input
stringlengths
1
130k
በ እና ዓም በብዙ አፍሪቃውያት ሀገራት ውስጥ ተቃውሞ ተካሂዷል።
በዚምባብዌ እና በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ወጣቶች በተጠሉት ፕሬዚደንቶቻቸው አንፃር በተደጋጋሚ ተቃውሞ አድርገዋል ።
በሴኔጋል እና በቡርኪና ፋሶም ተቃዋሚዎች አምባገነን መሪዎቻቸውን ከስልጣን አባረዋል።
በሌሎች አፍሪቃውያትሀገራት ግን ተቃውሞዎቹ ያን ያህል አልተሳኩም ይላሉ ፕሮፌሰር ዛካሪያ ማምፒሌ።
በዚህ ፈንታ ድምፃቸውን ለማሰማት ሌላ አማራጭ ያፈላልጋሉ ማለት ነው።
ትልቁ አደጋ ግን ተቃውሞው እንዴት እንደሚካሄድ እና ምን እንደሚያስከትል መተንበይ አለመቻሉ ነው።
እቅዱ በአፍሪቃ የወጣቶች ሰነድ የተቀመጡትን ዓላማዎች ከግብ የማድረስ እና የወጣቱንም አቅም በፖለቲካው እና በልማቱ ዘርፍ የማጎልበት ዓላማ ይዞ ተነስቷል።
ይሁን እንጂ የዚምባብዌ ተወላጇ የመብት ተሟጋች ሊንዳ ማዜሪሬ በሰነዱ ስለተቀመጡት አማላይ ቃላት መስማት አትፈልግም።
ኮሚሽነር ዘይኑ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፖሊስ ኢንጅንየሩ በሞቱበት ቦታ የነበሩ ማስረጃዎች እና መረጃዎችን የሚሰጡ ሰዎችን ይዞ እየመረመረ ነው ብለዋል።
የአሟሟታቸውን ሁኔታ የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ፈጥነን ለማቅረብ ርብርብ እያደረግን ነው።
ዉይይቱ ሲያበቃ ዛሬ ከቀትር በኋላ የነበረዉን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለዉን የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
የገበያ ማዕከሉ አሁን በሚገኝበት መብራት ኃይል በተባለው ቦታ እንኳ ቃጠሎ ሲገጥመው ሁለተኛ ጊዜው ነው ፡፡
የገበያ ማዕከሉ አሁን በሚገኝበት መብራት ኃይል በተባለው ቦታ እንኳ ቃጠሎ ሲገጥመው ሁለተኛ ጊዜው ነው፡፡
መልካም እንደልሆነ አጋጣሚ ደግሞ በሁለቱም የአደጋ ክስተት ንብረታቸው ተቃጥሎ የተጎዱ ወገኖች አሉ ፡፡
በሌላ በኩል ነጋዴዎቹ መደበኛ ስራቸውን ለመጀመር የብድር ገንዘብ እየተመቻቸ ስለመሆኑ መስማታቸውን ገልፀዋል ፡፡
ምንም እንኳን እስካሁን ተግባራዊ ባይደረግም ብድር ከችግሩ አገግሞ ወደ ስራ ለመግባት አያስችልም የሚሉት ነጋዴዎች መንግሥት የተለየ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡
ብድር ጫና ይፈጥራል የሚል ቅሬታ ስለመነሳቱ ያነሳሁላቸው ኃላፊው አብዛኞቹ ቀደም ሲል ከተቋሙ የወሰዱትን ብድር የመለሱ መሆናቸውን አረጋግጠናል ብለዋል ፡፡
የገበያ ማዕከሉ መልሶ ግንባታ እየተካሄደ በሚገኝበት ቦታ ተገኝቼ እንደተመለከትኩት እንዳንዶቹ ሱቆች በር በመግጠም ሥራ ለመጀመር ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ተመልክቻለሁ ፡፡
ባህል ሪታ ፓንክኸርስት የኢትዮጵያ ባለውለታ አዲስ አበባ ላይ ትዳር የመሰረቱት የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪዎች በትዳር ከ ዓመታት በላይ ዘልቀዋል።
ወ ሮ ሪታ ፓንክኸርስት በቤተ መፅሕፍት ባለሙያነታቸው በብሔራዊ ቤተ መፅሕፍት አገልግለዋል።
በኢትዮጵያዉያን ዘንድ ሕያዉ ሆነዉ ሲታወሱ ይኖራሉ ሀገራችን ሀገሯ ህዝባችን ህዝቧ ኑሯችን ኑሮዋ ሆኖ ስታገለግለን እድሜዋን ጨርሳ ከእኛው ዘንድ አረፈች።
ደህና ሁኚ ይላል ጋዜጠኛ የትነበርክ ታደለ በፌስቡክ ድረገፁ ያስቀመጠዉ ጽሑፍ።
ባለቤታቸዉ አጋፋዉ የኢትዮጵያ የታሪክ ተመራማሪ የፕሮፊሰር ሪቻርድ ፓንክኸርስት ከሁለት ዓመት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ይታወሳል።
በዚህ ዝግጅታችን የሪታ ፓንክኸርስትን የሕይወት ታሪክና በኢትዮጵያ ሳሉ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ እንቃኛለን።
በጎርጎረሳዉያኑ ዓ ም በሩሜንያ የተወለዱት ወ ሮ ሪታ ፓንክኸርስት በ ዓመታቸዉ ከወላጆቻቸዉ ጋር ወደ እንጊሊዝ ተሰደዱ።
ታዳጊዋ ሪታ በእንጊሊዝ ሃገር ካምብሪጅ ከተማ በሚገኝ የልጃገረዶች ት ቤት የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን ተከታትለዋል።
የከፍተኛ ትምህርታቸዉን በኦክስፎድ ዩንቨርስቲ ፈረንሳይኛና ሩስያንኛን በሚያካትተዉ የዘመናዊ ቋንቋች ጥናት በማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል።
ሪታ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን እንዳጠናቀቁ በመጀመርያ የተቀጠሩት ቻተም ሃዉስ በሚገኘዉ ፕሬስ ቤተ መፅሕፍት ዉስጥ ነዉ።
ከዝያም ሪታ የዝያን ግዜ የፍቅር ጓደኛቸዉ ሪቻርድን እና የሪቻርድን እናት ሲልቪያ ፓንክኸርስትን ተከትለዉ ወደ ኢትዮጵያ በጎርጎረሳዉያኑ ዓ ም ይመጣሉ።
የሪታ ፓንክኸርስት ልጅ አሉላ ፓንክኸርስት ስለእናቱ ማንነት እንዲነግረን ቀጠሮ ልንይዝ የደወልነት በለቅሶ ላይ ሳለ ነበር።
እንድያም ሆኖ ለነገ ቀጠረንና ግንቦት የእናቱ ግባዕተ መሬት ከተፈፀመ ከአንድ ቀን በኋላ በስልክ ስለናቱ አጫወተን።
እናቱ ሪታ በብሪታንያ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን አጠናቀዉ በመፀሐፍ ትርጉም በቋንቋ አስተማሪነት እንዲሁም በቤተ መፅሐፍ ዉስጥ ሲሰሩ ሳለ ሪቻርድን ይተዋወቃሉ።
ሪታ እናቴ አባቴን እንደ አጋጣሚ ለንደን ከተማ ላይ ተዋዉቃዉ ነበር።
አባቴ ከእናቴጋር ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ መወሰኑን ነግሮ አብራ እንድትመጣ ጋበዛት እስዋም ወድያዉኑ ከሱ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ወሰነች።
እናት እና አባትዋ ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ መወሰንዋን ሲሰሙ በጣም ሰግተዉ ነበር።
በዚሁ ዓመት እናትና አባቴ እዚሁ አዲስ አበባ ጋብቻቸዉን ፈፀሙ።
ሚዜዎቻቸዉ ሜትር አርቴስት አፈወርቅ ተክሌ እና መንግስቱ ለማ ነበሩ።
አዲስ አበባ ላይ ትዳር የመሰረቱት የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪዎች በትዳር ከ ዓመታት በላይ ዘልቀዋል።
በረጅም ዓመታት የስራ ዘመናቸው ወ ሮ ሪታ የኢትዮጵያን ባሕል የኢትዮጵያውያን ሴቶች ታሪክን እንዲሁም በኢትዮጵያ የቤተ መፅሕፍት ታሪክና ዕድገትን መርምረዋል ዘክረዋል።
ወደ ለንደን የተሰደዱት በወቅቱ በሃገሪቱ በነበረዉ አስከፊ ሁኔታ ልጆቻችንን ለማሳደግ ከባድነ ነበር የሚል ስጋት አድሮባቸዉ ስለነበረ ነዉ።
እግረ መንገድዋን አባቴ ሪቻርድ በሚያዘጋጀዉ ኢትዮጵያን ኦብዘርቬሽን በተባለዉ መጽሔት ላይ በጽሑፍ ታግዘዉ ነበር።
በቤተ መጻሕፍት በተለይ የአጼ ቴድሮስ በብራና ላይ የተፃፉ ደብዳቤዎችን እና ጽሑፎችን በተመለከተ የተለያዩ ጽሑፎችን በማቅረብ አስተዋዉቃለች።
አቶ አሉላ በቀይ ሽብር ጊዜ ወላጆቼ እኛን ይዘዉ ወደ ብሪታንያ ተሰደዉ ነበር ብለኸኛል እስቴ ስለ ስደት ታሪክ ንገረን
ኑሮዋቸዉ ሙሉ በሙሉ እዚሁ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ዉስጥ ነበር።
ደርግ ወደ ስልጣን በመጣ ጊዜ መጀመርያ ሁኔታዉ ተቀይሮ ብሩህ ተስፋ ይመስል ነበር ።
አማን አብዶ የአባቴ ተማሪ ነበር በጣም ጎበዝ ተማሪ በጣም የሚያደንቀዉ ተማሪ ነበር።
አካባቢዉ ላይ ታንኮች ገብተዉ አማን አብዶ በተገደለ ጊዜ እና ሁኔታዉ አሳሳቢ እየሆነ ሄደ።
አባቴ እንግሊዝ ለንደን እንደገባ ስራ አልነበረዉም ከዝያም ለንደን በሚገኝ ዩንቨርስቲ የአፍሪቃ ጥናት ተቋም ዉስጥ ለማስተማር የአንድ ዓመት ኮንትራት አገኘ።
እናቴም በቤተ መፅሐፍት ጉዳይ ሞያ በለንደን በአንድ ዩንቨርስቲ ዉስጥ ስራን ጀመረች።
እንድያም ሆኖ ወላጆቼ ለንደን ይኑሩ እንጂ ሃሳባቸዉ ወደ ኢትዮጵያ ነበር።
በዝያዉ በለንደን ሲኖሩ የመጀመርያዉ የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ የዓለም አቀፍ ጉባኤ ለንደን ላይ እንዲጀመር አብረዉ ነበር ስራን የሰሩት።
ከዝያም አባቴ ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ እድልን ሲያገኝ ለመመለስ ፈለገ።
ከዝያም አባቴ ተመልሶ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ማገልገል ጀመረ።
እናቴም እንዲሁ የተለያዩ የጥናት ጽሑፎችን እንዲሁም የተማሪዎች የመመረቅያ ጽሑፎችን አርትዓይ በማድረግ ሥራን መስራት እገዛን ጀመረች።
ለምሳሌ ለኢትዮጵያዉያን ወጣት ተማሪዎች በየዉጭ ትምህርት እድል እንዲያገኙ በአንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ዉስጥ በመስራት ትልቅ እገዛን አድርጋለች።
በተለይ ግቢዋ ዉስጥ የምትተክላቸዉን የተለያዩ ተክሎች አበቦች በጣም ትወድ ነበር።
በዚህም ወጣት አታክልተኞችን ለማበረታታት በሚደረገዉ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ስተዋጾን አበርክታለች።
በሃገሪቱ በሚካሄድ የአትክልት ትርኢት ዉድድር ላይ በዳኝነት ወንበር ላይ ትቀመጥ ነበር።
ወ ሮ ሪታ ፓንክኸርስት ባለፉት ስድስት አምስት ዓመታት ከባለቤታቸዉ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ታሪካቸዉን መፃፍ ጀምረዉ ነበር።
ኢትዮጵያን ወዳጅዋ ሲቭሊያ ፓንክኸርስት ለኢትዮጵያ ሰርተዉ እዉቀት ፍቅርን አስተላልፈዉ አልፈዋል።
የፓንክኸርስት ቤተሰቦች ለኢትዮጵያዉያ ያበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ትዉልድ ሲማርበት እንዲሁም በስራቸዉ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ ሕያዉ ሆነዉ ሲታወሱ ይኖራሉ።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከገዢው ፓርቲ የተለመደ ይትባህል ወጣ ባለ መልኩ ያቀረቡት ንግግር ብዙዎች ተስፋ እንዲሰንቁ አድርጓቸዋል፡፡
ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቶሎ ማሻሻያዎችን እንዲተገብሩ የሚጠይቁ ደጋግመው የሚያነሱት አንድ ጉዳይ አለ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፡፡
ባለፈው የካቲት ወር የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌ ለስድስት ወር እንደሚቆይ ቢቀመጥም ጠያቂዎቹ ግን አሁኑኑ ይነሳ ባይ ናቸው፡፡
ይህንን አቋማቸው በይፋ ካሳወቁት መካከል የኢትዮጵያ መንግስት ሁነኛ አጋር የሚባሉት አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ይገኙበታል፡፡
የአሜሪካንን ፈለግ የተከተለ የሚመስለው የአውሮፓ ህብረትም አዋጁ በቶሎ እንዲነሳ ፍላጎቱን ገልጿል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ ቀናት ያህል ታስሮ ባለፈው ሳምንት ተለቅቋል፡፡
በእስር በቆየበት የፖሊስ መምሪያ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሳችኋል በሚል ወደ ገደማ ተጠርጣሪዎች ታስረው መመልከቱን ይናገራል፡፡
አብዛኞቹ የተከሰሱበትን ጉዳይ ግን እንኳ በቅጡ እንደማያውቁ እና ሲያዙም ድብደባ እንደተፈጸመባቸው እንደነገሩት ይገልጻል፡፡
የፉሪ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር አየለ ደበላ እና የፉሪ የትራፊክ ፖሊስ ኃላፊ አለ፡፡
አብዛኞቹ የመጡት ከአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ዙሪያ ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ አማረ የሚባል መካኒሳ ጋር የተያዘ ፌስ ቡኩን እያየ የኮሎኔል ደመቀን ፎቶ አጋርተሃል ተብሎ ነው የመጣው፡፡
በሙሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተይዘው እኛ የነበርንበት ፖሊስ ጣቢያ ያሉ ከቤታቸው ከስራ ቦታቸው እና ከመንገድ ላይ የተያዙ ናቸው፡፡
እነርሱ አሁን ከእኛ የተለየ የሚያደርጋቸው ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል በተያዙበት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ቀን ላይ፡፡
አሁን ሲያዩን አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በአመጽ ወቅት ላይ ተሳትፎ ነበራችሁ ነው፡፡
ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ባህር ዳርም ተርጣሪዎች የተያዙበት ሁኔታ ተመሳሳይ እንደሆነ የዓይን እማኞች ይናገራሉ፡፡
የባህር ዳር ዩኒቨርስቲው መምህር እና ጓደኞቻቸው በቆዩበት ፖሊስ ጣቢያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታሰሩ ቁጥራቸው ወደ የሚጠጉ ሰዎች እንዳጋጠሟቸው ይናገራሉ፡፡
ባህር ዳር ከነማ ከደሴ ከነማ ጋር በነበረው ጨዋታ ዕለት ረብሻ ፈጥራችኋል ተብለው ተይዘው የነበሩ ወደ ወይም ልጆች ነበሩ፡፡
እንዲዚህ አይነት በትንንሽ ጉዳዩች ጽሁፍ በኪሳችሁ ይዛችሁ ስቴድየም ተገኝታችኋል ተብሎ የታሰሩ ልጆች ነበሩ፡፡
እንደዚህ አይነት ልጆች ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ብዙ እስረኛ ነው የነበረው፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈጸሚያ መመሪያ በመላው ሀገሪቱ የሚተገብሩ ብሎ ክልከላዎችን የዘረዘረ ሲሆን ለተወሰኑ ቦታዎች ደግሞ አራት ክልከላዎችን አስቀምጧል፡፡
አዋጁን እና መመሪያውን የፈተሹ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ክልከላዎቹ አሻሚ ትርጉም ያላቸው እና ግልጽነት የሚጎድላቸው ናቸው ሲሉ ይተቻሉ፡፡
መመሪያ ተብሎ የወጣውን የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ ስታየው ህግ በሚያረቅቁ ሰዎች ተጽፏል ብሎ ለመናገር በጣም ነው የሚያሳፍረው፡፡
ስለ አመክኖያዊ ትስስራቸው መሬት ላይ ሲተገበሩ ስለሚያመጡት ውጤት ምን ያህል ተጨባጭ ናቸው
ምን ያህል ከሰው እና ከማህበረሰብ የቀን ተቀን መስተጋብር ጋር አብረው ይሄዳሉ ስለሚለው ጉዳይ ብዙም ትኩረት የተሰጠ አይመስለኝም፡፡
ለህግ ደንቦች አረቃቀቅ ምንም ክብር በሌለው ሁኔታ የተረቀቀ አይነት ነው፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ያሉ ድንጋጌዎች በስፋት የተቀመጡ እና አሻሚዎች የሆኑ ናቸው፡፡
ምርመራ ለምን ያህል ጊዜ ያህል ይካሄዳል የሚሉት እንደዚሁ የሉም፡፡
ታሳሪዎቹ አላግባብ መታሰራቸውን የት አቤት ማለት እንደሚችሉ ለማወቅ ተቸግረዋል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የሚወሰዱ እንደዚህ አይነት እርምጃዎችን የመከታተል እና የመቆጣጠር ተግባር ያለው መርማሪ ቦርድ ግን ስራየን እያከናወነንኩ ነው ይላል።
መርማሪ ቦርዱ በአዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች ኢ ሰብዓዊ መሆናቸውን ካመነ እርምጃውን እንዲያስተካክል ለኮማንድ ፖስቱ ሀሳብ እንደሚሰጥ ተደንግጓል፡፡
ቦርዱ ከተሰጠው ስልጣን እና ተግባር አንዱ በአዋጁ ምክንያት የታሰሩ ግለሰቦችን እና የታሰሩበትን ምክንያት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፋ ማድረግ ነው፡፡
አራማጆች አክቲቪስቶች ግን በየአካባቢው የታሰሩ ሰዎች በቦርዱ ከተጠቀሰው በጣሙኑ እንደሚልቅ ይሟገታሉ።
የቦርዱ ሰብሳቢ በባለፈው ሳምንት መግለጫቸው ከህብረተሰቡ ከሚደርሷቸው ጥቆማዎች ብዙዎቹ ሰዎች እየታሰሩ ያሉት በቂም በቀል ነው የሚል እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በስልጣን ላይ በቆየባቸው ዓመታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲያውጅ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜው ነው፡፡
ባለፈው ዓመት ታውጆ የነበረው ተመሳሳይ ድንጋጌ ለ ወር ከቆየ በኋላ እንዲነሳ ተደርጓል፡፡
በሚኒስትሮች ምክር ቤት አማካኝነት በየካቲት የታወጀው የአሁኑ ድንጋጌ ሕገ መንግስቱን እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል በሚል እንደነበር ይታወሳል፡፡
የአምቦው ዩኒቨርስቲ መምህር ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ነባራዊ ሁኔታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈላጊ ነው ብዬ አላምንም ባይ ናቸው።
መቀመጫቸውን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረጉት የሰብዓዊ መብቶች ህግ ባለሙያው አቶ ዩሴፍ ተመሳሳይ አስተያየት አላቸው፡፡
በዓረብኛ ፊደል የተገኙ የኢትዮጵያ የፅሁፍ ቅርሶች መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።