headline
stringlengths 2
1.42k
| category
stringclasses 6
values | date
stringlengths 9
35
| views
stringlengths 1
7
| article
stringlengths 63
36.2k
| link
stringlengths 28
740
| word_len
int64 16
6.74k
| label
class label 6
classes |
---|---|---|---|---|---|---|---|
ኮሚሽኑ የአርቲስት ሃጫሉን ግድያን ተከትሎ የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሪፖርት ይፋ አደረገ | ሀገር አቀፍ ዜና | January 1, 2021 | Unknown | የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ኮሚሽን የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል 40 ከተሞች የተፈፀመውን የሠብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ያዘጋጀውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል።ኮሚሽነሩ ዶክተር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ ሌሎች ባለሙያዎች ሪፖርቱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጡ ነው።በከተሞቹ በተደረገው ዳሰሳ 30 ሙያተኞች መሳተፋቸው ተገልጿል።የቀረበው ሪፖርት ከአርቲስቱ ግድያ ቀን ጀምሮ እስከ ሶስት ቀን የነበረውን ሁኔታ የዳሰሰ ነው።በዳሰሳው ጉዳት ከደረሰባቸው የመንግስት አካላት ለ328 ሰዎች ቃለ መጠይቅ ተደርጓል፤ የፎቶግራፍ፣ የድምፅና ሌሎችም መረጃዎችና ማስረጃዎችም ተካተዋል።በዚህም 123 ሰዎች ተገድለዋል 520 ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%ae%e1%88%9a%e1%88%bd%e1%8a%91-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%ad%e1%89%b2%e1%88%b5%e1%89%b5-%e1%88%83%e1%8c%ab%e1%88%89%e1%8a%95-%e1%8c%8d%e1%8b%b5%e1%8b%ab%e1%8a%95-%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%89%b5/ | 76 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ለእድለኞች ሽልማት አበረከተ | ቢዝነስ | January 1, 2021 | Unknown | የአሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ 2ኛውን ዙር “የይመንዝሩ፤ ይቀበሉ፤ ይሸለሙ” መርኃግብር ለዕድለኞች የሽልማት አሰጣጥ ሥነሥርዓት አከናውኗል፡፡በመርኃግብሩ ዘጠኝ የሚጠጉ ሽልማቶች ለዕድለኞች ተበርክቷል፡፡የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ተፈሪ መኮንን ደንበኞች ከተለያዩ ሀገራ የሚላክላቸውን የውጭ ምንዛሬ በባንኩ ስመነዝሩ የማበረታቻ ሽልማቶች እንደምበረከትላቸው ገልጸው፣ በቀጣይ በተለያዩ ቅርንጫፎች የሽልማት ሥነሥርዓቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡በሽልማቱ የ1ኛ እና 3ኛ ዕጣ አሸናፊ አንድ ሰው መሆኑ መርኃግብሩን ልዩ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል፡፡ባንኩ በቀጣይ ከይመንዝሩ ይቀበሉ፤ ይሸለሙ መርኃግብር በተጨማሪ ለህፃናት፣ ለወጣቶች እና ለአረጋዊያን የሚሆኑ የቁጠባ መርኃግብሮችን በመዘርጋት እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡በአጭር ጊዜ ውስጥ የ3ኛው ዙር ይመንዝሩ፤ ይቀበሉ፤ ይሸለሙ መርኃግብር እንደምጀመርም ተጠቁሟል፡፡በብርሃኑ አበራ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a6%e1%88%ae%e1%88%9a%e1%8b%ab-%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%89%b0%e1%88%ad%e1%8a%93%e1%88%bd%e1%8a%93%e1%88%8d-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ad-%e1%88%88%e1%8a%a5%e1%8b%b5%e1%88%88%e1%8a%9e/ | 81 | 3ቢዝነስ
|
የአውሮፓ ሕብረትና ዩናይትድ ኪንግደም በአዲሱ ዓመት በይፋ ተለያዩ | ዓለም አቀፍ ዜና | January 1, 2021 | Unknown | የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መግባቱን ተከትሎ ዩናይትድ ኪንግደም ከአውሮፓ ሕብረት ጋር የነበራትን ግንኙነት በይፋ አቋርጣለች።ዩናይትድ ኪንግድም (ዩኬ)፤ ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ በጂኤምቲ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 5 ሰዓት [በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ደግሞ ከሌሊቱ 8 ሰዓት] ጀምሮ የአውሮፓ ሕብረት ሕግጋትን መከተል አቁማለች።ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዩኬ “ነፃነቷን በእጇ” ይዛለች ሲሉ ተደምጠዋል።አሁን ነገሮችን “በተለይ መልኩና በተሻቀለ ሁኔታ” ማከናወን እንችላለን ሲሉም አክለዋል።የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮ ዩናይትድ ኪንግደም “የሕብረቱ አጋር እና ጓደኛ ሆና ትቀጥላለች” ብለዋል።ዩናይትድ ኪንግደም ሕዝብ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ያለን ግንኙነት ይብቃን ሲል በሕዝበ ውሳኔ ፍላጎቱን ያሳወቀው በፈረንጆቹ 2016 ነበር።ነገር ግን ‘ብሬግዚት’ በተሰኘ ቅጥያ ስሙ የሚታወቀው ይህ ሂደት ከሦስት ዓመታት ውይይት በኋላ ተግባራዊ ሆኗል።ላለፉት 11 ወራት ሁለቱ አካላት እየተወያዩ ባሉበት ወቅት ዩኬ ለሕብረቱ የንግድ ሕግጋት ተገዢ መሆን ነበረባት።አሁን ዩናይትድ ኪንግደም 27 አገራት ካሉበት የአውሮፓ ሕብረት ሙሉ በሙሉ መውጣቷን ቢቢሲ ዘግቧል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8b%8d%e1%88%ae%e1%8d%93-%e1%88%95%e1%89%a5%e1%88%a8%e1%89%b5%e1%8a%93-%e1%8b%a9%e1%8a%93%e1%8b%ad%e1%89%b5%e1%8b%b5-%e1%8a%aa%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%8b%b0%e1%88%9d-%e1%89%a0/ | 124 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ከሆኑት ሬሚ ማሬሾ ጋር ተወያዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | January 1, 2021 | Unknown | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ከሆኑት ሬሚ ማሬሾ ጋር ተወያይተዋል፡፡ውይይቱ በአዲስ አበባ በፈረንሳይ ተቋራጮች የሚሰሩ ሜጋ ፕሮጀክችቶች አፈጻጸምን የተመለከተ እንደነበር ታውቋል፡፡በተጨማሪም በሁለቱ አገራት መካከል የቆየውን የሁለትዮሽ ትብብር እና ወዳጅነት አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት መደረጉን ከምክትል ከንቲባዋ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለከታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%88%9d-%e1%8a%a8%e1%8a%95%e1%89%b2%e1%89%a3-%e1%8a%a0%e1%8b%b3%e1%8a%90%e1%89%bd-%e1%8a%a0%e1%89%a4%e1%89%a4-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8d%88%e1%88%a8/ | 51 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንጋፋ አትሌቶች የገንዘብ ስጦታ ተበረከተ | ሀገር አቀፍ ዜና | January 1, 2021 | Unknown | የአንጋፋ አትሌቶች ማህበር የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ መቶ አንጋፋ አትሌቶች የ300 ሺህ ብር ስጦታ ዛሬ አበርክቷል፡፡ለአንጋፋ አትሌቶቹ ለእያንዳንዳቸው የ3 ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታውን የአንጋፋ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ኮማንደር ጌጤ ዋሚ አበርክተዋል፡፡በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን ተወካይ አቶ አሰፋ በቀለና የአዲስ አበባ አትሌትክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ቢኒያም ምሩፅ የተገኙ ሲሆን፣ ይህ ድጋፍ በቀጣይ በቋሚነት እንዲቀጥል እየሰራን ነው ብለዋል።ኮማንደር ጌጤ በዚሁ ወቅት እንዲህ ዓይነቱ የመደጋገፍ ባህል ወደፊትም መለመድ እንዳለበት መናገራቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8c%88%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%8b%93%e1%88%8d%e1%8a%95-%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%8a%95%e1%8b%ab%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%88%9b%e1%8b%b5%e1%88%a8%e1%8c%8d-%e1%88%88%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8c%8b/ | 75 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኮሚሽኑ ለመተከል ተፈናቃዮች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ | ሀገር አቀፍ ዜና | January 1, 2021 | Unknown | የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ለመተከል ተፈናቃዮች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡በኮሚሽኑ የአሶሳ አስተባባሪ ቪክቶሪያ ኮፓ ድጋፉን ዛሬ በአሶሳ ከተማ ለክልሉ አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን አስረክበዋል፡፡አስተባባሪዋ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ኮሚሽኑ የመተከልን ተፈናቃዮች ለመደገፍ ከክልሉ ጋር በመቀናጀት እየሠራ ነው፡፡ከድጋፉ መካከል 13 ሺህ ብርድ ልብሶች እንዲሁም የአልጋ አጎበሮች፣ ምንጣፎች፣ የተለያዩ የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶች ይገኙበታል፡፡ይህም ከአራት ሺህ በላይ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስተባባሪዋ አስረድተዋል፡፡ድጋፉን የተረከቡት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ታሲሳ በበኩላቸው፤ በመተከል ዞን የተፈናቀሉትን ወገኖቻችንን በመንግስት አቅም ብቻ ለመደገፍ አዳጋች በመሆኑ መንግሥት ኀብረተሰቡን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ረጂ ድርጅቶችም እንዲያግዙ ጥሪ መቅረቡን አስታውሰው፣ ጥሪውን ተቀብሎ ኮሚሽኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሰጠው ምላሽ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ድጋፉ በዞኑ በርካታ ተፈናቃዮች በሚገኙበት ቡለን እና ድባጤ ወረዳዎች በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚደርስ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%ae%e1%88%9a%e1%88%bd%e1%8a%91-%e1%88%88%e1%88%98%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8d-%e1%89%b0%e1%8d%88%e1%8a%93%e1%89%83%e1%8b%ae%e1%89%bd-%e1%8a%a830-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%ae%e1%8a%95-%e1%89%a5/ | 126 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በዳርፉር የተሰጠውን የሰላም ማስከበር ተግባር አጠናቀቀ | ዓለም አቀፍ ዜና | January 1, 2021 | Unknown | በሱዳን ዳርፉር በእ.አ.አ 2003 የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ወደ አካባቢው የገባው የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ማስከበር ተልእኮ ከ13 ዓመታት አገልግሎት በኋላ በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትላንት ባወጣው መግለጫ የሰላም አስከባሪ ተልእኮው መጠናቀቁን ተከትሎ የሱዳን መንግሥት በክልሉ ለሚገኙ ዜጎች ደህንነት እና አገልግሎት የመስጠት ሓላፊነቱን ይወስዳል ብሏል፡፡በሥልጣን ላይ ያለው ጊዜያዊ የሱዳን መንግሥትም በዴሞክራሲያዊ መንገድ ምርጫ በማድረግ በዳርፉር ያለውን ችግር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ተልእኮው እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ 1 ቀን 2021 ጀምሮ የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ፣ ለሠራተኞች እና እዚያ ለሚገኙ ንብረቱ ደህንነት ትኩረት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ቀስ በቀስ ለቅቆ ለመውጣት የስድስት ወራት ጊዜ እንዲሰጠው 15 አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አጽድቀውታል፡፡በ2003 በሱዳን ምዕራባዊው ክፍል በመንግሥት ወታደሮች እና በአማፅያን ቡድኖች መካከል የተቀሰቀሰውን የከፋ ግጭት ለማስቆም በ2007 የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይል በዳርፉር መሰማራቱ የሚታወስ ነው፡፡በዳርፉር የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልእኮ ስር በአሁኑ ወቅት ከ7ሺህ 500 በላይ ወታደሮች፣ ፖሊሶች፣ ሲቪል ሠራተኞች በአካባቢው ተሰማርተው እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡(ምንጭ፡-አልጀዚራ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%98%e1%8b%b5-%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%89%b0%e1%88%8d%e1%8b%95%e1%8a%ae-%e1%89%a0%e1%8b%b3%e1%88%ad%e1%8d%89/ | 152 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አንቀጽ 44 ላይ የነበራትን ተዓቅቦ አነሳች | ሀገር አቀፍ ዜና | January 1, 2021 | Unknown | ኢትዮጵያ ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠት (Extradition) የሚደነግገው የተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አንቀጽ 44 ላይ የነበራትን ተዓቅቦ አነሳች።የፌደራል ሥነ-ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን አንቀጽ 44 ላይ ያላትን ተዓቅቦ አንስታለች ብሏል።ኢትዮጵያ የኮንቬንሽኑን አንቀጽ 44 አስመልክቶ ተዓቅቦ እንዳላት የኮንቬንሽኑ ምዕራፍ ሦስት ውስጥ የተመለከተውን የሙስና ወንጀልን ወንጀል አድርጎ መደንገግና ምዕራፍ አራት ዓለም አቀፍ ትብብርን አስመልክቶ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2010 አስከ 2015 ባለው ጊዜ የነበራትን አፈጻጸም ለገምጋሚ አገራት አቅርባ ማስገምገሟን ኮሚሽኑ ገልጿል።የአፈጻጸም ግምገማን ተከትሎ ኢትዮጵያ እንድታስተካክል ተሰጥተዋት ከነበሩ ምክረ ሃሳቦች አንዱ ከላይ በተጠቀሰው የኮንቬንሽኑ አንቀጽ ላይ ያላት ተዓቅቦ እንደነበር ተመልክቷል።በዚህ ግምገማ መሠረት ኢትዮጵያ አንቀጽ 44 ላይ የነበራትን ተዓቅቦ ያነሳች ሲሆን የፕሮቶኮሉን ድንጋጌዎች በሙሉ በማክበር ግዴታዎቿን እንደምትወጣ አረጋግጣለች።አንቀጽ 44 ላይ ያላት ተዓቅቦ መነሳቱን መቀመጫውን ኦስትሪያ ቬና ላደረገው የተባበሩት መንግሥታት የአደገኛ ዕፅ እና ወንጀል መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀችም ኢዜአ ዘግቧል:: | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%89%a3%e1%89%a0%e1%88%a9%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%a5%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8d%80%e1%88%a8-%e1%88%99/ | 126 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት ተመሰረተ | ሀገር አቀፍ ዜና | January 1, 2021 | Unknown | በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት ተመሰረተ። የምክር ቤቱ የምስረታ ጉባኤ ላይ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን የወከሉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።ዘርፉ የበቃና በነጻነት የተደራጀ፣ በሃሳብ ልዕልና የሚያምን፣ አገራዊ ክብርን የሚያስጠብቅ፣ በራሱ የሚተማመን አምራች ዜጋን በማፍራት ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ጠቁመዋል።ድርጅቶቹ ለትርፍ ያልተቋቋሙ እንደመሆናቸው መጠን ለማህበረሰቡ የሚጠቅም ስራ መስራታቸውን የሚያረጋግጡበት እራሱን የቻለ ስርአት ማበጀት እንደሚገባቸውም ነው የተናገሩት።በቅርቡ የተሻሻለው የሲቪል ማኅበራት አዋጅም ምክር ቤቱ እንዲመሰረት ጉልህ ሚና መጫወቱንም ገልጸዋል።የምክር ቤቱ መመስረት ዘርፉ በጠንካራ ተቋም የመወከል እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።ድርጅቶቹ አሰራራቸውን ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለበት እንዲሆን በማድረግ ምክር ቤቱ የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናል ነው ያሉት።ምክር ቤቱ የሚያወጣቸውን የስነ-ምግባር ደንቦች በሁሉም የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ላይ ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑንም ጠቁመዋል።ምክር ቤቱ ማህበራቱ በስነ-ምግባር የታነጹ፣ የማህበረሰብ ጥቅም የሚሰሩ፣ ከሙስናና ከብልሹ አሰራር የፀዱ፣ ህብረተሰቡን በነጻነት የሚያገለግሉና እና ተቀባይነት ያላቸው እንዲሆኑም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%88%b2%e1%89%aa%e1%88%8d-%e1%88%9b%e1%8a%85%e1%89%a0%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%8b%b5%e1%88%ad%e1%8c%85%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%88%9d/ | 123 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሙያተኞች ድርጅት ለዩኒቨርሲቲዎች አቅም ግንባታ 91 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown | በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሙያተኞች ድርጅት ለአምስት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች አቅም ግንባታ የሚውል 91 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።ድጋፉን ያደረገው “ኢትዮጵያን ኖርዌጃን ፕሮፌሽናል ኦርጋናይዜሽን” የተሰኘ ድርጅት ነው።የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሳውዝ ኖርዌይ የኮምፒውተር ሳይንስ መምህር የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሸጋው አናጋው ድጋፉን በሚመለከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።ድርጅቱ ድጋፉን ያደረገው የኖርዌይ የልማት ተራድኦ ድርጅት ያዘጋጀውን ውድድር በማሸነፉ ያገኘውን ገንዘብ መሆኑንም ነው የተናገሩት።የኖርዌይ የተራድኦ ድርጅቱ በመላው ዓለም ለሚገኙ ታዳጊ አገራት የ1 ነጥብ 1 ቢሊየን የኖርዌይ ገንዘብ (ክሮነር) የሚያሸልም ውድድር አውጥቶ እንደነበር ነው ያስታወሱት።በውድድሩ ከተካፈሉት 199 አገራት መካከል ስልሳ የሚሆኑት ሽልማት ማግኘታቸውን ጠቅሰው፤ኢትዮጵያን ወክሎ በወድድሩ የተካፈለው ‘በኖሮዌይ የኢትዮጵያ ሙያተኞች ድርጅት’ ከተሸላሚዎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።ድርጅቱ በውድድሩ 20 ሚሊየን ክሮነር ወይም 91 ሚሊየን ብር መሸለሙን ነው የገለጹት።በሽልማቱ ያገኘውን ገንዘብ ለጎንደር፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ ደብረማርቆስና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች የአቅም ግንባታ ስራ እንዲውል ድጋፍ ማድረጉንም ተባባሪ ፕሮፌሰር ሸጋው አንጋው የገለጹት። ድጋፉም በ6 ዓመት ፕሮግራም ተግባራዊ እንደሚሆን ነው የተናገሩት።ልዩ ፍላጎት፣ሜዲካል ቴክኖሎጂ (ኢ ሄልዝ) እና ከኮምፒውተር ጋር የተገኛኙ የትምህርት ክፍሎች ደግሞ በድጋፉ ትኩረት የሚሰጥባቸው ዘርፎች መሆናቸውንም ገልጸዋል።በተጨማሪ ድርጅቱ 45 ለሚሆኑ የማስተርስ ተማሪዎች እና 15 የዶክትሬት ተማሪዎች በኖርዌይ የትምህርት እድል እንዲያገኙ የማመቻቸት ስራ እንደሚያከናውም ተናግረዋል።በኖርዌይ ያሉ ዩኒቨርስቲዎችና ምሁራን ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ እንደሚደረግም ነው ያነሱት።ድጋፉ በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃን ያካተተ መሆኑንም ተናግረዋል።በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው ሰላም፣ ልማትና እድገት የሚያደርጉትን አወንታዊ አስተዋፆ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8a%96%e1%88%ad%e1%8b%8c%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8c%88%e1%8a%98%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%88%99%e1%8b%ab%e1%89%b0%e1%8a%9e%e1%89%bd/ | 209 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የእናቶችና የህጻናት ጤናና ስርዓተ ምግብ ሁኔታን ለማሻሻል ያለመ የንቅናቄ መድረክ በጋምቤላ ተካሄደ | ሀገር አቀፍ ዜና | January 1, 2021 | Unknown | የእናቶች፣ የጨቅላ ህጻናትና የህጻናት ጤናና ስርዓተ ምግብ ሁኔታን ለማሻሻል ያለመ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ “የተጠናከረ የጋራ ጥረት ለተመጣጣኝ የጤና ልማት!” በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡በመድረኩ የተገኙት የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ኡሞድ ኡጅሉ እንደተናገሩት ንቅናቄው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈ ነው፡፡በመሆኑም በእናቶች፣ ጨቅላ ህጻናት እና ህጻናት ጤናና ስርዓተ ምግብ እንዲሁም በኤችይቪ ኤድስና ኮቪድ-19 መከላከል ዙሪያ በክልሉ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ያግዛል፡፡የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት በእናቶች፣ በጨቅላ ህጻናትና ህጻናት ጤናና ስርዓተ ምግብ ዘርፍ ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በተሰራው ስራ እንደሃገር በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ይሁንና አሁንም በዘርፉ ሀገሪቱ ያልተሻገረቻቸው በርካታ ችግሮች በመኖራቸው እነዚህ በቀጣይ 5 እና 10 ዓመት የጤናው ዘርፍ ስትራቴጂክ ዕቅድ ተካትተዋል፡፡ለአብነትም በጋምቤላ ክልል በ2012 ዓ.ም የቅድመ ወሊድ ክትትል 4 ጊዜ እና ከዚያ በላይ ያደረጉ እናቶች ቁጥር 23 በመቶ ብቻ መሆኑን ዶ/ር ሊያ አንስተዋል፡፡በሰለጠነ ባለሙያ የወለዱ እናቶች ሽፋን 40 በመቶ ላይ ሲሆን የህጻናት ክትባትም መሻሻል ከማሳየቱ በቀር አሁንም ዝቅተኛ ሽፋን እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡መቀንጨርን ከመቀነስ አኳያም በክልሉ የሚያበረታታ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰው ችግሩ አሁንም የተቀናጀ ጥረትን የሚጠይቅ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ በበኩላቸው በአገር ደረጃ የእናቶች፣ የጨቅላ ህጻናትና የህጻናት የጤና ችግሮች ሳይፈቱ የሚደረግ የልማት ጥረት አይሳካም ብለዋል፡፡የንቅናቄ መድረኩ ተመጣጣኝ የጤና ልማትን በክልሉ ለማረጋገጥ የሁሉም ባለድርሻ አካላትን የተጠናከረ የጋራ ጥረትን በማስተባበር በችግሩ አሳሳቢነት፣ መንስኤዎችና መፍትሄዎች ላይ ለመምከር ያለመ ነው፡፡የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን ከጤና ሚኒስቴር እና ከጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መድረክ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የአገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች መሳተፋቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a5%e1%8a%93%e1%89%b6%e1%89%bd%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8c%bb%e1%8a%93%e1%89%b5-%e1%8c%a4%e1%8a%93%e1%8a%93-%e1%88%b5%e1%88%ad%e1%8b%93%e1%89%b0-%e1%88%9d%e1%8c%8d%e1%89%a5/ | 235 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ወጣቱ በምክክር እና በሙግት የሚያምን ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ | ሀገር አቀፍ ዜና | January 1, 2021 | Unknown | የሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ከፍተኛውን ሚና የሚጫወተው ወጣቱ እንደመሆኑ ይህ የህበረተሰብ ክፍል ከትችት እና ከፅንፈኝነት ይልቅ በምክክር እና በሙግት የሚያምን ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ፡፡የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በየሶስት ወሩ የሚካሄድ ወጣቱን ያማከለ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡በዚህም በሀገሪቱ በሚገኙ 1 ሺህ 100 ከተሞች የሚከናወን ሲሆን በመጀመሪያው ዙር 5 ሚሊየን ወጣቶች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡በመጀመሪያ ዙር “የሀገረ መንግስት ግንባታ እና የወጣቶች ሚና” በሚል ርዕስ ምክክር ይካሄዳል፡፡መድረኩ ነፃና የትኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ የሚስተናገድበት እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡ይህ ቀጣይነት እንዳለው የተገለፀ የምክክር እና የሙግት መድረክ በምክንያት ላይ የተመሰረተ፣ በጉዳዮች ላይ ጥልቅ ዕውቀት ያለውን ወጣት ከማፍራት ባሻገር ሰላም የሰፈነባት፣ የተረጋጋች፣ የዴሞክራሲ ባህሏ ያደገና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡ወጣት ምሁራን ይሳተፋበታል የተባለው የመጀመሪያው ዙር የምክክር መድረክ የፊታችን ቅዳሜ በ4 የክልል ከተሞች ይጀመራል፡፡(በሳሙኤል ሃጎስ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%88%e1%8c%a3%e1%89%b1-%e1%89%a0%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%8a%ad%e1%88%ad-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%88%99%e1%8c%8d%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%88%9d%e1%8a%95-%e1%88%8a%e1%88%86/ | 118 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የምግብ፣ መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ዘርፍ 1.2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማስገኘት መታቀዱ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown | የምግብ፣ የመጠጥ እና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዘርፍ በ10 ዓመታት መሪ ዕቅድ 1.2 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት መታቀዱ ተገለጸ።ኢንስቲትዩቱ የውጭ ንግዱን ለማበረታታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የንቅናቄ መድረክ አዘጋጅቷል።ከኢንስቲትዩቱ ፍቃድ ወስደው የሚሰሩ 1 ሺ 390 በመጠጥ፣ ምግብ፣ አትክልትና የፍራፍሬ፣ በፋርማሲዩቲካል፣ በስኳር እና ጣፋጭ በቅባት እህሎች ማቀነባበር የተሰማሩ አምራች ድርጅቶች የሚገኙ ሲሆን፣ 65 የሚሆኑት አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛሉ ተብሏል።ከዘርፉ በ2012 በጀት አመት 38.1 ሚሊየን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ በ2013 ዓ.ም በአምስት ወራት ውስጥ 28.1 ሚሊየን ዶላር መገኘቱ ተገልጿል ።በአስር አመታት መሪ ዕቅድ ሊገኝ የታቀደው የ1.2 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አምራች እንዱስትሪውን በማበረታታት፣ የግብርና ማቀነባበሪያ የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪዎችን ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ፣ በቀጣይ አመታት የኃይል መቆራረጥ በማስቀረት እና የስኳር ምርትን በማሳደግ የሀገር ውስጥ ፍጆታን በማሟላት እንዲሁም ትርፍ ምርትን ወደ ውጭ በመላክ ለማግኘት የታሰበ እንደሆነ ተነግሯል።ኢትዮጵያ 80 በመቶ የመድኃኒት እና ፋርማሲዩቲካል ፍላጎቷን ከውጭ የምታስገባ በመሆኑ ይህንን ለመቀየር በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና ለዘርፉ በቂሊንጦ ራሱን የቻለ ኢንዱስትሪ ፖርክ መገንባቱ ተገልጿል።(በምንይሉ ደስይበለው) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%8c%8d%e1%89%a5%e1%8d%a3-%e1%88%98%e1%8c%a0%e1%8c%a5%e1%8a%93-%e1%8d%8b%e1%88%ad%e1%88%9b%e1%88%b2%e1%8b%a9%e1%89%b2%e1%8a%ab%e1%88%8d-%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%8b%b1%e1%88%b5/ | 151 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በትራንስፖርት ዘርፍ 30 በመቶ ቅድመ ክፍያ የተሽከርካሪ ግዢ መቅረቡ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown | በትራንስፖርት ዘርፉ የሚታየውን የአቅርቦት ችግር ለማገዝ በ30 በመቶ ቅድመ ክፍያ የተሽከርካሪ ግዢ መቅረቡን ሔሎ መኪና አስታወቀ።በትራንስፖርት ዘርፉ የሚታየውን የአቅርቦትና የግዢ ችግር ለመቅረፍ ሔሎ መኪና ከደቡብ ግሎባል ባንክ ጋር በመሆን ህብረተሰቡ በቀላሉ የመኪና ባለቤት የሚሆንበትን አማራጭ መፍጠሩን የድርጅቱ መሥራች አቶ ዳንኤል ዮሐንስ ገልጸዋል።ለተጠቃሚዎች የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች ያላገለገሉ አዳዲስና ዜሮ ዜሮ መኪናዎች መሆናቸውን ተናግረው ይህም መንግሥት የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ አኳያ ያስቀመጠውን የአካባቢ ጥበቃ መርህ የተከተለ ነው ብለዋል።ከደቡብ ግሎባል ባንክ ጋር በመሆን ተጠቃሚዎቹ በ30 በመቶ ቅድመ ክፍያ ከፍለው ቀሪውን 70 በመቶ ክፍያ በሰባት አመታት ውስጥ የሚከፍሉበት ስርዓት መዘጋጀቱንም ነው የገለጹት።የደቡብ ግሎባል ባንክ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር ወይዘሮ እንዳልሽ ወልደሚካኤል በበኩላቸው፣ ጉዳዩ አገራዊ አስተዋጽኦ ያለው የስራ ዐሳብ በመሆኑ ባንኩ ተቀብሎት ወደ ስራ መግባቱን አስታውቀዋል።ከቢዝነስ አጋርነት ባለፈ ማህበራዊ ሃላፊነትን መወጣትና በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ የሚታየውን ችግር የመቅረፍ አካል መሆኑንም ነው የገለጹት።በዚህም የተሽከርካሪዎቹ ባለቤት መሆን የሚፈልጉ የህብረተሰቡ ክፍሎች አስፈላጊ የሆኑ የዶክመንትና 30 በመቶ ቅድመ ክፍያውን ካሟሉ ብድሩን ያለ ምንም ውጣ ውረድ ማግኘት እንደሚቻል ተናግረዋል።ተሽከርካሪዎቹ ከግል ተጠቃሚነት ባለፈ በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አቅርቦቱ አጋዥ እንዲሆኑ በኮድ 3 እና ሁለት መዘጋጀታቸውም ተነግሯል። (ምንጭ ፡- ኢዜአ) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%88%ab%e1%8a%95%e1%88%b5%e1%8d%96%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%8d%8d-30-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%b6-%e1%89%85%e1%8b%b5%e1%88%98-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%8b%ab-%e1%8b%a8/ | 163 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የቦረናን እና የደቡብ ኦሞ ዞኖችን የሚያገናኘው መንገድ ከ2 ወር በኋላ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown | የቦረናን ዞን ከደቡብ ኦሞ ዞን የሚያገናኘው መንገድ ግንባታው ተጠናቆ ከሁለት ወር በኋላ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ፡፡የመንገዱ መገንባት የሁለቱን ዞኖች ብሎም የኦሮሚያ እና ደቡብ ክልል ህዝቦች በምጣኔ ሀብት፣ በንግድ እና በማህበራዊ ጉዳዮች ያሏቸውን ትስስሮች ለማጠናከር ይረዳልም ተብሏል፡፡በ2011 ዓ.ም የተጀመረው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ከቦረና ዞን ተልተሌ ከተማ እስከ ደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጂንካ ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን ለአካባቢው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እንደሚያስገኝም ይጠበቃል፡፡በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት አሰተባባሪ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የተመራው ልዑክ ፕሮጀክቱን የጎበኘ ሲሆን የተልተሌ ወረዳ በእርሻ የሚታወቅ አካባቢ መሆኑም ተመልክቷል።ይሁን እንጂ ለዘመናት የመንገድ መሠረተ ልማት ባለመኖሩ የአካባቢው አርሶአደሮች ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ለማቅረብ ረጅም መንገድ ለመጓዝ ይገደዱ እንደነበር ነው በጉብኝቱ ወቅት የተገለጸው።የመንገድ ፕሮጀክቱ 80 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ እየተገነባ ይገኛል።ግንባታው በሁለት ሎት ተከፍሎ እየተከናወነ ሲሆን በተያዘለት ጊዜና የጥራት ደረጃ እየተከናወነ አፈጻጸሙም 96 በመቶ ላይ መድረሱም ተጠቁሟል።የመንገዱን ወጭ የሚሸፍነው የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሲሆን የመንገዱ 10 ኪሎሜትር በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ውስጥ የሚገኝ ነው።መንገዱ የቱሪስት መዳረሻ የሆነውን የደቡብ ኦሞ ዞን ለሚጎበኙ ቱሪስቶች አማራጭ መንገድ በመሆን እንደሚያገለግልም ተነግሮለታል፡፡የመንገዱ መሰራት እንዳስደሰታቸው የጠቆሙት ዋልታ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የዘመናት ጥያቄያቸው እንደተመለሰላቸው ገልፀዋል።በሚልኪያስ አዱኛ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%a6%e1%88%a8%e1%8a%93%e1%8a%95-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8b%b0%e1%89%a1%e1%89%a5-%e1%8a%a6%e1%88%9e-%e1%8b%9e%e1%8a%96%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%8c%88/ | 176 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በንግድ ማስፋፊያ የስራ ዘርፍ ላይ ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown | የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ኮቪድ-19 በንግድ ማስፋፊያ የስራ ዘርፍ የጋረጠባቸው ፈተናዎች እና ያሉ ተስፋዎች ላይ ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር ውይይት እያደረገ ነው።የንግድ ስራን ውጤታማ ለማድረግ አንዱ የሆነው ንግድና ባዛር ሁነት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በመቋረጡ በኢትዮጵያ በዘርፉ ተዋናይ የሆኑ 700 ሁነት ፈጣሪ ድርጅቶች ስራቸውን አቁመው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ለስራአጥነት ተጋላጭ መሆናቸው ተገልጿል።በንግድ ስራ ማስፋፊያ ዘርፍ ያለው የማስተዋወቅ ተግባር በንግድና ባዛሮች ላይ በዘርፉ የእውቀት ውስንነት፣ ለንግድና ባዛር አመቺ የመሠረተ ልማት አለመኖር፣ ወጥ ህግና መመሪያ አለመኖር፣ ለድርጅቶች ማበረታቻ አለመኖር እና ሌሎችም ምክንያቶች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተዳምሮ ዘርፉን መጉዳቱና ለሀገሪቱ ማስገባት ያለበትን ገቢ ማሳጣቱ ተነግሯል።(በምንይሉ ደስይበለው) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%8b%b5-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8d%8b%e1%8d%8a%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%88%b5%e1%88%ab-%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%8d%8d-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8a%a8%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%8b%b5/ | 94 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ባለፉት ሁለት ዓመታት በሴት አርብቶ አደሮች ላይ በተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት መገኘቱ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown | ሴት አርብቶ አደሮቹ የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም እንዲኖራቸው ለማስቻል በተወሰዱ እርምጃዎች የተሻለ አቅም መፍጠር መቻላቸው ተገለጸ፡፡በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ የተመራው ልዑክ በጉጂ ዞን በሊበን ወረዳ ላይ ባደረገው ጉብኝት ሴት አርብቶ አደሮች ያሉበትን ደረጃ ተመልክቷል።አርብቶ አደሮቹ ከዚህ ቀደም ህይወታቸውን ለመምራት ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ይገደዱ እንደነበር ገልጸው፣ ይህ በህይወታቸው ላይ ለውጥ ለማምጣት እንዳላስቻላቸው አስታውሰዋል፡፡አሁን ላይ ግን የክልሉ መንግስት ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በፈጠረላቸው ዕድል ከሚኖሩበት አካባቢ ሳይርቁ የሚያስፈልጋቸውን የመኖ እና የውሃ አቅርቦት በማዘጋጀት ወደ ከብት አደልቦ መሸጥ እንዲገቡ መደረጋቸው ተመላክቷል።በቀበሌ ከሚደራጁ 40 ሰዎች 32ቱ ሴቶች እንዲሆኑ መደረጉንና ሴት አርብቶአደሮችም በተለያዩ ዙሮች የገንዘብ ብድር እንዲያገኙ በማመቻቸት ወደ ንግድ ስራ እንዲገቡ መደረጋቸውም ተገልጿል።በዚህም በየግላቸው ከ10 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ትርፍ ለማግኘት መቻላቸውን ሴት አርብቶ አደሮቹ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡ዛሬ ላይ ጥሩ የምጣኔ ሀብት ባለቤት መሆናቸውን ተከትሎ ፍላጎት እየጨመረ ቢመጣም ግን የገበያ ችግር እየገጠማቸው እንደሚገኝም አንስተዋል።የኦሮሚያ ክልል ገበያ ልማት ኤጄንሲ ቢሮ ኃላፊ አቶ አቡኔ ቱፋ፣ ችግሩ መኖሩ እንደሚታወቅ ገልጸው፣ ስራዎች እየተሰሩ እና ችግሮቹም እንደሚቀረፉ ጠቁመዋል።ዜጎቹ የተሻለ ህይወት እንዲኖራቸው ለማስቻል በተግባር የተደገፉ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም የሚያስፈልጉ መሠረተ ልማቶችን ከሟሟላት ጀምሮ የገበያ ማዕከላትን መገንባት እና የገበያ ትስስር እንዲፈጠር እየተሰራ እንደሚገኝ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡በዞኑ ዘጠኝ የእንስሳት የገበያ ማዕከላት እየተገነቡ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።(በሚልኪያስ አዱኛ) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-%e1%88%81%e1%88%88%e1%89%b5-%e1%8b%93%e1%88%98%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%88%b4%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%88%ad%e1%89%a5%e1%89%b6-%e1%8a%a0%e1%8b%b0%e1%88%ae/ | 192 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በመተከል ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም የሚሠራ ክልል አቀፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተቋቋመ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown |
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከቀዬቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚሠራ ክልል አቀፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተቋቁሟል።የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ መለሰ በየነ፣ የክልሉ መንግሥት ከፌዴራል መንግሥት እና ሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን በመተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።ለተፈናቀሉ ዜጎች አሁን እየተደረገ ካለው ሰብአዊ ድጋፍ ባሻገር በዘላቂነት ለማቋቋም ክልል አቀፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሜቴ መዋቀሩን አቶ መለሰ ተናግረዋል።ኮሚቴው በክልሉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ባለሀብቶችን፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል ድጋፍ እንደሚያሰባስብ ገልጸዋል።የተፈናቀሉ ዜጎችን ዜጎችን ካሉበት ችግር ለመታደግ እና በዘላቂነት ለማቋቋም በትኩረት እንደሚሠራም ጠቁመዋል።በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የገቢ ማሰባሰብ ሥራውን እንደሚሠራም አስታውቀዋል።ኮሚቴው በቀጣይ የሚያሳውቃቸውን የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለተፈናቀሉ ዜጎች የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክትም ጥሪ አቅርበዋል ፡፡(ምንጭ ፡- የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8d-%e1%8b%9e%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8d%88%e1%8a%93%e1%89%80%e1%88%89-%e1%8b%9c%e1%8c%8e%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%88%88%e1%88%9b%e1%89%8b%e1%89%8b/ | 135 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ይጀምራሉ- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown | የ2012 ዓ.ም የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እንደሚጀምሩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን የ2012 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ለማስቀጠል ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ መተላለፉ የሚታወስ ነው።ሆኖም በትግራይ ክልል በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የመማር ማስተማር ሂደቱ ተስተጓጉሎ የነበረ በመሆኑ በድጋሚ ጥሪ ማስተላለፍ ማስፈለጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው በደረሰበት ጉዳት ጥገና ላይ በመሆኑ ቀሪ ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመረቁት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ተገልጿል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%8b%a9%e1%8a%92%e1%89%a8%e1%88%ad%e1%88%b2%e1%89%b2-%e1%89%b0%e1%88%98%e1%88%ab%e1%89%82-%e1%89%b0%e1%88%9b%e1%88%aa%e1%8b%8e%e1%89%bd/ | 82 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዕድለኞች ሽልማት ሰጠ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown | የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ”ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” እና “ይቆጥቡ፣ይሸለሙ” ዕጣ ዕድለኞች ሽልማት የመስጠት ሥነስርዓት ተከናወነ፡፡የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ9ኛው ዙር የ”ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” እና የ”ይቆጥቡ፣ ይሸለሙ” የሽልማት መርኃግብር ዕጣ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓም በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ መውጣቱ ይታወቃል፡፡ይህንን ተከትሎ ተከትሎ በአዲስ አበባ ሁለት አፓርትመንቶች፣ ሶስት መለስተኛ የጭነት መኪኖች፣ 15 የቤት አውቶሞቢሎች እና 30 ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች በዛሬው ዕለት ለባለ እድለኞች ደርሰዋል።በዚህም አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የተወጣጡ ተሸላሚዎች ሽልማቶቻቸውን ተረክበዋል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቢ ሳኖን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ብሎም በማህበረሰብ ውስጥ የቁጠባን ባህል ለማዳበር በመላው ሀገሪቱ ቅርንጫፎቹን በማብዛት 1 ሺህ 624 ማድረሱን ገልጸው፣ ባንኩ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጅቡቲ እና ሱዳን ቅርንጫፍ ባንኮችን በመክፈት በአለም አቀፍ ደረጃ አገልግሎት እየሰጠ ነው ብለዋል።የቁጠባ ባህልን ለማዳበር የሴቶች የቁጠባ ሂደት፣ የወጣቶች እና ታዳጊዋች ለትምህርት የሚውል እና የጋብቻ ቁጠባን ማመቻቸቱንም ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።ላለፋት 10 አመታት በቆየው በዚህ የሽልማት ሂደት ከ8 ሺህ 350 የሚበልጡ ተገልጋዮች ተሸላሚ መሆን እንደቻሉ እና በ2004 ዓ.ም 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የነበረው የደንበኛ ቁጥር አሁን ላይ ወደ 26 ሚሊየን ከፍ ማለቱንም ተናግረዋል፡፡10ኛው ለ”ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” እና “ይቆጥቡ፣ይሸለሙ” መርኃግብር በቀጣይ በይፋ እንደሚጀመርም ለማወቅ ተችሏል።(በቁምነገር አህመድ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%8b%b5-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ad-%e1%88%88%e1%8b%ad%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8b%9d%e1%88%a9%e1%8d%a3-%e1%8b%ad%e1%88%b8/ | 177 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ወጋገን ባንክ ከታክስ በፊት 1.1 ቢሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown | ወጋገን ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት አመት ከታክስ በፊት 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።ባንኩ ይህንን ያስታወቀው ባካሄደው 27ኛ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጉባኤ ላይ ይፋ ባደረገው የኦዲት ሪፖርት ነው፡፡የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተፈራ ሞላ ምንም እንኳን በበጀት አመቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ በፈጠረው መቀዛቀዝ ምክንያት በብድር አከፋፈል እና አሰባሰብ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተከትሎ የብድር ወለድ ምጣኔ ቅናሽ የተደረገ ቢሆንም፣ ባንኩ በ2019/20 የበጀት አመት 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።በበጀት ዓመቱ የተገኘው ገቢ ከ2018/19 በጀት አመት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር 47 በመቶ ወይም 324 ብር ሚሊየን ብልጫ እንዳለውም ገልጸዋል።በባንኩ ደምበኞች የተከፈቱ የቁጠባ ሂሳቦች ብዛትም የ38 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 1 ነጥብ 8 ሚሊየን መድረሱን ምክትል ሰብሳቢው ገልጸዋል።የወጋገን ባንክ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 43 ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በመክፈት በበጀት አመቱ መጨረሻ አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ብዛት 383 ማድረሱንም ተናግረዋል።በተመሳሳይ ባንኩ በመላው ሀገሪቱ 2 መቶ 97 የኤቲኤም እና 273 የክፍያ ማስፈጸሚያ ፖስ ማሽኖችን በመትከል እንዲሁም የሞባይል የኢንተርኔት እና የወኪል ባንክ አገልግሎቶችን ከማስፋት አንፃር መልካም አፈፃፀም ማስመዝገቡም ተገልጿል።ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር በተጠናቀቀው የበጀት አመት በመንግስት የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን ለመደገፍ እና የኮሮና በሽታን ለመከላከል የሚደረገውን ሀገር አቀፍ ጥረት ለማገዝ ከ31 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉም ታውቋል።(በሔለን ታደሰ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%88%e1%8c%8b%e1%8c%88%e1%8a%95-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ad-%e1%8a%a8%e1%89%b3%e1%8a%ad%e1%88%b5-%e1%89%a0%e1%8d%8a%e1%89%b5-1-1-%e1%89%a2%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%89%b5/ | 184 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | በ250 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻልና የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት እንደሚገባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የምንገኝበት ወቅት አለም በቴክኖሎጂ አንድ የሆነበት በመሆኑ በከተማችንም ደህንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ ቴክኖሎጂን በማበልጸግ መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል።የአገልግሎት መስጫ ዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ተግባራዊ መሆን አገልግሎት ፈላጊውን አካል የጊዜ፣ የጉልበትና እንግልት እንደሚቀንስ ጠቅሰው ብልሹ አሰራሮችን ለመከታተል ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡የህብረተሰቡን አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ዛሬ የተተገበሩ መሰል የዲጂታል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በብዛት ማስፋፋት እንደሚገባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን አህመድ በበኩላቸው፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የዲጂታል መሠረተ ልማት ዝርጋታ አበረታች በመሆኑን ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ የወረፋ ማስጠበቂያ ሲስተም፣ ከተማ አቀፍ የሜይል ሲስተምና ሌሎች መሰል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችንም ስራ አስጀምረዋል።በአዲስ አበባ ከተማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አማካኝነት በ250 ሚሊዮን ብር ወጪ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የህብረተሰቡን አገልግሎት አሰጣጥ የማሻሻል የሚያስችሉ የኢ-ሰርቪስ መሰረተ ልማት ዝርታዎችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት መብቃታቸውን ከበአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8b%b2%e1%8c%82%e1%89%b3%e1%88%8d-%e1%89%b4%e1%8a%ad%e1%8a%96%e1%88%8e%e1%8c%82-%e1%88%98%e1%88%b0%e1%88%a8%e1%89%b0-%e1%88%8d%e1%88%9b%e1%89%b5-%e1%89%b0%e1%88%98%e1%88%ad%e1%89%86/ | 177 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በጋምቤላ ከተማ ሆስፒታሎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚደረጉት ጥረት የሚበረታታ ነው – ዶ/ር ሊያ ታደሰ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | በጋምቤላ ከተማ አጠቃላይና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ለህብረተሰቡ የተሻለ የህክምና አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።ሚኒስትሯ ከቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬና የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ ሆስፒታሎቹን ተመልክተዋል።ሚኒስትሯ እንዳሉት በዚህ ወቅት ሆስፒታሎችን በመሰረተ ልማት በማደራጀትና የተለያዩ የጥራት ማረጋገጫ ስራዎችን በማከናወን ለህፃናት፣ እናቶችና ሌሎች ታካሚዎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እየተደረገ ነው።ቀደም ሲል ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ እንደ ሌሎች አካባቢዎች በሆስፒታሎች ተቀዛቅዞ የነበረው የመደበኛ የህክምና አገልግሎት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በምልከታ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።ሆስፒታሎች ከመደበኛው የህክምና አገልግሎት በተጨማሪ የኮሮናቫይረስን በመከላከልና በማከም ረገድም እንዲሁ ሰፊ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በአሁኑ ወቅት እየጨመረ ቢሆንም ጋምቤላን ጨምሮ በሌሎችም የአገሪቱ አካባቢዎች በህብረተሰቡ ዘንድ መዘናጋት መኖሩን ጠቅሰው፤ ይህንን ችግር ለማቃለል የተጠናከረ የንቅናቄ ስራ በቅርቡ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ በሆስፒታሎች የሚጠበቀውን መሰረታዊ አገልግሎት ለማሟላት የሚደረጉት ጥረቶች መልካም መሆናቸውን ተናግረዋል።ቀደም ሲል በክልሉ ከፍተኛ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭት እንደነበረ ጠቁመው ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት ስራዎች የስርጭቱ መጠን የመቀነስ አዝማሚያ እንዳሳየ መገንዝብ እንደቻሉም ገልጸዋል።በሆስፒታሎቹ ምልከታ ያደረጉት ያሉትን ክፍተቶች በመለየት ፋውንዴሽናቸው የተለያዩ እገዛዎችን ለማድረግ በማሰብ መሆኑንም ገልጸዋል።ሚኒስቴሯና የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት በጋምቤላ እስከ ነገ በሚኖራቸው ቆይታ በኮሮናቫይረስ መከላከል፣ በጨቅላ ህጻናት የጤናና የስርዓተ ምግብ ዙሪያ ከዘርፉ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ኢዜአ ዘግቧል። | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8c%8b%e1%88%9d%e1%89%a4%e1%88%8b-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b-%e1%88%86%e1%88%b5%e1%8d%92%e1%89%b3%e1%88%8e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%bb%e1%88%88-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d/ | 189 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ራይዚንግ ኢትዮጵያ በሚል ሃሽታግ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀመረ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | ራይዚንግ ኢትዮጵያ በሚል ሃሽታግ የተሳሳቱ የመገናኛ ብዙኀን ትርክቶች ለማረቅና የኢትዮጵያን መልካም ጎን ለማስታዋወቅ ያለመ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ዛሬ ተጀምሯል፡፡በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ኢትዮጵያ እና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ትብብር የተዘጋጀው ዘመቻ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎችን እንደሚያስተባብር ተገልጿል፡፡በዘመቻው ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት እምቅ አቅም፣ ባህል፣ የቱሪስት መዳረሻዎችን፣ በጎ አድራጎትን እና ፕሮጀክቶችን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ያስተዋውቃልም ተብሏል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%88%ab%e1%8b%ad%e1%8b%9a%e1%8a%95%e1%8c%8d-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%89%a0%e1%88%9a%e1%88%8d-%e1%88%83%e1%88%bd%e1%89%b3%e1%8c%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%88%85%e1%89%a0/ | 52 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የተለያዩ ተቋማት በ’ገበታ ለሀገር’ ለመሳተፍ ገንዘብ ገቢ አደረጉ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | የተለያዩ ተቋማት በ’ገበታ ለሀገር’ ለመሳተፍ ቃል የገቡትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ደረሰኝ አስረክበዋል፡፡በዚህም መሰረት፣አዳማ ቆርቆሮ እና ሚስማር ፋብሪካ – 10 ሚሊየን ብርላየንስ ግሩፕ – 5 ሚሊየን ብርበላይነህ ክንዴ – 10 ሚሊየን ብርየኦሮሚያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን – 5 ሚሊየን ብርየኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን – 10 ሚሊየን ብርኬርቻንሺ ትሬዲንግ – 10 ሚሊየን ብርባለዛፍ አልኮል – 5 ሚሊየን ብርሆራ ትሬዲንግ – 15 ሚሊየን ብርኢትዮ ጋባና ትሬዲንግ – 5 ሚሊየን ብርጭላሎ የምግብ ማምረቻ ኮምፕሌክስ – 5 ሚሊየን ብር ገቢ ማድረጋቸው ታውቋል።መረጃውን ያገኘነው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነው፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%88%e1%8b%ab%e1%8b%a9-%e1%89%b0%e1%89%8b%e1%88%9b%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%8c%88%e1%89%a0%e1%89%b3-%e1%88%88%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%88%88%e1%88%98%e1%88%b3%e1%89%b0/ | 80 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
አሜሪካ በአዲሱ አይነት የኮቪድ-19 የተያዘ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች | ዓለም አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | በእንግሊዝ የተገኘውና በፈጣን ሁኔታ የሚተላለፈው አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ በአሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት መገኘቱን አሜሪካ ይፋ አድርጋለች።አዲስ ባህሪ ያለው ኮቪድ-19 ቫይረስ የተገኘው ምንም የቅርብ የጉዞ ታሪክ በሌለው የ20 ዓመት ግለሰብ ላይ ሲሆን ግለሰቡ በለይቶ ማቆያ መግባቱም ተገልጿል።የግዛቱ የጤና ባለስልጣናት ከግለሰቡ ጋር ግኑኝነት ያላቸውን ሰዎች እና አዲስ ባህሪይ ካለው ቫይረስ ጋር ንክኪ ያላቸውን ለመለየት እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።አዲስ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የኮቪድ-19 ክትባት ስርጭት ከታሰበው መረሃ ግብር ወደኃላ በመቅረቱ ክትባቱን ተግባራዊ ለማድረግ በተደረገው እንቅስቃሴ እንደሀገር ከባድ ፈተና ውስጥ ገብተናል ሲሉ የዶናልድ ትራምፕን አስተዳደር ወቅሰዋል።በአሜሪካ ከ19 ሚሊየን በላይ ሰዎች በኮቪድ- 19 የተያዙ ሲሆን ከ337 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።አዲስ ተገኘ የተባለው የኮቪድ-19 ስርጭቱ ከቀድሞው ቫይረስ በባህሪው ፈጣን ሲሆን በበሽታው የተጠቁት ላይ ግን የተለየ ባህሪ እንደሌለው የዘርፉ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው።አዲስ ባህሪ ያለው ቫይረሱ በአሜርካ እንደታየው ሁሉ በካናዳ እና በተለያዩ ሀገራትም እየተገኘ ሲሆን የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን የኮቪድ-19 ባገናዘበ መልኩ ክትባቱ በአሜሪካ እየተሰጠ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።የአሜሪካ መንግስት እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ 20 ሚሊየን ዜጎቹ የኮቪድ-19 ክትባት ሊሰጥ የታቀደ ሲሆን አስካሁን 2.1 ሚሊየን ሰዎች ክትባት መውሰዳቸውን የሀገሪቱ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል አስታውቋል።በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት የቀረበው አስትራዜኒክ የተባለውን የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለመስጠት እንግሊዝ ውሳኔ ላይ መድረሱዋንም አስታውቃለች።እንግሊዝ አስትራዜኒክ የተባለውን ክትባት ፋብሪካዎች በ100 ሚሊየን ዶዝ እንዲያመረቱ ያዘዘች ሲሆን የብዙዎችን የመከላከል አቅም በማሳደግ ወደ ቀደመ ጤንነታቸው እንዲመለሱ ያስችላልም ተብሏል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a0%e1%88%9c%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b1-%e1%8a%a0%e1%8b%ad%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%89%aa%e1%8b%b5-19-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8b%ab%e1%8b%98-%e1%88%b0/ | 204 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
በትግራይ ክልል አስቸኳይ እርዳታ ለሚሹ ወገኖች ድጋፉ ተጠናክሮ ቀጥሏል – ዶክተር ሙሉ ነጋ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 31, 2020 | Unknown | በትግራይ ክልል አስቸኳይ እርዳታ ለሚሹ ወገኖች እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ገልጸዋል።የትግራይ ክልል ካቢኔ አወቃቀርም በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት የሚገፋ ቡድን ወይም ግለሰብ እንደማይኖር ማረጋገጡን ጠቁመዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የፌዴራሉ መንግስት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ መግለጻቸው ይታወሳል።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ÷ጊዜያዊ አስተዳደሩ በክልሉ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል።ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራውን በጀመረበት ወቅት የታጠቁ ግለሰቦችን ትጥቅ ማስፈታት፣ የተቋረጡ ህዝባዊ አገልግሎቶችን ማስጀመርና የክልሉን ካቤኔ አዋቅሮ ወደ ስራ ማስገባት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራቱንም ነው የገለጹት።በአሁኑ ወቅት በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች በፈቃዳቸው ትጥቃቸውን ለጸጥታ አካላት እያስረከቡ ይገኛሉ ያሉት ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈፃሚው÷ ሸሽተው የነበሩ ሚኒሻዎችም ትጥቃቸውን አስረክበው በሰላም ወደ አካባቢያቸው እየተመለሱ ነው ብለዋል።በወንጀል የማይፈለጉ የመንግስት ሰራተኞችም ወደ ስራ ገበታቸው መመለሳቸውን ጠቁመው ÷የክልሉ ካቢኔም በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ባቀፈ መልኩ መዋቀሩን ገልጸዋል።የካቢኔ አወቃቀሩም ከዚህ በኋላ በትግራይ ክልል በአመለካከቱ ምክንያት የትኛውም ግለሰብ ሆነ ቡድን መገፋት እንደሌለበት ያረጋገጠ ነው ብለዋል።በተጨማሪም የመንግስት አገልግሎትና የፖለቲካ ፓርቲ የተለያዩ መሆኑን በተግባር ማሳየቱን ዶክተር ሙሉ ጠቁመዋል።የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳዳር አባላት በተለያዩ አካባቢዎች በተንቀሳቀሱበት ወቅት ጁንታው በመሰረተ ልማቶች ላይ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም ነው የተናገሩት።በተለይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጡ መስመሮች በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳታቸው ህዝባዊ አገልግሎቶችን በሁሉም አካባቢ በፍጥነት ማስጀመር አለመቻሉን ገልጸዋል።የፌደራል መንግስት ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ ከደቡብ ትግራይ ጀምሮ እስከ አዲግራት ድረስ የመብራት አገልግሎት ማስጀመር ማቻሉን ገልጸዋል።በቀጣይም አገልግሎቱን በሁሉም አካባቢ ለማስጀመር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት።ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር ባካሄድናቸው ውይይትች በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰናል ብለዋል።ዶክተር ሙሉ አያይዘውም በውይይት መድረኮች ላይ ተሳታፊዎቹ ያለምንም ገደብ ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ መቻላቸውንም ተናግረዋል።በክልሉ የአፈና ስርዓት ተንሰራፍቶ ከመቆየቱ ጋር ተያይዞ የውውይት መድረኮቹ አዲስ የነጻነት አየርን ያለማመዱ እንደነበሩ ነው የጠቆሙት።የትግራይ ክልልን መልሶ በማቋቋም ረገድ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ነው ዶክተር ሙሉ ተናግረዋል።ከዚህ አንጻር አሁን ላይ አስቸኳይ እርዳታ ለሚሹ ወገኖች እየተደረገ ያለው ድጋፍ በጥሩ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሰብአዊ ድጋፎች በሁሉም ቦታ ተደራሽ እንዲሆኑ የማጓጓዝ ስራ እያከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።የፌደራል መንግስቱ ከአስቸኳይ ድጋፍ በተጨማሪ ከበጀት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ዶክተር ሙሉ አንስተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በተቋቋመበት ወቅት የፌደራሉ መንግስት ለአስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፃቸው ይታወሳል።በተገባው ቃል መሰረትም ለክልሉ ሰብአዊ ድጋፍን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችና እገዛዎች እየተደረጉ መሆኑን ዶክተር ሙሉ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል። | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%89%b8%e1%8a%b3%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%88%ad%e1%8b%b3%e1%89%b3-%e1%88%88%e1%88%9a%e1%88%b9-%e1%8b%88/ | 354 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሪ በድጋሚ ተጀመረ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሪ በድጋሚ መጀመሩን የብሄራዊ ባንክ አስታወቀ::የብር ቅያሪው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንደሚከናወን ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%89%b0%e1%89%8b%e1%88%ad%e1%8c%a6-%e1%8b%a8%e1%8a%90%e1%89%a0%e1%88%a8%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%ae%e1%8c%8c/ | 32 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የወንጀለኛ መቅጫና ማስረጃ ረቂቅ ሕጎች ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ተከታትሎ ለማስፈጸም ያስችላሉ – ዶክተር ዳንኤል በቀለ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | የወንጀለኛ መቅጫና ማስረጃ ረቂቅ ሕጎች ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ተከታትሎ ለማስፈጸም የሚያስችሉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ገለጹ።የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በወንጀለኛ መቅጫና ማስረጃ ረቂቅ ህጎች ላይ የሚመክር መድረክ እያካሔደ ነው።ኮሚሽነሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የኢፌዴሪ ረቂቅ የወንጀለኛ ሕግ ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ መዘጋጀቱ ትልቅ እርምጃና ለዓመታት የታዩ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል ነው።ረቂቅ ሕጉ ከክስ ምስረታ እስከ ምርመራ ከምርመራ እስከ ፍርድ አሰጣጥ ያሉ ሒደቶችንና የዳኝነት ሕጎችን የሚፈትሽ መሆኑንም ገልጸዋል።“ሕጉ ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ተከታትሎ ለማስፈጸም የሚያስችል ነው” በማለት አስታውቀዋል።ለሚቀጥሉት ረጅም ዓመታት ገዢ ሆኖ የሚቀጥል ረቂቅ ሕግ ስለሆነ በጥልቀት መወያየትና መስራት ያስፈልጋል ሲሉም አመልክተዋል።ሕጉ ከሌሎች ሕጎች ጋር ተናባቢና ተጣጥሞ የሚሄድ መሆኑም መፈተሽ እንዳለበት ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።በመድረኩ ላይ ረቂቅ ሕጎቹ የያዟቸው ዝርዝር ጉዳዮች እየተዳሰሱ ይገኛሉ።(ምንጭ፡-ኢዜአ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%8a%95%e1%8c%80%e1%88%88%e1%8a%9b-%e1%88%98%e1%89%85%e1%8c%ab%e1%8a%93-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%88%a8%e1%8c%83-%e1%88%a8%e1%89%82%e1%89%85-%e1%88%95%e1%8c%8e%e1%89%bd-%e1%8a%a8/ | 116 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በኢትዮጵያ ታሪክ እና ፖለቲካ መካከል ጤናማ የሆነ ግንኙነት ሊዳብር ይገባል ተባለ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | የታሪክ ባለሙያዎች ሰሞኑን ባደረጉት “የታሪክ ባለሙያዎች የቢሾፍቱ ስምምነት” ምክክር ዙሪያ ለጋዜጠኞች በሰጡት ዝርዝር መረጃ፣ ታሪክ እና ፖለቲካ መካከል ጤናማ የሆነ ግንኙነት መዳበሩ ለሃገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።የታሪክ ምሁራኑ ፖለቲካና ፖለቲከኞች ታሪክ ላይ የሚያሳድሩትን ጤናማ ያልሆነ ጫናም ለማስተካከልና ችግሩን በሂደት ለመፍታት እንደሚሰራ ገልጸዋል።በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ የሚገኘው የብሔራዊ የማህበረሰብ ተኮር የምክከር መድረክ አንዱ አካል የሆነው የታሪክ ምሁራንና የታሪክ ፀሐፊያን የምክክር መድረክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለአራት ቀናት በቢሾፍቱ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ 60 የኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራንና የታሪክ ፀሐፊያን ተሳትፈውበታል።መድረኩ ለአገር ግንባታና ለብሔራዊ መግባባት አስተዋጽኦ ለማበርከት ያለመ መሆኑን ከሚነስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%89%b3%e1%88%aa%e1%8a%ad-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8d%96%e1%88%88%e1%89%b2%e1%8a%ab-%e1%88%98%e1%8a%ab%e1%8a%a8%e1%88%8d-%e1%8c%a4%e1%8a%93/ | 97 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የልማት ስትራቴጂ እቅድ ለማዘጋጀት ውይይት እያደረገ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የቀጣይ 5 አመት ብሔራዊ ስታቲስቲክስ ልማት ስትራቴጂ እቅድ ለማዘጋጀት ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን መሰብሰብ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ በቀጣይ 10 አመታት የብሔራዊ ስታቲስቲክ ስርዓቱ የሚመራበትን ፍኖተ-ካርታ እና ሶስተኛው ዙር የብሔራዊ ስታቲስቲክ ልማት ስትራቴጂ ሰነድ ለማዘጋጀት ቅድመ ዝግጅት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡የህዝብ እና ቤት ቆጠራ እንዲካሄድ እቅድ በመኖሩ ቅድመ ዝግጅትም ሲደረግ ነበር ያሉት አቶ ቢራቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለሶስት አመታት መራዘሙ በሌሎች የመረጃ አሰባሰቦች ላይ ዝቅተኛ አፈፃፀም እንዲኖር ማድረጉንም ጠቁመዋል።በሌላ መልኩ የኮቪድ-19 ወረርሽኝም የመረጃ አሰባሰብ ሂደቱ ላይ የራሱ ችግር እንደነበረው አንስተዋል።የምክክር መድረኩ ለቀጣዮቹ 3 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የአለም ባንክ ፤ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ስታቲስቲክስ ዲቪዥን ድጋፍ አድርገዋል ተብሏል።(በደረሰ አማረ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%8b%95%e1%8a%a8%e1%88%8b%e1%8b%8a-%e1%88%b5%e1%89%b3%e1%89%b2%e1%88%b5%e1%89%b2%e1%8a%ad%e1%88%b5-%e1%8a%a4%e1%8c%80%e1%8a%95%e1%88%b2-%e1%8b%a8%e1%88%8d%e1%88%9b%e1%89%b5/ | 112 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፉ ሀገራዊ ዐቅም በመፍጠር የውጪ ምንዛሬ የማግኘት አቅሟን ታጠናክራለች – ጠ/ሚ ዐቢይ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ማምረት የሚያስችል ሀገራዊ ዐቅም በመፍጠር የውጪ ገበያ እና የውጪ ምንዛሬ የማግኘት አቅሟን እንደምታጠናክር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ኢትዮጵያ እሴቶችን በመጨመር በየአካባቢው የሚገኙ ባህላዊ ማዕድን አውጪዎችን እና ማኅበረሰቦችን ሕይወት ማሻሻል የሚያስችሉ በርካታ የተፈጥሮ ማዕድን የታደለች ሃገር መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡ወርቅ፣ ቤዝ ብረቶች፣ ፖታሽ፣ ታንታለም፣ ሰንፔር፣ ኤመራልድ እና ኦፓልም በዚህ ረገድ ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡አያይዘውም በማዕድን ዘርፍ ማምረት የሚያስችል ሀገራዊ ዐቅምን በመፍጠር የውጪ ገበያ እና የውጪ ምንዛሬ የማግኘት አቅም ይጠናከራልም ነው ያሉት፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%89%a0%e1%88%9b%e1%8b%95%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%8d%89-%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%8b%90%e1%89%85%e1%88%9d-%e1%89%a0/ | 76 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኮቪድ-19 መከሰት ለኤችአይቪ/ኤድስ የሚሰጠውን ትኩረት እንዲቀንስ ማድረጉ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት ትኩረታቸውን ለኮቪድ-19 በማድረጋቸው ለኤችአይቪ/ኤድስ የሚሰጠውን ትኩረት እንዲቀንስ ማድረጉ ተገልጿል፡፡የኤችአይቪ/ኤድስ ቀን በአለም ለ34ኛ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለ33ኛ ጊዜ “ኤችአይቪ/ኤድስ ለመግታት አለም አቀፍ ትብበር እና የጋራ ሀላፊነት” በሚል መርህ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተከብሯል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኤችአይቪ/ኤድስ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ዳይሬክተር ሲስተር ፈለቀች አንዳርጌ መዲናዋ ከጋምቤላ ክልል በመቀጠል ከፍተኛ የስርጭት መጠን አስመስግባለች ብለዋል፡፡በጋምቤላ ክልል 4 ነጥብ 8 በመቶ የስርጭት መጠን ሲመዘገብ፤ በአዲስ አበባ 3 ነጥብ 2 በመቶ መመዝገቡን ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡በዚህም 30 በመቶ የስርጭት መጠን ከ15 እስከ 24 እድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ወጣቶች በመሆናቸው ችግሩን አሳሳቢ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ ከ669 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው እንዳላቸውና ከእነዚህም ከ114 ሺህ በላይ የሚሆኑት በአዲስ አበባ እንደሚገኙም ዳይሬክተሯ አመላክተዋል፡፡ላለፉት 20 አመታት ለኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት ለመቀነስ በተደረገው ጥረት በቫይረሱ የሚከሰተውን ሞት 52 በመቶ መቀነስ የተቻለ ሲሆን፣ በቫይረሱ አዲስ የመያዝ መጠን 49 በመቶ መቀነስ መቻሉንም አስረድተዋል፡፡(በነስረዲን ኑሩ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%ae%e1%89%aa%e1%8b%b5-19-%e1%88%98%e1%8a%a8%e1%88%b0%e1%89%b5-%e1%88%88%e1%8a%a4%e1%89%bd%e1%8a%a0%e1%8b%ad%e1%89%aa-%e1%8a%a4%e1%8b%b5%e1%88%b5-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%88%b0%e1%8c%a0%e1%8b%8d/ | 131 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በኢትዮጵያ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማቋቋም እንቅስቃሴ ተጀመረ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | በኢትዮጵያ የኬሚካል ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ፡፡የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ደዬሳ ለታ፣ ዘርፉ ለኢንዱስትሪው የጀርባ አጥንት በመሆኑ ሁሉን ኢንዱስትሪዎች መመገብ የሚችል የኬሚካል ማምረቻ ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡የኢትዮጵያ ኬሚካል ውጤቶች አምራቾች ዘርፍ ማህበር ባካሄደው አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ሀገሪቷ ከዘርፉ መጠቀም የሚገባትን ጥቅም ማግኘት እንድትችል በሚታዩ ክፍተቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሰራባቸው እንደሚገባ ተገልጿል፡፡የኢትዮጵያ ኬሚካል ውጤቶች አምራቾች ዘርፍ ማህበር ሰብሳቢ አቶ በቀለ ፀጋዬ የዘርፉን ችግሮች መቅረፍ እንደሚገባ ገልጸው፤ በተለይም ከውጭ ምንዛሪ፣ ፋይናንስና ብድር፣ ኤል ሲ አገልግሎት ክፍያ፣ የመሬት አቅርቦት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አለማግኘት እና ከጉምሩክ አሰራሮች ጋር ያሉ ሰፊ ክፍተቶች ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ብለዋል፡፡በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የብረታ ብረትና ኬሚካል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዮሃንስ ድንቃየሁ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር በምታደርገው ጥረት ዘርፉ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡ማህበሩ የ2012 በጀት አመት ክንውን ሪፖርትና የ2013 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት እና የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ አድርጓል፡፡(በህይወት አክሊሉ) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8a%ac%e1%88%9a%e1%8a%ab%e1%88%8d-%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%8b%b1%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%aa-%e1%8d%93%e1%88%ad%e1%8a%ad-%e1%88%88/ | 148 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ለጎርጎራ ፕሮጀክት “የንጉሥ እራት” መርሃ ግብር በጎንደር ከተማ ሊዘጋጅ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | በገበታ ለሃገር ለተካተተው የጎርጎራ ፕሮጀክት አንድ ቢሊየን ብር የሚያስገኝ “የንጉሥ እራት” የተሰኘ መርሃ ግብር በጎንደር ከተማ እንደሚዘጋጅ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ አስታወቁ።በጣና ሃይቅ ዳርቻ የምትገኘው ጥንታዊቷ የጎርጎራ ከተማ ‘በገበታ ለሃገር ፕሮጀክት’ ከሚለሙ ሶስት ስፍራዎች መካከል እንደ መሆኗ፥ በክልሉ የሚገኙ ባለሃብቶች የሚታደሙበት “የንጉስ እራት” የተሰኘ መርሃ ግብር በጎንደር ከተማ በማዘጋጀት አንድ ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ እቅድ መያዙን ከንቲባው ተናግረዋል።መርሃ-ግብሩ መቼ እንደሚከናወንና የአንድ እራት ዋጋ ተመን ስንት እንደሚሆን በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል።ፕሮጀክቱ የቱሪዝም ልማትን በማሳደግ ለሥራ እድል ፈጠራና የኢንቨስትመንት ፍሰትን በመጨመር ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ነው የተናገሩት።የአካባቢው ማህበረሰብ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ጭምር ፕሮጀክቱን እንዲደግፍ የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ከንቲባው ተናግረዋል።በ”ገበታ ለሃገር” ፕሮጀክት ከጎርጎራ በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል ወንጪና በደቡብ ክልል የኮይሻ ፕሮጀክቶች እንደሚለሙ የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%88%88%e1%8c%8e%e1%88%ad%e1%8c%8e%e1%88%ab-%e1%8d%95%e1%88%ae%e1%8c%80%e1%8a%ad%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8a%95%e1%8c%89%e1%88%a5-%e1%8a%a5%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%88%ad/ | 114 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ በሰላም ማስከበርና ጠንካራ ዲፕሎማሲ ምሳሌ እና ተጠቃሽ መሆን የምትችል ሀገር ናት – ምሁራን | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ በሰላም ማስከበር እና በጠንካራ ዲፕሎማሲ ምሳሌ እና ተጠቃሽ መሆን የምትችል ሀገር መሆኗን ዋልታ ያነጋገራቸው ምሁራን ገለጹ፡፡ኢትዮጵያ እና ሱዳን ወንድማማች ህዝቦች እንደመሆናቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ምንም አይነት ግጭት ሊከሰት እንደማይችል የሚገለጹት ምሁራን፣ ከጀርባ ሆኖ ይህንን የሚጠነስስ ኃይል አይሳካለትም ሲሉም ተናግረዋል፡፡ከዋልታ ጋር ቆይታ ያደረጉት በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ዲፕሎማሲና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህር እንዳለ ንጉሴ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ምርምርና ጥናት ተቋም መምህር መሀመድ ሀሰን በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ ያለው ውጥረት አሁንም እየተስተዋለ ቢሆንም፣ ውጥረቱ እንዲከሰት ያደረገው የውጭ ሀይል የሱዳን የውስጥ አለመረጋጋትን በመጠቀም ግጭቱን እያባባሰ እንዳለ ገልጸዋል፡፡በውጭ ኃይሎች እንዲህ አይነት ትንኮሳ ኢትዮጵያ ላይ የሚቀነባበረው ኢትዮጵያውያን ለጋራ ሰላማቸው ምን ያህል ተባባሪ ህዝቦች መሆናቸውን ካለማወቅ የተነሳ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ግብጽ በአሁን ሰአት በርካታ የውስጥ ችግር ያሉባት ሀገር እንደመሆኗ ሱዳንን ልታጋፍጣት እንጂ ልትረዳት እንደማትችል ራሱ የሱዳን መንግስት ጠንቅቆ ያውቃል ያሉት ምሁራን፣ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት ፈጽሞ እንደለላትም ጠቁመዋል፡፡ይህን የድንበር ላይ ግጭት ራሳቸው ሱዳን እና ኢትዮጵያ በውይይት ሊፈቱት የሚገባ ጉዳይ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ሰለም እና መረጋጋት እንዲመጣ ያላሰለሰ ጥረት ስታደርግ የቆየች ሀገር ስትሆን፣ በተለይም ይሄ ጥረቷ በሱዳን ፍሬ አፍርቶ ሱዳናውያን በይፋ በአደባባይ በመውጣት ኢትዮጵያን ያመሰገኑበት የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡በሁለቱ ሀገራት መንግስታት መካከል ያለው ዲፕለማሲያዊ ግንኙነት አሁን በጠንካራ ትስስር እንደቀጠለም ተመልክቷል፡፡ ይሁን እንጂ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያልተካለለ ድንበር በመኖሩ ላለፉት ረዥም አመታት ግጭት ሊባል የማይችል ጉዳይ ሲንጸባረቅ መቆየቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳወቁም የሚታወስ ነው፡፡(በሜሮን መስፍን) | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8d%8d%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%89%80%e1%8a%95%e1%8b%b5-%e1%89%a0%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%89%a0/ | 213 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ቦርዱ ቀጣዩን ምርጫ ተአማኒ የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ገለጸ።የቦርዱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስኪያጅ ወ/ት ሶሊያና ሽመልስ እንደገለጹት፤ ቦርዱ ቀጣዩ ምርጫ ቀደም ሲል ከተካሄዱ ምርጫዎች ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ ይገኛል።ምርጫው ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ቁሳቁሶች 90 በመቶ ተገዝተው መጠናቀቃቸውን ያመለከቱት ስራ አስኪያጇ፣ የተገዙት የምርጫ ቁሳቁሶቹና ህትመቶች ከዚህ በፊት ምርጫ ከተደረገባቸው ቁሳቁሶችና ህትመቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሆኑ አስታውቀዋል።የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹና የመራጭ ካርዶቹ ደግመው መታተም የማይችሉ፣ ከተነካኩ የሚያስታውቁ፣ የራሳቸው የሆነ ቀሪ ያላቸው፣ ኮፒ ለመደረግ የሚያስቸግሩ እንዲሁም የድምጽ መስጫ ሳጥኖቹ አስተማማኝና መራጩ ድምጽ ሲሰጥ በነጻነት ለመስጠት የሚያስችል መከለያዎች ያሉት እንደሆነም ጠቁመዋል።(ምንጭ፡- ኢፕድ) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a6%e1%88%ad%e1%8b%b1-%e1%89%80%e1%8c%a3%e1%8b%a9%e1%8a%95-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab-%e1%89%b0%e1%8a%a0%e1%88%9b%e1%8a%92-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%8b%b0%e1%88%ad%e1%8c%89-%e1%8b%a8/ | 109 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡ 8 ት/ቤቶች ለርክክብ ዝግጁ ሆኑ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 30, 2020 | Unknown | በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡ ተጨማሪ ስምንት ትምህርት ቤቶች ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታወቀ።የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፋንታው እንደገለጹት፤ ጽሕፈት ቤት የሚያስገነባቸው የትምህርት ተቋማት ፕሮጀክቶች በአብዛኛው በመጠናቀቅ ላይ ናቸው።ግንባታቸው ተጠናቆ ርክክብ የሚፈጸምባቸው ትምህርት ቤቶች በአፋር ክልል ዱብቲ፣ በጋምቤላ አኝዋሃ ዞን፣ በቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ እና መተከል ዞን ፣ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ዞን ፤ በዲላ ከተማ 02 እና 06 ቀበሌዎች፣ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ከተማ እና ዋግኸምራ ዞን ሳህላ ሰለምት ወረዳ የተገነቡ መሆናቸውን ገልፀዉ ጽህፈት ቤቱ ከ760 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪም አድርጓል ብለዋል፡፡ግንባታቸው ቀድመው የተጠናቀቁና ርክክባቸው ተፈጽሞ ስራ የጀመሩት አምስት ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፤ በአማራ ክልል ጎንደር ሎዛ ቀበሌ፣ ደቡብ ወሎ ጦሳ ሰላማ ቀበሌ፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሊበን ጭቋላ ቀበሌ፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞን ውጫሌ ወረዳ ጃክ ቀበሌ የሚገኙት መሆናቸውንና አሁን ላይ ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል።(ምንጭ፡- ኢፕድ) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%89%80%e1%8b%b3%e1%88%9b%e1%8b%8a%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%88%98%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%8c%bd%e1%88%95%e1%8d%88%e1%89%b5-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8c%88%e1%8a%90%e1%89%a1-8/ | 136 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ሊተዋወቁ እንደሚገባ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር በዘርፉ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማሳወቅ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡በቀጣይ 10 ዓመታት በዘርፉ ያሉ ዕድሎችን ለመጠቀም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በጥናት የተለዩ አካባቢዎችን ማስተዋወቅ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡ሚኒስቴሩ በማዕድን ዘርፍ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ አቅምና ፍላጎቱ ያላቸው ግለሰብ እና ተቋማት መሠማራት እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡የማዕድን ዘርፍ ቤተ ሙከራ፣ ጉድጓድ ቁፋሮ እንዲሁም ወርቅ ማጣሪያ ለማቋቋም በጋራ መሥራት እንደሚገባም አሳስቧል፡፡በኢትዮጵያ በነዳጅና ጋዝ ፍለጋ ዘርፍ የተሠማሩ 3 ኩባንያዎች እንዳሉም ተገልጿል፡፡ሚኒስቴሩ 63 የሚደርሱ በማዕድን ዘርፍ የተሠማሩ ድርጅቶች ፈቃድ ማቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡
(በሰሎሞን በየነ) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%9b%e1%8b%95%e1%8b%b5%e1%8a%95%e1%8a%93-%e1%8a%90%e1%8b%b3%e1%8c%85-%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%8d%8d-%e1%8b%ab%e1%88%89-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%89%a8%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%98/ | 78 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ የመቀሌ ጽህፈት ቤት በይፋ ሥራ ጀመረ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ በመቀሌ የሚገኘውን የፓርቲውን ዋና ጽህፈት ቤት በይፋ ሥራ አስጀመረ።በትግራይ ክልል ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩም ተገልጿል።የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል የጽህፈት ቤቱን ሥራ ማስጀመር አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በህወሓት ቡድን አምባገነንነት የፖለቲካ ፓርቲዎች በትግራይ ክልል ቢሮ ከፍተው መስራት የማይችሉበት ሁኔታ እንደነበር አስታውሰዋል።ቡድኑ ተወግዶ በትግራይ ክልል ለውጥ በመምጣቱ ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ሌሎች ህጋዊ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል።በዚህም ብልፅግና ቢሮውን በመቀሌ ከፍቶ በይፋ ሥራ መጀመሩን ገልጸው፤ “ሌሎች ህጋዊ ፓርቲዎችም በተመሳሳይ መንቀሳቀስ የሚችሉበት እድል ተፈጥሯል” ብለዋል።በትግራይ ክልል የተጀመረው የለውጥ ምዕራፍ ህዝቡን የሚያሳትፍና ወጣቱን በግንባር ቀደምትነት የለወጡ አራማጅ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል።ለውጡ በትግራይ ክልል ከዚህ ቀደም የነበሩ የማህበራዊ ፍትህ ችግሮችን የሚፈታ መሆኑን ጠቁመው፤ ለህዝቡ ፍትህን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ ሥራ እንደሚሰራም ጠቅሰዋል።በእውነትና በህብረ ብሔራዊነት በመታገዝ ትግራይን ወደ እውነተኛ ብልጽግና ለማሸጋገር እንደሚሰራም አቶ ነብዩ መግለጻቸውን ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%89%a5%e1%88%8d%e1%8c%bd%e1%8c%8d%e1%8a%93-%e1%8d%93%e1%88%ad%e1%89%b2-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%89%80%e1%88%8c-%e1%8c%bd%e1%88%85%e1%8d%88%e1%89%b5/ | 136 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየሰራ እነደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል፡፡በትግራይ ክልል ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተጀምሮ ባለበት በዚህ ወቅት የቀጠናውን አለመረጋጋት የሚፈልጉ አካላት የተሳሳተና አሉታዊ ነገሮችን በአለም አቀፍ መገናኛ እያሰራጩ ነው ተብሏል፡፡አምባሳደር ዲና የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ እነደሆነም ተናግረዋል፡፡ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ወደ ሱዳን ካርቱም አቅንተው በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተዋል ያሉት አምባሳደር ዲና፣ ሱዳን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ህግ በምታስከብርበት ወቅት ሱዳን የዲፕሎማሲ ድጋፏን አሳይታለች፤ ዜጎች ሲሰደዱም አስተናግዳለች፤ ይሄም እንደ በጎ ሊታይ የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡አሁን ላይ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ ውጥረቱ ቢቀንስም ሙሉ በሙሉ እንዲፈታ መንግስት እየሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው ግጭት የሁለቱን ሀገራት የቀደመ ታሪክ የማይመጥን ነው ተብሏል፡፡በቀጠናው አለመረጋጋት የሚያተርፉ አካላት ሁኔታዎች እንዲባባሱ እየሰሩ ነው የተባለ ሲሆን ሱዳናውያኑንም መሬቱ የናንተ ነው የሚል ቅስቀሳ በማድረግ በሀገራቱ መካከል ግጭት እንዲፈጠር ስለማድረጋቸው ተነስቷል፡፡በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ከመካከለኛው ምስራቅ 328 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡በሳምንቱ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ የዲፕሎማሲ ስራዎች መሰራታቸው የተነገረ ሲሆን ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን ማፍሰስ ከሚፈልጉ አካላት ጋር ውይይት መደረጉም ተነግሯል፡፡ለአንድ ወር ተቆርጦ የነበረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር በመጪው እሁድ እንደሚጀመርም ታውቋል፡፡(በመስከረም ቸርነት) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae-%e1%88%b1%e1%8b%b3%e1%8a%95-%e1%8b%b5%e1%8a%95%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8d%88%e1%8c%a0%e1%88%a8%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%8c%8d%e1%8c%ad%e1%89%b5/ | 190 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የጁንታው ቡድን የህግ ማስከበር ዘመቻው በንጹሃን ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ አድርጎ የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ላይ ይገኛል- አምባሳደር ግርማ ተመስገን | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | “የጁንታ ቡድን የህግ ማስከበር ዘመቻው በንጹሃን ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጽዳት እንደሆነ አድርጎ በሚከፍላቸው የመገናኛ ብዙሃን እና ግለሰቦች በኩል የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ላይ ይገኛል” ሲሉ በቱርክ የኢትዮጰያ አምባሳደር ግርማ ተመስገን ገለጹ።አምባሳደር ግርማ ተመስገን በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች እና ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ስላላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ ከአናዶሉ ኤጀንሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።የጁንታ ቡድን በትግራይ ክልል ሆኖ ለ20 አመታት የሀገር ሉዓላዊነት ሲያስከብር በነበረው መከላከያ ሰራዊት ላይ ይቅር የማይባል ጥቃት ከመፈጸሙ በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች ንጹሃኖች እንዲገደሉ አድርጓል ብለዋል፡፡አምባሳደር ግርማ መንግስት ወደ ህግ ማስከበር እርምጃው ተገዶ እንዴት እንደገባ ሲገልጹ ፤የጁንታው ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ አረመኔያዊ ጥቃት ፈጽሞ ”ቀይ መስመር ማለፉን” ተናግረዋል።የህወሃት ቡድን የጭካኔ ድርጊት ይህ ሆኖ ሳለ መንግስት የወሰደው ወታደራዊ ዘመቻን በተሳሳተ መንገድ የሚወስዱ አካላት ትክክለኛውን የዘመቻው መነሻ መረዳት ይኖርባቸዋል ነው ያሉት።የህግ ማስከበር ዘመቻው መቀሌ ከተማን በመቆጣጠር እንደተጠናቀቀ ያስረዱት አምባሳደር ግርማ ተመስገን በአሁኑ ወቅት አጣዳፊዎቹ የመንግስት ተግባራት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ማቋቋም፣ሰብዓዊ ዕርዳታ ማቅረብ መሆኑን ጠቁመዋል።ለዚህም የመሰረተ ልማቶችን እንደገና በመገንባት ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ስራዎች እየተሰሩ ነው።አምባሳደሩ የህወሃት ቡድን የመንግስትን የህግ ማስከበር እርምጃ አለማቀፋዊ ገጽታ ለማላበስ ሞክሯል ብለዋል።ቡድኑ ግጭቱን አለም አቀፋዊ ለማስመሰል ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱን እና ኢጋድና የአፍሪካ ህብረት ጉዳዩ የሃገር ውስጥየህግ ማስከበር ዘመቻ መሆኑን እንደተገነዘቡ ተናግረዋል።በሌላ በኩል በቱርክ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የሚደነቅ መሆኑን ለአናዶሉ ኤጀንሲ ገልጸዋል።አክለውም ቱርክ በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ቀድመው ከተረዱ ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗን ተናግረዋል።ለዚህም ያስረዱት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በዚሁ ጉዳይ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡አምባሳደሩ የሁለቱ ሀገራት ትብብር የረጅም ጊዜ አጋርነትና የጠንካራ ግንኙነት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።ኢትዮጵያ እና ቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 125ኛ አመት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አምባሳደር ግርማ ተመስገን ማናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8c%81%e1%8a%95%e1%89%b3%e1%8b%8d-%e1%89%a1%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8c%8d-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%89%a0%e1%88%ad-%e1%8b%98%e1%88%98%e1%89%bb%e1%8b%8d-%e1%89%a0/ | 252 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በጣሊያን ኤምባሲ ላለፉት 30 ዓመታት ተጠልለው የቆዩት ተከሳሾች መለቀቃቸውን ተከትሎ የጣሊያን መንግስት አድናቆቱን ገለፀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | በጣሊያን ኤምባሲ ላለፉት 30 ዓመታት ተጠልለው የቆዩት ተከሳሾች ካሉበት የተከለለ ውስን ስፍራ መለቀቃቸውን ተከትሎ የጣሊያን መንግስት አድናቆቱን ገለፀ፡፡በጣሊያን ኤምባሲ ላለፉት 30 ዓመታት ተጠልለው የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህና ሌተናል ጄኔራል አዲስ ተድላ ተጠልለው ካሉበት የተከለለ ውስን ስፍራ መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡ይህን ተከትሎም የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ኢማኑላ ክላውዲያ ዴል ሪ ለኢትዮጵያ መንግስት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ሚኒስትሯ ጣሊያን በየትኛውም ቦታ እና በማንኛውም ጊዜ የሞት ቅጣትን አትቀበልም ያሉ ሲሆን በርግጠኝነት አንድ የድሮ የታሪክ ገፅ ተቀይሯልም ብለዋል፡፡እንዲሁም ጣልያን እና ኢትዮጵያ ረጅም እና የበለፀገ መንገድን በጋራ ይጓዛሉ ማለታቸውን ከሚኒስትሯ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8c%a3%e1%88%8a%e1%8b%ab%e1%8a%95-%e1%8a%a4%e1%88%9d%e1%89%a3%e1%88%b2-%e1%88%8b%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-30-%e1%8b%93%e1%88%98%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%89%b0%e1%8c%a0%e1%88%8d%e1%88%88/ | 88 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የፑሽኪን አደባባይ – ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ግንባታን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታወቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | ከአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ በጎፋ ማዞሪያ ጎተራ ማሳለጫ ድረስ እየተሰራ የሚገኘው የመንገድ ፕሮጀክት የግንባታ ስራውን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቅ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8d%91%e1%88%bd%e1%8a%aa%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%8b%b0%e1%89%a3%e1%89%a3%e1%8b%ad-%e1%8c%8e%e1%89%b0%e1%88%ab-%e1%88%9b%e1%88%b3%e1%88%88%e1%8c%ab-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88/ | 26 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የሰላም ሚኒስቴር ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር የተግባር እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | የሰላም ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሰላማዊ የሆነ ሲቪል ሰራተኛ በመገንባ ህብረተሰቡን ማገልገል የሚችልና ዜጋውን የመገንባት አቅም ያለው የመንግስት ሰራተኛ ለመፍጠር ይቻል ዘንድ ከተቋሙ ጋር በጋራ መስራት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል ፡፡በልዩ ድጋፍና አርብቶ አደር አካባቢዎች የሰው ሀይል ማሟላትና ክትትል ማድረግ፣ የብሔራዊ በጎ ፍቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ተሳታፊዎች ድጋፍና ክትትል ማድረግ ፣ ለህዝብ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት የሰላም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን የሚሉ ጉዳዮች በሁለቱ ተቋማት የጋራ እቅድ ላይ ተካቷል፡፡የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ በዛብህ ገብረየስ እንደተናገሩት የተዘጋጀው የጋራ እቅደ በጋራ ለምናከናውናቸው ተግባራት የተሰጠንን ሀላፊነት ለመወጣት የሚያስችል እቅድ መሆኑን ገልፀው ኮሚሽኑ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ለመወጣት ዝግጁነትን ገልፀዋል፡(ምንጭ፡-የሰላም ሚኒስትር) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b4%e1%88%ad-%e1%8a%a8%e1%88%b2%e1%89%aa%e1%88%8d-%e1%88%b0%e1%88%ad%e1%89%aa%e1%88%b5-%e1%8a%ae%e1%88%9a%e1%88%bd%e1%8a%95/ | 96 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የጊዳቦ ግድብ የአርብቶ አደሩን ህይወት እየቀየረ መሆኑ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ወጭ የተገነባው የጊዳቦ ግድብ የአርብቶ አደሩን የህይወት አቅጣጫ እየቀየረ ነው ሲሉ የምስራቅ ጉጂ አርብቶ አደሮች ተናገሩ።በደቡብ በኩል በሲዳማ ክልል እና በምስራቅ በኩል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን የሚዋሰነው የጊዳቦ ግድብ ግንባታ 2002 ዓ.ም ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ተጓቶ በ2011ዓ.ም ወደ ስራ የገባ ቢሆንም አሁን ላይ የአካባቢውን ስነ ምህዳር እየቀየረ ነው ተብሏል፡፡የምስራቅ ጉጂ አካባቢ ማህበረሰቦች ከዚህ ቀደም ኑሯቸውን ሙሉሙሉ የመሠረቱት በእንስሳት እርባታ እንደነበር እና የእርሻ ልምዱም እንዳልነበራቸው ገልጸው አካባቢውን በመስኖ እንዲለማ ታስቦ የተገነባው የጊዳቦ ወንዝ የአካባቢውን አርብቶአደር ማህበረሰቡን አርሶአደር አድርጎታል ብለዋል።በእቅድ ከ300 በላይ የሚሆኑ አርብቶና አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ሲሆኑ በእርሻ ስራውም ስንዴን ጨምሮ የተለያዩ አትክልቶች ይመረታሉ።በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን የተናገሩት አርሶና አርብቶ አደሮቹ የከብት እርባታው ላይ በቂ የሆነ የህክምና አገልግሎት ባለመኖሩ የተነሳ በበሽታ እየተጎዱባቸው በመሆኑ መንግስት ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።በአካባቢው ላይ ጉብኝት እያደረገ ያለውን የክልሉን ልኡክ አየመሩ የሚገኙት በመስተዳድር ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ግርማ ዶ/ር አመንቴ በበኩላቸው ኑሮውን በእንስሳት እርባታ ላይ መስርቶ የነበረው የአካባቢው ነዋሪ ገበሬውን ማስተማር ከተቻለ ሁሉንም ማድረግ እንደሚችሉ ምስክር ናቸው ብለዋል፡፡መንግስታቸው አካባቢውን ለመለወጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር አመንቴ ሁሉንም የአካባቢውን አቅም ለመጠቀም ነዋሪዎቹ ያነሷቸውን የመስኖ ውሃ ተደራሽነትን ጨምሮ ሌሎች ጥያቄዎችን የክልሉ መንግስት ከሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት ጋር ተመካክሮ ምላሽ ለመስጠት መወሰኑን ገልጸዋል።ከዚህም በተጨማሪ የጊዳቦ ግድብን ጨምሮ በሌሎች የመስኖ ግድቦች ላይ እቅድ ተነድፎ ወደ ስራ መገባቱንም ተናግረዋል።በቀጣይ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተያያዥ የትምህርት ዘርፍ የተመረቁ ተማሪዎችን አደራጅቶ በማሰልጠን በነዚህ ግድቦች በመታገዝ ወደ ዘመናዊ የግብርና ምርት እና ንግድ እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል።(በሚልኪያስ አዱኛ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8c%8a%e1%8b%b3%e1%89%a6-%e1%8c%8d%e1%8b%b5%e1%89%a5-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%ad%e1%89%a5%e1%89%b6-%e1%8a%a0%e1%8b%b0%e1%88%a9%e1%8a%95-%e1%88%85%e1%8b%ad%e1%8b%88%e1%89%b5-%e1%8a%a5/ | 227 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔውን እያካሄደ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን እካሄደ ነው ፡፡ምክር ቤቱ በመተከል ዞን በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የህሊና ጸሎት በማድረግ ነው ጉባዔውን ማካሄድ የጀመረው።ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባዔው ከመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት ያነሳል ተብሎም እንደሚጠበቅም የቤንሻንጉል ጉምዝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%a4%e1%8a%95%e1%88%bb%e1%8a%95%e1%8c%89%e1%88%8d-%e1%8c%89%e1%88%99%e1%8b%9d-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%88%ad-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%89%b8/ | 58 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር በማሻቀብ ላይ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር በማሻቀብ ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሰፈሩት የጽኑ ሕሙማን ክፍል ያለውን ዐቅም ሁሉ አሟጦ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።በዚህ ወቅት፣ በፍጹም የጥንቃቄ ርምጃዎችን ቸል ልንል አይገባም።የራሳችንን ሕይወት እንታደግ፣ የሌሎችንም ሕይወት እናትርፍ! የአፍ እና የአፍንጫ ጭንብሎችን በአግባቡ በመጠቀም የጤና ባለሞያዎቻችንን እናግዝ ሲሉ መልዕክታቸውን አስፍረዋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%89%aa%e1%8b%b5-19-%e1%89%b3%e1%88%9b%e1%88%9a%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%89%81%e1%8c%a5%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%9b%e1%88%bb%e1%89%80%e1%89%a5-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8a%90%e1%8b%8d/ | 50 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ስርጭቱ እንደ አዲስ ያገረሸባት ደቡብ አፍሪካ ገደቦችን አስቀመጠች | ዓለም አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | በደቡብ አፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከአንድ ሚሊየን መሻገራቸውን ተከትሎ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አዲስ ጠበቅ ያሉ ገደቦችን አውጥተዋል፡፡ቤት ውስጥና ከቤት ውጪ ሰዎች መሰብሰብ፣ከመሸ በኋላ እንቅቃሴ ማድረግና ማንኛውም አይነት የአልኮል መጠጥም መሸጥ ተከልክሏል፡፡ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ደቡብ አፍሪካ በወረርሽኙ ምክንያት አስፈሪና አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መድረሷን ጠቅሰው አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ግድ አንዳላቸው አስረድተዋል፡፡አንዳንድ ሆስፒታሎችና የሕክምና ማዕከላት በርካታ ሰዎችን ተቀብለው እያስተናዱ እንደሆነና የግብአት እጥረት እያጋጠማቸው ስለመሆኑም እየገለጹ ነው።ይህንን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት ”501.V2 የሚባል አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተገኝቷል።በአሁኑ ሰአት በርካታ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ መሆኑ በጣም አሳሳቢ ያደርገዋል። የጥንቃቄ እርምጃዎቻችንን ችላ ማለታችን ነው ለዚህ ያበቃን” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ አክለውም አዲሶቹ ጥብቅ ገደቦች ከሰኞ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንና ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።”ከቀብር ስነ ስርአት ውጪ ማንኛውም አይነት ሰዎችን የሚያሰባስብ ማህበራዊ ክንውን ተከልክለሏል፣ ሰዎች ከመሸ በኋላ መንቀሳቀስ አይችሉም፣ ሁሉም ሱቆች፣ መጠጥ ቤቶችና ምግብ ቤቶች ልክ ከምሽቱ ሁለት አሰት ላይ መዘጋት አለባቸው” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።የአልኮል መጠጦችን መሸጥም ቢሆን የተከለከለ ሲሆን ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ ግዴታ ነው ሲል ቢቢሲ አስነብቧል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%88%b5%e1%88%ad%e1%8c%ad%e1%89%b1-%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8b%b0-%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8b%ab%e1%8c%88%e1%88%a8%e1%88%b8%e1%89%a3%e1%89%b5-%e1%8b%b0%e1%89%a1%e1%89%a5-%e1%8a%a0%e1%8d%8d/ | 158 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
የኢትዮጵያ የዳያስፖራ የምክክር መድረክ በደቡብ አፍሪካ ተካሄደ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በደቡብ አፍሪካ ከሚኖሩ የዳያሥፖራ አባላት፣ የኮሚዩኒቲ አመራሮችና የተለያዩ አደረጃጀቶች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች እና የሚዲያ አካላት በተገኙበት የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡በዳያስፖራው የተፈጠረውን መነሳሳትና የአንድነት ስሜት ቀጣይነት ባለው መልኩ በሀገር ልማትና ዕድገት ለማሳተፍ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታውቋል።የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሠላማዊት ዳዊት የዳያስፖራ አባላት በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በዕውቀት ሽግግር፣ ወደ ሃገር በሚላክ የውጭ ምንዛሪና በሌሎች ወሳኝ የሀገር ልማት ጉዳዮች ላይ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ ለማጠናከርና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል።በምክክር መድረኩ ኤጀንሲው ባለፉት ሁለት ዓመታት ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች በኤጀንሲው የሥራ ሃላፊዎች ቀርቧል።ኤጀንሲው ዳያስፖራው በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ያለምንም የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ለማገልገል የሚያስችል ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በማካሄድ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡ዳያስፖራው በትላልቅ ሃገራዊ ፕሮጀክቶች አሻራውን በማኖር ረገድ በተለይም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉም ተጠቅሷል፡፡ኤጀንሲው ዳያስፖራው በሀገራዊ ልማት በበለጠ እንዳይሳተፍ ማነቆ የሆኑት፣ በየደረጃው ፈጣን ምላሽ ያለመስጠት፣ የባለድርሻ አካላት በቅንጅት አለመስራት፣ የተጠና ፕሮጀክት አለመኖር፣ የመሰረተ ልማት አለመሟላት፣ በቂ ገንዘብ ሳይዙ መሬት የማግኘት ፍላጎት እንዲሁም ከኢንዱስትሪ ይልቅ ወደ አገልግሎት ዘርፍ የማዘንበል ችግሮች መኖራቸውንም አመላክቷል።ዳያስፖራው በሀገሩ ጉዳይ በያገባኛል መንፈስ እንዲሳተፍ ሃገራዊ የዳያስፖራ ምክር ቤት ለማቋቋም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በደቡብ አፍሪካ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።አሁን ላይም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት የተለያዩ አደረጃጀቶች ህብረት ለመመስረት ከማህበራት የተውጣጡ አደራጅ ኮሚቴ ለሟቋቋም መስማማታቸውን እና ህብረቱን ለመመስረት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ በሀገራዊ ዳያስፖራ ምክር ቤት የሚወክሏቸውን አመራር በመምረጥ ተሳትፏቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቀዋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8b%b3%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%8d%96%e1%88%ab-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%8a%ad%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%8b%b5%e1%88%a8%e1%8a%ad/ | 233 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በመቐለ ከተማ የባንክ አገልግሎት መስጠት ተጀመረ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown | በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የባንክ አገልግሎት በመቐለ ከተማ መጀመሩን የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ሀይለስላሴ አስታወቁ።ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ከሰሞኑ ባካሄደው ተከታታይ ውይይት የተነሳውን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ በተደረገው የተቀናጀ ስራ ከዛሬ ከሰአት በሁዋላ ጀምሮ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ከንቲባው ገልፀዋል።የከተማዋ ነዋሪና ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረትም የባንክ አገልግሎቱ ከዛሬ ከሰአት ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኖ ደንበኞች መጠቀም መጀመራቸው ነው የተገለፀው።የግል ባንኮችም አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ትዛዝ እንደተላለፈላቸው የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ አስታውቀዋል። (ምንጭ ፡- ኢፕድ) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%90%e1%88%88-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b-%e1%8b%a8%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ad-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8c%8d%e1%88%8e%e1%89%b5-%e1%88%98%e1%88%b5%e1%8c%a0%e1%89%b5/ | 75 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ምርጫ ቦርድ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሰረዘ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown |
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማለትም የመላው ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን እና የሲዳማ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን መሰረዙን አስታውቋል።ቦርዱ በታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሰረት ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እንዲያሟሉ ከተጠየቁት መካከል የሚከተሉት አራት ፓርቲዎች መስፈርቱን እንዳሟሉ አስታውቋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab-%e1%89%a6%e1%88%ad%e1%8b%b5-%e1%88%98%e1%88%b5%e1%8d%88%e1%88%ad%e1%89%b6%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8b%ab%e1%88%8b%e1%88%9f%e1%88%89-%e1%88%81%e1%88%88%e1%89%b5-%e1%8b%a8/ | 42 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
“ገበታ ለአገር ፕሮጀክት አገራዊ የአንድነት ስሜት ፈጥሯል”- የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown | የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት እንደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ አገራዊ የአንድነት ስሜት መፍጠሩን የሀይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ ገለጹ።የፋውንዴሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በአገሪቷ በተፈጥሮ ብቻ የተገኙ በርካታ ድንቅ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።እነዚህ የተፈጥሮ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ታሪካዊ አሻራ ያረፈባቸው እና እምቅ ሀብትና ቅርሶችን ጭምር የያዙ በመሆናቸው እንደ “ገበታ ለሀገር” አይነት ፕሮጀክቶች መጠናከር አለባቸው ብለዋል።ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷ ብቻ በቢሊየን ብር የሚቆጠር ገቢ ስለሚያመጣ ሀብቱን ጥቅም ላይ በማዋል ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻልም አንስተዋል።እንደ “ገበታ ለአገር” ያሉ ፕሮጀክቶችን አቅም በፈቀደ መጠን ማስፋት እንደሚገባና ሕዝቡም ለዚህ ድንቅ ዓላማ ድጋፍ በማድረግ መሳተፍ እንዳለበት ጠቁመዋል።ወይዘሮ ሮማን የ”ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የፈጠረውን አይነት አገራዊ የአንድነት ስሜት መፍጠሩንም ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቱሪዝም ዘርፍ እንዲያንሰራራ ያደርጋል ያሉትን “ገበታ ለሀገር” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል።በዚህም ትኩረት ተነፍጎት የቆየው የአገሪቷን የተፈጥሮ ሀብት የማልማት ስራ በጎርጎራ፣ በኮይሻና በወንጪ አካባቢዎች ለመስራት ታቅዶ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። ዘገባው የኢዜአ ነው፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8c%88%e1%89%a0%e1%89%b3-%e1%88%88%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%ad-%e1%8d%95%e1%88%ae%e1%8c%80%e1%8a%ad%e1%89%b5-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8b%b5/ | 144 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመንገድ ፣ የወደብ አገልግሎቶችን እና የመኪና ማቆሚያ ጣቢያዎችን ይዘት ለማሻሻል ተስማሙ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown | በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጅቡቲ ወደቦች ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ሊቀመንበር ክቡር አቶ አቡባከር ኦመር ሀዲ ጋር ውይይት አድርገዋል።በውይይቱ የመንገድ እና ወደብ ሥራ እንዲሁም፤ የመኪና ማቆሚያ አቅም ለማጎልበት ስምምነት ላይ ፡፡አምባሳደር ብርሃኑ ለሁለቱ አገራት ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክተው የዲኪል-ዳጉሩ መንገድ በፍጥነት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ መከታተል አስፈላጊ መሆኑን በአጽኖት አንስተዋል፡፡የቀሪው 80 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ተስማምተዋል ፡፡በተጨማሪም የዶራሌ ሁለገብ ወደብ እና የጅቡቲ ኮንቴይነር ተርሚናልን ከኢትዮጵያ-ጅቡቲ የባቡር ሀዲድ ጋር በማገናኘት የወደብ አገልግሎቶችን አቅም ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል ፡፡በውይይቱ የጅቡቲ ሆራይዘን ነዳጅ ማደያን እና በአዋሽ የሚገኘው የኢትዮጵያ የነዳጅ ማከማቻን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት ከስምምነት ላይ ተደርሷል።ይህም የነዳጅ ጭነት ፍሰትን በማቀላጠፍ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመከላከል ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተገልጿል ፡፡ከደረቅ የመኪና ማቆሚያ ተርሚናል ጋር ተመሳሳይ የሆነ አስተዳደራዊ አሠራር ለማስቀመጥ በማሰብ ለነዳጅ ተርሚናል የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ መንግሥት ያቀረበው ጥያቄም በወደብ እና በነፃ ዞን ባለሥልጣን ተቀባይነት ማግኘቱ ን ማወቅ የተቻለ ሲሆን፤ ሊቀመንበሩ የባለቤትነት ማረጋገጫ ወረቀቱን ለኢትዮጵያ ወገን በፍጥነት ለመስጠት ቃል መግባታቸዉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8c%85%e1%89%a1%e1%89%b2-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%8b%b5-%e1%8d%a3-%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%8b%b0%e1%89%a5-%e1%8a%a0/ | 166 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የኢትዮ- ኬንያ መንገድ የኢትዮጵያን የወደብ አማራጭ እንደሚያሰፋ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 29, 2020 | Unknown | የአፍሪካ አህጉር አቋራጭ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነውና በቅርቡ የተመረቀው የኢትዮ- ኬንያ መንገድ የኢትዮጵያን የወደብ አማራጭ የሚያሰፋ መሆኑ ተገለጸ።በኢትዮጵያ በኩል ከሀዋሳ ሞያሌ 500 ኪሎ ሜትር እና በኬንያ በኩል ደግሞ ከኢሲኦሎ እስከ ሞያሌ የ503 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ ተጠናቆ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መመረቁ ይታወሳል።የአፍሪካ አህጉር አቋራጭ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው መንገድ አዲስ አበባን ከካይሮ፣ ጋቦሮኒ፣ ኬፕ ታውን እና ኬንያ-ሞምባሳ የሚያገናኝ ከመሆኑም ባሻገር ደቡብ ሱዳንን-ከኬንያ ላሙ ወደብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ነው።በብሔራዊ ሎጅስቲክ ምክር ቤት የሎጅስቲክ ትራንስፎስሜሽን ጽህፈት ቤት የሎጅስቲክ ባለሙያው አቶ ተመስገን ይሁኔ ለኢዜአ እንዳሉት መንገዱ ለንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ትስስር ካለው ጠቀሜታ ባሻገር በወደብ ተጠቃሚነት የኢትዮጵያን የመደራደር አቅም የሚያሳድግ ነው።ግንባታው ሲጠናቀቅ በአንድ ጊዜ 32 መርከቦችን ማስተናገድ የሚችለውን የላሙ ወደብ ለመጠቀም መንገዱ ያለውን ፋይዳም አስረድተዋል።ወደቡ በተለይ ለደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ የወጪና ገቢ ንግድን ለማሳለጥም ከፍ ያለ ፋይዳ እንዳለው አስረድተዋል።በተለይም የኢንዱስትሪ መንደር ለሆኑት ሀዋሳ፣ ይርጋለምና ያቤሎ አካባቢዎች ጥሩ አማራጭ በመሆን ጊዜና ገንዘብ ይቀንሳል ብለዋል።የመንገዱ መገንባት ከትራንስፖርትና ወደብ ታሪፍ አንጻር አማራጭ በመሆን የኢትዮጵያን የወደብ መደራደር አቅም እንደሚያሳድግም ተናግረዋል።ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ያላትን የንግድ ትስስር ከማሳደግ በተጨማሪ ምርቶቿን ለአለም ገበያ የማቅረቢያ ዋና ኮሪደር ሆኖ ያገለግላልም ብለዋል።የመንገዱ መገንባት 3 ቀናትና ከዚያ በላይ ይፈጅ የነበረውን የየብስ ትራንስፖርት ጉዞ ወደ 10 እና 8 ሰአት ዝቅ አድርጎታል ብለዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው ኢትዮጵያና ኬንያ በሰላም ማስከበርና በፖለቲካ ዘርፍ ያላቸውን ጠንካራ ግንኙነት በምጣኔ ሃብትም የማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለቸው ገልጸዋል።በመሆኑም የኢትዮ-ኬንያ መንገድ በተለይ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ለማሳለጥ ከፍ ያለ ፋይዳ እንዳለው አንስተዋል።እንደ አምባሳደር ዲና ገለፃ “ሞያሌን የአካባቢው ዱባይ” የማድረግ ፍላጎትና እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው።ከሐዋሳ-ሞያሌ የሚዘልቀው 500 ኪ.ሜ መንገድ እና የጋራ ፍተሻ ኬላ የጉምሩክ፣ የኢሚግሬሽን፣ የጤና እና የደረጃ ድርብርብ ፍተሻ የሚያስቀር መሆኑንም ገልጸዋል።በዚህም የጉምሩክ ሥርዓቱን ግልጽ፣ ቀላል እና ቀልጣፋ ያደርገዋል ተብሏል።አፍሪካን ለማስተሳሰር በህብረቱ በእቅድ የተያዘው የትራንስ አፍሪካ ሃይዌይ መንገድ አካል የሆነው ይህ መንገድ ሌሎች የአፍርካ አገራትንም የሚያስተሳስር ይሆናል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae-%e1%8a%ac%e1%8a%95%e1%8b%ab-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%8b%b5-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8a%95-%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%8b%b0/ | 286 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ ተረከበ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown | በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ መረከቡን ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ አስታወቁ።በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመውና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች የተካተቱበት ግብረ ኃይል በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል።የፀጥታ ኃይሉን የሚመሩት ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እንደገለጹት፤ የንፁሃንን ሕይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የማደን ስራው ቀጥሏል።“በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአጭር ጊዜ የሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉም ተናግረዋል።ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በአሁኑ ወቅት በየደረጃው ከሚገኙ የማኅበረሰብ አባላትና አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን ወንጀለኞቹን በመለየት ለሕግ የማቅረቡ ስራም እንደሚቀጥል ሜጀር ጄኔራሉ ተናግረዋል።ከዚህ ጎን ለጎን የተፈናቀሉትን መልሶ የማቋቋምና የሕዝቡን የዕለት ተዕለት ኑሮ ቀድሞ ወደነበረበት የመመለስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ “በመተከል ዞን የተጀመረው የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተልዕኮ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል” ብለዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው። | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8c%a0%e1%89%85%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%a9-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%89%8b%e1%89%8b%e1%88%98%e1%8b%8d-%e1%8c%8d%e1%89%a5%e1%88%a8-%e1%8a%83%e1%8b%ad/ | 119 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የ10 አመታት የልማት እቅድን በተመለከተ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown | የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ኮሚሽን ባዘጋጀው የ10 አመታት የልማት እቅድን በተመከለተ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው፡፡በ10 አመታት የልማት እቅዱ ከተለተያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እየተደረገበት የሚገኝ ሲሆን፣ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የሚደረገው የ2 ቀናት ውይይት የውይይቱ አካል ነው ተብሏል።በውይይቱ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እቅድ ወዳሰብነው ውጤት ሊያደርሰን የሚችል መሳሪያ መሆኑን ገልጸው፣ ከለውጡ በፊት በነበረው ጊዜ ህዝቡን ለማድመጥ ባለመቻላችን በርካታ ችግርች ተከስተዋል ብለዋል።ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚመከርበት የልማት እቅዱ ባለድርሻ አካላት በየደረጃው የተሳተፉበት እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ባለፉት አመታት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ጨምሮ በአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ የ10 አመቱን እቅድ አስፈላጊነት እንዲሁም ልዩ ባህሪያትን ለተወያዮች አቅርበዋል።ኮሚሽኑ ያዘጋጀው ከ2013 እስከ 2022 የበጀት አመታት ድረስ ያለው የ10 አመት የልማት እቅድ ሰነድ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ታህሳስ 2 ቀን 2013 መፅደቁ ይታወሳል።(በቁምነገር አህመድ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a810-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%89%b3%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%88%8d%e1%88%9b%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%89%85%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%88%98%e1%88%88%e1%8a%a8%e1%89%b0-%e1%8a%a8%e1%88%85/ | 144 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ሜጀር ጄነራል ቹሃድ ዋሃሪ በደቡብ ሱዳን የተሰማራውን 14ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ጎበኙ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown | በተባበሩት መንግስታት በደቡብ ሱዳን የዩናሚስ ምክትል ሃይል አዛዥ ሜጀር ጄነራል ቹሃድ ዋሃሪ በ14ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የስራ ጉብኝት አደረጉ ፡፡የ14ኛ ሞተራይዝድ ዋና አዛዥ ኮ/ል መለስ መንግስቴ አቅራቢነት ፣ በግዳጅ አፈፃፀም እና ግዳጅን ለመፈፀም መሰናክል ስለሆኑ ችግሮች ሻለቃው ቀጣናውን ከተረከበ ጀምሮ የተከናወኑ ስራዎች አፈፃፀም ላይ ውይይት ተደርጓል ፡፡በተለይም በሃገራችን የሰሜኑ ክፍል እየተወሰደ ባለው ህግ ማስከበር ዘመቻ በሻለቃው ዋና አዛዥ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል ፡፡ሜጀር ጀነራል ቹሃድ በበኩላቸው ፣ ሻለቃው ቀጠናውን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ የደቡብ ሱዳን የሰላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልፀው ውጤታማ ስራ በማከናወናችሁ እንኮራባቹሃለን ብለዋል ፡፡በወቅቱ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ጉዳይ ሲከታተሉት መቆየታቸውን እና በተደረገላቸው ገለፃ ሁኔታውን በአግባቡ መረዳታቸውን ገልፀው ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ልማትን ተመኝተዋል።(ምንጭ ፡- የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ) | https://waltainfo.com/am/%e1%88%9c%e1%8c%80%e1%88%ad-%e1%8c%84%e1%8a%90%e1%88%ab%e1%88%8d-%e1%89%b9%e1%88%83%e1%8b%b5-%e1%8b%8b%e1%88%83%e1%88%aa-%e1%89%a0%e1%8b%b0%e1%89%a1%e1%89%a5-%e1%88%b1%e1%8b%b3%e1%8a%95-%e1%8b%a8/ | 107 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ከ75.5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown | በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ግምታዊ ዋጋቸው 75 ሚሊየን 574 ሺህ 275 ብር የሚገመት ዕቃ ከታህሳስ 9 እስከ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ተይዟል፡፡ከዚህ ውስጥ ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር የተያዘው 63 ሚሊየን 704 ሺህ 085 ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ሲሆን የተቀረው ደግሞ ከሀገር ሊወጣ ሲል የተያዘ ነው፡፡በተጠቀሰው ጊዜ ከተያዘው የኮንትሮባንድ እቃ ውስጥ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 312 ኩንታል ቡና፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ አደንዛዥ እፆች፣ መድኃኒቶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ የመለዋወጫ እቃዎች፣ የተለያዩ አልባሳት እና የቀንድ ከብቶች ይገኙበታል፡፡እቃዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩ 19 ተጠርጣሪ ግለሰቦች ደግሞ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት በፍተሻ፣ በብርበራ እና በተሽከርካሪ በመከታተል ሲሆን የጉምሩክ ሰራተኞች እና አመራሮች ከፌደራል እና ክልል ፖሊስ አባላት ጋር በቅንጅት በመስራት እነዚህን የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል፡፡(ምንጭ፡- የገቢዎች ሚኒስቴር ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a875-5-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%ae%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8c%8d%e1%88%9d%e1%89%b3%e1%8b%8a-%e1%8b%8b%e1%8c%8b-%e1%8b%ab%e1%88%8b%e1%89%b8%e1%8b%8d-%e1%8b%a8/ | 118 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ዶ/ር ሊያ ታደሰ በፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ጉብኝት አደረጉ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown | የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በባህር ዳር በሚገኘው ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል የንፁህና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆስፒታል የማድረግ እንቅስቃሴን ጎበኙ፡፡ሚኒስትሯ በማህበራዊ ገፃቸዉ እንደገለፁት በኤሌክትሮኒክስ የታገዘ የጤና መዛግብት አፈፃፀም እና የአገልግሎት መስጫ ቦታዎች ህሙማንን ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑ ለማስቻል የተሰራውን ስራም ጎብኝተዋል፡፡በጉብኝታቸው ወቅትም በቁርጠኝነት የሚሰሩ የሆስፒታሉንና የክልሉ ጤና ቢሮ አመራሮችንና ሰራተኞችን አመስግነዋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%b6-%e1%88%ad-%e1%88%8a%e1%8b%ab-%e1%89%b3%e1%8b%b0%e1%88%b0-%e1%89%a0%e1%8d%88%e1%88%88%e1%8c%88-%e1%88%95%e1%8b%ad%e1%8b%88%e1%89%b5-%e1%88%86%e1%88%b5%e1%8d%92%e1%89%b3%e1%88%8d-%e1%8c%89/ | 48 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በደቡብ አፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን አለፈ | ዓለም አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown | ደቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ አገራት መካከል ከአንድ ሚሊየን በላይ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን በመመዝገብ ቀዳሚዋ ሆነች።ይህ የሆነው የአገሪቱ ባለሥልጣናት በፍጥነት የሚስፋፋው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በአገሪቱ ውስጥ መገኘቱን ይፋ ካደረጉ ከቀናት በኋላ ነው።የተወሰኑ የደቡብ አፍሪካ ሆስፒታሎች እንዲሁም የሕክምና ማዕከላት በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሕሙማንን እየተቀበሉ መሆኑን ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን፣ ይህም ለኮሮናቫይረስ መከላከል የተመደበው ሀብት ላይ አደጋን ደቅኗል ነው የተባለው።ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቫይረሱ ይበልጥ እንዳይሰራጭ ለማድረግ ጠበቅ ያለ የእቅንቅስቀሴ ገደብ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።እሁድ ዕለት የአገሪቱ ጤና ሚኒስትር ዝዌሊ ምክሂዜ ይህንን አሳዛኝ ዜና ለአገራቸው ሕዝብ ይፋ አድርገዋል።አሁን ደቡብ አፍሪካ 1,004,413 በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች መኖራቸው በምርመራ ያረጋገጠች ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ 26,735 ያህሉ ሕይወታቸውን አጥተዋል።ባለፈው ሳምንት ብቻ 11,700 ደቡብ አፍሪካውያን በአንድ ቀን በቫይረሱ መያዛቸው የታወቀ ሲሆን፣ በዚህ የተነሳም ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነጻጸር በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በ39 በመቶ እንዲጨምር አድርጎታል።ከረቡዕ እስከ አርብ ድረስ ባሉት ቀናትም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በ14,000 መጨመሩ ተገልጿል።በደቡብ አፍሪካ አዲሱ 501.ቪ2 በመባል የሚታወቀው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ስርጭቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨመር እንዳደረገው ይታመናል።ይህ ዝርያ በደቡብ አፍሪካውያን ተመራማሪዎች በምሥራቃዊ ኬፕ አውራጃ እና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑ ተደርሶበታል።ከዚህ ሳምንት ቀደም ብሎ በዚሁ አዲስ የቫይረስ ዝርያ ምክንያት ዩናይትድ ኪንግደም ከደቡብ አፍሪካ የሚመጡ መንገደኞች ላይ እገዳ ጥላለች።በዩናይትድ ኪንግደም አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ መገኘቱ ይታወሳል።ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዳችው አፍሪካዊት አገር ሞሮኮ ስትሆን 432,079 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከእነዚህም መካከል 7,240 ያህሉ ሕይወታቸውን አጥተዋል።በመቀጠል ግብጽ 131,315 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 7,352 ሞተዋል፤ በተመሳሳይ በቱኒዚያም 130,230 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖራቸው ሲረጋገጥ 4,426 ሕይወታቸውን አጥተዋል። ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8b%b0%e1%89%a1%e1%89%a5-%e1%8a%a0%e1%8d%8d%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%89%a0%e1%8a%ae%e1%89%aa%e1%8b%b5-19-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8b%ab%e1%8b%99-%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%89%81%e1%8c%a5/ | 232 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
በአሚሶም የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ዘማቾች ሜዳይ ተሸለሙ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 28, 2020 | Unknown | በአሚሶም ሴክተር ሶስት ሰላም ማስከበር ተልኮ ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው ስድስተኛው ዙር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ዘማቾች ሜዳይ ተሸለሙ፡፡የሜዳልያውን የሴክተር ሶስት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አለሙ አየነ እና የ7ኛው ዙር ሰላም አስከባሪ አዛዥ ብ/ጄ ዘውዱ ሰጥአርጌ አልብሰዋል።ብ/ጄ አለሙ አየነ በስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ፣ መንግስትና ህዝባችን በከሃዲው ጁንታው እና በሌሎች ግብሮአበሮች ላይ በአጭር ግዜ ህግን በማስከበር ውጤታማ ኦፕሬሽን ተካሄዷል፤ ህገ መንግስቱም ተከብሯል፡፡መንግስትና ህዝባችን በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የማይደራደሩ መሆኑን ያስመሰከሩበት፣ በታሪክ ታላቅ ገድል የተፈፀመበት ነው ብለዋል፡፡ብ/ጄ አለሙ አባላቱ ፣ ተልዕኳቸውን ሃላፊነት በተሞላው መንፈስ የአፍሪካንና የአገራቸውን ክብር በማስጠበቅ በድል እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%88%9a%e1%88%b6%e1%88%9d-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%8a%a8%e1%89%a3%e1%88%aa-%e1%8b%98%e1%88%9b/ | 92 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጋምቤላ ባህላዊ የወርቅ ማምረቻና መሸጫ ቦታን ጎበኙ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡመድ ኡጁሉ ጋር በመሆን በጋምቤላ በጋምቤላ ባህላዊ የወርቅ ማምረቻና መሸጫ ቦታን ጎብኝተዋል።ሚኒሰትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው “ከሞቃታማው አየሯ ጀርባ ድንቅ ህዝብና ድንቅ ተፈጥሮ በያዘችው ጋምቤላ ክልል ተገኝቻለሁ” በማለት አስፍረዋል፡፡ጋምቤላ በወርቅና በተፈጥሮ ጋዝ ማዕድናት የታደለች ብትሆንም ከሀብቱ ጋምቤላም ኢትዮጵያም በሚገባው ልክ እየተጠቀሙ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ “በጉብኝቴ ሕገወጥ አዘዋዋሪዎችና የመሰረተልማት ችግር እንቅፋት መሆናቸውን ተረድቻለሁ፤ አብዛኛው የወርቅ ምርት በሕገወጥ መንገድ ከሀገር እየወጣ ይገኛል፤ ይህን አካሄድ ስርአት እናስይዛለን” ብለዋል።ኢንጂነር ታከለ ባህላዊ አምራቾችንም በተገቢው መንገድ በመደገፍ አቅማቸው እንዲያድግ እንሰራለን እና በየትኛውም የሀገራችን ጫፍ የሚገኝ የተፈጥሮ ፀጋ በተገቢው መንገድ ለህዝብና ሀገር ጥቅም እንዲውል ማድረግ የቅድሚያ ስራቸው እደሆነ ገልጸዋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%8c%82%e1%8a%90%e1%88%ad-%e1%89%b3%e1%8a%a8%e1%88%88-%e1%8a%a1%e1%88%9b-%e1%89%a0%e1%8c%8b%e1%88%9d%e1%89%a4%e1%88%8b-%e1%89%a3%e1%88%85%e1%88%8b%e1%8b%8a-%e1%8b%a8%e1%8b%88/ | 101 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በ’ገበታ ለሀገር’ ለመሳተፍ ገንዘብ ገቢ ላደረጉ ተቋማት አድናቆቱን ገለፀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በ’ገበታ ለሀገር’ ለመሳተፍ ገንዘብ ገቢ ላደረጉና ደረሠኙን በመላክ ላሳወቁ ተቋማት አድናቆቱን ገልጿል፡፡ተቋማቱ የሚከተሉት ናቸው፡-ሌሎች ተቋማትም የ5 እና የ10 ሚሊየን ብር አስተዋጾአቸውን ባንክ ያስገቡበትን ደረሰኝ በdineforethiopia@pmo.gov.et እንዲያደርሱት ጽ/ቤቱ ጠይቋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8c%a0%e1%89%85%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%8c%bd-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%8c%88%e1%89%a0%e1%89%b3-%e1%88%88%e1%88%80%e1%8c%88%e1%88%ad/ | 31 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ለሰብአዊ ድጋፍ የሚሆን ተጨማሪ የምግብ እህልና ሌሎች ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዙ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | ለሰብአዊ ድጋፍ የሚሆን ተጨማሪ የምግብ እህልና ሌሎች ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዙ መሆናቸው ተገለጸ።የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር መኮንን ሌንጂሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ተጨማሪ የምግብና ሌሎች ቁሳቁስ ወደ ስፍራው እየተጓጓዙ ነው።በትናትናው እለት ድጋፉን የጫኑ ዘጠኝ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ መቐሌ መጓዛቸውን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ በዚህም 2 ሺህ 900 ኩንታል ዱቄት፣ 280 ኩንታል መኮሮኒ፣ 438 ካርቶን የዱቄት ወተትና 200 ኩንታል ሩዝ አዳማ ከሚገኘው የኮሚሽኑ የእህል ማከማቻ መጋዘን ተጭኖ ወደ ስፍራው በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።በሰብአዊ እርዳታው እስካሁን ከ129 ሺህ ኩንታል በላይ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ወደ ስፍራው መጓጓዙንም ጠቅሰዋል።“የሚደረገው ሰብአዊ ድጋፍ ቀጣይነት ይኖረዋል” ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ በአገሪቱ ለ7 ወር የሚሆን የመጠባበቂያ የእህል ክምችት እንዳለም ተናግረዋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%88%88%e1%88%b0%e1%89%a5%e1%8a%a0%e1%8b%8a-%e1%8b%b5%e1%8c%8b%e1%8d%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%88%86%e1%8a%95-%e1%89%b0%e1%8c%a8%e1%88%9b%e1%88%aa-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%8c%8d%e1%89%a5-%e1%8a%a5/ | 103 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ከመሰረቱ ለማስቀረት በዚህ ዓመት የማኅበረሰብ ንቅናቄ እንደሚካሄድ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ከመሰረቱ ለማስቀረት በዚህ ዓመት የማኅበረሰብ ንቅናቄ እንደሚካሄድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።በድንበሮች አካባቢ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የነበረው ቁጥጥር በመላላቱ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር መጨመሩ ተገልጿል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰብሳቢነት የሚመሩት ብሔራዊ የሰዎች መነገድ፣ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና በሕገወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀልን መከላከልና መቆጣጠር ብሔራዊ ምክር ቤት የ2013 ዓ.ም ዓመታዊ ስብሰባውን አካሂዷል።በውይይቱ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በድንበሮች አካካቢ የነበረው ቁጥጥር የሰዎችን ፍልሰት ቀንሶት እንደነበር ተነስቷል።ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድንበሮች አካባቢ ቁጥጥር መቀነሱ ለሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ምክንያት እየሆነ ነው ተብሏል።በወረርሽኙ ሳቢያ በርካታ አገራት ድንበራቸውን መዝጋታቸውና የውጭ አገር የስራ ስምሪትም መቋረጡ ለሕገወጥ ስደት መጨመር ምክንያት ሆኗል ተብሏል።አብዛኞቹ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንደሆኑም ተመልክቷል።በሕጋዊ ፈቃድ ሽፋን በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር የተሰማሩ አካላት መኖራቸውም በውይይቱ ተነስቷል።የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሕገወጥ ወንጀል ከምንጩ ለማድረቅ የማኅበረሰብ ንቅናቄ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።የማኅበረሰብ ንቅናቄ በኤች.አይ.ቪ እና በኮቪድ ወቅት ያመጣውን ለውጥ ለአብነት በማንሳት ማኅበረሰቡ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን እንዲጠየፍና እንዲያወግዝ ንቅናቄ መካሄድ አለበት ብለዋል።ለንቅናቄው የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እድሮችና ሌሎች በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን አካላት መጠቀም እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።በአገሪቷ የሚገኙ ቀበሌዎችን ከሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ነጻ ማውጣት የንቅናቄ ዘመቻው አካል መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።ንቅናቄው ውጤት ተኮር፣ የታቀደና የሚሰሩ ስራዎችም በተጨባጭ ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።ክልሎች በቅንጅት እንዲሰሩ ያስገነዘቡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃላፊነቱን የማይወጣ ተጠያቂ እንደሚሆንም ገልጸዋል።ብሔራዊ የሰዎች መነገድ፣ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና በሕገወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀልን መከላከልና መቆጣጠር ብሔራዊ ምክር ቤት በ2007 ዓ.ም ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀልን ለመከላከል የተቋቋመ መሆኑን አስታውሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%88%95%e1%8c%88-%e1%8b%88%e1%8c%a5-%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8b%9d%e1%8b%8d%e1%8b%8d%e1%88%ad%e1%8a%95-%e1%8a%a8%e1%88%98%e1%88%b0%e1%88%a8%e1%89%b1-%e1%88%88%e1%88%9b%e1%88%b5/ | 255 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በህግ ከለላ ስር ላሉ ዜጎች ‘የዋስትና መብት’ ማረጋገጥ በሚል ለዳኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 26, 2020 | Unknown | በህግ ከለላ ስር ላሉ ዜጎች ‘የዋስትና መብት’ ማረጋገጥ በሚል ከዞን፣ ከወረዳ፣ ከፍተኛ እንዲሁም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለተውጣጡ ዳኞች ስልጠና በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ነው።የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከ“ጄስትስ ፎር ኦል ፒ ኤፍ” ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የውይይት መድረክ በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የፍትህ ስርዓትን ነፃ እና ገለልተኛ እንዲሆን የባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ነው ተብሏል።ዳኞችና የህግ ባለሙያዎች ገለልተኛ በመሆን ፈጣን የሆነ የጉዳዮች ፍሰት እንዲኖር ብሎም ፍርድ ሳያገኙ በማረሚያ የሚጉላሉ ሰዎች እልባት እንዲያገኙ ያግዛልም ነው የተባለው።የጀስትስ ፎር ኦል ፕሬዝዳንት ፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ በኦሮሞ ባህል የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች እና ሀደሲንቄዎች ሰላምና እርቅን በማስፈን በዳኝነት አሰጣጥ ያሉትን እሴቶች ጠብቆ በማቆየቱ የፍትህ ስርዓት በግብዓትነት መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል።ስልጠናው በቀጣይ ሰላምን ማስፈን፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር እንዲሁም በምርጫ ወቅት ምን አይነት የፍትህ አሰጣጥ ሊኖር ይገባል? በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ለሁለት ቀን ይቀጥላል።ከጀስትስ ፎር ኦል ላለፉት 28 አመታት በኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓቱ እንዲሻሻል ሲሰራ መቆየቱም ተገልጿል።(በሀኒ አበበ) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%85%e1%8c%8d-%e1%8a%a8%e1%88%88%e1%88%8b-%e1%88%b5%e1%88%ad-%e1%88%8b%e1%88%89-%e1%8b%9c%e1%8c%8e%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%8b%8b%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%8a%93-%e1%88%98%e1%89%a5%e1%89%b5/ | 133 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በኮንሶ ዞን በተከሰቱ ተከታታይ ግጭቶች በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል- ኢሰመኮ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | በኮንሶ ዞን በተከሰቱ ተከታታይ ግጭቶች በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል፡፡በደቡብ ክልል፣ የኮንሶ ዞን ከኅዳር 1 እስከ ኅዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተከሰቱ ተከታታይ ግጭቶች የደረሰው አሰቃቂ ግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት፤ የአካባቢው ሰብአዊ ቀውስ ዘላቂ እልባት ባለማግኘቱ እየተባባሰ መሄዱን እንደሚያሳይ ኮሚሽኑ አስታውቋል።ኮሚሽኑ ከኅዳር 12 ቀን እስከ ኅዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በሀይበና እና በአይዴ ቀበሌዎች፣ በአርባምንጭ፣ በጊዶሌ እና በካራት ከተማዎች ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ግኝቶች ይፋ አድርጓል፡፡በሪፖርቱ እንደተመለከተው ቢያንስ 66 ሰዎች ተገድለዋል፣ 39 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ብዙ ቤቶችና ንብረት በእሳት ተቃጥለዋል እንዲሁም ከመቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የኮንሶ ዞን እና አካባቢው ረዘም ላለ ጊዜ ሰላም አጥቶ የቆየበት ችግር ተገቢውን ትኩረት አላገኘም ብለዋል።በአካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከመኖሪያው መፈናቀሉንና ከመካከላቸው ለአምስተኛ ጊዜ የተፈናቀሉ ተጎጂዎች ጭምር መኖራቸው አሳዛኝ የሰብአዊ መብቶች ቀውስ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ስለሆነም ለተፈናቃዮች በአፋጣኝ አስፈላጊውን ድጋፍ ከማቅረብ ባሻገር፣ የፌዴራሉና የክልሉ መንግሥታት ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ ተቀናጅተው ዘላቂ ሰላም የሚያሰፍን መፍትሄ ሊሰጡ ይገባል ማለታቸውን የኮሚሽኑ ሪፖርት አስታውቋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8a%ae%e1%8a%95%e1%88%b6-%e1%8b%9e%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%b0%e1%89%b1-%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%89%b3%e1%89%b3%e1%8b%ad-%e1%8c%8d%e1%8c%ad%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%89%a0/ | 160 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ስዊድን በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገች | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | የስዊድን መንግስት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ድጋፉ በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ለተጎዱ ዜጎች የሚሰጥ ሲሆን በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር፣ በዓለም የምግብ ፕሮግራም እና በዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አማካኝነት ለተጎጂዎች የሚደርስ መሆኑን ከስዊድን ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%88%b5%e1%8b%8a%e1%8b%b5%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%88%88%e1%88%b0%e1%89%a5%e1%8b%93%e1%8b%8a-%e1%8b%b5%e1%8c%8b%e1%8d%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%8d/ | 47 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
6ኛው አገራዊ ምርጫ ግንቦት 28 እንዲካሄድ በጊዜያዊነት ቀን ተቆረጠለት | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን 6ኛ አገራዊ የምርጫ ለማካሄድ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው የተቀመጠ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮች የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 05 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሆን በረቂቁ ተመላክቷል።ግንቦት 28 እና 29 ቀን 2013 ዓ.ም ለአገር አቀፍ ምርጫ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ውጤት የሚገለጽባቸው ቀናት እንዲሆኑም በረቂቁ ተቀምጧል።ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ የምርጫ ውጤት የሚገለጽበት ጊዜ እንደሚሆንም የቦርዱ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አመልክቷል።የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ከየካቲት 08 ቀን እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲሆን ተቀምጧል።የመራጮች ምዝገባ የሚካሄድበት ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ በጊዜያዊነት ቀን ተቆርጦለታል።ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው የትግራይ ክልልን እንደማይመለከትም ተገልጿል። | https://waltainfo.com/am/6%e1%8a%9b%e1%8b%8d-%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab-%e1%8c%8d%e1%8a%95%e1%89%a6%e1%89%b5-28-%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8b%b2%e1%8a%ab%e1%88%84%e1%8b%b5-%e1%89%a0%e1%8c%8a/ | 119 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በዜጎች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ ይወስዳል – አቶ ደመቀ መኮንን | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | በዜጎች ላይ ጭካኔ በተሞላበት ጥቃት እየፈጸሙ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።አቶ ደመቀ በሰብሳቢነት የሚመሩት ብሔራዊ የሰዎች መነገድ፣ ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀል መከላከል እና መቆጣጠር ብሔራዊ ምክር ቤት የ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የውይይት መድረክ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል።በመርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን፣ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸመ ያለውን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት አንሥተዋል።በዜጎች ላይ የተፈጸመው ድርጊት ጭካኔ የተሞላበት የወንጀለኞች ተግባር መሆኑንም ጠቅሰዋል።ኢትዮጵያውያን የሚጋሩት እና የወረሱት የዳበረ እሴት ባለቤቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አንዳንዶች በዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እየፈጸሙ ነው” ብለዋል።“ይሄ ችግር ወደ የት እያመራ እንደሆነ ሁሉም ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል” የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።ዜጎችን እየጨፈጨፉ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አቶ ደመቀ አረጋግጠዋል።ለዚህም የተለያዩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ መሆኑን አብራርተው፣ “ድርጊቱን ለማስቆም እና ወንጀለኞችን ለማደን የሁሉም ጥረት እና ትብብር ያስፈልጋል” በማለት ተናግረዋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8b%9c%e1%8c%8e%e1%89%bd-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8c%a5%e1%89%83%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%8d%88%e1%8c%b8%e1%88%99-%e1%89%a3%e1%88%89-%e1%8b%88%e1%8a%95%e1%8c%80%e1%88%88%e1%8a%9e/ | 158 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የመጀመሪያው የሳይንስ ካውንስል የምክክር መድረክ ተካሄደ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር “ሳይንስ ለኢትዮጵያ ልማትና ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያው የሳይንስ ካውንስል የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በሃገሪቱ የሳይንስ ልማትን ለማስፋፋት እና ውጤት ለማምጣት ከተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያ ያቀደችውን የ10 አመት የልማት እቅድ ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከሳይንስ ዘርፉ ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡በመድረኩ በእንግድነት የተገኙት የጠቅላይ ሚንስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚንስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ሳይንስ ተፈጥሮን፣ አለማችንን እንዲሁም አከባቢያችንን የምንገልፅበትና የምንረዳበት መንገድ እንደመሆኑ ወጣቶችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ በማሰልጠን ለሳይንሳዊ ጥናትና ምርምሮች፣ ለፈጠራና ችግር ፈቺ ጥናቶች መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡በአለም ዙሪያ የሚከሰቱ ችግሮችን እና እክሎችን ከመቅረፍ አኳያ ሳይንስ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ከተለያዩ ሃገራት ተሞክሮ መውሰድ እንችላለን ያሉት ፕሮፌሰር ሂሩት፣ ኢትዮጵያም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በርካታ የቤት ስራ ይጠበቅባታል ብለዋል፡፡የሳይንስ ዘርፉን ውጤታማ በማድረግ ረገድ አሉ የተባሉትን ተግዳሮቶች በማንሳት አንዱና ዋነኛው የትብብርና ቅንጅት ስራዎች አለመኖርና አለመጠናከር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡በመድረኩም ሳይንስ ለሃገር እድገትና ብልፅግና ያለው ፋይዳ ዙሪያ በምሁራን ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡(በአመለወርቅ መኳንንት) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%aa%e1%8b%ab%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%88%b3%e1%8b%ad%e1%8a%95%e1%88%b5-%e1%8a%ab%e1%8b%8d%e1%8a%95%e1%88%b5%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%8a%ad/ | 147 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የሱዳን ታጣቂዎችና ሚሊሻዎች ከሰሞኑ የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው ጥቃት መፈፀማቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | የሱዳን ታጣቂዎችና ሚሊሻዎች ከሰሞኑ የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው ጥቃት መፈፀማቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ፡፡ሚሊሻዎቹ እና ታጣቂዎቹ የገበሬዎችን ማሳ በመዝረፍ እና በማፈናቀል በርካታ ህገ ወጥ ድርጊት መፈጸማቸውን አምባሳደር ዲና ከዋልታ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከሱዳን አመራሮች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ዲና፣ በሀለቱ ሀገራት መካከል ልዩነትን ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላትና ወደ ሱዳን የሸሸው የጁንታው ቡድን ሁኔታው እንዲባባስ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡የመሬት ይዞታ ባለቤትነት ጥያቄ በአንዳንድ የሱዳን ፖለቲከኞችም ይስተዋላል ያሉት ቃልአቀባዩ፣ ድርጊቱን በመደገፍ በሱዳን የሚገኙ መገናኛ ብዙኃንም ሲያራግቡት መቆየታቸውን አንስዋል፡፡ከሰሞኑ በሱዳን በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይም ብሔርን መነሻ ያደረገ ማጎሳቆል እንደደረሰባቸውም ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያ በህግ ማስከበር ሂደት ውስጥ መሆኗን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ የሚጥሩ አካላት ሁኔታዎችን ለማባባስ እየሰሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡(በመስከረም ቸርነት) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%b1%e1%8b%b3%e1%8a%95-%e1%89%b3%e1%8c%a3%e1%89%82%e1%8b%8e%e1%89%bd%e1%8a%93-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%88%bb%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8a%a8%e1%88%b0%e1%88%9e%e1%8a%91-%e1%8b%a8%e1%8a%a2/ | 115 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ100 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የሴቶች የስራ ፈጠራ ፕሮጀክትን ለማገዝ የሚውል የ100 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።ከባንኩ ትዊተር ገጽ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ድጋፉ ሴት ስራ ፈጣሪዎችን ስራዎቻቸውን ለማሳደግ የሚችሉበት ገንዘብ፣ ክህሎትና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8b%93%e1%88%88%e1%88%9d-%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8a%ad-%e1%8b%a8100-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%8b%b6%e1%88%8b%e1%88%ad/ | 33 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ጠ/ሚ ዐቢይ የፈረንጆችን ገና ለሚያከብሩ ማህበረሰቦች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፈረንጆቹ ገና ለሚያከብሩ የኢትዮጵያ ወዳጆችና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ መልካም የገና በዓል እና የደስታ በዓል ይሁንላችሁ ሲሉ ገልፀዋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8c%a0-%e1%88%9a-%e1%8b%90%e1%89%a2%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%8d%88%e1%88%a8%e1%8a%95%e1%8c%86%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8c%88%e1%8a%93-%e1%88%88%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%8a%a8%e1%89%a5%e1%88%a9-%e1%88%9b/ | 29 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከ18 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ አደረገች | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | አሜሪካ በትግራይ ክልል በተካሄደው የህግ የማስከበር ተግባር ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ከ18 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጓን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ አስታውቀዋል፡፡ድጋፉ በዩኤስጂ አጋሮች የተገኘ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ድርጅቶችን በማገዝ ከኢትዮጵያ ተፈናቅለው በሱዳን የሚገኙ ከ52 ሺህ በላይ ስደተኞችን ፍላጎት ለሟሟላት እና በጅቡቲ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎችን ለማገዝ ነው ተብሏል፡፡ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል፣ በጎርፍ የሚጠቁ ማህበረሰቦችን ለመርዳት እና ከኤርትራ ተፈናቅለው በኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጎችን ለማቋቋም የታሰበ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ድጋፉ መጠለያዎችን፣ አስፈላጊ የጤና እንክብካቤን፣ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታን፣ ትምህርትን፣ የአካባቢ ጽዳትና ንፅህና አገልግሎቶችን ለስደተኞች እና ለተፈናቀሉ ዜጎች ለማቅረብ እንደሚውል ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a0%e1%88%9c%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%88%88%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8a%a818-%e1%88%9a%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%8b%b6%e1%88%8b%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%88%8b%e1%8b%ad/ | 98 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።መጪውን 6ኛው አገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ከሲቪል ማህበራት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጣውን ውጤት ለዛሬው መድረክ ያቀርባል።ምርጫው ሊከናወን የሚችልባቸውን ቀናት ተግባራትና ሁኔታዎችን አስመልክቶ ምክክሮችን ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ከዚህ ቀደም ከተከናወኑ ምክክሮች በኋላ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ያስተዋውቃል ተብሎ ይጠበቃል።የምርጫ ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ በማድረግም በጊዜ ሰሌዳው ላይ ያሉ ቀዳሚ ተግባራትን አስመልክቶ ቦርዱ መረጃ እንደሚሰጥ ኢዜአ ዘግቧል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%89%a5%e1%88%94%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab-%e1%89%a6%e1%88%ad%e1%8b%b5-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab-%e1%88%a8/ | 82 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በመቀሌ ከተማ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፣ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል በላይ ስዩም እና የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ሃይለስላሴ ውይይቱን እየመሩ ይገኛል።በውይይቱም የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ በርካታ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።ተሣታፊዎቹ በውይይታቸው የሕወሓት ጁንታ የአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል።በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደርም መዋቅሩን እስከታችኛው የአስተዳደር እርከን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።ነዋሪዎቹ የመቀሌን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅም ህዝባዊ ፖሊሶች በአስቸኳይ ተደራጅተው በከተማው ስራ እንዲጀምሩ ጠይቀዋል።መንግስት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ሌሎች የመሠረተ ልማቶች በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ እንዳደረገ ሁሉ የኢንተርኔት አገልግሎትም ስራ ቢጀምር የተሻለ መሆኑን ጠቅሰዋል።በውይይቱ ማጠቃላያ ላይ ነዋሪዎቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች በመድረኩ ላይ በተገኙት አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሠጥ ኢዜአ ዘግቧል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%ab%e1%8b%ad-%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%88%8d-%e1%8c%8a%e1%8b%9c%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%89%b0%e1%8b%b3%e1%8b%b0%e1%88%ad-%e1%8a%a8%e1%88%98%e1%89%80/ | 129 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ማህበረሰቡ ክብረ በዓላትን ሲያከብር ቫይረሱን ሊከላከል ይገባል | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | ማህበረሰቡ በእምነት ተቋማት ሲገኝ እና ክብረ በዓላት ሲያከብር ራሱን ከኮሮናቫይረስ እየጠበቀ መሆን እንዳለበት ተገለጸ፡፡በኮቪድ-19 ዙሪያ እየተስተዋለ ያለውን መዘናጋት እና የቫይረሱን መስፋፋት በተመለከተ የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት እና ጤና ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሃፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጸው ምዕመኑ በአምልኮ ስነ- ስርዓቶች እና በሃይማኖት ጉባኤዎች ላይ ሲገኝ ርቀትን በመጠበቅ፣ የአፍና አፍንጫ ጭንብሎጭን በማድረግ እና ሌሎች መከላከያ መንገዶችን በመጠቀም ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡መጪው ወር እንደ ገና፣ ጥምቀት እና ሌሎች ክብር በዓላቶች የሚከበሩበት በመሆኑ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡በሃገሪቱ የጭንብል አጠቃቀም ከ70 በመቶ ወደ 50 በመቶ መቀነሱን የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዴታዋ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ማህበረሰቡ እንደ ሰርግ፣ ክብረ በዓላትና እና ሌሎች ዝግጅቶች በሚከውኑበት ወቅት ቫይረሱን እየተከላከሉ መሆን እንዳለበት ጠቁሟል፡፡ሚኒስትር ዴታዋ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የጽኑ ህሙማን የመተንፈሻ እጥረት እያጋጠመ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡(በሀኒ አበበ) | https://waltainfo.com/am/%e1%88%9b%e1%88%85%e1%89%a0%e1%88%a8%e1%88%b0%e1%89%a1-%e1%8a%ad%e1%89%a5%e1%88%a8-%e1%89%a0%e1%8b%93%e1%88%8b%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%88%b2%e1%8b%ab%e1%8a%a8%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%89%ab%e1%8b%ad/ | 130 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በተመድ በግጭት ቀጠና ውስጥ ያሉ ህጻናት ልዩ ተወካይ ጋር ተወያዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በተመድ በግጭት ቀጠና ውስጥ ያሉ ህጻናት ልዩ ተወካይ ቨርጂኒያ ጋምባ ጋር ተወያዩ፡፡አምባሳደር ታዬ በውይይታቸው በትግራይ ክልል ስላለው የሰብአዊ ድጋፍ ለልዩ ተወካይዋ ገለጻ አድርገዋል፡፡ከዚህ ባለፈም በህወሓት በኩል ህጻናትን ለጦር የመመልመልና ህጻናት ወታደሮችን የመጠቀም ጉዳይን በተመለከተ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8a%a0%e1%88%9d%e1%89%a3%e1%88%b3%e1%8b%b0%e1%88%ad-%e1%89%b3%e1%8b%ac-%e1%8a%a0%e1%8c%bd%e1%89%80%e1%88%b5%e1%88%8b%e1%88%b4-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%88%98%e1%8b%b5-%e1%89%a0%e1%8c%8d%e1%8c%ad/ | 50 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት ባደረሱ 42 ፀረ-ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ ተወሰደ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት ያደረሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ መከላከያ ሰራዊት ተከታትሎ በወሰደው እርምጃ 42ቱ ተደምስሰዋል፡፡የመከላከያ ሠራዊት በወሰደው እርምጃም ጸረ-ሠላም ኃይሎች ለጥፋት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና እና ቀስቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%89%a1%e1%88%88%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%88%a8%e1%8b%b3-%e1%89%a0%e1%8a%a9%e1%8c%82-%e1%89%80%e1%89%a0%e1%88%8c-%e1%89%a0%e1%8a%95%e1%8c%b9%e1%8a%83%e1%8a%95-%e1%8b%9c%e1%8c%8e%e1%89%bd/ | 53 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በመተከል ዞን እየተከሰተ ያለውን ችግር ከመሰረቱ ለማጥፋት በህብረትና በትኩረት መስራት ያስፈልጋል – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እየተከሰተ ያለውን ችግር ከመሰረቱ ለማጥፋት በህብረት እና በትኩረት መስራት እንደሚጠይቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል ያሉ ሲሆን፣ በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ ሲሉ ነው የገለፁት።ችግሩን በተለያየ መንገድ ለመፍታት የተደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት እንዳላመጣም በመግለፅ የጠላቶቻችን ዓላማ በጁንታው ላይ የሠነዘርነውን ብርቱ ኃይል ለመበተን ነው፤ ይህም የሚሳካ አይደለም ብለዋል።መንግሥት ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ አድርጓል፤ የምንፈልገውን ውጤት ለማግኘት ሁላችንም እንደ ከዚህ ቀደሙ በትኩረትና በኅብረት እንድንሠራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥሪ አቅርበዋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8d-%e1%8b%9e%e1%8a%95-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%b0%e1%89%b0-%e1%8b%ab%e1%88%88%e1%8b%8d%e1%8a%95-%e1%89%bd%e1%8c%8d%e1%88%ad-%e1%8a%a8/ | 90 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቀቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ሙሉ ወጪ የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቀጣይ ወር ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡በ13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ይህ ትምህርት ቤት 18 መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፅሀፍት፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የአስተዳደር ህንፃ፣ መጸዳጃ ቤትና ክሊኒክ ያሟላ ነው፡፡የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ፈንታ እንዳሉት÷ በቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው የተገነባው ዘመናዊ ትምህርት ቤት በከተማው የሚታየውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ችግር የሚፈታ ነው ፡፡የትምህርት ቤቱ ግንባታ ዘመን ተሻጋሪ እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ጥራት ያላቸውን የግንባታ ቁሳቁሶችን ከመጠቀም ጀምሮ ተገቢ የሆነ የባለሙያ ክትትል ተደርጎለታል ተብሏል፡፡የክልሉ ትምህርት ቢሮ ችግሩን በመረዳት እድሉን መስጠቱ በከተማ አስተዳደሩ ተማሪዎችና መምህራን ስም ምስጋና ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽህፈትቤት ኃላፊ ትምህርት ቤቱ አዲስ በመሆኑ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበርና ሌሎች ግብአቶችን ለማሟላት ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ግብአት ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የሚመለከተው የመንግስት ተቋም፣ የአካባቢው ማህበረሰብና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ድጋፍ እንዲያደርጉም የትምህርት ጽህፈት ቤቱ ጥሪ አቅርቧል :: (ምንጭ ፡- የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%89%80%e1%8b%b3%e1%88%9b%e1%8b%8a%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%88%98%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%8c%bd%e1%88%85%e1%8d%88%e1%89%b5-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8c%88%e1%8a%90%e1%89%a3/ | 160 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ለኢፈርት ድርጅቶች ገለልተኛ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ተሾመ | ፖለቲካ | December 25, 2020 | Unknown | በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቅራቢነት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በመ/ቁ 263499 ለኢፈርት ድርጅቶች ሰባት አባላት ያሉት ገለልተኛ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ሾሟል፡፡ድርጅቶቹን በባለአደራነት እንዲያስተዳድሩ ከተሾሙት አባላት መካከል አምስት ሰዎች ከግል ተቋማት የተውጣጡ ሲሆን፣ ሁለቱ ደግሞ ከገንዘብ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተውጣጡ መሆናቸውን የአፌዴሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡የጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደሩ አባላት ገለልተኝነት፣ የትምህርት ዝግጅት፣ የሙያ ሥነ ምግባር እና ትላልቅ የንግድ ድርጅቶችን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት፣ በቦርድ አመራርነት እንዲሁም አባልነት በመምራት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ መሆናቸውን ዶክተር ጌዲዮን ተናግረዋል፡፡ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ድርጅቶችን ወደ ሥራ ማስገባት፣ በእያንዳንዱ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ከሚሰሩ ብዛት ያላቸው ሠራተኞች የሥራ ዋስትና ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍና የድርጅቶቹን ንብረት ከብክነት በመከላከል በአግባቡ ጠብቆ ለመያዝ እንዲያመች በጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር እንደሚመራም አመልክተዋል፡፡ለኢፈርት ድርጅቶች ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር በመሾም ሂደት ውስጥ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የትግራይ ክልል ጊዜአዊ አስተዳደር ከፍተኛ ሙያዊ ድጋፍና አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አብራርተዋል፡፡የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው፣ አባላቱ ጥናት ሲያደርጉ እንደቆዩና ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገቡ ገልጸዋል፡፡የገንዘብ ሚኒስቴር እና ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከአባላቱ ጋር በቅርበት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ባለአደራ አስተዳደሩ በፍርድ ቤት ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገበት የማስተዳደር ሥራን የሚያከናውን ሲሆን፣ በየጊዜው የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሾመው ፍርድ ቤት እንዲሁም ለፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል ተብሏል፡፡የቦርዱ አባላት ከዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እና ከዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡(በትዝታ መንግስቱ) | https://waltainfo.com/am/%e1%88%88%e1%8a%a2%e1%8d%88%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%8b%b5%e1%88%ad%e1%8c%85%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%8c%88%e1%88%88%e1%88%8d%e1%89%b0%e1%8a%9b-%e1%8c%8a%e1%8b%9c%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%89%a3%e1%88%88/ | 215 | 5ፖለቲካ
|
የብልጽግና ፓርቲ እና የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ግንኙነታቸው በሚጠናክሩበት ጉዳይ መከሩ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | የሁለቱ ፓርቲዎች አመራሮች በቀጣይ የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቱን አጠናክረው ስለሚቀጥሉበት ጉዳይ በዌብናር ውይይት አካሄደዋል፡፡ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የተለያዩ ስኬታማ ልምዶች ያለው ፓርቲ እንደሆነ ገልጸው፤ የብልጽግና ፓርቲ የጀመረውን ሁለንተናዊ ሪፎርም ለማጠናከርና ውጤታማ ለማድረግ ከቻይና ፓርቲ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ዶ/ር ቢቂላ ኢትዮጵያ የህግ ማስከበር ስራ ላይ እንደነበረችና የህግ ማስከበሩ እንደተጠናቀቀ ለቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አመራሮች ገልጸዋል፡፡በትግራይ ክልል የነበረው የህግ ማስከበር ስራ በመጠናቀቁ የትግራይ ህዝብ ወደ ሰላማዊ የእለት ከእለት እንቅስቃሴው የተመለሰ ሲሆን በአገራችን በ2013 ዓ.ም ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ በብልጽግና ፓርቲ በኩል እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶችን አስረድተዋል፡፡በውይይቱ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ተገኝተው የኢትዮጵያና የቻይናን ቆየት ያለ ወዳጅነት አብራርተዋል፡፡ አምባሳደሩ ኢትዮጵያና ቻይና ስትራቴጅካዊ ወዳጆች እንደሆኑ ገልጽው አገሪቱ በብዙ ዘርፍ እንደተጠቀመች ነው የገለጹት፡፡ሁለቱ አገራት በአሁኑ ወቅት በበርካታ ጉዳዮች ላይ አብረው እየሰሩ እንደሚገኙ የገለጹት አምባሳደሩ በቻይና የኮቪድ ወረርሽኝ የተከሰተ ሰሞን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለፕሬዝዳንት ዥ ጅፒንግ ስልክ በመደወልና ኢትዮጵያ ከቻይና ጎን እንደሆነች በመግለጽ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ነበሩ ሲሉ ተናግረዋል፡፡የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን በወከል በውይይቱ የተገኙት የአፍሪካ ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክተር ሚስተር ዋንግ ሂሚንግ የብልጽግናና የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል የፓርቲያችን ፍላጎት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያ በአፍሪካ በተለይም ከምስራቅ አፍርካ አገራት ጋር ለምናደርገው ግንኙነት ኢትዮጵያን እንደማእከል እንደሚጠቀሙ ለዚህም ኢትዮጵያን እየመራት ከሚገኘው የብልጽግና ፓርቲ ጋር ጠንካራ ግንኙነት መመስረት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ፍላጎት ነው ብለዋል፡፡ቻይና በየትኛውም አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ፍላጎት እንደሌላት የገለጹት ሚስተር ዋንግ ሂሚንግ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮቿን በራሷ የመምራትና ህግና ስርዓት የማስፈን መብት ያላት አገር መሆኗን አብራርተዋል፡፡የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ብልጽግና ፓርቲ ለሚያካሂዳቸው የፓርቲ ሪፎርም ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጾል፡፡የብልጽግናና የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ግንኙነታቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ያስችላቸው ዘንድ በቅርቡ የመግባቢያ ሰነድ ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%a5%e1%88%8d%e1%8c%bd%e1%8c%8d%e1%8a%93-%e1%8d%93%e1%88%ad%e1%89%b2-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%89%bb%e1%8b%ad%e1%8a%93-%e1%8a%ae%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5-%e1%8d%93/ | 254 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቀቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 24, 2020 | Unknown | በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ሙሉ ወጪ የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቀጣይ ወር ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡በ13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ይህ ትምህርት ቤት 18 የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፅሀፍት፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የአስተዳደር ህንፃ፣ መጸዳጃ ቤትና ክሊኒክ ያሟላ ነው፡፡የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ፈንታ እንዳሉት፣ በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የተገነባው ዘመናዊ ትምህርት ቤት በከተማው የሚታየውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ችግር የሚፈታ ነው ፡፡የትምህርት ቤቱ ግንባታ ዘመን ተሻጋሪ እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ጥራት ያላቸውን የግንባታ ቁሳቁሶች ከመጠቀም ጀምሮ ተገቢ የሆነ የባለሙያ ክትትል ተደርጎለታል ተብሏል፡፡የክልሉ ትምህርት ቢሮ ችግሩን በመረዳት እድሉን በመስጠቱ በከተማ አስተዳደሩ ተማሪዎችና መምህራን ስም ምስጋና ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ትምህርት ቤቱ አዲስ በመሆኑ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበርና ሌሎች ግብአቶችን ለማሟላት ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ግብአት ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የሚመለከተው የመንግስት ተቋም፣ የአካባቢው ማህበረሰብና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ድጋፍ እንዲያደርጉም የትምህርት ጽህፈት ቤቱ ጥሪ አቅርቧል:: | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8b%b0%e1%89%a3%e1%88%ad%e1%89%85-%e1%89%a5%e1%88%ad%e1%88%83%e1%8a%95-2%e1%8a%9b-%e1%8b%b0%e1%88%a8%e1%8c%83-%e1%89%b5%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ad%e1%89%b5-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%8c%8d/ | 153 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በመተከል ዞን በተፈጠረው የጸጥታ ችግር የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 24, 2020 | Unknown | የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት በመተከል ዞን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ከፍተኛ እና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ሥር ማዋል ጀምሯል፡፡በዞኑ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር እጃቸው ያለበትን፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ስር እያዋለ ሲሆን እስካሁንም 5 አመራሮችን በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡በዚህም መሠረት፡-1ኛ. አቶ ቶማስ ኩዊ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ2ኛ. አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር3ኛ. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፡-የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር4ኛ. አቶ ባንዲንግ ማራ፡- የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ5ኛ. አረጋ ባልቢድ፡- የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩእነዚህ አመራሮች ከመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር እጃቸው እንዳለበት በመረጋገጡ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡የክልሉ መንግስት በዞኑ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ሲሆን፣ ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተሳትፎ ባደረጉ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡በመሆኑም ህብረተሰቡ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ወደ ሠላም ለመመለስ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንዲደግፍ የክልሉ መንግስት ጥሪ ማቅረቡን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%b0%e1%8a%a8%e1%88%8d-%e1%8b%9e%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%8d%88%e1%8c%a0%e1%88%a8%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%8c%b8%e1%8c%a5%e1%89%b3-%e1%89%bd%e1%8c%8d%e1%88%ad-%e1%8b%a8/ | 150 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
“የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ ነው “- ኢሰመኮ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | በመተከል በንፁሃን ላይ የደረሰውን ጥቃት ባለመከላከልም ሆነ በሌላ መልኩ ጥቃቱን የፈጸሙና ያባባሱ ሰዎችን ሕግ ፊት የማቅረብ ሂደት እንዲጀመር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ።“የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ ነው ” በሚል በመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ በንፁሃን ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ አውጥቷል።ኮሚሽኑ በመግለጫው በክልሉ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እተዳከመ መሄዱን በመግለጽ፤ የጥቃቱን ሂደት በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት እና ከተጎጂዎች ጋር በመነጋገር ሲከታተልና ሲያጣራ መቆየቱን አስታውቋል።ኮሚሽኑ ሁኔታውን እስካጣራበት ጊዜ ድረስ በቡለን ሆስፒታል 36 ተጎጂዎች እርዳታእየተደረገላቸው ሲሆን አብዛኞዎቹ በጥይት ሌሎቹ በቀስት የቆሰሉ መሆናቸውን አረጋግጧል በኩጂ ቀበሌ በሰው ሕይወት እና አካል ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የደረሱ ሰብሎችና የተሰበሰቡ ማሳዎች በእሳት መጋየታቸውም ጭምር መረጃ እንደደረሰው ገልጿል።በድባጤ ወረዳ ዶንበን ቀበሌ ስጋት የገባቸው ነዋሪዎች ከታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ቀዬአቸውን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነም ኮሚሽኑ መረጃ አለኝ ብሏል በመግለጫው።በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ተደጋጋሚነትና የክልሉን ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ አስመልክቶ፣ የፌዴራሉንና የክልሉን መንግሥታት የተጠናከረ ትብብርና ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሻ ኢሰመኮ ሲያሳስብ የቆየ ቢሆንም ጥቃቶቹ በመልክ እና በስፋት እየተባባሱ መምጣታቸው ነው የተገለጸው።በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸውን እና ለተፈናቀሉ ሰዎች የህክምና እና ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ እንዲሁም ተገቢው ማጣራትና ጥቃቱን ባለመከላከልም ሆነ በሌላ መልኩ ጥቃቱን የፈጸሙና ያባባሱ ሰዎችን ሕግ ፊት የማቅረብ ሂደት ከወዲሁ እንዲጀመርም ኮሚሽኑ አሳስቧል።በአካባቢው የሚገኘውን የፀጥታ ኃይልና መዋቅር የሰዎችን ደኅንነት ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በከፍተኛ ደረጃ በአፋጣኝ እንዲጠናከርም ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8b%b0%e1%8a%85%e1%8a%95%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%88%9b%e1%88%a8%e1%8c%8b%e1%8c%88%e1%8c%a5-%e1%89%80%e1%8b%b3%e1%88%9a%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8a%95-2/ | 208 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ሚኒስቴሩ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ማደራጃ አዋጅን ለማሻሻል እየመከረ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 25, 2020 | Unknown | የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ማደራጃ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት፣ ከሀገር አቀፍና ከክልል ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዘዳንቶች እና ከከልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊዎችና ሌሎች ዘርፉ ከሚመለከታው ኃላፊዎች ጋር ረቂቅ አዋጁን ለማሻሻልና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ሀሳብ የተካተተበትና የተሻለ አዋጅ ሆኖ ይዘጋጅ ዘንድ በኢንተር ኮንቲነታል ሆቴል ውይይት እያካሄደ ነው፡፡በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያና ሪጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እሸቴ አስፋው እንደገለፁት ሀገራችን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የምታደርገው ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር ግቡን ሊመታ የሚችለው በንግዱ ብሎም በአምራች ዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ሚናቸውን በአግባቡ ሲወጡ ነው፡፡የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቱ ለረጅም አመታት ያገለገለ በመሆኑ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ የንግዱን ማህበረሰብ ብሎም አምራቾችን ተጠቃሚ በማድረግ በኩል ጉድለቶች የሚታዩበት በመሆኑ ማሻሻል አስፈላጊ እንደሆነ አቶ እሸቴ አስፋው ገልፀዋል፡፡ሚኒስቴር ዴኤታው አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በውድድር ላይ የተመሰረተ የንግድ ስርዓት ለማስፈን ብሎም የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡በረቂቅ አዋጁ የምክክር መድረክ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዘዳንት ኢንጅነር መላኩ እዘዘው በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ 18 አመታትን ያሥቆጠረ በመሆኑ የዘርፉን የአሰራር ማነቆዎች በሚያስወግድ መልኩ ይሻሻል ዘንድ የሚመለከታቸውን የዘርፉ ተዋናዮች ሀሳብ እንዲያካትት ለማረግ በተለያዩ ጊዜያት ውይይት እንደተደረገበት ጠቅሰው የሀገር አቀፍና ክልል ዘርፍ ማህበራት ፕሬዘዳንቶችና የክልል ንግድና ኢንዱስት ቢሮ ኃላፊዎችም ለረቂቅ አዋጁ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን በማንሳት ለአዋጁ መሻሻል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል፡፡(ምንጭ ፡- የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር) | https://waltainfo.com/am/%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b4%e1%88%a9-%e1%8b%a8%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%8b%b5%e1%8a%93-%e1%8b%98%e1%88%ad%e1%8d%8d-%e1%88%9b%e1%88%85%e1%89%a0%e1%88%ab%e1%89%b5-%e1%88%9b%e1%8b%b0%e1%88%ab/ | 209 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በሥራ ቦታ የሚፈጠሩ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል ያለመ ውይይት ተካሄደ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 24, 2020 | Unknown | በሥራ ቦታ የሚፈጠሩ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል ያለመ ውይይት ተካሄደ፡፡የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በስራ ቦታ ላይ ሠራተኞች ራሳቸውን እንዴት መጠበቅ አለባቸው በሚል በተዘጋጁ ሁለት ጥናቶች ዙሪያ ከባለድርሻ ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ጥናቶቹ በሥራ ቦታ የሚፈጠሩ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል ያለመ ነው ተብሏል።በዓለም አቀፍ ደረጃ 6 ሺህ 300 የሚደርሱ ሰዎች በቀን ውስጥ በስራ ላይ በሚፈጠሩ አደጋዎች ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡና ከዚህም 550 ሰዎች ቆይቶ በሚፈጠሩ የሙያ ላይ በሽታዎች እንደምያዙ በጥናቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡በኢትዮጵያ በባህርዳር፣ ኮምቦልቻ እና ትግራይ ጨርቃጨርቅና ጋርሜንት ኢንዱስትሪዎች በተካሄደው ጥናት 7 ሺህ 992 ሰዎች አደጋ እንደምደርስባቸውና ለህክምና ወደ ሆስፒታል እንደሚሄዱ ተገልጿል፡፡5 ሺህ 276 ሰዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጤናማ ባልሆነ የስራ አካባቢ በመኖሩ ምክንያት አደጋ እንደምደርስባቸውም ለማወቅ ተችሏል፡፡የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በስራ ቦታዎች አደጋዎችንና የሙያ በሽታዎችን ለመቀነስ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን ለዋልታ ገልጸዋል፡፡በዚህም በኢንዱስትሪዎች እና ፋብሪካዎች የሚከሰተውን በሽታ ለመከላከል ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ጥናቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡በስራ ላይ አደጋዎችንና ከሙያ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ በሽታዎችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ክፍተት እንዳለው የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ችግሮችን እንዴት መፍታት ይቻላል በሚል በተካሄደው ጥናት ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረግን ነው ብለዋል፡፡የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ትምህርት ክፍል ዲን እና መምህር ፕሮፌሰር ዳመነ ኃይለማሪያም በበኩላቸው፣ በስራ ቦታ ሰራተኞች ጤና እንዲጠበቅ ኢንዱስትሪዎች እና ፋብሪካዎች ለሰራተኞች ምቹ እንዲሆኑ ከሚኒስቴሩ ጋር በጥምረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ጤናማ ሰራተኛ እንዲኖር ኢንዱስትሪዎች ምቹና ጤናማ አካባቢ መፍጠር ይኖርባቸዋል ያሉ ሲሆን፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡በቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ዙሪያ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተውበታል፡፡(በአድማሱ አራጋው) | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%88%a5%e1%88%ab-%e1%89%a6%e1%89%b3-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8d%88%e1%8c%a0%e1%88%a9-%e1%8a%a0%e1%8b%b0%e1%8c%8b%e1%8b%8e%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%89%80%e1%8b%b5%e1%88%9e-%e1%88%88%e1%88%98/ | 238 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ብሪታኒያ ከደቡብ አፍሪካ የገባ አዲስ የኮሮና ዝርያ ስጋት ውስጥ ጥሎኛል አለች | ዓለም አቀፍ ዜና | December 24, 2020 | Unknown | ታላቋ ብሪታኒያ አዲስ የኮሮና ዝርያ ያለባቸው 2 ሰዎችን ማግኘቷን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ማት ሐንኩክ አስታወቁ።በሎንዶንና በሰሜን ምዕራብ ኢንግላንድ የተገኙት ሁለቱ ሰዎች ደቡብ አፍሪካ ተጉዘው ከነበሩ ሰዎች ጋር ንክኪ እንደነበራቸው ተረጋግጧል።ባለፉት 15 ቀናት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዘው የነበሩ ዜጎች ወይም ከደቡብ አፍሪካ ከመጣ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው በሙሉ በአስቸኳይ ራሳቸውን ለይተው እንዲቀመጡ አደራ ተብለዋል።ይህ አዲስ ዝርያ ሰሞኑን በ70 ከመቶ ፍጥነት የመዛመት ጉልበት አለው ከተባለ ሌላ ዝርያ ጋር የሚያያዝ አይደለም።የደቡብ አፍሪካ ጤና ሚኒስትር ዝዌሊ ምሂዜ ይህ አዲስ ዝርያ አዲስ ጭንቀት ወልዷል ብለዋል። ወጣትና በጣም ጤነኛ የሆኑ ሰዎችን ጭምር የሚያንበረክክ ዝርያ እንደሆነም አብራርተዋል።ጤና ሚኒስትሩ ሲናገሩ “ደቡብ አፍሪካ ኤችአይቪ የመጣ ሰሞን የሆነችውን ዓይነት ምስቅልቅል ውስጥ አሁን ልትገባ አይገባትም’ ሲሉ ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ያድርጉ ብለዋል።ይህ ዝርያ ከተገኘ ወዲህ ሆስፒታሎች አካባቢ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ በሆነ አደገኛ ሁኔታ ላይ የሚገኙት ጤነኛና ወጣት የሆኑ ሰዎች ጭምር መሆኑ ነገሩን አሳሳቢ አድርጎታል። | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a5%e1%88%aa%e1%89%b3%e1%8a%92%e1%8b%ab-%e1%8a%a8%e1%8b%b0%e1%89%a1%e1%89%a5-%e1%8a%a0%e1%8d%8d%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%8b%a8%e1%8c%88%e1%89%a3-%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8b%a8%e1%8a%ae/ | 133 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ የእስራኤል ባለሀብቶችን ቀልብ ስቧል- አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 23, 2020 | Unknown | በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ የእስራኤል ባለሀብቶችን ቀልብ መሳቡን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ገለጹ።እስራኤል በኢትዮጵያ ለተጀመረው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራ ድጋፍ እንደምታደርግም አመልክተዋል።በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲና የእስራኤል አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት በመተባበር በኢንቨስትመንት ጉዳይ ላይ ያዘጋጁት የበይነ መረብ የውይይት መድረክ ትናንት ተካሄዷል።በውይይቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጽዮን ተክሉ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁንና በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ ተሳትፈዋል።በእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካና ላቲን አሜሪካ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሚስ ሚሃል ጉር-አርዬህ፣ የእስራኤል ባለሃብቶች የንግድ ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች ተወካዮች መሳተፋቸው ነው የተገለጸው።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጽዮን ተክሉ መንግስት ነጻነትን እና ብልጽግናን በኢትዮጵያ ለማስፈን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።“ከማሻሻያ እርምጃዎች ውስጥ በግሉ ዘርፍ የሚመራ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ልማት መፍጠር አንዱ ነው” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8a%ab%e1%88%84%e1%8b%b0-%e1%8b%ab%e1%88%88%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8a%ae%e1%8a%96%e1%88%9a-%e1%88%9b/ | 124 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአፍሪካ ህብረት ከቻይና አምባሳደር ሊዮ ዩሺ ጋር ተወያዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 23, 2020 | Unknown | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአፍሪካ ህብረት የቻይና አምባሳደር ሊዮ ዩሺ ጋር በአዲስ አበባ ስለሚገነቡት የአፍሪካ ህብረት ፕሮጀክቶች እና ተያያዥ የትብብር ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ።ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በውይይታቸው የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ /ሲ.ዲ.ሲ/ ዋና መስሪያ ቤትን ዕውን የማድረግ የትብብር አቅጣጫ ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል፡፡አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ህብረት መቀመጫና የአህጉሪቱ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ማዕከል ከተማ መሆኗን የጠቀሱት ምክትል ከንቲባዋ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ስራዎችና ፕሮጀክቶችን በትብብር መስራንት እንቀጥላለን ብለዋል።የአፍሪካ መንደር ፕሮጀክት እና የሲ.ዲ.ሲ አፍሪካ ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ እንዲገነቡ በማድረግ ረገድ ላደረጉት አስተዋጽኦም በከተማው አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል።የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል /ሲዲሲ/ ዋና መስሪያ ቤት የመሠረተ ድንጋይ ባለፈው ሳምንት የተቀመጠ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚገነባው የማዕከሉ ህንጻ ወጪው በቻይና መንግስት የሚሸፈን መሆኑ ተነግሯል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%8b%98%e1%88%ae-%e1%8a%a0%e1%8b%b3%e1%8a%90%e1%89%bd-%e1%8a%a0%e1%89%a4%e1%89%a4-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%89%a0%e1%88%9a%e1%8c%88/ | 127 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ እንደሚገነዘብ አስታወቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 23, 2020 | Unknown | በጄኔቭ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ዋና ኃላፊ ለሆኑት ፍራንኳይስ ሚያንዳ መንግስት በትግራይ ክልል ስለወሰደው የሕግ ማስከለበር ዘመቻ ገለፃ ሰጥተዋል።የሕወሀት ጁንታ የተደራጀ ምዝበራ እና በወታደራዊ ኃይል የታገዝ መጠነ ሰፊ የሕግ ጥሰት ሲፈፅም መቆየቱንና የአገሪቷን ሕልውና ጭምር አደጋ ላይ ለመጣል ሌት ተቀን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀውላቸዋል።በአገሪቱ እየተተገበረ ባለው መሠረታዊ የለውጥ ሥራ ዘርፈ ብዙ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ መሻሻሎች እየተመዘገቡ ቢሆንም፣ ይኼው ቡድን የለውጡ አካል ሆኖ በሠላማዊ መንገድ ከመንቀሳቀስ ይልቅ፣ ለውጡን ቀልብሶ ወደ ስልጣን በመመለስ የፖለቲካ ተጽዕኖውን እና የኢኮኖሚ ምዝበራውን ለማስቀጠል አገርን የማተራመስና ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርቶ መቆየቱን ገልጸዋል።መንግስት ያሳየውን ሆደ ሰፊነት እንደ ድክመት እና ፍርሀት በመውሰድ የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝን በማጥቃት እና ከባድ መሳሪዎችን በመዝረፍ ፈጽሞ ከስህተቱ የማይማር ድርጅት መሆኑን እንደሚያሳይም አብራርተዋል።በዚህ ተግባሩ ቀይ መስመር ያለፈ በመሆኑ፣ መንግስት የተጣለበትን ሕገ መንግስታዊ ስርዓት የማስከበር እና የአገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅ ወደ እርምጃ ለመግባት መገደዱን አከወለው ገልፀዋል።በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ዓላማ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ ከባድ የአገር ክህደት ወንጀል የፈፀመውን የሕወሀት ጁንታ ይዞ ለሕግ ለማቅረብ፣ ያሰማራቸውን የጥፋት ኃይሎች ትጥቅ በማስፈታት በክልሉ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ማድረግ መሆኑን ገለፃ ሰጥተዋል።በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት ጊዜያዊ አስተዳደር ተመስርቶ ሕዝቡን መልሶ ማቋቋምና አስፈላጊ የሰብዓዊ ድጋፍና እርዳታን ከሚመለከታቸው አገራዊ እና ዓለምአቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ተባብሮ የማቅረብ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ያወሱት አምባሳደሩ፤ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሉዓላዊና ሕጋዊ የውስጥ ጉዳይ ስለመሆኑ አስምረውበታል።በሕግ ማስከበር ዘመቻው ውስጥ መከላከያ ሰራዊት የሚወስዳቸው እርምጃዎች በተመረጡ ኢላማዎች ላይ ብቻ መሆኑን ገልጸው፤ በሠላማዊ ሠዎች ላይ ጥቃትና አደጋ እንዳይደርስ በከፍተኛ ጥንቃቄ የተከናወነ መሆኑን፣ የዜጎች የሰብዓዊ መብቶች እና ሰብዓዊ ጉዳዮች ቅድሚያ የተሰጠው በመሆኑን ገልጸዋል።ይህም መንግስት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ቁርጠኝነት እንዳለው የሚያሳይ መሆኑንም አብራርተዋል።በአሁኑ ወቅት ሕግ የማስከበር ዘመቻው መጠናቀቁን፣ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን እና ሕብረተሰቡ ወደ ዕለት ተዕለት ኑሮው እየተመለሰ መሆኑን ጠቅሰው፣ ከዚህ በኋላ የሚቀረው የጁንታው ቡድን አባላትን አድኖ ወደ ሕግ ፊት የማቅረብ ስራ መሆኑን እና ይህም በፌዴራል ፖሊስ በኩል እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።በተጨማሪም የስልክ፣ የመብራት እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች በተሻለ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን እንዲሁም የተፈናቀሉ ዜጎችም ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የመልሶ ማቋቋም ስራዎች እየተከናወኑ ስለመሆናቸው ገለፃ አድርገዋል።መንግስት ከዓለምአቀፍ የሰብዓዊ ተቋማት ጋር ተባብሮ እየሠራ መሆኑንና ይኼው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፣ ወደ ጎረቤት አገር የሸሹ ዜጎቻችንም ወደ አገራቸው ተመልሰው የሚቋቋሙበት ሁኔታ ከሚመለከታቸው የውስጥና የውጭ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ፣ ለዚሁም አራት የመጠለያ ካምፖች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል።በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ ለማጥናት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የጥናት ቡድኖችን ልኮ ካጣራ በኋላ የሰብዓዊ እርዳታ ኮሪዶር በመክፈት አስፈላጊውን ድጋፍ ማከፋፈል ላይ መሆኑን፣ በሠላም ሚኒስቴር አስተባባሪነትም ከዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ ለማቅረብ እንዲቻል እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስረድተዋል።የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ዋና ኃላፊ ፍራንኳይስ ሚያንዳ በበኩላቸው ጽህፈት ቤቱ እንደሰብዓዊ መብቶች ተቋም የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች እንዳይጣሱ፣ ተፈናቃዮች ተገቢው የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸውና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ለዚህም መንግስት አስፈላጊውን ሁኔታ እንዲያመቻች ከማበረታታት ባሻገር በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው አመልክተዋል።መንግስት እየወሰዳቸው የሚገኙ አዎንታዊ እንቅስቃሴዎችን በቅርበት እንደሚከታተልና እንደሚደግፍም ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%98%e1%8b%b5-%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%89%a5%e1%8b%93%e1%8b%8a-%e1%88%98%e1%89%a5%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%8a%a8%e1%8d%8d%e1%89%b0%e1%8a%9b-%e1%8a%ae%e1%88%9a%e1%88%bd%e1%8a%90/ | 467 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ ነው – ኢሰመኮ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 24, 2020 | Unknown | በመተከል በንፁሃን ላይ የደረሰውን ጥቃት ባለመከላከልም ሆነ በሌላ መልኩ ጥቃቱን የፈጸሙና ያባባሱ ሰዎችን ሕግ ፊት የማቅረብ ሂደት እንዲጀመር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ። “የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ ነው ” በሚል በመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ በንፁሃን ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ አውጥቷል።ኮሚሽኑ በመግለጫው በክልሉ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እተዳከመ መሄዱን በመግለጽ፤ የጥቃቱን ሂደት በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት እና ከተጎጂዎች ጋር በመነጋገር ሲከታተልና ሲያጣራ መቆየቱን አስታውቋል።ኮሚሽኑ ሁኔታውን እስካጣራበት ጊዜ ድረስ በቡለን ሆስፒታል 36 ተጎጂዎች እርዳታእየተደረገላቸው ሲሆን አብዛኞዎቹ በጥይት ሌሎቹ በቀስት የቆሰሉ መሆናቸውን አረጋግጧል በኩጂ ቀበሌ በሰው ሕይወት እና አካል ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የደረሱ ሰብሎችና የተሰበሰቡ ማሳዎች በእሳት መጋየታቸውም ጭምር መረጃ እንደደረሰው ገልጿል።በድባጤ ወረዳ ዶንበን ቀበሌ ስጋት የገባቸው ነዋሪዎች ከታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ቀዬአቸውን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነም ኮሚሽኑ መረጃ አለኝ ብሏል በመግለጫው።በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ተደጋጋሚነትና የክልሉን ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ አስመልክቶ፣ የፌዴራሉንና የክልሉን መንግሥታት የተጠናከረ ትብብርና ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሻ ኢሰመኮ ሲያሳስብ የቆየ ቢሆንም ጥቃቶቹ በመልክ እና በስፋት እየተባባሱ መምጣታቸው ነው የተገለጸው።በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸውን እና ለተፈናቀሉ ሰዎች የህክምና እና ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ እንዲሁም ተገቢው ማጣራትና ጥቃቱን ባለመከላከልም ሆነ በሌላ መልኩ ጥቃቱን የፈጸሙና ያባባሱ ሰዎችን ሕግ ፊት የማቅረብ ሂደት ከወዲሁ እንዲጀመርም ኮሚሽኑ አሳስቧል።በአካባቢው የሚገኘውን የፀጥታ ኃይልና መዋቅር የሰዎችን ደኅንነት ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በከፍተኛ ደረጃ በአፋጣኝ እንዲጠናከርም ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%8b%b0%e1%8a%85%e1%8a%95%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%88%9b%e1%88%a8%e1%8c%8b%e1%8c%88%e1%8c%a5-%e1%89%80%e1%8b%b3%e1%88%9a%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8a%95/ | 209 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማትን በዘላቂነት መምራት የሚያስችል መሪ ዕቅድ ይፋ ሆነ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 24, 2020 | Unknown | የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማትን በዘላቂነት መምራት የሚያስችል መሪ ዕቅድ ይፋ ሆነ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማትን በዘላቂነት መምራት የሚያስችል ስፓሻል መሪ ዕቅድ ይፋ ተደረገ።የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሸን የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ዕድገት ለማሳካትና ለመምራት የሚያስችል ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ስፓሻል ጥናት ረቂቅ ሪፓርት ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ዘለቄታዊ ልማት የሚመራ ስፓሻል ጥናት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።ጥናቱ እንደ አገር የመጀመሪያ መሆኑንና ኢትዮጵያ ያላትን ሀብት የመሬት ሁኔታ በማየት የተዘጋጀ ነው ብለዋል።አሁን ያሉትን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከመምራት ባለፈ ወደ ፊት የሚመሰረቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ከምስረታቸው ጀምሮ በማገዝና በመምራት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ፣ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስና በየትኛው አካባቢ ምን አይነት ኢንደስትሪ ፓርክ መገንባት አለበት የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማትን በዘላቂነት ለመምራት ይፋ በሆነው ስፓሻል መሪ ዕቅድ ላይ የመድረኩ ተሳታፊዎች እየተወያዮበት ሲሆን በዕቅዱ ላይ መሻሻል ያለባቸውን ነገሮች እንደሚያነሱ ይጠበቃል።(ምንጭ፡- ኢዜአ) | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%8b%b1%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%aa-%e1%8d%93%e1%88%ad%e1%8a%ae%e1%89%bd-%e1%88%8d%e1%88%9b%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%8b%98%e1%88%8b%e1%89%82%e1%8a%90%e1%89%b5/ | 149 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ለ“ትንሿ ኢትዮጵያ” ህጋዊ አውቅና ሰጠ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 24, 2020 | Unknown | በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ “ሊትል ኢትዮጵያ” ወይንም “ትንሿ ኢትዮጵያ” ለሚባለው አካባቢ የተሰጠው ስያሜ ህጋዊ አውቅና ማግኘቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍፁም አረጋ ተጋናግረዋል።አምባሳደር ፍፁም የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አስተዳደር እና የአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለ”ትንሿ ኢትዮጵያ” እውቅና እንዲያገኝ ላበረከቱት ድጋፍና አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።በዋሽንግጸን ዲሲ ለ”ትንሿ ኢትዮጵያ” የተሰጠው አውቅና ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማሳደጉም በላይ በማህበራዊ እና በባህላዊ ጉዳዮች ወዳጅነታቸውን እደሚያጎለብተው አምባሰደደሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ገልጸዋል። | https://waltainfo.com/am/%e1%8b%a8%e1%8b%8b%e1%88%bd%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%89%b0%e1%8a%95-%e1%8b%b2%e1%88%b2-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b-%e1%88%88%e1%89%b5%e1%8a%95%e1%88%bf-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5/ | 69 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ለ12ኛ ክፍል ፈተና 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገቡ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 23, 2020 | Unknown | ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚውሉ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር ወር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት ዕቅድ መያዙን ሚኒስቴሩ ገልጿል።ሚኒስቴሩ ከአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በመሆን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ዝግጅት በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥቷል።የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) በትምህርት ቤቶች ላይ ተተክለው ከሚኒስቴሩና የፈተናዎች ኤጀንሲ ሰርቨሮች ጋር የሚገናኙ 1 ሺህ 500 ቪሳት ቴክኖሎጂ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።መሳሪያዎቹን የሚተክሉ 250 ባለሙያዎች ስልጠና ወስደው ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።12 ሺህ ላፕቶፖች ደግሞ ለፈታኞች ለማከፋፈል ዝግጁ እንደሆኑ ያብራሩት ሚኒስትሩ፤ 450 ሺህ ታብሌቶች ደግሞ እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ መግለጻቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል። | https://waltainfo.com/am/%e1%88%8812%e1%8a%9b-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d-%e1%8d%88%e1%89%b0%e1%8a%93-450-%e1%88%ba%e1%88%85-%e1%89%b3%e1%89%a5%e1%88%8c%e1%89%b6%e1%89%bd-%e1%8a%a5%e1%88%b5%e1%8a%a8-%e1%89%b3%e1%88%85/ | 113 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በአብዬ የተሰማራው የ22ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ግዳጁን አጠናቀቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 23, 2020 | Unknown | በአብዬ የተሰማራው የ22ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ግዳጁን አጠናቆ ለተተኪው ለ25ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ማስረከቡ ተገለጸ።የ22ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አመራርና አባላት በነበራቸው የግዳጅ ቆይታ ስኬታማ ስራዎች ማከናወናቸውን የዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የኃይል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ ገልጸዋል።የዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የኃይል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ በርከክቡ ወቅት የሰላም አስከባሪ ሻለቃው የአካባቢው ማህበረሰብ ጎሳዎች እርስ በርስ ተከባብረው እንዲኖሩና ችግሮቻቸውን በጋራ ተጠቃሚነት መርህ እንዲፈቱ ባደረገው የማወያየትና የማደራደር ስራ በህብረተሰቡ ዘንድ አክብሮት የተቸረው ሚዛናዊና በገለልተኛ መርህ የተከናወነ እንደነበር ተናግረዋል።የ22ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ሰለሞን ተስፋ የተሰጣቸውን ቀጣና የዲንካና የሚስሪያ ጎሳዎች የጋራ መጠቀሚያ የሣር ግጦሽ እና የውሃ ኩሬ ያለበት በመሆኑ፣ ሁለቱም ጎሣዎች ሣይጋጩ በጋራ እንዲጠቀሙ በማድረግ፤ ችግሮች ሲከሰቱም በመፍታት ሀገሪቱ የሠጠችውን ግዳጅ አጠናቀናል ብለዋል፡፡የ25ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ሌንጮ ኤደኦ በበኩላቸው፣ በወሰዱት ስልጠናዎች መሠረት ሠራዊታቸው የተሠጠውን ግዳጅ ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።በዚህም ከ22ኛ ሻለቃ ያገኙትን ልምድና ተሞክሮ በመጠቀም የሀገሪቱን ስም እና ዝና በማስቀጠል አሻራችንን እናስቀጥላለን ሲሉ መግለፃቸውን ከኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%89%a5%e1%8b%ac-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b0%e1%88%9b%e1%88%ab%e1%8b%8d-%e1%8b%a822%e1%8a%9b-%e1%88%9e%e1%89%b0%e1%88%ab%e1%8b%ad%e1%8b%9d%e1%8b%b5-%e1%88%a0%e1%88%8b%e1%88%9d/ | 148 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች ቢወጡም የአፈፃፀም ክፍተት እንዳለባቸው ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 23, 2020 | Unknown | ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችሉ የህግ ማእቀፎች ቢወጡም የአፈፃፀም ክፍተት እንዳለባቸው ተገለጸ።በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ጋር “ሰላም ለሴቶች፤ ከጓዳ እስከ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እየተካሄደ ነው።በውይይቱ የወጣቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ፅጌረዳ ዘውዱ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ቢኖርም አሁንም የአፈፃፀም ክፍተት እንዳለበት ገልጸዋል።የህግና የፖሊሲ አፈፃፀም ጉድለትን ለማሳየት ወጣቶችና ሴቶች በሁሉም መልኩ ተሳታፊ መሆን እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።በዚህም በቀጣይ በተቀናጀ መልኩ ለመስራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ከየክልሉ ከተውጣጡ የወጣቶች ፎረም አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል።በሴቶች ጥቃት ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ተሞክሮም ከክልል የወጣቶች ፎረም አመራሮች ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።(በትዕግስት ዘላለም) | https://waltainfo.com/am/%e1%8d%86%e1%89%b3%e1%8b%8a-%e1%8c%a5%e1%89%83%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%88%88%e1%88%98%e1%8a%a8%e1%88%8b%e1%8a%a8%e1%88%8d-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%89%bd%e1%88%89-%e1%8b%a8%e1%88%85/ | 99 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|