label
class label
4 classes
headline
stringlengths
17
80
text
stringlengths
1
16.8k
headline_text
stringlengths
28
16.8k
url
stringlengths
36
49
0business
አውስትራሊያ ፡ የሒትለርን ቪዲዮ በመጠቀም ፌስቡክ ላይ በአለቆቹ የተሳለቀው ሠራተኛ 200 ሺህ ዶላር ተሰጠው
ስኮት ትሬሲ ይባላል፡፡ የግዙፉ የብሪቲሽ ፔትሮሊየም ኩባንያ (ቢፒ) ሠራተኛው ነበር፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት ከዕለታት በአንዱ ከሥራ ይባረራል፡፡ የተባረረው አርፍዶ ሥራ በመግባቱ ወይም እንዝህላል ሆኖ አይደለም፡፡ የገዛ መሥሪያ ቤቱ ላይ በመሳለቁ እንጂ፡፡ የተሳለቀበት መንገድ ግን ሳያስበው ዝነኛ አድርጎታል፡፡ ሰውየው በፌስቡክ ለቅርብ ጓደኞቹ አንድ ቪዲዮ ያጋራል፡፡ ቪዲዮው የተወሰደው 2004 ዓ.ም ላይ ዝነኛ ከነበረው ዳውንፎል (Downfall) የሆሊውድ ፊልም ላይ የተቀናበረ ነው፡፡ በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ በሰራተኛውና በአለቆች መካከል የነበረውን የደመወዝ ይጨመርልን ጥያቄና አታካራ ተመርኩዞ አለቆቹ ልክ እንደ ሂትለር ሆነው ሲቆጡ የሚያሳይ ቅንብር ነበር የሰራው፡፡ ይህንን ስላቀ-ምሥል (meme) ለቅርብ የፌስቡክ ጓደኞቹ ብቻ በማጋራቱ አለቆቹ ሰምተው በመቆጣታቸው መሥሪያ ቤቱ ሰውየውን ከሥራ ያባርረዋል፡፡ ሰውየው በዚህ ይናደድና ኩባንያውን ፍርድ ቤት ይገትረዋል፡፡ እንዴት በፌስቡክ ላይ ለጓደኞቼ በቀለድኩት ጥሩ ቀልድ ከሥራ እባረራለሁ ሲል ይከሳል፡፡ በቅድሚያ የመሥሪያ ቤቱ የሰራተኛ ማኅበር ጉዳዩ በሽምግልናና ግልግል ዳኝነት ይታይ ይልና ይኸው ይደረጋል፡፡ የግልግል ዳኝነቱ የሰውየው መባረር ትክክል ነው ብሎ ይፈርዳል፡፡ ሚስተር ትሬሲ ድሮም እናንተን ማመን ይልና ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዞት ይሄዳል፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ጠበቃ አቁሞ ሽንጡን ገትሮ ከተከራከረ በኋላ ፍርድ ቤት ሰውየው ያለ አግባብ ነው የተባረረው ሲል ይበይንለታል፡፡ በዚህም የተነሳ የብሪታኒያ ፔትሮል ኩባንያ (ቢፒ) ለሰራተኛው 200ሺህ ዶላር እንዲከፍለው ይወስንለታል፡፡ ይህም ላለፉት ሁለት ዓመታት ያጣውን ደመወዙንና ጥቅማጥቅሙን ጨምሮ የጡረታ አበሉንና የሞራል ጉዳት ካሳን ያካተተ ነው፡፡ ቢፒ የሚለው ሰውየው የሂትለርን ቪዲዮ (ምንም እንኳ ከፊልም የተወሰደ ቢሆንም) ተጠቅሞ በመሥሪያ ቤቱ ላይ ምሥለ-ስላቅ ሰርቶ በፌስቡክ ገጽ መለጠፉ ‹አሳፋሪም ነውርም› ነው፡፡ ከአንድ ትጉህ፣ ጨዋ ሠራተኛም የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ሚስተር ትሬሲ በበኩሉ እኔ ይህን ያደረኩት መጥፎ ልቦና ይዤ ሳይሆን ለቀልድ ነው፤ ቀልድ ደግሞ ለጤና ጥሩ ነው ብሏል፡፡ ፌዴራል ፍርድ ቤት በሰጠው ብይን ምሥለ-ስላቁ ላይ ያለው ሂትለር የቢፒ መሥሪያ ቤት አለቆችን አይወክልም፡፡ ስለዚህ ሚስተር ትሬሲ ነውረኛ ሊባል አይችልም ብሏል፡፡ ሰኞ ወደ ሥራ የተመለሰው የነዳጅ አውጪ ሰራተኛው ሚስተር ትሬሲ አካውንቱ ውስጥ 200ሺህ ዶላሩ ከገባለት በኋላ ዘንጦ ነው፡፡ ቢፒ ለሚስተር ትሬሲ 150 ሺህ ዶላር ብቻ ይበቃዋል፣ ምክንያቱም ሰራተኛው ባሰራጨው ቪዲዮ ስማችን ጎድፏል፣ በዚያ ላይ በፍርድ ቤት ክርክር ላይ ሳለ ሥራ ፈልጎ ማግኘት ይችል ነበር። በዚያን ጊዜ ለቦዘነው እኛ የመክፈል እዳ የለብንም ቢልም የሰራተኛው ጠበቃ በበኩሉ በዚያን ጊዜ ሥራ እንዳልፈለገ በምን አወቃችሁ ሲል ተከራክሯል፡፡ የግራ ቀኙን የሰማው ፍርድ ቤት ‹በቃ 200 ሺህ ዶላር› ለሰውየው ክፈሉት ብሏል፡፡ ገንዘቡ ሲሰላ ወደ ሳባት ሚሊዮን ብር ይጠጋል፡፡
አውስትራሊያ ፡ የሒትለርን ቪዲዮ በመጠቀም ፌስቡክ ላይ በአለቆቹ የተሳለቀው ሠራተኛ 200 ሺህ ዶላር ተሰጠው ስኮት ትሬሲ ይባላል፡፡ የግዙፉ የብሪቲሽ ፔትሮሊየም ኩባንያ (ቢፒ) ሠራተኛው ነበር፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት ከዕለታት በአንዱ ከሥራ ይባረራል፡፡ የተባረረው አርፍዶ ሥራ በመግባቱ ወይም እንዝህላል ሆኖ አይደለም፡፡ የገዛ መሥሪያ ቤቱ ላይ በመሳለቁ እንጂ፡፡ የተሳለቀበት መንገድ ግን ሳያስበው ዝነኛ አድርጎታል፡፡ ሰውየው በፌስቡክ ለቅርብ ጓደኞቹ አንድ ቪዲዮ ያጋራል፡፡ ቪዲዮው የተወሰደው 2004 ዓ.ም ላይ ዝነኛ ከነበረው ዳውንፎል (Downfall) የሆሊውድ ፊልም ላይ የተቀናበረ ነው፡፡ በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ በሰራተኛውና በአለቆች መካከል የነበረውን የደመወዝ ይጨመርልን ጥያቄና አታካራ ተመርኩዞ አለቆቹ ልክ እንደ ሂትለር ሆነው ሲቆጡ የሚያሳይ ቅንብር ነበር የሰራው፡፡ ይህንን ስላቀ-ምሥል (meme) ለቅርብ የፌስቡክ ጓደኞቹ ብቻ በማጋራቱ አለቆቹ ሰምተው በመቆጣታቸው መሥሪያ ቤቱ ሰውየውን ከሥራ ያባርረዋል፡፡ ሰውየው በዚህ ይናደድና ኩባንያውን ፍርድ ቤት ይገትረዋል፡፡ እንዴት በፌስቡክ ላይ ለጓደኞቼ በቀለድኩት ጥሩ ቀልድ ከሥራ እባረራለሁ ሲል ይከሳል፡፡ በቅድሚያ የመሥሪያ ቤቱ የሰራተኛ ማኅበር ጉዳዩ በሽምግልናና ግልግል ዳኝነት ይታይ ይልና ይኸው ይደረጋል፡፡ የግልግል ዳኝነቱ የሰውየው መባረር ትክክል ነው ብሎ ይፈርዳል፡፡ ሚስተር ትሬሲ ድሮም እናንተን ማመን ይልና ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዞት ይሄዳል፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ጠበቃ አቁሞ ሽንጡን ገትሮ ከተከራከረ በኋላ ፍርድ ቤት ሰውየው ያለ አግባብ ነው የተባረረው ሲል ይበይንለታል፡፡ በዚህም የተነሳ የብሪታኒያ ፔትሮል ኩባንያ (ቢፒ) ለሰራተኛው 200ሺህ ዶላር እንዲከፍለው ይወስንለታል፡፡ ይህም ላለፉት ሁለት ዓመታት ያጣውን ደመወዙንና ጥቅማጥቅሙን ጨምሮ የጡረታ አበሉንና የሞራል ጉዳት ካሳን ያካተተ ነው፡፡ ቢፒ የሚለው ሰውየው የሂትለርን ቪዲዮ (ምንም እንኳ ከፊልም የተወሰደ ቢሆንም) ተጠቅሞ በመሥሪያ ቤቱ ላይ ምሥለ-ስላቅ ሰርቶ በፌስቡክ ገጽ መለጠፉ ‹አሳፋሪም ነውርም› ነው፡፡ ከአንድ ትጉህ፣ ጨዋ ሠራተኛም የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ሚስተር ትሬሲ በበኩሉ እኔ ይህን ያደረኩት መጥፎ ልቦና ይዤ ሳይሆን ለቀልድ ነው፤ ቀልድ ደግሞ ለጤና ጥሩ ነው ብሏል፡፡ ፌዴራል ፍርድ ቤት በሰጠው ብይን ምሥለ-ስላቁ ላይ ያለው ሂትለር የቢፒ መሥሪያ ቤት አለቆችን አይወክልም፡፡ ስለዚህ ሚስተር ትሬሲ ነውረኛ ሊባል አይችልም ብሏል፡፡ ሰኞ ወደ ሥራ የተመለሰው የነዳጅ አውጪ ሰራተኛው ሚስተር ትሬሲ አካውንቱ ውስጥ 200ሺህ ዶላሩ ከገባለት በኋላ ዘንጦ ነው፡፡ ቢፒ ለሚስተር ትሬሲ 150 ሺህ ዶላር ብቻ ይበቃዋል፣ ምክንያቱም ሰራተኛው ባሰራጨው ቪዲዮ ስማችን ጎድፏል፣ በዚያ ላይ በፍርድ ቤት ክርክር ላይ ሳለ ሥራ ፈልጎ ማግኘት ይችል ነበር። በዚያን ጊዜ ለቦዘነው እኛ የመክፈል እዳ የለብንም ቢልም የሰራተኛው ጠበቃ በበኩሉ በዚያን ጊዜ ሥራ እንዳልፈለገ በምን አወቃችሁ ሲል ተከራክሯል፡፡ የግራ ቀኙን የሰማው ፍርድ ቤት ‹በቃ 200 ሺህ ዶላር› ለሰውየው ክፈሉት ብሏል፡፡ ገንዘቡ ሲሰላ ወደ ሳባት ሚሊዮን ብር ይጠጋል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-53732694
2health
ኤርትራውያን በካንሰር ለሚሰቃይ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር አሰባሰቡ
በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን እና ትውልደ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች በሕመም ለሚሳቃይ አንድ ኤርትራዊ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በላይ አሰባሰቡ። በኤርትራ ነዋሪ የሆነው እና የስድስት ልጆች አባት የሆነው ዮናስ ፀጋይ፤ ባለፈው አንድ ዓመት ሆድኪን ሊምፎማ በተባለ የደም ካንሰር አይነት ሲሰቃይ ቆይቷል። 'ዮናስ ፀጋይን እና ቤተሰቡን ይርዱ' በሚል በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የካናዳ ዶላር ማሰባሰብ ተችሏል። ለዮናስ የተሰባሰበው መዋጮ ማክሰኞ ጥር 09 ከሰዓት ላይ 637 ሺህ የካናዳ ዶላር (ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ) ደርሷል። በጎፈንድሚ ገጽ ላይ ተያይዞ በወጣው የእርዳታ ተማጽኖ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ፤ ዮናስ ፀጋይ በደም ካንሰር ምክንያት ከፍተኛ ሕመም ውስጥ እንደሚገኝ እና ሰዎች ለሕክምና ወጪ መዋጮ እንዲያደርጉለት ሲማጸን ይታያል። በስድስት ልጆቹ ተከቦ የሚታየው ዮናስ፤ በሕመሙ ምክንያት ሰውነቱ አብጦ እና እጆቹን በኃይል ሲያሽ ይታያል። ለዮናስ የቀረበው የእርዳታ አድርጉ ጥሪ በርካታ ምላሾችን በማግኘት በጎፈንዲሚ ገጽ ላይ ቀዳሚ ደረጃን ይዟል። ዮናስ በኤርትራ ወደ ጤና ተቋማት ቢሄድም ለተጨማሪ ሕክምና ከአገር ውጭ መጓዝ እንዳለበት ተነግሮታል። በድህነት ውስጥ የሚኖረው ዮናስ የሕክምና ወጪውን መሸፈን አለመቻሉን በመግለጽ አንድ የዩቲዩብ ገጽ የስድስት ልጆቹ አባት የሆነው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ለሌሎች አጋርቷል። ዮናስን ለማገዝ የጎፈንድሚ ገጽ በተከፈተ በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን ከ350 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ በማዋጣት ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል። የእርዳታ ገንዘብ አሰባሳቢዎች መካከል አንዱ የሆነው ዮሴፍ ወርቄ እንዲህ በፍጥነት በርካቶችን ያሳተፈ መዋጮ አጋጥሞት እንደማያውቅ ለቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ተናግሯል። አስተባባሪው እንደሚለው በሕመም የሚሰቃየው የዮናስ ተማጽእኖ የበርካታ ሰዎችን ልብ ተነክቷል። እንድ የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አግልግሎት (ኤንኤችኤስ) ድረ-ገጽ ከሆነ ዮናስ የሚሰቃይበት ሆድኪን ሊምፎማ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም ከነጭ የደም ሴል ጋር የተገናኘ የደም ካንስር አይነት ነው። ተቋሙ እንደሚለው ከሆነ ይህ የካንሰር ሕመም በጨረር ሕክምና (በኬሞቴራፒ) እንዲሁም በራዲዮቴራፒ ሕክምና ሊድን ይችላል።
ኤርትራውያን በካንሰር ለሚሰቃይ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር አሰባሰቡ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን እና ትውልደ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች በሕመም ለሚሳቃይ አንድ ኤርትራዊ ግለሰብ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በላይ አሰባሰቡ። በኤርትራ ነዋሪ የሆነው እና የስድስት ልጆች አባት የሆነው ዮናስ ፀጋይ፤ ባለፈው አንድ ዓመት ሆድኪን ሊምፎማ በተባለ የደም ካንሰር አይነት ሲሰቃይ ቆይቷል። 'ዮናስ ፀጋይን እና ቤተሰቡን ይርዱ' በሚል በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የካናዳ ዶላር ማሰባሰብ ተችሏል። ለዮናስ የተሰባሰበው መዋጮ ማክሰኞ ጥር 09 ከሰዓት ላይ 637 ሺህ የካናዳ ዶላር (ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ) ደርሷል። በጎፈንድሚ ገጽ ላይ ተያይዞ በወጣው የእርዳታ ተማጽኖ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ፤ ዮናስ ፀጋይ በደም ካንሰር ምክንያት ከፍተኛ ሕመም ውስጥ እንደሚገኝ እና ሰዎች ለሕክምና ወጪ መዋጮ እንዲያደርጉለት ሲማጸን ይታያል። በስድስት ልጆቹ ተከቦ የሚታየው ዮናስ፤ በሕመሙ ምክንያት ሰውነቱ አብጦ እና እጆቹን በኃይል ሲያሽ ይታያል። ለዮናስ የቀረበው የእርዳታ አድርጉ ጥሪ በርካታ ምላሾችን በማግኘት በጎፈንዲሚ ገጽ ላይ ቀዳሚ ደረጃን ይዟል። ዮናስ በኤርትራ ወደ ጤና ተቋማት ቢሄድም ለተጨማሪ ሕክምና ከአገር ውጭ መጓዝ እንዳለበት ተነግሮታል። በድህነት ውስጥ የሚኖረው ዮናስ የሕክምና ወጪውን መሸፈን አለመቻሉን በመግለጽ አንድ የዩቲዩብ ገጽ የስድስት ልጆቹ አባት የሆነው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ለሌሎች አጋርቷል። ዮናስን ለማገዝ የጎፈንድሚ ገጽ በተከፈተ በመጀመሪያዎቹ 12 ሰዓታት ውስጥ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን ከ350 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ በማዋጣት ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል። የእርዳታ ገንዘብ አሰባሳቢዎች መካከል አንዱ የሆነው ዮሴፍ ወርቄ እንዲህ በፍጥነት በርካቶችን ያሳተፈ መዋጮ አጋጥሞት እንደማያውቅ ለቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ተናግሯል። አስተባባሪው እንደሚለው በሕመም የሚሰቃየው የዮናስ ተማጽእኖ የበርካታ ሰዎችን ልብ ተነክቷል። እንድ የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አግልግሎት (ኤንኤችኤስ) ድረ-ገጽ ከሆነ ዮናስ የሚሰቃይበት ሆድኪን ሊምፎማ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም ከነጭ የደም ሴል ጋር የተገናኘ የደም ካንስር አይነት ነው። ተቋሙ እንደሚለው ከሆነ ይህ የካንሰር ሕመም በጨረር ሕክምና (በኬሞቴራፒ) እንዲሁም በራዲዮቴራፒ ሕክምና ሊድን ይችላል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60041868
0business
ኤለን መስክ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን በልጦ የዓለማችን 2ኛው ቢሊየነር ሆነ
የቴክኖሎጂ ፈጣሪው ኤለን መስክ በአጭር ጊዜ ውስጥ የዓለማችን 2ኛው ቢሊየነር ሆነ። መስክ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን በልጦ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የተቀመጠው። የኤለን መስክ ሀብት በአጭር ጊዜ የተምዘገዘገው ቴስላ የተባለው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያው በስቶክ ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ ነው። ይህ ድንገተኛ የሀብት ጭማሪ የኤለን መስክን የሀብት መጠን ከ7 ቢሊዮን ወደ 128 ቢሊዮን አድርሶታል። የቢሊየነሮችን ዝርዝር የሚያስቀምጠው ብሉምበርግ እንደሚለው ከሆነ በዚህ ሰዓት ኤለን መስክን የሚበልጠው የዓለማችን ቁንጮ ሀብታም የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ ብቻ ነው። ቴስላ የአሌክትሪክ አምራች በአሜሪካ የስቶክ ገበያ ትልልቆቹን 500 ኩባንያዎች ደረጃ በሚያስቀምጠው ኤስ ኤንድ ፒ (S&P 500) ዝርዝር እንደሚገባ ባስታወቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው የሀብት ግስጋሴው በአስደንጋጭ መልኩ ሽቅብ የወጣው። የዚህን ዜና መውጣት ተከትሎ በርካታ ሰዎች የቴስላ መኪናን ድርሻ ለመግዛት ሽሚያ እንዲፈጠር አድርጓል። የቴስላ ኩባንያ ጠቅላላ ግምትም ግማሽ ትሪሊዮን ዶላር አድርሶታል። ይህን ተከትሎ ምንም እንኳ የኤለን መስክ ድርሻ በቴስላ ኩባንያ ውስጥ አነስተኛ ቢሆንም የሰውየው ሀብት ጣሪያ እንዲነካ ምክንያት ሆኗል። ቴስላ ኩባንያው በዓለም ላይ ከፍተኛ ዋጋ ከሚሰጠው መኪና አምራች ኩባንያ ዋንኛው ነው። ሆኖም ከቶዮታ፣ ቮልስ ዋገን እና ጄኔራል ሞተርስ ጋር ሲነጻጸር የሚያመርታቸው መኪናዎች ብዛት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ማክሰኞ ዕለት መስክ ጀርመን በነበረ ጊዜ የአውሮጳ የመኪና ገበያ ውስጥ መኪና በገፍ የማምረት ሥራ ውስጥ መግባት እንዴት አዋጭ እንደሆነ ሲያስረዳ ነበር። አሜሪካ ብዙ ሰዎች ትልልቅ መኪና መንዳት ነው ምርጫቸው፤ እዚህ አውሮጳ ግን ትንንሽ ናቸው መኪናዎች፥ ቴስላ በርከት ያለ መኪና በማምረት የዋጋ ተፎካካሪ መሆን የሚችል ይመስለኛል ብሏል መስክ። ቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ለተከታታይ ዓመታት ኪሳራን ሲያስመዘግብ ቆይቶ ከዚያ በኃላ ግን ላለፉት ለ5 ተከታታይ ሩብ ዓመታት ትርፋማ እየሆነ ቆይቷል። የትርፍ እድገቱንየኮቪድ ወረርሽኝም አልበገረውም። መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው ቴስላ በኤስ ኤንደ ኤስ የስቶክ ማርኬት ግማሽ ትሪሊዮን የሀብት ግምት ዋጋ ይዞ በመግባት የመጀመርያው ነው። ቢልጌትስ በዓለም የቢሊየኖች ተርታ ለዘመናት ይዞት የቆየውን መሪነት የተነጠቀው በፈረንጆች 2017 ሲሆን አዲሱ ቢሊየነር ደግሞ የአማዞኑ ቤዞስ ነበር። የቢል ጌትስ ሀብት 127.7 ቢሊየን ዶላር ነው፤ ሆኖም ገንዘቡን በብዛት ለበጎ አድራጎት ስለሚሰጥ እንጂ ከዚህ በላይ የሀብት ግምት ይኖረው ነበር ይላል ብሉምበርግ። የጄፍ ቤዞስ ሀብት አሁን ላይ 182 ቢሊየን ደርሶለታል። ቤዞስም እንደ መስክ ሁሉ በዚህ ዓመት ገቢው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮለታል። ይህም ወረርሽኙ የበይነ መረብ ግዢ እንዲፋፋም እድል በመፍጠሩ ነው። ኤለን መስክ ባለፈው ሳምንት የኮቪድ ተህዋሲ ሳይዘኝ አልቀረም ብሎ በትዊተር ሰሌዳው ጽፎ ነበር። መጠነኛ ምልክቶችን ሲያሳይ ነበር። ኤሎን መስክ በፈጠራት የጠፈር ታክሲ "ስፔስ ኤክስ" 4 የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ወደ ዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ የተሳፈሩት በቅርብ ሳምንት ነበር። ኤሎን መስስ ተወልዶ ያደገው በፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ ሲሆን በ17 ዓመቱ ወደ ካናዳ ካቀና በኃላ ለትምህርት በልውውጥ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም ወደ አሜሪካ ፔኒሲልቬኒያ ዩኒቨርስቲ ገባ። በዚያው አጋጣሚ ነው አሜሪካ የቀረው። አሁን ነዋሪነቱ በአሜሪካ ሎሳአንጀለስ ካሊፎርኒያ ውስጥ ነው። 49 ዓመቱ ሲሆን የ7 ልጆች አባትም ነው።
ኤለን መስክ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን በልጦ የዓለማችን 2ኛው ቢሊየነር ሆነ የቴክኖሎጂ ፈጣሪው ኤለን መስክ በአጭር ጊዜ ውስጥ የዓለማችን 2ኛው ቢሊየነር ሆነ። መስክ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን በልጦ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የተቀመጠው። የኤለን መስክ ሀብት በአጭር ጊዜ የተምዘገዘገው ቴስላ የተባለው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያው በስቶክ ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ ነው። ይህ ድንገተኛ የሀብት ጭማሪ የኤለን መስክን የሀብት መጠን ከ7 ቢሊዮን ወደ 128 ቢሊዮን አድርሶታል። የቢሊየነሮችን ዝርዝር የሚያስቀምጠው ብሉምበርግ እንደሚለው ከሆነ በዚህ ሰዓት ኤለን መስክን የሚበልጠው የዓለማችን ቁንጮ ሀብታም የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ ብቻ ነው። ቴስላ የአሌክትሪክ አምራች በአሜሪካ የስቶክ ገበያ ትልልቆቹን 500 ኩባንያዎች ደረጃ በሚያስቀምጠው ኤስ ኤንድ ፒ (S&P 500) ዝርዝር እንደሚገባ ባስታወቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው የሀብት ግስጋሴው በአስደንጋጭ መልኩ ሽቅብ የወጣው። የዚህን ዜና መውጣት ተከትሎ በርካታ ሰዎች የቴስላ መኪናን ድርሻ ለመግዛት ሽሚያ እንዲፈጠር አድርጓል። የቴስላ ኩባንያ ጠቅላላ ግምትም ግማሽ ትሪሊዮን ዶላር አድርሶታል። ይህን ተከትሎ ምንም እንኳ የኤለን መስክ ድርሻ በቴስላ ኩባንያ ውስጥ አነስተኛ ቢሆንም የሰውየው ሀብት ጣሪያ እንዲነካ ምክንያት ሆኗል። ቴስላ ኩባንያው በዓለም ላይ ከፍተኛ ዋጋ ከሚሰጠው መኪና አምራች ኩባንያ ዋንኛው ነው። ሆኖም ከቶዮታ፣ ቮልስ ዋገን እና ጄኔራል ሞተርስ ጋር ሲነጻጸር የሚያመርታቸው መኪናዎች ብዛት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ማክሰኞ ዕለት መስክ ጀርመን በነበረ ጊዜ የአውሮጳ የመኪና ገበያ ውስጥ መኪና በገፍ የማምረት ሥራ ውስጥ መግባት እንዴት አዋጭ እንደሆነ ሲያስረዳ ነበር። አሜሪካ ብዙ ሰዎች ትልልቅ መኪና መንዳት ነው ምርጫቸው፤ እዚህ አውሮጳ ግን ትንንሽ ናቸው መኪናዎች፥ ቴስላ በርከት ያለ መኪና በማምረት የዋጋ ተፎካካሪ መሆን የሚችል ይመስለኛል ብሏል መስክ። ቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ለተከታታይ ዓመታት ኪሳራን ሲያስመዘግብ ቆይቶ ከዚያ በኃላ ግን ላለፉት ለ5 ተከታታይ ሩብ ዓመታት ትርፋማ እየሆነ ቆይቷል። የትርፍ እድገቱንየኮቪድ ወረርሽኝም አልበገረውም። መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው ቴስላ በኤስ ኤንደ ኤስ የስቶክ ማርኬት ግማሽ ትሪሊዮን የሀብት ግምት ዋጋ ይዞ በመግባት የመጀመርያው ነው። ቢልጌትስ በዓለም የቢሊየኖች ተርታ ለዘመናት ይዞት የቆየውን መሪነት የተነጠቀው በፈረንጆች 2017 ሲሆን አዲሱ ቢሊየነር ደግሞ የአማዞኑ ቤዞስ ነበር። የቢል ጌትስ ሀብት 127.7 ቢሊየን ዶላር ነው፤ ሆኖም ገንዘቡን በብዛት ለበጎ አድራጎት ስለሚሰጥ እንጂ ከዚህ በላይ የሀብት ግምት ይኖረው ነበር ይላል ብሉምበርግ። የጄፍ ቤዞስ ሀብት አሁን ላይ 182 ቢሊየን ደርሶለታል። ቤዞስም እንደ መስክ ሁሉ በዚህ ዓመት ገቢው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮለታል። ይህም ወረርሽኙ የበይነ መረብ ግዢ እንዲፋፋም እድል በመፍጠሩ ነው። ኤለን መስክ ባለፈው ሳምንት የኮቪድ ተህዋሲ ሳይዘኝ አልቀረም ብሎ በትዊተር ሰሌዳው ጽፎ ነበር። መጠነኛ ምልክቶችን ሲያሳይ ነበር። ኤሎን መስክ በፈጠራት የጠፈር ታክሲ "ስፔስ ኤክስ" 4 የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ወደ ዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ የተሳፈሩት በቅርብ ሳምንት ነበር። ኤሎን መስስ ተወልዶ ያደገው በፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ ሲሆን በ17 ዓመቱ ወደ ካናዳ ካቀና በኃላ ለትምህርት በልውውጥ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም ወደ አሜሪካ ፔኒሲልቬኒያ ዩኒቨርስቲ ገባ። በዚያው አጋጣሚ ነው አሜሪካ የቀረው። አሁን ነዋሪነቱ በአሜሪካ ሎሳአንጀለስ ካሊፎርኒያ ውስጥ ነው። 49 ዓመቱ ሲሆን የ7 ልጆች አባትም ነው።
https://www.bbc.com/amharic/55056387
2health
እንቅልፍ በመቀነስ የሥራ ጫናን ‘የመበቀል’ ልማድ
ማ ራዎ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት፤ በሳምንት ለስድስት ቀናት ትሠራ ነበር። ቻይና፣ ሻንጋይ ውስጥ ለሚገኝ መድኃኒት አምራች ትሠራ የነበረው ማ፤ በአጭር ጊዜ ነበር ሕይወቷ በሥራ የተዋጠው። ለመመገብ አጭር ሰዓት ብቻ ነበራት። ለመተኛትም እንዲሁ። "ከሥራ ውጪ ምንም የግል ሕይወት አልነበረኝም። ድብርት ይዞኝ ነበር" ትላለች። ሥራዋ ለግል ሕይወት ጊዜ ስላሳጥት እንቅልፏን መስዋዕት እያደረገች ለራሷ ጊዜ ለመስጠት ትሞክር ነበር። ካላት አጭር የመኝታ ጊዜ ቀንሳ ዜና ማንበብ፣ ቪድዮ ማየት ጀመረች። ብዙዎች እንደ ማ እንቅልፍ ትተው የተለያየ ተግባር ያከናውናሉ። ቀናቸው በሥራ ስለሚዋጥ ከምሽት ውጪ ክፍተት አያገኙም። ምሽት ላይ ከመተኛት ይልቅ ጊዜ በማጣት ሳቢያ ያልሠሩትን ነገር ያገባድዳሉ። ጋዜጠኛዋ ዳፊን ኪ ሊ "ቀናቸውን ባሻቸው መንገድ ማሳለፍ ያልቻሉ ሰዎች ማታ ከመጠን በላይ በማምሸት ለማካካስ ይሞክራሉ" ስትል ትዊተር ላይ ጽፋ ነበር። ጽሑፉን ከ4,500 በላይ ሰዎች ወደውታል። አንድ ሌላ ሰው ደግሞ "ቀኖቼ በኔ ሳይሆን በሌሎች ቁጥጥር ሥር ናቸው። ምሽቱ ግን የእኔ ነው" ሲል ጽፏል። በእንግሊዘኛ 'revenge bedtime procrastination' ይባላል። የሥራ ጫና የሚበዛባቸው ሰዎች ለእንቅልፍ ጊዜ ሲያገኙ ከመተኛት ይልቅ የተለያየ ሥራ ይሠራሉ። መጽሐፍ ያነባሉ፣ ቲቪ ያያሉ፣ ከሰዎች ጋር ያወራሉ ወዘተ. . . እንቅልፍን መበቀል እንደማለት ነው። እንቅልፍ ለምን እምቢ ይለናል? በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የጤና ቀውስ ነው። እአአ 2019 ላይ በ12 አገሮች የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው ከ11,000 በላይ ሰዎች መተኛት ከሚገባቸው ሰዓት ባነሰ 6.8 ሰዓት ብቻ ይተኛሉ። በየቀኑ በአማካይ ስምንት ሰዓት መተኛት ይመከራል። አንዳንዶች መተኛት የማይችሉት ስለሚጨነቁ ወይም በዙሪያቸው ያሉ ነገሮች ስለሚረብሿቸው ነው። አብላጫውን ቁጥር የሚይዙ ሰዎች የማይተኙት ግን በሥራ ጫና ወይም በትምህርት ምክንያት ነው። ቻይና የተሠራ ጥናት ከ1990ዎቹ ወዲህ የተወለዱ ሰዎች በአግባቡ እንደማይተኙ ያሳያል። በተለይም በግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋሞች የሚሠሩ እምብዛም አይተኙም። የ33 ዓመቷ ጉ ቢንግ የምትሠራው ዲጂታል ኤጀንሲ ውስጥ ነው። ከሌሊት ስምንት ሰዓት በፊት አትተኛም። እሷ ብቻ ሳትሆንም ጓደኞቿም ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነው የሚተኙት። ጉ ልተኛ ብትል እንኳን አምሽታ መሥራት ስላለባት መተኛት አትችልም። ለእንቅልፍ ጊዜ ስታገኝ ደግሞ የራሷን ሥራ መሥራት ስለምትጀምር ሳትተኛ ትቀራለች። "ጊዜዬን መሥሪያ ቤቱ ቀምቶኛል። ያለኝ ጊዜ ከሥራ ውጪ ያለው ሰዓት ብቻ ነው። ስለዚህ እንቅልፍ ትቼ የተሰረቅኩትን ሰዓት አካክሳለሁ" ትላለች። በሥራና በግል ሕይወት መካከል መስመር ጠፍቷል በሼፈልድ ዩኒቨርስቲ የሥነ ልቦና መምህርቷ ሲያራ ኬሊ፤ በሥራ እና በግል ሕይወት መካከል ያለው መስመር እየጠፋ ነው ይላሉ። አንድ ሰው ከሥራ ባልደረባው ጋር በማንኛውም ጊዜ ይነጋገራል። ይህ ግንኙነት ደግሞ ሥራና የግል ሕይወትን እያደበላለቀ ነው። ሥራ ሲበዛ የመዝናኛ ጊዜን እንደሚቀንስ እሙን ነው። መዝናኛ ጊዜ ለማግኘት ብሎ እንቅልፍን መስዋዕት ማድረግ ግን ጤናማ እንዳልሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ዘለግ ላለ ጊዜ እንቅልፍ ማጣት ለተለያየ የአዕምሮ ህመም ያጋልጣል። የሥነ ልቦና መምህርቷ ሲያራ ሰዎች መዝናኛ ሰዓት የግድ ማግኘት አለባቸው። የሥራ ጫና መዝናኛ ሰዓት ሲያሳጣቸው እንቅልፍ ትተው የሚዝናኑትም ለዚያ ነው። "ሠራተኞች መንፈሳቸውን የሚያዝናኑበት መንገድ ሊያገኙ ይገባል" ሲሉ አሠሪዎች ጉዳዩን እንዲያስቡበት ይመክራሉ። የሠራተኞች መብት ላይ የሚሠሩት የማኅበረሰብ ባለሙያ ሂውንግ ቹንግ፤ ሠራተኞች የእንቅልፍ እንዲሁም የመዝናኛ ሰዓት በሚያሳጣቸው መንገድ ሥራ ሊደራረብባቸው አይገባም ይላሉ። ይህንን ማድረግም የቀጣሪዎች ኃላፊነት ነው።
እንቅልፍ በመቀነስ የሥራ ጫናን ‘የመበቀል’ ልማድ ማ ራዎ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት፤ በሳምንት ለስድስት ቀናት ትሠራ ነበር። ቻይና፣ ሻንጋይ ውስጥ ለሚገኝ መድኃኒት አምራች ትሠራ የነበረው ማ፤ በአጭር ጊዜ ነበር ሕይወቷ በሥራ የተዋጠው። ለመመገብ አጭር ሰዓት ብቻ ነበራት። ለመተኛትም እንዲሁ። "ከሥራ ውጪ ምንም የግል ሕይወት አልነበረኝም። ድብርት ይዞኝ ነበር" ትላለች። ሥራዋ ለግል ሕይወት ጊዜ ስላሳጥት እንቅልፏን መስዋዕት እያደረገች ለራሷ ጊዜ ለመስጠት ትሞክር ነበር። ካላት አጭር የመኝታ ጊዜ ቀንሳ ዜና ማንበብ፣ ቪድዮ ማየት ጀመረች። ብዙዎች እንደ ማ እንቅልፍ ትተው የተለያየ ተግባር ያከናውናሉ። ቀናቸው በሥራ ስለሚዋጥ ከምሽት ውጪ ክፍተት አያገኙም። ምሽት ላይ ከመተኛት ይልቅ ጊዜ በማጣት ሳቢያ ያልሠሩትን ነገር ያገባድዳሉ። ጋዜጠኛዋ ዳፊን ኪ ሊ "ቀናቸውን ባሻቸው መንገድ ማሳለፍ ያልቻሉ ሰዎች ማታ ከመጠን በላይ በማምሸት ለማካካስ ይሞክራሉ" ስትል ትዊተር ላይ ጽፋ ነበር። ጽሑፉን ከ4,500 በላይ ሰዎች ወደውታል። አንድ ሌላ ሰው ደግሞ "ቀኖቼ በኔ ሳይሆን በሌሎች ቁጥጥር ሥር ናቸው። ምሽቱ ግን የእኔ ነው" ሲል ጽፏል። በእንግሊዘኛ 'revenge bedtime procrastination' ይባላል። የሥራ ጫና የሚበዛባቸው ሰዎች ለእንቅልፍ ጊዜ ሲያገኙ ከመተኛት ይልቅ የተለያየ ሥራ ይሠራሉ። መጽሐፍ ያነባሉ፣ ቲቪ ያያሉ፣ ከሰዎች ጋር ያወራሉ ወዘተ. . . እንቅልፍን መበቀል እንደማለት ነው። እንቅልፍ ለምን እምቢ ይለናል? በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የጤና ቀውስ ነው። እአአ 2019 ላይ በ12 አገሮች የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው ከ11,000 በላይ ሰዎች መተኛት ከሚገባቸው ሰዓት ባነሰ 6.8 ሰዓት ብቻ ይተኛሉ። በየቀኑ በአማካይ ስምንት ሰዓት መተኛት ይመከራል። አንዳንዶች መተኛት የማይችሉት ስለሚጨነቁ ወይም በዙሪያቸው ያሉ ነገሮች ስለሚረብሿቸው ነው። አብላጫውን ቁጥር የሚይዙ ሰዎች የማይተኙት ግን በሥራ ጫና ወይም በትምህርት ምክንያት ነው። ቻይና የተሠራ ጥናት ከ1990ዎቹ ወዲህ የተወለዱ ሰዎች በአግባቡ እንደማይተኙ ያሳያል። በተለይም በግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋሞች የሚሠሩ እምብዛም አይተኙም። የ33 ዓመቷ ጉ ቢንግ የምትሠራው ዲጂታል ኤጀንሲ ውስጥ ነው። ከሌሊት ስምንት ሰዓት በፊት አትተኛም። እሷ ብቻ ሳትሆንም ጓደኞቿም ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነው የሚተኙት። ጉ ልተኛ ብትል እንኳን አምሽታ መሥራት ስላለባት መተኛት አትችልም። ለእንቅልፍ ጊዜ ስታገኝ ደግሞ የራሷን ሥራ መሥራት ስለምትጀምር ሳትተኛ ትቀራለች። "ጊዜዬን መሥሪያ ቤቱ ቀምቶኛል። ያለኝ ጊዜ ከሥራ ውጪ ያለው ሰዓት ብቻ ነው። ስለዚህ እንቅልፍ ትቼ የተሰረቅኩትን ሰዓት አካክሳለሁ" ትላለች። በሥራና በግል ሕይወት መካከል መስመር ጠፍቷል በሼፈልድ ዩኒቨርስቲ የሥነ ልቦና መምህርቷ ሲያራ ኬሊ፤ በሥራ እና በግል ሕይወት መካከል ያለው መስመር እየጠፋ ነው ይላሉ። አንድ ሰው ከሥራ ባልደረባው ጋር በማንኛውም ጊዜ ይነጋገራል። ይህ ግንኙነት ደግሞ ሥራና የግል ሕይወትን እያደበላለቀ ነው። ሥራ ሲበዛ የመዝናኛ ጊዜን እንደሚቀንስ እሙን ነው። መዝናኛ ጊዜ ለማግኘት ብሎ እንቅልፍን መስዋዕት ማድረግ ግን ጤናማ እንዳልሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ዘለግ ላለ ጊዜ እንቅልፍ ማጣት ለተለያየ የአዕምሮ ህመም ያጋልጣል። የሥነ ልቦና መምህርቷ ሲያራ ሰዎች መዝናኛ ሰዓት የግድ ማግኘት አለባቸው። የሥራ ጫና መዝናኛ ሰዓት ሲያሳጣቸው እንቅልፍ ትተው የሚዝናኑትም ለዚያ ነው። "ሠራተኞች መንፈሳቸውን የሚያዝናኑበት መንገድ ሊያገኙ ይገባል" ሲሉ አሠሪዎች ጉዳዩን እንዲያስቡበት ይመክራሉ። የሠራተኞች መብት ላይ የሚሠሩት የማኅበረሰብ ባለሙያ ሂውንግ ቹንግ፤ ሠራተኞች የእንቅልፍ እንዲሁም የመዝናኛ ሰዓት በሚያሳጣቸው መንገድ ሥራ ሊደራረብባቸው አይገባም ይላሉ። ይህንን ማድረግም የቀጣሪዎች ኃላፊነት ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-56051981
5sports
ኳታር ለዓለም ዋንጫ እንዴት ተመረጠች፣ ውድድሩ ለምን ኅዳር ላይ ሆነ?
ሚሊዮኖች. . . ቢሊዮኖችም ሊሆን ይችላል፤ በጉጉት የሚጠብቁት የዓለም እግር ኳስ ፍልሚያ በቀጣይ ዓመት ኅዳር ላይ መካሄድ ይጀምራል። የዓለም ዋንጫ ውድድር ኅዳር ወር ላይ ሲሆን ይህ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። አዘጋጇ ደግሞ የመካከለኛ ምሥራቋ ቱጃር አገር ኳታር ናት። የዓለም ዋንጫ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሲያመራም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። አስካሁን ከሁለት አገራት በስተቀር በዚህ ተወዳጅ ፍልሚያ ላይ መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል። ሁለቱ አገራት ደግሞ በዚህ ሳምንት በሚደረገው ኢንተርኮንቲኔንታል ጥሎ ማለፍ ይለያሉ። ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ ፊፋ፣ ኳታር የዓለም ዋንጫን እንደትደግስ ወስኛለሁ ሲል ወሳኔው ብዙ አወዛግቦ ነበር። የዓለም ዋንጫ ይህ የፈረንጆች ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት በኢትዮጵያ ቀጣይ ዓመት ኅዳር 12 ጀምሮ ታኅሣሥ 09 ይቋጫል። ለወትሮው የዓለም ዋንጫ በኢትዮጵያ ክረምት ነበር የሚሰናዳው። ዘንድሮ ግን ሙቀቱ ከምላስ ላብ በሚያመነጭባት ዶሃ ሊካሄድ በመሆኑ የጊዜ ሰሌዳውን ማሻሻል ግድ ብሏል። ዶሃ ኅዳርና ታኅሣሥ ገደማ ቀዝቀዝ ትላለች። ሙቀቱ ወደ 18 ሴሊሺየስ ይወርዳል ማለት ነው? ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል። ኳታር ብርድ ብድር የሚሰማዎት ሙቀቱ ወደ 25 ሴሊሺየስ ሲደርስ ነው። ለወይናደጋ ሰው 25 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ማለት ልብስ አስወልቆ ዛፍ ጥላ ሥር የሚያስተኛ ነው። ዶሃ እንደሌላው አገር ወግ ደርሷት የዓለም ዋንጫን ሰኔና ሐምሌ ላዘጋጅ ብትል ሙቀቱ 40 ባስ ሲል ደግሞ 50 ዲግሪ የሚደርስ ሙቀት ያቃጥላታል። መቼም እግር ኳስ ወዳዱ ማኅበረሰብ ሮናልዶና ሜሲ ጥብስ እንዳሸተተ ውሻ ሲያለከልኩ ማየት አይሻም። እርግጥ ነው ዶሃ የዓለም ዋንጫን ላዘጋጅ ያለችው ረብጣዋን ተማምና ነው። ዶሃ "ግድ የለም በኔ ይሁንባችሁ፤ ሙቀቱ ተፈጥሮን በሚያስንቅ ማቀዝቀዣ በተገጠመለት ስታድዬም አጫውታችኋለሁ" ብላ ነበር። ነገር ግን ፊፋ በዚህ እንኳ አንስማማም አለ። ታድያ ውድድሩ ኅዳር ወር ላይ ቢካሄድ ምን ችግር አለው? ኅዳር እና ታኅሣሥ የአውሮፓ እግር ኳስ የሚደምቅበት ወቅት ነው። ነገር ግን ዘንድሮ በርካታ ተጫዋቾች አገራቸውን ወክለው ለመፋለም ወደ ኳታር የሚያመሩበት ወቅት ይሆናል። ዘንድሮ ኅዳር እና ታኅሣሥ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን ለማየት ካሰቡ ውሳኔዎን ለመቀየር ጊዜው አልረፈደም። የጣልያን ሴሪ አ እንዲሁም የስፔን ላሊጋም ኅዳር እና ታኅሣሥ እረፍት ይወጣሉ። የአውሮፓ እግር ኳስ ወደ ወትሮ ፕሮግራሙ የሚመለሰው ከዓለም ዋንጫ በኋላ ነው። ጊዜው በፈረንጆቹ 2010 ዓመተ ምህረት። አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና አውስትራሊያ እንዲሁም ኳታር የዓለም ዋንጫን እንድናሰዳ ዕድሉ ይሰጠን ሲሉ አመለከቱ። ፊፋ ጊዜ ወስዶ ጥያቄያቸውን ማጤን ጀመረ። ከዚያም ጊዜው ደርሶ 22 የፊፋ ሥራ አስፈፃሚ አባላት መጥተው እነሆ ምርጫችን ዶሃ ሆናለች አሉ። አንዲት የአራብ አገር የዓለም ዋንጫን ስትደግ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ነገር ግን ብዙ አገራት ኳታር 'በእጇ ተራምዳ' ይሆናል እንጂ እንዴት ልትመረጥ ቻለች ይሉ ጀመር። የኋላ ኋላ ኳታር ለፊፋ ሰዎች 3.7 ሚሊዮን ዶላር ለግሳለች ተብላ በይፋ ተከሰሰች። ነገር ግን ሁለት ዓመት ከፈጀ ምርመራ በኋላ ስሟ ነፃ ወጣ። በወቅቱ የፊፋ አለቃ የነበሩት ሴፕ ብላተር ለኳታር ድምፃቸውን ቢሰጡም፣ ትንሽ ቆይተው ተሳስተናል ማለት ጀመሩ። ብላተር አሁን ስዊትዘርላንድ ውስጥ በማጭበርበርና ሙስና ወንጀል ተከሰው ፍርዳቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ። ለረዥም ዓመታት ፊፋን የመሩት ብላተር፣ እኔ ጥፋት የለብኝም ሲሉ ያስተባብላሉ። ኳታር ከአምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎችም ክስ ቀርቦባታል። እኒህ የመብት ተሟጋች ተቋማት ስታድዬም ለመገንባት የመጡ የውጭ አገራት ዜጎች መብታቸው ተረግጧል ይላሉ። አገራት ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ማጣሪያ ማድረግ የጀመሩት ከሦስት ዓመታት በፊት ነው። ማጣሪያው የተደረገው በአህጉር ተከፋፍሎ ነበር። አህጉራት ምድብ መድበው ብሔራዊ ቡድኖችን ካፋለሙ በኋላ አሸናፊዎች ወደ ኳታር ያቀናሉ። ያለፈውን የዓለም ዋንጫ ያነሳችው ፈረንሳይ ወደ ኳታር ታቀናለች። የአውሮፓ ዋንጫን ያነሳችው ጣልያን ግን ዶሃ ላይ አትታይም። የሞሐመድ ሳላህ ግብፅም ወደ ዶሃ የሚወስዳትን ቲኬት መቁረጥ አልቻለችም። 32 አገራት በዚህ ውድድር ይሳተፋሉ። ከአንድ አህጉር የመጡ አገራት በአንድ ምድብ አይደለደሉም። ነገር ግን ይህ ሕግ ለአውሮፓ አይሠራም። ምክንያቱ ደግሞ ለአውሮፓ የተሰጠው ኮታ ከፍ ማለቱ ነው። ብራዚል፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይና ስፔን የዓለም ዋንጫን ለማንሳት ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው አገራት መካከል ናቸው። የኳታር የሕዝብ ቁጥር 2.9 ሚሊዮን ነው። ዕድሜ ለነዳጅ ምርቷ ይሁንና ኳታር ከባለፀጋ የዓለማችን አገርት መካከል ናት። ኳታር ለዓለም ዋንጫ ብላ ሰባት አዳዲስ ዘመናዊ ስታድዬሞች አቁማለች። ትንሿ አገር በዚህ አላበቃችም። የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ እንዲከናወንበት ብላ አንድ ከተማ ገንብታለች። ከ100 በላይ አዳዲስ ሆቴሎች፣ የባቡር ጣቢያ እንዲሁም መንገድ ለዓለም ዋንጫ በሚል የተገነቡ ናቸው። የዓለም ዋንጫ አዘጋጆች 1.5 ሚሊዮን ሰዎች ውድድሩን ለመታደም ዶሃ ይገባሉ ይላሉ። ኳታር ወግ አጥባቂ ሙስሊም አገር በመሆኗ ደጋፊዎች ባሕሪያቸውን እንዲያጤኑ ይመከራሉ። አንድ ቢራ እስከ 13 ዶላር [በአሁናዊ ገበያ 670 ብር] ሊሸጥ ይችላል። አልኮል መቅመስ የፈለገ ሰው ቅንጡ ወደሆኑ ሆቴሎች አቅንቶ ነው መጠቀም የሚችለው። አዘጋጆቹ ግን ደጋፊዎች እንደፈለጉ መጠጥ የሚጎነጩበት ሥፍራ እናሰናዳለን እያሉ ነው። ኳታር ውስጥ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ሕገ-ወጥ ነው። ለተመሳሳይ ፆታ ፍቅር እንሟገታለን የሚሉ ቡድኖች መንግሥታት ይህን እንዲቃወሙ ይጠይቃሉ። አንዳንድ የዌልስ ደጋፊዎች ደግሞ ወደ ዶሃ አንሄድም በማለት እየዛቱ ነው። የዓለም ዋንጫ አዘጋጆች "ሁሉም ሰው መምጣት ይችላል" ቢሉም ኳታር ግን በተመሳሳይ ፆታ ላይ ያላትን አቋም እንደማታላላ ግልጽ አደርጋለች።
ኳታር ለዓለም ዋንጫ እንዴት ተመረጠች፣ ውድድሩ ለምን ኅዳር ላይ ሆነ? ሚሊዮኖች. . . ቢሊዮኖችም ሊሆን ይችላል፤ በጉጉት የሚጠብቁት የዓለም እግር ኳስ ፍልሚያ በቀጣይ ዓመት ኅዳር ላይ መካሄድ ይጀምራል። የዓለም ዋንጫ ውድድር ኅዳር ወር ላይ ሲሆን ይህ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። አዘጋጇ ደግሞ የመካከለኛ ምሥራቋ ቱጃር አገር ኳታር ናት። የዓለም ዋንጫ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሲያመራም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። አስካሁን ከሁለት አገራት በስተቀር በዚህ ተወዳጅ ፍልሚያ ላይ መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል። ሁለቱ አገራት ደግሞ በዚህ ሳምንት በሚደረገው ኢንተርኮንቲኔንታል ጥሎ ማለፍ ይለያሉ። ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ ፊፋ፣ ኳታር የዓለም ዋንጫን እንደትደግስ ወስኛለሁ ሲል ወሳኔው ብዙ አወዛግቦ ነበር። የዓለም ዋንጫ ይህ የፈረንጆች ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት በኢትዮጵያ ቀጣይ ዓመት ኅዳር 12 ጀምሮ ታኅሣሥ 09 ይቋጫል። ለወትሮው የዓለም ዋንጫ በኢትዮጵያ ክረምት ነበር የሚሰናዳው። ዘንድሮ ግን ሙቀቱ ከምላስ ላብ በሚያመነጭባት ዶሃ ሊካሄድ በመሆኑ የጊዜ ሰሌዳውን ማሻሻል ግድ ብሏል። ዶሃ ኅዳርና ታኅሣሥ ገደማ ቀዝቀዝ ትላለች። ሙቀቱ ወደ 18 ሴሊሺየስ ይወርዳል ማለት ነው? ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል። ኳታር ብርድ ብድር የሚሰማዎት ሙቀቱ ወደ 25 ሴሊሺየስ ሲደርስ ነው። ለወይናደጋ ሰው 25 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ማለት ልብስ አስወልቆ ዛፍ ጥላ ሥር የሚያስተኛ ነው። ዶሃ እንደሌላው አገር ወግ ደርሷት የዓለም ዋንጫን ሰኔና ሐምሌ ላዘጋጅ ብትል ሙቀቱ 40 ባስ ሲል ደግሞ 50 ዲግሪ የሚደርስ ሙቀት ያቃጥላታል። መቼም እግር ኳስ ወዳዱ ማኅበረሰብ ሮናልዶና ሜሲ ጥብስ እንዳሸተተ ውሻ ሲያለከልኩ ማየት አይሻም። እርግጥ ነው ዶሃ የዓለም ዋንጫን ላዘጋጅ ያለችው ረብጣዋን ተማምና ነው። ዶሃ "ግድ የለም በኔ ይሁንባችሁ፤ ሙቀቱ ተፈጥሮን በሚያስንቅ ማቀዝቀዣ በተገጠመለት ስታድዬም አጫውታችኋለሁ" ብላ ነበር። ነገር ግን ፊፋ በዚህ እንኳ አንስማማም አለ። ታድያ ውድድሩ ኅዳር ወር ላይ ቢካሄድ ምን ችግር አለው? ኅዳር እና ታኅሣሥ የአውሮፓ እግር ኳስ የሚደምቅበት ወቅት ነው። ነገር ግን ዘንድሮ በርካታ ተጫዋቾች አገራቸውን ወክለው ለመፋለም ወደ ኳታር የሚያመሩበት ወቅት ይሆናል። ዘንድሮ ኅዳር እና ታኅሣሥ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን ለማየት ካሰቡ ውሳኔዎን ለመቀየር ጊዜው አልረፈደም። የጣልያን ሴሪ አ እንዲሁም የስፔን ላሊጋም ኅዳር እና ታኅሣሥ እረፍት ይወጣሉ። የአውሮፓ እግር ኳስ ወደ ወትሮ ፕሮግራሙ የሚመለሰው ከዓለም ዋንጫ በኋላ ነው። ጊዜው በፈረንጆቹ 2010 ዓመተ ምህረት። አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና አውስትራሊያ እንዲሁም ኳታር የዓለም ዋንጫን እንድናሰዳ ዕድሉ ይሰጠን ሲሉ አመለከቱ። ፊፋ ጊዜ ወስዶ ጥያቄያቸውን ማጤን ጀመረ። ከዚያም ጊዜው ደርሶ 22 የፊፋ ሥራ አስፈፃሚ አባላት መጥተው እነሆ ምርጫችን ዶሃ ሆናለች አሉ። አንዲት የአራብ አገር የዓለም ዋንጫን ስትደግ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ነገር ግን ብዙ አገራት ኳታር 'በእጇ ተራምዳ' ይሆናል እንጂ እንዴት ልትመረጥ ቻለች ይሉ ጀመር። የኋላ ኋላ ኳታር ለፊፋ ሰዎች 3.7 ሚሊዮን ዶላር ለግሳለች ተብላ በይፋ ተከሰሰች። ነገር ግን ሁለት ዓመት ከፈጀ ምርመራ በኋላ ስሟ ነፃ ወጣ። በወቅቱ የፊፋ አለቃ የነበሩት ሴፕ ብላተር ለኳታር ድምፃቸውን ቢሰጡም፣ ትንሽ ቆይተው ተሳስተናል ማለት ጀመሩ። ብላተር አሁን ስዊትዘርላንድ ውስጥ በማጭበርበርና ሙስና ወንጀል ተከሰው ፍርዳቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ። ለረዥም ዓመታት ፊፋን የመሩት ብላተር፣ እኔ ጥፋት የለብኝም ሲሉ ያስተባብላሉ። ኳታር ከአምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎችም ክስ ቀርቦባታል። እኒህ የመብት ተሟጋች ተቋማት ስታድዬም ለመገንባት የመጡ የውጭ አገራት ዜጎች መብታቸው ተረግጧል ይላሉ። አገራት ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ማጣሪያ ማድረግ የጀመሩት ከሦስት ዓመታት በፊት ነው። ማጣሪያው የተደረገው በአህጉር ተከፋፍሎ ነበር። አህጉራት ምድብ መድበው ብሔራዊ ቡድኖችን ካፋለሙ በኋላ አሸናፊዎች ወደ ኳታር ያቀናሉ። ያለፈውን የዓለም ዋንጫ ያነሳችው ፈረንሳይ ወደ ኳታር ታቀናለች። የአውሮፓ ዋንጫን ያነሳችው ጣልያን ግን ዶሃ ላይ አትታይም። የሞሐመድ ሳላህ ግብፅም ወደ ዶሃ የሚወስዳትን ቲኬት መቁረጥ አልቻለችም። 32 አገራት በዚህ ውድድር ይሳተፋሉ። ከአንድ አህጉር የመጡ አገራት በአንድ ምድብ አይደለደሉም። ነገር ግን ይህ ሕግ ለአውሮፓ አይሠራም። ምክንያቱ ደግሞ ለአውሮፓ የተሰጠው ኮታ ከፍ ማለቱ ነው። ብራዚል፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይና ስፔን የዓለም ዋንጫን ለማንሳት ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው አገራት መካከል ናቸው። የኳታር የሕዝብ ቁጥር 2.9 ሚሊዮን ነው። ዕድሜ ለነዳጅ ምርቷ ይሁንና ኳታር ከባለፀጋ የዓለማችን አገርት መካከል ናት። ኳታር ለዓለም ዋንጫ ብላ ሰባት አዳዲስ ዘመናዊ ስታድዬሞች አቁማለች። ትንሿ አገር በዚህ አላበቃችም። የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ እንዲከናወንበት ብላ አንድ ከተማ ገንብታለች። ከ100 በላይ አዳዲስ ሆቴሎች፣ የባቡር ጣቢያ እንዲሁም መንገድ ለዓለም ዋንጫ በሚል የተገነቡ ናቸው። የዓለም ዋንጫ አዘጋጆች 1.5 ሚሊዮን ሰዎች ውድድሩን ለመታደም ዶሃ ይገባሉ ይላሉ። ኳታር ወግ አጥባቂ ሙስሊም አገር በመሆኗ ደጋፊዎች ባሕሪያቸውን እንዲያጤኑ ይመከራሉ። አንድ ቢራ እስከ 13 ዶላር [በአሁናዊ ገበያ 670 ብር] ሊሸጥ ይችላል። አልኮል መቅመስ የፈለገ ሰው ቅንጡ ወደሆኑ ሆቴሎች አቅንቶ ነው መጠቀም የሚችለው። አዘጋጆቹ ግን ደጋፊዎች እንደፈለጉ መጠጥ የሚጎነጩበት ሥፍራ እናሰናዳለን እያሉ ነው። ኳታር ውስጥ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ሕገ-ወጥ ነው። ለተመሳሳይ ፆታ ፍቅር እንሟገታለን የሚሉ ቡድኖች መንግሥታት ይህን እንዲቃወሙ ይጠይቃሉ። አንዳንድ የዌልስ ደጋፊዎች ደግሞ ወደ ዶሃ አንሄድም በማለት እየዛቱ ነው። የዓለም ዋንጫ አዘጋጆች "ሁሉም ሰው መምጣት ይችላል" ቢሉም ኳታር ግን በተመሳሳይ ፆታ ላይ ያላትን አቋም እንደማታላላ ግልጽ አደርጋለች።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c51wglqrq46o
0business
ከኑሮ ውድነት ጋር ግብ ግብ የገጠሙት የመንግሥት ሠራተኞች
ረድኤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኝ የሥራ እድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት ውስጥ ሠራተኛ ነች። በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ ሁለቱም የመንግሥት ሠራተኞች ስማቸው ተቀይሯል። ሥራቸውን እንዳያጡ ሰግተዋል። ትውልድ እና እድገቷ አዲስ አበባ ነው። "ከቤተሰቤ ጋር ባይሆን በ 2700 ብር ደሞዝ ተቀጥሬ እንዴት እኖር ነበር?" ስትል ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት የነበራትን የመነሻ ደመወዝ ትናገራለች። አሁን እንደምንም አምስት ሺህ ብር ይደርሳታል። በቅርቡ ትዳር ይዛ ከቤተሰቦቿ ቤት የወጣችው ረድኤት የቤት ኪራይ ወጪዋ ሰባት ሺህ ብር ነው። እቁብም ትጥላለች፤ ሦስት ሺህ ብር። ይህ ከምግብ፣ ከጤና ከድንገተኛ ወጪዎች ውጪ ነው። "ከባለቤቴ ጋር ተጋግዘን ነው እንጂ ብቻዬን ብሆን እንዴት ይቻላል" ትላለች። "ደመወዝ ከተቀበልኩ በኋላ ከ15 ቀን በኋላ እጄ ላይ ገንዘብ አይቀርም" ትላለች። በምትሰራበት የሥራ እድል ፈጠራ ቢሮ የሥራ እድል ተፈጥሮላቸው የገቡ አዲስ ሠራተኞች በተለይም ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ባልደረቦቿ እጅግ ከባድ የሚባል ኑሮ እንደሚገፉ ትናገራለች። "ለእነሱ ምንም ከምንም አይሆንም። በጣም ያሳዝነኛል። ኪራይ እና ምግብ ችለው ለመኖር በጣም በችግር ነው የሚኖሩት" ስትል ረድኤት ታስረዳለች። በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛው ቀጣሪ እና የሥራ እድል ምንጭ መንግሥት ነው። የመንግሥት ሠራተኞች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ከተሻገረ 10 ዓመት ሊሞላው ነው። እንደ የአለም ባንክ መረጃ ከሆነ የደርግ ስርዓት ሲወድቅ 300 ሺህ የማይሞሉ ከ 200 ሺህ የማያንሱ የመንግሥት ሠራተኞች በኢትዮጵያ ነበሩ። ታዲያ ይህ ኃይል የዋጋ ግሽበት ወይም በተለምዶ የኑሮ ውድነት በሚባል ቀውስ ምክንያት እየተፈተነ ይገኛል። የዋጋ ግሽበት የገንዘብ የመግዛት አቅም ሲቀንስ የሚከሰት ነው። የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያሳየው እኤአ ከ 1970 እስከ 2019 ባለው ግዜ ውስጥ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት የተከሰተው በኢትዮጵያ ሚሌኒየም ወቅት ነበር። በወቅቱ የዋጋ ግሽበቱ 44 ነጥብ 4 ሆኖ ተመዝግቧል። እንዲሁም ደርግ በወደቀበት ዓመት የዋጋ ግሽበቱ 36 በመቶ ደርሶ እንደነበር የዓለም ባንክ መረጃ ያመላክታል። ከ 2005 ዓም ጀምሮ ለሶስት ዓመታት በአንድ ዲጂት ተወስኖ እና ተረጋግቶ የቆየው የዋጋ ግሽበት በ 2009 ዓ.ም አስር በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። በተለይ በመገባደድ ላይ ባለው ዓመት የተተኮሰው ግሽበት በተለይም የምግብ ምግብ ነክ ቁሶች ላይ የ 28̌ በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ይህንን ጭማሪ በቀላል ቋንቋ የሚያብራሩት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኙ አብዱልመናን መሃመድ «የመንግሥት ሰራተኞች ባለፈው ሁለት ዓመታት ብቻ የደመወዛቸውን 40 በመቶ ለዋጋ ግሽበት አስረክበዋል» ይላሉ። ይህ ማለት ከሁለት አመት በፊት 10 ሺህ ብር ደመወዝ የነበረው ሰው አሁን ላይ ባለው ግሽበት ሲሰላ ደመወዙ ወደ ስድስት ሺህ ብር አሽቆልቁሏል ማለት ነው። በመንግሥት መዋቅር "የስራ ሂደት አስተባባሪ" ማለት ዋና አለቃ ማለት ነው። "የእነርሱ ደመወዝ ኪስ የሚሞላ፤ ተለቅ ያለ ነው" ሲሉ ከስራቸው ያሉ ባለሞያዎች ያስባሉ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ባለ አንድ ተቋም ቡድን መሪ የሆነችው እመቤት ግን "የያዝነው ቦታማ ትልቅ ነው፤ ግን እኛም በችግር ነው የምንኖረው" ትላለች። እሷም የወር ደመወዟ 15 ቀን አይቆይላትም። እጇ ላይ 7500 ብር ቢደርስም አምስት ሺህ ብር "በጣም ጠባብ" ለምትላት ባለ ሁለት ክፍል ቤቷ ትከፍላለች። ሁለት ልጆች አሏት። "ቀነስ ያለ ትምህርት ቤት" ፈልጋ በወር 750 ብር ለአንድ ልጅ ትከፍላለች። ልጁን የሚያመላልስ ሰርቪስም ከፍያ ይጠይቃል። "የመንግሥት ሠራተኛ ከሆንሽ ልጅሽን የሚይዝ ሞግዚት ያስፈልጋል። የዘይት፣ የጤፍ ዋጋ ሰማይ ነው። ምን ያልተወደደ ነገር አለ?" በማለት "መኖር አዳግቶኛል" ስትል እመቤት ኑሮዋን ትገልጸዋለች። ከስምንት ዓመት ጀምሮ ቤት ለማግኘት ብትቆጥብም ህልም ሆኖ መቅረቱም ያስቆጫታል። ነገር ግን ደመወዝ ይጨመር ይሆን ብላ ትጠብቃለች። ረድኤትን እና እመቤትን የሚያስማማቸው አንድ ነገር አለ። በትምህርታቸው ለመግፋት ቢያቅዱም በገቢ እጥረት ምክንያት ትተውታል። ረድኤት እንደውም ጀምራ መክፈል ሲያቅታት ትታዋለች። እንደ እመቤት ሁሉ ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች የላባቸውን ውጤት ለዋጋ ግሽበት ሲያስረክቡ ውጤቱ አሳሳቢ መሆኑን የኢኮኖሚ ተንታኙ አብዱልመናን ይናገራሉ። "ይህ በኑሮ ደረጃ ላይ ከፍተኛ ጫና አለው። በተጨማሪም በሥራቸው ላይ ተነሳሽነት እና ደስታ ወይም እርካታ ማጣት ያጋጥማቸዋል። ይህ ለዝቅተኛ አፈጻጸም ብሎም ለሙስና በር ከፋች ነው" ሲሉ ባለሞያው ያብራራሉ። ለበርካታ ዓመታት የኑሮ ውድነቱ መሰረት የንግድ ሰንሰለቱ እንደሆነ ባለሞያዎች በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል። ይህም በተለይ ምርት ከገበሬው እስከ ሸማቹ እስከሚደርስ ባለው ሠንሰለት መሃል ያሉ ደላላዎችን ተወቃሽ ያደረገ ነበር። መንግሥት በተለይም ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች ላይ የሚታየውን ጭማሪ «ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው፣ የጥቂቶች አሻጥር» ሲል በተደጋጋሚ ይሰማል። ከሁለት ዓመታት በፊት ጀምሮ በ 2013 የተባባሰው ግሽበት ግን ምክንያቶቹ ከተለመደው የዘለሉ እንደሆኑ የኢኮኖሚ ባለሞያው አብዱል መናን ይናገራሉ። "አሁን ያጋጠመው የዋጋ ግሽበት ዋና መሰረቱ ብር ከሌሎች የውጪ ገንዘቦች አንጻር ዋጋው እንዲቀንስ በመደረጉ ምክንያት ነው። እንግዲህ ይህ የሆነው ለአስርት ዓመታት በዋጋ ግሽበት ሲናጥ ብሎም በፖለቲካ ያለመረጋጋት ውስጥ ባለ ኢኮኖሚ ላይ ነው" ሲሉ አዲስ ያሉትን ምክንያት ያብራራሉ። ይህ እንዲቆም ካስፈለገም መንግሥት የብርን ዋጋ የመቀነስ ፖሊሲውን ማቆም አለበት ሲሉም አብዱልመናን ይመክራሉ። እንዲሁም የባንኮችን ተቀማጭ ገንዘብ በመጨመር እና በሂደት የቁጠባ ወለድን ከፍ ማድረግን ጨምሮ የገንዘብ ፖሊሲውን ቆንጠጥ ማድረግ ችግሩን ያቃልለዋልም ይላሉ። ገንዘብ ዋጋ ለማጣቱ ምክንያት ከሚባሉት ነገሮች መካከል አንዱ መንግሥት እንዳሻው ከብሔራዊ ባንክ በመበደር ፈሰስ ማድረጉ ነው። ይህ ክስም አላግባብ የብር ኖት በማተም ኢኮኖሚው ውስጥ መክተት ሌላው ለዋጋ ግሸበቱ መሰረት እንደሆነ በባለሞያዎች ለአመታት ሲነሳ የቆየ ምክንያት ነው። አብዱልመናን ይህንን ችግር ለመቆጣጠር ቁልፍ የሚሉት ሌላው መፍትሄም ይሄንን ይመለከታል። "መንግስት ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ መጠን መቀነስ ይገባዋል" ሲሉ ያክላሉ።
ከኑሮ ውድነት ጋር ግብ ግብ የገጠሙት የመንግሥት ሠራተኞች ረድኤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኝ የሥራ እድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት ውስጥ ሠራተኛ ነች። በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ ሁለቱም የመንግሥት ሠራተኞች ስማቸው ተቀይሯል። ሥራቸውን እንዳያጡ ሰግተዋል። ትውልድ እና እድገቷ አዲስ አበባ ነው። "ከቤተሰቤ ጋር ባይሆን በ 2700 ብር ደሞዝ ተቀጥሬ እንዴት እኖር ነበር?" ስትል ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት የነበራትን የመነሻ ደመወዝ ትናገራለች። አሁን እንደምንም አምስት ሺህ ብር ይደርሳታል። በቅርቡ ትዳር ይዛ ከቤተሰቦቿ ቤት የወጣችው ረድኤት የቤት ኪራይ ወጪዋ ሰባት ሺህ ብር ነው። እቁብም ትጥላለች፤ ሦስት ሺህ ብር። ይህ ከምግብ፣ ከጤና ከድንገተኛ ወጪዎች ውጪ ነው። "ከባለቤቴ ጋር ተጋግዘን ነው እንጂ ብቻዬን ብሆን እንዴት ይቻላል" ትላለች። "ደመወዝ ከተቀበልኩ በኋላ ከ15 ቀን በኋላ እጄ ላይ ገንዘብ አይቀርም" ትላለች። በምትሰራበት የሥራ እድል ፈጠራ ቢሮ የሥራ እድል ተፈጥሮላቸው የገቡ አዲስ ሠራተኞች በተለይም ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ባልደረቦቿ እጅግ ከባድ የሚባል ኑሮ እንደሚገፉ ትናገራለች። "ለእነሱ ምንም ከምንም አይሆንም። በጣም ያሳዝነኛል። ኪራይ እና ምግብ ችለው ለመኖር በጣም በችግር ነው የሚኖሩት" ስትል ረድኤት ታስረዳለች። በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛው ቀጣሪ እና የሥራ እድል ምንጭ መንግሥት ነው። የመንግሥት ሠራተኞች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ከተሻገረ 10 ዓመት ሊሞላው ነው። እንደ የአለም ባንክ መረጃ ከሆነ የደርግ ስርዓት ሲወድቅ 300 ሺህ የማይሞሉ ከ 200 ሺህ የማያንሱ የመንግሥት ሠራተኞች በኢትዮጵያ ነበሩ። ታዲያ ይህ ኃይል የዋጋ ግሽበት ወይም በተለምዶ የኑሮ ውድነት በሚባል ቀውስ ምክንያት እየተፈተነ ይገኛል። የዋጋ ግሽበት የገንዘብ የመግዛት አቅም ሲቀንስ የሚከሰት ነው። የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያሳየው እኤአ ከ 1970 እስከ 2019 ባለው ግዜ ውስጥ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት የተከሰተው በኢትዮጵያ ሚሌኒየም ወቅት ነበር። በወቅቱ የዋጋ ግሽበቱ 44 ነጥብ 4 ሆኖ ተመዝግቧል። እንዲሁም ደርግ በወደቀበት ዓመት የዋጋ ግሽበቱ 36 በመቶ ደርሶ እንደነበር የዓለም ባንክ መረጃ ያመላክታል። ከ 2005 ዓም ጀምሮ ለሶስት ዓመታት በአንድ ዲጂት ተወስኖ እና ተረጋግቶ የቆየው የዋጋ ግሽበት በ 2009 ዓ.ም አስር በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። በተለይ በመገባደድ ላይ ባለው ዓመት የተተኮሰው ግሽበት በተለይም የምግብ ምግብ ነክ ቁሶች ላይ የ 28̌ በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ይህንን ጭማሪ በቀላል ቋንቋ የሚያብራሩት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኙ አብዱልመናን መሃመድ «የመንግሥት ሰራተኞች ባለፈው ሁለት ዓመታት ብቻ የደመወዛቸውን 40 በመቶ ለዋጋ ግሽበት አስረክበዋል» ይላሉ። ይህ ማለት ከሁለት አመት በፊት 10 ሺህ ብር ደመወዝ የነበረው ሰው አሁን ላይ ባለው ግሽበት ሲሰላ ደመወዙ ወደ ስድስት ሺህ ብር አሽቆልቁሏል ማለት ነው። በመንግሥት መዋቅር "የስራ ሂደት አስተባባሪ" ማለት ዋና አለቃ ማለት ነው። "የእነርሱ ደመወዝ ኪስ የሚሞላ፤ ተለቅ ያለ ነው" ሲሉ ከስራቸው ያሉ ባለሞያዎች ያስባሉ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ባለ አንድ ተቋም ቡድን መሪ የሆነችው እመቤት ግን "የያዝነው ቦታማ ትልቅ ነው፤ ግን እኛም በችግር ነው የምንኖረው" ትላለች። እሷም የወር ደመወዟ 15 ቀን አይቆይላትም። እጇ ላይ 7500 ብር ቢደርስም አምስት ሺህ ብር "በጣም ጠባብ" ለምትላት ባለ ሁለት ክፍል ቤቷ ትከፍላለች። ሁለት ልጆች አሏት። "ቀነስ ያለ ትምህርት ቤት" ፈልጋ በወር 750 ብር ለአንድ ልጅ ትከፍላለች። ልጁን የሚያመላልስ ሰርቪስም ከፍያ ይጠይቃል። "የመንግሥት ሠራተኛ ከሆንሽ ልጅሽን የሚይዝ ሞግዚት ያስፈልጋል። የዘይት፣ የጤፍ ዋጋ ሰማይ ነው። ምን ያልተወደደ ነገር አለ?" በማለት "መኖር አዳግቶኛል" ስትል እመቤት ኑሮዋን ትገልጸዋለች። ከስምንት ዓመት ጀምሮ ቤት ለማግኘት ብትቆጥብም ህልም ሆኖ መቅረቱም ያስቆጫታል። ነገር ግን ደመወዝ ይጨመር ይሆን ብላ ትጠብቃለች። ረድኤትን እና እመቤትን የሚያስማማቸው አንድ ነገር አለ። በትምህርታቸው ለመግፋት ቢያቅዱም በገቢ እጥረት ምክንያት ትተውታል። ረድኤት እንደውም ጀምራ መክፈል ሲያቅታት ትታዋለች። እንደ እመቤት ሁሉ ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች የላባቸውን ውጤት ለዋጋ ግሽበት ሲያስረክቡ ውጤቱ አሳሳቢ መሆኑን የኢኮኖሚ ተንታኙ አብዱልመናን ይናገራሉ። "ይህ በኑሮ ደረጃ ላይ ከፍተኛ ጫና አለው። በተጨማሪም በሥራቸው ላይ ተነሳሽነት እና ደስታ ወይም እርካታ ማጣት ያጋጥማቸዋል። ይህ ለዝቅተኛ አፈጻጸም ብሎም ለሙስና በር ከፋች ነው" ሲሉ ባለሞያው ያብራራሉ። ለበርካታ ዓመታት የኑሮ ውድነቱ መሰረት የንግድ ሰንሰለቱ እንደሆነ ባለሞያዎች በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል። ይህም በተለይ ምርት ከገበሬው እስከ ሸማቹ እስከሚደርስ ባለው ሠንሰለት መሃል ያሉ ደላላዎችን ተወቃሽ ያደረገ ነበር። መንግሥት በተለይም ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች ላይ የሚታየውን ጭማሪ «ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው፣ የጥቂቶች አሻጥር» ሲል በተደጋጋሚ ይሰማል። ከሁለት ዓመታት በፊት ጀምሮ በ 2013 የተባባሰው ግሽበት ግን ምክንያቶቹ ከተለመደው የዘለሉ እንደሆኑ የኢኮኖሚ ባለሞያው አብዱል መናን ይናገራሉ። "አሁን ያጋጠመው የዋጋ ግሽበት ዋና መሰረቱ ብር ከሌሎች የውጪ ገንዘቦች አንጻር ዋጋው እንዲቀንስ በመደረጉ ምክንያት ነው። እንግዲህ ይህ የሆነው ለአስርት ዓመታት በዋጋ ግሽበት ሲናጥ ብሎም በፖለቲካ ያለመረጋጋት ውስጥ ባለ ኢኮኖሚ ላይ ነው" ሲሉ አዲስ ያሉትን ምክንያት ያብራራሉ። ይህ እንዲቆም ካስፈለገም መንግሥት የብርን ዋጋ የመቀነስ ፖሊሲውን ማቆም አለበት ሲሉም አብዱልመናን ይመክራሉ። እንዲሁም የባንኮችን ተቀማጭ ገንዘብ በመጨመር እና በሂደት የቁጠባ ወለድን ከፍ ማድረግን ጨምሮ የገንዘብ ፖሊሲውን ቆንጠጥ ማድረግ ችግሩን ያቃልለዋልም ይላሉ። ገንዘብ ዋጋ ለማጣቱ ምክንያት ከሚባሉት ነገሮች መካከል አንዱ መንግሥት እንዳሻው ከብሔራዊ ባንክ በመበደር ፈሰስ ማድረጉ ነው። ይህ ክስም አላግባብ የብር ኖት በማተም ኢኮኖሚው ውስጥ መክተት ሌላው ለዋጋ ግሸበቱ መሰረት እንደሆነ በባለሞያዎች ለአመታት ሲነሳ የቆየ ምክንያት ነው። አብዱልመናን ይህንን ችግር ለመቆጣጠር ቁልፍ የሚሉት ሌላው መፍትሄም ይሄንን ይመለከታል። "መንግስት ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ መጠን መቀነስ ይገባዋል" ሲሉ ያክላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-58215116
3politics
ባልደራስ አቶ እስክንድር ነጋ በእስር ቤት 'የደኅንነት ስጋት ገጥሞታል' አለ
አዲስ አበባ በሚገኝ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፕሬዘዳንት አቶ እስክንድር ነጋ "ደኅንነታቸው አደጋ ላይ ወድቋል" ሲል ፓርቲያቸው ስጋቱን ገለጸ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ገለታው ዘለቀ፤ አቶ እስክንድር ቃሊቲ ከሚገኘውና በተለምዶው 'ዋይታ' ተብሎ ከሚጠራው የማረሚያ ቤቱ ክፍል ወይም ዞን ወደ ሌላ እንዲዘዋወሩ በመደረጉ ስጋቱ መፈጠሩን ለቢቢሲ ገልጸዋል። አቶ ገለታው በስም ያልጠቀሷቸው "ከእስር ቤቱ ውጪ ያሉ" ባሏቸው ወገኖች አማካይነት "በተቀናጀ ዘመቻ" ምክንያት አቶ እስክንድር ወደ ዞን ስምንት እንዲዘዋወሩ መደረጋቸውን ገልጸዋል። ይህ ሁኔታ የተከሰተው ፓርቲው በእስር ላይ የሚገኙ አመራሮቹና አባላቱ በመጪው ምርጫ ላይ በዕጩነት እንዲቀርቡ የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ መሆኑንም አቶ ገለታው ተናግረዋል። በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ በሚገኘው 'ዋይታ' ተብሎ በሚታወቀው ዞን ውስጥ ስምንት ሰዎች እንደሚገኙ የጠቀሱት አቶ ገለታው፤ አቶ እስክንድር አሁን የሚገኙበት ዞን ከቀደመው የተለየ መሆኑንና የደኅንንት ስጋት እንደገጠማቸው ተናግረዋል። ጨምረውም "አቶ እስክንድር ከእስረኞች ማስፈራሪያ እና ማስጨነቅ ደርሶባቸዋል" በማለት የፓርቲው ፕሬዝዳንት ባሉበት የእስር ቤት ክፍል ውስጥ የገጠማቸውን ችግር አመልክተዋል። አቶ እስክንድር አሁን ያሉበት ዞን ስምንት በከፍተኛ ወንጀል ተጠጥረው የታሰሩ ሰዎች የሚታሰሩበት መሆኑን የገለጹት አቶ ገለታው፤ "እስክንድር ተቸግሬአለሁ ብሎ አያውቅም፤ ቢብስበት ነው ከዋይታ ለመውጣት ያመለከተው። አሁን ግን የባሰ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው" ሲሉ አክለዋል። አቶ እስክንድር ለደኅንነታቸው ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው፣ እስካሁን ግን ምንም አይነት አካላዊ ጥቃት እንዳልደረሰባቸው ጠቅሰው፤ "[የጥቃት] ሙከራ እንደተደረገባቸው እና ከአንድ የማረሚያ ቤቱ የጥበቃ ኃላፊ ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው እንደተነገራቸው ገልጸዋል" ብለዋል አቶ ገለታው። ያለው ሁኔታ "ለሕይወቴ አደጋ እደሆነ ከጠባቂዎች ተነግሮኛል፤ እኔም ይህንን ታዝቤአለሁ" በሚል አቶ እስክንድር እንደነገሯቸው አቶ ገለታው አክለዋል። ይህንንም በተመለከተ ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ጋር መፍትሄ ለመፈለግ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን አመልክተው፤ ዛሬም ለማረሚያ ቤቱ ደብዳቤ ጽፈው እንደሚያስገቡ ተናረግዋል። ቢቢሲ በዚህ ጉዳይ ላይ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት ስልካቸው ባለመነሳቱ ሳይሳካለት ቀርቷል። በተያያዘ ዜና በእስር ላይ ያሉት ከፍተኛ አመራሮችና በመጪው ምርጫ እጩ የሆኑት ተወዳዳሪዎች የሆኑት እነ አቶ አስክንድር ነጋ ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲለቀቁ ጠበቆቻቸው ጠይቀዋል። ጠበቆቻቸው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ፍትኃብሔር ቸሎት በትናንትናው ዕለት ሰኔ 1፣ 2013 ዓ.ም ባስገቡት የአቤቱታ ደብዳቤ ነው ይህንነ የጠየቁት። በአቤቱታ ደብዳቤው መሰረት የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ፣ አስቴር ስዩም ፣ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ ለመጪው ምርጫ እጩ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የምርጫው ውጤት እስኪታወቅ ድረስ በእስር መቆየት ስለማይችሉ በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታሉ ጠይቀዋል። አዲስ ነገር አለ በሚል ከመደበኛው ቀጠሮ በፊት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ጉዳያቸው በውጪ ሆነው እንዲከታተሉ መጠየቃቸው በደብዳቤው ላይ ሰፍሯል። አመራሮቹ ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ ክሱ ተቋርጦ ከእስር እንዲለቀቁ ለፍርድቤቱ የቀረበው አቤቱታ ላይ ዐቃቤ ሕግ መልስ እንዲሰጥበት ለዓርብ ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ እንደተሰጠ የባልደራስ የሕግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሄኖክ አክሊሉ መግለፃቸው በፓርቲው ማህበራዊ ትስስር ገፅ ሰፍሯል። አቶ እስክንድር ነጋና ሌሎች የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ከተፈጸመ በኋላ ከተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ይገኛሉ። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከጥቂት ወራት በፊት በእስር ላይ የሚገኙት አባላቱ በዚህ ወር በሚካሄደው ምርጫ ላይ ዕጩ ሆነው እንዲቀርቡ ምርጫ ቦርድን ጠይቆ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ታሳሪዎቹ በዕጩነት እንዲመዘገቡ መወሰኑ ይታወሳል። በእስር ላይ ሆነው ፓርቲውን ወክለው በዕጩነት ከተመዘገቡት አባላቱ መካከል አቶ እስክንድር አንዱ ናቸው።
ባልደራስ አቶ እስክንድር ነጋ በእስር ቤት 'የደኅንነት ስጋት ገጥሞታል' አለ አዲስ አበባ በሚገኝ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፕሬዘዳንት አቶ እስክንድር ነጋ "ደኅንነታቸው አደጋ ላይ ወድቋል" ሲል ፓርቲያቸው ስጋቱን ገለጸ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ገለታው ዘለቀ፤ አቶ እስክንድር ቃሊቲ ከሚገኘውና በተለምዶው 'ዋይታ' ተብሎ ከሚጠራው የማረሚያ ቤቱ ክፍል ወይም ዞን ወደ ሌላ እንዲዘዋወሩ በመደረጉ ስጋቱ መፈጠሩን ለቢቢሲ ገልጸዋል። አቶ ገለታው በስም ያልጠቀሷቸው "ከእስር ቤቱ ውጪ ያሉ" ባሏቸው ወገኖች አማካይነት "በተቀናጀ ዘመቻ" ምክንያት አቶ እስክንድር ወደ ዞን ስምንት እንዲዘዋወሩ መደረጋቸውን ገልጸዋል። ይህ ሁኔታ የተከሰተው ፓርቲው በእስር ላይ የሚገኙ አመራሮቹና አባላቱ በመጪው ምርጫ ላይ በዕጩነት እንዲቀርቡ የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ መሆኑንም አቶ ገለታው ተናግረዋል። በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ በሚገኘው 'ዋይታ' ተብሎ በሚታወቀው ዞን ውስጥ ስምንት ሰዎች እንደሚገኙ የጠቀሱት አቶ ገለታው፤ አቶ እስክንድር አሁን የሚገኙበት ዞን ከቀደመው የተለየ መሆኑንና የደኅንንት ስጋት እንደገጠማቸው ተናግረዋል። ጨምረውም "አቶ እስክንድር ከእስረኞች ማስፈራሪያ እና ማስጨነቅ ደርሶባቸዋል" በማለት የፓርቲው ፕሬዝዳንት ባሉበት የእስር ቤት ክፍል ውስጥ የገጠማቸውን ችግር አመልክተዋል። አቶ እስክንድር አሁን ያሉበት ዞን ስምንት በከፍተኛ ወንጀል ተጠጥረው የታሰሩ ሰዎች የሚታሰሩበት መሆኑን የገለጹት አቶ ገለታው፤ "እስክንድር ተቸግሬአለሁ ብሎ አያውቅም፤ ቢብስበት ነው ከዋይታ ለመውጣት ያመለከተው። አሁን ግን የባሰ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው" ሲሉ አክለዋል። አቶ እስክንድር ለደኅንነታቸው ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው፣ እስካሁን ግን ምንም አይነት አካላዊ ጥቃት እንዳልደረሰባቸው ጠቅሰው፤ "[የጥቃት] ሙከራ እንደተደረገባቸው እና ከአንድ የማረሚያ ቤቱ የጥበቃ ኃላፊ ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው እንደተነገራቸው ገልጸዋል" ብለዋል አቶ ገለታው። ያለው ሁኔታ "ለሕይወቴ አደጋ እደሆነ ከጠባቂዎች ተነግሮኛል፤ እኔም ይህንን ታዝቤአለሁ" በሚል አቶ እስክንድር እንደነገሯቸው አቶ ገለታው አክለዋል። ይህንንም በተመለከተ ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ጋር መፍትሄ ለመፈለግ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን አመልክተው፤ ዛሬም ለማረሚያ ቤቱ ደብዳቤ ጽፈው እንደሚያስገቡ ተናረግዋል። ቢቢሲ በዚህ ጉዳይ ላይ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት ስልካቸው ባለመነሳቱ ሳይሳካለት ቀርቷል። በተያያዘ ዜና በእስር ላይ ያሉት ከፍተኛ አመራሮችና በመጪው ምርጫ እጩ የሆኑት ተወዳዳሪዎች የሆኑት እነ አቶ አስክንድር ነጋ ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲለቀቁ ጠበቆቻቸው ጠይቀዋል። ጠበቆቻቸው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ፍትኃብሔር ቸሎት በትናንትናው ዕለት ሰኔ 1፣ 2013 ዓ.ም ባስገቡት የአቤቱታ ደብዳቤ ነው ይህንነ የጠየቁት። በአቤቱታ ደብዳቤው መሰረት የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ፣ አስቴር ስዩም ፣ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ ለመጪው ምርጫ እጩ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የምርጫው ውጤት እስኪታወቅ ድረስ በእስር መቆየት ስለማይችሉ በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታሉ ጠይቀዋል። አዲስ ነገር አለ በሚል ከመደበኛው ቀጠሮ በፊት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ጉዳያቸው በውጪ ሆነው እንዲከታተሉ መጠየቃቸው በደብዳቤው ላይ ሰፍሯል። አመራሮቹ ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ ክሱ ተቋርጦ ከእስር እንዲለቀቁ ለፍርድቤቱ የቀረበው አቤቱታ ላይ ዐቃቤ ሕግ መልስ እንዲሰጥበት ለዓርብ ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ እንደተሰጠ የባልደራስ የሕግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሄኖክ አክሊሉ መግለፃቸው በፓርቲው ማህበራዊ ትስስር ገፅ ሰፍሯል። አቶ እስክንድር ነጋና ሌሎች የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ከተፈጸመ በኋላ ከተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ይገኛሉ። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከጥቂት ወራት በፊት በእስር ላይ የሚገኙት አባላቱ በዚህ ወር በሚካሄደው ምርጫ ላይ ዕጩ ሆነው እንዲቀርቡ ምርጫ ቦርድን ጠይቆ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ታሳሪዎቹ በዕጩነት እንዲመዘገቡ መወሰኑ ይታወሳል። በእስር ላይ ሆነው ፓርቲውን ወክለው በዕጩነት ከተመዘገቡት አባላቱ መካከል አቶ እስክንድር አንዱ ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-57397740
5sports
ኢንተር ሚላን የማንችስተር ዩናይትዱን ጄሲ ሊንጋርድ ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተነገረ
በዘንድሮው የጥር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቦች የሚያተኩሩባቸውን ተጫዋቾች እየጠቀሱ ነው። ምንም እንኳ እስካሁን በዝውውሩ ስማቸው የሚነሳ ትልልቅ ተጫዋቾች ቁጥር አናሳ ቢሆንም በርከት ያሉ ተጫዋቾች ግን በዝውውሩ ክለብ የቀይራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን፤ የማንችስተር ዩናይትድና የአንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነውን የ28 ዓመቱን ጄሲ ሊንጋርድን ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየቱን ሚረር ዘግቧል። ይህ የሚሆነው ግን ኢንተር ሚላን ዴንማርካዊው ክርስቲያን ኤሪክሰንን ካሰናበተ ነው ተብሏል። ሌላኛውን የዩናይትዱን አማካይ ፖል ፖግባን ደግሞ የፓሪስ ሴይንት ዠርሜኑ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቺቲኖ አጥብቀው እንደሚፈልጉት እና ቡድናቸውንም በ27 ዓመቱ ፈረንሳያዊ አማካይ ላይ መመስረት እንደሚፈልጉ ዴይሊ ስታር መረጃ ደርሶኛል ብሏል። ሜይል እንደጻፈው ከሆነ የአር ቢ ሌፕዚጉን ፈረንሳያዊ ተከላካይ ዳዮት ኡፓሜካኖ ለማስፈረም የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ውድድሩ ውስጥ ገብቷል። ይህንን ተጫዋች ማንችስተር ዩናይትድም እንደሚፈልገው ማንችስተር ኢቭኒንግ ኒውስ ዘግቧል። ላለፉት ወራት ከቡድን ስብስቡ ውስጥ ያልተካተተው የአርሰናሉ አማካይ ሜሱት ኦዚል፣ ምናልባት ወደ ቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ ሊያመራ እንደሚችል ሰን ጽፏል። የ32 ዓመቱ ኦዚል በአርሰናል ቆይታው ሊኖረው የሚችለውን 350 ሺህ ሳምንታዊ ደመወዙን ለሦስት ዓመታት ተቀናንሶ እየተከፈለው ወደ ፌነርባቼ ሊያመራ ይችላል ተብሏል። ሌላኛው የአርሰናሉ አማካይ ሉካስ ቶሬራ ወደ ፊዮረንቲና ሊያመራ እንደሚችል የስፔኑ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ዘግቧል። የ24 ዓመቱ ኡራጓያዊ አማካይ፣ ለስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ በውሰት ተሰጥቶ እየተጫወተ ቢቆይም እንደታሰበው ስኬታማ አልሆነለትም ተብሏል። ፉትቦል ኢንሳይደር እንደዘገበው የሊዮኑ ፈረንሳያዊ አጥቂ ሙሳ ደምበሌ ከዌስትሃም የቀረበለትን የጥር ወር ዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። ከአሁን በፊት ለሴልቲክ የተጫወተው ፈረንሳያዊው አጥቂ ምናልባትም የስፔኑን አትሌቲኮ ማድሪድ ለመቀላቀል ሳይቃረብ እንዳልቀረ የስፔኑ ማርካ ጋዜጣ አስነብቧል። ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ አማካይ ፈርናንዲንሆ ከሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት በውድድር ዓመቱ ይጠናቀቃል። በመሆኑም የ35 ዓመቱ ተጫዋች ወደ አገሩ ብራዚል ወይም ወደ ሌሎች የአውሮፓ ክለቦች ሊሄድ እንደሚችል ጎል አስነብቧል። ቱቶ መርካቶ እንደሚለው ደግሞ ግሪካዊውን የአርሰናል የመሃል ተከላካይ ለማስፈረም ጂንዋ ከስፔኑ ሪያል ቤቲስ ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል ተብሏል። ዌስትሃም ሴኔጋላዊውን የ22 ዓመት የዋትፎርድ አጥቂ እስማየላ ሳርን ለማስፈረም 30 ሚሊዮን ፓውንድ ማዘጋጁን ሰን ሰምቻለሁ ብሏል። የዌስትሃም አለቃ ዴቪድ ሞይስ የሪያል ማድሪዱን የፊት መስመር ተሰላፊ የ27 ዓመቱን ማሪያኖ ዲያዝን በውሰት ለማምጣት ፍላጎት እንዳላቸውም ሜይል ዘግቧል።
ኢንተር ሚላን የማንችስተር ዩናይትዱን ጄሲ ሊንጋርድ ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተነገረ በዘንድሮው የጥር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቦች የሚያተኩሩባቸውን ተጫዋቾች እየጠቀሱ ነው። ምንም እንኳ እስካሁን በዝውውሩ ስማቸው የሚነሳ ትልልቅ ተጫዋቾች ቁጥር አናሳ ቢሆንም በርከት ያሉ ተጫዋቾች ግን በዝውውሩ ክለብ የቀይራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን፤ የማንችስተር ዩናይትድና የአንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነውን የ28 ዓመቱን ጄሲ ሊንጋርድን ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየቱን ሚረር ዘግቧል። ይህ የሚሆነው ግን ኢንተር ሚላን ዴንማርካዊው ክርስቲያን ኤሪክሰንን ካሰናበተ ነው ተብሏል። ሌላኛውን የዩናይትዱን አማካይ ፖል ፖግባን ደግሞ የፓሪስ ሴይንት ዠርሜኑ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቺቲኖ አጥብቀው እንደሚፈልጉት እና ቡድናቸውንም በ27 ዓመቱ ፈረንሳያዊ አማካይ ላይ መመስረት እንደሚፈልጉ ዴይሊ ስታር መረጃ ደርሶኛል ብሏል። ሜይል እንደጻፈው ከሆነ የአር ቢ ሌፕዚጉን ፈረንሳያዊ ተከላካይ ዳዮት ኡፓሜካኖ ለማስፈረም የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ውድድሩ ውስጥ ገብቷል። ይህንን ተጫዋች ማንችስተር ዩናይትድም እንደሚፈልገው ማንችስተር ኢቭኒንግ ኒውስ ዘግቧል። ላለፉት ወራት ከቡድን ስብስቡ ውስጥ ያልተካተተው የአርሰናሉ አማካይ ሜሱት ኦዚል፣ ምናልባት ወደ ቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ ሊያመራ እንደሚችል ሰን ጽፏል። የ32 ዓመቱ ኦዚል በአርሰናል ቆይታው ሊኖረው የሚችለውን 350 ሺህ ሳምንታዊ ደመወዙን ለሦስት ዓመታት ተቀናንሶ እየተከፈለው ወደ ፌነርባቼ ሊያመራ ይችላል ተብሏል። ሌላኛው የአርሰናሉ አማካይ ሉካስ ቶሬራ ወደ ፊዮረንቲና ሊያመራ እንደሚችል የስፔኑ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ዘግቧል። የ24 ዓመቱ ኡራጓያዊ አማካይ፣ ለስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ በውሰት ተሰጥቶ እየተጫወተ ቢቆይም እንደታሰበው ስኬታማ አልሆነለትም ተብሏል። ፉትቦል ኢንሳይደር እንደዘገበው የሊዮኑ ፈረንሳያዊ አጥቂ ሙሳ ደምበሌ ከዌስትሃም የቀረበለትን የጥር ወር ዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። ከአሁን በፊት ለሴልቲክ የተጫወተው ፈረንሳያዊው አጥቂ ምናልባትም የስፔኑን አትሌቲኮ ማድሪድ ለመቀላቀል ሳይቃረብ እንዳልቀረ የስፔኑ ማርካ ጋዜጣ አስነብቧል። ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ አማካይ ፈርናንዲንሆ ከሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት በውድድር ዓመቱ ይጠናቀቃል። በመሆኑም የ35 ዓመቱ ተጫዋች ወደ አገሩ ብራዚል ወይም ወደ ሌሎች የአውሮፓ ክለቦች ሊሄድ እንደሚችል ጎል አስነብቧል። ቱቶ መርካቶ እንደሚለው ደግሞ ግሪካዊውን የአርሰናል የመሃል ተከላካይ ለማስፈረም ጂንዋ ከስፔኑ ሪያል ቤቲስ ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል ተብሏል። ዌስትሃም ሴኔጋላዊውን የ22 ዓመት የዋትፎርድ አጥቂ እስማየላ ሳርን ለማስፈረም 30 ሚሊዮን ፓውንድ ማዘጋጁን ሰን ሰምቻለሁ ብሏል። የዌስትሃም አለቃ ዴቪድ ሞይስ የሪያል ማድሪዱን የፊት መስመር ተሰላፊ የ27 ዓመቱን ማሪያኖ ዲያዝን በውሰት ለማምጣት ፍላጎት እንዳላቸውም ሜይል ዘግቧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55608009
2health
“እስክሞት ልታገል”፡ የኩላሊት ህሙማን መርጃ ያቋቋመው የኩላሊት ታማሚ
የህክምና ምርመራ ውጤት! ሕይወታችንን ባላሰብነው፣ ባልጠበቅነው መንገድ ይገለባብጣል። ለኢዮብ ተወልደመድኅን ያ ክፉ ጊዜ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ነበር። የኩላሊት ታማሚ እንደሆነ ሐኪሞች ሲገሩት። የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ኢዮብ ይህን ዜና ሲሰማ የሚገባበት ጠፋው። ባለቤቱ በድንጋጤ ከፍተኛ ሐዘን ተጫናት። አዲስ አበባ ውስጥ የተክለሐይማኖት ሰፈር ልጅ ነው። ከ1979 ዓ. ም. ጀምሮ ግን ለአምስት ዓመታት አሰበ ተፈሪ ኖሯል። ዘጠነኛ ክፍልን አብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ተምሮ 10ኛ ክፍል ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት በማታ ፈረቃ ገባ። የግድ ታናናሾቹን ማሳደግ ስለነበረበት ከ11ኛ ክፍል በላይ መቀጠል አልቻለም። ትምህርቱን አቋርጦ እንጨት ሥራ ያዘ። በእንጨትና አልሙንየም ሥራ ተቀጥሮ ለሦስት ዓመታት ሠራ። ጥሩ ገቢ ያገኝ ስለነበር ታናናሽ ወንድሞቹን፣ እናትና አባቱንም ያስተዳድር ጀመር። 1991 ዓ.ም. ላይ ከብድርና ቁጠባ ተቋም አነስተኛ ገንዘብ ተበድሮ ቤቱ የእንጨት ሥራ ከፈተ። ገቢው እያደገ መጣ። ንግዱ ሲጦፍ ከመንግሥት ቦታ ወስዶ እንጨት ሥራውን አስፋፋ። በልደታ ክፍለ ከተማ በከፈተው እንጨት ቤት ሙያውን ያስተምርም ነበር። ጥቅምት 2006 ዓ.ም. ላይ የኩላሊት ህመም አለብህ ሲባል ግን ነገሮች መስመር ሳቱ። ሥራውን ወዲያው አላቋረጠም። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደው መምጣቱ ግን አልቀረም። ከታመመ ከሁለት ዓመት በኋላ አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከጥቃቅንና መካከለኛ የንግድ ሰዎች አንዱ ብሎ ሸልሞታል። የኩላሊት ህመም አቅም ይነሳል። አካልን፣ ሥነ ልቦናን፣ ቤተሰብን፣ ጓደኛን፣ ሥራን ይፈትናል። ኢዮብ የገጠመውም ይኸው ነው። የኩላሊት ህክምና እድሜ ልክ የሚወስድ፣ ገንዘብንም የሚያሟጥጥ እንደሆነ ሲገነዘብ የባለቤቱና የሕጻናት ልጆቹ እጣ ፈንታ እንቅልፍ ነሳው። ቤተሰቤን ድሃ አድርጌ ከምሞት ምነው እኔው ቀድሜ ብሞት ሲል ያስብ እንደነበር ይናገራል። በአንድ ወር ውስጥ የኩላሊት እጥበት [ዳያለሲስ] ካላደረገ እንደሚሞት ሲነገረው ቤተሰቡና ጓደኞቹ ተረበሹ። በአፋጣኝ ኮርያ ሆስፒታል ወስደውት የኩላሊት እጥበት ጀመረ። ህመሙም ጋብ አለለት። ያኔ ሆስፒታሉ ውስጥ ያየው ነገር የሕይወት አቅጣጫውን እንዲቀይር እንዳደረገው ያስታውሳል። "አቅም የሌለው፣ መካከለኛ ገቢ ያለው፣ ባለ ሀብት ታካሚም አለ። ልዩነቱ በግልጽ ይታያል። በርካቶች ህክምናውን ለማድረግ አቅም አልነበራቸውም። እኔ ታክሜ ነጻነት ሳገኝ ለምኖ ያልሞላለት ሰው ግን ምን ያህል ነጻነቱን ያጣል? ስል አሰብኩ።" ለወራት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ የህክምናው ወጪ ከብዷቸው የሚያቋርጡ እንዳሉ ይሰማ ነበር። ወጪው ከአቅማቸው በላይ ሆኖ የሚሞቱትንም ቤቱ ይቁጠራቸው። "እስክሞት ልታገል" ኩላሊት መሥራት ሲያቆም የኩላሊት እጥበት ማድረግ ግዴታ ነው። ህመሙ የሌለባቸው ሰዎች ሰውነታቸው ውስጥ የሚከማች ቆሻሻን ሽንት በመሽናት ያስወግዳሉ። ታማሚዎች የኩላሊት እጥበት ካላደረጉ ቆሻሻው አይወጣም ማለት ነው። እናም ሰውነታቸው ይታፈናል፣ ያብጣል፣ ሲከፋም ሕይወታቸውን ያጣሉ። በሳምንት ሦስቴ የኩላሊት እጥበት ማድረግ የሚጠበቅበት ሰው በሳምንት አንዴ ብቻ ቢያደርግ ወይም ቢያቋርጥ ይህ መታፈን ይገጥመዋል። ምግብ መብላትም አይችልም። ኢዮብ በህመሙ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችን ሲያይ በቀረኝ ሕይወት የአቅሜን መርዳት አለብኝ ብሎ ወሰነ። ህሙማን የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙበት እና መንግሥት ከህመሙ ጋር በተያያዘ የሚያወጣቸው ውሳኔዎች ላይ ጫና ማሳደር የሚቻልበት ማኅበር አቋቋመ። 'ሞት በኩላሊት ይብቃ' የተጀመረው በ2007 ዓ.ም. ነው። በታመመበት ጊዜ በመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት አልነበረም። በግል ሆስፒታልም በውስን ቦታ፣ በውድ ገንዘብ ይከናወናል። ህክምናውን ለማግኘት የሚደረገው ጥረት አሁንም ድረስ ከባድ ነው። በመንግሥት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት በአንድ ዙር 500 ብር ያስከፍላል። በግል ሆስፒታሎች ደግሞ ከ1500 እስከ 3500 ብር ያወጣል። "መሞቴ አይቀርም እስክሞት ልታገል ብዬ ወሰንኩ። ለመንግሥት አካላት እና ለአንዳንድ ተቋማት ድምጼን ማሰማት ጀመርኩ። በመኪና እየዞሩ መቀስቀስ፣ ብሮሸር መለጠፍም ቀጠልኩ። ይኸው 8 ዓመት ኖርኩኝ። በጥቂት ቦታም ቢሆን በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ተጀምሯል። ይሄ በኩራት የምናገረው የልፋቴ ውጤት ነው።" ማኅበሩ ከምስረታው ጀምሮ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ120 በላይ ህሙማንን ደግፏል። ቁጥሩ ለቀን፣ ለሳምንት፣ ለአንድ ወር ወይም ለሁለት ወር የኩላሊት እጥበት ገንዘብ የሚከፈልላቸውን ይጨምራል። ወርሀዊ መዋጮ በማድረግ እና በጉልበት ሥራ የሚደግፉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ደበበ እሸቱ፣ ስዩም ተፈራ፣ ዳንኤል ተገኝ ታዋቂ የማኅበሩ አባላት ናቸው። ኢዮብ "አምባሳደሮቻችን" ይላቸዋል። ከ2007 ወዲህ ድጎማ ከተደረገላቸው ህሙማን መካከል አምስቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሞት በኩላሊት ይብቃ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በምኒሊክ እና በዘውዲቱ ሆስፒታሎች ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ለሁለት ዓመት ነጻ የኩላሊት እጥበት ከሚሰጣቸው 105 ህመምተኞች አንዱ ኢዮብ ነው። ያቋቋመው ማኅበር ከያዛቸው ፕሮጀክቶች አንዱ የኩላሊት ህሙማን ተደራጅተው ሥራ እንዲሠሩ ከክፍለ ከተሞች ጋር መነጋገር ነው። ይህም ለህክምና ገንዘብ ሲሉ ጎዳና ወጥተው ለመለመን የተገደዱ ወገኖችን ለመደገፍ ያለመ ነው። ፕሮጀክቱን የጤና ሚንስትር እና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ድጋፍ ሰጥቶት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአንድ ህመምተኛ የሥራ እድል ተፈጥሯል። በሌሎች ክፍለ ከተሞችም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ወጋገን ባንክ ለህመምተኞች መርጃ ገንዘብ የሚሰበሰብበት ሳጥን ተቀምጧል። በቋሚነት በሳምንት ለአንድ ህመምተኛ የኩላሊት እጥበት ክፍያ የሚያደርጉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ማኅበሩ በሰበሰበው ገንዘብ ሦስት ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሲሆን፤ ነጻ ህክምና የሚያገኙ እንዳሉም ይናገራል። "ኢትዮጵያ ውስጥ የኩላሊት እጥበት ክፍያ ከፍተኛ ስለሆነ ከ70 እስከ 80 በመቶ ያሚሆነው የኩላሊት ህመምተኛ በሳምንት አንዴ ወይም ሁለት ቀን ነው የሚያደርገው" ይላል። ማኅበሩ በሠራው ስሌት መሠረት አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ከ700 ያላነሱ የኩላሊት ህመምተኞች በግል ሆስፒታል ነው ህክምና የሚከታተሉት። ዝቅተኛ የሚባለውን የአንድ ዙር የኩላሊት እጥበት ወጪ 1500 ብር መክፈል የሚችሉ ውስን ናቸው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጎዳና ላይና በየሐይማኖት ተቋማት ከመለመን ውጪም አማራጭ የለውም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢዮብ ማኅበር የመዋጮ ፕሮጀክት ቀርጿል። ሐሳቡ በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር የሚያዋጡ አንድ ሚሊዮን ሰዎችን በማኅበሩ አባልነት መመዝገብ ነው። ፕሮጀክቱ ከሦስት ዓመት በፊት ሲጀመር ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጀምሮ፣ ታዋቂ ሰዎችና ሌሎች ሰዎችን ጨምሮ ወደ 3000 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል። ከአባላቱ የሚሰበሰበውን ገንዘብ የሚከታተል መተግበሪያ እያሠሩ ነው። ኢትዮ-ቴሌኮም አጭር የጽሑፍ መልዕክት (ኤስኤምኤስ) እየላከ ገንዘቡን ሰብስቦ በቀጥታ ወደ ጤና ሚንስትር እንዲያስገባ ለማድረግ ወጥነዋል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር ቢያዋጡ፤ በአንድ ዓመት በአጠቃላይ 120 ሚሊዮን ብር ይገኛል። ይህም ለነጻ የኩላሊት ህክምና እንዲውል እንደሚፈልግ ኢዮብ ይናገራል። "ይህ ገንዘብ በመሀል ምንም ሂደት ሳይኖር ከቴሌ ወደ ጤና ሚንስትር በቀጥታ ስለሚገባ ተአማኒነት ይኖረዋል" ይላል። ከጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር በጉዳዩ ላይ ከስድስት ወር በፊት እንደተነጋገረ ይገልጻል። "ሚንስትሯ በሐሳቡ ደስተኛ እንደሆኑና ለመደገፍ ፍቃደኛ እንደሆኑ ነግረውኛል። ገንዘቡ ከቴሌ ወደ ጤና ጥበቃ በቀጥታ እንዲገባ እንደምንፈልግ ስነግራቸው የሕግ አግባቡን ልይ ብለዋል።" የቀድሞው የጤና ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን ሐሳቡን ደግፈው የአባልነት መታወቂያ አውጥተዋል። የኢዮብ ውጥን ተሳክቶ በአንድ ዓመት 120 ሚሊዮን ብር ማግኘት ከተቻለ እስከ 500 ሰዎች ለዓመት በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት በነጻ ያገኛሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲደግፏቸው ለማድረግ መልዕክት እንደላኩና እስካሁን እንዳላገኟቸው የሚናገረው ኢዮብ በድጋሚ ጥያቄ እንደሚያቀርብላቸው ገልጿል። ሐሳቡ እውን ከሆነ "መዋጮው ኪስ አይጎዳም። ብንኖርም ባንኖርም ቋሚና ቀጣይ ይሆናል። ጤናማው ሰው የሚያዋጣው ገንዘብ ወደ ኋላ መገልገያው እንዲሆን የጤና መድኅን አካል ማድረግም ይቻላል" ሲል ተስፋውን ይናገራል። እንደ ኩላሊት፣ ካንሰር እና ልብ ያሉ ህመሞች ህክምና ሊሰጥባቸው እየተገባ ብዙዎች የሚሞቱባቸው ናቸው። ምናልባትም እንዲህ ባሉ የረድኤት ፕሮጀክቶች ችግሩን መቅረፍ ይቻላል ብሎ ያምናል። "ባለቤቴ- ጀግናዬ" ኢዮብ ከመታመሙ በፊት ለራሱና ለቤተሰቡ ሕይወት መለወጥ የሚተጋ ሰው ነበር። አሁን ግን የብዙዎችን ኃላፊነት ለመሸከም መርጧል። የማኅበሩ መስራች፣ ሥራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆን ሹፌር፣ ቀስቃሽ፣ ገንዘብ ሰብሳቢ የሆነባቸውን ጊዜያት ያስታውሳል። ሥራውን "ፈጣሪ እና ህሊናዬ የተደሰቱበት ስለሆነ ኩራት እና ደስታ ይሰማኛል" ሲል ይገልጸዋል። ለስምንት ዓመታት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ ወገቡ እና እግሩ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት በድጋፍ ነው የሚንቀሳቀሰው። እንደ ቀድሞው የማኅበሩን ሥራዎች እንዳያከናውንም አድርጎታል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የሰውነት ክብደቱ ከ56 ወደ 46 ኪሎ ቀንሷል። ብርታት ከሚሰጡት በዋነኛነት የሚጠቅሰው "ጀግናዬ" የሚላት ባለቤቱን ነው። "በጤናማነቴ ጊዜ ያፈራሁትን ከ1.5 ሚልዮን ብር በላይ ለማኅበሩ ሳውል ነገ ይሞታል ብላ ቅር አላላትም። ብር አንሶን የልጆቼን መኖርያ ቤት ስሸጥ እሷ የነበረንን ንግድ ቤት በመሸጥ ሹፌር ሆና ልጆቹን አስተማረች። ለዛሬ አብቅታኛለችና ጀግናዬ ናት።" ሲታመም የሩቅና የቅርብ ቤተሰብ፣ ጓደኛም በአብዛኛው እንደሸሸው ይናገራል። ከልጆቹ ጋር ሰፊ ጊዜ ባለማሳለፉ፣ እንዳሻቸው ባለማዝናናቱም ያዝናል። ከኩላሊት ታማሚዎች ጋር ስቴድየም ዙርያ፣ ባዛሮች ላይ እንዲሁም ወደ መንግሥትና የግል ተቋማት እየሄደ እርዳታ ለማሰባሰብ ይሞክራል። ህክምናውን ትቶ የማኅበሩን ጉዳይ የሚከታተልባቸው ጊዜያትም አሉ። የኩላሊት ህመም "ሳቄን፣ ደስታዬን፣ እግሬን አሳጥቶኛል" ይላል። ከዚህ በተቃራኒው "እውነተኛ ታጋይና ለወገን ቶርቋሪ አድርጎኛል" ሲል ያለበት ሁኔታ ይገልጻል። በእሱ ማኅበር ውስጥ ይረዱ ከነበሩ ህሙማን መካከል ኋላ ላይ በራሳቸው ማኅበር መስርተው መንቀሳቀስ የጀመሩ ሰዎች መኖራቸው ያስደስተዋል። ህሙማንን ሲረዳ ከሚያገኘው እፎይታ በተጨማሪ ቤተሰቡ ሐሴት ይሰጠዋል። "ሁሌም ሚስቴና ልጆቼ የተቃጠልኩትን ማቀዝቀዣዎቼ ናቸው" ይላቸዋል። ሐኪሞች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ እንዳለበት ነግረውታል። ኩላሊት የሚሰጠው የቤተሰብ አባል ቢያገኝም የወጪው ነገር አሳሳቢ ነው። የማኅበሩ ስኬት ከሚላቸው መካከል ብዙ ገንዘብ ባይኖራቸውም ለህሙማን ገንዘብ ለመለገስ የሚፈቅዱ ሰዎች ማግኘታቸውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን የሚያስደነግጥ ምስል ወይም የተጎዳ ሰው ቁስል ካልታየ በስተቀር በማኅበረሰቡ ዘንድ እምብዛም ሰዎችን የመርዳት ተነሳሽነት እንደሌለ አስተውሏል። የተጎዱ ሰዎችን ለይቶ በቀጥታ የመርዳት ልማድ ባለመኖሩ ማኅበረሰቡ እርዳታ የሚሰጠው ባገኘው አጋጣሚ፣ በየመንገዱ ለሚያገኘው ገንዘብ ጠያቂ ነው። ይህም በእርዳታ ስም የሚያጭበረብሩ እንዲበራከቱ መንገድ እንደከፈተም ያምናል። ሰዎች ባላቸው አቅም ተጎጂዎችን በእቅድ የመርዳት ባህል እንዲዳብሩ ይመኛል። የኩላሊት ህክምና በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሕግ አንድ ሰው ኩላሊቱ መሥራት ካቆመ ከቤተሰቡ ውጪ ኩላሊት ከሌላ ሰው መውሰድ አይችልም ይላል። ይህ ሕግ ቤተሰብ የሌላቸው ወይም ከቤተሰቦቻቸው ጋር የደም አይነታቸው የማይመሳሰል ሰዎችን ሕይወት አደጋ ውስጥ ጥሏል ይላል። ዘመድ፣ አብሮ አደግ ወይም ሌላ ለጋሽ ኩላሊት የሚሰጥበት አሠራር እንዲዘረጋ ለጤና ሚንስቴር ማሳሰቡንም ኢዮብ ይናገራል። ሌላው ክፍተት የኩላሊት ንቅለ ተከላ የሚከናወነው በጳውሎስ ሆስፒታል ብቻ መሆኑ ነው። ይህ አገልግሎት ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መነሳት ወዲህ መቋረጡም ሌላ ችግር ነው። በሌላ በኩል ንቅለ ተከላ ያደረጉ ሰዎች የመድኃኒት እጥረት ይገጥማቸዋል። የኩላሊት እጥበት የሚያደርጉ ሰዎችም እንዲሁ ተጓዳኝ የሰውነት መጠገኛ መድኃኒቶች ያጣሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ መድኃኒቶቹን ማግኘት ከባድ ነው። ያሉትም በጣም ውድ ናቸው። ኢዮብ ከታመመበት ከስምንት ዓመታት ወዲህ ብዙ ነገሮች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን አይክድም። "ትላንት የነበረውን ጨለማ ስለማውቀው የዛሬው የተሻለ ነው እላለሁ" ይላል። ሆኖም ግን አሁንም ያሉ ክፍተቶች እንዲሸፈኑ ይጠይቃል።
“እስክሞት ልታገል”፡ የኩላሊት ህሙማን መርጃ ያቋቋመው የኩላሊት ታማሚ የህክምና ምርመራ ውጤት! ሕይወታችንን ባላሰብነው፣ ባልጠበቅነው መንገድ ይገለባብጣል። ለኢዮብ ተወልደመድኅን ያ ክፉ ጊዜ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ነበር። የኩላሊት ታማሚ እንደሆነ ሐኪሞች ሲገሩት። የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ኢዮብ ይህን ዜና ሲሰማ የሚገባበት ጠፋው። ባለቤቱ በድንጋጤ ከፍተኛ ሐዘን ተጫናት። አዲስ አበባ ውስጥ የተክለሐይማኖት ሰፈር ልጅ ነው። ከ1979 ዓ. ም. ጀምሮ ግን ለአምስት ዓመታት አሰበ ተፈሪ ኖሯል። ዘጠነኛ ክፍልን አብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ተምሮ 10ኛ ክፍል ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት በማታ ፈረቃ ገባ። የግድ ታናናሾቹን ማሳደግ ስለነበረበት ከ11ኛ ክፍል በላይ መቀጠል አልቻለም። ትምህርቱን አቋርጦ እንጨት ሥራ ያዘ። በእንጨትና አልሙንየም ሥራ ተቀጥሮ ለሦስት ዓመታት ሠራ። ጥሩ ገቢ ያገኝ ስለነበር ታናናሽ ወንድሞቹን፣ እናትና አባቱንም ያስተዳድር ጀመር። 1991 ዓ.ም. ላይ ከብድርና ቁጠባ ተቋም አነስተኛ ገንዘብ ተበድሮ ቤቱ የእንጨት ሥራ ከፈተ። ገቢው እያደገ መጣ። ንግዱ ሲጦፍ ከመንግሥት ቦታ ወስዶ እንጨት ሥራውን አስፋፋ። በልደታ ክፍለ ከተማ በከፈተው እንጨት ቤት ሙያውን ያስተምርም ነበር። ጥቅምት 2006 ዓ.ም. ላይ የኩላሊት ህመም አለብህ ሲባል ግን ነገሮች መስመር ሳቱ። ሥራውን ወዲያው አላቋረጠም። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደው መምጣቱ ግን አልቀረም። ከታመመ ከሁለት ዓመት በኋላ አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከጥቃቅንና መካከለኛ የንግድ ሰዎች አንዱ ብሎ ሸልሞታል። የኩላሊት ህመም አቅም ይነሳል። አካልን፣ ሥነ ልቦናን፣ ቤተሰብን፣ ጓደኛን፣ ሥራን ይፈትናል። ኢዮብ የገጠመውም ይኸው ነው። የኩላሊት ህክምና እድሜ ልክ የሚወስድ፣ ገንዘብንም የሚያሟጥጥ እንደሆነ ሲገነዘብ የባለቤቱና የሕጻናት ልጆቹ እጣ ፈንታ እንቅልፍ ነሳው። ቤተሰቤን ድሃ አድርጌ ከምሞት ምነው እኔው ቀድሜ ብሞት ሲል ያስብ እንደነበር ይናገራል። በአንድ ወር ውስጥ የኩላሊት እጥበት [ዳያለሲስ] ካላደረገ እንደሚሞት ሲነገረው ቤተሰቡና ጓደኞቹ ተረበሹ። በአፋጣኝ ኮርያ ሆስፒታል ወስደውት የኩላሊት እጥበት ጀመረ። ህመሙም ጋብ አለለት። ያኔ ሆስፒታሉ ውስጥ ያየው ነገር የሕይወት አቅጣጫውን እንዲቀይር እንዳደረገው ያስታውሳል። "አቅም የሌለው፣ መካከለኛ ገቢ ያለው፣ ባለ ሀብት ታካሚም አለ። ልዩነቱ በግልጽ ይታያል። በርካቶች ህክምናውን ለማድረግ አቅም አልነበራቸውም። እኔ ታክሜ ነጻነት ሳገኝ ለምኖ ያልሞላለት ሰው ግን ምን ያህል ነጻነቱን ያጣል? ስል አሰብኩ።" ለወራት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ የህክምናው ወጪ ከብዷቸው የሚያቋርጡ እንዳሉ ይሰማ ነበር። ወጪው ከአቅማቸው በላይ ሆኖ የሚሞቱትንም ቤቱ ይቁጠራቸው። "እስክሞት ልታገል" ኩላሊት መሥራት ሲያቆም የኩላሊት እጥበት ማድረግ ግዴታ ነው። ህመሙ የሌለባቸው ሰዎች ሰውነታቸው ውስጥ የሚከማች ቆሻሻን ሽንት በመሽናት ያስወግዳሉ። ታማሚዎች የኩላሊት እጥበት ካላደረጉ ቆሻሻው አይወጣም ማለት ነው። እናም ሰውነታቸው ይታፈናል፣ ያብጣል፣ ሲከፋም ሕይወታቸውን ያጣሉ። በሳምንት ሦስቴ የኩላሊት እጥበት ማድረግ የሚጠበቅበት ሰው በሳምንት አንዴ ብቻ ቢያደርግ ወይም ቢያቋርጥ ይህ መታፈን ይገጥመዋል። ምግብ መብላትም አይችልም። ኢዮብ በህመሙ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችን ሲያይ በቀረኝ ሕይወት የአቅሜን መርዳት አለብኝ ብሎ ወሰነ። ህሙማን የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙበት እና መንግሥት ከህመሙ ጋር በተያያዘ የሚያወጣቸው ውሳኔዎች ላይ ጫና ማሳደር የሚቻልበት ማኅበር አቋቋመ። 'ሞት በኩላሊት ይብቃ' የተጀመረው በ2007 ዓ.ም. ነው። በታመመበት ጊዜ በመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት አልነበረም። በግል ሆስፒታልም በውስን ቦታ፣ በውድ ገንዘብ ይከናወናል። ህክምናውን ለማግኘት የሚደረገው ጥረት አሁንም ድረስ ከባድ ነው። በመንግሥት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት በአንድ ዙር 500 ብር ያስከፍላል። በግል ሆስፒታሎች ደግሞ ከ1500 እስከ 3500 ብር ያወጣል። "መሞቴ አይቀርም እስክሞት ልታገል ብዬ ወሰንኩ። ለመንግሥት አካላት እና ለአንዳንድ ተቋማት ድምጼን ማሰማት ጀመርኩ። በመኪና እየዞሩ መቀስቀስ፣ ብሮሸር መለጠፍም ቀጠልኩ። ይኸው 8 ዓመት ኖርኩኝ። በጥቂት ቦታም ቢሆን በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ተጀምሯል። ይሄ በኩራት የምናገረው የልፋቴ ውጤት ነው።" ማኅበሩ ከምስረታው ጀምሮ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ120 በላይ ህሙማንን ደግፏል። ቁጥሩ ለቀን፣ ለሳምንት፣ ለአንድ ወር ወይም ለሁለት ወር የኩላሊት እጥበት ገንዘብ የሚከፈልላቸውን ይጨምራል። ወርሀዊ መዋጮ በማድረግ እና በጉልበት ሥራ የሚደግፉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ደበበ እሸቱ፣ ስዩም ተፈራ፣ ዳንኤል ተገኝ ታዋቂ የማኅበሩ አባላት ናቸው። ኢዮብ "አምባሳደሮቻችን" ይላቸዋል። ከ2007 ወዲህ ድጎማ ከተደረገላቸው ህሙማን መካከል አምስቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሞት በኩላሊት ይብቃ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በምኒሊክ እና በዘውዲቱ ሆስፒታሎች ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ለሁለት ዓመት ነጻ የኩላሊት እጥበት ከሚሰጣቸው 105 ህመምተኞች አንዱ ኢዮብ ነው። ያቋቋመው ማኅበር ከያዛቸው ፕሮጀክቶች አንዱ የኩላሊት ህሙማን ተደራጅተው ሥራ እንዲሠሩ ከክፍለ ከተሞች ጋር መነጋገር ነው። ይህም ለህክምና ገንዘብ ሲሉ ጎዳና ወጥተው ለመለመን የተገደዱ ወገኖችን ለመደገፍ ያለመ ነው። ፕሮጀክቱን የጤና ሚንስትር እና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ድጋፍ ሰጥቶት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአንድ ህመምተኛ የሥራ እድል ተፈጥሯል። በሌሎች ክፍለ ከተሞችም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ወጋገን ባንክ ለህመምተኞች መርጃ ገንዘብ የሚሰበሰብበት ሳጥን ተቀምጧል። በቋሚነት በሳምንት ለአንድ ህመምተኛ የኩላሊት እጥበት ክፍያ የሚያደርጉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ማኅበሩ በሰበሰበው ገንዘብ ሦስት ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሲሆን፤ ነጻ ህክምና የሚያገኙ እንዳሉም ይናገራል። "ኢትዮጵያ ውስጥ የኩላሊት እጥበት ክፍያ ከፍተኛ ስለሆነ ከ70 እስከ 80 በመቶ ያሚሆነው የኩላሊት ህመምተኛ በሳምንት አንዴ ወይም ሁለት ቀን ነው የሚያደርገው" ይላል። ማኅበሩ በሠራው ስሌት መሠረት አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ከ700 ያላነሱ የኩላሊት ህመምተኞች በግል ሆስፒታል ነው ህክምና የሚከታተሉት። ዝቅተኛ የሚባለውን የአንድ ዙር የኩላሊት እጥበት ወጪ 1500 ብር መክፈል የሚችሉ ውስን ናቸው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጎዳና ላይና በየሐይማኖት ተቋማት ከመለመን ውጪም አማራጭ የለውም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢዮብ ማኅበር የመዋጮ ፕሮጀክት ቀርጿል። ሐሳቡ በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር የሚያዋጡ አንድ ሚሊዮን ሰዎችን በማኅበሩ አባልነት መመዝገብ ነው። ፕሮጀክቱ ከሦስት ዓመት በፊት ሲጀመር ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጀምሮ፣ ታዋቂ ሰዎችና ሌሎች ሰዎችን ጨምሮ ወደ 3000 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል። ከአባላቱ የሚሰበሰበውን ገንዘብ የሚከታተል መተግበሪያ እያሠሩ ነው። ኢትዮ-ቴሌኮም አጭር የጽሑፍ መልዕክት (ኤስኤምኤስ) እየላከ ገንዘቡን ሰብስቦ በቀጥታ ወደ ጤና ሚንስትር እንዲያስገባ ለማድረግ ወጥነዋል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር ቢያዋጡ፤ በአንድ ዓመት በአጠቃላይ 120 ሚሊዮን ብር ይገኛል። ይህም ለነጻ የኩላሊት ህክምና እንዲውል እንደሚፈልግ ኢዮብ ይናገራል። "ይህ ገንዘብ በመሀል ምንም ሂደት ሳይኖር ከቴሌ ወደ ጤና ሚንስትር በቀጥታ ስለሚገባ ተአማኒነት ይኖረዋል" ይላል። ከጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር በጉዳዩ ላይ ከስድስት ወር በፊት እንደተነጋገረ ይገልጻል። "ሚንስትሯ በሐሳቡ ደስተኛ እንደሆኑና ለመደገፍ ፍቃደኛ እንደሆኑ ነግረውኛል። ገንዘቡ ከቴሌ ወደ ጤና ጥበቃ በቀጥታ እንዲገባ እንደምንፈልግ ስነግራቸው የሕግ አግባቡን ልይ ብለዋል።" የቀድሞው የጤና ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን ሐሳቡን ደግፈው የአባልነት መታወቂያ አውጥተዋል። የኢዮብ ውጥን ተሳክቶ በአንድ ዓመት 120 ሚሊዮን ብር ማግኘት ከተቻለ እስከ 500 ሰዎች ለዓመት በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት በነጻ ያገኛሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲደግፏቸው ለማድረግ መልዕክት እንደላኩና እስካሁን እንዳላገኟቸው የሚናገረው ኢዮብ በድጋሚ ጥያቄ እንደሚያቀርብላቸው ገልጿል። ሐሳቡ እውን ከሆነ "መዋጮው ኪስ አይጎዳም። ብንኖርም ባንኖርም ቋሚና ቀጣይ ይሆናል። ጤናማው ሰው የሚያዋጣው ገንዘብ ወደ ኋላ መገልገያው እንዲሆን የጤና መድኅን አካል ማድረግም ይቻላል" ሲል ተስፋውን ይናገራል። እንደ ኩላሊት፣ ካንሰር እና ልብ ያሉ ህመሞች ህክምና ሊሰጥባቸው እየተገባ ብዙዎች የሚሞቱባቸው ናቸው። ምናልባትም እንዲህ ባሉ የረድኤት ፕሮጀክቶች ችግሩን መቅረፍ ይቻላል ብሎ ያምናል። "ባለቤቴ- ጀግናዬ" ኢዮብ ከመታመሙ በፊት ለራሱና ለቤተሰቡ ሕይወት መለወጥ የሚተጋ ሰው ነበር። አሁን ግን የብዙዎችን ኃላፊነት ለመሸከም መርጧል። የማኅበሩ መስራች፣ ሥራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆን ሹፌር፣ ቀስቃሽ፣ ገንዘብ ሰብሳቢ የሆነባቸውን ጊዜያት ያስታውሳል። ሥራውን "ፈጣሪ እና ህሊናዬ የተደሰቱበት ስለሆነ ኩራት እና ደስታ ይሰማኛል" ሲል ይገልጸዋል። ለስምንት ዓመታት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ ወገቡ እና እግሩ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት በድጋፍ ነው የሚንቀሳቀሰው። እንደ ቀድሞው የማኅበሩን ሥራዎች እንዳያከናውንም አድርጎታል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የሰውነት ክብደቱ ከ56 ወደ 46 ኪሎ ቀንሷል። ብርታት ከሚሰጡት በዋነኛነት የሚጠቅሰው "ጀግናዬ" የሚላት ባለቤቱን ነው። "በጤናማነቴ ጊዜ ያፈራሁትን ከ1.5 ሚልዮን ብር በላይ ለማኅበሩ ሳውል ነገ ይሞታል ብላ ቅር አላላትም። ብር አንሶን የልጆቼን መኖርያ ቤት ስሸጥ እሷ የነበረንን ንግድ ቤት በመሸጥ ሹፌር ሆና ልጆቹን አስተማረች። ለዛሬ አብቅታኛለችና ጀግናዬ ናት።" ሲታመም የሩቅና የቅርብ ቤተሰብ፣ ጓደኛም በአብዛኛው እንደሸሸው ይናገራል። ከልጆቹ ጋር ሰፊ ጊዜ ባለማሳለፉ፣ እንዳሻቸው ባለማዝናናቱም ያዝናል። ከኩላሊት ታማሚዎች ጋር ስቴድየም ዙርያ፣ ባዛሮች ላይ እንዲሁም ወደ መንግሥትና የግል ተቋማት እየሄደ እርዳታ ለማሰባሰብ ይሞክራል። ህክምናውን ትቶ የማኅበሩን ጉዳይ የሚከታተልባቸው ጊዜያትም አሉ። የኩላሊት ህመም "ሳቄን፣ ደስታዬን፣ እግሬን አሳጥቶኛል" ይላል። ከዚህ በተቃራኒው "እውነተኛ ታጋይና ለወገን ቶርቋሪ አድርጎኛል" ሲል ያለበት ሁኔታ ይገልጻል። በእሱ ማኅበር ውስጥ ይረዱ ከነበሩ ህሙማን መካከል ኋላ ላይ በራሳቸው ማኅበር መስርተው መንቀሳቀስ የጀመሩ ሰዎች መኖራቸው ያስደስተዋል። ህሙማንን ሲረዳ ከሚያገኘው እፎይታ በተጨማሪ ቤተሰቡ ሐሴት ይሰጠዋል። "ሁሌም ሚስቴና ልጆቼ የተቃጠልኩትን ማቀዝቀዣዎቼ ናቸው" ይላቸዋል። ሐኪሞች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ እንዳለበት ነግረውታል። ኩላሊት የሚሰጠው የቤተሰብ አባል ቢያገኝም የወጪው ነገር አሳሳቢ ነው። የማኅበሩ ስኬት ከሚላቸው መካከል ብዙ ገንዘብ ባይኖራቸውም ለህሙማን ገንዘብ ለመለገስ የሚፈቅዱ ሰዎች ማግኘታቸውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን የሚያስደነግጥ ምስል ወይም የተጎዳ ሰው ቁስል ካልታየ በስተቀር በማኅበረሰቡ ዘንድ እምብዛም ሰዎችን የመርዳት ተነሳሽነት እንደሌለ አስተውሏል። የተጎዱ ሰዎችን ለይቶ በቀጥታ የመርዳት ልማድ ባለመኖሩ ማኅበረሰቡ እርዳታ የሚሰጠው ባገኘው አጋጣሚ፣ በየመንገዱ ለሚያገኘው ገንዘብ ጠያቂ ነው። ይህም በእርዳታ ስም የሚያጭበረብሩ እንዲበራከቱ መንገድ እንደከፈተም ያምናል። ሰዎች ባላቸው አቅም ተጎጂዎችን በእቅድ የመርዳት ባህል እንዲዳብሩ ይመኛል። የኩላሊት ህክምና በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሕግ አንድ ሰው ኩላሊቱ መሥራት ካቆመ ከቤተሰቡ ውጪ ኩላሊት ከሌላ ሰው መውሰድ አይችልም ይላል። ይህ ሕግ ቤተሰብ የሌላቸው ወይም ከቤተሰቦቻቸው ጋር የደም አይነታቸው የማይመሳሰል ሰዎችን ሕይወት አደጋ ውስጥ ጥሏል ይላል። ዘመድ፣ አብሮ አደግ ወይም ሌላ ለጋሽ ኩላሊት የሚሰጥበት አሠራር እንዲዘረጋ ለጤና ሚንስቴር ማሳሰቡንም ኢዮብ ይናገራል። ሌላው ክፍተት የኩላሊት ንቅለ ተከላ የሚከናወነው በጳውሎስ ሆስፒታል ብቻ መሆኑ ነው። ይህ አገልግሎት ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መነሳት ወዲህ መቋረጡም ሌላ ችግር ነው። በሌላ በኩል ንቅለ ተከላ ያደረጉ ሰዎች የመድኃኒት እጥረት ይገጥማቸዋል። የኩላሊት እጥበት የሚያደርጉ ሰዎችም እንዲሁ ተጓዳኝ የሰውነት መጠገኛ መድኃኒቶች ያጣሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ መድኃኒቶቹን ማግኘት ከባድ ነው። ያሉትም በጣም ውድ ናቸው። ኢዮብ ከታመመበት ከስምንት ዓመታት ወዲህ ብዙ ነገሮች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን አይክድም። "ትላንት የነበረውን ጨለማ ስለማውቀው የዛሬው የተሻለ ነው እላለሁ" ይላል። ሆኖም ግን አሁንም ያሉ ክፍተቶች እንዲሸፈኑ ይጠይቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58126744
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በካናዳ አንዲት ጨቅላ ሕጻን ጭምብል ባለማጥለቋ በረራ ተሰረዘ
ነገሩ አስገራሚ ነው፡፡ በካናዳ አንዲት ጨቅላ ሕጻን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረጓ ብቻ ፖሊስ ተጠርቷል፣ በረራውም ተሰርዟል፡፡ ሕጻኗ ከተወለደች ገና 19 ወሯ ነው፡፡ ዌስት ጄት ደግሞ ሁሉም ተሳፋሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማጥለቅ እንዳለባቸው ያሳስባል፡፡ ጨቅላዋ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሲደረግላት እሪታዋን ታቀልጠዋለች፡፡ ብትባል ብትሰራ እምቢኝ ትላለች፡፡ እናትና አባት ያልሞከሩት ነገር የለም፡፡ ሕጻኗ ሞቼ እገኛለሁ አለች፡፡ የአየር መንገዱ አስተናጋጆችና ቤተሰብ አንድ ሁለት ሲባባሉ ነገሩ ተካሮ በረራ እስከመሰረዝ ደርሷል፡፡ አየር መንገዱ ግን ታሪኩ ሌላ ነው ይላል፡፡ የ19 ወር ጨቅላዋ አይደለችም ችግር የፈጠረችብኝ ብሏል ዌስትጄት፡፡ እንዲያውም በሷ ደረጃ ያሉ ሕጻናት ጭምብል እንዲያጠልቁም አይገደዱም ብሏል፡፡ ታዲያ ለምን በረራውን ሰረዛችሁ ሲባል ሌላ የጨቅላዋ ታላቅ እህት አለች፤ 3 ዓመቷ ነው፡፡ እሷ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አጥልቂ ስትባል እምቢ በማለቷ ነው በረራውን እንድንሰርዝ የተገደድነው ብሏል፣ ዌስትጄት፡፡ የሕጻናቱ እናትና አባት፣ እንዲሁም ተሳፋሪዎች ግን" ዌስትጄት ቀጣፊ ነው፣ ዋሽቷል፤ የ3 ዓመቷ ልጅ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነበር ሲሉ "ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ግርግር በሞባይል የተቀረጸ ቪዲዮም የ3 ዓመቷ ልጅ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነው የምትታየው፡፡ ፖሊስም በበኩሉ እኔ ስደርስ ታላቅየው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነበር ብሏል፡፡ ይህ የሆነው ማክሰኞ ነው፤ ከትናንት በስቲያ፡፡ በረራው ከካልጋሪ ተነስቶ ቶሮንቶ የሚደርስ ነበር፡፡ በረራ 652 ግን ከመነሻው ሳይሳካ ቀርቶ ሁሉም ተሳፋሪዎች ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደርገዋል፡፡ የልጆቹ አባት አቶ ኮድሀሪ እንዲህ ዓይነት ጉድ በፍጹም ያጋጥመኛል ብዬ በሕልሜም በእውኔም አስቤም ጠብቄም አላውቅም ብሏል ለቢቢሲ፡፡ ‹‹እኔና ባለቤቴ ከሁለቱ ሴት ልጆቻችን ጋር ነበርን፤ አውሮፕላኑ ሊነሳ ሲል የሦስት ዓመቷ ልጄ ቁርስ ቢጤ እየበላች ነበር፡፡ የበረራ አስተናጋጇ መጥታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንድታጠልቅ ነገረቻት፡፡ እኔና እናቷ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገናል፤ የ3 ዓመቷ ልጃችን ደግሞ እየበላች ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹የበረራ አስተናጋጇ ዌስትጄት በአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጉዳይ ጥብቅ ፖሊሲ እንደሚከተልና ልጃቸው ቁርሱ መብላቷን ትታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ካላጠለቀች በረራው እንደማይደረግ ነገረችን›› ይላል አባት፡፡ ‹‹ልጆች ደግሞ በአንድ ጊዜ መታዘዝ እሺ ስለማይሉ ማባበል ጀመርኩ፡፡ የ3 ዓመቷ ልጄ ትንሽ ካስቸገረችን በኋላ እሺ ብላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዋን አጠለቀች፡፡›› ‹‹ታናሽየው ግን እምቢኝ አለች፤ እንዲያውም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛውን ስናደርግላት ወደላይ አላት›› ይላል አባት፡፡ ‹‹ዌስትጄት ትእግስት አልፈጠረባቸውም፡፡ ትንሽዋ ልጄ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ስላላጠለቀች አውሮፕላኑ እንደማይበር ነገሩን፡፡›› እንዲያውም ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ እንደታዘዙና አንወርድም ካሉ ግን እንደሚታሰሩ እንደተነገራቸው ለቢቢሲ አስታውቋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከአውሮፕላኑ ለመውረድ ተስማማን ብሏል አባት ለቢቢሲ፡፡ አባት በረራው ከተሰረዘ በኋላ ተረዳሁ እንደሚለው ከሆነ ‹‹በካናዳ ትራንስፖርት ፖሊሲ መሰረት የ19 ወሯ ጨቅላ ልጃቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማጥለቅ አትገደድም ነበር፡፡›› ዌስትጄት ባወጣው መግለጫ ግን በረራው የተሰረዘው የ19 ወሯ ጨቅላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ስላላጠለቀች ሳይሆን የሷ ታላቅ የ3 ዓመቷ ህጻን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ነው ብሏል፡፡
ኮሮናቫይረስ፡ በካናዳ አንዲት ጨቅላ ሕጻን ጭምብል ባለማጥለቋ በረራ ተሰረዘ ነገሩ አስገራሚ ነው፡፡ በካናዳ አንዲት ጨቅላ ሕጻን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረጓ ብቻ ፖሊስ ተጠርቷል፣ በረራውም ተሰርዟል፡፡ ሕጻኗ ከተወለደች ገና 19 ወሯ ነው፡፡ ዌስት ጄት ደግሞ ሁሉም ተሳፋሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማጥለቅ እንዳለባቸው ያሳስባል፡፡ ጨቅላዋ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሲደረግላት እሪታዋን ታቀልጠዋለች፡፡ ብትባል ብትሰራ እምቢኝ ትላለች፡፡ እናትና አባት ያልሞከሩት ነገር የለም፡፡ ሕጻኗ ሞቼ እገኛለሁ አለች፡፡ የአየር መንገዱ አስተናጋጆችና ቤተሰብ አንድ ሁለት ሲባባሉ ነገሩ ተካሮ በረራ እስከመሰረዝ ደርሷል፡፡ አየር መንገዱ ግን ታሪኩ ሌላ ነው ይላል፡፡ የ19 ወር ጨቅላዋ አይደለችም ችግር የፈጠረችብኝ ብሏል ዌስትጄት፡፡ እንዲያውም በሷ ደረጃ ያሉ ሕጻናት ጭምብል እንዲያጠልቁም አይገደዱም ብሏል፡፡ ታዲያ ለምን በረራውን ሰረዛችሁ ሲባል ሌላ የጨቅላዋ ታላቅ እህት አለች፤ 3 ዓመቷ ነው፡፡ እሷ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አጥልቂ ስትባል እምቢ በማለቷ ነው በረራውን እንድንሰርዝ የተገደድነው ብሏል፣ ዌስትጄት፡፡ የሕጻናቱ እናትና አባት፣ እንዲሁም ተሳፋሪዎች ግን" ዌስትጄት ቀጣፊ ነው፣ ዋሽቷል፤ የ3 ዓመቷ ልጅ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነበር ሲሉ "ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ግርግር በሞባይል የተቀረጸ ቪዲዮም የ3 ዓመቷ ልጅ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነው የምትታየው፡፡ ፖሊስም በበኩሉ እኔ ስደርስ ታላቅየው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጋ ነበር ብሏል፡፡ ይህ የሆነው ማክሰኞ ነው፤ ከትናንት በስቲያ፡፡ በረራው ከካልጋሪ ተነስቶ ቶሮንቶ የሚደርስ ነበር፡፡ በረራ 652 ግን ከመነሻው ሳይሳካ ቀርቶ ሁሉም ተሳፋሪዎች ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደርገዋል፡፡ የልጆቹ አባት አቶ ኮድሀሪ እንዲህ ዓይነት ጉድ በፍጹም ያጋጥመኛል ብዬ በሕልሜም በእውኔም አስቤም ጠብቄም አላውቅም ብሏል ለቢቢሲ፡፡ ‹‹እኔና ባለቤቴ ከሁለቱ ሴት ልጆቻችን ጋር ነበርን፤ አውሮፕላኑ ሊነሳ ሲል የሦስት ዓመቷ ልጄ ቁርስ ቢጤ እየበላች ነበር፡፡ የበረራ አስተናጋጇ መጥታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንድታጠልቅ ነገረቻት፡፡ እኔና እናቷ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገናል፤ የ3 ዓመቷ ልጃችን ደግሞ እየበላች ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹የበረራ አስተናጋጇ ዌስትጄት በአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጉዳይ ጥብቅ ፖሊሲ እንደሚከተልና ልጃቸው ቁርሱ መብላቷን ትታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ካላጠለቀች በረራው እንደማይደረግ ነገረችን›› ይላል አባት፡፡ ‹‹ልጆች ደግሞ በአንድ ጊዜ መታዘዝ እሺ ስለማይሉ ማባበል ጀመርኩ፡፡ የ3 ዓመቷ ልጄ ትንሽ ካስቸገረችን በኋላ እሺ ብላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዋን አጠለቀች፡፡›› ‹‹ታናሽየው ግን እምቢኝ አለች፤ እንዲያውም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛውን ስናደርግላት ወደላይ አላት›› ይላል አባት፡፡ ‹‹ዌስትጄት ትእግስት አልፈጠረባቸውም፡፡ ትንሽዋ ልጄ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ስላላጠለቀች አውሮፕላኑ እንደማይበር ነገሩን፡፡›› እንዲያውም ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ እንደታዘዙና አንወርድም ካሉ ግን እንደሚታሰሩ እንደተነገራቸው ለቢቢሲ አስታውቋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከአውሮፕላኑ ለመውረድ ተስማማን ብሏል አባት ለቢቢሲ፡፡ አባት በረራው ከተሰረዘ በኋላ ተረዳሁ እንደሚለው ከሆነ ‹‹በካናዳ ትራንስፖርት ፖሊሲ መሰረት የ19 ወሯ ጨቅላ ልጃቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማጥለቅ አትገደድም ነበር፡፡›› ዌስትጄት ባወጣው መግለጫ ግን በረራው የተሰረዘው የ19 ወሯ ጨቅላ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ስላላጠለቀች ሳይሆን የሷ ታላቅ የ3 ዓመቷ ህጻን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ነው ብሏል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-54098154
5sports
አትሌቲክስ ፌደሬሽን፡ 'በኦሊምፒክ የሚሳተፉ ሯⶐች የሚመረጡት በቴክኒክ ኮሚቴ ነው' አለ
በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው በማራቶን የሚወደዳሩ አትሌቶችን የሚመርጠው ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ እንዲሆን ከስምምነት መደረሱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ። ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት በሆኑት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የሚመራ ሲሆን የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የኮሚቴው አባላት ናቸው። ይህንን በሚመለከት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ማክሰኞ መግለጫ ሰጥቷል። የዛሬው መግለጫ የአትሌቲክ ፌዴሬሽን፣ የኦሊምፒክ፣ የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን እና ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ ይሰጣሉ ተብሎ ነበር። ይሁን እንጂ ይህን መግለጫ የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ብቻ እንዲሰጥ ከስምምነት መደረሱ በመግለጫው ተጠቅሷል። አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሚያዚያ 23 በሰበታ ከተማ በተካሄደው የማራቶን ማጣሪያ ውድድር የተሻለ ሰዓት ያስመዘገቡ አትሌቶችን ይፋ አድርጎ እንደነበረ ይታወሳል። ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በተካሄደው ማጣሪያ ከ1 እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት አትሌቶች ሹራ ቂጣታ፣ ሌሊሳ ዴሲሳ፣ ሲሳይ ለማ እና ጫሉ ዳሶ መሆናቸው ይታወሳል። በሴቶች ደግሞ ትዕግስት ግርማ፣ ብርሀኔ ዲባባ፣ ሮዛ ደረጄ እና ዘይነባ ይመር የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። ፌዴሬሽኑ የማራቶን ተሳትፎ በቴክኒክ ኮሚቴው የሚወሰን ነው ከማለት ውጪ ሰበታ ከተማ ተካሂዶ በነበረው ማጣሪያ ውጤታ ያስመዘገቡ አትሌቶች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ያለው ነገር የለም። በሌላ በኩል ይህ ማጣሪያ አግባባ አይደለም በማለት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በማጣሪያው ላይ ሳይሳተፍ መቅረቱ ይታወሳል። አትሌት ቀነኒሳ 2016 በተካሄደው የሪዮ ኦሊምፒክ ተሳታፊ እንዳልነበር አስታውሶ፤ በኦሊምፒክ መድረክ አገሬን እንዳልወክል በፌደሬሸኑ እየተከለከልኩ ነው ሲል ቅሬታ አቅርቦ ነበር። በማራቶን የሚወዳደሩ አትሌቶችን በተመለከተ የቴክኒክ ኮሚቴው ውሳኔ ወደፊት ይፋ እንደሚደረግም ተነግሯል። በሌላ በኩል ከ800 ሜትር እስ 10ሺህ ያሉ ወድድሮች ኢትዮጵያ ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶችን ለመምረጥ 73 አትሌቶችን የሚያሳትፍ ማጣሪያ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። ይህ የማጣሪያ ውድድር በስዊትዘርላንድ ሄንግሎ ከተማ ከአንድ ወር ገደማ በኋላ እንደሚካሄድና ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ብቻ የሚያሳትፍ መሆኑም ተጠቅሷል። በዚህ መሠረት በሄንግሎ በሴቶች እና በወንዶች የ800፣ 1ሺህ 500፣ 3ሺህ፣ 5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ማጣሪያዎች ይከናወናሉ።
አትሌቲክስ ፌደሬሽን፡ 'በኦሊምፒክ የሚሳተፉ ሯⶐች የሚመረጡት በቴክኒክ ኮሚቴ ነው' አለ በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው በማራቶን የሚወደዳሩ አትሌቶችን የሚመርጠው ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ እንዲሆን ከስምምነት መደረሱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ። ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት በሆኑት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የሚመራ ሲሆን የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የኮሚቴው አባላት ናቸው። ይህንን በሚመለከት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ማክሰኞ መግለጫ ሰጥቷል። የዛሬው መግለጫ የአትሌቲክ ፌዴሬሽን፣ የኦሊምፒክ፣ የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን እና ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ ይሰጣሉ ተብሎ ነበር። ይሁን እንጂ ይህን መግለጫ የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ብቻ እንዲሰጥ ከስምምነት መደረሱ በመግለጫው ተጠቅሷል። አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሚያዚያ 23 በሰበታ ከተማ በተካሄደው የማራቶን ማጣሪያ ውድድር የተሻለ ሰዓት ያስመዘገቡ አትሌቶችን ይፋ አድርጎ እንደነበረ ይታወሳል። ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በተካሄደው ማጣሪያ ከ1 እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት አትሌቶች ሹራ ቂጣታ፣ ሌሊሳ ዴሲሳ፣ ሲሳይ ለማ እና ጫሉ ዳሶ መሆናቸው ይታወሳል። በሴቶች ደግሞ ትዕግስት ግርማ፣ ብርሀኔ ዲባባ፣ ሮዛ ደረጄ እና ዘይነባ ይመር የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። ፌዴሬሽኑ የማራቶን ተሳትፎ በቴክኒክ ኮሚቴው የሚወሰን ነው ከማለት ውጪ ሰበታ ከተማ ተካሂዶ በነበረው ማጣሪያ ውጤታ ያስመዘገቡ አትሌቶች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ያለው ነገር የለም። በሌላ በኩል ይህ ማጣሪያ አግባባ አይደለም በማለት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በማጣሪያው ላይ ሳይሳተፍ መቅረቱ ይታወሳል። አትሌት ቀነኒሳ 2016 በተካሄደው የሪዮ ኦሊምፒክ ተሳታፊ እንዳልነበር አስታውሶ፤ በኦሊምፒክ መድረክ አገሬን እንዳልወክል በፌደሬሸኑ እየተከለከልኩ ነው ሲል ቅሬታ አቅርቦ ነበር። በማራቶን የሚወዳደሩ አትሌቶችን በተመለከተ የቴክኒክ ኮሚቴው ውሳኔ ወደፊት ይፋ እንደሚደረግም ተነግሯል። በሌላ በኩል ከ800 ሜትር እስ 10ሺህ ያሉ ወድድሮች ኢትዮጵያ ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶችን ለመምረጥ 73 አትሌቶችን የሚያሳትፍ ማጣሪያ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። ይህ የማጣሪያ ውድድር በስዊትዘርላንድ ሄንግሎ ከተማ ከአንድ ወር ገደማ በኋላ እንደሚካሄድና ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ብቻ የሚያሳትፍ መሆኑም ተጠቅሷል። በዚህ መሠረት በሄንግሎ በሴቶች እና በወንዶች የ800፣ 1ሺህ 500፣ 3ሺህ፣ 5ሺህ እና 10ሺህ ሜትር ማጣሪያዎች ይከናወናሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-57076979
0business
ባይደን ለችግር ጊዜ ከተከማቸው ነዳጅ በርካታ ሚሊዮን በርሜል እንዲቀዳ አዘዙ
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አሜሪካ ለችግር ጊዜ በሚል ካከመቻችው ነዳጅ በገፍ እንዲቀዳ አዘዋል። ፕሬዝደንቱ ይህን ትዕዛዝ ያስተላለፉት እየናረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ለመዋጋት ነው። ባይደን እንዲወጣ ያዘዙት 180 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ በማከማቻው ታሪክ ትልቁ ነው። ዩክሬን ባለው ጦርነት ምክንያት ጣራ እየነካ የነበረው የነዳጅ ዋጋ ከባይደን ትዕዛዝ በኋላ ትንሽ ረገብ ብሏል። ነገር ግን አሜሪካ በየቀኑ ለመከራ ጊዜ ካስቀመጠችው ነዳጅ አንድ ሚሊዮን በርሜል ብትቀዳም ችግሩን ሙሉ በሙሉ አይቀርፈውም ይላሉ የዘርፉ ሰዎች። ባይደን፤ ከማከማቻው እንዲቀዳ የታዘዘው ነዳጅ አሜሪካ "የራሷን የነዳጅ ምርት እስክታሳልጥ ድረስ" እንዲያግዝ በሚል ነው ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ኩባንዎች ነዳጅን ከመንግሥት መውሰድ የመጨረሻ አማራጭ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ባይደን አረንጓዴ የኃይል ምንጭ የሚከተሉ ኩባንያዎች እንዲበረታቱ መክረዋል። በሚቀጥለው ኅዳር የግማሽ ዓመት ምርጫ ለማካሄድ ደፋ ቀና እያለች ያለችው አሜሪካን ጨምሮ የዓለም ሃገራት የኑሮ መወደድ እያማረራቸው ነው። ባይደን፤ ስትራቴጂክ ፔትሮሊዬም ሪዘርቭ ከተሰኘው የችግር ቀን ገንዳ ነዳጅ ለመቅዳት የወሰንነው "ያለዕቅዳችን" ነው ብለዋል። ይህ ግዙፍ የነዳጅ ማከማቻ ገንዳ የተመሠረተው በፈረንጆቹ 1974 ነው። ማከማቻው ቴክሳስና ሉዊዚያና መካከል በሚገኘው የገልፍ ኮስት ላይ በተንጣለለው የጨው ክምር አካባቢ ይገኛል። ይህ ገንዳ በፈረንጆቹ 2009 700 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ አቅፎ ነበር። ባለፈው መጋቢት ሲለካ ግን የነዳጅ ክምችቱ ወደ 568 ሚሊዮን በርሜል ወርዷል። አሜሪካ ከሳዐዲ ቀጥሎ ሁለተኛዋ ግዙፍ የነዳጅ አምራች ከሆነችው ሩሲያ ነዳጅ አልገዛም ካለች ወዲህ የነዳጅ እጥረት እያንገላታት ይመስላል። የነዳጅ ዋጋ መለከያ የሆነው ብሬንት ክሩድ ባለፈው የፈረንጆቹ ወር መጀመሪያ ዋጋ አሜሪካና አጋሮቿ ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ከጣሉ በኋላ አሿቅቧል። ምንም እንኳ የኃይል ዋጋ ቀስ በቀስ ቢወርድም ነዳጅ ግን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዋጋው 70 በመቶ ጨምሯል። አሜሪካ ውስጥ እየናረ የመጣው ኑሮ ሪፐብሊካን ጮቤ እንዲረግጡ እያደረጋቸው ነው። የባይደን ተቃዋሚዎች የኑሮ ውድነቱን በባይደን አስተዳደር አላከዋል። አሁን ደግሞ ነዳጅ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዋጋው ሲያሻቅብ የባይደን አስተዳደርን ከድጡ ወደ ማጡ መርቷቸዋል። ባለፈው ሐሙስ ሩሲያን ጨምሮ የነዳጅ አምራች ሃገራት ማሕበሩ ኦፔክ አባላት የነዳጅ ምርታቸውን ለመጨመር ተስማምተዋል። የኃይል ዋጋ ከዩክሬን ጦርነት በፊትም ቢሆን የዓለም ምጣኔ ሃብትን ሊፈታተነው እንደሚችል ግምት ነበር።
ባይደን ለችግር ጊዜ ከተከማቸው ነዳጅ በርካታ ሚሊዮን በርሜል እንዲቀዳ አዘዙ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አሜሪካ ለችግር ጊዜ በሚል ካከመቻችው ነዳጅ በገፍ እንዲቀዳ አዘዋል። ፕሬዝደንቱ ይህን ትዕዛዝ ያስተላለፉት እየናረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ለመዋጋት ነው። ባይደን እንዲወጣ ያዘዙት 180 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ በማከማቻው ታሪክ ትልቁ ነው። ዩክሬን ባለው ጦርነት ምክንያት ጣራ እየነካ የነበረው የነዳጅ ዋጋ ከባይደን ትዕዛዝ በኋላ ትንሽ ረገብ ብሏል። ነገር ግን አሜሪካ በየቀኑ ለመከራ ጊዜ ካስቀመጠችው ነዳጅ አንድ ሚሊዮን በርሜል ብትቀዳም ችግሩን ሙሉ በሙሉ አይቀርፈውም ይላሉ የዘርፉ ሰዎች። ባይደን፤ ከማከማቻው እንዲቀዳ የታዘዘው ነዳጅ አሜሪካ "የራሷን የነዳጅ ምርት እስክታሳልጥ ድረስ" እንዲያግዝ በሚል ነው ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ኩባንዎች ነዳጅን ከመንግሥት መውሰድ የመጨረሻ አማራጭ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ባይደን አረንጓዴ የኃይል ምንጭ የሚከተሉ ኩባንያዎች እንዲበረታቱ መክረዋል። በሚቀጥለው ኅዳር የግማሽ ዓመት ምርጫ ለማካሄድ ደፋ ቀና እያለች ያለችው አሜሪካን ጨምሮ የዓለም ሃገራት የኑሮ መወደድ እያማረራቸው ነው። ባይደን፤ ስትራቴጂክ ፔትሮሊዬም ሪዘርቭ ከተሰኘው የችግር ቀን ገንዳ ነዳጅ ለመቅዳት የወሰንነው "ያለዕቅዳችን" ነው ብለዋል። ይህ ግዙፍ የነዳጅ ማከማቻ ገንዳ የተመሠረተው በፈረንጆቹ 1974 ነው። ማከማቻው ቴክሳስና ሉዊዚያና መካከል በሚገኘው የገልፍ ኮስት ላይ በተንጣለለው የጨው ክምር አካባቢ ይገኛል። ይህ ገንዳ በፈረንጆቹ 2009 700 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ አቅፎ ነበር። ባለፈው መጋቢት ሲለካ ግን የነዳጅ ክምችቱ ወደ 568 ሚሊዮን በርሜል ወርዷል። አሜሪካ ከሳዐዲ ቀጥሎ ሁለተኛዋ ግዙፍ የነዳጅ አምራች ከሆነችው ሩሲያ ነዳጅ አልገዛም ካለች ወዲህ የነዳጅ እጥረት እያንገላታት ይመስላል። የነዳጅ ዋጋ መለከያ የሆነው ብሬንት ክሩድ ባለፈው የፈረንጆቹ ወር መጀመሪያ ዋጋ አሜሪካና አጋሮቿ ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ከጣሉ በኋላ አሿቅቧል። ምንም እንኳ የኃይል ዋጋ ቀስ በቀስ ቢወርድም ነዳጅ ግን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዋጋው 70 በመቶ ጨምሯል። አሜሪካ ውስጥ እየናረ የመጣው ኑሮ ሪፐብሊካን ጮቤ እንዲረግጡ እያደረጋቸው ነው። የባይደን ተቃዋሚዎች የኑሮ ውድነቱን በባይደን አስተዳደር አላከዋል። አሁን ደግሞ ነዳጅ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዋጋው ሲያሻቅብ የባይደን አስተዳደርን ከድጡ ወደ ማጡ መርቷቸዋል። ባለፈው ሐሙስ ሩሲያን ጨምሮ የነዳጅ አምራች ሃገራት ማሕበሩ ኦፔክ አባላት የነዳጅ ምርታቸውን ለመጨመር ተስማምተዋል። የኃይል ዋጋ ከዩክሬን ጦርነት በፊትም ቢሆን የዓለም ምጣኔ ሃብትን ሊፈታተነው እንደሚችል ግምት ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-60950886
3politics
በሆሮ ጉድሩ በታጣቂዎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ከ100 በላይ እንደሆኑ ኢሰመኮ ገለጸ
በባለፉት ሳምንታት በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ከ100 በላይ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። በሰላማዊነዋሪዎች ላይ ግድያውን የፈጸሙት መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ የአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎችና ግለሰቦች ባደረሱት ተከታታይ ጥቃት መሆኑንም ኢሰመኮ በትናንትናው ዕለት መስከረም 16፣ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። በዞኑ ኡሙሩ፣ ሆሮ ቡልቅ እና ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች ከነሐሴ 25 ቀን 2014ዓ.ም ባሉት ሶስት ሳምንታት በደረሰው ተከታታይ ጥቃትም ከግድያ በተጨማሪ ዘረፋዎችም ተፈፅሟል ብሏል። የግል ንብረት እና የቁም ከብቶች በነዚህ ታጣቂ ኃይሎች ተዘርፈዋል ያለው ኢሰመኮ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ያለ በቂ እርዳታ በፈታኝ ሁኔታ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች በሰላማዊ ነዋሪዎች እና በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ላይ ግድያ መፈጸማቸውን ገልጿል።   የመንግሥት መግለጫ ስለተገደሉት ሰዎች ብዛት ያለው ነገር የለም። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትም ሆነ የአማራ ኢ-መደበኛ ተብለው የተጠቀሱት ታጣቂዎች ስለ ጥቃቱ እስካሁን ያሉት የለም። በባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ኡሙሩ ወረዳ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰን ግድያ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በትኩረት እንዲሰራ ማሳሰቡን አስታውሷል። ኮሚሽኑ እንዳለው ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ60 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ70 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን እና ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጾ ነበር። በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ተጨማሪ የጸጥታ ስጋት እስካሁን በመቀጠላቸውም በአካባቢው ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች ተስፋፍተው መቀጠላቸው እጅግ አሳሳቢ መሆኑንም ገልጿል። ኢሰመኮ በዚሁ መግለጫ ላይ መንግሥት የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታውን በአግባቡ መወጣት እንደሚኖርበትም አሳስቧል። “የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥታት በአካባቢው ብሔርን መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃ ችግሩን በሚመጥን ደረጃ በማሳደግ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል” በማለት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ  አሳስበዋል። በአሁኑ ወቅት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሞበታል የተባለውን የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞንን ጨምሮ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ይንቀሳቀስባቸዋል በሚባሉት የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ባለፉት ዓመታት ሰላማዊ ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ባለሥልጣናት እንዲሁም ተቋማት ጥቃት ሲፈጸምባቸው ቆይቷል። በተለይ ካለፈው ዓመት አጋማሽ ወዲህ በአካባቢው ነዋሪ በሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ተደጋጋሚ ጥቃቶች መፈጸማቸው ይታወሳል። በእነዚህ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር አባላት የተገደሉ ሲሆን በርካታ ኦሮሞዎችም በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ተገድለዋል። መንግሥት እና ከጥቃቶቹ የተረፉ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች የበርካቶችን ሕይወት ለቀጠፉት ጥቃቶች የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ተጠያቂ ሲያደርጉ ቡድኑ ግን ድርጊቱን ሲያስተባብብል ቆይቷል። በተከታታይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከተገደሉትና ጉዳት ከደረሰባቸው ነዋሪዎች ባሻገር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንበረታቸው ተፈናቅለዋል።
በሆሮ ጉድሩ በታጣቂዎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ከ100 በላይ እንደሆኑ ኢሰመኮ ገለጸ በባለፉት ሳምንታት በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ከ100 በላይ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። በሰላማዊነዋሪዎች ላይ ግድያውን የፈጸሙት መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ የአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎችና ግለሰቦች ባደረሱት ተከታታይ ጥቃት መሆኑንም ኢሰመኮ በትናንትናው ዕለት መስከረም 16፣ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። በዞኑ ኡሙሩ፣ ሆሮ ቡልቅ እና ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች ከነሐሴ 25 ቀን 2014ዓ.ም ባሉት ሶስት ሳምንታት በደረሰው ተከታታይ ጥቃትም ከግድያ በተጨማሪ ዘረፋዎችም ተፈፅሟል ብሏል። የግል ንብረት እና የቁም ከብቶች በነዚህ ታጣቂ ኃይሎች ተዘርፈዋል ያለው ኢሰመኮ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ያለ በቂ እርዳታ በፈታኝ ሁኔታ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች በሰላማዊ ነዋሪዎች እና በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ላይ ግድያ መፈጸማቸውን ገልጿል።   የመንግሥት መግለጫ ስለተገደሉት ሰዎች ብዛት ያለው ነገር የለም። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትም ሆነ የአማራ ኢ-መደበኛ ተብለው የተጠቀሱት ታጣቂዎች ስለ ጥቃቱ እስካሁን ያሉት የለም። በባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ኡሙሩ ወረዳ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰን ግድያ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በትኩረት እንዲሰራ ማሳሰቡን አስታውሷል። ኮሚሽኑ እንዳለው ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ60 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ70 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን እና ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጾ ነበር። በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ተጨማሪ የጸጥታ ስጋት እስካሁን በመቀጠላቸውም በአካባቢው ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች ተስፋፍተው መቀጠላቸው እጅግ አሳሳቢ መሆኑንም ገልጿል። ኢሰመኮ በዚሁ መግለጫ ላይ መንግሥት የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታውን በአግባቡ መወጣት እንደሚኖርበትም አሳስቧል። “የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥታት በአካባቢው ብሔርን መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃ ችግሩን በሚመጥን ደረጃ በማሳደግ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል” በማለት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ  አሳስበዋል። በአሁኑ ወቅት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሞበታል የተባለውን የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞንን ጨምሮ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ይንቀሳቀስባቸዋል በሚባሉት የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ባለፉት ዓመታት ሰላማዊ ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ባለሥልጣናት እንዲሁም ተቋማት ጥቃት ሲፈጸምባቸው ቆይቷል። በተለይ ካለፈው ዓመት አጋማሽ ወዲህ በአካባቢው ነዋሪ በሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ተደጋጋሚ ጥቃቶች መፈጸማቸው ይታወሳል። በእነዚህ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር አባላት የተገደሉ ሲሆን በርካታ ኦሮሞዎችም በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ተገድለዋል። መንግሥት እና ከጥቃቶቹ የተረፉ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች የበርካቶችን ሕይወት ለቀጠፉት ጥቃቶች የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ተጠያቂ ሲያደርጉ ቡድኑ ግን ድርጊቱን ሲያስተባብብል ቆይቷል። በተከታታይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከተገደሉትና ጉዳት ከደረሰባቸው ነዋሪዎች ባሻገር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንበረታቸው ተፈናቅለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c2q4ex3k0n1o
5sports
በኮቪድ ምክንያት 11 ተጫዋቾች እንኳን ቢቀሩ ጨዋታ እንደማይሰረዝ ካፍ ገለጸ
በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሃገራት የኮቪድ1-9 ወረርሽኝ ቢያጋጥማቸውና 11 ተጫዋች ብቻ ቢቀራቸው እንኳ ጨዋታው እንደማይሰረዝ ካፍ ገልጿል። የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪው ካፍ ከአስራ አንዱ ተጫዋቾች አንዱም ግብ ጠባቂ ባይሆን ጨዋታው እንደማይሰረዝ አስታውቋል። ይህንን ማሟላት የማይችል ቡድን በተለምዶ ፎርፌ በሚባለው ሕግ መሠረት የ2-0 ሽንፈት ይጣልበታል ይላል ካፍ። ካፍ ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፈው ዛሬ ምሽት [እሑድ] ከሚጀምረው ውድድር በፊት በርካታ ሃገራት ተጫዋቾቻችን በኮቪድ ተይዘዋል ብለው ካማረሩ በኋላ ነው። ካፍ አክሎም "ለየት ያለ ምክንያት" ላላቸው ሃገራት የውድድሩ አጋጅ ኮሚቴ "አስፈላጊውን ውሳኔ ይሰጣል" ብሏል። ከሁሉም ቀድማ ካሜሩን የገባችው ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት የተወሰኑ ተጫዋቾቿ በኮቪድ ተይዘውባት እንደነበር ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቦ ነበር። ተጫዋቾችን ጨምሮ የአሠልጣኝ ቡድን አባላት በኮቪድ ተይዘው ለቀናት ካገገሙ በኋላ መመለሳቸውን ድረ-ገፁ ዘግቧል። ባለፈው አርብ ወደ ካሜሩን ማቅናት የነበረባት ግብፅ በኮቪድ ምክንያት ወደ አዘጋጇ ሃገር የምታደርገውን በረራ አራዝማ ነበር። አልፎም የግብፅ ብሔራዊ ቡድን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ልምምድ አለመሥራቱም ተሰምቷል። ዘጠኝ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን በማንሳት ክብረ ወሰን የጨበጡት ፈርዖኖቹ ቅዳሜ ዕለት ወደ ካሜሩን መብረራቸው ተሰምቷል። የአርሰናሉ አጥቂ ፒዬር-ኤሜሪክ ኦባሜያንግ በኮቪድ ከተያዙ ሁሉት የጋቦን ብሔራዊ ቡድን አባላት መካከል አንዱ ሆኗል። ጊኒ ደግሞ ተከላካዩ ሚካኤል ድሬስታምን፣ አማካዩ ሞርላዬ ሲላን እንዲሁም አጥቂው ሶማን ሩዋንዳ ጥላ ነው ወደ ካሜሩን ያቀናችው። ኬፕ ቨርድና ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የምትሳተፈው ጋምቢያ ባለፈው ሳምንት በርካታ ተጫዋቾቻቸው በኮቪድ መያዛቸውን ይፋ አድርገው ነበር። ቱኒዚያም እንዲሁም የተወሰኑ ተጫዋቾቿ በኮቪድ መጠቃታቸውን አሳውቃለች። ዛሬ ምሽት የሚጀምረው የአፍሪካ ዋንጫ በመጀመሪያው ጨዋታ አዘጋጇ ካሜሩን ከቡርኪና ፋሶ ሲያፋልም በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ትገጥማለች።
በኮቪድ ምክንያት 11 ተጫዋቾች እንኳን ቢቀሩ ጨዋታ እንደማይሰረዝ ካፍ ገለጸ በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሃገራት የኮቪድ1-9 ወረርሽኝ ቢያጋጥማቸውና 11 ተጫዋች ብቻ ቢቀራቸው እንኳ ጨዋታው እንደማይሰረዝ ካፍ ገልጿል። የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪው ካፍ ከአስራ አንዱ ተጫዋቾች አንዱም ግብ ጠባቂ ባይሆን ጨዋታው እንደማይሰረዝ አስታውቋል። ይህንን ማሟላት የማይችል ቡድን በተለምዶ ፎርፌ በሚባለው ሕግ መሠረት የ2-0 ሽንፈት ይጣልበታል ይላል ካፍ። ካፍ ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፈው ዛሬ ምሽት [እሑድ] ከሚጀምረው ውድድር በፊት በርካታ ሃገራት ተጫዋቾቻችን በኮቪድ ተይዘዋል ብለው ካማረሩ በኋላ ነው። ካፍ አክሎም "ለየት ያለ ምክንያት" ላላቸው ሃገራት የውድድሩ አጋጅ ኮሚቴ "አስፈላጊውን ውሳኔ ይሰጣል" ብሏል። ከሁሉም ቀድማ ካሜሩን የገባችው ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት የተወሰኑ ተጫዋቾቿ በኮቪድ ተይዘውባት እንደነበር ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቦ ነበር። ተጫዋቾችን ጨምሮ የአሠልጣኝ ቡድን አባላት በኮቪድ ተይዘው ለቀናት ካገገሙ በኋላ መመለሳቸውን ድረ-ገፁ ዘግቧል። ባለፈው አርብ ወደ ካሜሩን ማቅናት የነበረባት ግብፅ በኮቪድ ምክንያት ወደ አዘጋጇ ሃገር የምታደርገውን በረራ አራዝማ ነበር። አልፎም የግብፅ ብሔራዊ ቡድን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ልምምድ አለመሥራቱም ተሰምቷል። ዘጠኝ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን በማንሳት ክብረ ወሰን የጨበጡት ፈርዖኖቹ ቅዳሜ ዕለት ወደ ካሜሩን መብረራቸው ተሰምቷል። የአርሰናሉ አጥቂ ፒዬር-ኤሜሪክ ኦባሜያንግ በኮቪድ ከተያዙ ሁሉት የጋቦን ብሔራዊ ቡድን አባላት መካከል አንዱ ሆኗል። ጊኒ ደግሞ ተከላካዩ ሚካኤል ድሬስታምን፣ አማካዩ ሞርላዬ ሲላን እንዲሁም አጥቂው ሶማን ሩዋንዳ ጥላ ነው ወደ ካሜሩን ያቀናችው። ኬፕ ቨርድና ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የምትሳተፈው ጋምቢያ ባለፈው ሳምንት በርካታ ተጫዋቾቻቸው በኮቪድ መያዛቸውን ይፋ አድርገው ነበር። ቱኒዚያም እንዲሁም የተወሰኑ ተጫዋቾቿ በኮቪድ መጠቃታቸውን አሳውቃለች። ዛሬ ምሽት የሚጀምረው የአፍሪካ ዋንጫ በመጀመሪያው ጨዋታ አዘጋጇ ካሜሩን ከቡርኪና ፋሶ ሲያፋልም በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ትገጥማለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-59926712
5sports
አርሰናል 5 ሲያስቆጥር፤ ዩናይትድ በዴ ሂያ ጥረት 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል
ትናንት በተከናወኑ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። አርሰናል በኢሚሬትስ ስታዲየም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ መጨረሻ ላይ የሚገኙትን ኖቲንግሃም ፎረስተን አስተናግደው አምስት ጎሎዎችን አከናንበዋቸዋል። ገብርኤል ማርቲኔሊ፣ ሪስ ኔልሰን፣ ቶማስ ፓርቴ እና ማርቲን ኦዴጋርስ ለአርሰናል ጎል ያስቆጠሩ ተጨዋቾች ናቸው። መድፈኞቹ በድንቅ የጨዋታ ብቃት ያገኙት ሦስት ነጥብ በ31 ነጥቦች በሊጉ መሪነት እንዲቀጥሉ አስቸሏቸዋል። የመጀረሚያውን ጎል ለገርኤል ማርቲኔሊ አመቻቸቶ ያቀበለው ቡካዮ ሳካ በመጀመሪያው አጋማሽ በጉዳት ምክንያት ተቀይሮ ወጥቷል። ቡካዮ ሳካ ያጋጠመው ጉዳት ዝርዝር ይፋ ባይደረግም ተጨዋቹን ከኳታር የዓለም ዋንጫ የሚያስቀረው አይሆንም ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። የአርሰናል ቁልፍ ተጫዋች የሆነው የ21 ዓመቱ ቡካዮ ሳካ፤ በጋርዝ ሳውጌት ቡድን አባል በመሆን ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር ወደ ኳታር ያቀናል ተብሎ ይገመታል። የ14ኛው ሳምንት የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች የተጠናቀቁት በማንችስተር ዩናይትድ እና ዌስት ሃም ግጥሚያ ነበር። ማርከስ ራሽፎርድ ለማንስተር ዩናይትድ ያስቆጠራት 100ኛ ጎል ቡድኑ ሦስት ነጥብ እንዲሰበስብ አስችላለች። ከራሸፎድ ጎል እኩል የግብ ጠባቂው ዴቪድ ዴ ሂያ ድንቅ አቋም ክለቡ ሦስት ነጥቦችን ማሳካት ችሏል። ዴቪድ ዴ ሂያ በጨዋታው ማጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ የዌስት ሃም ተከላካዩ ከርትስ ዙማ የጭንቅላት ኳስ እንዲሁም የሚካሂል አንቶኒዮን እና የደክለን ራይስ ጠንካራ ምት ግብ ጠባቂው ይህን አቋም ያሳየው በኳታር የዓለም ዋንጫ ለስፔን ብሔራዊ ቡድን አለመመረጡ በስፋት ከተዘበ በኋላ ነው። ባለፈው ሳምንት በርካታ የሰፔን ጋዜጦች  ዴ ሂያበእግሩ መጨዋት አይችልም በሚል በአሰልጣኝ ሉዊስ ኤነሪኬ ስብስብ ውስጥ አለመካተቱን ዘግበዋል። የስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ከዴ ሂያ ይልቅ የብራይተኑን ሮበርት ሳንቼዝ፣ የብሬንት ፎርዱን ዴቪድ ራያ እና የቼልሲውን ኬፓ አሪዛባላጋን ይዘው ወደ ኳታር እንደሚያቀኑ የአገሪቱ ጋዜጦች በስፋት ዘግበዋል። የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ግን የግብ ጠባቂ ዋነኛ ስራ ጎል እንዳይቆጠር ማድረግ እንጂ በእግር የመጫወት ችሎታ አይደለም ሲሉ ግብ ጠባቂያቸውን ተከላክለዋል። “ሁሉም የራሱ አመለካከት አለው ለእኔ ግን ለግብ ጠባቂ የመጀመሪያው ነገር ጎሎች እንዳይቆጠሩ መከላከል ነው” ብለዋል። በሳምንት 375ሺህ ፓወንድ የሚከፈለው ዴ ሂያ የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋዩ ግብ ጠባቂ እንደሆነ ይታመናል።
አርሰናል 5 ሲያስቆጥር፤ ዩናይትድ በዴ ሂያ ጥረት 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል ትናንት በተከናወኑ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። አርሰናል በኢሚሬትስ ስታዲየም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ መጨረሻ ላይ የሚገኙትን ኖቲንግሃም ፎረስተን አስተናግደው አምስት ጎሎዎችን አከናንበዋቸዋል። ገብርኤል ማርቲኔሊ፣ ሪስ ኔልሰን፣ ቶማስ ፓርቴ እና ማርቲን ኦዴጋርስ ለአርሰናል ጎል ያስቆጠሩ ተጨዋቾች ናቸው። መድፈኞቹ በድንቅ የጨዋታ ብቃት ያገኙት ሦስት ነጥብ በ31 ነጥቦች በሊጉ መሪነት እንዲቀጥሉ አስቸሏቸዋል። የመጀረሚያውን ጎል ለገርኤል ማርቲኔሊ አመቻቸቶ ያቀበለው ቡካዮ ሳካ በመጀመሪያው አጋማሽ በጉዳት ምክንያት ተቀይሮ ወጥቷል። ቡካዮ ሳካ ያጋጠመው ጉዳት ዝርዝር ይፋ ባይደረግም ተጨዋቹን ከኳታር የዓለም ዋንጫ የሚያስቀረው አይሆንም ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። የአርሰናል ቁልፍ ተጫዋች የሆነው የ21 ዓመቱ ቡካዮ ሳካ፤ በጋርዝ ሳውጌት ቡድን አባል በመሆን ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር ወደ ኳታር ያቀናል ተብሎ ይገመታል። የ14ኛው ሳምንት የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች የተጠናቀቁት በማንችስተር ዩናይትድ እና ዌስት ሃም ግጥሚያ ነበር። ማርከስ ራሽፎርድ ለማንስተር ዩናይትድ ያስቆጠራት 100ኛ ጎል ቡድኑ ሦስት ነጥብ እንዲሰበስብ አስችላለች። ከራሸፎድ ጎል እኩል የግብ ጠባቂው ዴቪድ ዴ ሂያ ድንቅ አቋም ክለቡ ሦስት ነጥቦችን ማሳካት ችሏል። ዴቪድ ዴ ሂያ በጨዋታው ማጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ የዌስት ሃም ተከላካዩ ከርትስ ዙማ የጭንቅላት ኳስ እንዲሁም የሚካሂል አንቶኒዮን እና የደክለን ራይስ ጠንካራ ምት ግብ ጠባቂው ይህን አቋም ያሳየው በኳታር የዓለም ዋንጫ ለስፔን ብሔራዊ ቡድን አለመመረጡ በስፋት ከተዘበ በኋላ ነው። ባለፈው ሳምንት በርካታ የሰፔን ጋዜጦች  ዴ ሂያበእግሩ መጨዋት አይችልም በሚል በአሰልጣኝ ሉዊስ ኤነሪኬ ስብስብ ውስጥ አለመካተቱን ዘግበዋል። የስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ከዴ ሂያ ይልቅ የብራይተኑን ሮበርት ሳንቼዝ፣ የብሬንት ፎርዱን ዴቪድ ራያ እና የቼልሲውን ኬፓ አሪዛባላጋን ይዘው ወደ ኳታር እንደሚያቀኑ የአገሪቱ ጋዜጦች በስፋት ዘግበዋል። የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ግን የግብ ጠባቂ ዋነኛ ስራ ጎል እንዳይቆጠር ማድረግ እንጂ በእግር የመጫወት ችሎታ አይደለም ሲሉ ግብ ጠባቂያቸውን ተከላክለዋል። “ሁሉም የራሱ አመለካከት አለው ለእኔ ግን ለግብ ጠባቂ የመጀመሪያው ነገር ጎሎች እንዳይቆጠሩ መከላከል ነው” ብለዋል። በሳምንት 375ሺህ ፓወንድ የሚከፈለው ዴ ሂያ የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋዩ ግብ ጠባቂ እንደሆነ ይታመናል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2nk0077d3o
3politics
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን ሒደቱ ተቀባይነት ያለው መሆን አለበት አሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “አካታች ብሔራዊ ምክክሩ” ስኬታማ እንዲሆን ሒደቱ ተቀባይነት ያለው ሆኖ መከናወን አለበት አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ መጋቢት 23/2014 ባወጡት መግለጫ ብሔራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ፈተናዎቻችንን መቅረፍ የሚያስችለን ወርቃማ እድል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ብለዋል። “ይህን ወርቅ የሆነ አጋጣሚ . . . እንደ ዕንቁ አክብረንና ተከባክበን ከተጠቀምንበት ዋጋው ከፍ ያለና ታሪክ ቀያሪ ዕድል ይሆናል” ብለዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚደረግ ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር ኮሚሽን መመሥረቱ ይታወሳል። ይህ ኮሚሽን የተለያዩ አላማዎችን አንግበው በፖለቲካው መድረኩ ላይ ያሉ ኃይሎችን እንዲሁም ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ ልዮነቶች ጠበው አገራዊ መግባባት ላይ አንዲደረስ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይታመናል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው መግለጫቸው የብሔራዊ ምክክሩ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ የምክክር ሂደቱን በበላይነት የሚመራውን የምክክር ኮምሽን በተለያዩ መንገዶች መደገፍ፣ ማትጋትና ማጽናት አለብን ብለዋል። “በዚህ ጉዳይ ዳር ቆሞ መገኘት በታሪክ ፊት የሚያስወቅስ ተግባር ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሁሉም በባለቤትነት ስሜት ለምክክር ሂደቱ አስተዋጽዖ ማድረግ አለበት ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አስተዳደራቸው የምክክር ኮሚሽኑ በቅልጥፍና መሥራት እንዲችል አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም ብለዋል። ተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የውይይቱ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆኑ “የሂደቱ ባለቤት ለሂደቱ ቅልጥፍናና ስኬት አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደርጉ በትኅትና እጠይቃለሁ" ብለዋል። ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በዚህ የምክክር ሂደት ተሳትፎ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን 11 ኮሚሽነሮችን መሾሙ ይታወሳል። ምክር ቤቱ ከእነዚህ መካከል ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ እንዲሆኑ ሰይሟል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን ሒደቱ ተቀባይነት ያለው መሆን አለበት አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “አካታች ብሔራዊ ምክክሩ” ስኬታማ እንዲሆን ሒደቱ ተቀባይነት ያለው ሆኖ መከናወን አለበት አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ መጋቢት 23/2014 ባወጡት መግለጫ ብሔራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ፈተናዎቻችንን መቅረፍ የሚያስችለን ወርቃማ እድል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ብለዋል። “ይህን ወርቅ የሆነ አጋጣሚ . . . እንደ ዕንቁ አክብረንና ተከባክበን ከተጠቀምንበት ዋጋው ከፍ ያለና ታሪክ ቀያሪ ዕድል ይሆናል” ብለዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚደረግ ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር ኮሚሽን መመሥረቱ ይታወሳል። ይህ ኮሚሽን የተለያዩ አላማዎችን አንግበው በፖለቲካው መድረኩ ላይ ያሉ ኃይሎችን እንዲሁም ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ ልዮነቶች ጠበው አገራዊ መግባባት ላይ አንዲደረስ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይታመናል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው መግለጫቸው የብሔራዊ ምክክሩ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ የምክክር ሂደቱን በበላይነት የሚመራውን የምክክር ኮምሽን በተለያዩ መንገዶች መደገፍ፣ ማትጋትና ማጽናት አለብን ብለዋል። “በዚህ ጉዳይ ዳር ቆሞ መገኘት በታሪክ ፊት የሚያስወቅስ ተግባር ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሁሉም በባለቤትነት ስሜት ለምክክር ሂደቱ አስተዋጽዖ ማድረግ አለበት ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አስተዳደራቸው የምክክር ኮሚሽኑ በቅልጥፍና መሥራት እንዲችል አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም ብለዋል። ተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም የውይይቱ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆኑ “የሂደቱ ባለቤት ለሂደቱ ቅልጥፍናና ስኬት አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደርጉ በትኅትና እጠይቃለሁ" ብለዋል። ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በዚህ የምክክር ሂደት ተሳትፎ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን 11 ኮሚሽነሮችን መሾሙ ይታወሳል። ምክር ቤቱ ከእነዚህ መካከል ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ እንዲሆኑ ሰይሟል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60954318
0business
ቱርክ፡ ፕሬዝደንቱ የማዕከላዊ ባንክ ገዢውን ካባረሩ በኋላ የሃገሪቱ ገንዘብ 14 በመቶ ላሸቀ
የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን የሃገሪቱን ማዕከላዊ ባንክ አስተዳደሪ ማበረራቸውን ተከትሎ የቱርክ መገበያየ ሊራ 14 በመቶ ላሸቀ። የቀድሞ የባንክ ገዢ ናሲ አግባል፤ ሊራ በጣም ዘቅጦ ከነበረበት ከፍ አድርገው ለዚህ ያበቁ ሰው ናቸው የሚል ሙገሳ ይቸራቸዋል። ነገር ግን ፕሬዝደንት ኤርዶዋን ሳይታሰብ ባለፈው ቅዳሜ ሰውዬውን አንስተው በሌላ ተክተዋቸዋል። ቱርክ የማዕከላዊ ባንክ አስተዳዳሪ ስታባርር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይህ ሶስተኛው ነው። ባለፈው ኅዳር የተሾሙት አግባል ከ15 በመቶ በላይ እየሆነ የመጣውን የዋጋ ንረት ለማቀዛቀዝ የወለድ መጠንን ከፍ አድርገው ነበር። የሰውዬው መባረር የሃገር ቤትና የውጭ ኢንቨስተሮችን አስደንግጧል። አግባል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በወሰዷቸው እርምጃዎች በብዙዎች ዘንድ አድናቆት እንዲቸራቸው አድርጓቸው ነበር። ሊራ አንድ ወቅት ላይ በፈረንጆቹ 2021 አዳጊው የመገበያያ ገንዘብ ተብሎ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነፃፀር ያለውን ዝቅጠት በአምስት አሻሽሎ ነበር። ባለፈው ሳምንት ሰውዬው የወለድ መጠን 2 በመቶ እንዲጨምር ማድረጋቸውን ተከትሎ የቱርክ ሊራ ወደላይ ተመንድጎ ነበር። በሃገሪቱ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ ባለሃብቶች ቱርክ ጠበቅ ያለ የገንዘብ ፖሊሲ እንድትቀርፅ ሲወተውቱ ቆይተዋል። አሁን ፕሬዝደንት ኤርዶዋን የማዕከላዊ ባንኩን አስተዳደር በሌላ ለመተካት በማሰባቸው ምክንያት የሊራ ዋጋ እንዳሽቆለቆለ ሊቀር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። አዲሱ የማዕከላዊ ባንኩ ኃላፊ የባንኪንግ ፕሮፌሰር ናቸው። አልፎም የገዢው ፓርቲ የቀድሞ ሕግ አውጭ ነበሩ። ሰውዬው ከተባረሩት ኃላፊ በተቃራኒ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ወለድ መጨመር አስፈላጊ ነው ብለው አያምኑም። የቱርክ የወለድ መጠን 19 በመቶ ደርሷል። ይህም የውጭ ሃገር ኢንቨስተሮች ገንዘባቸው በሃገሪቱ እንዲያከማቹ አድርጓቸዋል።
ቱርክ፡ ፕሬዝደንቱ የማዕከላዊ ባንክ ገዢውን ካባረሩ በኋላ የሃገሪቱ ገንዘብ 14 በመቶ ላሸቀ የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን የሃገሪቱን ማዕከላዊ ባንክ አስተዳደሪ ማበረራቸውን ተከትሎ የቱርክ መገበያየ ሊራ 14 በመቶ ላሸቀ። የቀድሞ የባንክ ገዢ ናሲ አግባል፤ ሊራ በጣም ዘቅጦ ከነበረበት ከፍ አድርገው ለዚህ ያበቁ ሰው ናቸው የሚል ሙገሳ ይቸራቸዋል። ነገር ግን ፕሬዝደንት ኤርዶዋን ሳይታሰብ ባለፈው ቅዳሜ ሰውዬውን አንስተው በሌላ ተክተዋቸዋል። ቱርክ የማዕከላዊ ባንክ አስተዳዳሪ ስታባርር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይህ ሶስተኛው ነው። ባለፈው ኅዳር የተሾሙት አግባል ከ15 በመቶ በላይ እየሆነ የመጣውን የዋጋ ንረት ለማቀዛቀዝ የወለድ መጠንን ከፍ አድርገው ነበር። የሰውዬው መባረር የሃገር ቤትና የውጭ ኢንቨስተሮችን አስደንግጧል። አግባል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በወሰዷቸው እርምጃዎች በብዙዎች ዘንድ አድናቆት እንዲቸራቸው አድርጓቸው ነበር። ሊራ አንድ ወቅት ላይ በፈረንጆቹ 2021 አዳጊው የመገበያያ ገንዘብ ተብሎ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነፃፀር ያለውን ዝቅጠት በአምስት አሻሽሎ ነበር። ባለፈው ሳምንት ሰውዬው የወለድ መጠን 2 በመቶ እንዲጨምር ማድረጋቸውን ተከትሎ የቱርክ ሊራ ወደላይ ተመንድጎ ነበር። በሃገሪቱ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ ባለሃብቶች ቱርክ ጠበቅ ያለ የገንዘብ ፖሊሲ እንድትቀርፅ ሲወተውቱ ቆይተዋል። አሁን ፕሬዝደንት ኤርዶዋን የማዕከላዊ ባንኩን አስተዳደር በሌላ ለመተካት በማሰባቸው ምክንያት የሊራ ዋጋ እንዳሽቆለቆለ ሊቀር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። አዲሱ የማዕከላዊ ባንኩ ኃላፊ የባንኪንግ ፕሮፌሰር ናቸው። አልፎም የገዢው ፓርቲ የቀድሞ ሕግ አውጭ ነበሩ። ሰውዬው ከተባረሩት ኃላፊ በተቃራኒ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ወለድ መጨመር አስፈላጊ ነው ብለው አያምኑም። የቱርክ የወለድ መጠን 19 በመቶ ደርሷል። ይህም የውጭ ሃገር ኢንቨስተሮች ገንዘባቸው በሃገሪቱ እንዲያከማቹ አድርጓቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56480620
2health
የጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ወደ ውጪ የሚደረገውን ጉዞ ያስቀር ይሆን?
የሰበታ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አሕመድ አባዲ የሦስት ዓመት ልጃቸው በጭንቅላት ካንሰር በመታመሙ ከሰባት ወራት በፊት ታይላንድ ባንግኮክ ከተማ ወስደው አሳክመዋል። “ከዚያ ተመልሰን በሦስተኛው ወር ስናስመረምረው በአከርካሪ አጥንቱ ላይ ካንሰር ተገኘበት” ይላሉ አቶ አሕመድ። የልጃቸው የጤና በጣም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደነበር የሚናገሩት አቶ አህመድ፣ “መቀመጥ፣ መሄድ፣ መተኛት እና ምግብ መዋጥም አይችልም ነበር” ይላሉ። በዚህ ሰዓት ነበር አቶ አሕመድ ልጃቸውን እና ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ ጅማ ከተማ የሄዱት። ወደ ጅማ ያቀኑት በጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ልጃቸውን ለማሳየት እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለካንሰር ሕክምና ወደ ጅማ ያቀኑት አቶ አሕመድ ብቻ አይደሉም። የባቱ ከተማ ነዋሪው አቶ ሙላቱም ጅማ ድረስ ያመጣቸው ሕክምናውን በመፈለግ ነው። ከዚህ ቀደም በካንሰር እንደታመሙ የሄዱት ወደ ሐዋሳ ነበር። በሐዋሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለካንሰር የሚያስፈልገውን የኬሞቴራፒ ሕክምና ከወሰዱ በኋላ ለጨረር ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተልከው ነበር። በጥቁር አንባሳ ለጨረር ሕክምና ተመዝግበው ወረፋ እስኪደርሳቸው እየጠበቁ እነደነበር የሚናገሩት አቶ ሙላቱ “በጥቁር አንባሳ ሰው ይበዛል፣ ለጨረር ሕክምና ከተመዘገብኩ ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር በኋላ በቀደም’ለታ ጠሩኝ” ይላሉ። ዶ/ር አብዩ ለገሰ በጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ስፔሻሊስት እና ኃላፊ ናቸው። “አገልግሎቱን ከጀመረ ወደ አራት ዓመት ይሆናል። ስንጀምር በመርፌ የሚሰጠውን ወይንም የካንሰር ሜዲካል አንኮሎጂ በመስጠት ነበር። በእርሱ ጀምረን ከተጠናከረ ከሁለት ዓመት ተኩል በኋላ የጨረር ሕክምና ማሽን አስመርቀን አገልግሎቱን መስጠት ጀመርን” ይላሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ የካንሰር ጨረር ሕክምና (ራዲዮ ቴራፒ) የሚሰጠው በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ብቻ ነበር። የጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይህንን አገልግሎት የሚሰጥ ሁለተኛው ማዕከል ነው። “እኛ የምንሰጠው አገልግሎት ለጅማ አካባቢ ማኀበረሰብ ብቻ ሳይሆን ከመላው አገሪቱ ለሚመጡ ታካሚዎች ነው” ይላሉ ዶ/ር አብዩ። ከዚህ በፊት ወደ ውጭ አገራት በመሄድ ሕክምና ያገኙ የነበሩ ታማሚዎች በአሁኑ ጊዜ ወደ ማዕከሉ በመምጣት አገልግሎት እያገኙ መሆኑን የሚገልጹት ኃላፊው፣ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥም 4500 ለሚሆኑ ታካሚዎች የካንሰር ሕክምና መስጠታቸውን ይናገራሉ። አገልግሎት መሰጠት ከጀመረ ሰባት ወር የሆነው የሆስፒታሉ የጨረር ሕክምና (ራዲየሸን) ደግሞ 725 የሚሆኑ ታካሚዎችን አስተናግዷል። የካንሰር ሕክምና አገልግሎት ካለመስፋፋቱ ጋር በተያያዘ የካንሰር ሕሙማን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለወራት የሕክምና ቀጠሮን ይጠብቃሉ። በተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙት ደግሞ እንደ ቱርክ፣ ሕንድ እና ታይላንድ ወዳሉ አገራት በመጓዝ ሕክምና ያገኛሉ። የሰበታ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አሕመድ አባዲ፣ ልጃቸው የጭንቅላት ካንሰር መያዙን በተነገራቸወ ወቅት ታይላንድ ወስደው ነበር ያሳከሙት። ይሁን እንጂ ወደ አገር ቤት ተመልሰው የተወሰኑ ወራት ከቆዩ በኋላ በአከርካሪ አጥንቱ ላይ ካንሰር በመገኘቱ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ይዘውት መጥተዋል። የልጃቸው የጤና ሁኔታ በአስጊ ሁኔታ ላይ ደርሶ እንደነበር የሚያስታውሱት አቶ አህመድ፣ “አርብ እነርሱ ጋር ሄጄ፣ በልዩ ሁኔታ ካዩት በኋላ በሦስተኛው ቀን ማክሰኞ ዕለት የጨረር ሕክምና እንዲያገኝ አደረጉልኝ” ይላሉ። “15 የጨረር ሕክምና ነው የታዘዘለት። ከዚያም መካከል እስካሁን ሰባቱን ወስዷል። በእነዚሁ በወሰዳቸው ሰባቱ ሕክምና አስገራሚ ውጤት ነው ያየነው። አንደኛ በእግሩ እና በመቀመጫው ላይ የነበረው ችግር ተፈትቷል” በማለት ስለልጃቸው ጤንነት መሻሻል ይናገራሉ። ለሕክምና ከአገር መውጣት ኪስንም ስነ ልቦናንም እንደሚፈታተን አቶ አህመድ አልሸሸጉም። “አንደኛ የአውሮፕላን ቲኬት ራሱ በጣም ውድ ነው። ሌላው ደግሞ ከእኛ አገር ባህል ወጥተህ በሌላ አገር ውስጥ ትቸገራለህ። ክፍያውን የምትፈጽመው በውጭ ምንዛሪ ነው። ከህክምናው ውጪ ለሌሎች ወጪዎች የሚሆን የውጪ ምንዛሪ ማግኘት አስቸጋሪ ነው።” እንደ ቱርክ፣ ሕንድ እና ታይላንድ ባሉ የውጭ አገራት የሚሰጡ ሕክምናዎች ውድ መሆናቸውን የሚናገሩት የካንሰር ስፔሻሊስቱ ዶ/ር አብዩ፣ ማዕከላቸው ከፍተኛ ደረጃ ያለው ሕክምና እየሰጠ መሆኑን ያስረዳሉ። ይህም ዜጎች ወደ ውጭ አገር በመሄድ የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚደርስባቸውን እንግልት የሚያስቀር መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። በተጨማሪም የውጭ ምንዛሪን ከማስቀረት አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ያብራራሉ። ከዚህ በፊት ከመላው አገሪቱ ለሚመጡት ታካሚዎች የካንሰር ሕክምናን ሲሰጥ የነበረው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ከታካሚዎች ቁጥር መብዛት የተነሳ ለጨረር ሕክምና የረዥም ጊዜ ቀጠሮ እንዲጠብቁ ይደረግ ነበር። ዶ/ር አብዩ ይህንን ሲገልፁ፣ ቢያንስ አንድ ዓመት ያህል የሚወስድ ቀጠሮ እንደሚሰጥ ያስረዳሉ። በዚህም የቀጠሮ ጊዜያቸው ሳይደርስ እና ህክምናውን ሳያገኙ፣ ሕይወታቸው የሚያልፍ ነበሩ። በአሁኑ ወቅት በጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ታካሚዎች የጨረር ሕክምናን ለማግኘት ከሦስት እስከ አራት ወር ድረስ ብቻ ቀጠሮ ሊሰጣቸው እንደሚችል ኃላፊው ይናገራሉ። ይህም ሊሆን የቻለው፣ ከአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚመጡ ታካሚዎች ወደ ጅማ ለሕክምና በመሄዳቸው የተነሳ መሆኑን ይናገራሉ። በተቻለን መጠን እስከ አንድ ዓመት ቀጠሮ የሚያዝላቸው ህሙማን እንዳይኖሩ ጥረት እያደረግን ነው የሚሉት ዶ/ር አብዩ፣ የካንሰር ታማማዎችም ቢሆኑ የበሽታው ምልክቶች እንደታየባቸው ወዲያውኑ ሕክምና መጀመር አለባቸው ሲሉ ይመክራሉ። የካንሰር ህመምን ለማከም የሚሰጡት ሕክምናዎች ዋና ዋናዎቹ ሦስት መሆናቸውን ባለሙያው ይናገራሉ። እነርሱም ቀዶ ሕክምና፣ በመርፌ የሚሰጥ መድኃኒት እና የጨረር ሕክምና ናቸው።። የጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ከእነዚህ መካከል ሁለቱን፣ ማለትም በመርፌ የሚሰጠውን ሕክምና እና የጨረር ሕክምና (ራዲዮቴራፒ) አገልግሎቶችን ይሰጣል። በማዕከሉ  ለጨረር ሕክምናው የሚሆነው መሳርያ በጅማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ 20 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ ነው የተደራጀው። “አንድ ማሽን ነው ያለን። የማሽን እና እቃዎች ጉድለት አለብን” የሚሉት ዶ/ር አብዩ፣ በአሁኑ ሰዓትም ተጨማሪ ማሽን ለመግጠም የሚያስችል ተስማሚ ቦታ እንዳላቸው ይናገራሉ። ማዕከሉ ሁለት የካንሰር ስፔሻሊስቶች፣ የጨረር ማሽን ባለሙያ፣ አንድ ሜዲካል ፊዚስት፣  እንዲሁም ነርሶች እና የሬዲዮ ቴራፒ ባለሙያዎች ጋር የተደራጀ ነው። ዶ/ር አብዩ ወደ ማዕከላቸው በብዛት የሚመጡ የካንሰር ታማሚዎችን ሲያስረዱ፣  የማህፅን ጫፍ፣ የጡት እና የአንጀት ካንሰር ታማሚዎች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ይናገራሉ። ከእነዚህም በተጨማሪ የጡንቻ፣ የአጥንት እንዲሁም የደም ካንሰር ቀጥሎ በብዛት የሚስተዋሉ መሆናቸውን ስፔሻሊስቱ ይናገራሉ።
የጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ወደ ውጪ የሚደረገውን ጉዞ ያስቀር ይሆን? የሰበታ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አሕመድ አባዲ የሦስት ዓመት ልጃቸው በጭንቅላት ካንሰር በመታመሙ ከሰባት ወራት በፊት ታይላንድ ባንግኮክ ከተማ ወስደው አሳክመዋል። “ከዚያ ተመልሰን በሦስተኛው ወር ስናስመረምረው በአከርካሪ አጥንቱ ላይ ካንሰር ተገኘበት” ይላሉ አቶ አሕመድ። የልጃቸው የጤና በጣም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደነበር የሚናገሩት አቶ አህመድ፣ “መቀመጥ፣ መሄድ፣ መተኛት እና ምግብ መዋጥም አይችልም ነበር” ይላሉ። በዚህ ሰዓት ነበር አቶ አሕመድ ልጃቸውን እና ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ ጅማ ከተማ የሄዱት። ወደ ጅማ ያቀኑት በጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ልጃቸውን ለማሳየት እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለካንሰር ሕክምና ወደ ጅማ ያቀኑት አቶ አሕመድ ብቻ አይደሉም። የባቱ ከተማ ነዋሪው አቶ ሙላቱም ጅማ ድረስ ያመጣቸው ሕክምናውን በመፈለግ ነው። ከዚህ ቀደም በካንሰር እንደታመሙ የሄዱት ወደ ሐዋሳ ነበር። በሐዋሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለካንሰር የሚያስፈልገውን የኬሞቴራፒ ሕክምና ከወሰዱ በኋላ ለጨረር ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተልከው ነበር። በጥቁር አንባሳ ለጨረር ሕክምና ተመዝግበው ወረፋ እስኪደርሳቸው እየጠበቁ እነደነበር የሚናገሩት አቶ ሙላቱ “በጥቁር አንባሳ ሰው ይበዛል፣ ለጨረር ሕክምና ከተመዘገብኩ ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር በኋላ በቀደም’ለታ ጠሩኝ” ይላሉ። ዶ/ር አብዩ ለገሰ በጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ስፔሻሊስት እና ኃላፊ ናቸው። “አገልግሎቱን ከጀመረ ወደ አራት ዓመት ይሆናል። ስንጀምር በመርፌ የሚሰጠውን ወይንም የካንሰር ሜዲካል አንኮሎጂ በመስጠት ነበር። በእርሱ ጀምረን ከተጠናከረ ከሁለት ዓመት ተኩል በኋላ የጨረር ሕክምና ማሽን አስመርቀን አገልግሎቱን መስጠት ጀመርን” ይላሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ የካንሰር ጨረር ሕክምና (ራዲዮ ቴራፒ) የሚሰጠው በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ብቻ ነበር። የጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይህንን አገልግሎት የሚሰጥ ሁለተኛው ማዕከል ነው። “እኛ የምንሰጠው አገልግሎት ለጅማ አካባቢ ማኀበረሰብ ብቻ ሳይሆን ከመላው አገሪቱ ለሚመጡ ታካሚዎች ነው” ይላሉ ዶ/ር አብዩ። ከዚህ በፊት ወደ ውጭ አገራት በመሄድ ሕክምና ያገኙ የነበሩ ታማሚዎች በአሁኑ ጊዜ ወደ ማዕከሉ በመምጣት አገልግሎት እያገኙ መሆኑን የሚገልጹት ኃላፊው፣ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥም 4500 ለሚሆኑ ታካሚዎች የካንሰር ሕክምና መስጠታቸውን ይናገራሉ። አገልግሎት መሰጠት ከጀመረ ሰባት ወር የሆነው የሆስፒታሉ የጨረር ሕክምና (ራዲየሸን) ደግሞ 725 የሚሆኑ ታካሚዎችን አስተናግዷል። የካንሰር ሕክምና አገልግሎት ካለመስፋፋቱ ጋር በተያያዘ የካንሰር ሕሙማን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለወራት የሕክምና ቀጠሮን ይጠብቃሉ። በተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙት ደግሞ እንደ ቱርክ፣ ሕንድ እና ታይላንድ ወዳሉ አገራት በመጓዝ ሕክምና ያገኛሉ። የሰበታ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አሕመድ አባዲ፣ ልጃቸው የጭንቅላት ካንሰር መያዙን በተነገራቸወ ወቅት ታይላንድ ወስደው ነበር ያሳከሙት። ይሁን እንጂ ወደ አገር ቤት ተመልሰው የተወሰኑ ወራት ከቆዩ በኋላ በአከርካሪ አጥንቱ ላይ ካንሰር በመገኘቱ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ይዘውት መጥተዋል። የልጃቸው የጤና ሁኔታ በአስጊ ሁኔታ ላይ ደርሶ እንደነበር የሚያስታውሱት አቶ አህመድ፣ “አርብ እነርሱ ጋር ሄጄ፣ በልዩ ሁኔታ ካዩት በኋላ በሦስተኛው ቀን ማክሰኞ ዕለት የጨረር ሕክምና እንዲያገኝ አደረጉልኝ” ይላሉ። “15 የጨረር ሕክምና ነው የታዘዘለት። ከዚያም መካከል እስካሁን ሰባቱን ወስዷል። በእነዚሁ በወሰዳቸው ሰባቱ ሕክምና አስገራሚ ውጤት ነው ያየነው። አንደኛ በእግሩ እና በመቀመጫው ላይ የነበረው ችግር ተፈትቷል” በማለት ስለልጃቸው ጤንነት መሻሻል ይናገራሉ። ለሕክምና ከአገር መውጣት ኪስንም ስነ ልቦናንም እንደሚፈታተን አቶ አህመድ አልሸሸጉም። “አንደኛ የአውሮፕላን ቲኬት ራሱ በጣም ውድ ነው። ሌላው ደግሞ ከእኛ አገር ባህል ወጥተህ በሌላ አገር ውስጥ ትቸገራለህ። ክፍያውን የምትፈጽመው በውጭ ምንዛሪ ነው። ከህክምናው ውጪ ለሌሎች ወጪዎች የሚሆን የውጪ ምንዛሪ ማግኘት አስቸጋሪ ነው።” እንደ ቱርክ፣ ሕንድ እና ታይላንድ ባሉ የውጭ አገራት የሚሰጡ ሕክምናዎች ውድ መሆናቸውን የሚናገሩት የካንሰር ስፔሻሊስቱ ዶ/ር አብዩ፣ ማዕከላቸው ከፍተኛ ደረጃ ያለው ሕክምና እየሰጠ መሆኑን ያስረዳሉ። ይህም ዜጎች ወደ ውጭ አገር በመሄድ የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚደርስባቸውን እንግልት የሚያስቀር መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። በተጨማሪም የውጭ ምንዛሪን ከማስቀረት አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ያብራራሉ። ከዚህ በፊት ከመላው አገሪቱ ለሚመጡት ታካሚዎች የካንሰር ሕክምናን ሲሰጥ የነበረው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ከታካሚዎች ቁጥር መብዛት የተነሳ ለጨረር ሕክምና የረዥም ጊዜ ቀጠሮ እንዲጠብቁ ይደረግ ነበር። ዶ/ር አብዩ ይህንን ሲገልፁ፣ ቢያንስ አንድ ዓመት ያህል የሚወስድ ቀጠሮ እንደሚሰጥ ያስረዳሉ። በዚህም የቀጠሮ ጊዜያቸው ሳይደርስ እና ህክምናውን ሳያገኙ፣ ሕይወታቸው የሚያልፍ ነበሩ። በአሁኑ ወቅት በጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ታካሚዎች የጨረር ሕክምናን ለማግኘት ከሦስት እስከ አራት ወር ድረስ ብቻ ቀጠሮ ሊሰጣቸው እንደሚችል ኃላፊው ይናገራሉ። ይህም ሊሆን የቻለው፣ ከአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚመጡ ታካሚዎች ወደ ጅማ ለሕክምና በመሄዳቸው የተነሳ መሆኑን ይናገራሉ። በተቻለን መጠን እስከ አንድ ዓመት ቀጠሮ የሚያዝላቸው ህሙማን እንዳይኖሩ ጥረት እያደረግን ነው የሚሉት ዶ/ር አብዩ፣ የካንሰር ታማማዎችም ቢሆኑ የበሽታው ምልክቶች እንደታየባቸው ወዲያውኑ ሕክምና መጀመር አለባቸው ሲሉ ይመክራሉ። የካንሰር ህመምን ለማከም የሚሰጡት ሕክምናዎች ዋና ዋናዎቹ ሦስት መሆናቸውን ባለሙያው ይናገራሉ። እነርሱም ቀዶ ሕክምና፣ በመርፌ የሚሰጥ መድኃኒት እና የጨረር ሕክምና ናቸው።። የጅማ ዩኒቨርስቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ከእነዚህ መካከል ሁለቱን፣ ማለትም በመርፌ የሚሰጠውን ሕክምና እና የጨረር ሕክምና (ራዲዮቴራፒ) አገልግሎቶችን ይሰጣል። በማዕከሉ  ለጨረር ሕክምናው የሚሆነው መሳርያ በጅማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ 20 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ ነው የተደራጀው። “አንድ ማሽን ነው ያለን። የማሽን እና እቃዎች ጉድለት አለብን” የሚሉት ዶ/ር አብዩ፣ በአሁኑ ሰዓትም ተጨማሪ ማሽን ለመግጠም የሚያስችል ተስማሚ ቦታ እንዳላቸው ይናገራሉ። ማዕከሉ ሁለት የካንሰር ስፔሻሊስቶች፣ የጨረር ማሽን ባለሙያ፣ አንድ ሜዲካል ፊዚስት፣  እንዲሁም ነርሶች እና የሬዲዮ ቴራፒ ባለሙያዎች ጋር የተደራጀ ነው። ዶ/ር አብዩ ወደ ማዕከላቸው በብዛት የሚመጡ የካንሰር ታማሚዎችን ሲያስረዱ፣  የማህፅን ጫፍ፣ የጡት እና የአንጀት ካንሰር ታማሚዎች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ይናገራሉ። ከእነዚህም በተጨማሪ የጡንቻ፣ የአጥንት እንዲሁም የደም ካንሰር ቀጥሎ በብዛት የሚስተዋሉ መሆናቸውን ስፔሻሊስቱ ይናገራሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cx80yr27ezqo
2health
ኮሮረናቫይረስ፡ ጃፓናዊቷ የኮቪድ-19 ታማሚ በህይወት ካለ ሰው የሳንባ ንቅለ ተከላ በማድረግ የመጀመሪያ ሆነች
አንዲት የኮቪድ-19 ታማሚ ጃፓናዊት በህይወት ካሉ ሰዎች ሳንባ በመቀበል በዓለማችን የመጀመሪያዋ የኮሮናቫይረስ ህመምተኛ ለመሆን በቃች። ግለሰቧ በቀዶ ህክምና በአካሏ ላይ እንዲገባ የተደረገውን የሳንባ ክፍል ከልጇና ከባሏ የተበረከተ ነው ተብሏል። ታማሚዋ ሳንባው የተለገሳት በኮሮናቫይረስ ምክንያት የመተንፈሻ አካሏ እንደ አንድ የሰውነት ክፍሏ መደበኛውን ሥራውን መሥራት በማቆሙ ነው። በኪዮቶ የሚገኙ ሐኪሞች እንዳሉት ሴትየዋ በቅርብ ወራት ውስጥ አገግማ ወደ ሙሉ ጤናዋ ትመለሳለች። ጃፓን ውስጥ ከሞቱ ሰዎች ላይ የሚገኝን የሳንባ ልገሳ ለማግኘት ያለው ወረፋ ብዙ ጊዜን መጠበቅን ይጠይቃል። በሕይወት ካሉ ሰዎች ሳንባ ንቅለ ተከላ ለኮቪድ-19 በሽተኛ ሲለገስ ግን ይህ የመጀመሪያው ነው። ንቅለ ተከላው የተደረገበት የኪዮቶ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል የሳንባ መተካቱን ሂደት 11 ሰዓታት በፈጀ የቀዶ ህክምና ሂደት አጠናቆታል። ሐኪሞቹ እንዳሉት ሳንባውን የለገሱት ባልና ልጅ እንዲሁም ሳንባ የተለገሳት ታማሚ ሦስቱም በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። በቻይና፣ በአውሮፓና በአሜሪካ በተመሳሳይ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሳንባቸው ከጥቅም ውጪ የሆነባቸው ታማሚዎች የሞቱ ሰዎችን ሳንባ በመቀበል እየዳኑ ይገኛሉ። ነገር ግን ከሞቱ ሰዎች ሳንባ ማግኘት ተራን የመጠበቁ ሂደት በጃፓን ዓመታትን የሚወስድ ነው። ሌላ ተያያዥ በሽታ ያልነበረባት ይህች ጃፓናዊት ታካሚ ኮቪድ-19 ከተያዘች በኋላ በሕይወት ለመቆየት የግድ የሳንባ ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልጋት ከታወቀ በኋላ ባሏና ልጇ ይህን ልገሳ ለማድረግ አላቅማሙም። በሕይወት ከሚገኘው ልጇና ከባለቤቷ ለግለሰቧ የተሰጠው የተወሰነ የሳንባ ክፍላቸው ነው። የሚቀራቸው ሳንባ አነስተኛ በመሆኑ ሊፈጥርባቸው የሚችለው የጤና እክል ልገሳውን ከማድረጋቸው በፊት ተብራርቶላቸዋል። ንቅለ ተከላውን የመሩት ፕሮፌሰር ለጃፓኑ ኪዮዶ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ይህ በሕይወት ካሉ ሰዎች ሳንባን ወስዶ ለሌላ ሰው የመትከል ሂደት ትልቅ የሕክምና አምርታ ነው ብለዋል።
ኮሮረናቫይረስ፡ ጃፓናዊቷ የኮቪድ-19 ታማሚ በህይወት ካለ ሰው የሳንባ ንቅለ ተከላ በማድረግ የመጀመሪያ ሆነች አንዲት የኮቪድ-19 ታማሚ ጃፓናዊት በህይወት ካሉ ሰዎች ሳንባ በመቀበል በዓለማችን የመጀመሪያዋ የኮሮናቫይረስ ህመምተኛ ለመሆን በቃች። ግለሰቧ በቀዶ ህክምና በአካሏ ላይ እንዲገባ የተደረገውን የሳንባ ክፍል ከልጇና ከባሏ የተበረከተ ነው ተብሏል። ታማሚዋ ሳንባው የተለገሳት በኮሮናቫይረስ ምክንያት የመተንፈሻ አካሏ እንደ አንድ የሰውነት ክፍሏ መደበኛውን ሥራውን መሥራት በማቆሙ ነው። በኪዮቶ የሚገኙ ሐኪሞች እንዳሉት ሴትየዋ በቅርብ ወራት ውስጥ አገግማ ወደ ሙሉ ጤናዋ ትመለሳለች። ጃፓን ውስጥ ከሞቱ ሰዎች ላይ የሚገኝን የሳንባ ልገሳ ለማግኘት ያለው ወረፋ ብዙ ጊዜን መጠበቅን ይጠይቃል። በሕይወት ካሉ ሰዎች ሳንባ ንቅለ ተከላ ለኮቪድ-19 በሽተኛ ሲለገስ ግን ይህ የመጀመሪያው ነው። ንቅለ ተከላው የተደረገበት የኪዮቶ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል የሳንባ መተካቱን ሂደት 11 ሰዓታት በፈጀ የቀዶ ህክምና ሂደት አጠናቆታል። ሐኪሞቹ እንዳሉት ሳንባውን የለገሱት ባልና ልጅ እንዲሁም ሳንባ የተለገሳት ታማሚ ሦስቱም በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። በቻይና፣ በአውሮፓና በአሜሪካ በተመሳሳይ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሳንባቸው ከጥቅም ውጪ የሆነባቸው ታማሚዎች የሞቱ ሰዎችን ሳንባ በመቀበል እየዳኑ ይገኛሉ። ነገር ግን ከሞቱ ሰዎች ሳንባ ማግኘት ተራን የመጠበቁ ሂደት በጃፓን ዓመታትን የሚወስድ ነው። ሌላ ተያያዥ በሽታ ያልነበረባት ይህች ጃፓናዊት ታካሚ ኮቪድ-19 ከተያዘች በኋላ በሕይወት ለመቆየት የግድ የሳንባ ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልጋት ከታወቀ በኋላ ባሏና ልጇ ይህን ልገሳ ለማድረግ አላቅማሙም። በሕይወት ከሚገኘው ልጇና ከባለቤቷ ለግለሰቧ የተሰጠው የተወሰነ የሳንባ ክፍላቸው ነው። የሚቀራቸው ሳንባ አነስተኛ በመሆኑ ሊፈጥርባቸው የሚችለው የጤና እክል ልገሳውን ከማድረጋቸው በፊት ተብራርቶላቸዋል። ንቅለ ተከላውን የመሩት ፕሮፌሰር ለጃፓኑ ኪዮዶ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ይህ በሕይወት ካሉ ሰዎች ሳንባን ወስዶ ለሌላ ሰው የመትከል ሂደት ትልቅ የሕክምና አምርታ ነው ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56674361
3politics
የአፍሪካ አገራት መሪዎች በመንግሥት ምስረታ በዓለ ሲመት ላይ ምን አሉ?
ዛሬ መስከረም 24/2014 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ አዲስ መንግሥት መስረታ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ንግግር አድርገው ለኢትዮጵያና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ላይ የተጋበዙት የኡጋንዳው ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፤ በኡጋንዳ ሕዝብ ስም የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ጠቅላይ ሚንስትሩን "እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል። በኡጋንዳ የጎሳ እና የሃይማኖት ክፍፍል ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረ ገልጸው፤ የማንነት ፖለቲካ የሚፈጥረውን ልዩነት መቅረፍ ወደ ለውጥ ጎዳና እንደሚያሻግር ተናግረዋል። የደቡብ ሱዳኑ ሳልቫ ኪር በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰላም ለማለት እና እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ነው የመጣሁት። "ያለ እናንተ ድምጽ ወንድሜ ዐብይ ወደ ሥልጣን አይመጣም ነበር። ከጎኑ ቆማችሁ ወደ ሰላም ተሻገሩ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያን "ታላቋ እናታችን" ሲሉ አንቆለጳጵሰዋል። በደቡብ ሱዳን የተፈጠረው ቀውስ በኢትዮጵያ እንዲደገም እንደማይሹ እና ግጭቱ በሰላማዊ ውይይት እንዲፈታ ጠይቀዋል። በደቡብ ሱዳን እና ሱዳን መካከል ሰላም እንዲወርድ ኢትዮጵያ ያደረገችውን ጥረት ከታሪክ አጣቅሰዋል። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፣ በኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመነ መንግሥትም ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ላይ ፊቷን እንዳላዞረችም ሳልቫ ኪር ሳይጠቅሱ አላለፉም። የጂቡቲው ፕሬዘዳንት እስማኤል ጊሌ በበዓለ ሲመቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ማየት አስደስቶኛል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን "ከጂቡቲ ሕዝብ የተላከ የሚያበረታታ እና ተስፋ ሰጪ መልዕክት ይዤ ነው የመጣሁት" ብለዋቸዋል። ኢትዮጵያን የፓን አፍሪካኒዝም ተምሳሌት ብለው ካሞገሱ በኋላ፤ በምጣኔ ሀብት ረገድ በቀጠናው ያላትን ሚና ጠቅሰው "ኢትዮጵያ ከራሷ ጋር ሰላም እንድታወርድ፣ የቀድሞ ትልቅነቷን ዳግም እንድታድስ" ጠይቀዋል። ጦርነት በቀጠናው ያስከተለውን አስከፊ ገጽታ ከታሪክ አጣቅሰው፤ ኢትዮጵያም "ከልጆቿ ጋር እንድትታረቅ" እና ወደ ሰላም እንድትመለስ አሳስበዋል። እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ እንኳን ለኢሬቻ አደረሳችሁ፣ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ሲሉም በአማርኛ ንግግራቸውን አጠናቀዋል። የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በመስቀል አደባባይ ባደረጉት ንግግር፤ "ወንድሜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነህ ስለተመረጥክ እንኳን ደስ አለህ" ብለዋል። ኬንያ የኢትዮጵያን እድገት እና ሰላም ለመደገፍ ዝግጁ ናት ሲሉም ድጋፋቸውን ገልጸዋል። "ወንድሜ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንድትመራ፣ ሰላም እንድታመጣ፣ መረጋጋትን እንድታረጋግጥ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድ እንድታደርግ ሥልጣን ሰጥተውሀል። የመረጡህም ያልመረጡህም ያንተ ሕዝቦች ናቸው" ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። የአፍሪካ ሕዝቦች ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲሆኑ የረዳችው ኢትዮጵያ "እናታችን ናት" ካሉ በኋላ "እናት ሰላም ካጣች ቤተሰቧም ይታወካል" ሲሉ ኢትዮጵያ ወደ ሰላም እንድትመጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ሙሐመዱ ቡሀሪ፤ በበዓለ ሲመቱ ላይ በመገኘቴ ኩራት ይሰማኛል ብለዋል። በሰኔ ወር የተካሄደው ምርጫ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ "በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ እንደሚያምን አሳይቶኛል" ሲሉም ተናግረዋል። አይይዘውም በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ጠቅላይ ሚንስትሩ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ናይጄሪያ የኢትዮጵያን አንድነት እና ሉዓላዊነት መከበር እንደምትደግፍም ቡሀሪ ገልጸዋል። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ በበዓለ ሲመቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያውያን ፍላጎታቸውን የሚያስጠብቅ አስተዳደር በመምረጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ጨምሮ ሌሎችም ፈተናዎችን ለማለፍ አስተዳደሩ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስባል። አያይዘውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉን አቀፍ እድገት እንዲጎናጸፍ ጠቅላይ ሚንስትሩ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ እምነቴ ነው ብለዋል።
የአፍሪካ አገራት መሪዎች በመንግሥት ምስረታ በዓለ ሲመት ላይ ምን አሉ? ዛሬ መስከረም 24/2014 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ አዲስ መንግሥት መስረታ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ንግግር አድርገው ለኢትዮጵያና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ላይ የተጋበዙት የኡጋንዳው ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፤ በኡጋንዳ ሕዝብ ስም የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ጠቅላይ ሚንስትሩን "እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል። በኡጋንዳ የጎሳ እና የሃይማኖት ክፍፍል ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረ ገልጸው፤ የማንነት ፖለቲካ የሚፈጥረውን ልዩነት መቅረፍ ወደ ለውጥ ጎዳና እንደሚያሻግር ተናግረዋል። የደቡብ ሱዳኑ ሳልቫ ኪር በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሰላም ለማለት እና እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ነው የመጣሁት። "ያለ እናንተ ድምጽ ወንድሜ ዐብይ ወደ ሥልጣን አይመጣም ነበር። ከጎኑ ቆማችሁ ወደ ሰላም ተሻገሩ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያን "ታላቋ እናታችን" ሲሉ አንቆለጳጵሰዋል። በደቡብ ሱዳን የተፈጠረው ቀውስ በኢትዮጵያ እንዲደገም እንደማይሹ እና ግጭቱ በሰላማዊ ውይይት እንዲፈታ ጠይቀዋል። በደቡብ ሱዳን እና ሱዳን መካከል ሰላም እንዲወርድ ኢትዮጵያ ያደረገችውን ጥረት ከታሪክ አጣቅሰዋል። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፣ በኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመነ መንግሥትም ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ላይ ፊቷን እንዳላዞረችም ሳልቫ ኪር ሳይጠቅሱ አላለፉም። የጂቡቲው ፕሬዘዳንት እስማኤል ጊሌ በበዓለ ሲመቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ማየት አስደስቶኛል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን "ከጂቡቲ ሕዝብ የተላከ የሚያበረታታ እና ተስፋ ሰጪ መልዕክት ይዤ ነው የመጣሁት" ብለዋቸዋል። ኢትዮጵያን የፓን አፍሪካኒዝም ተምሳሌት ብለው ካሞገሱ በኋላ፤ በምጣኔ ሀብት ረገድ በቀጠናው ያላትን ሚና ጠቅሰው "ኢትዮጵያ ከራሷ ጋር ሰላም እንድታወርድ፣ የቀድሞ ትልቅነቷን ዳግም እንድታድስ" ጠይቀዋል። ጦርነት በቀጠናው ያስከተለውን አስከፊ ገጽታ ከታሪክ አጣቅሰው፤ ኢትዮጵያም "ከልጆቿ ጋር እንድትታረቅ" እና ወደ ሰላም እንድትመለስ አሳስበዋል። እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ እንኳን ለኢሬቻ አደረሳችሁ፣ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ሲሉም በአማርኛ ንግግራቸውን አጠናቀዋል። የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በመስቀል አደባባይ ባደረጉት ንግግር፤ "ወንድሜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነህ ስለተመረጥክ እንኳን ደስ አለህ" ብለዋል። ኬንያ የኢትዮጵያን እድገት እና ሰላም ለመደገፍ ዝግጁ ናት ሲሉም ድጋፋቸውን ገልጸዋል። "ወንድሜ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንድትመራ፣ ሰላም እንድታመጣ፣ መረጋጋትን እንድታረጋግጥ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድ እንድታደርግ ሥልጣን ሰጥተውሀል። የመረጡህም ያልመረጡህም ያንተ ሕዝቦች ናቸው" ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። የአፍሪካ ሕዝቦች ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲሆኑ የረዳችው ኢትዮጵያ "እናታችን ናት" ካሉ በኋላ "እናት ሰላም ካጣች ቤተሰቧም ይታወካል" ሲሉ ኢትዮጵያ ወደ ሰላም እንድትመጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ሙሐመዱ ቡሀሪ፤ በበዓለ ሲመቱ ላይ በመገኘቴ ኩራት ይሰማኛል ብለዋል። በሰኔ ወር የተካሄደው ምርጫ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ "በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ እንደሚያምን አሳይቶኛል" ሲሉም ተናግረዋል። አይይዘውም በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ጠቅላይ ሚንስትሩ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ናይጄሪያ የኢትዮጵያን አንድነት እና ሉዓላዊነት መከበር እንደምትደግፍም ቡሀሪ ገልጸዋል። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ በበዓለ ሲመቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያውያን ፍላጎታቸውን የሚያስጠብቅ አስተዳደር በመምረጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ጨምሮ ሌሎችም ፈተናዎችን ለማለፍ አስተዳደሩ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስባል። አያይዘውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉን አቀፍ እድገት እንዲጎናጸፍ ጠቅላይ ሚንስትሩ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ እምነቴ ነው ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58792454
0business
ከጉሊት እስከ ቅንጡ ሆቴል ግብይትን ያሳለጠው ኤም-ፔሳ ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል?
ከሁለት ወራት በኋላ በኢትዮጵያ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቀው ሳፋሪኮም፤ ኤም-ፔሳ የተባለውን የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት በአገሪቱ እንዲዘረጋ መንግሥት ፍላጎት እንዳለው ተዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝን ጠቅሰው የአገር ውስጥ እና የኬንያ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ሳፋሪኮም ኤም-ፔሳን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጀምር ይፈልጋል። ከዚህ ቀደም መንግሥት የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓትን ለውጭ አገራት ኩባንያዎች ክፍት እንደማያደርግ መግለጹ አይዘነጋም። አሁን ግን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሳፋሪኮም የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ኤም-ፔሳ ፈቃድ እንዲሰጥ የሚያስችል ሕጋዊ አሠራር እየተነደፈ እንደሚገኝ ተገልጿል። ሚኒስትር ዴኤታውን ያጣቀሱ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት፤ ሳፋሪኮም ለኤም-ፔሳ የፊታችን ግንቦት ፈቃድ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። መንግሥት ከዚህ ቀደም ባወጣው የቴሌኮም ጨረታ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ዝርጋታ አልተካተተም ነበር። በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው እና የኢትዮ-ቴሌኮምን ጨረታ ያሸነፈው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ ጥምረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት በተፈራረመበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ የተገኙት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ኢትዮጵያ ገበያውን ለኤም-ፔሳ ክፍት እንድታደርግ በተዘዋዋሪ መጠቆማቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለተኛውን የቴሌኮም ጨረታ ላልተወሰነ ጊዜ ቢያራዝመውም፤ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ዝርጋታን ከዝርዝሩ እንዳስወጣው ተገልጿል። ሳፋሪኮም ይህንን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለው ፈቃድ በቅርቡ እንደሚሰጠውም ታክሏል። ኤም-ፔሳ የሚሠራው እንዴት ነው? ኤም-ፔሳ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ነው። መሥራቹ የኬንያው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ሲሆን፤ አሁን ላይ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት እየተተገበረ ይገኛል። ኤም-ፔሳ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ከተጫነ በኋላ ገንዘብ ማስቀመጥ፣ ገንዘብ መቀበል፣ ክፍያ መፈጸም፣ የባንክ ተቀማጭ ገንዘብን ወደ ስልክ ማዘዋወር፣ ገንዘብ ለሌላ ኤም-ፔሳ ተጠቃሚ መላክ እና ሌላም የገንዘብ ልውውጥ ማካሄድ ይቻላል። እአአ በ2007 በሳፋሪኮም እና ቮዳፎን የተጀመረው ኤም-ፔሳ ኬንያ ውስጥ የሚተዳደረው በኬንያ ብሔራዊ ባንክ ነው። ኤም-ፔሳ የሚለው መጠሪያ ውስጥ ኤም ሞባይልን ሲወክል፣ ፔሳ ደግሞ በስዋሂሊ ገንዘብ ማለት ነው። የገንዘብ ልውውጥን የሚያሳልጡ የሳፋሪኮም ተወካዮች በተለያዩ መደብሮች ይገኛሉ። ለእነዚህ ተወካዮች ጥሬ ገንዘብ በመስጠት ወደ ኤም-ፔሳ ገንዘቡን እንዲያዘዋውሩ ማድረግ ይቻላል። በኤም-ፔሳ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ያለ ገንዘብን በጥሬ ገንዘብ ከተወካዮቹ የመውሰድ አማራጭም አለ። በተለይ ኬንያ ውስጥ ከጉሊት አንስቶ እስከ ቅንጡ ሆቴሎች ድረስ ክፍያ የሚፈጸመው በኤም-ፔሳ ነው። አገልግሎቱ በሚገኝባቸው ሌሎች አገራትም የውሃ እና መብራት ክፍያን ጨምሮ ለምርት እንዲሁም ለአገልግሎት ክፍያ ለመፈጸም ሁነኛ አማራጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በኤም-ፔሳ የገንዘብ ልውውጥ ሲደረግ ወይም ከሳፋሪኮም ተወካይ ገንዘብ ሲወሰድ በገንዘቡ ልክ የሚወሰን የአገልግሎት ክፍያ ይጠየቃል። ኤም-ፔሳን የትኞቹ አገራት ይጠቀማሉ? ወደ ዲጂታል የገንዘብ ልውውጥ እየተሻገረ ባለው ዓለም ውስጥ ከፍተኛ እውቅና ካተረፉ ተሞክሮዎች አንዱ ኤም-ፔሳ ነው። እአአ በ2010 በታዳጊ አገራት እጅግ ስኬታማው የሞባይል ገንዘብ መለዋወጫ ተብሎ ተሞካሽቷል። ከኬንያ አልፎ በታንዛንያ፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በግብፅ፣ በጋና፣ በሌሴቶ እና በሞዛምቢክ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የሳፋሪኮም ድረ ገጽ ይጠቁማል። ጀርመን፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና ቻይና ወዳሉ ባንኮች ገንዘብ ማዘዋወር ይቻላል። የቮዳፎን ድረ ገጽ እንደሚለው ኤም-ፔሳ ከ50 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት። ከአፍሪካ ትልቁ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት እንደሆነ የሚነገርለት ኤም-ፔሳ፤ የባንክ ደብተር ላላቸው ብቻ ሳይሆን የባንክ ተጠቃሚ ላልሆኑ ሰዎችም አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል። በተለይም የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ኤም-ፔሳ ተደራሽ መሆኑ ለንግድ ብቻ ሳይሆን ለገንዘብ ቁጠባም መንገድ እንደከፈተ ይገለጻል። ከገጠር እስከ ከተማ ጥሬ ገንዘብ ይለዋወጥ የነበረን ማኅበረሰብ ወደ ስልክ የገንዘብ ዝውውር በስኬታማ ሁኔታ እንዳሻገረ ይነገርለታል። ኤም-ፔሳ ጥቃቅን እና አነስተኛ ነጋዴዎችን የሚያበረታታ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት እንደሆነ የሳፋሪኮም ገጽ ይጠቁማል። ከተንቀሳቃሽ ስልክ የአየር ሰዓት ግዥ አንስቶ በተለያዩ አገልግሎት መስጫዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያዘዋውራል። ገንዘብ ለመቆጠብ እና ገንዘብ ለመበደር ኤም-ሸዋሪ የተባለ አዲስ አሠራርም ለተጠቃሚዎቹ ዘርግቷል። የቮዳፎን ድረ ገጽ እንደሚጠቁመው፤ ኤም-ፔሳ እንደ ዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ወርልድሬሚት፣ ሬሚትሊ እና ኤምኤፍኤስ አፍሪካ ያሉ ዓለም አቀፍ የገንዘብ መለዋወጫዎች ጋር ትስስር ፈጥሯል። በየዓመቱ ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከውጭ አገራት የሚነሳ የገንዘብ ዝውውር (remittance) ያስገኛል። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፤ የገንዘብ ልውውጥ ዲጂታል ቅርጽ ሲይዝ ተደራሽነቱ ይሰፋል፤ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ያማለከም ይሆናል። ኤም-ፔሳ እና ኤም-ብር ምን ያመሳስላቸዋል? ኤም-ብር ኢትዮጵያ ውስጥ ተንቀሳቃሽ ስልክን የተመረኮዘ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ነው። በኤም-ብር ተጠቃሚዎች መካከል ገንዘብ ለማስተላለፍ፣ በኤም-ብር ተወካይ በኩል ጥሬ ገንዘብን ወደ ስልክ ለመውሰድ ወይም ከስልክ ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ ለማውጣትም ይውላል። የተንቀሳቃሽ ስልክ የአየር ሰዓት መግዛትን ጨምሮ ውሃ እና መብራት ለመክፈል እንዲሁም ለሌሎችም የምርት እና የአገልግሎት ግዢዎች ኤም-ብርን መጠቀም ይቻላል። ኤም-ፔሳ እና ኤም-ብርን ጨምሮ ሌሎች ዓለም ላይ ያሉ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓቶች መሠረታዊ ሐሳባቸው ተመሳሳይ ቢሆንም በአገልግሎት ዓይነት እና ቅልጥፍና ይለያያሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮ-ቴሌኮምን ድርሻ ለተለያዩ የቴሌኮም ኩባንያዎች ግዥ ክፍት ሲያደርግ ከተነሱ ነጥቦች አንዱ፤ የውጭ ቴሌኮሞች ወደ ኢትዮጵያ መግባት በዘርፉ ውድድር በመፍጠር የአገልግሎት ጥራትን ያስጠብቃል የሚለው ነው። ወደ ዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓት የሚደረገውን ሽግግር ለማፋጠን በተለያዩ አገራት የተፈተሸ የሥራ ልምድ ያላቸው ተቋሞችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ማስገባትን በአወንታዊ ጎኑ የወሰዱት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች አሉ። ኤም-ፔሳ ኢትዮጵያን ያሰጋል? ኤም-ፔሳ የኢትዮ-ቴሌኮምን ጨረታ ያሸነፈው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ ጥምረት በሚመራው ሳፋሪኮም ከሚሰጡ የቴሌኮም አገልግሎቶች አንዱ ነው። ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕ፣ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽንና ሲዲሲ ግሩፕን የያዘው ጥምረት 850 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦ ነበር ጨረታውን ያሸነፈው። በመንግሥት የሚተዳደሩ እንደ ኢትዮ-ቴሌኮም ያሉ ተቋሞችን ለውጭ ኩባንያዎች ወይም የግል ባለሀብቶች የመክፈት ሐሳብ ደጋፊዎች እንዳሉት ሁሉ ነቃፊዎችም አያጣም። ለመንግሥት ከፍተኛ ዓመታዊ ገቢ የሚያስገኙ ድርጅቶችን ለሽያጭ ማቅረብ መንግሥት የሚያገኘውን ትርፍ እንደሚቀንስ እንዲሁም በአገር ውስጥ የገበያ ተወዳዳሪዎች ላይ አሉታዊ ጫና እንደሚያሳድርም የሚከራከሩ ይጠቀሳሉ። ለውጭ ኩባንያዎች ሁሉንም ዘርፎች ክፍት ከማድረግ ይልቅ እንደ ፋይናንስ ያዙ ዘርፎች በማዕከላዊ መንግሥት ሥር ሆነው እንዲዘልቁ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነው የሚል አስተያየት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይሰነዝራሉ። እንደ ሳፋሪኮም ያሉ ተቋሞች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን የሞባይልና የኢንተርኔት አገልግሎት ቢሰጡም፤ እንደ ኤም-ፔሳ ባለ አገልግሎት የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ የመግባታቸውን ጉዳይ በጥያቄ ምልክት የሚያስተናግዱት አሉ። ኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍን ለግል ባለሀብቶች ከከፈቱ የመጨረሻዎቹ አገራት አንዷ እንደሆነች ይነገራል። በሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት፤ ለኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ድጋፍ እንደሚያደርግ፣ ለበርካቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና የዜጎችን ሕይወት በበጎ እንደሚቀይር በምሥረታው ወቅት አስታውቋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በመታገዝ ከያዘችው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያዎች መካከል የቴሌኮምን ድርሻ መሸጥ እንደሚገኝበት ገልጻለች።
ከጉሊት እስከ ቅንጡ ሆቴል ግብይትን ያሳለጠው ኤም-ፔሳ ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል? ከሁለት ወራት በኋላ በኢትዮጵያ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቀው ሳፋሪኮም፤ ኤም-ፔሳ የተባለውን የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት በአገሪቱ እንዲዘረጋ መንግሥት ፍላጎት እንዳለው ተዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝን ጠቅሰው የአገር ውስጥ እና የኬንያ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ሳፋሪኮም ኤም-ፔሳን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጀምር ይፈልጋል። ከዚህ ቀደም መንግሥት የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓትን ለውጭ አገራት ኩባንያዎች ክፍት እንደማያደርግ መግለጹ አይዘነጋም። አሁን ግን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሳፋሪኮም የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ኤም-ፔሳ ፈቃድ እንዲሰጥ የሚያስችል ሕጋዊ አሠራር እየተነደፈ እንደሚገኝ ተገልጿል። ሚኒስትር ዴኤታውን ያጣቀሱ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት፤ ሳፋሪኮም ለኤም-ፔሳ የፊታችን ግንቦት ፈቃድ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። መንግሥት ከዚህ ቀደም ባወጣው የቴሌኮም ጨረታ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ዝርጋታ አልተካተተም ነበር። በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው እና የኢትዮ-ቴሌኮምን ጨረታ ያሸነፈው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ ጥምረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት በተፈራረመበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ የተገኙት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ኢትዮጵያ ገበያውን ለኤም-ፔሳ ክፍት እንድታደርግ በተዘዋዋሪ መጠቆማቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለተኛውን የቴሌኮም ጨረታ ላልተወሰነ ጊዜ ቢያራዝመውም፤ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ዝርጋታን ከዝርዝሩ እንዳስወጣው ተገልጿል። ሳፋሪኮም ይህንን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለው ፈቃድ በቅርቡ እንደሚሰጠውም ታክሏል። ኤም-ፔሳ የሚሠራው እንዴት ነው? ኤም-ፔሳ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ነው። መሥራቹ የኬንያው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ሲሆን፤ አሁን ላይ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት እየተተገበረ ይገኛል። ኤም-ፔሳ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ከተጫነ በኋላ ገንዘብ ማስቀመጥ፣ ገንዘብ መቀበል፣ ክፍያ መፈጸም፣ የባንክ ተቀማጭ ገንዘብን ወደ ስልክ ማዘዋወር፣ ገንዘብ ለሌላ ኤም-ፔሳ ተጠቃሚ መላክ እና ሌላም የገንዘብ ልውውጥ ማካሄድ ይቻላል። እአአ በ2007 በሳፋሪኮም እና ቮዳፎን የተጀመረው ኤም-ፔሳ ኬንያ ውስጥ የሚተዳደረው በኬንያ ብሔራዊ ባንክ ነው። ኤም-ፔሳ የሚለው መጠሪያ ውስጥ ኤም ሞባይልን ሲወክል፣ ፔሳ ደግሞ በስዋሂሊ ገንዘብ ማለት ነው። የገንዘብ ልውውጥን የሚያሳልጡ የሳፋሪኮም ተወካዮች በተለያዩ መደብሮች ይገኛሉ። ለእነዚህ ተወካዮች ጥሬ ገንዘብ በመስጠት ወደ ኤም-ፔሳ ገንዘቡን እንዲያዘዋውሩ ማድረግ ይቻላል። በኤም-ፔሳ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ያለ ገንዘብን በጥሬ ገንዘብ ከተወካዮቹ የመውሰድ አማራጭም አለ። በተለይ ኬንያ ውስጥ ከጉሊት አንስቶ እስከ ቅንጡ ሆቴሎች ድረስ ክፍያ የሚፈጸመው በኤም-ፔሳ ነው። አገልግሎቱ በሚገኝባቸው ሌሎች አገራትም የውሃ እና መብራት ክፍያን ጨምሮ ለምርት እንዲሁም ለአገልግሎት ክፍያ ለመፈጸም ሁነኛ አማራጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በኤም-ፔሳ የገንዘብ ልውውጥ ሲደረግ ወይም ከሳፋሪኮም ተወካይ ገንዘብ ሲወሰድ በገንዘቡ ልክ የሚወሰን የአገልግሎት ክፍያ ይጠየቃል። ኤም-ፔሳን የትኞቹ አገራት ይጠቀማሉ? ወደ ዲጂታል የገንዘብ ልውውጥ እየተሻገረ ባለው ዓለም ውስጥ ከፍተኛ እውቅና ካተረፉ ተሞክሮዎች አንዱ ኤም-ፔሳ ነው። እአአ በ2010 በታዳጊ አገራት እጅግ ስኬታማው የሞባይል ገንዘብ መለዋወጫ ተብሎ ተሞካሽቷል። ከኬንያ አልፎ በታንዛንያ፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በግብፅ፣ በጋና፣ በሌሴቶ እና በሞዛምቢክ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የሳፋሪኮም ድረ ገጽ ይጠቁማል። ጀርመን፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና ቻይና ወዳሉ ባንኮች ገንዘብ ማዘዋወር ይቻላል። የቮዳፎን ድረ ገጽ እንደሚለው ኤም-ፔሳ ከ50 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት። ከአፍሪካ ትልቁ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት እንደሆነ የሚነገርለት ኤም-ፔሳ፤ የባንክ ደብተር ላላቸው ብቻ ሳይሆን የባንክ ተጠቃሚ ላልሆኑ ሰዎችም አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል። በተለይም የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ኤም-ፔሳ ተደራሽ መሆኑ ለንግድ ብቻ ሳይሆን ለገንዘብ ቁጠባም መንገድ እንደከፈተ ይገለጻል። ከገጠር እስከ ከተማ ጥሬ ገንዘብ ይለዋወጥ የነበረን ማኅበረሰብ ወደ ስልክ የገንዘብ ዝውውር በስኬታማ ሁኔታ እንዳሻገረ ይነገርለታል። ኤም-ፔሳ ጥቃቅን እና አነስተኛ ነጋዴዎችን የሚያበረታታ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት እንደሆነ የሳፋሪኮም ገጽ ይጠቁማል። ከተንቀሳቃሽ ስልክ የአየር ሰዓት ግዥ አንስቶ በተለያዩ አገልግሎት መስጫዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያዘዋውራል። ገንዘብ ለመቆጠብ እና ገንዘብ ለመበደር ኤም-ሸዋሪ የተባለ አዲስ አሠራርም ለተጠቃሚዎቹ ዘርግቷል። የቮዳፎን ድረ ገጽ እንደሚጠቁመው፤ ኤም-ፔሳ እንደ ዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ወርልድሬሚት፣ ሬሚትሊ እና ኤምኤፍኤስ አፍሪካ ያሉ ዓለም አቀፍ የገንዘብ መለዋወጫዎች ጋር ትስስር ፈጥሯል። በየዓመቱ ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከውጭ አገራት የሚነሳ የገንዘብ ዝውውር (remittance) ያስገኛል። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፤ የገንዘብ ልውውጥ ዲጂታል ቅርጽ ሲይዝ ተደራሽነቱ ይሰፋል፤ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ያማለከም ይሆናል። ኤም-ፔሳ እና ኤም-ብር ምን ያመሳስላቸዋል? ኤም-ብር ኢትዮጵያ ውስጥ ተንቀሳቃሽ ስልክን የተመረኮዘ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓት ነው። በኤም-ብር ተጠቃሚዎች መካከል ገንዘብ ለማስተላለፍ፣ በኤም-ብር ተወካይ በኩል ጥሬ ገንዘብን ወደ ስልክ ለመውሰድ ወይም ከስልክ ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ ለማውጣትም ይውላል። የተንቀሳቃሽ ስልክ የአየር ሰዓት መግዛትን ጨምሮ ውሃ እና መብራት ለመክፈል እንዲሁም ለሌሎችም የምርት እና የአገልግሎት ግዢዎች ኤም-ብርን መጠቀም ይቻላል። ኤም-ፔሳ እና ኤም-ብርን ጨምሮ ሌሎች ዓለም ላይ ያሉ የተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ልውውጥና ግብይት ሥርዓቶች መሠረታዊ ሐሳባቸው ተመሳሳይ ቢሆንም በአገልግሎት ዓይነት እና ቅልጥፍና ይለያያሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮ-ቴሌኮምን ድርሻ ለተለያዩ የቴሌኮም ኩባንያዎች ግዥ ክፍት ሲያደርግ ከተነሱ ነጥቦች አንዱ፤ የውጭ ቴሌኮሞች ወደ ኢትዮጵያ መግባት በዘርፉ ውድድር በመፍጠር የአገልግሎት ጥራትን ያስጠብቃል የሚለው ነው። ወደ ዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓት የሚደረገውን ሽግግር ለማፋጠን በተለያዩ አገራት የተፈተሸ የሥራ ልምድ ያላቸው ተቋሞችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ማስገባትን በአወንታዊ ጎኑ የወሰዱት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች አሉ። ኤም-ፔሳ ኢትዮጵያን ያሰጋል? ኤም-ፔሳ የኢትዮ-ቴሌኮምን ጨረታ ያሸነፈው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ ጥምረት በሚመራው ሳፋሪኮም ከሚሰጡ የቴሌኮም አገልግሎቶች አንዱ ነው። ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕ፣ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽንና ሲዲሲ ግሩፕን የያዘው ጥምረት 850 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦ ነበር ጨረታውን ያሸነፈው። በመንግሥት የሚተዳደሩ እንደ ኢትዮ-ቴሌኮም ያሉ ተቋሞችን ለውጭ ኩባንያዎች ወይም የግል ባለሀብቶች የመክፈት ሐሳብ ደጋፊዎች እንዳሉት ሁሉ ነቃፊዎችም አያጣም። ለመንግሥት ከፍተኛ ዓመታዊ ገቢ የሚያስገኙ ድርጅቶችን ለሽያጭ ማቅረብ መንግሥት የሚያገኘውን ትርፍ እንደሚቀንስ እንዲሁም በአገር ውስጥ የገበያ ተወዳዳሪዎች ላይ አሉታዊ ጫና እንደሚያሳድርም የሚከራከሩ ይጠቀሳሉ። ለውጭ ኩባንያዎች ሁሉንም ዘርፎች ክፍት ከማድረግ ይልቅ እንደ ፋይናንስ ያዙ ዘርፎች በማዕከላዊ መንግሥት ሥር ሆነው እንዲዘልቁ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነው የሚል አስተያየት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይሰነዝራሉ። እንደ ሳፋሪኮም ያሉ ተቋሞች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን የሞባይልና የኢንተርኔት አገልግሎት ቢሰጡም፤ እንደ ኤም-ፔሳ ባለ አገልግሎት የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ የመግባታቸውን ጉዳይ በጥያቄ ምልክት የሚያስተናግዱት አሉ። ኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍን ለግል ባለሀብቶች ከከፈቱ የመጨረሻዎቹ አገራት አንዷ እንደሆነች ይነገራል። በሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት፤ ለኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ድጋፍ እንደሚያደርግ፣ ለበርካቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና የዜጎችን ሕይወት በበጎ እንደሚቀይር በምሥረታው ወቅት አስታውቋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በመታገዝ ከያዘችው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያዎች መካከል የቴሌኮምን ድርሻ መሸጥ እንደሚገኝበት ገልጻለች።
https://www.bbc.com/amharic/60329210
3politics
ኬንያ ከሰሃራዊ አረብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር ግንኙነቷን ማቋረጧን አስታወቀች
ከተሾሙ ቀናትን ያስቆጠሩት የኬንያው ፕሬዘዳንት ዊልያም ሩቶ አገራቸው ከሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ሳዲአር)ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ገለጹ። ፕሬዚዳንቱ ትላንት ረቡዕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይህንኑ መልዕክት አስፍረው የነበረ ሲሆን ከሰአታት በኋላ ግን ልጥፉን አንስተዋል። የቀድሞ የስፔን ቅኝ ግዛት የነበረው ይህ የምዕራብ ሰሃራ አካባቢ እ.ኤ.አ በ1975 ከቅኝ ግዛት ከተላቀቀ በኋላ ሞሮኮ ግዛቴ ነው በሚል በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ ሙከራዎችን አድርጋለች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሰሃራዊ ነባር ሕብረተሰቦች እና የሞሮኮ መንግስት መካከል ዘላቂ የግጭት ምክንያት ሆኖ ዘልቋል። ታዲያ የኬንያ አዲሱ ፕሬዘዳንት ዊሊያም ሩቶ ሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በኬንያ ያላትን ሕጋዊ ቆይታ እና ግንኙነት እንዲያበቃ ለማድረግ እርምጃዎች መጀመራቸውን ተናግረዋል። በምዕራብ ሰሃራ ያሉትን ያለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሄ የሚያገኙት የተባበሩት መንግስታት በሚያዘጋጀው ማዕቀፍ ብቻ ውስጥ ነው ብላ ኬንያ እንደምታምንም ተናግረዋል። የሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪ ብራሂም ጋሃሊ ማክሰኞ በተካሄደው የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በአለ ሲመት ላይ ተገኝተው ነበር። ፕሬዘዳንት ሩቶ ይህንን ውሳኔያቸውን ይፋ ያደረጉት የሞሮኮው ንጉስ መሀመድ ስድስተኛ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ከደረሳቸው ከጥቂት ሰአታት በኋላ ነበር። ከአርባ አመታት በላይ ሕጋዊ ቅቡልነት ያላት አገር ለመሆን እየሰራች የምትገኘው ሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የአፍሪካ ሕብረት ሙሉ አባል ስትሆን በርካታ አገራት ዕውቅና ሰጥተዋታል። በአሁን ሰአትም ከፊል ቅቡልነት ያላት አገር ናት። ሞሮኮ በበኩሏ ምዕራብ ሰሃራ ግዛቴ ነው የሚል ጠንካራ አቋሟን የምታራምድ ሲሆን በአካባቢው የሚኖሩ ሕዝቦች ፍላጎታቸውን እንዲያሳዩ የሕዝበ ውሳኔ ይደረግ የሚለውን ሃሳብም አትቀበልም። ይህ የሰሀራ በረሃ አካል የሆነው ክፍል እስካሁን ድረስ ያልተነካ የነዳጅ ዘይት ክምችት ያለበትን የባሕር ክፍል እንደሚይዝ ይታመናል። ከዛም ባሻገር ከፍተኛ የፎስፌት ክምችት ያለው ሲሆን በአሳ ሃብቱ የበለጸገ ነው።
ኬንያ ከሰሃራዊ አረብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር ግንኙነቷን ማቋረጧን አስታወቀች ከተሾሙ ቀናትን ያስቆጠሩት የኬንያው ፕሬዘዳንት ዊልያም ሩቶ አገራቸው ከሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ሳዲአር)ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ገለጹ። ፕሬዚዳንቱ ትላንት ረቡዕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይህንኑ መልዕክት አስፍረው የነበረ ሲሆን ከሰአታት በኋላ ግን ልጥፉን አንስተዋል። የቀድሞ የስፔን ቅኝ ግዛት የነበረው ይህ የምዕራብ ሰሃራ አካባቢ እ.ኤ.አ በ1975 ከቅኝ ግዛት ከተላቀቀ በኋላ ሞሮኮ ግዛቴ ነው በሚል በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ ሙከራዎችን አድርጋለች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሰሃራዊ ነባር ሕብረተሰቦች እና የሞሮኮ መንግስት መካከል ዘላቂ የግጭት ምክንያት ሆኖ ዘልቋል። ታዲያ የኬንያ አዲሱ ፕሬዘዳንት ዊሊያም ሩቶ ሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በኬንያ ያላትን ሕጋዊ ቆይታ እና ግንኙነት እንዲያበቃ ለማድረግ እርምጃዎች መጀመራቸውን ተናግረዋል። በምዕራብ ሰሃራ ያሉትን ያለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሄ የሚያገኙት የተባበሩት መንግስታት በሚያዘጋጀው ማዕቀፍ ብቻ ውስጥ ነው ብላ ኬንያ እንደምታምንም ተናግረዋል። የሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪ ብራሂም ጋሃሊ ማክሰኞ በተካሄደው የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በአለ ሲመት ላይ ተገኝተው ነበር። ፕሬዘዳንት ሩቶ ይህንን ውሳኔያቸውን ይፋ ያደረጉት የሞሮኮው ንጉስ መሀመድ ስድስተኛ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ከደረሳቸው ከጥቂት ሰአታት በኋላ ነበር። ከአርባ አመታት በላይ ሕጋዊ ቅቡልነት ያላት አገር ለመሆን እየሰራች የምትገኘው ሰሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የአፍሪካ ሕብረት ሙሉ አባል ስትሆን በርካታ አገራት ዕውቅና ሰጥተዋታል። በአሁን ሰአትም ከፊል ቅቡልነት ያላት አገር ናት። ሞሮኮ በበኩሏ ምዕራብ ሰሃራ ግዛቴ ነው የሚል ጠንካራ አቋሟን የምታራምድ ሲሆን በአካባቢው የሚኖሩ ሕዝቦች ፍላጎታቸውን እንዲያሳዩ የሕዝበ ውሳኔ ይደረግ የሚለውን ሃሳብም አትቀበልም። ይህ የሰሀራ በረሃ አካል የሆነው ክፍል እስካሁን ድረስ ያልተነካ የነዳጅ ዘይት ክምችት ያለበትን የባሕር ክፍል እንደሚይዝ ይታመናል። ከዛም ባሻገር ከፍተኛ የፎስፌት ክምችት ያለው ሲሆን በአሳ ሃብቱ የበለጸገ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn3rvr7v2e2o
3politics
ከሰሞኑ የጋምቤላ ጥቃት ጀርባ ያለው ቡድን ማን ነው?
ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም ማለዳ ላይ የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት-ሸኔ በጋራ በመሆን በጋምቤላ ከተማ ላይ ጥቃት በመክፈት ከተማዋ ለቀናት ከተለመደ እንቅስቃሴዋ ውጪ ሆና ቆይታለች። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጋትሉክ ቡኦም ፓል ጥቃታቸው የጀመረው ከከተማው 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ደምቢዶሎ መውጫ ላይ ከሚገኝ ጫካ በመነሳት እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለተወሰኑ ሰዓታት በርካታ የከተማዋን ክፍሎች ተቆጣጥረው እንደነበር የሚናገሩት ሊቀመንበሩ የመንግሥት ኃይሎች ወደ ከተማው በማፈግፈግ ውጊያው “በሕዝብ መካከል” ስለነበር፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና እርሳቸው በመነጋገር ከከተማው መውጣታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በወቅቱ የክልሉ መስተዳደርም ታጣቂዎቹ የተወሰነውን የከተማዋን ክፍል ተቆጣጥረው እንደነበርና ፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ጠንካራ እርምጃ አማጺያኑን በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ከተማዋ ማስወጣት መቻሉን አሳውቋል። አቶ ጋትሉክ  እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቃል አቀባይ ዕቅዳቸውን አሳክተው በወታደራዊ ካምፕ ላይ ጉዳት አድርሰው በርካታ መሣርያም መማረካቸውን ቢናገሩም፤ የክልሉ ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች ግን በርካታ የታጣቂዎቹ ቡድን አባላት በከተማዋ ውስጥ መገደላቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከማክሰኞው ጥቃት በኋላ ረቡዕ ዕለትም የጋምቤላ መደበኛ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሎ ቆይቶ፣ ሐሙስ ዕለት ነዋሪው ወደ ተለመደ ሥራው እየተንቀሳቀሰ መሆኑን እና ፀጥታ ኃይሉም ከጥቃቱ በኋላ በሕዝቡ ውስጥ ተደብቀዋል ያላቸውን የታጣቂ ቡድኑ አባላትን አድነው በመያዝ ላይ ናቸውን የክልሉ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጋምቤላ ነጻነት ግንባር በኮንፌዴሬሽን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያ ለመመስረት እንደሚታገሉና አሁን የፈጸሙት ጥቃት ዓላማ ከተማዋን መቆጣጣር እንደነበር አቶ ጋትሉክ ገልጸዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ላይ የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በታጣቂዎቹ ላይ “ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን፣ በወገን ጦር ላይም መጠነኛ ጉዳት መድረሱን” ተናግረው ነበር። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር በበኩላቸው ትልቅ ኪሳራ የደረሰው በመንግሥት ወገን ላይ እንደሆነና ከእነርሱ ወገን ሦስት ተዋጊዎቻቸው ሲሞቱ፣ ሌሎች ቁጥራቸውን ያልገለጿቸው ደግሞ መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩትና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ምስሎች እንዳሳዩት በርካታ የታጠቂው ቡድን አባላት ናቸው የተባሉ አስከሬኖች በጋምቤላ ከተማ መንገዶች ላይ ታይተዋል። መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት የፈረጀው እና ሸኔ በሚል የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የሕዝብ ግንኙነት እንደሆነ የሚነገረው ኦዳ ተርቢ፣ የቡድኑ ታጣቂዎች ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር የተሳካ የመቀናጅት ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጾ ነበር። በክልሉ ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑ እና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ግለሰብ ይህን ጥቃት የፈፀሙት ከውጪ የመጡ አካላት ብቻቸውን ሳይሆን በሕዝቡ እና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ እገዛ አድርገዋል ሲሉ ይወነጅላሉ። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ከከተማው በቅርብ ርቀት፣ አንፊሎ እና ድንበር አካባቢ መሽገው ይገኛሉ ያሉት ግለሰቡ፣ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ተፈናቃዮች ጋርም በመቀላቀል እገዛ እንደሚያገኙ ይናገራሉ። በጋምቤላ ከተማ ማክሰኞ ዕለት በነበረው ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ከተለያዩ ምንጮች አጣርቷል። ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ከተደረገው ብሔራዊ ምርጫ በኋላ መመስረቱ የሚነገረው የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትና ታጣቂዎች እንዳሉት ይናገራል። የድርጅቱ ሊቀ መንበርና ምክትል፣ የኢህአዴግ አጋር ድርጅት በመሆን ክልሉን ሲያስተዳድር የነበረው የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባል ሆነው በክልሉ በተለያየ የመንግሥት ኃላፊነት ላይ አገልግለዋል። በዚህም ሊቀ መንበሩ በተለያዩ የክልሉ መንግሥት ቢሮዎች ከምክትል ኃላፊነት እስከ የክልሉ ኮሌጅ ዲንነት ድረስ መስራታቸውንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ኃላፊነቶች ውስጥ ያገለገሉት አቶ ጋልዋክ፣ በባሕልና ቱሪዝም ቢሮ፣ በከተማና ልማት፣ በትምህርት ቢሮዎች ውስጥ በምክትል ኃላፊነቶች እንዲሁም በክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ እና ጥቃቅን እና አነስተኛ በከፍተኛ አመራርነት መስራታቸውን ይናገራሉ። ጋነግ “በዲሞክራሲ እና በፍትሕ የሚያምን፣ ለጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት የሚታገል ድርጅት ነው” እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን፣ ፓርቲው ከሌሎች በአገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ጋር አጋርነት በመፍጠር የፌደራሊስት ኃይሎች ግንባር ተሳታፊ ነበር። ይህ የፌደራሊስት ኃይሎች የተባለው ስብስብ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በተደጋጋሚ ወደ መቀለ በመመላለስ ከህወሓት ጋር ሲመክር እንደነበር ሊቀመንበሩ ያስታውሳሉ። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ጦርነቱ ሲቀሰቀስ አዲስ አበባ ውስጥ የነበሩት የግንባሩ ሊቀመንበር ጋትሉክ “ከሦስት ወራት በላይ ከህወሓት ጋር ግንኙነት ጋር አለህ በሚል” ታስረው መቆየታቸውን ይናገራሉ። ሊቀመንበሩ “የተጭበረበረ ነው” በሚሉት በ2013 ሰኔ ወር ላይ በተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ላይ መሳተፋቸውንና፣ “ከዚያ በኋላ ሊያስሩኝ ሲሞክሩ ወደ በረሃ ገባሁ” የሚሉት ጋልቶክ ለጋምቤላ ሕዝብ እኩልነት ትግል መጀመራቸውን ተናግረዋል። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ከቀናት በፊት በጋራ ሆኖ ጥቃት ከሰነዘረው የኦሮሞ የነጻነት ሠራዊት የመሣርያ እና ሥልጠና ድጋፍ እንደሚያገኝ ሊቀመንበሩ አረጋግጠዋል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ የሆነው ኩምሳ ድሪባም (ጃል መሮ) ለቢቢሲ ከግንባሩ አመራሮች ጋር የረዥም ጊዜ ትውውቅ እንዳላቸውና ለታጣቂዎቻቸውም ስልጠና ሲሰጡ እንደነበርም ገልጿል። ሊቀመንበሩ የሌላ አገር ዜግነት እንዳላቸውና በጋምቤላ ክልል ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ በሰሩባቸው ጊዜያት የሕዝብና የመንግሥት ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉ ክስ የሚቀርብባቸው ሲሆን፣ ይህ ጉዳይ እንደማይመለከታቸው ይናገራሉ። ሁለቱም ክሶች ከሊቀመንበሩ ጋር በተመሳሳይ ስም የሚታወቁት ምክትላቸውን የሚመለከት መሆኑንና ግለሰቡ የአሜሪካ ዜግነት እንዳለው አምነው፣ ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት ፈጽመዋል መባሉን “መሠረተ ቢስ ውንጀላ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል። የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ጋትሉክ ተብለው የሚጠሩ ሲሆን፣ ሊቀመንበሩ ጋትሉክ ቡኦም ፓል ምክትላቸው ደግሞ ጋትሉክ ፓልቴርጋር ይባላሉ። የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር እንጂ በቀጥታ ከህወሓት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሌለው ሊቀ መንበሩ ጠቅሰው ነገር ግን “ከህወሓት ጋር ያለን የዓላማ አንድነት ነው” በማለት ተናግረዋል። ከአንድ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግሥት ሸኔ የሚለውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን እና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይን (ህወሓት) በሽብርተኛነት በመፈረጅ ሕገ ወጥ ቡድኖች ማድረጉ ይታወሳል። በምዕራብኢትዮጵያ የሚገኘው የጋምቤላ ክልል ዋና ከተማው ጋምቤላ ሲሆን ከደቡብ ሱዳን፣ ከኦሮሚያ እና ከደቡብ ክልል ሕዝቦች ጋር ይዋሰናል። አኝዋክ፣ኮሞ፣መዠንገር፣ኑዌር እና ኦፖ የሚባሉ አምስት ብሔረሰቦች አሉት። በተጨማሪም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የተወጣጡ ሌሎች ብሔረሰቦችም የሚኖሩበት ክልልነው። ከዚህ ቀደም ባለው መረጃ የክልሉ ሕዝብ ብዛት ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ሲሆን በኢትዮጵያ ትንሽ ሕዝብ ከሚኖርባቸው ክልሎች አንዱ ነው። ለእርሻተስማሚ ለም መሬት ያለው የጋምቤላ ክልል፣ በተጨማሪም ከዓመት ዓመት የሚፈሱ ሁለት ግዙፍ ወንዞች ባለቤት ነው። ክልሉ በተለያዩ ጊዜያት ብሔርን መሠረት ያደረጉ ተደጋጋሚ ጥቃቶችና ግጭቶች ያጋጠሙት ሲሆን፣ በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን ሰርገው የሚገቡ ታጣቂዎችም ጥቃት ይፈጽሙበታል። እንደ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት መረጃ ከሆነ ክልሉ ከ480 ሺህ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መኖርያ ነው። ክልሉን የሚመራው የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕዴን) የተለያዩትን የክልሉ ብሔሮች ይወክሉ የነበሩ ቡድኖችን በማዋሃድ የተመሰረተ ነው። ጋሕዴን ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢህአዴግ አጋር ድርጅት የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ አባል ነው።
ከሰሞኑ የጋምቤላ ጥቃት ጀርባ ያለው ቡድን ማን ነው? ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም ማለዳ ላይ የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት-ሸኔ በጋራ በመሆን በጋምቤላ ከተማ ላይ ጥቃት በመክፈት ከተማዋ ለቀናት ከተለመደ እንቅስቃሴዋ ውጪ ሆና ቆይታለች። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጋትሉክ ቡኦም ፓል ጥቃታቸው የጀመረው ከከተማው 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ደምቢዶሎ መውጫ ላይ ከሚገኝ ጫካ በመነሳት እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለተወሰኑ ሰዓታት በርካታ የከተማዋን ክፍሎች ተቆጣጥረው እንደነበር የሚናገሩት ሊቀመንበሩ የመንግሥት ኃይሎች ወደ ከተማው በማፈግፈግ ውጊያው “በሕዝብ መካከል” ስለነበር፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና እርሳቸው በመነጋገር ከከተማው መውጣታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በወቅቱ የክልሉ መስተዳደርም ታጣቂዎቹ የተወሰነውን የከተማዋን ክፍል ተቆጣጥረው እንደነበርና ፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ጠንካራ እርምጃ አማጺያኑን በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ከተማዋ ማስወጣት መቻሉን አሳውቋል። አቶ ጋትሉክ  እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ቃል አቀባይ ዕቅዳቸውን አሳክተው በወታደራዊ ካምፕ ላይ ጉዳት አድርሰው በርካታ መሣርያም መማረካቸውን ቢናገሩም፤ የክልሉ ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች ግን በርካታ የታጣቂዎቹ ቡድን አባላት በከተማዋ ውስጥ መገደላቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከማክሰኞው ጥቃት በኋላ ረቡዕ ዕለትም የጋምቤላ መደበኛ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሎ ቆይቶ፣ ሐሙስ ዕለት ነዋሪው ወደ ተለመደ ሥራው እየተንቀሳቀሰ መሆኑን እና ፀጥታ ኃይሉም ከጥቃቱ በኋላ በሕዝቡ ውስጥ ተደብቀዋል ያላቸውን የታጣቂ ቡድኑ አባላትን አድነው በመያዝ ላይ ናቸውን የክልሉ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጋምቤላ ነጻነት ግንባር በኮንፌዴሬሽን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያ ለመመስረት እንደሚታገሉና አሁን የፈጸሙት ጥቃት ዓላማ ከተማዋን መቆጣጣር እንደነበር አቶ ጋትሉክ ገልጸዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ላይ የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በታጣቂዎቹ ላይ “ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን፣ በወገን ጦር ላይም መጠነኛ ጉዳት መድረሱን” ተናግረው ነበር። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር በበኩላቸው ትልቅ ኪሳራ የደረሰው በመንግሥት ወገን ላይ እንደሆነና ከእነርሱ ወገን ሦስት ተዋጊዎቻቸው ሲሞቱ፣ ሌሎች ቁጥራቸውን ያልገለጿቸው ደግሞ መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩትና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ምስሎች እንዳሳዩት በርካታ የታጠቂው ቡድን አባላት ናቸው የተባሉ አስከሬኖች በጋምቤላ ከተማ መንገዶች ላይ ታይተዋል። መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት የፈረጀው እና ሸኔ በሚል የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የሕዝብ ግንኙነት እንደሆነ የሚነገረው ኦዳ ተርቢ፣ የቡድኑ ታጣቂዎች ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር የተሳካ የመቀናጅት ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጾ ነበር። በክልሉ ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑ እና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ግለሰብ ይህን ጥቃት የፈፀሙት ከውጪ የመጡ አካላት ብቻቸውን ሳይሆን በሕዝቡ እና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ እገዛ አድርገዋል ሲሉ ይወነጅላሉ። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ከከተማው በቅርብ ርቀት፣ አንፊሎ እና ድንበር አካባቢ መሽገው ይገኛሉ ያሉት ግለሰቡ፣ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ተፈናቃዮች ጋርም በመቀላቀል እገዛ እንደሚያገኙ ይናገራሉ። በጋምቤላ ከተማ ማክሰኞ ዕለት በነበረው ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ከተለያዩ ምንጮች አጣርቷል። ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ከተደረገው ብሔራዊ ምርጫ በኋላ መመስረቱ የሚነገረው የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትና ታጣቂዎች እንዳሉት ይናገራል። የድርጅቱ ሊቀ መንበርና ምክትል፣ የኢህአዴግ አጋር ድርጅት በመሆን ክልሉን ሲያስተዳድር የነበረው የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባል ሆነው በክልሉ በተለያየ የመንግሥት ኃላፊነት ላይ አገልግለዋል። በዚህም ሊቀ መንበሩ በተለያዩ የክልሉ መንግሥት ቢሮዎች ከምክትል ኃላፊነት እስከ የክልሉ ኮሌጅ ዲንነት ድረስ መስራታቸውንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ኃላፊነቶች ውስጥ ያገለገሉት አቶ ጋልዋክ፣ በባሕልና ቱሪዝም ቢሮ፣ በከተማና ልማት፣ በትምህርት ቢሮዎች ውስጥ በምክትል ኃላፊነቶች እንዲሁም በክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ እና ጥቃቅን እና አነስተኛ በከፍተኛ አመራርነት መስራታቸውን ይናገራሉ። ጋነግ “በዲሞክራሲ እና በፍትሕ የሚያምን፣ ለጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት የሚታገል ድርጅት ነው” እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን፣ ፓርቲው ከሌሎች በአገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ጋር አጋርነት በመፍጠር የፌደራሊስት ኃይሎች ግንባር ተሳታፊ ነበር። ይህ የፌደራሊስት ኃይሎች የተባለው ስብስብ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት በተደጋጋሚ ወደ መቀለ በመመላለስ ከህወሓት ጋር ሲመክር እንደነበር ሊቀመንበሩ ያስታውሳሉ። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ጦርነቱ ሲቀሰቀስ አዲስ አበባ ውስጥ የነበሩት የግንባሩ ሊቀመንበር ጋትሉክ “ከሦስት ወራት በላይ ከህወሓት ጋር ግንኙነት ጋር አለህ በሚል” ታስረው መቆየታቸውን ይናገራሉ። ሊቀመንበሩ “የተጭበረበረ ነው” በሚሉት በ2013 ሰኔ ወር ላይ በተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ላይ መሳተፋቸውንና፣ “ከዚያ በኋላ ሊያስሩኝ ሲሞክሩ ወደ በረሃ ገባሁ” የሚሉት ጋልቶክ ለጋምቤላ ሕዝብ እኩልነት ትግል መጀመራቸውን ተናግረዋል። የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ከቀናት በፊት በጋራ ሆኖ ጥቃት ከሰነዘረው የኦሮሞ የነጻነት ሠራዊት የመሣርያ እና ሥልጠና ድጋፍ እንደሚያገኝ ሊቀመንበሩ አረጋግጠዋል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ የሆነው ኩምሳ ድሪባም (ጃል መሮ) ለቢቢሲ ከግንባሩ አመራሮች ጋር የረዥም ጊዜ ትውውቅ እንዳላቸውና ለታጣቂዎቻቸውም ስልጠና ሲሰጡ እንደነበርም ገልጿል። ሊቀመንበሩ የሌላ አገር ዜግነት እንዳላቸውና በጋምቤላ ክልል ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ በሰሩባቸው ጊዜያት የሕዝብና የመንግሥት ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉ ክስ የሚቀርብባቸው ሲሆን፣ ይህ ጉዳይ እንደማይመለከታቸው ይናገራሉ። ሁለቱም ክሶች ከሊቀመንበሩ ጋር በተመሳሳይ ስም የሚታወቁት ምክትላቸውን የሚመለከት መሆኑንና ግለሰቡ የአሜሪካ ዜግነት እንዳለው አምነው፣ ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት ፈጽመዋል መባሉን “መሠረተ ቢስ ውንጀላ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል። የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ጋትሉክ ተብለው የሚጠሩ ሲሆን፣ ሊቀመንበሩ ጋትሉክ ቡኦም ፓል ምክትላቸው ደግሞ ጋትሉክ ፓልቴርጋር ይባላሉ። የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር እንጂ በቀጥታ ከህወሓት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሌለው ሊቀ መንበሩ ጠቅሰው ነገር ግን “ከህወሓት ጋር ያለን የዓላማ አንድነት ነው” በማለት ተናግረዋል። ከአንድ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግሥት ሸኔ የሚለውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን እና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይን (ህወሓት) በሽብርተኛነት በመፈረጅ ሕገ ወጥ ቡድኖች ማድረጉ ይታወሳል። በምዕራብኢትዮጵያ የሚገኘው የጋምቤላ ክልል ዋና ከተማው ጋምቤላ ሲሆን ከደቡብ ሱዳን፣ ከኦሮሚያ እና ከደቡብ ክልል ሕዝቦች ጋር ይዋሰናል። አኝዋክ፣ኮሞ፣መዠንገር፣ኑዌር እና ኦፖ የሚባሉ አምስት ብሔረሰቦች አሉት። በተጨማሪም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የተወጣጡ ሌሎች ብሔረሰቦችም የሚኖሩበት ክልልነው። ከዚህ ቀደም ባለው መረጃ የክልሉ ሕዝብ ብዛት ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ሲሆን በኢትዮጵያ ትንሽ ሕዝብ ከሚኖርባቸው ክልሎች አንዱ ነው። ለእርሻተስማሚ ለም መሬት ያለው የጋምቤላ ክልል፣ በተጨማሪም ከዓመት ዓመት የሚፈሱ ሁለት ግዙፍ ወንዞች ባለቤት ነው። ክልሉ በተለያዩ ጊዜያት ብሔርን መሠረት ያደረጉ ተደጋጋሚ ጥቃቶችና ግጭቶች ያጋጠሙት ሲሆን፣ በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን ሰርገው የሚገቡ ታጣቂዎችም ጥቃት ይፈጽሙበታል። እንደ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት መረጃ ከሆነ ክልሉ ከ480 ሺህ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መኖርያ ነው። ክልሉን የሚመራው የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕዴን) የተለያዩትን የክልሉ ብሔሮች ይወክሉ የነበሩ ቡድኖችን በማዋሃድ የተመሰረተ ነው። ጋሕዴን ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢህአዴግ አጋር ድርጅት የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ አባል ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2mp4jrdzmo
0business
የምዕራባውያንን ማዕቀብ ለሚሸሹት ሩሲያውያን መሸሸጊያ የሆነችው ዱባይ
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ከቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የሩሲያ ባለጸጎች ከምዕራባውያን ማዕቀበ ለማምለጥ ዱባይን መዳረሻቸው እያደረጉ ነው። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቢሊየነር ሩሲያዊያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትሷ ዱባይ እየገቡ ነው። አንድ ሪፖርት በመጀመሪያዎቹ የ2022 ሦስት ወራት ዱባይ ውስጥ በሩሲያ ባለሀብቶች የተገዙ ንብረቶች መጠን በ67 በመቶ ጨምሯል ብሏል። ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ እስካሁን ድረስ የዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ አልጣለችም። ሩሲያ 'ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን' የምትለውን ወረራንም አላወገዘችም። ማዕቀብ ላልተጣለባቸው ሩሲያዊወያንም ቪዛ እየሰጠች ነው። የሞስኮ ወረራን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ወራት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያን አገራቸውን ጥለው ሳይወጡ አይቀርብም ይባላል። አንድ የሩሲያ ዜግነት ያለው የምጣሄ ሀብት ባለሙያ ጦርነቱ በተጀመረ በመጀመርያዎቹ 10 ቀናት ከ200ሺህ ያላነሱ ሩሲያውያን አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል ብሎ ነበር። አዳዲስ ኩባንያዎች በዱባይ ሲቋቋሙ ድጋፍ የሚያደርገው ቨርቱዞን በቅርብ ወራት ገበያው እንደደራላት ይገልጻል። "ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ከሩሲያውያን የሚቀርብልን የአግልግሎት ፍላጎት በአምስት እጥፍ ጨምሯል" ብለዋል የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ጆርጅ ሆጄኢግ። ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደሚሉት ከሆነ ሩሲያውያኑ ከአገራቸው እየሸሹ ያሉት ጦርነቱን ተከትሎ በሩሲያ ሊያጋጥም የሚችለው የምጣሄ ሀብት ድቀት ስለሚያሳስባቸው ነው። "ለአንጡራ ሀብታቸው ማረጋገጫ ስለሚፈልጉ ነው ወደዚህ የሚዘዋወሩት" ብለዋል። የሩሲያውያን ባለሀብቶች ወደ ዱባይ መትመም በከተማዋ የቅንጡ ቪላ እና አፓርትመንት ቤቶች ፍላጎትን ጣራ አድርሶታል። የቤት አሻሻጮችም የዋጋ ጭማሪ ሪፖርት እያደረጉ ነው። ሞደርን ሊቪንግ የተባለ ቤት አሻሻጭ ኩባንያ የሩሲያውያንን የቤት ፍላጎት ለማርካት የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪ የሽያጭ ባለሙያዎችን መቅጠሩን ለቢቢሲ ገልጿል። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቲያጎ ካለዳስ ወደ ዱባይ በአስቸኳይ መዘዋወር የሚፈልጉ ሩሲያውያን የሰልክ ጥሪ እንደሚደርሳቸው ይገልጻሉ። "ወደዚህ የሚመጡት ሩሲያውያን ግዢ የሚፈጽሙት ለኢንቨስትመንት ብቻ ሳይሆን ዱባይን ሁለተኛ ቤታቸው ለማድረግ ነው" ብለዋል። በግለሰብ ደረጃ ያሉ ባለሀብቶች ብቻ አይደሉም ወደ ዱባይ እያቀኑ ያሉት፤ ኩባንያዎች ከነሠራተኞቻቸው ወደ ዱባይ እየተመሙ ነው። ፉአድ ፋቱሌቭ ከዊዌይ ኩባንያ መሥራቾች መካከል አንዱ ነው። ፉአድ የብሎክቼይን ኩባንያው በሩሲያ እና ዩክሬን ቅርንጫፎች እንዳሉት ይናገራል። ከጦርነቱ በኋላ ግን እርሱ እና አጋሮቹን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቹን ወደ ዱባይ ማዘዋወራቸውን ይገልጻል። "ጦርነቱ በሥራችን ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል።" ፉአድ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች ሥራቸውን ለመሥራት ስላላስቻላቸው አገር ለመቀየር መገደዳቸውን ያስረዳል። እንደ ጄፒ ሞርጋን እና ጉግል ያሉ ዓለም አቀፍ ስም ያላቸው ኩባንያዎችም በሩሲያ ያላቸውን ቢሮ በመዝጋት ሠራተኞቻቸውን ወደ ዱባይ እያዘዋወሩ ነው። የባህረ ሰላጤው አገራት ዩኤኢ እና ሳዑዲ አረቢያ፣ ምዕራባውያኑ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ያቀረቡላቸውን ተደጋጋሚ ጥሪ ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ከወራት በፊት የሩሲያን ወረራ ለማውገዝ ድምጽ በሰጠበት ወቅት ጉዳዩን በድምጸ ታዕቅቦ ካለፉት አገራት መካከል ዩኤኢ አንዷ ነበረች። ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለማገድ የወጣው ውሳኔ ላይ አቡ ዳቢ በድምጸ ታዕቅቦ አልፋለች።
የምዕራባውያንን ማዕቀብ ለሚሸሹት ሩሲያውያን መሸሸጊያ የሆነችው ዱባይ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ከቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የሩሲያ ባለጸጎች ከምዕራባውያን ማዕቀበ ለማምለጥ ዱባይን መዳረሻቸው እያደረጉ ነው። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቢሊየነር ሩሲያዊያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትሷ ዱባይ እየገቡ ነው። አንድ ሪፖርት በመጀመሪያዎቹ የ2022 ሦስት ወራት ዱባይ ውስጥ በሩሲያ ባለሀብቶች የተገዙ ንብረቶች መጠን በ67 በመቶ ጨምሯል ብሏል። ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ እስካሁን ድረስ የዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ አልጣለችም። ሩሲያ 'ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን' የምትለውን ወረራንም አላወገዘችም። ማዕቀብ ላልተጣለባቸው ሩሲያዊወያንም ቪዛ እየሰጠች ነው። የሞስኮ ወረራን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ወራት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያን አገራቸውን ጥለው ሳይወጡ አይቀርብም ይባላል። አንድ የሩሲያ ዜግነት ያለው የምጣሄ ሀብት ባለሙያ ጦርነቱ በተጀመረ በመጀመርያዎቹ 10 ቀናት ከ200ሺህ ያላነሱ ሩሲያውያን አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል ብሎ ነበር። አዳዲስ ኩባንያዎች በዱባይ ሲቋቋሙ ድጋፍ የሚያደርገው ቨርቱዞን በቅርብ ወራት ገበያው እንደደራላት ይገልጻል። "ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ከሩሲያውያን የሚቀርብልን የአግልግሎት ፍላጎት በአምስት እጥፍ ጨምሯል" ብለዋል የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ጆርጅ ሆጄኢግ። ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደሚሉት ከሆነ ሩሲያውያኑ ከአገራቸው እየሸሹ ያሉት ጦርነቱን ተከትሎ በሩሲያ ሊያጋጥም የሚችለው የምጣሄ ሀብት ድቀት ስለሚያሳስባቸው ነው። "ለአንጡራ ሀብታቸው ማረጋገጫ ስለሚፈልጉ ነው ወደዚህ የሚዘዋወሩት" ብለዋል። የሩሲያውያን ባለሀብቶች ወደ ዱባይ መትመም በከተማዋ የቅንጡ ቪላ እና አፓርትመንት ቤቶች ፍላጎትን ጣራ አድርሶታል። የቤት አሻሻጮችም የዋጋ ጭማሪ ሪፖርት እያደረጉ ነው። ሞደርን ሊቪንግ የተባለ ቤት አሻሻጭ ኩባንያ የሩሲያውያንን የቤት ፍላጎት ለማርካት የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪ የሽያጭ ባለሙያዎችን መቅጠሩን ለቢቢሲ ገልጿል። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቲያጎ ካለዳስ ወደ ዱባይ በአስቸኳይ መዘዋወር የሚፈልጉ ሩሲያውያን የሰልክ ጥሪ እንደሚደርሳቸው ይገልጻሉ። "ወደዚህ የሚመጡት ሩሲያውያን ግዢ የሚፈጽሙት ለኢንቨስትመንት ብቻ ሳይሆን ዱባይን ሁለተኛ ቤታቸው ለማድረግ ነው" ብለዋል። በግለሰብ ደረጃ ያሉ ባለሀብቶች ብቻ አይደሉም ወደ ዱባይ እያቀኑ ያሉት፤ ኩባንያዎች ከነሠራተኞቻቸው ወደ ዱባይ እየተመሙ ነው። ፉአድ ፋቱሌቭ ከዊዌይ ኩባንያ መሥራቾች መካከል አንዱ ነው። ፉአድ የብሎክቼይን ኩባንያው በሩሲያ እና ዩክሬን ቅርንጫፎች እንዳሉት ይናገራል። ከጦርነቱ በኋላ ግን እርሱ እና አጋሮቹን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቹን ወደ ዱባይ ማዘዋወራቸውን ይገልጻል። "ጦርነቱ በሥራችን ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል።" ፉአድ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች ሥራቸውን ለመሥራት ስላላስቻላቸው አገር ለመቀየር መገደዳቸውን ያስረዳል። እንደ ጄፒ ሞርጋን እና ጉግል ያሉ ዓለም አቀፍ ስም ያላቸው ኩባንያዎችም በሩሲያ ያላቸውን ቢሮ በመዝጋት ሠራተኞቻቸውን ወደ ዱባይ እያዘዋወሩ ነው። የባህረ ሰላጤው አገራት ዩኤኢ እና ሳዑዲ አረቢያ፣ ምዕራባውያኑ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ያቀረቡላቸውን ተደጋጋሚ ጥሪ ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ከወራት በፊት የሩሲያን ወረራ ለማውገዝ ድምጽ በሰጠበት ወቅት ጉዳዩን በድምጸ ታዕቅቦ ካለፉት አገራት መካከል ዩኤኢ አንዷ ነበረች። ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለማገድ የወጣው ውሳኔ ላይ አቡ ዳቢ በድምጸ ታዕቅቦ አልፋለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-61330372
0business
ባለፈው ዓመት ለኑሮ መወደድ ምክንያት የሆኑት ዋነኛ ክስተቶች የትኞቹ ናቸው?
ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ ከዚህ በፊት ከታየው በከፍተኛ ሁኔታ የናረ የምርት እና የአገልግሎቶች ዋጋ መናር ተከስቷል። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ይህ ቪዲዮ የዓለምን ሕዝብን ክፉኛ ላስጨነቀው የዋጋ ንረት ሰበብ ለሆኑት መካከል ዋናዎቹን ይዳስሳል።
ባለፈው ዓመት ለኑሮ መወደድ ምክንያት የሆኑት ዋነኛ ክስተቶች የትኞቹ ናቸው? ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ ከዚህ በፊት ከታየው በከፍተኛ ሁኔታ የናረ የምርት እና የአገልግሎቶች ዋጋ መናር ተከስቷል። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ይህ ቪዲዮ የዓለምን ሕዝብን ክፉኛ ላስጨነቀው የዋጋ ንረት ሰበብ ለሆኑት መካከል ዋናዎቹን ይዳስሳል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cgr0n57lp2xo
2health
ዋነኛ ምልክቱ የጀርባ ሕመም የሆነው የደም ካንሰር ዓይነት
መልቲፕል ማይሎማ (Multiple myeloma) የደም ሥርዓትን የሚያጠቃ እና በብዛት ያልተለመደ የደም ካንሰር ዓይነት ነው። በብዛት በኩላሊት እና በአጥንት ላይ የተለያዩ እክሎችን ያስከትላል። በዚህም የተነሳ የሕመም ምልክቶቹ ከሌላ ሕመም ለመለየት አስቸጋሪ ያደርገዋል። ይህ ሕመም በሽታ ተከላካይ የሆኑትን ነጭ የደም ህዋሳትን፣ ፕላዝማ ህዋሳትን ያጠቃል። እነዚህ የተጠቁ ህዋሳት ደግሞ የተበላሹ ህዋሳትን በመፈጠር እየተባዙ፣ ጤናማ ያልሆነ የሰውነት በሽታ ተከላካይ ህዋሳትን ያመርታሉ። ይህም ኤም ፕሮቲን ( M-protein) ወይንም ሞኖክሎናል ፕሮቲን (monoclonal protein) ይሰኛል። እነዚህ ፕሮቲኖች የተለያዩ የሰውነት ክፍላችን ላይ ጉዳት ስለሚያደርሱ 'መልቲፕል' የሚል ስያሜን አግኝተዋል። በዚህ ካንሰር የተያዙ ሰዎች ተጨማሪ ምልክት ከማሳየታቸው በፊት ቀድሞ የጀርባ ሕመም ይኖራቸዋል። ይህ ምናልባት በሚተኙበት ወቅት ምቾት በማጣት የሚፈጠር ሊሆን ይችላል። ካልሆነም በስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ ጠንካራ ልምምድ ከማድረግ ወይንም ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ። በንግድ ሥራ የተሰማራው የ37 ዓመቱ ሉዊዝ ፈርናንዶ ፎንቴኔል በርካታ የህክምና ምርመራዎችን እና ክትትሎችን ካደረገ በኋላ ነው በዚህ የካንሰር ዓይነት መያዙ የታወቀው። “በጣም ነበር ሕመም የሚሰማኝ። ነገር ግን የመጀመሪያው ስብራት ከሰባት ወር በፊት ካጋጠመኝ በኋላ ነው ሕክምና ያገኘሁት።  ስለ ሕመሜ ያለኝን ጥርጣሬ ያነሳሁት እኔ ራሴው ነኝ። ኢንተርኔት ላይ የተወሰነ ነገር አንብቤ ስለነበር" በማለት ያስታውሳል። ልክ ሉዊዝ ፈርናንዶ እንዳጋጠመው ሁሉ፣ ይህ የካንሰር ዓይነት የአጥንትን ጥንካሬ በማዳከም ስብራት ሊከተል ይችላል። ይህ ደግሞ የሚከሰተው ከፍተኛ የፕላዝማ ሴሎች በመቅኒ ውስጥ እንዲፈጠሩ በማድረግ የሄማቶፖየቲክ ህዋሳት ሲቀንሱ ነው። በዚህ የካንሰር ዓይነት የተነሳም የኩላሊት ሥራ ሊስተጓጎል ይችላል። ምንም እንኳ ይህ የካንሰር ዓይነት በብዛት የሚያጋጥም ባይሆንም፣ ከደም የካንሰር ዓይነቶች መካከል በመከሰት ሁለተኛው ነው። በብራዚል ከ100 ሺህ ሰዎች መካከል አራቱ በዚህ የካንሰር ዓይነት ሊያዙ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል። ይህም ማለት በየዓመቱ 7600 አዳዲስ በዚህ ካንሰር የሚያዙ ሰዎች ይኖራሉ። ይህ የካንሰር ዓይነት እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑ ሰዎቸን የሚያጠቃ ቢሆንም በወጣቶችም ላይ ታይቶ ይታወቃል። መልቲፕል ማይሎማ በሽንት አልያም በደም ምርመራ ሊታወቅ እችላል። መልቲፕል ማይሎማ ፈጽሞ የሚፈውስ መድኃኒት ባይኖርም፣ ነገር ግን በዚህ የካንሰር ዓይነት የተያዙ ግለሰቦች ረዥም ጊዜ ጤናቸው ተሻሽሎ መኖር እንዲችሉ ማድረግ እንደሚቻል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በይበልጥ ቀድሞ የተደረሰበት ከሆነ የግለሰቦችን ጤና የበለጠ አደጋ ላይ ከመጣሉ በፊት ለመከላከል እንደሚቻል ያስረዳሉ። ይህንን የካንሰር ዓይነት ለማከም ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የመቅኒ ንቅለ ተከላ በማካሄድ ሕክምናው ይሰጣል። ሉዊዝ ፈርናንዶ የመቅኒ ንቅለ ተከላ ቢያካሄድም ሕመሙ ዳግም አገርሽቶበት መሰቃየቱን ያስታውሳል። ከ28 ዓመቴ ጀምሮ ከሕመም ውጪ ያሳለፍኩበትን ቀን አላስታውስም የሚለው ሉዊዝ፣ 28 ቀናት በሆስፒታል 21 ቀናት ደግሞ ቤቱ ሆኖ የተለያዩ መድኃኒቶችን ቅንብር እየወሰደ እና ክትትል እየተደረገለት ሕክምናውን አካሂዷል። በዓመታት ውስጥ ከበሽታው ጋር ተዋውቆ እንዴት መኖር እንዳለበት የተረዳው ሉዊዝ አሁን በተሻለ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ያስረዳል።
ዋነኛ ምልክቱ የጀርባ ሕመም የሆነው የደም ካንሰር ዓይነት መልቲፕል ማይሎማ (Multiple myeloma) የደም ሥርዓትን የሚያጠቃ እና በብዛት ያልተለመደ የደም ካንሰር ዓይነት ነው። በብዛት በኩላሊት እና በአጥንት ላይ የተለያዩ እክሎችን ያስከትላል። በዚህም የተነሳ የሕመም ምልክቶቹ ከሌላ ሕመም ለመለየት አስቸጋሪ ያደርገዋል። ይህ ሕመም በሽታ ተከላካይ የሆኑትን ነጭ የደም ህዋሳትን፣ ፕላዝማ ህዋሳትን ያጠቃል። እነዚህ የተጠቁ ህዋሳት ደግሞ የተበላሹ ህዋሳትን በመፈጠር እየተባዙ፣ ጤናማ ያልሆነ የሰውነት በሽታ ተከላካይ ህዋሳትን ያመርታሉ። ይህም ኤም ፕሮቲን ( M-protein) ወይንም ሞኖክሎናል ፕሮቲን (monoclonal protein) ይሰኛል። እነዚህ ፕሮቲኖች የተለያዩ የሰውነት ክፍላችን ላይ ጉዳት ስለሚያደርሱ 'መልቲፕል' የሚል ስያሜን አግኝተዋል። በዚህ ካንሰር የተያዙ ሰዎች ተጨማሪ ምልክት ከማሳየታቸው በፊት ቀድሞ የጀርባ ሕመም ይኖራቸዋል። ይህ ምናልባት በሚተኙበት ወቅት ምቾት በማጣት የሚፈጠር ሊሆን ይችላል። ካልሆነም በስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ ጠንካራ ልምምድ ከማድረግ ወይንም ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ። በንግድ ሥራ የተሰማራው የ37 ዓመቱ ሉዊዝ ፈርናንዶ ፎንቴኔል በርካታ የህክምና ምርመራዎችን እና ክትትሎችን ካደረገ በኋላ ነው በዚህ የካንሰር ዓይነት መያዙ የታወቀው። “በጣም ነበር ሕመም የሚሰማኝ። ነገር ግን የመጀመሪያው ስብራት ከሰባት ወር በፊት ካጋጠመኝ በኋላ ነው ሕክምና ያገኘሁት።  ስለ ሕመሜ ያለኝን ጥርጣሬ ያነሳሁት እኔ ራሴው ነኝ። ኢንተርኔት ላይ የተወሰነ ነገር አንብቤ ስለነበር" በማለት ያስታውሳል። ልክ ሉዊዝ ፈርናንዶ እንዳጋጠመው ሁሉ፣ ይህ የካንሰር ዓይነት የአጥንትን ጥንካሬ በማዳከም ስብራት ሊከተል ይችላል። ይህ ደግሞ የሚከሰተው ከፍተኛ የፕላዝማ ሴሎች በመቅኒ ውስጥ እንዲፈጠሩ በማድረግ የሄማቶፖየቲክ ህዋሳት ሲቀንሱ ነው። በዚህ የካንሰር ዓይነት የተነሳም የኩላሊት ሥራ ሊስተጓጎል ይችላል። ምንም እንኳ ይህ የካንሰር ዓይነት በብዛት የሚያጋጥም ባይሆንም፣ ከደም የካንሰር ዓይነቶች መካከል በመከሰት ሁለተኛው ነው። በብራዚል ከ100 ሺህ ሰዎች መካከል አራቱ በዚህ የካንሰር ዓይነት ሊያዙ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል። ይህም ማለት በየዓመቱ 7600 አዳዲስ በዚህ ካንሰር የሚያዙ ሰዎች ይኖራሉ። ይህ የካንሰር ዓይነት እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑ ሰዎቸን የሚያጠቃ ቢሆንም በወጣቶችም ላይ ታይቶ ይታወቃል። መልቲፕል ማይሎማ በሽንት አልያም በደም ምርመራ ሊታወቅ እችላል። መልቲፕል ማይሎማ ፈጽሞ የሚፈውስ መድኃኒት ባይኖርም፣ ነገር ግን በዚህ የካንሰር ዓይነት የተያዙ ግለሰቦች ረዥም ጊዜ ጤናቸው ተሻሽሎ መኖር እንዲችሉ ማድረግ እንደሚቻል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በይበልጥ ቀድሞ የተደረሰበት ከሆነ የግለሰቦችን ጤና የበለጠ አደጋ ላይ ከመጣሉ በፊት ለመከላከል እንደሚቻል ያስረዳሉ። ይህንን የካንሰር ዓይነት ለማከም ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የመቅኒ ንቅለ ተከላ በማካሄድ ሕክምናው ይሰጣል። ሉዊዝ ፈርናንዶ የመቅኒ ንቅለ ተከላ ቢያካሄድም ሕመሙ ዳግም አገርሽቶበት መሰቃየቱን ያስታውሳል። ከ28 ዓመቴ ጀምሮ ከሕመም ውጪ ያሳለፍኩበትን ቀን አላስታውስም የሚለው ሉዊዝ፣ 28 ቀናት በሆስፒታል 21 ቀናት ደግሞ ቤቱ ሆኖ የተለያዩ መድኃኒቶችን ቅንብር እየወሰደ እና ክትትል እየተደረገለት ሕክምናውን አካሂዷል። በዓመታት ውስጥ ከበሽታው ጋር ተዋውቆ እንዴት መኖር እንዳለበት የተረዳው ሉዊዝ አሁን በተሻለ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ያስረዳል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cw4pxx87kyeo
5sports
ሁለቱንም እጆቹን ያጣው ቻይናዊ አራት የፓራ ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ሰበሰበ
ቻይናዊው የፓራ ዋናተኛው ዤንግ ታኦ በቶኪዮ ፓራ ኦሎምፒክ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሸነፉና ክብረ ወሰኖችን መስበሩ በርካቶችን እያስገረመ ይገኛል። ዤንግ አካል ጉዳተኛ ሲሆን ሁለቱንም እጀቹን አጥቷል። ''ልጄ ተመልከቺ፤ ምንም እንኳን እጆች ባይኖሩኝም በጣም ፈጣን ዋናተኛ ነኝ'' ብሏል ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ ለሴት ልጁ በላከው የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት። ዤንግ ገና ታዳጊ ሳለ ነበር በኤሌክትሪክ ሾክ ምክንያት ሁለቱንም እጆቹን ያጣው። በቶኪዮ ፓራ ኦሎምፒክ ድሞ በነጻ ቀዘፋ፣ ባክስትሮክ እንዲሁም በተርፍላይ ዘርፎች የበላይነትን መውሰድ ችሏል። ሁሉም ድሎቹ ደግሞ በዓለም እና በፓራ ኦሎምፒክ ክብረ ወሰን ሆነው ተመዝግበዋል። ረቡዕ ዕለት በ50 ሜትር ነጻ ቀዘፋ በማሸነፍ የውድድሩን ክብረ ወሰን በእጁ ማስገባት የቻለ ሲሆን ያሸነፈውም የወርቅ ሜዳሊያ ለአገሩ ቻይና በፓራ ኦሎምፒክ ያገኘችው 500ኛ የወርቅ ሜዳሊያ ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህም በርካታ ቻይናውያን በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል ለዤንግ ያላቸውን ክብርና ፍቅር ሲገልጹለት ነበር። ቻይና የመጀመሪያውን የፓራ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊኦኣ ማግኘት የቻለችው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1984 ላይ ኒው ዮርክ ውስጥ በተካሄደው ውድድር ነበር። ዤንግ ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃል '' ይህ ውድድር የቶኪዮ የመጨረሻዬ ስለሆነ ያለኝን አቅም ሁሉ ሰብስቤ እንዲሁም ያለምንም ቁጭት ነው የተፎካከርኩት። እንደሚመስለኝ በህይወቴ ምርጡ ውድድር ነበር'' ብሏል። ሰኞ ዕለት ደግሞ ዤንግ በ50 ሜትር የጀርባ ቀዘፋ የፍጻሜ ውድድርን በ31.42 ሰከንዶች በሆነ ሰአት በማጠናቀቅ የዓለም ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችሏል። ድሉን ተከትሎም ዤንግ ለሁለት ዓመት ሴት ልጁ ባስተላለፈው ስሜታዊ የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት ተከትሎ በርካቶች ማበረታቻና አድናቆታቸውን እያጎረፉለት ይገኛሉ። ዤንግ ውድድሩን ለመጀመርና በኃይል ለመወርወር ከገንዳው ፊትለፊት ከሚገኝ ብረት ጋት የተያያዘ ፎጣ በጥርሱ በመያዝ የተጠቀመ ሲሆን በርካታ የምህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ድፍረቱን እና ጥንካሬውን እየገለጹ አድናቆታቸውን አጉርፈውለታል። አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ደግሞ ዤንግ ለቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅት በየቀኑ የ10 ኪሎሜትር ዋና ያደርግ ነበር። ገና የ13 ዓመት ታዳጊ ሳለ ወደ ውሃ ዋና ስፖርት የገባው ዤንግ በዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደር የጀመረው ደግሞ ከስድስት በኋላ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ በፓራ ኦሎምፒክ የተሳተፈው ደግሞ በአውሮፓውያኑ 2012 በተካሄደው የለንደን ኦሎምፒክ ሲሆን እስካሁን ድረስ ደግሞ 9 ሜዳሊያዎችን ሰብስቧል።
ሁለቱንም እጆቹን ያጣው ቻይናዊ አራት የፓራ ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ሰበሰበ ቻይናዊው የፓራ ዋናተኛው ዤንግ ታኦ በቶኪዮ ፓራ ኦሎምፒክ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሸነፉና ክብረ ወሰኖችን መስበሩ በርካቶችን እያስገረመ ይገኛል። ዤንግ አካል ጉዳተኛ ሲሆን ሁለቱንም እጀቹን አጥቷል። ''ልጄ ተመልከቺ፤ ምንም እንኳን እጆች ባይኖሩኝም በጣም ፈጣን ዋናተኛ ነኝ'' ብሏል ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ ለሴት ልጁ በላከው የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት። ዤንግ ገና ታዳጊ ሳለ ነበር በኤሌክትሪክ ሾክ ምክንያት ሁለቱንም እጆቹን ያጣው። በቶኪዮ ፓራ ኦሎምፒክ ድሞ በነጻ ቀዘፋ፣ ባክስትሮክ እንዲሁም በተርፍላይ ዘርፎች የበላይነትን መውሰድ ችሏል። ሁሉም ድሎቹ ደግሞ በዓለም እና በፓራ ኦሎምፒክ ክብረ ወሰን ሆነው ተመዝግበዋል። ረቡዕ ዕለት በ50 ሜትር ነጻ ቀዘፋ በማሸነፍ የውድድሩን ክብረ ወሰን በእጁ ማስገባት የቻለ ሲሆን ያሸነፈውም የወርቅ ሜዳሊያ ለአገሩ ቻይና በፓራ ኦሎምፒክ ያገኘችው 500ኛ የወርቅ ሜዳሊያ ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህም በርካታ ቻይናውያን በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል ለዤንግ ያላቸውን ክብርና ፍቅር ሲገልጹለት ነበር። ቻይና የመጀመሪያውን የፓራ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊኦኣ ማግኘት የቻለችው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1984 ላይ ኒው ዮርክ ውስጥ በተካሄደው ውድድር ነበር። ዤንግ ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃል '' ይህ ውድድር የቶኪዮ የመጨረሻዬ ስለሆነ ያለኝን አቅም ሁሉ ሰብስቤ እንዲሁም ያለምንም ቁጭት ነው የተፎካከርኩት። እንደሚመስለኝ በህይወቴ ምርጡ ውድድር ነበር'' ብሏል። ሰኞ ዕለት ደግሞ ዤንግ በ50 ሜትር የጀርባ ቀዘፋ የፍጻሜ ውድድርን በ31.42 ሰከንዶች በሆነ ሰአት በማጠናቀቅ የዓለም ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችሏል። ድሉን ተከትሎም ዤንግ ለሁለት ዓመት ሴት ልጁ ባስተላለፈው ስሜታዊ የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት ተከትሎ በርካቶች ማበረታቻና አድናቆታቸውን እያጎረፉለት ይገኛሉ። ዤንግ ውድድሩን ለመጀመርና በኃይል ለመወርወር ከገንዳው ፊትለፊት ከሚገኝ ብረት ጋት የተያያዘ ፎጣ በጥርሱ በመያዝ የተጠቀመ ሲሆን በርካታ የምህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ድፍረቱን እና ጥንካሬውን እየገለጹ አድናቆታቸውን አጉርፈውለታል። አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ደግሞ ዤንግ ለቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅት በየቀኑ የ10 ኪሎሜትር ዋና ያደርግ ነበር። ገና የ13 ዓመት ታዳጊ ሳለ ወደ ውሃ ዋና ስፖርት የገባው ዤንግ በዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደር የጀመረው ደግሞ ከስድስት በኋላ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ በፓራ ኦሎምፒክ የተሳተፈው ደግሞ በአውሮፓውያኑ 2012 በተካሄደው የለንደን ኦሎምፒክ ሲሆን እስካሁን ድረስ ደግሞ 9 ሜዳሊያዎችን ሰብስቧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58452725
3politics
በሞቃዲሾ የተከሰተው ውጊያ የለየለት ጦርነት እንዳይቀሰቅስ አስግቷል
በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሁለት ተጻራሪ ኃይሎች መካከል ውጊያ ተካሄደ። ትናንት እሁድ ከአገሪቱ ቤተ መንግሥቱት አቅራቢያ የከባባድ መሣሪያዎች ድምጽና የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። ሞርታር ጭምር የፕሬዝዳንቱ መቀመጫ ወደሆነው ቤተ መንግሥት ስለመተኮሱ ተሰምቷል። ውጊያው ምናልባትም ፕሬዝዳንት ፋርማጆን በሚደግፉና በሚቃወሙ የሠራዊት አካላት አልያም በታጣቂዎች መካከል ሳይካሄድ እንዳልቀረ ተጠርጥሯል። ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ወይም (ይበልጥ የሚታወቁበት ስማቸው ፋርማጆ) የሥልጣን ዘመናቸውን በሁለት ዓመት ማራዘማቸው እያነጋገረ ነበር። የፋርማጆ የሥልጣን ዘመን ባለፈው የካቲት ወር ማብቃት ነበረበት። የፋርማጆ ሥልጣናቸውን ማራዘም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ እየተወገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፋርማጆ ውሳኔ እንዳሳሰባቸው ከመግለጽ አልተቆጠቡም። ትናንት እሁድ በወጡ አንዳንድ ዘገባዎች እንደተመላከተው በአንዳንድ አካባቢዎች የተነሱ አለመግባባቶች እየሰፉ ሄደው ማዕከላዊ ሞቃዲሾን ሲያምሱ ውለዋል። አንዳንድ የአገሬው መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ግጭቱ በዋናነት የፋርማጆን መንግሥት በሚደግፉና በሚቃወሙ ታጣቂ ኃይሎች መካከል የተደረገ ነበር። የጎሣ መሪዎችም በግጭቱ ተሳትፎ ነበራቸው። እስከአሁን በትናንቱ ግጭት ስለደረሰው ጉዳት የተባለ ነገር የለም። የግል የሆነው 'ካሲማዳ' የወሬ ድረ ገጽ እንዳለው ጸረ ፋርማጆ ሰልፈኞች ወደ ጎዳና ወጥተው ጎማ ያቃጠሉ ሲሆን፤ አማጺ ወታደሮችም የተወሰኑ የሞቃዲሾ ሰሜናዊ ሰፈሮችን መቆጣጠር ችለው ነበር። የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ማህሙድ እና የተቃዋሚ መሪው አብዱራህማን አብዲሺኩር የመንግሥት ደጋፊ ታጣቂዎች ቤቶቻቸው ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተናግረዋል። በተለይ አብዱሺኩር በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ እንደጻፉት መከላከያ ኃይሉን ፖለቲካ ውስጥ ማስገባት አደጋ አለው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ትናንት ከሰዓት የሶማሊያ ደኅንነት ሚኒስትር ሐሰን ሐነደበይ ጂማሌ ስማቸውን ያልጠቀሷቸው አገሮች ከግጭቱ ጀርባ እንዳሉ አስታውቀዋል። እጃቸውን እንዲሰበስቡም አሳስበዋል። የደኅንነት ሚኒስትሩ በቴሌቪዥን ወጥተው እንደተናገሩት ታጣቂ ቡድን ወደ ሞቃዲሾ ተሰማርቶ አገሪቱን ለማመስ ተልዕኮ ተሰጥቶት ነበር። ሆኖም አክሽፈነዋል ብለዋል። ሶማሊያ ለአስርታት በጦርነት ስትታመስ የቆየች አገር ናት። ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ ግን የመረጋጋት ዝንባሌን ስታሳይ ቆይታለች። የፋርማጆ መንግሥትም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ ያለው ሆኖ ቆይቷል። ሆኖም የፋርማጆ ሕጋዊ የግዛት ዘመን በየካቲት ማብቃቱን ተከትሎ ምርጫ መዘግየቱ ያቺን አገር ወደለየለት ግጭት ውሰጥ እንዳይከታት ተሰግቷል። በሶማሊያ ምርጫ የሚካሄድበት መንገድ ከተመለደው ወጣ ያለና የተወሳሰበ ነው። በሶማሊያ የቀጥታ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሳይሆን የሚደረገው የጎሳ መሪዎች የሕዝብ ተወካዮችን ከመረጡ በኋላ የተመረጡት የሕዝብ ተወካዮች ናቸው ፕሬዝዳንቱን የሚመርጡት።
በሞቃዲሾ የተከሰተው ውጊያ የለየለት ጦርነት እንዳይቀሰቅስ አስግቷል በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሁለት ተጻራሪ ኃይሎች መካከል ውጊያ ተካሄደ። ትናንት እሁድ ከአገሪቱ ቤተ መንግሥቱት አቅራቢያ የከባባድ መሣሪያዎች ድምጽና የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። ሞርታር ጭምር የፕሬዝዳንቱ መቀመጫ ወደሆነው ቤተ መንግሥት ስለመተኮሱ ተሰምቷል። ውጊያው ምናልባትም ፕሬዝዳንት ፋርማጆን በሚደግፉና በሚቃወሙ የሠራዊት አካላት አልያም በታጣቂዎች መካከል ሳይካሄድ እንዳልቀረ ተጠርጥሯል። ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ወይም (ይበልጥ የሚታወቁበት ስማቸው ፋርማጆ) የሥልጣን ዘመናቸውን በሁለት ዓመት ማራዘማቸው እያነጋገረ ነበር። የፋርማጆ የሥልጣን ዘመን ባለፈው የካቲት ወር ማብቃት ነበረበት። የፋርማጆ ሥልጣናቸውን ማራዘም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ እየተወገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፋርማጆ ውሳኔ እንዳሳሰባቸው ከመግለጽ አልተቆጠቡም። ትናንት እሁድ በወጡ አንዳንድ ዘገባዎች እንደተመላከተው በአንዳንድ አካባቢዎች የተነሱ አለመግባባቶች እየሰፉ ሄደው ማዕከላዊ ሞቃዲሾን ሲያምሱ ውለዋል። አንዳንድ የአገሬው መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ግጭቱ በዋናነት የፋርማጆን መንግሥት በሚደግፉና በሚቃወሙ ታጣቂ ኃይሎች መካከል የተደረገ ነበር። የጎሣ መሪዎችም በግጭቱ ተሳትፎ ነበራቸው። እስከአሁን በትናንቱ ግጭት ስለደረሰው ጉዳት የተባለ ነገር የለም። የግል የሆነው 'ካሲማዳ' የወሬ ድረ ገጽ እንዳለው ጸረ ፋርማጆ ሰልፈኞች ወደ ጎዳና ወጥተው ጎማ ያቃጠሉ ሲሆን፤ አማጺ ወታደሮችም የተወሰኑ የሞቃዲሾ ሰሜናዊ ሰፈሮችን መቆጣጠር ችለው ነበር። የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ማህሙድ እና የተቃዋሚ መሪው አብዱራህማን አብዲሺኩር የመንግሥት ደጋፊ ታጣቂዎች ቤቶቻቸው ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተናግረዋል። በተለይ አብዱሺኩር በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ እንደጻፉት መከላከያ ኃይሉን ፖለቲካ ውስጥ ማስገባት አደጋ አለው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ትናንት ከሰዓት የሶማሊያ ደኅንነት ሚኒስትር ሐሰን ሐነደበይ ጂማሌ ስማቸውን ያልጠቀሷቸው አገሮች ከግጭቱ ጀርባ እንዳሉ አስታውቀዋል። እጃቸውን እንዲሰበስቡም አሳስበዋል። የደኅንነት ሚኒስትሩ በቴሌቪዥን ወጥተው እንደተናገሩት ታጣቂ ቡድን ወደ ሞቃዲሾ ተሰማርቶ አገሪቱን ለማመስ ተልዕኮ ተሰጥቶት ነበር። ሆኖም አክሽፈነዋል ብለዋል። ሶማሊያ ለአስርታት በጦርነት ስትታመስ የቆየች አገር ናት። ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ ግን የመረጋጋት ዝንባሌን ስታሳይ ቆይታለች። የፋርማጆ መንግሥትም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ ያለው ሆኖ ቆይቷል። ሆኖም የፋርማጆ ሕጋዊ የግዛት ዘመን በየካቲት ማብቃቱን ተከትሎ ምርጫ መዘግየቱ ያቺን አገር ወደለየለት ግጭት ውሰጥ እንዳይከታት ተሰግቷል። በሶማሊያ ምርጫ የሚካሄድበት መንገድ ከተመለደው ወጣ ያለና የተወሳሰበ ነው። በሶማሊያ የቀጥታ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሳይሆን የሚደረገው የጎሳ መሪዎች የሕዝብ ተወካዮችን ከመረጡ በኋላ የተመረጡት የሕዝብ ተወካዮች ናቸው ፕሬዝዳንቱን የሚመርጡት።
https://www.bbc.com/amharic/news-56884281
2health
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በድጋሚ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆኑ
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለማችንን ትልቁን የጤና ተቋም የዓለም የጤና ድርጅትን ለሁለተኛ ዙር እንዲመሩ ዳግም ተመረጡ። የዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛ ዕጩ ሆነው ዳግም መመረጣቸው የተረጋገጠው በጄኔቫ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉብዔ ላይ ነው። ዶክተር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ በብቸኛ ዕጩነት በቀረቡበት መድረክ ላይ ከተለያዩ የድርጅቱ አባል አገራት ለዕጪነት ለተሰጣቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። የዋና ዳይሬክተሩ ምርጫን በመደገፍ በቦትሰዋናው ተወካይ በኩል የአፍሪካ አገራት ቡድንን በመወከል ሊቀርብ የነበረውን መግለጫ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተቃውመውታል። በዚህም 45 የአፍሪካ አገራት ድጋፍ በሚል ቦትሰዋና ለዶ/ር ቴድሮስ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት እና የመልካም የሥራ ጊዜ ምኞት አስተላልፈዋል። ዶ/ር ቴድሮስ ያለፉት አምስት ዓመታት የተባበሩት መንግሥት ጤና ድርጅት ሲመሩ ቆይተዋል። በዚህ ወቅት የኮቪድ-19 ስርጭት እና ተቋማቸው ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የገባው ውዝግብ የሥልጣን ዘመናቸውን ፈታኝ ከዳረጉት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የዓለም ጤና ዳይሬክተሩ መመረጣቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ "በእኔ ላይ ላላችሁ መተማመን እና ለጣላችሁብኝ እምነት አመሰግናለሁ" ብለዋል። ዶ/ር ቴድሮስ ተቋሙን በይፋ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለሁለተኛ ዙር መምራት ይጀምራሉ። ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከመመረጣቸው በፊት እአአ ከ2012 እስከ 2016 ድረስ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከዚያ ቀደም ብሎ ደግሞ ለበርካታ ዓመታት የአገሪቱ የጤና ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ዶ/ር ቴድሮስ የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ሆነው ባገለገሉባቸው ዓመታት በኢትዮጵያ የጤና መሠረታዊ አገልግሎቶች መስፋፋታቸው እና የሕጻናት እና እናቶች ሞት መጠን መቀነሱ ይገለጻል። ዋና ዳይሬክተሩ በመጀመሪያው ዙር የዓለም ጤና ድርጅት የመሪነት ዘመናቸው ከገጠሟቸው ፈተናዎች መካከል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር ጦርነት በገጠመበት ጊዜ ለቡድኑ ድጋፍ ይሰጣሉ በሚል ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ከሰዋቸዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በድጋሚ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆኑ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለማችንን ትልቁን የጤና ተቋም የዓለም የጤና ድርጅትን ለሁለተኛ ዙር እንዲመሩ ዳግም ተመረጡ። የዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛ ዕጩ ሆነው ዳግም መመረጣቸው የተረጋገጠው በጄኔቫ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉብዔ ላይ ነው። ዶክተር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ በብቸኛ ዕጩነት በቀረቡበት መድረክ ላይ ከተለያዩ የድርጅቱ አባል አገራት ለዕጪነት ለተሰጣቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። የዋና ዳይሬክተሩ ምርጫን በመደገፍ በቦትሰዋናው ተወካይ በኩል የአፍሪካ አገራት ቡድንን በመወከል ሊቀርብ የነበረውን መግለጫ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተቃውመውታል። በዚህም 45 የአፍሪካ አገራት ድጋፍ በሚል ቦትሰዋና ለዶ/ር ቴድሮስ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት እና የመልካም የሥራ ጊዜ ምኞት አስተላልፈዋል። ዶ/ር ቴድሮስ ያለፉት አምስት ዓመታት የተባበሩት መንግሥት ጤና ድርጅት ሲመሩ ቆይተዋል። በዚህ ወቅት የኮቪድ-19 ስርጭት እና ተቋማቸው ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የገባው ውዝግብ የሥልጣን ዘመናቸውን ፈታኝ ከዳረጉት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የዓለም ጤና ዳይሬክተሩ መመረጣቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ "በእኔ ላይ ላላችሁ መተማመን እና ለጣላችሁብኝ እምነት አመሰግናለሁ" ብለዋል። ዶ/ር ቴድሮስ ተቋሙን በይፋ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለሁለተኛ ዙር መምራት ይጀምራሉ። ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከመመረጣቸው በፊት እአአ ከ2012 እስከ 2016 ድረስ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከዚያ ቀደም ብሎ ደግሞ ለበርካታ ዓመታት የአገሪቱ የጤና ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ዶ/ር ቴድሮስ የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ሆነው ባገለገሉባቸው ዓመታት በኢትዮጵያ የጤና መሠረታዊ አገልግሎቶች መስፋፋታቸው እና የሕጻናት እና እናቶች ሞት መጠን መቀነሱ ይገለጻል። ዋና ዳይሬክተሩ በመጀመሪያው ዙር የዓለም ጤና ድርጅት የመሪነት ዘመናቸው ከገጠሟቸው ፈተናዎች መካከል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር ጦርነት በገጠመበት ጊዜ ለቡድኑ ድጋፍ ይሰጣሉ በሚል ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ከሰዋቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61568901
2health
በአሜሪካ ሲካሄድ የነበረ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ተቋረጠ
ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ሲያካሂድ የነበረውን ምርምር አንድ በጎ ፍቃደኛ መታመሙን ተከትሎ ማቋረጡን አስታወቀ። ኩባንያው እንዳለው በክትባት ሙከራው ላይ እየተሳተፈ የነበረው በጎ ፍቃደኛ የጤና እክል የገጠመው ክትባት ለማግኘት ከሚደረገው ምርምር ጋር ተያይዞ ስለመሆኑ ይጣራል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፍቃደኞች በሚሳተፉበት ምርምር ላይ በጎ ፍቃደኞች የጤና እክል ሊገጥማቸው እንደሚችል ኩባንያው አስታውሶ፤ ለጥንቃቄ ሲባል ሶስተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው የሙከራ ምርምሩ እንቋዲረጥ ተደርጓል ብሏል። የበጎ ፍቃደኛውን ግላዊ መብት ለመጠበቅ ሲባል የተሳታፊው ማንነት እና ያጋጠመው ህመም እንደማይገለጽ ተጠቁሟል። የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ እንዲቋረጥ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዩናይትድ ኪንግደም በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራ ዜኔካ ጥምረት ሲካሄድ የነበረው ምርምር ላይ አንድ በጎ ፍቃደኛ ላይ የጤና መቃወስ ማጋጠሙን ተከትሎ ሙከራው ከተቋረጠ በኋላ ምርምሩ እንደገና መጀመሩ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ከ180 በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባት ምርምሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ አንዳቸውም የክሊኒካል ሙከራቸውን ማጠናቀቅ አልቻሉም። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ኩባንያ እያካሄደ ያለው የኮሮናቫይረስ ምርምር ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራ ዜኔካ የደረሱበት ደረጃ ላይ መድረስ የቻለ ነበር። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ሲያካሂድ በነበረው የምርምር ስራ ላይ በጎ ፍቃደኞችን መመልመል የጀመረው መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ነበር። ሙከራው 60ሺህ ተሳታፊዎችን በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ያሳትፋል ተብሎ ነበር።
በአሜሪካ ሲካሄድ የነበረ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ተቋረጠ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ሲያካሂድ የነበረውን ምርምር አንድ በጎ ፍቃደኛ መታመሙን ተከትሎ ማቋረጡን አስታወቀ። ኩባንያው እንዳለው በክትባት ሙከራው ላይ እየተሳተፈ የነበረው በጎ ፍቃደኛ የጤና እክል የገጠመው ክትባት ለማግኘት ከሚደረገው ምርምር ጋር ተያይዞ ስለመሆኑ ይጣራል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፍቃደኞች በሚሳተፉበት ምርምር ላይ በጎ ፍቃደኞች የጤና እክል ሊገጥማቸው እንደሚችል ኩባንያው አስታውሶ፤ ለጥንቃቄ ሲባል ሶስተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው የሙከራ ምርምሩ እንቋዲረጥ ተደርጓል ብሏል። የበጎ ፍቃደኛውን ግላዊ መብት ለመጠበቅ ሲባል የተሳታፊው ማንነት እና ያጋጠመው ህመም እንደማይገለጽ ተጠቁሟል። የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ እንዲቋረጥ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዩናይትድ ኪንግደም በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራ ዜኔካ ጥምረት ሲካሄድ የነበረው ምርምር ላይ አንድ በጎ ፍቃደኛ ላይ የጤና መቃወስ ማጋጠሙን ተከትሎ ሙከራው ከተቋረጠ በኋላ ምርምሩ እንደገና መጀመሩ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ከ180 በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባት ምርምሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ አንዳቸውም የክሊኒካል ሙከራቸውን ማጠናቀቅ አልቻሉም። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ኩባንያ እያካሄደ ያለው የኮሮናቫይረስ ምርምር ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራ ዜኔካ የደረሱበት ደረጃ ላይ መድረስ የቻለ ነበር። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ሲያካሂድ በነበረው የምርምር ስራ ላይ በጎ ፍቃደኞችን መመልመል የጀመረው መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ነበር። ሙከራው 60ሺህ ተሳታፊዎችን በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ያሳትፋል ተብሎ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/54526621
5sports
የዓለማችን ኮከብ አትሌት ሞ ፋራህ ለዘመናት የደበቀውን ምስጢር ይፋ አወጣ
ከዓለማችን ኮከብ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ሞ ፋራህ በህፃንነቱ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መወሰዱን እና ለአስገዳጅ የጉልበት ብዝበዛ መጋለጡን ይፋ አደረገ። በስፖርቱ ዘርፍ ለዩናይትድ ኪንግደም ባበረከተው አስተዋጽኦ በአገሪቱ ከፍተኛ ማዕረግ የሆነውን ‘ሰር’ የሚለውን መለያ ያገኘው ሞ ፋራህ ስሙ በወላጆቹ የተሰጠው ሳይሆን ሐሰተኛ ነው ብሏል። ፋራህ በህጻናት ላይ የሚደርሰውን የጉልበት ብዝባዛ ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት እውነተኛ ታሪኩን ይፋ በማውጣወት ያለፈበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለቢቢሲ ተርኳል።
የዓለማችን ኮከብ አትሌት ሞ ፋራህ ለዘመናት የደበቀውን ምስጢር ይፋ አወጣ ከዓለማችን ኮከብ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ሞ ፋራህ በህፃንነቱ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መወሰዱን እና ለአስገዳጅ የጉልበት ብዝበዛ መጋለጡን ይፋ አደረገ። በስፖርቱ ዘርፍ ለዩናይትድ ኪንግደም ባበረከተው አስተዋጽኦ በአገሪቱ ከፍተኛ ማዕረግ የሆነውን ‘ሰር’ የሚለውን መለያ ያገኘው ሞ ፋራህ ስሙ በወላጆቹ የተሰጠው ሳይሆን ሐሰተኛ ነው ብሏል። ፋራህ በህጻናት ላይ የሚደርሰውን የጉልበት ብዝባዛ ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት እውነተኛ ታሪኩን ይፋ በማውጣወት ያለፈበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለቢቢሲ ተርኳል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyrkz71kx1do
2health
የታንዛኒያው ፕሬዝደንት የኮቪድ-19 ክትባት ለታንዛኒያውያን አያስፈልግም አሉ
የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ የአገሪቱ ጤና ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመጠቀም ከመወሰናቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው አሉ። ማጉፉሊ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ የኮቪድ-19 ክትባት ሕዝቡን ሊጎዳ ይችላል ብለዋል። "የጤና ሚንስቴር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ጥናቶችን ሳያከናውኑ እነዚህን ክትባቶች ለመሞከር መፍጠን የለባቸውም። ሁሉም ክትባት ለእኛ ጠቃሚ አይደሉም፤ መጠንቀቅ አለብን። መሞከሪያ መሆን የለብንም" ሲሉ ማጉፉሊ ተናግረዋል። "ክትባቶች አደገኛ ናቸው። ነጩ ሰውዬ ክትባት አገኘሁ ካለ፤ ለኤድስ፣ ለካንሰር እና ለቲቢ እስካሁን ክትባት ሊኖረው ይገባል።" ፕሬዝደንቱ ይህን ይበሉ እንጂ የኮቪድ-19 ክትባቶች ለሰው ልጆች እንዲሰጡ የተፈቀደው በርካታ ምርመሮች እና ሙከራዎች ከተከናወነባቸው በኋላ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተሞክረው፣ ደህንነታቸው ተረጋግጦ፣ በመድሃኒት ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ በማግኘታቸው ነው ለሰዎች እየተሰጡ ያሉት በማለት የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ፊሊፓ ሮክስቢይ ትናገራለች። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ግን ዜጎቻቸውን ይህን ክትባት ከመውሰዳቸው በፊት ጥንቃቄ አድርጉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከክትባት ይልቅ ጸሎት ማድረግ እና ለባህላዊ መድሃኒት ቅድሚያ መስጠት የተሻለ አማራጭ ነው ሲሉ ታንዛኒያውያንን መክረዋል። "በርካታ አገራት የእንቅስቃሴ ገደቦችን አስተዋውቀዋል። በታንዛኒያ ግን የሰዎችን እንቅስቃሴ የመገደብ እቅድ የለንም። ፈጣሪያችን በሕይወት አለ፤ እርሱ ይጠብቀናል" ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ከወራት በፊት ታንዛኒያ ከኮቪድ-19 ነጻ ሆናለች ብለው ያወጁ ሲሆን፤ በከተሞች አከባቢ ስለጨመረው የሰዎች ሞት ቁጥር ላይ ግን ያሉት ነገር የለም። ማጉፉሊ አባል የሆኑበት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ግን፤ ታንዛኒያ መጀመሪያ ላይ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ቢቻላትም አሁን ላይ ግን የቫይረሱ ስርጭት እንደ አዲስ መስፋፋቱን አስታውቋል። የታንዛኒያ ጤና ሚንስቴር በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ፣ የሚሞቱ እና የሚያገግሙ ሰዎች አሃዝን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ካቆመ ወራቶች አልፈዋል።
የታንዛኒያው ፕሬዝደንት የኮቪድ-19 ክትባት ለታንዛኒያውያን አያስፈልግም አሉ የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ የአገሪቱ ጤና ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመጠቀም ከመወሰናቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው አሉ። ማጉፉሊ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ የኮቪድ-19 ክትባት ሕዝቡን ሊጎዳ ይችላል ብለዋል። "የጤና ሚንስቴር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ጥናቶችን ሳያከናውኑ እነዚህን ክትባቶች ለመሞከር መፍጠን የለባቸውም። ሁሉም ክትባት ለእኛ ጠቃሚ አይደሉም፤ መጠንቀቅ አለብን። መሞከሪያ መሆን የለብንም" ሲሉ ማጉፉሊ ተናግረዋል። "ክትባቶች አደገኛ ናቸው። ነጩ ሰውዬ ክትባት አገኘሁ ካለ፤ ለኤድስ፣ ለካንሰር እና ለቲቢ እስካሁን ክትባት ሊኖረው ይገባል።" ፕሬዝደንቱ ይህን ይበሉ እንጂ የኮቪድ-19 ክትባቶች ለሰው ልጆች እንዲሰጡ የተፈቀደው በርካታ ምርመሮች እና ሙከራዎች ከተከናወነባቸው በኋላ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተሞክረው፣ ደህንነታቸው ተረጋግጦ፣ በመድሃኒት ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ በማግኘታቸው ነው ለሰዎች እየተሰጡ ያሉት በማለት የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ፊሊፓ ሮክስቢይ ትናገራለች። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ግን ዜጎቻቸውን ይህን ክትባት ከመውሰዳቸው በፊት ጥንቃቄ አድርጉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከክትባት ይልቅ ጸሎት ማድረግ እና ለባህላዊ መድሃኒት ቅድሚያ መስጠት የተሻለ አማራጭ ነው ሲሉ ታንዛኒያውያንን መክረዋል። "በርካታ አገራት የእንቅስቃሴ ገደቦችን አስተዋውቀዋል። በታንዛኒያ ግን የሰዎችን እንቅስቃሴ የመገደብ እቅድ የለንም። ፈጣሪያችን በሕይወት አለ፤ እርሱ ይጠብቀናል" ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ከወራት በፊት ታንዛኒያ ከኮቪድ-19 ነጻ ሆናለች ብለው ያወጁ ሲሆን፤ በከተሞች አከባቢ ስለጨመረው የሰዎች ሞት ቁጥር ላይ ግን ያሉት ነገር የለም። ማጉፉሊ አባል የሆኑበት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ግን፤ ታንዛኒያ መጀመሪያ ላይ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ቢቻላትም አሁን ላይ ግን የቫይረሱ ስርጭት እንደ አዲስ መስፋፋቱን አስታውቋል። የታንዛኒያ ጤና ሚንስቴር በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ፣ የሚሞቱ እና የሚያገግሙ ሰዎች አሃዝን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ካቆመ ወራቶች አልፈዋል።
https://www.bbc.com/amharic/55825410
2health
ሲዲሲ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰራጭበት መንገድ ላይ የአሜሪካ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ አሳሰበ
የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የአሜሪካ ግዛቶች የጤና ኃላፊዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ቀድሞ የሚታደልበት አማራጭ ላይ ቀድመው እንዲዘጋጁ ማሳሰቡ ተነገረ። ሲዲሲ ትናንት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ላይ ክትባቱ ለበሽታው የበለጠ ተጋለጭ ለሆኑ ሰዎች እስከ ጥቅምት አጋማሽ ሊሰራጭ እንደሚችል ጠቁሟል። “ሲዲሲ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ በማሰብ ዝግጁ ሊሆን የሚችል የክትባት መጠን እና ጊዜን ለግዛቶች አሳውቋል። ከጥቅምት አጋማሽ እስከ ሕዳር መጨረሻ ድረስ መጠናቸው አነስተኛ ቢሆንም የክትባት ስርጭት ሊኖር ይችላል” ሲሉ የሲዲሲ ቃል አቀባይ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይመስ ደግሞ ቀደም ሲል ሲዲሲ ከሁሉም 50 የአሜሪካ ግዛቶች እና አምስት ግዙፍ ከተሞች ከስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ የእቅድ መረጃዎችን ጠይቋል። በኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ላይ ሲዲሲ ጥቅምት አጋማሽ ላይ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ አንድ ወይም ሁለት የኮቪድ-19 ክትባቶች ለስርጭት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ እንደ የጤና ባለሙያዎች፣ ለደህንነት ሰራተኞች እና እድሜያቸው የገፉ ሰዎችን የሚንከባከቡ ነርሶች እና ባልደረቦች ክትባቱ ያለ ክፍያ ይሰጣቸዋል ይላል የሲዲሲው ዶክመንት። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒዮ ፋውቺ ለኤምኤስኤንቢሲ ቴሌቪዥን ትናንት ሲናገሩ፤ ለኮቪድ-19 ክትባት ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥርን ከግምት በማስገባት እስከ ሕዳር ወር ድረስ የትኛው የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ይቻላል ብለዋል። ሞደርና፣ አስትራዜኔካ እና ፐፊዘር የተሰኙ መድሃኒት አምራቾች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት ለማዘጋጀት ጥረት ላይ ይገኛሉ።
ሲዲሲ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰራጭበት መንገድ ላይ የአሜሪካ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ አሳሰበ የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የአሜሪካ ግዛቶች የጤና ኃላፊዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት የበለጠ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ቀድሞ የሚታደልበት አማራጭ ላይ ቀድመው እንዲዘጋጁ ማሳሰቡ ተነገረ። ሲዲሲ ትናንት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ላይ ክትባቱ ለበሽታው የበለጠ ተጋለጭ ለሆኑ ሰዎች እስከ ጥቅምት አጋማሽ ሊሰራጭ እንደሚችል ጠቁሟል። “ሲዲሲ ግዛቶች ቀድመው እንዲዘጋጁ በማሰብ ዝግጁ ሊሆን የሚችል የክትባት መጠን እና ጊዜን ለግዛቶች አሳውቋል። ከጥቅምት አጋማሽ እስከ ሕዳር መጨረሻ ድረስ መጠናቸው አነስተኛ ቢሆንም የክትባት ስርጭት ሊኖር ይችላል” ሲሉ የሲዲሲ ቃል አቀባይ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይመስ ደግሞ ቀደም ሲል ሲዲሲ ከሁሉም 50 የአሜሪካ ግዛቶች እና አምስት ግዙፍ ከተሞች ከስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ የእቅድ መረጃዎችን ጠይቋል። በኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ላይ ሲዲሲ ጥቅምት አጋማሽ ላይ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ አንድ ወይም ሁለት የኮቪድ-19 ክትባቶች ለስርጭት ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ እንደ የጤና ባለሙያዎች፣ ለደህንነት ሰራተኞች እና እድሜያቸው የገፉ ሰዎችን የሚንከባከቡ ነርሶች እና ባልደረቦች ክትባቱ ያለ ክፍያ ይሰጣቸዋል ይላል የሲዲሲው ዶክመንት። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒዮ ፋውቺ ለኤምኤስኤንቢሲ ቴሌቪዥን ትናንት ሲናገሩ፤ ለኮቪድ-19 ክትባት ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥርን ከግምት በማስገባት እስከ ሕዳር ወር ድረስ የትኛው የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ እንደሚሆን መለየት ይቻላል ብለዋል። ሞደርና፣ አስትራዜኔካ እና ፐፊዘር የተሰኙ መድሃኒት አምራቾች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት ለማዘጋጀት ጥረት ላይ ይገኛሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-54012503
5sports
ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪምየር አሸናፊ ሆነ
ማንችስተር ሲቲ በአራት ዓመታት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆኗል። ትናንት ምሽት በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ በሌስተር ሲቲ መሸነፉን ተከትሎ ነው ሲቲዎች አሸናፊነታቸውን ያረጋገጡት። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን አሸናፊነቱን ያረጋገጠው ሦስት ጨዋታዎች እየቀሩ ከማንችስር ዩናትድ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት10 በመሆኑ ነው። ማንችስተር ሲቲ የዘንድሮውን ጨምሮ በአጠቃላይ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሰባት ጊዜ አሸናፊ መሆን ችለዋል። ይህ ደግሞ በዘጠኝ ዓመት ውስጥ አምስተኛ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫቸው ነው። ''በጣም አስገራሚና ከሌሎች ጊዜዎች በጣም የተለየ ድል ነው'' ብሏል ጋርዲዮላ። ''የዘንድሮው በጣም ከባድ ነበር። መቼም ቢሆን የዘንድሮውን ድላችንን እናስታውሰዋለን። የዚህ ቡድን እና የነዚህ ተጫዋቾች አሰልጣኝ በመሆኔ በጣም ኩራት ይሰማኛል። . . . 'ከዚህ በፊት ስፔን አሰልጥኛለሁ፣ ጀርመንም አሰልጥኛለሁ፤ ነገር ግን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በጣም ከባዱ ነው'' ብሏል ጋርዲዮላ። 50ኛ ዓመቱን የደፈነው ፔፕ ጋርዲዮላ በአውሮፓውያኑ 2016 የጀርመኑን ባየርን ሙኒክ ለቆ ነበር ወደ እንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ የመጣው። በእነዚህ ስምንት ዓመታት ደግሞ 8 ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል። ሲቲዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ የነበራቸውን ጨዋታ አሸንፈው ቢሆን ቀደም ብለው ዋንጫውን ማንሳተቸውን ማረጋገጥ ይችሉ የነበረ ቢሆንም በቼልሲ ሁለት ለአንድ ተሸንፈዋል። ማንችስተር ሲቲዎች ከሳምንታት በፊት በካራባዎ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ቶተንሀምን በማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳት የቻሉ ሲሆን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ደግሞ ከቼልሲ ጋር ይገናኛሉ። ሲቲዎች በሚቀጥለው ሳምንት ከኤቨርተን ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ የሚያነሱ ሲሆን በአዲሱ መመሪያ መሰረት ደግሞ እስከ 10 ሺ የሚደርሱ ደጋፊዎች ገብተው ጨዋታውንና ስነ-ስርአቱን መከታተል ይችላሉ። የማንችስተር ሲቲ አምበል ብራዚላዊው ፈርናንዲንሆነ ቡድኑን መምራት 'ትልቅ ክብር' እንደነበር ገልጿል። ''ይህን ዋንጫ በማንሳታችን በጣም ኮርቻለሁ፤ በጣም ተደስቻለሁ። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከዓለማችን በጣም ከባዱ ሊግ ነው። እያንዳንዱ ጨዋታ በጣም ከባድ ነው። ዋንጫውን ማንሳታችን ለእኔም ሆነ ለመላው ቡድኑ ትልቅ ስኬት ነው'' ብሏል። ሲቲን በቅርብ ርቀት ሲከታተል የነበረው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኙ ሶልሻየር በበኩሉ "የውድድር ዓመቱ ሊጠናቀቅ 10 እና 12 ቀናት እስከሚቀሩት ድረስ ተፎክረናል። ማንችስተር ሲቲ በጣም ምርጥ ቡድን ነበር'' ብሏል።
ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪምየር አሸናፊ ሆነ ማንችስተር ሲቲ በአራት ዓመታት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆኗል። ትናንት ምሽት በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ በሌስተር ሲቲ መሸነፉን ተከትሎ ነው ሲቲዎች አሸናፊነታቸውን ያረጋገጡት። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን አሸናፊነቱን ያረጋገጠው ሦስት ጨዋታዎች እየቀሩ ከማንችስር ዩናትድ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት10 በመሆኑ ነው። ማንችስተር ሲቲ የዘንድሮውን ጨምሮ በአጠቃላይ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሰባት ጊዜ አሸናፊ መሆን ችለዋል። ይህ ደግሞ በዘጠኝ ዓመት ውስጥ አምስተኛ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫቸው ነው። ''በጣም አስገራሚና ከሌሎች ጊዜዎች በጣም የተለየ ድል ነው'' ብሏል ጋርዲዮላ። ''የዘንድሮው በጣም ከባድ ነበር። መቼም ቢሆን የዘንድሮውን ድላችንን እናስታውሰዋለን። የዚህ ቡድን እና የነዚህ ተጫዋቾች አሰልጣኝ በመሆኔ በጣም ኩራት ይሰማኛል። . . . 'ከዚህ በፊት ስፔን አሰልጥኛለሁ፣ ጀርመንም አሰልጥኛለሁ፤ ነገር ግን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በጣም ከባዱ ነው'' ብሏል ጋርዲዮላ። 50ኛ ዓመቱን የደፈነው ፔፕ ጋርዲዮላ በአውሮፓውያኑ 2016 የጀርመኑን ባየርን ሙኒክ ለቆ ነበር ወደ እንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ የመጣው። በእነዚህ ስምንት ዓመታት ደግሞ 8 ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል። ሲቲዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ የነበራቸውን ጨዋታ አሸንፈው ቢሆን ቀደም ብለው ዋንጫውን ማንሳተቸውን ማረጋገጥ ይችሉ የነበረ ቢሆንም በቼልሲ ሁለት ለአንድ ተሸንፈዋል። ማንችስተር ሲቲዎች ከሳምንታት በፊት በካራባዎ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ቶተንሀምን በማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳት የቻሉ ሲሆን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ደግሞ ከቼልሲ ጋር ይገናኛሉ። ሲቲዎች በሚቀጥለው ሳምንት ከኤቨርተን ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ የሚያነሱ ሲሆን በአዲሱ መመሪያ መሰረት ደግሞ እስከ 10 ሺ የሚደርሱ ደጋፊዎች ገብተው ጨዋታውንና ስነ-ስርአቱን መከታተል ይችላሉ። የማንችስተር ሲቲ አምበል ብራዚላዊው ፈርናንዲንሆነ ቡድኑን መምራት 'ትልቅ ክብር' እንደነበር ገልጿል። ''ይህን ዋንጫ በማንሳታችን በጣም ኮርቻለሁ፤ በጣም ተደስቻለሁ። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከዓለማችን በጣም ከባዱ ሊግ ነው። እያንዳንዱ ጨዋታ በጣም ከባድ ነው። ዋንጫውን ማንሳታችን ለእኔም ሆነ ለመላው ቡድኑ ትልቅ ስኬት ነው'' ብሏል። ሲቲን በቅርብ ርቀት ሲከታተል የነበረው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኙ ሶልሻየር በበኩሉ "የውድድር ዓመቱ ሊጠናቀቅ 10 እና 12 ቀናት እስከሚቀሩት ድረስ ተፎክረናል። ማንችስተር ሲቲ በጣም ምርጥ ቡድን ነበር'' ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/57084282
2health
የታንዛኒያው ፕሬዝደንት የኮቪድ-19 ክትባት ለታንዛኒያውያን አያስፈልግም አሉ
የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ የአገሪቱ ጤና ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመጠቀም ከመወሰናቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው አሉ። ማጉፉሊ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ የኮቪድ-19 ክትባት ሕዝቡን ሊጎዳ ይችላል ብለዋል። "የጤና ሚንስቴር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ጥናቶችን ሳያከናውኑ እነዚህን ክትባቶች ለመሞከር መፍጠን የለባቸውም። ሁሉም ክትባት ለእኛ ጠቃሚ አይደሉም፤ መጠንቀቅ አለብን። መሞከሪያ መሆን የለብንም" ሲሉ ማጉፉሊ ተናግረዋል። "ክትባቶች አደገኛ ናቸው። ነጩ ሰውዬ ክትባት አገኘሁ ካለ፤ ለኤድስ፣ ለካንሰር እና ለቲቢ እስካሁን ክትባት ሊኖረው ይገባል።" ፕሬዝደንቱ ይህን ይበሉ እንጂ የኮቪድ-19 ክትባቶች ለሰው ልጆች እንዲሰጡ የተፈቀደው በርካታ ምርመሮች እና ሙከራዎች ከተከናወነባቸው በኋላ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተሞክረው፣ ደህንነታቸው ተረጋግጦ፣ በመድሃኒት ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ በማግኘታቸው ነው ለሰዎች እየተሰጡ ያሉት በማለት የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ፊሊፓ ሮክስቢይ ትናገራለች። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ግን ዜጎቻቸውን ይህን ክትባት ከመውሰዳቸው በፊት ጥንቃቄ አድርጉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከክትባት ይልቅ ጸሎት ማድረግ እና ለባህላዊ መድሃኒት ቅድሚያ መስጠት የተሻለ አማራጭ ነው ሲሉ ታንዛኒያውያንን መክረዋል። "በርካታ አገራት የእንቅስቃሴ ገደቦችን አስተዋውቀዋል። በታንዛኒያ ግን የሰዎችን እንቅስቃሴ የመገደብ እቅድ የለንም። ፈጣሪያችን በሕይወት አለ፤ እርሱ ይጠብቀናል" ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ከወራት በፊት ታንዛኒያ ከኮቪድ-19 ነጻ ሆናለች ብለው ያወጁ ሲሆን፤ በከተሞች አከባቢ ስለጨመረው የሰዎች ሞት ቁጥር ላይ ግን ያሉት ነገር የለም። ማጉፉሊ አባል የሆኑበት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ግን፤ ታንዛኒያ መጀመሪያ ላይ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ቢቻላትም አሁን ላይ ግን የቫይረሱ ስርጭት እንደ አዲስ መስፋፋቱን አስታውቋል። የታንዛኒያ ጤና ሚንስቴር በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ፣ የሚሞቱ እና የሚያገግሙ ሰዎች አሃዝን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ካቆመ ወራቶች አልፈዋል።
የታንዛኒያው ፕሬዝደንት የኮቪድ-19 ክትባት ለታንዛኒያውያን አያስፈልግም አሉ የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ የአገሪቱ ጤና ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመጠቀም ከመወሰናቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው አሉ። ማጉፉሊ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ የኮቪድ-19 ክትባት ሕዝቡን ሊጎዳ ይችላል ብለዋል። "የጤና ሚንስቴር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ጥናቶችን ሳያከናውኑ እነዚህን ክትባቶች ለመሞከር መፍጠን የለባቸውም። ሁሉም ክትባት ለእኛ ጠቃሚ አይደሉም፤ መጠንቀቅ አለብን። መሞከሪያ መሆን የለብንም" ሲሉ ማጉፉሊ ተናግረዋል። "ክትባቶች አደገኛ ናቸው። ነጩ ሰውዬ ክትባት አገኘሁ ካለ፤ ለኤድስ፣ ለካንሰር እና ለቲቢ እስካሁን ክትባት ሊኖረው ይገባል።" ፕሬዝደንቱ ይህን ይበሉ እንጂ የኮቪድ-19 ክትባቶች ለሰው ልጆች እንዲሰጡ የተፈቀደው በርካታ ምርመሮች እና ሙከራዎች ከተከናወነባቸው በኋላ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተሞክረው፣ ደህንነታቸው ተረጋግጦ፣ በመድሃኒት ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ በማግኘታቸው ነው ለሰዎች እየተሰጡ ያሉት በማለት የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ፊሊፓ ሮክስቢይ ትናገራለች። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ግን ዜጎቻቸውን ይህን ክትባት ከመውሰዳቸው በፊት ጥንቃቄ አድርጉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከክትባት ይልቅ ጸሎት ማድረግ እና ለባህላዊ መድሃኒት ቅድሚያ መስጠት የተሻለ አማራጭ ነው ሲሉ ታንዛኒያውያንን መክረዋል። "በርካታ አገራት የእንቅስቃሴ ገደቦችን አስተዋውቀዋል። በታንዛኒያ ግን የሰዎችን እንቅስቃሴ የመገደብ እቅድ የለንም። ፈጣሪያችን በሕይወት አለ፤ እርሱ ይጠብቀናል" ሲሉ ተደምጠዋል። ፕሬዝደንት ማጉፉሊ ከወራት በፊት ታንዛኒያ ከኮቪድ-19 ነጻ ሆናለች ብለው ያወጁ ሲሆን፤ በከተሞች አከባቢ ስለጨመረው የሰዎች ሞት ቁጥር ላይ ግን ያሉት ነገር የለም። ማጉፉሊ አባል የሆኑበት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ግን፤ ታንዛኒያ መጀመሪያ ላይ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ቢቻላትም አሁን ላይ ግን የቫይረሱ ስርጭት እንደ አዲስ መስፋፋቱን አስታውቋል። የታንዛኒያ ጤና ሚንስቴር በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ፣ የሚሞቱ እና የሚያገግሙ ሰዎች አሃዝን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ካቆመ ወራቶች አልፈዋል።
https://www.bbc.com/amharic/55825410
5sports
ስኮትላንድ እግር ኳስ ተጫዋቾች ‘የቴስታ’ ኳሶችን እንዳይመቱ ልታግድ ነው
በስኮትላንድ ያሉ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ከጨዋታ አንድ ቀን በፊት እና በኋላ ኳስ በጭንቅላት (በቴስታ) እንዳይመቱ ሊታገዱ ነው። ክለቦችም የጭንቃላት ኳስ የሚበዛባቸው የልምምድ ቀኖችን በሳምንት ወደ አንድ እንዲቀንሱ ተጠይቀዋል። ውሳኔው የግላስጎው ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ጥናት እግር ኳስ ተጫዋቾች ከሦስት እጥፍ በላይ ከጭንቅላት ጋር በተያያዘ በሽታ እንደሚሞቱ ማሳየቱን ተከትሎ የመጣ ነው። ባለሙያዎች ችግሩ ኳስን በተደጋጋገሚ በጭንቅላት ከመምታት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ጠቁመዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማኅበር ከ12 ዓመት በታች ቡድኖች በልምምድ ወቅት ኳስ በጭንቅላት እንዳይመቱ የሚያግድ ሕግ አለው። አዲሱ ሕግ በአገሪቱ ካሉ 50 የወንዶች እና የሴቶች የእግር ኳስ ክለቦች ጋር ውይይት በማድረግ እና የእግር ኳስ ማኅበሩ በጭንቅላት ኳስ ዙሪያ መረጃ ከሰበሰበ በኋላ ይተገበራል ተብሏል። ክለቦችም በልምምድ ወቅት የጭንቅላት ኳሶችን ሁኔታ በድንብ እንዲያጤኑ ተነግሯቸዋል። ዶክተር ጆን ማሊን ከ20 ዓመታት በላይ የስኮትላንድ እግር ኳስ ማኅበር ሐኪም ሆነው አገልግለዋል። በ2019 በተካሄደው እና የቀድሞ ተጫዋቾችን ከዲሜንሺያ (የጭንቅላት ህመም ሲሆን ከመርሳት እና ከማንነት ለውጥ ጋር ይያያዛል) ጋር ባያያዘው ጥናት ተሳትፈዋል። “ጥናቶቹ እየተጠናከሩ ቢሆንም እስካሁን ባለው ከ24 እስከ 48 ሰዓታት የሚቆይ የመርሳት ችግርን ያስከትላል። ኳስ በጭንቅላት ከተመታ በኋላ የአዕምሮ ፕሮቲኖች በደም ናሙና ውስጥ ተገኝተዋል።” “የጭንቅላት ኳስ የሚመቱ ተጫዋቾች የአዕምሮ ስካን ላይ ለውጥም ታይቷል። ስለዚህ ዋና ዓላማው በልምምድ ቦታ የጭንቅላት ኳሶችን በመቀነስ በጊዜ ሂደት የሚመጣውን ጉዳት መቀነስ ነው” ብለዋል። በአዲሱ ሕግ መሠረት ከጨዋታ በፊት የሚኖሩ የቅጣት ምትን ጨምሮ የጭንቅላት ኳስን የሚያካትቱ ልምምዶች ላይ ለውጥ ያመጣል። “ባለድርሻ አካላትን ለማካተት በሚል ጊዜ ወስደናል” ብለዋል ዶ/ር ማክሊን። “መሠረታዊ መረጃ ለማግኘት በልምምድ ወቅት ምን ያህል የጭንቅላት ኳስ እንደሚኖር ለማወቅ እንፈልጋለን።” “በቀመጠልም ከማኅበሩ፣ ከክለቦች እና ከአሰልጣኞች ጋር በመሆን ተጫዋቾችን እናሳትፋለን” ብለዋል። “ይህ የጋራ ኃላፊነት ሲሆን የተጫዋቾችንም ጤና ለመጠበቅ ያለመ ነው” ሲሉ አስረድተዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማኅበር ዋና ኃላፊ አንዲ ጎልድ እንዳሉት በጨዋታ ወቅት ስላለው የጭንቅላት ኳስ በቂ መረጃ አለ። የቅርብ ጊዜው ምርምር ግን “በልምምድ ወቅት የጭንቅላት ላይ ያለውን ጫና ለመረዳት በጣም ጠቃሚ ነው” ብለዋል። አክለውም “ለተጫዋቾቻን ጤና ሲባል በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውይይት ለማመቻቸት የሚያስፈልጉ መረጃዎችን እና አመለካከቶችን ስለሰጡን ክለቦችን፣ አሰልጣኞችን እና ተጫዋቾችን አመሰግናለሁ።” በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት መጀመሪያ ላይ የእንግሊዝ የእግር ኳስ ማኅበር በልምምድ ወቅት ተጫዋቾች በሳምንት 10 ከፍተኛ ተፅእኖ ያላቸውን የጭንቅላት ኳሶች ብቻ እንዲጠቀሙ የሚገድብ መመሪያ ለክለቦች አውጥቷል። የቀድሞ የሴልቲክ አምበል ቢሊ ማክኔል እና ከእንግሊዝ ጋር የዓለም ዋንጫን አነስቶ የነበረውና በኋላም የአየርላንድ ሪፐብሊክ አሰልጣኝ ለመሆን የቻለው ጃክ ቻርልተንን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በዲሜንሽያ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል።
ስኮትላንድ እግር ኳስ ተጫዋቾች ‘የቴስታ’ ኳሶችን እንዳይመቱ ልታግድ ነው በስኮትላንድ ያሉ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ከጨዋታ አንድ ቀን በፊት እና በኋላ ኳስ በጭንቅላት (በቴስታ) እንዳይመቱ ሊታገዱ ነው። ክለቦችም የጭንቃላት ኳስ የሚበዛባቸው የልምምድ ቀኖችን በሳምንት ወደ አንድ እንዲቀንሱ ተጠይቀዋል። ውሳኔው የግላስጎው ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ጥናት እግር ኳስ ተጫዋቾች ከሦስት እጥፍ በላይ ከጭንቅላት ጋር በተያያዘ በሽታ እንደሚሞቱ ማሳየቱን ተከትሎ የመጣ ነው። ባለሙያዎች ችግሩ ኳስን በተደጋጋገሚ በጭንቅላት ከመምታት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ጠቁመዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማኅበር ከ12 ዓመት በታች ቡድኖች በልምምድ ወቅት ኳስ በጭንቅላት እንዳይመቱ የሚያግድ ሕግ አለው። አዲሱ ሕግ በአገሪቱ ካሉ 50 የወንዶች እና የሴቶች የእግር ኳስ ክለቦች ጋር ውይይት በማድረግ እና የእግር ኳስ ማኅበሩ በጭንቅላት ኳስ ዙሪያ መረጃ ከሰበሰበ በኋላ ይተገበራል ተብሏል። ክለቦችም በልምምድ ወቅት የጭንቅላት ኳሶችን ሁኔታ በድንብ እንዲያጤኑ ተነግሯቸዋል። ዶክተር ጆን ማሊን ከ20 ዓመታት በላይ የስኮትላንድ እግር ኳስ ማኅበር ሐኪም ሆነው አገልግለዋል። በ2019 በተካሄደው እና የቀድሞ ተጫዋቾችን ከዲሜንሺያ (የጭንቅላት ህመም ሲሆን ከመርሳት እና ከማንነት ለውጥ ጋር ይያያዛል) ጋር ባያያዘው ጥናት ተሳትፈዋል። “ጥናቶቹ እየተጠናከሩ ቢሆንም እስካሁን ባለው ከ24 እስከ 48 ሰዓታት የሚቆይ የመርሳት ችግርን ያስከትላል። ኳስ በጭንቅላት ከተመታ በኋላ የአዕምሮ ፕሮቲኖች በደም ናሙና ውስጥ ተገኝተዋል።” “የጭንቅላት ኳስ የሚመቱ ተጫዋቾች የአዕምሮ ስካን ላይ ለውጥም ታይቷል። ስለዚህ ዋና ዓላማው በልምምድ ቦታ የጭንቅላት ኳሶችን በመቀነስ በጊዜ ሂደት የሚመጣውን ጉዳት መቀነስ ነው” ብለዋል። በአዲሱ ሕግ መሠረት ከጨዋታ በፊት የሚኖሩ የቅጣት ምትን ጨምሮ የጭንቅላት ኳስን የሚያካትቱ ልምምዶች ላይ ለውጥ ያመጣል። “ባለድርሻ አካላትን ለማካተት በሚል ጊዜ ወስደናል” ብለዋል ዶ/ር ማክሊን። “መሠረታዊ መረጃ ለማግኘት በልምምድ ወቅት ምን ያህል የጭንቅላት ኳስ እንደሚኖር ለማወቅ እንፈልጋለን።” “በቀመጠልም ከማኅበሩ፣ ከክለቦች እና ከአሰልጣኞች ጋር በመሆን ተጫዋቾችን እናሳትፋለን” ብለዋል። “ይህ የጋራ ኃላፊነት ሲሆን የተጫዋቾችንም ጤና ለመጠበቅ ያለመ ነው” ሲሉ አስረድተዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማኅበር ዋና ኃላፊ አንዲ ጎልድ እንዳሉት በጨዋታ ወቅት ስላለው የጭንቅላት ኳስ በቂ መረጃ አለ። የቅርብ ጊዜው ምርምር ግን “በልምምድ ወቅት የጭንቅላት ላይ ያለውን ጫና ለመረዳት በጣም ጠቃሚ ነው” ብለዋል። አክለውም “ለተጫዋቾቻን ጤና ሲባል በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውይይት ለማመቻቸት የሚያስፈልጉ መረጃዎችን እና አመለካከቶችን ስለሰጡን ክለቦችን፣ አሰልጣኞችን እና ተጫዋቾችን አመሰግናለሁ።” በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት መጀመሪያ ላይ የእንግሊዝ የእግር ኳስ ማኅበር በልምምድ ወቅት ተጫዋቾች በሳምንት 10 ከፍተኛ ተፅእኖ ያላቸውን የጭንቅላት ኳሶች ብቻ እንዲጠቀሙ የሚገድብ መመሪያ ለክለቦች አውጥቷል። የቀድሞ የሴልቲክ አምበል ቢሊ ማክኔል እና ከእንግሊዝ ጋር የዓለም ዋንጫን አነስቶ የነበረውና በኋላም የአየርላንድ ሪፐብሊክ አሰልጣኝ ለመሆን የቻለው ጃክ ቻርልተንን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በዲሜንሽያ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0jy82pyl2o
3politics
ሩሲያ በዩክሬን ላይ 'መጠነ ሰፊ ጥቃት ልትፈፅም' እንደምትችል አሜሪካ አስታወቀች
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ከፍተኛ ውጥረት የነገሰባት ዩክሬንን በተመለከተ በመጪው ማክሰኞ በቪዲዮ እንደሚነጋገሩ ዋይት ሃውስ አስታውቋል። ከሰሞኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሩሲያ በዩክሬን ላይ "መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመፈጸም" እቅድ እንዳወጣች የሚያሳይ ማስረጃ አገራቸው እንዳገኘች ገልጸዋል። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ግልጽ አይደለም ሲሉም አክለዋል። ሩሲያ በበኩሏ የማጥቃትም ሆነ የመውረር ሃሳብን ውድቅ አድርጋ ዩክሬን ሰራዊቷን በከፍተኛ ሁኔታ እያጠናከረች ነው ስትል ከሳታለች። የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ጄን ፓሳኪ ቅዳሜ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ፕሬዚዳንት ባይደን "ሩሲያንና ዩክሬንን በሚያዋስነው ድንበር ላይ ሩሲያ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ አሜሪካ ያላትን ስጋት እንዲሁም አሜሪካ ለዩክሬን ሉዓላዊነትና ግዛታዊ አንድነት የምታደርገውን ድጋፍ" በተመለከተ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ጋር በሚያደርጉት የስልክ ልውውጥ ያነሳሉ ብለዋል። ዩክሬን በበኩሏ ሃገራቱ በሚዋሰኑበት ድንበር ላይ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች፣ የኤሌክትሮኒክ የጦር መሳሪያዎችን እና 94 ሺህ ወታደሮችን ሩሲያ ማሰማራቷን ገልጻለች። በአውሮፓውያኑ 2014 ሩሲያ የክሪሚያን ግዛት ከዩክሬን ከወሰደች በኋላ ከፍተኛ የጦር መሳሪያና ወታደር በጋራ ድንበሩ ላይ ስታሰማራ የመጀመሪያው ነው። የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲይ ሬዝኒኮቭ የደህንነት ዘገባዎችን በመጥቀስ ሩሲያ በጥር ወር መጨረሻ ወታደራዊ ጥቃትን ልትፈፅም እንደምትችል ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ያለው የሩስያ ጦር እንቅስቃሴ በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ቀደም ሲል ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት የበለጠ ውጥረት እንዲነግስ አድርጎታል። በያዝነው ሳምንት አርብ ዕለት ፕሬዚዳንት ባይደን "በርካቶችን እያስጨነቀ ያለውንና ሊያደርግ ይችላል ብለው እየጠበቁት" ያለውን ጉዳይ "አስቸጋሪ፣ በጣም ፈታኝ እንዲሆን አደርገዋለሁ" ሲሉ ፑቲንን አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ ጠንከር ያለ እርምጃ ከወሰደች አሜሪካ እና የአውሮፓ አጋሮቿ ማዕቀብ ለመጣል ተወያይተዋል። ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ባትሆንም ከህብረቱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላት እና የአሜሪካ ጄቭሊን ፀረ ታንክ ሚሳኤሎችን ጨምሮ ከምዕራባውያን በርካታ የጦር መሳሪያዎች ድጋፎችን ታገኛለች።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ 'መጠነ ሰፊ ጥቃት ልትፈፅም' እንደምትችል አሜሪካ አስታወቀች የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ከፍተኛ ውጥረት የነገሰባት ዩክሬንን በተመለከተ በመጪው ማክሰኞ በቪዲዮ እንደሚነጋገሩ ዋይት ሃውስ አስታውቋል። ከሰሞኑ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሩሲያ በዩክሬን ላይ "መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመፈጸም" እቅድ እንዳወጣች የሚያሳይ ማስረጃ አገራቸው እንዳገኘች ገልጸዋል። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ግልጽ አይደለም ሲሉም አክለዋል። ሩሲያ በበኩሏ የማጥቃትም ሆነ የመውረር ሃሳብን ውድቅ አድርጋ ዩክሬን ሰራዊቷን በከፍተኛ ሁኔታ እያጠናከረች ነው ስትል ከሳታለች። የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ጄን ፓሳኪ ቅዳሜ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ፕሬዚዳንት ባይደን "ሩሲያንና ዩክሬንን በሚያዋስነው ድንበር ላይ ሩሲያ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ አሜሪካ ያላትን ስጋት እንዲሁም አሜሪካ ለዩክሬን ሉዓላዊነትና ግዛታዊ አንድነት የምታደርገውን ድጋፍ" በተመለከተ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ጋር በሚያደርጉት የስልክ ልውውጥ ያነሳሉ ብለዋል። ዩክሬን በበኩሏ ሃገራቱ በሚዋሰኑበት ድንበር ላይ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች፣ የኤሌክትሮኒክ የጦር መሳሪያዎችን እና 94 ሺህ ወታደሮችን ሩሲያ ማሰማራቷን ገልጻለች። በአውሮፓውያኑ 2014 ሩሲያ የክሪሚያን ግዛት ከዩክሬን ከወሰደች በኋላ ከፍተኛ የጦር መሳሪያና ወታደር በጋራ ድንበሩ ላይ ስታሰማራ የመጀመሪያው ነው። የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲይ ሬዝኒኮቭ የደህንነት ዘገባዎችን በመጥቀስ ሩሲያ በጥር ወር መጨረሻ ወታደራዊ ጥቃትን ልትፈፅም እንደምትችል ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ያለው የሩስያ ጦር እንቅስቃሴ በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ቀደም ሲል ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት የበለጠ ውጥረት እንዲነግስ አድርጎታል። በያዝነው ሳምንት አርብ ዕለት ፕሬዚዳንት ባይደን "በርካቶችን እያስጨነቀ ያለውንና ሊያደርግ ይችላል ብለው እየጠበቁት" ያለውን ጉዳይ "አስቸጋሪ፣ በጣም ፈታኝ እንዲሆን አደርገዋለሁ" ሲሉ ፑቲንን አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ ጠንከር ያለ እርምጃ ከወሰደች አሜሪካ እና የአውሮፓ አጋሮቿ ማዕቀብ ለመጣል ተወያይተዋል። ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ባትሆንም ከህብረቱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላት እና የአሜሪካ ጄቭሊን ፀረ ታንክ ሚሳኤሎችን ጨምሮ ከምዕራባውያን በርካታ የጦር መሳሪያዎች ድጋፎችን ታገኛለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-59537669
2health
ለህሙማን ሌላ ህመም የሆነባቸው የመንግሥት ጤና ተቋማት ዋጋ ጭማሪ
ሠላማዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። እናቷ ባለባቸው ህመም ምክንያት በየጊዜው ሐኪም ቤት ይመላለሳሉ። ሁሌም እንደምታደርገው እናቷ ላለባቸው ቀጠሮ በቅርቧ ወደሚገኘው ጤና ጣቢያ ይዛቸው ታቀናለች። ጤና ጣቢያውን ከቅርበቱም በላይ በዋጋውም ተመራጭ ነው። ስትደርስ የገጠማት ግን ከከዚህ በፊቱ የተለየ ነው። ዋጋው አይቀመስም። ካላቸው አቅም አንጻር ያልጠበቁትም ነው። "5 ብር የነበረው የካርድ ዋጋ 50 ብር ደርሷል።" "ካርድ ብቻም አይደለም። ሁሉም የአገልግሎቶች ዋጋ ጨምሯል" ትላለች ሠላማዊት። ህክምና ላይ ያለው ምርጫ ደግሞ አንድ ብቻ ነው፤ መታከም። ሠላማዊትም ወደ ግል የጤና ተቋም እንዳትሄድ ዋጋው ከዚህም ይብሳል። "ያለኝ አማራጭ ስልክ ደውዬ ተጨማሪ ብር በብድር እንዲያመጡልኝ ማድረግ ነው" ትላለች። ነጻ የነበሩ አገልግሎቶችም ዋጋ ተቆርጦላቸዋል። የመንግሥት የህክምና ተቋማት ዋጋ መናር አዲስ አበባ ላይ ብቻ አልታጠረም። ዶክተር ሱራፌል አየለ ይባላሉ። የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ሐኪም ናቸው። በሆስፒታሉ የአገልግሎት እና የህክምና ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ይላሉ። 'ትዕዛዙ ከፌዴራል የመጣ ነው' ያሉት ጭማሪ 'አስገራሚ' መሆኑን ለቢቢሲ አስረድተዋል። "ካርድ ማውጫ 5 ብር ነበር፣ አሁን 60 ብር ነው። ተኝቶ ለመታከም የአልጋ ክፍያ በቀን ከ10 ብር ወደ 180 ብር አድጓል። የላብራቶሪ እና ሌሎች ወጪዎችም በተመሳሳይ ጨምሯል" ብለዋል። እንደ ዶ/ር ሱራፌል ከሆነ ከዚህ ቀደም ነጻ የነበሩ አገልግሎቶችም ዋጋ ተቆርጦላቸዋል። "በነጻ ተኝተው ይታከሙ የነበሩ የምግብ እጥረት ያለባቸው ታካሚዎች (SAM Patients) አሁን ከሌላው እኩል ለአልጋ 180 ብር እየከፈሉ ነው። ልጁ በድህነቱ ምክንያት ምግብ አጥቶ የቀጨጨበት ወላጅም በቀን 180 ብር እንዲከፍል ይደረጋል" ይላሉ። ቢቢሲ ከተለያዩ ምንጮች ባደረገው ማጣራት በመንግሥት የህክምና ተቋማት የሚሰጡ ዋጋዎች ጭማሪ የተለያየ መሆኑን አረጋግጧል። ትኩረቱን በህክምና ባለሙያዎች ላይ ባደረገው ሐኪም በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ሐሳባቸውን ያሰፈሩት የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ዮናስ ላቀው 'የአማኑኤል ሆስፒታል የዋጋ ጭማሪ' በሚል ርዕስ የሚከተለውን አስቀምጠዋል። "በፊት የካርድ 5 ብር የነበረው 50 ብር ሆኗል። ለተኝቶ ህክምና ማስያዣ 400 ብር የነበረው 9,000 ብር ሆኗል። ለአልጋ በቀን 3 ብር የነበረው 118 ብር ሆኗል።" ከአዲስ አበባ የአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወደ ደግሞ ወራቤ እናቅና። ዶ/ር ፈድሉ ጀንፋ በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም ናቸው። እርሳቸው በሚሠሩበት ሆስፒታሉም በተመሳሳይ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ይገልጻሉ። የዋጋ ጭማሪው በተለያዩ ደረጃ የሚገለጽ መሆኑን ጠቁመው ለምሳሌ "የአልትራሳውንድ ዋጋ ከ150 ብር ወደ 300 ብር ከፍ ብሏል። ተኝቶ ታካሚዎች በቀን ለአልጋ ይከፍሉት የነበረው 47 ብር አሁን ወደ 170 ብር ከፍ ብሏል" ይላሉ። የዋጋ ጭማሪው ሁሉንም አይመለከትም ይህንን የዋጋ ክለሳ ያደረገው ጤና ጥበቃ ሚንስትር መሆኑን የሚገልጹት ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ የኢትዮጵያ ጤና መድኅን ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ናቸው። "ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው ዋጋ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ እና ከቆይታ፣ ከዋጋና ከብር የመግዛት አቅም አንጻር መስተካከል እንደነበረበት ይጠበቃል" ብለዋል። በተጨማሪም [በመንግሥት የጤና ተቋማት ላይ] አገልግሎት ላይ የሚቀርብ ቅሬታ አለ። "ቅሬታውን ለመፍታት ደግሞ ሃብት ያስፈልጋል" ይላሉ ወይዘሮ ፍሬይህይወት። "በነበረው አሠራር ለህክምናው ዘርፍ ከሚወጣው ወጪ 60 ወይንም 70 በመቶ የሚሆነው በመንግሥት ነበር የሚሸፈነው። ቀሪው ነው በኅብረተሰቡ" ብለዋል። የዋጋ ጭማሪው በጤና መድኅን ስር የታቀፉትን አይመለከትም። ዶ/ር ዮናስ ላቀው "ይህ ለውጥ የጤና ሚኒስትር በደነገገው መመሪያ መሠረት ነው። የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ያላቸው ታካሚዎች አሁንም በነጻ አገልግሎት ያገኛሉ። የሌላቸው ግን አገልግሎት ለማግኘት ክፍያ መፈፀም ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል። በዚህ ምክንያት ህክምና ማግኘት የሚገባቸው ሰዎች እያገኙ አይደለም። "የህሙማን ቁጥር መቀነስ እንዳለ ጠቅላላ ሐኪሞች (ጀነራል ፕራክቲሽነርስ) ይነግሩናል። ሆስፒታል ገብተው በመተኛት መታከም የሚገባቸው በገንዘቡ ምክንያት አልገቡም እንደሚባል ሰምቻለሁ" ያሉት ዶ/ር ፈድሉ ናቸው። የታካሚዎች ቁጥር በመቀነሱ የሚስማሙት ዶ/ር ሱራፌል "[ዋጋውን ሲያውቁ] በር ላይ ደርሰው ይመለሳሉ። አሁን አብዛኛዎቹ ታካሚዎች በዋጋ ጭማሪው ምክንያት እየተቸገሩ፣ ህክምና አቋርጠው ለመውጣት እየተገደዱ፣ አስፈላጊ መድሃኒቶችን ለመግዛት እና ምርመራዎችን ለማድረግ እየተቸገሩ ሲሆን የጤና መድኅን ተጠቃሚ የሆኑ ታካሚዎች ግን ያለ ምንም ችግር እየታከሙ ይገኛል" ብለዋል። በጤና መድኅን እጦት ምክንያት ወደ ህክምና ተቋማት የሚመጣ ሰው በመቅረቱ ወይም በክፍያው ምክንያት ተገቢውን ህክምና ባለማግኘቱ ህይወት ልናጣ እንችላለን ሲሉ ሃሳቡን የሚደግፉት ዶ/ር ፈድሉ ናቸው። የጤና መድኅን ያላቸውም በፈለጉት ቦታ መታከም አልቻሉም ሌላው በህክምና ባለሙያዎች የተነሳው አሠራሩ ሊተገበር ስለመሆኑ ቀደም ተብሎ ለኅብረተሰቡ ማሳወቅ እና ዝግጅት እንዲኖር መደረግ ነበረበት የሚል ነው። አሠራሩን ተግባራዊ ከማድረግ በፊት ኅብረተሰቡ እንዲያውቅ እና እንዲዘጋጅ የስድስት ወር ቅድመ ዝግጅ ቢደረግበት የተሻለ ይሆን ነበር ይላሉ ዶ/ር ፈድሉ። ወ/ሮ ፍሬህይወት ግን ኅብረተሰቡን ዝግጁ የማድረግ ሥራ የእነርሱ መሥሪያ ቤት አለመሆኑን በመጥቀስ ይህ የሚመለከተው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መሆኑን ጠቁመዋል። ሌላው የተነሳው ችግር የጤና መድኅን ያላቸው ሰዎችም ቢሆኑ በሁሉም የመንግሥት የጤና ተቋማት ላይ መጠቀም አለመቻላቸው ነው። "ያለው ዞናዊ አሠራር ነው። [በኛ ዞን የወጣ የጤና መድኅን] የሚሠራው በእኛ ዞን ብቻ ነው። ከአጎራባች ዞን ለሚመጡት አገልግሎት አይሰጥም። ስለዚህ ለመክፈል ይገደዳሉ። በዞን ብቻ መሆን የለበትም በክልል ደረጃ ወይንም በአገር አቀፍ ደረጃ መሆን አለበት" ይላሉ ዶ/ር ፈድሉ። ተመሳሳይ ችግር እንዳስተዋሉ ዶ/ር ሱራፌልም ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ ታካሚ ጎንደር ላይ ማግኘት ያልቻለውን ህክምና ለማግኘት ወደ ባህርዳር ቢያቀና ባለው የጤና መድኅን የሚሸፈን ባለመሆኑ ለመክፈል ይገደዳል ብለዋል። ይህ ደግሞ የጤና መድኅኑም ቢሆን ለሁሉም ነጻ ህክምና አያስገኝም ማለት መሆኑን አስረድተዋል። የጤና መድኅኑ በሁሉም የጤና ተቋማት አገልግሎት እንደማያስገኝ የሚስማሙት ወ/ሮ ፍሬህይወት "አሁን ያለው አሠራር የሪፈራል ሰንሰለቱን ጠብቆ ነው የሚሄደው" ይላሉ። ይህም ማለት አንድ ታካሚ የጤና መድኅኑን ካገኘበት አካባቢ ካለ የጤና ተቋም በመሄድ ህክምና ያገኛል። ህክምናው ነጻ ነው። ህክምናው ከዚያ ተቋም በላይ ከሆነ ሪፈር ተጽፎለት ወደሚቀጥለው የጤና ተቋም ሄዶ መታከም ይችላል። በዚህ መልኩ ሲኬድም ህክምናው ነጻ ነው። ስለዚህ የሪፈር ሰንሰለቱን ይዞ እንጂ በራሱ መንገድ ሁሉም ጋር በመሄድ ነጻ መታከም አይችልም ማለት ነው። ይህን ለመፍታት የጤና ተቋማት ከብዙ የጤና ተቋማት ጋር ውል እንዲገቡ እና አብረው እንዲሠሩ ለማድረግ እየተሠራ እንደሚገኝ ወ/ሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል። የጤና መድኅኑ ምዝገባ በዲጂታላይዝ አለመሆኑንም በምክንያትነት አቅርበዋል። ምዝገባው ዲጂታላይዝ አለመሆኑ ታካሚዎች በተለያዩ የጤና ተቋማት ሄደው ለመታከም ካርዱን ሲጠቀሙ ለማመሳከር እንቅፋት መሆኑ ነው የችግሩ መነሻ። ለሁሉም ያልተዘጋጀ የጤና መድኅን ሌላው ችግር ደግሞ የጤና መድኅኑ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ያማከለ መሆኑ ነው። የመንግሥት ሠራተኞች እና የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ በጤና መድኅኑ የማይታቀፉ መኖራቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ሱራፌል እነዚህ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለችግሩ ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። የጤና መድኅኑ መደበኛ ባልሆነ የሥራ ዘርፍ የተሠማሩ እና ወር ጠብቀው ቋሚ ደመወዝ የማያገኙ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። "አሁን ተግባራዊ የተደረገው የጤና መድኅን መደበኛ ባልሆነ ሥራ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ እና ከ10 በታች በሚቀጥሩ የሥራ ዘርፎች እና ዝቅተኛ የኑሮ መጠን ላይ ያሉትን እንደሚያቅፍ" ወይዘሮ ፍሬህይወት አረጋግጠዋል። በቅርቡ ደግሞ ሌሎችንም ለማካተት የሚያስችል አሠራር በመዘርጋት ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ ችግሩ እንደሚፈታ ተናግረዋል። የጠየቅናቸው የህክምና ባለሙያዎች በዋጋ ጭማሪው ላይ ብዙም ቅሬታ ያላቸው አይመስሉም። የማይስማሙት በተጨመረው ዋጋ መጠን እና በተጨመረበት ጊዜ ላይ ነው። ካነሷቸው ችግሮች ጎን ለጎን "አጠቃላይ ሃሳቡ ኅብረተሰቡን ወደ ጤና መድኅን ለማስገባት ይመስላል። ምክንያቱም ከኪስ ተከፍሎ አይቻልም። ሁሉም ሰው በከፈለው ገንዘብ ይታከማል። የሴክተሩ ገንዘብም ይሻሻላል። ዕቅዱ እንደ ምዕራባውያኑ እና አሜሪካ ለማድረግ ነው። በአጠቃላይ አሠራሩን እደግፈዋለሁ። ዕቅዱ የጤና ሴክተሩን ለማሳደግ ነው። የጤናውን ዘርፍ ለማሳደግም ያለመ ነው" የሚሉት ዶ/ር ፈድሉ ናቸው። "ለምን በዚህ መጠን ዋጋ እንደጨመረ ለማወቅ ባደረኩት ጥረት ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ከመጠን ባነሰ ዋጋ አገልግሎት ሲሰጡ ስለነበር ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተዳረጉ እና አሁን የወጣው ዋጋ ግን ተገቢው ክፍያ እንደሆነ ነው። በተጨማሪም በገጠር የሚኖረው ማኅበረሰብ የጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማበረታታት ነው" ይላሉ ዶ/ር ሱራፌል። "ሌላው ጥያቄ የሆነብኝ ነገር 'ሆስፒታሎች ይህን የዋጋ ጭማሪ ሲያደርጉ የሚሰጠው አገልግሎት ጥራትና ፍጥነቱ ከድሮው በተለየ ይጨምራል ወይ?' የሚለው ነው። ይህን በሂደት የምናየው ይሆናል። የታካሚዎቻችን መቸገር እና መንገላታት ግን ለህክምናውም ለሃኪሙም ከባድ ራስ ምታት ነው። ተገቢው ትኩረት እና መፍትሄ ያስፈልገዋል" ብለዋል። የሠላማዊት እናት ህክምናቸውን ተከታትለው አገግመዋል። እሷም በቀጣዩ ቀን ዓመታዊ ክፍያ ፈጽማ የጤና መድኅን አባል ሆነዋል። በየጊዜው በእናቷ ምክንያት ሐኪም ቤት የምትመላለሰው ሠላማዊት አሁን "እፎይ ብያለሁ" ብላለች። 40 ሚሊዮን ሰዎች በጤና መድን ታቅፈዋል የጤና መድህን ማለት አንድ ቤተሰብ በአመት የተወሰነ ብር በመክፈል የቤተሰቡ አባል ሲታመም በነጻ አገልግሎት የሚያገኝበት መንገድ ነው።የጤና መድኅን የተጀመረው ኅብረተሰቡ ባልተጠበቀ ወጪ ወዳልታሰበ ድህነት እንዳይገባ ለማድረግ ነው ይላሉ ፍሬህይወት። መደበኛ ያልሆነ የሥራ ዘርፍ እና በወር ቋሚ ደመወዝ የማይከፈላቸው ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። አሠራሩ ተግባራዊ ከተደረገ 10 ዓመት ይሆነዋል። 40 ሚሊዮን ያህል አባላት እንዳሉትም ለማወቅ ተችሏል። ካሉት አባላቱ መካከል 24 በመቶ ከድህነት ወለል በታች በመሆናቸው (8 ሚሊዮን ያህሉ መሆኑ ነው) ወጪያቸውን የሚሸፈነው በመንግሥት ነው። እንደ የአካባቢው በሚለያይ ክፍያ በዓመት አንድ ጊዜ በሚደረግ ክፍያ አባል መሆን ይቻላል። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት አዲስ አበባ ላይ አንድ አባወራ በዓመት 350 ብር በመክፈል ይመዘገባል። የጥቅም ማዕቀፉም የልብ እና የአዕምሮ ህክምናን ጨምሮ እስከ አዲስ አበባ ድረስ በመንግሥት የህክምና ተቋማት የሚሰጥ ይሆናል። አሁን በጤና ጥበቃ በመንግሥት የጤና ተቋማት ላይ ተደረገውን ጭማሪን ተከትሎ የጤና መድኅኑ ዓመታዊ ክፍያ ላይ ክለሳ በማድረግ ጭማሪ ሊኖር አንደሚችልም ወ/ሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የጤና ጥበቃን ሃሳብ ለማካተት በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ለህሙማን ሌላ ህመም የሆነባቸው የመንግሥት ጤና ተቋማት ዋጋ ጭማሪ ሠላማዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። እናቷ ባለባቸው ህመም ምክንያት በየጊዜው ሐኪም ቤት ይመላለሳሉ። ሁሌም እንደምታደርገው እናቷ ላለባቸው ቀጠሮ በቅርቧ ወደሚገኘው ጤና ጣቢያ ይዛቸው ታቀናለች። ጤና ጣቢያውን ከቅርበቱም በላይ በዋጋውም ተመራጭ ነው። ስትደርስ የገጠማት ግን ከከዚህ በፊቱ የተለየ ነው። ዋጋው አይቀመስም። ካላቸው አቅም አንጻር ያልጠበቁትም ነው። "5 ብር የነበረው የካርድ ዋጋ 50 ብር ደርሷል።" "ካርድ ብቻም አይደለም። ሁሉም የአገልግሎቶች ዋጋ ጨምሯል" ትላለች ሠላማዊት። ህክምና ላይ ያለው ምርጫ ደግሞ አንድ ብቻ ነው፤ መታከም። ሠላማዊትም ወደ ግል የጤና ተቋም እንዳትሄድ ዋጋው ከዚህም ይብሳል። "ያለኝ አማራጭ ስልክ ደውዬ ተጨማሪ ብር በብድር እንዲያመጡልኝ ማድረግ ነው" ትላለች። ነጻ የነበሩ አገልግሎቶችም ዋጋ ተቆርጦላቸዋል። የመንግሥት የህክምና ተቋማት ዋጋ መናር አዲስ አበባ ላይ ብቻ አልታጠረም። ዶክተር ሱራፌል አየለ ይባላሉ። የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ሐኪም ናቸው። በሆስፒታሉ የአገልግሎት እና የህክምና ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ይላሉ። 'ትዕዛዙ ከፌዴራል የመጣ ነው' ያሉት ጭማሪ 'አስገራሚ' መሆኑን ለቢቢሲ አስረድተዋል። "ካርድ ማውጫ 5 ብር ነበር፣ አሁን 60 ብር ነው። ተኝቶ ለመታከም የአልጋ ክፍያ በቀን ከ10 ብር ወደ 180 ብር አድጓል። የላብራቶሪ እና ሌሎች ወጪዎችም በተመሳሳይ ጨምሯል" ብለዋል። እንደ ዶ/ር ሱራፌል ከሆነ ከዚህ ቀደም ነጻ የነበሩ አገልግሎቶችም ዋጋ ተቆርጦላቸዋል። "በነጻ ተኝተው ይታከሙ የነበሩ የምግብ እጥረት ያለባቸው ታካሚዎች (SAM Patients) አሁን ከሌላው እኩል ለአልጋ 180 ብር እየከፈሉ ነው። ልጁ በድህነቱ ምክንያት ምግብ አጥቶ የቀጨጨበት ወላጅም በቀን 180 ብር እንዲከፍል ይደረጋል" ይላሉ። ቢቢሲ ከተለያዩ ምንጮች ባደረገው ማጣራት በመንግሥት የህክምና ተቋማት የሚሰጡ ዋጋዎች ጭማሪ የተለያየ መሆኑን አረጋግጧል። ትኩረቱን በህክምና ባለሙያዎች ላይ ባደረገው ሐኪም በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ሐሳባቸውን ያሰፈሩት የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ዮናስ ላቀው 'የአማኑኤል ሆስፒታል የዋጋ ጭማሪ' በሚል ርዕስ የሚከተለውን አስቀምጠዋል። "በፊት የካርድ 5 ብር የነበረው 50 ብር ሆኗል። ለተኝቶ ህክምና ማስያዣ 400 ብር የነበረው 9,000 ብር ሆኗል። ለአልጋ በቀን 3 ብር የነበረው 118 ብር ሆኗል።" ከአዲስ አበባ የአማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወደ ደግሞ ወራቤ እናቅና። ዶ/ር ፈድሉ ጀንፋ በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም ናቸው። እርሳቸው በሚሠሩበት ሆስፒታሉም በተመሳሳይ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ይገልጻሉ። የዋጋ ጭማሪው በተለያዩ ደረጃ የሚገለጽ መሆኑን ጠቁመው ለምሳሌ "የአልትራሳውንድ ዋጋ ከ150 ብር ወደ 300 ብር ከፍ ብሏል። ተኝቶ ታካሚዎች በቀን ለአልጋ ይከፍሉት የነበረው 47 ብር አሁን ወደ 170 ብር ከፍ ብሏል" ይላሉ። የዋጋ ጭማሪው ሁሉንም አይመለከትም ይህንን የዋጋ ክለሳ ያደረገው ጤና ጥበቃ ሚንስትር መሆኑን የሚገልጹት ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ የኢትዮጵያ ጤና መድኅን ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ናቸው። "ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው ዋጋ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ እና ከቆይታ፣ ከዋጋና ከብር የመግዛት አቅም አንጻር መስተካከል እንደነበረበት ይጠበቃል" ብለዋል። በተጨማሪም [በመንግሥት የጤና ተቋማት ላይ] አገልግሎት ላይ የሚቀርብ ቅሬታ አለ። "ቅሬታውን ለመፍታት ደግሞ ሃብት ያስፈልጋል" ይላሉ ወይዘሮ ፍሬይህይወት። "በነበረው አሠራር ለህክምናው ዘርፍ ከሚወጣው ወጪ 60 ወይንም 70 በመቶ የሚሆነው በመንግሥት ነበር የሚሸፈነው። ቀሪው ነው በኅብረተሰቡ" ብለዋል። የዋጋ ጭማሪው በጤና መድኅን ስር የታቀፉትን አይመለከትም። ዶ/ር ዮናስ ላቀው "ይህ ለውጥ የጤና ሚኒስትር በደነገገው መመሪያ መሠረት ነው። የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ያላቸው ታካሚዎች አሁንም በነጻ አገልግሎት ያገኛሉ። የሌላቸው ግን አገልግሎት ለማግኘት ክፍያ መፈፀም ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል። በዚህ ምክንያት ህክምና ማግኘት የሚገባቸው ሰዎች እያገኙ አይደለም። "የህሙማን ቁጥር መቀነስ እንዳለ ጠቅላላ ሐኪሞች (ጀነራል ፕራክቲሽነርስ) ይነግሩናል። ሆስፒታል ገብተው በመተኛት መታከም የሚገባቸው በገንዘቡ ምክንያት አልገቡም እንደሚባል ሰምቻለሁ" ያሉት ዶ/ር ፈድሉ ናቸው። የታካሚዎች ቁጥር በመቀነሱ የሚስማሙት ዶ/ር ሱራፌል "[ዋጋውን ሲያውቁ] በር ላይ ደርሰው ይመለሳሉ። አሁን አብዛኛዎቹ ታካሚዎች በዋጋ ጭማሪው ምክንያት እየተቸገሩ፣ ህክምና አቋርጠው ለመውጣት እየተገደዱ፣ አስፈላጊ መድሃኒቶችን ለመግዛት እና ምርመራዎችን ለማድረግ እየተቸገሩ ሲሆን የጤና መድኅን ተጠቃሚ የሆኑ ታካሚዎች ግን ያለ ምንም ችግር እየታከሙ ይገኛል" ብለዋል። በጤና መድኅን እጦት ምክንያት ወደ ህክምና ተቋማት የሚመጣ ሰው በመቅረቱ ወይም በክፍያው ምክንያት ተገቢውን ህክምና ባለማግኘቱ ህይወት ልናጣ እንችላለን ሲሉ ሃሳቡን የሚደግፉት ዶ/ር ፈድሉ ናቸው። የጤና መድኅን ያላቸውም በፈለጉት ቦታ መታከም አልቻሉም ሌላው በህክምና ባለሙያዎች የተነሳው አሠራሩ ሊተገበር ስለመሆኑ ቀደም ተብሎ ለኅብረተሰቡ ማሳወቅ እና ዝግጅት እንዲኖር መደረግ ነበረበት የሚል ነው። አሠራሩን ተግባራዊ ከማድረግ በፊት ኅብረተሰቡ እንዲያውቅ እና እንዲዘጋጅ የስድስት ወር ቅድመ ዝግጅ ቢደረግበት የተሻለ ይሆን ነበር ይላሉ ዶ/ር ፈድሉ። ወ/ሮ ፍሬህይወት ግን ኅብረተሰቡን ዝግጁ የማድረግ ሥራ የእነርሱ መሥሪያ ቤት አለመሆኑን በመጥቀስ ይህ የሚመለከተው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መሆኑን ጠቁመዋል። ሌላው የተነሳው ችግር የጤና መድኅን ያላቸው ሰዎችም ቢሆኑ በሁሉም የመንግሥት የጤና ተቋማት ላይ መጠቀም አለመቻላቸው ነው። "ያለው ዞናዊ አሠራር ነው። [በኛ ዞን የወጣ የጤና መድኅን] የሚሠራው በእኛ ዞን ብቻ ነው። ከአጎራባች ዞን ለሚመጡት አገልግሎት አይሰጥም። ስለዚህ ለመክፈል ይገደዳሉ። በዞን ብቻ መሆን የለበትም በክልል ደረጃ ወይንም በአገር አቀፍ ደረጃ መሆን አለበት" ይላሉ ዶ/ር ፈድሉ። ተመሳሳይ ችግር እንዳስተዋሉ ዶ/ር ሱራፌልም ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ ታካሚ ጎንደር ላይ ማግኘት ያልቻለውን ህክምና ለማግኘት ወደ ባህርዳር ቢያቀና ባለው የጤና መድኅን የሚሸፈን ባለመሆኑ ለመክፈል ይገደዳል ብለዋል። ይህ ደግሞ የጤና መድኅኑም ቢሆን ለሁሉም ነጻ ህክምና አያስገኝም ማለት መሆኑን አስረድተዋል። የጤና መድኅኑ በሁሉም የጤና ተቋማት አገልግሎት እንደማያስገኝ የሚስማሙት ወ/ሮ ፍሬህይወት "አሁን ያለው አሠራር የሪፈራል ሰንሰለቱን ጠብቆ ነው የሚሄደው" ይላሉ። ይህም ማለት አንድ ታካሚ የጤና መድኅኑን ካገኘበት አካባቢ ካለ የጤና ተቋም በመሄድ ህክምና ያገኛል። ህክምናው ነጻ ነው። ህክምናው ከዚያ ተቋም በላይ ከሆነ ሪፈር ተጽፎለት ወደሚቀጥለው የጤና ተቋም ሄዶ መታከም ይችላል። በዚህ መልኩ ሲኬድም ህክምናው ነጻ ነው። ስለዚህ የሪፈር ሰንሰለቱን ይዞ እንጂ በራሱ መንገድ ሁሉም ጋር በመሄድ ነጻ መታከም አይችልም ማለት ነው። ይህን ለመፍታት የጤና ተቋማት ከብዙ የጤና ተቋማት ጋር ውል እንዲገቡ እና አብረው እንዲሠሩ ለማድረግ እየተሠራ እንደሚገኝ ወ/ሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል። የጤና መድኅኑ ምዝገባ በዲጂታላይዝ አለመሆኑንም በምክንያትነት አቅርበዋል። ምዝገባው ዲጂታላይዝ አለመሆኑ ታካሚዎች በተለያዩ የጤና ተቋማት ሄደው ለመታከም ካርዱን ሲጠቀሙ ለማመሳከር እንቅፋት መሆኑ ነው የችግሩ መነሻ። ለሁሉም ያልተዘጋጀ የጤና መድኅን ሌላው ችግር ደግሞ የጤና መድኅኑ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ያማከለ መሆኑ ነው። የመንግሥት ሠራተኞች እና የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ በጤና መድኅኑ የማይታቀፉ መኖራቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ሱራፌል እነዚህ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለችግሩ ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። የጤና መድኅኑ መደበኛ ባልሆነ የሥራ ዘርፍ የተሠማሩ እና ወር ጠብቀው ቋሚ ደመወዝ የማያገኙ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። "አሁን ተግባራዊ የተደረገው የጤና መድኅን መደበኛ ባልሆነ ሥራ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ እና ከ10 በታች በሚቀጥሩ የሥራ ዘርፎች እና ዝቅተኛ የኑሮ መጠን ላይ ያሉትን እንደሚያቅፍ" ወይዘሮ ፍሬህይወት አረጋግጠዋል። በቅርቡ ደግሞ ሌሎችንም ለማካተት የሚያስችል አሠራር በመዘርጋት ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ ችግሩ እንደሚፈታ ተናግረዋል። የጠየቅናቸው የህክምና ባለሙያዎች በዋጋ ጭማሪው ላይ ብዙም ቅሬታ ያላቸው አይመስሉም። የማይስማሙት በተጨመረው ዋጋ መጠን እና በተጨመረበት ጊዜ ላይ ነው። ካነሷቸው ችግሮች ጎን ለጎን "አጠቃላይ ሃሳቡ ኅብረተሰቡን ወደ ጤና መድኅን ለማስገባት ይመስላል። ምክንያቱም ከኪስ ተከፍሎ አይቻልም። ሁሉም ሰው በከፈለው ገንዘብ ይታከማል። የሴክተሩ ገንዘብም ይሻሻላል። ዕቅዱ እንደ ምዕራባውያኑ እና አሜሪካ ለማድረግ ነው። በአጠቃላይ አሠራሩን እደግፈዋለሁ። ዕቅዱ የጤና ሴክተሩን ለማሳደግ ነው። የጤናውን ዘርፍ ለማሳደግም ያለመ ነው" የሚሉት ዶ/ር ፈድሉ ናቸው። "ለምን በዚህ መጠን ዋጋ እንደጨመረ ለማወቅ ባደረኩት ጥረት ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ከመጠን ባነሰ ዋጋ አገልግሎት ሲሰጡ ስለነበር ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተዳረጉ እና አሁን የወጣው ዋጋ ግን ተገቢው ክፍያ እንደሆነ ነው። በተጨማሪም በገጠር የሚኖረው ማኅበረሰብ የጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማበረታታት ነው" ይላሉ ዶ/ር ሱራፌል። "ሌላው ጥያቄ የሆነብኝ ነገር 'ሆስፒታሎች ይህን የዋጋ ጭማሪ ሲያደርጉ የሚሰጠው አገልግሎት ጥራትና ፍጥነቱ ከድሮው በተለየ ይጨምራል ወይ?' የሚለው ነው። ይህን በሂደት የምናየው ይሆናል። የታካሚዎቻችን መቸገር እና መንገላታት ግን ለህክምናውም ለሃኪሙም ከባድ ራስ ምታት ነው። ተገቢው ትኩረት እና መፍትሄ ያስፈልገዋል" ብለዋል። የሠላማዊት እናት ህክምናቸውን ተከታትለው አገግመዋል። እሷም በቀጣዩ ቀን ዓመታዊ ክፍያ ፈጽማ የጤና መድኅን አባል ሆነዋል። በየጊዜው በእናቷ ምክንያት ሐኪም ቤት የምትመላለሰው ሠላማዊት አሁን "እፎይ ብያለሁ" ብላለች። 40 ሚሊዮን ሰዎች በጤና መድን ታቅፈዋል የጤና መድህን ማለት አንድ ቤተሰብ በአመት የተወሰነ ብር በመክፈል የቤተሰቡ አባል ሲታመም በነጻ አገልግሎት የሚያገኝበት መንገድ ነው።የጤና መድኅን የተጀመረው ኅብረተሰቡ ባልተጠበቀ ወጪ ወዳልታሰበ ድህነት እንዳይገባ ለማድረግ ነው ይላሉ ፍሬህይወት። መደበኛ ያልሆነ የሥራ ዘርፍ እና በወር ቋሚ ደመወዝ የማይከፈላቸው ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። አሠራሩ ተግባራዊ ከተደረገ 10 ዓመት ይሆነዋል። 40 ሚሊዮን ያህል አባላት እንዳሉትም ለማወቅ ተችሏል። ካሉት አባላቱ መካከል 24 በመቶ ከድህነት ወለል በታች በመሆናቸው (8 ሚሊዮን ያህሉ መሆኑ ነው) ወጪያቸውን የሚሸፈነው በመንግሥት ነው። እንደ የአካባቢው በሚለያይ ክፍያ በዓመት አንድ ጊዜ በሚደረግ ክፍያ አባል መሆን ይቻላል። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት አዲስ አበባ ላይ አንድ አባወራ በዓመት 350 ብር በመክፈል ይመዘገባል። የጥቅም ማዕቀፉም የልብ እና የአዕምሮ ህክምናን ጨምሮ እስከ አዲስ አበባ ድረስ በመንግሥት የህክምና ተቋማት የሚሰጥ ይሆናል። አሁን በጤና ጥበቃ በመንግሥት የጤና ተቋማት ላይ ተደረገውን ጭማሪን ተከትሎ የጤና መድኅኑ ዓመታዊ ክፍያ ላይ ክለሳ በማድረግ ጭማሪ ሊኖር አንደሚችልም ወ/ሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የጤና ጥበቃን ሃሳብ ለማካተት በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
https://www.bbc.com/amharic/news-58220082
2health
ፕሬዝደንት ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ "ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው" አሉ
በአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል የማድረግ ግዴታ የለባቸውም መባሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው ብለዋል። ባለስልጣናት በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ከውስን ቦታዎች በስተቀር ያለጭምብል መንቀሳቀስ ይችላሉ ብለዋል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅም አይጠበቅባቸውም ተብሏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ "ኦቫል" ቢሮ ከሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ጋር ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው ያለጭምብል ታየተዋል። ይሁን እንጂ እንደ አወቶብስ፣ አውሮፕላንና ሆስፒታል ባሉ መሰባሰብን በሚጠይቁ ከበር መለስ አገልግሎቶች የሚሰጡባቸው ቦታዎች ላይ ግን ክትባት የተከተቡትም ቢሆኑ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታቸው ነው። ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ላገኙ ሰዎች የኮቪድ ክልከላዎች እንዲነሱላቸው በባይደን አስተዳደር ላይ ጫና ሲደረግበት ቆይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ የአሜሪካ የመምህራን ፌዴሬሽን ለፕሬዝዳንት ባይደን ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከፈቱ ጥሪ አቅርቧል። ይህ ጥሪ የተላለፈው ፋይዘር ያመረተውን ከትባት ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያሉ ህጻናት መከተብ እንዲችሉ ፍቃድ ከተሰጠ በኃላ ነው። አሁን ላይ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተሰምቷል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅም ግዴታቸ እንዳልሆነ አስታውቋል። በቲውተር ገጻቸው ያልተከተቡ ሰዎች 'ማስክ' ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ባይደን "ህጉ ቀላል ነው መከተብ ወይም እስከትከተቡ ጭምብል ማደረግ። ምርጫው የእናንተ ነው" ብለዋል። በአሜሪካ 35 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ክትባት ያገኘ ሲሆን የ ጆ ባይደን አስተዳደር ይሄ ቁጥር እስከ ሀምሌ ደረስ በእጥፍ አሳድጎ 70 በመቶ ለማደረስ አቅዷል።
ፕሬዝደንት ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ "ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው" አሉ በአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል የማድረግ ግዴታ የለባቸውም መባሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ማስካቸውን አውልቀው ይህ ለአሜሪካ ታላቅ ቀን ነው ብለዋል። ባለስልጣናት በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ከውስን ቦታዎች በስተቀር ያለጭምብል መንቀሳቀስ ይችላሉ ብለዋል። አካላዊ ርቀትን መጠበቅም አይጠበቅባቸውም ተብሏል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ "ኦቫል" ቢሮ ከሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ጋር ፕሬዝዳንቱ ራሳቸው ያለጭምብል ታየተዋል። ይሁን እንጂ እንደ አወቶብስ፣ አውሮፕላንና ሆስፒታል ባሉ መሰባሰብን በሚጠይቁ ከበር መለስ አገልግሎቶች የሚሰጡባቸው ቦታዎች ላይ ግን ክትባት የተከተቡትም ቢሆኑ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታቸው ነው። ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ላገኙ ሰዎች የኮቪድ ክልከላዎች እንዲነሱላቸው በባይደን አስተዳደር ላይ ጫና ሲደረግበት ቆይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ የአሜሪካ የመምህራን ፌዴሬሽን ለፕሬዝዳንት ባይደን ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከፈቱ ጥሪ አቅርቧል። ይህ ጥሪ የተላለፈው ፋይዘር ያመረተውን ከትባት ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 ያሉ ህጻናት መከተብ እንዲችሉ ፍቃድ ከተሰጠ በኃላ ነው። አሁን ላይ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተሰምቷል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅም ግዴታቸ እንዳልሆነ አስታውቋል። በቲውተር ገጻቸው ያልተከተቡ ሰዎች 'ማስክ' ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ባይደን "ህጉ ቀላል ነው መከተብ ወይም እስከትከተቡ ጭምብል ማደረግ። ምርጫው የእናንተ ነው" ብለዋል። በአሜሪካ 35 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ክትባት ያገኘ ሲሆን የ ጆ ባይደን አስተዳደር ይሄ ቁጥር እስከ ሀምሌ ደረስ በእጥፍ አሳድጎ 70 በመቶ ለማደረስ አቅዷል።
https://www.bbc.com/amharic/57111329
3politics
ቦክሰኛው ማኒ ፓኪዮ ለፕሬዘዳንትነት እንደሚወዳደር ይፋ አደረገ
በዓለም የቦክስ ውድድር መድረኮች ኮከብ የሆነው ፊሊፒንሳዊው ማኒ ፓኪዎ በቀጣይ ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደር ይፋ አደረገ። ፓኪዮ ገዢውን ፓርቲ በሚቀናቀነው ፒዲፒ-ላባን ፓርቲ አማካኝነት ነው ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኖ ለምርጫው የሚቀርበው። በበርካታ ድሎች ከታጀበው ቦክሰኝነቱ ባሻገር የ42 ዓመቱ ፓኪዎ በፊሊፒንስ ፓርላማ ውስጥ ሴናተርም ነው። በስልጣን ላይ የሚገኙት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ለሌላ የስልጣን ዘመን መወዳደር ባይችሉም አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ዕጩ አድርጎ አቅርቧቸዋል። ሂደቱን በቅርበት የሚከታተሉ ተቺዎች የዱቴርቴ ተግባር ስልጣንን የሙጥኝ የማለት ሙከራ ሲሉ ትችት እያቀረቡባቸው ይገኛሉ። ዱቴርቴ ከቅርብ ወዳጃቸው ክሪስቶፈር ቦንግ ጎ ጋር ለምርጫው እንዲቀርቡ የተመረጠ ቢሆንም ክሪስቶፈር ግን ወዳጃቸውን ዱተርቴንን ለመተካት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት የፕሬዚዳንት ዱቴርቴ ሴት ልጅ ሳራ ዱቴርቴ-ካርፒዮ አባቷን ለመተካት ለውድድር ልትቀርብ እንደምትችል ፍንጮች አሉ። ቦክሰኛው ማኒ ፓኪዮ በውድድር ሕይወቱ በስምንት የተለያዩ የክብደት ምድቦች አሸንፏል። በቅርቡም ከኩባዊ ተቀናቃኙ ጋር ባደረገው ግጥሚያ መሸነፉን ተከትሎ ከቦክሱ አለም ራሱን ለማግለል ማሰቡን አስታውቋል። የቀረበለትን የፕሬዘዳንትነት ጥያቄ በተቀበለበት ግዜም "እኔ ታጋይ ነኝ፤ በግጥሚያ መድረክ (ቦክስ) ሆነም ውጪ ታጋይ ሆኜ ቀጥላለሁ"ብሏል። በድቡብ ምስራቅ ኢሲያ በምትገኘው ፊሊፒስ እጅግ ዝነኛ የሆነው ፓኪዮ በምርጫው አሸንፎ ስልጣን የሚይዝ ከሆነ ድህነትን እና ሙስናን አዋጋለሁ ሲል ቃል ገብቷል።
ቦክሰኛው ማኒ ፓኪዮ ለፕሬዘዳንትነት እንደሚወዳደር ይፋ አደረገ በዓለም የቦክስ ውድድር መድረኮች ኮከብ የሆነው ፊሊፒንሳዊው ማኒ ፓኪዎ በቀጣይ ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደር ይፋ አደረገ። ፓኪዮ ገዢውን ፓርቲ በሚቀናቀነው ፒዲፒ-ላባን ፓርቲ አማካኝነት ነው ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኖ ለምርጫው የሚቀርበው። በበርካታ ድሎች ከታጀበው ቦክሰኝነቱ ባሻገር የ42 ዓመቱ ፓኪዎ በፊሊፒንስ ፓርላማ ውስጥ ሴናተርም ነው። በስልጣን ላይ የሚገኙት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ለሌላ የስልጣን ዘመን መወዳደር ባይችሉም አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ዕጩ አድርጎ አቅርቧቸዋል። ሂደቱን በቅርበት የሚከታተሉ ተቺዎች የዱቴርቴ ተግባር ስልጣንን የሙጥኝ የማለት ሙከራ ሲሉ ትችት እያቀረቡባቸው ይገኛሉ። ዱቴርቴ ከቅርብ ወዳጃቸው ክሪስቶፈር ቦንግ ጎ ጋር ለምርጫው እንዲቀርቡ የተመረጠ ቢሆንም ክሪስቶፈር ግን ወዳጃቸውን ዱተርቴንን ለመተካት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት የፕሬዚዳንት ዱቴርቴ ሴት ልጅ ሳራ ዱቴርቴ-ካርፒዮ አባቷን ለመተካት ለውድድር ልትቀርብ እንደምትችል ፍንጮች አሉ። ቦክሰኛው ማኒ ፓኪዮ በውድድር ሕይወቱ በስምንት የተለያዩ የክብደት ምድቦች አሸንፏል። በቅርቡም ከኩባዊ ተቀናቃኙ ጋር ባደረገው ግጥሚያ መሸነፉን ተከትሎ ከቦክሱ አለም ራሱን ለማግለል ማሰቡን አስታውቋል። የቀረበለትን የፕሬዘዳንትነት ጥያቄ በተቀበለበት ግዜም "እኔ ታጋይ ነኝ፤ በግጥሚያ መድረክ (ቦክስ) ሆነም ውጪ ታጋይ ሆኜ ቀጥላለሁ"ብሏል። በድቡብ ምስራቅ ኢሲያ በምትገኘው ፊሊፒስ እጅግ ዝነኛ የሆነው ፓኪዮ በምርጫው አሸንፎ ስልጣን የሚይዝ ከሆነ ድህነትን እና ሙስናን አዋጋለሁ ሲል ቃል ገብቷል።
https://www.bbc.com/amharic/58621504
5sports
ቶኪዮ ኦሊምፒክ፡ አውስትራሊያ የኦሊምፒክ ተሳታፊዎችን ለማስተዋወቅ የለቀቀችው ፎቶ አወዛገበ
የአውስትራሊያ ኦሊምፒክ ቡድን ተወዳዳሪዎችን ለማስተዋወቅ የለጠፈው ፎቶ ውግዘት ገጥሞታል። የአውስትራሊያን የኦሎምፒክ ቡድን ለማስተዋወቅ ይፋ የተደረገው ፎቶ ብዝሃነትን አያንጸባርቅም በሚል አንዲት ጥቁር ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ራሷን ከውድድሩ ልታቅብ እንድምትችል አስጠንቅቃለች። የአውስትራሊያን የኦሊምፒክና ፓራሊምፒክ [የአካል ጉዳተኞች የሚሳተፉበትን] ተሳታፊዎች ትጥቅን ለማስተዋወቅ የተለቀቀው ምስል ላይ የሚታዩ ሰዎች በሙሉ ተመሳሳይ የቆዳ ቀለም ያላቸው ናቸው። እናም በሀገሪቱ እውቅና ያላት ጥቁር የቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ ሊዝ ካምቤጅ ፎቶውን “ነጭ የተቀባ” ብላዋለች። የኦሎምፒክ ቡድኑን ብዛሃነትን ለማንጸባርቅ ከዚህ የተለየ ነገር መስራት ነበረበት ያለው ደግሞ የአውስትራሊያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ነው። በ2012 ኦሊምፒክ የነሀስ ሜዳሊያ ያገኘችው ካምቤጅ ጉዳዮ ቅር እንዳሰኛት መጀመሪያ የገለጸችው በኢንስታግራም ገጿ ነበር። ናይጄሪያዊ አባትና አውስትራሊያዊት እናት ያላት ቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ የተወለደችው ለንደው ውስጥ ነው። ይህ አነጋጋሪ ምስል ማሕበራዊ ድር አምባ ላይ ሲለጠፍ ከስሩ የተቀመጠው የመጀመሪያው አስተያየት “እኔን የማይወክልኝ ሀገርን እንዴት ሊወክል ይችላል?” ሲል ይጠይቃል። ከዚህ በፊት የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የቡድኑ ማልያ በሴቶች ልክ የለም መባሉን ተከትሎ ቁጣቸውን አሰምተው ነበር። የሃገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለወንዶች ያደላል ተብሎም የማሕበራዊ ድር አምባ ግርግር ተነስቶ ነበር።
ቶኪዮ ኦሊምፒክ፡ አውስትራሊያ የኦሊምፒክ ተሳታፊዎችን ለማስተዋወቅ የለቀቀችው ፎቶ አወዛገበ የአውስትራሊያ ኦሊምፒክ ቡድን ተወዳዳሪዎችን ለማስተዋወቅ የለጠፈው ፎቶ ውግዘት ገጥሞታል። የአውስትራሊያን የኦሎምፒክ ቡድን ለማስተዋወቅ ይፋ የተደረገው ፎቶ ብዝሃነትን አያንጸባርቅም በሚል አንዲት ጥቁር ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ራሷን ከውድድሩ ልታቅብ እንድምትችል አስጠንቅቃለች። የአውስትራሊያን የኦሊምፒክና ፓራሊምፒክ [የአካል ጉዳተኞች የሚሳተፉበትን] ተሳታፊዎች ትጥቅን ለማስተዋወቅ የተለቀቀው ምስል ላይ የሚታዩ ሰዎች በሙሉ ተመሳሳይ የቆዳ ቀለም ያላቸው ናቸው። እናም በሀገሪቱ እውቅና ያላት ጥቁር የቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ ሊዝ ካምቤጅ ፎቶውን “ነጭ የተቀባ” ብላዋለች። የኦሎምፒክ ቡድኑን ብዛሃነትን ለማንጸባርቅ ከዚህ የተለየ ነገር መስራት ነበረበት ያለው ደግሞ የአውስትራሊያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ነው። በ2012 ኦሊምፒክ የነሀስ ሜዳሊያ ያገኘችው ካምቤጅ ጉዳዮ ቅር እንዳሰኛት መጀመሪያ የገለጸችው በኢንስታግራም ገጿ ነበር። ናይጄሪያዊ አባትና አውስትራሊያዊት እናት ያላት ቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ የተወለደችው ለንደው ውስጥ ነው። ይህ አነጋጋሪ ምስል ማሕበራዊ ድር አምባ ላይ ሲለጠፍ ከስሩ የተቀመጠው የመጀመሪያው አስተያየት “እኔን የማይወክልኝ ሀገርን እንዴት ሊወክል ይችላል?” ሲል ይጠይቃል። ከዚህ በፊት የአውስትራሊያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የቡድኑ ማልያ በሴቶች ልክ የለም መባሉን ተከትሎ ቁጣቸውን አሰምተው ነበር። የሃገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለወንዶች ያደላል ተብሎም የማሕበራዊ ድር አምባ ግርግር ተነስቶ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-57027326
5sports
በኳታር የዓለም ዋንጫ ተጫዋቾች እና ተመልካቾች እንዳያደርጉ የተከለከሉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው?
እየተካሄደ ያለው የኳታር የዓለም ዋንጫ ውድድር በርካታ ድንቅ ነገሮች እየታዩበት ከመሆኑ በተጨማሪ ውዝግቦችንም እያስተናገደ ነው። ኳታር በባሕረ ሰላጤረው በረሃ ውስጥ አጀብ ያሰኙ ስታዲየሞችን ገንብታ በአረቡ ዓለም የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ በማስተናገድ ታሪክ አስመዝግባለች። በተጫማሪም ይህ የዓለም ዋንጫ ከቀደሙት በተለየ በርካታ ትችቶች የተሰነዘሩበት ነው። ኳታር ከእምነት እና ከሕጓ አንጻር የተለያዩ ክልከላዎችን የጣለች ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ ድጋፍ እና ውግዘት ከተለያዩ ወገኖች እየተሰነዘሩባት ነው። ታዲያ በዚህ የዓለም ዋንጫ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች ፈጽሞ እንዳያደርጉት የተከለከሉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው?
በኳታር የዓለም ዋንጫ ተጫዋቾች እና ተመልካቾች እንዳያደርጉ የተከለከሉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው? እየተካሄደ ያለው የኳታር የዓለም ዋንጫ ውድድር በርካታ ድንቅ ነገሮች እየታዩበት ከመሆኑ በተጨማሪ ውዝግቦችንም እያስተናገደ ነው። ኳታር በባሕረ ሰላጤረው በረሃ ውስጥ አጀብ ያሰኙ ስታዲየሞችን ገንብታ በአረቡ ዓለም የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ በማስተናገድ ታሪክ አስመዝግባለች። በተጫማሪም ይህ የዓለም ዋንጫ ከቀደሙት በተለየ በርካታ ትችቶች የተሰነዘሩበት ነው። ኳታር ከእምነት እና ከሕጓ አንጻር የተለያዩ ክልከላዎችን የጣለች ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ ድጋፍ እና ውግዘት ከተለያዩ ወገኖች እየተሰነዘሩባት ነው። ታዲያ በዚህ የዓለም ዋንጫ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች ፈጽሞ እንዳያደርጉት የተከለከሉት ነገሮች የትኞቹ ናቸው?
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1kg2n80jqo
0business
ኤሚሬትስ ገንዘቤን አላገኘሁም በሚል ወደ ናይጄሪያ የሚደርገውን በረራ ሊያቋርጥ ነው
ግዙፉ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ አየር መንገድ ወደ ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ የማደርገውን በረራ ሊያቋርጥ መሆኑን አስታወቀ። ዋና መቀመጫውን ዱባይ ያደረገው ኤሚሬትስ አየር መንገድ የናይጄሪያ በረራውን ከነሐሴ 26/2014 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚያቆም ገልጿል። ኤሚሬትስ ወደ ናይጄሪያ እና ከናይጄሪያ የሚያደርገውን በረራውን ለማቆም የወሰነው በአገሪቱ ያለውን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻሉ መሆኑን አስታውቋል። ኢሚሬትስ አየር መንገድ በአገሪቱ ሲሰጥ ለቆየው የአየር ትራንስፖርት አገለግሎቱ ከናይጄሪያ ማግኘት ያልቻለው 85 ሚሊዮን ዶላር እንዳለው አመልክቷል። አየር መንገዱ ገንዘቡን ማግኘት ባለመቻሉ ወደ ናይጄሪያ የሚያደርገውን የበረራ ቁጥር እንደሚቀንስ ለአገሪቱ አቪዬሽን ሚኒስቴር በደብዳቤ አስታውቆ ነበር። በደኅንነት እና ለመንገደኞች በሚሰጠው ምቾች የ2022 የዓለማችን ምርጥ 20 አየር መንገዶች ውስጥ መካተት የቻለው ኤሚሬትስ፤ ነሐሴ 2014 አጋማሽ ላይ የበረራ ቁጥሩን ከመቀነሱ በፊት በሳምንት ለ11 ጊዜ ያህል ወደ ናይጄሪያ መዳረሻዎች ይበር ነበር። ኤሚሬትስ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪ ላለመብረር መውሰኑን ተከትሎ መጉላለት ሊገጥማቸው የሚችሉ ደንበኖቹ የአየር ቲኬታቸውን በመሰረዝ ገንዘባቸውን ተመላሽ ማድረግ እንደሚችሉ አልያም ከሌሎች የአፍሪካ መዳረሻዎች መነሳት ወይም መብረር እንደሚችሉ አማራጭ ሰጥቷል። ከኤሚሬትስ በተጨማሪ ሌሎች ግዙፍ አየር መንገዶች በአፍሪካ ግዙፍ ከሚባሉት መዳረሻዎች መካከል አንዷ ከሆነችው ናይጄሪያ ያላቸውን ገንዘብ ማንቀሳቀስ አለመቻላቸውን በመግለጽ ቅሬታ ያሰማሉ። ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ወደ ናይጄሪያ የሚበሩ ሌሎች አየር መንገዶችም የኤሚሬትስን ውሳኔ ሊከተሉ ይችላሉ። አየር መንገዶች በናይጄሪያ ማንቀሳቀስ ያልቻሉት የገንዘብ መጠን 600 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተጠቅሷል። በአፍሪካ የሕዝብ ቁጥር ቀዳሚ የሆነችው ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ ባጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ የውጭ ኩባንያዎች ላቀረቡት ምርትና አገልግሎት ከአገሪቱ በሚያውጡት የውጭ ምንዛሬ መጠን ላይ ገደብ ጥላለች።
ኤሚሬትስ ገንዘቤን አላገኘሁም በሚል ወደ ናይጄሪያ የሚደርገውን በረራ ሊያቋርጥ ነው ግዙፉ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ አየር መንገድ ወደ ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ የማደርገውን በረራ ሊያቋርጥ መሆኑን አስታወቀ። ዋና መቀመጫውን ዱባይ ያደረገው ኤሚሬትስ አየር መንገድ የናይጄሪያ በረራውን ከነሐሴ 26/2014 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚያቆም ገልጿል። ኤሚሬትስ ወደ ናይጄሪያ እና ከናይጄሪያ የሚያደርገውን በረራውን ለማቆም የወሰነው በአገሪቱ ያለውን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻሉ መሆኑን አስታውቋል። ኢሚሬትስ አየር መንገድ በአገሪቱ ሲሰጥ ለቆየው የአየር ትራንስፖርት አገለግሎቱ ከናይጄሪያ ማግኘት ያልቻለው 85 ሚሊዮን ዶላር እንዳለው አመልክቷል። አየር መንገዱ ገንዘቡን ማግኘት ባለመቻሉ ወደ ናይጄሪያ የሚያደርገውን የበረራ ቁጥር እንደሚቀንስ ለአገሪቱ አቪዬሽን ሚኒስቴር በደብዳቤ አስታውቆ ነበር። በደኅንነት እና ለመንገደኞች በሚሰጠው ምቾች የ2022 የዓለማችን ምርጥ 20 አየር መንገዶች ውስጥ መካተት የቻለው ኤሚሬትስ፤ ነሐሴ 2014 አጋማሽ ላይ የበረራ ቁጥሩን ከመቀነሱ በፊት በሳምንት ለ11 ጊዜ ያህል ወደ ናይጄሪያ መዳረሻዎች ይበር ነበር። ኤሚሬትስ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪ ላለመብረር መውሰኑን ተከትሎ መጉላለት ሊገጥማቸው የሚችሉ ደንበኖቹ የአየር ቲኬታቸውን በመሰረዝ ገንዘባቸውን ተመላሽ ማድረግ እንደሚችሉ አልያም ከሌሎች የአፍሪካ መዳረሻዎች መነሳት ወይም መብረር እንደሚችሉ አማራጭ ሰጥቷል። ከኤሚሬትስ በተጨማሪ ሌሎች ግዙፍ አየር መንገዶች በአፍሪካ ግዙፍ ከሚባሉት መዳረሻዎች መካከል አንዷ ከሆነችው ናይጄሪያ ያላቸውን ገንዘብ ማንቀሳቀስ አለመቻላቸውን በመግለጽ ቅሬታ ያሰማሉ። ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ወደ ናይጄሪያ የሚበሩ ሌሎች አየር መንገዶችም የኤሚሬትስን ውሳኔ ሊከተሉ ይችላሉ። አየር መንገዶች በናይጄሪያ ማንቀሳቀስ ያልቻሉት የገንዘብ መጠን 600 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተጠቅሷል። በአፍሪካ የሕዝብ ቁጥር ቀዳሚ የሆነችው ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጄሪያ ባጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ የውጭ ኩባንያዎች ላቀረቡት ምርትና አገልግሎት ከአገሪቱ በሚያውጡት የውጭ ምንዛሬ መጠን ላይ ገደብ ጥላለች።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c848nyg3rplo
3politics
ሊዝ ትረስ፡ ስልጣን እንዲለቁ ያስገደዷቸው 3 መሠረታዊ ጉዳዮች
ሊዝ ትረስ ወደ ዶውኒንግ ስትሪት ከመጡ በ6ኛው ሳምንታቸው ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል። ገና በ45ኛ ቀናቸው ስልጣን መልቀቃቸው በዩኬ ታሪክ ለአጭር ጊዜ ስልጣን ላይ የቆዩ ሰው ያደርጋቸዋል። ሊዝ ትረስ የወግ አጥባቂ መሪነት ቦታን ከቦሪስ ጆንሰን ተረክበው ለ6 ሳምንታት የዩኬ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነዋል። ከዚህ ቀደም ዩኬን ለአጭር ጊዜ በጠቅላይ ሚንስትርነት የመሩት ጆርጅ ካኒንግ ነበሩ። ጆርጅ ካኒንግ ሞት ሳይቀድማቸው እአአ 1872 ላይ ዩኬን ለ119 ቀናት መርተው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሯን ስልጣን እንዲለቁ ያስገደዷቸውን ሦስት ምክንያቶች እንመልከት። ሊዝ ገና ወደ ስልጣን እንደመጡ ነበር ፈተና የበዛባቸው። ሊዝ ስልጣን በያዙ ሦስተኛ ሳምንታቸው ከፋይናንስ ሚንስትሩ ጋር በመሆን የ45 ቢሊዮን ፓዎንድ የታክስ ቅነሳ እቅድ አስተዋወቁ። ይህ ግን ብዙ ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮችን ይዞ በመምጣቱ ትችት አስከተለባቸው። ይህ እቅድ ሙሉ በሙሉ የተተወ ሲሆን የፋይንስ ሚንስትሩም ከስልጣናቸው ተባረዋል። ሊዝ ከበርካታ ቁጥር ካላቸው የፓርቲ አጋሮቻቸው ትችት በዝቶባቸው ነበር። አንዳንዶች ስልጣን እንዲለቁ ጭምር በአደባባይ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሴኡላ ብሬቨርማን ስልጣናቸውን ለቀቁ። ሊዝ የተፈጠረባቸውን ክፍተቶች ለመሙላት የቀድሞ ተቀናቃኞቻቸውን ግራንት ሻፕስ እና ጄረሚ ሃንትን መሾም ነበረባቸው። ትረስ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪነትን ቦታ ሲይዙ ቀጥሎ ደግሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ሲሆኑ ፈጽማቸዋለሁ ያሏቸውን ማድረግ አልቻሉም። በጽሐፍት ቤታቸው በር ላይ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ባስታወቁበት አጭሩ መግለጫቸው፤ “ወግ አጥባቂ ፓርቲ ለመረጠኝ ኃላፊነት መወጣት እንደማልችል ተረድቻለሁ” ብለዋል። ሊዝ ትረስን ለመተካት በቀጣይ ሳምንት የመሪነት ውድድር ይካሄዳል ይባል እንጂ ተሰናባቿን ጠቅላይ ሚንስትር ማን ሊተካ እንደሚችል እስካሁን አልታወቀም። አንድ ነገር ግን ግልጽ ነው። ጀረሚ ሃንት የዩኬ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን እንደማይወዳደሩ አስታውቀዋል። ሊዝ ትረስም እርሳቸውን የሚተካ መሪ እስኪገኝ ድረስ በስልጣን ላይ እንደሚቆዩ በዛሬው መግለጫቸው አስታውቀዋል። ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤት ከሕልፈታቸው በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የጠቅላይ ሚንስትርነት ሹመትን ያጸደቁት የሊዝ ትረስን ነበር። ንግሥት ኤልዛቤጥ በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ሊዝ ትረስ 15ኛ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ነበር።
ሊዝ ትረስ፡ ስልጣን እንዲለቁ ያስገደዷቸው 3 መሠረታዊ ጉዳዮች ሊዝ ትረስ ወደ ዶውኒንግ ስትሪት ከመጡ በ6ኛው ሳምንታቸው ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል። ገና በ45ኛ ቀናቸው ስልጣን መልቀቃቸው በዩኬ ታሪክ ለአጭር ጊዜ ስልጣን ላይ የቆዩ ሰው ያደርጋቸዋል። ሊዝ ትረስ የወግ አጥባቂ መሪነት ቦታን ከቦሪስ ጆንሰን ተረክበው ለ6 ሳምንታት የዩኬ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነዋል። ከዚህ ቀደም ዩኬን ለአጭር ጊዜ በጠቅላይ ሚንስትርነት የመሩት ጆርጅ ካኒንግ ነበሩ። ጆርጅ ካኒንግ ሞት ሳይቀድማቸው እአአ 1872 ላይ ዩኬን ለ119 ቀናት መርተው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሯን ስልጣን እንዲለቁ ያስገደዷቸውን ሦስት ምክንያቶች እንመልከት። ሊዝ ገና ወደ ስልጣን እንደመጡ ነበር ፈተና የበዛባቸው። ሊዝ ስልጣን በያዙ ሦስተኛ ሳምንታቸው ከፋይናንስ ሚንስትሩ ጋር በመሆን የ45 ቢሊዮን ፓዎንድ የታክስ ቅነሳ እቅድ አስተዋወቁ። ይህ ግን ብዙ ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮችን ይዞ በመምጣቱ ትችት አስከተለባቸው። ይህ እቅድ ሙሉ በሙሉ የተተወ ሲሆን የፋይንስ ሚንስትሩም ከስልጣናቸው ተባረዋል። ሊዝ ከበርካታ ቁጥር ካላቸው የፓርቲ አጋሮቻቸው ትችት በዝቶባቸው ነበር። አንዳንዶች ስልጣን እንዲለቁ ጭምር በአደባባይ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሴኡላ ብሬቨርማን ስልጣናቸውን ለቀቁ። ሊዝ የተፈጠረባቸውን ክፍተቶች ለመሙላት የቀድሞ ተቀናቃኞቻቸውን ግራንት ሻፕስ እና ጄረሚ ሃንትን መሾም ነበረባቸው። ትረስ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪነትን ቦታ ሲይዙ ቀጥሎ ደግሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ሲሆኑ ፈጽማቸዋለሁ ያሏቸውን ማድረግ አልቻሉም። በጽሐፍት ቤታቸው በር ላይ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ባስታወቁበት አጭሩ መግለጫቸው፤ “ወግ አጥባቂ ፓርቲ ለመረጠኝ ኃላፊነት መወጣት እንደማልችል ተረድቻለሁ” ብለዋል። ሊዝ ትረስን ለመተካት በቀጣይ ሳምንት የመሪነት ውድድር ይካሄዳል ይባል እንጂ ተሰናባቿን ጠቅላይ ሚንስትር ማን ሊተካ እንደሚችል እስካሁን አልታወቀም። አንድ ነገር ግን ግልጽ ነው። ጀረሚ ሃንት የዩኬ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን እንደማይወዳደሩ አስታውቀዋል። ሊዝ ትረስም እርሳቸውን የሚተካ መሪ እስኪገኝ ድረስ በስልጣን ላይ እንደሚቆዩ በዛሬው መግለጫቸው አስታውቀዋል። ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤት ከሕልፈታቸው በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የጠቅላይ ሚንስትርነት ሹመትን ያጸደቁት የሊዝ ትረስን ነበር። ንግሥት ኤልዛቤጥ በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ሊዝ ትረስ 15ኛ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cerd038x0yro
5sports
የሱዳኑ ክለብ ከጊዮርጊስ ጋር ያለው ግጥሚያ ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁንልኝ አለ
የሱዳኑ እግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገው የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁንልኝ ሲል ካፍን ጠየቀ። አል-ሂላል ኦምዱርማን እግር ኳስ ክለብ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሊደረግ የታሰበው ውድድር ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን (ካፍ) የጠየቀው በደኅንነት ስጋት ነው። በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዳግም ማገርሸቱ የደኅንነት ስጋት እንዳሳደረበት ክለቡ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ የገለጸ ሲሆን ካፍም ለጥያቄው ምላሽ እንደሚሰጠኝ ተስፋ አለኝ ብሏል። ከአንድ ሳምንት ገደማ በፊት ለወራት ከዘለቀ ውጥረት በኋላ የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት ለሦስተኛ ዙር ዳግም መቀስቀሱ ይታወሳል። ምንም እንኳ የሱዳኑ ክለብ የደኅንነት ስጋት ስላለብኝ ጨዋታው ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁን ብሎ ይጠይቅ እንጂ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን በቀለ በባህር ዳር ጨዋታ ለማድረግ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት የለም ብለዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሱዳኑ ክለብ የቀረበው ጥያቄ በይፋዊ መንገድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ የደረሰው ነገር እንደሌለ ከገለጹ በኋላ፤ መስከረም 1/2015 ዓ.ም. ለማድረግ ከታቀደው ጨዋታ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት የለም ብለዋል። “ኤልሜሪክ የተባለው የሱዳን ክለብ ከጂቡቲ ክለብ ጋር ያለው የመልስ ጨዋታ በባህር ዳር ስታዲየም እንዲደረግለት እየጠየቀ ያለው” ካሉ በኋላ ጨዋታውን ለማካሄድ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት እንደሌለ ተናግረዋል። ከአገር ውጪ የሚጫወቱ ኢትዮጵያን ተጫዋችን ለብሔራዊ ቡድን በመመልመል የሚታወቁት ፋርሃን ሞሐመድ ደግሞ የሱዳኑ ክለብ ይህን ጥያቄ ለካፍ ያቀረበው በኢትዮጵያ መጫወት ስላልፈለገ እንጂ በትክክል የደኅንነት ስጋት ኖሮበት አይደለም ብለዋል። “ግብጾች ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት በኢትዮጵያ ላለመጫወት ፍላጎት ስለሌላቸው እንጂ ትክክለኛ ስጋት ኖሯቸው አይደለም” ብለዋል። በተመሳሳይ ፋርሃን ከአል-ሂላል ጋር የአንድ ከተማ ክለብ የሆነው አልሜሪክ ከጂቡቲው ክለብ ጋር ግጥሚያውን በጂቡቲ ካደረገ በኋላ በሜዳው ማድረግ የነበረበትን የመልስ ጨዋታውን በባህር ዳር ስታዲየም ለማድረግ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረው የአል-ሂላል ክለብ ጥያቄ ምክንያታዊ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ፋርሃን ሞሐመድ ለክለቡ ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል ብዬ አልጠብቅም ብለዋል። የባለፈው ዓመት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ቻምፒዮንሲ ሊግ ተሳታፊ ሲሆን፤ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ፋሲል ከነማ ደግሞ አፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ ነው።
የሱዳኑ ክለብ ከጊዮርጊስ ጋር ያለው ግጥሚያ ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁንልኝ አለ የሱዳኑ እግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርገው የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁንልኝ ሲል ካፍን ጠየቀ። አል-ሂላል ኦምዱርማን እግር ኳስ ክለብ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሊደረግ የታሰበው ውድድር ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲሆን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን (ካፍ) የጠየቀው በደኅንነት ስጋት ነው። በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዳግም ማገርሸቱ የደኅንነት ስጋት እንዳሳደረበት ክለቡ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ የገለጸ ሲሆን ካፍም ለጥያቄው ምላሽ እንደሚሰጠኝ ተስፋ አለኝ ብሏል። ከአንድ ሳምንት ገደማ በፊት ለወራት ከዘለቀ ውጥረት በኋላ የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት ለሦስተኛ ዙር ዳግም መቀስቀሱ ይታወሳል። ምንም እንኳ የሱዳኑ ክለብ የደኅንነት ስጋት ስላለብኝ ጨዋታው ከኢትዮጵያ ውጪ ይሁን ብሎ ይጠይቅ እንጂ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን በቀለ በባህር ዳር ጨዋታ ለማድረግ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት የለም ብለዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሱዳኑ ክለብ የቀረበው ጥያቄ በይፋዊ መንገድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ የደረሰው ነገር እንደሌለ ከገለጹ በኋላ፤ መስከረም 1/2015 ዓ.ም. ለማድረግ ከታቀደው ጨዋታ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት የለም ብለዋል። “ኤልሜሪክ የተባለው የሱዳን ክለብ ከጂቡቲ ክለብ ጋር ያለው የመልስ ጨዋታ በባህር ዳር ስታዲየም እንዲደረግለት እየጠየቀ ያለው” ካሉ በኋላ ጨዋታውን ለማካሄድ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት እንደሌለ ተናግረዋል። ከአገር ውጪ የሚጫወቱ ኢትዮጵያን ተጫዋችን ለብሔራዊ ቡድን በመመልመል የሚታወቁት ፋርሃን ሞሐመድ ደግሞ የሱዳኑ ክለብ ይህን ጥያቄ ለካፍ ያቀረበው በኢትዮጵያ መጫወት ስላልፈለገ እንጂ በትክክል የደኅንነት ስጋት ኖሮበት አይደለም ብለዋል። “ግብጾች ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት በኢትዮጵያ ላለመጫወት ፍላጎት ስለሌላቸው እንጂ ትክክለኛ ስጋት ኖሯቸው አይደለም” ብለዋል። በተመሳሳይ ፋርሃን ከአል-ሂላል ጋር የአንድ ከተማ ክለብ የሆነው አልሜሪክ ከጂቡቲው ክለብ ጋር ግጥሚያውን በጂቡቲ ካደረገ በኋላ በሜዳው ማድረግ የነበረበትን የመልስ ጨዋታውን በባህር ዳር ስታዲየም ለማድረግ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረው የአል-ሂላል ክለብ ጥያቄ ምክንያታዊ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ፋርሃን ሞሐመድ ለክለቡ ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል ብዬ አልጠብቅም ብለዋል። የባለፈው ዓመት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ቻምፒዮንሲ ሊግ ተሳታፊ ሲሆን፤ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ፋሲል ከነማ ደግሞ አፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cw9d804p33lo
2health
ዩናይትድ ኪንግደም ጤነኛ ሰዎችን በኮቪድ ተህዋሲ 'ልትለክፋቸው' ነው
የኮቪድ ክትባትን በማግኘት ጥረት ውስጥ ከፊት ከሆኑ አገራት አንዷ የሆነችው ዩናይትድ ኪንግደም የተለየ አይነት የክትባት ሙከራ ለማድረግ ቀዳሚዋ አገር ልትሆን ነው። በጥር ወር ላይ 90 ጤነኛ ሰዎች ሆን ተብለው ለኮቪድ ተህዋሲ እንዲጋለጡ በማድረግ ነው አዲሱ ሙከራ የሚደረገው። ይህም ቶሎ ክትባት ለማግኘት ይረዳል ተብሏል። መንግሥት ከወዲሁ 33.6 ሚሊዮን ፓውንድ ለዚሁ ሙከራ መድቧል። ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግበታል የተባለው ይህ አዲስ የሙከራ ዘዴ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከአገሪቱ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ይሁንታን ማግኘት ይኖርበታል። በመድኃኒት ቅመማ ሂደት ‹ሂዩማን ቻሌንጅ› በሚል የሚታወቀው ይህ ጤነኞች ላይ በሽታ አምጪ ተህዋስን ሆን ብሎ በማጋባት ሙከራ ማድረግ ብዙም የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ከዚህ ቀደም በወባና በኢንፍሉዌዛ የመድኃኒት ግኝቶች ሂደት ውስጥ ተሞክሮ ውጤት ማስገኘቱን ኔቸር መጽሔት ዘግቧል። ሳይንቲስቶች በጥር ወር መጀመርያ ተግባራዊ ያደርጉታል በተባለው በዚህ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉት ሰዎች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 30 የሚሆን ፍጹም ጤነኛ የሆኑ በጎ ፈቃደኞች ብቻ ናቸው። ሙከራው አንድን ሰው ምን ያህል የተህዋሲው መጠን ነው ለበሽታ የሚያጋልጠው የሚለውንም ለማወቅ ይረዳል ተብሏል። ለበጎ ፈቃደኞቹ በቅድሚያ ተህዋሲው በትንሽ መጠን ይሰጣቸዋል። ፍጹም ጤነኛ ሰዎችን እንደ አይጥ መሞከርያ ማድረግ ቶሎ ውጤት ለማግኘት አስፈላጊ ነው የሚሉ በርካታ ቢሆንም መድኃኒት በሌለው በሽታ ሰዎችን ሆን ብሎ መበከል ከሕክምና ሥነ ምግባር አንጻር ተገቢ አይደለም ሲሉ ነገሩን የሚተቹትም በርካታ ናቸው። ተህዋሲው ለበጎ ፈቃደኞቹ የሚሰጣቸው በአፍንጫቸው በኩል ይሆናል ተብሏል። ለ24 ሰዓታትም ጥብቅ ክትትል ይደረግላቸዋል። በጎ ፈቃደኞቹ ለከፋ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ነው፤ ምክንያቱም ጤነኞችና ወጣቶች በመሆናቸውና በጥንቃቄ ስለሚመረጡ ነው ይላሉ ተመራማሪዎች። ቅድመ ጥንቃቄው አስተማማኝ በሚባል ደረጃ ላይ ሲደርስ በበጎ ፈቃደኞቹ በአንዳንዶቹ ላይ ሙከራ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ይሰጧቸዋል። ለኮቪድ ተህዋሲው ከመገላጣቸው በፊትም ክትባት እንዲወስዱ የሚደረጉ ይኖራሉ። ክትባቱን የወሰዱት ለተህዋሲው ተጋልጠው ተህዋሲው ይይዛቸዋል ወይስ አይዛቸውም የሚለውም ምላሽ ያገኛል። የዚህ ምርምር መሪ የኢምፔሪያል ኮሌጁ ዶ/ር ክሪስ ቺዩ ሰዎች ያን ያህልም ሐሳብ ሊገባቸው አይገባም ይላሉ። ‹‹እኔና ባልደረቦቼ በዚህ መንገድ ላለፉት 10 ዓመታት በርካታ ጤነኛ ሰዎች ላይ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ቫይረሶችን በመስጠት ስንሰራ ቆይተናል። እርግጥ ነው የትኛውም ጥናት ቢሆን የራሱ አደጋ የለውም አይባልም። ነገር ግን አደጋውን ለመቀነስ እንታገላለን›› ብለዋል። ረዳታቸው ፕሮፌሰር ፒተር ኦፔን ሻው በበኩላቸው ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲ ሆን ብሎ በመበከል ምርምር ማካሄድ በቀላሉ የሚታይ ነገር ባይሆንም ውጤት ለማግኘት ግን ወሳኝ ነው፤ ያግዛል ብለዋል። በአሁን ሰዓት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮቪድ ክትባቶች በመጨረሻ ምዕራፍ ሙከራ ላይ ሲሆኑ ውጤት ያስገኛሉ ተብለው በጉጉት እየተጠበቁ ካሉት መካከል የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ተጠቃሽ ነው። በጥር ወር ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲው በመበከል የሚደረገው ምርምር ሌላ ፍቱን መድኃኒት ቀድሞ ቢገኝም የሚቋረጥ አይሆንም። ክትባቶች ከተገኙ በኋላ የትኛው ክትባት እጅግ ውጤታማ ነው የሚለው ጥናት ይቀጥላል። ተህዋሲውን በገዛ ፈቃዳቸው ለመውሰድ የፈቀዱ የታላቋ ብሪታኒያ ዜጎች ለጊዜያቸውና ለደፋር ውሳኔያቸው የሚመጥን ነው የሚባል ገንዘብ ይከፈላቸዋል። ሙከራው ከተደረገባቸው በኋላም ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያለማቋረጥ የቅርብ ክትትል ይደረግባቸዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም ጤነኛ ሰዎችን በኮቪድ ተህዋሲ 'ልትለክፋቸው' ነው የኮቪድ ክትባትን በማግኘት ጥረት ውስጥ ከፊት ከሆኑ አገራት አንዷ የሆነችው ዩናይትድ ኪንግደም የተለየ አይነት የክትባት ሙከራ ለማድረግ ቀዳሚዋ አገር ልትሆን ነው። በጥር ወር ላይ 90 ጤነኛ ሰዎች ሆን ተብለው ለኮቪድ ተህዋሲ እንዲጋለጡ በማድረግ ነው አዲሱ ሙከራ የሚደረገው። ይህም ቶሎ ክትባት ለማግኘት ይረዳል ተብሏል። መንግሥት ከወዲሁ 33.6 ሚሊዮን ፓውንድ ለዚሁ ሙከራ መድቧል። ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግበታል የተባለው ይህ አዲስ የሙከራ ዘዴ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከአገሪቱ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ይሁንታን ማግኘት ይኖርበታል። በመድኃኒት ቅመማ ሂደት ‹ሂዩማን ቻሌንጅ› በሚል የሚታወቀው ይህ ጤነኞች ላይ በሽታ አምጪ ተህዋስን ሆን ብሎ በማጋባት ሙከራ ማድረግ ብዙም የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ከዚህ ቀደም በወባና በኢንፍሉዌዛ የመድኃኒት ግኝቶች ሂደት ውስጥ ተሞክሮ ውጤት ማስገኘቱን ኔቸር መጽሔት ዘግቧል። ሳይንቲስቶች በጥር ወር መጀመርያ ተግባራዊ ያደርጉታል በተባለው በዚህ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉት ሰዎች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 30 የሚሆን ፍጹም ጤነኛ የሆኑ በጎ ፈቃደኞች ብቻ ናቸው። ሙከራው አንድን ሰው ምን ያህል የተህዋሲው መጠን ነው ለበሽታ የሚያጋልጠው የሚለውንም ለማወቅ ይረዳል ተብሏል። ለበጎ ፈቃደኞቹ በቅድሚያ ተህዋሲው በትንሽ መጠን ይሰጣቸዋል። ፍጹም ጤነኛ ሰዎችን እንደ አይጥ መሞከርያ ማድረግ ቶሎ ውጤት ለማግኘት አስፈላጊ ነው የሚሉ በርካታ ቢሆንም መድኃኒት በሌለው በሽታ ሰዎችን ሆን ብሎ መበከል ከሕክምና ሥነ ምግባር አንጻር ተገቢ አይደለም ሲሉ ነገሩን የሚተቹትም በርካታ ናቸው። ተህዋሲው ለበጎ ፈቃደኞቹ የሚሰጣቸው በአፍንጫቸው በኩል ይሆናል ተብሏል። ለ24 ሰዓታትም ጥብቅ ክትትል ይደረግላቸዋል። በጎ ፈቃደኞቹ ለከፋ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ነው፤ ምክንያቱም ጤነኞችና ወጣቶች በመሆናቸውና በጥንቃቄ ስለሚመረጡ ነው ይላሉ ተመራማሪዎች። ቅድመ ጥንቃቄው አስተማማኝ በሚባል ደረጃ ላይ ሲደርስ በበጎ ፈቃደኞቹ በአንዳንዶቹ ላይ ሙከራ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ይሰጧቸዋል። ለኮቪድ ተህዋሲው ከመገላጣቸው በፊትም ክትባት እንዲወስዱ የሚደረጉ ይኖራሉ። ክትባቱን የወሰዱት ለተህዋሲው ተጋልጠው ተህዋሲው ይይዛቸዋል ወይስ አይዛቸውም የሚለውም ምላሽ ያገኛል። የዚህ ምርምር መሪ የኢምፔሪያል ኮሌጁ ዶ/ር ክሪስ ቺዩ ሰዎች ያን ያህልም ሐሳብ ሊገባቸው አይገባም ይላሉ። ‹‹እኔና ባልደረቦቼ በዚህ መንገድ ላለፉት 10 ዓመታት በርካታ ጤነኛ ሰዎች ላይ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ቫይረሶችን በመስጠት ስንሰራ ቆይተናል። እርግጥ ነው የትኛውም ጥናት ቢሆን የራሱ አደጋ የለውም አይባልም። ነገር ግን አደጋውን ለመቀነስ እንታገላለን›› ብለዋል። ረዳታቸው ፕሮፌሰር ፒተር ኦፔን ሻው በበኩላቸው ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲ ሆን ብሎ በመበከል ምርምር ማካሄድ በቀላሉ የሚታይ ነገር ባይሆንም ውጤት ለማግኘት ግን ወሳኝ ነው፤ ያግዛል ብለዋል። በአሁን ሰዓት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮቪድ ክትባቶች በመጨረሻ ምዕራፍ ሙከራ ላይ ሲሆኑ ውጤት ያስገኛሉ ተብለው በጉጉት እየተጠበቁ ካሉት መካከል የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ተጠቃሽ ነው። በጥር ወር ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲው በመበከል የሚደረገው ምርምር ሌላ ፍቱን መድኃኒት ቀድሞ ቢገኝም የሚቋረጥ አይሆንም። ክትባቶች ከተገኙ በኋላ የትኛው ክትባት እጅግ ውጤታማ ነው የሚለው ጥናት ይቀጥላል። ተህዋሲውን በገዛ ፈቃዳቸው ለመውሰድ የፈቀዱ የታላቋ ብሪታኒያ ዜጎች ለጊዜያቸውና ለደፋር ውሳኔያቸው የሚመጥን ነው የሚባል ገንዘብ ይከፈላቸዋል። ሙከራው ከተደረገባቸው በኋላም ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያለማቋረጥ የቅርብ ክትትል ይደረግባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/54617479
3politics
ባይደን የሚቀለብሷቸው የትራምፕ ውሳኔዎች የትኞቹ ናቸው?
አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን 50 ዓመታት በፖለቲካው ውስጥ አሳልፈዋል። በአስተዳደር ዘመናቸው ይወስዷቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ እርምጃዎች አንዱ አሜሪካን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መመለስ ነው። የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያስተላለፏቸው አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ባይደን ይቀለብሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።ከነዚህ መካከል በሙስሊም አገራት ዜጎች ላይ ተጥሎ የነበረው የጉዞ እገዳ ይገኝበታል። ከባይደን አጀንዳዎች አንዱ አሜሪካን ወደ ዓለም ጤና ድርጅት አባልነቷ መመለስ ነው። ትራምፕ ድርጅቱ ለቻይና የወገነ ነው ብለው ከድርጅቱ መውጣታቸው አይዘነጋም። ባይደን ከዓለም ጤና ድርጅት በተጨማሪ አሜሪካን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነትም ይመልሳሉ ተብሏል። ከሙስሊም አገራት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ሰዎች ላይ ተጥሎ የነበረውን ክልከላ ባይደን ያነሳሉ። ከነዚህ ባሻገር በወረርሽኙ ሳቢያ ከቤታቸው እንዲወጡ የተገደዱ ዜጎች ተጨማሪ የመኖሪያ ጊዜ ይፈቀድላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ከባይደን ተጠባቂ እርምጃዎች ዋና ዋናዎቹን እንመልከት፦ ጭምብል ማድረግ ግዴታ ይሆናል በወረርሽኙ ሳቢያ በአሜሪካ ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል። አዲሱ አስተዳደር በቀዳሚነት ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች አንዱም ኮሮናቫይረስ ነው። ባይደን ወረርሽኙን "አስተዳደራችን ከሚገጥመው ፈተናዎች አንዱ ነው" ብለውታል። ቫይረሱን ለመከላከል የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለመተግበርም ቃል ገብተዋል። የመንግሥት ይዞታ በሆኑ ቦታዎችና በጉዞ ወቅት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ከሚያስተላልፉት ውሳኔ አንዱ ይሆናል። በእርግጥ ባይደን ይህንን ውሳኔ የሚተገብሩበት የሕግ ማዕቀፍ የለም። ስለዚህም አገረ ገዢዎችን በግል ጥረታቸው ለማሳመን አቅደዋል። ባይደን ሥልጣን በያዙ በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ለ100 ሚሊዮን ሰዎች ክትባት ለመስጠት ወጥነዋል። ይህንን የሚተገብሩት ያሏቸውን ክትባቶች ባጠቃላይ ለዜጎች በማከፋፈል ሲሆን፤ ለሁለተኛ ዙር ክትባት ተብሎ የሚቀመጥ ጠብታ አይኖርም ማለት ነው። የምጣኔ ሀብት ውሳኔዎች ከቤታቸው በግድ እንዲወጡ ተወስኖባቸው ለነበሩ ሰዎች ጊዜ መስጠት ከባይደን አስተዳደር ከሚጠበቁ ውሳኔዎች ዋነኛው ነው። መንግሥት ለተማሪዎች የሚሰተውን የገንዘብ ድጋፍ ያስቀጥላሉም ተብሏል ካቢኔያቸው ለሠራተኛው ማኅበረሰብ እፎይታ የሚሰጥ የምጣኔ ሀብት ውሳኔ እንዲያሳልፍ ያዛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኮሮናቫይረስ ጫና ላሳደረበት የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት የ1.9 ትሪሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መታቀዱ ይታወሳል። ምክር ቤቱ እቅዱን ካጸደቀ አሜሪካውያን በነፍስ ወከፍ 1 ሺህ 400 ዶላር ያገኛሉ። በቀጣይ 100 ቀናት ውስጥ ትምህርት ቤቶች ጥንቃቄ በተሞላው መንገድ ይከፈታሉ። የትራምፕን አወዛጋቢ የግብር ቅነሳ ባይደን እንደሚቀለብሱ ተገልጿል። እአአ 2017 ላይ ትራምፕ ያሳለፉት የግብር ቅነሳ ባልተገባ መንገድ ሀብታሞችን የጠቀመ ነው ሲሉ ባይደን ይተቻሉ። ከዚህ ባሻገር ባይደን የአሜሪካ ድርጅቶች በውጪ አገራት በሚያደርጓቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚጣለውን ግብር ለመጨመር ወጥነዋል። ይህ እውን እንዲሆን የግብር ፖሊሲያቸውን ምክር ቤቱ ማጽደቅ አለበት። የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ባይደን ሥልጣን በያዙበት የመጀመሪያው ቀን አሜሪካን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚመልሱ አስታውቀዋል። የፓሪሱ ስምምነት የዓለምን የሙቀት መጠን ከ2.0 ሴንቲ ግሬድ በታች ማድረግን ያካትታል። ትራምፕ አሜሪካን ከዚህ ስምምነት አስወጥተዋት ነበር። ባይደን የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ጥብቅ እርምጃዎች እንደሚወስዱ ይጠበቃል። ይህም በመጀሪያዎቹ 100 የሥልጣን ቀናት ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ ውይይት ማካሄድን ያካትታል። በ2050 የአሜሪካን የካርቦን ልቀት ዜሮ የማድረስ እቅድም አላቸው። የስደተኞች ፖሊሲ ለውጥ ትራምፕ ሥልጣን በያዙ በሰባተኛ ቀን ነበር በሙስሊም አገራት ዜጎች ላይ የጉዞ እገዳ የጣሉት። እገዳው የኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሶርያ፣ የመን ዜጎችን እንዲሁም የቬንዝዌላ እና የሰሜን ኮርያ ዜጎችን የሚያግድ ነው። ይህ ውሳኔ በባይደን አስተዳደር ዘመን ይሻራሉ ተብለው ከሚጠበቁ መካከል ይጠቀሳል። ከ11 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰነድ አልባ ስደተኞች ዜግነት ማግኘት የሚችሉበትን ሥርዓት ለምክር ቤት እንደሚልኩ ተገልጿል። ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ህጻናት ዜግነት የሚያገኙበት ዝርዝር ውስጥ የሚገቡበት አሠራር በባይደን ዘመነ መንግሥት እውን ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት አንዱ ነው። ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ 545 ስደተኛ ልጆችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመመለስ ቃል ገብተው ነበር። ትራምፕ በተደጋጋሚ ያወሩለት የነበረውን በአሜሪካና ሜክሲኮ መካከል የሚገነባውን የድንበር ግድግዳ ፕሮጀክት ባይደን ያስቆሙታል። ዘረኛና ኢፍትሐዊ ውሳኔዎችን መሰረዝ ዘረኛና ኢፍትሐዊ የተባሉና በርካቶችን ከቤት ባለቤትነት እንዲሁም ከጤና መድህን ተጠቃሚነት ያገዱ ውሳኔዎችን ባይደን ይሰርዛሉ ተብሏል። በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ከሚወስዷቸው እርምጃዎች መካከል የፖሊስ ተቋምን ዳግመኛ ማዋቀር ቀዳሚው ነው። በወንጀል ተጠርጥረው በሚታሰሩ ሰዎች አነስተኛ የእስራት ጊዜ እንዲፈረድባቸው የሚያስችልና ማኅበረሰብ አቀፍ ፓሊስን የሚያስተገብር ፓሊሲም ከባይደን ይጠበቃል። የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች መብት ባይደን የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን ከጥቃት የሚከላከሉ እንዲሁም በትምህርት ቤትና በወታደራዊ አገልግሎት ዘርፍ ያለውን መድልዎ የሚገቱ ውሳኔዎች ለማስተላለፍ ቃል ገብተዋል። ይህንን ውሳኔ በምክር ቤቱ አማካይነት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳልፉ ግን ግልጽ አይደለም። ከባይደን ከሚጠበቁ ለውጦች ሌላው አሜሪካ ከወዳጅ አገሮቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ማደስ ነው።
ባይደን የሚቀለብሷቸው የትራምፕ ውሳኔዎች የትኞቹ ናቸው? አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን 50 ዓመታት በፖለቲካው ውስጥ አሳልፈዋል። በአስተዳደር ዘመናቸው ይወስዷቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ እርምጃዎች አንዱ አሜሪካን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት መመለስ ነው። የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያስተላለፏቸው አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ባይደን ይቀለብሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።ከነዚህ መካከል በሙስሊም አገራት ዜጎች ላይ ተጥሎ የነበረው የጉዞ እገዳ ይገኝበታል። ከባይደን አጀንዳዎች አንዱ አሜሪካን ወደ ዓለም ጤና ድርጅት አባልነቷ መመለስ ነው። ትራምፕ ድርጅቱ ለቻይና የወገነ ነው ብለው ከድርጅቱ መውጣታቸው አይዘነጋም። ባይደን ከዓለም ጤና ድርጅት በተጨማሪ አሜሪካን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነትም ይመልሳሉ ተብሏል። ከሙስሊም አገራት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ሰዎች ላይ ተጥሎ የነበረውን ክልከላ ባይደን ያነሳሉ። ከነዚህ ባሻገር በወረርሽኙ ሳቢያ ከቤታቸው እንዲወጡ የተገደዱ ዜጎች ተጨማሪ የመኖሪያ ጊዜ ይፈቀድላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ከባይደን ተጠባቂ እርምጃዎች ዋና ዋናዎቹን እንመልከት፦ ጭምብል ማድረግ ግዴታ ይሆናል በወረርሽኙ ሳቢያ በአሜሪካ ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል። አዲሱ አስተዳደር በቀዳሚነት ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች አንዱም ኮሮናቫይረስ ነው። ባይደን ወረርሽኙን "አስተዳደራችን ከሚገጥመው ፈተናዎች አንዱ ነው" ብለውታል። ቫይረሱን ለመከላከል የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለመተግበርም ቃል ገብተዋል። የመንግሥት ይዞታ በሆኑ ቦታዎችና በጉዞ ወቅት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ከሚያስተላልፉት ውሳኔ አንዱ ይሆናል። በእርግጥ ባይደን ይህንን ውሳኔ የሚተገብሩበት የሕግ ማዕቀፍ የለም። ስለዚህም አገረ ገዢዎችን በግል ጥረታቸው ለማሳመን አቅደዋል። ባይደን ሥልጣን በያዙ በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ለ100 ሚሊዮን ሰዎች ክትባት ለመስጠት ወጥነዋል። ይህንን የሚተገብሩት ያሏቸውን ክትባቶች ባጠቃላይ ለዜጎች በማከፋፈል ሲሆን፤ ለሁለተኛ ዙር ክትባት ተብሎ የሚቀመጥ ጠብታ አይኖርም ማለት ነው። የምጣኔ ሀብት ውሳኔዎች ከቤታቸው በግድ እንዲወጡ ተወስኖባቸው ለነበሩ ሰዎች ጊዜ መስጠት ከባይደን አስተዳደር ከሚጠበቁ ውሳኔዎች ዋነኛው ነው። መንግሥት ለተማሪዎች የሚሰተውን የገንዘብ ድጋፍ ያስቀጥላሉም ተብሏል ካቢኔያቸው ለሠራተኛው ማኅበረሰብ እፎይታ የሚሰጥ የምጣኔ ሀብት ውሳኔ እንዲያሳልፍ ያዛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኮሮናቫይረስ ጫና ላሳደረበት የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት የ1.9 ትሪሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መታቀዱ ይታወሳል። ምክር ቤቱ እቅዱን ካጸደቀ አሜሪካውያን በነፍስ ወከፍ 1 ሺህ 400 ዶላር ያገኛሉ። በቀጣይ 100 ቀናት ውስጥ ትምህርት ቤቶች ጥንቃቄ በተሞላው መንገድ ይከፈታሉ። የትራምፕን አወዛጋቢ የግብር ቅነሳ ባይደን እንደሚቀለብሱ ተገልጿል። እአአ 2017 ላይ ትራምፕ ያሳለፉት የግብር ቅነሳ ባልተገባ መንገድ ሀብታሞችን የጠቀመ ነው ሲሉ ባይደን ይተቻሉ። ከዚህ ባሻገር ባይደን የአሜሪካ ድርጅቶች በውጪ አገራት በሚያደርጓቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚጣለውን ግብር ለመጨመር ወጥነዋል። ይህ እውን እንዲሆን የግብር ፖሊሲያቸውን ምክር ቤቱ ማጽደቅ አለበት። የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ባይደን ሥልጣን በያዙበት የመጀመሪያው ቀን አሜሪካን ወደ ፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚመልሱ አስታውቀዋል። የፓሪሱ ስምምነት የዓለምን የሙቀት መጠን ከ2.0 ሴንቲ ግሬድ በታች ማድረግን ያካትታል። ትራምፕ አሜሪካን ከዚህ ስምምነት አስወጥተዋት ነበር። ባይደን የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ጥብቅ እርምጃዎች እንደሚወስዱ ይጠበቃል። ይህም በመጀሪያዎቹ 100 የሥልጣን ቀናት ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ ውይይት ማካሄድን ያካትታል። በ2050 የአሜሪካን የካርቦን ልቀት ዜሮ የማድረስ እቅድም አላቸው። የስደተኞች ፖሊሲ ለውጥ ትራምፕ ሥልጣን በያዙ በሰባተኛ ቀን ነበር በሙስሊም አገራት ዜጎች ላይ የጉዞ እገዳ የጣሉት። እገዳው የኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሶርያ፣ የመን ዜጎችን እንዲሁም የቬንዝዌላ እና የሰሜን ኮርያ ዜጎችን የሚያግድ ነው። ይህ ውሳኔ በባይደን አስተዳደር ዘመን ይሻራሉ ተብለው ከሚጠበቁ መካከል ይጠቀሳል። ከ11 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰነድ አልባ ስደተኞች ዜግነት ማግኘት የሚችሉበትን ሥርዓት ለምክር ቤት እንደሚልኩ ተገልጿል። ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ህጻናት ዜግነት የሚያገኙበት ዝርዝር ውስጥ የሚገቡበት አሠራር በባይደን ዘመነ መንግሥት እውን ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት አንዱ ነው። ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ 545 ስደተኛ ልጆችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመመለስ ቃል ገብተው ነበር። ትራምፕ በተደጋጋሚ ያወሩለት የነበረውን በአሜሪካና ሜክሲኮ መካከል የሚገነባውን የድንበር ግድግዳ ፕሮጀክት ባይደን ያስቆሙታል። ዘረኛና ኢፍትሐዊ ውሳኔዎችን መሰረዝ ዘረኛና ኢፍትሐዊ የተባሉና በርካቶችን ከቤት ባለቤትነት እንዲሁም ከጤና መድህን ተጠቃሚነት ያገዱ ውሳኔዎችን ባይደን ይሰርዛሉ ተብሏል። በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ከሚወስዷቸው እርምጃዎች መካከል የፖሊስ ተቋምን ዳግመኛ ማዋቀር ቀዳሚው ነው። በወንጀል ተጠርጥረው በሚታሰሩ ሰዎች አነስተኛ የእስራት ጊዜ እንዲፈረድባቸው የሚያስችልና ማኅበረሰብ አቀፍ ፓሊስን የሚያስተገብር ፓሊሲም ከባይደን ይጠበቃል። የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች መብት ባይደን የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን ከጥቃት የሚከላከሉ እንዲሁም በትምህርት ቤትና በወታደራዊ አገልግሎት ዘርፍ ያለውን መድልዎ የሚገቱ ውሳኔዎች ለማስተላለፍ ቃል ገብተዋል። ይህንን ውሳኔ በምክር ቤቱ አማካይነት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳልፉ ግን ግልጽ አይደለም። ከባይደን ከሚጠበቁ ለውጦች ሌላው አሜሪካ ከወዳጅ አገሮቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ማደስ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/55735398
5sports
እውቁ የቴኒስ ተጫዎች ጆኮቪች ከአውስትራሊያ ተባረረ
የዓለማችን ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ኮኮብ ኖቫክ ጆኮቪች በአውስትራሊያ ለመቆየት ባደረገው የመጨረሻ ፍርድ ቤት ክርክር ተረትቶ አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። ክትባት ለመቀበል አሻፈረኝ ያለው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቹ፤ የአገሪቱ መንግሥት "በጤና እና ባልተገባ ስነምግባር" ምክንያት ቪዛውን መሰረዙን ተከትሎ ጆኮቪች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስደውም ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ውድቅ አርጎበታል። በውሳኔው "በጣም ቅር ብሎኛል" ያለው ጆኮቪች ውሳኔው ተቀበሎ ወደ ዱባይ አቅንቷል። አገሩ ሰርቢያ 'በአውስትራልያ ኦፕን' የቴኒስ ውድድር ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ያደረገችው ጥረትም ፍሬ አልባ ሆኗል። የጆኮቪች ደጋፊዎች ከውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታውን አንድ ቀን ቀደም ብሎ የተወሰነውን ውሳኔ ከችሎቱ ውጪ ሆነው በቁዘማ ተከታትለዋል። ከደጋፊዎቹ መካከል አንዷ በውድድሩ ላይ የዚህ ዝነኛ ተጫዎች አለመኖር የእረፍት ጊዜዋን "ባዶ" እንደሚያደርግባት ተናግራለች። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን "ድንበሮቻችንን ለማጠናከር እና አውስትራሊያውያንን ለመጠበቅ የተደረገ ውሳኔ ነው" ሲሉ ውሳኔውን በአውንታ መቀበላቸው ገልጸዋል። ሆኖም ጠቅላይ ሚንስትሩ እና አስተዳደራቸው የጆኮቪችን ጉዳያ የያዙበት መንገድ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ እያስተቻቸው ነው። የጆኮቪች ጉዳይ መነሻ የአውስትራሊያ ኢሚግሬሽን ሚኒስትር አሌክስ ሃውክ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ቪዛውን ከሰረዙ በኋላ ነው። ምክንያት ያሉት ደግሞ በአገሪቱ የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ሊያስፋፋ የሚችል ስሜት አንጸባርቋል በሚል ነው። ትላንት እሁዱ በተደረገው የፍርድ ቤት ችሎት የጆኮቪች ጠበቃ ተጫዋቹን ቪዛ ለመቀማት በመንግስት የተሰጡት ማብራሪያዎች ምክንያታዊ አይደሉም ያሉ ሲሆን የቴኒስ ኮከቡን ከአገር ማባረር የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ያባብሳል ሲሉ አስረድተዋል። ዕውቁ ጆኮቪች በመጀመሪያ በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ በኮቪድ መያዙ ተረጋግጦ ነበር። ሆኖም ከዛ በኋላ በአውስትራሊያ የቴኒስ አስተዳደር እና በቪክቶሪያ የግዛት አስተዳደር ወደ አውስትራሊያ መግባት እንዲችል ፍቃድ ተሰጥቶት ነበር። ሆኖም የአውስትራሊያ የድንበር ዘብ የፌደራል የኮሮናቫይረስ መስፈርቶችን አላሟላም በሚል በፈረንጆቹ ጥር መግቢያ ላይ ቪዛው ተሰርዟል። የጠቅላይ ሚኒስትር ሞሪሰን መንግሥት "የአገሪቱን የግዛት አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎች እና እርምጃዎችን ለመውሰድ ተዘጋጅቷል" ብሏል። ሆንም የተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ አመራር እና ሴናተር የሆኑት ክሪስቲና ኬኔሊ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጆኮቪች ጉዳይን በተሳሳተ መንገድ በመምራት እራሳቸውን "በዓለም ፊት መሳቂያ" አድርገዋል ሲሉ ተችተዋቸዋል።
እውቁ የቴኒስ ተጫዎች ጆኮቪች ከአውስትራሊያ ተባረረ የዓለማችን ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ኮኮብ ኖቫክ ጆኮቪች በአውስትራሊያ ለመቆየት ባደረገው የመጨረሻ ፍርድ ቤት ክርክር ተረትቶ አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። ክትባት ለመቀበል አሻፈረኝ ያለው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቹ፤ የአገሪቱ መንግሥት "በጤና እና ባልተገባ ስነምግባር" ምክንያት ቪዛውን መሰረዙን ተከትሎ ጆኮቪች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስደውም ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ውድቅ አርጎበታል። በውሳኔው "በጣም ቅር ብሎኛል" ያለው ጆኮቪች ውሳኔው ተቀበሎ ወደ ዱባይ አቅንቷል። አገሩ ሰርቢያ 'በአውስትራልያ ኦፕን' የቴኒስ ውድድር ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ያደረገችው ጥረትም ፍሬ አልባ ሆኗል። የጆኮቪች ደጋፊዎች ከውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታውን አንድ ቀን ቀደም ብሎ የተወሰነውን ውሳኔ ከችሎቱ ውጪ ሆነው በቁዘማ ተከታትለዋል። ከደጋፊዎቹ መካከል አንዷ በውድድሩ ላይ የዚህ ዝነኛ ተጫዎች አለመኖር የእረፍት ጊዜዋን "ባዶ" እንደሚያደርግባት ተናግራለች። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን "ድንበሮቻችንን ለማጠናከር እና አውስትራሊያውያንን ለመጠበቅ የተደረገ ውሳኔ ነው" ሲሉ ውሳኔውን በአውንታ መቀበላቸው ገልጸዋል። ሆኖም ጠቅላይ ሚንስትሩ እና አስተዳደራቸው የጆኮቪችን ጉዳያ የያዙበት መንገድ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ እያስተቻቸው ነው። የጆኮቪች ጉዳይ መነሻ የአውስትራሊያ ኢሚግሬሽን ሚኒስትር አሌክስ ሃውክ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ቪዛውን ከሰረዙ በኋላ ነው። ምክንያት ያሉት ደግሞ በአገሪቱ የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ሊያስፋፋ የሚችል ስሜት አንጸባርቋል በሚል ነው። ትላንት እሁዱ በተደረገው የፍርድ ቤት ችሎት የጆኮቪች ጠበቃ ተጫዋቹን ቪዛ ለመቀማት በመንግስት የተሰጡት ማብራሪያዎች ምክንያታዊ አይደሉም ያሉ ሲሆን የቴኒስ ኮከቡን ከአገር ማባረር የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ያባብሳል ሲሉ አስረድተዋል። ዕውቁ ጆኮቪች በመጀመሪያ በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ በኮቪድ መያዙ ተረጋግጦ ነበር። ሆኖም ከዛ በኋላ በአውስትራሊያ የቴኒስ አስተዳደር እና በቪክቶሪያ የግዛት አስተዳደር ወደ አውስትራሊያ መግባት እንዲችል ፍቃድ ተሰጥቶት ነበር። ሆኖም የአውስትራሊያ የድንበር ዘብ የፌደራል የኮሮናቫይረስ መስፈርቶችን አላሟላም በሚል በፈረንጆቹ ጥር መግቢያ ላይ ቪዛው ተሰርዟል። የጠቅላይ ሚኒስትር ሞሪሰን መንግሥት "የአገሪቱን የግዛት አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎች እና እርምጃዎችን ለመውሰድ ተዘጋጅቷል" ብሏል። ሆንም የተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ አመራር እና ሴናተር የሆኑት ክሪስቲና ኬኔሊ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጆኮቪች ጉዳይን በተሳሳተ መንገድ በመምራት እራሳቸውን "በዓለም ፊት መሳቂያ" አድርገዋል ሲሉ ተችተዋቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/60020796
3politics
የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ከመንግሥት ባለሥልጣንና ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተወያዩ
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር አርብ አዲስ አበባ በመግባት ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር ተወያዩ። በቅርቡ የተሾሙት ልዩ መልዕክተኛው ካለፈው ሳምንት ማብቂያ በጀመሩት ጉዟቸው በቀዳሚነት ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና ግብፅ ከተጓዙ በኋላ ነው አዲስ አበባ ያቀኑት። ልዩ መልዕክተኛው አዲስ አበባ እንደገቡ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ከኦነግ እና ከኦፌኮ ሊቃነ መናብት ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ማይክ ሐመር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛነት ኃላፊነት ከተቀበሉ በኋላ የመጀመሪያ በሆነው ጉዟቸው አርብ ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸውን ያመለከተው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ከመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ይገናኛሉ ብሏል። ልዩ መልዕክተኛው በቀዳሚነት የተነጋገሩት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ሲሆን፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ስለሚደረገው ጥረት፣ የእርዳታ አቅርቦት እና በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አመልክቷል። ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት መሪነት ለተጀመረው የሰላም ጥረት ቁርጠኛ መሆኑን እና ለዚህም ተደራዳሪ ቡድን አቋቁሞ ሥራ መጀመሩን፣ ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መቀጠሉን እና የመብት ጥሰት ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ለማድረግ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አብራርተዋል። አቶ ደመቀ ጨምረውም መንግሥት ለሰላም ንግግር ያለውን ዝግጁነት በሚያሳይበት ጊዜ “በህወሓት በኩል የሚታየው ወላዋይ አቋም በአፍሪካ ኅብረት የሚካሄደውን የሰላም ጥረት ስጋት ላይ የሚጥል ነው” በማለት የተገኙ ውጤቶች ወደኋላ እንዳይመለሱ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቡድኑ ላይ አስፈላጊውን ጫና እንዲያሳርፍ መጠየቃቸውን ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ ገልጿል። ከልዩ መልዕክተኛው ጋር በተደረገው ውይይት ግንባታው እየተጠናቀቀ ያለውን ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ከሚያስማማ መፍትሄ ላይ ለመድረስ በመርኅ ላይ የተመሠረተ አቋም እንዳለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። ውይይቱን በተመለከተ ከልዩ መልዕክተኛው በኩል የተባለ ነገር ባይኖርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ማይክ ሐመር መንግሥት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እና በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እያስገኘ ያለውን ውጤት ማድነቃቸውን አመልክቷል። በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አርብ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳመለከተው ሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ፣ ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጋር በመሆን ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር መወያየተቻውን ገልጿል። አዲስ አበባ በሚገኘው በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ውስጥ የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከሌሎች ዲፕሎማቶች ጋር ሆነው ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ ጋር በተደረገው ውይይት ላይ በአጠቃላዩ የአገሪቱ ሰላም፣ በኢኮኖሚ እና በፓርቲዎቹ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን ኦነግ በፌስቡክ ገጹ አመልክቷል። ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለው ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት በተመለከተ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።
የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ከመንግሥት ባለሥልጣንና ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተወያዩ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሐመር አርብ አዲስ አበባ በመግባት ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር ተወያዩ። በቅርቡ የተሾሙት ልዩ መልዕክተኛው ካለፈው ሳምንት ማብቂያ በጀመሩት ጉዟቸው በቀዳሚነት ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና ግብፅ ከተጓዙ በኋላ ነው አዲስ አበባ ያቀኑት። ልዩ መልዕክተኛው አዲስ አበባ እንደገቡ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ከኦነግ እና ከኦፌኮ ሊቃነ መናብት ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ማይክ ሐመር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛነት ኃላፊነት ከተቀበሉ በኋላ የመጀመሪያ በሆነው ጉዟቸው አርብ ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸውን ያመለከተው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ከመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ይገናኛሉ ብሏል። ልዩ መልዕክተኛው በቀዳሚነት የተነጋገሩት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ሲሆን፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ስለሚደረገው ጥረት፣ የእርዳታ አቅርቦት እና በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አመልክቷል። ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት መሪነት ለተጀመረው የሰላም ጥረት ቁርጠኛ መሆኑን እና ለዚህም ተደራዳሪ ቡድን አቋቁሞ ሥራ መጀመሩን፣ ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መቀጠሉን እና የመብት ጥሰት ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ለማድረግ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አብራርተዋል። አቶ ደመቀ ጨምረውም መንግሥት ለሰላም ንግግር ያለውን ዝግጁነት በሚያሳይበት ጊዜ “በህወሓት በኩል የሚታየው ወላዋይ አቋም በአፍሪካ ኅብረት የሚካሄደውን የሰላም ጥረት ስጋት ላይ የሚጥል ነው” በማለት የተገኙ ውጤቶች ወደኋላ እንዳይመለሱ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቡድኑ ላይ አስፈላጊውን ጫና እንዲያሳርፍ መጠየቃቸውን ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ ገልጿል። ከልዩ መልዕክተኛው ጋር በተደረገው ውይይት ግንባታው እየተጠናቀቀ ያለውን ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ከሚያስማማ መፍትሄ ላይ ለመድረስ በመርኅ ላይ የተመሠረተ አቋም እንዳለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። ውይይቱን በተመለከተ ከልዩ መልዕክተኛው በኩል የተባለ ነገር ባይኖርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ማይክ ሐመር መንግሥት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እና በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እያስገኘ ያለውን ውጤት ማድነቃቸውን አመልክቷል። በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አርብ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳመለከተው ሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ፣ ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጋር በመሆን ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር መወያየተቻውን ገልጿል። አዲስ አበባ በሚገኘው በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ውስጥ የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከሌሎች ዲፕሎማቶች ጋር ሆነው ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ ጋር በተደረገው ውይይት ላይ በአጠቃላዩ የአገሪቱ ሰላም፣ በኢኮኖሚ እና በፓርቲዎቹ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን ኦነግ በፌስቡክ ገጹ አመልክቷል። ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለው ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት በተመለከተ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c80dpn08pn1o
5sports
እግር ኳስና ኮሮናቫይረስ፡ የኢትዮጵያን ስም በአውሮፓ ያስጠራችው ሎዛ
ሎዛ አበራ በማልታ በሴቶች ዘርፍ የ2019/2020 የውድድር ዘመን ምርጥ ተጫዋች በመሆን በማልታ የእግርኳስ ተጫዋቾች ማህበር ተሸልማለች። ሎዛ ለቢቢሲ አዲስ አይደለችም። የማልታውን ቡድን ቢርኪርካራ እንደተቀላቀለች እንዴት ነው ሕይወት በአውሮፓ ስንል አናግረናት ነበር። ከዚያ ቃለ ምልልስ በኋላ ሎዛ ብዙ ታሪክ ፅፋለች። ሪከርድ ሰብራለች። ሎዛ ለሌሎች አንጋፋ የስፖርት መገናኛ ብዙሃንም አዲስ አይደለችም። ከጎል ዶት ኮም ጀምሮ እስከ ካፍ ኦንላይን ስለሎዛ አውርተው አይጠግቡም። ቡድኗ ቢርኪርካራ ተቃናቃኙ ሂበርኒያንስን በማልታ ታሪክ ከፍተኛ በሆነ ጎል 17 ለምንም ሲረታ ሎዛ 7 ጎል መረብ ላይ አሳርፋለች። የተወሰኑ ኳሶችንም ለጎል አመቻችታ አቀብላለች። ሎዛ ከዚህ ታሪካዊ ጨዋታ በፊትና በኋላ በርካታ ጎሎችን በማስቆጠር ቡድኗ የማልቲዝ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ እንዲሆን አድርጋለች። ሎዛአሁንየትነች? ሎዛ አሁን ያለችው ትውድል ቀዬዋ ነው። ከምባታ ዞን የምትገኘው ዱራሜ ከተማ። አጥቂዋ ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ በመጣችበት ነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተከሰተው። በዚህ ምክንያት ወደ ማልታ ተመልሳ ማቅናት አልቻለችም። ለነገሩ የማልቲዝ ሊግ በወረርሽኙ ምክንያት ተቋርጦ ነበር። ሎዛ ኢትዮጵያ እያለች ቡድኗ ቢርኪርካራ የማልታ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑ ይፋ ሆነ። ኢትዮጵያዊት ተስፈኛ አጥቂ በማልታ ሊግ የመጀመሪያ ዓመት ቆይታዋ በ12 ጨዋታዎች 30 ጎሎች በማስቆጠር ኮከብ ጎል አግቢ ሆናለች። 'ከቢርኪርካራ ጋር ባለድል በመሆኔ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር በመልካም ሁኔታ ተጠናቋል' ትላለች ሎዛ። የወደፊት ዕቅድ የማልታ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ የቀጣዩ ዓመት ውድድር በመጪው ጥቅምት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ከአዳማ ከነማ ቢርኪርካራን መስከረም 2012 ላይ የተቀላቀለችው ሎዛ ከቡድኑ ጋር ያላት ውል ተጠናቋል። ለመሆኑ ውሏን ለማራዘም አስባ ይሆን? 'ከቢርኪርካራ ጋር የነበረኝ ውል የአንድ ዓመት ነው። እሱ ተጠናቋል። እርግጥ ነው ቢርኪርካራ ውሌን ለማራዘም ጥያቄ አቅርበዋል። እኔም ያቀረብኩላቸው ቅድመ ሁኔታ አለ። በእሱ የምንስማማ ከሆነ ልቀጥል እችላለሁ።' ሎዛ ከቢርኪርካራ ጋር የነበረኝ ቆይታ በጣም መልካም ነበር ትላለች። 'እርግጥ ነው አንድ ነገር ሲጀመር ሊከብድ ይችላል። ነገር ግን የማይለመድ የለም። ቡድኑ የነበረው ጥንካሬ ነበር። እዚያ ላይ የሁላችንም ጥረት ሲታከልበት ውጤታማ መሆን ችለናል።' እውን የማልታ የሴቶች ሊግ ለተጫዋቾች ጥሩ ክፍያ ይከፍላል ወይ የሚል ጥያቄ ከቢቢሲ የቀረበላት ሎዛ፤ ክፍያው እንኳ ቢቀር የማልታ ልምዱ ለወፊት የተሻለ ውድድር ውስጥ ራሷን እንድታገኝ እንደሚረዳት ትናገራለች። 'አንድን ነገር ለማሳካትስ ስታስብ ብዙ ነገሮችን ከግምት ታስገባለህ። እኔ ክፍያን እዚህ ውስጥ አልከተውም። የክፍያ ማነስ አለ እያልኩ ሳይሆን አላማዬ በዚህ ጉዞ ራሴን ለማሳየት፤ ወጥቼ መጫወት እንደምችል ለማሳየትና ፕሮፋይሌን ከፍ ለማድረግ ስለሆነ ተሳክቶልኛል ብዬ ነው የማስበው።' 'እርግጥ ነው የሃገሬ ምግብ ናፍቆኝ ነበር' ትላለች ከግማሽ ዓመት በላይ በአውሮጳዊቷ ትንሽዬ የጠረፍ ሃገር የቆየችው ሎዛ። ኮሮናቫይረስና እግር ኳስ ባለፈው ታኅሣሥ ድምፁ የተሰማው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሰው ልጅ ከጠበቀው በላይ ጥፋት አድርሷል፤ የተለመዱ የሕይወት መስተጋብሮችን እንዳይሆኑ አድርጓል። ወረርሽኙ ካመሰቃቀላቸው መስኮች አንዱ እግር ኳስ ነው። ይህ ወረርሽኝ በሎዛ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ሕይወት ላይ ያመጣው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? 'በጣም ከባድ ነው። እግር ኳስን ብቻ ሳይሆን ሌሎች መስኮችንም የጎዳና ለዓለም የመጣ ስለሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም።' ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ከውድድር ርቀው የነበሩ እግር ኳስ ተጫዋቾች አንዱ ፈተናቸው በያሉበት ሆነው የአካል ብቃታቸውን ጠብቀው መቆየት ነው። ሎዛስ? 'በአቅራብያዬ በሚገኙ ቦታዎች እየሄድኩ እሠራ ነበር። ሠፈር ውስጥም ቤትም ነው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የማደርገው። ራቅ ብሎ ሄዶ እንቅስቃሴ ለማድረግ ጊዜው ስለማይፈቅድ በምችለው መልኩ በአቅራቢያዬ ነበር እንቅስቃሴ ሳደርግ የነበረው።' ሎዛ እሷ ብቻ ሳትሆን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንና የቀድሞ ቡድኗ አዳማ ከነማ ተጫዎቾችን አልፎ አልፎ በስልክ እንደምታገኛቸው በታቻላቸው መጠን በአካባቢዎች እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳሉ ትናገራለች። አልፎም ሎዛ 'እንቅስቃሴ ማድረግ ከወረርሽኙ ሊታደገን ስለሚችል ሁሉም ሰው በያለበት የተቻለውን ያክል እንቅስቃሴ ቢያደርግ' ስትል ምክሯን ትለግሳለች። የሎዛ የአዲስ ዓመት ምኞት 'ሁላችንም ከምንወደው ሙያ ርቀን በቤታችን ነው ያለነው። ፈጣሪ ይህን ዓመት በሰላም አሻግሮ ይህንን ወረርሽኝ ያርቅልን፤ እንዲሁም ሁላችንንም ወደ ሥራ ይመልሰን ብዬ እመኛለሁ።' 'ስፖርተኛውም በስፖርቱ፤ ሌላውም በተሰማራበት መስክ በአዲሱ ዓመት የተሻለ ነገር እንሠራለን ብዬ ነው የማስበው።' ቢቢሲ፡ እናመሰግናለን ሎዛ፤ ለአንቺና ለቤተቦችሽ መልካም አዲስ ዓመት ማለት እንወዳለን። ሎዛ፡ እኔም አመሰግናለሁ። ለእናንተም መልካም አዲስ ዓመት!
እግር ኳስና ኮሮናቫይረስ፡ የኢትዮጵያን ስም በአውሮፓ ያስጠራችው ሎዛ ሎዛ አበራ በማልታ በሴቶች ዘርፍ የ2019/2020 የውድድር ዘመን ምርጥ ተጫዋች በመሆን በማልታ የእግርኳስ ተጫዋቾች ማህበር ተሸልማለች። ሎዛ ለቢቢሲ አዲስ አይደለችም። የማልታውን ቡድን ቢርኪርካራ እንደተቀላቀለች እንዴት ነው ሕይወት በአውሮፓ ስንል አናግረናት ነበር። ከዚያ ቃለ ምልልስ በኋላ ሎዛ ብዙ ታሪክ ፅፋለች። ሪከርድ ሰብራለች። ሎዛ ለሌሎች አንጋፋ የስፖርት መገናኛ ብዙሃንም አዲስ አይደለችም። ከጎል ዶት ኮም ጀምሮ እስከ ካፍ ኦንላይን ስለሎዛ አውርተው አይጠግቡም። ቡድኗ ቢርኪርካራ ተቃናቃኙ ሂበርኒያንስን በማልታ ታሪክ ከፍተኛ በሆነ ጎል 17 ለምንም ሲረታ ሎዛ 7 ጎል መረብ ላይ አሳርፋለች። የተወሰኑ ኳሶችንም ለጎል አመቻችታ አቀብላለች። ሎዛ ከዚህ ታሪካዊ ጨዋታ በፊትና በኋላ በርካታ ጎሎችን በማስቆጠር ቡድኗ የማልቲዝ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ እንዲሆን አድርጋለች። ሎዛአሁንየትነች? ሎዛ አሁን ያለችው ትውድል ቀዬዋ ነው። ከምባታ ዞን የምትገኘው ዱራሜ ከተማ። አጥቂዋ ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ በመጣችበት ነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተከሰተው። በዚህ ምክንያት ወደ ማልታ ተመልሳ ማቅናት አልቻለችም። ለነገሩ የማልቲዝ ሊግ በወረርሽኙ ምክንያት ተቋርጦ ነበር። ሎዛ ኢትዮጵያ እያለች ቡድኗ ቢርኪርካራ የማልታ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑ ይፋ ሆነ። ኢትዮጵያዊት ተስፈኛ አጥቂ በማልታ ሊግ የመጀመሪያ ዓመት ቆይታዋ በ12 ጨዋታዎች 30 ጎሎች በማስቆጠር ኮከብ ጎል አግቢ ሆናለች። 'ከቢርኪርካራ ጋር ባለድል በመሆኔ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር በመልካም ሁኔታ ተጠናቋል' ትላለች ሎዛ። የወደፊት ዕቅድ የማልታ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ የቀጣዩ ዓመት ውድድር በመጪው ጥቅምት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ከአዳማ ከነማ ቢርኪርካራን መስከረም 2012 ላይ የተቀላቀለችው ሎዛ ከቡድኑ ጋር ያላት ውል ተጠናቋል። ለመሆኑ ውሏን ለማራዘም አስባ ይሆን? 'ከቢርኪርካራ ጋር የነበረኝ ውል የአንድ ዓመት ነው። እሱ ተጠናቋል። እርግጥ ነው ቢርኪርካራ ውሌን ለማራዘም ጥያቄ አቅርበዋል። እኔም ያቀረብኩላቸው ቅድመ ሁኔታ አለ። በእሱ የምንስማማ ከሆነ ልቀጥል እችላለሁ።' ሎዛ ከቢርኪርካራ ጋር የነበረኝ ቆይታ በጣም መልካም ነበር ትላለች። 'እርግጥ ነው አንድ ነገር ሲጀመር ሊከብድ ይችላል። ነገር ግን የማይለመድ የለም። ቡድኑ የነበረው ጥንካሬ ነበር። እዚያ ላይ የሁላችንም ጥረት ሲታከልበት ውጤታማ መሆን ችለናል።' እውን የማልታ የሴቶች ሊግ ለተጫዋቾች ጥሩ ክፍያ ይከፍላል ወይ የሚል ጥያቄ ከቢቢሲ የቀረበላት ሎዛ፤ ክፍያው እንኳ ቢቀር የማልታ ልምዱ ለወፊት የተሻለ ውድድር ውስጥ ራሷን እንድታገኝ እንደሚረዳት ትናገራለች። 'አንድን ነገር ለማሳካትስ ስታስብ ብዙ ነገሮችን ከግምት ታስገባለህ። እኔ ክፍያን እዚህ ውስጥ አልከተውም። የክፍያ ማነስ አለ እያልኩ ሳይሆን አላማዬ በዚህ ጉዞ ራሴን ለማሳየት፤ ወጥቼ መጫወት እንደምችል ለማሳየትና ፕሮፋይሌን ከፍ ለማድረግ ስለሆነ ተሳክቶልኛል ብዬ ነው የማስበው።' 'እርግጥ ነው የሃገሬ ምግብ ናፍቆኝ ነበር' ትላለች ከግማሽ ዓመት በላይ በአውሮጳዊቷ ትንሽዬ የጠረፍ ሃገር የቆየችው ሎዛ። ኮሮናቫይረስና እግር ኳስ ባለፈው ታኅሣሥ ድምፁ የተሰማው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሰው ልጅ ከጠበቀው በላይ ጥፋት አድርሷል፤ የተለመዱ የሕይወት መስተጋብሮችን እንዳይሆኑ አድርጓል። ወረርሽኙ ካመሰቃቀላቸው መስኮች አንዱ እግር ኳስ ነው። ይህ ወረርሽኝ በሎዛ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ሕይወት ላይ ያመጣው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? 'በጣም ከባድ ነው። እግር ኳስን ብቻ ሳይሆን ሌሎች መስኮችንም የጎዳና ለዓለም የመጣ ስለሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም።' ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ከውድድር ርቀው የነበሩ እግር ኳስ ተጫዋቾች አንዱ ፈተናቸው በያሉበት ሆነው የአካል ብቃታቸውን ጠብቀው መቆየት ነው። ሎዛስ? 'በአቅራብያዬ በሚገኙ ቦታዎች እየሄድኩ እሠራ ነበር። ሠፈር ውስጥም ቤትም ነው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የማደርገው። ራቅ ብሎ ሄዶ እንቅስቃሴ ለማድረግ ጊዜው ስለማይፈቅድ በምችለው መልኩ በአቅራቢያዬ ነበር እንቅስቃሴ ሳደርግ የነበረው።' ሎዛ እሷ ብቻ ሳትሆን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንና የቀድሞ ቡድኗ አዳማ ከነማ ተጫዎቾችን አልፎ አልፎ በስልክ እንደምታገኛቸው በታቻላቸው መጠን በአካባቢዎች እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳሉ ትናገራለች። አልፎም ሎዛ 'እንቅስቃሴ ማድረግ ከወረርሽኙ ሊታደገን ስለሚችል ሁሉም ሰው በያለበት የተቻለውን ያክል እንቅስቃሴ ቢያደርግ' ስትል ምክሯን ትለግሳለች። የሎዛ የአዲስ ዓመት ምኞት 'ሁላችንም ከምንወደው ሙያ ርቀን በቤታችን ነው ያለነው። ፈጣሪ ይህን ዓመት በሰላም አሻግሮ ይህንን ወረርሽኝ ያርቅልን፤ እንዲሁም ሁላችንንም ወደ ሥራ ይመልሰን ብዬ እመኛለሁ።' 'ስፖርተኛውም በስፖርቱ፤ ሌላውም በተሰማራበት መስክ በአዲሱ ዓመት የተሻለ ነገር እንሠራለን ብዬ ነው የማስበው።' ቢቢሲ፡ እናመሰግናለን ሎዛ፤ ለአንቺና ለቤተቦችሽ መልካም አዲስ ዓመት ማለት እንወዳለን። ሎዛ፡ እኔም አመሰግናለሁ። ለእናንተም መልካም አዲስ ዓመት!
https://www.bbc.com/amharic/news-54101682
0business
ፓኪስታን ዜጎቿ የሻይ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ ጠየቀች
የፓኪስታን ዜጎች በአገሪቱ ያለውን የምጣኔ ሃብት ቀውስ ለማረጋጋት የሚጠጡትን የሻይ መጠን እንዲቀንሱ ተጠየቁ። የፓኪስታን ከፍተኛ ሚኒስትር አህሳን ኢቅባል፣ በቀን ጥቂት ብርጭቆ ሻይ መጎንጨት ፓኪስታን የሻይ ቅጠል ምርትን ከውጪ ለማስገባት የምታወጣውን ወጪ ይቀንሳል ብለዋል። በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከውጭ የሚገባ ማንኛውም ምርት ለመግዛት የሚበቃው ከሁለት ወር ላነሰ ጊዜ ብቻ ነው ተብሏል። ይህም አገሪቷን አስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ እንድትፈልግ አስገድዷታል። ፓኪስታን ባለፈው ዓመት ከ600 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ ሻይ ቅጠል ከውጭ በማስገባት ከዓለም ከፍተኛውን ሻይ ቅጠል አስመጪነት ቦታን ይዛለች። እንደ ፓኪስታን ሚዲያ ከሆነ ሚኒስትር ኢቅባል “የአገሬው ሰው የሻይ ፍጆታውን ወደ አንድ ወይም ሁለት ብርጭቆ እንዲቀንስ እጠይቃለሁ። ምክንያቱም ሻይ ቅጠል የምናስገባው በብድር ነው” ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የንግድ ተቋማት የሚጠቀሙትን የኤሌክትሪክ ኃይል ለመቆጠብ የንግድ ቦታቸውን ምሽት 2፡30 ላይ እንዲዘጉ ሚኒስትሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ተማፅኖው ለፓኪስታን ሕዝብ የቀረበው የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በተከታታይ እና በፍጥነት እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ ነው። ይህም በአገሪቱ፣ መንግሥት ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት የሚያወጣቸውን ወጪዎች በመቀነስ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ይዞ እንዲያቆይ አስገድዶታል። የአገሪቷ ሕዝቦች የሻይ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ መጠየቃቸው በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል። አብዛኛው ሰውም አገሪቷ የገጠማት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ቀውስ የሻይ ፍጆታን በመቀነስ ይፈታል የሚል እምነት የለውም። የፓኪስታን የውጭ ምንዛሬ ክምችት የካቲት ወር ላይ ከነበረው 16 ቢሊየን ዶላር በሰኔ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ወደ ከ10 ቢሊየን ዶላር በታች አሽቆልቁሏል። ባለፈው ወር የካራቺ ባለሥልጣናት በአገሪቷ ያለውን የውጪ ምንዛሬ ክምችት ለመጠበቅ በርካታ መሠረታዊ ያልሆኑ የቅንጦት እቃዎች እንዳይገቡ ገደብ ጥለው ነበር። በአገሪቷ ያለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ፣ ባለፈው ሚያዝያ ወር በተደረገው የምክር ቤት ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህንን ለተኩት ሸህባዝ ሸሪፍ መንግሥት ትልቅ ፈተና ሆኗል። ሸሪፍ ሥልጣን ተረክበው ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ የአገሪቷ ምጣኔ ሃብት በአግባቡ አልተመራም፤ ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመመለስም ከባድ ነው ሲሉ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰዋል። ባለፈው ሳምንት ካቢኔው፣ የተቋረጠውን የ6 ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም እንዲጀመር ዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት(አይኤምኤፍ)ን ለማሳመን የ47 ቢሊየን ዶላር በጀት አጽድቋል። አይኤምኤፍ እአአ በ2019 በውጭ ምንዛሬ እጥረት እና ለዓመታት በዘገየ እድገት ምክንያት የሚፈጠር የምጣኔ ሃብት ቀውስን ለማቃለል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም፣ አበዳሪዎች አገሪቷ ብድሩን ለመክፈል ያላትን የፋይናንስ አቅም ከጠየቁ በኋላ ቆሟል።
ፓኪስታን ዜጎቿ የሻይ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ ጠየቀች የፓኪስታን ዜጎች በአገሪቱ ያለውን የምጣኔ ሃብት ቀውስ ለማረጋጋት የሚጠጡትን የሻይ መጠን እንዲቀንሱ ተጠየቁ። የፓኪስታን ከፍተኛ ሚኒስትር አህሳን ኢቅባል፣ በቀን ጥቂት ብርጭቆ ሻይ መጎንጨት ፓኪስታን የሻይ ቅጠል ምርትን ከውጪ ለማስገባት የምታወጣውን ወጪ ይቀንሳል ብለዋል። በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከውጭ የሚገባ ማንኛውም ምርት ለመግዛት የሚበቃው ከሁለት ወር ላነሰ ጊዜ ብቻ ነው ተብሏል። ይህም አገሪቷን አስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ እንድትፈልግ አስገድዷታል። ፓኪስታን ባለፈው ዓመት ከ600 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ ሻይ ቅጠል ከውጭ በማስገባት ከዓለም ከፍተኛውን ሻይ ቅጠል አስመጪነት ቦታን ይዛለች። እንደ ፓኪስታን ሚዲያ ከሆነ ሚኒስትር ኢቅባል “የአገሬው ሰው የሻይ ፍጆታውን ወደ አንድ ወይም ሁለት ብርጭቆ እንዲቀንስ እጠይቃለሁ። ምክንያቱም ሻይ ቅጠል የምናስገባው በብድር ነው” ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የንግድ ተቋማት የሚጠቀሙትን የኤሌክትሪክ ኃይል ለመቆጠብ የንግድ ቦታቸውን ምሽት 2፡30 ላይ እንዲዘጉ ሚኒስትሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ተማፅኖው ለፓኪስታን ሕዝብ የቀረበው የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በተከታታይ እና በፍጥነት እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ ነው። ይህም በአገሪቱ፣ መንግሥት ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት የሚያወጣቸውን ወጪዎች በመቀነስ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ይዞ እንዲያቆይ አስገድዶታል። የአገሪቷ ሕዝቦች የሻይ ፍጆታቸውን እንዲቀንሱ መጠየቃቸው በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል። አብዛኛው ሰውም አገሪቷ የገጠማት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ቀውስ የሻይ ፍጆታን በመቀነስ ይፈታል የሚል እምነት የለውም። የፓኪስታን የውጭ ምንዛሬ ክምችት የካቲት ወር ላይ ከነበረው 16 ቢሊየን ዶላር በሰኔ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ወደ ከ10 ቢሊየን ዶላር በታች አሽቆልቁሏል። ባለፈው ወር የካራቺ ባለሥልጣናት በአገሪቷ ያለውን የውጪ ምንዛሬ ክምችት ለመጠበቅ በርካታ መሠረታዊ ያልሆኑ የቅንጦት እቃዎች እንዳይገቡ ገደብ ጥለው ነበር። በአገሪቷ ያለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ፣ ባለፈው ሚያዝያ ወር በተደረገው የምክር ቤት ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህንን ለተኩት ሸህባዝ ሸሪፍ መንግሥት ትልቅ ፈተና ሆኗል። ሸሪፍ ሥልጣን ተረክበው ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ የአገሪቷ ምጣኔ ሃብት በአግባቡ አልተመራም፤ ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመመለስም ከባድ ነው ሲሉ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰዋል። ባለፈው ሳምንት ካቢኔው፣ የተቋረጠውን የ6 ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም እንዲጀመር ዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት(አይኤምኤፍ)ን ለማሳመን የ47 ቢሊየን ዶላር በጀት አጽድቋል። አይኤምኤፍ እአአ በ2019 በውጭ ምንዛሬ እጥረት እና ለዓመታት በዘገየ እድገት ምክንያት የሚፈጠር የምጣኔ ሃብት ቀውስን ለማቃለል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም፣ አበዳሪዎች አገሪቷ ብድሩን ለመክፈል ያላትን የፋይናንስ አቅም ከጠየቁ በኋላ ቆሟል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1zzww9vrpo
3politics
ንግሥቲቱ እና አፍሪካ: ረጅም ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት
የያኔዋ ልዕልት ኤልዛቤጥ በኬንያ ገጠራማ ሥፍራ በሚገኘውና በአረንጓዴ ተክሎች፣ በረጃጅም ዛፎች እና በዱር አራዊት በተከበበው ትሬቶፕስ ሆቴል ሲደርሱ አባታቸው ንጉስ ጆርጅ ስድስተኛ አረፉ።በዚያም በ25 ዓመታቸው የንግሥትነት ሥፍራውን ያዙ። ንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ በሰባ ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ከ20 በላይ የአፍሪካ አገሮችን ጎብኝተዋል። በአንድ ወቅት ለቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ከማንኛውም ሰው በላይ የአፍሪካ አገራትን ጎብኝቻለሁ በማለት በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችን ፈገግ አሰኝተው ነበር። ንግሥት ሲሆኑም በርካታ አገራትን ያካተተ የአፍሪካ አህጉርን በግዛትነት ጠቅልለው ወርሰው ነበር። በግዛት ዘመናቸውም በአውሮፓውያኑ 1957 ነጻነቷን ካገኘችው ጋና ጀምሮ 14ቱም የአፍሪካ አገራት የእንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች ነጻነታቸውን አግኝተዋል። ንግሥቲቷ ነፃነታቸውን ካገኙ አገራትም ጋር ሞቅ ያለ ግንኙነትን መፍጠር ችለዋል፤ ይህን ማድረግ የቻሉትም በከፊል የብሪታንያ ግዛት ተተኪ የሆነውን የኮመንዌልዝ ድርጅትን በመመስረት ነው። በአውሮፓውያኑ 1961 ጋና ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ እንድትሆን ከመሩት እና የመጀመሪያዋ ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንክሩማህ ጋር ሲደንሱም ታይተዋል። በተለይም ኢምፓየር (ግዛት) የሚለው ቃል በአውሮፓውያኑ 1953 በነበረው የንግሥና በዓለ ሲመትና መሃላ ወቅት እንዲቀር ተደርጓል። ንግሥቲቱ ማረፋቸውን ተከትሎ ከአህጉሪቱ የተውጣጡ መሪዎች ብሪታንያ እና ኮመንዌልዝን ለረጅም ዓመታት በንግሥና ለመሩትን ንግሥት ኤልዛቤጥ ሃዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ንግሥናቸው የተጀመረበት ኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ “ከራስ ባለፈ ለሰው ልጅ የሚያገለግሉ ትልቅ ተምሳሌት የሆኑና እና የዩናይትድ ኪንግደም ብቻ ሳይሆን ኬንያ የተከበረች አባል የሆነችበት የኮመንዌልዝ ኅብረት ቁልፍ መሪ ናቸው” ሲሉ ገልጸዋቸዋል። የዚምባብዌ እና የዩናይትድ ኪንግደም ግንኙነት ለረጅም ዓመታት ሻክሮ የቆየ ሲሆን ሟቹ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ አገራቸው ከኮመንዌልዝ ኅብረት አባልነት ለቃ እንድትወጣ አድርገዋል። ሆኖም ተተኪያቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋ “የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለንጉሳዊው ቤተሰብ፣ ለዩናይትድ ኪንግደም እና ኮመንዌልዝ” በትዊተር ገጻቸው በፍጥነት ገልጸዋል። በአፍሪካ ትልቋ ግዛት የነበረችው ናይጄሪያ መሪ ሙሃማዱ ቡሃሪ በበኩላቸው፣ ረዘም ያለ የሀዘን መግለጫ በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩ ሲሆን “ከፍተኛ ሃዘንም ተሰምቶኛል” ብለዋል። "የዘመናዊቷ ናይጄሪያ የታሪክ ምዕራፍ፣ ዓለም አቀፋዊ ስብዕና እና የላቀ መሪ ከሆኑት ያለ ንግሥት ኤልዛቤጥ ሙሉ አይሆንም። ሕይወታቸውን ለሕዝባቸው፣ ለኮመንዌልዝ እንዲሁም መላው ዓለምን የተሻለ ቦታ ለማድረግ ሰጥተዋል” ብለዋል። የግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቻርለስ ሳልሳዊ ወደ ዙፋኑ መምጣታቸውንም ፕሬዚዳንቱ በደስታ ተቀብለውታል። አዲሷ የኮመንዌልዝ አባል የሆነችውና የፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛት የነበረችው ጋቦን ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎም ሀዘናቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። የአህጉሪቱ መሪዎች የሀዘን መግለጫቸውን ቢያስተላልፉም ሌሎች አፍሪካውያን በበኩላቸው በብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ወቅት የደረሰባቸውን ስቃይና በደል እየተናገሩ ሲሆን፣ ይህም በንጉሳዊ ቤተሰቦች ስም ተፈጽሟል እያሉ ነው። አንዳንድ የአፍሪካ ንጉሶችና ቤተሰቦችም ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ልዑል ማንጎሱቱ ቡተሌዚ፣ በደቡብ አፍሪካ ዙሉ ሕዝብ መሪ ንጉስ ሚሱዙሉ ካዝዌሊቲኒ ስም ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ከንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ ጋር ያላቸውን ወዳጅነትም በመጥቀስ ለእርሳቸውም በግላቸው የሀዘን መግለጫ ልከዋል። ንጉሥ ሚሱዙሊ፣ አባታቸው ዝዌሊቲኒ ከ50 ዓመታት ንግሥና በኋላ በቅርብ ጊዜ ያረፉ ሲሆን የንጉሥ ቻርለስንም ሁኔታ በቅርበት ይረዳሉ። ንግሥቲቱ ከደቡብ አፍሪካ ጋር የረጅም ጊዜ ታሪክ አላቸው። በአውሮፓውያኑ 1947 የ21ኛ ዓመት ልደታቸውን ያከበሩት በደቡብ አፍሪካ በጉብኝት ላይ ነበር። በኬፕታውን በሬድዮ ላይ በሰጡት መግለጫ ሕይወታቸውን ለኮመንዌልዝ ኅብረት እንደሰጡና ደቡብ አፍሪካም ሙሉ ሕይወታቸውን የኖሩበትን ያህል “በአገሬ ያለሁ ያህል ይሰማኛል” ብለዋል። የፖለቲካ አቋማቸውን በማንጸባረቅ የማይታወቁት ንግሥት ኤልዛቤጥ ለአስርት ዓመታት በአገሪቱ ውስጥ የነጮች ጥቂቶች አገዛዝ ካበቃ ከአንድ ዓመት በኋላ በአውሮፓውያኑ 1995 ደቡብ አፍሪካን ሲጎበኙ ጠንከር ያለ ንግግር አድርገዋል። “የእርቅ መንፈሱ ለዓለም ተምሳሌት የሆነ የሕዝብን አንድነት አምጥቷል። እኔም ተመልሼ መጥቼ ይህንን ተአምር ለመመልከት ችያለሁ” በማለት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። ንግሥቲቱ ከኔልሰን ማንዴላ ጋር መልካም ግንኙነት ነበራቸው። የንግሥቲቱን ማረፍ ተከትሎ የኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን፣ “[ ከኔልሰን ማንዴላ] ጋር በተደጋጋሚ በስልክ ያወሩ ነበር። ያለ ቅጥያ ክብር ስም በመጀመሪያ ስማቸው ነበር የሚጠራሩት ይህም የመከባበር እና የመውደድ ምልክት ነው” በማለት መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው አክሎም ማንዴላ ለንግሥቲቷ ልዩ ስም ነበራቸው “ሞትላሌፑላ፣ የሚል ሲሆን ትርጉሙም ከዝናብ ጋር መምጣት ማለት ነው” ለዚህም በአውሮፓውያኑ 1995 ሲመጡ ዝናብ ከመዝነቡ ጋር በመገጣጠሙ ነው።
ንግሥቲቱ እና አፍሪካ: ረጅም ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት የያኔዋ ልዕልት ኤልዛቤጥ በኬንያ ገጠራማ ሥፍራ በሚገኘውና በአረንጓዴ ተክሎች፣ በረጃጅም ዛፎች እና በዱር አራዊት በተከበበው ትሬቶፕስ ሆቴል ሲደርሱ አባታቸው ንጉስ ጆርጅ ስድስተኛ አረፉ።በዚያም በ25 ዓመታቸው የንግሥትነት ሥፍራውን ያዙ። ንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ በሰባ ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ከ20 በላይ የአፍሪካ አገሮችን ጎብኝተዋል። በአንድ ወቅት ለቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ከማንኛውም ሰው በላይ የአፍሪካ አገራትን ጎብኝቻለሁ በማለት በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችን ፈገግ አሰኝተው ነበር። ንግሥት ሲሆኑም በርካታ አገራትን ያካተተ የአፍሪካ አህጉርን በግዛትነት ጠቅልለው ወርሰው ነበር። በግዛት ዘመናቸውም በአውሮፓውያኑ 1957 ነጻነቷን ካገኘችው ጋና ጀምሮ 14ቱም የአፍሪካ አገራት የእንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች ነጻነታቸውን አግኝተዋል። ንግሥቲቷ ነፃነታቸውን ካገኙ አገራትም ጋር ሞቅ ያለ ግንኙነትን መፍጠር ችለዋል፤ ይህን ማድረግ የቻሉትም በከፊል የብሪታንያ ግዛት ተተኪ የሆነውን የኮመንዌልዝ ድርጅትን በመመስረት ነው። በአውሮፓውያኑ 1961 ጋና ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ እንድትሆን ከመሩት እና የመጀመሪያዋ ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንክሩማህ ጋር ሲደንሱም ታይተዋል። በተለይም ኢምፓየር (ግዛት) የሚለው ቃል በአውሮፓውያኑ 1953 በነበረው የንግሥና በዓለ ሲመትና መሃላ ወቅት እንዲቀር ተደርጓል። ንግሥቲቱ ማረፋቸውን ተከትሎ ከአህጉሪቱ የተውጣጡ መሪዎች ብሪታንያ እና ኮመንዌልዝን ለረጅም ዓመታት በንግሥና ለመሩትን ንግሥት ኤልዛቤጥ ሃዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ንግሥናቸው የተጀመረበት ኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ “ከራስ ባለፈ ለሰው ልጅ የሚያገለግሉ ትልቅ ተምሳሌት የሆኑና እና የዩናይትድ ኪንግደም ብቻ ሳይሆን ኬንያ የተከበረች አባል የሆነችበት የኮመንዌልዝ ኅብረት ቁልፍ መሪ ናቸው” ሲሉ ገልጸዋቸዋል። የዚምባብዌ እና የዩናይትድ ኪንግደም ግንኙነት ለረጅም ዓመታት ሻክሮ የቆየ ሲሆን ሟቹ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ አገራቸው ከኮመንዌልዝ ኅብረት አባልነት ለቃ እንድትወጣ አድርገዋል። ሆኖም ተተኪያቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋ “የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለንጉሳዊው ቤተሰብ፣ ለዩናይትድ ኪንግደም እና ኮመንዌልዝ” በትዊተር ገጻቸው በፍጥነት ገልጸዋል። በአፍሪካ ትልቋ ግዛት የነበረችው ናይጄሪያ መሪ ሙሃማዱ ቡሃሪ በበኩላቸው፣ ረዘም ያለ የሀዘን መግለጫ በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩ ሲሆን “ከፍተኛ ሃዘንም ተሰምቶኛል” ብለዋል። "የዘመናዊቷ ናይጄሪያ የታሪክ ምዕራፍ፣ ዓለም አቀፋዊ ስብዕና እና የላቀ መሪ ከሆኑት ያለ ንግሥት ኤልዛቤጥ ሙሉ አይሆንም። ሕይወታቸውን ለሕዝባቸው፣ ለኮመንዌልዝ እንዲሁም መላው ዓለምን የተሻለ ቦታ ለማድረግ ሰጥተዋል” ብለዋል። የግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቻርለስ ሳልሳዊ ወደ ዙፋኑ መምጣታቸውንም ፕሬዚዳንቱ በደስታ ተቀብለውታል። አዲሷ የኮመንዌልዝ አባል የሆነችውና የፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛት የነበረችው ጋቦን ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎም ሀዘናቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። የአህጉሪቱ መሪዎች የሀዘን መግለጫቸውን ቢያስተላልፉም ሌሎች አፍሪካውያን በበኩላቸው በብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ወቅት የደረሰባቸውን ስቃይና በደል እየተናገሩ ሲሆን፣ ይህም በንጉሳዊ ቤተሰቦች ስም ተፈጽሟል እያሉ ነው። አንዳንድ የአፍሪካ ንጉሶችና ቤተሰቦችም ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ልዑል ማንጎሱቱ ቡተሌዚ፣ በደቡብ አፍሪካ ዙሉ ሕዝብ መሪ ንጉስ ሚሱዙሉ ካዝዌሊቲኒ ስም ሀዘናቸውን ገልጸዋል። ከንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ ጋር ያላቸውን ወዳጅነትም በመጥቀስ ለእርሳቸውም በግላቸው የሀዘን መግለጫ ልከዋል። ንጉሥ ሚሱዙሊ፣ አባታቸው ዝዌሊቲኒ ከ50 ዓመታት ንግሥና በኋላ በቅርብ ጊዜ ያረፉ ሲሆን የንጉሥ ቻርለስንም ሁኔታ በቅርበት ይረዳሉ። ንግሥቲቱ ከደቡብ አፍሪካ ጋር የረጅም ጊዜ ታሪክ አላቸው። በአውሮፓውያኑ 1947 የ21ኛ ዓመት ልደታቸውን ያከበሩት በደቡብ አፍሪካ በጉብኝት ላይ ነበር። በኬፕታውን በሬድዮ ላይ በሰጡት መግለጫ ሕይወታቸውን ለኮመንዌልዝ ኅብረት እንደሰጡና ደቡብ አፍሪካም ሙሉ ሕይወታቸውን የኖሩበትን ያህል “በአገሬ ያለሁ ያህል ይሰማኛል” ብለዋል። የፖለቲካ አቋማቸውን በማንጸባረቅ የማይታወቁት ንግሥት ኤልዛቤጥ ለአስርት ዓመታት በአገሪቱ ውስጥ የነጮች ጥቂቶች አገዛዝ ካበቃ ከአንድ ዓመት በኋላ በአውሮፓውያኑ 1995 ደቡብ አፍሪካን ሲጎበኙ ጠንከር ያለ ንግግር አድርገዋል። “የእርቅ መንፈሱ ለዓለም ተምሳሌት የሆነ የሕዝብን አንድነት አምጥቷል። እኔም ተመልሼ መጥቼ ይህንን ተአምር ለመመልከት ችያለሁ” በማለት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። ንግሥቲቱ ከኔልሰን ማንዴላ ጋር መልካም ግንኙነት ነበራቸው። የንግሥቲቱን ማረፍ ተከትሎ የኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን፣ “[ ከኔልሰን ማንዴላ] ጋር በተደጋጋሚ በስልክ ያወሩ ነበር። ያለ ቅጥያ ክብር ስም በመጀመሪያ ስማቸው ነበር የሚጠራሩት ይህም የመከባበር እና የመውደድ ምልክት ነው” በማለት መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው አክሎም ማንዴላ ለንግሥቲቷ ልዩ ስም ነበራቸው “ሞትላሌፑላ፣ የሚል ሲሆን ትርጉሙም ከዝናብ ጋር መምጣት ማለት ነው” ለዚህም በአውሮፓውያኑ 1995 ሲመጡ ዝናብ ከመዝነቡ ጋር በመገጣጠሙ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c514xy2zzqqo
2health
የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ አዲስ አይነት የአእምሮ ጤና እክል ይዞ መጥቷል ተባለ
በኮሮናቫይረስ ከሚያዙ ሰዎች በእያንዳንዱ 17 ሰው አንድ ሰው ከባድ ጭንቀት፣ ድብርት እና እንቅልፍ ማጣት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያጋጥመው አንድ አሜሪካ ውስጥ የተሰራ ጥናት ጠቁሟል። ይህ ቁጥር ታዲያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸው እንዲህ አይነት የጤና እክል ከሌሎች በሽታዎች ጋር ሲነጻጸር እጥፍ እንደሆነ ደርሰንበታል ይላሉ ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች። በጥናቱ መሰረት ባልተጠበቀ ሁኔታ የቀደም የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በኮሮናቫይረስ የመያዝ እድላቸው ከጤናማ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር 65 በመቶ ከፍ ያለ እንደሆነ ደርሰንበታል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያትነት የተቀመጠው የአእምሮ ጤና ችግር ኣላባቸው ታማሚዎች ሰውነታቸው የሚገኝበት አካላዊ ጥንካሬ፣ የሚወስዷቸው መድሀኒቶችና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ናቸው። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑትና የጥናቱ መሪው ፖል ሀሪሰን እንደሚሉት ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ ለከባድ የአእምሮ ጤና እክል የመጋለጣቸው እድል አብሮ ይጨምራል። ''ሌላው ቀርቶ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጦ ነገር ግን ሆስፒታል ሳይሄዱ በቤታቸው የዳኑት እንኳን ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው'' ይላሉ። ተመራማሪዎቹ 62 ሺህ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ፈቃደኛ ሰዎችን ለሶስት ወራት ያክል ሲከታተሉ የነበረ ሲሆን ከእነሱ የሚያገኙትን መረጃ እንደ ጉንፋን፣ የኩላሊት ህመም እንዲሁም የአጥንት ስብራት ካጋጠማቸው ሰዎች ጋር አወዳድረውታል፥። በዚህም መሰረት በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች ከፍተኛ የአእምሮ ጤና መቃወስ ታይቶባቸዋል ተብሏል። በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች በከባድ ጭንቀት፣ ድብርት እና እንቅልፍ ማጣት የመጠቃት ዕድላቸው ከሌሎቹ አንጻር 18 በመቶ ከፍ ብሎ ታይቷል። እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች መጠራጠርን እና ፍርሃትን መቋቋም አለመቻል የተለመደ የአእምሮ ህመም ባህሪ እንደሆነ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። "ብዙ ጊዜ የጭንቀት ህመም ገና ባልተፈጠረና ባልታወቀ ነገር ላይ ይሆናል ብሎ አብዝቶ በመጨነቅ የሚመጣ ነው። ከዚህ አንፃር ኮሮናቫይረስ ከባድ ነገር ነው" ፕሮፌሰር ፖል ሀሪሰን አዲስ ነገር በሚያጋጥመን ጊዜ አዕምሯችን ለተፈጠረው ነገር በተለያየ መንገዶች ምላሽ ይሰጣል። በአሁኑ ወቅት መላውን ዓለም እያስጨነቀ ያለው ኮሮናቫይረስም በኑሯችን፣ በሥራችናና በአጠቃላይ ህይወታችን ላይ ከዚህ በፊት ያልነበረ ሁኔታን ፈጥሯል። በዚህም ሳቢያ አዕምሯችን ወረርሽኙን በተመለከተና ተያያዥ ነገሮችን በተለየ ሁኔታ ለመገንዘብ ተገዷል። ይህም ክስተት ነው በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ለተለያዩ የአእምሮ ጤና ችግሮች እያጋለጣቻው የሚገኘው። ሰዎች አይደለም እንዲህ ነገሮች ከበድ ባሉበት ወቅት አይደለም በደህናው ዘመን እንኳን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በአካል ማግኘት አስቸጋሪ ሲሆንና ሃሳብ ጭንቀታቸውን አይን አይናቸውን እያዩ ማካፈል ሳይችሉ ሲቀሩ ቀላል የማይባል ሥነ ልቦናዊ ጫና ይደርስባቸዋል።
የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ አዲስ አይነት የአእምሮ ጤና እክል ይዞ መጥቷል ተባለ በኮሮናቫይረስ ከሚያዙ ሰዎች በእያንዳንዱ 17 ሰው አንድ ሰው ከባድ ጭንቀት፣ ድብርት እና እንቅልፍ ማጣት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያጋጥመው አንድ አሜሪካ ውስጥ የተሰራ ጥናት ጠቁሟል። ይህ ቁጥር ታዲያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸው እንዲህ አይነት የጤና እክል ከሌሎች በሽታዎች ጋር ሲነጻጸር እጥፍ እንደሆነ ደርሰንበታል ይላሉ ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች። በጥናቱ መሰረት ባልተጠበቀ ሁኔታ የቀደም የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በኮሮናቫይረስ የመያዝ እድላቸው ከጤናማ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር 65 በመቶ ከፍ ያለ እንደሆነ ደርሰንበታል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያትነት የተቀመጠው የአእምሮ ጤና ችግር ኣላባቸው ታማሚዎች ሰውነታቸው የሚገኝበት አካላዊ ጥንካሬ፣ የሚወስዷቸው መድሀኒቶችና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ናቸው። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑትና የጥናቱ መሪው ፖል ሀሪሰን እንደሚሉት ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ ለከባድ የአእምሮ ጤና እክል የመጋለጣቸው እድል አብሮ ይጨምራል። ''ሌላው ቀርቶ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጦ ነገር ግን ሆስፒታል ሳይሄዱ በቤታቸው የዳኑት እንኳን ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው'' ይላሉ። ተመራማሪዎቹ 62 ሺህ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ፈቃደኛ ሰዎችን ለሶስት ወራት ያክል ሲከታተሉ የነበረ ሲሆን ከእነሱ የሚያገኙትን መረጃ እንደ ጉንፋን፣ የኩላሊት ህመም እንዲሁም የአጥንት ስብራት ካጋጠማቸው ሰዎች ጋር አወዳድረውታል፥። በዚህም መሰረት በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች ከፍተኛ የአእምሮ ጤና መቃወስ ታይቶባቸዋል ተብሏል። በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች በከባድ ጭንቀት፣ ድብርት እና እንቅልፍ ማጣት የመጠቃት ዕድላቸው ከሌሎቹ አንጻር 18 በመቶ ከፍ ብሎ ታይቷል። እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች መጠራጠርን እና ፍርሃትን መቋቋም አለመቻል የተለመደ የአእምሮ ህመም ባህሪ እንደሆነ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። "ብዙ ጊዜ የጭንቀት ህመም ገና ባልተፈጠረና ባልታወቀ ነገር ላይ ይሆናል ብሎ አብዝቶ በመጨነቅ የሚመጣ ነው። ከዚህ አንፃር ኮሮናቫይረስ ከባድ ነገር ነው" ፕሮፌሰር ፖል ሀሪሰን አዲስ ነገር በሚያጋጥመን ጊዜ አዕምሯችን ለተፈጠረው ነገር በተለያየ መንገዶች ምላሽ ይሰጣል። በአሁኑ ወቅት መላውን ዓለም እያስጨነቀ ያለው ኮሮናቫይረስም በኑሯችን፣ በሥራችናና በአጠቃላይ ህይወታችን ላይ ከዚህ በፊት ያልነበረ ሁኔታን ፈጥሯል። በዚህም ሳቢያ አዕምሯችን ወረርሽኙን በተመለከተና ተያያዥ ነገሮችን በተለየ ሁኔታ ለመገንዘብ ተገዷል። ይህም ክስተት ነው በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ለተለያዩ የአእምሮ ጤና ችግሮች እያጋለጣቻው የሚገኘው። ሰዎች አይደለም እንዲህ ነገሮች ከበድ ባሉበት ወቅት አይደለም በደህናው ዘመን እንኳን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በአካል ማግኘት አስቸጋሪ ሲሆንና ሃሳብ ጭንቀታቸውን አይን አይናቸውን እያዩ ማካፈል ሳይችሉ ሲቀሩ ቀላል የማይባል ሥነ ልቦናዊ ጫና ይደርስባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54885168
3politics
ሊዝ ትረስ ከንግሥቲቱ ጋር ከተገናኙ በኋላ በይፋ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ
ትናንት ሰኞ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት ሊዝ ትረስ ዛሬ ማክሰኞ ከንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ ጋር ከተገኙ በኋላ በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ። ሊዝ ትረስ ወደ ባልሞራል ቤተ-መንግሥት ተጉዘው ንግሥት ኤልዛቤጥን ያገኙት በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የተለመደ አካሄድን መከተል ስላለባቸው ነው። የዩኬ እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤጥ ዳግማዊት በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ሊዝ ትረስ 15ኛ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ንግሥቲቱን ያገኙት ቀደም ሲል ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለንግሥቲቱ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ካስገቡ በኋላ ነው። ሊዝ ትረስ ከባኪንግሃም ይልቅ ስኮትላንድ ወደ ሚገኘው ባልሞራል ቤተ-መንግሥት መሄድ ያስፈለጋቸው ንግሥቲቱ ለመንቀሳቀስ የጤና እክል ስለገጠማቸው ነው ተብሏል። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር በመጀመሪያው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቀናቸው ቀሪ የሥልጣን ዘመናቸውን የሚጀመሩት በሚከተሉት ተግባራት ይሆናል። በቅድሚያ ንግሥት ኤልዛቤት፣ ሊዝ ትረስ ካቢኔያቸውን አዋቅረው መንግሥት እንዲመሰርቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ግብዣ ያቀርባሉ። ሊዝ ትረስም ‘እጅ መሳም’ ተብሎ በሚጠራው ሥርዓት ግብዣውን ይቀበላሉ። ከዚያም በይፋ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሊዝ ትረስ ወደ መኖሪያ እና የሥራ ቦታቸው ወደሚሆነው 10 ዶውኒንግ ስትሪት በማቅናት ከጥቁሩ በር ፊትለፊት የመጀመሪያ ንግግራቸውን ያደርጋሉ። ሊዝ ትረስ በዚህ ንግግራቸው የአስተዳደራቸው ዋና ዓላማዎች ምን እንደሆኑ ያብራራሉ። ቀጥሎ ባሉት ቀናት ሊዝ ትረስ ከሚተገብሯቸው ተግባራት መካከል አንዱ ለዩኬ ጦር ኃላፊዎች ደብዳቤ መጻፍ ነው። በዚህ ጽሑፋቸው ዩናይትድ ኪንግደም የኒውክለር ጥቃት ቢፈጸምባት ምላሿ ምን ይሆናል የሚል ነው። ይህ ደብዳቤ ታዲያ የሚከፈተው ጦሩ ከዩኬ መንግሥት ጋር ግንኙነቱ ከተቋረጠ ነው። ሊዝ ትረስ ዛሬ በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት የዩኬ ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ነው። ባለፉት ዓመታት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሊዝ ትረስ፤ የወግ አጥባቂ መሪ ለመሆን ከቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ብርቱ ፉክክር ገጥሟቸው ነበር። ይሁን እንጂ የኋላ ኋላ ሊዝ ትረስ በሰፊ የድምጽ ብልጫ ሪሺ ሱናክን በመብለጥ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ እንዲሆኑ በፓርቲው አባላት ተመርጠዋል።
ሊዝ ትረስ ከንግሥቲቱ ጋር ከተገናኙ በኋላ በይፋ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ ትናንት ሰኞ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት ሊዝ ትረስ ዛሬ ማክሰኞ ከንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ ጋር ከተገኙ በኋላ በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ። ሊዝ ትረስ ወደ ባልሞራል ቤተ-መንግሥት ተጉዘው ንግሥት ኤልዛቤጥን ያገኙት በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የተለመደ አካሄድን መከተል ስላለባቸው ነው። የዩኬ እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤጥ ዳግማዊት በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው ሊዝ ትረስ 15ኛ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ንግሥቲቱን ያገኙት ቀደም ሲል ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለንግሥቲቱ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ካስገቡ በኋላ ነው። ሊዝ ትረስ ከባኪንግሃም ይልቅ ስኮትላንድ ወደ ሚገኘው ባልሞራል ቤተ-መንግሥት መሄድ ያስፈለጋቸው ንግሥቲቱ ለመንቀሳቀስ የጤና እክል ስለገጠማቸው ነው ተብሏል። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር በመጀመሪያው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቀናቸው ቀሪ የሥልጣን ዘመናቸውን የሚጀመሩት በሚከተሉት ተግባራት ይሆናል። በቅድሚያ ንግሥት ኤልዛቤት፣ ሊዝ ትረስ ካቢኔያቸውን አዋቅረው መንግሥት እንዲመሰርቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ግብዣ ያቀርባሉ። ሊዝ ትረስም ‘እጅ መሳም’ ተብሎ በሚጠራው ሥርዓት ግብዣውን ይቀበላሉ። ከዚያም በይፋ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሊዝ ትረስ ወደ መኖሪያ እና የሥራ ቦታቸው ወደሚሆነው 10 ዶውኒንግ ስትሪት በማቅናት ከጥቁሩ በር ፊትለፊት የመጀመሪያ ንግግራቸውን ያደርጋሉ። ሊዝ ትረስ በዚህ ንግግራቸው የአስተዳደራቸው ዋና ዓላማዎች ምን እንደሆኑ ያብራራሉ። ቀጥሎ ባሉት ቀናት ሊዝ ትረስ ከሚተገብሯቸው ተግባራት መካከል አንዱ ለዩኬ ጦር ኃላፊዎች ደብዳቤ መጻፍ ነው። በዚህ ጽሑፋቸው ዩናይትድ ኪንግደም የኒውክለር ጥቃት ቢፈጸምባት ምላሿ ምን ይሆናል የሚል ነው። ይህ ደብዳቤ ታዲያ የሚከፈተው ጦሩ ከዩኬ መንግሥት ጋር ግንኙነቱ ከተቋረጠ ነው። ሊዝ ትረስ ዛሬ በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት የዩኬ ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ነው። ባለፉት ዓመታት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሊዝ ትረስ፤ የወግ አጥባቂ መሪ ለመሆን ከቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ብርቱ ፉክክር ገጥሟቸው ነበር። ይሁን እንጂ የኋላ ኋላ ሊዝ ትረስ በሰፊ የድምጽ ብልጫ ሪሺ ሱናክን በመብለጥ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ እንዲሆኑ በፓርቲው አባላት ተመርጠዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cx9g7ydydlzo
0business
ዓለም ባንክ ለኮሮናቫይረስ ድንገተኛ እርዳታ 12 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ
የዓለም ባንክ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ትግል ውስጥ ያሉ አዳጊ አገራትን ያግዝ ዘንድ የ12 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል። ዓለም ባንክ ገንዘቡን የሚሰጠው በብድር፣ በእርዳታና በቴክኒክ ድጋፍ መልክ ሲሆን ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የዓለም መሪዎች ኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚያቸውን እንዳያሽመደምድ ብርቱ ዝግጅት ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው። ኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚዎች ላይ የሚያስከትለው መቀዛቀዝ አገራትን ችግር ውስጥ ሊከት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። ይህ የዓለም ባንክ እርዳታ አገራት የኮሮናቫይረስን ስርጭት በመከላከል ረገድ የጤና አገልግሎት ስርዓቶቻቸውን እንዲያጠናክሩና ቫይረሱ የሚያሳድረውን ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ለመቀነስ ከግል ዘርፍ ጋር እንዲሰሩ ለማስቻል ነው። "ለማድረግ እየሞከርን ያለነው የቫይረሱ ስርጭት እንዲገታ ነው" ብለዋል የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ። ዓለም ባንክ እንዳስታወቀው እርዳታውን በቅድሚያ የሚሰጠው በጣም ድሃ ለሆኑ አገራትና ለቫይረሱ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ለሆኑ አገሮች ነው። • ትዊተር በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሠራተኞቹ ከቤት እንዲሠሩ ፈቀደ • ጣልያን ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው አካባቢዎችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ዘጋች • ኮሮናቫይረስ የአእምሮ መረበሽን እያስከተለ ነው ተባለ ኮሮናቫይረስ በ70 አገራት ላይ እንደተሰራጨ የሚታወቅ ነው። ዓለም ባንክ ቃል የገባው ገንዘብ ግማሽ ያህሉ ከባንኩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን የሚገኝ ሲሆን አራት ቢሊዮን የሚሆነው ደግሞ ቀደም ሲል ከነበሩ ፈንዶች ተዘዋውሮ የሚመጣ እንደሆነ ተገልጿል። እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ 92 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 80 ሺህ የሚሆኑት ኬዞዎች የተመዘገቡት ቻይና ውስጥ ነው። በሌላ በኩል ሶስት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የሞቱ ሲሆን በተመሳሳይ ብዙዎቹ ሞቶች የተመዘገቡት በቻይና ነው። በዛሬው እለት 38 ሞቶች በቻይና የተመዘቡ ቢሆንም የቻይና መንግሥት እንቅስቃሴን የሚገቱ ጥብቅ እገዳዎችን በመጣሉ ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ አዳዲስ በኮሮናቫይረስ የመያዝ ሪፖርቶች ቀንሰዋል እየተባለ ነው።
ዓለም ባንክ ለኮሮናቫይረስ ድንገተኛ እርዳታ 12 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ የዓለም ባንክ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ትግል ውስጥ ያሉ አዳጊ አገራትን ያግዝ ዘንድ የ12 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል። ዓለም ባንክ ገንዘቡን የሚሰጠው በብድር፣ በእርዳታና በቴክኒክ ድጋፍ መልክ ሲሆን ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የዓለም መሪዎች ኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚያቸውን እንዳያሽመደምድ ብርቱ ዝግጅት ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው። ኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚዎች ላይ የሚያስከትለው መቀዛቀዝ አገራትን ችግር ውስጥ ሊከት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። ይህ የዓለም ባንክ እርዳታ አገራት የኮሮናቫይረስን ስርጭት በመከላከል ረገድ የጤና አገልግሎት ስርዓቶቻቸውን እንዲያጠናክሩና ቫይረሱ የሚያሳድረውን ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ለመቀነስ ከግል ዘርፍ ጋር እንዲሰሩ ለማስቻል ነው። "ለማድረግ እየሞከርን ያለነው የቫይረሱ ስርጭት እንዲገታ ነው" ብለዋል የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ። ዓለም ባንክ እንዳስታወቀው እርዳታውን በቅድሚያ የሚሰጠው በጣም ድሃ ለሆኑ አገራትና ለቫይረሱ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ለሆኑ አገሮች ነው። • ትዊተር በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሠራተኞቹ ከቤት እንዲሠሩ ፈቀደ • ጣልያን ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው አካባቢዎችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ዘጋች • ኮሮናቫይረስ የአእምሮ መረበሽን እያስከተለ ነው ተባለ ኮሮናቫይረስ በ70 አገራት ላይ እንደተሰራጨ የሚታወቅ ነው። ዓለም ባንክ ቃል የገባው ገንዘብ ግማሽ ያህሉ ከባንኩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን የሚገኝ ሲሆን አራት ቢሊዮን የሚሆነው ደግሞ ቀደም ሲል ከነበሩ ፈንዶች ተዘዋውሮ የሚመጣ እንደሆነ ተገልጿል። እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ 92 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 80 ሺህ የሚሆኑት ኬዞዎች የተመዘገቡት ቻይና ውስጥ ነው። በሌላ በኩል ሶስት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የሞቱ ሲሆን በተመሳሳይ ብዙዎቹ ሞቶች የተመዘገቡት በቻይና ነው። በዛሬው እለት 38 ሞቶች በቻይና የተመዘቡ ቢሆንም የቻይና መንግሥት እንቅስቃሴን የሚገቱ ጥብቅ እገዳዎችን በመጣሉ ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ አዳዲስ በኮሮናቫይረስ የመያዝ ሪፖርቶች ቀንሰዋል እየተባለ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/51716797
5sports
የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን?
ሄኖክ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚኖር ወጣት ነው። ከስድስት ወር በፊት በጓደኞቹ ገፋፊነት የጀመረው በስፖርት ውድድሮች ላይ ገንዘብ ማስያዝ መወራረድ ሱስ እየሆነበት እንደመጣ ይናገራል። ''ከገንዘብ ጋር የተያያዘ እንደመሆኑ መጠን እራስን ለመቆጣጠር ትንሽ ይከብዳል። በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረጉ በተለይ የእንግሊዝና ሌሎች የአውሮፓ ሊጎች ላይ ሳላስይዝ አላልፍም''ይላል። • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ በትንሹ ከ10 ብር ጀምሮ እስከ 200 ብር ድረስ በአንድ ጊዜ እንደሚያስይዝ የሚናገረው ሄኖክ የጨዋታዎቹን ውጤት ለማየትና ምን ያህል እንደበላ አልያም እንደተበላ ለማረጋገጥ ቁጭ ብሎ ሌሊቱን የሚያሳልፍበት ጊዜም እንዳለ ይናገራል። ሌላው ቢቀር ይላል ሄኖክ ''ማህበራዊ ሚዲያዎችን በተንቀሳቃሽ ስልኬ በመመልከት የማጠፋውን ጊዜ እንኳን ቀንሻለው። አጋጣሚው ሲኖረኝ ሁሌም የአቋማሪ ድርጅቱን መተግበሪያ ከፍቼ ማየት ነው የሚቀናኝ።'' በስፖርት ውድድሮች ውጤት ላይ ተመስርቶ መወራረድ በኢትዮጵያ እምብዛም የተለመደ ነገር አልነበረም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እንደ አቢሲኒያ፣ አክሱምና ሃበሻን የመሳሰሉ የስፖርት አወራራጅ ድርጀቶች የብዙ ወጣቶችን ቀልብ መሳብ ጀምረዋል። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው የአቢሲኒያ አወራራጅ ድርጅት መስራችና ባለቤት የሆነው አሸናፊ ንጉሤ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፈቃድ አግኝተው መስራት የጀመሩት ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ መሆኑን ይናገራል። አሸናፊ "ብዙ ሰዎች ከስፖርታዊ ውርርዶች ጋር በተያያዘ የተሳሳተ አመለካከት አላቸው" ብሎ ያምናል። በስፖርታዊ ውድድሮች ገንዘባቸውን ለማስያዝ የሳምንቱ መጨረሻ ቀናትን በጉጉት ከሚጠብቁት እንደ ሄኖክ ካሉ ተቋማሪዎች በተለየ ሱስ የማስያዝም ሆነ አላግባብ ወጪ ውስጥ አያስገባም ይላል። ''በስፖርት ውድድሮች ይሄኛው ቡድን ያሸንፋል ሌላኛው ይሸነፋል እያሉ መወራረድ የተለመደና ሁሌም የነበረ ነገር ነው'' የሚለው አሸናፊ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ፈቃድ አግኝቶ ተሳታፊዎች ልኩን ባላለፈ መልኩ እንዲወራረዱ ማድረጉ ከጉዳቱ ጥቅሙ እንደሚበልጥ ያስረዳል። ''በአሁኑ ጊዜ ወጣቶች ከሚታሰበው በላይ የስፖርት እውቀታቸው ጨምሯል። በዚህም ምክንያት ገንዘባቸውን ሲያስይዙ እራሱ በእውቀት ላይ ተመስርተው ነው። ገንዘባቸውን ከማስያዛቸው በፊት ሬድዮና ስፖርታዊ ድረገጾችን ተከታትለው ስለሆነ የሚመጡት ከውርርዱ በተጨማሪ መረጃ ቶሎ ቶሎ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል'' ይላል። በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቴድሮስ ነዋይ በበኩላቸው የስፖርት ውርርድ ድርጀቶች ተገቢውን ቅድመ ሁኔታዎች እስካሟሉ ድረስ ማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድሩት ጫና እንደሌለ ይናገራሉ። እስካሁን አስተዳደሩ 28 የሚሆኑ አወራራጅ ድርጅቶችን በህጋዊ መንገድ የመዘገበ ሲሆን 23 የሚሆኑት ፍቃድ ባገኙበት ዘርፍ ሥራቸውን እያከናወኑ ነው። ከነዚህ መካከል አራቱ በያዝነው 2012 ዓ.ም ፍቃድ ያገኙ ናቸው። አቶ ቴዎድሮስ እንደሚሉት የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባለፈው ዓመት ከአወራራጅ ድርጅቶች ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢም አግኝቷል። ''በመጀመሪያ መረሳት የሌለበት በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩትን ድርጅቶች አቋማሪ አንላቸውም። የስፖርት ውድድር አወራራጅ ድርጅቶች ብለን ነው የምንጠራቸው'' ይላሉ። ''ቁማር ሲሆን አንዱ የሚጎዳበት አንዱ ብቻ ደግሞ የሚጠቀምት ነው። ስለዚህ ምንም ማህበራዊ ፋይዳ ሊኖረመው አይችልም። እኛ ፈቃድ የምንሰጠው የስፖርት ውርርድ ባህሪው የሎተሪ ነው። ማህበረሰቡ በተለይም ወጣቶች ጊዜያቸውን በሌሎች ነገሮች ላይ ከሚያሳልፉ እየተዝናኑ እድላቸውን የሚሞክሩበት ነው።'' ''ማህበራዊ ፋይዳ ከሌለው እኛም ፈቃድ አንሰጥም'' የሚሉት አቶ ቴድዎሮስ ለዚህም ድርጅቶቹ ከውርርድ ከሚያገኙት ገቢ 20 በመቶውን በመረጡት ማህበራዊ የበጎ አድራጎት ተቋም ላይ እንዲያውሉ እንደሚገደዱ ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከድርጅቶቹ ገቢ 15 በመቶውን በኮሚሽን መልክ የሚወስድ ሲሆን ድርጅቶቹ ከደንበኞቻቸው ግብር ሰብስበውም ለመንግሥት ገቢ ያደርጋሉ። በተጨማሪ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውንም ይከፍላሉ። እነዚህ ሁሉ ሂደቶች ድርጅቶቹ ብዙ ትርፍ እንዳይግበሰብሱና የሚገኘው ገቢ ለተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች መዋላቸውን ማረጋገጫ እንደሚሰጣቸው አቶ ቴድሮስ ይናገራሉ። ሌላኛው ያነጋገርነውና በስፖርት ውድድሮች ገንዘብ ማስያዝ ከጀመረ ብዙ ጊዜ እንዳልሆነው የሚናገረው አሰግድ በሳምንት ቢያንስ አምስት ጨዋታዎች ላይ ገንዘቡን እንደሚያስይዝ ይናገራል። አብዛኛዎቹ ድርጅቶች ዘመናዊ አሰራር ስለሌላቸው በአካል ሄዶ ገንዘብ ማስያዝና መቀበል አድካሚ መሆኑን ይገልጻል። ''ብዙ ጊዜ በስሜ ገንዘብ ለማስገባትም ሆነ ካሸነፍኩኝ ገንዘቤን ለመቀበል ወደ አቋማሪ ድርጅቶቹ ቢሮ ድረስ መሄድ አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ ወደ ቢሮው የሚሄድ ጓደኛዬ ካለ ለእኔም እንዲያስገባልኝ የማደርግብትም ጊዜ አለ'' ይላል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ምንም እንኳን ውርርድን በተመለከተ ስለኢትዮጵያ በቂ የሆነ መረጃ ባይበኖርም በኬንያ፣ በደቡብ አፍሪካ ወይንም በናይጄሪያ የሚገኙ እድሜያቸው ከ18 እስከ 40 የሚደርሱ ሰዎች በአማካይ በቀን እስከ 15 ዶላር ድረስ እንደሚያስይዙ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከሚስተዋለው በተለየ ሄኖክ ገንዘቡን የሚያስይዝባቸው ድርጅቶ የሀገር ውስጥ ውድድሮችን እምብዛም እንደማያካትቱና በብዛት የአውሮፓ ሊጎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ይናገራል። እስከ 14 ሺህ ብር ድረስ ሁለት ጊዜ በውርርድ እንዳሸነፈ የሚናገረው ሄኖክ ገንዘቡን ከማስያዙ በፊት የተለያዩ መረጃዎችን እንደሚሰበስብና አማራጮቹን ለማብዛት እንደሚሞክር ነግሮናል። በስፖርታዊ ውድድሮች መወራረድ ጋር አብሮ የሚነሳ አንድ ችግር አለ። እሱም እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችና ተማሪዎች በዚሁ ተግባር ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ሊያጠፉ መቻላቸው ነው። አሰግድ አብዛኛዎቹ አወራራጅ ድርጅቶች ለመወራረድ ከሚመጡት ሰዎች መካከል ምን ያህሉ "እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን የሚቆጣጠሩ አይመስለኝም" ይላል። ''እኔ በግሌ ገንዘብ ለማስያዝ ስሄድ ትንንሽ ልጆችን እመለከታለው። ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ተስተናግደው ነው የሚሄዱት። በስልካቸው መተግበሪያዎችን አውርደው ሲጠቀሙም እምለከታለው" ሲል አሳሳቢ መሆኑን ይተቅሳል። የአቢሲኒያ አወራራጅ ድርጅት ባለቤት አሸናፊ ንጉሤ ግን እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በስፖርታዊ ውድድሮች እንዳይሳተፉ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ይናገራል። ''ማንኛውም ሰው ገንዘብ ለማስያዝም ሆነ አባል ለመሆን ወደ ቢሮዎቻችን ሲመጣ መታወቂያ እንጠይቃለን። በድረ ገጽና በስልክ መተግበሪያዎች ለሚጫወቱት ደግሞ የገንዘብ ዝውውር ለማድረግ በባንክ በኩል የሂሳብ ደብተር መክፈት ስላለባቸው የእድሜያቸውን ነገር በዚው እንቆጣጠረዋለን።'' ''ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንዲጫወቱ አንፈቅድም፤ አብረውት ሊመጡ የሚችሉትንም ጉዳቶች ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን'' ይላል። • አብረሃም መብራቱ፡ የየመንን ብሔራዊ ቡድን ለትልቅ ውድድር ያበቃ ኢትዮጵያዊ የስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የሚደረግ ውርርድ ዙሪያ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን ድርጅቶቹ እንዳያጫውቱ የሚከለክል መመሪያ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባይኖረውም ውርርዱ ላይ ህጻናት እንዳይሳተፉ ስምምነት እንዳላቸው የአስተዳደሩ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ገልጸዋል። ''እድሜያቸው ያልደረሰ ህጻናት የሚጫወቱ ከሆነ ተገቢውን እርምጃ ከመውሰድ ግን ወደኋላ አንልም። ጥቆማ ከደረሰንም የምንከታተል ሲሆን እስካሁን ግን ምንም የደረሰን ቅሬታም ሆነ ጥቆማ የለም'' ይላሉ። ውርርድ ሱስ የማስያዝ ባህሪ ሊኖረው ስለሚችል ወደፊት የዘርፉን አካሄድ በመመልከትና ተያይዘው የሚመጡ ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን አቶ ቴድሮስ ገልጸዋል። ለአሁኑ ግን በኢትዮጵያ ያለው የውርርድ ዘርፍ ገና ጀማሪ በሚባልበት ደረጃ በመሆኑ አካሄዱን መከታተልና ማህበረሰቡ እየተዝናና ሃላፊነቱን የሚወጣበትን መንገድ ማማቻቸት ላይ ትኩረት እንዳደረጉም አክለዋል። ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ መወራረድ ሙሉ በሙሉ መከልክል የለበትም የሚለው ሃሳብ ያሚያስማማቸው አሰግድና ሄኖክ አወራራጅ ድርጅቶችም ሆነ መንግሥት ውርርድ ሱስ ሊያስይዝ እንደሚችል በደንብ መረጃ ቢሰጡና ዘርፉ ጠበቅ ያለ ክትትል ቢደረግብት መልካም እንደሆነ ግን ያምናሉ። ከስፖርታዊ ውርርዶች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የወጣቶች ሥራ አጥነት፣ ለስፖርታዊ ውድድሮች ያለ ከፍተኛ ፍቅር፣ የላላ የቁማር ህግና ቀላል የተንቀሳቃሽ ስልክ ክፍያ መንገዶች መብዛት እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሃገራት ትልቅ ፈተና ሊደቅኑ እንደሚችሉ አንዳንዶች ስጋታቸውን ይገልጻሉ።
የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን? ሄኖክ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚኖር ወጣት ነው። ከስድስት ወር በፊት በጓደኞቹ ገፋፊነት የጀመረው በስፖርት ውድድሮች ላይ ገንዘብ ማስያዝ መወራረድ ሱስ እየሆነበት እንደመጣ ይናገራል። ''ከገንዘብ ጋር የተያያዘ እንደመሆኑ መጠን እራስን ለመቆጣጠር ትንሽ ይከብዳል። በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረጉ በተለይ የእንግሊዝና ሌሎች የአውሮፓ ሊጎች ላይ ሳላስይዝ አላልፍም''ይላል። • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ በትንሹ ከ10 ብር ጀምሮ እስከ 200 ብር ድረስ በአንድ ጊዜ እንደሚያስይዝ የሚናገረው ሄኖክ የጨዋታዎቹን ውጤት ለማየትና ምን ያህል እንደበላ አልያም እንደተበላ ለማረጋገጥ ቁጭ ብሎ ሌሊቱን የሚያሳልፍበት ጊዜም እንዳለ ይናገራል። ሌላው ቢቀር ይላል ሄኖክ ''ማህበራዊ ሚዲያዎችን በተንቀሳቃሽ ስልኬ በመመልከት የማጠፋውን ጊዜ እንኳን ቀንሻለው። አጋጣሚው ሲኖረኝ ሁሌም የአቋማሪ ድርጅቱን መተግበሪያ ከፍቼ ማየት ነው የሚቀናኝ።'' በስፖርት ውድድሮች ውጤት ላይ ተመስርቶ መወራረድ በኢትዮጵያ እምብዛም የተለመደ ነገር አልነበረም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እንደ አቢሲኒያ፣ አክሱምና ሃበሻን የመሳሰሉ የስፖርት አወራራጅ ድርጀቶች የብዙ ወጣቶችን ቀልብ መሳብ ጀምረዋል። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው የአቢሲኒያ አወራራጅ ድርጅት መስራችና ባለቤት የሆነው አሸናፊ ንጉሤ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፈቃድ አግኝተው መስራት የጀመሩት ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ መሆኑን ይናገራል። አሸናፊ "ብዙ ሰዎች ከስፖርታዊ ውርርዶች ጋር በተያያዘ የተሳሳተ አመለካከት አላቸው" ብሎ ያምናል። በስፖርታዊ ውድድሮች ገንዘባቸውን ለማስያዝ የሳምንቱ መጨረሻ ቀናትን በጉጉት ከሚጠብቁት እንደ ሄኖክ ካሉ ተቋማሪዎች በተለየ ሱስ የማስያዝም ሆነ አላግባብ ወጪ ውስጥ አያስገባም ይላል። ''በስፖርት ውድድሮች ይሄኛው ቡድን ያሸንፋል ሌላኛው ይሸነፋል እያሉ መወራረድ የተለመደና ሁሌም የነበረ ነገር ነው'' የሚለው አሸናፊ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ፈቃድ አግኝቶ ተሳታፊዎች ልኩን ባላለፈ መልኩ እንዲወራረዱ ማድረጉ ከጉዳቱ ጥቅሙ እንደሚበልጥ ያስረዳል። ''በአሁኑ ጊዜ ወጣቶች ከሚታሰበው በላይ የስፖርት እውቀታቸው ጨምሯል። በዚህም ምክንያት ገንዘባቸውን ሲያስይዙ እራሱ በእውቀት ላይ ተመስርተው ነው። ገንዘባቸውን ከማስያዛቸው በፊት ሬድዮና ስፖርታዊ ድረገጾችን ተከታትለው ስለሆነ የሚመጡት ከውርርዱ በተጨማሪ መረጃ ቶሎ ቶሎ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል'' ይላል። በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቴድሮስ ነዋይ በበኩላቸው የስፖርት ውርርድ ድርጀቶች ተገቢውን ቅድመ ሁኔታዎች እስካሟሉ ድረስ ማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድሩት ጫና እንደሌለ ይናገራሉ። እስካሁን አስተዳደሩ 28 የሚሆኑ አወራራጅ ድርጅቶችን በህጋዊ መንገድ የመዘገበ ሲሆን 23 የሚሆኑት ፍቃድ ባገኙበት ዘርፍ ሥራቸውን እያከናወኑ ነው። ከነዚህ መካከል አራቱ በያዝነው 2012 ዓ.ም ፍቃድ ያገኙ ናቸው። አቶ ቴዎድሮስ እንደሚሉት የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባለፈው ዓመት ከአወራራጅ ድርጅቶች ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢም አግኝቷል። ''በመጀመሪያ መረሳት የሌለበት በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩትን ድርጅቶች አቋማሪ አንላቸውም። የስፖርት ውድድር አወራራጅ ድርጅቶች ብለን ነው የምንጠራቸው'' ይላሉ። ''ቁማር ሲሆን አንዱ የሚጎዳበት አንዱ ብቻ ደግሞ የሚጠቀምት ነው። ስለዚህ ምንም ማህበራዊ ፋይዳ ሊኖረመው አይችልም። እኛ ፈቃድ የምንሰጠው የስፖርት ውርርድ ባህሪው የሎተሪ ነው። ማህበረሰቡ በተለይም ወጣቶች ጊዜያቸውን በሌሎች ነገሮች ላይ ከሚያሳልፉ እየተዝናኑ እድላቸውን የሚሞክሩበት ነው።'' ''ማህበራዊ ፋይዳ ከሌለው እኛም ፈቃድ አንሰጥም'' የሚሉት አቶ ቴድዎሮስ ለዚህም ድርጅቶቹ ከውርርድ ከሚያገኙት ገቢ 20 በመቶውን በመረጡት ማህበራዊ የበጎ አድራጎት ተቋም ላይ እንዲያውሉ እንደሚገደዱ ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከድርጅቶቹ ገቢ 15 በመቶውን በኮሚሽን መልክ የሚወስድ ሲሆን ድርጅቶቹ ከደንበኞቻቸው ግብር ሰብስበውም ለመንግሥት ገቢ ያደርጋሉ። በተጨማሪ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውንም ይከፍላሉ። እነዚህ ሁሉ ሂደቶች ድርጅቶቹ ብዙ ትርፍ እንዳይግበሰብሱና የሚገኘው ገቢ ለተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች መዋላቸውን ማረጋገጫ እንደሚሰጣቸው አቶ ቴድሮስ ይናገራሉ። ሌላኛው ያነጋገርነውና በስፖርት ውድድሮች ገንዘብ ማስያዝ ከጀመረ ብዙ ጊዜ እንዳልሆነው የሚናገረው አሰግድ በሳምንት ቢያንስ አምስት ጨዋታዎች ላይ ገንዘቡን እንደሚያስይዝ ይናገራል። አብዛኛዎቹ ድርጅቶች ዘመናዊ አሰራር ስለሌላቸው በአካል ሄዶ ገንዘብ ማስያዝና መቀበል አድካሚ መሆኑን ይገልጻል። ''ብዙ ጊዜ በስሜ ገንዘብ ለማስገባትም ሆነ ካሸነፍኩኝ ገንዘቤን ለመቀበል ወደ አቋማሪ ድርጅቶቹ ቢሮ ድረስ መሄድ አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ ወደ ቢሮው የሚሄድ ጓደኛዬ ካለ ለእኔም እንዲያስገባልኝ የማደርግብትም ጊዜ አለ'' ይላል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ምንም እንኳን ውርርድን በተመለከተ ስለኢትዮጵያ በቂ የሆነ መረጃ ባይበኖርም በኬንያ፣ በደቡብ አፍሪካ ወይንም በናይጄሪያ የሚገኙ እድሜያቸው ከ18 እስከ 40 የሚደርሱ ሰዎች በአማካይ በቀን እስከ 15 ዶላር ድረስ እንደሚያስይዙ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከሚስተዋለው በተለየ ሄኖክ ገንዘቡን የሚያስይዝባቸው ድርጅቶ የሀገር ውስጥ ውድድሮችን እምብዛም እንደማያካትቱና በብዛት የአውሮፓ ሊጎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ይናገራል። እስከ 14 ሺህ ብር ድረስ ሁለት ጊዜ በውርርድ እንዳሸነፈ የሚናገረው ሄኖክ ገንዘቡን ከማስያዙ በፊት የተለያዩ መረጃዎችን እንደሚሰበስብና አማራጮቹን ለማብዛት እንደሚሞክር ነግሮናል። በስፖርታዊ ውድድሮች መወራረድ ጋር አብሮ የሚነሳ አንድ ችግር አለ። እሱም እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችና ተማሪዎች በዚሁ ተግባር ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ሊያጠፉ መቻላቸው ነው። አሰግድ አብዛኛዎቹ አወራራጅ ድርጅቶች ለመወራረድ ከሚመጡት ሰዎች መካከል ምን ያህሉ "እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን የሚቆጣጠሩ አይመስለኝም" ይላል። ''እኔ በግሌ ገንዘብ ለማስያዝ ስሄድ ትንንሽ ልጆችን እመለከታለው። ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ተስተናግደው ነው የሚሄዱት። በስልካቸው መተግበሪያዎችን አውርደው ሲጠቀሙም እምለከታለው" ሲል አሳሳቢ መሆኑን ይተቅሳል። የአቢሲኒያ አወራራጅ ድርጅት ባለቤት አሸናፊ ንጉሤ ግን እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በስፖርታዊ ውድድሮች እንዳይሳተፉ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ይናገራል። ''ማንኛውም ሰው ገንዘብ ለማስያዝም ሆነ አባል ለመሆን ወደ ቢሮዎቻችን ሲመጣ መታወቂያ እንጠይቃለን። በድረ ገጽና በስልክ መተግበሪያዎች ለሚጫወቱት ደግሞ የገንዘብ ዝውውር ለማድረግ በባንክ በኩል የሂሳብ ደብተር መክፈት ስላለባቸው የእድሜያቸውን ነገር በዚው እንቆጣጠረዋለን።'' ''ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንዲጫወቱ አንፈቅድም፤ አብረውት ሊመጡ የሚችሉትንም ጉዳቶች ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን'' ይላል። • አብረሃም መብራቱ፡ የየመንን ብሔራዊ ቡድን ለትልቅ ውድድር ያበቃ ኢትዮጵያዊ የስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የሚደረግ ውርርድ ዙሪያ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን ድርጅቶቹ እንዳያጫውቱ የሚከለክል መመሪያ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባይኖረውም ውርርዱ ላይ ህጻናት እንዳይሳተፉ ስምምነት እንዳላቸው የአስተዳደሩ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ገልጸዋል። ''እድሜያቸው ያልደረሰ ህጻናት የሚጫወቱ ከሆነ ተገቢውን እርምጃ ከመውሰድ ግን ወደኋላ አንልም። ጥቆማ ከደረሰንም የምንከታተል ሲሆን እስካሁን ግን ምንም የደረሰን ቅሬታም ሆነ ጥቆማ የለም'' ይላሉ። ውርርድ ሱስ የማስያዝ ባህሪ ሊኖረው ስለሚችል ወደፊት የዘርፉን አካሄድ በመመልከትና ተያይዘው የሚመጡ ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን አቶ ቴድሮስ ገልጸዋል። ለአሁኑ ግን በኢትዮጵያ ያለው የውርርድ ዘርፍ ገና ጀማሪ በሚባልበት ደረጃ በመሆኑ አካሄዱን መከታተልና ማህበረሰቡ እየተዝናና ሃላፊነቱን የሚወጣበትን መንገድ ማማቻቸት ላይ ትኩረት እንዳደረጉም አክለዋል። ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ መወራረድ ሙሉ በሙሉ መከልክል የለበትም የሚለው ሃሳብ ያሚያስማማቸው አሰግድና ሄኖክ አወራራጅ ድርጅቶችም ሆነ መንግሥት ውርርድ ሱስ ሊያስይዝ እንደሚችል በደንብ መረጃ ቢሰጡና ዘርፉ ጠበቅ ያለ ክትትል ቢደረግብት መልካም እንደሆነ ግን ያምናሉ። ከስፖርታዊ ውርርዶች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የወጣቶች ሥራ አጥነት፣ ለስፖርታዊ ውድድሮች ያለ ከፍተኛ ፍቅር፣ የላላ የቁማር ህግና ቀላል የተንቀሳቃሽ ስልክ ክፍያ መንገዶች መብዛት እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሃገራት ትልቅ ፈተና ሊደቅኑ እንደሚችሉ አንዳንዶች ስጋታቸውን ይገልጻሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-49835538
0business
ኮሮናቫይረስ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ምን አሉ?
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ትናንት አርብ አመሻሽ ላይ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በተመለከተ በጽህፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥተወው ነበር። በዚህ መግለጫቸው ላይም የኢኮኖሚ፣ የጸጥታ፣ የጤና እና የማህበራዊ ጉዳዮች ኮሚቴ ተቋቁሞ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ሲከታተል መቆየቱን አስታውቀዋል። በዚህም መሠረት አዳዲስ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ተወስኗል በማለት ውሳኔዎቹን ገልፀዋል።. ማንኛውም ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ሰው ለ14 ቀናት በራሱ ወጪ ወደ ለይቶ ማቆያ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ከ 30 በላይ አገራት የሚያደርገውን በረራ እንዲያቋርጥ መወሰኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አየር መንገዱ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት አስታውቀዋል። "አየር መንገዱ 190 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ አጋጥሞታል። በዚህም ወደፊት ከፍተኛ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል ይጠበቃል" ብለዋል። የአምልኮ ስርዓቱ እና ልምዱ ለበሽታው ተጋላጭ ያደርጋል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከኦርቶዶክስ ኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም "በእነሱ [ኦርቶዶክስ ኃይማኖት አባቶች] በኩል መልዕክት እንደሚተላለፍ ይጠበቃል" ያሉ ሲሆን፤ የፕሮቴስታንት መሪዎችም ቴክኖሎጂን በመታገዝ አገልግሎት እንዲሰጡ አማራጭ መቀመጡን ተናግረዋል። በእስልምናም የሚደረጉ ሰላቶች ንክኪ ስለሚኖራቸው፤ የሃይማኖት መሪዎች እርምጃ እንደሚወስዱ እና መግለጫ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪ አስተላልፏል ብለዋል። በማረሚያ ቤቶች በሽታው ከገባ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ታራሚዎችን ወደ ሌሎች ቦታዎች ወስዶ ዘርዘር ለማድረግ ተጨማሪ ቦታዎች ተዘጋጅቷል ብለዋል። አክለውም አዳዲስ ታራሚዎች ምርመራ ሳይደረግላቸው ወደ ማረሚያ ቤት አይገቡም ብለዋል። እንዲሁም የቤተሰብ ጥየቃ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም መደረጉን ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፤ ህጻናትን የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰ እና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው እንዲለቀቁ መወሰኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከሰሞኑ የወረርሽኙን ስርጭት ተከትሎ በአዲስ አበባ በውጪ አገር ዜጎች ላይ የደረሰው ጥቃት ''ኢትዮጵያዊ ባህሪ የሌለው ነው'' በማለት ጥቃቱን አውግዘዋል። ከሰሞኑ በርካታ ወጣቶች ሰዎችን እጅ ማስታጠብ ጨምሮ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ሲያከናውኑ ነበር። መንግሥት የበጎ አድራጎት ሥራዎቹን በአክብሮት የሚመለከተው ነው ካሉ በኋላ፤ ነገር ግን አገልግሎቱን የሚሰጡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የእስካሁኑን የሕክምና ባለሙያዎችን ጥረት አድንቀዋል። የቫይረሱ ስርጭት የሚስፋፋ ከሆነም በሽታውን ለማሸነፍ ብዙ ጥረት ይጠበቅባችኋል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ከጃክ ማ፣ ከቢል ጊቴስ እና ከዓለም ባንክ በተገኙ ድጋፎች የዜጎች ሕይወት እንዳያልፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የመሽት መዝናኛ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ይሆናሉ ብለዋል። በጠባብ ቦታ ላይ በርካታ ሰዎች ስለሚያስተናግዱ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ዝግ ይደረጋሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። "በሽታውን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራችንን እስክናረጋግጥ ድረስ የምሽት መዝናኛዎች እንዲዘጉ ተወስኗል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት በሞከሩ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውሰው አሁንም ሕጋዊ የማስተካከያ እርምጃዎች መውሰድ ይቀጥላል ብለዋል። በክልሎች የሚገኙ ዋና ዋና ሆስፒታሎች ምረመራ የማድረግ አቅማቸውን ለማሳደግ ስራዎች ሲከናወኑ እንደነበረ አስታወሰዋል። ለዚህም የሚረዳ የምረመራ እና የማዳን ሥራ እንዲሰራ ተግባብተናል ብለዋል። ወረርሽኙ ከወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ስለሚኖረው ጫና ሲያስረዱ፤ "ምርጫ ቦርድ የራሱን ግምገማ እያካሄደ ነው፤ ግምገማውን መሰረት በማድረግ የመጨረሻው ውጤት ይፋ ይደረጋል" ብለዋል። የመጠጥ ውሃ እጥረት ባለባቸው ቦታዎች በቦቴ የማቅረብ ሠራዎች እየተካሄዱ እንደሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። በተለይ በከተማ አከባቢ ከፍተኛ የውሃ እጥረት መኖሩን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመግለጫቸው መጨረሻ ላይ "የብልጽግና ፓርቲ የገንዘብ መዋጮ ላይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችን እና የፖለቲካ ምሁሮችን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር በርካቶች ማዘናቸውን ሰምቻለሁ" ብለዋል። "ጉዳዩ የማይመለከታችሁ እና በንግግሬ እንድትከፉ የሆናችሁ፣ የተማራችሁ እና በተማራችሁበት ዘርፍ አገራችሁን በቅንነት የምታገለግሉ፣ ውጤትም ያመጣችሁ ሰዎች ጉዳዩ እናንተን የማይመለከት ቢሆንም፤ ጉዳዩ እናንተን የማይመለከት መሆኑን በግልጽ ባለማስቀመጤ እናንተን ይቅርታ እጠይቃለሁ" ብለዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ምን አሉ? ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ትናንት አርብ አመሻሽ ላይ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በተመለከተ በጽህፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥተወው ነበር። በዚህ መግለጫቸው ላይም የኢኮኖሚ፣ የጸጥታ፣ የጤና እና የማህበራዊ ጉዳዮች ኮሚቴ ተቋቁሞ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ሲከታተል መቆየቱን አስታውቀዋል። በዚህም መሠረት አዳዲስ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ተወስኗል በማለት ውሳኔዎቹን ገልፀዋል።. ማንኛውም ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ሰው ለ14 ቀናት በራሱ ወጪ ወደ ለይቶ ማቆያ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ከ 30 በላይ አገራት የሚያደርገውን በረራ እንዲያቋርጥ መወሰኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አየር መንገዱ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት አስታውቀዋል። "አየር መንገዱ 190 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ አጋጥሞታል። በዚህም ወደፊት ከፍተኛ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል ይጠበቃል" ብለዋል። የአምልኮ ስርዓቱ እና ልምዱ ለበሽታው ተጋላጭ ያደርጋል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከኦርቶዶክስ ኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም "በእነሱ [ኦርቶዶክስ ኃይማኖት አባቶች] በኩል መልዕክት እንደሚተላለፍ ይጠበቃል" ያሉ ሲሆን፤ የፕሮቴስታንት መሪዎችም ቴክኖሎጂን በመታገዝ አገልግሎት እንዲሰጡ አማራጭ መቀመጡን ተናግረዋል። በእስልምናም የሚደረጉ ሰላቶች ንክኪ ስለሚኖራቸው፤ የሃይማኖት መሪዎች እርምጃ እንደሚወስዱ እና መግለጫ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪ አስተላልፏል ብለዋል። በማረሚያ ቤቶች በሽታው ከገባ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ታራሚዎችን ወደ ሌሎች ቦታዎች ወስዶ ዘርዘር ለማድረግ ተጨማሪ ቦታዎች ተዘጋጅቷል ብለዋል። አክለውም አዳዲስ ታራሚዎች ምርመራ ሳይደረግላቸው ወደ ማረሚያ ቤት አይገቡም ብለዋል። እንዲሁም የቤተሰብ ጥየቃ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም መደረጉን ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፤ ህጻናትን የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰ እና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው እንዲለቀቁ መወሰኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከሰሞኑ የወረርሽኙን ስርጭት ተከትሎ በአዲስ አበባ በውጪ አገር ዜጎች ላይ የደረሰው ጥቃት ''ኢትዮጵያዊ ባህሪ የሌለው ነው'' በማለት ጥቃቱን አውግዘዋል። ከሰሞኑ በርካታ ወጣቶች ሰዎችን እጅ ማስታጠብ ጨምሮ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ሲያከናውኑ ነበር። መንግሥት የበጎ አድራጎት ሥራዎቹን በአክብሮት የሚመለከተው ነው ካሉ በኋላ፤ ነገር ግን አገልግሎቱን የሚሰጡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የእስካሁኑን የሕክምና ባለሙያዎችን ጥረት አድንቀዋል። የቫይረሱ ስርጭት የሚስፋፋ ከሆነም በሽታውን ለማሸነፍ ብዙ ጥረት ይጠበቅባችኋል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ከጃክ ማ፣ ከቢል ጊቴስ እና ከዓለም ባንክ በተገኙ ድጋፎች የዜጎች ሕይወት እንዳያልፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የመሽት መዝናኛ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ይሆናሉ ብለዋል። በጠባብ ቦታ ላይ በርካታ ሰዎች ስለሚያስተናግዱ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ዝግ ይደረጋሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። "በሽታውን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራችንን እስክናረጋግጥ ድረስ የምሽት መዝናኛዎች እንዲዘጉ ተወስኗል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት በሞከሩ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውሰው አሁንም ሕጋዊ የማስተካከያ እርምጃዎች መውሰድ ይቀጥላል ብለዋል። በክልሎች የሚገኙ ዋና ዋና ሆስፒታሎች ምረመራ የማድረግ አቅማቸውን ለማሳደግ ስራዎች ሲከናወኑ እንደነበረ አስታወሰዋል። ለዚህም የሚረዳ የምረመራ እና የማዳን ሥራ እንዲሰራ ተግባብተናል ብለዋል። ወረርሽኙ ከወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ስለሚኖረው ጫና ሲያስረዱ፤ "ምርጫ ቦርድ የራሱን ግምገማ እያካሄደ ነው፤ ግምገማውን መሰረት በማድረግ የመጨረሻው ውጤት ይፋ ይደረጋል" ብለዋል። የመጠጥ ውሃ እጥረት ባለባቸው ቦታዎች በቦቴ የማቅረብ ሠራዎች እየተካሄዱ እንደሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። በተለይ በከተማ አከባቢ ከፍተኛ የውሃ እጥረት መኖሩን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመግለጫቸው መጨረሻ ላይ "የብልጽግና ፓርቲ የገንዘብ መዋጮ ላይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችን እና የፖለቲካ ምሁሮችን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር በርካቶች ማዘናቸውን ሰምቻለሁ" ብለዋል። "ጉዳዩ የማይመለከታችሁ እና በንግግሬ እንድትከፉ የሆናችሁ፣ የተማራችሁ እና በተማራችሁበት ዘርፍ አገራችሁን በቅንነት የምታገለግሉ፣ ውጤትም ያመጣችሁ ሰዎች ጉዳዩ እናንተን የማይመለከት ቢሆንም፤ ጉዳዩ እናንተን የማይመለከት መሆኑን በግልጽ ባለማስቀመጤ እናንተን ይቅርታ እጠይቃለሁ" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/51986050
2health
ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካውያን የኮቪድ-19 ክትባት ምርጫ ለምን የተለያየ ሆነ?
አሜሪካ ሦስት ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የፈቀደች ሲሆን ሰዎች የሚፈልጉትን እየመረጡ ነው። ሦስቱም የኮቪድ-19 ክትባቶች በቫይረሱ መያዝና ተይዞ ሆስፒታል መግባትን እንዲሁም ሞትን በመከላከል ረገድ ውጤታማ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ የጤና ባለሥልጣናት ለዜጎች የሚሰጠው የተሻለው ክትባት ነው ብለዋል። ቢሆንም ከጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ይልቅ ፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶችን የሚመርጡ ብዙዎች ናቸው። በመጋቢት መጀመሪያ የዲትሮይት ከንቲባ ማይክ ዱጋን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትን ውድቅ አድርገው በአሜሪካ የቀረቡት ሌሎች ሁለት ክትባቶች የተሻሉ መሆናቸውን ለከተማዋ ነዋሪዎች ጠቁመዋል። በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት "የዲትሮይት ከተማ ነዋሪዎች የተሻለውን እንዲያገኙ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ" ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች አስተያየት ከሰጡ በኋላ ከንቲባው ክትባቱ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ስለመሆኑ "ሙሉ እምነት አለኝ" በማለት ገልጸዋል። እንደ ዱጋን ሁሉ አንዳንድ አሜሪካውያን ስለ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት እና ስለ አጠቃላይ ውጤታማነቱ ጥያቄ አንስተዋል። የጤና ባለሥልጣናት ግን እነዚህ ቁጥሮች ሙሉውን ገጽታ እንደማያሳዩ አስጠንቅቀዋል። አንዳንዶች ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ከመውሰድ ሳይከተቡ ቢዘገዩ እንደሚመርጡ ይናገራሉ። አንድ የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ ለቢቢሲ ሲናገሩ "የክትባት ቀጠሮ በነበረኝ ጊዜ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን እየሰጡ እንደሆነ ስለሰማሁ ሰርዤዋለሁ። ያንን ክትባት በጭራሽ አልወስድም" ብለዋል። እንደ ዶ/ር ማይክል አንድራሲክ ያሉ የጤና ባለሥልጣናት ማንኛውንም ፈቃድ ያገኘ ክትባት መውሰድ ጥሩ መሆኑን አሜሪካውያንን ለማሳመን እየሞከሩ ነው። "በአንድ በኩል ሰዎች ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ በጣም ተደስተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ውጤታማነቱን በተመለከተ ብዙ ግራ መጋባት አለ። ይህ ደግሞ ጥሩ አይደለም" ሲሉ በፍሬድ ሃች የክትባትና ተላላፊ በሽታ ክፍል ከፍተኛ የሳይንስ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንድራሲክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአሜሪካ ተቆጣጣሪዎች አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠውን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት በይፋ ያጸደቁት በየካቲት ነው። ይህም ፍቃድ ያገኘ የመጨረሻው ክትባት አድርጎታል። አዲስ የኤም አር ኤን ኤ ክትባት ቴክኖሎጂን ከሚጠቀሙት እና ሁለት ጊዜ ከሚሰጡት ከፋይዘር እና ከሞዴርና ክትባቶች በተለየ መልኩ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ጉዳት እንዳያደርስ የተደረገ ቫይረስን ይጠቀማል። ከዚያ የኮሮናቫይረስን ዘረ መል በከፊል ወደ ሰውነት ይወስዳል። ይህም ሰውነት አደጋውን ለይቶ እንዲያውቅ እና ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት እንዲዘጋጅ ያደርጋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በክትባቱ ላይ እምነት እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ በዚህ ወር ለአሜሪካኖች ከቀረበው በእጥፍ 100 ሚሊዮን ተጨማሪ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባቶች እንደምታዝ አስታውቀዋል። የብሔራዊ አለርጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ በበኩላቸው በአሜሪካ የሚገኙ ሁሉም ክትባቶች ጥሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትም "ደካማ ክትባት አይደለም" ብለዋል። አሳሳቢው ነገር ከሙከራዎች የሚወጣው የውጤታማነት መረጃ መለያየት ነው። የጤና ባለሥልጣናት ሦስቱም ክትባቶች መቶ በመቶ ቫይረሱን የመከላከል አቅም አላቸው ሲሉ አሳስበዋል። የፋይዘር እና የሞደርና ክትባቶች አዳዲሶቹ የቫይረሱ ዝርያዎች ከመስፋፋታቸው በፊት የተሞከሩ ሲሆን አዳዲሶቹ ዝርያዎች በሙከራዎች ላይ ልዩነት ይፈጥራሉ። በተጨማሪም የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ሁሉም ክትባቶች ከዓመታዊው የጉንፋን ክትባት የበለጠ ውጤታማ ናቸው ሲል ይገልጻል። እንደ ዶ/ር አንድራስክ ከሆነ "ዋናው ነገር ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን፣ ሞደርና እና ፋይዘር ከባድ በሽታን በመከላከል፣ ሆስፒታል መተኛትን በመቀነስ፣ ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን በመቀነስ ወይም መሞትን በመከላከል በማይታመን ሁኔታ ውጤታማ ናቸው።" የማኅበረሰብ ጤና ተሟጋቾች እንደሚሉት ከሆነ ሌላው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ጠቃሚ ጎን በአሜሪካ ውስጥ ብቸኛው አንድ ጊዜ የሚሰጥ ክትባት መሆኑን ነው። ራቅ ወዳሉ እና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎችም ለማሰራጨት የበለጠ ምቹ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ያንን ክትባት ብቻ ወደ አካባቢዎቹ መላክ መገለልን ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ። አክለውም "ሁሉም ክትባቶች ለሁሉም ሊደርሱ ይገባል ብዬ አስባለሁ። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ወደ ገጠር እና ድሃ ማኅበረሰቦች የመላክ ምክንያታዊነት በእንክብካቤ ተደራሽነት ምክንያት ነው ብዬ አስባለሁ" ብለዋል ዶ/ር አንድራስክ። እንደ ዶ/ር አንድራስክ ያሉ የማኅበረሰብ አመራሮች እና የጤና ባለሙያዎች በክትባቱ ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋፋት እና የተሳሳተ መረጃን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ነው። በአሜሪካ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ "የእኔ ተራ ሲደርስ ማንኛውንም ክትባት እወስዳለሁ" ይላሉ። ሌሎቹ አሳሳቢ ጉዳዮችስ ምንድን ናቸው? ዩ ኤስ ኮንፈረንስ ኦፍ ካቶሊክ ቢሾፕስ የተባለው እና በአሜሪካ የሚገኘውን ቤተክርስትያን የሚወክለው ጉባኤ በክትባቱ ዙሪያ "የሞራል ስጋት" መኖሩን መግለጹ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የስጋቱ ምንጭ ጽንስ በማስወረድ ከሚገኙ ሕዋሶች ክትባቱ ተመርቷል መባሉ ነው። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኢቦላ ክትባትን ለማዘጋጀት የዋለውን ተመሳሳይ ዘዴ ተጠቅሟል። በተጨማሪም የትኛውም የኮቪድ -19 ክትባት ምንም ዓይነት የሰው ህዋሳትን አልያዘም። ጉባኤው ምርጫ እስካለ ድረስ ካቶሊኮች አማራጭ ክትባቶች መውሰድ እንዳለባቸው መክሯል። በአሜሪካ ጉባኤ የተሰጠው ምክር ከቫቲካን አቋም ጋር የሚቃረን ይመስላል። ምክንያቱም ቫቲካን እንዲህ ያሉት ክትባቶች "ከሞራል አንጻር ተቀባይነት አላቸው" ስለምትል ነው። ሌሎች የካቶሊክ መሪዎችም የቤተክርስቲያኗ አባላት ከዚህ ክትባት መራቅ አለባቸው የሚለውን ሐሳብ እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። የሐርትፎርድ ሊቀ ጳጳስ እና ሌሎች የአካባቢው የሐይማኖት አባቶች በሰጡት መግለጫ ሁሉም ነዋሪዎች ለራሳቸው ጤና እና ለጋራ ጥቅም ሲሉ "ማንኛውንም ክትባት ለመቀበል የህሊና ነፃነት ሊሰማቸው ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ዶሮ በሽታ እና ሩቤላ ያሉ ሌሎች ብዙ ክትባቶች በተመሳሳይ መልኩ የተሠሩ ቢሆንም የካቶሊክ መሪዎች ስለ ለጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ያሰሙት ስጋት በአንዳንድ አሜሪካውያን ዘንድ ጥርጣሬ እንዲጨምር አድርጓል። ስጋቶችን የሚጋፈጠው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ብቻ አይደለም። አሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ለመፍቀድ እየተዘጋጀችበት የሚገኘው የኦክስፎርድ-አስትራዛኔካ ክትባት ከደም መርጋት ችግር ጋር በተያያዘ የአውሮፓ አገራት ታግዶ ነበር። የአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ ባሥልጣን ክትባቱ "ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ነው" ብሎ መግለጹን ተከትሎ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን እና ስፔን ክትባቱን መጠቀም መጀመራቸውን ተናግረዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካውያን የኮቪድ-19 ክትባት ምርጫ ለምን የተለያየ ሆነ? አሜሪካ ሦስት ክትባቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የፈቀደች ሲሆን ሰዎች የሚፈልጉትን እየመረጡ ነው። ሦስቱም የኮቪድ-19 ክትባቶች በቫይረሱ መያዝና ተይዞ ሆስፒታል መግባትን እንዲሁም ሞትን በመከላከል ረገድ ውጤታማ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ የጤና ባለሥልጣናት ለዜጎች የሚሰጠው የተሻለው ክትባት ነው ብለዋል። ቢሆንም ከጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ይልቅ ፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶችን የሚመርጡ ብዙዎች ናቸው። በመጋቢት መጀመሪያ የዲትሮይት ከንቲባ ማይክ ዱጋን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትን ውድቅ አድርገው በአሜሪካ የቀረቡት ሌሎች ሁለት ክትባቶች የተሻሉ መሆናቸውን ለከተማዋ ነዋሪዎች ጠቁመዋል። በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት "የዲትሮይት ከተማ ነዋሪዎች የተሻለውን እንዲያገኙ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ" ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች አስተያየት ከሰጡ በኋላ ከንቲባው ክትባቱ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ስለመሆኑ "ሙሉ እምነት አለኝ" በማለት ገልጸዋል። እንደ ዱጋን ሁሉ አንዳንድ አሜሪካውያን ስለ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት እና ስለ አጠቃላይ ውጤታማነቱ ጥያቄ አንስተዋል። የጤና ባለሥልጣናት ግን እነዚህ ቁጥሮች ሙሉውን ገጽታ እንደማያሳዩ አስጠንቅቀዋል። አንዳንዶች ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ከመውሰድ ሳይከተቡ ቢዘገዩ እንደሚመርጡ ይናገራሉ። አንድ የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ ለቢቢሲ ሲናገሩ "የክትባት ቀጠሮ በነበረኝ ጊዜ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን እየሰጡ እንደሆነ ስለሰማሁ ሰርዤዋለሁ። ያንን ክትባት በጭራሽ አልወስድም" ብለዋል። እንደ ዶ/ር ማይክል አንድራሲክ ያሉ የጤና ባለሥልጣናት ማንኛውንም ፈቃድ ያገኘ ክትባት መውሰድ ጥሩ መሆኑን አሜሪካውያንን ለማሳመን እየሞከሩ ነው። "በአንድ በኩል ሰዎች ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ በጣም ተደስተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ውጤታማነቱን በተመለከተ ብዙ ግራ መጋባት አለ። ይህ ደግሞ ጥሩ አይደለም" ሲሉ በፍሬድ ሃች የክትባትና ተላላፊ በሽታ ክፍል ከፍተኛ የሳይንስ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንድራሲክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአሜሪካ ተቆጣጣሪዎች አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠውን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት በይፋ ያጸደቁት በየካቲት ነው። ይህም ፍቃድ ያገኘ የመጨረሻው ክትባት አድርጎታል። አዲስ የኤም አር ኤን ኤ ክትባት ቴክኖሎጂን ከሚጠቀሙት እና ሁለት ጊዜ ከሚሰጡት ከፋይዘር እና ከሞዴርና ክትባቶች በተለየ መልኩ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ጉዳት እንዳያደርስ የተደረገ ቫይረስን ይጠቀማል። ከዚያ የኮሮናቫይረስን ዘረ መል በከፊል ወደ ሰውነት ይወስዳል። ይህም ሰውነት አደጋውን ለይቶ እንዲያውቅ እና ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት እንዲዘጋጅ ያደርጋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በክትባቱ ላይ እምነት እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ በዚህ ወር ለአሜሪካኖች ከቀረበው በእጥፍ 100 ሚሊዮን ተጨማሪ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባቶች እንደምታዝ አስታውቀዋል። የብሔራዊ አለርጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ በበኩላቸው በአሜሪካ የሚገኙ ሁሉም ክትባቶች ጥሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባትም "ደካማ ክትባት አይደለም" ብለዋል። አሳሳቢው ነገር ከሙከራዎች የሚወጣው የውጤታማነት መረጃ መለያየት ነው። የጤና ባለሥልጣናት ሦስቱም ክትባቶች መቶ በመቶ ቫይረሱን የመከላከል አቅም አላቸው ሲሉ አሳስበዋል። የፋይዘር እና የሞደርና ክትባቶች አዳዲሶቹ የቫይረሱ ዝርያዎች ከመስፋፋታቸው በፊት የተሞከሩ ሲሆን አዳዲሶቹ ዝርያዎች በሙከራዎች ላይ ልዩነት ይፈጥራሉ። በተጨማሪም የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ሁሉም ክትባቶች ከዓመታዊው የጉንፋን ክትባት የበለጠ ውጤታማ ናቸው ሲል ይገልጻል። እንደ ዶ/ር አንድራስክ ከሆነ "ዋናው ነገር ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን፣ ሞደርና እና ፋይዘር ከባድ በሽታን በመከላከል፣ ሆስፒታል መተኛትን በመቀነስ፣ ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን በመቀነስ ወይም መሞትን በመከላከል በማይታመን ሁኔታ ውጤታማ ናቸው።" የማኅበረሰብ ጤና ተሟጋቾች እንደሚሉት ከሆነ ሌላው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ጠቃሚ ጎን በአሜሪካ ውስጥ ብቸኛው አንድ ጊዜ የሚሰጥ ክትባት መሆኑን ነው። ራቅ ወዳሉ እና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎችም ለማሰራጨት የበለጠ ምቹ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ያንን ክትባት ብቻ ወደ አካባቢዎቹ መላክ መገለልን ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ። አክለውም "ሁሉም ክትባቶች ለሁሉም ሊደርሱ ይገባል ብዬ አስባለሁ። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ወደ ገጠር እና ድሃ ማኅበረሰቦች የመላክ ምክንያታዊነት በእንክብካቤ ተደራሽነት ምክንያት ነው ብዬ አስባለሁ" ብለዋል ዶ/ር አንድራስክ። እንደ ዶ/ር አንድራስክ ያሉ የማኅበረሰብ አመራሮች እና የጤና ባለሙያዎች በክትባቱ ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማስፋፋት እና የተሳሳተ መረጃን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ነው። በአሜሪካ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ "የእኔ ተራ ሲደርስ ማንኛውንም ክትባት እወስዳለሁ" ይላሉ። ሌሎቹ አሳሳቢ ጉዳዮችስ ምንድን ናቸው? ዩ ኤስ ኮንፈረንስ ኦፍ ካቶሊክ ቢሾፕስ የተባለው እና በአሜሪካ የሚገኘውን ቤተክርስትያን የሚወክለው ጉባኤ በክትባቱ ዙሪያ "የሞራል ስጋት" መኖሩን መግለጹ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የስጋቱ ምንጭ ጽንስ በማስወረድ ከሚገኙ ሕዋሶች ክትባቱ ተመርቷል መባሉ ነው። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኢቦላ ክትባትን ለማዘጋጀት የዋለውን ተመሳሳይ ዘዴ ተጠቅሟል። በተጨማሪም የትኛውም የኮቪድ -19 ክትባት ምንም ዓይነት የሰው ህዋሳትን አልያዘም። ጉባኤው ምርጫ እስካለ ድረስ ካቶሊኮች አማራጭ ክትባቶች መውሰድ እንዳለባቸው መክሯል። በአሜሪካ ጉባኤ የተሰጠው ምክር ከቫቲካን አቋም ጋር የሚቃረን ይመስላል። ምክንያቱም ቫቲካን እንዲህ ያሉት ክትባቶች "ከሞራል አንጻር ተቀባይነት አላቸው" ስለምትል ነው። ሌሎች የካቶሊክ መሪዎችም የቤተክርስቲያኗ አባላት ከዚህ ክትባት መራቅ አለባቸው የሚለውን ሐሳብ እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። የሐርትፎርድ ሊቀ ጳጳስ እና ሌሎች የአካባቢው የሐይማኖት አባቶች በሰጡት መግለጫ ሁሉም ነዋሪዎች ለራሳቸው ጤና እና ለጋራ ጥቅም ሲሉ "ማንኛውንም ክትባት ለመቀበል የህሊና ነፃነት ሊሰማቸው ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ዶሮ በሽታ እና ሩቤላ ያሉ ሌሎች ብዙ ክትባቶች በተመሳሳይ መልኩ የተሠሩ ቢሆንም የካቶሊክ መሪዎች ስለ ለጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ያሰሙት ስጋት በአንዳንድ አሜሪካውያን ዘንድ ጥርጣሬ እንዲጨምር አድርጓል። ስጋቶችን የሚጋፈጠው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ብቻ አይደለም። አሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ለመፍቀድ እየተዘጋጀችበት የሚገኘው የኦክስፎርድ-አስትራዛኔካ ክትባት ከደም መርጋት ችግር ጋር በተያያዘ የአውሮፓ አገራት ታግዶ ነበር። የአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ ባሥልጣን ክትባቱ "ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ነው" ብሎ መግለጹን ተከትሎ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን እና ስፔን ክትባቱን መጠቀም መጀመራቸውን ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56498267
0business
ዩናይትድ ኪንግደም ለታዳጊ አገራት ምርቶች የቀረጥ ቅነሳ ልታደርግ ነው
ዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ግንኙነቷን ለማሳደግ ከታዳጊ አገራት ከምታስገባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ምርቶች ላይ ቀረጥ ልትቀንስ ነው። ይህ ለታዳጊ አገራት የታሰበው የንግድ ዕቅድ በጥር ወር ተግባራዊ ይሆናል። ይህም ዩናይትድ ኪንግደም የአውሮፓ ኅብረት አባል በነበረችበት ጊዜ በነበረው ዕቅድ ላይ ይመሠረታል ተብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በስፋት የማይመረቱ እንደ ልብስ፣ ጫማ እና ምግቦች ያሉ ዕቃዎች ዝቅተኛ ወይም ዜሮ ታሪፍ ይጣልባቸዋል። ዕቅዱ 65 ታዳጊ አገራትን ያጠቃልላል ተብሏል። ዕቅዱ በማደግ ላይ ያሉ አገራት ያለ ታሪፍ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ከሚልኳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ምርቶች በተጨማሪ ሲሆን፣ ከአፍሪካ ወደ አገሪቱ የሚገቡ 99 በመቶ ሸቀጦችን የሚመለከት ነው። የዓለም አቀፍ ንግድ ቢሮ እንደገለጸው ዕቅዱ ንግድን “ዕድገት ለማስመዝገብ እና ድህነትን ለማጥፋት" እንዲሁም የእርዳታ ጥገኝነትን ለመቀነስ ዩናይትድ ኪንግደም የምታደርገው ጥረት አካል ነው። ዕቅዱ አገራት በሰብዓዊ መብት፣ በጉልበት ብዝበዛ ወይም በአየር ንብረት ለውጥ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት የማገድ ሥልጣንን ያካትታል። የዓለም አቀፍ ንግድ ኃላፊ የሆኑት አን-ማሪ ትሬቬሊያን እንዳሉት "የንግድ ፖሊሲያችንን እንደገና እየተቆጣጠርን የዩናይትድ ኪንግደም ንግዶችን የሚደግፉ ውሳኔዎችን ከመውሰድ ባለፈ በኑሮ ውድነት እና የታዳጊ አገራትን ኢኮኖሚ ​​ይደግፋል።" ከ65 ድሃ አገራት ከጨርቃ ጨርቅ እስከ ፍራፍሬ የሚደርሱ ምርቶች በዩናይትድ ኪንግደም ሲሸጡ፣ የአነስተኛ ወይም የዜሮ ታሪፍ ተጠቃሚ ይሆናሉ። ይህም ይበልጥ ተፎካካሪ ያደርጋቸዋል። አዲሱ ዕቅድ የተወሰኑትን ተጨማሪ ክፍያዎችም ይቀንሳል ተብሎም ይጠበቃል። ለውጦቹ አስመጪዎችን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ፓውንድ እንዲያድኑ ያግዛሉ። ሆኖም ሙሉ በሙሉ ቢተገበር እንኳን ለተጠቃሚዎች የሚደርሰው የዋጋ ቅናሽ አነስተኛ ሊሆን ይችላል። ለታዳጊ አገራት የሚሰጠው ዕርዳታን በመቀነሱ በምትኩ መንግሥት በንግድ የመደገፍ ፖሊሲ እንዳለው ያሳያል ተብሏል። ከወቅቶች መለዋወጥ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ምርቶች ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ መመረት በማይችሉበት ወቅት በምርቶቹ ላይ የሚጣለው አነስተኛ ታሪፍም ይነሳል። አንዳንድ ደንቦችም ቀላል ይሆናሉ፤ ለምሳሌ አንድ ምርት አብዛኛውን ግብዓቶቹን ከየት ነው የሚያገኘው በሚል የምርቱን መነሻ አገር የመወሰን ጉዳይም አንዱ ነው። በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ የተሰማራው የባንግላዲሹ የዲቢኤል ግሩፕ ሥራ አስኪያጅ መሐመድ ጃባር ዕቅዱ ለድርጅታቸው "ትልቅ ለውጥ" መሆኑን ጠቅሰዋል። “በለውጦቹ ምክንያት ጥጥ ቀድም ሲል ከምናገኝባቸው አገራት በተጨማሪ ከሌሎችም በርካታ አገራት ማግኘት እንችላለን ማለት ነው። ይህም ንግዱን የበለጠ ተወዳዳሪ እና የአቅርቦት ሰንሰለቶቻችንን በጣም ጠንካራ ያደርገዋል” ብለዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም ለታዳጊ አገራት ምርቶች የቀረጥ ቅነሳ ልታደርግ ነው ዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ግንኙነቷን ለማሳደግ ከታዳጊ አገራት ከምታስገባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ምርቶች ላይ ቀረጥ ልትቀንስ ነው። ይህ ለታዳጊ አገራት የታሰበው የንግድ ዕቅድ በጥር ወር ተግባራዊ ይሆናል። ይህም ዩናይትድ ኪንግደም የአውሮፓ ኅብረት አባል በነበረችበት ጊዜ በነበረው ዕቅድ ላይ ይመሠረታል ተብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በስፋት የማይመረቱ እንደ ልብስ፣ ጫማ እና ምግቦች ያሉ ዕቃዎች ዝቅተኛ ወይም ዜሮ ታሪፍ ይጣልባቸዋል። ዕቅዱ 65 ታዳጊ አገራትን ያጠቃልላል ተብሏል። ዕቅዱ በማደግ ላይ ያሉ አገራት ያለ ታሪፍ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ከሚልኳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ምርቶች በተጨማሪ ሲሆን፣ ከአፍሪካ ወደ አገሪቱ የሚገቡ 99 በመቶ ሸቀጦችን የሚመለከት ነው። የዓለም አቀፍ ንግድ ቢሮ እንደገለጸው ዕቅዱ ንግድን “ዕድገት ለማስመዝገብ እና ድህነትን ለማጥፋት" እንዲሁም የእርዳታ ጥገኝነትን ለመቀነስ ዩናይትድ ኪንግደም የምታደርገው ጥረት አካል ነው። ዕቅዱ አገራት በሰብዓዊ መብት፣ በጉልበት ብዝበዛ ወይም በአየር ንብረት ለውጥ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት የማገድ ሥልጣንን ያካትታል። የዓለም አቀፍ ንግድ ኃላፊ የሆኑት አን-ማሪ ትሬቬሊያን እንዳሉት "የንግድ ፖሊሲያችንን እንደገና እየተቆጣጠርን የዩናይትድ ኪንግደም ንግዶችን የሚደግፉ ውሳኔዎችን ከመውሰድ ባለፈ በኑሮ ውድነት እና የታዳጊ አገራትን ኢኮኖሚ ​​ይደግፋል።" ከ65 ድሃ አገራት ከጨርቃ ጨርቅ እስከ ፍራፍሬ የሚደርሱ ምርቶች በዩናይትድ ኪንግደም ሲሸጡ፣ የአነስተኛ ወይም የዜሮ ታሪፍ ተጠቃሚ ይሆናሉ። ይህም ይበልጥ ተፎካካሪ ያደርጋቸዋል። አዲሱ ዕቅድ የተወሰኑትን ተጨማሪ ክፍያዎችም ይቀንሳል ተብሎም ይጠበቃል። ለውጦቹ አስመጪዎችን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ፓውንድ እንዲያድኑ ያግዛሉ። ሆኖም ሙሉ በሙሉ ቢተገበር እንኳን ለተጠቃሚዎች የሚደርሰው የዋጋ ቅናሽ አነስተኛ ሊሆን ይችላል። ለታዳጊ አገራት የሚሰጠው ዕርዳታን በመቀነሱ በምትኩ መንግሥት በንግድ የመደገፍ ፖሊሲ እንዳለው ያሳያል ተብሏል። ከወቅቶች መለዋወጥ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ምርቶች ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ መመረት በማይችሉበት ወቅት በምርቶቹ ላይ የሚጣለው አነስተኛ ታሪፍም ይነሳል። አንዳንድ ደንቦችም ቀላል ይሆናሉ፤ ለምሳሌ አንድ ምርት አብዛኛውን ግብዓቶቹን ከየት ነው የሚያገኘው በሚል የምርቱን መነሻ አገር የመወሰን ጉዳይም አንዱ ነው። በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ የተሰማራው የባንግላዲሹ የዲቢኤል ግሩፕ ሥራ አስኪያጅ መሐመድ ጃባር ዕቅዱ ለድርጅታቸው "ትልቅ ለውጥ" መሆኑን ጠቅሰዋል። “በለውጦቹ ምክንያት ጥጥ ቀድም ሲል ከምናገኝባቸው አገራት በተጨማሪ ከሌሎችም በርካታ አገራት ማግኘት እንችላለን ማለት ነው። ይህም ንግዱን የበለጠ ተወዳዳሪ እና የአቅርቦት ሰንሰለቶቻችንን በጣም ጠንካራ ያደርገዋል” ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/crg7pp8x210o
3politics
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስልጣን አስረከበ
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አዲስ ለተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዛሬው ዕለት ስልጣን አስረክቧል። ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 24፣ 2014 ዓ.ም በስድስተኛው ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው የስልጣን ርክክቡን አዲስ ከተቋቋመው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር ያደረገው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል በመሆን በፌዴሬሽን ምክር ቤት እውቅናን ያገኘው በባለፈው ሳምንት መስከረም 20፣ 2014 ዓ.ም ነው። 11ኛውን ክልል ያቋቋሙት የምዕራብ ኦሞ ፣ የቤንች ሸኮ፣ የከፋ ፣ የዳውሮ ፣ የሸካ ዞኖችና የኮንታ ልዩ ወረዳ አፈ ጉባኤዎችም በስልጣን ርክክቡ ወቅትም ተገኝተው ነበር። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በምክር ቤቱ ተገኝተው ባደረጉትም ንግግር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመሆን ጥያቄ ሂደት ዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መካሄድ እንዲችል ክልላቸው ሲሰራ መቆየቱን መናገራቸውም ተዘግቧል። ርእሰ መስተዳድሩ አዲስ የተቋቋመው ክልል በፍጥነት አዲሱ ክልል በፍጥነት ወደ መሬት እንዲወርድ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንዳለበትና ከፋይናንስ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በኮሚቴ የሚታይና ለመንግስት የሚቀርብ መሆኑንም አስረድተዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እንዲመሠረት በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ላይ ድምጽ ለመስጠት ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመዝግበው ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ድምጽ መስጠታቸው ይታወሳል። በምርጫው ከተሳተፉት መካከልም አምስቱ ዞኖች እና አንዱ ልዩ ወረዳ ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰብ እና ሕዝቦች ክልል ሥር ወጥተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በመባል መዋቀራቸውን በመደገፍ 1 ሚሊዮን 221 ሺህ 92 ሰዎች ድምጽ ሰጥተዋል።
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስልጣን አስረከበ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አዲስ ለተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዛሬው ዕለት ስልጣን አስረክቧል። ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 24፣ 2014 ዓ.ም በስድስተኛው ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው የስልጣን ርክክቡን አዲስ ከተቋቋመው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር ያደረገው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል በመሆን በፌዴሬሽን ምክር ቤት እውቅናን ያገኘው በባለፈው ሳምንት መስከረም 20፣ 2014 ዓ.ም ነው። 11ኛውን ክልል ያቋቋሙት የምዕራብ ኦሞ ፣ የቤንች ሸኮ፣ የከፋ ፣ የዳውሮ ፣ የሸካ ዞኖችና የኮንታ ልዩ ወረዳ አፈ ጉባኤዎችም በስልጣን ርክክቡ ወቅትም ተገኝተው ነበር። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በምክር ቤቱ ተገኝተው ባደረጉትም ንግግር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመሆን ጥያቄ ሂደት ዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መካሄድ እንዲችል ክልላቸው ሲሰራ መቆየቱን መናገራቸውም ተዘግቧል። ርእሰ መስተዳድሩ አዲስ የተቋቋመው ክልል በፍጥነት አዲሱ ክልል በፍጥነት ወደ መሬት እንዲወርድ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንዳለበትና ከፋይናንስ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በኮሚቴ የሚታይና ለመንግስት የሚቀርብ መሆኑንም አስረድተዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እንዲመሠረት በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ላይ ድምጽ ለመስጠት ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመዝግበው ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ድምጽ መስጠታቸው ይታወሳል። በምርጫው ከተሳተፉት መካከልም አምስቱ ዞኖች እና አንዱ ልዩ ወረዳ ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰብ እና ሕዝቦች ክልል ሥር ወጥተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በመባል መዋቀራቸውን በመደገፍ 1 ሚሊዮን 221 ሺህ 92 ሰዎች ድምጽ ሰጥተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59151038
0business
መዳብ ተብሎ ድንጋይ የተሸጠለት ድርጅት 36 ሚሊዮን ዶላር ተጭበረበረ
ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 36 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት መዳብ ከቱርክ ኩባንያ የገዛው ድርጅት ቀለም የተቀባ ድንጋይ እንደደረሰው አስታወቀ። አንድ የሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴ በ36 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት የገዛውን መዳብ፤ አቅራቢ ኩባንያው ቀለም በተቀቡ ድንጋዮች ቀይሮ እንዳስረከበው ገልጿል። መቀመጫውን ጄኔቫ ያደረገው ሜርኩሪያ ኢነርጂ ግሩፕ 10,000 ቶን የመዳብ ግዢ መፈጸሙን ተከትሎ በጭነት ማጓጓዝ (ካርጎ) ወቅት ተጭበርብሬያለሁ ብሏል። ጭነቶቹ ቻይና ሲደርሱ በመዳቡ ምትክ ቀለም በተቀቡ ድንጋዮች የተሞሉ ኮንቴይነሮችን ሆነው ተገኝተዋል። የደኅንነት እና የፍተሻ ቁጥጥሮች ቢከናወኑም መጭበርበሩ መፈጸሙ ተነግሯል። ባለፈው ዓመት ሜርኩሪያ መዳረሻው ቻይና እንዲሆን ያቀደውን መዳብ ለመግዛት ተስማምቶ ከ300 በላይ ኮንቴይነሮች ውስጥ 6,000 ቶን ያህል መዳብ በስምንት መርከቦች ተጭነውለታል። ኢስታንቡል አቅራቢያ ከሚገኘው ወደብ ጭነቱ መጓጓዝ ከመጀመሩ በፊት፣ በከፊል የተጣራውን መዳብ በሚመስሉ ቀለም በተቀቡ የተጠረቡ ድንጋዮች ተቀይሯል። በዓለም ላይ ካሉ አምስት ታላላቅ የነዳጅ ነጋዴዎች አንዱ የሆነው ሜርኩሪያ በመዳብ አቅራቢው በቢኤትሳን ባኪር ላይ በቱርክ እና በእንግሊዝ ፍርድ ቤቶች ፍትህ ለማግኘት እየጣረ ነው። የቱርክ ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር የሚያያዙ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። ኩባንያው በመግለጫው ላይ "በዚህ የተደራጀ ወንጀል ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል" ካለ በኋላ ኢስታንቡል የፋይናንስ ወንጀሎች መምሪያን አመስግኗል። ቁልፎች ተሰብረዋል በአጣሪ ኩባንያ ምርመራ ከመካሄዱ በፊት መዳቦቹ ወደ መጀመሪያዎቹ ኮንቴነሮች የተጫኑ ይመስላል። ማጭበርበርን ለመከላከል ጥቅም ላይ የዋሉ ማህተሞች በዕቃዎቹ ላይ ተደርገዋል። ነገር ግን ኮንቴነሮቹ ተከፍተው መዳቦቹ በድንጋዮች ተተክተዋል ሲል የኢስታንቡል የሕግ ኩባንያ ኬዋይቢ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል። አጭበርባሪዎቹ እንዳይታወቅባቸው እውነተኛዎቹን ማህተሞች በሐሰተኞቹ ቀይረዋል። መርከቦቹ በባሕር ላይ በነበሩት ወቅት ለአምስት ጭነቶች ሜርኩሪያ ከ36 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከፍሏል። መርከቦቹ በዚያው ወር መጨረሻ በቻይናው ሊያንጉንግ ወደብ እስኪደርሱ ድረስ መጭበርበሩ አልታወቀም። "ገዢው በሻጩና በሁለት ተባባሪዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድ አቤቱታ አቅርቧል ድርጊቱ በተደራጀ መንገድ የተከናወነ የማጭበርበር ውጤት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል" ብሏል የቱርክ ፖሊስ በሰጠው መግለጫ። አንድ ነጋዴ የገዛቸው ንብረቶች ካልደረሱት በጭነት ኢንሹራንሱ ፖሊሲ መሠረት ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል። የቱርኩ ኩባንያ ከሰባት ስምምነቶች በአንዱ ብቻ ጭነቱን ለመካስ የሚውል እውነተኛ ኢንሹራንስ እንደሚገባ ሜርኩሪያ ደርሶበታል። የተቀረው በሙሉ የተጭበረበረ ነበር። ሮይተርስ ለሜርኩሪያ መዳቡን የሸጠውን የቱርክ ኩባንያ ቢኤትሳን ባኪርን ለማነጋገር ቢሞክርም ምላሽ አላገኘም። በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ችሎቶች በዚህ ሳምንት ይሰማሉ።
መዳብ ተብሎ ድንጋይ የተሸጠለት ድርጅት 36 ሚሊዮን ዶላር ተጭበረበረ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 36 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት መዳብ ከቱርክ ኩባንያ የገዛው ድርጅት ቀለም የተቀባ ድንጋይ እንደደረሰው አስታወቀ። አንድ የሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴ በ36 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት የገዛውን መዳብ፤ አቅራቢ ኩባንያው ቀለም በተቀቡ ድንጋዮች ቀይሮ እንዳስረከበው ገልጿል። መቀመጫውን ጄኔቫ ያደረገው ሜርኩሪያ ኢነርጂ ግሩፕ 10,000 ቶን የመዳብ ግዢ መፈጸሙን ተከትሎ በጭነት ማጓጓዝ (ካርጎ) ወቅት ተጭበርብሬያለሁ ብሏል። ጭነቶቹ ቻይና ሲደርሱ በመዳቡ ምትክ ቀለም በተቀቡ ድንጋዮች የተሞሉ ኮንቴይነሮችን ሆነው ተገኝተዋል። የደኅንነት እና የፍተሻ ቁጥጥሮች ቢከናወኑም መጭበርበሩ መፈጸሙ ተነግሯል። ባለፈው ዓመት ሜርኩሪያ መዳረሻው ቻይና እንዲሆን ያቀደውን መዳብ ለመግዛት ተስማምቶ ከ300 በላይ ኮንቴይነሮች ውስጥ 6,000 ቶን ያህል መዳብ በስምንት መርከቦች ተጭነውለታል። ኢስታንቡል አቅራቢያ ከሚገኘው ወደብ ጭነቱ መጓጓዝ ከመጀመሩ በፊት፣ በከፊል የተጣራውን መዳብ በሚመስሉ ቀለም በተቀቡ የተጠረቡ ድንጋዮች ተቀይሯል። በዓለም ላይ ካሉ አምስት ታላላቅ የነዳጅ ነጋዴዎች አንዱ የሆነው ሜርኩሪያ በመዳብ አቅራቢው በቢኤትሳን ባኪር ላይ በቱርክ እና በእንግሊዝ ፍርድ ቤቶች ፍትህ ለማግኘት እየጣረ ነው። የቱርክ ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር የሚያያዙ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። ኩባንያው በመግለጫው ላይ "በዚህ የተደራጀ ወንጀል ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል" ካለ በኋላ ኢስታንቡል የፋይናንስ ወንጀሎች መምሪያን አመስግኗል። ቁልፎች ተሰብረዋል በአጣሪ ኩባንያ ምርመራ ከመካሄዱ በፊት መዳቦቹ ወደ መጀመሪያዎቹ ኮንቴነሮች የተጫኑ ይመስላል። ማጭበርበርን ለመከላከል ጥቅም ላይ የዋሉ ማህተሞች በዕቃዎቹ ላይ ተደርገዋል። ነገር ግን ኮንቴነሮቹ ተከፍተው መዳቦቹ በድንጋዮች ተተክተዋል ሲል የኢስታንቡል የሕግ ኩባንያ ኬዋይቢ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል። አጭበርባሪዎቹ እንዳይታወቅባቸው እውነተኛዎቹን ማህተሞች በሐሰተኞቹ ቀይረዋል። መርከቦቹ በባሕር ላይ በነበሩት ወቅት ለአምስት ጭነቶች ሜርኩሪያ ከ36 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከፍሏል። መርከቦቹ በዚያው ወር መጨረሻ በቻይናው ሊያንጉንግ ወደብ እስኪደርሱ ድረስ መጭበርበሩ አልታወቀም። "ገዢው በሻጩና በሁለት ተባባሪዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድ አቤቱታ አቅርቧል ድርጊቱ በተደራጀ መንገድ የተከናወነ የማጭበርበር ውጤት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል" ብሏል የቱርክ ፖሊስ በሰጠው መግለጫ። አንድ ነጋዴ የገዛቸው ንብረቶች ካልደረሱት በጭነት ኢንሹራንሱ ፖሊሲ መሠረት ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል። የቱርኩ ኩባንያ ከሰባት ስምምነቶች በአንዱ ብቻ ጭነቱን ለመካስ የሚውል እውነተኛ ኢንሹራንስ እንደሚገባ ሜርኩሪያ ደርሶበታል። የተቀረው በሙሉ የተጭበረበረ ነበር። ሮይተርስ ለሜርኩሪያ መዳቡን የሸጠውን የቱርክ ኩባንያ ቢኤትሳን ባኪርን ለማነጋገር ቢሞክርም ምላሽ አላገኘም። በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ችሎቶች በዚህ ሳምንት ይሰማሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-56343133
3politics
ምርጫ ቦርድ ‘ኢሠፓ’ በሚል ስም የቀረበውን የፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ውድቅ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ)” በሚል ስያሜ የቀረበውን የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባ ጥያቄን ውድቅ አደረገ። ከ30 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብቸኛው ገዢ ፓርቲ የነበረው ኢሠፓ፣ ሕገወጥ ተብሎ ከአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ከተገለለ በኋላ በስሙ ለመደራጀት ጥያቄ የቀረበው ባለፈው ግንቦት ወር ነበር። ቦርዱ የኢ.ሕ.ድ.ሪ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ከመሠረቱ ፓርቲ ጋር በተመሳሳይ ስም ለመመዝገብ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገባቸውን ሕጋዊ ምክንያቶች ዘርዝሯል። ቦርዱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ መሠረት ለምዝባ ጥያቄ የቀረበበት የፓርቲ ስያሜ ቀድሞ ሕጋዊ ሰውነት ከነበረው ፓርቲ ስያሜ ጋር በመመሳሰል፣ በመራጮች ዘንድ ግርታን የሚፈጥር ሆኖ ከተገኘ ቦርዱ ሊቀበለው አይገባም ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ከደርግ ከሥልጣን መወገድ በኋላ የወጣው እና ያልተሻረው ‘ሰላማዊ ሰልፍ እና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ’ ኢሠፓ የተባለው ድርጅት ፀረ-ዲሞክራሲ እና ወንጀለኛ ደርጅት ነው በሚል በሕግ አፍርሶታል ብሏል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ጥያቄ የቀረበበት የፓርቲ ስያሜ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ከነበረ ፓርቲ ጋር ብቻ ሳይሆን የተመሳሰለው፣ "አሁንም ጸንቶ ባለ ሕግ ወንጀለኛ ተብሎ ከተፈረጀ እና ከፈረሰ ድርጅት ጋር ጭምር ነው" ብሏል ቦርዱ በደብዳቤው። ቦርዱ በዚህ ስያሜ የቀረበለትን የፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ቢቀበል ያልተሻረ ሕግን እንደተሻረ፤ እንዲሁም የፈረሰ ድርጅት ገደቡ ተላልፎ እንደገና እንደተቋቋመ የሚመስል ግንዛቤን የሚፈጥር በመሆኑ እንዳልተቀበለው ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም የስሙ መመሳሰል በምርጫ ወቅት ምራጮችን ሊያምታት ስለሚችል ቦርዱ በመቋቋሚያ በአዋጁ ቁጥር መሠረት “የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ)” በሚል ስያሜ የቀረበለትን የፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል። በቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ተፈርሞ የቦርዱን ውሳኔ በተላለፈበት ደብዳቤ ላይ፤ አስተባባሪዎቹ በሌላ ስያሜ ፓርቲ አቋቋመው የመደራጀት እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማድረግ መብታቸው የተጠበቀ መሆኑን አስታውሰዋል። ከንጉሣዊው ሥርዓት መውደቅ በኋላ በወታደሮች ቁጥጥር ስር የገባው የኢትዮጵያ መንግሥት በእርስ በርስ ጦርነት፣ በድረቅና  በከባድ የረሃብ አደጋ ስትናጥ የቆየችውን አገር ለ17 ዓመታት የመራው አስተዳደር በተለያዩ ቅርጾች መቆየቱ ይታወቃል። ንጉሡ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ከተለያዩ የአገሪቱ የጦር ክፍሎች የተዋቀረው ወታደራዊ ኮሚቴ ደርግ፣ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር መስርቶ ከቆየ በኋላ፣ ርዕዮት ዓለሙን ሶሻሊዝም በማድረግ ወደ መደበኛ መዋቅር ለመሸጋገር ዓመታት ወስዶበታል። በዚህም የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን (ኢሠፓአኮ) በማቋቋም ዝግጅት ሲያደርግ ከቆ በኋላ፣ ከ10ኛው የአብዮት በዓል ጋር በተያያዘ በመስከረም 1977 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲን (ኢሠፓ) የአገሪቱ ብቸኛው ገዢ ፓርቲ ሆኖ ተመስርቶ ነበር። ፓርቲው አሁን በስደት ላይ በሚገኙት በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም የሚመራ የነበረ ሲሆን፣ በመላው አገሪቱ ሰፊ መዋቅር ዘርግቶ አገሪቱን ሲመራ ቆይቷል። ነገር ግን ይህ ፓርቲ ከተመሰረተ ከአምስት ዓመት በላይ በሥልጣን ላይ ሳይቆይ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ለዓመታት የዘለቀውን የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲያካሄዱ የነበሩት የኤርትራ ነጻነት ግንባር እና ህወሓት በጦር ሜዳው የበላይነት አግኝተው ፓርቲውን ከሥልጣን አስወግደውታል። ይህንንም ተከትሎ በ17 ዓመቱ የደርግ የሥልጣን ዘመን በተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች ምክንያት ኢሠፓ ሕገ-ወጥ ፓርቲ ተብሎ፣ አባላት እና አመራሮቹ ለዓመታት በእስር ቆይተዋል። አብዛኞቹ የፓርቲው አመራሮችም በእድሜ እና በተለያዩ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለያዩ ሲሆን፣ ጥቂት የማይባሉት ደግሞ ከ20 ዓመታት እስር በኋላ ነጻ ወጥተው በኢትዮጵያና በተለያዩ አገራት ይገኛሉ። ከጥቂት ወራት በፊትም አስካሁን ማንነታቸው ይፋ ያልወጣ ግለሰቦች ተሰባስበው ከሦስት አስርት ዓመት በኋላ፣ በኢሠፓ ስም አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረባቸው በአውንታዊ እንዲሁም በአሉታዊ መልኩ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። እስካሁም ድረስ ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት ግለሰቦች የቀድሞ የፓርቲው አባላት እና አመራሮች መሆን አለመሆናቸው በይፋ የታወቀ ነገር የለም።
ምርጫ ቦርድ ‘ኢሠፓ’ በሚል ስም የቀረበውን የፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ውድቅ አደረገ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ)” በሚል ስያሜ የቀረበውን የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባ ጥያቄን ውድቅ አደረገ። ከ30 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብቸኛው ገዢ ፓርቲ የነበረው ኢሠፓ፣ ሕገወጥ ተብሎ ከአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ከተገለለ በኋላ በስሙ ለመደራጀት ጥያቄ የቀረበው ባለፈው ግንቦት ወር ነበር። ቦርዱ የኢ.ሕ.ድ.ሪ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ከመሠረቱ ፓርቲ ጋር በተመሳሳይ ስም ለመመዝገብ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገባቸውን ሕጋዊ ምክንያቶች ዘርዝሯል። ቦርዱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ መሠረት ለምዝባ ጥያቄ የቀረበበት የፓርቲ ስያሜ ቀድሞ ሕጋዊ ሰውነት ከነበረው ፓርቲ ስያሜ ጋር በመመሳሰል፣ በመራጮች ዘንድ ግርታን የሚፈጥር ሆኖ ከተገኘ ቦርዱ ሊቀበለው አይገባም ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ከደርግ ከሥልጣን መወገድ በኋላ የወጣው እና ያልተሻረው ‘ሰላማዊ ሰልፍ እና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት አዋጅ’ ኢሠፓ የተባለው ድርጅት ፀረ-ዲሞክራሲ እና ወንጀለኛ ደርጅት ነው በሚል በሕግ አፍርሶታል ብሏል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ጥያቄ የቀረበበት የፓርቲ ስያሜ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ከነበረ ፓርቲ ጋር ብቻ ሳይሆን የተመሳሰለው፣ "አሁንም ጸንቶ ባለ ሕግ ወንጀለኛ ተብሎ ከተፈረጀ እና ከፈረሰ ድርጅት ጋር ጭምር ነው" ብሏል ቦርዱ በደብዳቤው። ቦርዱ በዚህ ስያሜ የቀረበለትን የፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ቢቀበል ያልተሻረ ሕግን እንደተሻረ፤ እንዲሁም የፈረሰ ድርጅት ገደቡ ተላልፎ እንደገና እንደተቋቋመ የሚመስል ግንዛቤን የሚፈጥር በመሆኑ እንዳልተቀበለው ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም የስሙ መመሳሰል በምርጫ ወቅት ምራጮችን ሊያምታት ስለሚችል ቦርዱ በመቋቋሚያ በአዋጁ ቁጥር መሠረት “የኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ)” በሚል ስያሜ የቀረበለትን የፓርቲ ምዝገባ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል። በቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ተፈርሞ የቦርዱን ውሳኔ በተላለፈበት ደብዳቤ ላይ፤ አስተባባሪዎቹ በሌላ ስያሜ ፓርቲ አቋቋመው የመደራጀት እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማድረግ መብታቸው የተጠበቀ መሆኑን አስታውሰዋል። ከንጉሣዊው ሥርዓት መውደቅ በኋላ በወታደሮች ቁጥጥር ስር የገባው የኢትዮጵያ መንግሥት በእርስ በርስ ጦርነት፣ በድረቅና  በከባድ የረሃብ አደጋ ስትናጥ የቆየችውን አገር ለ17 ዓመታት የመራው አስተዳደር በተለያዩ ቅርጾች መቆየቱ ይታወቃል። ንጉሡ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ከተለያዩ የአገሪቱ የጦር ክፍሎች የተዋቀረው ወታደራዊ ኮሚቴ ደርግ፣ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር መስርቶ ከቆየ በኋላ፣ ርዕዮት ዓለሙን ሶሻሊዝም በማድረግ ወደ መደበኛ መዋቅር ለመሸጋገር ዓመታት ወስዶበታል። በዚህም የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን (ኢሠፓአኮ) በማቋቋም ዝግጅት ሲያደርግ ከቆ በኋላ፣ ከ10ኛው የአብዮት በዓል ጋር በተያያዘ በመስከረም 1977 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲን (ኢሠፓ) የአገሪቱ ብቸኛው ገዢ ፓርቲ ሆኖ ተመስርቶ ነበር። ፓርቲው አሁን በስደት ላይ በሚገኙት በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም የሚመራ የነበረ ሲሆን፣ በመላው አገሪቱ ሰፊ መዋቅር ዘርግቶ አገሪቱን ሲመራ ቆይቷል። ነገር ግን ይህ ፓርቲ ከተመሰረተ ከአምስት ዓመት በላይ በሥልጣን ላይ ሳይቆይ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ለዓመታት የዘለቀውን የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲያካሄዱ የነበሩት የኤርትራ ነጻነት ግንባር እና ህወሓት በጦር ሜዳው የበላይነት አግኝተው ፓርቲውን ከሥልጣን አስወግደውታል። ይህንንም ተከትሎ በ17 ዓመቱ የደርግ የሥልጣን ዘመን በተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች ምክንያት ኢሠፓ ሕገ-ወጥ ፓርቲ ተብሎ፣ አባላት እና አመራሮቹ ለዓመታት በእስር ቆይተዋል። አብዛኞቹ የፓርቲው አመራሮችም በእድሜ እና በተለያዩ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለያዩ ሲሆን፣ ጥቂት የማይባሉት ደግሞ ከ20 ዓመታት እስር በኋላ ነጻ ወጥተው በኢትዮጵያና በተለያዩ አገራት ይገኛሉ። ከጥቂት ወራት በፊትም አስካሁን ማንነታቸው ይፋ ያልወጣ ግለሰቦች ተሰባስበው ከሦስት አስርት ዓመት በኋላ፣ በኢሠፓ ስም አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረባቸው በአውንታዊ እንዲሁም በአሉታዊ መልኩ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። እስካሁም ድረስ ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት ግለሰቦች የቀድሞ የፓርቲው አባላት እና አመራሮች መሆን አለመሆናቸው በይፋ የታወቀ ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cg656qpdgypo
3politics
የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ከግድያ ሙከራ ለጥቂት አመለጡ
የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ክርስቲና ፈርናንዴዝ ዴ ኪርችነር ትላንት ሃሙስ ምሽት ከግድያ ሙከራ ለጥቂት አመለጡ። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በጥይት ከመመታት የዳኑት የተኳሹ መሳሪያ በመንከሱ ነው ተብሏል። ዴ ኪርችነር ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ሰላምታ በመስጠት ላይ ሳሉ ነበር አንድ ግለሰብ ከሕዝቡ መካከል ወጥቶ ፊታቸው ላይ ሽጉጡን አነጣጥሮ ለመተኮስ የሞከረው። የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ፊት ላይ ተነጣጥሮ የነበረው ጦር መሳሪያ አምስት ጥይቶች ጎርሶ የነበረው ቢሆንም ቃታው ሲሳብ ግን ሳይተኩስ ቀርቷል ብለዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ክሳቸውን በመከታተል ላይ ባሉበት በዚህ ወቅት ነው የግድያ ሙከራ የተፈጸመባቸው። የቀረበባቸውን ክስም ፖለቲካዊ አላማ የያዘ በሚል በተደጋጋሚ ውድቅ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ፖሊስ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የ35 አመቱ ብራዚላዊ ምክትል ፕሬዘዳንቷን ለመግደል በመሞከር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል። ግለሰቡ ምክትል ፕሬዝዳንቷን ለመግደል ምን እንዳነሳሳው ለመረዳት ምርመራ እየተደረገ እንደሆነም ተገልጿል። ትላንት ምሽት ንግግር ያደረጉት ፕሬዘዳንት ፈርናንዴዝ ጥቃቱን ያወገዙ ሲሆን በምክትላቸው ላይ የተደረገው የግድያ ሙከራ አርጀንቲና እእአ በ1983 ወደ ዲሞክራሲ ስርዓት ከተመለሰች ወዲህ ካጋጠሙ "እጅግ አሳሳቢ" ክስተቶች መካከል አንዱ ነው ብለዋል። ‘’ከምክትል ፕሬዘዳንቷ ጋር አለመስማማት እና ልዩነቶች ሊኖሩን ይችላሉ። ነገር ግን የጥላቻ ንግግሮች ሁከትን ይወልዳሉ። አመጽ እና ዴሞክራሲ ደግሞ አብረው የመሄድ እድል የላቸውም" ሲሉ ፕረዘዳንት ፈርናንዴዝ ተናግረዋል። ፕሬዘዳንቱ አክለውም አርብ ቀን ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲውል እና አርጀንቲናዊያን በሕይወት የመኖር መብትን በመደገፍ ብሎም ምክትል ፕሬዝዳንቷ ላይ የተቃጣውን ጥቃት የሚያወግዙበት ቀን እንዲሆን አውጀዋል። በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጩ ምስሎች እንደሚያሳዩት ተጠርጣሪው ወደ ግለሰቧ ጭንቅላት ሽጉጡን በማነጣጠር ለመተኮስ ሲሞክር ይታያል። ከዚያም ምክትል ፕሬዘዳንቷ ጎንበስ ብለው ወደ ታች ሲመለከቱ ይታያል። ነገር ግን ምንም ጥይት አልተተኮሰም። እ.ኤ.አ. ከ2007 እስከ 2015 መካከል ፕሬዝዳንት የነበሩት ዴ ኪርቸነር በስልጣን ዘመናቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በተጭበረበሩ ጨረታዎች አሸናፊዎችን በመምረጥ ክስ ቀርቦባቸዋል። አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ መሰረት ጥፋተኛ የሚባሉ ከሆነ የ12 አመት እስራት እና እድሜ ልክ ከፖለቲካ የመታገድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ሆኖም ዴ ኪርችነር የፓርላማው ጸሃፊ እና አባል በመሆናቸው ምክንያት ያለመከሰስ መብት አላቸው። እንዲሁም ቅጣት ቢጣልባቸው እንኳን በአገሪቱ ህግ መሰረት ቅጣቱ በሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ካልፀደቀ ወይም ከአንድ አመት ተኩል በኋላ በሚደረገው ምርጫ የሴኔት መቀመጫቸውን ካላጡ በስተቀር አይታሰሩም።
የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ከግድያ ሙከራ ለጥቂት አመለጡ የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ክርስቲና ፈርናንዴዝ ዴ ኪርችነር ትላንት ሃሙስ ምሽት ከግድያ ሙከራ ለጥቂት አመለጡ። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በጥይት ከመመታት የዳኑት የተኳሹ መሳሪያ በመንከሱ ነው ተብሏል። ዴ ኪርችነር ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ሰላምታ በመስጠት ላይ ሳሉ ነበር አንድ ግለሰብ ከሕዝቡ መካከል ወጥቶ ፊታቸው ላይ ሽጉጡን አነጣጥሮ ለመተኮስ የሞከረው። የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ፊት ላይ ተነጣጥሮ የነበረው ጦር መሳሪያ አምስት ጥይቶች ጎርሶ የነበረው ቢሆንም ቃታው ሲሳብ ግን ሳይተኩስ ቀርቷል ብለዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ክሳቸውን በመከታተል ላይ ባሉበት በዚህ ወቅት ነው የግድያ ሙከራ የተፈጸመባቸው። የቀረበባቸውን ክስም ፖለቲካዊ አላማ የያዘ በሚል በተደጋጋሚ ውድቅ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ፖሊስ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን የ35 አመቱ ብራዚላዊ ምክትል ፕሬዘዳንቷን ለመግደል በመሞከር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል። ግለሰቡ ምክትል ፕሬዝዳንቷን ለመግደል ምን እንዳነሳሳው ለመረዳት ምርመራ እየተደረገ እንደሆነም ተገልጿል። ትላንት ምሽት ንግግር ያደረጉት ፕሬዘዳንት ፈርናንዴዝ ጥቃቱን ያወገዙ ሲሆን በምክትላቸው ላይ የተደረገው የግድያ ሙከራ አርጀንቲና እእአ በ1983 ወደ ዲሞክራሲ ስርዓት ከተመለሰች ወዲህ ካጋጠሙ "እጅግ አሳሳቢ" ክስተቶች መካከል አንዱ ነው ብለዋል። ‘’ከምክትል ፕሬዘዳንቷ ጋር አለመስማማት እና ልዩነቶች ሊኖሩን ይችላሉ። ነገር ግን የጥላቻ ንግግሮች ሁከትን ይወልዳሉ። አመጽ እና ዴሞክራሲ ደግሞ አብረው የመሄድ እድል የላቸውም" ሲሉ ፕረዘዳንት ፈርናንዴዝ ተናግረዋል። ፕሬዘዳንቱ አክለውም አርብ ቀን ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲውል እና አርጀንቲናዊያን በሕይወት የመኖር መብትን በመደገፍ ብሎም ምክትል ፕሬዝዳንቷ ላይ የተቃጣውን ጥቃት የሚያወግዙበት ቀን እንዲሆን አውጀዋል። በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጩ ምስሎች እንደሚያሳዩት ተጠርጣሪው ወደ ግለሰቧ ጭንቅላት ሽጉጡን በማነጣጠር ለመተኮስ ሲሞክር ይታያል። ከዚያም ምክትል ፕሬዘዳንቷ ጎንበስ ብለው ወደ ታች ሲመለከቱ ይታያል። ነገር ግን ምንም ጥይት አልተተኮሰም። እ.ኤ.አ. ከ2007 እስከ 2015 መካከል ፕሬዝዳንት የነበሩት ዴ ኪርቸነር በስልጣን ዘመናቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በተጭበረበሩ ጨረታዎች አሸናፊዎችን በመምረጥ ክስ ቀርቦባቸዋል። አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ መሰረት ጥፋተኛ የሚባሉ ከሆነ የ12 አመት እስራት እና እድሜ ልክ ከፖለቲካ የመታገድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ሆኖም ዴ ኪርችነር የፓርላማው ጸሃፊ እና አባል በመሆናቸው ምክንያት ያለመከሰስ መብት አላቸው። እንዲሁም ቅጣት ቢጣልባቸው እንኳን በአገሪቱ ህግ መሰረት ቅጣቱ በሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ካልፀደቀ ወይም ከአንድ አመት ተኩል በኋላ በሚደረገው ምርጫ የሴኔት መቀመጫቸውን ካላጡ በስተቀር አይታሰሩም።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1lk573xk7o
0business
ክሪፕቶከረንሲዎች ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተጋለጡ የግብይት ባለሙያዎች አስጠነቀቁ
ክሪፕቶከረንሲን ጨምሮ ሌሎችም የበይነ መረብ ገንዘብ ማዘዋወሪያዎች አደጋ እንዳንዣበበባቸው የሆንግ ኮንግን የግብይት ተንታኞች ማስጠንቀቂያ ሰጡ። “ኢንቨስተሮች ከፍተኛ አደጋ ማንዣበቡን ይገንዘቡ” ሲል 'ሴኪውሪቲስ ኤንድ ፊውቸርስ' ኮሚሽን የተባለው የባለሙያዎች ማኅበር አሳውቋል። ማስጠንቀቂያውን የተሰጠው የክሪፕቶከረንሲ ገበያ በውዝግብ በተሞላበት ጊዜ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኤፍቲኤክስ ክሪፕቶከረንሲ መሥራች ሳም ባንክማን-ፍሬድ በዚህ ሳምንት ታስሮ ክስ ተመሥርቶበታል። “አንዳንድ የበይነ መረብ ሀብት ማከማቻዎች [virtual asset] በመርኅ አይመሩም። እንደ ባንክ ተቀማጭ ሒሳብም አይወሰዱም። ስለዚህ ኢንቨስተሮች ለገንዘባቸው ከለላ የላቸውም” ሲሉ ባለሙያዎቹ አስጠንቅቀዋል። “ኢንቨስተሮች እነዚህን አሠራሮች የማይረዷቸው ከሆነ ኪሳራ ሊገጥማቸው ስለሚችል ኢንቨስት እንዲያደርጉ አይመከርም” ሲሉም አክለዋል። የኤፍቲኤክስ ክሪፕቶከረንሲ መሥራች ሳም ባንክማን-ፍሬድ ባህማስ ውስጥ በተያዘ በሰዓታት ውስጥ የአሜሪካ አመራሮች በአገሪቱ ታሪክ “ከፍተኛው የፋይናንስ ማጭበርበር” ክስ መስርተውበታል። የሆንግ ኮንጉ ማኅበር ሊቀ መንበር ጌሪ ጊንስለር “ሳም በማጭበርበር ነው ቢዝነሱን ያዳበረው” ብለዋል። ሳም በዋስ ለመለቀቅ ቢጠይቅም አልተፈቀደለትም። የኤፍቲኤክስ ክሪፕቶከረንሲ ተፎካካሪ የሆነው ቢናንስ፣ ለተወሰነ ጊዜ መቋረጡን ተከትሎ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በክሪፕቶከረንሲው ኢንቨስት ተደርጎ የነበረ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ተነስቷል። የብሎክቼይን መረጃ ተቋም የሆነው ናንሳን እንደሚለው፣ የዓለም ትልቁ ክሪፕቶከረንሲ 1.9 ቢሊዮን ዶላር ተቀንሶበታል። የቢናንስ ዋና ኃላፊ ቻንፔንግ ዛሆ ግን የተቀነሰው ገንዘብ ወደ 1.4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ነው ብሏል። “አንዳንድ ቀን ገንዘብ ይቀነሳል (ወጪ ይደረጋል)። በሌላ ቀን ደግሞ ገንዘብ ይጨመራል (ገቢ ይደረጋል)። ይሄ የተለመደ የንግድ አካሄድ ነው” ሲል አክሏል። የበይነ መረብ ገንዘቡ ክሪፕቶከረንሲ በተለዋዋጭ የገቢ ሁኔታ ዋጋው ከፍና ዝቅ ሲል ቆይቷል። ትልቁ ክሪፕቶከረንሲ የሆነው ቢትኮይን ዘንድሮ 60 በመቶ ኪሳራ ገጥሞታል። ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎችም ገቢያቸው አሽቆልቁሏል። የገንዘብ ምንጭና ገንዘቡ የሚቀመጥበት ቦታ አለመታወቅ እንዲሁም ከመንግሥታት ቁጥጥር ውጪ መሆኑ፣ እንደ አደንዛዥ እጽ እና እገታ ያሉ ወንጀሎችን ያበረታታል የሚል ስጋት ይደመጣል።
ክሪፕቶከረንሲዎች ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተጋለጡ የግብይት ባለሙያዎች አስጠነቀቁ ክሪፕቶከረንሲን ጨምሮ ሌሎችም የበይነ መረብ ገንዘብ ማዘዋወሪያዎች አደጋ እንዳንዣበበባቸው የሆንግ ኮንግን የግብይት ተንታኞች ማስጠንቀቂያ ሰጡ። “ኢንቨስተሮች ከፍተኛ አደጋ ማንዣበቡን ይገንዘቡ” ሲል 'ሴኪውሪቲስ ኤንድ ፊውቸርስ' ኮሚሽን የተባለው የባለሙያዎች ማኅበር አሳውቋል። ማስጠንቀቂያውን የተሰጠው የክሪፕቶከረንሲ ገበያ በውዝግብ በተሞላበት ጊዜ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኤፍቲኤክስ ክሪፕቶከረንሲ መሥራች ሳም ባንክማን-ፍሬድ በዚህ ሳምንት ታስሮ ክስ ተመሥርቶበታል። “አንዳንድ የበይነ መረብ ሀብት ማከማቻዎች [virtual asset] በመርኅ አይመሩም። እንደ ባንክ ተቀማጭ ሒሳብም አይወሰዱም። ስለዚህ ኢንቨስተሮች ለገንዘባቸው ከለላ የላቸውም” ሲሉ ባለሙያዎቹ አስጠንቅቀዋል። “ኢንቨስተሮች እነዚህን አሠራሮች የማይረዷቸው ከሆነ ኪሳራ ሊገጥማቸው ስለሚችል ኢንቨስት እንዲያደርጉ አይመከርም” ሲሉም አክለዋል። የኤፍቲኤክስ ክሪፕቶከረንሲ መሥራች ሳም ባንክማን-ፍሬድ ባህማስ ውስጥ በተያዘ በሰዓታት ውስጥ የአሜሪካ አመራሮች በአገሪቱ ታሪክ “ከፍተኛው የፋይናንስ ማጭበርበር” ክስ መስርተውበታል። የሆንግ ኮንጉ ማኅበር ሊቀ መንበር ጌሪ ጊንስለር “ሳም በማጭበርበር ነው ቢዝነሱን ያዳበረው” ብለዋል። ሳም በዋስ ለመለቀቅ ቢጠይቅም አልተፈቀደለትም። የኤፍቲኤክስ ክሪፕቶከረንሲ ተፎካካሪ የሆነው ቢናንስ፣ ለተወሰነ ጊዜ መቋረጡን ተከትሎ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በክሪፕቶከረንሲው ኢንቨስት ተደርጎ የነበረ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ተነስቷል። የብሎክቼይን መረጃ ተቋም የሆነው ናንሳን እንደሚለው፣ የዓለም ትልቁ ክሪፕቶከረንሲ 1.9 ቢሊዮን ዶላር ተቀንሶበታል። የቢናንስ ዋና ኃላፊ ቻንፔንግ ዛሆ ግን የተቀነሰው ገንዘብ ወደ 1.4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ነው ብሏል። “አንዳንድ ቀን ገንዘብ ይቀነሳል (ወጪ ይደረጋል)። በሌላ ቀን ደግሞ ገንዘብ ይጨመራል (ገቢ ይደረጋል)። ይሄ የተለመደ የንግድ አካሄድ ነው” ሲል አክሏል። የበይነ መረብ ገንዘቡ ክሪፕቶከረንሲ በተለዋዋጭ የገቢ ሁኔታ ዋጋው ከፍና ዝቅ ሲል ቆይቷል። ትልቁ ክሪፕቶከረንሲ የሆነው ቢትኮይን ዘንድሮ 60 በመቶ ኪሳራ ገጥሞታል። ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎችም ገቢያቸው አሽቆልቁሏል። የገንዘብ ምንጭና ገንዘቡ የሚቀመጥበት ቦታ አለመታወቅ እንዲሁም ከመንግሥታት ቁጥጥር ውጪ መሆኑ፣ እንደ አደንዛዥ እጽ እና እገታ ያሉ ወንጀሎችን ያበረታታል የሚል ስጋት ይደመጣል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c72nyeppxm0o
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮርያ የኮቪድ-19 ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሕጓን አጠበቀች
በደቡብ ኮርያ ዋና ከተማ የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ሙዚየሞች፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ እንዲሁም መጠጥ ቤቶች ተዘግተዋል። ማክሰኞ ዕለት የቫይረሱ ስርጭት ለአምስተኛ ቀን ወደ ሶስት ዲጂት ከፍ ያለ ሲሆን በአብዛኛው እድሜያቸው በ40ዎቹ ውስጥ የሆኑ ሰዎች መጠቃታቸው ታውቋል። ደቡብ ኮርያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በፍጥነት በመቆጣጠር ስሟ በተደጋጋሚ ሲነሳ ነበር። ነገር ግን ከቤተ እምነቶች ጋር በተያያዘ የተቀሰቀሰው ዳግም ወረርሽኝ ስጋትን አጭሯል። ደቡብ ኮርያ ማክሰኞ ዕለት 246 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በምርመራ ስታረጋግጥ በአገሪቷ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 15,761 ደርሷል። አብዛኛዎቹ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ግለሰቦች በሳራንግ ዤይል ቤተ ክርስትያን ጋር የሚገናኙ ሲሆን፣ የቤተ እምነቷ ፓስተር የፕሬዝዳንት ሙን ዤ-ኢን ቀንደኛ አብጠልጣይ ናቸው። ይህ በደቡብ ኮርያ የተከሰተው አዲስ ወረርሽኝ በሌላ እምነት ስፍራም ይዛመታል የሚል ፍራቻ ቀስቅሷል። በደቡብ ኮርያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱ ሲታወቅ መነሻው የነበረው ሺንቼዮንጂ ቸርች ኦፍ ጂሰስ ነበር። ከዚህ ቤተ እምነት ጋር ግንኙነት ያላቸው 5,200 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው መገኘታቸው ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ 457 ከሳራንግ ዤይል ቤተክርስትያን ጋር ይያያዛል ተብሏል። ከእነዚህ መካከል አስር ግለሰቦች ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዋና ከተማዋ ሶል በተደረገ መንግሥትን በሚቃወም ሰልፍ ላይ ተሳትፈው እንደነበር ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የደቡብ ኮርያ ባለሥልጣታናት ማንኛውም ቤተ እምነት የአምልኮ ስርዓቱን በቤተ እምነቶች ውስጥ እንዳያካሂድ ያገዱ ሲሆን የቫይረሱ ስርጭት ታይቶባቸዋል የተባሉ ቤተ እምነቶችን ምዕመናን፣ ራሳቸውን ለይተው እንዲቀመጡ እና ምርመራ እንዲያደርጉ የመለየት ስራ እየሰሩ ነው። "አሁን ያለው ስርጭትን መቆጣጠር ካልቻልን ቀውስ ውስጥ እየገባን ነው፣ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያደርጋል፣ ይህ ደግሞ ህክምና ስርዓታችን እንዲንኮታኮትና ከፍተኛ የሆነ የምጣኔ ሃብት ድቀት እንዲደርስ ያደርጋል" ብለዋል የኮሪያ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ድርጅት ዳይሬክተር ዢዮንግ ኢኡን ኬኦንግ። ከዛሬ ረብዑ ጀምሮም 12 ለአደጋ ተጋላጭ የተባሉ የንግድ ዘርፎች በዋና ከተማዋ ሶል፣ ኢንቺዮን እና በተጎራባች የጊዮንጊ ግዛት እንዲዘጉ ተወስኗል፤ ከእነዚህም መካከል ፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች፣ አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ሙዚየሞችም የተዘጉ ሲሆን በቤት ውስጥ ከ50 ሰው በላይ፣ ከቤት ውጪ ደግሞ ከ100 ሰው በላይ ሆኖ መሰብሰብ ታግዷል።
ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮርያ የኮቪድ-19 ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሕጓን አጠበቀች በደቡብ ኮርያ ዋና ከተማ የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ሙዚየሞች፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ እንዲሁም መጠጥ ቤቶች ተዘግተዋል። ማክሰኞ ዕለት የቫይረሱ ስርጭት ለአምስተኛ ቀን ወደ ሶስት ዲጂት ከፍ ያለ ሲሆን በአብዛኛው እድሜያቸው በ40ዎቹ ውስጥ የሆኑ ሰዎች መጠቃታቸው ታውቋል። ደቡብ ኮርያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በፍጥነት በመቆጣጠር ስሟ በተደጋጋሚ ሲነሳ ነበር። ነገር ግን ከቤተ እምነቶች ጋር በተያያዘ የተቀሰቀሰው ዳግም ወረርሽኝ ስጋትን አጭሯል። ደቡብ ኮርያ ማክሰኞ ዕለት 246 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በምርመራ ስታረጋግጥ በአገሪቷ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 15,761 ደርሷል። አብዛኛዎቹ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ግለሰቦች በሳራንግ ዤይል ቤተ ክርስትያን ጋር የሚገናኙ ሲሆን፣ የቤተ እምነቷ ፓስተር የፕሬዝዳንት ሙን ዤ-ኢን ቀንደኛ አብጠልጣይ ናቸው። ይህ በደቡብ ኮርያ የተከሰተው አዲስ ወረርሽኝ በሌላ እምነት ስፍራም ይዛመታል የሚል ፍራቻ ቀስቅሷል። በደቡብ ኮርያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱ ሲታወቅ መነሻው የነበረው ሺንቼዮንጂ ቸርች ኦፍ ጂሰስ ነበር። ከዚህ ቤተ እምነት ጋር ግንኙነት ያላቸው 5,200 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው መገኘታቸው ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ 457 ከሳራንግ ዤይል ቤተክርስትያን ጋር ይያያዛል ተብሏል። ከእነዚህ መካከል አስር ግለሰቦች ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዋና ከተማዋ ሶል በተደረገ መንግሥትን በሚቃወም ሰልፍ ላይ ተሳትፈው እንደነበር ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የደቡብ ኮርያ ባለሥልጣታናት ማንኛውም ቤተ እምነት የአምልኮ ስርዓቱን በቤተ እምነቶች ውስጥ እንዳያካሂድ ያገዱ ሲሆን የቫይረሱ ስርጭት ታይቶባቸዋል የተባሉ ቤተ እምነቶችን ምዕመናን፣ ራሳቸውን ለይተው እንዲቀመጡ እና ምርመራ እንዲያደርጉ የመለየት ስራ እየሰሩ ነው። "አሁን ያለው ስርጭትን መቆጣጠር ካልቻልን ቀውስ ውስጥ እየገባን ነው፣ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያደርጋል፣ ይህ ደግሞ ህክምና ስርዓታችን እንዲንኮታኮትና ከፍተኛ የሆነ የምጣኔ ሃብት ድቀት እንዲደርስ ያደርጋል" ብለዋል የኮሪያ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ድርጅት ዳይሬክተር ዢዮንግ ኢኡን ኬኦንግ። ከዛሬ ረብዑ ጀምሮም 12 ለአደጋ ተጋላጭ የተባሉ የንግድ ዘርፎች በዋና ከተማዋ ሶል፣ ኢንቺዮን እና በተጎራባች የጊዮንጊ ግዛት እንዲዘጉ ተወስኗል፤ ከእነዚህም መካከል ፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች፣ አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ሙዚየሞችም የተዘጉ ሲሆን በቤት ውስጥ ከ50 ሰው በላይ፣ ከቤት ውጪ ደግሞ ከ100 ሰው በላይ ሆኖ መሰብሰብ ታግዷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53831241
2health
ኮሮናቫይረስ፡ 33 ሚሊዮን ፓውንድ ያሰባሰቡት የ100 አመቱ ሽማግሌ በኮቪድ-19 ሞቱ
በእንግሊዝ ለጤና ባለሙያዎች ያላቸውን ክብር ለመቸር 33 ሚሊዮን ፓውንድ በማሰባሰብ ከፍተኛ ስም ያተረፉት ካፕቴን ቶም ሙር በመቶ አመታቸው በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አልፏል። 33 ሚሊዮን ፓውንድ ለአገሪቱ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት ወይም ኤንኤችኤስ ማሰባሰብ የቻሉት የ100 አመቱ የዕድሜ ባለፀጋ በባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ከመተንፈሻ እክል ጋር በተያያዘ ቤድፎርድ ወደተባለ ሆስፒታል ተወስደው ነበር። ልጃቸው፣ ሃና ኢንግራም ሙር በባለፉት ሳምንታት በሳንባ ምች ህመም ሲሰቃዩ እንደነበርና በዚህ ሳምንት በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ ተናግራለች። ግለሰቡ የ2ኛው የዓለም ጦርነት ተዋጊ ሲሆኑ ከቤታቸው ጓሮ በሚገኘው ሜዳ 100 ዙር በመሮጥም ነው የእርዳታ ገንዘብ ያሰባሰቡት። ይህንንም ያደረጉት ከመቶኛ አመት ልደታቸው በፊት ነው። ልጆቻቸው ሃና ኢንግራም ሙርና ሉሲ ቲየክሴራ እንዳሉት "ውድ አባታችን ካፕቴን ሰር ቶም ሙር መሞታቸውን በታላቅ ሃዘን ነው የምንናገረው" ብለዋል። በመጨረሻው ሰዓትም ከአባታቸው ጎን በመሆናቸው ትልቅ ክብር እንደነበር ገልፀዋል። "ለሰዓታት ያልህ ስለ ልጅነታችን፣ ስለ ውዷ እናታችን ስናወራ ነበር። ረዥም ሰዓት ሳቅን፣ አለቀስን። አባታችን በባለፈው አመት አስቦትና አልሞት የማያውቀው ነገር ተሳክቶለታል። "ብለዋል አክለውም "ምንም እንኳን ለአጭር ወቅት ቢሆን በብዙዎች ልቦና ዘንድ የማይረሳ ነገርን ጥሏል። ለኛ አስደናቂ አባት፣ አያት ነው፤ ሁልጊዜም ቢሆን በልባችን ይኖራል" በማለት ኃዘናቸውን አጋርተዋል። የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ለአባታቸው ያደረጉላቸውን እንክብካቤ አድንቀዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ 33 ሚሊዮን ፓውንድ ያሰባሰቡት የ100 አመቱ ሽማግሌ በኮቪድ-19 ሞቱ በእንግሊዝ ለጤና ባለሙያዎች ያላቸውን ክብር ለመቸር 33 ሚሊዮን ፓውንድ በማሰባሰብ ከፍተኛ ስም ያተረፉት ካፕቴን ቶም ሙር በመቶ አመታቸው በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አልፏል። 33 ሚሊዮን ፓውንድ ለአገሪቱ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት ወይም ኤንኤችኤስ ማሰባሰብ የቻሉት የ100 አመቱ የዕድሜ ባለፀጋ በባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ከመተንፈሻ እክል ጋር በተያያዘ ቤድፎርድ ወደተባለ ሆስፒታል ተወስደው ነበር። ልጃቸው፣ ሃና ኢንግራም ሙር በባለፉት ሳምንታት በሳንባ ምች ህመም ሲሰቃዩ እንደነበርና በዚህ ሳምንት በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ ተናግራለች። ግለሰቡ የ2ኛው የዓለም ጦርነት ተዋጊ ሲሆኑ ከቤታቸው ጓሮ በሚገኘው ሜዳ 100 ዙር በመሮጥም ነው የእርዳታ ገንዘብ ያሰባሰቡት። ይህንንም ያደረጉት ከመቶኛ አመት ልደታቸው በፊት ነው። ልጆቻቸው ሃና ኢንግራም ሙርና ሉሲ ቲየክሴራ እንዳሉት "ውድ አባታችን ካፕቴን ሰር ቶም ሙር መሞታቸውን በታላቅ ሃዘን ነው የምንናገረው" ብለዋል። በመጨረሻው ሰዓትም ከአባታቸው ጎን በመሆናቸው ትልቅ ክብር እንደነበር ገልፀዋል። "ለሰዓታት ያልህ ስለ ልጅነታችን፣ ስለ ውዷ እናታችን ስናወራ ነበር። ረዥም ሰዓት ሳቅን፣ አለቀስን። አባታችን በባለፈው አመት አስቦትና አልሞት የማያውቀው ነገር ተሳክቶለታል። "ብለዋል አክለውም "ምንም እንኳን ለአጭር ወቅት ቢሆን በብዙዎች ልቦና ዘንድ የማይረሳ ነገርን ጥሏል። ለኛ አስደናቂ አባት፣ አያት ነው፤ ሁልጊዜም ቢሆን በልባችን ይኖራል" በማለት ኃዘናቸውን አጋርተዋል። የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ለአባታቸው ያደረጉላቸውን እንክብካቤ አድንቀዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55909539
2health
ኖርዌይ ፡ በአንድ ዋሻ ውስጥ ሲዝናኑ የነበሩ ሰዎች በጭስ ታፍነው ሆስፒታል ገቡ
በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ውስጥ በሚገኝ በአንድ ከመሬት በታች ባለ ዋሻ ውስጥ ተሰባስበው እየተዝናኑ ከነበሩ ሰዎች መካከል ከ20 የሚበልጡት በካርበን ሞኖክሳይድ ጭስ ታፍነው በመመረዛቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ። ግለሰቦቹ ሊገኙ የቻሉት በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች በዋሻው ውስጥ ከነበሩት መካከል የተወሰኑት ራሳቸውን ስተው ወደ ጎዳና በመውጣት ወዲያ ወዲህ ሲሉ ካገኟቸው በኋላ ነው። ከዚህም በኋላ ሌሎቹ ጓደኞቻቸው በጭሱ ታፍነው ከዋሻው ውስጥ በመውጣታቸው አምቡላንስ ተጠርቶ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርጓል። ባለስልጣናቱ የፓርቲው ታዳሚዎችን ለመመረዝ ያበቁት ወደ ዋሻው ይዘው ከገቡት አነስተኛ ጄኔሬተር በሚወጣ ጭስ ምክንያት ነው ብለው ያምናሉ። በጭሱ የመመረዝ ጉዳት ካጋጠማቸው 25 ሰዎች መካከል ሁለቱ በዋሻው ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ለማውጣት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች ናቸው። ግለሰቦቹ አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተም "እድለኞች ናቸው፤ የሁሉም የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ ነው። በጤናቸው ላይ ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም" ሲሉ በኦስሎ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ዋና ሐኪም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ከ20 በላይ ሰዎች በጭስ በታፈኑበት በዚህ ዝግጅት ላይ 200 የሚደርሱ ሰዎች ታድመውበት እንደነበር የኦስሎ ፖሊስ አስታውቋል። በተጨማሪም ታምመው ወደ ሆስፒታል ከገቡት የፓርቲው ታዳሚዎች ውጪ ያሉት ማቅለሽለሽ፣ የራስ ምታት፣ ራስን የመሳት ስሜት ካጋጠማቸው ወደ ሐኪም ቤት እንዲሄዱ ፖሊስ መክሯል። ፖሊሶች በአደጋው ስፍራ ከመድረሳቸው በፊት ከዋሻው ወጥቶ የሄደ የዝግጅቱ ታዳሚ እንዳለው በስፍራው በነበረው የታፈነ አየር ምክንያት በተደጋጋሚ ወደ ውጪ እየወጣ አየር ሲወስድ ነበር። የኦስሎ ፖሊስ በዋሻው ውስጥ ስለተካሄደው ዝግጅት ቀድሞ ጥቆማ የደረሰው ቢሆንም በወቅቱ ለምን እርምጃ መውሰድ እንዳልቻለ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ኖርዌይ ፡ በአንድ ዋሻ ውስጥ ሲዝናኑ የነበሩ ሰዎች በጭስ ታፍነው ሆስፒታል ገቡ በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ውስጥ በሚገኝ በአንድ ከመሬት በታች ባለ ዋሻ ውስጥ ተሰባስበው እየተዝናኑ ከነበሩ ሰዎች መካከል ከ20 የሚበልጡት በካርበን ሞኖክሳይድ ጭስ ታፍነው በመመረዛቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ። ግለሰቦቹ ሊገኙ የቻሉት በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች በዋሻው ውስጥ ከነበሩት መካከል የተወሰኑት ራሳቸውን ስተው ወደ ጎዳና በመውጣት ወዲያ ወዲህ ሲሉ ካገኟቸው በኋላ ነው። ከዚህም በኋላ ሌሎቹ ጓደኞቻቸው በጭሱ ታፍነው ከዋሻው ውስጥ በመውጣታቸው አምቡላንስ ተጠርቶ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርጓል። ባለስልጣናቱ የፓርቲው ታዳሚዎችን ለመመረዝ ያበቁት ወደ ዋሻው ይዘው ከገቡት አነስተኛ ጄኔሬተር በሚወጣ ጭስ ምክንያት ነው ብለው ያምናሉ። በጭሱ የመመረዝ ጉዳት ካጋጠማቸው 25 ሰዎች መካከል ሁለቱ በዋሻው ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ለማውጣት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ፖሊሶች ናቸው። ግለሰቦቹ አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተም "እድለኞች ናቸው፤ የሁሉም የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ ነው። በጤናቸው ላይ ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም" ሲሉ በኦስሎ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ዋና ሐኪም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ከ20 በላይ ሰዎች በጭስ በታፈኑበት በዚህ ዝግጅት ላይ 200 የሚደርሱ ሰዎች ታድመውበት እንደነበር የኦስሎ ፖሊስ አስታውቋል። በተጨማሪም ታምመው ወደ ሆስፒታል ከገቡት የፓርቲው ታዳሚዎች ውጪ ያሉት ማቅለሽለሽ፣ የራስ ምታት፣ ራስን የመሳት ስሜት ካጋጠማቸው ወደ ሐኪም ቤት እንዲሄዱ ፖሊስ መክሯል። ፖሊሶች በአደጋው ስፍራ ከመድረሳቸው በፊት ከዋሻው ወጥቶ የሄደ የዝግጅቱ ታዳሚ እንዳለው በስፍራው በነበረው የታፈነ አየር ምክንያት በተደጋጋሚ ወደ ውጪ እየወጣ አየር ሲወስድ ነበር። የኦስሎ ፖሊስ በዋሻው ውስጥ ስለተካሄደው ዝግጅት ቀድሞ ጥቆማ የደረሰው ቢሆንም በወቅቱ ለምን እርምጃ መውሰድ እንዳልቻለ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53967065
0business
ከ20 ሺህ ብር በላይ የሚወጣበት የኢትዮጵያ ዘመናዊ የንቅሳት ገበያ
ሰውነታቸው ላይ ንቅሳት ለማሳረፍ ወደ ንቅሳት ቤቶች ጎራ ከሚሉ ሰዎች መካከል በፍቅር ወይም በትዳር የተጣመሩ ጥንዶች ይገኙበታል። "ጥንዶቹ ፍቅራቸውን ለመግለጽ ሴቷ የወንዱን፣ ወንዱ ደግሞ የሴቷን ስም አሊያም የስም መጀመሪያ ፊደላትን መነቀስ የተለመደ ሆኗል" ይላል የንቅሳት ባለሙያው (ታቱ አርቲስት) ሔኖክ ጥላሁን። ሆኖም በጥንዶቹ መካከል ንፋስ ገብቶ መራራቅ ሲመጣ "ለየብቻ ይመጡና ንቅሳቱን ቀይርልኝ" ብለው እንደሚጠይቁት ይናገራል። ይህንን በመሰሉ አጋጣሚዎች የተሞላውን የንቅሳት ሥራ፤ ሰዎች ሐሳባቸውን ለማንጸባረቅ ያውሉታል። ዮሴፍ ተስፍዬ ይባላል። 28 ሺህ ብር አውጥቶ በሁለቱም እጆቹ ከትከሻው እስከ መዳፉ አንጓ 'የውስጤን ሐሳብ ይገልጹልኛል' ያላቸውን የተለያዩ ምስሎችና ጽሁፎች ተነቅሷል። ለእሱ የደስታ ምንጭ የሆነው ንቅሳቱ በተመልካቾች ዘንድ ሁለት ዓይነት አስተያየት ይቀርብበታል። አንዱ "ምን ነካህ?" ሲሆን ሌላኛው ደግሞ "ያምራል" የሚል ነው ይላል። ነገር ግን በሚሠራበት አካባቢ ንቅሳቱ እንዳይታይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግም ይናገራል። ሳምራዊት ተስፋዬ እና ኤልኤዘር ሙሴም በተመሳሳይ መነሻ የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸውን ተነቅሰዋል። ለመሆኑ በአዲስ አበባ ምን አይነት ንቅሳቶች ይዘወተራሉ? ምን ያህል ገንዘብስ ይወጣባቸዋል? የንቅሳቶች ይዘት እና ምክንያት የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክ ጥላሁን ቀደም ሲል ሥዕሎችን ይስል እንደነበር ይናገራል። እንደ ባለሙያው ገለጻ ንቅሳትም አንድ የጥበብ ዘርፍ በመሆኑ 'ሄና ታቱ' የሚል ድርጅት በመክፈት ንቅሳትን መተዳዳሪያው ካደረገ ከስምንት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። ንቅሳት የሚፈልጉ ሰዎች ከተዘጋጀ የንቅሳት ዝርዝር ውስጥ መርጠው ወይም የፈለጉትን ማንኛውንም አይነት ምስል አሊያም ጹሁፍን ወደ ንቅሳት መቀየር ይቻላል ይላል። በብዛት ወደ እሱ የሚመጡ ሰዎች ሰውነታቸው ላይ እንዲያርፍ የሚርጡት ይዘት ሐይማኖታዊ መሆኑን ይናገራል። በተጨማሪም ጥንዶች ፍቅራቸውን ለመግለጽ ተመሳሳይ ንቅሳት ወይም አንዱ የሌላውን ስም ይነቀሳሉ። የእናታቸውን ወይም የአባታቸውን ምስል ወይም ስም የተነቀሱ ደንበኞች እንዳሉት የሚጠቅሰው ሔኖክ፤ በሌላ በኩል መስቀል፣ የቅዱሳን ሥዕሎችና መሰል ሐይማኖታዊ ይዘቶች በብዛት እንደሚዘወተሩ ያስረዳል። ብዙዎች ንቅሳትን "የሚወዱትን ነገር መግለጫና ማሳያ አድርገው ነው የሚያዩት" ሲል ይጠቅሳል። ሳምራዊት የግራ እጇ ከክንዷ በታች ያለው ክፍል ሙሉ በሙሉ በንቅሳት የተሸፈነ ነው። "ስለ ወደደኝ አዳነኝ" እና "Be Happy" የሚሉ ጽሁፎች፣ ሳቅን የሚገልጽ የስሜት ነጸብራቅ ምስል (emoji)፣ አበባ እንዲሁም ሌሎች ምስሎች አሉ። ደረቷ ላይ "blessed" የሚል ጽሁፍና አንገቷ ላይ ደግሞ መስቀል ተነቅሳለች። ኤልዜር የደረቱ አብዛኛው ክፍል ንቅሳት ያረፈበት ሲሆን፤ የነብርና ንስር ምስሎችን ነው የተነቀሰው። ዮሴፍ ደግሞ ሰዓት፣ አበባ፣ ኮምፓስና መሰል ምስሎችን በቀይና ጥቁር ቀለሞች በእጆቹ ላይ ተነቅሷል። ሳምራዊት ለሐይማኖቷ ያላትን ፍቅር ለመግለጽና ውስጧ ያለውን የተለያየ ሰሜት ለማንጸባረቅ እንደተነቀሰች ትገልጻለች። ዮሴፍ እና ኤልኤዘር ውስጣቸው የሚያምንበትና የሚወዱት ሐሳብ ሰውነታቸው ላይ እንዲታይ በማለም ነው አካላቸውን በንቅሳት የሸፈኑት። በተለይ ኤልኤዘር ለቤተሰቦቹ ያለውን ፍቅር ለመግለጽ መነቀሱን ተናግሯል። እነ ሳምራዊት በጠቀሷቸው ምክንያቶች ይነቀሱ እንጂ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጠባሳን ለመሸፈን ወይም ባህላዊ ንቅሳቶችን ወደ ዘመነኛ ለመቀየር ወደ ንቅሳት ቤቶች የሚያመሩ ሰዎች እንዳሉም ሔኖክ ይገልጻል። የንቅሳት ገበያ ኤልኤዘር ንቅሳቱን በተለያየ ጊዜ ማድረጉን ያስረዳል። ለዚህም እስከ 20 ሺህ ብር አውጥቷል። ሳምራዊት ደግሞ 15 ሺህ ብር በመክፈል ነው ንቅሳቷን ያሠራችው። ዝቅተኛው የንቅሳት ርዝመት አምስት ወይም ስድስት ሴንቲ ሜትር እንደሚረዝምና 500 ብር እንደሚያስወጣ ሔኖክ ይገልጻል። ንቅሳቱ ከፍ እያለ ሲሄድ ዋጋ እንደሚጨምር እንዲሁም ጀርባ ላይ የሚሠሩ ንቅሳቶች በአንድ ጊዜ እንደማያልቁና እስከ ሦስት ቀናት ሊፈጁ እንደሚችሉ ተናግሯል። ይህም እስከ 15 ሺህ ብር የሚወጣበት ነው። ታዲያ ይህ ሥራ ዋና የገቢ ምንጬ ነው የሚለው ሔኖክ "በየቀኑ ሥራ አለ" ሲል አስረድቷል። ንቅሳት ለመሥራት የሚውሉ መሣሪያዎች ከዘመኑ ጋር እየተጓዙ ነው የሚለው የንቅሳት ባለሙያው፤ ግብዓቶችን አገር ውስጥ ማግኘት ግን ፈታኝ መሆኑን እና የንቅሳት መርፌ ሳይቀር ከውጪ አገራት እንደሚገባ ይገልጻል። "ንቅሳት ላይ ከቴክኖሎጂው በላይ የአርቲስቱ ጉዳይ [የባለሙያው አቅም] ነው ትልቁ ነገር" ሲልም ጨምሯል። የተመልካቾች አስተያየት እና ልዩ ገጠመኞች ዮሴፍ ንቅሳቴን ሲያዩ "የሚያማትቡ አሉ" ይላል። ኤልኤዘር ደግሞ "አንዳንድ ሰው የሚያየኝ እንደ ዱርዬ ነው። ባንክ ስገባ አንዳንድ ሰዎች ቦርሳቸውን የሚደብቁበት ጊዜ አለ" ሲል ገልጾታል። "ሁሉም ሰው አንድ አይደለም። ወጣቶቹ ይወዱታል። 'በጣም ያምራል' ይላሉ። ሌላው ደግሞ 'ኔጌቲቭ' አስተያየት ነው የሚሰጠው። 'ለምን እንዲህ አደርግሽ?' 'በሐይማኖት አይፈቀድም' ይላሉ" ያለችው ደግሞ ሳምራዊት ናት። የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክም በሥራው ብዙ ነገሮች እንደሚገጥሙት ይገልጻል። ፍቅረኞች ወይም ባለትዳሮች ፍቅራቸውን 'ለማጠንከር' በማሰብ ለመነቀስ ወደኛ ይመጣሉ የሚለው ሔሄኖክ፤ ከተሠራላቸው በኋላ ግን ተመልሰው የሚመጡ እንዳሉ ጠቅሷል። "ይመጡና ይሄን ነገር አልፈለኩትም። የዚያን ጊዜ በደንብ አላሰብኩበትም። ይሄን ነገር ማጥፋት እፈልጋለሁ ይላሉ። ያው ማጥፋት ከባድ ስለሆነ በሌላ ዲዛይን ይሸፈናል።" በሌላ በኩል ፊታቸው ላይ ንቅሳት ለማሠራት መጥተው እድሜያቸው ትንሽ ከሆነ "በኋላ እንዳይጸጽታቸው" ብለን እንመክራለንም ብሏል። "አንዳንዴ ሰዎች ንቅሳተቱን ሳይጨርሱ የሚሄዱበት አጋጣሚ አለ - አመመኝ በሚል" ሲልም ተናግሯል። አንዱን አጋጣሚ ሲያስታውስ፤ አንድ ደንበኛው "የቅዱስ ሚካኤልን ምስል ጀርባው ላይ ለመነቀስ መረጠ" ይላል። እናም ንቅሳቱ ተጀመረ። "ሥዕሉ መልአኩ ሰይጣኑን ሲረግጥ የሚያሳየው ነው። እኛ ከሥር እየሠራን ነው ወደ ላይ የምንሄደው። ሰይጣኑን ወደ ማገባደድ ደርሰን ወደ ላይ እየወጣን ስንሄድ 'በቃ አልቻልኩም ይቅርብኝ' አለ። ለመጨረስ በተከታታይ ብደውልለትም አልመጣም። እስካሁን ሰይጣኑን ይዞ ነው የሚዞረው" ሲል ያስታውሳል። ንቅሳቱ ሲሠራ በሚፈጠረው ህመም ምክንያት ንቅሳት ጀምረው ከሚያቋርጡ በተቃራኒው የንቅሳቱ መሣሪያ በሚፈጥው መጠነኛ ህመም 'እንደሚደሰት' ዮሴፍ አስረድቷል። ኤልኤዘር ደግሞ "አንድ ጊዜ ፀበል ለጠመቅ ሄጄ ቄሱ አልጠምቅህም ብለውኝ ነበር [ንቅሳቱን አይተው]" ብሏል። በሌላ በኩል ዮሴፍ "ሰዎች እንደ ቁም ነገረኛ ስለማይቆጥሩኝ፤ ሥራ ቦታ 'ታቱ' እንዳለኝ የማያውቅ ብዙ ሰው አለ" ሲል ገልጿል። ሳምራዊት በመነቀሷ ከቤተሰቧ አሉታዊ አስተያየት እንዳልገጠማትና እንዲያውም ስትነቀስ 15 ሺህ ብሩን ቤተሰቧ እንደከፈለላት ስትናገር፤ ከዚህ በተቃራኒ ኤልኤዘርና ዮሴፍ ቤተሰቦቻቸው ብዙም በአወንታዊ መንገድ አልተቀበሏቸውም። ንቅሳት እና ጤና የቆዳና የአባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ሐኪሙ ዶክተር ድጋፌ ጸጋዬ "ዘመናዊም ይሁን ባህላዊ ንቅሳት ሹል በሆኑ ነገሮች እየወጉ ቀለምን ቆዳ ውስጥ በመጨመር ጌጦችን የመፍጠር ልምድ ነው ብለን ልንገልጸው እንችላለን" ሲሉ ያስረዳሉ። ታዲያ ይህ ልምድ ከጤና አኳያ ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮች አሉትም ብለዋል። እንደ ዶ/ር ድጋፌ ገለጻ፤ ንቅሳት ቋሚ ሲሆን ሰዎች ግን ቀድመው ለንቅሳት የተነሱበት ፍላጎትና ስሜት በጊዜ ብዛት ሊቀየር ይችላል። በዚህም ምክንያት የተነቀሱ ሰዎች ከ40 ዓመታቸው በኋላ የሚጸጸቱበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል። በሌላ በኩል "ንቅሳት ያለበት ሰው ደም እንዲሰጥ አይመከርም" ያሉት ሀኪሙ፤ ለዚህም ምክንያቱ የንቅሳት መሣሪያዎች ለተላላፊ በሽታ ስለሚያጋልጡ ነው ብለዋል። ንቅሳት የቆዳ መቆጣት [allergic reactions] ሊፈጥር እንደሚችል ዶ/ር ድጋፌ ጠቅሰዋል። "የሰውነት አለርጂው ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል። ከተነቀሱ ከሳምንታት ብሎም ከ10 ወይም ከ15 ዓመታት በኋላ የቆዳ መቆጣት፣ የማሳከክ ወይም የማበጥ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል" ብለዋል። ንቅሳት የሚደረግበት ስፍራና የመሣሪያው ንጽህና ካልተጠበቀ ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ሊዳርግም ይችላል። "ንቅሳት ያደረገ ሰው ኤምአርአይ የሚባለውን ምርመራ ማድረግ ቢፈልግ እንደ ንቅሳቱ አይነትና የቀለም አይነት ንቅሳቱ ባለት ቦታ ላይ የቃጠሎ ቁስል ሊያጋጥም ይችላል" ሲሉም ያክላሉ። ቋሚ ንቅሳት መጥፋት ይችላል? አዎ መጥፋት ይችላል። "አብዛኛውን ንቅሳት በሌዘር [በጨረር] ማሽን ማጥፋት የሚቻልበት ዕድል አለ" ሲሉ ገልጸዋል - ዶ/ር ድጋፌ። ሕክምናው የብርሃንን ኃይል ወደ ሙቀት በመቀየር የሚሠራ መሆኑን የሚስረዱት ሐኪሙ፤ ጨረሩ ቆዳው ውስጥ ያለውን ቀለም በመሰባበር በደም አማካይነት እንዲወገድ ያደርጋል ብለዋል። ሕክምናው ተከታታይ ሲሆን፤ ለዘመናዊ ንቅሳት ከ6 እስከ 10 ጊዜ ቢሰጥ "ከፍተኛ ለውጥ ሊመጣ የሚችልበት አጋጣሚ አለ" ብለዋል - ቆዳን ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ባይመልሰውም። ሕክምናው በእያንዳንዱ የክትትል ዙር እስከ 2500 ብር ሊያስወጣ እንደሚችል የሚገልጹት ሐኪሙ፤ ሰዎች ንቅሳት ከማሠራታቸው በፊት ደጋግመው እንዲያስቡበት መክረዋል።
ከ20 ሺህ ብር በላይ የሚወጣበት የኢትዮጵያ ዘመናዊ የንቅሳት ገበያ ሰውነታቸው ላይ ንቅሳት ለማሳረፍ ወደ ንቅሳት ቤቶች ጎራ ከሚሉ ሰዎች መካከል በፍቅር ወይም በትዳር የተጣመሩ ጥንዶች ይገኙበታል። "ጥንዶቹ ፍቅራቸውን ለመግለጽ ሴቷ የወንዱን፣ ወንዱ ደግሞ የሴቷን ስም አሊያም የስም መጀመሪያ ፊደላትን መነቀስ የተለመደ ሆኗል" ይላል የንቅሳት ባለሙያው (ታቱ አርቲስት) ሔኖክ ጥላሁን። ሆኖም በጥንዶቹ መካከል ንፋስ ገብቶ መራራቅ ሲመጣ "ለየብቻ ይመጡና ንቅሳቱን ቀይርልኝ" ብለው እንደሚጠይቁት ይናገራል። ይህንን በመሰሉ አጋጣሚዎች የተሞላውን የንቅሳት ሥራ፤ ሰዎች ሐሳባቸውን ለማንጸባረቅ ያውሉታል። ዮሴፍ ተስፍዬ ይባላል። 28 ሺህ ብር አውጥቶ በሁለቱም እጆቹ ከትከሻው እስከ መዳፉ አንጓ 'የውስጤን ሐሳብ ይገልጹልኛል' ያላቸውን የተለያዩ ምስሎችና ጽሁፎች ተነቅሷል። ለእሱ የደስታ ምንጭ የሆነው ንቅሳቱ በተመልካቾች ዘንድ ሁለት ዓይነት አስተያየት ይቀርብበታል። አንዱ "ምን ነካህ?" ሲሆን ሌላኛው ደግሞ "ያምራል" የሚል ነው ይላል። ነገር ግን በሚሠራበት አካባቢ ንቅሳቱ እንዳይታይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግም ይናገራል። ሳምራዊት ተስፋዬ እና ኤልኤዘር ሙሴም በተመሳሳይ መነሻ የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸውን ተነቅሰዋል። ለመሆኑ በአዲስ አበባ ምን አይነት ንቅሳቶች ይዘወተራሉ? ምን ያህል ገንዘብስ ይወጣባቸዋል? የንቅሳቶች ይዘት እና ምክንያት የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክ ጥላሁን ቀደም ሲል ሥዕሎችን ይስል እንደነበር ይናገራል። እንደ ባለሙያው ገለጻ ንቅሳትም አንድ የጥበብ ዘርፍ በመሆኑ 'ሄና ታቱ' የሚል ድርጅት በመክፈት ንቅሳትን መተዳዳሪያው ካደረገ ከስምንት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። ንቅሳት የሚፈልጉ ሰዎች ከተዘጋጀ የንቅሳት ዝርዝር ውስጥ መርጠው ወይም የፈለጉትን ማንኛውንም አይነት ምስል አሊያም ጹሁፍን ወደ ንቅሳት መቀየር ይቻላል ይላል። በብዛት ወደ እሱ የሚመጡ ሰዎች ሰውነታቸው ላይ እንዲያርፍ የሚርጡት ይዘት ሐይማኖታዊ መሆኑን ይናገራል። በተጨማሪም ጥንዶች ፍቅራቸውን ለመግለጽ ተመሳሳይ ንቅሳት ወይም አንዱ የሌላውን ስም ይነቀሳሉ። የእናታቸውን ወይም የአባታቸውን ምስል ወይም ስም የተነቀሱ ደንበኞች እንዳሉት የሚጠቅሰው ሔኖክ፤ በሌላ በኩል መስቀል፣ የቅዱሳን ሥዕሎችና መሰል ሐይማኖታዊ ይዘቶች በብዛት እንደሚዘወተሩ ያስረዳል። ብዙዎች ንቅሳትን "የሚወዱትን ነገር መግለጫና ማሳያ አድርገው ነው የሚያዩት" ሲል ይጠቅሳል። ሳምራዊት የግራ እጇ ከክንዷ በታች ያለው ክፍል ሙሉ በሙሉ በንቅሳት የተሸፈነ ነው። "ስለ ወደደኝ አዳነኝ" እና "Be Happy" የሚሉ ጽሁፎች፣ ሳቅን የሚገልጽ የስሜት ነጸብራቅ ምስል (emoji)፣ አበባ እንዲሁም ሌሎች ምስሎች አሉ። ደረቷ ላይ "blessed" የሚል ጽሁፍና አንገቷ ላይ ደግሞ መስቀል ተነቅሳለች። ኤልዜር የደረቱ አብዛኛው ክፍል ንቅሳት ያረፈበት ሲሆን፤ የነብርና ንስር ምስሎችን ነው የተነቀሰው። ዮሴፍ ደግሞ ሰዓት፣ አበባ፣ ኮምፓስና መሰል ምስሎችን በቀይና ጥቁር ቀለሞች በእጆቹ ላይ ተነቅሷል። ሳምራዊት ለሐይማኖቷ ያላትን ፍቅር ለመግለጽና ውስጧ ያለውን የተለያየ ሰሜት ለማንጸባረቅ እንደተነቀሰች ትገልጻለች። ዮሴፍ እና ኤልኤዘር ውስጣቸው የሚያምንበትና የሚወዱት ሐሳብ ሰውነታቸው ላይ እንዲታይ በማለም ነው አካላቸውን በንቅሳት የሸፈኑት። በተለይ ኤልኤዘር ለቤተሰቦቹ ያለውን ፍቅር ለመግለጽ መነቀሱን ተናግሯል። እነ ሳምራዊት በጠቀሷቸው ምክንያቶች ይነቀሱ እንጂ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጠባሳን ለመሸፈን ወይም ባህላዊ ንቅሳቶችን ወደ ዘመነኛ ለመቀየር ወደ ንቅሳት ቤቶች የሚያመሩ ሰዎች እንዳሉም ሔኖክ ይገልጻል። የንቅሳት ገበያ ኤልኤዘር ንቅሳቱን በተለያየ ጊዜ ማድረጉን ያስረዳል። ለዚህም እስከ 20 ሺህ ብር አውጥቷል። ሳምራዊት ደግሞ 15 ሺህ ብር በመክፈል ነው ንቅሳቷን ያሠራችው። ዝቅተኛው የንቅሳት ርዝመት አምስት ወይም ስድስት ሴንቲ ሜትር እንደሚረዝምና 500 ብር እንደሚያስወጣ ሔኖክ ይገልጻል። ንቅሳቱ ከፍ እያለ ሲሄድ ዋጋ እንደሚጨምር እንዲሁም ጀርባ ላይ የሚሠሩ ንቅሳቶች በአንድ ጊዜ እንደማያልቁና እስከ ሦስት ቀናት ሊፈጁ እንደሚችሉ ተናግሯል። ይህም እስከ 15 ሺህ ብር የሚወጣበት ነው። ታዲያ ይህ ሥራ ዋና የገቢ ምንጬ ነው የሚለው ሔኖክ "በየቀኑ ሥራ አለ" ሲል አስረድቷል። ንቅሳት ለመሥራት የሚውሉ መሣሪያዎች ከዘመኑ ጋር እየተጓዙ ነው የሚለው የንቅሳት ባለሙያው፤ ግብዓቶችን አገር ውስጥ ማግኘት ግን ፈታኝ መሆኑን እና የንቅሳት መርፌ ሳይቀር ከውጪ አገራት እንደሚገባ ይገልጻል። "ንቅሳት ላይ ከቴክኖሎጂው በላይ የአርቲስቱ ጉዳይ [የባለሙያው አቅም] ነው ትልቁ ነገር" ሲልም ጨምሯል። የተመልካቾች አስተያየት እና ልዩ ገጠመኞች ዮሴፍ ንቅሳቴን ሲያዩ "የሚያማትቡ አሉ" ይላል። ኤልኤዘር ደግሞ "አንዳንድ ሰው የሚያየኝ እንደ ዱርዬ ነው። ባንክ ስገባ አንዳንድ ሰዎች ቦርሳቸውን የሚደብቁበት ጊዜ አለ" ሲል ገልጾታል። "ሁሉም ሰው አንድ አይደለም። ወጣቶቹ ይወዱታል። 'በጣም ያምራል' ይላሉ። ሌላው ደግሞ 'ኔጌቲቭ' አስተያየት ነው የሚሰጠው። 'ለምን እንዲህ አደርግሽ?' 'በሐይማኖት አይፈቀድም' ይላሉ" ያለችው ደግሞ ሳምራዊት ናት። የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክም በሥራው ብዙ ነገሮች እንደሚገጥሙት ይገልጻል። ፍቅረኞች ወይም ባለትዳሮች ፍቅራቸውን 'ለማጠንከር' በማሰብ ለመነቀስ ወደኛ ይመጣሉ የሚለው ሔሄኖክ፤ ከተሠራላቸው በኋላ ግን ተመልሰው የሚመጡ እንዳሉ ጠቅሷል። "ይመጡና ይሄን ነገር አልፈለኩትም። የዚያን ጊዜ በደንብ አላሰብኩበትም። ይሄን ነገር ማጥፋት እፈልጋለሁ ይላሉ። ያው ማጥፋት ከባድ ስለሆነ በሌላ ዲዛይን ይሸፈናል።" በሌላ በኩል ፊታቸው ላይ ንቅሳት ለማሠራት መጥተው እድሜያቸው ትንሽ ከሆነ "በኋላ እንዳይጸጽታቸው" ብለን እንመክራለንም ብሏል። "አንዳንዴ ሰዎች ንቅሳተቱን ሳይጨርሱ የሚሄዱበት አጋጣሚ አለ - አመመኝ በሚል" ሲልም ተናግሯል። አንዱን አጋጣሚ ሲያስታውስ፤ አንድ ደንበኛው "የቅዱስ ሚካኤልን ምስል ጀርባው ላይ ለመነቀስ መረጠ" ይላል። እናም ንቅሳቱ ተጀመረ። "ሥዕሉ መልአኩ ሰይጣኑን ሲረግጥ የሚያሳየው ነው። እኛ ከሥር እየሠራን ነው ወደ ላይ የምንሄደው። ሰይጣኑን ወደ ማገባደድ ደርሰን ወደ ላይ እየወጣን ስንሄድ 'በቃ አልቻልኩም ይቅርብኝ' አለ። ለመጨረስ በተከታታይ ብደውልለትም አልመጣም። እስካሁን ሰይጣኑን ይዞ ነው የሚዞረው" ሲል ያስታውሳል። ንቅሳቱ ሲሠራ በሚፈጠረው ህመም ምክንያት ንቅሳት ጀምረው ከሚያቋርጡ በተቃራኒው የንቅሳቱ መሣሪያ በሚፈጥው መጠነኛ ህመም 'እንደሚደሰት' ዮሴፍ አስረድቷል። ኤልኤዘር ደግሞ "አንድ ጊዜ ፀበል ለጠመቅ ሄጄ ቄሱ አልጠምቅህም ብለውኝ ነበር [ንቅሳቱን አይተው]" ብሏል። በሌላ በኩል ዮሴፍ "ሰዎች እንደ ቁም ነገረኛ ስለማይቆጥሩኝ፤ ሥራ ቦታ 'ታቱ' እንዳለኝ የማያውቅ ብዙ ሰው አለ" ሲል ገልጿል። ሳምራዊት በመነቀሷ ከቤተሰቧ አሉታዊ አስተያየት እንዳልገጠማትና እንዲያውም ስትነቀስ 15 ሺህ ብሩን ቤተሰቧ እንደከፈለላት ስትናገር፤ ከዚህ በተቃራኒ ኤልኤዘርና ዮሴፍ ቤተሰቦቻቸው ብዙም በአወንታዊ መንገድ አልተቀበሏቸውም። ንቅሳት እና ጤና የቆዳና የአባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ሐኪሙ ዶክተር ድጋፌ ጸጋዬ "ዘመናዊም ይሁን ባህላዊ ንቅሳት ሹል በሆኑ ነገሮች እየወጉ ቀለምን ቆዳ ውስጥ በመጨመር ጌጦችን የመፍጠር ልምድ ነው ብለን ልንገልጸው እንችላለን" ሲሉ ያስረዳሉ። ታዲያ ይህ ልምድ ከጤና አኳያ ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮች አሉትም ብለዋል። እንደ ዶ/ር ድጋፌ ገለጻ፤ ንቅሳት ቋሚ ሲሆን ሰዎች ግን ቀድመው ለንቅሳት የተነሱበት ፍላጎትና ስሜት በጊዜ ብዛት ሊቀየር ይችላል። በዚህም ምክንያት የተነቀሱ ሰዎች ከ40 ዓመታቸው በኋላ የሚጸጸቱበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል። በሌላ በኩል "ንቅሳት ያለበት ሰው ደም እንዲሰጥ አይመከርም" ያሉት ሀኪሙ፤ ለዚህም ምክንያቱ የንቅሳት መሣሪያዎች ለተላላፊ በሽታ ስለሚያጋልጡ ነው ብለዋል። ንቅሳት የቆዳ መቆጣት [allergic reactions] ሊፈጥር እንደሚችል ዶ/ር ድጋፌ ጠቅሰዋል። "የሰውነት አለርጂው ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል። ከተነቀሱ ከሳምንታት ብሎም ከ10 ወይም ከ15 ዓመታት በኋላ የቆዳ መቆጣት፣ የማሳከክ ወይም የማበጥ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል" ብለዋል። ንቅሳት የሚደረግበት ስፍራና የመሣሪያው ንጽህና ካልተጠበቀ ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ሊዳርግም ይችላል። "ንቅሳት ያደረገ ሰው ኤምአርአይ የሚባለውን ምርመራ ማድረግ ቢፈልግ እንደ ንቅሳቱ አይነትና የቀለም አይነት ንቅሳቱ ባለት ቦታ ላይ የቃጠሎ ቁስል ሊያጋጥም ይችላል" ሲሉም ያክላሉ። ቋሚ ንቅሳት መጥፋት ይችላል? አዎ መጥፋት ይችላል። "አብዛኛውን ንቅሳት በሌዘር [በጨረር] ማሽን ማጥፋት የሚቻልበት ዕድል አለ" ሲሉ ገልጸዋል - ዶ/ር ድጋፌ። ሕክምናው የብርሃንን ኃይል ወደ ሙቀት በመቀየር የሚሠራ መሆኑን የሚስረዱት ሐኪሙ፤ ጨረሩ ቆዳው ውስጥ ያለውን ቀለም በመሰባበር በደም አማካይነት እንዲወገድ ያደርጋል ብለዋል። ሕክምናው ተከታታይ ሲሆን፤ ለዘመናዊ ንቅሳት ከ6 እስከ 10 ጊዜ ቢሰጥ "ከፍተኛ ለውጥ ሊመጣ የሚችልበት አጋጣሚ አለ" ብለዋል - ቆዳን ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ባይመልሰውም። ሕክምናው በእያንዳንዱ የክትትል ዙር እስከ 2500 ብር ሊያስወጣ እንደሚችል የሚገልጹት ሐኪሙ፤ ሰዎች ንቅሳት ከማሠራታቸው በፊት ደጋግመው እንዲያስቡበት መክረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57390536
0business
በቱኒዝያ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፎካካሪ የፓርቲ አባላት ፕሬዚዳንት ሳዒድን ለመቃወም አደባባይ ወጡ
በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በቱኒዚያ ዋና ከተማ ጎዳናዎች ላይ የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ለመቃወም አደባባይ  ወጥተዋል። እርስ በእርስ ጭምር የሚቃረኑ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የተቃውሞ ሰልፎቹን በመዲናዋ ቱኒዝ አካሂደዋል። የተቀናቃኝ ፓርቲዎቹ ከ2011 ህዝባዊ አመጽ በኋላ የተገኘውን ዲሞክራሲያዊ ጉዞ እየቀለበሱ ነው ያሏቸውን ካይስ ሰኢድን "አምባገነን" ሲሉ አውግዘዋል። የምግብ እና የነዳጅ እጥረት ለፈጠረው የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስም ተጠያቂነት አለባቸው ብለዋል። የፕሬዝዳንት ሰኢድ ተቺዎች መፈንቅለ መንግሥት ከማድረግ ባለፈ ቱኒዚያን ወደ በአንድ ሰው የሚመራ ፍጹም አምባገነናዊነት  ለመመለስ ሞክረዋል ሲሉ ይከሷቸዋል። በአውሮፓውያኑ 2021 ጠቅላይ ሚኒስትሩን አሰናብተው ፓርላማውን ካገዱ በኋላ፣ ከአንድ ዓመት በኋላ ፕሬዝዳንቱ የአንድ ሰው አገዛዛቸውን የሚያፀድቀውን ህገ-መንግስት እንዲያልፍ ቢሞክሩም በተቃዋሚ ፓርቲዎች ድምጽ ውድቅ ተደርጓል። አዲሱ ህገ መንግስት በአውሮፓውያኑ 2011 ከተካሄደው የአረብ አብዮት በኋላ የተረቀቀውንና የቱኒዚያ የቀድሞ አምባገነን መሪውን ዚነ አል-አቢዲን ቤን አሊን ከስልጣን ያስወገደውን ተክቷል። ይህ የሃገሪቱ መሪ ሙሉ የሥራ አስፈጻሚውን እንዲቆጣጠር፣ የሠራዊቱ የበላይ አዛዥ እንዲሆን እና ያለ ፓርላማው እውቅና መንግስትን የመሾም አቅም ሰጥቷቸዋል። ፕሬዚዳንት ሰኢድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ውድቀትን ለመስበር አስፈላጊ ነበር ብለው ይሞግታሉ። ማሻሻያዎቹም የ2011 አብዮትን መንፈስ ያማከሉ እና ወደፊትም የተሻለ እንደሚሆን ተናግረዋል። ደጋፊዎቹ ውሳኔውን በደስታ ተቀብለዋል። ሃገሪቱ ብልሹ አሠራርን እና ሙስናን ለመቅረፍ ጠንካራ መሪ ትፈልጋለች በማለት ነው የሚደግፉት። ቅዳሜ ዕለት በማእከላዊ ቱኒዝ ሰልፈኞች “ውረድ፣ ውረድ” ሲሉ ተደምጠዋል። የተቃውሞ ሰልፉን ከጠሩት መካከል አንዱ የሆነው ናሽናል ሳልቬሽን ፎሮንት የተባለው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የቱኒዚያን ፓርላማ ከፍተኛ ወንበር የያዘውን ኤናህዳን የያዘ ነው። ​​ሰኢድ  ፓርላማውን በኋላ ላይ በትነዋል። የቱኒዚያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኤናሃዳ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አሊ ላራይድ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ሰልፉ “በካይስ ሰኢድ የስልጣን ዘመን ላይ ያለው ቁጣ” የሚያሳይ ነው። “ስልጣን እንዲለቁ እየነገርናቸው ነው።“ አክለውም ተስፋ መቁረጥ፣ ድህነት እና ሥራ አጥነት እያደገ መሆኑን ጠቅሰው ሰኢድ በስልጣን ላይ ከቆዩ "ቱኒዚያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አይኖራትም” ብለዋል። ናሽናል ሳልቬሽን ፍሮንትስልጣኑ የተገደበ አዲስ አዲስ ፓርላማ ለመምረጥ በታህሳስ ወር በሚካሄደው ምርጫ እንደማይሳተፍ አስታውቋል። የኢናሃዳ ርዕዮተ ዓለም ጋር ተቀናቃኝ የሆነው የፍሪ ዴስቶሪያን ፓርቲም በተመሳሳይ ቅዳሜ በዋና ከተማዋ የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅቷል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች በመስከረም ወር 9.1 በመቶ የደረሰውን የዋጋ ግሽበት ምክንያት የውሃ ወጪን መጨመሩን ለማስመልከት ባዶ ጀሪካኖችን ይዘው ነበር። በ60ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ጡረተኛው ሰኢድ “ምንም እየሠራ አይደለም፣ ነገሮችም እየባሱ ነው”  ብለዋል። በኤንናዳ የሚመራውን ሰላማዊ ሰልፍ ወደ 1 ሺህ 500 የሚጠጉ ሰዎች የተቀላቀሉ ሲሆን ወደ 1 ሺህ 000 የሚጠጉት ደግሞ በፒዲኤል ተቃውሞ ላይ ተገኝተዋል ሲል የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኤኤፍፒተናግሯል። በአውሮፓውያኑ 2011 የተካሄደው የቱኒዚያ አብዮት ከአረብ አብዮት ብቸኛው እና ስኬታማው እንደሆነ ቢነገርም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መረጋጋትን አላመጣም።
በቱኒዝያ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፎካካሪ የፓርቲ አባላት ፕሬዚዳንት ሳዒድን ለመቃወም አደባባይ ወጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በቱኒዚያ ዋና ከተማ ጎዳናዎች ላይ የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ለመቃወም አደባባይ  ወጥተዋል። እርስ በእርስ ጭምር የሚቃረኑ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የተቃውሞ ሰልፎቹን በመዲናዋ ቱኒዝ አካሂደዋል። የተቀናቃኝ ፓርቲዎቹ ከ2011 ህዝባዊ አመጽ በኋላ የተገኘውን ዲሞክራሲያዊ ጉዞ እየቀለበሱ ነው ያሏቸውን ካይስ ሰኢድን "አምባገነን" ሲሉ አውግዘዋል። የምግብ እና የነዳጅ እጥረት ለፈጠረው የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስም ተጠያቂነት አለባቸው ብለዋል። የፕሬዝዳንት ሰኢድ ተቺዎች መፈንቅለ መንግሥት ከማድረግ ባለፈ ቱኒዚያን ወደ በአንድ ሰው የሚመራ ፍጹም አምባገነናዊነት  ለመመለስ ሞክረዋል ሲሉ ይከሷቸዋል። በአውሮፓውያኑ 2021 ጠቅላይ ሚኒስትሩን አሰናብተው ፓርላማውን ካገዱ በኋላ፣ ከአንድ ዓመት በኋላ ፕሬዝዳንቱ የአንድ ሰው አገዛዛቸውን የሚያፀድቀውን ህገ-መንግስት እንዲያልፍ ቢሞክሩም በተቃዋሚ ፓርቲዎች ድምጽ ውድቅ ተደርጓል። አዲሱ ህገ መንግስት በአውሮፓውያኑ 2011 ከተካሄደው የአረብ አብዮት በኋላ የተረቀቀውንና የቱኒዚያ የቀድሞ አምባገነን መሪውን ዚነ አል-አቢዲን ቤን አሊን ከስልጣን ያስወገደውን ተክቷል። ይህ የሃገሪቱ መሪ ሙሉ የሥራ አስፈጻሚውን እንዲቆጣጠር፣ የሠራዊቱ የበላይ አዛዥ እንዲሆን እና ያለ ፓርላማው እውቅና መንግስትን የመሾም አቅም ሰጥቷቸዋል። ፕሬዚዳንት ሰኢድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ውድቀትን ለመስበር አስፈላጊ ነበር ብለው ይሞግታሉ። ማሻሻያዎቹም የ2011 አብዮትን መንፈስ ያማከሉ እና ወደፊትም የተሻለ እንደሚሆን ተናግረዋል። ደጋፊዎቹ ውሳኔውን በደስታ ተቀብለዋል። ሃገሪቱ ብልሹ አሠራርን እና ሙስናን ለመቅረፍ ጠንካራ መሪ ትፈልጋለች በማለት ነው የሚደግፉት። ቅዳሜ ዕለት በማእከላዊ ቱኒዝ ሰልፈኞች “ውረድ፣ ውረድ” ሲሉ ተደምጠዋል። የተቃውሞ ሰልፉን ከጠሩት መካከል አንዱ የሆነው ናሽናል ሳልቬሽን ፎሮንት የተባለው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የቱኒዚያን ፓርላማ ከፍተኛ ወንበር የያዘውን ኤናህዳን የያዘ ነው። ​​ሰኢድ  ፓርላማውን በኋላ ላይ በትነዋል። የቱኒዚያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኤናሃዳ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አሊ ላራይድ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ሰልፉ “በካይስ ሰኢድ የስልጣን ዘመን ላይ ያለው ቁጣ” የሚያሳይ ነው። “ስልጣን እንዲለቁ እየነገርናቸው ነው።“ አክለውም ተስፋ መቁረጥ፣ ድህነት እና ሥራ አጥነት እያደገ መሆኑን ጠቅሰው ሰኢድ በስልጣን ላይ ከቆዩ "ቱኒዚያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አይኖራትም” ብለዋል። ናሽናል ሳልቬሽን ፍሮንትስልጣኑ የተገደበ አዲስ አዲስ ፓርላማ ለመምረጥ በታህሳስ ወር በሚካሄደው ምርጫ እንደማይሳተፍ አስታውቋል። የኢናሃዳ ርዕዮተ ዓለም ጋር ተቀናቃኝ የሆነው የፍሪ ዴስቶሪያን ፓርቲም በተመሳሳይ ቅዳሜ በዋና ከተማዋ የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጅቷል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች በመስከረም ወር 9.1 በመቶ የደረሰውን የዋጋ ግሽበት ምክንያት የውሃ ወጪን መጨመሩን ለማስመልከት ባዶ ጀሪካኖችን ይዘው ነበር። በ60ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ጡረተኛው ሰኢድ “ምንም እየሠራ አይደለም፣ ነገሮችም እየባሱ ነው”  ብለዋል። በኤንናዳ የሚመራውን ሰላማዊ ሰልፍ ወደ 1 ሺህ 500 የሚጠጉ ሰዎች የተቀላቀሉ ሲሆን ወደ 1 ሺህ 000 የሚጠጉት ደግሞ በፒዲኤል ተቃውሞ ላይ ተገኝተዋል ሲል የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኤኤፍፒተናግሯል። በአውሮፓውያኑ 2011 የተካሄደው የቱኒዚያ አብዮት ከአረብ አብዮት ብቸኛው እና ስኬታማው እንደሆነ ቢነገርም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መረጋጋትን አላመጣም።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1jj288gqvo
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ስለ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እስከ አሁን የምናውቃቸው 10 ነጥቦች
ኮቪድ-19 ክትባት ተገኘለት እፎይ መባል በጀመረ ገና በሳምንቱ ከወደ ብሪታኒያ መጥፎ ዜና ተሰምቷል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ አዲስ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች መገኘት ነው ዜናው፡፡ በፈረንጆች ገና ይህ ያልተጠበቀ ዜና መሰማቱ ለጊዜው አውሮጳን እያመሳት ነው፡፡ ከብሪታኒያ የሚመጡ አውሮፕላኖች ላይ እግድ እያወጡ ያሉት የአውሮጳ አገራት ድንበራቸውን ጠርቅመው እየዘጉት ነው፡፡ 1ኛ፡- በብሪታኒያ በተለይም በሎንደንና አካባቢው እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የተህዋሲው ናሙና ተገኝቷል፡፡ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን በታመሙ ሰዎች ላይ በብዛት የሚታየው የቫይረስ ዓይነትም ይኸው ዝርያ መሆኑ ድንጋጤን ፈጥሯል፡፡ 2ኛ፡- ይህ የቫይረስ ዝርያ ሌሎች የተህዋሲ ዝርያዎችን በፍጥነት እየተካ ቦታውን እየያዘ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ 3ኛ፡- ራሱን የሚያባዛበት መንገድ ለየቅል መሆኑ ምናልባት ለቁጥጥር ያስቸግር ይሆን የሚል ስጋትን ጨምሯል፡፡ ከመተንፈሻ አካል ውጭ ያሉ ሴሎችንም ራሱን እየለወጠ የማጥቃት አቅም ሊኖረው ይችል ይhoን የሚል ስጋትም አለ፡፡ 4ኛ፡- ለመጀመርያ ጊዜ ይህ የተህዋሲ ዝርያ የተገኘው በመስከረም ወር ነበር፡፡ በጥቅምት ወር ሎንዶን አካባቢ በኮቪድ ከተያዙት ሲሶዎቹ የዚህ ተህዋሲ መልክ ተገኘባቸው፡፡ በታኅሣሥ ወር ደግሞ 75 ከመቶዎቹ ታማሚዎችን የለከፈው ይህ ልዩ ተህዋሲ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ 5ኛ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ ይህ ተህዋሲ እስከዛሬ ከነበረው ቫይረስ ጋር ሲወዳደር የመዛመት ዕደሉ በ70 ከመቶ የፈጠነ ነው ብለዋል፡፡ 6ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በጊዜ ሂደት ራሱን ቀይሮ ይሁን ወይም ከሌላ ቦታ መጥቶ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። 7ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በመላው ብሪታኒያ የተሰራጨ ቢሆንም አሁን ክምችቱ በብዛት የሚኘው በለንደንና አካባቢው ነው፡፡ ከለንደን በተጨማሪ በደቡብ ምሥራቅና በምሥራቅ ኢንግላንድም እንዲሁ በስፋት ተመዝግቧል፡፡ 8ኛ፡- ኔክስትስትሬይን የተሀዋሲ ዝርያዎችን የዘረ መል ኮድ የሚመዘግብ ድርጅት ሲሆን፣ ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ከብሪታኒያ ወደ ዴንማርክና አውስትራሊያ መዛመቱን ተናግሯል፡፡ ኔዘርላንድና ጣሊያንም ይህ አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ አገራቸው መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡ 9ኛ፡- ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ቅንጣት በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል የተባለ ሲሆን በኋላ ላይ የወጡ መረጃዎች ግን ከዚህ ብሪታኒያ ተገኘ ከተባለው ተህዋሲ ጋር የዝርያ ተመሳሳይነት የላቸውም ብለዋል፡፡ 10ኛ፡- ተህዋሲው ራሱን ቆርጦ እየቀጠለና እያባዛ ሊያመልጥ ቢችልም አሁን ወደ ገበያ እየገቡ ያሉ ክትባቶች ግን ማንነቱን ያጠፉታል፣ ፈውስም ይሆናል ተብሎ በስፋት ታምኗል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ እስከዛሬ ሌሎች ዝርያዎች ኖረውት ያውቃሉ? አዎ! ዛሬ በተለያየ ዓለም የምናገኘው የቫይረስ ዝርያ ቅንጣት ቻይና ዉሃን ከተማ ከተገኘው ዝርያ ጋር አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ አሁን በብዙ የአውሮጳ አገሮች የሚገኘው D614G የሚባል የተህዋሲ ዝርያ ዓይነት ነው። ተህዋሲው ራሱን እየቀየረ ሊመጣ ይችላል፡፡ ምናልባት መነሻው ሊሆን የሚችለው ደካማ የመከላከል አቅም ካለው በሽተኛ ራሱን ቀይሮ የተነሳ ተህዋሲ ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ታማሚ ተህዋሲውን ማሸነፍ ሲሳነው ሰውነቱ የተህዋሲው መራቢያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ እስከአሁን በዚህ ረገድ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ገና በደንብ መጠናት ይኖርበታል፡፡ ለጊዜው የሚታወቀው በከፍተኛ ፍጥነት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ብቻ ነው፡፡ ያም ሆኖ ብዙ ሰዎችን ማዳረስ ከቻለ ብዙ ሰዎች አልጋ ይይዛሉ፡፡ ይህ ደግሞ በተዘዋዋሪ ሞትን ሊጨምር ይችላል፡፡ መቶ በመቶ ባይሆንም አሁን የሚገመተው ክትባቶቹ ለዚህ ተህዋሲም ፈውስ እንደሆኑ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው አሁን ተሳኩ የተባሉት ክትባቶች የተህዋሲውን መላ አካሉንና ባህሪውን ሁሉ እንዲያጠቁ የተዘጋጁ ስለሆኑ ተህዋሲው ራሱን እያባዛ ራሱን ሊቀያይር ቢሞክርም እንኳ ከክትባቶቹ ያመልጣል ማለት ዘበት ነው ይላሉ ተመራማሪዎች፡፡
ኮሮናቫይረስ፡ ስለ አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እስከ አሁን የምናውቃቸው 10 ነጥቦች ኮቪድ-19 ክትባት ተገኘለት እፎይ መባል በጀመረ ገና በሳምንቱ ከወደ ብሪታኒያ መጥፎ ዜና ተሰምቷል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ አዲስ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች መገኘት ነው ዜናው፡፡ በፈረንጆች ገና ይህ ያልተጠበቀ ዜና መሰማቱ ለጊዜው አውሮጳን እያመሳት ነው፡፡ ከብሪታኒያ የሚመጡ አውሮፕላኖች ላይ እግድ እያወጡ ያሉት የአውሮጳ አገራት ድንበራቸውን ጠርቅመው እየዘጉት ነው፡፡ 1ኛ፡- በብሪታኒያ በተለይም በሎንደንና አካባቢው እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የተህዋሲው ናሙና ተገኝቷል፡፡ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን በታመሙ ሰዎች ላይ በብዛት የሚታየው የቫይረስ ዓይነትም ይኸው ዝርያ መሆኑ ድንጋጤን ፈጥሯል፡፡ 2ኛ፡- ይህ የቫይረስ ዝርያ ሌሎች የተህዋሲ ዝርያዎችን በፍጥነት እየተካ ቦታውን እየያዘ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ 3ኛ፡- ራሱን የሚያባዛበት መንገድ ለየቅል መሆኑ ምናልባት ለቁጥጥር ያስቸግር ይሆን የሚል ስጋትን ጨምሯል፡፡ ከመተንፈሻ አካል ውጭ ያሉ ሴሎችንም ራሱን እየለወጠ የማጥቃት አቅም ሊኖረው ይችል ይhoን የሚል ስጋትም አለ፡፡ 4ኛ፡- ለመጀመርያ ጊዜ ይህ የተህዋሲ ዝርያ የተገኘው በመስከረም ወር ነበር፡፡ በጥቅምት ወር ሎንዶን አካባቢ በኮቪድ ከተያዙት ሲሶዎቹ የዚህ ተህዋሲ መልክ ተገኘባቸው፡፡ በታኅሣሥ ወር ደግሞ 75 ከመቶዎቹ ታማሚዎችን የለከፈው ይህ ልዩ ተህዋሲ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ 5ኛ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ ይህ ተህዋሲ እስከዛሬ ከነበረው ቫይረስ ጋር ሲወዳደር የመዛመት ዕደሉ በ70 ከመቶ የፈጠነ ነው ብለዋል፡፡ 6ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በጊዜ ሂደት ራሱን ቀይሮ ይሁን ወይም ከሌላ ቦታ መጥቶ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። 7ኛ፡- አዲሱ የተህዋሲ ዝርያ በመላው ብሪታኒያ የተሰራጨ ቢሆንም አሁን ክምችቱ በብዛት የሚኘው በለንደንና አካባቢው ነው፡፡ ከለንደን በተጨማሪ በደቡብ ምሥራቅና በምሥራቅ ኢንግላንድም እንዲሁ በስፋት ተመዝግቧል፡፡ 8ኛ፡- ኔክስትስትሬይን የተሀዋሲ ዝርያዎችን የዘረ መል ኮድ የሚመዘግብ ድርጅት ሲሆን፣ ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ከብሪታኒያ ወደ ዴንማርክና አውስትራሊያ መዛመቱን ተናግሯል፡፡ ኔዘርላንድና ጣሊያንም ይህ አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ አገራቸው መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡ 9ኛ፡- ይህ ልዩ የተህዋሲ ዝርያ ቅንጣት በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል የተባለ ሲሆን በኋላ ላይ የወጡ መረጃዎች ግን ከዚህ ብሪታኒያ ተገኘ ከተባለው ተህዋሲ ጋር የዝርያ ተመሳሳይነት የላቸውም ብለዋል፡፡ 10ኛ፡- ተህዋሲው ራሱን ቆርጦ እየቀጠለና እያባዛ ሊያመልጥ ቢችልም አሁን ወደ ገበያ እየገቡ ያሉ ክትባቶች ግን ማንነቱን ያጠፉታል፣ ፈውስም ይሆናል ተብሎ በስፋት ታምኗል፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ እስከዛሬ ሌሎች ዝርያዎች ኖረውት ያውቃሉ? አዎ! ዛሬ በተለያየ ዓለም የምናገኘው የቫይረስ ዝርያ ቅንጣት ቻይና ዉሃን ከተማ ከተገኘው ዝርያ ጋር አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ አሁን በብዙ የአውሮጳ አገሮች የሚገኘው D614G የሚባል የተህዋሲ ዝርያ ዓይነት ነው። ተህዋሲው ራሱን እየቀየረ ሊመጣ ይችላል፡፡ ምናልባት መነሻው ሊሆን የሚችለው ደካማ የመከላከል አቅም ካለው በሽተኛ ራሱን ቀይሮ የተነሳ ተህዋሲ ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ታማሚ ተህዋሲውን ማሸነፍ ሲሳነው ሰውነቱ የተህዋሲው መራቢያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ እስከአሁን በዚህ ረገድ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ገና በደንብ መጠናት ይኖርበታል፡፡ ለጊዜው የሚታወቀው በከፍተኛ ፍጥነት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ብቻ ነው፡፡ ያም ሆኖ ብዙ ሰዎችን ማዳረስ ከቻለ ብዙ ሰዎች አልጋ ይይዛሉ፡፡ ይህ ደግሞ በተዘዋዋሪ ሞትን ሊጨምር ይችላል፡፡ መቶ በመቶ ባይሆንም አሁን የሚገመተው ክትባቶቹ ለዚህ ተህዋሲም ፈውስ እንደሆኑ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው አሁን ተሳኩ የተባሉት ክትባቶች የተህዋሲውን መላ አካሉንና ባህሪውን ሁሉ እንዲያጠቁ የተዘጋጁ ስለሆኑ ተህዋሲው ራሱን እያባዛ ራሱን ሊቀያይር ቢሞክርም እንኳ ከክትባቶቹ ያመልጣል ማለት ዘበት ነው ይላሉ ተመራማሪዎች፡፡
https://www.bbc.com/amharic/55391884
5sports
ከእነዚህ 7 ‘ውድ’ ተጨዋቾች ዝውውራቸውን የሚያጠናቅቁ ይኖሩ ይሆን?
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ ዝነኛ ሊጎች የወድድር ዘመናቸውን መጀመራቸውን ተከትሎ ክለቦች በየትኛው የሜዳ ክፍል ራሳቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው እየለዩ ነው። ቢቢሲ ስፖርት ወደ ሌሎች ክለቦች ሊዘዋወሩ የሚችሉ “ውድ” ያላቸውን 7 ተጫዋቾችና ያሏቸውን አማራጮች ተመልክቷል። ሮናልዶ ክለቡን መልቀቅ መፈለጉ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ተጫዋቹ ከአንዴም ሁለቴ ልቀቁኝ ሲል ተናግሯል። ሮናልዶ ክለቡን የሚለቀው በቻምፒየንስ ሊግ መጫወት ስለምፈልግ ነው ይበል እንጂ በቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ የሆነ አንድም ቡድን በሮናልዶ ላይ ፍላጎት አላሳየም። የ37 ዓመቱ ተጫዋች የሚጠይቀው ከፍተኛ ክፍያ ለክለቦች የሚቀመስ አልሆነም። የውድድር ዓመቱን አሳፋሪ በተባሉ ሽንፈቶች ለጀመረው ዩናይትድ ሮናልዶ በመልበሻ ክፍል ውስጥ አሉታዊ ተጽእኖ ፈጣሪ ነው የሚል ሪፖርት ዘ አትሌቲክ ይዞ ወጥቷል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ሮናልዶ አይሸጥም ይበሉ እንጂ ክለቡ ትናንት ማክሰኞ ነሐሴ 10/2014 ዓ.ም. በሮናልዶ ላይ የነበረውን አቋም በመቀየር ክለቡን እንዲለቅ እንደሚፈቅድ ተገልጿል። ይህን ተከትሎ የሮናልዶ ወኪል ተጫዋቹን ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ለማዘዋወር ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፉት ወራት የዲ ዮንግ ስም ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል። ዩናይትድ ለዲ ዮንግ 56 ሚሊዮን ፓዎንድ ለመክፈል ከባርሴሎና ጋር ከተስማማ በርካታ ሳምንታት ቢያልፉም የዝውውር ስምምነቱ ግን ፈቀቅ አላለም። የኔዘርላንዱ አማካይ ኑ ካምፕን የመልቀቅ ፍላጎት ባይኖረውም ባርሴሎና ግን ከገባበት የፋይናንስ ቀውስ እፎይታ ለማግኘት ዲ ዮንግን ሊሸጥ ይችላል። ይህ የዝውውር ስምምነት ተፈጻሚ እንዳይሆን ማነቆ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ ዲ ዮንግ በባርሴሎና ሳይከፍለው የቆየው ገንዘብ አንዱ መሆኑ ሪፖርት ተደርጓል። አሁን ላይ ደግሞ ቼልሲ ዲ ዮንግን ለመወሰድ ጥረት ጀምሯል። ቼልሲ በዚህ የዝውውር መስኮት ከ150 ሚሊዮን ፓዎንድ በላይ ወጪ በማድረግ በርካታ ተጫዋቾችን ሰብስቧል። ክለቡን በቅርቡ የተረከቡት አሜሪካዊው ባለሃብት አሁንም በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ለንደን ከማምጣት የቦዘኑ አይመስልም። ሮበርት ሎዋንዶውስኪ ወደ ባርሳ ማምራቱን ተከትሎ ኦባሚያንግ ወደ ቼልሲ ሊዘዋወር ይችላል። ቼልሲ ለቀድሞ የአርሰናል አምበል ኦባ እስከ 25 ሚሊዮን ፓዎንድ ሊጠየቅ ይችላል። ባርሳን ሊሰናበት የሚችለው ሌላኛው ተጫዋች ሜምፊስ ዴፓይ ነው። ባርሴሎና ራፊንሃን ከሊድስ ዩናይትድ ካዘዋወረ በኋላ፤ ዴፓይ በነጻ ዝውውር ወዳሻው ክለብ መሄድ እንደሚችል ክለቡ አሳውቆታል። የ28 ዓመቱ ሆላንዳዊ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ የክንፍ ተጫዋች ወደ ጣሊያኑ ጁቬንቱስ ሊያመራ ይችላል። አሁንም ቼልሲ ነው። ቼልሲ የሌስተሩን ተከላካይ በውድ ዋጋ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ለመውስደ የሚያመነታ አይመስልም። የመሃል ተከላካዩን ኩሊባሊን ከናፖሊ እንዲሁም የቀኝ ክንፍ ተመላላሹን ማርከ ኩከሪያልን ከብራይተን ያዘዋወሩት ሰማያዎዎቹ ለሌላ ተከላካይ ከፍተኛ ገንዘብ ለመክፈል ዝግጁ ይመስላሉ። ቼልሲ ለ21 ዓመቱ ፈረንሲያዊ 80 ሚሊዮን ፓዎንድ ሊያወጣ ይችላል የሚሉ ሪፖርቶች ወጥተዋል። ኤቨርተን የፊት መስመር አጥቂያቸውን ሪቻርልሰንን በቶተነሃም ተነጥቀዋል። ደካማ አቋም እያሳየ ባለው ኤቨርተን ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለው አንቶኒ ጎርደንም ወደ ቼልሲ ሊያመራ ይችላል። ቼልሲ ለአንቶኒ ጎርደን ያቀረበው የ40 እና የ45 ሚሊዮን ፓዎንድ የዝውውር ጥያቄዎች በኤቨርተን ውድቅ ተደርጎበታል። ቼልሲ ግን ዳግም ተጫዋቹን ለመውሰድ ሌላ ጥረት እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት በውሰት በቆየበት ሳውዛምፕተን 9 ጎሎችን በማስቆጠር ጥሩ ግዜን ያሳለፈው አጥቂው ብሮጃ የብዙ ክለቦችን ትኩረት ስቧል። አልባናዊው አጥቂ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ከተመለሰ በኋላ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ የመካተት እድልን አላገኘም። ይህም ወደ ሌላ ክለብ እንዲያማትር ሊያደርገው ይችላል የሚሉ ግምቶች አሉ። ዌስት ሃም፣ ኤቨርተን እና ኒው ካስትል የ20 ዓመቱን አጥቂ የመውሰድ ጽኑ ፍላጎት ካላቸው ክለቦች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
ከእነዚህ 7 ‘ውድ’ ተጨዋቾች ዝውውራቸውን የሚያጠናቅቁ ይኖሩ ይሆን? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ ዝነኛ ሊጎች የወድድር ዘመናቸውን መጀመራቸውን ተከትሎ ክለቦች በየትኛው የሜዳ ክፍል ራሳቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው እየለዩ ነው። ቢቢሲ ስፖርት ወደ ሌሎች ክለቦች ሊዘዋወሩ የሚችሉ “ውድ” ያላቸውን 7 ተጫዋቾችና ያሏቸውን አማራጮች ተመልክቷል። ሮናልዶ ክለቡን መልቀቅ መፈለጉ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ተጫዋቹ ከአንዴም ሁለቴ ልቀቁኝ ሲል ተናግሯል። ሮናልዶ ክለቡን የሚለቀው በቻምፒየንስ ሊግ መጫወት ስለምፈልግ ነው ይበል እንጂ በቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ የሆነ አንድም ቡድን በሮናልዶ ላይ ፍላጎት አላሳየም። የ37 ዓመቱ ተጫዋች የሚጠይቀው ከፍተኛ ክፍያ ለክለቦች የሚቀመስ አልሆነም። የውድድር ዓመቱን አሳፋሪ በተባሉ ሽንፈቶች ለጀመረው ዩናይትድ ሮናልዶ በመልበሻ ክፍል ውስጥ አሉታዊ ተጽእኖ ፈጣሪ ነው የሚል ሪፖርት ዘ አትሌቲክ ይዞ ወጥቷል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ሮናልዶ አይሸጥም ይበሉ እንጂ ክለቡ ትናንት ማክሰኞ ነሐሴ 10/2014 ዓ.ም. በሮናልዶ ላይ የነበረውን አቋም በመቀየር ክለቡን እንዲለቅ እንደሚፈቅድ ተገልጿል። ይህን ተከትሎ የሮናልዶ ወኪል ተጫዋቹን ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ለማዘዋወር ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፉት ወራት የዲ ዮንግ ስም ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል። ዩናይትድ ለዲ ዮንግ 56 ሚሊዮን ፓዎንድ ለመክፈል ከባርሴሎና ጋር ከተስማማ በርካታ ሳምንታት ቢያልፉም የዝውውር ስምምነቱ ግን ፈቀቅ አላለም። የኔዘርላንዱ አማካይ ኑ ካምፕን የመልቀቅ ፍላጎት ባይኖረውም ባርሴሎና ግን ከገባበት የፋይናንስ ቀውስ እፎይታ ለማግኘት ዲ ዮንግን ሊሸጥ ይችላል። ይህ የዝውውር ስምምነት ተፈጻሚ እንዳይሆን ማነቆ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ ዲ ዮንግ በባርሴሎና ሳይከፍለው የቆየው ገንዘብ አንዱ መሆኑ ሪፖርት ተደርጓል። አሁን ላይ ደግሞ ቼልሲ ዲ ዮንግን ለመወሰድ ጥረት ጀምሯል። ቼልሲ በዚህ የዝውውር መስኮት ከ150 ሚሊዮን ፓዎንድ በላይ ወጪ በማድረግ በርካታ ተጫዋቾችን ሰብስቧል። ክለቡን በቅርቡ የተረከቡት አሜሪካዊው ባለሃብት አሁንም በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ለንደን ከማምጣት የቦዘኑ አይመስልም። ሮበርት ሎዋንዶውስኪ ወደ ባርሳ ማምራቱን ተከትሎ ኦባሚያንግ ወደ ቼልሲ ሊዘዋወር ይችላል። ቼልሲ ለቀድሞ የአርሰናል አምበል ኦባ እስከ 25 ሚሊዮን ፓዎንድ ሊጠየቅ ይችላል። ባርሳን ሊሰናበት የሚችለው ሌላኛው ተጫዋች ሜምፊስ ዴፓይ ነው። ባርሴሎና ራፊንሃን ከሊድስ ዩናይትድ ካዘዋወረ በኋላ፤ ዴፓይ በነጻ ዝውውር ወዳሻው ክለብ መሄድ እንደሚችል ክለቡ አሳውቆታል። የ28 ዓመቱ ሆላንዳዊ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ የክንፍ ተጫዋች ወደ ጣሊያኑ ጁቬንቱስ ሊያመራ ይችላል። አሁንም ቼልሲ ነው። ቼልሲ የሌስተሩን ተከላካይ በውድ ዋጋ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ለመውስደ የሚያመነታ አይመስልም። የመሃል ተከላካዩን ኩሊባሊን ከናፖሊ እንዲሁም የቀኝ ክንፍ ተመላላሹን ማርከ ኩከሪያልን ከብራይተን ያዘዋወሩት ሰማያዎዎቹ ለሌላ ተከላካይ ከፍተኛ ገንዘብ ለመክፈል ዝግጁ ይመስላሉ። ቼልሲ ለ21 ዓመቱ ፈረንሲያዊ 80 ሚሊዮን ፓዎንድ ሊያወጣ ይችላል የሚሉ ሪፖርቶች ወጥተዋል። ኤቨርተን የፊት መስመር አጥቂያቸውን ሪቻርልሰንን በቶተነሃም ተነጥቀዋል። ደካማ አቋም እያሳየ ባለው ኤቨርተን ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለው አንቶኒ ጎርደንም ወደ ቼልሲ ሊያመራ ይችላል። ቼልሲ ለአንቶኒ ጎርደን ያቀረበው የ40 እና የ45 ሚሊዮን ፓዎንድ የዝውውር ጥያቄዎች በኤቨርተን ውድቅ ተደርጎበታል። ቼልሲ ግን ዳግም ተጫዋቹን ለመውሰድ ሌላ ጥረት እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት በውሰት በቆየበት ሳውዛምፕተን 9 ጎሎችን በማስቆጠር ጥሩ ግዜን ያሳለፈው አጥቂው ብሮጃ የብዙ ክለቦችን ትኩረት ስቧል። አልባናዊው አጥቂ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ከተመለሰ በኋላ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ የመካተት እድልን አላገኘም። ይህም ወደ ሌላ ክለብ እንዲያማትር ሊያደርገው ይችላል የሚሉ ግምቶች አሉ። ዌስት ሃም፣ ኤቨርተን እና ኒው ካስትል የ20 ዓመቱን አጥቂ የመውሰድ ጽኑ ፍላጎት ካላቸው ክለቦች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c51vzkg0ng0o
5sports
ለወራት በሩሲያ ቁጥጥር ስር የምትገኘው አሜሪካዊቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች በምን ሁኔታ ነው ያለችው?
በሚቀጥለው ወር አሜሪካ የሴቶች የቅርጫት ኳስ ውድድር ሲጀመር በሊጉ ውስጥ ደምቀው መውጣት ከቻሉት ኮከቦች መካከል አንደኛዋ አትኖርም። የፊኒክስ ሜርኩሪ ተጨዋቿ ብሪትኒ ግራይነር ካሳለፍነው የካቲት ወር ጀምሮ ሩሲያ ውስጥ ተይዛ የምትገኝ ሲሆን ዋይት ሀውስ እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምንም መረጃ መስጠት አልቻለም። የ31 ዓመቷ ብሪትኒ ገሪነር ሩሲያ ውስጥ ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ እስር ቤት እንደምትገኝ ይታመናል። ሩሲያ በምትገባበት ወቅት የአየር ማረፊያው ሰራተኞችች ባደረጉባት ምርመራ በቦርሳዋ ውስጥ የእጸ ፋርስ ዘይት ተገኝቷል የሚል ጥርጣሬም አለ። የተባለው ነገር እውነት ሆኖ ከተገኘና ብሪትኒ ግራይነር ጥፋተኛ የምትባል ከሆነ እስከ 10 ዓመት የሚደርስ እስር እንደሚጠብቃት ተገልጿል። ብሪትኒ ግራይነር በዓለማችን ምርጧ ሴት የቅርጫት ኳስ እንደሆነች በርካቶች ይስማማሉ። በቅርጫት ኳስ ሕይወቷም የኮሌጅ ቻምፒየንሺፕ፣ የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ውድድር፣ ዩሮሊግ እንዲሁም የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለች ድንቅ ስፖርተኛ ነች። ከአውሮፓውያኑ 2015 ጀምሮ ደግሞ የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ሊግ ለእረፍት ሲቋረጥ ወደ ሩሲያ በመሄድ ለአንድ ቡድን ትጫወታለች። ምንም እንኳን በርካቶች ብሪትኒ ግራይነር ዓለማችን ካየቻቸው ምርጥ የቅርጫት ኳስ ኮከቦች መካከል አንዷ እንደሆነች ቢስማሙም አሁን ላይ ላይ ግን ስላለችበት ሁኔታ ምንም አለመታወቁ ጥቂት የማይባሉ አሜሪካውያንን አስቆጥቷል። በሩሲያ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ከዋለች ሁለት ወር የሞላት አሜሪካዊቷ ስፖርተኛ ቤተሰቦችም ሆነ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት እና የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ሊግ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት አስተያየት አለመስጠትን መርጠዋል። ባሳለፍነው ወር የሞስኮ ፍርድ ቤት እንዳስታወቀው የብሪትኒ ግራይነርን ጉዳይ ለመከታተል ሲባል እስከ ግንቦት አጋማሽ ድረስ እንድትቆይ መወሰኑን አስታውቋል። የዋይት ሀውስ ፕረስ ሰክረተሪዋ ጄን ሳኪ ሰⶉ ዕለት በጉዳዩ ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ብዙም መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን ''በሌላ አገር በእስር ላይ ስለሚገኙ አሜሪካውያን ማውራት ብዙም ጠቃሚ አይደለም'' በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። ''ምናልባት ዜጋችንን ለማስመለስ የምናደርገውን ጥረት ሊያደናቅፈው ይችላል'' ብለዋል። '' በሩሲያ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሁሉም አሜሪካውያንን ቀጣይነት ባለው እና ጊዜውን በጠበቀ መልኩ መጎብኘት እንድንችል በተደጋጋሚ እየጣርን ነው። የብሪትኒ ጉዳይንም በተመለከተ በቅርበት እየተከታተልነው ነው'' ሲሉም አክለዋል። ብሪትኒ ገራይነር በዘንድሮው የቅርጫት ኳስ ሊግ ብትሳተፍ ኖሮ ለስምነተኛ ተከታታይ ዓመቷ ይሆነ የነበረ ሲሆን በሊጉም ከፍተኛ ድምቀትን ትፈጥር እንደነበር አድናቂዎቿ እና የቡድን አጋሮቿ ገልጸዋል። ልክ እንደ ብሪትኒ ሁሉ ሌሎች የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ሊጎች ውስጥ የሚሳተፉ ስፖርተኞች ሊጉ ሲዘጋ ወደ ሌሎች አገራት በመሄድ ይጫወታሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ተጨማሪ ገቢን ለማግኘት ነው። ለምሳሌ ሩሲያ አሜሪካ ከሚከፈላቸው አምስት እጥፍ ትከፍላለች።
ለወራት በሩሲያ ቁጥጥር ስር የምትገኘው አሜሪካዊቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች በምን ሁኔታ ነው ያለችው? በሚቀጥለው ወር አሜሪካ የሴቶች የቅርጫት ኳስ ውድድር ሲጀመር በሊጉ ውስጥ ደምቀው መውጣት ከቻሉት ኮከቦች መካከል አንደኛዋ አትኖርም። የፊኒክስ ሜርኩሪ ተጨዋቿ ብሪትኒ ግራይነር ካሳለፍነው የካቲት ወር ጀምሮ ሩሲያ ውስጥ ተይዛ የምትገኝ ሲሆን ዋይት ሀውስ እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምንም መረጃ መስጠት አልቻለም። የ31 ዓመቷ ብሪትኒ ገሪነር ሩሲያ ውስጥ ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ እስር ቤት እንደምትገኝ ይታመናል። ሩሲያ በምትገባበት ወቅት የአየር ማረፊያው ሰራተኞችች ባደረጉባት ምርመራ በቦርሳዋ ውስጥ የእጸ ፋርስ ዘይት ተገኝቷል የሚል ጥርጣሬም አለ። የተባለው ነገር እውነት ሆኖ ከተገኘና ብሪትኒ ግራይነር ጥፋተኛ የምትባል ከሆነ እስከ 10 ዓመት የሚደርስ እስር እንደሚጠብቃት ተገልጿል። ብሪትኒ ግራይነር በዓለማችን ምርጧ ሴት የቅርጫት ኳስ እንደሆነች በርካቶች ይስማማሉ። በቅርጫት ኳስ ሕይወቷም የኮሌጅ ቻምፒየንሺፕ፣ የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ውድድር፣ ዩሮሊግ እንዲሁም የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለች ድንቅ ስፖርተኛ ነች። ከአውሮፓውያኑ 2015 ጀምሮ ደግሞ የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ሊግ ለእረፍት ሲቋረጥ ወደ ሩሲያ በመሄድ ለአንድ ቡድን ትጫወታለች። ምንም እንኳን በርካቶች ብሪትኒ ግራይነር ዓለማችን ካየቻቸው ምርጥ የቅርጫት ኳስ ኮከቦች መካከል አንዷ እንደሆነች ቢስማሙም አሁን ላይ ላይ ግን ስላለችበት ሁኔታ ምንም አለመታወቁ ጥቂት የማይባሉ አሜሪካውያንን አስቆጥቷል። በሩሲያ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ከዋለች ሁለት ወር የሞላት አሜሪካዊቷ ስፖርተኛ ቤተሰቦችም ሆነ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት እና የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ሊግ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት አስተያየት አለመስጠትን መርጠዋል። ባሳለፍነው ወር የሞስኮ ፍርድ ቤት እንዳስታወቀው የብሪትኒ ግራይነርን ጉዳይ ለመከታተል ሲባል እስከ ግንቦት አጋማሽ ድረስ እንድትቆይ መወሰኑን አስታውቋል። የዋይት ሀውስ ፕረስ ሰክረተሪዋ ጄን ሳኪ ሰⶉ ዕለት በጉዳዩ ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ብዙም መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን ''በሌላ አገር በእስር ላይ ስለሚገኙ አሜሪካውያን ማውራት ብዙም ጠቃሚ አይደለም'' በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። ''ምናልባት ዜጋችንን ለማስመለስ የምናደርገውን ጥረት ሊያደናቅፈው ይችላል'' ብለዋል። '' በሩሲያ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሁሉም አሜሪካውያንን ቀጣይነት ባለው እና ጊዜውን በጠበቀ መልኩ መጎብኘት እንድንችል በተደጋጋሚ እየጣርን ነው። የብሪትኒ ጉዳይንም በተመለከተ በቅርበት እየተከታተልነው ነው'' ሲሉም አክለዋል። ብሪትኒ ገራይነር በዘንድሮው የቅርጫት ኳስ ሊግ ብትሳተፍ ኖሮ ለስምነተኛ ተከታታይ ዓመቷ ይሆነ የነበረ ሲሆን በሊጉም ከፍተኛ ድምቀትን ትፈጥር እንደነበር አድናቂዎቿ እና የቡድን አጋሮቿ ገልጸዋል። ልክ እንደ ብሪትኒ ሁሉ ሌሎች የአሜሪካ የሴቶች ቅርጫት ኳስ ሊጎች ውስጥ የሚሳተፉ ስፖርተኞች ሊጉ ሲዘጋ ወደ ሌሎች አገራት በመሄድ ይጫወታሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ተጨማሪ ገቢን ለማግኘት ነው። ለምሳሌ ሩሲያ አሜሪካ ከሚከፈላቸው አምስት እጥፍ ትከፍላለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-61058593
5sports
የሴቶች ዓለም ዋንጫ፡ ሴት እግር ኳሰኞች ስንት ይከፈላቸዋል? ዓለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ሃገራትስ?
የሴቶች እግር ኳስ ከጊዜ ጊዜ እያደገ የመጣ ይመስላል፤ ትኩረት መሳብም ጀምሯል። የዘንድሮውን የዓለም የሴቶች ዓለም ዋንጫ ጨዋታ 1 ቢሊዮን ተመልካቾች ይታደሙታል የሚል ግምት አለ። የሉሲዎቹ አምበል የሆነችው ሎዛ አበራ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር የሴቶች ክፍያ እዚህ ግባ የማይባል ነው ትላለች። በዓለም አቀፍ ደረጃስ? የባለፈው ዓለም ዋንጫ አሸናፊ የአሜሪካ አጥዊ የሆነችው ሆፕ ሶሎ የሴቶች እና የወንዶች ክፍያ ልዩነት ፊፋ ውስጥ ያለውን 'የወንድ የበላይነት' ያሳያል ስትል ትወቅሳለች። እስቲ ክፍያውን በቁጥር ከፋፍለን እንመልከተው። • እግር ኳስ ተጫዋቹ ወንድወሰን ዮሐንስ እንዴት ተገደለ? ፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የሴቶች የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ አሸናፊ የምትሆነው ብሔራዊ ቡድን 4 ሚሊዮን ዶላር [115 ሚሊዮን ብር ገደማ] ታገኛለች። ከባለፈው ዓለም ዋንጫ ክፍያ እጥፍ ማለት ነው። እያንዳንዳቸው ተሳታፊ ቡድኖች ደግሞ ከ750 ሺህ ዶላር [22 ሚሊዮን ብር ገደማ] ጀምሮ በነብስ ወከፍ ይቀበላሉ። ከሽልማት ወጪው በተጨማሪ ለዝግጅት በሚል እያንዳንዷ ቡድን 800 ሺህ ዶላር ከፊፋ ትቀበላለች። በጠቅላላው ፊፋ ለዘንድሮው ዓለም ዋንጫ 30 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል። ሩስያ አዘጋጅታ ፈረንሳይ በወሰደችው የ2018ቱ የወንዶች ዓለም ዋንጫ ፊፋ ለሽልማት ብሎ ያዘጋጀው ጠቅላላ ገንዘብ 400 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ነው፤ ከሴቶቹ ከአስር እጥፍ በላይ ማለት ነው። ለዝግጅት ተብሎ ለእያንዳንዱ ቡድን በነብስ ወከፍ የተሰጠው ደግሞ 1̋ሚሊዮን ዶላር ነው፤ ከሴቶቹ እጥፍ በላይ ማለት ነው እንግዲህ። አጀብ! የሚያስብል ሆኖ እንዳገኙት እንጠራጠርም። የወንዶቹ ክፍያ ከሴቶቹ በልጦ የመገኘቱ ጉዳይ ከሚያመጡት ገቢ ጋር መገናኘቱ ነው ብለው የሚከራከሩ አልጠፉም። ቢሆንም በፊፋ ሕግ መሠረት ከሴቶች እግር ኳስ የሚገኘው ገንዘብ ለሴቶች እግር ኳስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ወጪዎች የሚውል ነው። ፊፋ ለሃገራት የሚከፍለው ገንዘብ የተጨዋቾች ኪስ ሳይሆን ወደ ፌዴሬሽን ካዝና የሚገባ ነው። የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ድርሻ ቆንጠር አድርጎ ለተጨዋቾች መስጠትና የቀረውን ደግሞ ሌሎች መስኮች ላይ በተን በተን ማድረግ ይሆናል። ታድያ በፌዴሬሽኖች እና በእግር ኳስ ተጨዋቾች ማሕበር መካከል የሚደረግ ድርድር አለ። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ የአውስትራሊያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የትኛውንም ገንዘብ በሽልማት መልክ ሲያገኝ ተጨዋቾች 30 በመቶ እንዲያገኙ ተደራድሯል። ወደ ክለቦች ስንወርድ ደግሞ የተሻለ ክፍያ የሚያገኙት [ከወንዶች ሲነፃፀር ቁጥሩ እጅግ አናሳ ቢሆንም] በምዕራብ አውሮፓ የሚጫወቱቱ ናቸው። ገንዘቡ ደግሞ ከ1 ሺህ እስከ 2 ሺህ ዩሮ ይደርሳል፤ ጨዋታ ባለ ቁጥር ደግሞ የላብ መተኪያ የሚሆን ከ50-100 ዩሮ ያገኛሉ። እርግጥ ነው ስም ያላቸው ተጨዋቾች ከዚህ የተሻለ ይከፈላቸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ክፍያው ምን ያህል ዝቅ ያለ እንደሆነ መገመት አያዳግትም። ፊፋ የሴቶች ዓለም የዋንጫ አሸናፊ ሽልማትን ከባለፈው ዓለም ዋንጫ እጥፍ ማድረጉ አንድ እርምጃ ወደፊት ነው የሚሉ ባይጠፉም 'አሁንም ትንሽ ነው' ብለው የሚከራከሩ አልጠፉም። በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ፊፋ የሴቶች እግር ኳስ ላይ ከ400-500 ሚሊዮን ዶላር አፈሳለሁ ይላል። የአሜሪካ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የሃገሪቱን እግር ኳስ ማሕበር እኩል ክፍያን እውን አላደረገም በሚል ከሶታል። የአውስትራሊያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማሕበር ፊፋ የሴቶች እና የወንዶች የዓለም ዋንጫ ሽልማት እኩል መሆን አለበት ሲል እየሞገተ ነው። 2016 ላይ የአፍሪካ ዋንጫን የበላችው የናይጄሪያ ሴቶች ቡድን በክፍያ ጉዳይ ከፌዴሬሽን ጋር በነረው እሰጥ-አገባ አድማ አድርጋ ነበር። የኒው ዚላንድ ወንዶች እና ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት ከ2018 ጀምሮ ማንኛውም ዓይነት ክፍያ እኩል እንዲያገኙ የሚያደርግ ውል ደርሰዋል፤ በኖርዌይም እንዲሁ። ምንም እንኳ ልዩነቱ አሁንም የሰማይና ምድርን ያክል [የሎዛ አበራን አገላለፅ ለመጠቀም] ቢሆንም ከጊዜ ጊዜ ግን ለውጥ መምጣቱ አይካድም።
የሴቶች ዓለም ዋንጫ፡ ሴት እግር ኳሰኞች ስንት ይከፈላቸዋል? ዓለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ሃገራትስ? የሴቶች እግር ኳስ ከጊዜ ጊዜ እያደገ የመጣ ይመስላል፤ ትኩረት መሳብም ጀምሯል። የዘንድሮውን የዓለም የሴቶች ዓለም ዋንጫ ጨዋታ 1 ቢሊዮን ተመልካቾች ይታደሙታል የሚል ግምት አለ። የሉሲዎቹ አምበል የሆነችው ሎዛ አበራ ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር የሴቶች ክፍያ እዚህ ግባ የማይባል ነው ትላለች። በዓለም አቀፍ ደረጃስ? የባለፈው ዓለም ዋንጫ አሸናፊ የአሜሪካ አጥዊ የሆነችው ሆፕ ሶሎ የሴቶች እና የወንዶች ክፍያ ልዩነት ፊፋ ውስጥ ያለውን 'የወንድ የበላይነት' ያሳያል ስትል ትወቅሳለች። እስቲ ክፍያውን በቁጥር ከፋፍለን እንመልከተው። • እግር ኳስ ተጫዋቹ ወንድወሰን ዮሐንስ እንዴት ተገደለ? ፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የሴቶች የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ አሸናፊ የምትሆነው ብሔራዊ ቡድን 4 ሚሊዮን ዶላር [115 ሚሊዮን ብር ገደማ] ታገኛለች። ከባለፈው ዓለም ዋንጫ ክፍያ እጥፍ ማለት ነው። እያንዳንዳቸው ተሳታፊ ቡድኖች ደግሞ ከ750 ሺህ ዶላር [22 ሚሊዮን ብር ገደማ] ጀምሮ በነብስ ወከፍ ይቀበላሉ። ከሽልማት ወጪው በተጨማሪ ለዝግጅት በሚል እያንዳንዷ ቡድን 800 ሺህ ዶላር ከፊፋ ትቀበላለች። በጠቅላላው ፊፋ ለዘንድሮው ዓለም ዋንጫ 30 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል። ሩስያ አዘጋጅታ ፈረንሳይ በወሰደችው የ2018ቱ የወንዶች ዓለም ዋንጫ ፊፋ ለሽልማት ብሎ ያዘጋጀው ጠቅላላ ገንዘብ 400 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ነው፤ ከሴቶቹ ከአስር እጥፍ በላይ ማለት ነው። ለዝግጅት ተብሎ ለእያንዳንዱ ቡድን በነብስ ወከፍ የተሰጠው ደግሞ 1̋ሚሊዮን ዶላር ነው፤ ከሴቶቹ እጥፍ በላይ ማለት ነው እንግዲህ። አጀብ! የሚያስብል ሆኖ እንዳገኙት እንጠራጠርም። የወንዶቹ ክፍያ ከሴቶቹ በልጦ የመገኘቱ ጉዳይ ከሚያመጡት ገቢ ጋር መገናኘቱ ነው ብለው የሚከራከሩ አልጠፉም። ቢሆንም በፊፋ ሕግ መሠረት ከሴቶች እግር ኳስ የሚገኘው ገንዘብ ለሴቶች እግር ኳስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ወጪዎች የሚውል ነው። ፊፋ ለሃገራት የሚከፍለው ገንዘብ የተጨዋቾች ኪስ ሳይሆን ወደ ፌዴሬሽን ካዝና የሚገባ ነው። የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ድርሻ ቆንጠር አድርጎ ለተጨዋቾች መስጠትና የቀረውን ደግሞ ሌሎች መስኮች ላይ በተን በተን ማድረግ ይሆናል። ታድያ በፌዴሬሽኖች እና በእግር ኳስ ተጨዋቾች ማሕበር መካከል የሚደረግ ድርድር አለ። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ የአውስትራሊያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የትኛውንም ገንዘብ በሽልማት መልክ ሲያገኝ ተጨዋቾች 30 በመቶ እንዲያገኙ ተደራድሯል። ወደ ክለቦች ስንወርድ ደግሞ የተሻለ ክፍያ የሚያገኙት [ከወንዶች ሲነፃፀር ቁጥሩ እጅግ አናሳ ቢሆንም] በምዕራብ አውሮፓ የሚጫወቱቱ ናቸው። ገንዘቡ ደግሞ ከ1 ሺህ እስከ 2 ሺህ ዩሮ ይደርሳል፤ ጨዋታ ባለ ቁጥር ደግሞ የላብ መተኪያ የሚሆን ከ50-100 ዩሮ ያገኛሉ። እርግጥ ነው ስም ያላቸው ተጨዋቾች ከዚህ የተሻለ ይከፈላቸዋል። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ክፍያው ምን ያህል ዝቅ ያለ እንደሆነ መገመት አያዳግትም። ፊፋ የሴቶች ዓለም የዋንጫ አሸናፊ ሽልማትን ከባለፈው ዓለም ዋንጫ እጥፍ ማድረጉ አንድ እርምጃ ወደፊት ነው የሚሉ ባይጠፉም 'አሁንም ትንሽ ነው' ብለው የሚከራከሩ አልጠፉም። በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ፊፋ የሴቶች እግር ኳስ ላይ ከ400-500 ሚሊዮን ዶላር አፈሳለሁ ይላል። የአሜሪካ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን የሃገሪቱን እግር ኳስ ማሕበር እኩል ክፍያን እውን አላደረገም በሚል ከሶታል። የአውስትራሊያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማሕበር ፊፋ የሴቶች እና የወንዶች የዓለም ዋንጫ ሽልማት እኩል መሆን አለበት ሲል እየሞገተ ነው። 2016 ላይ የአፍሪካ ዋንጫን የበላችው የናይጄሪያ ሴቶች ቡድን በክፍያ ጉዳይ ከፌዴሬሽን ጋር በነረው እሰጥ-አገባ አድማ አድርጋ ነበር። የኒው ዚላንድ ወንዶች እና ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት ከ2018 ጀምሮ ማንኛውም ዓይነት ክፍያ እኩል እንዲያገኙ የሚያደርግ ውል ደርሰዋል፤ በኖርዌይም እንዲሁ። ምንም እንኳ ልዩነቱ አሁንም የሰማይና ምድርን ያክል [የሎዛ አበራን አገላለፅ ለመጠቀም] ቢሆንም ከጊዜ ጊዜ ግን ለውጥ መምጣቱ አይካድም።
https://www.bbc.com/amharic/48591305
2health
የኮሮናቫይረስ በአንዳንድ ምግቦች ላይ ለቀናት እንደሚቆይ ጥናት አረጋገጠ
የኮሮናቫይረስ በተለይም ታሽገው በሚሸጡ ምግቦች ላይ እንደሚቆይ የዩናትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ገለጹ። የአገሪቱ የምግብ ጥራት ኤጀንሲ ባሰራው ጥናት ሳይንቲስቶች ቫይረሱን ሆነ ብለው በተወሰኑ የምግብ ማሸጊያዎች ላይ በማድረግ ሙከራውን አድረገዋል። ይህም በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ ኬክ እና ዳቦ እንዲሁም የታሸጉ መጠጦች ሙከራው ተደርጎባቸዋል። ሳይንቲስቶቹ ሳይታጠቡ ወይም ሳይበስሉ ሊበሉ የሚችሉ ምግቦችን በመምረጥ ነው ጥናቱን ያካሄዱት። ነገር ግን ይህ ሸማቾች ላይ የሚያመጣው አደጋ ያነሰ መሆኑን ገልጸዋል። በአብዛኛው የምግብ ምርቶች ላይ ሳይንቲስቶቹ ያስቀመጡት የቫይረስ መጠን በ24 ሰአት ውስጥ ከፍተኛ ማሽቆልቆል ታይቶበታል። ነገር ግን በአንዳንድ ማሸጊያዎች ላይ ቫይረሱ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደሚቆይ የሳውዝ ሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ተናግረዋል። ሳርስ ኮቭ 2 የተሰኘውን የቫይረስ አይነት ወስደው ምርምሩን ያደረጉት አጥኚዎች እንደሚሉት ''እንደዚህ ያለ በንክኪ ብቻ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ የቫይረስ አይነትን በተመለከተ ያገኘነው ግኝት ትኩረት የሚገባው ነው'' ሲሉ ተናግረዋል። ሳይንቲስቶች ሸማቾች በተለይም ምግብ በሚያዘጋጁበት ወቅት እጃቸውን እንዲታጠቡ እና በጥሬው የሚበሉ ምግቦችን አጥበው እንዲመገቡ አሳስበዋል። ተመራማሪዎች በጥናታቸው የኮሮናቫይረስ በንክኪ ከሚተላለፈው ይልቅ በምራቅ ፍንጣቂዎች በአየር አማካይነት የበለጥ እንደሚተላለፍ አረጋግጠዋል። ጥናቱ እንዳረጋገጠው ቫይረሱ በተለይም ሸካራ ገጽ ባላቸው እንደ ብሮኮሊ ባሉ አትክልቶች ላይ እንደ ፖም ባሉ ልሙጥ ከሆኑት በበለጠ እንደሚቆዩም አረጋግጧል። ጥናቱ አክሎም ፖም በቅርፊቱ ላይ በያዘው ኬሚካል አማካኝነት በቂቃዎች ወይም በሰዓታት ውስጥ በላዩ ላይ ያረፈውን ቫይረስ መግደል እንደሚጀምርም አረጋግጧል። በኬክ እና ዳቦ ላይ በተደረጉ ሙከራዎችም በአንዳንድ ደረቅ ገጽ በላቸው ኬኮች ላይ ቫይረሱ በሰአታት ውስጥ ቁጥሩ መቀነሱን ተናግረዋል። ለዚህም ምናልባት ኬኮቹ በሚበስሉበት ወቅት እንቁላል ስለሚቀቡ እና ይህም እንቁላል ውስጥ ካለ አሲድ አማካኝነት ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል። በቺዝ እና ቀዝቃዛ ስጋ ቫይረሱን ለቀናት አንዳንዴም ለሳምንት ሊያቆዩ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ኮቪድ በፕላስቲካ እቃዎች ላይ እስከ አንድ ሳምንት ድረስ ሊቆይ ይችላል። በካርቶን ላይ ለተወሰኑ ቀናት ብሎም በአልሙኒየም ማሸጊያዎች ላይ የተወሰኑ ሰአታትን ሊቆይ እንደሚችል ሳይንቲስቶቹ ተናግረዋል።
የኮሮናቫይረስ በአንዳንድ ምግቦች ላይ ለቀናት እንደሚቆይ ጥናት አረጋገጠ የኮሮናቫይረስ በተለይም ታሽገው በሚሸጡ ምግቦች ላይ እንደሚቆይ የዩናትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ገለጹ። የአገሪቱ የምግብ ጥራት ኤጀንሲ ባሰራው ጥናት ሳይንቲስቶች ቫይረሱን ሆነ ብለው በተወሰኑ የምግብ ማሸጊያዎች ላይ በማድረግ ሙከራውን አድረገዋል። ይህም በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ ኬክ እና ዳቦ እንዲሁም የታሸጉ መጠጦች ሙከራው ተደርጎባቸዋል። ሳይንቲስቶቹ ሳይታጠቡ ወይም ሳይበስሉ ሊበሉ የሚችሉ ምግቦችን በመምረጥ ነው ጥናቱን ያካሄዱት። ነገር ግን ይህ ሸማቾች ላይ የሚያመጣው አደጋ ያነሰ መሆኑን ገልጸዋል። በአብዛኛው የምግብ ምርቶች ላይ ሳይንቲስቶቹ ያስቀመጡት የቫይረስ መጠን በ24 ሰአት ውስጥ ከፍተኛ ማሽቆልቆል ታይቶበታል። ነገር ግን በአንዳንድ ማሸጊያዎች ላይ ቫይረሱ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደሚቆይ የሳውዝ ሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ተናግረዋል። ሳርስ ኮቭ 2 የተሰኘውን የቫይረስ አይነት ወስደው ምርምሩን ያደረጉት አጥኚዎች እንደሚሉት ''እንደዚህ ያለ በንክኪ ብቻ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ የቫይረስ አይነትን በተመለከተ ያገኘነው ግኝት ትኩረት የሚገባው ነው'' ሲሉ ተናግረዋል። ሳይንቲስቶች ሸማቾች በተለይም ምግብ በሚያዘጋጁበት ወቅት እጃቸውን እንዲታጠቡ እና በጥሬው የሚበሉ ምግቦችን አጥበው እንዲመገቡ አሳስበዋል። ተመራማሪዎች በጥናታቸው የኮሮናቫይረስ በንክኪ ከሚተላለፈው ይልቅ በምራቅ ፍንጣቂዎች በአየር አማካይነት የበለጥ እንደሚተላለፍ አረጋግጠዋል። ጥናቱ እንዳረጋገጠው ቫይረሱ በተለይም ሸካራ ገጽ ባላቸው እንደ ብሮኮሊ ባሉ አትክልቶች ላይ እንደ ፖም ባሉ ልሙጥ ከሆኑት በበለጠ እንደሚቆዩም አረጋግጧል። ጥናቱ አክሎም ፖም በቅርፊቱ ላይ በያዘው ኬሚካል አማካኝነት በቂቃዎች ወይም በሰዓታት ውስጥ በላዩ ላይ ያረፈውን ቫይረስ መግደል እንደሚጀምርም አረጋግጧል። በኬክ እና ዳቦ ላይ በተደረጉ ሙከራዎችም በአንዳንድ ደረቅ ገጽ በላቸው ኬኮች ላይ ቫይረሱ በሰአታት ውስጥ ቁጥሩ መቀነሱን ተናግረዋል። ለዚህም ምናልባት ኬኮቹ በሚበስሉበት ወቅት እንቁላል ስለሚቀቡ እና ይህም እንቁላል ውስጥ ካለ አሲድ አማካኝነት ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል። በቺዝ እና ቀዝቃዛ ስጋ ቫይረሱን ለቀናት አንዳንዴም ለሳምንት ሊያቆዩ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ኮቪድ በፕላስቲካ እቃዎች ላይ እስከ አንድ ሳምንት ድረስ ሊቆይ ይችላል። በካርቶን ላይ ለተወሰኑ ቀናት ብሎም በአልሙኒየም ማሸጊያዎች ላይ የተወሰኑ ሰአታትን ሊቆይ እንደሚችል ሳይንቲስቶቹ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0j54rpdryo
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ኒውዚላንድ 14 በከሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች አገኘች
የኒውዚላንዷ ትልቋ ከተማ ኦክላንድ በድጋሚ የእንቅስቃሴ ገደብ ከተጣለባት በኋላ አዲስ 14 በኮሮረናቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ። በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ አራት አንድ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲሰማ መላው ኒውዚላንድ በድንጋጤ ተውጦ የነበረ ሲሆን የአሁኑ ደግሞ ነገሮችን አባብሷል። ከውጭ አገራት በቫይረሱ ተይዘው ከሚመጡ ሰዎች ውጪ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ አገሪቱ ላለፉት ሶስት ወራት ምንም በቫይረሱ የተያዘ ሰው አላገኘችም ነበር። ዛሬ ከተገኙት ተጨማሪ 14 ሰዎች መካከል 13ቱ ከዚሁ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን አንደኛው ግለሰብ ደግሞ ከሌላ አገር ወደ ኒውዚላንድ ገብቶ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ እንደሆነ ተገልጿል። ከትላንት ረቡዕ ጀምሮ ደግሞ በኦክላንድ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። '' ሁኔታው ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ማየት እንችላለን'' ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጃሲንዳ አርደርን። በሰጡት ጋዜታዊ መግለጫ ላይ አክለውም '' ጉዳዩ በተገቢው መንገድ ክትትል እየተደረገበት ነው፤ ፈጣንና ተገቢው እርምጃም ይወሰዳል'' ሲሉ ተደምጠዋል። ሁሉም ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን ኃላፊዎች ያስታወቁ ሲሆን ከነሱ ጋር በማንኛውም መንገድ ንክኪ የነበራቸው ሰዎችም ክትትል እንደሚደረግባቸው ገልጸዋል። ኒውዚላንድ እስካሁን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በወሰደቻቸው ፈጣንና ውጤታማ እርምጃዎች ከመላው ዓለም ምስጋናና ሙገሳ ሲጎርፍላት ነበር። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላም በመላው አገሪቱ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ግዴታ የተደረገ ሲሆን ቫይረሱ በተገኘባት ኦክላንድ ደግሞ ጠንከር ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። ከማክሰኞ በፊት በኒው ዚላንድ በአገር ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ሳታገኝ 102 ቀናት መቆየት የቻለች አገር ነበረች። የአገሪቱ የጤና ኃላፊዎችና ሰራተኞች ቫይረሱ ከየት እንደተነሳ ለማወቅ በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ተገልጿል። በኮቪድ-19 የተያዙት ሰዎች ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና የስራ ባልደረቦችም ተለይተው ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል። '' ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት ያለእረፍት እየሰራን ነው። ምንጩ ከየት እንደሆነም ለማወቅ የምንችለውን ነገር በሙሉ እያደረግን ነው'' ብለዋል ብሄራዊ የጤና ኃላፊው አሽሊ ብሉምፊልድ። ቫይረሱ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በድጋሚ ሲያገረሽ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም። በርካታ የአውሮፓ አገራት ሁኔታዎች መሻሻል ሲያሳዩ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ማንሳታቸውን ተከትሎ ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር መስፋፋት ጀምሯል። ቪየትናም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳታገኝ 99 ቀናት ሳታገኝ ከቆየች በኋላ ዳ ናንግ በተባለችው ከተማ ስርጭቱ በድጋሚ መጀመሩ የሚታወስ ነው። በኒውዚላንድ ወረርሽኙ በድጋሚ መቀስቀሱ ምናልባት በሌሎች ከተሞችም የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ሊያስገድድ እንደሚችል ተፈርቷል። አገሪቱ ደግሞ በሳምንታት ልዩነት ውስጥ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነበረች። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ምን አይነት ውሳኔዎች እንሚተላለፉ ነገ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
ኮሮናቫይረስ፡ ኒውዚላንድ 14 በከሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች አገኘች የኒውዚላንዷ ትልቋ ከተማ ኦክላንድ በድጋሚ የእንቅስቃሴ ገደብ ከተጣለባት በኋላ አዲስ 14 በኮሮረናቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ። በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ አራት አንድ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲሰማ መላው ኒውዚላንድ በድንጋጤ ተውጦ የነበረ ሲሆን የአሁኑ ደግሞ ነገሮችን አባብሷል። ከውጭ አገራት በቫይረሱ ተይዘው ከሚመጡ ሰዎች ውጪ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ አገሪቱ ላለፉት ሶስት ወራት ምንም በቫይረሱ የተያዘ ሰው አላገኘችም ነበር። ዛሬ ከተገኙት ተጨማሪ 14 ሰዎች መካከል 13ቱ ከዚሁ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን አንደኛው ግለሰብ ደግሞ ከሌላ አገር ወደ ኒውዚላንድ ገብቶ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ እንደሆነ ተገልጿል። ከትላንት ረቡዕ ጀምሮ ደግሞ በኦክላንድ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። '' ሁኔታው ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ማየት እንችላለን'' ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጃሲንዳ አርደርን። በሰጡት ጋዜታዊ መግለጫ ላይ አክለውም '' ጉዳዩ በተገቢው መንገድ ክትትል እየተደረገበት ነው፤ ፈጣንና ተገቢው እርምጃም ይወሰዳል'' ሲሉ ተደምጠዋል። ሁሉም ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን ኃላፊዎች ያስታወቁ ሲሆን ከነሱ ጋር በማንኛውም መንገድ ንክኪ የነበራቸው ሰዎችም ክትትል እንደሚደረግባቸው ገልጸዋል። ኒውዚላንድ እስካሁን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በወሰደቻቸው ፈጣንና ውጤታማ እርምጃዎች ከመላው ዓለም ምስጋናና ሙገሳ ሲጎርፍላት ነበር። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላም በመላው አገሪቱ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ግዴታ የተደረገ ሲሆን ቫይረሱ በተገኘባት ኦክላንድ ደግሞ ጠንከር ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። ከማክሰኞ በፊት በኒው ዚላንድ በአገር ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ሳታገኝ 102 ቀናት መቆየት የቻለች አገር ነበረች። የአገሪቱ የጤና ኃላፊዎችና ሰራተኞች ቫይረሱ ከየት እንደተነሳ ለማወቅ በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ተገልጿል። በኮቪድ-19 የተያዙት ሰዎች ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና የስራ ባልደረቦችም ተለይተው ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል። '' ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት ያለእረፍት እየሰራን ነው። ምንጩ ከየት እንደሆነም ለማወቅ የምንችለውን ነገር በሙሉ እያደረግን ነው'' ብለዋል ብሄራዊ የጤና ኃላፊው አሽሊ ብሉምፊልድ። ቫይረሱ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በድጋሚ ሲያገረሽ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም። በርካታ የአውሮፓ አገራት ሁኔታዎች መሻሻል ሲያሳዩ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ማንሳታቸውን ተከትሎ ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር መስፋፋት ጀምሯል። ቪየትናም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳታገኝ 99 ቀናት ሳታገኝ ከቆየች በኋላ ዳ ናንግ በተባለችው ከተማ ስርጭቱ በድጋሚ መጀመሩ የሚታወስ ነው። በኒውዚላንድ ወረርሽኙ በድጋሚ መቀስቀሱ ምናልባት በሌሎች ከተሞችም የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ሊያስገድድ እንደሚችል ተፈርቷል። አገሪቱ ደግሞ በሳምንታት ልዩነት ውስጥ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነበረች። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ምን አይነት ውሳኔዎች እንሚተላለፉ ነገ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53761579
2health
“እስክሞት ልታገል”፡ የኩላሊት ህሙማን መርጃ ያቋቋመው የኩላሊት ታማሚ
የህክምና ምርመራ ውጤት! ሕይወታችንን ባላሰብነው፣ ባልጠበቅነው መንገድ ይገለባብጣል። ለኢዮብ ተወልደመድኅን ያ ክፉ ጊዜ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ነበር። የኩላሊት ታማሚ እንደሆነ ሐኪሞች ሲገሩት። የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ኢዮብ ይህን ዜና ሲሰማ የሚገባበት ጠፋው። ባለቤቱ በድንጋጤ ከፍተኛ ሐዘን ተጫናት። አዲስ አበባ ውስጥ የተክለሐይማኖት ሰፈር ልጅ ነው። ከ1979 ዓ. ም. ጀምሮ ግን ለአምስት ዓመታት አሰበ ተፈሪ ኖሯል። ዘጠነኛ ክፍልን አብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ተምሮ 10ኛ ክፍል ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት በማታ ፈረቃ ገባ። የግድ ታናናሾቹን ማሳደግ ስለነበረበት ከ11ኛ ክፍል በላይ መቀጠል አልቻለም። ትምህርቱን አቋርጦ እንጨት ሥራ ያዘ። በእንጨትና አልሙንየም ሥራ ተቀጥሮ ለሦስት ዓመታት ሠራ። ጥሩ ገቢ ያገኝ ስለነበር ታናናሽ ወንድሞቹን፣ እናትና አባቱንም ያስተዳድር ጀመር። 1991 ዓ.ም. ላይ ከብድርና ቁጠባ ተቋም አነስተኛ ገንዘብ ተበድሮ ቤቱ የእንጨት ሥራ ከፈተ። ገቢው እያደገ መጣ። ንግዱ ሲጦፍ ከመንግሥት ቦታ ወስዶ እንጨት ሥራውን አስፋፋ። በልደታ ክፍለ ከተማ በከፈተው እንጨት ቤት ሙያውን ያስተምርም ነበር። ጥቅምት 2006 ዓ.ም. ላይ የኩላሊት ህመም አለብህ ሲባል ግን ነገሮች መስመር ሳቱ። ሥራውን ወዲያው አላቋረጠም። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደው መምጣቱ ግን አልቀረም። ከታመመ ከሁለት ዓመት በኋላ አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከጥቃቅንና መካከለኛ የንግድ ሰዎች አንዱ ብሎ ሸልሞታል። የኩላሊት ህመም አቅም ይነሳል። አካልን፣ ሥነ ልቦናን፣ ቤተሰብን፣ ጓደኛን፣ ሥራን ይፈትናል። ኢዮብ የገጠመውም ይኸው ነው። የኩላሊት ህክምና እድሜ ልክ የሚወስድ፣ ገንዘብንም የሚያሟጥጥ እንደሆነ ሲገነዘብ የባለቤቱና የሕጻናት ልጆቹ እጣ ፈንታ እንቅልፍ ነሳው። ቤተሰቤን ድሃ አድርጌ ከምሞት ምነው እኔው ቀድሜ ብሞት ሲል ያስብ እንደነበር ይናገራል። በአንድ ወር ውስጥ የኩላሊት እጥበት [ዳያለሲስ] ካላደረገ እንደሚሞት ሲነገረው ቤተሰቡና ጓደኞቹ ተረበሹ። በአፋጣኝ ኮርያ ሆስፒታል ወስደውት የኩላሊት እጥበት ጀመረ። ህመሙም ጋብ አለለት። ያኔ ሆስፒታሉ ውስጥ ያየው ነገር የሕይወት አቅጣጫውን እንዲቀይር እንዳደረገው ያስታውሳል። "አቅም የሌለው፣ መካከለኛ ገቢ ያለው፣ ባለ ሀብት ታካሚም አለ። ልዩነቱ በግልጽ ይታያል። በርካቶች ህክምናውን ለማድረግ አቅም አልነበራቸውም። እኔ ታክሜ ነጻነት ሳገኝ ለምኖ ያልሞላለት ሰው ግን ምን ያህል ነጻነቱን ያጣል? ስል አሰብኩ።" ለወራት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ የህክምናው ወጪ ከብዷቸው የሚያቋርጡ እንዳሉ ይሰማ ነበር። ወጪው ከአቅማቸው በላይ ሆኖ የሚሞቱትንም ቤቱ ይቁጠራቸው። "እስክሞት ልታገል" ኩላሊት መሥራት ሲያቆም የኩላሊት እጥበት ማድረግ ግዴታ ነው። ህመሙ የሌለባቸው ሰዎች ሰውነታቸው ውስጥ የሚከማች ቆሻሻን ሽንት በመሽናት ያስወግዳሉ። ታማሚዎች የኩላሊት እጥበት ካላደረጉ ቆሻሻው አይወጣም ማለት ነው። እናም ሰውነታቸው ይታፈናል፣ ያብጣል፣ ሲከፋም ሕይወታቸውን ያጣሉ። በሳምንት ሦስቴ የኩላሊት እጥበት ማድረግ የሚጠበቅበት ሰው በሳምንት አንዴ ብቻ ቢያደርግ ወይም ቢያቋርጥ ይህ መታፈን ይገጥመዋል። ምግብ መብላትም አይችልም። ኢዮብ በህመሙ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችን ሲያይ በቀረኝ ሕይወት የአቅሜን መርዳት አለብኝ ብሎ ወሰነ። ህሙማን የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙበት እና መንግሥት ከህመሙ ጋር በተያያዘ የሚያወጣቸው ውሳኔዎች ላይ ጫና ማሳደር የሚቻልበት ማኅበር አቋቋመ። 'ሞት በኩላሊት ይብቃ' የተጀመረው በ2007 ዓ.ም. ነው። በታመመበት ጊዜ በመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት አልነበረም። በግል ሆስፒታልም በውስን ቦታ፣ በውድ ገንዘብ ይከናወናል። ህክምናውን ለማግኘት የሚደረገው ጥረት አሁንም ድረስ ከባድ ነው። በመንግሥት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት በአንድ ዙር 500 ብር ያስከፍላል። በግል ሆስፒታሎች ደግሞ ከ1500 እስከ 3500 ብር ያወጣል። "መሞቴ አይቀርም እስክሞት ልታገል ብዬ ወሰንኩ። ለመንግሥት አካላት እና ለአንዳንድ ተቋማት ድምጼን ማሰማት ጀመርኩ። በመኪና እየዞሩ መቀስቀስ፣ ብሮሸር መለጠፍም ቀጠልኩ። ይኸው 8 ዓመት ኖርኩኝ። በጥቂት ቦታም ቢሆን በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ተጀምሯል። ይሄ በኩራት የምናገረው የልፋቴ ውጤት ነው።" ማኅበሩ ከምስረታው ጀምሮ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ120 በላይ ህሙማንን ደግፏል። ቁጥሩ ለቀን፣ ለሳምንት፣ ለአንድ ወር ወይም ለሁለት ወር የኩላሊት እጥበት ገንዘብ የሚከፈልላቸውን ይጨምራል። ወርሀዊ መዋጮ በማድረግ እና በጉልበት ሥራ የሚደግፉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ደበበ እሸቱ፣ ስዩም ተፈራ፣ ዳንኤል ተገኝ ታዋቂ የማኅበሩ አባላት ናቸው። ኢዮብ "አምባሳደሮቻችን" ይላቸዋል። ከ2007 ወዲህ ድጎማ ከተደረገላቸው ህሙማን መካከል አምስቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሞት በኩላሊት ይብቃ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በምኒሊክ እና በዘውዲቱ ሆስፒታሎች ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ለሁለት ዓመት ነጻ የኩላሊት እጥበት ከሚሰጣቸው 105 ህመምተኞች አንዱ ኢዮብ ነው። ያቋቋመው ማኅበር ከያዛቸው ፕሮጀክቶች አንዱ የኩላሊት ህሙማን ተደራጅተው ሥራ እንዲሠሩ ከክፍለ ከተሞች ጋር መነጋገር ነው። ይህም ለህክምና ገንዘብ ሲሉ ጎዳና ወጥተው ለመለመን የተገደዱ ወገኖችን ለመደገፍ ያለመ ነው። ፕሮጀክቱን የጤና ሚንስትር እና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ድጋፍ ሰጥቶት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአንድ ህመምተኛ የሥራ እድል ተፈጥሯል። በሌሎች ክፍለ ከተሞችም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ወጋገን ባንክ ለህመምተኞች መርጃ ገንዘብ የሚሰበሰብበት ሳጥን ተቀምጧል። በቋሚነት በሳምንት ለአንድ ህመምተኛ የኩላሊት እጥበት ክፍያ የሚያደርጉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ማኅበሩ በሰበሰበው ገንዘብ ሦስት ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሲሆን፤ ነጻ ህክምና የሚያገኙ እንዳሉም ይናገራል። "ኢትዮጵያ ውስጥ የኩላሊት እጥበት ክፍያ ከፍተኛ ስለሆነ ከ70 እስከ 80 በመቶ ያሚሆነው የኩላሊት ህመምተኛ በሳምንት አንዴ ወይም ሁለት ቀን ነው የሚያደርገው" ይላል። ማኅበሩ በሠራው ስሌት መሠረት አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ከ700 ያላነሱ የኩላሊት ህመምተኞች በግል ሆስፒታል ነው ህክምና የሚከታተሉት። ዝቅተኛ የሚባለውን የአንድ ዙር የኩላሊት እጥበት ወጪ 1500 ብር መክፈል የሚችሉ ውስን ናቸው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጎዳና ላይና በየሐይማኖት ተቋማት ከመለመን ውጪም አማራጭ የለውም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢዮብ ማኅበር የመዋጮ ፕሮጀክት ቀርጿል። ሐሳቡ በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር የሚያዋጡ አንድ ሚሊዮን ሰዎችን በማኅበሩ አባልነት መመዝገብ ነው። ፕሮጀክቱ ከሦስት ዓመት በፊት ሲጀመር ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጀምሮ፣ ታዋቂ ሰዎችና ሌሎች ሰዎችን ጨምሮ ወደ 3000 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል። ከአባላቱ የሚሰበሰበውን ገንዘብ የሚከታተል መተግበሪያ እያሠሩ ነው። ኢትዮ-ቴሌኮም አጭር የጽሑፍ መልዕክት (ኤስኤምኤስ) እየላከ ገንዘቡን ሰብስቦ በቀጥታ ወደ ጤና ሚንስትር እንዲያስገባ ለማድረግ ወጥነዋል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር ቢያዋጡ፤ በአንድ ዓመት በአጠቃላይ 120 ሚሊዮን ብር ይገኛል። ይህም ለነጻ የኩላሊት ህክምና እንዲውል እንደሚፈልግ ኢዮብ ይናገራል። "ይህ ገንዘብ በመሀል ምንም ሂደት ሳይኖር ከቴሌ ወደ ጤና ሚንስትር በቀጥታ ስለሚገባ ተአማኒነት ይኖረዋል" ይላል። ከጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር በጉዳዩ ላይ ከስድስት ወር በፊት እንደተነጋገረ ይገልጻል። "ሚንስትሯ በሐሳቡ ደስተኛ እንደሆኑና ለመደገፍ ፍቃደኛ እንደሆኑ ነግረውኛል። ገንዘቡ ከቴሌ ወደ ጤና ጥበቃ በቀጥታ እንዲገባ እንደምንፈልግ ስነግራቸው የሕግ አግባቡን ልይ ብለዋል።" የቀድሞው የጤና ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን ሐሳቡን ደግፈው የአባልነት መታወቂያ አውጥተዋል። የኢዮብ ውጥን ተሳክቶ በአንድ ዓመት 120 ሚሊዮን ብር ማግኘት ከተቻለ እስከ 500 ሰዎች ለዓመት በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት በነጻ ያገኛሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲደግፏቸው ለማድረግ መልዕክት እንደላኩና እስካሁን እንዳላገኟቸው የሚናገረው ኢዮብ በድጋሚ ጥያቄ እንደሚያቀርብላቸው ገልጿል። ሐሳቡ እውን ከሆነ "መዋጮው ኪስ አይጎዳም። ብንኖርም ባንኖርም ቋሚና ቀጣይ ይሆናል። ጤናማው ሰው የሚያዋጣው ገንዘብ ወደ ኋላ መገልገያው እንዲሆን የጤና መድኅን አካል ማድረግም ይቻላል" ሲል ተስፋውን ይናገራል። እንደ ኩላሊት፣ ካንሰር እና ልብ ያሉ ህመሞች ህክምና ሊሰጥባቸው እየተገባ ብዙዎች የሚሞቱባቸው ናቸው። ምናልባትም እንዲህ ባሉ የረድኤት ፕሮጀክቶች ችግሩን መቅረፍ ይቻላል ብሎ ያምናል። "ባለቤቴ- ጀግናዬ" ኢዮብ ከመታመሙ በፊት ለራሱና ለቤተሰቡ ሕይወት መለወጥ የሚተጋ ሰው ነበር። አሁን ግን የብዙዎችን ኃላፊነት ለመሸከም መርጧል። የማኅበሩ መስራች፣ ሥራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆን ሹፌር፣ ቀስቃሽ፣ ገንዘብ ሰብሳቢ የሆነባቸውን ጊዜያት ያስታውሳል። ሥራውን "ፈጣሪ እና ህሊናዬ የተደሰቱበት ስለሆነ ኩራት እና ደስታ ይሰማኛል" ሲል ይገልጸዋል። ለስምንት ዓመታት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ ወገቡ እና እግሩ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት በድጋፍ ነው የሚንቀሳቀሰው። እንደ ቀድሞው የማኅበሩን ሥራዎች እንዳያከናውንም አድርጎታል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የሰውነት ክብደቱ ከ56 ወደ 46 ኪሎ ቀንሷል። ብርታት ከሚሰጡት በዋነኛነት የሚጠቅሰው "ጀግናዬ" የሚላት ባለቤቱን ነው። "በጤናማነቴ ጊዜ ያፈራሁትን ከ1.5 ሚልዮን ብር በላይ ለማኅበሩ ሳውል ነገ ይሞታል ብላ ቅር አላላትም። ብር አንሶን የልጆቼን መኖርያ ቤት ስሸጥ እሷ የነበረንን ንግድ ቤት በመሸጥ ሹፌር ሆና ልጆቹን አስተማረች። ለዛሬ አብቅታኛለችና ጀግናዬ ናት።" ሲታመም የሩቅና የቅርብ ቤተሰብ፣ ጓደኛም በአብዛኛው እንደሸሸው ይናገራል። ከልጆቹ ጋር ሰፊ ጊዜ ባለማሳለፉ፣ እንዳሻቸው ባለማዝናናቱም ያዝናል። ከኩላሊት ታማሚዎች ጋር ስቴድየም ዙርያ፣ ባዛሮች ላይ እንዲሁም ወደ መንግሥትና የግል ተቋማት እየሄደ እርዳታ ለማሰባሰብ ይሞክራል። ህክምናውን ትቶ የማኅበሩን ጉዳይ የሚከታተልባቸው ጊዜያትም አሉ። የኩላሊት ህመም "ሳቄን፣ ደስታዬን፣ እግሬን አሳጥቶኛል" ይላል። ከዚህ በተቃራኒው "እውነተኛ ታጋይና ለወገን ቶርቋሪ አድርጎኛል" ሲል ያለበት ሁኔታ ይገልጻል። በእሱ ማኅበር ውስጥ ይረዱ ከነበሩ ህሙማን መካከል ኋላ ላይ በራሳቸው ማኅበር መስርተው መንቀሳቀስ የጀመሩ ሰዎች መኖራቸው ያስደስተዋል። ህሙማንን ሲረዳ ከሚያገኘው እፎይታ በተጨማሪ ቤተሰቡ ሐሴት ይሰጠዋል። "ሁሌም ሚስቴና ልጆቼ የተቃጠልኩትን ማቀዝቀዣዎቼ ናቸው" ይላቸዋል። ሐኪሞች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ እንዳለበት ነግረውታል። ኩላሊት የሚሰጠው የቤተሰብ አባል ቢያገኝም የወጪው ነገር አሳሳቢ ነው። የማኅበሩ ስኬት ከሚላቸው መካከል ብዙ ገንዘብ ባይኖራቸውም ለህሙማን ገንዘብ ለመለገስ የሚፈቅዱ ሰዎች ማግኘታቸውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን የሚያስደነግጥ ምስል ወይም የተጎዳ ሰው ቁስል ካልታየ በስተቀር በማኅበረሰቡ ዘንድ እምብዛም ሰዎችን የመርዳት ተነሳሽነት እንደሌለ አስተውሏል። የተጎዱ ሰዎችን ለይቶ በቀጥታ የመርዳት ልማድ ባለመኖሩ ማኅበረሰቡ እርዳታ የሚሰጠው ባገኘው አጋጣሚ፣ በየመንገዱ ለሚያገኘው ገንዘብ ጠያቂ ነው። ይህም በእርዳታ ስም የሚያጭበረብሩ እንዲበራከቱ መንገድ እንደከፈተም ያምናል። ሰዎች ባላቸው አቅም ተጎጂዎችን በእቅድ የመርዳት ባህል እንዲዳብሩ ይመኛል። የኩላሊት ህክምና በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሕግ አንድ ሰው ኩላሊቱ መሥራት ካቆመ ከቤተሰቡ ውጪ ኩላሊት ከሌላ ሰው መውሰድ አይችልም ይላል። ይህ ሕግ ቤተሰብ የሌላቸው ወይም ከቤተሰቦቻቸው ጋር የደም አይነታቸው የማይመሳሰል ሰዎችን ሕይወት አደጋ ውስጥ ጥሏል ይላል። ዘመድ፣ አብሮ አደግ ወይም ሌላ ለጋሽ ኩላሊት የሚሰጥበት አሠራር እንዲዘረጋ ለጤና ሚንስቴር ማሳሰቡንም ኢዮብ ይናገራል። ሌላው ክፍተት የኩላሊት ንቅለ ተከላ የሚከናወነው በጳውሎስ ሆስፒታል ብቻ መሆኑ ነው። ይህ አገልግሎት ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መነሳት ወዲህ መቋረጡም ሌላ ችግር ነው። በሌላ በኩል ንቅለ ተከላ ያደረጉ ሰዎች የመድኃኒት እጥረት ይገጥማቸዋል። የኩላሊት እጥበት የሚያደርጉ ሰዎችም እንዲሁ ተጓዳኝ የሰውነት መጠገኛ መድኃኒቶች ያጣሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ መድኃኒቶቹን ማግኘት ከባድ ነው። ያሉትም በጣም ውድ ናቸው። ኢዮብ ከታመመበት ከስምንት ዓመታት ወዲህ ብዙ ነገሮች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን አይክድም። "ትላንት የነበረውን ጨለማ ስለማውቀው የዛሬው የተሻለ ነው እላለሁ" ይላል። ሆኖም ግን አሁንም ያሉ ክፍተቶች እንዲሸፈኑ ይጠይቃል።
“እስክሞት ልታገል”፡ የኩላሊት ህሙማን መርጃ ያቋቋመው የኩላሊት ታማሚ የህክምና ምርመራ ውጤት! ሕይወታችንን ባላሰብነው፣ ባልጠበቅነው መንገድ ይገለባብጣል። ለኢዮብ ተወልደመድኅን ያ ክፉ ጊዜ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ነበር። የኩላሊት ታማሚ እንደሆነ ሐኪሞች ሲገሩት። የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ኢዮብ ይህን ዜና ሲሰማ የሚገባበት ጠፋው። ባለቤቱ በድንጋጤ ከፍተኛ ሐዘን ተጫናት። አዲስ አበባ ውስጥ የተክለሐይማኖት ሰፈር ልጅ ነው። ከ1979 ዓ. ም. ጀምሮ ግን ለአምስት ዓመታት አሰበ ተፈሪ ኖሯል። ዘጠነኛ ክፍልን አብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ተምሮ 10ኛ ክፍል ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት በማታ ፈረቃ ገባ። የግድ ታናናሾቹን ማሳደግ ስለነበረበት ከ11ኛ ክፍል በላይ መቀጠል አልቻለም። ትምህርቱን አቋርጦ እንጨት ሥራ ያዘ። በእንጨትና አልሙንየም ሥራ ተቀጥሮ ለሦስት ዓመታት ሠራ። ጥሩ ገቢ ያገኝ ስለነበር ታናናሽ ወንድሞቹን፣ እናትና አባቱንም ያስተዳድር ጀመር። 1991 ዓ.ም. ላይ ከብድርና ቁጠባ ተቋም አነስተኛ ገንዘብ ተበድሮ ቤቱ የእንጨት ሥራ ከፈተ። ገቢው እያደገ መጣ። ንግዱ ሲጦፍ ከመንግሥት ቦታ ወስዶ እንጨት ሥራውን አስፋፋ። በልደታ ክፍለ ከተማ በከፈተው እንጨት ቤት ሙያውን ያስተምርም ነበር። ጥቅምት 2006 ዓ.ም. ላይ የኩላሊት ህመም አለብህ ሲባል ግን ነገሮች መስመር ሳቱ። ሥራውን ወዲያው አላቋረጠም። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደው መምጣቱ ግን አልቀረም። ከታመመ ከሁለት ዓመት በኋላ አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከጥቃቅንና መካከለኛ የንግድ ሰዎች አንዱ ብሎ ሸልሞታል። የኩላሊት ህመም አቅም ይነሳል። አካልን፣ ሥነ ልቦናን፣ ቤተሰብን፣ ጓደኛን፣ ሥራን ይፈትናል። ኢዮብ የገጠመውም ይኸው ነው። የኩላሊት ህክምና እድሜ ልክ የሚወስድ፣ ገንዘብንም የሚያሟጥጥ እንደሆነ ሲገነዘብ የባለቤቱና የሕጻናት ልጆቹ እጣ ፈንታ እንቅልፍ ነሳው። ቤተሰቤን ድሃ አድርጌ ከምሞት ምነው እኔው ቀድሜ ብሞት ሲል ያስብ እንደነበር ይናገራል። በአንድ ወር ውስጥ የኩላሊት እጥበት [ዳያለሲስ] ካላደረገ እንደሚሞት ሲነገረው ቤተሰቡና ጓደኞቹ ተረበሹ። በአፋጣኝ ኮርያ ሆስፒታል ወስደውት የኩላሊት እጥበት ጀመረ። ህመሙም ጋብ አለለት። ያኔ ሆስፒታሉ ውስጥ ያየው ነገር የሕይወት አቅጣጫውን እንዲቀይር እንዳደረገው ያስታውሳል። "አቅም የሌለው፣ መካከለኛ ገቢ ያለው፣ ባለ ሀብት ታካሚም አለ። ልዩነቱ በግልጽ ይታያል። በርካቶች ህክምናውን ለማድረግ አቅም አልነበራቸውም። እኔ ታክሜ ነጻነት ሳገኝ ለምኖ ያልሞላለት ሰው ግን ምን ያህል ነጻነቱን ያጣል? ስል አሰብኩ።" ለወራት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ የህክምናው ወጪ ከብዷቸው የሚያቋርጡ እንዳሉ ይሰማ ነበር። ወጪው ከአቅማቸው በላይ ሆኖ የሚሞቱትንም ቤቱ ይቁጠራቸው። "እስክሞት ልታገል" ኩላሊት መሥራት ሲያቆም የኩላሊት እጥበት ማድረግ ግዴታ ነው። ህመሙ የሌለባቸው ሰዎች ሰውነታቸው ውስጥ የሚከማች ቆሻሻን ሽንት በመሽናት ያስወግዳሉ። ታማሚዎች የኩላሊት እጥበት ካላደረጉ ቆሻሻው አይወጣም ማለት ነው። እናም ሰውነታቸው ይታፈናል፣ ያብጣል፣ ሲከፋም ሕይወታቸውን ያጣሉ። በሳምንት ሦስቴ የኩላሊት እጥበት ማድረግ የሚጠበቅበት ሰው በሳምንት አንዴ ብቻ ቢያደርግ ወይም ቢያቋርጥ ይህ መታፈን ይገጥመዋል። ምግብ መብላትም አይችልም። ኢዮብ በህመሙ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችን ሲያይ በቀረኝ ሕይወት የአቅሜን መርዳት አለብኝ ብሎ ወሰነ። ህሙማን የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙበት እና መንግሥት ከህመሙ ጋር በተያያዘ የሚያወጣቸው ውሳኔዎች ላይ ጫና ማሳደር የሚቻልበት ማኅበር አቋቋመ። 'ሞት በኩላሊት ይብቃ' የተጀመረው በ2007 ዓ.ም. ነው። በታመመበት ጊዜ በመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት አልነበረም። በግል ሆስፒታልም በውስን ቦታ፣ በውድ ገንዘብ ይከናወናል። ህክምናውን ለማግኘት የሚደረገው ጥረት አሁንም ድረስ ከባድ ነው። በመንግሥት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት በአንድ ዙር 500 ብር ያስከፍላል። በግል ሆስፒታሎች ደግሞ ከ1500 እስከ 3500 ብር ያወጣል። "መሞቴ አይቀርም እስክሞት ልታገል ብዬ ወሰንኩ። ለመንግሥት አካላት እና ለአንዳንድ ተቋማት ድምጼን ማሰማት ጀመርኩ። በመኪና እየዞሩ መቀስቀስ፣ ብሮሸር መለጠፍም ቀጠልኩ። ይኸው 8 ዓመት ኖርኩኝ። በጥቂት ቦታም ቢሆን በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ተጀምሯል። ይሄ በኩራት የምናገረው የልፋቴ ውጤት ነው።" ማኅበሩ ከምስረታው ጀምሮ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ120 በላይ ህሙማንን ደግፏል። ቁጥሩ ለቀን፣ ለሳምንት፣ ለአንድ ወር ወይም ለሁለት ወር የኩላሊት እጥበት ገንዘብ የሚከፈልላቸውን ይጨምራል። ወርሀዊ መዋጮ በማድረግ እና በጉልበት ሥራ የሚደግፉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ደበበ እሸቱ፣ ስዩም ተፈራ፣ ዳንኤል ተገኝ ታዋቂ የማኅበሩ አባላት ናቸው። ኢዮብ "አምባሳደሮቻችን" ይላቸዋል። ከ2007 ወዲህ ድጎማ ከተደረገላቸው ህሙማን መካከል አምስቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሞት በኩላሊት ይብቃ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በምኒሊክ እና በዘውዲቱ ሆስፒታሎች ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ለሁለት ዓመት ነጻ የኩላሊት እጥበት ከሚሰጣቸው 105 ህመምተኞች አንዱ ኢዮብ ነው። ያቋቋመው ማኅበር ከያዛቸው ፕሮጀክቶች አንዱ የኩላሊት ህሙማን ተደራጅተው ሥራ እንዲሠሩ ከክፍለ ከተሞች ጋር መነጋገር ነው። ይህም ለህክምና ገንዘብ ሲሉ ጎዳና ወጥተው ለመለመን የተገደዱ ወገኖችን ለመደገፍ ያለመ ነው። ፕሮጀክቱን የጤና ሚንስትር እና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ድጋፍ ሰጥቶት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአንድ ህመምተኛ የሥራ እድል ተፈጥሯል። በሌሎች ክፍለ ከተሞችም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ወጋገን ባንክ ለህመምተኞች መርጃ ገንዘብ የሚሰበሰብበት ሳጥን ተቀምጧል። በቋሚነት በሳምንት ለአንድ ህመምተኛ የኩላሊት እጥበት ክፍያ የሚያደርጉ የማኅበሩ አባላት አሉ። ማኅበሩ በሰበሰበው ገንዘብ ሦስት ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሲሆን፤ ነጻ ህክምና የሚያገኙ እንዳሉም ይናገራል። "ኢትዮጵያ ውስጥ የኩላሊት እጥበት ክፍያ ከፍተኛ ስለሆነ ከ70 እስከ 80 በመቶ ያሚሆነው የኩላሊት ህመምተኛ በሳምንት አንዴ ወይም ሁለት ቀን ነው የሚያደርገው" ይላል። ማኅበሩ በሠራው ስሌት መሠረት አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ከ700 ያላነሱ የኩላሊት ህመምተኞች በግል ሆስፒታል ነው ህክምና የሚከታተሉት። ዝቅተኛ የሚባለውን የአንድ ዙር የኩላሊት እጥበት ወጪ 1500 ብር መክፈል የሚችሉ ውስን ናቸው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጎዳና ላይና በየሐይማኖት ተቋማት ከመለመን ውጪም አማራጭ የለውም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢዮብ ማኅበር የመዋጮ ፕሮጀክት ቀርጿል። ሐሳቡ በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር የሚያዋጡ አንድ ሚሊዮን ሰዎችን በማኅበሩ አባልነት መመዝገብ ነው። ፕሮጀክቱ ከሦስት ዓመት በፊት ሲጀመር ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጀምሮ፣ ታዋቂ ሰዎችና ሌሎች ሰዎችን ጨምሮ ወደ 3000 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል። ከአባላቱ የሚሰበሰበውን ገንዘብ የሚከታተል መተግበሪያ እያሠሩ ነው። ኢትዮ-ቴሌኮም አጭር የጽሑፍ መልዕክት (ኤስኤምኤስ) እየላከ ገንዘቡን ሰብስቦ በቀጥታ ወደ ጤና ሚንስትር እንዲያስገባ ለማድረግ ወጥነዋል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች በወር 10 ብር፣ በዓመት 120 ብር ቢያዋጡ፤ በአንድ ዓመት በአጠቃላይ 120 ሚሊዮን ብር ይገኛል። ይህም ለነጻ የኩላሊት ህክምና እንዲውል እንደሚፈልግ ኢዮብ ይናገራል። "ይህ ገንዘብ በመሀል ምንም ሂደት ሳይኖር ከቴሌ ወደ ጤና ሚንስትር በቀጥታ ስለሚገባ ተአማኒነት ይኖረዋል" ይላል። ከጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር በጉዳዩ ላይ ከስድስት ወር በፊት እንደተነጋገረ ይገልጻል። "ሚንስትሯ በሐሳቡ ደስተኛ እንደሆኑና ለመደገፍ ፍቃደኛ እንደሆኑ ነግረውኛል። ገንዘቡ ከቴሌ ወደ ጤና ጥበቃ በቀጥታ እንዲገባ እንደምንፈልግ ስነግራቸው የሕግ አግባቡን ልይ ብለዋል።" የቀድሞው የጤና ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን ሐሳቡን ደግፈው የአባልነት መታወቂያ አውጥተዋል። የኢዮብ ውጥን ተሳክቶ በአንድ ዓመት 120 ሚሊዮን ብር ማግኘት ከተቻለ እስከ 500 ሰዎች ለዓመት በመንግሥት ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት በነጻ ያገኛሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲደግፏቸው ለማድረግ መልዕክት እንደላኩና እስካሁን እንዳላገኟቸው የሚናገረው ኢዮብ በድጋሚ ጥያቄ እንደሚያቀርብላቸው ገልጿል። ሐሳቡ እውን ከሆነ "መዋጮው ኪስ አይጎዳም። ብንኖርም ባንኖርም ቋሚና ቀጣይ ይሆናል። ጤናማው ሰው የሚያዋጣው ገንዘብ ወደ ኋላ መገልገያው እንዲሆን የጤና መድኅን አካል ማድረግም ይቻላል" ሲል ተስፋውን ይናገራል። እንደ ኩላሊት፣ ካንሰር እና ልብ ያሉ ህመሞች ህክምና ሊሰጥባቸው እየተገባ ብዙዎች የሚሞቱባቸው ናቸው። ምናልባትም እንዲህ ባሉ የረድኤት ፕሮጀክቶች ችግሩን መቅረፍ ይቻላል ብሎ ያምናል። "ባለቤቴ- ጀግናዬ" ኢዮብ ከመታመሙ በፊት ለራሱና ለቤተሰቡ ሕይወት መለወጥ የሚተጋ ሰው ነበር። አሁን ግን የብዙዎችን ኃላፊነት ለመሸከም መርጧል። የማኅበሩ መስራች፣ ሥራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆን ሹፌር፣ ቀስቃሽ፣ ገንዘብ ሰብሳቢ የሆነባቸውን ጊዜያት ያስታውሳል። ሥራውን "ፈጣሪ እና ህሊናዬ የተደሰቱበት ስለሆነ ኩራት እና ደስታ ይሰማኛል" ሲል ይገልጸዋል። ለስምንት ዓመታት የኩላሊት እጥበት ሲያደርግ ወገቡ እና እግሩ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት በድጋፍ ነው የሚንቀሳቀሰው። እንደ ቀድሞው የማኅበሩን ሥራዎች እንዳያከናውንም አድርጎታል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የሰውነት ክብደቱ ከ56 ወደ 46 ኪሎ ቀንሷል። ብርታት ከሚሰጡት በዋነኛነት የሚጠቅሰው "ጀግናዬ" የሚላት ባለቤቱን ነው። "በጤናማነቴ ጊዜ ያፈራሁትን ከ1.5 ሚልዮን ብር በላይ ለማኅበሩ ሳውል ነገ ይሞታል ብላ ቅር አላላትም። ብር አንሶን የልጆቼን መኖርያ ቤት ስሸጥ እሷ የነበረንን ንግድ ቤት በመሸጥ ሹፌር ሆና ልጆቹን አስተማረች። ለዛሬ አብቅታኛለችና ጀግናዬ ናት።" ሲታመም የሩቅና የቅርብ ቤተሰብ፣ ጓደኛም በአብዛኛው እንደሸሸው ይናገራል። ከልጆቹ ጋር ሰፊ ጊዜ ባለማሳለፉ፣ እንዳሻቸው ባለማዝናናቱም ያዝናል። ከኩላሊት ታማሚዎች ጋር ስቴድየም ዙርያ፣ ባዛሮች ላይ እንዲሁም ወደ መንግሥትና የግል ተቋማት እየሄደ እርዳታ ለማሰባሰብ ይሞክራል። ህክምናውን ትቶ የማኅበሩን ጉዳይ የሚከታተልባቸው ጊዜያትም አሉ። የኩላሊት ህመም "ሳቄን፣ ደስታዬን፣ እግሬን አሳጥቶኛል" ይላል። ከዚህ በተቃራኒው "እውነተኛ ታጋይና ለወገን ቶርቋሪ አድርጎኛል" ሲል ያለበት ሁኔታ ይገልጻል። በእሱ ማኅበር ውስጥ ይረዱ ከነበሩ ህሙማን መካከል ኋላ ላይ በራሳቸው ማኅበር መስርተው መንቀሳቀስ የጀመሩ ሰዎች መኖራቸው ያስደስተዋል። ህሙማንን ሲረዳ ከሚያገኘው እፎይታ በተጨማሪ ቤተሰቡ ሐሴት ይሰጠዋል። "ሁሌም ሚስቴና ልጆቼ የተቃጠልኩትን ማቀዝቀዣዎቼ ናቸው" ይላቸዋል። ሐኪሞች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ እንዳለበት ነግረውታል። ኩላሊት የሚሰጠው የቤተሰብ አባል ቢያገኝም የወጪው ነገር አሳሳቢ ነው። የማኅበሩ ስኬት ከሚላቸው መካከል ብዙ ገንዘብ ባይኖራቸውም ለህሙማን ገንዘብ ለመለገስ የሚፈቅዱ ሰዎች ማግኘታቸውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን የሚያስደነግጥ ምስል ወይም የተጎዳ ሰው ቁስል ካልታየ በስተቀር በማኅበረሰቡ ዘንድ እምብዛም ሰዎችን የመርዳት ተነሳሽነት እንደሌለ አስተውሏል። የተጎዱ ሰዎችን ለይቶ በቀጥታ የመርዳት ልማድ ባለመኖሩ ማኅበረሰቡ እርዳታ የሚሰጠው ባገኘው አጋጣሚ፣ በየመንገዱ ለሚያገኘው ገንዘብ ጠያቂ ነው። ይህም በእርዳታ ስም የሚያጭበረብሩ እንዲበራከቱ መንገድ እንደከፈተም ያምናል። ሰዎች ባላቸው አቅም ተጎጂዎችን በእቅድ የመርዳት ባህል እንዲዳብሩ ይመኛል። የኩላሊት ህክምና በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሕግ አንድ ሰው ኩላሊቱ መሥራት ካቆመ ከቤተሰቡ ውጪ ኩላሊት ከሌላ ሰው መውሰድ አይችልም ይላል። ይህ ሕግ ቤተሰብ የሌላቸው ወይም ከቤተሰቦቻቸው ጋር የደም አይነታቸው የማይመሳሰል ሰዎችን ሕይወት አደጋ ውስጥ ጥሏል ይላል። ዘመድ፣ አብሮ አደግ ወይም ሌላ ለጋሽ ኩላሊት የሚሰጥበት አሠራር እንዲዘረጋ ለጤና ሚንስቴር ማሳሰቡንም ኢዮብ ይናገራል። ሌላው ክፍተት የኩላሊት ንቅለ ተከላ የሚከናወነው በጳውሎስ ሆስፒታል ብቻ መሆኑ ነው። ይህ አገልግሎት ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መነሳት ወዲህ መቋረጡም ሌላ ችግር ነው። በሌላ በኩል ንቅለ ተከላ ያደረጉ ሰዎች የመድኃኒት እጥረት ይገጥማቸዋል። የኩላሊት እጥበት የሚያደርጉ ሰዎችም እንዲሁ ተጓዳኝ የሰውነት መጠገኛ መድኃኒቶች ያጣሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ መድኃኒቶቹን ማግኘት ከባድ ነው። ያሉትም በጣም ውድ ናቸው። ኢዮብ ከታመመበት ከስምንት ዓመታት ወዲህ ብዙ ነገሮች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን አይክድም። "ትላንት የነበረውን ጨለማ ስለማውቀው የዛሬው የተሻለ ነው እላለሁ" ይላል። ሆኖም ግን አሁንም ያሉ ክፍተቶች እንዲሸፈኑ ይጠይቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58126744
5sports
የሞ ፋራህ የቀድሞ አሠልጣኝ ለአራት ዓመት ከአትሌቲክስ ታገዱ
የሞ ፋራህ ቀድሞ አሠልጣኝ፣ አልቤርቶ ሳላዛር፣ ከአበረታች መድሀኒት ጋር በተያያዘ ከስፖርት ለአራት ዓመት ታገዱ። የ61 ዓመቱ ሳላዛር የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነው ፋራህን ማፍራት የቻለው የናይክ ኦሪጎን ፕሮጀክት ከ2011 እስከ 2017 ድረስ ሲመሩ ቆይተዋል። ውሳኔው የተላለፈው በአሜሪካው የፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ ለአራት ዓመት ያህል ምርመራ ሲደረግ ከቆየና ለሁለት ዓመት ያህል በፍርድ ቤት ክርክር ከተካሄደ በኋላ ነው። ምርመራው የተጀመረው ቢቢሲ በ2015 ፓናሮማ የተሰኘ ፕሮግራሙ ላይ ጉዳዩን ካቀረበ በኋላ ነው። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች • የጤፍ ቢራ አሜሪካ ውስጥ ገበያ ላይ ዋለ • ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት ይህ የቢቢሲ ፕሮግራም ከአሜሪካው ፕሮፑብሊካ ድረገፅ ጋር በጋራ በመሆን በአሜሪካ ኦሪጎን ውስጥ በሚገኘው የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ስፍራ የሚሰጡ አበረታች መድሃኒቶችንና የሚካሄዱ ተገቢ ያልሆነ ተግባራትን አጋልጧል። የዩኬ ስፖርቶችን የሚቆጣጠረው ዩኬ አትሌቲክስ፣ የራሱን ምርመራ ያካሄደ ሲሆን ለስድስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮናው፣ እንግሊዛዊው ፋራህ፣ ከ አሜሪካዊው ሳላዛር ጋር እንዲሰራ ይሁንታውን ሰጥቶት ነበር። በናይክ እየተከፈላቸው በርካታ የሳላዛር አትሌቶችን የሚያክሙት ዶክተር ጄፍሪ ብራውን ደግሞ ለአራት ዓመት ታግደዋል። ፋራህ ከሳላዛር ጋር የተለያየው በ2017 መሆኑን ጠቅሶ ከአበረታች መድሃኒት ጋር በተያያዘ አለመሆኑን ግን ገልጿል።
የሞ ፋራህ የቀድሞ አሠልጣኝ ለአራት ዓመት ከአትሌቲክስ ታገዱ የሞ ፋራህ ቀድሞ አሠልጣኝ፣ አልቤርቶ ሳላዛር፣ ከአበረታች መድሀኒት ጋር በተያያዘ ከስፖርት ለአራት ዓመት ታገዱ። የ61 ዓመቱ ሳላዛር የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነው ፋራህን ማፍራት የቻለው የናይክ ኦሪጎን ፕሮጀክት ከ2011 እስከ 2017 ድረስ ሲመሩ ቆይተዋል። ውሳኔው የተላለፈው በአሜሪካው የፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ ለአራት ዓመት ያህል ምርመራ ሲደረግ ከቆየና ለሁለት ዓመት ያህል በፍርድ ቤት ክርክር ከተካሄደ በኋላ ነው። ምርመራው የተጀመረው ቢቢሲ በ2015 ፓናሮማ የተሰኘ ፕሮግራሙ ላይ ጉዳዩን ካቀረበ በኋላ ነው። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች • የጤፍ ቢራ አሜሪካ ውስጥ ገበያ ላይ ዋለ • ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት ይህ የቢቢሲ ፕሮግራም ከአሜሪካው ፕሮፑብሊካ ድረገፅ ጋር በጋራ በመሆን በአሜሪካ ኦሪጎን ውስጥ በሚገኘው የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ስፍራ የሚሰጡ አበረታች መድሃኒቶችንና የሚካሄዱ ተገቢ ያልሆነ ተግባራትን አጋልጧል። የዩኬ ስፖርቶችን የሚቆጣጠረው ዩኬ አትሌቲክስ፣ የራሱን ምርመራ ያካሄደ ሲሆን ለስድስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮናው፣ እንግሊዛዊው ፋራህ፣ ከ አሜሪካዊው ሳላዛር ጋር እንዲሰራ ይሁንታውን ሰጥቶት ነበር። በናይክ እየተከፈላቸው በርካታ የሳላዛር አትሌቶችን የሚያክሙት ዶክተር ጄፍሪ ብራውን ደግሞ ለአራት ዓመት ታግደዋል። ፋራህ ከሳላዛር ጋር የተለያየው በ2017 መሆኑን ጠቅሶ ከአበረታች መድሃኒት ጋር በተያያዘ አለመሆኑን ግን ገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-49889111
5sports
የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው
የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ከአንጎል ጤንነት ጋር በተያያዘ የወጣ ሪፖርትን ተከትሎ ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ እገዳ ለመጣል እያሰበ መሆኑ ተነገረ። በግላስጎው ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ባለሙያዎች እንደደረሱበት የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች አንጎልን እያዳከመ ለሞት በሚያበቃ የአንጎል በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ከሦስት ጊዜ በላይ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ከህክምና ባለሙያዎች ጋር ከተነጋገረ በኋላ ያሉ አማራጮች ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተነግሯል። አሜሪካ ውስጥ ከአምስት ዓመት በፊት ጀምሮ ታዳጊ ህጻናት ኳስ በጭንቅላታቸው እንዳይመቱ እገዳ ተጥሏል። • ''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በጭንቅላት (በቴስታ) ኳስ መምታት በአንጎል ደህንነት፣ በተለይም በህጻናት ላይ የሚኖረውን ውጤት በተመለከተ ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር ተከትሎ ስኮትላንድ ውስጥ ክልከላ ሊቀመጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው። አንድ ውስጥ አዋቂ እንዳሉት "ጉዳዩ ታዳጊዎች በእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት ኳስ በጭንቅላታቸው የመግጨት አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን በልምምድ ወቅት በተደጋጋሚ ኳስን በጭንቅላት መምታትን ይመለከታል" ብለዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ዋና የህክምና አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጆን ማክሊን ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ ኳስን በጭንቅላት በመምታት በታዳጊ ተጫዋቾች ላይ የሚፈጠረውን ጫና ለመቀነስ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ዶክተሩ እንዳሉት "ከስኮትላንድና ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ጋር በመሆን ተቀባይነት ያለው መመሪያ ለማዘጋጀት ሥራ ጀምረናል። " • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? "ለምሳሌም ለታዳጊዎች የሚሰጠውን ኳስ በጭንቅላት የመምታት ልምምድ የተወሰነ እንዲሆንና አንጎላቸው ለማገገም እንዲችል በሳምንት የሚሰጣቸው ስልጠና አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሆን ማድረግን የመሰለ ቀላል እርምጃ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ውስጥ አዋቂ እንዳሉት የማህበሩ አመራር ቡድን ታዳጊዎች ኳስ በጭንቅላታቸው መምታትን በተመለከተ የቀረበውን የባለሙያ አስተያየት ይደግፈዋል ብለዋል። በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ለተደረገው ጥናት መነሻ የሆነው የቀድሞው ዌስት ብሮም አጥቂ ጄፍ አስቴል ለህልፈት የተዳረገው በተደጋጋሚ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ነው የሚል አስተያየት ከተሰነዘረ በኋላ ነው። በ2002 (እኤአ) አስቴል ከሞተ በኋላ፣ በጥናቱ መዘግየት ቤተሰቦቹ ቁጣቸውን በመግለጻቸው፣ በእግር ኳስ ማህበሩና በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር አነሳሽነት ጥናቱ ተደርጓል። የሟቹ እግር ኳስ ተጫዋች ሴት ልጅ የሆነችው ዳውን ጥናቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ በውጤት "እንደደነገጠች" ተናግራለች።
የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ከአንጎል ጤንነት ጋር በተያያዘ የወጣ ሪፖርትን ተከትሎ ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ እገዳ ለመጣል እያሰበ መሆኑ ተነገረ። በግላስጎው ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ባለሙያዎች እንደደረሱበት የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች አንጎልን እያዳከመ ለሞት በሚያበቃ የአንጎል በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ከሦስት ጊዜ በላይ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ከህክምና ባለሙያዎች ጋር ከተነጋገረ በኋላ ያሉ አማራጮች ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተነግሯል። አሜሪካ ውስጥ ከአምስት ዓመት በፊት ጀምሮ ታዳጊ ህጻናት ኳስ በጭንቅላታቸው እንዳይመቱ እገዳ ተጥሏል። • ''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በጭንቅላት (በቴስታ) ኳስ መምታት በአንጎል ደህንነት፣ በተለይም በህጻናት ላይ የሚኖረውን ውጤት በተመለከተ ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር ተከትሎ ስኮትላንድ ውስጥ ክልከላ ሊቀመጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው። አንድ ውስጥ አዋቂ እንዳሉት "ጉዳዩ ታዳጊዎች በእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት ኳስ በጭንቅላታቸው የመግጨት አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን በልምምድ ወቅት በተደጋጋሚ ኳስን በጭንቅላት መምታትን ይመለከታል" ብለዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ዋና የህክምና አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጆን ማክሊን ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ ኳስን በጭንቅላት በመምታት በታዳጊ ተጫዋቾች ላይ የሚፈጠረውን ጫና ለመቀነስ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ዶክተሩ እንዳሉት "ከስኮትላንድና ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ጋር በመሆን ተቀባይነት ያለው መመሪያ ለማዘጋጀት ሥራ ጀምረናል። " • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? "ለምሳሌም ለታዳጊዎች የሚሰጠውን ኳስ በጭንቅላት የመምታት ልምምድ የተወሰነ እንዲሆንና አንጎላቸው ለማገገም እንዲችል በሳምንት የሚሰጣቸው ስልጠና አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሆን ማድረግን የመሰለ ቀላል እርምጃ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ውስጥ አዋቂ እንዳሉት የማህበሩ አመራር ቡድን ታዳጊዎች ኳስ በጭንቅላታቸው መምታትን በተመለከተ የቀረበውን የባለሙያ አስተያየት ይደግፈዋል ብለዋል። በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ለተደረገው ጥናት መነሻ የሆነው የቀድሞው ዌስት ብሮም አጥቂ ጄፍ አስቴል ለህልፈት የተዳረገው በተደጋጋሚ በጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ነው የሚል አስተያየት ከተሰነዘረ በኋላ ነው። በ2002 (እኤአ) አስቴል ከሞተ በኋላ፣ በጥናቱ መዘግየት ቤተሰቦቹ ቁጣቸውን በመግለጻቸው፣ በእግር ኳስ ማህበሩና በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር አነሳሽነት ጥናቱ ተደርጓል። የሟቹ እግር ኳስ ተጫዋች ሴት ልጅ የሆነችው ዳውን ጥናቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ በውጤት "እንደደነገጠች" ተናግራለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-50198595
0business
ኢትዮጵያ ከግዙፉ የወደብ አስተዳዳሪ ድርጅት ጋር ውል ገባች
ኢትዮጵያ ከዓለማችን ግዙፍ የወደብ አንቀሳቃሾች መካከል አንዱ ከሆነው ዲፒ ዎርልድ ጋር የስምምነት ውል ገብታለች። ስምምነቱ ኢትዮጵያን ከሶማሊንዱ በርበራ ወደብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ነው ተብሏል። የዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ ንብረት የሆነው ዲፒ ዎርልድ ፕሮጀክቱ "ቀጣናውን ለማበልፀግና ምጣኔ ሃብታዊ አቅምን ለማሳደግ ውይይት እንዲደረግ መንገድ ይከፋታል" ብሏል። ፕሮጀክቱ ከራስ ገዟ የሶማሊላንድ በርበራ ወደብ ሁለቱን ሃገራት እስከሚያገናኘው የዋጃሌ ከተማ ድረስ ይዘረጋል። የወደቡን ፕሮጀክት በትብብር የሚገነቡት የአቡ ዳቢ ዕድገት ፈንድና የዩናይትድ ኪንግደም ዓለም አቀፍ ዕድገት ናቸው። ግንባታው በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ዲፒ ዎርልድ ከኢትዮጵያ ጋር በተገባው ውል [ሜሞራንደም ኦፍ አንደርስታንዲንግ] ውል መሠረት ዕቃ አስመጪና ላኪ ድርጅቶች በጥምረት እንዲሰሩ ያስችላል ይላል። ድርጅቱ 1 ቢሊዮን ዶላር አፍስሶ ደረቅ ወደብ፣ ጎተራ፣ መጋዘን እንዲሁም ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸው ማከማቸዎች ለመገንባት አቅዷል። "በርካታ ሥራዎች ይፈጥራል፤ አዳዲስ ቢዝነሶችና ኢንቨስተመንቶች ወደ ኮሪደሩ እንዲመጡ ያስችላል፤ አልፎም ሃገሪቱ ከዓለም አቀፍ ንግድ ጋር ያላትን ግንኙነት ያጠናክራል" ብለዋል የዲፒ ዎርልድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሱልጣን አሕመድ ቢን ሱሌይማን። በርበራ ወደብ በቅርቡ ሰፊ የመልሶ ግንባታ እንደተሰራለት ይታወሳል። በፈረንጆቹ 2016 ሶማሊላንድ ዲፒ ዎርልድን ቀጥራ ወደቧን ሰፋ አድርጎ እንዲገናባላት የ30 ዓመት ስምምነት መፈራረሙ አይዘነጋም። በወቅቱ በየብስ የተከበበችው ኢትዮጵያ ከፕሮጀክቱ 19 በመቶ ድርሻ መጋራቷ ይታወሳል። 30 በመቶው ድርሻ የተያዘው በሶማሊላንድ ሲሆን የተቀረው 51 በመቶ ድርሻ የዲፒ ወርልድ ነው። ዲፒ ዎርልድ በ442 ሚሊዮን ዶላር ወደቡን ለማስፋፋትና በዓመት 2 ሚሊዮን 20 ቻማ ርዝማኔ ያላቸውን ኮንቴነሮች ለመትከል ተስማምቷል። ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሁሉም ጎረቤት ሃገራት ጋር የንግድ መስመር ለመዘርጋት እንቅስቃሴ ጀምራለች። ይህ እንቅስቃሴ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት አጋዥ ነው እየተባለ ነው። በስምምነቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ሃገራቸው "የወደብ መንገዶቿን የተሰባጠረ ለማድረግና ዕቃና አገልግሎት የሚመላለስበትን አማራጭ ለማስፋት እየሠራች ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከ95 በመቶ በላይ ዕቃዎችን የምታመላልሰው በጎረቤት ሃገር ጅቡቲ ወደብ በኩል ነው። በፈረንጆቹ 2018 ኢትዮጵያ 750 ኪሎ ሜትር የሚዘረጋ በኤሌክትሪክ የሚሠራ ባቡር ወደ ጅቡቲ ወደብ መዘርጋቷ ይታወሳል። የባቡር ግንባታው 4.5 ሚሊዮን ዶላር አውጥቷል። አሁን የተገባው የበርበራ ወደብ ስምምነት በጅቡቲ በኩል ያለውን የዕቃዎች ምልልስ ወደ 50 በመቶ ዝቅ ሊያደርገው ይችላል ሲሉ ባለሙያዎች ይገምታሉ።
ኢትዮጵያ ከግዙፉ የወደብ አስተዳዳሪ ድርጅት ጋር ውል ገባች ኢትዮጵያ ከዓለማችን ግዙፍ የወደብ አንቀሳቃሾች መካከል አንዱ ከሆነው ዲፒ ዎርልድ ጋር የስምምነት ውል ገብታለች። ስምምነቱ ኢትዮጵያን ከሶማሊንዱ በርበራ ወደብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ነው ተብሏል። የዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ ንብረት የሆነው ዲፒ ዎርልድ ፕሮጀክቱ "ቀጣናውን ለማበልፀግና ምጣኔ ሃብታዊ አቅምን ለማሳደግ ውይይት እንዲደረግ መንገድ ይከፋታል" ብሏል። ፕሮጀክቱ ከራስ ገዟ የሶማሊላንድ በርበራ ወደብ ሁለቱን ሃገራት እስከሚያገናኘው የዋጃሌ ከተማ ድረስ ይዘረጋል። የወደቡን ፕሮጀክት በትብብር የሚገነቡት የአቡ ዳቢ ዕድገት ፈንድና የዩናይትድ ኪንግደም ዓለም አቀፍ ዕድገት ናቸው። ግንባታው በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ዲፒ ዎርልድ ከኢትዮጵያ ጋር በተገባው ውል [ሜሞራንደም ኦፍ አንደርስታንዲንግ] ውል መሠረት ዕቃ አስመጪና ላኪ ድርጅቶች በጥምረት እንዲሰሩ ያስችላል ይላል። ድርጅቱ 1 ቢሊዮን ዶላር አፍስሶ ደረቅ ወደብ፣ ጎተራ፣ መጋዘን እንዲሁም ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸው ማከማቸዎች ለመገንባት አቅዷል። "በርካታ ሥራዎች ይፈጥራል፤ አዳዲስ ቢዝነሶችና ኢንቨስተመንቶች ወደ ኮሪደሩ እንዲመጡ ያስችላል፤ አልፎም ሃገሪቱ ከዓለም አቀፍ ንግድ ጋር ያላትን ግንኙነት ያጠናክራል" ብለዋል የዲፒ ዎርልድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሱልጣን አሕመድ ቢን ሱሌይማን። በርበራ ወደብ በቅርቡ ሰፊ የመልሶ ግንባታ እንደተሰራለት ይታወሳል። በፈረንጆቹ 2016 ሶማሊላንድ ዲፒ ዎርልድን ቀጥራ ወደቧን ሰፋ አድርጎ እንዲገናባላት የ30 ዓመት ስምምነት መፈራረሙ አይዘነጋም። በወቅቱ በየብስ የተከበበችው ኢትዮጵያ ከፕሮጀክቱ 19 በመቶ ድርሻ መጋራቷ ይታወሳል። 30 በመቶው ድርሻ የተያዘው በሶማሊላንድ ሲሆን የተቀረው 51 በመቶ ድርሻ የዲፒ ወርልድ ነው። ዲፒ ዎርልድ በ442 ሚሊዮን ዶላር ወደቡን ለማስፋፋትና በዓመት 2 ሚሊዮን 20 ቻማ ርዝማኔ ያላቸውን ኮንቴነሮች ለመትከል ተስማምቷል። ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሁሉም ጎረቤት ሃገራት ጋር የንግድ መስመር ለመዘርጋት እንቅስቃሴ ጀምራለች። ይህ እንቅስቃሴ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት አጋዥ ነው እየተባለ ነው። በስምምነቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ሃገራቸው "የወደብ መንገዶቿን የተሰባጠረ ለማድረግና ዕቃና አገልግሎት የሚመላለስበትን አማራጭ ለማስፋት እየሠራች ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከ95 በመቶ በላይ ዕቃዎችን የምታመላልሰው በጎረቤት ሃገር ጅቡቲ ወደብ በኩል ነው። በፈረንጆቹ 2018 ኢትዮጵያ 750 ኪሎ ሜትር የሚዘረጋ በኤሌክትሪክ የሚሠራ ባቡር ወደ ጅቡቲ ወደብ መዘርጋቷ ይታወሳል። የባቡር ግንባታው 4.5 ሚሊዮን ዶላር አውጥቷል። አሁን የተገባው የበርበራ ወደብ ስምምነት በጅቡቲ በኩል ያለውን የዕቃዎች ምልልስ ወደ 50 በመቶ ዝቅ ሊያደርገው ይችላል ሲሉ ባለሙያዎች ይገምታሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-57029652
2health
ኮሮናቫይረስ፡ የዓለም ጤና ድርጅት ለአዲሶቹ የኮቪድ ዝርያዎች የግሪክ ስያሜዎችን ሰጠ
የዓለም ጤና ድርጅት ለአዳዲሶቹ የኮቪድ-19 ዝርያዎች ስም ለመስጠት የሚያስችል ስርአት ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ከዚህ በኋላም ድርጅቱ የቫይረሱን አይነቶች ለመለየት የግሪክ ፊደላትን የሚጠቀም ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካና ሕንድ ውስጥ የታዩት አዳዲስ ዝርያዎች መጀመሪያ ስያሜ ይሰጣቸዋል። ለምሳሌም በዩናይትድ ኪንግደም የታየው አዲሱ ቫይረስ ዝርያ 'አልፋ' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። የደቡቡ አፍሪካው 'ቤታ' የተባለ ሲሆን በሕንድ በርካቶችን ያጠቃው የቫይረስ አይነት ደግሞ 'ዴልታ' ተብሎ እንደሚጠራ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ስያሜዎቹን ያስተዋወቅኩት አንደኛ በንግግር ወቅት ቀላል ለማድረግና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቫይረሱ ዙሪያ የሚኖሩ የተለያዩ ማግለሎችን ለማስቀረት ነው ብሏል። ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ወር መጀመሪያ አካባቢ የሕንድ መንግሥት በአገሪቱ የተገኘውን የኮቪድ-19 አዲስ ቫይረስ 'ቢ.1.617.2' የሚል ስያሜ መስጠቱን ተከትሎ በርካታ ትችቶችን አስተናግዶ ነበር። ''የትኛውም አገር አዲስ የቫይረሱ አይነቶችን ሪፖርት በማድረጉ መገለል ሊደርስበት አይገባም'' ብለዋል የዓለም ጤና ደርጅት ቴክኒካል መሪ የሆኑት ማሪያ ቫን ኬርኮቭ። አክለውም አገራት አዲሶቹ ቫይረሶች ላይ ጠበቅ ያለ የክትትልና የምርመራ ስራ እንዲያከናውኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። አዲሱ የቫይረሶቹ ስያሜ ከተለያዩ ነገሮች አንጻር ከግምት ውስጥ እንደገባ የተገለጸ ሲሆን የሁሉም ቫይረሶች ስም ዝርዝር በዓለም ጤና ድርጅት ድረገጽ ላይ ይፋ ተደርጓል። እነኚህ የግሪክ ፊደላት አሁን በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙትን ሳይንሳዊ ስሞች የሚተኩ አይደለም። አዲሶቹ የኮሮናቫይረስ አይነቶች ከ24 የሚበልጡ ከሆነ የተዘጋጀው ስርአት ፊደላት ያልቁበታል። በዚህም መሰረት አዲስ ስያሜ የመስጠት ስርአት ይዘረጋል ብለዋል ማሪያ ቫን ኬርኮቭ። ''እኛ እያልን ያለነው እንደ ቢ.1.617.2 ያሉ ሳይንሳዊ ስያሜዎችን ሙሉ በሙሉ መቀየር ሳይሆን ሁሉም ሰው የሚረዳው አይነት ስያሜ እንስጠው ነው። ስያሜው ቀለል ሲል ማህበረሰቡ በዕለት ተዕለት ግንኙነቱ ይጠቀማቸዋል'' ብለዋል። ሰኞ ዕለት የዩናይትድ ኪንግደም መንግስትን የሚያማክሩ ተመራማሪዎች አገሪቱ በሶስተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል። በዋነኛነት ሰዎችን እያጠቃ የሚገኘውም 'ዴልታ' የሚል ስያሜ የተሰጠው የሕንዱ ዝርያ ነው። ይህ ዝርያ 'አልፋ' የሚል ስያሜ ከተሰጠው የዩኬው ዝርያ በበለጠ መልኩ በቶሎ መሰራጨት የሚችል ሲሆን በዩኬ ለጨመረው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ምክንያት ነው። በሌላ በኩል በቬትናም የተስተዋለው አዲሱ የቫይረስ አይነት በሕንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም ከታዩት የቫይረሱ ዝርያዎች የተቀላቀለ ሲሆን በቀላሉ በአየር መተላለፍ የሚችል ነው።
ኮሮናቫይረስ፡ የዓለም ጤና ድርጅት ለአዲሶቹ የኮቪድ ዝርያዎች የግሪክ ስያሜዎችን ሰጠ የዓለም ጤና ድርጅት ለአዳዲሶቹ የኮቪድ-19 ዝርያዎች ስም ለመስጠት የሚያስችል ስርአት ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ከዚህ በኋላም ድርጅቱ የቫይረሱን አይነቶች ለመለየት የግሪክ ፊደላትን የሚጠቀም ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካና ሕንድ ውስጥ የታዩት አዳዲስ ዝርያዎች መጀመሪያ ስያሜ ይሰጣቸዋል። ለምሳሌም በዩናይትድ ኪንግደም የታየው አዲሱ ቫይረስ ዝርያ 'አልፋ' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። የደቡቡ አፍሪካው 'ቤታ' የተባለ ሲሆን በሕንድ በርካቶችን ያጠቃው የቫይረስ አይነት ደግሞ 'ዴልታ' ተብሎ እንደሚጠራ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ስያሜዎቹን ያስተዋወቅኩት አንደኛ በንግግር ወቅት ቀላል ለማድረግና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቫይረሱ ዙሪያ የሚኖሩ የተለያዩ ማግለሎችን ለማስቀረት ነው ብሏል። ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ወር መጀመሪያ አካባቢ የሕንድ መንግሥት በአገሪቱ የተገኘውን የኮቪድ-19 አዲስ ቫይረስ 'ቢ.1.617.2' የሚል ስያሜ መስጠቱን ተከትሎ በርካታ ትችቶችን አስተናግዶ ነበር። ''የትኛውም አገር አዲስ የቫይረሱ አይነቶችን ሪፖርት በማድረጉ መገለል ሊደርስበት አይገባም'' ብለዋል የዓለም ጤና ደርጅት ቴክኒካል መሪ የሆኑት ማሪያ ቫን ኬርኮቭ። አክለውም አገራት አዲሶቹ ቫይረሶች ላይ ጠበቅ ያለ የክትትልና የምርመራ ስራ እንዲያከናውኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። አዲሱ የቫይረሶቹ ስያሜ ከተለያዩ ነገሮች አንጻር ከግምት ውስጥ እንደገባ የተገለጸ ሲሆን የሁሉም ቫይረሶች ስም ዝርዝር በዓለም ጤና ድርጅት ድረገጽ ላይ ይፋ ተደርጓል። እነኚህ የግሪክ ፊደላት አሁን በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙትን ሳይንሳዊ ስሞች የሚተኩ አይደለም። አዲሶቹ የኮሮናቫይረስ አይነቶች ከ24 የሚበልጡ ከሆነ የተዘጋጀው ስርአት ፊደላት ያልቁበታል። በዚህም መሰረት አዲስ ስያሜ የመስጠት ስርአት ይዘረጋል ብለዋል ማሪያ ቫን ኬርኮቭ። ''እኛ እያልን ያለነው እንደ ቢ.1.617.2 ያሉ ሳይንሳዊ ስያሜዎችን ሙሉ በሙሉ መቀየር ሳይሆን ሁሉም ሰው የሚረዳው አይነት ስያሜ እንስጠው ነው። ስያሜው ቀለል ሲል ማህበረሰቡ በዕለት ተዕለት ግንኙነቱ ይጠቀማቸዋል'' ብለዋል። ሰኞ ዕለት የዩናይትድ ኪንግደም መንግስትን የሚያማክሩ ተመራማሪዎች አገሪቱ በሶስተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል። በዋነኛነት ሰዎችን እያጠቃ የሚገኘውም 'ዴልታ' የሚል ስያሜ የተሰጠው የሕንዱ ዝርያ ነው። ይህ ዝርያ 'አልፋ' የሚል ስያሜ ከተሰጠው የዩኬው ዝርያ በበለጠ መልኩ በቶሎ መሰራጨት የሚችል ሲሆን በዩኬ ለጨመረው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ምክንያት ነው። በሌላ በኩል በቬትናም የተስተዋለው አዲሱ የቫይረስ አይነት በሕንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም ከታዩት የቫይረሱ ዝርያዎች የተቀላቀለ ሲሆን በቀላሉ በአየር መተላለፍ የሚችል ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-57313043
3politics
ምርጫን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የሶማሊያ ውዝግብ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ያመራ ይሆን?
በሶማሊያ ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ መዘግየቱ አለመግባባትን እና በፖለቲከኞች መካከል አለመተማመንን አባብሷል። ይህንንም ተከትሎ በመዲናዋ ሞቃዲሾ የሰዎች ሕይወት የጠፋበት አመጽ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አገሪቱን ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። በመዲናዋ ሞቃዲሾ በፌዴራል ኃይሎች እና በታጠቁ የተቃዋሚ ታማኝ ኃይሎች መካከል ከቀናት በፊት በተነሳ ግጭት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱ ይቀጥላል በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች 'ሠላማዊ' ወደሚሏቸው መንደሮች ተሰደዋል። ክፍተቱ ለአል-ሻባብ የአፍሪካ ቀንዷን አገር የበለጠ ለማተራመስ መልካም አጋጣሚ ሊሆነው ይችላል። ታጣቂዎቹ ከቅርብ ወራት ወዲህ ብቻ በምርጫው ዙሪያ ውይይቶች በተካሄዱባቸው ቦታዎች ላይ በርካታ ጥቃቶችን አካሂደዋል። የአገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት የፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆን የስልጣን ዘመን በሁለት ዓመት ይራዘም ሲል ወሰነ። ከሁለት ሳምንት በፊት ከተላለፈው ውሳኔ በኋላ የአገሪቱ የፖለቲካ ክፍተቶች ተባብሰዋል። ከወራት ውይይቶች በኋላ ውሳኔው ሲጸድቅ የፌዴራል መንግሥቱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሕዝባዊ ምርጫዎችን እንዲያደራጅ ቢያዝም የአገሪቱን የምርጫ ቀውስ ማስቆም አልቻለም። የሶማሊያ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች የሥልጣን ማራዘሙን ውድቅ በማድረግ ፋርማጆን ሥልጣንን የሙጥኝ ብለዋል ሲሉ ከሰዋል። የተነሳባቸው ተቃውሞና ሊከተል የሚችለው ቀውስ ያሰጋቸው ፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ዘመናቸውን የማራዘም ፍላጎታቸውን እንዲተዉ አስገድዷቸዋል። ነገር ግን ውጥረቱ በጎሳ ፉክክር ይበልጥ እየከረረ ነው። ከአስርት ዓመታት የእርስ በእርስ እና የታጣቂዎች ግጭት በኋላ የተገኘውን አንፃራዊ መረጋጋት ሊቀለበስ የሚችልም ነው። ቁልፍ ተዋናዮች እና ምላሾች ተቃዋሚዎች የፋርማጆ ሥልጣን የካቲት 8 ስላበቃ ከእንግዲህ ለፕሬዝዳንትነታቸውን እውቅና አንሰጥም ብለዋል። ናሽናል ሳልቬሽን ፎረም (ብሔራዊ አገርን የማዳኛ መድረክ እንደማለት ነው) ተቋቁሟል። ፎረሙ ተሰሚ በሆኑ ተቃዋሚዎች የተቋቋመ ነው። የፋርማጆ ቀንደኛ ተቃዋሚ የሆኑት የምክር ቤት አፈ ጉባኤ አብዲ ሀሺ አብዱላሂ፣ የጁባላንድ እና ፑንትላንድ መሪዎችን ያካተተ ጥምረት ነው። ሕገ መንግሥታዊ ባልሆነው የሥልጣን ማራዘሚያ ላይ "አስፈላጊ እርምጃዎችን እንወስዳለን" ሲሉም ዝተዋል። የሴኔቱ አፈ ጉባኤ አብዱላሂ እንዳሉት፤ ፕሬዚዳንቱ የውሳኔ ሐሳቡን ለማጽደቅ የላይኛውን ምክር ቤት ሳያቀርቡ ማራዘማቸው ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ነው። የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒ እና የጁባው አቻቸው አህመድ መሐመድ ኢስላም በሞቃዲሾ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ነበር። "ሶማሊያን ከማይቀረው የትርምስ አዘቅት ውስጥ እንዳትገባ እንዲያድኑ" ጠይቀዋል። የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ምክር ቤት ፋርማጆን ለመተካት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ጥምረት ነው። በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሻሪፍ ሼህ አህመድ የሚመራ ሲሆን ፕሬዚዳንቱን "የጦር አበጋዝ" ብለዋቸዋል። የሃውያ ንዑስ ጎሳ አባላት ተደማጭነት ካላቸው ጎሳዎች መካከል ነው። ለአንድ ቀን በመዲናዋ ሞቃዲሾ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ ሥልጣን የማራዘሙን ውሳኔ ውድቅ አድርገውታል። አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና የአውሮፓ ሕብረት ሥልጣን የማራዘሙ ውሳኔ ሶማሊያ ወደ ሰላምና መንግሥት ግንባታ የምታደርገውን ጉዞ የሚያደናቅፍ ነው ብለዋል። ግንኙነታቸውን በድጋሚ እንደሚያጤኑትም አስጠንቅቀዋል። አሜሪካ "ሰላምና መረጋጋትን በማደናቀፍ" በሥልጣን ማራዘሙ በተሳተፉት ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል ዝታለች። የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ሥልጣን ማራዘሙን ውድቅ አድርጎታል። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ መሪዎች በምርጫ ውዝግቡ ዙሪያ ውይይት እንዲቀጥሉ ያቀረበውን ሐሳብ እንደሚደግፍ አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ከፍተኛ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም በታችኛው ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴዎች እና በጋልሙዱግ፣ በሂውማሌ እና በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ሰፊ ድጋፍ አላቸው፡፡ በቋፍ ላይ ያለ የፌዴራል ሥርዓት የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሥርዓት ሥር የሰደደውን የጎሳ ግጭት ለማቆም እና የአንድነት መንግሥት ለመመስረት የሚደረገውን ጥረት በመሰናከሉ የተመሠረተ ነው። ይህን ተከትሎም የተቆራረጠ እና ደካማ ቢሆንም ብሔራዊ ደኅንነት ግንባታው እያዘገመም ቢሆን እንዲጓዝ መንገዱን ጠርጓል። አገሪቱ ከ30 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት ሥርዓት ለመቀላቀል የፋይናንስ ተቋማቷን እንደገና አደራጅታለች። ምርጫው ያስከተለው አለመረጋጋት በማዕከላዊ መንግሥት እና ቀድሞውንም የፋርማጆን ሥልጣን 'በሚያኮስሱት' አንዳንድ የክልል መንግሥታት መካከል ውዝግቡን አጡዞታል። እአአ በመስከረም 2018 አምስት የአገሪቱ የክልል ፕሬዚዳንቶች በሥልጣን እና በሀብት ክፍፍል አለመግባባት ምክንያት ከፌዴራል መንግሥት ጋር እንደማይተባበሩ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ለምላሽ አልዘገዩም። ክልሎችን በራሳቸው ቁጥጥር ስር ማድረግ ጀመሩ። ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን በመንቀል አጋሮቻቸውን በጋልሙዱግ እና በደቡብ ምዕራብ ግዛቶች አስቀመጡ። የፌዴራሉ መንግሥት በፑንትላንድ እና በጁባላንድ ባሉ ምርጫዎች ላይ ተመሳሳይ ተጽዕኖ ማሳደር አልቻለም። የእነዚህ አካባቢ መሪዎች ፋርማጆ እንደገና እንዳይመረጡ እየሠሩ ነው። የፖለቲካ ህልውናቸው የተመሠረተው በዚሁ ላይ ነው። የመስከረም 17ቱ ስምምነት ብሔራዊው የምርጫ ኮሚሽን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያለው ሕዝባዊ ምርጫ ለማድረግ እንደማይቻል አስታውቋል። ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ለማዘጋጀት እስከ 13 ወር ድረስ እንደሚያስፈልገው እአአ ሰኔ 2020 ለሕዝብ እንደራሴዎች ገልጿል። የጁባላንድ፣ ፑንትንትላንድ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫውን መዘግየት ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም። እአአ ሐምሌ 2020 አስደንጋጭ ነበር የተባለለት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ኬይሬ ከሥልጣን መነሳት በምርጫው ሂደት ላይ ያላቸውን እምነት ይባስ ሸረሸረው። የጁባላንድ እና የፑንትላንድ መሪዎች በማዕከላዊው ዱሳማሬብ ከተማ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። በስብሰባው ላይ ከምርጫ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ስምምነት ተደርሷል። የአማጺያኑ አመራሮች አድሏዊ ነው ሲሉ የምርጫ ኮሚሽኑ እንዲፈርስ ጠይቀዋል። እአአ መስከረም 17 ቀን 2020 ከሳምንታት የዓለም አቀፍ ግፊት በኋላ በምርጫ ሁኔታዎች ላይ ስምምነት ተፈረመ። በስምምነቱ መሠረት ሁለት የምርጫ ክልሎች በእያንዳንዱ ክልል ይኖራሉ። ምርጫዎች የሚካሄዱት በየክልል ተሰብሳቢዎች ላይ ተመስርቶ ሲሆን በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ውስጥ 101 የምርጫ ልዑካን ድምጽ ይሰጣሉ። በአማጽያን ጥያቄ መሠረት ምርጫውን በበላይነት የሚቆጣጠር ብሔራዊ እና ክልላዊ የምርጫ ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ ተወሰነ። የጁባላንዱ ማዶቤ እና የፑንትላንዱ ዴኒ በፌዴራል መንግስት የተቋቋመውን የምርጫ ኮሚሽን ባለመቀበላቸው የስምምነቱ ትግበራ እንቅፋት ገጠመው። የጸጥታ አዛዦች እንዲነሱ እና ፓርላማው እንዲበተንም ጠይቀዋል። የምርጫውን መዘግየት አስቀድሞ የገመተው የፌዴራሉ ፓርላማ እአአ ኅዳር 2020 አዲስ ተመራጮች እስኪተኩ ድረስ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል። የዘር ፖለቲካ እና ግጭት በምርጫው ላይ በተፈጠረው ክፍፍል ላይ ብሔራዊ ማንነት እና የጎሳ ማንነት ልዩነትም ሚና ተጫውተዋል። አለመተማመን እየጠነከረ ሲሄድ ፖለቲከኞች እና ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናት ወደ ጎሳቸው መመሸግ ጀመሩ። እነዚህም በጎሳ ሚሊሻዎች፣ በጎበዝ አለቆች እና በቀድሞ የጦር መሪዎች የሚጠበቁ ናቸው። የተወሰኑ የተቃዋሚ የፓርቲ አመራሮች ለትጥቅ ትግል መዘጋጀት ያዙ። የጦር መሣሪያዎችና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የገዙም አሉ። በመዲናዋ ሞቃዲሾ የዘገየውን ምርጫ የሚቃወሙ ሰልፈኞችን በሚደግፉ ወታደሮች እና በፖሊስ መካከል መጋቢት 15 ቀን ግጭት ተፈጥሯል። የፖሊስ መኮንኖቹ በቱርክ የሰለጠነው ልዩው የሃርማድ የፖሊስ ኃይል አባላት ነበሩ። ከዚህ በፊት መንግሥት ፍላጎቱን በክልል መንግሥታት ላይ ለመጫን ልዩ ኃይሉን ይጠቀም ነበር። የቀድሞው የሞቃዲሾ የፖሊስ አዛዥ ሳዲቅ ኦማር ሃሰን (ሳዳቅ ጆን) በምርጫ ውዝግብ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀውን የፓርላማ ስብሰባ በማገድ እአአ ሚያዝያ 13 ፊታቸውን መንግሥት ላይ አዞሩ። ከኃላፊነት ተነስተው ማዕረጋቸውም ተገፈፈ። የቀድሞው የፖሊስ አዛዥ ከቀናት በኋላ በጎበዝ አለቆች እና ከጎሳቸው በተገኙ ሚሊሺያዎች እየተጠበቁ በከተማው በዳይናል አካባቢ ካምፕ መሠረቱ። መንግሥት የታጠቁ የጸጥታ ኃይሎችን በአቅራቢያው ወደሚገኙ አካባቢዎች በማሰማራቱ ውጥረቱ ዋና ከተማዋን አዳርሷል። በኋላ ላይ ሁኔታው ተረጋጋ። በፋርማጆ ላይ የተጀመረው አዲስ አመጽ የጎሳ ጦርነት ቀስቅሶ አገሪቱን በቀላሉ ወደ የእርስ በእርስ ግጭት እንዳያስገባ ያሰጋል። የፖለቲካ እና የደኅንነት አንድምታዎች የአልሻባብ ታጣቂዎች በ2011 ከሞቃዲሾ ከተባረሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦርነት ድባብ በከተማዋ ሰፍሯል። ጂሃዳዊው ቡድን ከአብዛኞቹ ዋና ዋና ከተሞች ተጠራርጎ ተባሯል። ብሔራዊው ጦር፣ በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ልዑክ እና በአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ ጥረት ቢያደረጉም ቡድኑም አሁንም በማዕከላዊ እና በደቡባዊ ክልሎች ኃይሉ እንዳለ ነው። አል-ሸባብ በሞቃዲሾ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽሟል። የተፈጠረውን ሁከት በመጠቀምም እንቅስቃሴዎቹን ለማጠናከር ሊጠቀምበት ይችላል። እንደመገናኛ ብዙሃን ከሆነ አዲስ ጉዳት የደረሰባቸው ሕንፃዎች፣ ታንኮች እና የጦር ተሽከርካሪዎች ላይ የታጠቁ ወታደሮች እና ዋና ዋና መንገዶች ተዘግተዋል። በግል በሚተዳደረው ራዲዮ ኩልሚዬ የሚሠራ አንድ ጋዜጠኛ እንደተናገረው፤ ትራፊክ እና የማዘጋጃ ቤት ፖሊሶች በጎዳናዎች የሉም። የአል-ሸባብ ጥቃትን ለመከላከል በዋና ዋና መንገዶች ላይ የተተከሉ የደኅንነት ካሜራዎችም ወድመዋል። በትጥቅ የተደገፈው አመጽ የፕሬዚዳንት ፋርማጆን የእውቅና ጥያቄ የከድጡ ወደ ማጡ የወሰደው ሲሆን፤ በምርጫ ውዝግብ ላይ የተከፈተውን የውይይት መስኮትም የሚዘጋ ነው።
ምርጫን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የሶማሊያ ውዝግብ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ያመራ ይሆን? በሶማሊያ ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ መዘግየቱ አለመግባባትን እና በፖለቲከኞች መካከል አለመተማመንን አባብሷል። ይህንንም ተከትሎ በመዲናዋ ሞቃዲሾ የሰዎች ሕይወት የጠፋበት አመጽ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አገሪቱን ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። በመዲናዋ ሞቃዲሾ በፌዴራል ኃይሎች እና በታጠቁ የተቃዋሚ ታማኝ ኃይሎች መካከል ከቀናት በፊት በተነሳ ግጭት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱ ይቀጥላል በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች 'ሠላማዊ' ወደሚሏቸው መንደሮች ተሰደዋል። ክፍተቱ ለአል-ሻባብ የአፍሪካ ቀንዷን አገር የበለጠ ለማተራመስ መልካም አጋጣሚ ሊሆነው ይችላል። ታጣቂዎቹ ከቅርብ ወራት ወዲህ ብቻ በምርጫው ዙሪያ ውይይቶች በተካሄዱባቸው ቦታዎች ላይ በርካታ ጥቃቶችን አካሂደዋል። የአገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት የፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆን የስልጣን ዘመን በሁለት ዓመት ይራዘም ሲል ወሰነ። ከሁለት ሳምንት በፊት ከተላለፈው ውሳኔ በኋላ የአገሪቱ የፖለቲካ ክፍተቶች ተባብሰዋል። ከወራት ውይይቶች በኋላ ውሳኔው ሲጸድቅ የፌዴራል መንግሥቱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሕዝባዊ ምርጫዎችን እንዲያደራጅ ቢያዝም የአገሪቱን የምርጫ ቀውስ ማስቆም አልቻለም። የሶማሊያ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች የሥልጣን ማራዘሙን ውድቅ በማድረግ ፋርማጆን ሥልጣንን የሙጥኝ ብለዋል ሲሉ ከሰዋል። የተነሳባቸው ተቃውሞና ሊከተል የሚችለው ቀውስ ያሰጋቸው ፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ዘመናቸውን የማራዘም ፍላጎታቸውን እንዲተዉ አስገድዷቸዋል። ነገር ግን ውጥረቱ በጎሳ ፉክክር ይበልጥ እየከረረ ነው። ከአስርት ዓመታት የእርስ በእርስ እና የታጣቂዎች ግጭት በኋላ የተገኘውን አንፃራዊ መረጋጋት ሊቀለበስ የሚችልም ነው። ቁልፍ ተዋናዮች እና ምላሾች ተቃዋሚዎች የፋርማጆ ሥልጣን የካቲት 8 ስላበቃ ከእንግዲህ ለፕሬዝዳንትነታቸውን እውቅና አንሰጥም ብለዋል። ናሽናል ሳልቬሽን ፎረም (ብሔራዊ አገርን የማዳኛ መድረክ እንደማለት ነው) ተቋቁሟል። ፎረሙ ተሰሚ በሆኑ ተቃዋሚዎች የተቋቋመ ነው። የፋርማጆ ቀንደኛ ተቃዋሚ የሆኑት የምክር ቤት አፈ ጉባኤ አብዲ ሀሺ አብዱላሂ፣ የጁባላንድ እና ፑንትላንድ መሪዎችን ያካተተ ጥምረት ነው። ሕገ መንግሥታዊ ባልሆነው የሥልጣን ማራዘሚያ ላይ "አስፈላጊ እርምጃዎችን እንወስዳለን" ሲሉም ዝተዋል። የሴኔቱ አፈ ጉባኤ አብዱላሂ እንዳሉት፤ ፕሬዚዳንቱ የውሳኔ ሐሳቡን ለማጽደቅ የላይኛውን ምክር ቤት ሳያቀርቡ ማራዘማቸው ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ነው። የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒ እና የጁባው አቻቸው አህመድ መሐመድ ኢስላም በሞቃዲሾ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ነበር። "ሶማሊያን ከማይቀረው የትርምስ አዘቅት ውስጥ እንዳትገባ እንዲያድኑ" ጠይቀዋል። የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ምክር ቤት ፋርማጆን ለመተካት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ጥምረት ነው። በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሻሪፍ ሼህ አህመድ የሚመራ ሲሆን ፕሬዚዳንቱን "የጦር አበጋዝ" ብለዋቸዋል። የሃውያ ንዑስ ጎሳ አባላት ተደማጭነት ካላቸው ጎሳዎች መካከል ነው። ለአንድ ቀን በመዲናዋ ሞቃዲሾ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ ሥልጣን የማራዘሙን ውሳኔ ውድቅ አድርገውታል። አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና የአውሮፓ ሕብረት ሥልጣን የማራዘሙ ውሳኔ ሶማሊያ ወደ ሰላምና መንግሥት ግንባታ የምታደርገውን ጉዞ የሚያደናቅፍ ነው ብለዋል። ግንኙነታቸውን በድጋሚ እንደሚያጤኑትም አስጠንቅቀዋል። አሜሪካ "ሰላምና መረጋጋትን በማደናቀፍ" በሥልጣን ማራዘሙ በተሳተፉት ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል ዝታለች። የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ሥልጣን ማራዘሙን ውድቅ አድርጎታል። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ መሪዎች በምርጫ ውዝግቡ ዙሪያ ውይይት እንዲቀጥሉ ያቀረበውን ሐሳብ እንደሚደግፍ አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ከፍተኛ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም በታችኛው ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴዎች እና በጋልሙዱግ፣ በሂውማሌ እና በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ሰፊ ድጋፍ አላቸው፡፡ በቋፍ ላይ ያለ የፌዴራል ሥርዓት የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሥርዓት ሥር የሰደደውን የጎሳ ግጭት ለማቆም እና የአንድነት መንግሥት ለመመስረት የሚደረገውን ጥረት በመሰናከሉ የተመሠረተ ነው። ይህን ተከትሎም የተቆራረጠ እና ደካማ ቢሆንም ብሔራዊ ደኅንነት ግንባታው እያዘገመም ቢሆን እንዲጓዝ መንገዱን ጠርጓል። አገሪቱ ከ30 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት ሥርዓት ለመቀላቀል የፋይናንስ ተቋማቷን እንደገና አደራጅታለች። ምርጫው ያስከተለው አለመረጋጋት በማዕከላዊ መንግሥት እና ቀድሞውንም የፋርማጆን ሥልጣን 'በሚያኮስሱት' አንዳንድ የክልል መንግሥታት መካከል ውዝግቡን አጡዞታል። እአአ በመስከረም 2018 አምስት የአገሪቱ የክልል ፕሬዚዳንቶች በሥልጣን እና በሀብት ክፍፍል አለመግባባት ምክንያት ከፌዴራል መንግሥት ጋር እንደማይተባበሩ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ለምላሽ አልዘገዩም። ክልሎችን በራሳቸው ቁጥጥር ስር ማድረግ ጀመሩ። ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን በመንቀል አጋሮቻቸውን በጋልሙዱግ እና በደቡብ ምዕራብ ግዛቶች አስቀመጡ። የፌዴራሉ መንግሥት በፑንትላንድ እና በጁባላንድ ባሉ ምርጫዎች ላይ ተመሳሳይ ተጽዕኖ ማሳደር አልቻለም። የእነዚህ አካባቢ መሪዎች ፋርማጆ እንደገና እንዳይመረጡ እየሠሩ ነው። የፖለቲካ ህልውናቸው የተመሠረተው በዚሁ ላይ ነው። የመስከረም 17ቱ ስምምነት ብሔራዊው የምርጫ ኮሚሽን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያለው ሕዝባዊ ምርጫ ለማድረግ እንደማይቻል አስታውቋል። ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ለማዘጋጀት እስከ 13 ወር ድረስ እንደሚያስፈልገው እአአ ሰኔ 2020 ለሕዝብ እንደራሴዎች ገልጿል። የጁባላንድ፣ ፑንትንትላንድ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫውን መዘግየት ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም። እአአ ሐምሌ 2020 አስደንጋጭ ነበር የተባለለት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ኬይሬ ከሥልጣን መነሳት በምርጫው ሂደት ላይ ያላቸውን እምነት ይባስ ሸረሸረው። የጁባላንድ እና የፑንትላንድ መሪዎች በማዕከላዊው ዱሳማሬብ ከተማ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። በስብሰባው ላይ ከምርጫ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ስምምነት ተደርሷል። የአማጺያኑ አመራሮች አድሏዊ ነው ሲሉ የምርጫ ኮሚሽኑ እንዲፈርስ ጠይቀዋል። እአአ መስከረም 17 ቀን 2020 ከሳምንታት የዓለም አቀፍ ግፊት በኋላ በምርጫ ሁኔታዎች ላይ ስምምነት ተፈረመ። በስምምነቱ መሠረት ሁለት የምርጫ ክልሎች በእያንዳንዱ ክልል ይኖራሉ። ምርጫዎች የሚካሄዱት በየክልል ተሰብሳቢዎች ላይ ተመስርቶ ሲሆን በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ውስጥ 101 የምርጫ ልዑካን ድምጽ ይሰጣሉ። በአማጽያን ጥያቄ መሠረት ምርጫውን በበላይነት የሚቆጣጠር ብሔራዊ እና ክልላዊ የምርጫ ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ ተወሰነ። የጁባላንዱ ማዶቤ እና የፑንትላንዱ ዴኒ በፌዴራል መንግስት የተቋቋመውን የምርጫ ኮሚሽን ባለመቀበላቸው የስምምነቱ ትግበራ እንቅፋት ገጠመው። የጸጥታ አዛዦች እንዲነሱ እና ፓርላማው እንዲበተንም ጠይቀዋል። የምርጫውን መዘግየት አስቀድሞ የገመተው የፌዴራሉ ፓርላማ እአአ ኅዳር 2020 አዲስ ተመራጮች እስኪተኩ ድረስ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል። የዘር ፖለቲካ እና ግጭት በምርጫው ላይ በተፈጠረው ክፍፍል ላይ ብሔራዊ ማንነት እና የጎሳ ማንነት ልዩነትም ሚና ተጫውተዋል። አለመተማመን እየጠነከረ ሲሄድ ፖለቲከኞች እና ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናት ወደ ጎሳቸው መመሸግ ጀመሩ። እነዚህም በጎሳ ሚሊሻዎች፣ በጎበዝ አለቆች እና በቀድሞ የጦር መሪዎች የሚጠበቁ ናቸው። የተወሰኑ የተቃዋሚ የፓርቲ አመራሮች ለትጥቅ ትግል መዘጋጀት ያዙ። የጦር መሣሪያዎችና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የገዙም አሉ። በመዲናዋ ሞቃዲሾ የዘገየውን ምርጫ የሚቃወሙ ሰልፈኞችን በሚደግፉ ወታደሮች እና በፖሊስ መካከል መጋቢት 15 ቀን ግጭት ተፈጥሯል። የፖሊስ መኮንኖቹ በቱርክ የሰለጠነው ልዩው የሃርማድ የፖሊስ ኃይል አባላት ነበሩ። ከዚህ በፊት መንግሥት ፍላጎቱን በክልል መንግሥታት ላይ ለመጫን ልዩ ኃይሉን ይጠቀም ነበር። የቀድሞው የሞቃዲሾ የፖሊስ አዛዥ ሳዲቅ ኦማር ሃሰን (ሳዳቅ ጆን) በምርጫ ውዝግብ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀውን የፓርላማ ስብሰባ በማገድ እአአ ሚያዝያ 13 ፊታቸውን መንግሥት ላይ አዞሩ። ከኃላፊነት ተነስተው ማዕረጋቸውም ተገፈፈ። የቀድሞው የፖሊስ አዛዥ ከቀናት በኋላ በጎበዝ አለቆች እና ከጎሳቸው በተገኙ ሚሊሺያዎች እየተጠበቁ በከተማው በዳይናል አካባቢ ካምፕ መሠረቱ። መንግሥት የታጠቁ የጸጥታ ኃይሎችን በአቅራቢያው ወደሚገኙ አካባቢዎች በማሰማራቱ ውጥረቱ ዋና ከተማዋን አዳርሷል። በኋላ ላይ ሁኔታው ተረጋጋ። በፋርማጆ ላይ የተጀመረው አዲስ አመጽ የጎሳ ጦርነት ቀስቅሶ አገሪቱን በቀላሉ ወደ የእርስ በእርስ ግጭት እንዳያስገባ ያሰጋል። የፖለቲካ እና የደኅንነት አንድምታዎች የአልሻባብ ታጣቂዎች በ2011 ከሞቃዲሾ ከተባረሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦርነት ድባብ በከተማዋ ሰፍሯል። ጂሃዳዊው ቡድን ከአብዛኞቹ ዋና ዋና ከተሞች ተጠራርጎ ተባሯል። ብሔራዊው ጦር፣ በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ልዑክ እና በአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ ጥረት ቢያደረጉም ቡድኑም አሁንም በማዕከላዊ እና በደቡባዊ ክልሎች ኃይሉ እንዳለ ነው። አል-ሸባብ በሞቃዲሾ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽሟል። የተፈጠረውን ሁከት በመጠቀምም እንቅስቃሴዎቹን ለማጠናከር ሊጠቀምበት ይችላል። እንደመገናኛ ብዙሃን ከሆነ አዲስ ጉዳት የደረሰባቸው ሕንፃዎች፣ ታንኮች እና የጦር ተሽከርካሪዎች ላይ የታጠቁ ወታደሮች እና ዋና ዋና መንገዶች ተዘግተዋል። በግል በሚተዳደረው ራዲዮ ኩልሚዬ የሚሠራ አንድ ጋዜጠኛ እንደተናገረው፤ ትራፊክ እና የማዘጋጃ ቤት ፖሊሶች በጎዳናዎች የሉም። የአል-ሸባብ ጥቃትን ለመከላከል በዋና ዋና መንገዶች ላይ የተተከሉ የደኅንነት ካሜራዎችም ወድመዋል። በትጥቅ የተደገፈው አመጽ የፕሬዚዳንት ፋርማጆን የእውቅና ጥያቄ የከድጡ ወደ ማጡ የወሰደው ሲሆን፤ በምርጫ ውዝግብ ላይ የተከፈተውን የውይይት መስኮትም የሚዘጋ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/56916800
2health
በኢትዮጵያ የተካሄደው እና አስር ባለሙያዎች የተሳተፉበት ተደራራቢ የልብ ቀዶ ሕክምና
የልብ ቀዶ ህክምና ከፍ ያለ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ህክምና ሲሆን በተለይ ተደራራቢ ችግር ሲኖር ደግሞ ሥራው በእጅጉ የተወሳሰበ ስለሚሆን ከፍ ያለ ልምድና ቴክኖሎጂ ባላቸው አገራት ውስጥ እንዲካሄድ ይመከራል። ሰኞ እሁድ 18/2013 ዓ.ም ከዚህ በፊት 'ኢትዮጵያ ውስጥ አልተደረገም' የተባለ እና ስድስት ሰዓታትን የፈጀ የልብ ቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኤሎዚየር የልብ ህክምና ማዕከል ውስጥ በአንድ ጊዜ ሁለት የቀዶ ህክምናው የተደረገላቸው ግለሰብ የ55 ዓመት ጎልማሳ ናቸው። በህመምተኛው ግለሰብ ልብ ላይ በአንድ ጊዜ የተሰራው ሁለት ቀዶ ህክምና ሲሆን፣ አንደኛው የልብ የደም ቧንቧዎች በሚዘጉበት ጊዜ የደም ቧንቧን ከሌላ የሰውነት ክፍል በመውሰድ የተዘጋው ቦታ ላይ በመተካት የተከናወነ የልብ የደም ስር ነቅሎ መትከል (ሲኤቢጂ) ነው። ሌላኛው ደግሞ 'ኦርቲክ ቫልቭ' ወይም ደግሞ አንደኛው የግራ የልብ ክፍል በር ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ደም ከቀኝ የልብ ክፍል ወደ አኦርታ (Aorta) መውጣት ሲቸገር የልብ በር ቀዶ ህክምና (ቫልቭ) የሚባለው ነው። በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተከናወነው ይህንን ስኬታማ የቀዶ ህክምና ካከናወኑት ሐኪሞች መካከል አንዱና በኢትዮጵያ የልብ ሕክምና ማዕከል ውስጥ የሚሰሩት ዶ/ር ፈቃደ አግዋር ለቢቢሲ እንደተናገሩት "እነዚህን ሁለት ቀዶ ህክምናዎች እኚህ ግለሰብ ላይ በአንድ ጊዜ ተደርገዋል። ይህ በቀዶ ሕክምና ሙያ በጣም ትልቅ የሚባል ስኬት ነው። ቀዶ ህክምናው በአገራችን ባለሙያዎች ሲሰራ የመጀመሪያው ነው።" ለስድስት ሰዓታት የተካሄደውን የቀዶ ህክምና ሂደት የመሩት ዶ/ር ፈቃደ እንደሚሉት አሁን በአንድ ህመምተኛ ላይ በአንድ ጊዜ የተከናወነው ቀዶ ህክምና በተናጠል ከሚሰራው ውስብስብና አስቸጋሪ ነው። በዚህ ሂደት ሁለቱን ቀዶ ህክምናዎች በአንድ ልብ ላይ ሲሰራ የልብንና የሳንባን ሥራ ተክቶ የሚሰራው ማሽን አገልግሎቱን አብቅቶ ወደተፈጥሯዊው ሂደት ሲመለስ እንዴት ይሆናል? የሚለው ዋነኛው አሳሳቢ ጉዳይ ሲሆን ባለሙያዎቹም አስፈላጊውን ጥንቃቄና ክትትል አድርገዋል። ይህ ተደራራቢ ቀዶ ህክምና አደጋን የሚያስከትል በመሆኑ እያንዳንዱን ለውጥ ባለሙያዎቹ በቅርበት ሲከታተሉት ነበር። "ከኦፕራሲዮን ስንወጣ ሐዘን ይዘን ልንወጣ እንችላለን። የማይነሳ ልብ ሊሆን ይችላል። በ24 ሰዓት ውስጥ ማንኛውም አደገኛ ነገር ሊከሰት ይችላል። ይህንን ሁሉ ነገር ከአዕምሯችን ጓዳ ውስጥ አድርገን ነበር የሰራው። ነገር ግን ሁሉም ነገሮች አልተከሰቱም" ብለዋል ዶ/ር ፈቃደ። ከመነሻው ቀዶ ህክምናው እስከ ሰባት ሰዓት የሚደርስ ጊዜን ሊወስድ ይችላል ተብሎ የታሰበ ቢሆንም በስድስት ሰዓታት ውስጥ በስኬት መጠናቀቁ ተነግሯል። ይህ እጅግ ከፍ ያለ ጥንቃቄን የሚፈልገው ተደራራቢ የልብ ቀዶ ህክምና ሂደት ሲከናወን ውጥረት የተሞላበት ቢሆንም ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠማቸው ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። "ምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ አልተፈጠረም ነበር። ጮክ ብለን እንኳን የተነጋገርንበት ጊዜ እንኳ አልነበረም። በስድስት ሰዓቱ ውስጥ በተቻለን አቅም ተረጋገግተን የአስቴር ዘፈንን እየሰማን ነበር የሰራነው" ብለዋል ዶ/ር ፈቃደ። የልብ ቀዶ ህክምና በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ህክምና መከናወን ከተጀመረ ጥቂት ዓመታት ብቻ ነው የተቆጠሩት። ከዚያ ውጪ ልብ ቀዶ ህክምና ይከናወን የነበረው ከውጪ አገር በሚመጡ ባለሙያዎች በተመላላሽነት፣ ለአጭር ጊዜ ነበር። የልብ ቀዶ ህክምና በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ሲከናወንባቸው በቆዩት አራት ዓመታት ውስጥ፣ አሁን በአንድ ጊዜ በተሳካ ሁኔታ በአንድ የልብ ታማሚ ላይ የተደረገው ቀዶ ህክምና ተደርጎ አይታወቅም። ነገር ግን ሁለቱንም ቀዶ ህክምናዎች በተናጠል ሲከናወኑ መቆየታቸውን ያስታወሱት ዶ/ር ፈቃደ፣ ሁለቱንም አንድ ላይ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ልምዱ ስላልነበረና ውስብስብ በመሆኑ ሳይደረግ መቆየቱን ይናገራሉ። ስለዚህም እንዲህ አይነቱ ተደራራቢ ቀዶ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎችም የነበራቸው አማራጭ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ወደ ውጪ አገር ሂዶ መታከም ነበር። ለዚህም ከ50 ሺህ ዶላር በላይ መክፈልን ይጠይቃል። በርካታ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ ተደራራቢ የልብ ችግር ሲያጋጥማቸው ህክምና ለማግኘት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ወደ ሕንድ፣ ቱርክና ታይላንድ ይሄዳሉ። ዶ/ር ፈቃደ እንደሚሉት በስኬት የተከናወነው ቀዶ ህክምና ለዘርፉ ታላቅ ዕመርታ ነው "የመጀመሪያው የቀዶ ህክምና ፈተናዎች ይኖሩታል። ነገር ግን አንድ ጊዜ በስኬት ከተከናወነ ለቀጣይ ህክምና መንገዱ ይከፈታል" በማለት ሰዎች ህክምናውን ለማግኘት ወደ ውጭ አገር መሄድ አይጠበቅባቸውም ብለዋል። የልብ ህመም በኢትዮጵያ ከአኗኗር ዘይቤ መለወጥ ጋር ተያይዞ ተላላፊ ካልሆኑ የጤና ዕክሎች መካከል የሚጠቀሱት የልብ ህመሞች እየተስፋፉ መሆናቸው ይነገራል። በተለይ ከፍ ያለ ሙያ፣ ጥንቃቄና ወጪን የሚጠይቁት የልብ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መሆናቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ። በኢትዮጵያም የተለያዩ የልብ ችግሮች የሚያጋጥማቸው ሰዎች ቁጥር ቀላል የሚባል እንዳልሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ፈቃደ፣ በስፋት የሚያጋጥመው ዋነኛው የልብ ቫልቭ ችግር መሆኑን ይገልጻሉ። የልብ በሮች መጥበብ ወይም ወደ ኋላ ማፍሰስ ደግሞ ሌላኛው እክል ነው። በተጨማሪም "የልብ የደም ቧንቧዎች መደፈን በአሁኑ ወቅት እየበዛ የመጣ ነው" ሲሉ ያክላሉ። "ከደም ግፊት እና ከስኳር ህመም ጋር ተያይዞ የሚመጣ የልብ የደም ስሮች መዘጋት ወይም ደግሞ 'ኮሮናሪ አርተሪ ዲዚዝ' የምንለው በአሁኑ ወቅት እየጨመረ ይገኛል።" የተሳካው ቀዶ ህክምና የተደረገላቸው ታካሚ ላይ ሁለት ተደራራቢ የልብ ችግሮች በአንድ ላይ በመከሰታቸው ችግሩን የተወሳሰበ በማድረግ ታማሚውን ለከፍተኛ ችግር እንዳጋለጣቸው ዶ/ር ፈቃደ ይናገራሉ። በ55 ዓመቱ ጎልማሳ ላይ በተደራራቢነት ያጋጠሙት የልብ ችግሮች በተለያዩ ሰዎች ላይ በተናጠል መከሰታቸው የተለመደ መሆኑን ሕክምና ባለሙያው ያስረዳሉ። ነገር ግን ሁለቱም አንድ ታካሚ ላይ በተደራራቢነት መከሰታቸው አልፎ አልፎ የሚያጋጥ ነው ሲሉም አክለዋል። ታካሚውና ቤተሰባቸው ታማሚው ወደ ህክምና ሲመጡ የገጠማቸው የልብ ችግር አንድ ብቻ እንደሆነ ነበር ያሰቡት። ነገር ግን ሐኪሞቹ ሰፋ ያለ ምርመራ ሲያደርጉ ሌላ ተደራቢ ችግር መኖሩ ተረዱ። ያለውን ሁኔታ የተገነዘቡት የታማሚው ቤተሰቦቹ ሁለቱንም ችግሮች በአንድ ጊዜ በቀዶ ህክምና ማስተካከል እንደሚያስፈልግ በተነገራቸው ጊዜ "እውነታውን ተቀብለው እምነታቸውን በእኛ ላይ ጣሉ" ይላሉ ዶ/ር ፈቃደ። ቀዶ ህክምናው ከቀኑ 8 ሰዓት ተጀምሮ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ተጠናቀቀ። ታካሚውም ከኦፕራሲዮኑ ከወጡ በኋላ በ4 ሰዓት ውስጥ መንቃት ቻሉ። "ሲቀጥልም ሰውነታቸው ሙሉ በሙሉ እንደሚሰራ ካረጋገጥን በኋላ ማሽኑን ከሰውነታቸው መንቀል ችለናል። በሚቀጥለው 24 ሰዓት ውስጥም ያስገባናቸውን ጎማዎች ሙሉ በሙሉ በማስወጣት ከአልጋ እንዲወጡ ተደረገ" ይላሉ ዶ/ር ፈቃደ። "ሁሉም ነገር የተሳካ ነበር። ታካሚውም ያስገባንላቸው ሁሉም ጎማዎች ወጥተውላቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመሳሳቅ እና ለመጨዋወት በቁ" በማለት የቀዶ ህክምናውን ስኬት በደስታ ይገልጹታል። ባለሙያዎች እንደሚሉእት ደረት ተከፍቶ የልብ ቀዶ ህክምና ከተደረገ በኋላ አጥንት እስኪገጥም ድረስ 12 ሳምንት ይፈልጋል። ታካሚው በሰባት ቀናት ውስጥ ከሆስፒታል እንደሚወጡና ምናልባት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው ይመለሳሉ። የመጨረሻው ስኬት ይህ የልብ የቀዶ ጥገና በርካታ ሙያተኞች የተሳተፉበት ተግባር ነበር። የልብ ቀዶ ህክምና ሐኪም፣ የልብ ቀዶ ህክምና አጋዥ፣ ሰመመን ሰጪ ሐኪሞች፣ የልብና የሳንባን ሥራ ተክቶ የሚሰራውን ማሽን የሚያንቀሳቅሱ ባለሞያዎች እና ሌሎችም በቡድኑ ውስጥ የተካተቱ ናቸው። በአጠቃላይ ከ10 በላይ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች ተሳትፈውበታል። በዚህ በአገሪቱ ውስጥ ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው በተባለው የተሳካ ተደራራቢ የልብ ቀዶ ህክምና የተሳተፉት ባለሙያዎች ሥራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ታካሚያቸው በደህና ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል። በዚህም ታካሚውን ከቀዶ ህክምና ጠረጴዛ ላይ አስነስተው የልብ ምታቸውን፣ የልብ የደም ግፊት መጠናቸውን፣ የሽንት በበቂ ሁኔታ መምጣትን፣ የልብ የኤሌክትሪካዊ ተግባርን፣ የሳንባ የኦክስጂን አቀባበል እና የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት መወሰን ነበር። "በሚገርም ሁኔታ እኚህ የመጀመሪያ ታካሚያችን የልባቸውን ሥራ የሚያግዝ ምንም አይነት መድኃኒት አላስፈለጋቸውም" የሚሉት ዶ/ር ፈቃደ "ስለዚህ በተመለከትነው ውጤት ስለተደሰትን አንድ ላይ ተቃቅፈን ፎቶ ተነሳን።"
በኢትዮጵያ የተካሄደው እና አስር ባለሙያዎች የተሳተፉበት ተደራራቢ የልብ ቀዶ ሕክምና የልብ ቀዶ ህክምና ከፍ ያለ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ህክምና ሲሆን በተለይ ተደራራቢ ችግር ሲኖር ደግሞ ሥራው በእጅጉ የተወሳሰበ ስለሚሆን ከፍ ያለ ልምድና ቴክኖሎጂ ባላቸው አገራት ውስጥ እንዲካሄድ ይመከራል። ሰኞ እሁድ 18/2013 ዓ.ም ከዚህ በፊት 'ኢትዮጵያ ውስጥ አልተደረገም' የተባለ እና ስድስት ሰዓታትን የፈጀ የልብ ቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኤሎዚየር የልብ ህክምና ማዕከል ውስጥ በአንድ ጊዜ ሁለት የቀዶ ህክምናው የተደረገላቸው ግለሰብ የ55 ዓመት ጎልማሳ ናቸው። በህመምተኛው ግለሰብ ልብ ላይ በአንድ ጊዜ የተሰራው ሁለት ቀዶ ህክምና ሲሆን፣ አንደኛው የልብ የደም ቧንቧዎች በሚዘጉበት ጊዜ የደም ቧንቧን ከሌላ የሰውነት ክፍል በመውሰድ የተዘጋው ቦታ ላይ በመተካት የተከናወነ የልብ የደም ስር ነቅሎ መትከል (ሲኤቢጂ) ነው። ሌላኛው ደግሞ 'ኦርቲክ ቫልቭ' ወይም ደግሞ አንደኛው የግራ የልብ ክፍል በር ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ደም ከቀኝ የልብ ክፍል ወደ አኦርታ (Aorta) መውጣት ሲቸገር የልብ በር ቀዶ ህክምና (ቫልቭ) የሚባለው ነው። በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተከናወነው ይህንን ስኬታማ የቀዶ ህክምና ካከናወኑት ሐኪሞች መካከል አንዱና በኢትዮጵያ የልብ ሕክምና ማዕከል ውስጥ የሚሰሩት ዶ/ር ፈቃደ አግዋር ለቢቢሲ እንደተናገሩት "እነዚህን ሁለት ቀዶ ህክምናዎች እኚህ ግለሰብ ላይ በአንድ ጊዜ ተደርገዋል። ይህ በቀዶ ሕክምና ሙያ በጣም ትልቅ የሚባል ስኬት ነው። ቀዶ ህክምናው በአገራችን ባለሙያዎች ሲሰራ የመጀመሪያው ነው።" ለስድስት ሰዓታት የተካሄደውን የቀዶ ህክምና ሂደት የመሩት ዶ/ር ፈቃደ እንደሚሉት አሁን በአንድ ህመምተኛ ላይ በአንድ ጊዜ የተከናወነው ቀዶ ህክምና በተናጠል ከሚሰራው ውስብስብና አስቸጋሪ ነው። በዚህ ሂደት ሁለቱን ቀዶ ህክምናዎች በአንድ ልብ ላይ ሲሰራ የልብንና የሳንባን ሥራ ተክቶ የሚሰራው ማሽን አገልግሎቱን አብቅቶ ወደተፈጥሯዊው ሂደት ሲመለስ እንዴት ይሆናል? የሚለው ዋነኛው አሳሳቢ ጉዳይ ሲሆን ባለሙያዎቹም አስፈላጊውን ጥንቃቄና ክትትል አድርገዋል። ይህ ተደራራቢ ቀዶ ህክምና አደጋን የሚያስከትል በመሆኑ እያንዳንዱን ለውጥ ባለሙያዎቹ በቅርበት ሲከታተሉት ነበር። "ከኦፕራሲዮን ስንወጣ ሐዘን ይዘን ልንወጣ እንችላለን። የማይነሳ ልብ ሊሆን ይችላል። በ24 ሰዓት ውስጥ ማንኛውም አደገኛ ነገር ሊከሰት ይችላል። ይህንን ሁሉ ነገር ከአዕምሯችን ጓዳ ውስጥ አድርገን ነበር የሰራው። ነገር ግን ሁሉም ነገሮች አልተከሰቱም" ብለዋል ዶ/ር ፈቃደ። ከመነሻው ቀዶ ህክምናው እስከ ሰባት ሰዓት የሚደርስ ጊዜን ሊወስድ ይችላል ተብሎ የታሰበ ቢሆንም በስድስት ሰዓታት ውስጥ በስኬት መጠናቀቁ ተነግሯል። ይህ እጅግ ከፍ ያለ ጥንቃቄን የሚፈልገው ተደራራቢ የልብ ቀዶ ህክምና ሂደት ሲከናወን ውጥረት የተሞላበት ቢሆንም ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠማቸው ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። "ምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ አልተፈጠረም ነበር። ጮክ ብለን እንኳን የተነጋገርንበት ጊዜ እንኳ አልነበረም። በስድስት ሰዓቱ ውስጥ በተቻለን አቅም ተረጋገግተን የአስቴር ዘፈንን እየሰማን ነበር የሰራነው" ብለዋል ዶ/ር ፈቃደ። የልብ ቀዶ ህክምና በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ህክምና መከናወን ከተጀመረ ጥቂት ዓመታት ብቻ ነው የተቆጠሩት። ከዚያ ውጪ ልብ ቀዶ ህክምና ይከናወን የነበረው ከውጪ አገር በሚመጡ ባለሙያዎች በተመላላሽነት፣ ለአጭር ጊዜ ነበር። የልብ ቀዶ ህክምና በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ሲከናወንባቸው በቆዩት አራት ዓመታት ውስጥ፣ አሁን በአንድ ጊዜ በተሳካ ሁኔታ በአንድ የልብ ታማሚ ላይ የተደረገው ቀዶ ህክምና ተደርጎ አይታወቅም። ነገር ግን ሁለቱንም ቀዶ ህክምናዎች በተናጠል ሲከናወኑ መቆየታቸውን ያስታወሱት ዶ/ር ፈቃደ፣ ሁለቱንም አንድ ላይ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ልምዱ ስላልነበረና ውስብስብ በመሆኑ ሳይደረግ መቆየቱን ይናገራሉ። ስለዚህም እንዲህ አይነቱ ተደራራቢ ቀዶ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎችም የነበራቸው አማራጭ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ወደ ውጪ አገር ሂዶ መታከም ነበር። ለዚህም ከ50 ሺህ ዶላር በላይ መክፈልን ይጠይቃል። በርካታ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ ተደራራቢ የልብ ችግር ሲያጋጥማቸው ህክምና ለማግኘት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ወደ ሕንድ፣ ቱርክና ታይላንድ ይሄዳሉ። ዶ/ር ፈቃደ እንደሚሉት በስኬት የተከናወነው ቀዶ ህክምና ለዘርፉ ታላቅ ዕመርታ ነው "የመጀመሪያው የቀዶ ህክምና ፈተናዎች ይኖሩታል። ነገር ግን አንድ ጊዜ በስኬት ከተከናወነ ለቀጣይ ህክምና መንገዱ ይከፈታል" በማለት ሰዎች ህክምናውን ለማግኘት ወደ ውጭ አገር መሄድ አይጠበቅባቸውም ብለዋል። የልብ ህመም በኢትዮጵያ ከአኗኗር ዘይቤ መለወጥ ጋር ተያይዞ ተላላፊ ካልሆኑ የጤና ዕክሎች መካከል የሚጠቀሱት የልብ ህመሞች እየተስፋፉ መሆናቸው ይነገራል። በተለይ ከፍ ያለ ሙያ፣ ጥንቃቄና ወጪን የሚጠይቁት የልብ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መሆናቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ። በኢትዮጵያም የተለያዩ የልብ ችግሮች የሚያጋጥማቸው ሰዎች ቁጥር ቀላል የሚባል እንዳልሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ፈቃደ፣ በስፋት የሚያጋጥመው ዋነኛው የልብ ቫልቭ ችግር መሆኑን ይገልጻሉ። የልብ በሮች መጥበብ ወይም ወደ ኋላ ማፍሰስ ደግሞ ሌላኛው እክል ነው። በተጨማሪም "የልብ የደም ቧንቧዎች መደፈን በአሁኑ ወቅት እየበዛ የመጣ ነው" ሲሉ ያክላሉ። "ከደም ግፊት እና ከስኳር ህመም ጋር ተያይዞ የሚመጣ የልብ የደም ስሮች መዘጋት ወይም ደግሞ 'ኮሮናሪ አርተሪ ዲዚዝ' የምንለው በአሁኑ ወቅት እየጨመረ ይገኛል።" የተሳካው ቀዶ ህክምና የተደረገላቸው ታካሚ ላይ ሁለት ተደራራቢ የልብ ችግሮች በአንድ ላይ በመከሰታቸው ችግሩን የተወሳሰበ በማድረግ ታማሚውን ለከፍተኛ ችግር እንዳጋለጣቸው ዶ/ር ፈቃደ ይናገራሉ። በ55 ዓመቱ ጎልማሳ ላይ በተደራራቢነት ያጋጠሙት የልብ ችግሮች በተለያዩ ሰዎች ላይ በተናጠል መከሰታቸው የተለመደ መሆኑን ሕክምና ባለሙያው ያስረዳሉ። ነገር ግን ሁለቱም አንድ ታካሚ ላይ በተደራራቢነት መከሰታቸው አልፎ አልፎ የሚያጋጥ ነው ሲሉም አክለዋል። ታካሚውና ቤተሰባቸው ታማሚው ወደ ህክምና ሲመጡ የገጠማቸው የልብ ችግር አንድ ብቻ እንደሆነ ነበር ያሰቡት። ነገር ግን ሐኪሞቹ ሰፋ ያለ ምርመራ ሲያደርጉ ሌላ ተደራቢ ችግር መኖሩ ተረዱ። ያለውን ሁኔታ የተገነዘቡት የታማሚው ቤተሰቦቹ ሁለቱንም ችግሮች በአንድ ጊዜ በቀዶ ህክምና ማስተካከል እንደሚያስፈልግ በተነገራቸው ጊዜ "እውነታውን ተቀብለው እምነታቸውን በእኛ ላይ ጣሉ" ይላሉ ዶ/ር ፈቃደ። ቀዶ ህክምናው ከቀኑ 8 ሰዓት ተጀምሮ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ተጠናቀቀ። ታካሚውም ከኦፕራሲዮኑ ከወጡ በኋላ በ4 ሰዓት ውስጥ መንቃት ቻሉ። "ሲቀጥልም ሰውነታቸው ሙሉ በሙሉ እንደሚሰራ ካረጋገጥን በኋላ ማሽኑን ከሰውነታቸው መንቀል ችለናል። በሚቀጥለው 24 ሰዓት ውስጥም ያስገባናቸውን ጎማዎች ሙሉ በሙሉ በማስወጣት ከአልጋ እንዲወጡ ተደረገ" ይላሉ ዶ/ር ፈቃደ። "ሁሉም ነገር የተሳካ ነበር። ታካሚውም ያስገባንላቸው ሁሉም ጎማዎች ወጥተውላቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመሳሳቅ እና ለመጨዋወት በቁ" በማለት የቀዶ ህክምናውን ስኬት በደስታ ይገልጹታል። ባለሙያዎች እንደሚሉእት ደረት ተከፍቶ የልብ ቀዶ ህክምና ከተደረገ በኋላ አጥንት እስኪገጥም ድረስ 12 ሳምንት ይፈልጋል። ታካሚው በሰባት ቀናት ውስጥ ከሆስፒታል እንደሚወጡና ምናልባት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው ይመለሳሉ። የመጨረሻው ስኬት ይህ የልብ የቀዶ ጥገና በርካታ ሙያተኞች የተሳተፉበት ተግባር ነበር። የልብ ቀዶ ህክምና ሐኪም፣ የልብ ቀዶ ህክምና አጋዥ፣ ሰመመን ሰጪ ሐኪሞች፣ የልብና የሳንባን ሥራ ተክቶ የሚሰራውን ማሽን የሚያንቀሳቅሱ ባለሞያዎች እና ሌሎችም በቡድኑ ውስጥ የተካተቱ ናቸው። በአጠቃላይ ከ10 በላይ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች ተሳትፈውበታል። በዚህ በአገሪቱ ውስጥ ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው በተባለው የተሳካ ተደራራቢ የልብ ቀዶ ህክምና የተሳተፉት ባለሙያዎች ሥራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ታካሚያቸው በደህና ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል። በዚህም ታካሚውን ከቀዶ ህክምና ጠረጴዛ ላይ አስነስተው የልብ ምታቸውን፣ የልብ የደም ግፊት መጠናቸውን፣ የሽንት በበቂ ሁኔታ መምጣትን፣ የልብ የኤሌክትሪካዊ ተግባርን፣ የሳንባ የኦክስጂን አቀባበል እና የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት መወሰን ነበር። "በሚገርም ሁኔታ እኚህ የመጀመሪያ ታካሚያችን የልባቸውን ሥራ የሚያግዝ ምንም አይነት መድኃኒት አላስፈለጋቸውም" የሚሉት ዶ/ር ፈቃደ "ስለዚህ በተመለከትነው ውጤት ስለተደሰትን አንድ ላይ ተቃቅፈን ፎቶ ተነሳን።"
https://www.bbc.com/amharic/news-58024877
3politics
የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አደገኛ ዕፅ አልተጠቀምኩም አሉ
ከዓለማችን ወጣት የአገር መሪዎች አንዷ የሆኑት የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የአደገኛ ዕፅ ምርመራ ማድረጋቸውን ይፋ አደረጉ። የ36 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ምርመራውን እንዲያደርጉ የተገደዱት በዚህ ሳምንት መባቻ በመሸታ ቤት መስመር ባለፈ ሁኔታ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል መውጣቱን ተከትሎ ነው። ትናንት ዐርብ አዲስ በወጣ ሌላ ተንቀሳቃሽ ምሥል ደግሞ፣ ሳና ማሪን ከአንድ የፊንላንድ ዕውቅ የሙዚቃ አቀንቃኝ ጋር ተጠጋግተው ሲደንሱ ይታያል። እነዚህ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች ለሕዝብ ከታዩ በኋላ ተቃዋሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትሯ የደም ምርመራ እንዲያደርጉ ሲወተውቱ ነበር። ሳና ማሪን ይህንኑ ጥያቄ በመቀበል የአደገኛ ዕፅ ምርመራ በማድረግ ውጤት እየተጠባበቁ ነው። የምርመራ ውጤት በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ ይደረጋል። ወጣቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና በተደጋጋሚ ‘አንዳችም ሕገ ወጥ ተግባር አልፈጸምኩም’ ሲሉ በሔልሲንኪ ለሚገኙ ዘጋቢዎች ተናግረዋል። ‘እንኳንስ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኜ ይቅርና በአፍላ ዕድሜዬም አደገኛ ዕፅ ያለበት ቦታ ድርሽ ብዬ አላውቅም’ ነው ያሉት፣ ሳና። ምርመራውን ያደረጉትም በሕዝብ ዘንድ ያለውን ብዥታ ለማጥራት እንደሆነም ተናግረዋል። በተጨማሪም የምርመራ ውጤቱ ይፋ እስኪደረግ ንጹህ ሆኖ የመገመት መብታቸው እንዲጠበቅም ተማጽነዋል። አንዳንድ ጋዜጠኞች ለጠቅላይ ሚኒስትሯ በምሽት በሚጨፍሩባቸው ጊዝያት አስቸኳይ የመንግሥት ውሳኔዎች አስፈልገው ቢሆን በስካር መንፈስ ውሳኔ ሰጥተው ያውቁ እንደሆን ጠይቀዋቸው ነበር። ማሪን ሲመልሱም እንዲህ ዓይነት አስቸኳይ ነገር በሌሊት መጥቶ አያውቅም ብለዋል። ማሪን በዚህ መሸታ ቤት እየጨፈሩ በነበረበት ወቅት እየተቀረጹ እንደሆነ ያውቁ እንደነበረም ይፋ አድርገዋል። ነገር ግን ተንቀሳቃሽ ምሥሉ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ እንዳላስደሰታቸው አልሸሸጉም። ‘እኔ የመሰለኝ ሰዎች የሥራ ሰዓትንና የመዝናኛ ሰዓትን ለይተው ይመለከታሉ፤ የሰው የግል ድንበር የት ጋ እንደሆነም ይረዳሉ ብዬ አስቤ ነበር’ ብለዋል። ከዓለም ወጣት መሪዎች አንዷ የሆኑት ማሪን በስፋት የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ላይ እየተገኙ ሲጨፍሩ በተደጋጋሚ ታይተው ያውቃሉ። ባለፈው ሳምንት እንዲያውም ባይልድ የተሰኘ የጀርመን ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትሯን ‘የዓለም አራዳዋ መሪ’ በሚል መርጧቸው ነበር። ባለፈው ሐሙስ ከተለቀቀው ቪዲዮ በኋላ ዐርብ ዕለት ደግሞ ከፊንላንዱ ሞዛቂ ኦላቪ ኡዚቪርታ ጋር ተቀራርበው ሲጨፍሩ የሚያሳይ ሌላ ምሥል ተለቆባቸው ነበር። አንድ ጋዜጠኛ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በዚህ ሞዛቂ እየተሳሙ እንደነበረ ጠይቋቸው ይህንኑ አስተባብለዋል። ‘እየሳመኝ አልነበረም፤ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብሎ እያወራኝ ነበር፤ ምናልባት ጉንጬን ሳም አድርጎት ሊሆን ይችላል’ ብለዋል። አክለውም፣ ‘አንድ ወንድ ጉንጬ ላይ ቢስመኝ ጉድ የሚያስብል ነገር አይደለም፤ ለባለቤቴ የምነግረው ትልቅ ጉዳይም ሊሆን አይችልም’ ሲሉ ክስተቱ ይህን ያህል በሚዲያ መራገቡን አጣጥለውታል። የጠቅላይ ሚኒስትሯ የሰሞኑ ውዝግብ በፊንላድ አዲስ ክርክርን አስነስቷል። ሚዲያዎች ጉዳዩን ለጥጠውታል ከሚለው ክርክር አንስቶ  የአንድ መሪ የግል መብት እስከምን ደረጃ ሊሄድ ይችላል የሚሉት ጉዳዮች በስፋት መነጋገሪያ ሆነዋል።
የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አደገኛ ዕፅ አልተጠቀምኩም አሉ ከዓለማችን ወጣት የአገር መሪዎች አንዷ የሆኑት የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የአደገኛ ዕፅ ምርመራ ማድረጋቸውን ይፋ አደረጉ። የ36 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ምርመራውን እንዲያደርጉ የተገደዱት በዚህ ሳምንት መባቻ በመሸታ ቤት መስመር ባለፈ ሁኔታ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል መውጣቱን ተከትሎ ነው። ትናንት ዐርብ አዲስ በወጣ ሌላ ተንቀሳቃሽ ምሥል ደግሞ፣ ሳና ማሪን ከአንድ የፊንላንድ ዕውቅ የሙዚቃ አቀንቃኝ ጋር ተጠጋግተው ሲደንሱ ይታያል። እነዚህ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች ለሕዝብ ከታዩ በኋላ ተቃዋሚዎች ጠቅላይ ሚኒስትሯ የደም ምርመራ እንዲያደርጉ ሲወተውቱ ነበር። ሳና ማሪን ይህንኑ ጥያቄ በመቀበል የአደገኛ ዕፅ ምርመራ በማድረግ ውጤት እየተጠባበቁ ነው። የምርመራ ውጤት በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ ይደረጋል። ወጣቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና በተደጋጋሚ ‘አንዳችም ሕገ ወጥ ተግባር አልፈጸምኩም’ ሲሉ በሔልሲንኪ ለሚገኙ ዘጋቢዎች ተናግረዋል። ‘እንኳንስ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኜ ይቅርና በአፍላ ዕድሜዬም አደገኛ ዕፅ ያለበት ቦታ ድርሽ ብዬ አላውቅም’ ነው ያሉት፣ ሳና። ምርመራውን ያደረጉትም በሕዝብ ዘንድ ያለውን ብዥታ ለማጥራት እንደሆነም ተናግረዋል። በተጨማሪም የምርመራ ውጤቱ ይፋ እስኪደረግ ንጹህ ሆኖ የመገመት መብታቸው እንዲጠበቅም ተማጽነዋል። አንዳንድ ጋዜጠኞች ለጠቅላይ ሚኒስትሯ በምሽት በሚጨፍሩባቸው ጊዝያት አስቸኳይ የመንግሥት ውሳኔዎች አስፈልገው ቢሆን በስካር መንፈስ ውሳኔ ሰጥተው ያውቁ እንደሆን ጠይቀዋቸው ነበር። ማሪን ሲመልሱም እንዲህ ዓይነት አስቸኳይ ነገር በሌሊት መጥቶ አያውቅም ብለዋል። ማሪን በዚህ መሸታ ቤት እየጨፈሩ በነበረበት ወቅት እየተቀረጹ እንደሆነ ያውቁ እንደነበረም ይፋ አድርገዋል። ነገር ግን ተንቀሳቃሽ ምሥሉ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ እንዳላስደሰታቸው አልሸሸጉም። ‘እኔ የመሰለኝ ሰዎች የሥራ ሰዓትንና የመዝናኛ ሰዓትን ለይተው ይመለከታሉ፤ የሰው የግል ድንበር የት ጋ እንደሆነም ይረዳሉ ብዬ አስቤ ነበር’ ብለዋል። ከዓለም ወጣት መሪዎች አንዷ የሆኑት ማሪን በስፋት የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ላይ እየተገኙ ሲጨፍሩ በተደጋጋሚ ታይተው ያውቃሉ። ባለፈው ሳምንት እንዲያውም ባይልድ የተሰኘ የጀርመን ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትሯን ‘የዓለም አራዳዋ መሪ’ በሚል መርጧቸው ነበር። ባለፈው ሐሙስ ከተለቀቀው ቪዲዮ በኋላ ዐርብ ዕለት ደግሞ ከፊንላንዱ ሞዛቂ ኦላቪ ኡዚቪርታ ጋር ተቀራርበው ሲጨፍሩ የሚያሳይ ሌላ ምሥል ተለቆባቸው ነበር። አንድ ጋዜጠኛ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በዚህ ሞዛቂ እየተሳሙ እንደነበረ ጠይቋቸው ይህንኑ አስተባብለዋል። ‘እየሳመኝ አልነበረም፤ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብሎ እያወራኝ ነበር፤ ምናልባት ጉንጬን ሳም አድርጎት ሊሆን ይችላል’ ብለዋል። አክለውም፣ ‘አንድ ወንድ ጉንጬ ላይ ቢስመኝ ጉድ የሚያስብል ነገር አይደለም፤ ለባለቤቴ የምነግረው ትልቅ ጉዳይም ሊሆን አይችልም’ ሲሉ ክስተቱ ይህን ያህል በሚዲያ መራገቡን አጣጥለውታል። የጠቅላይ ሚኒስትሯ የሰሞኑ ውዝግብ በፊንላድ አዲስ ክርክርን አስነስቷል። ሚዲያዎች ጉዳዩን ለጥጠውታል ከሚለው ክርክር አንስቶ  የአንድ መሪ የግል መብት እስከምን ደረጃ ሊሄድ ይችላል የሚሉት ጉዳዮች በስፋት መነጋገሪያ ሆነዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c9eydv2mdn1o
2health
በህንድ የተከሰተው የጥቁር ፈንገስ በሽታ በወረርሺኝነት እንዲታወጅ ጥሪ ቀረበ
በህንድ የሚገኙ ክልሎች ‹‹የጥቁር ፈንገስ›› አማካኝነት የሚከሰተው በሽታ በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በወረርሺኝነት እንዲታወጅ የአገሪቱ የጤና ሃላፊዎች ጠየቁ። ከዚህ ቀደም እንብዛም የማይታየው እና በዚህ ፈንገስ አማካኝነት የሚከሰተው የሚውኮርማይኮሲስ በሽታ እስከ 50 በመቶ ድረስ ገዳይ ሲሆን የሚተርፉ ሰዎችም አይናቸውን ወይም የመንጋጋ አጥንት ያጣሉ። ከቅርብ ወራት ጀምሮ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ከ ኮቪድ ያገገሙ እና በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች በሚውኮርማይኮሲስ ተይዘው ተገኝተዋል። የኮቪድ ህመምተኞችን ለማከም ከዋሉ መድሃኒቶች ጋር ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል ሃኪሞች ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል። በተለይም የስኳር ህመምተኞች ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ከሆኑ ከ 12 እስከ 15 ባሉት ቀናት ውስጥ ተጋላጭ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ሃኪሞቹ ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የህንድ የጤና ሚኒስትር የጽህፈት ቤት ሃላፊ ላቭ አጋርዋል በህንድ ላሉ 29 ክልሎች ይህንን ህመም ወረርሺኝ ብለው እንዲያወጁ በደብዳቤ ጠይቀዋል። ህመሙ ወረረሺኝ ተብሎ የሚታወጅ ከሆነ ከጤና ሚኒስቴር የተሸለ ትብብር አና ህክምና ለመስጠት ብሎም በእያንዳንዱ ክልል ያለውን ሁኔታ ለመከታተል ያስችላል ተብሏል። በኮሮና ቫይረስ እየተናጠች ባለችው ህንድ እስካሁን ድረስ ምን ያህል ሰዎች በሚውኮርማይኮሲስ እንደተያዙ በውል አይታወቅም። በህንድ ባጋጠመው ሁለተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ የስርጭት ማእበል በሁለተኛ ደረጃ ተጠቂ የሆነችው ማሃራሽትራ ክልል እስካሁን 1500 የሙኮርሚኮሲስ ታማሚዎችን ለይታለች። በህንድ ዋና ከተማ ሙምባይ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል በሁለት ወር ውስጥ 24 ህመምተኞችን መመልከቱ እና ይህ ባለፈው አመት ከታየው ስድስት ህመምተኛ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። ሃኪሞችም ፈንገሱ ወደ አእምሮ ሳይሰራጭ የህመምተኞችን ህይወት ለማትረፍ የመንጋጋ አጥንትን ወይም አይናቸውን ለማስወገድ መገደዳቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። በበርካታ የህንድ የመድሃኒት አምራቾች የሚመረተው እና ይህንን ህመም ለማከም የሚለው አምፎተሪሰን የተሰኘው መድሃኒት እጥረት መከሰቱም ታውቋል።
በህንድ የተከሰተው የጥቁር ፈንገስ በሽታ በወረርሺኝነት እንዲታወጅ ጥሪ ቀረበ በህንድ የሚገኙ ክልሎች ‹‹የጥቁር ፈንገስ›› አማካኝነት የሚከሰተው በሽታ በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በወረርሺኝነት እንዲታወጅ የአገሪቱ የጤና ሃላፊዎች ጠየቁ። ከዚህ ቀደም እንብዛም የማይታየው እና በዚህ ፈንገስ አማካኝነት የሚከሰተው የሚውኮርማይኮሲስ በሽታ እስከ 50 በመቶ ድረስ ገዳይ ሲሆን የሚተርፉ ሰዎችም አይናቸውን ወይም የመንጋጋ አጥንት ያጣሉ። ከቅርብ ወራት ጀምሮ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ከ ኮቪድ ያገገሙ እና በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች በሚውኮርማይኮሲስ ተይዘው ተገኝተዋል። የኮቪድ ህመምተኞችን ለማከም ከዋሉ መድሃኒቶች ጋር ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል ሃኪሞች ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል። በተለይም የስኳር ህመምተኞች ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ከሆኑ ከ 12 እስከ 15 ባሉት ቀናት ውስጥ ተጋላጭ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ሃኪሞቹ ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የህንድ የጤና ሚኒስትር የጽህፈት ቤት ሃላፊ ላቭ አጋርዋል በህንድ ላሉ 29 ክልሎች ይህንን ህመም ወረርሺኝ ብለው እንዲያወጁ በደብዳቤ ጠይቀዋል። ህመሙ ወረረሺኝ ተብሎ የሚታወጅ ከሆነ ከጤና ሚኒስቴር የተሸለ ትብብር አና ህክምና ለመስጠት ብሎም በእያንዳንዱ ክልል ያለውን ሁኔታ ለመከታተል ያስችላል ተብሏል። በኮሮና ቫይረስ እየተናጠች ባለችው ህንድ እስካሁን ድረስ ምን ያህል ሰዎች በሚውኮርማይኮሲስ እንደተያዙ በውል አይታወቅም። በህንድ ባጋጠመው ሁለተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ የስርጭት ማእበል በሁለተኛ ደረጃ ተጠቂ የሆነችው ማሃራሽትራ ክልል እስካሁን 1500 የሙኮርሚኮሲስ ታማሚዎችን ለይታለች። በህንድ ዋና ከተማ ሙምባይ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል በሁለት ወር ውስጥ 24 ህመምተኞችን መመልከቱ እና ይህ ባለፈው አመት ከታየው ስድስት ህመምተኛ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። ሃኪሞችም ፈንገሱ ወደ አእምሮ ሳይሰራጭ የህመምተኞችን ህይወት ለማትረፍ የመንጋጋ አጥንትን ወይም አይናቸውን ለማስወገድ መገደዳቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። በበርካታ የህንድ የመድሃኒት አምራቾች የሚመረተው እና ይህንን ህመም ለማከም የሚለው አምፎተሪሰን የተሰኘው መድሃኒት እጥረት መከሰቱም ታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57197231
0business
ልደት ፤ ወጣቱ ለልደቱ የተሰጠውን ውስኪ በመሸጥ የ40ሺህ ፖውንድ ቤት ሊገዛ ነው
ማቲው ሮብሰን ይባላል፡፡ አባቱ አንድ ነገር አስለምደውታል፡፡ በየዓመቱ ልደቱ ሲሆን 18 ዓመት ዕድሜ ያለው ውስኪ ገዝተው ይሰጡታል፡፡ ልጁ ውስኪውን ያጠራቅማል፡፡ አሁን 28 ዓመት ደርሷል፡፡ ሮብሰን የተወለደው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1992 ነው። በእነዚህ ሁሉ ዓመታት አባቱ በድምሩ 5ሺህ ፓውንድ አውጥተዋል፡፡ በየዓመቱ አንድ ውስኪ ለልደቱ ለመግዛት፡፡ እስከዛሬ 28 የውስኪ ጠርሙሶችን ገዝተውለታል፡፡ የውስኪው ዓይነት ማካላን የሚባል ነው፡፡ አሁን ዋጋው ንሯል፡፡ አባትየው ለ28 ጠርሙስ ውስኪ በ28 ዓመታት ውስጥ በድምሩ 5ሺህ ፓውንድ ብቻ ያውጡ እንጂ አሁን ላይ ውስኪዎቸ እስከ 40ሺህ ፓውንድ ይሸጣሉ፡፡ ሮብሰን እንደሚለው ውስኪ ለልጅ ተገቢ የልደት ስጦታ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን አባቴ ውስኪዎቹን በፍጹም እንዳልከፍታቸው ያስጠነቅቀኝ ስለነበር ለዚህ በቅቻለሁ ብሏል፡፡ የሮብሰን አባት ፒት ይባላሉ፡፡ ስኮትላንድ ነው የሚኖሩት፡፡ በ1974 የተመረተው ዊስኪ ለመጀመርያ ጊዜ የገዙለት እንዲሁ እንደዋዛ ነበር፡፡ "እንደቀልድ በየዓመቱ አንድ ውስኪ ብሰጠው 18 ዓመት ሲሆነው 18 ዊስኪ ይኖረዋል ብዬ አሰብኩ፡፡ ነገሩን ለማድመቅ ነው እንጂ ለልጄ የምሰጠው ስጦታ ግን ዊስኪ ብቻ አልነበረም" ብለዋል፡፡ አሁን ማካላን ዊስኪዎች ተፈላጊ ናቸው፡፡ እንደ ቅርስ የሚሰበሰቡ የዊስኪ አይነቶች ናቸው፡፡ የነበራቸው ዋጋም በጣም ጨምሯል፡፡ አሁን ዊስኪዎቹን ማርክ ሊትለር የተባለ እሳት የላሰ የዊስኪ ደላላ ሊሸጣቸው ነው፡፡ ምርጥ ስብስቦች ናቸው ብሏል ለቢቢሲ፡፡ ባለፉት ዓመታት የእነዚህ ውስኪዎቹ ዋጋ እጥፍ በእጥፍ ነው የጨመረው፡፡ ብናጣ ብናጣ እስከ 40ሺህ ፓውንድ እንሸጣቸዋለን ይላል፡፡ ዊስኪዎቹ የሚሸጡት ለኒውዮርክ ወይም ለእሲያ ገበያ ነው፡፡ ሮብሰን በ40ሺህ ፓውንዱ ቤት ለመግዛት እያሰበ ነው፡፡
ልደት ፤ ወጣቱ ለልደቱ የተሰጠውን ውስኪ በመሸጥ የ40ሺህ ፖውንድ ቤት ሊገዛ ነው ማቲው ሮብሰን ይባላል፡፡ አባቱ አንድ ነገር አስለምደውታል፡፡ በየዓመቱ ልደቱ ሲሆን 18 ዓመት ዕድሜ ያለው ውስኪ ገዝተው ይሰጡታል፡፡ ልጁ ውስኪውን ያጠራቅማል፡፡ አሁን 28 ዓመት ደርሷል፡፡ ሮብሰን የተወለደው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1992 ነው። በእነዚህ ሁሉ ዓመታት አባቱ በድምሩ 5ሺህ ፓውንድ አውጥተዋል፡፡ በየዓመቱ አንድ ውስኪ ለልደቱ ለመግዛት፡፡ እስከዛሬ 28 የውስኪ ጠርሙሶችን ገዝተውለታል፡፡ የውስኪው ዓይነት ማካላን የሚባል ነው፡፡ አሁን ዋጋው ንሯል፡፡ አባትየው ለ28 ጠርሙስ ውስኪ በ28 ዓመታት ውስጥ በድምሩ 5ሺህ ፓውንድ ብቻ ያውጡ እንጂ አሁን ላይ ውስኪዎቸ እስከ 40ሺህ ፓውንድ ይሸጣሉ፡፡ ሮብሰን እንደሚለው ውስኪ ለልጅ ተገቢ የልደት ስጦታ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን አባቴ ውስኪዎቹን በፍጹም እንዳልከፍታቸው ያስጠነቅቀኝ ስለነበር ለዚህ በቅቻለሁ ብሏል፡፡ የሮብሰን አባት ፒት ይባላሉ፡፡ ስኮትላንድ ነው የሚኖሩት፡፡ በ1974 የተመረተው ዊስኪ ለመጀመርያ ጊዜ የገዙለት እንዲሁ እንደዋዛ ነበር፡፡ "እንደቀልድ በየዓመቱ አንድ ውስኪ ብሰጠው 18 ዓመት ሲሆነው 18 ዊስኪ ይኖረዋል ብዬ አሰብኩ፡፡ ነገሩን ለማድመቅ ነው እንጂ ለልጄ የምሰጠው ስጦታ ግን ዊስኪ ብቻ አልነበረም" ብለዋል፡፡ አሁን ማካላን ዊስኪዎች ተፈላጊ ናቸው፡፡ እንደ ቅርስ የሚሰበሰቡ የዊስኪ አይነቶች ናቸው፡፡ የነበራቸው ዋጋም በጣም ጨምሯል፡፡ አሁን ዊስኪዎቹን ማርክ ሊትለር የተባለ እሳት የላሰ የዊስኪ ደላላ ሊሸጣቸው ነው፡፡ ምርጥ ስብስቦች ናቸው ብሏል ለቢቢሲ፡፡ ባለፉት ዓመታት የእነዚህ ውስኪዎቹ ዋጋ እጥፍ በእጥፍ ነው የጨመረው፡፡ ብናጣ ብናጣ እስከ 40ሺህ ፓውንድ እንሸጣቸዋለን ይላል፡፡ ዊስኪዎቹ የሚሸጡት ለኒውዮርክ ወይም ለእሲያ ገበያ ነው፡፡ ሮብሰን በ40ሺህ ፓውንዱ ቤት ለመግዛት እያሰበ ነው፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-54053425
2health
በኔዘርላንድስ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቀነስ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ
የኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት በአገራቸው የክረምት መግባትን ተከትሎ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ለሦስት ሳምንታት የመገበያያ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና ምግብ አቅራቢዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ እገዳ መጣሉን ገለጹ። ይህም በምዕራብ አውሮፓ የመጀመሪያዋ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ የጣለች አገር አድርጓታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጨናቂ እና ከባድ ውሳኔ ነው ያሉት እገዳ፤ መነሻው በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እና ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ነው ብለዋል። ሆኖም የአገሪቱን መንግሥት ውሳኔ ተቃውመው አደባባይ የውጡ ዜጎች ታይተዋል። በዚህም ሳቢያ ፖሊስ በሄግ በመቶዎች በሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን ለመበተን ውሃ ረጭቷል። በአሁኑ ወቅት በበርካታ የአውሮፓ አገራት የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየጨመረ ሲሆን ለዚህ ከተሰጡ ምክንያቶች አንዱ በብዙ አገራት ክትባት በብዛት እየተወሰደ አለመሆኑ ነው። በኔዘርላንድስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ክትባት ማግኘቱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሦስት ሳምንቱ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል። በኔዘርላንድስ ባለፈው አርብ የተመዘገበው ዕለታዊ የኮቪድ-19 አሐዝ 16 ሺህ 287 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ያመላክታል። ይህ ቁጥር ከሐሙስ ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ቢሆንም ካለፈው ሳምንት ጋር ሲወዳደር ግን በአንድ ሦስተኛ ከፍ ያለ ነው። የኔዘርላንድስ የክትባት ምጣኔ በአንጻራዊነት ከፍተኛ የሚባል ነው። በአገሪቱ ከ12 ዓመት በላይ ካሉ ሰዎች 82.4 በመቶ የሚሆኑት ሁለት ዙር የወረርስኙ መከላከያ ክትባት ያገኙ ሲሆን፤ ይህም ከጠቅላላው ሕዝብ 73 በመቶውን የሚይዝ ነው።
በኔዘርላንድስ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመቀነስ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ የኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት በአገራቸው የክረምት መግባትን ተከትሎ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ለሦስት ሳምንታት የመገበያያ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና ምግብ አቅራቢዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ እገዳ መጣሉን ገለጹ። ይህም በምዕራብ አውሮፓ የመጀመሪያዋ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ የጣለች አገር አድርጓታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጨናቂ እና ከባድ ውሳኔ ነው ያሉት እገዳ፤ መነሻው በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እና ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ነው ብለዋል። ሆኖም የአገሪቱን መንግሥት ውሳኔ ተቃውመው አደባባይ የውጡ ዜጎች ታይተዋል። በዚህም ሳቢያ ፖሊስ በሄግ በመቶዎች በሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን ለመበተን ውሃ ረጭቷል። በአሁኑ ወቅት በበርካታ የአውሮፓ አገራት የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየጨመረ ሲሆን ለዚህ ከተሰጡ ምክንያቶች አንዱ በብዙ አገራት ክትባት በብዛት እየተወሰደ አለመሆኑ ነው። በኔዘርላንድስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ክትባት ማግኘቱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሦስት ሳምንቱ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል። በኔዘርላንድስ ባለፈው አርብ የተመዘገበው ዕለታዊ የኮቪድ-19 አሐዝ 16 ሺህ 287 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ያመላክታል። ይህ ቁጥር ከሐሙስ ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ቢሆንም ካለፈው ሳምንት ጋር ሲወዳደር ግን በአንድ ሦስተኛ ከፍ ያለ ነው። የኔዘርላንድስ የክትባት ምጣኔ በአንጻራዊነት ከፍተኛ የሚባል ነው። በአገሪቱ ከ12 ዓመት በላይ ካሉ ሰዎች 82.4 በመቶ የሚሆኑት ሁለት ዙር የወረርስኙ መከላከያ ክትባት ያገኙ ሲሆን፤ ይህም ከጠቅላላው ሕዝብ 73 በመቶውን የሚይዝ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-59272479
5sports
በግማሽ ጨዋታ ጡት ማጥባት፡ የሴት ስፖርተኞች ታሪክ
"የተወሰኑ የቡድናችን አባል ነበሩ፤ ግማሽ ጨዋታ ሲሆን ወይ ጡት ለማጥባት ወይም ጡታቸውን ለማለብ ይሄዳሉ። ከዚያም ወደሜዳ ይመለሳሉ" ትላለች አንጎላዊ-አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኢታሊ ሉቃስ። "ይህንን ቀርቦ ማየትም ሆነ በዚህ ማለፍ የሚያስደምም ነው፤ ለየት ያለ ጥንካሬ ያስፈልጋል" በማለት ታስረዳለች። እናት መሆንና ታዋቂ ለሆነ የቅርጫት ኳስ ቡድን መጫወት እንዲሁም ለሁለቱም የሚሆን ጊዜ ማግኘት ቀላል አይደለም። እናትነትና ስፖርተኝነትን አመጣጥኖ መሄድም ፈታኝ ነው። በተለይም ሴት ስፖርተኞች በሚያረግዙበት ወቅት እርግዝናው በአካላቸው ላይ ሊያመጣ የሚችለው ለውጥ፣ አሰሪዎች ነፍሰጡር መሆናቸውን በሚያውቁበት ወቅት ሊከተል የሚችለው ጫና እንዲሁም አዲስ ህይወትን ወደ ስፖርቱ ዓለም ማምጣት የራሱ የሆኑ ፈታኝ ችግሮች አሉት። በዚህም ምክንያት ሴት ስፖርተኞች እናት መሆንን በከፍተኛ ሁኔታ ይፈሩታል። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት 'አፍሮ ባስኬት' ተብሎ በሚጠራው የአፍሪካውያን የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ውድድር በሴኔጋል ሲካሄድ ከ144ቱ ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች መካከል እናት የሆኑት 25ቱ ብቻ ናቸው። ይህ ቢሰላ አስራ ሁለት ቡድን ከሚይዝ ቡድን ውስጥ እናት የሆኑት ሁለት ብቻ ናቸው እንደማለት ነው። ምናልባት በስፖርቱ ዓለም ውስጥ እርጉዝ ሆነው ስፖርቱን ከቀጠሉት መካከል የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቿ ሴሪና ዊልያምስ ትገኝበታለች። ከሦስት ዓመት በፊትም የዓለም አቀፉን ሻምፒዮና ለ23ኛ ጊዜ ስታሸንፍ ልጇን አሌክሲስ ኦሎምፒያ ኦሃኒያን ነፍሰ ጡር ሆና ነው። ካሜሮናዊቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ባሌታ ሙኮኮ ነፍሰጡር መሆኗን አታውቅም ነበር፤ እርጉዝ መሆኗን የተረዳችው በጣም ዘግይታ ነው። ለፈረንሳዩ ቡድን ትጫወት በነበረበት ወቅት አንድ ቀን ጀርባዋን በፀና ታመመችና ወደ ሆስፒታል ሄደች፤ ዶክተሩም የሰባት ወር ነፍሰጡር እንደሆነች ነገራት። "ዓመቱን በሙሉ ቅርጫት ኳስ ተጫውቻለሁ። መጋፋት መውደቅ እንዲሁም መመታት ነበር። እርጉዝ መሆኔን አላወቅኩም። ልክ መጫወት ሳቆም ሆዴም እየገፋ መምጣት ጀመረ" ትላለች። አክላም "ልጅ ለመውለድ እንዲሁም ለመታረስ ጊዜው ነበረኝ። የወለድኩት ሰኔ ወር ነበር እናም እስከ ነሐሴ ድረስ ምንም አይነት ጨዋታ አልነበረኝም እናም ለማረፍ ጊዜ አግኝቻለሁ" በማለት ታስረዳለች። ምንም እንኳን እንደ ሴሪና ባሌታ ወደ ስፖርቱ ዓለም መመለስ ብትችልም፤ ነገር ግን እናት መሆንና ስፖርተኛ መሆን ከፍተኛ መስዋዕትነትን ይጠይቃል። በባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ሻምፒዮን ውድድር ላይ የዱላ ቅብብል የወርቅ ሜዳሊያዋን ያገኘችው ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ደስታዋን የገለፀችው ልጇን ዛየንን በውድድሩ ቦታ ላይ በማምጣት ነበር። በወቅቱም ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈለች ስትናገር የልጇ ዛየን ትምህርት እንዲሁም ስፖርት ነክ ውድድሮች ላይ መገኘት አለመቻሏን ነው። ምክንያቱም መቋረጥ የማይችሉ ስልጠናዎች ስለነበሯት ነው፤ ይህም በወቅቱ ፈታኝ ነበር ብላለች። ፅናትና ቁርጠኝነት ብቻ ሳይሆን ታዋቂ አትሌት ለመሆን መስዋዕትነት እንደሚያስፈልግ ባሌታ የተማረችው ነገር ነው። "የመጀመሪያ ልጄ የሚኖረው ከእናቴ ጋር ነው ምክንያቱም ስፖርቱ አብዛኛውን ጊዜዬን ስለሚወስድብኝ ብዙም አላየውም" የምትለው ባሌታ፤ "የማገኘው በበዓላት ወቅት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ቅዳሜና እሁድ ብቻ ነው። የሚቀጥለውን ልጄን በምወልድበት ጊዜ ግን ለአንድ ዓመት ቢሆን ስፖርቱን ቀጥ አደርገዋለሁ" በማለት እቅዷን አስረድታለች። ለሴት ስፖርተኞች በሚወልዱበት ወቅት ሥራ ማቋረጥ ግዴታ ይሆን? ሥራ ማቋረጡስ ለስፖርተኞች ምን አይነት ሁኔታን ያስከትል ይሆን? ቀድሞ ይከፈላቸው የነበረውን የገንዘብ መጠን ከወለዱ በኋላ ያገኙት ይሆን? ስድስት ጊዜ በመቶና ሁለት መቶ ሜትር ሩጫ የኦሊምፒክ ሻምፒዮና መሆን የቻለችው አሊሰን ፌሊክስ፤ እናት መሆኗን ተከትሎ ስፖንሰር የሚያደርጋት ናይክ ይከፍላት ከነበረው 70 በመቶ ቀንሶ ልክፈልሽ እንዳላት ገልፃለች። ምንም እንኳን ፌሊክስ ናይክ ያደረገውን ኢፍትሃዊነት በማጋለጥና በመሞገት ማሸነፍ ብትችልም ብዙ ሴት ስፖርተኞች ይህ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያስጨንቃቸው ቢቢሲ ያናገራቸው አትሌቶች ገልፀዋል። ይህ ብቻ አይደለም ልጅ ከወለዱ በኋላ ከአካላዊ ሁኔታ መቀያየር ጋር ተያይዞ መጫወትም ሆነ መወዳደር ቢከብዳቸውስ? የአይቮሪኮስቷ ቅርጫት ኳስ አምበል ማሪያማ ካዩቴ ይህ ነው ያጋጠማት። "በውድድር ላይ ተጎድቼ ሁለቱም ጉልበቴ ላይ ቀዶ ጥገና አደረግኩኝ። እናም የመጀመሪያ ጉልበቴን ቀዶ ጥገና ሳደርግ ለምን ልጅ አልወልድም እና ወደ ቅርጫት ኳሱ አልመለስም አልኩኝ። እና አሁን ማለት የምችለው ልጅ በመውለዴ እኮራለሁ" በማለት ጉዞዋን አስረድታለች። በሴቶች የስፖርት ዓለም ውስጥ እናትነት እንደ አንድ ችግር መታየቱ መቆም አለበት የምትለው የባሌታ አሰልጣኝ ናቶሻ ከሚንግስ፤ ይህም ጥያቄ ሊሆን አይገባም በማለት ትከራከራለች። "ኮሌጅ ውስጥ ስፖርተኞች የነበሩ ወልደው እንደገና ተመልሰው የሚወዳደሩ ስፖርተኞችን አውቃለሁ" በማለት የቅርጫት ኳስ አሰልጣኟ ናቶሻ አፅንኦት ሰጥታ ትናገራለች። "ሴት አትሌቶች በእናትነትና በስፖርት ህይወታቸው መካከል እንዲመርጡ መገደድ የለባቸውም። ዋናው ነገር በደንብ ጠንክረው መስራትና ቁርጠኝነትን ማሳየት አለባቸው። ምክንያቱም ለብዙ ሴቶች ከባድ የሚሆነው በእርግዝና ወቅት የሚፈጠረውን አካላዊ ሁኔታ ወደነበረበት መመለስ ነው። ለመጫወት ወደሚያበቃቸው አካላዊ ቅርፅም ሆነ ብቃት መመለስ አለባቸው።" የምትለው አሰልጣኟ "ቤተሰብ መመስረት ለሚፈልጉትም ምርጫቸው ነው። እኛም እናበረታታቸዋለን ቤተሰብ መመስረት የሚፈልጉትን የአትሌትነት ህይወታቸውን እንዳያቋርጡ የምንጎተጉታቸው ጉዳይ ነው።" አትሌቶች ልጅ ከወለዱ በኋላ ወደ ስፖርቱ መመለስ ለሚፈልጉትም ሆነ ቤተሰብ መመስረት ለሚሹ ዋናው ጉዳይ ከአሰልጣኞች ዘንድ የሚያገኙት ድጋፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አሰልጣኟ ታስረዳለች። "ከአሰልጣኞች እንዲሁም ከአስተዳደሩ ዘንድ የሚያገኙት ድጋፍ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል። ድጋፍ እስካለ ድረስ ቅርጫት ኳስ መጫወት የሚፈልጉ ስፖርተኛ እናቶች የትም መድረስ ይችላሉ" በማለት ሃሳቧን ታጠቃልላለች።
በግማሽ ጨዋታ ጡት ማጥባት፡ የሴት ስፖርተኞች ታሪክ "የተወሰኑ የቡድናችን አባል ነበሩ፤ ግማሽ ጨዋታ ሲሆን ወይ ጡት ለማጥባት ወይም ጡታቸውን ለማለብ ይሄዳሉ። ከዚያም ወደሜዳ ይመለሳሉ" ትላለች አንጎላዊ-አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኢታሊ ሉቃስ። "ይህንን ቀርቦ ማየትም ሆነ በዚህ ማለፍ የሚያስደምም ነው፤ ለየት ያለ ጥንካሬ ያስፈልጋል" በማለት ታስረዳለች። እናት መሆንና ታዋቂ ለሆነ የቅርጫት ኳስ ቡድን መጫወት እንዲሁም ለሁለቱም የሚሆን ጊዜ ማግኘት ቀላል አይደለም። እናትነትና ስፖርተኝነትን አመጣጥኖ መሄድም ፈታኝ ነው። በተለይም ሴት ስፖርተኞች በሚያረግዙበት ወቅት እርግዝናው በአካላቸው ላይ ሊያመጣ የሚችለው ለውጥ፣ አሰሪዎች ነፍሰጡር መሆናቸውን በሚያውቁበት ወቅት ሊከተል የሚችለው ጫና እንዲሁም አዲስ ህይወትን ወደ ስፖርቱ ዓለም ማምጣት የራሱ የሆኑ ፈታኝ ችግሮች አሉት። በዚህም ምክንያት ሴት ስፖርተኞች እናት መሆንን በከፍተኛ ሁኔታ ይፈሩታል። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት 'አፍሮ ባስኬት' ተብሎ በሚጠራው የአፍሪካውያን የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ውድድር በሴኔጋል ሲካሄድ ከ144ቱ ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች መካከል እናት የሆኑት 25ቱ ብቻ ናቸው። ይህ ቢሰላ አስራ ሁለት ቡድን ከሚይዝ ቡድን ውስጥ እናት የሆኑት ሁለት ብቻ ናቸው እንደማለት ነው። ምናልባት በስፖርቱ ዓለም ውስጥ እርጉዝ ሆነው ስፖርቱን ከቀጠሉት መካከል የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቿ ሴሪና ዊልያምስ ትገኝበታለች። ከሦስት ዓመት በፊትም የዓለም አቀፉን ሻምፒዮና ለ23ኛ ጊዜ ስታሸንፍ ልጇን አሌክሲስ ኦሎምፒያ ኦሃኒያን ነፍሰ ጡር ሆና ነው። ካሜሮናዊቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ባሌታ ሙኮኮ ነፍሰጡር መሆኗን አታውቅም ነበር፤ እርጉዝ መሆኗን የተረዳችው በጣም ዘግይታ ነው። ለፈረንሳዩ ቡድን ትጫወት በነበረበት ወቅት አንድ ቀን ጀርባዋን በፀና ታመመችና ወደ ሆስፒታል ሄደች፤ ዶክተሩም የሰባት ወር ነፍሰጡር እንደሆነች ነገራት። "ዓመቱን በሙሉ ቅርጫት ኳስ ተጫውቻለሁ። መጋፋት መውደቅ እንዲሁም መመታት ነበር። እርጉዝ መሆኔን አላወቅኩም። ልክ መጫወት ሳቆም ሆዴም እየገፋ መምጣት ጀመረ" ትላለች። አክላም "ልጅ ለመውለድ እንዲሁም ለመታረስ ጊዜው ነበረኝ። የወለድኩት ሰኔ ወር ነበር እናም እስከ ነሐሴ ድረስ ምንም አይነት ጨዋታ አልነበረኝም እናም ለማረፍ ጊዜ አግኝቻለሁ" በማለት ታስረዳለች። ምንም እንኳን እንደ ሴሪና ባሌታ ወደ ስፖርቱ ዓለም መመለስ ብትችልም፤ ነገር ግን እናት መሆንና ስፖርተኛ መሆን ከፍተኛ መስዋዕትነትን ይጠይቃል። በባለፈው ዓመት በዓለም አቀፉ ሻምፒዮን ውድድር ላይ የዱላ ቅብብል የወርቅ ሜዳሊያዋን ያገኘችው ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ደስታዋን የገለፀችው ልጇን ዛየንን በውድድሩ ቦታ ላይ በማምጣት ነበር። በወቅቱም ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈለች ስትናገር የልጇ ዛየን ትምህርት እንዲሁም ስፖርት ነክ ውድድሮች ላይ መገኘት አለመቻሏን ነው። ምክንያቱም መቋረጥ የማይችሉ ስልጠናዎች ስለነበሯት ነው፤ ይህም በወቅቱ ፈታኝ ነበር ብላለች። ፅናትና ቁርጠኝነት ብቻ ሳይሆን ታዋቂ አትሌት ለመሆን መስዋዕትነት እንደሚያስፈልግ ባሌታ የተማረችው ነገር ነው። "የመጀመሪያ ልጄ የሚኖረው ከእናቴ ጋር ነው ምክንያቱም ስፖርቱ አብዛኛውን ጊዜዬን ስለሚወስድብኝ ብዙም አላየውም" የምትለው ባሌታ፤ "የማገኘው በበዓላት ወቅት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ቅዳሜና እሁድ ብቻ ነው። የሚቀጥለውን ልጄን በምወልድበት ጊዜ ግን ለአንድ ዓመት ቢሆን ስፖርቱን ቀጥ አደርገዋለሁ" በማለት እቅዷን አስረድታለች። ለሴት ስፖርተኞች በሚወልዱበት ወቅት ሥራ ማቋረጥ ግዴታ ይሆን? ሥራ ማቋረጡስ ለስፖርተኞች ምን አይነት ሁኔታን ያስከትል ይሆን? ቀድሞ ይከፈላቸው የነበረውን የገንዘብ መጠን ከወለዱ በኋላ ያገኙት ይሆን? ስድስት ጊዜ በመቶና ሁለት መቶ ሜትር ሩጫ የኦሊምፒክ ሻምፒዮና መሆን የቻለችው አሊሰን ፌሊክስ፤ እናት መሆኗን ተከትሎ ስፖንሰር የሚያደርጋት ናይክ ይከፍላት ከነበረው 70 በመቶ ቀንሶ ልክፈልሽ እንዳላት ገልፃለች። ምንም እንኳን ፌሊክስ ናይክ ያደረገውን ኢፍትሃዊነት በማጋለጥና በመሞገት ማሸነፍ ብትችልም ብዙ ሴት ስፖርተኞች ይህ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያስጨንቃቸው ቢቢሲ ያናገራቸው አትሌቶች ገልፀዋል። ይህ ብቻ አይደለም ልጅ ከወለዱ በኋላ ከአካላዊ ሁኔታ መቀያየር ጋር ተያይዞ መጫወትም ሆነ መወዳደር ቢከብዳቸውስ? የአይቮሪኮስቷ ቅርጫት ኳስ አምበል ማሪያማ ካዩቴ ይህ ነው ያጋጠማት። "በውድድር ላይ ተጎድቼ ሁለቱም ጉልበቴ ላይ ቀዶ ጥገና አደረግኩኝ። እናም የመጀመሪያ ጉልበቴን ቀዶ ጥገና ሳደርግ ለምን ልጅ አልወልድም እና ወደ ቅርጫት ኳሱ አልመለስም አልኩኝ። እና አሁን ማለት የምችለው ልጅ በመውለዴ እኮራለሁ" በማለት ጉዞዋን አስረድታለች። በሴቶች የስፖርት ዓለም ውስጥ እናትነት እንደ አንድ ችግር መታየቱ መቆም አለበት የምትለው የባሌታ አሰልጣኝ ናቶሻ ከሚንግስ፤ ይህም ጥያቄ ሊሆን አይገባም በማለት ትከራከራለች። "ኮሌጅ ውስጥ ስፖርተኞች የነበሩ ወልደው እንደገና ተመልሰው የሚወዳደሩ ስፖርተኞችን አውቃለሁ" በማለት የቅርጫት ኳስ አሰልጣኟ ናቶሻ አፅንኦት ሰጥታ ትናገራለች። "ሴት አትሌቶች በእናትነትና በስፖርት ህይወታቸው መካከል እንዲመርጡ መገደድ የለባቸውም። ዋናው ነገር በደንብ ጠንክረው መስራትና ቁርጠኝነትን ማሳየት አለባቸው። ምክንያቱም ለብዙ ሴቶች ከባድ የሚሆነው በእርግዝና ወቅት የሚፈጠረውን አካላዊ ሁኔታ ወደነበረበት መመለስ ነው። ለመጫወት ወደሚያበቃቸው አካላዊ ቅርፅም ሆነ ብቃት መመለስ አለባቸው።" የምትለው አሰልጣኟ "ቤተሰብ መመስረት ለሚፈልጉትም ምርጫቸው ነው። እኛም እናበረታታቸዋለን ቤተሰብ መመስረት የሚፈልጉትን የአትሌትነት ህይወታቸውን እንዳያቋርጡ የምንጎተጉታቸው ጉዳይ ነው።" አትሌቶች ልጅ ከወለዱ በኋላ ወደ ስፖርቱ መመለስ ለሚፈልጉትም ሆነ ቤተሰብ መመስረት ለሚሹ ዋናው ጉዳይ ከአሰልጣኞች ዘንድ የሚያገኙት ድጋፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አሰልጣኟ ታስረዳለች። "ከአሰልጣኞች እንዲሁም ከአስተዳደሩ ዘንድ የሚያገኙት ድጋፍ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል። ድጋፍ እስካለ ድረስ ቅርጫት ኳስ መጫወት የሚፈልጉ ስፖርተኛ እናቶች የትም መድረስ ይችላሉ" በማለት ሃሳቧን ታጠቃልላለች።
https://www.bbc.com/amharic/sport-52284120
3politics
ጆ ባይደንና ፑቲን በነገር እየተቆራቆሱ ነው
ጆ ባይደን የሩሲያውን ኃያል ቭላድሚር ፑቲንን ‹ነፍሰ በላ› ብለው ከጠሩ በኋላ በሁለቱ መሪዎች መሀል አንድ ሁለት መባባሉ አይሏል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለተሰበቀባቸው የቃላት ጦር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ‹ሌባን ሌባ ቢሰርቀው ምን ሊደንቀው› ዓይነት ይዘት ያለው ምላሽ በመስጠት የጀመሩት ቭላድሚር ፑቲን ጆ ባይደን ፍቃዳቸው ከሆነ በቲቪ በቀጥታ ስርጭት ይግጠሙኝ ብለዋል፡፡ ቭላድሚር ፑቲን በቴሌቪዥን በሰጡት በዚህ ቃለ ምልልስ ባላንጣቸውን አሌክሴ ናቫልኒን በመርዝ ለመግደል እንዳልሞከሩ አስተባብለዋል፡፡ የአሜሪካው ፐሬዝዳንት ጆ ባይደን ለኤቢሲ ኒውስ ቴሌቪዥን ቀደም ብለው እንደተናገሩት ‹ነፍሰ በላው› ፑቲን በ2020 የአሜሪካ ምርጫ እጁን አስገብቶ መዶለቱን ጠቅሰው ለዚህም ‹ዋጋ መክፈሉ አይቀርም› ሲሉ ጠጠር ያለ ሂስ አቅርበዋል፡፡ ሩሲያ ይህን የጆ ባይደንን ንግግር ተከትሎ አምባሳደሯን ወደ አገር ቤት መጥራቷ ይታወሳል፡፡ ሩሲያ አምባሳደሯን አናቶሊ አንቶኖቭን ወደ ሞስኮ ከጠራች በኋላ እንዳለችው አሜሪካ ለሩሲያ ጋር ያላት ግንኙነት ተበላሽቶ ዳግም የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል ስትል ለችግሩ መባባስ ባይደንን ተችታለች፡፡ ጆ ባይደን በበኩላቸው የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ሪፖርትን መሠረት በማድረግ እንደገለጹት ፑቲን በአሜሪካ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት እጃቸውን አስገብተው ሊፈተፍቱ ሞክረዋል ሲሉ ሩሲያን ወቅሰዋል፡፡ ይህ የአሜሪካ የስለላ መሥሪያ ቤት ሪፖርታዥ እንደሚያትተው ሩሲያ ባለፈው ኅዳር የተካሄደውን የአሜሪካ ምርጫ የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እንዲያሸንፉ ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም፡፡ አሜሪካ ይህን የስለላ መሥሪያ ቤት ሪፖርት ተከትሎ በሚቀጥለው ሳምንት በሩሲያ ላይ ጫን ያለ ማዕቀብ እንደምትጥል እየተጠበቀ ነው፡፡
ጆ ባይደንና ፑቲን በነገር እየተቆራቆሱ ነው ጆ ባይደን የሩሲያውን ኃያል ቭላድሚር ፑቲንን ‹ነፍሰ በላ› ብለው ከጠሩ በኋላ በሁለቱ መሪዎች መሀል አንድ ሁለት መባባሉ አይሏል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለተሰበቀባቸው የቃላት ጦር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ‹ሌባን ሌባ ቢሰርቀው ምን ሊደንቀው› ዓይነት ይዘት ያለው ምላሽ በመስጠት የጀመሩት ቭላድሚር ፑቲን ጆ ባይደን ፍቃዳቸው ከሆነ በቲቪ በቀጥታ ስርጭት ይግጠሙኝ ብለዋል፡፡ ቭላድሚር ፑቲን በቴሌቪዥን በሰጡት በዚህ ቃለ ምልልስ ባላንጣቸውን አሌክሴ ናቫልኒን በመርዝ ለመግደል እንዳልሞከሩ አስተባብለዋል፡፡ የአሜሪካው ፐሬዝዳንት ጆ ባይደን ለኤቢሲ ኒውስ ቴሌቪዥን ቀደም ብለው እንደተናገሩት ‹ነፍሰ በላው› ፑቲን በ2020 የአሜሪካ ምርጫ እጁን አስገብቶ መዶለቱን ጠቅሰው ለዚህም ‹ዋጋ መክፈሉ አይቀርም› ሲሉ ጠጠር ያለ ሂስ አቅርበዋል፡፡ ሩሲያ ይህን የጆ ባይደንን ንግግር ተከትሎ አምባሳደሯን ወደ አገር ቤት መጥራቷ ይታወሳል፡፡ ሩሲያ አምባሳደሯን አናቶሊ አንቶኖቭን ወደ ሞስኮ ከጠራች በኋላ እንዳለችው አሜሪካ ለሩሲያ ጋር ያላት ግንኙነት ተበላሽቶ ዳግም የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል ስትል ለችግሩ መባባስ ባይደንን ተችታለች፡፡ ጆ ባይደን በበኩላቸው የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ሪፖርትን መሠረት በማድረግ እንደገለጹት ፑቲን በአሜሪካ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት እጃቸውን አስገብተው ሊፈተፍቱ ሞክረዋል ሲሉ ሩሲያን ወቅሰዋል፡፡ ይህ የአሜሪካ የስለላ መሥሪያ ቤት ሪፖርታዥ እንደሚያትተው ሩሲያ ባለፈው ኅዳር የተካሄደውን የአሜሪካ ምርጫ የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እንዲያሸንፉ ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም፡፡ አሜሪካ ይህን የስለላ መሥሪያ ቤት ሪፖርት ተከትሎ በሚቀጥለው ሳምንት በሩሲያ ላይ ጫን ያለ ማዕቀብ እንደምትጥል እየተጠበቀ ነው፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-56441604
5sports
ሜሲ ለስድስተኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ
የባርሴሎና እና የአርጀንቲናው የፊት መስመር ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች በመባል ለስድሰተኛ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆነ። የ32 ዓመቱ ሜሲ ባሎንዶርን ሲያሸንፍ እ.አ.አ. ከ 2015 በኋላ የመጀመሪያው ሲሆን ለክለቡና ለአገሩ 54 ግቦችን በማስቆጠር ባለፈው ዓመት ደግሞ ከባርሴሎና ጋር የላሊጋው አሸናፊ መሆን ችሏል። • ማንችስተር ዐይኑን የጣለባቸው የአቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ልጆች • ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች የሊቨርፑሉ ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ ደግሞ በዚህ ዓመት ሁለተኛውን ቦታ መያዝ ችሏል። አምስት ጊዜ ባሎንዶርን ማሸነፍ የቻለው የጁቬንቱስና የፖርቹጋር አጥቂው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሦስተኛ መሆኑ ታውቋል። በሴቶች ደግሞ ከአሜሪካ ጋር የዓል ዋንጫን ማሸነፍ የቻለችው ሜገን ራፊኖ የባሎንዶር አሸናፊ ስትሆን እንግሊዛዊቷ ሉሲ ብሮንዝ ሁለተኛ ሆናለች። የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ብራዚላዊው አሊሴን ቤከር ምርጥ በረኛ ሲባል ጀርመናዊው የባርሴሎና ግብ ጠባቂ ማርክ ቴር ስቴገን እና ብራዚላዊው የማንቸስተር ሲቲ በረኛ ኤደርሰን ሁለተኛና ሦስተኛውን ቦታ ይዘዋል። የጁቬንቱሱ የመሀል ተከላካይ ደ ሊክት ከ21 ዓመት በታች ምርጥ ተጫዋች ተብሎ በቀድሞ ባሎንዶር አሸናፊዎች ተመርጧል። ሜሲ ዘንድሮ የባሎንዶር አሸናፊ ሲሆን ውድድሩን ለ11ኛ ተከታታይ ጊዜ ከስፔን ላሊጋ የመጡ ተጫዋቾች እንዲያሸንፉ አድርጓል። • ከመጠጥ ቀጅነት ወደ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሜሲ በሽልማቱ ወቅት ''ምንም እንኳን ባሎንዶርን ያሸነፍኩት ለስድስተኛ ጊዜ ቢሆንም በጣም የተለየ ደስታ ተሰምቶኛል። ባለቤቴ ሁሌም ቢሆን ትልቅ ህልም እንዲኖረን ትነግረኛለች፤ ለዚህም እራሴን በጣም ዕድለኛ አድርጌ ነው የምቆጥረው።'' ሜሲ ለባርሴሎና እስካሁን 700 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን በስሙም 614 ግቦችን አስቆጥሯል። ከቡድኑም ጋር 10 የላሊጋና አራት ቻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ 34 ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።
ሜሲ ለስድስተኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ የባርሴሎና እና የአርጀንቲናው የፊት መስመር ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች በመባል ለስድሰተኛ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆነ። የ32 ዓመቱ ሜሲ ባሎንዶርን ሲያሸንፍ እ.አ.አ. ከ 2015 በኋላ የመጀመሪያው ሲሆን ለክለቡና ለአገሩ 54 ግቦችን በማስቆጠር ባለፈው ዓመት ደግሞ ከባርሴሎና ጋር የላሊጋው አሸናፊ መሆን ችሏል። • ማንችስተር ዐይኑን የጣለባቸው የአቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ልጆች • ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች የሊቨርፑሉ ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ ደግሞ በዚህ ዓመት ሁለተኛውን ቦታ መያዝ ችሏል። አምስት ጊዜ ባሎንዶርን ማሸነፍ የቻለው የጁቬንቱስና የፖርቹጋር አጥቂው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሦስተኛ መሆኑ ታውቋል። በሴቶች ደግሞ ከአሜሪካ ጋር የዓል ዋንጫን ማሸነፍ የቻለችው ሜገን ራፊኖ የባሎንዶር አሸናፊ ስትሆን እንግሊዛዊቷ ሉሲ ብሮንዝ ሁለተኛ ሆናለች። የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ብራዚላዊው አሊሴን ቤከር ምርጥ በረኛ ሲባል ጀርመናዊው የባርሴሎና ግብ ጠባቂ ማርክ ቴር ስቴገን እና ብራዚላዊው የማንቸስተር ሲቲ በረኛ ኤደርሰን ሁለተኛና ሦስተኛውን ቦታ ይዘዋል። የጁቬንቱሱ የመሀል ተከላካይ ደ ሊክት ከ21 ዓመት በታች ምርጥ ተጫዋች ተብሎ በቀድሞ ባሎንዶር አሸናፊዎች ተመርጧል። ሜሲ ዘንድሮ የባሎንዶር አሸናፊ ሲሆን ውድድሩን ለ11ኛ ተከታታይ ጊዜ ከስፔን ላሊጋ የመጡ ተጫዋቾች እንዲያሸንፉ አድርጓል። • ከመጠጥ ቀጅነት ወደ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሜሲ በሽልማቱ ወቅት ''ምንም እንኳን ባሎንዶርን ያሸነፍኩት ለስድስተኛ ጊዜ ቢሆንም በጣም የተለየ ደስታ ተሰምቶኛል። ባለቤቴ ሁሌም ቢሆን ትልቅ ህልም እንዲኖረን ትነግረኛለች፤ ለዚህም እራሴን በጣም ዕድለኛ አድርጌ ነው የምቆጥረው።'' ሜሲ ለባርሴሎና እስካሁን 700 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን በስሙም 614 ግቦችን አስቆጥሯል። ከቡድኑም ጋር 10 የላሊጋና አራት ቻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ 34 ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-50640646
2health
ኮሮናቫይረስ ፡ የአውሮፓ ሕብረት የክትባት አቅርቦት ውዝግብ ቀጥሏል
ሁለተኛው የኮሮናቫይረስ ክትባት አምራች አቅርቦትን አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የአውሮፓ ሕብረት የክትባት ስርጭትን ተስፋ አስቆራጭ አድርጎታል ተባለ፡፡ የዩናይትድ ኪንግደም መድኃኒት አምራች የሆነው አስትራዜኔካ የምርት ችግር መኖሩን መጥቀሱ አቅርቦቱ ከሚጠበቀው በታች ይሆናል ማለት ነው፡፡ የአውሮፓ ኮሚሽን በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እየሞከርኩ ነው ብሏል፡፡ በአንዳንድ የአውሮፓ ክፍሎች የፋይዘር-ባዮኤንቴክ ክትባት አቅርቦት በመቀነሱ ምክንያት ክትባቱ በመቆም ላይ ነው፡፡ ከኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ጋር ክትባቱን የሚሠራው አስትራዜኔካ በመግለጫው ስለ ሁኔታውን ቢጠቅስም ዝርዝር ጉዳዮችን አልሰጠም፡፡ "በአውሮፓው የአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ባለው የማምረቻ ጣቢያ ምክንያት ምርቱ መጀመሪያ ከሚጠበቀው በታች ይሆናል" ብሏል፡፡ ሮይተርስ ስማቸው ያልተጠቀሰ የአውሮፓ ሕብረት ባለሥልጣንን ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው፤ ኩባንያው በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ወደ ሕብረቱ ሊያደርስ ካሰበው የክትባት ብዛት ወደ 60 በመቶ የሚሆነውን ቅናሽ እንደሚያደርግ ለአውሮፓ ሕብረት ተናግሯል። የአስትራዜኔካ ክትባት በአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ ዘንድ ገና ፈቃድ ባያገኝም በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡ አስትራዜኔካ ቢያንስ 300 ሚሊዮን ክትባት ለማቅረብ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ተፈራርሟል፡፡ በመጋቢት ወር መጨረሻ ቃል ከተገባላቸው ሁለት ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶች፤ 600,000 ብቻ ማግኘቷን የኦስትሪያ ሚዲያዎች የዘገቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ከወራት በኋላ ይደርሰሉ ተብሏል። መዘግየቱ "ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የለውም" ሲሉ የኦስትሪያው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሩዶልፍ አንሾበር ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካው ኩባንያ ፋይዘር፤ በቤልጅየም ያለው ፋብሪካውን አቅም ለማሳደግ እየሠራ በመሆኑ ለሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት የሚልከውን የክትባት መጠን እንደሚቀንስ አስታውቋል። የአውሮፓ ሕብረት 600 ሚሊዮን ጠብታ ከፋይዘር ለመግዛት ተስማምቷል፡፡ የፋይዘር ክትባት መቀነስ በጀርመን እና በጣሊያን ውስጥ የሚገኙ በርካታ ክልሎች የመጀመሪያዎቹን ክትባቶች እንዲያቆሙ አስገድዷቸዋል፡፡ በማድሪድ ለህክምና ባለሙያዎች የሚሰጠው ክትባትም ቆሟል፡፡ የክትባት ቅነሳን አስመልክቶ ጣልያን እና ፖላንድ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን ብለው አስፈራርተዋል፡፡ የአውሮፓ ሕብረት የኦክስፎርድ-አስትራዛኔካ ክትባትን ሳያጸድቅ መቆየቱ ያማረረው የሃንጋሪ መንግሥት፤ የአውሮፓ ሕብረትን ይሁንታ ባያገኝም በርካታ የስፑትኒክ ቪ ክትባ ለመግዛት ከሩሲያ ጋር ተስማምቷል።
ኮሮናቫይረስ ፡ የአውሮፓ ሕብረት የክትባት አቅርቦት ውዝግብ ቀጥሏል ሁለተኛው የኮሮናቫይረስ ክትባት አምራች አቅርቦትን አስመልክቶ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የአውሮፓ ሕብረት የክትባት ስርጭትን ተስፋ አስቆራጭ አድርጎታል ተባለ፡፡ የዩናይትድ ኪንግደም መድኃኒት አምራች የሆነው አስትራዜኔካ የምርት ችግር መኖሩን መጥቀሱ አቅርቦቱ ከሚጠበቀው በታች ይሆናል ማለት ነው፡፡ የአውሮፓ ኮሚሽን በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እየሞከርኩ ነው ብሏል፡፡ በአንዳንድ የአውሮፓ ክፍሎች የፋይዘር-ባዮኤንቴክ ክትባት አቅርቦት በመቀነሱ ምክንያት ክትባቱ በመቆም ላይ ነው፡፡ ከኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ጋር ክትባቱን የሚሠራው አስትራዜኔካ በመግለጫው ስለ ሁኔታውን ቢጠቅስም ዝርዝር ጉዳዮችን አልሰጠም፡፡ "በአውሮፓው የአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ባለው የማምረቻ ጣቢያ ምክንያት ምርቱ መጀመሪያ ከሚጠበቀው በታች ይሆናል" ብሏል፡፡ ሮይተርስ ስማቸው ያልተጠቀሰ የአውሮፓ ሕብረት ባለሥልጣንን ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው፤ ኩባንያው በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ወደ ሕብረቱ ሊያደርስ ካሰበው የክትባት ብዛት ወደ 60 በመቶ የሚሆነውን ቅናሽ እንደሚያደርግ ለአውሮፓ ሕብረት ተናግሯል። የአስትራዜኔካ ክትባት በአውሮፓ ሕብረት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ ዘንድ ገና ፈቃድ ባያገኝም በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡ አስትራዜኔካ ቢያንስ 300 ሚሊዮን ክትባት ለማቅረብ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ተፈራርሟል፡፡ በመጋቢት ወር መጨረሻ ቃል ከተገባላቸው ሁለት ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶች፤ 600,000 ብቻ ማግኘቷን የኦስትሪያ ሚዲያዎች የዘገቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ከወራት በኋላ ይደርሰሉ ተብሏል። መዘግየቱ "ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የለውም" ሲሉ የኦስትሪያው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሩዶልፍ አንሾበር ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካው ኩባንያ ፋይዘር፤ በቤልጅየም ያለው ፋብሪካውን አቅም ለማሳደግ እየሠራ በመሆኑ ለሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት የሚልከውን የክትባት መጠን እንደሚቀንስ አስታውቋል። የአውሮፓ ሕብረት 600 ሚሊዮን ጠብታ ከፋይዘር ለመግዛት ተስማምቷል፡፡ የፋይዘር ክትባት መቀነስ በጀርመን እና በጣሊያን ውስጥ የሚገኙ በርካታ ክልሎች የመጀመሪያዎቹን ክትባቶች እንዲያቆሙ አስገድዷቸዋል፡፡ በማድሪድ ለህክምና ባለሙያዎች የሚሰጠው ክትባትም ቆሟል፡፡ የክትባት ቅነሳን አስመልክቶ ጣልያን እና ፖላንድ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን ብለው አስፈራርተዋል፡፡ የአውሮፓ ሕብረት የኦክስፎርድ-አስትራዛኔካ ክትባትን ሳያጸድቅ መቆየቱ ያማረረው የሃንጋሪ መንግሥት፤ የአውሮፓ ሕብረትን ይሁንታ ባያገኝም በርካታ የስፑትኒክ ቪ ክትባ ለመግዛት ከሩሲያ ጋር ተስማምቷል።
https://www.bbc.com/amharic/55777884
3politics
የኬንያ ፕሬዚዳንት የምርጫ አስፈጻሚዎችን አገዱ
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ነሐሴ የተካሄደውን ምርጫና አሸናፊ ያደረጋቸውን ውጤት ያልተቀበሉ አራት የምርጫ ኮሚሽነሮችን ከስራ አገዱ። ፕሬዚዳንት ሩቶ ዛሬ አርብ እንዳስታወቁት ፍርድ ቤት አራቱን ባለስልጣናት ህግ በመጣስ፣ በከባድ ስነ ምግባር ጉድለትና በብቃት ማነስ እንደሚመረምራቸውና ከስልጣናቸውም እንደሚባረሩ ገልጸዋል። ነገር ግን የተቃዋሚ ፓርቲው አመራርና ለአምስት ጊዜ በምርጫ የተወዳደሩት ራይላ ኦዲንጋ ውሳኔውን አውግዘው በመጪው 2027 ምርጫንም መንግሥት ለማጭበርበር ያለመ ነው ብለዋል። “አራቱ ኮሚሽነሮች እንዲባረሩ የተደረጉት ሩቶና አስተዳደራቸው የምርጫ ኮሚሽኑን እንደ አዲስ ለማዋቀርና በራሳቸው ሹመኞች ለመሙላት ነው። ሩቶ በ2022 እያቀደ ያለው በ2027 ምርጫ ለማጭበርበር ነው” ብለዋል ኦዲንጋ ፕሬዚዳንት ሩቶ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ያስታወቁት ነሐሴ በተደረገው ምርጫ ኮሚሽነሮቹ ባሳዩት ባህርይ ምክንያት እንዲታገዱ በብሔራዊ ምክር ቤቱ የቀረበውን ሃሳብ ተከትሎ ነው። ዊሊያም ሩቶ ተፎካካሪያቸውን ራይላ ኦዲንጋን 50.5 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸው ይታወሳል። ነገር ግን የምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀ መንበሩን ጨምሮ ከሰባት ኮሚሽነሮች ውስጥ አራቱ የምርጫው አኃዝ የተሳሳተ እና ውጤቱም “ግልጽ ያልሆነ” ብለውታል።
የኬንያ ፕሬዚዳንት የምርጫ አስፈጻሚዎችን አገዱ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ነሐሴ የተካሄደውን ምርጫና አሸናፊ ያደረጋቸውን ውጤት ያልተቀበሉ አራት የምርጫ ኮሚሽነሮችን ከስራ አገዱ። ፕሬዚዳንት ሩቶ ዛሬ አርብ እንዳስታወቁት ፍርድ ቤት አራቱን ባለስልጣናት ህግ በመጣስ፣ በከባድ ስነ ምግባር ጉድለትና በብቃት ማነስ እንደሚመረምራቸውና ከስልጣናቸውም እንደሚባረሩ ገልጸዋል። ነገር ግን የተቃዋሚ ፓርቲው አመራርና ለአምስት ጊዜ በምርጫ የተወዳደሩት ራይላ ኦዲንጋ ውሳኔውን አውግዘው በመጪው 2027 ምርጫንም መንግሥት ለማጭበርበር ያለመ ነው ብለዋል። “አራቱ ኮሚሽነሮች እንዲባረሩ የተደረጉት ሩቶና አስተዳደራቸው የምርጫ ኮሚሽኑን እንደ አዲስ ለማዋቀርና በራሳቸው ሹመኞች ለመሙላት ነው። ሩቶ በ2022 እያቀደ ያለው በ2027 ምርጫ ለማጭበርበር ነው” ብለዋል ኦዲንጋ ፕሬዚዳንት ሩቶ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ያስታወቁት ነሐሴ በተደረገው ምርጫ ኮሚሽነሮቹ ባሳዩት ባህርይ ምክንያት እንዲታገዱ በብሔራዊ ምክር ቤቱ የቀረበውን ሃሳብ ተከትሎ ነው። ዊሊያም ሩቶ ተፎካካሪያቸውን ራይላ ኦዲንጋን 50.5 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸው ይታወሳል። ነገር ግን የምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀ መንበሩን ጨምሮ ከሰባት ኮሚሽነሮች ውስጥ አራቱ የምርጫው አኃዝ የተሳሳተ እና ውጤቱም “ግልጽ ያልሆነ” ብለውታል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/crgj5g616y5o
3politics
የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላዎችን ለመዝጋት መወሰን የሚኖረው አንድምታ
ባለፈው ረቡዕ ኢትዮጵያ በአልጄሪያ ዋና ከተማዋ አልጀርስ የሚገኘው ኤምባሲዋን ለመዝጋት እንወደሰነችና ከአገሪቱ ጋር የሚኖራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ግን እንደሚቀጥል ኤምባሲው አስታውቋል። በተጨማሪም ኢምባሲው የሚዘጋው እየተካሄደ ባለው ማሻሻያና ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ እንደሆነም ገልጿል። በአልጀርስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ ካሏት ኢምባሲዎችና ቆንስላዎች መካከል ግማሽ ያህሉን እንደምትዘጋ ካሳወቁ በኋላ በይፋ መዘጋቱ የታወቀ የመጀመሪያው ኤምባሲ ነው። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ "አሁን በየቦታው ዶላር ከምንበትን ለስድስት ወር ወይም ለአንድ ዓመት ካሉን ኤምባሲዎች ቢያንስ 30ዎቹ መዘጋት አለባቸው። እነዚህ ተዘግተው አምባሳደራቸው እዚህ ሆኖ ይሰራል" በማለት ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ሊዘጉ እንደሚችሉ ጠቁመው ነበር። ከሰባት ዓመት በፊት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተቀላቀሉት እና አልጄሪያ በነበረው ኤምባሲ ለሦስት ዓመታት ያገለገሉት የዲፕሎማሲ ባለሙያው ሰመረ ኪዳነ ውሳኔው ድንገተኛና አስደንጋጭ ነው ይላሉ። ይህ ውሳኔ ከመምጣቱ ከአራት ወር በፊት ሥራቸውን መልቀቃቸውን ገልፀው፣ "ይህንን ስሰማ ግን ደንግጫለሁ፤ አልጠበቅኩትም። ብዙ የሰራሁበት ኤምባሲ ስለሆነ እና ጉዳቱም ከፍተኛ ስለሆነ ውሳኔው ከብዶኛል" ሲሉ የተፈጠረባቸውን ስሜት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ወር ለሁሉም ሚስዮኖች በጻፈው ደብዳቤ 'ሠራተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ስለተወሰነ በተመደቡበት ቦታ ሲገለገሉበት የነበረውን ንብረት አስረክበው እስከ ነሐሴ 15፣ 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ወደ ዋና መሥሪያ ቤት [አዲስ አበባ] ሪፖርት እንዲያደርጉ' አሳስቧል። ሆኖም የተለያዩ የኤምባሲና የቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ይሰሩ የነበሩ ሠራተኞች በኤምባሲዎች መዘጋትና በድንገተኛው ጥሪ ምክንያት ሥራቸውን አቁመው ወደ አገራቸው እንደማይመለሱ እየተነገረ ነው። ከእነዚህም መካከል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት በብራሰልስ የአውሮፓ ሕብረት ጉዳዮችን ሲከታተሉ የቆዩት መርከብ ነጋሽ አንዱ ናቸው። አቶ መርከብ ሲሰሩበት የነበረው በብራሰልስ የሚገኘው ኤምባሲ ሠራተኞች በአጠቃላይ ወደ አገር ቤት ተመልሰው ሪፖርት እንዲያደርጉ ደብዳቤ ደርሷቸዋል። በዚህም መሰረት አብዛኛው ዲፕሎማት ተመልሶ ስልጠና ተሰጥቶት እንደ አስፈላጊነቱ እንደገና ሊመደብም ላይመደብም ይችላል የሚል ማብራሪያ እንደተሰጣቸው የሚናገሩት አቶ መርከብ፣ "ይህ አሳማኝ አይደለም" ይላሉ። በዚህ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለሱና ሥራ እንዳቆሙ ተናግረዋል። ነገር ግን በመንግሥት እንዲዘጉ ከተወሰኑ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች መካከል የብራሰልሱ ኤምባሲ እንደማይገኝበት ቢቢሲ አረጋግጧል። አቶ መርከብ "ሪፖርት አላደረግኩም፤ ግን እዚህ የነበረኝን ኃላፊነት እና እቃ አስረክቤያለሁ። አልመለስም" በማለት ለዚህ መነሻ ሆኖኛል የሚሏቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣሉ። በትግራይ ክልል ያለው ጦርነት አንዱ ነው የሚሉት አቶ መርከብ፣ በክልሉ የተፈጠረው ቀውስ በቀጥታ ጫና እንደሚያደርስበት በመግለጽ "አገሪቷ ላይ ያለው ሁኔታ ስለሚታወቅ ከአሁን በኋላ ለዚህች አገር ለማገልገል ፍላጎት የለኝም" ብለዋል። ባለፉት ወራት እስከ 'መሰወር' የሚደርስ እስራትና እንግልት በትግራይ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ነው የሚለውን የአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾች ሪፖርቶች በመጥቀስም "ለራሴና ለቤተሰቦቼ ደኅንነት ስለሚያሰጋኝ ላለመመለስ ወስኛለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። መንግሥት ግን ለዚህ ውንጀላ ምላሽ ሲሰጥ 'ማንም በማንነቱ ምክንያት' እንዳልታሰረ በመግለጽ፤ መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎችን ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎች እንደሆኑ መግለጹ ይታወሳል። እስከ ባለፈው የሐምሌ ወር ለዘጠኝ ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጂቡቲና አቡዳቢ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተለያዩ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን ሲሰራ የቆየው ዳዊት ንጉሤ በበኩሉ ውሳኔውና እየቀረቡ ያሉ ምክንያቶች አጥጋቢ አይደሉም ይላል። በዚህም የተነሳ "ጥቂት የማይባሉ ባሉበት አገር ወይም ወደ ሌላ አገር በመሄድ የመቅረት አዝማሚያ" እንዳላቸውም ተናግሯል። "እኔ የማውቃቸው የሥራ ባልደረቦቼ ደንግጠዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ የመመለስ ፍላጎት የላቸውም። የጠራ ነገር ስለሌለ ወደ አገር ቤት ተመልሰንም ሥራ ላይ መቀጠል ላይኖር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።" ብሏል። እነዚህ ወደ አገራቸው አንመለስም የሚሉ የሚስዮኖቹ ልዑካን ከዚህ በፊት በፖለቲካዊ ውሳኔ የተመደቡና ልምድ የሌላቸው እንደሆኑ የሚተቹ ወገኖች አሉ። ወደ አገራቸው እንደማይመለሱ ለቢቢሲ የተናገሩት ሁለቱ ግለሰቦች ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በቀጥታ ወደ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ በመቀላቀል በተለያዩ የወደብ፣ ሕዝብ ለሕዝብ፣ የኢንቨስትመንትና ሌሎች የዲፕሎማሲ ሥራዎች የሰለጠኑና ሲሰሩበት የነበረ መሆናቸውን ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ላይ ኤምባሲዎች ብዙ ገንዘብ እንደሚወጣባቸው በመግለጽ ሚንስቴሩን፣ እንደ አዲስ በማጠናከር ብዙ አዲስ ወጣቶች ሰልጥነው ወደ መሥሪያ ቤቱ እንደተቀላቀሉ ተናግረዋል። ከዚህ ውጪ "ከኤምባሲዎች በማይተናነስ መልኩ ከአምባሳደር በላይ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን አሉ። ውጪ ያላችሁ ኢትዮጵያውያንም ለዚህ ተዘጋጁ፤ ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ አትችልም" የሚል መልዕክት አስተላልፈው ነበር። የኤምባሲዎች መዘጋት ምክንያት ምንድን ነው? ከቀናት በፊት መዘጋቱን ያሳወቀው በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳስታወቀው ለመዘጋቱ ምክንያት የሆነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለው አሉታዊ ጫና፣ የገንዘብ እጥረትና የምጣኔ ሀብት ቀውስ ነው ይላል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ማሻሻያዎችን በማካሄድ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዓለም የበለጠ የምትወከልበትን መንገድ እንደገና ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑ በመታመኑ እንደሆነ ኤምባሲው አስታውቋል። መንግሥት በአገሪቷ ካለው ለውጥ ጋር በተያያዘ መንግሥት በመሥሪያ ቤቱ የተሻሻለ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ለመዘርጋት የሁሉም ተቋማት አደረጃጀትና አሰራር እየተፈሸ መሆኑን በመጥቀስ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ላይ ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል። በዋናነት ግን በዓለም ደረጃ ያጋጠሙ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ግምት ውስጥ በማስገባት ማሻሻያ ለማድረግ መወሰኑንም ምንጮቻችን ገልጸዋል። ገንዘብ የለም ስለተባለ ብዙ ኤምባሲና ቆንስላ ጽህፈት ቤት አያስፈልግም በሚል የሚዘጉ፣ በአንድ አምባሳደር እንዲሰሩ የተደረጉ፣ ከአዲስ አበባ ይሸፈናሉ የተባሉና አንዳንዶቹም የሰው ኃይላቸው ተቀይሮ አልያም ተቀንሶ እንዲሰሩ የሚደረጉ እንዳሉ ተነግሯል። እስከ አሁን ግን ይህንን በተመለከተ የተሰጠ ዝርዝር ይፋዊ መረጃ የለም። ቢቢሲ ግን በሙስካት፣ ዘ-ሄግ፣ ደብሊን፣ ሎስ አንጀለስ፣ ሚኒሶታ፣ ፍራንክፈርት፣ ኢስታንቡል፣ ጓንጁ፣ ሻንጋይ፣ ቾንቺን፣ ሙምባይ፣ አቢጃን፣ ኩዌት፣ ጃካርታ፣ ካምቤራ፣ ብራዚሊያ፣ ኦታዋ፣ ሃቫና፣ ሐራሬ፣ ራባት፣ አልጀርስ፣ ካይሮ፣ ዳካር፣ አክራ፣ ኪጋሊ፣ ኪንሻሳ፣ ሴዑል፣ ዶሃ፣ ባህሬን፣ ስቶክሆልም የሚገኙ ሚስዮኖች እስከ ጥቅምት ወር ባለው ጊዜ እንደሚዘጉ ከምንጮቹ ካገኘው ሰነድ ላይ ተመልክቷል። እነዚህ ሚሲዮኖች ሲገለገሉባቸው የነበሩ እቃዎች ወደ አገር ቤት እንዲመለሱና ባሉበት እንዲታቀቡ ሲል፤ በአንዳንዶቹ ሚሲዮኖች የነበሩ እቃዎች ግን ረጅም ዓመታት ያገለገሉ ስለሆኑ የፌደራል መንግሥት ንብረት ማስወገድ መመሪያና የአገራቱን ሕግ በመከተል እንዲወገዱ አሳስቧል። ከዚህ በተጨማሪ ቢቢሲ ያገኘው ሰነድ፤ በኪጋሊ እና ታንዛኒያ ዶዶማ የነበሩ ኤምባሲዎች በ'ላፕቶፕ አምባሳደር' እና ከዋና መስሪያ ቤት [አዲስ አበባ] ሆኖው እንዲሰሩ መወሰኑን በመግለጽ ለሁሉም ሠራተኞች ስልጠና መዘጋጀቱን ያስረዳል። የትግራይ ጦርነት እና የኤምባሲዎች መዘጋት ጦርነቱ ብዙ ኪሳራ አድርሷል የሚሉት ሰመረ "የሁሉም ጦርነት ኪሳራ ብዙ ስለሆነ ያጋጠመው ኢኮኖሚያዊ ችግርም ከዚህ የሚመነጭ ይመስለኛል" ይላሉ። በሌላ በኩል መንግሥት በጦርነቱ ምክንያት ዓለም አቀፍ ጫና ሲደርስበት፣ በተለይ በአሜሪካና አውሮፓ ከባድ የዲፕሎማሲ ጫና አጋጥሞታል የሚለው ዳዊት በበኩሉ ይህንን ለመመከት ግን "ከዋና መሥሪያ ቤት በሚሰጠን መመሪያ መሠረት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማስረዳት ስንሰራ ነበር" ብሏል። ሆኖም ውጤታማ አልሆነም የሚል ድምዳሜ እንዳለው በመግለጽ "በእኔ ግምት የኤምባሲዎቹ መዘጋት ምክንያት ካለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት በተጨማሪ መንግሥት ተገቢውን የዲፕሎማሲ ሥራ አልሰሩም ያላቸውን በአሜሪካና አውሮፓ የሚገኙትን ጨምሮ እንዲዘጉና ዲፕሎማቶቹም እንዲመለሱ አድርጓል" ሲል ያስረዳል። በዚህ ጉዳይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም። ሆኖም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ወደ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች በላከው ደብዳቤ ለሠራተኞቹ አዲስ ስልጠና ለመስጠት እንዲሁም በተሻሻለ አደረጃጀትና የሰው ኃይል ለማጠናከር እንደሆነ ይገልጻል። ኤምባሲዎችን መዝጋት እና ማዘዋወር ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አዲስ አደለም የሚሉት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ከሳምንት በፊት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ መንግሥት በተለያዩ ዘርፎች የተሃድሶ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቅሰዋል። አሁን መንግሥት እየወሰዳቸው ያላቸው የተሃድሶ እርምጃዎች ብቃትን መጨመር ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውንም አክለው ተናግረዋል። እነዚህ ማሻሻያዎች በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እና በኤምባሲዎች እየተካሄደ መሆኑንም ያነሳሉ። በኤምባሲዎች ውስጥ የሚካሄደው ማሻሻያ ወጪን መቆጠብ እና 'ዲጂታላይዝ' ማድረግ ላይ ያተኮረ መሆኑን አምባሳደሩ ጨምረው ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሁን እያዳረገ ያለው የተሃድሶ እርምጃ "ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ ተቋም" መገንባት መሆኑን በማንሳት አሁን ካለው የትግራይ ጦርነት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አብራርተዋል። የኤምባሲዎቹ መዘጋት የሚፈጥረው ጫና አለ? ኢትዮጵያ ከኃይለሥላሴ ዘመን ጀምሮ በትልልቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች የምትታወቅ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት መስራችና አባል አገር ናት። በርካታ ዓለም ዓቀፋዊ ስምምነቶች ከፈረሙት መካከል እና በእነዚህም ስምምነቶች የምትገዛ ሆና ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት በማምጣት እውቅ ዲፕሎማቶች በማፍራት ትጠራለች። የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶች ባለሙያው ዳዊት "አሁን ይሄን ሁሉ ስኬት በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ታች ወርዷል፤ ያጋጠመን ችግር ከ50 ዓመታት በላይ የተገነባውን ዲፕሎማሲ የሚያፈርስ ነው" የሚል ቅሬታ አለው። መሥሪያ ቤቱ በሚቀጥሉት ዓመታት የዲፕሎማሲ አድማስ የማስፋት፣ ተጨማሪ ኤምባሲዎች የመከፈት እንጂ ይሄንን ያክል ቁጥር ያላቸው ሚስዮኖች የመዝጋት ዕቅድ ኖሮት አያውቅም የሚሉት ደግሞ መርከብ ነጋሽ ናቸው። ሆኖም "አገሪቷ ይሄንን የሚሸከም ኢኮኖሚያዊ አቅም የላትም፤ ይሁን እንጂ ለስብሰባዎችና ሌሎች ጉዳዮች ብዙ ገንዘብ የሚያወጣ መንግሥት ነው" በማለት ውሳኔውን ይተቻሉ። ሚሲዮኖቹ የአገር ጥቅም ለማስከበር የሚያግዙ ሥራዎች በመስራት እንደቆዩ የሚገልጹት ባለሙያዎቹ ውሳኔው ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የሕዝብ ጥቅም ማስከበር ላይ አሉታዊ ጫና እንዳያሳድር ስጋት አላቸው። ኤምባሲዎቹ የውጭ ኢንቨስትመንት በመሳብ፣ የአገር ውስጥ ምርቶች በመሸጥና ቱሪዝም መሳብ ላይ ትኩረት አድርገው ሲንቀሳቀሱ ነበሩም ይላሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ ብዙ ጥቅም የማታገኝባቸው ኤምባሲዎች እንዲሁም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው ሚስዮኖች የሉም ማለት ይቻላል? ስንል ጠይቀናል። የዲፕሎማሲ ባለሙያው ሰመረ፣ ሲጠና ክፍተት ያለበት አንድ ወይም ሁለት ሊኖር ይችላል፤ በአንዴ 30 ኤምባሲዎች መዝጋት ግን ሌላ ትርጉም ነው ያለው ይላሉ። "ብዙ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም አይገኝባቸውም የተባሉ አሉ፤ ብዙ ዜጋም የሌላቸው። ሆኖም እነዚህ ጽህፈት ቤቶች በመዝጋት ከሩቅ ውጤታማ ሥራ መስራት አይቻልም። ከዚህ ይልቅ እንዲጠናከሩ በማድረግ መፍትሄ ማምጣት ይቻል ነበር፤ የሚል እምነት አለኝ" ብለዋል። ይህ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ አለው የሚሉት ባለሙያው፡ "ምክንያቱም እንደምትፈልገው የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ፣ መሸጥ ወይም ከውጭ ማስገባት አይቻልም" ይላሉ።
የኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንስላዎችን ለመዝጋት መወሰን የሚኖረው አንድምታ ባለፈው ረቡዕ ኢትዮጵያ በአልጄሪያ ዋና ከተማዋ አልጀርስ የሚገኘው ኤምባሲዋን ለመዝጋት እንወደሰነችና ከአገሪቱ ጋር የሚኖራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ግን እንደሚቀጥል ኤምባሲው አስታውቋል። በተጨማሪም ኢምባሲው የሚዘጋው እየተካሄደ ባለው ማሻሻያና ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ እንደሆነም ገልጿል። በአልጀርስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ ካሏት ኢምባሲዎችና ቆንስላዎች መካከል ግማሽ ያህሉን እንደምትዘጋ ካሳወቁ በኋላ በይፋ መዘጋቱ የታወቀ የመጀመሪያው ኤምባሲ ነው። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ "አሁን በየቦታው ዶላር ከምንበትን ለስድስት ወር ወይም ለአንድ ዓመት ካሉን ኤምባሲዎች ቢያንስ 30ዎቹ መዘጋት አለባቸው። እነዚህ ተዘግተው አምባሳደራቸው እዚህ ሆኖ ይሰራል" በማለት ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ሊዘጉ እንደሚችሉ ጠቁመው ነበር። ከሰባት ዓመት በፊት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተቀላቀሉት እና አልጄሪያ በነበረው ኤምባሲ ለሦስት ዓመታት ያገለገሉት የዲፕሎማሲ ባለሙያው ሰመረ ኪዳነ ውሳኔው ድንገተኛና አስደንጋጭ ነው ይላሉ። ይህ ውሳኔ ከመምጣቱ ከአራት ወር በፊት ሥራቸውን መልቀቃቸውን ገልፀው፣ "ይህንን ስሰማ ግን ደንግጫለሁ፤ አልጠበቅኩትም። ብዙ የሰራሁበት ኤምባሲ ስለሆነ እና ጉዳቱም ከፍተኛ ስለሆነ ውሳኔው ከብዶኛል" ሲሉ የተፈጠረባቸውን ስሜት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ወር ለሁሉም ሚስዮኖች በጻፈው ደብዳቤ 'ሠራተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ስለተወሰነ በተመደቡበት ቦታ ሲገለገሉበት የነበረውን ንብረት አስረክበው እስከ ነሐሴ 15፣ 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ወደ ዋና መሥሪያ ቤት [አዲስ አበባ] ሪፖርት እንዲያደርጉ' አሳስቧል። ሆኖም የተለያዩ የኤምባሲና የቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ይሰሩ የነበሩ ሠራተኞች በኤምባሲዎች መዘጋትና በድንገተኛው ጥሪ ምክንያት ሥራቸውን አቁመው ወደ አገራቸው እንደማይመለሱ እየተነገረ ነው። ከእነዚህም መካከል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት በብራሰልስ የአውሮፓ ሕብረት ጉዳዮችን ሲከታተሉ የቆዩት መርከብ ነጋሽ አንዱ ናቸው። አቶ መርከብ ሲሰሩበት የነበረው በብራሰልስ የሚገኘው ኤምባሲ ሠራተኞች በአጠቃላይ ወደ አገር ቤት ተመልሰው ሪፖርት እንዲያደርጉ ደብዳቤ ደርሷቸዋል። በዚህም መሰረት አብዛኛው ዲፕሎማት ተመልሶ ስልጠና ተሰጥቶት እንደ አስፈላጊነቱ እንደገና ሊመደብም ላይመደብም ይችላል የሚል ማብራሪያ እንደተሰጣቸው የሚናገሩት አቶ መርከብ፣ "ይህ አሳማኝ አይደለም" ይላሉ። በዚህ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለሱና ሥራ እንዳቆሙ ተናግረዋል። ነገር ግን በመንግሥት እንዲዘጉ ከተወሰኑ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች መካከል የብራሰልሱ ኤምባሲ እንደማይገኝበት ቢቢሲ አረጋግጧል። አቶ መርከብ "ሪፖርት አላደረግኩም፤ ግን እዚህ የነበረኝን ኃላፊነት እና እቃ አስረክቤያለሁ። አልመለስም" በማለት ለዚህ መነሻ ሆኖኛል የሚሏቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣሉ። በትግራይ ክልል ያለው ጦርነት አንዱ ነው የሚሉት አቶ መርከብ፣ በክልሉ የተፈጠረው ቀውስ በቀጥታ ጫና እንደሚያደርስበት በመግለጽ "አገሪቷ ላይ ያለው ሁኔታ ስለሚታወቅ ከአሁን በኋላ ለዚህች አገር ለማገልገል ፍላጎት የለኝም" ብለዋል። ባለፉት ወራት እስከ 'መሰወር' የሚደርስ እስራትና እንግልት በትግራይ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ነው የሚለውን የአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾች ሪፖርቶች በመጥቀስም "ለራሴና ለቤተሰቦቼ ደኅንነት ስለሚያሰጋኝ ላለመመለስ ወስኛለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። መንግሥት ግን ለዚህ ውንጀላ ምላሽ ሲሰጥ 'ማንም በማንነቱ ምክንያት' እንዳልታሰረ በመግለጽ፤ መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎችን ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎች እንደሆኑ መግለጹ ይታወሳል። እስከ ባለፈው የሐምሌ ወር ለዘጠኝ ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጂቡቲና አቡዳቢ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተለያዩ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን ሲሰራ የቆየው ዳዊት ንጉሤ በበኩሉ ውሳኔውና እየቀረቡ ያሉ ምክንያቶች አጥጋቢ አይደሉም ይላል። በዚህም የተነሳ "ጥቂት የማይባሉ ባሉበት አገር ወይም ወደ ሌላ አገር በመሄድ የመቅረት አዝማሚያ" እንዳላቸውም ተናግሯል። "እኔ የማውቃቸው የሥራ ባልደረቦቼ ደንግጠዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ የመመለስ ፍላጎት የላቸውም። የጠራ ነገር ስለሌለ ወደ አገር ቤት ተመልሰንም ሥራ ላይ መቀጠል ላይኖር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።" ብሏል። እነዚህ ወደ አገራቸው አንመለስም የሚሉ የሚስዮኖቹ ልዑካን ከዚህ በፊት በፖለቲካዊ ውሳኔ የተመደቡና ልምድ የሌላቸው እንደሆኑ የሚተቹ ወገኖች አሉ። ወደ አገራቸው እንደማይመለሱ ለቢቢሲ የተናገሩት ሁለቱ ግለሰቦች ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በቀጥታ ወደ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ በመቀላቀል በተለያዩ የወደብ፣ ሕዝብ ለሕዝብ፣ የኢንቨስትመንትና ሌሎች የዲፕሎማሲ ሥራዎች የሰለጠኑና ሲሰሩበት የነበረ መሆናቸውን ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ላይ ኤምባሲዎች ብዙ ገንዘብ እንደሚወጣባቸው በመግለጽ ሚንስቴሩን፣ እንደ አዲስ በማጠናከር ብዙ አዲስ ወጣቶች ሰልጥነው ወደ መሥሪያ ቤቱ እንደተቀላቀሉ ተናግረዋል። ከዚህ ውጪ "ከኤምባሲዎች በማይተናነስ መልኩ ከአምባሳደር በላይ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን አሉ። ውጪ ያላችሁ ኢትዮጵያውያንም ለዚህ ተዘጋጁ፤ ኢትዮጵያ ከዚህ በላይ አትችልም" የሚል መልዕክት አስተላልፈው ነበር። የኤምባሲዎች መዘጋት ምክንያት ምንድን ነው? ከቀናት በፊት መዘጋቱን ያሳወቀው በአልጄሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳስታወቀው ለመዘጋቱ ምክንያት የሆነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለው አሉታዊ ጫና፣ የገንዘብ እጥረትና የምጣኔ ሀብት ቀውስ ነው ይላል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ማሻሻያዎችን በማካሄድ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዓለም የበለጠ የምትወከልበትን መንገድ እንደገና ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑ በመታመኑ እንደሆነ ኤምባሲው አስታውቋል። መንግሥት በአገሪቷ ካለው ለውጥ ጋር በተያያዘ መንግሥት በመሥሪያ ቤቱ የተሻሻለ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ለመዘርጋት የሁሉም ተቋማት አደረጃጀትና አሰራር እየተፈሸ መሆኑን በመጥቀስ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ላይ ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል። በዋናነት ግን በዓለም ደረጃ ያጋጠሙ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ግምት ውስጥ በማስገባት ማሻሻያ ለማድረግ መወሰኑንም ምንጮቻችን ገልጸዋል። ገንዘብ የለም ስለተባለ ብዙ ኤምባሲና ቆንስላ ጽህፈት ቤት አያስፈልግም በሚል የሚዘጉ፣ በአንድ አምባሳደር እንዲሰሩ የተደረጉ፣ ከአዲስ አበባ ይሸፈናሉ የተባሉና አንዳንዶቹም የሰው ኃይላቸው ተቀይሮ አልያም ተቀንሶ እንዲሰሩ የሚደረጉ እንዳሉ ተነግሯል። እስከ አሁን ግን ይህንን በተመለከተ የተሰጠ ዝርዝር ይፋዊ መረጃ የለም። ቢቢሲ ግን በሙስካት፣ ዘ-ሄግ፣ ደብሊን፣ ሎስ አንጀለስ፣ ሚኒሶታ፣ ፍራንክፈርት፣ ኢስታንቡል፣ ጓንጁ፣ ሻንጋይ፣ ቾንቺን፣ ሙምባይ፣ አቢጃን፣ ኩዌት፣ ጃካርታ፣ ካምቤራ፣ ብራዚሊያ፣ ኦታዋ፣ ሃቫና፣ ሐራሬ፣ ራባት፣ አልጀርስ፣ ካይሮ፣ ዳካር፣ አክራ፣ ኪጋሊ፣ ኪንሻሳ፣ ሴዑል፣ ዶሃ፣ ባህሬን፣ ስቶክሆልም የሚገኙ ሚስዮኖች እስከ ጥቅምት ወር ባለው ጊዜ እንደሚዘጉ ከምንጮቹ ካገኘው ሰነድ ላይ ተመልክቷል። እነዚህ ሚሲዮኖች ሲገለገሉባቸው የነበሩ እቃዎች ወደ አገር ቤት እንዲመለሱና ባሉበት እንዲታቀቡ ሲል፤ በአንዳንዶቹ ሚሲዮኖች የነበሩ እቃዎች ግን ረጅም ዓመታት ያገለገሉ ስለሆኑ የፌደራል መንግሥት ንብረት ማስወገድ መመሪያና የአገራቱን ሕግ በመከተል እንዲወገዱ አሳስቧል። ከዚህ በተጨማሪ ቢቢሲ ያገኘው ሰነድ፤ በኪጋሊ እና ታንዛኒያ ዶዶማ የነበሩ ኤምባሲዎች በ'ላፕቶፕ አምባሳደር' እና ከዋና መስሪያ ቤት [አዲስ አበባ] ሆኖው እንዲሰሩ መወሰኑን በመግለጽ ለሁሉም ሠራተኞች ስልጠና መዘጋጀቱን ያስረዳል። የትግራይ ጦርነት እና የኤምባሲዎች መዘጋት ጦርነቱ ብዙ ኪሳራ አድርሷል የሚሉት ሰመረ "የሁሉም ጦርነት ኪሳራ ብዙ ስለሆነ ያጋጠመው ኢኮኖሚያዊ ችግርም ከዚህ የሚመነጭ ይመስለኛል" ይላሉ። በሌላ በኩል መንግሥት በጦርነቱ ምክንያት ዓለም አቀፍ ጫና ሲደርስበት፣ በተለይ በአሜሪካና አውሮፓ ከባድ የዲፕሎማሲ ጫና አጋጥሞታል የሚለው ዳዊት በበኩሉ ይህንን ለመመከት ግን "ከዋና መሥሪያ ቤት በሚሰጠን መመሪያ መሠረት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማስረዳት ስንሰራ ነበር" ብሏል። ሆኖም ውጤታማ አልሆነም የሚል ድምዳሜ እንዳለው በመግለጽ "በእኔ ግምት የኤምባሲዎቹ መዘጋት ምክንያት ካለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት በተጨማሪ መንግሥት ተገቢውን የዲፕሎማሲ ሥራ አልሰሩም ያላቸውን በአሜሪካና አውሮፓ የሚገኙትን ጨምሮ እንዲዘጉና ዲፕሎማቶቹም እንዲመለሱ አድርጓል" ሲል ያስረዳል። በዚህ ጉዳይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም። ሆኖም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ወደ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች በላከው ደብዳቤ ለሠራተኞቹ አዲስ ስልጠና ለመስጠት እንዲሁም በተሻሻለ አደረጃጀትና የሰው ኃይል ለማጠናከር እንደሆነ ይገልጻል። ኤምባሲዎችን መዝጋት እና ማዘዋወር ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አዲስ አደለም የሚሉት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ከሳምንት በፊት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ መንግሥት በተለያዩ ዘርፎች የተሃድሶ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቅሰዋል። አሁን መንግሥት እየወሰዳቸው ያላቸው የተሃድሶ እርምጃዎች ብቃትን መጨመር ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውንም አክለው ተናግረዋል። እነዚህ ማሻሻያዎች በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እና በኤምባሲዎች እየተካሄደ መሆኑንም ያነሳሉ። በኤምባሲዎች ውስጥ የሚካሄደው ማሻሻያ ወጪን መቆጠብ እና 'ዲጂታላይዝ' ማድረግ ላይ ያተኮረ መሆኑን አምባሳደሩ ጨምረው ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሁን እያዳረገ ያለው የተሃድሶ እርምጃ "ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ ተቋም" መገንባት መሆኑን በማንሳት አሁን ካለው የትግራይ ጦርነት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አብራርተዋል። የኤምባሲዎቹ መዘጋት የሚፈጥረው ጫና አለ? ኢትዮጵያ ከኃይለሥላሴ ዘመን ጀምሮ በትልልቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች የምትታወቅ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት መስራችና አባል አገር ናት። በርካታ ዓለም ዓቀፋዊ ስምምነቶች ከፈረሙት መካከል እና በእነዚህም ስምምነቶች የምትገዛ ሆና ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት በማምጣት እውቅ ዲፕሎማቶች በማፍራት ትጠራለች። የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶች ባለሙያው ዳዊት "አሁን ይሄን ሁሉ ስኬት በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ታች ወርዷል፤ ያጋጠመን ችግር ከ50 ዓመታት በላይ የተገነባውን ዲፕሎማሲ የሚያፈርስ ነው" የሚል ቅሬታ አለው። መሥሪያ ቤቱ በሚቀጥሉት ዓመታት የዲፕሎማሲ አድማስ የማስፋት፣ ተጨማሪ ኤምባሲዎች የመከፈት እንጂ ይሄንን ያክል ቁጥር ያላቸው ሚስዮኖች የመዝጋት ዕቅድ ኖሮት አያውቅም የሚሉት ደግሞ መርከብ ነጋሽ ናቸው። ሆኖም "አገሪቷ ይሄንን የሚሸከም ኢኮኖሚያዊ አቅም የላትም፤ ይሁን እንጂ ለስብሰባዎችና ሌሎች ጉዳዮች ብዙ ገንዘብ የሚያወጣ መንግሥት ነው" በማለት ውሳኔውን ይተቻሉ። ሚሲዮኖቹ የአገር ጥቅም ለማስከበር የሚያግዙ ሥራዎች በመስራት እንደቆዩ የሚገልጹት ባለሙያዎቹ ውሳኔው ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የሕዝብ ጥቅም ማስከበር ላይ አሉታዊ ጫና እንዳያሳድር ስጋት አላቸው። ኤምባሲዎቹ የውጭ ኢንቨስትመንት በመሳብ፣ የአገር ውስጥ ምርቶች በመሸጥና ቱሪዝም መሳብ ላይ ትኩረት አድርገው ሲንቀሳቀሱ ነበሩም ይላሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ ብዙ ጥቅም የማታገኝባቸው ኤምባሲዎች እንዲሁም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው ሚስዮኖች የሉም ማለት ይቻላል? ስንል ጠይቀናል። የዲፕሎማሲ ባለሙያው ሰመረ፣ ሲጠና ክፍተት ያለበት አንድ ወይም ሁለት ሊኖር ይችላል፤ በአንዴ 30 ኤምባሲዎች መዝጋት ግን ሌላ ትርጉም ነው ያለው ይላሉ። "ብዙ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም አይገኝባቸውም የተባሉ አሉ፤ ብዙ ዜጋም የሌላቸው። ሆኖም እነዚህ ጽህፈት ቤቶች በመዝጋት ከሩቅ ውጤታማ ሥራ መስራት አይቻልም። ከዚህ ይልቅ እንዲጠናከሩ በማድረግ መፍትሄ ማምጣት ይቻል ነበር፤ የሚል እምነት አለኝ" ብለዋል። ይህ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ አለው የሚሉት ባለሙያው፡ "ምክንያቱም እንደምትፈልገው የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ፣ መሸጥ ወይም ከውጭ ማስገባት አይቻልም" ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-58386457
2health
በዩኬ የበረራ ሰልጣኝ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ ሕይወቷ ማለፉ በምርመራ ተረጋገጠ
በዩናይትድ ኪንግደም የንግድ አየር መንገድ አውሮፕላን ሰልጣኝ አብራሪ የነበረችው ግለሰብ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ ወደ አንጎል በተሰራጨ ኢንፌክሽን ሳቢያ ሕይወቷ ማለፉ በምርመራ ተረጋገጠ። ነዋሪነቷ ሰፎልክ፣ በሪይ ሴንት ኤድመንድስ የነበረው የ21 ዓመቷ ኦሪያና ፔፐር፣ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር በቤልጂየም፣ አንትወርፕ እያለች በወባ ትንኝ ከተነከሰች ከአምስት ቀናት በኋላ ሕይወቷ ማለፉ ተገልጿል። የሰፎልክ ከፍተኛ የወንጀል መርማሪ የሆኑት ናይጀል ፓርስሊይ፣ ወደፊት ጥሩ ሥራ የሚጠብቃት ወጣት ሞት እጅግ አሳዛኝ ነው ብለዋል። በኢፕስዊች ከተማ የሚገኘው የሰፎልክ መርማሪ ፍርድ ቤት፣ ኦሪያና በኦክስፎርድ በኢዚጄት የአብራሪ ሥልጠና ፕሮግራምን የጽሁፍ ፈተናዋን አልፋ የበረራ ብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ወደ ቤልጂየም ማቅናቷን አስረድቷል። ሰልጣኝ አብራሪዋ በአውሮፓውያኑ ሐምሌ መጀመሪያ ቀኝ ዐይኗ ላይ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ በሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ገብታ እንደነበርና የተነከሰችበት አካባቢ እብጠትና መመረዝ እንደታየበት ተነግሯል። የፀረ ተህዋስ መድኃኒት ቢታዘዝላትም ከሁለት ቀናት በኋላ ራሷን በመሳቷ የፍቅር ጓደኛዋ መልሶ ወደ ሆስፒታል ወስዷታል። ከዚያም ከሦስት ቀናት በኋላ ሕይወቷ ሊያልፍ ችሏል። የሞቷ ምክንያት በነፍሳት ንክሻ ምክንያት በሚፈጠር ኢንፌክሽን ሳቢያ ወደ አንጎል የሚሄደው የደም ሥር መዘጋት [ሴፕቲክ ኢምቦሊ] መሆኑን የሕክምና ማስረጃዎች አመልክተዋል። መርማሪው ፓርስሊይ፣ ኦሪያና የሞተችበትን ምክንያት ገለጻ ሲያደርጉ፣ ኦሪያና ሕይወቷ ሊያልፍ የቻለው ግንባሯ ላይ ባጋጠማት የነፍሳት ንክሻ በኋላ በተከሰተ አደገኛ የሆነ ኢንፌክሽን ነው ብለዋል። መርማሪው እንደዚህ ዓይነት አደጋ ከዚህ በፊት አይተው እንደማያውቁም ተናግረዋል። የምርመራ ውጤቱ በተነበበት ወቅትም የኦሪያና አባት ትሪስታን ልጃቸው “ከአባቷ እና ከወንድሟ ኦሊቨር ጋር እንደመብረር የሚያስደስታት ነገር አልነበረም” ብለዋል። ኦሪያና የምትወደውን ሰው አግኝታ፣ ሕልሟን ለማሳካት “የአውሮፕላን አብራሪነት ሥልጠና እየወሰደች ነበር” ሲሉም አክለዋል። የልጃቸው ሞት ምርመራ ከተሰማ በኋላ እናቷ ሉዊዛ በበኩላቸው፣ ለኦሪያና መታሰቢያ ከእንግሊዝ ሴት አብራሪዎች ማኅበር ጋር በመተባበር “ሌሎች ሴት አብራሪዎች ሙያውን እንዲቀላቀሉ ለማበረታታት ነጻ የትምህርት እድል ተዘጋጅቷል” ብለዋል።
በዩኬ የበረራ ሰልጣኝ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ ሕይወቷ ማለፉ በምርመራ ተረጋገጠ በዩናይትድ ኪንግደም የንግድ አየር መንገድ አውሮፕላን ሰልጣኝ አብራሪ የነበረችው ግለሰብ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ ወደ አንጎል በተሰራጨ ኢንፌክሽን ሳቢያ ሕይወቷ ማለፉ በምርመራ ተረጋገጠ። ነዋሪነቷ ሰፎልክ፣ በሪይ ሴንት ኤድመንድስ የነበረው የ21 ዓመቷ ኦሪያና ፔፐር፣ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር በቤልጂየም፣ አንትወርፕ እያለች በወባ ትንኝ ከተነከሰች ከአምስት ቀናት በኋላ ሕይወቷ ማለፉ ተገልጿል። የሰፎልክ ከፍተኛ የወንጀል መርማሪ የሆኑት ናይጀል ፓርስሊይ፣ ወደፊት ጥሩ ሥራ የሚጠብቃት ወጣት ሞት እጅግ አሳዛኝ ነው ብለዋል። በኢፕስዊች ከተማ የሚገኘው የሰፎልክ መርማሪ ፍርድ ቤት፣ ኦሪያና በኦክስፎርድ በኢዚጄት የአብራሪ ሥልጠና ፕሮግራምን የጽሁፍ ፈተናዋን አልፋ የበረራ ብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ወደ ቤልጂየም ማቅናቷን አስረድቷል። ሰልጣኝ አብራሪዋ በአውሮፓውያኑ ሐምሌ መጀመሪያ ቀኝ ዐይኗ ላይ በወባ ትንኝ ከተነከሰች በኋላ በሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ገብታ እንደነበርና የተነከሰችበት አካባቢ እብጠትና መመረዝ እንደታየበት ተነግሯል። የፀረ ተህዋስ መድኃኒት ቢታዘዝላትም ከሁለት ቀናት በኋላ ራሷን በመሳቷ የፍቅር ጓደኛዋ መልሶ ወደ ሆስፒታል ወስዷታል። ከዚያም ከሦስት ቀናት በኋላ ሕይወቷ ሊያልፍ ችሏል። የሞቷ ምክንያት በነፍሳት ንክሻ ምክንያት በሚፈጠር ኢንፌክሽን ሳቢያ ወደ አንጎል የሚሄደው የደም ሥር መዘጋት [ሴፕቲክ ኢምቦሊ] መሆኑን የሕክምና ማስረጃዎች አመልክተዋል። መርማሪው ፓርስሊይ፣ ኦሪያና የሞተችበትን ምክንያት ገለጻ ሲያደርጉ፣ ኦሪያና ሕይወቷ ሊያልፍ የቻለው ግንባሯ ላይ ባጋጠማት የነፍሳት ንክሻ በኋላ በተከሰተ አደገኛ የሆነ ኢንፌክሽን ነው ብለዋል። መርማሪው እንደዚህ ዓይነት አደጋ ከዚህ በፊት አይተው እንደማያውቁም ተናግረዋል። የምርመራ ውጤቱ በተነበበት ወቅትም የኦሪያና አባት ትሪስታን ልጃቸው “ከአባቷ እና ከወንድሟ ኦሊቨር ጋር እንደመብረር የሚያስደስታት ነገር አልነበረም” ብለዋል። ኦሪያና የምትወደውን ሰው አግኝታ፣ ሕልሟን ለማሳካት “የአውሮፕላን አብራሪነት ሥልጠና እየወሰደች ነበር” ሲሉም አክለዋል። የልጃቸው ሞት ምርመራ ከተሰማ በኋላ እናቷ ሉዊዛ በበኩላቸው፣ ለኦሪያና መታሰቢያ ከእንግሊዝ ሴት አብራሪዎች ማኅበር ጋር በመተባበር “ሌሎች ሴት አብራሪዎች ሙያውን እንዲቀላቀሉ ለማበረታታት ነጻ የትምህርት እድል ተዘጋጅቷል” ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cy7q2xzyp3jo
0business
ሊባኖሳውያን የራሳቸውን ገንዘብ ለማውጣት በባንኮች ላይ የሚፈጽሙት ዘረፋ
በሊባኖስ ለዓመታት በዘለቀው የምጣኔ ሃብት ቀውስ ምክንያት፣ ባንኮች ደንበኞቻቸው በሚያወጡት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጥለዋል። ይህ ደግሞ ተጠቃሚዎች ገንዘባቸውን ለማግኘት ኃይል እንዲጠቀሙ እያደረጋቸው ነው። ባለፉት ሳምንታት ዜጎች ካስቀመጡት ገንዘብ የፈለጉትን ያህል ለማውጣት ሽጉጥ ታጥቀወ ወደ ባንኮች በመሄድ ያራሳቸውን ገንዘብ በመሳሪያ በማስገደድ ለማውጣት እየሞከሩ ነው። ይህ ቪዲዮ በዚህ መንገድ ገንዘብ ለማውጣት በሞከሩ ሁለት ሊባኖሳውያን ታሪክ አማካይነት የችግሩን መባባስ ያሳያል።
ሊባኖሳውያን የራሳቸውን ገንዘብ ለማውጣት በባንኮች ላይ የሚፈጽሙት ዘረፋ በሊባኖስ ለዓመታት በዘለቀው የምጣኔ ሃብት ቀውስ ምክንያት፣ ባንኮች ደንበኞቻቸው በሚያወጡት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጥለዋል። ይህ ደግሞ ተጠቃሚዎች ገንዘባቸውን ለማግኘት ኃይል እንዲጠቀሙ እያደረጋቸው ነው። ባለፉት ሳምንታት ዜጎች ካስቀመጡት ገንዘብ የፈለጉትን ያህል ለማውጣት ሽጉጥ ታጥቀወ ወደ ባንኮች በመሄድ ያራሳቸውን ገንዘብ በመሳሪያ በማስገደድ ለማውጣት እየሞከሩ ነው። ይህ ቪዲዮ በዚህ መንገድ ገንዘብ ለማውጣት በሞከሩ ሁለት ሊባኖሳውያን ታሪክ አማካይነት የችግሩን መባባስ ያሳያል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cglg1k2np17o
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ድመትና ውሾች ኮቪድ እንደሚይዛቸው ተደረሰበት
የኮቪድ ቫይረስ በለማዳ የቤት ውስጥ እንሰሳት በተለይም በውሾችና በድመቶች ላይ በስፋት እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ። ጥናቱ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው 196 የኮቪድ ተህዋሲ የጎበኘው ቤተሰብ ላይ ባደረገው ምርምር ነው። በ196 አባወራዎች ላይ በተደረገው ይህ ምርምር 310 ድመቶችና ውሾች የተካተቱበት ነው። ከነዚህ ውስጥ ስድስት ድመቶችና ሰባት ውሾች ተህዋሲውን ተሸክመው ተገኝተዋል። 54ቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም ተህዋሲው ይዞ እንደለቀቃቸው የሚያሳይ የበሽታ ተከላካይ ቅንጣት ተገኝቶባቸዋል። ዶ/ር ኤልስ ብሮንስ በኡትሬች ዩኒቨርስቲ ተመራማሪና መምህር ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች ከድመትና ውሾቻቸው ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ ባያደርጉ ይመረጣል። "እዚህ ጋ ዋናው ነጥብ የእንሰሳቱ ጤና አይደለም" ይላሉ ዶ/ር ኤልስ። ዋናው ነጥብ የቤት እንሰሳቱ "ቫይረሱን ተሸካሚና አዘዋዋሪ ከመሆናቸው ላይ ነው።" አጥኚዎቹ ከቤት እንሰሳቱ ወደ ሰው ቫይረሱ ስለመተላለፉ በእርግጥ ያሉት ነገር ባይኖርም በውሻና በድመት ላይ ግን ተህዋሲው ጎልቶ የማይታይና እነሱም ቢሆን ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክቶችን እንደማያሳዩ ደርሰውበታል። ካሳዩም እጅግ ዝቅተኛ የሆኑ ምልክቶቹን ብቻ ነው የሚሆነው። በጥናቱ የተሳተፉ ተመራማሪዎች በርካታ የቤት እንሰሳት ቫይረሱን ያገኙት ከሰው ልጆች እንደሆነና ነገር ግን በተቃራኒው እንዳልሆነ ገምተዋል። የቤት እንሰሳቱ ባለቤቶች ተህዋሲውን ከድመትና ከውሻ የማግኘታቸው ዕድል ዜሮ ነው ልንል አንችልም፤ ነገር ግን ይህ የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው ብለዋል የእንሰሳት ሐኪምና የማይክሮባዮሎጂካል ዳያግኖስቲክ ሴንተር ባልደረባ ዶ/ር ብራውንስ። በሩሲያ የእንሰሳት ሐኪሞች ለቤት እንሰሳት የተህዋሲውን ክትባት መውጋት መጀመራቸው መዘገቡ ይታወሳል። ዶ/ር ብራውን ግን ይህን ማድረጉ ጥቅሙ አልታይ ብሏቸዋል። "ለጊዜው እንሰሳቱ ተህዋሲውን ወደ ሰው ስለማስተላለፋቸው አስተማማኝ የሆነ ሳይንሳዊ መረጃ አላገኘንም" ይላሉ።
ኮሮናቫይረስ፡ ድመትና ውሾች ኮቪድ እንደሚይዛቸው ተደረሰበት የኮቪድ ቫይረስ በለማዳ የቤት ውስጥ እንሰሳት በተለይም በውሾችና በድመቶች ላይ በስፋት እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ። ጥናቱ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው 196 የኮቪድ ተህዋሲ የጎበኘው ቤተሰብ ላይ ባደረገው ምርምር ነው። በ196 አባወራዎች ላይ በተደረገው ይህ ምርምር 310 ድመቶችና ውሾች የተካተቱበት ነው። ከነዚህ ውስጥ ስድስት ድመቶችና ሰባት ውሾች ተህዋሲውን ተሸክመው ተገኝተዋል። 54ቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም ተህዋሲው ይዞ እንደለቀቃቸው የሚያሳይ የበሽታ ተከላካይ ቅንጣት ተገኝቶባቸዋል። ዶ/ር ኤልስ ብሮንስ በኡትሬች ዩኒቨርስቲ ተመራማሪና መምህር ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች ከድመትና ውሾቻቸው ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ ባያደርጉ ይመረጣል። "እዚህ ጋ ዋናው ነጥብ የእንሰሳቱ ጤና አይደለም" ይላሉ ዶ/ር ኤልስ። ዋናው ነጥብ የቤት እንሰሳቱ "ቫይረሱን ተሸካሚና አዘዋዋሪ ከመሆናቸው ላይ ነው።" አጥኚዎቹ ከቤት እንሰሳቱ ወደ ሰው ቫይረሱ ስለመተላለፉ በእርግጥ ያሉት ነገር ባይኖርም በውሻና በድመት ላይ ግን ተህዋሲው ጎልቶ የማይታይና እነሱም ቢሆን ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክቶችን እንደማያሳዩ ደርሰውበታል። ካሳዩም እጅግ ዝቅተኛ የሆኑ ምልክቶቹን ብቻ ነው የሚሆነው። በጥናቱ የተሳተፉ ተመራማሪዎች በርካታ የቤት እንሰሳት ቫይረሱን ያገኙት ከሰው ልጆች እንደሆነና ነገር ግን በተቃራኒው እንዳልሆነ ገምተዋል። የቤት እንሰሳቱ ባለቤቶች ተህዋሲውን ከድመትና ከውሻ የማግኘታቸው ዕድል ዜሮ ነው ልንል አንችልም፤ ነገር ግን ይህ የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው ብለዋል የእንሰሳት ሐኪምና የማይክሮባዮሎጂካል ዳያግኖስቲክ ሴንተር ባልደረባ ዶ/ር ብራውንስ። በሩሲያ የእንሰሳት ሐኪሞች ለቤት እንሰሳት የተህዋሲውን ክትባት መውጋት መጀመራቸው መዘገቡ ይታወሳል። ዶ/ር ብራውን ግን ይህን ማድረጉ ጥቅሙ አልታይ ብሏቸዋል። "ለጊዜው እንሰሳቱ ተህዋሲውን ወደ ሰው ስለማስተላለፋቸው አስተማማኝ የሆነ ሳይንሳዊ መረጃ አላገኘንም" ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/57662274
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በታንዛኒያ 'የኮቪድ-19 ምልክቶችን ያሳዩ' በርካታ መነኮሳትና ካህናት መሞታቸው ተሰማ
በታንዛኒያ ስድሳ መነኮሳትና 25 ካህናት ባለፉት ሁለት ወራት መሞታቸውን የአገሪቱ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስታወቀች። እነዚህ ካህናትና መነኮሳት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይቶባቸው ነበር ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ህሙማን መረጃ ይፋ በማይሆንባት ታንዛኒያ ቤተ ክርስቲያኗ የአገሬው ሰው ከወረርሽኙ እንዲጠነቀቅ ምክሯን ለግሳለች። የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ወረርሽኙን ሲያጣጥሉ የተሰሙ ሲሆን ባለፈው ወር የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ታንዛኒያ ወረርሽኙን ለመከላከል ክትባት የመስጠት ዕቅድ የላትም ብለዋል። በተቃራኒው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ያላትን ስጋት ስትገልፅ ቆይታለች። የታንዛኒያ የካቶሊክ ኤፒስኮፓል ጉባኤ ፀሐፊ ቄስ ቻርለስ ኪቲማ እንዳስታወቁት የኮቪድ-19 ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል። "ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑትን ጥንቃቄዎች ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። በተለይም የእድሜ ባለፀጎችንና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸውን ሰዎች ትኩረት ልንሰጣቸው ይገባል" በማለት በዳሬሰላምከተማ በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ቄስ ቻርለስ እንዳሉት መነኮሳቱና ካህናቱ ምርመራ ባለማድረጋቸው በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ብላ ለማወጅ ቤተ ክርስቲያኗ ብትቸገርም ሁሉም የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይቶባቸዋል ተብሏል። በርካቶችም በከፍተኛ ሁኔታ ለመተንፈስ ተቸግረው እንደነበር ተገልጿል። "ዜጎች እየተመረመሩ አይደለም። ይሄ ትልቁ ፈተና ነው። ቤተ ክርስቲያኗ በአገሪቱ ውስጥ 500 የጤና ማዕከላት ቢኖሯትም ኮሮናቫይረስ መመርመር አልተፈቀደላትም። እንዲሁም የመመርመሪያ መሳሪያውም የለንም" ብለዋል። ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን በተመለከተ ከመንግሥታቸው በኩል የሚሰጡ አስተያየቶች በቅርቡ እንደተቀየረ ቢናገርም፤ ነገር ግን ታንዛኒያ ግልፅ የሆኑ መመሪያዎችን ባለማስቀመጧ ብዙዎች እንደማይጠነቀቁ ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያኗ የወረርሽኙን አስከፊነት በተመለከተ በተደጋጋሚ የምትናገር ሲሆን ጥር ወር ላይ የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡን ገልፃለች። ታንዛኒያ ካለፈው ዓመት የግንቦት ወር በኋላ የታማሚዎችን ቁጥር ማሳወቅ አቁማለች። የዓለም ጤና ድርጅት የታማሚዎችን ቁጥር እንድታሳውቅና በክትባቱ ላይ ያላትን አቋም እንድትቀይር ተማፅኗል።
ኮሮናቫይረስ፡ በታንዛኒያ 'የኮቪድ-19 ምልክቶችን ያሳዩ' በርካታ መነኮሳትና ካህናት መሞታቸው ተሰማ በታንዛኒያ ስድሳ መነኮሳትና 25 ካህናት ባለፉት ሁለት ወራት መሞታቸውን የአገሪቱ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስታወቀች። እነዚህ ካህናትና መነኮሳት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይቶባቸው ነበር ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ህሙማን መረጃ ይፋ በማይሆንባት ታንዛኒያ ቤተ ክርስቲያኗ የአገሬው ሰው ከወረርሽኙ እንዲጠነቀቅ ምክሯን ለግሳለች። የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ወረርሽኙን ሲያጣጥሉ የተሰሙ ሲሆን ባለፈው ወር የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ታንዛኒያ ወረርሽኙን ለመከላከል ክትባት የመስጠት ዕቅድ የላትም ብለዋል። በተቃራኒው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ያላትን ስጋት ስትገልፅ ቆይታለች። የታንዛኒያ የካቶሊክ ኤፒስኮፓል ጉባኤ ፀሐፊ ቄስ ቻርለስ ኪቲማ እንዳስታወቁት የኮቪድ-19 ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል። "ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑትን ጥንቃቄዎች ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። በተለይም የእድሜ ባለፀጎችንና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸውን ሰዎች ትኩረት ልንሰጣቸው ይገባል" በማለት በዳሬሰላምከተማ በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ቄስ ቻርለስ እንዳሉት መነኮሳቱና ካህናቱ ምርመራ ባለማድረጋቸው በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ብላ ለማወጅ ቤተ ክርስቲያኗ ብትቸገርም ሁሉም የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይቶባቸዋል ተብሏል። በርካቶችም በከፍተኛ ሁኔታ ለመተንፈስ ተቸግረው እንደነበር ተገልጿል። "ዜጎች እየተመረመሩ አይደለም። ይሄ ትልቁ ፈተና ነው። ቤተ ክርስቲያኗ በአገሪቱ ውስጥ 500 የጤና ማዕከላት ቢኖሯትም ኮሮናቫይረስ መመርመር አልተፈቀደላትም። እንዲሁም የመመርመሪያ መሳሪያውም የለንም" ብለዋል። ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን በተመለከተ ከመንግሥታቸው በኩል የሚሰጡ አስተያየቶች በቅርቡ እንደተቀየረ ቢናገርም፤ ነገር ግን ታንዛኒያ ግልፅ የሆኑ መመሪያዎችን ባለማስቀመጧ ብዙዎች እንደማይጠነቀቁ ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያኗ የወረርሽኙን አስከፊነት በተመለከተ በተደጋጋሚ የምትናገር ሲሆን ጥር ወር ላይ የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡን ገልፃለች። ታንዛኒያ ካለፈው ዓመት የግንቦት ወር በኋላ የታማሚዎችን ቁጥር ማሳወቅ አቁማለች። የዓለም ጤና ድርጅት የታማሚዎችን ቁጥር እንድታሳውቅና በክትባቱ ላይ ያላትን አቋም እንድትቀይር ተማፅኗል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56272129
2health
ጃዋር መሐመድ፡ እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው ተገለፀ
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በትናንት ውሎው በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና 14 ተጠርጣሪዎች የቅድመ ምርመራ መዝገብ ባለፈው ቀጠሮ የተሰጡ ትዕዛዞችን አፈፃፀምና የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ነበር ትናንት፣ ሐሙስ (ነሐሴ 14 2012) ቀጠሮ የያዘው። በትናንትናው ዕለትም ባለፈው ቀጠሮ ተሰጥተው ከነበሩ ትዕዛዞች አንደኛው ተጠርጣሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው የሚል ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ከኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት የተላከ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ማስረጃን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። በማስረጃው መሠረት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ሃምዛ አዳነ (ቦረና) እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው በችሎቱ ላይ ተነግሯል። በሌላ በኩል፣ በሌላ ቀጠሮ ትዕዛዝ ተሰጥቶበት የነበረው የአቶ ጃዋር መሐመድ የሕክምና ጉዳይ ነበር። ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሐመድ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። አቶ ጃዋር መሐመድ በትናንቱ ችሎት ሕክምና እንዳላገኙ እና አሁንም እየታመሙ እንደሆነ "ምግብ ስበላ ያስመልሰኛል፤ ያስቀምጠኛል" በማለት የጤንነታቸውን ሁናቴ አስረድተዋል። አቶ ጃዋር ለህይወታቸው ካላቸው ስጋት የተነሳ በማያውቁት ሃኪም መታከም እንደማይፈልጉ ጨምረው ተናግረዋል። በተለይ "ሃጫሉ ሞቷል፤ ጃዋር ነው የቀረው እየተባለ ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ህይወቴ ላይ ስጋት ስላለ ነው ጥብቅ ጥበቃ እያደረገልኝ ያለው፤ እኔም የመንግሥት የሕክምና ተቋማትን ንቄ ሳይሆን ለሕይወቴ ካለኝ ስጋት አንጻር ነው በግል ሀኪሜ መታከም የፈለግሁት" ሲሉ አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጀዋር መሐመድ ሰኞ ዕለት መርማሪ ፖሊስ እና አቃቤ ሕግ እርሳቸው ጋር በመገኘት የግል ሐኪማቸውን ጠርተው መታከም እንደሚችሉ ነግረዋቸው የነበረ ቢሆንም በወቅቱ ግን የሐኪማቸው ስልክ ስላልነበራቸው በነጋታው መጥተው እንዲያክሟቸው ቢጠሯቸውም እንዲያክሟቸው እንዳልተፈቀደ እና እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ አቃቤ ሕግ "በወቅቱ አስቸኳይ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ከነበር ሐኪማቸውን ጠርተው እንዲታከሙ ነግረናቸው ነበር። ይሁን እንጂ ስልካቸው የለኝም በማለት ሊታከሙ አልቻሉም። ከዚያ ውጪ ግን ባለው ደንብ መሰረት ነው መታከም ያለባቸው" በማለት ለችሎቱ አስረድቷል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም አቶ ጃዋር መሐመድ በፌደራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ሁኔታዎችን ማመቻቸቱንና እዚያ የሚታከሙ ከሆነም "ለሕይወታቸው ዋስትና" እንደሚሰጥ ተናግሯል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ የሕገ-መንግሥቱን አንቀጽ 21 በመጥቀስ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ በግል ሐኪማቸው የመታከም መብት እንዳላቸው ይህም እንዲፈፀም ትዕዛዝ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በተጠርጣሪዎች በጠበቆቻቸው በኩል እንደ ቅሬታ ሲነሳ የነበረው የካሜራ ጉዳይ ነው። ይህም ጠበቆች ደንበኞቻቸውን የሚያናግሩበት ስፍራ ላይ ምስልና ድምጽ የሚቀርጽ ካሜራ በመገጠሙ ምስጢራቸው በተጠበቀ መልኩ ደንበኞቻቸውን ማናገር እንዳልቻሉ ነሐሴ 11 2012 በነበራው የችሎት ውሎ ላይ ተናግረው ነበር። ፍርድ ቤቱም ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ምስጢራቸው በተጠበቀ መልኩ ማግኘት እንዲችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ ጠበቆች ትናንት ለችሎቱ እንዳስረዱት፣ ደንበኞቻቸውን ለማነጋገር ሰኞ፣ ረብዑ እና አርብ ቀጠሮ እንደተያዘላቸው ገልፀው ረብዑ እለትም ወደ ስፍራው ባመሩበት ወቅት ካሜራው እንደተገጠመ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀው ስልክ ቁጥራቸውን ትተው ሲስተካከል እንዲጠሯቸው በመንገር መመለሳቸውን ገልፀዋል። በእለቱም (ረብዑ 13/2012) ወደ አስር ሰዓት አካባቢ ተደውሎላቸው መጠራታቸውን፣ ይሁን እንጂ በመምሸቱ የተነሳ ደንበኞቻቸውን ሳያነጋግሩ መመለሳቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለችሎቱ ተናግረዋል። "ዛሬ እንዳነጋግራቸው ነው ተነጋግረን የተመለስነው፤ ዛሬ ጠዋት ስንሄድ ደግሞ ያለ ቀናችሁ ነው የመጣችሁት ገብታችሁ ማናገር አትችሉም ተብለን ተመልሰናል እና ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እያከበረ አይደለም" በማለት እንዲስተካከልላቸው በመጠየቅ ለችሎቱ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። ፖሊስ በበኩሉ የተገጠመው ካሜራ ቤተ መጻህፍትን ለመጠበቅ እንደሆነ በመናገር፣ ጠበቆች ከደንበኞቻቸው ጋር እንዲገናኙ ሌላ ስፍራ ማመቻቸታቸውንና መገናኘታቸውን ለዚህም ደግሞ ጠበቆች ወደ ቅጽር ግቢው ገብተው ደንበኞቻቸውን ሲያናግሩ የፈረሙበትን መዝገብ ማቅረብ እንደሚችሉ ለችሎቱ ተናግሯል። ይሁን እንጂ ጠበቆች "ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር ገብተን ደንበኞቻችንን አናግረን ስንወጣ ነው የምንፈርመው አሁን ገና ደንበኞቻችንን ሳናገኝ እንድንፈርም ይደረጋል፤ ገና ወደ ውስጥ ስንገባ፥ ሳናገኛቸው እየተመለስን ነው" ብለዋል። ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አድምጦ፣ ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ምስጢሩ በተጠበቀበት ስፍራ ማግኘት አለባቸው። ይህም መፈፀም አለበት፤ ይህ ካልተፈፀመ ግን ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ በመግለጽ ውሳኔ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የቅድመ ምርመራ መዝገብ ሥራ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በሙሉ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኦኤምኤን ጋዜጠኛው አቶ መለሰ ዲሪብሳን ጨምሮ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ስር ለሚገኙ ለአራት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራው አለመካሄዱን ጠበቃው አቶ ዋቤ ሐጂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ መለሰ፤ "ከእኛ ጋር ታስረው የነበሩ ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል። ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም ምርመራ እንዲደረግልን አዞ ነበር። ይሁን እንጂ እስካሁን ምርመራ አልተደረገልንም። ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እያከበረ አይደለም" ሲሉ ለችሎቱ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም አቶ መለሰ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ቤተሰቦቻቸውን በስልክ እያገኙ መሆኑን እና እርሳቸው ግን ይህን መከልከላቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። በስተመጨረሻም ችሎቱ የተጠርጣሪዎች እንዲሁም የአቃቤ ሕግ አቤቱታ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት እንዲሁም ደግሞ የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለነሐሴ 18 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ጃዋር መሐመድ፡ እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው ተገለፀ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በትናንት ውሎው በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና 14 ተጠርጣሪዎች የቅድመ ምርመራ መዝገብ ባለፈው ቀጠሮ የተሰጡ ትዕዛዞችን አፈፃፀምና የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ነበር ትናንት፣ ሐሙስ (ነሐሴ 14 2012) ቀጠሮ የያዘው። በትናንትናው ዕለትም ባለፈው ቀጠሮ ተሰጥተው ከነበሩ ትዕዛዞች አንደኛው ተጠርጣሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው የሚል ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ከኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት የተላከ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ማስረጃን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። በማስረጃው መሠረት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ሃምዛ አዳነ (ቦረና) እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው በችሎቱ ላይ ተነግሯል። በሌላ በኩል፣ በሌላ ቀጠሮ ትዕዛዝ ተሰጥቶበት የነበረው የአቶ ጃዋር መሐመድ የሕክምና ጉዳይ ነበር። ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሐመድ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። አቶ ጃዋር መሐመድ በትናንቱ ችሎት ሕክምና እንዳላገኙ እና አሁንም እየታመሙ እንደሆነ "ምግብ ስበላ ያስመልሰኛል፤ ያስቀምጠኛል" በማለት የጤንነታቸውን ሁናቴ አስረድተዋል። አቶ ጃዋር ለህይወታቸው ካላቸው ስጋት የተነሳ በማያውቁት ሃኪም መታከም እንደማይፈልጉ ጨምረው ተናግረዋል። በተለይ "ሃጫሉ ሞቷል፤ ጃዋር ነው የቀረው እየተባለ ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ህይወቴ ላይ ስጋት ስላለ ነው ጥብቅ ጥበቃ እያደረገልኝ ያለው፤ እኔም የመንግሥት የሕክምና ተቋማትን ንቄ ሳይሆን ለሕይወቴ ካለኝ ስጋት አንጻር ነው በግል ሀኪሜ መታከም የፈለግሁት" ሲሉ አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጀዋር መሐመድ ሰኞ ዕለት መርማሪ ፖሊስ እና አቃቤ ሕግ እርሳቸው ጋር በመገኘት የግል ሐኪማቸውን ጠርተው መታከም እንደሚችሉ ነግረዋቸው የነበረ ቢሆንም በወቅቱ ግን የሐኪማቸው ስልክ ስላልነበራቸው በነጋታው መጥተው እንዲያክሟቸው ቢጠሯቸውም እንዲያክሟቸው እንዳልተፈቀደ እና እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ አቃቤ ሕግ "በወቅቱ አስቸኳይ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ከነበር ሐኪማቸውን ጠርተው እንዲታከሙ ነግረናቸው ነበር። ይሁን እንጂ ስልካቸው የለኝም በማለት ሊታከሙ አልቻሉም። ከዚያ ውጪ ግን ባለው ደንብ መሰረት ነው መታከም ያለባቸው" በማለት ለችሎቱ አስረድቷል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም አቶ ጃዋር መሐመድ በፌደራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ሁኔታዎችን ማመቻቸቱንና እዚያ የሚታከሙ ከሆነም "ለሕይወታቸው ዋስትና" እንደሚሰጥ ተናግሯል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ የሕገ-መንግሥቱን አንቀጽ 21 በመጥቀስ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ በግል ሐኪማቸው የመታከም መብት እንዳላቸው ይህም እንዲፈፀም ትዕዛዝ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በተጠርጣሪዎች በጠበቆቻቸው በኩል እንደ ቅሬታ ሲነሳ የነበረው የካሜራ ጉዳይ ነው። ይህም ጠበቆች ደንበኞቻቸውን የሚያናግሩበት ስፍራ ላይ ምስልና ድምጽ የሚቀርጽ ካሜራ በመገጠሙ ምስጢራቸው በተጠበቀ መልኩ ደንበኞቻቸውን ማናገር እንዳልቻሉ ነሐሴ 11 2012 በነበራው የችሎት ውሎ ላይ ተናግረው ነበር። ፍርድ ቤቱም ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ምስጢራቸው በተጠበቀ መልኩ ማግኘት እንዲችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ ጠበቆች ትናንት ለችሎቱ እንዳስረዱት፣ ደንበኞቻቸውን ለማነጋገር ሰኞ፣ ረብዑ እና አርብ ቀጠሮ እንደተያዘላቸው ገልፀው ረብዑ እለትም ወደ ስፍራው ባመሩበት ወቅት ካሜራው እንደተገጠመ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀው ስልክ ቁጥራቸውን ትተው ሲስተካከል እንዲጠሯቸው በመንገር መመለሳቸውን ገልፀዋል። በእለቱም (ረብዑ 13/2012) ወደ አስር ሰዓት አካባቢ ተደውሎላቸው መጠራታቸውን፣ ይሁን እንጂ በመምሸቱ የተነሳ ደንበኞቻቸውን ሳያነጋግሩ መመለሳቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለችሎቱ ተናግረዋል። "ዛሬ እንዳነጋግራቸው ነው ተነጋግረን የተመለስነው፤ ዛሬ ጠዋት ስንሄድ ደግሞ ያለ ቀናችሁ ነው የመጣችሁት ገብታችሁ ማናገር አትችሉም ተብለን ተመልሰናል እና ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እያከበረ አይደለም" በማለት እንዲስተካከልላቸው በመጠየቅ ለችሎቱ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። ፖሊስ በበኩሉ የተገጠመው ካሜራ ቤተ መጻህፍትን ለመጠበቅ እንደሆነ በመናገር፣ ጠበቆች ከደንበኞቻቸው ጋር እንዲገናኙ ሌላ ስፍራ ማመቻቸታቸውንና መገናኘታቸውን ለዚህም ደግሞ ጠበቆች ወደ ቅጽር ግቢው ገብተው ደንበኞቻቸውን ሲያናግሩ የፈረሙበትን መዝገብ ማቅረብ እንደሚችሉ ለችሎቱ ተናግሯል። ይሁን እንጂ ጠበቆች "ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር ገብተን ደንበኞቻችንን አናግረን ስንወጣ ነው የምንፈርመው አሁን ገና ደንበኞቻችንን ሳናገኝ እንድንፈርም ይደረጋል፤ ገና ወደ ውስጥ ስንገባ፥ ሳናገኛቸው እየተመለስን ነው" ብለዋል። ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አድምጦ፣ ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ምስጢሩ በተጠበቀበት ስፍራ ማግኘት አለባቸው። ይህም መፈፀም አለበት፤ ይህ ካልተፈፀመ ግን ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ በመግለጽ ውሳኔ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የቅድመ ምርመራ መዝገብ ሥራ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በሙሉ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኦኤምኤን ጋዜጠኛው አቶ መለሰ ዲሪብሳን ጨምሮ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ስር ለሚገኙ ለአራት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራው አለመካሄዱን ጠበቃው አቶ ዋቤ ሐጂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ መለሰ፤ "ከእኛ ጋር ታስረው የነበሩ ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል። ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም ምርመራ እንዲደረግልን አዞ ነበር። ይሁን እንጂ እስካሁን ምርመራ አልተደረገልንም። ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እያከበረ አይደለም" ሲሉ ለችሎቱ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም አቶ መለሰ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ቤተሰቦቻቸውን በስልክ እያገኙ መሆኑን እና እርሳቸው ግን ይህን መከልከላቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። በስተመጨረሻም ችሎቱ የተጠርጣሪዎች እንዲሁም የአቃቤ ሕግ አቤቱታ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት እንዲሁም ደግሞ የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለነሐሴ 18 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
https://www.bbc.com/amharic/53852370
2health
የአሜሪካ ግዛቶች የኮቪድ-19 ክልከላዎችን ማንሳት ጀመሩ
የቴክሳስ፣ ሚሺጋን፣ ሉዊዚያና እና ሚሲሲፒ ግዛቶች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይሆንም አሉ። የግዛቶቹ አስተዳዳሪዎች ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ኮቪድ-19 በአሜሪካ ለአራተኛ ዙር ሊሰራጭ ይችላል የሚል ስጋት ባለበት ወቅት ነው። ሪፓብሊካኑ የቴክሳስ ገዢ ግሬግ አቦት፤ “ቴክሳስን 100% ለመክፈት ጊዜ አሁን ነው” ብለዋል። ቴክሳስ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይደለም በማለት ያወጀች ትልቋ የአሜሪካ ግዛት ነች። በዚህም መሰረት ከአንድ ሳምንት በኋላ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይሆንም። ዜጎችም በመንግሥት ተቋማት ማስክ ሳያደርጉ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፤ በገበያ ስፍራዎችም ማስክ ሳያደርጉ መገበያየት ይችላሉ። የሚሲሲፒ ገዢ በበኩላቸው በቀጣይ ቀናት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይሆንም ብለዋል። ታቴ ሪቭስ፤ “ማስክ የማድረግ ግዴታ እናነሳለን። የንግድ ተቋማትም ከነገ ጀምሮ በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ” ሲሉ ተናግረዋል። የባይደን አስተዳደር ግን አሁንም ቢሆን የኮሮናቫይረስ ክልከላዎች መተግበር አለባቸው የሚል ጽኑ አቋም አለው። የኮሮናቫይረስ ክትባት በአሜሪካ በስፋት በመከፋፈሉ፤ በርካታ አሜሪካውያን ክትባቱን በመውሰዳቸው ሕይወት ወደቀደመ መልኩ ለመመለስ ፍላጎት እንዲጨምር አድርጓል ተብሏል። ባይደን ትናንት አሜሪካ ለሁሉም አዋቂ አሜሪካውያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የኮቪድ-19 ክትባት ማቅረብ ይቻላታል ብለዋል። በቅርብ ሳምንታት በቫይረሱ የሚያዙ እና የሚሞቱ አሜሪካውያን ቁጥር ቀንሷል። ይሁን እንጂ የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) አገሪቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ የማታደርግ ከሆነ ወረርሽኙ ለ4ኛ ዙር ሊከሰት ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። አሜሪካ እስካሁን 28 ሚሊዮን ሕዝቧ በቫይረሱ መያዙን በምርመራ ያረጋገጠች ሲሆን፤ 516 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የአሜሪካ ግዛቶች የኮቪድ-19 ክልከላዎችን ማንሳት ጀመሩ የቴክሳስ፣ ሚሺጋን፣ ሉዊዚያና እና ሚሲሲፒ ግዛቶች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይሆንም አሉ። የግዛቶቹ አስተዳዳሪዎች ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ኮቪድ-19 በአሜሪካ ለአራተኛ ዙር ሊሰራጭ ይችላል የሚል ስጋት ባለበት ወቅት ነው። ሪፓብሊካኑ የቴክሳስ ገዢ ግሬግ አቦት፤ “ቴክሳስን 100% ለመክፈት ጊዜ አሁን ነው” ብለዋል። ቴክሳስ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይደለም በማለት ያወጀች ትልቋ የአሜሪካ ግዛት ነች። በዚህም መሰረት ከአንድ ሳምንት በኋላ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይሆንም። ዜጎችም በመንግሥት ተቋማት ማስክ ሳያደርጉ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፤ በገበያ ስፍራዎችም ማስክ ሳያደርጉ መገበያየት ይችላሉ። የሚሲሲፒ ገዢ በበኩላቸው በቀጣይ ቀናት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ግዴታ አይሆንም ብለዋል። ታቴ ሪቭስ፤ “ማስክ የማድረግ ግዴታ እናነሳለን። የንግድ ተቋማትም ከነገ ጀምሮ በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ” ሲሉ ተናግረዋል። የባይደን አስተዳደር ግን አሁንም ቢሆን የኮሮናቫይረስ ክልከላዎች መተግበር አለባቸው የሚል ጽኑ አቋም አለው። የኮሮናቫይረስ ክትባት በአሜሪካ በስፋት በመከፋፈሉ፤ በርካታ አሜሪካውያን ክትባቱን በመውሰዳቸው ሕይወት ወደቀደመ መልኩ ለመመለስ ፍላጎት እንዲጨምር አድርጓል ተብሏል። ባይደን ትናንት አሜሪካ ለሁሉም አዋቂ አሜሪካውያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የኮቪድ-19 ክትባት ማቅረብ ይቻላታል ብለዋል። በቅርብ ሳምንታት በቫይረሱ የሚያዙ እና የሚሞቱ አሜሪካውያን ቁጥር ቀንሷል። ይሁን እንጂ የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ) አገሪቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ የማታደርግ ከሆነ ወረርሽኙ ለ4ኛ ዙር ሊከሰት ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። አሜሪካ እስካሁን 28 ሚሊዮን ሕዝቧ በቫይረሱ መያዙን በምርመራ ያረጋገጠች ሲሆን፤ 516 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56262360
0business
ኢቲ 302 ቦይንግ 737፡ ልክ የዛሬ አንድ ዓመት በኢትዮጵያው አውሮፕላን ላይ ምን ተከሰተ?
ዕሑድ መጋቢት 1 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያዊያን አስደንጋጭ ዕለት ነበር። እርግጥ 'የኢትዮጵያ'' ታሪኩ የከፍታ ነው። የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ሲንደፋደፍ 'ET' ከፍ ብሎ በሯል፤ያውም ለዘመናት። በትርፍም፣ በአውሮፕላን ብዛትም፣ በበረራ ስፋትም፣ በመስተንግዶ ጥራትም ሞገስ ተለይቶት አያውቅም። በጥቅሉ ከፍ እንጂ ዝቅ ብሎ አያውቅም። በዚያች ሰንበት ግን 'ማክስ-8' ጎንበስ ካለበት ቀና አልል አለ። አብራሪዎቹ የቻሉትን ሞከሩ። አልሆነም። • ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በመግለጫ ምልልስ እየተወዛገቡ ነው የአውሮፕላኑ ሠሪዎች ጥፋቱን በአብራሪዎች ለመደፍደፍ የቀደማቸው አልነበረም። መጀመርያ ጥርጣሪያቸውን አስቀደሙ፤ ቀጥለው የሚዲያ ዘመቻ ከፈቱ። ችግሩ ከአብራሪዎቹ ካልሆነ ከአውሮፕላኑ ፈጣሪዎች እንደሚሆን አላጡትም። ጣት ወደነርሱ ሲቀሰር ደግሞ ሌላ ቁስል ይቀሰቅሳል፤ ኢንዶኒዢያ። ያን ቁስል መልሶ መነካካት የቦይንግን ስምና ዝና ጠራርጎ የሚወስድ ችግር ያስከትላል። ስለዚህ በቻሉት ሁሉ ነገሩን ከነገርሱ ማራቅ ነበረባቸው። ያን ዕለት ማለዳ ምን ሆነ? ከራሱ አልፎ ለአህጉሪቱ አየር መንገዶች በክፉ ጊዜ ደርሶላቸዋል። በዚህ ከፍታ ላይ እያለ ነበር ክፉው አጋጣሚ የተከሰተው። በማለዳ ዘመናዊውን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ወደ ናይሮቢ አሰማራ። ብዙ ጊዜ ሙሉ በሚባል ደረጃ ተጓዦችን የሚያስተናግደው የናይሮቢው በረራ 149 መንገደኞችን አሳፍሮ ነበር። ተጨማሪ 8 የአውሮፕላኑ ሠራተኞችም ነበሩበት። የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ወደ ናይሮቢ ኬንያ ለመብረር እንዲያኮበኩብ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን መልካም ፈቃድ ያገኘው ከጠዋት 02 ሠዓት ከ37 ደቂቃ ነበር። አውሮፕላኑ ክንፉን ዘርግቶ ተንደርድሮ ተነሳ። ልክ ከአንድ ደቂቃና ከ10 ሰከንዶች በኋላ ከተለመደው የተለየ ሁኔታ እንዳጋጠመ በአብራሪዎቹ ታወቀ። ረዳት አብራሪው ለዋና አብራሪው ይህንኑ አሳወቀ። ዋና አብራሪውም ችግሩን ለማስወገድ በማለት አውሮፕላኑ በራሱ ሥርዓት እንዲበር ጥረት ማድረግ ጀመረ። አብራሪዎቹ የገጠማቸውን ችግር ለማስተካከል ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም እንዳሰቡት ሊሳካላቸው አልቻለም። ወዲያውኑ ረዳት አብራሪው ስላጋጠማቸው ነገር ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሪፖርት አደረገ። ረዳት አብራሪው ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አውሮፕላኑን የመቆጣጠር ችግር እንደገጠመው አሳወቁ። ብዙም ሳይቆዩ አውሮፕላኑ ከአብራሪዎቹ ቁጥጥር ውጪ እየሆነ መጣ። አፍንጫውን ወደ ምድር እያገደለ አስቸገረ። አብራሪዎቹ ይህንን ለማስተካከል በከፍተኛ ጥድፊያ ጥረት እያደረጉ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር በመገናኘት 14ሺህ ጫማ ላይ መቆየት እንደሚሹ ገለጹ። አውሮፕላኑ ቀና ሊል አልቻለም። ጭራሽ አልታዘዝ አለ። የጀመሩት በረራ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ስላጋጠመው ወደ ተነሱበት ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መመለስ እንደሚፈልጉ አሳወቁ። ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ወዲያውኑ ፍቃድ አገኙ። ይህ ሁሉ የሆነው በደቂቃዎች ልዩነት ነበር። አሁንም አብራሪዎቹ አውሮፕላኑ ካዘቀዘቀበት ከፍ ለማድረግ ጥረታቸው አልተቋረጠም፤ አውሮፕላኑ ግን በስሪቱ ግድፈት እንደሆነ በሚገመት መልኩ አሻገረኝ አለ። ይባስ ብሎ ቁልቁል መምዘገዘግ ጀመረ። በመጨረሻም አብራሪዎቹ ከበረራ ተቆጣጣሪዎች ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ። የአቶ ተወልደ ትዝታ ከ150 በላይ ሰዎችን የያዘው የኢቲ302 የአውሮፕላን ሳይከሰከስ እንዳልቀረ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስጋት ቢገባቸውም ለደቂቃዎች ተስፋ አልቆረጡም ነበረ። ከደቂቃዎች በኋላም የአሰቃቂው አደጋ መከሰት የማይሸሹት እውነት ሆነ። የአደጋውን መከሰት ቀድመው የሰሙት የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሰንበት ቅዳሴን እየታደሙ ነበር። "የአደጋውን መድረስ ዜና የሰማሁት ጧት ነው። በእርግጥም በጣም ክው አድርጎኛል። በጣም፤ እጅግ በጣም ነው ያሳዘንኩት" ሲሉ መጋቢት አንድ ቀን ጠዋት የተፈጠረባቸውን ስሜት ያስታውሳሉ። እሁድ ረፋድ ላይ የአደጋውን መከሰት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጽህፈት ቤት በማኅበራዊ ገጹ ላይ አረዳ። በደረሰው አደጋም ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም ሐዘኑን ገለጸ። ከዚህ በኋላ አደጋው የዓለም መገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ርእስ ሆነ፤ የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ብርክ ያዘው። ተመሳሳይ አውሮፕላን የገዛ ሐሳብ ገባው። ሊገዛ ያሰበ ቀብዴን መልሱልኝ ማለት ጀመረ። የቦይንግ ገበያ ምስቅልቅል ውስጥ ገባ። በተለይ ከዚህ አደጋ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ የኢንዶኔዢያ ላየን ኤር አየር መንገድ አሰቃቂና በባህሪው ተመሳሳይ አደጋ አጋጥሞት እንደነበር ሲታወስ ነገሮች ወዴት እያመሩ እንደሆነ ግልጽ ነበር። ለአደጋው ምክንያት ተለያዩ መላ ምቶች ቢቀርቡም በአውሮፕላኑ ላይ ያለ ችግር ሊሆን እንደሚችል በመገለጹ ጥያቄዎች በአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ላይ በረታ። ይህንንም ተከትሎ ሌላ አደጋን ለማስቀረት እጅግ ዘመናዊ እንደሆኑ የተነገረላቸው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ስሪት አውሮፕላኖች ከበረራ ውጪ የማድረግ እርምጃን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች ወሰዱ። በኢትዮጵያ አውሮፕላን ላይ የደረሰው አደጋ እጅግ የከፋ ስለነበረ አንድም ሰው ከአደጋው አልተረፈም። ከአዲስ አበባ በ40 ኪሎ ሜትሮች አካባቢ ርቀት ላይ ከምትገኘው ቱሉ ፈራ ሜዳ ላይ የወደቀውን የአውሮፕላኑን ስብርባሪና የአደጋውን ሰለባዎች አካል ለማግኘት የቀናት ቁፋሮ አስፈልጎ ነበር። ለሟች ቤተሰቦች ሐዘኑ ድርብ ሆነ። ከአደጋው ጋር በተያያዘ አንዳንድ ወገኖች የአብራሪዎች ችግር አድርገው ለማቅረብ ቢሞክሩም የአደጋው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ግን አብራሪዎቹ ክስተቱን ለማስቀረት መጣራቸውንና በአውሮፕላኑ ላይ የተገጠመው የመቆጣጠሪያ ሥርዓት ለአደጋው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አመልክቶ ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማሪያምም ከመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ጋር በተያያዘ "ፓይለቶቹ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚጠበቅባቸውን ተገቢ እርምጃ በመውሰድ ያላቸውን ከፍ ያለ ሙያዊ ብቃት በማስመስከራቸው" አየር መንገዱ እንደሚኮራባቸው መስክረዋል። አደጋው በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ሕይወት ከማሳጣቱ ባሻገር ዘመናዊ የተባለውን አውሮፕላን ባመረተው ቦይንግ ኩባንያ ላይ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎችን አስከትሏል። በኩባንያው ላይ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ዋና ሥራ አስፈጻሚውም ከሥራቸው ተባረዋል። ተመሳሳዩን አውሮፕላን እንዲያመርትላቸው ያዘዙ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶችም ትዕዛዛቸውን ከመሰረዝ አልፈው ሥራ ላይ የነበሩትን ከበረራ ውጪ አደረጓቸው። በዚህም ባለዝናው የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ በወራት ጊዜ ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ኪሳራ አጋጠመው። ጉዳዩም ዛሬም ድረስ መቋጫ አላገኘም።
ኢቲ 302 ቦይንግ 737፡ ልክ የዛሬ አንድ ዓመት በኢትዮጵያው አውሮፕላን ላይ ምን ተከሰተ? ዕሑድ መጋቢት 1 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያዊያን አስደንጋጭ ዕለት ነበር። እርግጥ 'የኢትዮጵያ'' ታሪኩ የከፍታ ነው። የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ሲንደፋደፍ 'ET' ከፍ ብሎ በሯል፤ያውም ለዘመናት። በትርፍም፣ በአውሮፕላን ብዛትም፣ በበረራ ስፋትም፣ በመስተንግዶ ጥራትም ሞገስ ተለይቶት አያውቅም። በጥቅሉ ከፍ እንጂ ዝቅ ብሎ አያውቅም። በዚያች ሰንበት ግን 'ማክስ-8' ጎንበስ ካለበት ቀና አልል አለ። አብራሪዎቹ የቻሉትን ሞከሩ። አልሆነም። • ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በመግለጫ ምልልስ እየተወዛገቡ ነው የአውሮፕላኑ ሠሪዎች ጥፋቱን በአብራሪዎች ለመደፍደፍ የቀደማቸው አልነበረም። መጀመርያ ጥርጣሪያቸውን አስቀደሙ፤ ቀጥለው የሚዲያ ዘመቻ ከፈቱ። ችግሩ ከአብራሪዎቹ ካልሆነ ከአውሮፕላኑ ፈጣሪዎች እንደሚሆን አላጡትም። ጣት ወደነርሱ ሲቀሰር ደግሞ ሌላ ቁስል ይቀሰቅሳል፤ ኢንዶኒዢያ። ያን ቁስል መልሶ መነካካት የቦይንግን ስምና ዝና ጠራርጎ የሚወስድ ችግር ያስከትላል። ስለዚህ በቻሉት ሁሉ ነገሩን ከነገርሱ ማራቅ ነበረባቸው። ያን ዕለት ማለዳ ምን ሆነ? ከራሱ አልፎ ለአህጉሪቱ አየር መንገዶች በክፉ ጊዜ ደርሶላቸዋል። በዚህ ከፍታ ላይ እያለ ነበር ክፉው አጋጣሚ የተከሰተው። በማለዳ ዘመናዊውን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ወደ ናይሮቢ አሰማራ። ብዙ ጊዜ ሙሉ በሚባል ደረጃ ተጓዦችን የሚያስተናግደው የናይሮቢው በረራ 149 መንገደኞችን አሳፍሮ ነበር። ተጨማሪ 8 የአውሮፕላኑ ሠራተኞችም ነበሩበት። የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ወደ ናይሮቢ ኬንያ ለመብረር እንዲያኮበኩብ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን መልካም ፈቃድ ያገኘው ከጠዋት 02 ሠዓት ከ37 ደቂቃ ነበር። አውሮፕላኑ ክንፉን ዘርግቶ ተንደርድሮ ተነሳ። ልክ ከአንድ ደቂቃና ከ10 ሰከንዶች በኋላ ከተለመደው የተለየ ሁኔታ እንዳጋጠመ በአብራሪዎቹ ታወቀ። ረዳት አብራሪው ለዋና አብራሪው ይህንኑ አሳወቀ። ዋና አብራሪውም ችግሩን ለማስወገድ በማለት አውሮፕላኑ በራሱ ሥርዓት እንዲበር ጥረት ማድረግ ጀመረ። አብራሪዎቹ የገጠማቸውን ችግር ለማስተካከል ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም እንዳሰቡት ሊሳካላቸው አልቻለም። ወዲያውኑ ረዳት አብራሪው ስላጋጠማቸው ነገር ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሪፖርት አደረገ። ረዳት አብራሪው ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አውሮፕላኑን የመቆጣጠር ችግር እንደገጠመው አሳወቁ። ብዙም ሳይቆዩ አውሮፕላኑ ከአብራሪዎቹ ቁጥጥር ውጪ እየሆነ መጣ። አፍንጫውን ወደ ምድር እያገደለ አስቸገረ። አብራሪዎቹ ይህንን ለማስተካከል በከፍተኛ ጥድፊያ ጥረት እያደረጉ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር በመገናኘት 14ሺህ ጫማ ላይ መቆየት እንደሚሹ ገለጹ። አውሮፕላኑ ቀና ሊል አልቻለም። ጭራሽ አልታዘዝ አለ። የጀመሩት በረራ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ስላጋጠመው ወደ ተነሱበት ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መመለስ እንደሚፈልጉ አሳወቁ። ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ወዲያውኑ ፍቃድ አገኙ። ይህ ሁሉ የሆነው በደቂቃዎች ልዩነት ነበር። አሁንም አብራሪዎቹ አውሮፕላኑ ካዘቀዘቀበት ከፍ ለማድረግ ጥረታቸው አልተቋረጠም፤ አውሮፕላኑ ግን በስሪቱ ግድፈት እንደሆነ በሚገመት መልኩ አሻገረኝ አለ። ይባስ ብሎ ቁልቁል መምዘገዘግ ጀመረ። በመጨረሻም አብራሪዎቹ ከበረራ ተቆጣጣሪዎች ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ። የአቶ ተወልደ ትዝታ ከ150 በላይ ሰዎችን የያዘው የኢቲ302 የአውሮፕላን ሳይከሰከስ እንዳልቀረ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስጋት ቢገባቸውም ለደቂቃዎች ተስፋ አልቆረጡም ነበረ። ከደቂቃዎች በኋላም የአሰቃቂው አደጋ መከሰት የማይሸሹት እውነት ሆነ። የአደጋውን መከሰት ቀድመው የሰሙት የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሰንበት ቅዳሴን እየታደሙ ነበር። "የአደጋውን መድረስ ዜና የሰማሁት ጧት ነው። በእርግጥም በጣም ክው አድርጎኛል። በጣም፤ እጅግ በጣም ነው ያሳዘንኩት" ሲሉ መጋቢት አንድ ቀን ጠዋት የተፈጠረባቸውን ስሜት ያስታውሳሉ። እሁድ ረፋድ ላይ የአደጋውን መከሰት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጽህፈት ቤት በማኅበራዊ ገጹ ላይ አረዳ። በደረሰው አደጋም ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም ሐዘኑን ገለጸ። ከዚህ በኋላ አደጋው የዓለም መገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ርእስ ሆነ፤ የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ብርክ ያዘው። ተመሳሳይ አውሮፕላን የገዛ ሐሳብ ገባው። ሊገዛ ያሰበ ቀብዴን መልሱልኝ ማለት ጀመረ። የቦይንግ ገበያ ምስቅልቅል ውስጥ ገባ። በተለይ ከዚህ አደጋ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ የኢንዶኔዢያ ላየን ኤር አየር መንገድ አሰቃቂና በባህሪው ተመሳሳይ አደጋ አጋጥሞት እንደነበር ሲታወስ ነገሮች ወዴት እያመሩ እንደሆነ ግልጽ ነበር። ለአደጋው ምክንያት ተለያዩ መላ ምቶች ቢቀርቡም በአውሮፕላኑ ላይ ያለ ችግር ሊሆን እንደሚችል በመገለጹ ጥያቄዎች በአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ላይ በረታ። ይህንንም ተከትሎ ሌላ አደጋን ለማስቀረት እጅግ ዘመናዊ እንደሆኑ የተነገረላቸው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ስሪት አውሮፕላኖች ከበረራ ውጪ የማድረግ እርምጃን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች ወሰዱ። በኢትዮጵያ አውሮፕላን ላይ የደረሰው አደጋ እጅግ የከፋ ስለነበረ አንድም ሰው ከአደጋው አልተረፈም። ከአዲስ አበባ በ40 ኪሎ ሜትሮች አካባቢ ርቀት ላይ ከምትገኘው ቱሉ ፈራ ሜዳ ላይ የወደቀውን የአውሮፕላኑን ስብርባሪና የአደጋውን ሰለባዎች አካል ለማግኘት የቀናት ቁፋሮ አስፈልጎ ነበር። ለሟች ቤተሰቦች ሐዘኑ ድርብ ሆነ። ከአደጋው ጋር በተያያዘ አንዳንድ ወገኖች የአብራሪዎች ችግር አድርገው ለማቅረብ ቢሞክሩም የአደጋው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ግን አብራሪዎቹ ክስተቱን ለማስቀረት መጣራቸውንና በአውሮፕላኑ ላይ የተገጠመው የመቆጣጠሪያ ሥርዓት ለአደጋው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አመልክቶ ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማሪያምም ከመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ጋር በተያያዘ "ፓይለቶቹ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚጠበቅባቸውን ተገቢ እርምጃ በመውሰድ ያላቸውን ከፍ ያለ ሙያዊ ብቃት በማስመስከራቸው" አየር መንገዱ እንደሚኮራባቸው መስክረዋል። አደጋው በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ሕይወት ከማሳጣቱ ባሻገር ዘመናዊ የተባለውን አውሮፕላን ባመረተው ቦይንግ ኩባንያ ላይ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎችን አስከትሏል። በኩባንያው ላይ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ዋና ሥራ አስፈጻሚውም ከሥራቸው ተባረዋል። ተመሳሳዩን አውሮፕላን እንዲያመርትላቸው ያዘዙ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶችም ትዕዛዛቸውን ከመሰረዝ አልፈው ሥራ ላይ የነበሩትን ከበረራ ውጪ አደረጓቸው። በዚህም ባለዝናው የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ በወራት ጊዜ ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ኪሳራ አጋጠመው። ጉዳዩም ዛሬም ድረስ መቋጫ አላገኘም።
https://www.bbc.com/amharic/news-51797891
2health
የዝንጀሮ ፈንጣጣ ለኢትዮጵያ ምን ያህል ስጋት ነው?
በአሁኑ ጊዜ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ ቢያንስ በ13 አገራት ከ90 በላይ ሰዎች ላይ መከሰቱ የዓለም ጤና ድርጅት አረጋግጧል። በሽታው በስፋት የታየው በአሜሪካ እና በአውሮፓ አገራት ውስጥ ነው። በንክኪ የሚተላለፈው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከኮቪድ-19 ጋር ሲነጻጸር የመዛመት ፍጥነቱ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ እንደ ዩናይትድ ኪንግድም ያሉ አገራት "ችላ የምንለው አይደለም" ብለው በልዩ ትኩረት እየሰሩ ነው። ለመሆኑ ይህ በሽታ ኢትዮጵያን ያሳስባታል? በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲቲዩት የበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በኢትዮጵያ የመከሰት "ከፍተኛ ዕድል አለው ብለን እናስባለን" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ዳይሬክተሩ የወርርሽኞች አቅም እና የመተላለፊያ መንገዶቻቸው የበሽታውን አሳሳቢነቱን እንደሚወስኑ ያብራራሉ። "ብዙ አገራትን የሚያዳርሱ በሽታዎች ብዙ ጊዜ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚዛመቱት በትንፋሽ የሚተላለፉት በሽታዎች ናቸው" የሚሉት አቶ መስፍን ቀጥሎ ያለውን ደረጃ የሚይዙት ደግሞ በንክኪ የሚተላለፉት መሆኑናቸውን ጠቁመዋል። በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎች በፍጥነት የመዛመት ዕድላቸው ዝቅ ያለ ነው። "ያ ማለት ግን ከአገር ወደ አገር አይተላለፍም ማለት አይደለም።" እዚህ ጋር የዝንጀሮ ፈንጣጣ በንክኪ እንደሚተላለፍ ልብ በሉ። ዳይሬክተሩ በሽታው እስካሁን በኢትዮጵያ እንዳልተከሰተ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ በታሪክም በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ተመዝግቦ አያወቅም። ሆኖም በሽታው ከተከሰተባቸው አገራት የሚነሳ ማንኛውም ሰው የዝንጀሮ ፈንጣጣን "በቀላሉ" ወደ ኢትዮጵያ ይዞት ሊመጣ እንደሚችል ነው አቶ መስፍን የሚናገሩት። "የኢትዮጵያ ሁኔታ ከአፍሪካ አገሮች ወደ አውሮፓ እና ከአውሮፓ ወደ አፍሪካ አገራት ብዙ ትራንዚት እና ከፍተኛ የሰዎች ዝውውር ስላለ ከፍተኛ የመከሰት ዕድል አለው... ለሌሎችም አገራት ስጋት እስከሆነ ድረስ ለእኛም ስጋት መሆኑ አይቀርም፤ እኛም እየተንቀሳቀስን ያለነው ለአገራችንም ስጋት ነው ብለን ነው" ብለዋል። አቶ መስፍን ይህ በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ አገራት በስፋት እየታየ ያለው በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ "በተቻለ መጠን" አስፈላጊውን ተግባር እያከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል። ራስ ምታት እና ከ35.5 በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት [ትኩሳት] ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ውስጥ መካከል ይካተታሉ። በዚህም መነሻ በአገሪቱ በሁሉም ዓለምአቀፍ የየብስ እና የአየር በሮች ላይ የሙቀት ልኬት እየተከናወነ ነው። ከሚጠበቀው በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት ያላቸው ሰዎች ለዚሁ ዓላማ ወደተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት ተወስደው ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረግላቸው ያነሱት ኃላፊው፣ ለባለሙያዎች ሥልጣና እየተሰጠ እና በሽታው ቢያጋጥም የሚወሰዱ እርማጃዎችን በሚመለከት "የምላሽ መመሪያ" እየተዘጋጀ ነው ብለዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰትስ? አቶ መስፍን እንደሚሉት በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰት በሚል መነሻ አስፈላጊ ግብአቶችን የሟሟላት እና አቅም የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በሁሉም ክልሎች ይህንን በሽታ የሚቆጣጠሩ ግብረ ኃይሎችን ማቋቋም፣ የተያዙ ሰዎችን ጉዳይ ለመከታተል የሚስችሉ ሥርዓቶችን ማጎልበት፣ የፈጣን ምላሽ ቡድን ማዋቀር እና የአቅም ግንባታ ተግባራትን በክልሎች ለማከናወን "የዓለም ጤና ድርጀትን ጨምሮ ከሌሎች አጋሮች ጋር እየሰራን ነው" ሲሉም አክለዋል። ወደ አገሪቱ መግቢያ እና መውጫ በሆኑ በሮች በሚደረጉ ምርመራዎች እስካሁን ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር የተያያዘ አሳሳቢ ሁኔታ አለመከሰቱን ኃላፊው አመላክተዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው? የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በተሰኘ ቫይረስ የሚከሰተው በሽታው 'ስሞልፎክስ' ተብሎ የሚጠራው የፈንጣጣ ዝርያ ውስጥ የሚካተት ነው። ከሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት እና ቫይረሱ ካለባቸው ቁሶች ጋር በሚኖር ንክኪ የሚተላለፈው በሽታው ለምጀመሪያ ጊዜ እንደ አውሮፓውያኑ በ1958 በዝንጀሮ ላይ የተገኘ ነው። በ1978 ደግሞ በዲሞክራቲክ ኮንንጎ በሰው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቱ ተረጋግጧል። በገጠራማ የማዕከላዊ እና ምዕራባዊ አፍሪካ አገራት በፋት የሚያጠቃው የዝንጀሮ ፈንጣጣ እጅግ አሳሳቢ የሚባል አይደለም። በሽታውን 85 በመቶ መከላከል እንደሚችል የተረጋገጠ ክትባትም አለው። አንዳንድ ጊዜ ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ ሊጠፋ የሚችል ነው ። ሆኖም በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ምክንያት ህይወት አልፏል። የበሽታው የሞት ምጣኔ ከ3 እስከ 6 በመቶ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጀት ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል። ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የሰውነት እብጠት፣ የጀርባ እና የጡንቻ ህመም ደግሞ የበሽታው ምልክቶች ናቸው።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ ለኢትዮጵያ ምን ያህል ስጋት ነው? በአሁኑ ጊዜ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ ቢያንስ በ13 አገራት ከ90 በላይ ሰዎች ላይ መከሰቱ የዓለም ጤና ድርጅት አረጋግጧል። በሽታው በስፋት የታየው በአሜሪካ እና በአውሮፓ አገራት ውስጥ ነው። በንክኪ የሚተላለፈው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከኮቪድ-19 ጋር ሲነጻጸር የመዛመት ፍጥነቱ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ እንደ ዩናይትድ ኪንግድም ያሉ አገራት "ችላ የምንለው አይደለም" ብለው በልዩ ትኩረት እየሰሩ ነው። ለመሆኑ ይህ በሽታ ኢትዮጵያን ያሳስባታል? በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲቲዩት የበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በኢትዮጵያ የመከሰት "ከፍተኛ ዕድል አለው ብለን እናስባለን" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ዳይሬክተሩ የወርርሽኞች አቅም እና የመተላለፊያ መንገዶቻቸው የበሽታውን አሳሳቢነቱን እንደሚወስኑ ያብራራሉ። "ብዙ አገራትን የሚያዳርሱ በሽታዎች ብዙ ጊዜ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚዛመቱት በትንፋሽ የሚተላለፉት በሽታዎች ናቸው" የሚሉት አቶ መስፍን ቀጥሎ ያለውን ደረጃ የሚይዙት ደግሞ በንክኪ የሚተላለፉት መሆኑናቸውን ጠቁመዋል። በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎች በፍጥነት የመዛመት ዕድላቸው ዝቅ ያለ ነው። "ያ ማለት ግን ከአገር ወደ አገር አይተላለፍም ማለት አይደለም።" እዚህ ጋር የዝንጀሮ ፈንጣጣ በንክኪ እንደሚተላለፍ ልብ በሉ። ዳይሬክተሩ በሽታው እስካሁን በኢትዮጵያ እንዳልተከሰተ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ በታሪክም በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዘ ሰው ተመዝግቦ አያወቅም። ሆኖም በሽታው ከተከሰተባቸው አገራት የሚነሳ ማንኛውም ሰው የዝንጀሮ ፈንጣጣን "በቀላሉ" ወደ ኢትዮጵያ ይዞት ሊመጣ እንደሚችል ነው አቶ መስፍን የሚናገሩት። "የኢትዮጵያ ሁኔታ ከአፍሪካ አገሮች ወደ አውሮፓ እና ከአውሮፓ ወደ አፍሪካ አገራት ብዙ ትራንዚት እና ከፍተኛ የሰዎች ዝውውር ስላለ ከፍተኛ የመከሰት ዕድል አለው... ለሌሎችም አገራት ስጋት እስከሆነ ድረስ ለእኛም ስጋት መሆኑ አይቀርም፤ እኛም እየተንቀሳቀስን ያለነው ለአገራችንም ስጋት ነው ብለን ነው" ብለዋል። አቶ መስፍን ይህ በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ አገራት በስፋት እየታየ ያለው በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ "በተቻለ መጠን" አስፈላጊውን ተግባር እያከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል። ራስ ምታት እና ከ35.5 በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት [ትኩሳት] ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ውስጥ መካከል ይካተታሉ። በዚህም መነሻ በአገሪቱ በሁሉም ዓለምአቀፍ የየብስ እና የአየር በሮች ላይ የሙቀት ልኬት እየተከናወነ ነው። ከሚጠበቀው በላይ የሆነ የሰውነት ሙቀት ያላቸው ሰዎች ለዚሁ ዓላማ ወደተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት ተወስደው ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረግላቸው ያነሱት ኃላፊው፣ ለባለሙያዎች ሥልጣና እየተሰጠ እና በሽታው ቢያጋጥም የሚወሰዱ እርማጃዎችን በሚመለከት "የምላሽ መመሪያ" እየተዘጋጀ ነው ብለዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰትስ? አቶ መስፍን እንደሚሉት በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢከሰት በሚል መነሻ አስፈላጊ ግብአቶችን የሟሟላት እና አቅም የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በሁሉም ክልሎች ይህንን በሽታ የሚቆጣጠሩ ግብረ ኃይሎችን ማቋቋም፣ የተያዙ ሰዎችን ጉዳይ ለመከታተል የሚስችሉ ሥርዓቶችን ማጎልበት፣ የፈጣን ምላሽ ቡድን ማዋቀር እና የአቅም ግንባታ ተግባራትን በክልሎች ለማከናወን "የዓለም ጤና ድርጀትን ጨምሮ ከሌሎች አጋሮች ጋር እየሰራን ነው" ሲሉም አክለዋል። ወደ አገሪቱ መግቢያ እና መውጫ በሆኑ በሮች በሚደረጉ ምርመራዎች እስካሁን ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር የተያያዘ አሳሳቢ ሁኔታ አለመከሰቱን ኃላፊው አመላክተዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው? የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በተሰኘ ቫይረስ የሚከሰተው በሽታው 'ስሞልፎክስ' ተብሎ የሚጠራው የፈንጣጣ ዝርያ ውስጥ የሚካተት ነው። ከሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት እና ቫይረሱ ካለባቸው ቁሶች ጋር በሚኖር ንክኪ የሚተላለፈው በሽታው ለምጀመሪያ ጊዜ እንደ አውሮፓውያኑ በ1958 በዝንጀሮ ላይ የተገኘ ነው። በ1978 ደግሞ በዲሞክራቲክ ኮንንጎ በሰው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቱ ተረጋግጧል። በገጠራማ የማዕከላዊ እና ምዕራባዊ አፍሪካ አገራት በፋት የሚያጠቃው የዝንጀሮ ፈንጣጣ እጅግ አሳሳቢ የሚባል አይደለም። በሽታውን 85 በመቶ መከላከል እንደሚችል የተረጋገጠ ክትባትም አለው። አንዳንድ ጊዜ ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ ሊጠፋ የሚችል ነው ። ሆኖም በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ምክንያት ህይወት አልፏል። የበሽታው የሞት ምጣኔ ከ3 እስከ 6 በመቶ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጀት ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል። ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የሰውነት እብጠት፣ የጀርባ እና የጡንቻ ህመም ደግሞ የበሽታው ምልክቶች ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-61564071