label
class label 4
classes | headline
stringlengths 17
80
| text
stringlengths 1
16.8k
| headline_text
stringlengths 28
16.8k
| url
stringlengths 36
49
|
---|---|---|---|---|
3politics
| የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ሸኔ የፈጸማቸው ጥቃቶች ምን ያመለክታሉ? | መንግሥት ሸኔ የሚለው እና በሽብርተኝነት የፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባ ሦስት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል። የፌደራሉ እና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ሰላም እንዲያወርዱ የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ባለመሳካታቸው ወደ ጦርነት ገብተዋል። በመንግሥት በኩል የተለያዩ ወታደራዊ ዘመቻዎች ተደርገው፣ ታጣቂ ቡድኑ የአገሪቱ የደኅንነት ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል ቢባልም፣ ሰሞኑን የፈፀማቸው ጥቃቶች ግን የመንግሥትን እርምጃ ስኬታማነትን ጥያቄ ላይ ጥሎታል። ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ጥቃት ከፍቶ ከ40 በላይ የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል። በተመሳሳይ ዕለትም በቄለም እና ምሥራቅ ወለጋ፤ ደምቢዶሎ እና ጊምቢ ከተሞችም ጥቃት በመክፈት “የተሳካ ኦፕሬሽን” ማካሄዱን ገልጾ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም ቅዳሜ፣ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ ጥቃት ፈጽሞ ሴቶችና ህጻናት የሚገኙባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው ተገልጿል። ነገር ግን ቡድኑ ጥቃቱን የፈፀመው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ያደራጀው፣ ለየት ያለ የሚሊሻ ቡድን መሆኑን በመግለጽ ጥቃቱ ሲፈፀም ሠራዊቱ በአካባቢው እንዳልነበር ገልጿል። አክሎም ገለልተኛ በሆነ ወገን ምርመራ እንዲካሄድም ጥያቄ አቅርቧል። የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከሳምንታት በፊት የክልሉ እና የፌደራል መንግሥት ጀምረውት የነበረውን ወታደራዊ ዘመቻ አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጡ፣ የታጣቂው ቡድን የአገሪቱ ደኅንነት ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀው ነበር። ብሔራዊ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ምክር ቤት በበኩሉ የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን በገመገመበት ጊዜ በሕግ ማስከበር ዘመቻው ከሺህ በላይ ታጣቂዎች መገደላቸውን እና ዘመቻውም የተሳካ እንደነበር ገልጿል። የጋምቤላው፣ ደምቢዶሎ እና የጊምቢ ጥቃትም ከእነዚህ መግለጫዎች በኋላ የተከሰተ ነው። ከቶሌ ቀበሌ ጥቃት በፊት ያነጋገርናቸው የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ “በስፍራው የሚገኙ የመንግሥት አካላት [ለተከፈተው ጥቃት] እርምጃ መውሰዳቸውን ነው የማውቀው” በማለት ስለሰሞኑ ጥቃት ለቢቢሲ ተናግረዋል። “በጊምቢ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ቀበሌዎች ተኩስ ተከፍቷል። ልክ እንደ ደምቢዶሎ እና ጋምቤላ ሁሉ ተኩስ መክፈት ነበር። ግን እርምጃ ተወስዶባቸው ከተሞቹ ወደ ሰላማቸው ተመልሰዋል” ብለው ነበር። ታጣቂ ቡድኑ ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል ከተባለ በኋላ የዞን እና የክልል መቀመጫ የሆኑ ከተሞችን ገብቶ ጥቃት መፈፀሙ እንዴት ይታያል ተብለው ለተጠየቁት አቶ ከበደ ሲመልሱ “እኔ መንግሥት ታጣቂዎችን አጥፍቷቸዋል የሚል መረጃ የለኝም” ብለዋል። “. . .እርምጃ እየወሰድን ነው፤ ለአገር ደኅንነት ስጋት ሆነዋል። ለዚህም ነው በአዲስ መልክ እርምጃ እየወሰድን የምንገኘው።” የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቃል አቀባይ የሆኑት ኦዳ ተርቢ፣ ዘመቻዎቹን አስመልክቶ መንግሥት እያቀረበው ያለው ሪፖርት “የተለመደው ፕሮፓጋንዳ ነው” ሲሉ አጣጥለው አካባቢዎቹን “በስትራቴጂ” መልቀቃቸውን ተናግረው ነበር። የኦሮሞ ነጻነት ጦር አዛዥ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተገደሉበት የቶሌ ወረዳ ጥቃት በፊት ለቢቢሲ እንደተናገረው “አሁን፣ በረሃዎችን እና ገጠሮችን ብቻ ሳይሆን ጥበቃ ያላቸው ከተሞችም እየገባን ነው፤ የፖለቲካ ሰዎችን አስታጥቀው ቢያዘምቱም ጥበቃቸውን እያለፍን ነው” ሲል ተናግሯል። ከአንድ ሳምንት በፊት ታጣቂ ቡድኑ የጋምቤላ፣ የደምቢዶሎ እና የጊምቢ ከተሞችን የማጥቃታቸውን አስፈላጊነት ሲገልፁ፣ “አጥፍተናቸዋል የሚለውን የመንግሥትን ሐሰተኛ መረጃ እና ከፖሊስ በነጠቁት ያረጀ መሳርያ ነው የሚዋጉት ለሚለው [ፕሮፓጋንዳ] መልስ እንዲሆን ነው” ይላል መሮ። የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ላይ ከከፈቱት ጥቃት ጋር በተያያዘ 40 የሚሆኑ ግለሰቦች መገደላቸውን ቢቢሲ ከምንጮቹ ማረጋገጥ ችሎ ነበር። ኩምሳ ድሪባ ይህንን አስመልክቶ ሲናገር፣ በጦርነት በኩል መቁሰል እና መሞት ቢኖርም የደረሰው ጉዳት “የተባለውን አይደለም” ሲል ያስተባብላል። “እኛ ከተማይቱን ተቆጣጥረን በፈለግነው ሰዓት የፈለግነውን ፈጽመን ወጥተናል። ምን ፈጽማችሁ የሚለውን መግለጽ አያስፈልግም” ሲልም አክሏል። በተመሳሳይ ዕለት በተለይ በደምቢዶሎ ከተማ የመንግሥትን ኃይሎች ከሦስት ካምፖች ማባረር መቻላቸውን ኩምሳ ድሪባ ይናገራል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች፣ ታጣቂዎቹ ደምቢዶሎ ከተማ ማለዳ ከገቡ በኋላ ወደ ሆስፒታል አምርተው መድኃኒቶችን ጭነው መውጣታቸውን ተናግረዋል። ሚኒስቴር ዴታው አቶ ከበደም፣ ከተማ ውስጥ ገብተው ተኩስ መክፈታቸውን አረጋግጠዋል። የመንግሥት ታጣቂዎችም እርምጃ እንደወሰዱ ተናግረዋል። የታጣቂው ቡድን ዝርፊያ እና ግድያ እየፈፀመ ሕዝቡ እንዳያርስ እያደረገ ስለሆነ፣ መንግሥት እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል። ጃል መሮ ለዚህ ምላሽ ሲሰጥ “ሆስፒታል ገብተን ቁስለኞቻችንን አክመን ወጣን እንጂ ጭነን የወሰድነው መድኃኒት የለም” ይላል። የመከላከያ ሠራዊትን በሁሉም ስፍራ ማሰማራት ስለማይቻል፣ ሕዝቡ በዚህ በኩል የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ከበደ ጠይቀዋል። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተጋጋለበት ጊዜ ይህ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በምሥራቅ ወለጋ፣ ቤጊ እና ጊዳሚ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ነበር። ታጣቂዎች ከተሞች ገብተው መውጣታቸው፣ ለሕዝቡ ሰላም ስጋት አይሆንም ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ምላሽ ሲሰጡም “አሁን ሕዝቡን ይዘናል፤ መሬቱንም ሕዝቡንም የምንይዝበት ጊዜ አለ” ብለዋል። “ያለነው በጦርነት ውስጥ እንጂ ጭፈራ ቦታ ወይንም የእምነት ቤት አይደለም፤ በአንድ ሌሊት አገር መያዝ አይቻልም። እርምጃችንም በዚሁ ሂደት ውስጥ ያልፋል፤ ጦርነት ሞት እና መፈናቀልን ያዘ መሆኑ ይታወቃል” ብለዋል። ባለፉት ሦስት ዓመታት ታጣቂዎቹ በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች በሁለት ጦር መካከል ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ለቢበሲ ሲገልፁ ነበር። መንግሥትም፣ ሲከሰቱ ለነበሩት ግድያዎች እና መፈናቀሎች፣ በሽብርተኝነት የፈረጀውን ይህንን ታጣቂ ቡድን ሲከስ ቆይቷል። የኦሮሞ ነጻነት ጦር እና ግንባር በጋራ በ1976 (እኤአ) በወቅቱ የነበረውን ሥርዓት በመቃወም ነጻ አገር ለመመስረት በሚል ነበር የተቋቋሙት። የኦሮሞ ነጻነት ጦር፣ የግንባሩ የጦር ክንፍ ሆኖ ላለፉት 50 ዓመታት “ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት” ከተለያዩ ሥርዓቶች ጋር በትጥቅ ሲፋለም ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ አመራሩን በዋነኛነት ኤርትራ አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ክንፍ፣ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደ አገር ቤት ተመልሷል። በአገር ውስጥ ታጥቆ የነበረው ኃይል ግን የትጥቅ ትግልን የሙጥኝ በማለቱ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በይፋ ከጦሩ ራሱን መነጠሉን እንዲያሳውቅ አድርጓል። የኦሮሞ ነጻነት ጦር መሪ፣ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) “ዓላማችን የፖለቲካም የጦርም ግፊት የማይደርስበት የኦሮሞን ሕዝብ ነጻነትን ማረጋገጥ ነው፤ ነጻ እና ራሱን የቻለ ኦሮሞ እና ኦሮሚያን ለመመስረት እና የራስን እድል በራስ ለመወሰን ነው” ይላል። እንዲሁም “ኢትዮጵያ ውስጥ መጨቆን ቀርቶ፣ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በእኩልነት መኖር እፈልጋለሁ ካለም [የኦሮሞ ሕዝብ] እርሱን ለማስከበር እንታገላለን።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ሲወያዩ፣ ህወሓትን ጨምሮ በትጥቅ ትግል ከሚታገሉ የትኛውም አካላት ጋር በውይይት ችግሮችን ለመፍታት ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልፀው ነበር። የመንግሥት ኮሙኑኬሸን ጉዳዮች ቢሮ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ከበደም፣ የኦሮሞ ነጻነት ጦር ወደ ሰላማዊ ትግል እንዲመለስ እንፈለጋለን ብለዋል። “የኦሮሞ ሕዘብ ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ አልቋል የሚል እምነት ባይኖረኝም ጥያቄዎቹን በሰላማዊ መንገድ ማንሳት ይቻላል” ይላሉ። “ወደ ምሥራቅ ኦሮሚያ ያሉ ሕዝቦች፣ በአብዛኛው እያረሱ አይደለም። ቡናም እየሰበሰቡ አይደለም። ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስም አስቸጋሪ ነው። ዝርፊያ እና ንብረት ማቃጠል በዝቷል። ስለዚህ መንግሥት ሰላም ለማውረድ ትልቅ ፍላጎት አለው” ብለዋል። ጦሩ ወደ ሠላማዊ መንገድ ለመምጣት ዝግጁነት እንዳለው የተጠየቀው ጃል መሮ፣ “እንደ ሕጻን ልጅ በትንሽ ነገር ተደልሎ የሚገባ ኃይል የለም። የምንፈልገው ነገር አለ። እርሱን ትተን እጅ የምንሰጥበት ምክንያት የለም” ሲል መልሷል። አክሎም “እኛ በመረጥነው ስፍራ መንግሥትም እኛም ይሆንልናል በምንለው ሰው፣ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ጥሪ የሚቀርብልን ከሆነ፣ ለድርድር ዝግጁ ነን” ብሏል። ከዚህ ውጪ “እንደ ልጅ በከረሜላ ደልሎ የሚጠሩን ከሆነ የሚሞኝ የለም።” መንግሥት ሸኔ የሚለው ይህ ታጣቂ ቡድኑ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ በፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች ምክንያት ባለፈው ዓመት ከህወሓት ጋር ሽብርተኛ ቡድን መባሉ ይታወሳል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከህወሓት ጋር ግንኙነት አለው በሚል መንግሥት በተደጋጋሚ ሲከሰው የቆየ ሲሆን፣ ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰው ጦርነት ተስፋፍቶ የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራና አፋር ክልሎች ሲገቡ ሁለቱ ቡድኖች በጋራ መንግሥትን ለመውጋት እንደሚተባበሩ በይፋ አሳውቀዋል። | የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ሸኔ የፈጸማቸው ጥቃቶች ምን ያመለክታሉ? መንግሥት ሸኔ የሚለው እና በሽብርተኝነት የፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባ ሦስት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል። የፌደራሉ እና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ሰላም እንዲያወርዱ የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ባለመሳካታቸው ወደ ጦርነት ገብተዋል። በመንግሥት በኩል የተለያዩ ወታደራዊ ዘመቻዎች ተደርገው፣ ታጣቂ ቡድኑ የአገሪቱ የደኅንነት ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል ቢባልም፣ ሰሞኑን የፈፀማቸው ጥቃቶች ግን የመንግሥትን እርምጃ ስኬታማነትን ጥያቄ ላይ ጥሎታል። ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ጥቃት ከፍቶ ከ40 በላይ የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል። በተመሳሳይ ዕለትም በቄለም እና ምሥራቅ ወለጋ፤ ደምቢዶሎ እና ጊምቢ ከተሞችም ጥቃት በመክፈት “የተሳካ ኦፕሬሽን” ማካሄዱን ገልጾ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም ቅዳሜ፣ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ ጥቃት ፈጽሞ ሴቶችና ህጻናት የሚገኙባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው ተገልጿል። ነገር ግን ቡድኑ ጥቃቱን የፈፀመው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ያደራጀው፣ ለየት ያለ የሚሊሻ ቡድን መሆኑን በመግለጽ ጥቃቱ ሲፈፀም ሠራዊቱ በአካባቢው እንዳልነበር ገልጿል። አክሎም ገለልተኛ በሆነ ወገን ምርመራ እንዲካሄድም ጥያቄ አቅርቧል። የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከሳምንታት በፊት የክልሉ እና የፌደራል መንግሥት ጀምረውት የነበረውን ወታደራዊ ዘመቻ አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጡ፣ የታጣቂው ቡድን የአገሪቱ ደኅንነት ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀው ነበር። ብሔራዊ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ምክር ቤት በበኩሉ የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን በገመገመበት ጊዜ በሕግ ማስከበር ዘመቻው ከሺህ በላይ ታጣቂዎች መገደላቸውን እና ዘመቻውም የተሳካ እንደነበር ገልጿል። የጋምቤላው፣ ደምቢዶሎ እና የጊምቢ ጥቃትም ከእነዚህ መግለጫዎች በኋላ የተከሰተ ነው። ከቶሌ ቀበሌ ጥቃት በፊት ያነጋገርናቸው የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ “በስፍራው የሚገኙ የመንግሥት አካላት [ለተከፈተው ጥቃት] እርምጃ መውሰዳቸውን ነው የማውቀው” በማለት ስለሰሞኑ ጥቃት ለቢቢሲ ተናግረዋል። “በጊምቢ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ቀበሌዎች ተኩስ ተከፍቷል። ልክ እንደ ደምቢዶሎ እና ጋምቤላ ሁሉ ተኩስ መክፈት ነበር። ግን እርምጃ ተወስዶባቸው ከተሞቹ ወደ ሰላማቸው ተመልሰዋል” ብለው ነበር። ታጣቂ ቡድኑ ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል ከተባለ በኋላ የዞን እና የክልል መቀመጫ የሆኑ ከተሞችን ገብቶ ጥቃት መፈፀሙ እንዴት ይታያል ተብለው ለተጠየቁት አቶ ከበደ ሲመልሱ “እኔ መንግሥት ታጣቂዎችን አጥፍቷቸዋል የሚል መረጃ የለኝም” ብለዋል። “. . .እርምጃ እየወሰድን ነው፤ ለአገር ደኅንነት ስጋት ሆነዋል። ለዚህም ነው በአዲስ መልክ እርምጃ እየወሰድን የምንገኘው።” የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቃል አቀባይ የሆኑት ኦዳ ተርቢ፣ ዘመቻዎቹን አስመልክቶ መንግሥት እያቀረበው ያለው ሪፖርት “የተለመደው ፕሮፓጋንዳ ነው” ሲሉ አጣጥለው አካባቢዎቹን “በስትራቴጂ” መልቀቃቸውን ተናግረው ነበር። የኦሮሞ ነጻነት ጦር አዛዥ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተገደሉበት የቶሌ ወረዳ ጥቃት በፊት ለቢቢሲ እንደተናገረው “አሁን፣ በረሃዎችን እና ገጠሮችን ብቻ ሳይሆን ጥበቃ ያላቸው ከተሞችም እየገባን ነው፤ የፖለቲካ ሰዎችን አስታጥቀው ቢያዘምቱም ጥበቃቸውን እያለፍን ነው” ሲል ተናግሯል። ከአንድ ሳምንት በፊት ታጣቂ ቡድኑ የጋምቤላ፣ የደምቢዶሎ እና የጊምቢ ከተሞችን የማጥቃታቸውን አስፈላጊነት ሲገልፁ፣ “አጥፍተናቸዋል የሚለውን የመንግሥትን ሐሰተኛ መረጃ እና ከፖሊስ በነጠቁት ያረጀ መሳርያ ነው የሚዋጉት ለሚለው [ፕሮፓጋንዳ] መልስ እንዲሆን ነው” ይላል መሮ። የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ላይ ከከፈቱት ጥቃት ጋር በተያያዘ 40 የሚሆኑ ግለሰቦች መገደላቸውን ቢቢሲ ከምንጮቹ ማረጋገጥ ችሎ ነበር። ኩምሳ ድሪባ ይህንን አስመልክቶ ሲናገር፣ በጦርነት በኩል መቁሰል እና መሞት ቢኖርም የደረሰው ጉዳት “የተባለውን አይደለም” ሲል ያስተባብላል። “እኛ ከተማይቱን ተቆጣጥረን በፈለግነው ሰዓት የፈለግነውን ፈጽመን ወጥተናል። ምን ፈጽማችሁ የሚለውን መግለጽ አያስፈልግም” ሲልም አክሏል። በተመሳሳይ ዕለት በተለይ በደምቢዶሎ ከተማ የመንግሥትን ኃይሎች ከሦስት ካምፖች ማባረር መቻላቸውን ኩምሳ ድሪባ ይናገራል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች፣ ታጣቂዎቹ ደምቢዶሎ ከተማ ማለዳ ከገቡ በኋላ ወደ ሆስፒታል አምርተው መድኃኒቶችን ጭነው መውጣታቸውን ተናግረዋል። ሚኒስቴር ዴታው አቶ ከበደም፣ ከተማ ውስጥ ገብተው ተኩስ መክፈታቸውን አረጋግጠዋል። የመንግሥት ታጣቂዎችም እርምጃ እንደወሰዱ ተናግረዋል። የታጣቂው ቡድን ዝርፊያ እና ግድያ እየፈፀመ ሕዝቡ እንዳያርስ እያደረገ ስለሆነ፣ መንግሥት እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል። ጃል መሮ ለዚህ ምላሽ ሲሰጥ “ሆስፒታል ገብተን ቁስለኞቻችንን አክመን ወጣን እንጂ ጭነን የወሰድነው መድኃኒት የለም” ይላል። የመከላከያ ሠራዊትን በሁሉም ስፍራ ማሰማራት ስለማይቻል፣ ሕዝቡ በዚህ በኩል የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ከበደ ጠይቀዋል። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተጋጋለበት ጊዜ ይህ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በምሥራቅ ወለጋ፣ ቤጊ እና ጊዳሚ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ነበር። ታጣቂዎች ከተሞች ገብተው መውጣታቸው፣ ለሕዝቡ ሰላም ስጋት አይሆንም ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ምላሽ ሲሰጡም “አሁን ሕዝቡን ይዘናል፤ መሬቱንም ሕዝቡንም የምንይዝበት ጊዜ አለ” ብለዋል። “ያለነው በጦርነት ውስጥ እንጂ ጭፈራ ቦታ ወይንም የእምነት ቤት አይደለም፤ በአንድ ሌሊት አገር መያዝ አይቻልም። እርምጃችንም በዚሁ ሂደት ውስጥ ያልፋል፤ ጦርነት ሞት እና መፈናቀልን ያዘ መሆኑ ይታወቃል” ብለዋል። ባለፉት ሦስት ዓመታት ታጣቂዎቹ በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች በሁለት ጦር መካከል ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ለቢበሲ ሲገልፁ ነበር። መንግሥትም፣ ሲከሰቱ ለነበሩት ግድያዎች እና መፈናቀሎች፣ በሽብርተኝነት የፈረጀውን ይህንን ታጣቂ ቡድን ሲከስ ቆይቷል። የኦሮሞ ነጻነት ጦር እና ግንባር በጋራ በ1976 (እኤአ) በወቅቱ የነበረውን ሥርዓት በመቃወም ነጻ አገር ለመመስረት በሚል ነበር የተቋቋሙት። የኦሮሞ ነጻነት ጦር፣ የግንባሩ የጦር ክንፍ ሆኖ ላለፉት 50 ዓመታት “ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት” ከተለያዩ ሥርዓቶች ጋር በትጥቅ ሲፋለም ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ አመራሩን በዋነኛነት ኤርትራ አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ክንፍ፣ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደ አገር ቤት ተመልሷል። በአገር ውስጥ ታጥቆ የነበረው ኃይል ግን የትጥቅ ትግልን የሙጥኝ በማለቱ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በይፋ ከጦሩ ራሱን መነጠሉን እንዲያሳውቅ አድርጓል። የኦሮሞ ነጻነት ጦር መሪ፣ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) “ዓላማችን የፖለቲካም የጦርም ግፊት የማይደርስበት የኦሮሞን ሕዝብ ነጻነትን ማረጋገጥ ነው፤ ነጻ እና ራሱን የቻለ ኦሮሞ እና ኦሮሚያን ለመመስረት እና የራስን እድል በራስ ለመወሰን ነው” ይላል። እንዲሁም “ኢትዮጵያ ውስጥ መጨቆን ቀርቶ፣ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር በእኩልነት መኖር እፈልጋለሁ ካለም [የኦሮሞ ሕዝብ] እርሱን ለማስከበር እንታገላለን።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ሲወያዩ፣ ህወሓትን ጨምሮ በትጥቅ ትግል ከሚታገሉ የትኛውም አካላት ጋር በውይይት ችግሮችን ለመፍታት ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልፀው ነበር። የመንግሥት ኮሙኑኬሸን ጉዳዮች ቢሮ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ከበደም፣ የኦሮሞ ነጻነት ጦር ወደ ሰላማዊ ትግል እንዲመለስ እንፈለጋለን ብለዋል። “የኦሮሞ ሕዘብ ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ አልቋል የሚል እምነት ባይኖረኝም ጥያቄዎቹን በሰላማዊ መንገድ ማንሳት ይቻላል” ይላሉ። “ወደ ምሥራቅ ኦሮሚያ ያሉ ሕዝቦች፣ በአብዛኛው እያረሱ አይደለም። ቡናም እየሰበሰቡ አይደለም። ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስም አስቸጋሪ ነው። ዝርፊያ እና ንብረት ማቃጠል በዝቷል። ስለዚህ መንግሥት ሰላም ለማውረድ ትልቅ ፍላጎት አለው” ብለዋል። ጦሩ ወደ ሠላማዊ መንገድ ለመምጣት ዝግጁነት እንዳለው የተጠየቀው ጃል መሮ፣ “እንደ ሕጻን ልጅ በትንሽ ነገር ተደልሎ የሚገባ ኃይል የለም። የምንፈልገው ነገር አለ። እርሱን ትተን እጅ የምንሰጥበት ምክንያት የለም” ሲል መልሷል። አክሎም “እኛ በመረጥነው ስፍራ መንግሥትም እኛም ይሆንልናል በምንለው ሰው፣ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ጥሪ የሚቀርብልን ከሆነ፣ ለድርድር ዝግጁ ነን” ብሏል። ከዚህ ውጪ “እንደ ልጅ በከረሜላ ደልሎ የሚጠሩን ከሆነ የሚሞኝ የለም።” መንግሥት ሸኔ የሚለው ይህ ታጣቂ ቡድኑ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ በፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች ምክንያት ባለፈው ዓመት ከህወሓት ጋር ሽብርተኛ ቡድን መባሉ ይታወሳል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከህወሓት ጋር ግንኙነት አለው በሚል መንግሥት በተደጋጋሚ ሲከሰው የቆየ ሲሆን፣ ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰው ጦርነት ተስፋፍቶ የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራና አፋር ክልሎች ሲገቡ ሁለቱ ቡድኖች በጋራ መንግሥትን ለመውጋት እንደሚተባበሩ በይፋ አሳውቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c1rqpll30z7o |
3politics
| የደብረ ብርሃን መታወቂያ የሌላቸው ግለሰቦች በከተማዋ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ተገለጸ | በአማራ ክልል በደብረ ብርሃን የከተማዋ መታወቂያ የሌላቸው ግለሰቦች ከህዳር 16/2014 ዓ.ም ጀምሮ በቀን እንቅስቃሴ ከማድረግ መታገዳቸውን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚኒኬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ የከተማዋ ነዋሪዎችና የደብረ ብርሃን ከተማ መታወቂያ ያላቸው ግለሰቦች ብቻ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ ይችላሉ ብሏል። ለዚህም የከተማው አስተዳደር የሰጠው ምክንያት "በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ሰርጎ ገቦች በመግባት አካባቢን የማጥናትና መረጃ የመስጠት ሥራ እየሰሩ እንደሆነ ስለተደረሰበት ነው" ብሏል። "ሰርጎ ገቦችን መለየትና አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች ነጻ ለማድረግ፣ ለከተማውና ለነዋሪዎች ደኅንነት ሲባል በከተማው በየትኛውም አካባቢ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪና መታወቂያ ካላቸው ሰዎች ውጪ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም" ብሏል። በጦርነቱ ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ የተጠለሉ ነዋሪዎችም በተዘጋጀላቸው መጠለያ እንዲገቡም ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል። የትግራይ ኃይሎች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 225 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ሸዋ ሮቢት ከተማን መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል። ይህንን በተመለከተ ምንም ገለልተኛ ማረጋገጫ የለም። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጦርነቱን ለመምራት ከወሰኑ በኋላ ጦሩ ብዙ ስኬቶችን ማስመዝገቡን እና ድሉም "በጣም ቅርብ" ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማፂያኑን ለመዋጋት ወደ ጦር ግንባር በመሄድ ሠራዊቱን እመራለሁ ያሉ ሲሆን የትግራይ ተዋጊዎችም ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እያመሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አጎራባቾቹ አማራና አፋር ክልል የተዛመተው ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሰብዓዊ ቀውሶችን ማስከተሉን ቀጥሏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በረሃብ አፋፍ ላይ ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታትና የእርዳታ ድርጅቶች አመልክተዋል። | የደብረ ብርሃን መታወቂያ የሌላቸው ግለሰቦች በከተማዋ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ተገለጸ በአማራ ክልል በደብረ ብርሃን የከተማዋ መታወቂያ የሌላቸው ግለሰቦች ከህዳር 16/2014 ዓ.ም ጀምሮ በቀን እንቅስቃሴ ከማድረግ መታገዳቸውን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚኒኬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ የከተማዋ ነዋሪዎችና የደብረ ብርሃን ከተማ መታወቂያ ያላቸው ግለሰቦች ብቻ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ ይችላሉ ብሏል። ለዚህም የከተማው አስተዳደር የሰጠው ምክንያት "በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ሰርጎ ገቦች በመግባት አካባቢን የማጥናትና መረጃ የመስጠት ሥራ እየሰሩ እንደሆነ ስለተደረሰበት ነው" ብሏል። "ሰርጎ ገቦችን መለየትና አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች ነጻ ለማድረግ፣ ለከተማውና ለነዋሪዎች ደኅንነት ሲባል በከተማው በየትኛውም አካባቢ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪና መታወቂያ ካላቸው ሰዎች ውጪ በቀን እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም" ብሏል። በጦርነቱ ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ የተጠለሉ ነዋሪዎችም በተዘጋጀላቸው መጠለያ እንዲገቡም ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል። የትግራይ ኃይሎች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 225 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ሸዋ ሮቢት ከተማን መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል። ይህንን በተመለከተ ምንም ገለልተኛ ማረጋገጫ የለም። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጦርነቱን ለመምራት ከወሰኑ በኋላ ጦሩ ብዙ ስኬቶችን ማስመዝገቡን እና ድሉም "በጣም ቅርብ" ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማፂያኑን ለመዋጋት ወደ ጦር ግንባር በመሄድ ሠራዊቱን እመራለሁ ያሉ ሲሆን የትግራይ ተዋጊዎችም ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እያመሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አጎራባቾቹ አማራና አፋር ክልል የተዛመተው ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሰብዓዊ ቀውሶችን ማስከተሉን ቀጥሏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በረሃብ አፋፍ ላይ ሲሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታትና የእርዳታ ድርጅቶች አመልክተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59412878 |
3politics
| ታይዋን ለቻይና እንደማትንበረከክ መሪዋ ተናገሩ | በታይዋን ላይ ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት በአሁኑ ወቅት ፕሬዚዳንት ፃይ ኢንግ ዊን አገራቸው ለቻይና ጫና እንደማንትንበረከክና ባላት ዴሞክራሲያዊ የፅንሰ ሃሳብ መርሆች እየተዳደረች ትቀጥላለች በማለት ተናግረዋል። መሪዋ አክለውም "ስኬታችን በጨመረ ቁጥር ከቻይና የሚደርስብን ጫናም የከፋ ይሆናል" ብለዋል። በታይዋን ብሄራዊ ክብረ በዓል ንግግር ያደረጉት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸው "ውህደቱን ለማጠናቀቅ" ቃል ገብተዋል። ታይዋን ራሷን እንደ ሉዓላዊ ግዛት ብትቆጥርም በቻይና በኩል ተመሳሳይ አረዳድ የለም በተፃራሪው ከቻይና እንደተገነጠለች ግዛት ነው የምትመለከተው። ቻይና የምትለውንም ውህደት ለማሳካት ኃይል ልትጠቀም ትችላለች። ለዚህም እንደ ማሳያ የሚሆነው ቻይና ከቅርብ ወናት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጦር ጄት ወደ ታይዋን የአየር መከላከያ ቀጠና መላኳ ነው።አንዳንድ ተንታኞች በረራዎቹ ለታይዋን ፕሬዝዳንት እንደ ማስጠንቀቂያ ሊታዩ ይችላሉ ብለዋል። ፕሬዚዳንቷ በበኩላቸው "ታይዋን ለዴሞክራሲ በመወገን ቆማለች" በማለት ተናግረዋል። ደሴቲቷ ነፃነት፣ ዴሞክራሲ ወይም ሉዓላዊነትን በነፈገ መልኩ "ቻይና የዘረጋችልንን መስመር" እንድትወስድ ማስገደድ እንደማይቻል አስረድተዋል። የቻይና ወታደራዊ በረራዎች ወደ ታይዋን የአየር መከላከያ ቀጠና መስመር አልፈው መግባታቸው በብሔራዊ እና በአቪዬሽን ደህንነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቷ " ሁኔታው በባለፉት 72 ዓመታት በነበረው ወቅት የበለጠ የተወሳሰበ እና የማይገመት ነበር" ብለዋል። ታይዋን "በችኮላ እርምጃ አትወስድም" ቢሉም ነገር ግን መከላከያዋን ታጠናክራለች ብለዋል። መሪዋ ከቻይና አመራሮች ጋር በእኩል ደረጃ ለመወያየት ያቀረቡትን ሃሳብ በድጋሜ ቢያነሱም "ተገንጣይ" የሚል ስያሜ የሰጧቸው የቻይና አመራሮች ውድቅ አድርገውታል። ፕሬዚዳንቷ እንደገና በባለፈው ዓመት ሲመረጡ በከፍተኛ ድምፅ ሲሆን ቻይናን ለመገደደር ቃል ገብተዋል። ፕሬዚዳንቷ ንግግር ካደረጉ በኋላም የታይዋን ተዋጊ አውሮፕላኖች ሲያንዣብቡ ታይተዋል። ስለ ቻይና እና ታይዋን ጥቂት መሰረታዊ ነገሮች • ቻይና እና ታይዋን ለምን ደካማ ግንኙነት ኖራቸው? በአውሮፓውያኑ 1940 ዎቹ ቻይና እና ታይዋን በእርስ በእርስ ጦርነት ተከፋፈሉ። ነገር ግን ቻይና አሁንም ቢሆን ደሴቲቷ አስፈላጊ ከሆነ በኃይልም ቢሆን ትመለሳለች የሚል እምነት አላት። • ታይዋን የምትተዳደረው እንዴት ነው? ደሴቲቱ የራሷ ሕገ መንግሥት ፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሪዎች ፣ እና በጦሩ 300 ሺህ ገደማ የሚሆኑ የሰራዊት አባላት አሏት። •እንደ ሃገር ለታይዋን ማን እውቅና ሰጣት? ለታይዋን ዕውቅና የሰጧት ጥቂት አገሮች ብቻ ናቸው። በርካታዎቹ ቤጂንግን መቀመጫ ላደረገው የቻይና መንግሥት እውቅና ይሰጣሉ። አሜሪካ ከታይዋን ጋር ኦፊሴላዊ ግንኙነት የላትም ነገር ግን ደሴቲቱ እራሷን ለመከላከል የሚያስችል ድጋፍ እንድትሰጥ የሚጠይቅ ሕግ አላት። | ታይዋን ለቻይና እንደማትንበረከክ መሪዋ ተናገሩ በታይዋን ላይ ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት በአሁኑ ወቅት ፕሬዚዳንት ፃይ ኢንግ ዊን አገራቸው ለቻይና ጫና እንደማንትንበረከክና ባላት ዴሞክራሲያዊ የፅንሰ ሃሳብ መርሆች እየተዳደረች ትቀጥላለች በማለት ተናግረዋል። መሪዋ አክለውም "ስኬታችን በጨመረ ቁጥር ከቻይና የሚደርስብን ጫናም የከፋ ይሆናል" ብለዋል። በታይዋን ብሄራዊ ክብረ በዓል ንግግር ያደረጉት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸው "ውህደቱን ለማጠናቀቅ" ቃል ገብተዋል። ታይዋን ራሷን እንደ ሉዓላዊ ግዛት ብትቆጥርም በቻይና በኩል ተመሳሳይ አረዳድ የለም በተፃራሪው ከቻይና እንደተገነጠለች ግዛት ነው የምትመለከተው። ቻይና የምትለውንም ውህደት ለማሳካት ኃይል ልትጠቀም ትችላለች። ለዚህም እንደ ማሳያ የሚሆነው ቻይና ከቅርብ ወናት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጦር ጄት ወደ ታይዋን የአየር መከላከያ ቀጠና መላኳ ነው።አንዳንድ ተንታኞች በረራዎቹ ለታይዋን ፕሬዝዳንት እንደ ማስጠንቀቂያ ሊታዩ ይችላሉ ብለዋል። ፕሬዚዳንቷ በበኩላቸው "ታይዋን ለዴሞክራሲ በመወገን ቆማለች" በማለት ተናግረዋል። ደሴቲቷ ነፃነት፣ ዴሞክራሲ ወይም ሉዓላዊነትን በነፈገ መልኩ "ቻይና የዘረጋችልንን መስመር" እንድትወስድ ማስገደድ እንደማይቻል አስረድተዋል። የቻይና ወታደራዊ በረራዎች ወደ ታይዋን የአየር መከላከያ ቀጠና መስመር አልፈው መግባታቸው በብሔራዊ እና በአቪዬሽን ደህንነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቷ " ሁኔታው በባለፉት 72 ዓመታት በነበረው ወቅት የበለጠ የተወሳሰበ እና የማይገመት ነበር" ብለዋል። ታይዋን "በችኮላ እርምጃ አትወስድም" ቢሉም ነገር ግን መከላከያዋን ታጠናክራለች ብለዋል። መሪዋ ከቻይና አመራሮች ጋር በእኩል ደረጃ ለመወያየት ያቀረቡትን ሃሳብ በድጋሜ ቢያነሱም "ተገንጣይ" የሚል ስያሜ የሰጧቸው የቻይና አመራሮች ውድቅ አድርገውታል። ፕሬዚዳንቷ እንደገና በባለፈው ዓመት ሲመረጡ በከፍተኛ ድምፅ ሲሆን ቻይናን ለመገደደር ቃል ገብተዋል። ፕሬዚዳንቷ ንግግር ካደረጉ በኋላም የታይዋን ተዋጊ አውሮፕላኖች ሲያንዣብቡ ታይተዋል። ስለ ቻይና እና ታይዋን ጥቂት መሰረታዊ ነገሮች • ቻይና እና ታይዋን ለምን ደካማ ግንኙነት ኖራቸው? በአውሮፓውያኑ 1940 ዎቹ ቻይና እና ታይዋን በእርስ በእርስ ጦርነት ተከፋፈሉ። ነገር ግን ቻይና አሁንም ቢሆን ደሴቲቷ አስፈላጊ ከሆነ በኃይልም ቢሆን ትመለሳለች የሚል እምነት አላት። • ታይዋን የምትተዳደረው እንዴት ነው? ደሴቲቱ የራሷ ሕገ መንግሥት ፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሪዎች ፣ እና በጦሩ 300 ሺህ ገደማ የሚሆኑ የሰራዊት አባላት አሏት። •እንደ ሃገር ለታይዋን ማን እውቅና ሰጣት? ለታይዋን ዕውቅና የሰጧት ጥቂት አገሮች ብቻ ናቸው። በርካታዎቹ ቤጂንግን መቀመጫ ላደረገው የቻይና መንግሥት እውቅና ይሰጣሉ። አሜሪካ ከታይዋን ጋር ኦፊሴላዊ ግንኙነት የላትም ነገር ግን ደሴቲቱ እራሷን ለመከላከል የሚያስችል ድጋፍ እንድትሰጥ የሚጠይቅ ሕግ አላት። | https://www.bbc.com/amharic/news-58860861 |
2health
| ተመራማሪዎች የ53 ዓመቷን ሴት ቆዳ የ23 ዓመት የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ሠሩ | የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች የ53 ዓመቷን ሴት ቆዳ የ23 ዓመት እንዲመስል አድርገው መሥራት ችለዋል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህንን ፀረ ዕድሜ ግኝት ለሌሎችም የሰውነት ክፍሎች ማድረግ ይቻላል። የዚህ ጥናት ዓላማ ከዕድሜ መግፋት ጋር ለሚመጡ እንደ የስኳር በሽታ፣ የልብ በሽታና የነርቭ ችግሮች መፍትሔ ማፈላለግ ነው። ከ25 ዓመታት በፊት ዶሊ የተባለችውን በግ የፈጠረው ቴክኖሎጂ ነው ያረጀ ቆዳን የወጣት ያስመሰለው። የካምብሪጁ ባብራሃም ተቋም የጥናት ቡድን መሪ ፕሮፌሰር ዎልፍ ሪክ ናቸው። ይህ ግኝት ሰዎች ቢያረጁ በሽታ ሳያገኛቸው ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ድጋፍ ያደርጋል ብለው እንደሚያምኑ ለቢቢሲ ይገልጣሉ። "ስለዚህ ጉዳይ ስናልም ነው የኖርነው። በርካታ በሽታዎች ከዕድሜ መግፋት ጋር እየባሱ ይሄዳሉ፤ ታድወያ ሰዎችን ከዚህ ሰቀቀን መገላለግ ያስደስታል" ይላሉ። ነገር ግን ይላሉ ፕሮፌሰሩ፤ ጥናቱ ገና ጅምር እና ብዙ ሥራ የሚጠይቅ ነው ይላሉ። ይህ ግኝት ከቤተ-ሙከራ ወጥቶ ወደ ክሊኒክ ከመሄዱ በፊት ብዙ ውጣ ውረዶችን ማለፍ ይጠበቅበታል። ቢሆንም የቆዳ ዕድሜን ቀንሶ ማየት ትልቅ ድል እንደሆነ ፕሮፌሰሩ አይክዱም። የዚህ የተሸበሸበ ቆዳን መልሶ ወጣት የማድረግ ግኝት መላ ከ1990ዎቹ አንድ ጥናት የተመዘዘው ነው። በወቅቱ የኤደንብራ አጥኚዎች የቆዳ ሴል ወስደው ወደ ሽል ቀይረውት ዶሊ ብለው የጠሯትን በግ ፈጥረው ነበር። አጥኚዎቹ በጊዜው ዓላማቸው የቤተ-ሙከራ በግ አሊያም ሰው መፍጠር አልነበረም፤ ለሰው ልጅ የሚሆን ኢምብሮይክ ስቴም የተባለ ሴል መፍጠር እንጂ። ይህን ሴል ለውጥ ለሚያስፈልጋቸው የሰውነታችን ክፍሎች መቀየሪያ ማዋል ይችላሉ። ዶሊ የተፈጠረችበት መንገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል። የፕሮፌሰር ሪክ ቡድን የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ነው የ53 ዓመት ዕድሜ ያለውን ቆዳ የ23 ማስመሰል የቻሉት። "ለመጀመሪያ ጊዜ ጥናት ስናደርግበት የነበረው ቆዳ በ30 ዓመታት ወጣት መሆኑን ስሰማ የተሰማኝን ደስታ መቆጣጠር አቅቶኝ ነበር" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ጥናቱ አሁኑኑ ወደ ሥራ የማይገባው አሁን ባለበት ደረጃ ተግባራዊ ቢደረግ በካንሰር የመያዝ ዕድልን ስለሚጨምር ነው። ነገር ግን ቆዳን እንዲህ አሳምሮ ወጣት ማድረግ እንደሚቻል ከታወቀ የጎንዮሽ ጉዳቱ ዝቅ ያለ መላ መፈለግ አያዳግትም። "ዓላማችን ሰዎች ዕድሜያቸው እንዲጨምር ማድረግ አይደለም፤ ቀሪ ዘመናቸውን ጤናማ ሆነው እንዲኖሩ ማድረግ እንጂ። ሰዎች ጤናማ ሆነው ማርጀት ይችላሉ" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። አልፎም ሰዎች በአደጋ ምክንያት ቆዳቸው ጉዳት ሲደርስበት አዲሱ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል አጥኚው ይጠቁማሉ። ቀጣዩ እርምጃ ይህ ቴክኖሎጂ ልክ እነጡንቻ፣ ጉበትና የደም ሴል ላይ ሊሠራ ይችላል ወይ የሚለውን ማጥናት ነው። የዘርፉ ሰዎች የዚህ ቴክኖሎጂ ውጤት ገበያ ላይ ወጥቶ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ይላሉ። ይህ አዲስ ግኝት ሙሉ የሰውነት ክፍልን እንዳያረጅ ማድረግ አሊያም የማያስረጅ ክኒና ወደ መፍጠር ይወስደን ይሆን የሚለው ጥያቄ አሁን ምላሽ ሊያገኝ ይችላል ይላሉ ፕሮፌሰሩ። | ተመራማሪዎች የ53 ዓመቷን ሴት ቆዳ የ23 ዓመት የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ሠሩ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች የ53 ዓመቷን ሴት ቆዳ የ23 ዓመት እንዲመስል አድርገው መሥራት ችለዋል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህንን ፀረ ዕድሜ ግኝት ለሌሎችም የሰውነት ክፍሎች ማድረግ ይቻላል። የዚህ ጥናት ዓላማ ከዕድሜ መግፋት ጋር ለሚመጡ እንደ የስኳር በሽታ፣ የልብ በሽታና የነርቭ ችግሮች መፍትሔ ማፈላለግ ነው። ከ25 ዓመታት በፊት ዶሊ የተባለችውን በግ የፈጠረው ቴክኖሎጂ ነው ያረጀ ቆዳን የወጣት ያስመሰለው። የካምብሪጁ ባብራሃም ተቋም የጥናት ቡድን መሪ ፕሮፌሰር ዎልፍ ሪክ ናቸው። ይህ ግኝት ሰዎች ቢያረጁ በሽታ ሳያገኛቸው ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ድጋፍ ያደርጋል ብለው እንደሚያምኑ ለቢቢሲ ይገልጣሉ። "ስለዚህ ጉዳይ ስናልም ነው የኖርነው። በርካታ በሽታዎች ከዕድሜ መግፋት ጋር እየባሱ ይሄዳሉ፤ ታድወያ ሰዎችን ከዚህ ሰቀቀን መገላለግ ያስደስታል" ይላሉ። ነገር ግን ይላሉ ፕሮፌሰሩ፤ ጥናቱ ገና ጅምር እና ብዙ ሥራ የሚጠይቅ ነው ይላሉ። ይህ ግኝት ከቤተ-ሙከራ ወጥቶ ወደ ክሊኒክ ከመሄዱ በፊት ብዙ ውጣ ውረዶችን ማለፍ ይጠበቅበታል። ቢሆንም የቆዳ ዕድሜን ቀንሶ ማየት ትልቅ ድል እንደሆነ ፕሮፌሰሩ አይክዱም። የዚህ የተሸበሸበ ቆዳን መልሶ ወጣት የማድረግ ግኝት መላ ከ1990ዎቹ አንድ ጥናት የተመዘዘው ነው። በወቅቱ የኤደንብራ አጥኚዎች የቆዳ ሴል ወስደው ወደ ሽል ቀይረውት ዶሊ ብለው የጠሯትን በግ ፈጥረው ነበር። አጥኚዎቹ በጊዜው ዓላማቸው የቤተ-ሙከራ በግ አሊያም ሰው መፍጠር አልነበረም፤ ለሰው ልጅ የሚሆን ኢምብሮይክ ስቴም የተባለ ሴል መፍጠር እንጂ። ይህን ሴል ለውጥ ለሚያስፈልጋቸው የሰውነታችን ክፍሎች መቀየሪያ ማዋል ይችላሉ። ዶሊ የተፈጠረችበት መንገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል። የፕሮፌሰር ሪክ ቡድን የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ነው የ53 ዓመት ዕድሜ ያለውን ቆዳ የ23 ማስመሰል የቻሉት። "ለመጀመሪያ ጊዜ ጥናት ስናደርግበት የነበረው ቆዳ በ30 ዓመታት ወጣት መሆኑን ስሰማ የተሰማኝን ደስታ መቆጣጠር አቅቶኝ ነበር" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ጥናቱ አሁኑኑ ወደ ሥራ የማይገባው አሁን ባለበት ደረጃ ተግባራዊ ቢደረግ በካንሰር የመያዝ ዕድልን ስለሚጨምር ነው። ነገር ግን ቆዳን እንዲህ አሳምሮ ወጣት ማድረግ እንደሚቻል ከታወቀ የጎንዮሽ ጉዳቱ ዝቅ ያለ መላ መፈለግ አያዳግትም። "ዓላማችን ሰዎች ዕድሜያቸው እንዲጨምር ማድረግ አይደለም፤ ቀሪ ዘመናቸውን ጤናማ ሆነው እንዲኖሩ ማድረግ እንጂ። ሰዎች ጤናማ ሆነው ማርጀት ይችላሉ" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። አልፎም ሰዎች በአደጋ ምክንያት ቆዳቸው ጉዳት ሲደርስበት አዲሱ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል አጥኚው ይጠቁማሉ። ቀጣዩ እርምጃ ይህ ቴክኖሎጂ ልክ እነጡንቻ፣ ጉበትና የደም ሴል ላይ ሊሠራ ይችላል ወይ የሚለውን ማጥናት ነው። የዘርፉ ሰዎች የዚህ ቴክኖሎጂ ውጤት ገበያ ላይ ወጥቶ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ይላሉ። ይህ አዲስ ግኝት ሙሉ የሰውነት ክፍልን እንዳያረጅ ማድረግ አሊያም የማያስረጅ ክኒና ወደ መፍጠር ይወስደን ይሆን የሚለው ጥያቄ አሁን ምላሽ ሊያገኝ ይችላል ይላሉ ፕሮፌሰሩ። | https://www.bbc.com/amharic/news-61034943 |
3politics
| በጦር መሳሪያ ግዢ ምክንያት ፍጥጫ ውስጥ የገቡት ቱርክና አሜሪካ | የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቱርክ አቻቸው ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ዛሬ ሩሲያ ውስጥ ተገናኝተው ይነጋገራሉ። ሁለቱ መሪዎች ከሚመክሩባቸው ጉዳዮች መካከል የጦር መሳሪያ ግዢ እና የሶሪያ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳዎች ይሆናሉ ተብሏል። ቱርክ ከሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን መግዛቷ ከአሜሪካ ጋር ውዝግብ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። "አሜሪካ ክለከላ ማድረግ አትችልም" ቱርክ ከሩሲያ ለመግዛት ያሰብኩትን ጦር መሳሪያ በተመለከተ አሜሪካ ምንም አይነት ክልከላ ልታደርግ አትችልም ስትል የአሜሪካንን አቋም ተቃውማለች። የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ቱርክ በርካታ ቁጥር ያላቸው ስልታዊ የሚሳኤል ሥርዓቶችን ከሩሲያ ለመግዛት እቅድ እንዳላት አስታውቀዋል። ፕሬዝደንት ኤርዶሃን አገራቸው ለሁለትኛ ዙር ኤስ-400 ከምድር ወደ ሰማይ የሚወነጨፉ ሩሲያ ሠራሽ ሚሳኤሎችን ለመግዛት በዝግጅት ላይ መሆኗ በታወቀበት ጊዜ አሜሪካ ተቃውሞ አሰምታለች። በዚህም ሳቢያ ቱርክ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አጋሯ አሜሪካ ጋር ውዝግብ ውስጥ የከተታት ሲሆን ተጨማሪ ማዕቀብ ሊያስጥልባት ይችላል ተብሏል። አሜሪካ ሩሲያ ሰራሾቹ ኤስ-400 ሚሳኤሎች ለኤፍ-35 ተዋጊ ጄቶቼ ስጋት ናቸው ትላለች። ከዚህ በተጨማሪም ዋሽንግተን ሚሳኤሎቹ ለኔቶ የድንበር መከላከያ ሥርዓት አደጋ ናቸው ትላለች። ቱርክ በበኩሏ የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን አጥጋቢ በሆነ መልኩ ከኔቶ አባል አገራት መግዛት እንዳልቻለች በማመልከት ከሩሲያ ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰች ገልጻለች። "ሊኖረን ስለሚችለው የጦር መሳሪያ ዓይነት ከየትኛውም አገር በየትኛውም ደረጃ ማንም ጣልቃ መግባት አይችልም" ሲሉ ፕሬዝደንት ኤርዶሃን በአሜሪካው ሲቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ በቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል። "በዚህ ላይ ማንም ጣልቃ መግባት አይችልም። እንዲህ አይነት ውሳኔ የምንሰጠው እኛ ብቻ ነን" በማለት ኤርዶሃን የአሜሪካንን አቋም ተችተዋል። ከወራት በፊት ቱርክ የመጀመሪያወን ዙር ኤስ-400 ሚሳኤሎችን ከሩሲያ መግዛቷን ተከትሎ አሜሪካ የቱርክ መከላከያ ኢንደስትሪ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ እሰማኢል ዴሚር እና ሦስት የተቋሙ ሠራተኞች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። ከዚህ በተጨማሪም ቱርክ ተመሳሳይ የጦር መሳሪያ ግዢ የምትፈጽም ከሆነ ሌላ ማዕቀብ እንደሚጣልባት አሜሪካ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች። "በየትኛውም ደረጃ ቱርክ ኤስ-400 የሚሳኤል ሥርዓቶችን እንዳትይዝ ወይም የትኛውንም አይነት ሩሲያ ሰራሽ ጦር መሳሪያዎችን ከመግዛት እንድትቆጠብ እናሳስባለን" ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አሳስበዋል። ቃል አቀባዩ ጨምረውም አሜሪካ ቱርክን እንደ ወዳጅ አገር ነው የምትመለከታት ካሉ በኋላ፤ አለመግባባት ውስጥ ሆነን እንኳ ግንኙነታችንን ማጠናክር ነው የምንፈልገው ብለዋል። ይሁን እንጂ ቱርክ ሁለተኛውን ዙር ኤስ-400 ሚሳኤሎችን የምትረከብበትን መንገድ በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ንግግር እያደረገች ትገኛለች። ኤርዶሃን ዛሬ በሩሲያ ተገኝተው ከፕሬዝደንት ቭላድረሚር ፑቲን ጋር በሚያደርጉት ውይይት ዋነኛ ጉዳያቸው ኤስ-400 ሚሳኤሎች እና በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ያለው ግጭት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የቱርክ እና ሩሲያ የውጭ ፖሊሲ አቋም ቱርክ እና ሩሲያ የወዳጅነታቸውን ያህል ፍላጎታቸውን ለየቅል እንደሆነ በሚያሳዩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ይመራሉ። ቱርክ እና ሩሲያ በሶሪያ ጉዳይ የተለያየ ፍላጎት ነው ያላቸው። ሁለቱ አገራት በሶሪያ በተቃራኒ ጎራ የቆሙ ኃይሎችን ይደግፋሉ። ቱርክ የሶሪያውን ፕሬዝደንት ባሻር አል-አሳድን ከሥልጣን ለመግልበጥ የሚታገሉትን ኃይሎች ትደግፋለች። ሩሲያ በበኩሏ አሳድ በስልጣን እንዲቆዩ ድጋፍ ታደርጋለች። ቱርክ እና ሩሲያ ከዚህ ቀደም በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በሚገኘው ኢድሊብ ግዛት የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሷል እያሉ አንዳቸው ሌላኛው ላይ ጣት ሲቀስሩ ነበር። ሞስኮ ሶሪያ የገባሁት በአሳድ መንግሥት ይፋዊ ጥሪ ነው በማለት በጦርነት የምትታመሰውን አገር መልሶ ለመገንባታ የቱርክ ጣልቃ ገብነት እንቅፋት መሆኑን ስትጠቅስ ነበር። ቱርክ በበኩሏ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች ከጎረቤት አገር ወደ ቱርክ እየተሻገሩ ስለሆነ፤ የቀጠናውን ደኅንነት ለማስጠበቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን በሰሜን ሶሪያ አሰማርታ በአሳድ መንግሥት ላይ የተነሱ ወታደሮችን ትደግፋለች። ቱርክ በአሁን ወቅት ወደ 3.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያዊያን ስደተኞችን አስጠልላ ትገኛለች። ቱርክ እና ሩሲያ በሊቢያ ያላቸው አቋምም የተለያየ ነው። ቱርክ በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተሰጠውን መንግሥት ስትደግፍ፤ ዋግነር የተሰኘው ቅጠረኛው የሩሲያ ቡድን ደግሞ ለተቃዋሚው ጀነራል ኻሊፋ ሃፍጣር ጦር ይዋጋል። በአንድ ወቅት የኻፍጣር ጦር ትሪፖሊን ለመቆጣጠር ከጫፍ በደረሰ ወቅት ቱርክ ባሰማራቻቸው ወታደሮች ተገፍቶ እንዲሸሽ ሆኗል። ከሶሪያ በተጨማሪም ቱርክ እና ሩሲያ በሦስተኛ አገር ጉዳይ ጣልቃ ገብተው አቋማቸው ለየቅል የሆነበት አጋማጣሚም አልጠፋም። ከወራት በፊት በተካሄደው የአዘርባጅን እና የአርሜኒያ ጦርነት ቱርክ እና ሩሲያ የተለያየ ጎራን ደግፈው ቆመው ነበር። ቱርክ በዚህ ጦርነት አዘርባጃን በድል እንድትወጣ ቱርክ ሰራሹን ባይራክታር ቲቢ2 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖች) ጥቅም ላይ አውላ ነበር። ቱርክ ከወራት በፊት ለዩክሬን ድሮኖችን መሸጧ ሩሲያን ያበሳጨ ጉዳይም ነበር። ቱርክ እና ሩሲያ ወዳጅነት ምንም እንኳ ቱርክ እና ሩሲያ በሶሪያ፣ ሊቢያ፣ በአርሜኒያ-አዘርባጀን ጦርነት እንዲሁም በዩክሬን ጉዳይ ያላቸው አቋም ይለያይ እንጂ በጦር መሳሪያ ግዢ፣ ኢነርጂ እና ቱሪዝም መስኮች ጠንካራ ግንኙነት መመስረት ችለዋል። ቱርክ ከሩሲያ ከፍተኛ መጠን ያለውን ጋዝ የምታስገባ ሲሆን በተቃራዊው ቱርክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሩሲያ ጎብኚዎችን በየዓመቱ በማስተናገድ ጠቀም ያለ ገንዘብ ታገኛለች። | በጦር መሳሪያ ግዢ ምክንያት ፍጥጫ ውስጥ የገቡት ቱርክና አሜሪካ የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቱርክ አቻቸው ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ዛሬ ሩሲያ ውስጥ ተገናኝተው ይነጋገራሉ። ሁለቱ መሪዎች ከሚመክሩባቸው ጉዳዮች መካከል የጦር መሳሪያ ግዢ እና የሶሪያ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳዎች ይሆናሉ ተብሏል። ቱርክ ከሩሲያ የጦር መሳሪያዎችን መግዛቷ ከአሜሪካ ጋር ውዝግብ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። "አሜሪካ ክለከላ ማድረግ አትችልም" ቱርክ ከሩሲያ ለመግዛት ያሰብኩትን ጦር መሳሪያ በተመለከተ አሜሪካ ምንም አይነት ክልከላ ልታደርግ አትችልም ስትል የአሜሪካንን አቋም ተቃውማለች። የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ቱርክ በርካታ ቁጥር ያላቸው ስልታዊ የሚሳኤል ሥርዓቶችን ከሩሲያ ለመግዛት እቅድ እንዳላት አስታውቀዋል። ፕሬዝደንት ኤርዶሃን አገራቸው ለሁለትኛ ዙር ኤስ-400 ከምድር ወደ ሰማይ የሚወነጨፉ ሩሲያ ሠራሽ ሚሳኤሎችን ለመግዛት በዝግጅት ላይ መሆኗ በታወቀበት ጊዜ አሜሪካ ተቃውሞ አሰምታለች። በዚህም ሳቢያ ቱርክ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አጋሯ አሜሪካ ጋር ውዝግብ ውስጥ የከተታት ሲሆን ተጨማሪ ማዕቀብ ሊያስጥልባት ይችላል ተብሏል። አሜሪካ ሩሲያ ሰራሾቹ ኤስ-400 ሚሳኤሎች ለኤፍ-35 ተዋጊ ጄቶቼ ስጋት ናቸው ትላለች። ከዚህ በተጨማሪም ዋሽንግተን ሚሳኤሎቹ ለኔቶ የድንበር መከላከያ ሥርዓት አደጋ ናቸው ትላለች። ቱርክ በበኩሏ የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን አጥጋቢ በሆነ መልኩ ከኔቶ አባል አገራት መግዛት እንዳልቻለች በማመልከት ከሩሲያ ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰች ገልጻለች። "ሊኖረን ስለሚችለው የጦር መሳሪያ ዓይነት ከየትኛውም አገር በየትኛውም ደረጃ ማንም ጣልቃ መግባት አይችልም" ሲሉ ፕሬዝደንት ኤርዶሃን በአሜሪካው ሲቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ በቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል። "በዚህ ላይ ማንም ጣልቃ መግባት አይችልም። እንዲህ አይነት ውሳኔ የምንሰጠው እኛ ብቻ ነን" በማለት ኤርዶሃን የአሜሪካንን አቋም ተችተዋል። ከወራት በፊት ቱርክ የመጀመሪያወን ዙር ኤስ-400 ሚሳኤሎችን ከሩሲያ መግዛቷን ተከትሎ አሜሪካ የቱርክ መከላከያ ኢንደስትሪ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ እሰማኢል ዴሚር እና ሦስት የተቋሙ ሠራተኞች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። ከዚህ በተጨማሪም ቱርክ ተመሳሳይ የጦር መሳሪያ ግዢ የምትፈጽም ከሆነ ሌላ ማዕቀብ እንደሚጣልባት አሜሪካ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች። "በየትኛውም ደረጃ ቱርክ ኤስ-400 የሚሳኤል ሥርዓቶችን እንዳትይዝ ወይም የትኛውንም አይነት ሩሲያ ሰራሽ ጦር መሳሪያዎችን ከመግዛት እንድትቆጠብ እናሳስባለን" ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አሳስበዋል። ቃል አቀባዩ ጨምረውም አሜሪካ ቱርክን እንደ ወዳጅ አገር ነው የምትመለከታት ካሉ በኋላ፤ አለመግባባት ውስጥ ሆነን እንኳ ግንኙነታችንን ማጠናክር ነው የምንፈልገው ብለዋል። ይሁን እንጂ ቱርክ ሁለተኛውን ዙር ኤስ-400 ሚሳኤሎችን የምትረከብበትን መንገድ በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ንግግር እያደረገች ትገኛለች። ኤርዶሃን ዛሬ በሩሲያ ተገኝተው ከፕሬዝደንት ቭላድረሚር ፑቲን ጋር በሚያደርጉት ውይይት ዋነኛ ጉዳያቸው ኤስ-400 ሚሳኤሎች እና በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ያለው ግጭት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የቱርክ እና ሩሲያ የውጭ ፖሊሲ አቋም ቱርክ እና ሩሲያ የወዳጅነታቸውን ያህል ፍላጎታቸውን ለየቅል እንደሆነ በሚያሳዩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ይመራሉ። ቱርክ እና ሩሲያ በሶሪያ ጉዳይ የተለያየ ፍላጎት ነው ያላቸው። ሁለቱ አገራት በሶሪያ በተቃራኒ ጎራ የቆሙ ኃይሎችን ይደግፋሉ። ቱርክ የሶሪያውን ፕሬዝደንት ባሻር አል-አሳድን ከሥልጣን ለመግልበጥ የሚታገሉትን ኃይሎች ትደግፋለች። ሩሲያ በበኩሏ አሳድ በስልጣን እንዲቆዩ ድጋፍ ታደርጋለች። ቱርክ እና ሩሲያ ከዚህ ቀደም በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በሚገኘው ኢድሊብ ግዛት የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሷል እያሉ አንዳቸው ሌላኛው ላይ ጣት ሲቀስሩ ነበር። ሞስኮ ሶሪያ የገባሁት በአሳድ መንግሥት ይፋዊ ጥሪ ነው በማለት በጦርነት የምትታመሰውን አገር መልሶ ለመገንባታ የቱርክ ጣልቃ ገብነት እንቅፋት መሆኑን ስትጠቅስ ነበር። ቱርክ በበኩሏ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች ከጎረቤት አገር ወደ ቱርክ እየተሻገሩ ስለሆነ፤ የቀጠናውን ደኅንነት ለማስጠበቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን በሰሜን ሶሪያ አሰማርታ በአሳድ መንግሥት ላይ የተነሱ ወታደሮችን ትደግፋለች። ቱርክ በአሁን ወቅት ወደ 3.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያዊያን ስደተኞችን አስጠልላ ትገኛለች። ቱርክ እና ሩሲያ በሊቢያ ያላቸው አቋምም የተለያየ ነው። ቱርክ በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተሰጠውን መንግሥት ስትደግፍ፤ ዋግነር የተሰኘው ቅጠረኛው የሩሲያ ቡድን ደግሞ ለተቃዋሚው ጀነራል ኻሊፋ ሃፍጣር ጦር ይዋጋል። በአንድ ወቅት የኻፍጣር ጦር ትሪፖሊን ለመቆጣጠር ከጫፍ በደረሰ ወቅት ቱርክ ባሰማራቻቸው ወታደሮች ተገፍቶ እንዲሸሽ ሆኗል። ከሶሪያ በተጨማሪም ቱርክ እና ሩሲያ በሦስተኛ አገር ጉዳይ ጣልቃ ገብተው አቋማቸው ለየቅል የሆነበት አጋማጣሚም አልጠፋም። ከወራት በፊት በተካሄደው የአዘርባጅን እና የአርሜኒያ ጦርነት ቱርክ እና ሩሲያ የተለያየ ጎራን ደግፈው ቆመው ነበር። ቱርክ በዚህ ጦርነት አዘርባጃን በድል እንድትወጣ ቱርክ ሰራሹን ባይራክታር ቲቢ2 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖች) ጥቅም ላይ አውላ ነበር። ቱርክ ከወራት በፊት ለዩክሬን ድሮኖችን መሸጧ ሩሲያን ያበሳጨ ጉዳይም ነበር። ቱርክ እና ሩሲያ ወዳጅነት ምንም እንኳ ቱርክ እና ሩሲያ በሶሪያ፣ ሊቢያ፣ በአርሜኒያ-አዘርባጀን ጦርነት እንዲሁም በዩክሬን ጉዳይ ያላቸው አቋም ይለያይ እንጂ በጦር መሳሪያ ግዢ፣ ኢነርጂ እና ቱሪዝም መስኮች ጠንካራ ግንኙነት መመስረት ችለዋል። ቱርክ ከሩሲያ ከፍተኛ መጠን ያለውን ጋዝ የምታስገባ ሲሆን በተቃራዊው ቱርክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሩሲያ ጎብኚዎችን በየዓመቱ በማስተናገድ ጠቀም ያለ ገንዘብ ታገኛለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-58723013 |
2health
| በአሁኑ ዘመን ስለኤችአይቪ ከሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች በጥቂቱ | ፖል ቶርን ቤተሰቦቹን ለመጨረሻ ጊዜ ያያቸው ከአስርት ዓመታት በፊት ነው። የተለያዩት ልብ በሚሰብር ሁኔታ ነበር፤ የበላበትን ሰሃን ኤችአይቪ ይተላለፍብናል በሚል ፍራቻ ወረወሩት። ግንኙነታቸውም በዚያው አከተመ። ፖል ኤችአይቪ በደሙ መኖሩ የታወቀው በአውሮፓውያኑ 1988 ነበር። ይህንንም ተከትሎ የነርሲንግ ስልጠና ትምህርቱን ማቆም ነበረበት። "የ20ዎቹን ዕድሜዬን ያሳለፍኩት በፍርሃት ነው" ይላል። በአሁኑ ወቅት መኖሪያውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ፖል ስለ ቫይረሱ ብዙም አያሳስበውም። በቀን አንድ ክኒን መውሰድ እና በዓመት ሁለት ጊዜ ዶክተሩን ከማየት ውጪ ይህን ያህል ህይወቱን የሚያሰጋው ጉዳይ አይደለም። ህክምና የሚከታተሉና ጤንነታቸውን የሚጠብቁ በደማቸው ውስጥ የኤች አይ ቪ ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች እንደ ሌላው ሁሉ ህይወታቸውን በደስታ መኖር እንደሚችሉ ብዙዎች በዓመታት ተረድተዋል። እንዲሁም ምግብ በመጋራትና አብሮ ጊዜ በማሳለፍ በሽታው ይተላላፋል የሚሉ ያረጁና የተሳሳቱ አመለካከቶች በአብዛኛው ቢጠፋም አሁንም ቢሆን ጎጂ እና የተሳሳቱ መረጃዎች መሰራጨታቸው አልቀረም። 'መድኃኒት አለው' ኬንያዊቷ ዶሪን ሞራ ሞራቻ በደሟ ውስጥ በኤችአይቪ ቫይረስ ኖሮ የተወለደች ቢሆንም ሁኔታዋን ያወቀችው በ13 ዓመቷ በአውሮፓውያኑ 2005 በተደረገላት ምርመራ ነው። በአንድ ወቅት በታንዛኒያ ወደ የሚገኝ የባህል መድኃኒት አዋቂ ነኝ የሚል ግለሰብ ዘንድ የሄደችው ዶሪን እሷንም ሆነ እናቷን ከኤችአይቪ እንደሚፈውሳቸው ነገራቸው። "እሱ የሚሸጠውን ከዕፅዋት የሚቀመሙ መድኃኒቶችን ጠጥተን ከኤችአይቪ ነፃ መሆናችንን አምነን ተመልሰናል" ትላለች። በመቀጠልም ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ እንዳይባዛ የሚከለክለውን ፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት (አንታይሪትሮቫይራል) መድኃኒት መውሰድ አቆመች። ነገር ግን ትንሽ ቆይታ በሽታን የመከላከል አቅሟ በመዳከሟ የሳንባ ምች ታመመች። በደሟ ውስጥ ያለው የኤችአይቪ ቫይረስ መጠን መጨመሩንና በዚህም የተነሳ ሌላ ኢንፌክሽን ካጋጠማት እንደምትሞትም ዶክተሯ ነገራት። የኤችአይቪ ቫይረስ ካልታከመ ሰውነት ቀላል ህመሞችን መቋቋም ወደማይችልበት የኤድስ በሽታ ሊያመራ ይችላል። የባህል መድኃኒት አዋቂ የተባለው ሰውዬም "አጭበርባሪ" እንደሆነ ግልፅ ሆነላት። ለኤችአይቪ ምንም አይነት ክትባት ወይም መድኃኒት የለውም ነገር ግን ፈውስ አለው ብሎ ማመን የተለመደ ነው ሲሉ የዓለም አቀፍ ኤድስ ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶክተር አዲባ ካማሩልዛማን ተናግረዋል። በቅርቡ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችም ሁኔታ ተስፋን ፈንጥቋል። በቅርቡ በአርጀንቲና የምትኖር አንዲት ሴት በራሷ በሽታ የመከላከል አቅም ከኤችአይቪ ነፃ የሆነች ሁለተኛዋ ሰው ሆናለች። ግን እንዴት እና ለምን እንደሆነ እስካሁን ምክንያቱ አልተገለጸም። 'ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜ በሽታውን ያስተላልፋሉ የሚል እምነት' ጋናዊቷ ጆይስ ሜንሳህ ከደረሰባት መገለል ነፃ ለመውጣት ነበር ወደ ጀርመን ያቀናችው። ስለ ሁኔታዋ እንደምትናገረው በተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ ከቅርብ ሰዎች ጋር ካላት ግንኙነት ባሻገር ሥራዋን እንዳጣች ትናገራለች። በተለይም መገለሉ የሚመጣው ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜም ቢሆን ለትዳር አጋራቸው ወይም ለልጃቸው የማስተላለፍ ስጋት ደቅነዋል ከሚለው የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው ትላለች። "ግለሰቦች የኤችአይቪ ሁኔታቻውን ለቤተሰቦቻቸው ሲያሳውቁ ... ሰዎች መቶ በመቶ ደኅንነታቸው የተጠበቀ አይደለም የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው። ኤችአይቪ በደማቸው አለ ማለት ሁሌም በሽታውን ያስተላልፋሉ የሚል እምነት አለ" በማለት ጆይስ ትናገራለች። እንዲያውም በተጻራሪው ፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒቶችን ለረጅም ጊዜ ከወሰዱ በኋላ፣ ሰዎች ቫይረሱን በወሲብም ሆነ በሌላ መንገድ የማያስተላልፉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ። ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ግለሰቦች የዕድሜ ልክ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም ቫይረሱን ከሰው ወደ ሰው ማስተላለፍ ያቆማሉ። ህክምናዋን በየጊዜው የምትከታተለው ጆይስ አራት ልጆች ያሏት ሲሆን አንዱም ቫይረሱ በደሙ ውስጥ የለም። ህክምናው በስፋት እየተስፋፋ በመምጣቱም ከአውሮፓውያኑ 2010 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታው በግማሽ ቀንሷል። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ኑሯዋን በጋና ያደረገችው የጆይስ ሴት ልጅ ቫይረሱ በደሟ ውስጥ አለባት፣ እንዲሁም ሌሎችንም ልታሲዝ ትችላለች በሚል በቅርቡ ትምህርት ቤቷ ወደ ቤቷ እንድትመለስ አድርጓታል። ኤችአይቪ በደማቸው ያለ ሰዎች የዩናይትድ ኪንግደም የበጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢያን ግሪን "ኤችአይቪ ያለብን ሰዎቸቭ ብዙውን ጊዜ እራሳችንን እንደ በሽታ አምጪ አድርገን እንመለከታለን" ይላሉ። "ለብዙ ዓመታት ቫይረሱን ለሌላ ሰው አስተላልፋለሁ የሚል ከፍተኛ ስጋት ነበረብኝ።" ህክምናው ከደረሰበት ደረጃ አንፃር "ቫይረሱን በአሁኑ ወቅት እኔ በጭራሽ ወደሌላ ሰው ማስተላለፍ እንደማልችል ማወቄ ነፃነት ሰጥቶኛል" ይላሉ። 'ኤችአይቪ የለም' ኤችአይቪ ከዚህ ቀደም እንደሚታሰበው የሞት ፍርድ ባይሆንም፣ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች መደበኛና ጤናማ ህይወት መኖር ቢችሉም፣ አንዳንድ ዘመቻ አድራጊዎች ግን ቫይረሱ የሚናገሩት እንደሌለ መሆኑ ችግርን እየፈጠረ ነው። "በኤችአይቪ ህክምናና መከላከያው ላይ በዘመናት ውስጥ አስደናቂ ልኅቀቶች ታይተዋል። ነገር ግን ይህ ኤድስ አብቅቷል የሚለው ሁኔታ በመከላከል ሥራው ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። በተለይም የኤችአይቪ ፈውስ ፍለጋም ላይ እንዲሁ ጥረቶችን ከማድረግ አንፃር እክል ሆኗል" በማለት ዶክተር ካማልዛማን ይናገራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአውሮፓውያኑ 2020 መረጃ እንደሚያመለክተው በዓለም ዙሪያ ወደ 38 ሚሊዮን የሚጠጉ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ያለ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 700 ሺዎቹ ከኤድስ ጋር በተያያዙ በሽታዎች ሞተዋል። ይህም ቫይረሱ በጊዜ ባለመታከሙ ሊሆን እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ፖል እንደሚለው ታዳጊና ወጣቶች ሰዎች በሽታውን እንደ አዛውንት በሽታ ይመለከቱታል እናም በርካቶች "በአጠቃላይ ዝቅተኛ ግንዛቤ አላቸው" ብሏል ። "ኤችአይቪ ያለፈ ነገር ነው ብለው ያስባሉ" ሲል አክሏል። 'እኔ ኤችአይቪ የሚይዘኝ ሰው አይደለሁም' ልክ ወጣቶች እንደ አዛውንት ህመም እንደሚያዩት ብዙዎች ቫይረሱ ወንድ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን ብቻ የሚያጠቃ ነገር አድርገው ይመለከቱታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ካለባቸው ሰዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። ክሪስቲን ስቴግሊንግ የተባሉት የፍሮንትላይን ኤድስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሠራተኛ ታዳጊና ወጣት ሴቶችን ከሚገድሉ በሽታዎች ዋነኛው ኤድስ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን ካናገሯቸው ሴቶች ውስጥ በጣም ጥቂቶች ናቸው አደጋውን የተረዱት። "ሴቶች የወሲብ ግንኙነትን በተመለከተ ጥንቃቄ ማድረግና አለማድረግን በተመለከተ አስቸጋሪ ውይይቶች ማድረግ አለባቸው" ሲሉ ክሪስቲን ስቴግሊንግ ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት በርካታ መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም እየተሰራጩ ያሉ የተሳሳቱ መረጃዎች ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎችን ግንኙነቶቻቸው እንዲቋረጥ፣ ሥራ እንዳይኖራቸው እንዲሁም አልፎ ተርፎም ትክክለኛ ህክምናና ምርመራ እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል። | በአሁኑ ዘመን ስለኤችአይቪ ከሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች በጥቂቱ ፖል ቶርን ቤተሰቦቹን ለመጨረሻ ጊዜ ያያቸው ከአስርት ዓመታት በፊት ነው። የተለያዩት ልብ በሚሰብር ሁኔታ ነበር፤ የበላበትን ሰሃን ኤችአይቪ ይተላለፍብናል በሚል ፍራቻ ወረወሩት። ግንኙነታቸውም በዚያው አከተመ። ፖል ኤችአይቪ በደሙ መኖሩ የታወቀው በአውሮፓውያኑ 1988 ነበር። ይህንንም ተከትሎ የነርሲንግ ስልጠና ትምህርቱን ማቆም ነበረበት። "የ20ዎቹን ዕድሜዬን ያሳለፍኩት በፍርሃት ነው" ይላል። በአሁኑ ወቅት መኖሪያውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ፖል ስለ ቫይረሱ ብዙም አያሳስበውም። በቀን አንድ ክኒን መውሰድ እና በዓመት ሁለት ጊዜ ዶክተሩን ከማየት ውጪ ይህን ያህል ህይወቱን የሚያሰጋው ጉዳይ አይደለም። ህክምና የሚከታተሉና ጤንነታቸውን የሚጠብቁ በደማቸው ውስጥ የኤች አይ ቪ ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች እንደ ሌላው ሁሉ ህይወታቸውን በደስታ መኖር እንደሚችሉ ብዙዎች በዓመታት ተረድተዋል። እንዲሁም ምግብ በመጋራትና አብሮ ጊዜ በማሳለፍ በሽታው ይተላላፋል የሚሉ ያረጁና የተሳሳቱ አመለካከቶች በአብዛኛው ቢጠፋም አሁንም ቢሆን ጎጂ እና የተሳሳቱ መረጃዎች መሰራጨታቸው አልቀረም። 'መድኃኒት አለው' ኬንያዊቷ ዶሪን ሞራ ሞራቻ በደሟ ውስጥ በኤችአይቪ ቫይረስ ኖሮ የተወለደች ቢሆንም ሁኔታዋን ያወቀችው በ13 ዓመቷ በአውሮፓውያኑ 2005 በተደረገላት ምርመራ ነው። በአንድ ወቅት በታንዛኒያ ወደ የሚገኝ የባህል መድኃኒት አዋቂ ነኝ የሚል ግለሰብ ዘንድ የሄደችው ዶሪን እሷንም ሆነ እናቷን ከኤችአይቪ እንደሚፈውሳቸው ነገራቸው። "እሱ የሚሸጠውን ከዕፅዋት የሚቀመሙ መድኃኒቶችን ጠጥተን ከኤችአይቪ ነፃ መሆናችንን አምነን ተመልሰናል" ትላለች። በመቀጠልም ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ እንዳይባዛ የሚከለክለውን ፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት (አንታይሪትሮቫይራል) መድኃኒት መውሰድ አቆመች። ነገር ግን ትንሽ ቆይታ በሽታን የመከላከል አቅሟ በመዳከሟ የሳንባ ምች ታመመች። በደሟ ውስጥ ያለው የኤችአይቪ ቫይረስ መጠን መጨመሩንና በዚህም የተነሳ ሌላ ኢንፌክሽን ካጋጠማት እንደምትሞትም ዶክተሯ ነገራት። የኤችአይቪ ቫይረስ ካልታከመ ሰውነት ቀላል ህመሞችን መቋቋም ወደማይችልበት የኤድስ በሽታ ሊያመራ ይችላል። የባህል መድኃኒት አዋቂ የተባለው ሰውዬም "አጭበርባሪ" እንደሆነ ግልፅ ሆነላት። ለኤችአይቪ ምንም አይነት ክትባት ወይም መድኃኒት የለውም ነገር ግን ፈውስ አለው ብሎ ማመን የተለመደ ነው ሲሉ የዓለም አቀፍ ኤድስ ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶክተር አዲባ ካማሩልዛማን ተናግረዋል። በቅርቡ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችም ሁኔታ ተስፋን ፈንጥቋል። በቅርቡ በአርጀንቲና የምትኖር አንዲት ሴት በራሷ በሽታ የመከላከል አቅም ከኤችአይቪ ነፃ የሆነች ሁለተኛዋ ሰው ሆናለች። ግን እንዴት እና ለምን እንደሆነ እስካሁን ምክንያቱ አልተገለጸም። 'ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜ በሽታውን ያስተላልፋሉ የሚል እምነት' ጋናዊቷ ጆይስ ሜንሳህ ከደረሰባት መገለል ነፃ ለመውጣት ነበር ወደ ጀርመን ያቀናችው። ስለ ሁኔታዋ እንደምትናገረው በተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ ከቅርብ ሰዎች ጋር ካላት ግንኙነት ባሻገር ሥራዋን እንዳጣች ትናገራለች። በተለይም መገለሉ የሚመጣው ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜም ቢሆን ለትዳር አጋራቸው ወይም ለልጃቸው የማስተላለፍ ስጋት ደቅነዋል ከሚለው የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው ትላለች። "ግለሰቦች የኤችአይቪ ሁኔታቻውን ለቤተሰቦቻቸው ሲያሳውቁ ... ሰዎች መቶ በመቶ ደኅንነታቸው የተጠበቀ አይደለም የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው። ኤችአይቪ በደማቸው አለ ማለት ሁሌም በሽታውን ያስተላልፋሉ የሚል እምነት አለ" በማለት ጆይስ ትናገራለች። እንዲያውም በተጻራሪው ፀረ-ኤችአይቪ መድኃኒቶችን ለረጅም ጊዜ ከወሰዱ በኋላ፣ ሰዎች ቫይረሱን በወሲብም ሆነ በሌላ መንገድ የማያስተላልፉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ። ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ግለሰቦች የዕድሜ ልክ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም ቫይረሱን ከሰው ወደ ሰው ማስተላለፍ ያቆማሉ። ህክምናዋን በየጊዜው የምትከታተለው ጆይስ አራት ልጆች ያሏት ሲሆን አንዱም ቫይረሱ በደሙ ውስጥ የለም። ህክምናው በስፋት እየተስፋፋ በመምጣቱም ከአውሮፓውያኑ 2010 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታው በግማሽ ቀንሷል። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ኑሯዋን በጋና ያደረገችው የጆይስ ሴት ልጅ ቫይረሱ በደሟ ውስጥ አለባት፣ እንዲሁም ሌሎችንም ልታሲዝ ትችላለች በሚል በቅርቡ ትምህርት ቤቷ ወደ ቤቷ እንድትመለስ አድርጓታል። ኤችአይቪ በደማቸው ያለ ሰዎች የዩናይትድ ኪንግደም የበጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢያን ግሪን "ኤችአይቪ ያለብን ሰዎቸቭ ብዙውን ጊዜ እራሳችንን እንደ በሽታ አምጪ አድርገን እንመለከታለን" ይላሉ። "ለብዙ ዓመታት ቫይረሱን ለሌላ ሰው አስተላልፋለሁ የሚል ከፍተኛ ስጋት ነበረብኝ።" ህክምናው ከደረሰበት ደረጃ አንፃር "ቫይረሱን በአሁኑ ወቅት እኔ በጭራሽ ወደሌላ ሰው ማስተላለፍ እንደማልችል ማወቄ ነፃነት ሰጥቶኛል" ይላሉ። 'ኤችአይቪ የለም' ኤችአይቪ ከዚህ ቀደም እንደሚታሰበው የሞት ፍርድ ባይሆንም፣ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች መደበኛና ጤናማ ህይወት መኖር ቢችሉም፣ አንዳንድ ዘመቻ አድራጊዎች ግን ቫይረሱ የሚናገሩት እንደሌለ መሆኑ ችግርን እየፈጠረ ነው። "በኤችአይቪ ህክምናና መከላከያው ላይ በዘመናት ውስጥ አስደናቂ ልኅቀቶች ታይተዋል። ነገር ግን ይህ ኤድስ አብቅቷል የሚለው ሁኔታ በመከላከል ሥራው ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። በተለይም የኤችአይቪ ፈውስ ፍለጋም ላይ እንዲሁ ጥረቶችን ከማድረግ አንፃር እክል ሆኗል" በማለት ዶክተር ካማልዛማን ይናገራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአውሮፓውያኑ 2020 መረጃ እንደሚያመለክተው በዓለም ዙሪያ ወደ 38 ሚሊዮን የሚጠጉ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ያለ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 700 ሺዎቹ ከኤድስ ጋር በተያያዙ በሽታዎች ሞተዋል። ይህም ቫይረሱ በጊዜ ባለመታከሙ ሊሆን እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ፖል እንደሚለው ታዳጊና ወጣቶች ሰዎች በሽታውን እንደ አዛውንት በሽታ ይመለከቱታል እናም በርካቶች "በአጠቃላይ ዝቅተኛ ግንዛቤ አላቸው" ብሏል ። "ኤችአይቪ ያለፈ ነገር ነው ብለው ያስባሉ" ሲል አክሏል። 'እኔ ኤችአይቪ የሚይዘኝ ሰው አይደለሁም' ልክ ወጣቶች እንደ አዛውንት ህመም እንደሚያዩት ብዙዎች ቫይረሱ ወንድ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን ብቻ የሚያጠቃ ነገር አድርገው ይመለከቱታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ካለባቸው ሰዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። ክሪስቲን ስቴግሊንግ የተባሉት የፍሮንትላይን ኤድስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሠራተኛ ታዳጊና ወጣት ሴቶችን ከሚገድሉ በሽታዎች ዋነኛው ኤድስ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን ካናገሯቸው ሴቶች ውስጥ በጣም ጥቂቶች ናቸው አደጋውን የተረዱት። "ሴቶች የወሲብ ግንኙነትን በተመለከተ ጥንቃቄ ማድረግና አለማድረግን በተመለከተ አስቸጋሪ ውይይቶች ማድረግ አለባቸው" ሲሉ ክሪስቲን ስቴግሊንግ ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት በርካታ መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም እየተሰራጩ ያሉ የተሳሳቱ መረጃዎች ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸው ሰዎችን ግንኙነቶቻቸው እንዲቋረጥ፣ ሥራ እንዳይኖራቸው እንዲሁም አልፎ ተርፎም ትክክለኛ ህክምናና ምርመራ እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59493430 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን በአካላዊ ርቀት ምክንያት ለማፅናናት ያልቻለው ግለሰብ | በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን ለማፅናናት አቅፏት የነበረው እንግሊዛዊ አካላዊ ርቀትህን ጠብቅ መባሉ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳበሳጨው ገልጿል። ክሬይግ ቢክኔል ይህ የተነገረው ክራውንሂል በተባለው የቀብር ስነ ስርአት አስፈፃሚ ሰራተኛ ነው። ክሬይግም ሆነ ወንድሙ ወንበራቸውን ራቅ አድርገው እንዲቀመጡ ከመንገር በተጨማሪም የኃዘን ስነ ስርአቱም እንዲቋረጥ ተደርጓል። በኃዘን ልቧ ተሰብራ ከነበረው እናቱ ጎን ተቀምጦም በማፅናናትም ላይ እንደነበረ ተናግሯል። የሚልተን ኬይንስ ምክር ቤት በበኩሉ በተፈጠረው ሁኔታ ማዘኑንና ለወደፊቱም የተሻለ አማራጭ እንጠቀማለንም በማለት ምላሽ ሰጥቷል። የ43 አመቱ ክሬይግ በበኩሉ "እናቴን ማፅናናት እንደምፈልግ ለሁሉም ተናግሬ ነበር። በከፍተኛ ሁኔታ ሃዘኗም ጨምሮ ስብርብር ስትል አቀፍኳት" ብሏል። በአባቱ የኃዘን ስርአት ላይ ወንበሮቹ አካላዊ ርቀትን በሚያስጠብቅ መልኩ ተራርቀው የነበረ ሲሆን የናቱንም የበረታ ኃዘንም ተመልክቶ ወደናቱ የተጠጋ ሲሆን ወንድሙም ተከትሎት እናታቸውን ማፅናናት ጀመሩ። የቀብር አስፈፃሚ ሰራተኞቹም ወንበሮቹን በየቦታቸው እንዲመልሱና ማንቀሳቀስ አትችሉም ተብለዋል። በዚህ ሃዘን ላይ እያሉ እንዲህ መባላቸው ከፍተኛ ንዴትና ሃዘን እንደፈጠረበትም ገልጿል። "በከፍተኛ ሁኔታ የባዶነት ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል" ያለው ክሬይግ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልና በሰላም እንዲጠናቀቅም ከራሱ ጋር ትግል ማድረግ ነበረበት። "ፈታኝ ነበር። የአባቴ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልም ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረብኝ" ያለው ክሬይግ አክሎም "በጣም ያዘንኩበትና የፈራሁበትም ወቅት ነው፤ እንዲህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም" ብሏል። የሚልተን ኬይነስ ምክር ቤት በበኩሉ ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ሁኔታ ተፈፅሞ እንደማያውቅና ቤተሰቡንም በማሳዘናቸው ይቅርታ ጠይቀዋል። የኃዘንም ሆነ የቀብር አስፈፃሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ሰብሰብ ብለው ቢቀመጡም ችግር እንደሌለው ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በኃዘንም ሆነ በቀብር ስርአት ላይ መገኘት ያለባቸው 30 ሰዎች መሆናቸው በመመሪያው ላይ የተቀመጠ ሲሆን እነሱም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆኑንም አስፍሯል። | ኮሮናቫይረስ፡ በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን በአካላዊ ርቀት ምክንያት ለማፅናናት ያልቻለው ግለሰብ በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን ለማፅናናት አቅፏት የነበረው እንግሊዛዊ አካላዊ ርቀትህን ጠብቅ መባሉ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳበሳጨው ገልጿል። ክሬይግ ቢክኔል ይህ የተነገረው ክራውንሂል በተባለው የቀብር ስነ ስርአት አስፈፃሚ ሰራተኛ ነው። ክሬይግም ሆነ ወንድሙ ወንበራቸውን ራቅ አድርገው እንዲቀመጡ ከመንገር በተጨማሪም የኃዘን ስነ ስርአቱም እንዲቋረጥ ተደርጓል። በኃዘን ልቧ ተሰብራ ከነበረው እናቱ ጎን ተቀምጦም በማፅናናትም ላይ እንደነበረ ተናግሯል። የሚልተን ኬይንስ ምክር ቤት በበኩሉ በተፈጠረው ሁኔታ ማዘኑንና ለወደፊቱም የተሻለ አማራጭ እንጠቀማለንም በማለት ምላሽ ሰጥቷል። የ43 አመቱ ክሬይግ በበኩሉ "እናቴን ማፅናናት እንደምፈልግ ለሁሉም ተናግሬ ነበር። በከፍተኛ ሁኔታ ሃዘኗም ጨምሮ ስብርብር ስትል አቀፍኳት" ብሏል። በአባቱ የኃዘን ስርአት ላይ ወንበሮቹ አካላዊ ርቀትን በሚያስጠብቅ መልኩ ተራርቀው የነበረ ሲሆን የናቱንም የበረታ ኃዘንም ተመልክቶ ወደናቱ የተጠጋ ሲሆን ወንድሙም ተከትሎት እናታቸውን ማፅናናት ጀመሩ። የቀብር አስፈፃሚ ሰራተኞቹም ወንበሮቹን በየቦታቸው እንዲመልሱና ማንቀሳቀስ አትችሉም ተብለዋል። በዚህ ሃዘን ላይ እያሉ እንዲህ መባላቸው ከፍተኛ ንዴትና ሃዘን እንደፈጠረበትም ገልጿል። "በከፍተኛ ሁኔታ የባዶነት ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል" ያለው ክሬይግ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልና በሰላም እንዲጠናቀቅም ከራሱ ጋር ትግል ማድረግ ነበረበት። "ፈታኝ ነበር። የአባቴ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልም ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረብኝ" ያለው ክሬይግ አክሎም "በጣም ያዘንኩበትና የፈራሁበትም ወቅት ነው፤ እንዲህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም" ብሏል። የሚልተን ኬይነስ ምክር ቤት በበኩሉ ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ሁኔታ ተፈፅሞ እንደማያውቅና ቤተሰቡንም በማሳዘናቸው ይቅርታ ጠይቀዋል። የኃዘንም ሆነ የቀብር አስፈፃሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ሰብሰብ ብለው ቢቀመጡም ችግር እንደሌለው ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በኃዘንም ሆነ በቀብር ስርአት ላይ መገኘት ያለባቸው 30 ሰዎች መሆናቸው በመመሪያው ላይ የተቀመጠ ሲሆን እነሱም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆኑንም አስፍሯል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54460664 |
3politics
| በመቀለ ከተማ ከአንድ ዓመት በኋላ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመለሰ | የትግራይ ክልል መዲና መቀለ ከአንድ ዓመት በኋላ የኤሌከትሪክ አገልግሎት አገኘች። የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደገለጹት ከትናንት ማክሰኞች ኅዳር 26/2015 ዓ.ም. ጀምሮ በከተማዋ የኤሌክትሪክ አግልግሎት ተመልሷል። የእርስ በእርስ ጦርነቱን ተከትሎ መዲናዋን ጨምሮ አብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች መብራት፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት እና ባንክን የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጦባቸው ቆይቷል። ይሁን እንጂ የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት ጦርነቱን በማስቆም የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በክልሉ የመሠረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ እንቅስቃሴዎች እንደተጀመሩ ተገልጿል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ደም አፋሳሽ ጦርነት ያካሄዱት ሁለቱ ተዋጊ ኃይሎች በደረሱት ስምምነት መሠረት ህወሓት ትጥቅ ሊፈታ የተስማማ ሲሆን የፌደራሉ መንግሥት ደግሞ መሠረተ ልማቶችን የመመለስ እና ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ የበኩሉን ለመወጣት ኃላፊነት ወስዷል። ከኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጨማሪ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም የስልክ አገልግሎት በሽረ እንዳሥላሴ እና በአከባቢው የሙከራ ሥራ ጀምሯል። “በከተማዋ ሁሉም ቦታ ከትናንት (ማክሰኞ) ጀምሮ በሁሉም ቦታ መብራት አለ” ሲል አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግሯል። የኢትዮ-ቴሌኮም ቺፍ ኮምንኬሽን ኦፊሰር የሆኑት አቶ መሳይ ውብሸት ከሳምንት በፊት ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ በሽረ እንዳሥላሴ እና አካባቢው የሙከራ ሥራ እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመቀለ ኤሌክትሪክ መስመር ከብሔራዊ መቆጣጠሪያ ማዕከል ግሪድ ጋር መገናኘቱን ትናንት አስታውቆ ነበር። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ፤ የባለሙያዎች ቡድን ለጥገና ሥራ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ይዞ ወደ ክልሉ በቅርቡ ተሰማርቶ፣ የጥገና ሥራውን በአጭር ግዜ በማጠናቀቅ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲመለስ እንደሚሠራ አስታውቋል። ከነገ ጀምሮ ለጥገና ሥራው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማሟላት፣ ሠራተኞቹ ከሰሞኑ ወደ ክልሉ እንደሚሰማሩና በአጭር ጊዜ የጥገና ሥራውን በማጠናቀቅ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ኅብረተሰቡ መልሶ እንደሚያገኝ አክሏል። በቅርቡ በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ በረራዎችን መልሶ ለመጀመር ሙሉ ዝግጀቱን እንዳጠናቀቀ የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ ከሳምንት በፊት ለቢቢሲ ገልጸዋል። ለሁለት ዓመታት የተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ካስከተለው ሰብአዊ ጥፋት ባሻገር ከፍተኛ የንብረት ውድመት አስከትሏል። | በመቀለ ከተማ ከአንድ ዓመት በኋላ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመለሰ የትግራይ ክልል መዲና መቀለ ከአንድ ዓመት በኋላ የኤሌከትሪክ አገልግሎት አገኘች። የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደገለጹት ከትናንት ማክሰኞች ኅዳር 26/2015 ዓ.ም. ጀምሮ በከተማዋ የኤሌክትሪክ አግልግሎት ተመልሷል። የእርስ በእርስ ጦርነቱን ተከትሎ መዲናዋን ጨምሮ አብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች መብራት፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት እና ባንክን የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጦባቸው ቆይቷል። ይሁን እንጂ የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት ጦርነቱን በማስቆም የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በክልሉ የመሠረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ እንቅስቃሴዎች እንደተጀመሩ ተገልጿል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ደም አፋሳሽ ጦርነት ያካሄዱት ሁለቱ ተዋጊ ኃይሎች በደረሱት ስምምነት መሠረት ህወሓት ትጥቅ ሊፈታ የተስማማ ሲሆን የፌደራሉ መንግሥት ደግሞ መሠረተ ልማቶችን የመመለስ እና ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ የበኩሉን ለመወጣት ኃላፊነት ወስዷል። ከኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጨማሪ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም የስልክ አገልግሎት በሽረ እንዳሥላሴ እና በአከባቢው የሙከራ ሥራ ጀምሯል። “በከተማዋ ሁሉም ቦታ ከትናንት (ማክሰኞ) ጀምሮ በሁሉም ቦታ መብራት አለ” ሲል አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግሯል። የኢትዮ-ቴሌኮም ቺፍ ኮምንኬሽን ኦፊሰር የሆኑት አቶ መሳይ ውብሸት ከሳምንት በፊት ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ በሽረ እንዳሥላሴ እና አካባቢው የሙከራ ሥራ እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመቀለ ኤሌክትሪክ መስመር ከብሔራዊ መቆጣጠሪያ ማዕከል ግሪድ ጋር መገናኘቱን ትናንት አስታውቆ ነበር። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ፤ የባለሙያዎች ቡድን ለጥገና ሥራ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ይዞ ወደ ክልሉ በቅርቡ ተሰማርቶ፣ የጥገና ሥራውን በአጭር ግዜ በማጠናቀቅ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲመለስ እንደሚሠራ አስታውቋል። ከነገ ጀምሮ ለጥገና ሥራው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማሟላት፣ ሠራተኞቹ ከሰሞኑ ወደ ክልሉ እንደሚሰማሩና በአጭር ጊዜ የጥገና ሥራውን በማጠናቀቅ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ኅብረተሰቡ መልሶ እንደሚያገኝ አክሏል። በቅርቡ በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ በረራዎችን መልሶ ለመጀመር ሙሉ ዝግጀቱን እንዳጠናቀቀ የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ ከሳምንት በፊት ለቢቢሲ ገልጸዋል። ለሁለት ዓመታት የተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ካስከተለው ሰብአዊ ጥፋት ባሻገር ከፍተኛ የንብረት ውድመት አስከትሏል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cv25xw89qw1o |
3politics
| ብሔረ ተኮር ጥቃት ወደ ተፈጸመባቸው የወለጋ ዞኖች የፌደራሉ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለጸ | ባለፉት ቀናት ብሔር ተኮር ግጭት ወደ ተቀሰቀሰባቸው የወለጋ ዞኖች የአገር መከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለጸ። ባለፉት ቀናት በምሥራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በሚገኙ አካባቢዎች በተፈጸሙ ብሔር ተኮር ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸው እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መፈናቀላቸው ሲገለጽ ቆይቷል። ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ለተፈጠረው ግጭት እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን እና የአማራ ታጣቂዎችን ተጠያቂ ይደረጋሉ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም በሰሞኑ ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች መንግሥት ‘ሸኔ’ ብሎ የሚጠራው ቡድን እና የአማራ ታጣቂዎች መሆናቸው ለቢቢሲ አስታውቋል። “የፌደራል ኃይል አባላት አንገር ጉተን ከተማ ከገቡ በኋላ በአካባቢው የጸጥታ መሻሻል አለ” ሲሉ ግጭት ካጋጠመባቸው አንዷ በሆነችው የምሥራቅ ወለጋ ዞን የጊዳ አያና ወረዳ አንድ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ባለፉት ጥቂት ቀናት የተሰማራ ሲሆን በሆሮ ጉዱሩ ዞን ደግሞ ከአንድ ሳምንት በፊት ተሰማርቷል። በምዕራብ ኦሮሚያ እየተፈጠረ ስላለው ግድያ፣ መፈናቀል እና ንብረት መወደም ዝምታን የመረጠው የፌደራሉ መንግሥት ጦሩን ወደ ግጭት ቀጠናው ያሰማራው በርካቶች የዜጎች ደኅንነት እንዲረጋገጥ በስፋት እየጠየቁ ባሉበት ወቅት ነው። ፖለቲከኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ማኅበራት መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት እንዲጠብቅ ሲጠይቁ ነበር። የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በወለጋ ዞኖች በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞት፣ መፈናቀል እና ሰቆቃ በእጅጉ ያሳስበኛል ያለ ሲሆን፣ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ትናንት ማክሰኞ ኅዳር 27/2015 ዓ.ም. ጥሪ አቅርቧል። ፖለቲከኛው ጃዋር መሐመድ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ላለው ቀውስ መፍትሄ ናቸው ያላቸውን ምክረ ሃሳቦች የለገሰ ሲሆን፤ መንግሥት ተኩስ በማቆም ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ንግግር መጀመር አለበት ብሏል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና ሌሎችም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳዩን አስመልክተው ባወጧቸው መግለጫዎች፣ ወለጋ ውስጥ በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እንዳሳሰባቸውና መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል። የፌደራል መንግሥት ጦር በአካባቢዎች መሰማራቱ ይገለጽ እንጂ ግጭት ሸሽተው ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያሻቸው እየተገለጸ ይገኛል። ባለፉት ቀናት በወለጋ ዞኖች በተቀሰቀሱት ግጭቶች በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እስካሁን በውል ባይታወቅም፣ የምሥራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ግን ከ60 ያላነሱ ሰዎች በአንድ ጀምበር መገደላቸውን ተናግረዋል። ሰዎች በማንነታቸው ምክንያት የጥቃቶች ዒላማ መሆናቸውን የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጥቃቶቹ የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ምርመራ ላይ መሆኑን ለቢቢሲ አስታውቋል። | ብሔረ ተኮር ጥቃት ወደ ተፈጸመባቸው የወለጋ ዞኖች የፌደራሉ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለጸ ባለፉት ቀናት ብሔር ተኮር ግጭት ወደ ተቀሰቀሰባቸው የወለጋ ዞኖች የአገር መከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለጸ። ባለፉት ቀናት በምሥራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በሚገኙ አካባቢዎች በተፈጸሙ ብሔር ተኮር ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸው እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መፈናቀላቸው ሲገለጽ ቆይቷል። ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ለተፈጠረው ግጭት እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን እና የአማራ ታጣቂዎችን ተጠያቂ ይደረጋሉ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም በሰሞኑ ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች መንግሥት ‘ሸኔ’ ብሎ የሚጠራው ቡድን እና የአማራ ታጣቂዎች መሆናቸው ለቢቢሲ አስታውቋል። “የፌደራል ኃይል አባላት አንገር ጉተን ከተማ ከገቡ በኋላ በአካባቢው የጸጥታ መሻሻል አለ” ሲሉ ግጭት ካጋጠመባቸው አንዷ በሆነችው የምሥራቅ ወለጋ ዞን የጊዳ አያና ወረዳ አንድ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ባለፉት ጥቂት ቀናት የተሰማራ ሲሆን በሆሮ ጉዱሩ ዞን ደግሞ ከአንድ ሳምንት በፊት ተሰማርቷል። በምዕራብ ኦሮሚያ እየተፈጠረ ስላለው ግድያ፣ መፈናቀል እና ንብረት መወደም ዝምታን የመረጠው የፌደራሉ መንግሥት ጦሩን ወደ ግጭት ቀጠናው ያሰማራው በርካቶች የዜጎች ደኅንነት እንዲረጋገጥ በስፋት እየጠየቁ ባሉበት ወቅት ነው። ፖለቲከኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ማኅበራት መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት እንዲጠብቅ ሲጠይቁ ነበር። የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በወለጋ ዞኖች በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞት፣ መፈናቀል እና ሰቆቃ በእጅጉ ያሳስበኛል ያለ ሲሆን፣ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ትናንት ማክሰኞ ኅዳር 27/2015 ዓ.ም. ጥሪ አቅርቧል። ፖለቲከኛው ጃዋር መሐመድ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ላለው ቀውስ መፍትሄ ናቸው ያላቸውን ምክረ ሃሳቦች የለገሰ ሲሆን፤ መንግሥት ተኩስ በማቆም ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር ንግግር መጀመር አለበት ብሏል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና ሌሎችም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳዩን አስመልክተው ባወጧቸው መግለጫዎች፣ ወለጋ ውስጥ በዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እንዳሳሰባቸውና መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል። የፌደራል መንግሥት ጦር በአካባቢዎች መሰማራቱ ይገለጽ እንጂ ግጭት ሸሽተው ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያሻቸው እየተገለጸ ይገኛል። ባለፉት ቀናት በወለጋ ዞኖች በተቀሰቀሱት ግጭቶች በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እስካሁን በውል ባይታወቅም፣ የምሥራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ግን ከ60 ያላነሱ ሰዎች በአንድ ጀምበር መገደላቸውን ተናግረዋል። ሰዎች በማንነታቸው ምክንያት የጥቃቶች ዒላማ መሆናቸውን የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጥቃቶቹ የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ምርመራ ላይ መሆኑን ለቢቢሲ አስታውቋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/czq3yv3n2zwo |
2health
| የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ የዓለም ጤና ስጋት ነው ተብሎ ታወጀ | የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ወረርሽኝ አንገብጋቢ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አወጀ። በድርጅቱ ምደባ መሠረት ይህ ውሳኔ ከወረርሽኞች አሳሳቢነት አንጻር ከፍተኛው ደረጃ ሲሆን፣ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በዓለም ዙሪያ እየጨመረ በመሄዱ ነው የሕዝብ ጤና ስጋት ተብሎ እንዲፈረጅ የተወሰነው። ውሳኔው የተላላፈው የዓለም ጤና ድርጅት ከቀናት በፊት በቫይረሱ ዙሪያ ለሁለተኛ ጊዜ ማካሄድ በጀመረው የበሽታው የአስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴ ስብሰባ ማብቂያ ላይ ነው። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ በ75 አገራት ውስጥ ከ16,000 በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። አስካሁን በበሽታው ምክንያት አምስት ሰዎች መሞታቸውንም ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የዓለም ሕዝብ የጤና ስጋት ተብለው የተለዩ ሁለት በሽታዎች ያሉ ሲሆን፣ እነሱም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና ለማጥፋት ትግል እየተደረገበት ያለው ፖሊዮ ናቸው። በተካሄደው ስብሰባ ላይ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽን ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው ተብሎ ይወሰን በሚለው ላይ ከውሳኔ ላይ ለመድረስ የጋራ ስምምነት እንዳልነበረ ዶክትር ቴድሮስ ተናግረዋል። ነገር ግን ወረርሽኙ በፍጥነት በዓለም ዙሪያ እየተዛመተ በመሆኑ፣ በእርግጥም ቫይረሱ የዓለም ሕዝብ ጤና ስጋት ነው የሚለውን ውሳኔ ማሳለፋቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። “በዓለም ጤና ድርጅት ግምገማ የበሽታው ስጋት ከፍተኛ ስጋት ከሆነበት ከአውሮፓ በስተቀር በቀረው የዓለም ክፍል መካከለኛ ነው።” በዓለም ዙሪያ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሽታው የበለጠ መስፋፋት ዕድሉ በአሁኑ ጊዜ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ ወረርሽኙ በስፋት የበለጠ በዓለም ላይ የመስፋፋት ስጋት እንዳለ ግን ግልጽ ነው ሲሉ ባለሥልጣኑ አክለዋል። ይህን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ የዓለም የጤና ስጋት ነው ብሎ ድርጅቱ ማወጁ የመከላከያ ክትባት በፍጥነት እንዲዘጋጅና ቫይረሱ የበለጠ እንዳይዛመት ለማድረግ የሚያስፈልጉ የመከላከያ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረግ ያግዛል ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ። በተጨማሪም ድርጅቱ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች ለመጠበቅና የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት አገራት እርምጃ እንዲወስዱ የሚያደርግ መመሪያን እያዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል። “ይህ ወረርሽኝ በትክክለኛ ዕቅዶችና በትክክለኛ ቡድኖች አማካይነት ለማስቆም የሚቻል ነው” ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በመጀመሪያ የተገኘው በማዕከላዊ አፍሪካ ውስጥ እንደ አውሮፓውያኑ በ1950ዎቹ ነበር። | የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ የዓለም ጤና ስጋት ነው ተብሎ ታወጀ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ወረርሽኝ አንገብጋቢ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አወጀ። በድርጅቱ ምደባ መሠረት ይህ ውሳኔ ከወረርሽኞች አሳሳቢነት አንጻር ከፍተኛው ደረጃ ሲሆን፣ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በዓለም ዙሪያ እየጨመረ በመሄዱ ነው የሕዝብ ጤና ስጋት ተብሎ እንዲፈረጅ የተወሰነው። ውሳኔው የተላላፈው የዓለም ጤና ድርጅት ከቀናት በፊት በቫይረሱ ዙሪያ ለሁለተኛ ጊዜ ማካሄድ በጀመረው የበሽታው የአስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴ ስብሰባ ማብቂያ ላይ ነው። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ በ75 አገራት ውስጥ ከ16,000 በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። አስካሁን በበሽታው ምክንያት አምስት ሰዎች መሞታቸውንም ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የዓለም ሕዝብ የጤና ስጋት ተብለው የተለዩ ሁለት በሽታዎች ያሉ ሲሆን፣ እነሱም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና ለማጥፋት ትግል እየተደረገበት ያለው ፖሊዮ ናቸው። በተካሄደው ስብሰባ ላይ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽን ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው ተብሎ ይወሰን በሚለው ላይ ከውሳኔ ላይ ለመድረስ የጋራ ስምምነት እንዳልነበረ ዶክትር ቴድሮስ ተናግረዋል። ነገር ግን ወረርሽኙ በፍጥነት በዓለም ዙሪያ እየተዛመተ በመሆኑ፣ በእርግጥም ቫይረሱ የዓለም ሕዝብ ጤና ስጋት ነው የሚለውን ውሳኔ ማሳለፋቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። “በዓለም ጤና ድርጅት ግምገማ የበሽታው ስጋት ከፍተኛ ስጋት ከሆነበት ከአውሮፓ በስተቀር በቀረው የዓለም ክፍል መካከለኛ ነው።” በዓለም ዙሪያ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሽታው የበለጠ መስፋፋት ዕድሉ በአሁኑ ጊዜ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ ወረርሽኙ በስፋት የበለጠ በዓለም ላይ የመስፋፋት ስጋት እንዳለ ግን ግልጽ ነው ሲሉ ባለሥልጣኑ አክለዋል። ይህን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ የዓለም የጤና ስጋት ነው ብሎ ድርጅቱ ማወጁ የመከላከያ ክትባት በፍጥነት እንዲዘጋጅና ቫይረሱ የበለጠ እንዳይዛመት ለማድረግ የሚያስፈልጉ የመከላከያ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረግ ያግዛል ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ። በተጨማሪም ድርጅቱ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች ለመጠበቅና የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት አገራት እርምጃ እንዲወስዱ የሚያደርግ መመሪያን እያዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል። “ይህ ወረርሽኝ በትክክለኛ ዕቅዶችና በትክክለኛ ቡድኖች አማካይነት ለማስቆም የሚቻል ነው” ብለዋል ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በመጀመሪያ የተገኘው በማዕከላዊ አፍሪካ ውስጥ እንደ አውሮፓውያኑ በ1950ዎቹ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cjj40w44xy9o |
3politics
| ሩሲያ እና የክሬን፡ የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ታማኝ ሰዎች እነማን ናቸው? | የሩሲያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆናቸው በዩክሬን ላይ ለተፈጸመው ወረራ ዋነኛው ውሳኔ የሚተላለፈው በፕሬዝዳንት ፑቲን ነው። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ለሚሰጡት ውሳኔያቸው ከአስርት ዓመታት በፊት አንስቶ አብረዋቸው የሰሩ የቅርብ ታማኝ ሰዎቻቸው በሚሰጧቸው ምክር ላይም ይተማመናሉ። እየተካሄደ ካለው ጦርነት አንጻር የፑቲን የቅርብ ታማኝ ሰዎች እነማን ናቸው? ሰርጌይ ሹይጉ የፑቲን የረጅም ጊዜ ታማኝ የቅርብ ሰው የሆኑት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ሹይጉ ዩክሬንን በተመለከተ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ተመሳሳይ አቋምን ያንጸባርቃሉ። በዚህም ዩክሬንን ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ በማድረግ ሩሲያን ከምዕራባውያን ወታደራዊ ስጋት መጠበቅ የሚል አቋም አላቸው። ከቅርበታቸው የተነሳ ሚኒስትሩ ቀደም ሲል የፑቲን ተተኪ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰብ ነበር። ነገር ግን አሁንም ድረስ በሩሲያ መንግሥት ውስጥ ከፍ ያለ ተደማጭነት ያላቸው የፕሬዝዳንቱ የቅርብ ሰው ናቸው። ሰርጌይ ሹይጉ ከስምንት ዓመት በፊት ሩሲያ ከዩክሬን የተጠቀቻትን ክሪሚያን ስትይዝ ወታደራዊ ዘመቻውን በመምራት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም የፑቲን ተቃዋሚዎችን ከሩሲያ ውጪ እያደነ በመርዝ ያጠፋል የሚባለውን የወታደራዊ መረጃ ቡድንን የሚመሩት እኚሁ ግለሰብ ናቸው። የሩሲያ የደኅንት ተንታኝና ፀሐፊ የሆኑት አንድሬ ሶልዳቶቭ እንደሚሉት ሰርጌይ ሹይጉ፣ የጦር ሚኒስትር ብቻ ሳይሆኑ በአብዛኛው በታሪክ ላይ የተመሰረተው የሩሲያ መንግሥት ርዕዮተ ዓለምንም በከፊል የሚቃኙት ናቸው። ቫሌሪ ጌራሲሞቭ የአገሪቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የሆኑት ቫሌሪ ጌራሲሞቭ የዩክሬን ወረራ እና ወታደራዊ እርምጃውን በፍጥነት ማጣናቀቅ ኃላፊነታቸው የነበረ ቢሆንም፣ የተፈለገውን ያህል የተሳካላቸው አይመስሉም። ፑቲን ከ20 ዓመት በፊት በቼቺኒያ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ቫሌሪ ጌራሲሞቭ ሠራዊቱን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን፣ በክሪሚያ ወረራ፣ ከዩክሬን ወረራ በፊት ቤላሩስ ውስጥ የተደረገውን ወታደራዊ ልምምድን እንዲሁም ወረራውን በመማራት ከፊት ተሰልፈዋል። በተደነቃቀፈው የዩክሬን ወረራ ጅማሬ እና በሩሲያ ወታደሮች ዘንድ አለ በሚባል ዝቅተኛ ሞራል ምክንያት ወደ ጎን ተገፍተዋል የሚሉ አንዳንድ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው። ነገር ግን አንድሬ ሶልዳቶ እንደሚያምኑት ይህ ከእውነት የራቀ ምኞት ነው። ምክንያቱም ፑቲን በጦር ሜዳ የሚካሄዱ ነገሮችን በራሳቸው ሊከውኑና ሊቆጣጠሩ አይችሉም። ስለዚህም የቫሌሪ ጌራሲሞቭ ሚና እንዲሁ በቀላሉ የሚተካ እንዳልሆነ ያመለክታሉ። ኒኮላይ ፓትሩሼቭ ፓትሩሼቭ ምዕራባውያን ለሩሲያ መልካም አመለካከት የላቸውም ብለው በጽኑ የሚያምኑ ሲሆን ከአስርታት በፊት አንስቶ ከፑቲን ጋር የጠበቀ ቅርበት አላቸው። ከፓትሩሼቭ በተጨማሪ የአገር ውስጥና የውጭ ደኅንት ኃላፊዎቹ ቦርትኒኮቭ እና ናሪይሽኪን ሌሊን ግራድ ውስጥ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ከፑቲን ጋር አብረው የሰሩ ሲሆን፤ አሁን ድረስ የፕሬዝዳንቱ ቁልፍ ሰው ሆነው እንዳሉ ናቸው። ነገር ግን የፓትሩሼቭን ያህል በፑቲን ዘንድ ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች በታም ጥቂት እንደሆኑ ይነገራል። ሁለቱ በሶቪየት ዘመን ኬጂቢ ውስጥ የሰሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ሁለቱም የሩሲያን የስለላ ድርጅት አንዳቸው ከአንዳቸው በመረከብ መርተዋል። ከዩክሬን ወረራ ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የደኅንት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አሜሪካ ዋነኛ ግብ አድርጋ የያዘችው ሩሲያን እንድተርበታተን መድረግ ነው ሲሉ ጠንካራ ክስ አቅርበዋል። አሌክሳንደር ቦርትኒኮቭ የክሬምሊንን እርምጃ በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች እንደሚሉት ቦርትኒኮቭ ከሚመሯቸው የደኅንነት ተቋማት የሚቀርቡ መረጃዎችን ቭላድሚር ፑቲን ከየትኛውም ምንጭ በላይ ያምናሉ። በዚህም ቦርትኒኮቭ የፕሬዝዳንቱ የቅርብ ታማኝ ከሆኑት መካከል ይጠቀሳል። የሩሲያ የፌደራል ደኅንት መሥሪያ ቤትን (ኤፍኤስቢ) የመሪነት ቦታ የያዙት ቦርትኒኮቭ፣ ቦታውን ከሌላኛው የፑቲን የቅርብ ሰው ኒኮላይ ፓትሩሼቭ ነበር የተረከቡት። ይህ የሩሲያ የደኅንት መሥሪያ ቤት በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ሌሎች የደኅንት ተቋማት ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ማሳረፍ የሚችል ሲሆን የራሱ ልዩ ኃይልም አለው። አንድሬ ሶልዳቶቭ እንደሚያምኑት ቦርትኒኮቭ በሩሲያ የሥልጣን ማዕከል ውስጥ እጅጉን አስፋለጊ ሰው ቢሆኑም፣ ሌሎች እንደሚያደርጉት የመሪውን ሐሳብ የሚገዳደሩና ምክር የሚሰጡ ሰው አይደሉም ይላሉ። ሰርጌይ ናሪይሽኪን ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ለረጅም ጊዜ አብረው በቅርበት በመስራት ከሚጠቀሱት ባለሥልጣንት መካከል ሰርጌይ ናሪይሽኪን አንዱ ናቸው። ነገር ግን ከዩክሬን ወረራ በፊት በተካሄደውና በቴሌቪዥን በቀረበው የአገሪቱ የደኅንት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን ለናሪይሽኪን ያሳዩት ምላሽ፣ በብዙዎች ዘንድ በሁለቱ መካከል የነበረው ቅርበት መላላቱን የሚያመላክት ነው ይላሉ። ስለ ክስተቱ አስደንጋጭነት ቤን ኖብል ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን፣ የፑቲን በሚገርም ሁኔታ መረጋጋት በበርካቶች ዘንድ ጥያቄን አጭሯል። አጠቃላይ የስብሰባው ድባብም ግራ አጋቢና መልካማ ያልሆነ ምስል የተንጸባረቀበት ነበር። ሰርጌይ ናሪይሽኪን በ1990ዎቹ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ፣ በ2004 ፕሬዝዳንትንት ከሆኑ በኋላ፣ ቀጥሎም የአገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ሆነው ከፑቲን ጋር አብረው ሰርተዋል። በተጨማሪም የሩሲያ ታሪክ ማኅበር መሪ ሆነው ሰርተዋል። ሶልዳቶቭ እንደሚሉት ይህ የናሪይሽኪን የታሪክ ዕውቀት ፕሬዝዳንቱ ለሚወስዷቸው እርምጃዎች ርዕዮተ ዓለማዊ መሰረቶችን በመስጠት ያላቸውን ተፈላጊነት አጉልቶታል። ሰርጌይ ላቭሮቭ ምንም እንኳን በሩሲያ ውስጥ በሚሰጡ ቁልፍ ውሳኔዎች ላይ ጉልህ ሚና የላቸውም ተብሎ ቢታሰብም ሰርጌይ ላቭሮቭ ለ18 ዓመታት ቁንጮ ዲፕሎማት በመሆን የአገራቸውን ጉዳይ ለዓለም ሲያቀርቡ ቆይተዋል። የ71 ዓመቱ ላቭሮቭ የረጅም ዘመን አገልግሎት ፕሬዝዳንት ፑቲን አመራራቸው በዋናነት ለዘመናት የካበተ ልምድ ባላቸው ሩሲያውያን ላይ መሠረት ያደረገ መሆኑን ያሳያል። ነገር ግን ለረጅም ጊዜ ዩክሬንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ተገልለው እንደቆዩ የሚነገርላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ምንም እንኳን ግልፍተኛና ኃይለኛ ናቸው ቢባሉም ዩክሬንን በተመለከተ የፑቲን ጆሮ ባያገኙም ዲፕሎማሲያዊ ንግግርን በመፍትሔነት ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ቫለንቲና ማትቪዬንኮ በፑቲን የቅርብ ክበብ ውስጥ ብቸኛዋ ሴት የሆኑት ቫለንቲና ማትቪዬንኮ፣ የአገሪቱ የላይኛው ምክር ቤት የሩሲያ ኃይሎች ወደ ሌላ አገር ገብተው እንዲሰማሩ ያደረገውን ውሳኔ ሲያጸድቅ የበላይ ሆነው የመሩ ናቸው። ይህም ለዩክሬኑ ወረራ መንገድ ጠርጓል። ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ፑቲን ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ ሥልጣን ላይ እያሉ ጀምሮ አብረዋቸው ከመጡ ታማኝ ሰዎች መካከል አንዷ ሲሆኑ፣ ሩሲያ ክሪሚያን ወራ ስትይዝ በውሳኔው ውስጥ ተሳትፎ ነበራቸው። ቢሆንም ግን በቀዳሚ የውሳኔ ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የሚካተቱ ግለሰብ አይደሉም። እንደሁሉም የሩሲያ የደኅንነት ምክር ቤት አባል የቫለንቲና ማትቪዬንኮ ሚና ፕሬዝዳንት ፑቲን አብላልተውና ከውሳኔ ላይ ደርሰው የሚያመጧቸው ሐሳቦች የጋራ ውይይት ተደርጎባቸው የተሰጡ የሚመስል ገጽታ እንዲይዙ ማድረግ ነው። ቪክቶር ዞሎቶቭ የቀድሞው የፕሬዝዳንቱ የግል ጠባቂ ቪክቶር ዞሎቶቭ፣ ከስድስት ዓመት በፊት እንደ ኦእሬዝዳንቱ የግል ሠራዊት በራሳቸው በፑቲን የተቋቋመውን 'ሮስግቫርዲያ' የተባለውን የሩሲያን ብሔራዊ ዘብ ይመራሉ። ፑቲን የግል ጠባቂያቸው ብሔራዊ ዘቡን እንዲመሩ ማድረጋቸው የበለጠ ታማኝነትን ለማረጋገጥ የታለመ ነው። ቪክቶር ዞሎቶቭም ይሚመሩትን ዘብ ቁጥር አሁን 400,000 እንዳደረሱት ይነገራል። የዩክሬን ወረራ ሲታቀድ የአገሪቱ ሠራዊት በቀናት ውስጥ እንዲያጠናቅቀው ታቅዶ ነበር፤ ነገር ግን የታሰበው ሳይሆን ሲቀር የሩሲያ ብሔራዊ ዘብ የመሪነቱን ሚና ተረክቦ ጦርነቱን እያካሄደ ነው። የብሔራዊ ዘቡ ችግር የሚባለው መሪው ቪክቶር ዞሎቶቭ ወታደራዊ ስልጣናና ልምድ የሌላቸው መሆኑና ሠራዊታቸውም ታንክ የታጠቀ አለመሆኑ ለጥቃት ተጋላጭ እንዳደረገው ይነገራል። | ሩሲያ እና የክሬን፡ የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ታማኝ ሰዎች እነማን ናቸው? የሩሲያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆናቸው በዩክሬን ላይ ለተፈጸመው ወረራ ዋነኛው ውሳኔ የሚተላለፈው በፕሬዝዳንት ፑቲን ነው። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ለሚሰጡት ውሳኔያቸው ከአስርት ዓመታት በፊት አንስቶ አብረዋቸው የሰሩ የቅርብ ታማኝ ሰዎቻቸው በሚሰጧቸው ምክር ላይም ይተማመናሉ። እየተካሄደ ካለው ጦርነት አንጻር የፑቲን የቅርብ ታማኝ ሰዎች እነማን ናቸው? ሰርጌይ ሹይጉ የፑቲን የረጅም ጊዜ ታማኝ የቅርብ ሰው የሆኑት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ሹይጉ ዩክሬንን በተመለከተ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ተመሳሳይ አቋምን ያንጸባርቃሉ። በዚህም ዩክሬንን ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ በማድረግ ሩሲያን ከምዕራባውያን ወታደራዊ ስጋት መጠበቅ የሚል አቋም አላቸው። ከቅርበታቸው የተነሳ ሚኒስትሩ ቀደም ሲል የፑቲን ተተኪ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰብ ነበር። ነገር ግን አሁንም ድረስ በሩሲያ መንግሥት ውስጥ ከፍ ያለ ተደማጭነት ያላቸው የፕሬዝዳንቱ የቅርብ ሰው ናቸው። ሰርጌይ ሹይጉ ከስምንት ዓመት በፊት ሩሲያ ከዩክሬን የተጠቀቻትን ክሪሚያን ስትይዝ ወታደራዊ ዘመቻውን በመምራት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም የፑቲን ተቃዋሚዎችን ከሩሲያ ውጪ እያደነ በመርዝ ያጠፋል የሚባለውን የወታደራዊ መረጃ ቡድንን የሚመሩት እኚሁ ግለሰብ ናቸው። የሩሲያ የደኅንት ተንታኝና ፀሐፊ የሆኑት አንድሬ ሶልዳቶቭ እንደሚሉት ሰርጌይ ሹይጉ፣ የጦር ሚኒስትር ብቻ ሳይሆኑ በአብዛኛው በታሪክ ላይ የተመሰረተው የሩሲያ መንግሥት ርዕዮተ ዓለምንም በከፊል የሚቃኙት ናቸው። ቫሌሪ ጌራሲሞቭ የአገሪቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የሆኑት ቫሌሪ ጌራሲሞቭ የዩክሬን ወረራ እና ወታደራዊ እርምጃውን በፍጥነት ማጣናቀቅ ኃላፊነታቸው የነበረ ቢሆንም፣ የተፈለገውን ያህል የተሳካላቸው አይመስሉም። ፑቲን ከ20 ዓመት በፊት በቼቺኒያ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ቫሌሪ ጌራሲሞቭ ሠራዊቱን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን፣ በክሪሚያ ወረራ፣ ከዩክሬን ወረራ በፊት ቤላሩስ ውስጥ የተደረገውን ወታደራዊ ልምምድን እንዲሁም ወረራውን በመማራት ከፊት ተሰልፈዋል። በተደነቃቀፈው የዩክሬን ወረራ ጅማሬ እና በሩሲያ ወታደሮች ዘንድ አለ በሚባል ዝቅተኛ ሞራል ምክንያት ወደ ጎን ተገፍተዋል የሚሉ አንዳንድ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው። ነገር ግን አንድሬ ሶልዳቶ እንደሚያምኑት ይህ ከእውነት የራቀ ምኞት ነው። ምክንያቱም ፑቲን በጦር ሜዳ የሚካሄዱ ነገሮችን በራሳቸው ሊከውኑና ሊቆጣጠሩ አይችሉም። ስለዚህም የቫሌሪ ጌራሲሞቭ ሚና እንዲሁ በቀላሉ የሚተካ እንዳልሆነ ያመለክታሉ። ኒኮላይ ፓትሩሼቭ ፓትሩሼቭ ምዕራባውያን ለሩሲያ መልካም አመለካከት የላቸውም ብለው በጽኑ የሚያምኑ ሲሆን ከአስርታት በፊት አንስቶ ከፑቲን ጋር የጠበቀ ቅርበት አላቸው። ከፓትሩሼቭ በተጨማሪ የአገር ውስጥና የውጭ ደኅንት ኃላፊዎቹ ቦርትኒኮቭ እና ናሪይሽኪን ሌሊን ግራድ ውስጥ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ከፑቲን ጋር አብረው የሰሩ ሲሆን፤ አሁን ድረስ የፕሬዝዳንቱ ቁልፍ ሰው ሆነው እንዳሉ ናቸው። ነገር ግን የፓትሩሼቭን ያህል በፑቲን ዘንድ ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች በታም ጥቂት እንደሆኑ ይነገራል። ሁለቱ በሶቪየት ዘመን ኬጂቢ ውስጥ የሰሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ሁለቱም የሩሲያን የስለላ ድርጅት አንዳቸው ከአንዳቸው በመረከብ መርተዋል። ከዩክሬን ወረራ ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የደኅንት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አሜሪካ ዋነኛ ግብ አድርጋ የያዘችው ሩሲያን እንድተርበታተን መድረግ ነው ሲሉ ጠንካራ ክስ አቅርበዋል። አሌክሳንደር ቦርትኒኮቭ የክሬምሊንን እርምጃ በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች እንደሚሉት ቦርትኒኮቭ ከሚመሯቸው የደኅንነት ተቋማት የሚቀርቡ መረጃዎችን ቭላድሚር ፑቲን ከየትኛውም ምንጭ በላይ ያምናሉ። በዚህም ቦርትኒኮቭ የፕሬዝዳንቱ የቅርብ ታማኝ ከሆኑት መካከል ይጠቀሳል። የሩሲያ የፌደራል ደኅንት መሥሪያ ቤትን (ኤፍኤስቢ) የመሪነት ቦታ የያዙት ቦርትኒኮቭ፣ ቦታውን ከሌላኛው የፑቲን የቅርብ ሰው ኒኮላይ ፓትሩሼቭ ነበር የተረከቡት። ይህ የሩሲያ የደኅንት መሥሪያ ቤት በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ሌሎች የደኅንት ተቋማት ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ማሳረፍ የሚችል ሲሆን የራሱ ልዩ ኃይልም አለው። አንድሬ ሶልዳቶቭ እንደሚያምኑት ቦርትኒኮቭ በሩሲያ የሥልጣን ማዕከል ውስጥ እጅጉን አስፋለጊ ሰው ቢሆኑም፣ ሌሎች እንደሚያደርጉት የመሪውን ሐሳብ የሚገዳደሩና ምክር የሚሰጡ ሰው አይደሉም ይላሉ። ሰርጌይ ናሪይሽኪን ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ለረጅም ጊዜ አብረው በቅርበት በመስራት ከሚጠቀሱት ባለሥልጣንት መካከል ሰርጌይ ናሪይሽኪን አንዱ ናቸው። ነገር ግን ከዩክሬን ወረራ በፊት በተካሄደውና በቴሌቪዥን በቀረበው የአገሪቱ የደኅንት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን ለናሪይሽኪን ያሳዩት ምላሽ፣ በብዙዎች ዘንድ በሁለቱ መካከል የነበረው ቅርበት መላላቱን የሚያመላክት ነው ይላሉ። ስለ ክስተቱ አስደንጋጭነት ቤን ኖብል ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን፣ የፑቲን በሚገርም ሁኔታ መረጋጋት በበርካቶች ዘንድ ጥያቄን አጭሯል። አጠቃላይ የስብሰባው ድባብም ግራ አጋቢና መልካማ ያልሆነ ምስል የተንጸባረቀበት ነበር። ሰርጌይ ናሪይሽኪን በ1990ዎቹ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ፣ በ2004 ፕሬዝዳንትንት ከሆኑ በኋላ፣ ቀጥሎም የአገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ሆነው ከፑቲን ጋር አብረው ሰርተዋል። በተጨማሪም የሩሲያ ታሪክ ማኅበር መሪ ሆነው ሰርተዋል። ሶልዳቶቭ እንደሚሉት ይህ የናሪይሽኪን የታሪክ ዕውቀት ፕሬዝዳንቱ ለሚወስዷቸው እርምጃዎች ርዕዮተ ዓለማዊ መሰረቶችን በመስጠት ያላቸውን ተፈላጊነት አጉልቶታል። ሰርጌይ ላቭሮቭ ምንም እንኳን በሩሲያ ውስጥ በሚሰጡ ቁልፍ ውሳኔዎች ላይ ጉልህ ሚና የላቸውም ተብሎ ቢታሰብም ሰርጌይ ላቭሮቭ ለ18 ዓመታት ቁንጮ ዲፕሎማት በመሆን የአገራቸውን ጉዳይ ለዓለም ሲያቀርቡ ቆይተዋል። የ71 ዓመቱ ላቭሮቭ የረጅም ዘመን አገልግሎት ፕሬዝዳንት ፑቲን አመራራቸው በዋናነት ለዘመናት የካበተ ልምድ ባላቸው ሩሲያውያን ላይ መሠረት ያደረገ መሆኑን ያሳያል። ነገር ግን ለረጅም ጊዜ ዩክሬንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ተገልለው እንደቆዩ የሚነገርላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ምንም እንኳን ግልፍተኛና ኃይለኛ ናቸው ቢባሉም ዩክሬንን በተመለከተ የፑቲን ጆሮ ባያገኙም ዲፕሎማሲያዊ ንግግርን በመፍትሔነት ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ቫለንቲና ማትቪዬንኮ በፑቲን የቅርብ ክበብ ውስጥ ብቸኛዋ ሴት የሆኑት ቫለንቲና ማትቪዬንኮ፣ የአገሪቱ የላይኛው ምክር ቤት የሩሲያ ኃይሎች ወደ ሌላ አገር ገብተው እንዲሰማሩ ያደረገውን ውሳኔ ሲያጸድቅ የበላይ ሆነው የመሩ ናቸው። ይህም ለዩክሬኑ ወረራ መንገድ ጠርጓል። ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ፑቲን ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ ሥልጣን ላይ እያሉ ጀምሮ አብረዋቸው ከመጡ ታማኝ ሰዎች መካከል አንዷ ሲሆኑ፣ ሩሲያ ክሪሚያን ወራ ስትይዝ በውሳኔው ውስጥ ተሳትፎ ነበራቸው። ቢሆንም ግን በቀዳሚ የውሳኔ ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የሚካተቱ ግለሰብ አይደሉም። እንደሁሉም የሩሲያ የደኅንነት ምክር ቤት አባል የቫለንቲና ማትቪዬንኮ ሚና ፕሬዝዳንት ፑቲን አብላልተውና ከውሳኔ ላይ ደርሰው የሚያመጧቸው ሐሳቦች የጋራ ውይይት ተደርጎባቸው የተሰጡ የሚመስል ገጽታ እንዲይዙ ማድረግ ነው። ቪክቶር ዞሎቶቭ የቀድሞው የፕሬዝዳንቱ የግል ጠባቂ ቪክቶር ዞሎቶቭ፣ ከስድስት ዓመት በፊት እንደ ኦእሬዝዳንቱ የግል ሠራዊት በራሳቸው በፑቲን የተቋቋመውን 'ሮስግቫርዲያ' የተባለውን የሩሲያን ብሔራዊ ዘብ ይመራሉ። ፑቲን የግል ጠባቂያቸው ብሔራዊ ዘቡን እንዲመሩ ማድረጋቸው የበለጠ ታማኝነትን ለማረጋገጥ የታለመ ነው። ቪክቶር ዞሎቶቭም ይሚመሩትን ዘብ ቁጥር አሁን 400,000 እንዳደረሱት ይነገራል። የዩክሬን ወረራ ሲታቀድ የአገሪቱ ሠራዊት በቀናት ውስጥ እንዲያጠናቅቀው ታቅዶ ነበር፤ ነገር ግን የታሰበው ሳይሆን ሲቀር የሩሲያ ብሔራዊ ዘብ የመሪነቱን ሚና ተረክቦ ጦርነቱን እያካሄደ ነው። የብሔራዊ ዘቡ ችግር የሚባለው መሪው ቪክቶር ዞሎቶቭ ወታደራዊ ስልጣናና ልምድ የሌላቸው መሆኑና ሠራዊታቸውም ታንክ የታጠቀ አለመሆኑ ለጥቃት ተጋላጭ እንዳደረገው ይነገራል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60605493 |
5sports
| የ105 ዓመቷ እማማ ራምባይ በሩጫ ክብረ ወሰን ሰበሩ | ወ/ሮ ራምባይ 105 ዓመታቸው ነው። 100 ሜትርን በ45.40 ሰከንድ በመጨረስ በአዛውንቶች የተያዘውን የሕንድን ክብረ ወሰን ሰብረዋል። ይህንን ውድድር የሚያዘጋጀው አካል እስካሁን ትልቁ የውድድር ተሳታፊ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ነው። | የ105 ዓመቷ እማማ ራምባይ በሩጫ ክብረ ወሰን ሰበሩ ወ/ሮ ራምባይ 105 ዓመታቸው ነው። 100 ሜትርን በ45.40 ሰከንድ በመጨረስ በአዛውንቶች የተያዘውን የሕንድን ክብረ ወሰን ሰብረዋል። ይህንን ውድድር የሚያዘጋጀው አካል እስካሁን ትልቁ የውድድር ተሳታፊ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cglrkjmrvngo |
3politics
| ኢዜማ በሥልጣን ላይ ካሉ ሚኒስትሮች ትይዩ 22 የራሱን ሚኒስትሮች መሰየሙን አስታወቀ | የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ፣ ኢዜማ የመንግሥት ሥራዎችን የሚከታተሉ 22 ትይዩ የካቢኔ ሚኒስትሮችን አዋቅሮ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ። ኢዜማ የራሱን ትይዩ ካቢኔ ማቋቋሙን ባሳወቀበት መግለጫው እንዳመለከተው፣ ይህ ትይዩ ካቢኔ የዕለት ከዕለት የመንግሥት ተግባራትን መከታተል፣ የሚወጡ ረቂቅ ሕጎችን መተቸት፣ የፖሊሲ ንድፈ ሐሳቦችን ማውጣትና መሰል ሥራዎችን ያከናውናል። የፓርቲው ትይዩ ካቢኔ ፀሐፊ አቶ ይመስገን መሳፍንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ካቢኔውን ማቋቋም ያስፈለገበትን ምክንያት ለዲሞክራሲ፣ ለአገራዊ ለውጥ እንዲሁም አገሪቱ እንድትሄድበት በሚፈልገው የልማት መስክ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል በሚል መሆኑን ይናገራሉ። አክለውም አገራዊ ለውጡን ተቋማዊ ለማድረግ ወይንም ደግሞ በትክክል እየተመራ ስለመሆኑ የሚከታተል እና ድጋፍ የሚያደርግ የሰላ ትችቶችንም ለማቅረብ ይረዳል በሚል መቋቋሙን አመልክተዋል። ጨምረውም በኢዜማ የተዋቀረው ትይዩ ካቢኔ መንግሥት በአዋጅ ያቋቋማቸው 22 ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን የሚመሩ ሚኒስትሮችን እንደሾመው ሁሉ፣ ፓርቲው 22 ትይዩ ሚኒስትሮችን መሰየሙን ጠቅሰዋል። ኢዜማ የሰየማቸው ትይዩ ሚኒስትሮች ማንነትና ኃላፊነትን በሚመለከት ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ይመስገን ይህንን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ ተቆጥበዋል። የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚለው መሠረት የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህንን ትይዩ ካቢኔ አዋቅረው ሥራ መጀመራቸውን ያሳወቀው ኢዜማ፣ ይህ መንግሥታዊውን አስተዳደር ከሚያከናውነው መዋቅር በትይዩ የተቋቋመው ካቢኔ "በምንም መልኩ የተጠባባቂ መንግሥትነትና የባለአደራነት ስብስብ እንዳልሆነ" አመልክቷል። በካቢኔው በየተለያዩ ዘርፎችን የሚከታተሉ ትይዩ የካቢኔ ሚኒስትሮች የተሰየሙ ሲሆን እሱም ቡድኖችን በማዋቀር ኃላፊነትን በማከፋፈል ፓርቲውን ተፎካካሪ ማድረግ ዋነኛ የሥራ ድርሻቸው እንደሚሆን ገልጿል። አቶ ይመስገን አክለውም ፓርቲያቸው ትይዩ ካቢኔውን አዲስ መንግሥት እንደተመሰረተ ይፋ ማድረግ ያልቻለው አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር መሆኑን ጠቅሰው፣ ፓርቲያቸው የትይዩ ካቢኔውን ምሥረታ ያካሄደው ጥቅምት 08/2021 ዓ.ም እንደነበር አስታወሰዋል። ነገር ግን በዚያ ወቅት በአገሪቱ የሰሜናዊ ክፍል ጦርነት እየተካሄደ ይህንን ይፋ ማድረግ ከፓርቲያቸው እንደማይጠበቅ መሆኑ ስለታመነበት መዘግየቱን ጠቅሰዋል። ኢዜማ ይህንን ትይዩ ካቢኔ ሲያቋቁም በሥልጣን ላይ ያሉ ሕግ አውጪዎች ተፎካካሪዎቻቸው ምን እንደሚሉ እንዲያውቁ የሚያደርግና ለመራጩ ሕዝብ ደግሞ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ሌላም አማራጭ መፍትሔ እንዳለ ያሳያል ብሏል። ይህ ትይዩ ካቢኔ "ተጠባባቂ መንግሥት ወይም የባለአደራ ስብስብ" አለመሆኑን በአጽንኦት አመልክቶ፣ በሕግ አውጪ ወይም በሕግ አስፈጻሚ ውስጥ ቀጥተኛ ሚና ተጫዋች በማድረግ የዴሞክራሲ መሣሪያ፣ የሰላምና የልማት መገልገያ አድርጎ ለውጥ አምጪ ማድረግ ይጠበቃል ብሏል ኢዜማ። አዲሱ መንግሥት ሲዋቀር የኢዜማ አመራሮች እና አባላት ሥልጣን ማግኘታቸውን በማንሳት አይጋጭም ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ይመስገን፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፀደቀው የፓርቲው ሕገ ደንብ ላይ የትይዩ ካቢኔ ምሥረታ መስፈሩን አንስተው ሕጋዊ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የፓርቲያቸው አባላትም ከመንግሥት የቀረበላቸውን የአብረን እንስራ ጥያቄ ተቀብለው በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ መገኘታቸው እንደማይጋጭ በመጥቀስ፣ እንዲያውም የመንግሥት ሥራን ለመከታተል እና እግር በእግር ለመተቸት ጥሩ መደላደል ይፈጥራል ሲሉ አብራርተዋል። በኢዜማ ሕገ ደንብ የመሪው መዋቅር የትይዩ ካቢኔ እንደሚያዋቅር ይደነግጋል። የሕገ ደንቡ አንቀጽ 7.1.9 ፓርቲው ስልጣን ላይ ካልወጣ መሪው፣ ዋና ወይም ዋና ያልሆነ የፓርላማ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ እንደሚሆን ይደነግጋል። ትይዩ ካቢኔ ምንድን ነው? በምርጫ መንግሥት የመመስረት ድምጽ ያላገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትይዩ ካቢኔ/ሚኒስትር የመሰየም ልምድ በተለይ በእንግሊዝ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ሲተገበር የቆየ ነው። በምርጫ የበላይነትን ያገኘው ፓርቲ መደበኛውን የመንግሥት የሥራ አስፈጻሚ ተቋማትን ይዞ ሚኒስትሮችን በመሾም በተግባር የዕለት ከዕለት ኃላፊነቱን ለመወጣት ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎች ይህ ሥልጣን ስለማይኖራቸው በፓርቲያቸው መሪ አማካኝነት መንግሥትን ከሚመራው ካቢኔ ትይዩ ተመሳሳይ የሆነ ካቢኔን ሊያዋቅሩ ይችላሉ። በዚህም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ የመንግሥት አስተዳደር ዘርፎች ሥልጣን ላይ ካለው መንግሥት በተለየ ያላቸውን አማራጭ እንዲሁም ብቁ ባለሙያዎችን ለሕዝቡ ለማቅረብና ለማስተዋወቅ ይጠቀሙበታል። ትይዩ ካቢኔ/ሚኒስትር ሲዋቀር በኃላፊነት ላይ ካለው መዋቅር ጋር ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ግልባጭ ሲሆን በመንግሥት የሥልጣን መዋቅር ውስጥ ላሉ የሚኒስትርነት ቦታዎች በተመሳሳይ ተቃዋሚዎች የራሳቸውን ሰው ይሰይማሉ። እነዚህም ግለሰቦች የተመደቡባቸውን ቦታዎችን የሚመለከቱ ሕጎች፣ ክስተቶችና ሌሎችም ነገሮች በመያጋጥሙ ጊዜ የፓርቲያቸውን አቋምና አማራጭ ያንጸባርቃሉ። የትይዩ ካቢኔ አባላት በሥልጣን ላይ ካሉት ሚኒስትሮች በተመሳሳይ በፓርቲያቸው የሚሰየሙ በመሆናቸው ትይዩ ሚኒስትር ተብለው በበርካታ አገራት የሚጠሩ ቢሆንም በመንግሥት ውስጥ ተግባራዊ የሚሆን የአስፈጻሚነት ሥልጣን ግን የላቸውም። ' እንዲህ አይነቱ የተቃዋሚ ትይዩ የካቢኔ ሚኒስትሮች ካሏቸው መካከል ዩናይትድ ኪንግደም፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ጃፓን የሚጠቀሱ ሲሆን በርካታ አገራት ውስጥም ይገኛሉ። ከአፍሪካም በደቡብ አፍሪካና ሱዳን ውስጥ የተቃዋሚዎች ትይዩ ካቢኔ አላቸው። | ኢዜማ በሥልጣን ላይ ካሉ ሚኒስትሮች ትይዩ 22 የራሱን ሚኒስትሮች መሰየሙን አስታወቀ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ፣ ኢዜማ የመንግሥት ሥራዎችን የሚከታተሉ 22 ትይዩ የካቢኔ ሚኒስትሮችን አዋቅሮ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ። ኢዜማ የራሱን ትይዩ ካቢኔ ማቋቋሙን ባሳወቀበት መግለጫው እንዳመለከተው፣ ይህ ትይዩ ካቢኔ የዕለት ከዕለት የመንግሥት ተግባራትን መከታተል፣ የሚወጡ ረቂቅ ሕጎችን መተቸት፣ የፖሊሲ ንድፈ ሐሳቦችን ማውጣትና መሰል ሥራዎችን ያከናውናል። የፓርቲው ትይዩ ካቢኔ ፀሐፊ አቶ ይመስገን መሳፍንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ካቢኔውን ማቋቋም ያስፈለገበትን ምክንያት ለዲሞክራሲ፣ ለአገራዊ ለውጥ እንዲሁም አገሪቱ እንድትሄድበት በሚፈልገው የልማት መስክ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል በሚል መሆኑን ይናገራሉ። አክለውም አገራዊ ለውጡን ተቋማዊ ለማድረግ ወይንም ደግሞ በትክክል እየተመራ ስለመሆኑ የሚከታተል እና ድጋፍ የሚያደርግ የሰላ ትችቶችንም ለማቅረብ ይረዳል በሚል መቋቋሙን አመልክተዋል። ጨምረውም በኢዜማ የተዋቀረው ትይዩ ካቢኔ መንግሥት በአዋጅ ያቋቋማቸው 22 ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን የሚመሩ ሚኒስትሮችን እንደሾመው ሁሉ፣ ፓርቲው 22 ትይዩ ሚኒስትሮችን መሰየሙን ጠቅሰዋል። ኢዜማ የሰየማቸው ትይዩ ሚኒስትሮች ማንነትና ኃላፊነትን በሚመለከት ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ይመስገን ይህንን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ ተቆጥበዋል። የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚለው መሠረት የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህንን ትይዩ ካቢኔ አዋቅረው ሥራ መጀመራቸውን ያሳወቀው ኢዜማ፣ ይህ መንግሥታዊውን አስተዳደር ከሚያከናውነው መዋቅር በትይዩ የተቋቋመው ካቢኔ "በምንም መልኩ የተጠባባቂ መንግሥትነትና የባለአደራነት ስብስብ እንዳልሆነ" አመልክቷል። በካቢኔው በየተለያዩ ዘርፎችን የሚከታተሉ ትይዩ የካቢኔ ሚኒስትሮች የተሰየሙ ሲሆን እሱም ቡድኖችን በማዋቀር ኃላፊነትን በማከፋፈል ፓርቲውን ተፎካካሪ ማድረግ ዋነኛ የሥራ ድርሻቸው እንደሚሆን ገልጿል። አቶ ይመስገን አክለውም ፓርቲያቸው ትይዩ ካቢኔውን አዲስ መንግሥት እንደተመሰረተ ይፋ ማድረግ ያልቻለው አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር መሆኑን ጠቅሰው፣ ፓርቲያቸው የትይዩ ካቢኔውን ምሥረታ ያካሄደው ጥቅምት 08/2021 ዓ.ም እንደነበር አስታወሰዋል። ነገር ግን በዚያ ወቅት በአገሪቱ የሰሜናዊ ክፍል ጦርነት እየተካሄደ ይህንን ይፋ ማድረግ ከፓርቲያቸው እንደማይጠበቅ መሆኑ ስለታመነበት መዘግየቱን ጠቅሰዋል። ኢዜማ ይህንን ትይዩ ካቢኔ ሲያቋቁም በሥልጣን ላይ ያሉ ሕግ አውጪዎች ተፎካካሪዎቻቸው ምን እንደሚሉ እንዲያውቁ የሚያደርግና ለመራጩ ሕዝብ ደግሞ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ሌላም አማራጭ መፍትሔ እንዳለ ያሳያል ብሏል። ይህ ትይዩ ካቢኔ "ተጠባባቂ መንግሥት ወይም የባለአደራ ስብስብ" አለመሆኑን በአጽንኦት አመልክቶ፣ በሕግ አውጪ ወይም በሕግ አስፈጻሚ ውስጥ ቀጥተኛ ሚና ተጫዋች በማድረግ የዴሞክራሲ መሣሪያ፣ የሰላምና የልማት መገልገያ አድርጎ ለውጥ አምጪ ማድረግ ይጠበቃል ብሏል ኢዜማ። አዲሱ መንግሥት ሲዋቀር የኢዜማ አመራሮች እና አባላት ሥልጣን ማግኘታቸውን በማንሳት አይጋጭም ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ይመስገን፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፀደቀው የፓርቲው ሕገ ደንብ ላይ የትይዩ ካቢኔ ምሥረታ መስፈሩን አንስተው ሕጋዊ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የፓርቲያቸው አባላትም ከመንግሥት የቀረበላቸውን የአብረን እንስራ ጥያቄ ተቀብለው በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ መገኘታቸው እንደማይጋጭ በመጥቀስ፣ እንዲያውም የመንግሥት ሥራን ለመከታተል እና እግር በእግር ለመተቸት ጥሩ መደላደል ይፈጥራል ሲሉ አብራርተዋል። በኢዜማ ሕገ ደንብ የመሪው መዋቅር የትይዩ ካቢኔ እንደሚያዋቅር ይደነግጋል። የሕገ ደንቡ አንቀጽ 7.1.9 ፓርቲው ስልጣን ላይ ካልወጣ መሪው፣ ዋና ወይም ዋና ያልሆነ የፓርላማ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ እንደሚሆን ይደነግጋል። ትይዩ ካቢኔ ምንድን ነው? በምርጫ መንግሥት የመመስረት ድምጽ ያላገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትይዩ ካቢኔ/ሚኒስትር የመሰየም ልምድ በተለይ በእንግሊዝ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ሲተገበር የቆየ ነው። በምርጫ የበላይነትን ያገኘው ፓርቲ መደበኛውን የመንግሥት የሥራ አስፈጻሚ ተቋማትን ይዞ ሚኒስትሮችን በመሾም በተግባር የዕለት ከዕለት ኃላፊነቱን ለመወጣት ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎች ይህ ሥልጣን ስለማይኖራቸው በፓርቲያቸው መሪ አማካኝነት መንግሥትን ከሚመራው ካቢኔ ትይዩ ተመሳሳይ የሆነ ካቢኔን ሊያዋቅሩ ይችላሉ። በዚህም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ የመንግሥት አስተዳደር ዘርፎች ሥልጣን ላይ ካለው መንግሥት በተለየ ያላቸውን አማራጭ እንዲሁም ብቁ ባለሙያዎችን ለሕዝቡ ለማቅረብና ለማስተዋወቅ ይጠቀሙበታል። ትይዩ ካቢኔ/ሚኒስትር ሲዋቀር በኃላፊነት ላይ ካለው መዋቅር ጋር ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ግልባጭ ሲሆን በመንግሥት የሥልጣን መዋቅር ውስጥ ላሉ የሚኒስትርነት ቦታዎች በተመሳሳይ ተቃዋሚዎች የራሳቸውን ሰው ይሰይማሉ። እነዚህም ግለሰቦች የተመደቡባቸውን ቦታዎችን የሚመለከቱ ሕጎች፣ ክስተቶችና ሌሎችም ነገሮች በመያጋጥሙ ጊዜ የፓርቲያቸውን አቋምና አማራጭ ያንጸባርቃሉ። የትይዩ ካቢኔ አባላት በሥልጣን ላይ ካሉት ሚኒስትሮች በተመሳሳይ በፓርቲያቸው የሚሰየሙ በመሆናቸው ትይዩ ሚኒስትር ተብለው በበርካታ አገራት የሚጠሩ ቢሆንም በመንግሥት ውስጥ ተግባራዊ የሚሆን የአስፈጻሚነት ሥልጣን ግን የላቸውም። ' እንዲህ አይነቱ የተቃዋሚ ትይዩ የካቢኔ ሚኒስትሮች ካሏቸው መካከል ዩናይትድ ኪንግደም፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ጃፓን የሚጠቀሱ ሲሆን በርካታ አገራት ውስጥም ይገኛሉ። ከአፍሪካም በደቡብ አፍሪካና ሱዳን ውስጥ የተቃዋሚዎች ትይዩ ካቢኔ አላቸው። | https://www.bbc.com/amharic/news-59854356 |
5sports
| ኬንያዊቷ ነርስ በዓለም አቀፍ ውድድር አሸንፋ 250 ሺህ ዶላር ተሸለመች | ኬንያዊቷ ነርስ የዓለም አቀፉን የነርሶች ሽልማት ውድድርን በማሸነፍ 250 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተበረከተላት። በሰሜን ኬንያ መርሳቢት በሚገኘው ሆስፒታል የምትሰራው ነርስ ቀበሌ (Qabale) ዱባ ይህን ሽልማት ያሸነፈችው በምትኖርበት ማኅብረሰብ የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም ባደረገችው ጥረት ነው። በዚህ ውድድር ላይ ከ184 አገራት ከ24 ሺህ በላይ ነርሶች ተሳታፊ ሆነው ነበር። ነርስ ቀበሌ 'ቀበሌ ዱባ ፋውንዴሽን' በሚል መጠሪያ ያቋቋመችው ድርጅት ታዳጊ ሴቶችን ማብቃት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። "በድርጅቴ አማካኝነት ልዩ የሆነ ትምህርት ቤት ከፍቻለሁ። ይህ ትምህር ቤት ልጆች እና ወላጆቻቸውን ያስተምራል። እኔ ለተሻለ ነገ ትምህር ቁልፍ ነው ብዬ አምናለሁ" ብላለች በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ዱባይ ውስጥ በተካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ። ቀበሌ ያሸነፈችው 'ግሎባል ነርሲንግ አዋርድ' የተካሄደው ሐሙስ ግንቦት 04/2014 ዓ.ም. በዓለም የነርሶች ቀን ላይ ነው። ቀበሌ እአአ 2013 የነርስ ሙያ ትምህርቷን እየተከታተለች ሳለ በኬንያ በተካሄደ የቁንጅና ውድድር ላይ ተሳትፍ፤ 'ሚስ ቱሪዝም ኬንያ 2013' አሸናፊ ሆና ነበር። በዚህ ውድድር አሸናፊ መሆኗን ተከትሎ ባገኘችው ተሰሚነት የሴቶች እኩልነት እና የትምህርት እድል ላይ ብዙ ሰርታለች። በቀበሌ ፋውንዴሽን የተመሰረተው ትምህርት ቤት ቀን ላይ ሴት ልጆችን ከሰዓት በኋላ ደግሞ ወላጆቻቸውን ያስተምራል። ወደ ትምህርት ቤቷ የሚመጡት ጎልማሶች የሚቀስሙት፣ የመጻፍ እና ማንበብ ክህሎትን ብቻ ሳይሆን፤ ሴቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ መሠረታዊ የጤና ትምህርት ይሰጣቸዋል። ከወሊድ በኋላ ለሴቶች መደረግ ስላለበት እንክብካቤ፣ የሥነ-ተዋልዶ ጤና እና ስለሴቶች እኩልነት ስልጠና ይሰጣቸዋል። ይህ የቀበሌ ሥራ በአገሯ እና በተቀረው ዓለም እውቅናን አስገኝቶላታል። እአአ 2019 ላይም ሌላ ዓለም አቀፍ ሽልማትን በማግኘት አሸናፊ ነበረች። | ኬንያዊቷ ነርስ በዓለም አቀፍ ውድድር አሸንፋ 250 ሺህ ዶላር ተሸለመች ኬንያዊቷ ነርስ የዓለም አቀፉን የነርሶች ሽልማት ውድድርን በማሸነፍ 250 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተበረከተላት። በሰሜን ኬንያ መርሳቢት በሚገኘው ሆስፒታል የምትሰራው ነርስ ቀበሌ (Qabale) ዱባ ይህን ሽልማት ያሸነፈችው በምትኖርበት ማኅብረሰብ የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም ባደረገችው ጥረት ነው። በዚህ ውድድር ላይ ከ184 አገራት ከ24 ሺህ በላይ ነርሶች ተሳታፊ ሆነው ነበር። ነርስ ቀበሌ 'ቀበሌ ዱባ ፋውንዴሽን' በሚል መጠሪያ ያቋቋመችው ድርጅት ታዳጊ ሴቶችን ማብቃት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። "በድርጅቴ አማካኝነት ልዩ የሆነ ትምህርት ቤት ከፍቻለሁ። ይህ ትምህር ቤት ልጆች እና ወላጆቻቸውን ያስተምራል። እኔ ለተሻለ ነገ ትምህር ቁልፍ ነው ብዬ አምናለሁ" ብላለች በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ዱባይ ውስጥ በተካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ። ቀበሌ ያሸነፈችው 'ግሎባል ነርሲንግ አዋርድ' የተካሄደው ሐሙስ ግንቦት 04/2014 ዓ.ም. በዓለም የነርሶች ቀን ላይ ነው። ቀበሌ እአአ 2013 የነርስ ሙያ ትምህርቷን እየተከታተለች ሳለ በኬንያ በተካሄደ የቁንጅና ውድድር ላይ ተሳትፍ፤ 'ሚስ ቱሪዝም ኬንያ 2013' አሸናፊ ሆና ነበር። በዚህ ውድድር አሸናፊ መሆኗን ተከትሎ ባገኘችው ተሰሚነት የሴቶች እኩልነት እና የትምህርት እድል ላይ ብዙ ሰርታለች። በቀበሌ ፋውንዴሽን የተመሰረተው ትምህርት ቤት ቀን ላይ ሴት ልጆችን ከሰዓት በኋላ ደግሞ ወላጆቻቸውን ያስተምራል። ወደ ትምህርት ቤቷ የሚመጡት ጎልማሶች የሚቀስሙት፣ የመጻፍ እና ማንበብ ክህሎትን ብቻ ሳይሆን፤ ሴቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ መሠረታዊ የጤና ትምህርት ይሰጣቸዋል። ከወሊድ በኋላ ለሴቶች መደረግ ስላለበት እንክብካቤ፣ የሥነ-ተዋልዶ ጤና እና ስለሴቶች እኩልነት ስልጠና ይሰጣቸዋል። ይህ የቀበሌ ሥራ በአገሯ እና በተቀረው ዓለም እውቅናን አስገኝቶላታል። እአአ 2019 ላይም ሌላ ዓለም አቀፍ ሽልማትን በማግኘት አሸናፊ ነበረች። | https://www.bbc.com/amharic/61433343 |
2health
| ''ኮሮናቫይረስ በሁለት ዓመታት ውስጥ ሊጠፋ ይችላል'' ደ/ር ቴድሮስ አድሃኖም | የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገለጹ። ትላንት በሲዊዘርላንድ ጄኔቫ ባደረጉት ንግግር ዳይሬክተሩ ስፓኒሽ ፍሉ በጎርጎሮሳውያኑ 1918 በተከሰተበት ወቅት ለመጥፋት የወሰደበት ጊዜ ሁለት ዓመት ነበር ብለዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ዓለም አሁን ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ መራቀቅና ከፍተኛ ምርምሮች አንጻር የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገልጸዋል። ''በሌላ በኩል ደግሞ አሁን ባለው ከፍተኛ የሰዎች ማህበራዊ ትስስር ምክንያት የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሊሆንም ይችላል'' ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። ''ነገር ግን የሰው ልጅ የደረሰበት የቴክኖሎጂ ርቀት ቫይረሱን ለማስቆም የሚረዳ እውቀት በቶሎ እንዲያዳብር ይረዳዋል'' ካሉ በኋላ አሁንም ቢሆንም ግን ብሄራዊ አንድነትና ዓለማቀፍ ትብብር ላይ ከፍተኛ አጽንኦት ሰጥተው አልፈዋል። የ1918ቱ ስፓኒሽ ፍሉ ቢያንስ 50 ሚሊየን ሰዎችን የገደለ ሲሆን ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ቁጥር 800 ሺህ ነው። በአጠቃላይ ደግሞ 22.7 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ዶክተር ቴዎድሮስ በመግለጫቸው ላይ የግል መከላከያ መሳሪያዎች ወይም 'ፒፒኢ' ስርጭት በተመለከተ ሙስና እየተስተዋለ እንደሆነ ለቀረበላቸውም ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ጉዳዩን ''ወንጀል'' ነው በማለት ገልጸውታል። ''ማንኛውም አይነት ሙስና ተቀባይነት የለውም'' ብለዋል። ''ነገር ግን ከፒፒኢ ጋር የተያያዘ ሙስና ለእኔ በግሌ እንደ ነብስ ማጥፋት ነው የምቆጥረው። ምክንያቱም የጤና ባለሙያዎች ፒፒኢ የማያገኙ ከሆነ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣልን ነው። በተጨማሪም የሚያገለግሏቸው ሰዎችን ሕይወትም ነው ስጋት ውስጥ የምንከተው'' ብለዋል። | ''ኮሮናቫይረስ በሁለት ዓመታት ውስጥ ሊጠፋ ይችላል'' ደ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገለጹ። ትላንት በሲዊዘርላንድ ጄኔቫ ባደረጉት ንግግር ዳይሬክተሩ ስፓኒሽ ፍሉ በጎርጎሮሳውያኑ 1918 በተከሰተበት ወቅት ለመጥፋት የወሰደበት ጊዜ ሁለት ዓመት ነበር ብለዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ዓለም አሁን ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ መራቀቅና ከፍተኛ ምርምሮች አንጻር የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገልጸዋል። ''በሌላ በኩል ደግሞ አሁን ባለው ከፍተኛ የሰዎች ማህበራዊ ትስስር ምክንያት የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሊሆንም ይችላል'' ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። ''ነገር ግን የሰው ልጅ የደረሰበት የቴክኖሎጂ ርቀት ቫይረሱን ለማስቆም የሚረዳ እውቀት በቶሎ እንዲያዳብር ይረዳዋል'' ካሉ በኋላ አሁንም ቢሆንም ግን ብሄራዊ አንድነትና ዓለማቀፍ ትብብር ላይ ከፍተኛ አጽንኦት ሰጥተው አልፈዋል። የ1918ቱ ስፓኒሽ ፍሉ ቢያንስ 50 ሚሊየን ሰዎችን የገደለ ሲሆን ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ቁጥር 800 ሺህ ነው። በአጠቃላይ ደግሞ 22.7 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ዶክተር ቴዎድሮስ በመግለጫቸው ላይ የግል መከላከያ መሳሪያዎች ወይም 'ፒፒኢ' ስርጭት በተመለከተ ሙስና እየተስተዋለ እንደሆነ ለቀረበላቸውም ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ጉዳዩን ''ወንጀል'' ነው በማለት ገልጸውታል። ''ማንኛውም አይነት ሙስና ተቀባይነት የለውም'' ብለዋል። ''ነገር ግን ከፒፒኢ ጋር የተያያዘ ሙስና ለእኔ በግሌ እንደ ነብስ ማጥፋት ነው የምቆጥረው። ምክንያቱም የጤና ባለሙያዎች ፒፒኢ የማያገኙ ከሆነ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣልን ነው። በተጨማሪም የሚያገለግሏቸው ሰዎችን ሕይወትም ነው ስጋት ውስጥ የምንከተው'' ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53872753 |
0business
| ለነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት የሆነው የግብጹ መተላለፊያ መዘጋት | በሱዊዝ የመተላለፊያ መስመር ላይ ቆማ የባሕር ላይ ጉዞን ባስተጓጎለችው መርከብ ተነሳ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል። በመተላለፊያ መስመሩ መዘጋት ሰበብ የድፍድፍ ነዳጅ አቅርቦት ሊስተጓጎል ይችላል በሚል ስጋት ነው ረቡዕ ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የታየበት። በግብጹ የሱዊዝ የባሕር መተላለፊያ ቦይ ዳርቻ ላይ መንቀሳቀስ አቅቷት የዓለማችንን ወሳኝ የባሕር መስመርን የዘጋችውን የጭነት መርከብ ለማንቀሳቀስ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። የግብጽ ባለሥልጣናት እንዳሉት ኤቨር ጊቭን የተባለችው የጭነት መርከብ በመተላለፊያው መስመር ላይ መንቀሳቀስ አቅቷት የቆመችው ማክሰኞ ጠዋት በአካባቢው አሸዋ ያዘለ ከባድ አውሎ ነፋስ በተከሰተበት ጊዜ ነው። በዚህም ሳቢያ ከእስያ ወደ አውሮፓ አስፈላጊ ቁሶችን ጭነው በመተላለፊያው በኩል ለማቋረጥ የመጡ ከቦዩ ሰሜንና ደቡብ በኩል እጅግ በርካታ መርከቦች ማለፊያ አጥተው እንዲቆሙ ተገደዋል። በሰሜናዊ ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘውን ወሳኝ የባሕር ላይ መተላለፊያን ዘግታ የምትገኘው የጭነት መርከብ ባለቤት የሆነው ጃፓናዊ በመርከቧ ምክንያት በዓለም የንግድ ልውውጥ ላይ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ መጠየቁ ተነግሯል። በከባድ ንፋስ ምክንያት መስመሯን ስታ መተላለፊያውን የዘጋችውን መርከብ ለማንቀሳቀስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ የገለጸው የመርከቧ ባለቤት "ነገር ግን የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ" ላይ መሆናቸውን ገልጿል። አስካሁን ቢያንስ በመተላለፊያው በኩል ለማቋረጥ እየጠበቁ ያሉ ከ150 በላይ የጭነት መርከቦች ተሰልፈው እየተጠባበቁ መሆኑ ተነግሯል። ሜዲትራኒያንና ቀይ ባሕርን በሚያገናኘው በሱዊዝ መተላላፊያ ቦይ አውሮፓንና አስያን ለማገናኘት አጭሩ መስመር ሲሆን የዓለማችን 12 በመቶ የሚሆነው የንግድ ጭነት የሚያልፈው በዚሁ በኩል ነው። በአሁኑ ወቅት መርከቧን መንገድ እንድትለቅ ለማድረግ ስምንት ጎታች ጀልባዎች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ይህንን ሥራ እያከናወነ የሚገኘው ኩባንያ መተላለፊያውን ለማስከፈት ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ያስጠነቀቀ ሲሆን የመርከቧን ክብደት ለመቀነስ የጫነቻቸውን ኮንቴይነሮች መቀነስ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ተብሏል። | ለነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት የሆነው የግብጹ መተላለፊያ መዘጋት በሱዊዝ የመተላለፊያ መስመር ላይ ቆማ የባሕር ላይ ጉዞን ባስተጓጎለችው መርከብ ተነሳ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል። በመተላለፊያ መስመሩ መዘጋት ሰበብ የድፍድፍ ነዳጅ አቅርቦት ሊስተጓጎል ይችላል በሚል ስጋት ነው ረቡዕ ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የታየበት። በግብጹ የሱዊዝ የባሕር መተላለፊያ ቦይ ዳርቻ ላይ መንቀሳቀስ አቅቷት የዓለማችንን ወሳኝ የባሕር መስመርን የዘጋችውን የጭነት መርከብ ለማንቀሳቀስ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። የግብጽ ባለሥልጣናት እንዳሉት ኤቨር ጊቭን የተባለችው የጭነት መርከብ በመተላለፊያው መስመር ላይ መንቀሳቀስ አቅቷት የቆመችው ማክሰኞ ጠዋት በአካባቢው አሸዋ ያዘለ ከባድ አውሎ ነፋስ በተከሰተበት ጊዜ ነው። በዚህም ሳቢያ ከእስያ ወደ አውሮፓ አስፈላጊ ቁሶችን ጭነው በመተላለፊያው በኩል ለማቋረጥ የመጡ ከቦዩ ሰሜንና ደቡብ በኩል እጅግ በርካታ መርከቦች ማለፊያ አጥተው እንዲቆሙ ተገደዋል። በሰሜናዊ ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘውን ወሳኝ የባሕር ላይ መተላለፊያን ዘግታ የምትገኘው የጭነት መርከብ ባለቤት የሆነው ጃፓናዊ በመርከቧ ምክንያት በዓለም የንግድ ልውውጥ ላይ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ መጠየቁ ተነግሯል። በከባድ ንፋስ ምክንያት መስመሯን ስታ መተላለፊያውን የዘጋችውን መርከብ ለማንቀሳቀስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ የገለጸው የመርከቧ ባለቤት "ነገር ግን የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ" ላይ መሆናቸውን ገልጿል። አስካሁን ቢያንስ በመተላለፊያው በኩል ለማቋረጥ እየጠበቁ ያሉ ከ150 በላይ የጭነት መርከቦች ተሰልፈው እየተጠባበቁ መሆኑ ተነግሯል። ሜዲትራኒያንና ቀይ ባሕርን በሚያገናኘው በሱዊዝ መተላላፊያ ቦይ አውሮፓንና አስያን ለማገናኘት አጭሩ መስመር ሲሆን የዓለማችን 12 በመቶ የሚሆነው የንግድ ጭነት የሚያልፈው በዚሁ በኩል ነው። በአሁኑ ወቅት መርከቧን መንገድ እንድትለቅ ለማድረግ ስምንት ጎታች ጀልባዎች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ይህንን ሥራ እያከናወነ የሚገኘው ኩባንያ መተላለፊያውን ለማስከፈት ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ያስጠነቀቀ ሲሆን የመርከቧን ክብደት ለመቀነስ የጫነቻቸውን ኮንቴይነሮች መቀነስ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ተብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56506560 |
0business
| ኢኮኖሚ፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ200 ብር ኖት ይፋ አደረገች | ኢትዮጵያ በገበያ ላይ ባሉት የወረቀት ገንዘቦቿ ላይ ለውጥ ስታደርግ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በወረቀት ገንዘቧ ውስጥ ባለ 200 ብር ኖቶችን መጠቀም ጀመረች። ይህ ይፋ የሆነው ዛሬ [ሰኞ መስከረም 04/2013] ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትዊተር ገጻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክትና የብር ኖቶቹ ምሰል ነው። በዚህም መሠረተው ከዛሬ ጀምሮ አገሪቱ የ10፣ 50 እና 100 ብር ኖቶቿን ስትቀይር ከዚህ በፊት ያልነበረው የ200 ብር ኖትን ደግሞ መጠቀም ጀምራለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አዲሶቹን የገንዘብ ኖቶች ይፋ መድረግ ያስፈለገው ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናንና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቆጣጠር ያግዛሉ።በተጨማሪም አዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች እንዲኖራቸው የተደረጉት የደኅንነት ገጽታዎች አመሳስሎ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት እንደሚግዙ ተጠቁሟል። በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት የብር ኖቶች ወደ ዝውውር እንዲገቡ የተደረጉት ከ23 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ እንደነበረ ይታወሳል። ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራ ላይ በነበሩ የገንዘብ የወረቀት ገንዘቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ወደ አምሳ ዓመታት በሚጠጋው የንጉሡ የሥልጣን ዘመን አራት ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ተደርጓል። ወታደራዊው መንግሥት ዘውዳዊውን ሥርዓት አስወግዶ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም የንጉሡ ምስልን የያዙትን የመገበያያ ገንዘቦች ለውጦት ቆይቷል። በተመሳሳይም ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ለሰባት ዓመታት ያህል ቀድሞ የነበረውን ገንዘብ ሲጠቀም ቆይቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶቹ እንዲቀየሩ አድርጓል። በኢትዮጵያ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የነበሩት የገንዘብ ኖቶች 1፣ 5፣ 10፣ 50 እና 100 ብር የነበሩ ሲሆን፤ ለረጀም ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የገንዘብ ኖት 100 ብር ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም ግን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከዋሉት የብር ኖቶች መካከል የ2 ብር እና የ500 ብር ኖቶች ነበሩበት። ስለዚህም በአገሪቱ የወረቀት ገንዘብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የነበረው የብር ኖት ባለ 500 ብር ኖት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ከግብይት እንዲወጣ መደረጉን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል። ስለዚህም አሁን ከወረቀት የብር ኖቶች መካከል እንዲገባ የተደረገው የባለ 200 ብር ኖት በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሲሆን ወደገበያ ሲገባም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብር ኖት ለውጥ እንደሚደረግ በተለያዩ መንገዶች ሲነገር የቆየ ሲሆን፤ ከብር ዋጋ መቀነስ ጋር ተያይዞ 500 ዋጋ ያለው የብር ኖት ወደ ገበያ እንደሚገባ አንዳንድ ሰዎች ሲገልጹ ቆይተው ነበር። በአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች መደረግ ከጀመሩባቸው ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንደሚካሄድ በጉምሩክና በፖሊስ በኩል በተደጋጋሚ የሚወጡ ሪፖርቶች የሚያመለክቱ ሲሆን፤ ይህም ለውጥ ያስፈለገው ይህንኑ ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል። | ኢኮኖሚ፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ200 ብር ኖት ይፋ አደረገች ኢትዮጵያ በገበያ ላይ ባሉት የወረቀት ገንዘቦቿ ላይ ለውጥ ስታደርግ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በወረቀት ገንዘቧ ውስጥ ባለ 200 ብር ኖቶችን መጠቀም ጀመረች። ይህ ይፋ የሆነው ዛሬ [ሰኞ መስከረም 04/2013] ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትዊተር ገጻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክትና የብር ኖቶቹ ምሰል ነው። በዚህም መሠረተው ከዛሬ ጀምሮ አገሪቱ የ10፣ 50 እና 100 ብር ኖቶቿን ስትቀይር ከዚህ በፊት ያልነበረው የ200 ብር ኖትን ደግሞ መጠቀም ጀምራለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አዲሶቹን የገንዘብ ኖቶች ይፋ መድረግ ያስፈለገው ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናንና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቆጣጠር ያግዛሉ።በተጨማሪም አዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች እንዲኖራቸው የተደረጉት የደኅንነት ገጽታዎች አመሳስሎ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት እንደሚግዙ ተጠቁሟል። በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት የብር ኖቶች ወደ ዝውውር እንዲገቡ የተደረጉት ከ23 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ እንደነበረ ይታወሳል። ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራ ላይ በነበሩ የገንዘብ የወረቀት ገንዘቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ወደ አምሳ ዓመታት በሚጠጋው የንጉሡ የሥልጣን ዘመን አራት ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ተደርጓል። ወታደራዊው መንግሥት ዘውዳዊውን ሥርዓት አስወግዶ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም የንጉሡ ምስልን የያዙትን የመገበያያ ገንዘቦች ለውጦት ቆይቷል። በተመሳሳይም ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ለሰባት ዓመታት ያህል ቀድሞ የነበረውን ገንዘብ ሲጠቀም ቆይቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶቹ እንዲቀየሩ አድርጓል። በኢትዮጵያ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የነበሩት የገንዘብ ኖቶች 1፣ 5፣ 10፣ 50 እና 100 ብር የነበሩ ሲሆን፤ ለረጀም ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የገንዘብ ኖት 100 ብር ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም ግን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከዋሉት የብር ኖቶች መካከል የ2 ብር እና የ500 ብር ኖቶች ነበሩበት። ስለዚህም በአገሪቱ የወረቀት ገንዘብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የነበረው የብር ኖት ባለ 500 ብር ኖት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ከግብይት እንዲወጣ መደረጉን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል። ስለዚህም አሁን ከወረቀት የብር ኖቶች መካከል እንዲገባ የተደረገው የባለ 200 ብር ኖት በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሲሆን ወደገበያ ሲገባም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብር ኖት ለውጥ እንደሚደረግ በተለያዩ መንገዶች ሲነገር የቆየ ሲሆን፤ ከብር ዋጋ መቀነስ ጋር ተያይዞ 500 ዋጋ ያለው የብር ኖት ወደ ገበያ እንደሚገባ አንዳንድ ሰዎች ሲገልጹ ቆይተው ነበር። በአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች መደረግ ከጀመሩባቸው ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንደሚካሄድ በጉምሩክና በፖሊስ በኩል በተደጋጋሚ የሚወጡ ሪፖርቶች የሚያመለክቱ ሲሆን፤ ይህም ለውጥ ያስፈለገው ይህንኑ ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል። | https://www.bbc.com/amharic/54144151 |
0business
| የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ለምን በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ አያገኝም? | ኢትዮጵያውያንን እየፈተነ የሚገኘው የዋጋ ግሽበት በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ እንደማያገኝ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በመጋቢት ወር የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት የዋጋ ግሽበቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በ34.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጾ ነበር። የዋጋ ንረቱ ለምግብነት በሚውሉ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ እና እህሎች፣ ቅመማ ቅመም እና ዘይት፣ ቅቤ እና ቡና እንደሚጨምር ገልጾ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ከኑሮ ውድነቱ የተነሳ በሚያገኙት ደመወዝ ኑሮን መምራት አዳጋች እንዳደረባቸው ይናገራሉ። ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በአገሪቱ ውስጥ ለሚታየው የኑሮ ውድነት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ቁልፍ መፍትሔ ነው ቢሉም፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ግን ከፍተኛ አምራች በሆኑ አካባቢዎች በሰላም እጦት መታመሳቸው አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ይላሉ። አሁን ያጋጠመው የዋጋ ንረት በቅርብ ጊዜ በተፈጠሩ ምክንያቶች የተከሰተ እንዳልሆነ የሚታመን ሲሆን ለዚህም ለሁለት ዓመታት ያህል የመላውን ዓለም ምጣኔ ሀብት ያቀዛቀዘውን የኮሮናቫይረስወረርሽኝን ተከትሎ መሆኑን ጫናውን አጉልቶታል። ከዚህ ባሻገር ግን በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት፣ በተለያዩ ስፍራዎች ያጋጠሙ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች እንዲሁም የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በነዳጅ፣ በስንዴ እና በምግብ ዘይት ላይ ያስከተኩት ከፍተኛ ጭማሪ ችግሩን አባብሰውታል። ይህ በተደራራቢ ምክንያቶች እየጨመረ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚስተካከል እንዳልሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳም እንዲሁ በአንድ ውይይት ላይ የዋጋ ንረቱ እንዲሁ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ የሚያገኝ ችግር እንዳልሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ልክ እንደ አቶ ሽመልስ ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ ያገኛል ማለት “ማታለል ይሆናል” ይላሉ። ሌሎች ደግሞ መንግሥት ወሳኝ የሆኑ አፋጣኝ እርምጃዎችን ከወሰደ በፍጥነት መፍትሔ ሊመጣ ይችላል የሚል ተስፋ አላቸው። ይህ የሃሳብ ልዩነት የሚመነጨው የዋጋ ንረቱ ዋነኛ ምክንያቶች ምንድን ናቸው ከሚለው ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) የግብርና ምርት የሆኑት ፍራፍሬ እና ጥራጥሬ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ አንዳንዶቹ እስከ 100 ፐርሰንት ጭማሪ አሳይተዋል ይላሉ። እናም “በዚህ አገር ውስጥ ኑሮ ያልከበደው ከ5 በመቶ አይበልጥም” በማለት ተናግረዋል። እነርሱም ይላሉ ምሁሩ “በሙስና የከበሩ እና በንግድ ውስጥ በአቋራጭ የበለፀጉ ናቸው” በማለት የችግሩን አስከፊነት ያብራራሉ። ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጀምሮ በኑሮ ዝቅተኛው ወለል ላይ ከሚገኘው ላብ አደሩ ድረስ ለመኖር ከብዶታል ሲሉ የሚያስረዱት ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር)፣ የዋጋ ግሽበቱ ዋነኛ ምክንያት ምርታማ የሆኑ አካባቢዎች ሰላም ማጣታቸው መሆኑን ይገልጻሉ። አክለውም የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት ፈተና ውስጥ መግባቱ ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ዶ/ር ጉቱ፣ ልክ እንደ አቶ ሽመልስ ምርት እና ምርታማነት ቀንሷል የሚል አቋም አላቸው። ለዚህም ምክንያት ያሉትን ሲያስቀምጡ፣ በአምራች አካባቢዎች የጦርነት እንቅስቃሴ መኖሩ ነው። ሁለተኛው የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት በተለይ የኢኮኖሚ ደጋፊ የሚባሉ ምዕራባውያን አገራት ጋር ያለው ግንኙነት ጥሩ አለመሆን፣ አገሪቱን የምታገኛውን የኢኮኖሚ ድጋፍ እንዲሁም ከንግድ ጋር የተያያዘ የውጪ ምንዛሬ አሳጥቷታል ይላሉ። በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ በመጻፍ እና ትንታኔ በመስጠት የሚታወቁት አብዱልመናን መሐመድ በበኩላቸው “መንግሥት በተደጋጋሚ የዋጋ ግሽበቱ ብሎ የሚጠቅሰው ዋናውን ምክንያት ወደ ኋላ ሸሽጎ ነው” ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ምርት ደብቆ ዋጋ ጨምሮ ለመክበር የሚደረግ የነጋዴዎች እንቅስቃሴ መንግሥት የሚያነሳው ምክንያት ሲሆን፣ ይህ ግን ዋነኛው ምክንያት ግን አይደለም ይላሉ። “አሁን ላለው የዋጋ ግሽበት ዋነኛ ተጠያቂ መንግሥት ራሱ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ገንዘብ ማተም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ባንኮች ደግሞ ይህንን ገንዘብ ሲያበድሩ በኢኮኖሚ ውስጥ የሚዘዋወረው የብር መጠን ጨምሯል።” ይህ በጦርነት እና በፖለቲካ አለመረጋጋት ምጣኔ ሀብቷ የደከመባት አገር ውስጥ ገንዘብ በገበያ ውስጥ መብዛቱ ኑሮ ያስወድዳል ይላሉ። አብዱልመናን እንደሚሉት አሁን ያለው የዋጋ ግሽበት መነሻ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የተለቀቀው ገንዘብ ከአገሪቱ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር ያልተመጣጠ መሆኑ ነው። “መንግሥት ይህንን ማመን አይፈልግም። መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ብዙ ተበድሯል” የሚሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አብዱልመናን ይህ በአፋጣኝ መስተካከል እንዳለበት ይመክራሉ። አብዱልመናን ምርታማ የሆኑ አካባቢዎች ሰላም ማጣታቸው ለምርት መቀነስ ምክንያት መሆኑን ቢስማሙም፣ ኢኮኖሚው ሲቀዛቀዝ በገበያው ውስጥ ያለውን የገንዘብ ፍሰት መቀነስ ሲገባ መንግሥት ተቃራኒውን በማድረግ እንዳባባሰው ያምናሉ። ዶ/ር ጉቱ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት “አሁን ባለው ሁኔታ መፍትሔ የለውም። ይህ ተሰምሮበት በግልጽ ልንነጋገርበት ይገባል” ይላሉ። አክለውም “አሁን ባለው ፖለቲካ፣ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ሁኔታ በስድስትም ሆነ በዘጠኝ ወር ውስጥ ለሕዝቡ እፎይታ የሚሰጥ ነገር ማድረግ ይቻላል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው።” አገሪቱን ላጋጠማት የዋጋ ግሽበት በአጭር ጊዜ መፍትሔ የሚሆን ተስፋ የለም እንዲሉ ያደረጋቸውም “ችግሩ በጣም ውስብስብ” በመሆኑ የተነሳ እንደሆነ ይናገራሉ። ዶ/ር ጉቱ “የምርታማነት እጥረት ምክንያቱ ፖለቲካ ነው” ብለው “ነገሩ አሁን በተያዘበት መንገድ ደግሞ በአንድ እና በሁለት ዓመት ውስጥ እንኳን ወደ ቦታው የሚመለስ አይደለም” ይላሉ። ምርቶቻቸውን የሚሸጡልን እና የእኛን ከሚገዙ የውጪ አገራት ጋር ያለን ጥሩ ግንኙነት ሻክሯል፤ ይህንንም ወደ ቦታው መመለስ በሁለት እና ሦስት ወር የሚሆን አይደለም ይላሉ። አብዱልመናን በበኩላቸው መንግሥት ይህንን ችግር በሚገባ ተረድቶ በስድስት ወር እና በአንድ ዓመት ውስጥ የከሰተውን የዋጋ ግሽበት ወደ አንድ አሃዝ ለማውረድ ቁርጠኝነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። “የዚህ ችግር መንስዔ ከአቅርቦት ጋር ብቻ የተያያዘ እንደሆነ የሚያስቡ ከሆነ ችግሩ መፍትሔ አያገኝም” የሚሉት አብዱልመናን መንግሥት በራሱ በኩል ጠንከር ያሉ ቁርጠኛ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚያስፈለገው ይመክራሉ። ለዚህም መንግሥት በአፋጣኝ ማድረግ ያለበት “ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ መቀነስ ነው፤ ይህ ደግሞ ወገብን ማሰር ይጠይቃል። በተጨማሪ መንግሥት አስፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶችን ማስቆም፣ አስፈላጊ የሚባሉ ፕሮጀክቶችንም ቢሆን ለጊዜው መፍትሔ እስኪገኝ ማዘግየት አለበት” ሲሉ ይመክራሉ። እንዲሁም “የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም ከውጪ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ የማውረድ እንቅስቃሴ ወደ አገር ቤት የሚገቡ እቃዎችን ስለሚያንር በአስቸኳይ መቆም አለበት፤ መንግሥት እነዚህን እርምጃዎች የሚወስድ ከሆነ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ውጤት ማየት ይቻላል” ይላሉ አብዱልመናን። | የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ለምን በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ አያገኝም? ኢትዮጵያውያንን እየፈተነ የሚገኘው የዋጋ ግሽበት በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ እንደማያገኝ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በመጋቢት ወር የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት የዋጋ ግሽበቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በ34.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጾ ነበር። የዋጋ ንረቱ ለምግብነት በሚውሉ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ እና እህሎች፣ ቅመማ ቅመም እና ዘይት፣ ቅቤ እና ቡና እንደሚጨምር ገልጾ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ከኑሮ ውድነቱ የተነሳ በሚያገኙት ደመወዝ ኑሮን መምራት አዳጋች እንዳደረባቸው ይናገራሉ። ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በአገሪቱ ውስጥ ለሚታየው የኑሮ ውድነት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ቁልፍ መፍትሔ ነው ቢሉም፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ግን ከፍተኛ አምራች በሆኑ አካባቢዎች በሰላም እጦት መታመሳቸው አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ይላሉ። አሁን ያጋጠመው የዋጋ ንረት በቅርብ ጊዜ በተፈጠሩ ምክንያቶች የተከሰተ እንዳልሆነ የሚታመን ሲሆን ለዚህም ለሁለት ዓመታት ያህል የመላውን ዓለም ምጣኔ ሀብት ያቀዛቀዘውን የኮሮናቫይረስወረርሽኝን ተከትሎ መሆኑን ጫናውን አጉልቶታል። ከዚህ ባሻገር ግን በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት፣ በተለያዩ ስፍራዎች ያጋጠሙ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች እንዲሁም የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በነዳጅ፣ በስንዴ እና በምግብ ዘይት ላይ ያስከተኩት ከፍተኛ ጭማሪ ችግሩን አባብሰውታል። ይህ በተደራራቢ ምክንያቶች እየጨመረ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚስተካከል እንዳልሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳም እንዲሁ በአንድ ውይይት ላይ የዋጋ ንረቱ እንዲሁ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ የሚያገኝ ችግር እንዳልሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ልክ እንደ አቶ ሽመልስ ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ ያገኛል ማለት “ማታለል ይሆናል” ይላሉ። ሌሎች ደግሞ መንግሥት ወሳኝ የሆኑ አፋጣኝ እርምጃዎችን ከወሰደ በፍጥነት መፍትሔ ሊመጣ ይችላል የሚል ተስፋ አላቸው። ይህ የሃሳብ ልዩነት የሚመነጨው የዋጋ ንረቱ ዋነኛ ምክንያቶች ምንድን ናቸው ከሚለው ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) የግብርና ምርት የሆኑት ፍራፍሬ እና ጥራጥሬ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ አንዳንዶቹ እስከ 100 ፐርሰንት ጭማሪ አሳይተዋል ይላሉ። እናም “በዚህ አገር ውስጥ ኑሮ ያልከበደው ከ5 በመቶ አይበልጥም” በማለት ተናግረዋል። እነርሱም ይላሉ ምሁሩ “በሙስና የከበሩ እና በንግድ ውስጥ በአቋራጭ የበለፀጉ ናቸው” በማለት የችግሩን አስከፊነት ያብራራሉ። ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጀምሮ በኑሮ ዝቅተኛው ወለል ላይ ከሚገኘው ላብ አደሩ ድረስ ለመኖር ከብዶታል ሲሉ የሚያስረዱት ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር)፣ የዋጋ ግሽበቱ ዋነኛ ምክንያት ምርታማ የሆኑ አካባቢዎች ሰላም ማጣታቸው መሆኑን ይገልጻሉ። አክለውም የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት ፈተና ውስጥ መግባቱ ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ዶ/ር ጉቱ፣ ልክ እንደ አቶ ሽመልስ ምርት እና ምርታማነት ቀንሷል የሚል አቋም አላቸው። ለዚህም ምክንያት ያሉትን ሲያስቀምጡ፣ በአምራች አካባቢዎች የጦርነት እንቅስቃሴ መኖሩ ነው። ሁለተኛው የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት በተለይ የኢኮኖሚ ደጋፊ የሚባሉ ምዕራባውያን አገራት ጋር ያለው ግንኙነት ጥሩ አለመሆን፣ አገሪቱን የምታገኛውን የኢኮኖሚ ድጋፍ እንዲሁም ከንግድ ጋር የተያያዘ የውጪ ምንዛሬ አሳጥቷታል ይላሉ። በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ በመጻፍ እና ትንታኔ በመስጠት የሚታወቁት አብዱልመናን መሐመድ በበኩላቸው “መንግሥት በተደጋጋሚ የዋጋ ግሽበቱ ብሎ የሚጠቅሰው ዋናውን ምክንያት ወደ ኋላ ሸሽጎ ነው” ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ምርት ደብቆ ዋጋ ጨምሮ ለመክበር የሚደረግ የነጋዴዎች እንቅስቃሴ መንግሥት የሚያነሳው ምክንያት ሲሆን፣ ይህ ግን ዋነኛው ምክንያት ግን አይደለም ይላሉ። “አሁን ላለው የዋጋ ግሽበት ዋነኛ ተጠያቂ መንግሥት ራሱ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ገንዘብ ማተም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ባንኮች ደግሞ ይህንን ገንዘብ ሲያበድሩ በኢኮኖሚ ውስጥ የሚዘዋወረው የብር መጠን ጨምሯል።” ይህ በጦርነት እና በፖለቲካ አለመረጋጋት ምጣኔ ሀብቷ የደከመባት አገር ውስጥ ገንዘብ በገበያ ውስጥ መብዛቱ ኑሮ ያስወድዳል ይላሉ። አብዱልመናን እንደሚሉት አሁን ያለው የዋጋ ግሽበት መነሻ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የተለቀቀው ገንዘብ ከአገሪቱ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር ያልተመጣጠ መሆኑ ነው። “መንግሥት ይህንን ማመን አይፈልግም። መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ብዙ ተበድሯል” የሚሉት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አብዱልመናን ይህ በአፋጣኝ መስተካከል እንዳለበት ይመክራሉ። አብዱልመናን ምርታማ የሆኑ አካባቢዎች ሰላም ማጣታቸው ለምርት መቀነስ ምክንያት መሆኑን ቢስማሙም፣ ኢኮኖሚው ሲቀዛቀዝ በገበያው ውስጥ ያለውን የገንዘብ ፍሰት መቀነስ ሲገባ መንግሥት ተቃራኒውን በማድረግ እንዳባባሰው ያምናሉ። ዶ/ር ጉቱ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት “አሁን ባለው ሁኔታ መፍትሔ የለውም። ይህ ተሰምሮበት በግልጽ ልንነጋገርበት ይገባል” ይላሉ። አክለውም “አሁን ባለው ፖለቲካ፣ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ሁኔታ በስድስትም ሆነ በዘጠኝ ወር ውስጥ ለሕዝቡ እፎይታ የሚሰጥ ነገር ማድረግ ይቻላል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው።” አገሪቱን ላጋጠማት የዋጋ ግሽበት በአጭር ጊዜ መፍትሔ የሚሆን ተስፋ የለም እንዲሉ ያደረጋቸውም “ችግሩ በጣም ውስብስብ” በመሆኑ የተነሳ እንደሆነ ይናገራሉ። ዶ/ር ጉቱ “የምርታማነት እጥረት ምክንያቱ ፖለቲካ ነው” ብለው “ነገሩ አሁን በተያዘበት መንገድ ደግሞ በአንድ እና በሁለት ዓመት ውስጥ እንኳን ወደ ቦታው የሚመለስ አይደለም” ይላሉ። ምርቶቻቸውን የሚሸጡልን እና የእኛን ከሚገዙ የውጪ አገራት ጋር ያለን ጥሩ ግንኙነት ሻክሯል፤ ይህንንም ወደ ቦታው መመለስ በሁለት እና ሦስት ወር የሚሆን አይደለም ይላሉ። አብዱልመናን በበኩላቸው መንግሥት ይህንን ችግር በሚገባ ተረድቶ በስድስት ወር እና በአንድ ዓመት ውስጥ የከሰተውን የዋጋ ግሽበት ወደ አንድ አሃዝ ለማውረድ ቁርጠኝነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። “የዚህ ችግር መንስዔ ከአቅርቦት ጋር ብቻ የተያያዘ እንደሆነ የሚያስቡ ከሆነ ችግሩ መፍትሔ አያገኝም” የሚሉት አብዱልመናን መንግሥት በራሱ በኩል ጠንከር ያሉ ቁርጠኛ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚያስፈለገው ይመክራሉ። ለዚህም መንግሥት በአፋጣኝ ማድረግ ያለበት “ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ መቀነስ ነው፤ ይህ ደግሞ ወገብን ማሰር ይጠይቃል። በተጨማሪ መንግሥት አስፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶችን ማስቆም፣ አስፈላጊ የሚባሉ ፕሮጀክቶችንም ቢሆን ለጊዜው መፍትሔ እስኪገኝ ማዘግየት አለበት” ሲሉ ይመክራሉ። እንዲሁም “የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም ከውጪ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ የማውረድ እንቅስቃሴ ወደ አገር ቤት የሚገቡ እቃዎችን ስለሚያንር በአስቸኳይ መቆም አለበት፤ መንግሥት እነዚህን እርምጃዎች የሚወስድ ከሆነ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ውጤት ማየት ይቻላል” ይላሉ አብዱልመናን። | https://www.bbc.com/amharic/articles/crgzlx4jqglo |
5sports
| ስፖርት፡ እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጥቁር ስፖርተኛ ሐውልት ያቆመችው መቼ እንደሆነ ያውቃሉ? | ጃክ ሌዝሊ፤ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ማልያ አጥልቆ ታሪክ ከሠራ 100 ዓመታት ሊሞላው ቢሆን እንኳ በቅጡ የሚያስታውሰው ሰው አልነበረም። ይህ የሆነው በቆዳው ቀለም ብቻ ነው። ጊዜው 1925 ነበር። እንግሊዝ ከአየርላንድ ጋር ለነበራት የወዳጅነት ጨዋታ መልማዮች ተጫወቾችን እየመለመሉ ነበር። በወቅቱ ሌዝሊ የፕላይማውዝ ተጫዋች ነበር። መልማዮቹ የሚጫወትበት ሜዳ መጥተው ሲመለከቱ ሌዝሊን ጥቁር ሆኖ ያገኙታል። በዚህም ምክንያት ሌዝሊ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የተሰለፈ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን ታሪክ የሚሠራበትን አጋጣሚ መና ያደርጉበታል። ይኸው ሌዝሊ አሁን ገንዘብ ተዋጥቶለት ሃውልት ሊሰራለት እየታቀደ ነው። እስካሁን ቢያንስ 135 ሺህ ፓውንድ ተዋጥቶለታል። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 240 ስፖርተኞችን የሚዘክሩ ሃውልቶች አሉ። ከእነዚህ መካከል 10 ብቻ ናቸው ለጥቁርና አናሳ ቁጥር ላላቸው እንግሊዛውያን ክብር የቆሙት። ከአስሩ መካከል አምስት ለእግርኳስ ተጫዋቾች የቆሙ ሲሆን ጎልፍና ክሪኬት የመሳሰሉ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ምንም ዓይነት የጥቁር ግለሰብ ሐውልት የላቸውም። ለምን? ሼፊልድ ዩኒቨርሲቲ የሠራው አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው የጥቁር ስፖርተኞች ሐውልቶች ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩት ባለፉት 10 ዓመታት ነው። አብዛኛዎቹ ሐውልቶች በተለይ ደግሞ የእግር ኳስ ተጫዎቾች መታሰቢያዎች ተጫዎቾቹ ጫማ ከሰቀሉ ከ20ና 30 ዓመታት በኋላ ነው የሚሠሩት። አብዛኛዎቹ የጥቁር እግር ኳስ ተጫዋቾች ሐውልቶች ለምን ባለፉት 10 ዓመታት ተሰሩ የሚለውን ጥያቄ የሚመልሱት ዶ/ር ክሪስ ስትራይድ፤ በእንግሊዝ እግር ኳስ መድረክ ከ1980ዎቹ [በአውሮፓውያኑ] በፊት በጣም ጥቂት ተጫዋቾች ነበሩ ይላሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ካላት 240 ሐውልት መካከል 10 ሃውልቶች ለጥቁሮች መድባለች። ከእነዚህ መካከል ዘጠኙ የተገነቡት ባለፉት 10 ዓመታት ነው። ይህ ደግሞ የ1980ዎቹ ተጫዎቾች መታሰብ የጀመሩት አሁን መሆኑን ማሳያ ነው ይላሉ ምሁሩ። እንግሊዝ ውስጥ ከቆሙ የጥቁር ተጫዋቾች ሐውልቶች መካከል ጎልቶ የሚወጣው በአውሮፓውያኑ 2019 የተገነባው የሶስቱ የዌስት ብሮሚች አልቢዮን ተጫዎቾች ሃውልት ነው። ሎሪ ካኒንግሃም፣ ሲሪል ሬጂስና ብንዶን ባስቶን ዌስትብሮም በ1970ዎቹ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታዋቂው ቡድን እንዲሆን የጎላ ሚና ተጫውተዋል። እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጥቁር ስፖርተኛ ሃውልት ያቆመችው በአውሮፓውያኑ 2001 ነው። ይሄም የታዋቂው ቦክሰኛ ራንዲ ቱርፒን ነው። ከዚያ በመቀጠል ሐውልት የቆመለት ጥቁር ተጫዋች የአርሰናሉ ፈረንሳዊ አጥቂ ቲየሪ ሄንሪ ነው። ሴቶች? ዩናይትድ ኪንግደም በዓለማችን በርካታ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሃውልቶች ያሏት ሃገር ናት። በጠቅላላው በዓለማችን 700 የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሐውልት እንደቆመላቸው አንድ ጥናት ይጠቁማል። ነገር ግን ከእነዚህ ሐውልቶች መካከል ለሴት ስፖርተኞች መታሰቢያ የሆኑ ዘንድ የቆሙ ሐውልቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ሊሊ ፓር እንግሊዝ ውስጥ ሐውልት የተሰራላት የመጀመሪያዋ ሴት ስፖርተኛ ናት። በ1920ዎቹና 30ዎቹ ዲክ ለተሰኘው የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የተጫወተችው ሊሊ ሃማንቸስተር ውስጥ ሐውልት የተሰራላት ባለፈው ዓመት [2019] ነው። ከሊሊ በተጨማሪ ሃውልት የቆመላቸው እንግሊዛውያን ስፖርተኞች 3 ናቸው። እነዚህም ቴኒስ ተጫዋቿ ዶሮቲ ራውንድ፣ የኦሊምፒክ ሻምፒዮናዎቹ ሜሪ ፒተርስና ኬሊ ሆልምስ ናቸው። ከ1980ዎቹ በኋላ ያለው የእንግሊዝ እግር ኳስ በጥቁር ተጫዎቾች የደመቀ ነው። ያለፈው አስር ዓመትም ጥቁር የእግር ኳስ ፈርጦችን አፍርቷል። የእነዚህን ተጫዎቾች ሐውልት መች እናይ ይሆን? የበርካቶች ጥያዌ ነው። | ስፖርት፡ እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጥቁር ስፖርተኛ ሐውልት ያቆመችው መቼ እንደሆነ ያውቃሉ? ጃክ ሌዝሊ፤ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ማልያ አጥልቆ ታሪክ ከሠራ 100 ዓመታት ሊሞላው ቢሆን እንኳ በቅጡ የሚያስታውሰው ሰው አልነበረም። ይህ የሆነው በቆዳው ቀለም ብቻ ነው። ጊዜው 1925 ነበር። እንግሊዝ ከአየርላንድ ጋር ለነበራት የወዳጅነት ጨዋታ መልማዮች ተጫወቾችን እየመለመሉ ነበር። በወቅቱ ሌዝሊ የፕላይማውዝ ተጫዋች ነበር። መልማዮቹ የሚጫወትበት ሜዳ መጥተው ሲመለከቱ ሌዝሊን ጥቁር ሆኖ ያገኙታል። በዚህም ምክንያት ሌዝሊ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የተሰለፈ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን ታሪክ የሚሠራበትን አጋጣሚ መና ያደርጉበታል። ይኸው ሌዝሊ አሁን ገንዘብ ተዋጥቶለት ሃውልት ሊሰራለት እየታቀደ ነው። እስካሁን ቢያንስ 135 ሺህ ፓውንድ ተዋጥቶለታል። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 240 ስፖርተኞችን የሚዘክሩ ሃውልቶች አሉ። ከእነዚህ መካከል 10 ብቻ ናቸው ለጥቁርና አናሳ ቁጥር ላላቸው እንግሊዛውያን ክብር የቆሙት። ከአስሩ መካከል አምስት ለእግርኳስ ተጫዋቾች የቆሙ ሲሆን ጎልፍና ክሪኬት የመሳሰሉ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ምንም ዓይነት የጥቁር ግለሰብ ሐውልት የላቸውም። ለምን? ሼፊልድ ዩኒቨርሲቲ የሠራው አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው የጥቁር ስፖርተኞች ሐውልቶች ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩት ባለፉት 10 ዓመታት ነው። አብዛኛዎቹ ሐውልቶች በተለይ ደግሞ የእግር ኳስ ተጫዎቾች መታሰቢያዎች ተጫዎቾቹ ጫማ ከሰቀሉ ከ20ና 30 ዓመታት በኋላ ነው የሚሠሩት። አብዛኛዎቹ የጥቁር እግር ኳስ ተጫዋቾች ሐውልቶች ለምን ባለፉት 10 ዓመታት ተሰሩ የሚለውን ጥያቄ የሚመልሱት ዶ/ር ክሪስ ስትራይድ፤ በእንግሊዝ እግር ኳስ መድረክ ከ1980ዎቹ [በአውሮፓውያኑ] በፊት በጣም ጥቂት ተጫዋቾች ነበሩ ይላሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ካላት 240 ሐውልት መካከል 10 ሃውልቶች ለጥቁሮች መድባለች። ከእነዚህ መካከል ዘጠኙ የተገነቡት ባለፉት 10 ዓመታት ነው። ይህ ደግሞ የ1980ዎቹ ተጫዎቾች መታሰብ የጀመሩት አሁን መሆኑን ማሳያ ነው ይላሉ ምሁሩ። እንግሊዝ ውስጥ ከቆሙ የጥቁር ተጫዋቾች ሐውልቶች መካከል ጎልቶ የሚወጣው በአውሮፓውያኑ 2019 የተገነባው የሶስቱ የዌስት ብሮሚች አልቢዮን ተጫዎቾች ሃውልት ነው። ሎሪ ካኒንግሃም፣ ሲሪል ሬጂስና ብንዶን ባስቶን ዌስትብሮም በ1970ዎቹ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታዋቂው ቡድን እንዲሆን የጎላ ሚና ተጫውተዋል። እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጥቁር ስፖርተኛ ሃውልት ያቆመችው በአውሮፓውያኑ 2001 ነው። ይሄም የታዋቂው ቦክሰኛ ራንዲ ቱርፒን ነው። ከዚያ በመቀጠል ሐውልት የቆመለት ጥቁር ተጫዋች የአርሰናሉ ፈረንሳዊ አጥቂ ቲየሪ ሄንሪ ነው። ሴቶች? ዩናይትድ ኪንግደም በዓለማችን በርካታ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሃውልቶች ያሏት ሃገር ናት። በጠቅላላው በዓለማችን 700 የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሐውልት እንደቆመላቸው አንድ ጥናት ይጠቁማል። ነገር ግን ከእነዚህ ሐውልቶች መካከል ለሴት ስፖርተኞች መታሰቢያ የሆኑ ዘንድ የቆሙ ሐውልቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ሊሊ ፓር እንግሊዝ ውስጥ ሐውልት የተሰራላት የመጀመሪያዋ ሴት ስፖርተኛ ናት። በ1920ዎቹና 30ዎቹ ዲክ ለተሰኘው የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የተጫወተችው ሊሊ ሃማንቸስተር ውስጥ ሐውልት የተሰራላት ባለፈው ዓመት [2019] ነው። ከሊሊ በተጨማሪ ሃውልት የቆመላቸው እንግሊዛውያን ስፖርተኞች 3 ናቸው። እነዚህም ቴኒስ ተጫዋቿ ዶሮቲ ራውንድ፣ የኦሊምፒክ ሻምፒዮናዎቹ ሜሪ ፒተርስና ኬሊ ሆልምስ ናቸው። ከ1980ዎቹ በኋላ ያለው የእንግሊዝ እግር ኳስ በጥቁር ተጫዎቾች የደመቀ ነው። ያለፈው አስር ዓመትም ጥቁር የእግር ኳስ ፈርጦችን አፍርቷል። የእነዚህን ተጫዎቾች ሐውልት መች እናይ ይሆን? የበርካቶች ጥያዌ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-53763226 |
3politics
| ስልጣን በውርስ? ልጆቻቸውን ለስልጣን ያጩት የአፍሪካ መሪዎች | የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ንጌሶ ልጃቸውን ዴኒስ ክሪስቴልን ሚኒስትር አድርገው ሾሙ። ይህንን ሹመት ሚዲያዎች እንዲሁ በቀላሉ አላዩትም። ፕሬዚዳንቱ ልጃቸውን ሊተኩ በዝግጅት ላይ ናቸው በማለትም ነው ሪፖርት ያደረጉት። ስልጣን ዘላለማዊ እንዳለመሆኑ መጠን እንዲህ አይነት መተካካት ሊከሰት ይችላል። ለአርባ አንድ ዓመታት አገሪቷን የገዙት የ77 ዓመቱ ፕሬዚዳንት በቀጣዮቹ ዓመታትም እንዲያስተዳድሩ በመጋቢት ወር ምርጫ አሸንፌያለሁ ብለዋል። በቀጣዮቹ ዓመታትም ስልጣናቸውን አሳልፈው ለመስጠት ምንም አይነት ፍንጭ ባያሳዩም የአሁኑ የስልጣናቸው ወቅት ሲያልቅ ልጃቸውን ለመተካት እንደሚያስቡ አንዳንድ ፍንጮች እየተሰሙ ነው። የልጃቸው ዴኒስ ክሪስቴል በኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት መሆን አዲስ ነገር አይሆንም፤ በተለይም በማዕከላዊ አፍሪካ አካባቢ እንደሚታየው የልጆች ስልጣን መውረስ ተመሳሳይ እንጂ። በጎረቤት አገር ጋቦን የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኦማር ቦንጎ ኦንዲምባ አገሪቷን ከአውሮፓውያኑ 1967 አስከ 2009 የመሯት የኦማር ቦንጎ ልጅ ናቸው። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደግሞ በአውሮፓውያኑ 2001 የተገደሉት የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር የነበሩትን ላውረንት ዴዜሪ ካቢላን በመተካት ልጃቸው ጆሴፍ ካቢላ ለ17 ዓመታት በስልጣን ቆይተዋል። የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ቲዎዲሮ ኦቢያንግ ወደ ስልጣን የመጡት ጨቋኙ አጎታቸውን ፍራንሲስኮ ማሺያስ ንጉዌማን ከስልጣን በማስወገድ ነበር። አጎትየውም በ1979 ወደ ስልጣን የመጡ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ነበሩ። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ፕሬዚዳንቱ ልጃቸው እሳቸውን እንዲተካቸው ምክትል ፕሬዚዳንት አድርገው ሾመውታል። ከአማፂያን ጋር ሲዋጉ ቆስለው ባለፈው ወር ህይወታቸው ያለፈው የቻዱን ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢን በመተካት ልጃቸው ማህማት የሽግግሩ ወታደራዊ ምክር ቤት መሪ ሆኗል። ልጃቸው የጦር ጄኔራል ነው። በካሜሮንም እንዲሁ የስልጣን ሽግግር እንዲመጣ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። እንቅስቃሴው በማን እንደተጀመረ ግልፅ ባይሆንም የ88 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ፓውል ቢያ ልጃቸውን ፍራንክ ቢያን እንዲተኩት ዘመቻም ተጀምሯል። ፕሬዚዳንቱ ለሰባት ዓመት በስልጣን ላይ እንዲቆዩ የተመረጡ ቢሆንም ግማሹንም ጊዜ ገና አላጠነቀቁም። ከፖለቲካ ራሱን አግልሎ በግል ቢዝነስ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው ፍራንክ ከዚህ ዘመቻ ጀርባ እጁ በፍፁም እንደሌለበት የቅርብ ሰዎቹ ይናገራሉ። ነገር ግን ዘመቻውን የመቃወም፣ የማስተባበልም ሆነ አባቱን በስልጣን የመተካት ፍላጎትንም በጭራሽ አላሳየም። ስልጣን መወራረስ አዲስ ነገር አይደለም። በማዕከላዊ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአሜሪካም የቡሽና የኬኔዲ ቤተሰቦችን እንመልከት። በቅርቡም በኡጋንዳ የወቅቱን ፕሬዚዳንት ዩዌሩ ሙሴቪኒ ልጃቸው ሙሆዚ ካይኔሩግባ በመጪው 2026 በፕሬዚዳንታዊው ምርጫ ተወዳዳሪ እንዲሆን በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ተከፍተዋል። ነገር ግን ስልጣን የመወራረስ ጉዳይ በምዕራብ አፍሪካ በተለይ የተንሰራፋ ይመስላል። እነዚህ አካባቢዎች በነዳጅ የታደሉ ከመሆናቸው አንፃር የፖለቲካው ትስስር፣ የፔትሮሊየም ምጣኔ ሀብትና የኢምፓየር ግንባታ የተቆራኙ ናቸው። አመራሮቹ የነዳጁንም ምንጭ መቆጣጠር ስለሚያስችላቸው በውስጣቸውም መቆራቆዝ በርካታ ጊዜ ይፈጠራል። ለምሳሉ ያህል በኦቢያንግ ቤተሰቦች መካከል ግጭቶች አንዳሉ ይሰማል። አንዳንድ የቤተሰብ አባላት የፕሬዚዳንቱ ልጅና የነዳጅ ሚኒስትሩ ገብርኤል ምቤጋ ኦቢያንግ ሊማ አማራጭ ፕሬዚዳንት እንዲሆን ይፈልጋሉ። ጋቦን፡ የቤተሰብ ቁርሾ በአውሮፓውያኑ 2016 በጋቦን ምርጫ በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የቀድሞው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ጂን ፒንግ ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎን ያፋጠጠ ነበር። እነዚህ ፖለቲከኞች የጋብቻ ዝምድና አላቸው። የፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ እህት ፓስካሊን የጂን ፒንግ የቀድሞ ባለቤት ናት፤ ይህም ማለት ፕሬዚዳንት አሉ የጂን ፒንግ ሁለት ልጆች አጎት ናቸው። ነገር ግን ጂን ፒንግ በዋነኝነት የፖለቲካ አጀንዳቸውን ወደፊት በማምጣት በአገሪቱ የለውጥና እውነተኛ ዲሞክራሲ መሪ ነኝ በማለት ነበር በተቃዋሚ መሪነት በምርጫ የተወዳደሩት። በዚያን ወቅት በነበረው ምርጫ የተሸነፉት ጂን ፒንግ ከአምስት ዓመታት በኋላም መሸነፋቸውን አይቀበሉትም። በወቅቱ በርካቶች መራራ ያሉት የምርጫ ውድድርና የተአማኒነት ጥያቄ ያነሱበት ይህ ምርጫ በመጨረሻም ፕሬዚዳንት አሊን አሸናፊ አድርጓቸዋል። ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ ወደኋላ እየተመለከቱ አይደለም። በአሁኑ ወቅት ልጃቸውን ኑረዲን ቦንጎ ቫለንቲንን የፕሬዚዳንት ጉዳዮች ዋነኛ አስተባባሪ አድርገው በአውሮፓውያኑ 2019 ሾመውታል። ልጃቸውን ከመሾማቸው ከዓመት በፊት ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ ስትሮክ ታመው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለህክምና አቅንተው ነበር። በዚያን ወቅት የአገሪቱ ኤታማዦር ሹም ብሪስ ላክሩቼ አሊሃንጋ ፕሬዚዳንቱን ተክተው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ነበር። ፕሬዚዳንቱም ከህመማቸው አገግመው ተመለሱ ኤታማዦር ሹሙን ከስልጣናቸው አነሷቸው፤ በኋላም ከሥራ ተባረሩ በሙስና ወንጀልም በቁጥጥር ስር ዋሉ። ኤታማዦር ሹሙ ግን ይህንን ይክዳሉ። በአሁኑ ወቅት ልጃቸው ኑረዲን በዚህ ቁልፍ በሚባል ቦታ ላይ ተቀምጧል። አባቱንም በየቀኑ ያገኛል። የፕሬዚዳንቱንም ፍላጎቶች ለማስፈፀምና በጉዳዮች ላይ ለመወሰን ስልጣን አለው። በተለይም የፕሬዚዳንት አሊ የጤና ሁኔታ እያሽቆለቆለ ነው በሚባልበት በአሁኑ ወቅት ኑረዲን በስልጣን ሊተካቸው ይችላል የሚሉ ጉዳዮች ጎልተው እየወጡ ነው። ኑረዲን በዩናይትድ ኪንግደም ስመ ጥር በሆነው ኤተን ኮሌጅ ነው የተማረው፤ ወጣትነቱ እንዲሁም ያለው የዘመናዊነት ሁኔታው የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። የፈረንሳይ የሙስና ምርመራ ወደ ቻድ ስንመለስ ደግሞ ለሦስት አስርት ዓመታት አገሪቱን የመሯት ኢድሪስ ዴቢ የሞቱት ከአንድ ወር በፊት ነው። በእሳቸው ቦታ የተተካውን ልጃቸውን ማሃማት ከፍተኛ ተግዳሮቶች ተጋርጠውበታል። በሽግግሩ ምክር ቤት ውስጥ ያሉትን ወታደራዊ አጋሮቹ ጋር በመሆን በአገሪቱ የቆየን ወታደራዊ ልማድ ለማስቀጠል የጎሳዎች ድጋፍ ማግኘት አለበት። በሌላ በኩልም በአገር ውስጥና በዓለም አቀፉም ማኅበረሰብ በኩል ለፖለቲካ ውይይቶችና ትርጉም ያለው ዲሞክራሲ እንዲመጣ ጥረት እንዲያደርግ ከፍተኛ ጫና እየደረሰበት ነው። በኢኳቶሪያል ጊኒ ደግሞ ሌላኛው ስጋትና ሁኔታዎችን የተወሳሰበ ያደረገው ፈረንሳይ በአመራሮቹ ላይ በማነጣጠሯ ነው። የአገሪቷ መሪዎች ከሙስና በተገኘ ገንዘብ ንብረቶች በፈረንሳይ ገዝተዋል በሚልም የሙስና ምርመራ ጀምሬያለሁ ብላለች። የቦንጎም ሆነ የንጌሶ ቤተሰቦች በዚህ ኢላማ ሆነዋል። 13 የሚሆኑ የነዚህ ቤተሰብ አባላት እንዲሁም በቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር ቦንጎ ቤት ጠበቃ ሆኖ ይሰራ የነበረና በርካታ የፈረንሳይ ዜጎች የወንጀል ምርመራ ተከፍቶባቸዋል። በአውሮፓውያኑ 2015 የፈረንሳይ ዳኛ በፓሪስ የሚገኙ ሁለት ንብረቶች በመንግሥት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። የነዚህ ንብረት ትክክለኛ ባለቤቶችም የሳሱ ንጌሶ የወንድም ልጅ ዊልፍሪድ ንጌሶ ናቸው በሚል ነው። ከዚህም በተጨማሪ ቅንጡ የሚባሉ 15 መኪኖችም እንዲሁ እንዲያዙ ተወስኗል። ዊልፍሪድም ይፋዊ የሆነ ምርመራ ተከፍቶበት ነበር። በአውሮፓውያኑ 2016 ሳሱ ንጌሶ የተከፈተባቸው ምርመራ ውድቅ እንዲሆን የሞከሩ ሲሆን ይህንን ጉዳይም ቃል አቀባያቸው ፕሬዚዳንቱን ለማሳጣት የሚደረግ ትልቅ ማጭበርበር ነው በማለት ወርፈዋቸዋል። የፈረንሳይ ዳኞች ግን በዚህ ፍንክች አላሉም። በአውሮፓውያኑ 2017 የፕሬዚዳንቱ ልጅ ጁሊየንና ባለቤቷ ጋይ ጆንሰን፣ ሌላ የወንድም ልጅ ኤድጋር፣ የባለቤታቸው እህት ካትሪን ኢግናንጋ ምርመራ ተጀምሮባቸዋል ተብሏል። በአውሮፓውያኑ 2008-09 አጠራጣሪ በተባለው 22.4 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ዝውውርም መሪዎቹ ተወንጅለዋል። ኢኳቶሪያል ጊኒና ቅንጡ መኪኖቿ የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ልጅ ሌላኛው ቲዎዶሮ በፓሪስ የሚገኘው ቅንጡ ቤቱ በአውሮፓውያኑ 2012 በፖሊስ ተከበበ። ሁለት ቡጋቲ ቬይሮንስና ሮልስ ሮይስ ፓንቶም የተባሉት መኪኖቹም ተያዙ። መኪኖቹን በመያዝ ብቻ አልበቃም ቲዎዶሮ ራሱ 30 ሚሊዮን ዩሮ ቅጣት እንዲከፍሉ ታዘዘ። በዚህ የተበሳጨው መንግሥት ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ወሰደው። መከራከሪያውም ፎች ማንሽን የተባለው በፈረንሳይ የሚገኘው ቤት 107 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚያወጣና የአገሪቱም ኤምባሲ እንደሆነና ከምንም ነገር የሚጠብቃቸው የዲፕሎማሲያዊ ጥበቃ አለ በሚልም ነው። ነገር ግን ባለፈው ታኅሣሥ ፍርድ ቤቱ ይህንን መከራከሪያ ውድቅ አድርጎታል። የፈረንሳይ ፓርላማ በበኩሉ እነዚህ የተያዙ ንብረቶች በአገሪቱ ለሚገኙ መሰረተ ልማቶች ሊውሉ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ እያረቀቀ ነው። እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ግን በደንብ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው። በስዊዘርላንድ፣ ጁኔቫ የሚገኙ ባለስልጣናትም እንዲሁ በቴዎዶርና በሁለት ግለሰቦች ላይ ገንዘብ በማዘዋወር፣ የሕዝብ ሃብትን ያላግባቡ በመጠቀም በሚል ክስ ከፍተው ከሁለት ዓመት በፊትም ነው ጉዳዩ የተቋጨው። በዚህም መሰረት 25 ቅንጡ መኪናዎች አንዲሸጡ ታዘዘ ገንዘቡም ለእርዳታና ለልማት ድርጅቶች እንዲውል ተወሰነ። ከተሸጡት መኪኖችም መካከል ላምቦርጊኒ ቬኖኖ ሮድስታል በ9.1 ሚሊዮን ዶላር፣ ጥቁር ካርበን ኮይኒግሴግ 5.2 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠዋል። ሰባት ፌራሪዎች፣ ሁለት ላምቦርጊኒ፣ አምስት ቤንትሊ፣ ማዘራቲ፣ አስተን ማርቲን፣ ማክላረን የተባሉት መኪኖች በ26 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ተሸጡ። ግማሹ የተገዙት ስማቸው ያልተጠቀሰ ግለሰብ ሲሆን እሳቸውንም ወክሎ አንድ ጀርመናዊ ነው የተጫረተው። ነገር ግን ከአምስት ወራት በኋላ በኢኳቶሪያል ጊኒ መዲና ማላቦ ቲዎዶሮ በጨረታ ከተሸጡት አንደኛዋ መኪና ሲነዳ ታየ፤ ፎቶውንም በኢንስታግራም ቢለጠፍም በኋላ ግን አጥፍቶታል። ምንም እንኳን በነዚህ አገራት ስልጣን በውርስ የማስተላለፍ ሁኔታዎች ቢታይም እየተቀየረች ባለችው አፍሪና ለውጥን በሚሻ ወጣት መካከል የዘለቄታዊነቱን ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል። *የዚሀ ፅሁፍ አዘጋጅ በለንደን የሚገኘው ቻታም ሃውስ የአፍሪካ ፕሮግራም አማካሪው ፓውል ሜሊ ናቸው | ስልጣን በውርስ? ልጆቻቸውን ለስልጣን ያጩት የአፍሪካ መሪዎች የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ንጌሶ ልጃቸውን ዴኒስ ክሪስቴልን ሚኒስትር አድርገው ሾሙ። ይህንን ሹመት ሚዲያዎች እንዲሁ በቀላሉ አላዩትም። ፕሬዚዳንቱ ልጃቸውን ሊተኩ በዝግጅት ላይ ናቸው በማለትም ነው ሪፖርት ያደረጉት። ስልጣን ዘላለማዊ እንዳለመሆኑ መጠን እንዲህ አይነት መተካካት ሊከሰት ይችላል። ለአርባ አንድ ዓመታት አገሪቷን የገዙት የ77 ዓመቱ ፕሬዚዳንት በቀጣዮቹ ዓመታትም እንዲያስተዳድሩ በመጋቢት ወር ምርጫ አሸንፌያለሁ ብለዋል። በቀጣዮቹ ዓመታትም ስልጣናቸውን አሳልፈው ለመስጠት ምንም አይነት ፍንጭ ባያሳዩም የአሁኑ የስልጣናቸው ወቅት ሲያልቅ ልጃቸውን ለመተካት እንደሚያስቡ አንዳንድ ፍንጮች እየተሰሙ ነው። የልጃቸው ዴኒስ ክሪስቴል በኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት መሆን አዲስ ነገር አይሆንም፤ በተለይም በማዕከላዊ አፍሪካ አካባቢ እንደሚታየው የልጆች ስልጣን መውረስ ተመሳሳይ እንጂ። በጎረቤት አገር ጋቦን የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኦማር ቦንጎ ኦንዲምባ አገሪቷን ከአውሮፓውያኑ 1967 አስከ 2009 የመሯት የኦማር ቦንጎ ልጅ ናቸው። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደግሞ በአውሮፓውያኑ 2001 የተገደሉት የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር የነበሩትን ላውረንት ዴዜሪ ካቢላን በመተካት ልጃቸው ጆሴፍ ካቢላ ለ17 ዓመታት በስልጣን ቆይተዋል። የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ቲዎዲሮ ኦቢያንግ ወደ ስልጣን የመጡት ጨቋኙ አጎታቸውን ፍራንሲስኮ ማሺያስ ንጉዌማን ከስልጣን በማስወገድ ነበር። አጎትየውም በ1979 ወደ ስልጣን የመጡ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ነበሩ። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ፕሬዚዳንቱ ልጃቸው እሳቸውን እንዲተካቸው ምክትል ፕሬዚዳንት አድርገው ሾመውታል። ከአማፂያን ጋር ሲዋጉ ቆስለው ባለፈው ወር ህይወታቸው ያለፈው የቻዱን ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢን በመተካት ልጃቸው ማህማት የሽግግሩ ወታደራዊ ምክር ቤት መሪ ሆኗል። ልጃቸው የጦር ጄኔራል ነው። በካሜሮንም እንዲሁ የስልጣን ሽግግር እንዲመጣ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። እንቅስቃሴው በማን እንደተጀመረ ግልፅ ባይሆንም የ88 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ፓውል ቢያ ልጃቸውን ፍራንክ ቢያን እንዲተኩት ዘመቻም ተጀምሯል። ፕሬዚዳንቱ ለሰባት ዓመት በስልጣን ላይ እንዲቆዩ የተመረጡ ቢሆንም ግማሹንም ጊዜ ገና አላጠነቀቁም። ከፖለቲካ ራሱን አግልሎ በግል ቢዝነስ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው ፍራንክ ከዚህ ዘመቻ ጀርባ እጁ በፍፁም እንደሌለበት የቅርብ ሰዎቹ ይናገራሉ። ነገር ግን ዘመቻውን የመቃወም፣ የማስተባበልም ሆነ አባቱን በስልጣን የመተካት ፍላጎትንም በጭራሽ አላሳየም። ስልጣን መወራረስ አዲስ ነገር አይደለም። በማዕከላዊ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአሜሪካም የቡሽና የኬኔዲ ቤተሰቦችን እንመልከት። በቅርቡም በኡጋንዳ የወቅቱን ፕሬዚዳንት ዩዌሩ ሙሴቪኒ ልጃቸው ሙሆዚ ካይኔሩግባ በመጪው 2026 በፕሬዚዳንታዊው ምርጫ ተወዳዳሪ እንዲሆን በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ተከፍተዋል። ነገር ግን ስልጣን የመወራረስ ጉዳይ በምዕራብ አፍሪካ በተለይ የተንሰራፋ ይመስላል። እነዚህ አካባቢዎች በነዳጅ የታደሉ ከመሆናቸው አንፃር የፖለቲካው ትስስር፣ የፔትሮሊየም ምጣኔ ሀብትና የኢምፓየር ግንባታ የተቆራኙ ናቸው። አመራሮቹ የነዳጁንም ምንጭ መቆጣጠር ስለሚያስችላቸው በውስጣቸውም መቆራቆዝ በርካታ ጊዜ ይፈጠራል። ለምሳሉ ያህል በኦቢያንግ ቤተሰቦች መካከል ግጭቶች አንዳሉ ይሰማል። አንዳንድ የቤተሰብ አባላት የፕሬዚዳንቱ ልጅና የነዳጅ ሚኒስትሩ ገብርኤል ምቤጋ ኦቢያንግ ሊማ አማራጭ ፕሬዚዳንት እንዲሆን ይፈልጋሉ። ጋቦን፡ የቤተሰብ ቁርሾ በአውሮፓውያኑ 2016 በጋቦን ምርጫ በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የቀድሞው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ጂን ፒንግ ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎን ያፋጠጠ ነበር። እነዚህ ፖለቲከኞች የጋብቻ ዝምድና አላቸው። የፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ እህት ፓስካሊን የጂን ፒንግ የቀድሞ ባለቤት ናት፤ ይህም ማለት ፕሬዚዳንት አሉ የጂን ፒንግ ሁለት ልጆች አጎት ናቸው። ነገር ግን ጂን ፒንግ በዋነኝነት የፖለቲካ አጀንዳቸውን ወደፊት በማምጣት በአገሪቱ የለውጥና እውነተኛ ዲሞክራሲ መሪ ነኝ በማለት ነበር በተቃዋሚ መሪነት በምርጫ የተወዳደሩት። በዚያን ወቅት በነበረው ምርጫ የተሸነፉት ጂን ፒንግ ከአምስት ዓመታት በኋላም መሸነፋቸውን አይቀበሉትም። በወቅቱ በርካቶች መራራ ያሉት የምርጫ ውድድርና የተአማኒነት ጥያቄ ያነሱበት ይህ ምርጫ በመጨረሻም ፕሬዚዳንት አሊን አሸናፊ አድርጓቸዋል። ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ ወደኋላ እየተመለከቱ አይደለም። በአሁኑ ወቅት ልጃቸውን ኑረዲን ቦንጎ ቫለንቲንን የፕሬዚዳንት ጉዳዮች ዋነኛ አስተባባሪ አድርገው በአውሮፓውያኑ 2019 ሾመውታል። ልጃቸውን ከመሾማቸው ከዓመት በፊት ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ ስትሮክ ታመው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለህክምና አቅንተው ነበር። በዚያን ወቅት የአገሪቱ ኤታማዦር ሹም ብሪስ ላክሩቼ አሊሃንጋ ፕሬዚዳንቱን ተክተው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ነበር። ፕሬዚዳንቱም ከህመማቸው አገግመው ተመለሱ ኤታማዦር ሹሙን ከስልጣናቸው አነሷቸው፤ በኋላም ከሥራ ተባረሩ በሙስና ወንጀልም በቁጥጥር ስር ዋሉ። ኤታማዦር ሹሙ ግን ይህንን ይክዳሉ። በአሁኑ ወቅት ልጃቸው ኑረዲን በዚህ ቁልፍ በሚባል ቦታ ላይ ተቀምጧል። አባቱንም በየቀኑ ያገኛል። የፕሬዚዳንቱንም ፍላጎቶች ለማስፈፀምና በጉዳዮች ላይ ለመወሰን ስልጣን አለው። በተለይም የፕሬዚዳንት አሊ የጤና ሁኔታ እያሽቆለቆለ ነው በሚባልበት በአሁኑ ወቅት ኑረዲን በስልጣን ሊተካቸው ይችላል የሚሉ ጉዳዮች ጎልተው እየወጡ ነው። ኑረዲን በዩናይትድ ኪንግደም ስመ ጥር በሆነው ኤተን ኮሌጅ ነው የተማረው፤ ወጣትነቱ እንዲሁም ያለው የዘመናዊነት ሁኔታው የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። የፈረንሳይ የሙስና ምርመራ ወደ ቻድ ስንመለስ ደግሞ ለሦስት አስርት ዓመታት አገሪቱን የመሯት ኢድሪስ ዴቢ የሞቱት ከአንድ ወር በፊት ነው። በእሳቸው ቦታ የተተካውን ልጃቸውን ማሃማት ከፍተኛ ተግዳሮቶች ተጋርጠውበታል። በሽግግሩ ምክር ቤት ውስጥ ያሉትን ወታደራዊ አጋሮቹ ጋር በመሆን በአገሪቱ የቆየን ወታደራዊ ልማድ ለማስቀጠል የጎሳዎች ድጋፍ ማግኘት አለበት። በሌላ በኩልም በአገር ውስጥና በዓለም አቀፉም ማኅበረሰብ በኩል ለፖለቲካ ውይይቶችና ትርጉም ያለው ዲሞክራሲ እንዲመጣ ጥረት እንዲያደርግ ከፍተኛ ጫና እየደረሰበት ነው። በኢኳቶሪያል ጊኒ ደግሞ ሌላኛው ስጋትና ሁኔታዎችን የተወሳሰበ ያደረገው ፈረንሳይ በአመራሮቹ ላይ በማነጣጠሯ ነው። የአገሪቷ መሪዎች ከሙስና በተገኘ ገንዘብ ንብረቶች በፈረንሳይ ገዝተዋል በሚልም የሙስና ምርመራ ጀምሬያለሁ ብላለች። የቦንጎም ሆነ የንጌሶ ቤተሰቦች በዚህ ኢላማ ሆነዋል። 13 የሚሆኑ የነዚህ ቤተሰብ አባላት እንዲሁም በቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር ቦንጎ ቤት ጠበቃ ሆኖ ይሰራ የነበረና በርካታ የፈረንሳይ ዜጎች የወንጀል ምርመራ ተከፍቶባቸዋል። በአውሮፓውያኑ 2015 የፈረንሳይ ዳኛ በፓሪስ የሚገኙ ሁለት ንብረቶች በመንግሥት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። የነዚህ ንብረት ትክክለኛ ባለቤቶችም የሳሱ ንጌሶ የወንድም ልጅ ዊልፍሪድ ንጌሶ ናቸው በሚል ነው። ከዚህም በተጨማሪ ቅንጡ የሚባሉ 15 መኪኖችም እንዲሁ እንዲያዙ ተወስኗል። ዊልፍሪድም ይፋዊ የሆነ ምርመራ ተከፍቶበት ነበር። በአውሮፓውያኑ 2016 ሳሱ ንጌሶ የተከፈተባቸው ምርመራ ውድቅ እንዲሆን የሞከሩ ሲሆን ይህንን ጉዳይም ቃል አቀባያቸው ፕሬዚዳንቱን ለማሳጣት የሚደረግ ትልቅ ማጭበርበር ነው በማለት ወርፈዋቸዋል። የፈረንሳይ ዳኞች ግን በዚህ ፍንክች አላሉም። በአውሮፓውያኑ 2017 የፕሬዚዳንቱ ልጅ ጁሊየንና ባለቤቷ ጋይ ጆንሰን፣ ሌላ የወንድም ልጅ ኤድጋር፣ የባለቤታቸው እህት ካትሪን ኢግናንጋ ምርመራ ተጀምሮባቸዋል ተብሏል። በአውሮፓውያኑ 2008-09 አጠራጣሪ በተባለው 22.4 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ዝውውርም መሪዎቹ ተወንጅለዋል። ኢኳቶሪያል ጊኒና ቅንጡ መኪኖቿ የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ልጅ ሌላኛው ቲዎዶሮ በፓሪስ የሚገኘው ቅንጡ ቤቱ በአውሮፓውያኑ 2012 በፖሊስ ተከበበ። ሁለት ቡጋቲ ቬይሮንስና ሮልስ ሮይስ ፓንቶም የተባሉት መኪኖቹም ተያዙ። መኪኖቹን በመያዝ ብቻ አልበቃም ቲዎዶሮ ራሱ 30 ሚሊዮን ዩሮ ቅጣት እንዲከፍሉ ታዘዘ። በዚህ የተበሳጨው መንግሥት ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ወሰደው። መከራከሪያውም ፎች ማንሽን የተባለው በፈረንሳይ የሚገኘው ቤት 107 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚያወጣና የአገሪቱም ኤምባሲ እንደሆነና ከምንም ነገር የሚጠብቃቸው የዲፕሎማሲያዊ ጥበቃ አለ በሚልም ነው። ነገር ግን ባለፈው ታኅሣሥ ፍርድ ቤቱ ይህንን መከራከሪያ ውድቅ አድርጎታል። የፈረንሳይ ፓርላማ በበኩሉ እነዚህ የተያዙ ንብረቶች በአገሪቱ ለሚገኙ መሰረተ ልማቶች ሊውሉ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ እያረቀቀ ነው። እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ግን በደንብ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው። በስዊዘርላንድ፣ ጁኔቫ የሚገኙ ባለስልጣናትም እንዲሁ በቴዎዶርና በሁለት ግለሰቦች ላይ ገንዘብ በማዘዋወር፣ የሕዝብ ሃብትን ያላግባቡ በመጠቀም በሚል ክስ ከፍተው ከሁለት ዓመት በፊትም ነው ጉዳዩ የተቋጨው። በዚህም መሰረት 25 ቅንጡ መኪናዎች አንዲሸጡ ታዘዘ ገንዘቡም ለእርዳታና ለልማት ድርጅቶች እንዲውል ተወሰነ። ከተሸጡት መኪኖችም መካከል ላምቦርጊኒ ቬኖኖ ሮድስታል በ9.1 ሚሊዮን ዶላር፣ ጥቁር ካርበን ኮይኒግሴግ 5.2 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠዋል። ሰባት ፌራሪዎች፣ ሁለት ላምቦርጊኒ፣ አምስት ቤንትሊ፣ ማዘራቲ፣ አስተን ማርቲን፣ ማክላረን የተባሉት መኪኖች በ26 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ተሸጡ። ግማሹ የተገዙት ስማቸው ያልተጠቀሰ ግለሰብ ሲሆን እሳቸውንም ወክሎ አንድ ጀርመናዊ ነው የተጫረተው። ነገር ግን ከአምስት ወራት በኋላ በኢኳቶሪያል ጊኒ መዲና ማላቦ ቲዎዶሮ በጨረታ ከተሸጡት አንደኛዋ መኪና ሲነዳ ታየ፤ ፎቶውንም በኢንስታግራም ቢለጠፍም በኋላ ግን አጥፍቶታል። ምንም እንኳን በነዚህ አገራት ስልጣን በውርስ የማስተላለፍ ሁኔታዎች ቢታይም እየተቀየረች ባለችው አፍሪና ለውጥን በሚሻ ወጣት መካከል የዘለቄታዊነቱን ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል። *የዚሀ ፅሁፍ አዘጋጅ በለንደን የሚገኘው ቻታም ሃውስ የአፍሪካ ፕሮግራም አማካሪው ፓውል ሜሊ ናቸው | https://www.bbc.com/amharic/news-57359923 |
0business
| በሊባኖስ የወደቀ ኢኮኖሚ የተመሰሉት የፋሲካ ብስኩቶች | የሰዎች የምግብ አዘገጃጀትና አለባበስ በአብዛኛው ያላቸውን የኢኮኖሚ ደረጃ ያመላክታል። የግለሰብን ብቻም ሳይሆን የአገር ኢኮኖሚንም ማንፀባረቂያ መስታወት ነው። ሰው ኑሮውን ይመስላል እንደሚባለው ማለት ነው። ታዲያ ሊባኖሳውያን በአገራቸው ኢኮኖሚ የተመሰሉ የፋሲካ ብስኩቶችን አዘጋጅተዋል። በሊባኖስ የፋሲካ በዓልን ለሚያከብሩ የግሪክ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ባህላዊ ‘ማሞል’ ብስኩት መስራት ወይም መግዛት የተለመደ ነው። ማሞል የተሰኘው ይህ ብስኩት በውስጡ ቅቤ፣ ለውዝ፣ ፍራፍሬ፣ ሥጋ እየተሞላ የሚዘጋጅ ነው። ሊባኖሳውያን በዚህ ጣፋጭ ምግብ ይኮራሉ። በፋሲካ በዓል፣ በኢድ አልፈጥር እንዲሁም በኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ከማዕዳቸው የማይታጣ ምግብ ነው። በሊባኖስ ማሞል ብስኩትን አለማዘጋጀት ማለት በፋሲካ ዶሮ ወጥ፤ በኢድ አልፈጥር ገንፎን እንዳለመስራት ማለት ነው። ይህ ብስኩት በዓውድ ዓመት ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። በዘንድሮው የፋሲካ በዓል ግን ነገሮች ከወትሮው የተለየ ሆነዋል። ሪታ ስታምቦሊ የግሪክ ኦርቶዶክስ አማኝ ስትሆን ነዋሪነቷ ከቤሩት አንድ ሰዓት ያህል በመኪና በምታስጉዘው ዛህል ነው። ዘንድሮ እያዘጋጀች ያለችው ሞሞል ከወትሮው ለየት ይላል። ብስኩቱን ለመስራት ያድቦለቦለችው ሊጥ ውስጥ የቴምር ፍሬ እያስገባች ነው ያዘጋጀቸው። ለወትሮው ሥጋ ነበር የምትጨምርበት። “አሁን ኢኮኖሚው ወድቋል። ድህነት ውስጥ ነው ያለነው። ጉዟችን ወደ ኋላ ሆኗል። በፊት እንደምንኖረው እየኖርን አይደለም፤ ስጋ የምናገኘው በወር አንድ ጊዜ ነው” ትላለች። ሪታ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ ፀሐፊ ሆና ነው የምትሰራው። የአገሪቷ ኢኮኖሚ መላሸቅ ልክ እንደ ሌሎቹ ሊባኖሳዊያን የደመዋዟን የመግዛት አቅም አሳንሶታል። “ሁለት ልጆች አሉን። በኪራይ ቤት ነው የምንኖረው። እኔ እና ባለቤቴ እንሰራለን ግን ይህም ሆኖ ገቢያችን በቂ አይደለም” ትላለች። ምንም እንኳን ብስኩቷ ውስጥ መጨመር የምትወደው ፒስታሽዎ የተባለ ፍሬ ቢሆንም አሁን ግን ይህን ማድረግ አልቻለችም። ፒስታሽዎ እንደ ለውዝ ያለ ጠንካራ ሽፋን ያለው ውድ ፍሬ ነው። በዚህ ዓመት ግን ይህንን አትሰራም። የምትሰራው የማሞል ብስኩት ቁጥርም ከዚህ ቀደም ከምታደርገው አነስተኛ ነው። አሁን ብስኩቱ ውስጥ የምትጨምረውን የፒታሽዎ ፍሬ በቅቤ ተክታዋለች። ይህም ቢሆን ግን ዋጋው ቀላል አይደለም። "ቅቤው የደመወዜን አንድ ሦስተኛ ይወስዳል" ትላለች። በርካታ ሊባኖሳዊያን የምግብ ባንክ ጠባቂ ሆነዋል። የሶሪያ ስደተኞችን እና ለአደጋ የተጋለጡ ሊባኖሳውያንን የሚደግፈው የልማትና የእርዳታ ድርጅት የሚቀርብለት የእርዳታ ጥያቄ ጨምሯል። ሁኔታውም በጣማ የተባባሰ ሆኗል። በአገሪቷ ውስጥ ባለው ፖለቲካ እና አለመስማማት እርዳታዎችም ባክነዋል። እአአ በ2020 መጨረሻ ከኢራቅ የተገኘ የእርዳታ ስንዴ ለተረጂዎች መሰራጨት ሲገባው ስታዲየም ውስጥ አላግባብ መቀመጡ ተነግሯል። በዚያው ዓመት ነሃሴ ወር ላይ በቤሩት ወደብ ላይ የተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ ከሲሪላንካ የተገኘ የሻይ ቅጠል ድጋፍም ለፕሬዚደንቱ ጠባቂዎች ቤተሰቦች ተሰጥቷል። በአገቷ ያለውን አለመረጋጋት ተከትሎ የፖለቲካ ፓርቲዎች የራሳቸውን እርምጃ እየወሰዱ ነው። ሂዝቦላህ እና የጦር ድርጅቶች የራሳቸውን የገበያ ማዕከል ከፍተዋል። ነገር ግን በርካሽ የሚሸጡት ለራሳቸው አባላትና ደጋፊዎቻቸው ነው። ታዲያ በቤሩት ዝነኛው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና 'ሊባነን ፎር ቱሞሮው' በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት አምባሳደር የሆነው ጆሴፍ ታውክ ላለፉት ሦስት ቀናት ከቡድኑ ጋር ሆኖ 9 ሺህ የሚሆኑ ማሞል ብስኩቶችን አዘጋጅቷል። ብስኩቶቹን በማዘጋጀት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ይሰጣሉ። የመድሃኒትም ድጋፍ ያደርጋሉ። አገሪቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የአራት ቀናት ቤት ውስጥ የመቀመት ገደብ ጥላለች። በመሆኑም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የፋሲካ በዓልን ፤ ሙስሊሞችም የኢፍጣር ሥነ ሥርዓትን የሚያከብሩት ቤታቸው ሆነው ያላቸውን ነገር እየተቃመሱ ነው። | በሊባኖስ የወደቀ ኢኮኖሚ የተመሰሉት የፋሲካ ብስኩቶች የሰዎች የምግብ አዘገጃጀትና አለባበስ በአብዛኛው ያላቸውን የኢኮኖሚ ደረጃ ያመላክታል። የግለሰብን ብቻም ሳይሆን የአገር ኢኮኖሚንም ማንፀባረቂያ መስታወት ነው። ሰው ኑሮውን ይመስላል እንደሚባለው ማለት ነው። ታዲያ ሊባኖሳውያን በአገራቸው ኢኮኖሚ የተመሰሉ የፋሲካ ብስኩቶችን አዘጋጅተዋል። በሊባኖስ የፋሲካ በዓልን ለሚያከብሩ የግሪክ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ባህላዊ ‘ማሞል’ ብስኩት መስራት ወይም መግዛት የተለመደ ነው። ማሞል የተሰኘው ይህ ብስኩት በውስጡ ቅቤ፣ ለውዝ፣ ፍራፍሬ፣ ሥጋ እየተሞላ የሚዘጋጅ ነው። ሊባኖሳውያን በዚህ ጣፋጭ ምግብ ይኮራሉ። በፋሲካ በዓል፣ በኢድ አልፈጥር እንዲሁም በኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ከማዕዳቸው የማይታጣ ምግብ ነው። በሊባኖስ ማሞል ብስኩትን አለማዘጋጀት ማለት በፋሲካ ዶሮ ወጥ፤ በኢድ አልፈጥር ገንፎን እንዳለመስራት ማለት ነው። ይህ ብስኩት በዓውድ ዓመት ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። በዘንድሮው የፋሲካ በዓል ግን ነገሮች ከወትሮው የተለየ ሆነዋል። ሪታ ስታምቦሊ የግሪክ ኦርቶዶክስ አማኝ ስትሆን ነዋሪነቷ ከቤሩት አንድ ሰዓት ያህል በመኪና በምታስጉዘው ዛህል ነው። ዘንድሮ እያዘጋጀች ያለችው ሞሞል ከወትሮው ለየት ይላል። ብስኩቱን ለመስራት ያድቦለቦለችው ሊጥ ውስጥ የቴምር ፍሬ እያስገባች ነው ያዘጋጀቸው። ለወትሮው ሥጋ ነበር የምትጨምርበት። “አሁን ኢኮኖሚው ወድቋል። ድህነት ውስጥ ነው ያለነው። ጉዟችን ወደ ኋላ ሆኗል። በፊት እንደምንኖረው እየኖርን አይደለም፤ ስጋ የምናገኘው በወር አንድ ጊዜ ነው” ትላለች። ሪታ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ ፀሐፊ ሆና ነው የምትሰራው። የአገሪቷ ኢኮኖሚ መላሸቅ ልክ እንደ ሌሎቹ ሊባኖሳዊያን የደመዋዟን የመግዛት አቅም አሳንሶታል። “ሁለት ልጆች አሉን። በኪራይ ቤት ነው የምንኖረው። እኔ እና ባለቤቴ እንሰራለን ግን ይህም ሆኖ ገቢያችን በቂ አይደለም” ትላለች። ምንም እንኳን ብስኩቷ ውስጥ መጨመር የምትወደው ፒስታሽዎ የተባለ ፍሬ ቢሆንም አሁን ግን ይህን ማድረግ አልቻለችም። ፒስታሽዎ እንደ ለውዝ ያለ ጠንካራ ሽፋን ያለው ውድ ፍሬ ነው። በዚህ ዓመት ግን ይህንን አትሰራም። የምትሰራው የማሞል ብስኩት ቁጥርም ከዚህ ቀደም ከምታደርገው አነስተኛ ነው። አሁን ብስኩቱ ውስጥ የምትጨምረውን የፒታሽዎ ፍሬ በቅቤ ተክታዋለች። ይህም ቢሆን ግን ዋጋው ቀላል አይደለም። "ቅቤው የደመወዜን አንድ ሦስተኛ ይወስዳል" ትላለች። በርካታ ሊባኖሳዊያን የምግብ ባንክ ጠባቂ ሆነዋል። የሶሪያ ስደተኞችን እና ለአደጋ የተጋለጡ ሊባኖሳውያንን የሚደግፈው የልማትና የእርዳታ ድርጅት የሚቀርብለት የእርዳታ ጥያቄ ጨምሯል። ሁኔታውም በጣማ የተባባሰ ሆኗል። በአገሪቷ ውስጥ ባለው ፖለቲካ እና አለመስማማት እርዳታዎችም ባክነዋል። እአአ በ2020 መጨረሻ ከኢራቅ የተገኘ የእርዳታ ስንዴ ለተረጂዎች መሰራጨት ሲገባው ስታዲየም ውስጥ አላግባብ መቀመጡ ተነግሯል። በዚያው ዓመት ነሃሴ ወር ላይ በቤሩት ወደብ ላይ የተከሰተውን ፍንዳታ ተከትሎ ከሲሪላንካ የተገኘ የሻይ ቅጠል ድጋፍም ለፕሬዚደንቱ ጠባቂዎች ቤተሰቦች ተሰጥቷል። በአገቷ ያለውን አለመረጋጋት ተከትሎ የፖለቲካ ፓርቲዎች የራሳቸውን እርምጃ እየወሰዱ ነው። ሂዝቦላህ እና የጦር ድርጅቶች የራሳቸውን የገበያ ማዕከል ከፍተዋል። ነገር ግን በርካሽ የሚሸጡት ለራሳቸው አባላትና ደጋፊዎቻቸው ነው። ታዲያ በቤሩት ዝነኛው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና 'ሊባነን ፎር ቱሞሮው' በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት አምባሳደር የሆነው ጆሴፍ ታውክ ላለፉት ሦስት ቀናት ከቡድኑ ጋር ሆኖ 9 ሺህ የሚሆኑ ማሞል ብስኩቶችን አዘጋጅቷል። ብስኩቶቹን በማዘጋጀት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ይሰጣሉ። የመድሃኒትም ድጋፍ ያደርጋሉ። አገሪቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የአራት ቀናት ቤት ውስጥ የመቀመት ገደብ ጥላለች። በመሆኑም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የፋሲካ በዓልን ፤ ሙስሊሞችም የኢፍጣር ሥነ ሥርዓትን የሚያከብሩት ቤታቸው ሆነው ያላቸውን ነገር እየተቃመሱ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-56962261 |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ በቫይረሱ የተያዙ በመጀመሪያዎቹ ቀናት የማስተላለፍ እድላቸው ሰፊ መሆኑ ተጠቆመ | በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ምልክቶች በማያሳዩባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ውስጥ ቫይረሱን የማስተላለፍ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች ከሆነ ቫይረሱ ያለባቸውን ቀደም ብሎ በለይቶ ማቆያ ማስገባት ስርጭቱን ለማስቆም ወሳኝ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የጥናት ውጤቱ በላንሴት ማይክሮብ ላይ ታትሟል። ግለሰቦች የማስተላለፍ ዕድላቸው በብዙ ነገሮች ላይ የተመረኮዘ ሲሆን ራሱን የሚያባዛ ቫይረስ እና በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን ስርጭቱን ከሚወስኑት መካከል ናቸው። አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊት እና በቫይረሱ በተያዙ የመጀመሪያው ሳምንት በጣም አስተላላፊ ናቸው፡፡ በሆስፒታል ውስጥ የበሽታው ምልክት ያለባቸውንና ቫይረሱ የተገኘባቸውን ጨምሮ ሳይንቲስቶች በኮቪድ-19 ላይ 79 ዓለም አቀፍ ጥናቶችን መርምረዋል። ተመራማሪዎች ኢንፌክሽኑ ከጀመረ እስከ ዘጠኝ ቀናት ድረስ ከተወሰዱ የጉሮሮ ናሙናዎች ውስጥ ዋነኛ ቫይረሶችን መለየት እና ማባዛት ችለዋል፡፡ ምልክቶቹ በጀመሩበት ጊዜ ወይም በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የቫይረስ ስርጭት እንደሚኖር ከሰዎች የጉሮሮ ናሙና ማወቅ ችለዋል። ምልክቶቹ ከጀመሩ በአማካይ እስከ 17 ቀናት በአፍንጫ እና በጉሮሮ ናሙናዎች ንቁ ያልሆኑ የቫይረስ ቁርጥራጮች ተገኝተዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ እነዚህ ቁርጥራጮቻቸው ከዘጠኝ ቀናት በላይ ቢቀጥሉም አብዛኛዎቹ ሰዎች የማስተላለፍ ዕድላቸው አነስተኛ ነው ብለዋል፡፡ የሴንት አንድሪውስ ዩኒቨርስቲ ባልደረባው ዶ/ር ሙጌ ሴቪክ ለቢቢሲ እንደገለጹት ግኝቶቹ ሰዎች ገና በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት በጣም አስተላላፊ እንደሆኑ አሳይተዋል፡፡ "ሰዎች የሕመም ምልክቶችን እንዳሳዩ እንዲለዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምርመራ ውጤቶችን በሚያገኙበት ጊዜ በጣም አስተላላፊ የሚሆኑበትን ደረጃቸውን ያልፉ ይሆናል።" "ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ወዲያውኑ ራሳቸውን ያለዩበትን ምክንያት በመመልከት ይህንን እንዲያደርጉ ልንረዳቸው ይገባል" ብለዋል፡፡ ጥናቱ ምልክት የማያሳዩ ሰዎችን አላካተትም። ሆኖም ሌሎች ጥናቶችን እንደሚያስጠነቅቁት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊትም አስተላላፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ እና ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክት ሳይኖር ቫይረሱ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ የእንግሊዝ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ካላቸው ወዲያውኑ ራሳቸውን ቢያንስ ለ 10 ቀናት ማግለል አለባቸው፡፡ | ኮሮናቫይረስ ፡ በቫይረሱ የተያዙ በመጀመሪያዎቹ ቀናት የማስተላለፍ እድላቸው ሰፊ መሆኑ ተጠቆመ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ምልክቶች በማያሳዩባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ውስጥ ቫይረሱን የማስተላለፍ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ሳይንቲስቶች ከሆነ ቫይረሱ ያለባቸውን ቀደም ብሎ በለይቶ ማቆያ ማስገባት ስርጭቱን ለማስቆም ወሳኝ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የጥናት ውጤቱ በላንሴት ማይክሮብ ላይ ታትሟል። ግለሰቦች የማስተላለፍ ዕድላቸው በብዙ ነገሮች ላይ የተመረኮዘ ሲሆን ራሱን የሚያባዛ ቫይረስ እና በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን ስርጭቱን ከሚወስኑት መካከል ናቸው። አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊት እና በቫይረሱ በተያዙ የመጀመሪያው ሳምንት በጣም አስተላላፊ ናቸው፡፡ በሆስፒታል ውስጥ የበሽታው ምልክት ያለባቸውንና ቫይረሱ የተገኘባቸውን ጨምሮ ሳይንቲስቶች በኮቪድ-19 ላይ 79 ዓለም አቀፍ ጥናቶችን መርምረዋል። ተመራማሪዎች ኢንፌክሽኑ ከጀመረ እስከ ዘጠኝ ቀናት ድረስ ከተወሰዱ የጉሮሮ ናሙናዎች ውስጥ ዋነኛ ቫይረሶችን መለየት እና ማባዛት ችለዋል፡፡ ምልክቶቹ በጀመሩበት ጊዜ ወይም በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የቫይረስ ስርጭት እንደሚኖር ከሰዎች የጉሮሮ ናሙና ማወቅ ችለዋል። ምልክቶቹ ከጀመሩ በአማካይ እስከ 17 ቀናት በአፍንጫ እና በጉሮሮ ናሙናዎች ንቁ ያልሆኑ የቫይረስ ቁርጥራጮች ተገኝተዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ እነዚህ ቁርጥራጮቻቸው ከዘጠኝ ቀናት በላይ ቢቀጥሉም አብዛኛዎቹ ሰዎች የማስተላለፍ ዕድላቸው አነስተኛ ነው ብለዋል፡፡ የሴንት አንድሪውስ ዩኒቨርስቲ ባልደረባው ዶ/ር ሙጌ ሴቪክ ለቢቢሲ እንደገለጹት ግኝቶቹ ሰዎች ገና በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት በጣም አስተላላፊ እንደሆኑ አሳይተዋል፡፡ "ሰዎች የሕመም ምልክቶችን እንዳሳዩ እንዲለዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምርመራ ውጤቶችን በሚያገኙበት ጊዜ በጣም አስተላላፊ የሚሆኑበትን ደረጃቸውን ያልፉ ይሆናል።" "ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ወዲያውኑ ራሳቸውን ያለዩበትን ምክንያት በመመልከት ይህንን እንዲያደርጉ ልንረዳቸው ይገባል" ብለዋል፡፡ ጥናቱ ምልክት የማያሳዩ ሰዎችን አላካተትም። ሆኖም ሌሎች ጥናቶችን እንደሚያስጠነቅቁት ሰዎች የበሽታ ምልክቶች ከማሳየታቸው በፊትም አስተላላፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ እና ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክት ሳይኖር ቫይረሱ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ የእንግሊዝ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ካላቸው ወዲያውኑ ራሳቸውን ቢያንስ ለ 10 ቀናት ማግለል አለባቸው፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/55026691 |
5sports
| ሞሮኮ በስፔን ላይ ድል ስትቀዳጅ፣ ሮናልዶን ተክቶ የገባው 3 ጎሎችን አስቆጠረ | ትናንት በተደረጉ የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ግጥሚያዎች ያልተጠበቀ ውጤት ተመዝግቧል። አፍሪካዊቷ ሞሮኮ የእግር ኳስ ኃያሏ ስፔንን በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀላቅላለች። እአአ 1990 ላይ ካሜሮን፣ እአአ 2002 ላይ ሴኔጋል እንዲሁም እአአ 2010 ላይ ጋና ሩብ ፍጻሜን የተቀላቀሉ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ሲሆኑ ሞሮኮም ይህን ታሪክ መጋራት ችላለች። ሁለቱ ቡድኖች ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ውድድር ያለ ጎል በመጠናቀቁ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርተው ነበር። ቡድኖቹ በተጨማሪ ሰዓትም ጎል ማስቆጠር ባለመቻላቸው በፍጹም ቅጣት ምት መለየት ግድ ሆኗል። ስፔኖች የመጀመሪያዎቹን ሦስት ፍጹም ቅጣት ምቶች ስተዋል። ድንቅ ሆኖ ያመሸው የሞሮኮ ግብ ጠባቂ ያሲን ቦኖ ሁለት ፍጹም ቅጣት ምቶችን ማዳን ችሏል። ማድሪድ ተወልዶ ስፔን ያደገው ሞሮኳዊው አሽራፍ ሃኪሚ ወሳኟን ፍጹም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር ስፔንን ከኳታር አሰናብቷታል። ለዋንጫ ከተገመቱ አገራት መካከል አንዷ የነበረችውን ስፔን ያሸነፉት ሞሮኮዎች ከድላቸው በኋላ ብዙ አድናቆት እየደረሳቸው ይገኛል። የሞሮኮ ንጉስ መሐመድ አምስተኛ ሳይቀሩ ስልክ አንስተው መላው ቡድኑን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። ትናንት ምሽት በተካሄደው ሌላኛው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችላለች። ፖርቹጋል 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ተጋጣሚዋን ብትረታም ትልቁ መነጋገሪያ ሆኖ ያመሸው የክርስቲያኖ ሮናልዶ በተቀያሪ ወንበር ላይ መቀመጥ ነው። የፖርቹጋል አሠልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ ቡድናቸው ከስዊዘርላንድ ጋር በነበረው ጨዋታ ሮናልዶን በተቀያሪ ወንበር ላይ አድርገው ጨዋታቸውን ጀምረዋል። በምድብ ድልድሉ ፖርቹጋል የመጨረሻውን ጨዋታ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ስታደርግ ሮናልዶ ተቀይሮ ሲወጣ ባሳየው ምልክት ደስተኛ እንዳልነበሩ አሠልጣኙ አልሸሸጉም። ሮናልዶ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ግጥሚያዎችን ሲያደርግ በተቀያሪ ወንበር ላይ ሆኖ ጨዋታ የተጀመረው እአአ 2008 ላይ ነበር። በሮናልዶ ተተክቶ ሜዳ የገባው ጎንሳሎ ራሞስ ሦስት ጎሎችን አስቆጥሮ “ሃትሪክ” ሰርቷል። የ21 ዓመቱ የቤነፊካ አጥቂ ራሞስ ሦስት ጎሎችን ያስቆጠረው በዚህ የዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሰለፍ ዕድል ካገኘ በኋላ ነው። ሮናልዶ በ74ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ወደ ሜዳ ሲገባ በደጋፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ሮናልዶ ተቀይሮ ከገባ በኋላ በጨዋታ እንቅስቃሴ ጎል ቢያስቆጥርም ግቧ ከጨዋታ ውጪ ተብላ ተሽራለች። | ሞሮኮ በስፔን ላይ ድል ስትቀዳጅ፣ ሮናልዶን ተክቶ የገባው 3 ጎሎችን አስቆጠረ ትናንት በተደረጉ የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ግጥሚያዎች ያልተጠበቀ ውጤት ተመዝግቧል። አፍሪካዊቷ ሞሮኮ የእግር ኳስ ኃያሏ ስፔንን በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀላቅላለች። እአአ 1990 ላይ ካሜሮን፣ እአአ 2002 ላይ ሴኔጋል እንዲሁም እአአ 2010 ላይ ጋና ሩብ ፍጻሜን የተቀላቀሉ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ሲሆኑ ሞሮኮም ይህን ታሪክ መጋራት ችላለች። ሁለቱ ቡድኖች ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ውድድር ያለ ጎል በመጠናቀቁ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርተው ነበር። ቡድኖቹ በተጨማሪ ሰዓትም ጎል ማስቆጠር ባለመቻላቸው በፍጹም ቅጣት ምት መለየት ግድ ሆኗል። ስፔኖች የመጀመሪያዎቹን ሦስት ፍጹም ቅጣት ምቶች ስተዋል። ድንቅ ሆኖ ያመሸው የሞሮኮ ግብ ጠባቂ ያሲን ቦኖ ሁለት ፍጹም ቅጣት ምቶችን ማዳን ችሏል። ማድሪድ ተወልዶ ስፔን ያደገው ሞሮኳዊው አሽራፍ ሃኪሚ ወሳኟን ፍጹም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር ስፔንን ከኳታር አሰናብቷታል። ለዋንጫ ከተገመቱ አገራት መካከል አንዷ የነበረችውን ስፔን ያሸነፉት ሞሮኮዎች ከድላቸው በኋላ ብዙ አድናቆት እየደረሳቸው ይገኛል። የሞሮኮ ንጉስ መሐመድ አምስተኛ ሳይቀሩ ስልክ አንስተው መላው ቡድኑን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። ትናንት ምሽት በተካሄደው ሌላኛው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ፖርቹጋል ስዊዘርላንድን በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችላለች። ፖርቹጋል 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ተጋጣሚዋን ብትረታም ትልቁ መነጋገሪያ ሆኖ ያመሸው የክርስቲያኖ ሮናልዶ በተቀያሪ ወንበር ላይ መቀመጥ ነው። የፖርቹጋል አሠልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ ቡድናቸው ከስዊዘርላንድ ጋር በነበረው ጨዋታ ሮናልዶን በተቀያሪ ወንበር ላይ አድርገው ጨዋታቸውን ጀምረዋል። በምድብ ድልድሉ ፖርቹጋል የመጨረሻውን ጨዋታ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ስታደርግ ሮናልዶ ተቀይሮ ሲወጣ ባሳየው ምልክት ደስተኛ እንዳልነበሩ አሠልጣኙ አልሸሸጉም። ሮናልዶ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ግጥሚያዎችን ሲያደርግ በተቀያሪ ወንበር ላይ ሆኖ ጨዋታ የተጀመረው እአአ 2008 ላይ ነበር። በሮናልዶ ተተክቶ ሜዳ የገባው ጎንሳሎ ራሞስ ሦስት ጎሎችን አስቆጥሮ “ሃትሪክ” ሰርቷል። የ21 ዓመቱ የቤነፊካ አጥቂ ራሞስ ሦስት ጎሎችን ያስቆጠረው በዚህ የዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሰለፍ ዕድል ካገኘ በኋላ ነው። ሮናልዶ በ74ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ወደ ሜዳ ሲገባ በደጋፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ሮናልዶ ተቀይሮ ከገባ በኋላ በጨዋታ እንቅስቃሴ ጎል ቢያስቆጥርም ግቧ ከጨዋታ ውጪ ተብላ ተሽራለች። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c88k1mxdkvro |
3politics
| ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች ፑቲን ላይ ማዕቀብ እንደሚጣል ባይደን አስጠነቀቁ | ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ ማዕቀብ እንደሚጣል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስጠነቀቁ። ሩስያ በደቡብ ምዕራብ ድንበሯ ያለችውን ዩክሬንን ከወረረች "ትልቅ ቅጣት" እንደሚከተል ባይደን አሳስበዋል። ሌሎች የምዕራቡ ዓለም አገራትም ሩስያን እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ሩስያ ዩክሬንን የመውረር ዕቅድ የለኝም ብላ አሜሪካ እና ሌሎችም አገራት "ነገሩን እያጋጋሉ" ነው ስትል ትወቅሳለች። ሩስያ ይህን ብትልም ድንበሯ ላይ ወደ 100,000 ወታደሮች አሰማርታለች። ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች በቀጥታ ፑቲን ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ እንደሚጣል ነው ባይደን ያስጠነቀቁት። ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች "ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ትልቁ ወረራ" ይሆናል ብለዋል። የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) በምሥራቅ አውሮፓ ጠንካራ ክትትል እንደሚያደርግ ጠቅሰው "የትኛውም የኔቶ አባል ጥቃት ሲሰነዘርበት ኔቶ ይከላከለዋል" ሲሉ ተደምጠዋል። አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን የመላክ ዕቅድ እንደሌላት ባይደን በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ሩስያ በበኩሏ አሜሪካ እና ኔቶ ዩክሬንን በምዕራባውያን አማካሪዎች እና በጦር መሣሪያ "አጥለቅልቀዋታል" ስትል ከሳለች። በተባበሩት መንግሥታት የሩስያ ቋሚ መልዕክተኛ "ሩስያ ድንበር አካባቢ አሜሪካውያኑ ምን እያረጉ እንደሆነ ግልጽ አይደለም" ሲል መግለጫ አውጥቷል። ሩስያ የነዳጅ መስመር የምትቆርጥ ከሆነ ዝግጁ ሆኖ ለመጠበቅ የመላው ዓለም ነዳጅ አቅራቢዎች ወደ አውሮፓ የሚልኩትን ነዳጅ እንዲጨምሩ ባይደን ጠይቀዋል። የአውሮፓ ሕብረት ከሚያስገባው ድፍድፍ ነዳጅ አንስ ሦስተኛውን የምትልከው ሩስያ ናት። የዩናይት ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፤ የምዕራቡ ዓለም አገራት ሩስያ ላይ "ከባድ" የምጣኔ ሀብት ማዕቀብ እንደሚጥሉና አገራቸውም የኔቶ አባላትን ለመደገፍ ወታደሮች እንደምትልክ ተናግረዋል። ሩስያ ከዓለም አቀፉ የክፍያ ሥርዓት ስዊፍት እንደምትታገድ ቢናገሩም፤ በምላሹ የሩስያ ባለሥልጣናት አውሮፓ የሩስያን ምርቶች ገዝታ የምትከፍልበት ሥርዓት አይኖራትም ሲሉ አስፈራርተዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከሩስያ ጋር ውይይት በማድረግ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። አሜሪካ 8,500 ወታደሮቿ በተጠንቀቅ እንዲጠብቁ ማዘዟን ሩስያ "እጅግ አስጊ" ብላዋለች። አሜሪካ ከሩስያ በተጨማሪ የሩስያ አጋር የሆነችውን ቤላሩስም አስጠንቅቃለች። ሩስያ በበኩሏ ኔቶ ወደ ምሥራቅ የሚያደርገው መስፋፋት ያሰጋኛል ትላለች። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲማይር ዘለንስኪ በቴሌቭዥን ቀርበው ሕዝባቸውን ለማረጋጋት ሞክረዋል። "ሁሉም ነገር ቀላል ባይሆንም ተስፋ አለ። አካላችሁን ከቫይረስ፣ አእምሯችሁን ከውሸች፣ ልባችሁን ከፍርሃት ተከላከሉ" ብለዋል። ሩስያ እአአ በ2014 ክሬሚያን በግድ የግዛቷ አካል አድርጋለች። ክሬሚያ በሩስያ ግዛት ውስጥ ለመቆየት በሕዝበ ውሳኔ ስትወስን ዩክሬን ግን ሕገ ወጥ ስትል ሐሳቡን ውድቅ አድርጋለች። | ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች ፑቲን ላይ ማዕቀብ እንደሚጣል ባይደን አስጠነቀቁ ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ ማዕቀብ እንደሚጣል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስጠነቀቁ። ሩስያ በደቡብ ምዕራብ ድንበሯ ያለችውን ዩክሬንን ከወረረች "ትልቅ ቅጣት" እንደሚከተል ባይደን አሳስበዋል። ሌሎች የምዕራቡ ዓለም አገራትም ሩስያን እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ሩስያ ዩክሬንን የመውረር ዕቅድ የለኝም ብላ አሜሪካ እና ሌሎችም አገራት "ነገሩን እያጋጋሉ" ነው ስትል ትወቅሳለች። ሩስያ ይህን ብትልም ድንበሯ ላይ ወደ 100,000 ወታደሮች አሰማርታለች። ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች በቀጥታ ፑቲን ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ እንደሚጣል ነው ባይደን ያስጠነቀቁት። ሩስያ ዩክሬንን ከወረረች "ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ትልቁ ወረራ" ይሆናል ብለዋል። የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) በምሥራቅ አውሮፓ ጠንካራ ክትትል እንደሚያደርግ ጠቅሰው "የትኛውም የኔቶ አባል ጥቃት ሲሰነዘርበት ኔቶ ይከላከለዋል" ሲሉ ተደምጠዋል። አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን የመላክ ዕቅድ እንደሌላት ባይደን በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ሩስያ በበኩሏ አሜሪካ እና ኔቶ ዩክሬንን በምዕራባውያን አማካሪዎች እና በጦር መሣሪያ "አጥለቅልቀዋታል" ስትል ከሳለች። በተባበሩት መንግሥታት የሩስያ ቋሚ መልዕክተኛ "ሩስያ ድንበር አካባቢ አሜሪካውያኑ ምን እያረጉ እንደሆነ ግልጽ አይደለም" ሲል መግለጫ አውጥቷል። ሩስያ የነዳጅ መስመር የምትቆርጥ ከሆነ ዝግጁ ሆኖ ለመጠበቅ የመላው ዓለም ነዳጅ አቅራቢዎች ወደ አውሮፓ የሚልኩትን ነዳጅ እንዲጨምሩ ባይደን ጠይቀዋል። የአውሮፓ ሕብረት ከሚያስገባው ድፍድፍ ነዳጅ አንስ ሦስተኛውን የምትልከው ሩስያ ናት። የዩናይት ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፤ የምዕራቡ ዓለም አገራት ሩስያ ላይ "ከባድ" የምጣኔ ሀብት ማዕቀብ እንደሚጥሉና አገራቸውም የኔቶ አባላትን ለመደገፍ ወታደሮች እንደምትልክ ተናግረዋል። ሩስያ ከዓለም አቀፉ የክፍያ ሥርዓት ስዊፍት እንደምትታገድ ቢናገሩም፤ በምላሹ የሩስያ ባለሥልጣናት አውሮፓ የሩስያን ምርቶች ገዝታ የምትከፍልበት ሥርዓት አይኖራትም ሲሉ አስፈራርተዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከሩስያ ጋር ውይይት በማድረግ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። አሜሪካ 8,500 ወታደሮቿ በተጠንቀቅ እንዲጠብቁ ማዘዟን ሩስያ "እጅግ አስጊ" ብላዋለች። አሜሪካ ከሩስያ በተጨማሪ የሩስያ አጋር የሆነችውን ቤላሩስም አስጠንቅቃለች። ሩስያ በበኩሏ ኔቶ ወደ ምሥራቅ የሚያደርገው መስፋፋት ያሰጋኛል ትላለች። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲማይር ዘለንስኪ በቴሌቭዥን ቀርበው ሕዝባቸውን ለማረጋጋት ሞክረዋል። "ሁሉም ነገር ቀላል ባይሆንም ተስፋ አለ። አካላችሁን ከቫይረስ፣ አእምሯችሁን ከውሸች፣ ልባችሁን ከፍርሃት ተከላከሉ" ብለዋል። ሩስያ እአአ በ2014 ክሬሚያን በግድ የግዛቷ አካል አድርጋለች። ክሬሚያ በሩስያ ግዛት ውስጥ ለመቆየት በሕዝበ ውሳኔ ስትወስን ዩክሬን ግን ሕገ ወጥ ስትል ሐሳቡን ውድቅ አድርጋለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-60136557 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ስለ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እስከ አሁን የምናውቃቸው 10 ነጥቦች | ኮቪድ-19 ክትባት ተገኘለት እፎይ መባል በጀመረ ገና በሳምንቱ ከወደ ብሪታኒያ መጥፎ ዜና ተሰምቷል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ አዲስ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች መገኘት ነው ዜናው፡፡ በፈረንጆች ገና ይህ ያልተጠበቀ ዜና መሰማቱ ለጊዜው አውሮጳን እያመሳት ነው፡፡ ከብሪታኒያ የሚመጡ አውሮፕላኖች ላይ እግድ እያወጡ ያሉት የአውሮጳ አገራት ድንበራቸውን ጠርቅመው እየዘጉት ነው፡፡ 1ኛ፡- በብሪታኒያ በተለይም በሎንደንና አካባቢው እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የተህዋሲው ናሙና ተገኝቷል፡፡ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን በታመሙ ሰዎች ላይ በብዛት የሚታየው የቫይረስ ዓይነትም ይኸው ዝርያ መሆኑ ድንጋጤን ፈጥሯል፡፡ 2ኛ፡- ይህ የቫይረስ ዝርያ ሌሎች የተህዋሲ ዝርያዎችን በፍጥነት እየተካ ቦታውን እየያዘ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ 3ኛ፡- ራሱን የሚያባዛበት መንገድ ለየቅል መሆኑ ምናልባት ለቁጥጥር ያስቸግር ይሆን የሚል ስጋትን ጨምሯል፡፡ ከመተንፈሻ አካል ውጭ ያሉ ሴሎችንም ራሱን እየለወጠ የማጥቃት አቅም ሊኖረው ይችል ይhoን የሚል ስጋትም አለ፡፡ 4ኛ፡- ለመጀመርያ ጊዜ ይህ የተህዋሲ ዝርያ የተገኘው በመስከረም ወር ነበር፡፡ በጥቅምት ወር ሎንዶን አካባቢ በኮቪድ ከተያዙት ሲሶዎቹ የዚህ ተህዋሲ መልክ ተገኘባቸው፡፡ በታኅሣሥ ወር ደግሞ 75 ከመቶዎቹ ታማሚዎችን የለከፈው ይህ ልዩ ተህዋሲ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ 5ኛ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ ይህ ተህዋሲ እስከዛሬ ከነበረው ቫይረስ ጋር ሲወዳደር የመዛመት ዕደሉ በ70 ከመቶ የፈጠነ ነው ብለዋል፡፡ 6ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በጊዜ ሂደት ራሱን ቀይሮ ይሁን ወይም ከሌላ ቦታ መጥቶ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። 7ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በመላው ብሪታኒያ የተሰራጨ ቢሆንም አሁን ክምችቱ በብዛት የሚኘው በለንደንና አካባቢው ነው፡፡ ከለንደን በተጨማሪ በደቡብ ምሥራቅና በምሥራቅ ኢንግላንድም እንዲሁ በስፋት ተመዝግቧል፡፡ 8ኛ፡- ኔክስትስትሬይን የተሀዋሲ ዝርያዎችን የዘረ መል ኮድ የሚመዘግብ ድርጅት ሲሆን፣ ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ከብሪታኒያ ወደ ዴንማርክና አውስትራሊያ መዛመቱን ተናግሯል፡፡ ኔዘርላንድና ጣሊያንም ይህ አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ አገራቸው መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡ 9ኛ፡- ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ቅንጣት በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል የተባለ ሲሆን በኋላ ላይ የወጡ መረጃዎች ግን ከዚህ ብሪታኒያ ተገኘ ከተባለው ተህዋሲ ጋር የዝርያ ተመሳሳይነት የላቸውም ብለዋል፡፡ 10ኛ፡- ተህዋሲው ራሱን ቆርጦ እየቀጠለና እያባዛ ሊያመልጥ ቢችልም አሁን ወደ ገበያ እየገቡ ያሉ ክትባቶች ግን ማንነቱን ያጠፉታል፣ ፈውስም ይሆናል ተብሎ በስፋት ታምኗል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ እስከዛሬ ሌሎች ዝርያዎች ኖረውት ያውቃሉ? አዎ! ዛሬ በተለያየ ዓለም የምናገኘው የቫይረስ ዝርያ ቅንጣት ቻይና ዉሃን ከተማ ከተገኘው ዝርያ ጋር አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ አሁን በብዙ የአውሮጳ አገሮች የሚገኘው D614G የሚባል የተህዋሲ ዝርያ ዓይነት ነው። ተህዋሲው ራሱን እየቀየረ ሊመጣ ይችላል፡፡ ምናልባት መነሻው ሊሆን የሚችለው ደካማ የመከላከል አቅም ካለው በሽተኛ ራሱን ቀይሮ የተነሳ ተህዋሲ ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ታማሚ ተህዋሲውን ማሸነፍ ሲሳነው ሰውነቱ የተህዋሲው መራቢያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ እስከአሁን በዚህ ረገድ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ገና በደንብ መጠናት ይኖርበታል፡፡ ለጊዜው የሚታወቀው በከፍተኛ ፍጥነት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ብቻ ነው፡፡ ያም ሆኖ ብዙ ሰዎችን ማዳረስ ከቻለ ብዙ ሰዎች አልጋ ይይዛሉ፡፡ ይህ ደግሞ በተዘዋዋሪ ሞትን ሊጨምር ይችላል፡፡ መቶ በመቶ ባይሆንም አሁን የሚገመተው ክትባቶቹ ለዚህ ተህዋሲም ፈውስ እንደሆኑ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው አሁን ተሳኩ የተባሉት ክትባቶች የተህዋሲውን መላ አካሉንና ባህሪውን ሁሉ እንዲያጠቁ የተዘጋጁ ስለሆኑ ተህዋሲው ራሱን እያባዛ ራሱን ሊቀያይር ቢሞክርም እንኳ ከክትባቶቹ ያመልጣል ማለት ዘበት ነው ይላሉ ተመራማሪዎች፡፡ | ኮሮናቫይረስ፡ ስለ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እስከ አሁን የምናውቃቸው 10 ነጥቦች ኮቪድ-19 ክትባት ተገኘለት እፎይ መባል በጀመረ ገና በሳምንቱ ከወደ ብሪታኒያ መጥፎ ዜና ተሰምቷል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ አዲስ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች መገኘት ነው ዜናው፡፡ በፈረንጆች ገና ይህ ያልተጠበቀ ዜና መሰማቱ ለጊዜው አውሮጳን እያመሳት ነው፡፡ ከብሪታኒያ የሚመጡ አውሮፕላኖች ላይ እግድ እያወጡ ያሉት የአውሮጳ አገራት ድንበራቸውን ጠርቅመው እየዘጉት ነው፡፡ 1ኛ፡- በብሪታኒያ በተለይም በሎንደንና አካባቢው እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የተህዋሲው ናሙና ተገኝቷል፡፡ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን በታመሙ ሰዎች ላይ በብዛት የሚታየው የቫይረስ ዓይነትም ይኸው ዝርያ መሆኑ ድንጋጤን ፈጥሯል፡፡ 2ኛ፡- ይህ የቫይረስ ዝርያ ሌሎች የተህዋሲ ዝርያዎችን በፍጥነት እየተካ ቦታውን እየያዘ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ 3ኛ፡- ራሱን የሚያባዛበት መንገድ ለየቅል መሆኑ ምናልባት ለቁጥጥር ያስቸግር ይሆን የሚል ስጋትን ጨምሯል፡፡ ከመተንፈሻ አካል ውጭ ያሉ ሴሎችንም ራሱን እየለወጠ የማጥቃት አቅም ሊኖረው ይችል ይhoን የሚል ስጋትም አለ፡፡ 4ኛ፡- ለመጀመርያ ጊዜ ይህ የተህዋሲ ዝርያ የተገኘው በመስከረም ወር ነበር፡፡ በጥቅምት ወር ሎንዶን አካባቢ በኮቪድ ከተያዙት ሲሶዎቹ የዚህ ተህዋሲ መልክ ተገኘባቸው፡፡ በታኅሣሥ ወር ደግሞ 75 ከመቶዎቹ ታማሚዎችን የለከፈው ይህ ልዩ ተህዋሲ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ 5ኛ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ ይህ ተህዋሲ እስከዛሬ ከነበረው ቫይረስ ጋር ሲወዳደር የመዛመት ዕደሉ በ70 ከመቶ የፈጠነ ነው ብለዋል፡፡ 6ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በጊዜ ሂደት ራሱን ቀይሮ ይሁን ወይም ከሌላ ቦታ መጥቶ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። 7ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በመላው ብሪታኒያ የተሰራጨ ቢሆንም አሁን ክምችቱ በብዛት የሚኘው በለንደንና አካባቢው ነው፡፡ ከለንደን በተጨማሪ በደቡብ ምሥራቅና በምሥራቅ ኢንግላንድም እንዲሁ በስፋት ተመዝግቧል፡፡ 8ኛ፡- ኔክስትስትሬይን የተሀዋሲ ዝርያዎችን የዘረ መል ኮድ የሚመዘግብ ድርጅት ሲሆን፣ ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ከብሪታኒያ ወደ ዴንማርክና አውስትራሊያ መዛመቱን ተናግሯል፡፡ ኔዘርላንድና ጣሊያንም ይህ አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ አገራቸው መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡ 9ኛ፡- ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ቅንጣት በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል የተባለ ሲሆን በኋላ ላይ የወጡ መረጃዎች ግን ከዚህ ብሪታኒያ ተገኘ ከተባለው ተህዋሲ ጋር የዝርያ ተመሳሳይነት የላቸውም ብለዋል፡፡ 10ኛ፡- ተህዋሲው ራሱን ቆርጦ እየቀጠለና እያባዛ ሊያመልጥ ቢችልም አሁን ወደ ገበያ እየገቡ ያሉ ክትባቶች ግን ማንነቱን ያጠፉታል፣ ፈውስም ይሆናል ተብሎ በስፋት ታምኗል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ እስከዛሬ ሌሎች ዝርያዎች ኖረውት ያውቃሉ? አዎ! ዛሬ በተለያየ ዓለም የምናገኘው የቫይረስ ዝርያ ቅንጣት ቻይና ዉሃን ከተማ ከተገኘው ዝርያ ጋር አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ አሁን በብዙ የአውሮጳ አገሮች የሚገኘው D614G የሚባል የተህዋሲ ዝርያ ዓይነት ነው። ተህዋሲው ራሱን እየቀየረ ሊመጣ ይችላል፡፡ ምናልባት መነሻው ሊሆን የሚችለው ደካማ የመከላከል አቅም ካለው በሽተኛ ራሱን ቀይሮ የተነሳ ተህዋሲ ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ታማሚ ተህዋሲውን ማሸነፍ ሲሳነው ሰውነቱ የተህዋሲው መራቢያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ እስከአሁን በዚህ ረገድ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ገና በደንብ መጠናት ይኖርበታል፡፡ ለጊዜው የሚታወቀው በከፍተኛ ፍጥነት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ብቻ ነው፡፡ ያም ሆኖ ብዙ ሰዎችን ማዳረስ ከቻለ ብዙ ሰዎች አልጋ ይይዛሉ፡፡ ይህ ደግሞ በተዘዋዋሪ ሞትን ሊጨምር ይችላል፡፡ መቶ በመቶ ባይሆንም አሁን የሚገመተው ክትባቶቹ ለዚህ ተህዋሲም ፈውስ እንደሆኑ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው አሁን ተሳኩ የተባሉት ክትባቶች የተህዋሲውን መላ አካሉንና ባህሪውን ሁሉ እንዲያጠቁ የተዘጋጁ ስለሆኑ ተህዋሲው ራሱን እያባዛ ራሱን ሊቀያይር ቢሞክርም እንኳ ከክትባቶቹ ያመልጣል ማለት ዘበት ነው ይላሉ ተመራማሪዎች፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/55391884 |
5sports
| ያልተከተቡ ስፖርተኞች በአውስትራሊያ የሜዳ ቴኒስ መወዳደር አይችሉም ተባለ | የኮሮናቫይረስ ክትባት ያልወሰዱ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾች በ2022ቱ የአውስትራሊያ ኦፕን ላይ እንዲወዳደሩ አይፈቀድላቸውም ሲሉ የውድድሩ ዳይሬክተር ክሬግ ቲሊ ተናግሩ። ከቅርብ ወራት ወዲህ የአውስትራሊያ ፖለቲከኞች የሚሰጡት ተቃራኒ አስተያየት ጉዳዩን ግራ አጋቢ አድርጎት ነበር። በ2021 በወንዶች ዘርፍ አሸናፊ የሆነው ኖቫክ ጆኮቪች ስለ ክትባቱ ሁኔታ በይፋ መግለጽ እንደማይፈልግ ተናግሯል። "ኖቫክ ለመጫወት መከተብ እንዳለበት ያውቃል።መጥቶ ቢጫወት ደስ ይለናል" ብለዋል ቲሊ። "በሚቀጥለው የፈንጆቹ ዓመት በሜልበርን ከጥር 17 አስከ 30 የሚካሄደው ውድድር ሙሉ ተመልካች ባለበት እንደሚካሄድ ቲሊ አረጋግጠዋል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የቴኒስ ተጫዋቾች አልተከተቡም። እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ በዓለም አቀፉ የቴኒስ ማኅበር ዘርፍ ከተወዳደሩ ወንዶች 35 በመቶ ያህሉ ያልተከተቡ ነበሩ። የሴቶች ቴኒስ ማኅበር በተጫዋቾቹ ዘንድ ያለውን የክትባት መጠን ለቢቢሲ ስፖርት ይፋ አላደረገም። የሴቶች ቴኒስ ማኅበር ሁሉም ተወዳዳሪዎች ወደ ሜልቦርን መጓዝ እንደሚችሉ ማወቁን የሚገልጽ ደብዳቤ ለተጫዋቾች በጥቅምት ወር ልኳል። በደብዳቤው አክሎም ሁሉም ተጫዋቾች (ተከተቡም አልተከተቡም) በጉዟቸው 72 ሰዓታት ውስጥ ቫይረሱ እንደሌለባቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማሳየት አለባቸው ብሏል። ሆኖም የቪክቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ዳንኤል አንድሪውዝ በጥቅምት ወር ያልተከተበ የቴኒስ ተጫዋች ወደ አውስትራሊያ ለመግባት ቪዛ ይሰጠዋል ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ አውስትራሊያ በጉዞ እና በእንቅስቃሴ ላይ አንዳንድ ጥብቅ ገደቦች አሳልፋለች። ለ2021 ውድድር የተጓዙ ተጫዋቾች፣ ባለስልጣናት እና ደጋፊ ሠራተኞች አውስትራሊያ ሲደርሱ ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ተገደዋል። አንዳንዶች አብረዋቸው በተጓዙት ላይ የኮሮናቫይረስ ከተገኙኘ በኋላ ክፍላቸውን ለቀው እንዲወጡ አልተፈቀደላቸውም ነበር። በዚህም በክፍላቸው ውስጥ ጊዜያዊ ልምምዶችን እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል። | ያልተከተቡ ስፖርተኞች በአውስትራሊያ የሜዳ ቴኒስ መወዳደር አይችሉም ተባለ የኮሮናቫይረስ ክትባት ያልወሰዱ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾች በ2022ቱ የአውስትራሊያ ኦፕን ላይ እንዲወዳደሩ አይፈቀድላቸውም ሲሉ የውድድሩ ዳይሬክተር ክሬግ ቲሊ ተናግሩ። ከቅርብ ወራት ወዲህ የአውስትራሊያ ፖለቲከኞች የሚሰጡት ተቃራኒ አስተያየት ጉዳዩን ግራ አጋቢ አድርጎት ነበር። በ2021 በወንዶች ዘርፍ አሸናፊ የሆነው ኖቫክ ጆኮቪች ስለ ክትባቱ ሁኔታ በይፋ መግለጽ እንደማይፈልግ ተናግሯል። "ኖቫክ ለመጫወት መከተብ እንዳለበት ያውቃል።መጥቶ ቢጫወት ደስ ይለናል" ብለዋል ቲሊ። "በሚቀጥለው የፈንጆቹ ዓመት በሜልበርን ከጥር 17 አስከ 30 የሚካሄደው ውድድር ሙሉ ተመልካች ባለበት እንደሚካሄድ ቲሊ አረጋግጠዋል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የቴኒስ ተጫዋቾች አልተከተቡም። እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ በዓለም አቀፉ የቴኒስ ማኅበር ዘርፍ ከተወዳደሩ ወንዶች 35 በመቶ ያህሉ ያልተከተቡ ነበሩ። የሴቶች ቴኒስ ማኅበር በተጫዋቾቹ ዘንድ ያለውን የክትባት መጠን ለቢቢሲ ስፖርት ይፋ አላደረገም። የሴቶች ቴኒስ ማኅበር ሁሉም ተወዳዳሪዎች ወደ ሜልቦርን መጓዝ እንደሚችሉ ማወቁን የሚገልጽ ደብዳቤ ለተጫዋቾች በጥቅምት ወር ልኳል። በደብዳቤው አክሎም ሁሉም ተጫዋቾች (ተከተቡም አልተከተቡም) በጉዟቸው 72 ሰዓታት ውስጥ ቫይረሱ እንደሌለባቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማሳየት አለባቸው ብሏል። ሆኖም የቪክቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ዳንኤል አንድሪውዝ በጥቅምት ወር ያልተከተበ የቴኒስ ተጫዋች ወደ አውስትራሊያ ለመግባት ቪዛ ይሰጠዋል ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ አውስትራሊያ በጉዞ እና በእንቅስቃሴ ላይ አንዳንድ ጥብቅ ገደቦች አሳልፋለች። ለ2021 ውድድር የተጓዙ ተጫዋቾች፣ ባለስልጣናት እና ደጋፊ ሠራተኞች አውስትራሊያ ሲደርሱ ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ተገደዋል። አንዳንዶች አብረዋቸው በተጓዙት ላይ የኮሮናቫይረስ ከተገኙኘ በኋላ ክፍላቸውን ለቀው እንዲወጡ አልተፈቀደላቸውም ነበር። በዚህም በክፍላቸው ውስጥ ጊዜያዊ ልምምዶችን እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59357889 |
5sports
| ሲቲ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የሊግ ዋንጫን በማንሳት ታሪክ ሠራ | ማንቸስተር ሲቲ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የሊግ ዋንጫን በማንሳት ታሪክ ሲሰራ ቶተንሃም አሁንም ዋንጫ አልባው ቡድን ሆኗል። ሁለቱ ቡድኖች በግዙፉ ዌምብሊ ስታድየም ተገናኝተው ሲቲ በአያሜሪክ ላፖርት ጎል አንድ ለባዶ በመርታት ዋንጫ አንስቷል። ላፖርት ጨዋታው ሊገባደድ 8 ደቂቃ ሲቀረው ከኬቪን ደ ብራይን የተሻማለትን ኳስ በጭንቅላቱ ከመረብ በማዋሃድ የቶተንሃምን የዋንጫ ተስፋ አጨልሟል። ባለፈው ሳምንት ሰኞ ጆዜ ሞውሪንሆን ያባረሩት ቶተንሃሞች በጨዋታው ተበልጠው ታይተዋል። ጨዋታው ሁለት ሺህ ከእያንዳንዱ ቡድን እንዲሁም አራት ሺህ ተጨማሪ ተመልካቾች በአጠቃላይ 8 ሺህ ደጋፊዎች በተገኙበት ነበር የተካሄደው። ሲቲ ይህን ዋንጫ አራት ጊዜ በተከታታይ በማሸነፍ የሊቨርፑልን የ1980ዎቹን ክብረ ወሰን ተጋርቷል። አልፎም ዋንጫውን በአጠቃላይ 8 ጊዜ ዋንጫ በማንሳት ከሊቨርፑል ጋር እኩል ታሪክ መሥራት ችሏል። "ተጨዋቾቼ እያደረጉ ያሉት ይህን ነው። ለመጪው ዘመን የሲቲ ተጫዋቾች ታሪክ እየሠሩ ነው የሚሄዱት" ሲሉ የሲቲው አሠልጣኝ ፔፕ ጉዋርዲዮላ አስተያየት ሰጥተዋል። "ወደ ፍፃሜው ለመድረስ ማንቸስተር ዩናይትድንና አርሰናል ረትተን ነው የመጣነው። ስለዚህ ዋንጫውን ማንሳት ይገባናል ማለት እንችላለን።" ጉዋርዲዮላ ዋንጫውን ሲያነሱ ፊታቸው በደስታና በሻምፓኝ ረስርሶ ታይቷል። ሲቲ ዘንድሮ አራት ዋንጫ ለመብላት የነበራቸው ተስፋ ባለፈው ሳምንት ከቼልሲ ጋር የኤፍ ዋንጫ ፍልሚያን በመሸነፋቸው ከሽፏል። ነገር ግን ቶተንሃም የካራባዎ ዋንጫን ከመብላት የሚያግዳቸው ቡድን ሆኖ አልተገኘም። ፔፕ ጉዋርዲዮላ ይህ በአሠልጣኝነት ዘመናቸው 30ኛ ዋንጫቸው ነው። የፕሪሚዬር ሊጉን ዋንጫ አንደኛውን እጀታ የጨበጡ ይመስላል። ቻምፒዮንስ ሊግ ለመብላትም የማይወጡት ተራራ ያለ አይመስልም። ነገሮች እየተሳኩለት የማይመስለው ቶተንሃም በሦስት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ፍፃሜ ደርሶ ዋንጫው ለተቀናቃኝ ቡድን አስረክቦ ተመልሷል። የዋንጫ ጨዋታ እያላቸው ፖርቹጋላዊውን አሠልጣኝ ሆዜ ሞውሪንሆን ያባረሩት የቶተንሃሙ ሊቀ-መንበር ዳንኤል ሌቪ ቡድናቸው የፈረሰው ሱፐር ሊግን መቀላቀሉ አስተችቷቸው ነበር። ሌቪ፤ ቡድናቸው ለዋንጫ ደርሶ ልምድ ያላቸውን አሠልጣኝ አባረው ወጣት መተካታቸው ከደጋፊዎች ተቃውሞ እንዲደርሳቸው ምክንያት ሆኗል። ከቶተንሃም ጋር ዋንጫ አንስቶ የማያውቀው የእንግሊዙ አምበል ሃሪ ኬን ከጉዳት ተመልሶ በፍፃሜው ቢጫወትም ጫና መፍጠር አልቻለም። ደቡብ ኮሪያው ሄውንግ-ሚን ሰን ከፍፃሜው በኋላ ሲያነባ ታይቷል። ቶተንሃም አምስት ጊዜ ለፍፃሜ ደርሰው ሳያሸንፉ ቀርተዋል። ባለፉት አራት የፍፃሜ ጨዋታዎች ጎል ማስቆጠር እንኳን አልቻሉም። | ሲቲ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የሊግ ዋንጫን በማንሳት ታሪክ ሠራ ማንቸስተር ሲቲ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የሊግ ዋንጫን በማንሳት ታሪክ ሲሰራ ቶተንሃም አሁንም ዋንጫ አልባው ቡድን ሆኗል። ሁለቱ ቡድኖች በግዙፉ ዌምብሊ ስታድየም ተገናኝተው ሲቲ በአያሜሪክ ላፖርት ጎል አንድ ለባዶ በመርታት ዋንጫ አንስቷል። ላፖርት ጨዋታው ሊገባደድ 8 ደቂቃ ሲቀረው ከኬቪን ደ ብራይን የተሻማለትን ኳስ በጭንቅላቱ ከመረብ በማዋሃድ የቶተንሃምን የዋንጫ ተስፋ አጨልሟል። ባለፈው ሳምንት ሰኞ ጆዜ ሞውሪንሆን ያባረሩት ቶተንሃሞች በጨዋታው ተበልጠው ታይተዋል። ጨዋታው ሁለት ሺህ ከእያንዳንዱ ቡድን እንዲሁም አራት ሺህ ተጨማሪ ተመልካቾች በአጠቃላይ 8 ሺህ ደጋፊዎች በተገኙበት ነበር የተካሄደው። ሲቲ ይህን ዋንጫ አራት ጊዜ በተከታታይ በማሸነፍ የሊቨርፑልን የ1980ዎቹን ክብረ ወሰን ተጋርቷል። አልፎም ዋንጫውን በአጠቃላይ 8 ጊዜ ዋንጫ በማንሳት ከሊቨርፑል ጋር እኩል ታሪክ መሥራት ችሏል። "ተጨዋቾቼ እያደረጉ ያሉት ይህን ነው። ለመጪው ዘመን የሲቲ ተጫዋቾች ታሪክ እየሠሩ ነው የሚሄዱት" ሲሉ የሲቲው አሠልጣኝ ፔፕ ጉዋርዲዮላ አስተያየት ሰጥተዋል። "ወደ ፍፃሜው ለመድረስ ማንቸስተር ዩናይትድንና አርሰናል ረትተን ነው የመጣነው። ስለዚህ ዋንጫውን ማንሳት ይገባናል ማለት እንችላለን።" ጉዋርዲዮላ ዋንጫውን ሲያነሱ ፊታቸው በደስታና በሻምፓኝ ረስርሶ ታይቷል። ሲቲ ዘንድሮ አራት ዋንጫ ለመብላት የነበራቸው ተስፋ ባለፈው ሳምንት ከቼልሲ ጋር የኤፍ ዋንጫ ፍልሚያን በመሸነፋቸው ከሽፏል። ነገር ግን ቶተንሃም የካራባዎ ዋንጫን ከመብላት የሚያግዳቸው ቡድን ሆኖ አልተገኘም። ፔፕ ጉዋርዲዮላ ይህ በአሠልጣኝነት ዘመናቸው 30ኛ ዋንጫቸው ነው። የፕሪሚዬር ሊጉን ዋንጫ አንደኛውን እጀታ የጨበጡ ይመስላል። ቻምፒዮንስ ሊግ ለመብላትም የማይወጡት ተራራ ያለ አይመስልም። ነገሮች እየተሳኩለት የማይመስለው ቶተንሃም በሦስት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ፍፃሜ ደርሶ ዋንጫው ለተቀናቃኝ ቡድን አስረክቦ ተመልሷል። የዋንጫ ጨዋታ እያላቸው ፖርቹጋላዊውን አሠልጣኝ ሆዜ ሞውሪንሆን ያባረሩት የቶተንሃሙ ሊቀ-መንበር ዳንኤል ሌቪ ቡድናቸው የፈረሰው ሱፐር ሊግን መቀላቀሉ አስተችቷቸው ነበር። ሌቪ፤ ቡድናቸው ለዋንጫ ደርሶ ልምድ ያላቸውን አሠልጣኝ አባረው ወጣት መተካታቸው ከደጋፊዎች ተቃውሞ እንዲደርሳቸው ምክንያት ሆኗል። ከቶተንሃም ጋር ዋንጫ አንስቶ የማያውቀው የእንግሊዙ አምበል ሃሪ ኬን ከጉዳት ተመልሶ በፍፃሜው ቢጫወትም ጫና መፍጠር አልቻለም። ደቡብ ኮሪያው ሄውንግ-ሚን ሰን ከፍፃሜው በኋላ ሲያነባ ታይቷል። ቶተንሃም አምስት ጊዜ ለፍፃሜ ደርሰው ሳያሸንፉ ቀርተዋል። ባለፉት አራት የፍፃሜ ጨዋታዎች ጎል ማስቆጠር እንኳን አልቻሉም። | https://www.bbc.com/amharic/news-56884301 |
5sports
| አትሌት ቀነኒሳ 'ከዚህ ቀደም በበርሊን ማራቶን የፈጸምኩትን ስህተት አልደግምም' አለ | አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን እሁድ በሚካሄደው የበርሊን ማራቶን ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም በበርሊን ማራቶን የፈጸምኩትን ሰህተት አልደግምም አለ። አትሌት ቀነኒሳ ከሁለት ዓመት በፊት እአአ 2019 ላይ በጀርመን መዲና በተካሄደው የማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን ለመሻሻል ሁለት ሰኮንዶች ብቻ ቀርተዉት ውድድሩን ማሸነፉ ይታወሳል። "ከውድድሩ በፊት ክብረ ወሰን ለማሻሻል አእምሮዬን አላዘጋጀሁም ነበር። ክብረ ወሰኑን ለመሻሻል አእምሮዬን ባዘጋጅ ኖሮ፤ ክብረ ወሰኑ የዚያን ዕለት ይሰበር ነበር" ሲል ቀነኒሳ ኢንስታግራም ገጹ ላይ ባጋራው ቪዲዮ ተናግሯል። ቀነኒሳ በ2019ኙ የበርሊን ማራቶን ሁለት ሰከንዶች ብቻ ቀርተውት ክብረ ወሰን ሳያሻሽል መቅረቱ "ብዙ ጊዜ ያስደነግጠኛል" ያለ ሲሆን፤ እሁድ በሚደረገው ውድድር በኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተያዘውን ሪኮርድ ለማሻሻል እቅድ እንዳለው ገልጿል። ቀነኒሳ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ በማራቶን ይሳተፋል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ኢትዮጵያን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ በተደረገው ማጣሪያ ላይ ባለመሳተፉ ከቡድኑ ውጪ መሆኑ ይታወቃል። ከቀነኒሳ ስኬቶች መካከል አትሌት ቀነኒሳ ተመራጭ ከሚያደርጋቸው ውድድሮች መካከል የበርሊን ማራቶን አንዱ መሆኑን ይናገራል። "ብዙ ሰው የሚሳተፍበት ነው። ጥሩ የአየር ጸባይ ነው። ከተማውን እወደዋለሁ፤ ንፁህ ከተማ፤ ንፁህ አየር ነው ያለው" ብሏል። ቀነኒሳ በአሁኑ ወቅት ለውድድሩ የመጨረሻ ዝግጅቱን ከአገር ውጪ እያደረገ እንደሆነም ተናግሯል። ክብረ ወሰን የሚሻሻልበት የበርሊን ማራቶን በርሊን፣ ለንዶን፣ ቦስተን እና ኒው ዮርክ ከተሞች ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸውን የማራቶን ውድድሮችን ያዘጋጃሉ። የበርሊን ማራቶን ደግሞ በተለየ መልኩ ብዙ ጊዜ ክብረ ወሰኖች የሚሻሻሉበት የውድድር መድረክ ሆኖ ቆይቷል። በዘንድሮ ውድድር የማይሳተፈው ኢሉዩድ ኪፕቼጌ እአአ 2018 ላይ ተካሂዶ በነበረው የበርሊን ማራቶን 2፡01፡39 በሆነ ሰዓት የዓለም ክብረ ወሰንን ይዟል። ቀነኒሳ ደግሞ ከአንድ ዓመት በኋላ፤ ማለትም እአአ 2019 ላይ 2፡01፡41 በሆነ ሰዓት መጨረስ ችሏል። በበርሊን ማራቶን የተሻሻሉ ክብረ ወሰኖች በእሁዱ የበርሊን ማራቶን ሌሎች ተጠባቂ አትሌቶች ከአትሌት ቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ፤ አስደናቂ ውጤት ማስመዝገብ የሚችሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳታፊ ይሆናሉ። እአአ 2017 ላይ ኪፕቼጌን ተከትሎ ኢትዮጵያዊው ጉዬ አዶላ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። የ22 ዓመት ወጣት የሆነው ኦሊቃ አዱኛም በበርሊን ማራቶን ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል አንዱ ነው። ኦሊቃ እአአ 2020 ላይ የዱባይ ማራቶንን አሸንፏል። እአአ 2021 ላይ በጃፓን የሚካሄደውን ሌክ ቢዋ ማራቶን ውድድርን ያሸነፈው ጃፓናዊው ሂዴካዙ ሂጂካታ ሌላኛው ተጠባቂ አትሌት ነው። የበርሊን ማራቶን የወንዶች ውድድር እሁድ ጠዋት ይካሄዳል። የሴቶች የማራቶን ውድድር በሴቶች የበርሊን ማራቶን ውድድር የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸዋል። ሕይወት ገ/ኪዳን ሚላን ማራቶን ላይ ያስመዘገበችውን 2፡19፡25 ፈጣን ሰዓት ይዛ ውድድሩን ትጀምራለች። የ2015 የኮፐንሃገን እና ሊዝበን ማራቶን ሻምፒዮኗ ኬንያዊቷ ፒዩሪቲ ሪኦኖሪፖ ሌላኛዋ ተጠባቂ አትሌት ነች። | አትሌት ቀነኒሳ 'ከዚህ ቀደም በበርሊን ማራቶን የፈጸምኩትን ስህተት አልደግምም' አለ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን እሁድ በሚካሄደው የበርሊን ማራቶን ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም በበርሊን ማራቶን የፈጸምኩትን ሰህተት አልደግምም አለ። አትሌት ቀነኒሳ ከሁለት ዓመት በፊት እአአ 2019 ላይ በጀርመን መዲና በተካሄደው የማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን ለመሻሻል ሁለት ሰኮንዶች ብቻ ቀርተዉት ውድድሩን ማሸነፉ ይታወሳል። "ከውድድሩ በፊት ክብረ ወሰን ለማሻሻል አእምሮዬን አላዘጋጀሁም ነበር። ክብረ ወሰኑን ለመሻሻል አእምሮዬን ባዘጋጅ ኖሮ፤ ክብረ ወሰኑ የዚያን ዕለት ይሰበር ነበር" ሲል ቀነኒሳ ኢንስታግራም ገጹ ላይ ባጋራው ቪዲዮ ተናግሯል። ቀነኒሳ በ2019ኙ የበርሊን ማራቶን ሁለት ሰከንዶች ብቻ ቀርተውት ክብረ ወሰን ሳያሻሽል መቅረቱ "ብዙ ጊዜ ያስደነግጠኛል" ያለ ሲሆን፤ እሁድ በሚደረገው ውድድር በኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተያዘውን ሪኮርድ ለማሻሻል እቅድ እንዳለው ገልጿል። ቀነኒሳ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ በማራቶን ይሳተፋል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ኢትዮጵያን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ በተደረገው ማጣሪያ ላይ ባለመሳተፉ ከቡድኑ ውጪ መሆኑ ይታወቃል። ከቀነኒሳ ስኬቶች መካከል አትሌት ቀነኒሳ ተመራጭ ከሚያደርጋቸው ውድድሮች መካከል የበርሊን ማራቶን አንዱ መሆኑን ይናገራል። "ብዙ ሰው የሚሳተፍበት ነው። ጥሩ የአየር ጸባይ ነው። ከተማውን እወደዋለሁ፤ ንፁህ ከተማ፤ ንፁህ አየር ነው ያለው" ብሏል። ቀነኒሳ በአሁኑ ወቅት ለውድድሩ የመጨረሻ ዝግጅቱን ከአገር ውጪ እያደረገ እንደሆነም ተናግሯል። ክብረ ወሰን የሚሻሻልበት የበርሊን ማራቶን በርሊን፣ ለንዶን፣ ቦስተን እና ኒው ዮርክ ከተሞች ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸውን የማራቶን ውድድሮችን ያዘጋጃሉ። የበርሊን ማራቶን ደግሞ በተለየ መልኩ ብዙ ጊዜ ክብረ ወሰኖች የሚሻሻሉበት የውድድር መድረክ ሆኖ ቆይቷል። በዘንድሮ ውድድር የማይሳተፈው ኢሉዩድ ኪፕቼጌ እአአ 2018 ላይ ተካሂዶ በነበረው የበርሊን ማራቶን 2፡01፡39 በሆነ ሰዓት የዓለም ክብረ ወሰንን ይዟል። ቀነኒሳ ደግሞ ከአንድ ዓመት በኋላ፤ ማለትም እአአ 2019 ላይ 2፡01፡41 በሆነ ሰዓት መጨረስ ችሏል። በበርሊን ማራቶን የተሻሻሉ ክብረ ወሰኖች በእሁዱ የበርሊን ማራቶን ሌሎች ተጠባቂ አትሌቶች ከአትሌት ቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ፤ አስደናቂ ውጤት ማስመዝገብ የሚችሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳታፊ ይሆናሉ። እአአ 2017 ላይ ኪፕቼጌን ተከትሎ ኢትዮጵያዊው ጉዬ አዶላ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። የ22 ዓመት ወጣት የሆነው ኦሊቃ አዱኛም በበርሊን ማራቶን ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል አንዱ ነው። ኦሊቃ እአአ 2020 ላይ የዱባይ ማራቶንን አሸንፏል። እአአ 2021 ላይ በጃፓን የሚካሄደውን ሌክ ቢዋ ማራቶን ውድድርን ያሸነፈው ጃፓናዊው ሂዴካዙ ሂጂካታ ሌላኛው ተጠባቂ አትሌት ነው። የበርሊን ማራቶን የወንዶች ውድድር እሁድ ጠዋት ይካሄዳል። የሴቶች የማራቶን ውድድር በሴቶች የበርሊን ማራቶን ውድድር የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸዋል። ሕይወት ገ/ኪዳን ሚላን ማራቶን ላይ ያስመዘገበችውን 2፡19፡25 ፈጣን ሰዓት ይዛ ውድድሩን ትጀምራለች። የ2015 የኮፐንሃገን እና ሊዝበን ማራቶን ሻምፒዮኗ ኬንያዊቷ ፒዩሪቲ ሪኦኖሪፖ ሌላኛዋ ተጠባቂ አትሌት ነች። | https://www.bbc.com/amharic/58671329 |
0business
| አዲሱ ‘የማኅበራዊ ልማት ግብር’ ኑሮን ሊያስወድድብን ይሆን? | ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት በዜጎቹ እየጨከነ ይመስላል፡፡ የሚያስጨክነው የኪሱ መመናመን ይሆናል፡፡ በቀደም ለምሳሌ የነዳጅ ድጎማን አነሳ፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ ቀረጥ ልጥልባችሁ ነው እያለ ነው፡፡ ይህ እየሆነ ያለው ግሽበቱ 33 ከመቶ በደረሰበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ አዲስ ቀረጥ አስመጪዎች ላይ ብቻ የሚጣል ቢሆንም ቁንጥጫው እነርሱ ዘንድ ይቀራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ አስመጪዎች ምንም ነገር ሲጫንባቸው እንደ ትኩስ ድንች ወደ ሸማች ሲወረውሩት ነው የኖሩት፡፡ መንግሥት ‘ትኩሱ ድንች’ በነጋዴዎች አፍ እንዲቀር ለማድረግ ደግሞ መንገዱም፣ ስልቱም፣ መላውም የለውም፡፡ ከባድም ነው፤ ለቁጥጥር፡፡ ታዲያ ምን ተሻለ? የምጣኔ ሃብት አዋቂዎች መንግሥት እንደ ዘንድሮ የተፈተነበት ዓመት የለም ይላሉ፤ በብዙ ምክንያቶች። የሰሜኑ ጦርነት ዋነኛው ነው። የኮቪድ ወረርሽኝ እና የዩክሬኑ ጦርነትን ተከታትሎ መምጣት ሌላው ነው። የነዳጅ ዋጋ መናር ደግሞ ሦስተኛው ምክንያት ነው፡፡ የሁሉም ሉላዊ ምስቅልቅ ጦሶች ዳፋቸው ለሁሉም ተርፏል። እነዚህ ነገሮች ደግሞ ከማንም ቁጥጥር ውጪ መሆናቸው ነው ጉዳቱ፡፡ መፈናቀል እና የሰላም እጦት ምርት ያሳጣሉ። ምርት ማነስ ደግሞ ገቢን ይጎዳል። በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ መንግሥት እጅ አጥሮታል፡፡ ከበጀት ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ ፈተና ገጥሞታል። የዘንድሮ ዓመታዊ በጀት ከቀደመው በ100 ቢሊዮን ብር ገደማ ይልቃል። ጥቅሉ 800 ቢሊዮን ብር ተጠግቶ ነበር። ምን ዋጋ አለው፤ የበጀት ጉድለቱም ያን ያህል ሰፊ ሆነ። መንግሥት ባመነው ከ200 እስከ 300 ቢሊዮን ብር የበጀት ክፍተት ይጠበቃል። እርግጥ ነው የኢትዮጵያ በጀት ራሱን ችሎ አያውቅም፡፡ ሁሌም እርጥባን ይሻል፡፡ በድጎማ እና በእርዳታ ነው ሰኔን የሚዘልቀው። ነገር ግን አጋሮች ጀርባቸውን ሰጥተዋል፡፡ በራሳቸው ጉዳይ ተይዘዋል። ዩክሬን ላይ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ቀዳሚ አጀንዳቸው አይደለችም። ቀሪዎቹ ለጋሾች ደግሞ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከመንግሥት ጋር ተኳርፈዋል። ምን ይሻላል? ምስጥ እንጨትን እንደሚበላው ጦርነትም ምጣኔ ሃብትን ቦርቡሮ፣ ቀረጣጥፎ ይበላል፡፡ “ይህ ጦርነት፣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም በሕዝብ መዋጮ የተደረገ ጦርነት ነው” ይላሉ፣ ለዚህ ጽሑፍ ማዳበሪያ ያነጋገርናቸው የፋይናንስ ጉዳዮች ባለሙያ አቶ አብነት በላይ፡፡ ‘በቀጥታ’ የሚሉት የቀጥታ መዋጮውን ነው፡፡ ‘በተዘዋዋሪ’ የሚሉት ደግሞ ለጦርነት የዋለው ገንዘብ ምንጭ ዞሮ ዞሮ ከሕዝብ በግብር መልክ ለመሠረተ ልማት የተሰበሰበ ገንዘብ መሆኑን ከመረዳት ነው፡፡ “ያው ሕዝብ በታክስም በምንም ወደ መንግሥት ቋት ያስገባው ገንዘብ ነው ለጦርነት የዋለው።” መንግሥትን ይበልጥ ያሽመደመደውም ለዚሁ ነው፡፡ ዘንድሮ እጅ ያጠረው በጦርነቱ ብዙ ተቋማት በመውደማቸው ብቻ አይደለም፡፡ ኮቪድ የጎዳውን ኢኮኖሚ ነው ወዲያውኑ ጦርነት የተቀበለው፡፡ ቀድሞውኑም ኮቪድ በሁሉም ሆስፒታሎች ላይ ጫና አሳድሯል። መንግሥት ለመድኃኒት የሚያወጣው ወጪ በብዙ እጥፍ ንሯል። እያንዳንዱ ሆስፒታል የበጀት ጨምሩልኝ ጥያቄን እያነሳ ያለውም ለዚሁ ነው። ምን ይሻላል? በጤናው ዘርፍ ብቻ አይደለም ፈተናው፤ በትምህርት ግንባርም ነገሩ ተመሳሳይ ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፤ እሱም ከበቃን ነው ያሉት በቅርብ ነው። እንዲህ ዓይነት ወፍራም ገንዘብ መንግሥት የለውም። በቀድሞ ጊዜ ቢሆን ከዚያም ከዚህም ብሎ ማምጣት ይቻል ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን በልመናም በብድርም የሚሞላ አልሆነም። የዓለም ባንክ ራሱ 300 ሚሊዮን ዶላር ነው የሰጠው፡፡ “አሁን አሁን ረጂዎች ለመስጠት ቃል የሚገቡት ገንዘብ አንድ ወረዳንም መልሶ የሚያለማ አይደለም” ይላሉ የፋይናንስ አዋቂ አቶ አብነት በላይ። ታዲያ ምን ተሻለ? ግብር መጨመር? መንግሥት የበጀት ጉድለትን ዜጎችን አስጨንቆ መሙላት ይችል ይሆናል። ለምሳሌ ግብርን በመጨመር፡፡ ነገር ግን አደጋ አለው። የዋጋ ንረት ያስከትላል። እንደ ሰደድ እሳት የሚቀጣጠል ንረት ሊያመጣብን ይችላል። ዜጎች ላይ የሚጣል ግብር ቤንዚን የማርከፍከፍ ያህል ነው። ለምን ገንዘብ አይታተምም ታዲያ? እሱም አደጋ አለው፡፡ ከፍተኛ አደጋ፡፡ ብር የሚያትም መንግሥትና የአልኮል ሱሰኛ አንድ ናቸው፡፡ አንድ መለኪያና አንድ ረብጣ በጨመሩ ቁጥር ሁለቱም ይሰክራሉ፡፡ በተለይ ገንዘብ ደጋግሞ የሚያትም መንግሥት በግሽበት ራሱን እስኪጥል ይሰክራል፡፡ ስለዚህ ካልተገደደ አያደርገውም፡፡ መንግሥት አሁን ያለውን የግሽበት ራስ ምታቱን ማብረድ ይፈልጋል። ቀላል ግን አይደለም። ለምን? ምክንያቱም የወጪ-ገቢ ሚዛኑ ለተዛባ አገር የዋጋ ንረትን ማቆም፣ በወንፊት ውስጥ ውሃ ለማቆር የመሞከር ያህል ፈታኝ ስለሆነ ነው። በሌላኛው ግንባር ሌላም ራስ ምታት አለ። በዚህ አገር የራስ ምታቶቹ ብዛት ራሱ ሌላ ራስ ምታት ነው፡፡ በጦርነቱ አከርካሪው የተመታው ኢኮኖሚ ለማገገም ዓመታትን ይፈልጋል። እሱም ሌላ ጦርነት ካልተቀሰቀሰ ነው። የሰሜኑ ጦርነት ከሰብአዊ ጥፋቱ ባሻገር ብዙ መሠረተ ልማትን አውድሟል። ውድመቱን ለመጠገን ቢሊዮኖች ያስፈልጋሉ። አቶ አብነት ድምሩን ወደ 500 ቢሊዮን ብር ያደርሱታል፡፡ አፋር፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል፣ ኦሮሚያ…፡፡ ጦርነቱ ግማሽ አገር ነው ያወደመው ማለት ያስደፍራል። ይህን ሁሉ መልሶ ለመገንባት የአቶ አብነትን ግምት በግማሽ እንኳ ብንቀንሰው ሩብ ትሪሊዮን ብር ከየት ይታጨዳል፡፡ ወይ ግብር ካልተጨመረ፣ ወይ ደግሞ ገንዘብ ካልታተመ ከየት ይምጣ? ከማን ይሰብሰብ? አንድ መላ መፈጠር ነበረበት። ‘የማኅበራዊ ልማት ግብር’ (Social Welfare levy) የመጣው ታዲያ ከዚህ ሁሉ “የ9 ወር” ምጥ በኋላ ነው። ብዙውን ጊዜ መንግሥት ቁልፍ የሆኑ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ ሲፈተን የሚጣል የቀረጥ ዓይነት ነው። መንግሥት በቀረጥና ግብር የሰበሰበው ጠቅላላ ገንዘብ አንሶ ምኑን ከምኑ ላድርገው ብሎ ሲጨነቅ አዲስ ገቢ ማግኛ መንገድ ያስባል። ቀደም ሲል እንዳወሳነው የትኛውም አዲስ ገቢ መሰብሰቢያ መንገድ ግን ጦስ አለው። የዋጋ ንረት እና የገንዘብ ግሽበት የሚባሉ ሁለት ጣጠኞች አሉ። እነርሱን ነካክቶ ኢኮኖሚውን የሚያበግን ነገር ሁሉ በገንዘብ አስተዳደር ላይ የባሰ ቀውስ ይፈጥራል፡፡ የተሻለው ዘዴ እንዲህ ዓይነት ወጣ ያለ አዲስ ቀረጥን ማስተዋወቅ ነው ይላሉ ባለሙያዎች። ኢትዮጵያ ብቻም ሳትሆን በርካታ አገራት መሠረታዊ አቅርቦት ለሕዝባቸው ለማድረስ ብር ሲያጥራቸው ይህን ያደርጋሉ። ‘መሠረታዊ’ የሚባለው ነገር ከአገር አገር ቢለያይም፡፡ የፋይናንስ ባለሙያው አቶ አብነት ይህን ሊያስረዱ በቅርቡ የጎበኟትን ሩሜኒያን እንደ ምሳሌ ያነሳሉ። “ኢኮኖሚያቸው ዲጂታል እየሆነ ስለመጣ ‘የዲጂታል ሊትሬሲ’ መሠረታዊ ነገር እየሆነባቸው ሄደ። መንግሥት በየአካባቢው ኢንተርኔት ማቅረብ ግዴታ ሆነበት። አለበለዚያ ማኅበራዊ አገልግሎታቸን ማቅረብ ከባድ ሊሆንበት ሆነ። በሩሜኒያ ኢንተርኔት ወደ መሠረታዊ ነገር እየተጠጋ የመጣውም ለዚያ ነው” ይላሉ። አቶ አብነት የታክስ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ ናቸው። እንደ እርሳቸው ምልከታ ከሆነ እንዲህ በተተበተበ ችግር ውስጥ ላለ መንግሥት፣ ለ114 ሚሊዮን ሕዝብ መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት ቢከብደው የሚደንቅ አይሆንም። አንደኛ ከበጀቱ ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚይዘው ማኅበራዊ አገልግሎት ነው፡፡ ሁለተኛ ብዙዎቹ ማኅበራዊ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ በመንግሥት ቀጥተኛ ወጪ የሚሸፈኑ ናቸው፡፡ አቶ አብነት “ለኔ ኢትዮጵያ የዌልፌር ስቴት ሆና ነው የምትታየኝ፤ በአቅሟ” የሚሉትን ይህን ተመርኩዘው ነው፡፡ ለዚህም ይሆናል ይህ መንግሥት ወደ አዳዲስ የቀረጥ ዓይነቶች ማማተር የጀመረው። ያማተረው ግን ወደ ዌልፌር ታክስ ብቻ አይደለም፡፡ በሌላ ጊዜ የምንመለስባቸው የ‘ፕሮፐርቲ’ [የንብረት] ታክስ እና የነዳጅ ምርቶች ላይ ያለው ኤክሳይዝ ታክስም በመደርደርያችን ላይ ናቸው፡፡ ሌላም አለ፤ በሂደት ላይ ያለ፡፡ የኢትዮጵያ 2 ሺህ ከተሞች ራሳቸውን እንዲችሉ የመንገድ ክፍያን ለማስተዋወቅ በሙከራ ደረጃ ታስቧል፡፡ መንግሥት ራሱን ከበጀት ጭንቅ ለማውጣት ገና ወደ ብዙ አቅጣጫ እንደሚያማትር እነዚህ አመላካቾች ናቸው፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በነሐሴ ወር መባቻ ላይ ባካሄደው ስብሰባ ይህን አዲስ ረቂቅ መክሮና ዘክሮ አጽድቆታል። ይህ ግብር በሁሉም ወደ አገር ቤት በሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ የተጣለ ነው። ይሁንና ነዳጅ እና ማዳበሪያ ከዝርዝሩ ወጥተዋል። ይህ ለፋይናንስ አዋቂው አቶ አብነት ብልሃት የታከለበት አካሄድ ሆኖ ይታያቸዋል። ምክንያቱም ነዳጅ እና ማዳበሪያን የሚነኩ ቀረጦች ጦሳቸው ለሰፊው ሕዝብ ስለሚደርስ፡፡ ዲፕሎማቶች የሚያስገቧቸው ዕቃዎችም ከዚህ የዌልፌር ቀረጥ ነጻ ናቸው። ይህ የሆነው ኢትዮጵያ የቪየና ኮንቬንሽን ፈራሚ በመሆኗ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ ውጪ የሱር ታክስ ግዴታ ከሆነባቸው የገቢ ዕቃዎች ውጪ ባሉት ገቢ ዕቃዎች ሁሉ አዲሱ ቀረጥ ተጭኗል። መንግሥት እንደሚለው ከሆነ በአማካይ በየዓመቱ እስከ 22 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ያስችለዋል። እዚህ ቁጥር ላይ የተደረሰው በየዓመቱ የገቢ ዕቃዎች መጠንን ከግምት በማስገባት ነው። በየዓመቱ ወደ አገር ቤት እስከ 114 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሸቀጥ ይገባል። በእያንዳንዱ ገቢ ዕቃ 3 ከመቶ ግብር ሲሰላ ወደዚህ አሐዝ ይደረሳል። የማኅበራዊ ልማት (ሶሻል ዌልፌር) ቀረጥ የግብር ምጣኔው ሦስት በመቶ ነው። መንግሥት እንደሚለው ይህ ትንሹ የግብር መጠን ሲሆን ተጽእኖ እንዳይኖረው በሚል ነው ሰፊ መሠረት እንዲኖረው ተደርጎ የተበጀ ነው። አቶ አብነት ይህ የግብር ተመን ውድ ነው ወይስ አይደለም ብለው ለመበየን ይቸገራሉ። “በገቢ ዕቃዎች ላይ ከሚጣሉ የታክስ ዓይነቶች አንጻር ከታየ በጣም ዝቅተኛው የቀረጥ ምጣኔ ሊባል ይችላል። ከወደሙ መሠረተ ልማቶች ብዛትና ከሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ስፋት አንጻር ሲታይ ደግሞ በተቃራኒው ሊታሰብ ይችላል።” ይህ ግብር በሦስት መንገድ በሕዝብ ላይ ቀጥተኛ ጫና እንዳያደርስ የተሞከረ ይመስላል፤ የናረውን ኑሮ የበለጠ እንዳያንር። አንደኛው ግብሩ የተጣለው በአስመጪዎች ላይ ብቻ መሆኑ። ሁለተኛው የግበሩ ምጣኔ አነስተኛ ተደርጎ መሰላቱ። ሦስተኛ ይህ ግብር እንደ ነዳጅ እና ማዳበሪያ ባሉት ቁልፍ ነገሮች ላይ አለመጣሉ። ይሁንና አቶ አብነት “ዞሮ ዞሮ ገንዘቡን የምናዋጣው እኛ እንጂ መንግሥት እንደሚያስበው አስመጪ ነጋዴዎች አይደሉም” ይላሉ። ይህን የሚሉት ያለ ምክንያት አይደለም። በነጋዴ ላይ የተጣለ ግብር ሄዶ ሄዶ ለሸማቹ መከፋፈሉ እሙን ስለሆነ ነው። ይህ ሲጠቃለል አዲሱ ግብር በኑሯችን ላይ መጠነኛ ቁንጥጫ ላይኖረው አይችልም፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የገንዘብ ግሽበት፣ የዋጋ ንረት እና ምጣኔ ሃብታዊ ምስቅልቅ አጋጥሟል። ነዳጅ በዓለም ገበያ ሰማይ ነክቶ ነው አሁን ቀስ በቀስ ለማረፍ እያኮበኮበ ያለው። መንግሥት ግን ከነዳጅ ድጎማው ቀስ በቀስ እየወጣ ነው። በዚያ ላይ በጦርነት የደቀቀና ገና እያገገመ ያለን ኢኮኖሚ ይዞ ነው ያለው። ታዲያ በዚህ ሁኔታ ይህ አዲስ ግብር ነገሩን ከድጡ ወደ ማጡ አያደርገውም? ለንግድና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ አብነት፣ መንግሥት ይህን ቀረጥ ማስተዋወቁ መጥፎ እርምጃ የሚባል አይደለም። እንዲያውም ከሚያመጣው ጣጣ ይልቅ በጎ ጎኑ ይታያቸዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሕዝብ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ይላሉ፡፡ ይህን የሚሉት በምክንያት ነው። ዋናው ምክንያታቸው በመንግሥት ላይ ጫናው መበርታቱን ከመገንዘብ ይመነጫል፡፡ አንደኛ ረጂዎች በዩክሬን ጉዳይ ተጠምደዋል። የረጂዎች መታከት (donors fatigue) እየታየ ነው። ሁለተኛ በጦርነት የወደመው መሠረተ ልማት ቁጥር ሥፍር የለውም። መንግሥት ይህን ክፍተት በሌላ በየትኛውም መንገድ ሊሸፍነው አይቻለውም ባይ ናቸው። መንግሥት ይህን ገንዘብ በዌልፌር መልክ ከመሰብሰብ ሌላ አማራጭ አልነበረውም ወይ ተብለው ሲጠየቁም፣ “ይህን ሐሳብ ያመጡ ሰዎች መቼስ ብዙ አማራጮችን እንዳዩ እገምታለሁ” ይላሉ፡፡ ምናልባት ሌላው አማራጭ በሕዝብ ፈቃደኝነት ላይ በተመሠረተ ተሳትፎ ገንዘቡን መሰብሰብ ሊሆን ይችል ነበር ብለውም ይገምታሉ፡፡ ይሁንና ይህም ፈተናው ቀላል እንዳልሆነ ይረዳሉ፡፡ “ሕዝቡ ለግደቡ፣ ብሎም ለተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች፣ ለመፈናቀሎች በየጊዜው ገንዘብ አዋጣ እየተባለ ተዳክሟል” ይላሉ፡፡ ሌላው መንገድ ለአቶ አብነት ከነጋዴዎች በቀጥታና በፈቃድ ገንዘብ ማሰባሰብ ነው፡፡ ይሁንና “ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር፤ መንግሥት የነጋዴውን ፊት ለማየት የፈራ ይመስለኛል” ይላሉ፡፡ ከሕዝብም ከነጋዴም ዐይን እየሸሸ ያለው መንግሥት ታድያ ይህን ገንዘብ በእጅ አዙር ለመሰብሰብ የመረጠ ይመስላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ከግምት ሲገቡ መንግሥት ለመልሶ ማልማት ገንዘብ ለማምጣት ያሰበበት መንገድ ተገቢነቱ ይጎላባቸዋል፤ ለአቶ አብነት በላይ፡፡ ይልቅ እርሳቸውን የሚያሰጋቸው የ3 በመቶ ቀረጥ መጣል አይደለም። ከዚያ ይልቅ የሚያሳስባቸው ሁለት ነገር ነው፡፡ ይህ ገንዘብ ከተሰበሰበ በኋላ ለታለመለት ዓላማ ይውላል ወይ? የሚለው አንዱ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ፣ “በመልሶ ማልማት የገነባነውን መልሰን እንዳናወድመው ነው፡፡” ከፍርሃቶቻቸው የሚልቀው ግን ይህ ነው፡፡ “ከፊት ለፊታችንስ ሌላ አውዳሚ ጦርነት እንደሌለ በምን እርግጠኛ እንሆናለን?” | አዲሱ ‘የማኅበራዊ ልማት ግብር’ ኑሮን ሊያስወድድብን ይሆን? ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግሥት በዜጎቹ እየጨከነ ይመስላል፡፡ የሚያስጨክነው የኪሱ መመናመን ይሆናል፡፡ በቀደም ለምሳሌ የነዳጅ ድጎማን አነሳ፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ ቀረጥ ልጥልባችሁ ነው እያለ ነው፡፡ ይህ እየሆነ ያለው ግሽበቱ 33 ከመቶ በደረሰበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ አዲስ ቀረጥ አስመጪዎች ላይ ብቻ የሚጣል ቢሆንም ቁንጥጫው እነርሱ ዘንድ ይቀራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ አስመጪዎች ምንም ነገር ሲጫንባቸው እንደ ትኩስ ድንች ወደ ሸማች ሲወረውሩት ነው የኖሩት፡፡ መንግሥት ‘ትኩሱ ድንች’ በነጋዴዎች አፍ እንዲቀር ለማድረግ ደግሞ መንገዱም፣ ስልቱም፣ መላውም የለውም፡፡ ከባድም ነው፤ ለቁጥጥር፡፡ ታዲያ ምን ተሻለ? የምጣኔ ሃብት አዋቂዎች መንግሥት እንደ ዘንድሮ የተፈተነበት ዓመት የለም ይላሉ፤ በብዙ ምክንያቶች። የሰሜኑ ጦርነት ዋነኛው ነው። የኮቪድ ወረርሽኝ እና የዩክሬኑ ጦርነትን ተከታትሎ መምጣት ሌላው ነው። የነዳጅ ዋጋ መናር ደግሞ ሦስተኛው ምክንያት ነው፡፡ የሁሉም ሉላዊ ምስቅልቅ ጦሶች ዳፋቸው ለሁሉም ተርፏል። እነዚህ ነገሮች ደግሞ ከማንም ቁጥጥር ውጪ መሆናቸው ነው ጉዳቱ፡፡ መፈናቀል እና የሰላም እጦት ምርት ያሳጣሉ። ምርት ማነስ ደግሞ ገቢን ይጎዳል። በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ መንግሥት እጅ አጥሮታል፡፡ ከበጀት ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ ፈተና ገጥሞታል። የዘንድሮ ዓመታዊ በጀት ከቀደመው በ100 ቢሊዮን ብር ገደማ ይልቃል። ጥቅሉ 800 ቢሊዮን ብር ተጠግቶ ነበር። ምን ዋጋ አለው፤ የበጀት ጉድለቱም ያን ያህል ሰፊ ሆነ። መንግሥት ባመነው ከ200 እስከ 300 ቢሊዮን ብር የበጀት ክፍተት ይጠበቃል። እርግጥ ነው የኢትዮጵያ በጀት ራሱን ችሎ አያውቅም፡፡ ሁሌም እርጥባን ይሻል፡፡ በድጎማ እና በእርዳታ ነው ሰኔን የሚዘልቀው። ነገር ግን አጋሮች ጀርባቸውን ሰጥተዋል፡፡ በራሳቸው ጉዳይ ተይዘዋል። ዩክሬን ላይ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ቀዳሚ አጀንዳቸው አይደለችም። ቀሪዎቹ ለጋሾች ደግሞ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከመንግሥት ጋር ተኳርፈዋል። ምን ይሻላል? ምስጥ እንጨትን እንደሚበላው ጦርነትም ምጣኔ ሃብትን ቦርቡሮ፣ ቀረጣጥፎ ይበላል፡፡ “ይህ ጦርነት፣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም በሕዝብ መዋጮ የተደረገ ጦርነት ነው” ይላሉ፣ ለዚህ ጽሑፍ ማዳበሪያ ያነጋገርናቸው የፋይናንስ ጉዳዮች ባለሙያ አቶ አብነት በላይ፡፡ ‘በቀጥታ’ የሚሉት የቀጥታ መዋጮውን ነው፡፡ ‘በተዘዋዋሪ’ የሚሉት ደግሞ ለጦርነት የዋለው ገንዘብ ምንጭ ዞሮ ዞሮ ከሕዝብ በግብር መልክ ለመሠረተ ልማት የተሰበሰበ ገንዘብ መሆኑን ከመረዳት ነው፡፡ “ያው ሕዝብ በታክስም በምንም ወደ መንግሥት ቋት ያስገባው ገንዘብ ነው ለጦርነት የዋለው።” መንግሥትን ይበልጥ ያሽመደመደውም ለዚሁ ነው፡፡ ዘንድሮ እጅ ያጠረው በጦርነቱ ብዙ ተቋማት በመውደማቸው ብቻ አይደለም፡፡ ኮቪድ የጎዳውን ኢኮኖሚ ነው ወዲያውኑ ጦርነት የተቀበለው፡፡ ቀድሞውኑም ኮቪድ በሁሉም ሆስፒታሎች ላይ ጫና አሳድሯል። መንግሥት ለመድኃኒት የሚያወጣው ወጪ በብዙ እጥፍ ንሯል። እያንዳንዱ ሆስፒታል የበጀት ጨምሩልኝ ጥያቄን እያነሳ ያለውም ለዚሁ ነው። ምን ይሻላል? በጤናው ዘርፍ ብቻ አይደለም ፈተናው፤ በትምህርት ግንባርም ነገሩ ተመሳሳይ ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፤ እሱም ከበቃን ነው ያሉት በቅርብ ነው። እንዲህ ዓይነት ወፍራም ገንዘብ መንግሥት የለውም። በቀድሞ ጊዜ ቢሆን ከዚያም ከዚህም ብሎ ማምጣት ይቻል ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን በልመናም በብድርም የሚሞላ አልሆነም። የዓለም ባንክ ራሱ 300 ሚሊዮን ዶላር ነው የሰጠው፡፡ “አሁን አሁን ረጂዎች ለመስጠት ቃል የሚገቡት ገንዘብ አንድ ወረዳንም መልሶ የሚያለማ አይደለም” ይላሉ የፋይናንስ አዋቂ አቶ አብነት በላይ። ታዲያ ምን ተሻለ? ግብር መጨመር? መንግሥት የበጀት ጉድለትን ዜጎችን አስጨንቆ መሙላት ይችል ይሆናል። ለምሳሌ ግብርን በመጨመር፡፡ ነገር ግን አደጋ አለው። የዋጋ ንረት ያስከትላል። እንደ ሰደድ እሳት የሚቀጣጠል ንረት ሊያመጣብን ይችላል። ዜጎች ላይ የሚጣል ግብር ቤንዚን የማርከፍከፍ ያህል ነው። ለምን ገንዘብ አይታተምም ታዲያ? እሱም አደጋ አለው፡፡ ከፍተኛ አደጋ፡፡ ብር የሚያትም መንግሥትና የአልኮል ሱሰኛ አንድ ናቸው፡፡ አንድ መለኪያና አንድ ረብጣ በጨመሩ ቁጥር ሁለቱም ይሰክራሉ፡፡ በተለይ ገንዘብ ደጋግሞ የሚያትም መንግሥት በግሽበት ራሱን እስኪጥል ይሰክራል፡፡ ስለዚህ ካልተገደደ አያደርገውም፡፡ መንግሥት አሁን ያለውን የግሽበት ራስ ምታቱን ማብረድ ይፈልጋል። ቀላል ግን አይደለም። ለምን? ምክንያቱም የወጪ-ገቢ ሚዛኑ ለተዛባ አገር የዋጋ ንረትን ማቆም፣ በወንፊት ውስጥ ውሃ ለማቆር የመሞከር ያህል ፈታኝ ስለሆነ ነው። በሌላኛው ግንባር ሌላም ራስ ምታት አለ። በዚህ አገር የራስ ምታቶቹ ብዛት ራሱ ሌላ ራስ ምታት ነው፡፡ በጦርነቱ አከርካሪው የተመታው ኢኮኖሚ ለማገገም ዓመታትን ይፈልጋል። እሱም ሌላ ጦርነት ካልተቀሰቀሰ ነው። የሰሜኑ ጦርነት ከሰብአዊ ጥፋቱ ባሻገር ብዙ መሠረተ ልማትን አውድሟል። ውድመቱን ለመጠገን ቢሊዮኖች ያስፈልጋሉ። አቶ አብነት ድምሩን ወደ 500 ቢሊዮን ብር ያደርሱታል፡፡ አፋር፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል፣ ኦሮሚያ…፡፡ ጦርነቱ ግማሽ አገር ነው ያወደመው ማለት ያስደፍራል። ይህን ሁሉ መልሶ ለመገንባት የአቶ አብነትን ግምት በግማሽ እንኳ ብንቀንሰው ሩብ ትሪሊዮን ብር ከየት ይታጨዳል፡፡ ወይ ግብር ካልተጨመረ፣ ወይ ደግሞ ገንዘብ ካልታተመ ከየት ይምጣ? ከማን ይሰብሰብ? አንድ መላ መፈጠር ነበረበት። ‘የማኅበራዊ ልማት ግብር’ (Social Welfare levy) የመጣው ታዲያ ከዚህ ሁሉ “የ9 ወር” ምጥ በኋላ ነው። ብዙውን ጊዜ መንግሥት ቁልፍ የሆኑ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ለማቅረብ ሲፈተን የሚጣል የቀረጥ ዓይነት ነው። መንግሥት በቀረጥና ግብር የሰበሰበው ጠቅላላ ገንዘብ አንሶ ምኑን ከምኑ ላድርገው ብሎ ሲጨነቅ አዲስ ገቢ ማግኛ መንገድ ያስባል። ቀደም ሲል እንዳወሳነው የትኛውም አዲስ ገቢ መሰብሰቢያ መንገድ ግን ጦስ አለው። የዋጋ ንረት እና የገንዘብ ግሽበት የሚባሉ ሁለት ጣጠኞች አሉ። እነርሱን ነካክቶ ኢኮኖሚውን የሚያበግን ነገር ሁሉ በገንዘብ አስተዳደር ላይ የባሰ ቀውስ ይፈጥራል፡፡ የተሻለው ዘዴ እንዲህ ዓይነት ወጣ ያለ አዲስ ቀረጥን ማስተዋወቅ ነው ይላሉ ባለሙያዎች። ኢትዮጵያ ብቻም ሳትሆን በርካታ አገራት መሠረታዊ አቅርቦት ለሕዝባቸው ለማድረስ ብር ሲያጥራቸው ይህን ያደርጋሉ። ‘መሠረታዊ’ የሚባለው ነገር ከአገር አገር ቢለያይም፡፡ የፋይናንስ ባለሙያው አቶ አብነት ይህን ሊያስረዱ በቅርቡ የጎበኟትን ሩሜኒያን እንደ ምሳሌ ያነሳሉ። “ኢኮኖሚያቸው ዲጂታል እየሆነ ስለመጣ ‘የዲጂታል ሊትሬሲ’ መሠረታዊ ነገር እየሆነባቸው ሄደ። መንግሥት በየአካባቢው ኢንተርኔት ማቅረብ ግዴታ ሆነበት። አለበለዚያ ማኅበራዊ አገልግሎታቸን ማቅረብ ከባድ ሊሆንበት ሆነ። በሩሜኒያ ኢንተርኔት ወደ መሠረታዊ ነገር እየተጠጋ የመጣውም ለዚያ ነው” ይላሉ። አቶ አብነት የታክስ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ ናቸው። እንደ እርሳቸው ምልከታ ከሆነ እንዲህ በተተበተበ ችግር ውስጥ ላለ መንግሥት፣ ለ114 ሚሊዮን ሕዝብ መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት ቢከብደው የሚደንቅ አይሆንም። አንደኛ ከበጀቱ ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚይዘው ማኅበራዊ አገልግሎት ነው፡፡ ሁለተኛ ብዙዎቹ ማኅበራዊ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ በመንግሥት ቀጥተኛ ወጪ የሚሸፈኑ ናቸው፡፡ አቶ አብነት “ለኔ ኢትዮጵያ የዌልፌር ስቴት ሆና ነው የምትታየኝ፤ በአቅሟ” የሚሉትን ይህን ተመርኩዘው ነው፡፡ ለዚህም ይሆናል ይህ መንግሥት ወደ አዳዲስ የቀረጥ ዓይነቶች ማማተር የጀመረው። ያማተረው ግን ወደ ዌልፌር ታክስ ብቻ አይደለም፡፡ በሌላ ጊዜ የምንመለስባቸው የ‘ፕሮፐርቲ’ [የንብረት] ታክስ እና የነዳጅ ምርቶች ላይ ያለው ኤክሳይዝ ታክስም በመደርደርያችን ላይ ናቸው፡፡ ሌላም አለ፤ በሂደት ላይ ያለ፡፡ የኢትዮጵያ 2 ሺህ ከተሞች ራሳቸውን እንዲችሉ የመንገድ ክፍያን ለማስተዋወቅ በሙከራ ደረጃ ታስቧል፡፡ መንግሥት ራሱን ከበጀት ጭንቅ ለማውጣት ገና ወደ ብዙ አቅጣጫ እንደሚያማትር እነዚህ አመላካቾች ናቸው፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በነሐሴ ወር መባቻ ላይ ባካሄደው ስብሰባ ይህን አዲስ ረቂቅ መክሮና ዘክሮ አጽድቆታል። ይህ ግብር በሁሉም ወደ አገር ቤት በሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ የተጣለ ነው። ይሁንና ነዳጅ እና ማዳበሪያ ከዝርዝሩ ወጥተዋል። ይህ ለፋይናንስ አዋቂው አቶ አብነት ብልሃት የታከለበት አካሄድ ሆኖ ይታያቸዋል። ምክንያቱም ነዳጅ እና ማዳበሪያን የሚነኩ ቀረጦች ጦሳቸው ለሰፊው ሕዝብ ስለሚደርስ፡፡ ዲፕሎማቶች የሚያስገቧቸው ዕቃዎችም ከዚህ የዌልፌር ቀረጥ ነጻ ናቸው። ይህ የሆነው ኢትዮጵያ የቪየና ኮንቬንሽን ፈራሚ በመሆኗ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ ውጪ የሱር ታክስ ግዴታ ከሆነባቸው የገቢ ዕቃዎች ውጪ ባሉት ገቢ ዕቃዎች ሁሉ አዲሱ ቀረጥ ተጭኗል። መንግሥት እንደሚለው ከሆነ በአማካይ በየዓመቱ እስከ 22 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ያስችለዋል። እዚህ ቁጥር ላይ የተደረሰው በየዓመቱ የገቢ ዕቃዎች መጠንን ከግምት በማስገባት ነው። በየዓመቱ ወደ አገር ቤት እስከ 114 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሸቀጥ ይገባል። በእያንዳንዱ ገቢ ዕቃ 3 ከመቶ ግብር ሲሰላ ወደዚህ አሐዝ ይደረሳል። የማኅበራዊ ልማት (ሶሻል ዌልፌር) ቀረጥ የግብር ምጣኔው ሦስት በመቶ ነው። መንግሥት እንደሚለው ይህ ትንሹ የግብር መጠን ሲሆን ተጽእኖ እንዳይኖረው በሚል ነው ሰፊ መሠረት እንዲኖረው ተደርጎ የተበጀ ነው። አቶ አብነት ይህ የግብር ተመን ውድ ነው ወይስ አይደለም ብለው ለመበየን ይቸገራሉ። “በገቢ ዕቃዎች ላይ ከሚጣሉ የታክስ ዓይነቶች አንጻር ከታየ በጣም ዝቅተኛው የቀረጥ ምጣኔ ሊባል ይችላል። ከወደሙ መሠረተ ልማቶች ብዛትና ከሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ስፋት አንጻር ሲታይ ደግሞ በተቃራኒው ሊታሰብ ይችላል።” ይህ ግብር በሦስት መንገድ በሕዝብ ላይ ቀጥተኛ ጫና እንዳያደርስ የተሞከረ ይመስላል፤ የናረውን ኑሮ የበለጠ እንዳያንር። አንደኛው ግብሩ የተጣለው በአስመጪዎች ላይ ብቻ መሆኑ። ሁለተኛው የግበሩ ምጣኔ አነስተኛ ተደርጎ መሰላቱ። ሦስተኛ ይህ ግብር እንደ ነዳጅ እና ማዳበሪያ ባሉት ቁልፍ ነገሮች ላይ አለመጣሉ። ይሁንና አቶ አብነት “ዞሮ ዞሮ ገንዘቡን የምናዋጣው እኛ እንጂ መንግሥት እንደሚያስበው አስመጪ ነጋዴዎች አይደሉም” ይላሉ። ይህን የሚሉት ያለ ምክንያት አይደለም። በነጋዴ ላይ የተጣለ ግብር ሄዶ ሄዶ ለሸማቹ መከፋፈሉ እሙን ስለሆነ ነው። ይህ ሲጠቃለል አዲሱ ግብር በኑሯችን ላይ መጠነኛ ቁንጥጫ ላይኖረው አይችልም፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የገንዘብ ግሽበት፣ የዋጋ ንረት እና ምጣኔ ሃብታዊ ምስቅልቅ አጋጥሟል። ነዳጅ በዓለም ገበያ ሰማይ ነክቶ ነው አሁን ቀስ በቀስ ለማረፍ እያኮበኮበ ያለው። መንግሥት ግን ከነዳጅ ድጎማው ቀስ በቀስ እየወጣ ነው። በዚያ ላይ በጦርነት የደቀቀና ገና እያገገመ ያለን ኢኮኖሚ ይዞ ነው ያለው። ታዲያ በዚህ ሁኔታ ይህ አዲስ ግብር ነገሩን ከድጡ ወደ ማጡ አያደርገውም? ለንግድና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ አብነት፣ መንግሥት ይህን ቀረጥ ማስተዋወቁ መጥፎ እርምጃ የሚባል አይደለም። እንዲያውም ከሚያመጣው ጣጣ ይልቅ በጎ ጎኑ ይታያቸዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሕዝብ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ይላሉ፡፡ ይህን የሚሉት በምክንያት ነው። ዋናው ምክንያታቸው በመንግሥት ላይ ጫናው መበርታቱን ከመገንዘብ ይመነጫል፡፡ አንደኛ ረጂዎች በዩክሬን ጉዳይ ተጠምደዋል። የረጂዎች መታከት (donors fatigue) እየታየ ነው። ሁለተኛ በጦርነት የወደመው መሠረተ ልማት ቁጥር ሥፍር የለውም። መንግሥት ይህን ክፍተት በሌላ በየትኛውም መንገድ ሊሸፍነው አይቻለውም ባይ ናቸው። መንግሥት ይህን ገንዘብ በዌልፌር መልክ ከመሰብሰብ ሌላ አማራጭ አልነበረውም ወይ ተብለው ሲጠየቁም፣ “ይህን ሐሳብ ያመጡ ሰዎች መቼስ ብዙ አማራጮችን እንዳዩ እገምታለሁ” ይላሉ፡፡ ምናልባት ሌላው አማራጭ በሕዝብ ፈቃደኝነት ላይ በተመሠረተ ተሳትፎ ገንዘቡን መሰብሰብ ሊሆን ይችል ነበር ብለውም ይገምታሉ፡፡ ይሁንና ይህም ፈተናው ቀላል እንዳልሆነ ይረዳሉ፡፡ “ሕዝቡ ለግደቡ፣ ብሎም ለተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች፣ ለመፈናቀሎች በየጊዜው ገንዘብ አዋጣ እየተባለ ተዳክሟል” ይላሉ፡፡ ሌላው መንገድ ለአቶ አብነት ከነጋዴዎች በቀጥታና በፈቃድ ገንዘብ ማሰባሰብ ነው፡፡ ይሁንና “ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር፤ መንግሥት የነጋዴውን ፊት ለማየት የፈራ ይመስለኛል” ይላሉ፡፡ ከሕዝብም ከነጋዴም ዐይን እየሸሸ ያለው መንግሥት ታድያ ይህን ገንዘብ በእጅ አዙር ለመሰብሰብ የመረጠ ይመስላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ከግምት ሲገቡ መንግሥት ለመልሶ ማልማት ገንዘብ ለማምጣት ያሰበበት መንገድ ተገቢነቱ ይጎላባቸዋል፤ ለአቶ አብነት በላይ፡፡ ይልቅ እርሳቸውን የሚያሰጋቸው የ3 በመቶ ቀረጥ መጣል አይደለም። ከዚያ ይልቅ የሚያሳስባቸው ሁለት ነገር ነው፡፡ ይህ ገንዘብ ከተሰበሰበ በኋላ ለታለመለት ዓላማ ይውላል ወይ? የሚለው አንዱ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ፣ “በመልሶ ማልማት የገነባነውን መልሰን እንዳናወድመው ነው፡፡” ከፍርሃቶቻቸው የሚልቀው ግን ይህ ነው፡፡ “ከፊት ለፊታችንስ ሌላ አውዳሚ ጦርነት እንደሌለ በምን እርግጠኛ እንሆናለን?” | https://www.bbc.com/amharic/articles/cw97er27x2qo |
0business
| ኮሮናቫይረስ ያቀጣጠለው የቻይናና የአሜሪካ ፉክክር በአፍሪካ | ዘግየት ብሎ የኮሮናቫይረስ በተከሰተባት አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ አሜሪካና ቻይናም ለአህጉሪቱ ከፍተኛ ድጋፍ በመስጠት እኔ እበልጣለሁ በሚል እሰጣገባና እሽቅድምድሞሽ ተጠምደዋል። ሁለቱ አገራት እያደረጉት ያለው ፉክክር በአፍሪካ የቫይረሱን ስርጭት ከመቆጣጠር በዘለለ ኃያልነታቸውን የማስፈን ተግባር እንደሆነ የቢቢሲ አፍሪካ ዘጋቢው አንድሪው ሃርዲንግ ያትታል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ ከሰሞኑ "በአፍሪካ ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ትግል የሚደግፍ ከአሜሪካ በላይ አገር ከየትም አይመጣም" ያሉ ሲሆን አክለውም "ለዓለም አቀፉ የጤና ሥርዓት አሜሪካ እንደምታደርገው ድጋፍ የትኛውም አገር አድርጎ አያውቅም፤ መቼም አይደረግም" ብለዋል። ማይክ ፖምፔዮ ይሄንን ያሉት በአፍሪካ ውስጥ ካሉ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ነው። የቢቢሲው አንድሪው ሃርዲንግም 'አንዱ እኔ ነበርኩ" ይላል። ባለፈው ወርም እንዲሁ በትራምፕ አስተዳደደር የተለመደውን "ማንኛውም አገር ከእኛ በበለጠ አይሰራም" የሚለውን ንግግር ከአሜሪካ ባለስልጣናት የተሰማ ሲሆን፤ እንዲህ አይነት ተደጋጋሚ ንግግርም የሚሰማው አገሪቱ ለዓለም ጤና ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ ከማቋረጧ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ትችቶችን ፀጥ ለማሰኘት ነው። በተለይም አሜሪካ ለድርጅቱ ታደርገው የነበረውን ድጋፍ ይህ ዓለም አቀፍ ቀውስ ጣራ በነካበት ወቅት ከማቋረጧ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ወቀሳቸውን አሰምተዋል። አሜሪካም ከዚህ ለማምለጥ ጥረት እያደረገች ነው። ማይክ ፖምፔዮ አሜሪካ ለአፍሪካ አድርጋዋለች ብለው ከሚኮሩበት የገንዘብ እርዳታ መጠን በቅርቡ የተለገሰው 170 ሚሊዮን ዶላር ነው። ነገር ግን ይህ የገንዘብ መጠን ከቻይና እንደ አገር ከተሰጠው ቀርቶ ቻይናዊው ቢሊየነር ጃክማ ከሰጠው ጋር ሲወዳደር ያንሳል። ከሰሞኑ የአሜሪካና የቻይና ባለስልጣናት አህጉሪቷ ጋር በተያያዘ የሚያደርጓቸውን ንግግሮችን ለታዘበ አፍሪካ ለሁለቱ ኃያላት አገራት አዲሱ የቀዝቃዛ ጦርነት ሜዳ መሆኗን ለመረዳት አይቸገግርም። ከዚህ ቀደምም ሁለቱ አገራት የነበራቸው የቃላት ጦርነት በኮቪድ-19 ቀውስ የተባባሰ ሲሆን አህጉሪቷንም ማዕከል በማድረግ ወደ ውክልና ጦርነት እያመሩ ይመስላሉ። "የከሸፈው መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ" በቅርቡ በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ስር ያለው ግሎባል ታይምስ ይዞት በወጣው ፅሁፍ አገሪቱ እያራመደች ያለችው የፖለቲካ ሥርዓት የኮቪድ-19ን ስርጭት ለመግታት እንዴት እንደጠቀማት ያትታል። በመቀጠልም የከሸፈው የምዕራባውያን መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ በአፍሪካ አገራት ላይ ኢ-ፍትሃዊነት፣ ተበላላጭነት፣ የብሔርና የሐይማኖት መከፋፈል፣ ግጭት እንዲሁም የህይወት መጥፋትና የንብረት መውድም ማስከተሉን አስፍሯል። እናም አፍሪካውያን ከዚህ ከከሸፈ ሙከራ ራሳቸውን ገሸሽ በማድረግ የቻይናን የአንድ ፓርቲ መንገድ ሊከተሉ እንደሚገባም ምክር ለግሷል። በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ስር ያለ ዕለታዊ የቻይና ጋዜጣም እንዲሁ ቻይና በአህጉሪቷ መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ እያፈሰሰችው ያለችውን መዋዕለ ንዋይና ኢንቨስትመንት አፍሪካን ከታሪካዊ ጭቆና እንዲሁም አሁን ካለችበት መበዝበዝ ያድናታል ብሏል። "አፍሪካ ለምዕተ ዓመታት በባርነት ቀንበር፣ ቅኝ ግዛት፣ እጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ አሁን ደግሞ በኮሮናቫይረስ ቀውስ ውስጥ ገብታለች። የቻይና የመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ አላማም አህጉሪቱ ከዚህ አዙሪት እንድትወጣና እንድታገግም ነው" በሚልም አስፍሯል። የቻይና መንግሥት ለአፍሪካ እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት ማንቆለጳጰስ ለማይክ ፖምፔዮ አልተዋጠላቸውም። የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ በአፍሪካውያን ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍና ለረዥም ዘመናት የሚቆይ የእዳ ጫና እየከመረባቸው ነው ሲሉ ወርፈዋል። በቅርብ ቀናትም የቻይናና አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ አንድ ውይይትም ተደርጎ ነበር። የውይይቱ አስተናባሪ ሁለቱ አገራት በአህጉሪቱ ላይ የሚያደርጉትን እሽቅድምድም "መርዛማ" ብለውታል። በወቅቱም አንድ የቻይና ፐሮፌሰር ኮሮናቫይረስ ለአፍሪካውያን ጋዜጠኞች የቻይናን የሚዲያ እሴቶችና ጥሩ ተሞክሮ እንዲያደንቁ አድርጓቸዋል ብለዋል። "የምዕራባውያን ሚዲያ በጨለምተኛ ዜና የተሞላ ነው፤ ሁሌም አሉታዊ ነው" ያሉት ፕሮፌሰር ዛንግ ያንኪዩ በእንደዚህ አይነት ቀውስ ወቅት ግን ተስፋን የሚፈነጥቁ ታሪኮችን ሰዎች ማንበብ ይፈልጋሉ ብለዋል። በሌላ መንገድ አፍሪካውያን የቻይና የሚዲያ ሞዴል የሆነውን 'ገንቢ ጋዜጠኝነት'ን (constructive journalism) ይፈልጋሉ ብለዋል። በቅርቡም ፕሮፌሰሯ በኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ዘንድ ለገንቢ ጋዜጠኝነት ያላቸውን ጉጉትና ፍላጎት መታዘባቸውን አስረድተዋል። ነገር ግን ጥያቄው የአፍሪካ ጋዜጠኝነት እንዲህ በቀላሉ ተፅእኖ ውስጥ የሚወድቅ ነው? በንግግራቸው አወዛጋቢ የሚባሉት ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ መድኃኒቱ ፀረ-ተህዋሲ (ዲስኢንፌክታንት መጠቀም) እንዲሁም የፀሐይ ጨረር ፈውስ ነው ማለታቸው በአፍሪካውያን ዘንድ ያላቸውን ስም የበለጠ አላጠለሸውም ወይ ተብለው የተጠየቁት ማይክ ፖምፔዮ በቀጥታ አልመለሱም። ነገር ግን ትራምፕ የሚያደርጓቸው ንግግሮችን ብዙ ሰው እንደማይረዳው እንዲሁም በመንግሥት ቁጥጥር ስር ባሉ ሚዲያዎች ሆን ተብሎ ሌላ ትርጉም ይሰጣቸዋል ብለዋል። ከማይክ ፖምፔዮ ጋር የነበረው ቆይታ ለበርካታ ጋዜጠኞች እንግዳ የሆነ ክስተት የተስተናገደበት ነበር። ለአስርት ዓመታት አሜሪካ በአፍሪካ የምትከተለው ዲፕሎማሲ በተወሰነ ደረጃ አምባገነን መንግሥታትን የሚቃወም፣ ከሳንሱር ነፃና ገለልተኛ ጋዜጠኝነትን መሰረት ያደረገ ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሚተቿቸውን የአገራቸውን ጋዜጠኞች "ሐሰተኛ" "የሕዝብ ጠላት" በማለት መወንጀልና ማዋረድ የየዕለት ሥራቸው ሆኗል። ምናልባትም የአሜሪካና የቻይና ገንቢ የጋዜጠኝነት ሃሳብ መንግሥትን አለመተቸት ከሆነ እሳቤያቸው ተቀራርቧል ማለት ይቻላል። በቀድሞው የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር ወቅት አሜሪካ ፔፕፋር በተባለው ፕሮግራም ለኤድስ የሚውል እርዳታን ለአፍሪካ የጤና ሥርዓት ተለግሷል። አሜሪካ ካላት የውስጥ ትግልና መከፋፈል ጋር ተያይዞ በአሁኑ ሰዓት ቻይና የኮሮናቫይረስን ሽፋን በማድረግ በአፍሪካ ላይ ፖለቲካዊ አጀንዳዋን ለማስረፅና አሻራም ለማሳረፍ ጥረት እያደረገች ትገኛለች። የአፍሪካ አገራትም ሆነ ጋዜጠኞች ባለው የልዕለ ኃያላን ጉልበት ተጽእኖ ተንበርክከው የሚያሸረግዱ ላይሆኑ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን በርካታ አገራትም ባለባቸው ከፍተኛ የቻይና የብድር ጫና እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ባስከተለው የኢኮኖሚ ድቀት የተነሳ "የከሸፈ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን" ገሸሽ በማድረግ የቻይናን የፖለቲካ ሥርአት ይቀበሉ ይሆን? የምናየው ይሆናል። | ኮሮናቫይረስ ያቀጣጠለው የቻይናና የአሜሪካ ፉክክር በአፍሪካ ዘግየት ብሎ የኮሮናቫይረስ በተከሰተባት አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ አሜሪካና ቻይናም ለአህጉሪቱ ከፍተኛ ድጋፍ በመስጠት እኔ እበልጣለሁ በሚል እሰጣገባና እሽቅድምድሞሽ ተጠምደዋል። ሁለቱ አገራት እያደረጉት ያለው ፉክክር በአፍሪካ የቫይረሱን ስርጭት ከመቆጣጠር በዘለለ ኃያልነታቸውን የማስፈን ተግባር እንደሆነ የቢቢሲ አፍሪካ ዘጋቢው አንድሪው ሃርዲንግ ያትታል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ ከሰሞኑ "በአፍሪካ ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ትግል የሚደግፍ ከአሜሪካ በላይ አገር ከየትም አይመጣም" ያሉ ሲሆን አክለውም "ለዓለም አቀፉ የጤና ሥርዓት አሜሪካ እንደምታደርገው ድጋፍ የትኛውም አገር አድርጎ አያውቅም፤ መቼም አይደረግም" ብለዋል። ማይክ ፖምፔዮ ይሄንን ያሉት በአፍሪካ ውስጥ ካሉ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ነው። የቢቢሲው አንድሪው ሃርዲንግም 'አንዱ እኔ ነበርኩ" ይላል። ባለፈው ወርም እንዲሁ በትራምፕ አስተዳደደር የተለመደውን "ማንኛውም አገር ከእኛ በበለጠ አይሰራም" የሚለውን ንግግር ከአሜሪካ ባለስልጣናት የተሰማ ሲሆን፤ እንዲህ አይነት ተደጋጋሚ ንግግርም የሚሰማው አገሪቱ ለዓለም ጤና ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ ከማቋረጧ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ትችቶችን ፀጥ ለማሰኘት ነው። በተለይም አሜሪካ ለድርጅቱ ታደርገው የነበረውን ድጋፍ ይህ ዓለም አቀፍ ቀውስ ጣራ በነካበት ወቅት ከማቋረጧ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ወቀሳቸውን አሰምተዋል። አሜሪካም ከዚህ ለማምለጥ ጥረት እያደረገች ነው። ማይክ ፖምፔዮ አሜሪካ ለአፍሪካ አድርጋዋለች ብለው ከሚኮሩበት የገንዘብ እርዳታ መጠን በቅርቡ የተለገሰው 170 ሚሊዮን ዶላር ነው። ነገር ግን ይህ የገንዘብ መጠን ከቻይና እንደ አገር ከተሰጠው ቀርቶ ቻይናዊው ቢሊየነር ጃክማ ከሰጠው ጋር ሲወዳደር ያንሳል። ከሰሞኑ የአሜሪካና የቻይና ባለስልጣናት አህጉሪቷ ጋር በተያያዘ የሚያደርጓቸውን ንግግሮችን ለታዘበ አፍሪካ ለሁለቱ ኃያላት አገራት አዲሱ የቀዝቃዛ ጦርነት ሜዳ መሆኗን ለመረዳት አይቸገግርም። ከዚህ ቀደምም ሁለቱ አገራት የነበራቸው የቃላት ጦርነት በኮቪድ-19 ቀውስ የተባባሰ ሲሆን አህጉሪቷንም ማዕከል በማድረግ ወደ ውክልና ጦርነት እያመሩ ይመስላሉ። "የከሸፈው መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ" በቅርቡ በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ስር ያለው ግሎባል ታይምስ ይዞት በወጣው ፅሁፍ አገሪቱ እያራመደች ያለችው የፖለቲካ ሥርዓት የኮቪድ-19ን ስርጭት ለመግታት እንዴት እንደጠቀማት ያትታል። በመቀጠልም የከሸፈው የምዕራባውያን መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ በአፍሪካ አገራት ላይ ኢ-ፍትሃዊነት፣ ተበላላጭነት፣ የብሔርና የሐይማኖት መከፋፈል፣ ግጭት እንዲሁም የህይወት መጥፋትና የንብረት መውድም ማስከተሉን አስፍሯል። እናም አፍሪካውያን ከዚህ ከከሸፈ ሙከራ ራሳቸውን ገሸሽ በማድረግ የቻይናን የአንድ ፓርቲ መንገድ ሊከተሉ እንደሚገባም ምክር ለግሷል። በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ስር ያለ ዕለታዊ የቻይና ጋዜጣም እንዲሁ ቻይና በአህጉሪቷ መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ እያፈሰሰችው ያለችውን መዋዕለ ንዋይና ኢንቨስትመንት አፍሪካን ከታሪካዊ ጭቆና እንዲሁም አሁን ካለችበት መበዝበዝ ያድናታል ብሏል። "አፍሪካ ለምዕተ ዓመታት በባርነት ቀንበር፣ ቅኝ ግዛት፣ እጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ አሁን ደግሞ በኮሮናቫይረስ ቀውስ ውስጥ ገብታለች። የቻይና የመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ አላማም አህጉሪቱ ከዚህ አዙሪት እንድትወጣና እንድታገግም ነው" በሚልም አስፍሯል። የቻይና መንግሥት ለአፍሪካ እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት ማንቆለጳጰስ ለማይክ ፖምፔዮ አልተዋጠላቸውም። የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ በአፍሪካውያን ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍና ለረዥም ዘመናት የሚቆይ የእዳ ጫና እየከመረባቸው ነው ሲሉ ወርፈዋል። በቅርብ ቀናትም የቻይናና አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ አንድ ውይይትም ተደርጎ ነበር። የውይይቱ አስተናባሪ ሁለቱ አገራት በአህጉሪቱ ላይ የሚያደርጉትን እሽቅድምድም "መርዛማ" ብለውታል። በወቅቱም አንድ የቻይና ፐሮፌሰር ኮሮናቫይረስ ለአፍሪካውያን ጋዜጠኞች የቻይናን የሚዲያ እሴቶችና ጥሩ ተሞክሮ እንዲያደንቁ አድርጓቸዋል ብለዋል። "የምዕራባውያን ሚዲያ በጨለምተኛ ዜና የተሞላ ነው፤ ሁሌም አሉታዊ ነው" ያሉት ፕሮፌሰር ዛንግ ያንኪዩ በእንደዚህ አይነት ቀውስ ወቅት ግን ተስፋን የሚፈነጥቁ ታሪኮችን ሰዎች ማንበብ ይፈልጋሉ ብለዋል። በሌላ መንገድ አፍሪካውያን የቻይና የሚዲያ ሞዴል የሆነውን 'ገንቢ ጋዜጠኝነት'ን (constructive journalism) ይፈልጋሉ ብለዋል። በቅርቡም ፕሮፌሰሯ በኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ዘንድ ለገንቢ ጋዜጠኝነት ያላቸውን ጉጉትና ፍላጎት መታዘባቸውን አስረድተዋል። ነገር ግን ጥያቄው የአፍሪካ ጋዜጠኝነት እንዲህ በቀላሉ ተፅእኖ ውስጥ የሚወድቅ ነው? በንግግራቸው አወዛጋቢ የሚባሉት ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ መድኃኒቱ ፀረ-ተህዋሲ (ዲስኢንፌክታንት መጠቀም) እንዲሁም የፀሐይ ጨረር ፈውስ ነው ማለታቸው በአፍሪካውያን ዘንድ ያላቸውን ስም የበለጠ አላጠለሸውም ወይ ተብለው የተጠየቁት ማይክ ፖምፔዮ በቀጥታ አልመለሱም። ነገር ግን ትራምፕ የሚያደርጓቸው ንግግሮችን ብዙ ሰው እንደማይረዳው እንዲሁም በመንግሥት ቁጥጥር ስር ባሉ ሚዲያዎች ሆን ተብሎ ሌላ ትርጉም ይሰጣቸዋል ብለዋል። ከማይክ ፖምፔዮ ጋር የነበረው ቆይታ ለበርካታ ጋዜጠኞች እንግዳ የሆነ ክስተት የተስተናገደበት ነበር። ለአስርት ዓመታት አሜሪካ በአፍሪካ የምትከተለው ዲፕሎማሲ በተወሰነ ደረጃ አምባገነን መንግሥታትን የሚቃወም፣ ከሳንሱር ነፃና ገለልተኛ ጋዜጠኝነትን መሰረት ያደረገ ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሚተቿቸውን የአገራቸውን ጋዜጠኞች "ሐሰተኛ" "የሕዝብ ጠላት" በማለት መወንጀልና ማዋረድ የየዕለት ሥራቸው ሆኗል። ምናልባትም የአሜሪካና የቻይና ገንቢ የጋዜጠኝነት ሃሳብ መንግሥትን አለመተቸት ከሆነ እሳቤያቸው ተቀራርቧል ማለት ይቻላል። በቀድሞው የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር ወቅት አሜሪካ ፔፕፋር በተባለው ፕሮግራም ለኤድስ የሚውል እርዳታን ለአፍሪካ የጤና ሥርዓት ተለግሷል። አሜሪካ ካላት የውስጥ ትግልና መከፋፈል ጋር ተያይዞ በአሁኑ ሰዓት ቻይና የኮሮናቫይረስን ሽፋን በማድረግ በአፍሪካ ላይ ፖለቲካዊ አጀንዳዋን ለማስረፅና አሻራም ለማሳረፍ ጥረት እያደረገች ትገኛለች። የአፍሪካ አገራትም ሆነ ጋዜጠኞች ባለው የልዕለ ኃያላን ጉልበት ተጽእኖ ተንበርክከው የሚያሸረግዱ ላይሆኑ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን በርካታ አገራትም ባለባቸው ከፍተኛ የቻይና የብድር ጫና እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ባስከተለው የኢኮኖሚ ድቀት የተነሳ "የከሸፈ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን" ገሸሽ በማድረግ የቻይናን የፖለቲካ ሥርአት ይቀበሉ ይሆን? የምናየው ይሆናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-52975241 |
3politics
| ህወሓት በክልሉ ያሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን አስጠነቀቀ | የትግራይ ክልልን በበላይነት እየመራ የሚገኘው ህወሓት በትግራይ ክልል ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶችን የትግራይ ሕዝብን ትግል “እንዳያደናቅፉ” አስጠነቀቀ። ህወሓት ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ የክልሉ ቴሌቪዥን እንደዘገበው፣ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች “ሕዝባዊ ትግላችንን የሚያደናቅፉ እንቅስቃሴዎች አድርገዋል” ብሏል። በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት)፣ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ (ውናት) እንዲሁም ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) የተባሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጦርነቱን በተመለከተ እና በክልሉ አስተዳደር ላይ በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ በክልሉ ሁሉን አቀፍ የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም መጠየቃቸው ይታወሳል። ፓርቲዎቹ ክልሉን በማስተዳደር በኩል በህወሓት ሕጋዊነት ላይ ጥያቄ በማንሳት፣ ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን ጦርነት ለማብቃት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ይካሄዳል በተባለው ድርድር ላይ ህወሓት ትግራይን ወክሎ የመደራደርም ሆነ ክልሉን በብቸኝነት ማስተዳደር የለበትም ብለዋል። በትግራይ ሕዝብ የኮሙኒኬሽን ቢሮ እና መንግሥት አማካይነት ወጣ በተባለው መግለጫ፣ “ቀደምት ታጋዮች ለሕዝቡ ህልውና በተደጋጋሚ መስዋዕትንት እየከፈሉ” መሆኑን ጠቅሶ፣ ነገር ግን ተቃዋሚዎቹ “የሚከፈለውን መስዋዕትነት በሚያሳንስ ሁኔታ በትግራይ መንግሥት ላይ ክሶችን እያቀረቡ ነው” ብሏል። ጨምሮም ተቃዋሚዎቹ “በትግራይ ሕዝብ እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ ጦርነት ለማደናቀፍ ጥረት እያደረጉ ነው” ሲል ከሷቸዋል። ተቃዋሚዎቹ ህወሓት ከዚህ በፊት በፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት ያላገኘ ክልላዊ ምርጫዎች በማካሄድ ‘የሕዝብ ተቀባይነት’ አግኝቻለሁ በማለት ሥልጣኑን አጠናክሯል በማለት፣ ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ ከሥልጣኑ መወገዱን ጠቅሰው ሕጋዊ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል። ህወሓት በመግለጫው ላይ ተቃዋሚዎቹ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ከዚህ በኋላ እንደማይታገሰው አመልክቷል። “ምንም እንኳን የትግራይ መንግሥት እራሳቸውን ያርማሉ ብሎ ቢታገሳቸውም፣ ትግላችንን ከማደናቀፍ አልታቀቡም” ብሏል። ይህንንም በማንሳት በመግለጫው ላይ ተቃዋሚዎቹ በትግራይ ያለው ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ፈርሷል ስለዚህም የሽግግር መንግሥት ወይም የአንድነት መንግሥት እንዲቋቋም ጠይቀዋል ይህም “ትግሉን በሚያደናቅፍ ሁኔታ የትግራይ መንግሥት ሕጋዊ አይደለም አስከ ማለት ደርሰዋል” ብሏል። ጨምሮም ተቃዋሚ ቡድኖቹ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የተቀሰቀሰውን የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስቆም ህወሓት ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ለመደራደር ሥልጣን የለውም ብለዋል። “በአሁኑ ወቅት ትግላችንን የሚያደናቅፍ ተግባራት ላይ አተኩረዋል፤ የትግራይ ክልል መንግሥት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሰላም ንግግር ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን የለውም” ማለታቸውንም ጠቅሷል። ስለዚህም ተቃዋሚዎቹ “በቃችሁ ሊባሉ ይገባቸዋል። የትግራይ ሕዝብም ሥርዓት ሊያሲዛቸው ይገባል” ብሏል የህወሓት መግለጫ። ለ20 ወራት የዘለቀውን የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት ለመቋጨት ተዋጊ ኃይሎች ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ከተለያዩ ወገኖች ጥያቄ ሲቀርብ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የሚደራደሩ ሰባት አባላት ያሉት የኮሚቴ ይፋ ካደረገ በኋላ፤ ህወሓትም ከቀናት በፊት ከመንግሥት ጋር ድርድር የሚያደርግ ቡድን ማቋቋሙን ገልጿል። | ህወሓት በክልሉ ያሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን አስጠነቀቀ የትግራይ ክልልን በበላይነት እየመራ የሚገኘው ህወሓት በትግራይ ክልል ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶችን የትግራይ ሕዝብን ትግል “እንዳያደናቅፉ” አስጠነቀቀ። ህወሓት ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ የክልሉ ቴሌቪዥን እንደዘገበው፣ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች “ሕዝባዊ ትግላችንን የሚያደናቅፉ እንቅስቃሴዎች አድርገዋል” ብሏል። በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት)፣ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ (ውናት) እንዲሁም ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) የተባሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጦርነቱን በተመለከተ እና በክልሉ አስተዳደር ላይ በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ በክልሉ ሁሉን አቀፍ የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም መጠየቃቸው ይታወሳል። ፓርቲዎቹ ክልሉን በማስተዳደር በኩል በህወሓት ሕጋዊነት ላይ ጥያቄ በማንሳት፣ ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን ጦርነት ለማብቃት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ይካሄዳል በተባለው ድርድር ላይ ህወሓት ትግራይን ወክሎ የመደራደርም ሆነ ክልሉን በብቸኝነት ማስተዳደር የለበትም ብለዋል። በትግራይ ሕዝብ የኮሙኒኬሽን ቢሮ እና መንግሥት አማካይነት ወጣ በተባለው መግለጫ፣ “ቀደምት ታጋዮች ለሕዝቡ ህልውና በተደጋጋሚ መስዋዕትንት እየከፈሉ” መሆኑን ጠቅሶ፣ ነገር ግን ተቃዋሚዎቹ “የሚከፈለውን መስዋዕትነት በሚያሳንስ ሁኔታ በትግራይ መንግሥት ላይ ክሶችን እያቀረቡ ነው” ብሏል። ጨምሮም ተቃዋሚዎቹ “በትግራይ ሕዝብ እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ ጦርነት ለማደናቀፍ ጥረት እያደረጉ ነው” ሲል ከሷቸዋል። ተቃዋሚዎቹ ህወሓት ከዚህ በፊት በፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት ያላገኘ ክልላዊ ምርጫዎች በማካሄድ ‘የሕዝብ ተቀባይነት’ አግኝቻለሁ በማለት ሥልጣኑን አጠናክሯል በማለት፣ ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ ከሥልጣኑ መወገዱን ጠቅሰው ሕጋዊ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል። ህወሓት በመግለጫው ላይ ተቃዋሚዎቹ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ከዚህ በኋላ እንደማይታገሰው አመልክቷል። “ምንም እንኳን የትግራይ መንግሥት እራሳቸውን ያርማሉ ብሎ ቢታገሳቸውም፣ ትግላችንን ከማደናቀፍ አልታቀቡም” ብሏል። ይህንንም በማንሳት በመግለጫው ላይ ተቃዋሚዎቹ በትግራይ ያለው ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ፈርሷል ስለዚህም የሽግግር መንግሥት ወይም የአንድነት መንግሥት እንዲቋቋም ጠይቀዋል ይህም “ትግሉን በሚያደናቅፍ ሁኔታ የትግራይ መንግሥት ሕጋዊ አይደለም አስከ ማለት ደርሰዋል” ብሏል። ጨምሮም ተቃዋሚ ቡድኖቹ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የተቀሰቀሰውን የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስቆም ህወሓት ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ለመደራደር ሥልጣን የለውም ብለዋል። “በአሁኑ ወቅት ትግላችንን የሚያደናቅፍ ተግባራት ላይ አተኩረዋል፤ የትግራይ ክልል መንግሥት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሰላም ንግግር ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን የለውም” ማለታቸውንም ጠቅሷል። ስለዚህም ተቃዋሚዎቹ “በቃችሁ ሊባሉ ይገባቸዋል። የትግራይ ሕዝብም ሥርዓት ሊያሲዛቸው ይገባል” ብሏል የህወሓት መግለጫ። ለ20 ወራት የዘለቀውን የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት ለመቋጨት ተዋጊ ኃይሎች ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ከተለያዩ ወገኖች ጥያቄ ሲቀርብ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የሚደራደሩ ሰባት አባላት ያሉት የኮሚቴ ይፋ ካደረገ በኋላ፤ ህወሓትም ከቀናት በፊት ከመንግሥት ጋር ድርድር የሚያደርግ ቡድን ማቋቋሙን ገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/ce5yv034lx6o |
5sports
| የኮቢ ብራያንት ባለቤት የተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ባለቤትን ከሰሰች | ባለፈው ወር በሄሊኮፕተር አደጋ ባለቤቷ እውቁ ኮቢ ብራያንትን እና የ13 ዓመት ሴት ልጇን ያጣችው ቫኔሳ ብራያንት፣ በሄሊኮፕተሩ ባለቤት ላይ የመሰረተችው ክስ ጭብጥ በመጥፎ የአየር ሁኔታ ለመብረር መወሰኑ የአብራሪውን ግድየለሽነት ያሳያል የሚል ነው። የሄሊኮፕተሩ ባለቤት አይላንድ ኤክስፕረስ ሄሊኮፕተሮችና አብራሪዎች የተሰኘ ድርጅት ሲሆን፣ ፓይለቱ አራ ጆርጅ ዞባያን ማንኛውም ጠንቃቃ አብራሪ ሊያደርግ የሚገባውን ጥንቃቄ መውሰድ ነበረበት ይላል የቀረበው ክስ። ክሱ እንደሚለው በሄሊኮፕተሩ አደጋ ከኮቢ ብራያንት እና ልጁ ጋር የሞተው የሄሊኮፕተሩ አብራሪ ዞባያን ለበረራ ሲዘጋጅ የአየር ሁኔታ ትንታኔን ከግምት አላስገባም። አብራሪው ሁኔታዎች ከባድ ሆነው እያለም በራራውን ለማቋረጥ አልወሰነም፤ ለበረራው የይለፍ ፍቃድ የሰጠው አይላንድ ኤክስፕረስም ሄሊኮፕተሩ አስቻጋሪ በሆነ የአየር ሁኔታ እንደሚበር እያወቀ ፍቃድ ሰጥቷል ሲል ክሱ ያትታል። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ለጊዜው የተቀመጠ የገንዘብ መጠን ባይኖርም ቫኔሳ ብራያንት ከኩባንያው ካሳና ኩባንያው በወንጀል እንዲቀጣም ትፈልጋለች። • ታዋቂው አሜሪካዊ ስፖርተኛ ከነልጁ በሄሊኮፕተር አደጋ ሞተ • 2019 የአውሮፕላን አደጋ ተጎጂዎች ቁጥር የቀነሰበት ነው ተባለ • ከ33 ዓመት በፊት የተዘረፈው ዘውድ ለጨለቆት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚመለስ ተገለጸ ኮቢ እና ልጁን ይዞ የነበረው ሄሊኮፕተር ካላባሳስ ከተሰኘች ከተማ ከከፍታማ ቦታ ቁልቁል ወርዶ መከስከሱ ቀደም ሲል ተገልጿል። ሄሊኮፕተሩ በተነሳበት ወቅት የአየሩ ሁኔታ ጭጋጋማ ነበር። ምንም እንኳ የአየር ሁኔታው ከባድ የነበረ ቢሆንም ፓይለቱ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን ልዩ ፍቃድ በመጠየቅ እና ፍቃዱን በማግኘት መብረሩም ተገልጿል። አይላንድ ሄሊኮፕተርስ በአሁኑ ወቅት በረራ አቋርጧል። ትናንት በርካታ ሥመ ጥር ሰዎች በተገኙበት ኮቢ እና ልጁ ጊያና ተዘክረዋል። መርሃግብሩን ቢዮንሴ ብያንት ይወደው ነበር ባለችው ዜማዋ ጀምራለች። እንደ ማይክል ጆርዳን፣ ማጅክ ጆንሰን እና የብራያንት የቀድሞ ክለብ ጓደኛ የሆነው ሻኪል ኦኒል ያሉ የቅርጫት ኳስ ኮከቦች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል። | የኮቢ ብራያንት ባለቤት የተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ባለቤትን ከሰሰች ባለፈው ወር በሄሊኮፕተር አደጋ ባለቤቷ እውቁ ኮቢ ብራያንትን እና የ13 ዓመት ሴት ልጇን ያጣችው ቫኔሳ ብራያንት፣ በሄሊኮፕተሩ ባለቤት ላይ የመሰረተችው ክስ ጭብጥ በመጥፎ የአየር ሁኔታ ለመብረር መወሰኑ የአብራሪውን ግድየለሽነት ያሳያል የሚል ነው። የሄሊኮፕተሩ ባለቤት አይላንድ ኤክስፕረስ ሄሊኮፕተሮችና አብራሪዎች የተሰኘ ድርጅት ሲሆን፣ ፓይለቱ አራ ጆርጅ ዞባያን ማንኛውም ጠንቃቃ አብራሪ ሊያደርግ የሚገባውን ጥንቃቄ መውሰድ ነበረበት ይላል የቀረበው ክስ። ክሱ እንደሚለው በሄሊኮፕተሩ አደጋ ከኮቢ ብራያንት እና ልጁ ጋር የሞተው የሄሊኮፕተሩ አብራሪ ዞባያን ለበረራ ሲዘጋጅ የአየር ሁኔታ ትንታኔን ከግምት አላስገባም። አብራሪው ሁኔታዎች ከባድ ሆነው እያለም በራራውን ለማቋረጥ አልወሰነም፤ ለበረራው የይለፍ ፍቃድ የሰጠው አይላንድ ኤክስፕረስም ሄሊኮፕተሩ አስቻጋሪ በሆነ የአየር ሁኔታ እንደሚበር እያወቀ ፍቃድ ሰጥቷል ሲል ክሱ ያትታል። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ለጊዜው የተቀመጠ የገንዘብ መጠን ባይኖርም ቫኔሳ ብራያንት ከኩባንያው ካሳና ኩባንያው በወንጀል እንዲቀጣም ትፈልጋለች። • ታዋቂው አሜሪካዊ ስፖርተኛ ከነልጁ በሄሊኮፕተር አደጋ ሞተ • 2019 የአውሮፕላን አደጋ ተጎጂዎች ቁጥር የቀነሰበት ነው ተባለ • ከ33 ዓመት በፊት የተዘረፈው ዘውድ ለጨለቆት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚመለስ ተገለጸ ኮቢ እና ልጁን ይዞ የነበረው ሄሊኮፕተር ካላባሳስ ከተሰኘች ከተማ ከከፍታማ ቦታ ቁልቁል ወርዶ መከስከሱ ቀደም ሲል ተገልጿል። ሄሊኮፕተሩ በተነሳበት ወቅት የአየሩ ሁኔታ ጭጋጋማ ነበር። ምንም እንኳ የአየር ሁኔታው ከባድ የነበረ ቢሆንም ፓይለቱ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን ልዩ ፍቃድ በመጠየቅ እና ፍቃዱን በማግኘት መብረሩም ተገልጿል። አይላንድ ሄሊኮፕተርስ በአሁኑ ወቅት በረራ አቋርጧል። ትናንት በርካታ ሥመ ጥር ሰዎች በተገኙበት ኮቢ እና ልጁ ጊያና ተዘክረዋል። መርሃግብሩን ቢዮንሴ ብያንት ይወደው ነበር ባለችው ዜማዋ ጀምራለች። እንደ ማይክል ጆርዳን፣ ማጅክ ጆንሰን እና የብራያንት የቀድሞ ክለብ ጓደኛ የሆነው ሻኪል ኦኒል ያሉ የቅርጫት ኳስ ኮከቦች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/51625454 |
3politics
| በሕንድ የሚቀናበሩ ፀረ-ሙስሊም ሙዚቃዎች ቁጥር ለምን አሻቀበ? | ሳንዲፕ ቻቱርቬዲ 29 ዓመቱ ነው። አዲስ ሙዚቃ ከአድማጮቹ ጆሮ ለማድረስ ተፍ ተፍ እያለ ነው። በሰሜን ሕንድ በምትገኘው ኡታር ፕራዴሽ ግዛት አዮዲያህ ከተማ ከምትገኘው ሱቱዲዮ ተገኝቷል። ዘፈኑ ስለ አንድ መስጂድ ያወራል። የሒንዱ እምነት ተከታዮች በመስጂዱ የመጠቀም መብት እንዳላቸው ይገልጻሉ። ዘፈኑ በሙስሊሞች ላይ በሚሰነዝሩ ጥቃቶች የተሞላ ነው። ቻቱርቬዲ ሙዚቃው ወደ ዘርፉ ገበያ እንደሚያስገባውም ተማምኗል። የቻቱርቬዲ ሙዚቃ ዩቲዩብ እና ሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተሰራጩ ከሚገኙ ቀኝ ዘመም የሒንዱ ትርክቶች መካከል ናቸው። ትኩረታቸውም በሙስሊሞች ዙሪያ አደገኛ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ነው። ግጥሞቹ ስድብ አዘል ወይም ማስፈራሪያ የያዙ ናቸው። መሠረታቸው የሒንዱ እምነት ተከታዮች ለዘመናት ተበድለዋል የሚል ነው። አሁን ደግሞ የደረሰውን ኪሳራ መመለሻ ጊዜ ነው ይላሉ። እነዚህ ሙዚቃዎች የገቢ ምንጭ ከመሆናቸውም በላይ ዘፋኞችንም ወደ ታዋቂነት ማማ ያደርሳሉ የሚሉት ፀሐፊ እና የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ኒላንጃን ሙክሆፓድያይ ናቸው። ለእርሳቸው እነዚህ ሙዚቃዎች አይደሉም። “እነዚህ ጦርነት ካልተጀመረ ባዮች ናቸው። ሙዚቃ ጦርነት የሚያሸንፍ ይመስላቸዋል። ይህ ሙዚቃን ያለ ዓላማው መጠቀም ነው። ለዓመታትም ተግባራዊ ተደርጓል” ይላሉ። ቻቱርቬዲ የዩቲዩብ ቻናሉ ከመታገዱ በፊት ሙዚቃው በሚሊዮኖች ታይቷል። እገዳው የመጣው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቅሬታ ማስገባታቸውን ተከትሎ ነው። ሙስሊሞች ናቸው ሙዚቃው አግባብ አይደለም እያሉ ቅሬታ ያስገቡት ይላል። ቻቱርቬዲ “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮችን በማጣቱ” ቢቆጭም ከዩቲዩብ እያገኘ ያለውን ገንዘብ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም። የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለመስራት ግን 253 ዶላር ይፈጅበታል። “ከዩቲዩብ ብዙ ገንዘብ እያገኘሁ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ እንደ ብሔረተኛ-አብዮታዊ ዘፋኝ ያገኘሁት እውቅና ነው” ሲል በልበ ሙሉነት ተናግሯል። ቻቱርቬዲ አሁን ዩቲዩብ ላይ አዲስ ቻናል ከፍቷል። የለቀቃቸው አንዳንድ ቪዲዮዎች ያላቸው ዕይታ እምብዛም ነው። ይህንን በአዲሱ ዘፈኑ ለመለወጥ ተስፋ አድርጓል። ቻቱርቬዲ በሙዚቃው ብዙ ጊዜ ሙስሊሞችን ዒላማ አድርጓል ተብሎ ቢከሰስም ይቅርታ አይጠይቅም። “የራሴ ለማግኘት እጆቼን አጣጥፌ ብለምን ትስማማለህ? አትቀበልም። ስለዚህ ቀስቃሽ መሆን አለብን፣ አይደል?” ይላል። አፔንድራ ራና መቀመጫው ዴልሂ አቅራቢያ በምትገኘው ዳድሪ ነው። እሱም ተመሳሳይ ሙዚቃ ያዘጋጃል። ተልዕኮዬ ታሪክን “ማረም ነው” ይላል። ዘፈኖቹ የሂንዱ ተዋጊዎች ላይ ያነጣጠረ ነው። የሙስሊም ገዥዎችንም ተራ አድርጎ ይስላል። “ብዙ እውነት የሆኑ ነገሮች ተደብቀው ውሸት ተጭኖብናል” ሲል በትምህርት ቤቶች ስለሚሰጠው የታሪክ ትምህርት ተናግሯል። ራና ከዩቲዩብ ቪዲዮዎቹ ጥሩ ገቢ እያገኘ መሆኑን ያስረዳል። “ለሕንድ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘን ነው። ዩቲዩብ የሚከፍለው በዶላር ነው” ብሎ ዓይኑን ግድግዳው ላይ ዩቲዩብ ከፍተኛ ተከታይ ላላቸው ቻናሎች ወደሚሰጠው ሽልማት እና ወደ ሒንዱ ተዋጊ ምስሎች ወረወረ። ራና የአምልኮ እና የፍቅር ዘፈኖችን ከማቀናበር ወደ “ታሪካዊ” ሥራዎች ከተሸጋገረበት ጊዜ ጀምሮ በዳድሪ ኮከብ ለመሆን በቃ። በዩቲዩብ ላይ ወደ 400,000 የሚጠጉ ተከታዮች አሉት። ብዙዎቹ ዘፈኖቹም በሚሊዮን ለሚቆጠር ጊዜ ታይተዋል። የሙዚቃ ቪዲዮ ለመስራት 100 ዶላር እንደሚያስወጣው ራና ይናገራል። ቪዲዮዎችን መቅረጽን ጨምሮ ካሜራ እና ሌሎች የሙያ ባለቤቶችን ያካተተ ቡድን አለው። ሙክሆፓድያይ እንደሚሉት ከሆነ ሙዚቃን በቁጥር አናሳ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለማስጠቃት ማዋል ከበፊትም ጀምሮ የመጣ ነው። እአአ በ1989 በቀኝ ዘመሙ ቪሽዋ ሒንዱ ፓሪሻድ (ቪኤችፒ) ባዘጋጀው አወዛጋቢው የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም ምክንያት በ1992 ባብሪ የተባለ መስጂድ መፍረሱን ያስታውሳሉ። “ከዚያ በፊት የኦዲዮ ካሴቶች ኢንዱስትሪ ብቅ አለ። ሃይማኖታዊ እና ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይካተቱባቸው ነበር። ሰዎችን ለማነሳሳትም ሲባል እነዚህ ካሴቶች በተከታታይ ይጫወቱ ነበር” ብለዋል። ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላም ድምፁ እየጨመረ መጥቷል። “ሕንድ ውስጥ መኖር ከፈለክ ቫንዴ ማታራም (“እናቴ አመሰግንሽላሁ”) ማለትን ተማር…በአቅምህ መኖርንም ተማር” ወይም “ሒንዱዎችን ደካማ አድርጎ ማሰብ የጠላት ስህተት ነው” የሚሉ ሥራዎች ማን ላይ እንዳነጣጠሩ መገመት ከባድ አይደለም። እነዚህ ዘፈኖች ቀኝ ዘመም ድርጅቶች የካድሬዎቻቸውን “ቀልብ እንዲገዙ” ረድተዋቸዋል። የቀኝ ክንፍ ሒንዱ ራክሻ ዳል ቡድንን የሚመራው ፒንኪ ቻውድሪ “ወጣቶች ጉጉታቸውን እና ሞራላቸውን ከፍ ስለሚያደርጉ እነዚህን ዘፈኖች ይወዳሉ” ሲሉ እንዲህ ዓይነት ዘፈኖች ለወጣቶች ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚያግዙ ይከራከራሉ። “እነዚህን ዘፈኖች ሳዳምጥ ድንገቴ የሆነ ከፍተኛ ኃይል በፍጥነት ይሰማኛል። በአንድ ወቅት የተደረጉብንን ነገሮች እና አሁን የት እንደደረስን ያስታውሰኛል” ይላል ቪጃይ ያዳቭ። እንደዚህ አይነት ሙዚቃዎችን ማዳመጥ እንደሚወድ የሚናገረው የ23 ዓመቱ ያዳቭ ትምህርቱን እየተከታተለ የሚገኝ ሰዓሊ ነው። ያዳቭ “ድንገቴ የሆነ ከፍተኛ ኃይል” ሲል የተናገረው በሚያዝያ ወር በሚከበሩት የሒንዱ በዓላት ወቅት በበርካታ ግዛቶች ከፍተኛ ግጭቶች የተከሰቱበት ሁኔታን ያሳያል ተብሎ ይታመናል። በበዓላቱ ወቅት ሒንዱዎች ለሃይማኖታዊ ሰልፎች ወጥተው ሙስሊሞች ወደሚበዙባቸው አካባቢዎች ሲቃረቡ ቀስቃሽ ሙዚቃዎች በድምጽ ማጉያዎች ይስተጋባሉ። ከእነዚህ ግጭቶች ውስጥ የቻቱርቬዲ የ2016 ሙዚቃን ጨምሮ ጸያፍ እና ቀስቃሽ ዘፈኖች ሁከትን ለመቀስቀስ አስተዋጽኦ አድርገዋል ተብሏል። ቻቱርቬዲ እነዚህን ክሶች ውድቅ ያደርጋል። “በሙዚቃዬ ግንዛቤን ለመፍጠር እየሞከርኩ ነው። ምንም ነገር በፍቅር አይመጣም። መታገል እና የእኛ የሆነውን መንጠቅ አለብን” ይላል። | በሕንድ የሚቀናበሩ ፀረ-ሙስሊም ሙዚቃዎች ቁጥር ለምን አሻቀበ? ሳንዲፕ ቻቱርቬዲ 29 ዓመቱ ነው። አዲስ ሙዚቃ ከአድማጮቹ ጆሮ ለማድረስ ተፍ ተፍ እያለ ነው። በሰሜን ሕንድ በምትገኘው ኡታር ፕራዴሽ ግዛት አዮዲያህ ከተማ ከምትገኘው ሱቱዲዮ ተገኝቷል። ዘፈኑ ስለ አንድ መስጂድ ያወራል። የሒንዱ እምነት ተከታዮች በመስጂዱ የመጠቀም መብት እንዳላቸው ይገልጻሉ። ዘፈኑ በሙስሊሞች ላይ በሚሰነዝሩ ጥቃቶች የተሞላ ነው። ቻቱርቬዲ ሙዚቃው ወደ ዘርፉ ገበያ እንደሚያስገባውም ተማምኗል። የቻቱርቬዲ ሙዚቃ ዩቲዩብ እና ሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተሰራጩ ከሚገኙ ቀኝ ዘመም የሒንዱ ትርክቶች መካከል ናቸው። ትኩረታቸውም በሙስሊሞች ዙሪያ አደገኛ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ነው። ግጥሞቹ ስድብ አዘል ወይም ማስፈራሪያ የያዙ ናቸው። መሠረታቸው የሒንዱ እምነት ተከታዮች ለዘመናት ተበድለዋል የሚል ነው። አሁን ደግሞ የደረሰውን ኪሳራ መመለሻ ጊዜ ነው ይላሉ። እነዚህ ሙዚቃዎች የገቢ ምንጭ ከመሆናቸውም በላይ ዘፋኞችንም ወደ ታዋቂነት ማማ ያደርሳሉ የሚሉት ፀሐፊ እና የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ኒላንጃን ሙክሆፓድያይ ናቸው። ለእርሳቸው እነዚህ ሙዚቃዎች አይደሉም። “እነዚህ ጦርነት ካልተጀመረ ባዮች ናቸው። ሙዚቃ ጦርነት የሚያሸንፍ ይመስላቸዋል። ይህ ሙዚቃን ያለ ዓላማው መጠቀም ነው። ለዓመታትም ተግባራዊ ተደርጓል” ይላሉ። ቻቱርቬዲ የዩቲዩብ ቻናሉ ከመታገዱ በፊት ሙዚቃው በሚሊዮኖች ታይቷል። እገዳው የመጣው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቅሬታ ማስገባታቸውን ተከትሎ ነው። ሙስሊሞች ናቸው ሙዚቃው አግባብ አይደለም እያሉ ቅሬታ ያስገቡት ይላል። ቻቱርቬዲ “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮችን በማጣቱ” ቢቆጭም ከዩቲዩብ እያገኘ ያለውን ገንዘብ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም። የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ለመስራት ግን 253 ዶላር ይፈጅበታል። “ከዩቲዩብ ብዙ ገንዘብ እያገኘሁ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ እንደ ብሔረተኛ-አብዮታዊ ዘፋኝ ያገኘሁት እውቅና ነው” ሲል በልበ ሙሉነት ተናግሯል። ቻቱርቬዲ አሁን ዩቲዩብ ላይ አዲስ ቻናል ከፍቷል። የለቀቃቸው አንዳንድ ቪዲዮዎች ያላቸው ዕይታ እምብዛም ነው። ይህንን በአዲሱ ዘፈኑ ለመለወጥ ተስፋ አድርጓል። ቻቱርቬዲ በሙዚቃው ብዙ ጊዜ ሙስሊሞችን ዒላማ አድርጓል ተብሎ ቢከሰስም ይቅርታ አይጠይቅም። “የራሴ ለማግኘት እጆቼን አጣጥፌ ብለምን ትስማማለህ? አትቀበልም። ስለዚህ ቀስቃሽ መሆን አለብን፣ አይደል?” ይላል። አፔንድራ ራና መቀመጫው ዴልሂ አቅራቢያ በምትገኘው ዳድሪ ነው። እሱም ተመሳሳይ ሙዚቃ ያዘጋጃል። ተልዕኮዬ ታሪክን “ማረም ነው” ይላል። ዘፈኖቹ የሂንዱ ተዋጊዎች ላይ ያነጣጠረ ነው። የሙስሊም ገዥዎችንም ተራ አድርጎ ይስላል። “ብዙ እውነት የሆኑ ነገሮች ተደብቀው ውሸት ተጭኖብናል” ሲል በትምህርት ቤቶች ስለሚሰጠው የታሪክ ትምህርት ተናግሯል። ራና ከዩቲዩብ ቪዲዮዎቹ ጥሩ ገቢ እያገኘ መሆኑን ያስረዳል። “ለሕንድ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘን ነው። ዩቲዩብ የሚከፍለው በዶላር ነው” ብሎ ዓይኑን ግድግዳው ላይ ዩቲዩብ ከፍተኛ ተከታይ ላላቸው ቻናሎች ወደሚሰጠው ሽልማት እና ወደ ሒንዱ ተዋጊ ምስሎች ወረወረ። ራና የአምልኮ እና የፍቅር ዘፈኖችን ከማቀናበር ወደ “ታሪካዊ” ሥራዎች ከተሸጋገረበት ጊዜ ጀምሮ በዳድሪ ኮከብ ለመሆን በቃ። በዩቲዩብ ላይ ወደ 400,000 የሚጠጉ ተከታዮች አሉት። ብዙዎቹ ዘፈኖቹም በሚሊዮን ለሚቆጠር ጊዜ ታይተዋል። የሙዚቃ ቪዲዮ ለመስራት 100 ዶላር እንደሚያስወጣው ራና ይናገራል። ቪዲዮዎችን መቅረጽን ጨምሮ ካሜራ እና ሌሎች የሙያ ባለቤቶችን ያካተተ ቡድን አለው። ሙክሆፓድያይ እንደሚሉት ከሆነ ሙዚቃን በቁጥር አናሳ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለማስጠቃት ማዋል ከበፊትም ጀምሮ የመጣ ነው። እአአ በ1989 በቀኝ ዘመሙ ቪሽዋ ሒንዱ ፓሪሻድ (ቪኤችፒ) ባዘጋጀው አወዛጋቢው የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም ምክንያት በ1992 ባብሪ የተባለ መስጂድ መፍረሱን ያስታውሳሉ። “ከዚያ በፊት የኦዲዮ ካሴቶች ኢንዱስትሪ ብቅ አለ። ሃይማኖታዊ እና ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይካተቱባቸው ነበር። ሰዎችን ለማነሳሳትም ሲባል እነዚህ ካሴቶች በተከታታይ ይጫወቱ ነበር” ብለዋል። ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላም ድምፁ እየጨመረ መጥቷል። “ሕንድ ውስጥ መኖር ከፈለክ ቫንዴ ማታራም (“እናቴ አመሰግንሽላሁ”) ማለትን ተማር…በአቅምህ መኖርንም ተማር” ወይም “ሒንዱዎችን ደካማ አድርጎ ማሰብ የጠላት ስህተት ነው” የሚሉ ሥራዎች ማን ላይ እንዳነጣጠሩ መገመት ከባድ አይደለም። እነዚህ ዘፈኖች ቀኝ ዘመም ድርጅቶች የካድሬዎቻቸውን “ቀልብ እንዲገዙ” ረድተዋቸዋል። የቀኝ ክንፍ ሒንዱ ራክሻ ዳል ቡድንን የሚመራው ፒንኪ ቻውድሪ “ወጣቶች ጉጉታቸውን እና ሞራላቸውን ከፍ ስለሚያደርጉ እነዚህን ዘፈኖች ይወዳሉ” ሲሉ እንዲህ ዓይነት ዘፈኖች ለወጣቶች ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚያግዙ ይከራከራሉ። “እነዚህን ዘፈኖች ሳዳምጥ ድንገቴ የሆነ ከፍተኛ ኃይል በፍጥነት ይሰማኛል። በአንድ ወቅት የተደረጉብንን ነገሮች እና አሁን የት እንደደረስን ያስታውሰኛል” ይላል ቪጃይ ያዳቭ። እንደዚህ አይነት ሙዚቃዎችን ማዳመጥ እንደሚወድ የሚናገረው የ23 ዓመቱ ያዳቭ ትምህርቱን እየተከታተለ የሚገኝ ሰዓሊ ነው። ያዳቭ “ድንገቴ የሆነ ከፍተኛ ኃይል” ሲል የተናገረው በሚያዝያ ወር በሚከበሩት የሒንዱ በዓላት ወቅት በበርካታ ግዛቶች ከፍተኛ ግጭቶች የተከሰቱበት ሁኔታን ያሳያል ተብሎ ይታመናል። በበዓላቱ ወቅት ሒንዱዎች ለሃይማኖታዊ ሰልፎች ወጥተው ሙስሊሞች ወደሚበዙባቸው አካባቢዎች ሲቃረቡ ቀስቃሽ ሙዚቃዎች በድምጽ ማጉያዎች ይስተጋባሉ። ከእነዚህ ግጭቶች ውስጥ የቻቱርቬዲ የ2016 ሙዚቃን ጨምሮ ጸያፍ እና ቀስቃሽ ዘፈኖች ሁከትን ለመቀስቀስ አስተዋጽኦ አድርገዋል ተብሏል። ቻቱርቬዲ እነዚህን ክሶች ውድቅ ያደርጋል። “በሙዚቃዬ ግንዛቤን ለመፍጠር እየሞከርኩ ነው። ምንም ነገር በፍቅር አይመጣም። መታገል እና የእኛ የሆነውን መንጠቅ አለብን” ይላል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1d830zekro |
5sports
| አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ጥበበኛ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አረፈ | ከምድራችን የእግር ኳስ ኮከብ ተጫዋቾች መካከል ከቀዳሚዎቹ ውስጥ የሚጠቀሰው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በ60 ዓመት ዕድሜው አረፈ። የቀድሞው የአርጀንቲና ኮከብ ተጫዋች እና በኋላም የአገሩ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ያረፈው ቤቱ ውስጥ ሳለ በልብ ችግር እንደሆነ ተገልጿል። ማራዶና በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን በተከታይነትም ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ ሕክምና ይደረግለታል ተብሎ ነበር። የዓለማችን የምንጊዜም ታላላቅ ተጫዋቾች ከሚባሉት አንዱ የሆነው ማራዶና አርጀንቲና እአአ በ1986 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ስትሆን የቡድኑ አምበል የነበረ ሲሆን ድንቅ ችሎታውንና የታወቀባቸውን የኳስ ጥበቡን በማሳየት ዓለምን አስደምሞ ነበር። በተለይ በወቅቱ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ባደረገችው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ እሱ "የእግዜር እጅ" ያላትና ዳኞች ሳያዩ በእጁ ያስቆጠራት ግብ ዘወትር ትታወሳለች። በተጨማሪም ለስፔኑ ባርሴሎናና ለጣሊያኑ ናፖሊ ቡድኖች በአውሮፓ ውስጥ የተጫወተ ሲሆን፤ በጣሊያን ሴሪ አ ውስጥም ሁለት ጊዜ ዋንጫ ለማንሳት በቅቶ ነበር። የአርጀንቲና እግር ኳስ ማኅበር የማራዶና ሞት በተሰማ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ "በጀግናችን ሞት በጣሙን አዝነናል" በማለት "ሁልጊዜም በልባችን ውስጥ ትኖራለህ" ብሏል። ማራዶና ለአገሩ አርጀንቲና በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ በተደረጉ 91 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 34 ግቦችን አስቆጥሯል። ማራዶና የተከለከሉ አበረታች መድኃኒቶችንና ዕጽ በመጠቀም ስሙ በተደጋጋሚ ሲነሳ የቆየ ሲሆን ከስፖርትም እገዳ ተጥሎበት ነበር። ማራዶና ፕሮፌሽናል እግር ኳስን ከዛሬ 23 ዓመት በፊት በ37 ዓመት ዕድሜው ያቆመ ሲሆን፤ በአርጀንቲና ውስጥ ያሉ ቡድኖችን በአሰልጣኝነት ከመራ በኋላ የአገሩን ብሔራዊ ቡድንንም በማሰልጠን ለዓለም ዋንጫ አብቅቷል። ከዚያም በኋላ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና በሜክሲኮ ውስጥ የሚገኙ ቡድኖችን በተለያዩ ጊዜያት አሰልጥኖ ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ደግሞ የአገሩን አንድ ቡድን በማሰልጠን ላይ ነበር። | አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ጥበበኛ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አረፈ ከምድራችን የእግር ኳስ ኮከብ ተጫዋቾች መካከል ከቀዳሚዎቹ ውስጥ የሚጠቀሰው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በ60 ዓመት ዕድሜው አረፈ። የቀድሞው የአርጀንቲና ኮከብ ተጫዋች እና በኋላም የአገሩ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ያረፈው ቤቱ ውስጥ ሳለ በልብ ችግር እንደሆነ ተገልጿል። ማራዶና በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን በተከታይነትም ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ ሕክምና ይደረግለታል ተብሎ ነበር። የዓለማችን የምንጊዜም ታላላቅ ተጫዋቾች ከሚባሉት አንዱ የሆነው ማራዶና አርጀንቲና እአአ በ1986 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ስትሆን የቡድኑ አምበል የነበረ ሲሆን ድንቅ ችሎታውንና የታወቀባቸውን የኳስ ጥበቡን በማሳየት ዓለምን አስደምሞ ነበር። በተለይ በወቅቱ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ባደረገችው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ እሱ "የእግዜር እጅ" ያላትና ዳኞች ሳያዩ በእጁ ያስቆጠራት ግብ ዘወትር ትታወሳለች። በተጨማሪም ለስፔኑ ባርሴሎናና ለጣሊያኑ ናፖሊ ቡድኖች በአውሮፓ ውስጥ የተጫወተ ሲሆን፤ በጣሊያን ሴሪ አ ውስጥም ሁለት ጊዜ ዋንጫ ለማንሳት በቅቶ ነበር። የአርጀንቲና እግር ኳስ ማኅበር የማራዶና ሞት በተሰማ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ "በጀግናችን ሞት በጣሙን አዝነናል" በማለት "ሁልጊዜም በልባችን ውስጥ ትኖራለህ" ብሏል። ማራዶና ለአገሩ አርጀንቲና በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ በተደረጉ 91 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 34 ግቦችን አስቆጥሯል። ማራዶና የተከለከሉ አበረታች መድኃኒቶችንና ዕጽ በመጠቀም ስሙ በተደጋጋሚ ሲነሳ የቆየ ሲሆን ከስፖርትም እገዳ ተጥሎበት ነበር። ማራዶና ፕሮፌሽናል እግር ኳስን ከዛሬ 23 ዓመት በፊት በ37 ዓመት ዕድሜው ያቆመ ሲሆን፤ በአርጀንቲና ውስጥ ያሉ ቡድኖችን በአሰልጣኝነት ከመራ በኋላ የአገሩን ብሔራዊ ቡድንንም በማሰልጠን ለዓለም ዋንጫ አብቅቷል። ከዚያም በኋላ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና በሜክሲኮ ውስጥ የሚገኙ ቡድኖችን በተለያዩ ጊዜያት አሰልጥኖ ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ደግሞ የአገሩን አንድ ቡድን በማሰልጠን ላይ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-55074075 |
3politics
| በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ | በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ የነበሩት ፔይተን ክኖፍ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ታማኝ ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ። ፔይተን አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ መሰየም ከጀመረችበት ካለፈው ዓመት ጀምሮ ምክትል በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው ነው በዚህ ሳምንት ኃላፊነታቸውን የለቀቁት። ይህም በሰባት ወራት ውስጥ ብቻ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ቡድኑ ሥራቸውን የለቀቁ ሦስተኛው የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ያደርጋቸዋል። ፔይተን ከምክትል ልዩ መልዕክተኝነታቸው ባሻገር ከሦስት ወራት በፊት ዴቪድ ሳተርፊልድ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ በጊዜያዊነት የዋና ወኪልነት ቦታውን ሸፍነው ሲሰሩ ቆይተዋል። “እነዚህ ሦስት በርካታ ልምድ እና ብቃት ያላቸው ዲፕሎማቶች ይህንን ወሳኝ ኃላፊነት ወስደው በማገልገላቸው ደስተኞች ነን” ሲሉ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “በአፍሪካ ቀንድ ያለው ያለመረጋጋት እንዲሁም በቀጠናው ያሉት የፖለቲካ፣ የፀጥታ እንዲሁም የሰብአዊ ጉዳዮች ፈተናዎች የአሜሪካን ያልተቋረጠ ትኩረት ይፈልጋሉ” ሲሉም ፕራይስ ለቢቢሲ ገልጸዋል። አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ፔይተን ክኖፍ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኩ እንዲሁም ከመንግሥት ሥራ መልቀቃቸውን አረጋግጠዋል። ነገር ግን ለፔይተን ከኃላፊነታቸው መልቀቅ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከእራሳቸውም ሆነ ከሌሎች ምንጮች የተባለ ነገር የለም። በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ነበር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮችን በቅርበት የሚከታተሉ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማቶችን የሰየሙት። በጥር 2013 ዓ.ም. የመጀመሪያው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት ጄፍሪ ፌልትማን በቦታው ላይ ለአንድ ዓመት ገደማ ከቆዩ በኋላ ነበር ከኃላፊነታቸው የለቀቁት። በዚህ ዓመት ጥር ወር ተሹመው ወደ ኃላፊነቱ መጥተው የነበሩት ዴቪድ ሳተርፊልድም ከአራት ወራት በኋላ በተመሳሳይ ራሳቸውን ከኃላፊነቱ አግልለዋል። ከዋና መልዕክተኞቹ በተጨማሪ ለልዑኩ ምክትል በመሆን ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት ክኖፍ ፔይተንም አሁን የቀደሙ አለቆቻቸውን መንገድ ተከትለው ሥራቸውን ለቀዋል። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚከሰቱ ቀውሶችን በሚከታተለው በዓለም አቀፉ ክራይስስ ግሩፕ ውስጥ ከፍተኛ ተንታኝ የሆኑት ዊሊያም ዳቪሰን፣ ፔይተን “በቀጠናው በርካታ ልምድ እና ጥሩ ግንኙነት ያላቸው ዲፕሎማት” ነበሩ ሲል ይገልጿቸዋል። “እንደ እርሳቸው ያለ አቅም፣ ዕውቀት እና ልምድ ያለው ሰው አዲሱን ልዩ መልዕክተኛ ለመደገፍ መሾም አለበት ብዬ አምናለሁ” ሲል ዳቪሰን ይናገራል። በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን፣ ማይክ ሐመርን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርገው መሾማቸውን ገልጸው ነበር። “ይህ ሹመት በቀጠናው ላለን የዲፕሎማሲ ጥረቶች ቁርጠኝነት ማሳያ ነው። በተለይም አንገብጋቢ በሆነው የጋራ ሰላምን እና ብልጽግናን ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለማምጣት የሚደረገውን ሁሉን አካታች ሂደት ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል” ሲሉም ስለ አዲሱ መልዕክተኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መናገራቸው ይታወሳል። ክኖፍ ፔይተን እጅግ ተቀያያሪ እና ፈታኝ በሆነው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ መልክተኛ ሆነው ለተሾሙት ለሦስቱም መልዕክተኞች ምክትል ሆነው ያገለገሉ ሲሆን አብረዋቸውም በቀጠናው አገራት በርካታ ጉዞዎችን አድርገዋል። ፔይተን ከዚህ ከቀደም በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ኃላፊነቶቸን በመውሰድ በደቡብ ሱዳን እና በየመን አገልግለዋል። | በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ የነበሩት ፔይተን ክኖፍ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ታማኝ ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ። ፔይተን አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ መሰየም ከጀመረችበት ካለፈው ዓመት ጀምሮ ምክትል በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው ነው በዚህ ሳምንት ኃላፊነታቸውን የለቀቁት። ይህም በሰባት ወራት ውስጥ ብቻ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ቡድኑ ሥራቸውን የለቀቁ ሦስተኛው የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ያደርጋቸዋል። ፔይተን ከምክትል ልዩ መልዕክተኝነታቸው ባሻገር ከሦስት ወራት በፊት ዴቪድ ሳተርፊልድ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ በጊዜያዊነት የዋና ወኪልነት ቦታውን ሸፍነው ሲሰሩ ቆይተዋል። “እነዚህ ሦስት በርካታ ልምድ እና ብቃት ያላቸው ዲፕሎማቶች ይህንን ወሳኝ ኃላፊነት ወስደው በማገልገላቸው ደስተኞች ነን” ሲሉ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “በአፍሪካ ቀንድ ያለው ያለመረጋጋት እንዲሁም በቀጠናው ያሉት የፖለቲካ፣ የፀጥታ እንዲሁም የሰብአዊ ጉዳዮች ፈተናዎች የአሜሪካን ያልተቋረጠ ትኩረት ይፈልጋሉ” ሲሉም ፕራይስ ለቢቢሲ ገልጸዋል። አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ፔይተን ክኖፍ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኩ እንዲሁም ከመንግሥት ሥራ መልቀቃቸውን አረጋግጠዋል። ነገር ግን ለፔይተን ከኃላፊነታቸው መልቀቅ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከእራሳቸውም ሆነ ከሌሎች ምንጮች የተባለ ነገር የለም። በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ነበር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮችን በቅርበት የሚከታተሉ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማቶችን የሰየሙት። በጥር 2013 ዓ.ም. የመጀመሪያው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት ጄፍሪ ፌልትማን በቦታው ላይ ለአንድ ዓመት ገደማ ከቆዩ በኋላ ነበር ከኃላፊነታቸው የለቀቁት። በዚህ ዓመት ጥር ወር ተሹመው ወደ ኃላፊነቱ መጥተው የነበሩት ዴቪድ ሳተርፊልድም ከአራት ወራት በኋላ በተመሳሳይ ራሳቸውን ከኃላፊነቱ አግልለዋል። ከዋና መልዕክተኞቹ በተጨማሪ ለልዑኩ ምክትል በመሆን ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት ክኖፍ ፔይተንም አሁን የቀደሙ አለቆቻቸውን መንገድ ተከትለው ሥራቸውን ለቀዋል። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚከሰቱ ቀውሶችን በሚከታተለው በዓለም አቀፉ ክራይስስ ግሩፕ ውስጥ ከፍተኛ ተንታኝ የሆኑት ዊሊያም ዳቪሰን፣ ፔይተን “በቀጠናው በርካታ ልምድ እና ጥሩ ግንኙነት ያላቸው ዲፕሎማት” ነበሩ ሲል ይገልጿቸዋል። “እንደ እርሳቸው ያለ አቅም፣ ዕውቀት እና ልምድ ያለው ሰው አዲሱን ልዩ መልዕክተኛ ለመደገፍ መሾም አለበት ብዬ አምናለሁ” ሲል ዳቪሰን ይናገራል። በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን፣ ማይክ ሐመርን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርገው መሾማቸውን ገልጸው ነበር። “ይህ ሹመት በቀጠናው ላለን የዲፕሎማሲ ጥረቶች ቁርጠኝነት ማሳያ ነው። በተለይም አንገብጋቢ በሆነው የጋራ ሰላምን እና ብልጽግናን ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለማምጣት የሚደረገውን ሁሉን አካታች ሂደት ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል” ሲሉም ስለ አዲሱ መልዕክተኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መናገራቸው ይታወሳል። ክኖፍ ፔይተን እጅግ ተቀያያሪ እና ፈታኝ በሆነው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ መልክተኛ ሆነው ለተሾሙት ለሦስቱም መልዕክተኞች ምክትል ሆነው ያገለገሉ ሲሆን አብረዋቸውም በቀጠናው አገራት በርካታ ጉዞዎችን አድርገዋል። ፔይተን ከዚህ ከቀደም በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ኃላፊነቶቸን በመውሰድ በደቡብ ሱዳን እና በየመን አገልግለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cy7q55j4lqlo |
2health
| ኖቤል ሽልማት፡ 'ሄፒታይተስ ሲ'ን ያገኙት ተመራማሪዎች ኖቤል ተሸለሙ | የሄፒታይተስ ሲ ቫይረስን ያገኙት ሦስት ሳይንቲስቶች በሕክምና ዘርፍ የኖቤል ተሸላሚ ሆኑ። ሳይንቲስቶቹ እንግሊዛዊው ማይክል ሆግተን እና አሜሪካዊያኑ ሀርቪ አልተርና ቻርልስ ራይስ ናቸው። የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ እንዳለው፤ የሳይንቲስቶቹ ግኝት “በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ታድጓል”። ቫይረሱ የኩላሊት ካንሰር ያስከትላል። ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላም ያስፈልጋቸዋል። • ሕንድ የሰራችው አዲሱ ፈጣን የኮቪድ-19 መመርመሪያ • ከክትባቱ በኋላ ወደ ቀድሞ ሕይወት ለመመለስ ምን ያህል ጊዜ ያስፈልጋል? እአአ በ1960ዎቹ ደም የተለገሳቸው ሰዎች ባልታወቀ ህመም ሳቢያ ለሄፒታይተስ ይጋለጣሉ የሚል ስጋት ነበር። የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ደም ልገሳ አደገኛ የነበረበት ወቅት እንደነበረ ጠቁሟል። አሁን ግን ለአደጋ የሚያጋልጥ የደም ልገሳን መቅረፍ መቻሉም ተጠቁሟል። በተጨማሪም ፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች ማምረት ተችሏል። ኮሚቴው "በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ህመሙን መፈወስ ተችሏል። ይህም ሄፒታይተስ ሲን ከዓለም ማስወገድ እንደሚቻል ተስፋ አጭሯል“” ብሏል። ሆኖም ግን በየዓመቱ 70 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ። ከነዚህም 400,000 ይሞታሉ። ገዳዩ ቫይረስ ሄፒታይተስ ኤ እና ቢ የተገኙት በ1960ዎቹ ነበር። በ1972 አሜሪካ ውስጥ ምርምር እያደረጉ የነበሩት ፕ/ር ሀርቪ አልተር ከሁለቱ ቫይረሶች በተጨማሪ ሌላም ገዳይ ቫይረስ መኖሩን ደረሱበት። ብዙዎች ደም ከተለገሳቸው በኋላም ከህመማቸው አልተፈወሱም ነበር። ተመራማሪው፤ ህመም ካለባቸው ሰዎች ለቺምፓንዚዎች ደም መሰጠቱ ለበሽታው ስርጭት ምክንያት መሆኑን ደርሰውበታል። በወቅቱ ምንነቱ ያልታወቀው ህመም ‘ነን ኤ- ነን ቢ’ ወይም ኤም ቢም ያልሆነ ሄፒታይተስ ተብሎ ይጠራ ነበር። ፕ/ር ማይክል ሆግተን በ1989 የቫይረሱን ዘረ መለ መለየት ችለዋል። ከዛም ቫይረሱ ሄፒታይተስ ሲ ተብሏል። • ሩሲያና ቻይና በአሜሪካ ምርጫ ማን እንዲያሸንፍ ነው የሚፈልጉት? በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ይሠሩ የነበሩት ፕ/ር ቻርልስ ራይስ ደግሞ በ1997 ለጥናቱ መደምደሚያ ሰጥተዋል። ሄፒታይተስ ሲ ቫይረስ ላይ ዘረ መል አክለው በቺምፓንዚ ኩላሊት ውስጥ ከጨመሩ በኋላ በሽታው እንዴት እንደሚከሰት ደርሰውበታል። የኖቤል ኮሚቴ ዋና ጸሀፊ ፕ/ር ቶማስ ፐርልማን፤ ከሦስቱ ሳይንቲስቶች መካከል ለሁለቱ ደውለው ኖቤል ማሸነፋቸውን እንደነገሯቸው ገልጸዋል። “ሳነጋግራቸው ደስ ብሎኝ ነበር። ማሸነፋቸውን ሲሰሙ ተገርመዋል። ተደስተዋልም” ብለዋል። | ኖቤል ሽልማት፡ 'ሄፒታይተስ ሲ'ን ያገኙት ተመራማሪዎች ኖቤል ተሸለሙ የሄፒታይተስ ሲ ቫይረስን ያገኙት ሦስት ሳይንቲስቶች በሕክምና ዘርፍ የኖቤል ተሸላሚ ሆኑ። ሳይንቲስቶቹ እንግሊዛዊው ማይክል ሆግተን እና አሜሪካዊያኑ ሀርቪ አልተርና ቻርልስ ራይስ ናቸው። የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ እንዳለው፤ የሳይንቲስቶቹ ግኝት “በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ታድጓል”። ቫይረሱ የኩላሊት ካንሰር ያስከትላል። ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላም ያስፈልጋቸዋል። • ሕንድ የሰራችው አዲሱ ፈጣን የኮቪድ-19 መመርመሪያ • ከክትባቱ በኋላ ወደ ቀድሞ ሕይወት ለመመለስ ምን ያህል ጊዜ ያስፈልጋል? እአአ በ1960ዎቹ ደም የተለገሳቸው ሰዎች ባልታወቀ ህመም ሳቢያ ለሄፒታይተስ ይጋለጣሉ የሚል ስጋት ነበር። የኖቤል ሽልማት ኮሚቴው ደም ልገሳ አደገኛ የነበረበት ወቅት እንደነበረ ጠቁሟል። አሁን ግን ለአደጋ የሚያጋልጥ የደም ልገሳን መቅረፍ መቻሉም ተጠቁሟል። በተጨማሪም ፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች ማምረት ተችሏል። ኮሚቴው "በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ህመሙን መፈወስ ተችሏል። ይህም ሄፒታይተስ ሲን ከዓለም ማስወገድ እንደሚቻል ተስፋ አጭሯል“” ብሏል። ሆኖም ግን በየዓመቱ 70 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ። ከነዚህም 400,000 ይሞታሉ። ገዳዩ ቫይረስ ሄፒታይተስ ኤ እና ቢ የተገኙት በ1960ዎቹ ነበር። በ1972 አሜሪካ ውስጥ ምርምር እያደረጉ የነበሩት ፕ/ር ሀርቪ አልተር ከሁለቱ ቫይረሶች በተጨማሪ ሌላም ገዳይ ቫይረስ መኖሩን ደረሱበት። ብዙዎች ደም ከተለገሳቸው በኋላም ከህመማቸው አልተፈወሱም ነበር። ተመራማሪው፤ ህመም ካለባቸው ሰዎች ለቺምፓንዚዎች ደም መሰጠቱ ለበሽታው ስርጭት ምክንያት መሆኑን ደርሰውበታል። በወቅቱ ምንነቱ ያልታወቀው ህመም ‘ነን ኤ- ነን ቢ’ ወይም ኤም ቢም ያልሆነ ሄፒታይተስ ተብሎ ይጠራ ነበር። ፕ/ር ማይክል ሆግተን በ1989 የቫይረሱን ዘረ መለ መለየት ችለዋል። ከዛም ቫይረሱ ሄፒታይተስ ሲ ተብሏል። • ሩሲያና ቻይና በአሜሪካ ምርጫ ማን እንዲያሸንፍ ነው የሚፈልጉት? በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ይሠሩ የነበሩት ፕ/ር ቻርልስ ራይስ ደግሞ በ1997 ለጥናቱ መደምደሚያ ሰጥተዋል። ሄፒታይተስ ሲ ቫይረስ ላይ ዘረ መል አክለው በቺምፓንዚ ኩላሊት ውስጥ ከጨመሩ በኋላ በሽታው እንዴት እንደሚከሰት ደርሰውበታል። የኖቤል ኮሚቴ ዋና ጸሀፊ ፕ/ር ቶማስ ፐርልማን፤ ከሦስቱ ሳይንቲስቶች መካከል ለሁለቱ ደውለው ኖቤል ማሸነፋቸውን እንደነገሯቸው ገልጸዋል። “ሳነጋግራቸው ደስ ብሎኝ ነበር። ማሸነፋቸውን ሲሰሙ ተገርመዋል። ተደስተዋልም” ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54421300 |
2health
| ኢኳዶር ለሁሉም ዜጎቿ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ግዴታ አደረገች | ኢኳዶር እየተባበሰ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታትና እንደ ኦሚክሮን ያሉ ዝርያዎችን ጉዳት ለመቀነስ በሚል አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወድ የሚያስገድድ መመሪያ አወጣች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳለው አጠቃላይ ሕዝቡን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት ክምችት ያለ ሲሆን፣ የሕክምና ማስረጃ ያላቸው ሰዎች ብቻ ያለመከተብ መብት ይኖራቸዋል። ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ውስጥም ማንኛውም ዕድሜው ከአምስት ዓመት በላይ የሆነ ሰው በሙሉ ክትባቱን ይወስዳል ተብሏል። እስካሁን ድረስ ዕድሜያቸው ለክትባት ከደረሱ ሰዎች ውስጥ 77.2 በመቶ ያህሉ ሁለት ዙር ክትባት ሲወስዱ ከ900 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሰዎች ሦስተኛ ዙር ክትባታቸውን ወስደዋል። የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ ክትባቱ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል አቅም የፈጠረና ይህም በቫይረሱ ተይዘው ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎችን ቁጥር እና ሞትን ለመቀነስ ያገዘ ነው። በአገሪቱ ሕገ መንግሥት የተቀመጠው የዜጎችን ጤንነት የማስጠበቅ ግዴታ በመንግሥት ጫንቃ ላይ የወደቀ መሆኑንና እርሱን ለማስፈጸም ሕጉን መሠረት ተደርጎ የተሰጠ ውሳኔ መሆኑን የኢኳዶር ጤና ሚኒስቴሩ ገልጿል። አውስትራሊያ እና ጀርመን ተመሳሳይ ውሳኔ የመስጠት ዕቅድ ያላቸው አገራት ናቸው። ኢኳዶር ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ጥቅም ላይ የሚውል የክትባት የምስክር ወረቀት ለዜጎቿ አዘጋጅታለች። ወደ ሲኒማና ቴአትር ቤቶች ወይም የገበያ ማዕከላት ለመግባት ይህንን ወረቀት ማሳየት ግዴታ ይሆናልም ተብሏል። ኢኳዶር የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ከተከሰተ ጀምሮ 33 ሺህ 600 ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዘ ሞት መዝግባለች። | ኢኳዶር ለሁሉም ዜጎቿ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ግዴታ አደረገች ኢኳዶር እየተባበሰ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታትና እንደ ኦሚክሮን ያሉ ዝርያዎችን ጉዳት ለመቀነስ በሚል አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወድ የሚያስገድድ መመሪያ አወጣች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳለው አጠቃላይ ሕዝቡን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት ክምችት ያለ ሲሆን፣ የሕክምና ማስረጃ ያላቸው ሰዎች ብቻ ያለመከተብ መብት ይኖራቸዋል። ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ውስጥም ማንኛውም ዕድሜው ከአምስት ዓመት በላይ የሆነ ሰው በሙሉ ክትባቱን ይወስዳል ተብሏል። እስካሁን ድረስ ዕድሜያቸው ለክትባት ከደረሱ ሰዎች ውስጥ 77.2 በመቶ ያህሉ ሁለት ዙር ክትባት ሲወስዱ ከ900 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሰዎች ሦስተኛ ዙር ክትባታቸውን ወስደዋል። የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ ክትባቱ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል አቅም የፈጠረና ይህም በቫይረሱ ተይዘው ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎችን ቁጥር እና ሞትን ለመቀነስ ያገዘ ነው። በአገሪቱ ሕገ መንግሥት የተቀመጠው የዜጎችን ጤንነት የማስጠበቅ ግዴታ በመንግሥት ጫንቃ ላይ የወደቀ መሆኑንና እርሱን ለማስፈጸም ሕጉን መሠረት ተደርጎ የተሰጠ ውሳኔ መሆኑን የኢኳዶር ጤና ሚኒስቴሩ ገልጿል። አውስትራሊያ እና ጀርመን ተመሳሳይ ውሳኔ የመስጠት ዕቅድ ያላቸው አገራት ናቸው። ኢኳዶር ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ጥቅም ላይ የሚውል የክትባት የምስክር ወረቀት ለዜጎቿ አዘጋጅታለች። ወደ ሲኒማና ቴአትር ቤቶች ወይም የገበያ ማዕከላት ለመግባት ይህንን ወረቀት ማሳየት ግዴታ ይሆናልም ተብሏል። ኢኳዶር የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ከተከሰተ ጀምሮ 33 ሺህ 600 ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዘ ሞት መዝግባለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-59778546 |
3politics
| የኢትዮጵያና የቱርክ መሪዎች ውይይት በአንካራ | በትናንትናው ዕለት በቱርኳ መዲና አንካራ የተገናኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ፕሬዚዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶጋን የትግራይ ግጭት፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ የድንበር ውዝግብን በተመለከተ መክረዋል፤ እንዲሁም ወታደራዊ ስምምነቶችም ላይ መድረሳቸውም ተገልጿል። ሁለቱ አገራት ወታደራዊ የገንዘብ ስምምነትን ላይ መፈራረማቸው ቢገለፅም የስምምነቱ ዝርዝር አስካሁን ይፋ አልሆኑም። ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የትግራይን ጦርነት በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጠይቀው ግጭቱንም ለመፍታት አገራቸውም የምትችለውን ሁሉ ታደርጋለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአስቸጋሪ ወቅት እያለፈች መሆኑንም አስታውሰው ለትግራይ ግጭት ለዘብተኛ መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ ሃሳብ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አገራት ውስጥ ቁልፍ ሚና የምትጫወት ናት ያሉት ፕሬዚዳንቱ "የግዛት አንድነቷ መጠበቅም ሆነ ሰላም ለእኛ ጠቃሚ ነው" በማለት አገሪቷ ያላትን ስፍራ አፅንኦት ሰጥተዋል። ግጭቱ በሰላም እንዲፈታም ከፍተኛ ትኩረት መንግሥታቸው መስጠቱን ጠቅሰው "ካለበለዚያ ግጭቱ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የቀጠናው አጎራባቾች አገራትም መጎዳታቸው አይቀርም" ብለዋል። ፕሬዚዳንት ኤርዶጋንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ረቡዕ ዕለት ነሐሴ 12/2013 ዓ.ም በአንካራ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን የተናገሩት። የሁለቱ አገራት መሪዎች በተገናኙበት ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል በአልፋሽቃ ያለውን የድንበር ውዝግብና ፍጥጫም አንስተዋል። ግጭቱ በውይይት እንደሚቋጭ ተስፋ አድርገው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትናንትናው ዕለት እንዲሁም ከሱዳኑ ሽግግር ምክር ቤቱ ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አልቡህራን ጋር ከሳምንት በፊት ውይይት ማድረጋቸውን ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። "በሰላማዊ ሁኔታ እንዲቋጭም ማንኛውንም አይነት ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ነን። አደራዳሪነትንም ጨምሮ" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። የሁለቱ አገራት መሪዎች ለዘመናት የዘለቀውን ግንኙነታቸውን በተመለከተ እንዲሁም በምጣኔ ሀብት፣ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ያለው ትስስር በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የኢንቨስትመንት ግንኙነት 2.5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም በመሰረተ-ልማት፣ በትራንስፖርት፣ በጨርቃ ጨርቅና በሌሎችም ዘርፎች ላይ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ዓመታዊ የንግድ ግንኙነትም 650 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን ፕሬዚዳንቱም አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የሁለትዮሽ ንግድን እውን ለማድረግ መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች መገምገማቸውን ተናግረዋል። በርካታ የቱርክ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰው ከዚህም በተጨማሪ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንንም እኚሁ ኩባንያዎች መቅጠር መቻላቸውንም አስታውሰዋል። "በኢትዮጵያ ውስጥ የምናደርገው ይህ ኢንቨስትመንትም እንደሚጨምር ተስፋ አለን። በዚህ ረገድም አስፈላጊውን ድጋፍና እውቅና እንሰጣለን፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥት ኩባንያዎቻችንን እንደሚደግፍ እርግጠኞች ነን" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትም እንዲጠናከር አገራቸው አጥብቃ እንደምትሰራ የመንግሥታቸውን አቋም ገልፀዋል። ለቱርክ ኢንቨስተሮችም ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን በማለትም ለፕሬዚዳንቱ መልሰዋል። ሁለቱ አገራት በተለያዩ ዘርፎች ላይ ጠቃሚ ያሉትን ስምምነቶችን መፈራረማቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህም ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና፣ ማኅበራዊ ትብብሮችን ስምምነቶችንም ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል። የሁለቱ አገራት ግንኙነት የተመሰረተው "በመከባበር፣ በመተማመን እና በትብብር ላይ ነው" በማለት በዚህ አስፈላጊ ወቅትም ቱርክ አጋርነቷንና ወዳጅነቷን ማሳየቷን አድንቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንንም በተመለከተ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው "የቱርክ መንግሥት እና ሕዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር አገራችን ኢትዮጵያ መቼም አትረሳውም" በማለት አስፍረዋል። ኢትዮጵያ የቱርክን አጋርነትና ወዳጅነት ዋጋ እንደምትሰጥ ገልፀው በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የቱርክ 'ኮኦፐሬሽንና ኮኦርዲኔሽን ኤጀንሲ' በአዲስ አበባ ምስረታንም በመጥቀስ ምስጋናቸውን ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሁለቱን አገራት ጥንታዊ ስልጣኔ ተመሳሳይነት አስታውሰው 16ኛው ክፍለ ዘመንም ወደኋላ ያስቆጠረ ነው ብለዋል። ቱርክ ለብዙዎች አርዓያ የሆነ የአገር ግንባታ እንዳካሄደች በዚሁ አጋጣሚ ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በተለይም አገሪቱ በለውጥ ጎዳና እየሄደች ባለችበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸውንም ለማጠናከር እየሰሩ እንደሆነ ጠቅሰዋል። የሁለቱም አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የቀጠለ ነው እንዲሁም የቱርክ ፊልም ኢንዱስትሪ ለዚህም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በአውሮፓውያኑ 2015 ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰው "ኢትዮጵያ ምንጊዜም ቢሆን የመቻቻልና ልዩነቶች የሚከበሩባት ምድር ናት። ይህም የኢትዮጵያን የአገር ውስጥ እና የውጭ ግንኙነት መሰረት መንፈስን ያጠቃለለ ነው" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር በቱርክ ያደረጉትን የአንድ ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ረቡዕ ምሽት ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው ተገልጿል። | የኢትዮጵያና የቱርክ መሪዎች ውይይት በአንካራ በትናንትናው ዕለት በቱርኳ መዲና አንካራ የተገናኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ፕሬዚዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶጋን የትግራይ ግጭት፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ የድንበር ውዝግብን በተመለከተ መክረዋል፤ እንዲሁም ወታደራዊ ስምምነቶችም ላይ መድረሳቸውም ተገልጿል። ሁለቱ አገራት ወታደራዊ የገንዘብ ስምምነትን ላይ መፈራረማቸው ቢገለፅም የስምምነቱ ዝርዝር አስካሁን ይፋ አልሆኑም። ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የትግራይን ጦርነት በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጠይቀው ግጭቱንም ለመፍታት አገራቸውም የምትችለውን ሁሉ ታደርጋለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአስቸጋሪ ወቅት እያለፈች መሆኑንም አስታውሰው ለትግራይ ግጭት ለዘብተኛ መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ ሃሳብ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አገራት ውስጥ ቁልፍ ሚና የምትጫወት ናት ያሉት ፕሬዚዳንቱ "የግዛት አንድነቷ መጠበቅም ሆነ ሰላም ለእኛ ጠቃሚ ነው" በማለት አገሪቷ ያላትን ስፍራ አፅንኦት ሰጥተዋል። ግጭቱ በሰላም እንዲፈታም ከፍተኛ ትኩረት መንግሥታቸው መስጠቱን ጠቅሰው "ካለበለዚያ ግጭቱ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የቀጠናው አጎራባቾች አገራትም መጎዳታቸው አይቀርም" ብለዋል። ፕሬዚዳንት ኤርዶጋንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ረቡዕ ዕለት ነሐሴ 12/2013 ዓ.ም በአንካራ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን የተናገሩት። የሁለቱ አገራት መሪዎች በተገናኙበት ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል በአልፋሽቃ ያለውን የድንበር ውዝግብና ፍጥጫም አንስተዋል። ግጭቱ በውይይት እንደሚቋጭ ተስፋ አድርገው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትናንትናው ዕለት እንዲሁም ከሱዳኑ ሽግግር ምክር ቤቱ ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አልቡህራን ጋር ከሳምንት በፊት ውይይት ማድረጋቸውን ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። "በሰላማዊ ሁኔታ እንዲቋጭም ማንኛውንም አይነት ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ነን። አደራዳሪነትንም ጨምሮ" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። የሁለቱ አገራት መሪዎች ለዘመናት የዘለቀውን ግንኙነታቸውን በተመለከተ እንዲሁም በምጣኔ ሀብት፣ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ያለው ትስስር በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የኢንቨስትመንት ግንኙነት 2.5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም በመሰረተ-ልማት፣ በትራንስፖርት፣ በጨርቃ ጨርቅና በሌሎችም ዘርፎች ላይ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ዓመታዊ የንግድ ግንኙነትም 650 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን ፕሬዚዳንቱም አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የሁለትዮሽ ንግድን እውን ለማድረግ መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች መገምገማቸውን ተናግረዋል። በርካታ የቱርክ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰው ከዚህም በተጨማሪ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንንም እኚሁ ኩባንያዎች መቅጠር መቻላቸውንም አስታውሰዋል። "በኢትዮጵያ ውስጥ የምናደርገው ይህ ኢንቨስትመንትም እንደሚጨምር ተስፋ አለን። በዚህ ረገድም አስፈላጊውን ድጋፍና እውቅና እንሰጣለን፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥት ኩባንያዎቻችንን እንደሚደግፍ እርግጠኞች ነን" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትም እንዲጠናከር አገራቸው አጥብቃ እንደምትሰራ የመንግሥታቸውን አቋም ገልፀዋል። ለቱርክ ኢንቨስተሮችም ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን በማለትም ለፕሬዚዳንቱ መልሰዋል። ሁለቱ አገራት በተለያዩ ዘርፎች ላይ ጠቃሚ ያሉትን ስምምነቶችን መፈራረማቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህም ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና፣ ማኅበራዊ ትብብሮችን ስምምነቶችንም ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል። የሁለቱ አገራት ግንኙነት የተመሰረተው "በመከባበር፣ በመተማመን እና በትብብር ላይ ነው" በማለት በዚህ አስፈላጊ ወቅትም ቱርክ አጋርነቷንና ወዳጅነቷን ማሳየቷን አድንቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንንም በተመለከተ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው "የቱርክ መንግሥት እና ሕዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር አገራችን ኢትዮጵያ መቼም አትረሳውም" በማለት አስፍረዋል። ኢትዮጵያ የቱርክን አጋርነትና ወዳጅነት ዋጋ እንደምትሰጥ ገልፀው በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የቱርክ 'ኮኦፐሬሽንና ኮኦርዲኔሽን ኤጀንሲ' በአዲስ አበባ ምስረታንም በመጥቀስ ምስጋናቸውን ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሁለቱን አገራት ጥንታዊ ስልጣኔ ተመሳሳይነት አስታውሰው 16ኛው ክፍለ ዘመንም ወደኋላ ያስቆጠረ ነው ብለዋል። ቱርክ ለብዙዎች አርዓያ የሆነ የአገር ግንባታ እንዳካሄደች በዚሁ አጋጣሚ ጠቅሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በተለይም አገሪቱ በለውጥ ጎዳና እየሄደች ባለችበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸውንም ለማጠናከር እየሰሩ እንደሆነ ጠቅሰዋል። የሁለቱም አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የቀጠለ ነው እንዲሁም የቱርክ ፊልም ኢንዱስትሪ ለዚህም ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በአውሮፓውያኑ 2015 ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰው "ኢትዮጵያ ምንጊዜም ቢሆን የመቻቻልና ልዩነቶች የሚከበሩባት ምድር ናት። ይህም የኢትዮጵያን የአገር ውስጥ እና የውጭ ግንኙነት መሰረት መንፈስን ያጠቃለለ ነው" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር በቱርክ ያደረጉትን የአንድ ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ረቡዕ ምሽት ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው ተገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58265923 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ፈተና ውስጥ የገባው የግብርና ዘርፍ | ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ በርካታ ነገሮች ተቀያይረዋል። ሰው የማይንቀሳቀስባቸው ዋና ጎዳናዎች ታይተዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚታደሟቸው የእግር ኳስ ውድድሮች ያለ ድጋፍ ተካሂደዋል፣ የዓለም መሪዎች ሳይቀር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገው ታይተዋል። ምናልባት ለብዙዎችም ኮሮረናቫይረስ ሲባል በጭንቅላታቸው የሚመጡት ምስሎች እነዚህ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ወረርሽኙ በአይናችን ከምናያቸውና በቅርቡ ከምናስተውላቸው ነገሮች በተጨማሪ የበርካቶችን ሕይወት ከስረ መሰረቱ ቀይሯል፤ እንዳልነበር አድርጎ አበላሽቷል። ነገር ግን ወረርሽኙ ያስከተለው ጉዳት በሁሉም አገራትና አህጉራት ተመሳሳይ አይደለም። እንዳውም ንጽጽሩ በበርካቶች ዘንድ ግርምትን የፈጠረ ነው። አፍሪካ ውስጥ ብቻ በ36 አገራት የሚገኙ 73 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከባድ የምግብ እጥረት የጋጠማቸው ሲሆን በአውሮፓ ግን ግማሽ ሚሊየን የሚሆኑት ብቻ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል። ከዚህ በፊት በኢቦላ ወረርሽኝ ስትሰቃይ የነበረችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰው ደቡብ ሱዳን ደግሞ በወረርሽኙ ምክንያት ከፍተኛ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው አገራት ናቸው። በአፍሪካ የሚገኙ ገበሬዎች በክረምት ወር የሚዘሩትን ዘር ማግኘት ያልቻሉ ሲሆን በአሜሪካ ደግሞ የእርድ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች በመዘጋታቸው ከብቶቻቸውን ሳይፈልጉ ለማቆየት ተገድደዋል፣ ወተት ገዢ አጥተው ምርታቸውን ለመድፋት ተገድደዋል። የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝም በዓለማችን ላይ ያለውን የምግብ ስርጭት ስርአት ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል። ባደጉት አገራት ከግብርና ስራ ጋር የተከሰቱት ችግሮች ቀላል የሚባሉ ባይሆኑም ድሀ በሚባሉትና በማደግ ላሉት አገራት ግን ጉዳቱ ከፍተኛ ነው። በድሆቹ አገራት ግብርና በብዛት የጉልበት ስራ ላይ የተንጠለጠለ ሲሆን ዘር ከመዝራት አንስቶ እስከ መሰብሰብ ድረስ ባህላዊ በሆነና በርካታ ሰዎች በሚያሳትፍ መልኩ ነው የሚካሄደው። በአውሮፓ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ጋር ተያይዞ ተግባራዊ በተደረጉት የእንቅስቃሴ ገደብና ሌሎች እርምጃዎች ምክንያት በግብርናው ዘርፍ ላይ በጊዜያዊነት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ በርካታ ሰዎች ሕይወት የተመሰቃቀለ ሲሆን ምርቱን የሚሸጡትም ሰዎች ቢሆኑ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይህንን ተከትሎም የምግብ ስርጭቱ ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትና እጥረት ተከስቷል። ለምሳሌ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 75 ሺ ሰዎች በጊዜያዊነት በግብርና ስራ ላይ ተቀጥረው ይሰሩ ነበር። አብዛኛዎቹ ደግሞ ከሌሎች የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት የመጡ ናቸው። ወረርሽኙን ተከትሎ በተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦችና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎች ምክንያት ታዲያ እነዚህ ሰራተኞች በስራ ቦታቸው ላይ መገኘት ባለመቻላቸው አብዛኛዎቹ ወደመጡባቸው አገራት ተመልሰዋል። ገበሬዎችን የጉልበት ስራውን የሚሰራላቸው ሰው በማጣታቸው ተቸግረዋል። በአጠቃላይ በአውሮፓ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ጊዜያዊ ሰራተኞች ከስራ ውጪ መሆናቸውን ተከትሎ የግብርናው ዘርፍ ከፍተኛውን ጉዳት አስተናግዷል። በተመሳሳይ በአውስትራሊያም ቢሆን በአትክልት ምርት ላይ ተሰማርተው ከሚገኙ ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በጊዜያዊነት ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆኑ በአሜሪካ ደግሞ 10 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር ይይዛሉ። በካናዳ ያሉ ትልልቅ ማሳዎች ደግሞ ከ60 ሺ በላይ የሚሆኑ ከሌሎች አገራት የመጡ ሰራተኞችን ቀጥረው ያሰራሉ። በብራዚል ደግሞ ቡና አምራች ገበሬዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በጊዜያዊነት ቀጥረው ያሰሩ ነበር። ነገር ግን በእንቅስቃሴ ገደቡ ምክንያት እነዚህ ሰዎች በስራ ገበታቸው ላይ መገኘት አለመቻላቸው ዘርፉ ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት በተጨማሪ ሕይወታቸውን በዚሁ ስራ ላይ ላደረጉ ሰዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል። ከግብርናው ዘርፍ ሳንወጣ የከብት አርቢዎች ሕይወትም ቢሆን በዚሁ ወረርሽኝ ምክንያት ተጎድቷል። ምንም እንኳን ይሄ ዘርፍ በተለይም እርድ ላይ ያለው ሂደት ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በፊትም ከፍተኛ ንጽህና የሚፈልግ ቢሆንም ከኮቪድ-19 በኋላ ግን ነገሮች ከባድ ሆነዋል። በአውሮፓ 90 በመቶ የሚሆነው የስጋ ምርት እዛው የተመረተበት አገር ውስጥ አልያም አውሮፓ ውስጥ ነው ጥቅም ላይ የሚውለው። ነገር ግን ይህ ማለት ከእንቅስቃሴ ገደቡ ጋር በተያያዘ ችግር አያጋጥመውም ማለት አይደለም። ምርቱ ተቀናባብሮ ወደ ተጠቃሚዎች እስከሚደርስበት ባሉት የሂደት ስርአቶች ውስጥ የሚሰሩ በርካታ ሰዎች ከስራ ውጪ ሆነዋል አልያም ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ሆነዋል። እዚህም ጋር ተጠያቂው ኮሮረናቫይረስ ነው። በአፍሪካ ደግሞ በግብርና፣ ማዕድን እና ግንባታ ዘርፎች ላይ የኮሮናቫይረስ ጉዳትን ለመቀነስ አገራት ቀጣይነት ያለውና ውጤታማ እርምጃ በፍጥነት መውሰድ ግድ ይላቸዋል። ግብርና የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚደግፍ ዘርፍ እንደመሆኑ ደግሞ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ባለሙያዎች ከወዲሁ እያሳሰቡ ነው። በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት የዝናብ ወቅት ሲቃረብ የገበሬዎች ማሳ በተቻለ መጠን በሰብል እንዲሞላ ማድረግ አለባቸው። የአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መር ሽሽግር በሚያደርጉበት በዚህ ወቅት የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ትልቅ ስጋት ነው። ከዚህ በተጨማሪ መንግሥታት የከተማ ግብርና ላይ ያላቸውን መቀየር ግድ ይላቸዋል። ምክንያቱም ለብዙ ዓመታት ሲሰራበት የነበረውን የግብርና ስርአት ይዞ መቀጠል ስለማይቻል ዜጎች በቀላሉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በከተሞች አካባቢ እንዲ|ያመርቱ ማድረግ ከኮሮረናቫይረስ በኋላም አዋጭ አካሄድ ይሆናል። | ኮሮናቫይረስ፡ ፈተና ውስጥ የገባው የግብርና ዘርፍ ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ በርካታ ነገሮች ተቀያይረዋል። ሰው የማይንቀሳቀስባቸው ዋና ጎዳናዎች ታይተዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚታደሟቸው የእግር ኳስ ውድድሮች ያለ ድጋፍ ተካሂደዋል፣ የዓለም መሪዎች ሳይቀር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገው ታይተዋል። ምናልባት ለብዙዎችም ኮሮረናቫይረስ ሲባል በጭንቅላታቸው የሚመጡት ምስሎች እነዚህ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ወረርሽኙ በአይናችን ከምናያቸውና በቅርቡ ከምናስተውላቸው ነገሮች በተጨማሪ የበርካቶችን ሕይወት ከስረ መሰረቱ ቀይሯል፤ እንዳልነበር አድርጎ አበላሽቷል። ነገር ግን ወረርሽኙ ያስከተለው ጉዳት በሁሉም አገራትና አህጉራት ተመሳሳይ አይደለም። እንዳውም ንጽጽሩ በበርካቶች ዘንድ ግርምትን የፈጠረ ነው። አፍሪካ ውስጥ ብቻ በ36 አገራት የሚገኙ 73 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከባድ የምግብ እጥረት የጋጠማቸው ሲሆን በአውሮፓ ግን ግማሽ ሚሊየን የሚሆኑት ብቻ የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል። ከዚህ በፊት በኢቦላ ወረርሽኝ ስትሰቃይ የነበረችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰው ደቡብ ሱዳን ደግሞ በወረርሽኙ ምክንያት ከፍተኛ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው አገራት ናቸው። በአፍሪካ የሚገኙ ገበሬዎች በክረምት ወር የሚዘሩትን ዘር ማግኘት ያልቻሉ ሲሆን በአሜሪካ ደግሞ የእርድ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች በመዘጋታቸው ከብቶቻቸውን ሳይፈልጉ ለማቆየት ተገድደዋል፣ ወተት ገዢ አጥተው ምርታቸውን ለመድፋት ተገድደዋል። የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝም በዓለማችን ላይ ያለውን የምግብ ስርጭት ስርአት ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል። ባደጉት አገራት ከግብርና ስራ ጋር የተከሰቱት ችግሮች ቀላል የሚባሉ ባይሆኑም ድሀ በሚባሉትና በማደግ ላሉት አገራት ግን ጉዳቱ ከፍተኛ ነው። በድሆቹ አገራት ግብርና በብዛት የጉልበት ስራ ላይ የተንጠለጠለ ሲሆን ዘር ከመዝራት አንስቶ እስከ መሰብሰብ ድረስ ባህላዊ በሆነና በርካታ ሰዎች በሚያሳትፍ መልኩ ነው የሚካሄደው። በአውሮፓ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ጋር ተያይዞ ተግባራዊ በተደረጉት የእንቅስቃሴ ገደብና ሌሎች እርምጃዎች ምክንያት በግብርናው ዘርፍ ላይ በጊዜያዊነት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ በርካታ ሰዎች ሕይወት የተመሰቃቀለ ሲሆን ምርቱን የሚሸጡትም ሰዎች ቢሆኑ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይህንን ተከትሎም የምግብ ስርጭቱ ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትና እጥረት ተከስቷል። ለምሳሌ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 75 ሺ ሰዎች በጊዜያዊነት በግብርና ስራ ላይ ተቀጥረው ይሰሩ ነበር። አብዛኛዎቹ ደግሞ ከሌሎች የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት የመጡ ናቸው። ወረርሽኙን ተከትሎ በተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦችና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎች ምክንያት ታዲያ እነዚህ ሰራተኞች በስራ ቦታቸው ላይ መገኘት ባለመቻላቸው አብዛኛዎቹ ወደመጡባቸው አገራት ተመልሰዋል። ገበሬዎችን የጉልበት ስራውን የሚሰራላቸው ሰው በማጣታቸው ተቸግረዋል። በአጠቃላይ በአውሮፓ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ጊዜያዊ ሰራተኞች ከስራ ውጪ መሆናቸውን ተከትሎ የግብርናው ዘርፍ ከፍተኛውን ጉዳት አስተናግዷል። በተመሳሳይ በአውስትራሊያም ቢሆን በአትክልት ምርት ላይ ተሰማርተው ከሚገኙ ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በጊዜያዊነት ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆኑ በአሜሪካ ደግሞ 10 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር ይይዛሉ። በካናዳ ያሉ ትልልቅ ማሳዎች ደግሞ ከ60 ሺ በላይ የሚሆኑ ከሌሎች አገራት የመጡ ሰራተኞችን ቀጥረው ያሰራሉ። በብራዚል ደግሞ ቡና አምራች ገበሬዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በጊዜያዊነት ቀጥረው ያሰሩ ነበር። ነገር ግን በእንቅስቃሴ ገደቡ ምክንያት እነዚህ ሰዎች በስራ ገበታቸው ላይ መገኘት አለመቻላቸው ዘርፉ ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት በተጨማሪ ሕይወታቸውን በዚሁ ስራ ላይ ላደረጉ ሰዎች ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል። ከግብርናው ዘርፍ ሳንወጣ የከብት አርቢዎች ሕይወትም ቢሆን በዚሁ ወረርሽኝ ምክንያት ተጎድቷል። ምንም እንኳን ይሄ ዘርፍ በተለይም እርድ ላይ ያለው ሂደት ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በፊትም ከፍተኛ ንጽህና የሚፈልግ ቢሆንም ከኮቪድ-19 በኋላ ግን ነገሮች ከባድ ሆነዋል። በአውሮፓ 90 በመቶ የሚሆነው የስጋ ምርት እዛው የተመረተበት አገር ውስጥ አልያም አውሮፓ ውስጥ ነው ጥቅም ላይ የሚውለው። ነገር ግን ይህ ማለት ከእንቅስቃሴ ገደቡ ጋር በተያያዘ ችግር አያጋጥመውም ማለት አይደለም። ምርቱ ተቀናባብሮ ወደ ተጠቃሚዎች እስከሚደርስበት ባሉት የሂደት ስርአቶች ውስጥ የሚሰሩ በርካታ ሰዎች ከስራ ውጪ ሆነዋል አልያም ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ሆነዋል። እዚህም ጋር ተጠያቂው ኮሮረናቫይረስ ነው። በአፍሪካ ደግሞ በግብርና፣ ማዕድን እና ግንባታ ዘርፎች ላይ የኮሮናቫይረስ ጉዳትን ለመቀነስ አገራት ቀጣይነት ያለውና ውጤታማ እርምጃ በፍጥነት መውሰድ ግድ ይላቸዋል። ግብርና የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚደግፍ ዘርፍ እንደመሆኑ ደግሞ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ባለሙያዎች ከወዲሁ እያሳሰቡ ነው። በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት የዝናብ ወቅት ሲቃረብ የገበሬዎች ማሳ በተቻለ መጠን በሰብል እንዲሞላ ማድረግ አለባቸው። የአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መር ሽሽግር በሚያደርጉበት በዚህ ወቅት የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ትልቅ ስጋት ነው። ከዚህ በተጨማሪ መንግሥታት የከተማ ግብርና ላይ ያላቸውን መቀየር ግድ ይላቸዋል። ምክንያቱም ለብዙ ዓመታት ሲሰራበት የነበረውን የግብርና ስርአት ይዞ መቀጠል ስለማይቻል ዜጎች በቀላሉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በከተሞች አካባቢ እንዲ|ያመርቱ ማድረግ ከኮሮረናቫይረስ በኋላም አዋጭ አካሄድ ይሆናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54577100 |
2health
| “ከኮሮናቫይረስ ባገግምም አሁንም በሽታው ይገድለኛል ብዬ እፈራለሁ” | የ42 ዓመቱ ራጀሽ ቲዋሪ ከስልኩ የሰፋ መጠን ያለው ስክሪን ይፈራል። ቴሌቭዥን ወይም ኮምፒውተር አንዳች ጥቃት የሚያደርሱበት ፍጥረቶች ይመስሉታል። ራጀሽ ቅዠት የጀመረው በጽኑ ህሙማን ክፍል ዘለግ ላለ ጊዜ ከቆየ በኋላ ነበር። ሰኔ ላይ ኮሮናቫይረስ ይዞት ስለተዳከመ በቬንትሌተር እየታገዘ እንዲተነፍስ ተደርጓል። ራጀሽ ከሦስት ሳምንት በኋላ ተሽሎት ከሆስፒታል ቢወጣም ሙሉ በሙሉ እንዳላገገመ ተገነዘበ። “ሕክምናው ቢያሽለኝም ከሆስፒታል ከወጣሁ በኋላ የነበሩት የመጀመሪያ ሳምንታት በጣም ከባድ ነበሩ” ይላል። ወደ ቤት ሲመለስ ቤተሰቦቹ እጅግ ተደስተው ነበር። ቆየት ሲል ግን ራጀሽ እንደ ቀድሞው እንዳልሆነ አስተዋሉ። አንድ ቀን ቴሌቭዥን እያየ በጣም ጮኸ። ቲቪውን ለመስበርም ሞከረ። ከዛ በኋላ ቤተሰቡ ቲቪ መመልከትና ላፕቶፕ መጠቀም አቆመ። ራጀሽ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ሳለ የተመለከታቸው የሕክምና መሣሪያዎችን ለመርሳት እየታገለ ነው። የ49 ዓመቱ አሚት ሻርማም ተመሳሳይ ተሞክሮ አለው። ለ18 ቀናት በለይቶ ማቆያ ሳለ በየቀኑ ሰዎች ሲሞቱ አይቷል። ወጣት፣ አዛውንት፣ ሴት፣ ወንድ. . . በርካታ የኮቪድ-19 ታማሚዎች በሞት ሲለዩ አሚት ተመልክቷል። “ሁለት ሰዎች አጠገቤ ሞተው አስክሬናቸው ለረዥም ሰዓት አልተነሳም ነበር። ይህንን ከአዕምሮዬ ማውጣት አልቻልኩም። አሁንም ኮሮናቫይረስ ሊገለኝ ይችላል ብዬ እፈራለሁ” ይላል። አሚት አሰቃቂ ቆይታውን ለመርሳት እየታገለ ነው። ከኮሮናቫይረስ ካገገመ በኋላ ጭምት ሆኗል። ካወራም በበሽታው ሳቢያ ስለሞቱ ሰዎች እንደሚያወራ አጎቱ ይናገራሉ። ኮቪድ-19 የሚያስከትለው የአዕምሮ ጤና ቀውስ በሕንድ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች የአዕምሮ ጤና ቀውስ እየገጠማቸው ይገኛል። የሥነ ልቦና ሀኪሙ ዶ/ር ቫሰንት ሙንድራ “ገና ሆስፒታል ሳይደርሱ አዕምሯቸው ይዳከማል። ከዛ ኮቪድ-19 ደግሞ የስሜት ህዋሳትን የበለጠ ያዝላል” ይላሉ። ህሙማኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ አይፈቀድም። ሀኪሞቻቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ስለሚያደርጉም ፊታቸውን ማየት አይችሉም። ይህም ዶክተሮቻቸውን እንዳያምኑ ያደርጋቸዋል። የኮሮናቫይረስ ህሙማን ሲያገግሙ ብቸኝነት ሊሰማቸው ይችላል። አስጨናቂ ክስተትን ተከትሎ የሚከሰት ድብት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉም ዶ/ር ቫንሰት ያስረዳሉ። ከኮሮናቫይረስ ህሙማን ጋር የተያያዘ የአዕምሮ ህመም ተገቢውን ትኩረት አላገኘም። “በወረርሽኙ ወቅት እየታየ ያለው ሕንድ ለአዕምሮ ጤና ብዙም ቦታ እንደማትሰጥ ነው” የሚሉት ዶ/ር ሶሚትራ ፓትሬ ናቸው። የአዕምሮ ህሙማንን ለማከም በቂ ሆስፒታል እንዲሁም ባለሙያዎች የሉም። በትንንሽ ከተሞች ደግሞ ችግሩ ይከፋል። በከተማና በገጠር የሚኖሩ ሰዎች ለአዕምሮ ጤና ያላቸው ተደራሽነት እኩል አለመሆኑን ወረርሽኙ እንዳሳየ ዶክተሩ ይገልጻሉ። “የሕንድ መንግሥት ችግሩን በአፋጣኝ ካልፈታ የአዕምሮ ህመም ወረርሽኝ ይገጥመናል” ሲሉም ያክላሉ። ባለሙያው እንደሚሉት፤ የመጀመሪያው እርምጃ ሰዎች ስለ አዕምሮ ህመም ምልክቶች እንዲያውቁ ማድረግ ነው። በተለይም ለአነስተኛ ከተማ ነዋሪዎች ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። በደልሂው ፎርቲስ ሆስፒታል የአዕምሮ ጤና ክፍል ኃላፊ ካምና ቺቤር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በርካታ ሰዎች የአዕምሮ ህመም እንደገጠማቸው ይናገራሉ። የእንቅስቃሴ ገደቡና ወደፊት ምን እንደሚከሰት አለማወቅ ብዙዎችን ጭንቀትና ድብርት ውስጥ ከቷል። “ችግሩ ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ ነው” ብለዋል ኃላፊዋ። በድህረ ኮቪድ-19 ማገገሚያ እቅድ የአዕምሮ ጤና ጉዳይ እንዲገባ በርካታ ሀኪሞች እየጠየቁ ነው። | “ከኮሮናቫይረስ ባገግምም አሁንም በሽታው ይገድለኛል ብዬ እፈራለሁ” የ42 ዓመቱ ራጀሽ ቲዋሪ ከስልኩ የሰፋ መጠን ያለው ስክሪን ይፈራል። ቴሌቭዥን ወይም ኮምፒውተር አንዳች ጥቃት የሚያደርሱበት ፍጥረቶች ይመስሉታል። ራጀሽ ቅዠት የጀመረው በጽኑ ህሙማን ክፍል ዘለግ ላለ ጊዜ ከቆየ በኋላ ነበር። ሰኔ ላይ ኮሮናቫይረስ ይዞት ስለተዳከመ በቬንትሌተር እየታገዘ እንዲተነፍስ ተደርጓል። ራጀሽ ከሦስት ሳምንት በኋላ ተሽሎት ከሆስፒታል ቢወጣም ሙሉ በሙሉ እንዳላገገመ ተገነዘበ። “ሕክምናው ቢያሽለኝም ከሆስፒታል ከወጣሁ በኋላ የነበሩት የመጀመሪያ ሳምንታት በጣም ከባድ ነበሩ” ይላል። ወደ ቤት ሲመለስ ቤተሰቦቹ እጅግ ተደስተው ነበር። ቆየት ሲል ግን ራጀሽ እንደ ቀድሞው እንዳልሆነ አስተዋሉ። አንድ ቀን ቴሌቭዥን እያየ በጣም ጮኸ። ቲቪውን ለመስበርም ሞከረ። ከዛ በኋላ ቤተሰቡ ቲቪ መመልከትና ላፕቶፕ መጠቀም አቆመ። ራጀሽ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ሳለ የተመለከታቸው የሕክምና መሣሪያዎችን ለመርሳት እየታገለ ነው። የ49 ዓመቱ አሚት ሻርማም ተመሳሳይ ተሞክሮ አለው። ለ18 ቀናት በለይቶ ማቆያ ሳለ በየቀኑ ሰዎች ሲሞቱ አይቷል። ወጣት፣ አዛውንት፣ ሴት፣ ወንድ. . . በርካታ የኮቪድ-19 ታማሚዎች በሞት ሲለዩ አሚት ተመልክቷል። “ሁለት ሰዎች አጠገቤ ሞተው አስክሬናቸው ለረዥም ሰዓት አልተነሳም ነበር። ይህንን ከአዕምሮዬ ማውጣት አልቻልኩም። አሁንም ኮሮናቫይረስ ሊገለኝ ይችላል ብዬ እፈራለሁ” ይላል። አሚት አሰቃቂ ቆይታውን ለመርሳት እየታገለ ነው። ከኮሮናቫይረስ ካገገመ በኋላ ጭምት ሆኗል። ካወራም በበሽታው ሳቢያ ስለሞቱ ሰዎች እንደሚያወራ አጎቱ ይናገራሉ። ኮቪድ-19 የሚያስከትለው የአዕምሮ ጤና ቀውስ በሕንድ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች የአዕምሮ ጤና ቀውስ እየገጠማቸው ይገኛል። የሥነ ልቦና ሀኪሙ ዶ/ር ቫሰንት ሙንድራ “ገና ሆስፒታል ሳይደርሱ አዕምሯቸው ይዳከማል። ከዛ ኮቪድ-19 ደግሞ የስሜት ህዋሳትን የበለጠ ያዝላል” ይላሉ። ህሙማኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ አይፈቀድም። ሀኪሞቻቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ስለሚያደርጉም ፊታቸውን ማየት አይችሉም። ይህም ዶክተሮቻቸውን እንዳያምኑ ያደርጋቸዋል። የኮሮናቫይረስ ህሙማን ሲያገግሙ ብቸኝነት ሊሰማቸው ይችላል። አስጨናቂ ክስተትን ተከትሎ የሚከሰት ድብት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉም ዶ/ር ቫንሰት ያስረዳሉ። ከኮሮናቫይረስ ህሙማን ጋር የተያያዘ የአዕምሮ ህመም ተገቢውን ትኩረት አላገኘም። “በወረርሽኙ ወቅት እየታየ ያለው ሕንድ ለአዕምሮ ጤና ብዙም ቦታ እንደማትሰጥ ነው” የሚሉት ዶ/ር ሶሚትራ ፓትሬ ናቸው። የአዕምሮ ህሙማንን ለማከም በቂ ሆስፒታል እንዲሁም ባለሙያዎች የሉም። በትንንሽ ከተሞች ደግሞ ችግሩ ይከፋል። በከተማና በገጠር የሚኖሩ ሰዎች ለአዕምሮ ጤና ያላቸው ተደራሽነት እኩል አለመሆኑን ወረርሽኙ እንዳሳየ ዶክተሩ ይገልጻሉ። “የሕንድ መንግሥት ችግሩን በአፋጣኝ ካልፈታ የአዕምሮ ህመም ወረርሽኝ ይገጥመናል” ሲሉም ያክላሉ። ባለሙያው እንደሚሉት፤ የመጀመሪያው እርምጃ ሰዎች ስለ አዕምሮ ህመም ምልክቶች እንዲያውቁ ማድረግ ነው። በተለይም ለአነስተኛ ከተማ ነዋሪዎች ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። በደልሂው ፎርቲስ ሆስፒታል የአዕምሮ ጤና ክፍል ኃላፊ ካምና ቺቤር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በርካታ ሰዎች የአዕምሮ ህመም እንደገጠማቸው ይናገራሉ። የእንቅስቃሴ ገደቡና ወደፊት ምን እንደሚከሰት አለማወቅ ብዙዎችን ጭንቀትና ድብርት ውስጥ ከቷል። “ችግሩ ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ ነው” ብለዋል ኃላፊዋ። በድህረ ኮቪድ-19 ማገገሚያ እቅድ የአዕምሮ ጤና ጉዳይ እንዲገባ በርካታ ሀኪሞች እየጠየቁ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-54174457 |
5sports
| የዓለም ዋንጫ፡ ሴኔጋል ስትሸነፍ የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ልጅ ለአሜሪካ ጎል አስቆጥሯል | ባለቀ ሰዓት በተቆጠረባት ጎሎች ሴኔጋል የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታዋን በኔዘርላንድስ 2 ለ 0 ተሸንፋ ጀምራለች። የመጀመሪያውን ጎል የፒኤስቪ አጥቂ ኮዲ ጋክፖ አስቆጥሯል። ተቀይሮ የገባው ዳቪ ክላሰን ሁለተኛዋን ጎል ለብርቱካናማዎቹ ማስቆጠር ችሏል። የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ውጤታማ ባለመሆናቸው ጨዋታው ለረዥም ደቂቃዎች ጎል ሳይቆጠርበት ቀጥሏል። ሴኔጋሎች በጉዳት ያጡት አጥቂያቸው ሳዲዮ ማኔ ምን ያህል እንዳጎደላቸው የታየበት ጨዋታም ሆኗል። የሴኔጋል ደጋፊዎች ስታዲሙን አድምቀውት አምሽተዋል። የሴኔጋሉ ኢስማይላ ሳር በመጀመሪያው አጋማሽ የኔዘርላንድ ተከላካዮችን አስጨንቋል። የኔዘርላንዱ አማካይ ዲ ዮንግ ደግሞ ጨዋታውን በመቆጣጠር ብቃቱን ያሳየበት ምሽት ነበር። ድሉን ተከትሎ ብርቱካናማዎቹ በመክፈቻው ጨዋታ ኳታርን 2 ለ 0 ካሸነፈችው ኢኳዶር ጋር ምድቡን መምራት ችላል። ምሽት ላይ በተካሄደ ሌላ ጨዋታ የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ልጅ ለአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ኳስ እና መረብ ለማገናኘት በቅቷል። የፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ልጅ የሆነው ቲሞቲ ዊሃ አሜሪካ እና ዌልስ አንድ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ነው ለአሜሪካ ጎል ማስቆጠር የቻለው። ከክርስቲያን ፑሊሲች የተሻገረለትን ኳስ ቲም ዊሃ ድንቅ በሆነ ሁኔታ ከመረብ ጋር አገናኝቷል። በጨዋታው መገባደጃ ላይ ዌልስ አቻ ማድረግ የቻለችውን ጎል ጋሬት ቤል ከፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል። ፕሬዝዳንት ዊሃ በአሜሪካ የተወለደው ልጁ የዓለም ዋንጫ ላይ ሲሳተፍ ለመመልከት ዘጠኝ ቀናትን በኳታር አሳልፏል። የፕሬዝዳንቱ ጉዞ በሃገር ቤት ውዝግብ አስነስቷል። የሃገሪቱ የፋይናንስ ሚንስትር ፕሬዝዳንቱ 2ሺህ ዶላር ቀን አበል አለው ማለቱ ነው የውዝግቡ መነሻ። ተቺዎችም ፕሬዝዳንቱ ቃል የገባለትን “ደሃን የሚያቅፍ አጀንዳውን” የሚቃረን ነው ሲሉ ገልጸዋል። የዓለም ዋንጫው ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች እንግሊዝ ከኢራን ባደረጉት ጨዋታ ነው የተጀመረው። ጨዋታውን እንግሊዝ 6 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። እንግሊዝ የጎል ካዝናዋን የከፈተችው በጁድ ቤሊንግሃም የጭንቅላት ጎል ነው። ቡካዮ ሳካ እና ራሂም ስተርሊንግ ከእረፍት በፊት ባስቆጠሯቸው ጎሎች እንግሊዝ 3 ለ 0 መምራት ችላለች። ከእረፍት መልስ ሳካ ለራሱ ሁለተኛዋን ለቡድኑ ደግሞ አራተኛው ጎል አስቆጥሯል። መህዲ ታሬሚ ለኢራን የመጀመሪያዋን ጎል በ65ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል። ማርከስ ራሽፎርድ እና ጃክ ግሪሊሽ ቀሪዎቹን ጎሎች ተቀይረው ገብተው አስቆጥረዋል። ታሬሚ ሁለተኛዋን የኢራን ጎል ከፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል። የኳታር የዓለም ዋንጫ ሦስተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ይካሄዳሉ። ሊዮኔል ሜሲን የያያዘችው አርጀንቲና ቀን ሰባት ሰዓት ላይ በሉሳይል ስታዲየም ሳዑዲ አረቢያን ይገጥማሉ። በሜድቡ ሌላኛ ጨዋታ ሜክሲኮ እና ፖላንድ ስታዲየም 974 ላይ ይገናኛሉ። ኤጁኬሽን ሲቲ ስታዲየም ላይ ቱኒዝያ እና ዴንማርክ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። ፈረንሳይ ደግሞ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ከአውስትራሊያ ጋር ትጫወታለች። | የዓለም ዋንጫ፡ ሴኔጋል ስትሸነፍ የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ልጅ ለአሜሪካ ጎል አስቆጥሯል ባለቀ ሰዓት በተቆጠረባት ጎሎች ሴኔጋል የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታዋን በኔዘርላንድስ 2 ለ 0 ተሸንፋ ጀምራለች። የመጀመሪያውን ጎል የፒኤስቪ አጥቂ ኮዲ ጋክፖ አስቆጥሯል። ተቀይሮ የገባው ዳቪ ክላሰን ሁለተኛዋን ጎል ለብርቱካናማዎቹ ማስቆጠር ችሏል። የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ውጤታማ ባለመሆናቸው ጨዋታው ለረዥም ደቂቃዎች ጎል ሳይቆጠርበት ቀጥሏል። ሴኔጋሎች በጉዳት ያጡት አጥቂያቸው ሳዲዮ ማኔ ምን ያህል እንዳጎደላቸው የታየበት ጨዋታም ሆኗል። የሴኔጋል ደጋፊዎች ስታዲሙን አድምቀውት አምሽተዋል። የሴኔጋሉ ኢስማይላ ሳር በመጀመሪያው አጋማሽ የኔዘርላንድ ተከላካዮችን አስጨንቋል። የኔዘርላንዱ አማካይ ዲ ዮንግ ደግሞ ጨዋታውን በመቆጣጠር ብቃቱን ያሳየበት ምሽት ነበር። ድሉን ተከትሎ ብርቱካናማዎቹ በመክፈቻው ጨዋታ ኳታርን 2 ለ 0 ካሸነፈችው ኢኳዶር ጋር ምድቡን መምራት ችላል። ምሽት ላይ በተካሄደ ሌላ ጨዋታ የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ልጅ ለአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ኳስ እና መረብ ለማገናኘት በቅቷል። የፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ልጅ የሆነው ቲሞቲ ዊሃ አሜሪካ እና ዌልስ አንድ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ነው ለአሜሪካ ጎል ማስቆጠር የቻለው። ከክርስቲያን ፑሊሲች የተሻገረለትን ኳስ ቲም ዊሃ ድንቅ በሆነ ሁኔታ ከመረብ ጋር አገናኝቷል። በጨዋታው መገባደጃ ላይ ዌልስ አቻ ማድረግ የቻለችውን ጎል ጋሬት ቤል ከፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል። ፕሬዝዳንት ዊሃ በአሜሪካ የተወለደው ልጁ የዓለም ዋንጫ ላይ ሲሳተፍ ለመመልከት ዘጠኝ ቀናትን በኳታር አሳልፏል። የፕሬዝዳንቱ ጉዞ በሃገር ቤት ውዝግብ አስነስቷል። የሃገሪቱ የፋይናንስ ሚንስትር ፕሬዝዳንቱ 2ሺህ ዶላር ቀን አበል አለው ማለቱ ነው የውዝግቡ መነሻ። ተቺዎችም ፕሬዝዳንቱ ቃል የገባለትን “ደሃን የሚያቅፍ አጀንዳውን” የሚቃረን ነው ሲሉ ገልጸዋል። የዓለም ዋንጫው ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች እንግሊዝ ከኢራን ባደረጉት ጨዋታ ነው የተጀመረው። ጨዋታውን እንግሊዝ 6 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። እንግሊዝ የጎል ካዝናዋን የከፈተችው በጁድ ቤሊንግሃም የጭንቅላት ጎል ነው። ቡካዮ ሳካ እና ራሂም ስተርሊንግ ከእረፍት በፊት ባስቆጠሯቸው ጎሎች እንግሊዝ 3 ለ 0 መምራት ችላለች። ከእረፍት መልስ ሳካ ለራሱ ሁለተኛዋን ለቡድኑ ደግሞ አራተኛው ጎል አስቆጥሯል። መህዲ ታሬሚ ለኢራን የመጀመሪያዋን ጎል በ65ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል። ማርከስ ራሽፎርድ እና ጃክ ግሪሊሽ ቀሪዎቹን ጎሎች ተቀይረው ገብተው አስቆጥረዋል። ታሬሚ ሁለተኛዋን የኢራን ጎል ከፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል። የኳታር የዓለም ዋንጫ ሦስተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ይካሄዳሉ። ሊዮኔል ሜሲን የያያዘችው አርጀንቲና ቀን ሰባት ሰዓት ላይ በሉሳይል ስታዲየም ሳዑዲ አረቢያን ይገጥማሉ። በሜድቡ ሌላኛ ጨዋታ ሜክሲኮ እና ፖላንድ ስታዲየም 974 ላይ ይገናኛሉ። ኤጁኬሽን ሲቲ ስታዲየም ላይ ቱኒዝያ እና ዴንማርክ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። ፈረንሳይ ደግሞ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ከአውስትራሊያ ጋር ትጫወታለች። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cjr28r4g5yko |
2health
| የዝንጀሮ ፈንጣጣን መቆጣጠር እንደሚቻል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ | የዝንጀሮ ፈንጣጣ(ሞንኪፖክስ) ባልተለመደባቸው ከአፍሪካ ውጭ ባሉ አገራት የቫይረሱን ሥርጭት መቆጣጠር እንደሚቻል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። እስካሁን ድረስ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና አውስትራሊያ ትኩሳትና በሰውነት ላይ ሽፍታ የታየባቸው ከ100 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይሁን አንጂ ቁጥሩ ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ይጠበቃል፤ ነገር ግን ባለሙያዎች ሰፊ ሕዝብ ለዚህ አደጋ የመጋለጥ እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው ብለዋል። ቫይረሱ በመካከለኛው እና ምዕራብ አፍሪካ ገጠራማ አካባቢዎች የተለመደ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የሚከሰቱ አዳዲስ በሽታዎች መሪ ማሪያ ቫን ኬርክሆቭ ቫይረሱን መቆጣጠር የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። " ከሰው ወደ ሰው እንዳይተላለፍ ማቆም እንፈልጋለን" ያሉት መሪዋ፣ በቅርቡ በሽታው የተገኘባቸው አውሮፓንና ሰሜን አሜሪካን ጠቅሰው "በሽታው ወረርሽኝ ባልሆነባቸው አገራት ይህንን ማድረግ እንችላለን" ብለዋል። ቫይረሱ እስካሁን ከአፍሪካ ውጭ በ16 አገራት ተገኝቷል። ምንም እንኳን ይህ በ50 ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ ውጭ በስፋት የተከሰተ በሽታ ቢሆንም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ እንደማይተላለፍ እንዲሁም ህክምናውም ቢሆን ከኮሮናቫይረስ ጋር እንደማይወዳደር ባለሙያዎች ተናግረዋል። "ቫይረሱ የሚተላለፈው በሽታው ካለበት ሰው ጋር በሚኖር የቆዳ ንክኪ ነው። አብዛኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም ቀለል ያለ ህመም ነው ያጋጠማቸው" ብለዋል ቫን ካርክሆቭ። ሌላ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣንም አሁን የተከሰተውን ወረርሽኝ መንስዔ በተመለከተ ቀደም ብለው ሲሰራጩ የነበሩ መላምቶችን ተከትሎ በሰጡት ምላሽ፣ ሞንኪፖክስ ልውጥ ቫይረስ መሆኑን የሚያሳይ ምንም መረጃ አለመኖሩን ገልጸዋል። በዓለም ጤና ድርጅት የስሞልፖክስ ኃላፊ ሮሳመንድ " የቫይረሱ ዝርያ ራሱን የመለወጥ ባሕርይ የለውም። ይልቁንስ ዝርያዎቹ ባሉበት የመቆየት ባህርይ ነው ያላቸው" ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ባለሥልጣን የተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከሌሎቹ በበለጠ ለአደጋው ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። የአውሮፓ በሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳሬክተር ዶክተር አንድሪያ አሞን እንዳሉት በሰፊው ሕዝብ ዘንድ በሽታው የመተላለፍ እድሉ አነስተኛ ነው፤ ይሁን እንጂ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ለምሳሌ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈፅሙ ሰዎች ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው። የዝንጀሮ ፈንጣጣ (ሞንኪፖክስ) ቀደም ብሎ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ አለመሆኑ የተገለጸ ቢሆንም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት በሚኖር ቀጥተኛ ንክኪ ሊተላለፍ ይችላል። ዶክተር አሞን አክለውም የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመከላከልም ውጤታማ ነው የተባለውን ስሞልፖክስ ክትባት እንዳላቸው አገራት ማረጋገጥ እንዳለባቸው መክረዋል። 55 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በተገኙባት ዩናይትድ ኪንግደም፣ ባለሥልጣናት በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን ለ21 ቀናት እንዲያገሉ መክረዋል። አንድ ሰው በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈፅሞ ከሆነ ፣ አንሶላ እና ሌሎች አልባሳትን ተጋርቶ ከሆነ አሊያም የበሽታው መከላከያ የህክምና ቁሳቁሶችን በጋራ ተጠቅሞ ከሆነ ለበሽታው ተጋልጦ ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል። ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት፣ ማሳከክ፣ በኋላ ላይ ውሃ የሚቋጥር እብጠት የሚያስከትል ሽፍታ የበሽታው ምልክቶች ሲሆኑ እነዚህ ብዙውን ጊዜ ቀለል ያሉ ናቸው። አብዛኛው ሰውም ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ባሉት ጊዜ ውስጥ ከበሽታው ያገግማሉ። | የዝንጀሮ ፈንጣጣን መቆጣጠር እንደሚቻል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ የዝንጀሮ ፈንጣጣ(ሞንኪፖክስ) ባልተለመደባቸው ከአፍሪካ ውጭ ባሉ አገራት የቫይረሱን ሥርጭት መቆጣጠር እንደሚቻል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። እስካሁን ድረስ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና አውስትራሊያ ትኩሳትና በሰውነት ላይ ሽፍታ የታየባቸው ከ100 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይሁን አንጂ ቁጥሩ ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ይጠበቃል፤ ነገር ግን ባለሙያዎች ሰፊ ሕዝብ ለዚህ አደጋ የመጋለጥ እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው ብለዋል። ቫይረሱ በመካከለኛው እና ምዕራብ አፍሪካ ገጠራማ አካባቢዎች የተለመደ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የሚከሰቱ አዳዲስ በሽታዎች መሪ ማሪያ ቫን ኬርክሆቭ ቫይረሱን መቆጣጠር የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። " ከሰው ወደ ሰው እንዳይተላለፍ ማቆም እንፈልጋለን" ያሉት መሪዋ፣ በቅርቡ በሽታው የተገኘባቸው አውሮፓንና ሰሜን አሜሪካን ጠቅሰው "በሽታው ወረርሽኝ ባልሆነባቸው አገራት ይህንን ማድረግ እንችላለን" ብለዋል። ቫይረሱ እስካሁን ከአፍሪካ ውጭ በ16 አገራት ተገኝቷል። ምንም እንኳን ይህ በ50 ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ ውጭ በስፋት የተከሰተ በሽታ ቢሆንም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ እንደማይተላለፍ እንዲሁም ህክምናውም ቢሆን ከኮሮናቫይረስ ጋር እንደማይወዳደር ባለሙያዎች ተናግረዋል። "ቫይረሱ የሚተላለፈው በሽታው ካለበት ሰው ጋር በሚኖር የቆዳ ንክኪ ነው። አብዛኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም ቀለል ያለ ህመም ነው ያጋጠማቸው" ብለዋል ቫን ካርክሆቭ። ሌላ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣንም አሁን የተከሰተውን ወረርሽኝ መንስዔ በተመለከተ ቀደም ብለው ሲሰራጩ የነበሩ መላምቶችን ተከትሎ በሰጡት ምላሽ፣ ሞንኪፖክስ ልውጥ ቫይረስ መሆኑን የሚያሳይ ምንም መረጃ አለመኖሩን ገልጸዋል። በዓለም ጤና ድርጅት የስሞልፖክስ ኃላፊ ሮሳመንድ " የቫይረሱ ዝርያ ራሱን የመለወጥ ባሕርይ የለውም። ይልቁንስ ዝርያዎቹ ባሉበት የመቆየት ባህርይ ነው ያላቸው" ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ባለሥልጣን የተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከሌሎቹ በበለጠ ለአደጋው ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። የአውሮፓ በሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳሬክተር ዶክተር አንድሪያ አሞን እንዳሉት በሰፊው ሕዝብ ዘንድ በሽታው የመተላለፍ እድሉ አነስተኛ ነው፤ ይሁን እንጂ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ለምሳሌ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈፅሙ ሰዎች ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው። የዝንጀሮ ፈንጣጣ (ሞንኪፖክስ) ቀደም ብሎ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ አለመሆኑ የተገለጸ ቢሆንም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት በሚኖር ቀጥተኛ ንክኪ ሊተላለፍ ይችላል። ዶክተር አሞን አክለውም የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመከላከልም ውጤታማ ነው የተባለውን ስሞልፖክስ ክትባት እንዳላቸው አገራት ማረጋገጥ እንዳለባቸው መክረዋል። 55 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በተገኙባት ዩናይትድ ኪንግደም፣ ባለሥልጣናት በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን ለ21 ቀናት እንዲያገሉ መክረዋል። አንድ ሰው በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈፅሞ ከሆነ ፣ አንሶላ እና ሌሎች አልባሳትን ተጋርቶ ከሆነ አሊያም የበሽታው መከላከያ የህክምና ቁሳቁሶችን በጋራ ተጠቅሞ ከሆነ ለበሽታው ተጋልጦ ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል። ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት፣ ማሳከክ፣ በኋላ ላይ ውሃ የሚቋጥር እብጠት የሚያስከትል ሽፍታ የበሽታው ምልክቶች ሲሆኑ እነዚህ ብዙውን ጊዜ ቀለል ያሉ ናቸው። አብዛኛው ሰውም ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ባሉት ጊዜ ውስጥ ከበሽታው ያገግማሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-61561522 |
3politics
| ቦልሶናሮ ተሸንፈው ኢናሲዮ ሉላ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ | በብራዚል በተከናወነው ፕሬዝዳናታዊ ምርጫ ግራ ዘመሙ የቀድሞ ፕሬዝዳት ሊውዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የቀኝ አክራሪውን እና የወቅቱ ፕሬዝዳናት ጄር ቦልሶናሮን አሸንፈዋል። እጅግ መከፋፈል ከታየበት የሁለቱ ተቀናቃኞች የምርጫ ዘማቻ በኃላ ሉላ 50.9 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል። ይህ ውጤት እንደሚያሸንፉ እምነት ለነበራቸው የቦልሶናሮ ደጋፊዎች አስደንጋጭ ሆኗል። ሆኖም ይህ ምርጫ በአገሪቱ የፈጠረው መከፋፈል በቀላሉ የመጥፋት ዕድሉ ዝቅተኛ ነው። የዚህ ምርጫ ውጤት እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 በተካሄደው ምርጫ ላይ እስር ቤት በመሆናቸው እና እንዳይወዳደሩ ተግደው የነበሩትን ሉላ ወደ ፖለቲካው የመለሰ ነው። ፖለቲከኛው በዛ ወቅት የብራዚል መንግሥት የነዳጃ ኩባንያ የሆነው ፔትሮ ብራስ የውል ስምምነት ለማሰር ጉቦ ተቀብለዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤት ጥፋተኛ እንደሆኑ ወስኖባቸው ነበር። የተላለፈባቸው ብይን ተሰረዞ ወደ ፖለቲካ ህይወታቸው ከመመለሳቸው በፊት 580 ቀናትን በእስር ቤት አሳልፈዋል። ዳ ሲልቫ አሸናፊ መሆናቸውን ከረጋገጡ በኃላ ባደረጉት ንግግር “ከነ ሕይወቴ ሊቀብሩኝ ሞክረው ነበር። እኔ ግን እዚህ ደርሻለሁ” ብለዋል። የቅድመ ምርጫ ግምቶች ሉላ እንደሚያሸንፉ አመለክተው የነበረ ቢሆንም በመጀሪያው ዙር የውጤት ልዩነቱ ከተጠበቀው በታች ሆኗል። በዚህም በርካታ ብራዚላውያን የውጤቱን ትክክለኛነት ተጠራጥረው ነበር። የግራ ዘመሙን ፖለቲከኛ አሸናፊነት አንቀበልም የሚሉት የቦልሶናሮ ደጋፊዎች ዳ ሲልቫን “ሌባ” እያሉ የሚጠሯቸው ሲሆን ክሳቸው መሰረዙ ነጽህናቸውን የሳያል ማለት አይደለም ይላሉ። ጄር ቦልሶናሮ ቢሸነፉም ለሳቸው ቅርበት ያላቸው ህግ አውጪዎች የምክር ቤቱን አብላጫ መቀመጫ አግኝተዋል። ይህ ማለት ሉላ በፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው የሚያወጧቸው ፖሊሲዎች በምክር ቤቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ይገጥመዋል ማለት ነው። ሆኖም እንደ አውሮፓውያኑ ከ2003 እስከ 2010 ለሁለት የምርጫ ዘመን በስልጣን የነበሩት ሉላ ፖለቲካዊ ጥምረት ለመመሰረት አዲስ አይደሉም። በዘንድሮ ምርጫ መክትላቸው ሆነው የተወዳደሩት እና ከዚህ ቀደም ተቃዋሚያቸው የነበሩትን አልኪም ከጎናቸው ማሰለፍ ችለዋል። ዳ ሲልቫ አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኃላ ባደረጉት ንግግር በተለሳለሰ ሁኔታ የመረጧቸውን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ብራዚላውያንን እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል። “ይህ አገር ሰላም እና አንድነት ይፈልጋል። ይህ ሕዝብ ከዚህ በኃላ ጸብ አይፈልግም” ብለዋል። የ77 ዓመቱ ሉላ ፖለቲካን ከመቀላቀላቸው በፊት የብረታ ብረት ባለሙያ ነበሩ። | ቦልሶናሮ ተሸንፈው ኢናሲዮ ሉላ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ በብራዚል በተከናወነው ፕሬዝዳናታዊ ምርጫ ግራ ዘመሙ የቀድሞ ፕሬዝዳት ሊውዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የቀኝ አክራሪውን እና የወቅቱ ፕሬዝዳናት ጄር ቦልሶናሮን አሸንፈዋል። እጅግ መከፋፈል ከታየበት የሁለቱ ተቀናቃኞች የምርጫ ዘማቻ በኃላ ሉላ 50.9 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል። ይህ ውጤት እንደሚያሸንፉ እምነት ለነበራቸው የቦልሶናሮ ደጋፊዎች አስደንጋጭ ሆኗል። ሆኖም ይህ ምርጫ በአገሪቱ የፈጠረው መከፋፈል በቀላሉ የመጥፋት ዕድሉ ዝቅተኛ ነው። የዚህ ምርጫ ውጤት እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 በተካሄደው ምርጫ ላይ እስር ቤት በመሆናቸው እና እንዳይወዳደሩ ተግደው የነበሩትን ሉላ ወደ ፖለቲካው የመለሰ ነው። ፖለቲከኛው በዛ ወቅት የብራዚል መንግሥት የነዳጃ ኩባንያ የሆነው ፔትሮ ብራስ የውል ስምምነት ለማሰር ጉቦ ተቀብለዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤት ጥፋተኛ እንደሆኑ ወስኖባቸው ነበር። የተላለፈባቸው ብይን ተሰረዞ ወደ ፖለቲካ ህይወታቸው ከመመለሳቸው በፊት 580 ቀናትን በእስር ቤት አሳልፈዋል። ዳ ሲልቫ አሸናፊ መሆናቸውን ከረጋገጡ በኃላ ባደረጉት ንግግር “ከነ ሕይወቴ ሊቀብሩኝ ሞክረው ነበር። እኔ ግን እዚህ ደርሻለሁ” ብለዋል። የቅድመ ምርጫ ግምቶች ሉላ እንደሚያሸንፉ አመለክተው የነበረ ቢሆንም በመጀሪያው ዙር የውጤት ልዩነቱ ከተጠበቀው በታች ሆኗል። በዚህም በርካታ ብራዚላውያን የውጤቱን ትክክለኛነት ተጠራጥረው ነበር። የግራ ዘመሙን ፖለቲከኛ አሸናፊነት አንቀበልም የሚሉት የቦልሶናሮ ደጋፊዎች ዳ ሲልቫን “ሌባ” እያሉ የሚጠሯቸው ሲሆን ክሳቸው መሰረዙ ነጽህናቸውን የሳያል ማለት አይደለም ይላሉ። ጄር ቦልሶናሮ ቢሸነፉም ለሳቸው ቅርበት ያላቸው ህግ አውጪዎች የምክር ቤቱን አብላጫ መቀመጫ አግኝተዋል። ይህ ማለት ሉላ በፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው የሚያወጧቸው ፖሊሲዎች በምክር ቤቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ይገጥመዋል ማለት ነው። ሆኖም እንደ አውሮፓውያኑ ከ2003 እስከ 2010 ለሁለት የምርጫ ዘመን በስልጣን የነበሩት ሉላ ፖለቲካዊ ጥምረት ለመመሰረት አዲስ አይደሉም። በዘንድሮ ምርጫ መክትላቸው ሆነው የተወዳደሩት እና ከዚህ ቀደም ተቃዋሚያቸው የነበሩትን አልኪም ከጎናቸው ማሰለፍ ችለዋል። ዳ ሲልቫ አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኃላ ባደረጉት ንግግር በተለሳለሰ ሁኔታ የመረጧቸውን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ብራዚላውያንን እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል። “ይህ አገር ሰላም እና አንድነት ይፈልጋል። ይህ ሕዝብ ከዚህ በኃላ ጸብ አይፈልግም” ብለዋል። የ77 ዓመቱ ሉላ ፖለቲካን ከመቀላቀላቸው በፊት የብረታ ብረት ባለሙያ ነበሩ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c3g83xdpdzxo |
5sports
| ቻምፒየንስ ሊግ፡ ኔይማር ያነባበት፤ ሌዋንዶውስኪ የፈነደቀበት ምሽት | የጀርመኑ ባየርን ሚዩኒክ የፈረንሳዩን ፒኤስጂ በመርታት የኮሮናቫይረስ ዘመን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ባለድል ሆኗል። የቀድሞው የፒኤስጂ ተጫዋች ኪንግስሊ ኮማን በ59ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ነው የጀርመኑ ክለብ በአውሮፓ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውን ዋንጫ ለስድስተኛ ጊዜ ያነሳው። ባለፈው ኅዳር ወር ባየርን ሚዩኒክን በጊዜያዊነት የተረከቡት አሠልጣኝ ሃንስ ፍሊክ የጀርመን ቡንደስሊጋን ማንሳታቸው አይዘነጋም። አሁን ደግሞ የሥራ ማመልከቻቸው ላይ ቻምፒየንስ ሊግ ጨምረዋል። የፒኤስጂ የፈት መስመር አሸከርካሪዎች ብራዚላዊው ኔይማርና ፈረንሳዊው ወጣት ምባፔ በሃዘን አንገታቸውን ደፍተው ታይተዋል። የጨዋታው ኮከብ የነበረው የባየርን ግብ ጠባቂ ማኑዌል ኑዌር ኔይማርና ምባፔን አላነቃንቅ ብሎ አምሽቷል። ሁለቱ ቡድኖች ተፈራርተው የገቡበት ጨዋታው የታሰበውን ያክል አዝናኝና ጎል የተመረተበት ባይሆንም ባየርን ሚዩኒክ የተሻለ ቡድን ሆኖ አምሽቷል። የፒኤስጂው ምባፔ በባየርን የጎል ሳጥን ውስጥ በጆሽዋ ኪሚክ ተጠልፎ የወደቀ ቢመስልም የዕለቱ ዳኛ ጥፋቱ ፍፁም ቅጣት ምት የሚያሰጥ አይደለም ብለዋል። ጎል በማምረት የሚታወቁት ባየርኖች የተከላካይ መስመራቸው የሳሳ በመሆኑ በፒኤስጂ ከዋክብት ጉድ ይሆናሉ ተብሎ ቢገመትም ኔይማርና ምባፔ እንዲሁም ዲ ማሪያ ልዩነት መፍጠር አልቻሉም። በኢቫን ፔሪሲች ምትክ ኮማንን ያሰለፉት ሃንስ ፍሊክ ከስፖርት አዋቂዎች ምስጋና ተችሯቸዋል። ባየርን ሚዩኒክ ሁሉንም ጨዋታዎች በማሸነፍ ዋንጫው በማንሳት ታሪክ ከመሥራታቸው አልፎ የስፔንና አውሮፓ ኃያሉን ባርሴሎና በሩብ ፍፃሜው 8-2 በመርታት ብዙዎችን አጀብ አሰኝተዋል። ረብጣ ሚሊዮን ዶላሮች ተጫዋቾች ላይ ያፈሰሰው ፒኤስጂ ለሚቋምጥለት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ፍፃሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢደርስም ውጤታማ አልሆነም። ባየርን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ስድስት ጊዜ በማንሳት ከሊቨርፑል ጋር እኩል ተቀምጧል። ዋንጫውን ሪያል ማድሪድ 17 ጊዜ በማንሳት አንደኛ ሲሆን ኤሲ ሚላን 7 ጊዜ በማንሳት ሁለተኛ ነው። | ቻምፒየንስ ሊግ፡ ኔይማር ያነባበት፤ ሌዋንዶውስኪ የፈነደቀበት ምሽት የጀርመኑ ባየርን ሚዩኒክ የፈረንሳዩን ፒኤስጂ በመርታት የኮሮናቫይረስ ዘመን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ባለድል ሆኗል። የቀድሞው የፒኤስጂ ተጫዋች ኪንግስሊ ኮማን በ59ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ነው የጀርመኑ ክለብ በአውሮፓ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውን ዋንጫ ለስድስተኛ ጊዜ ያነሳው። ባለፈው ኅዳር ወር ባየርን ሚዩኒክን በጊዜያዊነት የተረከቡት አሠልጣኝ ሃንስ ፍሊክ የጀርመን ቡንደስሊጋን ማንሳታቸው አይዘነጋም። አሁን ደግሞ የሥራ ማመልከቻቸው ላይ ቻምፒየንስ ሊግ ጨምረዋል። የፒኤስጂ የፈት መስመር አሸከርካሪዎች ብራዚላዊው ኔይማርና ፈረንሳዊው ወጣት ምባፔ በሃዘን አንገታቸውን ደፍተው ታይተዋል። የጨዋታው ኮከብ የነበረው የባየርን ግብ ጠባቂ ማኑዌል ኑዌር ኔይማርና ምባፔን አላነቃንቅ ብሎ አምሽቷል። ሁለቱ ቡድኖች ተፈራርተው የገቡበት ጨዋታው የታሰበውን ያክል አዝናኝና ጎል የተመረተበት ባይሆንም ባየርን ሚዩኒክ የተሻለ ቡድን ሆኖ አምሽቷል። የፒኤስጂው ምባፔ በባየርን የጎል ሳጥን ውስጥ በጆሽዋ ኪሚክ ተጠልፎ የወደቀ ቢመስልም የዕለቱ ዳኛ ጥፋቱ ፍፁም ቅጣት ምት የሚያሰጥ አይደለም ብለዋል። ጎል በማምረት የሚታወቁት ባየርኖች የተከላካይ መስመራቸው የሳሳ በመሆኑ በፒኤስጂ ከዋክብት ጉድ ይሆናሉ ተብሎ ቢገመትም ኔይማርና ምባፔ እንዲሁም ዲ ማሪያ ልዩነት መፍጠር አልቻሉም። በኢቫን ፔሪሲች ምትክ ኮማንን ያሰለፉት ሃንስ ፍሊክ ከስፖርት አዋቂዎች ምስጋና ተችሯቸዋል። ባየርን ሚዩኒክ ሁሉንም ጨዋታዎች በማሸነፍ ዋንጫው በማንሳት ታሪክ ከመሥራታቸው አልፎ የስፔንና አውሮፓ ኃያሉን ባርሴሎና በሩብ ፍፃሜው 8-2 በመርታት ብዙዎችን አጀብ አሰኝተዋል። ረብጣ ሚሊዮን ዶላሮች ተጫዋቾች ላይ ያፈሰሰው ፒኤስጂ ለሚቋምጥለት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ፍፃሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢደርስም ውጤታማ አልሆነም። ባየርን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ስድስት ጊዜ በማንሳት ከሊቨርፑል ጋር እኩል ተቀምጧል። ዋንጫውን ሪያል ማድሪድ 17 ጊዜ በማንሳት አንደኛ ሲሆን ኤሲ ሚላን 7 ጊዜ በማንሳት ሁለተኛ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-53885866 |
0business
| በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሆነው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ከባለፈው ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ጭማሪ አሳየ? | የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መናሩን በምክንያትነት በመጥቀስ ከአራት ወራት በፊት ባወጣው የዋጋ ተመን ላይ ከሚያዝያ 30/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ መንግሥት ባለፉት አራት ወራት የነዳጅ ዋጋን ለመደጎም ባወጣው ወጪ ከፍተኛ ጫና ላይ መውደቁን ያተተ ሲሆን "በነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ በወር በአማካይ ወደ ተጠቃሚው መተላለፍ የነበረበት 10 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንዲመዘገብ" አድርጓል ሲል አክሏል። በዚህም ምክንያት ከእሁድ ሚያዝያ 30 ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ ተደርጓል። ቤንዚን በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣ ኬሮሲን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 51 ብር ከ78 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 78 ብር ከ87 ሳንቲም ሆኖ እንደሚሸጥ መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። ተግባራዊ ከተደረገው የተመን ማሻሻያ በፊት ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ታኀሣሥ ወር ላይ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ ጭማሪ አድርጋ ነበር። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በእነዚህ አራት ወራቶች ውስጥ የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ "በከፍተኛ ሁኔታ" መጨመሩን ገልጿል። በዚህም በታኅሣሥ ወር ቤንዚን በሜትሪክ ቶን 870 የአሜሪካን ዶላር ይሸጥ እንደነበር ጠቅሶ ከአራት ወራት በኋላ ዋጋው በ27 በመቶ በመጨመር 1028 የአሜሪካ ዶላር መግባቱን አስታውሷል። በተመሳሳይ ናፍጣ በሜትሪክ ቶን 730 የአሜሪካን ዶላር ይሸጥ ከነበረበት በ55 በመቶ ወይም በ408 ዶላር ጭማሪ በማሳየት ወደ 1138 የአሜሪካን ዶላር ማሻቀቡን አውስቷል። ሚኒስቴሩ በመግለጫው መንግሥት ለነዳጅ የሚያደርገውን ድጎማ ቢያቆም በአዲስ አበባ አንድ ሊትር ናፍጣ 73 ብር እንዲሁም የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ 66 ብር ከ78 ሳንቲም ይሆን ነበር ብሏል። "ሆኖም አገሪቱ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ከዓለም መሸጫ ዋጋ ልዩነትን 85 በመቶ የሚሆነውን ጫና መንግሥት በመሸከም፣ ቀሪውን 15 በመቶ ለተጠቃሚው እንዲተላለፍ በመወሰን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ክለሳ" ማድረጉን አሳውቋል። የነዳጅ ዋጋ በታኅሣሥ እና ሚያዚያ ምን ያህል ልዩነት አለው? መንግሥት በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩን በመግለጽ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቆ ነበር። ለመሆኑ ከታኅሣሥ እስከ ሚያዚያ መገባደጃ በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ በምን ያህል ጫማሪ አሳየ? በዋጋ ጭማሪው እንደ ጥቁር ናፋጣ ያሉ ምርቶች በሊትር እስከ 121 በመቶ ጭማሪ ወይም እስከ 28 ብር ያሻቀቡ ሲሆን ዝቅተኛው የዋጋ ማሻሻያ ጣሪያ ቤንዝን ላይ የተደረገው ሲሆን የ15 በመቶ ጭማሪ የታየበት ነበር። በታኅሣሥ ወር ቤንዚን ላይ በተደረገ የዋጋ ማስተካከያ በሊትር 31 ብር ከ74 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኖ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ተመን መሰረት በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ይሸጣል። በዚህ መሰረት የቤንዚን ዋጋ በ15 በመቶ ወይም በ4 ብር ከ87 ሳንቲም ጫማሪ አሳይቷል። በሌላ በኩል ከአራት ወራት በፊት ነጭ ናፍጣ በሊትር 28 ብር ከ94 ሳንቲም እንዲሸጥ ነበር የተወሰነው። አሁን ላይ ነጭ ናፍጣ በ22 በመቶ ወይም በ6 ብር ከ49 ሳንቲም በመጨመር በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም ይሸጣል። ነጭ ጋዝ ወይም ኬሮሲን 28 ብር ከ94 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን፣ በአዲሱ ተመን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም ይሸጣል። ይህም የ22 በመቶ ወይም 6 ብር ከ49 ሳንቲም ጭማሪ የታየበት ነው። ቀላል ጥቁር ናፍጣ በታኅሣሥ ወር የወጣለት ተመን 23 ብር ከ73 ሳንቲም የነበረ ሲሆን በአዲሱ የመሸጫ ዋጋ በ121 በመቶ ወይም 28 ብር 72 ጨምሮ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል። ይህ በተመሳሳይ የከባድ ጥቁር ናፍጣም ዋጋ በ121 በመቶ ወይም 28 ብር 49 በማሻቀብ በሊትር ሲሸጥበት ከነበረው 23 ብር ከ29 ሳንቲም ወደ 51 ብር ከ78 ከፍ ብሏል። የከባድ እና ቀላል ናፍጣ ዋጋ ማሻሻያ ከሌሎቹ የነዳጅ አይነቶች እጅግ ከፍተኛው ሆኖ የሚታይ ነው። የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ በሊትር ከ58 ብር ከ77 ሳንቲም ወደ 78 ብር ከ87 ሳንቲም ያሻቀበ ሲሆን የ33 በመቶ ወይም 20 ብር ጭማሪ አሳይቷል። የነዳጅ ምርቶች የዋጋ ጭማሪ በአራት ወራት ውስጥ - በሊትር ከወራት በፊት ሩሲያ እና ዩክሬን የገቡበት ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ እንዲያሻቅብ ሰበብ ሆኗል። ሩሲያ የዓለምን 10 በመቶ ገደማ የሚሆን የነዳጅ ምርት ታቀርባለች። | በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሆነው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ከባለፈው ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ጭማሪ አሳየ? የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መናሩን በምክንያትነት በመጥቀስ ከአራት ወራት በፊት ባወጣው የዋጋ ተመን ላይ ከሚያዝያ 30/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ መንግሥት ባለፉት አራት ወራት የነዳጅ ዋጋን ለመደጎም ባወጣው ወጪ ከፍተኛ ጫና ላይ መውደቁን ያተተ ሲሆን "በነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ በወር በአማካይ ወደ ተጠቃሚው መተላለፍ የነበረበት 10 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንዲመዘገብ" አድርጓል ሲል አክሏል። በዚህም ምክንያት ከእሁድ ሚያዝያ 30 ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ ተደርጓል። ቤንዚን በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣ ኬሮሲን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 51 ብር ከ78 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 78 ብር ከ87 ሳንቲም ሆኖ እንደሚሸጥ መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። ተግባራዊ ከተደረገው የተመን ማሻሻያ በፊት ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ታኀሣሥ ወር ላይ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ ጭማሪ አድርጋ ነበር። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በእነዚህ አራት ወራቶች ውስጥ የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ "በከፍተኛ ሁኔታ" መጨመሩን ገልጿል። በዚህም በታኅሣሥ ወር ቤንዚን በሜትሪክ ቶን 870 የአሜሪካን ዶላር ይሸጥ እንደነበር ጠቅሶ ከአራት ወራት በኋላ ዋጋው በ27 በመቶ በመጨመር 1028 የአሜሪካ ዶላር መግባቱን አስታውሷል። በተመሳሳይ ናፍጣ በሜትሪክ ቶን 730 የአሜሪካን ዶላር ይሸጥ ከነበረበት በ55 በመቶ ወይም በ408 ዶላር ጭማሪ በማሳየት ወደ 1138 የአሜሪካን ዶላር ማሻቀቡን አውስቷል። ሚኒስቴሩ በመግለጫው መንግሥት ለነዳጅ የሚያደርገውን ድጎማ ቢያቆም በአዲስ አበባ አንድ ሊትር ናፍጣ 73 ብር እንዲሁም የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ 66 ብር ከ78 ሳንቲም ይሆን ነበር ብሏል። "ሆኖም አገሪቱ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ከዓለም መሸጫ ዋጋ ልዩነትን 85 በመቶ የሚሆነውን ጫና መንግሥት በመሸከም፣ ቀሪውን 15 በመቶ ለተጠቃሚው እንዲተላለፍ በመወሰን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ክለሳ" ማድረጉን አሳውቋል። የነዳጅ ዋጋ በታኅሣሥ እና ሚያዚያ ምን ያህል ልዩነት አለው? መንግሥት በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩን በመግለጽ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቆ ነበር። ለመሆኑ ከታኅሣሥ እስከ ሚያዚያ መገባደጃ በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ በምን ያህል ጫማሪ አሳየ? በዋጋ ጭማሪው እንደ ጥቁር ናፋጣ ያሉ ምርቶች በሊትር እስከ 121 በመቶ ጭማሪ ወይም እስከ 28 ብር ያሻቀቡ ሲሆን ዝቅተኛው የዋጋ ማሻሻያ ጣሪያ ቤንዝን ላይ የተደረገው ሲሆን የ15 በመቶ ጭማሪ የታየበት ነበር። በታኅሣሥ ወር ቤንዚን ላይ በተደረገ የዋጋ ማስተካከያ በሊትር 31 ብር ከ74 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኖ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ተመን መሰረት በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ይሸጣል። በዚህ መሰረት የቤንዚን ዋጋ በ15 በመቶ ወይም በ4 ብር ከ87 ሳንቲም ጫማሪ አሳይቷል። በሌላ በኩል ከአራት ወራት በፊት ነጭ ናፍጣ በሊትር 28 ብር ከ94 ሳንቲም እንዲሸጥ ነበር የተወሰነው። አሁን ላይ ነጭ ናፍጣ በ22 በመቶ ወይም በ6 ብር ከ49 ሳንቲም በመጨመር በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም ይሸጣል። ነጭ ጋዝ ወይም ኬሮሲን 28 ብር ከ94 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረ ሲሆን፣ በአዲሱ ተመን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም ይሸጣል። ይህም የ22 በመቶ ወይም 6 ብር ከ49 ሳንቲም ጭማሪ የታየበት ነው። ቀላል ጥቁር ናፍጣ በታኅሣሥ ወር የወጣለት ተመን 23 ብር ከ73 ሳንቲም የነበረ ሲሆን በአዲሱ የመሸጫ ዋጋ በ121 በመቶ ወይም 28 ብር 72 ጨምሮ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል። ይህ በተመሳሳይ የከባድ ጥቁር ናፍጣም ዋጋ በ121 በመቶ ወይም 28 ብር 49 በማሻቀብ በሊትር ሲሸጥበት ከነበረው 23 ብር ከ29 ሳንቲም ወደ 51 ብር ከ78 ከፍ ብሏል። የከባድ እና ቀላል ናፍጣ ዋጋ ማሻሻያ ከሌሎቹ የነዳጅ አይነቶች እጅግ ከፍተኛው ሆኖ የሚታይ ነው። የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ በሊትር ከ58 ብር ከ77 ሳንቲም ወደ 78 ብር ከ87 ሳንቲም ያሻቀበ ሲሆን የ33 በመቶ ወይም 20 ብር ጭማሪ አሳይቷል። የነዳጅ ምርቶች የዋጋ ጭማሪ በአራት ወራት ውስጥ - በሊትር ከወራት በፊት ሩሲያ እና ዩክሬን የገቡበት ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ እንዲያሻቅብ ሰበብ ሆኗል። ሩሲያ የዓለምን 10 በመቶ ገደማ የሚሆን የነዳጅ ምርት ታቀርባለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-61369467 |
0business
| የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የአገሪቱን ሽግግር ለማደናቀፍ ይሞክራሉ ያሏቸውን አስጠነቀቁ | የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የአገሪቱን የሽግግር ሂደት ለማደናቀፍ ሙከራ የሚያደርጉ ያሏቸውን አካላት አስጠነቀቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት የአገሪቱን የሽግግር አስተዳደር በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ባሉ ወታደራዊና ሲቪል መሪዎች መካከል ያለው አለመግባባት እየተባባሰ ባለበት ጊዜ ነው። የሱዳን የሽግግር አስተዳደር የተቋቋመው ሰላሳ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ሲያስተዳድሩ የነበሩት ኦማር ሐሰን አልባሽር ከሁለት ዓመት በፊት በሕዝባዊ አመጽ ከሥልጣናቸው ከተወገዱ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አደገኛ ያሉትን በአገሪቱ የተከሰተውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማርገብ ብቸኛው መንገድ በውይይት ብቻ ሊሆን ይገባል ብለዋል። ነገር ግን አገሪቱን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ሱዳን በታቀደው መሰረት ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉ የጎላ ተጽእኖና ተሰሚነት ያላቸው የሠራዊቱ አባላት መኖራቸው ይነገራል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ ተሞክሮ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። የሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት በሱዳን የሽግግር አስተዳደር ላይና በአገሪቱ ቀጣይ ዕጣ ፋንታ ላይ ወሳኝ ሁኔታዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይገመታል። የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ደጋፊዎች አሁን ያለው የሱዳን መንግሥት በሌላ እንዲተካ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ ቅዳሜ ለማድረግ ጥሪ አቅርበዋል። በሚቀጥለው ሐሙስ ደግሞ ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትሸጋገር የሚጠይቅ ሌላ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል። በአሁኑ ጊዜ ሱዳን ከፖለቲካዊ ቀውሱ ባሻገር ከባድ ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ገጥሟታል። የአገሪቱ ዋነኛ ወደብ በተቃውሞ ሳቢያ በመዘጋቱ ከውጪ የሚገቡ ቁሳቁሶች ዋና ከተማዋን ካርቱምን ጨምሮ ወደ የትኛውም የአገሪቱ ክፍል መንቀሳቀስ ካቆመ ቀናት ተቆጥረዋል። በዚህም ምክንያት በአገሪቱ ውስጥ የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት ችግር ተከስቷል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ የያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። ነገር ግን የሱዳንን የሽግግር አስተዳደር በሚመሩት ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል ያለው ግንኙነት የሰከነ ሳይሆን ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣ ሲሆን፣ ምክንያቱም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅትን ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል። | የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የአገሪቱን ሽግግር ለማደናቀፍ ይሞክራሉ ያሏቸውን አስጠነቀቁ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የአገሪቱን የሽግግር ሂደት ለማደናቀፍ ሙከራ የሚያደርጉ ያሏቸውን አካላት አስጠነቀቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት የአገሪቱን የሽግግር አስተዳደር በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ባሉ ወታደራዊና ሲቪል መሪዎች መካከል ያለው አለመግባባት እየተባባሰ ባለበት ጊዜ ነው። የሱዳን የሽግግር አስተዳደር የተቋቋመው ሰላሳ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ሲያስተዳድሩ የነበሩት ኦማር ሐሰን አልባሽር ከሁለት ዓመት በፊት በሕዝባዊ አመጽ ከሥልጣናቸው ከተወገዱ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አደገኛ ያሉትን በአገሪቱ የተከሰተውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማርገብ ብቸኛው መንገድ በውይይት ብቻ ሊሆን ይገባል ብለዋል። ነገር ግን አገሪቱን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ሱዳን በታቀደው መሰረት ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉ የጎላ ተጽእኖና ተሰሚነት ያላቸው የሠራዊቱ አባላት መኖራቸው ይነገራል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ ተሞክሮ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። የሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት በሱዳን የሽግግር አስተዳደር ላይና በአገሪቱ ቀጣይ ዕጣ ፋንታ ላይ ወሳኝ ሁኔታዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይገመታል። የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ደጋፊዎች አሁን ያለው የሱዳን መንግሥት በሌላ እንዲተካ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ ቅዳሜ ለማድረግ ጥሪ አቅርበዋል። በሚቀጥለው ሐሙስ ደግሞ ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትሸጋገር የሚጠይቅ ሌላ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል። በአሁኑ ጊዜ ሱዳን ከፖለቲካዊ ቀውሱ ባሻገር ከባድ ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ገጥሟታል። የአገሪቱ ዋነኛ ወደብ በተቃውሞ ሳቢያ በመዘጋቱ ከውጪ የሚገቡ ቁሳቁሶች ዋና ከተማዋን ካርቱምን ጨምሮ ወደ የትኛውም የአገሪቱ ክፍል መንቀሳቀስ ካቆመ ቀናት ተቆጥረዋል። በዚህም ምክንያት በአገሪቱ ውስጥ የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት ችግር ተከስቷል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ የያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። ነገር ግን የሱዳንን የሽግግር አስተዳደር በሚመሩት ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል ያለው ግንኙነት የሰከነ ሳይሆን ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣ ሲሆን፣ ምክንያቱም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅትን ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58919817 |
2health
| የደም ግፊት ታካሚዎች ፓራሲታሞል አዘውትረው ከዋጡ ለልብ ድካም ሊዳርጋቸው ይችላል | ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች በሐኪም ትዕዛዝ አዘውትረው ፓራሲታሞል መጠቀማቸው ለልብ ድካም ሊያጋልጣቸው እንደሚችል አንድ ጥናት ጠቆመ። የኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ አጥኚዎች እንዳሉት ዶክተሮች ለታካሚዎቻቸው ለብዙ ወራት የሚወጣ ክኒና ሲያዙ ጥቅምና ጉዳቱን ከግምት ማስገባት አለባቸው። ሕመም ማስታገሻውን መድኃኒት ለራስ ምታትና ለትኩሳት መውሰድ ችግር እንደሌለው አጥኚዎቹ ይናገራሉ። አንዳንድ ሙያተኞች ደግሞ በርከት ባሉ ሰዎች ላይ ጥናት ተሰርቶ ውጤቱን ማረጋገጥ ተገቢ ነው ይላሉ። ፓራሲታሞል በመላው ዓለም የሚታወቅ ሕመም ለማስታገስ የሚዋጥ ሲሆን አንዳንዴ ጥልቅ ሕመም ለሚያስከትሉ በሽታዎችም ይመከራል። ነገር ግን ክኒናው ለረዥም ጊዜ መፍትሔ አይሰጥም። በፈረንጆቹ 2018 ግማሽ ሚሊዮን ስኮትላንዳዊያን ይህንን ማስታገሻ እንዲውጡ በሐኪም ታዘው ነበር። ይህም ከ10 ስኮትላንዳዊ አንዱ ፓራሲታሞል ይውጥ ነበር ማለት ነው። በዩናይት ኪንግደም ከፍተኛ የደም ግፊት ከሶስት ሰው አንድ ሰውን ያጠቃል። ጥናቱ 110 ፈቃደኛ ሰዎችን አካቶ የተሰራ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሁለት ሶስተኛው የደም ግፊት መድኃኒቶች ይውጡ የነበሩ ናቸው። የጥናቱ ተሳታፊዎች አንድ ግራም ፓራሲታሞል በቀን አራት ጊዜ ለሁለት ሳምንታት እንዲወስዱ ሆነ። ቀጥሎ ደግሞ ለሁለት ሳምንታት ክኒና የሚመስል ጥቅምም ጉዳትም የሌለው ቁስ እንዲውጡ ተደረጉ። ሙከራው እንዳሳየው ፓራሲታሞል የወሰዱት የደም ግፊታቸው ጨመረ። ይህም ማለት ለልብ ድካምና ስትሮክ የመጋለጣቸው ዕድል ከፍ አለ ማለት ነው ይላሉ የኤደንብራ ፕሮፌሰር ጄምስ ዲር። ዶክተሮች እንደ ደም ግፊት ዓይነት በሽታ ላለባቸው ታካሚዎች መጠኑ ያነሰ ፓራሲታሞል እንዲሰጧቸው አጥኚዎቹ ይመክራሉ። የጥናቱ መሪ የሆኑት ዶክተር ኢያን ማካንታዬር ይህ ጥናት ለአጭር ጊዜ ሕመምን ለማስታገስ የሚወሰድ ፓራሲታሞልን አይመለከትም ይላሉ። የለንደን ዩኒቨርሲቲው ዶክተር ዲፔንደር ጊል፤ አሁን በሰሩት ጥናት መሠረት ክኒናው በነጭ ስከትላንዳዊያን ላይ ለደም ግፊት መባባስ ምክንያት ሆኖ ቢታይም ብዙ የማይታወቁ ጉዳዮች እንዳሉ ያስረዳሉ። አንድ ከዚህ በፊት አሜሪካ ውስጥ የተሠራ ጥናት ለረዥም ጊዜ ፓራሲታሞል መጠቀም ለልብ ድካም ሊያጋልጥ እንደሚችል ጠቁሞ ነበር። ሌሎች አነስ ያሉ ጥናቶች ደግሞ በክኒናውና በልብ ድካም መካከል ያለውን ግንኙነት መለየት አልቻሉም። የኤንድብራ አጥኚዎች በፓራሲታሞልና ልብ ድካም መካከል ያለውን ግንኙነት ይህ ነው ብለው ባያስረዱም የጥናታቸው ውጤት ለሌላ ሰፋ ላለ ጥናት እንደሚጠቀም ተገልጧል። ነገር ግን የብሪታኒያው ኸርት ፋውንዴሽን ዶክተሮችና ታካሚዎቻቸው የትኛው መድኃኒት አስፈላጊ ካልሆነ መዋጡ ያለውን ጥቅምና ጉዳት እንዲያገናዝቡ አደራ ብሏል። ወደፊት የደም ግፊት ባለባቸው ሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሌለባቸው ሰዎች ላይም ፓራሲታሞል አዘውትሮ መጠቀም ያለውን ጉዳት መቃኘት አስፈላጊ እንደሆነ የዘርፉ ሙያተኞች እየተናገሩ ነው። | የደም ግፊት ታካሚዎች ፓራሲታሞል አዘውትረው ከዋጡ ለልብ ድካም ሊዳርጋቸው ይችላል ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች በሐኪም ትዕዛዝ አዘውትረው ፓራሲታሞል መጠቀማቸው ለልብ ድካም ሊያጋልጣቸው እንደሚችል አንድ ጥናት ጠቆመ። የኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ አጥኚዎች እንዳሉት ዶክተሮች ለታካሚዎቻቸው ለብዙ ወራት የሚወጣ ክኒና ሲያዙ ጥቅምና ጉዳቱን ከግምት ማስገባት አለባቸው። ሕመም ማስታገሻውን መድኃኒት ለራስ ምታትና ለትኩሳት መውሰድ ችግር እንደሌለው አጥኚዎቹ ይናገራሉ። አንዳንድ ሙያተኞች ደግሞ በርከት ባሉ ሰዎች ላይ ጥናት ተሰርቶ ውጤቱን ማረጋገጥ ተገቢ ነው ይላሉ። ፓራሲታሞል በመላው ዓለም የሚታወቅ ሕመም ለማስታገስ የሚዋጥ ሲሆን አንዳንዴ ጥልቅ ሕመም ለሚያስከትሉ በሽታዎችም ይመከራል። ነገር ግን ክኒናው ለረዥም ጊዜ መፍትሔ አይሰጥም። በፈረንጆቹ 2018 ግማሽ ሚሊዮን ስኮትላንዳዊያን ይህንን ማስታገሻ እንዲውጡ በሐኪም ታዘው ነበር። ይህም ከ10 ስኮትላንዳዊ አንዱ ፓራሲታሞል ይውጥ ነበር ማለት ነው። በዩናይት ኪንግደም ከፍተኛ የደም ግፊት ከሶስት ሰው አንድ ሰውን ያጠቃል። ጥናቱ 110 ፈቃደኛ ሰዎችን አካቶ የተሰራ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሁለት ሶስተኛው የደም ግፊት መድኃኒቶች ይውጡ የነበሩ ናቸው። የጥናቱ ተሳታፊዎች አንድ ግራም ፓራሲታሞል በቀን አራት ጊዜ ለሁለት ሳምንታት እንዲወስዱ ሆነ። ቀጥሎ ደግሞ ለሁለት ሳምንታት ክኒና የሚመስል ጥቅምም ጉዳትም የሌለው ቁስ እንዲውጡ ተደረጉ። ሙከራው እንዳሳየው ፓራሲታሞል የወሰዱት የደም ግፊታቸው ጨመረ። ይህም ማለት ለልብ ድካምና ስትሮክ የመጋለጣቸው ዕድል ከፍ አለ ማለት ነው ይላሉ የኤደንብራ ፕሮፌሰር ጄምስ ዲር። ዶክተሮች እንደ ደም ግፊት ዓይነት በሽታ ላለባቸው ታካሚዎች መጠኑ ያነሰ ፓራሲታሞል እንዲሰጧቸው አጥኚዎቹ ይመክራሉ። የጥናቱ መሪ የሆኑት ዶክተር ኢያን ማካንታዬር ይህ ጥናት ለአጭር ጊዜ ሕመምን ለማስታገስ የሚወሰድ ፓራሲታሞልን አይመለከትም ይላሉ። የለንደን ዩኒቨርሲቲው ዶክተር ዲፔንደር ጊል፤ አሁን በሰሩት ጥናት መሠረት ክኒናው በነጭ ስከትላንዳዊያን ላይ ለደም ግፊት መባባስ ምክንያት ሆኖ ቢታይም ብዙ የማይታወቁ ጉዳዮች እንዳሉ ያስረዳሉ። አንድ ከዚህ በፊት አሜሪካ ውስጥ የተሠራ ጥናት ለረዥም ጊዜ ፓራሲታሞል መጠቀም ለልብ ድካም ሊያጋልጥ እንደሚችል ጠቁሞ ነበር። ሌሎች አነስ ያሉ ጥናቶች ደግሞ በክኒናውና በልብ ድካም መካከል ያለውን ግንኙነት መለየት አልቻሉም። የኤንድብራ አጥኚዎች በፓራሲታሞልና ልብ ድካም መካከል ያለውን ግንኙነት ይህ ነው ብለው ባያስረዱም የጥናታቸው ውጤት ለሌላ ሰፋ ላለ ጥናት እንደሚጠቀም ተገልጧል። ነገር ግን የብሪታኒያው ኸርት ፋውንዴሽን ዶክተሮችና ታካሚዎቻቸው የትኛው መድኃኒት አስፈላጊ ካልሆነ መዋጡ ያለውን ጥቅምና ጉዳት እንዲያገናዝቡ አደራ ብሏል። ወደፊት የደም ግፊት ባለባቸው ሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሌለባቸው ሰዎች ላይም ፓራሲታሞል አዘውትሮ መጠቀም ያለውን ጉዳት መቃኘት አስፈላጊ እንደሆነ የዘርፉ ሙያተኞች እየተናገሩ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-60298844 |
5sports
| ስፖርት፡ በቻን የወንዶች እግር ኳስ ውድድር ላይ በዋና ዳኝነት የምትሳተፈው ሊዲያ ታፈሰ | ዛሬ ቅዳሜ ጥር 08/2013 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ የሚጀመረው 'ቻን' በመባል የሚታወቀው የአፍሪካ አገራት የእግር ኳስ ሻምፒዮና ውድድር ጨዋታዎችን እንዲዳኙ በአህጉሪቱ የእግር ኳስ የበላይ አካል ካፍ ከ31 አገራት 47 ዋና ዳኞችና ረዳት ዳኞችን ሰይሟል። ይህን የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ከሚዳኙት ዳኞች መካከል አራት ሴቶች ከወንዶች አቻዎቻቸው ጋር በአካላዊና ስፖርታዊ እንዲሁም የእግር ኳስ ጨዋታን በመረዳት ባላቸው ብቃት ተመዝነው እንደተመረጡ ተገልጿል። ለውድድሩ ዳኝነት ከተመረጡት 47 ዳኞች መካከል፣ 19ኙ በዋና ዳኝነት ጨዋታዎችን የሚመሩ ሲሆን ቀሪዎቹ በመስመር ዳኝነትና በቪዲዮ ዳኝነት የመሃል ዳኞችን የሚያግዙ ናቸው። ታዲያ ከ19ኙ ዋና ዳኞች መካከል ብቸኛዋ የመሃል ዳኛ ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ ናት። ሊዲያ በአገር ውስጥና በተለያዩ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮችን በመዳኘት ብቃቷን ያስመሰከረች ስትሆን የአፍሪካ የእግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ውስጥ አንዱ በሆነው 'የቻን' የወንዶች የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በዋና ዳኝነት ጨዋታ የምትመራ ቀዳሚዋ ሴት ሆናለች። ካፍ የሚያዘጋጃቸው የወንዶች የእግር ኳስ ውድድሮችን በመዳኘት በኩል ሴቶች እንዲሳተፉ ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ፣ በውድድሮቹ ሂደት ውስጥ ሴቶች የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመያዝ እንዲሳተፉ እያደረገ ነው። በዚህም መሠረት ከሊዲያ ታፈሰ በተጨማሪ በቻን ውድድር ላይ በረዳት ዳኝነት ከማላዊ፣ ከናይጄሪያና ከካሜሩን የተመረጡ ሴቶች ይሳተፋሉ። የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ሊዲያ ታፈሰ ወደ ስፖርት የገባቸው ጅማ ውስጥ ባዳበረችው የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ፍቅር ምክንያት ነው። ሊዲያ በታዳጊነቷ እግር ኳስ ትጫወት የነበረ ሲሆን ዋነኛው ስፖርቷ ግን ቅርጫት ነበር። አሁን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የወንዶች እግር ኳስ ሊግ ውስጥ በብቃታቸው ከሚጠቀሱ ዳኞች መካከል አንዷ የሆነችው ሊዲያ፣ መጀመሪያ ላይ ባገኘችው ስልጠና ተስባ ነበር ወደ ዳኝነቱ የገባችው። በዳኝነቱ ዘርፍ ከሴቶች አንጻር ከቀዳሚዎቹ ውስጥ የምትጠቀሰው ሊዲያ፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን መዳኘት በጀመረች ጊዜ፣ ጥያቄና ፈተናዎች ገጥመዋት እንደነበር ካፍ ድረ ገጽ ላይ በወጣው ታሪኳ ላይ ሰፍሯል። "በጣም አስቸጋሪ ነበር። አንዳንዶች ሌላ ሴት በሌለችበት ዘርፍ ላይ በእግር ኳስ ዳኝነት ለመሰማራት ለምን እንደወሰንኩ ሁሉ የሚጠይቁኝ ሰዎች ነበሩ" ትላለች። ሴት ዳኞችን ለማፍራት በታቀደ ፕሮጀክት ውስጥ ስልጠና አግኝታ፣ ከ15 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ልጆች የእግር ኳስ ጨዋታዎችን በዳኝነት በመምራት የጀመረችው ሊዲያ፤ በአገሪቱ ፐሪሚየር ሊግ ውስጥ ጨዋታዎችን በዳኝነት መምራት ችላለች። በዳኝነቱ ላይ ያሳደረችው ፍቅር ቢጠነክርም፣ ሴት ሆና የወንዶችን ጨዋታዎች ስትዳኝ እንደ እንግዳ ነገር የሚመለከቷት ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን ከወንዶች ጋር እግር ኳስ በምትጫወትበት ጊዜ ያዳበረችው በራስ መተማመን የወንዶችን ውድድሮች ያለችግር እንደትመራ እንደረዳት የምትናገረው ሊዲያ፤ የቤተሰቧ ድጋፍ ደግሞ ወሳኙ እንደነበር ታነሳለች። በአገር ውስጥ ውድድሮች ላይ ባሳየችው የዳኝነት ብቃት ለዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎች የታጨችው ሊዲያ፤ በመጀመሪያ ከ15 ዓመት በፊት ናይጄሪያና ላይቤሪያ አቡጃ ውስጥ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ውድድር ለዋንጫ ለማለፍ ያደረጉትን ግጥሚያ ዳኝታለች። "ያንን ጨዋታ አልረሳውም ምክንያቱም በጣም አስቸጋሪ ነበረ። ስታዲየሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምናውቀው በጣም ይተልቃል፣ ተመልካቹም የተለየ ነበር" ትላለች። በመቀጠልም የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ግጥሚያዎችን ያጫወተች ሲሆን በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደውን የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን በተከታታይ ለአራት ጊዜ በመዳኘት ለቀጣዩ እየተዘጋጀች ነው። ከዚህ በተጨማሪም ከአራት ዓመት በፊትና ከአንድ ዓመት በፊት የተካሄዱትን የፊፋ የሴቶች እግር ኳስ የዓለም ዋንጫን፣ እንዲሁም የፊፋ ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች የዓለም ዋንጫንና ከ20 ዓመት በታች ውድድሮች ላይ በዳኝነት ተሳትፋለች። ሊዲያ ልጇን በጸነሰችበትና ከወለደች በኋላም ወደምትወደው የዳኝነት ሙያዎ ለመመለስ ፈተናዎች ገጥመዋት ነበር። "ከእርግዝና በኋላ አካላዊ ለውጥ ያጋጥማል። ክብደቴ በጣም ጨምሮ ስለነበር ወደ ቀድሞ አቋሜ ለመመለስ በጣም መስራት ነበረብኝ። በርትቼ በመስራት መጨረሻ ላይ ተሳክቶልኝ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ እድሉን አገኘሁ" ብላለች። ለዚያ ውድድር በምትዘጋጅበት ጊዜ ጉዳት አጋጥሟት እንደነበር የምትናገረው ሊዲያ፣ ወደ አገሯ እንደምትመለስና በዚህ ምክንያት ከስፖርቱ ልትወጣ እንደሆነ ስጋት ፈጥሮባት ነበር። ነገር ግን በኋላ ላይ አገግማ ዛሬ ላይ ደርሳለች። ከጉዳቷ በኋላ ወደ ተጨማሪ ሰዓት የተሸጋገረውን የካሜሩንና የኮትዲቯርን የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መርታ ነበር። "ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ሲሸጋገር ሜዳ ውስጥ ከእግር ኳስ ተጫዋቾቹ በላይ ጠንካራ ነበርኩ። በጣም ደስ ብሎኝ ነበረ" ስትል ሊዲያ ታስታውሳለች። ሊዲያ በበርካታ ታላላቅ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ወሳኝ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ በዳኝነት ተሳትፋለች። ወደፊትም በታላቁ የአፍሪካ የወንዶች ዋንጫ ላይ በዳኝነት እንደምትሳተፍ ተስፋ አላት። ሊዲያ ከዳኝነቱ በተጨማሪ የፋርማሲ ባለሙያ ስትሆን፣ በዚህ የኮሮናቫይረስ ዘመን የእግር ኳስ ውድድሮች ለወራት ተቋርጠው በነበረበት ጊዜ በሙያዋ ወገኖቿን ለማገልግል ሰርታለች። በዚህም ሰዎች ራሳቸውንና ሌሎችን ከወረርሽኙ እንዲከላከሉ የህክምና መረጃዎችን በተለያዩ መንዶች ስትሰጥ ቆይታለች። በየትኛውም ጊዜ ከልምምድ ርቃ የማታውቀው ሊዲያ፣ እንደ ሴት በቤተሰቧና በእግር ኳስ ዳኝነት ሙያዋ መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅ እንደተሳካላት ትናገራለች። ለዚህ ደግሞ ከባሏና ከልጇ የምታገኘው ድጋፍና ማበረታታት በሙያዋ በስኬት እንደትቀጥል እንዳደረጋት ገልጻለች። በአፍሪካ አህጉር አሉ ከሚባሉ ኮከብ ሴት የእግር ኳስ ዳኞች መካከል ከፊት የምትጠቀሰው ሊዲያ ታፈሰ፣ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ውስጥ ወደፊት ለሚመጡ ሴት ዳኞች መልካም አርአያ እንደምትሆን ታምናለች። ወደፊትም ከሙሉ ጊዜ የእግር ኳስ ዳኝነት አረፍ ስትል በፋርማሲ ሙያዋ ከመቀጠል በተጨማሪ፣ በዳኝነቱ የእሷን እግር ተከትለው መሥራት የሚፈልጉትን የማሰልጠን ፍላጎት አላት። | ስፖርት፡ በቻን የወንዶች እግር ኳስ ውድድር ላይ በዋና ዳኝነት የምትሳተፈው ሊዲያ ታፈሰ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 08/2013 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ የሚጀመረው 'ቻን' በመባል የሚታወቀው የአፍሪካ አገራት የእግር ኳስ ሻምፒዮና ውድድር ጨዋታዎችን እንዲዳኙ በአህጉሪቱ የእግር ኳስ የበላይ አካል ካፍ ከ31 አገራት 47 ዋና ዳኞችና ረዳት ዳኞችን ሰይሟል። ይህን የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ከሚዳኙት ዳኞች መካከል አራት ሴቶች ከወንዶች አቻዎቻቸው ጋር በአካላዊና ስፖርታዊ እንዲሁም የእግር ኳስ ጨዋታን በመረዳት ባላቸው ብቃት ተመዝነው እንደተመረጡ ተገልጿል። ለውድድሩ ዳኝነት ከተመረጡት 47 ዳኞች መካከል፣ 19ኙ በዋና ዳኝነት ጨዋታዎችን የሚመሩ ሲሆን ቀሪዎቹ በመስመር ዳኝነትና በቪዲዮ ዳኝነት የመሃል ዳኞችን የሚያግዙ ናቸው። ታዲያ ከ19ኙ ዋና ዳኞች መካከል ብቸኛዋ የመሃል ዳኛ ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ ናት። ሊዲያ በአገር ውስጥና በተለያዩ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮችን በመዳኘት ብቃቷን ያስመሰከረች ስትሆን የአፍሪካ የእግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ውስጥ አንዱ በሆነው 'የቻን' የወንዶች የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በዋና ዳኝነት ጨዋታ የምትመራ ቀዳሚዋ ሴት ሆናለች። ካፍ የሚያዘጋጃቸው የወንዶች የእግር ኳስ ውድድሮችን በመዳኘት በኩል ሴቶች እንዲሳተፉ ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ፣ በውድድሮቹ ሂደት ውስጥ ሴቶች የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመያዝ እንዲሳተፉ እያደረገ ነው። በዚህም መሠረት ከሊዲያ ታፈሰ በተጨማሪ በቻን ውድድር ላይ በረዳት ዳኝነት ከማላዊ፣ ከናይጄሪያና ከካሜሩን የተመረጡ ሴቶች ይሳተፋሉ። የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ሊዲያ ታፈሰ ወደ ስፖርት የገባቸው ጅማ ውስጥ ባዳበረችው የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ፍቅር ምክንያት ነው። ሊዲያ በታዳጊነቷ እግር ኳስ ትጫወት የነበረ ሲሆን ዋነኛው ስፖርቷ ግን ቅርጫት ነበር። አሁን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የወንዶች እግር ኳስ ሊግ ውስጥ በብቃታቸው ከሚጠቀሱ ዳኞች መካከል አንዷ የሆነችው ሊዲያ፣ መጀመሪያ ላይ ባገኘችው ስልጠና ተስባ ነበር ወደ ዳኝነቱ የገባችው። በዳኝነቱ ዘርፍ ከሴቶች አንጻር ከቀዳሚዎቹ ውስጥ የምትጠቀሰው ሊዲያ፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን መዳኘት በጀመረች ጊዜ፣ ጥያቄና ፈተናዎች ገጥመዋት እንደነበር ካፍ ድረ ገጽ ላይ በወጣው ታሪኳ ላይ ሰፍሯል። "በጣም አስቸጋሪ ነበር። አንዳንዶች ሌላ ሴት በሌለችበት ዘርፍ ላይ በእግር ኳስ ዳኝነት ለመሰማራት ለምን እንደወሰንኩ ሁሉ የሚጠይቁኝ ሰዎች ነበሩ" ትላለች። ሴት ዳኞችን ለማፍራት በታቀደ ፕሮጀክት ውስጥ ስልጠና አግኝታ፣ ከ15 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ልጆች የእግር ኳስ ጨዋታዎችን በዳኝነት በመምራት የጀመረችው ሊዲያ፤ በአገሪቱ ፐሪሚየር ሊግ ውስጥ ጨዋታዎችን በዳኝነት መምራት ችላለች። በዳኝነቱ ላይ ያሳደረችው ፍቅር ቢጠነክርም፣ ሴት ሆና የወንዶችን ጨዋታዎች ስትዳኝ እንደ እንግዳ ነገር የሚመለከቷት ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን ከወንዶች ጋር እግር ኳስ በምትጫወትበት ጊዜ ያዳበረችው በራስ መተማመን የወንዶችን ውድድሮች ያለችግር እንደትመራ እንደረዳት የምትናገረው ሊዲያ፤ የቤተሰቧ ድጋፍ ደግሞ ወሳኙ እንደነበር ታነሳለች። በአገር ውስጥ ውድድሮች ላይ ባሳየችው የዳኝነት ብቃት ለዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎች የታጨችው ሊዲያ፤ በመጀመሪያ ከ15 ዓመት በፊት ናይጄሪያና ላይቤሪያ አቡጃ ውስጥ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ውድድር ለዋንጫ ለማለፍ ያደረጉትን ግጥሚያ ዳኝታለች። "ያንን ጨዋታ አልረሳውም ምክንያቱም በጣም አስቸጋሪ ነበረ። ስታዲየሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምናውቀው በጣም ይተልቃል፣ ተመልካቹም የተለየ ነበር" ትላለች። በመቀጠልም የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ግጥሚያዎችን ያጫወተች ሲሆን በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደውን የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን በተከታታይ ለአራት ጊዜ በመዳኘት ለቀጣዩ እየተዘጋጀች ነው። ከዚህ በተጨማሪም ከአራት ዓመት በፊትና ከአንድ ዓመት በፊት የተካሄዱትን የፊፋ የሴቶች እግር ኳስ የዓለም ዋንጫን፣ እንዲሁም የፊፋ ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች የዓለም ዋንጫንና ከ20 ዓመት በታች ውድድሮች ላይ በዳኝነት ተሳትፋለች። ሊዲያ ልጇን በጸነሰችበትና ከወለደች በኋላም ወደምትወደው የዳኝነት ሙያዎ ለመመለስ ፈተናዎች ገጥመዋት ነበር። "ከእርግዝና በኋላ አካላዊ ለውጥ ያጋጥማል። ክብደቴ በጣም ጨምሮ ስለነበር ወደ ቀድሞ አቋሜ ለመመለስ በጣም መስራት ነበረብኝ። በርትቼ በመስራት መጨረሻ ላይ ተሳክቶልኝ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ እድሉን አገኘሁ" ብላለች። ለዚያ ውድድር በምትዘጋጅበት ጊዜ ጉዳት አጋጥሟት እንደነበር የምትናገረው ሊዲያ፣ ወደ አገሯ እንደምትመለስና በዚህ ምክንያት ከስፖርቱ ልትወጣ እንደሆነ ስጋት ፈጥሮባት ነበር። ነገር ግን በኋላ ላይ አገግማ ዛሬ ላይ ደርሳለች። ከጉዳቷ በኋላ ወደ ተጨማሪ ሰዓት የተሸጋገረውን የካሜሩንና የኮትዲቯርን የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መርታ ነበር። "ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ሲሸጋገር ሜዳ ውስጥ ከእግር ኳስ ተጫዋቾቹ በላይ ጠንካራ ነበርኩ። በጣም ደስ ብሎኝ ነበረ" ስትል ሊዲያ ታስታውሳለች። ሊዲያ በበርካታ ታላላቅ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ወሳኝ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ በዳኝነት ተሳትፋለች። ወደፊትም በታላቁ የአፍሪካ የወንዶች ዋንጫ ላይ በዳኝነት እንደምትሳተፍ ተስፋ አላት። ሊዲያ ከዳኝነቱ በተጨማሪ የፋርማሲ ባለሙያ ስትሆን፣ በዚህ የኮሮናቫይረስ ዘመን የእግር ኳስ ውድድሮች ለወራት ተቋርጠው በነበረበት ጊዜ በሙያዋ ወገኖቿን ለማገልግል ሰርታለች። በዚህም ሰዎች ራሳቸውንና ሌሎችን ከወረርሽኙ እንዲከላከሉ የህክምና መረጃዎችን በተለያዩ መንዶች ስትሰጥ ቆይታለች። በየትኛውም ጊዜ ከልምምድ ርቃ የማታውቀው ሊዲያ፣ እንደ ሴት በቤተሰቧና በእግር ኳስ ዳኝነት ሙያዋ መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅ እንደተሳካላት ትናገራለች። ለዚህ ደግሞ ከባሏና ከልጇ የምታገኘው ድጋፍና ማበረታታት በሙያዋ በስኬት እንደትቀጥል እንዳደረጋት ገልጻለች። በአፍሪካ አህጉር አሉ ከሚባሉ ኮከብ ሴት የእግር ኳስ ዳኞች መካከል ከፊት የምትጠቀሰው ሊዲያ ታፈሰ፣ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ውስጥ ወደፊት ለሚመጡ ሴት ዳኞች መልካም አርአያ እንደምትሆን ታምናለች። ወደፊትም ከሙሉ ጊዜ የእግር ኳስ ዳኝነት አረፍ ስትል በፋርማሲ ሙያዋ ከመቀጠል በተጨማሪ፣ በዳኝነቱ የእሷን እግር ተከትለው መሥራት የሚፈልጉትን የማሰልጠን ፍላጎት አላት። | https://www.bbc.com/amharic/news-55681377 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በኤርትራ ቢራ በኩፖን መሸጥ ተጀመረ | የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎችና መጠጥ ቤቶቿን በዘጋችው ኤርትራ ቢራ በኩፖን (መሸመቻ ካርድ) መሸጥ መጀመሯ ተገልጿል። ብቸኛው ሜሎቲ ቢራ በሱቆች በመሸመቻ ካርድ አማካኝነት እየተሸጠ እንደሚገኝም ቢቢሲ ትግርኛ ከምንጮች ያገኘው መረጃ አመላክቷል። ደንበኞች ቢራውን ማግኘት የሚችሉት በሱቆች ብቻ ሲሆን አንድ ቢራም በአስር ናቅፋ (ወደ 25 ብር በሚጠጋ) ዋጋ እንደሚሸጥ ተገልጿል። ኩፖኑን (የመሸመቻ ካርዱን) የያዙ ሰዎችም በአንድ ሳምንት መግዛት የሚፈቀድላቸው የቢራ ብዛት ስምንት ጠርሙስ ብቻ ነው። በኤርትራ ዳቦ፣ ዘይት፣ ስኳርና ማሽላ የመሳሰሉትን መሰረታዊ ሸቀጦች በስርጭት (በመሸመቻ) ካርድ በቀበሌዎች ሲሆን መግዛት የሚቻለው፤ መጠኑም በቤተሰብ ቁጥሩ ይወሰናል። በተለይም ዳቦ ለመግዛት በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ተመዝግበውም በየእለቱ ጧት የቤተሰባቸውን ቁጥር መሰረት ባደረገ መልኩም እንዲገዙ ይፈቅድላቸዋል። ሜሎቲ ቢራም በተመሳሳይ መልኩ እንደ ዳቦና ስኳር በሱቆች በመሸመቻ ካርድ መሸጡ አንዳንድ የመጠጥ ቤት ባለቤቶችን ቅር አሰኝቷል። በአስመራ የሚገኝ ስሜ አይጠቀስ ያለ አንድ የመጠጥ ቤት ባለቤት ነጋዴ "የንግድ ፍቃድ ያለን ሰዎች ንግድ ቤታችሁን ዝጉ ተብለን፤ ለሰራተኞች ደሞዝ ክፈሉ ተብለን ስናበቃ እኛ ልንሸጠው የሚገባ ቢራ በሱቆች እየተሸጠ ይገኛል" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል። ነጋዴው እንደሚለው መጠጥ ቤቶቹ የተዘጉት የሰዎችን መሰባሰብ ለመቀነስ መሆኑን ቢረዳም ቢራው በሱቆች መሸጥ ለመጀመሩ ምክንያቱ ግልፅ አልሆነለትም። መጠጥ ቤቶቹ ሱቆች አሁን እያደረጉት እንዳለው ቢራ መሸጥ ይችሉም እንደነበር ይናገራል። "ሰባት ወር ሙሉ ከስራ ውጪ ሆነናል። ለሰራተኞቻችን ደግሞ ምንም ሳንሰራ ደመወዝ እንድንከፍል እየተገደድን ነው። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ደንበኞች ቢራ በሱቆች ገዝተው እየሄዱ ነው፤ ገበያችንንም እያሳጡን ነው" ይላል። በአሁኑ ወቅት ቢራ በሱቆች መሸጥ ከመጀመሩም ጋር ተያይዞ ወጣቶች በሱቆች ገዝተው ተሰባስበው እየጠጡ እንደሚያመሹም ምንጫችን ትዝብቱን ይገልጻል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሳልፋ የነበረችው ኤርትራ አዋጇን ቀስ በቀስ እያላላች ትገኛለች። ሰዎችም ከቦታ ወደ ቦታ እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ። በተለይም በአገሪቷ ከጥቂት ከጎረቤት አገራት የመጡ ሰዎች በስተቀር ይህ ነው በማይባል ሁኔታ ወረረሽኙ አለመኖሩ እንዲሁም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ባለመኖራቸው አዋጁ ለምን በይፋ እንደማይነሳ በርካቶች ይጠይቃሉ። በኤርትራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ጊዜ ጀምሮ የንግድ እንቅስቃሴ የቆመ ሲሆን በተለይ ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን ህዝብ ከመንግሥት ምንም ዓይነት ድጋፍ ስለማይደረግለት ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ በሆነና በፈታኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ይናገራሉ። በኤርትራ አንድ ብቻ የሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ። አንድ አይነት ቢራ፣ አንድ አውሮፕላን፣ አንድ ሥርዓት ያለው የባንክ አገልግሎት፣ እንድ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ፣ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ፣ አንድ የቴሌቪዝን ጣቢያ . . . ከ1939 ጀምሮ በኤርትራ ሲጠመቅ ቆይቷል። ይህ ለኤርትራ ብቸኛ የሆነው ቢራ በበርካቶች ዘንድ ትዝታ እና ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው። የቢራ ፈላጊውን እና የአቅርቦት መጠኑ ተመጣጣኝ ስላልነበረ ከቅርብ ዓመታት በፊት አንድ ሰው ሁለት ቢራ ብቻ ገዝቶ እንዲጠጣ ነበር የሚፈቀድለት። ከሁለት በላይ ደጋግሞ መጠጣት የፈለገ፤ ቢራ የማይጠጣ ሰው ወደ መጠጥ ቤት ይዞ በመሄድ የዚያን ሰው ኮታ ይጠጣ እንደነበር ሰምተናል። አሁን ላይ በቢራ ፋብሪካው በተካሄደ ለውጥ የቢራ አቅርቦቱን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስኑ የድንበር በሮች በተከፈቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ቢራ ምርቶች አሥመራን አጥለቅልቀዋት እንደነበረ በዚህም የአንድ ሜሎቲ ቢራ ዋጋ ከ25 ናቅፋ ከ11-15 እንደወረደ ነዋሪዎች ነግረውናል። | ኮሮናቫይረስ፡ በኤርትራ ቢራ በኩፖን መሸጥ ተጀመረ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎችና መጠጥ ቤቶቿን በዘጋችው ኤርትራ ቢራ በኩፖን (መሸመቻ ካርድ) መሸጥ መጀመሯ ተገልጿል። ብቸኛው ሜሎቲ ቢራ በሱቆች በመሸመቻ ካርድ አማካኝነት እየተሸጠ እንደሚገኝም ቢቢሲ ትግርኛ ከምንጮች ያገኘው መረጃ አመላክቷል። ደንበኞች ቢራውን ማግኘት የሚችሉት በሱቆች ብቻ ሲሆን አንድ ቢራም በአስር ናቅፋ (ወደ 25 ብር በሚጠጋ) ዋጋ እንደሚሸጥ ተገልጿል። ኩፖኑን (የመሸመቻ ካርዱን) የያዙ ሰዎችም በአንድ ሳምንት መግዛት የሚፈቀድላቸው የቢራ ብዛት ስምንት ጠርሙስ ብቻ ነው። በኤርትራ ዳቦ፣ ዘይት፣ ስኳርና ማሽላ የመሳሰሉትን መሰረታዊ ሸቀጦች በስርጭት (በመሸመቻ) ካርድ በቀበሌዎች ሲሆን መግዛት የሚቻለው፤ መጠኑም በቤተሰብ ቁጥሩ ይወሰናል። በተለይም ዳቦ ለመግዛት በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ተመዝግበውም በየእለቱ ጧት የቤተሰባቸውን ቁጥር መሰረት ባደረገ መልኩም እንዲገዙ ይፈቅድላቸዋል። ሜሎቲ ቢራም በተመሳሳይ መልኩ እንደ ዳቦና ስኳር በሱቆች በመሸመቻ ካርድ መሸጡ አንዳንድ የመጠጥ ቤት ባለቤቶችን ቅር አሰኝቷል። በአስመራ የሚገኝ ስሜ አይጠቀስ ያለ አንድ የመጠጥ ቤት ባለቤት ነጋዴ "የንግድ ፍቃድ ያለን ሰዎች ንግድ ቤታችሁን ዝጉ ተብለን፤ ለሰራተኞች ደሞዝ ክፈሉ ተብለን ስናበቃ እኛ ልንሸጠው የሚገባ ቢራ በሱቆች እየተሸጠ ይገኛል" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል። ነጋዴው እንደሚለው መጠጥ ቤቶቹ የተዘጉት የሰዎችን መሰባሰብ ለመቀነስ መሆኑን ቢረዳም ቢራው በሱቆች መሸጥ ለመጀመሩ ምክንያቱ ግልፅ አልሆነለትም። መጠጥ ቤቶቹ ሱቆች አሁን እያደረጉት እንዳለው ቢራ መሸጥ ይችሉም እንደነበር ይናገራል። "ሰባት ወር ሙሉ ከስራ ውጪ ሆነናል። ለሰራተኞቻችን ደግሞ ምንም ሳንሰራ ደመወዝ እንድንከፍል እየተገደድን ነው። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ደንበኞች ቢራ በሱቆች ገዝተው እየሄዱ ነው፤ ገበያችንንም እያሳጡን ነው" ይላል። በአሁኑ ወቅት ቢራ በሱቆች መሸጥ ከመጀመሩም ጋር ተያይዞ ወጣቶች በሱቆች ገዝተው ተሰባስበው እየጠጡ እንደሚያመሹም ምንጫችን ትዝብቱን ይገልጻል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሳልፋ የነበረችው ኤርትራ አዋጇን ቀስ በቀስ እያላላች ትገኛለች። ሰዎችም ከቦታ ወደ ቦታ እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ። በተለይም በአገሪቷ ከጥቂት ከጎረቤት አገራት የመጡ ሰዎች በስተቀር ይህ ነው በማይባል ሁኔታ ወረረሽኙ አለመኖሩ እንዲሁም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ባለመኖራቸው አዋጁ ለምን በይፋ እንደማይነሳ በርካቶች ይጠይቃሉ። በኤርትራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ጊዜ ጀምሮ የንግድ እንቅስቃሴ የቆመ ሲሆን በተለይ ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን ህዝብ ከመንግሥት ምንም ዓይነት ድጋፍ ስለማይደረግለት ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ በሆነና በፈታኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ይናገራሉ። በኤርትራ አንድ ብቻ የሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ። አንድ አይነት ቢራ፣ አንድ አውሮፕላን፣ አንድ ሥርዓት ያለው የባንክ አገልግሎት፣ እንድ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ፣ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ፣ አንድ የቴሌቪዝን ጣቢያ . . . ከ1939 ጀምሮ በኤርትራ ሲጠመቅ ቆይቷል። ይህ ለኤርትራ ብቸኛ የሆነው ቢራ በበርካቶች ዘንድ ትዝታ እና ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው። የቢራ ፈላጊውን እና የአቅርቦት መጠኑ ተመጣጣኝ ስላልነበረ ከቅርብ ዓመታት በፊት አንድ ሰው ሁለት ቢራ ብቻ ገዝቶ እንዲጠጣ ነበር የሚፈቀድለት። ከሁለት በላይ ደጋግሞ መጠጣት የፈለገ፤ ቢራ የማይጠጣ ሰው ወደ መጠጥ ቤት ይዞ በመሄድ የዚያን ሰው ኮታ ይጠጣ እንደነበር ሰምተናል። አሁን ላይ በቢራ ፋብሪካው በተካሄደ ለውጥ የቢራ አቅርቦቱን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስኑ የድንበር በሮች በተከፈቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ቢራ ምርቶች አሥመራን አጥለቅልቀዋት እንደነበረ በዚህም የአንድ ሜሎቲ ቢራ ዋጋ ከ25 ናቅፋ ከ11-15 እንደወረደ ነዋሪዎች ነግረውናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54703886 |
5sports
| በሩዋንዳ ለነፍሰጡር እናቶች የሚሆን የስፖርት እንቅስቃሴ ተጀመረ | ሩዋንዳ ለነፍሰጡር እናቶች የሚጠቅምና በጋራ የሚደረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደጀመረች ተገለጸ። ለመጀመሪያ ጊዜ በአገሪቱ በተካሄደው በዚህ የነፍሰጡር እናቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ ለቢቢሲ እንደተናገሩት መደሰታቸውንና ባለስልጣናትም ስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በዋና ከተማዋ ኪጋሊ ውስጥ በተካሄደው የመጀመሪያው የስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ ከ100 በላይ ነፍሰጡር እናቶች የተሳተፉ ሲሆን አላማውም የነፍሰጡር ሴቶችን አካላዊ ሁኔታን በተመለተ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለመለወጥ መሆኑን አዘጋጆቹ ተናግረዋል። • ፊደል ያልቆጠሩት ኢትዮጵያዊት የቀዶ ህክምና ባለሙያ • በጀርባቸው የሚተኙ ነፍሰጡሮች ህይወት የሌለው ልጅ እየወለዱ ነው አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅትና ስፖርታዊ እንቅስቃሴውን ያስተባበረው መሪ ኔልሰን ሙካሳ እንደገለጹት፤ በርካታ ሩዋንዳውያን አንዲት ሴት ስታረግዝ ከሁሉም አይነት አካላዊ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ አለባት ብለው ያምናሉ። "ነፍሰጡር እናት እንቅስቃሴ የማታደርግ ከሆነ ለራሷና ለተሸከመችው ልጇ ደህንነት በጣም አደገኛ ነው" ብለዋል ሙካሳ። በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ ተሳታፊ ከነበሩት ነፍሰጡር እናቶች መካከል አንዷ ሊብሬ ኡዊዜይማና ለቢቢሲ እንደገለጸችው በእርግዝናዋ ጊዜ ፈጽሞ አካላዊ እንቅስቃሴ አድርጋ አታውቅም። "ስላልለመድኩት በጣም ደክሞኝ ነበር፤ ነገር ግን ከሌሎች ነፍሰጡር ሴቶች ጋር አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረጌ በጣም ደስተኛ ነኝ" ብላለች። የሰባት ወር እርጉዝ የሆነችው ሩትም ሌሎች ተመሳሳይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ እንደምትፈልግ ተናግራለች። • የሴቶች የቆዳ ክሬሞች የደቀኑት አደጋ "በጣም ጥሩ ነገር ነው፤ ልምምድ አድርጌያለሁ። ዘና የማለት ስሜት ፈጥሮብኛል፤ በተጨማሪም የጽንሱ እንቅስቃሴም ደስ የሚል ስሜትን ፈጥሮብኛል" ስትል የተሰማትን ገልጻለች። በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ውስጥ የማህጸንና ጽንስ ሃኪም የሆኑት ዶክተር ጂያን ኒይሪንክዋያ ወደ ግል ክሊኒካቸው የሚመጡትን ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። "የእግር ጉዞ፣ ዋናና ሰዎነትን ማፍታታት ምንም አይነት አሉታዊ ተጽዕኖ በእርጉዝ ሴቶች ላይ የለውም" ይላሉ ዶክተር ጂያን። የስፖርታዊ እንቅስቃሴው አስተባባሪዎች በዝግጅታቸው ላይ ለታደሙ እርጉዝ ሴቶች የሚሆኑና ምንም አይነት የጎንዮሽ ውጤት የሌላቸውን የእንቅስቃሴ አይነቶችን መምረጣቸውን ገልጸዋል። ጨምረውም ወንዶች በዚሁ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። | በሩዋንዳ ለነፍሰጡር እናቶች የሚሆን የስፖርት እንቅስቃሴ ተጀመረ ሩዋንዳ ለነፍሰጡር እናቶች የሚጠቅምና በጋራ የሚደረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደጀመረች ተገለጸ። ለመጀመሪያ ጊዜ በአገሪቱ በተካሄደው በዚህ የነፍሰጡር እናቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ ለቢቢሲ እንደተናገሩት መደሰታቸውንና ባለስልጣናትም ስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በዋና ከተማዋ ኪጋሊ ውስጥ በተካሄደው የመጀመሪያው የስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ ከ100 በላይ ነፍሰጡር እናቶች የተሳተፉ ሲሆን አላማውም የነፍሰጡር ሴቶችን አካላዊ ሁኔታን በተመለተ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለመለወጥ መሆኑን አዘጋጆቹ ተናግረዋል። • ፊደል ያልቆጠሩት ኢትዮጵያዊት የቀዶ ህክምና ባለሙያ • በጀርባቸው የሚተኙ ነፍሰጡሮች ህይወት የሌለው ልጅ እየወለዱ ነው አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅትና ስፖርታዊ እንቅስቃሴውን ያስተባበረው መሪ ኔልሰን ሙካሳ እንደገለጹት፤ በርካታ ሩዋንዳውያን አንዲት ሴት ስታረግዝ ከሁሉም አይነት አካላዊ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ አለባት ብለው ያምናሉ። "ነፍሰጡር እናት እንቅስቃሴ የማታደርግ ከሆነ ለራሷና ለተሸከመችው ልጇ ደህንነት በጣም አደገኛ ነው" ብለዋል ሙካሳ። በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ ተሳታፊ ከነበሩት ነፍሰጡር እናቶች መካከል አንዷ ሊብሬ ኡዊዜይማና ለቢቢሲ እንደገለጸችው በእርግዝናዋ ጊዜ ፈጽሞ አካላዊ እንቅስቃሴ አድርጋ አታውቅም። "ስላልለመድኩት በጣም ደክሞኝ ነበር፤ ነገር ግን ከሌሎች ነፍሰጡር ሴቶች ጋር አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረጌ በጣም ደስተኛ ነኝ" ብላለች። የሰባት ወር እርጉዝ የሆነችው ሩትም ሌሎች ተመሳሳይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ እንደምትፈልግ ተናግራለች። • የሴቶች የቆዳ ክሬሞች የደቀኑት አደጋ "በጣም ጥሩ ነገር ነው፤ ልምምድ አድርጌያለሁ። ዘና የማለት ስሜት ፈጥሮብኛል፤ በተጨማሪም የጽንሱ እንቅስቃሴም ደስ የሚል ስሜትን ፈጥሮብኛል" ስትል የተሰማትን ገልጻለች። በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ውስጥ የማህጸንና ጽንስ ሃኪም የሆኑት ዶክተር ጂያን ኒይሪንክዋያ ወደ ግል ክሊኒካቸው የሚመጡትን ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። "የእግር ጉዞ፣ ዋናና ሰዎነትን ማፍታታት ምንም አይነት አሉታዊ ተጽዕኖ በእርጉዝ ሴቶች ላይ የለውም" ይላሉ ዶክተር ጂያን። የስፖርታዊ እንቅስቃሴው አስተባባሪዎች በዝግጅታቸው ላይ ለታደሙ እርጉዝ ሴቶች የሚሆኑና ምንም አይነት የጎንዮሽ ውጤት የሌላቸውን የእንቅስቃሴ አይነቶችን መምረጣቸውን ገልጸዋል። ጨምረውም ወንዶች በዚሁ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-50167137 |
3politics
| በእነ አቶ ጃዋር የሕክምና ጉዳይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝን ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ | የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ሰዎች የሕክምና ጉዳይን በማስመልከት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ በመረጡት የግል ሃኪም እና የግል ሕክምና ጣቢያ እንዲታከሙ መፍቀዱን በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ነበር። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቤቱታን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ተከሳሾች ግን በመረጡት ሃኪም የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ያለባቸው በግል ሆስፒታል ሳይሆን ተከሳሾች ታስረው በሚገኙበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ከእነ አቶ ጃዋር ጠበቆች መካከል አቶ ሚኪያስ ቡልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነን ጨምሮ ሌሎች በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ ተከሳሾች ከ25 ቀናት በላይ በረሃ አድማ ላይ እንደሚገኙ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። ተከሳሾቹ እያደረጉት ባለው የረሃብ አድማ ምክንያት የቅርብ የጤና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው የተከሳሾች የግል ሃኪም ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ከዚህ ቀደም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ተከሳሾች 'ለደህንነታችን እንሰጋለን' በማለት በመንግሥት የሕክምና አገልግሎት መስጫ ስፍራ ለመታከም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የተከሳሽ ጠበቆች እንደሚሉት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ በግል የጤና ተቋም እንዳይታከሙ የተከራከረው የተከሳሾችን ደህንነት በግል ሆስፒታል ማረጋገጥ አይቻልም በሚል ነው። የዛሬው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ "የላንድ ማርክ ሃኪሞች ተደራጅተው ተከሳሾች ባሉበት በመምጣት ሕክምና እንዲሰጣቸው ነው" በማለት ጠበቃው አቶ ሚኪያስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ፍርድ ቤቱ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቤቱታ የሕግ መሠረት የለውም ብሎ ውድቅ ካደረገ በኋላ ተከሳሾች ማረሚያ ቤት ሆነው ይታከሙ መባሉ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነው" በማለት የተከሳሽ ጠበቆች በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ደስተኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ጠቃው እንደሚሉት ደንበኞቻቸው ሆስፒታል ተኝተው መታከም የሚያስፈልጋቸው ከሆነ፣ የሆስቲታል ማሸኖች ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ እንዲሁም በጤና ባለሙያ የቅርብ ክትትል ቢያስፈልጋቸው በማረሚያ ቤት ሆነው መታከማቸው ይህን ስለማያሟላ፤ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ መልሰው እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም እነ አቶ ጃዋር የረሃብ አድማውን እንዲያቆሙ በሃይማኖት አባቶች እና ፖለቲከኞች ቢጠየቁም ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ይታወሳል። ከእነ አቶ ጃዋር ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ጠበቆች እና የቤተሰብ አባላት ምግብ እንዲበሉ ሲጠይቋቸው ቢቆዩም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ መሆኑን ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የረሃብ አድማው ተከሳሾችን የከፋ አደጋ ላይ እንዳይጥል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ አስነብቧል። | በእነ አቶ ጃዋር የሕክምና ጉዳይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝን ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ሰዎች የሕክምና ጉዳይን በማስመልከት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ በመረጡት የግል ሃኪም እና የግል ሕክምና ጣቢያ እንዲታከሙ መፍቀዱን በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ነበር። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቤቱታን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ተከሳሾች ግን በመረጡት ሃኪም የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ያለባቸው በግል ሆስፒታል ሳይሆን ተከሳሾች ታስረው በሚገኙበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ከእነ አቶ ጃዋር ጠበቆች መካከል አቶ ሚኪያስ ቡልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነን ጨምሮ ሌሎች በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ ተከሳሾች ከ25 ቀናት በላይ በረሃ አድማ ላይ እንደሚገኙ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። ተከሳሾቹ እያደረጉት ባለው የረሃብ አድማ ምክንያት የቅርብ የጤና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው የተከሳሾች የግል ሃኪም ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ከዚህ ቀደም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ተከሳሾች 'ለደህንነታችን እንሰጋለን' በማለት በመንግሥት የሕክምና አገልግሎት መስጫ ስፍራ ለመታከም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የተከሳሽ ጠበቆች እንደሚሉት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ በግል የጤና ተቋም እንዳይታከሙ የተከራከረው የተከሳሾችን ደህንነት በግል ሆስፒታል ማረጋገጥ አይቻልም በሚል ነው። የዛሬው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ "የላንድ ማርክ ሃኪሞች ተደራጅተው ተከሳሾች ባሉበት በመምጣት ሕክምና እንዲሰጣቸው ነው" በማለት ጠበቃው አቶ ሚኪያስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ፍርድ ቤቱ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቤቱታ የሕግ መሠረት የለውም ብሎ ውድቅ ካደረገ በኋላ ተከሳሾች ማረሚያ ቤት ሆነው ይታከሙ መባሉ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነው" በማለት የተከሳሽ ጠበቆች በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ደስተኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ጠቃው እንደሚሉት ደንበኞቻቸው ሆስፒታል ተኝተው መታከም የሚያስፈልጋቸው ከሆነ፣ የሆስቲታል ማሸኖች ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ እንዲሁም በጤና ባለሙያ የቅርብ ክትትል ቢያስፈልጋቸው በማረሚያ ቤት ሆነው መታከማቸው ይህን ስለማያሟላ፤ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ መልሰው እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም እነ አቶ ጃዋር የረሃብ አድማውን እንዲያቆሙ በሃይማኖት አባቶች እና ፖለቲከኞች ቢጠየቁም ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ይታወሳል። ከእነ አቶ ጃዋር ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ጠበቆች እና የቤተሰብ አባላት ምግብ እንዲበሉ ሲጠይቋቸው ቢቆዩም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ መሆኑን ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የረሃብ አድማው ተከሳሾችን የከፋ አደጋ ላይ እንዳይጥል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ አስነብቧል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56170346 |
2health
| 'በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ህሙማን መጨመርን ተክትሎ ኦሚክሮን መግባቱን ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ ነው' ጤና ሚኒስቴር | በኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ ኦሚክሮን ገብቶ ከሆነ ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ለቢቢሲ ገለጹ። ባለፈው ሳምንት ከተመረመሩ 53 ሺህ ሰዎች መካከል 8500 በቫይረሱ ሲያዙ፣ 34 ሰዎች ሞተዋል። በተጨማሪም 440 ሰዎች የጽኑ ሕሙማን ክፍል ገብተዋል። ካለፉት ሳምንታት በተለየ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ ኦሚክሮን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ መሆኑን ለማወቅ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝና ውጤቱ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይፋ እንደሚደረግ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል። "እስካሁን የነበረው አካሄድ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ከታኅሳስ 7/2014 ዓ. ም. ወዲህ ባሉት ቀናት በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው" ብለዋል። የዛሬ ሳምንት ገደማ ከሚመረመሩ ሰዎች 3% ብቻ ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ግን ቁጥሩ ወደ 28% እንዳደገ ገልጸዋል። "በሌሎች አገሮች የሚታየው ኦሚክሮን ዝርያ በኢትዮጵያም ምልክቶቹ ታይተዋል። በአስጊ ሁኔታ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። አሁን ናሙና እየመረመርን ነው። በናሙና እስክናረጋግጥ ድረስ ኦሚክሮን መግባቱን በይፋ ለመናገር ያስቸግራል" ሲሉ ዶ/ር ደረጄ አብራርተዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመርምረው 382 ሺህ ቫይረሱ ሲገኝባቸው፤ 6880 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ሕዝቧ ወደ 10 ሚሊዮን ገደማ ዜጎችን ከትባለች። ዶ/ር ደረጄ እንዳሉት፤ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ዜጎች ክትባት እንዲወስዱ ከማበረታታት ባሻገር ከዚህ ቀደም የተከተቡ ሰዎች ማጎልበቻ (ቡስተር) እንዲወስዱ እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ከ100 በላይ አገሮች ውስጥ የተገኘው የኦሚክሮን ዝርያ በፍጥነት በመሰራጨት ላይ ነው። በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ትናንት ከተመረመሩ 13147 ሰዎች መካከል 3793 ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስትር ገልጿል። "በቫይረሱ በድጋሚ የመያዝ ዕድል አለ። ማኅበረሰቡ ወረርሽኙ 'ውሸት ነው' ወይም 'ለፖለቲካ ነው' ሳይል ክትባት ይውሰድ። ስለ ክትባት ሐሰተኛ ወሬ ማሰራጨት ያቁም። ከዚህ ቀደም እንደነበረው ለሕሙማን አልጋ የጠፋበት ደረጃ እንዳንደርስ ተጠንቀቁ" ሲሉ አሳስበዋል። የጤና ሚኒስቴር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከሚወስዳቸው እርምጃዎች መካከል፤ የጤና ባለሙያዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ እንዲሁም ያልተከተቡ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የመንግሥት የነጻ ሕክምና ተጠቃሚ እንይሆኑ ማድረግ መሆኑን ዶ/ር ደረጄ ጠቅሰዋል። "አሁን ላይ ከሚመረመሩት ሰዎች አንድ ሦስተኛው ቫይረሱ እየተገኘባቸው ስለሆነ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ አለበት። ማኅበረሰቡ ማስክ ማድረግ፣ ክትባት መከተብም ይገባዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የጤና ሚኒስቴር የወረርሽኙን ስረጭት ለመከላከል የሚያወጣቸውን ሕጎች በማስተግበር ረገድ ሕግ አስፈጻሚው አካል ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል። በተጨማሪም የጥንቃቄ እርምጃዎችን ማኅበረሰቡ እንዲተገብር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እስከ ቀበሌ የሚወርድ ንቅናቄ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ለገና በዓል ከሚመጡ ዳያስፖራዎች ጋር በተያያዘ የምርመራ ውጤት እና የክትባት ሰርተፍኬት ከማረጋገጥ አንስቶ ክትባቱን አገር ውስጥ እስከማቅረብ ድረስ እንደሚዘጋጁ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል። | 'በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ህሙማን መጨመርን ተክትሎ ኦሚክሮን መግባቱን ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ ነው' ጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ ኦሚክሮን ገብቶ ከሆነ ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ለቢቢሲ ገለጹ። ባለፈው ሳምንት ከተመረመሩ 53 ሺህ ሰዎች መካከል 8500 በቫይረሱ ሲያዙ፣ 34 ሰዎች ሞተዋል። በተጨማሪም 440 ሰዎች የጽኑ ሕሙማን ክፍል ገብተዋል። ካለፉት ሳምንታት በተለየ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ ኦሚክሮን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ መሆኑን ለማወቅ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝና ውጤቱ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይፋ እንደሚደረግ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል። "እስካሁን የነበረው አካሄድ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ከታኅሳስ 7/2014 ዓ. ም. ወዲህ ባሉት ቀናት በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው" ብለዋል። የዛሬ ሳምንት ገደማ ከሚመረመሩ ሰዎች 3% ብቻ ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ግን ቁጥሩ ወደ 28% እንዳደገ ገልጸዋል። "በሌሎች አገሮች የሚታየው ኦሚክሮን ዝርያ በኢትዮጵያም ምልክቶቹ ታይተዋል። በአስጊ ሁኔታ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። አሁን ናሙና እየመረመርን ነው። በናሙና እስክናረጋግጥ ድረስ ኦሚክሮን መግባቱን በይፋ ለመናገር ያስቸግራል" ሲሉ ዶ/ር ደረጄ አብራርተዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመርምረው 382 ሺህ ቫይረሱ ሲገኝባቸው፤ 6880 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ሕዝቧ ወደ 10 ሚሊዮን ገደማ ዜጎችን ከትባለች። ዶ/ር ደረጄ እንዳሉት፤ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ዜጎች ክትባት እንዲወስዱ ከማበረታታት ባሻገር ከዚህ ቀደም የተከተቡ ሰዎች ማጎልበቻ (ቡስተር) እንዲወስዱ እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ከ100 በላይ አገሮች ውስጥ የተገኘው የኦሚክሮን ዝርያ በፍጥነት በመሰራጨት ላይ ነው። በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ትናንት ከተመረመሩ 13147 ሰዎች መካከል 3793 ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስትር ገልጿል። "በቫይረሱ በድጋሚ የመያዝ ዕድል አለ። ማኅበረሰቡ ወረርሽኙ 'ውሸት ነው' ወይም 'ለፖለቲካ ነው' ሳይል ክትባት ይውሰድ። ስለ ክትባት ሐሰተኛ ወሬ ማሰራጨት ያቁም። ከዚህ ቀደም እንደነበረው ለሕሙማን አልጋ የጠፋበት ደረጃ እንዳንደርስ ተጠንቀቁ" ሲሉ አሳስበዋል። የጤና ሚኒስቴር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከሚወስዳቸው እርምጃዎች መካከል፤ የጤና ባለሙያዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ እንዲሁም ያልተከተቡ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የመንግሥት የነጻ ሕክምና ተጠቃሚ እንይሆኑ ማድረግ መሆኑን ዶ/ር ደረጄ ጠቅሰዋል። "አሁን ላይ ከሚመረመሩት ሰዎች አንድ ሦስተኛው ቫይረሱ እየተገኘባቸው ስለሆነ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ አለበት። ማኅበረሰቡ ማስክ ማድረግ፣ ክትባት መከተብም ይገባዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የጤና ሚኒስቴር የወረርሽኙን ስረጭት ለመከላከል የሚያወጣቸውን ሕጎች በማስተግበር ረገድ ሕግ አስፈጻሚው አካል ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል። በተጨማሪም የጥንቃቄ እርምጃዎችን ማኅበረሰቡ እንዲተገብር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እስከ ቀበሌ የሚወርድ ንቅናቄ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ለገና በዓል ከሚመጡ ዳያስፖራዎች ጋር በተያያዘ የምርመራ ውጤት እና የክትባት ሰርተፍኬት ከማረጋገጥ አንስቶ ክትባቱን አገር ውስጥ እስከማቅረብ ድረስ እንደሚዘጋጁ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59778547 |
5sports
| የማራዶና ሬሳን የማቃጠሉ ሥነ ሥርዓት እንዲዘገይ ፍርድ ቤት ወሰነ | የእግር ኳሱ ንጉሥ አርጀንቲናዊው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አባታችን ነው የሚሉ ልጆች የማራዶና ሬሳ በሰላም እንዳያርፍ እያደረጉት ነው። ትናንት የአርጀንቲና አንድ ፍርድ ቤት የማራዶና ሬሳ ለዘረ መል (DNA)ምርመራ ስለሚፈለግ ‹ባለበት ይጠበቅ› የሚል ውሳኔን አሳልፏል፡፡ አሁን ሬሳው ለጊዜው ቦነስ አይረስ ውስጥ በሚገኝ በአንድ የግል መካነ መቃብር ላይ ያረፈ ሲሆን የዳኛው ውሳኔ ሬሳውን ወደ አመድነት የመቀየር ሥነ ሥርዓቱን ያዘገየዋል ተብሏል፡፡ ማራዶና ባለፈው ወር በተወለደ በ60 ዓመቱ ከልብ ጋር በተያያዘ በሽታ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡ ዳኛው ሬሳው ‹ በመልካም ሁኔታ እንዲቆይ ይደረግ› የሚለውን ውሳኔ ሊያስተላልፉ የቻሉት አንዲት ሴት ማራዶና አባቴ ሳይሆን አይቀርም በሚል ለፍርድ ቤቱ ማመልከቷን ተከትሎ ነው፡፡ ማራዶና አባቷ እንደሆነ ለማረጋገጥ የግድ የዘረመል ናሙና ስለሚያስፈልግ ነው ሬሳውን የማስወገዱ ሥነ ሥርዓት እንዲዘገይ የሆነው፡፡ ማራዶና በጋብቻ ያፈራቸው ሁለት ሴት ልጆች ብቻ ነው ያሉት፡፡ ከነዚህ ሴት ልጆች እናት ጋር ከተፋታ በኋላ ግን በትንሹ 6 ልጆችን ‹ልጆቼ ናቸው› ብሎ ተቀብሏቸዋል፡፡ ሆኖም እርሱ ከጋብቻ ውጪ የወለዳቸው ልጆች ቁጥር ከዚህ በብዙ እጥፍ ሊኖሩ እንደሚችሉ የአኗኗር ዘይቤውን የሚያውቁ ይገምታሉ፡፡ የሱን ሞት ተከትሎ ልጆቹ ነን ያሉ በርካታዎች ሲሆኑ አሁን ለጊዜው ለፍርድ ቤት ያመለከተችው የ25 ዓመቷ ማጋሊ ጊል ናት፡፡ ማጋሊ ጊል ማራዶና በሕይወት እያለ ልጄ ናት ብሎ እውቅና ሰጥቷት አያውቅም፡፡ ማጋሊ በጉዲፈቻ ያደገች ሲሆን እናቷን ከ2 ዓመት በፊት ባገኘቻት ጊዜ አባቴ ማን ነው ብላ ስትጠይቃት፣ አርማንዶ ማራዶና ሊሆን ይችላል እንዳለቻት አስታውሳለች፡፡ ማጋሊ ጊል በኢንስታግራም በለቀቀችው ቪዲዮ ሰዎች ገንዘብ በመሻት ያደረገችው አድርገው እንደሚያስቡ ጠቅሳ ነገር ግን አባቷን የማወቅ ሂደት ዓለም አቀፍ መብት ነው ብላለች፡፡ ማራዶና በኖቬምበር 25 መሞቱን ተከትሎ ቦነስ አይረስ በአንድ መካነ መቃብር ውስጥ ነው የተቀበረው፡፡ ፍርድ ቤት የማራዶና ሬሳ ወደ አመድነት የመቀየሩ ተግባር እንዲዘገይ መጀመርያ የወሰነው በአሟሟቱ ላይ የሬሳ ምርመራ እንዲደረግ በማስፈለጉ ነበር፡፡ ማራዶና በሕክምና ስህተት ነው እንጂ አይሞትም ነበር ብለው የሚገምቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በግል ሐኪሙ ላይ ፖሊስ መርመራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ የትናንቱ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግን የማራዶና ልጅ ነን የሚሉትን ለማስተናገድ በሚል የተራዘመ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ሮይተርስ የዜና ወኪል የማራዶናን ጠበቃ አናግሮ ባገኘው መረጃ መሰረት የማራዶና ዘረ መል ቅንጣት ማራዶና ከመሞቱ በፊት የተወሰደና የተቀመጠ ስለሆነ ሬሳውን የማቃጠሉ ሥነ ሥርዓት ማዘግየት አያስፈልግም ብሏል፡፡ ማራዶና የፋይናንስ አያያዙ የተዝረከረከ ስለነበረ በህጋዊ ልጆቹና ከጋብቻ ውጭ የተወለዱት ልጆቹ እንዲሁም የማራዶና ልጆች ነን እያሉ በመጡ ልጆች መሀል ዘለግ ያለ የፍርድ ሒደት ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ | የማራዶና ሬሳን የማቃጠሉ ሥነ ሥርዓት እንዲዘገይ ፍርድ ቤት ወሰነ የእግር ኳሱ ንጉሥ አርጀንቲናዊው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አባታችን ነው የሚሉ ልጆች የማራዶና ሬሳ በሰላም እንዳያርፍ እያደረጉት ነው። ትናንት የአርጀንቲና አንድ ፍርድ ቤት የማራዶና ሬሳ ለዘረ መል (DNA)ምርመራ ስለሚፈለግ ‹ባለበት ይጠበቅ› የሚል ውሳኔን አሳልፏል፡፡ አሁን ሬሳው ለጊዜው ቦነስ አይረስ ውስጥ በሚገኝ በአንድ የግል መካነ መቃብር ላይ ያረፈ ሲሆን የዳኛው ውሳኔ ሬሳውን ወደ አመድነት የመቀየር ሥነ ሥርዓቱን ያዘገየዋል ተብሏል፡፡ ማራዶና ባለፈው ወር በተወለደ በ60 ዓመቱ ከልብ ጋር በተያያዘ በሽታ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡ ዳኛው ሬሳው ‹ በመልካም ሁኔታ እንዲቆይ ይደረግ› የሚለውን ውሳኔ ሊያስተላልፉ የቻሉት አንዲት ሴት ማራዶና አባቴ ሳይሆን አይቀርም በሚል ለፍርድ ቤቱ ማመልከቷን ተከትሎ ነው፡፡ ማራዶና አባቷ እንደሆነ ለማረጋገጥ የግድ የዘረመል ናሙና ስለሚያስፈልግ ነው ሬሳውን የማስወገዱ ሥነ ሥርዓት እንዲዘገይ የሆነው፡፡ ማራዶና በጋብቻ ያፈራቸው ሁለት ሴት ልጆች ብቻ ነው ያሉት፡፡ ከነዚህ ሴት ልጆች እናት ጋር ከተፋታ በኋላ ግን በትንሹ 6 ልጆችን ‹ልጆቼ ናቸው› ብሎ ተቀብሏቸዋል፡፡ ሆኖም እርሱ ከጋብቻ ውጪ የወለዳቸው ልጆች ቁጥር ከዚህ በብዙ እጥፍ ሊኖሩ እንደሚችሉ የአኗኗር ዘይቤውን የሚያውቁ ይገምታሉ፡፡ የሱን ሞት ተከትሎ ልጆቹ ነን ያሉ በርካታዎች ሲሆኑ አሁን ለጊዜው ለፍርድ ቤት ያመለከተችው የ25 ዓመቷ ማጋሊ ጊል ናት፡፡ ማጋሊ ጊል ማራዶና በሕይወት እያለ ልጄ ናት ብሎ እውቅና ሰጥቷት አያውቅም፡፡ ማጋሊ በጉዲፈቻ ያደገች ሲሆን እናቷን ከ2 ዓመት በፊት ባገኘቻት ጊዜ አባቴ ማን ነው ብላ ስትጠይቃት፣ አርማንዶ ማራዶና ሊሆን ይችላል እንዳለቻት አስታውሳለች፡፡ ማጋሊ ጊል በኢንስታግራም በለቀቀችው ቪዲዮ ሰዎች ገንዘብ በመሻት ያደረገችው አድርገው እንደሚያስቡ ጠቅሳ ነገር ግን አባቷን የማወቅ ሂደት ዓለም አቀፍ መብት ነው ብላለች፡፡ ማራዶና በኖቬምበር 25 መሞቱን ተከትሎ ቦነስ አይረስ በአንድ መካነ መቃብር ውስጥ ነው የተቀበረው፡፡ ፍርድ ቤት የማራዶና ሬሳ ወደ አመድነት የመቀየሩ ተግባር እንዲዘገይ መጀመርያ የወሰነው በአሟሟቱ ላይ የሬሳ ምርመራ እንዲደረግ በማስፈለጉ ነበር፡፡ ማራዶና በሕክምና ስህተት ነው እንጂ አይሞትም ነበር ብለው የሚገምቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በግል ሐኪሙ ላይ ፖሊስ መርመራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ የትናንቱ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግን የማራዶና ልጅ ነን የሚሉትን ለማስተናገድ በሚል የተራዘመ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ሮይተርስ የዜና ወኪል የማራዶናን ጠበቃ አናግሮ ባገኘው መረጃ መሰረት የማራዶና ዘረ መል ቅንጣት ማራዶና ከመሞቱ በፊት የተወሰደና የተቀመጠ ስለሆነ ሬሳውን የማቃጠሉ ሥነ ሥርዓት ማዘግየት አያስፈልግም ብሏል፡፡ ማራዶና የፋይናንስ አያያዙ የተዝረከረከ ስለነበረ በህጋዊ ልጆቹና ከጋብቻ ውጭ የተወለዱት ልጆቹ እንዲሁም የማራዶና ልጆች ነን እያሉ በመጡ ልጆች መሀል ዘለግ ያለ የፍርድ ሒደት ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-55359562 |
5sports
| "19 ዓመታትን በእስር፣ አሁንም እየቆጠርን ነው" የፔን ተሸላሚው አማኑኤል ወንድም | "አስራ ዘጠኝ አመታት በእስር ፣ አሁንም እየቆጠርን ነው። በጣም ከፍተኛ ህመም አለው" ይህንን የተናገረው በቅርቡ አለም አቀፉን የፔን ሽልማት የተጎናፀፈውና በእስር ላይ የሚገኘው ኤርትራዊው ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ወንድም ዳንኤል ነው። በሰላ ትችቱ የሚታወቀውን ኤርትራዊ ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ለበርካቶች ደፋር ፀሃፊ ነው። ለዚህም ነው ፔን በሚፅፉት ወይም በሚናገሩት ነገር የሚደርስባቸውን ጫናና ጣልቃ ገብነት ተቋቁመው የበለጠ ወኔ ላሳዩ ፀሃፊዎች እውቅናን የሚሰጥበትን "አለም አቀፉ ደፋር ፀሃፊ" በሚል ስያሜም ሽልማቱን ያቀናጀው። ወንድሙን ለሁለት አስርት አመታት ያህል ላላየው ዳንኤል ምንም እንኳን በደንብ ሽልማቱ ይገባዋል ብሎ ቢያምንም ለሱም ቢሆን ለቤተሰቡ ከፍተኛ አድናቆትን እንደፈጠረባቸው አልደበቀም። ከሽልማቱ ጀርባም አማኑኤል አብሯቸው አለመሆንንም ለቤተሰቡ ማስታወስ የየቀኑ መራር እውነታ ነው። "በጣም በጣም ከፍተኛ ህመም አለው" በማለትም መሃል ላይ ኃዘኑን በሚያሳብቅ ድምፅ የሚተነፍሰው ዳንኤል "በነዚህ አመታት ውስጥ ሊያገባ ይችል ነበር፤ ልጆች ያፈራ ነበር። ትምህርቱን መቀጠል ይችል ነበር። ለአገሪቷም በርካታ ትልልቅ ነገሮችን ማድረግ ይችል ነበር። ከዚህ በላይ ህመም የሆነው ደግሞ መቼ እንደሚፈታ አለማወቃችን ነው። በህይወት ይኑርም፣ አይኑርም አናውቅም"ብሏል ኃዘን በተሞላ ድምፁ አማኑኤል በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት በኤርትራ የጋዜጠኝነት ታሪክ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የዘመን ጋዜጣም ዋና አዘጋጅ ነበር። በሰላ ትችቱም የሚታወቀው ጋዜጠኛ በወቅቱም በኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረውን ቅራኔም ይፋ በማውጣት ይፅፍ ነበር። በተለይም ከመቶ ሺዎች ህይወት በላይ የቀጠፈውን የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን አጥብቀው ከሚቃወሙት መካከልም ነው። ይህንኑም በፅሁፉ ላይ ያንፀባርቅ ነበር። ለፔን ሽልማትም ያበቃው ስለ ጦርነት አስከፊነት የሚያወሳበት ግጥሙ ነው። በዚህ ግጥሙም ምን ያህል ጦርነቱ የሁለት ወንድማማቾችና ቤተሰቦች ጦርነት እንደሆነም በተመረጡ ቃላቶች ያስታውሳል። በርካታ ቤተሰቦችን ልጅ አልባ፣ ወንድም አልባ፣ ባለቤት አልባ አድርጓል፤ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን ቀጥፏል። የጦርነቱን አስከፊነትና አስቀያሚነት አማኑኤል ሲያወሳም በሰላማዊ መንገድ ተደራድረው መፍታት የሚችሉትንና ፣ ጦርነት የመረጡትን ሁለቱንም መንግሥታት ይተቻል። ይህ የሰላ ትችቱ ግን ዋጋ ያስከፈለው ሲሆን ኤርትራም የግል ጋዜጦችን ዘጋች እንዲሁም የሚቀርቡበትን ትችት ዝም ለማሰኘት በጀመረው ዘመቻም የኤርትራ መንግሥት ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችንና ተማሪዎችን ለእስር ዳርጓል። አማኑኤልን ጨምሮ በርካታ የግል ጋዜጣ አዘጋጆችም በጎሮጎሳውያኑ 2001 ለእስር ተዳረጉ። አማኑኤልም ሆነ ሌሎች ፀሃፊዎች ያሉበት ሁኔታ የማይታወቅ ሲሆን እስካሁንም ያናገራቸው አካል የለም። ቤተሰቦች ድምፁን ሰምተው አያውቁም፤ ያለበትንም አያውቁም። "የኤርትራ መንግሥት አምባገነን ነው። መንግሥቱ ከሌሎች ለየት ያለ ነው። እንደ መንግሥት ደንብና አወቃቀር የለውም። ኤርትራ የምትመራው በአንድ ሰው ነው።በአገሪቱም ያለው በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያለ አንድ ሚዲያ ነው " የሚለው ዳንኡል ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናትም ቢሆኑ አማኑኤልን ሆነ ሌሎች እስረኞች ያሉበትን ቦታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተው ስለማያውቁም "ቤተሰቦቼ፣ ዘመዶቼ የት ነው የታሰሩት ተብሎ መጠየቅ አይቻልም፤ የሚጠየቅ አካልም የለም፤ ፖለቲከኛም ሆኑ ጋዜጠኛ" በማለት ዳንኤል ያስረዳል። አማኑኤል ሁለገብ ነው፤ ከጋዜጠኝነትም በላይ ገጣሚ፣ የሙዚቃ ግጥም ፀሃፊ፣ ሂሰኛና የሌሎችም ድርብርብ ባለሙያ ነው። ለሁለት አስርት አመታት የሚጠጋ በእስር ላይ የሚገኘው አማኑኤልን ጨምሮ ጥቂት ፀሃፊዎች በህይወት እንዳሉና በእስርም ላይ እንደሚገኙ ይታመናል።ታሳሪዎቹ ምንም ክስ እንዳልቀረበባቸውና መንግስትም መረጃ እንደማይሰጥ የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች ይገልጻሉ። ከዚህም በተጨማሪ የህክምና አቅርቦት ማጣት እንዲሁም ሌሎች እንግልቶችና ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሆነ ይታመናል። ገጣሚ አማኑኤል ለዚህ ሽልማት ያጨው ጃማይካዊ- ኢንግሊዛዊ ገጣሚ ሊንቶን ክዌሲ ጆንሰን "አንድ ዜጋ ፍጹም በማይታወቅ እስር ቤት ለ20 አመታት ማጎር የአምባገነን ስርአት ማሳያ ነው። በአፍሪካዊ ዲያስፖራነቴ ትብብርና ወገንተኝነቴን ለማሳየት ደግሞ ይሄን ሽልማት ለገጣሚ አማኑኤል አስራት እንዲሸለም መርጫለሁ" ማለቱን ፔን ኤርትራ ገልጿል። በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፈው የአማኑኤል ወንድም ከጋዜጠኛው ስራዎች አንዱ የሆነውን ግጥምም አቅርቧል። አማኑኤል አስራት በ2016 ከሌሎች ግብጻዊና ቱርካዊ ጸሃፍያን በመሆን በፔን ኦክስፋም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ሽልማት ተሰጥቶታል። | "19 ዓመታትን በእስር፣ አሁንም እየቆጠርን ነው" የፔን ተሸላሚው አማኑኤል ወንድም "አስራ ዘጠኝ አመታት በእስር ፣ አሁንም እየቆጠርን ነው። በጣም ከፍተኛ ህመም አለው" ይህንን የተናገረው በቅርቡ አለም አቀፉን የፔን ሽልማት የተጎናፀፈውና በእስር ላይ የሚገኘው ኤርትራዊው ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ወንድም ዳንኤል ነው። በሰላ ትችቱ የሚታወቀውን ኤርትራዊ ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ለበርካቶች ደፋር ፀሃፊ ነው። ለዚህም ነው ፔን በሚፅፉት ወይም በሚናገሩት ነገር የሚደርስባቸውን ጫናና ጣልቃ ገብነት ተቋቁመው የበለጠ ወኔ ላሳዩ ፀሃፊዎች እውቅናን የሚሰጥበትን "አለም አቀፉ ደፋር ፀሃፊ" በሚል ስያሜም ሽልማቱን ያቀናጀው። ወንድሙን ለሁለት አስርት አመታት ያህል ላላየው ዳንኤል ምንም እንኳን በደንብ ሽልማቱ ይገባዋል ብሎ ቢያምንም ለሱም ቢሆን ለቤተሰቡ ከፍተኛ አድናቆትን እንደፈጠረባቸው አልደበቀም። ከሽልማቱ ጀርባም አማኑኤል አብሯቸው አለመሆንንም ለቤተሰቡ ማስታወስ የየቀኑ መራር እውነታ ነው። "በጣም በጣም ከፍተኛ ህመም አለው" በማለትም መሃል ላይ ኃዘኑን በሚያሳብቅ ድምፅ የሚተነፍሰው ዳንኤል "በነዚህ አመታት ውስጥ ሊያገባ ይችል ነበር፤ ልጆች ያፈራ ነበር። ትምህርቱን መቀጠል ይችል ነበር። ለአገሪቷም በርካታ ትልልቅ ነገሮችን ማድረግ ይችል ነበር። ከዚህ በላይ ህመም የሆነው ደግሞ መቼ እንደሚፈታ አለማወቃችን ነው። በህይወት ይኑርም፣ አይኑርም አናውቅም"ብሏል ኃዘን በተሞላ ድምፁ አማኑኤል በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት በኤርትራ የጋዜጠኝነት ታሪክ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የዘመን ጋዜጣም ዋና አዘጋጅ ነበር። በሰላ ትችቱም የሚታወቀው ጋዜጠኛ በወቅቱም በኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረውን ቅራኔም ይፋ በማውጣት ይፅፍ ነበር። በተለይም ከመቶ ሺዎች ህይወት በላይ የቀጠፈውን የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን አጥብቀው ከሚቃወሙት መካከልም ነው። ይህንኑም በፅሁፉ ላይ ያንፀባርቅ ነበር። ለፔን ሽልማትም ያበቃው ስለ ጦርነት አስከፊነት የሚያወሳበት ግጥሙ ነው። በዚህ ግጥሙም ምን ያህል ጦርነቱ የሁለት ወንድማማቾችና ቤተሰቦች ጦርነት እንደሆነም በተመረጡ ቃላቶች ያስታውሳል። በርካታ ቤተሰቦችን ልጅ አልባ፣ ወንድም አልባ፣ ባለቤት አልባ አድርጓል፤ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን ቀጥፏል። የጦርነቱን አስከፊነትና አስቀያሚነት አማኑኤል ሲያወሳም በሰላማዊ መንገድ ተደራድረው መፍታት የሚችሉትንና ፣ ጦርነት የመረጡትን ሁለቱንም መንግሥታት ይተቻል። ይህ የሰላ ትችቱ ግን ዋጋ ያስከፈለው ሲሆን ኤርትራም የግል ጋዜጦችን ዘጋች እንዲሁም የሚቀርቡበትን ትችት ዝም ለማሰኘት በጀመረው ዘመቻም የኤርትራ መንግሥት ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችንና ተማሪዎችን ለእስር ዳርጓል። አማኑኤልን ጨምሮ በርካታ የግል ጋዜጣ አዘጋጆችም በጎሮጎሳውያኑ 2001 ለእስር ተዳረጉ። አማኑኤልም ሆነ ሌሎች ፀሃፊዎች ያሉበት ሁኔታ የማይታወቅ ሲሆን እስካሁንም ያናገራቸው አካል የለም። ቤተሰቦች ድምፁን ሰምተው አያውቁም፤ ያለበትንም አያውቁም። "የኤርትራ መንግሥት አምባገነን ነው። መንግሥቱ ከሌሎች ለየት ያለ ነው። እንደ መንግሥት ደንብና አወቃቀር የለውም። ኤርትራ የምትመራው በአንድ ሰው ነው።በአገሪቱም ያለው በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያለ አንድ ሚዲያ ነው " የሚለው ዳንኡል ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናትም ቢሆኑ አማኑኤልን ሆነ ሌሎች እስረኞች ያሉበትን ቦታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተው ስለማያውቁም "ቤተሰቦቼ፣ ዘመዶቼ የት ነው የታሰሩት ተብሎ መጠየቅ አይቻልም፤ የሚጠየቅ አካልም የለም፤ ፖለቲከኛም ሆኑ ጋዜጠኛ" በማለት ዳንኤል ያስረዳል። አማኑኤል ሁለገብ ነው፤ ከጋዜጠኝነትም በላይ ገጣሚ፣ የሙዚቃ ግጥም ፀሃፊ፣ ሂሰኛና የሌሎችም ድርብርብ ባለሙያ ነው። ለሁለት አስርት አመታት የሚጠጋ በእስር ላይ የሚገኘው አማኑኤልን ጨምሮ ጥቂት ፀሃፊዎች በህይወት እንዳሉና በእስርም ላይ እንደሚገኙ ይታመናል።ታሳሪዎቹ ምንም ክስ እንዳልቀረበባቸውና መንግስትም መረጃ እንደማይሰጥ የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች ይገልጻሉ። ከዚህም በተጨማሪ የህክምና አቅርቦት ማጣት እንዲሁም ሌሎች እንግልቶችና ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሆነ ይታመናል። ገጣሚ አማኑኤል ለዚህ ሽልማት ያጨው ጃማይካዊ- ኢንግሊዛዊ ገጣሚ ሊንቶን ክዌሲ ጆንሰን "አንድ ዜጋ ፍጹም በማይታወቅ እስር ቤት ለ20 አመታት ማጎር የአምባገነን ስርአት ማሳያ ነው። በአፍሪካዊ ዲያስፖራነቴ ትብብርና ወገንተኝነቴን ለማሳየት ደግሞ ይሄን ሽልማት ለገጣሚ አማኑኤል አስራት እንዲሸለም መርጫለሁ" ማለቱን ፔን ኤርትራ ገልጿል። በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፈው የአማኑኤል ወንድም ከጋዜጠኛው ስራዎች አንዱ የሆነውን ግጥምም አቅርቧል። አማኑኤል አስራት በ2016 ከሌሎች ግብጻዊና ቱርካዊ ጸሃፍያን በመሆን በፔን ኦክስፋም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ሽልማት ተሰጥቶታል። | https://www.bbc.com/amharic/54544011 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ የኮቪድ ክትባትን የሚቃወሙ ሰልፈኞች ከፖሊስ ተጋጩ | በአሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ግዛት፣ ሎስ አንጀለስ ከተማ የኮቪድ ክትባት ውሸት ነው የሚሉ ቀኝ አክራሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡ ከፖሊስ ጋር የተጋጩት ክትባት እየተሰጠበት የሚገኘውን የዶገር ስታዲየም በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሰልፈኞቹ ይህን የክትባት መስጠቱ ሂደት ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል እንዲስተጓጎል አድርገዋል፡፡ ቁጥራቸው 50 የሚሆኑ የጸረ ክትባት አቀንቃኞች ስታዲየሙን ለማዘጋት የቻሉት መግቢያውን በመዝጋት ጭምር ነው፡፡ ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ላይ የነበሩ በርካታ መኪኖች በነዚህ የክትባት ተቃዋሚዎች ምክንያት አገልግሎት ሳያገኙ ተመልሰዋል፡፡ ሰልፈኞቹ የኮቪድ ክትባት የተጭበረበረ ስለመሆኑ የሚያወሱ መፈክሮችን የያዙ ሲሆን ኅብረተሰቡን ‹አትከተቡ፤ እናንተ የቤተ ሙከራ አይጥ አይደላችሁም› እያሉ ሲቀሰቅሱ ታይተዋል፡፡ የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ቀኝ አክራሪ ሰልፈኞቹ ለክትባት የተሰለፉ ሰዎችን ‹ ነፍሳችሁን አድኑ፣ የውሸት ሳይንስ መጫወቻ አትሁኑ እያሉ እየጮኹ ሲቀሰቅሱ ነበር፡፡ የክትባት መስጫውን ሰልፈኞቹ የተቆጣጠሩትም በአገሬው አቆጣጠር ከቀኑ 8 ሰዓመት ጀምሮ ነው፡፡ የሎስ አንጀለስ ፖሊስ በትዊተር እንዳስታወቀው ስታዲየሙ አልተዘጋም፤ ክትባቱ ቀጥሏል ብሏል፡፡ የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሰን በስታዲየሙ እየተሰጠ የነበረው የክትባት ዘመቻ በሰልፈኞች ለጊዜው ቢስተጓጎልም ወደ ሥራ ተመልሷል ብለዋል፡፡ ጀርማን ጃኩዝ የተባለና ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ሲጠባበቅ የነበረ ዜጋ ለሎስ አንጀለስ ታይምስ ቁጣውን የገለጸ ሲሆን ‹‹ይህ የቀኝ አክራሪዎች ድርጊት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው› ብሏል፡፡ ‹‹ለሳምንታት ክትባት ለማግኘት ስጠባበቅ ነበር፡፡ እኔ የጥርስ ሐኪም ነኝ፡፡ በሽተኞቼን ሳክም በጣም ተጠግቻቸው ነው፡፡ ከኮቪድ መጠበቅ እሻለሁ፡፡ ክትባቱ ያስፈልገኛል፡፡ ተህዋሲውን ለመከላከል ብቸኛው መንገድ ክትባት ነው›› ሲል ሐሳቡን አጋርቷል፡፡ በአመዛኙ የትራምፕ ደጋፊ የነበሩ እንደሆኑ የሚገመቱና ቀኝ አክራሪ የሆኑት ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች አንዱ ‹‹ሲኤንኤን እያታለላችሁ ነው›› ይላል፡፡ ሌሎች መፈክሮች፣ ‹‹ጭምብላችሁን ቀዳዳችሁ ጣሉት››፣ ‹‹የሰው አይጥ አትሁኑ›› የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ከአሜሪካ ግዛቶች ካሊፎርኒያ በተህዋሲው ክፉኛ ከተጠቁት ተርታ ትመደባለች፡፡ 40ሺ የግዛቲቱ ነዋሪዎች በኮቪድ ሞተዋል፡፡ 3 ሚሊዮኑ ተህዋሲው አለባቸው፡፡ በመላው አሜሪካ በኮቪድ ተህዋሲ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች በሚቀጥለው ወር ግማሽ ሚሊዮን እንደሚያልፍ ይጠበቃል፡፡ | ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ የኮቪድ ክትባትን የሚቃወሙ ሰልፈኞች ከፖሊስ ተጋጩ በአሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ግዛት፣ ሎስ አንጀለስ ከተማ የኮቪድ ክትባት ውሸት ነው የሚሉ ቀኝ አክራሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡ ከፖሊስ ጋር የተጋጩት ክትባት እየተሰጠበት የሚገኘውን የዶገር ስታዲየም በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሰልፈኞቹ ይህን የክትባት መስጠቱ ሂደት ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል እንዲስተጓጎል አድርገዋል፡፡ ቁጥራቸው 50 የሚሆኑ የጸረ ክትባት አቀንቃኞች ስታዲየሙን ለማዘጋት የቻሉት መግቢያውን በመዝጋት ጭምር ነው፡፡ ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ላይ የነበሩ በርካታ መኪኖች በነዚህ የክትባት ተቃዋሚዎች ምክንያት አገልግሎት ሳያገኙ ተመልሰዋል፡፡ ሰልፈኞቹ የኮቪድ ክትባት የተጭበረበረ ስለመሆኑ የሚያወሱ መፈክሮችን የያዙ ሲሆን ኅብረተሰቡን ‹አትከተቡ፤ እናንተ የቤተ ሙከራ አይጥ አይደላችሁም› እያሉ ሲቀሰቅሱ ታይተዋል፡፡ የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ቀኝ አክራሪ ሰልፈኞቹ ለክትባት የተሰለፉ ሰዎችን ‹ ነፍሳችሁን አድኑ፣ የውሸት ሳይንስ መጫወቻ አትሁኑ እያሉ እየጮኹ ሲቀሰቅሱ ነበር፡፡ የክትባት መስጫውን ሰልፈኞቹ የተቆጣጠሩትም በአገሬው አቆጣጠር ከቀኑ 8 ሰዓመት ጀምሮ ነው፡፡ የሎስ አንጀለስ ፖሊስ በትዊተር እንዳስታወቀው ስታዲየሙ አልተዘጋም፤ ክትባቱ ቀጥሏል ብሏል፡፡ የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሰን በስታዲየሙ እየተሰጠ የነበረው የክትባት ዘመቻ በሰልፈኞች ለጊዜው ቢስተጓጎልም ወደ ሥራ ተመልሷል ብለዋል፡፡ ጀርማን ጃኩዝ የተባለና ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ሲጠባበቅ የነበረ ዜጋ ለሎስ አንጀለስ ታይምስ ቁጣውን የገለጸ ሲሆን ‹‹ይህ የቀኝ አክራሪዎች ድርጊት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው› ብሏል፡፡ ‹‹ለሳምንታት ክትባት ለማግኘት ስጠባበቅ ነበር፡፡ እኔ የጥርስ ሐኪም ነኝ፡፡ በሽተኞቼን ሳክም በጣም ተጠግቻቸው ነው፡፡ ከኮቪድ መጠበቅ እሻለሁ፡፡ ክትባቱ ያስፈልገኛል፡፡ ተህዋሲውን ለመከላከል ብቸኛው መንገድ ክትባት ነው›› ሲል ሐሳቡን አጋርቷል፡፡ በአመዛኙ የትራምፕ ደጋፊ የነበሩ እንደሆኑ የሚገመቱና ቀኝ አክራሪ የሆኑት ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች አንዱ ‹‹ሲኤንኤን እያታለላችሁ ነው›› ይላል፡፡ ሌሎች መፈክሮች፣ ‹‹ጭምብላችሁን ቀዳዳችሁ ጣሉት››፣ ‹‹የሰው አይጥ አትሁኑ›› የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ከአሜሪካ ግዛቶች ካሊፎርኒያ በተህዋሲው ክፉኛ ከተጠቁት ተርታ ትመደባለች፡፡ 40ሺ የግዛቲቱ ነዋሪዎች በኮቪድ ሞተዋል፡፡ 3 ሚሊዮኑ ተህዋሲው አለባቸው፡፡ በመላው አሜሪካ በኮቪድ ተህዋሲ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች በሚቀጥለው ወር ግማሽ ሚሊዮን እንደሚያልፍ ይጠበቃል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-55876977 |
2health
| ሰሜን ኮሪያ፡ ታመዋል ሲባሉ የነበሩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ድንገት ተከሰቱ | የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ታመዋል ከሚለው ጀምሮ፣ አብቅቶላቸዋል፣ ሞተዋል እየተባለም ብዙ ይወራባቸው ነበር፡፡ ድንገት በፓርቲ ስብሰባ ተከስተው መመርያ ሰጥተዋል፣ ትናንት፡፡ ሰሜን ኮሪያ ትልቅ አደጋ ከፊቷ ተደቅኗል ያሉት ኪም ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲሆን አዘዋል፡፡ ትልቅ አደጋ እየመጣ ነው ያሉት ኪም አደጋዎቹ በዋናነት ሁለት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡ አንዱ ኮሮና ቫይረስ ሲሆን ሌላው ደግሞ አውሎ ንፋስ ነው፡፡ ኪም ከሰሞኑ ጠፍተው ስለነበር የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ስለነበረ ምናልባት ሞተው ይሆን? ሲባል ነበር፡፡ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን አንድም ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘብኝም ስትል ታስተባብላለች፡፡ አይበለውና ወረርሽኙ ወደዚያች አገር ቢገባ ባላት ደካማ የጤና መሰረተ ልማት ከፍተኛ አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡ ይህ በእንዲህ ሳለ ባቪ የሚሰኝ አደገኛ አውሎ ነፋስ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሰሜን ኮሪያን ሊመታት ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ የፖሊትቢሮ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ኪም በስብሰባው ላይ ንግግር እያደረጉ ሲያጨሱ ይታዩ ነበር፡፡ በዚህ ንግግራቸው ኮቪድን በተመለከተ አንዳንድ ችግሮች ተስተውለዋል ብለዋል፡፡ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግን የሚያውቅ አልተገኘም፡፡ ፒዮንግያንግ ለረዥም ጊዜ ወረርሽኙ እኔ ጋ ድርሽ አላለም ስትል እያስተባበለች ቆይታለች፡፡ ነገር ግን ይህን የሰሜን ኮሪያን አስተያየት ብዙዎች በጥርጣሬ ነው የሚመለከቱት፡፡ አንድም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው የለም ስትል የነበረው ሰሜን ኮሪያ በቫይረሱ አጠባበቅ ዙርያ ችግሮች ታይተዋል ማለቷ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል፡፡ ሰሜን ኮሪያ ከጥርጣሬ የተነሳ አንዲት የድንበር ከተማ ሰዎች ተገለው እንዲቀመጡ ያደረገች ሲሆን ነገር ግን ከዚህ የዘለለ ስለተያዘ አንድም ሰው ተጠቅሶ አያውቅም፡፡ ኪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክብደት እየጨመሩ ስለሆነ በወጣትነታቸው ሊቀጠፉ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች በስፋት ይሰነዘሩ ነበር፡፡ በቅርቡም ለእህታቸው ኪም ዮ ጆንግ በርከት ያሉ ሥልጣኖችን ሰጥተዋት ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ እንደ ኑዛዜ የወሰዱት ሚዲያዎችም ነበሩ፡፡ ሰሜን ኮሪያ 25 ሚሊዮን ዜጎች አሏት፡፡ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿ የረሀብ አደጋ ገጥሟቸዋል ይላል የተባበሩት መንግሥታት፡፡ የረባ የንግድ ግንኙነት ከአገራት ጋር ያልመሰረተችው ሰሜን ኮሪያ ከቻይና ጋር የምታደርገው ንግድ ወሳኝ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ይህም በኮሮና ምክንያት እክል ገጥሞታል፡፡ በፒዮንግያንግ መቀመጫቸውን ያደረጉ በርካታ ግብረሰናይ ድርጅቶችና የኤምባሲ ሰራተኞች አገሪቱን ለቀው እንደወጡ ተዘግቧል፡፡ | ሰሜን ኮሪያ፡ ታመዋል ሲባሉ የነበሩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ድንገት ተከሰቱ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ታመዋል ከሚለው ጀምሮ፣ አብቅቶላቸዋል፣ ሞተዋል እየተባለም ብዙ ይወራባቸው ነበር፡፡ ድንገት በፓርቲ ስብሰባ ተከስተው መመርያ ሰጥተዋል፣ ትናንት፡፡ ሰሜን ኮሪያ ትልቅ አደጋ ከፊቷ ተደቅኗል ያሉት ኪም ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲሆን አዘዋል፡፡ ትልቅ አደጋ እየመጣ ነው ያሉት ኪም አደጋዎቹ በዋናነት ሁለት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡ አንዱ ኮሮና ቫይረስ ሲሆን ሌላው ደግሞ አውሎ ንፋስ ነው፡፡ ኪም ከሰሞኑ ጠፍተው ስለነበር የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ስለነበረ ምናልባት ሞተው ይሆን? ሲባል ነበር፡፡ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን አንድም ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘብኝም ስትል ታስተባብላለች፡፡ አይበለውና ወረርሽኙ ወደዚያች አገር ቢገባ ባላት ደካማ የጤና መሰረተ ልማት ከፍተኛ አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡ ይህ በእንዲህ ሳለ ባቪ የሚሰኝ አደገኛ አውሎ ነፋስ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሰሜን ኮሪያን ሊመታት ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ የፖሊትቢሮ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ኪም በስብሰባው ላይ ንግግር እያደረጉ ሲያጨሱ ይታዩ ነበር፡፡ በዚህ ንግግራቸው ኮቪድን በተመለከተ አንዳንድ ችግሮች ተስተውለዋል ብለዋል፡፡ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግን የሚያውቅ አልተገኘም፡፡ ፒዮንግያንግ ለረዥም ጊዜ ወረርሽኙ እኔ ጋ ድርሽ አላለም ስትል እያስተባበለች ቆይታለች፡፡ ነገር ግን ይህን የሰሜን ኮሪያን አስተያየት ብዙዎች በጥርጣሬ ነው የሚመለከቱት፡፡ አንድም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው የለም ስትል የነበረው ሰሜን ኮሪያ በቫይረሱ አጠባበቅ ዙርያ ችግሮች ታይተዋል ማለቷ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል፡፡ ሰሜን ኮሪያ ከጥርጣሬ የተነሳ አንዲት የድንበር ከተማ ሰዎች ተገለው እንዲቀመጡ ያደረገች ሲሆን ነገር ግን ከዚህ የዘለለ ስለተያዘ አንድም ሰው ተጠቅሶ አያውቅም፡፡ ኪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክብደት እየጨመሩ ስለሆነ በወጣትነታቸው ሊቀጠፉ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች በስፋት ይሰነዘሩ ነበር፡፡ በቅርቡም ለእህታቸው ኪም ዮ ጆንግ በርከት ያሉ ሥልጣኖችን ሰጥተዋት ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ እንደ ኑዛዜ የወሰዱት ሚዲያዎችም ነበሩ፡፡ ሰሜን ኮሪያ 25 ሚሊዮን ዜጎች አሏት፡፡ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿ የረሀብ አደጋ ገጥሟቸዋል ይላል የተባበሩት መንግሥታት፡፡ የረባ የንግድ ግንኙነት ከአገራት ጋር ያልመሰረተችው ሰሜን ኮሪያ ከቻይና ጋር የምታደርገው ንግድ ወሳኝ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ይህም በኮሮና ምክንያት እክል ገጥሞታል፡፡ በፒዮንግያንግ መቀመጫቸውን ያደረጉ በርካታ ግብረሰናይ ድርጅቶችና የኤምባሲ ሰራተኞች አገሪቱን ለቀው እንደወጡ ተዘግቧል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/53915684 |
0business
| #8 እሷ ማናት፡ "አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ"- ሐና ተክሌ | ሐና ተክሌ እባላለሁ። አዲስ አበባ አብነት፣ ቀበሌ 28 አካበቢ ነው ተወልጄ ያደግሁት። እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ግን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄጄ ኑሮዬን በዚያ አድርጌያለሁ። ባለትዳርና የሦስት ልጆች እናት ነኝ። በ2004* ሂልኮ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነበርኩ። ሁሌም የራሴን ሥራ መስራት እፈልግ ስለነበር በርካታ መጽሐፍትን ሳነብ የሕይወቴን መስመር ቀየርኩ። የሕይወት መስመሬ በትምህርት ብቻ አለመሆኑን ስረዳ የተለያዩ ነገሮችን በአማራጭነት መመልከት ጀመርኩ። ያኔ እጄ ላይ ከወደቀው እድል አንዱ ኔትወርክ ማርኬቲንግ ነው። በተለይ እናቴ ያሳደገችኝ ብቻዋን መሆኑ ወደዚህ ሥራ እንድገባ ምክንያት ሆኖኛል። • "የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ይኖራሉ" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ እናቴ ስድስት ልጆች ነበሯት እኔ ከሦስቱ ጋር ነው ያደግሁት። አምስተኛ ልጇ ነኝ። ልጆቿን ለማኖር ለረዥም ጊዜ በሥራ የኖረችው ዱባይ ነበር። ሁሌም የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ከትምህርት መልስ እናቶቻቸው ምሳ አዘጋጅተው፣ ቡና አጫጭሰው ሲጠብቋቸው እናታችን አጠገባችን ስለሌለችና ይህንን ማየት ባለመቻሌ አዝን ነበር። እንደ ሌሎች ልጆች እናቶች ቤት ቡና ቀራርቦ እናቴ እንድትጠብቀን የማድረግ የልጅነት ሕልሜ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ኔትወርክ ማርኬቲንግ ስሰማ ልቤ ውስጥ የነበረው ሰርቼ ውጤታማ ብሆን እናቴን ከዱባይ አምጥቼ ቤት ስገባ ዘወትር ባገኛት የሚለው ሀሳብ ነው ያነሳሳኝ። ከዚያም በዚሁ ሥራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓዝኩ፤ ደቡብ አፍሪካ የሄድኩት በአጋጣሚ ነው። ለሁለት ሳምንት ለሥራ በሄድኩበት ነው እዚያው የቀረሁት። የመጀመሪያውን አንድ ዓመት ወጣ ገባ እያልኩ ቆየሁ። ከዚያ በኋላ ግን ጠቅልዬ እዚያው መኖር ጀመርኩ። ወደ ደቡብ አፍሪካም የተጓዝኩት እዚያ ደንበኞችን ለማፈፍራት ነበር። በመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጉዞዬ ቢዝነሱ ስኬታማ ሆኖ ሰፍቶ ነበር። እስከ 2009 ድረስም ስሰራ ቆይቻለሁ። በኔትወርክ ማርኬቲንግ ውስጥ ከገንዘብ በተጨማሪም የአመራር፣ የተግባቦት፣ የሽያጭና አስተዳደር ክህሎቶችን አግኝቼበታለሁ። ኔትወርክ ማርኬቲንግ ብዙ አስተምሮኛል። ማግኘትና ማጣት ብዙ አስተምሮኛል። • ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት በራስ መተማመኔን የጨመረውም እርሱን እየሰራሁ ነው። ይህ የሥራ ሕይወት የተለያዩ በሮች እንዳሉትና በየትኛውም መንገድ ብጓዝ ስኬታማ እንደምሆን ያየሁበትም ነው። 2009 ላይ ግን ይህንን ሥራ አቁሜ ሌሎች ሥራዎችን ጀመርኩ። ከሕንድ እቃዎችን እያስመጣሁ ለቸርቻሪዎች መስጠት ጀመርኩ። በእርግጥ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥራዎችንም ሰርቻለሁ። ትርፍና ኪሳራውን አይቼ በ2015 ላይ አቆምኩት። በእርግጥ ሥራውን ያቆምኩት ስለከሰርኩ ነው ብል ይሻላል። 2013 ላይ ትዳር መስርቼ ወዲያው የመጀመሪያ ልጄን ወለድኩ። ልጆች ስወልድ ለልጆቼ የተሻለ ጥሪት የመቋጠር ፍላጎት በብርቱ ፈተነኝ። ባለቤቴ ጋቦናዊ ሲሆን የህይወት እቅዱ በሙሉ ተምሮ ስኬታማ መሆን ነው። የሒሳብ ትምህርት ያጠና ሲሆን ያን ጊዜ ሦስተኛ ዲግሪውን እየሰራ ነበር። ስንጋባ 35 ዓመቱ ነበር። እሱም 40 ዓመት ሳይሞላው ፕሮፌሰር ለመሆን በማለም እየጣረ ነበር። የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ክፍያ ደሞዙን ሳሰላው ባሌ በሚያገኘው ገንዘብ ልኖረው የምፈልገው ህይወት ሩቅ መሆኑ ተሰማኝ። ስለዚህ ከ2013 ጀምሮ የልቤን ፍላጎት ይዤ በየቀኑ አዳዲስ የንግድ ሀሳቦችን እመለከት ጀመር። ከዚያ እርሱ ከሥራ ወደቤት ሲመለስ ያገኘኋቸውን የንግድ ሀሳቦች እንመካከርባቸዋለን። ሁለተኛ ልጄን ከወለድኩ በኋላ ቢትኮይንን ተዋወቅሁ። 2015 ነሐሴ ወር ላይ ስለቢትኮይን ሰምቼ ለባለቤቴ ብነግረውም ሊቀበለኝ አልቻለም። • ስድስት መሠረታዊ ጥያቄዎች በጣና እምቦጭ ዙሪያ ስለቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ ልታስረዳኝ የሞከረችውን ልጅ ለስድስት ዓመት ልጅ እንደምታስረጂ አድርገሽ አስረጂኝ ብያት ብታስረዳኝም አልገባኝም ነበር። ጎግል ላይ በቀላሉ መረዳት የሚቻልበት መንገድን ጠይቄ ያገኘሁት መረጃ ግን ረዳኝ። ባለቤቴ የዘወትር ውትወታዬ ሲበረታበት አንድ ለሊት ቁጭ ብሎ ማንበብ ጀመረ። ባነበባቸው ጥናቶች ውስጥ የተሳተፉ ዩኒቨርስቲዎች፣ የተደረጉ ጥናቶች ቢዝነሱ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ አሳዩት። በኋላ ትኩረት ልሰጠው እንደሚገባ ነገረኝ። ከዚህ በኋላ ነው ቀላል የምለውንና አቅሜ የሚችለው ላይ የተሳተፍኩት። ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ 'ማይኒንግ' [በቢትኮይን ውስጥ ያለ ሥራ] ላይ መስራት ጀመርኩ። በዚህ ሥራ ላይ ተሰማርቼ ገና መስመር ሳይዝ ባለቤቴ በካናዳ ኦንታሪዮ ሪሰርች ኢንስቲትዩት የተመራማሪነት እድል አግኝቶ እኔና ልጆቼ ደቡብ አፍሪካ ቀርተን እርሱ ብቻውን እንዲሄድ ተስማማን። በዚህ ተስማምተን እርሱ ካናዳ ሄዶ ቤተሰቡን ለማስተዳደር ከሚያገኘው ገቢ ላይ ወደ ደቡብ አፍሪካ መላክ ነበረበት። ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቢትኮይን ገንዘብ ማግኘት ጀመርኩ። በስድስት ወር ውስጥ የእርሱን የዓመት ደሞዝ ያህል ማግኘት ጀመርኩ። ከዚያ በኋላ ወደ ካናዳ የመሄድ ሀሳቤን ተውኩት። ከስድስት ወር በኋላ ሊጠይቀን ሲመጣ ያለውን ለውጥ ተመለከተና ከሦስት ወር ቆይታ በኋላ የካናዳ ሥራውን ጥሎ እኔን ለመደገፍ መጣ። • ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው? በዚህ ሥራ ውስጥ ከተሰማራሁ በኋላ በአንድ ዓመት ከግማሽ ውስጥ አንድ ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ችያለሁ። ከዚያ በኋላም ቢዝነሱ እየሰፋ እና እየተጠቀምኩ ነው። ሚሊየነር መሆን ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው መንገዱ ክፍት ነው። ልጅ ወልደው ተደራራቢ ኃላፊነት ላለባቸው በቀላሉ ሊሰሩት የሚችሉት ሥራ ነው። እኔ በሰው አገር እየኖርኩ፣ ሦስት ልጆች እያሉኝ፤ ሁሉም ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ፤ መስራት ከቻልኩ ሌሎችም መስራት ይችላሉ። ለዚህ ሥራ ኢንተርኔትና ሀብታም የመሆን ፍላጎት እስካለ ድረስ መስራት ይቻላል። አትችይም የሚሉኝ ሰዎች ሁሌም ለሌላ ተጋድሎ ያነሳሱኛል። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሀገሩን ቋንቋ አትናገሪም ያሉኝ፣ ሴት መሆኔን ያስታወሱኝ ሰዎች በአጠቃላይ ዛሬ ለደረስኩበት አነሳስተውኛል። ባለቤቴ ቤት ውስጥ ከማርገዝና ከማጥባት ውጪ ሁሉንም ነገር ያግዘኛል፤ ይደግፈኛል። በዚህም እድለኛ ነኝ። ገንዘብ ለሁሉም ነገር መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ገንዘብ ሁሉንም ነገር ያቀላል። ስለዚህ ገንዘብ ሁሌም ለማግኘት ጠንክሬ እሰራለሁ። እንደ አፍሪካዊ የእኔ ሕይወት ሲቀየር የሌሎችም ሕይወት ስለሚቀየር የአንድን ሰው ሕይወት ለመለወጥ ጠንክሬ ነው የምሰራው። ብዙ አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ። ቢትኮይን ልክ እንደ ዶላር እንደ ዩሮ ሁሉ ገንዘብ ነው። ሌላው ቢትኮይንን ከአንድ ሰው ወደ ሌላው በቀላሉ ዋጋው ሳይሸራረፍ ማስተላለፍ ይቻላል። ቢትኮይን ለመላክ የሦስተኛ አካል ጣልቃ ገብነትን አስወግዷል። እኔ ቢትኮይን ማይኒንግ ላይ ከተሰማራሁ በኋላ ሁሌም ለሌሎች የምነግረው ቢትኮይንን ገዝተው ማስቀመጥ እንደሚችሉ፣ ቢትኮይን ንግድ ላይ የመሰማራት እድል መኖሩን አልያም ንግዳቸውን በቢትኮይን መገበያየት እንደሚችሉ ነው። ይህ ለሁሉም ሰው ያለ እድል ነው። ግን በጥንቃቄ መስራት ያስፈልጋል። በዓለም ላይ በርካታ አጭበርባሪዎች ስላሉ በሚገባ አጥንቶ መግባት ያስፈልጋል። ሚሊየነር መሆን ይቻላል ስል በአንድ ጀምበር መሆን ይቻላል እያልኩ አይደለም። ጠንክሮ መስራትን ይጠይቃል። እኔ የተሰማራሁበት ቢትኮይን ማይኒንግ ይባላል። ቢትኮይን ማይኒንግ ገንዘብ ማተም እንደማለት ነው፤ ቢትኮይን ማተም ነው። ለዚህ ሁሉ ግን ጠንከር ያለ ገንዘብ እንዲሁም ታማኝ አጋር ማግኘት ያስፈልጋል። • የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ 'ሊብራ' ጥያቄን አስነሳ • አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ አፍሪካን ያጥለቀልቅ ይሆን? እኔና ባለቤቴ 2015 ላይ 'አቺቨርስ ክለብ አካዳሚ' የተሰኘ ተቋም አቋቁመን ክሪፕቶከረንሲ አካዳሚ እና ኔትወርክ ማስተማር ጀመርን። ይህንንም ከፕሪቶሪያ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር ነው የምንሰራው። በአካዳሚያችን ፋንዳሜንታል ኦፍ ብሎክ ቼይን፣ ክሪፕቶከረንሲ ኤንድ ክሪፕቶ ፋይናንስ፣ ብሎክ ቼይን ፎር ቢዝነስን የተሰኙ ኮርሶች እናስተምራለን። እኔ ደግሞ በአቺቨርስ ኔትወርክ በኩል ወደ ተለያዩ አገራት እየሄድኩ ልምዴን አካፍላለሁ። ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር እንሰራለን። የምንሰራው በአፍሪካ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለማችን 33 አገራት ውስጥ ነው። እስካሁን 30 የሚሆኑ ሰዎች በሥራቸው ሚሊየን ዶላር እንዲያገኙ አድርገናል። ከእነዚህ ሰዎች መካከልም በሥራ ገበታቸው ላይ ሆነው የሚሰሩ አንዳንዶቹም የለቀቁ ይገኙበታል። በአፍሪካ ውስጥ በዚህ ትምህርት ሰፊውን ሥራ እየሰራን ነው። አሁን መቀመጫውን ፖላንድ ካደረገ ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራርመን እየሰራን ነው። እኔ ሰዎችን አስተምራለሁ፤ አፍሪካ ውስጥ ላለ ሰው ትልቅ እድል ነው። ማንም ሰው ቢሰማራበት ውጤታማ ሊሆን ይችላል። *ሁሉም የዘመን አቆጣጠሮች በአውሮፓዊያን ነው እሷ ማናት? የሚለው ጥንቅራችን ያሰቡበትን ዓላማ ለማሳካት ብዙ ውጣውረዶችን ያሳለፉ ሴቶችን ታሪክ የምናስቃኝበት ነው። | #8 እሷ ማናት፡ "አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ"- ሐና ተክሌ ሐና ተክሌ እባላለሁ። አዲስ አበባ አብነት፣ ቀበሌ 28 አካበቢ ነው ተወልጄ ያደግሁት። እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ግን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄጄ ኑሮዬን በዚያ አድርጌያለሁ። ባለትዳርና የሦስት ልጆች እናት ነኝ። በ2004* ሂልኮ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነበርኩ። ሁሌም የራሴን ሥራ መስራት እፈልግ ስለነበር በርካታ መጽሐፍትን ሳነብ የሕይወቴን መስመር ቀየርኩ። የሕይወት መስመሬ በትምህርት ብቻ አለመሆኑን ስረዳ የተለያዩ ነገሮችን በአማራጭነት መመልከት ጀመርኩ። ያኔ እጄ ላይ ከወደቀው እድል አንዱ ኔትወርክ ማርኬቲንግ ነው። በተለይ እናቴ ያሳደገችኝ ብቻዋን መሆኑ ወደዚህ ሥራ እንድገባ ምክንያት ሆኖኛል። • "የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ይኖራሉ" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ እናቴ ስድስት ልጆች ነበሯት እኔ ከሦስቱ ጋር ነው ያደግሁት። አምስተኛ ልጇ ነኝ። ልጆቿን ለማኖር ለረዥም ጊዜ በሥራ የኖረችው ዱባይ ነበር። ሁሌም የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ከትምህርት መልስ እናቶቻቸው ምሳ አዘጋጅተው፣ ቡና አጫጭሰው ሲጠብቋቸው እናታችን አጠገባችን ስለሌለችና ይህንን ማየት ባለመቻሌ አዝን ነበር። እንደ ሌሎች ልጆች እናቶች ቤት ቡና ቀራርቦ እናቴ እንድትጠብቀን የማድረግ የልጅነት ሕልሜ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ኔትወርክ ማርኬቲንግ ስሰማ ልቤ ውስጥ የነበረው ሰርቼ ውጤታማ ብሆን እናቴን ከዱባይ አምጥቼ ቤት ስገባ ዘወትር ባገኛት የሚለው ሀሳብ ነው ያነሳሳኝ። ከዚያም በዚሁ ሥራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓዝኩ፤ ደቡብ አፍሪካ የሄድኩት በአጋጣሚ ነው። ለሁለት ሳምንት ለሥራ በሄድኩበት ነው እዚያው የቀረሁት። የመጀመሪያውን አንድ ዓመት ወጣ ገባ እያልኩ ቆየሁ። ከዚያ በኋላ ግን ጠቅልዬ እዚያው መኖር ጀመርኩ። ወደ ደቡብ አፍሪካም የተጓዝኩት እዚያ ደንበኞችን ለማፈፍራት ነበር። በመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጉዞዬ ቢዝነሱ ስኬታማ ሆኖ ሰፍቶ ነበር። እስከ 2009 ድረስም ስሰራ ቆይቻለሁ። በኔትወርክ ማርኬቲንግ ውስጥ ከገንዘብ በተጨማሪም የአመራር፣ የተግባቦት፣ የሽያጭና አስተዳደር ክህሎቶችን አግኝቼበታለሁ። ኔትወርክ ማርኬቲንግ ብዙ አስተምሮኛል። ማግኘትና ማጣት ብዙ አስተምሮኛል። • ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት በራስ መተማመኔን የጨመረውም እርሱን እየሰራሁ ነው። ይህ የሥራ ሕይወት የተለያዩ በሮች እንዳሉትና በየትኛውም መንገድ ብጓዝ ስኬታማ እንደምሆን ያየሁበትም ነው። 2009 ላይ ግን ይህንን ሥራ አቁሜ ሌሎች ሥራዎችን ጀመርኩ። ከሕንድ እቃዎችን እያስመጣሁ ለቸርቻሪዎች መስጠት ጀመርኩ። በእርግጥ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥራዎችንም ሰርቻለሁ። ትርፍና ኪሳራውን አይቼ በ2015 ላይ አቆምኩት። በእርግጥ ሥራውን ያቆምኩት ስለከሰርኩ ነው ብል ይሻላል። 2013 ላይ ትዳር መስርቼ ወዲያው የመጀመሪያ ልጄን ወለድኩ። ልጆች ስወልድ ለልጆቼ የተሻለ ጥሪት የመቋጠር ፍላጎት በብርቱ ፈተነኝ። ባለቤቴ ጋቦናዊ ሲሆን የህይወት እቅዱ በሙሉ ተምሮ ስኬታማ መሆን ነው። የሒሳብ ትምህርት ያጠና ሲሆን ያን ጊዜ ሦስተኛ ዲግሪውን እየሰራ ነበር። ስንጋባ 35 ዓመቱ ነበር። እሱም 40 ዓመት ሳይሞላው ፕሮፌሰር ለመሆን በማለም እየጣረ ነበር። የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ክፍያ ደሞዙን ሳሰላው ባሌ በሚያገኘው ገንዘብ ልኖረው የምፈልገው ህይወት ሩቅ መሆኑ ተሰማኝ። ስለዚህ ከ2013 ጀምሮ የልቤን ፍላጎት ይዤ በየቀኑ አዳዲስ የንግድ ሀሳቦችን እመለከት ጀመር። ከዚያ እርሱ ከሥራ ወደቤት ሲመለስ ያገኘኋቸውን የንግድ ሀሳቦች እንመካከርባቸዋለን። ሁለተኛ ልጄን ከወለድኩ በኋላ ቢትኮይንን ተዋወቅሁ። 2015 ነሐሴ ወር ላይ ስለቢትኮይን ሰምቼ ለባለቤቴ ብነግረውም ሊቀበለኝ አልቻለም። • ስድስት መሠረታዊ ጥያቄዎች በጣና እምቦጭ ዙሪያ ስለቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ ልታስረዳኝ የሞከረችውን ልጅ ለስድስት ዓመት ልጅ እንደምታስረጂ አድርገሽ አስረጂኝ ብያት ብታስረዳኝም አልገባኝም ነበር። ጎግል ላይ በቀላሉ መረዳት የሚቻልበት መንገድን ጠይቄ ያገኘሁት መረጃ ግን ረዳኝ። ባለቤቴ የዘወትር ውትወታዬ ሲበረታበት አንድ ለሊት ቁጭ ብሎ ማንበብ ጀመረ። ባነበባቸው ጥናቶች ውስጥ የተሳተፉ ዩኒቨርስቲዎች፣ የተደረጉ ጥናቶች ቢዝነሱ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ አሳዩት። በኋላ ትኩረት ልሰጠው እንደሚገባ ነገረኝ። ከዚህ በኋላ ነው ቀላል የምለውንና አቅሜ የሚችለው ላይ የተሳተፍኩት። ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ 'ማይኒንግ' [በቢትኮይን ውስጥ ያለ ሥራ] ላይ መስራት ጀመርኩ። በዚህ ሥራ ላይ ተሰማርቼ ገና መስመር ሳይዝ ባለቤቴ በካናዳ ኦንታሪዮ ሪሰርች ኢንስቲትዩት የተመራማሪነት እድል አግኝቶ እኔና ልጆቼ ደቡብ አፍሪካ ቀርተን እርሱ ብቻውን እንዲሄድ ተስማማን። በዚህ ተስማምተን እርሱ ካናዳ ሄዶ ቤተሰቡን ለማስተዳደር ከሚያገኘው ገቢ ላይ ወደ ደቡብ አፍሪካ መላክ ነበረበት። ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቢትኮይን ገንዘብ ማግኘት ጀመርኩ። በስድስት ወር ውስጥ የእርሱን የዓመት ደሞዝ ያህል ማግኘት ጀመርኩ። ከዚያ በኋላ ወደ ካናዳ የመሄድ ሀሳቤን ተውኩት። ከስድስት ወር በኋላ ሊጠይቀን ሲመጣ ያለውን ለውጥ ተመለከተና ከሦስት ወር ቆይታ በኋላ የካናዳ ሥራውን ጥሎ እኔን ለመደገፍ መጣ። • ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው? በዚህ ሥራ ውስጥ ከተሰማራሁ በኋላ በአንድ ዓመት ከግማሽ ውስጥ አንድ ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ችያለሁ። ከዚያ በኋላም ቢዝነሱ እየሰፋ እና እየተጠቀምኩ ነው። ሚሊየነር መሆን ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው መንገዱ ክፍት ነው። ልጅ ወልደው ተደራራቢ ኃላፊነት ላለባቸው በቀላሉ ሊሰሩት የሚችሉት ሥራ ነው። እኔ በሰው አገር እየኖርኩ፣ ሦስት ልጆች እያሉኝ፤ ሁሉም ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ፤ መስራት ከቻልኩ ሌሎችም መስራት ይችላሉ። ለዚህ ሥራ ኢንተርኔትና ሀብታም የመሆን ፍላጎት እስካለ ድረስ መስራት ይቻላል። አትችይም የሚሉኝ ሰዎች ሁሌም ለሌላ ተጋድሎ ያነሳሱኛል። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሀገሩን ቋንቋ አትናገሪም ያሉኝ፣ ሴት መሆኔን ያስታወሱኝ ሰዎች በአጠቃላይ ዛሬ ለደረስኩበት አነሳስተውኛል። ባለቤቴ ቤት ውስጥ ከማርገዝና ከማጥባት ውጪ ሁሉንም ነገር ያግዘኛል፤ ይደግፈኛል። በዚህም እድለኛ ነኝ። ገንዘብ ለሁሉም ነገር መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ገንዘብ ሁሉንም ነገር ያቀላል። ስለዚህ ገንዘብ ሁሌም ለማግኘት ጠንክሬ እሰራለሁ። እንደ አፍሪካዊ የእኔ ሕይወት ሲቀየር የሌሎችም ሕይወት ስለሚቀየር የአንድን ሰው ሕይወት ለመለወጥ ጠንክሬ ነው የምሰራው። ብዙ አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ። ቢትኮይን ልክ እንደ ዶላር እንደ ዩሮ ሁሉ ገንዘብ ነው። ሌላው ቢትኮይንን ከአንድ ሰው ወደ ሌላው በቀላሉ ዋጋው ሳይሸራረፍ ማስተላለፍ ይቻላል። ቢትኮይን ለመላክ የሦስተኛ አካል ጣልቃ ገብነትን አስወግዷል። እኔ ቢትኮይን ማይኒንግ ላይ ከተሰማራሁ በኋላ ሁሌም ለሌሎች የምነግረው ቢትኮይንን ገዝተው ማስቀመጥ እንደሚችሉ፣ ቢትኮይን ንግድ ላይ የመሰማራት እድል መኖሩን አልያም ንግዳቸውን በቢትኮይን መገበያየት እንደሚችሉ ነው። ይህ ለሁሉም ሰው ያለ እድል ነው። ግን በጥንቃቄ መስራት ያስፈልጋል። በዓለም ላይ በርካታ አጭበርባሪዎች ስላሉ በሚገባ አጥንቶ መግባት ያስፈልጋል። ሚሊየነር መሆን ይቻላል ስል በአንድ ጀምበር መሆን ይቻላል እያልኩ አይደለም። ጠንክሮ መስራትን ይጠይቃል። እኔ የተሰማራሁበት ቢትኮይን ማይኒንግ ይባላል። ቢትኮይን ማይኒንግ ገንዘብ ማተም እንደማለት ነው፤ ቢትኮይን ማተም ነው። ለዚህ ሁሉ ግን ጠንከር ያለ ገንዘብ እንዲሁም ታማኝ አጋር ማግኘት ያስፈልጋል። • የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ 'ሊብራ' ጥያቄን አስነሳ • አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ አፍሪካን ያጥለቀልቅ ይሆን? እኔና ባለቤቴ 2015 ላይ 'አቺቨርስ ክለብ አካዳሚ' የተሰኘ ተቋም አቋቁመን ክሪፕቶከረንሲ አካዳሚ እና ኔትወርክ ማስተማር ጀመርን። ይህንንም ከፕሪቶሪያ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር ነው የምንሰራው። በአካዳሚያችን ፋንዳሜንታል ኦፍ ብሎክ ቼይን፣ ክሪፕቶከረንሲ ኤንድ ክሪፕቶ ፋይናንስ፣ ብሎክ ቼይን ፎር ቢዝነስን የተሰኙ ኮርሶች እናስተምራለን። እኔ ደግሞ በአቺቨርስ ኔትወርክ በኩል ወደ ተለያዩ አገራት እየሄድኩ ልምዴን አካፍላለሁ። ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር እንሰራለን። የምንሰራው በአፍሪካ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለማችን 33 አገራት ውስጥ ነው። እስካሁን 30 የሚሆኑ ሰዎች በሥራቸው ሚሊየን ዶላር እንዲያገኙ አድርገናል። ከእነዚህ ሰዎች መካከልም በሥራ ገበታቸው ላይ ሆነው የሚሰሩ አንዳንዶቹም የለቀቁ ይገኙበታል። በአፍሪካ ውስጥ በዚህ ትምህርት ሰፊውን ሥራ እየሰራን ነው። አሁን መቀመጫውን ፖላንድ ካደረገ ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራርመን እየሰራን ነው። እኔ ሰዎችን አስተምራለሁ፤ አፍሪካ ውስጥ ላለ ሰው ትልቅ እድል ነው። ማንም ሰው ቢሰማራበት ውጤታማ ሊሆን ይችላል። *ሁሉም የዘመን አቆጣጠሮች በአውሮፓዊያን ነው እሷ ማናት? የሚለው ጥንቅራችን ያሰቡበትን ዓላማ ለማሳካት ብዙ ውጣውረዶችን ያሳለፉ ሴቶችን ታሪክ የምናስቃኝበት ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-50909604 |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ በአውሮፓ ከተሞች "ኮቪድ-19 ውሸት ነው" የሚሉ ተቃውሞዎች እየተካሄዱ ነው | ከአርብ ጀምሮ እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎች መልከ ብዙ ቢሆኑም 'ጭራሽ ኮሮና የሚባል ቫይረስ ብሎ ነገር የለም፣ እየተጭበረበርን ነው' ብለው የሚያምኑ ሰልፈኞችም የተገኙበት ሆኗል፡፡ የብዙዎቹ ሰልፈኞች ጥያቄ ግን በኮሮና ምክንያት የተጣሉ ገደቦች ይነሱ የሚሉ ናቸው፡፡ በጀርመን በርሊን ሰፊ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ 300 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ የጀርመን ሰልፈኞች ያነሱት ተቃውሞ በዋናነት 'በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጥብቅ የተደረጉ መመሪያዎች ይነሱልን መረረን' የሚል ነው፡፡ በጀርመን ለተቃውሞው 40ሺ የሚጠጉ ሰዎች አደባባይ ወጥተዋል፡፡ በአመዛኙ ሰላማዊ ሆኖ የቆየው ተቃውሞ በነጭ አክራሪዎች ነውጥ ምክንያት መልኩን እየቀየረ መጥቷል፡፡ ድንጋይና ጠርሙስ መወራወርም ተጀምሯል፡፡ በበርሊን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የአውሮፓ ከተሞች ተመሳሳይ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡ በለንደን በዝነኛው ትራፋልጋር አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ብዙዎቹ "ኮሮናቫይረስ ብሎ ነገር የለም፤ እየተጭበረበርን ነው" የሚል ይዘት ያላቸው መፈክሮችን ይዘው ታይተዋል፡፡ በፓሪስ፣ በቪየና እንዲሁም በዙሪክ ይኸው ተቃውሞ በተመሳሳይ መንፈስ ቀጥሏል፡፡ በጀርመን የተካሄደው ተቃውሞ ፍትጊያ የበዛበትና ማኅበራዊ ርቀትን ለማስጠበቅ አስቸጋሪ እንደነበር ፖሊስ አምኗል፡፡ "ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ የሚቻለውን ለማድረግ ሙክረናል፡፡ በሰልፈኞች መሀል የኮሮናቫይረስ ደንቦችን ማስጠበቅ ግን አልቻልንም" ብሏል ፖሊስ በትዊተር ገጹ፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ካዋላቸው ሰዎች መሀል አንዱ "ኮሮናቫይረስ ብሎ ነገር የለም፣ ዉሸት ነው የሚለውን መላምት በማራገብ የሚታወቀው አቲላ ሂልድማን" ይገኝበታል፡፡ ሂልድማን ለሰልፈኞች ድምጽ ማጉያ ይዞ ተከታታይ ንግግር ሲያደርግ ነበር፡፡ ሂልድማን በጀርመን እውቅ የምግብ አብሳይ ባለሙያ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነጭ አክራሪዎችን አስተሳሰብ በመጋራት ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኗል፡፡ "ኮሮናቫይረስ የሚባል ነገር የለም፤ ጀርመን ከቢልጌትስ መወገኗን ታቁም" የሚሉ አስተሳሰቦችን ማራመድ በመጀመሩ ብዙ ተከታዮችን አፍርቷል፡፡ ብዙዎቹ ሰልፈኞቹ ጭምብል ማጥለቅና ሌሎች ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚወሰዱ መመርያዎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ስለሆኑ እንዳሻን እንሁን የሚል ጥያቄ ነው ያነሱት፡፡ ከሰልፈኞቹ መሀል እውቅ ሰዎችም ተገኝተውበታል፡፡ ለምሳሌ ሮበርት የጆን ኤፍ ኬኔዲ ልጅ ለሰልፉ ድጋፍ ከሰጡት መሀል ይገኝበታል፡፡ ሮበርት ኬኔዲ ጁንየር በሰው እጅ የተገደሉት የዝነኛው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የወንድም ልጅ ሲሆን ክትባትን በመቃወም ከፍተኛ ተከታይ ያፈራ ሰው ነው፡፡ ሮበርት ኬኔዲ በርሊን ድረስ በመምጣት ሰልፉን ተቀላቅሏል፡፡ ጀርመን እስካሁን 242,000 ሰዎች በኮቪድ-19 እንደተጠቁባት እና ከ10ሺ ሰዎች በታች እንደሞቱባት ይታወቃል፡፡ | ኮሮናቫይረስ ፡ በአውሮፓ ከተሞች "ኮቪድ-19 ውሸት ነው" የሚሉ ተቃውሞዎች እየተካሄዱ ነው ከአርብ ጀምሮ እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎች መልከ ብዙ ቢሆኑም 'ጭራሽ ኮሮና የሚባል ቫይረስ ብሎ ነገር የለም፣ እየተጭበረበርን ነው' ብለው የሚያምኑ ሰልፈኞችም የተገኙበት ሆኗል፡፡ የብዙዎቹ ሰልፈኞች ጥያቄ ግን በኮሮና ምክንያት የተጣሉ ገደቦች ይነሱ የሚሉ ናቸው፡፡ በጀርመን በርሊን ሰፊ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ 300 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ የጀርመን ሰልፈኞች ያነሱት ተቃውሞ በዋናነት 'በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጥብቅ የተደረጉ መመሪያዎች ይነሱልን መረረን' የሚል ነው፡፡ በጀርመን ለተቃውሞው 40ሺ የሚጠጉ ሰዎች አደባባይ ወጥተዋል፡፡ በአመዛኙ ሰላማዊ ሆኖ የቆየው ተቃውሞ በነጭ አክራሪዎች ነውጥ ምክንያት መልኩን እየቀየረ መጥቷል፡፡ ድንጋይና ጠርሙስ መወራወርም ተጀምሯል፡፡ በበርሊን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የአውሮፓ ከተሞች ተመሳሳይ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡ በለንደን በዝነኛው ትራፋልጋር አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ብዙዎቹ "ኮሮናቫይረስ ብሎ ነገር የለም፤ እየተጭበረበርን ነው" የሚል ይዘት ያላቸው መፈክሮችን ይዘው ታይተዋል፡፡ በፓሪስ፣ በቪየና እንዲሁም በዙሪክ ይኸው ተቃውሞ በተመሳሳይ መንፈስ ቀጥሏል፡፡ በጀርመን የተካሄደው ተቃውሞ ፍትጊያ የበዛበትና ማኅበራዊ ርቀትን ለማስጠበቅ አስቸጋሪ እንደነበር ፖሊስ አምኗል፡፡ "ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ የሚቻለውን ለማድረግ ሙክረናል፡፡ በሰልፈኞች መሀል የኮሮናቫይረስ ደንቦችን ማስጠበቅ ግን አልቻልንም" ብሏል ፖሊስ በትዊተር ገጹ፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ካዋላቸው ሰዎች መሀል አንዱ "ኮሮናቫይረስ ብሎ ነገር የለም፣ ዉሸት ነው የሚለውን መላምት በማራገብ የሚታወቀው አቲላ ሂልድማን" ይገኝበታል፡፡ ሂልድማን ለሰልፈኞች ድምጽ ማጉያ ይዞ ተከታታይ ንግግር ሲያደርግ ነበር፡፡ ሂልድማን በጀርመን እውቅ የምግብ አብሳይ ባለሙያ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነጭ አክራሪዎችን አስተሳሰብ በመጋራት ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኗል፡፡ "ኮሮናቫይረስ የሚባል ነገር የለም፤ ጀርመን ከቢልጌትስ መወገኗን ታቁም" የሚሉ አስተሳሰቦችን ማራመድ በመጀመሩ ብዙ ተከታዮችን አፍርቷል፡፡ ብዙዎቹ ሰልፈኞቹ ጭምብል ማጥለቅና ሌሎች ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚወሰዱ መመርያዎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ስለሆኑ እንዳሻን እንሁን የሚል ጥያቄ ነው ያነሱት፡፡ ከሰልፈኞቹ መሀል እውቅ ሰዎችም ተገኝተውበታል፡፡ ለምሳሌ ሮበርት የጆን ኤፍ ኬኔዲ ልጅ ለሰልፉ ድጋፍ ከሰጡት መሀል ይገኝበታል፡፡ ሮበርት ኬኔዲ ጁንየር በሰው እጅ የተገደሉት የዝነኛው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የወንድም ልጅ ሲሆን ክትባትን በመቃወም ከፍተኛ ተከታይ ያፈራ ሰው ነው፡፡ ሮበርት ኬኔዲ በርሊን ድረስ በመምጣት ሰልፉን ተቀላቅሏል፡፡ ጀርመን እስካሁን 242,000 ሰዎች በኮቪድ-19 እንደተጠቁባት እና ከ10ሺ ሰዎች በታች እንደሞቱባት ይታወቃል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-53963766 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በድሬዳዋ ከሃያ በላይ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ተያዙ | በድሬዳዋ 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ አረጋገጠ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። ወይዘሮ ስንታየሁ ለጤና ባለሙያዎቹ በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን በተመለከተም አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው "እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ "በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቫይረሱ ከተያዙት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል በድንገተኛ እና በጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚሰሩ ነርሶችና ዶክተሮች እንደሚገኙበት በመጥቀስ፤ በዚህ ክፍል የሚሰሩት ባለሙያዎች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ተጋላጭ መሆናቸውን አብራርተዋል። በድሬዳዋ እስካሁን ድረስ ስምንት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረገላቸው፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ከ500 በላይ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸውንና 17 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ400 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ማገገማቸውን የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ስንታየሁ ደበሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተያያዘ ዜና በምሥራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ 66 ታራሚዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ተካ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጊኒር ከተማ እና በወረዳው በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ በተደረገው የኮቪድ-19 ምርመራ እነዚህ ታራሚዎች ኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው ታራሚዎች ለህክምና ወደ ሮቤ ሆስፒታል መላካቸውንም ቢቢሲ ከኃላፊው መረዳት ችሏል። ኃላፊው በእነዚህ ፖሊስ ጣቢያዎች ታራሚዎች አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ በማያስችላቸው እና ያለ ምንም ጥንቃቄ መልኩ መታሰራቸው በሽታው እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች የፀረ ተህዋሲ ርጭት ተደርጓል። በቀላል ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እንዲወጡ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑንም ተናግረዋል። ታራሚዎቹን ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተሰቦችም በሽታውን ወደ ኅብረተሰቡ ይዘው በመሄድ ስርጭቱ ይስፋፋል የሚል ስጋት ቢኖርም እስካሁን ድረስ ከተጠረጠሩት ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተያዘ ሰው አለመገኘቱን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን 470 ሺህ የሚጠጋ ምርመራ ተደርጎ ወደ 21 ሺህ 452 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህም መካከል በወረርሽኙ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 380 ደርሷል። | ኮሮናቫይረስ፡ በድሬዳዋ ከሃያ በላይ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ተያዙ በድሬዳዋ 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ አረጋገጠ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። ወይዘሮ ስንታየሁ ለጤና ባለሙያዎቹ በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን በተመለከተም አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው "እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ "በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቫይረሱ ከተያዙት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል በድንገተኛ እና በጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚሰሩ ነርሶችና ዶክተሮች እንደሚገኙበት በመጥቀስ፤ በዚህ ክፍል የሚሰሩት ባለሙያዎች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ተጋላጭ መሆናቸውን አብራርተዋል። በድሬዳዋ እስካሁን ድረስ ስምንት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረገላቸው፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ከ500 በላይ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸውንና 17 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ400 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ማገገማቸውን የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ስንታየሁ ደበሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተያያዘ ዜና በምሥራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ 66 ታራሚዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ተካ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጊኒር ከተማ እና በወረዳው በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ በተደረገው የኮቪድ-19 ምርመራ እነዚህ ታራሚዎች ኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው ታራሚዎች ለህክምና ወደ ሮቤ ሆስፒታል መላካቸውንም ቢቢሲ ከኃላፊው መረዳት ችሏል። ኃላፊው በእነዚህ ፖሊስ ጣቢያዎች ታራሚዎች አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ በማያስችላቸው እና ያለ ምንም ጥንቃቄ መልኩ መታሰራቸው በሽታው እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች የፀረ ተህዋሲ ርጭት ተደርጓል። በቀላል ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እንዲወጡ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑንም ተናግረዋል። ታራሚዎቹን ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተሰቦችም በሽታውን ወደ ኅብረተሰቡ ይዘው በመሄድ ስርጭቱ ይስፋፋል የሚል ስጋት ቢኖርም እስካሁን ድረስ ከተጠረጠሩት ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተያዘ ሰው አለመገኘቱን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን 470 ሺህ የሚጠጋ ምርመራ ተደርጎ ወደ 21 ሺህ 452 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህም መካከል በወረርሽኙ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 380 ደርሷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53696685 |
3politics
| አሜሪካና ሩሲያ በተመድ ስብሰባ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ተፋጠጡ | ሩሲያ በዩክሬን ድንበር ላይ ከፍተኛ ሰራዊት ማስፈሯን ተከትሎ በተጠራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ላይ በአሜሪካና በሩሲያ ልዑካን መካከል ቁጣና ንዴት የተሞላበት ፍጥጫ እንደነበር ተገልጿል። ይህንን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ የጠራችው አሜሪካ ናት። በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ሩሲያ በድንበር ላይ እያደረገችው ያለው የጦር ስምሪት በአውሮፓ በአስርት አመታት ውስጥ ከታየው ትልቁ ነው ብለዋል። የሩሲያ አቻቸው በበኩላቸው አሜሪካ የማያስፈልግ ውዥንብር እየፈጠረች ነው በሩሲያ ጉዳዮች ላይ ተቀባይነት የሌለው ጣልቃ ገብነት እያደረገች ነው ሲሉ ከሰዋታል። ሩሲያ ዩክሬንን የምትወር ከሆነ ተጨማሪ ማዕቀብ እንጥላለን ሲሉ አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግድም ቃል ገብተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ ለክሬምሊን ቅርብ ከሆኑ ግለሰቦች እና ንግዶች ባለፈ መልኩ ሰፋ ያሉ ጉዳዮች ላይ የሚያነጣጥር ህግ እየተዘጋጀ ነው። የአሜሪካ ባለስልጣን በበኩላቸው ለክሬምሬሊን ቅርብ የሆኑ ግለሰቦች ከአለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት እንዲቆራረጡ የሚያደርግ ማዕቀብ ይጣላል ብለዋል። ሩሲያ 100 ሺህ የሚገመቱ ወታደሮች፣ ታንኮች፣ መድፍ እና ሚሳኤሎችን በዩክሬን ድንበር አካባቢ አስፍራለች። ሰኞ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዛ እንዳሉት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እቅድ ለማውጣቷ ምንም አይነት ማረጋገጫ እንደሌለ እና በድንበሩ ላይ ያለው የሰራዊት ግንባታዋ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተረጋገጠ አይደለም ብለዋል። ሩሲያ አብዛኛውን ጊዜ ጦሯን በፈለገችው ግዛቷ እንደምታሰማራ እና ይህ የዋሽንግተን ጉዳይ እንዳልሆነም አምባሳደር ቫሲሊ ተናግረዋል። ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ክፍት ስብሰባ እንዳይደረግ ብትከላከልም 10 ለሁለት በሆነ ድምፅ ተሸንፋ ጉባዔው ተደርጓል። የባይደን አስተዳደር “ውጥረቶችን በማነሳሳትና ትርክቶችን በመፍጠር ግጭቶች እንዲቀሰቀስ እየሰሩ ነው” ሲሉ አምባሳደሩ ወቅሰዋቸዋል። "ይህ በአገራችን የውስጥ ጉዳይ ላይ ተቀባይነት የሌለው ጣልቃ ገብነት ብቻ ሳይሆን አለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለአካባቢው ትክክለኛ ሁኔታ የተሳሳተ መረጃ እንዲኖረው እና በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ውጥረት ምክንያቶች መነሻ ነው በሚል ለማሳየት የሚደረግ ሙከራ ነው" ብለዋል። አምባሳደር ቶማስ ግሪንፊልድ በበኩላቸው አሜሪካ አሁንም ቢሆን ለዩክሬን ጉዳይ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዳለ እንደምታምን ቢያስረዱም፤ ነገር ግን ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች አገራቸው ቆራጥ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች። የዚህ ውጤትም “አሰቃቂ” ነው ብለዋል። "ይህ በአውሮፓ በአስርት አመታት ውስጥ ያላየነው ትልቁ የወታደር ማስፈር ነው" ሲሉ ተናግረዋል። “በአሁኑ ወቅት ይህንን እየተናገርን ባለንበት ወቅት ሩሲያ ተጨማሪ ኃይሎችን እና የጦር መሳሪያዎችን ወደ ድንበር እየላከች ነው” ብለዋል። ሞስኮ በአጎራባቿ ቤላሩስና በዩክሬን ሰሜናዊ ድንበር ላይ የምታሰማራውን ጦር ወደ 30 ሺህ ለማሳደግ አቅዳ ነበር ሲሉ አስረድተዋል። ሰኞ ምሽት ላይ የአሜሪካ መንግሥት ሰራተኞች ቤተሰብ አባላት ከቤላሩስ እንዲወጡ አሜሪካ አዛለች። ለዚህም “ያልተለመደው የሩሲያ ጦር ማስፈርን” ጠቅሳለች። ባለፈው ወር አሜሪካ በዩክሬን መዲና ኪየቭ የሚገኘውን ኤምባሲ ሰራተኞችና ቤተሰቦች እንዲወጡ አዛለች። | አሜሪካና ሩሲያ በተመድ ስብሰባ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ተፋጠጡ ሩሲያ በዩክሬን ድንበር ላይ ከፍተኛ ሰራዊት ማስፈሯን ተከትሎ በተጠራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ላይ በአሜሪካና በሩሲያ ልዑካን መካከል ቁጣና ንዴት የተሞላበት ፍጥጫ እንደነበር ተገልጿል። ይህንን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ የጠራችው አሜሪካ ናት። በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ሩሲያ በድንበር ላይ እያደረገችው ያለው የጦር ስምሪት በአውሮፓ በአስርት አመታት ውስጥ ከታየው ትልቁ ነው ብለዋል። የሩሲያ አቻቸው በበኩላቸው አሜሪካ የማያስፈልግ ውዥንብር እየፈጠረች ነው በሩሲያ ጉዳዮች ላይ ተቀባይነት የሌለው ጣልቃ ገብነት እያደረገች ነው ሲሉ ከሰዋታል። ሩሲያ ዩክሬንን የምትወር ከሆነ ተጨማሪ ማዕቀብ እንጥላለን ሲሉ አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግድም ቃል ገብተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ ለክሬምሊን ቅርብ ከሆኑ ግለሰቦች እና ንግዶች ባለፈ መልኩ ሰፋ ያሉ ጉዳዮች ላይ የሚያነጣጥር ህግ እየተዘጋጀ ነው። የአሜሪካ ባለስልጣን በበኩላቸው ለክሬምሬሊን ቅርብ የሆኑ ግለሰቦች ከአለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት እንዲቆራረጡ የሚያደርግ ማዕቀብ ይጣላል ብለዋል። ሩሲያ 100 ሺህ የሚገመቱ ወታደሮች፣ ታንኮች፣ መድፍ እና ሚሳኤሎችን በዩክሬን ድንበር አካባቢ አስፍራለች። ሰኞ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዛ እንዳሉት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እቅድ ለማውጣቷ ምንም አይነት ማረጋገጫ እንደሌለ እና በድንበሩ ላይ ያለው የሰራዊት ግንባታዋ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተረጋገጠ አይደለም ብለዋል። ሩሲያ አብዛኛውን ጊዜ ጦሯን በፈለገችው ግዛቷ እንደምታሰማራ እና ይህ የዋሽንግተን ጉዳይ እንዳልሆነም አምባሳደር ቫሲሊ ተናግረዋል። ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ክፍት ስብሰባ እንዳይደረግ ብትከላከልም 10 ለሁለት በሆነ ድምፅ ተሸንፋ ጉባዔው ተደርጓል። የባይደን አስተዳደር “ውጥረቶችን በማነሳሳትና ትርክቶችን በመፍጠር ግጭቶች እንዲቀሰቀስ እየሰሩ ነው” ሲሉ አምባሳደሩ ወቅሰዋቸዋል። "ይህ በአገራችን የውስጥ ጉዳይ ላይ ተቀባይነት የሌለው ጣልቃ ገብነት ብቻ ሳይሆን አለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለአካባቢው ትክክለኛ ሁኔታ የተሳሳተ መረጃ እንዲኖረው እና በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ውጥረት ምክንያቶች መነሻ ነው በሚል ለማሳየት የሚደረግ ሙከራ ነው" ብለዋል። አምባሳደር ቶማስ ግሪንፊልድ በበኩላቸው አሜሪካ አሁንም ቢሆን ለዩክሬን ጉዳይ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዳለ እንደምታምን ቢያስረዱም፤ ነገር ግን ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች አገራቸው ቆራጥ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች። የዚህ ውጤትም “አሰቃቂ” ነው ብለዋል። "ይህ በአውሮፓ በአስርት አመታት ውስጥ ያላየነው ትልቁ የወታደር ማስፈር ነው" ሲሉ ተናግረዋል። “በአሁኑ ወቅት ይህንን እየተናገርን ባለንበት ወቅት ሩሲያ ተጨማሪ ኃይሎችን እና የጦር መሳሪያዎችን ወደ ድንበር እየላከች ነው” ብለዋል። ሞስኮ በአጎራባቿ ቤላሩስና በዩክሬን ሰሜናዊ ድንበር ላይ የምታሰማራውን ጦር ወደ 30 ሺህ ለማሳደግ አቅዳ ነበር ሲሉ አስረድተዋል። ሰኞ ምሽት ላይ የአሜሪካ መንግሥት ሰራተኞች ቤተሰብ አባላት ከቤላሩስ እንዲወጡ አሜሪካ አዛለች። ለዚህም “ያልተለመደው የሩሲያ ጦር ማስፈርን” ጠቅሳለች። ባለፈው ወር አሜሪካ በዩክሬን መዲና ኪየቭ የሚገኘውን ኤምባሲ ሰራተኞችና ቤተሰቦች እንዲወጡ አዛለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-60211915 |
3politics
| በምዕራብ ጉጂ ዞን የጸጥታ ኃላፊን ጨምሮ 7 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ | በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አንድ የአካባቢው ባለሥልጣንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። በምዕራብ ጉጂ ዞን ውስጥ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በዞኑ የሚገኘው ገላና ወረዳ የጸጥታና የደኅንነት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ጃርሶ በካሎን ጨምሮ ሰባት ሰዎች በታጣቂዎቹ መገደላቸውን የወረዳው የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ገበየሁ ያደቴ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ገበየሁ እንዳሉት ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 14/2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን በአጠቃላይ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። ከደቡብ ክልል የአማሮ ወረዳ ጋር በሚዋሰነው በዚህ አካባቢ እንዲህ ያለው ጥቃት ሲፈጸም የመጀመሪያ አይደለም። ከዚህ በፊትም በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ግድያዎች መፈጸማቸው ይታወሳል። ባለፈው መጋቢት ወር ሁለቱ ወረዳዎች በሚያዋሰኑበት ሥፍራ ስብሰባ ላይ በነበሩ አመራሮችና ነዋሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ስድስት ደግሞ ቆስለው ነበር። በወቅቱ ጥቃቱን የፈጸሙት መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራውና እራሳቸውን 'የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት' የሚሉት ታጣቂዎች እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፤ አሁንም ለሰባት ሰዎች ህልፈት ምክንያት ለሆነው ጥቃት ይኸው ታጣቂ ቡድን በተጠያቂነት ይከሰሳል። በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ውስጥ በሰዎች ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶችና የንብረት ውድመቶች ጋር በተያያዘ ከሳምንታት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቡድኑን ሽብርተኛ ቡድን ብሎ መሰየሙ ይታወሳል። ከሳምንት በፊት የቀድሞ የምዕራብ ወለጋ ዞን ጸጥታ ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ አምስት የመንግሥት ሠራተኞች በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ በታጣቂ ቡድኑ መገደላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀው ነበር። የምዕራብ ጉጂው ጥቃት በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ገበየሁ ያደቴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጥቃቱ በታጣቂዎቹ የተፈጸመው ኃላፊውና ሌሎች የጸጥታ አካላት ለሥራ እየተጓዙ በነበረበት ጊዜ ነው። "በዚህም በወረዳው የጸጥታና የደኅንነት ኃላፊ አቶ ጃርሶ በካሎ የተመራ ቡድን የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቦሬ ቀበሌ እየተጓዘ ሳላ ጨልቤሳ ሾሮ በተባለ ሥፍራ ላይ ነው ጥቃቱ የተፈጸመባቸው" ብለዋል። በጥቃቱም ከወረዳው አስተዳደር ወገን የነበሩ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ከታጣቂዎቹ በኩል ደግሞ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል። በጥቃቱ ሁለት የሚሊሻ አባላት፣ ሦስት የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት፣ የወረዳው ጸጥታና ደኅንነት ኃላፊና እና የጽህፈት ቤቱ የደኅንነት ባለሙያ በአጠቃላይ 7 ሰዎች ተገድለዋል። በታጣቂዎቹ ከተገደሉት ባሻገር ሌሎች 7 ሰዎች ደግሞ በተለያየ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ዲላ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን አቶ ገበየሁ ገልጸዋል። በጥቃቱ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ሰባት ሰዎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ በጥቃቱ ወቅት ከታጣቂዎቹ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሁለት የታጣቂው አባላት መሞታቸው ተነግሯል። በአካባቢው የአመራር አባላትና የጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለመያዝ ጥቃቱ በተፈጸመበት ሥፍራ የተጠናከረ አሰሳና እርምጃ እየተወሰደ መሆኑም ኃላፊው ገልጸዋል። ጥቃቱ በተፈጸመበት የምዕራብ ጉጂ ዞን የገላና ወረዳ ታጣቂዎች ድንበር ላይ ባሉ የወረዳው ቀበሌዎች ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱና በተለያዩ ጊዜያትም በጸጥታና በሚሊሻ አባላት ላይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ጨምረው አመልክተዋል። ቅዳሜ ዕለት በታጣቂዎቹ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ሥርዓተ ቀብር እሁድ ዕለት መፈጸሙንም የኮምዩኒኬሽን ኃላፊው ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባወጣው መረጃ በዚህ ዓመት ብቻ በኦሮሚያ ክልል 'ሸኔ' በተባለው ታጣቂ ቡድን በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ18 በላይ በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ 112 የፖሊስ አባላት እንዲሁም 57 በሚሊሻ አባላት በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ ውስጥ ተገድለዋል። | በምዕራብ ጉጂ ዞን የጸጥታ ኃላፊን ጨምሮ 7 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አንድ የአካባቢው ባለሥልጣንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። በምዕራብ ጉጂ ዞን ውስጥ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በዞኑ የሚገኘው ገላና ወረዳ የጸጥታና የደኅንነት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ጃርሶ በካሎን ጨምሮ ሰባት ሰዎች በታጣቂዎቹ መገደላቸውን የወረዳው የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ገበየሁ ያደቴ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ገበየሁ እንዳሉት ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 14/2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን በአጠቃላይ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። ከደቡብ ክልል የአማሮ ወረዳ ጋር በሚዋሰነው በዚህ አካባቢ እንዲህ ያለው ጥቃት ሲፈጸም የመጀመሪያ አይደለም። ከዚህ በፊትም በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ግድያዎች መፈጸማቸው ይታወሳል። ባለፈው መጋቢት ወር ሁለቱ ወረዳዎች በሚያዋሰኑበት ሥፍራ ስብሰባ ላይ በነበሩ አመራሮችና ነዋሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ስድስት ደግሞ ቆስለው ነበር። በወቅቱ ጥቃቱን የፈጸሙት መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራውና እራሳቸውን 'የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት' የሚሉት ታጣቂዎች እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፤ አሁንም ለሰባት ሰዎች ህልፈት ምክንያት ለሆነው ጥቃት ይኸው ታጣቂ ቡድን በተጠያቂነት ይከሰሳል። በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ውስጥ በሰዎች ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶችና የንብረት ውድመቶች ጋር በተያያዘ ከሳምንታት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቡድኑን ሽብርተኛ ቡድን ብሎ መሰየሙ ይታወሳል። ከሳምንት በፊት የቀድሞ የምዕራብ ወለጋ ዞን ጸጥታ ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ አምስት የመንግሥት ሠራተኞች በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ በታጣቂ ቡድኑ መገደላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀው ነበር። የምዕራብ ጉጂው ጥቃት በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ገበየሁ ያደቴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጥቃቱ በታጣቂዎቹ የተፈጸመው ኃላፊውና ሌሎች የጸጥታ አካላት ለሥራ እየተጓዙ በነበረበት ጊዜ ነው። "በዚህም በወረዳው የጸጥታና የደኅንነት ኃላፊ አቶ ጃርሶ በካሎ የተመራ ቡድን የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቦሬ ቀበሌ እየተጓዘ ሳላ ጨልቤሳ ሾሮ በተባለ ሥፍራ ላይ ነው ጥቃቱ የተፈጸመባቸው" ብለዋል። በጥቃቱም ከወረዳው አስተዳደር ወገን የነበሩ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ከታጣቂዎቹ በኩል ደግሞ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል። በጥቃቱ ሁለት የሚሊሻ አባላት፣ ሦስት የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት፣ የወረዳው ጸጥታና ደኅንነት ኃላፊና እና የጽህፈት ቤቱ የደኅንነት ባለሙያ በአጠቃላይ 7 ሰዎች ተገድለዋል። በታጣቂዎቹ ከተገደሉት ባሻገር ሌሎች 7 ሰዎች ደግሞ በተለያየ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ዲላ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን አቶ ገበየሁ ገልጸዋል። በጥቃቱ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ሰባት ሰዎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ በጥቃቱ ወቅት ከታጣቂዎቹ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሁለት የታጣቂው አባላት መሞታቸው ተነግሯል። በአካባቢው የአመራር አባላትና የጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለመያዝ ጥቃቱ በተፈጸመበት ሥፍራ የተጠናከረ አሰሳና እርምጃ እየተወሰደ መሆኑም ኃላፊው ገልጸዋል። ጥቃቱ በተፈጸመበት የምዕራብ ጉጂ ዞን የገላና ወረዳ ታጣቂዎች ድንበር ላይ ባሉ የወረዳው ቀበሌዎች ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱና በተለያዩ ጊዜያትም በጸጥታና በሚሊሻ አባላት ላይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ጨምረው አመልክተዋል። ቅዳሜ ዕለት በታጣቂዎቹ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ሥርዓተ ቀብር እሁድ ዕለት መፈጸሙንም የኮምዩኒኬሽን ኃላፊው ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባወጣው መረጃ በዚህ ዓመት ብቻ በኦሮሚያ ክልል 'ሸኔ' በተባለው ታጣቂ ቡድን በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ18 በላይ በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ 112 የፖሊስ አባላት እንዲሁም 57 በሚሊሻ አባላት በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ ውስጥ ተገድለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57222409 |
0business
| የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሲብ ንግድን ማገድ ለምን አስፈለገው? | ከሰሞኑ የአዲስ አበባ አስተዳደር የጎዳና ልመናና የወሲብ ንግድን ለማገድ ረቂቅ ሕግ ማዘጋጀቱን ተከትሎ በብዙዎች ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ከእግዱ አላማ አንስቶ እስከተደረጉ ዝግጅቶች፣ እንዲሁም የአስተዳደሩ ሥልጣን ባሉና በተያያዙ ጉዳዮች ውይይቶች ቀጥለዋል። ረቂቅ ሕጉ በአሁኑ ወቅት ለካቢኔ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ብቻውን መወሰንም ስለማይችል ባለድርሻ አካላት በተለይም የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተያየት እንዲሰጡበትም እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ፌቨን ተሾመ አስረድተዋል። | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሲብ ንግድን ማገድ ለምን አስፈለገው? ከሰሞኑ የአዲስ አበባ አስተዳደር የጎዳና ልመናና የወሲብ ንግድን ለማገድ ረቂቅ ሕግ ማዘጋጀቱን ተከትሎ በብዙዎች ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ከእግዱ አላማ አንስቶ እስከተደረጉ ዝግጅቶች፣ እንዲሁም የአስተዳደሩ ሥልጣን ባሉና በተያያዙ ጉዳዮች ውይይቶች ቀጥለዋል። ረቂቅ ሕጉ በአሁኑ ወቅት ለካቢኔ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ብቻውን መወሰንም ስለማይችል ባለድርሻ አካላት በተለይም የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተያየት እንዲሰጡበትም እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ፌቨን ተሾመ አስረድተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-49444559 |
5sports
| በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለው እግር ኳስ ተጫዋች ሮቢንሆ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ | ብራዚላዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ሮቢንሆ እ.ኤ.አ. በ 2013 በሚላን ከተማ በቡድን በተፈጸመ የመድፈር ወንጀል የቀረበበትን ፍርድ ለመጨረሻ ግዜ ይገባኝ ቢልም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ውድቅ አደረገ። ትላንት ረቡዕ የተሰየመው የሮም ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ 37 ዓመቱን ኳስ ተጨዋች ተፈርዶበት የነበረውን የዘጠኝ ዓመት እስራት አጽንቷል። እ.ኤ.አ. በ 2017 ሮቢንሆ እና ሌሎች አምስት ብራዚላውያን የ22 ዓመቷን አልባኒያዊ ሴት በምሽት ክበብ ውስጥ የጾታዊ ጥቃት በማድረስ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት። ከዚህ ቀደም በታህሳስ 2020 ይግባኝ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ቢቀርብበትም ይግባኙ ውድቅ ተደርጎ ነበር። ሮቢንሆ የሚኖርበት ብራዚል በሕገ መንግስት ደረጃ መንግስት ዜጎቹን ለሌላ አገር አሳልፎ እንዳይሰጥ የሚከለክል መሆኑን ተከትሎ ቅጣቱን ይፈጽማል የሚል ግምት ባይኖርም ጣሊያን ደቡብ አሜሪካዊቷን አገር ቅጣቱን በአገሩ ውስጥ እንዲፈጽም መጠየቅ ትችላለች። ለብራዚል 100 ጊዜ የተጫወተው ሮቢንሆ በ2005 ኑሮውን ወደ ሪያል ማድሪድ ከማዛዋሩ የእግር ኳስ ህይወቱን በሳንቶስ ነበር የጀመረው። በአራት የውድድር ዘመናት ሁለት የላሊጋ ዋንጫዎችን አንስቷል። እ.ኤ.አ. በ 2008 ማንቸስተር ሲቲን ሲቀላቀል በወቅቱ የእግሊዝ ከፍተኛው ክፍያ 32.5m ፓውንድ ተከፍሎት ነበር። ነገር ግን በእንግሊዝ ቆይታው ውጤታማ ለመሆን ባለመቻሉ በጥር 2010 ለሳንቶስ በውሰት ተሰጥቷል። በኤስ ሚላን ቆይታው ሴሪአን አሸንፏል። በቻይና እና በቱርክ ላሉ ክለቦች ከተጫወተ በኋላ 2020 በአምስት ወር ኮንትራት ወደ ሳንቶስ ቢመለስም ፊርማው ከፍተኛ ትችት ማጋጠሙን ተከትሎ የብራዚሉ ክለብ ኮንትራቱን አቋርጦ "ተጫዋቹ በጣሊያን እየተካሄደ ባለው ጉዳይ በመከላከሉ ላይ ብቻ እንዲያተኩር" ስል ውሉን አቋርጫለሁ ሲል አስታወቆ ነበር። | በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለው እግር ኳስ ተጫዋች ሮቢንሆ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ ብራዚላዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ሮቢንሆ እ.ኤ.አ. በ 2013 በሚላን ከተማ በቡድን በተፈጸመ የመድፈር ወንጀል የቀረበበትን ፍርድ ለመጨረሻ ግዜ ይገባኝ ቢልም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ውድቅ አደረገ። ትላንት ረቡዕ የተሰየመው የሮም ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ 37 ዓመቱን ኳስ ተጨዋች ተፈርዶበት የነበረውን የዘጠኝ ዓመት እስራት አጽንቷል። እ.ኤ.አ. በ 2017 ሮቢንሆ እና ሌሎች አምስት ብራዚላውያን የ22 ዓመቷን አልባኒያዊ ሴት በምሽት ክበብ ውስጥ የጾታዊ ጥቃት በማድረስ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት። ከዚህ ቀደም በታህሳስ 2020 ይግባኝ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ቢቀርብበትም ይግባኙ ውድቅ ተደርጎ ነበር። ሮቢንሆ የሚኖርበት ብራዚል በሕገ መንግስት ደረጃ መንግስት ዜጎቹን ለሌላ አገር አሳልፎ እንዳይሰጥ የሚከለክል መሆኑን ተከትሎ ቅጣቱን ይፈጽማል የሚል ግምት ባይኖርም ጣሊያን ደቡብ አሜሪካዊቷን አገር ቅጣቱን በአገሩ ውስጥ እንዲፈጽም መጠየቅ ትችላለች። ለብራዚል 100 ጊዜ የተጫወተው ሮቢንሆ በ2005 ኑሮውን ወደ ሪያል ማድሪድ ከማዛዋሩ የእግር ኳስ ህይወቱን በሳንቶስ ነበር የጀመረው። በአራት የውድድር ዘመናት ሁለት የላሊጋ ዋንጫዎችን አንስቷል። እ.ኤ.አ. በ 2008 ማንቸስተር ሲቲን ሲቀላቀል በወቅቱ የእግሊዝ ከፍተኛው ክፍያ 32.5m ፓውንድ ተከፍሎት ነበር። ነገር ግን በእንግሊዝ ቆይታው ውጤታማ ለመሆን ባለመቻሉ በጥር 2010 ለሳንቶስ በውሰት ተሰጥቷል። በኤስ ሚላን ቆይታው ሴሪአን አሸንፏል። በቻይና እና በቱርክ ላሉ ክለቦች ከተጫወተ በኋላ 2020 በአምስት ወር ኮንትራት ወደ ሳንቶስ ቢመለስም ፊርማው ከፍተኛ ትችት ማጋጠሙን ተከትሎ የብራዚሉ ክለብ ኮንትራቱን አቋርጦ "ተጫዋቹ በጣሊያን እየተካሄደ ባለው ጉዳይ በመከላከሉ ላይ ብቻ እንዲያተኩር" ስል ውሉን አቋርጫለሁ ሲል አስታወቆ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-60034979 |
0business
| ከመንግሥት 550 ሚሊዮን ብር መዝብራ የተሰወረችው ዴንማርካዊት ተፈረደባት | ከመንግሥት አምስት መቶ አምሳ ሚሊዮን ብር መዝብራ የተሰወረችው ዴንማርካዊት ከሰሞኑ ክስ ተመስርቶባታል። በመንግሥት ማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ድርጅት ውስጥ ለአርባ ዓመታት የሠራችው ብሪታ ኔልሰን አቅማቸው ለደከሙ ግለሰቦች የገንዘብ እርዳታን የሚለግስን ተቋም ገንዘብ ትቆጣጠር እንደነበር ተገልጿል። ከሁለት ዓመታት በፊት በተደረገ ምርመራ ግን ገንዘቡን ኪሷን ለማደለብ ተጠቅማበታለች ተብሏል። የዴንማርክ ፍርድ ቤትም የስድስት ዓመት ተኩል እስር ከሰሞኑ ፈርዶባታል። • ከማዕከላዊ ስልጣን የተገፋው ህወሓት ከዬት ወደዬት? • ኢትዮጵያዊቷ ከ20 ዓመት በኋላ የኤርትራዊቷን ቤት ሊያስረክቡ ነው በዝቅተኛ ሙስናና መንግሥት ሁሉን ነገር ግልፅ በሆነ አሠራር በዓለም አቀፉ መድረክ ተምሳሌት በሆነችው ዴንማርክ ይህ የተለመደ ነገር አይደለም። ብሪታ ኔልሰን ውንጀላዎቹ በቀረቡባት ወቅት ደቡብ አፍሪካ ተሰውራ ነበር። ወደ ዴንማርክ ለመመለስ የወሰነችው ዓለም አቀፉ የወንጀል አጣሪና አዳኝ ኢንተርፖል የእስር ትዕዛዝ ካወጣባት በኋላ ነው። ለሃያ አምስት ዓመታትም ድርጅቱን በመመዝበርም ተወንጅላለች። • ውጤት ለማሻሻል ወሲብን ተጠቅመዋል የተባሉት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ታገዱ • ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ በሹመታቸው ዙሪያ ምን ይላሉ? ብሪታ ኔልሰን 'ሶሻልስትይሬልሰን' በሚባለው ብሄራዊ የጤናና ደህንነት ላይ የሚሠራው መንግሥታዊ ድርጅት ውስጥ ነው የሰራችው። የዴንማርክ መስማት የተሳናቸው ማኅበርን ጨምሮ ሌሎች የአካል ጉዳተኞችም በጀት የሚመደብላቸው ከዚህ ድርጅት ነበር፤ ገንዘብ መመደብም የሷ ኃላፊነት ነበር ተብሏል። ከሦስት ዓመታት በፊት በድርጅቱ ውስጥ ላደረገችው አስተዋፅኦ የብር ሜዳልያ ሽልማትም ተሸልማለች። ኖርዲክ ሌበር ጆርናል፤ ብሪታ ኔልሰን ለመመዝበር ያመቻት ምንም አይነት የተጠያቂነት መዋቅር ስላልነበረው ነው በማለት ፍርድ ቤቱ ላይ መከራከሪያ ሃሳብ አቅርቧል። የ65 አመቷ ብሪታ ኔልሰን በበኩሏ "ብሩን አካውንቴ ውስጥ መጨመር ቀላል ነበር፤ ከዚያም ወደ ባሃማስ ለመዝናናት መሄድ" ብላለች። | ከመንግሥት 550 ሚሊዮን ብር መዝብራ የተሰወረችው ዴንማርካዊት ተፈረደባት ከመንግሥት አምስት መቶ አምሳ ሚሊዮን ብር መዝብራ የተሰወረችው ዴንማርካዊት ከሰሞኑ ክስ ተመስርቶባታል። በመንግሥት ማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ድርጅት ውስጥ ለአርባ ዓመታት የሠራችው ብሪታ ኔልሰን አቅማቸው ለደከሙ ግለሰቦች የገንዘብ እርዳታን የሚለግስን ተቋም ገንዘብ ትቆጣጠር እንደነበር ተገልጿል። ከሁለት ዓመታት በፊት በተደረገ ምርመራ ግን ገንዘቡን ኪሷን ለማደለብ ተጠቅማበታለች ተብሏል። የዴንማርክ ፍርድ ቤትም የስድስት ዓመት ተኩል እስር ከሰሞኑ ፈርዶባታል። • ከማዕከላዊ ስልጣን የተገፋው ህወሓት ከዬት ወደዬት? • ኢትዮጵያዊቷ ከ20 ዓመት በኋላ የኤርትራዊቷን ቤት ሊያስረክቡ ነው በዝቅተኛ ሙስናና መንግሥት ሁሉን ነገር ግልፅ በሆነ አሠራር በዓለም አቀፉ መድረክ ተምሳሌት በሆነችው ዴንማርክ ይህ የተለመደ ነገር አይደለም። ብሪታ ኔልሰን ውንጀላዎቹ በቀረቡባት ወቅት ደቡብ አፍሪካ ተሰውራ ነበር። ወደ ዴንማርክ ለመመለስ የወሰነችው ዓለም አቀፉ የወንጀል አጣሪና አዳኝ ኢንተርፖል የእስር ትዕዛዝ ካወጣባት በኋላ ነው። ለሃያ አምስት ዓመታትም ድርጅቱን በመመዝበርም ተወንጅላለች። • ውጤት ለማሻሻል ወሲብን ተጠቅመዋል የተባሉት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ታገዱ • ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ በሹመታቸው ዙሪያ ምን ይላሉ? ብሪታ ኔልሰን 'ሶሻልስትይሬልሰን' በሚባለው ብሄራዊ የጤናና ደህንነት ላይ የሚሠራው መንግሥታዊ ድርጅት ውስጥ ነው የሰራችው። የዴንማርክ መስማት የተሳናቸው ማኅበርን ጨምሮ ሌሎች የአካል ጉዳተኞችም በጀት የሚመደብላቸው ከዚህ ድርጅት ነበር፤ ገንዘብ መመደብም የሷ ኃላፊነት ነበር ተብሏል። ከሦስት ዓመታት በፊት በድርጅቱ ውስጥ ላደረገችው አስተዋፅኦ የብር ሜዳልያ ሽልማትም ተሸልማለች። ኖርዲክ ሌበር ጆርናል፤ ብሪታ ኔልሰን ለመመዝበር ያመቻት ምንም አይነት የተጠያቂነት መዋቅር ስላልነበረው ነው በማለት ፍርድ ቤቱ ላይ መከራከሪያ ሃሳብ አቅርቧል። የ65 አመቷ ብሪታ ኔልሰን በበኩሏ "ብሩን አካውንቴ ውስጥ መጨመር ቀላል ነበር፤ ከዚያም ወደ ባሃማስ ለመዝናናት መሄድ" ብላለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-51557291 |
3politics
| የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ ታዩ | የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ መታየታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገለጹ። ቢቢሲ አቶ ዳውድ ዛሬ ረፋድ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ስብሰባ ለመቀመጥ ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አምርተው እንደነበር ከታማኝ ምንጮች ተረድቷል። የሊቀ መንበሩን ከእቁም እስር መለቀቅን ፓርቲያቸውም አረጋግጧል። የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ሽጉት ገለታ፤ "ታጉረው ከነበሩበት ቤታቸው መውጣት ችለዋል። መቶ በመቶ ተፈተዋል ማለት ባይቻለም ትልቅ ለውጥ ግን አለ። . . . ሰው አያነጋግራቸውም ነበር፣ ከቤት እንዲወጡ አይፈቀድላቸውም ነበር። ምርጫ ቦርድ ካነጋገራቸው በኋላ ግን ከቁም እስር ተለቀዋል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት የኦነግ የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደቆዩ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገልጾ ነበር። ይህም ድርጊት ከሕግ ውጪ መሆኑን በመጥቀስ በሊቀ መንበሩ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአፋጣኝ እንዲነሳ ቦርዱ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን እና ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን በደብዳቤ መጠየቁ ይታወሳል። ከአቶ ዳውድ የቁም እስር በተጨማሪ በርካታ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በእስር ላይ ይገኛሉ። የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ሚካኤል ቦረን እና አብዲ ረጋሳን ጨምሮ ኬነሳ አያና፣ ኮሎኔል ገመቹ አያና፣ ዳዊት አብደታ እና ለሚ ቤኛ በእስር ላይ ይገኛሉ። የኦነግ ቃል አቀባይ በቴ ኡርጌሳ ደግሞ ከጥቂት ቀናት በፊት ከእስር ቢለቀቁም፤ በእስር ላይ ሳሉ ያጋጠማቸውን የጤና መታወክ ተከትሎ በጤና ተቋም ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ። የፖለቲከኞቹ ጠበቆች ደንበኞቻችን በፍርድ ቤት በነጻ ቢለቀቁም ፖሊስ ነጻ ለማሰናበት ፍቃደኛ አይደለም ሲሉ ከዚህ በፊት ለቢቢሲ ተናግረዋል። | የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ ታዩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ መታየታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገለጹ። ቢቢሲ አቶ ዳውድ ዛሬ ረፋድ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ስብሰባ ለመቀመጥ ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አምርተው እንደነበር ከታማኝ ምንጮች ተረድቷል። የሊቀ መንበሩን ከእቁም እስር መለቀቅን ፓርቲያቸውም አረጋግጧል። የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ሽጉት ገለታ፤ "ታጉረው ከነበሩበት ቤታቸው መውጣት ችለዋል። መቶ በመቶ ተፈተዋል ማለት ባይቻለም ትልቅ ለውጥ ግን አለ። . . . ሰው አያነጋግራቸውም ነበር፣ ከቤት እንዲወጡ አይፈቀድላቸውም ነበር። ምርጫ ቦርድ ካነጋገራቸው በኋላ ግን ከቁም እስር ተለቀዋል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት የኦነግ የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም እስር ላይ እንደቆዩ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ገልጾ ነበር። ይህም ድርጊት ከሕግ ውጪ መሆኑን በመጥቀስ በሊቀ መንበሩ ላይ የተጣለው የመንቀሳቀስ ገደብ በአፋጣኝ እንዲነሳ ቦርዱ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን እና ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን በደብዳቤ መጠየቁ ይታወሳል። ከአቶ ዳውድ የቁም እስር በተጨማሪ በርካታ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በእስር ላይ ይገኛሉ። የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ሚካኤል ቦረን እና አብዲ ረጋሳን ጨምሮ ኬነሳ አያና፣ ኮሎኔል ገመቹ አያና፣ ዳዊት አብደታ እና ለሚ ቤኛ በእስር ላይ ይገኛሉ። የኦነግ ቃል አቀባይ በቴ ኡርጌሳ ደግሞ ከጥቂት ቀናት በፊት ከእስር ቢለቀቁም፤ በእስር ላይ ሳሉ ያጋጠማቸውን የጤና መታወክ ተከትሎ በጤና ተቋም ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ። የፖለቲከኞቹ ጠበቆች ደንበኞቻችን በፍርድ ቤት በነጻ ቢለቀቁም ፖሊስ ነጻ ለማሰናበት ፍቃደኛ አይደለም ሲሉ ከዚህ በፊት ለቢቢሲ ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60761359 |
0business
| ሰሜን ኮርያ፡ ፕሬዝዳንት ኪም የአገራቸው ምጣኔ ሀብት እቅድ አለመሳካቱን ተናገሩ | የሰሜን ኮርያ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን የአገራቸው የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት እቅድ "በሁሉም ዘርፎች ሊባል በሚችለ ሁኔታ" የተቀመጠለትን ግብ አለማሳካቱን ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የያሉት በፓርቲያቸው ጉባኤ መክፈቻ ላይ ነው። የሰሜን ኮርያ የሠራተኞች ፓርቲ ስብሰባ ሲያደርግ ይህ ስምንተኛው ብቻ ነው ተብሏል። ሰሜን ኮርያ ካለፈው ዓመት ታኅሣስ ወር ጀምሮ ምንም እንኳ አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው የለም ብትልም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚል ድንበሯን ዘግታለች። ይህም ከጎረቤቷና አጋሯ ቻይና ጋር ተቆራርጣ እንድትቀር አድርጓታል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 80 በመቶ መውደቁ ተገልጿል። በሰሜን ኮርያ አውሎ ንፋስ እና ጎርፍ ቤቶችን ያወደመ ሲሆን በኒውክለር ፕሮግራሟ የተነሳም ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥብቅ የሆነ ማዕቀብ ተጥሎባታል። ፕሬዝዳንት ኪም የሚሰሯቸውን ስህተቶች ሲያምኑ የመጀመሪያቸው አይደለም። በቴሌቪዥን በተላለፈው የፓርቲው ጉባኤ ላይ አዳራሹ በተሰብሳቢዎች ሞልቶ የታየ ሲሆን አንዳቸውም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አላደረጉም። ፕሬዝዳንቱ ወደ ስብሰባ አዳራሽ ሲገቡ ሁሉም ከመቀመጫቸው ተነስተው በጭብጨባ ተቀብለዋቸዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በ2016 ያስተዋወቁት የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት ስትራቴጂ "በሁሉም ዘርፍ ሊባል በሚችል ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ዝቅተኛ አፈጻጸም አስመዝግቧል "ስህተቶችን ደግሞ በይፋ መቀበል ያስፈልጋል" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ የፓርቲያቸው አባላትን የኮሮናቫይረስን በመከላከል ረገድ ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል። ሰሜን ኮርያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መጠርጠራቸውን ለዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሪፖርት ብታደርግም አንድም ሰው በቫይረሱ ተይዟል ብላ ሪፖርት አላደረገችም። ፕሬዝዳንት ኪም ለምክር ቤቱ አባላት አዲስ የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት እቅድ ያስተዋውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። | ሰሜን ኮርያ፡ ፕሬዝዳንት ኪም የአገራቸው ምጣኔ ሀብት እቅድ አለመሳካቱን ተናገሩ የሰሜን ኮርያ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን የአገራቸው የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት እቅድ "በሁሉም ዘርፎች ሊባል በሚችለ ሁኔታ" የተቀመጠለትን ግብ አለማሳካቱን ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የያሉት በፓርቲያቸው ጉባኤ መክፈቻ ላይ ነው። የሰሜን ኮርያ የሠራተኞች ፓርቲ ስብሰባ ሲያደርግ ይህ ስምንተኛው ብቻ ነው ተብሏል። ሰሜን ኮርያ ካለፈው ዓመት ታኅሣስ ወር ጀምሮ ምንም እንኳ አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው የለም ብትልም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚል ድንበሯን ዘግታለች። ይህም ከጎረቤቷና አጋሯ ቻይና ጋር ተቆራርጣ እንድትቀር አድርጓታል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 80 በመቶ መውደቁ ተገልጿል። በሰሜን ኮርያ አውሎ ንፋስ እና ጎርፍ ቤቶችን ያወደመ ሲሆን በኒውክለር ፕሮግራሟ የተነሳም ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥብቅ የሆነ ማዕቀብ ተጥሎባታል። ፕሬዝዳንት ኪም የሚሰሯቸውን ስህተቶች ሲያምኑ የመጀመሪያቸው አይደለም። በቴሌቪዥን በተላለፈው የፓርቲው ጉባኤ ላይ አዳራሹ በተሰብሳቢዎች ሞልቶ የታየ ሲሆን አንዳቸውም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አላደረጉም። ፕሬዝዳንቱ ወደ ስብሰባ አዳራሽ ሲገቡ ሁሉም ከመቀመጫቸው ተነስተው በጭብጨባ ተቀብለዋቸዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በ2016 ያስተዋወቁት የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት ስትራቴጂ "በሁሉም ዘርፍ ሊባል በሚችል ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ዝቅተኛ አፈጻጸም አስመዝግቧል "ስህተቶችን ደግሞ በይፋ መቀበል ያስፈልጋል" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ የፓርቲያቸው አባላትን የኮሮናቫይረስን በመከላከል ረገድ ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል። ሰሜን ኮርያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መጠርጠራቸውን ለዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሪፖርት ብታደርግም አንድም ሰው በቫይረሱ ተይዟል ብላ ሪፖርት አላደረገችም። ፕሬዝዳንት ኪም ለምክር ቤቱ አባላት አዲስ የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት እቅድ ያስተዋውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55561319 |
0business
| በአንድ ቀን 1 ቢሊዮን ዶላር ያተረፈው ጆርጅ ሶሮስ ማን ነው? | አንድ የደበተው ሰኞ ከሰዓት፤ በ2019 ኅዳር ወር ላይ መሆኑ ነው፣ ምንነቱ ያልታወቀ የፖስታ ጥቅል በኒውዮርክ የባለጸጎች መንደር በሚገኝ አንድ ግዙፍ ቤት ተቀመጠ፤ ደጅ የፖስታ ሰንዱቅ ውስጥ። ጥቅሉ አጠራጣሪ ነገሮች ነበሩት። አንደኛ የተመላሽ ስም በትክክል አልተጻበትም። ሁለተኛ በተላከበት ቀን ነው የደረሰው። ፖሊስ ተጠራጠረ፤ ኤፍቢአይ ተጠራ። የጆርጅ ሶሮስ ቪላ ተወረረ። • የዓለማችን ቁጥር አንድ ሃቀኛዋ ሃገር በዚያ ጥቅል ውስጥ የሶሮስ ፎቶ ነበር፤ ከፊት ለፊት የይገደል ምልክት ተጽፎበታል። 6 ኢንች የሚረዝም የፕላስቲክ ጎማ፣ ቁልቁል የሚቆጥር ሰዓት፣ ባትሪና የኤሌክትሪክ ሽቦዎች ነበሩበት፤ በጥቅሉ ፖስታ። ተመሳሳይ ጥቅል ወደ ኦባማና ሂላሪ ቤት ተልኳል። ደግነቱ አንዱም አልፈነዳም፤ ፖሊስ አክሽፎታል። ቀኝ ዘመም የአሜሪካ ሚዲያ ቶሎ ጣቱን የቀሰረው ወደ ሶሮስ ነበር። ራሱ ሶሮስ የሸረበው ሸር ነው በሚል። ሶሮስ እንዴት አድርጎ ወደ ራሱ ቦምብ ይልካል? ጥሩ ጥያቄ ነው። ነገር ግን የትራምፕ አክራሪ ደጋፊዎች በአመዛኙ ለርትዕ ፊት አይሰጡም ይባላል፤ ለፖለቲካ ተዋስኦ ክፍት አይደሉም፤ አመክንዮ ይቀፋቸዋል። የትራምፕ ደጋፊዎች የሚቀናቸው ሴራ ነው። የአሻጥር ፖለቲካ የነጭ አክራሪዎች ኦፒየም ነው። ስለዚህም አደባባይ ወጡ። ጆርጅ ሶሮስን ሊያወግዙ። "ትራምፓችን ሆይ! ሶሮስን እሰር! ሶሮስን ዘብጥያ አውርድልን" የሚል ድምጽ በዋይት ሃውስ ደጅ ላይ አስተጋባ። ደግነቱ ፖሊስ ቦምቦቹን በጥቅል የላከውን ሰው ደረሰበት። የ56 ዓመቱ የፍሎሪዳ ነዋሪ ሲዛር ሳዮክ ነበር። ሰውየው እንዲያውም ብዙዎች እንደገመቱት ሪፐብሊካን አልነበረም። ቤት ለቤት ፒዛ አዳይ እንጂ። • በትራምፕ የድጋፍ ደብዳቤ ወደ አሜሪካ ያቀናችው የአሲድ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያዊት ሆኖም አእምሮው በሴራ ፖለቲካ ናውዞ ነበር። እንደ ብዙዎቹ ቀኝ አክራሪዎች። ከሁሉም ፖለቲካ ጀርባ ጆርጅ ሶሮስ የሚባል ሰው አለ ብሎ ያምን ነበር፤ ሶሮስ የነጭ የበላይነትን ሊያጠፋ የተነሳ ጠላት ነው ብሎ ያስብ ነበር፤ የትራምፕ ጠላት ነው ብሎ ያምን ነበር፤ ስለዚህ መገደል አለበት በሚል ነው ቦምቡን በፖስታ የላከው። የዚህ ወንጀለኛ ፌስቡክ ሲበረበር ደግሞ ሌላ ጉድ ተገኘ። "ዓለም ከእንቅልፉ ሲነቃ የሶሮስን አሳዛኝ ዜና ይሰማል!" ይህ ግለሰብ ለጊዜው 20 ዓመት እስር ተከናንቧል። ጆርጅ ሶሮስ ግን አሁንም የሴራ ፖለቲካ ገፈት ቀማሽ እንደሆነ አለ። ከሁሉም የዓለም ፖለቲካ ለውጥ ጀርባ የሶሮስ እጅ አለ የሚል አስተሳሰብ ናኝቷል። ለመሆኑ ሶሮስ እንደሚገመተው የዓለም የአሻጥር ፖለቲካ ሾፌር ነው? ጆርጅ ሶሮስ ከፖለቲከኞች አፍ የሚጠፋ ስም አይደለም። አምባገነኖች በተለይ ይፈሩታል። የእነዚህ አምባገነኖች መቀመጫ እሲያም ይሁን አፍሪካ፣ ምሥራቅ አውሮፓም ይሁን ደቡብ አሜሪካ ወይም መካከለኛው ምሥራቅ... ብቻ መንግሥታቱ ከሚነሳባቸው ተቃውሞ ጀርባ የቢሊየነሩ ጆርጅ ሶሮስ እጅ እንዳለበት ይገምታሉ። እውነት አላቸው? ለመሆኑ ይሄ ለግራ ዘመም ፖለቲከኞች ብር ይረጫል የሚባለውና በልግስናው ስመ ገናናው ጆርጅ ሶሮስ ማን ነው? ትውልደ ሀንጋሪያዊ-አሜሪካዊው ሶሮስ የተወለደው በቡዳፔስት በ1930 ዎቹ መጀመርያ ከአይሁድ ቤተሰብ ነበር። እንዲያውም "ጆርጂዮ ሽዋትዝ" ነበር የቀድሞ ስሙ። በጊዜው በአውሮፓ በአይሁዳዊያን ላይ በነበረው ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት አባቱ ከግድያ ለማምለጥ፣ ቤተሰባቸውንም ለመታደተግ እንዲረዳቸው ሲሉ ነው የቤተሰባቸውን ስም ከሽዋትዝ ወደ "ሶሮስ" የቀየሩት። ስሙን መቀየር ብቻም ሳይሆን በተለይ ለጆርጅ አዲስ ማንነትና መታወቂያ ተዘጋጅቶለት ልክ አይሁድ ያልሆነ ሌላ አንድ ተራ የቤተሰብ አባል ተደርጎ እንዲኖር ተደረገ። በዚህም ያንን አስቸጋሪ ዘመን መሻገር ቻለ። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ ሶሮስ በ14 ዓመቱ የአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ልጅ እንደሆነ ተደርጎ መታወቂያ ወጥቶለት ለጥቂት ሳይገደል ቀርቷል። ሶሮስ ከግድያዎች ያምልጥ እንጂ በዚህ ወቅት የአይሁዶች ንብረት ሲዘረፍ፣ ክብራቸው ሲገፈፍ ዓይኑ በብረቱ ተመልክቷል። በዚያ ዘመን፣ በተለይም በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ግማሽ ሚሊዮን የሀንጋሪ አይሁዶች እንዲገደሉ የሆነው 8 ሳምንታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር። እንዲያውም በመላው ዓለም ካሉ አገራት እንደ ሀንጋሪ አይሁዶች በአጭር ጊዜ በስፋት የተረሸኑበት አገር የለም ይባላል፤ ወላ በጀርመንም ቢሆን። ሶሮስ ከናዚዎች ግድያ ተርፎ እፎይ ብሎ መኖር ሲጀምር ሀንጋሪ ወደ ኮምኒስት አገርነት ተለወጠች፤ ሌላ ፈተና። በዚህ ጊዜ ነበር ገና በ17 ዓመቱ ከቡዳፔስት ወደ ለንደን የሸሸው። ጎረምሳው ሶሮስ እንግሊዝ እንደገባ የሻይ ቤት አስተናጋጅ ሆነ። ከዚያም የባቡር አውራጅና ጫኝ ሆነ። ቀጥሎ ዩኒቨርስቲ ገባና ከዝነኛው የለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ በምጣኔ ሀብት ዘርፍ ዲግሪ ያዘ። እዚያ ዩኒቨርስቲ ሳለ ነበር አስተሳሰቡን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የለወጠለትን ሰው ያገኘው። ይህ ሰው ፈላስፋው ሰር ካርል ሬይመንድ ፖፐር ነበር። ፈላስፋው ፖፐር ልክ እንደ ሶሮስ ሁሉ አይሁድ ስደተኛ ነው። ኦስትሪያዊ አይሁድ። ጆርጅ ሶሮስ አስተሳሰቡ የተጠረበው በዚህ መምህሩ እንደሆነ ይታመናል። • ሐኪሞች ለቀዶ ህክምና የሚጠቀሙበት የናዚ መፅሐፍ የዚህ መምህሩ በፖለቲካ ፍልስፍና ዓለም የናጠ ሥራው "The open society and its enemies" ይሰኛል። ከዚህ ከመምህሩ የጥናት ሥራ በተወሰደ ስም ነው ኋላ ጆርጅ ሶሮስ ዓለም ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ ድርጅቱን የመሠረተው፤ ስሙም "ኦፕንሶሳይቲ ፋውንዴሽን" ይባላል። ብቻ ከዚህ በኋላ ጆርጅ ሶሮስ በ1970 የሶሮስ ፈንድን አቋቋመ። እሱን ዓለም የሚያውቀው ግን በሁለት ነገር ነው፤ አንዱ እሱ አምጦ በወለደውና ቀደም ሲል በጠቀስነው "ኦፕን ሶሳይቲ" በሚባለው ድርጅቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የእንግሊዝን ባንክ በእንብርክክ በማስኬዱ ነው። ከሁለተኛው እንጀምር... በ1992 እንግሊዞች "ጥቁሩ ረቡዕ" (ብላክ ወይንስዴይ) ብለው የሚያውቁት ታሪክ አለ። ብሪታኒያ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ የገባችበት አስገራሚ ቀን ነው። ይህ ቀን ለብሪታኒያ ጥቁር ነበር ካልን ለጆርጅ ሶሮስ ግን ነጭ ነበር፤ የእርሱ የብልጽግና በር የተከፈተው በዚች ቀን ነበር ማለት ይቻላል። ነገሩን በአጭሩ ለማስረዳት፡ ብዙዎቹ የአውሮፓ አገራት ዩሮን ወይም እሱን የሚመስል የጋራ ገንዘብ ለመፍጠር እያለሙ ነበር።ይህን መንገድ የሚጠርግ The European Exchange Rate Mechanism (ERM) የሚባል ህብረት ነበራቸው። ይህንን ለማሳካት ደግሞ አባል አገራት የገንዘባቸው ጥንካሬ ከተወሰነ መጠን ዝቅ እንዳይል ይጠበቅባቸው ነበር። የብሪታኒያ መንግሥት የሚገበያይበት ፖውንድ ስተርሊንግ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል የወለድ ምጣኔን ከፍ በማድረግ ጭምር ሞከረ። ሆኖም አልተሳካም። በዚህ ታሪካዊ ቀን እንግሊዝ ገንዘቧን ፓውንድን ከመውደቅ ማዳን አቃታት፤ ስላቃታትም ከአውሮፓ አገራት የውጭ ምንዛሬ መወሰኛ ኅብረት (ERM) ለመውጣት ተገደደች። ይህ "ጥቁሩ ረቡዕ" ብሪታኒያ ብሔራዊ ኪሳራን በአገር ደረጃ ያወጀችበት ዕለት ነበር። ጆርጅ ሶሮስ ከዚህ ቀን ቀደም ብሎ የፓውንድ መውደቅ አይቀሬ እንደሆነ በመተንበይ ፓውንድ አብዝቶ ከባንኮች ይበደር ነበር። በርካታ ፓውንድ እየተበደረ መልሶ ከባንክ ውጭ በርካሽ ይሸጠዋል። በተከታታይ ፓውንድ ዝቅ ባለ ዋጋ በመሸጥ ሌላ የገንዘብ ኖት በማከማቸቱ (በተለይም የጀርመን ማርክን) ብቻ በትንሹ በአንድ ቀን 1 ቢሊየን ዶላር ማትረፍ ችሏል። በዚህም የተነሳ ጆርጅ ሶሮስ "የእንግሊዝን ባንክ የያንበረከከው ሰው" በመባል ይታወቃል። ጆርጅ ሶሮስ በዚያ ዓመት እንግሊዝን 3.3 ቢሊዮን ፓውንድ አክስሯታል፤ በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ እንግሊዛዊ በተናጥል 15 ፓውንድ ለሶሮስ ከፍሏል ማለት ነው። በእንዲህ ዓይነት አስቀድሞ የገንዘብ ጥንካሬን በመተንበይ በዓመታት ውስጥ በበርካታ አገራት ውስጥ ቢሊዮን ዶላር ማጋበስ እንደቻለ ይነገርለታል፤ ሶሮስ። እንደ ፈረንጆቹ በ1979 የተመሠረተው ኦፕን ሶሳይቲ በአሁኑ ጊዜ በ120 አገራት እየሠራ ነው። በኢትዮጵያም ቢሮ ለመክፈት በሂደት ላይ እንደነበር አንድ ሰሞን መዘገቡ ይታወሳል። የአገር ቤቱ ሪፖርተር ጋዜጣ የእንግሊዝኛው ቅጂ በፈረንጆች ኅዳር 30 እትሙ እንደዘገበው ደግሞ ኦፕን ሶሳይቲ እገዛ ሊያደርግላቸው ካሰባቸው ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች መሀል አዲስ ስታንዳርድ የድረገጽ ጋዜጣና አዲስ ፎርቹን የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ይገኙበታል። ሁለቱ ሚዲያዎች ከ160 እስከ 200ሺህ ዶላር እንደሚለገሳቸውም ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። ሪፖርተር በዚሁ ዘገባው የድርጅቱን ኃላፊ ሩት ኦሜንዲን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ ኦፕንሶሳይቲ በቅርብ ጊዜ ቢሮውን አዲስ አበባ ይከፍታል። እስከዛሬ እውን አልሆነም። • የወንድ የዘር ፍሬን ልክ እንደ ዓይን፣ ኩላሊት መለገስ ይቻላልን? ሊበራል ዲሞክራሲን በማስፋፋት የተጠመደው ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን የብዙ አገሮች ራስ ምታት መሆኑ አልቀረም። በተለይ አገራት ወደ ዲሞክራሲ እንዲሸጋገሩ "አመጾችን ለማቀጣጠል የሚውል ገንዘብ ይረጫል" የሚባለው ኦፕን ሶሳይቲ በሰብአዊ መብትና በትምህርት ላይ ያሳደረው የላቀ አስተዋጽኦ የሚካድ አይደለም። ሚስተር ጆርጅ ሶሮስ ለሴራ ፖለቲካ ለመጀርመያ ጊዜ የተጋለጠው በ1990ዎቹ መጀመርያ ቢሆንም በተለይ በ2003 የኢራቅ ጦርነትን መቃወሙ በሪፐብሊካኖች ዘንድ ጥርስ እንዲነከስበት ሆኗል። "ያለኝን ሀብት በሙሉ ጆርጅ ቡሽን ለማስወገድ ብጠቀምበት አይቆጨኝም" ማለቱ ብዙ ሲያነጋግር ነበር፤ በዚያ ዘመን። ሶሮስ በ2018ቱ የአሜሪካ ምርጫም በተመሳሳይ ገንዘቡን ረጭቷል ተብሎ ይነገራል። ከባራክ ኦባማ መመረጥ ጀርባ ትልቁ ገንዘብ የሶሮስ ነው ተብሎም ይታመናል። እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት ፍቺ እንዳትፈጽም ለሚተጋ ቡድን ወደ 800 ሚሊዮን ዶላር ለግሷል። የጆርጅ ሶሮስ ስምን ገናና ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ የቅርቡ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የነበረው ፍጥጫ ነው። ዶናልድ ትራምፕን የሚያወግዙ ማናቸውም ሰልፎችን በከፍተኛ ገንዘብ ይደግፋል የሚባለው ሶሮስ፤ ከሆንዱራስ ተነስተው በሜክሲኮ አድርገው ወደ አሜሪካ በእግር የዘመቱ ሥራ አጦችን ያዘመተብን እሱ ነው የሚል ክስ ይቀርብበታል። ውግንናው ለትራምፕ እንደሆነ የሚነገርለት ፎክስ ኒውስ በተከታታይ በሰራቸው ዘገባዎች ጆርጅ ሶሮስ ሁሉም የአገራት ድንበሮች እንዲከፈቱና በሕዝቦች መካከል ያልተገደበ ዝውውር እንዲኖር ይሻል ሲል ከሶታል። ዶናልድ ትራምፕም በትዊተር ሰሌዳቸው ገንዘብ ለስደተኞች ሲታደል የሚያሳይ ቪዲዮ በመለጠፍ የገንዘቡ ምንጭ ሶሮስ እንደሆነ ለማመላከት ሞክረዋል። "ዱርዬዎች የአሜሪካንን ድንበር እንዲሰብሩ እየተከፈላቸው ነው" በሚል። በኋላ ጋዜጠኞች እንዳጣሩት ከሆነ ግን ትራምፕ ያጋሩት ቪዲዮ በጭራሽ በሆንዱራስ እንዳልተቀረጸና የቪዲዮው ምንጭም ጓቲማላ እንደሆነች ማረጋገጥ ችለዋል። ትራምፕ ግን ይህ ግድ አልሰጣቸውም። ከዚህ ትራምፕ ካራገቡት የሴራ ፖለቲካ በኋላም በአይሁዳዊያን ላይ የደረሰውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የሶሮስ ስም በድጋሚ አንሰራራ። በዚህ ጥቃት አንድ ነጭ የአይሁዶች ምኩራብ ውስጥ ገብቶ 11ዱን ከፈጀ በኋላ ግለሰቡ ጆርጅ ሶሮስ የላከው ተደርጎ ሲዘገብ ነበር። ኋላ ላይ ሲጣራ ግን እንዲያውም ወንጀለኛው የጆርጅ ሶሮስ ቀንደኛ ጠላት እንደሆነ ተደርሶበታል። • በኢትዮጵያ ካምፕ ውስጥ ባለ2 ፎቅ መኖሪያ የገነባው ስደተኛ ይህ አክራሪ ነጭ ሽብርተኛ ጽፎታል በተባለ ምሥጢራዊ ሰነድ ማወቅ እንደተቻለው "ጆርጅ ሶሮስ ቀስ በቀስ የነጮችን የበላይነት በአሜሪካና በአውሮፓ ለማጥፋት የሚሰራ ጠላት ነው" ብሎ ያምን ነበር። ይህ አክራሪ ነጭ ሽብርተኛ የታወረበት የሴራ ፖለቲካ እንደሚያትተው ዓለም ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ነጮችን የማዳከምና የነጮችን አገር በጥቁር ስደተኞች ቀስ በቀስ የመሙላት ሐሳብ አለ፤ ይህን ሐሳብ በገንዘብ የሚደግፈው ሰው ደግሞ ጆርጅ ሶሮስ ይባላል። ያንን ጥቃት እንዲያደርስ የተገፋፋውም ይህንን የጆርጅ ሶሮን እንቅስቃሴ ለመግታት ነው። የዶናልድ ትራምፕ ሰዎች እጅግ ከማይወዷቸው ቢሊየነሮች ግንባር ቀደሙ ጆርጅ ሶሮስ ነው። በትራምፕ ወዳጆች ዘንድም ሶሮስ ላይ ከባድ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶበት ነበር። "ሶሮስ ናዚ ነው"፤ "ኦባማና ሂላሪ የሶሮስ አሻንጉሊቶች ናቸው"፤ "አሜሪካን ለማፍረስ የሚተጋው አይሁድ ጠሉ ጆርጅ ሶሮስ ነው" የሚሉ ወሬዎች ኢንተርኔቱን ሞልተውት ነበር አንድ ሰሞን። • የወንድ የዘር ፍሬን ልክ እንደ ዓይን፣ ኩላሊት መለገስ ይቻላልን? የጦር መሣሪያ ቁጥጥር እንዲጠብቅ፤ ጸረ ትራምፕ ሰልፎች እንዲፋፋሙ እንዲሁም የፍሎሪዳ ጥቃትን ተከትሎ የተደረገው "ማርች ፎር አወር ላይቭስ ሙቭመንት" በሶሮስ ገንዘብ የተቀነባበሩ እንደሆነ ይታመናል። የትራምፕ ተቺዎችን ለመግደል ያለመ የጥቅል ፖስታ ቦምብ እደላ በተደረገበት ወቅትም በቁጥር አንድ የትራምፕ ጠላትነት የተፈረጀው ሶሮስ ነበር። ከመካከለኛው አሜሪካ ኑሮ መረረን ያሉ ስደተኞች ወደ አሜሪካ የእግር ጉዞ ሲጀምሩ ትራምፕ የግምብ አጥሩን ቶሎ እንገንባው በሚሉበት ወቅት ይህንን የሕዝቦች ስደትን የሚደግፈው ጆርጅ ሶሮስ ነው የሚሉ ወሬዎች መነዛት ጀምሩ። ትራምፕም ይህንኑ እንደሚጠረጥሩ ተናግረዋል። "እሱ ነው ቢሉኝ አልደነቅም፤ እሱ ስለመሆኑ አላውቅም፤ እሱ እንደሚሆን ግን እገምታለሁ፤ አያስደንቀኝም" ብለው ነበር ዶናልድ ትራምፕ ለጋዜጠኞች። የትራምፕ ልጅ በተዋናይት ሮሰን ባር የትዊተር ሰሌዳ ስለ ሶሮስ የተጻፈውን መራር ጥላቻ ማጋራቱም ምን ያህል ሶሮስ በነ ትራምፕ ቤተሰብ የማይወደድ ቢሊየነር እንደሆነ መገመት አስችሏል። ተዋናይት ባር የጻፈችውና የትራምፕ ልጅ ያጋራው ጽሑፍ እንዲህ ይላል። • ወደ ለንደን የሚሄደው አስደናቂው የትራምፕ ጓዝ "በነገራችሁ ላይ ጆርጅ ሶሮስ ናዚ ነው። የገዛ አይሁድ ጓደኛውን በጀርመን ማጎርያ ካምፕ ውስጥ አስገድሎ ገንዘቡን የዘረፈ ናዚ" ይህን ተከትሎ የሶሮስ ቃል አቀባይ "እንዲህ ዓይነት መሠረተ ቢስ ክሶች በሶሮስ ሳይሆን በመላው አይሁድ ሕዝብ ላይ የተቃጡ ስድቦች ናቸው፤ በተለይም በጅምላ ፍጅቱ ተጠቂዎች ላይ..." ብሏል። እርግጥ ነው ሶሮስ አገሮች ነጻ እንዲሆኑ፤ የሕዝቦች ነጻ እንቅስቃሴ እንዲኖር ይተጋል። ይህ ግን አገሮች ድንበር አይኑራቸው ከሚል ጽንሰ ሐሳብ የሚመነጭ አይደለም። የጆርጅ ሶሮስ ተቺዎች ሶሮስ በአገራት የውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ ይገባል፤ እጁም ረዥም ነው ይሉታል። እርግጥ ነው ለሂላሪና ለኦባማ የምርጫ ዘመቻ ትልቁን ገንዘብ ስለመስጠቱ የሚካድ አይደለም። ይህ ተግባሩ ግን በአሜሪካ ብቻ የሚወሰን አልሆነም። ሶሮስ በ1980ዎቹ የሀንጋሪ ኮምኒስቶችን ለማዳከም ገንዘቡን አውሎታል። ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን ለዲሞክራሲ እሴቶች የሚተጋ ነው። በዓመታት ውስጥ ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር ለዚህ ድርጅቱ ፈሰስ አድርጓል ሶሮስ። ይህ ገንዘብ በምንም መለኪያ ትንሽ አይደለም። • ትራምፕ ስለስደተኞች በተናገሩት ወቀሳ ደረሰባቸው "ይህን ድርጅት ያቆምኩት አስተማማኝ ዲሞክራሲን በመላው ዓለም ለመዘርጋት ነው" ይላል፤ እሱም ቢሆን። ሶሮስ በትውልድ አገሩ ሀንጋሪ ቢሊዮን ዶላሮችን በማፍሰስ የሰብአዊ መብት ፕሮጀክቶችንና በትምህርት ቤቶች ነጻ የምግብ እደላዎች እንዲኖሩ አስችሏል። ከሁሉም በላይ በኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ጭምር ዝነኛ የሆነውና የውጭ የትምህርት ዕድል በመስጠት የሚታወቀው የሴንትራል ዩሮፒያን ዩኒቨርስቲን (CEU) የመሠረተው ጆርጅ ሶሮስ ነው። "አንዳንድ ጊዜ ትልቅ ለማይመስሉ ነገር ግን ለምናምንባቸው ነገሮች መቆም አለብን" ይላል ሶሮስ። ከእነዚህ መሀል አንዱ በስደተኞች ላይ ያለው አቋሙ ነው። በአውሮፓ የሚገኙ ስደተኞችን ለማገዝ የሚተጋው ሶሮስ ከበርካታ አገራት መንግሥታት ጥላቻን አትርፏል። "የነጮች አህጉር የሆነችውን አውሮፓን በስደተኛ ልታጥለቀልቃት ነው ሀሳብህ" የሚል ክስ ይነሳበታል። እሱም "በስደተኛ ላይ ያለኝ አቋም ብዙ ጠላት አፍርቶልኛል" ይላል። • ማሽተት አለመቻል ምን ይመስላል? ለምሳሌ የገዛ ትውልድ አገሩ ሀንጋሪ ለሶሮስ ያላትን ጥላቻ በጎዳና ላይ ቢልቦርድ ጭምር ሰቅላዋለች። አሁን ያለው የሀንጋሪያዊያን መንግሥት በአመዛኙ ጥቁር ጠል የሚባል ነው። በሀንጋሪ ለስደተኞቸ ድጋፍ የሰጠ ዜጋ በእስር ይቀጣል። የሚደንቀው ታዲያ የዚህን የቅጣት ሕግ ስም ሳይቀር የሃንጋሪ መንግሥት "ስቶፕ ሶሮስ" ብሎ ነው የሚጠራው። ያው ስደተኞችን እያጋዘ የሚያመጣብን ጆርጅ ሶሮስ ነው በሚል። የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የሶሮስ ቀንደኛ ጠላት ናቸው። በስሎቫኪያ የጋዜጠኛ መገደልን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ የተደናገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ወቅት ባደረጉት ንግግር፡ "ይሄ የጆርጅ ሶሮስ እጅ ነው። በስሎቫኪያ የተነሳው ነውጥ የሶሮስ ሥራ ነው። እሱ ስደተኛ እንዳይመጣባቸው ለሚፈልጉ አገራት አይራራም። የጎዳና ላይ ነውጥ እያስነሳ ይገለብጣቸዋል" ብለው ነበር። ጆርጅ ሶሮስ ከአፍሪካ እስከ ምሥራቅ አውሮፓ፣ ከትራምፕ እስከ ሞዲ ስለሱ የሚባለውን ሲሰማ ምን ይላል? በእርግጥ የዓለም ፖለቲካን የሚዘውረው ሰው ጆርጅ ሳሮስ ነው? "የእኔ እጅ ረዥም እንደሆነ የሚነገረው የተጋነነ ነው። እንደሚባለው የእንግሊዝ ባንክን አላንኮታኮትኩትም። ገበያው ነው ያንኮታኮተው። እንደሚባለው ስደተኛን እያጋዝኩ ወደ አውሮፓና አሜሪካ አላስኮበልልም። ኦፕን ሶሳይቲን የመሠረትኩት ዲሞክራሲንና የዲሞክራሲ ተቋማትን ለማጎልበት ነው" ይላል። ጆርጅ ሳሮስ እንደ ትራምፕ የሚንቀው ሰው ያለ አይመስልም። "ትራምፕ አታላይና በራሱ ፍቅር የናወዘ ሰው ነው" ይላል። ትራምፕን ብሔራዊ ጥቅምን ሳይቀር ለግል ስምና ዝናው አሳልፎ ለመስጠት የማይሳሳ ነው ይለዋል። የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዠን ፒንግን ደግሞ በቴክኖሎጂ መላ ሕዝቡን ለመቆጣጠር የሚሞክር አምባገነን ይለዋል። ዓለማችን ሁለቱን መሪዎች ብታስወግድ የተሻለ እንኖር ነበር ይላል ሶሮስ። ሶሮስ በስዊዘርላንድ ዳቮስ በቅርቡ ባደረገው ንግግር ዘረኝነት በአገራት እየተስፋፋ መምጣቱ እንደሚያሳስበው ተናግሯል። ጥላቻ እንዳይነግስ ለሚሰሩ፣ የመቻቻል ፕሮጀክቶችን ለማጎልበት ደግሞ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 1 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ቃል ገብቷል። በዘረኞችና በሀሰት ወሬ አራጋቢዎች የምትሾረው ዓለም ለሶሮስ ታሳስበዋለች። ክሪቲካል ቲንኪንግ ወይም ምክንያታዊነትን ቶሎ ካላስፋፋን መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው ይላል ሶሮስ። ከመሞቴ በፊት ማድረግ ይመፍልገውም ይህንን ነው። | በአንድ ቀን 1 ቢሊዮን ዶላር ያተረፈው ጆርጅ ሶሮስ ማን ነው? አንድ የደበተው ሰኞ ከሰዓት፤ በ2019 ኅዳር ወር ላይ መሆኑ ነው፣ ምንነቱ ያልታወቀ የፖስታ ጥቅል በኒውዮርክ የባለጸጎች መንደር በሚገኝ አንድ ግዙፍ ቤት ተቀመጠ፤ ደጅ የፖስታ ሰንዱቅ ውስጥ። ጥቅሉ አጠራጣሪ ነገሮች ነበሩት። አንደኛ የተመላሽ ስም በትክክል አልተጻበትም። ሁለተኛ በተላከበት ቀን ነው የደረሰው። ፖሊስ ተጠራጠረ፤ ኤፍቢአይ ተጠራ። የጆርጅ ሶሮስ ቪላ ተወረረ። • የዓለማችን ቁጥር አንድ ሃቀኛዋ ሃገር በዚያ ጥቅል ውስጥ የሶሮስ ፎቶ ነበር፤ ከፊት ለፊት የይገደል ምልክት ተጽፎበታል። 6 ኢንች የሚረዝም የፕላስቲክ ጎማ፣ ቁልቁል የሚቆጥር ሰዓት፣ ባትሪና የኤሌክትሪክ ሽቦዎች ነበሩበት፤ በጥቅሉ ፖስታ። ተመሳሳይ ጥቅል ወደ ኦባማና ሂላሪ ቤት ተልኳል። ደግነቱ አንዱም አልፈነዳም፤ ፖሊስ አክሽፎታል። ቀኝ ዘመም የአሜሪካ ሚዲያ ቶሎ ጣቱን የቀሰረው ወደ ሶሮስ ነበር። ራሱ ሶሮስ የሸረበው ሸር ነው በሚል። ሶሮስ እንዴት አድርጎ ወደ ራሱ ቦምብ ይልካል? ጥሩ ጥያቄ ነው። ነገር ግን የትራምፕ አክራሪ ደጋፊዎች በአመዛኙ ለርትዕ ፊት አይሰጡም ይባላል፤ ለፖለቲካ ተዋስኦ ክፍት አይደሉም፤ አመክንዮ ይቀፋቸዋል። የትራምፕ ደጋፊዎች የሚቀናቸው ሴራ ነው። የአሻጥር ፖለቲካ የነጭ አክራሪዎች ኦፒየም ነው። ስለዚህም አደባባይ ወጡ። ጆርጅ ሶሮስን ሊያወግዙ። "ትራምፓችን ሆይ! ሶሮስን እሰር! ሶሮስን ዘብጥያ አውርድልን" የሚል ድምጽ በዋይት ሃውስ ደጅ ላይ አስተጋባ። ደግነቱ ፖሊስ ቦምቦቹን በጥቅል የላከውን ሰው ደረሰበት። የ56 ዓመቱ የፍሎሪዳ ነዋሪ ሲዛር ሳዮክ ነበር። ሰውየው እንዲያውም ብዙዎች እንደገመቱት ሪፐብሊካን አልነበረም። ቤት ለቤት ፒዛ አዳይ እንጂ። • በትራምፕ የድጋፍ ደብዳቤ ወደ አሜሪካ ያቀናችው የአሲድ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያዊት ሆኖም አእምሮው በሴራ ፖለቲካ ናውዞ ነበር። እንደ ብዙዎቹ ቀኝ አክራሪዎች። ከሁሉም ፖለቲካ ጀርባ ጆርጅ ሶሮስ የሚባል ሰው አለ ብሎ ያምን ነበር፤ ሶሮስ የነጭ የበላይነትን ሊያጠፋ የተነሳ ጠላት ነው ብሎ ያስብ ነበር፤ የትራምፕ ጠላት ነው ብሎ ያምን ነበር፤ ስለዚህ መገደል አለበት በሚል ነው ቦምቡን በፖስታ የላከው። የዚህ ወንጀለኛ ፌስቡክ ሲበረበር ደግሞ ሌላ ጉድ ተገኘ። "ዓለም ከእንቅልፉ ሲነቃ የሶሮስን አሳዛኝ ዜና ይሰማል!" ይህ ግለሰብ ለጊዜው 20 ዓመት እስር ተከናንቧል። ጆርጅ ሶሮስ ግን አሁንም የሴራ ፖለቲካ ገፈት ቀማሽ እንደሆነ አለ። ከሁሉም የዓለም ፖለቲካ ለውጥ ጀርባ የሶሮስ እጅ አለ የሚል አስተሳሰብ ናኝቷል። ለመሆኑ ሶሮስ እንደሚገመተው የዓለም የአሻጥር ፖለቲካ ሾፌር ነው? ጆርጅ ሶሮስ ከፖለቲከኞች አፍ የሚጠፋ ስም አይደለም። አምባገነኖች በተለይ ይፈሩታል። የእነዚህ አምባገነኖች መቀመጫ እሲያም ይሁን አፍሪካ፣ ምሥራቅ አውሮፓም ይሁን ደቡብ አሜሪካ ወይም መካከለኛው ምሥራቅ... ብቻ መንግሥታቱ ከሚነሳባቸው ተቃውሞ ጀርባ የቢሊየነሩ ጆርጅ ሶሮስ እጅ እንዳለበት ይገምታሉ። እውነት አላቸው? ለመሆኑ ይሄ ለግራ ዘመም ፖለቲከኞች ብር ይረጫል የሚባለውና በልግስናው ስመ ገናናው ጆርጅ ሶሮስ ማን ነው? ትውልደ ሀንጋሪያዊ-አሜሪካዊው ሶሮስ የተወለደው በቡዳፔስት በ1930 ዎቹ መጀመርያ ከአይሁድ ቤተሰብ ነበር። እንዲያውም "ጆርጂዮ ሽዋትዝ" ነበር የቀድሞ ስሙ። በጊዜው በአውሮፓ በአይሁዳዊያን ላይ በነበረው ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት አባቱ ከግድያ ለማምለጥ፣ ቤተሰባቸውንም ለመታደተግ እንዲረዳቸው ሲሉ ነው የቤተሰባቸውን ስም ከሽዋትዝ ወደ "ሶሮስ" የቀየሩት። ስሙን መቀየር ብቻም ሳይሆን በተለይ ለጆርጅ አዲስ ማንነትና መታወቂያ ተዘጋጅቶለት ልክ አይሁድ ያልሆነ ሌላ አንድ ተራ የቤተሰብ አባል ተደርጎ እንዲኖር ተደረገ። በዚህም ያንን አስቸጋሪ ዘመን መሻገር ቻለ። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ ሶሮስ በ14 ዓመቱ የአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ልጅ እንደሆነ ተደርጎ መታወቂያ ወጥቶለት ለጥቂት ሳይገደል ቀርቷል። ሶሮስ ከግድያዎች ያምልጥ እንጂ በዚህ ወቅት የአይሁዶች ንብረት ሲዘረፍ፣ ክብራቸው ሲገፈፍ ዓይኑ በብረቱ ተመልክቷል። በዚያ ዘመን፣ በተለይም በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ግማሽ ሚሊዮን የሀንጋሪ አይሁዶች እንዲገደሉ የሆነው 8 ሳምንታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር። እንዲያውም በመላው ዓለም ካሉ አገራት እንደ ሀንጋሪ አይሁዶች በአጭር ጊዜ በስፋት የተረሸኑበት አገር የለም ይባላል፤ ወላ በጀርመንም ቢሆን። ሶሮስ ከናዚዎች ግድያ ተርፎ እፎይ ብሎ መኖር ሲጀምር ሀንጋሪ ወደ ኮምኒስት አገርነት ተለወጠች፤ ሌላ ፈተና። በዚህ ጊዜ ነበር ገና በ17 ዓመቱ ከቡዳፔስት ወደ ለንደን የሸሸው። ጎረምሳው ሶሮስ እንግሊዝ እንደገባ የሻይ ቤት አስተናጋጅ ሆነ። ከዚያም የባቡር አውራጅና ጫኝ ሆነ። ቀጥሎ ዩኒቨርስቲ ገባና ከዝነኛው የለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ በምጣኔ ሀብት ዘርፍ ዲግሪ ያዘ። እዚያ ዩኒቨርስቲ ሳለ ነበር አስተሳሰቡን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የለወጠለትን ሰው ያገኘው። ይህ ሰው ፈላስፋው ሰር ካርል ሬይመንድ ፖፐር ነበር። ፈላስፋው ፖፐር ልክ እንደ ሶሮስ ሁሉ አይሁድ ስደተኛ ነው። ኦስትሪያዊ አይሁድ። ጆርጅ ሶሮስ አስተሳሰቡ የተጠረበው በዚህ መምህሩ እንደሆነ ይታመናል። • ሐኪሞች ለቀዶ ህክምና የሚጠቀሙበት የናዚ መፅሐፍ የዚህ መምህሩ በፖለቲካ ፍልስፍና ዓለም የናጠ ሥራው "The open society and its enemies" ይሰኛል። ከዚህ ከመምህሩ የጥናት ሥራ በተወሰደ ስም ነው ኋላ ጆርጅ ሶሮስ ዓለም ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ ድርጅቱን የመሠረተው፤ ስሙም "ኦፕንሶሳይቲ ፋውንዴሽን" ይባላል። ብቻ ከዚህ በኋላ ጆርጅ ሶሮስ በ1970 የሶሮስ ፈንድን አቋቋመ። እሱን ዓለም የሚያውቀው ግን በሁለት ነገር ነው፤ አንዱ እሱ አምጦ በወለደውና ቀደም ሲል በጠቀስነው "ኦፕን ሶሳይቲ" በሚባለው ድርጅቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የእንግሊዝን ባንክ በእንብርክክ በማስኬዱ ነው። ከሁለተኛው እንጀምር... በ1992 እንግሊዞች "ጥቁሩ ረቡዕ" (ብላክ ወይንስዴይ) ብለው የሚያውቁት ታሪክ አለ። ብሪታኒያ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ የገባችበት አስገራሚ ቀን ነው። ይህ ቀን ለብሪታኒያ ጥቁር ነበር ካልን ለጆርጅ ሶሮስ ግን ነጭ ነበር፤ የእርሱ የብልጽግና በር የተከፈተው በዚች ቀን ነበር ማለት ይቻላል። ነገሩን በአጭሩ ለማስረዳት፡ ብዙዎቹ የአውሮፓ አገራት ዩሮን ወይም እሱን የሚመስል የጋራ ገንዘብ ለመፍጠር እያለሙ ነበር።ይህን መንገድ የሚጠርግ The European Exchange Rate Mechanism (ERM) የሚባል ህብረት ነበራቸው። ይህንን ለማሳካት ደግሞ አባል አገራት የገንዘባቸው ጥንካሬ ከተወሰነ መጠን ዝቅ እንዳይል ይጠበቅባቸው ነበር። የብሪታኒያ መንግሥት የሚገበያይበት ፖውንድ ስተርሊንግ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል የወለድ ምጣኔን ከፍ በማድረግ ጭምር ሞከረ። ሆኖም አልተሳካም። በዚህ ታሪካዊ ቀን እንግሊዝ ገንዘቧን ፓውንድን ከመውደቅ ማዳን አቃታት፤ ስላቃታትም ከአውሮፓ አገራት የውጭ ምንዛሬ መወሰኛ ኅብረት (ERM) ለመውጣት ተገደደች። ይህ "ጥቁሩ ረቡዕ" ብሪታኒያ ብሔራዊ ኪሳራን በአገር ደረጃ ያወጀችበት ዕለት ነበር። ጆርጅ ሶሮስ ከዚህ ቀን ቀደም ብሎ የፓውንድ መውደቅ አይቀሬ እንደሆነ በመተንበይ ፓውንድ አብዝቶ ከባንኮች ይበደር ነበር። በርካታ ፓውንድ እየተበደረ መልሶ ከባንክ ውጭ በርካሽ ይሸጠዋል። በተከታታይ ፓውንድ ዝቅ ባለ ዋጋ በመሸጥ ሌላ የገንዘብ ኖት በማከማቸቱ (በተለይም የጀርመን ማርክን) ብቻ በትንሹ በአንድ ቀን 1 ቢሊየን ዶላር ማትረፍ ችሏል። በዚህም የተነሳ ጆርጅ ሶሮስ "የእንግሊዝን ባንክ የያንበረከከው ሰው" በመባል ይታወቃል። ጆርጅ ሶሮስ በዚያ ዓመት እንግሊዝን 3.3 ቢሊዮን ፓውንድ አክስሯታል፤ በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ እንግሊዛዊ በተናጥል 15 ፓውንድ ለሶሮስ ከፍሏል ማለት ነው። በእንዲህ ዓይነት አስቀድሞ የገንዘብ ጥንካሬን በመተንበይ በዓመታት ውስጥ በበርካታ አገራት ውስጥ ቢሊዮን ዶላር ማጋበስ እንደቻለ ይነገርለታል፤ ሶሮስ። እንደ ፈረንጆቹ በ1979 የተመሠረተው ኦፕን ሶሳይቲ በአሁኑ ጊዜ በ120 አገራት እየሠራ ነው። በኢትዮጵያም ቢሮ ለመክፈት በሂደት ላይ እንደነበር አንድ ሰሞን መዘገቡ ይታወሳል። የአገር ቤቱ ሪፖርተር ጋዜጣ የእንግሊዝኛው ቅጂ በፈረንጆች ኅዳር 30 እትሙ እንደዘገበው ደግሞ ኦፕን ሶሳይቲ እገዛ ሊያደርግላቸው ካሰባቸው ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች መሀል አዲስ ስታንዳርድ የድረገጽ ጋዜጣና አዲስ ፎርቹን የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ይገኙበታል። ሁለቱ ሚዲያዎች ከ160 እስከ 200ሺህ ዶላር እንደሚለገሳቸውም ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። ሪፖርተር በዚሁ ዘገባው የድርጅቱን ኃላፊ ሩት ኦሜንዲን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ ኦፕንሶሳይቲ በቅርብ ጊዜ ቢሮውን አዲስ አበባ ይከፍታል። እስከዛሬ እውን አልሆነም። • የወንድ የዘር ፍሬን ልክ እንደ ዓይን፣ ኩላሊት መለገስ ይቻላልን? ሊበራል ዲሞክራሲን በማስፋፋት የተጠመደው ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን የብዙ አገሮች ራስ ምታት መሆኑ አልቀረም። በተለይ አገራት ወደ ዲሞክራሲ እንዲሸጋገሩ "አመጾችን ለማቀጣጠል የሚውል ገንዘብ ይረጫል" የሚባለው ኦፕን ሶሳይቲ በሰብአዊ መብትና በትምህርት ላይ ያሳደረው የላቀ አስተዋጽኦ የሚካድ አይደለም። ሚስተር ጆርጅ ሶሮስ ለሴራ ፖለቲካ ለመጀርመያ ጊዜ የተጋለጠው በ1990ዎቹ መጀመርያ ቢሆንም በተለይ በ2003 የኢራቅ ጦርነትን መቃወሙ በሪፐብሊካኖች ዘንድ ጥርስ እንዲነከስበት ሆኗል። "ያለኝን ሀብት በሙሉ ጆርጅ ቡሽን ለማስወገድ ብጠቀምበት አይቆጨኝም" ማለቱ ብዙ ሲያነጋግር ነበር፤ በዚያ ዘመን። ሶሮስ በ2018ቱ የአሜሪካ ምርጫም በተመሳሳይ ገንዘቡን ረጭቷል ተብሎ ይነገራል። ከባራክ ኦባማ መመረጥ ጀርባ ትልቁ ገንዘብ የሶሮስ ነው ተብሎም ይታመናል። እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት ፍቺ እንዳትፈጽም ለሚተጋ ቡድን ወደ 800 ሚሊዮን ዶላር ለግሷል። የጆርጅ ሶሮስ ስምን ገናና ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ የቅርቡ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የነበረው ፍጥጫ ነው። ዶናልድ ትራምፕን የሚያወግዙ ማናቸውም ሰልፎችን በከፍተኛ ገንዘብ ይደግፋል የሚባለው ሶሮስ፤ ከሆንዱራስ ተነስተው በሜክሲኮ አድርገው ወደ አሜሪካ በእግር የዘመቱ ሥራ አጦችን ያዘመተብን እሱ ነው የሚል ክስ ይቀርብበታል። ውግንናው ለትራምፕ እንደሆነ የሚነገርለት ፎክስ ኒውስ በተከታታይ በሰራቸው ዘገባዎች ጆርጅ ሶሮስ ሁሉም የአገራት ድንበሮች እንዲከፈቱና በሕዝቦች መካከል ያልተገደበ ዝውውር እንዲኖር ይሻል ሲል ከሶታል። ዶናልድ ትራምፕም በትዊተር ሰሌዳቸው ገንዘብ ለስደተኞች ሲታደል የሚያሳይ ቪዲዮ በመለጠፍ የገንዘቡ ምንጭ ሶሮስ እንደሆነ ለማመላከት ሞክረዋል። "ዱርዬዎች የአሜሪካንን ድንበር እንዲሰብሩ እየተከፈላቸው ነው" በሚል። በኋላ ጋዜጠኞች እንዳጣሩት ከሆነ ግን ትራምፕ ያጋሩት ቪዲዮ በጭራሽ በሆንዱራስ እንዳልተቀረጸና የቪዲዮው ምንጭም ጓቲማላ እንደሆነች ማረጋገጥ ችለዋል። ትራምፕ ግን ይህ ግድ አልሰጣቸውም። ከዚህ ትራምፕ ካራገቡት የሴራ ፖለቲካ በኋላም በአይሁዳዊያን ላይ የደረሰውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የሶሮስ ስም በድጋሚ አንሰራራ። በዚህ ጥቃት አንድ ነጭ የአይሁዶች ምኩራብ ውስጥ ገብቶ 11ዱን ከፈጀ በኋላ ግለሰቡ ጆርጅ ሶሮስ የላከው ተደርጎ ሲዘገብ ነበር። ኋላ ላይ ሲጣራ ግን እንዲያውም ወንጀለኛው የጆርጅ ሶሮስ ቀንደኛ ጠላት እንደሆነ ተደርሶበታል። • በኢትዮጵያ ካምፕ ውስጥ ባለ2 ፎቅ መኖሪያ የገነባው ስደተኛ ይህ አክራሪ ነጭ ሽብርተኛ ጽፎታል በተባለ ምሥጢራዊ ሰነድ ማወቅ እንደተቻለው "ጆርጅ ሶሮስ ቀስ በቀስ የነጮችን የበላይነት በአሜሪካና በአውሮፓ ለማጥፋት የሚሰራ ጠላት ነው" ብሎ ያምን ነበር። ይህ አክራሪ ነጭ ሽብርተኛ የታወረበት የሴራ ፖለቲካ እንደሚያትተው ዓለም ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ነጮችን የማዳከምና የነጮችን አገር በጥቁር ስደተኞች ቀስ በቀስ የመሙላት ሐሳብ አለ፤ ይህን ሐሳብ በገንዘብ የሚደግፈው ሰው ደግሞ ጆርጅ ሶሮስ ይባላል። ያንን ጥቃት እንዲያደርስ የተገፋፋውም ይህንን የጆርጅ ሶሮን እንቅስቃሴ ለመግታት ነው። የዶናልድ ትራምፕ ሰዎች እጅግ ከማይወዷቸው ቢሊየነሮች ግንባር ቀደሙ ጆርጅ ሶሮስ ነው። በትራምፕ ወዳጆች ዘንድም ሶሮስ ላይ ከባድ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶበት ነበር። "ሶሮስ ናዚ ነው"፤ "ኦባማና ሂላሪ የሶሮስ አሻንጉሊቶች ናቸው"፤ "አሜሪካን ለማፍረስ የሚተጋው አይሁድ ጠሉ ጆርጅ ሶሮስ ነው" የሚሉ ወሬዎች ኢንተርኔቱን ሞልተውት ነበር አንድ ሰሞን። • የወንድ የዘር ፍሬን ልክ እንደ ዓይን፣ ኩላሊት መለገስ ይቻላልን? የጦር መሣሪያ ቁጥጥር እንዲጠብቅ፤ ጸረ ትራምፕ ሰልፎች እንዲፋፋሙ እንዲሁም የፍሎሪዳ ጥቃትን ተከትሎ የተደረገው "ማርች ፎር አወር ላይቭስ ሙቭመንት" በሶሮስ ገንዘብ የተቀነባበሩ እንደሆነ ይታመናል። የትራምፕ ተቺዎችን ለመግደል ያለመ የጥቅል ፖስታ ቦምብ እደላ በተደረገበት ወቅትም በቁጥር አንድ የትራምፕ ጠላትነት የተፈረጀው ሶሮስ ነበር። ከመካከለኛው አሜሪካ ኑሮ መረረን ያሉ ስደተኞች ወደ አሜሪካ የእግር ጉዞ ሲጀምሩ ትራምፕ የግምብ አጥሩን ቶሎ እንገንባው በሚሉበት ወቅት ይህንን የሕዝቦች ስደትን የሚደግፈው ጆርጅ ሶሮስ ነው የሚሉ ወሬዎች መነዛት ጀምሩ። ትራምፕም ይህንኑ እንደሚጠረጥሩ ተናግረዋል። "እሱ ነው ቢሉኝ አልደነቅም፤ እሱ ስለመሆኑ አላውቅም፤ እሱ እንደሚሆን ግን እገምታለሁ፤ አያስደንቀኝም" ብለው ነበር ዶናልድ ትራምፕ ለጋዜጠኞች። የትራምፕ ልጅ በተዋናይት ሮሰን ባር የትዊተር ሰሌዳ ስለ ሶሮስ የተጻፈውን መራር ጥላቻ ማጋራቱም ምን ያህል ሶሮስ በነ ትራምፕ ቤተሰብ የማይወደድ ቢሊየነር እንደሆነ መገመት አስችሏል። ተዋናይት ባር የጻፈችውና የትራምፕ ልጅ ያጋራው ጽሑፍ እንዲህ ይላል። • ወደ ለንደን የሚሄደው አስደናቂው የትራምፕ ጓዝ "በነገራችሁ ላይ ጆርጅ ሶሮስ ናዚ ነው። የገዛ አይሁድ ጓደኛውን በጀርመን ማጎርያ ካምፕ ውስጥ አስገድሎ ገንዘቡን የዘረፈ ናዚ" ይህን ተከትሎ የሶሮስ ቃል አቀባይ "እንዲህ ዓይነት መሠረተ ቢስ ክሶች በሶሮስ ሳይሆን በመላው አይሁድ ሕዝብ ላይ የተቃጡ ስድቦች ናቸው፤ በተለይም በጅምላ ፍጅቱ ተጠቂዎች ላይ..." ብሏል። እርግጥ ነው ሶሮስ አገሮች ነጻ እንዲሆኑ፤ የሕዝቦች ነጻ እንቅስቃሴ እንዲኖር ይተጋል። ይህ ግን አገሮች ድንበር አይኑራቸው ከሚል ጽንሰ ሐሳብ የሚመነጭ አይደለም። የጆርጅ ሶሮስ ተቺዎች ሶሮስ በአገራት የውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ ይገባል፤ እጁም ረዥም ነው ይሉታል። እርግጥ ነው ለሂላሪና ለኦባማ የምርጫ ዘመቻ ትልቁን ገንዘብ ስለመስጠቱ የሚካድ አይደለም። ይህ ተግባሩ ግን በአሜሪካ ብቻ የሚወሰን አልሆነም። ሶሮስ በ1980ዎቹ የሀንጋሪ ኮምኒስቶችን ለማዳከም ገንዘቡን አውሎታል። ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን ለዲሞክራሲ እሴቶች የሚተጋ ነው። በዓመታት ውስጥ ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር ለዚህ ድርጅቱ ፈሰስ አድርጓል ሶሮስ። ይህ ገንዘብ በምንም መለኪያ ትንሽ አይደለም። • ትራምፕ ስለስደተኞች በተናገሩት ወቀሳ ደረሰባቸው "ይህን ድርጅት ያቆምኩት አስተማማኝ ዲሞክራሲን በመላው ዓለም ለመዘርጋት ነው" ይላል፤ እሱም ቢሆን። ሶሮስ በትውልድ አገሩ ሀንጋሪ ቢሊዮን ዶላሮችን በማፍሰስ የሰብአዊ መብት ፕሮጀክቶችንና በትምህርት ቤቶች ነጻ የምግብ እደላዎች እንዲኖሩ አስችሏል። ከሁሉም በላይ በኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ጭምር ዝነኛ የሆነውና የውጭ የትምህርት ዕድል በመስጠት የሚታወቀው የሴንትራል ዩሮፒያን ዩኒቨርስቲን (CEU) የመሠረተው ጆርጅ ሶሮስ ነው። "አንዳንድ ጊዜ ትልቅ ለማይመስሉ ነገር ግን ለምናምንባቸው ነገሮች መቆም አለብን" ይላል ሶሮስ። ከእነዚህ መሀል አንዱ በስደተኞች ላይ ያለው አቋሙ ነው። በአውሮፓ የሚገኙ ስደተኞችን ለማገዝ የሚተጋው ሶሮስ ከበርካታ አገራት መንግሥታት ጥላቻን አትርፏል። "የነጮች አህጉር የሆነችውን አውሮፓን በስደተኛ ልታጥለቀልቃት ነው ሀሳብህ" የሚል ክስ ይነሳበታል። እሱም "በስደተኛ ላይ ያለኝ አቋም ብዙ ጠላት አፍርቶልኛል" ይላል። • ማሽተት አለመቻል ምን ይመስላል? ለምሳሌ የገዛ ትውልድ አገሩ ሀንጋሪ ለሶሮስ ያላትን ጥላቻ በጎዳና ላይ ቢልቦርድ ጭምር ሰቅላዋለች። አሁን ያለው የሀንጋሪያዊያን መንግሥት በአመዛኙ ጥቁር ጠል የሚባል ነው። በሀንጋሪ ለስደተኞቸ ድጋፍ የሰጠ ዜጋ በእስር ይቀጣል። የሚደንቀው ታዲያ የዚህን የቅጣት ሕግ ስም ሳይቀር የሃንጋሪ መንግሥት "ስቶፕ ሶሮስ" ብሎ ነው የሚጠራው። ያው ስደተኞችን እያጋዘ የሚያመጣብን ጆርጅ ሶሮስ ነው በሚል። የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የሶሮስ ቀንደኛ ጠላት ናቸው። በስሎቫኪያ የጋዜጠኛ መገደልን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ የተደናገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ወቅት ባደረጉት ንግግር፡ "ይሄ የጆርጅ ሶሮስ እጅ ነው። በስሎቫኪያ የተነሳው ነውጥ የሶሮስ ሥራ ነው። እሱ ስደተኛ እንዳይመጣባቸው ለሚፈልጉ አገራት አይራራም። የጎዳና ላይ ነውጥ እያስነሳ ይገለብጣቸዋል" ብለው ነበር። ጆርጅ ሶሮስ ከአፍሪካ እስከ ምሥራቅ አውሮፓ፣ ከትራምፕ እስከ ሞዲ ስለሱ የሚባለውን ሲሰማ ምን ይላል? በእርግጥ የዓለም ፖለቲካን የሚዘውረው ሰው ጆርጅ ሳሮስ ነው? "የእኔ እጅ ረዥም እንደሆነ የሚነገረው የተጋነነ ነው። እንደሚባለው የእንግሊዝ ባንክን አላንኮታኮትኩትም። ገበያው ነው ያንኮታኮተው። እንደሚባለው ስደተኛን እያጋዝኩ ወደ አውሮፓና አሜሪካ አላስኮበልልም። ኦፕን ሶሳይቲን የመሠረትኩት ዲሞክራሲንና የዲሞክራሲ ተቋማትን ለማጎልበት ነው" ይላል። ጆርጅ ሳሮስ እንደ ትራምፕ የሚንቀው ሰው ያለ አይመስልም። "ትራምፕ አታላይና በራሱ ፍቅር የናወዘ ሰው ነው" ይላል። ትራምፕን ብሔራዊ ጥቅምን ሳይቀር ለግል ስምና ዝናው አሳልፎ ለመስጠት የማይሳሳ ነው ይለዋል። የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዠን ፒንግን ደግሞ በቴክኖሎጂ መላ ሕዝቡን ለመቆጣጠር የሚሞክር አምባገነን ይለዋል። ዓለማችን ሁለቱን መሪዎች ብታስወግድ የተሻለ እንኖር ነበር ይላል ሶሮስ። ሶሮስ በስዊዘርላንድ ዳቮስ በቅርቡ ባደረገው ንግግር ዘረኝነት በአገራት እየተስፋፋ መምጣቱ እንደሚያሳስበው ተናግሯል። ጥላቻ እንዳይነግስ ለሚሰሩ፣ የመቻቻል ፕሮጀክቶችን ለማጎልበት ደግሞ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 1 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ቃል ገብቷል። በዘረኞችና በሀሰት ወሬ አራጋቢዎች የምትሾረው ዓለም ለሶሮስ ታሳስበዋለች። ክሪቲካል ቲንኪንግ ወይም ምክንያታዊነትን ቶሎ ካላስፋፋን መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው ይላል ሶሮስ። ከመሞቴ በፊት ማድረግ ይመፍልገውም ይህንን ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-51276518 |
5sports
| ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዓለም ዋንጫው ላይ አዲስ ታሪክ ጻፈ | ፖርቹጋል በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ ጋናን 3 ለ 2 ስታሰንፍ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ጎል በማስቆጠር የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። አጥቂው ከማንቸስተር ዩናይትድ በስምምነት እንዲለቅ ካደረገው አነጋጋሪ ቃለ መጠይቅ በኋላ ሲጫወት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የ37 ዓመቱ ተጫዋች ጎሏን ያስቆጠረው በፍጹም ቅጣት ምት ነው። የፖርቹጋሉ አጥቂ ቀደም ብሎ ያገኛቸውን ሁለት ዕድሎች ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል። ጋና ጎሉ ከተቆጠረባት በኋላ ባሳየችው መነሳሳት በአንድሬ አዬው ማካይነት አቻ ለመሆን በቅታለች። ጆአኦ ፌሊክስ እና ራፋኤል ሊአኦ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ፖርቹጋል 3 ለ 1 ለመምራት ችላለች። ኦስማን ቡካሪ ለጋና ሁለተኛ ጎል ማስቆጠር ቻለ። አፍሪካዊቷ ሃገር ባለቀ ሰዓት አቻ ለመሆን ያደረገችው ከፍተኛ ጥረት አልተሳካም። በምድቡ የሚገኙት ኡራጓይ እና ደቡብ ኮሪያ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል። በኤጁኬሽን ስታዲም በተደረገው ጨዋታ ደቡብ ኮሪያዎች የተሻለ ቢንቀሳቀሱም የጎል ዕድል መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። ትላንት የተደረጉት ጨዋታዎች የተጀመሩት ስዊዘርላንድ እና ካሜሩን ባደረጉት የምድብ ሰባት ፍልሚያ ነው። ስዊዘርላንድ ጨዋታውን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች። ብሪል ኤምቦሎ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ያሳረፈ ተጫዋች ሆኗል። ካሜሩን ተወልዶ ለስዊዘርላንድ የሚጫወተው አጥቂ ጎሉን ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን ከመግለጽ ተቆጥቧል። የማይበገሩት አንበሶች ካሳዩት እንቅስቃሴ አንጻር ተሸንፈው መውጣት አልነበረባቸውም ተብሏል። በሌላ የምድብ ሰባት ጨዋታ ለዋንጫው ትልቅ ግምት የተሰጣት ብራዚል ሰርቢያን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች። ጥንቃቄ የተሞላበትን የሰርቢያን አጨዋወት ሰብሮ ለመግባት ብራዚሎች 62 ደቂቃ ለመጠበቅ ተገደዋል። ሪቻርልሰን ደግሞ ጎሏን ያስቆጠረው ተጫዋች ነው። ከደቂቃዎች በኋላ ቄንጠኛ ጎል ከመረብ አሳርፎ ቡድኑን ለአሸናፊነት አብቅቷል። አሌክስ ሳንድሮ እና ካሰሚሮ በጎሉ ብረት የተመለሰባቸውን ጨምሮ ብራዚሎች በርካታ ዕድሎችን አምክነዋል። ኔይማር ተግድቶ የወጣ ሲሆን ብራዚሎች የህክምና ውጤቱን በተስፋ እየጠበቁ ነው። የዓለም ዋንጫው ቀጣይ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ። በምድብ ሁለት የሚገኙት ዌልስ እና ኢራን ቀን ሰባት ሰዓት በአህመድ ቢን አኪ ስታዲየም ይገናኛሉ። ኢራን በእንግሊዝ ተሸንፋ ዌልስ ደግሞ ከአሜሪካ አቻ ተለያይታ ነው የሚገናኙት። አዘጋጇን ኳታርን እና ሴኔጋልን የሚያገናኘው ጨዋታ ቀን 10 ሰዓጥ ይከናወናል። ሁለቱም ቡድኖች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በመሸነፋቸው ዛሬ የሚሸነፈው ቡድን ከምድቡ እንደማያልፍ ያረጋግጣል። ኔዘርላንድ እና ኢኳዶር ደግሞ ምሽት አንድ ሰዓት ይገናኛሉ። ሦስት ሦስት ነጥብ ስላላቸው የሁለቱ አሸናፊ በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ መግባቱን ያረጋግጣል። በዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ እንግሊዝ እና አሜሪካ ይጫወታሉ፥ እንግሊዝ ሦስት አሜሪካ ደግሞ አንድ ነጥብ ይዘው ነው ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑት። | ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዓለም ዋንጫው ላይ አዲስ ታሪክ ጻፈ ፖርቹጋል በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ ጋናን 3 ለ 2 ስታሰንፍ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ጎል በማስቆጠር የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። አጥቂው ከማንቸስተር ዩናይትድ በስምምነት እንዲለቅ ካደረገው አነጋጋሪ ቃለ መጠይቅ በኋላ ሲጫወት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የ37 ዓመቱ ተጫዋች ጎሏን ያስቆጠረው በፍጹም ቅጣት ምት ነው። የፖርቹጋሉ አጥቂ ቀደም ብሎ ያገኛቸውን ሁለት ዕድሎች ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል። ጋና ጎሉ ከተቆጠረባት በኋላ ባሳየችው መነሳሳት በአንድሬ አዬው ማካይነት አቻ ለመሆን በቅታለች። ጆአኦ ፌሊክስ እና ራፋኤል ሊአኦ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ፖርቹጋል 3 ለ 1 ለመምራት ችላለች። ኦስማን ቡካሪ ለጋና ሁለተኛ ጎል ማስቆጠር ቻለ። አፍሪካዊቷ ሃገር ባለቀ ሰዓት አቻ ለመሆን ያደረገችው ከፍተኛ ጥረት አልተሳካም። በምድቡ የሚገኙት ኡራጓይ እና ደቡብ ኮሪያ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል። በኤጁኬሽን ስታዲም በተደረገው ጨዋታ ደቡብ ኮሪያዎች የተሻለ ቢንቀሳቀሱም የጎል ዕድል መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። ትላንት የተደረጉት ጨዋታዎች የተጀመሩት ስዊዘርላንድ እና ካሜሩን ባደረጉት የምድብ ሰባት ፍልሚያ ነው። ስዊዘርላንድ ጨዋታውን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች። ብሪል ኤምቦሎ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ያሳረፈ ተጫዋች ሆኗል። ካሜሩን ተወልዶ ለስዊዘርላንድ የሚጫወተው አጥቂ ጎሉን ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን ከመግለጽ ተቆጥቧል። የማይበገሩት አንበሶች ካሳዩት እንቅስቃሴ አንጻር ተሸንፈው መውጣት አልነበረባቸውም ተብሏል። በሌላ የምድብ ሰባት ጨዋታ ለዋንጫው ትልቅ ግምት የተሰጣት ብራዚል ሰርቢያን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች። ጥንቃቄ የተሞላበትን የሰርቢያን አጨዋወት ሰብሮ ለመግባት ብራዚሎች 62 ደቂቃ ለመጠበቅ ተገደዋል። ሪቻርልሰን ደግሞ ጎሏን ያስቆጠረው ተጫዋች ነው። ከደቂቃዎች በኋላ ቄንጠኛ ጎል ከመረብ አሳርፎ ቡድኑን ለአሸናፊነት አብቅቷል። አሌክስ ሳንድሮ እና ካሰሚሮ በጎሉ ብረት የተመለሰባቸውን ጨምሮ ብራዚሎች በርካታ ዕድሎችን አምክነዋል። ኔይማር ተግድቶ የወጣ ሲሆን ብራዚሎች የህክምና ውጤቱን በተስፋ እየጠበቁ ነው። የዓለም ዋንጫው ቀጣይ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ። በምድብ ሁለት የሚገኙት ዌልስ እና ኢራን ቀን ሰባት ሰዓት በአህመድ ቢን አኪ ስታዲየም ይገናኛሉ። ኢራን በእንግሊዝ ተሸንፋ ዌልስ ደግሞ ከአሜሪካ አቻ ተለያይታ ነው የሚገናኙት። አዘጋጇን ኳታርን እና ሴኔጋልን የሚያገናኘው ጨዋታ ቀን 10 ሰዓጥ ይከናወናል። ሁለቱም ቡድኖች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በመሸነፋቸው ዛሬ የሚሸነፈው ቡድን ከምድቡ እንደማያልፍ ያረጋግጣል። ኔዘርላንድ እና ኢኳዶር ደግሞ ምሽት አንድ ሰዓት ይገናኛሉ። ሦስት ሦስት ነጥብ ስላላቸው የሁለቱ አሸናፊ በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ መግባቱን ያረጋግጣል። በዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ እንግሊዝ እና አሜሪካ ይጫወታሉ፥ እንግሊዝ ሦስት አሜሪካ ደግሞ አንድ ነጥብ ይዘው ነው ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑት። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c723dk17lwro |
3politics
| የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፉ | የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው ከመራጩ ሕዝብ 98 ከመቶ ድምጽ በማግኘት አሸነፉ። ብቸኛው ተፎካካሪያቸው የነበሩት ዛካሪያ ኢስማኢል ፋራህ 1.59 በመቶ ብቻ የመራጮችን ድምጽ ሊያገኙ መቻላቸው ተነግሯል። የዋነኛው ተቃዋሚ መሪው ዕጩ ባለፈው አርብ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድኔ በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ እንግልት ደርሶበታል በሚል ድምጽ ሳይሰጡ ራሳቸው ከውድድሩ አግልለው ነበር። ምርጫውን በበላይነት የመሩት የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሙሚን አሕመድ ሼክ አርብ ዕለት 177 ሺህ መራጮች ድምጽ መስጠታቸውን ተናግረዋል። በመጀመሪያ ላይ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡት ሰዎች ድምር 200 ሺህ እንደነበር ተዘግቧል። ኤስማኤል ጊሌ አሁን የ73 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ እንደ አውሮፓውያን ከ1999 ጀምሮ በጂቡቲ የፕሬዝዳንተንት የሥልጣን መንበር ላይ ቆይተዋል። የዘንድሮውን ምርጫም በከፍተኛ የበላይነት በማሸነፋቸው ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት ጂቡቲን እንዲመሩ ያስችላቸዋል ተብሏል። በቆዳ ስፋት አነስተኛ ሆና ነገር ግን በአፍሪካ ቀንድ ቁልፍ አካባቢያዊና ወታደራዊ ቦታ የያዘችው ጂቡቲ ጠቅላላ የሕዝብ ብዛቷ ከአንድ ሚሊዮን ያነሰ ነው። አሜሪካ፣ ቻይናና ፈረንሳይ በጂቡቲ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ገንብተዋል። የዓለም ባንክ በቅርብ ያወጣው አንድ መረጃ ከ14 ከመቶ በላይ የሚሆኑ ጂቡቲያዊያን በከፍተኛ የድህነት ውስጥ ነው የሚኖሩት ይላል። | የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፉ የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው ከመራጩ ሕዝብ 98 ከመቶ ድምጽ በማግኘት አሸነፉ። ብቸኛው ተፎካካሪያቸው የነበሩት ዛካሪያ ኢስማኢል ፋራህ 1.59 በመቶ ብቻ የመራጮችን ድምጽ ሊያገኙ መቻላቸው ተነግሯል። የዋነኛው ተቃዋሚ መሪው ዕጩ ባለፈው አርብ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድኔ በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ እንግልት ደርሶበታል በሚል ድምጽ ሳይሰጡ ራሳቸው ከውድድሩ አግልለው ነበር። ምርጫውን በበላይነት የመሩት የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሙሚን አሕመድ ሼክ አርብ ዕለት 177 ሺህ መራጮች ድምጽ መስጠታቸውን ተናግረዋል። በመጀመሪያ ላይ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡት ሰዎች ድምር 200 ሺህ እንደነበር ተዘግቧል። ኤስማኤል ጊሌ አሁን የ73 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ እንደ አውሮፓውያን ከ1999 ጀምሮ በጂቡቲ የፕሬዝዳንተንት የሥልጣን መንበር ላይ ቆይተዋል። የዘንድሮውን ምርጫም በከፍተኛ የበላይነት በማሸነፋቸው ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት ጂቡቲን እንዲመሩ ያስችላቸዋል ተብሏል። በቆዳ ስፋት አነስተኛ ሆና ነገር ግን በአፍሪካ ቀንድ ቁልፍ አካባቢያዊና ወታደራዊ ቦታ የያዘችው ጂቡቲ ጠቅላላ የሕዝብ ብዛቷ ከአንድ ሚሊዮን ያነሰ ነው። አሜሪካ፣ ቻይናና ፈረንሳይ በጂቡቲ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ገንብተዋል። የዓለም ባንክ በቅርብ ያወጣው አንድ መረጃ ከ14 ከመቶ በላይ የሚሆኑ ጂቡቲያዊያን በከፍተኛ የድህነት ውስጥ ነው የሚኖሩት ይላል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56702735 |
2health
| የካናዳዋ ግዛት ባልተከተቡት ላይ የጤና ግብር ልትጥል ነው | የካናዳዋ ኪዩቤክ ግዛት የኮቪድ-19 ክትባት ባልወሰዱ ነዋሪዎቿን የጤና ግብር ልታስከፍል ነው። ከዚህ ቀደም በካናዳ ካሉ ግዛቶች በወረርሽኙ መስፋፋት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ኩዩቤክ በአሁኑ ወቅትም የቫይረሱ ስርጭት አይሎባታል። ትናንት የክልሉ ገዢ ኪዩቤክ በካናዳ ክትባት ያልወሰዱትን በገንዘብ ስትቀጣ የመጀመሪያዋ ትሆናለች ብለዋል። እስካሁን ከግዛቷ ነዋሪዎች 12.8 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ነዋሪዎች ናቸው ክትባቱን ያልወሰዱት። ይሁን እንጂ በኮቪድ ተይዘው ሆስፒታል ከሚገቡት ወደ ግማሽ የሚጠጉት ያልተከተቡ ሰዎች ናቸው። የግዛቷ አስተዳዳሪ ፍራንኮኢስ ሌጋኡለተ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ያልወሰዱ ሰዎች "መዋጮ" መክፈል ይኖርባቸዋል ብለዋል። የክፍያ መጠኑ ባይገለጽም፤ ክፍያው "ቀላል" እንዳልሆነ ተናግረዋል። ግዛቷ የኮቪድ ስርጭቱን ለመግታት የሰዓት እላፊ ገደብ አስተዋውቃለች እንዲሁም ሰዎች አገልግሎት ፍለጋ ተቋማትን ከመጎብኘታቸው በፊት የክትባት ማስረጃ እንዲያሳዩ ትጠይቃለች። ይህ የግዛቱ አስተዳዳሪዎች ውሳኔ የተሰማው ባለፉት 24 ሰዓታት በኪዩቤክ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የ62 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ከተገለጸ በኋላ ነው። 8ሺህ 710 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአሁኑ ወቅት ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ 2ሺህ 742 ሰዎች ሆስፒታል የገቡ ሲሆን 244 የሚሆኑት በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ። ኪዩቤክ ክትባት ባልወሰዱት ላይ የገንዘብ መቀጮ ያስተዋወቀች ብቸኛዋ አይደለችም። አውሮፓዊቷ ግሪክ ከሳምንታት በኋላ ክትባት ያልወሰዱ እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆነቸው ሰዎችን በየወሩ 100 ዩሮ ክትባት እስኪወስዱ ድረስ እንዲከፍሉ ውሳኔ አስተላልፋለች። ሲንጋፖር ደግሞ የኮቪድ ክትባት ያልወሰዱ ሰዎች የጤና ክፍያዎችን ከኪሳቸው እንዲሸፍኑ አዛለች። | የካናዳዋ ግዛት ባልተከተቡት ላይ የጤና ግብር ልትጥል ነው የካናዳዋ ኪዩቤክ ግዛት የኮቪድ-19 ክትባት ባልወሰዱ ነዋሪዎቿን የጤና ግብር ልታስከፍል ነው። ከዚህ ቀደም በካናዳ ካሉ ግዛቶች በወረርሽኙ መስፋፋት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ኩዩቤክ በአሁኑ ወቅትም የቫይረሱ ስርጭት አይሎባታል። ትናንት የክልሉ ገዢ ኪዩቤክ በካናዳ ክትባት ያልወሰዱትን በገንዘብ ስትቀጣ የመጀመሪያዋ ትሆናለች ብለዋል። እስካሁን ከግዛቷ ነዋሪዎች 12.8 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ነዋሪዎች ናቸው ክትባቱን ያልወሰዱት። ይሁን እንጂ በኮቪድ ተይዘው ሆስፒታል ከሚገቡት ወደ ግማሽ የሚጠጉት ያልተከተቡ ሰዎች ናቸው። የግዛቷ አስተዳዳሪ ፍራንኮኢስ ሌጋኡለተ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ያልወሰዱ ሰዎች "መዋጮ" መክፈል ይኖርባቸዋል ብለዋል። የክፍያ መጠኑ ባይገለጽም፤ ክፍያው "ቀላል" እንዳልሆነ ተናግረዋል። ግዛቷ የኮቪድ ስርጭቱን ለመግታት የሰዓት እላፊ ገደብ አስተዋውቃለች እንዲሁም ሰዎች አገልግሎት ፍለጋ ተቋማትን ከመጎብኘታቸው በፊት የክትባት ማስረጃ እንዲያሳዩ ትጠይቃለች። ይህ የግዛቱ አስተዳዳሪዎች ውሳኔ የተሰማው ባለፉት 24 ሰዓታት በኪዩቤክ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የ62 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ከተገለጸ በኋላ ነው። 8ሺህ 710 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአሁኑ ወቅት ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ 2ሺህ 742 ሰዎች ሆስፒታል የገቡ ሲሆን 244 የሚሆኑት በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ። ኪዩቤክ ክትባት ባልወሰዱት ላይ የገንዘብ መቀጮ ያስተዋወቀች ብቸኛዋ አይደለችም። አውሮፓዊቷ ግሪክ ከሳምንታት በኋላ ክትባት ያልወሰዱ እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆነቸው ሰዎችን በየወሩ 100 ዩሮ ክትባት እስኪወስዱ ድረስ እንዲከፍሉ ውሳኔ አስተላልፋለች። ሲንጋፖር ደግሞ የኮቪድ ክትባት ያልወሰዱ ሰዎች የጤና ክፍያዎችን ከኪሳቸው እንዲሸፍኑ አዛለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-59954381 |
2health
| በትግራይ በሕጻናት ላይ የሚከሰቱ በሽታዎች እየጨመሩ መሆናቸው ተነገረ | በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት የክትባት መጠን በመቀነሱ በክትባት መከላከል የሚቻሉ በሕጻናት ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ ዓይነት በሽታዎች እየጨመሩ መሆኑ ተነገረ። የክልሉ የጤና ባለሥልጣናት እንዳሉት ክትባት የሚያገኙ ሕጻናት ቁጥር በመቀነሱ ልጆችን የሚያጠቁ ኩፍኝን፣ ፖሊዮን እና ቲታነስን የመሳሰሉ በሽታዎች እየጨመሩ ነው። ከትግራይ ጤና ቢሮ የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት ውስጥ በክልሉ መደበኛ የበሽታዎች መከላከያ ክትባቶችን የሚያገኙ ልጆች መጠን ከ10 በመቶ በታች አሽቆልቁሏል። የጤና ቢሮው ‘ጋቪ’ በመባል ለሚታወቀው በዓለም ዙሪያ ክትባቶችን የሚያቀርበው ዓለም አቀፍ ትብብር በጻፈው ደብዳቤ ላይ፤ “የጨቅላ ሕጻናት እና የልጆች ክትባትን ጨምሮ ሕይወት አድን የሆኑ መድኃኒቶች እና የሕክምና አቅርቦቶች እንዳያገኙ በመደረጋቸው” ለተለያዩ በሽታዎች ተዳርገዋል ብሏል። በዚህም ሳቢያ የኩፍኝ፣ የተቅማጥ፣ የማጅራት ገትር፣ የልጅነት ልምሻ [ፖሊዮ] እና የመሳሰሉ ወረርሽኞች በክልሉ ውስጥ መከሰታቸውን የጤና ቢሮው በጻፈው ደብዳቤ ላይ አመልክቷል። ለዚህም በምክንያትነት የተጠቀሰው በክልሉ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት የክትባት አቅርቦት በመቀነሱ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ባለመኖሩ ከትባቶችን በተገቢው መጠን አቀዝቅዞ ለማስቀመጥ ባለመቻሉ እና በገጠር አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ወደ ጤና ተቋማት ለክትባት መምጣት ባለመቻላቸው እንደሆነ የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል። የኩፍኝ ወረርሽኝ በክልሉ ውስጥ ካሉ 35 ዞኖች በ10 ዞኖች ውስጥ መከሰቱን ሪፖርት መደረጉን የገለጸው ቢሮው፣ እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 ዜሮ የነበረው በጨቅላ ሕጻናት ላይ የሚከሰት ቲታነስ አሁን 25 መድረሱን አመልክቷል። በመጪው ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ሁለተኛ ዓመቱን በሚይዘው በትግራይ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በርካታ የጤና ተቋማት ላይ ውድመት ማጋጠሙንና ከሥራ ውጪ መሆናቸውን ከዚህ በፊት የወጡ ሪፖርቶች አመለክተዋል። ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት በቅርቡ መቀስቀሱ ደግሞ በክልሉ ውስጥ ያለውን የጤና አገልግሎት የአቅርቦት ችግር የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል። | በትግራይ በሕጻናት ላይ የሚከሰቱ በሽታዎች እየጨመሩ መሆናቸው ተነገረ በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት የክትባት መጠን በመቀነሱ በክትባት መከላከል የሚቻሉ በሕጻናት ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ ዓይነት በሽታዎች እየጨመሩ መሆኑ ተነገረ። የክልሉ የጤና ባለሥልጣናት እንዳሉት ክትባት የሚያገኙ ሕጻናት ቁጥር በመቀነሱ ልጆችን የሚያጠቁ ኩፍኝን፣ ፖሊዮን እና ቲታነስን የመሳሰሉ በሽታዎች እየጨመሩ ነው። ከትግራይ ጤና ቢሮ የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት ውስጥ በክልሉ መደበኛ የበሽታዎች መከላከያ ክትባቶችን የሚያገኙ ልጆች መጠን ከ10 በመቶ በታች አሽቆልቁሏል። የጤና ቢሮው ‘ጋቪ’ በመባል ለሚታወቀው በዓለም ዙሪያ ክትባቶችን የሚያቀርበው ዓለም አቀፍ ትብብር በጻፈው ደብዳቤ ላይ፤ “የጨቅላ ሕጻናት እና የልጆች ክትባትን ጨምሮ ሕይወት አድን የሆኑ መድኃኒቶች እና የሕክምና አቅርቦቶች እንዳያገኙ በመደረጋቸው” ለተለያዩ በሽታዎች ተዳርገዋል ብሏል። በዚህም ሳቢያ የኩፍኝ፣ የተቅማጥ፣ የማጅራት ገትር፣ የልጅነት ልምሻ [ፖሊዮ] እና የመሳሰሉ ወረርሽኞች በክልሉ ውስጥ መከሰታቸውን የጤና ቢሮው በጻፈው ደብዳቤ ላይ አመልክቷል። ለዚህም በምክንያትነት የተጠቀሰው በክልሉ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት የክትባት አቅርቦት በመቀነሱ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ባለመኖሩ ከትባቶችን በተገቢው መጠን አቀዝቅዞ ለማስቀመጥ ባለመቻሉ እና በገጠር አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ወደ ጤና ተቋማት ለክትባት መምጣት ባለመቻላቸው እንደሆነ የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል። የኩፍኝ ወረርሽኝ በክልሉ ውስጥ ካሉ 35 ዞኖች በ10 ዞኖች ውስጥ መከሰቱን ሪፖርት መደረጉን የገለጸው ቢሮው፣ እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 ዜሮ የነበረው በጨቅላ ሕጻናት ላይ የሚከሰት ቲታነስ አሁን 25 መድረሱን አመልክቷል። በመጪው ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ሁለተኛ ዓመቱን በሚይዘው በትግራይ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በርካታ የጤና ተቋማት ላይ ውድመት ማጋጠሙንና ከሥራ ውጪ መሆናቸውን ከዚህ በፊት የወጡ ሪፖርቶች አመለክተዋል። ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት በቅርቡ መቀስቀሱ ደግሞ በክልሉ ውስጥ ያለውን የጤና አገልግሎት የአቅርቦት ችግር የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cmjdp7xy23no |
3politics
| አል ቡርሐን እራሳቸውን የሱዳን ጊዜያዊ መሪ አድርገው ሾሙ | በሱዳን የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት በመምራት ወታደሩ ሥልጣን እንዲይዝ ያደረጉት ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሐን አዲስ ምክር ቤት ሲመሠርቱ እራሳቸውን ደግሞ መሪ አድርገው ሰይመዋል። ሐሙስ ዕለትም ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። ጄነራል ቡርሐን፤ ምክትላቸው መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎችን ከጥቅምት 25ቱ መፈንቅለ መንግሥት በፊት በነበራቸው ሥልጣን እንዲቆዩ አድርገዋል። 14 አባላት ያሉት የሽግግር ምክር ቤት ሲቪል ዜጎችን ቢያካትትም ከመፈንቅለ መንግሥቱ በፊት ሥልጣን ላይ ከነበረው የፖለቲካ ጥምረት አንድም ወኪል አልተካተተም። ከሥልጣን የተባረሩት የሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ሐምዛ ባሎል አዲሱን የአል ቡርሐን እርምጃ የመፈንቅለ መንግሥቱ ቅጥያ አድርገው ገልጸዋል። ሕዝቡ "አሸንፎ ሽግግሩን ያስቀጥላል" ብለዋል። ምክር ቤቱ የተቋቋመው መፈንቅለ መንግሥቱን ለመቀልበስ ከአገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ አካላትም ጫናው በጨመረበት ወቅት ነው። በሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ተወካይ ቮልከር ፔርዝስ፤ የጦሩ ዋና አዛዥ ጄነራል አል ቡርሐን የሰጡት የአንድ ወገን የምክር ቤት ሹመት፤ አገሪቱ ወደ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለመመለስ እንድትቸገር ያደርጋታል ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኛው የሱዳንን ፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብት ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ በአስቸኳይ ድርድር እንዲካሄድ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ጦሩ የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን ሙሉ ነጻነት መመለስን ጨምሮ ሌሎች "የመተማመኛ እርምጃዎችን" እንዲወስድም አሳስበዋል። | አል ቡርሐን እራሳቸውን የሱዳን ጊዜያዊ መሪ አድርገው ሾሙ በሱዳን የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት በመምራት ወታደሩ ሥልጣን እንዲይዝ ያደረጉት ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሐን አዲስ ምክር ቤት ሲመሠርቱ እራሳቸውን ደግሞ መሪ አድርገው ሰይመዋል። ሐሙስ ዕለትም ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። ጄነራል ቡርሐን፤ ምክትላቸው መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎችን ከጥቅምት 25ቱ መፈንቅለ መንግሥት በፊት በነበራቸው ሥልጣን እንዲቆዩ አድርገዋል። 14 አባላት ያሉት የሽግግር ምክር ቤት ሲቪል ዜጎችን ቢያካትትም ከመፈንቅለ መንግሥቱ በፊት ሥልጣን ላይ ከነበረው የፖለቲካ ጥምረት አንድም ወኪል አልተካተተም። ከሥልጣን የተባረሩት የሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ሐምዛ ባሎል አዲሱን የአል ቡርሐን እርምጃ የመፈንቅለ መንግሥቱ ቅጥያ አድርገው ገልጸዋል። ሕዝቡ "አሸንፎ ሽግግሩን ያስቀጥላል" ብለዋል። ምክር ቤቱ የተቋቋመው መፈንቅለ መንግሥቱን ለመቀልበስ ከአገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ አካላትም ጫናው በጨመረበት ወቅት ነው። በሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ተወካይ ቮልከር ፔርዝስ፤ የጦሩ ዋና አዛዥ ጄነራል አል ቡርሐን የሰጡት የአንድ ወገን የምክር ቤት ሹመት፤ አገሪቱ ወደ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለመመለስ እንድትቸገር ያደርጋታል ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኛው የሱዳንን ፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብት ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ በአስቸኳይ ድርድር እንዲካሄድ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ጦሩ የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን ሙሉ ነጻነት መመለስን ጨምሮ ሌሎች "የመተማመኛ እርምጃዎችን" እንዲወስድም አሳስበዋል። | https://www.bbc.com/amharic/59258061 |
5sports
| ዩናይትድን ከቶተነሃም ያፋጠጠው የ11ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት | የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን አንድንድ ጊዜ የሚሰጠው ግምት አስደንጋጭ የሚባል ነው። ባለፈው ሳምንት ሊቨርፑል በሜዳው በማንቸስተር ሲቲ 4 ለ 1 እንደሚሸነፍ ግምቱን አስቀምጦ ነበር። በሊቨርፑል ዙሪያ ስሀተት ሲሰራ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በርንማውዞች ምን ይበሉ? ያለፉትን 10 ሳምንታት ጨዋታዎች በሙሉ እንደሚሸነፉ ግምቱን አስቀምጧል። የ11ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ትላንት ምሽት ተጀምረዋል። ሱቶን በብራይተን የበላይነት ይጠናቀቃል ያለው የብራይተን እና ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታ ያለጎል አቻ ተጠናቋል። ክሪስታል ፓላስ እና ዎልቭስ ደግሞ አንድ አቻ ይለያያሉ ሲል ግምቱን አስቀምጦ ነበር። ፓላስ ግን ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሌሎች ጨዋታዎችን ግምት እንደሚከተለው እንቃኛለን። አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ ማድረግ የነበረባቸው ይህ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። በርንማውዝ ከ ሳውዝሃምፕተን የትኛውም የበርንማውዝ ደጋፊ በማይጠብቀው መልኩ ቡድኑ ያሸንፋል ብዬ ግምቴን ላስቀምጥ። በርንማውዝ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ይኖርበታል። ሳውዝሃምፕተኖች ከዌስትሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ አንድ ነጥብ ማግኘታቸው ዕድለኛ ያደርጋቸዋል። በርንማውዞች ከፉልሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ ያስቆጠሩት የመጀመሪያ ጎል ድንቅ ነበር። ግምት፡ 2 – 1 ቼልሲዎች ባለፈው እሁድ አስቶን ቪላን ማሸነፍ ችለዋል። ከብሬንትፎርድ ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም። ከብራይተን ጋር በነበራቸው ጨዋታ አጥቂ ክፍላቸው ወደ አቋሙ የተመለሰ መስሏል። ቼልስ በጥሩ አቋም ላይ ካልተገኘ እና ብሬንትፎርዶች በተመሳሳይ መልኩ ከተጫወቱ አንድ ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 1 – 1 ሊቨርፑል ከ ዌስት ሃም ከሰሞኑ ከሊቨርፑል ደጋፊዎች ብዙ ትችት አስተናግጃለሁ። ሊቨርፑል ከሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ በተለይም የኋላ መስመሩ አስደናቂ ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ ደጋፊው ከጎናቸው የቆመበት እና አንፊልድ ወደ ቀድሞ አቋሙ የተመለሰበት አጋጣሚ ነበር። ወደ አቋማቸው ለመመለስ በተገቢው መንገድ ላይ ያሉ ይመስለኛል። የዌስትሃም የኋላ መስመር መሳሳት የሚረዳቸው ሲሆን ጂያንሉካ ሳማካ ደግሞ ጎል ያስቆጥራል። ግምት፡ 3 – 1 ኒውካስል ኦልትራፎድ ላይ አለማሸነፉ ትንሽ ዕድለ ቢስ ያደርገዋል። ቡድኑ ሚዛኑን ያገኘ ይመስላል። በመከላከል በኩል ጥሩ ሲሆኑ የተወሰኑ ዕድሎችንም ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ለመፍጠር ችለዋል። እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ውስጥ ለምን እንደተቀመጡ መረዳት የሚቻል ሲሆን አሁን ካላቸው ነጠብ የተሻለም ማግኘት ነበረባቸው። ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች የተሸነፉት ኤቨርተኖች በዚህ ጨዋታም ይቸገራሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 – 0 ማንቸስተር ዩናይትዶች ከኒውካስል ጋር ዕድል ያመለጣቸው ይመስለኛል። የስፐርስ ጨዋታ ሌላ ጉዳይ ነው። ሃሪ ኬን ዕድል ካገኘ ጎል የማስቆጠር ብቃቱ ላይ ይገኛል። ዩናይትድ ደግሞ ጥርስ አልባ መሆኑን ባለፈው ሳምንት አሳይቷል። ቡድኑ ክርስቲያን ኤሪክሰንን በህምም ምክንያት ማጣቱ የጎዳው ሲሆን ለዚህ ለቀድሞ ክለቡ ጨዋታም ላይደርስ ይችላል። ኤሪክሰን ቢሰለፍም አንቶኒዮ ኮንቴ በመልሶ ማጥቃት የሚያሸንፍ ይመስለኛል። ግምት፡ 1 – 3 ፉልሃም ከ አስቶን ቪላ አስቶን ቪላዎች ባለፈው ሳምንት ከቼልሲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ ቢሆኑም በዚያው አልቀጠሉበትም። አሰልጣኝ ስቴቨን ዤራርድ ጫና ውስጥ የወደቀ ሲሆን ደጋፊዎችም ፊታቸውን ያዞሩበት ይመስላል። ስለዚህ በዚህ ጨዋታ ጥሩ ውጤት ይጠብቃል። ፉልሃም እና ብርንማውዝ ባለፈው ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ ፉልሃሞች አደገኛ እንደሆኑ ተመልክቻለሁ። ይህ ጨዋታ አቻ ይጠናቀቃል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1 – 1 ሌስተር ከ ሊድስ ሌስተሮች ተጽዕኖ ፈጠሪ የሆነውን ተጫዋቻቸውን ጀምስ ማዲሰንን በቅጣት አያገኙም። በአርሰናል የተሸነፉበትን ጨምሮ ሊድሶች በዘንድሮው ዓመት እንደአጨዋወታቸው የሚገባቸውን ውጤት ያላገኙባቸው ጨዋታዎች አሉ። በዚህ ጨዋታ ግን ይህንን የሚቀይሩበት እንደሚሆን እገምታለሁ። አጨዋወታቸውንም የምወደው ሲሆን ተገቢውንም ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 1 – 4 | ዩናይትድን ከቶተነሃም ያፋጠጠው የ11ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን አንድንድ ጊዜ የሚሰጠው ግምት አስደንጋጭ የሚባል ነው። ባለፈው ሳምንት ሊቨርፑል በሜዳው በማንቸስተር ሲቲ 4 ለ 1 እንደሚሸነፍ ግምቱን አስቀምጦ ነበር። በሊቨርፑል ዙሪያ ስሀተት ሲሰራ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በርንማውዞች ምን ይበሉ? ያለፉትን 10 ሳምንታት ጨዋታዎች በሙሉ እንደሚሸነፉ ግምቱን አስቀምጧል። የ11ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ትላንት ምሽት ተጀምረዋል። ሱቶን በብራይተን የበላይነት ይጠናቀቃል ያለው የብራይተን እና ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታ ያለጎል አቻ ተጠናቋል። ክሪስታል ፓላስ እና ዎልቭስ ደግሞ አንድ አቻ ይለያያሉ ሲል ግምቱን አስቀምጦ ነበር። ፓላስ ግን ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሌሎች ጨዋታዎችን ግምት እንደሚከተለው እንቃኛለን። አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ ማድረግ የነበረባቸው ይህ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። በርንማውዝ ከ ሳውዝሃምፕተን የትኛውም የበርንማውዝ ደጋፊ በማይጠብቀው መልኩ ቡድኑ ያሸንፋል ብዬ ግምቴን ላስቀምጥ። በርንማውዝ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ይኖርበታል። ሳውዝሃምፕተኖች ከዌስትሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ አንድ ነጥብ ማግኘታቸው ዕድለኛ ያደርጋቸዋል። በርንማውዞች ከፉልሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ ያስቆጠሩት የመጀመሪያ ጎል ድንቅ ነበር። ግምት፡ 2 – 1 ቼልሲዎች ባለፈው እሁድ አስቶን ቪላን ማሸነፍ ችለዋል። ከብሬንትፎርድ ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም። ከብራይተን ጋር በነበራቸው ጨዋታ አጥቂ ክፍላቸው ወደ አቋሙ የተመለሰ መስሏል። ቼልስ በጥሩ አቋም ላይ ካልተገኘ እና ብሬንትፎርዶች በተመሳሳይ መልኩ ከተጫወቱ አንድ ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 1 – 1 ሊቨርፑል ከ ዌስት ሃም ከሰሞኑ ከሊቨርፑል ደጋፊዎች ብዙ ትችት አስተናግጃለሁ። ሊቨርፑል ከሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ በተለይም የኋላ መስመሩ አስደናቂ ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ ደጋፊው ከጎናቸው የቆመበት እና አንፊልድ ወደ ቀድሞ አቋሙ የተመለሰበት አጋጣሚ ነበር። ወደ አቋማቸው ለመመለስ በተገቢው መንገድ ላይ ያሉ ይመስለኛል። የዌስትሃም የኋላ መስመር መሳሳት የሚረዳቸው ሲሆን ጂያንሉካ ሳማካ ደግሞ ጎል ያስቆጥራል። ግምት፡ 3 – 1 ኒውካስል ኦልትራፎድ ላይ አለማሸነፉ ትንሽ ዕድለ ቢስ ያደርገዋል። ቡድኑ ሚዛኑን ያገኘ ይመስላል። በመከላከል በኩል ጥሩ ሲሆኑ የተወሰኑ ዕድሎችንም ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ለመፍጠር ችለዋል። እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ውስጥ ለምን እንደተቀመጡ መረዳት የሚቻል ሲሆን አሁን ካላቸው ነጠብ የተሻለም ማግኘት ነበረባቸው። ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች የተሸነፉት ኤቨርተኖች በዚህ ጨዋታም ይቸገራሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 – 0 ማንቸስተር ዩናይትዶች ከኒውካስል ጋር ዕድል ያመለጣቸው ይመስለኛል። የስፐርስ ጨዋታ ሌላ ጉዳይ ነው። ሃሪ ኬን ዕድል ካገኘ ጎል የማስቆጠር ብቃቱ ላይ ይገኛል። ዩናይትድ ደግሞ ጥርስ አልባ መሆኑን ባለፈው ሳምንት አሳይቷል። ቡድኑ ክርስቲያን ኤሪክሰንን በህምም ምክንያት ማጣቱ የጎዳው ሲሆን ለዚህ ለቀድሞ ክለቡ ጨዋታም ላይደርስ ይችላል። ኤሪክሰን ቢሰለፍም አንቶኒዮ ኮንቴ በመልሶ ማጥቃት የሚያሸንፍ ይመስለኛል። ግምት፡ 1 – 3 ፉልሃም ከ አስቶን ቪላ አስቶን ቪላዎች ባለፈው ሳምንት ከቼልሲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ ቢሆኑም በዚያው አልቀጠሉበትም። አሰልጣኝ ስቴቨን ዤራርድ ጫና ውስጥ የወደቀ ሲሆን ደጋፊዎችም ፊታቸውን ያዞሩበት ይመስላል። ስለዚህ በዚህ ጨዋታ ጥሩ ውጤት ይጠብቃል። ፉልሃም እና ብርንማውዝ ባለፈው ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ ፉልሃሞች አደገኛ እንደሆኑ ተመልክቻለሁ። ይህ ጨዋታ አቻ ይጠናቀቃል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1 – 1 ሌስተር ከ ሊድስ ሌስተሮች ተጽዕኖ ፈጠሪ የሆነውን ተጫዋቻቸውን ጀምስ ማዲሰንን በቅጣት አያገኙም። በአርሰናል የተሸነፉበትን ጨምሮ ሊድሶች በዘንድሮው ዓመት እንደአጨዋወታቸው የሚገባቸውን ውጤት ያላገኙባቸው ጨዋታዎች አሉ። በዚህ ጨዋታ ግን ይህንን የሚቀይሩበት እንደሚሆን እገምታለሁ። አጨዋወታቸውንም የምወደው ሲሆን ተገቢውንም ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 1 – 4 | https://www.bbc.com/amharic/articles/c80p4lnr1p0o |
5sports
| ፖሊስ የኮቢ ብሪያንት አሟሟት አሰቃቂ ምስሎችን አሳይቷል ስትል ባለቤቱ ከሰሰች | በባለፈው አመት በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወቱን ያጣው ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብሪያንት ባለቤት የአሟሟቱን ሁኔታ የሚመለከቱ አሰቃቂ ምስሎችን አውጥቷል ስትል ፖሊስን ከሳለች። አሰቃቂ ምስሎች አውጥተዋል ያለቻቸውን የሎስ አንጀለስ ግዛት ፖሊሶች ስምም ጠቅሳለች። ፖሊሶች በቸልተኝነትና የግል ኑሯቸውን በጣሰ መልኩ እነዚህን ፎቶዎች አውጥተዋል በማለት የግዛቱን የፖሊስ ኃላፊዎች የከሰሰችው። "በሚዲያ የፍርድ ሂደቱ እንዲካሄድ ስለማንፈልግ ምንም ነገር ከማለት ተቆጥበናል" በማለት የፖሊስ ኃላፊው ምላሽ ሰጥተዋል። ስመ ጥሩው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢና ልጁን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች በባለፈው አመት በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ መሞታቸው የሚታወስ ነው። በያዝነው ሳምንት ረቡዕ ቫኔሳ አሰቃቂ ፎቶን አውጥተዋል ያለቻቸውን አራት የፖሊሶች ስም በኢንስታግራም ገጿ አስፍራለች። ቫኔሳ እንደምትለው ፖሊሶቹ የዘጠኙን ሰዎች አስከሬን ፎቶዎች ካነሱ በኋላ አንደኛው ፖሊስ በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ የኮቢን ፎቶ እያሳየ ነበር ብላለች። ሌሎቹ ደግሞ ህፃናት ያሉበት፣ ወላጆቻቸውንና አሰልጣኞቻቸውን አሰቃቂ ፎቶዎች ለበርካቶች ሲያሳዩ ነበር ብላለች። የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ በየካቲት ወር ላይ ውስጣዊ የፖሊስ የምርመራ መዝገብን ጠቅሶ ፖሊሶች የሟቾችን አሰቃቂ ፎቶዎች አጋርተዋል ብሏል። ቫኔሳ እንደምትለው የ13 አመት ልጇ ጂያና የአስከሬን ፎቶ ሳይቀር "ለአሉባልታ ብቻ" ለዕይታ ውሏል ብላለች። የፖሊሶቹ ስም ይፋ እንዳይወጣ ባለፈው ሳምንት ለፍርድ ቤት ጥያቁ ቢቀርብም ዳኛው በበኩላቸው ስማቸው ይፋ እንዲሆን አዟል። የሎስ አንጀለስ ግዛት ፖሊስ ኃላፊ አሌክስ ቪላኑቫ የቫኔሳን ትዊተር አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ የፍርድ ቤቱን ምላሸ እንጠብቃለን ብለዋል። ቫኔሳ ስምንት ፖሊሶች ለራሳቸው ጥቅም እንዲውል በሚል በርካታ ፎቶዎች ያነሱ ሲሆን አንደኛው ግለሰብም ከ25-100 ፎቶዎችን አንስቷል ብላለች። | ፖሊስ የኮቢ ብሪያንት አሟሟት አሰቃቂ ምስሎችን አሳይቷል ስትል ባለቤቱ ከሰሰች በባለፈው አመት በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወቱን ያጣው ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብሪያንት ባለቤት የአሟሟቱን ሁኔታ የሚመለከቱ አሰቃቂ ምስሎችን አውጥቷል ስትል ፖሊስን ከሳለች። አሰቃቂ ምስሎች አውጥተዋል ያለቻቸውን የሎስ አንጀለስ ግዛት ፖሊሶች ስምም ጠቅሳለች። ፖሊሶች በቸልተኝነትና የግል ኑሯቸውን በጣሰ መልኩ እነዚህን ፎቶዎች አውጥተዋል በማለት የግዛቱን የፖሊስ ኃላፊዎች የከሰሰችው። "በሚዲያ የፍርድ ሂደቱ እንዲካሄድ ስለማንፈልግ ምንም ነገር ከማለት ተቆጥበናል" በማለት የፖሊስ ኃላፊው ምላሽ ሰጥተዋል። ስመ ጥሩው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢና ልጁን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች በባለፈው አመት በደረሰ የሄሊኮፕተር አደጋ መሞታቸው የሚታወስ ነው። በያዝነው ሳምንት ረቡዕ ቫኔሳ አሰቃቂ ፎቶን አውጥተዋል ያለቻቸውን አራት የፖሊሶች ስም በኢንስታግራም ገጿ አስፍራለች። ቫኔሳ እንደምትለው ፖሊሶቹ የዘጠኙን ሰዎች አስከሬን ፎቶዎች ካነሱ በኋላ አንደኛው ፖሊስ በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ የኮቢን ፎቶ እያሳየ ነበር ብላለች። ሌሎቹ ደግሞ ህፃናት ያሉበት፣ ወላጆቻቸውንና አሰልጣኞቻቸውን አሰቃቂ ፎቶዎች ለበርካቶች ሲያሳዩ ነበር ብላለች። የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ በየካቲት ወር ላይ ውስጣዊ የፖሊስ የምርመራ መዝገብን ጠቅሶ ፖሊሶች የሟቾችን አሰቃቂ ፎቶዎች አጋርተዋል ብሏል። ቫኔሳ እንደምትለው የ13 አመት ልጇ ጂያና የአስከሬን ፎቶ ሳይቀር "ለአሉባልታ ብቻ" ለዕይታ ውሏል ብላለች። የፖሊሶቹ ስም ይፋ እንዳይወጣ ባለፈው ሳምንት ለፍርድ ቤት ጥያቁ ቢቀርብም ዳኛው በበኩላቸው ስማቸው ይፋ እንዲሆን አዟል። የሎስ አንጀለስ ግዛት ፖሊስ ኃላፊ አሌክስ ቪላኑቫ የቫኔሳን ትዊተር አስመልክቶ በሰጡት ምላሽ የፍርድ ቤቱን ምላሸ እንጠብቃለን ብለዋል። ቫኔሳ ስምንት ፖሊሶች ለራሳቸው ጥቅም እንዲውል በሚል በርካታ ፎቶዎች ያነሱ ሲሆን አንደኛው ግለሰብም ከ25-100 ፎቶዎችን አንስቷል ብላለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-56453317 |
3politics
| ተቃውሞ ተጠናክሮ በቀጠለባት አውሮፓ፤ ኦስትሪያ የእንቅስቃሴ ገደብ ጣለች | የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አዲስ የወጡ የእንቅስቃሴ ገደቦች አውሮፓ ተቃውሞ እየገጠማቸው ባለበት ወቅት አውሮፓዊቷ ኦስትሪያ አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላለች። ከትላንት ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ኦስትሪያውያን ከቤት እንዲሠሩ የታዘዙ ሲሆን መሠረታዊ አገለግሎት የማይሰጡ የንግድ ተቋማትም ተዘግተዋል። የተለያዩ የአውሮፓ አገራት እንደ አዲስ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን የጣሉ ሲሆን ይህም ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነው። የእንቅስቃሴ ገደቡን በመቀወም በኔዘርላንድስ፣ ቤልጂየም፣ ክሮሺያ እና ዴንማርክ ሰዎች ድምጻቸው አሰምተዋል። በኔዘርላንድስ እና ቤልጂየም ደግሞ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። በአህጉሪቱ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ቅዳሜ ዕለት በአውሮፓ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ሃንስ ክሉጅ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በመላው አውሮፓ እንደ ክትባት መውሰድን እና የፊት እና አፍ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግን የመሰሉ እርምጃዎች በጥብቅ ካልተተገበሩ፤ በሚቀጥለው የፀደይ ወራት በቫይረሱ ምክንያት ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ሊመዘገብ ይችላል። ባለፈው ሳምንት ኦስትሪያ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ሕጋዊ ግዴታ ያደረገች የመጀመሪያዋ አውሮፓ አገር ሆናለች። ሕጉ በየካቲት ወር ተግባራዊ ይሆናል። በአጎራባቿ ጀርመን ያሉ ፖለቲከኞች ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ እየመከሩ ነው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ኦስትሪያ ለአራተኛው ጊዜ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላለች። የአገሪቱ ባለስልጣናት ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ፀጉር ቤቶች፣ ቲያትር ቤቶች እና መሠረታዊ አገልግሎት የማይሰጡ የንግድ ተቋማት እንዲዘጉ አዘዋል። የአገሪቱ ጤና ሚንስትር ዎልፍጋንድ ሙቸክስታይን፤ "ከባድ የሆነውን የእንቅስቃሴ ገደብ መጣል ብቸኛው አማራጭ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በኦስትሪያ መዲና ቪዬና የእንቅስቃሴ ገደብ ከመተግበሩ በፊት አደባባይ ወጥተው የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። በተለያዩ የአውሮፓ አገራት በሳምንቱ መጨረሻ ኮቪድ-19 ለመከላከል የወጡ እና ጠንከር ያሉ ገደቦችን በመቃወም በርካቶች አደባይ የወጡ ሲሆን አንድ አንድ አገራት ላይ ተቃውሞው ወደ ሁከት ተቀይሮ ታይቷል። | ተቃውሞ ተጠናክሮ በቀጠለባት አውሮፓ፤ ኦስትሪያ የእንቅስቃሴ ገደብ ጣለች የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አዲስ የወጡ የእንቅስቃሴ ገደቦች አውሮፓ ተቃውሞ እየገጠማቸው ባለበት ወቅት አውሮፓዊቷ ኦስትሪያ አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላለች። ከትላንት ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ኦስትሪያውያን ከቤት እንዲሠሩ የታዘዙ ሲሆን መሠረታዊ አገለግሎት የማይሰጡ የንግድ ተቋማትም ተዘግተዋል። የተለያዩ የአውሮፓ አገራት እንደ አዲስ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን የጣሉ ሲሆን ይህም ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ነው። የእንቅስቃሴ ገደቡን በመቀወም በኔዘርላንድስ፣ ቤልጂየም፣ ክሮሺያ እና ዴንማርክ ሰዎች ድምጻቸው አሰምተዋል። በኔዘርላንድስ እና ቤልጂየም ደግሞ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። በአህጉሪቱ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ቅዳሜ ዕለት በአውሮፓ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ሃንስ ክሉጅ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በመላው አውሮፓ እንደ ክትባት መውሰድን እና የፊት እና አፍ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግን የመሰሉ እርምጃዎች በጥብቅ ካልተተገበሩ፤ በሚቀጥለው የፀደይ ወራት በቫይረሱ ምክንያት ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ሊመዘገብ ይችላል። ባለፈው ሳምንት ኦስትሪያ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ሕጋዊ ግዴታ ያደረገች የመጀመሪያዋ አውሮፓ አገር ሆናለች። ሕጉ በየካቲት ወር ተግባራዊ ይሆናል። በአጎራባቿ ጀርመን ያሉ ፖለቲከኞች ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ እየመከሩ ነው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ኦስትሪያ ለአራተኛው ጊዜ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላለች። የአገሪቱ ባለስልጣናት ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ፀጉር ቤቶች፣ ቲያትር ቤቶች እና መሠረታዊ አገልግሎት የማይሰጡ የንግድ ተቋማት እንዲዘጉ አዘዋል። የአገሪቱ ጤና ሚንስትር ዎልፍጋንድ ሙቸክስታይን፤ "ከባድ የሆነውን የእንቅስቃሴ ገደብ መጣል ብቸኛው አማራጭ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በኦስትሪያ መዲና ቪዬና የእንቅስቃሴ ገደብ ከመተግበሩ በፊት አደባባይ ወጥተው የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። በተለያዩ የአውሮፓ አገራት በሳምንቱ መጨረሻ ኮቪድ-19 ለመከላከል የወጡ እና ጠንከር ያሉ ገደቦችን በመቃወም በርካቶች አደባይ የወጡ ሲሆን አንድ አንድ አገራት ላይ ተቃውሞው ወደ ሁከት ተቀይሮ ታይቷል። | https://www.bbc.com/amharic/59370725 |
3politics
| ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የተዘጋጀው ብሔራዊ ቀብር ‘ውድ ነው’ ያለው ጃፓናዊ ራሱን አቃጠለ | ለቀድሞው የጃፓን ፕሬዝዳንት የተዘጋጀውን ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመቃወም አንድ ጃፓናዊ ራሱን በእሳት አቃጠለ። ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ በሰው እጅ ለተገደሉት ሺንዞ አቤ ቀብር በመቶዎች የሚቆጠሩ የውጭ አገራት መሪዎች ተጠርተዋል። የጃፓን መንግሥት ያዘጋጀችው ይህ ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት በሚቀጥለው ሳምንት መስከረም 17/2015 ዓ.ም. ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህንን ሥነ ሥርዓት በመቃወም ትላንት ማክሰኞ አንድ ጃፓናዊ ራሱን በእሳት ማቃጠሉ ተዘግቧል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አቅራቢያ ግለሰቡ ራሱን ሲያቃጥል የተመለከቱ የዐይን እማኞች ለፖሊስ ደውለው አሳውቀዋል ። ፖሊሶቹ በቦታው ደርሰው እሳቱን ካጠፉ በኋላ ግለሰቡን ወደ ሆስፒታል ወስደዋል። ግለሰቡ ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ነፍሱን ያውቅ ነበር ተብሏል። ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰበትና አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ገና አልታወቀም። ግለሰቡ በ70ዎቹ ዕድሜ ክልል እንደሚገኝ የጃፓን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። መንግሥት ስለ ግለሰቡ ተቃውሞ እስካሁን አስተያየቱን አልሰጠም። ሆኖም የሺንዞ አቤን ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚቃወሙ ጃፓናውያን ቁጥር ባለፉት ወራት እየጨመረ መጥቷል። አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች ለቀብሩ ከፍተኛ ወጪ እየወጣ ነው ብለው ያምናሉ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ለፓርቲያቸው ቅስቀሳ ሲያደርጉ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል። ግለሰቡ ራሱን ከማቃጠሉ አስቀድሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አካባቢ ቀብሩን ሲቃወም እንደነበረ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ይገኛሉ። ፖሊስ ግን ገና አላረጋገጠም። ግለሰቡ ራሱን ያቃጠለበት አካባቢ ቀብሩን የሚቃወም መልዕክት ያዘሉ ወረቀቶች እደተገኙም ተዘግቧል። ጃፓንን ለረዥም ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ሺንዞ አቤ ግድያ ጃፓንን ሲያስደነግጥ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አውግዞታል። ጃፓን ውስጥ እንዲህ ያለ በአደባባይ ላይ የሚከሰት ፖለቲካዊ ቀውስ ወይም የተኩስ ጥቃት የተለመደ አይደለም። በበተጨማሪም በአገሪቱ ውስጥ ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓትም አልተለመደም። የሺንዞ አቤን ብሔራዊ ቀብር እየተቃወሙ የሚገኙ ጃፓናውያን፣ ወደ 11.4 ሚሊዮን ዶላር የሕዝብ ገንዘብ የሚጠይቀውን ሥነ ሥርዓት ኮንነዋል። ኮንስቲትዩሽናል ዴሞክራቲክ ፓርቲ የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ በቀጣዩ ሳምንት በሚካሄደው ብሔራዊ ቀብር እንደማይሳተፍ አስታውቋል። ሺንዞ አቤን ተኩሶ የገደላቸው ግለሰብ እንዳለው፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ዩኒፊኬሽን ከሚባል እምነት ጋር ትስስር ስላላቸው ነው የገደላቸው። ይህ እምነት የቤተሰቦቹን ሃብት አሟጦ እንደወሰደም ተናግሯል። የጃፓን የሕዝብ ተወካዮች ከዚህ እምነት ጋር ትስስር አላቸው በሚል ሌሎችም ጃፓናውያን ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። | ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የተዘጋጀው ብሔራዊ ቀብር ‘ውድ ነው’ ያለው ጃፓናዊ ራሱን አቃጠለ ለቀድሞው የጃፓን ፕሬዝዳንት የተዘጋጀውን ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመቃወም አንድ ጃፓናዊ ራሱን በእሳት አቃጠለ። ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ በሰው እጅ ለተገደሉት ሺንዞ አቤ ቀብር በመቶዎች የሚቆጠሩ የውጭ አገራት መሪዎች ተጠርተዋል። የጃፓን መንግሥት ያዘጋጀችው ይህ ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት በሚቀጥለው ሳምንት መስከረም 17/2015 ዓ.ም. ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህንን ሥነ ሥርዓት በመቃወም ትላንት ማክሰኞ አንድ ጃፓናዊ ራሱን በእሳት ማቃጠሉ ተዘግቧል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አቅራቢያ ግለሰቡ ራሱን ሲያቃጥል የተመለከቱ የዐይን እማኞች ለፖሊስ ደውለው አሳውቀዋል ። ፖሊሶቹ በቦታው ደርሰው እሳቱን ካጠፉ በኋላ ግለሰቡን ወደ ሆስፒታል ወስደዋል። ግለሰቡ ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ነፍሱን ያውቅ ነበር ተብሏል። ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰበትና አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ገና አልታወቀም። ግለሰቡ በ70ዎቹ ዕድሜ ክልል እንደሚገኝ የጃፓን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። መንግሥት ስለ ግለሰቡ ተቃውሞ እስካሁን አስተያየቱን አልሰጠም። ሆኖም የሺንዞ አቤን ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚቃወሙ ጃፓናውያን ቁጥር ባለፉት ወራት እየጨመረ መጥቷል። አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች ለቀብሩ ከፍተኛ ወጪ እየወጣ ነው ብለው ያምናሉ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ለፓርቲያቸው ቅስቀሳ ሲያደርጉ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል። ግለሰቡ ራሱን ከማቃጠሉ አስቀድሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አካባቢ ቀብሩን ሲቃወም እንደነበረ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ይገኛሉ። ፖሊስ ግን ገና አላረጋገጠም። ግለሰቡ ራሱን ያቃጠለበት አካባቢ ቀብሩን የሚቃወም መልዕክት ያዘሉ ወረቀቶች እደተገኙም ተዘግቧል። ጃፓንን ለረዥም ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ሺንዞ አቤ ግድያ ጃፓንን ሲያስደነግጥ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አውግዞታል። ጃፓን ውስጥ እንዲህ ያለ በአደባባይ ላይ የሚከሰት ፖለቲካዊ ቀውስ ወይም የተኩስ ጥቃት የተለመደ አይደለም። በበተጨማሪም በአገሪቱ ውስጥ ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓትም አልተለመደም። የሺንዞ አቤን ብሔራዊ ቀብር እየተቃወሙ የሚገኙ ጃፓናውያን፣ ወደ 11.4 ሚሊዮን ዶላር የሕዝብ ገንዘብ የሚጠይቀውን ሥነ ሥርዓት ኮንነዋል። ኮንስቲትዩሽናል ዴሞክራቲክ ፓርቲ የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ በቀጣዩ ሳምንት በሚካሄደው ብሔራዊ ቀብር እንደማይሳተፍ አስታውቋል። ሺንዞ አቤን ተኩሶ የገደላቸው ግለሰብ እንዳለው፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ዩኒፊኬሽን ከሚባል እምነት ጋር ትስስር ስላላቸው ነው የገደላቸው። ይህ እምነት የቤተሰቦቹን ሃብት አሟጦ እንደወሰደም ተናግሯል። የጃፓን የሕዝብ ተወካዮች ከዚህ እምነት ጋር ትስስር አላቸው በሚል ሌሎችም ጃፓናውያን ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cl432pp7py8o |
5sports
| ሴኔጋላዊው የፒኤስጂ ተጫዋች ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ድጋፍ አልሰጠም መባሉ አነጋጋሪ ሆነ | የፒኤስጂው ኢድሪሳ ጋና ጌዬ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪን ድጋፍ ለመግለጽ የቀረበውን መለያ ለመልበስ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል መባሉ አነጋጋሪ ሆነ። ሴኔጋላዊው የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን አማካይ ኢድሪሳ ጌዬ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪን ድጋፍ ለመግለጽ የቀረበውን መለያ አለብስም ብሏል ሲል አንድ ጋዜጣ ዘግቧል። የፈረንሳይ ሊግ፤ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ለሚያደርጉት እንቅስቃሴን ድጋፉን ለመግለጽ ተጫዋቾች መለያቸው ላይ የሚሰፍረውን ቁጥር በቀስተ ደመና ቀለም እንዲሆን አድርጓል። ባሳለፍነው ሳምንት በነበሩት የሊግ ፍልሚያዎች ተጫዋቾች ይህን መለያ ለብሰው ሜዳ ገብተዋል። አማካዩ ኢድሪሰ ጌዬ ግን ይህን መለያ ለብሶ ወደ ሜዳ ለመግባት ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ በስፋት ተዘግቧል። የፒኤስጂው አሰልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቸቲኖ አማካዩ ሳይሰለፍ የቀረው “በግላዊ ምክንያቶች” ነው ከማለት ውጪ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። አጥባቂ የእልምና እምነት ተከታይ የሆነው ኢድሪሳ ይህን መለያ ለብሼ ወደ ሜዳ አልገባም ብሏል የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ድጋፍ እና ነቀፌታ እያስተናገደ ይገኛል። ለኢድሪሳ ድጋፋቸውን ከሰጡት መካከል የሴኔጋሉ ፕሬዝደንት ማኪ ሳል ይገኙበታል። ፕሬዝደንቱ የኢድሪሳ “ኃይማኖታዊ መርሆች መከበር አለባቸው” ብለዋል። በተቃራኒው በቅርቡ በተካሄደው የፈረንሳይ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እጩ የነበሩት ቫለሪ ፔክሬስ ተጫዋቹ ላይ እገዳ መጣል አለበት ብለዋል። ፕሬዝደንታዊ እጩዋ “የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪን ጥላቻ ለመግታት ለሚደረገው ጥረት ኢድሪሳ ጋና ፍቃደኛ አለመሆን ያለ ቅጣት መታለፍ የለበትም” ሲሉ ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል። ሃይማኖተኛ ሕዝብ ባላት ሴኔጋል የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በብዙዎች ዘንድ ጸያፍ ድርጊት ተደርጎ ይቆጠራል። በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በአምስት ዓመት እስር እና በ2500 ዶላር ያስቀጣል። በዚህ ምክንያት በአገሪቱ የሚገኙ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ማንነታቸውን በመደበቅ ለመኖር ይገደዳሉ። | ሴኔጋላዊው የፒኤስጂ ተጫዋች ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ድጋፍ አልሰጠም መባሉ አነጋጋሪ ሆነ የፒኤስጂው ኢድሪሳ ጋና ጌዬ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪን ድጋፍ ለመግለጽ የቀረበውን መለያ ለመልበስ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል መባሉ አነጋጋሪ ሆነ። ሴኔጋላዊው የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን አማካይ ኢድሪሳ ጌዬ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪን ድጋፍ ለመግለጽ የቀረበውን መለያ አለብስም ብሏል ሲል አንድ ጋዜጣ ዘግቧል። የፈረንሳይ ሊግ፤ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ለሚያደርጉት እንቅስቃሴን ድጋፉን ለመግለጽ ተጫዋቾች መለያቸው ላይ የሚሰፍረውን ቁጥር በቀስተ ደመና ቀለም እንዲሆን አድርጓል። ባሳለፍነው ሳምንት በነበሩት የሊግ ፍልሚያዎች ተጫዋቾች ይህን መለያ ለብሰው ሜዳ ገብተዋል። አማካዩ ኢድሪሰ ጌዬ ግን ይህን መለያ ለብሶ ወደ ሜዳ ለመግባት ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ በስፋት ተዘግቧል። የፒኤስጂው አሰልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቸቲኖ አማካዩ ሳይሰለፍ የቀረው “በግላዊ ምክንያቶች” ነው ከማለት ውጪ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። አጥባቂ የእልምና እምነት ተከታይ የሆነው ኢድሪሳ ይህን መለያ ለብሼ ወደ ሜዳ አልገባም ብሏል የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ድጋፍ እና ነቀፌታ እያስተናገደ ይገኛል። ለኢድሪሳ ድጋፋቸውን ከሰጡት መካከል የሴኔጋሉ ፕሬዝደንት ማኪ ሳል ይገኙበታል። ፕሬዝደንቱ የኢድሪሳ “ኃይማኖታዊ መርሆች መከበር አለባቸው” ብለዋል። በተቃራኒው በቅርቡ በተካሄደው የፈረንሳይ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እጩ የነበሩት ቫለሪ ፔክሬስ ተጫዋቹ ላይ እገዳ መጣል አለበት ብለዋል። ፕሬዝደንታዊ እጩዋ “የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪን ጥላቻ ለመግታት ለሚደረገው ጥረት ኢድሪሳ ጋና ፍቃደኛ አለመሆን ያለ ቅጣት መታለፍ የለበትም” ሲሉ ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል። ሃይማኖተኛ ሕዝብ ባላት ሴኔጋል የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በብዙዎች ዘንድ ጸያፍ ድርጊት ተደርጎ ይቆጠራል። በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በአምስት ዓመት እስር እና በ2500 ዶላር ያስቀጣል። በዚህ ምክንያት በአገሪቱ የሚገኙ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ማንነታቸውን በመደበቅ ለመኖር ይገደዳሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-61492225 |
2health
| በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች መጨመሩን ተከትሎ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መመሪያዋን አሻሻለች | በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ፣ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዝ የተሻሻለ መመሪያ መውጣቱ ተገልጿል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናት ማስክ እንዲያደርጉ፣ በሰርግ፣ በቀብር እንዲሁም በስብሰባዎች ላይ የሚገኙ ሰዎች ብዛት ከአምሳ እንዳይበልጥ፣ በካፌዎችና በሬስቶራንቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዳይቀመጡ የሚሉና ሌሎች ዝርዝሮች ተካትተውበታል። የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያወጡት ይህ መመሪያ ከነሐሴ 13 ፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ማንኛውም ሰው ማስክ ሳያደርግ እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድ ሲሆን ይህም ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናትን እንደሚጨምር የጤና ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አስገዳጅ የማይሆነው ከስድስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንዲሁም በማስረጃ የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ወይም መሰል ችግር ካለባቸው በስተቀር ሁሉም ዜጎች ሲንቀሳቀሱ ማስክ ማድረግ አለባቸው። የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎች በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከመደረግ በተጨማሪ ሁለት የአዋቂ እርምጃ (አካላዊ ርቀት) መጠበቅ አስገዳጅ ነው ተብሏል። በማንኛውም መንግስታዊ እና የግል ተቋም አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ላይ ሰራተኞችና ደንበኞች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ ወይም አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲገለገሉና ማስክ እንዲያደርጉ ያስገድዳል። በእነዚህ የአገልግሎት ስፍራዎች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግም ተከልክሏል። ማንኛውም የመንግሥታዊ እና የግል ተቋማት በመግቢያና መውጫ በሮች የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን ማቅረብና አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው ብሏል። በአስከሬን ማስተካከል፣ ግነዛና ማጓጓዝ ወቅትም ሊደረጉ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎችም መመሪያው አስቀምጧል። ከቀብር በኋላ ሀዘን ለማስተዛዘን በድንኳን፣ በቤት ውስጥ ወይም ለዚሁ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ለቅሶ የሚደርሰው ሰው ከ50 እንዳይበልጥ ያዛል። አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አለባቸው ይላል። በስብሰባም ወቅት በተመሳሳይ የኮቪድ-19 ጥንቃቄዎችን በተከተለ መልኩ እስከ 50 ሰው መሰብሰብ ይቻላል። ከ50 ሰዎች በላይ መሰብሰብ ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ስብሰባው ሊደረግበት የታሰበበት ስፍራ ጠቅላላ ስፋት ከግምት ውስጥ ሊገባ እንደሚገባ ጠቁሞ በዚህም መሰረት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛ በማይበልጥ መሆን አለበት። እንዲሁም ልዩ ፈቃድ ከሰላም ሚኒስቴር እንዲሁም ከክልሉ፣ ዞን እና ወረዳ የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች መገኘት አለበት። ስብሰባውንም የጠራው አካል የመከላከያ ዘዴዎቹ መተግበራቸውን ማረጋገጥ ይገባዋል ይላል። የሃይማኖት ስነ ስርዓትን በተመለከተ ሃይማኖታዊ አገልግልቶች አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ሊፈፀሙ እንደሚገባ መመሪያው አስቀምጧል። የሃይማኖት ስርዓት የሚከናወንባቸው ስፍራዎችም እንዲሁ መያዝ ከሚችሉት አንድ አራተኛ በማይበልጥ ስርዓቱን እንዲያካሂዱ ተቀምጧል። በእነዚህ የእምነት ተቋማት ቅጥር ግቢ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ ነው። የቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶችን በተመለከተም ለልደት፣ ምረቃ፣ ማህበር እና ቀብር እና ከቀብር መልስ ያሉ ስነ ስርዓቶች ውጭ እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበራዊ በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለም ነው። ሰርግን በተመለከተም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን የኮቪድ-19 መከላከያ የንፅህና እርምጃዎች በተገበረ መልኩ ከ50 በማይበልጡ ሰዎች ማካሄድ እንደሚቻል ተቀምጧል። የአደባባይ በዓላትን አከባበር ጋር ተያይዞ ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ የአደባባይ ላይ በዓላት የወረርሽኙ ስርጭት እስኪረጋጋ ድረስ ባይደረጉ በማለትም ምክረ-ኃሳብ አስቀምጧል። በዓላቱ የሚደረጉ ከሆነ ግን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መደረጉን እንዲሁም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ብሏል። ስፍራዎቹም ከሚይዙት ቦታ ከአንድ አራተኛ ቦታ በማይበልጥ ሰው ስርዓቱ ሊካሄድ እንደሚገባም ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብሏል። ስፖርታዊ ውድድሮችም በተመለከተ በተመሳሳይ ስፍራው ከሚይዘው የታዳሚ ብዛት ከአንድ አራተኛ በማይበልጥ እንዲሆን ተቀምጧል። አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ካፌዎች፣ ባር፣ ሬስቶራንቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የመዝናኛ እና መጫዎቻ አገልግሎቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ አይችሉም። በእያንዳንዱ ጠረጴዛ የሁለት ሜትር ርቀት መጠበቅ አለበት። አገልግሎትን የሚሰጡም ሆነ ደንበኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እየታየ በሌላ መመሪያ እስኪወሰን ድረስ የአረጋዊያን መጦሪያዎች ስፍራዎች እና የማገገሚያ ማዕከላት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በአካል መጠየቅ የተከለከለ መሆኑን አስፍሮ ነገር ግን እርዳታ ማቅረብ የሚፈልጉ ከተቋሙ አስተዳደር ድረስ በመቅረብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉም ጠቁሟል። በማረሚያ ቤቶች ላይ ታራሚን ለመጠየቅ አካላዊ ርቀትን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ የኮቪድ- 19 መከላከያን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ተብሏል። በቤት ውስጥ ማቆያ እና እንክብካቤን በተመለከተ ቀለል ባለ በኮቪድ-19 የተያዘ ታማሚ በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 ህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል። ህመምተኞቹ ከሌላው የቤተሰብ አባላት ራሳቸውን መለየት፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ ቢያንስ ለ10 ተከታታይ ቀናት መለየትና ከቤት አለመውጣት ይጠበቅባቸዋል። ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ቫይረሱ እንዳለበት እያወቀ ወደ ሃገር ውስጥ መግባት፣ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት የተከለከለ ነው። ከትራንዚት መንገደኛ በስተቀር በአገሪቱ አለም አቀፍ ማረፊያ በኩል የሚገባ ከአስር አመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ተጓዥ ከ120 ሰዓት ወይም አምስት ቀን በላይ ያልሆነው የተረጋጋጠ ምርመራ ኔጌቲቭ ውጤት ይዞ መምጣትና ለሰባት ቀናት መንገደኞች ራሳቸውን ለይተው ማቆየት አለባቸው። ነገር ሰባት ቀናት ራሳቸውን ለመለየት የማይገደዱት በ90 ቀናት ውስጥ ኮቪድ-19 ታመው ያገገሙ፣ ዲፕሎማቶች፣ የኮቪድ-19 ክትባትን በተሟላ ሁኔታ ወስደው ያጠናቀቁ ከሆነ ለተለያዩ ስብሰባዎች የሚመጡ ቱሪስቶች ወይም ለድንገተኛ ጉዳይ የሚመጡ መንገደኞች ናቸው። ለተለያዩ ጉባዔ የሚመጡ ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግና ውጤታቸው ኔጌቲቭ መሆን አለበት። ማንኛውም ፖዘቲቭ ሰው ወደ ሃገር ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው።. በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚያልፉ የትራንዚት መንገደኞችን በተመለከተም በረራቸው እስኪደርስ ድረስ አየር መንገዱን ለቆ መሄድ ወይም አየር መንገዱ ከለያቸው ሆቴሎች ውጪ ወደ ከተማ መግባት አይችሉም። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳምንታት በፊት ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ እንደሆነ አስታውቋል። በተለያዩ የዓለም ሀገራት መረጃዎች እና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱ ታውቋል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ሲሆን በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 የዴልታ ቫይረስ መኖሩ ባይረጋገጥም የሶስተኛ ዙር ወረርሽኝ መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየት መጀመራቸውም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሁለተኛው ዙር ካበቃ በኋላ በተወሰነ መልኩ በማህበረሰቡ መዘናጋቶች እንዲሁም የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ባለመተግበራቸው ሶስተኛው ዙር ሊከሰት የሚችልበት ምልክቶች እየታዩ ነው። ተቋሙ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎቹ እንዲከበሩና ማስክ ማድረግ፣የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ እና ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 መከላከከልና መቆጣጠር እንደሚቻልም አሳሳስቧል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተርር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው "ከፊታችን የተጋረጠብንን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንዲያልፍ፣ የጥንቃቄ መንገዶችን፣ ክልከላዎችና ግዴታዎች እያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ አመራር፣ የህግ አስከባሪ አካላት በከፍተኛ የሃላፊነት መንፈስ በመተግበርና በማስፈፀም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ" ማለታቸውም በመግለጫው ላይ ሰፍሯል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ 295 ሺህ 19 ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 268 ሺህ 252 ግለሰቦች ከኮቪድ-19 ቫይረስ አገግመዋል እንዲሁም 4ሺህ 553 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አጠቃላይ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥርም 2,335 ሺህ 71 ሲሆን አገሪቷ በአጠቃላይ 3,134 ሺህ 967 ምርመራዎችን አካሂዳለች። | በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች መጨመሩን ተከትሎ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መመሪያዋን አሻሻለች በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ፣ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዝ የተሻሻለ መመሪያ መውጣቱ ተገልጿል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናት ማስክ እንዲያደርጉ፣ በሰርግ፣ በቀብር እንዲሁም በስብሰባዎች ላይ የሚገኙ ሰዎች ብዛት ከአምሳ እንዳይበልጥ፣ በካፌዎችና በሬስቶራንቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዳይቀመጡ የሚሉና ሌሎች ዝርዝሮች ተካትተውበታል። የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያወጡት ይህ መመሪያ ከነሐሴ 13 ፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ማንኛውም ሰው ማስክ ሳያደርግ እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድ ሲሆን ይህም ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናትን እንደሚጨምር የጤና ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አስገዳጅ የማይሆነው ከስድስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንዲሁም በማስረጃ የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ወይም መሰል ችግር ካለባቸው በስተቀር ሁሉም ዜጎች ሲንቀሳቀሱ ማስክ ማድረግ አለባቸው። የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎች በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከመደረግ በተጨማሪ ሁለት የአዋቂ እርምጃ (አካላዊ ርቀት) መጠበቅ አስገዳጅ ነው ተብሏል። በማንኛውም መንግስታዊ እና የግል ተቋም አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ላይ ሰራተኞችና ደንበኞች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ ወይም አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲገለገሉና ማስክ እንዲያደርጉ ያስገድዳል። በእነዚህ የአገልግሎት ስፍራዎች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግም ተከልክሏል። ማንኛውም የመንግሥታዊ እና የግል ተቋማት በመግቢያና መውጫ በሮች የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን ማቅረብና አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው ብሏል። በአስከሬን ማስተካከል፣ ግነዛና ማጓጓዝ ወቅትም ሊደረጉ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎችም መመሪያው አስቀምጧል። ከቀብር በኋላ ሀዘን ለማስተዛዘን በድንኳን፣ በቤት ውስጥ ወይም ለዚሁ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ለቅሶ የሚደርሰው ሰው ከ50 እንዳይበልጥ ያዛል። አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አለባቸው ይላል። በስብሰባም ወቅት በተመሳሳይ የኮቪድ-19 ጥንቃቄዎችን በተከተለ መልኩ እስከ 50 ሰው መሰብሰብ ይቻላል። ከ50 ሰዎች በላይ መሰብሰብ ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ስብሰባው ሊደረግበት የታሰበበት ስፍራ ጠቅላላ ስፋት ከግምት ውስጥ ሊገባ እንደሚገባ ጠቁሞ በዚህም መሰረት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛ በማይበልጥ መሆን አለበት። እንዲሁም ልዩ ፈቃድ ከሰላም ሚኒስቴር እንዲሁም ከክልሉ፣ ዞን እና ወረዳ የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች መገኘት አለበት። ስብሰባውንም የጠራው አካል የመከላከያ ዘዴዎቹ መተግበራቸውን ማረጋገጥ ይገባዋል ይላል። የሃይማኖት ስነ ስርዓትን በተመለከተ ሃይማኖታዊ አገልግልቶች አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ሊፈፀሙ እንደሚገባ መመሪያው አስቀምጧል። የሃይማኖት ስርዓት የሚከናወንባቸው ስፍራዎችም እንዲሁ መያዝ ከሚችሉት አንድ አራተኛ በማይበልጥ ስርዓቱን እንዲያካሂዱ ተቀምጧል። በእነዚህ የእምነት ተቋማት ቅጥር ግቢ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ ነው። የቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶችን በተመለከተም ለልደት፣ ምረቃ፣ ማህበር እና ቀብር እና ከቀብር መልስ ያሉ ስነ ስርዓቶች ውጭ እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበራዊ በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለም ነው። ሰርግን በተመለከተም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን የኮቪድ-19 መከላከያ የንፅህና እርምጃዎች በተገበረ መልኩ ከ50 በማይበልጡ ሰዎች ማካሄድ እንደሚቻል ተቀምጧል። የአደባባይ በዓላትን አከባበር ጋር ተያይዞ ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ የአደባባይ ላይ በዓላት የወረርሽኙ ስርጭት እስኪረጋጋ ድረስ ባይደረጉ በማለትም ምክረ-ኃሳብ አስቀምጧል። በዓላቱ የሚደረጉ ከሆነ ግን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መደረጉን እንዲሁም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ብሏል። ስፍራዎቹም ከሚይዙት ቦታ ከአንድ አራተኛ ቦታ በማይበልጥ ሰው ስርዓቱ ሊካሄድ እንደሚገባም ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብሏል። ስፖርታዊ ውድድሮችም በተመለከተ በተመሳሳይ ስፍራው ከሚይዘው የታዳሚ ብዛት ከአንድ አራተኛ በማይበልጥ እንዲሆን ተቀምጧል። አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ካፌዎች፣ ባር፣ ሬስቶራንቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የመዝናኛ እና መጫዎቻ አገልግሎቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ አይችሉም። በእያንዳንዱ ጠረጴዛ የሁለት ሜትር ርቀት መጠበቅ አለበት። አገልግሎትን የሚሰጡም ሆነ ደንበኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እየታየ በሌላ መመሪያ እስኪወሰን ድረስ የአረጋዊያን መጦሪያዎች ስፍራዎች እና የማገገሚያ ማዕከላት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በአካል መጠየቅ የተከለከለ መሆኑን አስፍሮ ነገር ግን እርዳታ ማቅረብ የሚፈልጉ ከተቋሙ አስተዳደር ድረስ በመቅረብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉም ጠቁሟል። በማረሚያ ቤቶች ላይ ታራሚን ለመጠየቅ አካላዊ ርቀትን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ የኮቪድ- 19 መከላከያን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ተብሏል። በቤት ውስጥ ማቆያ እና እንክብካቤን በተመለከተ ቀለል ባለ በኮቪድ-19 የተያዘ ታማሚ በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 ህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል። ህመምተኞቹ ከሌላው የቤተሰብ አባላት ራሳቸውን መለየት፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ ቢያንስ ለ10 ተከታታይ ቀናት መለየትና ከቤት አለመውጣት ይጠበቅባቸዋል። ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ቫይረሱ እንዳለበት እያወቀ ወደ ሃገር ውስጥ መግባት፣ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት የተከለከለ ነው። ከትራንዚት መንገደኛ በስተቀር በአገሪቱ አለም አቀፍ ማረፊያ በኩል የሚገባ ከአስር አመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ተጓዥ ከ120 ሰዓት ወይም አምስት ቀን በላይ ያልሆነው የተረጋጋጠ ምርመራ ኔጌቲቭ ውጤት ይዞ መምጣትና ለሰባት ቀናት መንገደኞች ራሳቸውን ለይተው ማቆየት አለባቸው። ነገር ሰባት ቀናት ራሳቸውን ለመለየት የማይገደዱት በ90 ቀናት ውስጥ ኮቪድ-19 ታመው ያገገሙ፣ ዲፕሎማቶች፣ የኮቪድ-19 ክትባትን በተሟላ ሁኔታ ወስደው ያጠናቀቁ ከሆነ ለተለያዩ ስብሰባዎች የሚመጡ ቱሪስቶች ወይም ለድንገተኛ ጉዳይ የሚመጡ መንገደኞች ናቸው። ለተለያዩ ጉባዔ የሚመጡ ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግና ውጤታቸው ኔጌቲቭ መሆን አለበት። ማንኛውም ፖዘቲቭ ሰው ወደ ሃገር ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው።. በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚያልፉ የትራንዚት መንገደኞችን በተመለከተም በረራቸው እስኪደርስ ድረስ አየር መንገዱን ለቆ መሄድ ወይም አየር መንገዱ ከለያቸው ሆቴሎች ውጪ ወደ ከተማ መግባት አይችሉም። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳምንታት በፊት ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ እንደሆነ አስታውቋል። በተለያዩ የዓለም ሀገራት መረጃዎች እና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱ ታውቋል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ሲሆን በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 የዴልታ ቫይረስ መኖሩ ባይረጋገጥም የሶስተኛ ዙር ወረርሽኝ መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየት መጀመራቸውም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሁለተኛው ዙር ካበቃ በኋላ በተወሰነ መልኩ በማህበረሰቡ መዘናጋቶች እንዲሁም የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ባለመተግበራቸው ሶስተኛው ዙር ሊከሰት የሚችልበት ምልክቶች እየታዩ ነው። ተቋሙ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎቹ እንዲከበሩና ማስክ ማድረግ፣የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ እና ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 መከላከከልና መቆጣጠር እንደሚቻልም አሳሳስቧል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተርር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው "ከፊታችን የተጋረጠብንን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንዲያልፍ፣ የጥንቃቄ መንገዶችን፣ ክልከላዎችና ግዴታዎች እያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ አመራር፣ የህግ አስከባሪ አካላት በከፍተኛ የሃላፊነት መንፈስ በመተግበርና በማስፈፀም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ" ማለታቸውም በመግለጫው ላይ ሰፍሯል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ 295 ሺህ 19 ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 268 ሺህ 252 ግለሰቦች ከኮቪድ-19 ቫይረስ አገግመዋል እንዲሁም 4ሺህ 553 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አጠቃላይ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥርም 2,335 ሺህ 71 ሲሆን አገሪቷ በአጠቃላይ 3,134 ሺህ 967 ምርመራዎችን አካሂዳለች። | https://www.bbc.com/amharic/58297000 |
5sports
| ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከወራት በፊት ለፈጸመው ጥቃት የሁለት ጨዋታ ቅጣት ተጣለበት | የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች የነበረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከአንድ የኤቨርተን ደጋፊ እጅ ላይ ሞባይል ስልክ መትቶ በማስጣሉ ከሁለት የአገር ውስጥ ጨዋታዎች እገዳ ተጥሎበታል። የ37 ዓመቱ ሮናልዶ ይህንን ድርጊት የፈጸመው ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ላይ በጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም ሽንፈት ከገጠማቸው በኋላ በስታዲየሙ መተላላፊ በኩል ሲወርድ መሆኑ ተገልጿል። ከቡድኑ ማንችስተር ዩናይትድ እና ከአሰልጣኑ ኤሪክ ቴን ሃግ ጋር በተፈጠረው የግንኙነት መሻከር ምክንያት፣ ባለፈው ማክሰኞ ሮናልዶ እና ቡድኑ በጋራ በደረሱት ስምምነት ተጫዋቹ ተሰናብቷል። ሮናልዶ ከወራት በፊት በአንድ ተመልካች ላይ ፈጽሞታል ከተባለው ጥቃት ጋር ተያይዞ ከሁለት ጨዋታ ከመታገዱ በተጨማሪም፣ የእግር ኳስ ማኅበሩ የ50,000 ፓወንድ ቅጣትም ጥሎበታል። ይህ የጨዋታ ዕገዳ ግን ዛሬ ከአፍሪካዋ ተወካይ ጋር በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያዋን ግጥሚያ ለምታደርገው ለአገሩ ፖርቱጋል ከመሰለፍ አያግደውም ተብሏል። በኳታሩ የዓለም ዋንጫ በምድብ 'ሸ' ከጋና፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከኡራጓይ ጋር የተደለደለችውን የፖርቱጋልን ብሔራዊ ቡድን በአምበልነት የሚመራው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትልቅ ኃላፊነት ይጠብቀዋል። ከማንችስተር ዩናይትድ ከተሰናበተ በኋላ በአሁኑ ወቅት የሚጫወትበት ቡድን የሌለው ሮናልዶ፣ የተጣለበት የክለብ ጨዋታ ዕገዳ በአንግሊዝም ሆነ በሌላ አገር በቀጣይ በሚቀላቀው ቡድን ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል። ነገር ግን ይህ ቅጣት ቡድኑ በሚያደርገው የአገር ውስጥ የሊግ ጨዋታ ላይ እንጂ ሻምፒዮን ሊግን በመሳሰሉ አህጉራዊ የክለቡ ተሳትፎዎች ላይ ተፈጻሚ አይደረግም ተብሏል። ሮናልዶን ለሁለት ጨዋታ ዕገዳ የዳረገውን ድርጊት በተመለከተ በእንግሊዝ የእግር ኳስ ማኅበር በኩል ገለልተኛ ማጣራት ከተካሄደ በኋላ ነው ተገቢ ያልሆነ እና ጎጂ ጥፋት ፈጽሟል ተብሎ ጥፋተኛ የተባለው። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ሮናልዶ ከፖሊስ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ሲሆን፣ ጥቃት አድርሶበታል የተባለው ወጣት የእግር ኳስ ተመልካችን ከክስተቱ በኋላ ይቅርታ መጠየቁም ተነግሯል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበር ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተገቢ ያልሆነ ባህሪይ ማሳየቱን እንዳመነ፣ ነገር ግን ጎጂ ፀባይ የተባለውን እንዳልተቀበለው ገልጸወል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ቀድሞ ክለቡ ማንችስተር ዩናይትድ ከተመለሰ በኋላ የነበረው ቆይታውን እንዲያበቃ ያደረገው አወዛጋቢ ቃለ ምልልስ ከሰጠ በኋላ ነበር። በቃለ ምልልሱ ሮናልዶ ቡድኑን ክፉኛ ያብጠለጠለ ሲሆን፣ ለአሰልጣኙ ኤሪክ ቴን ሃግም “አክብሮት እንደሌለው” ከገለጸ በኋላ መነጋገሪያ ሆኖ ትችትና ድጋፍ ከተለያዩ ወገኖች ደርሶታል። ይህ ሁኔታ የፈጠረው መቃቃርም ተጫዋቹ በቡድኑ ውስጥ የመቀጠሉን ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ አስገብቶ ከቆየ ከሳምንት በኋላ በስምምነት ከኦልትራፎርድ ተሰናብቷል። ነገር ግን ሮናልዶ በቀጣይ ወደ የትኛው አገር እና ቡድን ሊያመራ እንደሚችል አስካሁን የታወቀ ነገር የለም። | ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከወራት በፊት ለፈጸመው ጥቃት የሁለት ጨዋታ ቅጣት ተጣለበት የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች የነበረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከአንድ የኤቨርተን ደጋፊ እጅ ላይ ሞባይል ስልክ መትቶ በማስጣሉ ከሁለት የአገር ውስጥ ጨዋታዎች እገዳ ተጥሎበታል። የ37 ዓመቱ ሮናልዶ ይህንን ድርጊት የፈጸመው ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ላይ በጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም ሽንፈት ከገጠማቸው በኋላ በስታዲየሙ መተላላፊ በኩል ሲወርድ መሆኑ ተገልጿል። ከቡድኑ ማንችስተር ዩናይትድ እና ከአሰልጣኑ ኤሪክ ቴን ሃግ ጋር በተፈጠረው የግንኙነት መሻከር ምክንያት፣ ባለፈው ማክሰኞ ሮናልዶ እና ቡድኑ በጋራ በደረሱት ስምምነት ተጫዋቹ ተሰናብቷል። ሮናልዶ ከወራት በፊት በአንድ ተመልካች ላይ ፈጽሞታል ከተባለው ጥቃት ጋር ተያይዞ ከሁለት ጨዋታ ከመታገዱ በተጨማሪም፣ የእግር ኳስ ማኅበሩ የ50,000 ፓወንድ ቅጣትም ጥሎበታል። ይህ የጨዋታ ዕገዳ ግን ዛሬ ከአፍሪካዋ ተወካይ ጋር በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያዋን ግጥሚያ ለምታደርገው ለአገሩ ፖርቱጋል ከመሰለፍ አያግደውም ተብሏል። በኳታሩ የዓለም ዋንጫ በምድብ 'ሸ' ከጋና፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከኡራጓይ ጋር የተደለደለችውን የፖርቱጋልን ብሔራዊ ቡድን በአምበልነት የሚመራው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትልቅ ኃላፊነት ይጠብቀዋል። ከማንችስተር ዩናይትድ ከተሰናበተ በኋላ በአሁኑ ወቅት የሚጫወትበት ቡድን የሌለው ሮናልዶ፣ የተጣለበት የክለብ ጨዋታ ዕገዳ በአንግሊዝም ሆነ በሌላ አገር በቀጣይ በሚቀላቀው ቡድን ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል። ነገር ግን ይህ ቅጣት ቡድኑ በሚያደርገው የአገር ውስጥ የሊግ ጨዋታ ላይ እንጂ ሻምፒዮን ሊግን በመሳሰሉ አህጉራዊ የክለቡ ተሳትፎዎች ላይ ተፈጻሚ አይደረግም ተብሏል። ሮናልዶን ለሁለት ጨዋታ ዕገዳ የዳረገውን ድርጊት በተመለከተ በእንግሊዝ የእግር ኳስ ማኅበር በኩል ገለልተኛ ማጣራት ከተካሄደ በኋላ ነው ተገቢ ያልሆነ እና ጎጂ ጥፋት ፈጽሟል ተብሎ ጥፋተኛ የተባለው። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ሮናልዶ ከፖሊስ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ሲሆን፣ ጥቃት አድርሶበታል የተባለው ወጣት የእግር ኳስ ተመልካችን ከክስተቱ በኋላ ይቅርታ መጠየቁም ተነግሯል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበር ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተገቢ ያልሆነ ባህሪይ ማሳየቱን እንዳመነ፣ ነገር ግን ጎጂ ፀባይ የተባለውን እንዳልተቀበለው ገልጸወል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ቀድሞ ክለቡ ማንችስተር ዩናይትድ ከተመለሰ በኋላ የነበረው ቆይታውን እንዲያበቃ ያደረገው አወዛጋቢ ቃለ ምልልስ ከሰጠ በኋላ ነበር። በቃለ ምልልሱ ሮናልዶ ቡድኑን ክፉኛ ያብጠለጠለ ሲሆን፣ ለአሰልጣኙ ኤሪክ ቴን ሃግም “አክብሮት እንደሌለው” ከገለጸ በኋላ መነጋገሪያ ሆኖ ትችትና ድጋፍ ከተለያዩ ወገኖች ደርሶታል። ይህ ሁኔታ የፈጠረው መቃቃርም ተጫዋቹ በቡድኑ ውስጥ የመቀጠሉን ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ አስገብቶ ከቆየ ከሳምንት በኋላ በስምምነት ከኦልትራፎርድ ተሰናብቷል። ነገር ግን ሮናልዶ በቀጣይ ወደ የትኛው አገር እና ቡድን ሊያመራ እንደሚችል አስካሁን የታወቀ ነገር የለም። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c5180mk7p53o |
5sports
| አርሰናል፣ ዩናይትድ፣ ሊቨርፑል. . .ከዓለም ዋንጫ በፊት የመጨረሻውን ጨዋታ እነማን ያሸነፋሉ? | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሳምንታት ከዓይን ሊርቅ የአንድ ሳምንት ዕድሜ ይቀረዋል። ሊጉ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ምክንያት ይቋረጣል። የአስራ ስድስተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሑድ ይከናወናሉ። የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታን ክሪስ ሱቶን የሊጉን አስር ጨዋታ ግምት አስቀምጧል። ተጫዋቾች ድካም ላይ በመሆናቸው ከዓለም ዋንጫው በፊት አሰልጣኞች ከአቋም ጋር በተያያዘ እረፍት ለመስጠት ትልቅ ውሳኔ የሚሰጡበት ሳምንት ነው። ፔፕ ጋርዲዮላ ኃላፊነቱ ለክለቡ ስለሆነ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሲቲ ነው። ሲቲ ባለፈው ሳምንት በ10 ተጫዋቾች ከብዙ ልፋት በኋላ ከፍጹም ቅጣት ምት በተገኘች ጎል ቢያሸንፍም በዚህ ሳምንት ነገሮች ይቀሉታል። ብሬንትፎርዶች ከሜዳቸው ውጭ ጥሩ አይደሉም። ዘንድሮ ከሜዳቸው ውጭ ማሸነፍም አልቻሉም። ግምት፡ 4 - 0 ሁለቱ ቡድኖች በሳምንቱ አጋማሽ በካራባኦ ዋንጫ ሲገናኙ ተጨዋቾቻቸውን ቀይረዋል። በርንዝማውዝ ማሸነፉን ተከትሎም አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ላይ ጫናዎች በርትተዋል። ይህ ጨዋታ ከሳምንቱ አጋማሽ እንደሚለይ እሙን ነው። ኤቨርተን የፊት መስመሩ ክፍተት አለበት በርንማውዝ ደግሞ በሁለት ጎል ከመምራት ነጥብ መጣል ቀጥለዋል። ግምት፡ 1- 1 ናታን ጆንስ ሳውዝሃምፕተንን ይዘው ወደ አንፊልድ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀናሉ። ዘንድሮ ለሊቨርፑል የምሰጠው ግምት በብዛት ባይሳካም ከቶተንሃም ጋር የነበራቸውን ጨዋታ በትክክል ገምቼ ነበር። በአቋም መዋዠቅ ምክንያት ቀዮቹ ስለማሸነፋቸው እርግጠኛ አይደለሁም። ክሎፕ ከዓለም ዋንጫው በፊት ድል ለማስመዝገብ እንደሚትሩ እገምታለሁ። ግምት፡ 3- 0 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ክሪስታል ፓላስ ማንም የሰንጠረዡ ግርጌ ላይ በመሆን ወደ ዓለም ዋንጫው እረፈት ማቅናት ስለማይፈልግ ፎረስት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደርጋል። ፎረስት ባለፈው ሳምንት ከብሬንትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ ነበር። በኋላ ግን ተፍረከረኩ። በጨዋታው አንድ ነጥብ ከማግኘት ባለፈ በሳምንቱ አጋማሽ በተካሄድ የካራባኦ ዋንጫ ጨዋታ ቶተንሃምን አሸንፈዋል። ፓላስ ደግሞ ጥሩ ከመጫወት ባለፈ የፊት መስመሩ ድንቅ ነው። ብዙ ጨዋታን መግደል የሚችሉ ተጫዋቾች አሏቸው። ግምት፡ 1- 2 የስፐርሱ አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ ተጫዋቾቻቸው መዳከማቸውን ገልጸዋል። የሊድሱ ጄሴ ማርሽ ደግሞ ከሊቨርፑል ድል በኋላ ከበርንማውዝም ሦስት ነጥብ ነጥቀዋል። የቶተንሃምን ተከላካይ መስመር ማመን ቢከብድም ለመጥፎው የሳምንቱ አጋማሽ ሽንፈት ምላሽ ይሰጣሉ። ይህ ሁለቱም ቡድኖች ሊያሸንፉት የሚችሉት ዓይነት ጨዋታ ቢሆንም ግምት የምሰጠው ለቶተንሃም ነው። ግምት፡ 3 - 1 ሌስተር እያንሰራራ ሲሆን በዚህ ወቅት ውድድሩ እንዲቋረጥም አይፈልገም። የቡድኑ ተከላካይ መስመር ድንቅ ሲሆን ሃርቪ ባርነስ እና ጀምስ ማዲሰንም በጥሩ ብቃት ላይ ናቸው። ይህ ፉክክር ያለበት ጨዋታ ሲሆን ዌስት ሃም ወደ ብቃቱ ጥግ ባይደርስም የሚሸነፍ አይመስለኝም። ግምት፡ 1- 1 ቼልሲዎች ባለፈው ሳምንት ከአርሰናል ጋር ጥሩ አልነበሩም። አርሰናሎች የራሳቸው አጨዋወት ሲኖራቸው ሰማያዊዎቹ ግን ወደ ፊት ሲሄዱ ምን መሥራት እንዳሰቡ የሚያውቁ አይመስልም ነበር። ኒውካስሎች የትኛውም ውጤት ቢመዘገብ እስከ አራት ባለው ደረጃ ውስጥ የሚቆዩ ሲሆን በደረጃቸውም ሆነ በአጨዋወታቸው ደስተኞች ናቸው። ብዙ ጎሎች የሚቆጠሩበት ጨዋታ ባይሆንም ኒውካስሎች የሚያሽነፉ ይመስለኛል። ግምት፡ 1 0 ዎልቭሶች በዚህ ጨዋታ በስቲቭ ዴቪስ ቢመሩም አዲስ አሰልጣኝ በመሾማቸው ለአርሰናል ከባድ ይሆናል። የአርሰናል ደጋፊዎች ትኩረታቸው ሊጉ ላይ በመሆኑ በሳምንቱ አጋማሽ ከካራባኦ ዋንጫ መውጣታቸው አያሳስባቸውም። ቡድኑ ቼልሲን ሲያሸንፍ በራስ መተማመን የነበረው ሲሆን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታም ለዋንጫ እንደሚፎካከሩ ጠቁመዋል። ካላቸው የአጥቂ እና የተከላካይ መስመር ጥንካሬ አንጻር ጨዋታውን ያሸንፋሉ። ግምት፡ 0 - 2 ብራይትን ከ አስቶን ቪላ አዲስ አሰልጣኝ በመሾም ባለፈው ሳምንት ማንቸስተር ዩናይትድን ያሸነፉት ቪላዎች ድላቸውን ማስቀጥ ይፈልጋሉ። ከተከታታይ ድል በኋላ ብራይተኖች ጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። አሁን ባላቸው አቋም እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ቢያጠናቅቁ ይገባቸዋል። ግምት፡ 2 - 1 አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ በመጀመሪያዎቹ ወራት የዩናይትድ ቆይታቸው ደስተኛ ቢሆኑም ችግሮችን በሙሉ እንዳልፈቱ ባለፈው ሳምንት ተመልክተናል። ቡድኑም የዓለም ዋንጫውን እረፈት በመጠቀም መደራጀት ያለበት ይመስለኛል። አሰልጣኙ ሃሪ ማጓየርን አጥቂ በማድረግ እና ሮናልዶን አምበል በማድረግ ግራ አጋቢ ውሳኔ አሳልፈዋል። ከሜዳ ውጭ ሦስት ጊዜ የተሸነፈው ቡድናቸው ተመሳሳይ ዕጣ ይጠብቀዋል። ፉልሃም ባለፈው ሳምንት በ10 ተጫዋች ካሸነፋቸው ሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ መጥፎ ባይሆኑም የማሸነፍ መተማመን አልነበራቸውም። በሜዳቸው ድንቅ ድል በማስመዝገብ ወደ ዓለም ዋንጫው ይጓዛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 2 - 1 | አርሰናል፣ ዩናይትድ፣ ሊቨርፑል. . .ከዓለም ዋንጫ በፊት የመጨረሻውን ጨዋታ እነማን ያሸነፋሉ? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሳምንታት ከዓይን ሊርቅ የአንድ ሳምንት ዕድሜ ይቀረዋል። ሊጉ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ምክንያት ይቋረጣል። የአስራ ስድስተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሑድ ይከናወናሉ። የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታን ክሪስ ሱቶን የሊጉን አስር ጨዋታ ግምት አስቀምጧል። ተጫዋቾች ድካም ላይ በመሆናቸው ከዓለም ዋንጫው በፊት አሰልጣኞች ከአቋም ጋር በተያያዘ እረፍት ለመስጠት ትልቅ ውሳኔ የሚሰጡበት ሳምንት ነው። ፔፕ ጋርዲዮላ ኃላፊነቱ ለክለቡ ስለሆነ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሲቲ ነው። ሲቲ ባለፈው ሳምንት በ10 ተጫዋቾች ከብዙ ልፋት በኋላ ከፍጹም ቅጣት ምት በተገኘች ጎል ቢያሸንፍም በዚህ ሳምንት ነገሮች ይቀሉታል። ብሬንትፎርዶች ከሜዳቸው ውጭ ጥሩ አይደሉም። ዘንድሮ ከሜዳቸው ውጭ ማሸነፍም አልቻሉም። ግምት፡ 4 - 0 ሁለቱ ቡድኖች በሳምንቱ አጋማሽ በካራባኦ ዋንጫ ሲገናኙ ተጨዋቾቻቸውን ቀይረዋል። በርንዝማውዝ ማሸነፉን ተከትሎም አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ላይ ጫናዎች በርትተዋል። ይህ ጨዋታ ከሳምንቱ አጋማሽ እንደሚለይ እሙን ነው። ኤቨርተን የፊት መስመሩ ክፍተት አለበት በርንማውዝ ደግሞ በሁለት ጎል ከመምራት ነጥብ መጣል ቀጥለዋል። ግምት፡ 1- 1 ናታን ጆንስ ሳውዝሃምፕተንን ይዘው ወደ አንፊልድ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀናሉ። ዘንድሮ ለሊቨርፑል የምሰጠው ግምት በብዛት ባይሳካም ከቶተንሃም ጋር የነበራቸውን ጨዋታ በትክክል ገምቼ ነበር። በአቋም መዋዠቅ ምክንያት ቀዮቹ ስለማሸነፋቸው እርግጠኛ አይደለሁም። ክሎፕ ከዓለም ዋንጫው በፊት ድል ለማስመዝገብ እንደሚትሩ እገምታለሁ። ግምት፡ 3- 0 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ክሪስታል ፓላስ ማንም የሰንጠረዡ ግርጌ ላይ በመሆን ወደ ዓለም ዋንጫው እረፈት ማቅናት ስለማይፈልግ ፎረስት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደርጋል። ፎረስት ባለፈው ሳምንት ከብሬንትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ ነበር። በኋላ ግን ተፍረከረኩ። በጨዋታው አንድ ነጥብ ከማግኘት ባለፈ በሳምንቱ አጋማሽ በተካሄድ የካራባኦ ዋንጫ ጨዋታ ቶተንሃምን አሸንፈዋል። ፓላስ ደግሞ ጥሩ ከመጫወት ባለፈ የፊት መስመሩ ድንቅ ነው። ብዙ ጨዋታን መግደል የሚችሉ ተጫዋቾች አሏቸው። ግምት፡ 1- 2 የስፐርሱ አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ ተጫዋቾቻቸው መዳከማቸውን ገልጸዋል። የሊድሱ ጄሴ ማርሽ ደግሞ ከሊቨርፑል ድል በኋላ ከበርንማውዝም ሦስት ነጥብ ነጥቀዋል። የቶተንሃምን ተከላካይ መስመር ማመን ቢከብድም ለመጥፎው የሳምንቱ አጋማሽ ሽንፈት ምላሽ ይሰጣሉ። ይህ ሁለቱም ቡድኖች ሊያሸንፉት የሚችሉት ዓይነት ጨዋታ ቢሆንም ግምት የምሰጠው ለቶተንሃም ነው። ግምት፡ 3 - 1 ሌስተር እያንሰራራ ሲሆን በዚህ ወቅት ውድድሩ እንዲቋረጥም አይፈልገም። የቡድኑ ተከላካይ መስመር ድንቅ ሲሆን ሃርቪ ባርነስ እና ጀምስ ማዲሰንም በጥሩ ብቃት ላይ ናቸው። ይህ ፉክክር ያለበት ጨዋታ ሲሆን ዌስት ሃም ወደ ብቃቱ ጥግ ባይደርስም የሚሸነፍ አይመስለኝም። ግምት፡ 1- 1 ቼልሲዎች ባለፈው ሳምንት ከአርሰናል ጋር ጥሩ አልነበሩም። አርሰናሎች የራሳቸው አጨዋወት ሲኖራቸው ሰማያዊዎቹ ግን ወደ ፊት ሲሄዱ ምን መሥራት እንዳሰቡ የሚያውቁ አይመስልም ነበር። ኒውካስሎች የትኛውም ውጤት ቢመዘገብ እስከ አራት ባለው ደረጃ ውስጥ የሚቆዩ ሲሆን በደረጃቸውም ሆነ በአጨዋወታቸው ደስተኞች ናቸው። ብዙ ጎሎች የሚቆጠሩበት ጨዋታ ባይሆንም ኒውካስሎች የሚያሽነፉ ይመስለኛል። ግምት፡ 1 0 ዎልቭሶች በዚህ ጨዋታ በስቲቭ ዴቪስ ቢመሩም አዲስ አሰልጣኝ በመሾማቸው ለአርሰናል ከባድ ይሆናል። የአርሰናል ደጋፊዎች ትኩረታቸው ሊጉ ላይ በመሆኑ በሳምንቱ አጋማሽ ከካራባኦ ዋንጫ መውጣታቸው አያሳስባቸውም። ቡድኑ ቼልሲን ሲያሸንፍ በራስ መተማመን የነበረው ሲሆን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታም ለዋንጫ እንደሚፎካከሩ ጠቁመዋል። ካላቸው የአጥቂ እና የተከላካይ መስመር ጥንካሬ አንጻር ጨዋታውን ያሸንፋሉ። ግምት፡ 0 - 2 ብራይትን ከ አስቶን ቪላ አዲስ አሰልጣኝ በመሾም ባለፈው ሳምንት ማንቸስተር ዩናይትድን ያሸነፉት ቪላዎች ድላቸውን ማስቀጥ ይፈልጋሉ። ከተከታታይ ድል በኋላ ብራይተኖች ጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። አሁን ባላቸው አቋም እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ቢያጠናቅቁ ይገባቸዋል። ግምት፡ 2 - 1 አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ በመጀመሪያዎቹ ወራት የዩናይትድ ቆይታቸው ደስተኛ ቢሆኑም ችግሮችን በሙሉ እንዳልፈቱ ባለፈው ሳምንት ተመልክተናል። ቡድኑም የዓለም ዋንጫውን እረፈት በመጠቀም መደራጀት ያለበት ይመስለኛል። አሰልጣኙ ሃሪ ማጓየርን አጥቂ በማድረግ እና ሮናልዶን አምበል በማድረግ ግራ አጋቢ ውሳኔ አሳልፈዋል። ከሜዳ ውጭ ሦስት ጊዜ የተሸነፈው ቡድናቸው ተመሳሳይ ዕጣ ይጠብቀዋል። ፉልሃም ባለፈው ሳምንት በ10 ተጫዋች ካሸነፋቸው ሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ መጥፎ ባይሆኑም የማሸነፍ መተማመን አልነበራቸውም። በሜዳቸው ድንቅ ድል በማስመዝገብ ወደ ዓለም ዋንጫው ይጓዛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 2 - 1 | https://www.bbc.com/amharic/articles/c2595g1ew0ro |
5sports
| ቻይና ከክረምት ኦሊምፒክ እራሳቸውን የሚያገሉ አገራት 'የእጃቸውን ያገኛሉ' ስትል አስጠነቀቀች | ቻይና ከምታስተናግደው የቤይጂንግ የክረምት የኦሊምፒክ ጨዋታዎች እራሳቸውን የሚያገሉ አገራት "ለሚፈጽሙት ስህተት ዋጋ ይከፍሏታል" ስትል አስጠንቅቃለች። ቻይና ሰብአዊ መብት እየጣሰች ነው በማለት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አውስትራሊያና ካናዳ የመንግሥት ተወካዮቻቸውን እንደማይልኩ ይፋ አድርገዋል። ቻይና ዊጋ ሙስሊሞች ላይ ሰብአዊ ጥሰት ትፈፅማለች የሚል ወቀሳ ይሰነዝርባታል። ቀጣዩን የክረምት ኦሊምፒክ የምታዘጋጀው ፈረንሳይ ግን ከአጋሮቿ በተለየ እስካሁን ተወካዮቿን እንደማትልክ አላሳወቀችም። የዘንድሮው የክረምት ኦሊምፒክ በሚቀጥለው የካቲት ቤይጂንግ ላይ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል። "አሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና አውስትራሊያ የኦሊምፒክ ጨዋታውን እንደ ፖለቲካ መድረክ ተጠቅመውበታል" ሲሉ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ተናግረዋል። የቻይና ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ረቡዕ ዕለት ቤይጂንግ "ወትሮውንም ቢሆን 'በአንሳተፍም ፖለቲካ' የናወዙ የአሜሪካና የምዕራቡ ዓለም ፖለቲከኞችን የመጋበዝ ዕቅድ የላትም" ብሏል። በዲፕሎማሲ ምክንያት አልሳተፍም ስትል መጀመሪያ ድምጿን ያሰማችው አሜሪካ ስትሆን፤ አውስትራሊያ፣ ካናዳና ዩናይትድ ኪንግደም ተከታትለው ተመሳሳይ ሐሳባቸውን አሰምተዋል። ይህ የአገራቱ አቋም ግን አትሌቶችን በጨዋታው ከመሳተፍ አያግዳቸውም። ይህን እርምጃ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚደገፍ ብሎታል። "የመንግሥት ተወካዮችን መላክ የፖለቲካ ውሳኔ ነው። ኮሚቴው በዚህ ውሳኔ እጁን አያስገባም" ብለዋል የኮሚቴው ፕሬዝደንት ቶማስ ባህ። ከክረምት ጨዋታዎች እራሳቸውን የሚያገሉ አገራትና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየሻከረ መጥቷል። አሜሪካ፤ ቻይና በዢያንዢያንግ ግዛት ያሉ የዊጋና ሌሎች አናሳ ሙስሊም ማኅበረሰቦች ላይ የዘር ማጥፋት ፈጽማለት ስትል ትከሳለች። ቻይና የሚቀርቡባትን ሁሉንም የሰብአዊ መብት ጥሰት ክሶች የምታጣጥል ሲሆን፤ በዢያንዢያንግ ግዛት ያሉት የማቆያ ካምፖች የዊጋ ሙስሊሞችንና ሌሎችን "መልሶ ለማስተማር" የሚውሉ ናቸው ትላለች። ሌላው ቻይና የምትወቀስበት ጉዳይ በሆንግ ኮንግ ባለው ሁኔታና በቅርቡ የቻይና ባለሥልጣንን በወሲባዊ ጥቃት ምክንያት ከተናገረች በኋላ ለሳምንታት ሳትታይ በቆየችው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቿ ፔንግ ሹዋይ ነው። የሴቶች ቴኒስ ማኅበር ባለፈው ሳምንት ቻይና የሚደረጉ ሁሉም የቴኒስ ውድድሮች የፔንግ ሁኔታ እስኪታወቅ ድረስ እንዲቋረጡ አዟል። ቻይና ከካናዳ ጋር ያላት ግንኙነት የቆረቆዘው የቻይናው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመታሠሩ ምክንያትና በምትኩ ቻይና ሁሉት ካናዳዊያንን በማገቷ ምክንያት ነው። ሦስቱም ግለሰቦች በያዝነው ዓመት መባቻ ተለቀዋል። ሌላኛው የመንግሥት ተወካዮቼን አልክም ያለችው አገር ኒው ዚላንድ ስትሆን፤ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ቢያሳስባትም ተወካዮቿን ከመላክ የተቆጠበችው በኮቪድ ምክንያት ነው። እንደ ጃፓን ያሉ ጎረቤት አገራትም ከጨዋታዎቹ እራሳቸውን ያርቃሉ የሚል ግምት አለ። ጣልያን እሳተፋለሁ ስትል ፑቲን የቻይናን ግብዣ ተቀብለው በሥፍራው እንደሚገኙ አሳውቀዋል። | ቻይና ከክረምት ኦሊምፒክ እራሳቸውን የሚያገሉ አገራት 'የእጃቸውን ያገኛሉ' ስትል አስጠነቀቀች ቻይና ከምታስተናግደው የቤይጂንግ የክረምት የኦሊምፒክ ጨዋታዎች እራሳቸውን የሚያገሉ አገራት "ለሚፈጽሙት ስህተት ዋጋ ይከፍሏታል" ስትል አስጠንቅቃለች። ቻይና ሰብአዊ መብት እየጣሰች ነው በማለት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አውስትራሊያና ካናዳ የመንግሥት ተወካዮቻቸውን እንደማይልኩ ይፋ አድርገዋል። ቻይና ዊጋ ሙስሊሞች ላይ ሰብአዊ ጥሰት ትፈፅማለች የሚል ወቀሳ ይሰነዝርባታል። ቀጣዩን የክረምት ኦሊምፒክ የምታዘጋጀው ፈረንሳይ ግን ከአጋሮቿ በተለየ እስካሁን ተወካዮቿን እንደማትልክ አላሳወቀችም። የዘንድሮው የክረምት ኦሊምፒክ በሚቀጥለው የካቲት ቤይጂንግ ላይ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል። "አሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና አውስትራሊያ የኦሊምፒክ ጨዋታውን እንደ ፖለቲካ መድረክ ተጠቅመውበታል" ሲሉ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ተናግረዋል። የቻይና ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ረቡዕ ዕለት ቤይጂንግ "ወትሮውንም ቢሆን 'በአንሳተፍም ፖለቲካ' የናወዙ የአሜሪካና የምዕራቡ ዓለም ፖለቲከኞችን የመጋበዝ ዕቅድ የላትም" ብሏል። በዲፕሎማሲ ምክንያት አልሳተፍም ስትል መጀመሪያ ድምጿን ያሰማችው አሜሪካ ስትሆን፤ አውስትራሊያ፣ ካናዳና ዩናይትድ ኪንግደም ተከታትለው ተመሳሳይ ሐሳባቸውን አሰምተዋል። ይህ የአገራቱ አቋም ግን አትሌቶችን በጨዋታው ከመሳተፍ አያግዳቸውም። ይህን እርምጃ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚደገፍ ብሎታል። "የመንግሥት ተወካዮችን መላክ የፖለቲካ ውሳኔ ነው። ኮሚቴው በዚህ ውሳኔ እጁን አያስገባም" ብለዋል የኮሚቴው ፕሬዝደንት ቶማስ ባህ። ከክረምት ጨዋታዎች እራሳቸውን የሚያገሉ አገራትና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየሻከረ መጥቷል። አሜሪካ፤ ቻይና በዢያንዢያንግ ግዛት ያሉ የዊጋና ሌሎች አናሳ ሙስሊም ማኅበረሰቦች ላይ የዘር ማጥፋት ፈጽማለት ስትል ትከሳለች። ቻይና የሚቀርቡባትን ሁሉንም የሰብአዊ መብት ጥሰት ክሶች የምታጣጥል ሲሆን፤ በዢያንዢያንግ ግዛት ያሉት የማቆያ ካምፖች የዊጋ ሙስሊሞችንና ሌሎችን "መልሶ ለማስተማር" የሚውሉ ናቸው ትላለች። ሌላው ቻይና የምትወቀስበት ጉዳይ በሆንግ ኮንግ ባለው ሁኔታና በቅርቡ የቻይና ባለሥልጣንን በወሲባዊ ጥቃት ምክንያት ከተናገረች በኋላ ለሳምንታት ሳትታይ በቆየችው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቿ ፔንግ ሹዋይ ነው። የሴቶች ቴኒስ ማኅበር ባለፈው ሳምንት ቻይና የሚደረጉ ሁሉም የቴኒስ ውድድሮች የፔንግ ሁኔታ እስኪታወቅ ድረስ እንዲቋረጡ አዟል። ቻይና ከካናዳ ጋር ያላት ግንኙነት የቆረቆዘው የቻይናው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመታሠሩ ምክንያትና በምትኩ ቻይና ሁሉት ካናዳዊያንን በማገቷ ምክንያት ነው። ሦስቱም ግለሰቦች በያዝነው ዓመት መባቻ ተለቀዋል። ሌላኛው የመንግሥት ተወካዮቼን አልክም ያለችው አገር ኒው ዚላንድ ስትሆን፤ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ቢያሳስባትም ተወካዮቿን ከመላክ የተቆጠበችው በኮቪድ ምክንያት ነው። እንደ ጃፓን ያሉ ጎረቤት አገራትም ከጨዋታዎቹ እራሳቸውን ያርቃሉ የሚል ግምት አለ። ጣልያን እሳተፋለሁ ስትል ፑቲን የቻይናን ግብዣ ተቀብለው በሥፍራው እንደሚገኙ አሳውቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59599811 |
5sports
| በናይጄሪያውያን ልብ ዘንድ የነገሰው የቦክስ ሻምፒዮኑ አንቶኒ ጆሹዋ | ቅዳሜ ምሽት እንግሊዛዊው አንቶኒ ጆሹዋ ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የቦክስ ግጥሚያውን ከቡልጋሪያው ኩብራት ፑሌቭ ጋር ያደርጋል። በርካታ ነገሮችን ከስረ መሰረቱ በቀየረው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ይህንን ፍልሚያ በቅርብ ሆነው ማየት የሚችሉት አንድ ሺህ ሰዎች ብቻ ናቸው። ፍልሚያው ዝም ብሎ አይደለም አንቶኒ የሶስት ጊዜ ከባድ ሚዛን ሻምፒዮንነቱን የሚያስጠበቅበትም ነው። ኤስኤስኤ በተባለው ትልቅ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን ሚሊዮኖች አድናቂዎቹም በቴሌቪዥን፣ ሬድዮ ይከታተሉታልም ተብሎ ይጠበቃል። በተለይም በናይጄሪያ የሚኖረው ድጋፍ ይህ ነው የሚባል አይሆንም። የ31 አመቱ ቦክሰና ለእንግሊዝ በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ቢያስገኝላትም በናይጄሪያ ያለው የጀግነነት ቦታ ለየት ያለ ነው። በተለይም የቤተሰቡ የትውልድ ስፍራ ነው በሚባለው የደቡብ ምዕራብ ግዛት ሳጋሙ ከአምልኮት ባልተናነሰ መልኩ ነው የሚታየው። ጅማሮው የአንቶኒ ወላጆች ብቻ ሳይሆን ቅድመ አያቶቹም በሳጋሙ ስመ ጥር ናቸው። ቅድመ አያቱ ዳንኤል አደባነምቦ ጆሹዋ የመሬት ከበርቴና ኃብታም ነጋዴ ነበሩ። እምነታቸውን ወደ ክርስትና ከቀየሩም በኋላ የመጨረሻ ስማቸውን እንደቀየሩ ይታመናል። ዳንኤል አንደኛውን ልጃቸው አይዛክ ኦላሴኑ ጆሹዋን ለትምህርት ወደ እንግሊዝ ላኩት። እሱም ትምህርቱን ጨርሶ አየርላንዳዊ ሴት አግብቶ ወደ ናይጄሪያ ተመለሰ። ሰባት ልጆችም ወለዱ። የነሱም አንደኛው ልጅ ሮበርት እዛው የሳጋሙ ተወላጅ የሆነችውን የታ ኦዱሳንያን አግብቶ ቦክሰኛውን አንቶኒና እህቱን ጃኔትን ወለዱ። አንቶኒ ትውልዱም ሆነ እድገቱ እንግሊዝ ነው ለአያቱ ትልቅ ክብር ያለው አንቶኒ አጠቃላይ ትውልዱም በግዛቲቷም ሆነ በናይጄሪያ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው ናቸው። ናይጄሪያ በልቡ ያለችው ቦክሰኛ አንቶኒ ጆሹዋ በናይጄሪያዊ ቤተሰቦቹ ትልቅ ክብርና ኩራት አለው። በቀኝ ጀርባው በኩል የአፍሪካ ካርታ ያለበትና ናይጄሪያ ደምቃ የምትታይበት ንቅሳት አለው። በፍልሚያዎቹም ላይ የናይጄሪያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደርጋል። ወደ ፍልሚያ ሜዳውም ሲገባ በናይጄሪያ ሙዚቃ ታጅቦ ነው። በቅርቡ ከአንዲ ሩይዝ ጁኒየር ጋር በነበረው ግጥሚያም የታዋቂዎቹን በበርና ቦይና ፌሚ ኩቲን ሙዚቃ ታጅቦ ነበር የገባው። ፌሚ ኩቲ የአፍሮ ቢት ፈጣሪው ፌላ ኩቲ ልጅ ነው። ለናይጄሪያ ሙዚቃ ጥልቅ ፍቅር ያለው አንቶኒ በማህበራዊ ሚዲያዎችም ላይ አብሮ እየዘፈነ ያሉ ቪዲዮዎች ማሳያ ናቸው። የናይጄሪያ ምግብ እያበሰለም በርካታ ቪዲዮዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቹ ላይ ለቋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለተጠቁ ቤተሰቦቹም በርካታ ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶችም ወደ ናይጄሪያ ልኳል። በቅርቡም ናይጄሪያውያን የፖሊስ የጭካኔ በትርን በቃን ብለው በመቃወም ሲነሱ አንቶኒም ድጋፉን በማሳየት ከአገሪቷም ሆነ ከህዝቡ ጋር ያለውን ፅኑ ቁርኝት አሳይቷል። የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪም አድናቂው ናቸው። ከፕሬዚዳንቱ ጋር በባለፈው አመት የተገናኙ ሲሆን አንቶኒም የሻምፒዮንነት ቀበቶዎቹን አሳይቷቸዋል። ታዋቂው የናይጄሪያ ቦክሰኛ ሰውነቱ በጡንቻ የተሞላው፣ ስርአት የተላበሰ፣ ቀስ ብሎ መናገር የሚወደው አንቶኒ የብዙዎችን ቀልብ የሚስብ ፈገግታም አለው። በቦክሱ ዘርፍ ዘንድ ያስመዘገበው ድል በአገሪቱ የስፖርት ታሪክ ትልቅ ስም የተከለ አድርጎታል። በአሜሪካው ቅርጫት ኳስ ዘንድ የኤንቢኤ ጨዋታ ታዋቂነትን ካተረፈው ሐኪም ኦላጁዎን ቀጥሎ ናይጄሪያዊ ዝርያ ያለው ትልቁ ስፖርተኛ ነው። ከአንቶኒ በፊትም ቢሆን ናይጄሪያዊ ዝርያ ያላቸው የከባድ ሚዛን ቦክስ ሻምፒዮኖች ቢኖሩም የአንቶኒን ያህል ተወዳጅነት ያገኘ የለም። ሄንሪ አክንዋንዴና ሳሙኤል ፒተር ሁለቱም የከባድ ሚዛን ቦክሽ የሻምፒዮንነት ስፍራ ቢቆናጠጡም ዝናቸውም ሆነ ተወዳጅነታቸው ከአንቶኒ ጋር አይወዳደርም። አንቶኒ በናይጄሪያውያን ልብ ዘንድ ነግሷል። በሳጋሙ የአንቶኒ አድናቂዎች ክለብ ከሶስት አመት በፊትም ተመስርቷል። "አንቶኒ ሳጋሙን በአለም ላይ አሳውቋታል" በማለት የአንቶኒ ጆሹዋ ደጋፊዎች ክለብ መስራች አዚዝ አደኩንሌ ኦኩኖረን ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግረዋል። "መጨረሻ ላይ ከአንዲ ሩይዝ ጋር ያደረገውን ግጥሚያ ህዝቡ ሁሉ እንዲከታተለው ለማድረግ በትልልቅ ስክሪኖችና በፕሮጀክተር አሳይተናል" "በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹም ፍልሚያውን ሊያዩ ወጥተው ነበር። አንዳንዶችም ፍልሚያውን ለመታደም ከአዋሳኝ ግዛቶች ተጉዘዋል" ይላል አዚዝ "የመጪውንም ውድድር ታሳያላችሁ ወይ የሚል በርካታ ጥያቄዎችም እየጎረፉልን ነው" በማለትም አዚዝ ያስረዳል። የሚዲያን ቀልብ የተቆጣጠረው ቦክሰኛ በናይጄሪያ የሚገኙት ቴሌቪዥን፣ ድረ-ገፅ፣ ጋዜጣ፣ መፅሄት በአጠቃላይ የትኛውም አይነት ሚዲያ ስለ አንቶኒ አውርተው አይጠግቡም። በወላጆቹ ትውልድ ቦታም ግጥሚያው በበለጠ ድምቀት ይኖረዋል በሚል ነዋሪው ብቻ ሳይሆን ሚዲያዎቹም ወደ አካባቢው አቅንተዋል። ውድድሮቹን በቴሌቪዥን መከታተል ለማይችሉም ማህበራዊ ሚዲያዎችን አማራጭ አድርገዋል፤ ደማቅም ነው፤ በውይይትና አስተያየት የተሞላ ምልከታም ነው። በባለፈው አመት ወደ ሳጋሙ መጥቶ የነበረው አንቶኒ የአካባቢውን ባህላዊ መሪና ኃላፊዎች ቢያገኝም የአድናቂዎቹን ክለብ ግን አላገኛቸውም። ሆኖም ለነ አዚዝ ይኼ ምንም ማለት አይደለም፤ መውደዳቸውም ትንሽም ቢሆን አይቀንስም። "ምንም ማለት አይደለም። አሁንም ቢሆን ልጃችንና ተወካያችን ነው" ይላል አዚዝ "አባቱ፣ አያቱ፣ ቅድመ አያቱና ዘሩ ከዚህ መሆኑን እናውቃለን። እናም መቼም ቢሆን እንደግፈዋለን። አንድ ቀንም እሱም እኛን ተመልክቶ ይደግፈን ይሆናል" ይላል አዚዝ አክሎም "ለስኬቱ መፀለያችንን አናቆምም። ግን አሻራውን የሚያስታውስ እንደ ጂም፣መዝናኛ ማዕከል ወይም ሆስፒታል ቢገነባ እንወዳለን። በርካቶች ተመልክተው ሊያስታውሱት የሚችሉት ነገር ቢሆን ጥሩ ነው" በማለትም ያስረዳል። የወጣቱ አርዓያ አንቶኒ አሻራውን በወጣቶች ላይ እያሳረፈ ይገኛል፤ በተለይም በንግድ መዲናዋ ከተማ ሌጎስ። ወጣት ናይጄሪያውያን አንቶኒ አስደናቂውንና ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ ጉዞውን ያውቁታል። በእንግሊዝ ከበጥባጭነትና ረባሽ ወጣት መንገዱን ፈልጎ ወደ ሙያዊ እንዲሁም የሃብት ስኬት መድረሱ በርካቶችን የሚያነቃቃ ነው። የሱን ፈለግም በመከተል በርካታ የአማተር ቦክስ ሜዳዎች እንደ አሸን እየፈሉ ነው። የመንግሥትና የህዝብ ትምህርት ቤቶችም ከትምህርት በኋላና ቅዳሜና እሁድ የቦክስ ሜዳዎችም ሆነው እያገለገሉ ነው። ምንም እንኳን የተሟላ ቁሳቁስም ሆነ ብቁ አሰልጣኝ ባይኖርም በርካቶች የሱን ፈለግ በመከተል ላይ ናቸው። ሌካን ሙይቢ ወይም በቅፅል ስሙ 'ሞተሩ' በተስፋ ከተሞሉ አማተር ቦክሰኞች አንዱ ነው። የ21 አመቱ የመኪና መካኒክ ቅፅል ስሙንም ያገኘው በጥንካሬው፣ በስራው፣ በሚሰነዝነረው ጡጫም ነው። ከሳጋሙ በ35 ኪሎሜትር ርቀት ሞዌ በምትባል አካባቢ ነዋሪ የሆነው ሌካን አንቶኒን እንደ ጀግናው ነው የሚያየው። "ወደ ቦከስ ስፖርት ያስገባኝ ማይክ ታይሰን ነው። ነገር ግን ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል ደግሞ ያሳየኝ አንቶኒ ነው ምክንያቱም እሱም እንደ እኔ ናይጄሪያዊ ነው" በማለትም ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግሯል። የፌስቡክ ገፁንም በማየት የአንቶኒ ምን ያህል አድናቂም እንደሆነና ያለውንም ፅናት መረዳት ይቻላል። የአንቶኒ ጆሹዋ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች እንዲሁም የሌሎች ስፖርተኞች የፌስቡክ ገፁን ሞልተውታል። ሌካንም ቦክስ ሲለማመድ፣ እንዲሁም እዚህ ግባ በማይባሉ የመለማመጃ መሳሪያዎች የሚያደርገው ዬየቀን ትግልም ቪዲዮ ለስፖርቱ ያለውን ፍቅር ያሳያል። የአንቶኒንም ቪዲዮ ለሰዓታት በዩቲዩብ በመከታተተል ችሎታውንም ለማሻሻል ጥረት ያደርጋል። "ከሱ ብዙ እማራለሁ። ከፍተኛ የሆነ ጉልበት ቢኖረውም ኃይሉን ለመቆጠብ የሚጠቀመው ቴክኒክ አለው" ይላል። አክሎም " ጡጫ በሚሰነዝርበት ወቅት በተጠና መልኩ ነው። ተፋላሚውንም በደንብ ባወቀ መልኩም ነው የሚሰነዝረው። ቀድሞም በደንብ ይረዳቸዋል" ይላል። "ህልሜ ከሱ ጋር አንድ ቀን መሰልጠን እንዲሁም መፋለም እፈልጋለሁ። ከሱ ብዙ የምማረው አለ" በማለትም ይናገራል። ሌካን ከአንቶኒ ጋር መሰልጠንም ሆነ መፋለም ህልሙ ቢሆንም ለአብዛኛው ናይጄሪያዊ አድናቂዎቹ አንቶኒ ፍልሚያውን ናይጄሪያ ቢያደርግ ትልቅ ነገር ነው። | በናይጄሪያውያን ልብ ዘንድ የነገሰው የቦክስ ሻምፒዮኑ አንቶኒ ጆሹዋ ቅዳሜ ምሽት እንግሊዛዊው አንቶኒ ጆሹዋ ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የቦክስ ግጥሚያውን ከቡልጋሪያው ኩብራት ፑሌቭ ጋር ያደርጋል። በርካታ ነገሮችን ከስረ መሰረቱ በቀየረው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ይህንን ፍልሚያ በቅርብ ሆነው ማየት የሚችሉት አንድ ሺህ ሰዎች ብቻ ናቸው። ፍልሚያው ዝም ብሎ አይደለም አንቶኒ የሶስት ጊዜ ከባድ ሚዛን ሻምፒዮንነቱን የሚያስጠበቅበትም ነው። ኤስኤስኤ በተባለው ትልቅ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን ሚሊዮኖች አድናቂዎቹም በቴሌቪዥን፣ ሬድዮ ይከታተሉታልም ተብሎ ይጠበቃል። በተለይም በናይጄሪያ የሚኖረው ድጋፍ ይህ ነው የሚባል አይሆንም። የ31 አመቱ ቦክሰና ለእንግሊዝ በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ቢያስገኝላትም በናይጄሪያ ያለው የጀግነነት ቦታ ለየት ያለ ነው። በተለይም የቤተሰቡ የትውልድ ስፍራ ነው በሚባለው የደቡብ ምዕራብ ግዛት ሳጋሙ ከአምልኮት ባልተናነሰ መልኩ ነው የሚታየው። ጅማሮው የአንቶኒ ወላጆች ብቻ ሳይሆን ቅድመ አያቶቹም በሳጋሙ ስመ ጥር ናቸው። ቅድመ አያቱ ዳንኤል አደባነምቦ ጆሹዋ የመሬት ከበርቴና ኃብታም ነጋዴ ነበሩ። እምነታቸውን ወደ ክርስትና ከቀየሩም በኋላ የመጨረሻ ስማቸውን እንደቀየሩ ይታመናል። ዳንኤል አንደኛውን ልጃቸው አይዛክ ኦላሴኑ ጆሹዋን ለትምህርት ወደ እንግሊዝ ላኩት። እሱም ትምህርቱን ጨርሶ አየርላንዳዊ ሴት አግብቶ ወደ ናይጄሪያ ተመለሰ። ሰባት ልጆችም ወለዱ። የነሱም አንደኛው ልጅ ሮበርት እዛው የሳጋሙ ተወላጅ የሆነችውን የታ ኦዱሳንያን አግብቶ ቦክሰኛውን አንቶኒና እህቱን ጃኔትን ወለዱ። አንቶኒ ትውልዱም ሆነ እድገቱ እንግሊዝ ነው ለአያቱ ትልቅ ክብር ያለው አንቶኒ አጠቃላይ ትውልዱም በግዛቲቷም ሆነ በናይጄሪያ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው ናቸው። ናይጄሪያ በልቡ ያለችው ቦክሰኛ አንቶኒ ጆሹዋ በናይጄሪያዊ ቤተሰቦቹ ትልቅ ክብርና ኩራት አለው። በቀኝ ጀርባው በኩል የአፍሪካ ካርታ ያለበትና ናይጄሪያ ደምቃ የምትታይበት ንቅሳት አለው። በፍልሚያዎቹም ላይ የናይጄሪያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደርጋል። ወደ ፍልሚያ ሜዳውም ሲገባ በናይጄሪያ ሙዚቃ ታጅቦ ነው። በቅርቡ ከአንዲ ሩይዝ ጁኒየር ጋር በነበረው ግጥሚያም የታዋቂዎቹን በበርና ቦይና ፌሚ ኩቲን ሙዚቃ ታጅቦ ነበር የገባው። ፌሚ ኩቲ የአፍሮ ቢት ፈጣሪው ፌላ ኩቲ ልጅ ነው። ለናይጄሪያ ሙዚቃ ጥልቅ ፍቅር ያለው አንቶኒ በማህበራዊ ሚዲያዎችም ላይ አብሮ እየዘፈነ ያሉ ቪዲዮዎች ማሳያ ናቸው። የናይጄሪያ ምግብ እያበሰለም በርካታ ቪዲዮዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎቹ ላይ ለቋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለተጠቁ ቤተሰቦቹም በርካታ ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶችም ወደ ናይጄሪያ ልኳል። በቅርቡም ናይጄሪያውያን የፖሊስ የጭካኔ በትርን በቃን ብለው በመቃወም ሲነሱ አንቶኒም ድጋፉን በማሳየት ከአገሪቷም ሆነ ከህዝቡ ጋር ያለውን ፅኑ ቁርኝት አሳይቷል። የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪም አድናቂው ናቸው። ከፕሬዚዳንቱ ጋር በባለፈው አመት የተገናኙ ሲሆን አንቶኒም የሻምፒዮንነት ቀበቶዎቹን አሳይቷቸዋል። ታዋቂው የናይጄሪያ ቦክሰኛ ሰውነቱ በጡንቻ የተሞላው፣ ስርአት የተላበሰ፣ ቀስ ብሎ መናገር የሚወደው አንቶኒ የብዙዎችን ቀልብ የሚስብ ፈገግታም አለው። በቦክሱ ዘርፍ ዘንድ ያስመዘገበው ድል በአገሪቱ የስፖርት ታሪክ ትልቅ ስም የተከለ አድርጎታል። በአሜሪካው ቅርጫት ኳስ ዘንድ የኤንቢኤ ጨዋታ ታዋቂነትን ካተረፈው ሐኪም ኦላጁዎን ቀጥሎ ናይጄሪያዊ ዝርያ ያለው ትልቁ ስፖርተኛ ነው። ከአንቶኒ በፊትም ቢሆን ናይጄሪያዊ ዝርያ ያላቸው የከባድ ሚዛን ቦክስ ሻምፒዮኖች ቢኖሩም የአንቶኒን ያህል ተወዳጅነት ያገኘ የለም። ሄንሪ አክንዋንዴና ሳሙኤል ፒተር ሁለቱም የከባድ ሚዛን ቦክሽ የሻምፒዮንነት ስፍራ ቢቆናጠጡም ዝናቸውም ሆነ ተወዳጅነታቸው ከአንቶኒ ጋር አይወዳደርም። አንቶኒ በናይጄሪያውያን ልብ ዘንድ ነግሷል። በሳጋሙ የአንቶኒ አድናቂዎች ክለብ ከሶስት አመት በፊትም ተመስርቷል። "አንቶኒ ሳጋሙን በአለም ላይ አሳውቋታል" በማለት የአንቶኒ ጆሹዋ ደጋፊዎች ክለብ መስራች አዚዝ አደኩንሌ ኦኩኖረን ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግረዋል። "መጨረሻ ላይ ከአንዲ ሩይዝ ጋር ያደረገውን ግጥሚያ ህዝቡ ሁሉ እንዲከታተለው ለማድረግ በትልልቅ ስክሪኖችና በፕሮጀክተር አሳይተናል" "በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹም ፍልሚያውን ሊያዩ ወጥተው ነበር። አንዳንዶችም ፍልሚያውን ለመታደም ከአዋሳኝ ግዛቶች ተጉዘዋል" ይላል አዚዝ "የመጪውንም ውድድር ታሳያላችሁ ወይ የሚል በርካታ ጥያቄዎችም እየጎረፉልን ነው" በማለትም አዚዝ ያስረዳል። የሚዲያን ቀልብ የተቆጣጠረው ቦክሰኛ በናይጄሪያ የሚገኙት ቴሌቪዥን፣ ድረ-ገፅ፣ ጋዜጣ፣ መፅሄት በአጠቃላይ የትኛውም አይነት ሚዲያ ስለ አንቶኒ አውርተው አይጠግቡም። በወላጆቹ ትውልድ ቦታም ግጥሚያው በበለጠ ድምቀት ይኖረዋል በሚል ነዋሪው ብቻ ሳይሆን ሚዲያዎቹም ወደ አካባቢው አቅንተዋል። ውድድሮቹን በቴሌቪዥን መከታተል ለማይችሉም ማህበራዊ ሚዲያዎችን አማራጭ አድርገዋል፤ ደማቅም ነው፤ በውይይትና አስተያየት የተሞላ ምልከታም ነው። በባለፈው አመት ወደ ሳጋሙ መጥቶ የነበረው አንቶኒ የአካባቢውን ባህላዊ መሪና ኃላፊዎች ቢያገኝም የአድናቂዎቹን ክለብ ግን አላገኛቸውም። ሆኖም ለነ አዚዝ ይኼ ምንም ማለት አይደለም፤ መውደዳቸውም ትንሽም ቢሆን አይቀንስም። "ምንም ማለት አይደለም። አሁንም ቢሆን ልጃችንና ተወካያችን ነው" ይላል አዚዝ "አባቱ፣ አያቱ፣ ቅድመ አያቱና ዘሩ ከዚህ መሆኑን እናውቃለን። እናም መቼም ቢሆን እንደግፈዋለን። አንድ ቀንም እሱም እኛን ተመልክቶ ይደግፈን ይሆናል" ይላል አዚዝ አክሎም "ለስኬቱ መፀለያችንን አናቆምም። ግን አሻራውን የሚያስታውስ እንደ ጂም፣መዝናኛ ማዕከል ወይም ሆስፒታል ቢገነባ እንወዳለን። በርካቶች ተመልክተው ሊያስታውሱት የሚችሉት ነገር ቢሆን ጥሩ ነው" በማለትም ያስረዳል። የወጣቱ አርዓያ አንቶኒ አሻራውን በወጣቶች ላይ እያሳረፈ ይገኛል፤ በተለይም በንግድ መዲናዋ ከተማ ሌጎስ። ወጣት ናይጄሪያውያን አንቶኒ አስደናቂውንና ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ ጉዞውን ያውቁታል። በእንግሊዝ ከበጥባጭነትና ረባሽ ወጣት መንገዱን ፈልጎ ወደ ሙያዊ እንዲሁም የሃብት ስኬት መድረሱ በርካቶችን የሚያነቃቃ ነው። የሱን ፈለግም በመከተል በርካታ የአማተር ቦክስ ሜዳዎች እንደ አሸን እየፈሉ ነው። የመንግሥትና የህዝብ ትምህርት ቤቶችም ከትምህርት በኋላና ቅዳሜና እሁድ የቦክስ ሜዳዎችም ሆነው እያገለገሉ ነው። ምንም እንኳን የተሟላ ቁሳቁስም ሆነ ብቁ አሰልጣኝ ባይኖርም በርካቶች የሱን ፈለግ በመከተል ላይ ናቸው። ሌካን ሙይቢ ወይም በቅፅል ስሙ 'ሞተሩ' በተስፋ ከተሞሉ አማተር ቦክሰኞች አንዱ ነው። የ21 አመቱ የመኪና መካኒክ ቅፅል ስሙንም ያገኘው በጥንካሬው፣ በስራው፣ በሚሰነዝነረው ጡጫም ነው። ከሳጋሙ በ35 ኪሎሜትር ርቀት ሞዌ በምትባል አካባቢ ነዋሪ የሆነው ሌካን አንቶኒን እንደ ጀግናው ነው የሚያየው። "ወደ ቦከስ ስፖርት ያስገባኝ ማይክ ታይሰን ነው። ነገር ግን ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል ደግሞ ያሳየኝ አንቶኒ ነው ምክንያቱም እሱም እንደ እኔ ናይጄሪያዊ ነው" በማለትም ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግሯል። የፌስቡክ ገፁንም በማየት የአንቶኒ ምን ያህል አድናቂም እንደሆነና ያለውንም ፅናት መረዳት ይቻላል። የአንቶኒ ጆሹዋ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች እንዲሁም የሌሎች ስፖርተኞች የፌስቡክ ገፁን ሞልተውታል። ሌካንም ቦክስ ሲለማመድ፣ እንዲሁም እዚህ ግባ በማይባሉ የመለማመጃ መሳሪያዎች የሚያደርገው ዬየቀን ትግልም ቪዲዮ ለስፖርቱ ያለውን ፍቅር ያሳያል። የአንቶኒንም ቪዲዮ ለሰዓታት በዩቲዩብ በመከታተተል ችሎታውንም ለማሻሻል ጥረት ያደርጋል። "ከሱ ብዙ እማራለሁ። ከፍተኛ የሆነ ጉልበት ቢኖረውም ኃይሉን ለመቆጠብ የሚጠቀመው ቴክኒክ አለው" ይላል። አክሎም " ጡጫ በሚሰነዝርበት ወቅት በተጠና መልኩ ነው። ተፋላሚውንም በደንብ ባወቀ መልኩም ነው የሚሰነዝረው። ቀድሞም በደንብ ይረዳቸዋል" ይላል። "ህልሜ ከሱ ጋር አንድ ቀን መሰልጠን እንዲሁም መፋለም እፈልጋለሁ። ከሱ ብዙ የምማረው አለ" በማለትም ይናገራል። ሌካን ከአንቶኒ ጋር መሰልጠንም ሆነ መፋለም ህልሙ ቢሆንም ለአብዛኛው ናይጄሪያዊ አድናቂዎቹ አንቶኒ ፍልሚያውን ናይጄሪያ ቢያደርግ ትልቅ ነገር ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-55292093 |
2health
| ባለሙያዎች በኮቪድ ምክንያት የጠፋን የማሽተት ስሜት ለመመለስ 'የማሽተት ሥልጠና' ውሰዱ አሉ | በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተከትሎ የማሽተት ስሜታቸውን በፍጥነት መመለስ ያልቻሉ ሰዎች የማሽተት ሥልጠና እንዲወስዱ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ ሰጡ። ባለሙያዎቹ የማሽተት ስሜትን ለመመለስ የስትሮይድስ ህክምና ከመከታተል ይልቅ 'የማሽተት ስልጠና' መውሰዱ የተሻለ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ የማሽተት ስልጠና ለወራት የተለያዩ ሽታዎችን በማሽተት አእምሮን እንደገና በማሰልጠን የተለያዩ ሽታዎችን እንዲለይ የማድረግ ሂደት ነው። የዓለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን እንደሚለው የማሽተት ስልጠና ዋጋው ርካሽ እና ሂደቱም ቀላል ነው። ከስቴሮይድስ ሕክምና ጋር ሲነጻጸርም፤ የማሽተት ስልጠናው የጎንዮሽ ጉዳቶች የሉትም። ከትኩሳት እና ከማያቋርጥ ሳል በተጨማሪ የመሽተት እና የጠዓም ስሜት ማጣት ከኮሮናቫይረስ ዋና ዋና ምልክቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው። ማሽተት አለመቻል ብዙውን ጊዜ ሕመሙ ካለፈ በኋላ በፍጥነት ይመለሳል። ሆኖም ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ ከህመሙ ከስምንት ሳምንት በኋላም የማሽተት ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ሪፖርት አድርገዋል። የኢስት አንግሊያ ዩኒቨርሲቲ ኖርዊች የሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባው ፕሮፌሰር ካርል ፊልፖት እንደሚሉት ኮርቲኮስትሮይድስ ማሽተትን የመመለስ አቅሙ በጣም ጥቂት ነው። "የታወቁ የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉት ከቫይረሱ በኋላ በሚመጣ የማሽተት ስሜት ማጣትን ለማከም መታዘዝ የለባቸውም ብለን እንመክራለን" ብለዋል። "እንደ ዕድል ሆኖ በኮቪድ-19 የተነሳ ሽታ ማጣት የሚገጥማቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች በፍጥነት የማሽተት ስሜታቸውን መልሰው ያገኛሉ" ብለዋል። ከስቴሮይድ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል የደም ግፊት እና የስሜት መለዋወጥ ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው። ዓለም አቀፍ የአለርጂ እና ሪህኖሎጂ ኦረም መጽሔት ላይ በወጣው ጽሑፍ መሠረት ተመራማሪዎቹ "የማሽተት ሥልጠና"ን በአማራጭነት አቅርበዋል። ይህም ተለይተው የሚታወቁ እና በቀላሉ የሚለዩ ሽታ ያላቸውን አራት ነገሮችን ማሽተትን ያካትታል። ለምሳሌ ብርቱካን፣ አዝሙድ፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቡናን በቀን ሁለት ጊዜ ማሽተት። ፕሮፌሰር ፊልፖት እንዳሉት ጥናቶች 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ከስድስት ወር በኋላ የማሽተት ስሜታቸውን ሙሉ በሙሉ መልሰው ያገኛሉ። በዚህ ጊዜ ካልተመለሰ ግን አእምሮ ሽታ እንዲለይ እና የተለያዩ ሽታዎችን እንደገና እንዲያውቅ "የማሸተት ስልጠና" ይረዳል። | ባለሙያዎች በኮቪድ ምክንያት የጠፋን የማሽተት ስሜት ለመመለስ 'የማሽተት ሥልጠና' ውሰዱ አሉ በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተከትሎ የማሽተት ስሜታቸውን በፍጥነት መመለስ ያልቻሉ ሰዎች የማሽተት ሥልጠና እንዲወስዱ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ ሰጡ። ባለሙያዎቹ የማሽተት ስሜትን ለመመለስ የስትሮይድስ ህክምና ከመከታተል ይልቅ 'የማሽተት ስልጠና' መውሰዱ የተሻለ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ የማሽተት ስልጠና ለወራት የተለያዩ ሽታዎችን በማሽተት አእምሮን እንደገና በማሰልጠን የተለያዩ ሽታዎችን እንዲለይ የማድረግ ሂደት ነው። የዓለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን እንደሚለው የማሽተት ስልጠና ዋጋው ርካሽ እና ሂደቱም ቀላል ነው። ከስቴሮይድስ ሕክምና ጋር ሲነጻጸርም፤ የማሽተት ስልጠናው የጎንዮሽ ጉዳቶች የሉትም። ከትኩሳት እና ከማያቋርጥ ሳል በተጨማሪ የመሽተት እና የጠዓም ስሜት ማጣት ከኮሮናቫይረስ ዋና ዋና ምልክቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው። ማሽተት አለመቻል ብዙውን ጊዜ ሕመሙ ካለፈ በኋላ በፍጥነት ይመለሳል። ሆኖም ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ ከህመሙ ከስምንት ሳምንት በኋላም የማሽተት ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ሪፖርት አድርገዋል። የኢስት አንግሊያ ዩኒቨርሲቲ ኖርዊች የሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባው ፕሮፌሰር ካርል ፊልፖት እንደሚሉት ኮርቲኮስትሮይድስ ማሽተትን የመመለስ አቅሙ በጣም ጥቂት ነው። "የታወቁ የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉት ከቫይረሱ በኋላ በሚመጣ የማሽተት ስሜት ማጣትን ለማከም መታዘዝ የለባቸውም ብለን እንመክራለን" ብለዋል። "እንደ ዕድል ሆኖ በኮቪድ-19 የተነሳ ሽታ ማጣት የሚገጥማቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች በፍጥነት የማሽተት ስሜታቸውን መልሰው ያገኛሉ" ብለዋል። ከስቴሮይድ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል የደም ግፊት እና የስሜት መለዋወጥ ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው። ዓለም አቀፍ የአለርጂ እና ሪህኖሎጂ ኦረም መጽሔት ላይ በወጣው ጽሑፍ መሠረት ተመራማሪዎቹ "የማሽተት ሥልጠና"ን በአማራጭነት አቅርበዋል። ይህም ተለይተው የሚታወቁ እና በቀላሉ የሚለዩ ሽታ ያላቸውን አራት ነገሮችን ማሽተትን ያካትታል። ለምሳሌ ብርቱካን፣ አዝሙድ፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቡናን በቀን ሁለት ጊዜ ማሽተት። ፕሮፌሰር ፊልፖት እንዳሉት ጥናቶች 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ከስድስት ወር በኋላ የማሽተት ስሜታቸውን ሙሉ በሙሉ መልሰው ያገኛሉ። በዚህ ጊዜ ካልተመለሰ ግን አእምሮ ሽታ እንዲለይ እና የተለያዩ ሽታዎችን እንደገና እንዲያውቅ "የማሸተት ስልጠና" ይረዳል። | https://www.bbc.com/amharic/56870718 |
3politics
| የሱዳን ፖሊስ መንፈንቅለ መንግሥቱን ለመቀወም አደባባይ በወጡት ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሰ | የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች በመዲናዋ ካርቱም ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ይቋቋም በሚል የተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸው ተሰምቷል። በተቃውሞ ሰልፉ እየተሳተፉ የሚገኙ በርካታ መምህራንም በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሌሊቱን ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ተቃዋሚዎች ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ጫና የማሳደር እንቅስቃሴ ለማጠናከር ጎማዎችን በማቃጠል እና ድንጋይ በመጠቀም የተለያዩ መንገዶችን ዘግተዋል። ጥያቄያቸውም በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን የያዘው ወታደራዊ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም መንገዱን ይክፈት የሚል ነው። የአረብ ሊግ አገራት መሪዎች መፈንቅል መንግሥቱን ካደረጉት ወታደሮች ጋር ድርድር ለማድረግ ወደ መዲናዋ ካርቱም መግባታቸውን ተከትሎ ነው ሰልፈኞች በድጋሚ ወደ አደባባይ መውጣት የጀመሩት። ከመጀመሪያው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ በጠቅላይ ሚንስትርነት የተመረጡት አብደላ ሀምዶክ በአሁኑ ሰዓት በቤታቸው የቁም እስረኛ ሆነው የሚገኙ ሲሆን ወታደሮቹም አብረዋቸው እንዲሰሩ ጫና እያሳረፉባቸው ስለመሆኑ ተዘግቧል። ባለፈው ወር የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ጀነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሀን መንግሥት ከሲቪሎች ጋር ስልጣን ለመጋራት ያደረገውን ስምምነት ያፈረሱ ሲሆን በርካታ የሲቪል መሪዎችንም በቁጥጥር ስር አውለዋል። አስከትለውም በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። ምንም እንኳን በአገሪቱ ባለው የኢንተርኔ መቆራረጥ ምክንያት በርካታ ሰዎች የሁለት ቀን የተቃውሞ ሰልፍ መጠራቱን ያልሰሙ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ መምህራን ግን በትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በር ላይ በመሰባሰብ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። "ጀነራሉ የወሰዱትን እርምጃ ለመቃወም በዝምታ የታጀበ ሰልፍ በሚኒስቴሩ በር ላይ አካሂደናል" ሲል ሞሀመድ አል አሚን የተባለው መምህር ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግሯል። "ትንሽ ቆይቶ ግን ፖሊስ መጥቶ አስለቃሽ ጭስ መተኮስ ጀመረ። እኛ ምንም አላደረግንም ነበር። በዝምታ መንገድ ላይ በመቆም የጽሁፍ መልእክቶችን ነበር ያስተላለፍነው። ለምን አስለቃሽ ጭስ እንደተተኮሰብን አላውቅም" ብሏል። በሰሜናዊ የካርቱም ክፍል የጸጥታ ኃይሎች ዋና ዋና መንገዶችን በጥብቅ እየተቆጣጠሩ ሲሆን አስለቃሽ ጭስ፣ ፈንጂዎችና ዱላዎችን ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ ሮይተርስ ዘግቧል። አብዛኛው የካርቱም ነዋሪ በአሁኑ ሰዓት ቁጣ ላይ መሆኑን ቢቢሲ ተዘዋውሮ ማስተዋል ችሏል። በርካቶችም ወደ መንደራቸው የሚወስዱ መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው። ምንም እንኳን ከሁሉም አቅጣጫ የተቃውሞ ድምጾች እየተሰሙ ቢሆንም ወታደራዊው መንግሥት ግን ምንም ስህተት እንዳልሰራ እየገለጸ ነው። "ይህ መፈንቅለ መንግሥት እንዳልነበረ በጊዜ ብዛት የሚታይ ይሆናል። የሲቪል መንግሥት መስርተን ምርጫም እንዲካሄድ አናደርጋለን" ብለዋል አድሚራል ፋታህ አል ራህማን። | የሱዳን ፖሊስ መንፈንቅለ መንግሥቱን ለመቀወም አደባባይ በወጡት ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሰ የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች በመዲናዋ ካርቱም ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ይቋቋም በሚል የተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸው ተሰምቷል። በተቃውሞ ሰልፉ እየተሳተፉ የሚገኙ በርካታ መምህራንም በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሌሊቱን ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ተቃዋሚዎች ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ጫና የማሳደር እንቅስቃሴ ለማጠናከር ጎማዎችን በማቃጠል እና ድንጋይ በመጠቀም የተለያዩ መንገዶችን ዘግተዋል። ጥያቄያቸውም በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን የያዘው ወታደራዊ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም መንገዱን ይክፈት የሚል ነው። የአረብ ሊግ አገራት መሪዎች መፈንቅል መንግሥቱን ካደረጉት ወታደሮች ጋር ድርድር ለማድረግ ወደ መዲናዋ ካርቱም መግባታቸውን ተከትሎ ነው ሰልፈኞች በድጋሚ ወደ አደባባይ መውጣት የጀመሩት። ከመጀመሪያው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ በጠቅላይ ሚንስትርነት የተመረጡት አብደላ ሀምዶክ በአሁኑ ሰዓት በቤታቸው የቁም እስረኛ ሆነው የሚገኙ ሲሆን ወታደሮቹም አብረዋቸው እንዲሰሩ ጫና እያሳረፉባቸው ስለመሆኑ ተዘግቧል። ባለፈው ወር የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ጀነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሀን መንግሥት ከሲቪሎች ጋር ስልጣን ለመጋራት ያደረገውን ስምምነት ያፈረሱ ሲሆን በርካታ የሲቪል መሪዎችንም በቁጥጥር ስር አውለዋል። አስከትለውም በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። ምንም እንኳን በአገሪቱ ባለው የኢንተርኔ መቆራረጥ ምክንያት በርካታ ሰዎች የሁለት ቀን የተቃውሞ ሰልፍ መጠራቱን ያልሰሙ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ መምህራን ግን በትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በር ላይ በመሰባሰብ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። "ጀነራሉ የወሰዱትን እርምጃ ለመቃወም በዝምታ የታጀበ ሰልፍ በሚኒስቴሩ በር ላይ አካሂደናል" ሲል ሞሀመድ አል አሚን የተባለው መምህር ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግሯል። "ትንሽ ቆይቶ ግን ፖሊስ መጥቶ አስለቃሽ ጭስ መተኮስ ጀመረ። እኛ ምንም አላደረግንም ነበር። በዝምታ መንገድ ላይ በመቆም የጽሁፍ መልእክቶችን ነበር ያስተላለፍነው። ለምን አስለቃሽ ጭስ እንደተተኮሰብን አላውቅም" ብሏል። በሰሜናዊ የካርቱም ክፍል የጸጥታ ኃይሎች ዋና ዋና መንገዶችን በጥብቅ እየተቆጣጠሩ ሲሆን አስለቃሽ ጭስ፣ ፈንጂዎችና ዱላዎችን ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ ሮይተርስ ዘግቧል። አብዛኛው የካርቱም ነዋሪ በአሁኑ ሰዓት ቁጣ ላይ መሆኑን ቢቢሲ ተዘዋውሮ ማስተዋል ችሏል። በርካቶችም ወደ መንደራቸው የሚወስዱ መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሟቸውን እየገለጹ ነው። ምንም እንኳን ከሁሉም አቅጣጫ የተቃውሞ ድምጾች እየተሰሙ ቢሆንም ወታደራዊው መንግሥት ግን ምንም ስህተት እንዳልሰራ እየገለጸ ነው። "ይህ መፈንቅለ መንግሥት እንዳልነበረ በጊዜ ብዛት የሚታይ ይሆናል። የሲቪል መንግሥት መስርተን ምርጫም እንዲካሄድ አናደርጋለን" ብለዋል አድሚራል ፋታህ አል ራህማን። | https://www.bbc.com/amharic/news-59174010 |
5sports
| የአፍሪካ ዋንጫ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ተወሰነ | በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ እንዲገፋ መወሰኑን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ አስታወቁ። ውድድሩ በሚቀጥለው ዓመት ከሰኔ አስከ ሐምሌ ባለው ጊዜ አይቮሪኮስት ውስጥ እንዲካሄድ መርሃ-ግብር ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም፣ ወቅቱ በአገሪቱ ከባድ ዝናብ የሚጥልበት በመሆኑ ነው ለቀጣይ ዓመት የተሸጋገረው። ደቡብ አፍሪካዊው የካፍ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር እየተካሄደባት ካለችው ሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት ባስተላለፉት መልዕክት "በሚኖረው የአየር ሁኔታ ምክንያት ምንም ማድረግ አንደፍርም” ብለዋል። የዓለም ዋንጫ ከሌላው ጊዜ በተለየ በሚቀጥለው ዓመት ኅዳርና ታኅሣሥ ወር ላይ የሚካሄድ በመሆኑ፣ የአፍሪካ ዋንጫን ወደፊት ከማምጣት ይልቅ ወደ ቀጣይ ዓመት ማሸጋገሩ የግድ ሆኗል። በዚህም ምክንያት የአፍሪካ ዋንጫ በዚህ ዓመት ካሜሩን ውስጥ እንደተካሄደው ሁሉ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ በጥርና የካቲት ይከናወናል። የአውሮፓ ክለቦች በውድድር ላይ ሳሉ ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ተጫዋቾችን እንዲለቁ በመጠየቅ የሚነሳውን ውዝግብ ለማስቀረት ሲባል ካፍ በ2017 (እአአ) የአፍሪካ ዋንጫ በተለመደው ሁኔታ ሲካሄድባቸው ከነበሩት ጥርና የካቲት ወራት ወደ ሰኔ እና ሐምሌ ለማዘዋወር ወስኗል። "በአውሮፓ ክለቦች ምክንያት ጥር ለውድድሩ አመቺ ወቅት አይደለም፣ ነገር ግን ለአሁን ያለን ብቸኛው አመራጭ እሱ ነው” ሲሉ የካፍ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። በቀድሞው የካፍ ፕሬዝዳንት ኢሳ ሃያቱ የአመራር ዘመን የአህጉሪቱ መለያ የሆነውን የእግር ኳስ ውድድር ማካሄጃ ወቅት ወደ ሌላ ወቅት የማሸጋገሩ ጉዳይ ተቀባይነት ሳያገኝ ቆይቷል። ሃያቱን የተኩት ማዳጋስካራዊው አህመድ አህመድ የአፍሪካ እግር ኳስን ለመምራት ወደ ሥልጣን በመጡ በአራት ወራት ውስጥ ከአባል አገራት ባለሥልጣናት ጋር በመነጋገር ለውጥ አድርገዋል። የካፍ ዋና ፀሐፊ ቬሮን ሞሴንጎ ኦምባ እንዳሉት ምንም እንኳን በአህጉሪቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ያለው የአየር ሁኔታ ልዩነት ቢኖረውም ውድድሩን ቀድሞ ወደ ነበረበት ጥርና የካቲት የመመለስ ፍላጎት የለም። ሰኔ እና ነሐሴ የዝናብ ወቅት መሆኑ እየታወቀ የውድድር ጊዜውን ወደ ሌላ ጊዜ የማሸጋገሩ ውሳኔ ለምን ዘገየ የሚለውን ጥያቄ ካፍ “ለአስተናጋጇ አገር አመቺነት” ሲባል መሆኑን ከመግለጽ ባለፈ ከባለሥልጣንት የተሰጠ ማብራሪያ የለም። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ዋና ፀሐፊ የእግር ኳስ ውድድሩ የሚካሄድበት ወቅት በአንድ ዓመት መገፋቱን ያሳወቁት የአፍሪካ የሴቶች አግር ኳስ ዋንጫ ውድድር እየተካሄደ ከሚገኝበት ከሞሮኮ ነው። | የአፍሪካ ዋንጫ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ተወሰነ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ እንዲገፋ መወሰኑን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ አስታወቁ። ውድድሩ በሚቀጥለው ዓመት ከሰኔ አስከ ሐምሌ ባለው ጊዜ አይቮሪኮስት ውስጥ እንዲካሄድ መርሃ-ግብር ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም፣ ወቅቱ በአገሪቱ ከባድ ዝናብ የሚጥልበት በመሆኑ ነው ለቀጣይ ዓመት የተሸጋገረው። ደቡብ አፍሪካዊው የካፍ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር እየተካሄደባት ካለችው ሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት ባስተላለፉት መልዕክት "በሚኖረው የአየር ሁኔታ ምክንያት ምንም ማድረግ አንደፍርም” ብለዋል። የዓለም ዋንጫ ከሌላው ጊዜ በተለየ በሚቀጥለው ዓመት ኅዳርና ታኅሣሥ ወር ላይ የሚካሄድ በመሆኑ፣ የአፍሪካ ዋንጫን ወደፊት ከማምጣት ይልቅ ወደ ቀጣይ ዓመት ማሸጋገሩ የግድ ሆኗል። በዚህም ምክንያት የአፍሪካ ዋንጫ በዚህ ዓመት ካሜሩን ውስጥ እንደተካሄደው ሁሉ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ በጥርና የካቲት ይከናወናል። የአውሮፓ ክለቦች በውድድር ላይ ሳሉ ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ተጫዋቾችን እንዲለቁ በመጠየቅ የሚነሳውን ውዝግብ ለማስቀረት ሲባል ካፍ በ2017 (እአአ) የአፍሪካ ዋንጫ በተለመደው ሁኔታ ሲካሄድባቸው ከነበሩት ጥርና የካቲት ወራት ወደ ሰኔ እና ሐምሌ ለማዘዋወር ወስኗል። "በአውሮፓ ክለቦች ምክንያት ጥር ለውድድሩ አመቺ ወቅት አይደለም፣ ነገር ግን ለአሁን ያለን ብቸኛው አመራጭ እሱ ነው” ሲሉ የካፍ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። በቀድሞው የካፍ ፕሬዝዳንት ኢሳ ሃያቱ የአመራር ዘመን የአህጉሪቱ መለያ የሆነውን የእግር ኳስ ውድድር ማካሄጃ ወቅት ወደ ሌላ ወቅት የማሸጋገሩ ጉዳይ ተቀባይነት ሳያገኝ ቆይቷል። ሃያቱን የተኩት ማዳጋስካራዊው አህመድ አህመድ የአፍሪካ እግር ኳስን ለመምራት ወደ ሥልጣን በመጡ በአራት ወራት ውስጥ ከአባል አገራት ባለሥልጣናት ጋር በመነጋገር ለውጥ አድርገዋል። የካፍ ዋና ፀሐፊ ቬሮን ሞሴንጎ ኦምባ እንዳሉት ምንም እንኳን በአህጉሪቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ያለው የአየር ሁኔታ ልዩነት ቢኖረውም ውድድሩን ቀድሞ ወደ ነበረበት ጥርና የካቲት የመመለስ ፍላጎት የለም። ሰኔ እና ነሐሴ የዝናብ ወቅት መሆኑ እየታወቀ የውድድር ጊዜውን ወደ ሌላ ጊዜ የማሸጋገሩ ውሳኔ ለምን ዘገየ የሚለውን ጥያቄ ካፍ “ለአስተናጋጇ አገር አመቺነት” ሲባል መሆኑን ከመግለጽ ባለፈ ከባለሥልጣንት የተሰጠ ማብራሪያ የለም። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ዋና ፀሐፊ የእግር ኳስ ውድድሩ የሚካሄድበት ወቅት በአንድ ዓመት መገፋቱን ያሳወቁት የአፍሪካ የሴቶች አግር ኳስ ዋንጫ ውድድር እየተካሄደ ከሚገኝበት ከሞሮኮ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cxr6ll129pro |
0business
| የሊባኖስ ዋነኛ ኃይል ማመንጫዎች ሥራ በማቆማቸው መብራት ተቋረጠ | በሊባኖስ ሁለት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ሥራ በማቆማቸው ሳቢያ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል መብራት ጠፍቷል። ሁለቱ ማመንጫዎች ነዳጅ በመጨረሳቸው ነው አገልግሎት መስጠት ያቆሙት። በሊባኖስ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላለ ከአገር ውጭ ለሚገኙ የኃይል አቅራቢ ድርጅቶች ገንዘብ መክፈል አልተቻለም። የመድኃኒት መደብሮች የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ስለገጠማቸው የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል። ዴር አማር እና ዛህራኒ የተባሉት ኃይል ማመንጫዎች የሊባኖስን 40 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ይሸፍናሉ። እነዚህ ኃይል ማመንጫዎች መሥራት ያቆሙት አርብ ዕለት እንደሆነ ተገልጿል። ሁለቱን የኃይል ማመንጫዎች የሚያስተዳድረው ኤሌክትሪሲት ዱ ሊባን (ኢዲኤል) የተባለ ድርጅት ነው። ኃይል ማመንጫዎቹን የሚያንቀሳቅስ ነዳጅ ጭነው የነበሩ መርከቦች በዶላር ካልተከፈላቸው ነዳጁን እንደማያወርዱ ተናግረዋል። ዛህል በተባለት የሊባኖስ ከተማ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ ተጠይቀዋል። በአገሪቱ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጥ በተጨማሪ ውሃም በፈረቃ መከፋፈል ጀምሯል። ባለፉት 18 ወራት ሊባኖስ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ገጥሟታል። መገበያያቸው የሊባኖስ ፓውንድም ዋጋ አጥቷል። የካንሰር እና የልብ ሕክምና የሚሰጡ አንዳንድ ሆስፒታሎች የመድኃኒት እጥረት ገጥሟቸዋል። የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉት መድኃኒት መደብሮች ማኅበር እንደሚለው በመዲናዋ ቤይሩት 80 በመቶ የመድኃኒት መደብሮች ተዘግተዋል። ከዕለት ወደ ዕለት በአገሪቱ የኑሮ ሁኔታ እያሽቆለቆለ በመጣባት ሊባኖስ፤ ግማሽ ያህሉ ዜጎች በድህነት ውስጥ እንዲኖሩ ምክንያት ሆኗል። በአገሪቱ በሙስና የተወነጀሉ ፖለቲከኞች ከሥልጣን እንዲወርዱ በሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎችም ትናጣለች። ላለፉት አስር ዓመታት በሊባኖስ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሲቆራረጥ ነበር። መብራት በፈረቃ ስለሚለቀቅ ነዋሪዎች ጄነሬተር ለመጠቀም ይገደዳሉ። አሁን ግን አብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በጨለማ ተውጧል። ጄነሬተሮችን የሚያንቀሳቅስ ነዳጅ በቀላሉ ስለማይገኝ ጄነሬተርን እንደ አማራጭ መጠቀመም አይቻልም። | የሊባኖስ ዋነኛ ኃይል ማመንጫዎች ሥራ በማቆማቸው መብራት ተቋረጠ በሊባኖስ ሁለት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ሥራ በማቆማቸው ሳቢያ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል መብራት ጠፍቷል። ሁለቱ ማመንጫዎች ነዳጅ በመጨረሳቸው ነው አገልግሎት መስጠት ያቆሙት። በሊባኖስ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላለ ከአገር ውጭ ለሚገኙ የኃይል አቅራቢ ድርጅቶች ገንዘብ መክፈል አልተቻለም። የመድኃኒት መደብሮች የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ስለገጠማቸው የሥራ ማቆም አድማ አድርገዋል። ዴር አማር እና ዛህራኒ የተባሉት ኃይል ማመንጫዎች የሊባኖስን 40 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ይሸፍናሉ። እነዚህ ኃይል ማመንጫዎች መሥራት ያቆሙት አርብ ዕለት እንደሆነ ተገልጿል። ሁለቱን የኃይል ማመንጫዎች የሚያስተዳድረው ኤሌክትሪሲት ዱ ሊባን (ኢዲኤል) የተባለ ድርጅት ነው። ኃይል ማመንጫዎቹን የሚያንቀሳቅስ ነዳጅ ጭነው የነበሩ መርከቦች በዶላር ካልተከፈላቸው ነዳጁን እንደማያወርዱ ተናግረዋል። ዛህል በተባለት የሊባኖስ ከተማ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ ተጠይቀዋል። በአገሪቱ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጥ በተጨማሪ ውሃም በፈረቃ መከፋፈል ጀምሯል። ባለፉት 18 ወራት ሊባኖስ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ገጥሟታል። መገበያያቸው የሊባኖስ ፓውንድም ዋጋ አጥቷል። የካንሰር እና የልብ ሕክምና የሚሰጡ አንዳንድ ሆስፒታሎች የመድኃኒት እጥረት ገጥሟቸዋል። የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉት መድኃኒት መደብሮች ማኅበር እንደሚለው በመዲናዋ ቤይሩት 80 በመቶ የመድኃኒት መደብሮች ተዘግተዋል። ከዕለት ወደ ዕለት በአገሪቱ የኑሮ ሁኔታ እያሽቆለቆለ በመጣባት ሊባኖስ፤ ግማሽ ያህሉ ዜጎች በድህነት ውስጥ እንዲኖሩ ምክንያት ሆኗል። በአገሪቱ በሙስና የተወነጀሉ ፖለቲከኞች ከሥልጣን እንዲወርዱ በሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎችም ትናጣለች። ላለፉት አስር ዓመታት በሊባኖስ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሲቆራረጥ ነበር። መብራት በፈረቃ ስለሚለቀቅ ነዋሪዎች ጄነሬተር ለመጠቀም ይገደዳሉ። አሁን ግን አብዛኛው የአገሪቱ ክፍል በጨለማ ተውጧል። ጄነሬተሮችን የሚያንቀሳቅስ ነዳጅ በቀላሉ ስለማይገኝ ጄነሬተርን እንደ አማራጭ መጠቀመም አይቻልም። | https://www.bbc.com/amharic/news-57787745 |
3politics
| ኢንጂኒየር ስለሺ በአሜሪካ፣ ጄነራል ባጫ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ | ባለፉት ዓመታት የውሃ፣ ኢነርጂ እና መስኖ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ዶ/ር ኢ/ነ ስለሺ በቀለ በአሜሪካ እንዲሁም ጄነራል ባጫ ደበሌ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ። ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአምባሳደርነት ሹመት የተሰጣቸው ዲፕሎማቶች የተመደቡባቸውን አገራት ይፋ አድርገዋል። በዚህ መሠረት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሲነሳ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱ ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶክተር ኢንጂኒየር ስለሺ በቀለ መቀመጫቸውን ዋሸንግተን ዲሲ በማድረግ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሆኑ ተመድበዋል። ቀደም ሲል በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ፍጹም አረጋ የነበሩ ሲሆን አሁን ይፋ በተደረገው የምደባ ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም። ዶክተር ኢንጂኒየር ስለሺ በቀለ የውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ከዚያም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድንበር ተሻጋሪ ወሃዎችን አማካሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን ወክለው አዲስ አበባ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመረጣቸው ይታወሳል። እንዲሁም ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ስማቸው ጎልቶ የወጡት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች አምባሳደር ባጫ ደበሌ እና አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም ኬንያ እና ግብፅ ተመድበዋል። ጄነራል ባጫ ከትግራዩ ጦርነት መቀስቀስ በኋላ በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከጥቂት ወራት በፊት ነበር የሙሉ ጄነራልነት ሹመትን ያገኙት። አምባሳደር ተፈራ ደርበው ጃፓን የተመደቡ ሲሆን፣ አምባሳደር ደሴ ዳልኬ-ደቡብ ኮሪያ፣ አምባሳደር ዳባ ደበሌ-ሩዋንዳ፣ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው-አውስትራሊያ፣ አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ-ስዊዲን፣ አምባሳደር ፍቃዱ በየነ-ኤርትራ ተመድበዋል። ከዚህ በተጨማሪም ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ሆኖ በተለያዩ አገራት የሚሰሩ እና ምክትል የሚሲዮን መሪ አምባሳደሮች መሾማቸውን ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል። | ኢንጂኒየር ስለሺ በአሜሪካ፣ ጄነራል ባጫ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ ባለፉት ዓመታት የውሃ፣ ኢነርጂ እና መስኖ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ዶ/ር ኢ/ነ ስለሺ በቀለ በአሜሪካ እንዲሁም ጄነራል ባጫ ደበሌ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ። ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአምባሳደርነት ሹመት የተሰጣቸው ዲፕሎማቶች የተመደቡባቸውን አገራት ይፋ አድርገዋል። በዚህ መሠረት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሲነሳ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱ ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶክተር ኢንጂኒየር ስለሺ በቀለ መቀመጫቸውን ዋሸንግተን ዲሲ በማድረግ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሆኑ ተመድበዋል። ቀደም ሲል በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ፍጹም አረጋ የነበሩ ሲሆን አሁን ይፋ በተደረገው የምደባ ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም። ዶክተር ኢንጂኒየር ስለሺ በቀለ የውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ከዚያም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድንበር ተሻጋሪ ወሃዎችን አማካሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን ወክለው አዲስ አበባ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመረጣቸው ይታወሳል። እንዲሁም ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ስማቸው ጎልቶ የወጡት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች አምባሳደር ባጫ ደበሌ እና አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም ኬንያ እና ግብፅ ተመድበዋል። ጄነራል ባጫ ከትግራዩ ጦርነት መቀስቀስ በኋላ በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከጥቂት ወራት በፊት ነበር የሙሉ ጄነራልነት ሹመትን ያገኙት። አምባሳደር ተፈራ ደርበው ጃፓን የተመደቡ ሲሆን፣ አምባሳደር ደሴ ዳልኬ-ደቡብ ኮሪያ፣ አምባሳደር ዳባ ደበሌ-ሩዋንዳ፣ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው-አውስትራሊያ፣ አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ-ስዊዲን፣ አምባሳደር ፍቃዱ በየነ-ኤርትራ ተመድበዋል። ከዚህ በተጨማሪም ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ሆኖ በተለያዩ አገራት የሚሰሩ እና ምክትል የሚሲዮን መሪ አምባሳደሮች መሾማቸውን ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60776787 |
2health
| ኮቪድ -19፡ ልጆች ኮሮናቫይረስን ያስተላልፋሉ? | ደቡብ ኮርያ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ልጆች ኮሮናቫይረስን አፍንጫቸው ላይ ይዘው እስከ ሦስት ሳምንታት መቆየት ይችላሉ። ከዚህ ቀደም የተሠሩ ጥናቶች፤ በርካታ ልጆች መጠነኛ የበሽታውን ምልክት እንደሚያሳዩ ወይም እስከነጭራሹ ምልክት እንደማይታይባቸው ይጠቁማሉ። እነዚህ ግኝቶች ልጆች ምን ያህል በሽታውን ያሰራጫሉ? ለሚለውና እስካሁን ግልጽ ምላሽ ላልተገኘለት ጉዳይ ፍንጭ ይሰጣሉ። ለወራት እንቅስቃሴ አቁመው በነበሩ አገሮች ትምህርት ቤቶች እየተከፈቱ ነው። አካላዊ ርቀትና ንጽህናን መጠበቅ መዘንጋት እንደሌለበትም ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ኮቪድ-19 እና ልጆችን በተመለከተ ሦስት ዋና ጥያቄዎች እንዳሉ የሚናገሩት የሮያል ኮሌጅ ፕሮፌሰር ራሰል ቪነር ናቸው። የሚከተሉት ጥያቄዎቻቸው ናቸው፦ ልጆች በቫይረሱ እንደሚያዙ በጥናቱ ተረጋግጧል። ፕ/ር ራሰል እንደሚሉት፤ ከፀረ እንግዳ አካላት (አንቲቦዲ) ምርመራ በተገኘ መረጃ መሠረት በተለይም ከ12 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከአዋቂዎች ባነሰ ለቫይረሱ ይጋለጣሉ። • የ2013 የትምህርት ዘመንን ለማስጀመር ምን እየተሰራ ነው? • ኮሮናቫይረስ በማገርሸቱ ደቡብ ኮሪያ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው እንዲዘጉ አዘዘች ልጆች በቫይረሱ ከተያዙ የአዋቂዎች ያህል እንደማይታመሙም ሳይንቲስቶች እርግጠኛ ናቸው። እንዲያውም በርካታ ልጆች የበሽታውን ምልክት አያሳዩም። እምብዛም መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ያስተላልፋሉ የሚለው ነው። የደቡብ ኮርያው ጥናትም እዚህ ላይ ያተኮረ ነው። የደቡብ ኮርያው ጥናት ምን ይላል? ጥናቱ የተሠራው 91 ልጆች ላይ ነው። መጠነኛ ወይም ምንም ምልክት የማያሳዩ ልጆች እስከ ሦስት ሳምንት ድረስ ቫይረሱ እንደሚቆይ ከናሙና መረዳት ተችሏል። አፍንጫቸው ላይ የቫይረሱ ምልክት መገኘቱ፤ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ማስተላልፍ እንደሚችሉ እንደሚጠቁም የጥናቱ ጸሐፊዎች አስረድተዋል። ደቡብ ኮርያ በምታካሂደው ምርመራና በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች በምትለይበት ሂደት አማካይነት፤ የበሽታውን ምልክት የማያሳዩ ሰዎች ሳይቀሩ ይገኛሉ። ህሙማን ከተለዩ በኋላ ከቫይረሱ ነፃ እስኪሆኑ በተደጋጋሚ ተመርምረዋል። ጥናቱ ልጆች ቫይረሱን እንደሚሸከሙ፣ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፉ እንደሚችሉም ጠቁሟል። ሆኖም ግን ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ አልሰጠም። ልጆች አፍንጫ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ማለት የአዋቂዎች ያህል ቫይረሱን ያስተላልፋሉ ማለት አይደለም። በሕፃናት ሕክምና ክፍል የሚሠሩት ዶ/ር ሮበርታ ዲባሲ ልጆች ቫይረሱን ሊያስተላልፉ አይችሉም ማለት እንደማይቻል ያስረዳሉ። የቫይረሱ ዘረ መል ከመተንፈሻ አካላት በሚወሰድ ናሙና ላይ መገኘቱ በሽታውን ከማስተላለፍ ጋር የግድ እንደማይተሳሰር የሚናገሩት ደግሞ የሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ ፕ/ር ካሉም ሰምፕል ናቸው። የጥናቱ ድምዳሜ ምንድን ነው? ልጆችም ይሁን አዋቂዎች መጠነኛ ወይም ምንም አይነት ምልክት ካላሳዩ በሽታውን የማስተላለፍ እድላቸው አናሳ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ። የማያስሉ ወይም የማያስነጥሱ ሰዎች ቫይረሱን ወደ አየር እምብዛም አይለቁም። ሆኖም ግን ምልክት የማያሳዩ ሰዎች በሽታውን አያሰራጩም ማለት አይደለም። ዶክተሩ እንደሚሉት፤ አብዛኞቹ ልጆች በተወሰነ ደረጃ ወይም ሊታይ በማይችል ሁኔታ ነው በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት። በማኅበረሰቡ ውስጥ ቫይረሱን ሊያሰራጩ ግን ይችላሉ። | ኮቪድ -19፡ ልጆች ኮሮናቫይረስን ያስተላልፋሉ? ደቡብ ኮርያ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ልጆች ኮሮናቫይረስን አፍንጫቸው ላይ ይዘው እስከ ሦስት ሳምንታት መቆየት ይችላሉ። ከዚህ ቀደም የተሠሩ ጥናቶች፤ በርካታ ልጆች መጠነኛ የበሽታውን ምልክት እንደሚያሳዩ ወይም እስከነጭራሹ ምልክት እንደማይታይባቸው ይጠቁማሉ። እነዚህ ግኝቶች ልጆች ምን ያህል በሽታውን ያሰራጫሉ? ለሚለውና እስካሁን ግልጽ ምላሽ ላልተገኘለት ጉዳይ ፍንጭ ይሰጣሉ። ለወራት እንቅስቃሴ አቁመው በነበሩ አገሮች ትምህርት ቤቶች እየተከፈቱ ነው። አካላዊ ርቀትና ንጽህናን መጠበቅ መዘንጋት እንደሌለበትም ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ኮቪድ-19 እና ልጆችን በተመለከተ ሦስት ዋና ጥያቄዎች እንዳሉ የሚናገሩት የሮያል ኮሌጅ ፕሮፌሰር ራሰል ቪነር ናቸው። የሚከተሉት ጥያቄዎቻቸው ናቸው፦ ልጆች በቫይረሱ እንደሚያዙ በጥናቱ ተረጋግጧል። ፕ/ር ራሰል እንደሚሉት፤ ከፀረ እንግዳ አካላት (አንቲቦዲ) ምርመራ በተገኘ መረጃ መሠረት በተለይም ከ12 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከአዋቂዎች ባነሰ ለቫይረሱ ይጋለጣሉ። • የ2013 የትምህርት ዘመንን ለማስጀመር ምን እየተሰራ ነው? • ኮሮናቫይረስ በማገርሸቱ ደቡብ ኮሪያ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው እንዲዘጉ አዘዘች ልጆች በቫይረሱ ከተያዙ የአዋቂዎች ያህል እንደማይታመሙም ሳይንቲስቶች እርግጠኛ ናቸው። እንዲያውም በርካታ ልጆች የበሽታውን ምልክት አያሳዩም። እምብዛም መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ያስተላልፋሉ የሚለው ነው። የደቡብ ኮርያው ጥናትም እዚህ ላይ ያተኮረ ነው። የደቡብ ኮርያው ጥናት ምን ይላል? ጥናቱ የተሠራው 91 ልጆች ላይ ነው። መጠነኛ ወይም ምንም ምልክት የማያሳዩ ልጆች እስከ ሦስት ሳምንት ድረስ ቫይረሱ እንደሚቆይ ከናሙና መረዳት ተችሏል። አፍንጫቸው ላይ የቫይረሱ ምልክት መገኘቱ፤ ልጆች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ማስተላልፍ እንደሚችሉ እንደሚጠቁም የጥናቱ ጸሐፊዎች አስረድተዋል። ደቡብ ኮርያ በምታካሂደው ምርመራና በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች በምትለይበት ሂደት አማካይነት፤ የበሽታውን ምልክት የማያሳዩ ሰዎች ሳይቀሩ ይገኛሉ። ህሙማን ከተለዩ በኋላ ከቫይረሱ ነፃ እስኪሆኑ በተደጋጋሚ ተመርምረዋል። ጥናቱ ልጆች ቫይረሱን እንደሚሸከሙ፣ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፉ እንደሚችሉም ጠቁሟል። ሆኖም ግን ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ አልሰጠም። ልጆች አፍንጫ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ማለት የአዋቂዎች ያህል ቫይረሱን ያስተላልፋሉ ማለት አይደለም። በሕፃናት ሕክምና ክፍል የሚሠሩት ዶ/ር ሮበርታ ዲባሲ ልጆች ቫይረሱን ሊያስተላልፉ አይችሉም ማለት እንደማይቻል ያስረዳሉ። የቫይረሱ ዘረ መል ከመተንፈሻ አካላት በሚወሰድ ናሙና ላይ መገኘቱ በሽታውን ከማስተላለፍ ጋር የግድ እንደማይተሳሰር የሚናገሩት ደግሞ የሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ ፕ/ር ካሉም ሰምፕል ናቸው። የጥናቱ ድምዳሜ ምንድን ነው? ልጆችም ይሁን አዋቂዎች መጠነኛ ወይም ምንም አይነት ምልክት ካላሳዩ በሽታውን የማስተላለፍ እድላቸው አናሳ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ። የማያስሉ ወይም የማያስነጥሱ ሰዎች ቫይረሱን ወደ አየር እምብዛም አይለቁም። ሆኖም ግን ምልክት የማያሳዩ ሰዎች በሽታውን አያሰራጩም ማለት አይደለም። ዶክተሩ እንደሚሉት፤ አብዛኞቹ ልጆች በተወሰነ ደረጃ ወይም ሊታይ በማይችል ሁኔታ ነው በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት። በማኅበረሰቡ ውስጥ ቫይረሱን ሊያሰራጩ ግን ይችላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-53957592 |
0business
| ቢትኮይን ፡ በኤል ሳልቫዶር የቢትኮይንን ሕጋዊ መገበያያነት በመቃወም ሰልፍ ተደረገ | በላቲን አሜሪካዋ አገር ኤል ሳልቫዶር በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች መንግሥት ቢትኮይንን እንደ ሕጋዊ የመገበያያ ገንዘብ በመቀበሉ ቁጣቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጡ። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ናይብ ቡኬሌ ክሪፕቶከረንሲ በውጭ አገር የሚሰሩ ሳልቫዶራውያን ገንዘባቸውን በቀላሉ ወደ አገራቸው እንዲልኩ ይረዳቸዋል ብለዋል። ሰልፈኞቹ ግን በከፋ ድህነት ውስጥ የምትገኘውን ኤል ሳልቫዶር ወደ በለጠ የዋጋ ግሽበት ብሎም ያለመረጋጋት ይወስዳታል ብለው ይሰጋሉ። ከሰልፈኞቹ መካከል የተወሰኑት አንድ አዲስ የቢትኮይን ማሽን በእሳት ሲያቃጥሉ ሌሎች «ቡኬሌ አምባገነን» የሚል መፈክር ይዘው ታይተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ኤል ሳልቫዶር ከአሜሪካ ዶላር በተጨማሪ ክርፒቶከረንሲን እንደ ሕጋዊ የመገበያያ ዘዴዋ በመጠቀም የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። በዋና ከተማዋ ሳን ሳልቫዶር የተሰበሰቡት ሰልፈኞቹ ይህንን ሰልፍ ያካሄዱት አገራቸው 200ኛውን የነፃነት በዓሏን በምታከብርበት ቀን ነው። « እምቢ ለቢትኮይን» እና «ሕገ -መንግሥቱ ይከበር» የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ላይ ከታዩት መካከል ናቸው። ሰልፈኞቹ ፕሬዚዳንቱ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ቆይታቸውን ለማራዘም አቅደው ተንቀሳቅሰዋል ሲሉም ይከሳሉ። ምንም እንኳን ሕገ-መንግሥታዊ ገደብ ቢቀመጥም ቡኬሌ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ለፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፈቅዶላቸዋል። «ዛሬ ማለዳ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር- በቃ! ማለት ነው። መንግሥት እያደረገ ያለው እብሪተኛ እና አምባገነናዊ ተግባር ነው» ሲሉ አንድ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ ግለሰብ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ነገር ግን ፕሬዝደንት ቡኬሌ አሁንም በኤል ሳልቫዶር ጠንካራ ድጋፍ አላቸው። በቅርቡ አንድ የአገር ውስጥ ጋዜጣ ባደረገው የሕዝብ አስተያየት ጥሪ 85.7% የሚሆኑ ድምጽ ሰጪዎች ለፕሬዝደንቱ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። | ቢትኮይን ፡ በኤል ሳልቫዶር የቢትኮይንን ሕጋዊ መገበያያነት በመቃወም ሰልፍ ተደረገ በላቲን አሜሪካዋ አገር ኤል ሳልቫዶር በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች መንግሥት ቢትኮይንን እንደ ሕጋዊ የመገበያያ ገንዘብ በመቀበሉ ቁጣቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጡ። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ናይብ ቡኬሌ ክሪፕቶከረንሲ በውጭ አገር የሚሰሩ ሳልቫዶራውያን ገንዘባቸውን በቀላሉ ወደ አገራቸው እንዲልኩ ይረዳቸዋል ብለዋል። ሰልፈኞቹ ግን በከፋ ድህነት ውስጥ የምትገኘውን ኤል ሳልቫዶር ወደ በለጠ የዋጋ ግሽበት ብሎም ያለመረጋጋት ይወስዳታል ብለው ይሰጋሉ። ከሰልፈኞቹ መካከል የተወሰኑት አንድ አዲስ የቢትኮይን ማሽን በእሳት ሲያቃጥሉ ሌሎች «ቡኬሌ አምባገነን» የሚል መፈክር ይዘው ታይተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ኤል ሳልቫዶር ከአሜሪካ ዶላር በተጨማሪ ክርፒቶከረንሲን እንደ ሕጋዊ የመገበያያ ዘዴዋ በመጠቀም የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። በዋና ከተማዋ ሳን ሳልቫዶር የተሰበሰቡት ሰልፈኞቹ ይህንን ሰልፍ ያካሄዱት አገራቸው 200ኛውን የነፃነት በዓሏን በምታከብርበት ቀን ነው። « እምቢ ለቢትኮይን» እና «ሕገ -መንግሥቱ ይከበር» የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ላይ ከታዩት መካከል ናቸው። ሰልፈኞቹ ፕሬዚዳንቱ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ቆይታቸውን ለማራዘም አቅደው ተንቀሳቅሰዋል ሲሉም ይከሳሉ። ምንም እንኳን ሕገ-መንግሥታዊ ገደብ ቢቀመጥም ቡኬሌ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ለፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፈቅዶላቸዋል። «ዛሬ ማለዳ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር- በቃ! ማለት ነው። መንግሥት እያደረገ ያለው እብሪተኛ እና አምባገነናዊ ተግባር ነው» ሲሉ አንድ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ ግለሰብ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ነገር ግን ፕሬዝደንት ቡኬሌ አሁንም በኤል ሳልቫዶር ጠንካራ ድጋፍ አላቸው። በቅርቡ አንድ የአገር ውስጥ ጋዜጣ ባደረገው የሕዝብ አስተያየት ጥሪ 85.7% የሚሆኑ ድምጽ ሰጪዎች ለፕሬዝደንቱ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58554994 |
5sports
| ሴኔጋል ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮን ሆነች | ሴኔጋል ግብጽን 4 ለ 2 በመለያ ምት በመርታት የመጀመሪያዋን የአፍሪካ ዋንጫ ለማንሳት በቃች። ጨዋታው በሁለቱ የሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ እና መሐመድ ሳላህ መካከል የተደረገ ፍልሚያ ተብሎ በብዙዎች በከፍተኛ ጉጉት የተጠበቀ ነበር። ጨዋታው ያለምንም ጎል በመጠናቀቁ ነበር ወደ መለያ ምት የተሸጋገረው። ማኔ በሰባተኛው ደቂቃ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል። የቼልሲው የግብ ዘብ ኤዱዋርድ ሜንዲ በበኩሉ በመለያ ምቱ ወቅት ሞኢሃናደድ ላሺን ኳስ አድኖ ለቡድኑን አሸናፊነት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የፈርንኦቹ ግብ ጠባቂ ጋባስኪም ድንቅ ሆኖ አምሽቷል። ሴኔጋል ከዚህ ቀደም በሁለት የፍጻሜ ጨዋታዎች ከተሸነፈች በኋላ በመጨረሻም የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ለመሆን በቅታለች። ግብጽ ውድድሩን በማሸነፍ ክብረወሰኗን ወደ ስምንት የምታሳድግበትን ዕድል ሳትጠቀም ቀርታለች። የሴኔጋሉ አሰልጣኝ አሊዩ ሲሴ "ጠንክረህና ጸንተህ ከሠራህ የምትፈልገውን እንደምታገኝ ያሳያል" ሲሉ ድሉን ገልጸውታል። "በጣም ስሜታዊ ሆኛለሁ ምክንያቱም የሴኔጋል ህዝብ ይህን ዋንጫ ለ60 ዓመታት ናፍቋል" ብለዋል አሰልጣኙ። በውድድሩ ላይ አራቱም የግብጽ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ወደ ተጨማሪ ሰዓት ተሸጋግረዋል። ፈርኦኖቹ አይቮሪኮስትን እና አስተናጋጇ ካሜሩንን በመለያ ምት አሸንፈው ነበር ለፍጻሜው የደረሱት። ጨዋታው ወደ መለያ ምት ከመሸጋገሩ በፊት ጋባስኪ ቀደም ሲል በውድድሩ ላይ አራት መለያ ምቶችን አድኖ ነበር። ግብጻዊው ተከላካይ መሀመድ አብደልሞኔ መለያ ሳይጠቀምበት የቀረ ሲሆን በፍጥነት ጋባስኪ የቡና ሳርን ኳስ ለመዳን ችሎ ነበር። የላሺን መለያ ምት በሜንዲ ሲድን የመጨረሻዋን ኳስ ማኔ አስቆጥሮ ለዋንጫ ሴኔጋሎች ዋንጫውን አንስተዋል። የሊቨርፑል የቡድን አጋሩ ሳላህ አምስተኛ መቺ በመደረጉ የመለያ ምቱን እንኳን ለመምታት ዕድል አላገኘም። ሴኔጋል በፈረንጆቹ 2002 እና 2019 ለፍጻሜ ቀርባ ተሽንፋለች። ሳላህ በሴኔጋል ተከላካዮች ቁጥጥር ስር ባመሸበት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ሙከራዎችን አድርጓል። በሁለተኛው አጋማሽ ፈርኦኖቹ ጎል ለማስቆጠር ያደረጉት ሙከራ ፍሬ ሳያፈራ ቀርቷል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጭማሪው ሰዓት ሞቅ ብሎ ተከናውኗል። በመጨረሻም ድሉ ላለፉት ሦስት ዓመታት የአፍሪካን የሃገራት ደረጃ ለመራችው ሴኔጋል ሆኗል። አሰልጣኝ አልዩ ሲሴም በተጫዋችነት በ2002 ወሳኟን የመለያ ምት ከሳቱ እና ከሦስት ዓመት በፊት በፍጻሜው ከተሸነፉ በኋላ ያገኙት ድል ሆኖ ተመዝግቧል። ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ከአንድ ዓመት በኋላ በአይቮሪ ኮስት ይከናወናል። ሁለቱ ቡድኖች በሚቀጥለው ወር ለኳታር የዓለም ዋንጫ ለማነፍ በድጋሚ ተገናኝተው በደርሶ መልስ ስለሚጫወቱ ግብጽ በቅርቡ የመበቀል ዕድል ይኖራታል። | ሴኔጋል ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮን ሆነች ሴኔጋል ግብጽን 4 ለ 2 በመለያ ምት በመርታት የመጀመሪያዋን የአፍሪካ ዋንጫ ለማንሳት በቃች። ጨዋታው በሁለቱ የሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ እና መሐመድ ሳላህ መካከል የተደረገ ፍልሚያ ተብሎ በብዙዎች በከፍተኛ ጉጉት የተጠበቀ ነበር። ጨዋታው ያለምንም ጎል በመጠናቀቁ ነበር ወደ መለያ ምት የተሸጋገረው። ማኔ በሰባተኛው ደቂቃ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል። የቼልሲው የግብ ዘብ ኤዱዋርድ ሜንዲ በበኩሉ በመለያ ምቱ ወቅት ሞኢሃናደድ ላሺን ኳስ አድኖ ለቡድኑን አሸናፊነት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የፈርንኦቹ ግብ ጠባቂ ጋባስኪም ድንቅ ሆኖ አምሽቷል። ሴኔጋል ከዚህ ቀደም በሁለት የፍጻሜ ጨዋታዎች ከተሸነፈች በኋላ በመጨረሻም የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ለመሆን በቅታለች። ግብጽ ውድድሩን በማሸነፍ ክብረወሰኗን ወደ ስምንት የምታሳድግበትን ዕድል ሳትጠቀም ቀርታለች። የሴኔጋሉ አሰልጣኝ አሊዩ ሲሴ "ጠንክረህና ጸንተህ ከሠራህ የምትፈልገውን እንደምታገኝ ያሳያል" ሲሉ ድሉን ገልጸውታል። "በጣም ስሜታዊ ሆኛለሁ ምክንያቱም የሴኔጋል ህዝብ ይህን ዋንጫ ለ60 ዓመታት ናፍቋል" ብለዋል አሰልጣኙ። በውድድሩ ላይ አራቱም የግብጽ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ወደ ተጨማሪ ሰዓት ተሸጋግረዋል። ፈርኦኖቹ አይቮሪኮስትን እና አስተናጋጇ ካሜሩንን በመለያ ምት አሸንፈው ነበር ለፍጻሜው የደረሱት። ጨዋታው ወደ መለያ ምት ከመሸጋገሩ በፊት ጋባስኪ ቀደም ሲል በውድድሩ ላይ አራት መለያ ምቶችን አድኖ ነበር። ግብጻዊው ተከላካይ መሀመድ አብደልሞኔ መለያ ሳይጠቀምበት የቀረ ሲሆን በፍጥነት ጋባስኪ የቡና ሳርን ኳስ ለመዳን ችሎ ነበር። የላሺን መለያ ምት በሜንዲ ሲድን የመጨረሻዋን ኳስ ማኔ አስቆጥሮ ለዋንጫ ሴኔጋሎች ዋንጫውን አንስተዋል። የሊቨርፑል የቡድን አጋሩ ሳላህ አምስተኛ መቺ በመደረጉ የመለያ ምቱን እንኳን ለመምታት ዕድል አላገኘም። ሴኔጋል በፈረንጆቹ 2002 እና 2019 ለፍጻሜ ቀርባ ተሽንፋለች። ሳላህ በሴኔጋል ተከላካዮች ቁጥጥር ስር ባመሸበት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ሙከራዎችን አድርጓል። በሁለተኛው አጋማሽ ፈርኦኖቹ ጎል ለማስቆጠር ያደረጉት ሙከራ ፍሬ ሳያፈራ ቀርቷል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጭማሪው ሰዓት ሞቅ ብሎ ተከናውኗል። በመጨረሻም ድሉ ላለፉት ሦስት ዓመታት የአፍሪካን የሃገራት ደረጃ ለመራችው ሴኔጋል ሆኗል። አሰልጣኝ አልዩ ሲሴም በተጫዋችነት በ2002 ወሳኟን የመለያ ምት ከሳቱ እና ከሦስት ዓመት በፊት በፍጻሜው ከተሸነፉ በኋላ ያገኙት ድል ሆኖ ተመዝግቧል። ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ከአንድ ዓመት በኋላ በአይቮሪ ኮስት ይከናወናል። ሁለቱ ቡድኖች በሚቀጥለው ወር ለኳታር የዓለም ዋንጫ ለማነፍ በድጋሚ ተገናኝተው በደርሶ መልስ ስለሚጫወቱ ግብጽ በቅርቡ የመበቀል ዕድል ይኖራታል። | https://www.bbc.com/amharic/60253411 |
2health
| በቀን ሦስት ጊዜ ባንመገብስ? ቁርስ፣ ምሳና እራት ልማድ ወይስ አስፈላጊ የምግብ ጊዜ? | ምግብ ከእጅ ወደ አፍ፣ ከአፍ ደግሞ ወደ ሆድ የሚላክ ነገር ብቻ አይደለም። ምግብ የባህል አካል ነው። ያለ ምግብ ውሎን፣ አዳርን፣ በዓልን ማሰብ ከባድ ነው። በየዓይነቱ አዘጋጅቶ ገበታውን ሙሉ አድርጎ ወዳጅ ዘመድን መጋበዝ የፍቅርና የወዳጅነት መግለጫ ነው። እዚህ ላይ ትንሽ ኢትዮጵያዊነት እንጨምርበት ካልን 'በሞቴ' እያሉ መጎራረስ ይቻላል። ይህም ምግብ በሰው ልጆች አካላዊ እና አዕምሮአዊ ዕድገት ውስጥ ካለው ቁልፍ ተግባር አልፎ ማኅበራዊ ትስስርን የሚገነባ ተጨማሪ መንገድ መሆኑን ያመላክት ይሆናል። የሆነው ሆኖ የምግብ ዋነኛ ዓላማዎች ሁለት ናቸው - ለሰውነት ጉልበት እና ኃይልን መስጠት እንዲሁም በሽታ የመከላከልን ሥርዓትን ማዳበር። የምግብ ተግባር ይህ ከሆነ በቀን ስንት ጊዜ፣ ምን እና እንዴት እንመገብ? ስንት ጊዜ የሚለውን እናቆየው! 'ሰው የሚመገበውን ይመስላል' የዕለት ተግባራችንን በበቂ ጉልበት ለመከወን፤ የበሽታ መከላከል አቅማችንንም ለማደርጀት ምን እንመገብ የሚል ጥያቄ ሲነሳ የምግብ ስብጥር [food diversity] የሚል ሃሳብ ይነሳል። ምን ማለት ነው? ለምሳሌ አቮካዶ እና እንቁላል [በተለይ አስኳሉ] በበርካታ ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ምን አልባትም አቻ የሌላቸው ምግቦች ናቸው። ነገር ግን እነርሱን ብቻ መመገብ ይጎዳል ባይባል እንኳን ለሰውነት ከሚያስፈልጉ እና ጠቃሚ ከሆኑ ሌሎች ንጥረ ነገሮች ውጪ ያደርጋል። እናም በቀን ውስጥ የተለያዩ የምግብ አይነቶችን መመገብ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን በአንድ ጊዜ ለመግኘት ያግዛል። ይህ የምግብ ስብጥር ይባላል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሳይንስ እና ሥነ ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ቃለአብ ባዬ በሥነ ምግብ ጉዳይ ላይ በዓለም ዙሪያ የሚሰሩ ተመራማሪዎች ያዘጋጇቸው የአመጋገብ መመሪያዎች በሌሎች ጉዳዮች የተለያዩ ሃሳቦችን ሊያንጸባርቁ ቢችሉም ምግብን ማሰባጠር በተመለከተ "ሁሉም ማለት ይቻላል" ተመሳሳይ አቋም አላቸው ይላሉ። እንደ እርሳቸው ገለጻ የምንመገባቸው ምግቦች አይነት "በተቻለ መጠን" በበዛ ቁጥር "የሚያስፈልገንን ኃይል እና ንጥረ ነገር የሟሟላት ዕድላችን ከፍ ይላል።" "እኛ ሰዎች ማለት የበላነው ምግብ ነን" የሚሉት በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሳይንስ እና የሥነ ምግብ መምህሩ ዶ/ር ይኹኔ አየለ ደግሞ "ሰውነታችን በአጠቃላይ በትክክለኛ የተፈጥሮ ሂደቱ ሥራውን ይከውን ዘንድ ቢያንስ 53 ዓይነት ሚኒራሎች/ማዕድናት እና ቫይታሚኖች ያስፈልጉታል" ሲሉ ያብራራሉ። "በምድር ላይ እነዚህን ሁሉ ሚኒራሎችና አስፈላጊ ነገሮችን አሟልቶ የያዘ አንድ ምግብ ልናገኝ አንችልም" ስለዚህ "በተቻለ መጠን ባለን አቅም" ምግቦችን የማሰባጠርን አስፈላጊነት ይመክራሉ። ጎመን በሥጋ ዶ/ር ይኹኔ ለምግብ ስብጥር ከሚሰጧቸው ምሳሌዎች አንዱ አትክልት እና የእንስሳት ተዋፅኦን በጋራ መመገብን ነው። በኢትዮጵያ የተለመደውን ጎመን በሥጋ ስብጥርን በተመለከተ ለዓለም ትምህርት የሚሆን ሲሉ ይገልጹታል። እንደ እርሳቸው ገለጻ አይረን/የብረት ማዕድንን ከሥጋ 70 በመቶ፣ ከአትክልቶች ደግሞ እስከ 17 በመቶ ይገኛል። ይህ ሁኔታ ሥጋን 'ቸር' አትክልትን ደግሞ 'ንፉግ' ያሰኘዋል ይላሉ። ታዲያ ጎመን በሥጋ ጋር ይህ አይሰራም፤ ሁለቱ በጋራ ሲዘጋጁ ጎመን አትክልታዊ ባህሪው ተቀይሮ 'ቸር' ይሆናል። ለየብቻ ሲዘጋጁ ከሚገኘው ንጥረ ነገር የላቀ ጠቀሜታን ያቀርባል። አትክልት፣ የእንስሳት ተዋፅኦ፣ የእህል ዘር፣ ፍራፍሬና የቅባት እህል በሰፊው የምግብ አይነቶች/ዘርፎች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የምግብ አይነቶች በዓለም ጤና ድርጅት እና የምግብ እና እርሻ ድርጅት በተዘጋጁ የሥነ ምግብ መመሪያዎች ውስጥ ከተካተቱ 10 የምግብ አይነቶች/ዘርፍ ውስጥ የተጠቀሱ ናቸው። ታዲያ በቀን ውስጥ እነዚህ የምግብ አይነቶችን አሰባጥሮ መመገብ ነው ባለሙያዎቹ የሚመክሩት ነው። ነገሩ እነዚህን ሁሉ ለሟሟላት ያውም በየቀኑ አቅም ከየት ይመጣል? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም። ዶ/ር ይኹኔ ግን መልስ አላቸው - መቼም ውድ የሚሆነው የእንስሳት ተዋፅኦ ነው። ስለዚህ የእንስሳቱን ተዋፅኦ ዝቅ አድርጎ ከሌሎች ምግቦች ጋር መጠቀም። "ሽሮ ላይ እንቁላል ወይም ቋንጣ ጣል ማድረግ" ሲሉ ያስቀምጣሉ። ይህስ ባይቻል? ንፍሮ እና ቆሎ ከእጽዋት የሚገኙትን ምግቦች ማሰባጠር። ዶ/ር ይኹኔ እዚህ ጋርም በኢትዮጵያ የሚዘወተር እና ሊበረታታ የሚገባው የሚሉት ምሳሌ አላቸው - ከተለያዩ ጥራጥሬዎች የሚዘጋጅ ንፍሮ። እያንዳንዱ ጥራጥሬ የራሱ ጥቅም ያለው እና አንዱ የሌለው በሌላኛው ስለሚተካ የሥነ ምግብ ጠቀሜታውን ከፍ ያደርገዋል። ከዚህም ባሻገር የገብስ ቆሎ ሲዘጋጅ ለውዝ፣ ኑግ እና መሰል ጥራጥሬዎችን ያካትታል። ይህ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሊበለጽግ የሚገባው እና በሳይንስ እጅግ የሚደገፈው ምግብን የማሰባጠር ልማድ እንዳለ የሚያረጋግጥ ነው ይላሉ። ስለዚህ ሥጋው ጋር ማን አድርሶን ቢባል እንኳን ተፈጥሮ በአይነት በአይነት ያቀረበቻችውን አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎችና ጥራጥሬዎች ማሰባጠር የተለያዩ ጠቀሜታዎችን ያስገኛል። ዶ/ር ቃለአብ የምግብ አይነቶች/ዘርፎች በውስጣቸው በተለያዩ ቀለማት የሚቀመጡ ምግብን ስለያዙ "ምግባችን ምን ያህል ቀለም አለው?" ብሎ መጠየቅ የምግቡን ስብጥር ሊያመላክት ይችላል። በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የምግብ ሥርዓት እና ሥነ ምግብ ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ "ጥግብ!" ብዬ በላሁ ማለት በቀን ውስጥ ለሰውነት የሚያስፈልገንን ንጥረ ነገር ስለማግኘታችን ያረጋግጣል ማለት አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ። ስለዚህም በ24 ሰዓት ውስጥ በዓለም ጤና ድርጅት እና የምግብ እና እርሻ ድርጅት በተዘጋጁ የሥነ ምግብ መመሪያዎች ውስጥ ከተካተቱ 10 የምግብ አይነቶች/ዘርፍ ውስጥ ቢያንስ አምስቱን ለማካተት መሞከር ተገቢ ነው ይላሉ። ኃላፊው ይህንን መመሪያ ኢትዮጵያ እንደምትቀበለው እና በጤና ሚኒስቴርም የሚመከር መሆኑን ይጠቅሳሉ። የምግብ ሰሃናችን ምን ምን ይዟል? በአሜሪካ በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ላስቬጋስ በምግብ ዝግጅት እና ሥነ ምግብ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ሼፍ አዲስዓለም ብዙአየሁ "በቀን ውስጥ ሰውነት የሚያስፈልገውን ምግብ ተመግቤያለሁ ወይ?" ብሎ መጠየቅ ይገባል ሲሉ ይገልጻሉ። ይህንን ጥያቄ በቀላሉ የምግብ ሰሃኑ ሊመልሰው እንደሚችል ጠቅሰዋል። "የምግብ ሰሃናችን ግማሹ አትክልት መሆን ነው ያለበት። ጥቅል ጎመን ሊሆን ይችላል፤ ካሮት፣ ቀይስር፣ የሀበሻ ጎመን፣ ቲማቲም፣ ዝኩኒ አይነት ነገር" ሊሸፈን ይችላል። የሰሃኑ አንድ አራተኛ ወይም ሩብ ደግሞ ፕሮቲን አዘል በሆነ ምግብ መሸፈን ይገባል። "ለምሳሌ ቦሎቄ፣ እንቁላል፣ ዓሳ፣ የዶሮ ሥጋ ወይም የከብት ሥጋን የመሰሉ ምግቦች መያዝ ይኖርበታል" የተቀረው ደግሞ ካርቦ ሃይድሬትን እንደ ሩዝ፣ ፓስታ ወይም ዳቦ አይነት ምግቦችን ቢያካትት ይመከራል ሲሉ ገልጸዋል። ሰሃኑ ላይ እንደ እንጀራ ያለ ማባያ ሲከተት ደግሞ በርከት ያለ ንጥረ ነገር የመገኘት እድሉን ከፍ ያደርገዋል። የሰሃኑ ግማሹ ክፍል አቮካዶን በመሰሉ ፍራፍሬዎች ሊተካ እንደሚችልም ጠቁመዋል። ከዚህ ባሻገር ደግሞ ከመደበኛ የምግብ ሰዓት ባሻገር የተለያዩ አይነት ፍራፍሬዎችን መመገብ እጅግ የሚያበረታታ ነው። እንደ ሼፍ አዲስዓለም ገለጻ ምግቦችን ማሰባጠር የተለያዩ የሰውነት ክሎች የሚፈልጓቸውን ንጥረ ነገሮች በተመጣጠነ ሁኔታ እንዲያገኝ ያስችላል። በዚህ ምክረ ሃሳብ መሰረት ምሳ ፓስታ በዳቦ የበላን ሰው አስቡት! እንዴት እንመገብ? ከምግቦች ስብጥር ባሻገር የአመጋገብ ሁኔታ በጤና ሥርዓተ ምግብ ውስጥ ወሳኝ ቦታ አለው። በኢትዮጵያ ያለው ለምግብ የተለየ ሰዓት የመስጠት ልማድ ሊበረታታ ይገባል ይላሉ የሥነ ምግብ ባለሙያዎቹ። ከዚህ ልማድ በተቃራኒ እየመጡ ያሉ ልማዶች ከጅምሩ መቅረፍ ቢቻል ተገቢ ነው የሚሉት ዶ/ር ቃለአብ ናቸው። ዶ/ር ቃለአብ መኪና እያሽከረከሩ፣ ሥራ እየሰሩ፣ ስልክ እየተጠቀሙ ወይም ሌላ ትኩረትን ሊስብ የሚችል ነገር ላይ ተጠምዶ ምግብ መመገብ ከሚያስፈልገው መጠን በላይ ምግብ ለመውሰድ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። "ተጽዕኖ ከሚፈጥሩ ነገሮች በጸዳ መልኩ ቁጭ ብሎ ጊዜ ወስዶ ረጋ ብሎ መመገብ ያለውን ጥቅም በሳይንሱ በሂደት እየተረዳነው ነው" የሚሉት ዶ/ር ቃለአብ "በጋራ ምግብን የፍቅር እና የጥሩ ጊዜ ማሳለፊያ አድርጎ ቁጭ ብሎ መመገብ ከንጥረ ነገር ባለፈ አመጋገባችን ላይ ወሳኝነት ስላለው እና የምግብ መጠን ቁጥጥርን" ስለሚያግዝ እጅግ የሚበረታታ ነው ይላሉ። የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምግብ መምህሩ ዶ/ር ይኹኔ በበኩላቸው የቅርብ ጊዜ ጥናቶች የጋራ ገበታ ያላቸውን ፋይዳ እያረጋገጡ እንደሆነ ይገልጻሉ። በጋራ እየተጨዋወቱ መመገብ የተመጠነ ምግብ በተሻለ ሁኔታ ለማግኘት እና በተረጋጋ ሁኔታ ሥርዓተ ምግብን ለመከወን ይረዳል። በሌላ በኩል ዶ/ር ቃለአብ "ያለማቋረጥ ቶሎ ቶሎ መብላት አይመከርም" ሲሉ ያስረዳሉ። ያለማቋረጥ ቶሎ ቶሎ መመገብ [binge eating] ለሆድ መነፋት ከማጋለጥ ጀመሮ በአጠቃላይ የአመጋገብ ሥርዓት ላይ ጫና እስከማድረስ የዘለቀ ጉዳት አለው። በቀን ስንት ጊዜ እንመገብ? ነገሩ አከራካሪ ነው። ቢቢሲ እንዳነጋገራቸው ባለሙያዎች ገለጻ ግን በቀን ስንት ጊዜ እንመገብ የሚለው ጥያቄ እምብዛም አያሳስብም። ዋናው ጉዳይ በቀን ውስጥ ሰውነት የሚፈልገውን ንጥረ ነገሮችን የያዙ ምግቦችን አሰባጥሮ መመገብ ላይ ነው። ይህ ሲሆን በተለያየ መጠንና በተለያየ ሰዓት ሊሆን ይችላል። ይህ ሃሳብ የሚመለከተው ግን በጥቅሉ የጎላ የጤና ችግር የሌለባቸውን ወይም በሌላ የተለየ ሁኔታ ውስጥ የሌሉ አዋቂ ሰዎችን ነው። ህጻናት በተለየ ሁኔታ በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ መመገብ ሊኖርባቸው ይችላል። ስለዚህ ለአዋቂ ሰዎች ቁርስ፣ ምሳና እራት አስፈላጊና መዘለል የማይገባው ነው፤ የሚለው ጉዳይ ወደ ልማድና ባህል ያዘነበለ ነው። ሳይንሱ እንደ መመሪያ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ማግኘት ያለበትን የንጥረ ነገር፣ የኃይል መጠን ይገልጻል። ስለዚህ ከሳይንስ አንጻር ከታየ የምናወዳድረው በቀን ውስጥ የተመገበው የቀን ፍላጎቱን አሟልቷል ወይስ አላሟላም የሚለውን እንደሆነ ዶ/ር ቃለአብ ያብራራሉ። ጨምረውም "ስለዚህ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ሁለቴ በልቶ ሊሆን ይችላል፤ ሦስት ጊዜ በልቶ ሊሆን ይችላል፤ ከሳይንስ አንጻር የሚገመገመው ግን ሰውነቱ በቀን ከሚያስፈልገው የኃይል እና የንጥረ ነገር ፍላጎቱ አንጻር ነው" በማለት የረሃብ ስሜትን ግን ቸል ማለት እንደማይገባና ተገቢውን ምላሽ መሰጠት ይገባል ብለዋል። ሆኖም በቀን ውስጥ ሦስት ጊዜ መመገብ ለተመጋቢውና ለሥርዓተ ምግብ የተመቸ ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የሥነ ምግብ ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማስረሻ ወሳኙ ነገር በቀን የምናገኘው የንጥረ ነገር መጠን መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀን ከሦስት ጊዜ በላይ መመገብ የሰውነት ክብደትን እንዲጨምር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። በእድሜና በጤና ሁኔታ የተለያየ ቢሆንም ምግብ በጨጓራ ውስጥ በአማካይ እስከ አራት ስዓት እንደሚቆይ የሚያስረዱት ዶ/ር ይሁኔ ደግሞ "ጨጓራ መጨናነቅ ስለሌለበት የበላነው ምግብ በአራት ሰዓት ውስጥ ተፈጭቶ ወደ ሰውነት ከተሰራጨ በኋላ" ቀጣዩን ምግብ መመገብ እንደሚመከርና "ሆድ እስኪሞላና ጨጓራ እስኪጨናነቅ" መመገብ እንደማይገባ ይመክራሉ። ታዲያ በዚህ ስሌት መሰረት ከ24 ሰዓቱ 8ቱ ለእንቅልፍ ቢተውና የቀረው ቢከፋፈል ወደ ተለመደው የምግብ ሰዓት እንደሚያደላ አስረድተዋል። ባለሙያዎቹ ያተኮሩበት ሌላኛው ነጥብ በቀን ስንት ጊዜ እንመገብ የሚለው ጥያቄ ሰዎች ያላቸው የሥራና አካላዊ እንቅስቃሴ ሁኔታ ላይ የተመረኮዘ ነው። ብዙ የሚንቀሳቀስ፣ ጉልበት የሚያወጣና ቢሮ ውስጥ የሚሰራ ሰው ተመሳሳይ የምግብ ጊዜና መጠን ሊኖራቸው አይችልም። 'ላቡ ጠብ' እስኪል የሚደክም ሰው ያን የሚተካ ምግብ ማግኝት ይኖርበታል። ምግቡ ስንት ቀለማት አሉት የሚለው ጉዳይ ሳይዘነጋ። | በቀን ሦስት ጊዜ ባንመገብስ? ቁርስ፣ ምሳና እራት ልማድ ወይስ አስፈላጊ የምግብ ጊዜ? ምግብ ከእጅ ወደ አፍ፣ ከአፍ ደግሞ ወደ ሆድ የሚላክ ነገር ብቻ አይደለም። ምግብ የባህል አካል ነው። ያለ ምግብ ውሎን፣ አዳርን፣ በዓልን ማሰብ ከባድ ነው። በየዓይነቱ አዘጋጅቶ ገበታውን ሙሉ አድርጎ ወዳጅ ዘመድን መጋበዝ የፍቅርና የወዳጅነት መግለጫ ነው። እዚህ ላይ ትንሽ ኢትዮጵያዊነት እንጨምርበት ካልን 'በሞቴ' እያሉ መጎራረስ ይቻላል። ይህም ምግብ በሰው ልጆች አካላዊ እና አዕምሮአዊ ዕድገት ውስጥ ካለው ቁልፍ ተግባር አልፎ ማኅበራዊ ትስስርን የሚገነባ ተጨማሪ መንገድ መሆኑን ያመላክት ይሆናል። የሆነው ሆኖ የምግብ ዋነኛ ዓላማዎች ሁለት ናቸው - ለሰውነት ጉልበት እና ኃይልን መስጠት እንዲሁም በሽታ የመከላከልን ሥርዓትን ማዳበር። የምግብ ተግባር ይህ ከሆነ በቀን ስንት ጊዜ፣ ምን እና እንዴት እንመገብ? ስንት ጊዜ የሚለውን እናቆየው! 'ሰው የሚመገበውን ይመስላል' የዕለት ተግባራችንን በበቂ ጉልበት ለመከወን፤ የበሽታ መከላከል አቅማችንንም ለማደርጀት ምን እንመገብ የሚል ጥያቄ ሲነሳ የምግብ ስብጥር [food diversity] የሚል ሃሳብ ይነሳል። ምን ማለት ነው? ለምሳሌ አቮካዶ እና እንቁላል [በተለይ አስኳሉ] በበርካታ ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ምን አልባትም አቻ የሌላቸው ምግቦች ናቸው። ነገር ግን እነርሱን ብቻ መመገብ ይጎዳል ባይባል እንኳን ለሰውነት ከሚያስፈልጉ እና ጠቃሚ ከሆኑ ሌሎች ንጥረ ነገሮች ውጪ ያደርጋል። እናም በቀን ውስጥ የተለያዩ የምግብ አይነቶችን መመገብ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን በአንድ ጊዜ ለመግኘት ያግዛል። ይህ የምግብ ስብጥር ይባላል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሳይንስ እና ሥነ ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ቃለአብ ባዬ በሥነ ምግብ ጉዳይ ላይ በዓለም ዙሪያ የሚሰሩ ተመራማሪዎች ያዘጋጇቸው የአመጋገብ መመሪያዎች በሌሎች ጉዳዮች የተለያዩ ሃሳቦችን ሊያንጸባርቁ ቢችሉም ምግብን ማሰባጠር በተመለከተ "ሁሉም ማለት ይቻላል" ተመሳሳይ አቋም አላቸው ይላሉ። እንደ እርሳቸው ገለጻ የምንመገባቸው ምግቦች አይነት "በተቻለ መጠን" በበዛ ቁጥር "የሚያስፈልገንን ኃይል እና ንጥረ ነገር የሟሟላት ዕድላችን ከፍ ይላል።" "እኛ ሰዎች ማለት የበላነው ምግብ ነን" የሚሉት በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሳይንስ እና የሥነ ምግብ መምህሩ ዶ/ር ይኹኔ አየለ ደግሞ "ሰውነታችን በአጠቃላይ በትክክለኛ የተፈጥሮ ሂደቱ ሥራውን ይከውን ዘንድ ቢያንስ 53 ዓይነት ሚኒራሎች/ማዕድናት እና ቫይታሚኖች ያስፈልጉታል" ሲሉ ያብራራሉ። "በምድር ላይ እነዚህን ሁሉ ሚኒራሎችና አስፈላጊ ነገሮችን አሟልቶ የያዘ አንድ ምግብ ልናገኝ አንችልም" ስለዚህ "በተቻለ መጠን ባለን አቅም" ምግቦችን የማሰባጠርን አስፈላጊነት ይመክራሉ። ጎመን በሥጋ ዶ/ር ይኹኔ ለምግብ ስብጥር ከሚሰጧቸው ምሳሌዎች አንዱ አትክልት እና የእንስሳት ተዋፅኦን በጋራ መመገብን ነው። በኢትዮጵያ የተለመደውን ጎመን በሥጋ ስብጥርን በተመለከተ ለዓለም ትምህርት የሚሆን ሲሉ ይገልጹታል። እንደ እርሳቸው ገለጻ አይረን/የብረት ማዕድንን ከሥጋ 70 በመቶ፣ ከአትክልቶች ደግሞ እስከ 17 በመቶ ይገኛል። ይህ ሁኔታ ሥጋን 'ቸር' አትክልትን ደግሞ 'ንፉግ' ያሰኘዋል ይላሉ። ታዲያ ጎመን በሥጋ ጋር ይህ አይሰራም፤ ሁለቱ በጋራ ሲዘጋጁ ጎመን አትክልታዊ ባህሪው ተቀይሮ 'ቸር' ይሆናል። ለየብቻ ሲዘጋጁ ከሚገኘው ንጥረ ነገር የላቀ ጠቀሜታን ያቀርባል። አትክልት፣ የእንስሳት ተዋፅኦ፣ የእህል ዘር፣ ፍራፍሬና የቅባት እህል በሰፊው የምግብ አይነቶች/ዘርፎች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የምግብ አይነቶች በዓለም ጤና ድርጅት እና የምግብ እና እርሻ ድርጅት በተዘጋጁ የሥነ ምግብ መመሪያዎች ውስጥ ከተካተቱ 10 የምግብ አይነቶች/ዘርፍ ውስጥ የተጠቀሱ ናቸው። ታዲያ በቀን ውስጥ እነዚህ የምግብ አይነቶችን አሰባጥሮ መመገብ ነው ባለሙያዎቹ የሚመክሩት ነው። ነገሩ እነዚህን ሁሉ ለሟሟላት ያውም በየቀኑ አቅም ከየት ይመጣል? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም። ዶ/ር ይኹኔ ግን መልስ አላቸው - መቼም ውድ የሚሆነው የእንስሳት ተዋፅኦ ነው። ስለዚህ የእንስሳቱን ተዋፅኦ ዝቅ አድርጎ ከሌሎች ምግቦች ጋር መጠቀም። "ሽሮ ላይ እንቁላል ወይም ቋንጣ ጣል ማድረግ" ሲሉ ያስቀምጣሉ። ይህስ ባይቻል? ንፍሮ እና ቆሎ ከእጽዋት የሚገኙትን ምግቦች ማሰባጠር። ዶ/ር ይኹኔ እዚህ ጋርም በኢትዮጵያ የሚዘወተር እና ሊበረታታ የሚገባው የሚሉት ምሳሌ አላቸው - ከተለያዩ ጥራጥሬዎች የሚዘጋጅ ንፍሮ። እያንዳንዱ ጥራጥሬ የራሱ ጥቅም ያለው እና አንዱ የሌለው በሌላኛው ስለሚተካ የሥነ ምግብ ጠቀሜታውን ከፍ ያደርገዋል። ከዚህም ባሻገር የገብስ ቆሎ ሲዘጋጅ ለውዝ፣ ኑግ እና መሰል ጥራጥሬዎችን ያካትታል። ይህ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሊበለጽግ የሚገባው እና በሳይንስ እጅግ የሚደገፈው ምግብን የማሰባጠር ልማድ እንዳለ የሚያረጋግጥ ነው ይላሉ። ስለዚህ ሥጋው ጋር ማን አድርሶን ቢባል እንኳን ተፈጥሮ በአይነት በአይነት ያቀረበቻችውን አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎችና ጥራጥሬዎች ማሰባጠር የተለያዩ ጠቀሜታዎችን ያስገኛል። ዶ/ር ቃለአብ የምግብ አይነቶች/ዘርፎች በውስጣቸው በተለያዩ ቀለማት የሚቀመጡ ምግብን ስለያዙ "ምግባችን ምን ያህል ቀለም አለው?" ብሎ መጠየቅ የምግቡን ስብጥር ሊያመላክት ይችላል። በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የምግብ ሥርዓት እና ሥነ ምግብ ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ "ጥግብ!" ብዬ በላሁ ማለት በቀን ውስጥ ለሰውነት የሚያስፈልገንን ንጥረ ነገር ስለማግኘታችን ያረጋግጣል ማለት አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ። ስለዚህም በ24 ሰዓት ውስጥ በዓለም ጤና ድርጅት እና የምግብ እና እርሻ ድርጅት በተዘጋጁ የሥነ ምግብ መመሪያዎች ውስጥ ከተካተቱ 10 የምግብ አይነቶች/ዘርፍ ውስጥ ቢያንስ አምስቱን ለማካተት መሞከር ተገቢ ነው ይላሉ። ኃላፊው ይህንን መመሪያ ኢትዮጵያ እንደምትቀበለው እና በጤና ሚኒስቴርም የሚመከር መሆኑን ይጠቅሳሉ። የምግብ ሰሃናችን ምን ምን ይዟል? በአሜሪካ በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ላስቬጋስ በምግብ ዝግጅት እና ሥነ ምግብ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ሼፍ አዲስዓለም ብዙአየሁ "በቀን ውስጥ ሰውነት የሚያስፈልገውን ምግብ ተመግቤያለሁ ወይ?" ብሎ መጠየቅ ይገባል ሲሉ ይገልጻሉ። ይህንን ጥያቄ በቀላሉ የምግብ ሰሃኑ ሊመልሰው እንደሚችል ጠቅሰዋል። "የምግብ ሰሃናችን ግማሹ አትክልት መሆን ነው ያለበት። ጥቅል ጎመን ሊሆን ይችላል፤ ካሮት፣ ቀይስር፣ የሀበሻ ጎመን፣ ቲማቲም፣ ዝኩኒ አይነት ነገር" ሊሸፈን ይችላል። የሰሃኑ አንድ አራተኛ ወይም ሩብ ደግሞ ፕሮቲን አዘል በሆነ ምግብ መሸፈን ይገባል። "ለምሳሌ ቦሎቄ፣ እንቁላል፣ ዓሳ፣ የዶሮ ሥጋ ወይም የከብት ሥጋን የመሰሉ ምግቦች መያዝ ይኖርበታል" የተቀረው ደግሞ ካርቦ ሃይድሬትን እንደ ሩዝ፣ ፓስታ ወይም ዳቦ አይነት ምግቦችን ቢያካትት ይመከራል ሲሉ ገልጸዋል። ሰሃኑ ላይ እንደ እንጀራ ያለ ማባያ ሲከተት ደግሞ በርከት ያለ ንጥረ ነገር የመገኘት እድሉን ከፍ ያደርገዋል። የሰሃኑ ግማሹ ክፍል አቮካዶን በመሰሉ ፍራፍሬዎች ሊተካ እንደሚችልም ጠቁመዋል። ከዚህ ባሻገር ደግሞ ከመደበኛ የምግብ ሰዓት ባሻገር የተለያዩ አይነት ፍራፍሬዎችን መመገብ እጅግ የሚያበረታታ ነው። እንደ ሼፍ አዲስዓለም ገለጻ ምግቦችን ማሰባጠር የተለያዩ የሰውነት ክሎች የሚፈልጓቸውን ንጥረ ነገሮች በተመጣጠነ ሁኔታ እንዲያገኝ ያስችላል። በዚህ ምክረ ሃሳብ መሰረት ምሳ ፓስታ በዳቦ የበላን ሰው አስቡት! እንዴት እንመገብ? ከምግቦች ስብጥር ባሻገር የአመጋገብ ሁኔታ በጤና ሥርዓተ ምግብ ውስጥ ወሳኝ ቦታ አለው። በኢትዮጵያ ያለው ለምግብ የተለየ ሰዓት የመስጠት ልማድ ሊበረታታ ይገባል ይላሉ የሥነ ምግብ ባለሙያዎቹ። ከዚህ ልማድ በተቃራኒ እየመጡ ያሉ ልማዶች ከጅምሩ መቅረፍ ቢቻል ተገቢ ነው የሚሉት ዶ/ር ቃለአብ ናቸው። ዶ/ር ቃለአብ መኪና እያሽከረከሩ፣ ሥራ እየሰሩ፣ ስልክ እየተጠቀሙ ወይም ሌላ ትኩረትን ሊስብ የሚችል ነገር ላይ ተጠምዶ ምግብ መመገብ ከሚያስፈልገው መጠን በላይ ምግብ ለመውሰድ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። "ተጽዕኖ ከሚፈጥሩ ነገሮች በጸዳ መልኩ ቁጭ ብሎ ጊዜ ወስዶ ረጋ ብሎ መመገብ ያለውን ጥቅም በሳይንሱ በሂደት እየተረዳነው ነው" የሚሉት ዶ/ር ቃለአብ "በጋራ ምግብን የፍቅር እና የጥሩ ጊዜ ማሳለፊያ አድርጎ ቁጭ ብሎ መመገብ ከንጥረ ነገር ባለፈ አመጋገባችን ላይ ወሳኝነት ስላለው እና የምግብ መጠን ቁጥጥርን" ስለሚያግዝ እጅግ የሚበረታታ ነው ይላሉ። የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምግብ መምህሩ ዶ/ር ይኹኔ በበኩላቸው የቅርብ ጊዜ ጥናቶች የጋራ ገበታ ያላቸውን ፋይዳ እያረጋገጡ እንደሆነ ይገልጻሉ። በጋራ እየተጨዋወቱ መመገብ የተመጠነ ምግብ በተሻለ ሁኔታ ለማግኘት እና በተረጋጋ ሁኔታ ሥርዓተ ምግብን ለመከወን ይረዳል። በሌላ በኩል ዶ/ር ቃለአብ "ያለማቋረጥ ቶሎ ቶሎ መብላት አይመከርም" ሲሉ ያስረዳሉ። ያለማቋረጥ ቶሎ ቶሎ መመገብ [binge eating] ለሆድ መነፋት ከማጋለጥ ጀመሮ በአጠቃላይ የአመጋገብ ሥርዓት ላይ ጫና እስከማድረስ የዘለቀ ጉዳት አለው። በቀን ስንት ጊዜ እንመገብ? ነገሩ አከራካሪ ነው። ቢቢሲ እንዳነጋገራቸው ባለሙያዎች ገለጻ ግን በቀን ስንት ጊዜ እንመገብ የሚለው ጥያቄ እምብዛም አያሳስብም። ዋናው ጉዳይ በቀን ውስጥ ሰውነት የሚፈልገውን ንጥረ ነገሮችን የያዙ ምግቦችን አሰባጥሮ መመገብ ላይ ነው። ይህ ሲሆን በተለያየ መጠንና በተለያየ ሰዓት ሊሆን ይችላል። ይህ ሃሳብ የሚመለከተው ግን በጥቅሉ የጎላ የጤና ችግር የሌለባቸውን ወይም በሌላ የተለየ ሁኔታ ውስጥ የሌሉ አዋቂ ሰዎችን ነው። ህጻናት በተለየ ሁኔታ በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ መመገብ ሊኖርባቸው ይችላል። ስለዚህ ለአዋቂ ሰዎች ቁርስ፣ ምሳና እራት አስፈላጊና መዘለል የማይገባው ነው፤ የሚለው ጉዳይ ወደ ልማድና ባህል ያዘነበለ ነው። ሳይንሱ እንደ መመሪያ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ማግኘት ያለበትን የንጥረ ነገር፣ የኃይል መጠን ይገልጻል። ስለዚህ ከሳይንስ አንጻር ከታየ የምናወዳድረው በቀን ውስጥ የተመገበው የቀን ፍላጎቱን አሟልቷል ወይስ አላሟላም የሚለውን እንደሆነ ዶ/ር ቃለአብ ያብራራሉ። ጨምረውም "ስለዚህ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ሁለቴ በልቶ ሊሆን ይችላል፤ ሦስት ጊዜ በልቶ ሊሆን ይችላል፤ ከሳይንስ አንጻር የሚገመገመው ግን ሰውነቱ በቀን ከሚያስፈልገው የኃይል እና የንጥረ ነገር ፍላጎቱ አንጻር ነው" በማለት የረሃብ ስሜትን ግን ቸል ማለት እንደማይገባና ተገቢውን ምላሽ መሰጠት ይገባል ብለዋል። ሆኖም በቀን ውስጥ ሦስት ጊዜ መመገብ ለተመጋቢውና ለሥርዓተ ምግብ የተመቸ ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የሥነ ምግብ ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማስረሻ ወሳኙ ነገር በቀን የምናገኘው የንጥረ ነገር መጠን መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀን ከሦስት ጊዜ በላይ መመገብ የሰውነት ክብደትን እንዲጨምር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። በእድሜና በጤና ሁኔታ የተለያየ ቢሆንም ምግብ በጨጓራ ውስጥ በአማካይ እስከ አራት ስዓት እንደሚቆይ የሚያስረዱት ዶ/ር ይሁኔ ደግሞ "ጨጓራ መጨናነቅ ስለሌለበት የበላነው ምግብ በአራት ሰዓት ውስጥ ተፈጭቶ ወደ ሰውነት ከተሰራጨ በኋላ" ቀጣዩን ምግብ መመገብ እንደሚመከርና "ሆድ እስኪሞላና ጨጓራ እስኪጨናነቅ" መመገብ እንደማይገባ ይመክራሉ። ታዲያ በዚህ ስሌት መሰረት ከ24 ሰዓቱ 8ቱ ለእንቅልፍ ቢተውና የቀረው ቢከፋፈል ወደ ተለመደው የምግብ ሰዓት እንደሚያደላ አስረድተዋል። ባለሙያዎቹ ያተኮሩበት ሌላኛው ነጥብ በቀን ስንት ጊዜ እንመገብ የሚለው ጥያቄ ሰዎች ያላቸው የሥራና አካላዊ እንቅስቃሴ ሁኔታ ላይ የተመረኮዘ ነው። ብዙ የሚንቀሳቀስ፣ ጉልበት የሚያወጣና ቢሮ ውስጥ የሚሰራ ሰው ተመሳሳይ የምግብ ጊዜና መጠን ሊኖራቸው አይችልም። 'ላቡ ጠብ' እስኪል የሚደክም ሰው ያን የሚተካ ምግብ ማግኝት ይኖርበታል። ምግቡ ስንት ቀለማት አሉት የሚለው ጉዳይ ሳይዘነጋ። | https://www.bbc.com/amharic/news-60150890 |
0business
| በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ቻይና አሜሪካንን በልጣ ከዓለም 1ኛ ሆነች | ቻይና በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት (FDI) ለመጀመርያ ጊዜ አሜሪካንን በመብለጥ የምድራችን ቁጥር አንድ አገር ለመሆን በቃች። ትናንት እሑድ ይፋ በተደረገ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት መሠረት ቻይና አዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተው በአጭር የጊዜ ሂደት አሜሪካንን ለመብለጥ ችላለች። ይህ የተባበሩት መንግሥታት ያወጣው መረጃ እንደሚያትተው ወደ ቻይና ድርጅቶች አዳዲስ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ4 ከመቶ ተመንድጓል። በሌላ አነጋገር በፈረንጆቹ 2020 ወደ ቻይና የተመሙ አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ወደ አሜሪካ ከተመሙት አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች በእጅጉ ያላቁ ናቸው። ይህ የሚያሳየው ቻይና በዓለም ዙርያ ያላት ተጽእኖ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ነው ብሏል ሪፖርቱ። ከውጭ አገራት ወደ አሜሪካ የሚገቡ አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ባለፈው ዓመት (2020) በግማሽ መቀነሳቸውን ዘገባው አትቷል። ሆኖም ወደ ቻይና የሚተሙ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንቶች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው የመጡት። በዚህም ምክንያት ነው ቻይና ከአሜሪካ ልቃ እንድትገኝ ያስቻላት። ቻይና ባለፈው ዓመት ብቻ 163 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገሯ አዲስ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፈሶላታል። አሜሪካ ግን 134 ቢሊዮን ብቻ ነው ወደ አገሯ የቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ የቻለችው። ይህን አሐዛዊ ዘገባ ያወጣው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በንግድና በልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) ላይ ነው። በ እአአ 2019 አሜሪካ የ251 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ ችላ ነበር። በዚህ ጊዜ ቻይና የ140 ቢሊዮን የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ነበር ማግኘት የቻለችው። ምንም እንኳ ቻይና በተገባደደው የፈረንጆች ዓመት አዲስ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ አሜሪካንን ቀድማ አንደኛ ብትሆንም በጠቅላላ የውጭ ኢንቨስትመንት ክምችት ግን አሁንም ዓለምን የምትመራው አሜሪካ ናት። ይህም የሚያሳየው ለዓመታት አሜሪካ የአዳዲስ የውጭ ኢንቨስትመንቶች መዳረሻ ተመራጭ አገር እንደነበረችና የውጭ ኢንቨስትምነት ምን ያህል የተከማቸባት አገር መሆኗን ነው ይላል ሪፖርቱ። የምጣኔ ሀብት አዋቂዎች ግን በአዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የታየው የአሰላለፍ ልዩነት አሁን ቻይና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ወሳኝ የሆነ ተጽእኖ ማሳረፍ መጀመሯን አመላካች ነው ይላሉ። በአሜሪካ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ2016 የትራምፕን መምጣት ተከትሎ ነበር ወደ 472 ቢሊዮን ዶላር የተመነደገው። ያን ጊዜ ቻይና 134 ቢሊዮን ዶላር ላይ ነበረች። ያን ጊዜ የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ ኩባንያዎች ቶሎ ቻይናን እየለቀቁ ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ከፍተኛ ማበረታቻ እየሰጠ ነበር። በተመሳሳይ የትራምፕ አስተዳደር የቻይና ኩባንያዎች ለደኅንነት ስጋት ስለሚሆኑ በየጊዜው ይመረመራሉ በሚል በአሜሪካ የነበራቸው ሚና ለማንኳሰስ ሞክሯል። ይህ የትራምፕ አስተዳደር በዚህ መንገድ ተጽእኖ ለመፍጠር በመቻሉ ሊሆን ይችላል ባለፉት ዓመታት የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የበላይነት በአሜሪካ ተይዞ የቆየው። ሆኖም ባለፈው ዓመት (2020) የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮቪድ ወረርሸኝ የተነሳ ሲቀዛቀዝ የቻይና ኢኮኖሚ ግን ቶሎ ማንሰራራት ችሏል። በ2020 የቻይና የአገር ውስጥ ጥቅል ምርት መጠን (GDP) በ2.3% ማደጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ።. ይህም ቻይናን በኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የኢኮኖሚ ድቀት ብዙም ያልተሰማት ብቸኛዋ የዓለም አገር አድርጓታል። ብዙ ኢኮኖሚስቶች በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የቻይና ኢኮኖሚ በፍጥነት ማንሰራራቱ አስገርሟቸዋል። በ2020 በዓለም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በጠቅላላው በ42% ወድቋል። ብዙውን ጊዜ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የሚባለው አንድ የውጭ ኩባንያ በሌላ አገር ውስጥ ያሉ ኩባንያዎችን በመግዛት ወይም ከራሱ ኩባንያ ጋር እንዲጣመሩ በማድረግ ወይም በአዲስ ኩባንያ አዲስ ሥራ ለመጀመር መዋእለ ነዋዩን ማፍሰስ ሲጀምር ነው። | በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ቻይና አሜሪካንን በልጣ ከዓለም 1ኛ ሆነች ቻይና በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት (FDI) ለመጀመርያ ጊዜ አሜሪካንን በመብለጥ የምድራችን ቁጥር አንድ አገር ለመሆን በቃች። ትናንት እሑድ ይፋ በተደረገ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት መሠረት ቻይና አዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተው በአጭር የጊዜ ሂደት አሜሪካንን ለመብለጥ ችላለች። ይህ የተባበሩት መንግሥታት ያወጣው መረጃ እንደሚያትተው ወደ ቻይና ድርጅቶች አዳዲስ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ4 ከመቶ ተመንድጓል። በሌላ አነጋገር በፈረንጆቹ 2020 ወደ ቻይና የተመሙ አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ወደ አሜሪካ ከተመሙት አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች በእጅጉ ያላቁ ናቸው። ይህ የሚያሳየው ቻይና በዓለም ዙርያ ያላት ተጽእኖ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ነው ብሏል ሪፖርቱ። ከውጭ አገራት ወደ አሜሪካ የሚገቡ አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ባለፈው ዓመት (2020) በግማሽ መቀነሳቸውን ዘገባው አትቷል። ሆኖም ወደ ቻይና የሚተሙ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንቶች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው የመጡት። በዚህም ምክንያት ነው ቻይና ከአሜሪካ ልቃ እንድትገኝ ያስቻላት። ቻይና ባለፈው ዓመት ብቻ 163 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገሯ አዲስ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፈሶላታል። አሜሪካ ግን 134 ቢሊዮን ብቻ ነው ወደ አገሯ የቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ የቻለችው። ይህን አሐዛዊ ዘገባ ያወጣው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በንግድና በልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) ላይ ነው። በ እአአ 2019 አሜሪካ የ251 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ ችላ ነበር። በዚህ ጊዜ ቻይና የ140 ቢሊዮን የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ነበር ማግኘት የቻለችው። ምንም እንኳ ቻይና በተገባደደው የፈረንጆች ዓመት አዲስ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ አሜሪካንን ቀድማ አንደኛ ብትሆንም በጠቅላላ የውጭ ኢንቨስትመንት ክምችት ግን አሁንም ዓለምን የምትመራው አሜሪካ ናት። ይህም የሚያሳየው ለዓመታት አሜሪካ የአዳዲስ የውጭ ኢንቨስትመንቶች መዳረሻ ተመራጭ አገር እንደነበረችና የውጭ ኢንቨስትምነት ምን ያህል የተከማቸባት አገር መሆኗን ነው ይላል ሪፖርቱ። የምጣኔ ሀብት አዋቂዎች ግን በአዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የታየው የአሰላለፍ ልዩነት አሁን ቻይና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ወሳኝ የሆነ ተጽእኖ ማሳረፍ መጀመሯን አመላካች ነው ይላሉ። በአሜሪካ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ2016 የትራምፕን መምጣት ተከትሎ ነበር ወደ 472 ቢሊዮን ዶላር የተመነደገው። ያን ጊዜ ቻይና 134 ቢሊዮን ዶላር ላይ ነበረች። ያን ጊዜ የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ ኩባንያዎች ቶሎ ቻይናን እየለቀቁ ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ከፍተኛ ማበረታቻ እየሰጠ ነበር። በተመሳሳይ የትራምፕ አስተዳደር የቻይና ኩባንያዎች ለደኅንነት ስጋት ስለሚሆኑ በየጊዜው ይመረመራሉ በሚል በአሜሪካ የነበራቸው ሚና ለማንኳሰስ ሞክሯል። ይህ የትራምፕ አስተዳደር በዚህ መንገድ ተጽእኖ ለመፍጠር በመቻሉ ሊሆን ይችላል ባለፉት ዓመታት የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የበላይነት በአሜሪካ ተይዞ የቆየው። ሆኖም ባለፈው ዓመት (2020) የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮቪድ ወረርሸኝ የተነሳ ሲቀዛቀዝ የቻይና ኢኮኖሚ ግን ቶሎ ማንሰራራት ችሏል። በ2020 የቻይና የአገር ውስጥ ጥቅል ምርት መጠን (GDP) በ2.3% ማደጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ።. ይህም ቻይናን በኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የኢኮኖሚ ድቀት ብዙም ያልተሰማት ብቸኛዋ የዓለም አገር አድርጓታል። ብዙ ኢኮኖሚስቶች በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የቻይና ኢኮኖሚ በፍጥነት ማንሰራራቱ አስገርሟቸዋል። በ2020 በዓለም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በጠቅላላው በ42% ወድቋል። ብዙውን ጊዜ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የሚባለው አንድ የውጭ ኩባንያ በሌላ አገር ውስጥ ያሉ ኩባንያዎችን በመግዛት ወይም ከራሱ ኩባንያ ጋር እንዲጣመሩ በማድረግ ወይም በአዲስ ኩባንያ አዲስ ሥራ ለመጀመር መዋእለ ነዋዩን ማፍሰስ ሲጀምር ነው። | https://www.bbc.com/amharic/55792460 |
0business
| ናይጄሪያ ምግብ ከውጪ ለማስገባት ገንዘብ የለኝም አለች | የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሐሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፈጠረው ችግር የተነሳ አገራቸው ምግብ ከውጪ ለማስገባት "ገንዘብ የላትም" አሉ። በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ከኢትዮጵያ ቀድማ የመጀመሪያውን የሆነችው ናይጄሪያ የውጪ ምንዛሪ ችግር ስላጋጠማት የአገሪቱ አርሶ አደሮች ሕዝቡን መቀልብ የሚችል መጠን ያለው ምግብ እንዲያመርቱ ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል። ቡሐሪ ይህንን የተናገሩት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሚከሰትን የምግብ ዋስትና ችግር በተመለከተ ስጋቶች በመፈጠራቸውና በአገሪቱም በምግብ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ተከትሎ ነው። እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት የአገሪቱ አርሶ አደሮች እንኳን በዚህ በወረርሽኙ ወቅት ይቅርና ከዚያ በፊትም 200 ሚሊዮን የሚደርሰውን ሕዝብ የምግብ ፍላጎት ማሟላት አይችሉም ነበር። ምንም እንኳን የናይጄሪያ የግብርና ዘርፍ በርካታ ሰዎች የተሰማሩበት ዋነኛ መስክ ቢሆንም፤ ከነዳጅ ዘይት በሚገኝ ገቢ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ጥገኛ በሆነው የአገሪቱ መዕተዓኘየ ሐዓዕጠዕ ተነሳ ትኩረት ተነፍጎት ቆይቷል። ናይጄሪያ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በድንበሮቿ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ከታይላንድ በሕገ ወጥ መንገድ የሚገባውን የሩዝ ምርት በመግታት በአገር ውስጥ ለሚመረተውን ሩዝ ገበያ ለማመቻቸት ጥረት ስታደርግ ነበር። ናይጄሪያ ከውጪ የሚመጣ የሩዝ ምርት ላይ ክልከላ ከመጣሏ ቀደም ብሎ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊየን ቶን በላይ ሩዝ ከታይላንድ ታስገባ ነበር። አገሪቱን በሚያዋስኗት አገራት ድንበር በኩል የሚገባው ሩዝ የተከለከለ በመሆኑ በወደብ በኩል ብቻ ነው ሩዝ ወደ ናይጄሪያ እየገባ ያለው። በዚህም ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣሉ ዋጋውን አስወድዶታል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ በኋላ ናይጄሪያ ውስጥ የምግብ ዋጋ ላይ ጭማሪ የተከሰተ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዘይት ዋዳ በመውደቁ ምክንያት ደግሞ መንግሥት ያገኘው የነበረው በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እንደተነበየው በአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት ናይጄሪያ በዚህ ዓመት ኢኮኖሚዋ በ1.5 በመቶ ያሽቆለቁላል። | ናይጄሪያ ምግብ ከውጪ ለማስገባት ገንዘብ የለኝም አለች የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሐሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፈጠረው ችግር የተነሳ አገራቸው ምግብ ከውጪ ለማስገባት "ገንዘብ የላትም" አሉ። በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ከኢትዮጵያ ቀድማ የመጀመሪያውን የሆነችው ናይጄሪያ የውጪ ምንዛሪ ችግር ስላጋጠማት የአገሪቱ አርሶ አደሮች ሕዝቡን መቀልብ የሚችል መጠን ያለው ምግብ እንዲያመርቱ ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል። ቡሐሪ ይህንን የተናገሩት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሚከሰትን የምግብ ዋስትና ችግር በተመለከተ ስጋቶች በመፈጠራቸውና በአገሪቱም በምግብ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ተከትሎ ነው። እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት የአገሪቱ አርሶ አደሮች እንኳን በዚህ በወረርሽኙ ወቅት ይቅርና ከዚያ በፊትም 200 ሚሊዮን የሚደርሰውን ሕዝብ የምግብ ፍላጎት ማሟላት አይችሉም ነበር። ምንም እንኳን የናይጄሪያ የግብርና ዘርፍ በርካታ ሰዎች የተሰማሩበት ዋነኛ መስክ ቢሆንም፤ ከነዳጅ ዘይት በሚገኝ ገቢ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ጥገኛ በሆነው የአገሪቱ መዕተዓኘየ ሐዓዕጠዕ ተነሳ ትኩረት ተነፍጎት ቆይቷል። ናይጄሪያ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በድንበሮቿ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ከታይላንድ በሕገ ወጥ መንገድ የሚገባውን የሩዝ ምርት በመግታት በአገር ውስጥ ለሚመረተውን ሩዝ ገበያ ለማመቻቸት ጥረት ስታደርግ ነበር። ናይጄሪያ ከውጪ የሚመጣ የሩዝ ምርት ላይ ክልከላ ከመጣሏ ቀደም ብሎ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊየን ቶን በላይ ሩዝ ከታይላንድ ታስገባ ነበር። አገሪቱን በሚያዋስኗት አገራት ድንበር በኩል የሚገባው ሩዝ የተከለከለ በመሆኑ በወደብ በኩል ብቻ ነው ሩዝ ወደ ናይጄሪያ እየገባ ያለው። በዚህም ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣሉ ዋጋውን አስወድዶታል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ በኋላ ናይጄሪያ ውስጥ የምግብ ዋጋ ላይ ጭማሪ የተከሰተ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዘይት ዋዳ በመውደቁ ምክንያት ደግሞ መንግሥት ያገኘው የነበረው በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እንደተነበየው በአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት ናይጄሪያ በዚህ ዓመት ኢኮኖሚዋ በ1.5 በመቶ ያሽቆለቁላል። | https://www.bbc.com/amharic/news-52796481 |
2health
| ንግሥት ኤልዛቤት ሆስፒታል ገብተው እንደነበር ተገለጸ | የዩናይትድ ኪንግደሟ ንግሥት ኤልዛቤት ቀዳሚ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ረቡዕ ምሽት ሆስፒታል ገብተው እንደነበር የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አስታወቀ። የ95 ዓመቷ ንግሥት ኤልዛቤት ማእከላዊ ለንደን በሚገኝ አንድ የግል ሆስፒታል ውስጥ ህክምናቸውን ተከታትለው ዊንድሰር ወደ ሚገኘው መኖሪያቸው መመለሳቸውን ተገልጿል። አሁን በመልካም ሁኔታ ላይ ናቸው የተባሉት ንግሥቲቱ ወደ ሰሜን አየርላንድ ለመጓዝ የነበራቸውን እቅድ ሰርዘዋል። የህክምና ባለሙያዎች ንግሥቲቷ ወደተለመደው ሥራቸው ከመመለሳቸው በፊት ለጥቂት ቀናት እረፍት ማድረግ እንደሚገባቸው መክረዋል ተብሏል። ሐሙስ ምሽት ስለንግሥቲቱ መግለጫ የሰጠው የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት እንዳለው "ንግሥቲቱ ረቡዕ ዕለት ወደ ሆስፒታል ያቀኑት የተለመደ ክትትል ለማድረግ ሲሆን ሐሙስ ምሳ ሰዓት አካባቢ ተመልሰዋል፤ መንፈሳቸውም ተነቃቅቷል" ብሏል። ንግሥቲቱ ወደ ንጉሥ ኤድዋርድ ሰባተኛ ሆስፒታል የተወሰዱት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ምክንያት እንዳልሆነም ተገልጿል። ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ ሆስፒታል ውስጥ ለህክምና ሲኣሳልፉ ከፈረንጆቹ ከ2013 በኋላ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ማዕከላዊ ለንደን የሚገኘው ንጉሥ ኤድዋርድ ሰባተኛ የግል ሆስፒታል በንጉሣውያን ቤተሰቦች ይዘወተራል። በቅርቡ በሞት የተለዩት የንግሥቲቱ ባለቤትን ጨምሮ ንጉሣዊያን ቤተሰቦች የሚታከሙት በዚሁ ሆስፒታል ነው። ንግሥቲቷ ወደ ሰሜን አየርላንድ መሄዳቸውን ትተው ወደ ሆስፒታል ያቀናሉ የሚለው ዜና ጭንቀት እንዳይፈጥር ተሰግቶ ነበር። ምንም እንኳ ኤልዛቤት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በተሳተፉባቸው ዝግጅቶች ላይ ነቃ ብለው ቢታዩም ዕድሜያቸው ለጤናቸው ስጋት ሊሆን እንደሚችል አያጠርጥርም። ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ስለ ንግሥቲቱ የጤንነት ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠበው ግላዊ ሕይወታቸውን ለመጠበቅ ነው ተብሏል። ምንም እንኳ ቤተ-መንግሥቱ ምንም መረጃ ላለመስጠት አስቦ የነበረ ቢሆንም ዘ ሰን የተሰኘው ጋዜጣ ያወጣው ፅሑፍ ነው የቤተ-መንግሥቱን ሰዎች መረጃ እንዲያወጡ ያስገደዳቸው። ንግሥቲቱ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በርካታ ቦታዎችን እየተዘዋወሩ ሲጎበኙ፤ የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲታደሙ ነበር የከረሙት። የንግሥት ኤልዛቤት የዕለተ ከዕለት ተግባር መመዝገቢያ እንደሚያሳየው በፈረንጆቹ የጥቅምት ወር ብቻ 16 ዝግጅቶችን ታድመዋል። ይህ ወደ ሰሜን አየርላንድ ሊያደርጉ ያሰቡትን ጉብኝት ሳይጨምር ነው። ቤተ-መንግሥቱ እንዳለው ንግሥቲቱ ወደ ሰሜን አየርላንድ ለማድረግ ያሰቡት ጉብኝት አለመሳካቱ ቢያበሳጫቸውም የዶክተር ምክርን ሰምተው ዕረፍት እያደረጉ ይገኛሉ። ንግሥቲቱ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚካሄደው የግላስጎው የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። | ንግሥት ኤልዛቤት ሆስፒታል ገብተው እንደነበር ተገለጸ የዩናይትድ ኪንግደሟ ንግሥት ኤልዛቤት ቀዳሚ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ረቡዕ ምሽት ሆስፒታል ገብተው እንደነበር የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አስታወቀ። የ95 ዓመቷ ንግሥት ኤልዛቤት ማእከላዊ ለንደን በሚገኝ አንድ የግል ሆስፒታል ውስጥ ህክምናቸውን ተከታትለው ዊንድሰር ወደ ሚገኘው መኖሪያቸው መመለሳቸውን ተገልጿል። አሁን በመልካም ሁኔታ ላይ ናቸው የተባሉት ንግሥቲቱ ወደ ሰሜን አየርላንድ ለመጓዝ የነበራቸውን እቅድ ሰርዘዋል። የህክምና ባለሙያዎች ንግሥቲቷ ወደተለመደው ሥራቸው ከመመለሳቸው በፊት ለጥቂት ቀናት እረፍት ማድረግ እንደሚገባቸው መክረዋል ተብሏል። ሐሙስ ምሽት ስለንግሥቲቱ መግለጫ የሰጠው የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት እንዳለው "ንግሥቲቱ ረቡዕ ዕለት ወደ ሆስፒታል ያቀኑት የተለመደ ክትትል ለማድረግ ሲሆን ሐሙስ ምሳ ሰዓት አካባቢ ተመልሰዋል፤ መንፈሳቸውም ተነቃቅቷል" ብሏል። ንግሥቲቱ ወደ ንጉሥ ኤድዋርድ ሰባተኛ ሆስፒታል የተወሰዱት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ምክንያት እንዳልሆነም ተገልጿል። ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ ሆስፒታል ውስጥ ለህክምና ሲኣሳልፉ ከፈረንጆቹ ከ2013 በኋላ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ማዕከላዊ ለንደን የሚገኘው ንጉሥ ኤድዋርድ ሰባተኛ የግል ሆስፒታል በንጉሣውያን ቤተሰቦች ይዘወተራል። በቅርቡ በሞት የተለዩት የንግሥቲቱ ባለቤትን ጨምሮ ንጉሣዊያን ቤተሰቦች የሚታከሙት በዚሁ ሆስፒታል ነው። ንግሥቲቷ ወደ ሰሜን አየርላንድ መሄዳቸውን ትተው ወደ ሆስፒታል ያቀናሉ የሚለው ዜና ጭንቀት እንዳይፈጥር ተሰግቶ ነበር። ምንም እንኳ ኤልዛቤት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በተሳተፉባቸው ዝግጅቶች ላይ ነቃ ብለው ቢታዩም ዕድሜያቸው ለጤናቸው ስጋት ሊሆን እንደሚችል አያጠርጥርም። ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ስለ ንግሥቲቱ የጤንነት ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠበው ግላዊ ሕይወታቸውን ለመጠበቅ ነው ተብሏል። ምንም እንኳ ቤተ-መንግሥቱ ምንም መረጃ ላለመስጠት አስቦ የነበረ ቢሆንም ዘ ሰን የተሰኘው ጋዜጣ ያወጣው ፅሑፍ ነው የቤተ-መንግሥቱን ሰዎች መረጃ እንዲያወጡ ያስገደዳቸው። ንግሥቲቱ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በርካታ ቦታዎችን እየተዘዋወሩ ሲጎበኙ፤ የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲታደሙ ነበር የከረሙት። የንግሥት ኤልዛቤት የዕለተ ከዕለት ተግባር መመዝገቢያ እንደሚያሳየው በፈረንጆቹ የጥቅምት ወር ብቻ 16 ዝግጅቶችን ታድመዋል። ይህ ወደ ሰሜን አየርላንድ ሊያደርጉ ያሰቡትን ጉብኝት ሳይጨምር ነው። ቤተ-መንግሥቱ እንዳለው ንግሥቲቱ ወደ ሰሜን አየርላንድ ለማድረግ ያሰቡት ጉብኝት አለመሳካቱ ቢያበሳጫቸውም የዶክተር ምክርን ሰምተው ዕረፍት እያደረጉ ይገኛሉ። ንግሥቲቱ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚካሄደው የግላስጎው የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-58991734 |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ በእንግሊዝ ለበርካታ ሕዝብ የኮቢድ-19 ክትባት የሚሰጡ ማዕከላት ሊከፈቱ ነው | እንግሊዝ በመላው አገሪቱ በሰባት ቦታዎች ላይ በሚቋቋሙ የኮሮናቫይረስ የክትባት መስጫ ማዕከላት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ልትከትብ መሆኑን አስታወቀች። የእንግሊዝ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት በዚህ ሳምንት ተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትንም ይከፈታል ተብሏል። መንግሥት በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ እድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የጤና ሠራተኞች እንዲሁም ተያያዥ የጤና ችግር ያለባቸውን በመላዋ ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ 15 ሚሊዮን ሰዎችን ያህል ሰዎች ለመከተብ እቅድ ይዟል። የጤና ሚኒስትሩ ማት ሐንኮክ የመንግሥትን የክትባት አሰጣጥ እቅድ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ሚኒስትሩ "ይህ ምክረ ሃሳብ ከወረርሽኙ ለመውጣት የመሰረት ድንጋይ የምንጥልበት ነው" ብለዋል። መንግሥት በየቀኑ ለምን ያህል ሰዎች ክትባቱን እንደሰጠ የሚያሳይ አሃዛዊ መረጃም ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ሃንኮክ እሁድ እለት እንዳሉት በዩናይትድ ኪንግደም 2 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ተከትበዋል። በእንግሊዝ በየቀኑ ወደ 200 ሺህ ያህል ክትባቶች መስጠት ተችሏል። ዩናይትድ ኪንግደም ወረርሽኙ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ 80 ሺህ ያህል ሰዎችን በተህዋሲው ምክንያት አጥታለች። በአገሪቱ ከፍተኛ በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች የሚገኙባት ከተማ ሱሬይ ስትሆን፣ በከተማዋ ጊዜያዊ የቀብር ማስፈፀሚያ ቢሮ በሆስፒታል ውስጥ እንዲከፈት ተደርጓል። ይህ የሆነው የቀብር አስፈጻሚዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ አስከሬኖችን መቀበላቸው ከተሰማ በኋላ ነው። ቢያንስ 200 አስከሬኖች ከዚህ ቀደም የጦር ኃይሉ ሆስፒታል በነበረበት ስፍራ በጊዜያዊነት የተቀመጡ ሲሆን፣ ተመሳሳይ ጊዜያዊ ማቆያ በቅርቡ እንደሚከፈት የአካባቢው አስተዳደር ለቢቢሲ ገልጿል። ቅዳሜ እለት ሳይንቲስቶች እጅግ ጥብቅ የሆነ የእንቅስቃሴ ገደብ በእንግሊዝ ያስፈልጋል ሲሉ ምክራቸውን ሰጥተዋል። የጤና ሚኒስትሩም የአገሪቷን ሕዝቦች የተቀመጠውን የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲያከብሩ ተማጽነዋል። ሃንኮክ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ "ሁልጊዜ ገደቡን ባላላን ቁጥር ውጤቱ የከፋ ነው የሚሆነው" ሲሉ ተደምጠዋል። አክለውም "እንደ ማኅበረሰብ በጋራ ልናደርግ የምንችለው በየቤታችን መቆየት ነው" ብለዋል። በእንግሊዝ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዲወጡ የሚፈቀደው ምግብ ለመግዛት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ወይንም ከቤታቸው ሆነው መስራት ለማይችሉ ወደ ሥራቸው ለመሄድ ብቻ ነው። ተመሳሳይ ሕግ በስኮትላንድ፣ በዌልስ እንዲሁም በሰሜን አየር ላንድም ተጥሏል። የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ ጤና አገልግሎት የሚሰጠው ይህ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት በታሪኩ ትልቁ ነው ተብሏል። ክትባቱ በቤት ውስጥ እንክብካቤ ለሚያገኙ አዛውንቶች፣ እስከ ጥር ወር አጋማሽ ድረስ ተሰጥቶ ያበቃል የተባለ ሲሆን፤ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰቡ ክፍሎች ደግሞ እስከ የካቲት ወር አጋማሽ ድረስ የሚሰጥ ይሆናል። | ኮሮናቫይረስ ፡ በእንግሊዝ ለበርካታ ሕዝብ የኮቢድ-19 ክትባት የሚሰጡ ማዕከላት ሊከፈቱ ነው እንግሊዝ በመላው አገሪቱ በሰባት ቦታዎች ላይ በሚቋቋሙ የኮሮናቫይረስ የክትባት መስጫ ማዕከላት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ልትከትብ መሆኑን አስታወቀች። የእንግሊዝ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት በዚህ ሳምንት ተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትንም ይከፈታል ተብሏል። መንግሥት በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ እድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የጤና ሠራተኞች እንዲሁም ተያያዥ የጤና ችግር ያለባቸውን በመላዋ ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ 15 ሚሊዮን ሰዎችን ያህል ሰዎች ለመከተብ እቅድ ይዟል። የጤና ሚኒስትሩ ማት ሐንኮክ የመንግሥትን የክትባት አሰጣጥ እቅድ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ሚኒስትሩ "ይህ ምክረ ሃሳብ ከወረርሽኙ ለመውጣት የመሰረት ድንጋይ የምንጥልበት ነው" ብለዋል። መንግሥት በየቀኑ ለምን ያህል ሰዎች ክትባቱን እንደሰጠ የሚያሳይ አሃዛዊ መረጃም ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ሃንኮክ እሁድ እለት እንዳሉት በዩናይትድ ኪንግደም 2 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ተከትበዋል። በእንግሊዝ በየቀኑ ወደ 200 ሺህ ያህል ክትባቶች መስጠት ተችሏል። ዩናይትድ ኪንግደም ወረርሽኙ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ 80 ሺህ ያህል ሰዎችን በተህዋሲው ምክንያት አጥታለች። በአገሪቱ ከፍተኛ በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች የሚገኙባት ከተማ ሱሬይ ስትሆን፣ በከተማዋ ጊዜያዊ የቀብር ማስፈፀሚያ ቢሮ በሆስፒታል ውስጥ እንዲከፈት ተደርጓል። ይህ የሆነው የቀብር አስፈጻሚዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ አስከሬኖችን መቀበላቸው ከተሰማ በኋላ ነው። ቢያንስ 200 አስከሬኖች ከዚህ ቀደም የጦር ኃይሉ ሆስፒታል በነበረበት ስፍራ በጊዜያዊነት የተቀመጡ ሲሆን፣ ተመሳሳይ ጊዜያዊ ማቆያ በቅርቡ እንደሚከፈት የአካባቢው አስተዳደር ለቢቢሲ ገልጿል። ቅዳሜ እለት ሳይንቲስቶች እጅግ ጥብቅ የሆነ የእንቅስቃሴ ገደብ በእንግሊዝ ያስፈልጋል ሲሉ ምክራቸውን ሰጥተዋል። የጤና ሚኒስትሩም የአገሪቷን ሕዝቦች የተቀመጠውን የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲያከብሩ ተማጽነዋል። ሃንኮክ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ "ሁልጊዜ ገደቡን ባላላን ቁጥር ውጤቱ የከፋ ነው የሚሆነው" ሲሉ ተደምጠዋል። አክለውም "እንደ ማኅበረሰብ በጋራ ልናደርግ የምንችለው በየቤታችን መቆየት ነው" ብለዋል። በእንግሊዝ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዲወጡ የሚፈቀደው ምግብ ለመግዛት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ወይንም ከቤታቸው ሆነው መስራት ለማይችሉ ወደ ሥራቸው ለመሄድ ብቻ ነው። ተመሳሳይ ሕግ በስኮትላንድ፣ በዌልስ እንዲሁም በሰሜን አየር ላንድም ተጥሏል። የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ ጤና አገልግሎት የሚሰጠው ይህ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት በታሪኩ ትልቁ ነው ተብሏል። ክትባቱ በቤት ውስጥ እንክብካቤ ለሚያገኙ አዛውንቶች፣ እስከ ጥር ወር አጋማሽ ድረስ ተሰጥቶ ያበቃል የተባለ ሲሆን፤ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰቡ ክፍሎች ደግሞ እስከ የካቲት ወር አጋማሽ ድረስ የሚሰጥ ይሆናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55614498 |
5sports
| 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ | ቀድሞኝ ዶሃ የከተመው የሥራ ባልደረባዬ አንድ መልዕክት ስልኬ ላይ አኖረልኝ። 'ልብስ ይዘህ እንዳትመጣ' የሚል። መጀመሪያ መልዕክቱ ፈገግ አሰኘኝ። የወዳጄ መልዕክት ቀጭን ትዕዛዝ መሆኑ የገባኝ የዶሃን አየር ፀባይ በተመለከተ መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ድረ ገፆች ጎራ ባልኩበት ጊዜ ነው። ሃማድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንኳን እኔ 'ሦስተኛ ዓለም' ከሚሉት ቀጠና የመጣ ይቅርና አሜሪካውያንና እንግሊዛዊያንን በአግራሞት አፍ ያስከፍታል። እንዴት ያን የሚያክል ህንፃ እንደ ቤተ-መቅደስ በመልካም መዓዛ ይታወዳል? ሀሉም ነገር ተብለጨለጨብኝ። • በቤተ መንግሥት ግቢ የተገነባው አንድነት ፓርክ በውስጡ ምን ይዟል? • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ ዶሃ የገባሁት ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ ነበር። ቪዛና ሌሎቹ ኮተቶቼን አጠናቅቄ ከአየር መንገድ ስወጣ 2 ሰዓት ገደማ ሆኗል። ልክ ከአየር መንገዱ ስወጣ የተቀበለኝ ጥፊ ነው። አዎ ጥፊ! ወበቁ ይጋረፋል። ያስደነግጣል። "ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነው የመጣኸው?" አንድ በደንቡ የለበሰ ሰው ጠየቀኝ። "አዎ!"። "በል ተከተለኝ" . . . ምን አማራጭ አለኝ. . . በፈገግታ የተሞላው ቃጣሪ [የኳታር ዜጋ] ለአንድ ሕንዳዊ አቀበለኝ። "ጌታዬ፤ ወደ ሆቴል ነው ወደ ስታድዬም?"። ኧረግ 'ጌታዬ'፤ ኧረ ልጅ ዓለም በለኝ ልለው አሰብኩና ከአፌ መለስኩት። የሆቴሌን ስም የነገርኩት ሕንዳዊ ሹፌር ሻንጣዎቼን የመኪናው ሳንዱቅ ውስጥ ጨምሮ ጉዞ ጀመርን። • በበዴሳ ከተማ ታዳጊውን ለመታደግ የሞከሩ 4 ሰዎች የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ ልክ ወደ መኪናዋ ስዘልቅ የተሰማኝ ቅዝቃዜ. . . የሆነ ነገር አንቆኝ ስታገል ቆይቼ በስተመጨረሻ የተገላገልኩ ያክል ተሰማኝ። የዶሃ መለያዋ ምንድነው? ቢሉ ሰው ሰራሽ ማጤዣዋ [ኤሲ] እልዎታለሁ። ከኤርፖርት ወደ ሆቴል የነበረውን ጉዞ በሕንፃዎች መካከል እየተሹለኮለክን አለፍነው። የሕንፃ ጫካ አይቶ፤ 'ቬጋስ ተንቆጥቁጣ' ሲል ያቀነቀነው ዘፋኝ ዶሃን አላያትም ማለት ነው? እያልኩ ወደ ማረፊያዬ ደረስኩ። ኤሲ፣ ኤሲ፣ ኤሲ. . . ኑሮ በዶሃ በኤሲ የተቃኘ ነው። ወደ መኪና ሲገቡ ኤሲ፤ ወደ መገበያያ ሥፍራ ሲገቡ ኤሲ. . . ሌላው ቀርቶ 50 ሺህ ውጦ አላየሁም የሚለው ኻሊፋ ዓለም አቀፍ ስታድዬም ኤሲ ተገጥሞለታል። ለ50 ሺህ ሰው አየር ማቀዝቀዣ! የምዕራብ እስያዊቷ ሃገር ኳታር የሕዝብ ቁጥር 2.8 ሚሊዮን ይገመታል። ከዚህ ውስጥ አረብ ወይም ቃጣሪ ተብለው የሚጡት የአገሪቱ ዜጎች 15 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ሲነገር፤ የተቀሩቱ ከሌሎች አገራት የመጡ ዜጎች ናቸው። የሕንድ፣ ኔፓል፣ እና ፊሊፒንስ ዜጎች ኳታርን ሞልተዋታል። በንጉሳዊ አገዛዝ የምትተዳደረው ኳታር በዓለም ሦስተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ያለባት አገር ነች። የዜጎቿ የነብስ ወከፍ ገቢም በዓለም አሉ ከሚባሉት የሚመደብ ነው። ዶሃ ውስጥ ያለ ፓስፖርት ወይም ሕጋዊ ማስረጃ መንቀሳቀስ ቀላል አይደለም። ይህንን ስል በየመንገዱ ፖሊስ እያስቆመ 'ፓስፖርት ወዲህ በል' ይላል ማለቴ አይደለም። ዶሃ የመጀመሪያ ተግባሬ የነበረው ሲም ካርድ ማውጣት ነበር። ወደ አንዱ የቴሌኮም ድርጅት ሄጄ ሲም ካርድ ፈልጌ ነው አመጣጤ ማለት፤ 'ፓስፖርት እባክዎን ጌታዬ'፤ ኧረ ልጅ ዓለም ይበቃል. . .አሁንም በውስጤ። ሰውዬው ፓስፖርቴን ከተቀበለ በኋላ ወደ አነስተኛ ማሽን ሲያስጠጋት ሚስጥሬ ሁሉ ስክሪኑ ላይ ተዘረገፈ። የትውልድ ቀንና ቦታ፤ ለምን ያህል ጊዜ ዶሃ እንደመጣሁ. . . • ስቶርምዚ በካምብሪጅ የጥቁር ተማሪዎች ቁጥር እንዲጨምር አስተዋፅኦ አድርጓል ተባለ ቀጣይ ተግባሬ ደግሞ ዶላር ወደ ኳታሪ ሪያል መመንዘር። እዚህም ያስተናገደኝ ሰው ፓስፖርቴን ለአንድ ማሽን ቢያቀብል ሙሉ መረጃዬ ተዘረገፈ። አንድ ዶላር በ3 ሪያል ሂሳብ መንዝሬ ሳበቃ የዶሃ መንግሥት እንዴት የዜጎቹን ሚስጥር እንደሚቆጣጠር እየገረመኝ ሹልክ አልኩ። ዶሃ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች ጥያቄ ይወዳሉ። በተለይ ሕንዶችና እና ኔፓሎች። ጋዜጠኛ እኔ ሳልሆን እነሱ ነበር የሚመስሉት። ታዲያ ጨዋታቸው ደስ ይላል። 'ከየት ነው የመጣኸው?' የሁሉም ጥያቄ ነች። ከዚህ ነው የመጣሁት፣ አመጣጤ ደግሞ ለዚህ ነው. . . እኔም መልሴን አዘጋጅቼ መጠባበቅ ያዝኩ። ከሆቴል ወደ ስታድዬም መሄድ ነበረብኝና 'ኡበሬን' መዥረጥ አድርጌ ታክሲ ብጠራ ፀጋይ ከች። የአገር ሰው መቼም የሃገር ነው ብዬ ተንገብግቤ ነበር ፀጋይ 'ሰላም ነህ ወንድሜ?' ስል እጄን የሰጡት። ፀጋይ አማርኛ ሁለተኛ ቋንቋው እንደሆነ ቢያሳብቅም አቀላጥፎ ይናገራል። ፀጋይ ኤርትራዊ ነው። ዶሃ ከከተመ በርካታ ዓመታት ሆነውታል። ባለቤቱና ልጆቹ ኑሯቸው አስመራ ነው። በዓመትም ይሁን በሁለት እየተመላለሰ እንደሚጎበኛቸው አጫወተኝ። ታድያ ኑሮ በዶሃ እንዴት ነው?፤ "ይገርምሃል እኔ ዶሃን በደንብ ነው የማውቃት። መቼም ቃጣሪዎች በቁጥር ትንሽ እንደሆኑ ታውቃለህ። ግን ገንዘቡ ያለው በእነርሱ እጅ ነው። እዚህ አገር የማታገኘው ዓይነት የውጭ ዜጋ የለም። ከአፍሪቃ እና እስያ ሃገራት የሚመጡት ተውና ከአሜሪካ እና ከአውሮጳ ሳይቀር እዚህ መጥተው የሚሠሩ ብዙ ናቸው።" • የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው ፀጋይ የማይጠገብ ጨዋታውን እየመገበኝ ስታድየም ደረስን። ስልክ ተለዋውጠን ተለያየን። ከዚያ ቀን በኋላ ወደ ምፈልገበት ቦታ ሲያደርሰኝ የነበረው ፀጋይ ነበር። ጨዋታው የሚጠገብ አይደለም። ስለ ዶሃ ብዙ አጫወተኝ። አንገቴን እስኪያመኝ ቀና ብዬ የማያቸው መጨረሻ የሌላቸው ሕንፃዎችን ከነስማቸው እየዘረዘረልኝ ጉዞዬን አሰመረው። "እዚያ ጋር ይታይሃል? ፎቶ እና ቪድዬ ማንሳት ክልክል ነው የሚል የተለጠፈበት አጥር?"። ወደ ጠቆመኝ ቦታ እየተመለከትኩ ጭንቅላቴን በአዎንታ ወዘወዝኩ። "የአልጃዚራ ዋና መሥሪያ ቤት ነው። ገና ምኑን አይተህ፤ መጨረሻ የለውም።" እውነትም መጨረሻ የለውም። በዶሃ ቆይታዬ ፖሊስ ያየሁት ስታድየም ዙሪያ ብቻ ነው። ዶሃ ተፈልጎ የማይገኘው ሌላው የትራፊክ አደባባይ ነው፤ አዎ! አደባባይ። ብዙዎቹ መንገዶቹ ማሳለጫቸው መስቀለኛ ነው። በአቅጣጫ ጠቋሚ የትራፊክ መብራቶች ተሞልተዋል። ታዲያ፤ መሽቷል፣ አልያም ትራፊክ የለም በሚል ተልካሻ ምክንያት መብራት መጣስ ጣትን ወደ እሳት እንደመስደድ ነው። አንድ ጋናዊ ሹፌር እንደነገረኝ የትራፊክ መብራት መጣስ እስከ 6000 የቃጣር ሪያል ያስቀጣል። ወደ 59 ሺህ ብር ገደማ ማለት ነው። ተሽከርካሪዎች ጥፋት መፈፀም አለመፈፀማቸውን መርምረው የሚያሳብቁ ካሜራዎች በየቦታው ተተክለዋል። "እያየህ ግባበት ነው" ያለው ፀጋይ ወዶ አይደለም። • ግብጽ በአባይ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች ፀጋይም ሆነ ሌሎች ያጋጠሙኝ አሽከርካሪዎች እንዲሁም የዶሃ ነዋሪዎች በአንድ ጉዳይ ይስማማሉ። ዶሃ ለኑሮና ሥራ ምቹ ናት። ዋናው ነገር ሕጉን ማክበር ነው። ሕግ ጥሰው የተገኙ እንደሆነ የፀጥታ ሰዎች ካሉበት መጥተው ነው የሚለቅምዎት ሲሉ ብዙዎች ያስረዱኝ። ዶሃ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንዳሉ ፀጋይ አጫውቶኛል። እኔም ወዲያ ወዲህ ስቅበዘበዝ ያገኘኋቸው እና ለሰላምታ የተጠመጠምኩባቸው የዶሃ ምድር ይቁጠራቸው። ኳታር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 25 ሺህ ይገመታል። ይህም የጠቅላላው ሕዝብ ቁጥሩን 0.8 በመቶ ድርሻ ይይዛል። በቤት ሠራተኝነት የተሰማሩ፣ አሽከርካሪዎች፣ የጥበቃ ሠራተኞች. . . እንዲሁም ሌሎች የሥራ መስኮች ኢትዮጵያውያን ተሠማርተው ኑሯቸውን የሚገፉባቸው መስኮች ናቸው። ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን 'ፕሮፌሽናል' ተብለው የሚጠሩ የሥራ መስኮችም ውስጥ ተሰማርተው ይገኛሉ። እርግጥ ነው የአትሌቲክስ ቡድናቸውን ለመደገፍ ኻሊፋ ስታድየም የተገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በርካታ ነበር። በባንዲራ ጉዳይ ጎራ ከፍለው ቢቀመጡም። ምን ያህል ኤርትራውያን ኳታርን መጠለያቸው እንዳደረጉ ግን ውል ያለው መረጃ የለም። ፀጋይ፤ ቢበዛ 5 ሺህ ገደማ ብንሆን ነው ሲል አጫውቶኛል። • "ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች እንደው አንድ ቀን የቡና ጥም ከዶሃ ሙቀት ጋር ተቀላቅሎ ቢያንገላታኝ ስታርባክስ የተሰኘ ቡና መሸጫ ሱቅ ገባሁ። ታዲያ ከፊት ለፊት የተቀበለኝ ኢትዮጵያ የሚል ስም ደረቱ ላይ የለጠፈ የታሸገ ቡና ነው። ጀበናችንም ከረጢቱ ላይ ተስላ ትታየኛለች። ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ኮለምቢያ አለች። በገዛ ቡናችን እንደባይተዋር ተሰልፌ ተራዬ ሲደርስ ሸምቼ ወንበሬን ስቤ ተቀመጥኩ። አንድ 'ሱፐርማርኬት' ገብቼ ቡናዎች ከተደረደሩበት ሥፋራ ባቀናም የኢትዮጵያ ስም የተለጠፈበት አንድ እሽግ አይቻለሁ። የሚደንቀው ነገር የኢትዮጵያን ስም እንደ ታርጋ የሚጠቀሙት እኒህ እሽግ ቡናዎች ዋጋቸው ከሌሎቹ ወደድ ያለ መሆኑ ነው። ምናልባት እኔ ነገሮች ተመቻችተውልኝ ስለጎበኘኋት ይሆን? ብቻ ዶሃ አትጠገብም። ጊዜ ቢያጥረኝ እንጂ ከእግር እስከ ራሷ ብጎበኛት ደስታዬ ወደር አልነበረውም። በቻልኩት መጠን ግን በርካታ ሥፍራዎችን ሲቻል ወደ ውስጥ ዘልቄ ሳይሆን ሲቀር ከቅርብ ርቀት ማየት ችያለሁ። የዶሃ ቅርሶች አብዛኛዎች ሰው ሰራሽ ናቸው። ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች፣ የሕንድ ውቅያኖስ ላይ የተንሳፈፉ ሆቴሎች፣ ሌላው ቀርቶ ሰው ሰራሽ ደሴቶችና ጫካዎች የከበቧት ናት፤ ዶሃ። • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ ቃጣሪዎች ዶሃ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ማሳያዎች ብዙዎች ናቸው። ከብዙ ሃገራት ተቃውሞ ቢገጥመውም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበራት ፌዴሬሽን የዘንድሮውን ውድድር ከማምጣት አልተቆጠበም። በገንዘብ ገዙት እንጂ እንዴት በዚህ በረሃ ላይ የሩጫ ውድድር ይካሄዳል እያሉ ሃሜት እና ምሬት ሲያሰሙ ያደመጥኳቸው አሉ። ነገር ግን ኳታር ዝግጅቱን በድል ጀምራ በድል አጠናቃዋለች። የመጀመሪያዎቹ ቀናት የተመልካች ድርቅ መቶት የነበረው ግዙፉ ስታድየማቸው እያደር ደምቆላቸዋል። አሁን ሁሉም 2022ን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸው። የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን። 'ገንዘብ ካለ. . . 'የሚለውን አባባል እውን ያደረጉት ቃጣሪዎች የሚሳናቸው ያለ አይመስልም። | 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ ቀድሞኝ ዶሃ የከተመው የሥራ ባልደረባዬ አንድ መልዕክት ስልኬ ላይ አኖረልኝ። 'ልብስ ይዘህ እንዳትመጣ' የሚል። መጀመሪያ መልዕክቱ ፈገግ አሰኘኝ። የወዳጄ መልዕክት ቀጭን ትዕዛዝ መሆኑ የገባኝ የዶሃን አየር ፀባይ በተመለከተ መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ድረ ገፆች ጎራ ባልኩበት ጊዜ ነው። ሃማድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንኳን እኔ 'ሦስተኛ ዓለም' ከሚሉት ቀጠና የመጣ ይቅርና አሜሪካውያንና እንግሊዛዊያንን በአግራሞት አፍ ያስከፍታል። እንዴት ያን የሚያክል ህንፃ እንደ ቤተ-መቅደስ በመልካም መዓዛ ይታወዳል? ሀሉም ነገር ተብለጨለጨብኝ። • በቤተ መንግሥት ግቢ የተገነባው አንድነት ፓርክ በውስጡ ምን ይዟል? • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ ዶሃ የገባሁት ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ ነበር። ቪዛና ሌሎቹ ኮተቶቼን አጠናቅቄ ከአየር መንገድ ስወጣ 2 ሰዓት ገደማ ሆኗል። ልክ ከአየር መንገዱ ስወጣ የተቀበለኝ ጥፊ ነው። አዎ ጥፊ! ወበቁ ይጋረፋል። ያስደነግጣል። "ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነው የመጣኸው?" አንድ በደንቡ የለበሰ ሰው ጠየቀኝ። "አዎ!"። "በል ተከተለኝ" . . . ምን አማራጭ አለኝ. . . በፈገግታ የተሞላው ቃጣሪ [የኳታር ዜጋ] ለአንድ ሕንዳዊ አቀበለኝ። "ጌታዬ፤ ወደ ሆቴል ነው ወደ ስታድዬም?"። ኧረግ 'ጌታዬ'፤ ኧረ ልጅ ዓለም በለኝ ልለው አሰብኩና ከአፌ መለስኩት። የሆቴሌን ስም የነገርኩት ሕንዳዊ ሹፌር ሻንጣዎቼን የመኪናው ሳንዱቅ ውስጥ ጨምሮ ጉዞ ጀመርን። • በበዴሳ ከተማ ታዳጊውን ለመታደግ የሞከሩ 4 ሰዎች የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ ልክ ወደ መኪናዋ ስዘልቅ የተሰማኝ ቅዝቃዜ. . . የሆነ ነገር አንቆኝ ስታገል ቆይቼ በስተመጨረሻ የተገላገልኩ ያክል ተሰማኝ። የዶሃ መለያዋ ምንድነው? ቢሉ ሰው ሰራሽ ማጤዣዋ [ኤሲ] እልዎታለሁ። ከኤርፖርት ወደ ሆቴል የነበረውን ጉዞ በሕንፃዎች መካከል እየተሹለኮለክን አለፍነው። የሕንፃ ጫካ አይቶ፤ 'ቬጋስ ተንቆጥቁጣ' ሲል ያቀነቀነው ዘፋኝ ዶሃን አላያትም ማለት ነው? እያልኩ ወደ ማረፊያዬ ደረስኩ። ኤሲ፣ ኤሲ፣ ኤሲ. . . ኑሮ በዶሃ በኤሲ የተቃኘ ነው። ወደ መኪና ሲገቡ ኤሲ፤ ወደ መገበያያ ሥፍራ ሲገቡ ኤሲ. . . ሌላው ቀርቶ 50 ሺህ ውጦ አላየሁም የሚለው ኻሊፋ ዓለም አቀፍ ስታድዬም ኤሲ ተገጥሞለታል። ለ50 ሺህ ሰው አየር ማቀዝቀዣ! የምዕራብ እስያዊቷ ሃገር ኳታር የሕዝብ ቁጥር 2.8 ሚሊዮን ይገመታል። ከዚህ ውስጥ አረብ ወይም ቃጣሪ ተብለው የሚጡት የአገሪቱ ዜጎች 15 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ሲነገር፤ የተቀሩቱ ከሌሎች አገራት የመጡ ዜጎች ናቸው። የሕንድ፣ ኔፓል፣ እና ፊሊፒንስ ዜጎች ኳታርን ሞልተዋታል። በንጉሳዊ አገዛዝ የምትተዳደረው ኳታር በዓለም ሦስተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ያለባት አገር ነች። የዜጎቿ የነብስ ወከፍ ገቢም በዓለም አሉ ከሚባሉት የሚመደብ ነው። ዶሃ ውስጥ ያለ ፓስፖርት ወይም ሕጋዊ ማስረጃ መንቀሳቀስ ቀላል አይደለም። ይህንን ስል በየመንገዱ ፖሊስ እያስቆመ 'ፓስፖርት ወዲህ በል' ይላል ማለቴ አይደለም። ዶሃ የመጀመሪያ ተግባሬ የነበረው ሲም ካርድ ማውጣት ነበር። ወደ አንዱ የቴሌኮም ድርጅት ሄጄ ሲም ካርድ ፈልጌ ነው አመጣጤ ማለት፤ 'ፓስፖርት እባክዎን ጌታዬ'፤ ኧረ ልጅ ዓለም ይበቃል. . .አሁንም በውስጤ። ሰውዬው ፓስፖርቴን ከተቀበለ በኋላ ወደ አነስተኛ ማሽን ሲያስጠጋት ሚስጥሬ ሁሉ ስክሪኑ ላይ ተዘረገፈ። የትውልድ ቀንና ቦታ፤ ለምን ያህል ጊዜ ዶሃ እንደመጣሁ. . . • ስቶርምዚ በካምብሪጅ የጥቁር ተማሪዎች ቁጥር እንዲጨምር አስተዋፅኦ አድርጓል ተባለ ቀጣይ ተግባሬ ደግሞ ዶላር ወደ ኳታሪ ሪያል መመንዘር። እዚህም ያስተናገደኝ ሰው ፓስፖርቴን ለአንድ ማሽን ቢያቀብል ሙሉ መረጃዬ ተዘረገፈ። አንድ ዶላር በ3 ሪያል ሂሳብ መንዝሬ ሳበቃ የዶሃ መንግሥት እንዴት የዜጎቹን ሚስጥር እንደሚቆጣጠር እየገረመኝ ሹልክ አልኩ። ዶሃ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች ጥያቄ ይወዳሉ። በተለይ ሕንዶችና እና ኔፓሎች። ጋዜጠኛ እኔ ሳልሆን እነሱ ነበር የሚመስሉት። ታዲያ ጨዋታቸው ደስ ይላል። 'ከየት ነው የመጣኸው?' የሁሉም ጥያቄ ነች። ከዚህ ነው የመጣሁት፣ አመጣጤ ደግሞ ለዚህ ነው. . . እኔም መልሴን አዘጋጅቼ መጠባበቅ ያዝኩ። ከሆቴል ወደ ስታድዬም መሄድ ነበረብኝና 'ኡበሬን' መዥረጥ አድርጌ ታክሲ ብጠራ ፀጋይ ከች። የአገር ሰው መቼም የሃገር ነው ብዬ ተንገብግቤ ነበር ፀጋይ 'ሰላም ነህ ወንድሜ?' ስል እጄን የሰጡት። ፀጋይ አማርኛ ሁለተኛ ቋንቋው እንደሆነ ቢያሳብቅም አቀላጥፎ ይናገራል። ፀጋይ ኤርትራዊ ነው። ዶሃ ከከተመ በርካታ ዓመታት ሆነውታል። ባለቤቱና ልጆቹ ኑሯቸው አስመራ ነው። በዓመትም ይሁን በሁለት እየተመላለሰ እንደሚጎበኛቸው አጫወተኝ። ታድያ ኑሮ በዶሃ እንዴት ነው?፤ "ይገርምሃል እኔ ዶሃን በደንብ ነው የማውቃት። መቼም ቃጣሪዎች በቁጥር ትንሽ እንደሆኑ ታውቃለህ። ግን ገንዘቡ ያለው በእነርሱ እጅ ነው። እዚህ አገር የማታገኘው ዓይነት የውጭ ዜጋ የለም። ከአፍሪቃ እና እስያ ሃገራት የሚመጡት ተውና ከአሜሪካ እና ከአውሮጳ ሳይቀር እዚህ መጥተው የሚሠሩ ብዙ ናቸው።" • የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው ፀጋይ የማይጠገብ ጨዋታውን እየመገበኝ ስታድየም ደረስን። ስልክ ተለዋውጠን ተለያየን። ከዚያ ቀን በኋላ ወደ ምፈልገበት ቦታ ሲያደርሰኝ የነበረው ፀጋይ ነበር። ጨዋታው የሚጠገብ አይደለም። ስለ ዶሃ ብዙ አጫወተኝ። አንገቴን እስኪያመኝ ቀና ብዬ የማያቸው መጨረሻ የሌላቸው ሕንፃዎችን ከነስማቸው እየዘረዘረልኝ ጉዞዬን አሰመረው። "እዚያ ጋር ይታይሃል? ፎቶ እና ቪድዬ ማንሳት ክልክል ነው የሚል የተለጠፈበት አጥር?"። ወደ ጠቆመኝ ቦታ እየተመለከትኩ ጭንቅላቴን በአዎንታ ወዘወዝኩ። "የአልጃዚራ ዋና መሥሪያ ቤት ነው። ገና ምኑን አይተህ፤ መጨረሻ የለውም።" እውነትም መጨረሻ የለውም። በዶሃ ቆይታዬ ፖሊስ ያየሁት ስታድየም ዙሪያ ብቻ ነው። ዶሃ ተፈልጎ የማይገኘው ሌላው የትራፊክ አደባባይ ነው፤ አዎ! አደባባይ። ብዙዎቹ መንገዶቹ ማሳለጫቸው መስቀለኛ ነው። በአቅጣጫ ጠቋሚ የትራፊክ መብራቶች ተሞልተዋል። ታዲያ፤ መሽቷል፣ አልያም ትራፊክ የለም በሚል ተልካሻ ምክንያት መብራት መጣስ ጣትን ወደ እሳት እንደመስደድ ነው። አንድ ጋናዊ ሹፌር እንደነገረኝ የትራፊክ መብራት መጣስ እስከ 6000 የቃጣር ሪያል ያስቀጣል። ወደ 59 ሺህ ብር ገደማ ማለት ነው። ተሽከርካሪዎች ጥፋት መፈፀም አለመፈፀማቸውን መርምረው የሚያሳብቁ ካሜራዎች በየቦታው ተተክለዋል። "እያየህ ግባበት ነው" ያለው ፀጋይ ወዶ አይደለም። • ግብጽ በአባይ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች ፀጋይም ሆነ ሌሎች ያጋጠሙኝ አሽከርካሪዎች እንዲሁም የዶሃ ነዋሪዎች በአንድ ጉዳይ ይስማማሉ። ዶሃ ለኑሮና ሥራ ምቹ ናት። ዋናው ነገር ሕጉን ማክበር ነው። ሕግ ጥሰው የተገኙ እንደሆነ የፀጥታ ሰዎች ካሉበት መጥተው ነው የሚለቅምዎት ሲሉ ብዙዎች ያስረዱኝ። ዶሃ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንዳሉ ፀጋይ አጫውቶኛል። እኔም ወዲያ ወዲህ ስቅበዘበዝ ያገኘኋቸው እና ለሰላምታ የተጠመጠምኩባቸው የዶሃ ምድር ይቁጠራቸው። ኳታር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 25 ሺህ ይገመታል። ይህም የጠቅላላው ሕዝብ ቁጥሩን 0.8 በመቶ ድርሻ ይይዛል። በቤት ሠራተኝነት የተሰማሩ፣ አሽከርካሪዎች፣ የጥበቃ ሠራተኞች. . . እንዲሁም ሌሎች የሥራ መስኮች ኢትዮጵያውያን ተሠማርተው ኑሯቸውን የሚገፉባቸው መስኮች ናቸው። ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን 'ፕሮፌሽናል' ተብለው የሚጠሩ የሥራ መስኮችም ውስጥ ተሰማርተው ይገኛሉ። እርግጥ ነው የአትሌቲክስ ቡድናቸውን ለመደገፍ ኻሊፋ ስታድየም የተገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በርካታ ነበር። በባንዲራ ጉዳይ ጎራ ከፍለው ቢቀመጡም። ምን ያህል ኤርትራውያን ኳታርን መጠለያቸው እንዳደረጉ ግን ውል ያለው መረጃ የለም። ፀጋይ፤ ቢበዛ 5 ሺህ ገደማ ብንሆን ነው ሲል አጫውቶኛል። • "ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች እንደው አንድ ቀን የቡና ጥም ከዶሃ ሙቀት ጋር ተቀላቅሎ ቢያንገላታኝ ስታርባክስ የተሰኘ ቡና መሸጫ ሱቅ ገባሁ። ታዲያ ከፊት ለፊት የተቀበለኝ ኢትዮጵያ የሚል ስም ደረቱ ላይ የለጠፈ የታሸገ ቡና ነው። ጀበናችንም ከረጢቱ ላይ ተስላ ትታየኛለች። ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ኮለምቢያ አለች። በገዛ ቡናችን እንደባይተዋር ተሰልፌ ተራዬ ሲደርስ ሸምቼ ወንበሬን ስቤ ተቀመጥኩ። አንድ 'ሱፐርማርኬት' ገብቼ ቡናዎች ከተደረደሩበት ሥፋራ ባቀናም የኢትዮጵያ ስም የተለጠፈበት አንድ እሽግ አይቻለሁ። የሚደንቀው ነገር የኢትዮጵያን ስም እንደ ታርጋ የሚጠቀሙት እኒህ እሽግ ቡናዎች ዋጋቸው ከሌሎቹ ወደድ ያለ መሆኑ ነው። ምናልባት እኔ ነገሮች ተመቻችተውልኝ ስለጎበኘኋት ይሆን? ብቻ ዶሃ አትጠገብም። ጊዜ ቢያጥረኝ እንጂ ከእግር እስከ ራሷ ብጎበኛት ደስታዬ ወደር አልነበረውም። በቻልኩት መጠን ግን በርካታ ሥፍራዎችን ሲቻል ወደ ውስጥ ዘልቄ ሳይሆን ሲቀር ከቅርብ ርቀት ማየት ችያለሁ። የዶሃ ቅርሶች አብዛኛዎች ሰው ሰራሽ ናቸው። ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች፣ የሕንድ ውቅያኖስ ላይ የተንሳፈፉ ሆቴሎች፣ ሌላው ቀርቶ ሰው ሰራሽ ደሴቶችና ጫካዎች የከበቧት ናት፤ ዶሃ። • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ ቃጣሪዎች ዶሃ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ማሳያዎች ብዙዎች ናቸው። ከብዙ ሃገራት ተቃውሞ ቢገጥመውም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበራት ፌዴሬሽን የዘንድሮውን ውድድር ከማምጣት አልተቆጠበም። በገንዘብ ገዙት እንጂ እንዴት በዚህ በረሃ ላይ የሩጫ ውድድር ይካሄዳል እያሉ ሃሜት እና ምሬት ሲያሰሙ ያደመጥኳቸው አሉ። ነገር ግን ኳታር ዝግጅቱን በድል ጀምራ በድል አጠናቃዋለች። የመጀመሪያዎቹ ቀናት የተመልካች ድርቅ መቶት የነበረው ግዙፉ ስታድየማቸው እያደር ደምቆላቸዋል። አሁን ሁሉም 2022ን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸው። የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን። 'ገንዘብ ካለ. . . 'የሚለውን አባባል እውን ያደረጉት ቃጣሪዎች የሚሳናቸው ያለ አይመስልም። | https://www.bbc.com/amharic/news-50020788 |
3politics
| በኬንያ ፖለቲከኞች ለድምጽ ሰጪዎች ጉቦ እየሰጡ የገንዘብ እጥረት አጋጠመ | በኬንያ ምርጫ ዕጩዎች የመራጮችን ድምጽ ለማግኘት ጉቦ እየሰጡ በመሆናቸው የ100 እና የ200 ሽልንግ የገንዘብ ኖቶች እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ። በኬንያ ባንኮች የ100 እና 200 ሽልንግ [የኬንያ ገንዘብ] ኖት እጥረት ያጋጠመው ፖለቲከኞች ለመራጮች ጉቦ እየከፈሉት መሆኑን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፍሬድ ማቲያንጊ ተናግረዋል። ኬንያ ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ በአገሪቱ በሚካሄዱ ምርጫዎች ዕጩዎች የመራጮችን ድምጽ በገንዘብ የመግዛት ሪፖርት አዲስ አይደለም። ፍሬድ ማቲያንጊ “ገንዘብ በቦርሳ የያዙ ሰዎች መንገድ ላይ ተሰልፈው ለሚገኙ ዜጎች 200 ሽልንግ ሲሰጧቸው ሳትመለከቱ አይቀርም” ማለታቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል፣ ኤኤፍፒ ዘግቧል። ሚኒስትሩ ቀጣዩ የአገሪቱ ፓርላማ በሕገ-ወጥ መንገድ በተገኘ ገንዘብ የመራጮችን ድምጽ ገዝተው ወንበር በያዙ ፖለቲከኞች ሊሞላ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የኬንያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን መደጋፍ በሚመለከት መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት፤ መሰል የፖለቲከኞች ተግባር አገሪቱ በሙስና ላይ እያካሄደች ያለውን ጦርነት አደጋ ውስጥ የሚጥል ነው ብለዋል። ፍሬድ ማቲያንጊ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦች ሥልጣን ቢጨብጡ እራሳቸውን ለመከላከል ሲሉ የአገሪቱን ሕግ እና መመሪያዎችን ሊቀይሩ ይችላሉም ብለዋል። በኬንያ ከዚህ ቀደም በነበሩ ምርጫዎች ዕጩዎች ለመመረጥ ከሚያስተዋውቋቸው ርዕዮተ ዓለሞች ይልቅ ዝናቸው እና ለምርጫ ወጪ የሚደርጉት የገንዘብ መጠን በውጤት ላይ ለውጥ ያመጣል። ከ22 ሚሊዮን በላይ መራጮች ለተመዘገቡበት ምርጫ ማስፈጸሚያ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር 400 ሚሊዮን ዶላር በጀት መድባለች። ይህ ገንዘብ ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው ተብሏል። ኬንያውያን ከሳምንት በኋላ ለሁለት የሥልጣን ዘመናት አገሪቱን ያስተዳደሩትን ኡሁሩ ኬንያታን የሚተካ አዲስ ፕሬዝዳንት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን እና የግዛት አስተዳዳሪዎችን ይመርጣሉ። ኬንያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት በምክትል ፕሬዝዳንቱ ዊሊያም ሩቶና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ መካከል ጠንካራ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። | በኬንያ ፖለቲከኞች ለድምጽ ሰጪዎች ጉቦ እየሰጡ የገንዘብ እጥረት አጋጠመ በኬንያ ምርጫ ዕጩዎች የመራጮችን ድምጽ ለማግኘት ጉቦ እየሰጡ በመሆናቸው የ100 እና የ200 ሽልንግ የገንዘብ ኖቶች እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ። በኬንያ ባንኮች የ100 እና 200 ሽልንግ [የኬንያ ገንዘብ] ኖት እጥረት ያጋጠመው ፖለቲከኞች ለመራጮች ጉቦ እየከፈሉት መሆኑን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፍሬድ ማቲያንጊ ተናግረዋል። ኬንያ ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ በአገሪቱ በሚካሄዱ ምርጫዎች ዕጩዎች የመራጮችን ድምጽ በገንዘብ የመግዛት ሪፖርት አዲስ አይደለም። ፍሬድ ማቲያንጊ “ገንዘብ በቦርሳ የያዙ ሰዎች መንገድ ላይ ተሰልፈው ለሚገኙ ዜጎች 200 ሽልንግ ሲሰጧቸው ሳትመለከቱ አይቀርም” ማለታቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል፣ ኤኤፍፒ ዘግቧል። ሚኒስትሩ ቀጣዩ የአገሪቱ ፓርላማ በሕገ-ወጥ መንገድ በተገኘ ገንዘብ የመራጮችን ድምጽ ገዝተው ወንበር በያዙ ፖለቲከኞች ሊሞላ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የኬንያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን መደጋፍ በሚመለከት መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት፤ መሰል የፖለቲከኞች ተግባር አገሪቱ በሙስና ላይ እያካሄደች ያለውን ጦርነት አደጋ ውስጥ የሚጥል ነው ብለዋል። ፍሬድ ማቲያንጊ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦች ሥልጣን ቢጨብጡ እራሳቸውን ለመከላከል ሲሉ የአገሪቱን ሕግ እና መመሪያዎችን ሊቀይሩ ይችላሉም ብለዋል። በኬንያ ከዚህ ቀደም በነበሩ ምርጫዎች ዕጩዎች ለመመረጥ ከሚያስተዋውቋቸው ርዕዮተ ዓለሞች ይልቅ ዝናቸው እና ለምርጫ ወጪ የሚደርጉት የገንዘብ መጠን በውጤት ላይ ለውጥ ያመጣል። ከ22 ሚሊዮን በላይ መራጮች ለተመዘገቡበት ምርጫ ማስፈጸሚያ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር 400 ሚሊዮን ዶላር በጀት መድባለች። ይህ ገንዘብ ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው ተብሏል። ኬንያውያን ከሳምንት በኋላ ለሁለት የሥልጣን ዘመናት አገሪቱን ያስተዳደሩትን ኡሁሩ ኬንያታን የሚተካ አዲስ ፕሬዝዳንት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን እና የግዛት አስተዳዳሪዎችን ይመርጣሉ። ኬንያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት በምክትል ፕሬዝዳንቱ ዊሊያም ሩቶና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ መካከል ጠንካራ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cq5vdxky4qyo |
2health
| በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ6 ሺህ በላይ ሆነ | በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስድስት ሺህ ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ባለፉት ጥቂት ወራት በአገሪቱ ውስጥ በወረርሽኙ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ መጨመሩን በየዕለቱ የሚወጣው መረጃ የመለክታል። የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ እንደተናገሩት በኮሮናቫይረስ ተይዘው ለሞት ከተዳረጉት ሰዎች መካከል ሁሉም በሚባል ደረጃ ያልተከተቡ ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ ከሰኔ ወር አጋማሽ ጀምሮ እሰከ ነሐሴ ወር አጋማሽ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በወረርሽኙ ከሞቱ ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ ብቻ የመጀመሪያውን የኮቪድ መከላከያ ክትባት የወሰደ ሲሆን ሌሎቹ በሙሉ ያልተከተቡ መሆናቸው ተገልጿል። በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወደ ሦስት ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች መከላከያ ክትባቱን ማግኘታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል። በሽታው በአገሪቱ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ ለሞት የተዳረጉ ሰዎች አሃዝ አስከ ትላንት ድረስ ከስድስት ሺህ በታች የነበረ ሲሆን ሰኞ ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም 36 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 6026 ደርሷል። የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበሽታው የሚያዙ፣ በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ለመጨመሩ በአገሪቱ ውስጥ አደገኛው የዴልታ ዝርያ መኖሩ፣ በአንድ ስፍራ በብዛት የሚደረጉ መሰባሰቦችና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን ጨምሮ የበሽታውን የመከላከያ መመሪያዎች በአግባቡ ተግባራዊ አለማድረግ ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ጨምረውም በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑንና ባለፈው ሳምንት ብቻ 308 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ይህም ወረርሽኙ ከበኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ ከፍተኛው የሞት አሃዝ ሆኖ እንደተመዘገበ ሚኒስትሯ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በየዕለቱ በአማካይ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የሚረጋገጥ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት በየቀኑ በአማካይ 44 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል። በአገሪቱ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምረመራ መደረግ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ አስከ ትናንት ድረስ 3,557,710 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው በ355,001ዱ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህ ውስጥም 324,450ው ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን 6,026ቱ ደግሞ ህይወታቸው ማለፉንም የጤና ሚኒስቴር አመልክቷል። | በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ6 ሺህ በላይ ሆነ በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስድስት ሺህ ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ባለፉት ጥቂት ወራት በአገሪቱ ውስጥ በወረርሽኙ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ መጨመሩን በየዕለቱ የሚወጣው መረጃ የመለክታል። የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ እንደተናገሩት በኮሮናቫይረስ ተይዘው ለሞት ከተዳረጉት ሰዎች መካከል ሁሉም በሚባል ደረጃ ያልተከተቡ ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ ከሰኔ ወር አጋማሽ ጀምሮ እሰከ ነሐሴ ወር አጋማሽ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በወረርሽኙ ከሞቱ ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ ብቻ የመጀመሪያውን የኮቪድ መከላከያ ክትባት የወሰደ ሲሆን ሌሎቹ በሙሉ ያልተከተቡ መሆናቸው ተገልጿል። በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወደ ሦስት ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች መከላከያ ክትባቱን ማግኘታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል። በሽታው በአገሪቱ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ ለሞት የተዳረጉ ሰዎች አሃዝ አስከ ትላንት ድረስ ከስድስት ሺህ በታች የነበረ ሲሆን ሰኞ ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም 36 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 6026 ደርሷል። የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበሽታው የሚያዙ፣ በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ለመጨመሩ በአገሪቱ ውስጥ አደገኛው የዴልታ ዝርያ መኖሩ፣ በአንድ ስፍራ በብዛት የሚደረጉ መሰባሰቦችና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን ጨምሮ የበሽታውን የመከላከያ መመሪያዎች በአግባቡ ተግባራዊ አለማድረግ ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ጨምረውም በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑንና ባለፈው ሳምንት ብቻ 308 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ይህም ወረርሽኙ ከበኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ ከፍተኛው የሞት አሃዝ ሆኖ እንደተመዘገበ ሚኒስትሯ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በየዕለቱ በአማካይ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የሚረጋገጥ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት በየቀኑ በአማካይ 44 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል። በአገሪቱ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምረመራ መደረግ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ አስከ ትናንት ድረስ 3,557,710 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው በ355,001ዱ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህ ውስጥም 324,450ው ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን 6,026ቱ ደግሞ ህይወታቸው ማለፉንም የጤና ሚኒስቴር አመልክቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58858520 |
3politics
| ጆ ባይደን የካፒቶል ሒል ነውጠኞችን እና ትራምፕን አወገዙ | ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የካፒቶል ሒል ነውጠኞችን እና አውራቸውን ዶናልድ ትራምፕን አወገዙ። ፕሬዝዳንቱ በካፒቶል ሒል ቅጥር ባደረጉት ንግግር ነውጠኞቹ ‹የአሜሪካን ዲሞክራሲ ጉሮሮ ላይ ቢላ የሰነቀሩ› ሲሉ በጠንካራ ቃላት አውግዘዋቸዋል። የባይደን ንግግር በቀጥታ ለሰፊው የአሜሪካ ሕዝብ ተላልፏል። ጆ ባይደን የጥር 6 የካፒቶል ሒል አመጽን አንደኛ ዓመት መታሰቢያን በማስመልከት ነው ይህን ንግግር ያደረጉት። የዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ልክ የትናንትና አንድ ዓመት ነበር የአስተዳደር ሕንጻና የሕዝብ እንደራሴዎች መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚገኝበትን፣ የአሜሪካ የዲሞክራሲ ምልክት ተደርጎ የሚታየውን ካፒቶል ሒልን በኃይል በመውረር ያልታሰበ ጥቃት የፈጸሙት። በወቅቱ የአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴዎች የጆ ባይደንን ምርጫ ለማጽደቅ ሸንጎ ላይ ነበሩ። ይህ ዓይነቱ ክስተት በአሜሪካ ምድር ይሆናል ተብሎ ያልተጠበቀ ስለነበረ ድርጊቱ ዓለምን አስደንግጦ ነበር። ትናንት ሐሙስ ጆ ባይደን ንግግራቸውን ካደረጉ ከሰዓታት በኋላ ተቀዳሚያቸው የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ቁጣ የተቀላቀለበት የመልስ መግለጫ አውጥተዋል። የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ይህን ትራምፕና ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው ፈጸሙት በሚባለው ያልተገባ ድርጊት ለማውገዝ፣ ዕለቱንም ለማሰብ የተለያዩ የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓቶችን አዘጋጅተዋል። በርካታ የሕዝብ እንደራሴዎችም ዕለቱን ለማሰብ በሚዘጋጁ መሰናዶዎች በዕለቱ ያዩትን እና የታዘቡትን ለሕዝብ ያጋራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተዋቀረው ሀቅ አፈላላጊ ቡድን በዚህ ዕለት የዛሬ ዓመት በትክክል ምን እንደተፈጠረና ማንስ ተጠያቂ መደረግ እንዳለበት አሁንም እየመረመረ ይገኛል። እስከ አሁን 700 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በዚህ በጠንካራ ቃላት በታጀበው የትናንቱ የመታሰቢያ ንግግራቸው ጆ ባይደን ትራምፕን ‹በአፍቅሮተ- ራሰ የተሞላ ሰውዬ› ሲሉ አብጠልጥለዋቸዋል። "እሱ ከአሜሪካ ዲሞክራሲ ይልቅ ግድ የሚለው የራሱ አለልክ የተወጠረ ምሥለ-ራስ ነበር፤ ይህ ምሥለ ራስ ደግሞ በሽንፈቱ የተነሳ ቆስሎ ነበር" ሲሉ ዶናልድ ትራም ያን አመጽ የቀሰቀሱት በራስ ወዳድነትና አልሸነፍ ባይነት የተነሳ እንደሆነ አመላክተዋል። | ጆ ባይደን የካፒቶል ሒል ነውጠኞችን እና ትራምፕን አወገዙ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የካፒቶል ሒል ነውጠኞችን እና አውራቸውን ዶናልድ ትራምፕን አወገዙ። ፕሬዝዳንቱ በካፒቶል ሒል ቅጥር ባደረጉት ንግግር ነውጠኞቹ ‹የአሜሪካን ዲሞክራሲ ጉሮሮ ላይ ቢላ የሰነቀሩ› ሲሉ በጠንካራ ቃላት አውግዘዋቸዋል። የባይደን ንግግር በቀጥታ ለሰፊው የአሜሪካ ሕዝብ ተላልፏል። ጆ ባይደን የጥር 6 የካፒቶል ሒል አመጽን አንደኛ ዓመት መታሰቢያን በማስመልከት ነው ይህን ንግግር ያደረጉት። የዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ልክ የትናንትና አንድ ዓመት ነበር የአስተዳደር ሕንጻና የሕዝብ እንደራሴዎች መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚገኝበትን፣ የአሜሪካ የዲሞክራሲ ምልክት ተደርጎ የሚታየውን ካፒቶል ሒልን በኃይል በመውረር ያልታሰበ ጥቃት የፈጸሙት። በወቅቱ የአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴዎች የጆ ባይደንን ምርጫ ለማጽደቅ ሸንጎ ላይ ነበሩ። ይህ ዓይነቱ ክስተት በአሜሪካ ምድር ይሆናል ተብሎ ያልተጠበቀ ስለነበረ ድርጊቱ ዓለምን አስደንግጦ ነበር። ትናንት ሐሙስ ጆ ባይደን ንግግራቸውን ካደረጉ ከሰዓታት በኋላ ተቀዳሚያቸው የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ቁጣ የተቀላቀለበት የመልስ መግለጫ አውጥተዋል። የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ይህን ትራምፕና ነውጠኛ ደጋፊዎቻቸው ፈጸሙት በሚባለው ያልተገባ ድርጊት ለማውገዝ፣ ዕለቱንም ለማሰብ የተለያዩ የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓቶችን አዘጋጅተዋል። በርካታ የሕዝብ እንደራሴዎችም ዕለቱን ለማሰብ በሚዘጋጁ መሰናዶዎች በዕለቱ ያዩትን እና የታዘቡትን ለሕዝብ ያጋራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተዋቀረው ሀቅ አፈላላጊ ቡድን በዚህ ዕለት የዛሬ ዓመት በትክክል ምን እንደተፈጠረና ማንስ ተጠያቂ መደረግ እንዳለበት አሁንም እየመረመረ ይገኛል። እስከ አሁን 700 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በዚህ በጠንካራ ቃላት በታጀበው የትናንቱ የመታሰቢያ ንግግራቸው ጆ ባይደን ትራምፕን ‹በአፍቅሮተ- ራሰ የተሞላ ሰውዬ› ሲሉ አብጠልጥለዋቸዋል። "እሱ ከአሜሪካ ዲሞክራሲ ይልቅ ግድ የሚለው የራሱ አለልክ የተወጠረ ምሥለ-ራስ ነበር፤ ይህ ምሥለ ራስ ደግሞ በሽንፈቱ የተነሳ ቆስሎ ነበር" ሲሉ ዶናልድ ትራም ያን አመጽ የቀሰቀሱት በራስ ወዳድነትና አልሸነፍ ባይነት የተነሳ እንደሆነ አመላክተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/59905057 |
5sports
| የዓለም ዋንጫ፡ አርጀንቲና ወደ ቀጣዩ ዙርፍ ስታልፍ ያሸነፈቻት ሳዑዲ በጊዜ ተሰናብታለች | አርጀንቲና በኳታር የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ የደረሰባትን ሽንፈት በመቀልበስ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ችላለች። የሊዮኔል ሜሲ ሃገር ምድቡን በአንደኝነት በመምራት ጭምር ነው ለማለፍ የቻለችው። አርንጀንቲና ትላንት ምሽት ፖላንድን 2 ለ 0 በማሸነፍ ነው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈችው። አርጀንቲና አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ ያገኘችውን ፍጹም ቅጣት ምት አምበሉ ሊዮኔል ሜሲ ሳይጠቀምብት ቀርቷል። ማክ አሊስተር አርጀንቲናን ቀዳሚ የምታድርገውን ጎል በ46ኛው ደቂቃ አስቆጠረ። አልቫሬዝ ደግሞ ሁለተኛዋን ኳስ ከመረብ አሳርፏል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ አርጀንቲናን በማሸነፍ ድንቅ አጀማመር ያደረገችው ሳዑዲ አረቢያ ፍጻሜዋ አላማረላትም። በሜክሲኮ 2 ለ 1 ተሰንፋለች። ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ተጭና የተጫወተችው ሜክሲኮ የበላይ ለመሆን ችላለች። ሄነሪ ማርቲን የመጀሪያዋን ጎል በ47ኛው ደቂቃ አስቆጠረ። ሊዊስ ቻቬዝ ደግሞ ሌላኛዋን ጎል ለሜክሲኮ አስቆጥሯል። ጨዋታው በዚሁ ውጤት ተጠናቀቀ ሲባል ሳዑዲ ባለቀ ሰዓት በሳሌም አል ዳውሳሪ አንድ ጎል አስቆጥራለች። አርጀንቲና ምድቡን በስድስት ነጥብ አንደኛ በመሆን አጠናቃለች። ፖላንድ እና ሜክሲኮ አራት አራት ነጥብ ቢይዙም በጎል ክፍያ ፖላንድ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ሳዑዲ አርጀንቲናን በማሸነፍ ባገኘችው ሦስት ነጥብ ምድቡን በአራተኝነት አጠናቃለች። በምድብ አራት ደግሞ ቱኒዝያ ፈረንሳይን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች። በርካታ የመጀመሪያ ተሰላፊ ተጫዋቾቿን ቀይራ ወደ ሜዳ የገባችው ፈረንሳይ በቱኒዝያ ተሸንፋለች። ዋህቢ ካዚ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ያሳረፈ ተጫዋች ሆኗል። ፈረንሳይ ቋሚ ተጫዋቾቿን ቀይራ ውጤቱን ለመቀልበስ ብትሞክርም አልተሳካላትም። አንቶኒ ግሪዝማን ባለቀ ሰዓት ያስቆጠራት ጎል ከጨዋታ ውጭ በመሆኑ ተሽራለች። ድሉ በርካታ በፈረንሳይ የተወለዱ ተጫዋቾችን ላሰለፈችው ቱኒዝያ ጣፋጭ ሆኖ አምሽቷል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ አውስትራሊያ እና ዴንማርክ ተገናኝተዋል። አውስትራሊያ በ60ኛው ደቂቃ በማቲው ሌኪ ብቸኛ ጎል ለማሸነፍ ችላለች። ከምድቡ ቀድማ ማለፏን ያረጋገጠቸው ፈረንሳይ በስድስት ነጥብ አንደኛ ለመሆን በቅታለች። ትላንት ያሸነፈችው አውስትራሊያ በተመሳሳይ ስድስት ነጥብ ሁለተኛ ሆና ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች። ቱኒዝያ በአራት ነጥብ ሦስተኛ ስትሆን ዴንማርክ በአንድ ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ሆነው ጨርሰዋል። በጥሎ ማለፉ የምድብ ሦስት እና አራት ቡድኖች የሚገናኙ ይሆናል። አርጀንቲና ከአውስትራሊያ ቅዳሜ ምሽት ትጫወታለች። ፈረንሳይ ደግሞ ፖላንድን እሑድ ታስተናግዳለች። የምድብ አምስት እና ስድስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ። 12፡00 ሰዓት ላይ ክሮሽያ እና ቤልጂየም እንዲሁም ካናዳ እና ሞሮኮ ይገናኛሉ። ምድብ ስድስትን ክሮሺያ በአራት ነጥብ ትመራለች። ሞሮኮ በተመሳሳይ አራት ነጥብ ሁለተኛ ናት። ቤልጂየም ሦስት ነጥብ ሲኖራት ካናዳ ያለምንም ነጥብ በምድቡ ግርጌ ላይ ትገኛለች። ክሮሺያ፣ ሞሮኮ እና ቤልጂየም ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋ አላቸው። ምሽት 4፡00 ሰዓት ደግሞ ጃፓን ከስፔን እንዲሁም ኮስታሪካ ከጀርመን ይጫወታሉ። ምድብ አምስትን ስፔን በአራት ነጥብ ትመራለች። ጃፓን እና ኮስታሪካ አራት አራት ነጥብ አላቸው። ጀርመን በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች። የዚህ ምድብ አራቱም ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋ አላቸው። | የዓለም ዋንጫ፡ አርጀንቲና ወደ ቀጣዩ ዙርፍ ስታልፍ ያሸነፈቻት ሳዑዲ በጊዜ ተሰናብታለች አርጀንቲና በኳታር የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ የደረሰባትን ሽንፈት በመቀልበስ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ችላለች። የሊዮኔል ሜሲ ሃገር ምድቡን በአንደኝነት በመምራት ጭምር ነው ለማለፍ የቻለችው። አርንጀንቲና ትላንት ምሽት ፖላንድን 2 ለ 0 በማሸነፍ ነው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈችው። አርጀንቲና አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ ያገኘችውን ፍጹም ቅጣት ምት አምበሉ ሊዮኔል ሜሲ ሳይጠቀምብት ቀርቷል። ማክ አሊስተር አርጀንቲናን ቀዳሚ የምታድርገውን ጎል በ46ኛው ደቂቃ አስቆጠረ። አልቫሬዝ ደግሞ ሁለተኛዋን ኳስ ከመረብ አሳርፏል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ አርጀንቲናን በማሸነፍ ድንቅ አጀማመር ያደረገችው ሳዑዲ አረቢያ ፍጻሜዋ አላማረላትም። በሜክሲኮ 2 ለ 1 ተሰንፋለች። ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ተጭና የተጫወተችው ሜክሲኮ የበላይ ለመሆን ችላለች። ሄነሪ ማርቲን የመጀሪያዋን ጎል በ47ኛው ደቂቃ አስቆጠረ። ሊዊስ ቻቬዝ ደግሞ ሌላኛዋን ጎል ለሜክሲኮ አስቆጥሯል። ጨዋታው በዚሁ ውጤት ተጠናቀቀ ሲባል ሳዑዲ ባለቀ ሰዓት በሳሌም አል ዳውሳሪ አንድ ጎል አስቆጥራለች። አርጀንቲና ምድቡን በስድስት ነጥብ አንደኛ በመሆን አጠናቃለች። ፖላንድ እና ሜክሲኮ አራት አራት ነጥብ ቢይዙም በጎል ክፍያ ፖላንድ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ሳዑዲ አርጀንቲናን በማሸነፍ ባገኘችው ሦስት ነጥብ ምድቡን በአራተኝነት አጠናቃለች። በምድብ አራት ደግሞ ቱኒዝያ ፈረንሳይን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች። በርካታ የመጀመሪያ ተሰላፊ ተጫዋቾቿን ቀይራ ወደ ሜዳ የገባችው ፈረንሳይ በቱኒዝያ ተሸንፋለች። ዋህቢ ካዚ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ያሳረፈ ተጫዋች ሆኗል። ፈረንሳይ ቋሚ ተጫዋቾቿን ቀይራ ውጤቱን ለመቀልበስ ብትሞክርም አልተሳካላትም። አንቶኒ ግሪዝማን ባለቀ ሰዓት ያስቆጠራት ጎል ከጨዋታ ውጭ በመሆኑ ተሽራለች። ድሉ በርካታ በፈረንሳይ የተወለዱ ተጫዋቾችን ላሰለፈችው ቱኒዝያ ጣፋጭ ሆኖ አምሽቷል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ አውስትራሊያ እና ዴንማርክ ተገናኝተዋል። አውስትራሊያ በ60ኛው ደቂቃ በማቲው ሌኪ ብቸኛ ጎል ለማሸነፍ ችላለች። ከምድቡ ቀድማ ማለፏን ያረጋገጠቸው ፈረንሳይ በስድስት ነጥብ አንደኛ ለመሆን በቅታለች። ትላንት ያሸነፈችው አውስትራሊያ በተመሳሳይ ስድስት ነጥብ ሁለተኛ ሆና ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች። ቱኒዝያ በአራት ነጥብ ሦስተኛ ስትሆን ዴንማርክ በአንድ ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ሆነው ጨርሰዋል። በጥሎ ማለፉ የምድብ ሦስት እና አራት ቡድኖች የሚገናኙ ይሆናል። አርጀንቲና ከአውስትራሊያ ቅዳሜ ምሽት ትጫወታለች። ፈረንሳይ ደግሞ ፖላንድን እሑድ ታስተናግዳለች። የምድብ አምስት እና ስድስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ። 12፡00 ሰዓት ላይ ክሮሽያ እና ቤልጂየም እንዲሁም ካናዳ እና ሞሮኮ ይገናኛሉ። ምድብ ስድስትን ክሮሺያ በአራት ነጥብ ትመራለች። ሞሮኮ በተመሳሳይ አራት ነጥብ ሁለተኛ ናት። ቤልጂየም ሦስት ነጥብ ሲኖራት ካናዳ ያለምንም ነጥብ በምድቡ ግርጌ ላይ ትገኛለች። ክሮሺያ፣ ሞሮኮ እና ቤልጂየም ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋ አላቸው። ምሽት 4፡00 ሰዓት ደግሞ ጃፓን ከስፔን እንዲሁም ኮስታሪካ ከጀርመን ይጫወታሉ። ምድብ አምስትን ስፔን በአራት ነጥብ ትመራለች። ጃፓን እና ኮስታሪካ አራት አራት ነጥብ አላቸው። ጀርመን በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች። የዚህ ምድብ አራቱም ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋ አላቸው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/clkzl9zjrzno |