source
stringlengths 4
528
| target
stringlengths 3
393
| source_lang
stringclasses 1
value | target_lang
stringclasses 1
value |
---|---|---|---|
Since April 2018, the government has eased media restrictions, allowing once-banned leaders of opposition parties and activists back to Ethiopia, providing security details for them, including Mohammed. | ከሚያዝያ 2018 ጀምሮ መንግሥት ሚዲያ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ በማርገብ በፊት የታገዱ የተቃዋሚ መሪዎችን እና አክቲቪስቶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ በማድረግ ጃዋርን ጨምሮ የጥበቃ ከለላ ሲያደርግላቸው ከርሟል። | English | Amharic |
In the updates, Mohammed warned that if any of the armed men attempted to move closer, his protective team would defend themselves and if blood gets spilled, he would blame the government. | የጃዋር መሐመድ የፌስቡክ ጽሑፍ. ስክሪንሾቱ የተወሰደው ጥቅምት 15, 2012 ነው። ጃዋር መሐመድ በዚህ ጽሑፉ ታጣቂዎቹ ለመጠጋት ከሞከሩ ጠባቂዎቹ ራሳቸውን እንደሚከላከሉ እና ደም ከፈሰሰ መንግሥትን ተጠያቂ እንደሚያደርግ ገልጿል። | English | Amharic |
In the hours after his updates, amid concern and anticipation from both supporters and detractors, Mohammed appeared on a Facebook live stream broadcast by the Oromia Media Network (OMN) TV station, which he co-founded and currently serves as executive director. | ይህንን ጽሑፍ በጻፈ ጥቂት ሰዓታት ውስጥ፣ ጃዋር በደጋፊዎቹ እና ተቃዋሚዎቹ ሲጠበቅ እንደነበረው ሁሉ፣ ራሱ ባቋቋመው እና ዋና ዳይሬክተር ሆኖ በሚመራው ኦኤምኤን ቴሌቪዥን እና ፌስቡክ ላይቭ ቀርቦ ንግግር አድርጓል። | English | Amharic |
During the stream, he escalated his clash with government authorities and accused them of a plot to get him killed. | በቪዲዮ መልዕክቱ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ያለውን ግጭት በማካበድ የግድያ ሴራ ነው በማለት ወቀሳ አቅርቧል። | English | Amharic |
But government authorities, including Prime Minister Abiy Ahmed, denied Mohammed’s allegation, saying if they wanted him to get killed, they would not have provided him with security in the first place. | ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የመንግሥት ባለሥልጣናት ግን ወቀሳውን በመካድ ሊገድሉት ቢፈልጉ መጀመሪያውንም የደኅንነት ጥበቃ እንደማያቆሙለት ተናግረዋል። | English | Amharic |
His allegations sparked off a chain of reactions that started with supporters gathering in front of his residence in Addis Ababa. | የጃዋር ውንጀላ የግብረ ምላሽ ክስተቶችን አከታትሎ በመጫሩ ደጋፊዎቹ አዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ደጃፍ ተሰባስበው ነበር። | English | Amharic |
There were street protests in parts of Oromia, Ethiopia’s largest region, which in turn triggered violence at rallies, followed by what news media described as “communal violence” in the region. | የአደባባይ ተቃውሞዎችም በተለያዩ ኦሮሚያ አካባቢዎች ተቀስቅሰዋል። ተቃውሞዎቹ አመፅ በማስከተላቸው ሚዲያዎች “የቡድን ግጭት” ያሉትን አስከትሏል። | English | Amharic |
Vocal minority groups who accuse the Oromia administration of discriminatory practice also held protests in Adama Nazeret, a city located in eastern Oromia; episodes of sporadic violence led to deaths among both minority groups. | የኦሮሚያ አስተዳደርን በአግላይነት የሚወቅሱት በአዳማ ያሉ ነዋሪዎች ተቃውሞ በማድረግ ተቃውሞው ነውጥ በማስከተል ለነፍስ መጥፋት መንሥኤ ሆኗል። | English | Amharic |
In one of the deadliest episodes of Ethiopia’s numerous violence cycles, at least 86 people were killed, and several injured between October 21-23, 2019, in Oromia. | ከጥቅምት 11 እስከ 13፣ በዚህ ብዙ ነፍስ ከቀጠፉ ነውጦች መካከል አንዱ በሆነው የነውጥ አዙሪት ሳቢያ ቢያንስ 86 ሰዎች በኦሮሚያ የተገደሉ ሲሆን፣ ብዙዎችም ቆስለዋል። | English | Amharic |
The post-violence social media circulation of images and videos shows Ethiopians have inflicted extreme violence and atrocities upon their fellow citizens that led to widespread fear and communal tension. | ከነውጡ በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲዞሩ የነበሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት፣ ኢትዮጵያውያን በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ፅንፍ የረገጠ ነውጥ እና ጭካኔን ማድረጋቸው ፍርሐት እና የቡድን ውጥረት አንሰራፍቷል። | English | Amharic |
As violence subsided in the region, a new battle began online over interpretations and the assignation of blame. | ነውጡ በክልሉ ሲበረታ፣ ኢንተርኔት ላይ ደግሞ ትንታኔው እና ጥፋተኛውን የመበየን ግብግቡ ተጧጡፏል። | English | Amharic |
The heightened polarization along ethnic lines filled Ethiopian social media with starkly different interpretations of the violence: “Ethnic cleansing” and “genocide” terms were used by Amhara nationalists, Ethiopian nationalists and Ethiopian Orthodox Tewahedo followers, while Oromo and Sidama nationalists used phrases like “government-prompted violence.” | በዘውግ የተካረረው የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሚድያ ለነውጡ የተለያዩ ቅፅል ሥሞችን ሰጥተውታል። የአማራ ብሔርተኞች፣ የኢትዮጵያ ብሔርተኞች እና የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች “የዘውግ ማፅዳት” እና “ጭፍጨፋ” እያሉ ሲገልጹት፣ የኦሮሞ እና ሲዳማ ብሔርተኞች ደግሞ “መንግሥት መር ነውጥ” ነው ብለውታል። | English | Amharic |
These interpretations strained relations between mostly Amhara and Oromo elites that led to mutual name-calling fraught with disinformation and misinformation. | እነዚህ ትርጓሜዎች በተለይ በአማራ እና ኦሮሞ ልኂቃን መካከል በተዛባ እና በተሳሳተ መረጃ ሥም መለጣጠፎች አስከትሏል። | English | Amharic |
Mohammed’s critics were unsparing in assessing blame as they spread stories, images and memes on Facebook, Twitter and YouTube that pinned responsibility on him. | ጃዋርን በተጠያቂነት የሚፈርጁት ተቃዋሚዎቹ ጽሑፎችን፣ ምስሎችን እና ቀልዶችን በፌስቡክ፣ ትዊተር እና ዩቱዩብ በማሰራጨት ጃዋርን ተጠያቂ ሲያደርጉ ለነገ አይሉም። | English | Amharic |
For them, he caused the violence by falsely alleging an assassination plot and deliberately stirring up nationalist sentiment. | ለእነርሱ፣ ጃዋር የግድያ ሙከራ እንደተደረገበት በሐሰት በማስመሰል እና ብሔርተኛ ስሜትን ሆነ ብሎ በመቀስስ ነውጡን አስከትሏልተለ። | English | Amharic |
Also, one of the hacked emails Seyoum Teshome published on October 25, 2019, claims that Mohammed and the TPLF were covertly working to incite violence in Oromia with the purpose of preventing the EPRDF merger. | በተጨማሪም፣ አንዱ በስዩም ተሾመ ጥቅምት 15 የተለጠፈው እና ከተጠለፈ ኢሜይል ተገኘ ነው የተባለው መረጃ ጃዋር መሐመድ የኢሕአዴግን ውሕደት በመቃወም ከሐወሓት አባላት ጋር በኦሮሚያ አመፅ ለመቀስስ አብሮ እንደሠራ ያወራል። | English | Amharic |
Opponents characterized the violent incident as a massacre caused because of Mohammed's Facebook posts, a narrative that has gained widespread traction on Ethiopian Twitter under a hashtag “#October2019massacre.” They called for a tough response from Prime Minister Abiy (an Oromo), whom they routinely accuse of either being too soft on Mohammed or secretly working with him. | ነውጡ እና እልቂቱ የተከሰተው በጃዋር መሐመድ የፌስቡክ ጽሑፎች ሳቢያ ነው የሚሉት ተቃዋሚዎቹ፥ ትዊተር ላይ “#October2019massacre” በሚል ሐሽታግ መልዕክቶቻቸውን አስተጋብተዋል። ብዙ ጊዜ ለጃዋር በመራራት ወይም ደግሞ በምሥጢር አብረውት በመሥራት ከሚከወቅሷቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም ቁርጥ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል። | English | Amharic |
Most Oromo advocates and politicians who showed solidarity with Mohammed said Oromos were waiting for the opportunity to protest, with his murder plot allegation as the last straw. | የጃዋር ደጋፊዎች ደግሞ በበኩላቸው የኦሮሚያ ተቃውሞዎችን ጃዋርን ከግድያ ያተረፈ ድል አድርገው ሲያቀርቡ ሰልፈኞቹንም እንደጀግና ቆጥረዋቸዋል። እነርሱም በበኩላቸው ተጠያቂነቱን አማራ ብሔርተኞች እና ሌሎች የተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ ለጥፈዋል። | English | Amharic |
In one widely shared protest video on Facebook, protesters were heard hurling insults at Abiy, calling him “Habesha”, a term popularly used to refer to Ethiopians as a whole, but Oromo nationalists use it to accuse an Oromo person who is yielding to non-Oromo interests. | በከፍተኛ ሁኔታ ከተሰራጩት የቪዲዮ መልዕክቶች በአንዱ ተቃዋሚዎች ዐቢይን “ሐበሻ” እያሉ ሲጠሯቸው ተስተውሏል። ሐበሻ የሚለን ቃል ኢትዮጵያውያንን ለመለየት የሚጠቅም ቢሆንም የኦሮሞ ብሔርተኞች ግን የኦሮሞን ጥቅም ኦሮሞ ላልሆኑ አሳልፎ የሚሰጥን ሰው ለመጥራት ይጠቀሙበታል። | English | Amharic |
Mohammed is something of a protest guru, a media executive and political strategist in his community. | ጃዋር በደጋፊው ማኅበረሰብ ውስጥ የተቃውሞ መሪ፣ የሚዲያ ኀላፊ እና የፖለቲካ ስልት ቀያሽ ተደርጎ ነው የሚታየው። | English | Amharic |
With nearly 1.8 million followers on Facebook, he used his page to guide street protest, raise money and solicit information from groups inside EPRDF that helped to bring down the once-dominant TPLF, which for years had blocked social media and arrested and tortured bloggers. | ፌስቡክ ላይ ባሉት 1.8 ሚሊየን ተከታዮች አማካይነት የጎዳና ላይ ተቃውሞዎችን መርቷል፣ ገንዘብ አሰባስቧል፣ በአንድ ወቅት በኢሕአዴግ የበላይ የነበረውን እና ማኅበራዊ ሚዲያን ከመዝጋቱም ባሻገር ብሎገሮችን አስሮ ያሰቃየውን ሕወሓት ለመጣል ከውስጥ ሰዎች መረጃ አሰባስቦበታል። | English | Amharic |
Even then, EPRDF was able to actively use social media to mobilize support, spread disinformation and attack opponents, including Mohammed. In fact, the true precursor for the current dizzying disinformation swirling Ethiopian social media began back in 2014. | ያኔም ቢሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ጃዋርን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚዎችን በተዛባ መረጃ ለማጥቃት እና ድጋፍ ለማሰባሰብ ማኅበራዊ ሚዲያን ተጠቅሟል። በርግጥ በማኅበራዊ ሚዲያ ለአሁኑ የመረጃ መዛባት ባሕል መሠረት የተጣለው በ2014 ነበር። | English | Amharic |
For several years, paid online commentators tied to the EPRDF had posted comments that favored party policies and attacked opponents. | ለበርካታ ዓመታት፣ ተከፋይ የኢንተርኔት አስተያየት ሰጪዎች ገዢው ፓርቲንና ፖሊሲዎቹን የሚደግፉ እና ተቃዋሚዎችን የሚያጠቁ ጽሑፎችን ሲያበረክቱ ነበር። | English | Amharic |
The commentators were known as cocas, an Amharic expression roughly translated into English as “contemptible cadres.” | እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች ‘ኮተታም ካድሬ’ ወይም ሲጨመቅ ‘ኮካ’ የሚል ቅፅል ሥም ተሰጥቷቸው ነበር። | English | Amharic |
The cocas apparently were hired by members of the EPRDF coalition in an attempt to manipulate public opinion. | ኮካዎች በኢሕአዴግ ግንባር አባላት ሕዝባዊ አስተያየትን ለመከርከም የተቀጠሩ ናቸው። | English | Amharic |
The cocas used to unite easily around stories and memes generated by the EPRDF. For example, when Tedros Adahanom, a member of TPLF, ran for an election to lead the World Health Organization (WHO) as Director-General in 2017, he mobilized thousands of supporters on Facebook and created the impression that he has widespread support. | ኮካዎች በኢሕአዴግ በተዘጋጁ ጽሑፎች እና ቀልዶች ዙሪያ በቀላሉ ይተባበሩ ነበር። ለምሳሌ ያክል የሕወሓት አባሉ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር-ጄነራል ለመሆን ሲወዳደሩ ትልቅ ድጋፍ ያላቸው ለማስመሰል ፌስቡክ ላይ ያሉ ኮካዎችን አሰማርተዋል። | English | Amharic |
Likewise, Mohammed has exploited the seismic changes unfolding inside the EPRDF. On his Facebook page, he often posts and provides a punditry analysis on OMN’s Facebook live streaming service, pitching himself as a person who receives top secrets from the EPRDF. | በተመሳሳይ፣ ጃዋር ኢሕአዴግ ውስጥ ተገልጦ ያላለቀውን መሬት አንቀጥቅጥ ለውጥ እየተጠቀመበት ነው። በራሱ እና የኦኤምኤን ፌስቡክ ገጽ፣ ከኢሕአዴግ ውስጥ ጥብቅ ምሥጢሮች እንደሚደርሱት በማቅረብ ጥንታኔ ያቀርባል። | English | Amharic |
He posts with no particular schedule, sometimes several times in a day, some days not at all. His posts provide information about what he often calls the collective interest, grievances and alleged threats of the Oromo people. | ጽሑፎቹን የሚያቀርበው ያለምንም ጊዜ ዕቅድ ነው። አንዳንዴ በቀን በርካታ መረጃዎችን ይለቃል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ምንም ሳይል ያልፋል። መረጃዎቹ የኦሮሞ ሕዝብን ፍላጎት፣ ብሶት እና ስጋት የሚያንፀባርቁ ናቸው ብሎ ያምናል። | English | Amharic |
OMN’s Facebook page, with 1 million followers, is one of the fastest-growing pages among Ethiopia’s media organizations. | የኦኤምኤን ፌስቡክ ገጽ አንድ ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት ሲሆን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት በርካታ ተከታዮችን እያፈራ ካሉ ገጾች መካከል አንዱ ነው። | English | Amharic |
Mohammed ranks first among Ethiopian political figures in a number of followers of his verified Facebook page of 1.8 million followers. No other Ethiopian public figure who has some political sway is even close. | ጃዋር የእርሱ መሆኑ በተረጋገጠው እና 1.8 ሚሊዮን ተከታዮች ባለው ፌስቡክ ገጹ የትኛውም ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሰው አይፎካከረውም። | English | Amharic |
How identity-driven conflicts fuel Ethiopia's incendiary social media rhetoric | ማንነትን መነሻ ያደረጉ ግጭቶች የኢትዮጵያን የማህበራዊ ሚዲያ የሐሳብ ልዉዉጥ እንዴት ሊያጋግሉ እንደሚችል | English | Amharic |
An army of social media personalities stoke inflammatory content | የሚያጋጭ ይዘትን የሚቆሰቁስ የማህበራዊ ሚዲያ ግለሰቦች ሰራዊት | English | Amharic |
Heads of states from several eastern African countries gathered in October 2019 in Ethiopia’s capital, Addis Ababa, to celebrate the grand opening of Unity Park, an urban park located within the imperial palace. | ከተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ መሪዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ቤተ-መንግስት ውስጥ የተሰራውን የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነ-ስርዓት ለማክበር በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም የሀገሪቷ ዋና ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ ተገኝተው ነበር። | English | Amharic |
The park — the personal initiative of Ethiopia’s reformist Prime Minister Abiy Ahmed — contains Ethiopia’s historical, ethnic and culture galleries. | ይህ ፓርክ የለውጡ መሪ በሆኑት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አሕመድ የግል ተነሳሽነት የተገነባ ሲሆን የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ብሔር ብሔረሰብ እና ባህልን የሚያሳዩ ማዕከለ-ስዕላትን(galleries) አካቶ ይዟል። | English | Amharic |
It also maintains a display of a colossal wax statue of Ethiopia’s past rulers including Emperor Menelik II and Emperor Haile Selassie — two monarchs whose combined reigns lasted about 70 years. | በተጨማሪም የኢትዮጵያ ቀደምት ነገሥታት ከሆኑት፣ በድምሩ ለ70 ዓመታት በንግስና የቆዩትን የዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ እና አፄ ኃይለስላሴን ባለቀለም የሰም ሀውልት ይዟል። | English | Amharic |
The park aims to tell the story of all Ethiopians and celebrate the country’s diverse ethnicities, religions, cultures, historical figures, and endemic plants and animals. | ይህ ፓርክ የሁሉም ኢትዮጵያኖችን ታሪክ ለማንፀባረቅ እንዲሁም የሀገሪቱን የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ሀይማኖቶች፣ባህሎች፣ታሪካዊ ቅርሶች እና ብርቅዬ እፅዋትና እንስሳትን ለማክበርና ለመዘከር ታልሞ የተዘጋጀ ነው። | English | Amharic |
But a quick scroll through the news about the park’s opening on social media revealed politicized, nationalistic reactions with two mutually exclusive narratives that fell largely along ethnic lines of the two major ethnolinguistic groups: Amhara and Oromo. | ነገር ግን በማህበራዊ ሚዲያ የቀረቡ ዘገባዎች ምልከታ እንደሚያሳየው የፓርኩን መመረቅ ተከትሎ ፖለቲካና ዘር ተኮር የሆኑ አፀፋዎች፣ በተለይም በሁለቱ ታላላቅ የአማራና ኦሮሞ ብሔሮች መካከል በጎሳ መስመሮች ላይ ያረፉ እርስ በእርስ የሚደረጉ ትርክቶች ተስተናግደው ነበር። | English | Amharic |
At the core of this divide is two mirror-opposite reactions to the unveiling of the monuments that depict two emperors sitting on their thrones — adorned with imperial regalia: They represent entrenched fault lines in Ethiopian politics. | በዚህ ክፍፍል በዋነኝነት ሁለቱ ቀደምት መሪዎች በነገስታት አልባሳት አጌጠውና በዙፋናቸው ተቀምጠው የሚያሳዩትን ሀውልቶች አስመልክቶ ሁለት ፅንፍ የያዙ ግብረ-መልሶች ይገኛሉ ። እነዚህም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሥር የሰደዱ የስህተት መስመሮችን የሚወክሉ ናቸው፡፡ | English | Amharic |
Wax Statue of Haile Selassie. | የአፄ ኃይለ ስላሴ የሰም ሀውልት | English | Amharic |
Photo courtesy of Edom Kassaye. | ፎቶ፡ በኤዶም ካሳዬ | English | Amharic |
Amhara nationalists were largely pleased even though some slammed it, describing it as Abiy’s vanity project — Abiy himself identifies as Oromo. | አብዛኛው የአማራ ብሔርተኞች በፕሮጀክቱ ደስተኞች ቢሆኑም ጥቂቶች ግን አብይ ራሱን እንደ ኦሮሞ ስለሚለይ ‘የአብይ ከንቱ ፕሮጀክት’ ሲሉ አጣጥለውታል። | English | Amharic |
Meanwhile, several Oromo politicians and campaigners were furious — particularly, prominent opposition politician Jawar Mohammed, who was irked. | ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና ተሟጋቾች ቁጣቸውን አሰምተው የነበረ ሲሆን በተለይም በሁኔታው ተበሳጭቶ የነበረው ታዋቂው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ ተጠቃሽ ነው። | English | Amharic |
Jawar said that building wax statues for Emperor Menelik II and Emperor Haile Selassie is an affront to Oromos and to all other ethnic groups crushed by the emperors. | አቶ ጃዋር ለዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ እና አፄ ኃይለስላሴ ሀውልት ማሰራት ማለት በአፄዎቹ ስርዓት ስር ለተጨቆኑ ኦሮሞዎችና ሌሎች ብሔሮች ስደብ ነው ሲል ተናግሯል። | English | Amharic |
Emperor Menelik II is widely regarded as the first modern Ethiopian monarch who transformed the Ethiopian State. | ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ሀገሪቷን በለውጥ ጎዳና ያስኬዱ የመጀመሪያው ዘመናዊ የኢትዮጵያ ንጉስ ተደርገው በሰፊው ይወሰዳሉ። | English | Amharic |
He is venerated as a symbol of freedom and forgiveness; he is also blamed for kicking people in southern Ethiopia off their land and privileging Amharic language and Christianity. | እሳቸውም የነፃነት እና የይቅርታ ምልክት ተደርገውም ክብር የሚሰጣቸው ቢሆንም በሌላ በኩል የደቡብ ክልል ነዋሪዎችን ከመሬታቸው በማፈናቀል አማርኛ ቋንቋና ክርስትናን የታደለ ልዩ መብት ሰጥተዋል ተብለውም ይወቀሳሉ። | English | Amharic |
The next day, Jawar along with Lencho Leta, a veteran politician and a founding member of Oromo Liberation Front (OLF) led a pilgrimage to the east-central district of Hetosa of Oromia, Ethiopia’s largest region, to visit the Anole Martyrs memorial monument, the historical site that signifies an enduring grievance of Oromo nationalists over what they call Emperor Menelik’s II brutal killings, cultural marginalization and loss of their ancestral land in the late 19th century. | በቀጣዩ ቀን አቶ ጃዋር የፖለቲካ አርበኛና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መስራች አባል ከሆኑት ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር በመሆን የአኖሌ የሰማዕታትን የመታሰቢያ ሀውልት ለመጎብኘት ስፋት ባላት ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ወደምትገኘው ማዕከላዊ ምስራቅ ሄጦሣ አውራጃ ተጉዘው ነበር። ይህ ስፍራ በ19ኛው ክ/ዘመን መገባደጃ የኦሮሞ ህዝብ በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ የደረሰባቸውን ለብዙ ጊዜ የቆየ የጭካኔ ግድያዎች፣ የባህል መገለል፣ የአባቶቻቸውን መሬት ማጣትና በደል የሚያመለክት ታሪካዊ ቦታ ነው። | English | Amharic |
Weeks later in a television interview, Jawar said: | ከሳምንታት በኋላ ጃዋር በቴሌቪዥን በሰጠው ቃለ መጠይቅ እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር። | English | Amharic |
This was not a one-off case. | ይህ የአንድ ጊዜ ጉዳይ አልነበረም። | English | Amharic |
After Abiy lifted the oppressive lid off the nation in April 2018 — ending 27 years of dictatorship — controversies about cultural events, flags, political rallies, monuments and the significance of past rulers began to take up the bulk of Ethiopia’s social media conversations — which were often laced with inflammatory language. | ዶ/ር አብይ በመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም ወደስልጣን መጥተው የ27 ዓመታትን የጭቆና ቀንበር ካስወገዱ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ግጭት በለበሱ ቋንቋዎች ስለተለያዩ ጉዳዮች ማለትም ታሪካዊ ክስተቶችን፣ ባንዲራን፣ ፖለቲካዊ ተቃውሞን፣ ታሪካዊ ሀውልቶችን እና ስለ ቀደምት መሪዎች የተነሱት አርዕስቶች ሰፊውን ቦታ መያዝ ጀምረው ነበር። | English | Amharic |
It is a recurring pattern. | ይህም ተደጋጋሚ ሂደት ነው። | English | Amharic |
Briefly, it runs like this: A government official, opposition leader, journalist or prominent celebrity opines about a historical figure’s significance, let’s say, | በአጭሩ የሚሆነው አንዲህ ነው፤ አንድ የመንግስት ባለስልጣን፣ የተቃዋሚ መሪ፣ ጋዜጠኛ ወይም ዝነኛ ግለሰብ አንድን በታሪክ ታዋቂ የሆነን ሰው አስመልክቶ አስተያየት ይሰጣል። | English | Amharic |
Emperor Menelik II, on one of the popular social media platforms. Within minutes, social media platforms are swarmed by hundreds of supportive or scathing responses. | ለምሳሌ በአንድ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ ስለ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ቢጻፍ በደቂቃዎች ውስጥ ማህበራዊ ሚዲያው በመቶዎች በሚቆጠሩ የድጋፍና የተቃውሞ ምላሾች ይሞላል። | English | Amharic |
These culturally-charged exchanges reinforce an atmosphere of resentment across numerous online spaces among different Ethiopian ethnic groups — or more accurately, their elites. | እነዚህ ባህልን መሰረት ያደረጉ እሰጥ-አገባዎች በማህበራዊ ሚዲያ በተለያዩ ብሔሮች በተለይም በምሁሮቻቸው መካከል ቂም የተሞላ ድባብ እንዲጠነክር ያደርጋሉ። | English | Amharic |
These jabs entrench the feeling that one’s ethnic group is threatened with extinction as the object of another’s aggression. | እነዚህ ጥቃቶች አንዱ የብሔር ቡድን በሌላው ፀብ ምክንያት ለመጥፋት አደጋ ተጋልጧል የሚል ስሜት ስር አንዲሰድ ይዳርጋሉ። | English | Amharic |
Multiple TV stations that sprouted after April 2018 as a major part of Ethiopia’s fast-changing media landscape have tended to echo and amplify this division — with fatal consequences. | ከመጋቢት 2018 ዓ.ም በኋላ በሀገሪቱ በፍጥነት እየተለወጠ የመጣው የሚዲያ ስነ-ምህዳር ውጤት አንድ አካል የሆኑትና በስፋት ወደ ህዝብ የመጡት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ይህንን ክፍፍል ሲያስተጋቡና ሲያጋግሉ፣ ክፉ መዘዞችንም አስከትለዋል። | English | Amharic |
For example, communal violence rocked Oromia after Jawar wrote on his Facebook page alleging that government authorities had plotted to assassinate him in October 2019. | ለምሳሌ አቶ ጃዋር ጥቅምት 2019 ዓ.ም ላይ የመንግስት ሀላፊዎች የግድያ ሙከራ ሊያደርጉበት እንዳሴሩ በፌስቡክ ገፁ ላይ መግለፁን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የጋራ ጥቃት ተቀስቅሶ ነበር። | English | Amharic |
The regional coup plot in the Amhara region in June 2019 can also nominally be connected to ultra-nationalist social media narratives. | በሰኔ 2019 ዓ.ም በአማራ ክልል የተደረገው የመፈንቅለ-መንግስት ሴራ ከፅንፈኞች የማህበራዊ ሚዲያ ትርክት ጋር በመደበኛነት የተገናኘ ሊሆን ይችላል። | English | Amharic |
In many cases, an army of Facebook and YouTube personalities, government supporters, opposition figures, political parties and diaspora journalists often participate in or seed inflammatory information into an already complex, confusing and heightened social media ecosystem — often as a way of gaining support for their causes. | የፌስቡክ እና ዩቲውብ ተጠቃሚ ግለሰቦች፣ የመንግስት ደጋፊዎች፣ ተቃዋሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የዲያስፖራ ጋዜጠኞች በብዙ ጉዳዮች ላይ ከጅማሬውም በተወሳሰበው፣ ግራ በሚያጋባው እና በተጋጋለው የማህበራዊ ሚዲያ ድባብ ላይ ፀብ አቀጣጣይ መረጃዎችን በመዝራት በተደጋጋሚ ይሳተፋሉ። ይህንንም በአብዛኛው ለራሳቸው ዓላማ ድጋፍ የማግኛ መንገድ አድርገው ይጠቀሙበታል። | English | Amharic |
How two opposition figures stoke support | ሁለት የተቃዋሚ መሪዎች ድጋፍን እንዴት ሊቆሰቁሱ እንደሚችሉ | English | Amharic |
Two opposition figures, Jawar Mohammed, member of Oromo Federalist Congress and Eskinder Nega, a former political prisoner and a chair of a recently formed political party, Balderas for Genuine Democracy, are spokesmen who stand out for the way they use social media to garner support. | ሁለቱ የተቃዋሚ መሪዎች ማለትም የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ) አባል የሆነው አቶ ጃዋር መሐመድ እና የቀድሞ የፖለቲካ እስረኛ እና በቅርብ የተቋቋመው የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፖለቲካ ፓርቲ ሊቀ-መንበር የሆነው አቶ እስክንድር ነጋ የበለጠ ድጋፍን ለማግኘት ማህበራዊ ሚዲያን የሚጠቀሙበት መንገድ ጎልተው እንዲወጡ ያደርጋቸዋል። | English | Amharic |
Jawar, with nearly 1.9 million Facebook followers — often enthusiastic supporters — positions himself as a defender of Oromo interests. | አቶ ጃዋር ወደ 1.9 ሚሊዮን የሚጠጉ የፌስቡክ ተከታዮች ያሉት ሲሆን አብዛኛዎቹም ጉጉ ወይም ቀናተኛ ደጋፊዎች ናቸው። እሱም ራሱን የኦሮሞ ጥቅም ተሟጋች አድርጎ ያስቀምጣል። | English | Amharic |
With a massive following, he commands symbolic importance to the Oromo youth movement known as Qeerroo and is generally portrayed as their leader. | ብዙ ተከታዮቹ የሆኑት ቄሮ የተሰኙት የኦሮሞ ወጣቶች እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስፈላጊነት እንዳላቸው በጥብቅ ይናገራል ። በአጠቃላይም እንደ መሪያቸው ይገለፃል። | English | Amharic |
Eskinder, on the other hand, has become increasingly reliant on Twitter as a means of bolstering support. | በሌላ በኩል እስክንድር ትዊተርን በይበልጥ ድጋፉን የማሳደጊያ መንገድ አድርጎ ይጠቀምበታል። | English | Amharic |
Although Eskinder was late to join Twitter, he developed a sizable following and his comments often provoke furious reactions from detractors. | ምንም እንኳን ትዊተርን ዘግይቶ ቢቀላቀልም ብዙ ተከታዮችን በሚገባ ማፍራት ችሏል። የሚሰጣቸው (ላልቶ ይነበብ) አስተያየቶችም ብዙ ጊዜ ከተቃዋሚዎች ቁጣና ንዴት ያዘሉ አፀፋዎችን ሲያስከትሉ ይስተዋላል። | English | Amharic |
His embrace of the platform is seen as a political imperative as mobile devices and mobile connectivity have become more widespread. | የተንቀሳቃሽ ስልኮችና የተንቀሳቃሽ ስልክ ትስስር እየጨመረ በመጣበት በዚህ ጊዜ ይህንን መድረክ መቀበሉ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው ተደርጎ ይወሰዳል። | English | Amharic |
Eskinder routinely uses his Twitter handle to accuse Qeerroo members of committing genocide against religious and ethnic minorities in Oromia. | የትዊተር ገፁን በመደበኛነት የቄሮ አባላት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ አናሳ የሀይማኖት እና የብሔር ቡድኖች ላይ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ለመወንጀል ይጠቀምበታል። | English | Amharic |
His framing of Qeerroo resonates with thousands of Twitter accounts that represent Amhara nationalists and Ethiopian Orthodox Tewahedo Church followers. | ይህ ለቄሮ ያለው ምልከታ በሺዎች በሚቆጠሩ የአማራ ብሄርተኞች አና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ በሆኑ ግለሰቦች የትዊተር አካውንት መልሶ ይስተጋባል። | English | Amharic |
Although Jawar and Eskinder dominate two different platforms — Facebook and Twitter — their negative chemistry is equally apparent. | ምንም እንኳን ጃዋር እና እስክንድር ሁለት የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች (platforms) ማለትም ፌስቡክና ትዊተርን ቢቆጣጠሩም አሉታዊ የሆነ ‘ኬሚስትሪያቸው’ ግን እኩል ግልጽ ሆኖ የሚያይ ነው። | English | Amharic |
Both manage to articulate sharply opposing views on issues like Ethiopian federal structure, the legal status of Ethiopia’s capital Addis Ababa, an enclaved multi-ethnic city within the border of Oromia, the history of Emperor Menelik II and the Ethiopian constitution. | ሁለቱም በከፍተኛ ሁኔታ የሚቃረኑ ዕይታዎችን ያንፀባርቃሉ። ለምሳሌ፤ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መዋቅርን፣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማና የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ እንዲሁም በኦሮሚያ ድንበር ውስጥ የምትገኘው የአዲስ አበባ ከተማን ህጋዊ ሁኔታ፣ የዳግማዊ አፄ ሚኒሊክን ታሪክ እና የኢትዮጵያ ህገ-መንግስትን አስመልክቶ ያሉ ጉዳዮች ላይ የሚቃረኑ አቋሞችን ይገልፃሉ። | English | Amharic |
They aim to strengthen their already solid connections with their followers on social media. | እነዚህ ግለሰቦች ከደጋፊዎቻቸው ጋር ያላቸውን የቀደመ ጠንካራ ግንኙነት በማህበራዊ ሚዲያው በኩል ይበልጡን ማጠንከር ይፈልጋሉ። | English | Amharic |
The reactions, comments, retweets and shares on Facebook and Twitter are higher than any other opposition figures. | በፌስቡክና ትዊተር የሚያገኙት ምላሾች ፣ አስተያየቶች እና ማጋራቶች(retweets and shares) ከሌሎች ተቃዋሚዎች በእጅጉ የሚልቅ ነው። | English | Amharic |
And for all the differences between Eskinder and Jawar, they both do their fair share of injecting misleading information into Ethiopia's information ecosystem. | እናም በመካከላቸው ላሉት ልዩነቶች ሁሉ አሳሳች መረጃዎችን በሀገሪቱ የመረጃ ስነ-ምህዳር ውስጥ በማሰራጨት የየራሳቸው ድርሻ ይጫወታሉ። | English | Amharic |
Often, Eskinder spins and overblows Ethiopian exceptionalism, destruction of historical sites and emphasizes atrocities committed in the Oromia region. | አቶ እሰክንድር ብዙ ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ ልዩነቶች፣ የታሪካዊ ስፈራዎችን ውድመት እና በተለይም በኦሮሚያ ክልል ስለተፈፀሙ የጥፋት ጉዳዮችን በማጋነን ሌላ መልክ በመስጠት አዙሮ ያስቀምጣል። | English | Amharic |
For instance, in the following tweet, Eskinder wrote approvingly that Amharic was selected to be included among the working languages of the African Union. But Amharic was never selected: | ለምሳሌ ከዚህ በታች በሚታየው ትዊት፣ እስክንድር አማርኛ ቋንቋ ከአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋ መካከል አንዱ ሆኖ መመረጡን ቢያሰፍርም አማርኛ ቋንቋ ግን የስራ ቋንቋ ሆኖ በጭራሽ ተመርጦ አያውቅም። | English | Amharic |
Since September 2018, the two have been locked in a long-running battle that played out most recently in November 2019 in the United States, when both toured to raise funds from members of Ethiopian diaspora groups for their political projects in Ethiopia. | ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሁለቱም ተቃዋሚዎች በረዥም የትግል ጎዞ ውስጥ የቆዩ ሲሆን በተለይም በቅርቡ በሕዳር 2019 ዓ.ም ሁለቱም በኢትዮጵያ ላሏቸው የፖለቲካ ፕሮጀክቶች ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት ገንዘብ ለማሰባሰብ ወደ አሜሪካ ጉዞ ማድረጋቸው ያላቸውን ፉክክር አሳይቷል። | English | Amharic |
No moment better captured the rivalry and the ideological contestation between the two men than their tour in the United States as their supporters played a game of cat-and-mouse throughout their tours. | በአሜሪካ በነበራቸው ጉዞ ወቅት በደጋፊዎቻቸው መካከል የነበረው የአይጥና ድመት ጨዋታ በሁለቱ ተቃራኒ ወገኖች መካከል ያለውን ውጥረት በሚገባ ያሳየ አጋጣሚ ነው። | English | Amharic |
Jawar’s tour had come on the heels of several tumultuous days in which communal violence spread across Oromia, which led to the death of 86 people after his allegation on Facebook sparked off a chain of reactions that started with his supporters gathering in front of his residence in Addis Ababa. | የአቶ ጃዋር ጉብኝት በርካታ የሁከት ቀናቶች የተስተናገዱበት ነበር። በፌስቡክ ገፁ ላይ ያቀረበው ውንጀላ በደጋፊዎቹ ዘንድ የጫረው በርካታ ስሜቶች በአዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በር ላይ እንዲሰበሰቡ በማድረግ የጀመረ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል የጋራ አመፅ በመስፋፋቱ ምክንያት የ86 ሰዎች ህይወት እንዲያልፍም ምክንያት ሆኖ ነበር። | English | Amharic |
His detractors say his Facebook post caused the death of 86 people — and Eskinder, in particular, pinned the responsibility on him. | ተቃዋሚዎቹ ለ86 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የእርሱ የፌስቡክ ልጥፍ(post) ነው ይላሉ። አቶ እስክንድርም በተለየ ሁኔታ ሀላፊነቱን ወደ አቶ ጃዋር ጠቁሟል። | English | Amharic |
Jawar denied that his posts had anything to do with the violence, claiming instead that his actions actually prevented worse violence. | ይሁን እንጂ አቶ ጃዋር የእሱ ፌስቡክ ልጥፍ(post) ከተነሳው ግጭት ጋር የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ አስተባብሎ ይልቁንም የሱ ተግባር የከፋ ግጭት እንዳይፈጠር እንዳደረገ ይናገራል። | English | Amharic |
As he traveled across the United States, his supporters showed solidarity, coordinating town hall meetings and raising funds in various US cities with sizable Oromo populations. | በመላው አሜሪካ ጉዞ ባደረገበት ወቅት ደጋፊዎቹ የኦሮሞ ህዝቦች በብዛት በሚኖሩባቸው የተለያዩ ከተማዎች ውስጥ የአዳራሽ ስብሰባዎችን በማስተባበርና ገንዘብ በማሰባሰብ አንድነታቸውን አሳይተዋል። | English | Amharic |
People opposing Jawar, — most of whom are members of Eskinder’s support base — held a series of rallies opposing Jawar’s town hall meetings. | በአብዛኛው የአቶ እስክንድር ደጋፊ የሆኑ የአቶ ጃዋር ተቃዋሚዎች በአሜሪካ የተደረገውን የከተማ አዳራሽ ስብሰባዎችን በመቃወም ተከታታይ ተቋውሞችን አካሂደው ነበር። | English | Amharic |
Like Eskinder, Jawar also has a habit of using questionable persuasion techniques. He often accuses authorities of the Amhara regional state of being nostalgic for Ethiopia’s imperial era and highlights violence that targets minorities in the Amhara region. | ልክ እንደ አቶ እስክንድር ሁሉ አቶ ጃዋርም አጠያያቂ የማሳመን ዘዴዎችን የመጠቀም ልማድ አለው። ብዙ ጊዜም የአማራ ባለስልጣናትን የአፄዎችን ዘመን አፍቃሪ ናቸው፤ አንዲሁም በአማራ ክልል በአናሳ ብሔሮች ላይ የሚያነጣጥር ጥቃትንም ይፈፅማሉ በማለት ይወቅሳቸዋል። | English | Amharic |
After he completed his US tour, Jawar accused authorities of Amhara regional state of organizing and funding what he described as a “hateful, shameful and violent campaign.” | የአሜሪካ ጉዞውን አጠናቆ ከተመለሰ በኋላ የአማራ ክልላዊ መንግስት ባለስልጣናትን በጥላቻ የተሞላ፣ አሳፋሪ የሁከት ዘመቻን አደራጅተዋል፤ እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል የሚል ወቀሳ አቅርቦ ነበር። | English | Amharic |
As proof of his accusation, he accompanied his note with a photograph that showed a top-level Amhara regional state official, Yohannes Buayalew, posing with Yoni Magna, a diaspora-based social media personality who is notorious for his rants, insults and conspiracy theories. | ለወቀሳው ማስረጃ ይሆነውም ዘንድ የአማራ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያሌው እና ዲያስፖራ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የሆነው፣ ስድብ እና ፀብ ቃስቃሽ ሀሳቦች በማንሳት ከሚታወቀው ዮኒ ማኛ ጋር የተነሱትን ፎቶ ከፅሁፉ ጋር አያይዞ አቅርቦ ነበር። | English | Amharic |
The attempt is to insinuate that Amhara regional state officials have worked with Yoni Magna, — who was also seen at one of the demonstrations. | ይህ ሙከራ የአማራ ክልል ሀላፊዎች ከተቃውሞዎቹ በአንዱ ላይ ታይቶ ከነበረው ከዮኒ ማኛ ጋር አብረው ሰርተዋል የሚል ስሜት ለመፍጠር ነበር። | English | Amharic |
Some people did openly hurl bigoted slurs used to refer to an individual of Oromo ancestry during the protests, but there is no evidence to suggest that these rallies were in fact organized and funded by Ethiopian authorities. | አንዳንድ ተቃዋሚ ሰልፈኞች የኦሮሞ ተወላጆችን በግልፅ በፀያፍ ቃላት ሲጠሯቸው የነበረ ቢሆንም እነዚህ ተቃውሞዎች በትክክልም በኢትዮጵያ ባለስልጣናት መዘጋጀታቸውን እና በገንዘብ መደገፋቸውን የሚያሳይ ማስረጃ የለም። | English | Amharic |
Ultra-nationalist sentiment through songs | የፅንፈኝነት ስሜት በሙዚቃዎች ውስጥ | English | Amharic |
Until now, inflammatory language has been confined to writing, memes, short clips, graphics and pictures. But as the role of social media gains ground, the terrain of ethnic tension has expanded to YouTube music videos. | እስካሁን ድረስ ፀብ ቀስቃሽ መልዕክቶች ሲሰራጩባቸው የነበሩ መንገዶች ፅሁፎች፣ ሚሞች(memes)፣ አጫጭር ክሊፖች፣ ግራፊክስና ስዕሎች ነበሩ። አሁን ግን ማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ካደገ በኋላ የብሔር ሽኩቻ ውጥረት ወደ ዩቲውብ ቪዲዎች ተስፋፍቷል። | English | Amharic |
In a flood of Afan Oromo and Amharic language music videos, singers promote nationalistic narratives that assert the superiority of their group — sometimes even promoting conflict with the other group. | ብዛት ባላቸው የኦሮምኛና የአማርኛ መዚቃ ቪዲዮች ላይ ዘፋኞች የብሔር ትርክትን የሚያንፀባርቁ፣ የራሳቸውን ወገን የበላይ አድርገው የሚስሉና አንዳንዴም ከሌላው ወገን ጋር ፀብን የሚቀሰቅሱ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ይደመጣሉ። | English | Amharic |
Some of the most nationalistic expressions in songs focus on the homeland, flag and historical figures. Praising Emperor Menelik II as a liberator or denouncing him as a monster has long been a recurring theme. | ከብዙዎቹ ዘፈኖች መካከል አንዳንዶቹ የሀገር መሬት፣ባንዲራ እና የድሮ ታሪኮች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክን እንደ ነፃ አውጪ ወይንም እንደ ጭራቅ ማውገዝ ለረጅም ጊዜ ሲደጋገም የቆየ ገጽታ ነው። | English | Amharic |
In fact, there is a Facebook page that went up in 2013 to highlight the atrocities committed by a soldier of Emperor Menelik II. | በእርግጥ በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ወታደሮች የተፈፀሙትን ጭፈጨፋዎች ለማሳየት በ2005 ዓ.ም የተከፈተ የፌስቡክ ገፅ ይገኛል። | English | Amharic |
But the launch of Unity Park elicited several Oromo music videos that focus on ethnic origins of government authorities. | ነገር ግን የአንድነት ፓርክ መከፈት የመንግስት ሀላፊዎችን የዘር ምንጭ አስመልክቶ ብዙ የኦሮምኛ የሙዚቃ ቪዲዮዎች እንዲሰሩ አነሳስቶ ነበር። | English | Amharic |
Because the park is Abiy’s project, some songs portray him as a person who committed ethnic treason by honoring Emperor Menelik II. One song depicted him as a sellout; another one questions if he is an Oromo at all. | አንድነት ፓርክ የአብይ ፕሮጀክት ስለሆነም አንዳንዶቹ ዘፈኖች ዶ/ር አብይ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክን በማክበር ብሔሩን የካደ እንደሆነ አድርገው ይገልፁታል።አንዱ ዘፈን ብሔሩን አሳልፎ የሰጠ ከሃዲ አድርጎ ሲገልፀው፣ ሌላው ደግሞ ከነጭራሹም ኦሮሞ መሆኑን ጥያቄ ውስጥ ይከታል። | English | Amharic |
Caalaa Daggafaa, an Afan Oromo singer, accused Abiy of being a sellout for praising past monarchs. He rails against the statue of Menelik II, whom he described as a monster. | የአፋን ኦሮሞ ዘፋኝ የሆነው ጫላ ደገፋ ዶ/ር አብይ ያለፉ ነገስታትን በማወደሱ ምክንያት ብሔሩን የካደ ነው ብሎ ይወቅሰዋል። እንደ ጭራቅ ለሚገልፃቸው ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ተብሎ የተሰራውን ሀውልትም ይቃወማል። | English | Amharic |
In the same video, he pays respect for the armed forces of the Oromo Liberation Front, describing them as heroes doing a tough job by continuing the struggle for the emancipation of the Oromo people. | በተመሳሳይ ቪዲዮ ኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) ‘የኦሮሞ ህዝብ ነጻነት ትግልን በፅናት ያስቀጠሉ ጀግኖች’ በማለት ያለውን አክብሮት ይገልጻል። | English | Amharic |
Meanwhile, Amharic singers deliver odes to Menelik II, describing him as a unifier and liberator. | ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማርኛ ቋንቋ ዘፋኞች ደግሞ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክን የአንድነት እና የነፃነት ተምሳሌት አድርገው ይገልጿቸዋል። | English | Amharic |
In one music video, Dagne Walle, a rising Amharic singer, swings toward the camera, wielding his rifle while humming that he has inherited valor from Menelik II — alluding to the emperor as his father. | ታዋቂነትን እያተረፈ የመጣው የአማርኛ ሙዚቀኛ ዳኜ ዋሌ በአንድ ሙዚቃ ቪዲዮው ላይ ጠመንጃውን ይዞ በካሜራው ፊት በማወዛወዝ ጀግንነቱን የወረሰው አባት ብሎ ከሚገልፃቸው ዳግማዊ አፄ ሚኒልክ እንደሆነ ይናገራል። | English | Amharic |
Footage of crowds with traditional cloth armed with rifles, stomping their feet while waving Ethiopian flags, and a roaring lion punctuates the music video, titled “Wey Finkich” (“Hell No”). | ‘ወይ ፍንክች’ በተሰኘ የሙዚቃ ቪዲዮ ባህላዊ አልባሳት የለበሱና ጠመንጃ የታጠቁ ብዙ ሰዎች የኢትዮጵያን ባንዲራ እያውለበለቡ መሬቱን በእልህ ሲረግጡት ይታያል። የሚያጋሳ አንበሳም የቪዲዮው ማጀቢያ ሆኖ ቀርቧል። | English | Amharic |
These songs rack up a huge number of views on YouTube — reaping advertising dollars while hardening ethnic polarization. | እነዚህ የሙዚቃ ቪዲዮዎች በዩቲውብ ላይ ብዛት ያላቸው ተመልካቾችን ያፈሩ ሲሆን የዘር ግጭትን እያቀጣጠሉ በዛውም ከዩቲውብ የሚገኝ ዶላርን ያጭዳሉ። | English | Amharic |