headline
stringlengths
2
1.42k
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
9
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
63
36.2k
link
stringlengths
28
740
word_len
int64
16
6.74k
label
class label
6 classes
የሱዳን ወታደራዊ ምክርቤት እና የተቃዋሚዎች ጥምረት ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ላይ ከስምምነት መድረሳቸው ተነገረ
ፖለቲካ
August 3, 2019
Unknown
የሱዳን ወታደራዊ ምክርቤት እና የተቃዋሚዎች ጥምረት ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ላይ ከስምምነት መድረሳቸው ተነገረሱዳንን እያስተዳደረ ያለው ወታደራዊ ምክር ቤትና ዋነኛው የተቃዋሚዎች ጥምረት በሀገሪቱ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት በር ይከፍታል በተባለለት ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ላይ ከስምምነት ደርሰዋል ተብሏል።ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ መረጋጋት የተሳናት ሱዳን፤ወታደራዊው ምክር ቤት ስልጣኑን ከተቆናጠጠ በኋላም የሲቪል መንግስት ይመስረት በሚል ተቃዋሚዎች ድምጻቸውን ሲያሰሙ በመቆየታቸው መረጋጋት ተስኗት ቆይቷል።በዚህም ምክንያት አገሪቷን እያስተዳደረ ያለው ወታደራዊ ምክር ቤቱና ዋነኛው የተቃዋሚዎች ጥምረት ከስምምነት ለመድረስ በርካታ ውይይቶችን ቢያደርጉም ሳይሳካ መቆየቱ ይታወሳል፡፡አሁን ግን ሁለቱ ሐይሎች የሽግግር መንግሥት ለመመስረት በር ይከፍታል በተባለለት ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ላይ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪው ሞሀመድ ሀሰን ሌባት ስምምነቱን ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን ከመግለጽ ተቆጥበዋል ተብሏል፡፡በሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌው ላይ እየተካሄደ የነበረው ድርድር በመራዘሙ በሀገሪቱ የተከሰተው ግጭት መቋጫ እንዲያጣ አድርጎት መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ሲጠበቅ የነበረው ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌው ላይ ከስምምነት መደረሱ እንደተሰማም የሱዳን ጎዳናዎች ደስታቸውን በሚገልጹ ዜጎች መሞላቱ ተዘግቧል።ሰነዱ ባለፈው ወር በወታደራዊ ምክርቤቱና በተቋዋሚዎች መካከል የሶስት አመት የሽግግር መንግስት ለመመስረት የተቀመጠውን ስምምነት ይዘረዝራል፡፡ዘገባው የቢቢሲ ነው።
https://waltainfo.com/am/33316/
152
5ፖለቲካ
553 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረብያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 2, 2019
Unknown
በሳዑዲ አረብያ ጂዛን ግዛት ኢዋ እና ሲጂን ነዓም በተሰኙ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 280 ኢትዮጵያውያን ትናንት  ሀምሌ 25 ቀን 2011 ዓም ከሌሊቱ በ8፡30  ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።ኢትዮጵያዊያኑ ከ5 ዓመት እስከ 30 ዓመት ድረስ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ መንግስት ጅዳ በሚገኘው የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት በኩል የሳዑዲ መንግስት ምህረት እንዲያደርግላቸው በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።ቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኮንሱላር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ዮሃንስ ሾዴ እና ሌሎች አካላት በተገኙበተ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።በተመሳሳይ በጅዳ እና ጂዛን ግዛት ያለ ህጋዊ የጉዞ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 273 ኢትዮጵያውን ረቡዕ ሀምሌ 24 ቀን 2011 ዓም ምሽት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ከእነዚህ ተመላሾች ውስጥ 75ቱ ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወንዶች ናቸው።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተለያዩ ሀገራት በእስር ላይ የሚገኙ ኢትጵያውያንን በማስፈታት በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩም በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው  እንዲመለሱ  እየሰራ መሁኑን ለዋልታ በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡  
https://waltainfo.com/am/32614/
140
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአማራ ክልል ከ4 ሚሊየን በላይ ወጣቶችን በበጎ ፈቃድ ተግባራት ለማሳተፍ እየተሰራ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 2, 2019
Unknown
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ወጣቶችን በያዝነው ክረምት በበጎ ፈቃድ ተግባራት እያሳተፈ ነው፡፡የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አባይነህ መላኩ የ2011 ዓ.ም ክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሐምሌ 3፣ 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በክልሉ 129 ወረዳዎች 2 ሚሊየን 425 ሺህ 580 ወጣቶች ወደ ሥራ መሰማራታቸውንም ነው አቶ አባይነህ የተናገሩት፡፡ የተሰማሩባቸው ተግባራትም ማጠናከሪያ ትምህርት፣ ችግኝ ተከላ፣ ጤና እንክብካቤ፣ ደም ልገሳ እና ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፎች ናቸው ብለዋል፡፡ቀድመው ወደ ሥራ የገቡትን ጨምሮ በያዝነው ክረምት 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ወጣቶችን በበጎ ፈቃድ ተግባራት ለማሰማራት እንደታሰበም የቢሮው መረጃ ያሳያል፡፡ከአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ይህም መንግስትና ኅብረተሰቡ ለሥራው የሚያወጡትን 9 ቢሊዮን የሚጠጋ ብር ማስቀረት እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡  
https://waltainfo.com/am/32613/
108
0ሀገር አቀፍ ዜና
ቻይና 206 ሚሊየን ብር የሚያወጣ እህል ለገሰች
ሀገር አቀፍ ዜና
August 2, 2019
Unknown
የቻይና መንግስት 206 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 7ሺህ 408 ሜትሪክ ቶን ስንዴና 579 ሜትሪክ ቶን ነጭ ሩዝ የሰብዓዊ እርዳታ ማድረጉ ተገለጸ፡፡ድጋፉ የተከናወነው ቀደም ሲል የሁለቱ አገሮች መንግስታት ባደረጉት ስምምነት መሰረት ነው፡፡የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሣ ድጋፉ በሀገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች ለተፈናቀሉ እና ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች እንዲውል እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ የቻይና መንግሰትም ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን በበኩላቸው እንደኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያሉ አገራት የምግብ ዋስትናቸውን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ግብርናቸውን ማዘመን እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡በመድረኩ የተሳተፉት ሌሎች አገራትም ከዚህ ቀደም መቶ ሚሊየን የቻይና ገንዘብ ዮዋን በየዓመቱ በቀጣይነት ለመስጠት ቃል ገብተው የነበረ ሲሆን፣ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32615/
101
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሞቃዲሾ ከተማ ከንቲባ በቦንብ ጥቃት ህይወታቸው አለፈ
ፖለቲካ
August 2, 2019
Unknown
የሞቃዲሾ ከተማ ከንቲባ አብዱራህማን ዑመር ህይወታቸው ያለፈው በጽህፈት ቤታቸው በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት መሆኑ ተገልጿል፡፡ከንቲባው ከቦንብ ጥቃቱ  በኋላ በኳታር ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ  ህይወታቸው ማለፉን ነው የሶማሊያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የገለፁት፡፡በብሪታኒያ የተወለዱት ከንቲባው  የሌበር ፓርቲ አባል ሆነው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በጦርነት የስትታመስ የቆየችውን ሶማሊያ  መልሶ በመገንባቱ ሂደት አስተዋፅኦ ለማድረግ በማሰብ ነበር ወደ ሶማሊያ ያቀኑት።የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ አብዱላሂ የከንቲባውን ህልፈት ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሃዘን ማወጃቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/33315/
67
5ፖለቲካ
በጎማ ከተማ ሶሰተኛው የኢቦላ ታማሚ ተገኘ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 2, 2019
Unknown
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሩዋንዳ አዋሳኝዋ ጎማ ከተማ ሶሰተኛው የኢቦላ ታማሚ መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡በዚህም ከቫይረሱ ስርጭት ስጋት ጋር በተያያዘ ሩዋንዳ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷ ተነግሯል፡፡ ይሁንና የሩዋንዳ የጤና ሚኒስቴር ይህን አስተባብሏል፡፡የ2 ሚሊየን ዜጎች መኖሪያ የሆነችው በሩዋንዳ አዋሳኝ አካባቢ በምትገኘው የዴሞክራቲክ ሪፓፕሊክ ኮንጎ ጎማ ከተማ ሶስተኛዋ የአንድ አመት ሴት ልጅ የኢቦላ ቫይረስ ታማሚ መገኘቷን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡ምንም እንኳ አሁን ላይ ህፃኗ በሆስፒታል ብትሆንም በትናንትናው ዕለት ህይወቱ ያለፈው አባቷ በበሽታው እንደተያዘ ከመረጋገጡ በፊት ከቤተሰቦቹ ጋር ለበርካታ ቀናት ቆይቷል ነው የተባለው፡፡በዚህም ቫይረሱ ወደ ቤተሰቦቹ እና ሌሎች ያልታወቁ ሰዎች ተሰራጭቶ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡ምንጭ፡- አልጀዚራ
https://waltainfo.com/am/33458/
93
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ያለማንም ረዳት እንዲጓዙ ፈቀደች
ሀገር አቀፍ ዜና
August 2, 2019
Unknown
ባለፈው አርብ ይፋ የተደረገው አዲሱ ሕግ፤ እድሜያቸው ከ21 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች ያለወንድ ረዳቶቻቸው ወይም አጋሮቻቸው ፈቃድ ፓስፖርት ለማውጣት ማመልከት እንዲችሉ ይፈቅዳል።ማንኛውም አዋቂ የሆነ ሰው ፓስፖርት ኖሮት ከአንድ አገር ወደሌላ እንዲጓዝ የሚያደርገው ሕግም ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ መብት ረገድ ሴቶችን ከወንዶች እኩል አድርጓቸዋል።ሕጉ ጨምሮ እንዳስቀመጠው ሴቶች የውልደትን፣ ጋብቻንና ፍቺን ማስመዝገብ እንዲችሉም ተፈቅዷል።ከዚህም በተጨማሪም የሴቶችን የሥራ እድል የሚመለከተውን የሥራ ቅጥር ሕግ ተመልክቷል። በዚህ ሕግ ማንኛውም የአገሪቱ ዜጋ ያለምንም ልዩነት፤ ያለ ፆታ፣ የአካል ጉዳት ወይም እድሜ መድልዎ እኩል የመሥራት መብት እንዳላቸው አትቷል።እስካሁን ድረስ የሳዑዲ ሴቶች ፓስፖርት ለማግኘትና ወደ ሌላ አገር ጉዞ ለማድረግ ከትዳር አጋራቸው፣ ከአባታቸው አሊያም ከሌላ ወንድ ዘመዳቸው ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸው ነበር።ከዚህ ቀደም የሳዑዲ አረቢያው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን ሴቶች ማሽከርከር እንዳይችሉ የሚከለክለውን ሕግ ማንሳታቸው ይታወሳል።ይህም በአገሪቷ ለሴቶች እድሎች እየተከፈቱ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው ተብሏል።ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን የሴቶችን በሥራ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ከነበረው 22 በመቶ ወደ 30 በመቶ ከፍ በማድረግ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በ2030 ለማሳደግ ዓላማ ይዘው እየሠሩ መሆናቸውን ከሦስት ዓመታት በፊት አስታውቀው ነበር።ይሁን እንጂ በርካታ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው ሴቶች የሚደርስባቸውን የፆታ መድልዎ ምክንያት በማድረግ በካናዳና በተለያዩ አገራት ጥገኝነት ይጠይቃሉ።ባለፈው ጥር ወር የ18 ዓመቷ ራሃፍ መሀመድ አልቁኑን በካናዳ ጥገኝነት ተሰጥቷታል። ራሃፍ ከሳዑዲ አረቢያ የተሰደደች ሲሆን ወደ አውስትራሊያ ለመግባት ሞክራ ነበር። በመጨረሻም በታይላንድ ባንኮክ አየር ማረፊያ ሆቴል ተይዛ ዓለም አቀፍ እርዳታ እንዲደረግላት ጠይቃለች።ይህች ሴት በአገሯ ላይ እንደሁለተኛ ዜጋ ተቆጥራላች ሲሉ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቅሬታቸውን ያሰሙ ነበር። (ምንጭ፡- ቢቢሲ)  
https://waltainfo.com/am/34122/
215
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢራን በባህረ ሰላጤ ‘ህገወጥ’ የነዳጅ ዘይት ጫኝ መርከብ መያዟ ተገለፀ
ቢዝነስ
August 5, 2019
Unknown
ኢራን በባህረ ሰላጤ ህገወጥ ነው ያለችውን የነዳጅ ዘይት ጫኝ መርከብ መያዟን የሀገሪቱ ሚዲያ አስታውቋል። የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ ኮማንደር በባህረሰላጤው በኩል ለአረብ ሀገራት በህገወጥ መንገድ ነዳጅ ዘይት ሊያስገባ ሲል መያዛቸውን መግለፃቸው ነው የተዘገበው፡፡ መርከቧ ከ700 ሺ በላይ ሊትር ነዳጅ ዘይት ስትንቀሳቀስ እንደነበርና ሰባት የመርከቧ ሰራተኞች አብረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። ኢራን በህገወጥ መንገድ የነዳጅ ዘይት ይዣለሁ ስትል ይህ ሁለተኛው ነው፤ ከሳምንታት በፊትም የኢራን የባህር ጠረፍ ጠባቂ የፓናማ ሰንደቅ አላማ የነበራትን መርከብ አግተው ነበር። የኢራን አብዮታዊ ዘብ በድረገፁ እንዳሳወቀው፣ በወቅቱ መርከቧ የተያዘችው የባህር ኃይሉ የተደራጀ ህገወጥ የነዳጅ ዘይት ዝውውርን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጥረት ነው። ባለፈው ወርም የእንግሊዝ ባንዲራን ታውለበልብ የነበረች ነዳጅ ጫኝ መርከብ በሃርሙዝ ስርጥ የውሃ ክልል ላይ እንደታገተች ነው። አሜሪካ እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ2015 በሁለቱ ሀገራት የተደረሰው የኒውክሌር ስምምነት ራሷን ካገለለች በኋላ በኢራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ መጣሏን ተከትሎ በባህረ ሰላጤው አካባቢ ውጥረት መንገሱ ተገልጿል። በኦማን ባህረ ሰላጤ ለተፈፀሙ ሁለት የተለያዩ የነዳጅ መርከብ ጥቃቶች አሜሪካ ኢራንን መወንጀሏ የሚታወስ ነው። በሃርሙዝ የቀጠና የበረራ ቅኝት ላይ የነበረ ሰው አልባ የአሜሪካ አውሮፕላን መትታ የጣለችው ኢራን በበኩሏ ይህንን ውንጀላ ውድቅ አድርጋለች። እስካሁን ድረስ ነዳጅ ዘይት ጫኝ መርከቧ ባለቤትነት ያልታወቀ ሲሆን፣ የፋርስ ዜና ወኪል እንደዘገበው መርከቧን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ የተከናወነው ባለፈው ረቡዕ እለት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የመርከቧ ሰራተኞች ዜግነታቸው ግልፅ አልተደረገም። ነዳጅ ዘይት ጫኝ መርከቧ ቡሸህር የሚባል ቦታ የተወሰደች ሲሆን፣ ነዳጁም ለባለስልጣናቱ እንደተላለፈም ዘገባው ጨምሮ አስነብቧል። ከየትኛውም ሀገርም መርከቤ ጠፍቶብኛል ወይም ታግቶብኛል የሚል መግለጫም እንዳልወጣም ተገልጿል። የቢቢሲ አረብኛው ኤዲተር ሰባስቲያን የነዳጅ ዘይት ጫኝ መርከቧ ምንም እንኳን ትልቅ ባትሆንም በቀጠናው ያለውን ውጥረት ሊያባብሰው እንደሚችል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33557/
240
3ቢዝነስ
የመቀንጨር ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት በቅንጅት መስራት ይገባል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 1, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ በህጻናት ላይ የሚታየውን የመቀንጨር ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ችግሩ ባለባቸው ቦታዎች የበጀት ድጋፍ ማጠናከርና ዘርፉን መሰረት አድርገው የሚሰሩ ዘርፎች ተቀናጅተው መስራት አለባቸው ተባለ፡፡ለዚህ ስኬትም በኢትዮጵያ የችግሩን መንስኤዎች ለመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማመላከት ችግሩ በሚታይባቸው ቦታዎች ጥናት ተደርጓል፡፡ ጥናቱን ያዘጋጁት “አክሽን አጌነስት ሃንገር” እና “ዋተር ኤይድ” የተባሉ ድርጅቶች ናቸው፡፡በጉዳዩ ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ድርጅቶች በቅንጅት እና በመናበብ አለመስራት፣ የህብረተሰቡ የግንዛቤ እጥረት፣ የበጀት እጥረት ችግሩ እንዲቀጥል የሚያደርጉ ምክንያቶች እንደሆኑ በጥናቱ ተመላክተዋል፡፡ህጻናት ጤናማ አዕምሮና አካል ኖሯቸው ብቁ ዜጎች እንዲሆኑ በጥናቱ የተለዩ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ የዋተር ኤይድ የሴክተር ግንባታ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ጽጌሬዳ አብርሃም ገልጸዋል፡፡በንጽህና ጉድለት የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎችን ከምንጫቸው ለማጥፋት በውሃና ሥነምግብ ላይ ትኩረት ያደረገ ግንዛቤ ለህብረተሰቡ መሰጠት ይኖርበታል ያሉት ደግሞ  የ”ዋሽ” ቴክኒካል ዳይሬክተር  አቶ ተክለማሪያም አያሌው ናቸው፡፡በየደረጃው  ያሉ የአመራር አካላትና በዘርፉ ላይ የሚሰሩ ተቋማት መረጃዎችን በመጋራትና በመናበብ ቢሰሩ ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻልም የ”አክሽን አጌነስት ሃንገር” የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ፓኖስ ናቭሮዚዲስ ገልፀዋል፡፡በኢትዮጵያ 39 በመቶ ያህል ህጻናት የመቀንጨር ችግር እንዳለባቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር 2030 የህጻናትን የመቀንጨር ችግር ከምድረገጽ ለማጥፋት ሃገራት ተስማምተው እየሰሩ ነው፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32611/
157
0ሀገር አቀፍ ዜና
ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚደረገው የሰራተኞች የሥራ ስምሪት በይፋ ተጀመረ
ቢዝነስ
August 1, 2019
Unknown
መርሃ ግብሩን የኢትዮጵያ መንግስትን በመወከል የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በመወከል ደግሞ በኢትዮጵያ የሳዑዲ አምባሳደር ሳኒ ጀማል አብደላ አስጀምረዋል፡፡ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ  ቀደም ሲል የነበራቸውን የቆየ ግንኙነት ለማጠናከር በበርካታ ዘርፎች እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡ሚኒስትሯ  ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚያቀኑ ዜጎችም የሀገራቸው አምባሳደር በመሆን ለሄዱበት ዓለማ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ሰራተኞቹ የሀገሪቱን ህግ በማክበር እንዲንቀሳቀሱና በህገወጥ ደላሎች የማማለያ ቃላት እንዳይሸነገሉም አሳስበዋል፡፡በኢትዮጵያ የሳዑዲ አምባሳደር ሳኒ ጀማል በበኩላቸው የሥራ ስምሪቱ ተቋርጦ የነበረው ስምሪቱ ህጋዊና ሙያዊ በሆነ ሁኔታ እንዲቀጥል በማሰብ ነው ብለዋል፡፡በቀጣይም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ባለሙሙዎች ሀገራቸው እንደምትፈልግና  ስምሪትም እንደምትጀምር መግለፃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/23889/
95
3ቢዝነስ
በአረንጓዴ አሻራ የታየው አንድነት በሌሎች መስኮችም ይደገማል- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
ፖለቲካ
August 2, 2019
Unknown
ከሰሞኑ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ህዝቡ ያሳየውን አንድነት በቀጣይ ዓመት በተለያዩ መስኮች ለመድገም መታሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡መንግስት ህዝቡ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንዲሳተፍ ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ ለሰጠውን መልካም ምላሽ ያመሰገኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በቀጣይም ይህን ተግባር በሌሎች መስኮች ለመድገም ዝግጅት መኖሩን አንስተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለጋዜጠኞች የሰጡት ማብራሪያ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ባጠነጠነው ማብራሪያቸው ኢህአዴግ ወደ ውህድ ፓርቲ ለመምጣት ጥናቶች እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡ከሰላምና ፀጥታ ጋር በተያያዘ የህግ የበላይነትን ለማስከበር መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ነው በመግለጫቸው የጠቆሙት፡፡ከሰኔ 15 ጥቃት በኋላ መንግስት የዜጎችን ድምፅ ለማፈን ጥረቶችን እያደረገ ነው ተብሎ ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄም መንግስት ድምፅ ለማፈን ፍላጎት እንደሌለው በመልሳቸው አንስተዋል፡፡ከመፈንቅለ መንግስቱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት መካከል 120 ያህሉ መፈታታቸውንና በድርጊቱ ተሳትፈዋል ተብሎ የተጠረጠሩትንም በማጣራት የመፍታት ሂደት ይቀጥላል ብለዋል።የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በመንግስት በኩል ጥረቶች እየጸደረጉ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አስተማማኝ የህግ ማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸውና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ማህበራዊ ይዘት ባላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31277/
150
5ፖለቲካ
የሻደይ አሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በጋራ እየተሰራ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 1, 2019
Unknown
የሻደይ አሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የአማራና የትግራይ ክልሎች በጋራ እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛት አብዩ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት የሻደይ አሸንዳ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የትግራይና አማራ ክልሎች በቅንጅት እየሰሩ ነው።በአማራና ትግራይ ክልሎች በተለያዩ አካባቢዎች የሚከበር መሆኑን የገለጹት ሃላፊው፥ ሁለቱ ክልሎች በዓሉን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ መስማማታቸውን አንስተዋል፡፡ በዓሉ “የኢትዮጵያ ልጃገረዶች ጨዋታ” በሚል ስያሜ በመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ቅርስነት ለማስመዝገብ በሁለቱ ክልሎች መካከል እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ምክክር ተደርጎ ስምምነት ላይ መደረሱን አክለዋል።በዓሉ በቅርስነት ለመመዝገብ በሒደት ላይ መሆኑን ያነሱት አቶ ግዛት፥ ኢትዮጵያም በዓሉን በቅርስነት ለማስመዝገብ ስትሰራ መቆየቷን አስታውሰዋል።በዓሉ በአማራ ክልል በወረዳና በዞን ደረጃ ከነሃሴ 16 እስከ 18 ቀን 2011 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን፥ በክልል ደረጃ ደግሞ በባህር ዳር ከተማ ከነሃሴ 19 እና 20 ቀን በድምቀት የሚከበር መሆኑ መገለፁን የዘገበው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ነው።
https://waltainfo.com/am/32612/
132
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኬንያ የመንግስታቱ ድርጅት አልሸባብን በአሸባሪ ድርጅትነት እንዲፈርጅ ጥሪ ልታቀርብ ነው
ፖለቲካ
August 1, 2019
Unknown
ኬንያ የሶማሊያው ታጣቂ ቡድን አልሸባብ በመንግስታቱ ድርጅት የአሸባሪ ቡድኖች ስም ዝርዝር እንዲካተት ለድርጅቱ ይፋዊ ጥያቄ ለማቅረብ ማቀዷን አስታውቃለች።ይህ የገሪቱ እርምጃ  አክራሪዎችን ለመከላከል የበለጠ ትኩረት የሰጠ ነው ተብሏል፡፡እ.አ.አ በ2010 ከአልቃይዳ ጋር በኋላም ከእስላሚክ ስቴት ጋር እንደሚተባበር የገለጸው አልሸባብ እስካሁን በተመድ የአሸባሪዎች መዝገብ ላይ አልተካተተም።የመንግስታቱ ድርጅት አሸባሪነትን እንደ ዓለም አቀፍ ስጋት የሚመለከተው ቢሆንም እስካሁን በድርጅቱ የአሸባሪዎች ስም ዝርዝር ተካተው ያሉት አልቃይዳ እና በኢራቅና ሶሪያ የሚንቀሳቀሰው እስላሚክ ስቴት ብቻ ናቸው።ምንጭ፦ ዘ ኢስት አፍሪካን
https://waltainfo.com/am/33314/
70
5ፖለቲካ
ኢህአዴግ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም አለው – ጠ/ሚ ዐቢይ
ፖለቲካ
August 1, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫቸውም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ከጥያቄዎቹም ከምርጫ ጋር የተያያዘው አንዱ ነበር።በዚህም በሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ይራዘም የሚሉ እና ወቅቱን ጠብቆ ይካሄድ የሚሉ የራሳቸው ምክንያት ያላቸው አካላት እንዳሉ አንስተዋል።ነገር ግን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባው ምርጫ ከማካሄድ ጋር በተያያዘ በዝርዝር እንደተወያየበትና ምርጫው አይደረግም የሚል አቋም እንደሌለው አስታውቀዋል።ኢህአዴግ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም አለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ለዚህም በቂ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም አያይዘው ጠቅሰዋል።ይሁን እንጂ ኢህአዴግ ምርጫው ይካሄድ የሚለው ላይ ብቻውን ውሳኔ ማሳለፍ አይችልም ያሉ ሲሆን፥ ሁሉን የፖለቲካ ፓርቲዎች በማሳተፍና በህዝቡ ይሁንታ የምርጫው ሁኔታ ላይ ከስምምነት በመድረስ እንደሚከናወንም አብራርተዋል።ከዚህ ጋር አያይዘውም አዲስ የምርጫ ህግ እየተዘጋጀ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ህጉ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሚመለከታቸውን አካላት ባሳተፈ መልኩ መዘጋጀቱን አንስተዋል። ሰሞኑን በህወሃትና በአዴፓ መካከል ባለው ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄም፥ ህወሃትና አዴፓ በየፊናቸው ያወጡት መግለጫ በፖለቲካው ዓለም የሚያጋጥም መሆኑን አንስተዋል።ሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለረጅም ዓመታት ለህዝብ ጥቅም ሲሉ አብረው ታግለዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር አብይ፥ በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ግን እንዲህ አይነት ንትርኮች አልታጡም ብለዋል።አሁንም በህወሃትና አዴፓ መካከል የተፈጠረው ነገር የሚያጋጥም መሆኑን በማንሳት፥ መግለጫው ግን በዚያ መንገድ ባይሆን ይመረጥ እንደነበረ አንስተዋል።ነገር ግን ጥይት እስከሌለው ድረስ በፖለቲካ ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶች አስደንጋጭ ሊሆኑ እንደማይገባም ነው ያስታወቁት።በቀጣይም የመግለጫ ምልልሱን እንዴት እንፍታው የሚለው ላይ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ትኩረት ሰጥተውበት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ሁለቱ ድርጅቶች ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ መድረክ እንደሚዘጋጅ አስታውቀዋል።የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ውህደትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ውህደቱን በተመለከተ ጥናት ሲደረግበት እንደቆየ እና ወደፊትም ሰፋፊ ውይይቶች እንደሚካሄዱበት ጠቅሰዋል።ከእህት ድርጅቶች ዘንድ ከውህደቱ በፊት መስተካከል አለባቸው በሚል የተነሱ ነጥቦች እንዳሉ በመጠቆም፤ ነገር ግን ውህደቱን መቀበል የማይፈልጉ ፓርቲዎች አሉ በሚል መውሰድ አይገባም ብለዋል።ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ተያይዞም ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ተቀባይነት እንደነበረ አሁን ግን እየተሸረሸረ መጥቷል በሚለው ለቀረበላቸው ጥያቄም፥ ተቀባይነት እንደነበረ አሁን ግን እየተሸረሸረ መጥቷል በሚለው በማስረጃ የተደገፈ አይደለም ብለዋል።ከዚህ ጋር ተያይዞ የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ እንደማሳያ መቅረብ እንደሌለበትና፤ ዳያስፖራው ለሀገሩ ሲል ትረስት ፈንዱን መደገፍ እንዳለበት ተናግረዋል።አሁንም ቢሆን ከሰብአዊ መብት አያያዘ ጋር ከለውጡ ወዲህ ወደኋላ የተመለሰ ነገር እንደሌለና እሳቸውም ይሁን ሀገርን የሚመራው ድርጅት በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው ገልፀዋል።ከህግ ማስከበር ጋር ተያይዞ ሁሉም ህግ ይከበር ይላል እንጂ የራሱን ወንጀለኛ አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለም ያሉ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት ህግ ይከበር በሚል የሚነሱ ቅሬታዎች እንደ ቂም መወጣጫ እየተቆጠሩ መምጣታቸውን አንስተዋል።ይሁን እንጂ መንግስት ህግ መከበር አለበት የሚል አቋም እንዳለው እና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጠል አስታውቀዋል።ከኢኮኖሚው አንፃርም በተለይም ከውጭ ምንዛሬ አንፃር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከዚህ በፊት ከነበሩ ዓመታት በተሻለ ገቢ መግባቱን በመጥቀስ፤ ነገር ግን የፍላጎት መጨመር ክፍተት ፈጥሮ እንደነበረ አስታውሰዋል።በውጭ ምንዛሬ ረገድ የተሰራውን ስራ በማጠናከር ችግሮቹን መቅረፍ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም አስታውቀዋል። የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን በተመለከተም፤ ክልል የመሆን ጥያቄው ለረጅም ዓመታት የነበረ መሆኑን እና ከለውጡ በኋላ ጎልቶ መውጣቱን አንስተዋል።የክልልነት ጥያቄው ከፖለቲካ በተጨማሪ የሀብት ክፍፍል እና ህጋዊ ሂደቶች ያስፈልጉታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ የክልልነት ጥያቄውን መሰረት በማድረግ ህዝበ ውሳኔው ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚከናወንም አስገንዝበዋል።ከችግኝ ተከላ ጋር በተያያዘ ህዝቡን በድጋሚ በማመስገን በቀጣይም ህዝቡ በተከላው ያሳየውን ርብርብ ችግኞቹን ተንከባክቦ ማሳደግ ላይ እንዲደግመውም ጥሪ አቅርበዋል።ከዚህ ጋር በተያያዘ የችግኝ ተከላውን ለማስፈጸም የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ የተተከሉ ችግኞችን የመከታተል ስራ እና ለቀጣይ ዓመት ችግኝ ተከላ ከወዲሁ ሰፋፊ የቅድመ ዝግጀት ስራዎችን ቀጥሎ እንደሚሰራም አስታውቀዋል። 
https://waltainfo.com/am/31276/
514
5ፖለቲካ
ሆስፒታሉ 10ሺ ለሚሆኑ ዜጎች የሞራ ግርዶሽ የአይን ህክምና በነጻ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 31, 2019
Unknown
ሆስፒታሉ 10ሺ ለሚሆኑ ዜጎች የሞራ ግርዶሽ የአይን ህክምና በነጻ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀየአለርት ሆስፒታል አልባሳር ኢንተርናሽናል ከተሰኘ ሳኡዲ በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የፊታችን ሐምሌ 27 እና 28 የሞራ ግርዶሽ የአይን ህክምና በነጻ ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።የአለርት ሆስፒታል ከሚታወቅበት የቆዳ ህክምና ባሻገር ከተለያዩ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሚሰጣቸው የአይን ህክምናዎች ብዙዎችን ከአይነ ስውርነት መታደጉን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለምሰገድ ጫኔ ለዋልታ ገልጸዋል፡፡፡ሆስፒታሉ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ አልባሳር ከተሰኘ አለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅትና በሳኡዲ ከሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በመተባበር 10ሺ ለሚሆኑ ዜጎች የአይን ህክምና ለመስጠት ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡ህክምናው በሳኡዲ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የተቸገሩ ዜጎቻቸውን ለመርዳት ባደረጉት ጥረት የተገኘ ድጋፍ መሆኑን የገለጹት አቶ አለምሰገድ፤ በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በመረዳዳት ዜጎችን ማገዝ የሚችሉ መሆኑን አመልክተዋልል።ህክምናው ለአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ላሉ ነዋሪዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ የአይን ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በተጠቀሰው ቀን ማንነታቸውን የሚያሳይ መታወቂያ በመያዝ ህክምናውን ማግኘት ይችላሉ ብለዋል።
https://waltainfo.com/am/32609/
143
0ሀገር አቀፍ ዜና
ደኢህዴን ባቀረበው ጥናት ላይ የተደረገው ውይይት ስምምነት ላይ በመድረስ ተጠናቀቀ
ፖለቲካ
August 1, 2019
Unknown
ላለፉት ሰባት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የደቡብ ኢትዮጰያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች መድረክ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታና ድርጅቱ ባስጠናው የክልልነት ጥያቄ ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቀቀ።በምክክር መድረኩ የሰባት ቀናት ቆይታ ዙሪያ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ለአመራር መድረኩ በቀረቡ አጀንዳዎች ዙሪያ የተደረገው ውይይት ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ነበር።በሀገሪቱ ተጀመረውን ለውጥ በድርጅት ውስጥም ሆነ በውጪ ሊያደናቅፍ የሚያስችል የአመለካከት መዛባት ያለበት በመሆኑ ይህን በማረም የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ስምምንት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር ለማስቆም የህግ የበላይነትን የማስከበር ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር በመሆኑን በጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ የተጀመረው ሰላምና ጸጥታን የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመድረኩ አቋም እንደተያዘ ተናግረዋል።የኮማንድ ፖስቱ ተግባር የህዝብ የነቃ ተሳትፎ እንዲጎለብት በማድረግ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተማማኝ እንዲሆን የሚሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን ህጋዊ መስመር ለማስያዝ በተወሰኑ አካባቢዎች የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ሌሎችም በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው እንዲንቀሳቀሱ አመራሩ በትኩረት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል።የህዝብ የመብት ጥያቄዎች በሆታና በግርግር ለማዛባት የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ አመራሩ ይህን በተመለከተ የጋራ አቋም መያዙን ገልጸዋል።በክልል የመደራጀት ጥያቄ ህገ-መንግስታዊ ቢሆንም በአንድ ጊዜ በርከት ያለ የክልልነት ጥያቄ በመቅረቡ በጥንቃቄ ካልተያዘና ካልታየ የሚያስከትለውን አደጋ ለማስቀረት ደኢህዴን ባስጠናው ጥናት ዙሪያ ውይይት መደረጉን ጠቁመዋል።በጥናቱ ዙሪያም የጋራ መግባባት ላይ እንደተደረሰና መላው የክልሉ ህዝብ ውይይት ሊያደርግበት እንደሚገባ በመድረኩ መወሰኑን ተናግረዋል።“በድርጅቱ ዙሪያ በተለያዩ ምክንያቶች በህዝቡ ዘንድ እየተሸረሸረ የመጣውን ዕምነት ለመመለስ አመራሩ ግልጽነትን በማስፈን ተግባሩን ማከናወን ተገቢ መሆኑን መድረኩ አምኖበታል” ብለዋል።መድረኩ በቆይታው በአመራሩ ዘንድ መነሳሳትና መግባባት የሰፈነበት አንድ አቋም ይዞ የወጣበት በመሆኑ መላው የክልሉ ህዝብ ከድርጅቱ ጎን እንዲሰለፍ ለማድረግ የጋራ ስምምነት ላይ መደረሱን አቶ ሞገስ ገልጸዋል። 
https://waltainfo.com/am/31274/
240
5ፖለቲካ
በግብፅ 130 ታራሚዎች የረሃብ አድማ አደረጉ
ፖለቲካ
August 1, 2019
Unknown
አመንስቲ ኢንተርናሽናል እንደገለፀው በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በሚገኘው ማረምያ ቤት ውስጥ የሚገኙ 130 ታራሚዎች በሰብአዊ መብት አያያዝ ጉድለትና ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው በመደረጉ ከስድስት ሳምንታት በላይ የረሃብ አድማ በማድረግ ተቃውሟቸው አንፀባርቀዋል፡፡ ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት በደቡባዊ ካይሮ በሚገኘው ማረሚያ ቤት የስራ ሃላፊዎቹ ታራሚዎቹን በመደብደብ እና በኤሌክትሪክ ሾክ እየቀጧቸው እንደሆነ አመንስቲ ኢንተርናሽናል ታራሚዎቹን ዋቢ አድርጎ ገልጿል፡፡የህግ ታራሚዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ ግልፅ የሆነ ወንጀል እየሰሩ ያሉ የማረምያ ቤቱ የስራ ሃላፊዎች የግብፅ ህዝብና አለም አቀፍ ማህበረሰብ ሊያወግዛቸው እንደሚገባ አመንስቲ ኢንተርናሽናል መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/33313/
78
5ፖለቲካ
የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ ሀምዛ ቢን ላደን መሞቱን የአሜሪካ ባለስልጣናት አስታወቁ
ፖለቲካ
August 1, 2019
Unknown
የአልቃይዳ መስራች ኦሳማ ቢን ላደን ወንድ ልጅ ሀምዛ ቢን ላደን፣ መሞቱን የአሜሪካ የስለላ ባለስልጣናት መናገራቸው ተገልጿል፡፡የሀምዛን ቢን ላደን አማሟት እንዴት እና የት እንደሆነ ግን  የተባለ ነገር የለም፡፡የአሜሪካ መንግስት የካቲት ወር ላይ ሀምዛ የት እንዳለ ለጠቆመ የ1 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ በጉርሻ መልክ እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡30 ዓመት ይሆነዋል ተብሎ የሚገመተው ሀምዛ ቢን ላደን በአሜሪካና ሌሎች ሀገራት ላይ ጥቃት እንዲፈፀም የሚጠይቅ የተንቀሳቃሽ ምስልና ድምፅ   መልዕክት አስተላልፎ እንደነበር ተገልጿል፡፡በጉዳዩ ላይ ረቡዕ ዕለት በሪፖርተሮች የተጠየቁት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም እና የኋይት ሃውስ የሀገር ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን አስተያየታቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል።ሀምዛ ቢን ላደን እ.ኤ.አ.በ 2011 ግንቦት ወር ላይ በፓኪስታን በአሜሪካ ልዩ ሀይል የተገደለውን የአባቱን ገዳዮች ለመበቀል ጂሃዲስቶች ጥቃት እንዲፈፅሙ ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን÷ ሳዑዲ አረቢያ ዜግነት እንደነጠቀችውም አይዘነጋም፡፡የአሜሪካ መንግስት እንደሚለው እ.ኤ.አ.በ 2011 በፓኪስታን አቦታባድ በአባቱ ቤት በተደረገው ፍተሻ የተገኙ ሰነዶች እንደሚያሳዩት ሀምዛ አልቃይዳን እንዲመራ ታጭቶ ነበር።(ምንጭ፦ ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33976/
131
5ፖለቲካ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
ፖለቲካ
August 1, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።ምክር ቤቱ ለሶስት ቀናት በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ የአስተዳድሩን የ2012 ረቂቅ በጀት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።ከዚህ ባለፈም የተለያዩ ሹመቶችን የሚያፀድቅ መሆኑ ተገልጿል።እንዲሁም ምክር ቤቱ የከተማዋን ፍርድ ቤቶች የ2011 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን በማዳመጥ የሚያፀድቅ መሆኑን ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።።ጉባኤው ለሶስት ቀናት እንደሚቀጥል ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31275/
58
5ፖለቲካ
2ኛው የትግራይ አለም አቀፍ የዳያስፖራ ፌስቲቫል በመቐለ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 1, 2019
Unknown
ሁለተኛው የትግራይ አለም አቀፍ የዳያስፖራ ፌስቲቫል በመቐለ መካሄድ ጀመሯል፡፡ፌስቲቫሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በተገኙበት ነው የተከፈተው፡፡የትግራይ አለም አቀፍ የዳያስፖራ ፌስቲቫል የክልሉን ህዝብ ከድህነት ለማላቀቅ በሚያስችል ጉዳዮች ላይ በማተኮር የሚካሄድ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡የመክፈቻ ስነ ስርዓት የፌስቲባሉ አካል የሆነ አውደ ርዕይ በዛሬው እለት በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር በደብረፂዮን ተከፍቷል፡፡የትግራይ አለም አቀፍ ዳይስፖራ ፌስቲቫል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32610/
68
0ሀገር አቀፍ ዜና
2ኛው ዓለምአቀፍ የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
July 31, 2019
Unknown
2ኛው ዓለምአቀፍ የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ጉባዔ በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት የስብሰባ ማዕከል እየተካሄደ ነዉ።የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ጉባዔውን በይፋ በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በማደግ ላይ ላሉ አገራት ድህነትን ለመቀነስና ለወጣቶች የሥራ እድል በመፍጠር ረገድ ዘርፉ ጉልህ ድርሻ አለው፡፡   የኢትዮጵያን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በመደገፍ ድርሻውን ለተወጡት ድርጅቶች ሚኒስትሯ ምስጋና አቅርበዋል፡፡  የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብዲዋስ አብዱላሂ በበኩላቸው ጉባዔውን የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ያለበትን ደረጃ ለማሳየት፣ በዘርፉ ያሉ ችግሮችንና ለችግሮቹ መፍቻ የሚሆኑ ዓለምአቀፍ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡በመደረኩ የተለያዩ አገራት በተለይም እንደ ማሌዢያ፣ ፊሊፒንስ እና ኢንዶኒዢያ ተሞክረሮ ምን እንደሚመሰል ከቀረበ በኃላ ውይይት ይደረግበታል ብለዋል፡፡  የባለድርሻ አካላት፣ የተባባሪ ድርጅቶች እና የመንግስትን ድጋፍና ጥረት በማጎልበት ከዘርፉ የሚጠበቀውን ጥራት ያለው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና እውን በማድረግ በተለይም ወጣቱ በሥራ ዕድል ፈጠራና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ለሀገሪቱ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ወደ ላቀ ምዕራፍ ማሸጋጋር እንደሚቻል ሚኒስትር ዴኤታው አክለው ገልጸዋል፡፡በኢትዮጵያ 1ሺህ 500 የሚጠጉ የግልና የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት እንደሚገኙ በመድረኩ ተገልጿል፡፡  ጉባዔው"ክህሎትን ማጎልበት ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት" በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 22 የተጀመረ ሲሆን እስከ ሐምሌ 24/2011 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።   
https://waltainfo.com/am/32606/
176
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሱዳን በሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ዘጋች
ፖለቲካ
July 31, 2019
Unknown
ሱዳን አምስት ተማሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ አመፅ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ስጋት በሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጋ አድርጋለች፡፡የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት  በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ እንዲዘጉ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ሰኞ እለት ተማሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዋና ከተማዋን ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተቃዋሚዎች መሰባሰብ እንደጀመሩ ነው የተነገረው፡፡በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት ባለፈው ሰኞ ከተገደሉት አምስት ወጣቶች መካከል አራቱ ተማሪዎች  መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡በተማረዎች መገደል የተቆጡት ተማሪዎችም ዩኒፎርሞቻቸውን እንደለበሱ በካርቱምና በሌሎች ከተሞች ለተቃውሞ  ወጥተዋል፡፡የሽግግር ምክር ቤቱም ተቃውሞችን ለመቆጣጠርም መዋለ ህፃናት፣ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ እዲዘጉ መወሱን  ሱና የዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ከተገደሉት ተማሪዎች በተጨማሪ 62 ሰዎች የአካል ጉዳት እንዳጋጠማቸው የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡(ምንጭ፦ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33312/
100
5ፖለቲካ
ምክር ቤቱ የአካባቢ ምርጫ ከቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ ወሰነ
ፖለቲካ
July 31, 2019
Unknown
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫ ከቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል፡፡ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡በዚህም በ2011 ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች አባለት ምርጫና የአካባቢ ምርጫ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ ማካሄድ ባለመቻሉ ከቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል፡፡ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሃምሌ 4 ቀን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፃፈው ድብዳቤ፤ የሁለቱን ከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤት ምርጫን በተቀመጠው ጊዜ ማለትም ዘንድሮም ማካሄድ አይቻልም ማለቱ ይታወሳል።በቀረው አጭር የአመቱ ጊዜ ምርጫ አስፈፃሚዎችን መመልመል፣ ማደራጀትና ስልጠና ለመስጠት በቂ ጊዜ አለመኖሩን ቦርዱ በምክንያትነት አቅርቧል።በዚህ ውሳኔ መስረትም አሁን በስራ ላይ ያሉት የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች በስራቸው ይቀጥላሉ።ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባንክ ሥራ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጅን እየተመለከተ ይገኛል።በተመሳሳይ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጉምሩክ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ በመርመር ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
https://waltainfo.com/am/31273/
175
5ፖለቲካ
አስፈጻሚ አካሉ የህግ የበላይነትን በማስከበር ላይ መላላት ይስተዋልበታል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 31, 2019
Unknown
በህግ የበላይነት ዙሪያ በተደረገው ጥናት የህግ አስፈጻሚ አካሉ መላላት እንደሚስተዋልበት ተለይተዋል ተባለ፡፡ምንም እንኳን በኢትዮጲያ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ለውጦች ቢመዘገቡም የህግ የበላይነት አለመስፈን በሀገሪቱ ጎልቶ የሚስተዋል ድርጊት ነው፡፡የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ መቼም ቢሆን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው የሚሉት የጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎው ሽፕ ኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት  ፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ በዚህ ረገድ መንግስት በትኩረት ሊሰራ ይገባልም ይላሉ፡፡በህግ የበላይነት ዙሪያ በተለይ ከከተማ ውጭ ግጭቶች የተነሱባቸው ቦታዎች ላይ ጥናት አድርገናል የሚሉት አቶ ዳንኤል የጥናቱ ግኝቶች የህግ አስፈጻሚ አካሉ ላይ መላላት እንደሚስተዋል እና የተደራጁ ቡድኖች የፍትህ ስረአት ላይ ጣልቃ በመግባት ፍትህ እንዳይሰፍን ማድረጋቸውን ያሳያልም ነው የሚሉት፡፡በኢትዮጲያ የህግ የበላይነት ይሰፍን ዘንድም የመንግስት መጠንከር፤የጸጥታ ሀይሉ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራት እና ህዝቡ ለሰላም የሚሰጠው ትኩረት በጥናቱ የተቀመጡ የመፍተሄ አቅጣጫዎች ስለመሆናቸውም ነው የተጠቆመው፡፡  
https://waltainfo.com/am/32607/
115
0ሀገር አቀፍ ዜና
በድሬዳዋ ባህላዊ የዛፍ ስር እርቅ በነሐሴ 4 ሊካሄድ ነዉ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 31, 2019
Unknown
በድሬዳዋ  አልፎ አልፎ  የሚስተዋለውን  የሰላም  መደፍረስ  በኢትዮጵያውያን ባህላዊ የእርቅ ስርዓት እልባት ለመስጠት የሚያስችል የሰላም ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው፡፡ነሃሴ 04 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚካሄደው ፌስቲቫሉ በድሬዳዋ ተወላጆች የተዘጋጀ ሲሆን ባህላዊ የዛፍ ስር እርቅ ስነስርዓት የሚደረግበት መሆኑንም አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ኢትዮጵያ የርካታ እሴቶች ባለቤት፣ ከህዝቦቷም አልፎ ለዓለም የሚበቃም የቱባ ባህል ባለቤት ሃገር ናት፡፡ ባህላዊ የሽምግልና ስነስርዓት ደግሞ ከነዚህ ቱባ እሴቶች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡የኢትዮጵያ የሽምግልና ባህል እንደየህዝቦቷ አከባቢያዊ ወግ ቢለያይም ፍትህን በመስጠት ግን ከሳይንሳዊው የዘመናዊው የፍርድ ቤቶች ሂደትም ተፎካካሪ መሆኑን በርካቶች ይመሰክራሉ፡፡በድረዳዋ ያለ፣ ለዘመናት ጥቅም ላይ ሲውል የነበረም፤ የተኮራረፈን በፍጹም ይቅርታ የሚያስታርቁበት “muka jala” ወይም “Geed Hoost” የሚሉት የዛፍ ስር የእድርቅ ስርዓት በዚህ ረገድ የሚነሳ አንዱ ተምሳሌት ነው፡፡ሰው ሁሉ በስብዕናው ብቻ ተከባብሮ እንደሚኖርባት በርካቶች ሲመሰክሩላት የነበረው፣ ብዙዎችም የፍቅር ከተማ ሲሉ የሚያነሷት ድሬዳዋ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሰላም እሴቷ መሸርሸር መጀመሩ አሳስቦናል ያሉት ተወላጆቿ፣ ለህዝቦቿ የለመዱት ፍቅር ይመለስላቸው ዘንድ ነሃሴ 04 ቀን 2011 ዓ.ም፣ የዛፍ ስር ባህላዊ የእርቅ ፌስቲቫል ተሰናዳ፡፡የኢትዮጵያዊ አንድነት ተምሳሌት ድሬዳዋ በተዘነጉቱ ባህሏ የእርቅ እሴቷ ተምሳሌታዊ ሰላሟን ታሰፍን ዘንድ፤ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች፣ እናቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ተወካዮች በዚሁ ፌስትቫል ታዳሚ ይሆናሉ፡፡ ድሬ ዳዋም ከራሷ የተረፈን ሰላምና ፍቅር ለሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎችም ታተርፍ ዘንድ ልጆቿ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡በዚህ የካበተ ባህላዊ የአብሮነትና የፍቅር እሴቷ ዳግም የፍቅር ተምሳሌትነቷንም ለመላው ኢትዮጵያ እንደምታስተምር በተለያዩ ዓለማትና የኢትዮጵያ ክፍል ባሉ ልጆቿ ትልቅ ተስፋ አለ፡፡
https://waltainfo.com/am/32608/
202
0ሀገር አቀፍ ዜና
በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 353,633,660 ችግኞች ተተከሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 30, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 353,633,660 ችግኞች ተተከሉበኢትዮጵያ ሐምሌ 22/2011 በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን በመላ ሃገሪቱ 353 ሚሊየን 633 ሺህ 660 ችግኞች መተከላቸው ተረጋግጧል።  በአገሪቷ በአረንጓዴ አሻራ ቀን 200ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ በተደረገው ዘመቻ በአንድ ጀምበር በመላ ሀገሪቱ 353 ሚሊየን 633 ሺህ 660 ችግኞች ተተክሏል። ይህም በህንድ ከዚህ ቀደም ተይዞ ከነበረው የ66 ሚሊየን ችግኝ በእጅጉ የላቀ መሆኑ ተረጋግጧል።በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ፤ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድርና ከንቲባዎች፤ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተለያዩ ቦታዎች በመገኘት ችግኝ ተክለዋል። በዘመቻው መላው የአገሪቱ ህዝብ አንድ ሆኖ ሲሳተፍ ተስተውሏል።
https://waltainfo.com/am/32602/
97
0ሀገር አቀፍ ዜና
በፓኪስታን ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ 17 ሰዎች ሞቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 30, 2019
Unknown
በፓኪስታን ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሶ 17 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ።አውሮፕላኑ በመኖሪያ ሰፈር የተከሰከሰ ሲሆን፥ በውስጡ ያሉ አባላትና 12 የአካባቢው ነዋሪዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።አውሮፕላኑ በወቅቱ ለልምምድ በረራ ላይ እንደነበረና  የአደጋው መንስኤ እስካሁን አለመታወቁን ነው የሬውተርስ ዘገባ ያመለከተው።አደጋው የደረሰበት ስፍራ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት የሚካሄድበት መሆኑ ተገልጿል።የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እስካሁን 12 ነዋሪዎችን ከአደጋው መታደግ ችለዋል።
https://waltainfo.com/am/34121/
49
0ሀገር አቀፍ ዜና
የዙና ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 30, 2019
Unknown
የዙና ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ጌታሰው በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ300 ሺህ ብር ተቀጡ።የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው ዕለት የዙና ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ጌታሰውን ጉዳይ ተመልክቷል።አቶ ዘሪሁን ከ109 ግለሰቦች ሲኖትራክ ተሽከርካሪ አስመጣለሁ በማለት በአጠቃላይ ከ73 ሚሊየን ብር በላይ በማጭበርበር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በዙና ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ጌታ ሰው ላይ 122 ክሶችን መመስረቱም ይታወሳል።በዚህም ከ109 ግለሰቦች ከ 2 ሚሊየን 600 ሺህ እስከ 314 ሺህ ብር መኪና አስመጣለው በማለት ባጠቃላይ ከ73 ሚሊየን ብር በላይ ተቀብላለው መሰወራቸው በክሱ ተመላክቶ ነበር።በክሱ መሰረትም አቃቤ ህግ አለኝ ያለውን የሰነድ ማስረጃ እና የግል ተበዳዮችን ምስክርነት አቅርቦ አሰምቷል።ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት 13 ክሶችን ውድቅ በማድረግ ተከሳሹን በ109 ክሶች ጥፋተኛ ብሏል።በዚህ መሰረትም ፍርድ ቤቱ የዙና ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ጌታሰው በ14 ዓመት ፅኑ እስራትና በ300 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/32605/
157
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ ልኡክ በምዕራብ ጎንደር ዞን ጉብኝት እያካሄደ ነው
ቢዝነስ
July 30, 2019
Unknown
በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሚመራ የልኡካን ቡድን በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ መንደር እየጎበኘ ነው። ከኢንዱስትሪ መንደሩ በተጨማሪ የልዑካን ቡድኑ በአካባቢው ባለሃብቶች እየተከናወነ ያለውን የሰሊጥ ልማት ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ከጉብኝቱ በኋላም በኢንዱስትሪ መንደሩ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ከተሰማሩ የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች እንዲሁም ሠራተኞቻቸው ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በጉብኝቱ የኢትዮ-ቴሌኮምና የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ኃይል ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና ሌሎች አመራሮች ተሳታፊ መሆናቸውን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/23888/
74
3ቢዝነስ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
ፖለቲካ
July 30, 2019
Unknown
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነው በዛሬው እለት በአሶሳ ከተማ ማካሄድ የጀመረው።በጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የክልሉ መንግስት የ2011 በጀት ዓመት የመንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ሲሆን ውይይት የሚደረግበት ይሆናል።ምክር ቤቱ በቆይታው የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ የሚያፀድቅ ሲሆን፥ የ2012 አጠቃላይ በጀት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።በዛሬው እለት መካሄድ የጀመረው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ እስከ ሐምሌ 25 2011 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
https://waltainfo.com/am/31270/
91
5ፖለቲካ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የስራ ዘመን የሚያበቃበት ቀነ ገደብ እስካልተቀመጠ ድረስ ስራውን እንደሚቀጥል ገለፀ
ፖለቲካ
July 30, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክርቤት የስራ ዘመን የሚያበቃበት ቀነ ገደብ አስካልተቀመጠ ድረስ ስራውን እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡ምክር ቤቱ በኦዲት ግኝት ከተያዙ 42 ተቋማት የሰበሰበውን 50 ሚሊየን ብር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ምክር ቤቱ 6ኛ አመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከሐምሌ 25 እስከ 27፣ 2011 ዓ.ም እንደሚያካሂድም ነው የገለፀው፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የስራ ዘመን 2010 ላይ መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክር ቤቱን የስራ ዘመን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ይታወሳል፡፡ይህንኑ ጉዳይ በሚመለከት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን ተጨባጭ መረጃ ከሌላቸው አካላት የምክር ቤቱ የስራ ዘመን ሰኔ 30/2011 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ስህተት መሆኑን የምክር ቤቱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም እንቻለው ገልጸዋል፡፡ የምክር ቤቱ የስራ ዘመን የሚያበቃበት የጊዜ ገደብ እስካልተቀመጠ ድረስም ምክር ቤቱ ስራውን እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት፡፡ምክር ቤቱ የፋይናንስ ስርዓቱ በሚፈቅደው መልኩ በጀቱን እየተጠቀመ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ፣ በጀቱ እንደጸደቀ ወደ መደበኛ ስራው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31271/
129
5ፖለቲካ
በአገር አቀፍ ደረጃ የተተከለው ችግኝ እስካሁን 141 ሚሊዮን ደረሰ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 30, 2019
Unknown
ሐምሌ 22 ቀን 2011 በዛሬው ዕለት 200 ሚሊዮን የዛፍ ችግኝ በመትከል ዕለቱን የአረንጓዴ አሻራ ቀን ለማድረግ በሚካሄደው ዘመቻ እስካሁን ድረስ 141 ሚሊዮን ችግኝ መተከሉ ተረጋግጧል።ኢትዮጵያ ለዓለም አረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ካዘጋጁ አገሮች አንዷና የመሪነት ሚናዋን እየተጫወተች ያለች አገር ናት።ሀገሪቱ ‘የዜጎች የአረንጓዴ አሻራ ቀን’ በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ችግኞችን በመተከል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ ክብረወሰን ለማስመዝገብ አቅዳ ስትሰራ ነበር።በመሆኑም በዛሬው ዕለት በገጠርም ሆነ በከተማ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አገር ዜጎች በነቂስ ወጥተው እየተሳተፉ ይገኛሉ።ለክረምት ችግኝ ተከላ ዘመቻው ከ4 ነጥብ 7 ቢሊየን በላይ ችግኝ ተዘጋጅቷል።በኦሮሚያ 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን፣ በአማራ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን፣ በደቡብ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ችግኞች ተዘጋጅተዋል።
https://waltainfo.com/am/32599/
97
0ሀገር አቀፍ ዜና
በኃይልና በጉልበት፣ በአመፅና በሁከት ሰላምን አናገኘውም – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
ፖለቲካ
July 29, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፍትሕና በምህረት አውድ ውለን ካልሆነ በቀር በኃይልና በጉልበት በአመፅና በሁከት ሰላምን ብንፈልገው አናገኘውም ሲሉ ተናገሩ፡፡“በጦርነትና ግጭት ውስጥ ስንመላለስ የምንቀማው ክብር ሕይወታችንን፣ አካላችንን፣ በድካም ያፈራነውን ሀብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን ታላቁን የሕሊና ሰላማችንንም ነው የምናጣው ብለዋል፡፡”ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአረንጓዴ አሻራ ቀን በወላይታ ሶዶ ችግኝ ተክለዋል።በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና አምባሳደር ተሾመ ቶጋን ጨምሮ፥ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የዞኑ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር የወላይታ ህዝብ የአላማ ፅናት፣ አኩሪ ባህልና ታሪክ ያለው ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወላይታ ህዝብ የሚተክለው ችግኝ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ  በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ህይዎቱ ላለፈውና የአካባቢው ተወላጅ ለሆነው ዮሴፍ አያሌው መታሰቢያ ይሆናል ብለዋል።የወላይታ ህዝብ ከእርቅ፣ ሽምግልና እና ዳኝነት ጋር በተያያዘ አኩሪ ባህል እንዳለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አንስተዋል።ወጣቱ ትውልድ ይህን አኩሪ ባህል ማስቀጠል ይገባዋልም ነው ያሉት።ህዝቡ በሄደበት አካባቢ በፍቅር በመኖር እንደሚታወቅ ጠቅሰው፥ ይህን የአብሮነት እሴት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።መላው ህብረተሰብም የተከለው ችግኝ ይፀድቅ ዘንድ መንከባከብና መጠበቅ እንደሚገባውም አስረድተዋል።በሶዶ ከተማ ስምንት ችግኝ መትከያ ቦታዎች የተለዩ ሲሆን፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንደኛው በመገኘት ችግኝ ተክለዋል።በዛሬው እለት በመላ ኢትዮጵያ 200 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ቀን በመትከል በዓለም የክብር መዝገብ ላይ ለመስፈር እየተደረገ ባለው ዘመቻ ኢትዮጵያ በሕንድ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን ተረክባለች፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31269/
195
5ፖለቲካ
በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳ በአንድ ቀን 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞች ተተከሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 30, 2019
Unknown
በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳ በአንድ ቀን 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞች ተተከሉበሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳ በአንድ ቀን 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።የጽቤቱ ሃላፊ አቶ ዳኜ ደሳለኝ እንደገለጹት፤ ሐምሌ 22/2011 በአረንጓዴ አሻራው ዘመቻ በወረዳው 1 ነጥብ 1ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ተችሏል።በወረዳው በተያዘው ክረምት እየተተከሉ ያሉ ችግኞችን የተከለው አካል የሚንከባከብበትን አሰራር ማስቀመጣቸውን የገለጹት ሃላፊው፤ የተተከሉትን ችግኞች እንዲጸድቁ የተለየ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።ሐምሌ 22/2011 በነበረው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የወረዳው አመራሮች፣ ሰራተኞች፣ ነዋሪዎችና የጸጥታ አካላትም ጭም ተሳታፊ እንደነበሩ አቶ ዳኜ
https://waltainfo.com/am/32604/
92
0ሀገር አቀፍ ዜና
ምክትል ከንቲባው በአቡነ ጴጥሮስ የ83ኛ ዓመት የሰማዕትነት የመታሰቢያ ስነ-ስርዓት የአበባ ጉንጉን አኖሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
ኢ/ር ታከለ ኡማ በአቡነ ጴጥሮስ የ83ኛ ዓመት የሰማዕትነት የመታሰቢያ ስነ-ስርዓት ላይበመገኘት የአበባ ጉንጉን አኖሩ።ምክትል ከንቲባው በሰማዕቱ መታሰቢያ ስፍራ  ከነጋ ለሁለተኛ ጊዜ ችግኝ ተክለዋል።ኢ/ር ታከለ ኡማ በአቡነ ጴጥሮስ የሰማዕትነት የመታሰቢያ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግርም አድርገዋል፡፡የአባታችን አቡነ ጴጥሮስ መስዋዕትነት ዛሬ ላለነው ትውልድ ብዙ መልዕክት አለው ያሉት ኢ/ር ታከለ፤ ለሀገር የሚከፈል መስዋዕትነት የራስን ህይወት አሳልፎ እስከመስጠት መሆኑን ትምህርት የሰጠን ነው ብለዋል፡፡ብፁዕነታቸው በአቡነ ጴጥሮስ የ83ኛ ዓመት የመታሰቢያ ስነ-ስርዓት በሃውልታቸው ስር መታሰቢያቻው በተለያዩ ስነ ስርዓት ታስቦ ውላል። መረጃውን ከንቲባ ጽ/ቤት አገኘነው።
https://waltainfo.com/am/32601/
76
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠ/ሚ ዐቢይ በችግኝ ተከላ ለተመዘገበው ስኬት ለህብረተሰቡ ምስጋና አቀረቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 30, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐቢይ አህመድ በአረንጓዴ አሻራ ቀን የተመዘገበውን ስኬት አስመልክተው ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ህብረተሰቡ በዕለቱ ለመከወን የተያዘውን እቅድ በማለፍ ላስገኘው አመርቂ ውጤት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች ለአረንጓዴ አሻራ  ስኬት ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።በብሔራዊ የአረንጓዴ አሻራ ቀን ትላንት ማምሻውን 12፡00 ላይ ሲገባደድ በዕለቱ በአገር አቀፍ ደረጃ የተተከለው አጠቃላይ የዛፍ ችግኝ መጠን 353 ሚሊየን 633 ሺህ 660 መሆኑን የዘመቻው ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ኮሚቴው እንዳለው በዕለቱ በመላ አገሪቱ ቢያንስ 200 ሚሊዮን የዛፍ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የመንግስትን ጥሪ ተከትሎ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ባደረገው የተቀናጀ ርብርብ በዕለቱ 353 ሚሊዮን 633 ሺህ 660 ችግኞችን ለመትከል መቻሉን ኮሚቴው ገልጿል፡፡በዚህም ከዚህ ቀደም በአንድ ጀምበር 66 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል 1 ነጥበብ 3 ቢሊዮን ህዝብ ባላት ህንድ ተይዞ የቆየውን የድንቃድንቅ መዝገብ ክብረ ወሰን በ5 እጥፍ ገደማ ለማሻሻል ተችሏል። 
https://waltainfo.com/am/32603/
137
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለሁለተኛ ጊዜ በወላይታ ዩኒቨርሲቲ ችግኝ ተከሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለሁለተኛ ጊዜ በወላይታ ዩኒቨርሲቲ ችግኝ ተከሉዛሬ ማለዳ በአርባምንጭ ችግኝ የተከሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ወላይታ አቅንተው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲም ችግኝ ከነጋ ለሁለተኛ ጊዜ ተክለዋል። በሶዶ ስታዲየምም አቀባበል የተደረገላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሐይማኖት አመራሮች፣ ከተለያዩ ማህበረሰብ ተወካዮችና ከተቃዋሚ ፓርቲዎችም ጋር ዛሬ ከሰዓት ውይይት ያደርጋሉ ተብለው ይጠበቃሉ።  በዛሬው ሐምሌ 22፣ 2011 ዓ.ም 200 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገር አቀፍ ፕሮግራም እስካሁን ባለው መረጃ ከ142  ሚሊዮን ችግኞች በላይም እንደተተከሉ ተገልጿል።
https://waltainfo.com/am/32600/
72
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሰሜን ወሎ ዞን 11.12 ሚሊየን ችግኞች እየተተከሉ መሆኑ ተገለፀ
ቢዝነስ
July 29, 2019
Unknown
በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ በአረንጓዴ አሻር ቀን መርሀ-ግብር በዞኑ ከ11 ነጥብ 12 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ይተከላሉ፡፡በዞኑ 11 ነጥብ 12 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል 280 ሺህ ሕዝብ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በተከላው እየተሳተፈ ነው።የአንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ወይንየ ቀበሌ ፈለገ ሠላም ተፋሰስ ላይ እየተካሄደ ነው፡፡የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ወልደትንሳኤ መኮንን ‹‹በዛሬው ቀን የሚካሄደው የችግኝ ተከላ የዞኑን፣ የክልሉን እና የሀገሪቱን ብዝኃ ሕይወት ለማተካከል አጋዥ ይሆናል›› ብለዋል።በዚሁ ተፋሰስ ከ90 ሺህ በላይ ችግኞች እየተተከሉ ሲሆን ተከላ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ችግኞቹን ከመትከል ባለፈም የጽድቀት መጠናቸውን በመከታተል በቀጣይ ችግኞቹ ጥቅም እንዲሰጡ ለማድረግ እንደሚሠራም አቶ ወልደትንሳኤ ተናግረዋል።የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ ጎባው ‹‹የግብርና ኅልውናችን ስለሆነ ችግኞችን ከመትከል በዘለለ የጽድቀት መጠናቸውንም መከታተልና መንከባከብ ቀጣይ የግብርና ቢሮ ሥራ ይሆናል›› ብለዋል።በተመሳሳይ ሁኔታ በምዕራብ ጎጃም ዞን የአረንጓዴ አሻራ ቀንን ምክንያት በማድረግ ችግኝ እየተተከለ ነው፡፡የምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሠላም ከተማ ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና የፀጥታ ኃይል አባላት በጋራ በመሆን ችግኝ እየተከሉ ነው፡፡በፍኖተ ሠላም ከተማ ዛሬ ብቻ 45 ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉ ይጠበቃል፡፡ (ምንጭ፡- አብመድ) 
https://waltainfo.com/am/23885/
167
3ቢዝነስ
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በማዕከላዊ ጎንደር ችግኝ ተከሉ
ቢዝነስ
July 29, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወረዳ ምንዝሮ ቀበሌ ችግኝ ተከሉ።ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህም ችግኝ ተክለዋል።በቀበሌው 6 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ ዛሬ ብቻ 24 ሺህ በተለያዩ የችግኝ ዝርያዎች ይተከላሉ።በችግኝ ተከላው ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፈዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ አርሶ አደሮች እና ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
https://waltainfo.com/am/23884/
51
3ቢዝነስ
ከኃይሌ ጋርመንት እስከ አቃቂ መዳረሻ ከ13 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ችግኞች ተክለዋል
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
በአዲስ አበባ ከኃይሌ ጋርመንት እስከ አቃቂ መዳረሻ ድረስ ከ13 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡በችግኝ ተከላው የመዲናዋ ነዋሪዎች፣ በመዲናዋ የሚኖሩ የሀረር ተወላጆች፣ የፖሊስ አባላት፣ ወጣቶች እና ህጻናት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ነዋሪዎቹ ዛሬ ችግኝ በመትከል ብቻ የሚያበቃ ሃላፊነት ሳይሆን የተረከቡት፣ በቀጣይ ችግኙ እስኪፀድቅ ተገቢውን እንክብካቤ በማድረክ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል፡፡  ከልጆቻቸው ጋር ችግኝ ሲተክሉ ያገኘናቸው ነዋሪዎችም ለልጆቻቸው መልካም ተግባርን ለማስተማር ምቹ አጋጣሚን እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡  
https://waltainfo.com/am/32598/
63
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከ27 ሚሊዮን በላይ ችግኞች እስካሁን ተተክለዋል
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
ዛሬ ይህ ዘገባ አስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ27 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ በቀለ በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡ኦሮሚያ ከ14 ሚሊዮን በላይ በመትከል ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ ደቡብ ክልል ከ7 ሚሊዮን በላይ በመትከል 2ኛ ደረጃን ይዟል፡፡በተያያዘ በአፋር ክልል የሰመራና አካባቢዋ ነዋሪዎች በከተማይቱ ዙሪያና በሰመራ ዩኒቨርስቲ በመገኘት የዛፍ ችግኞችን ተክለዋል፡፡በመርሃ-ግብሩ ላይ የክልሉን ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳትፈውበታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32597/
68
0ሀገር አቀፍ ዜና
ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ችግኝ ተከሉ
ቢዝነስ
July 29, 2019
Unknown
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ችግኝ ተከሉ፡፡ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ጠዴ አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን አስጀምረዋል፡፡አገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ታላቅ ትርጉም እንዳለውና ሰውን ከተፈጥሮ ጋር የማዋደድ ተግባር አንደሆነም  ፕሮግራሙን ባስጀመሩበት ወቅት ገልፀዋል፡፡በዛሬው ዕለት 200 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል በመላ ሃገሪቱ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ነዋሪዎች በመረሃ ግብሩ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡  
https://waltainfo.com/am/23886/
65
3ቢዝነስ
የተከልነውን ብቻ ሳይሆን ተተክሎ ያገኘነው ችግኝ ሁሉ መንከባከብ ያስፈልጋል ተባለ
ቢዝነስ
July 29, 2019
Unknown
የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በድሬዳዋ እየተከናወነ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።የአስተዳድሩ ም/ከንቲባ አህመድ ቡህ በተለምዶ ከተሞች ፎረም በሚባለው ፓርክ ተገኝተው ችግኝ ከተከሉ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት "ድሬዳዋን ከዛፍ ነጥሎ ማሰብ አሳን ከውሀ ነጥሎ የማሰብ ያህል በጣም ከባድ ነው። ምክንያቱም ድሬዳዋና ዛፍ ያላቸው ትስስር ከተቆረቆረችበት ጊዜ የሚጀመርና ዘመናትን ያስቆጠረ በመሆኑ ድሬዳዋን ከዛፎቿ ውበትና ጥላ ነጥሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው።ይህንን ጉዳይ ለማረጋገጥም የድሬዳዋ ከተማነት 'ሀ' ብሎ የተጀመረባትና የከተማችን እምብርት የሆነችው'ከዚራ' ዋነኛ መለያዋ የዛፎቿ ውበት መሆኑንና ከቀደመው ዘመን ጀምሮ የአገራችንአንጋፋና ወጣት ድምፃዊያን በውበትዋ ተስበውና በፍቅሯ ተማርከው በከዚራ ጥላው ስር እያሉ ደጋግመው ማቀንቀናቸውን ማስታወስ ይበቃል ብለዋል።ይህም የድሬዳዋ ሕዝብ ከከተማችን ምስረታ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ዛፍ ተክሎ የማሳደግ የዳበረ ነባር ባሕል እንዳለው ከማረጋገጡም ባሻገር እያንዳንዱ ነዋሪ በዚህ ክረምት የተከለውን ችግኝ በራሱ ተነሳሽነት በፍቅር ተንከባክቦ እንደሚያሳድግ መተማመኛ የሚሰጥ ነው" ሲሉም ተናገረዋል።ም/ከንቲባው አክለውም በዚህ አረንጓዴ አሻራችንን በምናኖርበት ቀን ሁላችንም እራሳችን የተከልነውን ብቻ ሳይሆን ተተክሎ ያገኘነው ችግኝ ሁሉ በመልካም ሁኔታ አድጎናትልቅ ዛፍ ሆኖ ለእኛና ለልጆቻችን ውበትና ጥላ እንዲሆነን በጉልበትም ይሁን በገንዘብ በምንችለው ሁሉ የበኩላችንን ለማድረግ ለራሳችን ቃል እንግባ ሲሉም ጥሪአቅርበዋል።(ምንጭ :- የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት) 
https://waltainfo.com/am/23887/
167
3ቢዝነስ
ማይክሮሊንክ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
ማይክሮሊንክ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ለ20ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 515 ተማሪዎች በኦሮሚያ የባሕል ማዕከል አዳራሽ አስመረቀ፡፡   ተመራቂዎቹ በኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ አካውንቲንግ እና ፋይናንስ የትምህርት መስኮች ሲሰጣቸው የነበረውን ትምህርት አጠናቀው መመረቃቸውን የኮሌጁ ዲን አቶ በአካል እሸቱ ተናግረዋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 64 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውንም ዲኑ አክለው ገልጸዋል፡፡ኮሌጁ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና አካውንቲንግ ትምህርቶች ችግር ፈቺ የሆኑ የመመረቂያ ሥራዎችን እንዲያከናወኑ ባደረገው ጥረት በመስኖ ሥራ፣ ዳታ ማኔጅመንት እና ኤሌክትሮኒክ ግብይት ላይ ትኩረት ያደረጉ ውጤታማ ሥራዎች መሰራታቸው ታውቋል፡፡ኮሌጁ በግል ኮሌጅነት ያለውን የባለቤትነት ድርሻ በሽርክና የሕዝብ ኩባንያ የሚሆንበትን አሰራር በመጪው ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ እና በኮምፒውተር ሳይንስና ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የትምህርት መስኮች በሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ለማስተማር ማቀዱን ከኮሌጁ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡   
https://waltainfo.com/am/32595/
106
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ በደማቅ ሁኔታ በሁሉም ክፍለከተሞች ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
በመላ ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት 200 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ቀን በመትከል በአለም የክብር መዝገብ ላይ ለመስፈር ዘመቻው በማለዳው ተጀምሯል።በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጭነት በዛሬው እለት በአንድ ጀንበር 200 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ሲደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።በዚህ መሰረት ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ዜጎች 200 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል ዘመቻቸውን ጀምረዋል።ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ሁሉም ክልሎች አስፈላጊውን ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል።የዚህ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን በአዲስ አበባ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በኮልፌ ቀራኒዮ ፖርክ ውስጥ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመሆን አስጀምረዋል።ህንድ በአለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር ወይንም በ12 ሰዓታት 66 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል በአለም የክብር መዝገብ ላይ በቀዳሚነት ሰፍራ ትገኛለች። 
https://waltainfo.com/am/32592/
108
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኤጀንሲው ሰራተኞች የችግኝ ተከላ አካሄዱ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
የጋምቤላ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ ቀን ዛሬ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።በችግኝ ተከላው መርሐ ግብር ላይ በውጭ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆችም ተሳትፈዋል፡፡የኤጀንሲው ዋና ኃላፊ አቶ ሰናይ አኩዎር እንዳሉት ኤጀንሲው በተለይም የአካባቢን መራቆትና በረሃማነት ለመቀነስ እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ግብን ለማሳካት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ችግኞችን ከመትከል ባለፈ መንከባከብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡በችግኝ ተከላው ከተሳተፉ በውጭ ከሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች መካከል መቶ አለቃ እኩኝ ኡፒየው በሰጡት አስተያየት ከ25 ዓመታት ቆይታ በኋላ ተመልሰው ለአገራቸውና ተወልደው ላደጉበት አካባቢ የአረንጓዴ አሻራ በማስቀመጣቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32596/
74
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በአርባ ምንጭ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ተሳተፉ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጋሞጎፋ ዞን አርባምንጭ ከተማ በመገኘት የችግኝ ተከላውን መርሃ ግብር ከሰላም ሚኒስቴር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጋር በመሆን አስጀምረዋል ።በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የ200 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዝግጅቱ ተጠናቆ ዜጎች በየአቅራቢያቸው የዛፍ ችግኞችን በመትከል ላይ ናቸው፡፡በመላ ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት 200 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ቀን በመትከል በአለም የክብር መዝገብ ላይ ለመስፈር ዘመቻው በማለዳው ተጀምሯል።በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጭነት በዛሬው እለት በአንድ ጀንበር 200 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ሲደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።በዚህ መሰረት ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ዜጎች 200 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል ዘመቻቸውን ጀምረዋል።ሕንድ በአለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር ወይንም በ12 ሰዓታት 66 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል በአለም የክብር መዝገብ ላይ በቀዳሚነት ሰፍራ ትገኛለች።
https://waltainfo.com/am/32594/
110
0ሀገር አቀፍ ዜና
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ለችግኝ ተከላ ጎንደር ገቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ በሚገኘው በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር ለመሳተፍ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ትላንት ማምሻውን ጎንደር ገብተዋል፡፡ፕሬዝዳንቷ ጎንደር ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ሙሉቀን አዳነና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ እስከ ምሽት 12፡00 የችግኝ ተከላ መርሀ ግብ ይካሄዳል፤ በዚህም 200 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል አዲስ ዓለማቀፍ ክብረ ወሰን እንደሚመዘገብ ይጠበቃል፡፡ (ምንጭ፡- ኢ.ፕ.ድ) 
https://waltainfo.com/am/32591/
80
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአዊ ብሔርሰብ አስተዳዳር ከ245 ሺህ በላይ ኅብርተሰብ በችግኝ ተከላ እየተሳተፈ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
July 29, 2019
Unknown
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዛሬ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን ከ245 ሺህ በላይ ዜጎች እየተሳተፉ መሆኑን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡በብሔርሰብ አስተዳደሩ ሀገራዊ ዕቅዱን ለማሳካት ዛሬ ከ8 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለተከላ እንደ ተዘጋጀም የግብርና መምሪያ ኃላፊው አቶ አጀበ ስንሻው ተናግርዋል። እስከ ዛሬ ደግሞ ከ78 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ያገኘነው መርጃ ያመላክታል።ዛሬ እንደ ብሔርሰብ አስተዳዳር በፋግታ ለኮማ ወርዳ ችግኝ እንደሚተከል ነው ኃላፊው የተናገሩት። በፋግታ ለኮማው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ሚኒስትሮችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32593/
74
0ሀገር አቀፍ ዜና
በከተሞች የሙቀት መጠን መጨመር ተፅዕኖን ለመቀነስ ሃምሌ 22 በሚካሂደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን ሁሉም እንዲሳተፍ ተጠየቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 28, 2019
Unknown
ለሙቀት መጠን መጨመር በከተሞች የሚካሂደው እንቅስቃሴ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ ሃምሌ 22 በሚካሂደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን ሁሉም በነቂስ ወጥቶ መሳተፍ አለበት ተብሏል፡፡የአለም የሙቀት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣ የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ ይህንንም መቆጣጠር እንዲቻል እ.አ.አ 2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከተለያዩ የአለም ሀገራት ጋር በፓሪስ የአለምን ሙቀት ከ2 ዲግሬ ሴሊሽየስ በላይ እንዳይጨምር መስማማታቸው ይታወቃል፡፡በአለም ዙሪያ ኢንዳስትሪዎች ከመስፋፋታቸው በፊት የነበረው የአየር ሁኔታ ከአሁኑ ጋር ሲነፃፀር የሙቀት መጠኑ በአንድ ዲግሪ እንደጨመረም ይነገራል፡፡በዚህ አካሄድ በ2021 ላይ የዓለም ሙቀት ከ3 እስከ 5 ዲግሪ ሰሊሺየስ የሚጨምር ይሆናል።ለዚህ ደግሞ በዋነኝነት የሚጠቀሰው የኢንደስትሪዎች መስፋፋት የተሸከርካሪ ጭስ እና የደን ጭፍጨፋ ነው፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ በዋነኝነት በከተሞች የሚሰራው የአረንጓዴ ልማት ስራ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ እንደሆነም ይታወቃል፡፡በመሆኑም ኢትዮጵያም በዚህ አመት በያዘችው እቅድ መሰረት በከተሞች የሚደረገው የችግኝ ተከላ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ የብሄራዊ የቴክኒክ ኮሜቴ አባላቱ አስታውቀዋል፡፡ኢትዮጵያም ለአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ትኩረት በመስጠት ስትሰራ የቆየች ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለመሰለፍ ለምታደርገው ጥረት የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/32590/
153
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአማራ ክልል በሰኔ 15ቱ ጉዳይ የተጠረጠሩ 57 ተከሳሾች ከእስር ተፈቱ
ፖለቲካ
July 27, 2019
Unknown
ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል በተፈጠረው የከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና ተያያዥ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች የተጠረጠሩ 57 ተከሳሾች ከእስር ተፈቱ።ተጠርጣሪዎቹ ትናንት በባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት 13ኛ ወንጀል ችሎት ለሦስተኛ ጊዜ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቶ፥ ከተጠርጣሪዎች መካከል ከወንጀሉ ነፃ የተባሉ 57 ተጠርጣሪዎች እንዲለቀቁ ተደርጓል።በዚህ መዝገብ 218 ተጠርጣሪዎች የተያዙ ቢሆንም ቀደም ሲል 103ቱ ጉዳያቸው ተጣርቶ መለቃቀቸው ይታወሳል።ቀሪዎቹ ችሎት ከቀረቡት መካከል ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረና ኮሎኔል ባምላኩ ዓባይን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ይገኙበታል።የተጠርጣሪ ጠበቆች ኮሎኔል አለበል አማረና ኮሎኔል ባምላኩ ዓባይ እስካሁን ተጨባጭ ማስረጃ እንዳልተገኘባቸው በምርመራ ቡድኑ መረጋገጡን ጠቅሰዋል።እንዲሁም ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ የተፈጠረውን ችግር ለመመከት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውን እየተካሄደ ባለው ምርመራ መረጋገጡንና እስካሁን ማስረጃ አለመገኘቱን ጠበቆቹ አስረድተዋል።በመሆኑም በስም ተጠቃሾቹ በጉዳዩ የተሳተፉ አለመሆናቸው በተካሄደው ምርመራ እየታየ በመሆኑ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሳይሰጣቸው መዝገቡ ተዘግቶ እንዲለቀቁ ችሎቱን ጠይቀዋል።ከተጠርጣሪ እስረኞች መካከል የመቁሰል አደጋ ያለባቸው ተጠርጣሪዎች ስማቸው ተዘርዝሮ ሕክምና እንዲያገኙ ችሎቱ እንዲያዝም ነው ጠበቆቹ የጠየቁት።ኮሎኔል አለበል አማረ በበኩላቸው “ከታሰርን ጀምሮ አመላካች ውጤት ባለመገኘቱ ቤተሰቦቻችን እየተጎዱ በመሆኑና የመንግሥት ሠራተኞች በመሆናችን ፍርድ ቤቱ ጉዳያችንን በአግባቡ መዝኖ ሊለቀን ይገባል” ብለዋል።ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ደግሞ “ችግሩ እንዳይሰፋና ወደ ከፋ ጫፍ ሁኔታ እንዳይሄድ ያስቆምኩት እኔ ነኝ” በማለት ለችሎቱ ተናግረዋል።“እስካሁን በምርመራ መዝገቡም ማስረጃ ማቅረብ አልተቻለም፤ ምንም በሌለ ጉዳይ መታሰሬ አግባብ ባለመሆኑ ልለቀቅ ይገባል” ሲሉም ችሎቱን ጠይቀዋል።መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ የተጠርጣሪዎች ጉዳይ በጥንቃቄና በፍጥነት እየታየ ነፃነታቸው የተረጋገጠላቸው እየተፈቱ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል።ይሁን እንጅ ከታሰሩት መካከል ቀጥታና በተዘዋዋሪ የተሳተፉ እንዲሁም ከችግሩ ነፃ የሆኑ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ በመጥቀስ፥ ጉዳዩ በሰውና በቴክኒክ ማስረጃ እንዲጣራ ተደርጎ ከወንጀሉ ንጹህ የሆኑ ሰዎች እንደሚፈቱ አስታውቋል።“ከጉዳዩ ነፃ የሆኑ ሰዎችን በምንም መንገድ ቢሆን አላግባብ የሚወነጅል የለም፤ ማጣራቱ ለተጠርጣሪዎችም ቢሆን ጠቀሚ ነው” ብሏል ፖሊስ።በመሆኑም እስካሁን ያልተጣሩና መጣራት ያለባቸውን ጉዳዮች በሰውና በቴክኒክ ማስረጃ ለማጣራት የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው መጠየቁን የአማራ ብዙሃ መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/31266/
270
5ፖለቲካ
ባለሃብቶች ከየአካባቢዉ ወጣቶች ጋር በጋራ መስራት እንዳለባቸዉ ተገለፀ
ቢዝነስ
July 28, 2019
Unknown
በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ የባለሃብቶችና ወጣቶች የጋራ የሰላም ጉባኤ ተካሄደ፡፡በወረዳዉ ባለፈዉ አንድ አመት ከመልካም አስተዳደር፤ ከወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራና ከመሰረተ ልማት ችግሮች ጋር በተያያዘ ባለሃብቶች ስራ መስራት ሳይችሉ መቅረታቸዉ ተወስቷል፡፡የአብሸጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መላኩ ብርሃኔ እንደገለፁት በወረዳዉ በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ከ21 በላይ ባለሃብቶች ባለፉት 11 ወራት ወጣቱ ባነሳዉ የፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ምክኒያት ሙሉ በሙሉ ስራ አቁመዉ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡የወጣቶችን ጥያቄ መነሻ በማድረግ የወረዳ አስተዳደሩ ባካሄደዉ ጥናት በባለሃብቶቹ በትርፍነት ተይዞ የነበረ 300 ሄክታር መሬት ማግኘቱንና ለወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ማዋሉን ገልፀዋል፡፡በወረዳዉ ከመንግስት የስራ ማስኬጃ በመቀነስ ተመርቀዉ ስራ አጥ ለነበሩ 115 ወጣቶች የስራ ቅጥር መፈፀሙንም አቶ መላኩ ገልፀዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/23882/
96
3ቢዝነስ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በግብጽ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተሰጠውን የግንባታ ቦታ ጎበኙ
ፖለቲካ
July 28, 2019
Unknown
  የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በግብጽ ካይሮ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ግንባታ የተሰጠውን ቦታ ትናንት ጎብኝተዋል፡፡ በካይሮ እምብርት ዛማሊክ አካባቢ ነው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የግንባታ ቦታ የተሰጠው፡፡ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የግብጽ ኤምባሲ እንዲገነባ በሰጠችው ቦታ ትክ እና የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር በተደረሰው ስምምነት መሠረት ነው ለኢትዮጵያ በካይሮ ቦታ የተሰጣት፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ በግብጽ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የተላከ መልዕክትንም ለፕሬዝዳንት አል ሲሲሰ አድርሰዋል፡፡ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በነበራቸው ቆይታም ኢትዮጵያ የጋራ ጥቅምን መሠረት ያደረጉ ግንኙነቶችን ከግብጽ ጋር ማጠናከር እንደምትፈልግ አስታውቀዋል፡፡ኢትዮጵያና ግብጽ ለኤምባሲ ግንባታ የሚውል የቦታ ልውውጥ ስምምነት የተፈራረሙት በግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለሥላሴ እና በግብጹ ንጉሥ ፋሩክ አማካኝነት እንደነበር በግብጽ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡ (አብመድ)  
https://waltainfo.com/am/31268/
107
5ፖለቲካ
የሚኒስትሮች ም/ቤት ባካሄደው 72ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ፖለቲካ
July 28, 2019
Unknown
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 72ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።ምክር ቤቱ በስብሰባው በቅድሚያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተዘጋጅተው በቀረቡ የመድን ስራ እና የአነስተኛ ስራ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው የተወያየው።በዚህ መሰረትም የመድን ስራ አዋጅና የአነስተኛ ፋይናንስ ስራ አዋጅ በአሁኑ ወቀት ለማሻሻል መንስኤ የሆነው በሀገር ደረጃ እየተካ ካለው መጠነ ሰፊ የለውጥ ማዕቀፍ አንፃር የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ መሳተፍ እንዲችሉ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የመድን ስራ አዋጁን እና የአነስተኛ ፋይናንስን ስራ አዋጅን ለማሻሻል ረቂቅ አዋጁን አዘጋጅቶ አቅርቧል።ምክር ቤቱ በቀረቡት ረቂቅ የማሻሻያ አዋጆች ላይ ከተወያየ በኋላ ይፀድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።በመቀጠልም ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ ማረሚያ ቤት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል።በዚህም የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የኢፌዴሪ ህግ መንግስትንና ህገ መንግስቱን መሰረት አድርገው የወጡ ህጎችን፣ሀገር የተቀበላቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው የእስረኛ አያያዝ ደረጃዎችን ባከበረ ሁኔታ በፍርድ ቤቶች በሚሰጡ ውሳኔዎች ማስፈፀም በሚያስችሉ ሁኔታ መደራጀት እና ማረሚያ ቤቶች የእስረኞችን ሰብዓዊ ክብርና መብት በማክበር እንዲሁም የእስረኞች ግላዊ ሁኔታ በሚጠይቀው የፍርድ አፈፃፀም እርምት ስልቶችን ተግባራዊ በማድረግና ከህብረተሰቡ የሚቀላቀሉበትን ስርዓት ለመደንገግ የሚስችል ረቂቅ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቧል።ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል ተቀብሎ ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወከዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል ።በመጨረሻም ምክር ቤቱ በገንዘብ ሚኒስቴር የቀረቡትን የተለያዩ የብድር ስምምነቶች እና የማፅደቂያ አዋጆች ላይ ከተወያየ በኋላ የተገኙት ብድሮች ከሃገሪቱ የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ የሚጣጣሙ እና ጫናቸው ያልበዛ በመሆኑ አዋጆች ይፀድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል።
https://waltainfo.com/am/31267/
243
5ፖለቲካ
የጋምቤላ ክልል የ2012 በጀት 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ሆነ ፀደቀ
ቢዝነስ
July 28, 2019
Unknown
የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለ2012 የበጀት ዓመት የልማት እቅድ ማስፈፀሚያ 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በጀት፣ዓዋጆችንና ሹመት በማጽደቅ ተጠናቀቀ። የክልሉን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በአዲሱ በጀት ዓመት ባለድርሻ አካላት እንዲሰሩ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አሳስበዋል። ጉባዔው በሁለት ቀናት ቆይታው በክልሉ በ2011 እቅድ አፈፃፀም ላይ ከመከረ በኋላ የ2012 በጀት ዓመት የልማትና መልካም አስተዳደር ግቦችን ለማሳካት 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በጀት አጽድቋል፡፡ ከጸደቀው በጀት መካከል 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ለክልል መንግሥት፣ ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ፣ ለመደበኛና ለመጠባበቂያ ተመድቧል። ቀሪው ለዞንና ለወረዳዎች እንደተመደበ ተብራርቷል። የጸደቀው በጀት ከክልሉ ከተለያዩ የገቢ ምንጮች፣ከፌደራል መንግሥት ድጎማ እንዲሁም ከውጭ ብድርና እርዳታ እንደሚሸፈንም ተመልክቷል፡፡ በክልሉ የጸደቀው በጀት ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ251 ሚሊየን ብር በላይ ብልጫ እንዳለውም ተገልጿል።
https://waltainfo.com/am/23883/
115
3ቢዝነስ
ጠ/ሚ ዐቢይ ሐምሌ 22 በመላ ሀገሪቱ 200 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል በተያዘው መርሃ ግብር ዙሪያ መልዕክት አስተላለፉ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 27, 2019
Unknown
ለብዙ ዘመናት ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሲስተጋባ የኖረውና ‹ለምለሟ ሀገሬ› የሚለው እድሜ ጠገብ ዜማ የልጆቻችን የዛሬ እውነታ የእኛ ደግሞ ከጆሯችን ሁሌም ያለ ቅርብ ትዝታ ነው፡፡ትናንት እውነት እና ሀሴት የነበረው፤ ዛሬ ግን ምኩን እና ቁጭት ሆኖ የቀረው ዝማሬ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ኅሊና ውስጥ አብዝቶ ይመላለሳል፡፡እውነት ነው ሀገራችን ለምለም ነበረች- ዛሬ ግን አይደለችም፤ ምክንያቱም አባቶቻችን ያቆዩልንን እኛም በተራችን ለልጀቻችን አላቆየንም- እናም ልምላሜዋን እና አረንጓዴ ውበቷን ከትዝታ ብቻ አወዳጅተን አደራችንን በልተናል፡፡ዜማዎቻችን ብቻ ሳይሆኑ ተረቶቻችንም ሀገራችን በደን የተሞላች እንደነበረች ይነግሩናል፡፡ በተረቶቻችን ውስጥ የምናገኛቸውን ብዙዎቹን እንስሳት ዛሬ በአካባቢያችን አናገኛቸውም፡፡በየቋንቋችን ስማቸው ብቻ የቀረው የዛፍ ዓይነቶች ሀገራችን ዓይነተ ብዙ ደን እንደነበራት ቋሚ ምስክሮች ናቸው፡፡የዛፎች ጉዳይ ለእኛ የውበት ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ የህልውና ጉዳይ ነው፤ የእምነት ጉዳይ ነው፤ የባህ ልጉዳይ ነው፤ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው፤ ዛፍ ማለት እኛ ነን- እኛ ማለት ያለ ዛፍ ምንም ነን፡፡የበረሃማነት መስፋፋትና የአየር ንብረት መዛባት ያስከተለው ቀውስ ሀገራችንን አደጋ ላይ ከመጣል አልፎ የስሟ መገለጫ እስከመሆን ደርሷል፡፡ባለፉት ዐርባ ዓመታት ብቻ እያሠለሰ የሚመታን ድርቅ በምግብ እህል ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ትግል ተፈታትኖታል፤ ወገኖቻችንንም ከክብር ማማ አውርዶ የተረጅነት ወለል ላይ አስቀምጦብናል፡፡የዝናብ ወቅቶቻችን እየተዛቡ፣ ለጎረቤት ይተርፉ የነበሩት ወንዞቻችን እየጎደሉ፤ ምንጮቻችን እየነጠፉ፤ ወይናደጋው በረሐ፣ ደጋው ቆላ እየሆነ የህልውና አደጋ ጋርጦብናል፡፡ የራሳችንን ህልውና በራሳችን ጥርስ ግጠነው- የነበረውን አፍርሰን እንዲያ ያልነበርን መስለናል፡፡ከተሞቻችን በአንድ በኩል በኢንዱስትሪዎችና በተሽከርካሪዎች ጢስ ይበከላሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ዛፎቻቸውን ጨርሰው ከአንድ ፀሐይ ቢሆኑም የሦስት ፀሐይ ያህል በገረረ ንዳድ ተንቀልቅለው ህያው በድኑን ያቃጥላሉ፡፡ከተሞቻችን የከተማ መቃጠያ መሆናቸው ቀርቶ የከተማ መኖሪያ እንዲሆኑ ደናማ ከተሞች መሆን አለባቸው፡፡ወገባችንን አሥረን የምንሠራቸው ግድቦች በደለል እየተሞሉና በውኃ እጥረት እየተመቱ ልፋታችንን መና እያስቀረነው ነው፡፡እጃችንን በእጃችን እየበላን ጸጸት ቁጭታችን ብዙ ነው፡፡ ይህ ቁጭት እና መብሰክሰካችን የይቻላል ስሜታችንን አቀጣጥሎ ወደ አረንጓዴ ሰገነታችን በሀይል ካንደረደረን እሰየው፤ ቁጭት ብቻ ከሆነ ግን ዋይታችንን የማይቋጭ ያው ከንቱ ቁጭት ብቻ ነው፡፡ሐይቆቻችን የነበራቸውን ቦታ እየለቀቁ፣ አንዳንዶቹ ከነባር ይዞታቸው ሲሸሹ ሌሎቹ ጨርሰው እየደረቁ ነው፡፡ሀዘናችን መሪር ሆኗል፡፡ ለነ ሀረማያ ያፈሰስነው እንባ ገና ከጉንጫችን ሳይደርቅ የሌሎች ሀይቅ ጅረቶቻችንም ህልውና ጉዳይም ለሌላ ሀዘን እያጨን ነጋችንን ጽልም አርጎታል፡፡በዚህም የተነሣ በዓሣ ሀብታችን ላይ ፈተና እየተደቀነ ነው፡፡ በሐይቆቻችን ላይ ሠፍረው ይኖሩ የነበሩት አዕዋፋት ሀገር ጥለው እየኮበለሉ በሐይቆች ውስጥ የሚኖሩ እንስሳትም ዘራቸው እየተመናመነ ነው፡፡እንባችንን ከአይናችን ለመክላትና ዋይታችንን ወደ ዝማሬ ለመቀየር ማን ይምጣ? ለእኛ ህመም እና ስቃይ ማሻሪያው እና ፈውሱም ያለው እኛው እጅ ነው፡፡ዓለም ያደነቃቸው ታላላቅ ቤተ እምነቶቻችን የተሠሩት ከሀገር በቀል ዛፎች በተገኙ እንጨቶች ነበር፡፡በውስጣቸው የምናገኛቸው ቅርሶችና ንዋያተ ቅዱሳት የተዘጋጁት ከኢትዮጵያውያን እንጨቶች ነበር፡፡ሥዕሎቻችን፣ ቅርፆቻችንና የወግ ዕቃዎቻችን በሙሉ የደኖቻችን ውጤቶች ነበሩ፡፡ቀደምቶቻችን የተጠበቡባቸው ዓምዶችና ወጋግራዎች፣ በሮችና መስኮቶች፣ ጣራዎችና አቴናዎች የደኖቻችን ትሩፋቶች ነበሩ፡፡ትውፊታዊ ክዋኔዎቻችን ደኖቻችንን አበክረው ይፈልጓቸዋል፡፡ አረንጓዴው አለማችን የሁሉ ነገራችን አልፋ እና ኦሜጋ ነው፡፡ሰርግ ሀዘናችን- ስግደት ሶላታችን- ልደት ሞታችን- አምልኮ ከበሯችን ወግ እና ጨወታችን እንኳን ከዛፍ- ደኖቻችን ጋር እጅጉን ተሰናስሏል፡፡ ህይወታችን ከደኖቻችን ጋር የተያያዘ ነው፡፡የደኖቻችን መመናመን በጎ ዕሴቶቻችን እንዲመናመኑ አድርጎብናል፡፡ ዕርቅ፣ ሸንጎ፣ ውይይት፣ ታሪክ ነገራ፣ በባህላችን ውስጥ የሚከወኑት በዋርካዎቻችን ሥር ነው፡፡በሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ እና ትውስታ ውስጥ አረንጓዴ ደኖቻችን የደግነት፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የህይወትእና የተስፋ ውካዮች ናቸው፡፡ በገጠሬው ሕይወትና በከተሜው ትዝታ ውስጥ የሚገኙት የዱር ፍሬዎች የባህላችን አካላት ነበሩ፡፡ሌላው ቀርቶ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎቻችን እንኳን የሚዘጋጁት ከደን ውጤቶቻችን ነው፡፡ በባህላችን የአንድ ዋርካ መውደቅ የአንድ እንጨት መውደቅ ሳይሆን የአንድ ትልቅ ሰው፤ የአንድ ትልቅ ሽማግሌ መውደቅ ምልክት ነው፡፡በሀገራችን ብዙ ወገኖቻችን ኑሯቸውን በደኖችና በደን ውጤቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የደን ፍሬዎችን ለቅመው፣ የደን ቅጠሎችን ሰብስበው፣ የደን ውጤቶችን ቆርጠው፣ የደን ውጤቶችን ወደ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ቀይረው፣ በመሸጥ ኑሯቸውን የመሠረቱ ናቸው፡፡የሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጮች በአንድም በሌላም መንገድ ከደን ውጤቶቻችን ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ደኖቻችንና የዱር እንስሶቻችን የቱሪዝም ገቢያችን መሠረቶች፣ የአይናችን ማረፊያ ጌጦች፣ የባህል- ወግ እና እምነታችንም መከሰቻ ናቸው፡፡እነዚህን ሁሉ ስንመለከት ነው የዛፍ ጉዳይ ለእኛ የቅንጦት ጉዳይ የማይሆነው፡፡ ከዚህ በፊትም እንደምለው ይህች ሀገር ከአባቶቻችን የወረስናት ብቻ ሳትሆን ከልጆቻችንም የተዋስናት መሆኗንም ማሰብ ተገቢ ነው፡፡እኛም በተራችን ለልጆቻችን ስናስረከባት ከነበረሀዋ፣ ከነንዳዷ፣ ከነ ድርቋ እና ከነደለሏ እንዳይሆን የቤት ስራችንን እንሰራ ዘንድ ይገባናል፡፡ከልጆቻችን ነፍስ ላይ የነጠቅነውን በምቹ ሀገር የመኖር የህልውና መሰረት ሳንውል ሳናድር ከመመለስ እና ከመተካት የሞራል፣ የእምነት እና የሰብአዊነት ጽኑ ጥያቄ ጋር የተፋጠጥንበት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡የሀገራችንን የደን ሽፋን እንዲያገግም ማድረግ ህልውናችንን ማጽናት፣ እምነታችንን መጠበቅ፣ ባህላችንን ማበልጸግ፣ ኢኮኖሚያችንን ማዳበር ነው፡፡አራት ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ስንነሣ ለህልውናችን፣ ለእምነታችን፣ ለባህላችንና ለኢኮኖሚያችን ስንል ታጥቀን መነሣታችንም ጭምር ነው፡፡ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያሳየው ተነሣሽነት ይህን ዓላማ እንደተረዳው የሚያሳይ ነው፡፡ይህንን ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት እስካሁን ባደረግነው አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ ርብርብ ቢልየኖች ችግኞችን ተክለናል፡፡ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን በምናደርገው ብሔራዊ የችግኝ ተከላ ቀን 200 ሚሊየን ችግኞችን በአንድ ቀን በመትከል የዓለምን ክብረ ወሰን እንሰብረዋለን፡፡ የያዝነው ክረምት ከማለፉ በፊትም አራት ቢሊየን ችግኞችን ተክለን ግባችንን እንመታለን፡፡ይህን ስኬት ለማምጣት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና የክልል አመራሮች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ በችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች የሚገኙ ሠራተኞች፣ የግብርና ባለሙያዎችና ምሁራን፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ኮሜዲያን፣ የሚዲያ ኃላፊዎችና ጋዜጠኞች፣ ነጋዴዎችና ታላላቅ ኮርፖሬሽኖች፣ ወጣቶችና ሕጻናት፣ አጓጓዦችና የጉልበት ሠራተኞች ላደረጉት ምትክ የማይገኝለት አስተዋጽኦ በራሴና በኢፌዴሪ መንግሥት ስም ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ለአንድ ሃገር ጉዳይ፣ አንድ ሆነን በዓላማ ከተነሣን የሚሳነን ነገር እንደማይኖር የአረንጓዴ አሻራ ስኬታችን ምስክር ነው፡፡ከደን የተራቆተችውን ሀገራችንን ለማልበስ እንደተነሣነው ሁሉ ከሰላም ከፍቅርና ከይቅርታ እየተራቆተች የመጣችውን ሀገራችንንም አንድ ሆነን ማልበስ አለብን፡፡አራት ቢሊየን ዛፍ በአንድ ክረምት መትከል ከቻልን አራቱን አስፈላጊ ሀገራዊ ዕሴቶችን፡- ሰላምን፣ ይቅርታን፣ ፍቅርንና አንድነትን መትከልና ማሳደግ አያቅተንም፡፡ በፍጹም፡፡በቀሪው ጊዜ የተከልናቸውን ችግኞች በመጠበቅ፣ በመንከባከብና ለፍሬ በማብቃት መትከል ብቻ ሳይሆን ማሳደግም እንደምንችል እናሳይ፡፡ዛፍ ብሔር፣ ቋንቋ፣ እምነትና ርእዮተ ዓለም የለውም፡፡ ሁሉም ዛፍ የሁላችንም ነው፡፡ የሠራነው ሥራም ከእነዚህ ሁሉ በላይ ነው፡፡ክብካቤና ጥበቃውም እነዚህን ልዩነቶች ሁሉ አልፎ ሊደረግ የሚገባው ነው፡፡ሐምሌ 22 ቀን ሁላችንም ማልደን በመውጣት፣ ችግኞችንም በተገቢ መንገድ በመትከል፣ አረንጓዴ አሻራችንን እናሳርፍ፡፡ ነገንም ዛሬ እንትከል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32588/
808
0ሀገር አቀፍ ዜና
የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ስራው የአካባቢውን ነዋሪዎች በቱሪዝም ገቢ የላቀ ተጠቃሚ አድርጓቸዋል
ሀገር አቀፍ ዜና
July 27, 2019
Unknown
በፈረንሳይ ባሮኒስ ግዛት ከሁለት ዓስርት ዓመታት በፊት የተጀመረው የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ስራ በአነስተኛ የግብርና ምርቶች ብቻ ጥገኛ የነበሩትን የአካባቢው ነዋሪዎች በቱሪዝም ገቢ ተጠቃሚ አድርጓቸዋል።በፈረንሳይ የባሮኒስ ግዛት የአካባቢ መራቆት ያሳሰባቸው የአካባቢው ተቆርቋሪዎች ከሁለት ዓስርት ዓመታት በፊት የጀመሩት የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ስራ በአነስተኛ የግብርና ምርቶች ብቻ ጥገኛ ለነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎችም ከቱሪዝም ገቢ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ከሁለት አስርተ አመታት በፊት አካባቢውን በመከለል የተፈጥሮ ሐበት ጥበቃ ስራ በመስራት አካባቢውን የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ በሚል የተጀመረው ጥረት አሁን ላይ ፍሬ አፍርቷል ተብሏል፡፡አካቢውን ፓርክ ለማድረግ ጥብቅ ህግ በማውጣት ከፍተኛ የእንክብካቤ ያደረጉት የአካባቢው ነዋሪዎች ተራራማ አካባቢያቸውን ውበት አላብሰው ከቱሪዝም ገቢው ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ዘ-ኢኮኖሚስት ዘግቧል፡፡በአሁኑ ጊዜ የተፈጥሮ ሐበት ጥበቃ ስራው እውቅና አግኝቶ የባሮኒስ ግዛት አስተዳደር   ፓርክ በፈረንሳይ ከሚገኙ ጥብቅ ፓርኮች መካል አንዱ ለመሆን ችሏል ነው የተባለው፡፡በመሆኑም በአነስተኛ የግብርና ምርቶች ብቻ ጥገኛ ለነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎችም ቱሪዝም ሌላ የገቢ ምንጭ ሆኗቸዋል ተብሏል፡፡እ.ኤ.አ በ2015 51ኛው በፈረንሳይ የባሮኒስ ፓርክ በሚልም እውቅና አግኝቷል። ፓርኩ 1ሺ800 እስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት ሲኖረው፤ ጥቅጥቅ ደን እና ተፈጥሯዊ ፏፏቴዎችን በውስጡ መያዝ ችሏል፡፡በተደረገው የተፈጥሮ ሐብት ስራ ፓርኩ ለተራራ መውጣት፣ ለብስክሌት ውድድር፣ ለፈረስ ግልቢያና ለመሳሳሉ ስፖርታዊ ውድድሮች በፈረንሳውያን ዘንድ ተመራጭ ፓርክ ለመሆን ችሏል፡፡እነደ ዘ-ኢኮኖሚስት ዘገባ ይህ በባሮኒስ አስተዳር የተከናወነው ውጤታማ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ፤ ፈረንሳይ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያከናወነችው ስኬታማ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ማሳያም ተብሏል ፡፡በፈረንሳይ እ.ኤ.አ 1990 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የአካባቢ እንብካቤና የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ስራ የሀገሪቱን የደን ሽፋን በሰባት በመቶ እንዲጨመርም አድርጎታል፡፡ይህም ከጥቅል ከሀገሪቱ የቆዳ ስፋት ውስጥ የደን ሽፋኑን ወደ 31 በመቶ እንዲያድግ አድርጎታል፡፡ይህም ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ፈረንሳይን 4ተኛዋ ሰፊ የደን ሽፋን ያላት ሀገር ያደርጋታል፡፡ ስዊዲን፣ ፈንላድና ስፔን በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 3ተኛ ያለውን ደረጃ ይይዛሉ፡፡የደን ልማት ስራ ውጤቱን የፈረንሳይ ብቻ ሳይሆን የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የሚጋሩት ስኬት መሆኑን የዘገበው የዘ-ኢኮኖሚስት፤ የህብረቱ አባላት ባለፉት 25 ዓመታት በጥቅል ውጤታማ የደን ልማት ስራ አከናውነዋል ብሏል፡፡ በአውሮፓ ህብረት ሀገራት መካከል በጥቅል ከ1990 እስከ 2015 በተሰራው ውጤታማ የተፈጥሮ ሐብጥ ጥበቃ ስራ የአካባቢው የደን ሽፋን በ90ሺ000 ስኩየር ኪሎ  ሜትር እንዲጨምር አስችሏል፡፡ይህም የህብረቱ ሀገራት  ባለፉት 25 ዓመታት የፖርቹጋልን የቆዳ ስፋት የሚያክል መሬት በደን መሸፈን መቻላቸው ነው የተዘገበው፡፡ከአውሮፓ ሀገራት በደን ሽፋን ቀዳሚ የሆነችው ስዊዲን ከቆዳ ስፋቷ 28 ሚሊዮን ሄክታር መሬቷ በደን የተሸፈነው ሲሆን፤ ይህም የሀገሪቱን 68.9 በመቶ ቆዳ ይሸፍናል፡፡ ፊንላንድ 22 ሚሊዮን ሄክታር፣ ስፔን 18.4 ሚሊዮን ሄክታር መሬታቸው በደን የተሸፈነ ነው፡፡በአህጉረ አውሮፓ ባፉት ሶስት አስርት ዓመታት ከኢንዱስትሪያል የኢኮኖሚ መሰረታቸው ጎን ለጎን የአካባቢ እንክብካቤና የደል ልማት ስራ ቀዳሚ ተግባር በማድረግ አበክረው ሰርተዋል፡፡በአንጻሩ በጥቅል በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ 1990 ጀምሮ በአፍሪካ ደረጃ የእጽዋት ሽፋን እየተመናመ መሆኑ ነው ዘኢኮኖሚስት የሚያትተው፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እ.ኤ.አ ከ1990 እስከ 2016 የደቡብ አፍሪካን የቆዳ ሽፋን የሚያክል ማለትም 1.3 ሚሊዮን ስኩየር ኪሎ ሜትር ደን ወድሟል ተብሏል፡፡በአፍሪካ ከባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ወዲህ የሙቀት መጨመር፤ የዝናብ እጥረት ድርቅ እና ረሀብ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተከሰቱ መሆኑን ዘ- ኢኮኖሚስት ጠቅሷል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/34120/
426
0ሀገር አቀፍ ዜና
አሜሪካ ስደተኞችን ፍርድ ቤት ሳታቀርብ ወደመጡበት አገር መመለስ ልትጀምር ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
July 27, 2019
Unknown
አሜሪካ ስደተኞችን ፍርድ ቤት ሳታቀርብ ወደመጡበት አገር መመለስ ልትጀምር ነው የአሜሪካ መንግሥት የስደተኞች ፍርድ ቤትን አልፎ ስደተኞችን በፍጥነት ወደ መጡበት አገር ለመመለስ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱ ተገለጸ። በአዲሱ ደንብ መሰረት ማንኛውም ማስረጃ የሌለው ስደተኛና በተከታታይ ለሁለት ዓመት አሜሪካ ውስጥ እንደነበር ማረጋገጥ ያልቻለ ግለሰብ ወደ መጣበት አገር እንዲመለስ ይደረጋል። ፖሊሲው ዛሬ ይፋ ተደርጎ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች በአፋጣኝ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል ተብሏል። አሜሪካን ሲቪል ሊበርቲስ ዩኒየን የተባለ የመብት ተሟጋች ቡድን ፖሊሲውን በመቃወም ፍርድ ቤት ወስዶ ለመሟገት ማሰቡን ተናግሯል። የአሜሪካ የስደተኞች ፖሊሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥብቅ እየሆነ እየመጣ መሆኑን የሚያስረዱ አካላት አገሪቱ በደቡብ በኩል ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስናት አካባቢ የምታደርገውን በመጥቀስ የጉዳዩን አሳሳቢነት ያብራራሉ። የአገር ውስጥ ደህነንነት መሥሪያ ቤቱ ተጠባባቂ ዋና ጸሀፊ ኬቨን ማክአሌናን፤ "ይህ ለውጥ በድንበር አካባቢ ያለብንን ጫናና የአቅም ጉዳይ ያነሳልናል" ሲሉ አሞካሽተውታል። አክለውም "ቀጣይነት ላለው የስደተኞች ቀውስ ምላሽ የሚሰጥ" ብለውታል። የአሜሪካ የስደተኞች ጉዳይ ላይ ትንታኔ የሚሰጡ ባለሙያዎች በበኩላቸው, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለ2020 ምርጫ ስደተኞችን መቆጣጠርን ቁልፍ ጉዳይ ለማድረግ መወሰናቸውን ያሳያል ይላሉ። ከዚህ ቀደም ሰዎች ወደ መጡበት አገር ወዲያውኑ እንዲመለሱ የሚደረገው ከአሜሪካ ድንበር በ160 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ውስጥ ሲገኙና አሜሪካ ከገቡ ከሁለት ሳምንት በታች የሆናቸው ከሆኑ ብቻ ነበር። በአገሪቱ የትኛውም አካባቢ የሚገኙ ስደተኞች ወይንም ከሁለት ሳምንት በላይ የሆናቸው ግለሰቦች ጉዳያቸው ወደ ፍርድ ቤት ተመርቶ ሕጋዊ ውክልና የማግኘት መብታቸው ተጠብቆ እንዲቆዩ ይደረግ ነበር። አዲሱ ሕግ ግን ማንኛውም ስደተኛ በየትኛውም የአገሪቱ ስፍራ ቢገኝ በቁጥጥር ስር ከዋለ ያለ ጠበቃ ውክልና ወደመጣበት እንዲመለስ ይደረጋል።  ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያበቃ ምክንያት ያላቸው፤ የጥገኝነት ጉዳዮችን የሚከታተለውን ባለሙያ የማናገር መብት አላቸው ይላል። ሰኞ ዕለት ፖሊሲው በተዋወቀ በሰአታት ውስጥ የመብት ተሟጋች ድርጅቱ አሜሪካን ሲቪል ሊብረቲስ ዩኒየን ጉዳዩን ፍርድ ቤት በመውሰድ ለመሞገት ማሰቡን አስታውቋል። "ይህንን የትራምፕ እቅድ ለማስቆም በፍጥነት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደን ክስ እንመሰርታለን" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። "በአሜሪካ ለረዥም ጊዜ የቆዩ ስደተኞች በትራፊክ ደህንነት ጥሰት ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ ሰዎች ያነሰ በፍርድ ቤት የመከራከር እድል አላቸው" ሲሉም ምሬታቸውን ገልፀዋል። በሲቪልና ሰብዓዊ መብቶችን ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት ቫኒታ ጉፕታ፣ የፕሬዝዳንት ትራምፕን እቅድ የስደተኞች ጉዳይ የሚያየውን ተቋም "ወረቀታችሁን አሳዩን ወደሚል ፈርጣማ ኃይል" እየቀየሩት ነው ብለዋል። የሕግ ባለሙያ የሆኑት ጃኪ ስቲቨንስ በበኩላቸው፣ ወደመጣችሁበት አገር ተብለው ከሚመለሱ ሰዎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው እንደሚገኙበት ገልፀዋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34119/
328
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ፖለቲካ
July 27, 2019
Unknown
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 72ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ከስብሰባው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የዛፍ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/31265/
54
5ፖለቲካ
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለድንበር አጥር ማስገንቢያ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ፈቀደ
ፖለቲካ
July 27, 2019
Unknown
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሜክሲኮ ድንበር አቅራቢያ ለማስገንባት ላቀዱት የግንብ አጥር 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ፈቀደ።ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከሜክሲኮ በምትዋሰነው ድንበር የስደተኞችን ፍልሰት ለመቆጣጠር በሚል መከላከያ ግንብ የመገንባት እቅድ አላቸው።ለዚህም 6 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ወጪ እንዲደረግላቸው ቢጠይቁም÷ይህ ከኮንግረሱ ተቃውሞ ማስተናገዱን ተከትሎ ተፈጻሚ ሳይሆን ቆይቷል።ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም የትራምፕ አስተዳደር ያስፈልገኛል ካለው ገንዘብ ውስጥ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላሩን ይጠቀም ዘንድ ይሁንታን ሰጥቷል።ፈቃዱን ተከትሎም ትራምፕ በካሊፎርኒያ፣ አሪዞና እና ኒው ሜክሲኮ ግዛቶች ለሚገነባው መከላከያ ግንብ ገንዘቡን መጠቀም ይችላሉ ነው የተባለው።ይሁንና የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፈቃድ ግን ከዴሞክራቶች እና ከበርካታ ግዛቶች ተቃውሞ እንደገጠመው የዘገበው ሬውተርስ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/33975/
96
5ፖለቲካ
ችግኞች መጽደቃቸው ተረጋግጦ ለተከሏቸው አካላት የምስክር ወረቀት እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 26, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር የሚካሄድበትን ‹‹የአረንጓዴ አሻራ›› ቀን በተመለከተ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ መግለጫ ሰጥቷል።ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም በአማራ ክልል በአንድ ቀን 100 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል መታሰቡን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ማርቆስ ወንዴ ገልጸዋል።በተያዘው ክረምት በአማራ ክልል ከ2 ቢሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል መታቀዱን ምክትል ቢሮ ኃላፊው አስታውቀው፤ እስካሁንም 800 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል ብለዋል።ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 እስከ ምሽቱ 12:00 በአንድ ጀምበር በአገሪቱ ከሚኖረው 200 ሚሊዮን ችግኞች ተከላ፤ ከእቅዱ ውስጥ ግማሹን መትከል ደግሞ አማራ ክልል ኃላፊነት ወስዷል ብለዋል።ዋናው ጉዳይ ችግኝ መትከሉ ሳይሆን መንከባከቡ እንደሆነ የገለጹት ምክትል ቢሮ ኃላፊው ፤ ግለሰቦችና ተቋማት ችግኞችን ስለማጽደቃቸው ክትትል እንደሚደረግና ከሁለት ዓመት በኋላ ችግኞቹን በሚገባ ማጽደቁ ተረጋግጦ የምስክር ወረቀት እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡የሀሰት ሪፖርትን ለመከላከል፣ ስለተተከሉትና ስለጸደቁት ችግኞች ብዛትም ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል አሠራር እንደተዘጋጀም ሃላፊው ገልጸዋል። (ምንጭ፡ አብመድ)
https://waltainfo.com/am/32587/
125
0ሀገር አቀፍ ዜና
ለሠላም ከሌሎች ክልሎች ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 27, 2019
Unknown
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለአማራ ሕዝብ ክልል ሕዝብ ሠላምና ደኅንነት የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ክልሎች ሠላምና ፀጥታም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ርዕሰ መስተዳድሩ ለክልሉ ሕዝብ ሠላምና ደኅንነት ሲባል ከሌሎች ክልሎች ጋር በሠላም ጉዳይ ለመሥራት በራቸው ድረስ ለመሄድ ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡የአማራ ክልል ሠላምና ፀጥታ በቅድሚያ የሚጠቅመው የክልሉን መሆኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥የአማራ ክልል ሕዝብ ከክልሉም ውጭ ስለሚኖር የሌሎች ክልሎች ሠላምና ፀጥታ የአማራ ክልልም ጉዳይ በመሆኑ ከክልሎች ጋር አብረን ለመሥራት ተዘጋጅተናል ነው ያሉት፡፡ወደ ስልጣን የመጣሁበት ወቅት የክልሉ ሕዝብ በታሪኩ አይቶት በማያውቀው መልኩ አሳዛኝ ክስተት የተፈጠረበት ነው፥ ያሉት አቶ ተመስገን ክልሉን ከዚህ ችግር ለማውጣትና የፀጥታ ስጋት የማይፈጠርበት እንዲሆን እየተሰራ ነው ብለዋል።የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ማስጠበቅ የፀጥታ ኃይሉ ብቻ ኃላፊነት አለመሆኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና ብዙኃን መገናኛ ድርጅቶች ለክልሉ ሕዝብ ሠላም አበክረው ሊሠሩ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡የሕዝቡን የሠላምና የፀጥታ ስጋቶች በመለየት መሥራት የሚዲያው ተቀዳሚ ተግባር መሆኑንም ጠቁመዋል ።ከዚህ ባለፈም ሚዲያዎች የምጣኔ ሀብት፣ ማኅበራዊና ባሕላዊ እሴቶችን ሽፋን መስጠት አእንዳለባቸው መጠቆማቸውን አብመድ ዘግቧል፡
https://waltainfo.com/am/32589/
149
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
July 26, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤዝሊ ጋር ተወያይተዋል።በውይይታቸውም የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ለመቀጠል በሚችልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል።የዓለም የምግብ ፕሮግራም በምግብ ደህንነት፣በተመጣጠነ ምግብ፣ በአቅም ግንባታ ዘርፎች እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ኢትዮጵያን እየደገፈ መሆኑ ይታወቃል።ከውይይቱ በኋላም በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኝ መትከላቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/31262/
62
5ፖለቲካ
ሐምሌ 22 በአዲስ አበባ 3 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል
ቢዝነስ
July 26, 2019
Unknown
ሐምሌ 22 በአዲስ አበባ ከተማ የሶስት ሚሊየን ችግኞች ተከላ ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡ዛሬ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት የአረንጓዴ አሻራ የንቅናቄ መድረክ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል፡፡በንቅናቄ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።ኢንጂነር ታከለ ኡማ በንቅናቄ መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ከተማ አስተዳደሩ በዚህ የአንድ አመት ጉዞው ካከናወናቸው በርካታ ተግባራቶች ውስጥ የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎች ዋነኞቹ እንደሆኑ ጠቅሰው፣ በተለይ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ለተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ማሰባሰብ እንዲሁም የችግኝ ተከላ ተግባራት መልካም ውጤት የታየባቸው ናቸው ብለዋል፡፡   ምክትል ከንቲባው አያይዘውም እንደገፁት ሐምሌ 22 በአገራቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ በአዲስ አበባ ደረጃ 3 ሚሊየን የሚሆኑ ችግኞች እንደሚተከሉና ለዚህም የሚሆን ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ጉድጓዶች መቆፈራቸውንና ቀሪዎቹ በመጪዎቹ ጥቂት ቀናቶች ውስጥ እንደሚጠናቀቁም ነው የተናገሩት።ሐምሌ 22 በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ማስጀመሪያ ይሆን ዘንድ ከተለያዩ የከተማዋ ነዋሪዎች የተውጣጡ ተወካዮች ከምክትል ከንቲባው እጅ ችግኞች ተረክበዋል።   ትላንት “ለምለሚቱ ኢትዮጵያ” ትባል ነበር ያም የሆነው ትላንት አባቶች መሰዋእት ሆነው ሀገሪቱን ለዛሬዎቹ ትውልዶች ስላቆዩ መሆኑን የገለፁት ከንቲባው፣ ዛሬ እና ነገን መልካም ለማድረግ ልዩነታችንን ትተን አንድ በመሆን የተጣለብንን ኃላፊት ልንወጣ ይገባናል ሲሉም ለመላው የከተማዋ ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።  
https://waltainfo.com/am/23881/
184
3ቢዝነስ
በሞቃዲሾ የሚገኘው የቱርክ ወታደራዊ ካምፕ 152 የሶማሊያ ወታደሮችን አሰለጠነ
ፖለቲካ
July 26, 2019
Unknown
በሶማሊያ ሞቃዲሾ የሚገኘው የቱርክ ወታደራዊ ካምፕ 152 የሶማሊያ ወታደሮች ማሰልጠኑን አስታወቀ፡፡በቱርክ አጋዥነት በሶማሊያ የሚደረገው ወታደራዊ ስልጠና ሀገሪቱን ከሚያምሳት የሽብርተኝነት አደጋ ለመታደግ መሆኑንም ቱርክ ገልፃለች፡፡ቱርክ በአፍሪካ ከከፈተቻቸው ወታደራዊ ካምፖች መካከል በ2017 እ.አ.አ በሞካዲሾ የከፈተችው ይጠቀሳል፡፡ይህ ካምፕ ከ1 ሺህ 500 በላይ የሶማሊያ ወታደሮችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማሰማራቱን የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር ሁሉሲ አካር አስታውቀዋል፡፡ቱርክ በሶማሊያ አሰልጥና ካስመረቀቻቸው ወታደሮች መካከልም 81 የሚደርሱት በመቶ አለቃ ማዕረግና ከ71 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በ50 አለቃ ማዕረግ እንደተመረቁ እና የሰላም ማስከበር ስራቸውን እንደሚሰሩ ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት፡፡የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ 152 የሶማሊያ ወታደሮችን በመገኘት ያስመረቁ ሲሆን÷ ቱርክ በሶማሊያ ሽብርተኝነትን ለማጥፋት እያደረገች ስላለው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡በሞቃዲሾ ቱርክ ካስመረቀቻቸው ወታደሮች ጎን ወታደራዊ መጠለያዎችን እና ትምህርት ቤቶችን መገንባቷን የዘገበው ሲጂቲኤን ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/33311/
109
5ፖለቲካ
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤን ማካሄድ ጀመረ
ፖለቲካ
July 26, 2019
Unknown
የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ የምርጫ ጊዜ 4ኛ የስራ ዘመን መደበኛ ጉባኤን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ላክዴር ላክባክ በጉባዔው መክፈቻ እንደተናገሩት፤ ለህዝቦች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ ዕድገት ሰላም ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚፈጠሩ ግጭቶችን ጥበብ በተሞላበት መንገድ መፍታት ይገባዋል፡፡በክልሉ የተጀመረውን ለውጥ ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ግለሰቦችና ቡድኖችን በጋራ መታገል እንደሚገባም አፈጉባኤው አሳስበዋል፡፡የ2011 ዓ.ም በጀት አመት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፃፀም በክልሉ ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የቀረበ ሲሆን፤ አሁን ያለውን የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ህብረተሰቡን ያሳተፉ ስራዎች ተሰርተዋል ተብሏል፡፡አቶ ኡሞድ አያይዘውም የክልሉን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት በተደረገው ጥረትም በኤርትራ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ክልሉ መግባታቸውን አውስተዋል፡፡ምክር ቤቱ በሚኖረው የሁለት ቀናት ስብሰባ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት የ2011 እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፤ የ2012 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት እንዲሁም ሌሎች አዋጆችንና ሹመቶችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡በአረንጓዴ አሻራ ዘመቻው በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በሚደረገው እንቅስቃሴ የምክር ቤት አባላት ህዝቡን በማስተባበርና አርአያ በመሆ እንዲሳተፉም ተጠይቋል። የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት በላከልን መረጃ መሰረት።
https://waltainfo.com/am/31263/
155
5ፖለቲካ
የ2011 በጀት ዓመት የውጭ ዲሎማሲያዊ ተግባራት ስኬታማ እንደነበሩ ተገለጸ
ፖለቲካ
July 26, 2019
Unknown
በ2011 በጀት ዓመት የተከናወኑ የውጭ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራት ስኬታማ እንደነበሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ የሚኒስቴሩን የ2011 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም አስመልክተው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ የትኩረት አቅጣጫ በሆኑት በኢኮኖሚ እና ዜጋ መር ዲፕሎማሲ፣ የአሜሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያ አውስትራሊያ ዓለምአቀፍ ተቋማት እንዲሁም የሚኒሰቴሩ አዲስ የሰው ኃይል ስምሪት አንፃር ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡   የኢትዮ ኤርትራ የንግድ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የንግድ ስምምነቶች እየተዘጋጁ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልጸዋል፡፡ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ልውውጥ ህጋዊ ማድረጉ በሁለቱ ሀገራት መካከል አሁን ላይ የታየውን ሰላማዊ ግንኙነት የሚያጠናክርና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ይሆናልም ነው ያሉት፡፡ኢትዮጵያ ባለፈው በጀት ዓመት ከጅቡቲ፣ ኬንያና ሌሎች የቀጠናው ሀገራት ጋር በቀጠናው ሰላምና በኢኮኖሚው መስክ ዙሪያም ሰፊ ስራ ማከናወኗን ገልጸዋል።በሱዳን ተፈጥሮ የነበረው ችግር ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለስ ኢትዮጵያ የበኩሏን ድርሻ መወጣቷንም አስታውሰዋል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አክሊሉ ሃይለሚካኤል በበኩላቸው ባሳለፍነው በጀት ዓመት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና ቆንስላ ጉዳዮች ዙሪያ ከእቅድ በላይ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡በበጀት ዓመቱ 168 ቢዝነስ ፎረሞች ተዘጋጅተው 1 ሺህ 150 ኩባንያዎች ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው፣ 225 ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ጠቁመዋል፡፡የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ከውጭ ባለሃብቶች ጋር በሽርክና እንዲሰሩ ለማድረግ በተከናወነው ተግባርም 67 ትስስሮች መፈጠራቸውን ጠቅሰዋል።ያሳለፍነው በጀት ዓመት በተለያዩ ሀገራት በእስር ላይ የነበሩ ከ27 ሺህ በላይ ዜጎች ከእስር ተፈተው ወደ ሀገራቸው የተመለሱበት እንደነበርም ገልጸዋል። በተጨማሪም በውጭ ሀገራት የነበሩና የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው 112 ሺህ 615 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ብለዋል፡፡ አሁንም ከ4 ሺህ በላይ ዜች በተመሳሳይ ሆኔታ በተለያዩ የውጭ ሀገራት በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ለማስመለስ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡የአህጉራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ማርቆስ ተክሌ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የገቢ አጋር እንደሆኑ የሚገለጽላቸው  የአሜሪካ፣ አውሮፓ እና እስያ አህጉራትና አገራትን ጨምሮ አለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ያለውን የለውጥ ሂደት እንደሚደግፉ የማስገንዘብ ሥራ ተከናውኖ አመርቂ ውጤቶች ተገኝተውበታል፡፡ አገራቱ ለውጡ ተቋማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ጠንካራ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ታውቋል፡፡    
https://waltainfo.com/am/31264/
269
5ፖለቲካ
አቶ አገኘሁ ተሻገር የሰላም ግንባታና የሕዝብ ደህንነት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ
ፖለቲካ
July 25, 2019
Unknown
አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ የአቶ አገኘሁ ተሻገርን የክልሉ የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ሃላፋነት ሹመትን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።አቶ አገኘሁ ላለፉት 20 ዓመታት በክልሉ በልዩ ልዩ የኃላፊነት ቦታዎች መስራታቸው ተገልጿል፡ከሰላምና ጸጥታ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ልምድ ያላቸው በመሆኑ ለወቅቱ የክልሉ የሰላምና ደኅንነት ሁኔታ መረጋጋት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም አስተያየት ተሰጥቷል፡፡ዘገባው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31259/
67
5ፖለቲካ
የአማራ ክልል ምክር ቤት የ230 ዳኞችን ሹመት አጸደቀ
ፖለቲካ
July 25, 2019
Unknown
የአማራ ክልል ምክር ቤት የ230 ዳኞችን ሹመት አጸደቀየአማራ ክልል ምክር ቤት በተለያዩ ደረጃዎች የሚመደቡ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፤ የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸውን ደግሞ ከሥራ አሰናብቷል፡፡የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በአራተኛ ቀን ውሎው ከሰዓት በፊት ከተመለከታቸው ጉዳዮች ውስጥ የዳኞች ሹመት ይገኝበታል፡፡በዕጩነት የቀረቡት ዳኞች በሥነ ምግባራቸው ጥሩ ስለመሆናቸው አስተያዬት የተሰጠባቸው፣ በመመልመያ መስፈርቱ ተወዳድረው የተመረጡ እና የትምህርት ደረጃውንም ያሟሉ ናቸው ተብሏል፡፡በዚህም መሰረት 10 ዳኞች ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት፣ ሁለት ዳኞች ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትነት፣ 18 ዳኞች ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኝነት፣ 200 ዳኞች ለወረዳ ፍርድ ቤት ዳኝነት ተሹመዋል፡፡የሁሉም ዳኞች ሹመት በሙሉ ድምጽ ነው የጸደቀው፡፡ምክር ቤቱ አምስት ዳኞችን በስነ ምግባር ጉድለት ከሥራ አሰናብቷል ሲልየዘገበው የአማራ መገናኛ ብዙሀን ነው።
https://waltainfo.com/am/31260/
111
5ፖለቲካ
ሃምሌ 22 ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር 54 ሚሊየን ብር ተመድቧል
ሀገር አቀፍ ዜና
July 25, 2019
Unknown
በዘንድሮ በጀት ዓመት ከ4 ቢሊዮን ችግኝ በላይ ለመትከል እቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡ የዚህ አካል የሆነውና ሃምሌ 22 ቀን የሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አሰፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ሃምሌ 22 ቀን በአንድ ጀንበር 200 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል የተያዘው እቀድ የተሳካ እንዲሆን 54 ሚሊየን ብር መመደቡም ተገልጿል፡፡ለዚህም 46 ሚሊየኑ ለክልሎች 8 ሚሊየኑ ደግሞ ለፌደራል ከተሞች እንደተመደበ የብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡በእለቱም ያጋጥማሉ ተብለው የታሰቡ ችግሮችን ቀድሞ በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫም እንደተቀመጠላቸው የተነገረ ሲሆን÷ ይህም የተሳካ እንዲሆን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየተሰራ ይገኛል፡፡ከማለዳው 12 ሰአት እሰከ ምሽት 12 በሚካሄደው በዚህ መርሃግብር ላይ እያንዳንዱ ዜጋም ሆነ ተቋማት በተዘጋጀለቸው ቦታ በመገኝት በባለሞያዎች በመታገዝ የችግኝ ተከላውን ማከናወን እንደሚገባቸውም ተገልጿል፡፡አሁን ላይ በሀገሪቱ ያለው የደን ሽፋን 15 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱንና ይህንን ለማሻሻል የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀከትን ለማሳካት ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32585/
126
0ሀገር አቀፍ ዜና
ለህግ የበላይነት መከበር ሁሉም በጋራ መስራት እንዳለበት ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 25, 2019
Unknown
የፍትህ እኩልነትን ለማረጋገጥ የህግ የበላይነትን የማክበርና የማስከብር ሃላፊነትን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በጋራ እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡መሰረቱን ህዝብ ያደረገ የፍትህ ስርዓት ለማፈን የፌዴራል የፍትህና ህግ መምሪያ እና ስልጠና ተቋም ከሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡በሀገር አቀፍ ለውጡን የሚደግፍ እና የህዝብን እኩልነት የሚያረጋግጥ የፍትህ ስርዓት እንዲኖር የዘርፉ ተቋማት የህግ የበላይነትን ዋና ዓላማቸዉ አድርገው መስራትም አለባቸው ብሏል የስልጠና ተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር፡፡ስልጠናው የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤህግ ከሆላንዱ በህግላት ትኩረቱን አድርጎ ከሚሰራው "ዘ ሄግ ኢንስቲቱዩት ፎር ኢኖቬሽን ኦፍ ሎው " ከተባለ ድርጅት ጋራ በመተባበር የተሰጠው ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/32586/
79
0ሀገር አቀፍ ዜና