source
stringlengths
4
528
target
stringlengths
3
393
source_lang
stringclasses
1 value
target_lang
stringclasses
1 value
Nigeria’s Muhammadu Buhari, 76, also has scant regard for human rights, freedom of expression, or political dissent.
የ76 ዓመቱ የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ለሰብዓዊ መብቶች፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እና የፖለቲካ ተቃውሞ ያላቸው ትኩረት ያነሰ ነው፡፡
English
Amharic
But given the weakness of the competition, might it be rather too early to definitively sing Abiy's praises?
ግን ከቀረቡት ድክመቶች ጋር ስናወዳድረው፣ ለአቢይ በርካታ ውዳሴዎች መቅረባቸው በጣም የቀደመ ሆኖ ይታያል ወይ?
English
Amharic
After awarding the 2009 Nobel Peace Prize to Barack Obama in the early days of his administration, one would have thought that the Nobel Committee would be more circumspect about awarding another fledgling sitting president. Obama, for instance, did not keep the peace in Libya; rather, he created a situation of chaos that rages there until now.
የ2009ኙ የኖቤል የሰላም ሽልማት ለባራክ ኦባማ በመጀመሪያወቹ የስልጣን ቀናት ከተበረከተ በኋላ፣ ማንም ሰው እንደሚረዳው፣ የኖቤል ኮሚቴ የተሾመን ፕሬዝደንት ወዲያወኑ ጥንቁቅ ሆኗል፡፡ ለአብነት ያህል፣ ኦባማ ሊቢያ ውስጥ ሰላም አላመጡም፡፡ ይልቅስ እስካሁን ሊረግቡ ያልቻሉ ችግሮች እንዲፈጠሩ አድርገዋል፡፡
English
Amharic
Other laureates have also failed to live up to their promise, notably Myanmar politician Aung San Suu Kyi, who won the prize in 1991 while under house arrest and has since, as de facto government leader of the country, presided over the ethnic cleansing of Rohingya Muslims.
ሌሎች ተሸላሚ ሎሬቶችም የገቡትን ቃል መፈፀም አልቻሉም፡፡ በዋናነት የሚጠቀሱት፣ የማይናማሯ ፖለቲከኛ ኡንግ ሳን ሱ ኪ፣ የቁም እስር ላይ እያሉ ሽልማቱን ቢያሸንፉም፣ የሃገሪቱ መንግስት ዋና መሪ ከሆኑ በኋላ ግን በሮሂኒጊያ ሙስሊምች ላይ የተፈፀመውን የዘር ጭፍጨፋ መርተዋል፡፡
English
Amharic
North Vietnamese leader Le Duc Tho famously rejected the award — jointly presented to him and the controversial Henry Kissinger in 1973 — on the grounds that peace had not yet been restored in his country.
የሰሜን ቬይትናም መሪ ሊ ዱች ቶ፣ ሃገራቸው ሰላም አጥታ ባልተረጋጋችበት ወቅት ከሄኔሪ ኬሲንገር ጋር 1973 የቀረበላቸውን ሽልማት አለመቀበላቸው በደንብ ይታወቃል፡፡
English
Amharic
One assumes the Committee grants such awards in the anticipatory hope that it would encourage the laureate would to remain on a promising path of progress.
ማንም ሰው እንደሚረዳው፣ ኮሚቴው እንዲህ ያሉ ሽልማቶችን የሚያበረክተው፣ ተሸላሚው ቃል በገባው አካሄድ እንዲቀጥል በተስፈኛነት ለማበረታታት አስቦ ነው፡፡
English
Amharic
But it would make more sense to wait until the end of an administration and objectively assess whether an individual has in fact lived up to their promise and really deserves the award.
ነገር ግን ሽልማቱ ትርጉም የሚሰጠው እስከ አስተዳደሩ መጨረሻ ተቆይቶ፣ ግለሰቡ ቃላቸውን መኖራቸው እና ሽልማቱ የሚገባቸው መሆኑን አስተውሎ መስጠቱ ነው የሚጠቅመው፡፡
English
Amharic
Another reason for caution is that most of the African leaders mentioned above did not start out as despots. Museveni fought and kicked out the murderous dictator Idi Amin.
ለመጠንቀቅ የሚቀርበው ሌላኛው ምክንያት፣ ከላይ የተጠቀሱት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ መሪዎች አነሳሳቸው ጨቋኝ ሆነው አለመታየታቸው ነው፡፡
English
Amharic
When Magufuli took the reins of power, he was the poster boy for transparency and frugal governance.
ሙሴቬኒ ተፋልመው፣ ነፍሰ-ገዳዩን ኤዲ አሚንን ከስልጣናቸው አባርረዋል፡፡ ማግፉሊ ስልጣን በያዙበት ወቅት፣ የግልፅነት እና ወጪ ቆጣቢ አመራር አቀንቃኝ ነበሩ፡፡
English
Amharic
Buhari’s integrity and apparent zero-tolerance for corruption made him the “Messiah” for which Nigeria long yearned.
ቡሃሪ ለአንድነት እና ለሙስና ያላቸው ትዕግስት-አልባነት፣ ናይጄሪያ ለረዥም ጊዜ የጠበቀቻቸው ‹‹መሲህ›› አስመስሏቸው ነበር፡፡
English
Amharic
Even the late Robert Mugabe of Zimbabwe was once one of Africa’s foremost freedom fighters — only to leave office in disgrace after 37 tumultuous years.
በቅርቡ ያረፉት ሮበርት ሙጋቤ እንኳ፣ የአፍሪካ አንጋፋ የነፃነት ታጋይ ነበሩ፤ ስልጣናቸው ከ37 ፈታኝ ዓመታት በኋላ ያለምህረት ቢፈነቀሉም፡፡
English
Amharic
Critics also say that the PM “relies on his charisma to drive change,” rather than make use of institutional structures of government.
ተቺዎች ጨምረው እንደሚናገሩት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ለውጡን ለመምራት በተክለ-ሰብዕናቸው ላይ ተንተርሰዋል››፤ መንግስታዊ ተቋማትን ከማዋቀር ይልቅ፡፡
English
Amharic
While this might be efficient and useful for cutting through government bureaucracy, it might not provide an adequate foundation for sustainable long-term reforms.
ይህ የመንግስት ቢሮክራሲን ለመቀነስ የተሟላ እና ጠቃሚ ሊሆን ቢችልም፣ አስተማማኝ የረዥም ጊዜ ለውጦችን መሰረት ለመጣል አያስፈልግም፡፡
English
Amharic
Will Abiy be different from the others and continue on the path of peace and reform?
አቢይ ከሌሎች ተለይተው፣ በሰላም እና የለውጥ መንገድ ላይ መጓዛቸውን ይቀጥላሉ?
English
Amharic
Or will he follow the infamous route that his contemporaries in the continent have travelled? For both Ethiopia and Africa’s sake, I hope it is the former.
ወይስ የእርሳቸው የአህጉር ዘመነኛዎች በተጓዙበት የታወቀ መንገድ ይከተላሉ? ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ አክራሞት፣ ቀዳሚው ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
English
Amharic
Sudan’s democratic spring is turning into a long and ugly summer
የሱዳን የዴሞክራሲ ፀደይ ማለቂያ ወደሌለው አስቀያሚ የበጋ ንዳድ እየተቀየረ ነው
English
Amharic
Will Sudan go directly from one Arab winter to another without an intervening Spring?
ሱዳን ከአንዱ የአረብ ክረምት ወደ ሌላኛው ፀደይን ሳታይ ትሸጋገር ይሆን?
English
Amharic
When protesters forced Omar al-Bashir out of power in Sudan this April after 30 years of dictatorial role, it was an unalloyed good for the world.
ተቃዋሚዎች በሚያዚያ ወር ከ30 አምባገነናዊ አገዛዝ ዓመታት በኋላ ኦማር አል በሽርን ከሥልጣን ሲያባርሩት ለመላው ዓለም መልካም ዜና ነበር።
English
Amharic
Bashir has been wanted by The Hague since 2008 for genocide and war crimes in Darfur, and his ouster was a key step towards a free and democratic Sudan, as well as justice for Darfuris.
በሽር እአአ ከ2008 ጀምሮ በዘር ጭፍጨፋ እና የዳርፉር ጦር ወንጀል በሔግ ሲፈለጉ ነበር። ከሥልጣን መወገዳቸው ለሱዳን ዴሞክራሲ ቁልፍ እርምጃ ሲሆን፥ ለዳርፉሮች ደግሞ ፍትሕ ነው።
English
Amharic
But what’s followed in Sudan has been far less encouraging.
ከዚያ በኋላ የተከሰተው ግን ተስፋ አስቆራጭ ነው።
English
Amharic
Sudan’s military has promised elections, but not for as much as two years.
የሱዳን ሠራዊት ምርጫ ለማድረግ ቃል ገባ ግን ይህ በሁለት ዓመታት ውስጥ አይሆንም።
English
Amharic
The Transitional Military Council (TMC), the military leaders now in charge of the country, have included Bashir confidantes like Lt. General Ahmed Awad Ibn Auf, who was suspected of leading Janjawid militia massacres in Darfur.
አገሪቱን አሁን እየመሩ ያሉት ወታደራዊ መሪዎች የሚመራው የሽግግሩ ወታደራዊ ምክር ቤት የበሽርን የቅርብ አማካሪዎች፣ ለምሳሌ የጃንጃውድ የዳርፉር ወታደራዊ ጭፍጨፋ በመምራት የሚጠረጠሩት ሌተ/ጄነራል አሕመድ አዋድ ኢብን ኡፍን ይጨምራል።
English
Amharic
Many Sudan observers believe that Mohamed Hamdan Dagalo, known as Hemedti, is the person really pulling the strings on the TMC, where he serves as vice president.
ብዙ የሱዳን ጉዳይ ታዛቢዎች በወታደራዊ ምክርቤት ውስጥ ነገሮችንን እያከረሩ ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ በቅፅል ሥማቸው ሔምድቲ ናቸው።
English
Amharic
Hemedti not only recruited and led many of the Janjawid fighters who brutally suppressed dissent in Darfur—he has also been accused of having recruited child soldiers from Darfur to fight in Yemen’s bloody civil war on behalf of the Saudis.
ሔምድቲ በዳርፉር የተቃውሞ ድምፆችን በኀይል የጨፈለቁትን የጃንጃዊድ ተዋጊዎች ከመምራታቸውም ባሻገር ሕፃናት ወታደሮችን ከዳርፉር በመመልመል የየመን ደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ሳውዲን ወክለው እንዲዋጉ አድርገዋቸዋል።
English
Amharic
Despite the obvious dangers, Sudanese pro-democracy protesters are back out in the streets, demanding immediate transition to a civilian government.
አደጋው ግልጽ ቢሆንም የሱዳን የዴሞክራሲ ኀይሎች ግን አደባባይ ተመልሰው ወጥተው በአስቸኳይ ሲቪል የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም እየጠየቁ ነው።
English
Amharic
Their demands have been met with brutal violence.
ጥያቄያቸው አስከፊ ጥቃት ነው ያስከተለባቸው።
English
Amharic
On June 3, security forces including the Rapid Support Forces (RSF)—whose members are veterans of the Janjawid militias responsible for Darfur’s worst massacres—killed over 100 protesters, dumping bodies into the Nile River, raping and robbing civilians stopped at military checkpoints.
በጁን 3፣ በዳርፉር ጭፍጨፋ ተጠያቂ የሆኑት የጃንጃዊድ ሠራዊት የቀድሞ አባላት የተገነባው ፈጥኖ ደራሽ ኀይሎች ከመቶ በላይ ሰዎችን ገድሎ ሬሳቸውን ናይል ወንዝ ውስጥ ወርውሮታል። በወታደራዊ ፍተሻ ጣቢያዎች የተገኙ ሰዎችን አስቁመው፣ ደፍረዋል። ዘርፈዋል።
English
Amharic
Despite these horrific incidents, Sudanese citizens have continued to fight, launching a mass general strike on Sunday June 9.
እነዚህ ዘግናኝ ክስተቶች እያሉም የሱዳን ዜጎች ትግላቸውን ቀጥለዋል። እሁድ ጁን 9 ሰፊ ጠቅላላ አድማ ሲያደርጉ ነበር።
English
Amharic
The struggle over the internet
የበይነመረቡ ትግል
English
Amharic
As with most conflicts today, there’s an important information component to the struggle between activists and the Sudanese military.
ዛሬ ዛሬ እንደሚከሰቱት ብዙ ግጭቶች፣ በአክቲቪስቶቹና በወታደሮቹ መካከል ያለውን ትግል የሚገልጽ መረጃ አለ።
English
Amharic
The protests that ousted Bashir and have confronted the military have been organized by groups of middle-class Sudanese like the Sudanese Professionals Association and the Central Committee of Sudan Doctors using social media, especially Facebook.
በሽርን ከሥልጣን ያስወገዳቸውን እና ወታደሩን እየተጋፈጡ ያሉትን ተቃውሞዎች ያስተባበሩት መካከለኛ ገቢ ያላቸው እንደ የሱዳን ባለሙያዎች ማኅበር እና የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ ያሉ ሱዳኖች ማኅበራዊ ሚዲያን በተለይም ፌስቡክን በመጠቀም ነው።
English
Amharic
Since the June 3 massacre, Sudan’s mobile internet has been largely shut down, making online organizing and reporting on conditions on the ground vastly more difficult.
ከጁን 3ቱ ጭፍጨፋ በኋላ፣ የሱዳን በይነመረብ በሰፊው ተዘግቶ ከርሟል፤ ይህም በይነመረብ ላይ ማስተባበሩን እና ሪፖርት የማድረጉን ሥራ መሬት ላይ አስቸጋሪ እንዲሆን አድርጎታል።
English
Amharic
Sudan’s government previously shut down the internet for 68 days to combat the protests that ultimately led to Bashir’s ouster.
የሱዳን መንግሥት ከዚህ በፊት ለ68 ቀናት በይነመረብ በመዝጋት ተቃውሞዎችን በመከላከል የበሽርን ከሥልጣን መሰናበት ለማስቆም ሞክሮ ነበር።
English
Amharic
Facebook was an especially significant force in bringing women into the streets to protest against Bashir.
ፌስቡክ ሴቶች በሽርን ጎዳና ላይ እንዲቃወሙ በማስቻል የተለየ ሚና ተጫውቷል።
English
Amharic
Tamerra Griffin reported on a set of women-only Facebook groups that were initially used to share gossip, but which were mobilized to identify abusive state security officials, who were then hounded and sometimes chased out of their own neighborhoods.
ታሜራ ግሪፊን በፊት ወሬ ለመለዋወጫ ይጠቀሙበት የነበረ እና በኋላ ግን ጎንታይ የፀጥታ ሠራቶችን ለማጋለጥ እና አንዳንዴም ከመኖሪያ ሥፍራቸው እስኪሹሹ ድረስ ዒላማ እንዲሆኑ በማድረግ ሴቶች ብቻ ይጠቀሙበት የነበረ የፌስቡክ ገጽ እንደነበረ ይፋ አድርጋለች።
English
Amharic
The presence of women in the protest movements and the Zagrounda chant—a women’s ululation—has become a signature of the uprising.
በተቃውሞ ንቅናቄዎቹ ውስ የሴቶች መኖር እና የዛግሮንዳ ዝማሬያቸው— ሴቶቹ በአደባባይ ተቃውሞ ወቅት ያወጧቸው የነበሩ መፈክራዊ ዜማዎች — የአብዮቱ ፊርማ ሆኗል።
English
Amharic
Bashir memorably declared that the government could not be changed through WhatsApp or Facebook.
በሽር መንግሥት በዋትሳፕ ወይም ፌስቦክ እንደማይለወጥ መናገራቸው ይታዋሳል።
English
Amharic
His ouster suggests that the power of social networks as tools for mobilization is routinely underestimated by governments.
የእርሳቸው መባረር እንደሚያሳየው የማኅበራዊ አውታሮች ንቅናቄ መፍጠሪያ መሣሪያነት ላይ መንግሥታት ተደጋጋሚ ማናናቅ እንደሚያደርጉ ነው።
English
Amharic
But now social media seems to be leveraged at least as much by the military as by the opposition.
አሁን ግን ተቃዋሚዎች የሚጠቀሙበትን ያክል ወታደራዊ ኀይሉም ማኅበራዊ ሚዲያዎችን እየተጠቀመባቸው ነው።
English
Amharic
The internet has not been completely shut down—the government has been able to maintain its presence on Facebook, which features at least four pages controlled by the RSF, which are advertising the militia veterans’ version of events.
በይነመረብ ሙሉ ለሙሉ አልተዘጋም። በፈጥኖ ደራሽ ኀይሉ ቁጥጥር ሥር ያለው እና የቀድሞ ወታደሮቹን ተግባራት የሚያሳየው የመንግሥት የፌስቡክ ገጽ አሁንም አለ።
English
Amharic
Sudanese activist Mohamed Suliman is organizing a petition campaign, demanding Facebook remove these pages in recognition that they promote violence against peaceful protesters in Sudan.
የሱዳን አክቲቪስቶች ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ አመፅ የሚያበረታቱ መሆኑን አውቆ ፌስቡክ እነዚህ የመንግሥት ገጾች እንዲያግዳቸው ፊርማ እያሰባሰቡ ነው።
English
Amharic
In addition to combatting Sudanese propaganda on Facebook, Sudanese activists inside the country and in the diaspora are looking for ways to return internet access to the general population, so they can continue organizing protests and document government violence.
የሱዳንን የፌስቡክ ፕሮፓጋንዳ ከመዋጋትም በተጨማሪ አገር ውስጥ ያሉ እና ስደተኛ የሱዳን አክቲቪስቶች ተቃውሞ ማስተባበራቸውን ለመቀጠል እና የመንግሥትን የመብት ጥሰቶች ለመመዘገብ ይችሉ ዘንድ በይነመረብ ለብዙኀኑ መልሶ የሚዳረስበትን መንገድ እየፈለጉ ነው።
English
Amharic
Activists are organizing information-sharing networks on top of SMS and voice phone calls, but I’m also getting calls from Sudanese friends who wonder whether technologies like Google’s Loon could be used to put a cloud of connectivity over Khartoum.
አክቲቪስቶቹ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት እና በድምፅ ጥሪ የመረጃ ልውውጥ ኔትዎርኮችን እያደራጁ ነው። ነገር ግን ለኔም የሱዳን አክቲቪስቶችእንደ ጉግል ሉን ያሉ ቴክኖሎጂዎች ካርቱም ላይ የመገናኛ ዘዴ መፍጠር ይችሉ እንደሁ ለመጠየቅ እየደወሉልኝ ነው።
English
Amharic
(The answer: maybe. Loon acts as an antenna for existing telecoms networks, and those networks in Sudan have been forced to cut off connectivity. In addition, a balloon floating 20km over a city is a very attractive missile target.)
(መልሱም፦ ሉን ቴሌኮም አውታሮች እንደ አንቴና ሆኖ ነው የሚያገለግለው። የሱዳን አውታሮች ደግሞ ከግንኙነት ውጪ ተደርገዋል። በተጨማሪም፣ ከከተማው 20 ኪሜ ከፍ ብሎ የሚንሳፈፍ ባሉን በቀላሉ የሚሳኤል ታርጌት ሊሆን ይችላል።)
English
Amharic
Until very recently, the few Sudanese who had access via ADSL had been opening their wifi networks or sharing passwords with friends and inviting them to post messages from their houses.
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ፣ በኤዲኤስኤል (በስልክ ገመድ የሚዳረስ ኢንተርኔት አገልግሎት) ያላቸው ጥቂት ሱዳናውያን ዋይፋይ በማብራት እና የይለፍ ቃላቸውን ለወዳጆቻቸው በመስጠት ከቤታቸው መረጃዎችን እንዲለጥፉ እና እንዲለዋወጡ እያደረጉ ነበር።
English
Amharic
A couple of days ago I was seeing reports—unconfirmed—that even ADSL has been turned off. This may signal the start of a new phase of the crackdown.
ከሁለት ቀናት በፊት – ማረጋገጥ ባልችልም – ኤዲኤስኤልም ተዘግቷል የሚሉ መረጃዎችን እያየሁ ነበር። ይህ አዲስ ተቃውሞዎቹን ለመበተን እንቅስቃሴ መጀመሪያቸው ይሆን ይሆናል።
English
Amharic
On the morning of June 10 Yassir Arman, a major figure in the Sudan Peoples Liberation Movement, which fought a war against Khartoum leading to the independence of South Sudan, was deported from Khartoum to Juba by military helicopter.
ጁን 10፣ የሱዳን ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ደቡብ ሱዳን እንዳትገነጠል ባደረገው ውጊያ ታዋቂው ያሲን አርማን ከካርቱም ወደ ጁባ በወታደራዊ ሔሊኮፕተር ተገዶ ተልኳል።
English
Amharic
One major channel for information from Sudan in the future may be from Sudanese who are in touch with organizers on the ground who have been forced to flee the country and report from neighboring countries.
ሌላኛው ዋናው የሱዳን የመረጃ መንገድ ምናልባት ከሱዳን ወደ ጎረቤት አገራት የተሰደዱ ነገር ግን ሱዳን ውስጥ ተቃውሞዎችን ከሚያደራጁ ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በዚያ በኩል የሚያገኙት መረጃ ነው።
English
Amharic
Countries are known by the company they keep, and the military government’s supporters are well resourced: Saudi Arabia and the United Arab Emirates have provided $3 billion in aid to the military leaders.
አገራት በአጋሮቻቸው ነው የሚታወቁት። ወታደራዊው መንግሥትም ብዙ የወዳጅ ሀብት አለው፦ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለወታደራዊ አመራሮቹ የ3 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጥተዋል።
English
Amharic
Given the Trump administration’s tight ties to the Saudi and UAE governments — which have extended to overruling Congress in selling arms to those regimes — it seems unlikely that a petition to the White House to recognize the RSF as a terrorist organization will meet with approval any time soon.
የትረራም አመራርም ቢሆን ከአረብ ኢሜሪትስ ጋር ባለው ለነዚህ አገራት መሣሪያ መሸጥ የሚከለክለውን የኮንግረስ ውሳኔ እስከመሻር የሚያደርስ ጥብቅ ትሥሥር ኋይት ሀውስ ፈጥኖ ደራሹን ኀይል በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲመዘግበው የተዘጋጀው ፊርማ ማሰባሰብ በቅርቡ ውጤት ያመጣል ብሎ መጠበቅ አያስኬድም።
English
Amharic
(By contrast the African Union — which has a regrettable history of ignoring misbehavior by African military rulers — has suspended Sudan after this weekend’s crackdown.
(በተቃራኒው የአፍሪካን ወታደራዊ አገዛዞች ቸል በማለት የሚያስቆጭ ታሪክ ያለው የአፍሪካ ኅብረት ሱዳን በዚህ ሳምንት ካደረገችው ተቃውሞን የመጨፍለቅ ሥራ በኋላ ከአባልነት አግዷታል።
English
Amharic
A few things we can do to help
እኛ ልናደርግ የምንችላቸው ጥቂት ነገሮች
English
Amharic
It’s hard to know what to do as a private citizen when faced with a situation like the one in Sudan. Some thoughts on what might actually be helpful:
ሱዳን ውስጥ እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር እኛ እንደ አንድ ዜጋ የምናደርገው ይጠፋናል። አንዳንድ ሐሳቦች ምን ማድረግ እንደምንችል ሊየመላክቱ ይችላሉ፦
English
Amharic
– Pay attention and ask others to do so as well.
– ሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ እና ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቁ።
English
Amharic
All governments, including military governments, are limited in what actions they can take by public perception.
ሁሉም መንግሥታት – ወታደራዊ መንግሥታትን ጨምሮ – የሚወስዱት እርምጃ ሕዝባዊ ዕሳቤውን እየተመከቱ ነው።
English
Amharic
If Saudi Arabia and the United Arab Emirates understand that people are actually watching what the Sudanese military is doing, it may limit their willingness to support a government run in part by experienced génocidaires.
የሳዑዲ እና የአረብ ኢምሬትስ አገራት ሰዎች የሱዳን ሠራዊት ምን እየሠራ እንደሆነ የሚከታተሉ ከመሰላቸው ልምድ ባላቸው የዘር ጨፍጫፊዎች እየተመራ ያለውን መንግሥት ለመደገፍ ፈቃደኝነታቸው ሊገደብ ይችላል።
English
Amharic
Reporter Yousra Elbagir is reporting from the ground in Khartoum and her Twitter feed is deeply helpful. Declan Walsh, the New York Times bureau chief, is doing excellent reporting from the ground.
and ሪፖርተር ዩሰራ ኤልባጊር ከካርቱም፣ ሱዳን ሆና ዜና እየሠራች ነው፤ ትዊቶቿ በጣም ጠቃሚ ናቸው። Declan Walsh, the New York Times bureau chief, is doing የኒዎርክ ታይምስ ቢሮ ኀላፊ ዴክላን ዋልሽም ከመሬት ላይ ጠቃሚ ሪፖርት እያወጣ ነው።
English
Amharic
Reem Abbas, a Sudanese journalist and blogger, is sharing excellent content, much of it in Arabic.
ሪም አባስ የተባለው ሱዳናዊ ጋዜጠኛ እና ጦማሪም በአብዛኛው በአረቢኛ በርካታ ጽሑፎችን እያጋራ ነው።
English
Amharic
Al Jazeera’s synthesis of the conflict has been excellent, but I worry that their reliance on Skype interviews to cover events may limit their coverage going forward:
የአልጄዚራም የግጭት አዘጋገብ በጣም ጥሩ ነው። ነገር ግን በእስካይፕ ኢንተርቪው ላይ ብቻ ጥገኛ መሆናቸው የወደፊት ሽፋን አሰጣጣቸው ላይ እንቅፋት ይፈጥራል ብዬ እሰጋለሁ፦
English
Amharic
– In the spirit of getting people interested in what’s going on in Sudan, I recommend Hasan Minhaj’s occasionally silly but good-hearted Patriot Act episode on Sudan’s pro-democracy movement and the military government’s violent reaction.
– ሰዎች ሱዳን ውስጥ እየሆነ ያለውን ነገር ወደው እንዲከታተሉት የሐሰን ሚንጃህን – አልፎ አልፎ ቂላቂል የሆነ ነገር ግን ጥሩ ልብ ካለው የአርበኝነት ተግባር የሚመነጩ የሱዳን የዴሞክራሲ ንቅናቄ እና የመንግሥት የኀይል ምላሽ ምን እንደመሚመስል የሚያሳዩ ቪዲዮዎች መከታተሉ ይጠቅማል።
English
Amharic
– Pressure organizations that are helping legitimate the military government. That includes Facebook, which should not be hosting pages for the Rapid Support Forces, or for any entities associated with the transitional military government.
– ወታደራዊ መንግሥቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ የግፊት አድራጊ ድርጅቶች – እነ ፌስቡክን ጨምሮ ከፈጥኖ ደራሽ ኀይሉ የሚመጡ ጽሑፎችንም ይሁን ሌሎች መሰል ይዘቶች በማስተናገድ ወታደራዊ የሽግግር መንግሥቱን መርዳት የለባቸውም።
English
Amharic
Sudan’s two telecom operators — MTN and Zain — are international companies which could (in theory) be pressured to violate the military’s demands that they shut down.
የሱዳን በይነመረብ አገልግሎት አቅራቢዎች – ኤምቲኤን እና ዛይን – ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ናቸው፤ በኀልዩት ደረጃ የወታደራዊ መንግሥቱን ትዕዛዝ በግፊት ብዛት እምቢ ብለው በይነመረቡን ሊከፍቱት ይችላሉ።
English
Amharic
Zain is a Kuwaiti company, which means they are heavily influenced by Saudi Arabia, but MTN as a South African company might be susceptible to shareholder pressure, lawsuits, etc.
ዛይን የኩዌት ኩባንያ ነው። በሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሥር ሊወድቁ ይችላሉ። ነገር ግን ኤምቲኤን የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ነው። የአክሲዮን ባለቤቶቹ ግፊት ወይም የሕግ ተጠያቂነት ጉዳይ ሊያሰጋው ይችላል።
English
Amharic
The Internet Society has released a statement calling for Sudan to turn the internet back on.
ወዘተ. የኢንተርኔት ሶሳይቲ የተባለው ድርጅት ሱዳን በይነመረቡን መልሳ እንድትከፍተው ጥሪ አቅርቧል።
English
Amharic
It’s unclear whether they would be an organizing point for protests to pressure MTN.
ምናልባት ይህ ሶሳይቲ ኤምቲኤን ላይ ተፅዕኖ ለማድረስ ማደራጃ ይሁን አይሁን ግልጽ አይለደም።
English
Amharic
– It can be difficult to get money to the ground in Sudan.
– ሱዳን ውስጥ ገንዘብ ማሰባሰብ አስቸጋሪ ይሆናል።
English
Amharic
While the Trump administration removed some financial sanctions on Sudan in 2017, other sanctions stemming from the Darfur conflict remain in place.
የትራም አስተዳደር የሱዳን መንግሥት ላይ የተጣለውን የፋይናንስ እገዳ እኤአ በ2017 ቢያነሳም ሌሎች የዳርፉር ግጭትን ተከትሎ የተጣሉ ዕቀባዎች አሁንም አሉ።
English
Amharic
My friends in Sudan have pointed me to Bakri Ali and the University of Khartoum Alumni Association USA, a US 501c3 which is using their tax-exempt status to deliver aid to democracy protesters.
ሱዳን ውስጥ ያሉ ጓደኞች በክሪ አሊ እና አሜሪካ ያለው የካርቱም አልሙናዮች ማኅበር ከታክስ ነጻ የሆነ US 501c3 ዕድላቸውን በመጠቀም አገር ውስጥ ያለውን የዴሞክራሲ ንቅናቄ እየደገፉ እንደሆነ ጠቁመውኛል።
English
Amharic
It can be hard, in retrospect, to remember the excitement and enthusiasm that accompanied the Egyptian revolution and the broader Arab Spring.
በሌላ በኩል፣ የግብጽ አብዮት እና ሰፊው የዐረብ ፀደይ የፈጠሩትን ፈንጠዝያና ተስፋ ማስታወስ ከባድ ያደርገዋል።
English
Amharic
But after only a year of a democratically elected Muslim Brotherhood government, a military dictatorship took over.
የሙዝሊም ብራዘርሁድ መንግሥት በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከተመረጠ ዓመት በኋላ ወታደራዊው አምባገነን ሥልጣን ነጥቋል።
English
Amharic
The fear right now is that Sudan could go directly from one dictatorship to another — from one Arab winter to another without an intervening Spring.
አሁን የነገሠው ፍርሐት ሱዳን ከአንዱ አምባገነን ወደ ሌላው አምባገነን ልትሸጋገር ነው የሚል ወን።
English
Amharic
Some Sudanese protesters have been using the slogan “Victory or Egypt”, looking at the return to dictatorship as the worst possible outcome.
ከዐረብ ክረምት ወደ ሌላ ክረምት ፀደይ ሳታይ ትከርማለች የሚል ነው። አንዳንድ የሱዳን ተቃዋሚዎች “ሱዳን ወይም ግብጽ” የሚል መፈክር ይዘው የሱዳን ወደ አምባገነንነት መመለስ የመጨረሻ አስቀያሚው ውጤት መሆኑን አመልክተዋል።
English
Amharic
The worse outcome is even worse — it’s the prospect of systemic military violence like in Darfur, without intervention by the international community.
ከዚህም በላይ የሚከፈው ውጤት ግን ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ ሳይገባ የዳርፉሩን ዓይነት ጭፍጨፋ ሊከሰት ይችላል የሚለው ስጋት ነው።
English
Amharic
The same folks are in charge, and we are already looking away.
ያንን ጭፍጨፋ የፈፀሙት ሰዎች አሁን ኀላፊነት ተሰጥቷቸዋል። እኛ ደግሞ ፊት ነስተናቸዋል።
English
Amharic
In Ethiopia’s disinformation epidemic, the crumbling ruling coalition is the elephant in the room
በኢትዮጵያ የመረጃ-ማዛባት ወረርሽኝ ውስጥ እየፈረሰ ያለው የገዢው ግንባር ዋነኛ ተዋናይ ነው
English
Amharic
At least 80 people were killed in acts of communal violence
በቡድን ግጭት ሳቢያ ቢያንስ 80 ሰዎች ተገድለዋል
English
Amharic
This story is the second in a two-part series on online disinformation and politics in Ethiopia.
ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ የመረጃ ማዛባት ጉዳይ ከተጻፉት ሁለት ጽሑፎች ሁለተኛው ነው።
English
Amharic
You can read the first part here.
የመጀመሪያውን እዚህ ማንበብ ይችላሉ።
English
Amharic
On November 17, all except one ethnic party that comprises Ethiopia’s ruling coalition, the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front — the EPRDF —declared that they have agreed to merge.
ሕዳር 7 ቀን ከአንዱ ድርጅት በስተቀር የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ለመዋሐድ መስማማታቸውን አወጁ።
English
Amharic
Tigray People's Liberation Front, (TPLF) the most senior of the four parties, determined to reject the agreement and delay the merger, setting the stage for convulsions in the messy political transition instigated by Prime Minister Abiy Ahmed that began in April 2018.
ከአባል ድርጅቶቹ ሁሉ አንጋፋው ሕወሓት ውሕደቱን በመቃወም እንዲዘገይ በማለት መድረኩን በ2010 ሥልጣን ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ሲቆጣጠሩ ወደ ጀመረው የፖለቲካ ትርምስ ለቋል።
English
Amharic
However, the move is expected to lessen the country's ethnic divisions and violence incited by hate speech, disinformation and misinformation on social media.
ነገር ግን የውሕደቱ እርምጃ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በጥላቻ ንግግር፣ በመረጃ ማዛባት እና የተሳሳተ መረጃ መስጠት የተመሠረተውን የዘውግ ክፍፍል እና ነውጥ ለማለዘብ ይረዳል ተብሎ ይጠበቃል።
English
Amharic
The announcement comes after several universities in Ethiopia have become a focus of vicious misinformation battles among political groups following the killing, in November 2019, of two Oromo students at Woldia University, a university located in Ethiopia’s northern Amhara region:
የውሕደቱ ዜና የታወጀው በሕዳር ወር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአማራ ክልል በሚገኘው ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ሁለት የኦሮሞ ተማሪዎች በደቦ መገደላቸውን ተከትሎ የተዛባ መረጃ መሻኮቻ ሆነው ትኩረት በሳቡበት ወቅት ነበር።
English
Amharic
On November 10, 2019, it was reported that an obscure fight broke out between Oromo and Amhara students at Woldia University.
ጥቅምት 29፣ 2019 በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ኦሮሞ እና አማራ ተማሪዎች መካከል ምንነቱ ያልታወቀ ግጭት መቀስቀሱ ተነግሮ ነበር።
English
Amharic
Then, a swirl of rumors, spread by social media, had warned of attacks by one group of students against the other, and this set off widespread panic among students studying in universities located outside their home states.
ከዚያ በማኅበራዊ ሚዲያዎች አንዱ ቡድን ሌላውን ቡድን እያጠቃ ነው የሚል አሉባልታ ተሰራጨ። ይህም በተለይ ከቀያቸው ርቀው የሚማሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ።
English
Amharic
Government authorities have pleaded for calm, and Prime Minister Abiy denounced the rumor-mongering and vowed if local authorities do not enforce the law and restore calm, the government will shut down universities.
የመንግሥት ባለሥልጣናት መረጋጋት እንዲሰፍን ጠየቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው የአሉባልታ መንዛቱን ነገር አውግዘው የአካባቢው ባለሥልጣናት በፍጥነት ሕግ በማስከበር ተማሪዎቹን ካላረጋጉ ዩኒቨርሲቲዎቹን እንደሚዘጉ በዛቻ አስጠነቀቁ።
English
Amharic
The panic at the country’s several universities has not only underscored the deep roots of ethnic tensions in Ethiopia, where ethnic tensions are usually simplified as a conflict between Amhara versus Oromo, but also a symptom of a complex and deadly power struggle inside the EPRDF.
በአገሪቱ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተዛመተው ድንጋጤ በኢትዮጵያ ስር የሰደደውን የዘውግ ውጥረት ከመቀስቀሱም ባሻገር ብዙ ጊዜ በኦሮሞ እና አማራ መካከል እንዳለ ግጭት ተደርጎ የሚቃለለውን ነገር ግን ነፍስ እየቀጠፈ ያለውን የኢሕአዴግ ውስጥ ለውስጥ ውስብስብ የሥልጣን ሽኩቻ የሚያሳይ ነበር።
English
Amharic
EPRDF is the coalition of four ethnic parties. Members from these four parties: Amhara Democratic Party (ADP), Oromo Democratic Party (ODP), Southern Ethiopian People's Democratic Movement (SEPDM) and Tigrayan People's Liberation Front (TPLF), currently make up Ethiopia’s top leadership.
ኢሕአዴግ የአራት ፓርቲዎች ግንባር ነው። አባላቱም፣ አዴፓ፣ ኦዴፓ፣ ደኢሕዴን እና ሕወሓት ሲሆኑ፣ አገሪቱን የሚመሩትም እነርሱው ናቸው።
English
Amharic
Since 1991, the EPRDF has been the central actor in Ethiopian politics.
ከ1983 ወዲህ ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ማዕከላዊ ተዋናይ ነበር።
English
Amharic
However, over the last two years, it has practically disappeared as a cohesive coalition, although it continues to govern the country.
ይሁንና እስካሁን አገሪቷን እየመራ ቢሆንም ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ በተግባር እየከሰመ የመጣ ግንባር ነው።
English
Amharic
The party is entangled in a deadly and incessant power struggle, mostly along ethnic lines among its four members, supporters and members of each ethnic party are taking their fight to social media.
ፓርቲው መቋጫ በሌለው ነፍስ እስከመቅጠፍ የዘለቀ የሥልጣን ሽኩቻ ተተብትቧል። በተለይ በአራቱ የዘውግ ቡድኖች ሥም በተደራጁት ፓርቲዎች ደጋፊዎች እና አባላት መካከል የማኅበራዊ ሚዲያ ግጭት አለ።
English
Amharic
Members of the coalition, particularly, ADP, ODP and TPLF, were openly flirting with belligerent nationalist opposition groups.
የግንባሩ አባላት፣ በተለይም አዴፓ፣ ኦዴፓ እና ሕወሓት በየክልሉ ካሉ ነውጠኛ ብሔርተኛ ተቃዋሚዎች ጋር በግልጽ ሲዳሩ ነው የከረሙት።
English
Amharic
They are battling each other by leaking embarrassing stories to opposition media outlets that add fuel to the ongoing misinformation.
ለተቃዋሚ ሚዲያዎች አሳፋሪ ታሪኮችን አሳልፈው እየሰጡ የወትሮው የተዛባ መረጃ ስርጭት ላይ ነዳጅ በማርከፍከፍ እርስ በርስ እየተናከሱ ነው።
English
Amharic
The stories they leak are sometimes completely made up.
የሚያሾልኳቸው መረጃዎች አንዳንዴ ሙሉ ለሙሉ ፈጠራ ናቸው።
English
Amharic
More often, they are misleading or biased, put together to serve the purposes of these parties in their power struggle.
ከዚያም በላይ አሳሳች እና ወገንተኝነት የተጫናቸው መረጃዎች ናቸው። ዞሮ ዞሮ ተደምረው ለፓርቲ ውስጥ የሥልጣን ሽኩቻቸው አስተዋፅዖ ያደርጋሉ።
English
Amharic
For instance, in October, amid rising tension, Seyoum Teshome, a prominent social media commentator, started to publish a series of dubious screengrabs of email exchanges allegedly hacked from the email account of a top TPLF member.
በጥቅምት ወር ለምሳሌ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ታዋቂ የሆነው ስዩም ተሾመ ለማመን የሚቸግሩ የኢሜይል ቅጂዎችን ከአንድ ከፍተኛ የሕወሓት ባለሥልጣን የተቀዳ ነው በሚል መለጠፍ ጀመረ።
English
Amharic
Teshome, a strong supporter of Prime Minister Abiy, has been imprisoned two times in 2016, 2018, for unknown reasons.
ስዩም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና ደጋፊ ሲሆን በ2009 እና በ2010 ባልታወቀ ምክንያት ሁለት ጊዜ ታስሯል።
English
Amharic
The hacked emails alleged that top TPLF members were planning to incite chaos across universities in Ethiopia, in order to erode Ethiopians’ trust in Prime Minister Abiy's ability to guarantee security in the country.
የተጠለፉት ኢሜይሎች በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አመፅ በመቀስቀስ ኢትዮጵያውያን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላይ እና በአገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ላይ እምነት እንዲያጡ ለማድረግ የሕወሓት አባላት እያቀዱ ነበር ይላል።
English
Amharic
Jawar Mohammed's ‘assassination plot': A disinformation case
የጃዋር መሐመድ ‘የግድያ ሴራ'፡ የተዛባ መረጃ ጉዳይ
English
Amharic
On October 21, Jawar Mohammed, a prominent Oromo political activist and former ally to then-Prime Minister Abiy, wrote several Facebook updates in which he reported events that transpired around near the gate of his residence in Addis Ababa, Ethiopia’s capital.
ጥቅምት 21፣ ቀደም ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አጋር የነበረው እና ታዋቂው የኦሮሞ ፖለቲካ ተሟጋች ጃዋር መሐመድ የፌስቡክ ገጹ ላይ በአዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ አካባቢ ያንዣበበ ሁኔታን ገልጿል።
English
Amharic
Collectively, his posts in three different languages, Afan Oromo, Amharic and English reported a squad of federal policemen who came near his home after midnight and ordered his government-assigned protective team to pack and leave.
ጃዋር መልዕክቱን ያስተላለፈው በኦሮምኛ፣ አማርኛ እና እንግሊዝኛ ሲሆን፥ ጥቅል መልዕክቱ ከዕኩለ ሌሊት በኋላ ቤቱ የመጡ የፌዴራል ፖሊስ አባላት መንግሥት የቀጠረለትን የፀጥታ አካላት ጠቅልለው እንዲወጡ ማዘዛቸውን ነው።
English
Amharic