input
stringlengths
1
130k
የሴት ልጅ ግርዛት አዉሮጳን ማስጋቱ የሴት ልጅ ግርዛት በተለያዩ ሃገራት ተግባራዊ እንደሚሆን ሲነገር የቆየ ጉዳይ ነዉ።
አሁን አሁን ግን በሰዎች ከሀገር ወደሀገር መዟዟር ምክንያት ቀድሞ በማይታወቅበት አካባቢ ሁሉ እየተዳረሰ መሆኑ እየተነገረ ነዉ።
አዉሮጳ ዉስጥ በልማድም ሆነ በባህል ያልነበረዉ ይህ ድርጊት ዛሬ የበርካቶች ስጋት ከሆነ ሰነባበተ።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱ አዉሮጳ ዉስጥ በየዓመቱ ታዳጊ ሴቶች ለግርዛት ይጋለጣሉ።
ይህን ጎጂ ልማድ ለመግታት የሚንቀሳቀሱ ተቋማትም የአዉሮጳ ኅብረት የተጠናከረ ርምጃ እንዲወስድ ግፊት እያደረጉ ነዉ።
አዉሮጳ ዉስጥ ስዊድን ናት በመጀመሪያ ሴት ልጆች ግርዛት እንዳይፈጸምባቸዉ በህግ የደነገገች አገር።
በጎርጎሪዮሳዊዉ ዓ ም በመሠረቱት ጎበዝ በተሰኘዉ ተቋም አማካኝነትም የባህል ልዉዉጥና ማኅበራዊ እንዲሁም ጤና ነክ ጉዳዮችን የሚመለከቱ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ።
ጎበዝ የተሰኘዉ ተቋም በተለይ የሴቶችን ጤንነት በሚመለከት የሴት ልጅ ግርዛት እንዲቆም የበኩሉን ጥረት እንደሚያደርግ ነዉ የተረዳነዉ።
የኔዘርላንድ መንግስት ግን መረጃ ማዳረሱንና ለቤተሰቦችም ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ገፍቶበታል በነገራችን ላይ በዚህ አገልግሎት ከሚሳተፉ ሶስቱ የኔዘርላንድ ዜጎች ናቸዉ።
የሚያስከትለዉ ስቃይም በወቅቱ ሲፈጸም ብቻ ሳይሆን ለአንዳንዶች የእድሜ ልክ መሆኑንም የደረሰባቸዉን በእማኝነት የሚጠቅሱ መረጃዎች ሞልተዋል።
ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ በተለያዩ እርከኖች በሚገኙ የመንግሥት መዋቅሮች ስቅየት ይፈጸም እንደነበር ተናግረዋል።
ምንም ይሁን ማን ሕገ መንግሥትን ማክበር አለበት የሚል እሳቤ መያዝ ያስፈልጋል።
ኃላፊነትን የሚሰማን መንግሥት ስንሆን ደግሞ የዚህ ጉዳይ መዛነፍ ኃላፊነት መውሰድ ያለብን እኛ ነን ብለዋል።
ሕገ መንግሥቱ የደኅንነት ተቋማት መከላከያውን ጨምሮ ከፓርቲ ገለልተኛ ሆነው ሕግ እና አገር የሚጠብቁ መሆን አለባቸው ብሎ ያስገድዳል።
ሲሉ የጠየቁት ጠቅላይ ምኒስትሩ እንደዛ ካላደራጀንው ኢ ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ተቋም ፈጥረናል ማለት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ሕገ መንግሥቱ በፍርድ ቤት የታሰረ ሰው ግረፉ ጭለማ ቤት አስቀምጡ ይላል እንዴ
ይኼን ሕገመንግሥታዊ ያልሆነ ድርጊት በእያንዳንዱ ቀበሌ በእያንዳንዱ ወረዳ በእያንዳንዱ ዞን ሲፈጸም ቆይቷል።
ጠቅላይ ምኒስትሩ ነፍጥ አንግበው መንግሥታቸውን ለመጣል ኤርትራ የገቡ ተቃዋሚዎች እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ምኒስትሩ በንግግራቸውም ሆነ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቀረቡላቸው ጥያቄዎች ኢትዮጵያ የገጠሟትን አንገብጋቢ ጉዳዮች አንስተዋል።
የአገራቸው ኤኮኖሚ የገጠመውን ፈተና የፖለቲካውን ውጥንቅጥ የፍትኅ ሥርዓቱን ችግሮች ስለ ሙስናና በተለያዩ አካባቢዎች ስለሚታዩ ግጭቶች ማብራሪያ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ምኒስትሩ እንዳሉት በ ዓ ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት ብቻ ኢትዮጵያ ሚሊዮን ዶላር ለዕዳ ስትከፍል ቢሊዮን ዶላር ተበድራለች።
አጠቃላይ የአገሪቱ የብድር መጠን ደግሞ ወደ ቢሊዮን ዶላር አሻቅቧል።
የሁለቱ ሐገራት ባለሥልጣናት ግን የሥምምነቱ ይዘት በተደጋጋሚ ጋዜጣዊ መግለጫ መብራራቱ እና በዓምደ መረብ መሰራጨቱን ይናገራሉ።
አፍሪቃ የአንጎላ ምርጫ ዘመቻ አንጎላ ከ ቀናት በኋላ አዲስ ምክር ቤት እና አዲስ ፕሬዚደንት ትመርጣለች።
በጎርጎሮሳዊው ዓ ም ስልጣን ላይ ሲመጡ አንጎላ ከፖርቱጋል ቅኝ አገዛዝ ተላቃ ነፃነቷን ካገኘች ገና አራት ዓመቷ ነበር።
በአንጎላ የርስበርሱ ጦርነት ከ ዓመታት በኋላ ምርጫው በ ዓም ተካሂዷል።
የያኔው ምርጫ በሀገሪቱ ከዚያን ጊዜ በኋላ እንደተካሄዱት ምርጫዎች ሁሉ ፕሬዚደንት ዶሽ ሳንቶሽን እና ፓርቲያቸው አሸናፊዎች ሆነዋል።
የተቃዋሚ ወገኖች ምርጫቹን እኩል እድል ያላገኙባቸው እና የመንግሥት የማጭበርበር ተግባር የታየባቸው ነው በሚል በጥብቅ ይነቅፋሉ።
ይሁንና ምርጫውን የታዘቡ ዓለም አቀፍ ቡድኖች የምርጫውን ውጤት ሲቀበሉ ነው የታዩት።
በዘንድሮው የአንጎላ ምርጫ በመዲናይቱ ሉዋንዳ ለሚገኙት የምክር ቤት መንበሮች ስድስት ፓርቲዎች በተፎካካሪነት ቀርበዋል።
በምርጫው ውጤት የአብላጫውን ድምፅ በሚያገኘው ፓርቲ የእጩዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሙ በአንደኛነት የሚቀርበው እጩ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ይሆናል።
በዘንድሮው ምርጫ አንድ በግልጽ የሚታወቅ ጉዳይ ቢኖር ፕሬዚደንት ኤድዋርዶ ዶሽ ሳንቶሽ የሀገሪቱ መሪ እንደማይሆኑ ነው።
በምርጫው እንደማይወዳደሩ ቀደም ሲል ካስታወቁ በኋላ ፓርቲው በመጨረሻ ባካሄደው ጉባዔው ዦዋዎ ሉሬንቾን ቀዳሚው እጩ አድርጎ ሰይሟል።
ከምርጫው በኋላ ሉሬንቾ ቀጣዩ የአንጎላ ፕሬዚደንት መሆናቸው እንደማይቀር ማንም አልተጠራጠረም።
የተቃዋሚ ወገን በአሁኑ ጊዜም ቢሆን በቂ የማሸነፍ እድል የለውም።
እርግጥ በወቅቱ በሚታየው ከፍተኛ የህዝብ ብሶት የተነሳ የተቃዋሚ ወገን ከገዢው ፓርቲ የተወሰነ ድምፅ መንጠቁ አይቀርም።
ይሁን እንጂ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የተከፋፈሉ እና ጠንካራ መሪም የሌላቸው ናቸው።
ምን ለመስራት እንደሚፈልጉም መልዕክታቸውን ለህዝብ በሚገባ መልኩ ማስተላለፍ አልቻሉም።
እስካሁን እንደሚታየው በሀገሪቱ ያሉት ፓርቲዎች እኩል የመፎካከር እድል አላቸው ሊባል አይችልም።
እርግጥ ሁሉም ፓርቲዎች በመንግሥት ራድዮ እና ቴሌቪዥን ማስታወቂያዎቻቸውን ማስተላለፍ ይችላሉ።
ይህ ግን ብቸኛው ምሳሌ ነው ከዚህ በተረፈ ግን ፓርቲዎች በጠቅላላ በአንድ ዓይን ታይተው እኩል እድል ይሰጣቸዋል ብሎ ማሰቡ ስህተት ነው።
ምክንያቱም ይላሉ የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ንቱ ሁሌም ሲደረግ እንደቆየው ገዢው ፓርቲ ከሌሎቹ በተለየ ለራሱ ሰፊ እድል ሰጥቶዋል።
ቴካ ንቱ ካለፉት ዓመታት ወዲህ በጀርመን የኤሰን ከተማ ሲሆን የሚኖሩት ለምርጫው ዘመቻ እረፍት ወስደው ወደ አንጎላ ሄደዋል።
ባለፉት ምርጫዎች የተቃዋሚው ወገን በጠቅላላ ከ የምክር ቤት መንበሮች መካከል ዎቹን እንኳን አለማግኘቱ በጣም የሚያሳዝን ነው።
ብዙ የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደሚገምቱት በምርጫ ዘመቻ ወቅት ብዙም የማይታዩት የአንጎላ ፕሬዚደንት ዶሽ ሳንቶሽ በጠና ሳይታመሙ አልቀሩም።
የፖርቱጋል ሳምንታዊ መጽሄት ኤስፕሬሶ ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው እየተበላሸ የሄደው የፕሬዚደንቱ ጤንነት የአንጎላ አመራር አባላትን እጅግ አሳስቧል።
ርዕሰ ብሔሩ ፕሬዚደንቱ አንድ ነገር ቢሆኑ ይህ ለ ኤምፒኤልኤ ድንገተኛ አይሆንበትም የዶሽ ሳንቶሽን ተተኪ በማዘጋጀት ዦአዎ ሉሬንሶን መርጧል።
በመሆኑም ፕሬዚደንቱ ድንገት በምርጫ ዘመቻ ወቅት እንኳን ቢሞቱ ፓርቲው ችግር አያጋጥመውም።
ከፍተኛ የመንግሥት ቦታዎችን ለመያዝ የስልጣን ሽኩቻ ሊነሳ ይችላል ባይ ናቸው።
ምክንያቱም ኾዜ ኤድዋርዶ ዶሽ ሳንቶሽ ዋና ዋና የሚባሉትን የመንግሥት ስልጣን ቦታዎችን ለርሳቸው ታማኝ ለሆኑ ሰዎች ሰጥተዋል።
ለምሳሌ ልጃቸው ኢዛቤል ዶሽ ሳንቶሽ የሀገሪቱን የነዳጅ ዘይት ተቋም ሶናንጎልን ወንድ ልጃቸው የመንግሥቱን የነዳጅ ዘይት መስሪያ ቤትን በኃላፊነት ይመራሉ።
የፖሊስ የጦር ኃይሉ እና የስለላ ድርጅቱም በዶሽ ሳንቶሽ ታማኞች ነው የተያዘው።
እነዚህ ባለስልጣናት ዶሽ ሳንቶሽ ስልጣናቸውን በሚለቁበትም ጊዜ ይህንኑ ስልጣናቸውን እንደያዙ መቆየት ይችላሉ።
የአንጎላ ምክር ቤት በመጨረሻው ጉባዔው ወቅት ተሰናባቹ ፕሬዚደንት የሾሟቸው ባለስልጣናት እንዳይነኩ የሚያዝ አንድ ህግ በከፍተኛ ድምፅ አፅድቋል።
ህጉን በምክር ቤት የሚወከሉት ሁለቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዩኒታ እና ካዛ ሲኤ ቢቃወሙትም ከ የምክር ቤት መንበሮች ብቻ በመያዛቸው ሕጉ አልፏል።
የሕጉ ማለፍ በጣም አነጋጋሪ እንደነበር ዜጠኛ ኾዜ አዳልቤርቶ አስታውሷል።
ኤድዋርዶ ዶሽ ሳንቶሽ ፕሬዚደንቱ ትተውልን የሚሄዱት ሕግ ብዙ ክርክር አስነስቶ ነበር።
እና ለጦር ኃይሉ ለፖሊሱ እና ለስለላው ተቋም የሚፈልጓቸውን ሰዎች መሾም ይፈልጋሉ ብዬ ነው የማስበው።
የአፍሪቃ ዋንጫ አስተናጋጅ ለሳምንታት የዘለቀ ደም አፋሳሽ አመፅ መካከለኛው አፍሪቃ የምትገኘው ሀገር ብሩንዲን አጨናንቋል።
የሀገሪቱ ጦር ከአማፂያን ጋር እየተታኮሰ በርካታ ሰዎች መሞታቸውም ተረጋግጧል።
ከዚህም በተጨማሪ ማንነታቸው ያልታወቁ እና የወታደር የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች በርካታ የመንግሥት ፓርቲ አባሎችን መግደላቸው ተሰምቷል።
በሚመጣው ግንቦት እና ሰኔ ወር ብሩንዲ ውስጥ ምክር ቤታዊ እና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይካሄዳል።
የገዢው ፓርቲ መሪ ፒር ንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ዙር በፕሬዘደንትነት እቀርባለው ማለት ግጭቱን ይበልጥ አፋፍሞታል።
የብሩንዲ ህገ መንግሥት ለአንድ መሪ የስልጣን ዘመን ቢበዛ የምርጫ ዙር ነው ያስቀመጠው።
ጥቃቶች ሲፈፀሙ የሚታየው ልክ በገዢው ፓርቲ እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ግጭት ሲነሳ ነው።
እንደ ቦኒምፓ ተቃዋሚዎች ገዢው መንግሥት የምርጫ ምዝገባውን እያጭበረበረ ነው ብለው ያምናሉ ይላሉ።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቦኒምፓ ሲቪል ማሕበረሰቡም ቢሆን በምርጫው የምዝገባ አሠራር ደስተኛ እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት።
ሆን ተብሎ ተቃዋሚዎችን ለማስፈራራት እና ለማሸማቀቅ ሲባል ፍተሻ ይካሄድ ነበር።
የመብት ተሟጋቹ ቦኒምፓ መንግሥትን የሚቃወም አስተያየት በመስጠታቸው ታስረው እንደነበር ይናገራሉ።
ጋዜጠኞችም ቢሆኑ ነፃነት እንደሌላቸው እና ለህይወታቸው እንደሚሰጉ ነው የሚናገሩት።
የተባለው የተቃዋሚዎች የሬዲዮ ጣቢያ ባልደረባ የሆነ አንድ ጋዜጠኛ ለዶይቸ ቬለ እንደተናገረው በቅርቡ ከተጣለበት ጥቃት ለጥቂት ነው የተረፈው።
የመካከለኛው አፍሪቃ የግንኙነት መረብ ባልደረባ ጌዚነ አሜስ ለተቃዋሚዎች እና የመብት ተሟጋቾች የመፈናፈኛው እድል እጅግ ውስን ነው።
ይህም ማለት ሀሳብ የመስጠት እና የመሰብሰብ መብታቸው የቀነሰ ነው።
መንግሥት ደግሞ በሲቪል ማህበረሰብ እና የመብት ተሟጋቾች ላይ ጭቆናውን ቀጥሏል።
በዛ ላይ መንግሥት እና ተቃዋሚዎች አንድ ዓይነት ህግ የላቸውም ይላሉ።
ይህም ግልፅ የሚሆነው ለምሳሌ ተቃዋሚዎች ልክ ከምርጫዎቹ ሁለት ሳምንታት አስቀድመው ብቻ ነው የመሰብሰብ እና የምርጫ ዘመቻ የማካሄድ መብት ያላቸው።
ይልቁንስ ተቃዋሚዎች የምርጫ ሂደቱን ሊያበላሹ ብሎም መንግሥትን ሊገለብጡ ነው የተነሳሱት።
ይህም በዚህ ላይ የሚደረገው አፀፋ አመፅ ማስነሳቱን ለማየት ነው።
እንደ ጌዚነ አሜስ ብሩንዳዊያኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ መንግሥት ቃል የሚገባውን እንደማይወጣው ተገንዝበዋል።
አሜስ ህዝቡ ምርጫ አድክሞታል ይህ ግን የግድ በመንግሥት ምክንያት ብቻ አይደለም ይላሉ።
እና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የሀገሪቱን ከመቶ ማስተዳደሪያ እንደሚሸፍን ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጌዚነ አሜስ ደግሞ የአውሮፓ ሕብረት አንድ አይነት ርምጃ ያስፈልገዋል ባይ ናቸው።
የብሩንዲን ወቅታዊ ልማት ወጥ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት አንድ አይነት ውሳኔ ያስፈልጋል በግልፅ የፕረስ ሀሳብን በነፃ የመግለፅ እና የመሰብሰብን ነፃነት የሚጠይቅ።
በተለይ የሀገሪቱ መንግሥት ዝግጅቱን ከጥሩ ገፅታው ብቻ ለማሳያ እየተጠቀመበት እንደሆነ የመብት ተሟጋቾች ይናገራሉ።
ተረኛ የነበረችው ሞሮኮ ባለፈው ህዳር ወር ነበር በምዕራብ አፍሪቃ የተዛመተውን ገዳዩን የኤቦላ ቫይረስ ፍራቻ ውድድርን እንደማታዘጋጅ ያስታወቀችው።
በአለም አቀፍ ዘንድ ገፅታውን ለመቀየር ሲሞክር ይህ የመጀመሪያው ጊዜ አይደለም ይላሉ ከሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል ቪክቶር ኖጉሪያ ።
እንደ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለዓመታት የኤኳቶሪያል ጊኒን መንግሥት የሰብአዊ መብትን አያከብርም ሲሉ ተችተዋል።
ልዩ ለግድያ የተዘጋጀ ቦታ አለ ከዚህም በተጨማሪ የፕረስም ሆነ ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት የተጨቆነ ነው።
አምንስቲ ኢንተርናሽናል ባለፉት አመታት የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ክስ ሳይመሰረትባቸው በዘፍቃድ እየታሰሩ እና እየተገረፉ ነው ሲል ዘግቧል።
እንደዚሁ ድርጅት ዘገባ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ቢያንስ አራት እስረኞች ተገድለዋል።
ኤኳቶሪያል ጊኒ ለሁለት ሳምንታት ያክል ብቻ ነው የሞት ብይኗን ያቋረጠችው።
ይህም የፖርቹጋል ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት ማህበረሰን ለመቀላቀል መስፈርቶችን ማሟላት ስለነበረባት እንደሆነ ይነገራል።
የተፈጥሮ ሀብትን በተመለከተ ኤኳቶሪያል ጊኒ በዘይት እና በጋዝ ከአፍሪቃ ሀብታም ከሆኑት ሀገራት ተርታ ትመደባለች።
የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከጥሬ ሀብት የውጭ ገበያ የሚገኘውን ገንዘብ ለራሳቸው በግል ባንካቸው እንደሚያስገቡ ይተቻሉ።
ሀገሪቱ የዘይት ሀብት ስላላት የህዝቡ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት ጋር ሲነፃጸር በአማከይ ከፍተኛ ነው።
ይላሉ ከሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኖጉሪያ እኢአ ከ ዓም ጀምሮ ፕሬዚዳንት ቴውድሮ ኦቢያንግ ንጉማ ሀገሪቱን ይመራሉ።
የመብት ተሟጋቹ እንደሚሉት ፕሬዚዳንቱ ይህንን አጋጣሚ ለጥሩ ስም እየተጠቀሙበት ነው።
ነገር ግን በሌላ በኩል ስላለው የሀገሪቱም ገፅታ ትኩረት እንዲሰጥ ይጠቅማል።
ነገር ግን ጋዜጠኞች በዚህ ጉዳይ ላይ ፍላጎቱ ካላቸው በሀገሪቱ ትኩረት ስላላገኘው ነገር ሊዘግቡ ይችላሉ።
በርግጥ የዘንድሮው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅ ሀገር ኤኳቶሪያል ጊኒ ከዚሁ ዝግጅት በምን እንደምትጠቀም በቀጣዩ ሳምንታት የሚታይ ይሆናል።