label
class label
4 classes
headline
stringlengths
17
80
text
stringlengths
1
16.8k
headline_text
stringlengths
28
16.8k
url
stringlengths
36
49
0business
ኒውዮርክ ታይምስና መሰል ታላላቅ የዜና ምንጮች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንዲከፍሉ እየተፋለሙ ነው
በበይነ መረብ ያሉ የዜና ድረገፆች ችግር ላይ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹም ኑሮ ከበደን ብለው ከገበያ ወጥተዋል፡፡ችግሩ የተፈጠረው ሰዎች በበይነመረቡ ዓለም ይዘቶቻቸውን በነጻ ማግኘታቸው ነው፡፡ ብዙ የተለፋባቸው የዜና ዘገባዎች ሰልባጅ ሆነዋል፡፡አሁን አዲስ ዘመቻ ጀምረዋል፤ አሳታሚዎች፡፡ ይከፈለን የሚል፡፡ እነ ጉጉል፣ እነ አፕልና እነ ፌስቡክ ቢሊዮን ዶላሮችን በትርፍ ሲዝቁ የዜና ድረገፆች ግን እየኮሰመኑ መሆኑ ፍትሐዊ አይደለም የሚሉ እንቅስቃዎች እዛም እዚም ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡ ጋዜጣና መጽሔት አሳታሚዎች ለነ ጉገል አጭር ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ክፈሉን!ጉግልና ፌስቡክ ከዚህ በፊት ለተመረጡ ይዘቶች ክፍያ እንፈጽማለን ብለው ነበር፡፡ ይህንንም በተወሰነ ደረጃ ጀምረውታል፡፡ ይሁንና አታሚዎች እንደሚሉት ገቢው የልብ አያደርስም፡፡የዓለም ግዙፉ ጋዜጣ ኒውዮርክ ታይምስ አፕል ኩባንያ ትርፌን እየወሰደብኝ ነው ሲል ቅሬታ አቅርቧል፡፡ የአውስትራሊያ ጋዜጦችም ተመሳሳይ ጥያቄ ከማንሳት አልፈው ክስ ለመመስረት እየተዘጋጁ ነው፡፡አፕል ጋዜጦቹ በመተግበሪያ ቋቱ (አፕል ስቶር) በኩል ሲሸጡ ከእያንዳንዱ ሽያጭ 30 በመቶ ትርፍ ይወስዳል፡፡ ቢያንስ ይህን እንዲተው ወይም የትርፍ ህዳጉን እንዲቀንስ ነው አሳታሚዎቹ እየጠየቁ ያሉት፡፡በዚህ ሳምንት መጀመርያ ጉግል ከአውስራሊያ አሳታሚዎች ጋር ጠብ ውስጥ ገብቷል፡፡ አሳታሚዎቹ የሚሉት ጉግል የሚከፍለን ብር በጭራሽ የልብ አያደርስም፣ ይጨመር ነው፡፡ የበይነመረቡን ዓለም የተቆጣጠሩት አፕል፣ ጉጉልና ፌስቡክ ለአሳታሚዎች አጥጋቢ ክፍያ ለመፈጸም ዳተኛ ሆነዋል፡፡የአሜሪካ ግዙፎቹን ጋዜጦች ማለትም ኒውዮርክ ታይምስን፣ ዋሺንግተን ፖስትን እና ዎልስትሪት ጆርናልን በገበያና ንግድ ጉዳዮች የሚወክለው ዲጂታል ኮንቴንት ኔክስት የተባለው ኩባንያ ለአፕል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡ ቅሬታው አፕል ለምን ከትርፋችን 30 ከመቶ ይወስድብናል የሚል ነው፡፡ የአይፎን ስልኮች አምራቹ አፕል በመተግበሪያ ቋቱ (አፕ ስቶር) እነዚህ ጋዜጦች ሲሸጡ ከትርፋቸው ከ15 እስከ 30 ከመቶ ኮሚሽን ይበላል፡፡ ነገር ግን አማዞን ‹አንዳንድ ደንቦችና ግዴታዎችን ስለሚያሟላ› የዚህን ያህል የትርፍ ኮሚሽን አይወሰድበትም፡፡አሁን አሳታሚዎቹ እያሉት ያሉት አማዞን የሚያሟላቸውና እኛ የማናሟላው ደንብና ግዴታዎች ምንድን ናቸው፤ ይገለጽልን ነው፡፡ አፕል ከአሳታሚዎች ብቻ ሳይሆን ከጌም አምራቾችም ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ ገብቷል፡፡ኤፒክ ጌምስ በዓለም የዝነኛው ፎንትናይት ቪዲዮ ጌም አምራች ነው፡፡ ይህ ጌም ከአፕል ስቶር ሲገዛ አፕል የትርፉን 30 ከመቶ ይወስድበታል፡፡ ይህ ያበሳጨው ኤፒክ ጌምስ ኩባንያ ጉዳዩን ፍርድ ቤት ወስዶታል፡፡ በአውስትራሊያ የሸማቾች ውድድር ኮሚሽን አዲስ ሕግ አርቅቋል፡፡ ሕጉ እነ ጉግልና ፌስቡክ እንዲሁም ጉግል ፕሌይ ከገጾቻቸው በኩል ለሚለጥፏቸው ማናቸውም የጋዜጣና መጽሔት ይዘቶች ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚጠይቅ ነው፡፡ ጉግል በበኩሉ አሁን ከፍ ያለ የይዘት ጥራት ያላቸው ጋዜጦችና መጽሔቶችን ገንዘብ መክፈል ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ የአውስትራሊያ የገበያ ቁጥጥር ባለሥልጣን ‹‹አሳታሚዎች የሚከፈላቸውን ዋጋ መደራደር እንዲችሉ የመጫወቻ ሜዳው ፍትሐዊ እንዲሆን ጠይቋል፡፡ የቢዝነስ አዋቂዎች እንደሚገምቱት እነዚህ ግዙፍ ኩባንያዎች በበይነ መረብ ለታየ ነገር ሁሉ ክፍያ ሊፈጽሙ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ሙያዊ ከፍታው ደርዝ ያለው፣ በጥራትና በትጋት የተሰራ የዜና ዘገባ ክፍያ ሊታሰብለት ይገባል ባይ ናቸው፡፡‹‹ርካሽ ነገር ርከሽ ነው፡፡ የትም በነጻ ሊገኝ ይችላል፡፡ ሙያውን የጠበቀና ብዙ የተለፋበትን ይዘት ግን እንደ መናኛ ነገር በበይነ መረብ ለጥፎ ምንም አለመክፈል በምንም መመዘና ተገቢ አይደለም፡፡ እነዚህ ይዘቶች በገንዘብ ካልተደገፉ ይጠፋሉ፡፡›› ይላሉ በስዊዘርላንድና በሲንጋፖር ቢዝነስ ትምህርት ቤቶች ፕሮፌሰር የሆኑት ማይክል ዋዴ፡፡ ‹‹ጉግል፣ ፌስቡክና ሌሎች የጋዜጦችን ምርት እየቦጨቁ በነጻ ሲዘሮት ኖረዋል፣ ለረዥም ጊዜ፤ ይህ ነገር ሊያበቃ ይገባል ብለዋል ፐሮፌሰሩ ለቢቢሲ፡፡ ጉግል በበኩሉ በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፍ የፈቃድና የአከፋፈል ፕሮግራም ለማውጣት እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህ ሲጠናቀቅ ከፍ ላሉ የጋዜጣ ሥራዎች ክፍያ መፈጸም ይጀምል ብሏል፡፡ ይህ የክፍያ ፕሮግራም በዚህ ዓመት መጨረሻ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የጉግል ቃል አቀባይ ‹‹ሰዎች ግልብ መረጃዎች እንዳይነዷቸው፣ ጠለቅ ያለና ውስብስ ዜናዎችን ማግኘት አለባቸው፣ የሚያነቃ፣ የጠራ መረጃን ለሚሰጥ ነገር መጋለጥ አለባቸው፤ ይህ እንዲሆን አሳታሚዎች ገንዘብ ሊያገኙ ይገባል፡፡ ስለዚህ መክፈል እንጀምለን›› ብለዋል፡፡ዶ/ር ሪጫርድ ስሚዝ እንዲህ ይላሉ፡፡‹‹ጉጉልን የሚያኖረው አሳታሚው የፈጠረው መረጃኮ ነው፡፡ስለዚህ መረጃ ፈጣሪው ከሌለ ጉግል ራሱ የለም፡፡ ለራሱ ህልውና ሲል ትርፉን ማጋራት ይኖርበታል››
ኒውዮርክ ታይምስና መሰል ታላላቅ የዜና ምንጮች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንዲከፍሉ እየተፋለሙ ነው በበይነ መረብ ያሉ የዜና ድረገፆች ችግር ላይ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹም ኑሮ ከበደን ብለው ከገበያ ወጥተዋል፡፡ችግሩ የተፈጠረው ሰዎች በበይነመረቡ ዓለም ይዘቶቻቸውን በነጻ ማግኘታቸው ነው፡፡ ብዙ የተለፋባቸው የዜና ዘገባዎች ሰልባጅ ሆነዋል፡፡አሁን አዲስ ዘመቻ ጀምረዋል፤ አሳታሚዎች፡፡ ይከፈለን የሚል፡፡ እነ ጉጉል፣ እነ አፕልና እነ ፌስቡክ ቢሊዮን ዶላሮችን በትርፍ ሲዝቁ የዜና ድረገፆች ግን እየኮሰመኑ መሆኑ ፍትሐዊ አይደለም የሚሉ እንቅስቃዎች እዛም እዚም ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡ ጋዜጣና መጽሔት አሳታሚዎች ለነ ጉገል አጭር ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ክፈሉን!ጉግልና ፌስቡክ ከዚህ በፊት ለተመረጡ ይዘቶች ክፍያ እንፈጽማለን ብለው ነበር፡፡ ይህንንም በተወሰነ ደረጃ ጀምረውታል፡፡ ይሁንና አታሚዎች እንደሚሉት ገቢው የልብ አያደርስም፡፡የዓለም ግዙፉ ጋዜጣ ኒውዮርክ ታይምስ አፕል ኩባንያ ትርፌን እየወሰደብኝ ነው ሲል ቅሬታ አቅርቧል፡፡ የአውስትራሊያ ጋዜጦችም ተመሳሳይ ጥያቄ ከማንሳት አልፈው ክስ ለመመስረት እየተዘጋጁ ነው፡፡አፕል ጋዜጦቹ በመተግበሪያ ቋቱ (አፕል ስቶር) በኩል ሲሸጡ ከእያንዳንዱ ሽያጭ 30 በመቶ ትርፍ ይወስዳል፡፡ ቢያንስ ይህን እንዲተው ወይም የትርፍ ህዳጉን እንዲቀንስ ነው አሳታሚዎቹ እየጠየቁ ያሉት፡፡በዚህ ሳምንት መጀመርያ ጉግል ከአውስራሊያ አሳታሚዎች ጋር ጠብ ውስጥ ገብቷል፡፡ አሳታሚዎቹ የሚሉት ጉግል የሚከፍለን ብር በጭራሽ የልብ አያደርስም፣ ይጨመር ነው፡፡ የበይነመረቡን ዓለም የተቆጣጠሩት አፕል፣ ጉጉልና ፌስቡክ ለአሳታሚዎች አጥጋቢ ክፍያ ለመፈጸም ዳተኛ ሆነዋል፡፡የአሜሪካ ግዙፎቹን ጋዜጦች ማለትም ኒውዮርክ ታይምስን፣ ዋሺንግተን ፖስትን እና ዎልስትሪት ጆርናልን በገበያና ንግድ ጉዳዮች የሚወክለው ዲጂታል ኮንቴንት ኔክስት የተባለው ኩባንያ ለአፕል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡ ቅሬታው አፕል ለምን ከትርፋችን 30 ከመቶ ይወስድብናል የሚል ነው፡፡ የአይፎን ስልኮች አምራቹ አፕል በመተግበሪያ ቋቱ (አፕ ስቶር) እነዚህ ጋዜጦች ሲሸጡ ከትርፋቸው ከ15 እስከ 30 ከመቶ ኮሚሽን ይበላል፡፡ ነገር ግን አማዞን ‹አንዳንድ ደንቦችና ግዴታዎችን ስለሚያሟላ› የዚህን ያህል የትርፍ ኮሚሽን አይወሰድበትም፡፡አሁን አሳታሚዎቹ እያሉት ያሉት አማዞን የሚያሟላቸውና እኛ የማናሟላው ደንብና ግዴታዎች ምንድን ናቸው፤ ይገለጽልን ነው፡፡ አፕል ከአሳታሚዎች ብቻ ሳይሆን ከጌም አምራቾችም ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ ገብቷል፡፡ኤፒክ ጌምስ በዓለም የዝነኛው ፎንትናይት ቪዲዮ ጌም አምራች ነው፡፡ ይህ ጌም ከአፕል ስቶር ሲገዛ አፕል የትርፉን 30 ከመቶ ይወስድበታል፡፡ ይህ ያበሳጨው ኤፒክ ጌምስ ኩባንያ ጉዳዩን ፍርድ ቤት ወስዶታል፡፡ በአውስትራሊያ የሸማቾች ውድድር ኮሚሽን አዲስ ሕግ አርቅቋል፡፡ ሕጉ እነ ጉግልና ፌስቡክ እንዲሁም ጉግል ፕሌይ ከገጾቻቸው በኩል ለሚለጥፏቸው ማናቸውም የጋዜጣና መጽሔት ይዘቶች ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚጠይቅ ነው፡፡ ጉግል በበኩሉ አሁን ከፍ ያለ የይዘት ጥራት ያላቸው ጋዜጦችና መጽሔቶችን ገንዘብ መክፈል ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ የአውስትራሊያ የገበያ ቁጥጥር ባለሥልጣን ‹‹አሳታሚዎች የሚከፈላቸውን ዋጋ መደራደር እንዲችሉ የመጫወቻ ሜዳው ፍትሐዊ እንዲሆን ጠይቋል፡፡ የቢዝነስ አዋቂዎች እንደሚገምቱት እነዚህ ግዙፍ ኩባንያዎች በበይነ መረብ ለታየ ነገር ሁሉ ክፍያ ሊፈጽሙ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ሙያዊ ከፍታው ደርዝ ያለው፣ በጥራትና በትጋት የተሰራ የዜና ዘገባ ክፍያ ሊታሰብለት ይገባል ባይ ናቸው፡፡‹‹ርካሽ ነገር ርከሽ ነው፡፡ የትም በነጻ ሊገኝ ይችላል፡፡ ሙያውን የጠበቀና ብዙ የተለፋበትን ይዘት ግን እንደ መናኛ ነገር በበይነ መረብ ለጥፎ ምንም አለመክፈል በምንም መመዘና ተገቢ አይደለም፡፡ እነዚህ ይዘቶች በገንዘብ ካልተደገፉ ይጠፋሉ፡፡›› ይላሉ በስዊዘርላንድና በሲንጋፖር ቢዝነስ ትምህርት ቤቶች ፕሮፌሰር የሆኑት ማይክል ዋዴ፡፡ ‹‹ጉግል፣ ፌስቡክና ሌሎች የጋዜጦችን ምርት እየቦጨቁ በነጻ ሲዘሮት ኖረዋል፣ ለረዥም ጊዜ፤ ይህ ነገር ሊያበቃ ይገባል ብለዋል ፐሮፌሰሩ ለቢቢሲ፡፡ ጉግል በበኩሉ በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፍ የፈቃድና የአከፋፈል ፕሮግራም ለማውጣት እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህ ሲጠናቀቅ ከፍ ላሉ የጋዜጣ ሥራዎች ክፍያ መፈጸም ይጀምል ብሏል፡፡ ይህ የክፍያ ፕሮግራም በዚህ ዓመት መጨረሻ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የጉግል ቃል አቀባይ ‹‹ሰዎች ግልብ መረጃዎች እንዳይነዷቸው፣ ጠለቅ ያለና ውስብስ ዜናዎችን ማግኘት አለባቸው፣ የሚያነቃ፣ የጠራ መረጃን ለሚሰጥ ነገር መጋለጥ አለባቸው፤ ይህ እንዲሆን አሳታሚዎች ገንዘብ ሊያገኙ ይገባል፡፡ ስለዚህ መክፈል እንጀምለን›› ብለዋል፡፡ዶ/ር ሪጫርድ ስሚዝ እንዲህ ይላሉ፡፡‹‹ጉጉልን የሚያኖረው አሳታሚው የፈጠረው መረጃኮ ነው፡፡ስለዚህ መረጃ ፈጣሪው ከሌለ ጉግል ራሱ የለም፡፡ ለራሱ ህልውና ሲል ትርፉን ማጋራት ይኖርበታል››
https://www.bbc.com/amharic/news-53863156
2health
ኮሮናቫይረስ፡ አንዳንድ ሰዎች ለምን ቶሎ ከኮቪድ-19 አያገግሙም?
ብዙዎች ከኮሮናቫይረስ በቀላሉ፣ በአጭር ጊዜ ያገግማሉ። አንዳንዶች ላይ ግን በሽታው ይበረታል። ለወራት መተንፈስ የሚቸገሩ፣ የሚደክማቸውም አሉ። አጭር ርቀት ተጉዘው በጣም እንደሚደክማቸው የተናገሩ ሰዎች አሉ። በሽታው ዘለግ ላለ ጊዜም ይቆይባቸዋል። ኮቪድ-19 አንዳንዶች ላይ ለወራት የሚቆይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው ለምንድን ነው? ለሚለው ገና ግልጽ መልስ አልተገኘም። ኮሮናቫይረስ ለምን ረዥም ጊዜ ይቆያል? በሽታው ረዥም ጊዜ የቆየባቸው ሰዎች በአጠቃላይ ተመሳሳይ ምልክት አያሳዩም። ሆኖም ሁሉም እንደሚደክማቸው ይናገራሉ። ትንፋሽ ማጠር፣ ሳል፣ የጡንቻ ህመም፣ የስሜት ህዋሳት ህመም፣ ራስ ምታት እንዲሁም የልብ፣ ኩላሊት፣ አንጀት እና ሳምባ በሽታ የሚገጥማቸውም አሉ። በተጨማሪም ድብርት፣ ጭንቀት እና በግልጽ ለማሰብ መቸገር ይስተዋላል። ጄድ ግሬይ ክርስቲ “እንዲህ አይነት ድካም ተሰምቶኝ አያውቅም” ስትል ስሜቱን ገልጻለች። ፕ/ር ዴቪድ ስትሬይን “በሽታው አንዳንዶች ላይ እንደሚቆይ አንጠራጠርም” ብለዋል። በሮም ሆስፒታል 143 ታማሚዎች ላይ የተሠራ ጥናት፤ 87 በመቶ የሚሆኑት ከሁል ወራት በኋላ ከምልክቶቹ ቢያንስ ሁለቱ እንደታዩባቸው ይጠቁማል። ከግማሽ በላዩ ይደክማቸዋል። ዩኬ ውስጥ የሚሠራ መተግበሪያ እንደሚያሳየው፤ 12 በመቶ ህሙማን ከ30 ቀናት በኋላ የበሽታው ምልክት ታይቶባቸዋል። ከ50 ሰዎች አንዱ ከ90 ቀናት በኋላ ምልክት አሳይተዋል። ዘለግ ላለ ጊዜ የሚታመሙት በሽታው ከመጀመሪያውም የበረታባቸው ሰዎች ብቻ አይደሉም። ደብሊን ውስጥ የተሠራ ጥናት በበሽታው ከተያዙ ከአሥር ሳምንት በኋላ ድካም የገጠማቸው እንዳሉ ያሳያል። አንድ ሦስተኛው ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ አልቻሉም። ፕ/ር ክሪስ ብራይትሊንግ እንደሚናገሩት፤ ሳምባቸው የተጎዳ ሰዎች ለኒሞኒያ ተጋልጠዋል። ቫይረሱ ከሰውነት ቢወጣም አንዳንድ አካል ላይ እንደሚቀር ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ፕ/ር ቲም ስፔክተር “ዘለግ ላለ ጊዜ ተቅማጥ ከተከሰተ ቫይረሱ አንጀት ውስጥ ቀርቷል ማለት ነው። ማሽተት ካቀተ ደግሞ ቫይረሱ በህዋሳት ውስጥ ቀርቷል” ይላሉ። ቫይረሱ ህዋሳትን ሲያጠቃ፤ ሰውነት በሽታውን ለመከላከል ከመጠን በላይ ሲሞክር፤ አካላችን ይጎዳል። በሽታው የሰውነታችንን እንቅስቃሴም ያስተጓጉላል። የደም ዝውውር ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር የስኳር መጠናቸውን ለመቆጣጠር የተቸገሩ ህሙማን አሉ። የአንጎል መዋቅር ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የሚጠቁም መረጃ ቢኖርም እስካሁን አልተረጋገጠም። ህመሙ የተለመደ ነው? በቫይረስ ከተያዙ በኋላ መድከም ወይም ማሳል የተለመደ ነው። ከአሥር ሰዎች አንዱ ለወራት የሚቆይ የህዋሳት ህመም ሊገጥመው ይችላል። እአአ በ1918 ከተከሰተው ወረርሽኝ ወዲህ ጉንፋን የፓርኪንሰን በሽታን የሚመስል ምልክት ያለው ህመም እንደሚያስከትል ታይቷል። ኮቪድ-19ን ተከትሎ የተለያዩ የህመም ምልክቶች ሊስተዋሉ እንደሚችሉ ፕ/ር ክሪስ ያስረዳሉ። “ቫይረሱ የተለያዩ ሰዎችን በተለያየ መንገድ ይጎዳል። ህዋሳት ላይ የሚያስከትለው ችግርም ይለያያል። አንዳንዶች ላይ ሲበረታ፣ ለሌሎች ይቀላል” ይላሉ። ሙሉ በሙሉ ማገገም ይቻላል? ኮሮናቫይረስ ለረዥም ጊዜ የሚቆይባቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ይመስላል። ሆኖም ግን በሂደት የሚከሰተው አይታወቅም። ፕ/ር ክሪስ ሰዎችን ለ25 ዓመታት ለመከታተል እንደወሰኑና ህመሙ ከአንድ ዓመት በላይ ይቆይባቸዋል ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ። ሆኖም ግን ሰዎች አሁን ቢያገግሙም በሽታው ዘላቂ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው የሚችልበት እድል አለ። በጣም የሚደክማቸው ሰዎች ስሜቱ ዘለግ ላለ ጊዜ ሊቆይባቸው ይችላል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ወጣቶችም ሳይቀር ለልብ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ። ስለዚህም ከኮሮናቫይረስ በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ላይ ጫና እንዳያሳድሩና እንዲያርፉ ይመከራል። አድካሚ ሥራ ካለባቸው በተከታታይ ከማከናወን ይልቅ በተለያየ ሰዓት መተግበር አለባቸው። በተጨማሪም በጠበቁት ፍጥነት ካላገገሙ ወደ ህክምና መስጫ መሄድ ይጠበቅባቸዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ አንዳንድ ሰዎች ለምን ቶሎ ከኮቪድ-19 አያገግሙም? ብዙዎች ከኮሮናቫይረስ በቀላሉ፣ በአጭር ጊዜ ያገግማሉ። አንዳንዶች ላይ ግን በሽታው ይበረታል። ለወራት መተንፈስ የሚቸገሩ፣ የሚደክማቸውም አሉ። አጭር ርቀት ተጉዘው በጣም እንደሚደክማቸው የተናገሩ ሰዎች አሉ። በሽታው ዘለግ ላለ ጊዜም ይቆይባቸዋል። ኮቪድ-19 አንዳንዶች ላይ ለወራት የሚቆይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው ለምንድን ነው? ለሚለው ገና ግልጽ መልስ አልተገኘም። ኮሮናቫይረስ ለምን ረዥም ጊዜ ይቆያል? በሽታው ረዥም ጊዜ የቆየባቸው ሰዎች በአጠቃላይ ተመሳሳይ ምልክት አያሳዩም። ሆኖም ሁሉም እንደሚደክማቸው ይናገራሉ። ትንፋሽ ማጠር፣ ሳል፣ የጡንቻ ህመም፣ የስሜት ህዋሳት ህመም፣ ራስ ምታት እንዲሁም የልብ፣ ኩላሊት፣ አንጀት እና ሳምባ በሽታ የሚገጥማቸውም አሉ። በተጨማሪም ድብርት፣ ጭንቀት እና በግልጽ ለማሰብ መቸገር ይስተዋላል። ጄድ ግሬይ ክርስቲ “እንዲህ አይነት ድካም ተሰምቶኝ አያውቅም” ስትል ስሜቱን ገልጻለች። ፕ/ር ዴቪድ ስትሬይን “በሽታው አንዳንዶች ላይ እንደሚቆይ አንጠራጠርም” ብለዋል። በሮም ሆስፒታል 143 ታማሚዎች ላይ የተሠራ ጥናት፤ 87 በመቶ የሚሆኑት ከሁል ወራት በኋላ ከምልክቶቹ ቢያንስ ሁለቱ እንደታዩባቸው ይጠቁማል። ከግማሽ በላዩ ይደክማቸዋል። ዩኬ ውስጥ የሚሠራ መተግበሪያ እንደሚያሳየው፤ 12 በመቶ ህሙማን ከ30 ቀናት በኋላ የበሽታው ምልክት ታይቶባቸዋል። ከ50 ሰዎች አንዱ ከ90 ቀናት በኋላ ምልክት አሳይተዋል። ዘለግ ላለ ጊዜ የሚታመሙት በሽታው ከመጀመሪያውም የበረታባቸው ሰዎች ብቻ አይደሉም። ደብሊን ውስጥ የተሠራ ጥናት በበሽታው ከተያዙ ከአሥር ሳምንት በኋላ ድካም የገጠማቸው እንዳሉ ያሳያል። አንድ ሦስተኛው ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ አልቻሉም። ፕ/ር ክሪስ ብራይትሊንግ እንደሚናገሩት፤ ሳምባቸው የተጎዳ ሰዎች ለኒሞኒያ ተጋልጠዋል። ቫይረሱ ከሰውነት ቢወጣም አንዳንድ አካል ላይ እንደሚቀር ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ፕ/ር ቲም ስፔክተር “ዘለግ ላለ ጊዜ ተቅማጥ ከተከሰተ ቫይረሱ አንጀት ውስጥ ቀርቷል ማለት ነው። ማሽተት ካቀተ ደግሞ ቫይረሱ በህዋሳት ውስጥ ቀርቷል” ይላሉ። ቫይረሱ ህዋሳትን ሲያጠቃ፤ ሰውነት በሽታውን ለመከላከል ከመጠን በላይ ሲሞክር፤ አካላችን ይጎዳል። በሽታው የሰውነታችንን እንቅስቃሴም ያስተጓጉላል። የደም ዝውውር ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር የስኳር መጠናቸውን ለመቆጣጠር የተቸገሩ ህሙማን አሉ። የአንጎል መዋቅር ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የሚጠቁም መረጃ ቢኖርም እስካሁን አልተረጋገጠም። ህመሙ የተለመደ ነው? በቫይረስ ከተያዙ በኋላ መድከም ወይም ማሳል የተለመደ ነው። ከአሥር ሰዎች አንዱ ለወራት የሚቆይ የህዋሳት ህመም ሊገጥመው ይችላል። እአአ በ1918 ከተከሰተው ወረርሽኝ ወዲህ ጉንፋን የፓርኪንሰን በሽታን የሚመስል ምልክት ያለው ህመም እንደሚያስከትል ታይቷል። ኮቪድ-19ን ተከትሎ የተለያዩ የህመም ምልክቶች ሊስተዋሉ እንደሚችሉ ፕ/ር ክሪስ ያስረዳሉ። “ቫይረሱ የተለያዩ ሰዎችን በተለያየ መንገድ ይጎዳል። ህዋሳት ላይ የሚያስከትለው ችግርም ይለያያል። አንዳንዶች ላይ ሲበረታ፣ ለሌሎች ይቀላል” ይላሉ። ሙሉ በሙሉ ማገገም ይቻላል? ኮሮናቫይረስ ለረዥም ጊዜ የሚቆይባቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ይመስላል። ሆኖም ግን በሂደት የሚከሰተው አይታወቅም። ፕ/ር ክሪስ ሰዎችን ለ25 ዓመታት ለመከታተል እንደወሰኑና ህመሙ ከአንድ ዓመት በላይ ይቆይባቸዋል ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ። ሆኖም ግን ሰዎች አሁን ቢያገግሙም በሽታው ዘላቂ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው የሚችልበት እድል አለ። በጣም የሚደክማቸው ሰዎች ስሜቱ ዘለግ ላለ ጊዜ ሊቆይባቸው ይችላል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ወጣቶችም ሳይቀር ለልብ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ። ስለዚህም ከኮሮናቫይረስ በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ላይ ጫና እንዳያሳድሩና እንዲያርፉ ይመከራል። አድካሚ ሥራ ካለባቸው በተከታታይ ከማከናወን ይልቅ በተለያየ ሰዓት መተግበር አለባቸው። በተጨማሪም በጠበቁት ፍጥነት ካላገገሙ ወደ ህክምና መስጫ መሄድ ይጠበቅባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54441793
5sports
ሊዮኔል ሜሲ የነገሠበት የኳታር የዓለም ዋንጫ ዋና ዋና ክስተቶች
ከመነሻው ክስና ውዝግብ የገጠመው የኳታር የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅነት ድንቅ ክስተቶችን አስተናግዶ ሁሉን አጀብ ባሰኘ ሁኔታ ለፍጻሜ በቅቷል። አርጀንቲናን ጨምሮ የዓለማችን ታላላቅ ቡድኖች ሽንፈት ሲገጥማቸው፣ ሞሮኮና ሌሎች ብዙም ትኩረት ያልተሰጣቸው ቡድኖች ደግሞ ታሪክ ሰርተዋል። በመጨረሻም የ35 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ሊዮኔል ሜሲን የዋንጫ ባለቤት በማድረግ ደማቅ ታሪክ እንዲጽፍ ያስቻለው የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ሂደት ምን ይመስል ነበር?
ሊዮኔል ሜሲ የነገሠበት የኳታር የዓለም ዋንጫ ዋና ዋና ክስተቶች ከመነሻው ክስና ውዝግብ የገጠመው የኳታር የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅነት ድንቅ ክስተቶችን አስተናግዶ ሁሉን አጀብ ባሰኘ ሁኔታ ለፍጻሜ በቅቷል። አርጀንቲናን ጨምሮ የዓለማችን ታላላቅ ቡድኖች ሽንፈት ሲገጥማቸው፣ ሞሮኮና ሌሎች ብዙም ትኩረት ያልተሰጣቸው ቡድኖች ደግሞ ታሪክ ሰርተዋል። በመጨረሻም የ35 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ሊዮኔል ሜሲን የዋንጫ ባለቤት በማድረግ ደማቅ ታሪክ እንዲጽፍ ያስቻለው የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ሂደት ምን ይመስል ነበር?
https://www.bbc.com/amharic/articles/c726pgwgxwjo
2health
ዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ከ80 እስከ 180 ሺህ የሚደርሱ የጤና ሠራተኞችን ሳይገድል አይቀርም አለ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የጤና ሠራተኞችን ክፉኛ መጎዳቱንና ከ80,000 እስከ 180,000 የሚደርሱትን ግድሎ ሊሆን እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። የጤና ሠራተኞች ለክትባት ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፤ የክትባቱን ኢፍትሃዊ ስርጭትን ተችተዋል። ሞቱ የተመዘገበው በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ከጥር 2020 እስከ ግንቦት ባለው ጊዜ ነው። ቀደም ሲል ሌላ ከፍተኛ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣን የክትባት እጥረት ወረርሽኙ እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ ሊያስቀጥለው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። በዓለም ዙሪያ 135 ሚሊዮን የጤና ሠራተኞች እንዳሉ ይገመታል። "ከ 119 አገራት የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአምስት የጤና ሠራተኞች በአማካይ ሁለቱ ሙሉ በሙሉ ክትባት አግኝተዋል" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። "ይህ ቁጥር በተለያዩ አገራት እና በኢኮኖሚ ቡድኖች ውስጥ ያለውን ትልቅ ልዩነት ይሸፍናል።" በአፍሪካ ውስጥ ከ10 የጤና ሠራተኞች መካከል አንዱ ብቻ ሙሉ በሙሉ ክትባት ሲወስድ ከፍተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ስምንቱ ተከትበዋል። ቀደም ሲል ለድሃ አገራት በቂ ክትባት አለመስጠቱ የኮቪድ-19 ቀውስ "በቀላሉ ወደ 2022 ሊጎትት ይችላል" ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊ ዶ/ር ብሩስ አይልዋርድ ገልጸዋል። በአብዛኛዎቹ አህጉራት 40 በመቶ ሰዎች ክትባት ሲያገኙ ይህ ቁጥር በአፍሪካ ከአምስት በመቶ በታች ነው። አብዛኛው የኮቪድ-19 ክትባት ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ወይም በከፍተኛ መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ጥቅም ላይ ውሏል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተሰጡት ክትባቶች 2.6 በመቶውን ብቻ ትይዛለች። ክትባቶችን በፍትሃዊነት ለማሰራጨት በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው ዓለም አቀፍ ፕሮግራም የሆነው የኮቫክስ የመጀመሪያው ሃሳብ ሃብታሞቹን ጨምሮ ሁሉም አገራት ከአንድ ማዕከል ክትባቶችን ማግኘት መቻላቸውን ለማረጋገጥ እንደነበር የቢቢሲ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዘጋቢ ኑሃሚን ግሪምሌይ ጽፋለች። ነገር ግን አብዛኛዎቹ የቡድን 7 አገራት ከአምራቾች ጋር የራሳቸውን አንድ ለአንድ ስምምነት ማድረግ ከጀመሩ በኋላ ከስምምነቱ ወደ ኋላ ለመመለስ ወሰኑ። የመድኃኒት አምራቾች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት ቅድሚያ እንዲሰጡ ሃብታም አገራት በክትባት ለመግዛት ያላቸውን ወረፋ እንዲተው ዶ/ር አይልዋርድ ጥሪ አቅርበዋል። "በትክክለኛ በመንገድ ላይ እንዳሆንን ልንናገር እችላለሁ። በእርግጥ ማፋጠን አለብን። ካልሆነ ግን ምን እንደሚፈጠር ያውቃሉ? ይህ ወረርሽኝ ከሚያስፈልገው በላይ ለአንድ ዓመት ያህል ይቀጥላል" ብለዋል። ዘ ፒፕልስ ቫክሲን የተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሕብረት በመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች እና በሃብታም አገራት ቃል ከተገባው ከሰባት ክትባት አንዱ ለድሃ አገራት እየደረሰ መሆኑን የሚጠቁሙ አዳዲስ አሃዞችን አውጥቷል። ኦክስፋምን እና ዩኤንኤድስን ያካተተው ሕብረት በኮቫክስ በኩል ለራሳቸው ሕዝብ ክትባቶችን እየገዙ ነው በሚል ካናዳ እና እንግሊዝን ነቅፈዋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ዩናይትድ ኪንግደም 539,370 የፋይዘር ክትባቶችን ከኮቫክስ የተቀበለች ሲሆን ካናዳ ከአንድ ሚሊዮን ገደማ የአስትራዜኔካ ክትባት ወስዳለች። ኮቫክስ በመጀመሪያ በዚህ ዓመት መጨረሻ ሁለት ቢሊዮን ክትባቶችን ለማድረስ ቢያቅድም እስካሁን ያሳካው 371 ሚሊዮን ብቻ ነው።
ዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ከ80 እስከ 180 ሺህ የሚደርሱ የጤና ሠራተኞችን ሳይገድል አይቀርም አለ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የጤና ሠራተኞችን ክፉኛ መጎዳቱንና ከ80,000 እስከ 180,000 የሚደርሱትን ግድሎ ሊሆን እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። የጤና ሠራተኞች ለክትባት ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፤ የክትባቱን ኢፍትሃዊ ስርጭትን ተችተዋል። ሞቱ የተመዘገበው በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ከጥር 2020 እስከ ግንቦት ባለው ጊዜ ነው። ቀደም ሲል ሌላ ከፍተኛ የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣን የክትባት እጥረት ወረርሽኙ እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ ሊያስቀጥለው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። በዓለም ዙሪያ 135 ሚሊዮን የጤና ሠራተኞች እንዳሉ ይገመታል። "ከ 119 አገራት የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአምስት የጤና ሠራተኞች በአማካይ ሁለቱ ሙሉ በሙሉ ክትባት አግኝተዋል" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። "ይህ ቁጥር በተለያዩ አገራት እና በኢኮኖሚ ቡድኖች ውስጥ ያለውን ትልቅ ልዩነት ይሸፍናል።" በአፍሪካ ውስጥ ከ10 የጤና ሠራተኞች መካከል አንዱ ብቻ ሙሉ በሙሉ ክትባት ሲወስድ ከፍተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ስምንቱ ተከትበዋል። ቀደም ሲል ለድሃ አገራት በቂ ክትባት አለመስጠቱ የኮቪድ-19 ቀውስ "በቀላሉ ወደ 2022 ሊጎትት ይችላል" ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊ ዶ/ር ብሩስ አይልዋርድ ገልጸዋል። በአብዛኛዎቹ አህጉራት 40 በመቶ ሰዎች ክትባት ሲያገኙ ይህ ቁጥር በአፍሪካ ከአምስት በመቶ በታች ነው። አብዛኛው የኮቪድ-19 ክትባት ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ወይም በከፍተኛ መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ጥቅም ላይ ውሏል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተሰጡት ክትባቶች 2.6 በመቶውን ብቻ ትይዛለች። ክትባቶችን በፍትሃዊነት ለማሰራጨት በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው ዓለም አቀፍ ፕሮግራም የሆነው የኮቫክስ የመጀመሪያው ሃሳብ ሃብታሞቹን ጨምሮ ሁሉም አገራት ከአንድ ማዕከል ክትባቶችን ማግኘት መቻላቸውን ለማረጋገጥ እንደነበር የቢቢሲ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዘጋቢ ኑሃሚን ግሪምሌይ ጽፋለች። ነገር ግን አብዛኛዎቹ የቡድን 7 አገራት ከአምራቾች ጋር የራሳቸውን አንድ ለአንድ ስምምነት ማድረግ ከጀመሩ በኋላ ከስምምነቱ ወደ ኋላ ለመመለስ ወሰኑ። የመድኃኒት አምራቾች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት ቅድሚያ እንዲሰጡ ሃብታም አገራት በክትባት ለመግዛት ያላቸውን ወረፋ እንዲተው ዶ/ር አይልዋርድ ጥሪ አቅርበዋል። "በትክክለኛ በመንገድ ላይ እንዳሆንን ልንናገር እችላለሁ። በእርግጥ ማፋጠን አለብን። ካልሆነ ግን ምን እንደሚፈጠር ያውቃሉ? ይህ ወረርሽኝ ከሚያስፈልገው በላይ ለአንድ ዓመት ያህል ይቀጥላል" ብለዋል። ዘ ፒፕልስ ቫክሲን የተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሕብረት በመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች እና በሃብታም አገራት ቃል ከተገባው ከሰባት ክትባት አንዱ ለድሃ አገራት እየደረሰ መሆኑን የሚጠቁሙ አዳዲስ አሃዞችን አውጥቷል። ኦክስፋምን እና ዩኤንኤድስን ያካተተው ሕብረት በኮቫክስ በኩል ለራሳቸው ሕዝብ ክትባቶችን እየገዙ ነው በሚል ካናዳ እና እንግሊዝን ነቅፈዋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ዩናይትድ ኪንግደም 539,370 የፋይዘር ክትባቶችን ከኮቫክስ የተቀበለች ሲሆን ካናዳ ከአንድ ሚሊዮን ገደማ የአስትራዜኔካ ክትባት ወስዳለች። ኮቫክስ በመጀመሪያ በዚህ ዓመት መጨረሻ ሁለት ቢሊዮን ክትባቶችን ለማድረስ ቢያቅድም እስካሁን ያሳካው 371 ሚሊዮን ብቻ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-58991731
0business
ለ50 ዓመታት ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ እንቆቅልሽ በቀናት ውስጥ የፈታችው ተማሪ
አሜሪካዊቷ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለ50 ዓመት የበርካቶችን አእምሮ የፈተነውንና ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ ቀመር በቀላሉ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ በትርፍ ሰዓቷ ፈትታዋለች። ሊሳ ፒኪሪሎ ሦስተኛ ዲግሪዋን በዩኒቨርስቲ ኦፍ ቴክሳስ እየሰራች ነው። ከዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሯ ካሜሮን ጎርደን ጋር እያወራች በነበረበት ወቅት እግረ መንገዷን ለወሬያቸው ማጣፈጫ በሚል የሰራችውን የሒሳብ ስሌት፣ ያቃለለችውን የሒሳብ ቀመር አነሳች። "መጮህ ጀመረ 'እንዴት በጣም ደስተኛ አልሆንሽም?'" እንዳላት ፒኪሪሎ በኳንታ ለሚታተመው የሳይንስ ዜናን የሚሰራጨው ድረገጽ ተናግራለች። "እብድ ነው የሆነው" በማለትም የነበረውን ሁኔታ ያስታወሰችው። ወይዘሪት ፒኪሪሎ ሦስተኛ ዲግሪዋን ሳትይዝ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያሰጣት የሒሳብ ቀመር 'ኮንዌይ ኖት ፕሮብሌም' ይሰኛል። ኮንዌይ ኖት ፕሮፕሌም (Conway knot problem) በብሪታንያዊው ሒሳብ ሊቅ ጆን ሆርቶን ኮንዌይ በ1970 የተቀመረ ነው። ፒካሪሎ ግን ስለዚህ መልመጃ የሰማችው ለመጀመሪያ ጊዜ እአአ በ2018 በአንድ ሴሚናር ላይ መሆኑን ታስታውሳለች። ፕሮፌሰር ጎርደን "ምን ያህል እድሜ ጠገብ ዝነኛ የሒሳብ መልመጃ መሆኑን ያወቀች አይመስለኝም" ብለዋል። የወይዘሪት ፒኪሪሎ ሥራ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የታተመ ሲሆን እርሷም ይህንን የጥያቄ ጎምቱ፣ የመልመጃዎች አውራ በመፍታቷ በማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝታለች። "የኮንዌይ ኖት መልመጃ ለረዥም ዓመታት በሒሳብ ሊቃውንት ሊፈታ ሳይችል ቆይቷል" ያሉት ስፔናዊው ተመራማሪ ያቬር አራማዮና ናቸው። ይህ የሒሳብ ቀመር እንደምን ያለ ነው? ሒሳባዊ ቋጠሮ (Mathematical knots) የአንድ የሒሳብ ዘርፍ ሲሆን የሚመደብበትም ክፍል ቶፖሎጂ ይሰኛል። በቀላል ቋንቋ፣ ቶፖሎጂ የሚያጠናው ቁሶች ቅርጻቸውን ሲቀይሩ፣ ሲጎብጡ፣ ሲጠመዘዙ እና ሲወጠሩ-ነገር ግን ሳይሰበሩ እንዴት ያለ ጠባይ እንደሚያሳዩ ነው። ኖት ቲዎሪ (የጥልፍልልፎሽ ኀልዮት) የቶፖሎጂ አንዱ ዘርፍ ነው። ከእውኑ ዓለም ምሳሌዎች በተጻራሪው፣ ሒሳባዊ ቋጠሮ መጨረሻዎቹ የተሳሰረ ነው። በእርግጥ ቀላሉ ቋጠሮ የቀለበት ቅርጽ አለው፤ እናም ሊዋሃድ አይችልም። ነገር ግን የበለጠ ውስብስብ ይሆናል፤ ይህም አንዱ በአንዱ ላይ ሲጠላለፍና ሲቆላለፍ ነው። ይህንን በቀላሉ ለማስረዳት ገመድን ማሰብ በቂ ነው የሚሉት ማሪታኒያ ሲልቬሮ ናቸው። በሴቪሊ ዩኒቨርስቲ የሒሳብ ሊቅ የሆኑት እኚህ ምሁር "የጥልፍልልፎሽ ኀልዮት በአንድ ገመድ ላይ የሚከሰትን ቅርጽ አልባነት ያጠናል" ሲሉ ያክላሉ። "በሌላ ቋንቋ፣ ገመዱን እንዴት አድርገን እንደምንጠመዝዝ፣ እንደምናጎብጠው፣ እንደምናጥፈው፣ እንደምንጨምቀው. . .ገመዱን ለመቁረጥ የማናደርገው ነገር ማለት ነው። ያ ክልክል ነው።" ቶፖሎጂ ታዲያ በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ውስጥ ቁልፍ ቦታ አለው። የምጣኔ ሃብት ገበያዎችን እንዲሁም የዲኤንኤ ሞሎኪውልስን ቅርጽ ለማጥናት ይውላል። ከኖት ፕሮብሌም ጀርባ ያለው ሰው ጆን ሆርቶን ኮንዌይ በሚያዚያ ወር በተወለደ በ82 ዓመቱ በኮሮናበቫይረስ ምክንያት ሞቷል። ሊቨርፑል የተወለደው ይህ የሒሳብ ሊቅ በዘርፉ ምሁራን ዘንድ ተወዳጅ እንደነበር ይነገርለታል። ወይዘሪት ፒኪሪሎ 11 ጊዜ የተጠላለፈን የኮንዌይ ኖት ነው ተመሳሳዩን በመስራት "አቻ ጥልፍልፍ" መፍታት የቻለችው። እርሷ በአቻነት የሰራችው ጥልፍልፎሽን የእውቁን የሒሳብ ሊቅ የ50 ዓመት ሚስጥር ለመፍታት ተጠቀመችበት። "ቀን ቀን ለመስራት አልፈልግም ነበር፤ ያ ለሒሳብ የሚመች አይመስለኝም. . . ልክ የቤት ሥራ እንደተሰጠኝ በማሰብ ቤት ወስጄ ነው የሰራሁት" ብላለች። ወይዘሪት ፒኪሪሎ በአሜሪካ ማይን በምትባል ገጠራማ ስፍራ ተወልዳ ያደገች ሲሆን ሒሳብን ያጠናችው በቦስተን ኮሌጅ ነው።
ለ50 ዓመታት ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ እንቆቅልሽ በቀናት ውስጥ የፈታችው ተማሪ አሜሪካዊቷ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለ50 ዓመት የበርካቶችን አእምሮ የፈተነውንና ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ ቀመር በቀላሉ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ በትርፍ ሰዓቷ ፈትታዋለች። ሊሳ ፒኪሪሎ ሦስተኛ ዲግሪዋን በዩኒቨርስቲ ኦፍ ቴክሳስ እየሰራች ነው። ከዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሯ ካሜሮን ጎርደን ጋር እያወራች በነበረበት ወቅት እግረ መንገዷን ለወሬያቸው ማጣፈጫ በሚል የሰራችውን የሒሳብ ስሌት፣ ያቃለለችውን የሒሳብ ቀመር አነሳች። "መጮህ ጀመረ 'እንዴት በጣም ደስተኛ አልሆንሽም?'" እንዳላት ፒኪሪሎ በኳንታ ለሚታተመው የሳይንስ ዜናን የሚሰራጨው ድረገጽ ተናግራለች። "እብድ ነው የሆነው" በማለትም የነበረውን ሁኔታ ያስታወሰችው። ወይዘሪት ፒኪሪሎ ሦስተኛ ዲግሪዋን ሳትይዝ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያሰጣት የሒሳብ ቀመር 'ኮንዌይ ኖት ፕሮብሌም' ይሰኛል። ኮንዌይ ኖት ፕሮፕሌም (Conway knot problem) በብሪታንያዊው ሒሳብ ሊቅ ጆን ሆርቶን ኮንዌይ በ1970 የተቀመረ ነው። ፒካሪሎ ግን ስለዚህ መልመጃ የሰማችው ለመጀመሪያ ጊዜ እአአ በ2018 በአንድ ሴሚናር ላይ መሆኑን ታስታውሳለች። ፕሮፌሰር ጎርደን "ምን ያህል እድሜ ጠገብ ዝነኛ የሒሳብ መልመጃ መሆኑን ያወቀች አይመስለኝም" ብለዋል። የወይዘሪት ፒኪሪሎ ሥራ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የታተመ ሲሆን እርሷም ይህንን የጥያቄ ጎምቱ፣ የመልመጃዎች አውራ በመፍታቷ በማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝታለች። "የኮንዌይ ኖት መልመጃ ለረዥም ዓመታት በሒሳብ ሊቃውንት ሊፈታ ሳይችል ቆይቷል" ያሉት ስፔናዊው ተመራማሪ ያቬር አራማዮና ናቸው። ይህ የሒሳብ ቀመር እንደምን ያለ ነው? ሒሳባዊ ቋጠሮ (Mathematical knots) የአንድ የሒሳብ ዘርፍ ሲሆን የሚመደብበትም ክፍል ቶፖሎጂ ይሰኛል። በቀላል ቋንቋ፣ ቶፖሎጂ የሚያጠናው ቁሶች ቅርጻቸውን ሲቀይሩ፣ ሲጎብጡ፣ ሲጠመዘዙ እና ሲወጠሩ-ነገር ግን ሳይሰበሩ እንዴት ያለ ጠባይ እንደሚያሳዩ ነው። ኖት ቲዎሪ (የጥልፍልልፎሽ ኀልዮት) የቶፖሎጂ አንዱ ዘርፍ ነው። ከእውኑ ዓለም ምሳሌዎች በተጻራሪው፣ ሒሳባዊ ቋጠሮ መጨረሻዎቹ የተሳሰረ ነው። በእርግጥ ቀላሉ ቋጠሮ የቀለበት ቅርጽ አለው፤ እናም ሊዋሃድ አይችልም። ነገር ግን የበለጠ ውስብስብ ይሆናል፤ ይህም አንዱ በአንዱ ላይ ሲጠላለፍና ሲቆላለፍ ነው። ይህንን በቀላሉ ለማስረዳት ገመድን ማሰብ በቂ ነው የሚሉት ማሪታኒያ ሲልቬሮ ናቸው። በሴቪሊ ዩኒቨርስቲ የሒሳብ ሊቅ የሆኑት እኚህ ምሁር "የጥልፍልልፎሽ ኀልዮት በአንድ ገመድ ላይ የሚከሰትን ቅርጽ አልባነት ያጠናል" ሲሉ ያክላሉ። "በሌላ ቋንቋ፣ ገመዱን እንዴት አድርገን እንደምንጠመዝዝ፣ እንደምናጎብጠው፣ እንደምናጥፈው፣ እንደምንጨምቀው. . .ገመዱን ለመቁረጥ የማናደርገው ነገር ማለት ነው። ያ ክልክል ነው።" ቶፖሎጂ ታዲያ በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ውስጥ ቁልፍ ቦታ አለው። የምጣኔ ሃብት ገበያዎችን እንዲሁም የዲኤንኤ ሞሎኪውልስን ቅርጽ ለማጥናት ይውላል። ከኖት ፕሮብሌም ጀርባ ያለው ሰው ጆን ሆርቶን ኮንዌይ በሚያዚያ ወር በተወለደ በ82 ዓመቱ በኮሮናበቫይረስ ምክንያት ሞቷል። ሊቨርፑል የተወለደው ይህ የሒሳብ ሊቅ በዘርፉ ምሁራን ዘንድ ተወዳጅ እንደነበር ይነገርለታል። ወይዘሪት ፒኪሪሎ 11 ጊዜ የተጠላለፈን የኮንዌይ ኖት ነው ተመሳሳዩን በመስራት "አቻ ጥልፍልፍ" መፍታት የቻለችው። እርሷ በአቻነት የሰራችው ጥልፍልፎሽን የእውቁን የሒሳብ ሊቅ የ50 ዓመት ሚስጥር ለመፍታት ተጠቀመችበት። "ቀን ቀን ለመስራት አልፈልግም ነበር፤ ያ ለሒሳብ የሚመች አይመስለኝም. . . ልክ የቤት ሥራ እንደተሰጠኝ በማሰብ ቤት ወስጄ ነው የሰራሁት" ብላለች። ወይዘሪት ፒኪሪሎ በአሜሪካ ማይን በምትባል ገጠራማ ስፍራ ተወልዳ ያደገች ሲሆን ሒሳብን ያጠናችው በቦስተን ኮሌጅ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-53160666
5sports
ቶኪዮ ኦሎምፒክ 2020፡ ለተሰንበት ከሲፈን፤ ስለ ሁለቱ ስመ ጥር አትሌቶች ሊታወቁ የሚገቡ ነጥቦች
በሁለት ቀን ልዩነት የ10ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን ማሻሻል የቻሉት አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና ሲፈን ሐሰን በትልቁ የአትሌቲክስ መድረክ ላይ በ10ሺህ ሜትር ተፋጠዋል። እነዚህ አትሌቶች በትልቅ የአትሌቲክስ መድረክ ላይ ሲገናኙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በሪዮ ኦሎምፒክ የ10ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል ወርቅ የወሰደችው አልማዝ አያና እና የወቅቱ ተፎካካሪዋ ቪቪያን ቼሪዩት በቶኪዮ ኦለምፒክ ተሳታፊ ባለመሆናቸው የፊታችን ቅዳሜ በሚደረገው የ10ሺህ ሜትር ፍጻሜ የወርቅ ሜዳሊያ ከሲፈን ወይም ከለተሰንበት እንደማያልፍ ይጠበቃል። በዚህ ውድድር ሌሎች ተጠባቂ ከሆኑት ተወዳዳሪዎች መካከል ኢትዮጵያውያኖቹ ጽጌ ገ/ሰላማ እና ጸሃይ ገመቹ እንዲሁም በርቀቱ ብዙ ልምድ ያላት ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ተጠቃሽ ናቸው። እአአ 2019 ላይ በኳታር ዶሃ በተዘጋጀው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተገናኝተው ሲፈን ወርቁን ስትወስድ ለተሰንበት በሁለተኛነት አጠናቃለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሚሳተፍባቸው ርቀቶች በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና የኔዘርላንድስ ዜጋ የሆነችው ሲፈን ዋነኛ ተፎካካሪ መሆኗን ገልጿል። ሲፈን በ1500 ሜትር፣ በ5ሺህ ሜትር እና በ10ሺህ ሜትር ወርቅ ለማምጣት ቆርጣ ተነስታለች። በ5ሺህ ሜትር እቅዷን ያሳካች ሲሆን በ1500 ሜትርም ማጣሪያውን አልፋለች። ብዙ ልምድ ያካበተችው የ28 ዓመቷ ሲፈን በቶኪዮ ኦሊምፒክ ታሪክ ለመስራት ወጥናለች። በሌላ በኩል ገና የ23 ዓመት ወጣት የሆነችው ለተሰንበት ግደይ በኦሊምፒክ መድረክ ስትወዳደር ይህ የመጀመሪያዋ ይሁን እንጂ የምትገኝበትን ወቅታዊ አቋም ከግምት በማስገባት የ10ሺህ ሜትር ድሉን ለለተሰንበት የሚሰጡ በርካቶች ናቸው። እአአ 1992 በባርሴሎና ኦሊምፒክ የየዛኔዋ የ23 ዓመት ወጣት፣ አትሌት ደራርቱ ቱሉ በ10ሺህ ሜትር ለአገሯ ወርቅ አስገኝታ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላም በሲድኒ ኦሊምፒክ በተመሳሳይ ርቀት ወርቅ አምጥታለች። በዘንድሮ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ለተሰንበት ኖሯት ሲፈን የማይኖራት ብቸኛው ነገር የደራርቱ ቱሉ ድጋፍ ነው። "ሁለቱም ልጆች የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው። እንደ ዜጋችን ለተሰንበትን እንጠብቃለን። የምንደግፈውም ለተሰንበትን ነው። ይሁን እንጂ ሲፈንም የኛው ልጅ ነች። የምንኮራባት እና የምንወዳት ልጅ" ትላለች አትሌት ደራርቱ ቱሉ። ደራርቱ ቱሉ ከለተሰንበት ጋር ልምምድ ስታደርግ እና ስታበረታታት ታይታለች። ለተሰንበት እና ሲፈን ለተሰንበት ተማሪ ሳለች በስፖርት ክፍለ ጊዜ 'አልሮጥም' በማለቷ 'ወላጅ አምጪ' ተብላ ነበር። ዛሬ ላይ ግን ለተሰንበት በሩጫው ሌላ ዓለም ውስጥ ነው ያለችው። የወቅቱ የ10ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በእጇ ይገኛል። ሲፈን ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄዳው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን በ1500 ሜትር እና በ10ሺህ ሜትር ሁለት ወርቅ በመውሰድ ታሪክ ሰርታለች። ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፈን በኦሊምፒክ ስትሳተፍ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። በሪዮ ኦሎምፒክ 800 ሜትር 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የፊታችን ቅዳሜ ለተሰንበት በርቀቱ የኢትዮጵያን የበላይነት ለማረጋገጥ፤ ሲፈን ደግሞ በአንድ የኦሊምፒክ መድረክ ሦስት ወርቅ የማግኘት ሕልሟን ለማሳካት ይሮጣሉ። ሲፈን ለለተሰንበት ስጋት ትሆን? "አዎ ያሳስበናል፤ ለምን? በዓለም ቁጥር አንድ የምትባለ አትሌት ቀርቶ ሌላም አትሌት መናቅ የለበትም። ስለዚህ ጥንቃቄ ይፈልጋል። በቂ የሆነ ወድድር አድርጋለች [ለተሰንበት]። ጤንነቷ ጥሩ ነው። የአእምሮ ዝግጅቷም ጥሩ ነው። አስቀድመን በደንብ አዘጋጅተናታል" በማለት ደራርቱ ትናገራለች። ለስደሰተኛ ጊዜ በኦሊምፒክ የሚሳተፉት እና ለተሰንበትን በዋነኛነት የሚያሰለጥኑት አሰልጣኝ ኮማንደር ሁሴን ሸቦ፣ በለተሰንበት አሁናዊ አቋም ጥርጥር ባይገባቸውም ሲፈን ጠንካራ ተፎካካሪያቸው እንደምትሆን ያምናሉ። ሲፈንን ለማሸነፍ የተቀመጠው ስልት ኮማንደር ሁሴን አትሌት ሲፈን ለኢትዮጵያ አትሌቶች ስጋት ልትሆን የምትችልባቸውን ምክንያቶች እንዲህ ያስረዳሉ። "በ5ሺህ እና በ10ሺህ ርቀቶች አሁን ባላት ልምድ እና ችሎታ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለውም"። ሌላኛው ደግሞ ሲፈን በመጨረሻ ዙር ላይ ፍጥነት እንዳላት አሰልጣኙ ይናገራሉ። "ሲፈን በውድድር መጨረሻ ላይ ከለተሰንበት የበለጠ ፍጥነት አላት" በማለት ያስረዳሉ። ለዚህም የአትሌቲክስ ቡድን ሲፈንን ለማሸነፍ መላ መዘየዱን አሰልጣኙ ይናገራሉ። "እንደ ታክቲክ ለተሰንበት ማድረግ ያለባት እሷን [ሲፈንን] ከእራሷ ሳታርቅ ዙሩን አክርራ ሄዳ፣ አንድ ሁለት ዙር እስኪቀር ድረስ አኩል ከሮጡ ልትፈተን [ሲፈን] ትችላለች" ሲፈን በዚህ ኦሊምፒክ በሦስት ውድድሮች ነው የምትካፈለው። የመጨረሻው ደግሞ የ10ሺህ ሜትር ውድድር ነው። በዚህ ውድድር ተሳታፊ በምትሆን ጊዜም ድካም ሊጫናት ይችላል። "ይህ የሚሳካ ከሆነ አስደናቂ ነገር ነው [ሲፈን በሦስት ውድድር ወርቅ የማግኘት እቅድ]። ሁለት ውድድር አጠናቅቃ ሦስተኛው ላይ 10ሺህ ሜትር መሮጥ ይቅርና በዛ ሙቀት ቦታ፣ ሁለት ውድድር ማድረግ በራሱ በጣም ከባድ ነው። ሦስተኛው ውድድር ላይ በጣም ይከብዳታል የሚል ጥርጣሬ አለኝ" በማለት ኮማንደር ሁሴን ይናገራሉ። በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚካሄድባት ጃፓን በአሁኑ ወቅት ያለው ሙቀት ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ሞቃታማ ወደሆኑ እንደ መተሃራ እና አዋሽ ከተሞች ልምምድ ሲያደርግ መቆየቱን ደራርቱ ቱሉ ለቢቢሲ ተናገራ ነበር።
ቶኪዮ ኦሎምፒክ 2020፡ ለተሰንበት ከሲፈን፤ ስለ ሁለቱ ስመ ጥር አትሌቶች ሊታወቁ የሚገቡ ነጥቦች በሁለት ቀን ልዩነት የ10ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን ማሻሻል የቻሉት አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና ሲፈን ሐሰን በትልቁ የአትሌቲክስ መድረክ ላይ በ10ሺህ ሜትር ተፋጠዋል። እነዚህ አትሌቶች በትልቅ የአትሌቲክስ መድረክ ላይ ሲገናኙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በሪዮ ኦሎምፒክ የ10ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል ወርቅ የወሰደችው አልማዝ አያና እና የወቅቱ ተፎካካሪዋ ቪቪያን ቼሪዩት በቶኪዮ ኦለምፒክ ተሳታፊ ባለመሆናቸው የፊታችን ቅዳሜ በሚደረገው የ10ሺህ ሜትር ፍጻሜ የወርቅ ሜዳሊያ ከሲፈን ወይም ከለተሰንበት እንደማያልፍ ይጠበቃል። በዚህ ውድድር ሌሎች ተጠባቂ ከሆኑት ተወዳዳሪዎች መካከል ኢትዮጵያውያኖቹ ጽጌ ገ/ሰላማ እና ጸሃይ ገመቹ እንዲሁም በርቀቱ ብዙ ልምድ ያላት ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ተጠቃሽ ናቸው። እአአ 2019 ላይ በኳታር ዶሃ በተዘጋጀው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተገናኝተው ሲፈን ወርቁን ስትወስድ ለተሰንበት በሁለተኛነት አጠናቃለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሚሳተፍባቸው ርቀቶች በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና የኔዘርላንድስ ዜጋ የሆነችው ሲፈን ዋነኛ ተፎካካሪ መሆኗን ገልጿል። ሲፈን በ1500 ሜትር፣ በ5ሺህ ሜትር እና በ10ሺህ ሜትር ወርቅ ለማምጣት ቆርጣ ተነስታለች። በ5ሺህ ሜትር እቅዷን ያሳካች ሲሆን በ1500 ሜትርም ማጣሪያውን አልፋለች። ብዙ ልምድ ያካበተችው የ28 ዓመቷ ሲፈን በቶኪዮ ኦሊምፒክ ታሪክ ለመስራት ወጥናለች። በሌላ በኩል ገና የ23 ዓመት ወጣት የሆነችው ለተሰንበት ግደይ በኦሊምፒክ መድረክ ስትወዳደር ይህ የመጀመሪያዋ ይሁን እንጂ የምትገኝበትን ወቅታዊ አቋም ከግምት በማስገባት የ10ሺህ ሜትር ድሉን ለለተሰንበት የሚሰጡ በርካቶች ናቸው። እአአ 1992 በባርሴሎና ኦሊምፒክ የየዛኔዋ የ23 ዓመት ወጣት፣ አትሌት ደራርቱ ቱሉ በ10ሺህ ሜትር ለአገሯ ወርቅ አስገኝታ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላም በሲድኒ ኦሊምፒክ በተመሳሳይ ርቀት ወርቅ አምጥታለች። በዘንድሮ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ለተሰንበት ኖሯት ሲፈን የማይኖራት ብቸኛው ነገር የደራርቱ ቱሉ ድጋፍ ነው። "ሁለቱም ልጆች የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው። እንደ ዜጋችን ለተሰንበትን እንጠብቃለን። የምንደግፈውም ለተሰንበትን ነው። ይሁን እንጂ ሲፈንም የኛው ልጅ ነች። የምንኮራባት እና የምንወዳት ልጅ" ትላለች አትሌት ደራርቱ ቱሉ። ደራርቱ ቱሉ ከለተሰንበት ጋር ልምምድ ስታደርግ እና ስታበረታታት ታይታለች። ለተሰንበት እና ሲፈን ለተሰንበት ተማሪ ሳለች በስፖርት ክፍለ ጊዜ 'አልሮጥም' በማለቷ 'ወላጅ አምጪ' ተብላ ነበር። ዛሬ ላይ ግን ለተሰንበት በሩጫው ሌላ ዓለም ውስጥ ነው ያለችው። የወቅቱ የ10ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በእጇ ይገኛል። ሲፈን ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄዳው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን በ1500 ሜትር እና በ10ሺህ ሜትር ሁለት ወርቅ በመውሰድ ታሪክ ሰርታለች። ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፈን በኦሊምፒክ ስትሳተፍ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። በሪዮ ኦሎምፒክ 800 ሜትር 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የፊታችን ቅዳሜ ለተሰንበት በርቀቱ የኢትዮጵያን የበላይነት ለማረጋገጥ፤ ሲፈን ደግሞ በአንድ የኦሊምፒክ መድረክ ሦስት ወርቅ የማግኘት ሕልሟን ለማሳካት ይሮጣሉ። ሲፈን ለለተሰንበት ስጋት ትሆን? "አዎ ያሳስበናል፤ ለምን? በዓለም ቁጥር አንድ የምትባለ አትሌት ቀርቶ ሌላም አትሌት መናቅ የለበትም። ስለዚህ ጥንቃቄ ይፈልጋል። በቂ የሆነ ወድድር አድርጋለች [ለተሰንበት]። ጤንነቷ ጥሩ ነው። የአእምሮ ዝግጅቷም ጥሩ ነው። አስቀድመን በደንብ አዘጋጅተናታል" በማለት ደራርቱ ትናገራለች። ለስደሰተኛ ጊዜ በኦሊምፒክ የሚሳተፉት እና ለተሰንበትን በዋነኛነት የሚያሰለጥኑት አሰልጣኝ ኮማንደር ሁሴን ሸቦ፣ በለተሰንበት አሁናዊ አቋም ጥርጥር ባይገባቸውም ሲፈን ጠንካራ ተፎካካሪያቸው እንደምትሆን ያምናሉ። ሲፈንን ለማሸነፍ የተቀመጠው ስልት ኮማንደር ሁሴን አትሌት ሲፈን ለኢትዮጵያ አትሌቶች ስጋት ልትሆን የምትችልባቸውን ምክንያቶች እንዲህ ያስረዳሉ። "በ5ሺህ እና በ10ሺህ ርቀቶች አሁን ባላት ልምድ እና ችሎታ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለውም"። ሌላኛው ደግሞ ሲፈን በመጨረሻ ዙር ላይ ፍጥነት እንዳላት አሰልጣኙ ይናገራሉ። "ሲፈን በውድድር መጨረሻ ላይ ከለተሰንበት የበለጠ ፍጥነት አላት" በማለት ያስረዳሉ። ለዚህም የአትሌቲክስ ቡድን ሲፈንን ለማሸነፍ መላ መዘየዱን አሰልጣኙ ይናገራሉ። "እንደ ታክቲክ ለተሰንበት ማድረግ ያለባት እሷን [ሲፈንን] ከእራሷ ሳታርቅ ዙሩን አክርራ ሄዳ፣ አንድ ሁለት ዙር እስኪቀር ድረስ አኩል ከሮጡ ልትፈተን [ሲፈን] ትችላለች" ሲፈን በዚህ ኦሊምፒክ በሦስት ውድድሮች ነው የምትካፈለው። የመጨረሻው ደግሞ የ10ሺህ ሜትር ውድድር ነው። በዚህ ውድድር ተሳታፊ በምትሆን ጊዜም ድካም ሊጫናት ይችላል። "ይህ የሚሳካ ከሆነ አስደናቂ ነገር ነው [ሲፈን በሦስት ውድድር ወርቅ የማግኘት እቅድ]። ሁለት ውድድር አጠናቅቃ ሦስተኛው ላይ 10ሺህ ሜትር መሮጥ ይቅርና በዛ ሙቀት ቦታ፣ ሁለት ውድድር ማድረግ በራሱ በጣም ከባድ ነው። ሦስተኛው ውድድር ላይ በጣም ይከብዳታል የሚል ጥርጣሬ አለኝ" በማለት ኮማንደር ሁሴን ይናገራሉ። በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚካሄድባት ጃፓን በአሁኑ ወቅት ያለው ሙቀት ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ሞቃታማ ወደሆኑ እንደ መተሃራ እና አዋሽ ከተሞች ልምምድ ሲያደርግ መቆየቱን ደራርቱ ቱሉ ለቢቢሲ ተናገራ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-58073431
5sports
አትሌቲክስ፡ ለተሰንበት ግደይ የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች
ኢትዮጵያዊቷ ሯጭ ለተሰንበት ግደይ በትናንትናው ዕለት የአምስት ሺህ ሜትር ርቀት ክብረ ወሰን ሰብራለች። ቫለንሺያ በተደረገው በዚህ ውድድር በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት አመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች ተብሏል። የ22 ዓመቷ ሯጭ የገባችበትም ሰዓትም 14 ደቂቃ ከ6.62 ሰኮንዶች ሲሆን የጥሩነሸ ደግሞ 14 ደቂቃ ከ11.15 ሰኮንዶች ነበር። በትናንትናው ዕለት ከሷ በተጨማሪ ኡጋንዳዊው ጆሹዋ ቼፕተጊ በቀነኒሳ በቀለ ለአስራ አምስት ዓመታት ተይዞ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በስድስት ሰኮንዶች በማሻሻልም ሰብሯል። የ24 ዓመቱ ሯጭ የገባበትም ሰዓት 26 ደቂቃ ከ11 ሰኮንዶች ነው ተብሏል። በስፔኗ ቫለንሺያ ከተማም ሁለት ክብረ ወሰኖች የተሰበሩበት እለትም ሆኗል። "በጣም ተደስቻለሁ" በማለትም ለተሰንበት ከሩጫው በኋላ ተናግራለች። ከዓመት በፊት በዶሃ ተካሂዶ የነበረውን የአለም ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ብር አግኝታ የነበረ ሲሆን " ለረዥም ጊዜ ሳልመው የነበረ ነው። ለኔ በጣም ትልቅ ነው" በማለትም ተናግራለች በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረው 26፡ 17፡53 ሰዓት በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ለረዥም ጊዜ በመያዝ ታሪካዊ የተባለ ክብረ ወሰን ነው። ጆሹዋ በአስር ወራትም ውስጥ አራት የአለም ክብረ ወሰኖችን መጨበጥ ችሏል። በታህሳስ ወር የ10 ኪሎ ሜትር የመንገድና በየካቲት ወር እንዲሁም የ5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ክብረ ወሰኖችን ይዟል። ነሐሴ ወር ላይ በነበረው የሞናኮ ዳይመንድ ሊግም በቀነኒሳ በቀለ ለ16 አመታት ተይዞ የነበረውን የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንም በሁለት ሰኮንዶች በማሻሻል ሰብሯል። 'የዓለም ሬኮርድ (ክብረ ወሰን) ቀን' በተባለው በዚህ ውድድርም በቫለንሺያ ቱሪያ ስታዲየም 400 ሰዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
አትሌቲክስ፡ ለተሰንበት ግደይ የ5 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች ኢትዮጵያዊቷ ሯጭ ለተሰንበት ግደይ በትናንትናው ዕለት የአምስት ሺህ ሜትር ርቀት ክብረ ወሰን ሰብራለች። ቫለንሺያ በተደረገው በዚህ ውድድር በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት አመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሽላለች ተብሏል። የ22 ዓመቷ ሯጭ የገባችበትም ሰዓትም 14 ደቂቃ ከ6.62 ሰኮንዶች ሲሆን የጥሩነሸ ደግሞ 14 ደቂቃ ከ11.15 ሰኮንዶች ነበር። በትናንትናው ዕለት ከሷ በተጨማሪ ኡጋንዳዊው ጆሹዋ ቼፕተጊ በቀነኒሳ በቀለ ለአስራ አምስት ዓመታት ተይዞ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በስድስት ሰኮንዶች በማሻሻልም ሰብሯል። የ24 ዓመቱ ሯጭ የገባበትም ሰዓት 26 ደቂቃ ከ11 ሰኮንዶች ነው ተብሏል። በስፔኗ ቫለንሺያ ከተማም ሁለት ክብረ ወሰኖች የተሰበሩበት እለትም ሆኗል። "በጣም ተደስቻለሁ" በማለትም ለተሰንበት ከሩጫው በኋላ ተናግራለች። ከዓመት በፊት በዶሃ ተካሂዶ የነበረውን የአለም ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ብር አግኝታ የነበረ ሲሆን " ለረዥም ጊዜ ሳልመው የነበረ ነው። ለኔ በጣም ትልቅ ነው" በማለትም ተናግራለች በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረው 26፡ 17፡53 ሰዓት በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ለረዥም ጊዜ በመያዝ ታሪካዊ የተባለ ክብረ ወሰን ነው። ጆሹዋ በአስር ወራትም ውስጥ አራት የአለም ክብረ ወሰኖችን መጨበጥ ችሏል። በታህሳስ ወር የ10 ኪሎ ሜትር የመንገድና በየካቲት ወር እንዲሁም የ5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ክብረ ወሰኖችን ይዟል። ነሐሴ ወር ላይ በነበረው የሞናኮ ዳይመንድ ሊግም በቀነኒሳ በቀለ ለ16 አመታት ተይዞ የነበረውን የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንም በሁለት ሰኮንዶች በማሻሻል ሰብሯል። 'የዓለም ሬኮርድ (ክብረ ወሰን) ቀን' በተባለው በዚህ ውድድርም በቫለንሺያ ቱሪያ ስታዲየም 400 ሰዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54459888
5sports
የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት
የዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ ያለፈው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተሰርዘው ነበር። ይህም ሕዳር ላይ ከሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ጋር ተደማምሮ ለፕሮግራም መጣበብ ተጨማሪ ራስ ምታት ሆኗል። የስምንተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ይከናወናሉ። በዚህ ሳምንትም ሦስት ጨዋታዎች ለሌላ ጊዜ ተላልፈዋል። አርብ፣ ቅዳሜ እና እሑድ የሚካሄዱትን ሰባት ጨዋተዎች ግምት ቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ እንደሚከተለው ቃኝቷቸዋል። አስቶን ቪላ ከ ሳውዝ ሃምፕተን አሰልጣኝ ዤራርድ ጫና ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት ይህ ጨዋታ ለቪላ ትልቅ ትርጉም አለው። ሳውዝ ሃምፕተን ከቪላ የተሻለ ጥሩ አጀማመር አሳይቷል። የቪላ ደጋፊዎች ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ያገኛሉ። ጨዋታው ጥሩ ፉክክር የሚኖረው ሲሆን ቪላ ያሸንፋል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 – 1 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ፉልሃም 2-0 ከመምራት በበርንማውዝ ለተሸነፉት ፎረስቶች ይህ ጨዋታ ወሳኝ ነው። ሽንፈቱ ለቡድኑም ሆነ ለደጋፊዎቹ ጥሩ አይመስለኝም። ከፉልሃም ጋር በሚኖረው ጨዋታቸው የሚሰጡት ምላሽ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት ሁለቱ ቡድኖች በሻምፒዮንሺፑ ለይ ሲገናኙ ፉልሃም 4 ለ 0 አሸንፏል። አሌክሳንደር ሚትሮቪች ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል። ዘንድሮም የተለየ ውጤት አልጠብቅም። ግምት፡ 0 – 2 ዎልቭስ ከ ማንችስተር ሲቲ ባለፈው ሁለቱ ቡድኖች ተጫውተው ማንቸስተር ሲቲ 5 ለ 1 ሲያሸንፍ በሜዳው ውስጥ ነበርኩ። በዕለቱ ኬቪን ደ ብሩይን ድንቅ ነበር። ዎልቭሶች አሁን ኤርሊንግ ሃላንድንም እንዴት ማስቆም እንዳለባቸው ሊጨነቁ ይገባል። ዎልቭሶች ጎል እንደሚያስቆጥሩ ባስብም ሲቲ ያሸንፋል። ግምት፡ 1 - 3 ብራይትን ከ ክሪስታል ፓላስ ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል። ኒውካስል ከ በርንማውዝ የኒውካስሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሆዊ የቀድሞ ክለባቸውን ለማሸነፍ ይጫወታሉ። ማሸነፍ እንደሚችሉም ብዙ ምክንያት ማስቀመጥ ይቻላል። ኒውካስል በማጥቃት የሚጫወት ሲሆን የተወሰኑ ጎሎችንም ማስቆጠር አለባቸው። ብርንማውዞች ባለፈው ከፎረስት ጋር ከመመራት ተነስተው ባሸነፉበት መነሳሳት ለመቀጠል ይሞክራሉ። ብርንማውዞች ከዚህ ጨዋታ ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አላስብም። ቶተንሃም ከ ሌስተር ቶተንሃም በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በስፖርቲንግ ሊዝበን ተሸንፏል። ባለፉት ሳምንታት ውጤታቸው ሜዳ ውስጥ ያለውን አቋማቸውን ያሳያል ብዬ አላስብም። ሌስተሮች በማጥቃት መስመር ጥሩ ቢሆንም የተከላካይ ስፍራ ላይ ብዙ ክፍተት አለባቸው። ሶን ሁዩንግ ሚን በዚህ ጨዋታ ወደ ጎል ማስቆጠር ይመለሳል ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 4 – 1 ብሬንትፎርድ ከ አርሴናል ብሬንትፎርዶች ባለፈው ውድድር ዓመት ወደ ሊጉ እንደመጡ አርሴናልን በማሸነፍ ጥሩ አጀማመር አድርገዋል። በዚህ ጨዋታም ትልቅ ፉክክር ይኖራል። አርሰናሎች ባለፉት 12 ወራት ተሻሽለዋል። ብሬንትፎርዶች ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊድስ ጋር ያላቸውን አቅም ማሳየት ችለዋል። ስለዚህ በዚህ ጨዋታ አርሰናል የሚፈተንበት ይሆናል። ከዚህ ጨዋታ ብርንትፎርዶች ነጥብ እንደሚያገኙ ይሰማኛል። ግምት፡ 1 - 1 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሊድስ ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል። ኤቨርትን ከዌስት ሃም ሁለቱም ቡድኖች ዕድለኞች አይደሉም እንጂ አሁን ካላቸው የተሻለ ነጥብ ማግኘት ነበረባቸው። ኤቨርተኖች በሊጉ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ። ከሊቨርፑል ጋር ጥሩ የነበሩ ሲሆን ለማሸነፍ የሚከብዱ ሆነዋል። ማሸነፍ የሁለቱም ቡድኖች የውድድር ዓመት የሚያቃና ይሆናል። ዌስት ሃም ሦስት ነጥብ ያሳካል ብዬ አስባለሁ። ባለፈው ዓመት በሁለቱም ጨዋታዎች ዌስትሃሞች ያሸነፉ ሲሆን ዘንድሮም የተለየ አይሆንም። ግምት፡ 1 - 2 ቼልሲ ከ ሊቨርፑል ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል።
የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት የዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ ያለፈው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተሰርዘው ነበር። ይህም ሕዳር ላይ ከሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ጋር ተደማምሮ ለፕሮግራም መጣበብ ተጨማሪ ራስ ምታት ሆኗል። የስምንተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ይከናወናሉ። በዚህ ሳምንትም ሦስት ጨዋታዎች ለሌላ ጊዜ ተላልፈዋል። አርብ፣ ቅዳሜ እና እሑድ የሚካሄዱትን ሰባት ጨዋተዎች ግምት ቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ እንደሚከተለው ቃኝቷቸዋል። አስቶን ቪላ ከ ሳውዝ ሃምፕተን አሰልጣኝ ዤራርድ ጫና ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት ይህ ጨዋታ ለቪላ ትልቅ ትርጉም አለው። ሳውዝ ሃምፕተን ከቪላ የተሻለ ጥሩ አጀማመር አሳይቷል። የቪላ ደጋፊዎች ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ያገኛሉ። ጨዋታው ጥሩ ፉክክር የሚኖረው ሲሆን ቪላ ያሸንፋል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 – 1 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ፉልሃም 2-0 ከመምራት በበርንማውዝ ለተሸነፉት ፎረስቶች ይህ ጨዋታ ወሳኝ ነው። ሽንፈቱ ለቡድኑም ሆነ ለደጋፊዎቹ ጥሩ አይመስለኝም። ከፉልሃም ጋር በሚኖረው ጨዋታቸው የሚሰጡት ምላሽ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት ሁለቱ ቡድኖች በሻምፒዮንሺፑ ለይ ሲገናኙ ፉልሃም 4 ለ 0 አሸንፏል። አሌክሳንደር ሚትሮቪች ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል። ዘንድሮም የተለየ ውጤት አልጠብቅም። ግምት፡ 0 – 2 ዎልቭስ ከ ማንችስተር ሲቲ ባለፈው ሁለቱ ቡድኖች ተጫውተው ማንቸስተር ሲቲ 5 ለ 1 ሲያሸንፍ በሜዳው ውስጥ ነበርኩ። በዕለቱ ኬቪን ደ ብሩይን ድንቅ ነበር። ዎልቭሶች አሁን ኤርሊንግ ሃላንድንም እንዴት ማስቆም እንዳለባቸው ሊጨነቁ ይገባል። ዎልቭሶች ጎል እንደሚያስቆጥሩ ባስብም ሲቲ ያሸንፋል። ግምት፡ 1 - 3 ብራይትን ከ ክሪስታል ፓላስ ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል። ኒውካስል ከ በርንማውዝ የኒውካስሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሆዊ የቀድሞ ክለባቸውን ለማሸነፍ ይጫወታሉ። ማሸነፍ እንደሚችሉም ብዙ ምክንያት ማስቀመጥ ይቻላል። ኒውካስል በማጥቃት የሚጫወት ሲሆን የተወሰኑ ጎሎችንም ማስቆጠር አለባቸው። ብርንማውዞች ባለፈው ከፎረስት ጋር ከመመራት ተነስተው ባሸነፉበት መነሳሳት ለመቀጠል ይሞክራሉ። ብርንማውዞች ከዚህ ጨዋታ ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አላስብም። ቶተንሃም ከ ሌስተር ቶተንሃም በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በስፖርቲንግ ሊዝበን ተሸንፏል። ባለፉት ሳምንታት ውጤታቸው ሜዳ ውስጥ ያለውን አቋማቸውን ያሳያል ብዬ አላስብም። ሌስተሮች በማጥቃት መስመር ጥሩ ቢሆንም የተከላካይ ስፍራ ላይ ብዙ ክፍተት አለባቸው። ሶን ሁዩንግ ሚን በዚህ ጨዋታ ወደ ጎል ማስቆጠር ይመለሳል ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 4 – 1 ብሬንትፎርድ ከ አርሴናል ብሬንትፎርዶች ባለፈው ውድድር ዓመት ወደ ሊጉ እንደመጡ አርሴናልን በማሸነፍ ጥሩ አጀማመር አድርገዋል። በዚህ ጨዋታም ትልቅ ፉክክር ይኖራል። አርሰናሎች ባለፉት 12 ወራት ተሻሽለዋል። ብሬንትፎርዶች ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊድስ ጋር ያላቸውን አቅም ማሳየት ችለዋል። ስለዚህ በዚህ ጨዋታ አርሰናል የሚፈተንበት ይሆናል። ከዚህ ጨዋታ ብርንትፎርዶች ነጥብ እንደሚያገኙ ይሰማኛል። ግምት፡ 1 - 1 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሊድስ ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል። ኤቨርትን ከዌስት ሃም ሁለቱም ቡድኖች ዕድለኞች አይደሉም እንጂ አሁን ካላቸው የተሻለ ነጥብ ማግኘት ነበረባቸው። ኤቨርተኖች በሊጉ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ። ከሊቨርፑል ጋር ጥሩ የነበሩ ሲሆን ለማሸነፍ የሚከብዱ ሆነዋል። ማሸነፍ የሁለቱም ቡድኖች የውድድር ዓመት የሚያቃና ይሆናል። ዌስት ሃም ሦስት ነጥብ ያሳካል ብዬ አስባለሁ። ባለፈው ዓመት በሁለቱም ጨዋታዎች ዌስትሃሞች ያሸነፉ ሲሆን ዘንድሮም የተለየ አይሆንም። ግምት፡ 1 - 2 ቼልሲ ከ ሊቨርፑል ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c9rkxzv0rn2o
5sports
በኢትዮጵያዊቷ መስከረም የተጠነሰሰው የአፍሪካ ሴቶች እግር ኳስ ቻምፒዮንስ ሊግ ተጀመረ
የመጀመሪያው ቶታልኤነርጂስ ካፍ የአፍሪካ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ባለፈው አርብ በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ተጀመረ። ይህ በአፍሪካ ታሪክ የመጀሪያው የሆነው ውድድር ለሁለት ሳምንታት የሚዘልቅ ነው። የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪ የሆነው ካፍ በማኅበራዊ ሚድያ ገፆቹ ውድድሩን በማስመልከት ሰፊ ዘገባ እያወጣ ይገኛል። የካፋ የሴቶች እግር ኳስ ክፍል ነባር ማኔጀር የሆኑት መስከረም ታደሰ ይህንን ውድድር ከጠነሰሱና ካሳኩ ሰዎች መካከል በመሆን ታሪክ መሥራታቸው እየተነገረላቸው ይገኛል። መስከረም ባለፈው ወር ከካፍ ድረ ገጽ ጋር ባደረጉት ቆይታ "ይህ ውድድር እውን ሆኖ ማየቴ ትልቅ ደስታ ሰጥቶኛል" ብለው ነበር። የቶታልኤነርጂስ ካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳታፊ ለመሆን 32 የአፍሪካ ክለቦች ቀጣናዊ የማጣሪያ ውድድር አድርገው ነበር። ይህንን ቀጣናዊ ውድድር ያሸነፉ ስምንት የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ክለቦች በዚህ ታሪካዊ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ። የማሊ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሞሮኮና የአስተናጋጇ ግብፅ ክለቦች በዚህ የ15 ቀናት ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል። ያለፈው ዓመት የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ አሸናፊ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ኬንያ አቅንታ የማጣሪያ ውድድር ማድረጓ አይዘነጋም። ታድያ በዚህ ታሪካዊ ውድድር ኢትዮጵያን ለመወከል ከጫፍ ደርሳ የነበረችው የንግድ ባንክ ቡድን በማጣሪያው የፍፃሜ ጨዋታ በኬንያዋ ኢሂጋ ኩዊንስ ተሸንፋ መውደቋ ይታወቃል። ምንም እንኳን ንግድ ባንክ በዚህ ውድድር ላይ አገሯን መወከል ባትችልም ዋና ዳኛ ሊድያ ታፈሰ ወደ ግብፅ በማቅናት ኢትዮጵያን ትወክላለች። ዋና ዳኛ ሊድያ በውድድር ሁለተኛ ቀን [ቅዳሜ] በሞሮኮዋ አርሚ ሮያል ራባትና በናይጄሪያዋ ሪቨርስ አንግልስ መካከል የሚደረገውን ፍልሚያ ትዳኛለች። ሊድያን ጨምሮ በፈረንጆቹ 2023 አውስትራሊያ የሚደረገውን የሴቶች ዓለም ዋንጫ ለመዳኘት የተመለመሉ የአፍሪካ ሴት የእግር ኳስ ዳኞች ይህን ውድድር ይዳኛሉ። በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ አል-ሰላም ስታድዬም የሚደረገው ይህ ታሪካዊ ውድድር ለአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ቡድኖች ትልቅ መድረክ ሆኖ ታይቷል። ውድድሩ በሱፐር ስፖርት፣ በቤይን ስፖርት፣ በካናል ፕላስ፣ በካፍ ድረ-ገፅና በፊፋ የዩትዩብ ገፅ እንደሚተላለፍ ካፍ አስታውቋል።
በኢትዮጵያዊቷ መስከረም የተጠነሰሰው የአፍሪካ ሴቶች እግር ኳስ ቻምፒዮንስ ሊግ ተጀመረ የመጀመሪያው ቶታልኤነርጂስ ካፍ የአፍሪካ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ባለፈው አርብ በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ተጀመረ። ይህ በአፍሪካ ታሪክ የመጀሪያው የሆነው ውድድር ለሁለት ሳምንታት የሚዘልቅ ነው። የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪ የሆነው ካፍ በማኅበራዊ ሚድያ ገፆቹ ውድድሩን በማስመልከት ሰፊ ዘገባ እያወጣ ይገኛል። የካፋ የሴቶች እግር ኳስ ክፍል ነባር ማኔጀር የሆኑት መስከረም ታደሰ ይህንን ውድድር ከጠነሰሱና ካሳኩ ሰዎች መካከል በመሆን ታሪክ መሥራታቸው እየተነገረላቸው ይገኛል። መስከረም ባለፈው ወር ከካፍ ድረ ገጽ ጋር ባደረጉት ቆይታ "ይህ ውድድር እውን ሆኖ ማየቴ ትልቅ ደስታ ሰጥቶኛል" ብለው ነበር። የቶታልኤነርጂስ ካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳታፊ ለመሆን 32 የአፍሪካ ክለቦች ቀጣናዊ የማጣሪያ ውድድር አድርገው ነበር። ይህንን ቀጣናዊ ውድድር ያሸነፉ ስምንት የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ክለቦች በዚህ ታሪካዊ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ። የማሊ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሞሮኮና የአስተናጋጇ ግብፅ ክለቦች በዚህ የ15 ቀናት ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል። ያለፈው ዓመት የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ አሸናፊ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ኬንያ አቅንታ የማጣሪያ ውድድር ማድረጓ አይዘነጋም። ታድያ በዚህ ታሪካዊ ውድድር ኢትዮጵያን ለመወከል ከጫፍ ደርሳ የነበረችው የንግድ ባንክ ቡድን በማጣሪያው የፍፃሜ ጨዋታ በኬንያዋ ኢሂጋ ኩዊንስ ተሸንፋ መውደቋ ይታወቃል። ምንም እንኳን ንግድ ባንክ በዚህ ውድድር ላይ አገሯን መወከል ባትችልም ዋና ዳኛ ሊድያ ታፈሰ ወደ ግብፅ በማቅናት ኢትዮጵያን ትወክላለች። ዋና ዳኛ ሊድያ በውድድር ሁለተኛ ቀን [ቅዳሜ] በሞሮኮዋ አርሚ ሮያል ራባትና በናይጄሪያዋ ሪቨርስ አንግልስ መካከል የሚደረገውን ፍልሚያ ትዳኛለች። ሊድያን ጨምሮ በፈረንጆቹ 2023 አውስትራሊያ የሚደረገውን የሴቶች ዓለም ዋንጫ ለመዳኘት የተመለመሉ የአፍሪካ ሴት የእግር ኳስ ዳኞች ይህን ውድድር ይዳኛሉ። በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ አል-ሰላም ስታድዬም የሚደረገው ይህ ታሪካዊ ውድድር ለአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ቡድኖች ትልቅ መድረክ ሆኖ ታይቷል። ውድድሩ በሱፐር ስፖርት፣ በቤይን ስፖርት፣ በካናል ፕላስ፣ በካፍ ድረ-ገፅና በፊፋ የዩትዩብ ገፅ እንደሚተላለፍ ካፍ አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59166789
3politics
የዶናልድ ትራምፕ አዲሱ ማሕበራዊ ሚድያ ምን ዋጠው?
ባለፈው ዓመት ጥቅምት ላይ ነበር የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አብዮታዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ እከፍታለሁ ሲሉ ቃል የገቡት። "ትሩዝ ሶሻልን ፈጥርያለሁ። ትላልቅ ኩባንያዎች በእውነት ስም ለመሞገት ስል" ብለው ነበር። "እንግዲህ የምንኖርበት ዘመን ታሊባን ትዊተር ላይ ብዙ ተከታዮች ያፈራበት፤ እናንተ የምትወዱት ፕሬዝደንታችሁ ግን ድምፁ የታፈነበት ነው" ሲሉ ምሬታቸው ገልጠዋል በወቅቱ። ትራምፕ እንደፎከሩ አልቀሩም። ትሩዝ ሶሻል የተባለውን ማሕበራዊ ድር አምባ በፈረንጆቹ የካቲት 21 ይፋ አደረጉ። ነገር ግን ከስድስት ሳምንታት በኋላ የዶናልድ ትራምፕ አዲሱ ድር አምባ በችግር ተተብትቧል። ቢያንስ 1.5 ሚሊዮን ሰዎች ትራምፕን ብለው ይህን ድር አምባ ለመጠቀም ቢመዘገቡም በቀላሉ የቀድሞውን ፕሬዝደንት ማግኘት አልቻሉም። ይህን ማበራዊ ሚዲያ ለመጠቀም የተመዝጋቢዎች ቁጥር 1.4 ሚሊዮን ደርሷል። ትሩዝ ሶሻል በትዊተር አምሳል ነው የተሠራው። ትራምፕ ከዚህ በኋላ መተግበሪያዬን መጠቀም አይችሉም ብሎ እስከወዲያኛው ባሰናበተው ትዊተር አምሳል። ትዊተር ትራምፕን ከአምባው ያገደው ምርጫው በግድ "ተጭበርብሯል" ብለው ሃሳዊ ንግግር አሰራጭተዋል፤ አመፅም ቀስቅሰዋል በሚል ነው። ትራምፕ ከትዊተር በሞት ይፍታህ የተባረሩት በፈረንጆቹ ጥቅምት 8 ነበር። 'ትሩዝ ሶሻል' ትዊተርን ይምሰል እንጂ አንድሮይድ ስልክ ለሚጠቀሙ ሰዎች አልተሠራም፤ በድረ-ገፅም ማግኘት አይቻልም። አልፎም ይህ ድር አምባ ከአሜሪካ ውጭ ላሉ ተጠቃሚዎች ክፍት አይደለም። "ትልቅ ውድቀት ነው" ነው ይላሉ የኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ሚድያና ፓለቲክስ ማዕከል ኃላፊው ጆሽዋ ታከር። ስማቸው እንዳይጠቀስ የሻቱ አንድ ሪፐብሊካን የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ ደግሞ "ምን እየሆነ እንዳለ የሚያውቅ ሰው የለም" ሲሉ ሹክ ብለዋል። የካቲት 21 ትሩዝ ሶሻል አፕ ስቶር ከተሰኘው የአይኦኤስ መተግበሪያ ማውረዳጅ ላይ ብዙ ሰዎች ያወረዱት መተግበሪያ ሆኖ ነበር። ነገር ግን ያወረዱት ሰዎች ሊጠቀሙበት አልቻሉም። ብዙዎች ችግሩ በጥቂት ቀናት ተቀርፎ ዶናልድ ትራምፕ እንደተለመደው አወዛጋቢ ፅሑፋቸውን ጣል ያደርጋሉ ተብሎ ቢጠበቅ ጠብ የሚል ነገር ጠፋ። እነ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ፌስቡክና እና ኢንስታግራም ብዙ ሰዎች ያወረዷቸው 10 መተግበሪያዎች ሆነው ታሪክ ሲፅፉ የትራምፕ ትሩዝ ሶሻል ከቁንጮ 100 ተርታ ውጭ ነው። አንደምንም ብለው ትሩዝ ሶሻልን መጠቀም የቻሉ ሰዎች ደግሞ ውስጥ ሲገባ ዝምታው ይጮኻል ይላሉ። አብዛኛዎቹ ቀኝ ዘመም የአሜሪካ ፖለቲከኞች እስካሁን ትሩዝ ሶሻልን ለመቀላቀል እያመነቱ ነው። አሁን ደግሞ መተግበሪያውን ከአፕ ስቶር የሚያወርዱት ሰዎች ቁጥርም እየቀነሰ ነው። "ከሳምንታት በፊት ነበር ትሩዝ ሶሻልን ለመጠቀም የተመዘገብኩት። ነገር ግን እስካሁን ተጠባባቂ ወንበር ላይ ነኝ" ሲል አንድ ግለሰብ ትዊተር ላይ ለጥፎ ነበር። የትሩዝ ሶሻል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴቪን ኑኔዝ ድር አምባው በመጋቢት ወር መጨረሻ "ሙሉ በመሉ ሥራ ይጀምራል" ብለዋል። ነገር ግን መተግበሪያው ለምን እንደዚህ በችግር እንደተበተበ ለብዙዎች ግራ የገባ ሆኗል። አንዳንዶች ትሩዝ፤ ራምብል ከተሰኘው በዩቲዩብ አምሳል ከተሠራው የተንቀሳቃሽ ምስል መጋሪያ ድር ጋር መጣመሩ ነው ያንቀራፈፈው ይላሉ። በወግ አጥባዊ አሜሪካዊያን ዘንድ ታዋቂ የሆነው ራምብል የትሩዝ የጀርባ አጥንት ይሆናል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ችግሩን በቀናት ልዩነት መፍታት አልተቻለም? የብዙዎች ጥያቄ ነው። "በስድስት ሳምንታት ሳይሆን በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊፈታ ይገባ ነበር" ይላሉ ሪፐብሊካኑ የትራምፕ የቅርብ ሰው። "ሁሌም ሲጀመር ችግር አያጣውም። ነገር ግን አሁን ተፈቶ ልንጠቀመው በተገባ ነበር። ምን እየሆነ እንዳለ የገባው ሰው የለም።" ትራምፕ በዚህ የትሩዝ ቀርፋፋ አጓጓዝ ደስተኛ አይደሉም። ምንም እንኳ ከ750 ሺህ በላይ ተከታዮች ቢያፈሩም ከአንድ ወር በላይ ምንም ነገር አልጠፉም። የሲሊከን ቫሊይ ግዙፍ ድር አምባዎችን ይፎካከራል የተባለው ትሩዝ ለጊዜው ቆሞ መራመድ የተሳነው ይመስላል።
የዶናልድ ትራምፕ አዲሱ ማሕበራዊ ሚድያ ምን ዋጠው? ባለፈው ዓመት ጥቅምት ላይ ነበር የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አብዮታዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ እከፍታለሁ ሲሉ ቃል የገቡት። "ትሩዝ ሶሻልን ፈጥርያለሁ። ትላልቅ ኩባንያዎች በእውነት ስም ለመሞገት ስል" ብለው ነበር። "እንግዲህ የምንኖርበት ዘመን ታሊባን ትዊተር ላይ ብዙ ተከታዮች ያፈራበት፤ እናንተ የምትወዱት ፕሬዝደንታችሁ ግን ድምፁ የታፈነበት ነው" ሲሉ ምሬታቸው ገልጠዋል በወቅቱ። ትራምፕ እንደፎከሩ አልቀሩም። ትሩዝ ሶሻል የተባለውን ማሕበራዊ ድር አምባ በፈረንጆቹ የካቲት 21 ይፋ አደረጉ። ነገር ግን ከስድስት ሳምንታት በኋላ የዶናልድ ትራምፕ አዲሱ ድር አምባ በችግር ተተብትቧል። ቢያንስ 1.5 ሚሊዮን ሰዎች ትራምፕን ብለው ይህን ድር አምባ ለመጠቀም ቢመዘገቡም በቀላሉ የቀድሞውን ፕሬዝደንት ማግኘት አልቻሉም። ይህን ማበራዊ ሚዲያ ለመጠቀም የተመዝጋቢዎች ቁጥር 1.4 ሚሊዮን ደርሷል። ትሩዝ ሶሻል በትዊተር አምሳል ነው የተሠራው። ትራምፕ ከዚህ በኋላ መተግበሪያዬን መጠቀም አይችሉም ብሎ እስከወዲያኛው ባሰናበተው ትዊተር አምሳል። ትዊተር ትራምፕን ከአምባው ያገደው ምርጫው በግድ "ተጭበርብሯል" ብለው ሃሳዊ ንግግር አሰራጭተዋል፤ አመፅም ቀስቅሰዋል በሚል ነው። ትራምፕ ከትዊተር በሞት ይፍታህ የተባረሩት በፈረንጆቹ ጥቅምት 8 ነበር። 'ትሩዝ ሶሻል' ትዊተርን ይምሰል እንጂ አንድሮይድ ስልክ ለሚጠቀሙ ሰዎች አልተሠራም፤ በድረ-ገፅም ማግኘት አይቻልም። አልፎም ይህ ድር አምባ ከአሜሪካ ውጭ ላሉ ተጠቃሚዎች ክፍት አይደለም። "ትልቅ ውድቀት ነው" ነው ይላሉ የኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ሚድያና ፓለቲክስ ማዕከል ኃላፊው ጆሽዋ ታከር። ስማቸው እንዳይጠቀስ የሻቱ አንድ ሪፐብሊካን የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ ደግሞ "ምን እየሆነ እንዳለ የሚያውቅ ሰው የለም" ሲሉ ሹክ ብለዋል። የካቲት 21 ትሩዝ ሶሻል አፕ ስቶር ከተሰኘው የአይኦኤስ መተግበሪያ ማውረዳጅ ላይ ብዙ ሰዎች ያወረዱት መተግበሪያ ሆኖ ነበር። ነገር ግን ያወረዱት ሰዎች ሊጠቀሙበት አልቻሉም። ብዙዎች ችግሩ በጥቂት ቀናት ተቀርፎ ዶናልድ ትራምፕ እንደተለመደው አወዛጋቢ ፅሑፋቸውን ጣል ያደርጋሉ ተብሎ ቢጠበቅ ጠብ የሚል ነገር ጠፋ። እነ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ፌስቡክና እና ኢንስታግራም ብዙ ሰዎች ያወረዷቸው 10 መተግበሪያዎች ሆነው ታሪክ ሲፅፉ የትራምፕ ትሩዝ ሶሻል ከቁንጮ 100 ተርታ ውጭ ነው። አንደምንም ብለው ትሩዝ ሶሻልን መጠቀም የቻሉ ሰዎች ደግሞ ውስጥ ሲገባ ዝምታው ይጮኻል ይላሉ። አብዛኛዎቹ ቀኝ ዘመም የአሜሪካ ፖለቲከኞች እስካሁን ትሩዝ ሶሻልን ለመቀላቀል እያመነቱ ነው። አሁን ደግሞ መተግበሪያውን ከአፕ ስቶር የሚያወርዱት ሰዎች ቁጥርም እየቀነሰ ነው። "ከሳምንታት በፊት ነበር ትሩዝ ሶሻልን ለመጠቀም የተመዘገብኩት። ነገር ግን እስካሁን ተጠባባቂ ወንበር ላይ ነኝ" ሲል አንድ ግለሰብ ትዊተር ላይ ለጥፎ ነበር። የትሩዝ ሶሻል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴቪን ኑኔዝ ድር አምባው በመጋቢት ወር መጨረሻ "ሙሉ በመሉ ሥራ ይጀምራል" ብለዋል። ነገር ግን መተግበሪያው ለምን እንደዚህ በችግር እንደተበተበ ለብዙዎች ግራ የገባ ሆኗል። አንዳንዶች ትሩዝ፤ ራምብል ከተሰኘው በዩቲዩብ አምሳል ከተሠራው የተንቀሳቃሽ ምስል መጋሪያ ድር ጋር መጣመሩ ነው ያንቀራፈፈው ይላሉ። በወግ አጥባዊ አሜሪካዊያን ዘንድ ታዋቂ የሆነው ራምብል የትሩዝ የጀርባ አጥንት ይሆናል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ችግሩን በቀናት ልዩነት መፍታት አልተቻለም? የብዙዎች ጥያቄ ነው። "በስድስት ሳምንታት ሳይሆን በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊፈታ ይገባ ነበር" ይላሉ ሪፐብሊካኑ የትራምፕ የቅርብ ሰው። "ሁሌም ሲጀመር ችግር አያጣውም። ነገር ግን አሁን ተፈቶ ልንጠቀመው በተገባ ነበር። ምን እየሆነ እንዳለ የገባው ሰው የለም።" ትራምፕ በዚህ የትሩዝ ቀርፋፋ አጓጓዝ ደስተኛ አይደሉም። ምንም እንኳ ከ750 ሺህ በላይ ተከታዮች ቢያፈሩም ከአንድ ወር በላይ ምንም ነገር አልጠፉም። የሲሊከን ቫሊይ ግዙፍ ድር አምባዎችን ይፎካከራል የተባለው ትሩዝ ለጊዜው ቆሞ መራመድ የተሳነው ይመስላል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60979022
5sports
የዓለማችን የሜዳ ቴኒስ ኮከብ ራፋኤል ናዳልን የገጠሙት የ97 ዓመቱ አዛውንት
የሜዳ ቴኒስ ጨዋታን ከነፍሳቸው የሚወዱት ዩክሬናዊው ስታኒስላቭስኪ ለ50 ዓመታት ሜዳ ቴኒስ እየተጫወቱ ቆይተዋል። አሁን ዕድሜያቸው 97 ዓመት ደርሷል። ነገር ግን አሁንም ጨዋታውን አላቆሙም። ሰሞኑን ከ20 ጊዜ በላይ የዓለማችንን ታላቁን የሜዳ ቴኒስ ውድድርን ካሸነፈው ስፔናዊ ኮከብ ራፋኤል ናዳል ጋር ያደረጉት ጨዋታ በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በእጅጉ መነጋገሪያ ሆኗል።
የዓለማችን የሜዳ ቴኒስ ኮከብ ራፋኤል ናዳልን የገጠሙት የ97 ዓመቱ አዛውንት የሜዳ ቴኒስ ጨዋታን ከነፍሳቸው የሚወዱት ዩክሬናዊው ስታኒስላቭስኪ ለ50 ዓመታት ሜዳ ቴኒስ እየተጫወቱ ቆይተዋል። አሁን ዕድሜያቸው 97 ዓመት ደርሷል። ነገር ግን አሁንም ጨዋታውን አላቆሙም። ሰሞኑን ከ20 ጊዜ በላይ የዓለማችንን ታላቁን የሜዳ ቴኒስ ውድድርን ካሸነፈው ስፔናዊ ኮከብ ራፋኤል ናዳል ጋር ያደረጉት ጨዋታ በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በእጅጉ መነጋገሪያ ሆኗል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59372312