input
stringlengths
1
130k
ድዋሌ ያሉትን ከማለታቸዉ ከብዙ ዓመታት በፊት የሶማሌዎችን መገዳዳያ ትልቅ እስር ቤት ጥሩ ሐገር ለማድረግ ብዙ ተሞክሮ ነበር።
የጨረሻዉ ጉባኤ ቃል ዛቻ ከቀድሞዋ የሶማሊያ ቅኝ ገዢና የበላይ ጠባቂ ርዕሠ ከተማ ተሰማ።
እንደ ወታደር ሱዳን ዘመተዉ ለሱዳን ነፃነት የሚፋለሙ አማፂያንን ወግተዋል።
እንደ ሚንስትር ሶማሊያ ሲገቡም ፓኪስታንም ሱዳኑም የሐገራቸዉን ጦር ሲወጉ ያዩቸዉ ሙስሊሞች ቅኝ ገዢ ጦራቸዉን ሲወጉ አዩ።
የብሪታንያ የኋላ ተወዳጅ ጠቅላይ ሚንስትር ለየቅኝ ተገዢዎቹ ሐገራት መዉደም ተጠያቂዎቹ ቅኝ ገዢዎች ሳይሆኑ እስልምና ነዉ ብለዉ አረፉ።
ይህንን እምነታቸዉን ዘ ሪቨር ዎር ባሉት መፅሐፋቸዉ በሰፊዉ አተተቱት።
ባለፈዉ ሳምንት ሐሙስ ለንደን ላይ የመከረዉን ዓለም አቀፍ ጉባኤ የመሩት ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬሳ ሜይ የቸርችል ፓርቲ መሪ ናቸዉ።
ምናልባት ፖለቲካዊ ሥብዕናቸዉንም አድናቂ ሊሆኑ ይችላሉም ለጉባኤተኞች የነገሩት ግን የሶማሊያ ቀዉስ በጣም እንዳሳሰባቸዉ ነዉ።
ይሕን ያክል የዓለም ማሕበረሰብ ተወካዮች እዚሕ አዳራሽ መገኘታቸዉም ሶማሊያን ማረጋጋት አስፈላጊ እንደሆነ ሥላመኑበት ነዉ።
ተገቢዉን እርምጃ እንደምንወስድ ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ የምንገነባዉም የረጅም ጊዜም ትንሳኤ ተስፋ እንደሚሆን ማረጋገጥ አለብን።
ሰኔ ጁቡቲ ላይ እንዲሕ እንዳሁኑ በሶማሊያ ጉዳይ ላይ የተነጋገረ ጉባኤ ነበር።
ዓላማዉ ለሶማሊያን ማዕከላዊ መንግሥ መመሥረት ሐገሪቱን ማረጋጋት ሕዝቧን መርዳት የሚል ነበር።
የፕሬዝደንት ዓሊ መሕዲ መሐመድ የመልዕክተኞች ቡድን ሞቃዲሾ በገባ ማግሥት ጁቡቲ ላይ የተባለ የታቀደ ቃል የተገባዉ ሁሉ በነበር ቀረ።
ከጅቡቲዉ እስከ ሐሙሱ ጉባኤ ድረስ ከጅቡቲ ሁለት እስከ ናይሮቢ ከካይሮ እስከ ብራስልስ ከአዲስ አበባ እስከ ለንደን ጉባኤዎች ተደርገዋል።
ለንደን ዉስጥ ብቻ በ እና በ ሁለት ጉባኤዎች ተደርገዋል።
ዉጤቱ አንዲቷን ሐገር የሶማሊያ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ የሶማሊ ላንድ የፑንት ላንድ የጋልሙዱግ የአዛኒያ ወደሚባሉ ትናንሽ ሐገር ወይም መንግሥትነት መከፋፈል ነዉ።
ከ ጀምሮ የተደረገዉ ጉባኤ ሥብሰባ የጦር ዘመቻ ርዳታ በጥፋት ዉጤት የተጣፋዉም ሶማሌዎች ሠላም ሥለማይፈልጉ አይደለም።
ሶማሊ ላንድ ከቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ዋና ከተማ ለንደን ዉስጥ ቆስላ ከፍታለች።
አንድ ሰሞን የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የሶማሊላንድ ወደብን በግልፅ ይጠቀም ነበር።
የአረብ ሐገራት ከሶማሊላንድ ጋር ከጦር ሰፈር እስከ ንግድ የሚደርስ ግንኙነት አላቸዉ።
ዩናይትድ ስቴትስ አረቦችም ሆኑ ኢትዮጵያ ሶማሊ ላንድን እንደ መንግሥት አያዉቁትም።
አብረዋት ለሚሰሯት ሐገር የመንግስትነት እዉቀና ያልሰጡበት ምክንያት በርግጥ ያነጋግራል።
ሶማሌን ሠላም ለማድረግ ከሶማሌዎች መሐል የመሐመድ አብዱላሒ መሐመድ መንግሥትን መርጦ ወዳጅን ማስታጠቅ አሸባብን ነጥሎ በሞቃዲሾ መንግሥት ማስመታት ነዉ።
ከዚሕ በፊት ከ ጀምሮ ተሞክሮ መክሸፉ እንደገና ተደግሞ እንደገና መጨናገፉ እንጂ ድቀቱ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተረሽ እንደሚሉት ዘንድሮም ረሐብ እያንዣበበ ነዉ።
ከ ሺሕ የሚበልጡ ሕፃናት ደግሞ ለሕይወታቸዉ በሚያሰጋ ረሐብ እየተሰቃዩ ነዉ።
የበለፀገዉ ዓለም ዘግይቶም ቢሆን ረሐብተኛዉን ሕዝብ እንደሚረዳ በለንደኑ ጉባኤ ላይ ቃል ገብቷል።
ከሶማሌዎች መሐል ታማኝ ሶማሌዎች የተጋበዙበት ጉባኤ ያሳለፈዉ ዉሳኔ የጦርነት ረሐብ ዑደቱን ማስቀረት መቻሉ ግን ሲበዛ አጠራጣሪ ነዉ።
የቀድሞዉ የሶማሊላንድ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አብዱላሂ መሐመድ ዱዋሌ እኛ ጨቅላ ዴሞክራሲን እየተንከባከብን ነበር ይላሉ ዓለም ግን ጀርባችንን ይዠልጠናል።
የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኤማኑዌል ማክሮ አዲስ የጀርመን እና ፈረንሳይ ወዳጅነት ውል ተፈራረሙ።
ሜርክል እና ማክሮ አገሮቻቸውን በሚያዋስነው ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው ድንበራቸው የሚካሄደውን የጋራ ትብብር ማሳደግ ፍላጎት አላቸው።
ይህ በመሆኑም አንደኛ በአውሮጳ ህብረት ውስጥ ጀርመን እና ፈረንሳይ የያዙትን ኃላፊነት እንደአዲስ መመልከት አለብን።
ሶስተኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጋራ ርምጃ መውሰድ በሚያስችለን የጋራ ሚና ላይ መግባባት ላይ መድረስ ይኖርብናል።
የቤልጂየም ፖሊስ በጂሃዲስትነት የጠረጠራቸዉን ሁለት ከሶሪያ የተመለሱ መሆናቸዉ የተገለጸ ጥቃት አድራሾች ሲገድል አንዱን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተነግሯል።
ፖሊስ የሽብር እቅዱን ያከሸፈዉ ከብራስልስ መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከጀርመን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘዉ የቨርቬርስ ከተማ ባካሄደዉ አሰሳ ነዉ።
የቤልጂየም ጠቅላይ ሚኒስትር ፖሊስ የወሰደዉ ርምጃ መንግሥታቸዉ ሽብርን ማስፋፋት የሚሹትን ለመዋጋት መቁረጧን ያሳያል ብለዋል።
ባለፈዉ ሳምንት ፓሪስ ላይ ከደረሰዉ የሽብር ጥቃት በኋላ ጀርመንን ጨምሮ አብዛኞቹ የአዉሮጳ ሃገራት ከፍተኛ ጥንቃቄና ቁጥጥራቸዉን አጠናክረዋል።
በኬሚሴ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሒዷል ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የወታደሮቹ ተልዕኮ በመንግሥቱ ጦር እና በዓማፅያን መካከል የሚካሄደው ውጊያ ዒላማ ያደረገው የአካባቢው ሲቭል ሕዝብ ጉዳት እንዳይደርስበት መከላከል እንደሆነ አንሚስ አመልክቷል።
ስለአሳሳቢው ሁኔታም ከተቃዋሚ ቡድኖች መሪዎች እና ከመንግሥት ተወካዮች እንዲሁም በወዝግቡ አብዝተው ከተጎዱት ተፈናቃዮች ጋር ተወያይተዋል።
ሎውኮክ በማዕከላይ ኢኳቶርያ ግዛት ያነጋገሯቸው የተቃዋሚው ኤስፒኤልኤ አይ ኦ ተጠባባቂ መሪ ፒተር ሊዦ ጆሴፍ ለሕዝብ መቆሙን አረጋግጠውላቸዋል።
ሕዝቡ የድርድሩ ማዕከል በሚሆንበትም ጊዜ በሀገሪቱ ሰላም እንደሚወርድ እርግጠኞች ነን።
የነፍስ ግድያ እና ክብረ ንፅህና መድፈርን እንደ ጦር መሳሪያ የጠቀሙባቸዋል።
እነዚህ ሁሉ ዓለም አቀፍ ሕጎችን የጣሱ ግዙፍ ወንጀሎች ናቸው።
በአሁኑ ጊዜ ሰባት ሚልዮን ሕዝብ የሰብዓዊ ርዳታ ያስፈልገዋል ሁኔታዎችም እየከፉ በመሄድ ላይ ናቸው።
በመሆኑም ውዝግቡ የሚመለከታቸው ሁሉ ሰላም ለማውረድ እንዲጥሩ ዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ባለስልጣን ማርክ ሎዎኮክ ተማፅነዋል።
በሀገሪቱ የሚታየውን ሰብዓዊ ስቃይ ለመቀነስ የኃይሉን ተግባር ማብቃት የመጀመሪያው እና ብቸኛው ዋነኛ ጉዳይ ይሆናል።
ስለዚህ የሚያስፈልገን ወደ ርዳታ ፈላጊው ሕዝብ መድረስ የምንችልበት ፈጣን አስተማማኝ እና ገደብ ያላረፈበት መንገድ ነው።
የአፍሪቃ ህብረት በየቀኑ ሲብሎችን የሚገድሉትን ወይም ሲብሎች ለሚገደሉበት ድርጊት ድርሻ የሚያበረክቱትን ለመቅጣት በሚወስደውን ርምጃ አንጻር መቆም ለማንም ቢሆን ትክክለኛ አይደለም።
የአፍሪቃ ህብረት ከኢጋድእና ከሌሎች አጋሮች ጋር ባንድነት በመሆን ሰላም ለማውረድ የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉትን ለመቅጣት ሳያመነታ እና ሳያሰልስ መስራቱን ይቀጥላል።
ድርድሩን በሸምጋይነት እየመራ ያለው ኢጋድ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች የፈረሟቸውን የሰላም ስምምነቶች እንዲያከብሩ ጥረት ቢያደርግም እስካሁን አልተሳካለትም።
እንዲሁም ሌላው ደግሞ የስልጣን ክፍፍሉ ተመጣጣኝነት ብሎም የካቢኔው አደላደል ሶስተኛው በሀገሪቱ የሚኖሩት ግዛቶች ቁጥር ይጠቀሳሉ።
ምን ያህል ግዛቶች ሊኖሩ ይገባል የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ አንዳንዶች ሲሉ መንግሥት ብሏል ይህ ጉዳይ መፍትሔ ሊገኝለት ይገባል።
ሌላው የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞችን እያወዛገበ የሚገኘው ጉዳይ የፀጥታውን ጥያቄ ይመለከታል።
የሀገሪቱ መንግሥት ዓማፅያን ቡድኖች በብሔራዊው ጦር ውስጥ እንዲዋኃዱ ሲጠይቅ ተቃዋሚዎች የመንግሥቱ የኤስፒኤል ጦር ተበትኖ አዲስ ጦር እንዲቋቋም ነው የሚፈልጉት።
በድርድሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ሱዳን አንግሊካን ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ጃስቲን ባዲአራማ ተቀናቃኞቹ ወገኖች ልዩነታቸውን በማስወገድ ውዝግቡን ባፋጣን እንዲያበቁ አሳስበዋል።
እና ሕዝባቸውን የሚወዱ ከሆነ ሕዝቡ ከመጥፋቱ በፊት የሕዝቡን ፍላጎት በማድመጥ ሰላምን መቀበል አለባቸው።
ይዘት ሼክ አንታ ዲዮፕ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት ነጻነታቸውን በመቀዳጃቸው ዋዜማ በአህጉሪቱ በሚገኙ አብዛኞቹ ምሁራን ዘንድ አንድ መጽሐፍ ተወዳጅ ነበር።
መጽሐፉ የኔግሮ ሃገራት እና ባህል በሚል ርዕስ በሴኔጋሊያዊው ሼክ አንታ ዲዮፕ የተከተበ ነው።
በርካታ መጽሐፍትን ላሳተሙት ፕሮፌሰር አንታ ዲዮፕ ይህ የመጀመሪያ መጽሐፋቸው ነው።
ፕሮፌሰሩ ከዘረኝነት ጭፍን ጥላቻ የተላቀቀ አጠቃላይ የአፍሪቃ ታሪክን የመጻፍን መንገድ የከፈቱ ናቸው ይባልላቸዋል።
አዲስ አበባን ያስጨነቀው እስርና መግለጫ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የምርጫ ቅስቀሳ በደቡብ ክልል የምርጫ ምልክቶችን የያዘዉ የናሙና ፖስተር በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች አለመለጠፉንም መድረክ አክሎ ገልጿል።
የኤርትራ ኛ ዓመት የነፃነት ዕለት ኤርትራ ተቺዎች እንደሚሉት አሁን የአፍሪቃ ሰሜን ኮሪያ ናት።
ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች በቅርቡ ባወጣዉ የፕረስ ነፃነት ዝርዝር ከኤርትራ የባሰች ሐገር ብትኖር አንድ ናት።
ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ የራስዋን መንግሥት በይፋ ከመሠረተች ዛሬ ዓመት ደፈነች።
የቀድሞዎቹ አማፂያን የመሠረቱት መንግሥት ትንሺቱን ምሥራቅ አፍሪቃዊት ሐገር የመላዉ አፍሪቃ የልማት ዕድገት አብነት እንደሚያደርጓት ተስፋ ሰጥተዉ ነበር።
ተስፋዉ ግን የዶቸ ቬለ ዳንኤል ፔልስ እንደዘገበዉ ብዙ አልቆየም።
ኤርትራ ዛሬ ብዙ ተንታኞች እንደሚተቹት የአፍሪቃ ሰሜን ኮሪያ ናት።
ስዊድን የምትኖረዉ ኤርትራዊት ሜሮን እስጢፋኖስ ዛሬ ለዋለዉ የኤርትራ የነፃነት ቀን ደንታ የላትም።
በትግሪኛ የሐገር ነፃነት ማለት የሰዎች ነፃነት ማለትም ነዉ ትላለች የ ዓመቷ የመብት ተሟጋች።
በዚሕም ምክንያት ቀጠለች ሜሮን ዳንኤል ፔልስ እንደጠቀሰዉ ብዙ ሰዎች ማንም ሰዉ ነፃ ሳይወጣ የነፃነት ቀን የምናከብረዉ ለምድነዉ
የዛሬ ሃያ አምስት ዓመት የዛሬን ቀን የኤርትራ ነፃነት ሲታወጅ ርዕሠ ከተማ አስመራ በደስታ ፌስታ ፈንጠዝያ ተደበላልቃ ነበር።
ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በደስታ ባሕር ይዋኝ ለነበረዉ ሕዝባቸዉ ባደረጉት ንግግር ዛሬ የኤርትራ ዳግማዊ ልደት ነዉ።
አዲሲቱ ሐገር የመላዉ አፍሪቃ የልማት ዕድገት ተስፋ እንደምትሆንም የፕሬዝደንት ኢሳያስ መንግሥት ቃል ገብቶ ነበር።
ብሪታንያዊቱ የኤርትራ ጉዳይ አጥኚና ደራሲ ሚሼኤላ ሮንግ እንሚሉት ደግሞ በ አስመራን የጎበኙበት ወቅት ልዩ ጊዜ ነበር ።
ኤርትራ ከሙስና የፀዳች መንግሥቷ ለሁሉም ክፍት የፈለገዉ ሰዉ በፈለገ ጊዜ ሚንስትሩን ማናገር የሚችልባት ሐገር ነበረች።
በ ዎቹ ተሰደዉ የነበሩ ኤርትራዉያን በብዛት ወደ ሐገራቸዉ እየተመለሱ መዋዕለ ንዋያቸዉን ሥራ ላይ እያዋሉ ነበር።
ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያዋስነዉ ድንበር በቅጡ ባለመካለሉ በ ሌላ ጦርነት ፈነዳ።
ኢሳያስ የቀድሞ ሚንስትሮች እና ታጋዮችን ሳይቀር የሚተቿቸዉን ሁሉ ባንድ ጊዜ እስር ቤት ወረወሯቸዉ ደራሲ ሮንጎ እንዳሉት።
ዲፕሎማቶች ሳይቀሩ ከአስመራ ዉጪ መንቀሳቀስ የሚችሉት መንግሥትን አስፈቅደዉ ነዉ።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የኤርትራ ጉዳይ ልዩ አጥኚ ሺይላ ኬታሩት የሰብአዊ መብት ጥሰቱ አሳሳቢ ነዉ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የዛሬ ሁለት ዓመት የኤርትራ መንግሥትን ሰዎችን በባርነት በማሰቃየት በመድፈር እና ማንገላታት ተጠያቂ አድርጎታል።
ሰብአዊ መብት ከሚጣስባቸዉ እና ወጣቶችን ለስደት ከሚዳርጉ ምክንያቶች አንዱ ብሔራዊ አገልግሎት ነዉ።
በትወራ ደረጃ ዓመት የሞላዉ ኤርትራዊ ለተወሰነ ጊዜ ወታደራዊ እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚሰጥበት ግዳጅ ነዉ።
ብዙዎች ግን ለመንግሥት ገደብ የለሽ አገልግሎት የሚሰጥበት ነዉ ባዮች ናቸዉ።
ኤርትራ ዉስጥ ምርጫ ላለመደረጉም ከኢትዮጵያ ጋር ያለዉ ግጭት መፍትሔ አለማግኘቱን ተጠያቂ ያደርጋሉ።
የኤርትራ ስደተኞች ቁጥር እየተበራከተ ከመጣ ወዲሕ ጀርመንን ጨምሮ ጥቂት ምዕራባዉያን መንግሥታት ከአስመራ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ለማሻሻል አንዳድ እንቅስቃሴዎችን ጀምረዋል።
በ የቀድሞዉ የጀርመን የልማት ሚንስትር ጌርድ ሙለር አስመራን ሲገበኙ ባመቱ አንድ የኤርትራ ከፍተኛ የባለሥልጣናት ቡድን በርሊንን ጎብኝቷል።
ይላሉ አንዳድ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ተዋኞች ከኤርትራ መንግሥት ጋር ለመገናኘት ጥሪት እያፈሰሱ ነዉ።
ከኤርትራ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ወደነበረበት ለመመለስ ባለፉት ሰወስት ዓመታት እየጣሩ ነዉ።
ከዚሕ ቀደም ያነሳሁት መሠረታዊዉ የሰብአዊ መብት ይዞታ በተጨባጭ ምን መሻሻል ተገኝቷል
ከቅርብ ዓመታት ወዲሕ ሥለ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጤና ማጣት የሚናፈሰዉ አሉባልታ እየተደጋገመ ነዉ።
ሰዉዬዉ አንድ ቀን አንድ ነገር ቢሆኑ ምናልባት ለዉጥ ሊመጣ ይቻላል ባዮች አሉ።
ደራሲ ሮንግ ግን ሥልጣኑ ከብዙዎቹ የኢሳያስ ጄኔራሎች ካንዱ እጅ አያመልጥም ባይ ናቸዉ ደራሲዋ።
ብሔራዊ ሸንጎዉ እና የፍትሕ ሥርዓቱን የመሳሰሉ ተቋማት ትክክለኛ ሥልጣን የላቸዉም።
ሥለዚሕ ኢሳያስ አፈወርቂ ጡረታ ቢወጡ ወይም ቢሞቱ ብዙ ጄኔራሎች አሉ።
ከነሱ በታች ደግሞ የወጣቱን ስሜት የሚጋሩ ወጣት የጦር መኮንኖች አሉ።
ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ለመመስረት የሚደረግ እንቅስቃሴ ይኖራል ብዩ ግን አላምንም።
እንደ ሚመስለኝ አንዱ ጄኔራል ሥልጣኑን ከኢሳያስ የመዉረስ እድሉ ሰፊ ነዉ።