የእኔና የእናንት የሁላችን መጽሃፍ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡መደመር ያለፈውን መልካም ወረት ይዞ በመቀጠል፣ የትናንትናውን ስህተት በማረም ያምናል፤ ነገን ደግሞ የተሻለ ለማድረግ ያልማልም ነው ያሉት፡፡መደመር ልዩነቶች የሉንም ብሎ አይነሳም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ልዩነቶችን እንደ ፀጋ ይቆጥራል ብለዋል፡፡የሰው በመተርጎም እና በመተንተን ፋንታ የራስን አማራጭ ሃሳብ ማመንጨት ሊበረታታ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ዐቢይ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 50 ዓመታት ሲሰራባቸው የቆዩ አስተሳሰቦች ከውጭ የቀዳናቸው ናቸው፣ መደመር ግን ሀገርኛ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡አብዮታዊ ዴሞክራሲ የዛሬ 101 ዓመት ሌኒን የፈጠረው ነው፤ ካፒታሊዝምን ሳናይ ሶሻሊዝምን ለመገንባት ያስችለናል ብሎ፤ እኛ ደግሞ ካፒታሊዝምን ለመገንባት ያስችለናል ብለን ነው የምንታትረውም ብለዋል፡፡መደመርን ለማወቅ ሰው የራሱን ተፈጥሮ መመርመር በቂው ነው ሲሉም በንግግራቸው ገልጸዋል፡፡፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢህአደግ ፓርቲ ውህደትን በሚመለከት ባደረጉት ንግግርም የፓርቲ ውህደት ጉዳይ አላለቀም፤ 1 ዓመት ከ6 ወር ሲጠና የቆየ ቢሆንም እኛ በመደመር ስለምናምን አሁንም ውይይቱን አልቋጨነውም ነው ያሉት፡፡“የኢህአዴግ ፓርቲዎች ውህደት ፌዴራሊዝምን ይጨፈልቃል ለሚባለው ግን እስካሁን በሄድንባቸው መንገዶች እንኳን ትግራይ የኩናማንና የኦሮብን ማንነት አልጨፈለቀም፣ ብአዴን የአገውን፣ የአርጎባውን፣ የቅምንቱንና የኦሮሞውን ማንነት አልጨፈለቀም፣ ደኢህዴንም የ56ቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄሮች ማንነት አልጨፈለቀም፣ ታዲያ በአዲሱ ውህደት እንዴት ሆኖ ነው የአሃዳዊነትና ጨፍላቂ መሆን የሚቻለው? ወሬው አሉባልታ ብቻ ነው” ሲሉም አስረድተዋል፡፡፡፡“ለራሱ 1 መሆን ያቃተው ኢህአዴግስ አሁን ባለበት ሁኔታ እንዴት ነው ኢትዮጵያን አንድ የሚያደርገው? እንዴት ነው አንድ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ማህበረሰብ መመስረት የሚችለው?” በማለትም አክለዋል፡፡መጪው ምርጫ በሃሳብ ብቻ ተወዳድሮ የሚያሸንፍበት በመሆኑ ሁላችንም ለዚያ እንዘጋጅ፤ የበለፀገች ኢትዮጵያም እውን ከመሆን የሚያግዳት የለም ሲሉም ገልጸዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/31426/
246
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፋር እና ከሶማሌ ክልል አመራሮች ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
October 18, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፋር እና ከሶማሌ ክልል አመራሮች ጋር ተወያዩ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፋርና የሶማሌ ክልላዊ ብሔራዊ መንግሥት አመራሮችን አግኝተው በክልሎቹ የጸጥታ ሁኔታን ላይ ተወያይተዋል።በውይይቱ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።በአፋር እና ሶማሌ ክልል ከሰሞኑ የሰላምና ጸጥታ መረጋጋት እንዲፈጠር የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች መካሄዳቸው ይታወሳል።
https://waltainfo.com/am/31420/
63
5ፖለቲካ
ኢህአዴግ ወደ አንድ ፓርቲ ለመዋሃድ የሚያደርገውን ጥረት እንዲያፋጥን ተጠየቀ
ፖለቲካ
October 18, 2019
Unknown
የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከተለያዩ ክልሎች ከተውጣጡ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና አካላት ጋር ለሁለት ቀናት ውይይት አካሂዷል፡፡ውይይቱ “ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ስኬቶች እና ተግዳሮቶች “እንዲሁም “ምርጫና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ በሚሉ ርዕሶችና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ኢህአዴግ ወደ አንድ ፓርቲ ለመዋሃድ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከእስካሁኑ በተሻለ ሀገራዊ ተልዕኮን ለመወጣት እንደሚያሥችለው የውይይቱ ተሳታፊዎች ለዋልታ ቴሌቭዥን ገልፀዋል፡፡የኢህአዴግ ውሳኔ ስትራቴጂካዊ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ አጋር ፓርቲዎችም ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት በጋራ እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡አስተያየት ሰጪዎቹ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከመለያየትና መወቃቀስ ይልቅ የወደፊቱን በመመልከት ሁሉም በጋራ ሊሰራ የሚያስፈልግበት በመሆኑ፤ ፓርቲው ውህደቱን በፍጥነት ተግባራዊ ሊያደርግ ይገባል ነው ያሉት፡፡ውህደቱን አለመቀበል መብት ቢሆንም እኛን ደግፋችሁና የውህደቱን ሃይሎች ተቃውማችሁ ከጎናችን ቁሙ በማለት ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትና ለኤርትራ እና ሌሎች የውጭ ሀገራት ጥሪ እያቀረቡ ያሉ ግን ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31421/
118
5ፖለቲካ
በዓለም ባንክ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው ብልጽግና የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
ቢዝነስ
October 18, 2019
Unknown
በዓለም ባንክ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው እድገትና ብልጽግና የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ጠየቁ፡፡ሚኒስትሩ በዓለም ባንክ የዋሽንግተን ቢሮ ከሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር በአገራችን ውስጥ እየተካሄዱ ባሉ ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።መንግስት አገር በቀል የኢኮኖሚ መርህ ቀርፆ ወደ ስራ ለመግባት መዘጋጀቱን፣ የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ እየተሰራ መሆኑን፣ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚ ግንባታው ጉልህ ሚና እንዲጫወት በመንግስት በኩል ሙሉ ቁርጠኝነት መኖሩን፣ ከጎረቤት አገራት እና አለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር ያለው ትብብርም እያደገ መምጣቱን ሚንስትሩ ገልጸዋል።በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጽያዊያን ለአገራቸው እድገትና ብልጽግና የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበውላቸዋል።ሰራተኞቹም በቻሉት ሁሉ የአገራቸውን የልማት ጉዞ ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።አምባሳደር ፍጹም አረጋ በበኩላቸው፤ በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዳያስፖራውን አስተባብሮ ለአገር ጠቃሚ ሚናውን እንዲወጣ ከምንጊዜውም በላቀ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። (ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
https://waltainfo.com/am/24017/
117
3ቢዝነስ
በችግሮች የተከበበው የኢህአዴግ አደረጃጀት የኦሮሞ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥያቄዎችን ለመመለስ የማይመች ነው- የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ
ፖለቲካ
October 18, 2019
Unknown
የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) በችግሮች የተከበበው የኢህአዴግ አደረጃጀት የኦሮሞ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥያቄዎችን ለመመለስ የማይመች መሆኑን ገልጿል፡፡ፓርቲው በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ያገኙት የኖቤል የሰላም ሽልማት ማግኘትን ተከትሎ የአገሪቱ ህዝቦች ደስታና ድጋፍ በልዩ አድናቆት ይመለከታል፡፡ትናንት እንደ ፓርቲ አሸናፊ ሆነን እዚህ ደረጃ የደረስነው የኦሮሞ ህዝብ ይዘንና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆነን ነው ያለው የፓርቲው መግለጫ፣ አሁንም ከኦሮሞ ህዝብ እና ከኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመሆን አሸናፊ ሆነን እንደምንሻገር ጥርጣሬ የለንም ብሏል ፓርቲው፡፡ፓርቲው በተለያዩ የአመራር እርከኖች ላይ ያሉ አመራሮች በአመለካከትና በተግባር በአንድነት እንዲሰሩ ለማድረግ እንደምሰራ ገልጿል፡፡እስከ አሁን ምላሽ ያገኙ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን መነሻ በማድረግ እስከ አሁን ምላሽ ላለገኙ የህዝብ ጥያቄ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅጣጫ እንደተቀመጠ ፓርቲው ገልጿል፡፡በርካታ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ቋንቋዎች፣ ባህሎች ባሉበት አገር ውስጥ የፌዴራሊዚም ስርዓት አማራጭ የሌለው ስርዓት ስለሆነ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ብዝሃነትን ማዕከል ያደረገ እውነተኛ ፌዴራሊዝም እንዲገነባና የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩልነትና ነፃነት እንዲከበር የማያወላዳ አቋም እንዳለው ፓርቲው ገልጿል፡፡በተለያዩ ችግሮች የተከበበው የኢህአዴድ አደረጃጀት የኦሮሞ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥያቄ ለለመለስ የማይመች መሆኑ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ውይይት ካደረገበት በኋላ ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡የኢህአዴግ አደረጃጀትን በመዘመን በዘመናዊ አሰራር የሚመራ ፓርቲ ለመመስረት የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሀሳብን በመደመር ሀሳብ ለመተካት ውይይት ሲደረግበት መቆየቱን ያስታወሰው ፓርቲው፣ የመደመር ሀሳብ ከዚህ ቀደም የነበሩት ስኬቶችን ይበልጥ ለማጠናከርና ያሚታዩ ችግሮችን መፍታት የአዲስ ትውልድ መብትና ጥቅም ያስከብራል ብሎ ፓርቲው እንደሚያምን ተገልጿል፡፡ህዝቡ ፓርቲው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ህዝቡ ያገኘውን መብቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ በመሆናቸው ማህበረሰቡ ለተፈፃሚነቱ ትብብር እንዲያደርግ ፓርቲው ጥሪ ማቅረቡን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/31418/
222
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሊቢያ ከፍተኛ ምክር ቤት ልዑካንን በፅህፈት ቤታቸው አነጋገሩ
ፖለቲካ
October 18, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሊቢያ ከፍተኛ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ካሊድ አል-ሚሽሪ የተመራውን ልዑካን ቡድን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።የሊቢያ ከፍተኛ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ካሊድ አል-ሚሽሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሰላም ሽልማትን በማግኘታቸው ደስታቸውን ከመግለጻቸውም ባሻገር በአመራራቸው ያስገኟቸውን ለውጦች አስመልክቶ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።አክለውም በሊቢያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለሚደረገው ቀጣይ ጥረት እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ሊቢያ ያለችበትን አሳሳቢ ሁኔታ አስመልክቶ ሀሳባቸውን ገልጸው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ እንዲሁም ክልላዊ ተቋማት አማካኝነት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።ሊቢያውያን በሀገራቸው ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ እንዲበረቱና በአንድነት ጥረት እንዲያደርጉም ማሳሰባቸውን ከጠቅላ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው ዘገባ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31419/
89
5ፖለቲካ
የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ሶስት ወራት ከእቅዱ በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ
ቢዝነስ
October 18, 2019
Unknown
የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ሶስት ወራት 56 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ  57 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን አስታወቀ፡፡ሚኒስቴሩ የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የገቢ አፈፃፀምና ህገወጥ ድርጅቶች ላይ የተሰራውን ኦፕሬሽን ግኝትን አስመልከቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡በሩብ ዓመቱ ገቢ ከታቀደው በላይ መሰብሰብ መቻሉን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ ገቢው ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ12 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ብልጫ ማሳየቱን ጠቁሟል፡፡በዚሁም ከሀገር ውስጥ ገቢ 31 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 24 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር እና ከሎቴሪ ሽያጭ 46 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ እንደተቻል የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመግለጫው አስታውቀዋል፡፡በተያዘው በጀት ዓመት የግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ ለመክፈል ያሳዩት ተነሳሽነት እንደትልቅ ለውጥ የታየ ነው ብለዋል፡፡166 ድርጅቶች በህገ ወጥ ድርጊት ተሰማርተው መያዛቸውን የተናገሩት ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች፤ ከነዚህ 16ቱ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡በስራቸው ላይ ተግዳሮት የሆነውን የታክስ ስወራና ማጭበርበር የተሰማሩ ኃላፊነት የማይሰማቸው እንዳሉ ሁሉ በኃላፊነት በተገቢው መልኩ ግዴታቸውን የሚወጡትን የማበረታት ስራ እየተሰራ መሆኑንና ከነዚህም ውስጥ 163 የግብር ከፋዮች ተሸላሚ መሆን ችለዋል ብለዋል፡፡የግብር ከፋዮችን ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ከ19 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮችን ማስተማር እንደተቻለም ሚኒስትሯ ገልጸው፤በህገወጥ ስራ የተሰማሩ አካላት ለህግ የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳስበዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/24018/
178
3ቢዝነስ
ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ከሩሲያ አቻቸው ቪላድሚር ፑቲን ጋር ለመወያየት ቀጠሮ መያዛቸው ተገለጸ
ፖለቲካ
October 17, 2019
Unknown
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲብ ጣይብ ኤርዶን ወደ ሩሲያ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን ጋር ለመወያየት ቀጠሮ መያዛቸው ተገለጸ፡፡መሪዎቹ ቱርክ በሶሪያ ላይ የሰነዘረችውን ወታደራዊ ዘመቻ በሚመለከት እንደሚመክሩ የተገለጸ ሲሆን፣ የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ለሶስትዮሽ ውይይት የመሪዎቹን ስብሰባ ሊቀላቀሉ ይችላሉ የሚለው ቅድመ ግምት ውድቅ መሆኑም ታውቋል፡፡ቱርክ በሰሜን ሶሪያ የሰነዘረችውን ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ የሶሪያ መንግስት ወታደሮቹን ከኩርድ አማጺያን ጋር እንዲቀላቀሉ ወደ ድንበር ከተማ ማሰማራቱ ይታወሳል፡፡ቱርክ በሶሪያ ላይ የሰነዘረችው ጥቃት በተለያዩ ሀገራት ውግዘት እየደረሰበት ቢገኝም እሷ ግን በዘመቻዋ ቀጥላለች፡፡ ጥቃቱም ስምንተኛ ቀኑን ቢያስቆጥርም አንካራ ወደ ኋላ የምትመለሰው አሸባሪዎች ከተሰገሰጉባት የሶሪያ ኩርድ ግዛት ማጽዳት ከቻልን ብቻ ነው ሲሉም ኤርዶጋን ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡የጥቃቱ አላማ በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያዎች ላይ በኩርድ አማጺያን የሚመራውን ሀይል ከድንበር አቅራቢያው ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ በማድረግ ለሶሪያውያን ከስደት ተመላሾች ደህንነቱ የተጠበቀ ስፍራን ማመቻቸት እንደሆነ ከቱርክ በኩል እየተገለጸ ይገኛል፡፡ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶጋን ወደ ሩሲያ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመወያየት ቀጠሮ መያዛቸውን ትናንት የወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ሲሆን፣ ሩሲያ የሶሪያ ዋነኛ ወታደራዊ ድጋፍ ሰጭ ሀገር እንደሆነችም ይታወቃል፡፡መሪዎቹ ቱርክ በሶሪያ ላይ የሰነዘረችውን ወታደራዊ ዘመቻ በሚመለከት እንደሚመክሩ የቱርክ ፕሬዘዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የመሪዎቹ ውይይት በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ የፊታችን ጥቅምት 11 እንደሚካሄድ ከቱርክ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የወጣው መረጃ ይጠቁማል፡፡የመሪዎቹ የውይይቱ የትኩረት አቅጣጫን በተመለከተ መረጃው ዝርዝር ጉዳዮችን ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ የሁለቱን መሪዎች ስብሰባ የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ለሶስትዮሽ ውይይት ሊቀላቀሉ ይችላሉ የሚለውን ቅድመ ግምት ውድቅ አድርገውታል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/34016/
211
5ፖለቲካ
የሕግ መረጃን ማግኘት አዳጋች መሆኑን ጥናት አመለከተ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 17, 2019
Unknown
የሕግ ጽሑፎችን ወይም የሕግን መረጃን ማግኘት አዳጋች መሆኑን የፍትህና የሕግ ምርምር ስልጠና ኢንስቲትዩት ያካሄደው ጥናት አመለከተ፡፡ ኢንስቲትዩቱ በ2011 በጀት ዓመት የሕግ ጽሑፎችን ወይም የሕግን መረጃ ማግኘት በተመለከተ ባደረገው ጥናት ችግሩን መሻገር እንዳልተቻለ ዛሬ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያከናወነው ባለው የምክክር መድረክ ላይ ተገልጿል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ የህግ ተመራማሪ ወ/ሮ የትናየት ደሳለኝ ጥናቱን ሲያቀርቡ እንደገለፁት ጥናቱ በፌዴራል ደረጃ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች፣ የፖሊስ ኮሚሽን ፍርድ ቤቶችና ጠቅላይ አቃቤ ሕግ እንደተከናወነና በቀጣይም ችግሮቹን ለመቅረፍና የመንግስት ፖሊሲን ለመደገፍ ያስችላል፡፡ ሕግና ሕግ ነክ መረጃዎች ያላቸውን ልዩ ባሕሪይ ታሳቢ ያደረገ የህግ ማዕቀፍ አለመኖር፣ አማራጭ የመረጃ መስጫ መንገዶች በተገቢው ሁኔታ ተደራሽ አለመሆን፣ መረጃ ማግኘት በግለሰቦች መልካም ፈቃድኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑ፣ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎች አለመኖራቸው እና የግንዛቤ እጥረት ለችግሩ መባባስ ጥናቱ የለያቸው ምክንያቶች ናቸው፡፡ በፍትህ ተቋማት የሚገኙ ቤተመጽሐፍት ከሌሎች የሕዝብ ቤተመጽሐፍት ጋር በመስራት ሕግና የሕግ መጽሐፍተን ተደራሽ ማድረግ፣ መረጃ መስጫ ሱቆችን መክፈት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ሕብረተሰቡ በስፋት እንዲሳተፉ ማድረግ የሚሉት ደግሞ ጥናቱ በመፍትሔነት ያስቀመጣቸው ሐሳቦች እንደሆኑ ወ/ሮ የትናየት አመልክተዋል፡፡ በምክክር መድረኩ “የእርሻ መሬት ይዞታና የማስተላለፍ መብት” በሚለው የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ዜጎች ባላቸው የመሬት ይዞታ ዋስትና ተገቢውን የሕግ ከለላ አለማግኘታቸው ተገልጿል፡፡ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ እና ደቡብ ሕዝቦች፣ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ክልሎች በተደረገው ጥናት ወደ ፍርድ ቤት ከሚመጡ የፍትሃብሄር ጉዳች ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት የእርሻ መሬት ይዞታን የሚመለከቱ ስመሆኑ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ በሕገመንስግሰቱ አንቀፅ 40 ንዑስ ቁጥር 4 ላይ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘት መብት ብቻ ሳይሆን ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው ሲል ቢደነገግም ይህ መብታቸው ግን እምብዛም ሲከበር አይታይም ተብሏል፡፡ የአርሶ አደሩ የእርሻ መሬት በህግ ከተቀመጠው ውጪ በባህልና በተለምዶ ማስተላለፍ፣ ከህግ ውጪ ያሉ አሰራሮችና ክፍተቶች መበራከት፣ የተደራጀ የእርሻ መሬት አያያዝ ሥርዓት አለመዘርጋት፣ ህጎች መብትን የሚሰጡት ለክልሎች ነዋሪዎች በመሆኑ የዜጎችን ተዘዋውሮ የመስራት መብት የገደቡ መሆናቸው በጥናቱ የተመለከቱ ችግሮች ናቸው፡፡ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ባለሙያዎችን በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ፣ የገጠር መሬት ጉዳይን ሊዳኝ የሚችል ራሱን የቻለ ተቋም መፍጠር፣ ለልማት ለሚነሱ አርሶአደሮችን የሚሰጣቸውን የገንዘብ ካሳ ተለዋጭ ቦታ በመስጠት ቢሆን እና ከገጠር መሬት ጋር ያለ መረጃ የተደራጀና በቴክኖሎጂ የታገዘ ቢሆን የሚሉት ደግሞ ጥናቱ በመፍትሄ ሐሳብነት ያመላከታቸው መሆኑን በምክከር መድረኩ ላይ ተነስቷል፡፡
https://waltainfo.com/am/32807/
316
0ሀገር አቀፍ ዜና
ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሀገር አቀፍ የእውቅና መድረክ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል
ሀገር አቀፍ ዜና
October 17, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የዓለም የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን በማስመልከት የሰላም ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የእውቅና መድረክ የፊታችን እሁድ በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል፡፡በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በሚሊኒየም አዳራሽ የሚከናወነው ይህ የደስታ መግለጫ ዝግጅት እሁድ ጥቅምት 9፣2012 ዓ.ም ከቀኑ 11 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት እንደሚዘልቅ የሰላም ሚኒስቴር ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ባሳለፍነው ሳምንት ጠ/ሚር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የ2012 ኖቤል ሰላም ሎሬት ተሸላሚ መሆናቸው ይታወሳል፡፡
https://waltainfo.com/am/32806/
80
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ብዛት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ44 ሚሊዮን በላይ መድረሱ ተገለጸ
ቢዝነስ
October 17, 2019
Unknown
የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ብዛት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 44.45 ሚሊዮን መድረሱን እና በዚህም የዕቅዱን 99.5 በመቶ መፈጸሙን ቴሌኮሙ አስታውቋል።የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የመስሪያ ቤቱን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ስራ አፈፃጸም በሚመለከት ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።በሩብ ዓመቱ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ10.4 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተጠቅሷል።ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎች ሲያደርግ መቆየቱ ተነግሯል።እንደ ኢቢሲ ዘገባ ተቋሙ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 10.1 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።በዚህም ድርጅቱ የእቅዱን 98 በመቶ ማሳካት መቻሉን የገለጹት ወይዘሪት ፍሬህይወት፣ ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 56 በመቶው ከድምጽ አገልግሎት 29 በመቶው ደግሞ ከሞባይል ዳታ የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል።እንዲሁም ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 41.1 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው ከዓለም አቀፍ አገልግሎቶች የተገኘ መሆኑን ነው ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናገሩት።የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ተመሳሳይ ሩብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ21 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።
https://waltainfo.com/am/24016/
137
3ቢዝነስ
ቱርክ ሶሪያ ላይ የከፈተችውን ጥቃት ለማቋረጥ ተስማማች
ፖለቲካ
October 18, 2019
Unknown
ቱርክ በሰሜን ሶሪያ የከፈተችውን ጥቃት በኩርዶች የሚመራው ጦር እስኪወጣ ድረስ ለማቋረጥ ተስማማች።ስምምነቱ የተደረሰው የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ እና የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በአንካራ ተገናኝተው ከመከሩ በኋላ ነው ተብሏል።ሁሉም ውጊያዎች ለቀጣይ አምስት ቀናት የሚቋረጡ ሲሆን፣ አሜሪካ የኩርድ ወታደሮች ስፍራውን ለቅቀው እንዲወጡ እንደምታደርግ ማይክ ፔንስ ተናግረዋል።ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ይህንን ይስማሙ እንጂ በዚህ ጉዳይ ያላቸው የኩርዶች አቋም አልታወቀም።ኮማንደር ማዝሎኡም ኮባኒ እንደሚሉት ከሆነ በኩርዶች የሚመራው ጦር ጠንካራ ውጊያ በሚደረግባቸው የድንበር ከተሞች ሆኖ ስምምነቱን ሲመለከት ነበር።እነዚህ ውጊያ የሚደረግባቸው ከተሞች ራስ አል አዪን እና ጣል አባይድ የሚሰኙ ሲሆን፣ "የሌሎቹን አካባቢዎች ዕጣ ፈንታ አልተነጋገርንም" ብለዋል።መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው በሶሪያ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚከታተል አንድ ቡድን እንዳለው፤ ምንም እንኳ ተኩስ ለማቆም ስምምነት ላይ ቢደረስም በራስ አል አዪ አሁንም ተኩስ እንደቀጠለ ነው።ባለፉት ስምንት ቀናት በአካባቢው በነበረው ውጊያ 72 ንፁሃን ዜጎች የሞቱ ሲሆን 300 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል።ቱርክ ባለፈው ሳምንት በድንበር አካባቢ ጥቃት የከፈተችው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሶሪያና በቱርክ ድንበር አካባቢ ሰፍሮ የነበረውን ሠራዊታቸውን እንዲወጣ ካደረጉ በኋላ ነው።ቱርክ ለጥቃቱ ምክንያት አድርጋ የምታቀርበው የኩርድ ሚሊሻ ቡድኖችን ከስፍራው ማስወጣትን ሲሆን እነዚህ ቡድኖች በቱርክ በኩል እንደ አሸባሪ ነው የሚታዩት።ቱርክ በዚህ የድንበር አካባቢ 2 ሚሊዮን ስደተኞችን ለማስፈር ያቀደች ቢሆንም፤ ይህንን እርምጃ የሚተቹ ወገኖች ግን በአካበቢው የኩርዶችን ዘር ለማጥፋት የሚወሰድ ርምጃ ሲሉ ኮንነውታል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ አጋር የነበሩትን የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ጦርን በመተዋቸው እየተወቀሱ ይገኛሉ።ይህ ቡድን አሜሪካ ከ አይ ኤስ ጋር ባደረገችው ጦርነት ከጎኗ ተሰልፎ ተዋግቷል።ረቡዕ እለት ትራምፕ ኩርዶችን "መልዓክ አይደሉም" በማለት የድንበር አካባቢውን ደግሞ "የእኛ ድንበር አይደለም፤ የሕይወት መስዋዕትነት መክፈል የለብንም" ሲሉ ተደምጠዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቱርክ ተኩስ ለማቆም መስማማቷን ምክትል ፕሬዝዳንታቸው ከቱርክ ይፋ ከማድረጋቸው ቀደም ብሎ ትዊተራቸው ላይ "የሚሊዮኖች ሕይወት ይድናል" በማለት ጽፈዋል።ማይክ ፔንስም ስምምነቱን በገለፁበት ወቅት የዶናልድ ትራምፕን "ጠንካራ አመራር" እውቅና ሰጥተዋል።ማይክ ፔንስ ከኤርዶጋን ጋር ከመገናኘታቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ትራምፕ ለቱርክ አቻቸው "ድርቅ አትበል፤ ሞኝ አትሁን" የሚል ደብዳቤ ጽፈውላቸው ነበር።ስምምነቱ ከተደረሰ በኋላም "እንዴት ያለ መሪ ነው፤ ትክክለኛውን ነገር ያደረገ" ሲሉ አሞካሽተዋቸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/34017/
293
5ፖለቲካ
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊስ ዙሪያ ያተኮረ መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
October 17, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊስ ዙሪያ ያተኮረ  መድረክ በአዲስ አበባ  እየተካሄደ ነው፡፡በአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ከ250 በላይ የውጪ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ባለሙያዎች ፣ የልዩ ልዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም የኢጋድ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው፡፡በሰላም  ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን ኢትዮጵያ በፈጣን ሀገራዊ ለውጥ ላይ እንደምትገኝ ገልፀው ፤ ለዘላቂ ሰላምና ቀጣናዊ ትብብር እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታው አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ በበኩላቸው መሰል መድረኮች ጠቃሚ ሀሳብ የሚንፀባረቅባቸው በመሆኑ ለፖሊሲ ማሻሻያ ግብዓት ሆነው ያገለግላሉ ብለዋል፡፡የአፍሪካ ቀንድ በለውጥ ተስፋ መንገድ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት ሚኒስትር ድኤታው፤  ቀጣናዊ ትስስርን በማሳደግ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ/ እንዲጠናከር የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የዓለም የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ላደረገችው ጥረት እውቅና የሰጠእንደሆነ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡መድረኩ ለሁለት ቀናት ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32808/
132
0ሀገር አቀፍ ዜና
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የተገነባው ትምህርት ቤት ተመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 17, 2019
Unknown
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት አማካኝነት የተገነባው የሎዛ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትበ ዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡በ20 ሚሊዮን ብር ወጭ የተገነባው ትምህርት ቤቱን በይፋ የከፈቱት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሲሆኑ የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የፌደራል የትምህርት ዘርፍ አመራሮች እና ሌሎች እንግዶችም በምረቃው ላይ ተገኝተዋል፡፡ትምህርት ቤቱ 28 የመማሪያ እና አራት የቤተ ሙከራ ክፍሎች፣ ቤተ መፃሕፍት እና የአስተዳደር ሕንጻ የተሟላለት ነው።ትምህርት ቤቱ በአካባቢው የሚገኙ የአምስት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ወደ ሁለተኛ ደረጃ ሲሸጋገሩ በአቅራቢያቸው ለመማር ያስችላቸዋል ተብሏል።በክልሉ የትምህርት ተደራሽነትን ለማሳዳግ እንደሚረዳም ነው የተገለፀው፡፡በቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት አማካኝነት በሀገሪቱ ከሚገነቡ 20 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አራቱ በአማራ ክልል ውስጥ በጎንደር፣ ደባርቅ፣ ዋግ ኽምራ እና ደቡብ ወሎ ዞን እንደሚገነቡ ታውቋል።ምንጭ፦ኢቢሲ
https://waltainfo.com/am/32805/
108
0ሀገር አቀፍ ዜና
አማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ከፍተኛ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እንደሚካሄድባቸው ጥናት አመለከተ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 17, 2019
Unknown
አማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ከፍተኛ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እንደሚካሄድባቸው ጥናት አመለከተ፡፡በኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት ለመውጣት በሚያደርጉት ጥረት ለችግር እየተዳረጉ እንደሆነ ጥናት አመላክቷል፡፡ችግሩን ለመከላልም በህገ ወጥ መንገድ ድንበርን የማሻገር ወንጀልን የተመለከተውን አዋጅ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቃል፡፡የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የችግሩን አሳሳቢነት የጋራ ለማድረግና መፍትሄዎችን ለማመላከት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የሰዎች ንግድን እና በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን በተመለከተ አዲስ አበባ ላይ ምክክር አድርጓል፡፡ ዓለም አቀፍ የሰዎች ዝውውር ሁኔታን የዳሰሰ የመነሻ ጽሁፍ ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡በተለይ በኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ለመውጣት በሚያደርጉት ጥረት ለችግር እየተዳረጉ እንደሆነ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ፀረ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ግብረ ሀይል ጽህፈት ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ ፈትያ ሰይድ መንግስት የወንጀሉን አሳሳቢነት በመረዳት ተመላሽ ስደተኞችን ለማገዝ እና ወንጀሉን ለመከላከል እየሰራ ነው ብለዋል፡፡በህገ ወጥ መንገድ ድንበርን የማሻገር ወንጀልን የተመለከተውን አዋጅ ለማሻሻል እየተሰራ እደሆነ የተናገሩት ተጠባባቂ ኃላፊዋ፤ ማሻሻያውም ዜጎች የሚያነሷቸውን ችግሮች እንዲፈታ ታሳቢ ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከ35 ሺህ በላይ ህጻናት፣ ወጣቶች እና ሴቶች በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ መያዘቸውን በቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ ተመላክቷል፡፡በህገ ወጥ ዝውውሩ አማራ ክልል 32 በመቶ፣ ኦሮሚያ ክልል 31 በመቶ፣ ትግራይ ክልል ደግሞ 29 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ ድርሻ እንደሚይዙም ነው የተገለጸው፡፡ ደቡብ አፍሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ ደግሞ ዜጎቹ በብዛት የሚሄዱባቸው ሀገሮች ናቸው፡፡ (ምንጭ፡-አብመድ)
https://waltainfo.com/am/32803/
208
0ሀገር አቀፍ ዜና
ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ከአለም የምግብ ልማት ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተርና ከአለምአቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
ቢዝነስ
October 17, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአለም የምግብ ልማት ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌይ ጋር ተወያይተዋል።ውይይቱ በሰብዓዊ ድጋፍ እና በዘላቂ ልማት ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን ተቋሙ ከመንግሥት ጋር በቀጣይ የበለጠ ተቀናጅቶ በመስራት ረገድ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።ከዚህ ባለፈም ተቋሙ በቀጣይ ከመንግስት ጋር የበለጠ ተቀናጅቶ መስራት በሚችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በጣልያን ቆይታቸው ከኢፋድ [IFAD] ፕሬዚዳንት ጊልበርት ሁንግቦ ጋር ተገናኝተው መክረዋል፡፡በሃገሪቱ የተጀመሩ የመስኖ ሃብት ልማት እና የእንስሳት ሃብት ምርታማነትን የማሳደግ እንቅስቃሴ ዙሪያ ተወያይተዋል።ተቋሙ በሃገሪቱ በግብርና ልማት ዙሪያ የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች እንደሚያጠናክር እና በቀጣይ የድጋፍ ፕሮግራሞች በጥናት አስደግፎ እንደሚቀጥል ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠዋል።
https://waltainfo.com/am/24013/
103
3ቢዝነስ
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ይጀምራል
ፖለቲካ
October 17, 2019
Unknown
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ማካሄድ ይጀመራል።ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድም ነው የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኝነት እና የኮንፈረንስ አገልግሎት ፅህፈት ቤት ያስታወቀው፡፡የፅህፈት ቤቱ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ታረቀኝ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት ምክር ቤቱ በሦስት የቀን ውሎው የ2012 ዓ.ም በጀት፣ የስራ አስፈፃሚ፣ የክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የዋና ኦዲተር የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ረቂቅ እድቅ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ የፍርድ ቤቶች አደረጃጀት፣ የዳኝነት የአገልግሎት ክፍያ፣ የዳኞች ጉባኤ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ተሻሽሎው የወጡ ረቂቅ አዋጆች እና ሌሎች አዋጆችን ጨምሮ 5 የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ ከተወያየ በኋላ እንደሚያፀድቅ አቶ ሙሉጌታ ታረቀኝ አክለው ገልፀዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/31417/
104
5ፖለቲካ
በመዲናዋ ከሚገኙ ወረዳዎች ግማሽ ያህሉ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ ናቸው
ሀገር አቀፍ ዜና
October 17, 2019
Unknown
በአዲስ አበባ ከሚገኙ ወረዳዎች ግማሽ ያህሉ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ መሆናቸውን የከተማው ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየው ለኢቲቪ እንደተናገሩት፤ በከተማዋ ካሉ 121 ወረዳዎች 62ቱ የዲጂታል መታወቂያ እየሰጡ ናቸው፡፡አገልግሎቱ የሚሰጠው በቴሌኮም ኔትወርክ እገዛ እንደመሆኑ የዚህ መሰረተ ልማት ጥራትና ተደራሽነት ጉድለት የዲጂታል መታወቂያው በሁሉም የከተማዋ አስተዳደር እንዳይሰጥ እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል አቶ ዮናስ፡፡ከዚህ ባሻገር የሰው ሀይል እጥረት፣ ስራውን ማስፈጸሚያ በቂ ቢሮ ያለመኖር እና ለሰራተኞች የሚከፈል ደሞዝ አናሳ መሆኑ አገልግሎቱን በመዲናዋ ሙሉ ለሙሉ ለመተግበር ችግር መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡በቀጣይ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ጥረት የሚደረግ ሲሆን የኢንተርኔት ተደራሽነትና ጥራት መጓደል ለማከስተካከልም የሚመለከተው አካል ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ ሀላፊው ጠይቀዋል፡፡አገልግሎቱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 62 ወረዳዎች መስጠት ከተጀመረበት ሐምሌ 15 ጀምሮ 44 ሺህ ዲጂታል መታወቂያዎች ለህብረተሰቡ ተከፋፍሏል፡፡አገልግሎቱ በዋናነት በቦሌ፣ ጉለሌ፣ ኮልፌ፣ ንፋስ ስልክ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች በተሸላ ደረጃ እየተሰጠ መሆኑ ተመልክቷል፡፡የዲጂታል መታወቂያ ከአንድ በላይ ግላዊ ማንነትን ለመቀነስ ብሎም ተመሳስሎ የሚሰሩ ህገወጥ መታወቂያዎችን ለመከላከል እንዲሁም አጠቃላይ የአገልግሎት ዘርፉን ለማዘመን ታስቦ ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል፡፡ከተማ አስተዳደሩ የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት በሰኔ ወር 2011 ዓ.ም በሁሉም ክፍለ ከተሞች መስጠት እንደሚጀመር መግለጹን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/32804/
168
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአለም ባንክና የአለም የፋይናንስ ተቋም አመታዊ ጉባኤ በዋሽንግተን እየተካሄደ ነው
ቢዝነስ
October 17, 2019
Unknown
የአለም ባንክና የአለም የፋይናንስ ተቋም አመታዊ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡በኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በጉባኤው እየተሳተፈ ነው፡፡በጉባኤው በአለም ዓቀፍ ዋና ዋና የኢኮኖሚ፣ የልማት፣ የፋይናንስ፣ የድህነት ቅነሳ፣ የቴክኖሎጂ ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችና እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል።በጉባኤው ከአለም ባንክ አባል ሀገራት የተወከሉ ከ2 ሺህ 800 በላይ ጉባያተኞችን ጨምሮ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ፣ የፋይናንስ ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡ከጉባኤው ጎን ለጎን የሁለትዮሽ የተናጥል ውይይቶችና ስምምነቶች እንደሚደረጉ እንደሚጠበቅ ከአለም የፋይናንስ ተቋም ድረ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/24014/
79
3ቢዝነስ
በፅንስ ማቋረጥ ታስራ የነበረችው ሞሮካዊቷ ጋዜጠኛ ምህረት ተደረገላት
ሀገር አቀፍ ዜና
October 17, 2019
Unknown
ሞሮካዊቷ ጋዜጠኛ ከጋብቻ በፊት ወሲብ በመፈፀም እንዲሁም በፅንስ ማቋረጥ አንድ አመት ተፈርዶባት የነበረ ቢሆንም የሞሮኮው ንጉስ መሃመድ አራተኛ ምህረት እንዳደረጉላት የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።የሃገሪቱ ፍትህ ሚኒስትር በእንደዚህ አይነት ጉዳይ የንጉሱ ጣልቃ መግባት "ርህራሄቸውና ምህረታቸውን የሚያሳይ ነው" ብለዋል።የ28 አመቷ ጋዜጠኛ ሃጃር ራይሱኒ በትናንትናው ዕለት ከእጮኛዋ ጋር ከእስር ቤት ስትወጣ ጣቶቿን ከፍ አድርጋ የድል ምልክት አሳይታለች። እጮኛዋም ምህረት ተደርጎለታል ተብሏል። በሞሮኮ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ወሲብ እንዲሁም ፅንስ ማቋረጥ ወንጀል ነው።ምንም እንኳን መንግሥት ለእስሯ የሰጠው ምክንያት የፅንስ ማቋረጥና ከጋብቻ በፊት የሚፈፀም ወሲብ ቢሆንም፤ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በበኩላቸው በነፃ ጋዜጣ ላይ የተደረገ አፈና ነው ብለዋል። ጋዜጠኛዋ መንግሥትን በመተቸት በሚታወቀው አክባር አል ያውም ነው የምትሰራው።በነሐሴ ወር ከሱዳናዊ እጮኛዋ ጋር ከማህፀን ክሊኒክ ስትወጣ የታየች ሲሆን፤ የፅንስ ማቋረጡን ክስም አልተቀበለችም።ወደ ክሊኒኩ የሄደችውም ያጋጠማትን መድማት ለመታከም እንደሆነ ተናግራ ነበር።ክሱንም ሆነ ውሳኔውን ፖለቲካዊ ፍርድ ነው ብላ ያወገዘች ሲሆን መስከረም ወር ላይ አንድ አመት እንድትታሰር ተወስኖባት ነበር።ጉዳዩን የያዘው አቃቤ ህግ በበበኩሉ የጋዜጠኛዋ እስር ከስራዋ ጋር እንደማይገናኝና የሄደችበት ክሊኒክም በህገወጥ ፅንስ ማቋረጥ ጥርጣሬ በፖሊስ ክትትል ሲደረግበት የነበረ ነው ብሏል።እጮኛዋም አንድ አመት ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን በዶክተሩ ላይ ሁለት አመት እስር ተወስኖበታል። የዶክተሩ ረዳትም ሆነ ነርስ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙም የሙያ ፈቃዳቸውን ለተወሰነ ጊዜ በማገድ ብቻ ታልፈዋል።
https://waltainfo.com/am/33483/
182
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከማዕድን ዘርፍ ተጠቃሚ ለመሆን ግልጽነት ያለዉ አሰራር ያስፈልጋል – የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር
ቢዝነስ
October 16, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ የሚገኘውን የማዕድን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ግልጽነት የሰፈነበት አሰራር መኖር እንዳለበት ተጠቆመ።ዛሬ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የማዕድን ግልፀኝነት ኢኒሼቲቭ የቦርድ ጉባኤ ላይ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርካቶ ኢትዮጵያ በማዕድን ሀብት የበለፀገች ብትሆንም ሀብቱ በሚፈለገው ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲውል እየተደረገ አለመሆኑ ገልጸዋል።በመሆኑም ከዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ህብረሰተቡን ያሳተፈ ግልፀኝነት የሰፈነበት አሰራር መኖሩ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ሚኒስቴሩ ችግሩን ለማቃለል በእቅድ እየሰራ መሆኑንና፣ በተለይም የህብረሰተቡን ግንዛቤ በማሳደግ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋማት እና መንግስት በጋራ እንዲሰሩ እየተደረገ መሆኑን ዶክተር ሳሙኤል አክለው ገልጸዋል፡፡በዓለም አቀፉ የማዕድን ግልፀኝነት ኢኒሼቲቭ የቦርድ ጉባኤ ከ52 ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎችን ገምግመዋል፡፡ኢትዮጵያ አለም አቀፉ የማዕድን ግልጸኝነት ኢኒሼቲቭን የተቀላቀለችዉ በአውሮፓውያ የጊዜ አቆጣጠር በ2012 እንደነበር ይታወሳል፡፡   
https://waltainfo.com/am/24011/
107
3ቢዝነስ
ኬንያ በአንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር የሰራችውን የባቡር መንገድ ልትመርቅ ነው
ቢዝነስ
October 16, 2019
Unknown
ኬንያ የባቡር መንገዷ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን የኬንያ ባቡር መንገድ አስታውቋል።አዲሱ የኬንያ የባቡር መስመር ከመዲናዋ ናይሮቢ ወደ ናይቫሻ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሏል።መስመሩ ለጊዜው አገልግሎት የሚሰጠው ለሰዎች ሲሆን የጭነት ማጓጓዝ አገልግሎት ደረቁ ወደብ እስኪገነባ ድረስ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡ ግንባታውም ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚወስድም ተገምቷል።ለዚህም በአካባቢው የሚኖሩ የማሳይ ማህበረሰብ ግንባታውን በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ በመውሰዳቸው እንደሆነ ተገልጿል።በቻይና ኮሚዩኒኬሽንና ግንባታ ኩባንያ የተገነባው ይህ መስመር 120 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው ሲሆን 1.4 ቢሊዮን ዶላር ፈጅቷል።የተጓዦች አገልግሎት ከአስራ ሁለቱ ጣቢያዎች በአራቱ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀመር ዘ ቢስነስ ደይሊ ኒውስፔፐር የኬንያ የባቡር አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ፊሊፕ ማይንጋን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።የመጀመሪያው የባቡር መንገድ ከመዲናዋ ናይሮቢ ወደ ሞምባሳ ከሁለት አመት በፊት በተመረቀበት ወቅት ከፍተኛ ደስታና ፈንጠዝያ የነበረ ሲሆን ይህ መስመር ግን እንደ መጀመሪያው አልሆነም ተብሏል። በወቅቱም ኬንያ ለምርጫ ስትዘጋጅ ነበር።የአዲሱ የባቡር መንገድ ዋጋ ከአለም አቀፉ ስታንዳርድ አንፃር ጋር ሲታይ ሶስት እጥፍ እንዲሁም መጀመሪያ ያወጣል ተብሎ ከተገመተው አራት እጥፍ ነው ተብሏል።መንግሥት ዋጋው እንዲህ ለምን ናረ ለሚለው የሰጠው ምክንያት የመልክአ ምድሩ አስቸጋሪነት ድልድዮችንና ቱቦችን በመገንባት ላልታሰበ ወጪ እንደተዳረጉ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለመሬት ካሳ ተከፍሏል ተብሏል።ከዚህ ወጪ ውስጥ 80% የተገኘው ከቻይና በተገኘ ብድር ነው።የባቡር መስመሩ የመጀመሪያ እቅድ ከሞምባሳ- ኪሱሙን በመሻገር ኡጋንዳ ይደርሳል ተብሎ ነበር።አገሪቷ ይህንን የባቡር መስመር ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ብድር ያስፈልጋታል ተብሏል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/32908/
199
3ቢዝነስ
ኢትዮጵያ በ2025 ከካርበን ልቀት ነፃ የሆነ የአረንጓዴ ልማት ስራ ለማከናወን ማቀዷን ገለጸች
ሀገር አቀፍ ዜና
October 16, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ በአውሮፓውያን ጊዜ አቆጣጠር በ2025 ከካርበን ልቀት ነፃ የሆነ የአረንጓዴ ልማት ስራ ለማከናወን ማቀዷን የውሃ፣ መስኖና ኢኔርጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡የውሃ፣ መስኖና ኢኔርጂ ሚኒስቴር እና በፊንላንድ መንግስት በጋራ ባካሄዱት የውይይት መድረክ ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ በከባቢ አየር ብክለት ላይ ያላቸው ሚና በጣም ውስን ቢሆንም በከባቢ አየር ለውጥ ምክንያት እየደረሰባቸው ያለው ችግር ግን ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡የውሃ፣ መስኖና ኢኔርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጀነር ስለሺ በቀለ የአየር ብክለትን የሚያምቅ አቅም ወይም አሰራር ባለመኖሩ በኢትዮጵያ በ2025 የካርቦን ልቀቱ ዜሮ የሆነ የአረንጓዴ ልማት ስራ ለመስራት መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡ አሁን ላይ ኢትዮጵያ 97 በመቶ ከታዳሽ ኃይል እያመነጨች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የፊንላንዱ ፕሬዝዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ላይ እየሰራች ያለችው ስራ ለሌሎች ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ፕሬዝዳንቱ አክለውም የዓለም ህዝቦች በከባቢ አየር ብክለት ምክንያት ከባድ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ ቅፅበታዊ ለሆነው ችግር ቅፅበታዊ መፍትሔ እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችው እንቅስቃሴም ሌሎቹን የሚያበረታታና የመሪነት ሚናን የሚያሳይ ነው፤ ፊንላንድም እስከ ፈረንጆቹ 2030 የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እየሰራች ነው ብለዋል፡፡ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ የምድር ሙቀት በአማካኝ በ1 ነጥብ 62 ድግሪ ፋራናይት ጨምሯል፡፡ በተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተፈጠረ ያለው የበረዶ መቅለጥ፣ ሰደድ እሳት፣ አውሎንፋስን ያዘለ ከባድ ዝናብና ሌሎቹም ጉዳቶች ማሳያዎች መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡  
https://waltainfo.com/am/32801/
176
0ሀገር አቀፍ ዜና
400 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 16, 2019
Unknown
ከሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በእስር ላይ የነበሩ 400 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሃገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል ።በዛሬው እለት ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ኢትዮጵያውያን ቀይ ባህርን አቋርጠው ሲጓዙ በሳዑዲ ዓረቢያ የፀጥታ ሀይል ተይዘው በእስር ላይ የቆዩ ናቸው ተብሏል።ኢትዮጵያውያኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ዮሃንስ ሾዴ ተገኝተው አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።የዛሬዎቹን ተመላሾች ጨምሮ በበጀት ዓመቱ ባለፉት 3 ወራት 32 ሺህ 890 ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ሀገራት ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ  ተደርጓል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በመከተል በተለያዩ ሃገራት የሚኖሩና መሰል ችግር ያጋጠማቸውን ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ፈቃድ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል።
https://waltainfo.com/am/32802/
111
0ሀገር አቀፍ ዜና
የጸጥታ መደፍረስ የተስተዋለባቸውን የጎንደር አካባቢዎች የፌዴራል የፀጥታ ኃይል እንዲያረጋጋ መመሪያ ተላላፈ
ፖለቲካ
October 17, 2019
Unknown
የጸጥታ መደፍረስ የተስተዋለባቸውን ማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች፣ ጎንደር ከተማና ቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር የፌዴራል የፀጥታ ኃይል ህጋዊ እርምጃ ወስዶ ወደ ተሟላ ሰላም እና መረጋጋት እንዲያሸጋግር መመሪያ ተላላፈ።የአማራ ብሔራዊ ክልል የደኅንነትና የፀጥታ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ  በአካባቢዎቹ ማንነትን ሽፋን በማድረግ ባለፉት አምስት ዓመታት የዘለቀው የጸጥታ መደፍረስ ለሰው ህይዎትና ለንብረት ጥፋት ምክንያት ሆኖ መቀጠሉን አንስቷል።ችግሩ  አካባቢውን ወደ ተሟላ ትርምስ የሚያስገባና ለክልሉ ብሎም ለመላው ሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት ወደ መሆን ተሸጋግሯልም ነው ያለው።በመሆኑም የክልሉ መንግሥት ለፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን ጣልቃ ገብቶ እንዲያስተካክል በጠየቀው መሠረት የፌዴራል የፀጥታ ኃይል መከላከያን ጨምሮ ማንኛውም ህጋዊ እርምጃ ወስዶ ቀጠናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሟላ ሰላም እና መረጋጋት እንዲያሸጋግር መመሪያ መተላለፉን አስታውቋል።በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች፣ በጎንደር ከተማ እንዲሁም በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር ማንነትን ሽፋን በማድረግ ባለፉት አምስት ዓመታት የዘለቀው የጸጥታ መደፍረስ ለሰው ህይዎትና ለንብረት ጥፋት ምክንያት ሆኖ መቀጠሉ የሚታወስ ነው፡፡ የክልሉ መንግስት ህግና ሥርዓትን በተከተለ አኳኋን ለተነሱ የማንነት ጥያቄዎች የቅማንት ብሔረሰብን ጨምሮ ምላሽ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ ለተነሱ የማንነት ጥያቄዎችና መልሶች ቅሬታ ያቀረበ ኃይል፣ ቡድንና ማኅበረሰብ ህግና ሥርዓትን በተከተለ መንገድ ሀሳባቸውን፣ ጥያቄያቸውንና ቅሬታቸውን አቅረበው መስተናገድ እየተቻለና ለዚህም በርካታ ዕድሎች ብሎም ጊዜያት ተሰጥተው እያለ በሃይል ፍላጎትን ለማሳካት መሞከር ጸረ ህገ መንግስትና የለዬለት ጸረ ሰላም ተግባር መሆኑ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡ የቅማንት የራስ አሥተዳድር ኮሚቴ የተከተለው አቅጣጫም ከላይ የተገለጹ ተግባራትን በመፈጸም ፍላጎትን በኃይል በብሔረሰቡና በክልሉ መንግስት ላይ የመጫን ኢ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ይህንን ለመቀልበስ የሚወሰድ አጸፋዊ እርምጃም በአንጻሩ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ ከመስከረም 15/2012 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተው ግጭትና እያደረሰ ያለው ከፍተኛ ጉዳትም የዚህ መገለጫ ነው፡፡ ለአካባቢው ጸጥታ መደፍረስ ምክንያት ሆኗል፤ ለሌሎች የጥፋት ሃይሎችም ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር እያደረገ ነው፡፡ በዚህም የተለያዬ ኢ መደበኛ አደረጃጀትን ይዘው የሚንቀሳቀሱና በጸረ ሰላም ተግባር ላይ የተሰማሩ ቡድኖችና ግለሰቦችም ትልቅ መሳሪያ አድርገው እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ በዚህም በሰው ህይዎትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በክልልና በፌዴራል መንግስት በትዕግስትና በአርቆ አስተዋይነት ችግሩን በሰላማዊ አግባብ ለመፍታት በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም ወደ ውጤት ሊቀየር አልቻለም፡፡ ይባስ ብሎም አካባቢውን ወደ ተሟላ ትርምስ የሚያስገባና ለክልሉ ብሎም ለመላው ሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት ወደ መሆን ተሸጋግሯል፡፡ የሰው ህይወትና ንብረት በየቀኑ ይጠፋል፡፡ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በከፍተኛ ደረጃ ተዳክመዋል፡፡ ከጎንደር-መተማ ያለው አከባቢ የንግድ መስመር ከመሆኑ ጋር ተያይዞም በገቢና ወጪ ንግድ ላይም ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ በመሆኑም የክልሉ መንግሥት ለፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን ጣልቃ ገብቶ እንዲያስተካክል በጠየቀው መሠረት የፌዴራል የፀጥታ ኃይል መከላከያን ጨምሮ ማንኛውም ህጋዊ እርምጃ ወስዶ ቀጠናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሟላ ሰላም እና መረጋጋት እንዲያሸጋግር መመሪያ ተላልፏል፡፡ የተላለፈውን መመሪያ በመከተል የክልሉ የፀጥታና ደኅንነት ካውንስል በማዕከላዊ፣ በምዕራብ ጎንደር፣ በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር እና በጎንደር ከተማ ቀጥለው የቀረቡ ክልከላዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ መመሪያ ሠጥቷል፡፡1.ማንኛውም የኃይል እንቅስቃሴን የኃይል እርምጃ በመውሰድ የሰው ህይወትና ንብረትን ከአደጋ ማዳን፣ በድርጊቱ ላይ የተሳተፉትን በኃይል መቆጣጠር፣ ለህግ ማቅረብ፣ ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃን በመውሰድ የኃይል ተግባርን ፍፁም እንዳይቀጥል ማድረግ፣2.አሁንም የሰላም አማራጮችን ለማስፋትና በአከባቢው ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር ሲባል በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ግጭት የገቡ ቡድኖች እና ግለሰቦች በአስቸኳይ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ በመመለስ ያሏቸውን ልዩነቶች እንዲፈቱ ጥሪ ተላልፏል፡፡ ከዚያ ውጪ ምንም ዓይነት የኃይል እርምጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡3.ማንኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን በቀጠናው ላይ ለሚደረገው የፀጥታ ኃይል ስምሪት የመተባበር፣ ወንጀለኛን አሳልፎ የመስጠትና የአከባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረገውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ድጋፍ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ይህንን የሚያደናቅፍ ማንኛውም ተግባር በህጋዊ እርምጃ የሚስተካከል ይሆናል፡፡ 4.በግልፅ በታወቁ የፀጥታ ኃይሎች ከተያዙት ትጥቅና መሳሪያ ውጪ በተጠቀሱት የክልሉ ዞኖች ላልተወሰነ ጊዜ ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለና የሚወረስ ይሆናል፡፡5.የቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር ከዚህ ቀደም በተወሰነው ህጋዊ ውሳኔ መሠረት በአፋጣኝ በሕዝብ ይሁንታ የሚደራጅ የራስ አስተዳድርን በማቋቋም ሁሉም አገልግሎት እንዲጀምር ማድረግ፡፡ ይህንን የሚያደናቅፍ የኃይል እርምጃ ፍፁም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡6.በተለያየ ምክንያትና ሰበብ ተደናግሮም ይሁን በንቃት በኃይል ፍላጎትን ለማሳካት በተደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ የነበረውን ኃይል፣ ቡድንና ግለሰብ እስከ ጥቅምት 20/2012 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለስ የክልሉ መንግሥት በድጋሜ ይቅርታ አድርጎለታል፡፡ በሰው ግድያ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች ጉዳያቸው በህግ አግባብ የሚታይ መሆኑ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡7.በየዞኑ፣ በየወረዳውና ቀበሌ ውስጥ፣ አቅራቢያና አከባቢ ለሚፈጠሩ ወንጀሎች ፀረ-ሰላም ድርጊቶችና እንቅስቃሴዎች በየደረጃው ያለው አመራር፣ ነዋሪና ዜጋ የመቆጣጠር፣ የማሳወቅ፣ እርምጃ እንዲወስድ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ተጠያቂነትን ከማስከተልም በተጨማሪ በአከባቢው የሚገኘው ትጥቅ ሙሉ በሙሉ ተራግፎ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡8.በኢ- መደበኛ አደረጃጀትና ባልተሠጠ ኃላፊነት ህግን ለማስከበር በሚል ሰበብ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ የተከለከለ ነው፤ ተጠያቂነትም ያስከትላል፡፡9. ከጎንደር-መተማ ፣ ከጎንደር-ሁመራ፣ ከጎንደር-ባሕር ዳር፣ ከጎንደር- ደባርቅ የሚወስዱ መንገዶች እንዲሁም በጎንደር ከተማና ዙሪያው ብሎም ሁሉም መጋቢና ዋና ዋና መንገዶች በማንኛውም ጊዜ ነፃ ይሆናሉ፡፡ የሕዝብ እንቅስቃሴም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ነፃ ይሆናል፡፡ ይህንን ለማደናቀፍ የሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል፡፡10.የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ ክልል የፀጥታ ኃይል፣ በየደረጃው ያለው የክልሉ መስተዳድር፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት በቅንጅትና በጥምረት በመሰማራት በአከባቢው ላይ የተሟላ ሰላምና መረጋጋትን እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡11.በመጨረሻም ሁሉም የሰላም ኃይሎች ማለትም የሃይማኖተ አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ብሔርን እና ማንነትን ሳይለይ በአከባቢያችን የተሟላ ሰላም እንዲረጋገጥ ለፀጥታ ኃይሉ የተሟላ ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡የአማራ ብሔራዊ ክልል የደኅንነትና የፀጥታ ካውንስል፡፡ጥቅምት 05/2012 ዓ.ም
https://waltainfo.com/am/31416/
717
5ፖለቲካ
የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ስጦታ አበረከቱ
ፖለቲካ
October 16, 2019
Unknown
የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ሽልማት አበርክተውላቸዋል፡፡የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ስጦታውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አበርክተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆናቸውን አባላቱ መደሰታቸውን የገለፁት አቶ ለማ ፤ ሽልማቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትግል የተሰጠ እውዕና መሆኑን ገልፀዋል፡፡በተያየዘ ዜና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።ማዕከላዊ ኮሚቴው የክልሉ መንግስት የስራ አፈፃፀምን በመገምገም አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡በተጨማሪም በለውጥ ጉዞ ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ በመምከር የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኦሮሚያ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31414/
91
5ፖለቲካ
የዓለም ምግብ ቀን ለ39ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 16, 2019
Unknown
የዓለም ምግብ ቀን ለ39ኛ ጊዜ "የዛሬ ጥረት ለነገ ስኬት" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ተከብሯል፡፡በዓሉ በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት፤ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጋላጭ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዓለም ላይ ከ800 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ለምግብ እጥረት ተጋላጭ መሆናቸውም በዚሁ ወቅት የተገለጸ ሲሆን፤፣ ችግሩን በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2030 ከዓለም ለማስወገድ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ከኢትዮጵያም የምግብ እጥረት ችግርን ለመቅረፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ የምግብና ስነ-ምግብ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በማድረስ መንግስትና በዘርፉ የሚሰሩ አጋር አካላት በጋራ እየሰራ እንደሆነ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የግብርና ሚኒስትር አማካሪ ዶ/ር ኢያሱ አብርሃ ተናግረዋል፡፡በሀገሪቱ የሚታየውን የምግብ እጥረት ለመቀነስና የተመጣጠነ ምግብን ተደራሽ በማድረግ ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር በዋናነት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም ዶ/ር ኢያሱ ገልጸዋል፡፡በገጠር አካባቢ የሚታየውን የምግብ እጥረት ችግር ለመቅረፍ በአርሶአደሩ የሚያመርተውን ምግብ እንዲመገብ ለማድረግ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንደሚሰራም አክለው  ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተወካይ ወ/ሮ ፋጡማ ሰይድ በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ የሚታየውን የምግብ እጥረት ችግር ለመቅረፍ መንግስት ብቻ ሳይሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡በአዲስ አበባ የተጀመረው የትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም ችግሩን ለመቅረፍ የበኩሉን እስተዋጽኦ እንደሚያበረክትና መሰል ፕሮግራሞች በተለያዩ ቦታዎች ተግባራዊ ቢሆኑ ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻል የበዓሉ ታዳሚዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡የዓለም የምግብ ቀን ለ39ኛ ጊዜ ሲሆን፤ በዓሉ "የዛሬ ጥረት ለነገ ስኬት" በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
https://waltainfo.com/am/32799/
190
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ
ፖለቲካ
October 16, 2019
Unknown
የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረየኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ዛሬ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል።ማዕከላዊ ኮሚቴው እንደ ፓርቲና እንደ መንግስት ያለውን አፈጻጸም በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል ተብሏል፡፡የፓርቲው የውስጥ አንድነትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሪፎርም ጉዳይም የውይይቱ አጀንዳ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ለአገራዊ ለውጡ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮች ተለይተው የመፍትሔ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ከኦሮሚያ  ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
https://waltainfo.com/am/31415/
58
5ፖለቲካ
የዓለም የሜቲሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ጽ/ቤቱን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው
ቢዝነስ
October 16, 2019
Unknown
የዓለም የሜቲሮሎጂ ድርጅት (WMO) የአፍሪካ ጽ/ቤቱን በአዲስ አበባ ሊከፍት መሆኑን አስታውቋል፡፡የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ህይወት ሞሲሳ የዓለም የሜቲሮሎጂ ድርጅት (WMO) ሴክሪተሪ ጀነራል ፒተሪ ታላስን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ወ/ሮ ህይወት በውይታቸው የዓለም የሜቲሮሎጂ ድርጅት (WMO) የአፍሪካ ጽ/ቤቱን በይፋ ለማስጀመር መወሰኑ እንዳስደሰታቸውና በጋራ ለመስራትም ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ሴክሪተሪ ጀነራል ፒተሪ ታላሰን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ እያስመዘገበች ያለችው እድገት ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ በመሆኑ ሀገሪቱን ተመራጭ ካደረጓት ጉዳዮች መካከል ዋንኛው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ድርጅቱ በአዲስ አበባ ጽ/ቤቱን መክፈቱ የኢትዮጵያ አቭዬሽን ድርጅት እየያከናወነ ለሚገኘው ድህንነቱን የጠበቀ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ተጨማሪ አቅም ከመሆኑም በላይ ለቴክኒካዊ ድጋፍና ጥራት ያለውና ተአማኒ መረጃ ከመስጠት አኳያ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል፡፡ሴክሪተሪ ጀነራሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሰላም የኖቤል ሽልማት ማግኘታቸው እንዳስደሰታቸው ለወ/ሮ ህይወት መግለፃቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/24010/
117
3ቢዝነስ
የሀዋሳ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ በኑሯቸው ላይ እክል እየፈጠረ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 16, 2019
Unknown
የሀዋሳ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ በጤናቸው ላይ እክል እየፈጠረ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ስምንት ክፍለ ከተሞችና 32 ቀበሌዎች ያሏት ሀዋሳ ከከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ቆሻሻ መስገጃው ለመኖሪያ ቦታዎች ይበልጥ እየተጠጋ ነው፡፡በመሆኑም በከተማዋ በተለምዶ ዳያስፖራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ነዋሪዎች በቆሻሻው ምክንያት ለልዩ ልዩ የመተንፈሻ አካላት ችግሮች መጋለጣቸውን በህክምና ማስረጃ አስደግፈው ለዋልታ አስረድተዋል፡፡ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ ላለፉት ሰባት ዓመታት ቢያመለክቱም ሰሚ ማጣታቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ የሰጡት የከተማዋ ከንቲባ ጥራቱ በየነ አዲሱ አመራር ለነዋሪዎቹ ቅሬታ ቅድሚያ በመስጠት የ45 ቀናት የድርጊት መርሃ ግብር አውጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ከከተማ እድገት ጋር ተያዞ አሁን ያለው ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ በአዲስ ለመተካት የዲዛይን ስራ መጠናቀቁንም ከንቲባው ገልፀዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32800/
103
0ሀገር አቀፍ ዜና
በኢትዮጵያ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለመጠቀም ያለው ልምድ ውስንነት የሚታይበት መሆኑ ተገለጸ
ቢዝነስ
October 16, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለመጠቀም ያለው ልማድም ውስንነት የሚታይበት በመሆኑ፤ ደረጃዎችን የጠበቁ ምርቶች የማምረትና የመጠቀም ባህል ማሳደግ እንደሚገባ የዘርፉ ባለሙያዎችና የአማራች ዘርፍ ባለቤቶች ገልጸዋል፡፡በኢትዮጵያ የአማርች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በርካታ ቢሆኑም የዓለም አቀፍ ደረጃን አሟልተው ያሉት ግን ከ130 አይበልጡም ተብሏል፡፡ባጠቃላይ አሁን ላይ በአገሪቷ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለመጠቀም ያለው ልማድ ውስንነት የሚታይበት መሆኑ ተነግሯል፡፡በተለይ ከዋጋ ጋር በማነፃፀር ዝቅተኛውን የመጠቀም ልማድ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታይ መሆኑ ተነስቷል፡፡ ይህ አስተሳስብ በትምህርና ስልጠና መዳበር እንዳለበትም ነው የዘርፉ ባለሙያዎች የገለጹት፡፡እንደ ኮርያ፣ ጃፓን እና ሲንጋፖር ያሉ ሀገራት ለእደገታቸው ቁልፍ ተደርጎ የሚወሰደው ምርቶቻቸውን በደረጃ መጠቀማቸው መሆኑን ባለሙያዎቹ በአብነት ገልጸዋል፡፡ዓለም ያለችበትን ነባራዊና አሁናዊ ሁኔታን በማጤን እኩል መሮጥ እንዲቻል ውስጣዊ አቅም በማጎልበት በተለይ አእምሮ ላይ አና የተቋማት መሰረተ ልማት ላይ አተኩሮ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ የሚድሮክ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው አስረድተዋል፡፡የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የተቋማት አማካሪ ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው በበኩላቸው የግሉ ዘርፍ ላይ መሰራት ያላባቸውን ጉዳዮች ቆም ብሎ በማሰብ ማበረታት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ ደራጃዎች ኤጀንሲ በበኩሉ ዘርፉን ለማጠናከር በጥናትና ምርምር ችግሮችን መፍታት የሚያስችል መዋቅር መዘርጋቱንና ለፖሊሲና ስትራቴጂ ጠቃሚ የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ እየሰራው መሆኑን አስታውቋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/24012/
166
3ቢዝነስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፊንላንዱ ፕሬዚደንት ሳውሊ ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
October 15, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፊንላንዱ ፕሬዚደንት ሳውሊ ኒሲቶ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡ፕሬዚደንቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸውላቸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም ሽልማቱ 10 በመቶ እውቅና፣ 90 በመቶ ደግሞ ለሰላም በርትተው እንዲሠሩ አደራም ጭምር እንደ ሆነ ጠቁመው ለውጡ ያስገኛቸውን ዋና ዋና ስኬቶች እንዲሁም የፊንላንድ መንግሥት ድጋፍ ሊያደርግባቸው የሚችልባቸውን የልማት አቅጣጫዎች አመላክተዋል።ሁለቱ መሪዎች የጋራ ጥቅምን እውን በሚያደርግ መልኩ የአፍሪካና የአውሮፓን ግንኙነት በማጠናከር ሂደት ላይ መምከራውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31410/
74
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከወራት በፊት በልደታ የተከሏቸውን ችግኞች ተንከባከቡ
ቢዝነስ
October 16, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከወራት በፊት በልደታ የተከሏቸውን ችግኞች ተንከባከቡ፡፡ኢትዮጵያውያን አገራቸውን አረንጓዴ ለማድረግ እንደ አንድ ሆነው ክረምቱን በሙሉ ችግኝ ሲተክሉ መቆየታቸው ይታወቃል።እንደ ሕዝብ አረንጓዴ አሻራቸውን ለማሳረፍ፣ ለዚህም ችግኞቻቸው አድገው ዛፍ እስከሚሆኑ ለመንከባከብ እና ውሀ ለማጠጣት ቃል መግባታቸውም ይታወሳል።በዚሁ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከወራት በፊት በልደታ አካባቢ የተከሏቸውን ችግኞች መንከባከብ ጀምረዋል።ችግኞቻቸውን በመንከባከብና ውኃ በማጠጣት ዛፍ ያደርጓችው ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመላ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።(ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/24009/
66
3ቢዝነስ
ቱርክ የአሜሪካን የተኩስ አቁም ጥሪ ውድቅ አደረገች
ፖለቲካ
October 16, 2019
Unknown
ቱርክ የአሜሪካን አስቸኳይ የተኩስ አቁም ጥሪ ውድቅ አድርጋለች፡፡ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶሃን ጦሩ ማጥቃቱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።የጣይብ ኤርዶሃን አስተያየት የተሰማው ከአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ማይክ ፔንስና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ ወደ ቱርክ ለመብረር በተዘጋጁበት ወቅት ነው።ሁለቱ የአሜሪካ ሹማምንት በቱርክና በኩርዶች መካከል ሰላም እንዲወርድ ይጥራሉ ተብሏል።የተኩስ አቁም በፍፁም አናውጅም ያሉት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን፣ አክለውም " ጫና እያሳደሩብን ያሉት እርምጃችንን እንድናቆም ነው። ማዕቀብም ጥለዋል። ዓላማችን ግልፅ ነው። ስለማዕቀቡ አንጨነቅም" ብለዋል።የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት " ቱርክ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ለማድረግ ካልተስማማችና ካልተገበረች" እንዲሁም በድንበሩ አካባቢ ስደተኞችን ለማስፈር ለመደራደር ፈቃደኛ ካልሆነች ማዕቀቡ ይበልጥ እንደሚጠብቅ አስጠንቅቀዋል።ቱርክ ኩርዶችን ከድንበር አካባቢ ማራቅ የዚህ ጥቃቷ ግብ እንደሆነ በፕሬዝዳንቷ በኩል ደጋግማ ተናግራለች።በኩርዶች የሚመራው የሶሪያ ዲሞክራቲክ ግንባር በቱርክ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ነው።አንካራ ከዚህ ቀደም በድንበሩ አቅራቢያ 30 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን "ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና" መመስረት እንደምትፈልግ አስታውቃለች። በዚህ ስፍራም ቱርክ የሚገኙ 2 ሚሊየን ሶሪያውያን ስደተኞችን የማስፈር ዕቅድ አላት።በሳምንቱ መጨረሻ አካባቢ በሩሲያ የሚደገፉ የሶሪያ ወታደሮች ከኩርዶች ጋር በመደራደር በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ላይ በመግፋት የቱርክ ወታደሮችንና አፍቃሪ ቱርክ አማፂያንን ርምጃ ለመግታት ሞክረዋል።ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ጦር ከቀጠናው መውጣቱ በተገለፀበት ቅፅበት ቱርክ ጦሯን በሶሪያ የድንበር ከተሞች በማዝመት መጠነ ሰፊ ጥቃት መክፈቷን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡።ይህንን የአሜሪካ መንግሥትን እርምጃ የሚተቹ አካላት የአሜሪካ ድርጊት ለቱርክ ጥቃት ይኹንታን የሰጠ ነው ይላሉ።አሜሪካ ግን ይህንን በማስተባበል ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች።እስካሁን ድረስ በርካታ ተዋጊዎች ሲሞቱ ከ160 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ያሳያል።
https://waltainfo.com/am/34015/
206
5ፖለቲካ
በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ የተጻፈው “መደመር” መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል
ፖለቲካ
October 16, 2019
Unknown
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት በመደመር እሳቤ ላይ የተጻፈው መጽሀፍ የፊታችን ቀዳሜ ጥቅምት 8 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚመረቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገልፀዋል።አቶ ንጉሱ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የመደመር እሳቤን በተመለከተ የተጻፈው መጽሀፍ በአማርኛ፣ በአፋን-ኦሮሞ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች የተጸፈ ነው።የመፅሃፉ ምረቃም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ አዲስ አበባን ጨምሮ በ20 ከተሞች በአንድ ቀን የሚከናወንም ይሆናል።በዋናነትም በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራ እና ሀረር ከተሞች ይመረቃል። በውጭ አገርም በተወሰኑ ከተሞች በተለይም በዋሽንግተን ዲሲ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ሚኒሶታ እና ናይሮቢ የምረቃ ስነ ስርዓቱ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል።በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይም የየከተሞቹ ነዋሪዎች፣ ባለስልጣናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ሴቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። መሰናዶዉም የአካባቢውን ባህላዊ ይዘት በያዘ መልኩ እንሚከናወን ነው የገለፁት፡፡እንደ አቶ ንጉሱ ማብራሪያ መጽሀፉ በ1 ሚሊየን ኮፒ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ህትመቱ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት ማተሚያ ቤቶች ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ታትሟል። የኢንግሊዘኛው ቅጂ ግን ከሶስት ወራት በኋላ እንደሚደርስ አስታውቀዋል።መጽሀፉ በአሁኑ ወቅት በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የተሰራጨ ሲሆን፤ በቀጣይም በተለያዩ የዓለም ሀገራት ለሽያጭ እንደሚቀርብ ተጠቁሟል።የአንዱ መጽሀፍ ዋጋ 300 ብር (ሶስት መቶ ብር) ሲሆን ከመጽሀፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በአገሪቱ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት ይውላል።
https://waltainfo.com/am/31411/
177
5ፖለቲካ
የታሰበው የፓርቲ ውህደት የችኮላ እንቅስቃሴ መሆኑን ህወሃት አስታወቀ
ፖለቲካ
October 16, 2019
Unknown
በኢህአዴግ እየታሰበ የፓርቲ ውህደት ለመፈፀም እየተደረገ ያለው የችኮላ እንቅስቃሴ መሆኑን ህወሃት አስታወቀ።በአሁኑ ወቅት በአገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች እየተበራከቱ፣ ጥፋት በጥፋት ላይ እየተደራረበ፣ የጥፋቱ ስፋትና መጠን በየቀኑ እየጨመረ ወደ ከፋ አገር የመበተን ደረጀ እየደረሰ መሆኑን ማዕከላዊ ኮሚቴው በመግለጫው ጠቅሷል፡፡ለቀናት ሲካሂድ የቆየው የህወሓት ማዕካላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰበባ ተጠናቀቀ።ማዕከላዊ ኮሚቴው በስብሳበው የ2011 ዓ.ም ቁልፍ እና ዓበይት ተግባራትን በዝርዝር ገምግሟል።በተለይም መልካም አስተዳደርን በማስፈን እና ልማትን በማረጋገጥ በኩል ያሉትን አፈፃፀሞች ተመልክቷል።በ2011 ዓ.ም የነበሩ ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጥንካሬዎችን እና ጉድለቶችን በዝርዝር በማየት ያሉትን ተግዳሮቶች ለመከላከል የሚያስችል አቅጣጫ በማስቀመጥ እና ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።የማዕከላዊ ኮሚቴው መግለጫ ሙሉ ሐሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 2/ 2012 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 7 ቀናት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በ2011 ዓ/ም ተይዘው የነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች፤ ድርጅታዊና ፖለቲካዊ ስራዎች በተለይ ደግሞ በአዲሱ የፖለቲካ መድረክ የትግራይ ህዝብ ህልውና፣ ደህንነትና ዋስትና ለማስጠበቅ የተካሄደ ሁለንተናዊ የመመከት ትግል እና ይህንን መሰረት በማድረግ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር ገምግሟል፡፡ በዚህ ልዩ የትግል ምዕራፍ የታዩ ጥንካሬዎችንና ጉድለቶችን በመገምገም ሊወሰድ የሚችል ትምህርት በመለየት በዚህ ዓመት ሊሰሩ የሚገባቸው ልማታዊና ፖለቲካዊ ዕቅዶችንም አጽድቋል፡፡በተጨማሪም አሁን ያለው ተጨባጭ አገራዊ ሁኔታዎችንና ዕድገቶችን በመገምገም በቀጣይ ለሚኖረው ትግል መሰረት ያደረገ የመመከትና ደህንነትን የማረጋገጥ አቅጣጫዎችንና ዕቅዶችን በዝርዝር ተወያይቶ በዚህ ዓመት ሊኖር የሚችለውን ሁለንተናዊ ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡ ባለፈው ዓመት ተይዘው የነበሩ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ዕቅዶችን በቀጣይነት ለማስፋትና ለማጎልበት የሚያስችል ዘርፈብዙ ጥረት እየተካሄደ ቆይቷል፡፡ ከጀመርነው የፀረ- ድህነት ትግል ለአፍታም ሳንዘናጋ፣ በዋነኛው አጀንዳችን ላይ ለመረባረብ የሚያስችል አቅጣጫ ይዘን ሰፊ ርብርብ ስናደርግ ቆይተናል፡፡ በህዝባችን የተደራጀ ትግልና እንቅስቃሴ ከትክክለኛ መንገዳችን ሳንወጣ በልማት እቅዶቻችን ላይ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ ስንሰራ ቆይተናል፡፡የሁሉም ዘመቻዎቻችንና ርብርቦቻችን ትኩረት የህዝባችን ደህንነትና ህልውና ከማስጠበቅ አንፃር እየቃኘንና ቅድሚያ ሰጥተን፣ የሁሉም ነገር ማጠንጠኛ ልማትና የህዝባችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መሆኑን በማመን ሁሉም ነገር ትተው ከነ አካቴው ወደ ጥፋት በገቡና ይባስ ብለው እኛንም ጎትተው ከመንገዳችን ሊያስወጡን በሚጥሩ ሀይሎች ሳንደናገር ስራችንን ማእከል አድርገን ከፍተኛ ርብርብ ስናደርግ ቆይተናል፡፡ልማታዊ ዲሞክራሲያዊው መስመራችንን ጨብጠን የህዝባችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለይ ደግሞ የወጣቶችንና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማስፋት የሚያግዙ ተግባሮች በትግራይ እንዲከናወኑ ስናደርግ ቆይተናል።ህዝባችን በየጊዜው የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ በመልካም አስተዳደር መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የቆዩ ችግሮች ፈትተን የህዝባችን ፍላጎቶች ለመመለስ የቀበሌን መዋቅር ለማስተካከል የተጀመረው የሪፎርም ስራ ተስፋ በሚሰጥ ደረጃ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ ስፋትና ጥልቀት ባለው ሁኔታ ሲደረግ የነበረው የወረዳ ሪፎርም ጥናትም ህዝባችን ልማትና ውጤታማ አገልግሎት እንዲያገኝ በሚያስችል መልኩ በዚህ ዓመት በከፍተኛ ትኩረት ለመፈፀም እንስቃሴ እየተደረገ ቆይቷል፡፡ ይህ በቀጣይ ለሚኖሩን ስራዎች እንደ አንድ ትልቅ መነሻ ሆኖ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ያግዛል፡፡ይሁን እንጂ በልማት ስራዎቻችን በሚፈለገው መጠንና ስፋት በሚጠበቀው መጠን ውጤት ያላስመዘገብንባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ በዋናነት በመልካም አስተዳደር ጉዳይ አሁንም ችግሮቻችን ሰፋፊ መሆናቸውን አይተናል፡፡ እየተጠራቀሙ በመጡ ችግሮች ሳቢያና በማስፈፀም አቅማችን ጉድለት ምክንያት ያልፈታናቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ በተለይም በወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት ላይ አሁንም ሰፊ ችግር እንዳለ፣ በገጠርም በከተማም እየታየ ያለው የመሬት አስተዳደር ችግር፣ አገልግሎት በመስጠት ዙርያ ያለው ችግርና መንገላታት፣ ለልማት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ዙርያ ያሉ መዘግየቶችና እንቅፋቶች እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ችግሮች የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በዝርዝር የተመለከታቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ችግሮች በዚሁ ዓመት “በጊዜ የለም” መንፈስ እንዲፈቱ ከፍተኛ ጥረትና ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተመለክተናል፡፡ የልማት ስራችን የሁሉም ቋጠሮ መሆኑን በመገንዘብ፣ ለዘላቂ ህልውናችንና ደሕንነታችን መረጋገጥ ባለው ትርጉም ተገንዝበን በላቀ ቁርጠኝነትና ወኔ ልንዘምትና ልንገሰግስ ይገባል፡፡ ከዚህ የልማት እንቅስቃሴ የወጣቶችንና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የላቀ ርብርብ ይደረጋል ብቻ ሳይሆን የእንቅስቃሴው አስኳል ይሆናል፡፡ ከዚህም አልፎ በእያንዳንዱ አከባቢ ያለው ፀጋ ግምት ውስጥ ያስገባ የልማት አደረጃጀትና ስምሪት እንዲደረግ እና በዚሁ ላይ የሚመሰረት በገጠርም ይሁን በከተማ ወደ አዲስ የልማት እንቅስቃሴ የሚያስገቡ አቅጣጫዎችንም የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ለይቷል፡፡ የተጀመረው የቀበሌና የወረዳ ሪፎርም ስራ ተጠናክሮ ወደ ተግባር እንዲገባና በመልካም አስተዳደር መሰረታዊ ለውጥ እንዲያመጣ እንቅስቃሴ እንዲደረግ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አቅጣጫዎችን ለይቶ አስቀምጧል።የተከበርክ የትግራይ ህዝብ፤ባለፈው ዓመት በአንድ በኩል ፀረ ድህነት ትግል በማካሄድ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የትምክህት ኃይሎችን በመመከት ላይ ቆይተናል። የትግራይ ህዝብንና ህወሓትን ለማንበርከክ ከሁሉም አቅጣጫዎች ሲያጋጥመን የቆየው ፈተና ቀላል አልነበረም። እንደፈለግነው እንዳንሆን ማለፊያ የከለከሉን እና የጎን ውጋት እየሆኑብን ያሉት “የትግራይ ህዝብና ህወሓት ናቸው” ብለው ማለቂያ የሌለው ሴራና በደል ለመፈፀም ያልሞከሩት ፀረ-ህዝብ ተግባር አልነበረም። ይሁን እንጂ ምኞታቸውና ዓላማቸው ስለተገነዘብን በትክክለኛ መንገድ ያደረግነው ፍትሃዊ ትግልና የመመከት ተግባር የጠላቶቻችን ምኞትና ህልም አምክነን ወደፊት እየተራመድን እንገኛለን። በህዝባችን ፅኑ አንድነትና ስምረት፣ በበሳል ንቃትና ምክንያታዊ ትግል፣ በማይነጥፍ ወኔ የተሳካ የመመከት ተግባር ስናከናውን ቆይተናል። ይህ ከትግራይ ህዝብ ጥረትና ትግስት ውጭ እንደማይሳካ እሙን ነበር። ያለፈው የሩቅና የቅርብ ታሪክህ እንደሚያሳየው ከትግልህና ከጥረትህ ውጭ መብትህንና ጥቅምህን ለማስከበር ፍቃድ የሚሰጥህ አካል አልነበረም፤ አሁንም አይኖርም። ሁሉ ጊዜ ለፍትህና ለእኩልነት እንደቆምክ፣ ትክክለኛ መስመርህንና ዓላማህን ይዘህ በፅናት እየታገልክ፣ በሁሉም የትግል ምዕራፎች ያጋጠሙህ መሰናክሎችንና እንቅፋቶችን እየጠራረግክ በመጓዝ ላይ ትገኛለህ። ወደፊትም ብቸኛው መንገድህ ይህና ይህ ብቻ ነው። በዚህ እልህ አስጨራሽ የትግል ምዕራፍ ያካሄድከው ወደር የለሽ የመመከት ተግባር በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ፤ በተለይም ደግሞ የትግራይ ወጣቶች፣ ምሁራንና ሴቶች ለፈፀማችሁትና እየፈፀማችሁ ላላችሁት ገድል የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የተሰማውን ክብርና ኩራት በዚህ አጋጣሚ ሊገልጽላችሁ ይወዳል።የተከበርክ የትግራይ ህዝብአሁንም ቢሆን ሁኔታዎች እየከበዱና እየባሱ በመምጣታቸው ደህንነትህንና ህልውናህን ለማስጠበቅ የምታደርገው ትግል ይበልጥ አጠናክረህ ልትቀጥልበት ይገባል፡፡ ሁሉም ህዝብ ሊገነዘበው የሚገባ ሃቅ ሊገጥመን የሚችለው ፈተና እና ፈተናውን ለመሻገር የሚጠይቀን ትግልና ጥረት እጅግ እየከበደ ሊመጣ ይችላል። ወደፊት መራመድ ሲያቅታቸው፣ በራሳቸው ድክመትና ፀረ-ህዝብ ተግባራቸው ፈተና ሲበዛባቸው ወደ ሌላ ወገን እየለጠፉ እያደናገሩ ዕድሚያቸውን ለማራዘም ጥረት ማድረጋቸው አይቀርም፡፡ አንድነትህንና ፅናትህን ለማደፍረስ በውስጣችን የሚታዩ ችግሮችን እንደ ዕድል ለመጠቀም እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ አልፎ አልፎ የሚታየውን ከባቢያዊነትም ይሁን በሃይማኖት ስም በመካከልህ ልዩነት ለመፍጠር ያላሳለሰ ተግባር እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ ይህን ለማስጽፈፀም ታስቦ የሚላከው ባንዳ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም፡፡ ይህ እንደሚሆን ተገንዝበህ እንደወትሮህ አንድነትህን አጠናክረህ፣ በአንድ ላይ ሆነህ ለላቀ ትግል ተዘጋጅ፡፡ የምንጊዜም ዋስትናህና የድል አድራጊነት ምስጢር አንድነትህ፣ መስመርህና ፅናትህ ነው፡፡ የትግራይ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ባለሃብቶችና ምሁራን አሁንም እንደቀድሞ በአንድነት ፀንታችሁ ሊኖረን ለሚችለው ትግል በላቀ ደረጃ ልትዘጋጁ ይገባል፡፡ መላው የድርጅቱ ኣባላትና አመራሮችም የላቀ ፅናትና ተነሳሽነት የሚጠይቀውን ትግል ህዝባችንን ይዘን ወደ ዘላቂ ድል ለመገስገስ መሪ ሚናችሁን ልትፈፅሙ ይገባል፡፡ ከዚህ ባለፈ የትግራይ ህዝብ ህልውናና ደህንነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ትግል የነበረውን የትግል አቅሞች ሁሉ ለማንቀሳቀስ ይሰራል፡፡ በትግራይ ውስጥ ካሉ ፖለቲካዊ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበራትም በጋራ ለመስራት ህወሓት የተለየ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ሊያረጋግጥላችሁ ይወዳል፡፡የተከበርክ የትግራይ ህዝብ፤የህወሓት ማእላዊ ኮሚቴ በስፋት ካያቸው መሰረታዊ ጉዳዮች አንዱ በሀገራችን እየታየ ያለው ፈጣን አደጋና ወዲፊትም ሊኖረው የሚችል አጠቃላይ ሁኔታ የሚመለከት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በአገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች እየተበራከቱ፣ ጥፋት በጥፋት ላይ እየተደራረበ፣ የጥፋቱ ስፋትና መጠን በየቀኑ እየጨመረ ወደ ከፋ አገር የመበተን ደረጀ እየደረሰ ነው፡፡ አደጋው ወደ ከፋ ደረጃ እንዲሄድ እያደረገ ያለው አንዱ ምክንያት የፓርቲ ውህደት ለመፈፀም እየተደረገ ያለው የችኮላ እንቅስቃሴ ነው፡፡ የፓርቲ ውህደት ጥያቄ በኢህአዴግ ውስጥ በተለያየ ጊዚያት እየተነሳ የቆየና ይህንን ለማድረግ ደግሞ ሊሟሉ የሚገባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች እንዲታዩና በጥናት ላይ በመመስረት እንዲመለሱ መግባባት ላይ የተደረሰበት ጉዳይ ነው፡፡ ህወሓትም ቢሆን በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ የተለየ እምነት አልነበረውም፡፡ ሆኖም ግን ይህን ለማድረግ በሁሉም መሰረታዊ የመስመር ጥያቄዎች፣ ፕሮግራም፣ ስትራቴጂ ወደ አንድ የሚያስተሳስር አመለካካተና እምነት በሁሉም እህት ድርጅቶች ሲፈጠር ብቻ ነው መተግበር የሚችለው፡፡ አንድ ሊያደርግ የሚችል የጋራ የአመለካከትና የተግባር አንድነት በሌለበት ወቅት አንድ ድርጅት እንደ ድርጅት መጠን ህልውና ሊኖረው አይችልም፡፡ ከውህደት በፊት የሚያዋሃህድ አመለካከትና እምነት መለየት አለብን፡፡ ኢህአዴግንና አገርን እየበተኑ ካሉት የተገዙ ደባል አመለካከቶች የሚለይ መስመር እና አጥር በጠራ መልኩ ሳይለይና ሳይቀመጥ ውህደትን ማሰብ አይቻልም፡፡ በደፈረሰ አመለካከትና በአንድነት ሊሰምሩ በማይችሉ እሳትንና ጭድ አስተሳሰቦችን በተሸከመ ኢህአዴግ አይደለም ውህደት ቀርቶ በግምባርነት ለመቀጠል የማይችል የተበተነ ድርጅት ነው አሁን ያለው፡፡ እንደዚህ ያለ የተበተነ ድርጅት ወደ አንድ ፓርቲ ውህደት ይመጣል ብሎ ማሰብ በራሱ ድርጅቱን ከመበተን አልፎ አገርን የሚበትን ተግባር ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ከዚህም አልፎ በቅርቡ ከግንባሩ እምነትና መተዳደሪያ ደንብ ውጭ የፓርቲ ውህደት ለመፈፀም እየተደረገ ያለው ሩጫ ችግሩ እንዲባባስ የሚያደርግ ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አካሄድ እየሰፋ መምጣቱን የሚያሳይ ነው፡፡ የቅርፅ ውህደት ብቻ ሳይሆን በይዘትና በያዘው ፕሮግራሙ በመሰረቱ የተለወጠ አዲስ ፓርቲ ለመመስረት ነው ጥረት እየተደረገ ያለው፡፡ ይህ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝቦች ኢህአዴግ ለያዘው ፕሮግራም መሰረት አድርገው የሰጡት አገርን የመምራት ስልጣን ያከትማል ማለት ነው፡፡ አገርን ለመምራት ሓላፊነት ያልተሰጠው አዲስ ፓርቲ እንዲመሰረት ነው እየተደረገ ያለው፡፡ እንዲህ ያለ አዲስ ፓርቲ በሃገራችን ፖለቲካዊ ድርጅቶች የምዝገባ ህግ ያላለፈ፣ በህዝቦች ፈቃደኝነት በስልጣን ላይ ለመቆየትም ሆነ ስልጣን ለመያዝ ለመወዳደር የማይችል ህገ-ወጥ ድርጅት ነው የሚሆነው፡፡ በመሆኑም በውህደት ስም በፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ መንገድ አዲስ አሃዳዊ ድርጅት ሊመሰረት አይገባም፡፡ በሁሉም መለኪያዎች አንድ ፓርቲ ለመሆን የሚያስችል መነሻና ምክንያት በሌለበት ኢህአዴግን አፍርሶ ሌላ ፓርቲ ለማቋቋም ማሰብ አገርን የሚበትን ተግባር ነው፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ እንደ ግንባር ተደራጅቶ ችግሮችን በትግል እየፈታ አገር ሊመራ ይገባል፡፡ ከጊዜ አንፃርም ይህ ሊቆይ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ አጋር ድርጅቶችም በውህደት ስም እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ህልውናችሁን የሚያጠፋ መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል፡፡ ይሁን እንጂ አጋር ድርጅቶች ወደ ኢህአዴግ በሙሉ አባልነት ገብታችሁ በጋራ ትግልና ጥረት አገርን የሚያድን ተግባር ሊትፈፅሙ እንደሚገባ ህወሓት በፅናት ያምናል፡፡ ከዚህ ውጭ ህወሓት በእንደዚህ ያለ አገርን የሚበትን ተግባር ውስጥ ገብቶ ሊንቦጫረቅ እንደማይፈልግ ሊታወቅ ይገባል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በውህደት ስም ኢህአዴግን ለማፍረስ የሚደረገው እንቅስቃሴ ሓላፊነት በተሞላበት ተገቢውን ትግል እንድታደርጉ ህወሓት ጥሪውን ያቀርብላችኋል፡፡የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችህገ መንግስታችንና ህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓታችን የሚሸረሽሩና የሚጥሱ ተግባራት በየቀኑ ማየት የተለመደ ተግባር ሆኗል። በዚሁ ወቅት የትምክህት ሐይሎች በአመለካከትና በተግባራዊ እንቅስቃሴ ጉልበት ፈጥረው አገር የሚያምሱበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በብዙ የአገራችን አከባቢዎች የሰላም እጦት እየተስፋፋ፣ በዚሁም ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ መንግስት የማይቆጣጠራቸው አከባቢዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ። ለመብቱና ለማንነቱ ለታገለ ህዝብ በርካታ ግፍና በደል የሚፈፀምበት፣ ዜጎች በእርጋታ የማይኖሩበት፣ በማንነታቸው ምክንያት በዜጎች ላይ ግፍ የሚፈፀምበት፣ ለህይወታቸውና ንብረታቸው ዋስትና ያጡበት፣ በዚች አገር ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ህውከትና መፈናቀል የተበራከተበት፣ መንግስት የዜጎች ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እየተቸገረ የመጣበት፣ ከዚህ አልፎም የአገሪቱ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች እና የአማራ ክልል አመራሮች እስከመግደል ተግባር የተፈፀመበት፣ ሌላ ቀርቶ የነዚህ ምርጥ ጀነራሎችና መሪዎች ግድያ እንኳን በአግባቡ በማጣራት ለህዝብ ግልፅ ለማድረግ በማይቻልበት፣ የህግ በላይነት እየተጣሰ፣ የዜጎች ህይወት መጥፋትና መፈናቀል ማዳን የማይችል መንግስትና ስርዓት ወደ መሆን ተሸጋግረዋል ማለት ብቻ ሳይሆን ይህንን ለማስቆምና ለመግታትም ዋና ተግባሩ ያላደረገና ቁርጠኝነትም የሌለው ሆኗል።የህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ወደ ጎን በመተው ሌላ ጉዳይ ላይ በማትኮር የአገሪቱ ኢኮኖሚ እየተዳከመ ወደ ከፍተኛ ድቀትና ማሽቆልቆል እየገባ ነው። የአገሪቱ ልማት የሚመራውና የሚደግፈው አጥቶ፣ ልማታዊ አቅሞች እየመከነ፣ ስራ አጥነት እየተባባሰ፣ የህዝብ ኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰማይ የሚሰቀልበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በዚህ ምክንያትም ችግር በችግር ችግር እየተመሰቃቀለና እየተደራረበ በመሄድ ላይ ይገኛል። የህዝባችን ዋስትና የሆነው ህገ መንግስታችንና ህብረ ብሄራዊ ፌዴራል ስርዓታችን በማፍረስ አሃዳዊ ስርዓትን መልሶ ለመትከል እየሰራ ያለውና በዋናነት ይህንን አደጋና ጥፋት እየፈጠረና እየመራ የሚገኘው ትምክህተኛው ሀይልና በዙርያው የተሰባሰበ ፀረ ህዝብ ሐይል ነው።በውስጣቸው ያለውን ድክመትና ፀረ-ህዝብ ተግባር ከመፍታትና ከማጥራት ይልቅ የሁሉም ችግር “ሶስተኛ ወገን አለው” የሚል የቆየ ዘፈን ሲደጋግሙ እየታየ ነው፡፡ ለአማራ ህዝብ የማይመለከተውና ያልተገባ ምስል እያስያዙና “ትምክህተኛ ተብለሃል!” እያሉ በዚህ ተሸፋፍነው በህዝቦች መካከል የቆየውን ዝምድናና ወንደማማችነት ለማደፍረስ እየጣሩ ይገኛሉ፡፡ የአማራ ህዝብ ትምክህተኞችን ታግሎ በእኩልነት የሚኖርባት አዲሲቷ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትመሰረት የማይተካ ሚና የተጫወተ ህዝብ ነው፡፡ የትግራይና የአማራ ህዝቦች በጋራ ትግላቸው ትምክህተኛውን አሸንፈዋል፡፡ ለወደፊትም ቢሆን እነዚህ ህዝብ ለህዝብ አጋጭተው እንዲባላ በማድረግ መኖር የሚፈልጉና ሓላፊነታቸውን ትተው ለጥፋት የተሰማሩ ሓይሎች በተደራጀ መንገድ ሊታገላቸው ይገባል፡፡ መላው የሀገራችን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችም ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓታችንን ለማዳን በሚደረገው ወሳኝ ትግል ከማንኛውም ጊዜ በላይ አገራችንን ለማዳን ሊረባረብ ይገባል፡፡ሕብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ሓይሎች የጀመራችሁትን ትግልና ሰፊ ትብብር መድረኮች አማራጭ የሌለው መሆኑን ተገንዝባችሁ ትግላችሁን አጠናክራችሁ ልትቀጥሉበት ይገባል፡፡ ህወሓትም የተጀመረውን ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ሊያረጋግጥላችሁ ይወዳል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሕገ-መንግስት፣ ሰላምና የህዝቦችና የአገርን ደሕንነት በመጠበቅ የላቀ ሓላፊነት ያለብህ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ አገራችን እያጋጠማት ያለውን አደጋ በሚገባ ተገንዝበህ ከጥፋት ለማዳን እያደረገው ያለው ርብርብ፣ ለዚች ልዩ ታሪክና ክብር ያላት ሃገር ሉኣላዊነቷንና ሰላሟን በመጠበቅ ረገድ ዛሬም እንደወትሮ በላቀ ደረጃ ህዝባዊ ሓላፊነትህን ተቋማዊ እንድትህን አጠናክረህ በምታደርገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴም የትግራይ ህዝብና ህወሓት ከጎንህ ሆነው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚፈፅሙ ልናረጋግጥ እንወዳለን፡፡በህገ- መንግስቱ መሰረት ስድስተኛው አገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ በያዝነው ዓመት የግድ መካሄድ ያለበት ነው፡፡ በመሆኑም ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ምርጫው በወቅቱ እንዲካሄድ በተደጋጋሚ አቋማቸውን እየገለፁ ቆይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ምርጫው ለማካሄድ የሚያስችል ምንም ዓይነት ዝግጅት እየተደረገ አይደለም፡፡ “በቂ ዝግጅት አላደረግንም” ተብሎ ምርጫውን ለማራዘም የሚደረገው ጥረት ፈፅሞ ተቀባይነት ሊኖሮው አይችልም፡፡ በአገራችን ያሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ነፃ የመወዳደር ዕድል አግኝተው ህዝብ በነፃ ፍላጎቱ የሚመርጠውን መንግስት ወደ ስልጣን እንዲመጣ በህዝብ ፍፁም ፈቃድ በስልጣን ላይ እንዲቆይ የሚያደርግ ህገ-መንግስታዊ መብት በጥብቅ መከበር አለበት፡፡ ይህ በማይሆንበት ወቅት መላው የአገራችን ህዝቦች መብታችሁንና ሕገ-መንግስታዊ ስልጣናችሁን አደጋ ላይ እየጣለ መሆኑን አውቃችሁ የላቀ ትግል ልታደርጉ በሚጠይቅ አስገዳጅ ጊዜ ላይ እንገኛለን።የተከበርክ የኤርትራ ህዝብ  የትግራይና የኤርትራ ህዝብ ለጋራ መብትና ጥቅም በጋራ የታገሉ ወንድማማች ህዝቦች ናቸው፡፡የነበረውና አሁንም ያለው ዝምድናና መደጋገፍ ወደ ዘላቂ አስተማማኝ ደረጃ ለማድረስ ባለፈው ዓመት የተጀመረው የሰላም ጭላንጭል በዚህ ዓመትም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ በጋራ ለዘላቂ ሰላም ተደጋግፈን ልንሰራ ይገባል፡፡ የጀመርነው አዲስ እፎይታና ሰላም ዋስትና ያለው እንዲሆንም የሁለቱም ህዝቦች ትስስርና ግንኙነት እንዲጠናከር መስራት አለብን፡፡ የትግራይ ህዝብና ህወሓትም ይህንን ለማጠናከር ከነሱ የሚፈለገውን ሁሉ እንደሚፈፅሙ ደጋግመን ልናረጋግጥልህ እንወዳለን፡፡የማንሻገረው ፈተና አይኖርም ዘልአለማዊ ክብርና መጎስ ለስማእቶቻችን!የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴጥቅምት 4/ 2012 ዓ/ምመቐለ
https://waltainfo.com/am/31412/
1,875
5ፖለቲካ
ም/ጠ/ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጣሊያን የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
October 16, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ ም/ጠ/ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጣሊያን የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሮም በሚካሄደው የኢትዮ ጣሊያን የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሓላፊዎችና የንግዱ ማህበረሰብ ልዑካን ቡድንን በመምራት ጣሊያን ተገኝተዋል፡፡በዚህም ሀገራቱ ያላቸውን ዲፕሎማሲና የልማት ትብብሮቻቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከጣሊያን ሴኔት ፕሬዝዳንት ማሪያ ኤልዛቤታ አልበርቲ ጋር በሮም ተወያይተዋል፡፡ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ በተለይም ከኤርትራ ጋር የቆየውን የሻከረ ግንኙነት የተሻለ ለማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተጫወቱት ሚና ለሌሎች ሀገራት በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ የ2019ኙን የዓለም የኖቤል ሽልማት በማሸነፋቸው ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክም አስተላልፈዋል፡፡ጣሊያንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ አብረው በጋራ እንደሚሰሩም በነበረው ውይይት ላይ ተነስቷል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብና የእርሻ ድርጅት ፋኦ ዋና ዳይሬክተር ጄነራል ኩን ዶንግ ዩን ጋር ተወያይተዋል፡፡በውይይቱ ወቅትም ዓለም አቀፉ የምግብና የእርሻ ድርጅት ፋኦ በኢትዮጵያ ያለውን የለውጥ ሂደትና ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎችን እንደሚደግፍ ነው ያረጋገጡት፡፡ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ በሚከፈተው የኢትዮ ጣሊያን የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ተገኝተው ፣ከተለያዩ ተቋማት መሪች ጋርም ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/31413/
172
5ፖለቲካ
የደቡብ ከልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
ፖለቲካ
October 15, 2019
Unknown
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡በጉባኤው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ ጉባኤው የሚካሄደው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የ2019 ዓ.ም የኖቤል ተሸላሚ በሆኑበት ወቅት መሆኑ ለየት እንደሚያደርገው ገልጸው የእንኳን ደስ አሎት መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሸለም የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሽልማት መሆኑን አውስተው የሰላም ዋጋ ምን ያክል ውድና መተኪያ የሌለው መሆኑን በመገንዘብ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ከመሪያችን ጎን መሰለፍ ይገባናል ብለዋል፡፡አፈ ጉባኤዋ በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ እንቀቅስቃሴ ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙትም መልካም ውጤቶችና አዳዲስ ተስፋዎችን ጭምር በህዝቡ ውስጥ መፍጠሩን ገልፀዋል፡፡መንግስት በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ ያሣየው ቁርጠኝነት ይበል የሚያሰኝ ሲሆን ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት እንዲገልጹ፣ የተለያዩ የፖለቲካ አቋሞች እንዲደመጡ ለማስቻል እየተሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ እንደሆነም አንስተዋል፡፡በተጨማሪም በያዝነው በጀት ዓመት ትላልቅ ሀገራዊ ኩነቶች እንደ ምርጫና የህዝብና ቤት ቆጠራ እንደሚካሄድ ገልጸው ፤ ምርጫው የተሳካ እንዲሆን ለማስቻል ከመንግስት በተጨማሪ ህዝብና የምክር ቤት አባላት ሚናቸውን እንዲወጡም አፈ ጉባኤዋ አሳስበዋል፡፡የተያያዝነው 2012 ዓ.ም የዕትዕ የመጨራሻ ዓመት እንደመሆኑ መጠን የቀሩ ተግባራትን ለቅመን በመፈፀምና የለውጡን ጉዞ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ብሎም የህበረተሰባችንን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፎች ርብርብ ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡ጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ውይይቱን የምቀጥል ሲሆን በጧቱ ክፍለ ጊዜ የምክር ቤቱ 5ኛ ዙር 4ኛ ስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ለምክር ቤቱ ከቀረበ በኃላ ምክር ቤቱም ውይይት አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ምክር ቤቱ እስከ ጥቅምት 7፣ 2012 ዓ.ም በሚያካሂደው ስብሰባ በክልሉ መንግስት የዓመቱ የትኩረት አቅጣጫዎችን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።ዘገባው የክልሉ ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31408/
237
5ፖለቲካ
21ኛዉ ዓመታዊ የጤና ዘርፍ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
October 15, 2019
Unknown
21ኛዉ ዓመታዊ የጤና ዘርፍ ጉባኤ “ዘርፈ ብዙ ትብብር ለጤናማና የበለጸገች ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ነው በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን በ2011 በጀት ዓመት በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የጋጠሙ ችግሮችና የ2012 ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡በዚህም መንግስት የዜጎቹን ጤና የማሻሻል ሥራን ቁልፍ ተግባሩ አድርጎ በትጋት በመስራት ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት ሚኒስትሩ ፤ በዚህም የጤና ዘርፍ የሚመራበትን የጤና ፖሊሲና ስትራቴጂ በመቅረጽ የዜጎቹን ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡በቅርቡ ይፋ በሆነው እአአ የ2019 መለስተኛ የሥነ-ህዝብና የጤና ዳሰሳ ጥናት የጤና አገልግሎት አሰጣጡ ውጤት እንደሚያሳየው 5ኛ የልደት ዓመታቸው ሳያከብሩ የሚሞቱ ህፃናት እአአ በ2016 ከነበረው 67 ሞት ከ1 ሺህ፤ በህይወት ከተወለዱት ወስጥ ወደ 55 ሞት ከ1 ሺህ ወርዷል፡፡ይህ ከፍተኛ መሻሻል የታየበት ሲሆን ለዚህ ውጤት መመዝገብ በእናቶችና ህፃናት ጤና በተከታታይ ዓመታት የተተገበሩ ፕሮግራሞች መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው ነው ሚኒስትሩ ያነሱት፡፡የሥርዓተ ምግብን አገልግሎት በተመለከተ የመቀንጨር፣ መቀጨጭ እና ክብደት መቀነስ መለኪያዎቻችን በየጊዜው መሻሻል እንዳሳየና ለዚህም በመለስተኛ የሥነ-ህዝብና የጤና ዳሰሳ ጥናት በተገኘው መረጃ መሰረት መቀንጨር እአአ 2016 ከነበረበት 38 ከመቶ በ2019 ወደ 37 ከመቶ መቀነሱን አንስተዋል፡፡የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል ጤና ቢሮዎችና አጋሮቹ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ባለፉት ዓመታት መዘናጋት እየጨመረ የመጣውን የኤችኤቪ በሽታ ስርጭት ለመግታት ለ2020 የተቀመጠውን የሶስቱን ዘጠናዎች ዒላማ ለማሳካት መጠነ ሰፊ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡በጉባኤው ላይ የፌዴራል እና የሁሉም ክልል የጤና ቢሮ ኃላፊዎች እና ተወካዮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እና የውጭ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ለአራት ቀናት በሚቆየው ጉባኤው የ2011 የጤናው ዘርፍ ስራ አፈፃፀም እና የ2012 የጤና እቅዶች ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32797/
226
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሸጎሌ የአውቶብስ ዴፖ ተመረቀ
ቢዝነስ
October 15, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመደበለት 555 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የሸጎሌ የአውቶብስ ዴፖ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡ዴፖው የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ኢንጂነር ሰለሞን ኪዳኔ እንዲሁም ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው የተመረቀው፡፡የአውቶቢስ ማቆሚያ ዴፖው የራሱ ገራዥ ፣ መኪና ማጠቢያ ፣ ነዳጅ ማዲያ በውስጡ ያካተተ ሲሆን በተገነባለት ህንጻ ውስጥ የንግድ ማዕከላት ፣ የመዝናኛ ቦታዎችና አረንጓዴ  ሥፍራዎች ተካተዋል፡፡ዴፖው ከቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነ ንግስት ጀምሮ በእንጨትና ቆርቆሮ ተሰርቶ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን አሁን በዘመናዊ መልክ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡ዴፖው አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ከአውቶብስ ደህንነት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን እንደሚፈታ እና ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችልም ነው በምረቃው ወቅት የተገለፀው፡፡ለተሸከርካሪ እጥበት የሚውለው ውሃ ከከርሰ ምድር የተገኘ መሆኑም ተመላክቷል፡፡212 አውቶብሶችን በአንድ ጊዜ ለማቆም እንደሚያስችል የተነገረው ዴፖው፤ 52 ሺህ ካሬ ሜትር ስፍራ ላይ ያረፈ ነው፡፡ 
https://waltainfo.com/am/24007/
131
3ቢዝነስ
የሕዳሴው ግድብ የማመንጨት አቅም እንደማይቀንስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ
ቢዝነስ
October 15, 2019
Unknown
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የማመንጨት አቅሙ ሊቀንስ ነው ተብሎ እየተነገረ ያለው መረጃ ትክክል አለመሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በ16 ተርባይኖች በዓመት በአማካይ 15 ሺህ 670 ጊጋዋት በሰዓት ኃይል የማመንጨት ዕቅድ ተይዞ ወደ ግንባታ መገባቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይገልፃል፡፡ይሁንና በአሁኑ ሰዓት አማራጭ ጥናቶች ከተደረጉ በኋላ የተርባይኖቹን ቁጥር በመቀነስ እና የማመንጨት አቅማቸውን በመጨመር ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ መሥራት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የግድቡ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ለኢቲቪ ተናግረዋል።በዚህም ቀደም ሲል ከታቀዱት 16 ተርባይኖች አሁን 3ቱ መቀነሳቸውን ነው የገለጹት። የአንድ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ የማመንጨት አቅም የሚወሰነው ግድቡ በሚይዘው የውኃ መጠን እና ውኃው ከተርባይን ማዕከል በሚኖረው ከፍታ ላይ እንጂ በተርባይኖች ብዛት አለመሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡የተርባይኖች ቁጥር በጨመረ ቁጥር የሚጨምረው ኃይል እንደማይኖርም አስምረውበታል።በዚህም 16 የነበሩ ተርባይኖች ወደ 13 በማድረግ በዓመት የሚጠበቀውን 15 ሺህ 670 ጊጋዋት በሰዓት የማመንጨት አቅም በመፍጠር ቀድሞ በነበረው መንገድ ያንኑ ኃይል ማመንጨት እንደሚቻል መደምደሚያ ላይ ተደርሶ እየተሠራ መሆኑንም ኢንጅነር ክፍሌ ገልፀዋል።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ሞገስ መኮነን በበኩላቸው “ግብፆች ከዚህ በፊት በነበረ ድርድራቸው የግድቡን ከፍታ ቀንሱ፤ ውኃ የሚይዘውን ጊዜ አራዝሙ” የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማቅረብ እና ተፅዕኖ ለማሳደር ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበር አስታውሰው ከዚህ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩት መረጃዎች ትክክል አለመሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ግድቡ የሚይዘው የውኃ መጠን፣ ከፍታው እና የማመንጨት አቅሙ ሳይቀንስ በ13 ተርባይኖች ውጤታማ በሆነ መልኩ ቀድሞ ማመንጨት የታሰበውን ኃይል ለማመንጨት በሚያስችል ሁኔታ እየተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል።በአሁኑ ጊዜም የግድቡ ግንባታ 68.5 በመቶ ላይ መድረሱን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/24008/
218
3ቢዝነስ
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከፊንላንድ ፕሬዝደንት ሶሊ ኒኒስቶ ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
October 15, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የፊንላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሶሊ ኒኒስቶን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡የፊንላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሶሊ ኒኒስቶ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ኦፊሴላዊ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ማታ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተጨማሪ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮች ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ፕሬዝዳንት ሶሊ ኒኒስቶ በአየር ንብረት ለውጥ እና የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረታቸውን ባደረጉ ሁለት ትላልቅ ኮንፈረንሶች ላይም ንግግር ያደርጋሉ።እንዲሁም በፊንላንድ ድጋፍ የሚደረግለትን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።ምንጭ፡-ኢቢሲ
https://waltainfo.com/am/31409/
74
5ፖለቲካ
የአፍሪካ አገራት የህፃናትን መብት ለመጠበቅ የገቧቸዉን ስምምነቶች እንዲያከብሩ ተጠየቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 15, 2019
Unknown
በጦርነት ተጎጂ የሆኑ ህፃናትን መታደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በሚመክረው ዉይይት ባለፉት 20 አመታት በጦርነት ምክንያት 5 ሚሊየን ህፃናት በሞቱባት አፍሪካ የህፃናት መብት እንዲከበርና ችግሩ እልባት እንዲያገኝ ተጠይቋል፡፡በዉይይት መድረኩ ከኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ናይጄሪያና ኮንጎ የተገኙ ህፃናት ተሳትፈዋል፡፡ በዉይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የሴቭ ዘ ችልድረን ዳይሬክተር ያ ቬል አገራት የህፃናትን መብት ለመጠበቅ የገቧቸዉን አለምአቀፍ ስምምነቶች ሊያከብሩ ይገባል ብለዋል፡፡የአፍሪካ ህብረት ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ቶማስ ክዌሲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያገኙት የሰላም የኖቤል ሽልማት ለሰላም ያደረጉት ጥረት ማሳያ እንደሆነ ተናግረዉ ለአህጉሩ ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል ብለዋል፡፡በአፍሪካ የመሳሪያ ድምፅ እንዳይሰማ የተደረሰዉ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ዑመድ በበኩላቸዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአፍሪካ ሰላም እንዲሰፍን እየሰሩ መሆኑንና የኖቤል ሽልማቱም ይህን እንደሚያሳይ ተናገረዋል፡፡በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት አመታት በነበረዉ የዉስጥ መፈናቀል ችግር የደረሰባቸዉን ህፃናት መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32798/
129
0ሀገር አቀፍ ዜና
የደቡብ ክልል በኮንታ ልዩ ወረዳ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሐዘን ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 15, 2019
Unknown
ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በኮንታ ልዩ ወረዳ ሰሞኑን እየጣለ ያለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከተሎ በመሬት ናዳ ምክንያት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ በደረሰው ከፍተኛ አደጋ የደቡብ ክልል የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።በአደጋው የበርካታ ዜጎቻችን ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ ለሟች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች የክልሉ መንግስት መጽናናትን ተመኝቷል።የክልሉ መንግስት የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ አስመልክቶ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላትን ወደ ስፍራው ያንቀሳቀሰ መሆኑን እና ለተጎጂ ቤተሰቦች አልባሳት እና መድሀኒቶች ወደ ስፍራው መላኩንም ክልሉ አስታውቋል።በቀጣይ ተጨማሪ ድጋፍ ወደ ስፍራው እንደሚላክና በአካባቢው የሚጥለው ከባድ ዝናብ የተነሳ ለመሰል አደጋ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከአደጋ የመከላከል ስራ ትኩረት የሚሰጠው እንደሚሆንም የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ገልጿል።በልዩ ወረዳ ከባድ ዝናብን ተከትሎ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱም ተገልጿል።
https://waltainfo.com/am/32796/
113
0ሀገር አቀፍ ዜና
አሜሪካ ቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች
ቢዝነስ
October 15, 2019
Unknown
አሜሪካ ቱርክ በሶሪያ ድንበር ላይ እየወሰደችው ላለው የጦር ጥቃት ምላሽ ሁለት የቱርክ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችንና ሶስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቱርኩ አቻቸው ጣይብ ኤርዶጋን ስልክ የደወሉ ሲሆን፣ የስልክ ልውውጡም በፍጥነት ተኩስ የሚቆምበት ላይ እንደነበር ምክትል ፕሬዝዳንቱ ማይክ ፔንስ ተናግረዋል።ማይክ ፔንስ አክለውም ወደ ቱርክ " በተቻለ ፍጥነት" እንደሚሄዱ ተናግረዋል።የሶሪያ ጦር ወደ ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የገባ ሲሆን፣ ይህም በቱርክ ከሚረዱ አማፂያን ተግዳሮት ገጥሞታል።የሶሪያ ጦር ወደ አካባቢው የተሰማራው እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ የአሜሪካ አጋር ከነበረው በኩርዶች ከሚመራው ጦር ጋር ከተደራደረ በኋላ ነው።ቱርክ ከሶሪያ ጋር በሚያዋስናት አካባቢ ጦሯን አሰማርታ ውጊያ የጀመረችው በአካባቢው "ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና" ለመፍጠር መሆኑን ደጋግማ ትናገራለች። ይህ "ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና" ስፍራ በሶሪያ ግዛት ውስጥ 30 ኪሎ ሜትርን የሚሸፍን ሲሆን፣ በዚሁ ቦታ ቱርክ በአሁን ሰዓት በግዛቷ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ 2 ሚሊየን የሶሪያ ስደተኞችን የማስፈር ሃሳብ አላት።እነዚህ ስደተኞች አብዛኞቹ ኩርዶች ስላልሆኑ ይህንን የቱርክ ሀሳብ የሚተቹ አካላት ጉዳዩ አንድ ብሔር ላይ ያተኮረ ጥቃት ነው ሲሉ የአንካራን መንግሥት ይተቻሉ።ሰኞ ዕለት ከዋሺንግተን ለጋዜጠኞች ቃላቸውን የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ ስቴቨን ማንቺን ማዕቀቡን "በጣም ጠንካራ" በማለት የቱርክ ኢኮኖሚን እንደሚጎዳ ተናግረዋል።የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ ላይ ማዕቀቡ ሁለት የቱርክ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችን የሚመለከት ሲሆን፣ እነዚህ ተቋማትም የመከላከያና የኃይል እንዲሁም የሀገር ውስጥ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ናቸው ብለዋል።"የቱርክ መንግሥት ባህሪ ንፁኃንን ለአደጋ ያጋለጠ እንዲሁም ቀጠናውን የሚያተራምስ ነው። በተጨማሪም አይኤስን ለማሽመድመድ የሚደረገውን ጥረት ፍሬ ቢስ የሚያደርግ ነው" ይላል መግለጫው።በግጭቱ እስካሁን ድረስ 160 ሺህ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው መሸሻቸውን የተባበሩት መንግሥታት ያስታወቀ ሲሆን 50 ንፁኃን በሶሪያ ውስጥ 18 ደግሞ በደቡብ ቱርክ ድንበር ላይ መገደላቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።የኩርድ ኃይሎች 56 ተዋጊዎቻቸው መገደላቸውን የተናገሩ ሲሆን ቱርክ በበኩሏ 3 ወታደሮቿና 16 አፍቃሪ ቱርክ አማፂያን መሞታቸውን ገልጻለች።ቱርክ ወደ ሶሪያ ጦሯን ያዘመተችው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በድንገት በስፍራው የነበረ የአሜሪካ ጦር እንዲወጣ ካዘዙ በኋላ ነው።ይህ የአሜሪካ እርምጃ ቱርክ በአካባቢው በሚገኙ በኩርዶች የሚመራው ጦር ላይ ጥቃት ለመክፈትና የድንበር ከተሞችን በእጇ ለማስገባት ሰበብ ሆኗታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/33564/
285
3ቢዝነስ
በሱዳን የተጀመረዉ የሰላም ድርድር በሁለቱም ወገኖች ዕርቅ ለማዉረድ ያላቸዉን ፍላጎት ማሳያ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
ፖለቲካ
October 15, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ሱዳን በተካሄደዉ የዕርቅ ምክክር መድረክ ላይ ከጥቂት ወራት በፊት የሲቪል መንግስት ለመመስረት የተፈረመዉን ስምምነት አንስትዉ ዛሬ በሱዳን የሽግግር መንግሥት እና የሱዳን ታጣቂዎች ቡድን መካከል የተጀመረዉ የሰላም ድርድር በሁለቱም ወገኖች ሰላም ለማምጣትና ዕርቅ ለማዉረድ ያላቸዉን ፍላጎት ማሳያ ነዉ ብለዋል::ሁለቱም ወገኖች ስምምነት ላይ ደርሰዉ ያላቸዉን አቅም አካታች የሆነችና የበለጸገች ሱዳን ለመገንባት እንዲያተኩሩ ጥሪ አቅርበዋል::ጠቅላይ ሚንስትሩ በደቡብ ሱዳን የነበራቸዉን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት መሪዎች ምክክር መድረክ አገባደዉ አዲስ አበባ መመለሳቸውን ከጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31405/
84
5ፖለቲካ
የተባበሩት የአረብ ኢምሬትስ አዲስ ለሚገነባው የፓርላማ ህንፃ 370 ሚሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ
ፖለቲካ
October 15, 2019
Unknown
የፌዴራል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መንግሥት ኢትዮጵያ ለምታስገነባው አዲስ የፓርላማ ህንፃ 370 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል መግባቱን አስታወቀ::በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ ተስፋዬ ዳባ እንደገለፁት፤ የምክር ቤቱ ዲፕሎማሲ ሥራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ማዕከል በማድረግ የመንግሥትን የልማት ግብ ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው::በምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የሚመራ የልዑካን ቡድን በቅርቡ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ያደረገው የሥራ ጉብኝትና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ውጤታማ እንደበርም አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች መግባባት ላይ ደርሰው የአረብ ኢምሬትስ ገንዘቡን ለመርዳት ቃል በመግባትም በወዳጅነት መፈራረም ችለዋል፡፡የአዲሱ የፓርላማ ህንፃ ግንባታ ለምክር ቤቱ አባላት ጠቃሚ ሚና እንዳለው ያብራሩት አቶ ተስፋዬ፤ ለአባላቱ ሥራቸውን በአግባቡ ለማከናወን ምቹ ዐውድ የሚኖረውና ሥራቸውን በተሻለ መልኩ እንዲያከናውኑ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የልዑካን ቡድን ከአረብ ኢምሬትስ አቻቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ሁለቱ ሀገራት በፓርላማዎቻቸው መሃል የሚደረግ ትብብርን ለማሳደግና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውንም ገልጸዋል፡፡የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ግንኙነት በሁሉም አቅጣጫ እየተሻሻለ እና የልማት ትብብሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ ዕድገት እያሳየ ይገኛል:: በአገልግሎት ላይ ያለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህንፃ አባላት እንዲሰበሰቡ እኤአ በ1930ዎቹ የተሠራ መሆኑ ይታወሳል፡፡ (ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
https://waltainfo.com/am/31406/
169
5ፖለቲካ
የሃዋሳን የቀድሞ ሰላምና እና መልካም ስም ለመመለስ እየሰራ መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር ገለፀ
ፖለቲካ
October 15, 2019
Unknown
የሃዋሳ ከተማ ከ2010 ጀምሮ በገጠማት የሰላም እጦት የጠለሸዉ ስሟን ለማደስ የከተማ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑን ከንቲባዉ ገለፁ፡፡የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ለዋልታ እንደገለፁት በከተማዋ ገፅታዋን የሚገነቡ አረንጓዴ ፓርኮች ልማት ስራ የተጀመረ ሲሆን በከተማዋ የሚገኙ 4ሺ የሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተሰራ ነዉ፡፡በ1952 ዓ.ም የተቆረቆረችዉ ሃዋሳ ዘንድሮ 60ኛ አመቷን የምታከብር ሲሆን በልማት፤ በኢንቨስትመንት፤ በፍቅርና መቻቻል የነበራትን ተምሳሌትነት ለመመለስ ይሰራል ብለዋል፡፡በከተማዋ አዲስ የተዋቀረዉ አስተዳደር ባለፉት ጊዜያት በተከሰቱ ጉዳዮችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከነዋሪወች ጋር በየደረጃዉ መድረክ ከፍቶ አየተወያየ መሆኑም ተመልክቷል፡፡በአሁኑ ሰዓት በኮማንድ ፖስት ስር የምትገኘዉ ሃዋሳ ወደቀድሞ ሰላሟ ሙሉ በሙሉ እየተመለሰች መሆኑን ነዋሪዎቿ ለዋልታ ገልፀዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/31407/
96
5ፖለቲካ
የቱኒዚያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ካይስ ሳይድ በሰፊ የድምፅ ልዩነት አሸነፉ
ፖለቲካ
October 15, 2019
Unknown
የሕግ ፕሮፌሰር የሆኑት ካይስ ሳይድ 72.71 ከመቶ ድምጽ በማግኘት የቱኒዚያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሰፊ ልዩነት ማሸነፍ መቻላቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አረጋግጧል፡፡አንድ ሚሊዮን ድምፅ ካገኙት ተፎካካሪያቸው ናቢል ካሮይ በተሻለ ፕሮፌሰር ሳይድ 2.7 ሚሊዮን ድምጽ ማግኘታቸውን ነው ኮሚሽኑ የገለፀው፡፡አብዛኛውን የምርጫ ዘመቻ በእስር ላይ ያሳለፉ ካሮይ ሰኞ ማለዳ ላይ የምርጫ ጉዟቸውን በሽንፈት ደምድመዋል፡፡እሁድ እለት የምርጫ ውጤት ከታወቀ በኋላ አሸናፊ የሆኑት ካይስ ሳይድ የተገኘውን ድል “በሕገ-መንግስታዊ ህጋዊነት ውስጥ ያለ አብዮት” ሲሉ ነው የገለፁት።90 ከመቶ የሚሆኑት ከ18 እስከ 25 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች ለ61 አመቱ ካይስ ሳይድ ድምጽ እንደሰጡ ነው የተገለፀው። (ምንጭ፡- አልጀዚራ)
https://waltainfo.com/am/33345/
87
5ፖለቲካ
የጅግጅጋ – ሃርሞካሌ (104 ኪ.ሜ) የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 14, 2019
Unknown
ከጅግጅጋ እስከ ሃርሞካሌ (104 ኪ.ሜ) የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረከጅግጅጋ ከተማ እስከ ሃርሞካሌ መገንጠያ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ሥራ ተጀመረ፡፡ለመንገድ ፕሮጀክቱ ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ላይ የውል ስምምነት የተፈረመ ሲሆን ላለፉት ዘጠኝ ወራትም የግንባታ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱ ተመልክቷል፡፡የኮንክሪት አስፋልት መንገድ ግንባታ የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ትናንት በጅግጅጋ ከተማ ሲካሄድ እንደተገለጸው ከጅግጅጋ እስከ ሃርሞካሌ መገንጠያ የሚገነባው መንገድ 104 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው።መንገዱ ከድሬዳዋ እስክ ደወሌ ከተሰራው የክፍያ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ሲሆን ቀደምሲል ከጅግጅጋ ተነስቶ  በሐረር-ደንገጎ በኩል 202 ኪሎ ሜትር የነበረውን ጉዞ ወደ 99 ኪሎ ሜትር ይቀንሳል፡፡የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጅክቱ ከመንግስት በተመደበ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚሰራ ተናግረዋል።አዲስ የሚገነባው መንገድ ከጅግጅጋ ተነስቶ ቱሊ ጉሌድ፣ ሎወናጂ፣ ዱልዓድ፣ ሰመካብ፣ ሃርሙካሌ የተባሉ አምስት የወረዳና የቀበሌ ከተሞችን የሚያገናኝ ነው።ግንባታውን የሚያከናውነው ሥራ ተቋራጭ “የቻይና ሲቪል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን” ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን የሚያከናው ደግሞ “ኤስ.ጂ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር” ነው፡፡የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስተፌ ሙሀመድ በግንባታ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ፕሮጅክቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ የተሳለጠ የትራስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ያደርጋል።በተለይ ለአካባቢው አርሱ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የሰብል እና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶቻቸው ተገቢውን ዋጋ እንዲያገኙ በማስቻልም የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማለታቸውን ኢዜአ ነው የዘገበው።ከጅግጅጋ እስከ ሃርሞካሌ (104 ኪ.ሜ) የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረ—————————-ከጅግጅጋ ከተማ እስከ ሃርሞካሌ መገንጠያ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ሥራ ተጀመረ፡፡ለመንገድ ፕሮጀክቱ ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ላይ የውል ስምምነት የተፈረመ ሲሆን ላለፉት ዘጠኝ ወራትም የግንባታ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱ ተመልክቷል፡፡የኮንክሪት አስፋልት መንገድ ግንባታ የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ትናንት በጅግጅጋ ከተማ ሲካሄድ እንደተገለጸው ከጅግጅጋ እስከ ሃርሞካሌ መገንጠያ የሚገነባው መንገድ 104 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው።መንገዱ ከድሬዳዋ እስክ ደወሌ ከተሰራው የክፍያ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ሲሆን ቀደምሲል ከጅግጅጋ ተነስቶ  በሐረር-ደንገጎ በኩል 202 ኪሎ ሜትር የነበረውን ጉዞ ወደ 99 ኪሎ ሜትር ይቀንሳል፡፡የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጅክቱ ከመንግስት በተመደበ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚሰራ ተናግረዋል።አዲስ የሚገነባው መንገድ ከጅግጅጋ ተነስቶ ቱሊ ጉሌድ፣ ሎወናጂ፣ ዱልዓድ፣ ሰመካብ፣ ሃርሙካሌ የተባሉ አምስት የወረዳና የቀበሌ ከተሞችን የሚያገናኝ ነው።ግንባታውን የሚያከናውነው ሥራ ተቋራጭ “የቻይና ሲቪል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን” ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን የሚያከናው ደግሞ “ኤስ.ጂ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር” ነው፡፡የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስተፌ ሙሀመድ በግንባታ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ፕሮጅክቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ የተሳለጠ የትራስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ያደርጋል።በተለይ ለአካባቢው አርሱ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የሰብል እና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶቻቸው ተገቢውን ዋጋ እንዲያገኙ በማስቻልም የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማለታቸውን ኢዜአ ነው የዘገበው።
https://waltainfo.com/am/32794/
389
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሰላም ጉዳይ ጊዜ እንደማይሰጠው ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 14, 2019
Unknown
የዕርቅና የሰላም ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው በመሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና ታላላቅ ሰዎች ዕርቅ በማምጣቱ በኩል ብዙ እንደሚጠበቅባቸው የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው አስታውቀዋል።የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው የብሔራዊ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ዛሬ በጽ/ቤታቸው አነጋግረዋል፡፡ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሻገሩ የመጡ ቁርሾዎችን እና አለመግባባቶችን አክመን ለነገ ለሀገራችን ትውልድ ኢትዮጵያ የፍቅር፣ የመግባባት እና ሁሉም ዜጎቿ በእኩል ተባብረው የሚኖሩባት ሀገር አድርገን የምናስረክብበት ጊዜው አሁን ነው ብለዋል።የክልሉን ሰላም ማስፈንና መግባባት መፍጠር፣ አብሮነትን ማጠናከር፣ የተፈጠሩ ግጭቶችን በዕርቅ መፍታት ከሁሉም ተቀዳሚ ስራችን ሲሆን በዚህም አመርቂ ውጤትም እየታየበት በመሆኑ በእናንተ ሲደገፍ ደግሞ የበለጠ አቅም ይሆነናል ሲሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አክለዋል።የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስና የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነ ኢየሱስ ሱራፌል በበኩላቸው፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ በህዝቦቿ አንድነት እና ጥረት ብልጽግና አንድነቷ ተጠብቆ ሰላሟ እንዲረጋገጥ ዕውነትና ፍትህ ላይ ያተኮረ ዕርቀ ሰላም ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል።ምንጭ፡- የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬቴሪያት
https://waltainfo.com/am/32795/
141
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጃፓን ነፋስ በቀላቀለ ዝናብ መመታቷን ተከትሎ 110 ሺህ የነፍስ አድን ሠራተኞችን አሰማራች
ሀገር አቀፍ ዜና
October 14, 2019
Unknown
ባሳለፍነው ቅዳሜ ጃፓን 'ታይፎን ሃግቢስ" በተባለ ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ከተመታች በኋላ ከ110 ሺህ በላይ የነፍስ አድን ሠራተኞችን ለፍለጋ እና ለነፍስ አድን ሥራ ላይ አሰማርታለች።'ታይፎኑ' በአስርት ዓመታት ውስጥ ካጋጠመው በጣም ከባዱ እንደሆነ ተነግሯል። በአደጋውም 37 ሰዎች ሲሞቱ 20 የሚሆኑት የደረሱበት አልታወቀም።ክስተቱ ሦስት የራግቢ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች እንዲሰረዙ ምክንያት ሆኗል።በሺህዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች፣ የእሳት አደጋ ሠራተኞች፣ የድንበር ጠባቂዎች እና ወታደሮች በመሬት መንሸራተት እና በጎርፉ ሳቢያ ለተጎዱ ሰዎች ለመድረስ እየሠሩ ይገኛሉ።በጃፓን ስምንት የሚሆኑ ግዛቶች በጎርፉ የተጎዱ ሲሆን፣ በመካከለኛው ግዛት ናጋኖ፤ የነፍስ አድን ሠራተኞች ቡድን በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለመታደግ ወገባቸው ድረስ የሚያጠልቅ ውሃ ውስጥ ገብተው እየፈለጉ ነው ተብሏል።በናጋኖ የባቡር ማቆሚያ ቦታም በጎርፍ ተሞልቶ የነበረ ሲሆን፤ 10 ፈጣን ባቡሮች በጎርፉ ተውጠዋል። እያንዳንዱ ባቡር 30 ሚሊየን ዶላር ያወጣል ተብሎ ይገመታል።የጃፓን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት፤ የነፍስ አድን ሠራተኞቹ በጎርፉ ምክንያት የተወሰዱ እና ግምት ውስጥ ያልገቡ ቤቶች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ ብሏል።እሁድ ዕለት የኤሌክትሪክ ኃይል ከተቋረጠባቸው 262 ሺህ መኖሪያ ቤቶች አሁን ላይ ቁጥሩ ወደ 92 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ዝቅ ቢልም፤ 120 ሺህ የሚሆኑት የውሃ አቅርቦት የላቸውም።በአደጋው ከ7 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው የነበረ ሲሆን፤ በመጠለያ ውስጥ የነበሩት ግን 50 ሺህ ብቻ ነበሩ ተብሏል።የጃፓን ዋና መዲና ቶክዮ በአንፃራዊ መልኩ ከአደጋው የተረፈች ቢሆንም ሌሎች ከተሞች ግን በጎርፉ ተመትተዋል።በሃኮኔ ከተማ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ አንድ ሜትር ጥልቀት ያለው ጎርፍ ያጋጠመ ሲሆን፣ በጃፓን በ48 ሰዓታት ውስጥ ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው ተብሏል።በናጋኖ፤ ከችኩማ ወንዝ ሞልቶ የፈሰሰው ጎርፍ መኖሪያ ቦታዎች በጎርፍ እንዲጥለቀለቅ አድርጎታል።ጃፓን በታይፎን የተመታችው ባለፈው ወር ብቻ ሲሆን፣ 30 ሺህ የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል፤ ቤቶቹ እስካሁንም ድረስ አልተጠገኑም ተብሏል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34140/
236
0ሀገር አቀፍ ዜና
እነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ
ፖለቲካ
October 14, 2019
Unknown
ከሰኔ 15 ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በማረፊያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ እና ኮሎኔል ባምላኩ ዐባይ እያንዳንዳቸው በአስር ሺህ ብር ዋስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተለቀቁ፡፡በሰኔ 15 ጥቃት ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየተጣራ በእስር የቆዩት ተጠርጣሪዎቹ ባለፈው ሐሙስ ዋስትና ጠይቀው ነበር፤ መዝገቡን ተመልከቶ ውሳኔ ለመስጠትም ለዛሬ ተቀጥሮ ነበር፡፡በዋስትናው ዙሪያ መዝቡን ተመልክቶ አስተያዬት ለመስጠትም ለዛሬ ቀጠሮ ተሰጥቶ ነበር፡፡ በቀጠሮው መሠረትም ዐቃቤ ሕግ አስተያዬት ሰጥቷል፡፡ከምርመራ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የተጣሩ መሆናቸውንና ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም የሚለው ጭብጥ ዋስትና የሚያስከለክል አለመሆኑን ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ መግለጹን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክልል ዐቃቤ ሕግ ኢዮብ ጌታቸው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲወጡ አዝዟል፡፡በዚህ መሠረትም ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና አቅርበው ከሰዓት በኋላ መውጣታቸውን አቶ ኢዮብ ለአብመድ አረጋግጠዋል፡፡ ሲል የአማራ ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/31404/
131
5ፖለቲካ
በ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ በአማካይ የ10 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ እቅድ መያዙ ተገለጸ
ቢዝነስ
October 14, 2019
Unknown
በ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ በአማካይ የ10 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ እቅድ መያዙን የፕላንና ልማት ኮሚሽን ገለጸ፡፡የፕላንና ልማት ኮሚሽን በአስር አመት መሪ የልማት ዕቅድ (2013-2022) መነሻዎች፣ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ የትኩረት መስኮች እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፍ ዙሪያ ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች ጋር ውይይት አድረጓል፡፡የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋ በውይይቱ ላይ እንዳሉት፤ የ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች እና መስኮች ተለይተዋል፡፡የዕቅዱ መነሻ ነጥብ በ2022 አመተ ምህረት ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት መሆን የሚለው ርእይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡እቅዱ በግብርና፣ አምራች ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን ሀብት፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ የሰው ሃብት፣ የከተማ እና የመሰረተ ልማቶች ላይ ትኩረቱን ማድረጉን ነው የገለጹት፡፡በተለይም በመሰረተ ልማት፣ ቱሪዝም፣ የማዕድን ሀብት ልማት እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፎችች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል ነው ያሉት፡፡በመሰረተ ልማት፣ ፋይናንስ፣ የተንዝዛና ገዳቢ የሆነ የመንግስት ቢሮክራሲ እና የግሉ ዘርፍ የአቅም እና የአመለካከት ችግር በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ከሚስተዋሉ ችግሮች ማሳያዎች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸው ብለዋል፡፡የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከ2013 አስከ 2022 ባሉት አስር አመታት በአማካይ የ10 በመቶ እቅድ ለማዝመዘግብ እቅድ መጣሉን ገልጸዋል፡፡ይህም አመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ምጣኔ በ2022 የሀገሪቱ የነፍስ ወከፍ ገቢ 3ሺህ 260 የአሜሪካ ዶላር ለማድረግ እንደሚያስችል ኮሚሽነሯ መግለፃቸውን ከፕላንና ልማት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/24005/
173
3ቢዝነስ
የዓለም የደረጃዎች ቀን ተከበረ
ቢዝነስ
October 14, 2019
Unknown
የዓለም የደረጃዎች ቀን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ተከበረ፡፡የዓለም የደረጃዎች ቀንን በየዓመቱ የዓለም አቀፍ የደረጃዎች ድርጅት፣ ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮ ቴክኒካል ኮሚሽን እና ዓለም አቀፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሕብረት አባል የሆኑ ብሄራዊ ድርጅቶች የሚገኙባቸው አገሮች ሁሉ በተለያዩ ዝግጅቶች ያከብሩታል፡፡የአምራች፣ አገልግሎት ሰጪዎችና፣ የአስፈፃሚ አካላት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ቀኑን ለማክበር በተዘጋጀው የምክክር መድረክ ታድመዋል፡፡በኢትዮጵያ የምርትና አገልግሎት ጥራትና ደረጃን የሚያስጠብቅና ተወዳዳሪነትን የማሳደግ ስራው ውጤታማ አለመሆኑን የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡የግንዛቤ እጥረት፣ ደረጃዎችን የማስተግበር አቅም ማነስ፣ የቁጥጥር ሥርዓቱ ደካማ መሆን እና የፖሊሲ ትስስር አለመኖሩ የዘርፉ እድገት ዋና ዋና ችግሮች እንደሆኑ ነው በምክክር መድረኩ ላይ የተጠቆመው።ዓለም በምትገኝበት 4ኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ምርትና አገልግሎት ማቅረብ ካልተቻለ የገበያ ተወዳዳሪነትን ያሳጣል ተብሏል።ለዘርፉ እድገትም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር እንዲሰሩ ተጠይቋል።በዓሉ “የቪዲዮ ደረጃዎች ዓለም አቀፍ መድረክን የይፈጥራሉ!” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ23 ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ50 ጊዜ ተከብሯል፡፡
https://waltainfo.com/am/24006/
129
3ቢዝነስ
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የኢጋድ አባል አገራት የመሪዎች የምክክር ስብሰባ ላይ ለመካፈል ጁባ ገቡ
ፖለቲካ
October 14, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢጋድ አባል አገራት የመሪዎች የምክክር ስብሰባ ላይ ለመካፈል ጁባ ገብተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካን ቡድናቸው ጁባ ሲደርሱ በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲያት አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን የሱዳን የሽግግር መንግስትን ከታጣቂ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ለማስታረቅ በሚደረግ የኢጋድ አባል አገራት የመሪዎች የምክክር ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ጁባ እንዳመሩ ነው የተገለጸው፡፡(ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)
https://waltainfo.com/am/31403/
58
5ፖለቲካ
የካቢኔ አባላት በጠ/ሚ ጽ/ቤት በመገኘት ዶ/ር ዐቢይ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለጹ
ፖለቲካ
October 14, 2019
Unknown
የካቢኔ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በመገኘት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለጹ።በዚሁ ወቅት የካቢኔ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የወርቅ ሀብል በማበርከት ለአመራራቸው እና ለተገኘው ስኬት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡በአፍሪካ ካርታ አምሳያ የተሰራው የወርቅ ሐብል "እውነት ፍቅር ያሸንፋል" የሚል ጽሑፍ ተቀርጾበታል። (ምንጭ፡- የጠ/ሚ ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/31399/
47
5ፖለቲካ
ካሊፎርኒያ ከእንስሳት ፀጉር የሚሰሩ ምርቶችን በማገድ የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ግዛት ሆነች
ቢዝነስ
October 14, 2019
Unknown
ካሊፎርኒያ፤ ከእንስሳት ፀጉር የሚሠሩ ምርቶች እንዳይመረቱና እንዳይሸጡ በማገድ የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ግዛት ሆነች።በመሆኑም የግዛቷ ነዋሪዎች ከ2023 ጀምሮ ከእንስሳት ፀጉር የተሠሩ ምርቶችን መሸጥም ሆነ አልባሳት፣ ጫማ፣ ቦርሳዎችን መሥራት አይችሉም።ውሳኔው እገዳው እንዲጣል ለተወሰነ ጊዜ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩትን የእንስሳት መብት ተሟጋቾች አስደስቷል።የግዛቷ አስተዳዳሪ ጌቪን ኒውሰም፤ ከድመት፣ ከውሻና ከፈረስ በስተቀር ሌሎችን እንስሳት በሰርከስ ትዕይንት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የሚከለክለውን ረቂቅ ሕግም ፈርመዋል።ነገር ግን ሕጉ በሰሜን አሜሪካ የሚዘወተረውን የኮርማ እና የፈረስ ግልቢያ ስፖርት ላይ ተግባራዊ አይሆንም።"በእንስሳት ደህንነት ጥበቃ ዙሪያ ካሊፎርኒያ መሪ ናት፤ ዛሬ ደግሞ አስተዳዳሩ ከእንስሳት ፀጉር የተሠሩ ምርቶችን እንዳይሸጥ ለማድረግ ሕግ አውጥቷል" ሲሉ አስተዳዳሪው ጋቪን በመግለጫቸው ተናግረዋል።እገዳው ግን በቆዳ ምርቶች ላይ ማለትም በላም፣ በአጋዘን፣ በበግና በፍየል ቆዳ ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን የሳንፍራንሲስኮ ክሮኒቸል ዘግቧል።ከዚህም በተጨማሪ በእንስሳት አምሳያ ከእንስሳት ምርቶች የሚሠሩ አሻንጉሊቶች ላይ ተግባራዊ እንደማይሆንም ተነግሯል።ይህንን ሕግ ጥሶ የተገኘም እስከ 500 ዶላር ቅጣት፤ ሕጉን በተደጋጋሚ ለጣሰም እስከ 1000 ዶላር ያስቀጣል።የአሜሪካ ሁዩማን ሶሳይቲ አሜሪካ የግዛቷን አስተዳደር እና ሕግ አውጪዎቹን እንዲሁም የካሊፎርኒያ ዜጎች ገበያቸው በእንስሳት ፀጉር የተሠሩ ምርቶች ፍላጎቶችን እንዲያስተናግዱ ባለመፍቀዳቸው አድናቆቱን ችሯል።ይሁን እንጂ ውሳኔው የእንስሳት ተዋፅኦ የማይጠቀሙትን አክራሪ ቬጋኖች (እንስሳትንም ሆነ የእንስሳት ተዋፅኦ የማይጠቀሙ) አጀንዳ ለማስተናገድ ከፀጉር የሚሠሩ ምርቶችን በመከልከል፤ በምንለብሰውና በምንመገበው ላይ እገዳ ለመጣል አንድ እርምጃ ነው ሲል ፈር ኢንፎርሜሽን ካውንስል ተችቶታል።ባሳለፍነው ግንቦት ወር አንድ በፋሽን የተሠማራ ድርጅት እስከ 2020 ድረስ የእንስሳትን ፀጉር መጠቀም እንደሚያቆም አስታውቆ ነበር።በየካቲት ወርም እንዲሁ የእንግሊዙ ሰልፍሪጅስ ከየካቲት 2020 ጀምሮ የእንስሳት ቆዳ ውጤቶችን መሸጥ ሊያግድ እንደሚችል ማስታወቁ ይታወሳል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33563/
215
3ቢዝነስ
የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች እየተከበረ ነው
ፖለቲካ
October 14, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች እየተከበረ ነው፡፡የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ የሰንደቅ ዓላማ ቀን እያከበረ ሲሆን፣ በበዓሉ ላይ የተገኙት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያ ምሰሶ የሆነውና የአንድነታችን መገለጫ የሆነው ሰንደቅ ዓላማ ስር በመሰለፍ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በእኩልነትና በፍቅር አብሮ መስራት እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡የትግራይ ክልልም "ሰንደቅ ዓላማችን ለህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርአታችንና ለህገ መንግስታችን ሉኣላዊነት " በሚል መሪ ቃል የሰንደቅ አላማ ቀንን በመቐለ ከተማ፣ በመቐለ ዩኒቨርስቲ በሚገኘው ስፖርት አካዳሚ ስታዲየም በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደሚገኝ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/31401/
82
5ፖለቲካ
ሰንደቅ ዓላማ ፍቅርና ዜግነት የሚገለፅበት እንጂ የፖለቲካ መሳሪያ መሆን የለበትም- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ
ፖለቲካ
October 14, 2019
Unknown
ሰንደቅ ዓላማ ፍቅርና ዜግነት የሚገለፅበት እንጂ የፖለቲካ መሳሪያ መሆን እንደሌለበት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገልፀወዋል፡፡12ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ አላማችን የብዝኃነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ሃሳብ በተለይ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሲከበር ነው ፕሬዚዳንቷ ይህን ያሉት ፡፡በስነስርዓቱ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ፣ የፌደሬሽን ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ መሃመድ ረሺድ ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እንዲሁም የምክር ቤቱ አባላት ተሳትፈዋል፡፡ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ዛሬ የሚከበረው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በብዙ መልኩ አንድምታው ብዙ መሆኑን በመጥቀስ፤ ኢትዮጵያ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ አንድነትና መቻቻልን የሚሰብኩ ዜጎችን አጥብቃ ትሻለች ብለዋል፡፡ሰንደቅ ዓላማ ፍቅርና ዜግነት የሚገለፅበት እንጂ የፖለቲካ መሳሪያ መሆን የለበትም ነው ያሉት ፡፡የሰንደቅ ዓለማ የብሄራዊ ማንነት እና የሉዓላዊነታችን መገለጫ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ፤ የሀሳብ ልዩነት ቢኖር እንኳን በሚያስተሳስሩን ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለመቻቻልና አንድነት ቅድሚያ መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡ሀገሪቱ የተመሰረተችባቸው እሴቶች በሙሉ በሰንደቋ እንደሚወከል ያስታወሱት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፤ አዲሱ ትውልድ ስለ ሰንደቅ ዓለማ ትርጉም በማስመዝገብ በኩል ሁሉም ሃላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል ነው ያሉት፡፡ፕሬዚዳንቷ የምንችለውን እናበርክት፤ አንድ ሆነን ብዙ ተዓምራትን እንስራ ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 3 የተቀመጠውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ትርጓሜ መሰረት በማድረግ የወጣ የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 እንዲሁም በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር በተደነገገው መሰረት ነው ዛሬ የተከበረው፡፡
https://waltainfo.com/am/31400/
206
5ፖለቲካ
በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ
ፖለቲካ
October 14, 2019
Unknown
በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ።በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ሜጉ ቀበሌ የታጠቁ ኃይሎች በፈፀሙት ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ መሆኑን የአፋር ክልል የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አህመድ ኡመድ ለኢቢሲ ተናግረዋል።በጥቃቱ እስካሁን 16 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከእነዚህም መካከል 3ቱ ህፃናት እና 4ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው ብለዋል።ጥቃቱ በተሸከርካሪ የታገዘ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን የሰነድ ማስረጃዎችን ማግኘት እንደተቻለም ነው ም/ል ኮሚሽነሩ የተናገሩት፡፡በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ህፃናት በዱቡቲ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት መሆኑን አስታውቋል፡፡“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ” የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዦር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።
https://waltainfo.com/am/31402/
124
5ፖለቲካ
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት የ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጀት እና የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ
ፖለቲካ
October 12, 2019
Unknown
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ በነበረው 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችና አዋጆችን በማፅደቅ ተጠናቋል።በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ ለ2012 በጀት ዓመት ለክልሉ ስራ ማስፈጸሚያ የሚውል 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጀት አፅድቋል።ትናንት አመሻሽ ላይ በተጠናቀቀው የክልሉ ም/ቤት ጉባኤ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አብዱልማሊክ በከር ሀገራዊ ለውጡን በአዲስ የለውጥ ሀይል ለማስቀጠል እንዲቻል ባቀረቡት የመተካት ጥያቄ መሰረት ምክር ቤቱ በምትካቸውም ወ/ሮ ሚስራ አብደላን የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።በተጨማሪም አቶ ሰለሞን ኩቹ ሮባን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ሃላፊ አድርጎ ሾሟል።ምክር ቤቱ አቶ አብዱልሀኪም አብዱልማሊክ የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢር ሀላፊ፣አቶ በቀለ ተመስገን የሀረር ማዘጋጃቤት ዋና ስራ አስኬያጅ፣ አቶ አብዱልሀኪም አብዲ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ቢሮ ሀላፊ፣ አቶ ናሲር ዩያ ሀሰን የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ፣ አቶ ዲኒ ረመዳንን የባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አድርጎ ሲሾም ሌሎች ሰባት የተለያዩ ሹመቶችንም ሰጥቷል።ምክር ቤቱ የክልሉ አዳዲስ የሴክተር መስሪያ ቤቶች አወቃቀርን እንደገና ለማደራጀትና ሥልጣንና ተግባራቸውን ዳግም ለመወሰን የቀረበውን አዋጅም መርምሮ አፅድቋል።በዚህም ቁጥራቸው ዘጠኝ የነበረው የክልሉ ካቢኔ ወደ 14 የክልል ካቢኔ አባላት ከፍ እንዲል መደረጉን ከሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
https://waltainfo.com/am/31396/
180
5ፖለቲካ
ከ4 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሀገር መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት አባላት የአንድነት ፓርክን ጎበኙ
ቢዝነስ
October 12, 2019
Unknown
ከ4 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሀገር መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት አባላት የአንድነት ፓርክን ጎበኝተዋል፡፡በደማቅ ሁኔታ ተመርቆ የተከፈተው የአንድነት ፓርክ በ2 ሺህ የሃገር መከላከያ እና በ2 ሺህ የፖሊስ ሰራዊት አባላትን በማስጎብኘት ስራውን በይፋ ጀምሯል፡፡መደበኛ የክፍያ ጉብኝት ከሚጀምርበት ከመጪው ሰኞ በፊት ፓርኩን እንዲጎበኙ ከተመረጡት የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ የሃገር መከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊት አባላት በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችን ተዟዙረው ሲጎበኙ ውለዋል፡፡በመጪዎቹ ሁለት ቀናትም አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች እና ታዳጊ ህፃናት ፓርኩን ቅድሚያ ወስደው ከሚጎበኙት የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ይገኙበታል ተብሏል፡፡የአንድነት ፓርክን ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መገኘት ሲኖርበት በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመሁኔታዎች ካላሟሉ ፓርኩን መጎብኘት አይችሉም።የሚከለከልጎብኚዎች ይዘው መምጣት የሌለባቸው ነገሮች። – ስለት – ተቀጣጣይ ቁሶች – የጦር መሳሪያዎች – ምግብ መጠጦች እና ጣፋጭ ነገሮች – ማስቲካ – የመዋቢያ ቁሶች – የግል ካሜራዎች – ስልኮች ታብሌቶች እና ማንቸውንም የምስልና ድምጽ መቅረጫ መሳሪያዎችን – ሲጋራ እና አደንዛዥ ዕጾችስነምግባርበፓርኩ ውስጥ ማድረግ የተከለከሉ ተግባራትና ባህሪያት። – መጮህና መረበሽ – ከአስጎብኚ ውጪና ከተመደቡበት የጉብኝት ቡድን ውጪ መንቀሳቀስ – በታሪካዊ ህንጻዎቹ ላይ መደገፍ – ቅርሶችንና እንስሳትን መነካካት – እንስሳትን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ መቅረብ – እንስሳትን መመገብ – እንስሳትን ማስቆጣት (ጠጠር መወርወር፣ በአካላዊ እንቅስቃሴ ማስፈራራት፣ አላስፈላጊ ድምጽ ማውጣት) – ከተቀመጡ የቆሻሻ ማስወገጃ እቃ ውጪ ቆሻሻ መጣል – ሲጋራና ሌሎች አደንዛዥ እጾችን መጠቀም – የቤት እንስሳትን ይዞ መምጣት – መንገድ ከተበጀለት ዉጪ መራመድ እና አጥሮችን ከልክ በላይ መጠጋትም ሆነ መደገፍ – ማንኛዉንም በ ፓርኩ የሚገኝ የኤሌትሮኒክስ ቁስ ያለፍቃድ መንካት(ምንጭ፡-አንድነት ፓርክ)
https://waltainfo.com/am/24003/
223
3ቢዝነስ
የከተማ ሴቶች የሰላም እሴት ግንባታ ላይ የሚያተኩር የምክክር መድረክ በሃዋሳ ተካሄደ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 12, 2019
Unknown
የሴቶችን ተሳታፊነት የማረጋገጥና የማሳደግ ተግባር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዚሁ ወቅት ገልፀዋል፡፡የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ፣ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስትና የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር የጋራ ትብብር ባዘጋጁትና የከተማ ሴቶች የሰላም እሴት ግንባታ ላይ ባተኮረው የምክክር መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ኢንጂነር አይሻ በከተማ ልማትና የሰላም ግንባታ ስራ ላይ እኛ ሴቶች ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆን ያለብን የአለማችንን ግማሹን ህዝብ ስለምንወክል ብቻ ሳይሆን በሰላም መደፍረስ ምክንያት ለበርካታ ችግሮች ቀጥተኛ ተጋላጭ በመሆናችንም ጭምር ነው ብለዋል፡፡ሚኒስትሯ አክለውም በዓለም ላይ የታየው ተሞክሮም ይህንኑ የሚያመላከት በመሆኑ የከተሞቻችን ዕድገት ጋር ከሴቶችን እኩልነትና ተጠቃሚነት ጋር ያለው ትስስር ለማጥበቅ በርትተን መስራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት ብለዋል፡፡በምክክር መድረኩ ላይ ተገኙት የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም በበኩላቸው፤ ሴቶች በተፈጥሮ በተሰጣቸው ፀጋና ትሩፋት ትውልዱን ከእኩይ አስተሳሰብ በራቀ መንገድ ማሳደግና መቅረፅ፣ ብሎም ለፍቅር ተገዢና ሩህሩህ አድርጎ ለማሳደግ ትልቅ ሚና ያላቸው በመሆኑ በሙሉ አቅማቸው ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል፡፡በዚህ የምክር መድረክ ላይ የተገኙት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ገ/ ማርያም በከተማ ልማት ስራዎች የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ የግድ መሆኑን ጠቅሰው ፤ ለዚህም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡የሃዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥረቱ በየነም ሴቶችን በበቂ ሁኔታ ያላካተተ ልማት ውጤታማ እንደማይሆን በመግለፅ በከተማዋ በሚካሄዱ የልማት እንቅስቃሴዎች ሁሉ ሴቶችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲመራ ትኩረት ሰጥተናል ብለዋል፡፡የከተማ ሴቶች በሰላም እሴት ግንባታ ላይ ያላቸውን ሚና በተመለከተ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ፣ የከተማ ልማትን ኮንስትራክሽን ሚኒትስር ዴኤታዎችና ከየክልሉ የተወጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ፤የመወያያ ፅሁፍም ቀርቦ ውይይት እንደተካሄደበት ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
https://waltainfo.com/am/32793/
249
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከ1 ነጥብ 8 ቢልየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የዋርዴር-ቀብሪደሐር መንገድ ግንባታ በይፋ ተጀመረ
ቢዝነስ
October 12, 2019
Unknown
ከ1 ነጥብ 8 ቢልየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የዋርዴር-ቀብሪደሐር መንገድ በይፋ ተጀምሯል።የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ ም/ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስተፌ መሀመድ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂ.ሀብታሙ ተገኘ ፣ ከፌደራል ጥሪ የተደረገላቸው ባለስልጣናት እንዲሁም የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት መንገዱን በይፋ የማስጀመር ስነ-ስርዓቱ ተካሂዷል።138.8 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውን የአስፋልት መንገድ ግንባታ ስራ ፕሮጀክት የሚያከናውነው ማክሮ የተባለ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጭ ድርጅት ነው። የማማከርና የቁጥጥር ስራ የሚከናውኑት ደግሞ ቤስት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ፒልሲ እና ሂቴክ ኮንሰልቲንግ በጋራ በመሆን ነው።የዋርዴር-ቀብሪደሐር መንገድ ፕሮጅክት የጎን ስፋት በዞን 21.5 በወረዳ 19ሜትር እና በቀበሌ 12 ሜትር ስፋት ሲሆን በገጠር የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 10 ሜትር ስፋት ይኖረዋል።ይህ የመንገድ በኮንትራት ውሉ መሰረት በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ ወጪም በኢትዮጵያ መንግስት ይሸፈናል፡፡የመንገድ ፕሮጀክቱ በአስፋልት ደረጃ መገንባቱ በዋነኝነት የሚኖረው ጠቀሜታ ከዚህ ቀደም ከዋርዴር ተነስቶ ቀብሪደሐር ለመድረስ ከ3 ስዓት በላይ ይፈጅ የነበረ ሲሆን መንገዱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ይወስድ የነበረውን ጊዜ በግማሽ እንደሚያሳጥር ይጠበቃል።በአጠቃላይ በቂ የሆነ የመንገድ መሰረተ ልማት ያልነበረውን የአካባቢውን ሕብረተሰብ የዘመናዊ ትራንስፖርት ተጠቃሚ በማድረግ ከፊል አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮችን ምርታቸውን በቀላሉና በተቀላጠፈ ሁኔታ ወደተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ለማመላለስ ያስችላል መባሉን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
https://waltainfo.com/am/24004/
176
3ቢዝነስ
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የድጋፍ ስልፎች እየተካሄዱ ነው
ፖለቲካ
October 13, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ  አህመድ ባገኙት የኖቤል ሰላም ሽልማት የተሰማቸው ደስታ በመግለጽ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የድጋፍ ስልፎች እየተካሄዱ ነው አምቦ፣ ፍቼ፣ መቱ፣ ቡኖ በደሌ ፣ ነገሌ፣  ጅማ እና በሌሎችም የኦሮሚያ ከተሞች የድጋፉ ሰልፉ እየተካሄደ ይገኛል።በተለይ በነገሌ ከተማ እየተካሄደ ባለስ ሰልፍ  ከ10ሺ በላይ የሚገመቱ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን የስልፉ አስተባበሪ አቶ ባጫ ጅማ ለኢዜአ  ገልጸዋል።የህግ የበላይነት እንዲከበር የድርሻችንን እንወጣለን፣ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎች አጥብቀን እንቃወማለን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ያገኙት የኖቤል ሽልማት የሀገራችንን ቀጣይ ሰላምና አንድነት የሚያሳይ ነው የሚሉ መፈክሮች በነዋሪዎች ከተስተጋቡት መካከል ይገኙበታል።በተመሳሳይ የኢሉአባቦርእና ቡኖበደሌ ዞኖች ነዋሪዎች በየከተሞቻቸው እያደረጉት ባለው ስልፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸው መደሰታቸውን ባሰሙት መፈክርና በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ሰላምና ብልፅግና እንዲረጋገጥ የሚያደርጉትን ጥረትእንደግፋለን ፣ የመደመር ፍልስፍና ኢትዮጵያንና የአፍሪካ ቀንድን ሰላም የሚያረጋግጥ ነው ሲሉም ባሰሙት መፈክሮች ገልጸዋል።በሰልፉ ወጣቶች ሴቶች ፣ የመንግስት ሰራተኞችንና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው። 
https://waltainfo.com/am/31397/
134
5ፖለቲካ
አምባሳደር ፍፁም አረጋ ከሂዉማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ኢዳ ሳዉየር ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
October 13, 2019
Unknown
አምባሳደር ፍፁም አረጋ ከሂዉማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ኢዳ ሳዉየር ጋር ዛሬ ተወይተዋል፡፡ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ ምክትል ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።አምባሳደር ፍፁም በበኩላቸው ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ሰፊ ማሻሻሎችን ማድረጓን ገልፀው ከተቋሙ ጋር በቅርበት ለመስራት ዝግጁ ነች ብለዋል።የተቋሙ ኃላፊዎችም በቅርቡ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ምክትል ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
https://waltainfo.com/am/31398/
50
5ፖለቲካ
አሜሪካ በቱርክ ላይ ማዕቀብ ልትጥል እየተሰናዳች ነው
ፖለቲካ
October 12, 2019
Unknown
አሜሪካ በቱርክ ላይ ማዕቀብ ልትጥል እየተሰናዳች ነው ተባለ፡፡ቱርክ በሶሪያ በኩርዶች ይዞታ ሥር የሚገኙ አካባቢዎች ላይ ጥቃት መፈፀሟን እንድታስቆም አሜሪካ ላይ ጫና እየበረታባት ነው።የመከላከያ ሚኒስትሩ ፀኃፊ ማርክ ኤስፐር "ጠበቅ ያለ ርምጃ" ሊወሰድ እንደሚችል ሲያስጠነቅቁ፤ የገንዘብ ሚኒስትሩ ፀኃፊ ስቴቨን ሙንቺን በበኩላቸው፤ አዲስ ማዕቀብ ሊጣል የሚችልበትን ዕድል ተናግረዋል።መከላከያ ሚኒስትር ፀኃፊው አክለውም ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን "መዘዙ ብዙ የሆነ ርምጃ" እንደወሰዱ በመናገር ድርጊቱ "የአይ ኤስ ወታደሮች ታስረውበት ያለውን ሥፍራ አደጋ ላይ የሚጥል ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።የገንዘብ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቱርክ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችል ረቂቅ እንዲዘጋጅ ማዘዛቸውን ተናግረዋል። "ከፈለግን የቱርክን ኢኮኖሚ ቀጥ እናደርገዋለን" ሲሉ አክለዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ "ቱርኮች የሰው ሕይወት እንዲቀጥፉ አንፈልግም፤ ማዕቀብ መጣል ካለብን እናደርገዋለን" ብለዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የዲሞክራቶችና ሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎቹ በጋራ ተቀምጠው ቱርክ ላይ ጫና የሚደረግበትን ጉዳይ እየተነጋገሩ ነው።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጦራቸውን ከሥፍራው ለማውጣት መወሰናቸው ቱርክ ወታደሮቿን ወደ ሥፍራው አሰማርታ ጥቃት እንድትከፍት እድሉን ሰጥቷታል ሲሉ የሚከስሱ አሜሪካውያን ቁጥርም ቀላል አይደለም።የቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ግን ወታደራዊ ዘመቻው እንደሚቀጥል ተናግረዋል።እንደየተባበሩት መንግሥታት ከሆነ የቱርክ ጦር ጥቃት ከከፈተበት ረቡዕ እለት ጀምሮ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሸሽተዋል።በአካባቢው እየደረሰ ያለው ቀውስ እየበረታ በሄደበት በአሁን ሰዓት የአሜሪካ ጦር የቱርክ ጦር ጥቃት እንዳሳሰበው መናገር ጀምሯል።አርብ ዕለት ፔንታጎን እንዳለው በሰሜናዊ ሶሪያ አቅራቢያ በሚገኝ የጦር ካምፑ አቅራቢያ ከቱርክ የተተኮሰ መሣሪያ ወድቋል።የባህር ኃይሉ ካፒቴን ብሩክ ዴዋልት እንዳሉት ደግሞ አካባቢው "የአሜሪካ ጦር እንዳለበት ይታወቃል።"ካፒቴኑ"ሁሉም የአሜሪካ ጦር ባልደረቦች ላይ ጉዳት አለመድረሱን አረጋግጠናል" ብለዋል በመግለጫቸው ላይ፤ "አሜሪካ ከቱርክ የምትፈልገው ወዲያውኑ ራሳችንን ወደ መከላከል የምንገባበት ነገር እንዳይከሰት ነው" ሲሉም አስጠንቅቀዋል።ቱርክ ግን ሆን ተብሎ የተደረገ አይደለም ስትል አስተባብላለች።በኩርዶች የሚመራው የሶሪያ ዲሞክራሲያው ኃይል ጦር በቀጠናው የአሜሪካ ዋነኛ አጋር ነበር። አሁን ግን ከቱርክ ምድር ጦርና አየር ኃይል ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰበት ይገኛል።ቱርክና ሶሪያ በሚጋሩት 120 ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው ድንበር ላይ ጥቃቱ እንደተከፈተ ማወቅ ተችሏል።በርካታ የሶሪያ ዲሞክራሲያው ኃይል ጦር እና የሌሎች አማፂያን ጦር ታጣቂዎች መገደላቸውም ታውቋል፡፡ቱርክ ላይ የሚጣለው ማዕቀብ ባለሥልጣናቷ ላይ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ሲሆን፣ ይህንን ጥቃት ይደግፋሉ የሚባሉ ባንኮችም እጣው ሊደርሳቸው እንደሚችል የዲሞክራቶችና የሪፐብሊካን ተወካዮች ተናግረዋል።ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን በበኩላቸው "ከግራም ከቀኝም ይህንን ጉዳይ አቁሙ የሚል ማስፈራሪያ እየደረሰን ነው" በማለት " ነገር ግን ከአቋማችን ፈቀቅ አንልም" ብለዋል። (ምንጭ፡ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34014/
316
5ፖለቲካ
የአሜሪካ ኤምባሲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደስታ መልእክት አስተላለፈ
ፖለቲካ
October 11, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 100ኛው የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸውን አስመልከቶ የደስታ መልእክት አስተላልፏል።ኤምባሲው በመልእክቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ሰላም እና ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲኖር ለማስቻል ላደረጉት ጥረት እና ከጎረቤት ኤርትራ ጋር የነበረው ግጭት እንዲፈታ ለወሰዱት እርምጃ” የኖቤል ሽልማት ማግኘታቸውን ጠቅሷል።በዚህም መላው ኢትዮጵያውያን ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ የኩራት ሁነት ሲያከብሩ ደስታውን እንደሚጋራ ገልጿል።ይህ የክብር ሽልማት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመራር በአገሪቱ ውስጥ አመርቂ እመርታ ለመምጣቱ ማሳያ ነው ብሏል።በተጨማሪም ዶ/ር ዐቢይ ከኤርትራ ጋር የነበረውን ግንኙነት ማደስን ጨምሮ የፖለቲካ ምኅዳሩን በማስፋት፣ የፕሬስ ነፃነትን በማጠናከር እና የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት የወሰዱት እርምጃ የዴሞክራሲ እሴቶችን ለማጎልበት ብሎም ሁሉን አቀፍ ልማት ለማምጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል ብሏል።በመሆኑም አሜሪካ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ዴሞክራሲያዊት እና የበለጸገች አገር ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ አሁንም ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።(ምንጭ:- የአሜሪካ ኤምባሲ)
https://waltainfo.com/am/31392/
123
5ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከአሜሪካ ኮንግረስ የዴሞክራሲ አጋርነት ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
October 11, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከአሜሪካ ኮንግረስ የዴሞክራሲ አጋርነት ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡በውይይቱ ወቅት ፕሬዝዳን ሳህለወርቅ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ሁሉን አቀፍ የለውጥ እንቅስቃሴ በተመለከተ ለልኡካን ቡድኑ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ መንግስት ዴሞክራሲዊትና የበለጸገች ሀገር እውን ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት አብራርተዋል፡፡የለውጥ እንቅስቃሴው ጥልቀት ያለው እና መሰረታዊ በሆነ መልኩ እየተከናነወነ የሚገኝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡የልኡካን ቡድኑ በበኩላቸው፣ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በመካሄድ ላይ ባለው ለውጥ የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችን ለማወቅ ከፍተኛ ፍላጎት ስላላቸው ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ኢትዮጵያ የጀመረችው የለውጥ እንቅስቃሴ ዳር እንዲደርስ አሜሪካም ድጋፏን መስጠት እንደምትቀጥል ነው የኮሚቴው አባላት ያረጋገጡት፡፡ (ምንጭ፡-የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/31394/
82
5ፖለቲካ
የተለያዩ ሀገራት መሪዎችና ድርጅቶች ለጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት እያስተላለፉ ነው
ፖለቲካ
October 11, 2019
Unknown
የተለያዩ ሀገራት መሪዎችና ድርጅቶች ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት እያስተላለፉ ነው፡፡ግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸው የአንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ወንድም የኢትዮጵያ ህዝቦች የ2019 የኖቤል ሽልማት ዶክተር ዐቢይ አህመድ በማሸናፈቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡በሌላ በኩል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማህማት፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ፣ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ ፎርማጆ፣ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ፣ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን የውጭ ፖሊሲ ጉዳዮች ኃላፊና የኮሚሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ፍሬድሪካ ፍሬድሪካ ሞግሔረኒን የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የባህል እና የሳይንስ ድርጅት/ዩኒስኮ/፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ መሃማትን ጨምሮ  በርካታ መሪዎችና ታዋቂ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የ2019ኙን የሰላም የኖቤል ሽልማት በማሸነፋቸው የተሰማቸው ደስታ ገልፀዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/31393/
127
5ፖለቲካ
የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆን ኢትዮጵያውን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለፈፀሟቸው በጎ ስራዎች የተሰጠ እውቅና ነው- የኢህአዴግ ምክር ቤት
ሀገር አቀፍ ዜና
October 12, 2019
Unknown
የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆን ኢትዮጵያውን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለፈፀሟቸው በጎ ስራዎች የተሰጠ እውቅና ነው- የኢህአዴግ ምክር ቤትየጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆን መላ ኢትዮጵያውን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለፈፀሟቸው በጎ ስራዎች በሙሉ የተሰጠ እውቅና በመሆኑ ድሉ የሀገሪቱም መሆኑን የኢህአዴግ ምክር ቤት ገለፀ።የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአለም የሰላም ኖቤል አሸናፊነት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ሀገራችን በተከተለቸው የለውጥ አቅጣጫ ላይ ያለውን መተማመንና ተስፋ ያረጋገጠ በመሆኑ የኢህአዴግ ምክር ቤት ለዶ/ር አቢይ አህመድ በተለይ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ ብሏል የኢህአዴግ ምክር ቤት።ምክር ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ባለፈው አንድ አመት ከመንፈቅ በድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ ቀጥተኛ አመራር በሀገሪቱ ዴሞክራሲን ለማስፈን፣ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ በርካታ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ መቆየታቸውን አንስቷል።ሀገሪቱ ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር ያላትን ግንኙነት በሰላም፣ በመተባበርና በጋራ ብልፅግና ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ እንዲሁም የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ከግጭት የፀዳ እንዲሆን ሊቀመንበሩ ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል ነው ያለው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ሀገር መሪነት ከመጡ ሁለት አመት እንኳን ያልሞላቸው ቢሆኑም ከሀገር አልፎ አለም ያደነቀውንና የደገፈውን ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል ብሏል።በርግጥም በሀገር አቀፍም ይሁን በውጭ በተንቀሳቀሱባቸው ወቅቶች ሁሉ ስለ ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት በመናገርና ይህንኑም በተግባር በማሳየት ያበረከቱት አስተዋፆ ለዚህ ልዩ ክብር የሚያበቃቸው መሆኑንም በመግለጫው ጠቁሟል።በለውጡ የተገኙ ስኬቶችን ከማንም በላይና ቀድመን የምንገነዘባቸውና የፍሬዎቹም ተቋዳሽ እኛው ኢትዮጵያውን ብንሆንም አለም አቀፉ ህብረተሰብ ደግሞ ለዚህ ድላችን በዛሬው እለት በአለም ትልቁን የክብር ሽልማት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በማጎናፀፍ እውቅናውን ቸሯልም ብሏል።ይህ ሽልማት አለም አቀፉ ህብተሰብ ሀገሪቱ በተከተለችው የለውጥ አቅጣጫ ላይ ከመተማመን ባለፈ እስካሁን የተመዘገቡ ስኬቶች ዘላቂነት እንደሚኖራቸው ተስፋ ማሳደሩን አመልካች መሆኑንም አስታውቋል።ይህ ድል መላ ኢትዮጵያውን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለፈፀሟቸው በጎ ስራዎች በሙሉ የተሰጠ እውቅና በመሆኑ ድሉም የሀገራችን ድል ነው ብሏል።በሊቀ መንበራችን ለዚሀ ክብር መብቃት ስሟ ከፍ ብሎ የሚጠራው ሀገራችን ስትሆን አንገታቸውን ቀና አድርገው መሄድ የቻሉት ደግሞ መላ ኢትዮጵያውያን ናቸው ብሏል ምክር ቤቱ።ከምንም በላይ ደግሞ ሀገሪቱ እንደቀደመው ሁሉ በየመስኩ አንቱታንና ተቀባይነትን ያተረፉ ጀግኖችን ማፍራት የምትችል መሆኗን አሳይቶናልም ብሏል።የጠቅላይ ሚኒስትራችን እና አጠቃላይ የለውጥ አመራሩ ጥረት ፍሬ በማፍራቱ ያገኘነው ይህ ሽልማት እንደ መሪ ድርጅት በሊቀ መንበራችን ፋና ወጊነት የጀመርነውን ሰላም የማስፈን፣ የዜጎችን መብትና እኩልነት የማረጋገጥ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች የማረጋገጥ ስራችንን አጠናክረን እንድንቀጥል የሞራል ስንቅ የሚሆነን ነው ይላል መግለጫው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በመሪነት ዘመናቸው ከእስካሁኑም የላቀ ስኬት በማስመዝገብ የፓርቲያችንን፣ የመላ የሀገራችንን ህዝቦችንና የሀገራችን ኩራት ሆነው እንደሚቀጥሉ የኢህአዴግ ምክር ቤት ያለውን ሙሉ እምነት ይገልፃል ያለው ምክር ቤቱ፥ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን የመሪያችንን አርዓያ ተከትለን በየተሰማራንበት የስራ መስክ ሁሉ የላቀ ስኬት ለማስመዝገብ እንድንረባረብ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጥሪውን ያስተላልፋል ብሏል። 
https://waltainfo.com/am/32792/
393
0ሀገር አቀፍ ዜና
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ሽልማት በማስመልከት በነገው ዕለት በመላ ኦሮሚያ የደስታ መግለጫ ሰልፎች ይካሄዳሉ
ፖለቲካ
October 12, 2019
Unknown
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይን የሰላም የኖቤል ሽልማት በማስመልከት በነገው ዕለት በመላ ኦሮሚያ የደስታ መግለጫ ሰልፎች የሚደረጉ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።የኦሮሚያ ክልል መንግስትና ሕዝብ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሽልማት በማስመልከትም የደሰታ መግለጫ መልእክት አስተላልፏል።የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን የሰላም የኖቤል ሽልማት በማስመልከት አሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የደስታ መግለጫ ስልፎች ይደረጋሉ ተብሏል።የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በሰጡት መግለጫ፤ ድሉ የአንድ ሰው ብቻ ሳይሆን የመላው ህዝብ ድል ነው ብለዋል።ይህ ትልቅ እውቅና የተገኘው ሕዝቡ አንድነቱን በማጠናከሩና በመደማመጡ የመጣ ትልቅ ድልም መሆኑን ተናግረዋል።”ይህ የተገኘው ድል እጥፍ ክብርና ድል ነው” ያሉት አቶ ዴሬሳ የክልሉ ህዝብ ደስታው ከተነገረ ጀምሮ በተለያዩ መልኩ ስሜቱን እየገለጸ ይገኛል ብለዋል።በተለይ ደግሞ የክልሉ ሕዝብ በሰላማዊ ሰልፍ ደስታውን ለመግለጽ በተለያየ መልኩ ጥያቄዎችን እያቀረበ ይገኛል ነው ያሉት።የክልሉ መንግስት ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ሕዝቡ በተናበበና በተቀናጀ ሁኔታ ደስታውን እንዲገልፅ ይደረጋል ብለዋል።ለሰልፉ አስፋለጊው የፀጥታ ጥብቃ ተደርጎለት በቀጣይ እሁድ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የሚካሄድ ይሆናል ነው ያሉት አቶ ዴሬሳ።በቀጣይም የተሻለ ድል እና ውጤት ይገኝ ዘንድ ሕዝቡ አንድነቱን ጠብቆ እንዲሄድም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። (ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/31395/
160
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 11, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡በኖርዌይ መዲና ኦስሎ በሚዘጋጀው የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸንፋሉ ተብለው ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ሰዎች አንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀደም ሲል ታይም መፅሄት ማስነበቡ ይታወሳል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ከሁለት አስርት አመታት ፍጥጫ እልባት በመስጠት፤ ሰላም በማምጣት፣ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታትና ሌሎች ባመጧቸውም መሻሻሎች ሽልማቱን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ በእንግሊዝ የተለያዩ ፖለቲካዊ ትንበያዎችን በመስጠት የሚወራረደው ላድብሮክ 80% (4/1) ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ግምት ማስቀመጡም አይዘነጋም።ዓመታዊው ሽልማት በአለም ውስጥ ለሰላም አስተዋፅኦ ያደረጉ ግለሰቦችን ወይም ድርጅቶችን እውቅና በመስጠት ይታወቃል።ባለፈው ዓመት የኮንጎ ዜግነት ያለው ዶክተር ዴኒስ ሙክዌጋና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ናዲያ ሙራድ ወሲባዊ ጥቃትን ለጦርነት መሳሪያነት መጠቀሚያነት ለማቆም በሰሩት ስራ አሸናፊ ሆነዋል።በዚህ ዓመት ሽልማት 301 ዕጩዎች ያሉ ሲሆን፤ 223 ግለሰቦች እንዲሁም 78 ድርጅቶች መሆናቸውንም የኖቤል ተቋም አስታውቋል። ምንም እንኳን እነማን ዕጩዎች እንደሆኑ ባይታወቁም የተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ግምቶቻቸውን እያስቀመጡ ቆይተዋል።ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ በቀጠል የ16 ዓመቷ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ግሬታ ተንበርግና የኒውዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ግምትን ያገኙ ግለሰቦች ነበሩ፡፡
https://waltainfo.com/am/32791/
157
0ሀገር አቀፍ ዜና
የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ከዳር ለማድረስ አሜሪካ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች
ፖለቲካ
October 11, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስቀጠል አሜሪካ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በዴቪድ ፕራይስ የተመራውን የአሜሪካ ልዑካን ቡድን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ለልዑካን ቡድኑ በሀገሪቷ የተከናወኑ ቁልፍ የለውጥ ስራዎችን አስመልክቶ ገለጻ ተድርጎለታል፡፡የፊታችን ግንቦት 2012 ዓ.ም የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናደርጋለን ሲሉም የልዑካን ቡድን መሪው ተናግረዋል፡፡የተጀመረውን ለውጥ በአግባቡ ለማስተዳደር መንግስት ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ ተሳትፎን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ነው አቶ ታገሰ ለልዑካን ቡድኑ የተናገሩት፡፡ምክር ቤቱ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ጥያቄዎች ለማስተናገድና ለመፍታት በምክር ቤቱ በርካታ የለውጥ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ሀገራዊ ለውጡን በዘላቂነት ለማስቀጠል የአሜሪካ ኤምባሲ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ሲሆን፣ ኤምባሲው እያደረገው ላለው ጥረት አፈ- ጉባኤው አመስግነዋል፡፡(ምንጭ፡-የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት)
https://waltainfo.com/am/31391/
106
5ፖለቲካ
በቤተ መንግስት ግቢ የተሰራው የአንድነት ፓርክ በይፋ ተመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 11, 2019
Unknown
የመደመር እሳቤ ማሳያ እንደሆነ የተገለፀው የአንድነት ፓርክ በታላቁ ቤተመንግስት የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ በብሄራዊ ቤተ መንግስት ግቢ በሚገኘው የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገቡት የኬኒያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ፣ የኡጋንዳው ፕሬዘዳንት ዮሪ ሙሶቬኒ፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሙሃመድ አብዱላሂ ሙሃመድ፣ የደቡብ ሡዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ማያርዲት እና የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ አምዶክ ተሳትፈዋል፡፡በተጨማሪም አምባሳደሮች፣ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና ከተለያየ መስሪያ ቤት የተጋበዙ በርካታ እንግዶችም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡የኢትዮጵያ ያለፉ ታሪካዊና ማህበራዊ እሴቶች እየተዘከሩና ለመጪው ትውልድ እየጎለበተ እንድሄድ ሁሉም ታሪኩን እንዲጎበኝ በማሰብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሃሳብ አመንጪነት በታላቁ ቤተ መንግስት የተገነባው የአንድነት ፓርክ የኢትዮጵያን ገጽታ በመገንባት ረገድም ጉልህ ሚናን ይጫወታል ተብሎ ታምኖበታል።የአንድነት ፓርክ ለጋራ ግብ በአንድነት በመቆም የፍፃሜውን ምዕራፍ ዘመን ተሻጋሪ በሆነ የሕብረት አቅም ማጠናቀቅ የመቻል ተምሳሌት እንደሆነ ተገልጿል።ፕሮጀክቱ በግዝፈቱ በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ባይመስልም፤ በተያዘለት አጭር ጊዜ እውን መሆኑ ይበል አሰኝቷል፡፡በታላቁ ቤተመንስት ማምሻውን በተካሄደ ስነ-ስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የአንድነት ፓርክ እውን እንዲሆን እንዲሁም ሀገራዊ ለውጡ እንዲሳካ ድጋፍ እያደረጉ ለሚገኙ ተቋማትና አካላትና ግለሰቦች እውቅና እንዲሁም ሜዳሊያ ሰጥተዋል፡፡በዝግጅቱ ንግግር ያደረጉት የኡጋንዳው ፕሬዘዳንት ዮሪ ሙሶቬኒ የአንድነት ፓርክ ትክክለኛ የአመለካከት ለውጥ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ይህን ሀሳብ ላመነጩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ እና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ንግግር አድርገዋል፡፡ያለፉትን ታሪካዊና ማህበራዊ እሴቶቻችን እየዘከርንና ለመጪው ትውልድ እያጎለበትን እንሂድ በማለት የጋበዘው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፤ ከሰኞ ጥቅምት 3 ፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ህብረተሰቡ 200 ብር በመክፈል ፓርኩን እንዲጎበኝ ጥሪ አቅርቧል፡፡በተጨማሪም 1 ሺህ ብር በመክፈል በአስጎብኚ በመታገዝ በቪአይፒ ትኬት ቤተ መንግስቱን መጎብኘት እንደሚቻልም ነው የተገለፀው፡፡የጉብኝቱ መርሃ ግብሩ በይፋ ሲከፈትም የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በቤተ መንግስት ግቢ የተሰራውን የአንድነት ፓርክ ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡ቅዳሜ እና እሁድ የእድሜ ባለፀጎች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች ቤተ መንግስቱን እንደሚጎበኙ ተነግሯል።በቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ የተሰራው አንድነት ፓርክ በ40 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፤ ለግንባታው 5 ቢሊየን ብር ወጪ ጠይቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32788/
303
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ላይ የሞት ቅጣት ልትጥል ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
October 11, 2019
Unknown
የኡጋንዳ ስነ-ምግባርና ግብረገብነት ሚኒስትር እ.አ.አ. በ2014 ቀርቶ የነበረውን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን በሞት የሚቀጣውን ህግ በድጋሚ ሊያስተዋውቅ መሆኑን ገለጸ።ሚኒስትሩ ሲሞን ሎኮዶ አዲሱ ረቂቅ ወደ ህግነት ሲቀየር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ሲፈፅሙ የተገኙ የሞት ፍርድ ይጠብቃቸዋል ብለዋል። ''አሁን በስራ ላይ ያለው የወንጀለኛ መቅጫ ህጋችን ውስንነት ይታይበታል። ተግባሩ ወንጀል መሆኑን ብቻ ነው የሚገልጸው። በዚህ ተግባር ተሰማርቶ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ማድረግ እንፈልጋለን። ጥፋተኛ የተባሉትም የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል።'' ሚኒስትሩ አክለውም ''የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ለኡጋንውዳውያን ተፈጥሯዊ አይደለም። የዚሁ ሃሳብ አቀንቃኞች በትምህርት ቤቶች ጭምር ተፈጥሯዊና ምንም ችግር የሌለው ነው በማለት አባላትን ሲመለምሉ ነበር'' ብለዋል። በ2014 የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ረቂቅ ህጉን ለማጽደቅና ጠበቅ ያለ ቅጣት እንዲኖር ፊርማቸውን ቢያኖሩም በዛው ዓመት የሃገሪቱ ሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ውድቅ አድርጎት ነበር። ሲሞን ሎኮዶ እንደገለጹት ረቂቅ ህጉ በመጪዎቹ ሳምንታት ለተወካዮች ምክር የሚቀርብ ሲሆን፣ በአሁኑ ግን የፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ እና የህዝብ ተወካዮችን ድጋፍ አግኝቷል። ለህዝብ ተወካዮች ቀርቦም ሁለት ሶስተኛ ድምጽ አግኝቶ ተግባራዊ እንደሚሆን እንገምታለን ሲሉ ተደምጠዋል ሚኒስትሩ። ከአምስት ዓመት በፊት ሃገሪቱ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ስትጀምር አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት የቪዛ ክልከላ፣ ድጋፍ ማቆምና ወታደራዊ ልምምድ እስከ ማገድ ደርሰው ነበር። ሚኒስትሩ ግን ማንኛውም አይነት ምላሽ እንደማያስቆማቸውም ሲገልፁ ''ማንም እንዲያስፈራራን አንፈቅድም። እርምጃው በተለይ በበጀትና አስተዳደር ዙሪያ ያሉ ደጋፊዎቻችንን እንደሚያስቆጣ እናውቃለን። ነገር ግን የእኛ ያልሆነ ባህልን ሊጭኑብን ለሚያስቡ ሰዎች አንገታችንን ደፍተን ማሳየት አንፈልግም'' ብለዋል ሲል ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/33482/
209
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአዲስ አበባ ዘመናዊ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል ግንባታ እሁድ ይጀምራል
ቢዝነስ
October 11, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል ህንጻ ግንባታ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡የግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓቱ እሁድ ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ የከተማዋና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ይከናወናል፡፡ህንጻው ከመሬት ስር የሚገነቡ አራት ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን፤ ከትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል በተጨማሪ መረጃ ማደራጃ ክፍሎች፣ የወንጀልና የአደጋ መከላከያ መረጃ ቢሮዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ያካትታል፡፡ፕሮጀክቱ ከመሬት ስር የሚጠናቀቅ ሲሆን ከመሬት በላይ ለአረንጓዴ ልማት እንደሚውል ተገልጿል፡፡በማዕከሉ በሚገጠሙ ግዙፍ የቴሌቪዥን ስክሪኖች አማካኝነት የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ በቀጥታ ማየትና መቆጣጠር የሚቻል በመሆኑ የከተማዋን የትራፊክ ቁጥጥር ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ያግዛል ተብሎ ይታመናል፡፡ማዕከሉ የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ በመቆጣጠር ከሚያበረክተው አስተዋጽዖ በተጨማሪ በከተማዋ የጸጥታ፣ የአደጋ ቁጥጥርና የወንጀል ቁጥጥር ስራዎችም ላይ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታል ተብሏል፡፡በማዕከሉ ውስጥ የትራፊክ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የትራፊክ መብራቶችን የቆይታ ጊዜ እንደ ትራፊክ ፍሰቱ መጠን የመቀያየርና ልዩ ልዩ የትራፊክ ፍሰት ማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የማድረግ ስራም ይከናወንበታል፡፡በተጨማሪም አሽከርካሪዎች የመንገዶችን የትራፊክ ሁኔታ ቀድመው እንዲያውቁና አማራጭ መንገዶችን እንዲፈልጉ መረጃ የመስጠት፣ የትራፊክ ህጎችን የሚተላለፉ አሽከርካሪዎችን የመለየት እንዲሁም የትራፊክ ፍሰት፣ የአደጋ እና የደህንነት መረጃዎች ወደሚመለከታቸው ልዩ ልዩ ተቋማት በጊዜው እንዲተላለፉ ማድረግ ያስችላል፡፡የማዕከሉ ግንባታ ሙሉ ወጪ በከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፈን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የተገኘ መረጃ አመልክቷል፡፡በዕለቱ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ሴክተር መስሪያ ቤቶች ህንጻ ግንባታም እንደሚጀመር ተጠቁሟል፡፡
https://waltainfo.com/am/24002/
186
3ቢዝነስ
የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከብ በሳዑዲ አረቢያ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ መመታቷ ተነገረ
ፖለቲካ
October 11, 2019
Unknown
የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከብ በቀይ ባህር ሳዑዲ አረቢያ አቅራቢያ በሮኬት ተመትታ መጋየቷን የኢራን ሚዲያዎች ገልፀዋል።ንብረትነቷ የኢራን ብሄራዊ የነዳጅ ኩባንያ እንደሆነ የተገለፀው ነዳጅ ጫኝ መርከብ የሳዑዲ የወደብ ከተማ ከሆነችው ጀዳ 97 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በእሳት መያያዟን የኢራን ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ አስታውቋል።መርከቧ በሽብርተኞች በተፈፀመ ጥቃት በእሳት ሳትያያዝ እንዳልቀረ  ተገምቷል፡፡ፍንዳታው በመርከቧ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ ጭናው የነበረው የነዳጅ ዘይት ወደ ባህሩ እየፈሰሰ እንደሚገኝ የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ምንጭ፡- አልጀዚራ
https://waltainfo.com/am/34013/
66
5ፖለቲካ
12ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በጥቅምት 3 እንደሚከበር ተገለጸ
ፖለቲካ
October 10, 2019
Unknown
12ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ “ሰንደቅ አላማችን የብዝሀነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚከበር ተገለጸ፡፡ቀኑ ሲከበር መንግስት የሚተገብራቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎች፣ ስለ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች፣ ስለ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና በፌዴራል ስርዓቱ ውስጥ ስለህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት የጋራ መግባባት በሚፈጥር መልኩ በመወያየት እንደሚሆንም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡በሕገ-መንግሥቱም ሆነ በአዋጆች ዕውቅና ያገኘውን ሰንደቅ ዓላማ ማክበርና በጋራ ከፍ አድርጎ ማውለብለብ ተገቢ እንደሆነም ምክር ቤቱ አሳስቧል፡፡የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰንደቅ ዓላማ የአገራችን ሉዓላዊነትና የሕዝቦች በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት መገለጫ ነው፡፡ (ምንጭ፡-የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት)
https://waltainfo.com/am/31390/
92
5ፖለቲካ
ዓለም አቀፍ የእይታ ቀን እየተከበረ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
October 10, 2019
Unknown
ዓለም አቀፍ የእይታ ቀንን በማስመልከት በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ ተማሪዎች ነፃ የዓይን ምርመራና ሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው፡፡ቀኑን በማስመልከት በግላኮማ፣ ትራኮማ እና የዓይን ግርዶሽ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ የዓይን ህክምና ባለሙያዎች በተገኙበት በትምህርት ቤቱ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ በዕለቱ ተገኝተው እንደተናገሩት በኢትዮጵያ የዓይን ብርሃናቸውን ከሚያጡት 80 በመቶ የሚሆኑት በወቅቱ ባለመመርመራቸውና በአግባቡ ሕክምና ባለመውሰዳቸው መዳን እየቻሉ ለዓይነ ስውርነት እየተጋለጡ ነው፡፡  የጤና ሚኒስቴር ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በትምህርት ቤቶች የምርመራ የንጽህና አጠባበቅ ሥልጠናዎችን በመስጠት ለዓይን ብርሃን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ዶክተር ሊያ አክለው ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም ችግሩን ለመቅረፍ እንዲቻል በ2011 ዓ.ም ለ80 ሺህ ዜጎች የአይን ሞራ ግርዶሽ ገፈፋ፣ ለ610 ሺህ ያህሉ ደግሞ የትራኮማ ህክምና አገልግልት መሰጠቱ ታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ 330ሺህ ያህሉ ሕክምናውን ለመውሰድ እየተጠባበቁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡በኢትዮጵያ የዓይን ሞራ ግርዶሽ 50 በመቶ፣ ትራኮማ 11 በመቶ እንዲሁም 5 በመቶ ያህል ዜጎች በግላኮማ ህመም እንደሚጠቁና ችግሩን ለመቅረፍ እንዲቻል ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡የነፃ የዓይን ምርመራና ሕክምና አገልግሎቱና ውይይቱ አስከ ነገ ድረስ “ለእይታችን ቅድሚያ እንስጥ!” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32789/
165
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ሰላምን ለማስፈን እያደረገችው ያለው ጥረት ተደነቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 10, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ሰላምን ለማስፈን እያደረገችው ያለውን ጥረት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር/ዩኤንኤችሲአር/ አደነቀ፡፡ኮሚሽነሩ ሀገሪቱ በየጊዜው እያሻሻለች ባለው ፖሊሲዋ አማካኝነት ለስደተኞች የምታደርገውን ድጋፍም አድንቋል፡፡በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ የተመራ ልዑክ በ70ኛው የድርጅቱ ከፍተኛ ኮሚሽነሮች ስራ አስፈፃሚ ጉባኤ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አመራር በሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንና በደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ሁኔታዎችን በማመቻቸት የተጫወቱት ሚናን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አዲሱ ቀብኔሳ ኢብሳ አድንቀዋል፡፡ኢትዮጵያ ከ940 ሺህ የሚልቁ ስደተኞች ተቀብላ በማስተናገድ ላይ እንደምትገኝ ያስታወሱት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራሉ፤ አለምአቀፉ ማህበረሰብ ስደተኞችን በመደገፍ ረገድ የሚታዩበት ክፍተቶችን መድፈን እንደሚገባም ነው የገለፁት፡፡የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የተሻለ ህይወትን ለመምራት የሚፈልጉ ዜጎችን በመደገፍ እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንዲያጠናክርም ጠይቀዋል፡፡ከመስከረም 26 እስከ 30፣ 2012 ዓ.ም በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ጉባኤ ከ120 ሀገራት የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው ዘገባ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32790/
144
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢትዮጵያ እና የብሪታኒያ ደህንነት በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ
ፖለቲካ
October 10, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ የደህንነት አገልግሎት በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል ተስማሙየብሪታኒያ ሴክሬት ኢንተለጀንስ ሰርቪስ በአፍሪካ ቀንድ እያደገ የመጣውን ሽብርተኝነት ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በቅንጅት ለመከላከል ተስማማ፡፡ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ከእንግሊዙ ሴክሬት ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ኃላፊ ሰር አሌክስ ያንገር ጋር በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ባለው ወቅታዊ የፀጥታና የሽብርተኝነት ስጋት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ኮሚሽነር ደመላሽ ከሀላፊው ጋር ባደረጉት ዉይይት በአፍሪካ ቀንድ የሽብር እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉትን የአልሸባብና የአይኤስ የሽብር ቡድኖች እንቅስቃሴን ለመግታት ሁለቱ ሀገራት የጀመሩትን የመረጃ ልውውጥ አጠናክረው በመቀጠል በአፍሪካ ቀንድ የሚስተዋለውን የሽብርተኝነት አደጋ ለመከላከል በጋራ እንደሚሰሩ መግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል፡፡ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በሰው ኃይል፣ በአደረጃጀት፣ በአሰራርና በቴክኖሎጂ ራሱን ለማጠናከር የሚያስችሉ የሪፎርም ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የጠቆሙት ኮሚሽነር ደመላሽ፤ ተቋሙ ተልእኮውን በተሻለ መንገድ ለመፈፀም የሚያስቸለውን አመቺ የሆኑ የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑን ለኃላፊው አብራርተውላቸዋል፡፡የእንግሊዙ ሴክሬት ኢንተለጀንስ ሰርቪስ በመረጃና ደህንነት ዘርፍ ያለውን የዳበረ ልምድ ለኢትዮጵያው አቻ ተቋም ለማካፈል ስምምነት ላይ የተደረሰ መሆኑን በመግለጽ፤ ይህ ሁለቱም በአካባቢው ያለውን የሽብር አደጋና አለመረጋጋት በጋራ ለመከላከል ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ኮሚሽነር ደመላሽ ገልጸዋል፡፡የሁለቱ አገራት የመረጃና ደህንነት ተቋማት የቆየ ግንኙነት እንዳላቸው የጠቀሱት ዳይሬክተር ጄነራል ኮሚሽነር ደመላሽ፤ ይህን የቆየ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ መግባባት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል፡፡የእንግሊዙ ሴክሬት ኢንተለጀንስ ሰርቪስ ኃላፊ ሰር አሌክስ ያንገር በበኩላቸው በሁለቱ አገራት የፀጥታና የደህንነት የጋራ ጉዳዮች እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ዙሪያ ከዳይሬክተር ጄነራሉ ጋር ውይይት መደረጉን ገልፀው፤ በቀጣይ የፀረ-ሽብር እንቅስቃሴን በተመለከተ ስለሚኖራቸው የጋራ ትብብር መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡በተጨማሪም ሰር አሌክስ ያንገር በቅርቡ ኢትዮጵያ በሽብርተኞች ላይ የወሰደቸውን እርምጃ አድንቀው፤ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት እያካሄደ ያለው ሪፎርም ትልቅ የለውጥ እርምጃ በመሆኑ በቀጣይ ተቋማቸው ለአገልግሎቱ የአቅም ግንባታና የተሞክሮ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ (ምንጭ፡- ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት)
https://waltainfo.com/am/31386/
260
5ፖለቲካ
ምክር ቤቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላለፈ
ፖለቲካ
October 10, 2019
Unknown
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ምክር ቤቱ በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባው የምክር ቤቱን 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ አፅድቋል፡፡የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ መስከረም 26፣2012 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ መክፈቻ መደበኛ ስብሰባ ላይ ያቀረቡትን እቅድ አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን በማድመጥ አፅድቋል፡፡የመድን ስራ ዐዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ ዐዋጅን መርምሮ ያፀደቀ ሲሆን ፤ በሰው መነገድና ሰዎችን በህገ ወጥ መልኩ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ ዐዋጅን ጨምሮ 10 ረቂቅ አዋጆችን ለዝርዝር እይታ እና ምርመራ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል። ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ረቂቅ ዐዋጅ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት በማረሚያቤቶች የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳይደገሙ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት በምክር ቤቱ አባላት ተነስቷል፡፡በተጨማሪም ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ጋር ለልማት ፖሊሲ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት እና ከአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት ጋር  የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረቡ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።ከብድር ጋር ተያይዞ ሀገሪቱ የመክፈል አቅሟ በተዳከመበት ወቅት የብድር ስምምነት መፈፀሙ እንዴት ይታያል የሚሉና ብድሮች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ባለጋገጠ መልኩ ስራ ላይ እንዲውሉ ጥንቃቄ እንዲደረግ ሃሳብ ቀርቧል፡፡ከዚህ በፊት በተፈቀዱ ብድሮች ዙሪያም በቀጣይ በቂ ማብራሪያ እንደሚሰጥና የምክርቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡ምክርቤቱ በተጨማሪ የአነስተኛ ፋይናንስ ሥራ አዋጅን ለማሻሻል፣ የፌዴራል ድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ስርዓትና ተቋማዊ አደረጃጀትን ለመወሰን ፣የመድን ሥራ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31389/
214
5ፖለቲካ
በአንድነት ፓርክ ምረቃ ላይ የተጋበዙ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ነው
ፖለቲካ
October 10, 2019
Unknown
አዲሱ የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪርና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሐመድ አብደላሂ በአንድነት ፓርክ ምረቃ ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡መሪዎቹ ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ የገቡት በታላቁ ቤተ መንግስት በተገነባው የአንድነት ፓርክ ይፋዊ የምርቃ ስነ ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት ለመገኘት ነው፡፡መሪዎቹ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ከፍተኛ የመንግስት ባስልጣናትና የየሀገራቱ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አባላት ተቀብለዋቸዋል፡፡በአንድነት ፓርክ ይፋዊ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ መሪዎችም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
https://waltainfo.com/am/31388/
79
5ፖለቲካ