id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-41981820
https://www.bbc.com/amharic/news-41981820
ከስደት ወደ ባለሃብትነት-የኢትዮጵያዊው የስደት ኑሮ በአውስትራሊያ
አቶ ዳዊት ኢተፋ ይባላሉ። በስዕል ተሰጥኦ ያላቸውና በኢትዮጵያ በነበሩበት ጊዜ በተለያዩ ክፍለሃገራት በመዘዋወር ሲሰሩ የቆዩ ናቸው። አቶ ዳዊት የሚያከብሯት ጥበብ ከሚወዷት ሃገራቸው እንዲወጡም ምክንያት ሆነች። እንዴት? ይኸው የአቶ ዳዊት አስደናቂ የሕይወት ጉዞ ከራሳቸው አንደበት።
ከሀገሬ የወጣሁት እ.አ.አ በ1980 ነው። እዚህ ውሳኔ ላይ እንድደርስ ያደረጉኝ የተለያዩ ምክንያቶች ነበሩኝ። አንደኛ በኢሉባቡር ክፍለሃገር 'እንባ' የተሰኘ ስዕል ሰራሁና ባሮ በሚባል ሆቴል ውስጥ ሰቀልኩት። ''የሆቴሉ ባለቤት በጣም ሲረዱኝ የነበሩና የተከበሩ በመሆናቸው የእርሳቸውንም ፈቃድ እንኳን ሳልጠይቅ እንደስጦታ አድርጌ ነበር የሰቀልኩት። ከዚያም መንግሥትን የሚያሳፍርና የሚያዋርድ የፖለቲካ ሥራ ነው ተባልኩና በአካባቢው ባለስልጣናት ፊት ቀረብኩኝ። በእስር ቤት ውስጥ ለ1 ወር ስቃይና መከራ ካደረሱብኝ በኋላ አንድ ሰላማዊ እንደሆንኩ የሚያውቀኝ መቶ አለቃ ዋስ ሆኖኝ ከእስር ቤት ተለቀቅኩኝ። ከዚያ በኋላ እዚያ የነበሩኝን ሥራዎች ሳልጨርስ ሳልወድ በግድ አካባቢውን ለቅቄ ወጣሁ። ለጥቆም ''የሃምቢሳ እናትና ኑሮዋ'' የተሰኘ ስዕል ሠራሁና ምዕራብ ወለጋ በቢላ ከተማ ውስጥ ሰቀልኩ። ስዕሉ አንዲት የኦሮሞ እናት የምታሳልፈውን ህይወት ለማሳየት በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ነበር። የሃምቢሳ እናት ደሃ ነች፤ ሃምቢሳ ዛሬም በሕይወት አለ፤ የሃምቢሳ ልጅ አምና እሬቻ ላይ ከሞቱት ውስጥ እንዱ እንደሆነ ሰምቼ በጣም ነበር ያዘንኩት። ስዕሉ ጸረ-አብዮት ነው ተብሎ ተወሰደና ወደ ሌላ ተላከ፤ ስዕሎችን የምሰራበት ስቱድዮም ታሽጎ እኔንም ለማሰር ሲያፈላልጉኝ አምልጬ የሽሽት ጉዞዬን ወደ ድሬዳዋ አደረግኩኝ። ከሰባት ዓመት የሽሽት ኑሮ በኋላ መንግሥት በመለወጡ በ1983 እ.አ.አ ወደ ነቀምቴ መጣሁና 'ኦሮሚያ የኦሮሞ ነች' የሚል ስዕል ሰራሁና በነቀምት ከተማ መሃል ሰቀልኩ። ይህም ሌላ ስደት አመጣብኝ ስዕሉን አውርደው ካቃጠሉት በኋላ ሠሪውንም እናቃጥላለን ብለው አካባቢው ያለው የፀጥታ ጠባቂዎች እኔን ለመያዝ ፍተሻ ጀመሩ። እኔም ተደብቄ ከቆየሁ በኋላ ከዚያው በመሸሽ አዲስ አበባ ገባሁ። እዚያም ብዙ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲበዛብኝ ወደ ነገሌ ቦረና ብሄድም ሁኔታዎች ሲብስቡኝ ወደ ኬንያ ተሻገርኩ። ወደ ኬንያ ከመጣሁበት ቀን ጀምሮ የአዕምሮ እረፍት አገኘሁ፤ ይህ ማለት ችግር አለልደረሰብኝም ማለት አይደለም። ፖሊሶች በየቦታው እያስቆሙ ያስቸግሩኝ ነበር። እድለኛ ሆኜ ሂደቱ ተፋጥኖልኝ በስተመጨረሻም አውስትራሊያ ገባሁ። ነጻነትና እኩልነት የተረጋገጠበት የሰላም ሀገር በመሆኑና ትልቅ እረፍት በማግኘቴ የወደፊት ህይወቴ ላይ በማተኮር ሥራዬ ላዬ ተጠመድኩኝ። ከማውቀው ስራ በመነሳት ስዕልና የማስታወቂያ ሥራ ጀመርኩኝ። የምወደውና ተሰጥኦዬ ነው ወደምለው ሙያ እንድመለስና በሁለት እግሬ እንድቆም አደረገኝ። በመቀጠልም ቤት ገዝቼ አድሼ አሰማምሬ በመሸጥ ገቢ ማግኘት ጀመርኩኝ፤ በዚህም ተሳካልኝ። ከዚህ በኋላም ከባለቤቴ ጋር በመሆን የአበባ ማሳመሪያና መሸጫ ሱቅ ከፈትን። ባለቤቴም አበቦችን ማሰማመርና አስጊጦ ማቅረብ ስለምትወድ ይህ ስራችንም የተሳካ ሆነልን። በተለይም በዚህ ሀገር የተለያዩ ወቅቶችን በመከተልና በቀን ተቀን ኑሮ ውስጥ አበባ ምን ያህል ተፈላጊ መሆኑን መገንዘብ መቻላችን ደግሞ ወደ አበባ እርሻ እንድንገባ አደረገን። ከዚያም 10 ሄክታር የሚያክል መሬት በራሳችን ገንዘብ በመግዛት የዛሬ ሰባት ዓመት የአበባ እርሻ ጀመርን። አሁን በ9 ሄክታር መሬት ላይ የአበባ ማሳደግ ስራ እየሰራን እንገኛለን። ዘጠኝ ሄክታር በዚህ ሀገር ትንሽ ቦታ ነው። ነገር ግን ጥሩ ጅምርና ለወደፊት ሊያድግ የሚችል መሆኑ ጥርጥር የለውም። የሥራ ዕድልም መፍጠር ችለናል። ለእኔ ስኬት ማለት አንድ ሰው በሚሰራው ሥራ መደሰት ማለት ነው፤ በምንሠራቸው ነገሮች ደስተⶉች ነን። ህልማችንም እየተሳካልን ነው ስለዚህ ለእኔ ስኬት ማለት ይህ ነው። በሕይወቴ ለሆነው ስኬት ሁሉ የአባቴና የእናቴ ድርሻ ከፍተኛ ነው። በማይመች ሁኔታም ውስጥ በእርሻውም ሆነ በንግዱ ዘርፍ ታላላቅ ጥረቶችን በማድረግ እስከ ጉምሩክ ሱዳን ድረስ እየሄዱ ሲነግዱ እያዩ ከማደግ በላይ ጥንካሬን የሚሰጥና የሚያነሳሳ ነገር የለም። ሁኔታዎች ቢመቻቹ ወደ ሃገሬ ብሄድና በልማት ሥራ ላይ ብሳተፍ ደስ ይለኝ ነበር ነገር ግን ይህ አሁን የሚመስል ነገር አይደለም። ያ ቀን ግን ቢቆይም እንደሚመጣ አምናለሁ። በፎቶ የህዝቡን ባህልና ወግ ማንሳትና በሙዚየም አስቀምጦ ለሚመጣ ትልውድ ማስተላለፍ ትልቁ ምኞቴ ነው። አቶ ዳዊት ኢተፋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት
news-54575536
https://www.bbc.com/amharic/news-54575536
"ሕዝብን ከማገልገል በላይ ክብር የለም"- አዲሱ የባህርዳር ምክትል ከንቲባ
በትናንትናው ዕለት፣ ጥቅምት 6፣ 2013 ዓ.ም ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።
የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በስራ አመራርና ፍልስፍና ቻይና አገር ከሚገኘው ኋጁንግ ዩኒቨርስቲ በቅርቡ አጠናቀው የመጡት ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የምሁራን ተሳትፎና አደረጃጀት ዘርፍ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አማካሪ፣ የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ፣ የሕዝብ ግንኙነትና የከተማ አደረጃት አማካሪና በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ ምክትል አስተዳደሪና ግብርና ጽኅፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ካገለገሉባቸው መካከል የተወሰኑት ናቸው። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በመልክዓምድርና አካባቢ ጥናት ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲና ሁለተኛ ዲግሪ በመልካም አስተዳደርና በአመራር ጥበብ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በተለያዩ የአመራር ቦታዎችም ላይ ሆነው አገልግለዋል። በባሕርዳር ከተማ አስተዳደር በተቀዳሚ ምክትል ከንቲባነታቸውን ሹመት፣ ሊያከናውኗቸው ያሰቧቸውን እቅዶችና ሌሎች ጉዳዮች በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ቢቢሲ፦ በትናንትናው ዕለት ሹመቱን ሲቀበሉ ምን እሰራለሁ? ምን ለውጥ አመጣለሁ ብለው ነው ሹመቱን የተቀበሉት? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደርን በተቀዳሚ ምክትል ከንቲባነት እንድመራ የድርጅትና የመንግሥት ኃላፊነት ሲሾመኝ፣ አንደኛ ይሄ ተልእኮ ነው። የፓርቲው አባል ነኝ፤ ከፓርቲዬ የተሰጠኝን ተልዕኮ መቀበል የግድ ስለሚል ይህንን የተሰጠኝን ተልዕኮ ተረክቤ ከዚህ በፊት በግንባር ላይ እየሰሩ ካሉ አመራሮች ጋር በመካከር፤ በቀጣይ ባህር ዳር የኢንቨስትመንት መዳረሻ፣ ኢንዱስትሪ የተስፋፋባት፣ ሰላም የሰፈነባት፣ ፍትሃዊነት የተረጋገጠባት እና የሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ ስራዎችን ህዝብ ጋር በመካከር ለመስራት ነው። የባህር ዳር ከተማ እንድታድግ እንድትበለፅግ የከተማዋ ነዋሪዎች ፍላጎት ነው። እኔም ይህንን ኃላፊነት የከተማዋን ነዋሪ ፍላጎት ለማሳካት በበኩሌ የሚጠበቅብኝን አስተዋፅኦ ለማበርከት ነው። በቀጣይ አመራሩ ጋር ተነጋግረን፤ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሂደን ከዚህ በፊት የተጀመሩ ስራዎችን፣ የታቀዱ እቅዶችንና ጅምሮችን ለማስቀጠል እናስባለን። በአዳዲስ የከተማ አስተዳደር ስርአቱን ዘመኑ በሚጠይቀው ልክ ለማዘመን አቅሜ የፈቀደውን ያህል የተጣለብኝን አደራና ለመወጣት ዝግጁነት የያዝኩ ብቻ መሆኔን ነው የማረጋግጠው በዚህ ሰዓት። ምክንያቱም አሁን ገና ወደ ስራ እየገባሁ ነው። ከዚህ በፊት ይሄ ስራ እንደሚሰጠኝ ባለማወቄ እንዲሁም ይሄ ተልእኮ በመሆኑም ጊዜ ወስጄ ችግሮችን ለይቼ ከአመራሩ እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ ተወያይተን የከተማዋን አጠቃላይ እድገት አንድ ደረጃ ወደፊት የሚያራምድ የአመራር ስርአት ለመዘርጋት ነው በግሌ ለማድረግ ያሰብኩት። ቢቢሲ፡ በተለያየ የስራ ኃላፊነት ከመስራትዎ አንፃር እንዲሁም ከተማዋን ያውቁታል ብዬ ከማሰብም ከዚህ በፊት በነበሩ ሂደቶች ምን ክፍተት አዩ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ከዚህ በፊት የሰራሁባቸው የአመራር ተልእኮዎች በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ውስጥ አይደለም። በምእራብና ምስራቅ ጎጃም የሚባሉ ዞኖች ነው ሳገለግል የቆየሁት፤ በመሃልም የውጭ የትምህርት እድል አግኝቼ ትምህርቴንም ተከታትዬ ነው የተመለስኩት። አሁን ገና ትምህርቴን አጠናቅቄ ከምረቃ በኋላ የተሰጠኝ አዲስ የስራ ስምሪት ነው። በአሁኑ ወቅት ባህርዳር ከተማ ላይ እንዲህ አይነት ጉድለቶች አሉ ብሎ ለመናገር ግምገማ ያላካሄድኩበት በመሆኔ ገና የተሰጠኝን ተልዕኮ ተቀብዬ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅት ላይ ነኝ። ክፍተቶቹን ወይም ጠንካራ ጎኖች እነዚህ ናቸው ብዬ አሁን ባለሁበት ሰዓት ላይ ልናገር አልችልም። ምክንያቱም ገና ያልተገመገመ ነገር ይዤ በዚህ ላይ አስተያየት መስጠት ይከብደኛል። ቢቢሲ፡ የድህረ ምረቃዎን ትምህርት የተከታተሉት በቻይና ነው። የተለያዩ የቻይና ከተሞችን ለማየት እድል አግኝተው ከሆነ ከዛ የቀዱት ነገር አለ ወደዚህ ባመጣው ብለው ያሰቡት? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ቻይና የደረሰችበት የከተማ ልማት እና የኛ አገር ምንም እንኳን ለማወዳደር ልዩነቱ የሰፋ ነው። እዚያ ያየሁዋቸውን አንዳንድ ነገሮች በተለይም የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ላይ፤ የዘመናዊና ቀልጣፋ የአሰራር ስርአት ከመዘርጋት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ የአገልግሎት አቅርቦት ላይ የተሻለ ነገር አይቻለሁ። አቅም በፈቀደ መጠን ከኛ አገር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ስርአት ጋር የተገናዘበ የከተማ ስርአት አገልግሎት አቅርቦት ለማድረግ የዩኒቨርስቲ ምሁራንን እንዲሁም በዘርፉ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን በማማከር አሰራርን ለማዘመን ጥረት ማድረግ የሚገባ መሆኑ ይሰማኛል። እዚህ ላይም አቅሜ የፈቀደውን አስተዋፅኦ ለማድረግ ጥረት አደርጋለሁ ብዬ አስባለሁ። ቢቢሲ፡ ምክትል ከንቲባ ሆነው በትናንትናው ዕለት ተሾመዋል። በስልጣን ላይ ሆኜ እሰራለሁ ብለው ቅድሚያ የሚሰጧቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ በትናንትናው ዕለት ቃለ መሃላ ከፈፀምኩ በኋላ ለምክር ቤቱ ያቀረብኩት የመክፈቻ ንግግር ነበር። ከአመራሩም ሆነ ህብረተሰቡን በማሰለፍ ብንረባረብባቸው አጠቃላይ የከተማይቱን እድገት ያፋጥናል ብዬ የማምንባቸውን አቅጣጫዎች አቅም በፈቀደ መጠን ለማስቀመጥ ሞክሬያለሁ። ከነዚህም መካከልም በተለይ በከተማ የመጀመሪያው ስራ- ኢትዮጵያ በሽግግር ላይ ያለች አገር ናት። ፖለቲካዊ ለውጦች እያካሄደችም ትገኛለች። አሁን ያለው ፓርቲ ከኢህአዴግ ወደ ብልፅግና የተሸጋገረበት፣ አመራሩ ከላይ እስከ ታች በአዲስ እየተደራጀና እየተጠናከረ ያለበት፣ አዳዲስ አስተሳሰቦች ወደ መንግሥት አሰራር የገቡበት ማግስት ላይ ነው ወደ ስራ እየገባሁ ያለሁት። ከዚህ ጋር የተጣጣመ የትኩረት አቅጣጫ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን አስቀምጫለሁ። ከነዚህም መካከል በተለይም የከተማው አስተዳደር ውስጥ የህግ የበላይነትን ማስፈን፣ ሰላምን ማረጋገጥ የመልካም አስተዳደሮችን ለይቶ በህዝቡ ተሳትፎ መፍታት የሚሉት ይገኙበታል። የከተማዋ ያላትን ስመ ገናናነትና የከተማዋ እድገትን ሊመጥን የሚችል የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ስራ ላይ በተለይም የእንጨት ልማት ፕሮጀክቶች ላይ አተኩረን የእለት ተግባራችን አድርገን መንቀሳቀስ ይገባል። የከተማውን የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት ችግር፣ ከዚህም የዘለሉ ሌሎች ተደራራቢ ጥያቄዎችን የህዝብ መድረኮች እየፈጠርን በመልቀም እንደ መንግሥት አቅም መፈታት የሚገባቸውን ቅድሚያ እየሰጠን እንሰራለን የሚሉ አቅጣጫዎች ነው ለማስቀመጥ የተሞከረው። በተለይም የወጣቱን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ የስራ እድል መስኮችን በመፍጠር ላይ ያተኮረ ስራ እንሰራለን። የስራ እድል ፈጠራ ለሰፊው ህዝብ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው ይሄ ከተማ ላይ ያለ የድህነት ቅነሳ አካል ነው። እነኚህ ጉዳዮች መልክ ከያዙ ከተማዋ ወደተሻለ ህይወት ውስጥ የምንገባበት አጋጣሚ ስለሚኖር እነዚህ ላይ አተኩረን ብንሰራ የሚል እሳቤ ይዤ ነው ወደ ስራ እየገባሁ ያለሁት። እንግዲህ ቀጣዩን ከእግዚአብሔር ጋር ከህብረተሰቡ፣ ከቅርብ አመራር ጋር በመሆን የምንችለውን ሁሉ በቅንነት ግልፅ (ትራንስፓረንት) በሆነ መንገድ፣ ህዝቡን አሳታፊ በሆነ መንገድ የከተማ አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎቱ አለኝ። ያው ውጤቱን የምናየው ይሆናል። ቢቢሲ፡ የጠቀሷቸውን ተግባሮች ለማከናወን ምን አይነት ተግዳሮት ይገጥመኛል ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ በባለፉት ሶስት አመታትና ከዚያ በላይ ከአመራር ስርአት ውጭ ብሆንም በተለምዶ የሚታወቁ የከተማ ስራን ለመስራት የሚገዳደሩ ችግሮች አሉ። እኛንም ትንሽ ይፈትነናል ብለን የምናስበው ከተማ የተለያዩ ፍላጎቶች አሉት። ግማሹ ህጋዊ በሆነ መንገድ ከተማ እንዲለማ የመፈለግ፤ ግማሹ ደግሞ በህገወጥ ወይም በአቋራጭ መንገድ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተቃራኒ ፍላጎቶች የሚሳተፉበት መድረክ ነው። ፖለቲካዊ ፍላጎቱ ብዙና የተለያዬ የሆነበትና ሌሎች እንዲሁም ውስብስብ ችግሮች ያሉበት ነው- የከተማ ስራ። ስለዚህ እነዚህን ችግሮች አጣጥሞ ለመምራት የሚያስችል ብቁና ቅቡልነት ያለው በስነ ምግባር የታነፀ አመራር የመፍጠር፣ የማሰማራትና ከህብረተሰቡ ጋር አዋህዶ የማሰራት ሂደት ፈታኝ ሊሆን ይችላል። እዚህ ላይ እኛም አተኩረን እንረባረባለን። ነገር ግን የሰው ልጅ ፍላጎት የተወሰነ ባለመሆኑ ህጋዊ ስርአት ተከትሎ በሚሰራበት ጊዜ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ሊነኩ ይችላሉ። በዚያን ጊዜ ማማረር ሊከሰት ይችላል።እኛ እነዚህን አስቀድመን ስለምናውቅ በተቻለ መጠን ከአመራሩ ጋር ተነጋግረን የሁሉንም ዜጎች ፍላጎት አጣጥሞ ከህግና ስርአት ውጭ ሳይሆን ከተማዋን በከተማ እቅድ (ፕላን) ማስተዳደር። በዚያም መሰረት እንድትመራ የማድረግ ስራ እንሰራለን። እንግዲህ እዚህ ላይ ህብረተሰቡም ያግዘናል ብዬ ተስፋ የማደርገው ህጋዊነትን ብቻ ተከትለን ስንሰራ ከጎናችን የሚሆን ከሆነ ለውጥ እናመጣለን። ነገር ግን በመሃል አንዳንድ መንጠባጠቦች፤ ከዚህ ባፈነገጠ መንገድ መጠቀም የሚፈልጉ ኃይሎች ትንሽ ያስቸግሩን ይሆናል፤ በውይይት እየፈታን እንሄዳለን። እንሻገራለዋን የሚል ተስፋ እንዲሁም እምነት አለኝ። በመወያየት የማይፈታ ችግር የለም ተብሎ ስለሚታሰብ ዋናው ነገር አመራሩንም ህዝቡንም ያሳተፈ የአመራር ዘይቤን መከተል፤ እነዚህን ተግዳሮቶች እናልፋቸዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ከዚህ በዘለለ በስራ ሂደት የሚፈጠሩ ችግሮች ይኖራሉ እንደዬ አፈጣጠራቸውና እንደ አመጣጣቸው እንመልሳለን ብዬ አስባለሁ። ቢቢሲ፡ባህርዳር ከተማን የተለያየ ከንቲባዎች መርተዋታል፤ ባለን መረጃ ቶሎ ቶሎ የመቃየየር ሁኔታም አለ። ከዚህ ቀደም የነበሩት ከንቲባ በውበት፣ በፅዳት ጋር ተያይዞም ይወደሳሉ። እርስዎስ በየትኛው በኩል እወደሳለሁ ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ከዚህ በፊት የነበሩ ከንቲባዎች ባህርዳር ዛሬ ለደረሰችበት የእድገት ደረጃ የየበኩላቸውን አሻራ ጥለው አልፈዋል። በርካታ ጥሩ ጥሩ የሚባሉ ከተማዋን ወደፊት ያራመዱ ተግባራትን ፈፅመዋል። ይሄም የሚያስመሰግናቸው ነው። በዚያኑ ልክ ግን የሰው ልጅ ወደ ስራ በሚሰማራበት ወቅት ጥንካሬዎች እንዳሉ ድክመቶችም ሊኖሩ ይችላሉ። እኛ መከተል የምንፈልገው እነሱ ሰርተውት በሄዱት ላይ ተጨማሪ ስራ እየሰራን ጥሩውን እያስቀጠልን ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ መቀጠል። ድክመት ነበሩ ተብለው የሚታሰቡ ጉዳዮች ላይ ደግሞ ደግመው እንዳይፈፀሙ እያስተካከልን ነው ለመሄድ ያሰብነው። በቅርብ ከለቀቁት ከንቲባ ጋር ተያይዞ በርካታ ተስፋ ሰጭ ብዙ ደስ ደስ የሚሉ ስራዎችን ጀምረው የሄዱ መስሎ ነው የሚሰማኝ። እርሳቸው የጀመሯቸውን በጎ ተግባራት አጠናክረን እንቀጥላለን። ከዚህ ውጭ ደግሞ ክፍተት በምንላቸው ነገሮችን እንሞላለን። እሱ በምን ይሳካልዎታል ለሚለው? እሱን በቀጣይ በተግባር ብናየው ይሻላል። ምክንያቱም አሁን ወደ ስራ ባልተገባበት ሰዓት ላይ በዚህ ስራ የተሳካልኝ እሆናለሁ ማለት የአካባቢውን ሁኔታ በደንብ ሳላይ፣ ገምግሜ ክፍተቱን በጥሩ ሁኔታ ለይቼ ባልገባሁበት ወቅት ላይ ይሄ ውጤታማ ያደርገኛል፣ አያደርገኝም ብሎ ለመናገር የሚያስቸግረኝ ይመስለኛል። ቢቢሲ፦ ሹመቱ ያልጠበቁት ይመስላል። በርግጥ እሾማለሁ ብለው ላያስቡ ይችላሉ። ለዚህ ሹመት የሚታጩ ሰዎች አካባቢውን በደንብ የሚረዳ ፣ ከተማውን በደንብ የሚያውቅ፣ ክፍተት ሊሞላ የሚችል፣ ጎዶሎውን ሊያውቅ ይችላል ተብሎ የሚታሰብ ሰው ነው ብዬ አስባለሁ…. ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ልክ ነው፤ ሹመት በሚሰጥበት ጊዜ በበለጠ አካባቢውን የሚያውቅ ሰው ቢሆን ይመረጣል። አካባቢውን በማወቅ ብዙ ችግር ያለብኝ አይመስለኝም። ከዚህ በፊት ባህርዳር ላይ የተወሰነ ጊዜ ሰርቻለሁ። ባህርዳር ዩኒቨርስቲ እንዲሁም አሁን ካለው አመራር ጋር በመቀናጀት በአመራርነት ብዙ ጊዜ ስላሳለፍኩኝ መረጃዎቹም አሉኝ። እውነት ለመናገር እሾማለሁ ብዬ አልጠበቅኩም። እኔ ትምህርቴን ጨርሸ ስመጣ፤ በድርጅታችን አሰራር መሰረት የፖለቲካ ሹመት የሚሰጠው ተነግሮ አይደለም። የትምህርት እድል ተሰጥቶኝ ተምሬ ስመጣ አመራር ቦታ ላይ እንደምመደብ አውቃለሁ፤ የትኛው ቦታ እንደሆነ የሚወስነው የፓርቲው ፅህፈት ቤት ነው። አንድ ሰው ካለው የትምህርት ዝግጅት፣ የስራ ባህርይና ሌሎችም ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ገብተው ነው ሹመት የሚሰጠው። እንግዲህ ፓርቲው በዚህ ቦታ ላይ ሲመድበኝ ለዚህ ስራ ይመጥናል የሚል እምነት ይዟል ማለት ነው። እኔ ግን እንደ አንድ አመራርና አባል የተሰጠኝን ተልእኮ ስፈፅም ቆይቼ፣ ትምህርቴን አጠናቅቄ መምጣቴንና ሌላ ተጨማሪ ተልዕኮ ፓርቲዬ እንዲሰጠኝ እየጠበቅኩ ስለነበር የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ሆኜ እሾማለሁ ብዬ አልጠበቅኩም። ይሄ ተልእኮ ሲሰጠኝ ግን ህዝቡን ከማገልገል በላይ ሌላ ክብር ስለሌለ ፤ ህዝብን ማገልገል ኩራት ስለሆነ፤ ከዚህም በላይ ኃላፊነት ስለሌለ ከታመነብኝና ይህንን ስራ ይሰራል ብሎ ሹመቱን የሰጠኝ አካል አለ። ምክር ቤቱም ይህንን የቤት ሰራ ወስዶ ተቀብሎ ካፀደቀው በኔ በኩል ባገለግል ምንም ችግር የለውም። የተማርኩትም ህዝቡን ለማገልገል ነው። ቢቢሲ፡ ነፃ ሆኜ እስራለሁ፤ ነፃ ሆኜ ያሰብኳቸውን ነገሮች አሳካለሁ ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ፈተናዎች ይኖራሉ። ይሄ ግልፅ ነገር ነው። ከተማ ላይ ብዙ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች አሉ። ያንን ሁሉ ፍላጎት ለሟሟላት ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ጠንቅቄ አውቃለሁ። ነገር ግን አቅም በፈቀደ መጠን ህሊናዬ የሚገፋኝን ለመስራት ዝግጁ ነኝ። ከዚህ በፊትም የአመራር ህይወቴ ልምዱም ስላለኝ የምችለውን ሁሉ ለመስራት እሞክራለሁ። የፓርቲ አመራሮችም ድጋፍ እንደሚያደርጉልኝም ሙሉ ቃል ገብተውልኛል። በተቻለ መጠን ህሊናዬ የሚያምንበትን ነገር ለመስራት እንቅስቃሴ አደርጋለሁ፤ እታገላለሁ። ከአቅም በላይ ሲሆን ደግሞ ብዙ አማራጮች አሉ ማለት ነው። ግን እኔ ከአቅም በላይ የሚሆን ነገር ይገጥመኛል ብዬ አላስብም። በአሁኑ ሰዓት ፓርቲውም ሆነ መንግሥት የሚፈልገው የህብረተሰቡን ፍላጎት ማሟላት ነው። የህብረተሰቡን ፍላጎት ተረድተን በምንቀሳቀስበት ወቅት የሚመጣውን እንቅፋት የሚታገል በርካታ ኃይል ከጎን አለ።ይህንን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የምሞክረው ይሆናል ማለት ነው። ቢቢሲ፡ ነፃ ሆነው እንዳይሰሩ ችግር ሊገጥምዎት ይችላል በስራ አጋጣሚ የሚገጥም ነው። እነዚህ ችግሮች ከየት በኩል ይመጣል ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ወደ ስራ ሳይገባ እንደዚህ አይነት ትንበያዎች (ፕሪዲክሽን) መስጠት ያሳስታል (ሚስሊድ ያደርጋል)። ምክንያቱም እኔ ዛሬ ተንብዬ ከዚህ አካባቢ ችግር ይመጣብኛል ብዬ ብናገር፤ ይመጣብኛል ብለሽ የምታስቢውን አካባቢ ማሳሰብም ስለሚሆን ወደ ስራ ገብቶ በተግባር ላይ የሚገጥም ችግርን ፊት ለፊት መጋፈጥ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ይመስለኛል። ችግር የሌለው ስራ የለም። ህዝብን መምራት ትልቅ ከባድ እና አስቸጋሪ ነው። እያንዳንዱ አመራር ይህንን አውቆ ነው የሚገባው ። ምንጊዜም ወደ ስራ ስንገባ ችግሮች እንደሚኖሩ አውቃለሁ። እንደየአመጣጣቸው ለመመለስ ራሴን አዘጋጅቻለሁ።
news-53204134
https://www.bbc.com/amharic/news-53204134
"በአጼ ምኒልክ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበርኩ" ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት '114 ዓመቱ' አዛውንት
በአጼ ምኒልክ ዘመን የአምስት ዓመት ህጻን እንደነበሩ የሚናገሩት አዛውንት የኮሮናቫይረስተገኝቶባቸው የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው ከበሽታው ማገገም እንደቻሉ የተነገረው በዚህ ሳምንት አጋማሽ ላይ ነበረ።
ግለሰቡ ከኮሮናቫይረስ ቢያገግሙም ለተጨማሪ ሕክምና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል መዘዋወራቸው ተገልጾ ነበር። በካቲት 12 ሆስፒታልም የጀመሩትን ሕክምና ጨርሰው ያለመሳርያ እገዛ መተንፈስ በመጀመራቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። እኚህ የ114 ዓመት እድሜ ባለጸጋ አባ ጥላሁን ወልደሚካኤል ናቸው። አባ ጥላሁን አሁን ባሉበት የእድሜና የጤና ሁኔታ ምክንያት ለተጨማሪ የጤና ችግር እንዳይጋለጡ በማሰብ ቢቢሲ ይህንን ቪዲዮ በልጅ ልጃቸው በአቶ ቢኒያም ልዑልሰገድ እንዲቀረጽ አድርጓል።ሐሙስ እለት ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ዳይሬክተር የፌስቡክ ሰሌዳ ላይ የተገኘው መረጃ አንድ የ114 ዓመት አዛውንት ከኮሮናቫይረስ ማገገማቸውን የሚያበስር ነበር።
45974841
https://www.bbc.com/amharic/45974841
የቢቢሲ የምርመራ ቡድን ቻይና ሙስሊም ዜጎቿን በማጎሪያ እያሰቃየች እንደሆነ ደርሶበታል
ወትሮም ቻይና ለምዕራባዊያን ምስጢር ናት። ለሙስሊም ዜጎቿ ደግሞ ጀሐነም። የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ቡድን ይፋ ባደረገው ልዩ ጥንቅር ቻይና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ዜጎችን የምታጉርበት የበረሃ ካምፕ መኖሩን አጋልጧል።
ቻይና ለሙስሊም ዜጎቿ ምድራዊ ሲኦል ሆናለች "የዕደ ጥበብ ማሰልጠኛ" በሚል ሽፋን ለዓመታት የቆየው ይህ ካምፕ አስተሳሰብን የሚያጥብ፣ ጉልበትን የሚያዝል፥ እምነትን የሚሸረሽር፣ ኅቡዕ የግዞት ማዕከል ነበር ተብሏል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ በማዕከሉ ገብተው የሚወጡ ዜጎች ሃይማኖታቸውን ብቻ ሳይሆን ጨርቃቸውን ሊጥሉ ይችላሉ። • ለእነ ባራክ ኦባማ የተላከው ጥቅል ቦምብ • ባህር አቋራጩ የቻይና ድልድይ ተከፈተ • የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ ብሔር- አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ቻይና በበኩሏ "የአክራሪ ሙስሊሞች ሞገደኛ አስተሳሰብ የምገራበት ከፍተኛ የትምህርትና ሥልጠና ተቋሜ ነው" ትላለች። ካምፑ የት ይገኛል? ዢንዣንግ በሚሰኘው የምዕራብ ቻይና ክፍለ ግዛት ዳባቼንግ በምትባል ትንሽዬ አውራጃ ይገኛል፤ እልም ባለ በረሃ ውስጥ። የዚህ የግዞት ማዕከል አጥር ሁለት ኪሎ ሜትር ይረዝማል፣ 16 ሰማይ ጠቀስ የጥበቃ ማማዎችም አሉት። ቻይና የገዛ ሙስሊም ዜጎቿን እያፈነች በዚህ የግዞት ካምፕ ስታሰቃይ እንደኖረች የማያወላዳ መረጃ ተገኝቷል። የማጎሪያ ካምፑ የሳተላይት ምሥል እንዴት ተደረሰበት? ከ2015 ወዲህ በዚህ ጭው ያለ በረሃ የግንባታ ቁሳቁሶች ሲንቀሳቀሱ ግርምትን ፈጥሮ ነበር፤ በዚህ ስፍራ ምን ይገነባ ይሆን? የሚሉ ጥርጣሬዎች የበረከቱበት ጊዜም ነበር። ከሚያዚያ 2018 ወዲህ ግን የሳተላይት ምሥሎች አንዳች ግንባታን ማሳየት ጀመሩ። እጅግ ግዙፍ፣ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት የበረሃ ካምፕ መሆኑም ተረጋገጠ። አጥሩ ብቻ 2 ኪሎ ሜትር ይረዝማል። እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ በሺ የሚቆጠሩ የሰው 'ዋርዲያዎች' የሚኖሩበት፣ 16 የስለላ ማማዎች የተቸነከሩበት ካምፕ። ያም ሆኖ በዚህ ዘመን ከተፈጸሙ የጅምላ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አንዱ በዚህ በረሃ እንደሚፈጸም የሚያውቅ አልነበረም። የቢቢሲ የምርመራ ጉዞ ዘገባ የቢቢሲ የምርምር ጋዜጠኞች ቡድን በማለዳ ኡሩምኪ አየር ማረፊያ ደረስን። ቡድናችን ከአየር መንገድ ወጥቶ ወደ ደባቼንግ እስኪደርስ ድረስ ቢያንስ አምስት መኪናዎች እየተከታተሉን ነበር። ከነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ነጭ ለባሾች ነበሩ። ወደዚህ ካምፕ የመጠጋቱ ነገር ለመርማሪ ቡድኑ ፈተና እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው። ወደ ሥፍራው እየተቃረብን ስንመጣ አንዳች ኃይል እንደሚያስቆመን ገምተን ነበር። በመቶ ሜትሮች ርቀት ካምፑን ስንቃረብ ያልጠበቅነውን ተመለከትን። ያ በሳተላይት የአሸዋ ቁልል ይመስል የነበረው መጋዘን ሌላ መልክ ይዟል። ከጎኑም የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታ እየተካሄደ ነበር። ክሬኖች፣ ስካቫተርና ሌሎች የግንባታ መሣሪያዎች ይንኳኳሉ። በመልክ የተሰደሩ ባለ አራት ፎቅ ቡላማ ሕንጻዎች ይታያሉ። ይህ ሁሉ ጭው ባለ በበረሃ ውስጥ የሚታይ ትዕይንት ነው። ካሜራችን መቅረጽ እንደጀመረ ከየት መጡ ሳንል ፖሊሶች ወረሩን። መኪናችን በደኅንነቶች እንዲቆም ተደረገ። ካሜራችንን እንድናጠፋ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጠን። ያም ሆኖ ካሜራችን አንድ ምስል አስቀርቶ ነበር። ዓለም ምንነቱን የማያውቀውን ካምፕ ምስል። እነማን ይታጎሩበታል? በቻይና ምዕራባዊ ክፍል የሚገኝ ሶላት የማይሰገድበት መስጊድ ወደዚህ ካምፕ ለመወርወር ቻይናዊ ሙስሊም መሆን በቂ ነው። የአካባቢው ተወላጆችን ስለዚህ ካምፕ ምንነት ስንጠይቃቸው በፍርሃት ይደነብሩ ነበር። ገሚሶቹ ደግሞ ትምህርት ቤት እንደሆነ ብቻ ይናገራሉ። ከዓለም ዕይታ የተደበቀ ትምህርት ቤት። "በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች፤ በአስተሳሰብ ጤና የራቃቸው ሰዎች የሚማሩበት ነው" አለን ሌላ ነዋሪ። ቻይና በተደጋጋሚ ሙስሊም ዜጎቿን ማጎርያ ውስጥ እንደማትወረውራቸው ስታስተባብል ኖራለች። ይህን ክስ ተከትሎ የቻይና ቴሌቪዥን በፕሮፓጋንዳ ተጠምዷል። ንጹሕ መማሪያ ክፍሎችን፤ አመስጋኝ ተማሪዎችን ወዘተ በማሳየት። ሆኖም በዚህ ትምህርት ቤት መመረቅ የለም፤ ግዞት ነው። መግባት እንጂ መውጣት ሕልም ነው። በቴሌቪዥን የሚቀርቡት ተማሪዎችም ይህ "ትምህርት ቤት" እንዴት ሕይወታቸውንና መንፈሳቸውን እንዳደሰ ነው የሚናገሩት። ነገርየው ቃለ መጠይቅ ሳይሆን ኑዛዜ ነበር። ይህ ማጎርያ የተገነባው በተለይ ለዢያንዣንግ ነዋሪዎች ነው፤ ኢጉርስ ይባላሉ። ብዙዎች ከአናሳ የቻይና ዘውግ የተገኙ ናቸው። 1.5 ቢሊዮን ከሚሆነው የቻይና ሕዝብ 10 ሚሊዮን ቢሆኑ ነው። ቻይንኛን አይናገሩም። ቋንቋቸውም ቱርኪክ ነው። የዚህ ግዛት ሙስሊም ነዋሪዎች ነጠላ ማጣፋት ሻሽ ማገልደም፥ በሂጃብ መጀቦን አይሞክሯትም። ረመዳን መጾም በጠኔ ያስገርፋል፣ ሶላት መስገድ ለግዞት ይዳርጋል። ጢንም ማንዠርገግ ከፍተኛ የሥነ ምግባር ጥሰት ነው። ቻይና ክፍል ሃይሞኖት አንድ ነው፤ እሱም ኮሚኒዝም፤ መማለድም በሺ ዣን ፒንግ። አብዱልሰላም ሙሐሜት ምስክርነት ቢቢሲ ስምንት ከሚሆኑ የኢጉር ዘውግ አባላት ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ነዋሪነታቸው ከቻይና ወዲያ ባሕር ማዶ ነው። ምስክርነታቸው መርማሪ ቡድኑ ከደረሰበት ውጤት ጋር ስምም ነው። አብዱሰላም ሙሐመት የ41 ዓመት ጎልማሳ ነው። ቀብር ላይ የቁርዓን ጥቅስ ተናግረሃል በሚል በ2014 ወደ ካምፑ መወሰዱን ያስታውሳል። "በካምፑ ውስጥ በጠዋት ተነስተህ ትሰለፋለህ። ከባድ የሰውነት እንቅስቃሴ እንድትሠራ ትገደዳለህ። በፍጥነት ትሮጣለህ። በፍጥነት መሮጥ ያልቻሉትን ማሰቃያ ራሱን የቻለ ክፍል አለ" ይላል ሌላው የቀድሞ ታራሚ አብሌት ሱርሱን። "ሁልጊዜ መዝሙር ያዘምሩናል፤ 'ደሜና አጥንቴ ለኮሚኒስት ፓርቲ፤ ቻይና ትቅደም' የሚል መዝሙር። ሕጎችን ያሸመድዱናል። ያስተማሩንን በደንብ ካላስታወስን ግን ከፍተኛ ቅጣት ይጠብቀናል።" ይላል አብሌት። አብሌት በለስ ቀንቷቸው ከግዞት ካምፑ ማምለጥ ከቻሉ እድለኛ ዜጎች አንዱ ነው። አሁን በቱርክ አገር ጥገኝነት ጠይቆ ይገኛል። "እኔ እዚያ ሳለሁ የ74 ዓመት አዛውንት ከ8 ልጆቻቸው ጋር ፍዳቸውን ያዩ ነበር፤ ሙስሊም የሆነ አንድም ቻይናዊ የቀረ አይመስለኝም" ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል። ሶላት የማያውቁ መስጊዶች መስጊዶች ለቱሪስቶች የጉብኝት መዳረሻ እንጂ ሶላት መስገጃ አልሆኑም የቢቢሲ የምርመራ ጋዜጠኞች ቡድን ቀድሞ የኡግር ባሕል ማዕከል ተደርጋ በምትታሰበው ካሻጉር በተባለችው ከተማ ቅኝት አድርጎ ነበር። በዚች ከተማ የሚገኙ ሰዎች ቤተሰቦቻቸው ወዴት እንደሄዱ ሲጠየቁ ለመናገር ይፈራሉ። የከተማው ነዋሪ ግዞት ነው ያለው። የከተማዋ ትልቁ መስጊድ ወደ ሙዝየምነት ተቀይሯል። መርማሪ ቡድኑ የዙሁር ሶላትን ለማየት መስጂድ በር ላይ ነበር። ለሶላት ብቅ ያለ የለም። አዛንም የለም። መስጊዱ በር ላይ ቆሞ የነበረ አንድ ፖሊስ " ሶላት ስንት ሰዓት ነው የሚጀመረው" ብለን ጠየቅነው። " ስለ ሶላት የማውቀው ነገር የለም፤ እዚህ ያለሁት ቱሪስቶችን ለመርዳት ነው" አለ። ከመስጊዱ አቅራቢያ ጢማቸውን ሙልጭ አድርገው የተላጩ ሸምገል ያሉ ሰዎችን ተመለከትን። "ሰጋጆች ወዴት ጠፉ?" ስንል ጠየቅናቸው። አንደኛው አዛውንት ዝም እንድንል በእጃቸው ምልክት ሰጡን። ሌላኛው አንሾኳሸኩ "ኸረ መስጊድ የሚመጣ ሰው የለም!" ወደ መስጊዱ በር በመመለስ ደጃፉን የሚያጸዳ ፖሊስ ዘንድ ሄድን። ቱሪስቶች ከመስጊዱ እየተጠጉ ፎቶ ይነሱ ነበር። መስጊዱ ለቱሪስት እንጂ ለሶላት ሰጋጆች ቦታ የለውም። ሶላት ሰጋጆች ግዞት ተወስደዋል።
52831055
https://www.bbc.com/amharic/52831055
አምነስቲ በአማራና በኦሮሚያ የሚፈፀሙ ግድያዎችና እስሮች እንዲቆሙ ጠየቀ
የመብቶች ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ባለፈው የምዕራባውያን ዓመት ልዩ ልዩ መንግስታዊ የፀጥታ ኃይሎች እና ከእነርሱ ጋር በትብብር የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኢመደበኛ ቡድኖች አሰቃቂ የሰብዐዊ መብት ጥሰቶችን ፈፅመዋል ሲል ወነጀለ።
አምነስቲ ዛሬ ይፋ ባደረገው የሰባ ሁለት ገፅ ጥናታዊ ዘገባው ለአንድ ዓመት ያህል በሁለቱ ክልሎች ባደረግኩት ምርመራ በኦሮሚያ ምስራቅ እና ምዕራብ ጉጂ እንዲሁም በአማራ ምዕራብ እና መካከለኛ ጎንደር ዞኖች የመከላከያ ሠራዊት፣ የክልል ልዩ ፖሊስ፣ የየአጥቢያ ባለስልጣናት እና ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው የወጣት ቡድኖች አባላት በመብት ጥሰቶቹ ተሳትፈዋል ብሏል። "ከሕግ ማስከበር ባሻገር፣ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች የተፈፀሙ የሰብዐዊ መብት ጥሰቶች" የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በፀጥታ ኃይሎች የሚፈፀሙ ህገወጥ ግድያዎች፣ የጅምላ እስሮች፣ በግዳጅ ማፈናቀል እና የንብረት ማውደሞች በአፋጣኝ መቆም እንዳለባቸው በይፋ ትዕዛዝ እንዲሰጡ ጠይቋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደስልጣን መምጣት በኋላ በአገሪቱ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶችን በማስከበር ረገድ ከታዩ አዎንታዊ እርምጃዎች ጎን ለጎን ፖለቲካዊ እና ብሔር ተኮር ውጥረቶች አብረው ታይተዋል፤ እነዚህ ውጥረቶችም በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሃረሪ፥ ድሬዳዋ እና የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልሎች እና አስተዳደሮች የትጥቅ እንቅስቃሴዎች እና የማኅበረሰብ ግጭቶች መቀስቀስ ምክንያት ሆነዋል ይላል አምነስቲ። ኦሮሚያ በጎርጎሳውያኑ 2019 መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በምዕራብ እና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች ፀጥታ ማስከበርን ግብ ያደረገ ግብረ ኃይል አቋቋሟል። ግብረ ኃይሉ የቀበሌ ሚሊሻዎችን፥ የኦሮሚያ ልዩ እና መደበኛ ፖሊስ ኃይሎችን እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊትን እንቅስቃሴዎችን በማስተባበር በሁለቱ ዞኖች ያለውን የቀድሞውን የኦሮሞ ነፃነት ጦር (ኦኤልኤ) የተባለውን ታጣቂ ቡድን የመመከት ዓላማ እንዳለው ይገለፃል አምነስቲ በኦሮሚያ ተፈፅመዋል ያላቸውን ጥሰቶች ሲዘረዝር። በጎርጎሳውያኑ በጥር 2019 በምስራቅ ጉጂ ዞን በምትገኘው ጉሮ ዶላ ወረዳ እና በምዕራብ ጉጂ ዞን በምትገኘው የዱግዳ ዳዋ ወረዳ 39 ሰዎች መገደላቸውን በምርመራዬ ደርሸበታለሁ ይላል አምነስቲ። ከእነዚህም መካከል 23 ያህሉ በጎሮ ዶላ ወረዳ በመከላከያ ሠራዊት እና በኦሮሚያ ፖሊስ የተገደሉ ናቸው ሲል የሚከሰው የመብት ተሟጋቹ ሪፖርት 16 ያህሉ ደግሞ በዱግዳ ዳዋ ወረዳ ርሸና ከችሎት ውጭ በሚመስል አኳኋን ለመገደላቸው ተዐማኒ ማስረጃ አለኝ ይላል። ዘገባው ቀጥሎም ከወራት በኋላ፣ በወርሃ ጥቅምት በጎሮ ዶላ ወረዳ በምትገኘው ራሮ ቀበሌ፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጨደቻ መኢሳ፣ አብዱላሂ ጎሉ ሃላኬ እና ቃንቄ ኡታራ ሹሬ ከታሰሩባቸው ህዋሳት ካወጧቸው በኋላ የተባሉ ዘመዳማቾችን በጥይት ተኩሰው ገድለዋቸዋል ይላል። ዘመዳማቾቹ ለእስር የተዳረጉት በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የቀድሞው የኦሮሞ ነጻነት ጦርን በመደገፍ ተጠርጥረው ነው። በነሐሴ ወርም ቢሆን ቦዲሻ ጩሉቃ የተባለ የእነ አብዱላሂ የቅርብ ዘመድ እንዲሁ በመከላከያ ሠራዊት ከታሰረ በኋላ ተገድሏል- እንደ አምነሰቲ። በታሰረ በቀጣዩ ቀን ቤተሰቦቹ በጥይት መበሳሳቱ የሚታይ ሬሳውን ቁጥቋጦ ውስጥ አግኝተውታል። "ወታደሮች በሬ እናራርድ እና ወደቀብር ስፍራውም [በአካባቢው ልማድ እንደሚደረገው] ምግብ እንዳንወስድ ከልክለውናል። ለሸኔ ወታደሮች ምግብ ልትወስዱ ነው አሉን፤ ምንም እንኳ የተቀበረው ከተማው ውስጥ ቢሆንም" ስትል የቦዲሻ ዘመድ የሆነችው ቦናኒ ጃለታ ነግራኛለች ይላል አምነስቲ። መሰል ግድያዎች በጎርጎሳውያኑ ታህሳስ 4 ቀን (በኦሮሚያ ፖሊስ ልዩ ኃይል)፣ የካቲት 3 ቀን 2019 (በመከላከያ ሠራዊት)፣ በነሐሴ 2019 (በመከላከያ ሠራዊት)፣ በጥር እና ግንቦት 2019፣ በታህሳስ 2018 (በመከላከያ ሠራዊት) ተፈፅመዋል ይላል የመብት ተሟጋቹ ድርጅት። ይቀጥልናም ከግድያዎቹም ባሻገር ዘፈቀዳዊ እስር ተፈፅሟል፤ በእስር ወቅትም ስቅይት ተከናውኗል፤ ገና ምርመራ ላይ ብሆንም የአስገድዶ መደፈር ክስም ቀርቦልኛል ብሏል። ከቀያቸው በግድ የተፈናቀሉ እና ንብረቶቻቸው የወደሙባቸውም አሉ- እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል። አማራ በጎርጎሳውያኑ ከመስከረም 2018 እስከ ጥቅምት 2019 ድረስ በምዕራብ እና መካከለኛው ጎንደር ዞኖች በሚገኙ የቅማንት እና አማራ ማኅበረሰብ አባላት መካከል ግጭት ጨምሮ እንደነበር በመጥቀስ ነው አምነስቲ በአማራ ክልል ተፈፅመዋል ያላቸውን የሰብዐዊ መብት ጥሰቶች መዘርዘር የሚጀመረው። በቋራ፣ መተማ እና ጭልጋ ወረዳዎች የክልሉ ፖሊስ አባላት እና የአካባቢው ሚሊሻዎች የቅማንት ማኅበረሰብ አባላት ላይ ጥቃት አድርሰዋል የሚለው የመብት ተሟጋቹ በአቅራቢያ የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አሃዶች ጉዳዩን ለማስቆም የወሰዱት ምንም ዓይነት እርምጃ የለም ይላል። በጎርጎሳውያኑ በጥር 10 እና 11 እንዲሁም በመስከረም 2019 የጣልቃ ግቡልን ተማፅኖ ቢቀርብላቸውም የሠራዊቱ አባላት ከቸልታቸው አልተናጠቡም ይላል አምነስቲ። • ትራምፕ 'ቀላል ጉንፋን ነው' ያሉት ቫይረስ የ100ሺህ ዜጎቻቸውን ህይወት ነጠቀ እንደ አምነስቲ ዘገባ ከሆነ በጥር 2019 ቢያንስ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 58 ሰዎች ተገድለው በጅምላ መቀበራቸው ተዘግቧል። ከጎንደር ከተማ የፀጥታ ቢሮ አገኘሁት ባለው መረጃ በመመስረትም በጎርጎሳውያኑ በመስከረም እና ጥቅምት 2019 በከተማዋ ዙርያ ተቀስቅሶ የነበረውን ማኅበረሰባዊ ግጭት ለ43 ሰዎች ሞት እና ለ12 ሰዎች መቁሰል ምክንያት ሆኗል። የክልል የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የፀጥታ ኃይሎች፣ በተለይም የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት በስፍራው ባይሰማሩ ኖሮ የተጠቂዎች ቁጥር ከዚህም ሊልቅ ይችል እንደነበር ነግረውኛል ብሏል። በጎርጎሳውያኑ ጥር 10 ቀን 2019 ከሰዐት በኋላ ላይ በመተማ ዮሃንስ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጎበዝ አለቃ እና ፋኖ የሚባሉ ኢ-መደበኛ የወጣት ቡድኖች ቀበሌ ሦስት የሚባለውን መንደር በመክበብ ነዋሪዎችን በጠመንጃ፣ በድንጋይ እና በፈንጅ አጥቅተዋል- ይላል የአምነስቲ ዘገባ። ይህም መንደር በብዛት የቅማንት ማኅበረሰብ አባላት የሚኖሩበት ነው። የመከላከያ ሠራዊት አባላት በቦታው ደርሰው ነዋሪዎቹን ሲታደጉ ጥቃቱ ለ24 ሰዓት ገደማ ተከናውኖ ነበር። የዐይን ምስክሮች እንደነገሩኝ ጥቃቱን ለማድረስ ለቀናት ያህል ዝግጅት ሲደረግ ነበር፤ የወጣት ቡድኖቹ ጥቃት በክልሉ ልዩ ፖሊስ እና በአጥቢያው ሚሊሻዎች የታገዘ ነበር፤ ከመንደሩ አቅራቢያ ባለፈው የሰፈራ ጣብያቸው የሚገኙት የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ለሃያ አራት ሰዐታት ያህል ምንም አላደረጉም ነበር ይላል። በለጠ መንግስቱ የተባሉ የዐይን እማኝ "ሠራዊቱ የመጣው፤ ጉዳቱ ሁሉ ከደረሰ በኋላ ነው። 1600 የሚሆኑ የቅማንት ማኅበረሰብ አባላት ወደጦር የሰፈራ ጣብያ ተወስደዋል" ብለውኛል ይላል አምነስቲ። በጎርጎሳውያኑ ጥር 12 ቀን 2019 "የሞቱትን መተማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስትያን ስንቀብር 58 ሬሳ ቆጥሬያለሁ" ብለዋል በዘገባው የተካተቱት እኝሁ የዐይን እማኝ። • በጥቁር አሜሪካዊው ግድያ ምክንያት ተቃዋሚዎች እና ፖሊስ ተጋጩ አምነስቲ የሳተላይት ምስሎችን በመጠቀም በጎርጎሳውያኑ ጥር 11 ቀን ብዙ የቅማንት ማኅበረሰብ አባላት በሚኖሩበት መንደር እሳት እና ጭስ እንደነበርና በከተማዋ ሰሜን ምዕራባዊ አቅጣጫ ያሉ ሁለት አካባቢዎች የተቃጠሉ እንደሚመስል ደርሼበታል ብሏል። ከጎንደር ከተማ በስተስሜን በሚገኙ እና በብዛት የቅማንት ነዋሪዎች ባሉባቸው አርባባ፣ ወለቃ እና ሳይና ቀበሌዎች የበቀል የሚመስል ጥቃት በአማራ ማኅበረሰብ አባላት ላይ ደርሷል ያሉ ሰዎችንም አናግሬያለሁ ይላል ዘገባው። ይህ የምላሽ ጥቃትም ጥቅምት 14 ጀምሮ፣ እስከ ጥቅምት 16 ቀጥሏል። በእነዚህ ማኅበረሰባዊ ግጭቶች ቢያንስ 130 ሰዎች መገደላቸውን ለዚህም የፀጥታ ኃይሎች ቸልታ አስተዋፅዖ እንዳለው ያትታል አምነስቲ። የመንግስት አካላት አስተያየት አምስነቲ ለልዩ ልዩ የመንግስት አካላት እንደየሚናቸው ምክረ ኃሳቦችን ያቀረበ ሲሆን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለመከላከያ ሚኒስትር፣ ለሰላም ሚኒስትር፣ ለፖሊስ ኮሚሽን እና ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፀጥታ ኃይሎችን የሚቆጣጠር ተዐማኒ፣ ገለልተኛ እና ሲቪል ተቋም ስለመመስረት፣ ጥቃት አድራሾቹን ስለመለየት እና ለፍርድ ስለማቅረብ፣ በጥቃቶች ላይ በቀጥታ የተሳተፉ የሠራዊት አካላትን ስለመበተን፣ በየጊዜው መንግሥት ህገ ወጥ ግድያዎችን ለመመርመር እና ለፍርድ ለማቅረብ የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ይፋ ስለማድረግ የሚያወሱ ይገኙባቸዋል። • 'ጨለምተኛው' ፕሮፌሰር "ዓለም ለ10 ዓመታት ትማቅቃለች" አሉ ዘገባውን በሚያጠናቅርበት ጊዜ በአዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ አይምባ፣ ወለቃ እና ሃዋሳ የሚገኙ ከ80 በላይ ግለሰቦችን ማናገሩን የሚገልፀው አምነስቲ፣ በግኝቱ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡት የሰላም ሚኒስትርን፣ የመከላከያ ሚኒስትርን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንን፣ የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ እና አስተዳደር ጉዳዮች ፅህፈት ቤትን፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን፣ የአማራ ፀጥታ ቢሮን እና የአማራ ፖሊስ ኮሚሽንን መጠየቁን ይናገራል። ይሁንና ለጥያቄው ምላሽ ያገኘው ከአማራ ክልል ፀጥታ ቢሮ ብቻ መሆኑንን ገልፆ ቢሮውን ያመሰግናል።
news-52989990
https://www.bbc.com/amharic/news-52989990
"ኮሮናቫይረስ ስጋት ሆኖ ከቀጠለ ሁሉም የፌደራልና የክልል ምክር ቤቶች ሥራቸውን ይቀጥሉ"
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኮሮናቫይረስ ስርጭት በኢትዮጵያ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ ሁሉም የፌደራልና የክልል ምክር ቤቶች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ በሚል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ማጽደቁ ተነገረ።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ባከናወነበት ወቅት መሆኑን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዘሃን ዘግበዋል። የምክር ቤቱ የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምርጫን ከማራዘም ጋር በተያያዘ የቀረበለትን የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ጥያቄ ከመረመረ በኋላ፤ የቫይረሱ ስርጭት በአገሪቱ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ ሁሉም የፌደራልና የክልል ምክር ቤቶች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ወስኗል። ከዚህ በተጨማሪም፤ ኮሚቴው የሚመለከታቸው አካላት የቫይረሱን ስርጭትና ጉዳት ገምግመው፤ ቫይረሱ የሚያስከትለው ጉዳት መቀነሱን ወይንም ጉዳት ማድረስ ማቆሙን ማረጋገጥ ሲችሉ አገራዊው ምርጫ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ማካሄድ እንደሚቻል የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል። ኮሚቴው ባቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ለመስጠት በመወያየት ላይ ይገኛል።
news-56111933
https://www.bbc.com/amharic/news-56111933
በዱባይ የሴቶች መብቶች የትኞቹ ናቸው?
በቅርቡ ዓለምን ካስደነገጡ ጉዳዮች በአንዱ እንጀምር- የልዕልት ላቲፋ ጉዳይ። ልዕልቷ የዱባዩ ገዥ ልጅ ናት፡፡
ልዕልቷ በድብቅ ተቀርጾ ቢቢሲ እጅ በገቡት ተንቀሳቃሽ ምስሎች በጎርጎሮሳዊያኑ 2018 ለመሸሽ ከሞከረችበት ጊዜ አንስቶ አባቷን በከተማው እንዳገቷትና አባቷን ከመክሰስ ባለፈ ሕይወቴም አደጋ ላይ ነው ትላለች። ስለ ጉዳዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን (UAE) እጠይቃለሁ ብሏል፡፡ ልዕልቷ ለመሰደድ የተነሳች ብቸኛዋ የቤተሰቡ አባል አይደለችም፡፡ ልዕልት ሀያ ቢንት ሁሴን 45 ዓመቷ ሲሆን የልዕልት ላቲፋ አባት ሚስት ናት። በጎርጎሮሳዊያኑ ሰኔ 2019 ወደ ጀርመን ተሰዳ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቃለች፡፡ የላቲፋ እህት ሻምሳም ለማምለጥ ሞክራለች፡፡ በባህረ ሰላጤው ባለስልጣኖች በሆኑት በአንዱ ላይ የሚቀርቡት የጭቆና፣ የማጎሳቆል እና የቁጥጥር ውንጀላዎች የሚረብሹ ናቸው፡፡ ሴቶች በሕይወታቸው ውስጥ መብቶቻቸው እና ዕድሎቻቸው በወንዶች እንዴት ይወሰናል? የሚለውን እንመልከት፦ በዱባይ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ስለሚኖሩሴቶች ምን ማለት ይችላል? በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሴቶች ማሽከርከር፣ መምረጥ፣ መሥራት፣ ንብረት ማፍራት እና መውረስ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ከዓለም ኢንፎርሜሽን ፎረም የተገኘው ሪፖርት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ክልል በጾታ እኩልነት ሁለተኛ ደረጃን እንደያዘች ያስቀምጣል። ሆኖም ዐውዱን መረዳት አስፈላጊ ነው። በዓለም አቀፉ የሥርዓተ ፆታ (Gender Gap) ዘገባ መሠረት አካባቢው ከሌሎቹ አንጻር በጣም ዝቅተኛ ውጤት ነበረው። ከእስራኤል በስተቀር አንዳቸውም እስከ 100 ባለው ደረጃ ውስጥ ውስጥ አልገቡም፡፡ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከዓለም 153 ሀገራት 153ኛ ደረጃን ይዛለች። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የፀረ መድልዎ ሕግ ቢኖራትም፤ ፆታን መሠረት ያደረጉ አድሎዎች በሕጉ ፍቺ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ ሴቶች መብቶች ቢኖራቸውም፣ በግላዊ ሕጉ መሠረት ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት በወንድ “ሞግዚት” መፅደቅ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ይህም ማለት ሴቶች ብዙውን ጊዜ ፈቃድ እንዲያገኙ የሚፈቅደው የትዳር ጓደኛ ወይም ሌላ ወንድ ዘመድ ነው፡፡ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሕጎች እንደ ጎረቤት ሳዑዲ አረቢያ ጥብቅ ወይም ሰፋ ያሉ ባይሆኑም በሴቶች ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡ ሴቶች መብቶች በሚኖራቸው ወቅትም በፍርድ ቤት የመከላከሉ ጉዳይ በተግባር ሲታይ ከባድ ነው፡፡ ጋብቻና ፍቺ ፈተና ከገጠመው የሴቶች የግል ሕይወት አንዱ ጋብቻ ነው። አንድ ሴት ለማግባት የወንድ ሞግዚት ፈቃድ ያስፈልጋታል፡፡ ሌላው ደግሞ የልጆችን ጥበቃ እና ውርስን ያካትታል። በሕግ ያልተስተካከሉ ግን በተግባር የሚከናወኑ ኦፊሴላዊ ያልሆኑ የአሳዳጊነት ዓይነቶችም አሉ ሲሉ የሂዩማን ራይትስ ዋች ተመራማሪ የሆኑት ሂባ ዛያዲን ለቢቢሲ ዜና ተናግረዋል፡፡ "በእርግጥ በሕጉ በማይገኙባቸው አንዳንድ አጋጣሚዎችም ሴቶች ሥራ ለማግኘት በሚያመለክቱበት ጊዜ ወይም ቤት ለመከራየት ሲፈልጉ ከአሳዳጊዎቻቸው ፈቃድ ይጠይቃሉ። ይህ ግን በሕጉ ውስጥ የለም። ጋብቻን እና ፍቺን በተመለከተ ግን በሕጎቹ ውስጥ በጣም ግልጽ ተቀምጧል” ብለዋል፡፡ ፍቺም ሌላው ለሴቶች ከባድ ጉዳይ ነው፡፡ ወንዶች በተናጥል መፍታት ቢችሉም፣ ሴቶች መፋታት ከፈለጉ ለፍርድ ቤት ማመልከት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በቤት ውስጥ የሚፈጸሙጥቃቶች ሴቶች ላይ ያለው መድልዎ በቤት ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችም ያጠቃልላል፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ቢያንስ በመሬት ላይ አንዳንድ አዎንታዊ የሕግ ለውጦች ተደርገዋል፡፡ ለምሳሌ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሕግ በግልፅ ወንዶች ሚስቶቻቸው ላይ ጠበኛ እንዲሆኑ ይፈቅድ ነበር። ነገር ግን በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 ላይ ተሰርዟል፡፡ የሴቶች ለባሎቻቸው “ታዛዥ” እንዲሆኑ የሚጠይቀው ሕግ ደግሞ በ2019 ተሽሯል፡፡ ባለፈው መጋቢት ለመጀመሪያ ጊዜ ሴቶች ጥበቃ እንዲያገኙ የሚያስችል አዲስ ሕግም ተፈጻሚ ሆኗል፡፡ ተጨማሪ የሕግ ማሻሻያዎች ባለፈው ዓመት መጨረሻም ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ሕጎቹ ብዙም ርቀት አይሄዱም የሚሉ ደምጾች ተሰምተዋል፡፡ አዲሱ ሕግ የቤት ውስጥ ጥቃትን የሚወስነው በዳኛ የግል አስተያየት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በተግባር የጥቃት ሰለባዎች ጥበቃ አሁንም ደካማ ነው ማለት ይቻላል፡፡ “በግዛቲቱ በጾታ እኩልነት ላይ ጥላቻን የሚያሳዩ ሕጎች አሉ። በሕገ መንግስቱ ላይ የፃፋቸውን እጅግ አስጸያፊ ነገሮችን በማስወገድ ይመስላል” ሲሉ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል የባህረ ሰላጤው ተመራማሪ ዴቪን ኬኒ ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ አምነስቲ በጎርጎሮሳዊያኑ 2014 በአገሪቱ አድሎአዊ ሕጎችን የሚተች ዘገባን ካወጣበት ወቅት ጀምሮ ምርምራ ለማድረግ ወደ አረብ ኤምሬትስ መግባት አልቻለም፡፡ “ስለሆነም በስርዓተ ፆታ ጥያቄዎች ላይ ያላቸው አመለካከት ምን እንደሆነ ለማየት በሚወጡት ሕጎች ላይ የመመስረት አዝማሚያ ነበረን። ለውጦች ተደርገውም በእነዚያ ሕጎች ውስጥ ብዙ ኢ-ፍትሀዊነት አለ፡፡ ይህ በማኅበራዊ ወይም በመንግሥት አመለካከቶች ላይ ምንም ዓይነት ጥልቅ ለውጦችን አያመለክትም” ብለዋል። በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውስጥ የሚኖር ወይም የሚጎበኝ ማንኛውም ሰው ለሕጎቹ ተገዢ ነው። ቱሪስቶች በዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡ በዱባይ በእረፍት ላይ ሳሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችም አሉ። ለምሳሌም በጎርጎሮሳዊያኑ 2017 አንዲት እንግሊዛዊ ሴት ካላገባችው ወንድ ጋር በስምምነት ወሲብ ፈጽማ በመያዟ የአንድ ዓመት እስራት ተፈረዶባታል፡፡ የማስፈራሪያ መልዕክቶችን ስለላከላት ለባለስልጣናት ሪፖርት ስታደርግ ነበረ ሁለቱ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸማቸውን ያወቁት፡፡ በእውነቱ እነዚህ ሕጎች በእኩልነት የሚተገበሩ መሆን አለመሆኑ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ የመደብ ክፍፍል ቀደም ሲል ይፋዊ ያልሆነውን መደብ ሕግ ተደርጎ ተቀምል። በመደቡ አናት ላይ የሚገኙት ሀብታም ሴቶች ሲሆኑ የኤሚሬትስ ሴቶች ሁለተኛ፣ ቀጥሎ ደግሞ ስደተኛ የቤት ሠራተኞች ይመጣሉ፡፡ “የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ይህንን የመደብ ክፍፍል ወደ ተቋማዊነት እየቀየረች ይመስላል፡፡ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ የሕግ ማሻሻያ ሲተዋወቅ የመንግሥት የዜና ወኪል የሆነውን ዋምን ጨምሮ በሌሎችም ዓላማው ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ አገሪቱን የበለጠ ለማሳደግ እና ጥሩ የኢንቨስትመንት አካባቢን በመፍጠር የውጭ ዜጎችን ለመማረክ ነው በሚል በይፋ ዘግበዋል” ሲሉ ኬኒ ገልጸዋል። “ውርስ እና ፍቺ የሚመለከቱ ህጎች ላይ የተደረጉት ለውጦች የሚመለከታቸው ለኤሚሬትስ ሴቶች ሳይሆን የውጭ አገር ሠራተኞችን (expatriates) የሚመለከት ነው ተብሎ በብሔራዊ ጋዜጣ በግልፅ ተዘግቧል” ይላሉ። እንደ ዓለም አቀፉ የሠራተኛ ድርጅት (ILO) መረጃ ከሆነ በጎርጎሮሳዊያኑ 2017 አነስተኛ ደመወዝ ያላቸው ስደተኛ ሠራተኞች “እጅግ በጣም የዝቅተኛ ተጠቃሚ መደብ ላይ ቢሆኑም” ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጠቅላላ የህዝብ ቁጥር 80% ያህሉን ይሸፍናሉ ይላሉ ኬኒ፡፡ በተለይም ከደቡባዊ እና ደቡብ ምስራቅ እስያ የመጡ የቤት ሠራተኛ ሴት ስደተኞች ከባድ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፡፡ እንደ ኬኒ ገለጻ በማይታመን ሁኔታ ውስን መብቶች አላቸው። የወንጀል ሕጉን አንቀጽን በመጥቀስ ‘በመስማማት ክብርን መጣስ’ ሊያስከሰስ ይችላል ይላሉ፡፡ በተግባር ግን የስምምነት ወሲብ ላይ ለማነጣጠር ጥቅም ላይ ይውላል ይላሉ፡፡ “በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በእርግዝና ምክንያት ወደ ሆስፒታል የሚያቀኑ ሴት ስደተኛ የጉልበት ሠራተኞች ለእርግዝናው ኃላፊነት የሚወስድ አባት ሲያጡ በዚህ ሕግ መሠረት ክስ ይመሠረትባቸዋል” ብለዋል፡፡ ከጋብቻ ውጭ ያረገዙ ሴቶች እስከ አንድ ዓመት እስራት ይጠብቃቸዋል። ስደተኛ ሠራተኞች ቅጣቱ የሚፈጸምባቸው አገሪቱን ከመልቀቃቸው በፊት፡፡ ባለፈው ዓመት ጋርዲያን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባለሥልጣንን ጠቅሶ እንደገለጸው፤ በአገሪቱ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኛ ሴቶች ከጋብቻ ውጭ የተወለዱ ልጆች አሏቸው፡፡ የተደፈሩ ተጎጂዎችም ከጋብቻ ውጭ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን በሚመለከቱ ሕጎች ጉዳያቸው ታይቶ ክስ ይመሠረትባቸዋል፡፡ በጎርጎሮሳዊያኑ 2015 የቢቢሲ አረብኛ ምርመራ እንዳመለከተው የመድፈር ተጎጂዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶች በየአመቱ በዚህ ሕግ ለእስር ተዳርገዋል። ለዚህ ደግሞ የቤት ሠራተኞች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡
54040197
https://www.bbc.com/amharic/54040197
ኮሮናቫይረስ ፡ በአፍሪካ ከሚደረገው የኮቪድ-19 ክትባት ምርምር ጀርባ ያለችው ኢትዮጵያዊት
ምህረት አማረ ሱዳን ውስጥ ተወልዳ እድገቷ አሜሪካ ሲሆን፤ አሁን በሥራዋ አማካኝነት አፍሪካ ውስጥ መሥራቷ እንደሚያስደስታት ትናገራለች።
ምህረት አማረ ለአሥር ዓመታት በቁስልና በቆዳ ሪጄነሬሽን [ማገገም] የህክምና ላይ በመሰማራት ትሠራ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በኮቪድ-19 ክትባት ምርምር ላይ በመሳተፍ ላይ ትገኛለች። በባዮሎጂ የትምህርት ዘርፍ ተመርቃ በጥናትና ምርምር ላይ አትኩራ እየሠማራች ያለችው ለተለያዩ በሽታዎች መፍትሔ ለማግኘት ካላት ፍላጎት እንደነበር ትገልፃለች። ምህረት ለ10 ዓመታት በጥናትና ምርምር ዘርፍ ላይ ከሠራች በኋላ ፍላጎቷን ሰፋ በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚከሰቱና አሳሳቢ ለሆኑ የጤና እክሎች መፍትሔ ለማግኘት ጥረት ወደሚደረግበት ዘርፍ መዘዋወርን መረጠች። ይህንንም ተከትሎ ወደ ትምህርት ዓለም በመመለስ ሁለተኛ ዲግሪዋን በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን በማጠናቀቅ ወደ ጥናትና ምርምር ፖሊሲ ማኔጅመንት ተዘዋወረች። በምርምር ተቋሙ ውስጥም ምክትል ዳይሬክተር ሆና በምዕራብ አፍሪካ ውስጥ በኮቪድ-19 ዙሪያ በአህጉሪቱ ውስጥ በመሥራቷ ኩራት እንዲሰማት ከማድረጉ በላይ አፍሪካዊት በመሆኗ ደግሞ ትልቅ ትርጉም እንደሚሰጣት ትናገራለች። "እንዲህ ዓይነት ሥራ ላይ ስንሰማራ ባህልን መመልከት ያስፈልጋል" የምትለው ምህረት የምታከናው ተግባራ የተሳካ እንዲሆን አፍሪካዊ መሆኗ በጣም እንደሚጠቅማት ታምናለች። በዚህም አሁን እየሰራችበት ያለው የሄንሪ ጃክሰን ፋውንዴሽንም ሆነ "ለአህጉሪቱ ጥሩ ነገር እያበረከትኩ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ" ስትል ምህረት ትናገራለች። ዋልተር ሪድ አርሚ ኢንስቲትዩት ኦፍ ሪሰርች ወይም ውሬይር በመባል የሚታወቀው ድርጅት በአፍሪካ ውስጥ ከተሰማራ 50 ዓመት የሆነው ሲሆን ምህረት የምትሰራበት ድርጅት ደግሞ ይህንኑ የምርምር ተቋም የሚያግዝ ፋውንዴሽን ነው። በእዚህ ውስጥ የምህረት የሥራ ድርሻ የሚደረጉ የጥናት ፕሮግራሞችን በበላይነት መቆጣጠር ሲሆን፤ በአሁን ሰዓት ለኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት ጥናትና ምርምር የሚደረገውን ሩጫ በቅርብ የመከታተል ኃላፊነት አላት። "ሥራችን በላይቤሪያ፣ በጋና እና በናይጄሪያ ላይ የሚያተኩር ነው" የምትለው ምህረት ከ6 ዓመታት በፊት ብዙ ሰዎች ለሞት የዳረገውን የኢቦላ በሽታ በቅርበት በመመልከት ወረርሽኙ አጥቅቷቸው የነበሩ አገራት ውስጥ ያሉትን የጤና ተቋማትን የማጠናከር አስፈላጊነት መረዳታቸውን ትገልፃለች። ይህ በተለይ በመካከለኛው እና ምዕራብ አፍሪካ በሚገኙ አገራት ውስጥ ከተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ብዙ ልምድና ትምህርት መወሰድ መቻሉንም ምህረት ትናገራለች። በዚህም ምክንያት "በአፍሪካ ውስጥ በተለይ በምዕራብ አፍሪካ የኢቦላ ወረርሽኝ ጉዳት ከፍተኛ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ግን ተሞክሮውን እንደ ልምድ በመውሰድ ለኮቪድ-19 እየጠቀመን ነው" ትላለች። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተስፋፋ ጀምሮ የምህረት ሥራ ለኮቪድ-19 ክትባት ጥናት የሚያስፈልገውን እርዳታ ከማበርከትም በተጨማሪ ለህክምና ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ የመከላከያ አልባሳትን (ፒፒኢ) እና ጭምብሎችን የመሳሰሉ መገልገያዎችን ለተለያዩ ማዕከላት እንደሚያበረክቱና ሥልጠናዎችንም እንደሚሰጡ ትናገራለች። በአሁን ጊዜ በውሬይር ሥር እየተመራ ያለውን የኮሮናቫይረስ የክትባት ምርምር ለምዕራብ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለመላው አህጉሩ እንዲዳረስ በማሰብ ጥናቱ እየተካሄደ መሆኑን ትገልፃለች። "ጥናቱን መምራት ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ የሥራው ሂደት ውጤታማ በሆነ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ በመሆኑ ደስተኞች ነን። በተለይ በእንስሳት ላይ ስናካሂድ የነበረው ምርምር የፈለግነውን ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከያ አቅም [ኢምዩኒቲ] የመጎልበት ምልክቶች እያሳየ ነው" የምትለው ምህረት ከጥቂት ጊዜ ቆይታ በኋላም ሙከራው ወደ ሰው እንደሚያድግ ጠቁማለች። በምዕራብ አፍሪካ ያሉት ቤተ ሙከራዎች ቀደም ሲል ለምርምርና ለሙከራ አስፈላጊ የሆኑ መሣሪዎች ያልነበራቸው ሲሆን፤ ምህረት አማረ በምትመራው ፕሮግራም ሥር ጥናትና ምርምሩን ለማሳካት የሚያስፈልገውን በሙሉ ማሟላት መቻላቸውን ትናገራለች። በዚህም ምክንያት "ከአካባቢ አገራት ይወሰዱ የነበሩ ናሙናዎች ወደ ሌላ በመላክ ይደረግ የነበረው ምርመራ ቀርቶ፤ አሁን የተሟላ ቤተ ሙከራ በመኖሩ ሁሉም ምርመራ እዚሁ መደረግ ተችሏል" የምትለው ምህረት የክትባት ጥናቱ የመጀመሪያው ዙር ምርምር በምዕራብ አፍሪካ ከተደረገ በኋላ "የሁለተኛው ዙር የመጨረሻ ፍተሻና ማረጋገጫው አሜሪካ በሚገኙ ቤተ ሙከራዎች ውስጥ ይከናወናል" ብላለች። እንደ ምህረት ምልከታ በኮሮናቫይረስና በሌሎች በሽታዎች ላይ ጥናትና ምርምር በሚካሄድባቸው በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ የተለየውና የሚያስደምመው ነገር መላው ሠራተኞች አፍሪካውያን መሆናቸው ነው። "ናሙናውን ከሚሰበስቡት ጥናትና ምርምር እስከሚያደርጉት ባለሙያዎች በሙሉ አፍሪካውያን ነን" ትላለች። ጨምራም ማዕከላቱ አሜሪካ ውስጥ ካሉት አቻ ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ "ለጊዜው ወደ ክትባት የሚያመሩት ሥራዎች በአሜሪካ እየተሠሩ ቢሆንም ሥራው በትብብር የሚሠራ በመሆኑ ጥረቱ ፍሬያማ ቢሆን የሁሉንም ድርጅቶች ስም የሚያስጠራ የጋራ ውጤት ነው" በማለት ትገልጻለች። ባለንበት ዘመን መላውን ዓለም ያስጨነቀውን የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት በአፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን ጥረት ከሚያስተባብሩት ባለሙያዎች መካከል አንዷ የሆነችው ምህረት ወደ ሳይንሱ ትምህርት እንድታዘነብል የወላጆቿ ግፊት ወሳኝ ሚና እንደነበረው ታምናለች። ምህረት በመጀመሪያ የሕክምና ዶክተር የመሆን ፍላጎት ኖሯት ተነስታ ከዘርፉ ሳትርቅ በመካከል ላይ ግን በዶክተርነት ማዕረግ ወደ የላቦራቶሪው ዘርፍ ልቧ ማዘንበሉን ትናገራለች። "በማይክሮስኮፕ ውስጥ የሚታየውን ዓለም የማየት ዕድሉን ካገኘሁበት ጊዜ አንስቶ ከሕክምና ወደ ላቦራቶሪ ሥራው ገብቼ ለዓመታት ቆይቻለሁ" በማለት ጅማሬዋን ታስታውሳለች። በዘርፉ ሴቶችን የሚያበረታታ ነገር እንዳልነበረ የምትናገረው በጀመረችው ለመግፋት አላመነታችም ነበረ "ምንም ነገር፤ ማድረግ ከምፈልገው ነገር እንዲገታኝ አልፈቅድም" የምትለው ምህረት ህልሟን ለማሳካት ወደ ዘርፉ ማኔጅመንት እንድታዘነብል እንዳደረጋት ትናገራለች። ይህንን ለውጥ ለማድረግ እየተዘጋጀች በነበረችበት ወቅት ውሳኔዋን ያወቁ ባልደረቦቿ በነበረችበት የላቦራቶሪ ሥራ ላይ እንድትቆይ ይመክሯት እንደነበር የምትናገረው ምህረት እሷ ግን ፍላጎቷን እውን ለማድረግ በውሳኔዋ መፅናቷን ታስረዳለች። ምህረት ለዘርፉ የሚያስፈልጋትን ትምህርቷን [ኤም.ቢ.ኤ] አጠናቃ አሁን እየመራችው ባለው የጥናትና ምርምር ሥራ ውስጥ መገኘቷ በጣም ደስተኛ እንዳደረጋት በኩራት ትናገራለች። "ወደ ትምህርት ተመልሼ ለመማር ስወስን ልጅ እያሳደኩኝ ነበረ። ሁኔታው በተወሰነ ደረጃ ፈታኝ ቢሆንም የማይቻል ሆኖ አላገኘሁትም" በማለት ሴቶች በተለያዩ ኃላፊነቶች ውስጥ ሆነው እንኳን ያሰቡትን ማሳካት እንደሚችሉ የእራሷን ተሞክሮ በመጥቀስ የደረሰችበትን ታወሳለች። ወደፊት ደግሞ "ብችል ለአፍሪካ እድገት አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ የተለያዩ ሥራዎችን መሥራት እመኛለሁ" የምትለው ምህረት፤ "ሲጀመር አሁን የምሠራበትን ድርጅት የተቀልቀልኩት ቀስ በቀስ ወደ አገር ቤት እንዲወስደኝ በማሰብ ነው" ትላለች። ምህረት በትምህርቷና በሥራዋ ያሳካችውን ህልሟን በማስፋት አሁን ደግሞ ሌላ ህልም ሰንቃ በቀጣይ ለአህጉሯ አፍሪካ የተለያዩ ነገሮችን የማበርከት ዕቅድ ይዛለች። "ከጊዜ ጋር ለአፍሪካ የማበረክታቸ ብዙ ነገሮች እንደሚኖሩ ተስፋ አለኝ" ስትል ምህረት አማረ በነገ ዕቅዷ ላይ ትኩረት አድርጋለች። ምን ይዛ ትመጣ ይሆን?
48768098
https://www.bbc.com/amharic/48768098
"ከጄ/ል አሳምነው ጋ በምንም ጉዳይ ያወራሁበት አጋጣሚ የለም" እስክንድር ነጋ
ቅዳሜ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት አባላት እየታሰሩ እንደሆነ ጋዜጠኛና የመብት ታጋይ እስክንድር ነጋ ገልጿል። በዚህ ጉዳይ ላይ ቢቢሲ ከእስክንድር ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል። ቢቢሲ፦ የባልደራስ አባላት ታስረዋል የሚባል መረጃ አለ ምን ያህል እውነት ነው?
እስክንድር፦የባላደራው ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከሆነው ስንታየሁ ቸኮል ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ የአመራር አባል የሆኑት በኃይሉ ማሞና መርከቡ ኃይሉ የተለያዩ የአመራር አባላት ታስረዋል፤ እስሩም ቀጥሏል። እኔም ጉዳያቸውን ለማጣራት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሄጄ ሞክሬያለሁ፤ ነገር ግን በወቅታዊ ጉዳዮች ሳቢያ ታስረዋል ከሚል ውጭ ምንም ዓይነት መረጃ የሚሰጠኝ ሰው አላገኘሁም። የታሰሩት እዛው አዲስ አበባ ውስጥ ነው። ቢቢሲ፦ እስክንድር ታስሯል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነበር። የባህርዳር ቆይታህን ልትነግረን ትችላለህ? •የጄኔራሎቹና የአዴፓ አመራሮች ግድያ፡ እውነቱን ማን ይንገረን? •ከሃገር እንዳይወጣ ተከልክሎ የነበረው እስክንድር ነጋ እገዳው ተነሳለት እስክንድር፦ እሑድ ዕለት ሕዝባዊ ስብሰባ ስለነበረን ወደ ባህርዳር የሄድኩት ቅዳሜ 11 ሰዓት አካባቢ ነበር፤ ስብሰባው እሑድ ነበር፤ የአምሳ ደቂቃ በረራ ናት፤ አየር ላይ በነበርኩበት ሰዓት ነው ይሄ የተከሰተው። አውሮፕላኑ ሲያርፍ ይሄ ነገር ተከስቶ ነው የጠበቀኝ፤ ወደ ውጭ መውጣትም ስላልቻልኩኝ "ለደህንነትህ" ብለው እዛው አየር ማረፊያ ነው ያደርኩት። እዚያው እንድናድር የተደረገው የአዲስ አበባ ባልደራስ ምክር ቤት አባላት ብቻ ነን። እሑድ ግን ማን እንደከለከለ ባናውቅም ተመልሰን ወደ አዲስ አበባ በአየር እንዳንሄድ ተከልክለናል። በኋላ መመለስ ትችላለችሁ ተብለን ተጨማሪ ገንዘብ ከፍለን፤ ትኬት ገዝተናል፤ ፍተሻ አልፈን፣ ከገባን በኋላ አውሮፕላን ልንገባ ስንል አትሄዱም ተብለን ተጠርተን ተመልሰናል። እዛው ኤርፖርት የተወሰነ ጊዜ ከተቀመጥን በኋላ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ባትችሉም ወደ ባሕር ዳር መግባት ትችላላችሁ ተባልን። ከዚያ በኋላ ወደ ባህርዳር ከተማ ገብተን 30 ደቂቃም ሳንቆይ ተለያየን። እኔና ስንታየሁ በመኪና ወደ አዲስ አበባ ተመልሰናል። እኛ ከተመለስን በኋላ ግን ሌሎች ሦስት አባላት በአየር እንዲመለሱ ተፈቅዶላቸው በአየር ተመልሰዋል። የአዲስ አበባ ጉዟችን አስቸጋሪ ነበር፤ 22 ሰዓት ሳያቋርጥ ያለምንም እረፍት መንገድ ላይ ቆይተን ነው አዲስ አበባ የገባነው። ዝርዝር ውስጥ አልገባም፤ ግን በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ተጉዘን ነው ዛሬ ሌሊት 10፡30 ሰዓት የገባነው። ጠዋት ላይ ስንታየሁና ሌሎች አባላት ተይዘዋል። •"ቤቶች ከመፍረሳቸው በፊት ዜጎች መጠለያ የማግኘት መብታቸው መከበር አለበት" ባለአደራ ምክር ቤት ቢቢሲ፦ ባህርዳር አየር ማረፊያ በነበራችሁበት ወቅት አዲስ አበባና ባህር ዳር እየሆነ ስላለው ነገር መረጃ ታገኙ ነበር? እስክንድር፦ አዎ እዚያው ሎቢ ወስጥ ቴሌቪዥን ስለነበር። ቢቢሲ፦ ጀኔራል አሳምነው ጋር አውርታችኋል ወይ? ንግግር ነበራችሁ ወይ? ምክንያቱም በአማራ ክልል አስተዳደር ውስጥ ለናንተ ሕዝባዊ ስብሰባ ፍቃድ ይሰጥ ወይስ አይሰጥ የሚል ልዩነት ነበር የሚል ነገር ስለሚወራ ነው። እስክንድር፦ አላወራንም። በፍጹም፤ እኔ እኮ ተጋባዥ ነኝ። የጋበዘኝ ባሕርዳር ውስጥ ያለ ኮሚቴ አለ። ለዚያ ነው የሄድኩት፤ አዘጋጅ ስላልሆንኩ ስለስብሰባው የማስፈቅደው ነገር የለም። እኔንም ከእሳቸው ጋር ሊያገናኘን የሚችል ቅንጣት ነገር የለም። ከጄኔራሉ ጋ ተገናኝቼ በምንም ጉዳይ ያወራሁበት አጋጣሚ የለም። እዚያ ላይ የተፈጠረው ነገር ፓርቲው ላይ የተፈጠረ ነው። ይህን አሳቦ እኛን ማሳደድ ግን ተገቢም አይደለም፤ ፍትሃዊም አይደለም። ቢቢሲ፦ መንግስት አጋጣሚውን በመጠቀም እያጠቃን ነው ብለህ ታምናለህ? እስክንድር፦በግልጽ እየታየ ነው እኮ። እኛን ከዚህ ጉዳይ ጋር የምንገናኝበት ቅንጣት ታክል ግንኙነት የለም። ቅንጣት ታክል ነው የምልህ። አጠቃላይ ፓርቲው ጋር የተፈጠረ ነገር ነው። እኛ እንኳን አሁን እና ድሮም በጨለማው ዘመን በሰላማዊ መንገድ ነው ስንታገል የነበረው። አሁንም ተልዕኮ የሰጠን ሕዝብ በዚሁ እንድንቀጥል ነው የሚፈቅድልን። ለተፈጠረው ችግር የፓርቲው ሰዎች ማብራሪያ እየሰጡ ነው። እነሱን ማዳመጥ ነው። የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም ጉዳዩን በዝርዘር ለህዝብ አቅርበዋል፤ እነሱን መከታተል ብቻ ተጨማሪ መረጃ ሳያስፈልግ ጉዳዩን መረዳት ይቻላል። እኛን ቅንጣት ታህል ከዚህ ጉዳይ ጋ የሚያገናኘን ነገር የለም። ይህ ግልጽ በሆነበት ሁኔታ እኛን በዚህ አሳቦ ለእስር መዳረግ ኢፍትሃዊ ነው። ቢቢሲ፦እስክንድር በግልህ አደጋ ይደርስብኛል ብለህ ትሰጋለህ? በመንግስት በኩልስ ጥበቃ ይደረግልሃል? እስክንድር፦በመንግስት በኩል ጥበቃ አይደረግልኝም፤ አልፈልግምም። ጥበቃ የሚያስፈልገኝ ሰውም አይደለሁም። እኔ ሙሉ ለሙሉ ጠባቂዬ እግዚአብሔር ነው ብዬ ስለማምን። በተለያየ አጋጣሚ ከፍተኛ አደጋ አለ። ሌላው ቀርቶ መንገድ ስንመጣ እጅግ አስጊ ነገሮችን አይተናል። ስጋቶች የሉብኝም፤ ምንም አይሰማኝም ብዬ ብናገር ትክክል አይሆንም፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች በቪዲዮ ጭምር የሚሆነውን ታያለህ፤ አሁን ደግሞ የእስር እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ከዚህ ከዚህ አኳያ ምንም አይሰማኝም ልልህ አልችልም፤ ሰው ነኝ፤ የልጅ አባት ነኝ፤ ሚስት አለኝ፤ ቤተሰብ አለኝ፤ ቢያንስ ለነርሱ ለቤተሰቤ ብዬ ለህይዎቴ ዋጋ እሰጣለሁ፤ ከዚያ ባለፈ ግን ጥበቃ አያስፈልገኝም። ቢቢሲ፦ምናልባት እንቅስቃሴህን መገደብ እንዳለብህ ይሰማሃል፤ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር? እስክንድር፦ ምን አጠፋንና ነው ረገብ ማለት የሚያስፈልገን? ወደ ኃይል እርምጃ አልገባን? ወይም ሰላም የሚያደፈርስ ነገር አልሰራን? አቋም መወሰድ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ግን አቋም እንወስዳለን። ከእውነት ጋር እንሞግታለን። ከዚህ በፊትም እኮ ከእውነት ጋር ወግነን ነው ዋጋ የከፈልነው። አሁንም ከእውነት ጋር መወገን ዋጋ የሚያስከፍል ከሆነ ዋጋ እንከፍላለን። ቀይ መስመር አለ፤ እሱን አናልፍም። ሰላማዊ ነን። እንኳን የኃይል ርምጃ ልንወስድ ጠጠር እንኳ አንወረውርም። ይሄንን እንዴት ማለዘብ እንደሚቻል እኔ አይገባኝም።
news-57278890
https://www.bbc.com/amharic/news-57278890
[ምልከታ] በትግራይ የዘር ጭፍጨፋ ክሶችና የረሃብ ስጋት
ከሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በትግራይ የዘር ጭፍጨፋ እየተፈጸመ ነው ማለታቸው ብዙዎችን አነጋግሯል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የትግራይ ተወላጁ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፤ ጥቅምት ላይ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና በህወሓት ኃይሎች መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ "እንዳልናገር ድምጼ ታፍኖ ነበር። በፍርሃት መናገር አልቻልኩም ነበር" ብለዋል። በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለው ሰቆቃ የአቡነ ማቲያስን እንዲሁም የበርካታ የትግራይ ተወላጆችን ልብ ሰብሯል። በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ዳያስፓራዎች በተለያዩ አገራት መዲናዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። በተጨማሪም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ንቅናቄ በማድረግ "የዘር ጭፍጨፋ እየተፈጸመ ነው" ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በጅምላ ጥቃት ተፈጽሟል የሚለውን ክስ የተጋነነና ፖለቲካዊ መነሻ ያለው ሲል ያጣጥላል። ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከተናገሩ በኋላ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባልተለመደ መልኩ ቅዱስ ሲኖዶሱ ራሱን ከፓትርያርኩ ንግግር ገሸሽ አድርጓል። የዘር ጭፍጨፋ ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ነው። በርካቶችን እጅግ ከማስቆጣቱ ባሻገር የዘር ጭፍጨፋ ሲፈጸም በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቁ ተሟጋቾችም አሉ። ይህ ልዩ እርምጃ የዘር ጭፍጨፋን ለማስቆም ወታደር መላክን ይጨምራል። የዘር ጭፍጨፋ የሚለውን ቃል የፈጠሩት የአይሁድ ተወላጁ ፖላንዳዊ ጠበቃ ራፋኤል ለምኪን ናቸው። ቃሉን ጥቅም ላይ ያዋሉት አሰቃቂውን የናዚ ጭፍጨፋ ለመግለጽ ነበር። የተባበሩት መንግሥታት እአአ በ1948 የዘር ጭፍጨፋ ስምምነትን ሲያጸድቅ በዓለም አቀፍ መዛግብት ውስጥ መጠቀስ ጀምሯል። የጥላቻ ንግግር የናዚ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በኑረንበርግ ለፍርድ ሲቀርቡ ዐቃቤ ሕግ የከሰሳቸው ሰብዓዊ መብትን በገፈፉ ወንጀሎች ነው። ይህ ማለት በመንግሥት ወይም እንደ መንግሥት ባለ መዋቅር በስልታዊ ሁኔታ የሰዎች መብት ተጥሷል ማለት ነው። የዘር ጭፍጨፋ ሲተረጎም የጥቃት አድራሹ ኢላማ ከግምት ይገባል። ይህም ጥቃት አድራሹ "የአንድን አገር፣ ብሔር፣ ዘር ወይም ሐይማኖት አባላት በሙሉ ወይም በከፊል ለማጥፋት ሲነሳ" ማለት ነው። እስካሁን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በትግራይ ሰብዓዊ ወንጀሎች መፈጸማቸውን ሪፖርት አድርገዋል። ይህ ሊለወጥ ይችላል። አንዳንድ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን፤ ህወሓት ፈጽሟቸዋል የሚባሉ ወንጀሎችን በሙሉ የትግራይ ሕዝብ ላይ በማላከክ እና የሚያንቋሽሽ ቃል በመጠቀም ለትግራይ ተወላጆች ጥላቻ አሳይተዋል። "የቀን ጅብ" የመሰሉ ቃላት ሕዝቡ ላይ ጥላቻን ለመፍጠር ውለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ህወሓት በመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ሰፊውን ድርሻ ይዞ ዘልቋል። በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል የነበረው መካረር ጫፍ የነካው የብሔራዊ ምርጫ ቀን ሲዛወር በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ሲካሄድ ነው። ይህ መካረር ተባብሶ ጥቅምት ላይ ሁለቱ ኃይሎች ወደ ጦርነት አምርተዋል። የትግራይ ተወላጆች መከላከያ ሠራዊቱን ጨምሮ ከተለያዩ የመንግሥት ሥራ እየተባረሩ እንደተባረሩ ሪፖርቶች ወጥተዋል። እንቅስቃሴያቸው፣ መኖሪያቸው እና ንግዳቸው እንደታገደም ተገልጿል። እነዚህ ክሶች ግድያን፣ መድፈርንና የማስራብን ያህል ባይሆኑም የዘር ጭፍጨፋ እየተካሄደ ነው ለሚል ክስ መነሻ ይሆናሉ። በትግራይ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል የሚሉ ክሶች ከሁሉም አቅጣጫዎች ተሰምተዋል። በትግራዩ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታች ይነገራል የዘር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል የሚል ውሳኔ ሊሰጥ የሚችለው በከፍተኛ ደረጃ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ፍርድ ነው። ፍርድ ቤቱ ይህንን ጉዳይ ሊመለከት የሚችለው በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ነው። ምክር ቤቱ ላይ አፍሪካ ያሳደረችውን ጥርጣሬ እንዲሁም የቻይና እና የሩሲያን ተቃውሞ ከግምት በማስገባት ግን ይህ ውሳኔ የሚተላለፍ አይመስልም። በዘር ጭፍጨፋ የተፈረደበት የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪ የሌላ አገር ዜግነት ያለው አንድ ኢትዮጵያዊ በወንጀል ሊከሰስ፣ ሊፈረድበትም ይችላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የማሰር መብት ባላቸው እንደ ፈረንሳይ እና ቤልጅየም ባሉ አገራት የእስር ማዘዣ ሊወጣበትም ይችላል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በዘር ጭፍጨፋ ተጠያቂን ወንጅላለች። የአገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ከ"ፖለቲካ ቡድኖች" ውጪ ያሉትን በዘር ጭፍጨፋ ያካትታል። ይህ ጥያቄ ማጫሩ አይቀርም። ኢትዮጵያ የተጠቀመችው ራፋኤል ለምኪን ለተባበሩት መንግሥታት የጻፋቸውን ቆየት ያሉ ማጣቀሻቆች ናቸው። ይህም ሶቭየት ሕብረት የፖለቲካ ቡድኖችን ኢላማ ማድረግ በተባበሩት መንግሥታት የዘር ጭፍጨፋ ስምምነት መካተት የለበትም በሚል የተከራከረችበት ወቅት ነው። ምግብ መከልከል አንድ የዘር ጭፍጨፋ መንገድ ነው ይላሉ። 'አክሲስ ሩል' በተባለው መጽሐፋቸው ከናዚዎች የጋዝ ቻምበርና ገዳይ ቡድን በበለጠ የምግብ መጠን ከመቀነስ ምግብ ወደ መከልከል ስለተሻገረው የናዚ እርምጃ ጽፈዋል። በእንግሊዘኛው 'ስታርቬሽን ክራይምስ' የሚባለው ሆነ ብሎ ሰውን የማስራብ ወንጀልን ይገልጻል። ቃሉን መጀመሪያ ላይ የተጠቀሙት ብሪጅት ኮንሊይ ይባላሉ። ቃሉ የሚገልጸው፤ ረሀብን እንደ ጦርነት መሣሪያ፣ እንደ ጭቆና መንገድ ወይም ሰዎችን ለመቅጣት መጠቀምን ነው። የተባበሩት መንግሥታት፣ አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ባለፈው ሳምንት ባወጡት መግለጫ፤ በትግራይ አስጊ ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል። ይህ ቀውስ የዝርፊያ፣ በግዳጅ የማፈናቀል እንዲሁም ምግብ፣ ውሃ እና የጤና አገልግሎትን የመግታት ውጤት ነው። በተጨማሪም መደፈር የደረሰባቸው ሴቶች ራሳቸውን እና ልጆቻቸውን መንከባከብ ያለመቻላቸው እና ሰብዓዊ እርዳታ የመገታቱም ማሳያ ነው። ከሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ተፈናቅለዋል ከ30 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ የመንግሥቱ ኃይለማርያም ዘመን ባለሥልጣናትን በልዩ ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ አቅርባለች። የፖለቲካ ግድያ ክስ በዘር ጭፍጨፋ እንዲታይ ተወስኖም ነበር። ዋነኛ ትኩረቱ አገዛዙ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን በፖለቲካ አቋማቸው የረሸነበት "ቀይ ሽብር" ነበር። መንግሥቱ ኃይለማርያም በሌሉበት በዘር ጭፍጨፋ የተፈረደባቸው ይህ አሰቃቂ ወንጀል ከተፈጸመ ከ40 ዓመታት በኋላ ነበር። የመብት ተሟጋቾች ፍርድ ቤት ውሳኔ እስከሚሰጥ መጠበቅ አይሹም። ለዘር ጭፍጨፋ ማስረጃ ተጠናቅሮ እስከሚቀርብ ድረስ የሰዎች ሕይወት ይቀጠፋል። ይህንን ከግምት በማስገባት የመብት ተሟጋቾች እና ዲፕሎማቶች ብሔር ተኮር ግድያ የሚገለጽበት መንገድ ፈጥረዋል። እአአ በ1990 ዩጎዝላቪያ ስትበተን ዘር ማጥፋት የሚል ቃል ጥቅም ላይ ውሎ ነበር። ይህ ቃል በሕግ የተደነገገ አይደለም። የዘር ጭፍጨፋ ውስጥ ያሉና ዘር ማጥፋትንም የሚገልጹ ድርጊቶች አሉ። እነዚህም ቡድን ለይቶ መግደል፣ መድፈር እና ማፈናቀል ናቸው። ከወራት በፊት በአሜሪካ የወጣ ሪፖርት በትግራይ "ዘር ማጥፋት እየተፈጸመ ነው" ብሏል። ከዩጎዝላቪያ ጦርነት አሥር ዓመታት በኋላ የአሜሪካ የጦር ወንጀሎች ልዩ ቃል አቀባይ ዴቪድ ሸፈር በእንግሊዘኛ 'አትሮሲቲ ክራይምስ' የሚል ቃል መስርተዋል። ይህን ያደረጉት አንድ ቡድን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የዘር ጭፍጨፋ ነው ወይስ አይደለም? ከሚለው የሕግ ክርክር ለመውጣት ነው። "መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የዘር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል ወይም እየተፈጸመ ነው የሚል የሕግ ውሳኔ እስከሚተላለፍ ድረስ እርምጃ ከመውሰድ መታቀብ የለባቸውም" ሲሉ ያስረዳሉ። በአንድ አገር አውድ ትርጉም የሚሰጥና አንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሚሰነዘርበትም ጊዜ አለ። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋል ነው። በክልሎች መካከል የሚገኝ ድንበር እንዲሁም በየክልሉ የሚኖሩ የሌላ ብሔር ተወላጆች ጉዳይ ለዚህ እንደ ምክንያት ይጠቀሳል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሞ፣ አማራ፣ ሶማሊ እና ጉምዝ ማኅበረሰቦች ዘንድ ይህ ግጭት በስፋት እየታየ ነው። የእነዚህ ማኅበረሰቦች ቃል አቀባዮች የዘር ጭፍጨፋ እየተፈጸመ ነው ሲሉ ይከሳሉ። የዘር ጭፍጨፋ እየተፈጸመ ነው ማለት አንቂ ደውል ይሁን እንጂ ይህ እርምጃ ይወሰድ አይልም። በ2004 ዳርፉር ውስጥ የዘር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል የሚል ዓለም አቀፍ ንቅናቄ ነበር። የመብት ተሟጋቾቹ ያሰቡት የዘር ጭፍጨፋ መፈጸሙን መንግሥት ካመነ ወታደሮች እንደሚላኩ ነው። አንድ ተቃዋሚ በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ ላይ "ከኢራቅ ውጡ፤ ዳርፉር ግቡ!" የሚል መፈክር አስነብቧል። ነገር ግን ይህንን ማድረግ ግዴታ አይደለም። የአሜሪካ ምርመራ የሱዳን መከላከያ እና የጃንጃዊድ ሚሊሻ የዘር ጭፍጨፋ መፈጸማቸውን ግን ያሳያል። የያኔው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የምርመራውን ውጤት ቢቀበሉም ግኝቱ የአሜሪካን ፖሊሲ እንደማይለውጥ አስታውቀዋል። ይህ ፖሊሲ ሰብዓዊ እርዳታ እና ሰላም የማስጠበቅ ተልዕኮ ላይ ያተኮረ ነው። ዳርፉር ውስጥ በርካታ ሰዎች አሁን ድረስ ፍትህን የጠበቁ ነው የዘር ጭፍጨፋ ክርክሮች ዳርፉር ውስጥ የዘር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም የሚለው ክርክር፤ እልቂቱን ለማስቆም መወሰድ የሚገባውን እርምጃ አጓቷል። አሜሪካ የተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ ነው ስትል የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ መርማሪ ግን የዘር ጭፍጨፋ አላለውም። የተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ የሱዳንን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አስደስቷል። የተባበሩት መንግሥታት "ከዘር ጭፍጨፋ ያልተናነሰ ወንጀል ተፈጽሟል" ቢልም እንኳን ለዚህ ገለጻ እምብዛም ትኩረት አልተሰጠውም። ኋላ ላይ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዘዳንት ኦማር አልበሽር ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል። አልበሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ በሱዳን አመራሮች ታስረዋል። ለፍርድ ቤቱ ተላልፈው ግን አልተሰጡም። የሚሊሻ መሪው አሊ አብደል ራህማን "ኩሻይብ" ላይ በ31 የጦር ወንጀል እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክሶች የፍርድ ሂደት ቢከፈትም በዘር ጭፍጨፋ አልተከሰሰም። አልበሽር በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ከሆነ ዐቃቤ ሕግ በዘር ጭፍጨፋ ለመክሰስ መወሰን አለበት። አሁን በዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ሥልጣን ላይ ያሉት በዳርፉር እና በዩጎዝላቪያ የዘር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም የሚለውና ጠባሳ ትቶ ያለፈውን ክርክር ያራመዱ ሰዎች ናቸው። ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ትግራይ ከዳርፉር ጋር እየተነጻጸረች ነበር። አንድ ባለሥልጣን እንዳሉት፤ ቀውሱን ማስቆም ባልቻሉ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የፋይናንስ ማዕቀብ ለመጣል እቅድ አለ። ቀውሱ፤ ሰብዓዊ ወንጀል ስለመሆኑ ለማጣራት ምርመራ እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል። ሆኖም ግን የዘር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል ወይስ አልተፈጸመም የሚለውን ለመፈተሽ እምብዛም ፍላጎት የለም። ይህም ለችግሩ መፍትሔ ከማበጀት ይልቅ ነገሮችን ወደማባባስ ላለመውሰድ በመፍራት ይሆናል። *የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ አሌክስ ደዋል በአሜሪካው ተፍትስ ዩኒቨርስቲ በሚገኘው የፍሌቸር የሕግ እና ዲፕሎማሲ ትምህርት ቤት ውስጥ የወርልድ ፒስ ፋውንዴሽን ዋና ዳይሬክተር ናቸው። ኢትዮጵያን እንዲሁም ሌሎች የአፍሪካ አገራትን የሚዳስሱ የትንተና ጽሑፎቻቸው ያዘጋጃሉ።
48605407
https://www.bbc.com/amharic/48605407
ኢትዮቴሌኮም ኢንተርኔት ለምን እንደተቋረጠ መግለፅ እንደማይችል አስታወቀ
በትናንትናው ዕለት የተቋረጠው ኢንተርኔት ወደ አመሻሹ ላይ ቢመለስም ሌሊት እንዲሁም ጠዋት ላይ ተቋርጦ ነበር። ኢንተርኔት የተቋረጠበትን ምክንያት ለመረዳት ቢቢሲ የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሪት ጨረር አክሊሉን ጠይቋል። እሳቸውም ኢንተርኔት መቋረጡን አምነው ምክንያቱን ግን ኢትዮ ቴሌኮም መግለፅ እንደማይችል አስረድተዋል።
"ምናልባት ሌላ አካል ምክንያቱን ሊገልፀው ይችል ይሆናል። ይሄ ነው ብለን መግለፅ የምንችለው አይደለም" ብለዋል •በኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ተመለሰ •ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በደንበኞች ላይ የሚያደርሰው እንግልት ያሳዘናቸው መሆኑን ገልፀው ይቅርታ የጠየቁት ወይዘሪት ጨረር፤ እንደ አገልግሎት ሰጪም ኩባንያው ላይ የሚፈጥረው ተፅእኖ ቀላል እንዳልሆነ ተናግረዋል። ነገር ግን ኢንተርኔት አገልግሎት የሚቋረጠው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያትና ሌላ አማራጭ ሳይኖር ሲቀር ነው ይላሉ። "እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው መቋረጡ ከዚህ ከሚያመጣው መስተጓጎል በበለጠ ችግር ሲኖርና ሃገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ነው እንዲህ አይነት ውሳኔ የሚተላለፈው፤ ያው ከሃገር ጥቅም የሚበልጥ ጉዳይ የለም" ብለዋል። •ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በመበደል ከዓለም ቀዳሚ ሃገራት አንዷ ነች ተባለ የሳይበር ደህንነትንና በዓለም ላይ የኢንተርኔትን ስርጭት የሚቆጣጠረው ኔት ብሎክስ የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በትናትንናው ዕለት እንዲሁም ዛሬ ጥዋት አገሪቷ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት መቋረጡን በትዊተር ገፁ ያሰፈረ ሲሆን እንደ ምክንያትም የጠቀሰው በትናንትናው ዕለት በተጀመረውን ሃገር አቀፍ ፈተና ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ማጭበርበሮችን ለመከላከል እንደሆነ ነው። ምንም እንኳን በብዙ አካላት ዘንድ ሀገር አቀፍ ፈተና ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ማጭበርበሮችን ለመቆጣጠር ነው የሚሉ ምክንያቶች ቢሰጡም ወይዘሪት ጨረር "ምክንያቱ ይህ ነው አልልም፤ በደፈናው በሃገር አቀፍ ፈተና ነው የሚል ምክንያት መስጠት አስቸጋሪ ነው" ይላሉ። በአሁኑ ወቅት ምን እንደተፈጠረ ይህ ነው የሚል ምክንያት ባይሰጡም ለወደፊት እንደሚገለፅ ተስፋ አላቸው።
news-45728981
https://www.bbc.com/amharic/news-45728981
ትራምፕ "በአሜሪካ ለወጣቶች አስፈሪና ፈታኝ ጊዜ ነው"
ትራምፕ በአሜሪካ ጊዜው ለወጣቶች አስፈሪና ፈታኝ ነው አሉ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት አሁን ወቅቱ ለወጣቶች አስፈሪና አስቸጋሪ ጊዜ ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በዋይት ሐውስ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። • የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ወሲባዊ ጥቃት አላደረስኩም አሉ • ቢል ኮዝቢ ወደ ዘብጥያ ወረዱ •የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች "ሕይወቴን በሙሉ ስሰማ የኖርኩት 'ጥፋተኛ መሆንህ እስካልተረጋገጠ ድረስ ነፃ ነህ ' የሚለውን ነው፤ አሁን ግን 'ንፁህ መሆንህ እስኪረጋገጥ ድረስ ወንጀለኛ ነህ'፤ ይህ ደግሞ በጣም በጣም አስቸጋሪ ፍረጃ ነው" ብለዋል። "በአሜሪካ ወጣቶች ላላጠፉት ጥፋት ወንጀለኛ ሆኖ መገኘት ፈታኝ ጊዜ ነው" ይህ የትራምፕ አስተያየት የተሰማው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ሹመት በእጩነት ያቀረቧቸውና በወሲብ ቅሌት ለተጠረጠሩት ብሬት ካቫናህ ያላቸውን ድጋፍ በድጋሚ በገለፁበት ወቅት ነው። ዳኛ ካቫናይ ላይ የሚሰጠው ድምፅ የዘገየው እርሳቸው የካዱትን የወሲብ ቅሌት ተግባር ኤፍ ቢ አይ እያጣራ በመሆኑ ነው። ትራምፕ የሀገሪቱ ሃገሪቱ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሹመቱን እንደሚያፀድቀው ሙሉ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል። ይህ ሹመት ከፀደቀ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድቤት ስልጣን ለረጅም ዓመታት በወግ አጥባቂዎቹ እጅ ይቆያል ማለት ነው። ፕሬዝዳንቱ የኤፍ ቢ አይ የምርመራ ውጤትን እየጠበቁ መሆኑን ገልፀው ምንም ዓይነት ነገር ማቋረጥ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። • ከጥንት ሮማውያን እስከ ትዊተር የደረሰው የ# ምልክት • አቶ ጌታቸው አሰፋ የሀዋሳውን ጉባኤ ይታደማሉ?
news-52825882
https://www.bbc.com/amharic/news-52825882
“ኢትዮጵያ ክትባቱ ሲገኝ ተጠቃሚነቷን ማረጋገጥ አለባት” ዶ/ር ኢዮብ ገብረመስቀል
ኮሮናቫይረስ የበርካቶቻችን አኗኗር ከለወጠ ሦስት ወር አልፎታል። የዓለም ልሂቃን ለበሽታው ክትባት ወይም መድኃኒት ለማግኘት ቀን ከሌት መመራመራቸውን ቀጥለዋል።
ዶ/ር ኢዮብ ገብረመስቀል አንዳንድ አገራት ለበሽታው ይሆናል ብለው ያመኑትን ክትባት በተለያየ ደረጃ እየሞከሩ ነው። ቢሆንም አሁንም ድረስ ስለ ኮቪድ-19 ያልታወቁ እንዲሁም ገና በምርምር ላይ ያሉ ጉዳዮች በርካታ ናቸው። ለምሳሌ በሽታውን ከመከላከል አቅም (Immunity) ጋር በተያያዘ አጥኚዎች ገና መልስ ያላገኙላቸው ብዙ ጥያቄዎች አሉ። በሽታው ከየት መጣ፣ በሰውነታች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እንዴት ያለ ነው? ዓለም በድህረ ኮሮናቫይረስ ምን ትመስል ይሆን? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎችን በዩናይትድ ኪንግደሟ ለንደን በሚገኘው ክዊንስ ሆስፒታል በድንገተኛ ክፍል ለሚሠሩት ዶ/ር ኢዮብ ገብረመስቀል አቅርበናል። ቫይረሱ ሰውነትን የሚጎዳው እንዴት ነው? ቫይረሱ የሚሰራጭባቸው አራት ዋና ዋና መንገዶች አሉ። በሽታው ያለበት ሰው ሲስል፣ ሲያስነጥስ ወይም ሲተነፍስ ቫይረሱ አየር ላይ በመንሳፈፍ ወደ ሌላ ሰው ይጋባል። ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ሲኖር በሽታው ይተላለፋል። በወረርሽኙ የተያዘ ግለሰብ የነካውን ማንኛውም ቁሳ ቁስ የሚነካ ሰውም ለበሽታው ይጋለጣል። ዶ/ር ኢዮብ እንደሚናገሩት፤ አጥኚዎች እስካሁን ያልደረሱበት ቫይረሱ በደም፣ በሽንትና በአይነ ምድር ስለመተላለፉ ነው። እነዚህ ውስጥ ቫይረሱ እንዳለ ቢታወቅም የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች ስለመሆናቸው ገና እየተጠና ነው። በቫይረሱ የተያዘ ሰው የሚያሳየውን ምልክት በደረጃ እንመልከት፦ ከአንደኛው ቀን እስከ አምስተኛው ቀን- ቫይረሱ በዋነኛነት ወደ ሰውነት የሚገባው በአፍንጫና በአፍ ነው። በአይን የሚገባበት ጊዜም አለ። በእነዚህ ቀናት ቫይረሱ የሚራባው በአፍንጫና በጉሮሮ ውስጥ ነው። የአፍንጫ መታፈን፣ የንፍጥ መንጠባጠብ፣ ትኩሳትና ሌላም የጉንፋን አይነት ምልክት ሊሰማ ይቻላል። የበሽታው ምርመራ ከአፍንጫና ከጉሮሮ በሚወሰድ ናሙና የሚካሄደውም ለዚህ ነው። ከአምስተኛው ቀን እስከ ሰባተኛና አስረኛ ቀን- ቫይረሱ ከአፍንጫና ከጉሮሮ በመተንፈሻ ትቦ በኩል አርጎ ወደ ሳምባ ይወርዳል። በዚህ ወቅት ይደክማል። ሳል ይጀምራል። ትኩሳት ከፍ ይላል፤ ሲብስም ያንቀጠቅጣል። ከአስረኛ ቀን ወዲያ- አደገኛ ወቅት ነው። ቫይረሱ ሳምባ ውስጥ የአየር መቀያየሪያ ወንፊቶች (Alveoli) ያጠቃል። እነዚህ ለመተንፈስ አስፈላጊ የሳምባ አካላት ናቸው። ቫይረሱ አስከትሎም የሰውነት ህዋሳትትን ይወራል። ሰውነት ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚ ቫይረስ ጋር ሲገናኝ አዲስ ስለሚሆንበት እንዴት ማጥፋት እንዳለበት አያውቅም። ግን ቫይረሱን ይወጋል። ይህ ሳምባ ውስጥ የሚደረገው ትግል አንዳንዶችን ሕይወታቸውን ያሳጣል። • በአፍሪካ ስላለው የኮሮናቫይረስ ዘገምተኛ አካሄድ ምን ማለት ይቻላል? • 'ጨለምተኛው' ፕሮፌሰር "ዓለም ለ10 ዓመታት ትማቅቃለች" አሉ በመጨረሻ የአየር መቀያየሪያ ወንፊቶች በውሃና በመግል ይሸፈናሉ። ታማሚዎች መተንፈስ ያዳግታቸዋል። አንዳንዶች ኦክስጅን ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ለመተንፈስ የሚረዳ መሣሪያ (Ventilator) አጋዥ ነው። ወንፊቶቹ ሲጎዱ ኦክስጅን በጣም የሚያስፈልጋቸው አዕምሮ፣ ልብ፣ ኩላሊት አቅም ያጣሉ። የልብ መድከም፣ የአዕምሮ መዛል ወይም መወዛገብ፣ ሰመመን፣ ራስን መሳትም ሊከተል ይችላል። ዶ/ር ኢዮብ እንደሚናገሩት፤ ኮሮናቫይረስ በያዛቸው ሰዎች ላይ አዲስ የታየው ነገር በልብና በሳምባ መካከል ያለው የደም ዝውውር መርጋቱ ነው። ይህም እጅግ አደገኛ ነው። ቫይረሱ በተለያዩ ቁሳቁሶች ላይ ለምን ያህል ጊዜ ይኖራል? በሽታው በግንባር ቀደምነት የሚተላለፈው በትንፋሽ ነው። ጉዳት የሚያመጣው የመተንፈሻ ስርዓት ላይ ነው። ስለዚህም ምግብ ስንበላ ጨጓራችን ውስጥ ቢገባ ምንም ችግር እንደማያመጣ ዶክተሩ “ኮሮናቫይረስ ስስ ስለሆነ የጨጓራ አሲዳችን ያሟሟዋል” በማለት ያስረዳሉ። በተለያዩ ቁሳቁሶች ላይ ምን ያህል መቆየት ይችላል የሚለው አሁንም ድረስ እየተጠና ነው። ዶ/ር ኢዮብ እንደሚሉት፤ ከ18 ዓመታት በፊት ተነስቶ የነበረውን የሳርስ በሽታ መነሻ በማድረግ የተሠሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ኮሮናቫይረስ በፕላስቲክና በብረት ላይ እስከ 72 ሰዓት ይቆያል። መዳብ ላይ አራት ሰዓት፣ ካርቶን ላይ 24 ሰዓት፣ መስታወት ላይ አራት ቀን፣ እንጨት ላይ አራት ቀን እና ወረቀት ላይ አራት ቀን ይቆያል። “ስናስልና ስናስነጥስ ደግሞ አየር ላይ ለሦስት ሰዓት ይቆያል” ይላሉ። የሚመከር ምግብ አለ? አንዳንድ የደም አይነት ያላቸውን በበለጠ ያጠቃል የሚባለውስ እውነት ነው? የድንገተኛ ክፍል የህክምና ባለሙያው ዶ/ር ኢዮብ፤ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሚል በተለየ የሚመከር ምግብ ባይኖርም የተመጣጠነ ምግብ ሁሌም ያስፈልጋል ይላሉ። የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ያጎለብታልና። በበሽታው ላለመያዝ እጅን አዘውትሮ መታጠብና አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንዳሉ ሆነው፤ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፍ ራሱን ማግለል ይገባዋል። ለወረርሽኙ በግንባር ቀደምነት ተጋላጭ የሆኑ ስኳር፣ ደም ብዛት፣ የኩላሊት በሽታና ልብ ድካም ያለባቸው ሰዎች ህመማቸውን በአግባቡ መቆጣጠር አለባቸው። • "በኮሮናቫይረስ ምክንያት እናታችንን ተላቅሰን መቅበር ሳንችል ቀረን" • በኮሮናቫይረስ ምክንያት ኢትዮጵያውያን እየተፈተኑባት ያለችው ኢስሊ “የደም ብዛት መድኃኒት መውሰድ፣ የስኳር መጠንን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው። ችላ ካሏቸው ግን ሰውነታቸው ኮሮናቫይረስን ሊከላከል አይችልም።” የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሰው በሚበዛባቸው ቦታዎች ማድረግ የበሽታውን ተጋላጭነት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል። በገበያ ሥፍራ፣ አውቶብስና ታክሲ ላይ፣ በእምነት ተቋማት ጭምብል ማድረግ ይመከራል። በተጨማሪም እንደ አሽከርካሪዎች፣ ነጋዴዎች ያሉና ሥራቸው ከብዙ ሰው ጋር የሚያገናኛቸው፣ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦች ጭምብልና ጓንት እንዲያደርጉ ይመከራል። በሌላ በኩል ለቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጋለጥ የደም አይነት አለ? የሚለው ጥያቄ በበርካቶች ዘንድ ሲናፈስ ነበር። ዶ/ር ኢዮብ፤ “ይህ በሳይንሳዊ መረጃ የተደገፈ አይደለም” ይላሉ። ከ18 ዓመታት በፊት የሳርስ በሽታ ሲሰራጭም መሰል መረጃ ተሰራጭቶ እንደነበር ያስታውሳሉ። ነገር ግን “ሰዎች ይህን ሰምተው የሚያደርጉትን ጥንቃቄ ሊቀንሱ፣ ሊያዘናጉም አይገባም” ሲሉ ይመክራሉ። ኮቪድ-19 ቻይና ውስጥ ሲከሰት ይወጡ የነበሩ መረጃዎች በሽታው በዋናነት እድሜያቸው የገፋ ሰዎችንና የተለያዩ በሽታዎች ያሉባቸውን እንደሚያጠቃ ያሳይ ነበር። አሁን ግን ምንም በሽታ የሌለባቸውንና ወጣቶችንም ማጥቃቱ አስፈሪ እንዳደረገው ሀኪሙ ይገልጻሉ። “በእድሜ የገፉ ማለትም 55 ዓመትና ከዛ በላይ የሆኑ የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። በጠና ሊታመሙ ይችላሉ። እኔ ሳክማቸው የነበሩ የ90 እና 91 ዓመት ሴቶች ሞተዋል። በተለያየ ምክንያት የሰውነት መድህናቸው ዝቅ ያለ (Immunosuppressed) ተጋለጭ ናቸው። ለምሳሌ ኤችአይቪ፣ ካንሰር፣ የቁርጭምጭሚት ህመም፣ የቆዳ በሽታ ያለባቸው ይጠቀሳሉ።” ዶክተር እዮብ ገብረ መስቀል (ከመሃል) ከባልደረቦቻቸው ጋር በበሽታው የተያዙ ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄ ኮቪድ-19 በምጣኔ ኃብት የበለጸጉ አገራትን የጤና ሥርዓት አቃውሷል። ሆስፒታሎች ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ ህሙማን በላይ ያሉባቸው አገራትም ብዙ ናቸው። በሽታው ያልጠናባቸው ሰዎች ራሳቸውን አግልለው በቤት ውስጥ እንዲያገግሙ የሚደረግባቸው ሁኔታዎች አሉ። ይህም በሽታውን ወደ ሌሎች ሰዎች ላለማስተላለፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠይቃል። አንድ ሰው ትኩሳት ሲኖረው፣ ጣዕምና ሽታ የሚለይባቸው ህዋሳት አልሠራ ሲሉት፣ አፍንጫውና ጉሮሮው ሲታፈን፣ የጀርባና የእግር መዳከም ሲሰማው ራሱን ማግለል አለበት። ቢያንስ ለ14 ቀናት መቆየት ይገባዋል። ዶ/ር ኢዮብ እንደሚሉት፤ በ14 ቀን እየተሻለው ወይም በሽታው እየጸናበት ይሄዳል። አንዳንዴ ያገገመ ቢመስልም እስከ 21 እስከ 28 ቀንም ቫይረሱ ሊኖርበት ይችላል። • በየደቂቃው በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ • በአዲስ አበባ ኮሮናቫይረስን የመቆጣጠር እድል አምልጦ ይሆን? “የበሽታው ምልከት ያለው ሰው ጭምብል ማድረግ አለበት። ከቤተሰቡ ጋር ንክኪ ማድረግ የለበትም። ተቀራርበው ረዘም ላለ ጊዜ መቆየት የለባቸውም። በሽታው ያለበት ሰው ከሌለበት ሰው ጋር ከ15 ደቂቃ በላይ ከቆየ በሽታው ሊተላለፍ እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ። እጅ በተደጋጋሚ መታጠብ እና ግለሰቡ የሚጠቀምባቸውን ቁሳቁሶች በሳሙና እና ለብ ባለ ውሃ ማጠብም አስፈላጊ ነው። ቫይረሱ ስስ ነው። ሳሙናና ውሃ ሲነካው ይፈረካከሳል።” ባለሙያው እንደሚናገሩት፤ ብዙ በለይቶ ማቆያ ያሉ ሰዎች ከሰባት ቀን በኋላ ቢሻላቸውም የሚብስባቸውም አሉ። በሽታው የሚብሰውና አደገኛ የሚሆነው ከሰባተኛ እስከ 12ተኛ ባለው ቀን መካከል ነው። ስለዚህ አንድ ሰው በነዚህ ቀናት ውስጥ እየተሻለው ካልመጣ፣ እየተዳከመ ከሄደ በአፋጣኝ ወደ ህክምና መሄድ አለበት። ግለሰቡ ተዳክሞ ወይም የሞት አፋፍ ላይ ደርሶ ወደ ሆስፒታል ከሄደ ሊደረግለት የሚችለው ድጋፍ ውስን ስለሆነ ከሰባት ቀን በኋላ ከፍተኛ ክትትል እንደሚያሻም ያክላሉ። ከበሽታው ማገገም ምን ማለት ነው? በበሽታው የተያዙ ሰዎች በድጋሚ ሊያዙ ይችላሉ ወይስ በሽታውን የመከላከል አቅም (Immunity) ያዳብራሉ? የሚለው ገና ምርምር እየካሄደበት ነው። ዶ/ር ኢዮብ፤ ከሌሎች በሽታዎች በተገኘ እውቀት መሠረት ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ለአጭር ጊዜ በሽታውን የመከላከል አቅም ያዳብራሉ ይላሉ። ሀሳቡን እንዲህ አብራርተውታል. . . “ነገር ግን ለረዥም ጊዜ የሚሆን በሽታን የመከላከል አቅም ይኖራቸዋል ተብሎ አይታሰብም። በክረምት ከሚይዘን ጉንፋን (Seasonal Flu) ጋር ተመሳሳይ ባህሪ አለው። አንድ ሰው በዚህ ዓመት ጉንፋን ከያዘው ብዙ ጊዜ በድጋሚ ጉንፋኑ አይዘውም። ምክንያቱም በዚህ ዓመት ያለው የጉንፋን ቫይረስ ተመሳሳይ ነው። በሚቀጥለው ዓመት ግን ቫይረሱ ይቀየራል። ሰውየው ለሚቀጥለው ዓመት ቫይረስ የሚሆን በሽታ የመከላከል አቅም ስለማይኖረው በበሽታው ይያዛል። ኮሮናቫይረስም ተመሳሳይ ነው የሚል ግምት አለ። ተመራማሪዎች ክትባት ለማግኘት እየተጣጣሩ ያሉት ለዚሁ ነው። ክትባት ሰውነት ሁሌ ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ያደርጋል። Antibody Test [ፀረ እንግዳ አካላት] ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ትግል በከፍተኛ ደረጃ ወደፊት ይወስደዋል።” ኮሮናቫይረስ ይጠፋል? ዓለም በድህረ ኮሮናቫይረስ ምን ትመስል ይሆን? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው። ወረርሽኙ ከምድረ ገፅ ይጠፋል ወይስ አኗኗራችንን እስከወዲያኛው ቀይሮ አብሮን ይኖራል? የሚሉትም መልስ አላገኙም። ዶ/ር ኢዮብ ሌሎች ተመሳሳይ ቫይረሶች እና በሽታዎችን መነሻ አድርገው እንደሚያስረዱት ከሆነ፤ አንድ ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው መተላለፍ ከጀመረ ወይም ከለመደ በኋላ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት አይቻልም። ኮሮናቫይረስ ወቅት ጠብቆ እንደሚመጣ ጉንፋን (Seasonal Flu) ሆኖ ይቆያል። “ሆኖም ግን አሁን የሚያደርስብን አይነት ጉዳት ያደርስብናል የሚል እምነት የለኝም። ምክንያቱን የብዙዎቻችን ሰውነት እየለመደው ይመጣል። ክትባቶችና በድኃኒቶች መፈጠራቸውም አይቀርም” ሲሉ ያብራራሉ። የሰው ልጆችን ሲቀጥፉ የነበሩ በሽታዎች ብዙዎቹን መቆጣጠር ችለናል። በዶክተሩ ገለጻ፤ ባለፈው 20 ዓመት ብቻ ኮሮናቫይረስ ሲከሰት ሦስተኛው ነው። ኮሮናቫይረስ 1፣ ኮሮናቫይረስ 2፣ ሜርስ (Middle East Respiratory Syndrome) መከሰታቸውን ያጣቅሳሉ። ሜርስ ከሌሊት ወፍ በግመሎች አልፎ ሰውን ያጠቃ በሽታ ነው። “እነዚህ ቫይረሶች የመጡበት የሌሊት ወፍ ወደ 500 የሚሆኑ ሌሎች ቫይረሶች አሉት። ከእንስሳ እየዘለሉ ወደ ሰው የሚመጡ ቫይረሶች ወደፊትም ይገጥሙናል።” ከእንቅስቃሴ ገደብ መነሳት በኋላ ዓለም ምን ትመስል ይሆን? Herd Immunity (ኸርድ ኢሚውኒቲ) ምንድን ነው? ለኮሮናቫይረስ ይሠራል? ይህ አንድ በሽታ በማኅበረሰቡ ውስጥ እንዳይሰራጭ በሽታውን የመቋቋም አቅም መገንባት ማለት ነው። በተደጋጋሚ ሲጠቀስ የሚሰማው ኸርድ ኢሚውኒቲ ለኮሮናቫይረስ ይሠራል ወይ? ስንል የጠየቅናቸው ዶ/ር ኢዮብ “መፍትሔ አይሆንም። ፍትሐዊ አይደለም። ያለንበትን ወቅት ያሻግረናል ብዬም አላምንም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እንደ ባለሙያው ማብራሪያ ይህ ማኅበረሰባዊ በሽታ የመከላከል አቅም ሊገነባ የሚችለው በሁለት መንገድ ነው። አንደኛው በክትባት ነው። ለምሳሌ ፖልዮ፣ ፈንጣጣ፣ ኩፍኝን ለመሰሉ በሽታዎች ክትባት በመስጠት በማኅበረሰቡ በሽታው እንዳይሰራጭ ማድረግ ተችሏል። ሁለተኛው መንገድ አንድን ማኅበረሰብ ለበሽታው አጋልጦ፣ ከተጋለጡት ውስጥ የተረፉት ወይም ያልሞቱት በተፈጥሮ በሽታን የመቋቋም አቅም መገንባት ነው። ይህ ለኮቪድ-19 እንደማይሠራ እንዲህ አብራርተውልናል. . . “በሽታው እንደልቡ እንዲፈነጭ በማድረግ፣ ከዛ የተረፈው ማኅበረሰብ ሰውነቱ ጥንካሬ ይገነባል የሚለው አያስኬድም። ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ የሆኑ እድሜያቸው የገፋ፣ ህመም ያለባቸውና በሽታ የመከላከል አቅማቸው የደከመ (Immunosuppressed) ሰዎችን ለይቶ በማስቀመጥ በማኅበረሰቡ ውስጥ ‘ኸርድ ኢሚውኒቲ’ እንዲገነባ ማድረግ መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ይሄ ማለት ኮሮናቫይረስ ማንን እንደሚያጠቃ እውቀት አለን ማለት ነው። ነገር ግን ቫይረሱ አሁን ላይ በሽታ የሌለባቸውን እንዲሁም ወጣቶችን እየገደለ ነው። ብዙ ሰው ያሳጣል። ምጣኔ ኃብታዊ ቀውስም ይፈጥራል። በዓለም ላይ ያለ ማንም መንግሥት እንደ መፍትሔ ቢያቀርበው ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ማለት አይቻልም። ብቸኛው አማራጭ ክትባት ነው።” ተመራማሪዎች ክትባት ወይም መድኃኒት ለማግኘት ተቃርበዋል? ተመራማሪዎች ከፍተኛ መረባረብ ላይ ናቸው። በቀጣይ ሁለት ዓመታት ክትባት ወይም መድኃኒት ከተፈጠረ መልካም ነው ይላሉ ዶ/ር ኢዮብ። ከዚህ ቀደም ክትባት ወይም መድኃኒት የማግኘት ሂደት ከአስር እስከ 15 ዓመታትም ይወስድ ነበር። እስካሁን በፍጥነት የተገኘው ክትባት የኢቦላ ሲሆን፤ አምስት አመት ወስዷል። ኮሮናቫይረስ ግን ይህን ያህል ጊዜ ይወስዳል ተብሎ አይታመንም። “ኮሮናቫይረስ 1 ከኮሮናቫይረስ 2 ጋር ተመሳሰይ ስለሆነና ባለፉት 18 ዓመታት ብዙ የመድኃኒትና ክትባት ጥናቶች ስለተደረጉ ጊዜ አይወስድም የሚል እምነት አለ” ይላሉ። ለኮሮናቫይረስን መድኃኒት ወይም ክትባት ለመፍጠር ለዓለም ጤና ድርጅት ወደ 600 ማመልከቻዎች ገብተዋል። በዘርፉ ጥሩ ሂደት ላይ ካሉ አገሮች ቻይና፣ ጀርመን፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደምና እስራኤልን መጥቀስ ይቻላል። ዶክተሩ አጽንኦት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ክትባት ወይም መድኃኒት ሲገኝ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች በምን ያህል ፍጥነት ይቀርባል የሚለው እንደሆነ ይናገራሉ። “ከኤችአይቪ የተማርነው ነገር መድኃኒት ወይም ክትባት ሲፈጠር አምራቾቹ በኢትዮጵያና በተቀሩት የአፍሪካ አገራት ላይ ከባድ የድርድር ጫና እንደሚፈጥሩ ነው። በኤችአይቪ ጊዜ መድኃኒት እያለ ተከልክለን ነበር። ያኔ የደረሰብን በደል ሊደገም አይገባም” በማለት ይገልጻሉ። ይህ በኮሮናቫይረስ እንዳይደገም፣ ኢትዮጵያና ሌሎችም የአህጉሪቱ አገራት ክትባቱ ሲገኝ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ካሁኑ መዘጋጀት እንዳለባቸውም ያስረግጣሉ። ኢትዮጵያና የክትባቱ ተስፋ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገራት ለበሽታው ክትባት ለማግኘት ምርምር ላይ ናቸው። የተለያዩ የሙከራ ደረጃዎች መታለፋቸውም ይገለጻል። ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የሚመሩት የዓለም ጤና ድርጅት፤ በቫይረሱ ላይ በሚደረጉ ምርምሮችን አገራት እንዲባበሩ ‘Solidarity Trial’ የተባለ አሠራር አለው። በዚህ ከ70 በላይ አገራት በተሳተፉበት መዋቅር ኢትዮጵያውያኑ ፕ/ር ጣሰው ወልደሀና (የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት)፣ ፕ/ር አበባው ፍቃዱ (ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ)፣ ፕ/ር አሸናፊ ታዘበው አማረ (ከጎንደር ዩኒቨርስቲ) መሳተፋቸው ለዶ/ር ኢዮብ ተስፋ ይሰጣቸዋል። “ድምጻችን እንዲሰማ፣ ክትባት ሲገኝ ተጠቃሚ እንድንሆንም ያደርጋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ክትባት ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ያበረታታል።” ይላሉ። ኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀትን ከዘመነኛው ሳይንስ ጋር በማጣመር ክትባቱን ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ያክላሉ። የተራቀቀ የጤና ተቋም በሌላት ኢትዮጵያ፤ ብዙሃኑ በቀላሉ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ይቸገራሉ። ይህም የበሽታውን ሥርጭት አስጊ ያደርገዋል። በበቂ ሁኔታ ውሃ አለመዳረሱ፣ አብዛኛው ማኅበረሰብ በተጠጋጋ ሁኔታ መኖሩም ችግሩን ያባብሰዋል። የህክምና ባለሙያው አገሪቱ ቅድሚያ መስጠት ያለባት ወረርሽኙን ለመከላከል እንደሆነ ይናገራሉ። “ዋና መመሪያ ፖሊሲዋ መሆን ያለበት በሽታውን መከላከል ነው። ያላትን አቅም በሙሉ ተጠቅማ በሽታው እንዳይስፋፋ እርምጃ መውሰድ አለባት። በሁለተኛ ደረጃ የመድኃኒትና ክትባት ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያድጋትን ፖሊሲ መከተል አለባት። ክትባት ሲገኝ ተጠቃሚነቷን ማረጋገጥ አለባት።” አንዳንድ አገራት የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት እንቅስቃሴ የመገደብ እርምጃ ወስደዋል። የኢትዮጵያን ደካማ ምጣኔ ኃብት ከግምት በማስገባት ይህ ውሳኔ ከባድ እንደሚሆን ብዙዎች ይስማሙበታል። ዶክተሩ በበኩላቸው ምናልባትም በተመረጡ ቦታዎች ብቻ በከፊል እንቅስቃሴ ማቆም እንደ አማራጭ ሊወሰድ ይችላል ይላሉ። የቫይረሱ ሥርጭት በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋቸው የአዲስ አበባ አካባቢዎች እንቅስቃሴ ሊገታ እንደሚችል የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ መናገራቸውም ይታወሳል።
news-54114328
https://www.bbc.com/amharic/news-54114328
ኮሮናቫይረስ ፡ ክትባቱን ቀድሞ የሚያገኘው ማን ይሆን? እንዴትስ ይከፋፈላል?
ተመራማሪዎች ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ የሚሆን ክትባት ማግኘት ሲችሉ በፍጥነት ለመላው ዓለም በሚበቃ መልኩ ማዘጋጀት አዳጋች ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም።
የምርምር ላብራቶሪዎችና ትልልቅ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ከዚህ በፊት አንድን ክትባት ለማዘጋጀት፣ ለመፈተሽ፣ ለማምረትና ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ የሚወስደውን ጊዜ በመሻር በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ክትባቱ በእርግጠኝነት ሲገኝም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማከፋፈልም የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው። ነገር ግን በሀብታም አገራት መካከል ክትባቱን ለማግኘት በሚደረገው እሽቅድድም ተጋላጭ የሆኑት የዓለማችን ማኅበረሰቦቸ ተጎጂ ይሆናሉ። ክትባቱን ማነው ቀድሞ የሚያገኘው? ምን ያህል ያስወጣ ይሆን? የእንቅስቃሴ ገደቦች ተጥለው በሚገኙበት በዚህ ወቅት ክትባቱን እንዴት በፍጥነት በሁሉም ቦታ ማዳረስ ይቻላል? የሚሉት ወሳኝ ጥያቄዎች አልተመለሱም። ከዚህ ቀደም በነበረው ተሞክሮ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውሉ ክትባቶችን ለማዘጋጀት፣ ለመሞከርና ለማሰራጨት ዓመታትን ይወስድ ነበር። እንደዚያም ሆኖ ክትባቶች ስኬታማ የማይሆኑበት አጋጣሚዎች አሉ። የሰው ልጅ የፈንጣጣ በሽታን ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት 200 ዓመታት ወስዶበታል። ምንም እንኳን ክትባት ቢገኝላቸውም እንደ ፖሊዮ፣ ቲታነስ፣ ቲቢ እና የመሳሰሉ በሽታዎች ደግሞ አሁንም ድረስ አብረውን ይኖራሉ። ክትባቱ መቼ ዝግጁ መሆን ይችላል? በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያሳትፉ የሙከራ ሥራዎች በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በሚገኙ የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተከናወኑ ይገኛሉ። በደህናው ዘመን ከአምስት እስከ አስር ዓመታት ይወስድ የነበረው ፍቱን ክትባት የማግኘቱ ሥራ አዋጪ እንደማይሆን የተገነዘቡት አንዳንድ አገራት፤ ደርሰንበታል ያሉት የክትባት አይነትን በብዛት ለማምረት በዝግጅት ላይ ናቸው። አምራቾችም ለክትባቱ የሚረዳ በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ፈሰስ ለማድረግ ተዘጋጅተው እየጠበቁ ነው። ባሳለፍነው ወር ደግሞ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ ማግኘቱን ተናግረው ነበር። በአገራቸው ላለፉት ሁለት ወራት በሰዎች ላይ ሙከራ እየተደረገበት የነበረው ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል መፈቀዱን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል። ክትባቱ አስፈላጊውን የምርመራ ሂደት ማለፉን የገለጹት ፑቲን፤ ልጃቸው ክትባቱን እየወሰደች እንደምትገኝም ተናግረዋል። ጥቅምት ወይም ኅዳር ላይ ክትባቱን በጅምላ የመስጠት እቅድ እንዳለ የአገሪቱ አመራሮች ቢናገሩም፤ ባለሙያዎች የሩሲያ የክትባት ምርምር እየሄደ ያለበት ፍጥነት ላይ ጥያቄ አንስቷል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ሩሲያ ክትባት ስታመርት ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እንድትከተል ማሳሰቡም አይዘነጋም። የሩሲያ ክትባት ድርጅቱ በሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ይገኛሉ ብሎ ከዘረዘራቸው ክትባቶች መካከል አደይለም። እነዚህ ክትባቶች በሰዎች ላይ ተሞክረው ተጨማሪ ምርምር መካሄድ አለበት። ፕሬዘዳንት ፑቲን ግን፤ በሞስኮው ጋማሊያ ተቋም ውስጥ የተሠራው ክትባት ቫይረሱን “በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል” ነው ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ክርስቲያን ሊንድሜር "አንዳንዴ በግላቸው ምርምር የሚያካሂዱ ሰዎች ውጤታም እንደሆኑ ይናገራሉ። ይህም እጅግ መልካም ዜና ነው" ብለዋል። ቃል አቀባዩ አያይዘውም፤ ውጤታማ ክትባት በማግኘት እና በምርምር ደረጃዎች በማለፍ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለም አስምረውበታል። በመላው ዓለም ክትባቱን ለማግኘት ሙከራ በማድረግ ላይ የሚገኙት ቀሪዎቹ ተቋማት ደግሞ ክትባታቸው በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት ፈቃድ እንደሚገኝ ተስፋ አድርገዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ግን እስከ ፈረንጆቹ 2021 አጋማሽ ድረስ በርከት ያሉ ለኮቪድ-19 የሚሆኑ ክትባቶችን ላንመለከት እንችላለን ሲል ተደምጧል። የእንግሊዙ ግዙፍ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ አስትራዜኔካ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየበለጸገ የሚገኘውን ክትባት ለማምረት ፈቃድ ያገኘ ሲሆን ለዩናይትድ ኪንግደም 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማምረት ተስማምቷል። ለተቀረው ዓለም ደግሞ 2 ቢሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ለማከፋፈል አቅሙ እንዳለው አስታውቋል። ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተባሉት ሌሎች ግዙፍ ኩባንያዎች ደግሞ ለኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት እስካሁን ድረስ 1 ቢሊየን ዶላር ወጪ ማድረጋቸውን በመግለጽ በያዝነው ዓመት የፈረንጆቹ ጥቅምት ወር ላይ የማምረት ፈቃድ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል። ፈቃድ የሚያገኙ ከሆነ ደግሞ የፈረንጆቹ 2020 ከማለቁ በፊት ቢያንስ 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን እንዲሁም ከዚያ በኋላ ደግሞ በ2021 ተጨማሪ 1.3 ቢሊየን ብልቃጦችን ማምረት አለባቸው። ከእነዚህ ትልልቅ ድርጅቶች በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ 20 የሚሆኑ መድኃኒት አምራቾች ክሊኒካል ሙከራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁሉም ስኬታማ እንደማይሆኑ ይታወቃል፤ ብዙ ጊዜ ክትባት ለመስራት ላይ ታች ከሚሉት ድርጅቶች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ተሳክቶላቸው ማምረት የሚጀምሩት። የክትባት ፖለቲካ የእንግሊዙ አስትራዜኒካ በቅልጥፍና ያመርተዋል የተባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ክትባት መድኃኒት በዋናነት እንዲደርስ የታሰበው ደግሞ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች ነው። አስትራዜኒካ በበኩሉ ለፍጥነት እንዲረዳው ከሌሎች ሁለት ኩባንያዎች ጋር ስምምነት አድርጓል። ከእነዚህ መካከል የመጀመሪያው የሕህንዱ ሴሩም ኢንዲያ አንዱ ሲሆን፤ ይህ መድኃኒት አምራች በዓለም ላይ መድኃኒትን በከፍተኛ መጠን በማምረት አቅሙ ተስተካካይ የለውም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባስተላለፉት መልዕክት ''እየጠበቅን ያለው ክትባት ለሁሉም የሰው ልጆች በእኩል የሚደርስ የሕዝብ ክትባትን ነው'' ካሉ በኋላ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በየአቅሙ ርብርብ እንዲያደርግም ተማጽነዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለጊዜው ስማቸው ካልተጠቀስ ስድስት መድኃኒት አምራቾች ጋር ስምምነት መፈረሙ ተሰምቷል። አሜሪካም ብትሆን እስከ ጥር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 300 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማግኘት እየሰራች ነው። ነገር ግን ሁሉም የዓለማችን አገራት በዚህ ፍጥነት ክትባቶቹን ማግኘት አይችሉም። ከዚህ ቀደም ከትባቶችን በማከፋፈል የሚታወቁት እንደ 'ሜድሲንስ ሳንስ ፍሮንቲርስ' ያሉ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ደግሞ አገራት ከመድኃኒት አምራች ድርጅቶቹ ጋር የሚያደርጉት ድርድር የክትባት ፉክክር እንዳይፈጥር ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። በዚህም ድርጅቶቹ የሚያመርቱትን ክትባት በሙሉ ሃብታም አገራት የሚቀራመቱት ከሆነ ደሃዎቹ አገራት ሊዘነጉ ነው ማለት ነው። ከዚህ በፊት በነበሩ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት የሕይወት አድን ክትባቶች ስርጭት ጉዳይ በርካታ አገራት ህጻናትን ከተላላፊ በሽታዎች መከላከል እንዳይችሉና ለሚሊየኖች ሞት ምክንያት ሆኗል። አንዲት ብልቃጥ ክትባት ምን ያክል ይጠየቅባት ይሆን? በአሁኑ ጊዜ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ክትባት ለማግኘት እና ለማምረት ፈሰስ እየተደረገ ነው። ለዚህም ወጪውን ከሞላ ጎደል እየሸፈኑ የሚገኙት ባለጸጋ አገራት ናቸው። እያደጉ ያሉ አገራት ክትባቱን በርካሽም ሆነ በነጻ ለማግኘት ድርድር ላይ ናቸው። የክትባቶች ዋጋ አገራት በሚያዙት መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። ለምሳሌ ሞደርና የተባለው መድኃኒት አምራች ኩባንያ ለኮቪድ-19 ይሆናል ያለውን ክትባት በብልቃጥ ከ32 እስከ 37 ዶላር ድረስ እንደሚሸጥ ገልጿል። አስትራዜኒካ ደግሞ ክትባቱን ባመረተበት ዋጋ እንደሚሸጠው አልያም እጅግ በጣም በረከሰ ዋጋ እንደሚያከፋፍለው አስቃውቋል። በሕንድ የሚገኘው በዓለማችን ትልቁ የክትባት አምራች ኩባንያ ሴረም ኢንስቲትዩት ደግሞ ከጋቪ እና ከቢልና ሜሊንዳ ፋውንዴሽን የ150 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያገኘ ሲሆን እስከ 100 ሚሊየን ክትባቶችን ለዝቅተኛ ገቢ አገራት ለማቅረብ ተስማምቷል። የዓለም ጤና ድርጅት፣ ዩኒሴፍ እና ሌሎች ድርጅቶች ክትባቱ ከተገኘ በአግባቡ ማሰራጨት የሚያስችል ሥርዓት ቀደም ብለው ዘርግተዋል። ማቀዝቀዣ ያላቸው መኪኖች፣ በፀሐይ የሚሰሩ ማቀዝቀዣዎች እና ማከማቻ መጋዘኖች ከዚህ በፊት ለነበሩ ክትባቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ ነበር። እነዚሁ መገልገያዎችም ለኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይጠበቃል።
news-53609386
https://www.bbc.com/amharic/news-53609386
ምርጫ፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለትግራይ ክልል የጻፈው ደብዳቤ ወዴት ያደርሳል?
የትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ ኮሚሽን አቋቁሞ በምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎችንና ግለሰቦችን መዝግቧል። በቅርብ ቀንም ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን፣ የመራጮች ምዝገባ መቼ እንደሚሆንና የምርጫ ቅስቀሳ ከመቼ እስከመቼ እንደሚካሄድ እንደሚያስታውቅ ተናግሯል።
በዚህ መሃል የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግሥት ምርጫ ለማካሄድ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ "በአፋጣኝ እንዲያቆም" የሚጠይቅ ደብዳቤ ሐምሌ 21/2012 መጻፉ ተሰምቷል። ክልሉ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ በሚጥል ድርጊቱ የሚቀጥል ከሆነ፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ እና በሌሎች ሕጎች የተሰጠውን ስልጣን ለመተግበር እንደሚገደድም አስጠንቅቋል። የሕግ ምሁር የሆኑት አደም ካሴ (ዶ/ር) የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል የሚያካሂደው ምርጫ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥቱ እና ሌሎች ሕጎች የተሰጡትን ሥልጣኖች ለመተግበር ይገደዳል ሲል የትኞቹ ሕጎች መጥቀሱ ነው? ስንል ጠይቀናቸዋል። አደምም (ዶ/ር) ሲመልሱ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 ንዑስ አንቀጽ ዘጠኝ፣ ከዚያም በተጨማሪ ይህንኑ አንቀጽ ለማስፈፀም የወጣው አዋጅ ቁጥር 359 አንቀጽ 12 በግልጽ ጉዳዩን እንደሚያብራሩ ይጠቅሳሉ። ከዚያም በተጨማሪ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤ ላይ ያልተጠቀሰው ነገር ግን፣ የፌደሬሽን ምክር ቤቱን ሙሉ ስልጣንና ሌሎች ነገሮች የሚግዛውም ይህንኑ ለማስፈጸም እንደሚያገለግል ይናገራሉ። አደም (ዶ/ር) አክለውም አዋጅ ቁጥር 251 መኖሩንም ይገልጻሉ። በተጨማሪም በምክር ቤቱ ደብዳቤ ላይ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 51 እና 55 (2) መጠቀሳቸውን፣ እንዲሁም ምርጫን በሚመለከት ሕጎችን የማውጣት ስልጣን ያለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑን መደንገጉን መጠቀሳቸውን ያነሳሉ። ምርጫ የማካሄድ ስልጣን በፌደራል እና በክልል የሚደረጉ ምርጫዎችን በገለልተኝነት ማካሄድ የሚችለው፤ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብቻ መሆኑ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 102 መደንገጉንም በደብዳቤው ላይ መጠቀሱን አደም (ዶ/ር) ገልፀዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤ የትግራይ ክልል ስድስተኛውን ዙር ምርጫ በክልሉ እንዲካሄድ ወስኖ እየተንቀሳቀሰ ያለው፤ የተጠቀሱትን የሕገ መንግሥት አንቀጾች እና ባለፈው ዓመት የጸደቀውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ በጣሰ መልኩ መሆኑን በደብዳቤ በሚገባ ማስቀመጡን አደም (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገልፀዋል። አክለውም በደብዳቤው ላይ "ምክር ቤቱ እንደሚለው ሕገ መንግሥቱን ሊያፈርስ የሚችል ሁኔታ አለ ወይ? የሚለው ሁኔታ በሰጠው ትርጓሜ ድምዳሜ ላይ የደረሱ ይመስላል" ሲሉ ይገልጻሉ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤ የትግራይ ክልል እርምጃ "ሕገ መንግስቱን የሚቃረን፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል እና የኢትዮጵያን የፌደራል ሥርዓት የሚጎዳ አካሄድ" መሆኑን ይገልጻል። እንደ ሕግ ምሁሩ ማብራሪያ ከሆነ የፌደራል ሥርዓት ዋና መተዳደሪያው፣ የስልጣን ክፍፍሉን በማክበር ላይ የተመሰረተ ነው። "የፌደራል መንግሥቱ ለክልሎች የተሰጠውን ስልጣን ማክበር፣ ክልሎችም የፌደራሉን ስልጣን ማክበር አለባቸው" ይላሉ። አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ችግር የሚያደርገው በሌላ አገር የሕገ-መንግሥት ፍርድ ቤት በመኖሩ ተጥሷል አልተጣሰም የሚለውን የሚያየው ገለልተኛ ፍርድ ቤት መሆኑን ያስረዳሉ። ይህ ፍርድ ቤት የክልል መንግሥት የፌደራል መንግሥቱን ስልጣን ወስዷል ወይ የፌደራል መንግሥትስ የክልል ተቀራምቷል የሚለውን የሚወስነው ራሱን የቻለ ነጸ ፍርድ ቤት መሆኑን ይናገራሉ። በእኛ አገር ያለው ችግር ብለው አደም (ዶ/ር) ሲያስቀምጡ ይህንንም የሚወስነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑ ነው። አሁን ግን ሕገ መንግሥቱንም የመተርጎም፤ ማለትም አንድ ክልል የፌደራሉን ስልጣን ወስዷል አልወሰደም የሚለውን መወሰንም ሆነ የዚያን ውጤትም የመወሰን ሥልጣን ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑ ነገሩን ያጣርሰዋል ሲሉ ያለውን ክፍተት ያሳያሉ። የፌደሬሽን ምክር ቤት ምን እርምጃ ሊወስድ ይችላል? የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ መጨረሻ ላይ ባካሄደው ስብሰባ፤ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ እንዲራዘም ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። ምክር ቤቱ ከውሳኔው ላይ የደረሰው፤ ምርጫ ማራዘምን በተመለከተ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት የውሳኔ ሀሳብ ካቀረበለት በኋላ ነበር። በሰኔ ወር ምርጫን በተመለከተ ምክር ቤቱ የሰጠው ውሳኔ ትርጓሜ ነው የሚሉት አደም (ዶ/ር) ሕገ መንግሥቱን ማክበር አለባችሁ አለበለዚያ ግን ሕገ መንግስቱ አንቀጽ 62 ንዑስ አንቀጽ ዘጠኝ የሚለውን ስለሚያዛባ የፌደራል ጣልቃ ገብነትን እናዛለን በሚል አስቀምጠውታል ብለዋል። እንደ አደም ካሴ (ዶ/ር) ከሆነ የፌደራል ጣልቃ ገብነት በተለይ አዋጅ ቁጥር 359 አንቀጽ 12 እና ቀጥሎ ያሉትን በመጥቀስ ሙሉ ዝርዝር ባይኖርም በተለይ ሁለት ነገሮችን እንደሚያወጣ ይናገራሉ። የፌደራል ፖሊስን ወይም መከላከያ ሠራዊትን ማሰማራት አንደኛው የፌደራል ፖሊስን ወይንም መከላከያ ሠራዊትን ሊያሰማራ ይችላል ይላል። ከዚያም አልፎ የክልሉን ምክር ቤትና ካቢኔ አውርዶ ጊዜያዊ አስተዳደርን ሊያቋቁም እንደሚችል ይደነግጋል ሲሉ ይጠቅሳሉ። እንግዲህ ይህ እንደመጨረሻ አማራጭ መቅረቡን የሚናገሩት አደም (ዶ/ር) እነዚህ ነገሮች የግድ መሆን አለባቸው ማለት ግን አለመሆኑን ያሰምሩበታል። የፌደራል ጣልቃ ገብነት የሚለው ሰፋ ያለ ትርጓሜ ቢኖረውም በአዋጁ ላይ በግልጽ የተጠቀሱት እነዚህ መሆናቸውን ያመለክታሉ። በሕጉ ማዕቀፍ ዋናው ጥያቄ ሕገ መንግሥቱ ተጥሷል አልተጣሰም የሚለው መሆኑን በመናገርም፤ በዚህ ሃሳብ ከተስማማን ምን እርምጃ ይወስዳል የሚለው ግልጽ መሆኑን ይናገራሉ። ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ሕገ መንግሥቱ ተጥሷል አልተጣሰም ብሎ የሚወስነው አካል የፌደራሉ ፖለቲካዊ ተቋም በመሆኑ ሁኔታውን ፈታኝ እንደሚያደርገው ያስረዳሉ። ይህ ደግሞ ውሳኔው የተወሰነው ለፖለቲካዊ ጥቅም ተብሎ ነው ወደ ሚል አንድምታ እንደሚወስድ ይጠቅሳሉ። እንደውም ይላሉ አደም (ዶ/ር) የፌዴሬሸን ምክር ቤት የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ጣልቃ ግባ ብሎ ካዘዘ እምቢ ማለት እንደማይቻልና "ትዕዛዝ" መሆኑንም ይናገራሉ። ሌሎች አማራጮች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በትግርኛ ቋንቋ በሰጡት ቃለመጠይቅ ላይ በዚሁ ጉዳይ ተጠይቀው የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ እንደማይገባ እቅዱም ሆነ ፍላጎቱ እንደሌለው መናገራቸውን በማስታወስ ነገር ግን በዚህ አንቀጽ መሰረት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ካዘዘ እምቢ የማለት አማራጭ እንደሌለ ያብራራሉ። በዚህም ከኃይል እርምጃ ይልቅ ሌሎች አማራቾች ሊኖሩ እንደሚችሉ አደም (ዶ/ር) በመጥቀስ ቀለል ያለው ከፌደራል መንግሥቱ ለክልሎች የሚሰጠውን የበጀት ድጎማ ማቆም መሆኑን በማብራሪያቸው ላይ ይጠቅሳሉ። ከዚህ ባለፈ የመሰረታዊ ፖለቲካዊ መብቶችን ይጥሳል ብሎ የሚል ከሆነ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በጋራ በመሰብሰብ ውሳኔ ሊያሳልፉ እንደሚችሉም ይገልፃሉ። እንደ ሕግ ምሁሩ ከሆነ ዋናው ጥያቄ 'የትግራይ ክልል ምርጫ ማከናወኑ ወይም ለማከናወን መወሰኑ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ያፈርሳል ወይ?' የሚለውን መመለስ እንዳለበት ያስረዳሉ። እንደ አገር ሕግ የበላይነትን ማስከበር ላይ የፖለቲካ ሥርዓታችን ጠንካራ ቢሆን ኖሮ ይህ ጥያቄ አያስፈልግም ነበር የሚሉት አደም (ዶ/ር)፤ "አንድ የፖለቲካ ሥርዓት በሕግ በተዘረጋው ሜዳ ላይ የምንጫወተው ጨዋታ ነው" ካሉ በኋላ የፌደራል ሥርዓቱ የሚቆመው በሥልጣን ክፍፍሉ መከባበር ላይ መሆኑን ይናገራሉ። ያ ካልተከበረ ዛሬ በምርጫ ጉዳይ አይሆንም እንደተባለው ሁሉ በሌላ ጊዜ በሌላ ጉዳይ ላይ አይሆንም ሊባል እንደሚችል ያነሳሉ። ጨምረውም አሁን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥረዓቱ ከባድ ፈተና ውስጥ መሆኑን በመጥቀስ የፌዴሬሸን ምክር ቤት ይህንን ማለቱ እንደማስጠንቀቂያ ጥሩ ቢሆንም፤ ነገር ግን ቶሎ ወደ ውሳኔ ከመግባት ይልቅ በመነጋገር ወደ መፍትሄ መምጣት አስፈላጊ መሆኑን ያሰምሩበታል። የፌዴሬሸን ምክር ቤት አሁን የጻፈውም ደብዳቤ ሆነ በሰኔ መጨረሻ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ከሕግ አንጻር ትክክል እንደሆነ በመጥቀስም፤ የትግራይ ክልል አይሆንም የሚል እንኳ ቢሆን ሕገ መንግሥቱ ይፈቅድልናል፣ ሕገ መንግሥቱ ላይ የቀረበው ትርጓሜ ስህተት ነው በማለት የራሳቸውን ትርጓሜ ማቅረብ መፍትሄ መሆን እንደነበረበት ያነሳሉ። በመርህ ደረጃ የሕገ መንግሥት የበላይነት፣ የሕግ የበላይነት መከበር አለበት የሚሉት አደም (ዶ/ር) ነገር ግን አስቸጋሪ ውሳኔ መሆኑን አልሸሸጉም። በፌደራልና በክልሎች መካከል ያለውን የሥልጣን ክፍፍል የሚወስነው የፌዴሬሽነ ምክር ቤት ሲሆን ያንን ደግሞ የሚያስፈጽመው የሚኒስትሮች ምክር ቤት መሆኑን በመጥቀስ ይህንን የምክር ቤቱን ውሳኔ የማስፈፀም ኃላፊነት የእነርሱ መሆኑን ይናገራሉ። በተለይ ደግሞ ሰኔ ላይ የነበረው ውሳኔ የፌደራል ምርጫን ብቻ ሳይሆን የክልል ምርጫንም እንደሚሸፍን ግልጽ ነበር ደብዳቤውም ይህንን ግልጽ አድርጎታል የሚሉት አደም (ዶ/ር)፤ የትግራይ ክልል በሕገ መንግሥቱ መሰረት ሥልጣን አለን በሚል የተንቀሳቀሱት የትግራይ ክልል አመራሮች ስህተት መስራታቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤ በግልጽ አስቀምጦታል ብለዋል። ደብዳቤው በግልጽ የሚያሳየው ሕገመንግሥቱን የመተርጎም ስልጣን ያለው የፌደሬሸን ምክር ቤት፣ የምርጫ ሕግ የማውጣት የምርጫ ሕግን የማስፈፀም፣ የምርጫ ቦርድ የማቋቋም የፌደራል መሆኑን በማስቀመጥ የትግራይ ክልል ሕገ መንግስታዊ መብቴ ነው በሚል የወሰደውን እርምጃ ይህንን የሚያፋልስ መሆኑን ያስረዳሉ።
news-44808893
https://www.bbc.com/amharic/news-44808893
የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ቀጣይ ፈተናዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ስልጣን ከተረከቡ ሶስት ወራትን አስቆጠሩ። በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በውጪ ግንኙነቱና በሌሎችም ዘርፎች የተወሰዱ እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው የሚሉ ወገኖች ጠቅላይ ሚንስትሩን እያሞጋገሱ ነው።
የተጨባጭ ለውጥ ሳይሆን ቃል የመግባት ደረጃ ላይ ነን ያሉ በበኩላቸው ከመፍረዳችን በፊት በእውን የሚተገበረውን እንጠብቅ የሚል አቋም አንጸባርቀዋል። አገሪቷን ወደ ሶስት ዓመት ገደማ የናጣት የተቃውሞ ወጀብ ረገብ ማለቱ ከጠቅላዩ መመረጥ ጋር በአንድም በሌላም መንገድ ይገናኛል። ዛሬ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ሳይሆን የ 'ለውጡን እንደግፋለን' ሰልፍ ይስተዋል ጀምሯል። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 100 ቀናት • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እርምጃዎች የት ድረስ? • የኢትዮጵያና ኤርትራን የአብሮነት እርምጃ ምን ይፈትነዋል? ጠቅላይ ሚንስትሩ ተመርጠው ብዙም ሳይቆዩ መገናኛ ብዙሀንን በሰበር ዜና ያጥለቀለቁ ውሳኔዎች ያስተላልፉ ያዙ። ሞት ተፈርዶባቸው የነበሩ ታራሚዎች ነጻ ወጡ። አሸባሪ ተብለው በነበሩ አካለት ምትክ መንግስት "አረ አሸባሪዎቹስ እኛ ነን" አለ። ከኤርትራ ጋር እርቀ ሰላም የማውረድ ጅማሮ ታየ። ወቅታዊ ዜናዎችን ያደመጡ ኢትዮጵያን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችም "እንዲህ ከሆነማ ወደሀገራችን እንመለሰላን" ብለው ሻንጣቸውን አነሱ። መንግስት አላስነካም ብሏቸው የነበሩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ቴሌ ኮሙኑኬሽን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ መንግስታዊ ተቋማትን ለሀገር ውስጥና ለውጪ ባለሀብቶች ድርሻ እሰጣለሁ አለ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ 100 የሥራ ቀናት በቁጥር ሲቀመጡ ምን ይመስላሉ? በየዘርፉ የተስተዋሉ ተስፋ ሰጪ ውሳኔዎች እንዳሉ ሆነው አገሪቷን ለወደፊት የሚጠብቋት ፈተናዎችስ የትኞቹ ናቸው? ፖለቲካዊ ውጥረት በአሜሪካ ጆርጂያ ጉኔት ኮሌጅ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት ዮሃንስ ገዳሙ (ዶ/ር) እንደሚሉት የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የወደፊት ጉዞ ፈተናዎች ሶስት ናቸው። የመጀመሪያው ፈተና ከገዛ ፓርቲያቸው እንደሚመነጭ ይናገራሉ። የፓርቲው የቀድሞ ልሂቃን የአሁኑ የለውጥ ጅማሮ ላይ ወደ ጎን ተገፍተዋል። የሂደቱ አካል ሆነውም አልታዩም። መገፋቱ ለልሂቃኑ እረፍት የነሳ እንደሆነ የሚያወሱት ዶ/ር ዮሃንስ ጠቅላይ ሚንስትሩን በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲጎነትሉ መታየታቸውን እንደ ማስረጃ ይጠቅሳሉ። • ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት • ሄሎ አስመራ እዚህም እዚያም ብቅ ብቅ ከሚሉ ብሄር ተኮር ግጭቶችና የሚያስከትሉት የህዝብ መፈናቀል አንፃር የፓርቲው ውስጣዊ ነውጥ እምብዛም ችግር አይሆንም ይላሉ ዶ/ር ዮሃንስ። በሁለተኛነት የሚጠቅሱት ተግዳሮት የህዝቦች ከቀያቸው መፈናቀል እጅግ አሳሳቢ ከሆነ ሰነባብቷል። የአማራ ክልል ተወላጆች እንዲሁም የኦሮሞ ክልልና የጌዲዮ ማህበረሰቦች መፈናቀል ይጠቀሳል። "ይህ የሆነው" ይላሉ መምህሩ "ይህ የሆነው ብሄርተኝነት ክፋት ሆኖ አይደለም። ሆኖም አሁን የሚታየው ብሄርተኝነት መጥፎ መሆኑ ነው" ይላሉ። ይህ እሳቸው ከሚከተሉት 'የኢትዮጵያዊነት ይቅደም መርህ' ጋር ይጋጫል ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። አሁን ያለውን ጽንፈኛ ብሄርተኝነት ለመግታት የአስተሳሰብ ለውጥ አብዮት ማምጣት ያሻል። ያ እስኪመጣ ግን ጠንካራ አመራር መስጠት ያስፈልጋል ይላሉ። በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ስርአት ውሰጥ ያለው ሁለት አይነት የአደረጃጀት ስርአት ማለትም ክልሎች ያደጉና ታዳጊ ተብለው መከፋፈላቸው ሌላው ችግር ነው። ታዳጊ የተባሉት ክልሎች ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገራት ጋር የሚያዋስኑ ናቸው። በክልሎቹ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ ከመጋጨታቸው ባሻገር ከጎረቤት አገራት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ሊያሻክሩ ይችላሉ። መምህሩ "ግጭቶቹ ለአገሪቱ ሉአላዊነት ራሱ አደጋ ሆነዋል" የሚሉትም በዚህ ምክንያት ነው። እንደ መፍትሄ የሚያስቀምጡት የፌደራል መንግስት በክልል ጉዳዮች ጣልቃ ገብቶ ውሳኔ መስጠት ባይችልም ጠንካራ አመራር እንዲሰጥ ነው። በተጨማሪም ማስጠንቀቂያ በማስተላለፍና የፌደራል መንግስቱን አቋም በመገናኛ ብዙሃንን በማስተላለፍ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያስረዳሉ። ሶስተኛው ጠቅላይ ሚንስትሩ እስከ አሁን ያስመዘገቧቸውን ድሎች እንዴት ያስቀጥላሉ? የሚለው ነው። ከኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ ብንነሳ አገራቱ በቀጣይ በሚስማሙባቸው ጉዳዮች ይደሳታሉን? የኢትዮጵያንስ ጥቅም እንዴት ማስከበር ይቻላል? የሚሉትን መመልከት ያስፈልጋል። የህግ ማሻሻያዎችን፣ የሰንደቅ አላማ ጉዳይና ህገ መንግስዊ እስከሆኑት ጉዳዮች ድረስ ዳግም መመልከት ያስፈልጋል። መምህሩ "በእርግጥ ይህ በአንድ ቀን ወይም በአንድ ወር የሚፈታ አይደለም። ሁሉም ደረጃ በደረጃ የሚታይ ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመቶ ቀን ቆይታቸው ያመጡትን ለውጥ ካየን የማስፈፀም ብቃታቸው በጣም ጥሩ ስለሆነ በቀጣይ የሚመጣውን ለመተንበይ ቀላል ነው" ይላሉ። ያልተመለሱ የኢኮኖሚ ጥያቄዎች አገሪቱ ከውስጣዊ የፖለቲካ ውጥረትና የደህንነት ስጋቶች በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ መሰናክሎችም ያሉባት መሆኑ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድን አስተዳደር ፈተና ውስጥ መክተቱ አይቀሬ ነው። በኪዊን ማሪ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ለንደን የምጣኔ ሐብት መምህሩ ነመራ ገበየሁ (ዶ/ር) "ፖለቲካዊ መሰናክሎች ችላ ባይባሉም የበለጠ የሚያሰጉኝ የሚጠብቁን የምጣኔ ሀብት ፈተናዎች ናቸው" ይላሉ። • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች • የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? • ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ? በኢኮኖሚው የላቀ ድርሻ የተያዘው በጥቂት ሙሰኞች ከመሆኑ በላይ እነዘህ ግለሰቦች በተለያየ መንገድ በዝባዥ መሆናቸው ያሰጋቸዋል። ግለሰቦቹ ያላቸውን የአቅም የበላይነት ተገን አድርገው ኢኮኖሚውን ጠልፈው መጣል የሚችሉ መሆናቸው የአዲሱ አስተዳደር ራስ ምታት ይሆናል። መምህሩ በአሁን ወቅት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰውን የዶላር እጥረት በአብነት ይጠቅሳሉ። "ባለፉት አራት ወራት የተባባሰውን የዶላር እጥረት ብንመለከት ለነዚህ ግለሰቦች ዶላርን ከመደበኛው ገበያ ወደ ጥቁር ገበያ ማዘዋወር እጅግ ቀላል ነው" ሲሉ ይገልጻሉ። ይህም የዋጋ ንረትና የስራ አጥነት መንሰራፋትን ያስከትላል። ህዝቡ በዚህ ሳቢያ ወደ ተቃውሞ ካመራ ሀገሪቱ ዳግም ባለመረጋጋት መናጧ እንዳማይቀር ይገልጻሉ። መንግስታዊ ተቋማት ወደ ግለሰቦች ይዞታ የሚዘዋወሩበት ውሳኔ መተላለፉም ሌላው ስጋታቸው ነው። ውሳኔው አገሪቱን የባሰ የኢኮኖሚ ውጥንቅጥ ውስጥ እንደሚዘፍቃት ያስረዳሉ። እንደ ምክንያት የሚያስቀምጡት መንግስታዊ ተቋማቱን የመግዛት አቅም ያላቸው ሙሰኞችና ኪራይ ሰብሳቢዎች መሆናቸውን ነው። የኋላ ኋላ በማህበረሰቡ መሀከል ያለው የገንዘብ አቅም ልዩነት እየሰፋ ስለሚሄድ ሀገሪቱም ትታመሳለች የሚሉት ዶ/ር ነመራ መንግስት ጠንካራና የማያዳግም እርማጃ እንዲወስድ ያሳስባሉ። ቀጠናዊ ትስስርና የወደፊት ፈተናዎች ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ከያዙ በኋላ ከአገር ውጪ መጀመሪያ የጎበኙት ጅቡቲን ነበር። አስከትለውም ኤርትራና ኬንያን ጨምሮ ወደ ቀጠናው ሌሎች አገሮችም አቅንተዋል። በጉብኝቶቹ ከአቻዎቻቸው ጋር በዋነኛነት ስለኢኮኖሚያዊ ትስስር ተነጋግረዋል። የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አገሮችን በኢኮኖሚ ከማስተሳሰር ባሻገር የቀጠናውን ሰላምና መረጋጋት በማስጠበቅ ረገድ ውይይቶቹ ጠቃሚ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህሩ አቶ አዳነ አለማየሁ ይናገራሉ። የኤርትራን ጉብኝት ብንወስድ የሁለቱ ሀገሮች ለሰላማዊ ግንኙነት ማኮብኮብ ከአገራቱ ባሻገር ለቀጠናውም አለመረጋጋትም እልባት ይሰጣል። "ለኢትዮጵያ አለመረጋጋት ተጠያቂ የሚሆኑ ኤርትራ ያስጠለለቻቸው ሀይሎች ለማስከን ይረዳል" ይላል መምህሩ። • የኢትዮጵያ የዕዳ መጠን እየጨመረ ነው • የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች ላለፉት 20 አመታት ሁለቱ አገራት ሳይታኮሱ ጦርነት ውስጥ ነበሩ። ሰላም ማጣት ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያቸው ላይም ተጽእኖ አሳድሯል። የአገራቱ መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝቶ መነጋገር እሰየው ቢያሰኝም በጥንቃቄ መታየት ያለባቸው ነጥቦችም አሉ። ሁለቱ አገሮች እርቀ ሰላም አውርደው እንደ ሁለት አገራት እንዲቀጥሉ በመሀከላቸው ያሉ መሰረታዊ መስመሮች መጠበቅ አለባቸው። የሁለቱ ሀገር ዜጎች አንዳቸው በሌላቸው ሀገር ምን መብት ይኖራቸዋል? የሚለውም የህግ ማእቀፍ ያስፈልገዋል።ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመር ፍጹም ሰላም ነግሷል ማለት አይደለምና። በመምህር አዳነ አገላለጽ "ዝም ብሎ ድንበር ከፍቶ 'ኑ ግቡ! ኑ ውጡ!' መባባሉ የተጨማሪ ግጭቶች መነሻ እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል።" • ጥያቄን ያዘለው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ሁለቱ አገራት በራሳቸው ተነሳሽነት ማለትም ያለ ሶስተኛ ወገን አሸማጋይነት ወደ ስምምንት መምጣታቸው መልካም ነው። ይህን መሰረት በማድረግም ስለ አልጀርስ ስምምነት አፈጻጸም ተወያይተው አንዳች ውጤት እንደሚያስመዘግቡ ብዙዎች ተስፋ አድርገዋል። ሁለቱ አገሮች የጀመሩት የሰላም ጉዞ ምናልባትም አለመተማመናቸውን ይሽር ይሆናል። የጎሪጥ መተያየትን ማስቀረት ግን የነገሩ መጨረሻ አይደለም። ለወደፊት ለሚጠበቁ ውሳኔዎች ግብአት እንጂ። መልካም ግንኙነቱ ካደገ ኢትዮጵያ ጥቅሟን የምታስከብርበት መንገድ መቀየስ እንዳለባት አቶ አዳነ ያስረዳሉ። "ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ የምትፈልገው ወደብ ነው" የሚሉት መምህሩ በዋነኛነት የጅቡቲ፣ የኤርትራና የሱዳን ጉብኝት ፍሬያማ እንደሚሆን ያምናሉ። የኢትዮጰያ ኢኮኖሚ ተሽመድምዶ እንዳይቀር የአጎራባቾቿን ወደብ መጠቀም የግድ ይላታል። ለዚህም ቁልፉ የቀጠናው ሀገራት ራሳቸው እየተጠቀሙ ጎረቤቶቻቸውንም የሚጠቅሙበትን ትስስር እውን ማድረግ ነው። የቀጠናው አገሮች በኢኮኖሚ ከተሳሰሩ ለጥቅማቸው ሲሉ ወደ ግጭት ከመግባት እንደሚቆጠቡ መምህሩ መላ ምቱን እንዲህ ያስቀምጣሉ። • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? "የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግርና እንቅስቃሴ የቀጠናው ሀገራትን ወንድማማችነት ያጠናክራል። አገሮቹ ኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ ያጠፋል። መንግስታቱም ጥሩ ምላሽ ሰጥተዋል።" በሌላ በኩል የቀጠናው አገሮች በውስጣዊ የፖለቲካ ቀውስ፣ በተዳከሙ ወይም አቅም ባጡ መንግስታት፣ በምዕራባውያን ጣልቃ ገብነትና በአክራሪነት ይፈተናሉ። ቀጠናው የአሜሪካ፣ የቻይና የቱርክና የሌሎች አገሮችም ፍላጎት አለበት። መምህሩ እንደሚለው ቻይና 'በክልሉ ያለኝን ኢንቨስትመንት ለመጠበቅ' ብላ ወታደሮች ለማስፈር እንቅስቃሴ መጀመሯ ለህልውናችን አደጋ ነው ይላሉ። ከቀጠናው አገሮች መሀከል የመንግስታት አቅም ማጣት የመፈራረስ ስጋት የፈጠረባቸው መኖራቸው እሙን ነው። ጠንካራ መንግስት ማጣታቸው የግጭት መንስኤ መሆኑ ከአገራቱ አልፎ ለቀጠናውም አስጊ ነው። ከቀጠናው አገሮች ምን ያህሉ ዴሞክራሲያዊ ናቸው? ሌላው ጥያቄ ነው። የመንግስታቱ አምባገነንነት እርስ በእርስ የሚፈጸሟቸው ስምምነቶች ፍሬያማ መሆናቸው ላይ ጥያቄ እንደሚያጭር መምህሩ ይናገራሉ። ሌላው ፈተና አክራሪነት ነው። አልሸባብ በምስራቅ አፍሪካ እስላማዊ መንግስት ማቋቋም ይፈልጋል። ለጥቅማቸው ሲሉ ይህንን ተግባር የሚደግፉ አገራትም ስጋት ናቸው። የአካባባቢው መንግስታት የሽብር ጥቃቶችን እንዴት ይቋቋማሉ? ከኢትዮጵያ ጀምሮ በተቀሩትም የቀጠናው አገሮች ጽንፍ የወጣ ጎሰኝነትና ብሄርተኛነት አጥልቷል። እነዚህ መሰናክሎች እልባት እስካልሰጣቸው ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ያዳግታል።
51716798
https://www.bbc.com/amharic/51716798
የኤርትራ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያው አባ ብርሃነእየሱስ ጉዳይ መንግሥትን ማብራሪያ ጠየቀች
ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ እንዳይገቡ አሥመራ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የታገዱት የኢትዮጵያው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ካርዲናል ብርሃነእየሱስ ጉዳይን በማስመልከት የኤርትራ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የኤርትራ መንግሥትን ማብራሪያ መጠየቋን ቫቲካን ኒውስ ዘገባ አለመለከተ።
የኤርትራ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥያቄ ያቀረበችው ለኤርትራው ብሔራዊ የሐይማኖት ጉዳዮች ቢሮ ነው። ለቢሮው የቀረበው 'ማብራሪያ ይሰጠን' ደብዳቤ በኤርትራ የጳጳሳት ጉባኤ ዋና ፀሃፊ አባ ተስፋጊዮርጊስ ክፍሎም የተፈረመ ነው። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ካርዲናል ብርሃነእየሱስ አሥመራ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ የታገዱት ከሌሎች የቤተክርስቲያኒቱ ሁለት አባቶች ጋር ነበር። አባ ብርሃነእየሱስና አብረዋቸው የነበሩት አባቶች ወደ አሥመራ ያመሩት በኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ኪዳነምህረት ደብር በሚደረግ ትልቅ ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት እንደነበር ተገልጿል። አባቶቹ ወደ አሥመራ እንዳይገቡ በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ መከልከላቸውን በማስመልከት ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ ከታገዱት አባቶች አንዱ የነበሩት አባ ፍቅሬ ወልደትንሳኤ "ልዑኩ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ ማሟላት የሚገባውን ነገር ሁሉ አሟልቶ በተገቢው ሂደት አልፏል። መንገደኞች እንደደረሱ የሚሰጥ ቪዛም ለአንድ ወር ተብሎ ተሰጥቷል" ብለው ነበር። ሁሉን ነገር ጨራርሰውና ቪዛቸውን ተቀብለው ከአውሮፕላን ማረፊያው ሊወጡ ሲሉ ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ የሚል ትዕዛዝ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት መምጣቱ እንደተገለፀላቸውና ነገሮች በዚያ መልኩ እንደሄዱም አስረድተዋል አባ ፍቅሬ ወልደትንሳኤ። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አባቶች አሥመራ ከደረሱ በኋላ ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ በመከልከላቸው በአየር ማረፊያው ውስጥ ለበርካታ ሰዓታት መጉላላታቸው ተነግሯል።
45279886
https://www.bbc.com/amharic/45279886
"ረጅም ታሪክ ቢኖረንም ህገ መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ ባህል ግን የለንም"ረዳት ፕሮፌሰር መረሳ
ወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለብዙዎች ይህ ነው ብሎ ለመግለጽ የሚያስቸግር መልክ ይዟል።
በዚህ ምክንያት አገሪቷ ተመልሳ ከ1983 ዓ.ም በከፋ መልኩ ወደ መስቀለኛ መንገድ መመለሷን የፖለቲካል ሳይንስና ስትራቴጂካዊ ጥናት ሙሁሩ ረዳት ፕሮፌሰር መረሳ ጸሃየ ይናገራሉ። የዚህ ችግር መሰረታዊ ምክንያት በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው አለመግባባት፣ በኦሮሚያ ክልል ተነስቶ መላ አገር ያዳረሰው ፖለቲካዊ ተቃውሞን መንግስት መፍታት ባለመቻሉና በመጨረሻም ህዝቦች ወደ ብሄር ተኮርና ሌሎች ግጭቶች ማምራታቸው እንደሆነ ያስቀምጣሉ። •በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው •በመቀሌው አውሮፕላን ማረፊያ ታግተው የነበሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት ተለቀቁ .ዶ/ር አብይ በግላቸው ለውጥ ያመጣሉ? የእነዚህ ችግሮች ድምር ውጤት አገራዊ አንድነትና ደህንነትን አደጋ ላይ የጣለ ከባድ ፖለቲካዊ ችግር እንደተፈጠረ የሚናገሩት ረዳት ፕሮፌሰር ጸሃየ በዚህ ወቅት የአገሪቱ እጣ ምን ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ እንደሆነ ምሁሩ ይናገራሉ። እነዚህን ውስብስብ አገራዊ ችግሮች መንግስት እንዴት መፍታት ይችላል? የአገሪቷ ፖለቲካዊ አስተሳሰብስ ወዴት ያመራ ይሆን? ቢቢሲ፡ በእርስዎ እይታ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በምን ደረጃ ይገኛል? ረዳት ፕሮፌሰር መረሳ፡ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ የጣለና ነገን መገመት የማይቻል ሆኗል። የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች ዉስጥ ያለው ችግር ለአገራዊ ቀውስና የአመራር እጦት ምክንያት ሆኗል። መንግሥትም ህግና ስርአትን ለማስከበር የተቸገረበት፣ ዜጎች ለአካላዊና ስነ ልቦናዊ ጥቃት የተጋለጡበትና የተፈናቀሉበት ሁኔታ ስላለ በሚያስፈራ መልኩ አገሪቷ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች ማለት ይቻላል። ሌላው በፌደራልና ክልል መንግስታት መካከል ያለው ግንኙት ጥሩ አይደለም። በኤርትራ የነበሩ ተቃዋሚ ሃይሎች ደግሞ በሙሉ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። እነዚህ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣም ፖለቲካዊ ፍልስፍና እና ራዕይ የሌላቸው ሲሆኑ መንግሥት ያለው ተቀባይነት እንዲዳከም ህግና ስርአት ለማክበር የሚፈተንበት ለዜጎች ለጥቃትና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ ችግሮች እየተፈጠሩ አሉ። ለዚህ ነው መስቀለኛ መንገድ ላይ ነን ያልኩት። •"ሽብር ምንድን ነው ፣ አሸባሪ ማን ነው?" ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቢቢሲ፡ "ብሄር ተኮር" ጥቃቶች አገሪቷ ላይ እየተፈጸሙ ነው ? ይህ ከምን የተነሳ ይመስልዎታል? ረዳት ፕሮፌሰር መረሳ፡ አንደኛ ኢትዮጵያ በታሪክ የአገር ግንባታ ችግር ያለበት ናት። የብዙ ብሄሮች አገር ስለሆነች አገራዊ ግንባታ (ኔሽን ቢዩልዲንግ) የሚባለው ሂደት ሊያግባባን አልቻለም። ለዚህ አንድነቷንና ተቀባይነቷን የሚፈታተኑ ሦስት የፖለቲካ አስተሳሰቦች አሉ። የመገንጠል ፖለቲካዊ አስተሳሰብ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ ልማትና ዲሞክራሲ ማምጣት የምትችል አገር አይደለችም፤ ጊዜ ሳንወስድ የራሳችን አገራዊ ነጻነት ሊኖረን ይገባል የሚል ፖለቲካዊ አስተሳሰብ አለ። በሌላ በኩል ብዝኃነት አደጋ ስለሆነ ኢትዮጵያ አንድ ብሄር፣ ቋንቋና ህዝብ ማስተናገድ አለባት የሚል አሃዳዊ አስተሳሰብ ሲኖር ሁለቱንም ጫፍ ኢትዮጵያ ካላት ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ፌደራላዊ ስርአት ነው የሚያዋጣን የሚሉም አሉ። እነዚህ ሦስቱን ማስታረቅ አለመቻሉ ኢትዮጵያ ሁሉም የሚቀበላት አገር እንዳትሆን አድርጓታል። ላለፉት 27 አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አመራር ይዞ የቆየው የፌደራሊዝም ስርአት አገሪቷ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ህገ መንግስታዊና ፖለቲካዊ እውቅና ቢሰጥም እንኳ ላለፉት ሦስትና አራት አመታት ግን ይህን ህልዉና በሚፈትን መልኩ የፌደራሊዝም አስተሳሰብ ችግር ውስጥ ወድቋል። ስለዚህ ፌደራሊዝም ስርዓቱ ለጊዜውም ይሁን ለዘለአለሙ ተዳክሟል ማለት ይቻላል። ሌላው ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አቅም ችግር ያለባት አገር ናት። ብዙ የተማረና ስራ የሚፈልግ የሰው ሀይል ቢኖርም እንኳ መንግስት ስራ ሊፈጥርለት አልቻለም። የአገሪቷ ኢኮኖሚ አድጓል ቢባልም ህዝቡን የሚመግብና ስራ የመፍጠር አቅም ያለው አልሆነም። •ሙስጠፋ ኡመር የሶማሌ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ ተቃውሞ ሲጀምር የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንና የስራ እጦት ምክንያቶች ነበሩ። ወጣቱ ስራ እያጣ በሄደ ቁጥር መንግሥት ያለው ተቀባይነት እየተዳከመ ወጣቱ በብሄር እንዲደራጅና የራሱን ጥቅም ሌሎች እንደወሰዱበት አድርጎ በመረዳት ወደ ጥፋት እንቅስቃሴ እንዲሄድ ምክንያት ይሆኗል። ያለንን አገራዊ አቅም ከአገራዊ ግንባታው አለመመጣጠኑኢትዮጵያ በህዝቦቿ ዘንድ ያላትን ተቀባይነት ፈተናላይ በመጣል መንግሥት ደግሞ ህግና ስርአት ለማክበር ተቸግሮ በርካታ የዜጎች መፈናቀልና ብሄር ተኮር ጥቃቶች ሲደርሱ እየታየ ነው። በአጠቃላይ ኢህአዴግ ተዳክሞ በሚገርም መልኩ አንድ መሆን አቅቶት የዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ ወድቆ የአገር መከላኪያውም የዜጎቹን ደህንነት እንዳይጠብቅ ጠንካራ ፖለቲካዊ አመራር ሳያገኝ ቆይቷል። ቢቢሲ፡ ይሄ ሁሉ ግን ባንዴ የመጣ ሳይሆን ያለፉት 27 አመታት ዉጤት ነው ይባላል? ረዳት ፕሮፌሰር መረሳ፡ ኢትዮጵያ ሦስት መሰረታዊ ጥያቄዎች ነበሯት። የብሄር እኩልነት፣ መሬትና የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ሲሆኑ፤ እነዚህ የአገር ግንባታው ችግር አካል ናቸው። በአጼ ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ አሁን የያዘችውን ቅርጽ ስትይዝ እነዚህ ችግሮች ይዛ ነው የተፈጠረችው። ሌላው አርሶ አደሩ ከእርሻ ተነስቶ ወደ ኢንዱስትሪያል ካፒታል ሊሸጋገር እየተገባ፤ እስከ አሁን በእርሻ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ነው ያለን። ወጣቱ ስራ አጥቶ ተስፋ ቆርጧል ሲባል መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር ስለሌለ፤ የተማረው ስራ አጥ እየሆነ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ያላት ኢኮኖሚያዊ ችግር አሁን ላለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ምክንያት ሆኗል። • ጎዳና ተዳዳሪዎችን በህክምና መታደግ በዚህ ምክንያት ላለፉት 25 አመታት አድጓል ሲባል የነበረው ኢኮኖሚ ትክክለኛ ኢኮኖሚያዊ እድገት አለመሆኑና ይልቁንም በረድኤትና ምጽዋት የተመሰረተ መሆኑ ችግር ፈጥሯል። ሌላዉ መሰረታዊ የኢትዮጵያ ችግር የምንለው ረዥም ታሪክ አለን ህገ መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ ባህል የለንም። ህገ መንግስቱ ለነበሩት ጥያቅዎች እዉቅና ቢሰጥም አቶ መለስ ዜናዊ "ቢግ ማን ፖሊስ" ገንብቶ ነው ያለፈው። በዚህ ጊዜ ክልሎች ቋንቋቸዉን ባለማሳደጋቸው፣ ኢኮኖሚያዊ አቅምና ስራ ባለመፍጠራቸው፣ ዲሞክራሲ ባለማስፋታቸው፤ ገዢው ፓርቲ ደግሞ ለዲሞክራሲያዊ ሽግግር በሚጠቅም መልኩ ባለመደገፉ ባለፈው ምርጫ መቶ በመቶ አሸንፌአለሁ ሲል ከአሁን በኋላ መንግሥትን በምርጫ መቀየር እንደማይቻል በማሳየት ተስፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ ተፈጠረ። ስለሆነም መንግሥት በምርጫ ሳይሆን በአመጽ ነው የምንቀይረው የሚል ስሜት ፈጠረ። ከአቶ መለስ በኋላ የመጡት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ የነበረው ስርአት ለማስቀጠል አቅም ስላነሳቸውና አራቱንም ድርጅቶች አስተባብረው መምራት አልቻሉም ነበር። 10ኛ የድርጅቱ ጉባኤ በተካሄደ በአንድ ወር በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። ስለሆነ ችግሩ የኢህአዴግ አመራሮች የፈጠሩት ችግር ነው። ችግሩ የህገ መንግሥት ሳይሆን ዲሞክራሲ ባለመስፋቱ፣ የኢትዮጵያ ህልውና ከኢህአዴግ ህልዉና ጋር በመተርጎሙ፤ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ማዳከም ላይ ሲሰሩ የነበሩ ስራዎች፣ ዜጎች ምርጫ ላይ እምነት ማጣታቸዉና ከአመጹ በኋላ ኢህአዴግ ችግሩን የሚፈታበት አቅም ማጣቱ ናቸው። ቢቢሲ፡ ምን መደረግ አለበት ይላሉ? ረዳት ፕሮፌሰር መረሳ፡ አሁን፡ የኢህአዴግ ህጋዊ የፖለቲካል ኢኮኖሚ አስተሳሰብ በተግባር ደረጃ አለ ብሎ ለመናገር ይከብዳል። አብዮታዊ ልማታዊ ነው ሊበራል አይታወቅም። አንድ የሚገለጽበት "ፖፕሊዝም" ነው። አለ የሚባለው ዲሞክራሲም የሰበር ዜና ዲሞክራሲ ነው። ሰበር ዜና እያሉ ህዝቡን ከአንድ አጀንዳ ወደ ሌላ አጀንዳ ሲያሸጋግሩት ነው እያየን ያለነው። ኢህአዴግ እስከ ምርጫ ጊዜ የቀሩትን ጊዜያት ቢያጤን ነው የሚሻለው። አገር ቀውስ ላይ ነች፤ ህዝብ ግጭት እየለመደ በሄደ ቁጥር መንግስት ላይ ያለውን እምነት እያጣ የራሱን አማራጭ እየወሰደ ይሄዳል። መንግሥት እንዳለውም ሰፊ የጦር መሳርያ መስፋፋት አለ። ይህ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እንዳንገባ ያሰጋል። የብዙ ዜጎች መፈናቀልና ብሄር ተኮር ጥቃቶች ሲፈፀሙ እያየን ነው። ወደ አገር ቤት የገቡት ሀይሎችም ታሪካዊ ቅራኔ አላቸው። ይህን ለማስታረቅ የሽግግር መንግስት መምጣት አለበት። መንግሥት በአገሪቷ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶችን በማስተባበር አገሪቷን ማዳን ካልቻለ መጨረሻው ከባድ ነው። ይህ የዜጎችንና የአገር ደህንነትን ወደ ነበረበት ይመልሳል የሚል ተስፋ አለኝ። ቢቢሲ፡ በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል ክፈትት ያለ ይመስላል? ረዳት ፕሮፌሰር መረሳ፡ የኢትዮጵያውያን የፍትህና የዲሞክራሲ ትግል ለ17 አመታት የተሸከመው የትግራይ ትግል ነበር። ይህ የህወሃት ትግል በሌሎች ብሄሮች በሁለት መንገድ ታየ። ይህ ትግል እራሳችንን ለማስተዳደርና ማንነታችንም ለማሳደግ ጥሩ ነገር አድርጎልናል የሚሉ ሲኖሩ ፤ በሌላ በኩል ታሪካችንን ወስዶብናል የሚሉም አሉ። ህወሀት ፌደራል ላይ ተቀምጦ የትግራይን ጥቅም ጨፍልቋል። አገራዊ ቀዉሱ ሲፈጠር ሁሉም የትግራዋይና የህወሀት ጠላት ሆነ። ህወሀት አሁን ስልጣን ስለሌለው ማድረግ የሚችለው ክልሉን ማስተዳደር ስለሆነ ወደ አፈራው ክልል ተመልሷል። የትግራይ ህዝብ ደግሞ ዲሞክራሲን በማስፋት መሰረታዊ ጥቅሞቹን የምታከብር አገር ነው የሚፈልገው። የህወሀት አመራሮች ችግር የለባቸውም እያልኩኝ አይደለም። አሁን የህወሀት መሪዎችን እየወቀሱ ያሉትን ግን አብረው ሲያጠፉ የነበሩ ናቸው። ስለዚህ ፍጥጫው ህወሀትን ማዳከምን ያለመ ነው።
50415676
https://www.bbc.com/amharic/50415676
የህወሓት ልሳን ሃገራዊ ምርጫ የሚራዘም ከሆነ ትግራይ የራሷን ምርጫ ታካሂዳለች ብሏል
የህወሓት ልሳን የሆነው ወይን መጽሄት በትናንትናው ዕለት ይዞት በወጣው 48 ገጽ ያለው ዕትም በሀገር ደረጃ በዘንድሮው ዓመት ሊካሄድ ዕቅድ የተያዘለት ሃገራዊ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች የሚስተጓጎል ከሆነ ትግራይ ክልል የራሱን ክልላዊ ምርጫ በማካሄድ 'ዲ ፋክቶ ስቴት' ለመሆን ወደ የሚያስችለውን 'ቁመና' (status) ለመገንባት ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።
ዕትሙ የዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ቀነ ገደብ እንዲካሄድ የሚያትት ሲሆን፣ ቢስተጓጎል ግን ሕገ-መንግስቱን መጣስ ብቻ ሳይሆን 'ወደ ለየለት የፖለቲካ አለመረጋጋት' ሊያመራ እንደሚችል ገልጿል። አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች፣ በሀገር ውስጥ የተንሰራፋውን የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ግጭት ሳይቆም ሃገራዊ ምርጫ ሊካሄድ ስለማይችል ጊዜው መራዘም እንዳለበት ያሳስባሉ። • ህወሓት: "እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም" • "ለስልጣን ተብሎ የሚፈጠር ውህደትን ህወሓት ፈጽሞ አይቀበለውም" አቶ ጌታቸው ረዳ በተቃራኒው ደግሞ በሕገ-መንግስቱ መሠረት የተመረጠ መንግስት ካልቀጠለ ሁኔታው ከዚህ ወደ ባሰ ቀውስ ስለሚገባ ምርጫ መካሄድ እንዳለበት የሚናገሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ። ከእነዚህም መካከል ህወሓት አንዱ ሲሆን በተደጋጋሚ ምርጫው መካሄድ አለበት በማለት አጥብቆ ሲሞግት ይደመጣል። ይህንን አቋሙን ትናንት በታተመው ወይን መጽሔትም ላይ ሲያስቀምጥ "ምርጫው ከተራዘመ ሊፈጠር የሚችለውን የሕጋዊ ቅቡልነት እጦት (Legitimacy crisis) መላ የትግራይ ህዝብ ባሳተፈ እና በትግራይ ህዝብ ህልውና እና ደህንነት ጽኑ እምነት ያላቸውን በክልሉ የተቋቋሙት የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመሆን በክልሉ ህጋዊ ምርጫ በማካሄድ እንፈታለን" ብሏል። "እንደ ሃገር ሊያጋጥም ከሚችለው የፖለቲካ አለመረጋጋት በተነጻጻሪ የተሻለ እና መንግሥታዊ መዋቅርን (Institutions) የገነባ እንዲሁም ራሱን ችሎ የቆመ መንግሥት (De facto state) ለመመስረት የሚያስችል ስራዎች ማሳለጥ ተገቢ ነው" ይላል በመፅሔቱ ላይ የሰፈረው ሀሳብ። በወይን መጽሔት ላይ የሰፈረው ይህ ጽሁፍ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን 'አምባገነን' ሲል የገለፀ ሲሆን፤ "ዋነኛው አጀንዳችን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓላማ 'ሃገራዊ ምርጫውን አራዝሞ የፌደራል ስርዓቱን በመገርሰስ በአንድ ግለሰብ የሚመራ ስርዓት የማቆም ፍላጎት መሆኑን' ሁሉም እንዲረዳው ማድረግ ነው" ካለ በኋላ ይህን አስተሳሰብ የሚሸከም ምቹ ሁኔታ እንዳይኖር አስፈላጊዉን የፖለቲካ እና የሚድያ ስራዎች እንደሚሰራ አትቷል። "የቡድኑ መሪ ፍላጎት ቢቻል ቢቻል ፍጹም አምባገነናዊ አካሄድ የተረጋገጠበት አሃዳዊ ስርዓትን ለማቆም መሆኑን ፍጹም ጥራጣሬ ሊገባን አይገባም" ሲልም ጽሁፍ ያስረግጣል። ኢህአዴግን ከግንባርነት ወደ ውሁድ ፓርቲነት ለመቀየር የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገልፁ እንደነበር ይታወሳል። ህወሓት ከዚህ በፊት በአቋም ደረጃ የውህደቱ ደጋፊ እንደነበር ቢገልፅም፣ ከጥቂት ወራት በፊት ባወጣው መግለጫ ግን "የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አይደለም ውሁድ ፓርቲ ሊሆኑ ከዚህ ቀደም የነበራቸውን ግንኙነት እየሻከረ መጥቷል" በማለት ውህደቱ ግዜው እንዳልሆነ ገልጿል። ህወሓት አክሎም በይፋም የውህደቱ አካል እንዳማይሆን በተደጋጋሚ አስታውቋል። ጽሁፉ በመጨረሻም "ትግራይ መንግስታዊ ቁመና (Defacto state - ራሱን ችሎ የቆመ ነገር ግን በዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ እውቅና ያላገኘ መንግሥት) ያላት ክልል የማድረጉ ስራ የትግራይ ምሁራን እና ተመራማሪዎች ጥናት አካሂደውበት በአፋጣኝ ወደ ተግባር ሊቀየር እንደሚገባ" አስፍሯል።
news-56387887
https://www.bbc.com/amharic/news-56387887
ጥላሁን ገሠሠ፡ ከ20 ዓመታት በፊት የተቀዳው የሙዚቃው ንጉሥ 'ምርቃት'
ያላዜመበት አርዕስት የለም። በሙዚቃ ሥራዎቹ ያልመዘዘው የሕይወት ሰበዝ፣ ያልዳሰሰው የኑሮ ቋጠሮ፣ ያልደረሰበት የሐሳብ ጥግ የለም ይላሉ በርካቶች።
አገርና ሰንደቅ፤ ሰላምና ፍቅር፤ ትዝታና ናፍቆት፤ ማግኘትና ማጣት፤ ሳቅና ለቅሶ፤ ሕይወትና ሞት፤ መውደቅና ስኬት፤ ጥያቄና ምፀት፤ ጊዜና ቀጠሮ፤ ነጻነትና ፍትሕ፤ መውደድና መጥላት፤ እውነትና እብለት፤ ዝምታና ጩኸት፤ ፅድቅና ኩነኔ፤ ሐብትና ድህነት፤ ተፈጥሮና ውበት፤ መጠጥና ምግብ፤ ስለሳር ቅጠሉም. . . ሌላም ሌላም። እልፍ ሥራዎችን ሰርቷል። ቆጥሮ የደረሰበት ስለመኖሩም እንጃ። የጠየቅናቸውም "እሱ መሥራት እንጂ ቆጠራው ላይ መቼ አለበት" ነው ያሉት። ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ እንደ ብላቴና የሙዚቃን እግር የሙጥኝ ብሎ ጥበብን ከፍ አድርጓታል። ሙዚቃ እራሷ በእሱ ስም ትጠራ የሚሉለትም አሉ። ሙዚቃዎቹ በእድሜና በዘመን የሚለዩ አይደሉም። ትውልድ እየተቀባበለው የሚሻገሩ እንጂ። ታዲያ ሙዚቃ ወዳጁ ብትሆንም እንደ ክፉ ባልንጀራም ፍዳውን አብልታዋለች። ፖለቲካዊ ይዘት አላቸው በተባሉ ሥራዎቹ ቡጢና እርግጫ፤ እንዲሁም እስርን ቀምሶባታል። የሙዚቃው ንጉሥ ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ። ጥላሁን በሞት ከተለየ አስራ ሁለት ዓመታት ተቆጥረዋል። በስኳር ህመም ሲሰቃይ የነበረው ጥላሁን ድንገት ባጋጠመው ህመም፤ በ68 ዓመቱ ይችን ዓለም የተሰናበተው ሚያዚያ 12/2001 ዓ.ም ነበር። ምንም እንኳን በሞት ከተለየ ዓመታት ቢነጉዱም ድምጹ ከሙዚቃ አፍቃሪዎች ጆሮ ርቆ አያውቅም። ጀማሪ ድምጻዊያንም የእሱን ሥራ የብቃታቸው ጥግ ሚዛን አድርገው ሲያነሱ ሲጥሉ ነው የሚውሉት። በየሙዚቃ ውድድሮቹ ተወዳዳሪዎች ይዘዋቸው ከሚቀርቡ ሥራዎችም አብዛኞቹ የእርሱ ናቸው። አሁን ደግሞ 'የመጨረሻው' የሙዚቃ እስትንፋሱ ለአድማጭ ጆሮ በቅቷል - ምርቃት። 'ምርቃት' የአልበሙ መጠሪያ ነው። በውስጡ አስር ዘፈኖችን ይዟል። ዜማው የሞገስ ተካ፤ ያቀናበረው ደግሞ አንጋፋው የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋሱ ክብረወርቅ ሺዮታ ነው። በግጥም ሥራዎቹም ሞገስ ተካን ጨምሮ ያየህይራድ አላምረው፣ ሶስና ታደሰና አለምፀሐይ ወዳጆ ተሳትፈውበታል። 'ምርቃት' 'ምርቃት' ሕይወቱ ካለፈ ከ12 ዓመታት በኋላ ነው የወጣው። ይህ አልበም የጥላሁን ስንተኛው ሥራ እንደሆነ ግን በቁጥር ያወቀ አላገኘንም። በግምት ከ300 ወይም ከ400 በላይ የሙዚቃ ሥራዎችን ሳያበረክት እንዳልቀረ ግን ባለቤቱ ወ/ሮ ሮማን በዙ ይናገራሉ። ወ/ሮ ሮማን "ጥላሁን ምን ያህል ሥራዎችን እንደሰራ ባለሙያም፤ ቤተሰብም መናገር መቻል ነበረበት። ግን ይህን ያህል ሥራ አለው ማለት ያልቻልነው፤ ታሪክ የማሰባሰቡ ሥራ ላይ ደካማ ስለሆንን ነው" ሲሉም ይወቅሳሉ። በእርግጥ ከሙት ዓመቱ በኋላ የሰራቸውን ሥራዎች ሰብስቦ በታሪክ ለማስቀመጥ ሲንቀሳቀሱ ነበር የቆዩት። ሆኖም ዳር አልደረሰላቸውም። ይህን አልበም ያቀናበረው እውቁ የሙዚቃ አቀናባሪም "ካሉ አርቲስቶች በጣም ቁጥሩ የበለጠ ሥራ የሠራ አርቲስት እንደሆነ እንጂ ቁጥሩን አላውቀውም፤ ግን በርካታ ነው" ብሏል። አገራዊ ዜማ ከአልበሙ የማይታጣው ጥላሁን፤ በዚህ አልበሙም ስለ አገር አዚሟል። ". . . ሴራው ይክሸፍበት የመታብሽ አድማ እጁን ሳር ያድርገው፤ ጉልበቱን ቄጠማ . . ." ብሎላታል አገሩን ሲመርቅ፤ ጠላቶቿን ሲረግም። ይህ የሙዚቃ አልበም ስለፍቅር፣ ፍትሕ፣ እርቅ፣ አገር እንዲሁም ስለራሱ ሕይወት የሚያነሱ ሥራዎች የተካተቱበት ነው። 'ቆሜ ልመርቅሽ' የተሰኘው አገራዊ ዜማ፤ አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር የሚሄድ በመሆኑ በርካቶች የትንቢት ያህል ቆጥረውታል። ወ/ሮ ሮማንም "'ቆሜ ልመርቅሽ'ን ለየት የሚያደርገው የአገራችንን የአሁኑን ሁኔታ የሚያንፀባርቅ መሆኑ ነው" ይላሉ። 'ያኔ ባለሙያዎቹ ምን ታይቷቸው ነበር?' ያስባለ እንደሆነም ተናግረዋል። አልበሙ በሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲንና በአቶ አብነት ገብረመስቀል ፕሮዲዩስ መደረጉን የገለጹት ወ/ሮ ሮማን፤ 'ምርቃት' ለሕዝብ እንዲደርስ ላደረጉት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል። ይህ ሙዚቃ በምን ሁኔታ ነበር የተሰራው? የሙዚቃ አቀናባሪው አበጋሱ ለጥላሁን ሥራዎች እንግዳ አይደለም። ከዚህ ቀደም የወጡ አራት አልበሞቹን ከሙላቱ አስታጥቄና ቴዲ ማክ ጋር በመሆን እንደገና አቀናብሯል። የአሁኑን ጨምሮ ሁለት አዲስ አልበሞችንም ሰርቷል። ይህንን አልበም በማቀናበሩም "በጣም እድለኛ እንደሆንኩ ነው የሚሰማኝ" ይላል። አበጋሱ እንደሚለው ይህ አልበም መጀመሪያ ከተቀረጸ 20 ዓመት ገደማ ይሆነዋል። የቀረጸውም እራሱ ነበር። የተጀመረው አሜሪካ በአበጋሱ ስቱዲዮ፤ የተጠናቀቀው ደግሞ አዲስ አበባ። 'ምርቃት' በአበጋሱ እጅ ለ18 ዓመታት ያህል ቆይቷል። "ከእኔ ጋር መሆኑ ትልቅ እድል ነው፤ በጣም ደስተኛ ነኝ" ይላል አበጋሱ። በአልበሙ ላይ የምንሰማቸው የጥላሁን ድምፆች ከህመም ጋር እየታገለ ያወጣቸው ናቸው። የልምምድ እንጂ የመጨረሻ ያለቀላቸው ቅጂዎች አልነበሩም። በዚያ ላይ ደግሞ በህመሙ ምክንያት ወጣ ገባ እየተባለ የተሰራ። አበጋሱ እንደሚለው በጊዜው ጥላሁን ጥሩ ቀኖችም፤ መጥፎ ቀኖችም ነበሩት። የሁኔታዎችና የስሜት ለውጦችም እንዲሁ። "ትዝታዎች ውስጥ የሚገባበት ጊዜም ነበር። የዝምታ ድባቦችም ነበሩ። ጥሩ ግንኙነቶችም ነበሩን። ታሪኮችን እጠይቀው ነበር። እኔ ከእርሱ መውሰድ እፈልግ ነበር። ጋሽ ጥላሁን ህልመኛ ነው፤ በራሱ ዓለም የሚሆንበት ጊዜም ነበር" ይላል አበጋሱ-በወቅቱ የነበረውን ሲያስታውስ። በእርግጥ ያኔ ሙዚቃውን እንደ ሥራ እንጂ፤ ሰው ጋ እንዲህ ዓይነት ስሜት ይፈጥራል ብሎ አላሰበም ነበር። ድምጻዊ ሚኒሊክ ወስናቸው፣ ጥላሁን ገሠሠ፣ አለማየሁ እሸቴና ማህሙድ አሕመድ [ከግራ ወደ ቀኝ] ጥላሁን ሌሎች ያልወጡ ሥራዎች ይኖሩት ይሆን? አበጋሱ ይህ አልበም የጥላሁን የመጨረሻ ሥራ እንደሆነ ነው የሚያስበው። "በእርግጥ እንደ ጥላሁንና ማህሙድ ዓይነት የመዝፈን ፍቅር ያላቸው ባለሙያዎች የሆነ ቦታ ሄደው 'ሙዳቸው' ከመጣ ሊዘፍኑ ይችላሉ። በዚህ ምክንያት ያልወጡ ይኖሩ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ" ይላል። ወ/ሮ ሮማንም 'ይህን የሚያውቁት ባለሙያዎች ናቸው' የሚል ምላሽ ሰጥተውናል። አልበሙ ይህን ያህል ዓመት ለምን ቆየ? አበጋሱ እንደሚለው ሥራው ሳይጠናቀቅ ጥላሁን ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ ነገሮች እንደታሰቡት አልሆኑም። ከ20 ዓመታት በፊት የተቀዳን ድምፅ አሁን ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ማጣጣም ፈተና ነበር ይላል። ብዙ ድካሞችና ልፋቶች ነበሩት። የመጨረሻ ቅጂም ስላልነበር ጥላሁን በወቅቱ የነበረበት እውነተኛ ስሜት በድምፁ ተይዟል። አንዳንዴ ከጀርባ የሚሰሙ ድምፆች ነበሩ። ያንን ማፅዳቱም ጊዜ ፈጅቷል። ቢሆንም ግን "በውጤቱ ረክቻለሁ" ብሏል አበጋሱ። ከዚህም ባሻገር የነበሩበት የሥራ ጫናዎችም፤ አልበሙ የአፍላ ወጣት እድሜ ያህል ቆይቶ እንዲወጣ ምክንያት ሆነዋል። አበጋሱ እንዳለው ሙዚቃዎቹን አሳምሮ ለማውጣት የተጠቀመው የተለየ ቴክኒክ የለም። ድምፁን ማሻሻልም አልተፈለገም። ይሁን እንጂ በተለያየ ጊዜና በተለያየ የሙዚቃ 'ኪይ' ሲለማመድ ስለነበር እነርሱን ለማጣጣም "'አውቶ ቲዩን'[የድምፅ ፒች ማስተካከያ] በትንሹ በመጠቀም ስሜቱን ለማውጣት ሙከራ አድርገናል" ብሏል። "አንድም ቀን ያለ ስሜት ሲዘፍን አይቼው አላውቅም" ጥላሁን አንድን ዜማ ሲቀበል ወደ ራሱ በማምጣቱና ወደ ራሱ ቅላጼና ገለጻ በማጣጣም ችሎታው ለአበጋሱ ለየት ይልበታል። "ከጥላሁን ጀርባ ከባድ ስሜት አለ። መመሰጥ አለው። ከስሜት ጋር ቁርኝት አለው" የሚለው አበጋሱ አንድም ቀን ያለ ስሜት ሲዘፍን አይቶት እንደማያውቅ ይናገራል። "በህመም ላይ ሆኖም ሲቀረጽ ያ ተፅእኖ አያሳድርበትም ነበር። ታሞም ይመሰጣል። እንደዚያ መሆን ሲያቅተው 'በቃኝ ቤት ውሰደኝ' ይለኛል" ይላል አበጋሱ። አበጋሱ እንደሚለው ጥላሁን ስሜት ከሌለው ለሙዚቃ የሚገባውን ነገር ያልሰጠ ይመስለዋል። ወ/ሮ ሮማንም ሥራዎቹ በግርድፍ ያሉ ስለነበሩ እንደዚህ ይሰራል የሚል ሃሳብ እንዳልነበራቸው ገልፀው፤ "ታሞ የነበረ ድምፅ እኮ ራሱ ታሪካዊ ነው" ይላሉ። "ጥላሁን የሙዚቃ ጥጉን አስቀምጦ የሄደ ባለሙያ ነው። እያቃሰተም፤ እያለቀሰም ቢዘፍነው ታሪክ ነው" ብለዋል ወ/ሮ ሮማን። የዋለውን ያህል ያልተዋለለት ጥላሁን ጥላሁን ይህችን ዓለም ከተሰናበተ ድፍን 12 ዓመታት ተቆጥረዋል። ነገር ግን ከዘመን አይሽሬ ሙዚቃዎቹ በስተቀር ለስሙ መጠሪያ አንድም ማስታወሻ አልቆመለትም፤ አልተሰየመለትም። ለምን? ይህ የብዙዎች ጥያቄ ነው። ባለቤቱ ወ/ሮ ሮማን ለጥላሁን በስሙ መንገድ ለማሰየም፤ አደባባይ ለማሰራት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን በር ሲያንኳኩ ነው የቆዩት። ግን በአሰቡት ልክ አልሄደላቸውም። "ጥላሁን የገንዘብ ሰው አይደለም። እያነባ እያለቀሰ 'አገሬ አገሬ' እያለ የሞተ ሰው ነው። ይህንን ሥራ ለሰራ ሰው፤ አደባባይ ለመሥራት እንኳን 12 ዓመት 12 ወር መፍጀት አልነበረበትም" ይላሉ ወጥተው የወረዱትን በማስታወስ። ለነገሩ ወደ መሿለኪያ አካባቢ አደባባይ ለማሰራት ፈቃድ አግኝተው ነበር። ይሁን እንጂ ኋላ ላይ ቀለበት መንገድ ተሰርቶበት በመፍረሱ ሳይሆን መቅረቱን ይናገራሉ። ተለዋጭ ቦታ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ሰሚ ሳያገኙ ቆይተዋል። "አሁን ከረዥም ዓመታት በኋላም ቢሆን፤ በአገር ደረጃ መታየት የነበረበት ባለሙያ በክብር ስለታየልን ደስ ብሎናል" ብለዋል ወ/ሮ ሮማን። ድምጻዊ ጥላሁን ገሠሠ እና ባለቤቱ ሮማን በዙ ይህን ያህል ደጅ መጥናት ለምን? ያልናቸው ወ/ሮ ሮማን ዝርዝር መልስ አልሰጡም። "ምንም እንኳን ጥላሁን የአገር ሐብት ቢሆንም፤ የሚመጣውም፤ የሚሄደውም መንግሥት ጥላሁንን እንዴት ያየዋል የሚለው ራሱን የቻለ ጥያቄ ነው" ሲሉ በደምሳሳው አልፈውታል። "ባለታሪክን የምናደንቀውና የምናወድሰው ጊዜና ወቅት እየጠበቅን መሆን የለበትም" ሲሉም በተለያየ ሙያ ላይ ብዙ ጀግኖች አስታዋሽ አጥተው ደብዛቸው ጠፍቶ የቀሩ ስለመኖራቸው ያወሳሉ። በዚህ መንግሥት የታየው ጭላንጭል ግን ተስፋ ሰጭ ነው ብለዋል። በጥላሁን ስም ምን ለመስራት ታስቧል? ጥላሁን በሕይወት እያለም፤ ከህልፈቱ በኋላም በስሙ ለመስራት የተያዙ ፕሮጀክቶች እንደነበሩ ወ/ሮ ሮማን ይናገራሉ። ወ/ሮ ሮማን እንደሚሉት ጥላሁን የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች በነጻ የሚታከሙበት የስኳር ህሙማን ሆስፒታል ለማቋቋም ቃል ገብቶ ነበር። እርሱም ጤንነቱ የተጓደለው በዚሁ በሽታ ነበር። በሕይወት ሳለም ሆስፒታሉን ለማሰራት የተወሰነ እንቅስቃሴ አድርገዋል። ግን ይህ እውን ሳይሆን ነው ሕይወቱ ያለፈው። "ከስኳር ህሙማን ማኅበር ጋር ለመስራት ተስማምተን፤ የሆስፒታሉ ዲዛይን ተቀርጾ እዚያ ላይ ነው በእንጥልጥል የቆመው" ብለዋል ወ/ሮ ሮማን። ሙዚቃዎቹን እንዲሰባሰቡ ለማድረግ ሞክረውም በቤተሰብ አቅም ይህን ማድረግ ሳይቻል ቀርቷል። አሁን ምላሽ ያገኘው የአደባባይ ጉዳይም የእቅዳቸው አካል ነበር። የሙዚቃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሌሎች መታሰቢያዎችን ለመስራት እየታሰበ መሆኑን ወ/ሮ ሮማን ተናግረዋል። "ባለሙያውም፣ ባለሃብቱም፣ መንግሥትም ተረባርቦ እቅዱ እውን እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።
news-44559498
https://www.bbc.com/amharic/news-44559498
በጎርፍ አደጋ ወቅት የሚደረጉ አምስት ጥንቃቄዎች
በኢትዮጵያ ከሰሞኑ በደረሱ የጎርፍ አደጋዎች በርካቶች ተጎድተዋል።
ጎርፍ ከመከሰቱ በፊት አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት መቆጣጠር ወይም መቀነስ ይቻላል። ጎርፍ ሊያስከትላቸው የሚችላቸውን ጉዳት ለመቆጣጠር ወይም ለመቀነስ የሚከተሉት አምስጥ ነጥቦች ወሳኝነት አላቸው። 1. ማዳሪያዎችና ሌሎች ከረጢቶችን በአሸዋ ሞልቶ ከበር ደጃፍ ላይ መደርደር እንደ አማራጭ ጎርፍ ወደ ቤት እንዳይገባ፤ በቤት ዙሪያ የውሃ መፍሰሻ ቦይ ወይንም ጉድጓድ መቆፈር ይችላሉ። በርና መስኮቶችን በደንብ መዝጋቶን አይዘንጉ። 2. እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ያለበትን ሁኔታ ያጣሩ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ያለበትን ሁኔታ ማወቅ ሌሎች ጥንቃቄዎችን በተረጋጋ መንፈስ ለማድረግ ይጠቅማል። የታሰሩ የቤት እንስሳት ካሉ መፍታት እንዳይረሱ። 3. በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ማንኛውም መጠቀሚያዎችን ከሶኬት ላይ ይንቀሉ ከጎርፍ አደጋ ጋር ተያይዞ ስዎች ሊጠነቀቁት የሚገባ ነገር የኤሌክትሪክ አደጋ ነው። ከቤት ውስጥ ባለፈ በውጪም ቢሆን የወደቁ የኤሌክትሪክ ሽቦዎች ካሉጥንቃቄ ያድርጉ። የተቆፈሩ ጉድጓዶች ካሉ ሰዎች ገብተው እንዳይወድቁ በደንብ ይክደኗቸው። 4.ቆሻሻ ወደ ውጪ እንዳይወጣ መጸዳጃ ቤቶችን በደንብ ይዝጉ እንደ ጸረ ተባይ እና የመሬት ማዳበሪያ ያሉ መርዝነት ያላቸው ነገሮችን ጎርፉ የማይደርስበት ከፍ ወዳለ ቦታ ያስቀምጧቸው። ምክንያቱም የተበከለ ውሃ ሌላ ተጨማሪ በሽታ ይዞ ሊመጣ ይችላል። 5. ከፍ ወዳለ ቦታ ይሂዱ፤ አልያም የቤተትዎ ጣራ ላይ ይውጡ የጎርፍ አደጋ በሚያጋጥሞት ጊዜ ቤት ውስጥ ሆነው ራሶን መከላከል ካልቻሉ፤ ወደ ጣራ ላይ ወይንም ከፍ ወዳለ ቦታ ይውጡ። በጎርፍ ውስጥ መራመድ ደግሞ አይመከርም።
news-54252805
https://www.bbc.com/amharic/news-54252805
አሜሪካ ኢራን ላይ የጣለችውን አዲስ ማዕቀብ ይፋ አደረገች
አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ ማዕቀብ ጥላለች።
አሜሪካ የተባበሩት መንግሥታት በኢራን ላይ ዳግም ማዕቀብ እንዲጥል የጠየቀች ቢሆንም ሌሎች የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አባል አገራት የአሜሪካንን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል። እአአ 2015 ላይ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ኢራን የደረሱትን ስምምነት ተከትሎ ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሞቿ ላይ ገደብ ለማድረግ የተስማማች ሲሆን፤ ኃያላን አገራቱ ደግሞ በምላሹ ኢራን ላይ ተጥሎ የሚገኘውን ማዕቀብ ለማቃለል ተስማምተዋል። ትራምፕ ግን ከሁለት ዓመታት በፊት ይህ ስምምነት ለኢራን ጥቅም ያደላ ነው በማለት አሜሪካ ስምምነቱን ጥላ መውጣቷን ይፋ ማድረጋቸው አይዘነጋም። ትራምፕ በኢራን ላይ ማዕቀቡ ዳግም እንዲጣል ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ አሜሪካ በተናጠል ማዕቀብ ጥላለች። በዚህ መሠረት ለኢራን የጦር መሳሪያ የሚሸጥ አገርም ሆነ ኩባንያ በአሜሪካ ቅጣት ይጣልበታል። ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ ከጸጥታው ምክር ቤት አባል አገራት አቋም በተለየ መልኩ ከኢራን ኒውክሌር ፕሮግራም ጋር ግንኙነት አላቸው ባለቻቸው ከ20 በላይ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። የአሜሪካ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ኢራን ከሚፈቀድላት በላይ ዩራኒየም ማበልጸግ ጀምራለች እያሉ ይከሳሉ። የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲም በተመሳሳይ ኢራን የደረሰችበትን ስምምነት በመተላለፍ ዩራኒየም እያበለጸገች ነው ይላል። ኤጀንሲው እንዳለው ኢራን 2ሺህ 105 ኪሎ ግራም የሚመዝን የበለጸገ ዩራኒየም አከማችታለች። በዚህም ምክንያት አሜሪካ በኢራን ላይ ተፈጻሚነቱ እንዲገታ ተደርጎ የነበረው የተመድ ማዕቀብ ተፈጻሚ እንዲሆን በተደጋጋሚ ስትወተውት ቆይታለች። ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት አባል አገራት የአሜሪካንን ጥያቄ ወድቅ አድርገውታል።
sport-45047214
https://www.bbc.com/amharic/sport-45047214
ኢትዮጵያዊው ጀማል ይመር በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ
ኢትዮጵያዊው ጀማል ይመር በአፍሪካ የአዋቂዎች የአትሌቲክስ ውድድር በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አንዱአምላክ በልሁ እና ዩጋንዳዊውን ቲሞቲ ቶሮቲችን አስከትሎ ነው አሸናፊ የሆነው።
በናይጄሪያ አሳባ ዴልታ እየተካሄደ በሚገኘው ውድድር ጀማል 29 ደቂቃ ከ08 ደቂቃ በማስመዝገብ ለሃገሩ በውድድሩ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ትላንት ለሀገሩ አስመዝግቧል። በተጨማሪም በቀጣይ ወር ኦስትራቭ ቼክ ሪፐብሊክ ውስጥ በሚካሄደው አህጉር አቀፍ ውድድር ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል። ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊያው ያገኘው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አንዱአምላክ በልሁ ነው። •የቀድሞዎቹ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተገናኙ •ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ •"ፍቃዱ ተክለማርያም የሀገር ቅርስ ነው"
news-55129514
https://www.bbc.com/amharic/news-55129514
ትግራይ ፡ የቀድሞው የሠሜን ዕዝ አዛዥ ሳይመረዙ እንዳልቀሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ
በሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት የዕዙ አዛዥ ሳይመረዙ እንዳልቀረ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስተሩ እንዳሉት፤ የሠሜን ዕዝ አዛዥ የነበሩት ጄነራል ድሪባ ግጭቱ ከመፈጠሩ ከሁለት ሳምንት በፊት "ስብሰባ ከእነሱ ጋር ውሎ፣ ምሳ ከበላ በኋላ ታሞ እራሱን ስቶ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ገብቷል" ብለዋል። ጨምረውም ከጄነራሉ ጋር የነበሩ ሰዎች "አቅምሰውት ነው" የሚል መረጃ እንዳመጡና እንዲህ ያለው ጉዳይ በህክምና እስኪጣራ ድረስ እንዲቆይ "ብለን አፈንነው" ካሉ በኋላ፤ ጄነራል ድሪባ ባጋጠማቸው ችግር ምክንያት አስካሁን አገግመው ወደሥራቸው እንዳልተመለሱ ገልጸዋል። ይህንንም ተከትሎ ጄነራሉን በመተካት የሠሜን ዕዝን የሚመራ ጄነራል ለመመደብ መገደዳቸውንና የህወሓት አመራሮች አዲሱን ተሿሚ አንቀበልም ማለታቸውን በመግለጽ "ለካ እሱን በማኮላሸትና የሚመጣውን እምቢ የማለት ፍላጎት ነበረ" ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህም በኋላ "የሠሜን ዕዝ አዛዥ ጄነራል ድሪባ ታመሙ፣ አዲስ የተመደበውን ጀነራል አንቀበልም አሉ ከዚያም ጥቃት ፈጽመው የዕዙን ምክትል አዛዥ ጀነራል አደምን አፈኑ" ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት ከምክር ቤቱ አባላት ስለወቅታዊ ጉዳዮች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ላይ ነው። የአገሪቱ ከፍተኛው ሠራዊትና የመከላከያ መሳሪያዎች ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የሠሜን ዕዝ ስር እንደሚገኝ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ቀደም በርካታ ተደጋጋሚ ትንኮሳዎች በህወሓት በኩል ተደርጎ ነበር በማለት፤ "በተደጋጋሚ መሳሪያውን ለማስወጣት ጥረት ቢደረግም ፈቃደኛ አልሆኑም" ብለዋል። በመጨረሻም ጥቅምት 24/2013 ዓ. ም ምሽት 5 ሰዓት 30 አካባቢ በሠራዊቱ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጸው፤ በእሳቸው ትዕዛዝም መጀመሪያ ጥቃትን መከላከልና ወደ ጎንደርና ወልዲያ እንዳይስፋፋ ለማድረግ ጥረት መደረጉን አመልክተዋል። ስለ ወቅታዊ ሁኔታ ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የመከላከያ ሠራዊት መቀለ እና ሌሎችም የትግራይ ከተሞችን እንደተቆጣጠረ ገልጸው በዘመቻው "አንድም ንጹህ ሰው አልተገደለም" ብለዋል። ቀጣዩ እርምጃ በክልሉ አመራር ላይ የነበሩ የህወሓት አባላትን ይዞ ለፍርድ ማቅረብ እንደሆነም አክለዋል። አያይዘውም፤ ዘመቻውን አስታኮ እየተገለጹ ያሉ የደስታ መግለጫዎች ቀና የሆነ መንገድ እንዲላበሱ አሳስበዋል። ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ የተለያዩ አገሮች ድርድር እንዲያሄዱ ሲጠይቁ እንደነበር አስታውሰው፤ አንዳንዶቹ ለአገሪቱ በጎ ከማሰብ ቢሆንም አንዳንዶች ግን ውስጣዊ ችግርን ለመፍታት ይሳናቸዋል ከሚል የተሳሳተ እሳቤ የተነሱ መሆናቸውን አስምረውበታል። እንደ ኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያና ሱዳን ያሉ አገሮችን ጠቅላይ ሚንስትሩ ያመሰገኑ ሲሆን፤ በተለይ ከኤርትራ ጋር ሰላም መውረዱ ከወቅታዊው ሁኔታ አንጻር ትክክለኛ ውሳኔ እንደነበር አስረድተዋል። ግጭቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ባለፈው ሁለት ዓመት ተኩል ውስጥ ብቻ በአገሪቱ ሆን ተብሎ የተቀሰቀሱ 113 ግጭቶች መከሰታቸውን ተናግረዋል። እነዚህ ግጭቶች ብሔርንና ሐይማኖትን መሰረት ያደረጉ መሆናቸውንና ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ እንደተከሰቱ አመልክተው፤ ከእነዚህ በርካታ ሰዎች ከሞቱባቸውና ከፍተኛ ንብረት ከወደመባቸው ግጭቶች ጀርባ የሥልጣን የበላይነትን መልሰው ለመያዝ ሲጥሩ የነበሩት የህወሓት አመራሮች እንዳሉ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፤ ከእነዚህ ግጭቶች መካከል በኦሮሚያ 37፣ በአማራ 23፣ በጋምቤላ 7፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ፣ በቤኒሻንጉል፣ በደቡብ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በድሬዳዋ፣ በሐረሪና በሲዳማ በክልሎች እንደሆነ አመልክተዋል። ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ሰፊ የቀውስ ዕቅድ ነበረ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህ ዕቅድ ተጨማሪ አስር የሚደርሱ ሌሎች ሰዎች በመግደል፣ ግድያውን የብሔር መልክ በማስያዝ ከባድ ጉዳት ለማድረስ ታስቦ እንደነበረ ተናግረዋል። ይህ የምክር ቤቱ ስብሰባ የተካሄደው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህወሓት ኃይሎች በአገሪቱ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸው፤ ወታደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ ከሦስት ሳምንታት በኋላ የፌደራሉ ሠራዊት ዋና ከተማዋን ጨምሮ ትግራይን መቆጣጠሩን ካሳወቀ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ ባለፉት ሳምንታት በትግራይ ክልል የተከሰተው ቀውስ ላይ አተኩረው ከምክር ቤቱ አባላት የቀረቡትን ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ በሰጡት ማብራሪያ ላይ በአገሪቱ የለውጥ እርምጃዎች መወሰድ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ መንግሥታቸው የገጠመውን ፈተና በዝርዝር አስረድተዋል። በለውጡ ሰሞን ስለተከሰቱ ነገሮች መንግሥት ቀደም ብሎ በህወሓት ላይ እርምጃ መውሰድ ቢችል ኖሮ አሁን በትግራይ ውስጥ ያጋጠመውን አይነት ቀውስ ለማስቀረት ይቻል ነበር በማለት ከምክር ቤቱ አባላት ለተሰጠው አስተያየት ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለውጡ ከመጀመሩ በፊትና ከጀመረ በኋላም ከባድ ፈተናዎችን እንደተጋፈጡ ተናግረዋል። ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት የአገሪቱን ከፍተኛ ስልጣን ይዘው ከነበሩ የደኅንንትና የመከላከያ አመራሮች እሳቸውን ጨምሮ ለውጥ እንዲመጣ ጥረት ሲያደርጉ በነበሩት ሰዎች ላይ ውንጀላዎች፣ ማሳደዶችና ግድያ ለመፈጸም መከራና ማዋከብ ነበረ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። በለውጡ ሰሞን በስልጣን ላይ የበላይ ሆኖ ለመቀጠል ፍላጎት የነበረው ቡድን በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ላይ መፈንቅለ መንግስት ለማደረግ ሲያሴር እንደነበረ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ ሲያሳውቁ ደግሞ እየታዘዘ በታማኝነት ቦታውን የሚይዝ ሰው ለመተካት ጥረት ሲደረግ ነበር ብለዋል። በዘህም ሳቢያ ከእነሱ ፈቃድ ውጪ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ ሰዎችን ተስፋ ለማስቆረጥና ለማስወገድ በደኅንነቱና በታጠቁ ወታደሮች ከባድ ክትትል ይደረግባቸው እንደበር አመልክተዋል። በዚህም ስጋት ውስጥ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩና አጋሮቻቸው በገዢው ኃይል በወቅቱ እስር ወይም ግድያ ቢፈጸምባቸው ትግሉ እንዲቀጥልና ያለውን ሁኔታ የሚያመልክቱ የቪዲዮና የጽሁፍ መልዕክቶች አዘጋጅተው በሚታመኑ ሰዎች እጅ እንዲቀመጥ እስከማድረግ ተገደው እንደነበር ገልጸዋል። በዚህ ሁኔታው ውስጥ እንዳሉም ከመመረጣቸው ከቀናት ቀደም ብሎ የለውጡ መሪዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸው እንደነበርና፤ ከዚያ በፊት ግን ከጦርነት ያልተናነሰ ውዝግብ ተካሂዶ ምሽት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን የኢህአዴግ ሊቀ መንበር ለማድረግ በምርጫ በድምጽ ሲወሰን ቡድኑ "የመጀመሪያው ሽንፈት አጋጠማቸው" ሲሉ አብራርተዋል። የህወሓት አመራሮች ፍላጎት የነበረው "እኛን በማስወገድ መንግሥት ያልሆኑ ግን መንግሥት የሚመስሉ ሰዎችን ማስቀመጥ ነበር፤ በመቃብራችን ላይ ነው እኛ ያማንፈልገው ሰው አገርን የሚመራው ሲሉ ነበር" በማለት የነበረውን ሁኔታ ገልጸውታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ከለውጡ በኃላ በአዲስ አስተሳሰብ ቂምና ጥላቻን በመተው በይቅርታ ላይ የተመሰረተ አካሄድን በመከተል "አቃፊ አገረ መንግሥት እንገንባ የሚል ሀሳብ ለማራመድ ተሞክሯል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ይሁን እንጂ በስብከት አገር መምርት አይቻልም፣ ደካማ መንግሥት ነው ያለው በሚል እሳቤው በተፈለገው መንገድ ለውጥ ሊያመጣ አልተቻለም" ብለዋል። ጫናውና ክትትሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላም መቀጠሉን የሚናገሩት ዐብይ፤ በተሾሙበት ዕለት የግል ጠባቂዎቻቸውን ወደ ጽህፈት ቤታቸው ይዘው መግባት እንደማይችሉ በአገሪቱ ደኅንነት ሹም እንደተነገራቸው በመጥቀስ "በወቅቱ እንኳንስ አገር ልመራ፤ የግል ጠባቂዎቼን እንኳን ማዘዝ አልችልም ነበር" ብለዋል። ቤታቸውና ጽህፈት ቤታቸው በደኅንነት ሠራተኞች ቁጥጥጥር ስር በመሆኑ በነጻነት የዕለት ከዕለት ስራቸውን ለመስራት ከማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደነበሩ "እንኳንስ የአገርን ደኅንነት ልጠብቅ ይቅርና የልጆቼን ደኅንነት እንኳን ማረጋገጥ በማልችልበት ሁኔታ ውስጥ ነበርኩ" ሲሉ ምን ያህል የአገሪቱ የደኅንነት ተቋም ከሕግ በላይ እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም ሳቢያ በወቅቱ "ዘመናዊ እስር ቤት ውስጥ የነበረ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆኔን ተረዳሁ" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መታፈን መገደል ሊያጋጥም ይችላል በሚል ለቤተሰባቸው ደኅንንት በመስጋት ቀድሞ ወደሚኖሩበት አገር እንዲመለሱ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የታቀደ ሥራን መጀመር ከለውጡ በፊትና በለውጡ ሰሞን ከባድ ያለመረጋጋት ችግር ገጠመው የሶማሌ ክልል ላይ ትኩረት አድርገው መስራት እንደጀመሩ ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አገሪቱን ለማናጋት የሚፈልገው ቡድን የሶማሌ ክልልን ማዕከል በማድረጉ ይህንን ችግር ለመፍታት ወደ ክልሉ ለመሄድ ባሰቡ ጊዜ የደኅንንት ሹሙ "አልሻባብ ይገድልሀል መሄድ አትችልም ተባልኩ፤ ነገር ግን ሥራዬን ልስራ ብዬ ሄድኩ" ይላሉ። በመቀጠልም፤ "ወደ መቀለ ስሄድ የሕዝቡ አቀባበል ድንጋጤ ፈጠረባቸው፣ አምቦ፣ ባሕር ዳር ለመሄድ ስነሳ ኦነግና የቅማንት ኮሚቴ ይገድልሃል ተባልኩ ነገር ግን አልቀረሁም" በማለት ደኅንነቱ አገሪቱን ለማረጋጋት በሚሰሩ ሥራዎች ውስጥ ሁሉ ጣልቃ ሲገባ እንደነበር ሌሎች ምሳሌዎችንም በመጥቀስ የነበረውን ፈተና አስቀምጠዋል። የአገሪቱ የመከላከያና የደኅንነት ተቋማት የአንድ ቡድን መጠቀሚያ በመሆናቸው ከዚያ በኋላ በእንዲህ አይነት ሁኔታ መቀጠልና አገርን መገንባት አስቸጋሪ መሆኑ በመታመኑ ከሌሎች የለውጡ አመራር አባላት ጋር በመሆን በጥናት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ "በመከላከያና በደኅንነቱ ውስጥ ያሉትን በመንግሥት ውስጥ ያሉ መንግሥታትን የማንሳት ውሳኔ ላይ ተደረሰ" በማለት ለውጥ እንደተጀመረ ገልጸዋል። ለውጥ በመከላከያ በአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ያለው አብዛኛው የአመራርነት ቦታ ከትግራይ በመጡ ሰዎች የተያዘ በመሆኑ በአሃዝ አስደግፈው ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ይህ በተገቢው ልክ መሆን ይኖርበታል ተብሎ የለውጥ ሥራ ተጀምሯል። ኢትዮጵያን የሚመስል መከላከያ ሠራዊት ለመገንባት እየተሰራ ነው" ብለዋል። ባለፉት ሦስት አስርታት ሠራዊቱ የአንድ ፓርቲ መመሪያን ይከተል ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ እንደ አብነትም የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት መመሪያን አንስተው "ከአገሪቱ ሕገ መንግሥት ጋር የሚቃረንና የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ርዕዮትን በመጠበቅ እሳቤ ላይ የተመሰረተ ነበር" ብለዋል። በዚህም መሠረት ባለፉት ሁለት ዓመታት የመከላከያ ሠራዊቱ ላይ መንግሥት ሰፊ የለውጥ እርምጃ ማድረጉን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተለይ እጅግ ወሳኝ ተልዕኮዎችን የሚወጣ ልዩ ኃይል (ስፔሻል ፎርስ) እና አየር ኃይል ላይ ሰፊ ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም በሠራዊቱ ላይ ከተደረገው ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ሪፐብሊካን ዘብ (ሪፐብሊካን ጋርድ) አስፈላጊነቱ እያበቃ ስለሆነ ወደ መከላከያው እንደሚካተት አስታውቀዋል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየው አለመግባባት ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ መካረሩ ይታወሳል። ተከትሎም የፌደራል መንግሥቱን ውሳኔ ባለመቀበል ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል የተካሄደው የተናጠል ምርጫ የፌደራል መንግሥቱን ተቀባይነት ካለማግኘቱ በተጨማሪ በአገሪቱ ምክር ቤቶች ሕገ ወጥ ተብሎ ውድቅ ተደርጓል። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የክልሉን አስተዳዳሪዎች ሕገ መንግሥቱን በመጣስና ከሕግ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በማለት የፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ ክልል ክልል አስተዳደር ጋር የነበረውን የቀጥታ ግንኙነት አቋርጦ የበጀት ዕቀባ ጥሎ ነበር። አለመግባባቱና መካሰሱ ያለማቋረጥ በቀጠለበት ሁኔታ ጥቅም 24/2013 ዓ.ም ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትግራይ ክልል በነበረው የፌደራሉ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ይፋ ካደረጉ በኋላ የፌደራሉ ሠራዊት በትግራይ ክልል ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ይታወሳል። መንግሥት "ሕግ የማስከበር" ባለውና ከሦሰት ሳምንታት በላይ በተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ቁጥሩ በትክክል ባይታወቅም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ተሰደዋል። ባለፈው ቅዳሜ የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ሰር ከዋለች በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሳውቀዋል።
news-52703738
https://www.bbc.com/amharic/news-52703738
ኮሮናቫይረስ፡ በዓለማችን ምርጥ የጤና ሥርዓት ያላቸው አምስቱ አገራት እነማን ናቸው?
ዓለም ከኮሮናቫይረስ ጋር ፍልሚያ ውስጥ ገብታለች። የፍልሚያው ስኬት በአገራት የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ውጤታማነት ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ ቫይረሱ በሰዎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በመቀነስና መስፋፋቱን በመቆጣጠር በኩል አገራት ቀደም ሲል በዘረጉት የጤና ሥርዓት መካከል ግልጽ የሆነ ቁርኝት እንዳለ ባለሙያዎች ይስማማሉ። በፈረንጆቹ 2019 መቀመጫውን ለንደን ባደረገው ተቋም የተጠናው 'ዘ ሌጋተም ፕሮስፐሪቲ ኢንዴክስ' በ12 መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ተመርኩዞ በ167 የዓለም አገራት ላይ ያደረገውን የምጣኔ ሃብት እና ብልጽግና ፖሊሲዎች እንዲሁም ተጨባጭ ሁኔታዎችን በመተንተን ደረጃ አውጥቷል። የዚህ የሁኔታዎች አመልካች ዝርዝር ያስቀመጠው የጤና ሁኔታ ደረጃ በየአገራቱ ያሉ ሰዎች ምን ያህል ጤናማ እንደሆኑ እና የጤና ተቋማትን አገልግሎት የማግኘት ዕድል ላይ ተመረኮዞ የተዘጋጀ ነው። በተጨማሪም በጤናው ዘርፍ ወደፊት ተራምደዋል የሚባሉት አገራት የኮሮናቫይረስን እንዴት እየተቆጣጠሩ እንደሆነ ለመገንዘብ የህክምና ባለሙያዎችንና የዜጎችን ምላሽ ሰብስቧል። ጃፓን የሩቅ ምሥራቋ አገር ጃፓን በመረጃ ጠቋሚው የጤና ዝርዝር ውስጥ ከቀዳሚዎቹ ተርታ ላይ ትገኛለች። ኮቪድ-19ን በእንጭጩ ለመቆጣጠር በወሰደችው እርምጃ ብትወደስም የቫይረሱ ስርጭት መስፋፋት አገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ እንድታውጅ አስገድዷታል። ቫይረሱን ሳይስፋፋ ለመቆጣጠር ባላት አቅም ምክንያት የመንቀሳቀስ እገዳ እንዳትጥል አድርጓታል። ነዋሪዎች ያለምንም የቫይረሱ ምልክት የኮቪድ-19 ምርመራ ባይደረግላቸውም የሳምባ ምች ምርመራ ማደረግ ይችላሉ። "ይህም ታማሚው በፍጥነት ሕክምና እንዲያገኝ ያስችላል። ጃፓን ብዙ አስጊ ታካሚዎች የሌሏት ለዚህ ነው" ሲሉ መቀመጫቸውን በቶኪዮ ያደረጉት ዶክተር ሚካ ዋሺዮ ያስረዳሉ። የጃፓናዊያን የጤና ግንዛቤ የኮቪድ-19 ተፅዕኖን ቀንሷል። "ቀድሞውንም ቢሆን ብዙ ጃፓኖች የፊት ጭንብል የማድረግና ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ዓመታዊ የጤና ምርመራ ማድረጋቸው አስከፊ ጉዳት እንዳይከሰት ረድቷል" ይላሉ። ይህም ሆኖ ፈተና ሊደቀን ይችላል። ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች በተለመደው ሁኔታ ሆስፒታል መሆን ሲገባቸው መንግሥት ተጨማሪ ሃብት ለማሰባሰብ በሚል አልጋዎችን በከፍተኛ ደረጃ ለታመሙ እያስቀመጠ ነው ይላሉ ዋሺዮ። ደቡብ ኮሪያ ደቡብ ኮሪያ ከፈረንጆቹ 2015 የሜርስ ወረርሽኝ ልምድ ኮቪድ-19ን ለመከላከል ዝግጁ ናት። ሆስፒታሎች ለዚህ በሚሆን መልኩ በባለሙያዎችና መሣሪያዎች ተዘጋጅተዋል። 51 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት አገር ከ450 ሺህ በላይ ሰዎችን ስትመረምር በቅርብ ጊዜ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ47 እስከ 53 ብቻ ነው። የኮሪያ የጤና ሥርዓት ለዜጎች የጤና ኢንሹራንስን ስለሚሸፍን ለኮቪድ-19 ምርመራና ህክምና አስተዋጽኦ አድርጓል። "ምስጋና ለጤና ኢንሹራንስ እና ለመንግሥት ድጋፍ ይሁንና በአነስተኛ ዋጋ ምርመራው በስፋት ተካሂዷል" ሲሉ መቀመጫቸውን በሴኡል ያደረጉት ዶክተር ብራንደን ቢ ሱህ ተናግረዋል። "ወረርሽኙ እንደተከሰተ ብዙ ሰዎች ቀደም ብለው በመርመራቸው ተገቢው እርምጃ በወቅቱ ተወስዷል" ብለዋል። መንግሥት እና ተቋማትም ውጤታማ የጤና እርምጃዎችን ለመተግበር በፍጥነት ተንቀሳቀሰዋል። "መንግሥት አዲስ እርምጃ በመውሰድ በጭምብል አቅርቦት ላይ በየቀኑ ሠርቷል" ይላሉ የሴኡል ሠራተኛው ዮንቦክ ሊ። "በብዙ ቦታዎች የሰውነት ሙቀት ይለካል። የኮሪያ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል እንዲሁም ሌሎችም የመንግሥት ተቋማት በግንባር ቀደምነት እየሠሩ ሲሆን ሕዝቡም ለጥረቶቻቸው ከፍተኛ አድናቆት እያሳየ ነው" ብለዋል። መንግሥት ቀደም ተብሎ ጣልቃ መገባቱ ተስፋን ሰጥቷል። "ወረርሽኙ እየቀነሰ ሲሆን ሰዎች ሁሌም ጭምብል እያደረጉ ነው። ከቤት ውጪም እንቅስቀሴ ጀምረዋል" ብለዋል ሱህ። ወረርሽኑ ከተስፋፋባቸው ቦታዎች አንዷ የሆነችው የዴጉ ከተማ ነዋሪዋ ዎን-ጄኦንግ ዋንግ ህይወት እንደቀደመው እየተመለሰ መሆኑን እየታዘቡ ነው። እስራኤል ኮቪድ-19 በዉሃን ሲከሰት በፍጥነት እርምጃ ከወሰዱ አገራት አንዷ እስራኤል ናት። ወረርሽኙ ከተከሰተ በሚል የጤና ሚንስቴር የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ድንጋጌን ጥር ላይ አጽድቋል። በተለይም አስጊ ወደተባሉ አገራት አላስፈላጊ ጉዞ እንዳይደረግ እና ለይቶ ማቆያን ተግባራዊ ማድረጓ የወረርሽኙን ክስተት ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጓል። እስራኤል ውስጥ ትክክለኛ ምርመራ በፍጥነት ተጀምሯል። ከመተንፈሻ አካላት ውስጥ ኮሮና ቫይረስን መለየት የሚያስችል አሰራር በአገሪቱ ቤተ-ሙከራዎች መዳረሱን የቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲው ባልደረባ ዶክተር ኪታም ሙህሴን ያስረዳሉ።"ከሚሊዮን ሰዎች መካከል ብዙዎችን በመመርመር ቀዳሚ ከሆኑት አገራት እስራኤል አንዷ ናት" ብለዋል። "በምናደርገው የምርመራ ብዛት እኮራለሁ። ብዙ ቁጥር በመመርመራችን ነው ብዙ ሰው ቫይረሱ እንዳለበት ያወቅነው" ይላሉ የከፋር ሳባ ነዋሪው ታሊያ ክሌይን ፒሬዝ። "ሞት መጠኑ ዝቅተኛ የሆነው ቀደም ብለን ኳራንቲን ማድረግ በመጀመራችን ነው" ሲሉ ያስረዳሉ። በሕዝብ ላይ የተመሠረተ የጤና አጠባበቅ ሥርዓቱም ለተቀናጀ ምላሽ ምክንያት ሆኗል፡፡ "ወጪው ስለሚሸፈንላቸው ሰዎች የሕክምና ዕርዳታ ለማግኘት አይፈሩም" ሲሉ የእስራኤሉ ሼባ ሜዲካል ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አርኖን አፌክ ገልጸዋል። "የህክምና ዋጋ ወሳኝ ነው። ምክንያቱም ሰዎች ምልክቶችን ሲያዩ በሽታውን ከማስፋፋታቸው በፊት ይታከማሉ።" ለጤናው ዘርፍ በቂ ድጋፍ ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው ባይደረግም ፈጣን እርምጃዎች ይወሰዳሉ ይላሉ አፌክ። "ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ሁለት እርምጃ ቀድመን እንገኛለን። ታካሚዎች ሲመጡ ዝግጁ እንሆናለን" ብለዋል። ጀርመን ጀርመን ከብዙዎቹ የአውሮፓ ጎረቤቶቿ አንፃር ሲታይ አነስተኛ የሞት ምጣኔ አላት። በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ ብትባለም ባለሙያዎች ግን ሙሉ ለሙሉ ሥራውን አላጠናቀቀችም ይላሉ። "በጀርመን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምርመራና አነስተኛ የሞት ምጣኔው ለብዙዎች ግርምት እንዲሁም የአገሪቱን የጤና አጠባበቅ ደረጃ ያሳያል" ሲሉ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ደ ቬሪኮርት ገልጸዋል። ሰፊ ምርመራው ታማሚዎችንና ምልክት ያሳዩትን በመለየት ስርጭትን ለመቀነስ አግዟል። አገሪቱ ጥንቃቄ ካላደረገች ይህ ዝቅተኛ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች መጠን አደጋ ሊያስከትል ይችላል። "አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እና ባህሪን መቀየር ቫይረሱ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስ መቀጠል አለበት" ብለዋል ደ ቬሪኮርት። ነዋሪዎች ነገሮች በቅርቡ ወደ ቀድሞው ሁኔታ ላይመለሱ ይችላሉ ቢሉም ተስፋ ግን አልቆረጡም። "በጣም የከበደኝ እናቴ ከቤት እንዳትወጣ ማድረግ ነው። ለዚህ ነው ጭንብል አዘጋጅቼ ከሦስት ሳምንት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አብረን ወደ ሱቅ የወጣነው" ሲሉ አንድ ነዋሪ ተናግረዋል። አክለውም "የአዳዲስ ተጠቂዎች ቁጥር በመቀነሱ ዕገዳዎችን በማላለቱ ዙሪያ ላይ ማስብ አስፈላጊ ይመስለኛል። የመንግሥት ኃላፊዎች በሽታውን እየተቆጣጠሩ ወደ መደበኛ ህይወታችን እንድንመለስ ይረዱናል ብዬ አምናለሁ" ብለዋል። ውጤታማው የአገሪቱ የጤና ሥርዓት አገር አቀፍ ምላሽን ለማድረግ ዝግጁ ነው። "ብዙ አልጋዎች ፣በጣም ብዙ የጽኑ ህሙማን ክፍሎችና ብዙ ዶክተሮች አሉ። እነዚህን ለማስተዳደር ሁሉም የመንግሥት መዋቅር ኃላፊነት አለበት" ሲሉ ደ ቨሪኮርት አስረድተዋል። አውስትራሊያ አውስትራሊያ እንደ ጠቅላይ ሚንስትሯ ገለጻ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ፍጥነቱን ከአምስት በመቶ በታች አድርጋለች። በአውስትራሊያ የመንግሥትና የግል በሆነው "ቅይጥ" የጤና አጠባበቅ ሥርዓቷ መጥፎ ሁኔታዎችን ለመቋቋም ተዘጋጅታለች። ይህ በሁለቱ እገዛ የሚደረግ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት አገሪቱን ዝግጁ እንዳደረጋት በሜልበርን ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶክተር አሌክስ ፖልያኮቭ አስረድተዋል። በተጨማሪም በአገር ውስጥ የቫይረሱ መተላለፍ ምጣኔ ዝቅተኛ ሲሆን፣ መንግሥትም ከውጪ ለመጡ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ በማዘጋጀትና በበሽታው ከተጠቁ ግለሰቦች ጋር ንክኪ ያላቸውን በፍጥነት እየለየ ነው። "የአገር ውስጥ ስርጭት አነስተኛ ሲሆን በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሚሆን እገምታለሁ። ይህ ነው ስርጭቱን መቆጣጠር ማለት" ብለዋል። አሁን ባለው ፍጥነት ከቀጠለ አውስትራሊያ በቂ የጽኑ ህሙማን አልጋዎችና የመተንፈሻ መሣሪያዎች አሏት። "ከግል ሥርዓቱ የሚገኘው ተጨማሪ አቅም አብዛኛዎቹ ሰዎች ህክምና በወቅቱ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል" ብለዋል ፖልያኮቭ። የእንቅስቃሴ ዕገዳዎች ከቀለሉ በኋላ ነዋሪዎች ወደ ቀድሞ ህይወታቸው ይመለሳሉ "ሁሌም በየሳምንቱ እንደምናደርገው ከጓደኞቼ ጋር እየሳቅን በምንወደው ካፌ ቡና መጠጣትን እናፍቃለሁ" ሲሉ መቀመጫቸውን ሲድኒ ያደረጉት የጉዞ ጸሐፊዋ ጄኒፈር ደ ሉካ ተናግረዋል።
news-46630111
https://www.bbc.com/amharic/news-46630111
«ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር» አዲስ ዓለማየሁ
አቶ አዲስ ዓለማየሁ ለሥራ ጉዳይ ወደ ናይሮቢ ብቅ ባለበት አጋጣሚ አግኝተን፤ እስኪ ስለ ሥራ ፈጠራ አጫውተን ብለነው ነበር። መልካም ፍቃዱ ኾኖ ይህን አጭር የትጋት ታሪኩን አካፍሎናል።
አዲስ አበባ ተወለድኩ፤ በስምንት ዓመቴ ወደ ኬንያ መጣሁ። ናይሮቢ ካደግኩ በኋላ ወደ ካናዳና አሜሪካ ለትምህርትና ለኑሮ አቀናሁ። የሆነ ቀን "ከየት ነህ?" የማልባልበት አገር ናፈቀኝ። በ2000 በፈረንጆች ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ። ለአምስት ዓመት በ"USAID" ተቀጥሬ ሠራሁ። የኢትዮጵያን ምርት ለአሜሪካ ማስተዋወቅ ነበር ዋና ሥራዬ። በዚያ ቆይታዬ "ኢትዮጵያ 101" ኮርስ እንደወስድኩ ነው የምቆጥረው። ለምን በለኝ፤ የግል ሴክተሩ እንዴት እንደሚሠራ፣ የመንግሥት ፖሊሲዎች ምን እንደሚመስሉ የተማርኩት ከዚያ ነው። ደግሞም ሰው አውቄበታለሁ። ከዚያ ወጥቼም "አፍሮ ኤፍኤምን" መሠረትኩ፤ በሽርክና። ከሦስት ዓመት በፊት ደግሞ ቃና ቲቪን ከአጋሮቼ ጋር በመሆን ከፈትኩ። "251 ኮሚኒኬሽንስ" የሚባለውን የብራንዲንግ፣ የማርኬቲንግና የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን የሚሠራ ኩባንያም መሥርቻለሁ። ደበቡ አፍሪካ ውስጥም አንድ ኩባንያ አለ፤ አፍሪካ ኮሚኒኬሽን ግሩፕ የሚባል። ከአገሬው ሸሪኮች ጋር በመሆን ነው የጀመርነው። አራዳ ሞባይል የሚባል ከቮዳኮም ጋር ደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የሲም ካርድ አገልግሎት የሚሰጥ ነው። ከዚያ ውጭም የጀማመርኳቸው አዳዲስ ቢዝነሶች አሉ። • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ ምን አሳካህ? በ"251 ኮሚኒኬሽንስ" በርካታ ስኬታማ ሥራዎችን ከዓለም ባንክ፣ ከኮካኮላ፣ ከጌትስ ፋውንዴሽን፣ ከ"ገርል ኢፌክት" ጋር በመሆን ሠርተናል። ለምሳሌ "የኛ" የሚለው መለያ ስም (Brand) ከኛ ቤት ነው የወጣው፤ "ሹም ሹፌር" የዲያጆ መለያ ስም ከኛ ቤት ነው የወጣው። 'ፍክትክት' የማልታ ጊነስ ስም ከነ መለያ ምልክቱና ከነዲዛይኑ እኛ ነን የሠራነው። "ኢትዮጵያ" የሚለው አዲሱ የቱሪዝም አርማ የኛ ሥራ ነው። "ቃና" ከስሙ ጀምሮ መለያው ሁሉ ከኛ ቤት ነው የወጣው። "ቃና ቲቪ እንዴት ተጀመረ?" የመጀመርያው ሐሳብ የነበረው "MTV"ን የሚመስል ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመር ነበር፤ የሙዚቃ ቻናል። ይህን ለማሳካት ደቡብ አፍሪካ ሄጄ ከ"MTV" ሰዎች ጋር አውርቻለሁ። ስኬታማ እንደሚሆን ለምን እርግጠኛ ሆንኩ? ከመቶ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አለን፤ ኢትዮጵያ ውስጥ አማካይ ዕድሜ 17 ነው፤ የሙዚቃ ቻናል ተወዳጅ ሊሆን እንደሚችል አሰብኩ። ኾኖም የMTV ሰዎችን ሳናግራቸው የፕሮዳክሽን ወጪያቸው ከፍተኛ በመሆኑ በአገር ውስጥ ማስታወቂያ ይሸፈናል ብለው እንደማያምኑ ነገሩኝ። ነገሩን በራሴ መግፋት እንዳለብኝ ወሰንኩ፡፡ ከኢልያስ ሹትዝ ጋር አወራንበት። አሁን የቃና ሸሪክ ነው። ጥናት እናስጠና አለኝ። 'የምን ጥናት ነው ሁለት ቲቪ ቻናል ለመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ባለበት አገር' አልኩ። ብቻ ለ2 ወራት ጥናት አደረግን። ቤቱ ቲቪ ያለው አብዛኛው ሰው ሳተላይት አለው፤ ግን አረብኛ ነው የሚያየው፡፡ ስለዚህ በአማርኛ ተርጉመን ብናቀርብስ የሚል ነገር ተነሳ። ጣሊያን ብትሄድ የሆሊውድ ፊልም በጣሊያንኛ ነው የምታየው፤ ጀርመን ብትሄድ፣ ፈረንሳይ ብትሄድ እንደዚሁ...እኛ በምንድነው የምንለየው? በዚህ ሂደት ውስጥ እያለን 'ሞቢ ግሩፕ'ን አገኘን። ሞቢ ሁለት የአፍጋኒስታን ወንድማማቾች የመሠረቱት ኩባንያ ነው፤ አውስትራሊያ ያደጉና ወደ አፍጋን ተመለስው የመጀመርያን ኤፍ ኤም የጀመሩ፤ ከዚያ የማስታወቂያ ድርጅት፣ ከዚያም በአካባቢው አገራት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች. . . የጀመሩ ወንድማማቾች ናቸው። ራሴን በእነርሱ ውስጥ አየሁት። በምትሠራው ሥራ ሁሉ ራዕይህን የሚጋራ፣ አብሮህ የሚያልም፣ አብሮህ 'ሪስክ' የሚወሰድ ከሌለ ማደግ አስቸጋሪ ነው። እኔ በዚህ ረገድ ዕድለኛ ሳልሆን አልቀርም። • በሳተላይቶች ዙሪያ ሰባት አስደናቂ እውነታዎች ቃና ቲቪ ተመልካቹ ቀንሷል? እውነት ነው፤ በርካታ ቻናሎች መጥተዋል። የሕዝቡ አስተያየት ተቀይሯል። ሕዝቡ በፖለቲካና በወቅታዊ ጉዳይ ተይዟል። ድሮ በነበረው ሁኔታ ሰው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አያይም ነበር፡፡ አሁን ግን ይከታተላል። ዜናው ራሱ ድራማ ሆኗል [ሳቅ]። ወጣቱ በሚገባው ቋንቋ ለማቅረብ እንሞክራለን። 'ሽቀላ' የምትባል ነገር ጀምረናል። የሥራ ፈጠራን ለማበረታት። ሐሳብ ይዞ በፍርሃት የተቀመጠን ወጣት ለማነቃቃት ነው። አዲስ ስቱዲዮ ከፍተናል፤ ወደፊት ያሰብናቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ. . . ቃና ለምን ተቃውሞ በዛበት? የትም ዓለም ያለ ነው። አዲስ ነገር ይዘህ ስትመጣ ነባሩ አሠራር ይጋፈጥሃል። አሁን ራይድ መምጣቱ ታክሲዎችን አበሳጭቷል። እዚህ ናይሮቢ ኡበር ሲጀምር እንደዛ ነበር። የተለመደውን ነገር የሚቀይር አሰራር ይዘህ ስትመጣ ያለ ነው። በዓለም ትልቁ ሆቴል አንድ የሆቴል ክፍል የለውም፤ ኤይአርቢኤንቢ! በዓለም አንደኛ የታክሲ ካምፓኒ አንድ ታክሲ የለውም፤ ኡበር! በዓለም ትልቁ ሚዲያ ካምፓኒ አንድ ጣቢያ የለውም፤ ፌስቡክ ይቺ ናት አዲሷ ዓለማችን። ሁሉም ሰው ነጋዴ መሆን ይችላል? አይችልም። ትልቁ ስህተት እሱ ነው። እነማን ናቸው ቢዝነስ መጀመር የሚችሉት ካልከኝ፤ ደፋሮች እልሀለው። ደፋር መሆን አለብህ። ብዙ ሰው የራስ ቢዝነስ ሲባል በጎ በጎውን ብቻ ነው የሚያየው። የራስህ አለቃ መሆንን፣ በፈለከው ሰዓት ቢሮ መግባት መውጣት መቻልህን...። እውነት ለመናገር ብዙ ጭንቀት አለው። ጧት ስትነሳ ስለራስህ ቤተሰቦች ብቻ ሳይሆን ስለሁሉም ሠራተኞችህ ነው የምታስበው። ከነሱም አልፈህ ስለ ሠራተኞችህ ቤተሰቦች ታስባለህ። የሰራተኛህ ቤተሰብ በሙሉ ያንተ ቤተሰብ ነው። አንድ ሰራተኛ የ 3 እና 4 ቤተሰቡን አባል ይመግባል። ስለዚህ መቶ ሰራተኛ ካለህ ሦስት መቶ አራት መቶ ሰው ባንተ ላይ ነው። ያ ኃላፊነት ቀላል አይደለም፤ ያስጨንቃል። ከዚያ ሌላ ካንተ ቁጥጥር ውጭ ያሉ ጉዳዮች አሉ፤ የታክስ ጉዳይ አለ፣ የውጭ ምንዛሬ ጭንቀት አለ፣ ቢሮክራሲ አለ፣ መዓት ነው ጭንቀቱ። ደመወዝ መክፈል ጭንቅ የሚሆንበትም ጊዜ አለ። ይህን ሁሉ ጭንቀት የሚችል ሰው በጣም ጥቂት ነው። ሁሉም ሰው ነጋዴ የማይሆነውም ለዚሁ ነው። ወድቄ እነሳለሁ ማለት የሚችል ሰው መሆን አለበት። በየቀኑ ከባድ ውሳኔዎችን መወሰን የሚችል ሰው መሆን አለበት። ሁሉም ሰው ነጋዴ መሆን አይችልም። አንዳንድ ሰው ተቀጥሮ መኖር ያለበት ነው። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ አፍሮ ኤፍ ኤም እንዴት ተጀመረ? አፍሮ ኤምኤምን ለምን ጀመርክ ብትለኝ እንግሊዝኛ ጣቢያ አልነበረም። ዞር ብለህ ስታየው አፍሪካ ኅብረት አለ፤ ያ ሁሉ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አለ። ብዙ ከውጭ የሚመጡ ኢትዮጵያዊያን አሉ። ወጣቱ ደግሞ እንግሊዝኛ ሙዚቃ መስማት ይፈልጋል። ያኔ ምንም አልነበረም። አሁን ናይሮቢ ስንት ናቸው? ከ80 በላይ ሬዲዮ ጣቢያ አለ። አንዳዴ ጥናት ማስጠናትም የማያስፈልገበት ሁኔታ አለ፤ ምክንያቱም ፍላጎቱ ካለው ሕዝብ ጋር በጭራሽ አይመጣጠንም። ቃና ሲጀምር ሦስተኛ የቲቪ ጣቢያ ነበር። ለመቶ ምናምን ሚሊዮን ሕዝብ። ወደፊት ምን አሰብክ. . . ብሩህ አእምሮ ያላቸው ወጣቶች አሉ። አዳዲስ የቢዝነስ ሐሳብ ያላቸው። ከዚህ በኋላ ከነዚህ ወጣቶች ጋር መሥራት እፈልጋለሁ። አብሬያቸው ለማደግ ነው የምፈልገው። ኢትዮጵያ ውስጥ ቢዝነስ መጀመር ያዋጣል? ከሕዝቡ 73 በመቶ ዕድሜው ከ30 ዓመት በታች ነው። አማካይ ዕድሜ 17 ነው። ይህ ማለት ሥራ ሲይዝ ቤት የሚገዛ፣ ምግብ የሚገዛ፣ ልብስ የሚገዛ፣ ሲያገባ ደግሞ ዳይፐር የሚገዛ ነው። የሸማችነት ጊዜ ገና ያልተጀመረበት ሕዝብ ነው። መጪው ጊዜ ለቢዝነስ ብሩህ ነው። ወጣቶች ለምን ቢዝነስ መጀመር ይፈራሉ? ወጣቶችን ቢሮክራሲው ይፈትናቸዋል። አንደኛ 'ኢንተርፕረነርሺፕ' የተለየ ጭንቅላትና ሞራል ያስፈልገዋል፤ ፊት ለፊትህ ያለው ብዙ ፈተና ስለሆነ። የትምህርት ሥርዓቱ ሥራ ፈልገን እንድነገባ እንጂ ሥራ እንድንፈጥር የተዘረጋ ሲስተም የለውም። ስለ ፈጠራ፣ ስለ ሥራ አመራር፣ ስለቢዝነስ ብዙ አያስተምሩንም። ከቤተሰብ ይጀምራል፤ አንድ ልጅ የራሴን ሥራ ነው መሥራት የምፈልገው ሲል ምን ያህል ወላጅ ነው 'በርታ! ጎበዝ! የኔ ልጅ!' የሚለው? ዕቁብም ጥሎ እንካ ሞክር የሚል አለ? ልጄ ወደፊት ነጋዴ ነው የሚሆነው ብሎ የሚያወራው የትኛው ቤተሰብ ነው? በቢዝነስ ሐቀኛ የሚባል መንገድ አለ? በሕጉ መመራት ነው። ሕጉን ተከትለህ ብዙ ዕድል አለ። ከካናዳ ወደዚህ ስመጣ አባቴ የመከረኝ ነገር ነበር። "ስሜን የሚያሰድብ ነገር እንዳትሠራ። የአቶ ዓለማየሁ ልጅ እንደዚህ አደረገ እንዳታስብል ብሎኝ" ነበር። አጭሯ መንገድ ሁሌም አለች። አጭር መንገድ ብወስድ ትግሉ አጭር ይሆንልኝ ነበር። ሆኖም ያንን አልመረጥኩም። አጭሩን መንገድ ሰው የሚመርጠው እኩል የጀመሩ ሌሎች ሰዎች በአጭሩ ሲበለጽጉ ስለሚያይ ነው። ግን እሱ የሚተኛውና አንተ የምትተኛው እንቅልፍ አንድ አይደለም። ቢዝነስ እንዴት ጀመርክ? ቢዝነስ ማለት የሰውን ችግር መፍታት ማለት ነው፤ በአጭሩ። የሰው ልጅ መሬት ላይ መቀመጥ ስለሰለቸው ነው ወንበር የሠራው፤ ስለበረደው ነው የሚለበስ የሰፋው። እያንዳንዱ ችግር የቢዝነስ ሐሳብ ነው። ችግር ስመለከት ቢዝነስ ነው የማየው። ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር። እኔ ለመጀመርያ ጊዜ ለሰው ዕቃ አቅርቤ ገንዘብ ያገኘሁት ከእናቴ ነው። ጓሮ አትክልት እያሳደኩ ለእናቴ እሸጥላት ነበር። ከታናሽ ወንድሜ ጋር አትክልት እያሳደግን እንሸጥላት ነበር። ለሁሉም ሰው እግዜር ስጦታ ይሰጠዋል አይደል? ለኔ የሰጠኝ የምለው ሁልጊዜ አዲስ ሐሳብ ከአእምሮዬ እንዳይጠፋ ማድረጉ ነው። ከስረህ ታውቃለህ? ሦስት አራቴ ከስሪያለሁ፤ ገበያው የማይፈልገው አገልግሎትና ምርት አምጥቼ ከስሪያለሁ፤ አሁን ወጣቶች ላይ ቶሎ ቢዝነስ ሰርቶ 'ቪትዝ' የመግዛት ባህሪ አያለሁ። ቢዝነስ አልጋ በአልጋ አይደለም። መልፋት ይፈልጋል። እኔ እንጀራ ጋግሬ እሸጣለሁ ካልኩኝ 30 ምጣድ አያስፈልገኝም። እቤት ባለው ምጣድ ነው መጀመር ያለብኝ። ማንም ሲጀመር ገንዘብ ኖሮት አያውቅም። "251 ኮሚኒኬሽንስን" ስንጀምር በ40ሺህ ብር ገደማ ነው። ወጣቱ ያስፈራሃል? ይህ ሁሉ ወጣት ገበያ ነው። በዚያ መጠን አስፈሪ ነው። ወጣት ሆነህ፣ ትምህርትህን ጨርሰህ፣ ዲግሪ ይዘህ ሥራ ማጣት ተስፋ አስቆራጭ ነው። ይሄን በሚሊዮን ስታባዘው ደግሞ ለአገሩ የሚያስፈራ ሁኔታ ነው። ከሁሉም በላይ ሥራ የሚፈጥሩ ኢንዱስትሪዎች ላይ ማተኮር አለብን። እዚህ ኬንያ የመጣሁትም በአይሲቲ በኩል እንዴት ለወጣቱ ሥራ መፍጠር ይቻላል በሚለው ላይ ለመነጋገር ነው። ዓለም ወደዚያ እየሄደች ነው። ቴሌኮም ሲስፋፋ ብዙ ዕድል ይፈጥራል። አይቲ ኩባንያዎች ያንን ነው እየጠበቁ ያሉት። ብዙ ወጣቶች ላፕቶፕ ይዘው ፈጣን ኢንተርኔት የሚያቀርብላቸውን ብቻ እየጠበቁ ነው። ያን ካገኙ ከዓለም ጋር ተገናኝተው ሥራ መሥራት ይችላሉ። ሌላ ምንም አይፈልጉም። ላፕቶፓቸው ቢሯቸው ይሆናል። ፋይናንስ መቅረብ አለበት። ኢትዮጵያ አንዱ ትልቁ ችግር ዕውቀትና ገንዘብ አለመገናኘታቸው ነው። ዕውቀት ያለው ገንዘብ የለውም፤ ገንዘብ ያለው ሐሳብ የለውም። በየቢሮው የቢዝነስ ፕላን በጓሮ የሚሠረቀው እኮ ለዚህ ነው። ብር ያለው ሐሳብ የሌለው ብዙ ነው። ብዙ ሰው ፎቅ የሚሠራው ገንዘቡ ባንክ ከሚቀመጥ አንድ ነገር ልሥራበት በሚል ነው። ወጣቶች ላይ መዋል አለበት። በመንግሥት በኩልም ማበረታቻ መኖር አለበት። በሌላ ሰው ዕውቀትና በሌላ ሰው ጉልበት ገንዘብ መሥራት ማለት ቀላል ነገር አይደለም። ሁሉም ትልልቅ ቢዝነሶች የተፈጠሩት በዚህ መንገድ ነው። ፌስቡክ የተፈጠረው በዚህ መንገድ ነው። ሐሳብ ካለው ወጣት ጋር በገንዘቤ ገንዘብ መሥራት የማምንበት ነገር ነው። ሌላው ቢዝነስ ለመሥራት ውጣ ውረዱ መቀነስ አለበት። በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ቢዝነስ ለመክፈት አይደለም ለመዝጋት እንኳ ቀላል አይደለም። ከናይሮቢና ከአዲስ አበባ ማን ይበልጣል? ጥለውን ሄደዋል። እኛን የገደለን የደርግ 17 ዓመት ነው። ቢዝነስ ቆመ። የነበረው ተወረሰበት። የተማረው ተገደለ፤ ጥሎ ሄደ። ከዚያ 'ሀ' ብለን ነው የጀመርነው። ባለፈው 27 ዓመትም ቢሆን ነጋዴ እንደ ሌባ የሚታይበት ሁኔታ ነው የነበረው። ነጋዴ ከሆንክ ልትበላ ልትዘርፍ የወሰንክ ተደርጎ ነበር የሚታየው። 'ነጋዴ ሀብት ይፈጥራል፤ ሥራ ይፈጥራል፤ ነጋዴ አጋር ነው' ብሎ የሚያስብ መንግሥት አልነበረም፤ አሁን ግን ተስፋ አለ። እኛ በአገራችን እስከዚህም ነን። እስከ 40 ዓመታችን ቤተሰባችን ጋር ስለምንኖር ይመስለኛል። በአገራችን ስንኖር ሥራ ላይ ብዙም አይደለንም። ከአገር ስንወጣ ነብር ነን። ማንም አይችለንም። እንደኛ አራዳ ነጋዴ በዓለም የለም። ነገሮች መልክ ከያዙ መንግሥት የግሉን ዘርፍ ከደገፈ አካባቢውን እንደምንቆጣጠር ምንም ጥርጥር የለኝም። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?
news-53904361
https://www.bbc.com/amharic/news-53904361
እምቦጭ ፡ አረሙን ከጣና ሀይቅ ላይ ማጥፋት ያልተቻለው ለምንድን ነው?
የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ልማትና ጥበቃ ኤጀንሲ እንደሚገልፀው ከሆነ በአሁኑ ወቅት በጣና ሀይቅ ላይ ያለው የእምቦጭ አረም መጠን 900 ሄክታር አካባቢን የሸፈነ ነው።
የእምቦጭ አረም ማስወገጃ ማሽን ይህንን መጤ አረም ለማስወገድ ከፌደራል መንግሥት ጀምሮ የተለያዩ አካላት በገንዘብ፣ በቁሳቁስና በሙያ ርብርብ ያደረጉ ቢሆንም አሁንም ግን እምቦጭ ከመጥፋት ይልቅ እየተስፋፋ ይገኛል። አለም ዓቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማህበር የሰሞኑን ጨምሮ ሁለት ማሽኖችን ከአውሮፓ እና አሜሪካ ገዝቶ ወደ ጣና ልኳል። ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አንድ ማሽን ሰርቷል። ባሕር ዳር ውስጥ ሙላት የተባሉ ግለሰብ የሰሩትን ማሽን ጨምሮ ቁጥራቸው ስድስት የሆኑ ማሽኖች እምቦጭን ለማጨድ ተዘጋጅተዋል። ፌደራሉ መንግሥትም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የአረሙ ማስወገጃ ማሽን ለመግዛት 300 ሚሊዮን ብር መመደቡን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ከወራት በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር መግለጻቸው አይዘነጋም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወደ ስልጣን በመጡ በጥቂት ወራት ጊዜ ውስጥም ወደ ስፍራው በማምራት አረሙ በሃይቁ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ተመልክተው ለአካባቢው አርሶ አደሮች "እምቦጭን እናጠፋዋለን" የሚል ተስፋ መስጠታቸው የሚታወስ ነው። ታዲያ እምቦጭን እስካሁን ለምን ማጥፋት ሳይቻል ቀረ? የጣና ሀይቅ፣ በመጤ አረም መወረሩ ከታወቀ ዘጠኝ ዓመታት ተቆጥረዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ መጤ አረሙ ሀይቁን መውረሩ የታወቀው በ2004 ዓ.ም ነበር። ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ሀይቁን ከዚህ ወራሪ አረም ለመታደግ አልፎ አልፎ ዘመቻዎች ቢደረጉም፣ እምቦጩ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የሀይቁን መግቢያ በሮች ጥቅጥቅ አድርጎ ዘግቷል። በተለይ በሃይቁ ሰሜንና ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኙት የፎገራ፣ ሊቦከምከም፣ ጎንደር ዙሪያና ደምቢያ ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። እነዚህ አካባቢዎች ከፍተኛ ለም መሬት ያላቸውና በሀይቁ ዳርቻ የተለያዩ የሰብል ዓይነቶች የሚመረትባቸው ናቸው። የአካባቢው ነዋሪም ከአሳ ማስገር ጀምሮ የተለያዩ ምጣኔ ሃብታዊ ጠቀሜታዎችን ከሀይቁ በማግኘት ኑሮን ይመራ ነበር። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ኑሯቸው የተመሰረተው በጣና ሃይቅ ዙሪያ ነው። ዶ/ር አብዩ ዋሌ አለም አቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማህበር ውስጥ የማናጅመንት አባል ሲሆኑ በእምቦጭ ዙሪያ የተለያዩ ምርምሮችን ሰርተዋል። የዶ/ሩ ጥናት እንደሚያመለክተው በፈረንጆቹ 2017 ከመስከረም አስከ ህዳር ባሉት ወራት ብቻ አረሙ በቀን 14 ሄክታርን ይወር ነበር። በአሁኑ ወቅት የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት 385 ኪሎ ሜትር ከሚረዝመው አጠቃላይ የጣና ዙሪያ እስከ 120 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የሀይቁ ጠርዝ በእምቦጭ ተሸፍኗል። በእነዚህ አካባቢዎች በቀላሉ ወደ ሀይቁ መግባት የማይታሰብ ነው። በመሆኑም በሃይቁ ጫፍ አካባቢ እየኖሩ ከጣና፣ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከሚያገኙ ግለሰቦች መካከል በ120 ኪሎ ሜትር ዙሪያ የሰፈሩት ነዋሪዎች ከጣና ሀይቅ ጋር እንዳይገናኙ አረሙ ከልክሏቸዋል። እምቦጭ አረም እምቦጭ ለምን አልጠፋም? እምቦጭ በ2004 ዓ.ም ሃይቁን መውረሩ ከታወቀ በኋላ የመጀመሪያው የመከላከያ መንገድ ተደርጎ የተወሰደው በሰው ኃይል በማስወገድ ከሃይቁ ውጭ እያወጡ መከመርና ማድረቅ ነው። ይህ አሁን ድረስ ቀዳሚ መፍትሄ ተደርጎ የሚሰራበት የእምቦጭ አረም መከላከያ መንገድ ነው። ቢሆንም ግን በዚህ መንገድ እምቦጭን ለማጥፋት የተሰሩት ሥራዎች በአካባቢው የሚኖረው አርሶ አደር የሚናፍቀውን ለውጥ ማምጣት አልቻሉም። የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ልማትና ጥበቃ ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አያሌው ወንዴ ለዚህ ዋነኛው "የመቀናጀት ችግር ነው" ይላሉ። እንደ እርሳቸው ገለጻ በጉዳዩ ላይ ያገባናል የሚሉ አካላት ለሀይቁ ህልውና መፍትሄ ነው የሚሉትን የመፍትሄ ሃሳብ በግል ከመያዝ ባለፈ በጋራ የተመከረበት ጥቅልና ሁሉም ሊከተለው የሚችለው ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት አልተቻለም ባይ ናቸው። የዶ/ር አያሌው መሥሪያ ቤት ከመቋቋሙ በፊት ይህን ሥራ በዋናነት ይመራ የነበረው የክልሉ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ነበር። ይሁንና በሀይቁ ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል ሌሎች በጎ አድራጊና መንግሥታዊ ተቋማትም ተሳታፊ ነበሩ። መቀመጫውን በአሜሪካን አገር ያደረገውና በዶ/ር ሰለሞን ክብረት የሚመራው "አለም ዓቀፍ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማህበር " አረሙ ሊወገድ የሚችልበትን የአምስት ዓመት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀትና የአረሙ ማስወገጃ ማሽን ገዝቶ በማበርከት ቀዳሚ ተሳታፊ ነው። ማህበሩ ሰሞኑን በ5.8 ሚሊዮን ብር ገዛሁት ያለውን ሁለተኛውን የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን ባሀር ዳር አድርሶ ለክልሉ መንግሥት አስረክቧል። ይህ ማሽን 28 ሜትር ኪዩብ አረም በአንዴ ማረምና መሸከም የሚችል ሲሆን 75 የፈረስ ጉልበትም አለው ተብሏል። አለም ዓቀፍ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማህበር በውጭ ሃገር በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን የተመሰረተ የበጎ አድራጎት ማህበር ሲሆን፣ አባላቱም በነጻ ለሃገራቸው ድጋፍ ለማድረግ የተሰባሰቡ በአካባቢ ጥበቃና ውሃ አያያዝ ዙርያ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው በጎ ፍቃደኞች ናቸው። ማህበሩ ሌላ የእምቦጭ ማጨጃ ማሽን በካናዳ አሰርቶ የጨረሰ ሲሆን ሰሞኑንም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልክ ገልጿል። የባህርዳርና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎችም በሀይቁ ላይ ሥራ ከሚሰሩ መንግሥታዊ ተቋማት መካከል ናቸው። ይሁንና ሁሉም በየራሳቸው መንገድ የድርሻቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ከመጣራቸው ባለፈ በአንድ የአሰራር ሰንሰለት የታሰሩ አልነበሩም። ይህንን ችግር ለመፍታት ባለፈው ዓመት የአማራ ክልል መንግሥት "የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ልማትና ጥበቃ ኤጀንሲን" አቋቁሟል። በአረሙ አወጋገድ ላይ በተለይ በደምቢያ ወረዳ ምርምር ያደርጉ የነበሩት ዶ/ር አያሌው ወንዴ ይህንን ተቋም እንዲመሩ ተደርጓል። አሁንም ግን ችግሩ አልተቀረፈም። ይህ የሆነበትን ምክንያትም "የተለያየ ሃሳብ በመኖሩ ነው" ይላሉ ዶ/ር አያሌው። በሌላ በኩል ዶ/ር ሰለሞን የክልሉ መንግሥት በቂ ትኩረት አለመስጠቱ ችግሩ እንዳይፈታ ማድረጉን ይገልጻሉ። የጣና ጉዳይ ለክልሉ መንግሥት "የህዝብ ጥያቄ ትኩሳት ሲያቃጥለው ብቻ የሚያነሳው አጀንዳ መሆን የለበትም" የሚሉት ዶ/ር ሰለሞን፣ "ብዙ ባለሙያዎች ተሳትፈውበት የተዘጋጀ የአምስት ዓመት ፍኖተ ካርታ አለ፤ ፍኖተ ካርታው ሀይቁን ከተጋረጠበት ችግር ለመታደግ መሠራት ያለባቸውን ዝርዝር ሥራዎችና ስትራቴጂዎች አስቀምጧል። ይህን ለመተግበር የሚያስፈልገውን ሃብትና መዋቅር በእያንዳንዱ የሃይቁ ቀበሌ ይዘርጋ" በማለት የክልሉን መንግሥት ይመክራሉ። ጣናን ይታደጋል ተብሎ የተቋቋመውን መሥሪያ ቤት የሚመሩት ዶ/ር አያሌው ወንዴ ደግሞ "የተለያየ ሃሳብ መጥቷል፤ ለውጥ ግን አልመጣም" በማለት እስካሁን የነበረው እምቦጭን የማስወገድ ዘመቻ ውጤቱ እምብዛም መሆኑን ይገልጻሉ። በመሆኑም ከክልል እስከ ፌደራል የሚገኙ በጣና ጉዳይ የሚያገባቸው ተቋማት "ቅንጅት ፈጥረን ሁላችንም ድርሻችንን እንውሰድ" የሚል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ዶ/ር አያሌው ገልጸዋል። ከሁለት ዓመት በፊት እምቦጭን ለመከላከል የተለያዩ ሥራዎች በስፋት መሰራት ጀምረው ነበር። ከእነዚህ መካከል አንዱ የመከላከል ስራውን በገንዘብ ለመደገፍ የሚያስችል የፋይናንስ ማሰባሰብ ስራ ይገኝበታል። ቢቢሲ ከተለያዩ ምንጮችን ማረጋገጥ እንደቻለው ለዚሁ ተግባር ተብሎ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ከግለሰቦችና ተቋማት ተሰብስቧል። የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ልማትና ጥበቃ ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አያሌው "አሁን ላይ የፋይናንስ ችግር የለብንም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከአሁን በኋላም አረሙን የማስወገድ ስራ በክፍያ አርሶ አደሩን ለማሰራት ማቀዳቸውን አብራርተዋል። የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ይረዳሉ ተብለው የተለያዩ ማሽኖች በስጦታ ቢቀርቡም፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ሀይቁ የገቡ ብዙዎቹ ማሽኖች አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም። ለምን አገልግሎታቸው እንደተቋረጠ የተጠየቁት ዶ/ር አያሌው "ሲበላሹ የምንጠግንበት ጋራጅ የለንም፣ የአቅም ማነስ አለብን" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በሌላ በኩል ማሽኑን ያበረከቱት አካላት ማሽኑ እንደሚሰራ ቢያረጋግጡም የእነ ዶ/ር አያሌው መስሪያ ቤት ግን በማሽኖቹ መሥራት ላይ እምነት የለውም። በመሆኑም በሁለቱ አካላት ላይ ያልተቋጨ ስምምነት መኖሩን ዶ/ር አያሌው ገልጸዋል። እንደ ዶ/ር አያሌው መረጃ ከሆነ በዚህ ወቅት በሀይቁ ላይ ያለው የእምቦጭ አረም መጠን 900 ሄክታር አካባቢ የሸፈነ ነው። ይህን በመንቀል ለማጥፋት ወይም ስርጭቱን ለመግታትና ለማዳከም 10 አባላት ያሉት ኮሚቴ መቋቋሙን ገልጸዋል። በዋናነት በክፍያ አርሶ አደሩን ማሰራት የሚለው አማራጭ እንዳለ ሆኖ እምቦጭ ያለበትን አካባቢ አጥሮ ማቆየት፣ ያሉት ማጨጃ ማሽኖችን መጠቀምና ሌሎች ጀልባዎችን በመከራየት አረሙን ማስወገድ የሚሉት መፍትሄዎች መቀመጣቸውንም አብራርተዋል። በሌላ በኩል የአለም ዓቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማህበር ዶ/ር ሰለሞን ክብረት "እንቦጭ አረም ለጣና ሃይቅ ከተደቀኑ ችግሮች አንዱ እንጅ ብቸኛው አይደለም" ይላሉ። በመሆኑም ጣና ሃይቅን በዘላቂነት ለመታደግ "የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን መሥራት፣ የአፈር መሸርሸርን መቀነስና ከተሞች ወደ ሀይቁ የሚለቁትን ፍሳሽ አጣርተው እንዲለቁ ግዴታ ማስቀመጥ" የሚሉት ዋነኛ የሀይቁን ደኅንነት ማስጠበቂያ መሣሪያዎች ሊሆኑ እንደሚገባ ያስገነዝባሉ።
news-53523042
https://www.bbc.com/amharic/news-53523042
አካል ጉዳት፡ በርካታ አካል ጉዳተኞችን ከዊልቸር ላይ ያነሳው ኢትዮጵያዊ
በተፈጸመበት ሰቆቃ ሁለት እግሮቹን ያጣው ከፍያለው ተፈራ "መጀመሪያ ተኩስ ሲከፍቱብን 3 ልጆች ወዲያው ሞቱ። እኔ አንድ እግሬ ወዲያው ተቆረጠ፤ ቀኝ እግሬን ደግሞ ያለፈቃዴ ከቁርጭምጭሚቴ ከፍ ብለው ቆረጡት።
በቃሊቲ በእስር ላይ እያለሁ በጣም ያመኝ ነበር። መሞት እፈልግ ነበር፤ ግን አልቻልኩም። መፀዳጃ ቤት መሄድ ስፈልግ እጄን ይዘው ይወረውሩኝ ነበር" ይላል። አሁን ግን ከፍያለው ቆሞ መራመድ ችሏል። እንዴት? * * * * ኮሎኔል ለገሰ ተፈራ በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ወቅት በግንባር ተሰልፈው ተዋግተዋል። በዚህም ጊዜ ከጦርነቱ ሙሉ አካላቸውን ይዘው አልተመለሱም። ጉዳት አጋጠማቸው፤ አንድ እግራቸውን አጡ። የሚገርመው እርሳቸው በኢትዮጵያ ወገን ሆነው በሚዋጉበት ጊዜ አካላቸውን ሲያጡ፤ ወንድማቸው ደግሞ ለኤርትራ ተሰልፈው ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ይናገራሉ። ኮሎኔል ለገሰ አንድ እግራቸውን ቢያጡም አሁን ቆመው በመራመድ ወደ ሚፈልጉበት ቦታ ለመሄድ ይችላሉ። እንዴት? አቶ ንጉሤ ጤናው ድግሞ የቀድሞ ሠራዊት አባል ነበሩ። በዚያ ወቅት በነበረው ጦርነት ከጉልበታቸው በታች የእግራቸውን ክፍል አጥተዋል። ጡረታ ስለሌላቸው አሁን ላይ መጽሐፍት በመሸጥ ነው የሚተዳደሩት። ግን ያሰቡትን ለመፈጸም ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ይችላሉ። እንዴት? ሌላኛዋ በሁለት ዓመት ከስድስት ወሯ በመኪና አደጋ አንድ እግሯን ያጠችው ታዳጊ የአቶ ሰለሞንን ድጋፍ ከማግኘቷ በፊት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነበረች። አዲስ አበባ ውስጥ ሰው ሰራሽ እግር ቢሰራላትም ለእርሷ ምቹና ለጤናዋ ተስማሚ ባለመሆኑ ተቸግራ ቆይታለች። በአባቷ ድጋፍ ትምህርት ቤት ትሄድ የነበረችው ታዳጊ አሁን ከጓደኞቿ ጋር ራሷን ችላ ወደ ፈለገችው ስፍራ መሄድ የሚያስችላት ሰው ሰራሽ እግር አዘጋጅቶ እንደ ልቧ እንድትሮጥ አስችሏታል። ማን? እነዚህ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ለአገራቸው ሲሉ አካላቸውን ያጡ ግለሰቦች፤ እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ፤ እንዳይሰሩ ሆነዋል። የእነዚህ ግለሰቦች ሕይወት እንዲለወጥ አስተዋፅኦ በማድረግ በኩል የሰው ሰራሽ አካልና የአካል ድጋፍ ባለሙያው የአቶ ሰለሞን አማረ ስም በብዙዎች ይነሳል። ለእነዚህ የአካል ጉዳት ላጋጠማቸው ወገኖቹ በሙያው ሰው ሰራሽ አካል ሰርቶ በነፃ አበርክቶላቸዋል። "እነሱ ከከፈሉት ዋጋ አንፃር እኔ የማደርገው ኢምንት ነው" ይላል ሰለሞን። በእርግጥ እነሱን አንደ አብነት አነሳን እንጂ ለበርካቶች ይህንኑ ችሮታውን አልሰሰተም። አቶ ሰለሞን ነዋሪነቱ ለንደን ነው። በሰው ሰራሽም ሆነ በተፈጥሮ የአካል ክፍላቸውን ላጡ አካል ጉዳተኞች ሰው ሰራሽ አካልን የአካል ድጋፍ በመስራት ሙያ ላይ ነው የተሰማራው። "ይህ የሙያ ዘርፍ አሁን በኢትዮጵያ የሚሰጥ የትምህርት ዘርፍ አይደለም" የሚለው አቶ ሰለሞን፤ እርሱም እድሉን ያገኘው በአንድ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ትምህርት ክፍል በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ድርጅት ለተወሰኑ ተማሪዎች ትምህርቱ ሲሰጥ ነበር። በወቅቱ ትምህርት ይሰጥ የነበረው በጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኝ የሰው ሰራሽ አካልና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅት እንደነበርም ያስታውሳል። በጊዜው በቂ ሙያተኛ ስላልነበረ ትምህርቱን እንኳን ሳይጨርስ በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ወደ ሥራ ገባ። አቶ ሰለሞን እንደነገረን ያኔ በሥራ ላይ የነበሩት ባለሙያዎች አራት ብቻ ነበሩ። ከዚያ በኋላ ግን ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በዘርፉ ትምህርት ክፍል መክፈቱንና እምብዛም ሳይገፋበት መዘጋቱን ይናገራል። ሰለሞን እንደ አጋጣሚ የጀመረው ትምህርት ፍላጎት አሳድሮበት በለንደን ሳውዝ ባንክ ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ የትምህርት እድል አግኝቶ ወደ ወደዚያው አቀና። በትርፍ ሰዓቱም ሥራ እየሰራ ልምዱን አጎለበተ። በተለያየ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ ባቀናበት ወቅትም የሰው ሰራሽ አካል መስሪያ ግብዓቶችን በመያዝ የበርካቶችን ሕይወት ቀይሯል። ከኮሎኔል ለገሰ ጋር የአባትና የልጅ ግንኙነት እንዳለው የሚናገረው አቶ ሰለሞን፤ የሰራላቸውን ሰው ሰራሽ እግር በቀየረላቸው ጊዜ "መስዋዕትነት መክፈላችንን የሚረዳ አለ ወይ?" በማለት በደስታ እያለቀሱ እንደጠየቁት ያስታውሳል። "ከፍያለው ተፈራንም ቢሆን በቴሌቪዥን ካልሆነ በአካል አላውቀውም። አገኘዋለሁ ብዬም አስቤ አላውቅም" የሚለው አቶ ሰለሞን፤ በአጋጣሚ ለአንድ ግለሰብ ሰው ሰራሽ እግር ለመስራት ባቀናበት ወቅት ለሥራው ትብብር በሚያደርጉለት የጳውሎስ ሆስፒታሉ ዶ/ር ወንድማገኝ አማካኝነት እንደተገናኙ ያስታውሳል። "ወደ ሕንድ ተልኮ እንዲሰራለት ተደርጎ ነበር። እስኪ አንተ አግዘው ነበር" ያሉት እርሳቸው። በዚህ አጋጣሚም ከከፍያለው ጋር ተገናኝተው መኖሪያ ቤቱ ድረስ በመሄድ ሁለት ሰው ሰራሽ እግር የሰራለት። የሙያ ፍላጎቱ እንዴት አደረበት? ሰለሞን ከአካል ጉዳተኞች ጋር የቤተሰብ ያህል ቅርበት አለው። አንድ እጁና እግሩን ካጣ እንደ ወንድም እንደ አባትም የሚያሳድገው ልጅ ጋር አብረው ይኖሩ ነበር። ያም ሙያውን እንዲወደው አድርጎታል። "እርሱን አንድም ቀን አካል ጉዳት እንዳለበት አስቤው አላውቅም፤ ማንም ሰው የሚሰራውን በብቃት ያከናውናል" ይላል። ምንም እንኳን የኢኮኖሚና የሥነ ልቦና ችግሮችን ጨምሮ በርካታ ፈተናዎች ቢኖሩም አካል ጉዳተኝነት የፈለጉትን ነገር ከማድረግ ግን እንደማይገታ ይናገራል። ይህ ተግዳሮት የሚገጥማቸውም ሕብረተሰቡም ሆነ መንግሥት እንዲሁም አንዳንድ ተቋማት ለእነሱ የሚገቡ ነገሮችን ስለማያደርጉ ነው ሲልም ይወቅሳል። ለምሳሌ ደረጃ መውጣትና አውቶብስ መሳፈር የመሳሰሉት ምቹ ያልሆኑ ሁኔታዎች ስሜታቸውን ይጎዳዋል ይላል። በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ደግሞ በሚችለው አቅም ማገዝ ደስታ እንደሚሰጠው ይናገራል። አቶ ሰለሞን ሰው ሰራሽ የአካል ክፍሎችን የሚሰራውም በተለያየ ጊዜ ያሰባሰባቸውን ግብዓቶች በመጠቀም ሲሆን አገልግሎቱን የሚሰጠው በነፃ ነው። "በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰው ሰራሽ አካሎችን ሰርቻለሁ" በዚህ የሙያ ዘርፍ ከተሰማራ አንስቶ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰው ሰራሽ የአካል ክፍሎችን ሰርቷል። ሰለሞን እንደሚለው በሙያው አንድ ሰው በወር ቢያንስ 10 ሰው ሰራሽ አካል መስራት ይችላል። በትርፍ ሰዓትም ሥራው ይሰራል። ድንገተኛ ሥራዎችም አሉ። ከአገር ከመውጣቱ በፊት ደግሞ በሙያው ከ10 ዓመታት በላይ አገልግሏል። በመሆኑም በዚህ ስሌት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰው ሰራሽ አካሎችን እንደሰራ ይናገራል። "በኢትዮጵያ ውስጥ በሙያው ብቁ የሆነ የሰው ኃይልና ትምህርት ቤትም የለም። ለዚህ ተብሎ የሚገባው ቁሳቁስም ጥራቱን የጠበቀ አይደለም። አካል ጉዳተኞች ግን በሚሊየን የሚቆጠሩ ናቸው" የሚለው ሰለሞን፤ ሙያው በኢትዮጵያ ውስጥ ትኩረት እንዳልተሰጠው ይገልፃል። ሰለሞን የመሥሪያ ቁሳቁሶቹም የአውሮፓና የሌሎቹ በጣም ልዩነት እንዳለውና አገር ውስጥ ያለው ፕላስቲክ ርካሽ ቢሆንም ምቾት እንደሌለው ይጠቅሳል። ይህንንም የታዘበው ወደ አውሮፓ ከሄደ በኋላ ሲሆን "በአገር ውስጥ አገልግሎት ላይ የሚውሉት፤ ምቾት የማይሰጡ ሌላ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ናቸው። ለጤና ተስማሚ አይደለም። ይህም በሌላ ሊተካ ይገባል" ሲል ይመክራል። ይህ የከነከነው አቶ ሰለሞን ታዲያ ለንደን ከሄደ ጀምሮ አንድ ቀን አገር ቤት ብገባ እያለ በግሉ አካል ጉዳተኞችን ለመርዳት የሚጠቅሙ ቁሶችን በየቀኑ ይሰበስብ ነበር። ከአስራ አንድ ዓመታት በኋላ ለአንድ ሰው ሰው ሰራሽ እግር ለመስራት ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ 5 ሻንጣ ማቴሪያል ይዞ ገባ። አጋጣሚውን በመጠቀምም ከፍተኛ ችግር ያለባቸውንና ለሚያውቃቸውን 12 መምህራንና ተማሪዎች ዘመናዊ ሰው ሰራሽ እግር በነፃ እንደሰራላቸው ነግሮናል። ከዚያ በኋላም ለበርካታ ሰዎችን ሕይወት መሻሻል ምክንያት ሆኗል። እንደ ሰለሞን ከሆነ አንድ የአዋቂ ሰው ሰራሽ እግር ቢያንስ 5 ሺህ ፓውንድ (240ሺህ 758 ብር) ያስወጣል፤ የሕፃናት ደግሞ 2 ሺህ ፓውንድ (96ሺህ 303 ብር)። በቀጣይ ምን ለመስራት አሰበ? አቶ ሰለሞን በቀጣይ መስራት የሚፈልጋቸው የአጭርና የረዥም ጊዜ እቅዶች አሉት። በቅርቡ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑና አብዛኞቹ ሁለት እግራቸውን ላጡ 20 ሰዎች ሰው ሰራሽ አግር ለመስራት ወደ ኢትዮጵያ ይሄዳል። እነዚህ ግለሰቦች አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። ከመካከላቸውም ወታደሮች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ አናፂና ሐኪሞች ይገኙበታል። በኢትዮጵያና በኤርትራ መካካል የተፈጠረውን ሰላምም በማሰብ በአገራቱ ጦርነት ወቅት አካላቸውን ላጡ ለአንድ የኢትዮጵያና ለአንድ የኤርትራ ወታደር ሰው ሰራሽ አካል መስራት የዚህ እቅዱ አካል ነው። አቶ ሰለሞን ይህን ሁሉ የሚያደርገው አስፈላጊውን ወጪ ሁሉ እራሱ እየሸፈነ ሲሆን፤ የመሥሪያ ቦታ በመስጠት የሚተባበረው ጳውሎስ ሆስፒታል መሆኑን ተናግሯል። የሰው ሰራሽ አካል ለመስራት አገር ውስጥ የሚጠቀሙበትን ማቴሪያል አሁን ባለው ዘመናዊ ቴክኖሎጂና ማቴሪያል መለወጥ እንዲሁም ቴክኖሎጂውን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት የመስሪያ ቦታ አግኝቶ አካል ጉዳተኞችን በስፋት ማገልገልን ደግሞ የረጅም ጊዜ እቅዱ ነው። "ስለአንድ ፓርቲና ግለሰብ አይደለም ያለው...... እንቅስቃሴው መጠናከር አለበት":- ከፍያለው ተፈራ
news-53544143
https://www.bbc.com/amharic/news-53544143
በካንሰር ትሞታለህ ተብሎ ብዙ ያየው ታዳጊ ህይወትና ምኞት
የካሊፎርኒያው ታዳጊ ጄፍ ሄኒግሰን የጭንቅላት ካንሰር እንዳለበት ሲታወቅ ቢበዛ በሕይወት ሊቆይ የሚችለው ለሁለት ዓመታት እንደሆነ ተነግሮታል።
ይሄኔ ነው አንድ ድርጅት የሚመኘው ነገር ካለ እውን ሊያደርግለት ቃል የገባው። ነገር ግን ጄፍ እንደ እኩዮቹ ዲዝኒላንድ [የሕፃናት መጫወቻ ስፍራ] ውሰዱኝ አሊያም የምወደውን እግር ኳስ ተጫዋች አገናኙኝ አላለም። ይልቁንም ጄፍ እንዲህ አለ "እኔ የምመኘው ዓለም ሰላም እንድትሆን ነው።" በአውሮፓውያኑ በ1986፤ የ15 ዓመቱ ጄፍ ብስክሌት እየነዳ ወደ አንድ ሱቅ እየሄደ ሳለ ነበር በመኪና የተገጨው። ጄፍ በወቅቱ ምንም ዓይነት የአደጋ ጊዜ መከላከያ አላደረገም ነበር። በደረሰበት አደጋ ወዲያው ራሱን የሳተው ጄፍ። ከሰዓታት በኋላ ራሱን በአንድ ሆስፒታል አልጋ ላይ አገኘው። ነገር ግን አደጋው ብዙም ስላልጎዳው የዚያኑ ዕለት ከሆስፒታል እንዲወጣ ተደረገ። ነገር ግን ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ጄፍ ራሱን እየሳተ ይወድቅ ጀመር። ይሄን ጊዜ በድጋሚ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ የጭንቅላት ሲቲ ስካን እንዲነሳ ተደረገ። ጭንቅላቱ ውስጥ በአደጋው ምክንያት የደረሰ አደጋ ቢኖር ጄፍ አይደነቅም ነበር። ነገር ግን የምርመራው ውጤት የከፋ ውጤት ይዞ መጣ - የጭንቅላት ዕጢ። በወቅቱ "ሁለት ነገሮች በአእምሮዬ ውስጥ ተመላለሱ" ይላል ጄፍ። አንደኛው ትምህርት ቤት ሲዘጋ ከሴት ጓደኛው ጋር ጥሩ የፍቅር ጊዜ ማሳለፍ፤ ሁለተኛው ደግሞ የጀመረውን የፈጠራ ሥራ ማጠናቀቅ። ጄፍ ተስፋ ያለው ታዳጊ ነበር። ሕልሙ ደግሞ ለአሜሪካው የህዋ ምርመር ተቋም ናሳ መሥራት ነበር። ጄፍ ለናሳ መሥራት ብቻ ሳይሆን ተቋሙ ከሩሲያ አቻው ጋር ከመቀናቀን ይልቅ አብሮ መሥራት ቢቻል ብሎ ይመኝ ነበር። "ታዳጊ ብሆን እንኳ ሁለቱ አገራት አብረው ቢሠሩ ትልቅ ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል አምን ነበር" ይላል ጄፍ። "የኒውክሌር ጦር መሣሪያን አንዳችን በአንዳችን ላይ መደገን ትርጉሙ ምን እንደሆነ አይገባኝም ነበር። ከዚህ ይልቅ ህዋ ላይ ወጥተን አብረን መሥራት እንችላለን።" ጄፍ በዚያ ዓመት ክረምት ላይ ሊያደርግ ያሰባቸው ሁለት ነገሮች አልተሳኩለትም። እንዲያውም በፍጥነት ቀዶ ጥገና እንዲደረግለት ታዘዘ። ስድስት ሰዓታት ከፈጀ ቀዶ ጥገና በኋላ ዶክተሮች ዕጢውን ማውጣት እንደተሳናቸው አመኑ። ከዚያ በኋላ ዕጢው ወደ ካንሰር ሊያድግ ይችላል፣ አይችልም የሚለውን ለመለየት ሰባት ቀናት መቆየት ግዴታ ሆነ። "ዶክተሯን ወደእኔ ስትመጣ ፊቷን አይቼ መልካም ዜና ነው ወይስ መጥፎ የሚለውን መለየት አልቻልኩም። ከዚያ እንዲህ አለችኝ 'ይህንን ስነግርህ እያዘንኩ ነው፤ የጭንቅላት ካንሰር አለብህ። በጣም በፍጥነት እያደገ ነው።' "ከዚህ በኋላ ምን ያህል ጊዜ አለኝ ስል ጠይቅኳት።" "ምናልባት ሁለት ዓመታት።" ጄፍ ከወላጆቹ ጋር ጄፍ የጨረር ሕክምና ጀመረ። ኪሞቴራፒም ይከታተል ገባ። በተቻለው መጠን ትምህርቱን መከታተል ያዘ። ካንሰር ያለባቸው ወጣቶች የተሰባሰቡበት ቡድን አባልም ሆነ። "ስላደረጓቸው ነገሮች ይነግሩኛል። በጣም የምንወደውን አትሌት ተዋወቅን፤ ዲዝኒላንድ ሄድን ይሉኛል። እኔ ይሄ የሕፃናት ምኞት ይመስለኝ ነበር ስላቸው እኛ እኮ ሕፃናት ነን ይሉኛል። የእኔ ምኞት ግን ይህ አልነበረም።" የጄፍ እናት ሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሕፃናት የመጨረሻ ምኞት እውን የሚያደርግ አንድ ድርጅት አግኝታ መፃፃፍ ጀመረች። ከዚያም ከድርጅቱ ሁለት ሰዎች መጥተው "ጄፍ ምኞትህ ምንድነው?" ሲሉ ጠየቁት። ጄፍ መጀመሪያ እንዲህ አለ። "እውነቱን ንገሩኝና በቀጣዩ የህዋ ጉዞ ላይ አሳፍሩኝ ብላችሁ ታሳፍሩኛላችሁ?" ሰዎቹ ጄፍን በምስኪን ዓይን እያዩት "ኧረ በፍፁም" አሉት። ባይሆን ሊሆን የሚችል ምኞት ተመኝ በሚል ዓይን ያዩት ጀመር። "ሶቪየት ሕብረት ሄጄ ሚካይል ጎርባቼቭን ማግኘት እፈልጋለሁ። የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ፉክክር እና የቀዝቃዛው ጦርነት እንዲቆም ላማክራቸው እፈልጋለሁ።" ጄፍ ይሄንን ሲል በክፍሉ ውስጥ ዝምታ ሰፈነ። ሰዎቹ ግን "ሦስተኛ ምኞት የለህም እንደው ቀለል ያለ ዓይነት መልክ ያለው?" ፊታቸውን ጄፍ ላይ ተከሉ። ጄፍ ግን ከዚህ ውጪ ምኞት እንደሌለው ፈርጠም ባለ አተያዩ ይነግራቸው ጀመር። ሰዎቹ የሚቻላቸውን እንደሚያደርጉ ነገር ግን ሁሉም ይሳካል ብለው ቃል እንደማይገቡ ነግረውት ሄዱ። ጄፍ ወደ ሞስኮ በሄደበት ጊዜ ድርጅቱ፤ ጄፍ ከሌሎች አሜሪካውያን ወጣቶች ጋር ሶቪዬት ሕብረትን እንዲጎበኝ አመቻቸ። በዚህ ጉዞ ላይ ከተቻለ ጎርባቾቭ ለማግኘት ነበር የድርጅቱ ዓላማ። ወጣቶቹ ሞስኮ ሲደርሱ ሰላይ እንደሚያጋጥማቸው ጠርጥረው ነበር። ዓላማቸውም እሱ ነበር። ነገር ግን ሌኒንጋርድ ውስጥ ምንም ዓይነት ሰላይ እየተከተላቸው እንዳልሆነ ሲያውቁ እንደመብሸቅ አደረጋቸው። ነገር አንድ ወጣት የሆነ ሰው እየተከተላቸው እንደሆነ አስተዋለ። ሰውዬው ወጣቶቹ የገቡበት ይገባል፤ ሲወጡ ይወጣል። ሰላዩ ብቻውን አልነበረም። ጄፍና ወጣቶቹ ያረፉበት ሆቴል ግድግዳው ተበስቶ ማደመጫ ገመድ እንደተዘረጋ አወቁ። አልፎም አንዷ ወጣት ወደ ክፍሏ ስትገባ ሁለት ወንዶች ቦርሳዋን ሲበረብሩ አገኘቻቸው። "ይሄን ስናውቅ በጣም ደንግጠን ነበር። እኔ ቦርሳዬ ውስጥ ለጎርባቾቭ ስጦታ ይዤ ነበር። እሱን እንዲወስዱብኝ አልፈልግኩም" ይላል ጄፍ። የድርጅቱ ሰዎች ሕልሙን እውን ለማድረግ እየሠሩ እንደሆነ ደጋግመው ይነግሩታል። ነገር ግን ሕልሙ እውን ሊሆን ትንሽ ሲቃረብ የሆነ ደንቃራ ያጋጥመዋል። የሆቴሉ መጠባበቂያ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ሳለ የጎርባቾቭ መልዕክኛ መጥቶ የሶቪዬት ሕብረቱ መሪ ጄፍን ሊያገኙት እንደማይችሉ ነገረው። ነገር ግን ሌላ በአገሪቱ መንግሥት ውስጥ ኃያል ሰው ሊያስተዋውቁት ስላሰቡ ሻንጣውን ሸክፎ እንዲከተላቸው ነገሩት። ጄፍ ሻንጣውን በጉልበቱ እንደታቀፈ በሽንጠ ረዥም መኪና ከሞስኮ ከተማ ወጣ ብላ ወደምትገኝ ከተማ ተወሰደ። ስለሚተዋወቀው ሰው ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። "የሄድንበት ቦታ ከሚኖሩ ጥንዶች ጋር መልካም ጊዜ አሳለፍኩ። እራት በላን፤ ስለምንኖርባት ዓለም ብዙ ተጫወትን።" ጄፍ ስለጥንዶቹ ያወቀው ወደ ሞስኮ ከተመለሰ በኋላ ነው። እራት የበላው ከኤቭጌኒ ቬሊኮቭ ጋር ነበር። ሰውዬው በኒውክሌር መሣሪያዎች ዙሪያ የሶቪዬት ሕብረት ቀኝ እጅ የሆኑ ሰው ናቸው። ጄፍ ጎርባቾቭን ማግኘት ባይችልም በሶቪዬት ሕብረት የኒውክሌር ውሳኔ ከፍተኛ ሚና ካላቸው ሰው ጋር እራት መብላትና መጫወት ችሏል። ለጎርባቾች የያዘውን ስጦት ለመልዕክተኛቸው አስረክቦ በቀጣዩ ቀን ወደ ትውልድ አገሩ አሜሪካ ተመለሰ። "አባቴ፤ ጎርባቾቭን አገኘኸው ብሎ ሲጠይቀኝ አላገኙሁትም ብዬ መለስኩለት። ጉዞዬ የከሰረ ሆኖ የተሰማኝ በዚህ ጊዜ ነው።" እንደተፈራው የጄፍ ዕጢ ወደ ሞት አፋፍ ይገፋዋል ቢባልም ከሕክምናው በኋላ እየተሻለው መጣ። እሱም ትምህርቱን ይገፋበት ጀመር። ጄፍ አሁን ወደ ለንደን ተዛውሮ ኢኮኖሚክስ ካጠና በኋላ ወደ አሜሪካ ተመልሶ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ገባ። ከዚያም ተመርቆ ሲወጣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቀጥሮ ይሠራ ጀመር። ዕጢውም አልታይ አለ። በታዳጊነቱ 'ትሞታለህ' ተብሎ የተነገረው ጄፍ 37ኛ ዓመቱን ደፈነ። በዚህ ጊዜ ሚስቱን ይዞ ወዳደገበት መኖሪያ ቤት ሄደ። "በወቅቱ አስከፊ ሕይወት እያሳለፍኩ ነበር" ይላል ጄፍ። በተደጋጋሚ ራሱን እየሳተ ሥራ መሥራት ባለመቻሉ ከተባበሩት መንግሥታት ሥራው እንዲቀነስ ሆነ። ትዳሩም የተቃና አልነበረም። በልጅነቱ ክፍሉ ያገኛቸውን ዕቃዎች ሲበረብር አንድ በጥሩ እንግሊዝኛ የተፃፈ ደብዳቤ አገኘ። ደብዳቤው ላይ ያገኘውን ስልክ ቁጥር ሲመታ ሩሲያኛ ከምትናገር ሴት ጋር ተገናኘ። ጄፍ ያገኘው ደብዳቤ ከዓመታት በፊት የተጻጻፈው ነበር። ይህን ጊዜ በዚያ ወቅት ይሰማኝ የነበረው ሁሉ ተመልሶ መጣ ይላል ጄፍ። ይህ ክስተት ሕይወቱን እንደ አዲስ እንዲቃኝ እንዳደረገው ይናገራል። ጄፍ አሁን 49 ዓመቱ ነው። ፀሐፊ ነው። የመጀመሪያ መፅሐፉ 'ዋርሄድ' የተሰኘ ሲሆን ስለእራሱ የሕይወት ጉዞ የፃፈው ነው። በቅርቡም ጤና ምርመራ ለማድረግ ወደ ሆስፒታል ሄዶ ዕጢው ሙሉ በሙሉ እንደጠፋ የሚያመላክት ማስረጃ አግኝቷል። ቢሆንም ዶክተሮች የሚጥል በሽታ ሊያጋጥመው እንደሚችል ነግረውታል። ጄፍ፤ ሩሲያና አሜሪካ አሁንም በዓይነ ቁራኛ መተያየታቸው ቁጭት ያሳድረበታል። ሁለቱም አገራት የኒውክሌር መሣሪያ ክምችት እንዳላቸው ሲያስብ ደግሞ ስጋት ይገባዋል። የነገር ግን ሁለቱ አገራት ብቻ ሳይሆን የሌሎችም አገራት የኒውክሌር መሣሪያ ክምችት አሁን ድረስ የጄፍ ጭንቀት አካል ናቸው።
news-51355847
https://www.bbc.com/amharic/news-51355847
የኮሮናቫይረስ ስጋትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኮሮናቫይረስ ስርጭት አሁንም የዓለም ስጋት ሆኖ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ቫይረሱ ሊዛመትባቸው ይችላሉ ተብለው ከፍተኛ ስጋት ካለባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን የዓለም ጤና ድርጅት ከቀናት በፊት አስታውቋል። ኢትዮጵያ ለቫይረሱ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ያደረጋት ከቻይና ጋር ያላት ቀጥተኛ እና ከፍተኛ መጠን ያለው የተጓዥ ቁጥር መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ከቀናት በፊት አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና በረራ ባደረገ ቁጥር ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ የሚሰራጭበትን አጋጣሚን ከፍ ያደርጋል የሚሉ የተቃውሞ ድምጾች እንደቀጠሉ ናቸው። • ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና • በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩት ኢትዮጵያውያን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ተነገረ አየር መንገዱ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ መሰረዝ አለበት ብለው ከሚከራከሩት መካከል አንዱ የጤና ባለሙያው ዶ/ር የሺዋስ መኳንንት ይገኙበታል። ዶ/ር የሺዋስ የበሽታውን ባህሪ እና የአገሪቱን የጤና ሥርዓት ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በሽታው ወደ አገር ቢገባ የሚያስከትለው ኪሳራ በቀላሉ የሚተመን አይሆንም ይላሉ። "ባለን የጤና ሥርዓት አይደለም ኮሮናቫይረስ፤ ቀላል የሚባሉ ወረርሽኞችን መቆጣጠር አቅቶናል" የሚሉት ዶ/ር የሺዋስ እንደማሳያነት ከዚህ ቀደም ድሬዳዋ አካባቢ ቺኩንጉኒያ የሚባል ወረርሺኝ ተነስቶ መሠረታዊ የሆኑ መድሃኒቶች እጥረት አጋጥሞ እንደነበረ ያስታውሳሉ። "እኔ ድሬዳዋ ነው የምሰራው። ባለፈው ክረምት ላይ ቺኩንጉንያ የሚባል ቫይረስ ተከስቶ ፓራሲታሞል ጠፍቶ ታማሚዎችን ሆስፒታል አስተኝተን የሰውነት ሙቀት ስናወርድ የነበረው በውሃ በተነከረ ጨርቅ ነበር። ይህ የጤና ሥርዓት ኮሮናቫይረስን ይከላከላል ማለት ከባድ ነው" ይላሉ። • በቻይና የተከሰተው አዲስ ቫይረስ ምን ያህል አስጊ ነው? • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? "የሙቀት መጠንን በመለካት በሽተኛን በትክክል መለየት አይቻልም። አንድ ሰው የበሽታውን ምልክት ሳያሳይ 14 ቀናት ሊቆይ ይችላል። ወደ አገር ውስጥ የሚገቡት ሰዎች ከማንም ጋር ሳይገናኙ መቆየት ይኖርባቸዋል። እነዚህ ሰዎች ግን ከማህብረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ነው የሚገኙት። "አንድ ምልክቱን ያሳየ ሰው አክሱም ላይ አለ ሲባል በጣም ነው ያዘንኩት። ቫይረሱ እኮ በ 6 ጫማ [2 ሜትር ገደማ] ርቀት ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል። ይህ ሰው አክሱም እስኪደርስ ከስንት ሰዎች ጋር ተገናኝቶ ይሆን?" ሲሉ ይጠይቃሉ ዶክትሩ። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከትናንት በስቲያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እስከ ጥር 24/2012 ድረስ 47,162 ተጓዦች በቦሌ አየር ማረፊያ በኩል የሙቀት መለያ ምርመራ እንደተደረገላቸው እና ከእነዚህም ውስጥ 1,695ቱ የመጡት ቫይረሱ ሪፖርት ከተደረገባቸው አገራት መሆኑን አስታውቋል። ከቻይና የሚመጡ ሁሉንም ተጓዦች በሃገር ውሰጥ በሚቆዩበት ወቅት አድራሻቸው ተመዝግቦ ለአስራ አራት ቀናት ክትትል ይደረግባቸዋልም ተብሏል። ክትትል ይደረግባቸዋል የተባሉት ከ1600 በላይ ሰዎች ወደ ማህብረሰቡ ተቀላቅለዋል። • ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው? • ኮሮናቫይረስ፡ የወቅቱ አሳሳቢው የዓለማችን የጤና ስጋት ከእነዚህ መካከል በጣት የሚቆጠሩት ሰዎች እንኳ ቫይረሱ ቢኖርባቸው እስካሁን ባላቸው ቆይታ የሚገናኟቸው ሰዎችን እንዲሁም የተገናኟቸው ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ጋር ሊፈጥሩት የሚችሉትን ግነኙነት በማስላት ቫይረሱ በቀላሉ ሊሰራጭ እንደሚችል ስጋታቸውን የሚገልጹ በርካቶች ናቸው። በቅርቡ አውስትራሊያ ከቻይና ዜጎቿን ማስወጣቷ ይታወሳል። አውስትራሊያ የሰውንት ሙቀት ለክታ ወደ አገር ከማስገባት ይልቅ፤ ከቻይና ተመላሽ ዜጎቿን ለ14 ቀናት ርቃ በምትገኝ ደሴት ላይ ለማቆየት ነው የወሰነችው። የዩናትድ ኪንግደም መንግሥትም ከቻይና የተመለሱ እንግሊዛውያንን ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ስፍራ ለማቆየት ተመሳሳይ እርምጃ ወስዷል። ኢንስቲትዩቱ ግን ቫይረሱ ቢከሰት 4 ተርሸከርካሪዎች እና አራት የጤና ተቋማትን ጨምሮ በተጠንቀቅ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ቡድን መኖሩን አሳውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች ሰጋት ወደ ቻይና የሚበሩ የኢትዮጵያ አየር መንግድ ሠራተኞች ለበሽታው ልንጋለጥ እንችላል የሚል ስጋት እንዳደረባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቫይረሱ ከተከሰተ በኋላ ወደ ቻይና የበረሩ የበረራ አስተናጋጆች እና በሌላ የበረራ መስመር ላይ የበረሩ ካፒቴን፤ አየር መንገዱ ወደ ቻይና መብረሩ ለኮሮናቫይረስ ሊያጋልጣቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በቅርቡ ከአዲስ አበባ - ባንኮክ- ሆንግ ኮንግ - ባንኮክ - አዲስ አበባ የበረረች የበረራ አስተናጋጅ፤ እሷም ሆነች የሥራ ባልደረቦቿ በአሁኑ ወቅት ወደ ቻይና የመብረር ፍላጎት የለንም ትላለች። "አሁን ባለው ሁኔታ ማንም ሰው ወደ ቻይና የመብረር ፍላጎት የለውም። ሥራችን ንክኪ የበዛበት ነው። ሰዎች የተጠቀሙትን ሶፍቶችን እና ማንኪያዎችን እንነካለን። ተቆጥበህ የምትርቀው ነገር አይደልም። ካለው ነገር አንጻር ማንም ሰው መሄድ አይፈልግም። ነገሩን ከባድ የሚያደርገው ደግሞ ወደ ቻይና ስንበር በተወሰኑ በረራዎች ላይ ጓንት እና የአፈ መተንፈሻ እንድናደርግ አይፈቀድም" ትላለች። • ካሜሮናዊው በኮሮናቫይረስ በመያዝ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ • አውስትራሊያ ከቻይና ተመላሾችን ራቅ ወዳለች ደሴት ማጓጓዝ ጀመረች ቢቢሲ ያነጋገራት ሌላ የበረራ አስተናጋጅ እንደምትለው ከሆነ፤ ወደ ቻይና ከሚደረጉ በረራዎች መካከል ለቫይረሱ ስርጭት "አስጊ አይደለም" በሚባሉት ላይ ማስክ (አፍ መሸፈኛ) ማድረግ እንደማይፈቀድላቸው አስረድታለች። እንደ የበረራ አስተናጋጆቹ ከሆነ፤ ምንም እንኳን የቫይረሱ ስጋት በሁሉም በረራዎች ላይ ያለ ቢሆንም የቫይረሱ ስርጭት "አስጊ አይደለም" ወደተባሉ ከተሞች ስንጓዝ ማስክ ማድረግ እንደማይፈቀድላቸው ይናገራሉ። "እኔ የበረርኩበትን እንደምሳሌ ልንገርህ ከአዲስ-ባንኮክ ስንበር እንድናደርግ አልተፈቀደልንም። ከባንኮክ ወደ ሆንግ ኮንግ ስንበር ግን ማስክ እንድናደርግ ይፈቀዳል። ከሆንግ ኮንግ ወደ ባንኮክ ስንበር ማስክ አድርገን ነበር፤ መልሶ ደግሞ ከባንኮክ ወደ አዲስ አበባ ስንበር እንድናደርግ አልተፈቀደልንም" በማለት ታስረዳለች። • ከቻይና ውጪ የመጀመሪያው ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ሞተ • ቻይና አሜሪካን ኮሮናቫይረስን አስመልክቶ ፍራቻ እየነዛች ነው ስትል ወነጀለች የበረራ አስተናጋጆች በተመረጠ በረራ ላይ ብቻ ማስክ እንድናደርግ ተገደናል ከማለታቸው በተጨማሪ፤ አየር መንገዱ ለሠራተኞቹ በቂ የማስክ እቅርቦት እንደማያደርግ ይናገራሉ። "ስለ ቫይረሱ አጠቃላይ መረጃ የያዘ ባለ ሦስት ገጽ ወረቀት ተሰጥቶናል። በቂ ማስክ ግን የለም" በማለት እርሷ እና ባልደረቦቿ አንድ ማስክ ሳይቀይሩ ለስድስት ተከታታይ በረራዎች ለመጠቀም መገደዳቸውን ትናገራለች። በሌላ የበረራ መስመር ላይ የሚበር ካፒቴን እንደሚለው ከሆነ ደግሞ ቻይናን ከተቀረው አፍሪካ ጋር የሚያገናኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። "እኔ ወደ ቻይና ባልበር እንኳ በርካታ ከቻይና የሚነሱ መንገደኞች በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና ወደ ተቀሩት መዳረሻዎች ይዘን እንበራለን። ይህ ስጋት አሳድሮብናል" ይላል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሠራተኞቹ ለተነሳውን ቅሬታ እና ስጋት ምላሽ እንዲሰጠ በተደጋጋሚ በስልክ እና በኢሜይል ጠይቀናል። አየር መንገዱ ለጥያቄያችን ምላሽ እንደሚሰጥ ቢናገርም እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። በበሽታው መስፋፋት ምክንያት በተፈጠረ ስጋት በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጓቸውን በረራዎች አቋርጠዋል። አብዛኞቹ አየር መንገዶች የአውሮፓና የአሜሪካ አገራት ሲሆኑ አምስት የአፍሪካ አገራትም አየር መንገዶቻቸው ወደ ቻይና እንዳይጓዙ አድርገዋል። ወረርሽኙ በፈጠረው ስጋትና ሌሎች አየር መንገዶች በወሰዱት እርማጃ ከበርካታ ኢትዮጵያዊያን ከአፍሪካ ትልቁ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርጋቸውን በረራዎች እንዲያቆም ቢጠይቁም አየር መንገዱ አሁንም ሥራውን አላቋረጠም። • አምስት የአፍሪካ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ አቋረጡ አየር መንገዱ ለቀረቡለት ጥሪዎች በሰጠው ምላሽ ላይ ምንም እንኳን በርካታ መንገደኞችን ከቻይና ቢያጓጉዝም አብዛኞቹ ወደ ተለያዩ አገራት ትራንዚት የሚያደርጉ መሆናቸውን አመልክቷል። በተጨማሪም መንገደኞች ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ በሌሎች አየር መንገዶች አማካይነት እንደሚገቡ፣ አየር መንገዱ የስታር አልያንስ አባል በመሆኑ ከሌሎች አየር መንገዶች የቻይና መንገደኞችን እንደሚያጓጉዝ በመጥቀስ "አየር መንገዱ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ ቢያቆምም ባያቆምም መንገደኞች መምጣታቸው ስለማይቀር ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዘ ስጋት መቀጠሉ አይቀርም" ብሏል።
48035902
https://www.bbc.com/amharic/48035902
መአዛን በስለት ወግቶ ለሞት የዳረጋት ግለሰብ አሁንም ከፖሊስ እንዳመለጠ ነው
(በዚህ ጽሑፍ ውስጥ መአዛ ሆስፒታል ሳለች ጉዳቷን የሚያሳይ ፎቶ አካተናል። ፎቶው ሊረብሽ ስለሚችል አንባቢዎች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን።)
የመአዛ ካሳ የቀድሞ ፎቶና ሆስፒታል ከገባች በኋላ የተነሳ ፎቶ ጥር 2 ቀን 2011 ዓ. ም. በሥራ ባልደረባዋ በስለት ተወግታ፤ ከሁለት ወራት በኋላ መጋቢት 5 ህይወቷ ያለፈው የመአዛ ካሳ ገብረመድሀን ጉዳይ የበርካቶች መነጋገሪያ ከሆነ ሰነባብቷል። በተለይም መአዛ ላይ ጥቃት በማድረስ ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረው ግለሰብ ማምለጡን ተከትሎ ብዙዎች የሕግ አስፈጻሚ አካል ላይ ጥያቄ እያነሱ ነው። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግነኙነት ሀላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ተጠርጣሪው ያመለጠው እንዲጠብቀው ተመድቦ በነበረው ፖሊስ ቸልተኝነት ከሆነ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረው እንደነበረ ይታወሳል። ተጠርጣሪው በአንድ ፖሊስ አጃቢነት ለህክምና ከእስር ቤት ወጥቶ ካመለጠ ሳምንታት ተቆጥረዋል። ተጠርጣሪውን እንዲጠብቅ ተመድቦ የነበረው ፖሊስ ለምርመራ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ ቢሆንም፤ በዋስ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ተሰውሯል። • ፆታዊ ትንኮሳን ደርሶብኛል በማለቷ ተቃጥላ እንድትሞት የተደረገችው ወጣት ለመሆኑ የመአዛ ቤተሰብ አሁን ምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? የተጠርጣሪው መጥፋት እና አጅቦት የነበረው ፖሊስ መሰወር ያጫረው ጥያቄስ? (በዚህ ጽሑፍ ውስጥ መአዛ ሆስፒታል ሳለች ጉዳቷን የሚያሳይ ፎቶ አካተናል። ፎቶው ሊረበሽ ስለሚችል አንባቢዎች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን።) ሀምሌ 2010 በ30 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው መአዛ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ውስጥ በፋይናንስ ሀላፊነት የተቀጠረችው ሀምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደነበረ ታላቅ እህቷ ውዴ ካሳ ትናገራለች። እህቷ እንደምትናገረው፤ መአዛ ከተቀጠረች በኋላ ለተወሰኑ ሳምንታት ስልጠና ላይ ነበረች። ታህሳስ 2011 ላይ የጤና እክል ገጥሟት የነበረ ቢሆንም መሥሪያ ቤቱ ውስጥ ሥራ በዝቷል ተብላ ጥር ላይ ከእረፍት ተመልሳ ግማሽ ቀን እንድትሠራ ተደረገ። • "በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" የውዴ ቤት ለመአዛ መሥሪያ ቤት ቅርብ ስለሆነ አልፎ አልፎ ምሳ አብረው ይበላሉ። መአዛ ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠረው የሥራ ባልደረባዋ ምሳ ሲበሉም ሆነ ሻይ ሲጠጡ አልፎ አልፎ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ውዴ ታስታውሳለች። "አብረው ብዙ ጊዜ ባይሰሩም ስለሷ ያጠና ነበር። በአይነ ቁራኛ ይከታተላት ነበር። በአንድ ወቅት አሟት ስትተኛ ቤቷን አጠያይቆ ጠይቋት ነበር።'' የምትለው ውዴ፤ በመአዛና በግለሰቡ መካከል ከሥራ ባልረደባነት ያለፈ ግንኙነት እንደሌለ ገልጻ "በሱ ልብ ያለውን ግን አላውቅም" ትላለች። ጥር 2011 መአዛ ጥቃቱ የደረሰባት ጥር 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ነበር። መአዛ በሕይወት ሳለች ለፖሊስ የሰጠችውን ቃል አጣቅሳ ውዴ እንደምትለው፤ ግለሰቡ "ጥር 2 ሁሉም ነገር ያበቃል" ሲል ይዝት ነበር። • የተደፈረችው የ3 ዓመት ህፃን በአስጊ ሁኔታ ትገኛለች ውዴ እንደምትለው፤ በበዓል ማግስት የመሥሪያ ቤት ባልደረቦቿ ጋር የአውደ አመት ዳቦ እየበሉ የታሸገ ውሃ ይጠጡ ነበር። ከረፋዱ አምስት ሰአት አካባቢ የመአዛ ጓደኞች ከቢሮ ወጥተው እሷም እስከምትከተላቸው ይጠብቋት ነበር። መአዛ መሥሪያ ቤቷ ውስጥ ወንበሯ ላይ ተቀምጣ ሳለች የሆነውን ውዴ ትናገራለች። "ስሟን ጠርቶ ዞር ስትል ቀኝ ጡቷ ስር በቢላ ወጋት። ጨጓራዋ ተቀደደ። ቢላውን አማስሎ ሲያወጣው አንጀቷ ተበጣጠሰ። እንደምንም አምልጣ ወደ ኮሪደር ስትሄድ ተከትሎ በተደጋጋሚ ይወጋት ነበር። ሰዎች እየተጯጯሁ ለማስቆም ይሞክሩ ነበር። ኋላ ላይ አስጥለዋት ወደ አለርት ሆስፒታል ወሰዷት።" የመአዛ ደም ኦ-ኔገቲቭ (o-) ስለሆነ ደም ለማግኘት አስቸጋሪ ነበር። ምሽት 1 ሰአት ድረስ ቀዶ ጥገና ማድረግም አልተቻለም ነበር። ሀኪሞች ለመአዛ ቤተሰቦች እንደነገሯቸው ጨጓራዋ ውስጥ የነበረው አሲድ ወደ ሰውነቷ ፈሶ ነበር። ከሳምንት በኋላ ወተት ስትጠጣ ስለወጣ ጥር 8 ሁለተኛ ቀዶ ጥገና ተደረገላት። "አንጀቷ ስለተጎዳ የመትረፍ እድል የላትም ቢባልም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ እያሳየች ነበር። ለሁለት ወር ከ15 ቀን ሆስፒታል ተኝታለች።" መአዛ ከጥቃቱ በኋላ ሆስፒታል ሳለች የተነሳ ፎቶ ተጠርጣሪው ጥቃቱን ባደረሰበት ዕለት ማለትም ጥር 2 ጎተራ ወረዳ 7 ፖሊስ መምሪያ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ተደረገ። በወቅቱ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ፖሊስ ምርመራውን አለመጨረሱን እንደተናገረ ውዴ ትገልጻለች። የካቲት 2011 ውዴና የተቀረው ቤተሰብ የመአዛን ሕይወት ለመታደግ በሚያደርጉት ሩጫ ተይዘው የነበረ ቢሆንም የካቲት 4 ፍርድ ቤት ሄደው ስለጉዳዩ ጠይቀዋል። "ስንሄድ ችሎት አልተሰየመም ተብለን ነበር። የሚከሰሰው ነፍስ በማጥፋት ሙከራ ወይስ በአካል ማጉደል ወንጀል የሚለው አልተለየም ነበር።" በዚህ ወቅት ግለሰቡ ህክምና እንደሚፈልግ ለፍርድ ቤት አሳውቆ ፍርድ ቤት ፈቀደለት። • "ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ ከአንድ ጠባቂ ፖሊስ ጋር ወደ ሆስፒታል ሄዶ ሳለ እንደጠፋ የተገለጸውም በዚህ ጊዜ ነበር። ሆኖም ማምለጡ ለመአዛ ቤተሰቦች አለመነገሩን ውዴ ትናገራለች። መአዛ ሆስፒታል ሳለች የግለሰቡ ቤተሰቦች መአዛ የምትገኘበት ሆስፒታል ድረስ በመሄድ ለማግባባት ጥረት ያደርጉ እንደነበር ውዴ ትናገራለች። የተጠርጣሪው ቤተሰቦችም ውዴን ከተጠርጣሪው ጋር በስልክ በማገናኘት "አሁን ተሽሏታል ብለሽ መስክሪልኝ፤ እሷን እኛ እናሳክምልሻለን" ማለቱን ውዴ ትናገራለች ታክላለች። ጥቃቱ ሳያንስ ለማግባባት በተደገረው ጥረት እጅግ የተበሳጨችው ውዴ ቤተሰቦቹ ወደ ሆስፒታል መምጣታቸው ስጋት ውስጥ ከትቷት እንደነበርም ትገልጻለች። መጋቢት 2011 መአዛ የጤናዋ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ፣ ሰዎች ለመጠየቅ ሲደውሉላትም "ቤት መጥታችሁ ታዩኛላችሁ" ትል እንደነበረ እህቷ ትናገራለች። ውዴ እንደምትለው፤ መአዛ ከተኛችበት ክፍል በዊልቸር ይዘዋት ይወጡ ነበር። ሀኪሞችም ለውጥ ማሳየቷን አረጋግጠውላቸው ነበር። ሆኖም ከመሞቷ ከጥቂት ቀናት በፊት መሸበር፣ መጮህ ጀመረች። "እማዬ እያለች ትጮሀ ነበር። ጥቃቱን ያደረሰባት ሰው እንደታሰረ ብታውቅም 'ይታሰር' ትል ነበር። ትፈራ ነበር። ትጨነቅ ነበር። ብቻዋን መሆን አትፈልግም ነበር።" በማለት ውዴ የእህቷ ህይወት ከማለፉ በፊት የነበራተን ሁኔታ ታስረዳለች። ሀኪሞች ከጥቃት በኋላ (ፖስት ትራውማ) የሚፈጠር መረበሽ ነው እንዳሉ ውዴ ታስረዳለች። ሆኖም ከፍተኛ ማገገም አሳይታ የነበረችው እህቷ የተፈጠረባት ጭንቀትና ያገኘችው የህክምና ማብራሪያ አብሮ የሚሄድ ሆኖ አላገኘችውም። መአዛ ያረፈችው መጋቢት 15 ቀን ጠዋት ላይ ነበር። መጋቢት 16 ከተቀበረች በኋላ ግለሰቡ ከፖሊስ ቁጥጥር ማምለጡን ቤተሰቡ መስማቱን ውዴ ትናገራለች። "ለሽፋን 'አፍቅሬያታለሁ' ማለቱን ሰምተናል። ባለትዳርና የልጆች አባት ነው። እጁ ላይ ካቴና ያለ ሰው ያመልጣል ብለን አልጠረጠርንም። አሁን ለራሳችንም ሕይወት ሰግተናል። ማንን ማመን እንዳለብን፣ የት መሄድ እንዳለብን አናውቅም። አሮጊት እና ህጻናት ይዘን ግራ ተጋብተናል። ምስቅልቅላችን ወጥቷል።" • ሴት ተማሪዎች የቦኮ ሃራምን ጥቃት ማምለጥ ቻሉ ለፓሊስ ስልክ እየደወሉ "ተይዟል ወይ?" ብሎ ከመጠየቅ ባለፈ ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ ውዴ በሀዘን ተውጣ ትገልጻለች። ከሚያዝያ 2011 ወዲህ መአዛ የሁለት ልጆች እናት ነበረች። ሁለት ልጆችም ታሳድግ ነበር። የመጀመሪያ ልጇ 7 ዓመቷ ሲሆን ሁለተኛ ልጇ ደግሞ ሦስት ዓመት ሞልቶታል። "ልጇ ጠዋት የእናቷ ፎቶ ስር ሻማ አብርታ 'ለእናቴን እየጸለይኩ ነው' ትላለች። ጥቁር ለብሳ 'የእናቴን ሀዘን ልወጣ ትላለች'። መአዛ የተቀበረችበት ቤተክርስቲያን እየሄደች ብዙ ጊዜ የሰፈር ሰዎች መልሰዋታል። ትንሹ ልጇ ሆስፒታል ያለች ስለሚመስለው 'መአዛ ጋር አንሂድ' ይላል።" ውዴ ይህን የምትናገረው እንባ እየተናነቃት ነው። መአዛ እናታቸውን ጧሪ፣ ቤተሰቡን ሰብሳቢ እንደነበረችም ትናገራለች። መአዛ የፊታችን ክረምት ላይ ከሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ትመረቅ ነበር። ፍትህ ወዴት አለሽ? መአዛ ህክምና ላይ ሳለችና ከሞተች በኋላም ቤተሰቡን በማገዝና ጉዳዩ ትኩረት እንዲቸረው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመጻፍ ሲተባበሩ ከነበሩ በጎ ፍቃደኞች አንዷ ኤደን ጸጋዬ ናት። የተጠርጣሪው ማምለጥ እንዳለ ሆኖ የፖሊሱ መሰወር እና የመአዛ ቤተሰብ ጉዳዩን እንዳያውቅ መደረጉ ተደማምሮ "በሴቶች ላይ ጥቃት ሲደርስ ህግ አስፈጻሚ አካልን ማመን ይቻላልን?" የሚል ጥያቄ እንድታነሳ አድርጓታል። ጥቃት አድርሶ የተያዘ ሰው የሚያዝበት መንገድ ብቻ ሳይሆን አንዲት ሴጥ ጥቃት ደርሶባት ወይም ስጋት አድሮባት ለፖሊስ ለመጠቆም ወደ ሕግ ቦታ ስትሄድ ያለው አቀባበል ሴቶች በስርዓቱ ያላቸው እምነት አንዲሸረሸር ያደርጋል ትላለች። • የተነጠቀ ልጅነት "ምርመራ ሲደረግ የተጠቃችን ሴት መልሶ ማጥቃት የሚመስል ንግግር ይደረጋል። ከዛም ባላይ በነፍስ ግድያ የተጠረጠረ ግለሰብ ማምለጡ እንደ ቀላል ነገር ሲታይ እምነት ያሳጣል። አጥቂዎች የሚገባቸውን እያገኙ አይደለም" ትላለች ኤደን። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሁለቱን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሰር ለማዋል አስፈላጊውን መረጃ ያሰባሰቡ ሲሆን፤ የደረሱበትን ደረጃ በቅርብ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ፖሊስ ከሴቶች ጥቃት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ስለሚይዝበት መንገድ ስለሚነሳው ቅሬታ ኮማንደሩ ሲመልሱ፤ "አንድ ፖለስ ማምለጡ ሁሉም ፖሊስ ላይ እምነት ሊያሳጣ አይገባም። በተፈጸመው ነገር ሁላችንም አዝነናል። ከአንድ ጠንቃቃ ፖሊስ የሚጠበቅ አይደለም። በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ጥብቅ እርምጃ እንወስዳለን።"
news-52996563
https://www.bbc.com/amharic/news-52996563
"በአንድ ምሽት ቤታችን ወደ ኮሮናቫይረስ ማዕከልነት ተቀየረ"
እንደ ህንድ ባሉ አገራት ከተለያየ ትውልድ የተወጣጡ ቅድመ አያት፣ አያት፣ አጎት፣ አክስት ልጆች፣ ዘመድ አዝማዱ ተሰባስቦ የሚኖርበት ሁኔታ በቅድመ ኮሮናቫይረስ ወቅት የሲሳይ፣ ደስታና መፈቃቀር ጊዜ ነበር።
የነ ሙኩል ቤተሰቦች አስራ ሰባት ናቸው ማን ያውራ የነበረ እንዲሉ የእነ ሙኩል ጋርግ አስራ ሰባት አባላት ያሉት ቤተሰብም፤ ደስታና ሃዘን ሲፈራረቅ፣ ሠርጉ በዓሉን፤ ክፉውን ደጉን እያዩ መከራም ሆነ ሌላው ሳይፈትናቸው አብረው ኖረዋል። መቼም የሰውን ልጅ አኗኗር ስር ነቀል ለውጥ እያስከተለ ያለው የኮሮናቫይረስ፤ መሰባሰብን ከሩቁ እንዲሸሽ ብዙዎችን አስገድዷል። ለእነ ሙኩል ቤተብም በሽታው ሌላ አደጋን ጋርጦ ነበር፤ ከአኗናራቸው፣ ከትውፊታቸው ሊነቅል የሚችል አደጋ። ዕለቱ አርብ ሚያዝያ 16/2012 ነበር። ሙኩል የሃምሳ ሰባት ዓመት አጎቱ ሙቀት፣ ሙቀት ሲላቸው ብዙም አላስጨነቀውም ነበር። ሆኖም ነገሩ በእሳቸው አልተወሰነም በአርባ ስምንት ሰዓታትም ውስጥ ሌሎች ሁለት የቤተሰቡ አባላትም ታመሙ። ከፍተኛ የሙቀት መጠን፤ የድምፃቸው መሻከር፣ መጎርነንና ሳልም መከታተል ጀመረ። ሙኩልም ያው የወቅቱ ጉንፋን ነው ብሎ ችላ አለው፤ ኮሮናቫይረስ ሊሆን ይችላል የሚለውን ማመንም ሆነ መቀበል አልፈለገም። "በቤታችን ውስጥ አንዳንዴ አምስት፣ ስድስት ሰው ይታመማል፤ ከሰው ሰውም ይጋባል እና ምንም መረበሽ አያስፈልግም" ራሱን ለማፅናናት የተናገረው ነበር። በቀጣዮቹ ቀናትም አምስት ተጨማሪ የቤተሰቡ አባላት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ሲያሳዩ ልቡ መሸበር ጀመረ። በቀናትም ውስጥ ከአስራ ሰባቱ ውስጥ አስራ አንዱ ታመሙ፤ ሲመረመሩም አስራ አንዱም በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ። "ከውጭ ያገኘነው ሰው የለም፤ ወደ ቤታችን የመጣም ሰው የለም። ሆኖም ኮሮናቫይረስ ቤታችን ገብቶ በርካታ የቤተሰባችን አባላት ታመዋል" በማለት በድረገፁ ላይ የፃፈው ሙኩል በመቶዎች የሚሆኑ አስተያየቶችን ከአንባቢዎች ተቀብሏል። ህንድ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አስገዳጅ የቤት ውስጥ መቀመጥ ውሳኔን ያስተላለፈችው መጋቢት 16/2012 ዓ.ም ሲሆን እስከዚህ ሳምንትም ድረስ እየተራዘመ ቆይቷል። አርባ በመቶ የሚሆኑት ህንዳውያን ከተለያየ ትውልድ የተውጣጡ ቤተሰቦች በአንድ ጣራ ነው የሚኖሩት። በአንድ ቤት ውስጥ እንዲሁ በተለያየ እድሜ ያሉ ቤተሰቦች ሰብሰብ ብለው ከመኖራቸው አንፃር ድንገት አንድ ሰው እንኳን በቫይረሱ ቢያዝ ሌሎችም የመጋለጣቸው ዕድል በጣም ከፍተኛ ነው። እንዲህ እንደ ሙኩል ላሉ ትልቅ ቤተሰቦች ደግሞ አካላዊ ርቀት መጠበቅ የማይታሰብም ቅንጦትም ነው። ከውጪው ዓለም ተነጥለው ቤት ውስጥ ተቀምጠው ባሉበት ሰዓት ሰው እንዴትስ ከቤተሰቡ ይርቃል? "የብቸኝነት ስሜት ተሰማን" በሰሜናዊ ደልሂ በተጨናነቀ ሰፈር ኑሯቸውን ያደረጉት እነ ሙኩል ቤታቸው ሦስት ፎቅ ነው። የ33 ዓመቱ ሙኩል፣ የ30 ዓመት ባለቤቱ፣ የስድስትና ሁለት ዓመት ልጆቻቸው፣ ወላጆቹና ከአያቶቹ ጋር ሆነው በሦስተኛ ፎቅ ላይ ይኖራሉ። ከእነሱ በታች ባሉት ሁለት ፎቆች ደግሞ የአባቱ ወንድሞች (አጎቶቹ) ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖራሉ። በአጠቃላይ አስራ ሰባት አባላት ያሉት ቤተሰብ በእድሜ ደረጃ ቢታዩ ከአራት ወር ጨቅላ እስከ 90 ዓመት አያት የሚኖሩበት ነው። እንዲህ ሰብሰብ ብለው የሚኖሩበት ነው ሲባል የተጨናነቀ ሊመስል ይችላል። ነገሩ ወዲህ ነው። ቤታቸው የተንጣለለና ሰፊ ነው። እያንዳንዱ ፎቅ አንድ የቴኒስ ሜዳ እጥፍ በሚባል ሁኔታ 250 ካሬ ሜትር የሚሸፍን፣ ሦስት መኝታ ክፍሎች ከመታጠቢያ ቤቶች ጋርና በርካታ ማዕድ ቤቶችን የያዘ ነው። በተንጣለለ ቤት ቢኖሩም ቫይረሱን በፍጥነት ከመዛመት አላገደውም። ከፎቅ፣ ፎቅም ተሻግሮ ሁሉንም ትልልቅ ሰዎች ሊያጠቃ ችሏል። በቫይረሱ መጀመሪያ ተያዘ የተባለው የሙኩል አጎት ሲሆን እንዴት ቫይረሱ እንደያዘውም ለቤተሰቡ ግልፅ አይደለም፤ ከጥርጣሬ በስተቀር። "ምናልባት ከአትክልት መቸርቸሪያ ቦታ ይሆናል፤ ወይም ደግሞ እቃ ልንገዛ መደብር በሄድንበት ወቅትም ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ወቅቶች ብቻ ነው ከቤት የወጣነው" ይላል ሙኩል። መታመም ሲጀምሩ ጥርጣሬ ቢኖራቸውም በመጀመሪያው ወቅት በፍራቻና በእፍረት ተሸብብው አልተመረመሩም። "አስራ ሰባት ብንሆንም የብቸኝነት ስሜት ተሰማን። በቫይረሱ ተይዘን ብንሞት ቀብራችን ላይ ማንም አይመጣም የሚለውን ስናስበው ጭንቀት ነው የለቀቀብን። ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ የመጣው መገለልና አድልዎ በቀላሉ የሚታይ አይደለም" ብሏል። እናም ሳምንታትም ቆዩ ፤ የሃምሳ አራት ዓመቷ አክስቱ ትንፋሽ ሲያጥራት ሆስፒታል ለመውሰድ ተገደዱ። እነሱም መመርመር እንዳለባቸውም ወሰኑ። "የህመም ወር" የግንቦት ወርን ሙሉ ከቫይረሱ ጋር እየታገሉ ነው ያሳለፉት። ሙኩል ዶክተሮች ጋር በየቀኑ ይደውላል፤ ረዥም ሰዓትም ያወራል። በተቻለ መጠንም ቤተሰቡ እንዳይገናኝ በማድረግም በዋትስአፕ ያወራሉ። "የህመም ምልክታቸውን እያየን የቤተሰቡን አኗኗር መቀያየር ጀመርን። ለምሳሌ ባልና ሚስትም ቢሆኑ ከፍተኛ ሙቀት ካላቸው በአንድ ክፍል ውስጥ እንዳይሆኑ ማድረግ ነበረብን" በማለት ያስረዳል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በቫይረሱ ከተያዙት ከአስራ አንዱ ውስጥ ስድስቱ ላይ ስኳር፣ የልብ ህመምና፣ የደም ግፊት መኖሩም አሳሳቢ ነበር። "በአንድ ምሽትም ነው ቤታችን ወደ ኮሮናቫይረስ ማዕከልነት የተቀየረው። እየተፈራረቅንም እንደ ነርስ በመሆን አንዳችን አንዳችንን መንከባከብ ነበረብን" ይላል ሙኩል። "በተለያየ እድሜ ላይ የሚገኙ ሰዎች በአንድ ጣራ ስር ሲኖሩ አደጋ የሚሆነው በእድሜ ለገፉት ነው" በማለት ዶክተር ፓርቶ ሳሮቲ ሬይ ያስረዳሉ። ሙኩልንም በጣም ያስጨነቀው የዘጠና ዓመቱ አያቱ ጉዳይ ነበር። ነገር ግን የቫይረሱ ሁኔታ በበርካታ የጤና ባለሙያዎች ዘንድ እንኳን ሚስጥራዊነቱ ቀጥሎ ለነ ሙኩል ቤተሰቦችም አንዳንድ ያልተጠበቁ ክስተቶችን አስተናግደዋል። በሰላሳዎቹ እድሜ ላይ የሚገኙት እሱም ሆነ ባለቤቱ ምንም ምልክት የማያሳዩ ህሙማን መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡን ያስደነቀው አያቱ ምልክት አለማሳያታቸው ነው። ከዚህም በተጨማሪ ተደራራቢ ህመም ያለባቸው የቤተሰቡ አባላት ህመሙ ሳይጠናባቸው ምንም ችግር የሌለባት አክስቱ ጠንቶባት ወደ ሆስፒታል ተወሰደች። ሙኩል በድረገፁ ላይ የጻፈው ጦማር አላማም ከሚያነቡት ሰዎች የሃሳብ እርዳታን በመሻት ቤተሰቡ የደረሰበትን ጭንቀት ለማጋራት ብሎ ነው። "መጀመሪያ አካባቢ ሰዎች ምን ያስባሉ በሚል ብዙ ተጨንቀን ነበር። ነገር ግን ከጽሁፌ በኋላ የተሰጡትን አስተያየቶች ሳነብ ብዙዎች በቫይረሱ መያዝ የሚያሳፍር አይደለም፤ አይዟችሁ የሚሉም ማፅናኛ ስለነበር ቀለል አለን" ይላል። ግንቦት በገባ ሁለተኛ ሳምንትም ምልክቶች መጥፋት ጀመሩ፤ ብዙዎቹም ሲመረመሩም ነፃ ሆኑ። ሆስፒታል የገባችው አክስቱም ነፃ ተብላ ወጣች። ክፉውን ጊዜም አለፉት፤ እፎይም ማለት ጀመሩ። ግንቦት ሦስተኛ ሳምንት አካባቢም እሱን ጨምሮ ሦስት የቤተሰቡ አባላት ከኮሮናቫይረስ ነፃ አልነበሩም። ሆኖም ግንቦት 24/2012 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ ሲመረመሩ ነፃ ተባሉ። "ክፉና ደጉን ያየንበት ጊዜ" በህንድ ያሉ ትልልቅ ቤተሰቦች የድጋፍና እንክብካቤ ምንጭ ቢሆኑም ከሃብት ክፍፍልም ጋር በተያያዘ ግጭቶችም ይነሳሉ። በዚህ ክፉ ወቅት ግን አንዱ ላንዱ መቆሙ፣ እንክብካቤም በቀላሉ ማግኘት መቻል መልካም ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል። "የእድሜ ባለፀጋ የሆነ ሰው ያለምንም እርዳታ በለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት እንዴት ይታሰባል? ምንም እንኳን ችግሮች ቢኖሩም በአንድ ቤት ውስጥ አብሮ መኖር ትንሾች ትልልቆችን የሚንከባከቡበት እድል ይፈጥራል፤ ይህም መኖሩ መልካም ነው" ይላሉ ዶክተር ጆን። በህንድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ250 ሺህ መብለጡን ተከትሎ ወረርሽኙ ለእንዲህ አይነት ቤተሰቦችም ስጋት ደቅኗል። ወጣቶች በዕድሜ ጠገብ ያሉ ቤተሰቦቻቸው ላይ በሽታውን እንዳያዛምቱ ፍራቻ አድሮባቸዋል። "ለምዕተ ዓመታት ዘመድ አዝማድና ቤተሰብ አብሮ ኖሯል። ይህንንም የምዕራባውያን እሴቶችም ሆነ ቅኝ ግዛት ሊሸረሽረው አልቻለም" በማለት በካንፑር በሚገኘው ሲኤስጄኤም ዩኒቨርስቲ የማኅበረሰብ ጥናት መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ኪራን ላምባ ጅሃ ያስረዳሉ። "ኮሮናቫይረስም ይህንን የኑሮ ዘያችንን፣ ትውፊታችንን አይሸረሽርም" ብለዋል ፕሮፌሰሯ። እነ ሙኩልም በፕሮፌሰሯ ሃሳብ ይስማማሉ። ቫይረሱ ፈትኗቸዋል፤ አስተምሯቸዋል እንዲሁም ሌላም፣ ሌላም ግን በአንድነትም ተወጥተውታል። ከቫይረሱ በፊት የነበረው የቤተሰቡ አኗኗርና ሃብት የ90ዎቹን የቦሊውድ ፊልም ይመስል እንደነበር ሙኩል በመቀለድ ያስታውሳል። "በዚህ አንድ ወር ውስጥ አንድ ላይ እንዳሳለፍነው ወቅት መቼም ቢሆን አብረን ሆነን አናውቅም ነበር። ቤተሰቡ በህብረት መሆኑ አስደሳች ነበር" ለሚለው ሙኩል በየተራ ሲታመሙ ማየት ግን ቀላል አልነበረም። "ቤተሰቡ ክፉውንም ደጉንም ያየበት ወቅት ነው፤ ጠንካራም አድርጎናል" ይላል። አክሎም "ምንም እንኳን ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ መያዝ ሁኔታ እንዳለ ብንረዳም፤ በአሁኑ ሰዓት ግን ቫይረሱን መርታት በመቻላችን የተሰማንን ደስታ አብረን እያከበርን ነው" ብሏል።
news-56651317
https://www.bbc.com/amharic/news-56651317
ሕዳሴ ግድብ፡ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በኪንሻሳ ያደረጉት ውይይት ያለውጤት ተጠናቀቀ
ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ የመጠቀም ያላትን ተፈጥሯዊ መብትን የሚቃረን ማንኛውንም ስምምነት እንደማትፈርም አስታወቀች።
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለውጤት ተጠናቋል። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ባወጣችው መግለጫ ነው "ብሔራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ ስምምነት ውስጥ እንደማትገባ" በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂሚኒስቴር በኩል ይፋ ያደረገችው። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ "ፍትሃዊና ምክንያታዊ የሆነውን፣ የአሁንና የወደፊቱን የአባይን ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚገድብ ማንኛውንም ስምምነት አትፈርምም" ሲል ሚኒስቴሩ የአገሪቱን አቋም ገልጿል። ዲሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ በተካሄደው ደቡብ አፍሪካ፣ አሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት በታዛቢነት በተገኙበት በዚህ ድርድር ላይ የተለያዩ ጉዳዮች ተነስተው የሦስቱ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በአፍሪካ ሕብረት አማካይነት ተወያይተዋል። ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ ድርድሩ ላይ ደቡብ አፍሪካ፣ የአውሮፓ ሕብረትና አሜሪካ በታዛቢነት እንዲቀጥሉ የተስማማች ሲሆን ሱዳንና ግብጽ ግን ከአፍሪካ ሕብረት እኩል ሚና እንዲኖራቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ተቀባይነት እንዳላገኘ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ይህንን ሃሳብ ውድቅ ያደረገቸው "የአፍሪካ ሕብረትን ሚና የሚያሳንስ ነው" በሚል እንደሆነ ሚኒስቴሩ ገልጾ፤ ነገር ግን ታዛቢዎቹ የድርድሩን ሂደት እንዲደግፉና ሦስቱም አገራት በጋራ ሲስማሙ ብቻ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ተስማምታለች። በውይይቱ ማብቂያ ላይ በዲሞክራቲክ ኮንጎና በአፍሪካ ሕብረት የቀረበውን ረቂቅ መግለጫ ኢትዮጵያ መቀበሏን ያመለከተው መግለጫው ግብጽና ሱዳን ግን ሳይቀበሉት ቀርተዋል በማለት "ሁለቱ አገራት ድርድሩ አውንታዊ ውጤት እንዳይኖረው እንቅፋት ሆነዋል" ሲል ወቅሷል። ግብጽና ሱዳንም በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ ሲያደርጉት የነበረው ውይይት ያለ ውጤት መጠናቀቁን በመግለጽ ኢትዮጵያን ተጠያቂ አድርገዋል። ሮይተርስ የዜና ወኪል ሁለቱ አገራት ለድርድሩ የቀረበውን ሐሳብ ኢትዮጵያ ሳትቀበለው አንደቀረች መግለጻቸውን ዘግቧል። "ይህ የኢትዮጵያ አቋም በቅን ልቦና ለመደራደር ፖለቲካዊ ፈቃደኝነቱ እንደሌላት በድጋሚ የሚያሳይ ነው" ሲል የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። የሱዳን መስኖና የውሃ ሀብት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ደግሞ "ይህ የኢትዮጵያ ግትር አቋም ሱዳን ሕዝቧንና ደኅንነቷን ለመጠበቅ ሌሎች አማራጮችን እንድትፈልግ ያደርጋታል" ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል። የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው እንደገና በተጀመረው በዚህ የሦስቱ አገራት ውይይት ላይ ከስምምነት ለመድረስ የሚያስችል እርምጃ ባለማሳየቱ ስኬታማ ሊሆን አልቻለም። የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በድርድሩ ዙሪያ ማክሰኞ ማታ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው ግን ለድርድሩ ስኬታማ አለመሆን "ሱዳንና ግብጽ የያዙት ግትር አቋምን" እንደምክንያት አቅርቧል። ሚኒስቴሩ በግድቡ አሞላል፣ ውሃ አያያዝ እንዲሁም አለቃቀቅን በተመለከተ ከስምምነት ለመድረስ ኢትዮጵያ ዝግጁ እንደሆነች ጠቅሶ፤ ነገር ግን "ሁለቱ አገራት ድርድሩ የኢትዮጵያን የውሃ ድርሻ የሚገድብና አለን የሚሉትን የውሃ ክፍፍል የሚያፀና አስገዳጅ ስምምነት ካልተደረሰ የሚል አቋም በመያዛቸው" ከውጤት አለመደረሱን ገልጿል። ጨምሮም ግብጽና ሱዳን በተደጋጋሚ ሲሉት የነበረውን አስገዳጅ ስምምነት ሳይደረግ የግድቡ ሙሌት መከናወን የለበትም የሚለው ሃሳብ "የሕግ መሠረት የሌለውና ኢትዮጵያ የላትን የተፈጥሮ ሃብት የመጠቀም መብት የሚጋፋ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም" ሲል ውድቅ አድርጎታል። በዚህም መሠረት የግድቡ ሁለተኛ ዓመት የውሃ ሙሌት ከዚህ በፊት በተደረሰው የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት መሰረት በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ መሰረት ይካሄዳል ሲል የኢትዮጵያን አቋም በድጋሚ ይፋ ገልጿል። በዲሞክራቲክ ኮንጎ መዲና ኪንሻሳ የተካሄደው ድርድር ለሁለት ቀናት የታሰበ የነበረ ቢሆንም አገራቱ ከሚያስማማ ነጥብ ላይ መድረስ ስላልቻሉ ለሦስተኛ ቀን ማክሰኞ ዕለት ቀጥሎ ተካሂዶ እንደነበር ተነግሯል። ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ተቋርጦ ቆይቶ አሁን የተካሄደው ድርድር ያለውጤት ቢጠናቀቅም በቀጣይ በሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ግንባታው ከተጀመረ አስረኛ ዓመቱን የያዘው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና ቀጣይ የሥራ ሂደትን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል ለዓመታት ሲካሄድ የቆየው ድርድር ውጤት ሳያስገኝ እስከአሁን ዘልቋል። አሁን የአፍሪካ ሕብረት በሚያሸማግለው ይህ ድርድር ቀደም ሲል በአዲስ አበባ፣ በካርቱም፣ በካይሮና በዋሽንግተን ላይ የሦስቱ አገራት ልዑካን ተገናኝተው ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ ከቆየ በኋላ በበይነ መረብ አማካይነት ቀጥሎ ነበር። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጭምር የተሳተፉበት የዋሽንግተኑ ድርድር ከስምምነት ለመድረስ ከጫፍ ደርሶ ነበር ተብሎ የተነገረለት ቢሆንም ኢትዮጵያ የቀረበው ሐሳብ ብሔራዊ ጥቅሜን የሚያስጠበቅ አይደለም ስትል ከፊርማው ራሷን አግልላለች። ኢትዮጵያ አምስት ቢሊየን የሚጠጋ ዶላር አውጥታ እየገነባችው ያለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ 20 በመቶ ያህል የቀረው ሲሆን፤ ግድቡ በአፍሪካ ካሉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች በሙሉ ቀዳሚውነው ተብሏል። ግድቡ ተጠናቅቆ ሙሉ ለሙሉ ሥራውን ሲጀምር ከ5ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም አለው። ግድቡ ባለፈው ዓመት የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ያደረገ ሲሆን ሁለተኛውን ዙር ደግሞ በመጪው ክረምት እንደሚከናወን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። ወደ 80 በመቶ የሚጠጋው የግድቡ የግንባታ ሥራ መከናወኑ የተነገረ ሲሆን በመጪው ዓመትም በተወሰነ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል። ግብጽና ሱዳን ግድቡ የውሃ አቅርቦታችንን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል በሚል ከግንባታው መጀመር አንስቶ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቢቆዩም፤ ከግማሽ በላይ ለሚሆነው ሕዝቧና እያደገ ላለው የኢንዱስትሪ ዘርፏ ኤሌክትሪክ ለማቅረብ ዋነኛ ግቧ አድርጋ የተሳችው ኢትዮጵያ በግንባታውና ቀጥላ ወደ ማጠናቀቁ ተቃርባለች። የአባይ ወንዝን 85 በመቶ ውሃ የምታመነጨው ኢትዮጵያ፣ የግድቡን ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ከማከናወኗ በፊት አሳሪና ሕጋዊ ስምምነት እንድትፈርም እየወተወቱ ያሉት ሱዳንና ግብጽ ባቀረቡት ሐሳብ ላይ ሳትስማማ ቆይታለች። የግብጽ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ባለፈው ማክሰኞ፣ ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው ግድብ ሳቢያ አገራቸው በምታገኘው የውሃ መጠን ላይ ተጽእኖ የሚፈጠር ከሆነ 'የከፋ አካባቢያዊ ችግር' ይፈጠራል ሲሉ አስጠነቅቀው ነበር። ፕሬዝዳንቱ "ማንም ከግብጽ ውሃ ላይ አንዲት ጠብታ መውሰድ አይችልም፤ ይህ ከሆነ ደግሞ ከሚታሰበው በላይ አደገኛ አለመረጋጋት በአካባቢው ይፈጠራል" ብለዋል። ኢትዮጵያ ግድቡን የምትጠቀመው ውሃውን በግዛቷ ውስጥ ለሚያስቀሩ ፕሮጀክቶች እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ብታስረዳም ሱዳን በተለይም ግብጽ የትኛውም አይነት በውሃው ላይ የሚከናወን ሥራ የእነሱን ይሁንታ ሳያገኝ መካሄድ እንደሌለበት ሲገልጹ ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ባደረጉት ንግግር "ውሃ አሞላሉን በተመለከተ ተደራድረን ስናበቃ እንሙላ ካልን ክረምቱ ያልፍና በዓመት 1 ቢሊየን ዶላር እናጣለን" ሲሉ የውሃ ሙሌቱን ማዘግየት እንደማይቻል አመልክተዋል። የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የሆኑት ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂ.) ኢትዮጵያ ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በምንም ዓይነት መልኩ እንደማታራዝመውና ለዚህም የሚያበቃ አሰራርና ምክንያትም እንደሌለ ተናግረዋል። ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በስልክ የተወያዩት የአሜሪካው ውጩ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን፣ አሜሪካ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ አለመግባበት በውይይትና ሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ፍላጎት እንዳላት መግለጻቸው የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የህዳሴው ግድብ ውዘግብ በግብጽ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና እና በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ግብጻውያን ስጋት ነውን?
44450098
https://www.bbc.com/amharic/44450098
ትራምፕና ኪም ተጨባበጡ
ዶናልድ ትራምፕና ኪም ጆንግ ኡን ከብዙ እሰጥ አገባ በኋላ በሲንጋፖሯ ሴንቶሳ ደሴት በሚገኝ ዘመናዊ ሆቴል ተገናኝተው ተጨባብጠዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ "ጥሩ ነገር ተሰምቶኛል ፤ ጥሩ ውይይት እናደርጋለን፤ ውጤታማ ይሆናል ብዬ አስባለሁ" ሲሉ ለታሪካዊው አጋጣሚ ያላቸውን ስሜት ገልፀዋል። ኪም በበኩላቸው "እዚህ ለመገናኘት ቀላል አልነበረም፤ በርካታ እንቅፋቶች ነበሩብን፤ ነገር ግን እነርሱን አልፈን እዚህ ደርሰናል" ብለዋል። መሪዎቹ አስተርጓሚዎች ብቻ በተገኙበት ለአርባ ደቂቃ የዘለቀ የአንድ ለአንድ ውይይት አድርገዋል። የአሜሪካ ፕሬዚደንትና የሰሜን ኮሪያው መሪ ለድርድር ሲቀመጡ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ሲሆን በአገራቱ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ እንዲሁም የጦር መሳሪያ ቅነሳ ላይ መክረዋል። ሁለቱ መሪዎች በምን ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ የታወቀ ነገር የለም። ጉባዔውን አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች የኪም ፕሮፖጋንዳ ሲሉት ሌሎች ወደ ሰላም የሚያደርስ መንገድ ነው ሲሉ ገልፀውታል።
news-48996255
https://www.bbc.com/amharic/news-48996255
“. . . በዘር ተከፋፍለን በደልነው፤ ‘እናንተ የኔ ባሮች አይደላችሁም፤ ሒዱ ውጡ’ ብሎ አባረረን” ሐጂ ዑመር ኢድሪስ
በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ መንግሥትና የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላለፉ ሲሆን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ነው። ከትናንት በስቲያ የሐይማኖት አባቶች አገር አቀፍ የፀሎትና የምህላ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች፥ ከመጋቢት 28፣ 2012 ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ እና ኢትዮጵያዊያን በቤታቸው ሆነው በጸሎትና የፈጣሪን ምህረት የሚለምኑበት ጊዜ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ የተለያዩ የሐይማኖት መሪዎች ተገኝተው ፀሎት አድርገዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስም በዕለቱ ተገኝተው ዱዓ አድርገዋል። በንግግራቸውም "አላህ በተደጋጋሚ ተናግሯል፤ አስጠንቅቋል። አላህ በነፋስ አስጠነቀቀን፣ አላህ በጎርፍ አስጠነቀቀን፤ ዓለም ግን አሻፈረኝ አለች። አሁን መድኃኒት የሌለው በሽታ አመጣብን። በቅርብ መድኃኒቱ ይገኛል (ኢንሻአላህ)። ዋናው ግን የእኛ መመለስ ነው" ብለዋል። ሐጂ ዑመር አክለውም፤ "በቤተክርስቲያን እና በመስጊድ ስንት ክፉ ነገር ፈፀምን፤ አላህም ተቆጣ። በዘር ተከፋፍለን በደልነው፤ 'እናንተ የኔ ባሮች አይደላችሁም፤ ሒዱ ውጡ' ብሎ አባረረን። በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መስጊድ እና ቤተክርስቲያን ተዘጉ። ከዚህ በላይ በምን ይናገረን?" ሲሉ ተደምጠዋል። ንግግራቸው በርካቶችን ያስደመመ ነበር። በርካታ ሰዎች ንግግራቸውን በድምፅና በፅሁፍ በማድረግ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተቀባባሉት ይገኛሉ። ይህን ተከትሎ ቢቢሲ ከወራት በፊት ከተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ሊያጋራችሁ ወዷል። ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ባለፈው ቅዳሜ በሚሌኒየም አዳራሽ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል። ይህንኑ ተከትሎ ከሙፍቲህ ሐጂ ዑመር ጋር ያደረግነውን አጭር የስልክ ቃለ ምልልስ እነሆ፤ [ማስታወሻ፡ በርሳቸው የተነገሩ የአረብኛ ቃላትን ሙሉ በሙሉ ከመግደፍ ይልቅ በቅንፍ አቻ የአማርኛ ትርጉም መስጠትን ወደናል።] እንኳን ደስ አለዎት ሐጂ፤ ያውቁ ነበር እንዴ እንደሚሸለሙ? መቼ ነበር የሰሙት? ወላሂ አሁን ለታ..ማነው ሐሙስ ማታ ነው ታከለ፣የተከበሩ ምክትል ከንቲባ፣ ደውለው የነገሩኝ። 'ቅዳሜ እንዲህ ያለ ነገር ስላለ እንዲትመጡልን' ብለው ምክትል ከንተባው ደወሉልኝ። አሁን ለታ ማታ። በጣም ነው የደነገጥኩት፣ እኔ እንዳው።ይሄ ነገር መስመሬም ስላልሆነ ደሞም ያሰብኩትም፣ የጠረጠርኩትም ስላልሆነ በጣም በጣም ነው 'ያኣጀበኝ' [የደነቀኝ]፤ አለቀስኩኝ የሚገርምህ ነገር...ወላሂ አለቀስኩኝ... • "መንግሥት የሚደግፈው የሙስሊሙን ሕብረተሠብ ነው" ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሐጂ! ለምን የተሸለሙ ይመስሎታል ግን...? ምን አልከኝ...ልጄ! በምን ምክንያት የተሸለሙ ይመስሎታል...ምን ስላበረከቱ...? ወላሂ እንግዲህ የሽልማቱ ምክንያት የልፋት ውጤት ነው የሚመስለኝ። እንግዲህ አዲስ አበባም 54 ዓመቴ ነው ከመጣሁ። እንግዲህ እዛም አገራችን 'ስቀራ' [ቅዱስ ቁርዓንን ስማር]፣ ሳስቀራ [ሳስተምር]...በሌላም በሌላም ለሕዝብ ልፋቴ በጠቅላላ ወደ 70 ዓመት ይሆናል። አንድ ቀን ለልጆቼ ወይ ለራሴ ብዬ አላቅም። በየክፍለ አገሩ በየዞኑ በየወረዳው እዞራለሁ። በኢትዮጵያ በሙሉ 'ፈትዋ' ሳደርግ ነው የኖርኩት። ደግሞ በኋላ አንድነት ብለን የዛሬ 11 ዓመት ገደማ ጀምረን ነበር። ኋላ አንድነቱ ደስ ያላላቸው ሰዎች አፍርሰውት ነበር። [እኔንም] ተው አሉኝ፣ ተውኩት። አላህ ደግሞ ጊዜያት አምጥቶት የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ እሳቸው ናቸው እንግዲህ ወደ አንድነት እንድንሄድ ያደረጉን። 'ጀዛቸውን' [ውለታቸውን] አላህ ይክፈላቸው። • በኮምቦልቻ ከተማ በተከሰተ ግጭት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ • ቴምር በረመዳን ለምን ይዘወተራል? አላኩሊሃል [ያም ሆነ ይህ] ሽልማቱ መሠረቱ የመሰለኝ አንደኛው በሙስሊሙና በክርስቲያኑ መካከል ሰላምና አንድነት የምፈልግ መሆኔና በዚህም መልፋቴ። ሁለተኛ በመንግሥት እና በሕዝበ ሙስሊሙ መካከል የሚያቀራርብ ሰላም መፈልጌ፤ ሦስተኛ ሙስሊሙና ሙስሊሙ ደግሞ ከመቃረን፣ ከመዳማት [ወጥቶ] አንድ መሆን አለበት እያልኩ እንግዲህ ወደ 40 ዓመታት መድከሜ ይመስለኛል። ዋናው ይሄ ይመስለኛል። ከይህ ሌላ 'አላኩሊሃል' [እንዲሁ በአጠቃላይ] የሙስሊም አገልግሎት በብዙ ዓይነት ነው። በማስተማር በዳእዋ [የስብከት አገልግሎት]። ቁርዓን እንዲሁ በሁለት በሦስት ዓይነት ተርጉሚያለሁ። ሌሎችም የተውሂድ ኪታቦችን [መጻሕፍትን] ብዙ የተረጎምኳቸው አሉ። ሌላ በአረብኛ ደግሞ 'ዱአ'ን [ጸሎትን] በተመለከተ የነብያችንም ውዳሴ በተመለከተ ወደ 80 መጽሐፎች በአማርኛ ደርሻለሁ። እንግዲህ መቼም 'አላኩሊሃል' [ከሞላ ጎደል] ሕይወቴን መቼም የጨረስኩት ሕዝብን በሚያቀራርብ ነገር ነው። አሁንም ደግሞ ዶ/ር ዐቢይ አንድነት ኮሚቴ ሰብሳቢ አድርጎኝ በዚያ ምክንያት አንድነት ባይገኝ ኖሮ ብዙ ደም እንደሚፋሰስ ሙስሊሙ በጣም በጣም ከባድ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ነበር ጥርጣሪያችን፤ አልሀምዱሊላህ ይኸው መቼም አንድነቱ ተከናውኖ ጀምረነዋል። አላህ መጨረሻውን ቢያሳምረው መቼም። • ለሲዳማ ክልልነት 'ይሁንታ ተሰጠ' በሚል በርካቶች ደስታቸውን እየገለጹ ነው በአጠቃላይ ስለ ሙስሊሙም ሆነ ስለ ክርስቲያኑ፣ ስለመንግሥትም ሆነ ስለ ሕዝብ በለፋሁት ልፋትና በተጨነኩት ምክንያት ይመስለኛል [የተሸለምኩት]።..ብዙ አልቅሻለሁ፤ ብዙ ለቅሶ ነው ያለቀስኩት [ይህ እንዲሆን]። በዚያ መነሻ አላህ ይህን [ስጦታ] ያመጣው ይሆናል እንጂ የምለው... እኔ [ይህ ይመጣል ብዬ] የጠረጠርኩት ጉዳይ አይደለም። መንግሥትም ይሄን ጉዳይ ያስብበታል ብዬ ትዝ አላለኝ...። ለሃይማኖት አባት እንደዚህ ያለ ደረጃና ሽልማት መሸለም በተለይ በአገራችን እኮ ይሄ የመጀመርያ ነው፤ ታይቶም አይታወቅም፤ ተሰምቶም አይታወቅም። ለክርስቲያኖች አልተሠራም፣ እንኳን ለሙስሊሙና። እኔ ብቻ ሳይሆን የሚያስደስተኝ ሙስሊም ሁላ ሊደሰትበት የሚገባ ነው። በሕይወት ያሉት አደለም የሞቱት የታገሉት አባቶቻችን ሁላ ውጤት ነው የሚል አመለካከት ነው ያለኝ መቼም... ሐጂ ዑመር፤ ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን የሌላ እምነት ተከታዮችም'ኮ እንደ ሃይማኖት አባት ለርስዎ መልካም ስሜት ያላቸው ይመስለኛል፤...ሰዎች ያንን ይነገርዎታል? እርስዎስ ያውቃሉ ይሄን? አውቃለሁኝ'ና፤ አሁንም ሳይሆን ፊትም ቀደም ባለ ጊዜ መጅሊስ ባለ ጊዜ ከ[ሃይማኖት] አባቶች ጋራ ስንሰባሰብ፣ ስንነጋገር ወዲያው እዚያው ጽፈው ይሰጡኛል። 'እርስዎ ንግግርዎ ወርቅ ነው፤ ብር እንኳ አይደለም፣ ወርቅ ነው' ይሉኛል። ሁለተኛ ደግሞ አጠቃላይ ነው ስለሃይማኖትህ ብቻ፣ ስለመስጊድ ብቻ ሳይሆን አንተ የምትናገረው ስለ አጠቃላይ ስለ ሙስሊሙም ስለክርስቲያኑም፣ ስለሆነ ንግግርህ መልካም ነው ይሉኛል። 'እንዳው ሙስሊሞች ጥሩ መሪ ሰጥቷቸዋል' እያሉ ሁልጊዜ ጽሑፍም ይሰጡኛል። ባሁን ደግሞ እኔንጃ ከሙስሊሙ የበለጠ ክርስቲያኑ ነው ደስ ያለው የሚመስለኝ። በትናንቱ ሁኔታ ከሙስሊሙ የባሰ ክርስቲያኑ ነው ደስ ያለው።[እሑድ' ለታ ነበር ያነጋገርናቸው] በሄድኩበት 'አብረነህ ፎቶ እንነሳ፣ ዕድሜህ ይቆይልን' የማይል አንድ እንኳ የለም። • "ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?" እኔም ደሞ ሙስሊምና ክርስቲያን ልዩነት የለኝም። የብሔር፣ የሃይማኖት ልዩነት አላውቅም፤ ድሀ ሀብታም አልልም። የተማረ ያልተማረ አልልም። እምነቴና አመለካከቴ እኩልነት የተመረኮዘ ስለሆነ የዚያ ውጤት ቢሆን ነው እንጂ [ተሸለምኩ] የምለው በጣም እንደው [የሰው ፍቅር] ካቅሜ በላይ ነው። ይህን በጣም አመሰግናለሁ። ዕድሜዎ ስንት ደረሰ ሐጂ? አሁንም ምናልባት ወደ 85ኛ ሳልጀምር አልቀርም... ይመስለኛል። ከጠ/ሚ ዐቢይ መምጣት ጋ ብዙ ተስፋዎች ነበሩ፤ አሁን ደግሞ 'ይቺ አገር መፍረሷ ነው፤ የሃይማኖትም ሆነ የብሔር እልቂት አይቀርላትም' የሚል ፍርሃት አለ። እርስዎ እንደው በቀረው የሕይወት ዘመንዎ ይህ ክፉ አጋጣሚ ይመጣል ብለው ይጨነቃሉ? እኛ እንግዲህ በንጉሡ ጊዜ መቼም ዳር እስከ ዳር የኢትዮጵያ ሰላም ነበረ፥ እኛ የምናውቀው እንኳ በአገራችን በገጠር እንኳ በመንግሥት የተባለ እንደሁ የተቀመጠው አይነሳም፣ የቆመው አይቀመጥም። እግሩ ሊራመድ አንስቶ እንደሆነ መሬት አያስቀምጥም። ያንን ወቅት አይተናል። በደርግም ደግሞ ያንን እልቂት፣ ያንን ረብሻም፣ ያንን 'ፊትና'ም [የሕይወት ፈተና] ደግሞ አይተናል። ከዚያም በኢህአዴግ እንዲሁ ያየነውን አይተናል። አሁን ግን የኔ አመለካከትና እንደኔ ሐሳብ ተሆነ ለእውነቱ እኔ ሰው አለሥራው ማመስገን አላውቅም። ዶ/ር ዐቢይ በተመረጡ ጊዜ በማግሥቱ ሲጠይቁኝ 'ባካችሁ ተስድስት ወር በኋላ ጠይቁኝ፤ አሁን አመስግኜ በኋላ ማማረር አልፈልግም' ነው ያልኳቸው። እና አሁን ያሉት መሪ አመለካከታቸው አንድነት፣ ሰላም፣ ልማት፣ ዕድገት ስለሆነ 'የሚያአጅብ' [የሚደንቅ] እኮ ነው። አይተንም ሰምተንም አናውቅም። የደካሞች ቤት እኮ እየተሠራ ነው'ኮ በምክትል ከንቲባና በዶ/ር ዐቢይ አመራር። የሽማግሌዎች የባልቴቶች ቤት እየተሠራ ነው። • አል ሻባብ የጎሳ መሪዎችን አስጠነቀቀ መቼም አሁን ችግር እፈጥራለሁ ቢል ችግር ፈጣሪውም ይሳካለታል ብዬ ምንም ሐሳብ የለኝም። ጥርጣሬም የለኝም። ይሄን [መልካም ጅማሮ] መቼም የማይቀበል አእምሮ ያለው ሰው፣ አለ ብዬ አልገምትምና ሁሌም አገራችን ታድጋለች፣ ትለማለች፣ አንድነታችን ይጠናከራል የሚል ሐሳብ ነው ያለኝ እንጂ እኔ አገር ይፈርሳል፣ ሽግር ይፈጠራል አልልም። በዚህ ረመዳን ወቅት በሙስሊም አካባቢ ሰላም ይከርማል ወይ ብሎ ሰው ጥርጣሬም ነበረው፤ አላህ ግን ሰላም አክርሞናል። ሐሳቤ የኔ አመለካከትም ይኸው ነው። ከይህ ሌላ ያለውን ደግሞ 'ረበል አለሚን አላህ' [የዓለማቱ ጌታ] ያውቃል። አላህ ደግሞ ችግር ፈጣሪውን ወደ ሰላም እንዲመለስ፣ ሥልጣን ፈላጊውም በመንገዱ እንጂ አለመንገዱ እንዳይፈልግ አላህን እንለምናለን፤ ዱአ አናደርጋለን። ዓለማዊ ትምህርትን ምን ያህል ገፍተውበታል ሐጂ? ዓለማዊ ትምህርት የለኝም፤ እኛ ከቶም ሀሁ ማለት ያን ጊዜ ፊደል በ'መሻኪኮቻችን' [በሃይማኖት አዋቂዎች ዘንድ] እና እንደ 'ኩፍር' [ከሃይማኖቱ ማፈንገጥ] ነበር የምንቆጥረው። እኛ ነን ከተማ ከገባን በኋላ አሁን ደረሳውንም ተማሩ ያልነው። ያን ጊዜ ከተማረ በሴት ወይ በሥልጣን ደልለው 'ያከፍሩታል' [ሃይማኖቱን ያስጥሉታል] ተብሎ በወሎ ኡለማው በጣም ያስጠነቅቅ ነበር። ስለዚህ እኔ ሃይማኖታዊ እንጂ ዓለማዊ ትምህርት የለኝም። ግን የሚገርመው ዓለማዊ ትምህርት የተማሩትን ጽፈው ያመጡትን ማስተካከል እችላለሁ። ይሄ የተፈጥሮ ጸጋ ይመስለኛል። ከወሎ ብዙዎቹ ወደ አልአዝሃር ዩኒቨርስቲ እየሄዱ ይማሩ ነበር በዚያን ጊዜ?እንዴት ሳይሄዱ ቀሩ? አልአዝሃር አልሄድኩም። ከወሎ ብቻ ነው የተማርኩት፤ ሐጂ መሀመድ ሳኒ ዘንዳ መጣሁ እንጂ ..። ደግሞስ ለሃይመኖት ትምህርት አል አዝሃርም ሆነ ማንም ሆነ እንደው ዲግሪ ለመቀበሉ፣ ስም ለማውጣት ነው እንጂ በትምህርት በኩል እኮ የአገራችንን 'ዑለማ' [የሥነ መለኮት ምሁር] የመሰለ አንድ እንኳ በዓለም አይገኝም። ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው የአገራችን 'ዑለማዎች' ናቸው። ችግሩ ብቻ ወደ ከተማ አልገቡም፤ እና ወደ አመራሩም ኪታብ ወደማበጀቱ [መጽሐፍ መድረሱ] ውስጥ አልገቡም ነው እንጂ አገራችን ዑለማዎችን የሚያህል አንድም የለም፤ በየትም። • በሊቢያ የሚገኙ የስደተኛ ማጎሪያዎች እንዲዘጉ ተጠየቀ እርስዎ የቀድመው ተወዳጅ የሃይማኖት አባት ሐጂ መሐመድ ሳኒ ሀቢብ ተማሪ ነዎት እንዴ? አዎ እርሳቸው ዘንዳ 'ሐዲስ 'ልቀራ'፣ ሌላውን 'ፊቂሁን' [ኢስላማዊ ሕግ] ነህው [የአረብኛ ሰዋሰው] ጨርሼ እዛ ተመልሼ ሼክነት ልወጣ ነበር ሼኮቹ የላኩኝ። አላህ እሳቸውን እዚህ [አዲ'ሳባ] አመጣ፣ እሳቸውን ብዬ እዚህ መጣሁኝ፤ እዚህ ሕዝብ ያዘኝ፣ በዚያው ቀረሁ፣ እሳቸውም እዚሁ ቀሩ። በሚሊንየም አዳራሽ በብዙ ሙያ ዘርፍ ለተመረቁ ብዙ ሺህ ተማሪዎች ንግግር ሲያደርጉ ነበር። እርስዎ ግን የቱ ትምህርት ዘርፍ ይበልጥብዎታል? [ሳቁ] እኔ ይሄን ይሄን አልልም። ሁሉም ጠቃሚ ነው። ያስተዳደሩን ብታየው፣ አለ አስተዳደር አይሆንም። የኢኮኖሚውን ብታየው አለ ኢኮኖሚስት ታልሆነ መቼም ይሆንም። የማስተማርም ሙያ ብታየው አስተማሪ ከሌለ ተማሪ የለ። እና ዕውቀት ሁሉም አስፈላጊ ነው። ሁሉም አንገብጋቢ ነው። ግን እገሌ ከእገሌ ትምሀርት ይሻላል አልልም። ዝንባሌው እንጂ በኔ በኩል ሁሉም እኩል ጠቃሚ ነው፤ ሁሉም ጥሩ ነው የሚል አመለካከት ነው ያለኝ፤ እኔንኳ ጥያቄዬ የነበረው ሐጂ... እርስዎ ዝንባሌዎ ምን ነበር? ከዓለማዊው ትምህርት... ወላሂ እኔ ብማር ኖሮ የምማረው ኢኮኖሚን በተመለከተ ይመስለኛል። እኔ ሼክነቱ በቀረ ነጋዴ ነበር የምሆነው። ሥልጣንን አልወደውም። የአመራር ትምህርት አልመርጥም። የኢኮኖሚ ትምህርት ነበር የምመርጠው ይሆናል። የግል ሕይወት በተመለከተ ትንሽ ጥያቄ ላንሳልዎ? ስንት ቤት አለዎ...?ስንት መኪና? [በአጭሩ ከሳቁ በኋላ] እኔ የምኖርበት ብታየው ያስቀሃል፣ ያስገርምሃል። እላይ መርካቶ ቤት ነበረኝ። እኔ መስጊድ እሠራለሁ እንጂ መኖርያ ቤት አልሠራም ብዬ የሚመጣው ሁላ 'የሙፍቲ ቤት ይሄ ነውንዴ?' ጉድ አረ ይሄን ቤት ለውጡ' ያላለኝ ሰው የለም። አሁን ደግሞ አዲስ ቦታ ነው ያለሁት። • የጋዜጠኛዋ መገደል ለምን የዓለም መነጋገሪያ ሆነ? አሁን የት አካባቢ ነው የሚኖሩት ታዲያ? እዚህ ጋርመንት የሚባል ሐና ማርያም ይባላል። በሱ አሻጋሪ ነው የምኖረው። አሁን እዚህ ከመጣሁ ሦስት ዓመቴ ነው። ሰፊ ቦታ ነው። ቆርቆሮ ነው፤ ግድግዳውም፣ ጣሪያውም ቆርቆሮ በቆርቆሮ ነው። ግን ሰፊ ነው። ይሄን ያህል'ኮ ጭንቅ የለኝም፤ እኔ አዲስ አበባ ይሄን ያህል 54 ዓመት ስቀመጥ ሙተአሊም [ተማሪዎቼ] ጋ ነው የምቀመጠው። የምበላው ሙተአሊም ጋ ነው። ገንዘቤን ለሙተአሊም ነው የማወጣው። ይሄን ያህል የደላ ኑሮም የለኝም። ስንት ልጆች አለዎት? ዐሥራ አንድ ነበሩ። አንድ ሞቷል። አሁን 10 አሉ። እርስዎ የመጡት ከወሎ አካባቢ ይመሰለኛል እና እዛ ደግሞ ሙስሊምና ክርስቲያኑ በመተሳሰብ ተፋቅሮ የመኖር ጠንካራ ባህል አለው። የተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ከዚያ አካባቢ ምን ሊቀስም ይችላል? ወላሂ እኛ እንግዲህ እስካለንበት ሕይወት ድረስ በወሎ ክፍለ አገር የብሔር ወሬ ጭራሽ የለም። ሁለተኛ የሃይማኖትም ልዩነት የለም። ወጣቶች ሙሽርነት እንኳ አብረው ይሞሸራሉ። ልዩነት ነገር አናውቅም፤ ሙስሊሙ ቤተክርስቲያን ሲገነባ ይረዳል፤ክርስቲያኑ ደግሞ መስጂድ ሲሠራ ይረዳል። የሚገርመው ክርስቲያኑ ደረሳ [መንፈሳዊ ተማሪዎች] ጠርቶ፣ አርዶ፤ አሳርዶ ሰደቃ [ዝክር] ይሰደቃል [ያበላል]። ይሄ ወሎን በተመለከተ ነው። ሌላው ቀርቶ ክርስቲያኑ አገር የሚባለው ጎጃም ሎማኔ የሚባል ከተማ መስጊድ ለምርቃት ሄጄ 'እገሌ ክርስቲያን ለመስጊድ ይሄን ያህል ረድቷል፤ እገሌ ደግሞ ይሄን ረድቷል፤ ከተባለ በኋላ በመጨረሻ 'ማርያም ቤተክርስቲያን 3ሺ ብር ረድታለች' ብለው ነው ያቀረቡልን። እንደዚያ ተባልኩኝ። • ባለጊዜው የግመል ወተት ይሄ ነው ሕዝባችን። የፖለቲካ ሰዎች በታተኑት እንጂ የኢትዮያ ሕዝብ የብሔር ልዩነት አያቅም፤ የሃይማኖት ልዩነት አያውቅ። ይሄ አሁን [በሃይማኖት መቃቃር] መጤ ተግባር ነው። እና እንዲህ ያለውን አሁንም ቢሆን ከሕዝቡ ልብ ላይ እንዲፋቅና እንዲለቅ ማድረግ ያስፈልጋል። ለመፋቅ ወደፊት ብዙ ዓመታት ይጠይቃል ነው እንጂ የምለው መልቀቁ መቼም እንደማይቀር ነው። ባለሥልጣኖች እንዲሁ ለሥልጣናቸው ሲሉ [ሕዝቡ ላይ] መርዝ ነሰነሱበት እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ አልነበረም። እኛ ተወሎ በዚህ በአርሲ በባሌ በጅማ የመጣ እንደሆነ ተከብሮ ተረድቶ ነበር የሚኖረው። ባሌን ያቀና የወሎ 'ኡለማ' ነው፤ አርሲን ያቀና የወሎ ኡለማ ነው፤ ጅማን በአባጂፋር ጊዜ ያቀና የወሎ ኡለማ ነው፤ ልዩነቱ እኮ በአገራችን አናውቅም ፤ ከመጣበት አናውቅም፤ በሽታው ከመጣበት ይመለስልን እያልን ነው [ዱአ የምናደርገው]። እየከፋ የመጣውን ዘረኝነትንስ በተመለከተስ ምን ይላሉ ሐጂ... ዘረኝነትን በተመለከተ ሃይማኖታችን 'ቆሻሻ ነው' ብሎ ነው የሚለው። ነብያችን (አለሂሰላቱ ወሰላም) 'ወደ ዘረኝነት መጠጋት፣ እኔ የገሌ ዘር ነኝ ብሎ በቀለም፣ በሀብት ወይ በሌላ ማድላት፣ መኩራራት ይሄ የሚሸት ነገር [ክርፋት] ነው' ነው ብለው ነው ያስተማሩት። አሁንም ዘረኝነት ሕዝባችን ቆሻሻነቱን አውቆ እንዲጠነቀቅ ከማስተማር በስተቀር ሌላ ምንም መፍትሄ የለውም። ይለቃል የሚል አመለካት ነው ያለኝ። መልቅቁ ግን ጊዜ ሊወስድ ይችላል። አንድ በሽታ በአካል ከተሰራጨ መድኃኒቱ ጊዜ ይፈልጋል እኮ፤ ጊዝያዊ በሽታ የሆነ እንደሆነ በአንድ መርፌ በኪኒኒ ይመለሳል። ውሎ ያደረ በሽታ ሕክምና ያስፈልገዋል። [የዘረኝነት] በሽታው ትንሽ ዓመታት ወስዶ ስለነበረ አሁንም ደግሞ ለማስለቀቅ ጥንካሬና ጊዜ ይጠይቃል። አመሰግናለሁ ሐጂ! በአገር ጉዳይና በኔ ጉዳይ አስበህ ለመጠየቅህ በጣም አመሰግናለሁ ልጄ፤ ለአገራችንም ሰላም እመኛለሁ፤ ወሰላሙ አለይኩም።
news-55349967
https://www.bbc.com/amharic/news-55349967
ትግራይ ፡ ግጭት ሸሽተው ለስደት የተዳረጉ የሁለት ሐኪሞች ምሥክርነት
ሁለት ኢትዮጵያዊያን ሐኪሞች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ያዩትን አሰቃቂ ሁኔታ ለቢቢሲ አጋርተዋል።
ሐኪሞቹ ሱዳን ውስጥ በሚገኙ የስደተኛ ካምፖች ይሰራሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ ተፈራ ሑመራን ጥሎ የሸሸ ሐኪም ነው። በኋላ ደግሞ አደባይ የምትባለዋን ከተማ ጥሎ ወደ ሱዳን ሄደ። ለቢቢሲ እንደተናገረው ሁለቱም ቦታዎች ለሕይወቱ አደገኛ ነበሩ። ሁለተኛው ሐኪም ስሙን ለመናገር አይሻም። ለአንዲት ሕይወቷ አደገኛ ሁኔታ ላይ ለነበረች ሴት በሞተር ሳይክል ላይ ሆኖ ሕክምና እንዳደረገላት ይናገራል፤ ነገር ግን አሁን በህይወት ትኑር አያውቅም። ሁለቱም ሐኪሞች ዘግናኝ የሚባሉ የንጹሐንን ሞት እንደተመለከቱ ለቢቢሲ ተርከዋል። መነሻ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እግረኛና አየር ኃይሉ በህወሓት ላይ ዘመቻ እንዲያካሂድ ትዕዛዝ የሰጡት የክልሉ ልዩ ኃይል በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ነበር። ሠራዊቱ ኅዳር 19/2013 ዓ.ም መቀለን ሲቆጣጠር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ሠራዊት በንጹሐን ላይ አንድም ጉዳት አላደረሰም ብለው ነበር። በተመሳሳይ፣ ምንም እንኳ ህወሓት ወደ ኤርትራ ሚሳይሎችን የተኮሰ ቢሆንም የኤርትራ መንግሥት በዚህ ጦርነት እጁን እንዳላስገባ አስተባብሏል። ገለልተኛ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት በአካባቢው የግንኙነት መስመሮች ሙሉ በሙሉ ባለመጀመራቸው አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። 30ሺህ ነዋሪዎች ያሏት የሑመራ ከተማ በዚህ ጦርነት ጉዳት ከደረሰባቸወ ቀዳሚ ከተሞች አንዷ ናት። ግጭቱ የተጀመረውም ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ነበር። የሁለቱን ሐኪሞች ምሥክርነት እንደሚከተለው ይቀርባል። ማሳሰቢያ፡ ይህ ጽሑፍ የጦርነት ጉዳቶችን የሚገልጹና የሚያውኩ አንቀጾችን መያዙን ከወዲሁ እናሳስባለን። የዶ/ር ቴዎድሮስ ምሥክርነት የከባድ ጦር መሣሪያ ድብደባዎች ነበሩ። ድብደባዎቹ በሑመራ ከተማ ሁሉንም ቦታዎች ኢላማ ያደረጉ ነበሩ። የገበያ ሥፍራዎችን፣ የቤተ ክርስቲያን አካባቢን፣ የመስጊዶች አካባቢን፣ ብሎም የሆስፒታል ግቢ ላይ ድብደባ ነበር። በመጀመሪያው ቀን ወደ 15 ሬሳ መቀበላችንን አስታውሳለሁ። እንዲሁም 75 ቁስለኞችንም ተቀብለን ነበር። ከሰዓት በኋላም ድብደባው አላቋረጠም ነበር። ወደ ሑመራ ከተማ ድብደባው ይመጣ የነበረው ከምሥራቅ አቅጣጫ ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በምሥራቅ አቅጣጫ ነበረ። ከሰሜን አቅጣጫ ደግሞ ከሑመራ በቅርብ ርቀት ላይ ከሚገኘው ከኤርትራ በኩልም ይተኮስ ነበረ። ድብደባው ከኤርትራ በኩልም ይመጣ እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም። በሁለተኛው ቀን፣ ድብዳው በጠዋት ነበር የተጀመረው። ልክ 5፡00 ሰዓት አካባቢ ግን ረገብ ማለት ጀመረ። ያን ቀን 8 አስከሬኖች ተቀብለናል። በርካታ የቆሰሉ ሰዎችንም ተቀብለናል። ከዚህ በኋላ ግን ነገሩ ለእኛም ሆነ ለበሽተኞቻችን ደኅንነት አስጊ እንደሆነ ተረዳን። ስለዚህ ከዚያ ቦታ ለመልቀቅ ወሰንን። የቆሰሉ በሽተኞቻችንን ተሳቢ መኪና ላይ ጫንናቸው። ከዚያም ወደ አደባይ ከተማ ሄድን። አደባይ ከሑመራ 30 ኪሎ ሜትር ብትርቅ ነው። እዚያ ድብደባ አልነበረም። ነገር ግን ጦርነቱ ቀጥሎ ነበር። በአደባይ ክሊኒክ ውስጥ በሽተኞቻችንን ማከሙን ቀጠልን። በርካታ ንጽሐን ከሑመራ እየመጡ ነበር። በመጀሪያው ቀን የምናክማቸው ሰዎች ከድብደባው ጉዳት የደረሰባቸወ ነበሩ። የመንግሥት ወታደሮች ሑመራ ከተማ ከገቡ ወዲህ ግን ወደእኛ እየመጡ የነበሩ ሰዎች የድብደባ ምልክት እና በስለት ጉዳት የደረሰባቸው ነበሩ። እንደነገሩን ከሆነ ደረት ላይ ባጅ ያለበት ዩኒፎርም የለበሱ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት እና ፋኖ የሚባሉ ዩኒፎርም የማይለብሱ የሚሊሻ አባላት ሑመራ ደርሰው ነበር። በምዕራብ ትግራይ የተለያዩ ቦታዎች የሚከተሉት ሁኔታዎች ተከስተዋል፡- አደባይ ሆነን ቁስለኞችን የማከሙን ነገር ለሁለት ቀናት ቀጠልንበት። ከዚያም ውጊያው በጣም እየተባባሰ መጣ። ወደ ክሊኒኩም እየቀረበ ነበር። አሁን ደግሞ በሽተኞቻችንን ጦርነቱ ብዙም ወዳዳልተፋፋበት ወደ ሌላ የትግራይ ክፍል በጭነት መኪና መውሰድ አለብን አልን። ወደዚያም በእግር ተጓዝን። ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘው ሁመራ እዚያው ጫካ ውስጥ ለሁለት ቀናት ተደበቅን። በሦስተኛው ቀን ሁኔታው ለደኅንነታችን አስፈሪ እየሆነ መጣ። ምክንያቱም ግድያው ትርምሱ በአደባይ ከተማ እየተፋፋመ መሄዱ ነበር። ከአደባይ አቅጣጫ ድብልቅልቅ ያለ የተኩስ ድምጽ ይሰማን ነበር። ከዚህ በኋላ ነበር በእግር ወደ ሱዳን የድንበር ከተማ ሐምዲያት የተሻገርነው። ሐምዲያት እኛ ከነበርነበት 50 ኪሎ ሜትር ቢርቅ ነው። ሚሊሻዎች ግን በጫካው ውስጥ እየተሸሎኮለኩ በተከዜ በኩል ይከተሉን ነበር። አሁን ያለሁት በስደተኞች መጠለያ ውስጥ ነው። አሁንም እዚህ በሽተኞችን እየረዳሁ እገኛለሁ። ከብዙ የትግራይ አካባቢዎች በሽተኞች መምጣታቸውን አላቆመም። ከድንበር 300 ኪሎ ሜትር ከራቁ አካባቢዎች ጭምር የሚመጡ በሽተኞች አሉ። (ወደ ካምፑ የመጡ በሽተኞች) የሰዎችን ሬሳን በየመንገዱ እየተመለከቱ እንደመጡ ይነግሩናል። የኤትርራ ሠራዊት ቤቶችን እንዳቃጠለ፣ ሰብል እንዳወደመና ብዙ ሰብአዊ ጥፋቶችን እንዳደረሰ የሚነግሩኝ በሽተኞችም አሉ። ይህ ሁሉ የሆነው በጨለማ ነው፤ ኢንተርኔት በሌለበት፣ ኤሌክትሪክ በሌለበት ባንክ በተዘገባት ሁኔታ። ትግራይ ውስጥ ምን እየሆነ እንደሆነ በትክክል የሚያውቅ ማንም የለም። የተናገርኩት ካየሁትና ከሰማሁት ነው። እውነት ነው የምመሰክረው። በቀጣይ ገለልተኛ ቡድን ተልኮ ሁሉንም ነገር ያጣራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ስሙን መግለጽ የማይሻው ሐኪም ምሥክርነት: ሑመራ ላይ የመሣሪያ ድብደባው ከመጀመሩ ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ከፌዴራልና ከክልል ኃይሎች የተጎዱ ወታደሮችና ነዋሪዎችን እየተቀበልን እናክም ነበር። ጉዳቶቹ በአብዛኛው ከተኩስና ከከባድ መሣሪያ ጋር የተያያዙ ነበሩ። ነገር ግን ቁጥራቸው ብዙም አልነበረም። ይህ ሁኔታ መቆየት የቻለው ግን የኤርትራና የኢትዮጵያ ሠራዊት ጥቃት እስኪከፍት ብቻ ነበር። ሆስፒታላችን ፊት ለፊት በነበረ ቦታ ራሱ ፍንዳታ ነበር። ከዚህ በኋላ የሚመጡት በሽተኞቻችን ንጹሐን ነበሩ። በዚያ ቀን ብቻ እኔ በነበርኩበት የሆስፒታሉ ክፍል 200 ሰዎችን ተቀብለናል። ወደ 50 የሚሆኑት ደግሞ ሆስፒታል ሲደርሱ ሙት ነበሩ። ወጣቶች የቆሰሉ ሰዎችን በባጃጅ እየጨኑ ወደኛ ያመጧቸው ነበር። የሆስፒታል አልጋ እጥረት ነበር። አንዳንዶቹ በሽተኞችን እናክም የነበረው በሆስፒታል ወለል ላይ ሆነው ነበር። ሌሎችን ደግሞ ደጅ ላይ ጭምር። ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት በተለያዩ ህመሞች ሆስፒታል የነበሩ 200 በሽተኞች ነበሩን። ግጭቱ ሲጀመር ግን አብዛኞቹ አልጋቸውን ለቆሰሉ በሽተኞች መልቀቅ ነበረባቸው፤ የራሳቸውን ህምም ትተው ቁስለኞቹን ይንከባከቧቸውም ነበር። ነገር ግን እንደ ሐኪም ብዙ ሕይወት ማዳን አልተቻለምን። ምክንያቱም በደም ባንክ ውስጥ በቂ የደም ክምቸት አልነበረንም። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥርም ከአቅም በላይ ነበር። ስለዚህ ማድረግ የቻልነው የተወሰነ የመጀመርያ ደረጃ እርዳታ መስጠት ብቻ ነበር። ብዙ በሽተኞች አይናችን እያየ (መዳን እየቻሉ) እጃችን ላይ ይሞቱ ነበር። ያን ቀን ብቻ እስከ ምሽት 4፡00 ሰዓት ስንሠራ አመሸን። የነበርንበት ቦታ ለደኅንነት አስጊ እየሆነ ስለመጣ አንዳንድ የሆስፒታል ባልደረቦቻችን ወደ አደባይ መሄድ ጀመሩ። ሌሎች ግን እዚያው ለመቆት ወሰኑ። ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሐምዳይት ሱዳን ውስጥ እኔም ወደ አደባይ ሄድኩኝ። የተወሰኑ በሽተኞችን ከእኛ ጋር ይዘን ለመሄድ መኪና አዘጋጀን። ስድስት በሽተኞች ከኢትዮጵያ ሠራዊት አብረውን ነበሩ። አደባይ እንደደረስን በክሊኒኩ ውስጥ በጠዋት ሥራ ጀመርን። 10 የሚሆኑ በሽተኞች ከሑመራ የመጡ ነበሩ። ሆዷ ላይ የቆሰለች አንዲት እናት ወንድ ልጇ ይዟት መጥቶ ነበር። አንጀቷ ከሆዷ በኩል ተንጠልጥሎ ደም እየፈሰሳትም ነበር። ልጇ ከሑመራ ድረስ በሞተር ሳይክል ተሸክሟት መምጣቱ ጥንካሬው ይገርማል። አሁን በሕይወት ትኑር አትኑር አላውቅም። ሆኖም የመጀመርያ እርዳታ አድርጌላት ነበር። በዚህ ሁኔታ ለሦስት ቀናት ያህል በሽተኞቹን ለመርዳት ሞከርን። ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት መጥተው እያከምናቸው የነበሩ ወታደሮችን ይዘዋቸው ሄዱ። በአደባይ በንጽሐን ላይ ሲተኮስ ነበር። እኛም ከአደባይ ቅርብ በነበረበ ቦታ ሄደን መደበቅ ነበረብን። ማታ ማታ ግን ተመልሰን ወደ ክሊኒኩ እየሄድን በሽተኞችን እናክም ነበር። በአምስተኛው ቀን፣ ከዚህ በኋላ ለሕይወታችን አስጊ ነው ብለን ወደ ሱዳን ሄድን። ከሑመራ ይዘናቸው የመጣናቸውን አንቲባዮቲክና ሌሎች መድኃኒቶችን በክሊኒኳ ውስጥ ለነበሩ ባልደቦች ትተንላቸው ወጣን። 'እጁ የተቆረጠው ወጣት' ብዙ ሰዎች ለአራት ቀናት ያህል ሱዳን ለመግባት ተጉዘዋል። እኔ ግን ዕድለኛ ነኝ። ሞተር ያለው ልጅ አውቅ ስለነበር እኔና ባለቤቴን በሞተር ድንበር ድረስ ወሰደን። በአንድ ቀን ከግማሽ ሐምዳይት ገባን። ስንደርስ አንድ ወጣት አየሁ። ጭንቅላቱ ላይ ከመቁሰሉም በላይ እጁ ተቆርጧል። ከማይካድራ እንደመጣ ነገረኝ። ለአምስት ቀናት መድኃኒት ሰጠሁት። እዚህ በጣም ብዙ ሰዎችን አገኘሁ። ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ናቸው። በማይካድራ በነበረው ጥቃት ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ቢሆንም በእጄ ላይ የማክምበት መሳሪያ ስላልነበረኝ የሕክምና እርዳታ ልሰጣቸው አልቻልኩም። [መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በማይካድራ ከ600 በላይ የአማራ ተወላጆች በህወሓት ሚሊሻዎች መገደላቸውን መግለጹ ይታወቃል።] አሁን ወደ ኡም ራኮባ የስደተኞች ካምፕ ገብቻለሁ። ከሀምዳይት የ8 ሰዓት የመኪና ጉዞ ይርቃል። እዚህ በብዛት የሱዳን ህመምተኞች ናቸው የሚመጡት። ብዙዎቹ የደረት ኢንፌክሽንና ተቅማጥ ነው ያለባቸው። እንደምንረዳቸው እንነግራቸዋለን። ሆኖም አገር ቤትን ሳስብ ያመኛል። ኦክሲጅን አጥተው የሚሞቱትን ወገኖቼን ሳስብ፣ በጥይት ተመተው የቆሰሉ ዜጎችን ሳስብ ያመኛል። እንዲሞቱ የተፈረደባቸው ናቸው። ደግሞም ጥፋተኝነት ይሰማኛል። እነሱን ሳስብ ድብታ ውስጥ እገባለሁ፤ የአእምሮ ሰላሜን አጣለሁ።
48518761
https://www.bbc.com/amharic/48518761
የአክሱም ሙስሊሞች ጥያቄ መቼ ምላሽ ያገኝ ይሆን?
የታሪክ ተመራማሪዎች አክሱም ከ3 ሺህ ዓመት በላይ ያስቆጠረች ጥንታዊ ከተማ ነች ሲሉ፤ የሃይማኖት አባቶች ደግሞ አክሱም ከ6 ሺህ ዓመት በላይ ያስቆጠረች ከተማ ናት ይላሉ።
ከአክሱም 15 ኪሎሜትር ርቀት ርቃ በምትገኘው ውቅሮማራይ ሙስሊሞች ጸሎት ሲያደርሱ በዓለማችን ከታዩት ጥንታዊ እና ትልልቅ ስልጣኔዎች መካከል የአክሱም ስልጣኔ አንዱ ነው። የሙሴ ጽላት እንደሚገኝባት የሚታመነው አክሱም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራ ይሰጣታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በከተማዋ የእስልምና እምነት ተከታዮች ያላቸው የሃይማኖት ነጻነት ጉዳይ እያወዛገበ መልስ ሳያገኝ እስካሁን ድረስ ቆይቷል። • በረመዳን ፆም ምግብ የበሉ 80 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ አቶ አዚዝ መሐመድ ሳልህ (ስማቸው የተቀየረ) ተወልደው ያደጉት በአክሱም ከተማ ሲሆን በከተማዋ ቢያንስ ከ26 ዓመታት በላይ ኖረዋል። የአቶ አዚዝ አባት 12 ልጆችን ወልደው ሙሉ ዕድሜያቸውን ያሳለፉትም በአክሱም ከተማ ነው። ''አክሱም ውስጥ ሙስሊም እና ክርስትያን በሃዘን ይሁን በደስታ ተለያይተን አናውቅም'' የሚሉት አቶ አዚዝ፤ የሚቆረቁራቸው ነገር እንዳለ ግን አልሸሸጉም። ''አትስገዱ ብሎ የከለከለን ሰው የለም፤ በየቤታችን መስገድ እንችላለን። አርብ ሲሆን ግን መንገድ ላይ ያውም ፀሐይ ላይ ነው የምንሰግደው። ክርስትያን ወንድሞቻችን 'ትንሽ ቦታ ሰጥተናቸው ለምን ጥላ ስር አይሰግዱም?' ብለው አለማሰባቸው ቅር ያሰኛል'' በማለት ቅሬታቸው ይገልጻሉ። • ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች • በአክሱም ዩኒቨርስቲ ግጭት የተጠረጠሩ ተያዙ በተጨማሪ ''የእስልምና መሪዎቻችን 'ተናግረናል፤ አመለክተናል' ይሉናል እስካሁን ግን ያየነው ነገር ግን የለም'' ይላሉ። ሌላኛው የአክሱም ከተማ ነዋሪ እና የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑት አቶ አብዱ መሐመድ ዓሊ (ስማቸው የተቀየረ) ለቢቢሲ ሃሳባቸውን አካፍለዋል። ሃሳብ ከመስጠታቸው በፊት ጋዜጠኞች መሆናችንን የሚያሳይ መረጃ ጠይቀውን ካረጋገጡ በኋላ የሚከታተለን ሰው አለመኖሩን ለማጣራት ግራና ቀኝ አማተሩ። አቶ አብዱ ተወልደው ያደጉት አክሱም ከተማ ማይሹም በሚባል አካባቢ ነው። አቶ አብዱ በአክሱም ከተማ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሆኑ ሰዎች ቁጥር መጨመርን ተከትሎ መስገጃ ቦታ አስፈልጓቸው እንደነበረ ያስታውሳሉ። በኩረ ሊቃውንት ጎደፋ መርሃ፣ በትረ ትጉሃን አምሳሉ ስቡህ እና ሊቀ ካህናት ተክለሃይማኖት በንጉሡ ዘመን የእስልምና እምነት ተከታይ ባልሆኑ ሰዎች መኖሪያ ቤት ጭምር ከአንድ ብር ከሃምሳ ሳንቲም እስከ ሦስት ብር እየከፈሉ ይሰግዱ እንደነበረ ያስረዳሉ። የእምነቱ ተከታዮች ቁጥር ሲበራከት ግን ከንጉሡ ዘመን ጀምረው መስጊድ መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው መጠየቅ እንደጀመሩ አቶ አብዱ ያስታውሳሉ። ''አክሱም ገዳም ነው፤ መስጊድ እንድትሰሩ አንፈቅድላችሁም'' የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ያስታውሳሉ። ቆይቶም አክሱም ውስጥ ማይ ዓኾ በሚባል ስፍራ መስጅድ መስሪያ ቦታ ከተሰጣቸው በኋላ በጭቃና እንጨት መስራት ሲጀምሩ፤ ሰዎች እንዳቃጠሉባቸው ይናገራሉ። ''መስጅድ ብቻ አይደለም፤ መኖሪያ ቤትም አልነበረንም። ደርግ ወደ ስልጣን ሲመጣ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እኩል ናቸው ብሎ መሬት ሰጠን። ነገርግን 'አክሱም ገዳም ስለሆነ መስጅድ ልትሰሩበት አይፈቀድም' ሲሉን እንሰማለን። ማን ነው እንደዚህ ያለው? ከየት የመጣ ህግ ነው?'' ለሚለው ጥያቄ ግን መልስ የለም ይላሉ። • የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ • የቱሉ ፈራ ደጋግ ኢትዮጵያዊ ልቦች "እየኖርን ያለነው ከወንድሞቻችን ጋር ነው" የሚሉት አቶ አብዱ ቀደም ሲል 'ሰማይ አምድ የለው፤ እስላም ሃገር የለው' ይባል የነበረው ኋላ ቀር አባባል በደርግ ጊዜ መቅረቱን ነገር ግን ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣም ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንደቀጠሉ ይገልጻሉ። በተጨማሪ ''ወደ አክሱም የሚመጣ ማንኛውም አስተዳዳሪ መስጅድ መስሪያ ቦታ እንዳትሰጥ ተብሎ ውስጥ ለውስጥ ይነገረዋል'' ይላሉ አቶ አብዱ አህመድ። ''የአክሱም ከተማ አስተዳደር 'መስጅድ መፍቀድ የእኛ ስልጣን አይደለም' ሲሉን የ3500 ሰዎች ፊርማ በማሰባሰብ ወደ ትግራይ ክልል አስተዳደር በመሄድ ቅሬታ አቅርበን፤ 'መልስ እንሰጣችኋለን፤ ታገሱ' አሉን። እስካሁን የተሰጠን ምላሽ ግን የለም።'' ሲሉ ያክላሉ። ''አርብ ሲሆን በተከራየነው እና መስጅድ ብለን በምናምነው ቦታ ተሰባስበን እንሰግዳለን። ድምጽ ማጉያ ከተጠቀምን ግን 'ለምን ጮክ አላችሁ? ማርያምን ደፈራችኋት?ድምጽ ቀንሱ፤ ያልነበራችሁን ጠባይ አታምጡ' ይሉናል። ይህ ደግሞ በነጻነት እንዳንሰግድ ጫና ይፈጥርብናል። የምንጸልይበት እና የምንቀበርበት መሬት የፈጣሪ ስጦታ ነው'' ሲሉ ያማርራሉ። አክሱም ውስጥ የሚገኘው የእስልምና ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኪራይ ለ12 ዓመታት እንደከፈለላቸው አቶ አብዱ ገልጸው፤ በ2010 ጥቅምት ወር ግን 'ከአሁን በኋላ አንከፍልላችሁም' ተብለናልም ይላሉ። ''ጽህፈት ቤቱ ገቢ ስለሌለው ክፈሉልን ብለን ቅሬታ አቅርበን እምቢ ብለውናል" በማለት እስካሁን እንዳልተግባቡ ይናገራሉ። • ዴንማርክ ሙሉ የፊት ገጽታን የሚሸፍን 'ሂጃብ' አገደች ከእምነት ስፍራ ጥያቄው ባሻገር ደግሞ የሙስሊሞች መቃብር እንዲታጠር ጠይቀው እንዳልተፈጸመ፣ ሙስሊሞች እርድ የሚፈጽምበት ቦታ ቢሰጣቸውም ሥጋ የሚከፋፈሉበት ቦታ ግን እንዳላገኙ ይጠቅሳሉ። በአክሱም የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች የሚፈጽሙበት ቦታ ሲጠይቁ ዘመናት ተቆጥረዋል። የደርግ ሥርዓት በወደቀበት የመጀመሪያ ዓመታት አክሱም ውስጥ በሃይማኖት ሰበብ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱም ይታወሳል። የአክሱም ፅዮን ማሪያም ቤተክርስቲያን ''አክሱም ከአንድ ቤተክርስትያን በላይ መሸከም አትችልም'' የአክሱም ገደማትና አድባራት ምክትል አስተዳደር በኩረ ሊቃውንት ጎደፋ መርሃ አክሱም ውስጥ የተለያየ እምነት ያላቸው ሰዎች በሰላም መኖር እንደሚችሉ ይናገራሉ። "ነገር ግን አንዲት ቤተ-ክርስትያን ነች ያለችው፤ ከዚያ ውጭ ሌላ ከተጨመረ ግን የነበረውን ታሪክ ማበላሸት ነው" የሚል የጸና እምነት አላቸው። "አንዲት ቤተ-ክርስቲያን ግን የተለያዩ እምነቶች በሰላም እና መቻቻል የሚኖሩባት ከተማ ነች" ይላሉ አክሱምን። ''አዲስ መንግሥት በመጣ ቁጥር 'መስጅድ ይሰራልን' እያሉ የሚጠይቁ ሰዎች አሉ" የሚሉት ምክትል አስተዳደሪው፤ ይህንን ጥያቄ የሚያቀርቡት ደግሞ ከሌላ ቦታ የመጡ ሙስሊሞች ናቸው ይላሉ። ምሳሌም ሲጠቅሱ "የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ከተከፈተ ጀምሮ ጥያቄዎች በማንሳት አክሱም ውስጥ ተወልደው ባደጉት ላይ ተጽኖ እየተፈጠረ ነው። አክሱም ተወልደው ያደጉት ግን ምን የጎደለብን ነገር የለም ነው የሚሉት።" ይላሉ። "አንድ ሙስሊም ሲሞት፤ ቄስ፣ ዲያቆን እና ምዕመናን ሄደው ይቀብራሉ፣ ያስተዛዝናሉ፣ ያጽናናሉ። በሰርግ ጊዜም እንደዚሁ። የሚካኤል፣ የማርያም ጸበል ሲኖርም ይመጣሉ። አብረን ነው የምንኖረው። እኔ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነኝ። የልብ ጓደኛዬ ሙስሊም ነው። ልዩነት የለንም'' በማለትም ይናገራሉ። • የሞት ፍርደ ውድቅ የተደረገላት አሲያ ቢቢ ካናዳ ገባች • ቴምር በረመዳን ለምን ይዘወተራል? ከዚህ አንጻር አቶ አብዱ መሃመድ ከውጭ የሚገፋፋቸው ኃይል አለ በሚለው ሃሳብ አይስማሙም። ከአሁን በፊትም እስላማዊ ትምህርት ቤት ለመስራት ተፈቅዶላቸው መንግሥት መሬት ሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም እስካሁን ተግባራዊ እንዳልተደረገ ያስታውሳሉ። በአክሱም የሚኖሩት ሙስሊሞችና ክርስትያኖች ጥብቅ ትስስር እንዳላቸው የሚናገሩት በኩረ ሊቃውንት ጎደፋ ''መስጂድ የሚጠይቀው ሰው አሜሪካ ያለው ነው። ድሬዳዋ እና ጂማ ሆነው 'ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች' እያሉ ሰው የሚያነሳሱ ምን አገባቸው? እኛ ተከባብረን ነው የምንኖረው'' ሲሉ ይጠይቃሉ። ጨምረውም አክሱም ውስጥ አስራ ሦስት የሙስሊሞች መስገጃ ቦታዎች እንዳሉና "'መስጅድ የለም' የሚሉት አዲስ አበባ ያሉት ናቸው። 'ምልክት ይደረግበት' ይላሉ። ምልክት ከፈለጉ ከአክሱም 15 ኪሎ ሜትር ውቅሮ ማራይ ወይም አድዋ ሄደው መጠቀም ይችላሉ።'' አክሱም ውስጥ አይታሰብም በኩረ ሊቃውንት ጎደፋ መርሃ አክሱም ውስጥ መስጂድ መሰራት የለበትም ብለው ከሚያምኑ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው "አክሱም ውስጥ መስጅድ እንዲሰራ ባለመፈቀዱ ሙስሊሞች ይከፉ ይሆናል። እኛ ኦርቶዶክሶች ደግሞ ለምሳሌ መስጅድ ይሰራ የሚል ትእዛዝ ቢመጣ እንሞታለን" በማለት እንደማይቀበሉት ይናገራሉ። ለዚህ እንደ ዋና ምክንያት የሚያስቀምጡት ወላጆቻቸው ለዘመናት ያቆዩት ታሪክ እንዲለወጥ አለመፈለጋቸው መሆኑን ጠቅሰው "ወላጆቻችን በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ከዚች አንድ ስንዝርም እንዳትቀንሱ እንዳትጨምሩ ብለውን ቃል አስገብተውን ነው ያለፉት" በማለት በከተማዋ መስጅድ መገንባት እንደሌለበት ይሞግታሉ። ከሚቀርበው ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ክርክር ባሻገር የከተማዋ ሙስሊም ነዋሪዎች ጥያቄ ከሰብዓዊ መብት አንጻርም መታየት አለበት የሚሉ ሰዎች በርካቶች ናቸው። የአክሱም ገደማትና አድባራት ምክትል አስተዳደሪው ግን ይህን "መብት የሁለቱም ወገን ጥያቄን የሚያቅፍ መሆን አለበት" ብለው ይቃወማሉ። "ለብዙ ዘመናት ቅድመ አያቶቻቸው ያልነበራቸውን ነገር እንዴት አሁን ይጠይቃሉ። ወላጆቻቸው ያቆዩላቸው ነገር ብንከለክላቸው ኖሮ አሁን ጥያቄ ማንሳት ይቻል ነበር። መስጅድ ላይ ምልክት ይደርግበት ማለት ግን ያልነበረ ነገር ነው፤ ታሪክ ማበላሸትም ነው" ሲሉ ይከራከራሉ። • ወደ ለንደን የሚሄደው አስደናቂው የትራምፕ ጓዝ ሙስሊም እናቶች በውቅሮማራይ መስጂድ ውስጥ አክሱም ክርስትያናዊት ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት መሪዎች በአክሱም ከተማ በያሬዳዊ ቃና የታጀበ ቃለ እግዚአብሔር ብቻ ነው መሰማት ያለበት የሚል ጠንካራ ኣቋም አላቸው። የተቀደሰ ስፍራ ነው ብለውም ያምናሉ። የአክሱም ገደማትና አድባራት ምክትል አስተዳደሪ የሆኑት በኩረ ሊቃውንት ጎደፋ መርሃ "ሙስሊሞች መካን አክብረው እንደሚይዙዋት ሁሉ፤ አክሱምም ለእኛ መካ ማለት ነች። አክሱም ውስጥ ሌላ ድምጽ መሰማት የለበትም። አላህ ወአክበር የሚል ድምጽ ከተሰማ፡ አክሱም ገዳም መሆኗ አበቃ ማለት ነው" ይላሉ። የአክሱም ፅዮን ማርያም አገልጋይ የሆኑት በትረ ትጉሃን አምሳሉ ስቡህ በበኩላቸው "ጽላተ ሙሴ ባለበት ስፍራ ሌሎች እምነቶች ሊኖሩ አይገባም። ይሄ እምነት እንጂ ጭካኔ አይደለም። በጉልበት እንዲሰራ ከተፈለገ ግን ጦርነት ማወጅ ማለት ነው" በማለት ጉዳዩ አላስፈላጊ መዘዝ እንዳያስከትል ያሳስባሉ። ከአክሱም በ15 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ውቅሮማራይ የምትባል አነስተኛ ከተማ ትገኛለች። በአንድ መስጊድ በርከት ያሉ እስልምና አማኞች ተሰብስበው እየሰገዱ ነው። ሴቶች ደግሞ የሚበላና የሚጠጣ እያቀረቡ ነበር። ከመካከላቸውም እድሜያቸው ከ50 እንደሚያልፍ የሚናገሩት እናት "በከተማችን አምስት መስጊዶች አሉ። አክሱም የማርያም ጽዮን መቀመጫ ነች ብለው ስለሚያምኑ በአክሱም ከተማ ግን ከጥንትም መስጊድ ኖሮ አያውቅም። በመመካከርና በሰላም መስጂድ ቢሰራ ጥሩ ነው፤ ከዚያ ውጪ ግን እኛ ከወላጆቻችን አንበልጥም። ሰላም ነው የምንፈልገው" ይላሉ። ከአክሱም 15 ኪሎሜትር ርቀት ርቆ ውቅሮማራይ ከተማ የሚገኘው መስጂድ ተግባብተን መስራት እንፈልጋለን በአጸደ እንዳ'ሚካኤል ቤተክርስትያን የሚያገለግሉት ሊቀ ካህናት ተክለሃይማኖት በአክሱም ከተማ ውስጥ መስጂድ እንዲሰራ የመፍቀድም ሆነ የመከልከሉ ነገር በመንግሥት የሚወሰን ጉዳይ እንዳልሆነ ይናገራሉ። እንደ እርሳቸው እምነት ይህ የሆነው "መንግሥት መስጊድ ይሰራ ብሎ ቢፈቅድ በነገታው የሚከተለውን አደጋ ስለተረዳ እንጂ ክርስትያንን ወዶ ሙስሊሙን ስለጠላ አይደለም" በማለት ጉዳዩን ከአክሱም ህዝብ ባሻገር የትግራይ ህዝብ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብን የሚመለከት ነው እንደሆነ ይጠቅሳሉ። መካ ለሙስሊሞች ቅዱስ ቦታ እንደሆነው ሁሉ አክሱምም ለኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ቅዱስ ቦታ ነው የሚሉት ሊቀ ካህኑ "በመካ ቤተ ክርስትያን ቢሰራም ባይሰራም በእኛ ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም። እኛ ግን አንፈቅድም" ሲሉ ፈርጠም ብለው ይናገራሉ። በአክሱም ከተማ ጋር ተያይዞ ስለሚነሳው የእስልምና እምነት ተከታዮች መስጂድ እንዲኖራቸው የመፈለግ ጥያቄን በተመለከተ የከተማ አስተዳደር የሚሰጠው ምላሽ ካለ ለቀረበላቸው ጥያቄ አስተያየት ለመስጠት ፈቃኛ ሳይሆን ቀርቷል። የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ዋና ጸሐፊ አቶ መሐመድ ካሕሳይ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ በኩል መስጂድ እንዲኖር ፍላጎቱ እንዳለ ጠቅሰው "ሕዝበ ሙስሊሙና ክርስትያኑ አምኖበት ነው ይህ ነገር እውን እንዲሆን የምንፈልገው። ተግባብተን ነው መስጂድ መስራት የምናስበው" ብለዋል።
news-56398438
https://www.bbc.com/amharic/news-56398438
ሶሪያ፡ ሩሲያ፣ ኢራን፣ ቱርክ፣ አሜሪካና ሌሎችም የተሳተፉበት የሶሪያ ጦርነት 10 ዓመታት ሆነው
በሶሪያ ፕሬዝዳንት ላይ ከ10 ዓመት በፊት የተጀመረው ሕዝባዊ አመጽ አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ መጠነ ሰፊ የእርስ በእርስ ጦርነት ተቀይሮ ከ380 ሺህ በላይ ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል። ከተሞችን ሲያወድም ቀውሱ ሌሎች አገራትን ስቧል። የሶሪያ ጦርነት እንዴት ተጀመረ?
በከባድ መሳሪያ ሁለት ልጆቹ የተገደሉበት አባት የሶሪያው ፕሬዝዳንት ባሻር አል አሳድ አባታቸውን ሃፌዝ አል አሳድን ተክተው ወደ መንበረ ስልጣን የመጡት በአውሮፓውያኑ 2000 ነበር። ግጭቱ ከመጀመሩ በፊትም ብዙ ሶሪያውያን የነበረውን ከፍተኛ የሥራ አጥነት፣ ሙስናና የፖለቲካ ነፃነት እጦት እያማረሩ ነበር። በጎረቤት አገራት ጨቋኝ ገዥዎችን የሚቃወሙ አመጾች ተቀጣጥለው ነበር። ከዚህ በመነሳሳትም የዛሬ አስር ዓመት በደቡባዊዋ የዴራ ከተማ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ይስፈን የሚሉ ሰልፎች አደባባይ ወጡ። የሶሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ለመጨፍለቅ ኃይል ተጠቅሞ ተቃዋሚዎችን መግደል ሲጀምር ፕሬዚዳንቱ ስልጣናቸውን እንዲለቁ የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች በመላው አገሪቱ ተቀጣጠሉ። አመጹም እርምጃውም ጎን ለጎን ተጠናከረ። የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች ነፍጥ አነሱ፤ መጀመሪያ ራሳቸውን ለመከላከልና በኋላም አካባቢዎቻቸውን ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ነጻ ለማድረግ። ፕሬዝዳንት አል አሳድ "በውጭ የሚደገፉ ሽብርተኞች" ያሏቸውን እንደሚጨፈልቁ ቃል ገቡ። አመፁ በፍጥነት ተባብሶ አገሪቱ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ገባች። በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማፅያን ቡድኖች በየቦታው አበቡ። ግጭቱም በአሳድ ደጋፊዎችና ተቃዋሚ ሶርያውያን መካከል ባሻገር ሲሆን ጊዜ አልወሰደበትም። የውጭ ኃይሎች እጃቸውን አስገቡ። ገንዘብ፣ የጦር መሣሪያዎችን እና ተዋጊዎችን በመላክ የሚፈልጉትን ይደግፉ ጀመር። እንደ እስላማዊ መንግሥት (አይ ኤስ) እና አልቃይዳ ያሉትም ጽንፈኛ ቡድኖች የራሳቸውን ዓላማ በመያዝ ተሳታፊ ሆኑ። ይህም እንደ ትልቅ ስጋት ለሚያዩዋቸው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባላት ዘንድ ትልቅ ሥጋት ፈጠረ። ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን የሚፈልጉት የሶሪያ ኩርዶች ከአሳድ ኃይሎች ጋር ባይዋጉም ለግጭቱ ሌላ ገጽታን ሰጡት። ጸረ መንግሥት ተቃውሞው በተጀመረበት ጊዜ ምን ያህል ሰዎች ሞቱ? መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የሶርያ ኦብዘርቫቶሪ ፎር ሂዩማን ራይትስ (ኤስኦኤችአር) ሶሪያ ውስጥ የመረጃ ምንጮች አሉት። ድርጅቱ እስካለፈው ዓመት ድረስ 387,118 ሰዎች መሞታቸውን መዝግቧል። ከእነዚህም መካከል 116,911 ሰላማዊ ሰዎች ናቸው። ይህ ቁጥር ጠፍተዋል ወይም መረጃቸው ያለተገኙትን 205,300 ሰዎችን አላካተተም። እንዲሁም በመንግሥት ቁጥጥር ስር ባሉ እስር ቤቶች ውስጥ በስቃይ ሞተዋል የተባሉ 88,000 ሰዎችንም አልተደመሩም። ከተለያዩ አክቲቪስቶች መረጃ የሚያገኘው ቫዮሌሽን ዶክመንቴሽን ሴንተር ደግሞ በሠላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ጨምሮ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግ ጥሰቶች እና በሰብዓዊ መብቶች ሕግ ጥሰቶችን መዝግቧል። እስካለፈው ዓመት ታኅሣስ ድረስ 135,634 ሠላማዊ ሰዎችን ጨምሮ 226,374 ከጦርነቱ ጋር የተዛመዱ ሰዎችን ሞት መዝግቧል። የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት ድርጅት- ዩኒሴፍ ደግሞ ወደ 12,000 የሚጠጉ ሕፃናት ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል ሲል አስታውቋል። የቆሰለ ህጻን ህክምና ሲደረግለት የጦርነቱ ተሳታፊዎች እነማን ናቸው? የመንግሥት ቁልፍ ደጋፊዎች ሩሲያ እና ኢራን ናቸው። ቱርክ፣ ምዕራባዊያን ኃይሎች እና በርካታ የባሕረ ሰላጤ አረብ አገራት ላለፉት አስርት ዓመታት ተቃዋሚዎችን በተለያየ ደረጃ ደግፈዋል። ሩሲያ ከጦርነቱ በፊትም በሶሪያ ውስጥ ወታደራዊ ካምፕ ነበራት። በ2015 (እአአ) አሳድን በመደገፍ የአየር ጥቃት ዘመቻ ጀምራለች። ይህም የጦርነቱን የበላይነት ወደ መንግሥት ወገን እንዲያጋድል ወሳኝ ነበር። የሩሲያ ጦር ጥቃት የሚያተኩረው "አሸባሪዎች" ላይ ብቻ እንደሆነ ቢገልጽም አክቲቪስቶች ግን በመደበኛነት ዋና ዋና አማፅያን እና ሠላማዊ ሰዎች ይገድላሉ ብለዋል። ኢራንም በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን አሰማርታለች። አሳድን ለመርዳት በሚልም በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንዳወጣች ይታመናል። አብዛኞቹ የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ንቅናቄ አባላት የሆኑበትና በሺህዎች የሚቆጠሩ የሺአ ሙስሊም ታጣቂዎች በኢራን የትጥቅ፣ የስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸዋል። ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን እና የመንንም እንዲሁ ከሶሪያ ጦር ጎን ሆነው ተዋግተዋል። አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በመጀመሪያ "አክራሪ ያልሆኑ" ብለው ለሚያስቧቸው አማጺ ቡድኖች ድጋፍ ይሰጡ ነበር። ጂሃዲስቶች በታጠቁ ተቃዋሚዎች ላይ የበላይ ከሆኑበት ጊዜ አንስቶ ለጦርነት የማይውል እርዳታ ለመስጠት ቅድሚያ ሰጥተዋል። በአሜሪካ የሚመራው ዓለም አቀፍ ጥምረትም እንዲሁ ከ2014 (እአአ) ጀምሮ በሶሪያ ውስጥ የአየር ጥቃት እያደረሰ ነው። ይህም የኩርድ እና የአረብ ሚሊሻዎች ጥምረት የሆነው የሶሪያ ዴሞክራቲክ ፎርስን (ኤስ ዲ ኤፍ) በማገዝ በሰሜን ምሥራቅ በአይ ኤስ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የነበሩ ቦታዎችን ለማስለቀቅ ለማገዝ ነው። ቱርክ ለተቃዋሚዎች ከፍተኛ ድጋፍ ታደርጋለች። ትኩረቷ ግን የአማጺ ቡድኖችን በመጠቀም በአብዛኛው በኤስ ዲ ኤፍ ስር ያሉትን የኩርድ ዋይ ፒ ጂ ሚሊሺያን በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው። ቡድኑንም ቱርክ ውስጥ የታገደው የኩርድ አማጺያን ቡድን ተቀጥላ ነው በሚል ክስ ታቀርባለች። የቱርክ ወታደሮች እና አጋር አማፅያን በሶሪያ ሰሜናዊ ድንበር ዙሪያ ሰፋፊ ቦታዎችን በመያዝ የመንግሥት ኃይሎች የመጨረሻዋን የተቃዋሚዎች ይዞታ ኢድሊብን እንዳያጠቁ ጣልቃ ገብተዋል። የኢራን ተጽዕኖን ለመከላከል ከፍተኛ ፍላጎት ያደረባት ሳዑዲ አረቢያ ጦርነቱ ሲጀመር አማጺያኑን አስታጥቃ በገንዘብ ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች። ይህም የባሕረ ሰላጤው ተቀናቃኟ ኳታርም እንዳደረገችው መሆኑ ነው። እስራኤል በበኩሏ ኢራን በሶሪያ ውስጥ ያላት "ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት" በጣም እንደሚያሳስባት ትገልጻለች። ኢራን የጦር መሣሪያዎችን ወደ ሄዝቦላህ እና ወደ ሌሎች የሺአ ሚሊሺያዎች መላክ በጣም ስላስጨነቃት እነሱን ለማደናቀፍ በማሰብ በተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶችን ሰንዝራለች። በቱርክ የሚደገፉ የሶሪያ አማጺያን ሕዝቡ ላይ የደረሰው ጉዳት ምን ያህል ነው? እንደ ኤስ ኦ ኤች አር ከሆነ ግጭቱ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት ከመሆን አልፎ ከ2.1 ሚሊዮን በላይ ሠላማዊ ዜጎች አደጋ ወይም ቋሚ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከጦርነቱ በፊት 22 ሚሊዮን እንደሆነ ከሚገመተው የሶሪያ ሕዝብ ቁጥር ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ቤታቸውን ለቀው ተሰደዋል። ወደ 6.7 ሚልዮን የሚሆኑት በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ናቸው። ከእነዚህም አብዛኛዎቹ በመጠለያ ጣብያዎች ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን 5.6 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ በውጭ አገር በስደት ላይ ይገኛሉ። 93 በመቶ የሚሆኑትን የሚያስተናግዱት ሊባኖስ፣ ዮርዳኖስ እና ቱርክ በቅርብ ዓመታት ታሪክ ውስጥ ትልቁን የስደተኞች ቁጥር ለመቋቋም ተቸግረዋል። አንድ ሚሊዮን የሶሪያ ስደተኛ ልጆች በስደት እያሉ ተወልደዋል። እስከዚህ ዓመት ጥር ወር ድረስ በሶርያ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የሰብአዊ ዕርዳታ ፈላጊዎች እንደነበሩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ያመለክታል። ስድስት ሚሊዮን የሚሆኑት በከፍተኛ ደረጃ እርዳታ የሚሹ ናቸው። ከ12 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት በየቀኑ በቂ ምግብ ለማግኘት እየተቸገሩ ነው። ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ሕፃናትም በተመጣጣኝ የምግብ እጥረት ተጎድተዋል። ባለፈው ዓመት የሰብዓዊ ቀውሱ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ተባብሷል። የሶሪያ ምንዛሬ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን የምግብ ዋጋ ታሪካዊ በሚባል ደረጃ እንዲያሻቅብ አስገድዷል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽን ማጋጠሙ ደግሞ የአገሪቱ የምርመራ አቅም ውስን መሆን እና በተደቆሰው የጤና አጠባበቅ ሥርዓት ሲጨመር እግሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል። ከአስር ዓመቱ ጦርነት በኋላ በመላ አገሪቱ ያሉ ሁሉም መሠረተ ልማቶችም ከጥቅም ውጭ መሆናቸው ቀጥለዋል። የተባበሩት መንግሥታት የሳተላይት መረጃ እንደሚያሳየው የአሌፖ ከተማ በ2016 መገባደጃ በድጋሚ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ከመዋሏ በፊት ብቻ ከ35 ሺህ በላይ መሠረተ ልማቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ወይም እንደወደሙ ጠቁሟል። የህክምና ማዕከላት ጥበቃ ቢያስፈልጋቸውም እስካለፈው ዓመት መጋቢት ድረስ በ350 የተለያዩ የህክምና ተቋማት ላይ 595 ጥቃቶች ተሰንዝረው 923 የሕክምና ባለሙያዎች መሞታቸውን ፊዚሽያን ፎር ሂዩማን ራይትስ የተሰኘው ድርጅት መዝግቧል። እንዲህ ያሉት ጥቃቶች የአገሪቱን ግማሽ ሆስፒታሎች ብቻ ሙሉ በሙሉ እንዲሠሩ አስገድዷቸዋል። አብዛኞቹ የሶርያ ባህላዊ ቅርሶችም ወድመዋል። የአይ ኤስ ታጣቂዎች የጥንታዊቷ የፓልሚራ ከተማ ክፍሎችን ሆን ብለው ማፈንዳታቸውን ጨምሮ በዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ የተመዘጉ ስድስቱ የአገሪቱ ቅርሶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የተባበሩት መንግሥታት የጦር ወንጀል መርማሪዎች ሁሉንም ወገኖች "እጅግ በጣም አስከፊ ጥሰቶች" በመፈፀም ይከሳሉ። የተፈናቀሉ የሶሪያ ህጻናት ከመተለያ ካምፓቸው ለቀው ለመውጣት ተዘጋጅተው አሁን አገሪቱን የሚቆጣጠረው ማነው? መንግሥት የሶሪያን ታላላቅ ከተሞችን እንደገና ቢቆጣጠርም ሰፊው የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም በአማፅያን፣ በጂሃዲስቶች እና በኩርድ በሚመራው ኤስ ዲ ኤፍ ቁጥጥር ስር ናቸው። ዋነኛው የተቃዋሚዎች ምሽግ የሚገኘው በሰሜናዊ ምዕራብ ኢድሊብ እና በአጎራባች የሰሜን ሀማ እና የምዕራብ አሌፖ ክፍሎች ነው። አካባቢው ሀያት ታህሪር አል-ሻም (ኤች ቲ ኤስ) በሚባለው እና ከአልቃኢይዳ ጋር ግንኙነት ባለው የጂሃዳዊ ኅብረት የበላይነት የተያዘ ሲሆን ለዋነኞቹ አማፅያንም መኖሪያም ነው። አንድ ሚሊዮን ህፃናትን ጨምሮ በግምት ወደ 2.7 ሚሊዮን የተፈናቀሉ ሰዎች የሚኖሩት አካባቢ ነው። ብዙዎቹ በመጠለያዎች ውስጥ በአስከፊ ሁኔታ ይገኛሉ። መንግሥት ኢድሊብን እንደገና ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት ለማስቆም ባለፈው ዓመት መጋቢት ላይ ሩሲያ እና ቱርክ የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራርመዋል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ አንፃራዊ መረጋጋት ቢኖርም ስምምነቱ በማንኛውም ጊዜ ሊፈርስ እንደሚችል ይሰጋል። ጦርነቱ መቼ ያከትማል? በቅርብ ጊዜ የሚሆን አይመስልም። ሁሉም ግን ፖለቲካዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ ይስማማሉ። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የጄኔቫ ስምምነት እንዲተገበር ጥሪ አቅርቧል። ስምምነቱ "በጋራ ስምምነት የተቋቋመ የሽግግር አስተዳዳር" እንዲመሠረት ይደግፋል። በጄኔቫ በተባበሩት መንግሥታት አማካይነት የሚመሩ የሠላም ድርድሮች ለዘጠኝ ዙር ያህል ቢሞከርም ፍሬ አልባ ሆነዋል። ፕሬዝዳንት አሳድ ከስልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው ከሚሉት ከየትኞቹም የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ አልሆኑም። ሩሲያ፣ ኢራን እና ቱርክም ከሦስት ዓመታት በፊት 'አስታና' በመባል የሚታወቅ ትይዩ የፖለቲካ ውይይቶችን ጀመረዋል። በቀጣዩ ዓመት በተባበሩት መንግሥታት ቁጥጥር ስር ለሚካሄድ ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ የሚያግዝ አዲስ ሕገ-መንግሥት ለመፃፍ 150 አባላት ያሉት ኮሚቴ ለማቋቋም ከስምምነት ተደርሷል። ነገር ግን ይህ ሂደት ምንም አይነት እርምጃ አለማሳየቱን የተባበሩት መንግሥታት ልዩ መልዕክተኛ ጂር ፔደርሰን በምሬት ተናግረዋል።
49137219
https://www.bbc.com/amharic/49137219
በቦይንግ 737 ማክስ 8 አደጋ የፌደራል አቬይሽን ባለስልጣን በሰው 800 ሚሊየን ዶላር ካሳ ተጠየቀ
አቶ ዘካሪያስ አስፋው ሸንቁጥ የአቶ ሙሉጌታ አስፋው ሸንቁጥ ወንድም ናቸው። መጋቢት 1 ማለዳ ወደ ናይሮቢ 157 መንገደኞች ጭኖ ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ከነበሩት መካከል አንዱ ነበሩ።
አቶ ዘካሪያስ እንደሚሉት አውሮፕላኑ እሁድ ማለዳ ሊከሰከስ እርሳቸውና ወንድማቸው ማታ ቤተሰቦቻቸው ቤት አብረው እራት በልተው ሲጫወቱ አምሽተዋል። ቤታቸው አቅራቢያም እየተንሸራሸሩ ስለሁለቱም የግል ሕይወት የሆድ የሆዳቸውን አውግተዋል። አቶ ሙሉጌታ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት እንደነበሩ ይናገራሉ። አቶ ሙሉጌታ ወደ ናይሮቢ ለመጓዝ የተነሱት ከሥራቸው ጋር በተያያዘ ለስብሰባና ለስልጠና እንደነበር ይናገራሉ። አቶ ዘካሪያስ በወንድማቸው ሞት እርሳቸው፣ የአቶ ሙሉጌታ ባለቤትና ልጆቻቸው እንዲሁም ወላጆቻቸው በሀዘን ስሜታቸው መጎዳቱን ይገልጣሉ። • ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ማምረት ላቆም እችላለሁ ሲል አስጠነቀቀ • "ኦሮሞ እና ማዳጋስካርን የሚያገናኝ ፖለቲካ እንዳለ አላውቅም" የትነበርሽ ንጉሤ እርሳቸውና የሟች የአቶ ሙሉጌታ ባለቤት ወንድም በአሜሪካ ስለሚኖሩ ከዚህ አደጋ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ማናቸውንም ሕጋዊ ጉዳዮች ለማስጨረስ ከወንድማቸው ባለቤት ሕጋዊ ውክልና መውሰዳቸውን ይናገራሉ። ለዚህም የአየር መንገድ ጉዳዮችን በመያዝና ጥብቅና በመቆም የሚታወቁ ጠበቆችን በማፈላለግ አውሮፕላን አምራቹን ቦይንግን ከሰዋል። አቶ ሼክስፒር ፈይሳ በአሜሪካ ሲያትል ነዋሪ ሲሆኑ በጥብቅና ላይ ከ18 ዓመታት በላይ ልምድ እንዳላቸው ይናገራሉ። የአቶ ዘካሪያስ ወንድምንና ሌሎች በዚህ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ኬኒያውያንን ጉዳይ ይዘው ቦይንግ ላይ ክስ መመስረታቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የእርሳቸው የጥብቅና ድርጅት፣ ከፍሪድመን ሩበን እንዲሁም ፓወር ሮጀርስ የሕግ ቢሮዎች ጋር አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል። አቶ ሼክስፒር እንደሚሉት ሲያትልና ቺካጎ ውስጥ ከአየር ትራንስፖርት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ልምድ ያላቸውን ጠበቆች በማሰባሰብ፤ በኢትዮጵያና በኬኒያ ከሚኖሩ የአደጋው ሰለባዎች ቤተሰቦች ጋር በመነጋገር ቦይንግንና በዚህ አውሮፕላን ማምረት ሂደት ውስጥ የተሳተፉትን መክሰሳቸውን ይናገራሉ። ቦይንግ ላይ የመሰረቱት ክስ እንደደረሰው የተናገሩት አቶ ሼክስፒር መልሳቸውን እየተጠባበቁ መሆኑን ገልጠዋል። ቦይንግ ላይ የ37ገፅ ያለው ክስ መመስረቱን ተናግረው የክሱ ጭብጥን ሲያስረዱ ቦይንግ በርካታ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስህተቱን ባለማረም፣ በተለይ የኢንዶኔዢያው ላየን ኤር ጥቅምት ላይ ተከስክሶ፤ አውሮፕላኑን እስካ ለበት ጉድለት ለኢትዮጵ ሕዳር 2018 ላይ ማስረከባቸው አንደ አንድ ምክንያት ይጠቅሳሉ። እንዲሁም ቦይንግ አውሮፕላኑ ችግር እንዳለበት እያወቀ ሆን ብሎ ለኢትዮጵያና ለሌላ ሀገሮች መሸጡ፣ ለአሜሪካን አየር መንገዶች የሚሸጠውና ለሌሎች ኢትዮጵያን ለመሰሉ ሀገራት የሚሸጠው የተለየ መሆኑን በዚህም የሰው ሕይወት በመጥፋቱ ለሰዎቹ ካሳ ከዚህም አልፎ ቦይንግ ራሱ እንዲቀጣ የሚል ክስ ማቅረባቸውን ይናገራሉ። • ስለ አልጋዎ ማወቅ ያለብዎት 13 ነጥቦች ቦይንግ ክስ ላይ የገንዘብ ካሳ መጠን እንዳላስቀመጡ ገልፀው ለጠፋው የሰው ሕይወት እና ኩባንያው ዳግመኛ እንዲህ አይነት ጥፋትን እንዳይደግም ማስተማሪያ የሚሆን የመቀጣጫ ቅጣት በሰው እስከ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር ድረስ ይቀጣል የሚል ግምት እንዳላቸው ገልፀዋል። ቦይንግ በ2018 በዓመት 110 ቢሊየን ዶላር ያተረፈ ኩባንያ ነው። ጥያቄ ለፌደራል አቬይሽንአስተዳደር አቶ ሼክስፒር እንደሚሉት ET 302 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ውስጥ 157 ሰዎች ተሳፍረው የነበረ ቢሆንም እስካሁን ቦይንግ ላይ ክስ የመሰረቱት ገሚሶቹ መሆናቸውን ጠቅሰው ከእነርሱ ውጪ እስካሁን ድረስ ማንም ይህንን ተቋም አለመክሰሱን ይናገራሉ። ተቋሙ የቦይንግ አውሮፕላኖች መብረር ይችላሉ የሚል ፈቃድ የሚሰጥ መንግሥታዊ ተቆጣጣሪ ተቋም ሲሆን ክሳቸው እንደሚያስረዳው ተቋሙ ሥራውን ትቶ ከአምራቹና ነጋዴው ኩባንያ ጋር "ሴራ" ውስጥ መግባታቸውን በመጥቀስ እንደከሰሱ ተናግረዋል። የፌደራል አቬይሽን ባለስልጣን አንድ አውሮፕላን ተሰርቶ ሲያልቅ ወደ ገበያ ከመቅረቡ በፊት መፈተሽ፣ መመርመርና ለበረራ ብቁ ሆኖ ካገኘው ሰርተፊኬት የሚሰጥ ተቋም ነው። ነገርግን በቂ የሰው ኃይልና ገንዘብ የለንም በሚል የመፈተሽና የመመርመሩን ኃላፊነት ለራሱ ለቦይንግ ሰጥቶት ነበር። • "እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ የፌደራል አቬይሽን አስተዳደር የአውሮፕላኖች ደህንነት ላይ ቁጥጥር የሚደርግ ከመሆኑ በተጨማሪ የተለያዩ ቅሬታዎች ሲቀርቡለት አውሮፕላኖቹ እንዳይሸጥና እንዳይበሩ የማድረግ ስልጣን ቢኖረውም ይህንን ሳያደርግ በመቅረቱ የቦይን 737 ማክስ አሰቃቂ አደጋዎች ደርሰዋል። ለዚህ ደግሞ ቦይንግ ከፈረንሳዩ የአውሮፕላን አምራች ኤር ባስ ጋር ባለበት ፉክክር ምክንያት አስፈላጊውን ቁጥጥርን ቸል በማለቱ በዚህ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ሳቢያ የኢንዶኔዢያውን አደጋ ጨምሮ ከ300 በላይ ሰዎች ሊሞቱ ችለዋል ይላሉ። በክሳቸው ላይ ለደንበኞቻቸው በሰው የ800 ሚሊየን ዶላር ካሳ መጠየቃቸውን የተናገሩት አቶ ሼክስፒር የአሜሪካ መንግሥት ለክሳቸው መልስ ለመስጠት እስከ አምስት ወር ድረስ የጊዜ ገደብ እንዳለው ገልፀዋል። የማይመልሱ ከሆነ ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ አስገድደን ለደንበኞቻችን ፍትሕ ለማግኘት እንሞክራለን ብለዋል። ቦይንግ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በወንጀል እየተመረመረ እንደሆነ የጠቀሱት ጠበቃ ሼክስፒር የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትና የወንጀል መርማሪው አካል ኤፍ ቢ አይ በወንጀል እየመረመራቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል። ይህ በቦይንግ ታሪክ ውስጥ ተደርጎ አያውቅም ያሉት ጠበቃው የሚያሳየን ወንጀሉ ከፍ ያለና ከፍትሀ ብሔር፣ ከገንዘብና ቸልተኝነት አልፎ ወንጀል መሆኑን ነው ይላሉ። "እኛ መረጃ እያላቸው፣ እያወቁ የደበቁ ሰዎች አሉ ብለን ነው የምናምነው" የሚሉት አቶ ሼክስፒር በአሜሪካም፣ በአውሮፕላን ማምረት ታሪክም፣ ምናልባት በፋብሪካዎች ታሪክም ትልቁ ክስ ነው የሚሆነው ይላሉ። የቦይንግ ይቅርታ ቦይንግ በተፈጠረው አደጋ የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ ይቅርታ መጠየቁ ይታወሳል። ይህ ግን ለአቶ ዘካሪያስ የሚዋጥ አይደለም። ይቅርታ የሚጠየቀው የተጎዳውን ሰው ነው የሚሉት አቶ ዘካሪያስ ቦይንግ ግን በመገናኛ ብዙኀን ላይ ወጥቶ ይቅርታ የጠየቀው አጠቃላይ ማህበረሰቡን መሆኑን በማንሳት በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖች ቦይንግን ከሚያክል ኩባንያ የሀዘን መግለጫ ፓስት ካርድ እንኳን እንዳልደረሳቸው ያነሳሉ። "የእኔ እናትና አባት እኮ ኢንተርኔት የላቸውም፤ የእኔ እናትና አባት እኮ ቦይንግ ያለውን ነገር በቴሌቪዥን ሊያዩ አይችሉም " በማለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋው ከተፈጠረበት ዕለት አንስቶ እስከ አንድ ሳምንት ድረስ ቤተሰቦቻቸው ቤት በመመላለስ፣ አበባና ካርድ በመላክ፣ ላላቸው ጥያቄዎች ሁሉ አቅማቸው በፈቀደ መልስ በመስጠት ሐዘናቸውን መጋራቱን ይገልጣሉ። • በእነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ለሀምሌ 29 ተቀጠሩ በተጨማሪም ቦይንግ በመግለጫው ላይ አውሮፕላኑ ከመሬት ለቅቆ አየር ላይ በቆየባት ስድስት ደቂቃ ውስጥ ያለውን ጉዳይ ብቻ በማንሳት ለአውሮፕላኑ መከስከስ አብራሪዎቹን ጥፋተኛ ለማድረግ መሞከሩን በመጥቀስ፤ ነገር ግን ትልቁ ስህተት የተሰራው አውሮፕላኑን ከ737 ወደ 737 ማክስ የተደረገውን የዲዛይን ለውጥ፣ ዋጋ ለመቀነስ የሚረዱ ነገሮች ማንም እንዲያውቅና እንዲናገር አይፈልጉም በማለት ቦይንግ ወጥቶ በተናገረ ቁጥር በአደጋው ወንድሙን እንዳጣ ቤተሰብ ይጎዳኛል ይላሉ። "ቦይንግ አዝነናል ቢል፣ የምንችለውን እናደርጋለን ሊል ይችላል ግን እየዋሸን ነው።" ፍትህ የሚናፍቁት ቤተሰቦች አቶ ዘካሪያስ እንደቤተሰብ ሐዘን ላይ ብቻ ሳንሆን ፍትህም እንዲከናወን እንፈልጋለን በማለት ያለባቸውን ተደራራቢ ጫና ይናገራሉ። ያጣነው ለቤተሰቡ ኩራት የነበረ ሰው ነው በማለት ባለቤቱና ልጆቹም እንዲሁም እናትና አባቱ የደረሰባቸውን ሐዘን ያስረዳሉ። እናታችን የስኳር ሕመምተኛ ስለነበረች የሐዘኑ ሰሞን ለእርሷም ለቤተሰቡም ከባድ ወቅት ነበር የሚሉት አቶ ዘካሪያስ በተደጋጋሚ የስኳር መጠናቸው ከፍ ብሎ እንደነበር ሐዘናቸው ብርቱ እንደሆነ ይናገራሉ። ለዚህም ይህንን ጉዳይ ወደ ፍትህ አደባባይ ለመውሰድ እኔና የባለቤቴ ወንድም ለመጋፈጥ የወሰንነው ይላሉ። የተሰራው ስህተት እንዳይሸፋፈን እና ግልፅ እንዲወጣ ቦይንግን መብረር ትችላለህ ብሎ የምስክር ወረቀት የሚሰጠውን አካል ፌደራል አቬይሽን አስተዳደር መክሰሱ ጥቅም አለው ይላሉ። • ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው "የኢትዮጵያ አየር መንገድም ቢሆን የአሜሪካ ፌደራል አቬይሸን የሰጠውን ምስክርነት ነው አምኖ አውሮፕላኑን ሊገዛ የሚችለው" የሚሉት አቶ ዘካሪያስ እነዚህን ቦይንግ ሰራሽ አውሮፕላኖች እራሱ አረጋግጦ መብረር ይችላሉ ሲል እንደሚሸጡና ወደ ሥራ እንደሚገቡ ይናገራሉ። ስለዚህ ይህ መስሪያ ቤት መከሰሱ የተፈጠረውን ችግር ከማወቅ አንጻር ቦይንግ 737 ማክስ ላይ ያልተመለከተንው ምን ነበር የሚለውን በጥልቀት ማወቅ እንዲቻል ይጠቅማል ይላሉ። ሁለተኛው ደግሞ ይላሉ አቶ ዘካሪያስ "ከአሁን በኋላ ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት ይህ መስሪያ ቤት ለገዛ ስማቸው ሲሉና በቦይንግ የሚበረውን ማህበረሰብ እምነት መልሰው ለማግኘት ሲሉ መጠንቀቅ ይጀምራል" ይላሉ። በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ አሜሪካውያኑን ጨምሮ ከ30 በላይ ዜጎች መሆናቸውን አስታውሰው ለሌሎች ዜጎች ብቻ ሳይሆን ለአሜሪካውያንም ተጠያቂ በመሆናቸው ጥንቃቄያቸውን ይጨምራል ሲሉ ያስረዳሉ። ከምንም በላይ ይህ ሕጋዊ አካሄድ ምንም አይነት ውሳኔ አመጣ ምንም፤ መጠየቅ ያለባቸው አካላት ሁሉ መጠየቅ አለባቸው ብለው እንደሚያምኑ ገልጠው ቀላል ጉዳይ እንዳልሆነ ይናገራሉ። ጥያቄው ለፌደራል አቬይሽን አስተዳደር መቅረቡ የአውሮፕላን አምራቾችን የመቆጣጠርና ፈቃድ የመስጠት ሥራውን በአግባቡ እንዲያከናውን የሚያስገድድ እንደሆነ የሚናገሩት የሕግ ባለሙያው አቶ ሼክስፒር ፈይሳ፤ በዚህም የአውሮፕላኖች ደህንነትን አስተማማኝ በማድረግ የተጓዦች ደህንነት እንዲጠበቅ ያደርጋል ይላሉ። በተጨማሪም በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ሰዎች የፌደራል አቬይሽን አስተዳደርን ተጠያቂ በማድረግ የተሟላ ፍትህን እንዲያገኙ ለማድረግ እንደሚያስችል ይጠቁማሉ። በአደጋው ብቁ ያልሆነ አውሮፕላን በማቅረብ ቦይንግ ቀዳሚ ተጠያቂ ቢሆንም የፌደራል አቬይሽን አስተዳደር ግንን ከኢንዶኔዢያው አደጋ በኋላ በኢትዮጵያው አየር መንገድ ላይ ችግሩ እንዳይከሰት ማድረግ ይችል ነበር ይላሉ አቶ ሼክስፒር። ቦይንግን በማንኛውም ሰዓት መክሰስ ይቻላል? በአደጋው ቤተሰባቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያን እስካሁን ድረስ ቦይንግን ያልከሰሱ ኢትዮጵያውያን ይወክለናል የሚሉትን ጠበቃ በሚገባ መርጠው ክሳቸውን ቢያቀርቡ የተሻለ እንደሚሆን ይመክራሉ። ቦይንግን መክሰስ የሚቻለው አደጋው ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ መሆኑን ጠቅሰው፤ ክሱ በቆየ ቁጥር ታሪኩ እየተረሳ እንደሚሄድ፣ የጉዳዩ አስፈላጊነትም እየቀዘቀዘ እንደሚሄድ ይናገራሉ። በቆዩ ቁጥር ማስረጃዎቹ እየደከሙ ሊሄዱ ስለሚችሉ ሀሳባቸውን ሰብሰብ አድርገው ተገቢውን የህግ አካሄድ ቢጀምሩ መልካም መሆኑን ይናገራሉ።
news-49758790
https://www.bbc.com/amharic/news-49758790
የኤርትራ ወጣቶችና ምኞታቸው
ከሶስት ሳምንታት በፊት ቢቢሲ በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን ከ15 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድርን ለመዘገብ ፍቃድ አግኝቶ ወደ አሥመራ አቅንቶ ነበር።
አሥመራ በተካሄደው ፌስቲቫል ላይ የባህል ጨፈራቸውን የሚያሳዩ ኤርትራውያን ወጣቶች በኤርትራ በነበርን ቆይታ ያየነውን እና የሰማነውን በሶስት ክፍሎች አሰናድተናል። ሶስተኛው ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል። ሁለተኛውን ክፍል ለማንበበ ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። ማሳሰቢያ፡ በኤርትራ በነበረን ቆይታ የዘገባ ርዕሶቻችን እና እንቅስቃሴዎቻችን የተገደቡ ነበሩ። በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት እንደ የጎሮጎሲያኑ የቀን አቆጣጠር ነው። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች አንድ በዕድሜ የገፉ አባት በአሥመራ ከተማ ከፑሽኪን ሃውልት ስር ተቀምጠው እግርዎ አሥመራ እንደረገጠ ቀድመው ሊያስተውሉ ከሚችሏቸው መካከል አንዱ፤ አሥመራ አዛውንት የሚበዛባት እና ወጣት ብዙም የማይታይባት ከተማ ስለመሆኗ ነው። • አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ • የአሥመራን ጎዳናዎች በፎቶ የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ከጠቅላለው ህዝብ እድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ቁጥር ከ65 በመቶ ይሆናል ይላል። ይህ ግን ለኤርትራ የሚሰራ አይመስልም። ግራ ቀኞችን ቢያማትሩ በብዛት የሚመለከቱት እድሜያቸው ጠና ያለ አዛውንቶችን ነው። 'ወጣቱ ወዴት አለ?' ብለው ራስዎትን መጠየቅዎ አይቀርም። እያደጉ ባሉ የአፍሪካ ሃገራት ወጣቱ ትውልድ የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ሃገሩን ጥሎ የመሸሹ ዜና የተለመደ ሆኗል። 2016 ላይ የወጣ አንድ ሪፖርት እንደሚጠቁመው ከአፍሪካ ሃገራቸውን ጥለው ከሚወጡ ወጣት አፍሪካውያኖች አብዛኛዎቹ ኤርትራውያን ናቸው። የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ወጣቶች የተሻለን ህይወት ፍለጋ ሃገር ጥለው እንደሚሰደዱ አደባባይ የሚያውቀው ሃቅ ነው። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ በድንበር በኩል ሃገር ጥለው የሚወጡ ወጣቶች ቁጥር እጅጉን ማሻቀቡን ነዋሪዎች ነግረውናል። ሆኖም፤ በዚህ ያክል መጠን ከተማዋ ወጣት አልባ መሆኗ የሚያስደንቅ ነው። በአሥመራ 'ERITREA' ወይም 'Proud Eritrean' [ኩሩ ኤርትራዊ] ተብሎ የተጻፈባቸው ከነቴራ ለብሰው የሚታዩ ወጣቶች ብዙ ናቸው። ይህ እና ሌሎች ምክንያቶች ተደማምረው አሥመራን "አድማ ላይ ያለች ከተማ" አስመስለዋታል። አንድ ከተማ አድማ ላይ ስትሆን በራቸውን የሚዘጉ የንግድ ተቋማት ብዙ ናቸው። መንገድ ላይ የሚታዩ የተሽከርካሪዎች ቁጥር አነስተኛ ነው። በአሥመራም ያስተዋልነው እንዲሁ ነው። ብዙ የንግድ እንቅስቃሴ አይታይም። የትራፊክ ፍሰቱ ቀሰስተኛ ነው። ፓስፖርት የለም አንድ ኤርትራዊ ፓስፖርት ማግኘት የሚችለው የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠለትን ብሔራዊ አገልግሎት አጠናቆ ከመንግሥት አካል ፓስፖርት ለማግኘት ይሁንታን ሲያገኝ ነው። በእነዚህ መስፈርቶች ምክንያት ወጣቶች ፓስፖርት የማግኘት እድላቸው እጅግ አነስተኛ ነው። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች • በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል ''ፓስፖርት ማግኘት የማይታሰብ ነገር ነው" ይላል በአንድ ምሽት ለእራት አብሮን ያመሸ ወጣት። "ብሄራዊ አገልግሎት ጨርሰህ፣ ከመንግሥት ቢሮ ደብዳቤ ተጽፎልህ ፓስፖርት ስታገኝ የ40 ወይም የ45 ዓመት ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ትሆናለህ" ይላል። ከሁነኛ የመረጃ ምንጮች እንደሰማነው በቁጥር ቀላል የማይባሉ ኤርትራውያን ወጣቶች ድንበር በማቋረጥ ወደ ኢትዮጰያ ከተሻገሩ በኋላ ኢትዮጵያዊ ነን በማለት ፓስፖርት ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ ፊታቸውን እያዞሩ ነው። ቋንቋ ትግርኛ እና አረብኛ የኤርትራ የሥራ ቋንቋዎች ሲሆኑ፤ በአሥመራ እንግሊዘኛ በስፋት ይነገራል። በእድሜ ገፋ ያሉት ካልሆኑ በቀር ወጣቶች አማርኛ መናገር ይከብዳቸዋል። ትግርኛ የማይችሉ ከሆነ በእንግሊዘኛ ነው ሊግባቡ የሚችሉት። ብዙዎቹ ወጣቶቹ ባማረ ዘዬ እንግሊዘኛ ጥሩ አድርገው መናገራቸው ግርምትን ፈጥሮብናል። በአሥመራ ከተማ ብዙ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት መኖሩ ለዚሁ ሳይጠቅማቸው አልቀረም። የቅኝ ገዢው ጣሊያን ብዙ አሻራ ያረፈባት አሥመራ፤ በቋንቋ ረገድ ግን ጣሊያንኛን የሚያወሩ ሰዎች አላጋጠሙንም። በእድሜ ገፋ ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ግን ጣሊያንኛ እንደሚያወሩ ሰምተናል። ዘናጮቹ የአሥመራ ልጆች የአሥመራ ወጣቶች በተለይ እንስቶቹ የለበሱትን ከሚጫሙት ጫማ ጋር አዋህደው ሽር ይላሉ። የልብስ መሸጫ ቡቲኮች አይታዩም። በአሥመራ የሚገኙ ቡቲኮችን ቆጥረው ሊጨርሱ ይችላሉ። ይህ ማጋነን አይደለም። ታዲያ እንዲህ የሚዘንጡት ወጣቶች የሚለብሱትን ልብስ፤ የሚጫሙትን ጫማ ከየት እየገዙት ነው? ብልን አንድ የታክሲ ሹፌርን ጠየቅነው ''ባህር ማዶ ዘመድ የሌለው የለም፤ ልብስ ይላካል'' ሲል መለሰልን። • ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ አሥመራ ያሉ ቡና ቤቶች ከሰኞ እስከ ሐሙስ የሚሰሩት እስከ እኩለ ለሊት ብቻ ነው። የምሽት ክበቦችም ቢሆኑ በዚሁ ቀጭን ትዕዛዝ ስር የወደቁ ናቸው። ከአርብ እስከ እሁድ ድረስ ግን ይህ ገደብ የለም። በአሥመራ የመንገድ ላይ የወሲብ ንግድ ፈጽሞ የተከለከለ ነው። ስድስት ወራት ያሳስራል። ከ15 ዓመት በታች የኤርትራ ብሔራዊ ቡድንን ለመደገፍ ከስታዲየም የተገኙ ደጋፊዎች። ስፖርት በብስክሌት ግልቢያ የሚታወቁት ኤርትራውያን ለእግር ኳስ ጥልቅ ፍቅር እንዳላቸው ታዝበናል። አሥመራ እግር ኳስ በስሜት የሚታይባት ከተማ ነች። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ደግሞ ተወዳጁ ሊግ ነው። ጥንት ፊልም እና ቲያትር ይታይባቸው የነበሩት የአሥመራ ሲኒማ ቤቶች፤ ዛሬ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የሚናፍቁ ኳስ ወዳጆች ይታደሙበታል። የአርሰናል እና ማንችስተር ደጋፊዎች በብዛት ያሉባት ከተማ ናት አሥመራ። • የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ሲታወስ አንዱ የአርሰናል ደጋፊ ''ቼልሲን የሚደግፉት ከቆላ የሚመጡት ናቸው" ብሎ ከተሳለቀ በኋላ፤ "ፕሬዝደንቱ ራሱ የአርሰናል ደጋፊ ናቸው'' በማለት በልበ ሙሉነት ይናገራል። ብሔራዊ አገልግሎት ብሔራዊ አገልግሎት የተጀመረው 1994 ላይ ሲሆን የኤርትራ መንግሥት 'ኤርትራ የወረራ ስጋት ያለባት ሃገር ናት' በማለት ወጣቶችን በየዓመቱ ሳዋ ተብሎ ወደሚጠራው ካምፕ እየወሰደ ወታደራዊ ስልጠና ይሰጣል። "ታዳጊዎችን ማብቂያ ለሌለው ባርነት እየተዳረጉ ነው" የሚል ክስ በተደጋጋሚ የሚቀርብበት የኤርትራ መንግሥት፤ ከኢትዮጵያ ጋር የሰላም ስምምነት ከተደረሰም በኋላ ብሔራዊ አገልግሎቱን እንዳስቀጠለ ነው። በሳዋ ማሰልጠኛ ማዕከል ማስተማር የነበረበትና ባለፈው ዓመት ኤርትራን ጥሎ የተሰደደው የ25 ዓመቱ ወጣት ለሂማን ራይትስ ዋች "የፊዚክስ ትምህርትን ለማስተማር ከተመለመልክ፤ እድሜ ልክህን የፊዚክስ መምህር ሆነህ ትቀራለህ" ሲል ተናግሯል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ማናቸው? ፕሬዝደንት ኢሳያስ ስለ ግል ህይወታቸው በአደባባይ አይናገሩም። ስለ እርሳቸው የሚያውቁት ጥቂቶች ናቸው። 1936 ላይ በአሥመራ የተወለዱት ኢሳያስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው በከፍተኛ ውጤት ማጠናቀቅ በመቻላቸው፤ በቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ገብተው የምህንድስና ትምህርት እንዲከታተሉ የሚያስችላቸው ቢሆንም ትምህርታቸውን አቋርጠው የኤርትራ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባርን ለመቀላቀል ወደ ሱዳን አቀኑ። ፕሬዝደንት ኢሳያስ ታጋይ ከነበሩት ሳባ ኃይሌ ጋር ትዳር መስረተው በአሁኑ ወቅት የሁለት ወንዶች እና የአንዲት ሴት አባት ናቸወ። በ1962 ዓ.ም የኤርትራ ነጻነት ግንባር ውስጡ በተፈጠረ አለመስማማት በሦስት ተከፈለ። ከ10 ያልበለጡ አባላት የነበሩት የኢሳያስ አፈወርቁ ቡድን ወደ ደቡባዊ ምሥራቁ ኤርትራ በመሄድ ትግሉን ጀመረ። • የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? • የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ጦስ በሶማሊያ? ከአንድ ዓመት በኋላ ኢሳያስ የብሄር እና የኃይማኖት ልዩነቶችን ለማጥበብ እና የተቀናጀ ትግልን ስለማካሄድ የሚያትት "ትግላችን እና ግቡ" የተሰኘ ማኒፌስቶ ጽፈው ነበር። 1979 ላይ የግንባሩ ሊቀመንበር ተደርገው የተመረጡት ኢሳያስ፤ 1985 ላይ የተደረገውን ህዝበ ውሳኔ ተከትሎ የኤርትራ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት እና የብሔራዊ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ተደረገው ተመረጡ። በቁመተ ረዥሙ ብቻም ሳይሆን ለረዥም ዓመታት ሃገር ያስተዳደሩም መሪ ለመሆን የበቁት ፕሬዝደንት ኢሳያስ የመንግሥት የሥራ አስፈጻሚን እና የፍትህ አካሉን በቁጥጥራቸው ስር እንዲሆን አድርገዋል።
41799605
https://www.bbc.com/amharic/41799605
በቤኒሻንጉል ጥቃትን በመፍራት ሰለባዎች ወደመኖሪያቸው መመለስን ፈርተዋል
ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሃሮ ዴዴሳ ቀበሌ የተቀሰቀሰውና ለሕይወት መጥፋት እንዲሁም ለንብረት መውደም ምክንያት የሆነው ግጭት ግላዊ ጠብ የጫረው ነው ቢባልም ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጥቃቱ ሰለባዎች ግን ማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ይናገራሉ።
በተለያዩ ጊዜያት ከምዕራብ ጎጃም ዞን ለስራ ወደአካባቢው አቅንተው ኑሯቸውን በመሰረቱ የአማራ ተወላጆች እና በጉሙዝ ብሔረሰብ አባላት ውጥረቶች እና ግጭቶች አዲስ ያለመሆናቸውን የሚያስረዱት የጥቃቱ ሰለባዎች ከሁለቱም ወገን ሰዎች መሞታቸውን ይገልፃሉ፤ ከሟቾቹ መካከል የኦሮሞ ተወላጆችም ይገኙበታል ተብሏል። በግጭቱ ማግስት የአማራ ክልል የብዙኃን መገናኛ ድርጅት የቤኒሻንጉል ክልል የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ መንግስቱ ቴሶን ጠቅሶ ባቀረበው ዘገባ ክስተቱን ወደግል ጠብ ዝቅ አድርጎት እንደነበር ይታወሳል። በ1997 ዓ.ም ከከሰላ አካባቢ ስራ ፍለጋ ወደስፍራው ካቀና በኋላ ኑሮውን በቀበሌው ደናባ ጎጥ የመሰረተው የ36 ዓመቱ ባይህ ታፈረ በግጭቱ የተገደሉ ሰባት ሰዎችን አስከሬን መመልከቱን ይናገራል፤ ሟቾቹ ስድስቱ የአማራ አንዱ ደግሞ የጉሙዝ ተወላጆች ናቸው ይላል። ባይህ በደረሰባቸው ድብደባ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የገጠማቸውን የስምንት እና የአስራ አንድ ዓመት ልጆቹን በነቀምት አጠቃላይ ሆስፒታል በማስታመም ላይ የሚገኝ ሲሆን በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት "ወደአገራችሁ እንመልሳችኋለን" የሚል ዛቻ ከአገሬው ሰው ጎልቶ ይሰማ ነበር ይላል። ይህ መንፈስም ከሌሎች ቦታዎች የመጡ ናቸው የተባሉ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዲነጣጠር ምክንያት ሆኗል ሲል ያምናል። "በየጠላ ቤቱ፣ በየአረቄ ቤቱ ብናባርራችሁ መንግስት መለሳችሁ፤ አሁንም ግን ዋጋችሁን እንሰጣችኋለን ይሉናል" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል፤ "መንግስት መሳሪያችን ቢነጥቀንም ቀስትና ጩቤ አለን ሁሉ እንባላለን።" ይላል ባይህ የቤኒሻንጉል ክልል በሕገ መንግስቱ መሰረት "ነባር ሕዝቦች" ናቸው በሚል ዕውቅና የሰጣቸው ለበርታ፣ ጉሙዝ፣ሽናሻ፣ ማዖ እና ኮሞ ብሔሮች ሲሆን "መጤ" ናቸው ከሚባሉ የሌላ ብሔር ተወላጅ ሕዝቦች ጋር ግጭቶች ሲፈጠሩ አሁን የመጀመሪያው አይደለም። በ2006 ዓ.ም በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ጥቃትን በመሸሽ ከአካባቢው ተፈናቅለው በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም አካባቢ ሰፍረው የቆዩ ሲሆን፤ ቆይቶም ወደክልሉ እንዲመለሱ መደረጋቸው ይታወሳል። የቤኒሻንጉል ክልል የኮሚኒኬሽን ጽሐፈት ቤት ኃላፊው አቶ መንግስቱ የተከሰተው ግጭት የብሔር መልክ የለውም ይበሉ እንጅ፤ የሃሮ ደዴሳ ገብርዔል ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ የሆኑት ቄስ እንኳሆነ ቸሬ "ምንም በማናውቀው ጉዳይ መደብደባችን ወገን ናችሁ ቢባል ነው እንጅ" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቄስ እንኳሆነ ከልጃቸው ጋር ወደስራ በሚሄዱበት ሰዓት በድንገት ጥቃት እንደደረሰባቸው ነው የሚናገሩት። ከባድ ድብደባ ለሕይወቱ የሚያሰጋ ሁኔታ የዳረገው ልጃቸው ሆስፒታል ውስጥ ይገኛል። ባይህ ጥቃት አድራሾቹ በሕፃናት ላይ እንደሚበረቱ ይናገራል፤ "ልጆቻችን እዚሁ ተወልደው ስላደጉ ጉምዝኛ ቋንቋ ችለዋል። እነርሱ ይሄንን አልወደዱትም፤ ቋንቋችንን ሰረቃችሁን ይላሉ" ብሏል። እርሱና መሰል የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች መሬት በመከራየትና እርሱን አርሰው የመሬት ባለቤት ከሆኑ የአካባቢው ተወላጆች ጋር ምርቱን በመካፈል እንደሚተዳደሩ ሲያስረዳ "ውል እንገባለን። በውሉ መሰረት ተስማምተን፤ ሽማግሌ አስቀምጠን ነው የምንሰራው። ውሉን ከፈፀምን በኋላ የእነርሱን ድርሻ እንሰጣለን። የራሳችንንም እንወስዳለን። ይህ ሲሆን ግን ጎጃሜ እኛ አገር መጥቶ ለምን ይደሰታል ነው የሚሉት" ይላል። በስራ መካከል ግጭቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ በሽማግሌዎች የማይፈታ ከሆነ በጎጥና በቀበሌ የአስተዳደር አካላት ፍትህን ማግኘት አዳጋች ነው ይላል። ቄስ እንኳሆነ የቀጣይ ቀናት እርምጃቸውን ማሰብ አይፈልጉም፤ ትኩረታቸው ሁሉ የልጃቸው ጤና መመለስ ላይ ነው። "ከዚያ ወዲያ ያለውን እግዚያብሄር ነው የሚያውቀው ። ደውለን ስንጠይቅ አሁንም ብዙ ሰዎች ጫካ እንዳሉ ናቸው። ያለዕህል ውሃ መመለስ ፈርተዋል" በማለት ይናገራሉ። ባይህ ደግሞ ወደነቀምት ከመጣ በኋላ የቅርብ ጎረቤቱን ጨምሮ አራት ሰዎች -ሁለት የአማራ ተወላጆች እና ሁለት ከእነርሱ ጋር አብረው የሚሰሩ የኦሮሞ ብሔር አባላት- በቢላዋ ተወግተው ተገድለው እንደተገኙ በስልክ ከወዳጆቹ መስማቱን ያብራራል። ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያፈራውን ንብረት ሙሉ ለሙሉ እንደተዘረፈ የሚናገረው ባይህ ፤ ወደ ቤኒሻንጉል ክልል የመመለስና ሕይወቱን ዳግም የመገንባት ፍላጎት የለውም። "የቀረችኝን ነገር ለቃቅሜ ሕይወቴን ይዤ ከዚህ ቦታ መውጣት ነው የምፈልገው" ይላል። ይህንንም ተከትሎ የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ዛሬ በፌስቡክ ድረ-ገፃቸው የፃፉት መረጃ እንደሚያሳየው የስምንት ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን ቁጥራቸው ያልተገለፁ ቤቶችም ተቃጥለዋል። ከዚህም ጥቃት ጋር ተያይዞ የመከላከያ ሰራዊት እና ፖሊስ ሁኔታውን ለማረጋጋት እየሰሩ መሆናቸውን የአቶ ንጉሱ ጥላሁን ፅሁፍ ጠቅሶ 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ምንም እንኳን የቤኒሻንጉል ጉሙዝም ሆነ የአማራ ክልል አመራሮች ጉዳዩን ወደ ግለሰባዊ ፀብ አውርደውት የነበረ ቢሆንም ጉዳዩን በጥልቀት እያጤኑት እንደሆነ አቶ ንጉሱ ጠቅሰዋል። የሁለቱም ክልል ሀላፊዎች በቦታው ላይ የማረጋጋት ስራ እየሰሩ እንደሆነ አቶ ንጉሱ ጠቅሰው የክልሉ አመራሮች እና የብአዴን አስተባባሪዎች ህዝብ የማወያየት ስራ እንደጀመሩ ጨምረው ጠቅሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ በቦታው የተሰማራው ቡድን እያሰባሰበ እንደሆነ አቶ ንጉሱ ጠቅሰዋል።
news-45650024
https://www.bbc.com/amharic/news-45650024
በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት
የተወለደችው እንደ አውሮፓውያኑ በ1983 ነው። ትምኒት ገብሩ ትባላለች። በ 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ዘርፍ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ ባለሙያዎች አንዷ ነች። አሁን ካሊፎርንያ ውስጥ የምትኖረው ትምኒት ጉግል ውስጥ ሪሰርች ሳይንቲስት ናት።
ትምኒት ገብሩ በ 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' የጥቁር ሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ 'ብላክ ኢንኤአይ' የተባለ ተቋምን ከመሰረቱት አንዷ ናት። የፈጠራ ሥራዎችን አካታችነት በሚፈትሹ ጥናቶቿ፤ እንዲሁም ቴክኖሎጂና የሰብአዊ መብት ጥያቄን በማስተሳሰርም ትታወቃለች። ትምኒት ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ያደረችው ቃለ ምልልስ እነሆ። እስኪ ስለ አስተዳደግሽ አጫውችን. . . ተወልጄ ያደግኩት አዲስ አበባ ነው። መዋለ ህጻናት ቅድስት ሀና፤ እስከ ዘጠነኛ ክፍል ናዝሬት ስኩል ተማርኩ። አስረኛ ክፍል ስደርስ ለአንድ ዓመት አየርላንድ ሄድኩ። ሁለተኛ ደረጃና ዩኒቨርስቲ እዚህ አሜሪካ ጨረስኩ። • ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት • አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ ትምኒት በትግርኛ ምኞት ማለት ነው። እናትና አባቴ ወንድ ልጅ፤ እህቶቼ ደግሞ ሴት እንድትወለድ ነበር የፈለጉት። ስወለድ እህቶቼ ትምኒት አሉኝ። የመጨረሻ ልጅ ነኝ። ህጻን ሳለሁ ትምህርት እወድ ነበር። ስታመም ራሱ ከትምህርት ቤት መቅረት አልወድም ነበር። ሒሳብና ፊዚክስ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ዘፈንና እስክስታም በጣም ነበር የሚያስደስተኝ። እንዲያውም እህቴ ከ 30 ዓመት በፊት ስዘፍንና ተረት ሳወራ ቀድታኛለች። አዘውትረሽ የምትሰሚው፣ የምትዘፍኝው ዘፈን ነበር? በጣም የምወደው ዝንቦችን ስለማጥፋት የተዘፈነውን ነው። [ሳቅ እየተናነቃትና እያንጎራጎረች] "ልጆች ልጆች እንተባበር. . . ዝንቦቹን ለማጥፋት ከሰፈር" የሚለውን. . . ወደ ሳይንሱ ያዘነበልሽው በዚህ አይነት ሙዚቃ ተስበሽ ይሆን? ከዚህ ጋር የሚያያዝ አይመስለኝም። ወደ ሳይንስ ያዘነበልኩት አባቴ ኤሌክትሪካል ኢንጅነር ስለነበረ ነው። በአስር ዓመት የሚበልጡኝ ሁለት እህቶቼም ኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ነበር ያጠኑት። እንደ ጥቁር ሴት የአሜሪካን ኑሮ እንዴት አገኘሽው? መጀመሪያ ደስ አላለኝም ነበር። እዚህ ሀገር የተለያየ የክፍል ደረጃ (ኦነር፣ ስታንዳርድ የሚባል) አለ። መጀመሪያ ትምህርት ቤት የሄድኩ ቀን ልዩነቱን ስላላወቅኩ ለኬምስትሪ 'ስታንዳርድ' የሚባል ክፍል ሄድኩ። አስተማሪው በዛ ዓመት የሚያስተምረውን ሲናገር «ይህንን ባለፈው ዓመት አየርላንድ ተምሬዋለሁ የሚቀጥለው ክፍል ልግባ» አልኩት። «ብዙዎች እንዳንቺ ከሌላ ሀገር መጥተው በጣም ከባድ ትምህርትን የሚወጡ ይመስላቸዋል። የዚህን ሀገር ፈተና ብትፈተኝ [ግን] ትወድቂያለሽ» አለኝ። የማያውቀኝ ሰው ለምን እንዲህ ይለኛል? ብዬ ተገረምኩ። ብዙ አስተማሪዎች ጥሩ ውጤት ሳመጣ ይገርማቸው ነበር። • የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት • ስለጉግል የማያውቋቸው 10 እውነታዎች ኮሌጅ ለማመልከት የሚያግዝ አማካሪ «የትም አትገቢም» ብሎኛል። እናቴ «ለምን ልጄን እንዲህ ትላታለህ? ፈተና ፈትናት እንጂ ማስፈራራት አትችልም» ብላው ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ዲፕረስድ ሆኜ [ተደብቼ] ነበር ያሳለፍኩት። ኮሌጅ የተሻለ ነበር። ሥራው ላይ ስንመጣ፤ በኛ ሙያ ብዙ ሴቶች የሉም። ብዙ ጥቁሮች የሉም። ስለዚህ በማሰብ ብዙ ስትናደጂ ከስራሽ ትርቂያለሽ። [አንዳንዴ] ስለ ሌላ ነገርም ማሰብ አለብሽ። ወደ 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' የገባሽው እንዴት ነው? ወደ 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' መግባት እፈልጋለሁ ብዬ አይደለም የገባሁት። ፒኤችዲ ጀምሬ መሀል ላይ ነው የገባሁበት። ያኔ ብዙ ሰው 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' አይለውም ነበር። በ'ሜዲካል ኢሜጂንግ' ዘርፍ ላይ ፍላጎት ነበረኝ። ለምሳሌ ገጠር የሚኖሩና ሆስፒታል የማያገኙ ሰዎች በስልካቸው እንዴት ህክምና ማግኘት እንደሚችሉ እያጠናሁ ነበር። 'ኦፕቲክስ' የሚባል የፊዚክስ ስፔሻሊቲ [ዘርፍ] እያጠናሁ ሳለ ወደ 'ኢሜጅ ፕሮሰሲንግ' መጠጋት ጀመርኩ። ፎቶ ከወሰድሽ በኋላ ፎቶ ውስጥ የምትፈልጊውን አይነት መረጃ ለማግኘት በሂሳብ ወይም በሌላ አይነት 'አልጎሪትም' [በመጠቀም] 'ፕሮሰስ' ታደርጊያለሽ። 'ሲማ ፕሮሰሲንግ' የሚባል ዘርፍ ሳጠና ለ'ኮምፒውተር ቪዥን' ፍላጎት አሳደርኩ። 'ኮምፒውተር ቪዥን' እየሰራሁ ሳለ ወደ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ገባሁ። ከጥናቶችሽ መካከል ስለ 'ፌሽያል ሪኮግኒሽን ሲስተም' (የሰዎችን ፊት ገጽታ በማየት ማንነታቸውን የሚያሳውቅ መተግበሪያ) የሰራሽው ይጠቀሳል። የአሜሪካ ኑሮ ተሞክሮሽን የተመረኮዘ ነው? ጥናቱን የጀመረችው 'ኤምአይቲ ሚዲያ ላብ' የምትሰራ ጆ የምትባል ጓደኛዬ ናት። ጥቁር ሴት ነች። ለአንድ ፕሮጀክት 'ፌስ ሪኮግኒሽን' ስትጠቀም ፊቷን 'ዲቴክት' ማድረግ [ማንበብ] አልቻለም። እንደሌለች ነው የሚቆጥረው. . . ነጭ 'ማስክ' [ጭንብል] ፊቷ ላይ ስታደርግ ግን ያነባል። 'ፌስ ሪኮግኒሽን' ነጮችና ጥቁሮች ላይ እኩል አይሰራም። ከጓደኛዬ ጋር የጻፍነው ጥናት የሚያሳየው በተለይ ጠቆር ያሉ ሴቶች ላይ በደንብ አለመስራቱን ነው። • ከአንታርክቲካ በስተቀር ስድስቱን አህጉሮች ያዳረሰችው ኢትዮጵያዊት • ሁሉንም በደህንነት ካሜራ የምትመለከተው ቻይና ሌሎች ሰዎች [ጥቁር ያልሆኑ ተመራማሪዎች] ይህን ሳያጠኑ እኛ ያጠናነው ለምን እንደሚያስፈልግ ስለሚገባን ነው። አፍሪካውያን 'የፌስ ሪኮግኒሽን' ቴክኖሎጂ እኛ ጋርም ይሰራል ብለው ቢወስዱት አይሰራም። [ጥናቱ] ለራስሽ የሚጠቅም ቴክኖሎጂን ራስሽ መስራት እንዳለብሽ ያሳያል። ወደ አፍሪካ የሚወሰዱ የፈጠራ ሥራዎችን ካነሳሽ አይቀር ሂደቱን እንዴት ታይዋለሽ? ብዙ ቴክኖሎጂ ወደ አፍሪካ ይወሰዳል። አንድ የሰራሁት ጥናት፤ አሜሪካ ውስጥ መኪና ሲሰራ የአደጋ ተጋላጭነትን ለማጥናት የሚውለው አሻንጉሊት ላይ ያተኩራል። የሚጠቀሙት አሻንጉሊት የጎልማሳ ወንድ መልክ [ተክለ ሰውነት] ያለው ነበር። ታዲያ የመኪና አደጋ ሲደርስ ከሚሞቱት አብዛኞቹ ሴቶች ነበሩ። ችግሩ የመጣው አብዛኛው መኪና የተሞከረው ወንድ በሚመስል አሻንጉሊት ስለሆነ ነው። ይሄ ክፍተት የታየው [ክፍተቱ እንዳለ የታወቀው] ከ15 ዓመት በፊት ነበር። ከዛም የሴቶች አይነት መልክ [ተክለ ሰውነት] ያላቸው አሻንጉሊቶች ለሙከራ ይዋሉ የሚል ህግ ወጣ። ብዙ ሴት ኢንጂነሮች [በሙከራው] ቢሳተፉ ኖሮ እነሱን የሚመስል ሰው ላይ የመኪና አደጋ ሲደርስ ምን ይሆናል? ብለው ይጠይቁ ነበር። መኪናው ሲሰራም ለወንዶች አደጋ የማያመጣ ብቻ ሳይሆን፤ ለሴቶችና ለልጆችም የሚሆን ይሆን ነበር። መኪና ሲሞከር እዚህ ሀገር [የምዕራቡ ዓለም ሹፌሮች] እንዴት እንደሚነዱ እየታየ [እየተጠና] ነው። አፍሪካ ውስጥ ግን ዝም ብለን ሌላ ሀገር የተሰራ መኪና እያመጣን እንጠቀማለን። አሁን ደግሞ ራሱን የሚያሽከረክር መኪና እየመጣ ነው። ሌላ ቦታ ተሞክሮ ወደ አፍሪካ ሲመጣ እንዴት እንደሚሰራ አናውቅም። የአፍሪካ መንገድ ላይ እንዴት እንደሚሄድ አይታወቅም። ስለዚህ ሌላ ሰው [ለሌላ ሀገር] የሰራውን ቴክኖሎጂ ማምጣት አደገኛ ይመስለኛል። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚተገበሩ አብዛኞቹ ፈጠራዎችም አገር በቀል አይደሉም። ይሄ በጣም ያሳዝነኛል። በኢትዮጵያ ጠረጴዛ እንኳን ባህላዊ አሰራር አለው። በጥበብ የሚሰራ. . . የሚያምር. . . ጥራት ያለው። ሁሉም ሰው እሱን ትቶ ከውጪ ያስመጣል። ሰው የራሱን ባህል ሳያከብር፤ በራሱ ባህል እንዴት አይነት ጥበብ እንዳለ ሳይስብ፤ ዝም ብሎ ውጪ የተሰራውን ለማምጣት ሲሞክር ለሀገሪቷም ጥሩ አይሆንም። እኛ ምን መስራት እንችላለን? ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል። የኛው ሰው፤ ለኛ የሚሆን ነገር መስራት እንዲችል ማድረግ አለብን። ከውጪ ማምጣት ብቻ ከሆነ፤ ሀገር ውስጥ የሚሰራ አይኖርም። ለሀገሪቷ የሚጠቅማት ነገርም አይመጣም። ትምኒት፣ 'ዳታ አክቲቪስት' (ዲጂታል መረጃን ያማከለ የመብት ተሟጋች) መሆንሽን እንዴት ነው የምትገልጭው? አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የመብት ተሟጋች ብለው የሚያስቡት ፖለቲካ ውስጥ የገባ ሰውን ብቻ ነው። ስለ ቴክኖሎጂ ሲያስቡ ስለ መብት ሙግት አያስቡም። ምክንያቱም ብዙዎች ስለ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንጂ አሰራር አያስቡም። ቴክኖሎጂ ግን ከመብት ሙግት ጋር የተያያዘ ነው። ለአብዛኛው ሰው የማይሰራ ቴክኖሎጂ ከሰራሽ ለሰው የማይሆን ነገር እየሰራሽ ነው ማለት ነው። ኢትዮጵያውያን፣ አፍሪካውያን ሴቶች ለራሳቸው የሚሆን ነገር እንዲሰራ ከፈለጉ ቴክኖሎጂ ውስጥ መግባት እንዳለባቸው እንዲያውቁ እፈልጋለሁ። ኒውስዊክ ላይ ስለ 'ጂኖሚክ ሪቮሊሽን' [የዘር ቅንጣት ጥናት] ዘገባ አንብቤ ነበር። 'ሂውማን ጂኖም' [የሰዎች የዘር ቅንጣት] ጥናት ሲሰራ ከአፍሪካ የተጠቀሙት [የወሰዱት] ናሙና ከአንድ በመቶ በታች ነበር። ነገር ግን ዓለም ላይ ካለው የዘር ቅንጣት በበለጠ በጣም የተሰባጠረው የአፍሪካ ነው። መድሀኒት ሲያጠኑ [ሲሰሩ] በአብዛኛው ጊዜ የአፍሪካውያንን የዘር ቅንጣት አያዩም። ለምሳሌ ለካንሰር መድሀኒት ሲሰራ ያደረጉትን ጥናት [ከአንድ በመቶ በታች ናሙና የተወሰደበትን] ከተከተለ መድሀኒቱ ለአብዛኛው አፍሪካውያን የማይሰራ ነው። ይሄንን እንደ ሰብአዊ መብት ጥሰት ነው የማየው። 'ዳታ አክቲቪዝም' ሳይሆን 'ቴክኖሎጂ አክቲቪዝም' ሲባል እንደዚህ አይነት ነጥቦች ይነሳሉ። ትምኒት ገብሩ በልጅነትሽ ትወጅው የነበረውን ሙዚቃ ገፋሽበት ወይስ. . . በህጻንነቴ ፒያኖ እጫወት ነበር። አሁንም እጫወታለሁ። በሙዚቃ 'ሜጀር' [ዋና ትምህርት] ባላደርግም ትምህርት ቤት እያለሁ የፒያኖ ትምህርት እወስድ ነበር። እለማመድም ነበር። አሁንም ጊዜ ሲኖረኝ እጫወታለሁ። እንደ ድሮው ግን አልዘፍንም. . . ኢትዮጵያ ውስጥ የምታከናውኛቸው ፕሮጀክቶች እንዴት እየሄዱ ነው? ክረምት ላይ 'አዲስ ኮደር' የሚል ስልጠና ነበረን። ጓደኛዬ ጂላኒ ኔልሰን የጀመረው ፕሮጀክት ነበር። መስከረም ላይ ባህር ዳር የአይሲቲ ኮንፈረንስ ነበር። 'ብላክ ኢን ኤአይ' የሚባል ተቋም አለን። ብዙ ጥቁሮች 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ውስጥ አይሳተፉም፤ ቢሳተፉም ሌላው ማህበረሰብ አያያቸውም። ስለዚህ በኮንፈረንሶች ወይም ሌላም ቦታ የመሳተፍ እድል እንዲያገኙ እንሰራለን። ውስጡ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሉ። ታህሳስ ላይ ትልቅ 'የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ኮንፈረንስ አለን። ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚሰሩትን ጥናት ለማቅረብ እንደሚመጡ ተስፋ አደርጋለሁ። 'ብላክ ኢን ኤአይ' የጥቁር ሴቶችን ተሳትፎ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ከማሳደግ አንጻር ያመጣው ለውጥ አለ? ከጀመርነው አንድ ዓመቱ ነው። በአንድ ዓመት ብዙ ለውጥ እንደመጣ አይቻለሁ። «ከዚህ ሙያ ልወጣ ነበር፤ ወደናንተ ተቋም ከመጣሁ በኋላ ግን ጥናት መስራት ጀምሬያለሁ' ብለው ኢሜል ያደርጉልናል። ሥራ ያገኙ፤ ማስተርስና ፒኤችዲ ማጥናት የጀመሩም አሉ። በእኛ ወርክሾፕ ተገናኝተው በጥምረት መስራት የጀመሩም አሉ። 'ዳታ ሳይንስ አፍሪካ' የሚባል የምሥራቅ አፍሪካ ኮንፈረንስ አለ። ብዙ ጊዜ የሚካሄደው ኬንያ፣ ታንዛንያና ዩጋንዳ ነው። በሚቀጥለው ዓመት ግን ወደ ኢትዮጵያ ለመውሰድ እያሰቡ ነው። [ሁለንተናዊ] ለውጥ ለማምጣት ጊዜ ይወስዳል። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኮንፈረንሱ ስሄድ፤ ከ8,500 ሰዎች ስድስት ጥቁሮች ብቻ ነበሩ። አፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካ፣ አሜሪካ. . . እንዳለ ተደምሮ ስድስት ሰው ብቻ! አስቢው? በጣም ትንሽ ሰው ነው። ባለፈው ዓመት ወርክሾፕ ላይ 200 ጥቁሮች ነበሩ። በዚህ ዓመት እስከ 500 ሰዎች እየጠበቅን ነው። ከ8,500 ጋር ሲነጻጸር [ቁጥሩ] ያን ያህል አይደለም። ስለዚህ በጣም ብዙ መስራት አለብን። ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት ወጣቶች በ'አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ'ዘርፍ ጅማሮ እያሳዩ ነው። ሆኖም የጎላ አይደለም። ዘርፉ እንዲጎለብት ምን መደረግ አለበት? ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን [አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ] እየታወቀ የመጣ ይመስለኛል። ችግሩ ኢትዮጰያ ውስጥ ጎበዝ የተባለው ሰው ባጠቃላይ ህክምና ማጥናት ነው የሚፈልገው። ሰዎች ወደ ቴክኖሎጂው እንዲገቡ እድል መስጠት አለብን። የግል የቴክኖሎጂ ድርጅቶች መጀመር አለባቸው። ለምሳሌ ኬንያ ውስጥ ብዙ የቴክኖሎጂ ተቋሞች አሉ። ኢትዮጵያ ውስጥም መጀመር አለበት። እንደ አይስአዲስ ያሉ ድርጅቶች [መኖራቸው] በጣም ነው ደስ የሚለኝ። መንግሥት ራሱ እንደዚህ አይነት ነገር ማበረታታት አለበት። ሰዎች የራሳቸውን [የቴክኖሎጂ] ድርጅት እንዲጀምሩ ወይም ትልልቅ [ዓለም አቀፍ] ድርጅቶች እንዲመጡ መደረግ አለበት። በኢትዮጵያውያን፤ ለኢትዮጵያ የሚሆን ተቋም [ቢበራከት] ጥሩ ነው። መንግሥት ገንዘብ የሚሰጠው የጥናት ተቋም ያስፈልጋል። የዩኒቨርስቲ አስተማሪዎች በደንብ እየተከፈላቸው በትኩረት ጥናት እንዲሰሩ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። ባለፈው ዓመት ባህር ዳር ውስጥ በተካሄደው የአይሲቲ ኮንፈረንስ ለ'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ጊዜ ተሰጥቷል። ዘርፉ መታወቅ እየጀመረ ነው። ግን የተዋቀረ አካሄድ መኖር አለበት። ሁሉም ሰው የሚሳተፍበት እቅድም መኖር አለበት። 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' በአንዳንዶች እይታ የወደፊቱን ዓለም አስፈሪ የሚያደርግ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ዓለምን የተሻለ ለማድረግ ተስፋ የሚጥሉበትም አሉ። እነዚህ ሁለት ጽንፎች ባንቺ እንዴት ይታያሉ? አንዳንዶች ማሽኖች ከሰዎች የበለጠ ሲያውቁ ሰውን ያጠፋሉ ይላሉ። አብዛኛውን ጊዜ እንደዚህ የሚሉ ሰዎች 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ውስጥ የሚሰሩ አይደሉም። ለምሳሌ ኢላን ማስክ እንዲህ ይላል። ግን የ'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ባለሙያ አይደለም። ባለሙያ ያልሆኑ ሰዎች እንዲህ ሲሉ ያናድደኛል። አዲስ ፋሽን ሆኖ መጣ ስለተባለ ብቻ ስለሙያው የሚያወሩ ሰዎችም በጣም ያናድዱኛል። 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' እንደ ሁሉም ቴክኖሎጂ ለጥሩም፤ ለመጥፎም መዋል ይችላል። ለምሳሌ አንድ ድርጅት የአልትራሳውንድ ማሽን ለመግዛት ብዙ ገንዘብ ያወጣል። በስልክ ላይ የሚሰካ በጣም ትንሽ የአልትራሳውንድ መሳሪያ ይህን ይቀርፋል። በሌላ በኩል አሜሪካ ውስጥ ሰው ለመግደል ድሮን ይጠቀማሉ። የዚህ ተቃዋሚ ነኝ። ምክንያቱም ሁሉም ሰው በፍትሀዊ መንገድ ይፈረድበታል እንጂ ዝም ብሎ ሰው መግድል ያለብሽ አይመስለኝም። ይሄ የ'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ችግር ሳይሆን የሰው አመለካከት፣ የፖሊሲ፣ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ጉዳይ ነው። 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' የዛሬ 100፣ 200. . . ዓመት ምን ሚና ይኖረዋል? ለወደፊት ምን አይነት ዓለም ይታይሻል? 200 ዓመት ወደፊት ማየት አልችልም። ቴክኖሎጂ የሚገመት አይደለም። ምን አይነት እድገት እንደሚመጣ አናውቅም። ሌላው ነገር ቆሞ 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ብቻ ካደገ አንድ ነገር ይመጣል። ግን ቴክኖሎጂ ባጠቃላይ አንድ ላይ ነው የሚቀየረው። ለምሳሌ የጂን [የዘር ቅንጣት] ጥናት ብዙ አይነት ነው። ብዙ ነገር ሊቀየር ይችላል። [በሌለ በኩል] 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ሁሉንም የምንሰራውን ሥራ ስለሚሰራ ሰዎች መስራት አይኖርባቸውም። ሰዎች ካልሰሩ እንዴት ገንዘብ ያገኛሉ? 'ዩኒቨርሳል ቤዚክ ኢንካም' [ሁሉን አቀፍ መሰረታዊ ገቢ] መኖር አለበት የሚሉ አሉ። በጣም የሚያሳስበኝ 'ክላይሜት ቼንጅ' [የአየር ንብረት ለውጥ] ነው። በአየር ንብረት ለውጥ ሁላችንም ካልሞትን፣ ካልጠፋን [በአሁኑ እና በወደፊቱ ዓለም መካከል] ይሄን ያህል የተጋነነ የሆነ ልዩነት የሚኖር አይመስለኝም። ቴክኖሎጂ ጥሩ ነገር ይሆናል ብዬ ሳስብ. . . አፍሪካ ውስጥ የድሮን ጥናት የሚሰሩ ጀማሪዎች አሉ። እናም መንገድ ሳያስፈልግ በድሮን መድሃኒት ማዳረስ ይቻል ይሆናል. . . ትልልቅ ሆስፒታል መስራት አያስፈልግ ይሆናል። በትንንሽ መሳሪያ ህክምና መስጠት ይቻልም ይሆናል። ራሳቸውን የሚያሽከረክሩ መኪኖች ሲኖሩ አይነ ስውሮች በራሳቸው መንቀሳቀስ ይችላሉ። ሊሆንም፣ ላይሆንም ይችላል። ግን [ጥያቄው] ሰዎች እንዴት አድርገን ነው [ቴክኖሎጂን] የምንጠቀመው? ብዙ ጦርነት ይኖራል? ኢ-ፍትሀዊነት ይኖራል? በጣም ጥቂት ሰዎች ብዙ ገንዘብ ኖሯቸው ብዙዎች ገንዘብ ከሌላቸው 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ያባብሰዋል። ምን አይነት ፖለቲካዊ ሁኔታ ይኖረናል? ሰዎች እንዴት እብረን እንኖራለን? አካባቢያችንን እንጠብቃለን? [ጥያቄዎቹ ናቸው]። በአየር ንብረት ለውጥ መጀመሪያ የሚጠፉት ደሴቶች ናቸው። ከዛ በኋላ በጣም የሚጎዱት የመሬት ወገብ ላይ ያሉ ሀገሮች ናቸው። የሚጎዱት እንደ ኢትዮጵያና እንደ ኬንያ. . . በአብዛኛው አፍሪካ ውስጥ ያሉት ሀገሮች ናቸው። ስለዚህ ጉዳይ እያሰብን አለመሆኑ ያሳዝነኛል። ቴክኖሎጂን ለምን መጠቀም ነው የምንፈልገው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ከቻልን፤ በ'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ምን አይነት ኑሮ ይኖረናል የሚለውን ጥያቄ መመለስ እንችላለን። ለ'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ'አቻ አማርኛ አግኝተሽለታል? እኔ አላውቅም። ሰለሞን [የ 'ቴክቶክስ' አዘጋጅ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ] ሰው ሰራሽ ክህሎት ይለዋል። ተስማማሽበት? አዎ. . . ሌላ ምን ማለት ይቻላል? ክህሎት፣ ችሎታ ነው። 'ኢንተለጀንስ'ን በአማርኛ ሲተረጎም ግን. . . ለመሆኑ የምትወጂው በዓል የቱ ነው? እ. . . እንቁጣጣሽ እንቁጣጣሽ ከሌላው በዓል በምን ተለየ? ሁሉም ነገር «በዓል ነው» ብሎ ይነግርሻል። አደይ አበባው. . . አየሩ. . . [ዘመን] እየተለወጠ እንደሆነ ይነግርሻል። ሆያ ሆዬ ሲጨፈር ራሱ. . . ጭፈራ ደስ ይለኛል። በዓልን ከኢትዮጵያ ውጪ እንዴት ታሳልፊያለሽ? ከጓደኞቼ ጋር ተገናኝቼ 'ዘኒ' የሚባል የኢትዮጵያ ሬስቶራንት እንሄዳለን። እንበላለን፤ እንጠጣለን። ቡና ማፍላት አልችልም. . . መማር አለብኝ። እና ጓደኞቼ ቡና ያፈላሉ። እናቴና ቤተሰብ ቤት መሄድ ከቻልኩ እሄዳለሁ። እነሱ የሚኖሩት ቦስተን ነው። እናቴ ቆንጆ ላዛኛ ትሰራለች። ቀይ ወጥ፣ ዶሮ ወጥ ሰርታ አብረን እናሳልፋለን። የምትወጂው ምግብና መጠጥ ምንድን ነው? ሽሮ በጥቅል ጎመን እወዳለሁ፤ [እየሳቀች] ሽሮ «የሞጃ ምግብ አይደልም ቢባልም» እወደዋለሁ። ጣፋጭ በተለይም ቸኮሌት እወዳለሁ። ቡና በወተት እወዳለሁ። ሁሌ ጠዋት ስነሳ ቡና በወተት እጠጣለሁ። የምታዘወትሪው የቴሌቭዥን ዝግጅትስ? 'ብሮድ ሲቲ' የተባለውን ተከታታይ ፊልምና 'ደይሊ ሾው ዊዝ ትሬቨር ኖሀ' እወዳቸዋለሁ። ቴክ ቶክና ሄለን ሾው ቃለ መጠይቅ ካደረጉኝ በኋላ እከታተላቸዋለሁ። ያንቺ ምርጡ መጽሐፍ የቱ ነው? ከሥራዬ ጋር የሚገናኙት ላይ አተኩራለሁ። 'ዌፐንስ ኦፍ ማት ዲስታራክሽን' የምወደው መጽሐፍ ነው። የምትወጂው ሙዚቃስ? ከአዲስ አበባ ከመጣሁ በኋላ ሙሉ ቀን የማዳምጠው የሮፍናን አልበምን [ነጸብራቅ] ነው። የምታዘወትሪው ድረ ገጽ አለ? ፌስቡክና ትዊተር እንዳሉ ሆነው፣ 'ስታክ ኦቨር ፍሎ'፣ 'ሬድዮ ላቭ ፖድካስት' እና 'አፍሪካ ኢዝ ኤ ካንትሪ' የተባሉትን እከታተላለሁ። የሚያስደንቅሽ ሳይንሳዊ ፈጠራ ምንድን ነው? [እንደ ሳይንስ ሙያተኛነቷ አንዱን መምረጥ አስቸጋሪ መሆኑን ካስረዳች በኋላ] ቴክኖሎጂ ጥሩ የሚሆነው በሰው አመለካከት ልክ ነው። ለምሳሌ ተንቀሳቃሽ ስልክ በእጅ ተይዞ ስንት ነገር እንደሚሰራ ሲታሰብ ያስደንቃል። የምታደንቂው ሳይንቲስትስ? አብዛኞቹ የማከብራቸው ሳይንቲስቶች ሳይሆኑ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ናቸው። የማደንቃቸው ሰዎች በማህበረሰባቸው ውስጥ ለውጥ ማምጣት የቻሉ ናቸው። ሜሪ ኪዩሪ ሁለት ጊዜ ኖቤል ሽልማት አግኝታለች። መጀመሪያ ለሷ ሊሰጧት አልፈለጉም። ለባሏ መስጠት ነበር የፈለጉት። ባሏ ግን ከሷ ጋር ካልተካፈልኩኝ መውሰድ አልፈልግም አለ። መጀመሪያ የተመራመረችው እሷ እንደሆነች ያውቅ ነበር። ወንዶች ለሴቶች መታገል አለባቸው። ሴቶች ብቻችንን ይህንን ትግል ማሸነፍ አንችልም። በሳይንስ ውስጥ አሁን ያለውን ኢ-ፍትሀዊነት ሳስብ፤ በሷ ጊዜ ደግሞ ምን [ያህል ከባድ] ነበር ብዬ አስባለሁ። በዚያ መድልዎ ሁለት ኖቤል ሽልማት ማግኘቷ ያስገርመኛል። የምትወጂው አባባል አለ? አለ፤ 'just do it'! በአማርኛ ሲተረጎም 'ይቻላል' ቢባልም እንደ እንግሊዘኛው አይሆንም። ሰዎች አስሬ እንዲህ ባረግ ከማለት ማድረግ አለባቸው። ሰዎች አቅማቸውን አያውቁም። የይቻላል መንፈስ ካላቸው ግን ያደርጉታል። ምን አይነት አለባበስ ያስደስትሻል? ሽሮ ሜዳ የሚሸጡትን ምቹ የሀበሻ ልብሶች እወዳቸዋለሁ። ከጎበኘሻቸው ቦታዎች የማትረሽው የቱን ነው? የኬንያን ላሙ አልረሳውም። ቦታው የሚያምር፣ ሰዎቹም ደስ የሚሉ ናቸው። ኩባም የማይረሳኝ ቦታ ነው። ለወደፊትስ የት መሄድ ትፈልጊያለሽ? ሞዛምቢክ፣ ባህር ዳርቻ። የትምኒት መደበኛ ቀን ምን ይመስላል? [እየሳቀች] እንቅልፍ እወዳለሁ። ከስምንት እስከ አስር ሰአት በደንብ እተኛለሁ. . . ስነሳ ቡና በወተት እጠጣለሁ. . . ውሾች እመግባለሁ. . . ኢሜል አደርጋለሁ. . . ጠዋት ላይ አነባለሁ፣ ሙያውም ብዙ ማንበብ ስለሚጠይቅ ጥናትና ምርምሮች አነባለሁ. . . እሮጣለሁ. . . ዮጋ እሰራለሁ. . . ከጓደኖቼ ጋር ምሳ እበላለሁ. . . [እየሳቀች] ጊዜ ማጥፋት በደንብ እችላሉ. . . ዘፈን እየሰማሁ፣ ልብስ እያጠብኩ ሶስት አራት ሰአት ይሄዳል። ከዛ እራት ይበላል. . .
news-49506683
https://www.bbc.com/amharic/news-49506683
"ቁጥራችን ትንሽ ስለሆን ነው መሰል፤ ትዝም አንላቸው" የኢትዮጵያ ዐይነ ሥውራን ማኅበር
ባሳለፍነው ሰኞ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ገደማ የ26 ዓመቱ ዐይነስውር ለጉዳይ ባቀናበት አቃቂ ክፍለ ከተማ የአሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ሕይወቱ ማለፉን የኢትዮጵያ ዐይነ ሥውራን ብሔራዊ ማህበር የህዝብ ግንኙነትና የቅርንጫፎች ኃላፊ አቶ ገብሬ ተሾመ ለቢቢሲ ገለፁ።
• በንቅለ ተከላ ዕይታው የተመለሰለት ኢትዮጵያዊ ታዳጊ • ዓይናሞችን ዓይነ ስውር የሚያደርገው እራት በአደጋው ሕይወቱ ያለፈው ድረስ ሁናቸው በብሔራዊ ዐይነ ሥውራን ማህበር ሥር በሚተዳደረው የወላይታ ዐይነ ሥውራን ትምህርት ቤት ትምህርቱን ተከታትሏል። በዘንድሮ ዓመትም በኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በመምህራን ማሰልጠኛ ፕሮግራም በዲፕሎማ ተመርቋል። ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ ከሌሎች ተመራቂዎች ጋር ሥልጠና ወስደው የሥራ ቦታ ለመመደብ እጣ ይወጣላቸዋል። እጣው ሲወጣም ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ይደርሰዋል። የተመደበበት ክፍለ ከተማ ከሚኖርበት አቃቂ ክፍለ ከተማ ስለሚርቅ ወደተመደበበት ክፍለ ከተማ ሄዶ እንዲቀይሩት ጥያቄ ያቀርባል። እዚያም አቃቂ ክፍለ ከተማን እንዲጠይቅ ስለነገሩት ወደ ክፍለ ከተማው ያቀናል። ጥያቄውን ለማቅረብ ወዳቀናበት አቃቂ ክፍለ ከተማ 7ኛ ፎቅ ደርሶ ወደ ታች ለመውረድ የአሳንሰሩን ቁልፍ ይጫነዋል። ተከፈተለት። አሳንሰሩ ግን ወለል አልነበረውም፤ 21 ሜትር በሚገመተው የአሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ተምዘግዝጎ ወድቆ ይህንን ዓለም ተሰናበተ። አቶ ገብሬ እንደሚሉት እስካሁን ለማህበሩ ከደረሱት የሞትና የአካል ጉዳት ሪፖርቶች በአሳንሰር ምክንያት የሞት አደጋ ሲያጋጥም ይህ የመጀመሪያው ነው። "አሁን የተፈጠረው አደጋ እንኳንስ ለዐይነ ሥውር ለዐይናማም ቢሆን እጅግ አደገኛ ነው" የሚሉት አቶ ገብሬ በኮንስትራክሽን ሕግ መሠረት በ2001 ዓ.ም በወጣ የህንፃ ኮድ ላይ ያለውን ደንብና መመሪያ ያጣቅሳሉ። በመመሪያው ላይ አሳንሰሮች ከውጭም ሆነ ከውስጥ የብሬል ፅሁፍ እንዲኖራቸው እንዲሁም ድምፅ እንዲኖራቸው ይደነግጋል፤ ነገርግን ሃገር ውስጥ የሚገጣጠሙ አሳንሰሮች ይህንን የሚያሟሉ አይደሉም ሲሉ ይኮንናሉ። "ከውጭ የሚመጡት አሳንሰሮች ብሬል ተገጥሞላቸው ይመጣሉ፤ ድምፅም አላቸው፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ድምፁን ስለማይከፍቱት አይሰሩም" ይላሉ። በትክክል አገልግሎት የሚሰጡትም በጣም ጥቂቶች እንደሆኑ የታዘቡትን አጋርተውናል። • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" • የምልክት ቋንቋ በብዛት የሚነገርባት መንደር ምንም እንኳን እርሳቸው ያለ ረዳት ብዙ ጊዜ አሳንሰር ውስጥ የመግባት ልምድ ባይኖራቸውም የገጠማቸው አለ። "አሳንሰር ውስጥ ገብቼ የነካኋቸው አብዛኞቹ ቁልፎች አይሰሩም ነበር። የሚሰሩት 9ኛ ፎቅና ምድር ላይ ያለው ብቻ ነበር የሚሰራው፤ እኔ መሄድ የፈለኩት ደግሞ 5ኛ ፎቅ፤ ከላይ ታች ስል በኋላ ላይ በሰዎች እርዳታ ወጣሁ" ሲሉ ሲንገላቱ የዋሉበትን ቀን ያስታውሳሉ። ከዚህ ቀደምም ዐይነ ሥውራን በመንገድ መቆፋፈር፣ በመኪና አደጋ፣ ከድልድይና ፎቅ ላይ በመውደቅ አደጋ ለሞትና አካል ጉዳት መዳረጋቸውን ይናገራሉ። በአንድ ወቅት አንድ ዐይነ ስውር የውጭው በረንዳ [ከለላ] ከሌለው የትምህርት ቤት ህንፃ ወድቆ ከባድ አካል ጉዳት እንደደረሰበት ያነሳሉ። ከድልድይ ላይም እንዲሁ ከለላ ባለመኖሩ የአንድ አባት ሕይወት ሲያልፍ በቅርብ ጊዜም የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪ ውሃ ቀድታ ስትመለስ ከድልድይ ላይ ወድቃ ሕይወቷ እንዳለፈ ይናገራሉ። "ቁጥራችን ትንሽ ስለሆነ ነው መሰል ትዝ አንላቸውም" የሚሉት አቶ ገብሬ አካል ጉዳትን በተመለከተ 'ደረጃው ይለያያል እንጂ ያልተነካ አለ' ለማለት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ። ከአባላቶቻቸው በጥቆማ ያገኙትንና ሰኞ እለት ያጋጠመው ይህን አደጋ በተመለከተ ማህበሩ የተለያዩ መረጃዎች እያሰባሰበና የሚመለከተውን አካል ለማነጋገር ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። አደጋው በርካቶችን አስቆጥቷል። የህግ ባለሙያዋና የአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋቿ ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴም በፌስቡክ እንዲሁም በትዊተር ገጿ ላይ ቁጣዋን አስፍራለች። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ተስፋየ ወሰንየለህ አደጋው ሰኞ ጠዋት ከ 3፡00-4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ እንዳጋጠመ ገልፀውልናል። ተመራቂው ዐይነ ሥውር የሥራ ምደባ ቦታውን ለማስለወጥ በክፍለ ከተማው ውስጥ ትምህርት ቢሮ አምርቶ እንደነበርም ያረጋግጣሉ። "ከ7ኛ ፎቅ ወደ 3ኛ ፎቅ ለመውረድ በሚሞክርበት ሰዓት ነው የወደቀው" የሚሉት ኃላፊው ከነበረበት 7ኛ ፎቅ ወደ 3ኛ ፎቅ ስለተነገረው ወደዚያ ለመሄድ በሚሞክርበት ጊዜ አደጋው እንደደረሰበት ያስረዳሉ። ኮማንደሩ እንደሚሉት አሳንሰሩን ሌሎች ሰዎች እየተገለገሉበት ስለነበር በእንቅስቃሴ ላይ ነበር። ይሁን እንጂ ግለሰቡ አሳንሰሩ የቆመ መስሎት በሩን ከፈተው። አሳንሰሩ በእንቅስቃሴ ላይ ስለነበር እርሱ ያለበት ቦታ ላይ የአሳንሰሩ ወለል አልነበረምና ጉድጓዱ ውስጥ እንደገባ ያብራራሉ። የክፍለ ከተማው ህንፃ በዚህ ዓመት አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን አሳንሰሩ ብዙ ጊዜ ብልሽት እንደሚያጋጥመው ለቢቢሲ ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ኮማንደሩ አክለዋል።
news-55984275
https://www.bbc.com/amharic/news-55984275
ትግራይ፡ በአንዲት ሴት የስልክ ጥሪ ለመጀመሪያው ግጭት የተቀሰቀሰችው ከተማ -ቅራቅር
በፌደራል መንግሥቱና የትግራይን ክልል ያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባት እየተባባሰ ጥቅምት 24 2013 ዓ.ም ላይ ወደ ወታደራዊ ግጭት ሲሸጋገር ቀዳሚ የውጊያ ቦታዎች የነበሩት ቅራቅርና ዳንሻ የተባሉት በአማራና ትግራይ ክልሎች መካከል የሚገኙት አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ነበር።
በፌደራል መንግሥቱ እና ትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር የነበረው ህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ግጭት ያመራው ጥቅምት 24 2013 ምሽት የሕወሃት ኃይሎች የሰሜን እዝን ማጥቃታቸው ከተገለፀ በኋላ ነው። ቀዳሚው ወታደራዊ ግጭት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጠገዴ ወረዳ፣ ቅራቅር ከተማ ነበር የተከሰተው። ግጭቱ በተቀሰቀሰ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በክልሉ የነበረ የስልክ ግንኙነት የተቋረጠ ሲሆን ለተወሰኑ ሳምንታት ከገለልተኛ ወገኖች ስለግጭቱ መረጃ ማግኘት ፈተና ሆኖ ቆይቷል። በወቅቱ ከትግራይ ልዩ ኃይል በኩል ወደ ቅራቅር የሚደረግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ መኖሩን የአካባቢው ጸጥታ ኃይል የተገነዘበው "በአንዲት ስልክ ጥሪ" ሰበብ መሆኑን የቅራቅር የፖሊስ አባላት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ድንገተኛዋ የስልክ ጥሪ ጠገዴ ወረዳ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኝ ሲሆን ከተማው ቅራቅር ትባላለች። ከዚህ ወረዳ ቀጥሎ ደግሞ በትግራይ ክልል ስር ይተዳደር የነበረው ጸገዴ ወረዳ ይገኛል። ከተማውም ከተማ ንጉሥ ወይም ማክሰኞ ገበያ ይባላል። ነዋሪዎች እንደሚሉት የቅራቅር ከተማ የትግራይና የአማራ ክልል የሚዋሰኑበት ስትሆን የሁለቱም ክልሎች የልዩ ኃይል ፖሊሶቻቸውን በከተማዋ አቅራቢያ ወደ ድንበር ላይ አስጠግተው ለብዙ ጊዜ አቆይተዋል። ረዳት ኢንስፔክተር አሸብር ሲሳይ በትግራይ ክልል ውስጥ ይተዳደር በነበረው ጸገዴ ወረዳ ውስጥ የከተማ ንጉሥ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ነበር። ለ15 ዓመታት በፖሊስነት ካገለገለ በኋላ በነበረው ሁኔታ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ ባለቤቱንና ልጆቹን ትቶ ወደ አማራ ክልል ማምራቱን ይናገራል። ከዚያ በኋላ ኑሮውን በአጎራባቿ የአማራ ክልል ጠገዴ ወረዳ አደረገ። እዚያም ረዳት ኢንስፔክተር አሸብር በሙያው በወረዳው ፖሊስ ውስጥ የወንጀል መርማሪ በመሆን መሥራት ሲጀምር ቤቱን እሱ ወዳለበት ወደ ቅራቅር ከተማ እንዲመጡ አድርጎ ኑሮውን መምራት ቀጠለ። በዚህ ሁኔታ ባለቤቱ ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ በተለያዩ ጊዜያት ትግራይ ክልል ውስጥ ወደሚገኘውና የትውልድ ቦታዋ ወደ ሆነው ጸገዴ ወረዳ ንጉሥ ከተማ ታመራ ነበር። በጥቅምት አጋማሽ ላይም ባለቤቱ እህቷ በጸና ስለታመመች ለመጠየቅ ከሄደች ከቀናት በኋላ ያልጠበቀችው ነገር ተከሰተ። ማክሰኞ ምሽት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም። እርሷ በእንግድነት በተገኘችበት አካባቢና በአቅራቢያው ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ ድንገተኛ የተኩስ ልውውጥ መከፈቱን ታስታውሳለች። ተኩሱ ከባድም፣ ያልተጠበቀም ስለነበር ሁሉም ሰው እጅጉን ደንግጦ ነበር። እሷም በዚህ ድንጋጤ ውስጥ ሆና ለባለቤቷ ደወለች። "እዚህ በሚገኙ የመከላካያ ካምፖች ላይ ጦርነት ተከፍቷል። በዳንሻ በኩልም ተኩስ መጀመሩን ሰምተናል፤ እባካችሁ ራሳችሁን ጠብቁ" የሚል መልዕክት ከምሽቱ 5፡30 አካባቢ ከባለቤቱ መቀበሉን ኢንስፔክተር አሸብር ያስታውሳል። ይህች የስልክ በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት ስለመጀመሩ ለቅራቅር ከተማ ነዋሪዎች ያስታወቀች የመጀመሪያዋ ጥሪ ነች። ከእንቅልፉ ተነስቶ በሚስቱ በኩል ግጭት መጀመሩን የሰማው ኢንስፔክተር አሸብር፣ ቀጣዩ ሥራው ይመለከታቸዋል ለሚላቸው አካላት ክስተቱን መንገር ሆነ። "በዚህም ምክንያት ወዲያውኑ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ እና ለአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ደውዬ ሁኔታውን አሳወቅኩ" በማለት የነበረውን ሁኔታ ያብራራል። ተጨማሪ ማረጋገጫ ፍለጋ አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ የጠገዴ ወረዳ አስተዳዳሪ ናቸው። በአካባቢያቸው የሚያዩት ሁኔታ አስጊ እንደሆነ ቢገምቱም ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም ግን ያልጠበቁት ሁኔታ መከሰቱን ያስታውሳሉ። በወቅቱ ከጠኑበት ተቀስቅሰው ጦርነት መጀመሩን ሲሰሙ፣ ከተጨማሪ ሰው ስለክስተቱ ለማረጋገጥ መረጃው ይኖረዋል ብለው ከሚያምኑት ሰው ደውለው ማጣራት ነበረባቸው። ይህንን ያረጋግጡልኛል ብለው ያሰቡት ደግሞ በምዕራብ ዕዝ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ሙሉዓለም አድማሱን ነበር። ጄነራሉም "ነገሮች ተበላሽተዋል፤ እናንተም ላይ ጥቃት ሊፈጸምባችሁ ስለሚችል ራሳችሁን ተከላከሉ" የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ይናገራሉ። ወዲያውም "በየቤቱ ያረፈውን የአካባቢውን ሚሊሻና ታጣቂ ቤት ለቤት እየሄዱ እንዲቀሰቅሱ ለአባላቶቻቸው ትእዛዝ ሰጥተው፣ እየመጣ የነበረውን ጥቃት ለመከላከል ቦታ ቦታ ማስያዝና ማሰማራት እንዲሁም ተጨማሪ ኃይል ከአጎራባች ወረዳዎች ለማምጣት ጥረት ተደረገ" ሲሉ አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። የጠገዴ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጀምበሩ ሙሉ፣ ከኢንስፔክተር አሸብር ባለቤት የደረሳቸው የስልክ ጥሪ አስቀድሞ "ኃይል ለማደራጀት ጠቅሞናል" ሲሉ ይናገራሉ። የባልደረባቸው ሚስት ስልክ ባትደውል ኖሮ "ውጤቱ ሊቀየር ይችል ነበር" ያሉት ዋና ኢንስፔክተር ጀምበሩ፣ ከስልክ ልውውጡ በኋላ በአካባቢው ያለውን ኃይል ለመከላከል ማዘጋጀት እንደቻሉ ያስታውሳሉ። ቀራቅርን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተደረገ ውጊያ ከእኩለ ሌሊቱ በኋላ በከተማዋ አንድ ወገን ተጀመረ የሚሉት ተኩስ ለሁለት ሰዓታት ያህል የቆየ ነበር። ከሌሊቱ 9፡30 አካባቢ ሲሆን ከከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኘው የቅራቅር ትምህርት ቤት አካባቢ ዋናው ጦርነት እንደተጀመረ በወቅቱ የአማራ ልዩ ኃይልን ይመሩ ከነበሩት አዛዦች መካከል አንዱ ዋና ሳጅን ማናለኝ ወርቄ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እናም "ከሌሊቱ 9፡30 ሲሆን ለጥቃት የመጣው ኃይል ካሉበት አካባቢ የውሻ ድምጽ ሰማን፤ ያ የውሻ ጩኸት ወደ እኛ እየመጡ መሆናቸውን አመላካች ነበር" ያሉት ዋና ሳጅን ማናለኝ፣ ወዲያውኑ ኃይላቸው እንዲዘጋጅ ማዘዛቸውን ያስታውሳሉ። በጠገዴ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የስምሪት ኃላፊ የሆኑት አስር አለቃ ዋኘው፣ እንዳሉት ከዚያ በኋላ ውጊያው ለረጅም ሰዓታት መቀጠሉን ያስታውሳሉ። "በጦር ዝግጅት የተሻሉ ቢሆኑም ቀድመን ቦታ ይዘን ስለነበር ለመከላከል አልተቸገርንም። ቅራቅር በወታደራዊ አተያይ ገዢ መሬት ስለሆነች፣ የቡድን መሣሪያ ለማስቀመጥ ሲባል ቀድመው ለመያዝ አቅደው ነበር" ብለዋል። አካባቢው ኃይል ከአቅራቢያ ከተሞች በመጡ ታጣቂዎች እየታገዘ "ያለምግብና ውሃ" ለሰዓታት ከተማዋ እንዳትያዝ ውጊያው መቀጠሉን ያስታውሳሉ። ጥቅምት 24/2013 ከምሽቱ 5፡30 ላይ በረዳት ኢንስፔክተር አሸብር ባለቤት የተደረገችው የስልክ ጥሪ ስልክ በኋላ የተጀመረው ግጭት፣ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት 30 ቀጥሎ አካባቢውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል። ሕይወት እንደቀድሞው በተከታዩ ቀንም ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ከተማ ንጉሥን በመያዝ ወደ ሌሎች አካባቢዎች መሰማራታቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖሊስ አባላት ይናገራሉ። ከዚህ በኋላ በትግራይ ኃይሎች በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት መካከል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ፣ ውጊያው በሌሎች አካባቢዎች ቀጥሏል። ምንም እንኳን ቅራቅር የመጀመሪያው ግጭት ቢካሄድባትም ከአንድ ቀን በኋላ ህይወት እንደ ቀድሞው እንደቀጠለ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በፌደራሉ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ከተገለፀ በኋላበኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የአገሪቱ ሠራዊት እርምጃ እንዲወስድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ለሳምንታት የቆየ ወታደራዊ ግጭት ተካሂዷል። መንግሥት "ሕግን ማስከበር" ያለው ወታደራዊ ዘመቻም በሦስተኛ ሳምንቱ የትግራይ ክልል ዋና ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ ማብቃቱ ቢነገርም የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ ሌሎች የረድዔት ድርጅቶች ውጊያው ቀጥሏል በማለት ሪፖርት አውጥተዋል። የፌደራል መንግሥት በበኩሉ በአሁኑ ጊዜም በሕግ ተፈላጊ ናቸው የተባሉ የህወሓት አመራሮችን ለመያዝ ክትትል እተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
news-44883441
https://www.bbc.com/amharic/news-44883441
ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች
የውጭ ምንዛሬ ችግር ያጋጠማት ኢትዮጵያ ለአንድ ዓመት የሚያስፈልጋትን ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረቧን የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋን በመጥቀስ ሮይተርስ ዘገበ።
"ነዳጅ ለማስገባት እየተነጋገርን ነው። ዝርዝሮቹ ገና አላለቁም። በፕሮግራም የተያዘና መደበኛ የነዳጅ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ነው" ማለታቸውን ዘገባው ያመለክታል። • ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ? • ጠቅላይ ሚኒስትር • የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች በዶላር እጥረትና የመንገድ መሠረተ-ልማት ችግር ምክንያት እስከ 1 ነጥብ 6 ሚልዮን ቶን የሚገመት ንብረት በጂቡቱ ወደብ ተከማችቶ እንደሚገኝ ዘገባው ጨምሮ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር ውስጥ እንደምትገኝ በመግለጽ ሰሞኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የውጭ ሃገር ገንዘብ በእጃቸው የሚገኝ ዜጎች በባንኮች እንዲመነዝሩ ጥሪ ማቅረባቸው ኣስታውሷል።
49594627
https://www.bbc.com/amharic/49594627
ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ
ዲያቆን ፈንታ ታደሠ ወደ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት በየቀኑ ያቀናሉ።
ይህ ግን ለሃይማኖታዊ አገልግሎት ብቻ አይደለም። ከአገልግሎቱ ጎን ለጎን ቅርሱን እያስጎበኙ ኑሯቸውን ስለሚመሩ ጭምርም ነው። የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት በ12ኛው ክፍለ ዘመን ከአንድ አለት ተፈልፍለው የተሠሩ ናቸው። በቁጥር 11 የሆኑት አብያተ ክርስቲያናት፤ በ1970 ዓ. ም. በዓለም አቀፉ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ተብለው ተመዝግበዋል። ዲያቆን ፈንታ እነዚህን ድንቅ ቅርሶች ሲያስጎበኙ ከጊዜ ወደ ጊዜ አደጋ ላይ እየወደቁ መሆኑን መገንዘብ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል። "ዕድሜ ተጨምሮበት፣ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያትም እየተጎዱ ነው" ይላሉ። • ከላሊባላ ጥገና ጀርባ ያለው ማን ነው ? በዚህ ሀሳብ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ጽጌሥላሴ መዝገቡም ይስማማሉ። "ከ800 ዓመት በላይ ዕድሜ በማስቆጠራቸው እርጅና ይታይባቸዋል። አልፎ አልፎም ተሰነጣጥቀዋል። ችግሮቹ ሁለት ናቸው። አንዱ በእድሜ ምክንያት የደረሰባቸው ጫና ሲሆን ሁለተኛው ሰው ሠራሽ ጉዳት ነው" ይላሉ። ችግሮቹን ለመቅረፍ ሲባል በተለያዩ ወቅቶች የጥገና ሥራዎች ተከናውነዋል። "የተለያዩ ባለሙያዎች ሊጠገኑት ሞክረዋል። በግብጻዊያን እና በጣልያናዊያን መሃንዲሶች የተሠሩ ሥራዎች አሉ። አንዳንዶቹ ጥሩ ሲሆኑ፤ ሌሎቹ ደግሞ ችግሮቹን ያባባሱ ናቸው" ሲሉ አባ ጽጌሥላሴ ያስረዳሉ። ቤተ ገብርኤል የተሻለ እድሳት እንዳገኘ የሚገልጹት ዲያቆን ፈንታ፤ በዕድሳቱ ምክንያት ተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው አብያተ ክርስትያናት መኖራቸውንም ይጠቁማሉ። • አሜሪካ ለላሊበላ ቤተክርስትያን ጥበቃ ፕሮጀክት 13.7 ሚሊዮን ብር ሰጠች ቤተ አማኑኤል የተቀባው ቀለም ከፍተኛ ሽታ በማምጣቱ፤ ቀለሙን ፍቆ ለማስለቀቅ የተደረገው ሙከራ የህንጻው ግድግዳ ላይ ጉዳት አድርሷል። ቤተ ጎልጎታ ደግሞ፤ የዝናብ ውሃ ለማውረድ ጣራው ላይ በተለያዩ አቅጣጫዎች ቦይ መሳይ ማፍሰሻ ቢሠራለትም፤ በአራት በኩል ተሰባስቦ የሚወርደው ውሃ ታችኛውን የቅርሱን አካል በመቦርቦር ላይ ይገኛል። እሳቸው እንደሚሉት፤ ከዚህ ሁሉ በላይ አሳሳቢ የሆነው የአብያተ ክርስትያናቱ መጠለያ ነው። በ2000 ዓ. ም. አብያተ ክርስትያናቱን ከአደጋ ለመከላከል ሲባል መጠለያ እንዲሠራላቸው ተደርጎ ነበር። ይህ መጠለያ ደግሞ ቅርሶቹ ላይ ጫና በማሳደሩ የብዙዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል። "እነዚህ ቅርሶች ህልውናችን ናቸው" የሚሉት የላሊበላ ከተማ ነዋሪው አቶ ተገኘ ዋሲሁን፤ "ቅርሶቹ ለእኛ ሃብታችን እና ህልውናችን ናቸው። ሰማያዊ ስጦታ፤ ምድራዊ ርስታችን ናቸው። በተወሰነ የጊዜ ገደብ ለቅርሱ ተብሎ መጠለያ ቢሠራለትም፤ እስካሁን ባለመነሳቱ ለከፋ አደጋ ሊያደርሰው ይችላል" ሲሉ ስጋታቸውን ለቢቢሲ አስርድተዋል። • ያልታበሰው የላሊበላ እንባ ሌላው የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ ቀለሙ ገላው በበኩላቸው፤ "የተሰቀለው ብረት ካለው ክብደት እንጻር ስጋት ደቅኗል። በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ምላሽ አላገኘም" ይላሉ። እሳቸው እንደሚሉት፤ ከብረት የተሠራው መጠለያ በአምስት ዓመት ውስጥ ይነሳል ቢባልም ለ12 ዓመታት ያህል አልተነሳም። "ብረቱ ካለመነሳቱ በተጨማሪ ብረቱ ያረፈበት ከቤተክርስትያናቱ መሠረት ጋር ተመሳሳይ መሆኑም ስጋት ፈጥሯል" ይላሉ። ዲያቆን ፈንታ በበኩላቸው ብረቱ ላይ ፍተሻ እንዳልተደረገ ይናገራሉ። እሳቸው እንደሚሉት፤ ከ10 ሜትር በላይ የሚረዝመው ብረት የቆመው ከህንጻው በላይ ነው። ለምሶሶነት የሚያገለግለው ብረት መሬት ውስጥ ተቆፍሮ የተቀበረ መሠረት የለውም። ስለዚህም ብረቱ ቢንቀሳቀስ ቅርሱ ላይ ቢወድቅ ይችላል። "ዓለም ሁለተኛ ሊሠራው ይቅርና እንዲህ ተብሎ ተሠራ ለማለት የሚከብደውን ቅርስ አደጋ ላይ ጥሏል" ይላሉ። በተለይ ቤተ አማኑኤል ላይ ያለው መጠለያ፤ ሸራው በስብሶ፣ ቀዳዳ በመፍጠሩ ዝናብ ሰርጎ እየገባ ቅርሱ ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። "ቤተ መስቀል መሃል ለመሃል ተሰንጥቋል። ቤተ መድኃኒዓለም ጣርያው አፈር ብቻ ሆኗል። ውስጡ ላይም ጉዳት አድርሶበታል" ይላሉ ዲያቆን ፈንታ ስለችግሩ ሲያስረዱ። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? በዚህ ሐሳብ አባ ጽጌሥላሴም ይስማማሉ። አሁን ያለው መጠለያ ለአራተኛ ጊዜ የተቀየረ መሆኑን ይናገራሉ። "የብረቱ እግር የቆመው ዋሻ ወይም ቤተ መቅደስ ላይ ነው። መጠለያው ሲሠራ የነበረው የንፋስ መጠን አሁን በእጥፍ ጨምሯል። ንፋስ ሲኖር ብረቱ ይንቀሳቀሳል። ከባድ ንፋስ ቢመጣና ብረቱ ቢወድቅ ቤተክርስትያኑን ያፈርሰዋል። እግሩ ቢሰምጥም ከስር ያለው መቅደስ ላይ ሊወድቅ ይችላል" ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። የአማራ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ግዛት አብዩ፤ "ከዕድሜ እና ከአያያዝ ጋር በተያያዘ ጉዳት እየደረሰ በመሆኑ ጊዜያዊ መፍትሔ ሲሰጥ ነበር። አሁን ሲባባስ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል" ብለዋል። ጉዳዩ ይበልጥ ትኩረት እንዲያገኝ መስከረም 27፣ 2011 ዓ. ም. ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጎ ነበር። ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ልዑካንም ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ሄደው አቤት ብለዋል። ችግሩን ቦታው ድረስ በመሄድ የተመለከቱት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ፤ ጉዳዩን ለፈረንሳይ መንግሥት አቅርበው ድጋፍ በጠየቁት መሠረት አዎንታዊ ምላሽ አግኝተዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንም ቅርሱን ጎብኝተዋል። በጎ ምላሽም ሰጥተዋል። "የፈረንሳይ መንግሥት ለቅርሱ ጥበቃ አድርገው መሥራት እንደሚችሉ ቃል ገብተዋል። ሙሉ ለሙሉ የፈረንሳይ መንግሥት የሚሰራው ሲሆን፤ የአገር ውስጥ እና የፈረንሳይ ባለሙያዎችን ያካተተ የቴክኒክ ቡድን ኮሚቴ ተዋቅሯል" ብለዋል አቶ ግዛት። አባ ጽጌሥላሴ ከዚያ በኋላ ተስፋ እንዳላቸው ይናገራሉ። "ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴ አለ። የተለያዩ ባለሙያዎች ተካተውበታል። ከመስከረም ጀምሮ ጥናቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል። እኛም ጥገና ይካሄዳል የሚል ተስፋ ነው ያለን" ብለዋል። ለሥራው የፈረንሳይ መንግስት ከአንድ ሚሊዮን ዩሮ በላይ መድቧል። አቶ ግዛት አብዩ፤ ከመስከረም ጀምሮ የቴክኒክ ሥራ እንደሚጀመር፣ የአማራ ክልልን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ገንዘብ በመመደብ ከቅርሱ ውጭ ያሉ ነገሮች እንደሚሠሩም ገልጸዋል። ዲያቆን ፈንታ እንደሚሉት፤ እንደ ላሊበላ አይነት ቅርስ ባለመኖሩ ባለሙያዎች ቅርሱን ለመጠገን ሲቸገሩ ይስተዋላል። "ቅርሱ ከምድር ውስጥ አለት ተፈልፍሎ ዓለም ከሚሠራው ጥበብ በተለየ ነው የተሠራው። ይህን ለመጠገን ባለሙያዎች ሲጨነቁ እናያለን። ጥበቡን ግለጽላቸው ነው የምንለው። እንደዚህ ዓይነት ሥራ በሌላው ዓለም ስለሌለ አንዳንዶቹ ቅርሶቹን መሞከሪያ ነው የሚያደርጓቸው። አንዱ መጥቶ ሠርቶ ይሄዳል፤ ሌላው መጥቶ ትክክል አይደለም በሚል ያንን ያነሳል፤ የራሱን ይቀይራል። በዚህ መልኩ በአብዛኛው ሰው ሠራሽ ችግር ነው የጎዳው" ይላሉ። • "የዘረፉትን ቅርስ በውሰት እንመልስ ማለታቸው ተገቢ አይደለም" ሚኒስትር ሂሩት ካሳው አባ ጽጌሥላሴ እንደሚሉት፤ በቤተ መድኃኒዓለም እና በቤተ አማኑኤል ትልቁ ጉዳት አንዱ ባለሙያ መጥቶ የሠራውን ሌላው መጥቶ በመዶሻ እና መቆርቆሪያ ማንሳቱ ነው። አቶ ግዛት እንደሚናገሩት፤ ቅርሶቹ ላይ መጠለያው ስጋት ቢደቅንም፤ ማንሳቱ የሚወስነው በባለሙያዎች የተቋቋመው የቴክኒክ ቡድን ነው። "ጉዳት የማያደርስ ከሆነ ይቆያል። የሚጎዳ ከሆነ ደግሞ ያነሳል" ሲሉ ያስረዳሉ። ዲያቆን ፈንታ "ባይናገር እንኳን እንደ መምህር የሚያስተምር፣ እንደዳቦ እየተቆረሰ የተሠራ፣ በዚህ ዘመን ማንም ሰው ሊሠራው የማይችል ድንቅ ጥበብ በመሆኑ፤ እንጠግናለን ተብሎ የተጀመረው ሃሳብ በአጭር ጊዜ ውስጥ መከናወን አለበት። አንዴ ከፈረሰ ከሃዘን ውጭ የሚጠቅመን ነገር የለም" ይላሉ ። የዲያቆን ፈንታ ሕልም ሁለት ነው። አንድም ጥንታዊ የሆነውን ቅርስ መጠበቅ። በሌላ በኩል ደግሞ ቅርሱን በማስጎብኘት የሚያገኙትን ጥቅም ማስቀጠል።
news-42532609
https://www.bbc.com/amharic/news-42532609
አንዳንድ ነጥቦች በሥራ አስፈፃሚው መግለጫ ዙሪያ
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ቁልፍ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ በስፋት ስለተነገረ ሁሉም ውጤቱን ሲጠብቅ ነበር። ስብሰባው ከሁለት ሳምንታት በላይ በዝግ ሲካሄድ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ 2500 በሚጠጉ ቃላት የተዘጋጀ ሰፊ መግለጫ አውጥቷል።
የሥራ አስፈፃሚው መግለጫ በዋናነት ሕዝብን የሚያውኩ እንቅስቃሴዎችን መቆጣጠር፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን መመለስ፣ አባል ድርጅቶች ግልፅነትና ተጠያቂነትን እንዲያሰፍኑ ማድረግ፣ በመንግሥታዊ አገልግሎት ላይ ለውጥ ማምጣት፣ ሕዝብን፣ ምሁራንን እነዲሁም የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማሳተፍ፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ማስከበርን የመሳሰሉ ሰፊ ጉዳዮችን አካቷል። መግለጫው ከወጣ በኋላ በርካቶች በይዘቱ ላይ ውይይቶች እያደረጉ ነው። አንዳንድ የመግለጫው ሃሳቦችም ጥያቄን ከማጫር ባሻገር የተለያዩ ትርጉሞችን እያስከተሉ ናቸው። ሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴው ያወጣው መግለጫ ሃገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ቁልፍ ነጥቦችን ያነሳ እንደሆነ የሚገልፁ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ የሚጠብቁትን ሁሉንም የሚያስማማ ጉዳዮችን የያዘ አይደለም የሚሉ አሉ። በተለይ ደግሞ ''መርህ አልባ ግንኙነት'' በሚል የተጠቀሰው ሃሳብ በርካቶችን ግራ ያጋባና ለተለያዩ መላምቶች የተጋለጠ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል። በተጨማሪም ''በአፍራሽ ተግባር ውስጥ የተሰማሩ የግልና የመንግሥት ሚዲያ ተቋማት አካሄዳቸውን የሚያስተካክሉበት ሁኔታ'' ለመፍጠር የተቀናጀ እርምጃ እንደሚወሰድ መጠቀሱ ሌላኛው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው። የመግለጫው ይዘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክና የሥነ-ጥበብ ታሪክ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቶ አበባው አያሌው በተለያዩ ምክንያቶች ከመግለጫው የጠበቁትን አላገኙም። ለምሳሌም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የመንግሥት ኃላፊዎች ኢትዮጵያዊነታችንን ትተን በአብዛኛው ልዩነታችን ላይ አተኩረናል የሚሉ አንድምታዎች ያሏቸው ንግግሮችን መስማታቸው ነበር። "እነዚህ ሰዎች ይህንን ጉዳይ ከልባቸው ገዝተውት አንድ ነገር ላይ ይደርሳሉ ብዬ አስቤ ነበር" ይላሉ አቶ አበባው። መግለጫው ግን እንደውም ኢትዮጵያዊነትን ትቶ የብሄርን ጉዳይ የሚያጠናክር በድርጅቱ ጉዳይ ላይ ብቻ ያተኮረ ሆኖ አግኝተውታል። "የድርጅቱን ድክመት እንጂ ሀገሪቱ ወዴት ትሄዳለች የሚለውን አላሳየም" የሚሉት አቶ አበባው "እውነት ሃገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ዳስሶ መፍትሄ ከማስቀመጥ ይልቅ በፓርቲዎቹ መካከል ያለውን ግብግብ መፍታት ላይ ብቻ ያተኮረ ሆኗል" ብለዋል። ለፍልስፍና መምህሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋም የኢትዮጵያ ህዝብ እየጠየቀ ያለው እና መግለጫው የተለያዩ ናቸው። እየተጠየቀ ያለው የሕዝቦች ጥያቄ በአራት ነጥቦች ዙሪያ ነው የሚሉት ዶ/ር ዳኛቸው፤ መግለጫው ግን እነዚህን ጉዳዮች ከመመልከት ይልቅ ሀገሪቱ ውስጥ ጥቃቅን ስህተቶች እና ችግሮች የተፈጠሩ ነው ያስመለሰው ይላሉ። በአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህርና ጦማሪ የሆኑት አቶ ስዩም ተሾመ ልክ እንደ ዶ/ር ዳኛቸው ሁሉ የሥራ አስፈፃሚው መግለጫ የተለመደ የፓርቲው ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ ይናገራሉ። "እነዚህ የሥራ አስፈፃሚ አባላት በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የለውጥ ፍላጎት ለማፈን አላማ አድርገው እስከተሰበሰቡ ድረስ ምንም ነገር አልጠብቅም" የሚሉት አቶ ስዩም "ይህን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማፈን የሚፈልግ ኃይል 17 ቀን አይደለም 17 ዓመት ቢሰበሰብ ለውጥ አያመጣም ምክንያቱም ለውጡ የተፈጥሮ ሂደቱን ተከትሎ የመጣ ነው" ይላሉ። የመድረክ ሥራ አስፈፃሚና የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሙላቱ ገመቹም የስራ አስፈፃሚው መግለጫ ሕዝባችን የሚጠብቀው አይደለም ብለዋል። ሕዝቡ እያለ ያለው የሥርዓት ለውጥ ያስፈልጋል ሆኖ ሳለ መግለጫው ግን ስለጥገናዊ ለውጥ ያወራል። ከዚያ ይልቅ የተለያየ ፍላጎት ያላቸው አካላት በጠረጴዛ ዙሪያ ተሰባስበው ሀገሪቱ ያለችበት ችግር እንዲፈታ ከመምከር ይልቅ፤ ጠቡን ከግለሰቦች ጋር ያለ በማስመሰል ስህተታችንን ተቀብለናል እንዲህ አይነት ማስተካከያ እናደርጋለን ማለት መፍትሔ አይሆንም። የህዝባችን የትግል እንቅስቃሴንም አይመልስም ሲሉ ያስረዳሉ። ኢህአዴግ 26 ዓመት ሙሉ አጥፍቻለሁ በሚል የህዝቡን ይሁንታ ለማግኘት ይጥራል። ነገር ግን ይህን እንደ ስልት በመጠቀም ለውጥ አለማምጣት ለህዝባችንም ሆነ ለሀገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ ጠቃሚ አይሆንም ሲሉ ይናገራሉ። አቶ አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር) ከዚያ ይልቅ ሀገሪቱንም ሆነ ፓርቲያቸውን ለማዳን ህዝቡ የጠየቀውን ጥያቄ መመለስ ነበረባቸው። ይህ ካልሆነ የህዝብ ጥያቄ መቀጠሉ አይቀርም ብለዋል። ያ ደግሞ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር እንዳይኖር በር ይዘጋል ሲሉ ያክላሉ። በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከሚሳተፉ እና በብዛት መንግሥትን በመደገፍ ሃሳቡን በማካፈል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ አቶ ዘርአይ ኃ/ማርያም የኢህአዴግ መግለጫ እንደ ከዚህ ቀደሙ በባዶ ቃላት የተሞላ እና የሀገሪቱን ችግሮች በተጨባጭ ያላገናዘበ ሳይሆን ሀገሪቷና ህዝቦቿ የገቡበትን አዘቅት ፍንትው አድርጎ ያሳየ በመሆኑ "ረክቼበታለሁ" ይላል። ኢህአዴግ ባወጣው መግለጫ መሰረት ለሀገሪቱ ቀውስ ናቸው የሚላቸውን የራሱ ከፍተኛ አመራሮች ላይም እርምጃ ወስዶ ወደ ተግባር ካልገባ ግን መግለጫው ከወረቀት በዘለለ ትርጉም ሊኖረው አይችልም ይላል። "መርህ አልባ ግንኙነቶች" እንደ አቶ ዘርአይ መርህ አልባ ቡድነኝነት ማለት በአስተሳሰብና በዓላማ የማይናኙ ቡድኖች ለጊዜያዊ ጥቅም ሲወዳጁ የሚፈጠረው ግንኙነት ነው። የኢህአዴግ ብሄራዊ ድርጅቶችም የእዚሁ ሰለባ ሆነው መቆየታቸውን የአባል ፓርቲዎቹ መሪዎች በሚያስተዳድሯቸው ሚዲያዎች ሲሰጡት የነበረውን መግለጫ ያስታውሳል። "የህወሀት እና ብአዴን አመራሮች በግላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት፤ የህወሀት አመራሮች የአማራ ህዝብን እንደእራሳቸው ህዝብ አድርገው አለመውስድ እንዲሁም የብአዴን አመራሮች የትግራይን ህዝብ እንደእራሳቸው ህዝብ አድርገው እስካለመውሰድ ደርሰዋል" ይላል። በተጨማሪም አቶ ዘርአይ በተመሳሳይ የኦህዴድ እና የኢትዮጵያ ሶማሌ አመራሮች በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረውን የድንበር ግጭት ከኢህአዴግ መርህ ውጭ የሁለት ሃገራት ጦርነት እስኪመስል ድረስ ነበር በሚዲያዎቻቸው ሲያሰራጩ የነበረው፤ በማለት የግንባሩ ብሄራዊ ድርጅቶች በመርህ አልባ ግንኙነት ተጠቅተው እንደነበር ያብራራል። ለአቶ አበባው ግን መግለጫው መርህ አልባ ግንኙነቶች ሲል በሁለት ብሄራዊ ድርጅቶች መካከል የሚኖር ማንኛውም ግንኙነት ያለ ኢህአዴግ እውቅና ሊካሄድ አይችልም የሚል ነው። እነዚህ በአማራ እና በኦሮሞ መካከል የተካሄዱ ህዝባዊ ግንኙነቶች በበጎ አልታዩም። እንዲሁም እነዚህ በክልላዊ ወይም በብሄራዊ ፓርቲዎች መካከል በራስ ተነሳሽነት የተካሄዱ ግንኙነቶች የፖለቲካ ጫና ያሳድርብኛል ብሎ የሚፈራ ወገን መኖሩን ያሳያል ይላሉ። "በእነዚህ ህዝቦች መካከል የሚደረግ የጎንዮሽ ግንኙነት የሚከለከልበት መንገድ የለም። ይህ ለ25 አመታት ሲሰራበት ከነበረው መንገድ በወጣ መልኩ የድርጅቱን አሰራር ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ስጋትም የፈጠረ ይመስለኛል" ሲሉ ያክላሉ አቶ አበባው። መግለጫው በኦሮሞና በአማራ ሕዝቦች ግንኙነት ላይ ውሃ የቸለሰ ነው ያሉት ደግሞ ዶ/ር ዳኛቸው ናቸው። ከዚህ በፊት በውጊያ የተገኘውን መርህ ያለው ግንኙነት ተብሎ አሁን ህዝቦች በሰላም እንቀራረብ፣ እንተሳሰብ በአንድ ጎዳና እንሂድ ሲሉ አንድ መንግሥት ጥሩ አደረጋችሁ ማለት ሲገባው ለጠባብ ጥቅም ሲባል ብሎ እንዴት ይኮንናል ሲሉ ይጠይቃሉ። አቶ ስዩም ልክ እንደ ዶ/ር ዳኛቸው ሁሉ ይህንን ሃሳብ በጥያቄ ይሞግታሉ። "በአንድ ሃገር ውስጥ በጋራ ሥርዓት የሚተዳደሩ የጋራ ታሪክ ያላቸው፣ የወደፊት አብሮነት ባላቸው ህዝቦች መካከል በጋራ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸው እና የተሻለ ግንኙነት እና ጥምረት መፍጠራቸው በምን መስፈርት ነው መርህ አልባ የሚሆነው ብለን መጠየቅ ይኖርብናል'' ይላሉ። እንግዲያውስ መርሁ ምንድን ነው ብለን ስንል ይህ ግንኙነት እንዳይፈጠሩ ከዚህ በፊት የተቀመጠ የመለያየት፣ ልዩነትን የማጉላት መርህ ነበር ማለት ነው። ይህ ደግሞ የፓርቲው መርህ እንደሆነ ያሳየናል ይላሉ። ለአቶ ስዩም ልዩነትን በማጉላት በሁለት ህዝቦች መካከል ቁርሾ እና ቂምን መሰረት ያደረገ ሥርዓት የሚገነባ የአፓርታይድ ሥርዓት ነው። ህዝቦች እንዲለያዩ እንዳይተባበሩ መስራት እና ከሆነም እርምጃ እወስዳለሁ ማለት ጤናማነት አይደለም ይላሉ አቶ ስዩም። እንደ አቶ ሙላት ደግሞ የህዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ቦታ የታየውን ከሕዝብ ጋር የመወገን እና ሕዝብ ላይ አናስተኩስም ያሉትን በጎሪጥ የሚያይ ሃሳብ ነው። አቶ ስዩም ተሾመ መምህር እና ጦማሪ "አፍራሽ ዘገባ ያቀረቡ የመገናኛ ብዙሃን" ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ወደ ጎን ትተው በብሄሮች መካከል ጥርጣሬን በመፍጠር ሲሳተፉ የነበሩ የመንግሥትም ሆነ የግል መገናኛ ብዙሃን ከእርምት ጀምሮ፤ በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን ጋዜጠኞችም ሆኑ አመራር አካላት ወደ ፍርድ ቤት እስከ መውሰድ የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል ብለው እንደሚጠብቁ አቶ ዘርአይ ያስረዳሉ። እንደ ዶ/ር ዳኛቸው አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ላይ ማስተካከያ እናደርጋለን የሚለው ሃሳብ ላይ ገዢው ፓርቲ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር እና መልሶ የራሱን ድምፅ ብቻ የሚሰማበት ልሳኑ ሊያደርጋቸው ማሰቡን ያሳያል። ከአሁን በኋላም እያንዳንዱ ዘገባ ርእዮተ አለሙ ልክ መሆኑን እንደሚያረጋግጡ እና ከፈት ብሎ የነበረውን የመገናኛ ብዙሃኑን ነፃነት እንዘጋለን ማለቱ እንደሆነ ያስቀምጡታል። አቶ ስዩምም ከዶ/ር ዳኛቸው ሃሳብ ጋር ይስማማሉ "ኢህአዴግ የተለየ ሃሳብ ለመስማት ዝግጁ አይደለም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህዝብ ጥያቄ የሚያራምዱ የመገናኛ ብዙሃን ላይ ደስተኛ አለመሆኑንም ማሳያ ነው" ብለዋል። ሃሳብ በራሱ የአመፅ እና የብጥብጥ ምክንያት ሊሆን አይችሉም የሚሉት አቶ ስዩም፤ ይልቁንም ክፍተቶችን ለማየት እና ለማስተካከል በር ከፋች ናቸው ሲሉ ይናገራሉ። በዚህ ወቅት አንዳንድ የክልል መገናኛ ብዙሃን የፓርቲያቸው ልሳን ከመሆን ወጥተው የሕዝቡን ብሶት ማሰማት ጀምረዋል የሚሉት አቶ አበባው፤ ያንን ያሰሙበት መንገድ ምን ያክል ትክክል ነው የሚለው ሊያጠራጥር ይችላል ብለዋል። ምናልባት ግን ከአሁን በኋላ ኢህአዴግ የሚፈልገውን ነገር ብቻ የሚያቀነቅኑ ይሆናል ማለት ነው ይላሉ። ለአቶ ሙላቱ የሚዲያ ተቋማቱ ውስጥ ውሃ ቀጠነ የሚል የተለመደ ግምገማ ማካሄድ እና በግምገማው ጋዜጠኞቹ ላይ እንደተለመደው አንተ የዚህ ድርጅት ተላላኪ ነህ አንተ ደግሞ ከዚህኛው ወገን ጋር ትሰራለህ በሚል ለማዋከብ እንጂ የሚመጣ ለውጥ የለውም ይላሉ። ለአቶ ሙላት ከሥርዓቱ ጋር አልወገኑም የሚባሉ ሰራተኞች ከሥራቸው እና ከሃላፊነታቸው መነሳት የሚጠበቅ ነው።
45742796
https://www.bbc.com/amharic/45742796
በካማሼ ዞን ግጭት እጃቸው አለበት የተባሉ የፓሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈፀመው ጥቃት እጃቸው አለበት የተባሉ የክልሉ 10 የልዩ ፖሊሰ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ሃላፊ አቶ ታከለ ቶሎሳ ለቢቢሲ ቢናገሩም የቤኒሻንጉል ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበራ ባየታ ግን የክልሉ ፖሊስ በድርጊቱ ውስጥ እንደሌለበት ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ፖሊስና መከላከያ ሁኔታውን ለማረጋጋት ሲሞክሩ የታጠቁ ኃይሎች ተኩስ በመክፈት ጉዳት አድርሰውባቸዋል ሲሉ የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ሃላፊ አቶ ታከለ ነግረውናል። ከጥቃቱ ጀርባ የታጠቁ ኃይሎች እንዳሉ ከቀያቸው የተፈናቀሉና በተለያየ ቦታ ተጠልለው የሚገኙ ግለሰቦች ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጤና ባለሙያዎች ጥቃት ደረሰባቸው • "ማንም ቢሆን ኢትዮጵያን ለብቻዬ ሰራኋት ሊል አይቻለውም" ጠ/ሚ ዐብይ • ሮናልዶ "ደፍሮኛል" ያለችው ሴት ከመብት ተሟጋቾች ድጋፍ አገኘች ዘይነባ የተባሉት ከሳሲጋ የተፈናቀሉ ግለሰብ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን የታጠቁ ኃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸውና ንብረታቸውን ጥለው እንደሸሹ ገልፀውልናል። "አብራኝ ስትሸሽ የነበረችውን ጓደኛዬን በሚዘገንንና በሚያሰቅቅ ሁኔታ በስለት ተገድላለች " ብለዋል። መከላከያ ኃይል አስር ታጣቂዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገለፁት ኃላፊው እነዚህ በቁጥጥር ስር የዋሉ ኃይሎች የመኖሪያ ቤቶችን ሲያቃጥሉና ንብረት ሲያወድሙ በመታየታቸው እንደተያዙ አስረድተዋል። ታጥቀው ተኩስ የከፈቱት ሃይሎች ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት መሆናቸውንም አክለው ተናግረዋል። ግለሰቦቹ በቤኒሻንጉል ክልል በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ 8 በሚባለው ስፍራ እንደሚገኙም ጨምረው አስረድተዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል አስተዳደሪ አቶ አበራ ባየታ በዚህ ግጭት ፍፁም የክልሉ ኃይል አልተሳተፈም ሲሉ አስተባብለዋል። አክለውም የክልሉ ልዩ ኃይል በሎጅጋንፎይ ጮጌ ከተማ ላይ ነው ያለው ካሉ በኋላ በቁጥርም ምን ያህል እንደሆነ ይታወቃል ብለዋል። በተጨማሪም "በፍፁም በጥቃት ላይ የተሰማራ የክልሉ ልዩ ኃይል የለንም" በማለት ለምላሻቸው አፅንኦት ሰጥተውታል። እንዲህ ዓይነት ጥቃቶች እንዲፈፀም የሚያቀነነባብሩ አካላቶችን በማጣራት መንግሥት አስፈላጊውን ምርመራ በማካሄድ የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየሰራ ነው ሲሉ የተናገሩት የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ሃላፊ ሁኔታው አሁንም ሙሉ በሙሉ እንዳልቆመና የተፈናቃዮችም ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ አስረድተዋል።
news-51750602
https://www.bbc.com/amharic/news-51750602
መንግሥት በታጣቂዎች ላይ ዘመቻ በሚያካሂድበት ምዕራብ ኢትዮጵያ ህይወት ምን ይመስላል?
በምዕራብ ኦሮሚያ በተለይ ደግሞ ቄለም ወለጋና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያለው የሠላም ሁኔታ የተረጋጋ እንዳልሆነ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል።
በተጠቀሱት አካባቢዎች እንደሚንቀሳቀስ በሚነገረው ታጣቂ ቡድንና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል በሚፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ በተለያዩ ጊዜያት በሰዎች ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል። ከቅርብ ወራት ወዲህም መንግሥት በአካባቢው ያሉትን ታጣቂዎች ለመቆጣጠር እየወሰዳ ያለውን እርምጃ ተከትሎ የግንኙነት መስመሮች የተቋረጡ ሲሆን በዚህም ሳቢያ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ይናገራሉ። በአካቢው ያለውን ሁኔታና የነዋሪዎችን ስጋት ለመረዳት በቅርቡ የቢቢሲ ዘጋቢዎች በአንጻራዊ ሁኔታ የተረጋጋች ወደ ሆነችው የነቀምቴ ከተማ አቅንተው ነበር። በቄለም ወለጋና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ባለው የጸጥታ ስጋት ሳቢያ ጥቂት የማይባሉ የሁለቱ ዞኖች ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ጥለው ወደ ነቀምቴ መጥተዋል። በሁለቱም በኩል እየተጎዳን ነው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የ42 ዓመቱ ጎልማሳ ከምዕራብ ወለጋ ዞን ላሎ አሳቢ ወረዳ የመጡ ሲሆን በአካባቢያቸው ያለውን የጸጥታ ሁኔታ "ለመናገር አስቸጋሪ" በሚል ይገልጹታል። በወረዳቸው ውስጥ ቀንም ሆነ ሌት ሠላም እንደሌለና ነዋሪው የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በሙሉ ምን ይፈጠር ይሆን በሚል ስጋት የተመላ እንደሆ ይናገራሉ። "ሠላም ስለሌለ ቀን ብር ይዘህ ስትንቀሳቀስ የመንግሥት ወታደሮችን ትፈራለህ፤ ሌሊት ደግሞ በጫካ ያሉትን ታጣቂዎች ትፈራለህ። ስለዚህ በአካባቢው መነገድም ሆነ ወጥቶ መግባት ከባድ ሆኗል።" ከዚህም የተነሳ እንደእሳቸው በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ነቀምቴና ወደ ሌሎች ከተሞች ለመሰደድ መገደዳቸውን ይናገራሉ። "ከሁለቱም ኃይሎች ያጋጥመኛል የሚለውን ጥቃት ለማምለጥ አቅም ያለው በሙሉ ኑሮውን እየተወ ቤተሰቡን በመያዝ እየተሰደደ ነው" ይላሉ። ግለሰቡ በአካባቢው ባለ ጫካ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ባሉት ታጣቂዎችና መንግሥት ባሰማራቸው ወታደሮች እንቅስቃሴ ሳቢያ በነዋሪው ላይ እየደረሰ ያለው ጫናና ጉዳት በነዋሪው ዘንድ መረጋጋት እንዳይኖር እንዳደረገ ይናገራሉ። "ቀን ላይ በአካባቢው የተሰማራው የመንግሥት ሠራዊት አነጋግሮን ከሄደ ጫካ ያሉት ታጣቂዎች የመንግሥት ሰላይ ነህ በማለት ሌሊት መጥተው በመውሰድ፤ ምንም ሳያጣሩ እርምጃ ይወስዳሉ። "የመንግሥት ወታደሮች ደግሞ 'ታጣቂዎቹ ማታ እዚህ መጥተው ነበር፤ እናንተም ምግብ ሰጥታችኋል' በማለት ነዋሪውን ሰብስበው ይቀጣሉ" በማለት ስጋቱ ከሁለቱም ወገን በመሆኑ አካባቢያቸውን ጥለው እንዲሸሹ እንዳደረጋቸው ይጠቅሳሉ። በአካባቢዎቹ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ነዋሪው የተለመደውን የዕለት ከዕለት ተግባሩን ማከናወን እንዳልቻለና አንዳንዶችም ለችግርና ለረሃብ እየተጋለጡ ነው ይላሉ። በአካባቢው እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ታጣቂዎች በተመለከተም "ሕዝቡ ጫካ ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱት ማንነት እንዲናገር ሲጠየቅ ለህይወቱ ስለሚሰጋ አይናገርም። መንግሥትም ታጣቂዎቹ ሕዝቡ ውስጥ በመሆናቸው ሊለያቸው አልቻለም" ሲሉ የችግሩን ውስብስብነት ይናገራሉ። በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቼ ነበር የሚሉት ግለሰቡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በአካባቢው በተከሰተው አለመረጋጋት መክንያት ቀያቸውን ትተው ወደ ነቀምቴ እንዲሄዱ ከማድረጉ ባሻገር ሥራቸውን መስራት ስላልቻሉ ከባንክ የወሰዱትን ብድር ለመክፈል መቸገራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ለወራት የዘለቀው ያለመረጋጋት በአካባቢዎቹ ውስጥ ባለው የንግድና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ላይ ተጽእኖ በመፍጠሩ ብዙዎቹ ሥራ ማቆማቸውን ጠቅሰው፤ በዚህ ምክንያትም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ነዋሪው የሚበላውንም ሊያጣ ይችላል በማለት ይሰጋሉ። በተጨማሪም በአካባቢዎቹ የስልክና የሌሎች መገናኛ አገልግሎቶች ለወራት መቋረጣቸው ሕዝቡ ስላለበት ሁኔታ በሌሎች አካባቢዎች ለሚገኙት ቤተሰቦቻቸውና በአጠቃላይ ሌሎችም እንዲያውቁ ለማድረግ ተቸግረው መቆየታቸውንም አንስተዋል። "ትንሹም ትልቁም ስጋት ውስጥ ነው" ቀደም ሲል ሲኖርበት ከነበረው ቄለም ወለጋ ሸሽቶ ነቀምቴ የሚገኘውና ለደኅንነቱ በመስጋት ስሙን ለመናገር ያለፈለገው ወጣት ከቢቢሲ ጋር መነጋገሩ እራሱ ችግር ሊያስከትልበት ይችላል የሚል ስጋት ቢኖረውም የሚያውቀውን ለመናገር ፈቃደኛ ነበር። ወጣቱ እንደሚለው እነዚህ የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ከሌሎቹ ተለይተው በኮማንድ ፖስት ስር እንዲሆኑ በመደረጋቸው በነዋሪው ላይ የሥነ ልቦና ጫና እየፈጠረ ነው። "በእኛ አካባቢ ትልቁም ትንሹም በስጋት ውስጥ ነው የሚኖረው" በማለት ሁሉም ነዋሪ ከሁለቱም ኃይሎች አንጻር እየተጎዳ መሆኑን አመልክቷል። አክሎም "ይህንን ቃለ መጠይቅ ሳደርግ ከባድ ስጋት ውስጥ ሆኜ ነው። ከታየሁ ምን ሊገጥመኝ እንደሚችል በደንብ አውቃሉ" በማለት ለመናገርም አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለ ለቢቢሲ ገልጿል። ወጣቱ በመንግሥት ኃይሎችና በታጣቂዎቹ መካከል ያለው ሁኔታ በቶሎ መፍትሄ አግኝቶ ወደ ተረጋጋ ህይወት መመለስ ይፈልጋል ለዚህም ሠላማዊ መንገድ መፈለግ አለበት ይላል። "ግጭቱ በሁለት ወንድማማቾች መካከል የሚደረግ በመሆኑ በጦርነት እስከመጨረሻው መፍትሄ ያገኛል ብዬ አላምንም" በማለት ለችግሩ በውይይት ሠላማዊ መቋጫ እንዲገኝ ይመኛል። በአካባቢዎቹ ባለው ስጋት የተሞላበት ሁኔታ ነዋሪው ሕዝብ እየተጎዳ እንደሆነና የጸጥታው ሁኔታ ከከተማ ይልቅ በገጠሩ አካባቢ አሳሳቢ እንደሆነና ብዙም መሻሻል እንደሌለ አመልክቷል። ነቀምቴ የቢበሲ ዘጋቢዎች በነቀምቴ ከተማ በነበራቸው ቆይታ እንደተገነዘቡት በከተማዋ ውስጥ ከጊንቢና ከደንቢ ዶሎ የተሻለ መረጋጋት ስላለ በአቅራቢያ ባሉ ወረዳዎች የሚኖሩ ሰዎች ካለባቸው ስጋት ለመሸሽ ወደ ከተማዋ መጥተው ይኖራሉ። በከተማዋ ያለው የንግድ እንቅስቃሴ ቀን ላይ መደበኛና ሞቅ ያለ ሲሆን አመሻሽ አንድ ሰዓት ላይ ግን በመንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሰው ሰው ቁጥር በጣም ስለሚቀንስ ጭር ይላል። በከተማዋ ያሉ ባለሦስት ጎማ ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ስለማይፈቀድላቸው፤ ከአስራ ሁለት ሰዓት በኋላ የባጃድ አሽከርካሪዎች ሥራ የሚያቆሙበት ጊዜ እየደረሰ መሆኑን ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው። በዚህም ሳቢያ የከተማዋ እንቅስቃሴ ምሽት ላይ ይቀዘቅዛል። በነቀምቴ ከተማ ያሉት ባጃጆች በር እንዲኖራቸው ስለማይፈቀድ ሁሉም በር አልባ ሆነው ወዲያ ወዲህ ሲሉ በሌሎች ከተሞች ውስጥ ካሉ ተሽከርካሪዎች ለየት ብለው ይታያሉ። በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ስፍራዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች ሰፍረው ስለሚገኙ እነሱ ባሉባቸው አካባቢዎች አቅራቢያ ማለፍ ለእግረኞች የተከለከለ መሆኑን የሚገልጹ ምልክቶች ይታያሉ። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ከተማዋ የሚመጣ እንግዳ የጎላ የጸጥታ ችግርም ሆነ ስጋት አያጋጥመውም፤ ነዋሪዎች ግን የጸጥታ አካላት አንድ ችግር ቢያጋጥም ሊወስዱት ይችላሉ የሚሉትን እርምጃ በመስጋት በጊዜ ወደ ቤታቸው መሰብሰብን ይመርጣሉ። በአጠቃላይ በኮማንድ ፖስት ስር የምትገኘው ነቀምቴ ቀን ቀን መደበኛ ሞቅ ያለ እንቅስቃሴ ቢኖራትም አመሻሽ ላይ ንግድ ቤቶች በጊዜ ስለሚዘጉና ሰዉም ቀድሞ ወደቤቱ ስለሚገባ የነቀምቴ ምሽት ጭር ይላል። መንግሥት ምን ይላል? የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹም የሆኑት ጄነራል ብርሃኑ ጁላ በቅርቡ ለቢቢሲ ሰጥተውት በነበረው ቃል ላይ መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ "የተለየ" ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ተናግረው ነበረ። ጄነራሉ እንዳሉት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ ይለመኑ እንደነበርና "ልመናው ሲበዛባቸው መጠናከር ጀመሩ፤ ሕዝቡ ላይ የሚደርሰው በደል ተጠናክሮ ቀጠለ። ሕዝብ ያስፈራራሉ፣ ሕዝብ ይዘርፋሉ፣ ያስቃያሉ፣ አፍነው 70 እና 60 ኪሎ ሜትር ይዘው ሄደው ለሁለት ሳምንት ደብድበው ይለቃሉ" በማለት መንግሥት እርምጃ ለመውሰድ የተገደደበትን ምክንያት ተናግረዋል። ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ሠራዊቱ በሕዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ስለሚባለው ክስም በሰጡት ምላሽ "እኔ ያደራጀሁት እና እኔ የምመራው ወታደር ሕዝብ አይነካም። የመንግሥት ወታደር ሕዝብ ላይ ጉዳት አድርሶ ከሆነ ግን መንግሥት ይጠየቃል። እኔም በግሌ ሕዝቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ እክሳለሁ" በማለት አስተባብለዋል።
news-46041930
https://www.bbc.com/amharic/news-46041930
ትራምፕ አሜሪካ ለተወለዱ ልጆች የምትሰጠውን ዜግነት ለማስቀረት እየጣሩ ነው
በተለያዩ ምክንያቶች ተሰደው ወደ አሜሪካ የገቡ ሰዎች የመኖሪያም ሆነ የዜግነት መብት ባያገኙ እንኳን አሜሪካ ውስጥ የተወለዱ ልጆቻቸው በቀጥታ የአሜሪካ ዜግነትን ያገኛሉ።
ከዚህ አልፎም ለጉብኝትም ሆነ ለህክምና ወደ አሜሪካ የሄደች እናት በቆይታዋ ወቅት ልጇን ከወለደች ፍላጎቱ ካላት ልጇ የአሜሪካ ዜግነት እንድታገኝ/እንዲያገኝ ማድረግ ትችላለች። ለዚህም አቅሙ ያላቸው የእኛ ሃገር እናቶችን ጨምሮ በርካቶች መውለጃ ጊዜያቸው ሲቃረብ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንደሚያቀኑ ይነገራል። አሁን ግን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከ150 ዓመታት በፊት በአሜሪካ ህገ መንግሥት አንቀጽ 14 ላይ የሰፈረው ማንኛውም በአሜሪካ ምድር ላይ የተወለደ ሰው ዜግነት ያገኛል የሚለውን ህግ ለማስቀረት እየሰሩ እንደሆነ አስታውቀዋል። • የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? "ህጉን ለመቀየር ሃሳቤን ሳቀርብ ሁሌም ህገ መንግሥቱ መሻሻል አለበት ይሉኛል፤ እኔ ደግሞ እንደውም ምንም ማሻሻል አያስፈልገውም ባይ ነኝ'' ብለዋል። "በተጨማሪ ምክር ቤቱ ካጸደቀው መቀየር እንደሚቻል ነግረውኝ ነበር፤ ነገር ግን በፕሬዝዳንቱ ቀጥተኛ ትዕዛዝም መቀየር እንደሚቻል ተነግሮኛል።" ይህ የፕሬዝዳንቱ አስተያየት ደግሞ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል። ሰዎችም እንዲህ አይነት አከራካሪ የህገ መንግሥቱን ክፍል ፕሬዝዳንቱ በቀጭን ትዕዛዝ መቀየር ይችላሉ ወይ? በማለት ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። 1. በመወለድ የሚገኝ ዜግነት ምንድነው? የአሜሪካ ህገ መንግሥት አንቀጽ 14 የመጀመሪያ አረፍተ ነገር በመወለድ ስለሚገኝ ዜግነት ያትታል። ''ማንኛውም አሜሪካ ውስጥ የተወለደ ወይም ተገቢውን ግዴታዎች የተወጣ ሰው የአሜሪካ ዜጋ የመሆን ሙሉ መብት አለው'' ይላል። የስደተኞች ወደ አሜሪካ መጉረፍ ያሳሰባቸው ሰዎች ህጉ የህገ ወጥ ስደተኞች 'ማግኔት' ነው በማለት ማንኛዋም ሴት አሜሪካ መጥታ መውለድን የሚያበረታታው ህግ እንዲቀር ይከራከራሉ። • ሳዑዲ ለሮቦት ዜግነት ሰጠች እንደውም አብዛኛዎቹ እናቶች በህገ ወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው ወደ አሜሪካ በመግባት ነው ልጆቻቸውን የሚወልዱት። የዚህ ሃሳብ አቀንቃኞች ህጉን የወሊድ ቱሪዝም የሚል ስም ሰጥተውታል። "የሚወለዱት ህጻናት ቢያንስ ለ85 ዓመታት ከነሙሉ ጥቅማጥቅሞቹ የአሜሪካ ዜጋ ሆነው ይቆያሉ፤ ይህ የማይሆን ነገር ነው'' ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። ፒው የተባለ የምርምር ማዕከል በአውሮፓውያኑ 2015 በሰራው አንድ ጥናት መሰረት 60 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካዊያን ህጉን የሚደግፉ ሲሆን፤ 37 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ህጉ መቀየር አለበት ባይ ናቸው። 2. አሜሪካ ውስጥ በመወለድ የሚገኝ ዜግነት መነሻው ምንድነው? ስለጉዳዩ የሚያወራው አንቀጽ 14 በአሜሪካ ህገ መንግሥት ውስጥ የተካተተው በአውሮፓውያኑ 1868 ልክ የእርስ በርስ ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ነበር። አንቀጽ 13 የባሪያ ንግድን በ1865 ሲከለክል አንቀጽ 14 ደግሞ በአሜሪካ የሚገኙ ነጻ የወጡ ባሪያዎችን የዜግነት መብት ጥያቄ የሚመልስ ሆነ። በአሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ክርክሮች ጥቁሮች የአሜሪካ ዜጋ መሆን እንደማይችሉ ተወስኖ የነበረ ሲሆን፤ አንቀጽ 14 ለዚህ ክርክር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መልስ የሰጠ ነው። • በኢትዮጵያ አደገኛ ከሆኑት መንገዶች አንዱ የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈ ነው አሜሪካ ውስጥ የተወለዱ የስደተኛ ልጆች ዜግነት ማግኘት አለማግኘትን በተመለከተ የአሜሪካው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ውሳኔ ያስተላለፈው በ1898 ነበር። ሰውዬው ዎንግ ኪም የሚባል የ24 ዓመት ወጣት ነው። ቤተሰቦቹ በስደት ወደ አሜሪካ መጥተው ነው እሱ የተወለደው። የቤተሰቦቹን ሃገር ለመጎብኘት ወደ ቻይና ሄዶ ሲመለስ ግን የአሜሪካ ዜጋ አይደለህም ስለዚህ መግባት አትችልም ተብሎ ተከለከለ። ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ወስዶ በክርክሩ አሸነፈ። ከዚህ አጋጣሚ በኋላም ማንኛውም አሜሪካ ውስጥ የተወለደ ሰው ቤተሰቦቹ ከየትኛውም የዓለም ክፍል ይምጡ፣ ምንም አይነት የኑሮ ደረጃ ይኑራቸው የአሜሪካ ዜግነት ማግኘት እንደሚችሉ ተወሰነ። ከዚህ ውሳኔም በኋላ የአሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይህንን ጉዳይ በድጋሚ አይቶት አያውቅም። 3. በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን በትራምፕ ውሳኔ ብቻ መቀየር ይቻላል? ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚስማሙት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቀጭን ትዕዛዝ የህገ መንግሥቱን አንድ ክፍል መቀየር አይችሉም። ሁሉም ነገር በህግና ደንብ መሰረት ስለሚሰራ በቀላሉ ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው ብለዋል። በቨርጂንያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ፕሮፌሰርና የህገ መንግሥት ኤክስፐርት የሆኑት ሳይክሪሽና ፕራካሽ እንደሚሉት፤ "ይህ ሃሳብ ብዙ ሰዎችን የማያስደስትና በፍርድ ቤት ብቻ መወሰን የሚችል ነገር ነው። ፕሬዝዳንቱ ለብቻው መወሰን የሚችለው ነገር አይደለም።" • የኢትዮጵያ እና የጂ-20 ወዳጅነት ባለሙያው ሲያብራሩ ፕሬዝዳንቱ ምናልባት የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ዜግነትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ጠበቅ ያለ ህግ እንዲያወጡ ሊያዙ ይችላሉ፤ ነገር ግን ህጉን የማስቀየር ስልጣን የላቸውም። ይሄ አካሄድ የማያባራ ክርክር የሚያስነሳ ሲሆን በመጨረሻ ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለውሳኔ መቅረቡ አይቀርም። "ነገር ግን ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የአሜሪካ ዜግነት ከሌላቸው ወይም በህጋዊ መንገድ ወደ አሜሪካ ካልገቡ ሰዎች የሚወለዱ ልጆች ዜግነት ስለማግኘት አለማግኘታቸው ውሳኔ አላሳለፈም" ሲሉ 'በርዝራይት ሲቲዝንስ' መጽሃፍ ደራሲ ማርታ ጆንስ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረወዋል። 4. ከዚህ ውሳኔ ጀርባ ምን አለ? በመወለድ የሚገኝ የአሜሪካ ዜግነትን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እየሰሩት ያለውን ነገር በቀጣይ ሳምንት ከሚካሄደው የአጋማሽ ወቅት ምርጫ ጋር አያይዞ መመለክት አስፈላጊ ነው። መንግሥት ከ5ሺህ በላይ ወታደሮችን ወደ ሜክሲኮ ድንበር ማሰማራቱና የፕሬዝዳንቱ ከዜግነት ጋር የተያያዘ አስተያየታቸው የአሜሪካዊያንን ትኩረት ወደ ኢሚግሬሽን ጉዳዮች ለማዞር ነው ተብሏል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ2016 የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ሲጀምሩም የኢሚግሬሽን ጉዳይ ዋናው ነጥባቸው የነበረ ሲሆን፤ ለማሸነፋቸውም እንደ ምክንያት ይጠቅሱታል። 5. ተመሳሳይ ህግ ያላቸው ሃገራት አሉ? ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተያየታቸውን ሲሰጡ አሜሪካ በመወለድ የዜግነት መብት የምትሰጥ የዓለማችን ብቸኛዋ ሀገር ናት ብለው ነበር። ነገር ግን ተሳስተዋል፤ የአሜሪካ ጎረቤት የሆኑት ካናዳና ሜክሲኮን ጨምሮ 33 የዓለማችን ሃገራት በሃገራቸው ለተወለዱ ህጻናት የዜግነት መብት ይሰጣሉ። • ታንዛኒያ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን አድና ልታስር ነው አብዛኞቹ የአውሮፓ ሃገርም ሆነ የምሥራቅ እሲያ ሃገራት በመወለድ የዜግነት መብት የማይሰጡ ሲሆን፤ እንግሊዝ ግን ከቤተሰቦች መካከል አንዳቸው እንግሊዛዊ ከሆኑ አልያም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸው የዜግነት መብት ትሰጣለች። 6. ከዚህ ዜግነት መብት የሚጠቀመው ማነው? ፒው የተባለው የምርምር ማዕከል በሰራው ጥናት መሰረት በአውሮፓውያኑ 2014 ዓ.ም ብቻ 275 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት ከህገወጥ ስደተኞኛ ቤተሰቦች አሜሪካ ውስጥ ተወልደዋል። በአውሮፓውያኑ በ1990ዎቹ እና በ2000 አካባቢ በህገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ ከገቡ ቤተሰቦች ወይም ህጋዊ ወረቀት ከሌላቸው ቤተሰቦች የሚወለዱ ህጻናት ቁጥር እጅግ ጨምሯል። በ2006 ከፍተኛ የሚባለውን ቁጥር አስመዘግቦ ከዚያ በኋላ ግን መቀነስ አሳይቷል። ምንም እንኳን የምርምር ተቋሙ ስደተኞቹ ከየትኞቹ ሃገራት በብዛት ወደ አሜሪካ እንደሚገቡ ትክክለኛ ቁጥር ማግኘት ባይችልም፤ ሦስት አራተኛ የሚሆኑት ህገወጥ ስደተኞች ከላቲን አሜሪካ ሃገራት እንደሚመጡ ያስቀምታል።
news-53080079
https://www.bbc.com/amharic/news-53080079
ከአስተናጋጅነት ምርጡን የአፍሪካ ባንድ የመሰረተው ሙዚቀኛ
በኬንያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ስመጥር ከሆኑት አንዱ የሆነው ጆን ንዜንዜ ከሰሞኑ ህይወቱ አልፏል።
በግራ በኩል ያለው ጆን ንዜንዜና ሲሆን በቀኝ በኩል ደግሞ የመጀመሪያ ሙዚቃውን አብሮ የቀረፀው ዳውዲ ካባካ ኬንያ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችበት ወቅት፤ ግድያ፣ ስቃይና መቆርቆዝ የጥቁሮች እውነታ በነበረበት በዚያ ዘመን በሚያቀነቅናቸው ዘፈኖቹ ተስፋን መፈንጠቅ የቻለ ነው። ድምጻዊ፣ ጊታር ተጫዋች፣ እንዲሁም ዳንሰኛው ጆን ንዜንዜ የኬንያን ትዊስት የተባለውንም የሙዚቃ አይነትም ከፍ ወዳለ ስፍራ በማድረስ አሻራውን ያኖረ ሙዚቀኛ ነው። በጎርጎሳውያኑ 1960ና 1970ዎቹም በምሥራቅ አፍሪካ በፈንክ የሙዚቃ አይነት ምርጥ ሥራዎችን ካበረከቱት ባንዶች መካከልም አንዱ የእሱ ነበር። "ታዋቂ ስትሆን በተወሰነ መልኩ እብሪተኛ ወይም ትዕቢተኛ መሆንህ አይቀርም። እኔም በእብሪተኛነቴ ነው የእራሴን ኤይር ፊየስታ ማታታ ባንድ የመሰረትኩት" በማለት ከመሞቱ በፊት ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጿል። ባንዱ ከኮንጎ የመጡ ስደተኞችንም ያካተተ ሲሆን በዓለም ላይ እውቅና ለማግኘትም የወሰደበት ጊዜ ጥቂት ዓመታትን ነው። በጎርጎሳውያኑ 1968ም በአልጀሪያ ተካሂዶ በነበረው የመላው አፍሪካ የሙዚቃ ፌስቲቫልም በተደረገው ውድድር ባንዱ ሦስተኛ ወጥቷል። ከአንድ ዓመት በኋላም በአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ለብዙ ወራት ቆይታ በማድረግ በርካታ ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። ቢቢሲ አፍሪካ ምርጡ የአፍሪካ ባንድ በሚል በ1971 ሽልማትን የሰጣቸው ሲሆን በወቅቱም ስመ ጥር ከነበሩት ከአሜሪካዊው ጄምስ ብራውንና ኦሲቢሳ ቡድንም ጋር አብረው ለንደን ውስጥ አቀንቅነዋል። በጎርጎሳውያኑ 1972 በዩናይትድ ኪንግደም የሙዚቃ ስራቸውን ሲያቀርቡ በዚህ በለንደን በነበራቸው ቆይታ ከፍተኛ ሙገሳና ውደሳን ቢጎናጸፉም የባንዱ መጨረሻም ሆነ። የባንዱ በርካታ አባላት ኬንያውያኑም ሆነ የኮንጎ ዜግነት ያላቸው በእንግሊዝ ለመቆየት በመወሰናቸው የባንዱም ፍጻሜ ሆነ። "ወደ ኬንያ ልንመለስ ስንል ኮንጎዎቹ የባንዳችን አባላት ኬንያ ውስጥ በስደተኝነት ከምንኖር እዚሁ ብንቆይ ይሻላል አሉ። በርካቶችም ለንደን ለመቆየት በመወሰናቸው ባንዱ ፈረሰ በማለት" ጆን ይናገራል። ባንዱ ቢፈርስም ጆንን ብቻውን የሚወደውን ሙዚቃ ከመቀጠል አላገደውም። ሌሎች ባንዶችንም ተቀላቅሎ ተጫውቷል። በመዲናዋ ናይሮቢም ፊልኮ ለሚባል ስቱዲዮም ለተለያዩ ሙዚቀኞችም ፕሮዲውስ አድርጓል። የሙዚቃውን ዓለም እንዴት ተቀላቀለ? በወቅቱ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው የኬንያዋ መዲና በጎርጎሳውያኑ 1940 ነው የተወለደው። ትምህርቱን የተከታተለው በናይሮቢ እንዲሁም የቤተሰቦቹ የትውልድ ቦታ በሆነችው ምዕራብ ኬንያ ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም አቁሞ በሆቴል ውስጥ በአስተናጋጅነት ተቀጠረ። የሙዚቃ ጉዞው ግን የተጠነሰሰው ከዚያ በፊት ነው፤ በአስራዎቹ እድሜ ላይ እያለ የአባቱን ጊታር አንስቶ የሙዚቃ ህይወቱን 'ሀ' ብሎ ጀመረ። የኬንያ መዲና ናይሮቢ በጎርጎሳውያኑ 1940ዎቹ በጊዜው ስመ-ጥር በነበረው ኖርፎክ ሆቴል ነው በአስተናጋጅነት የተቀጠረው። የሆቴሉ ሠራተኞችም ያድሩ የነበረው በዚያው በሆቴሉ ውስጥ ነበር። ክፍሉን ይጋራው ከነበረው ዳውዲ ካባካም ጋር ሙዚቃዎችን ማቀናበር እንዲሁም መቅረፅ ጀመሩ። ወደ በኋላ ግን ዳውዲ ብቻውን ሙዚቃዎቹን እንዳቀናበረ በተደጋጋሚ በመናገሩ ጆን ደስተኛ አልነበረም። ለሙዚቃዎቹ ዳውዲ በብቸኝነት ስሙ በሬድዮ መነገሩ ያናደደው ጆን ከሌሎች ሙዚቀኞች ጋር በመሆን ለሕዝብ ጆሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የደረሰውን 'አንጀሊክ' የተሰኘ ነጠላ ዜማውን ቀረፀ። ከሁሉ በላይ ሙዚቃው በሬድዮ በመጫወቱ በወቅቱ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረለት ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር "ገንዘቡ አይደለም፤ ዋናው ለእኔ ሙዚቃዬ ነው" ብሏል። በኬንያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ታዋቂ ከሆኑ ዘፈኖች ውስጥ አንዱ የሆነው 'አንጀሊክ' የሴት ፍቅረኛው ወደ ቤት እንድትመለስ የሚማፀን ሙዚቃ ነው። ከአንጀሊክ በፊት ከዳውዲ ጋር አግኔታ ስለምትባለው ፍቅረኛውም ዘፍኖ ነበር። በወቅቱ ጆን ያላወቀው አግኔታ የዳውዲም ፍቅረኛ መሆኗን ነው። ግጥሙም ላይ አግኔታን እንዴት ናይሮቢ እንደተዋወቃት፤ ይዋደዱ እንደነበርና በወቅቱ ባል ወይም ጓደኛ እንዳላት ሲጠይቃት እንደሌላት መንገሯን እናም አንድ ቀን እሷ ቤት ሄደው አብረው በተኙበት ወቅት በር ተንኳኳ። ማነው ሲልም "የቤቱ ባለቤት ነኝ" አለው። ግጥሙም ላይ አግኔታ ይህ ሥራ ኣሳፋሪ ነው ይላታል። ሁለት ፍቅረኛ መያዝ ይላል። ከሰውየው ጋርስ ተጣልቼ ቢሆን? ተጎዳድተንስ ቢሆን? ምን ታደርጊ ነበር በማለት በግጥሙም ይጠይቃል። ጆን ሙዚቃው በራሱ እውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የሴቶቹን እውነተኛ ስም ግን ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል። በሚስረቀርቅ ዜማ የብዙዎች ልብ ውስጥ መግባት የቻለው ሙዚቀኛ ዝናንም ማትረፍ የቻለው ፍቅርን በውብ ቃላት መግለፅ በመቻሉ ነው። በወቅቱ በተለያየ ጊዜ ይወዳቸው ለነበሩ ሴቶች የነበረውን ፍቅር ገልጿል፤ ልብ ስብራቱንም እንዲሁ። "ሴቶችን በሙዚቃህ ማስደሰት ካልቻልክ ሙዚቃህ ብዙ ትርጉም አይኖረውም። ሴቶች ሙዚቃህን ሲወዱ ነው ወንዶችም የሚከተሉት" በማለትም በአንድ ወቅት ተናግሮ ነበር። "ወጣቶች ነበርን፤ ፍቅርም ውስጥ ነበርን" በማለት አክሏል። ጆን በመድረክ አዘፋፈኑ እንዲሁም ታዳሚዎቹን በዘፈኖቹ በመማረክ ከፍተኛ ሙገሳና ውደሳን አትርፏል። ከዚህ የመድረክ ስጦታውም ጋር ተያይዞ በርካታ የዘመኑ ዘፋኞች ሙዚቃቸው ከጥበቡ ይልቅ ለቴክኖሎጂ ከፍተኛ ስፍራ በመስጠታቸው ሥራቸውንም ሆነ ሙዚቃውን አያውቁትም በማለትም ተችቷቸዋል። "አንዳንድ ሙዚቀኞች የትኛው የሙዚቃ መሳርያ ቁልፎች ላይ ዘፈኖቹ እንደሚያርፍ እንኳን አያውቁም፤ አቀናባሪው ብቻ ነው የሚያውቀው" ብሏል። የእሱ ሙዚቃዎች ከግጥም ይዘታቸውም ጋር ተያይዞ ከትውልድ ወደ ትውልድ መሸጋገር እንደቻሉም በኩራትም ይናገራል። "የእኔ ሙዚቃ የግጥም ጥልቀት ነበረው፤ ሙዚቃውም ጊዜ ተወስዶበት በደንብ ተደርጎ ነው የተሰራው። የዘመኑ ግን ዛሬ ተሰርተው ለነገ ይቀርባሉ። ወዲያውም ይሰለቻሉ" በማለት ከአምስት ዓመት በፊት ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር። ከአንጀሊክ በተጨማሪ በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻሉት በስዋሂሊ ከተቀነቀኑት መካከል 'ኒናሙይሊላ ሱዛና' (ለሱዛን እያለቀስኩ ነው)፣ 'ኒ ቪዙሪ ኩዋ ና ቢቢ' (ሚስት ሲኖርህ መልካም ነው)፣ 'ማርሻይ ያ ዋሬምቦ' (የሴቶች ሽቶ) የመሳሰሉ ሙዚቃዎቹ ይገኙበታል። ነገር ግን ለቢቢሲ እንደተናገረው የአንጀሊክን ያህል ድንበሮችን የተሻገረ እንዲሁም በሌላው ዓለምም መግነን የቻለ ሙዚቃ እንደሌለው ተናግሮ ነበር። በጎርጎሳውያኑ 2004 ወራትን ባስቆጠረው የመርከብ ጉዞ ላይ ጃፓንን ጨምሮ በሲንጋፖርና በሌሎች አገራትም ለወራት ያህል ተጫውቷል። "የሆነ ደረጃ ላይ ከደረስክ በሙዚቃህ ገንዘብ ታገኝበታለህ። አንጀሊክ በርካታ አገራት ወስዶኛል" ብሎም ነበር። በጎርጎሳውያኑ 2014ም ከሌላ ኬንያዊ ሙዚቀኛ ፒተር አክዋቢ ጋር በመሆን በአሜሪካ የሙዚቃ ጉዞ ያደረገ ሲሆን በስሚዝሶኒያን ፌስቲቫልም ላይ ተጫውቷል። ከተወዳጅ ሙዚቀኛነቱም በተጨማሪ ለሌሎች ሙዚቀኞች ያለውን ድጋፍም በተለያየ መንገድ ያሳይ የነበረ አርቲስት ነው። እንደ ሌሎች አገራት በኬንያ የሚገኙ ሙዚቀኞች ሥራዎችም በሕገወጥ መንገድ ተባዝተው ጎዳናዎች ላይ ይቸረቸራሉ። የተለያዩ የምሽት ክበቦችም ሆኑ የመዝናኛ ቦታዎች ያለ ሙዚቀኞቹ ፈቃድ ያጫውታሉ። ይህንንም ለመታገል ከቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ጋር የሚሰራ የኬንያ የሙዚቃ ቅጅ መብቶች ማኅበርን ከሌሎች ሙዚቀኞች ጋር በመሆን መስርቷል። የቦርድ አባልም ሆኖ ለብዙ ዓመታት አገልግሏል። የኬንያ መንግሥት ሙዚቀኛው በአስርት ዓመታት ውስጥ ላበረከተውም ጉልህ ሚና በጎርጎሳውያኑ 2009 ሽልማት አበርክቶለታል። ከሌሎች አራት ስመ ጥር ሙዚቀኞችም ጋር በመሆን የአገሪቱን ከፍተኛ ሽልማት በወቅቱ ከነበሩት ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ እጅ ተቀብሏል። በጎርጎሳውያኑ 2016 ጡረታ የወጣ ሲሆን፤ ኑሮውንም በምዕራብ ኬንያ በምትገኘው ካይሞሲ በምትባል ግዛት አድርጎ ነበር። የ80 ዓመቱ ሙዚቀኛ በካንሰር ህመም ሲሰቃይ ቆይቶ ህይወቱ ያለፈው ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር። የኬንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ለሙዚቀኛው የነበራቸውን አድናቆት እንዲሁም የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀዋል "ለሙዚቃ የተሰጠች ነፍስ ነበረው። ድምፁ የሚገርም ነበር። በሙዚቃዎቹ ላይ ያሳየው ፈጠራና ችሎታ የዘመኑ ወርቃማ ሙዚቀኛ ብለው አያንሰውም" ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ አክለውም "ጥሎልን ባለፈው ድንቅ ሙዚቃዎቹ ሁልጊዜም እናስታውሰዋለን። ስሙ ከመቃብር በላይ ነው። አንረሳህም" ብለዋል።
news-50883360
https://www.bbc.com/amharic/news-50883360
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ኢትዮጵያ ውስጥ ደብዛው የጠፋው ኤርትራዊው ኤርሚያስ ምርመራ እንዲጠናቀቅ መመሪያ ሰጠ
ከሁለት አመታት በፊት ከስዊድን አዲስ አበባ በገባ በሁለት ሳምንቱ ደብዛው ጠፋ የተባለው ኤርትራዊ ስዊድናዊው ኤርሚያስ ተክኤን አስመልክቶ የጠቅላይ አቃቤ ህግ የምርመራው ጉዳይ በተቻለ ፍጥነት እንዲጠናቀቅ ሲል መመሪያ መስጠቱን በስዊድን የኤርሚያስ ጠበቃ የሆኑት አቶ ሙሴ ኤፍሬም ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ይህንን መመሪያ ያስተላለፈው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ምክትል ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት በላከው ደብዳቤ ነው። ሕዳር 3/2012 ዓ.ም የተፃፈውን ደብዳቤ ቢቢሲ ማግኘት የቻለ ሲሆን ምርመራው ተመዝግቦ በሂደት ላይ የሚገኝ ከሆነ ከሚመለከታቸው የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች በጋራ በመሆን የተጀመረው ምርመራ በተቻለ ፍጥነት የሚጠናቀቅበትና፤ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች ተጠያቂ የሚሆኑበት ሁኔታ እንዲከናወን ብሏል። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች • የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ስለመዘጋቱ መረጃ የለኝም፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ሙሴ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የሰጠው መመሪያ ዓርብ ዕለት ታህሳስ 10/2012 ዓ.ም እንደደረሳቸው ገልጸው፤ ይህም ሁኔታ ትልቅ ተስፋ እንደሰጣቸው አክለዋል። "እስካሁን ባለው የሃገሪቷን ህግ ተከትለን ስንሄድ ነበር። ይሁን እንጂ ከአሁን በኋላ የምናየው ለውጥ ከሌለ ትዕግስታችን በማለቁ ወደ አፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቤቱታ እናቀርባለን" ብለዋል። የኤርሚያስ ተኪኤ ቤተሰቦችና ጠበቆች፤ የኢትዮጵያ ፖሊስ ለዚህ ጉዳይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተሻለ የምርመራ እውቀትና ክህሎት ያላቸው የመርማሪዎች ቡድን በማደራጀት ምርመራውን በጥልቀትና በፍጥነት እንዲካሄድ የስራ መመሪያ ይሰጥልን ብለው በጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም አመልክተው ነበር። ኤርትራዊ -ስዊድናዊ ኤርሚያስ ተኪኤ ማን ነው? ኤርሚያስ ትውልዱ ኤርትራዊ ሲሆን ዜግነቱ ደግሞ ስዊድናዊ ነው። ኤርሚያስ አዲስ አበባ የገባው ሚያዝያ 26፣ 2010 ዓ.ም ሲሆን፤ አዲስ አበባ በሚገኘው አርክ ሆቴል እስከ ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ.ም ቆይቷል ። • "አሁን ያገኘነው ሰላም ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው"- ዘማሪ ሳሙኤል ተስፋሚካኤል • ኤርትራ በቤተ ክርስቲያን ስር ያሉ የጤና ተቋማትን ወሰደች ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ አራት ሰዓት ሲሆን ዳህላክ (ኤፍሬም) የተባለ ግለሰበብ ጠርቶት በመኪና ከወሰደው በኋላ ደብዛው መጥፋቱን ቤተሰቡና ጠበቆቹ ማሳወቃቸውን የጠቅላይ አቃቤ ህግ ደብዳቤ ያስረዳል። ጉዳዩንም ለማጣራት ወዳረፈበት ሆቴል መሄዳቸውን ጠቅሰው ከሆቴሉ ያገኙትንም መረጃ ይዘው ሰኔ 22፣ 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ክፍል ምርመራ እንዲጣራላቸው አመልክተው፤ ምስክርነት ሰጥተው ቢመለሱም እስካሁን ድረስ ያለበትን እንደማያውቁና ደብዛው እንደጠፋ ባቀረቡት አቤቱታ መግለፃቸውን ይኸው የጠቅላይ አቃቤ ህግ ደብዳቤ ያስረዳል። አስመራ ተወልዶ ያደገው ኤርሚያስ ባለትዳር ሲሆን በስዊድን አገር በስደት ከ12 ዓመታት በላይ ኖሯል። • ኤርትራ፡ ''እናቶች ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር ታስረዋል'' ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ በሚል ስዊድን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቪዛ ጠይቆ፤ ኤምባሲው በሰጠው ፍቃድ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። ኤርሚያስ፤ ከዚህ ቀደምም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ እንደነበር ቤተሰቦቹ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
news-45004379
https://www.bbc.com/amharic/news-45004379
ደቡብ ኢትዮጵያ፡ ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ
በዞን ወይም በክልል እንደራጅ ጥያቄዎች በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተነሱ ነው። ከእነዚህም መካከል የኮንሶዎች በዞን እንደራጅ ጥያቄ አንዱ ነው። ትናንት ኮንሶዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከወጡ በኋላ የተደረጉ ለውጦችን ለማበረታት ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ የተስተጋባውም ይሀ ጥያቄ ነበር።
የኮንሶው ባህላዊ ንጉሥ ካላ ገዛኸኝ የኢንጂነሪንግ ምሩቅ ናቻው የኮንሶ ዞን የመሆን ጥያቄ፣ በኮንሶ የቀደሙ ተቃውሞዎች በጊዴሎና በአርባ ምንጭ የሚገኙ እስረኞች ጉዳይ የሰላማዊ ሰልፉ ዋነኛ አጀንዳዎች ነበሩ። በሌላ በኩል ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ኮንሶዎች እንደሚገባው አልወከሉንም ያሏቸው በክልል፣ በፌደሬሽንና በህዝብ ተወካዮች ያሉ እንደራሴዎቻቸው እንዲነሱ ያቀረቡት ጥያቄም ዳግም በሰላማዊ ሰልፉ ተነስቷል። ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ኮንሶዎች የዞን ጥያቄ ካነሱ ጀምሮ የትናንትናው ለ23ኛ ጊዜ ያደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ነው። የኮንሶዎችን በዞን እንደራጅ ጥያቄ ተከትሎም ቀውሶች ደርሰዋል። የሰው ህይወት ጠፍቷል። ብዙዎች ለእስርና ስደት ተዳርገዋል። ታስረው ከነበሩት መካከል የኮንሶ ብሄር ባህላዊ ንጉሥ ካላ ገዛኸኝ ወልደ ዳዊት አንዱ ነበሩ። በእርከን አሰራራቸው በአለም አቀፍ መድረክ የተነገረላቸው ኮንሶዎች ያነሱት ጥያቄ ብዙ እንዳልተባለለት እና እንዳልተነገረለት ብዙዎች ይስማማሉ። የኮንሶ ጥያቄ? ካላ ገዛኸኝ እንደሚሉት የኮንሶ ብሄር በዞን እንደራጅ ጥያቄ፤ ባሉበት የደቡብ ክልል ያለ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲሁም ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር አንድ ላይ በሚገኙበት ዞን የብሄሩ አባላት በማንነታቸው የሚደርስባቸው ጉዳትና ብሶት የወለደው ነው። "ቀበሌዎች ተቀንሰውብናል። በዞኑ በነበረ የስልጣን ሽኩቻ ከአጎራባች ብሄረሰቦች ጋር የነበረን ግንኙነትም ሻክሮ ነበር" የሚሉት ካላ ገዛኸኝ ነገሮች ይሻሻላሉ በሚል አራት ዓመታትን በተስፋ ከጠበቁ በኋላ በዞን እንደራጅ ጥያቄያቸውን እንዳነሱ ይናገራሉ። • ከሞት መንጋጋ ያመለጠችው የሐመሯ ወጣት • ካለሁበት 41: ከባሌ እስከ ቻድ የተደረገ የነጻነት ተጋድሎ በህዝብ ብዛት፣ በተማረ የሰው ሃይል፣ በገቢ ምንጭና በኢኮኖሚ አቅም ህገመንግስቱ ከሚያስቀምጠው መስፈርት አንፃር ጥያቄው ተገቢ እንደነበር ያምናሉ። የጥያቄውን መነሳት ተከትሎ አካባቢው ላይ በተፈጠረ ቀውስ ብዙዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ህይወት መጥፋቱን፣ ብዙዎች ከስራ መባረራቸውንና መታሰራቸውን ይገልጻሉ። እሳቸውም ለሳምንታት ታስረው እንደነበር ያስታውሳሉ። በመጨረሻ በተሰጣቸው መልስ ኮንሶዎች ደስተኛ ነበሩ። መልሱ ግን 'ዞን መሆን አትችሉም' የሚል ነበር። ካላ ገዛኸኝ እንደሚሉት እንደ ፍላጎትህ እንዳሰብከው አይሆንልህም የተባለው የኮንሶ ብሄር ነገሩን ከደስታም በላይ በሆነ ስሜት ነበር የተቀበለው። የፈለጉትን ስለተከለከሉ ደስታ እንዴት? "የደቡብ ክልል ለዚህ ዓይነት ጥያቄ በፅሁፍ መልስ ሲሰጥ የኮንሶ የመጀመሪያው ነበር። እኛም በምላሹ ክልሉን አመስግነናል። ተከልክለው እንዴት ይደሰታሉ የሚለው በክልሉ ዘንድ አግራሞትን ፈጥሮ ነበር" በማለት ጊዜውን ያስታውሳሉ። መልሱ ምንም ይሁን ምን ደስታ የተሰማቸው ጉዳያቸው በቁም ነገር በመታየቱ ብቻ ነበር። ይህ ደግሞ በራሱ የሚያሳየው ነገር አለ። ቦታ የማግኘትና የመደጥ የኮንሶዎች ንፁህ ፍላጎት። ከዚያም ጥያቄአቸውን ህግ እንደሚፈቅደው ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት ይዘው ሄዱ። በዚህ እርምጃቸው ግን ክልሉ ደስ ስላልተሰኘ የተለያዩ እርምጃዎችን እንደወሰደባቸው ይገልፃሉ። ጥያቄያቸውን ይዘው አዲስ አበባ ላይ ከቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲሁም ከፌደራል ጉዳዮችና ከአርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር እየተወያዩ ነበር። የያኔው አፈ ጉባኤ ጉዳዩ ክልሉን ይመለከታል በማለት ወደ ክልሉ ሲመልሱት ውሳኔው ህገመንግስቱን የተከተለ አይደለም በማለት ቅሬታቸውን አስገብተው አቤቱታቸው ተቀባይነት አግኝቶ እያለ ዳግም መታሰራቸውን ይናገራሉ። ካላ ገዛኸኝ ከሁለት ዓመት እስር በኋላ ከበርካታ የፖለቲካ እስረኞች ጋር የተለቀቁት ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነው። የኮንሶው ንጉስ ካላ ገዛኸኝ እንደ አውሮፓውያኑ በ2013 የኮንሶው ንጉስ ካላ ገዛኸኝ ለአንድ አለም አቀፍ ስብሰባ ከወንድማቸው ጋር በሞስኮ ተገኝተው ነበር ካላ የቤተሰባቸው መጠሪያ ሲሆን ኦክላ (ንጉስ) የሚል ማእረግ አላቸው። እሳቸው ከዘጠኙ የኮንሶ ጎሳዎች ከርቺሳ ከሚባለው ጎሳ ሲሆኑ በዚህ ጎሳ ግጭት ቢፈጠር ለማብረድና እርቅ ለማውረድ በፍትህ ጉዳይ ለመዳኘትም የሚታመነው የካላ ቤተሰብ እንደሆነ ያስረዳሉ። ካላ ገዛኸኝ ከመከላከያ ኢንጂነሪነግ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በኢንጂነሪንግ ዲፕሎማ ያገኙ ሲሆን የአባታቸውን ህልፈት ተከትሎ ስራቸውን አቋርጠው በአባታቸው ምትክ ህዝባቸውን ለማገልገል ወደ ቀያቸው ተመለሱ። ካላ ገዛኸኝ የኮንሶ ባህላዊ መሪ በመሆን የኮንሶ ጥያቄ መሪ የሆኑትም በዚሁ መልክ ነው። የኮንሶን ጥያቄ ለማራመድ ለተሰጣቸው ሃላፊነት ትልቅ ዋጋ ይሰጣሉ። ከኮንሶ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩ ብዞዎች ቢለቀቁም አሁንም በእስር ላይ ያሉ አሉ። ያለፈውን እንደ አንድ አጋጣሚ ቆጥረው አሁንም የዞን እንሁን ጥያቄያቸውን እንደሚያሰሙ ካላ ገዛኸኝ ይናገራሉ። "ጉዳቶች ደርሰዋል። ግን ያለፈ አልፏል ወደ ኋላ ማየትና በቀል እንደማያስፈልግ ነው ህዝቡን እየመከርኩ ያለሁት። በዚሁ እንቀጥላለን" ብለዋል።
news-51588510
https://www.bbc.com/amharic/news-51588510
ምዕራብ ኦሮሚያ፡ "መንግሥት ጠንከርና መረር ያለ እርምጃ ለመውሰድ ተገዷል" ጄነራል ብርሃኑ ጁላ
በምዕራብ ኦሮሚያ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ መንግሥት የአካባቢውን ደህንነት ለማስጠበቅ የጸጥታ ኃይል ወደ ስፍራው ማሰማራቱን መግለፁ ይታወሳል።
"ጃል መሮ አንድም ቀን መሳሪያ ተኩሶ አያውቅም፤...[ይልቁኑ] ታዳጊዎችን ከቀያቸው ሰብስቦ እያስጨረሳቸው ነው" መንግሥት የጸጥታ አስከባሪ ኃይል ወደ ስፍራው ያሰማራሁት ታጥቆ የሚንቀሳቀሱና የአካባቢው ነዋሪ ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ነው ቢልም፤ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ደግሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች ላይ እጁ አለበት ሲሉ ይኮንናሉ። • በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል? • በምዕራብ ኦሮሚያ በ12 ወራት ቢያንስ 8 የአካባቢው ባለስልጣናት ተገድለዋል ቢቢሲ በዚህ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከምክትል ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ጋር ቆይታ አድርጓል። "እኔ የምመራው ወታደር ሕዝብ አይነካም" የአገር መከላከያ ሠራዊት በምዕራብ ኦሮሚያ በስፋት ተሰማርቶ የሚገኝ ሲሆን፤ አካባቢውም ያለ ስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት በኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ሥር ይገኛል። የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ አካባቢው ከተሰማራ በኋላ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው መባሉን ምክትል ኢታማዦር ሹሙ አጥብቀው ይቃወማሉ። "ይህ ስህተት ነው" የሚሉት ምክትል ኢታማዦር ሹሙ፤ በአካባቢው ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው ኃይል ሁለት ዓመት እንዳስቆጠረ አስታውሰው፤ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እርምጃ ለመውሰድ ሠራዊት ወደ ሥፍራው ማዝመቱን ተናግረዋል። "የሠራዊት ሥራ ሕዝብን ከሽፍታ መለየት ነው። ለሕዝብ ከለላ መስጠት፣ ሽፍቶች ላይ ደግሞ እርምጃ መውሰድ ነው። በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚባለው ግን ከዚህ የተለየ ነው። ምን እንደሚባል እናውቃለን። የመከላከያ ሠራዊት አባላት 'ፕሮፌሽናል' ናቸው። ሕዝብን ከሽፍታ ይለያሉ። . . . የአገር መከላከያ ሠራዊት ሕዝብ ላይ ጉዳት አያደርስም። ሕዝቡም 'ሽፍታን አስወግዱልን' ነው እያለ ያለው እንጂ መከላከያ ይህን ጉዳት አደረሰብኝ አይደለም ያለው።" ይላሉ። • ኦነግና ኦፌኮ አባሎቻችን እየታሰሩብን ነው አሉ ምክትል ኢታማዦር ሹሙ መከላከያ ሠራዊት በሕዝብ ላይ ገዳት አደረሰ እየተባለ ያለው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መሆኑን ተናግረው፤ ትክክለኛውን መረጃ ለማግኘት መጠየቅ ያለበት የአካባቢው ሕዝብ ነው ባይ ናቸው። "እናንት ራሳችሁ ስትጠይቁ ስለሚያስፈሯሯቸው በሚስጥር ጠይቋቸው ከዛ እውነቱን ትረዳላችሁ" "እኔ ያደራጀሁት እና እኔ የምመራው ወታደር ሕዝብ አይነካም። የመንግሥት ወታደር ሕዝብ ላይ ጉዳት አድርሶ ከሆነ ግን መንግሥት ይጠየቃል። እኔም በግሌ ሕዝቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ እክሳለሁ።" "የተለየ ኦፕሬሽን" የአገር መከላከያ ምክትል ኢታማዦር ሹሙ እንደሚሉት ከሆነ፤ ጦሩ በአሁኑ ወቅት "የተለየ" ነው ያለውን ኦፕሬሽን በምዕራብ ኦሮሚያ እያካሄደ ይገኛል። "ከዚህ ቀደም ወደ ሰላም እንዲመጡ ይለመኑ ሁሉ ነበር። ልመናው ሲበዛባቸው ይልቁን መጠናከር ጀመሩ፤ ሕዝቡ ላይ የሚደርሰው በደል ተጠናክሮ ቀጠለ። ሕዝብ ያስፈራራሉ፣ ሕዝብ ይዘርፋሉ፣ ያስቃያሉ፣ አፍነው 70 እና 60 ኪሎ ሜትር ይዘው ሄደው ለሁለት ሳምንት ደብድበው ይለቃሉ። በዚህ መሰል ዘግናኛ ተግባር የሚታወቀው አል-ሸባብ ነበር። አል ሸባብ ራሱ አሁን እንዲህ አይነት ተግባር አይፈጽምም" በማለት መንግሥት "ጠንከር እና መረር" ያለ እርምጃ ለመውሰድ መገደዱን ያስረዳሉ። "ይህ ቡድን ሊድን የማይችል፤ አዕምሮው የተበላሸ መሆኑ በመንግሥት ታምኖበታል። የደፈጣ ተዋጊ ስነ-ምግባር እንኳ የሌላቸው ናቸው እኮ" በማለት ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የሚዋግዋቸውን ኃይሎች ባህሪ ይገልጻሉ። "መሮ አንድም ቀን መሳሪያ ሳይቱኩስ . . . ታዳጊዎችን እያስጨረሰ ነው" ምዕራብ ኦሮሚያ በኮማንድ ፖስት ሥር መተዳደር ከጀመረ ወዲህ በርካቶች ሰዎች በተዳጋጋሚ ለእስር እየታደረግን ነው እያሉ ቅሬታ ሲያቀርቡ ይሰማል። ምክትል ኢታማዦሩ ግን ይህ ፍጹም ስህተት ነው ይላሉ። "ይህ ሐሰት ነው። የስነ-ልቦና ጦርነት የሚባል ነገር አለ። አንድ ወታደር ሳይገድሉ 80 ወታደር ገደልን 100 ማረክን ይላሉ፣ መልሰው ደግሞ እንዲህ በሚባል ቀበሌ ውስጥ መከላከያ ገብቶ ሰው ገደለ ብለው ሐሰት ይነዛሉ። ገንዘብ እያወጡ የሚልኩላቸውን ደጋፊዎቻቸውን ለማስደሰት በማሰብ ያላገኙትን ድል አገኘን እያሉ ያወራሉ። እውነቱ ግን አንድም ቀን ከእኛ ጋር ፊት ለፊት ተዋግተው አያውቁም። ሁሌም ሲሸሹ ነው የሚመቱት። እየሸሹ ነው የሚያዙት። ከእኛ ጋር ፊት ለፊት እንኳ ተገናኘቶ የመዋጋት አቅም የላቸውም። ስለዚህ በእነሱ በኩል የሚመጣው ሁሉ እውነት ብሎ መቀበል ስህተት ነው" ይላሉ። • በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦሮሚያ የመንግሥት ኃላፊ በታጣቂዎች ተገደሉ • ጃል መሮ ከህወሃት ጋር እየሠራ ነው? በአሁኑ ወቅት በትግል ስሙ 'መሮ' ተብሎ በሚታወቀው ኩምሳ ድሪባ ከሚመራው ኃይል ውጪ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ሌላ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል አለመኖሩን የሚናገሩት ምክትል ኢታማዦር ሹሙ፤ መሮ የሚመራው ኃይልም ቢሆን መንግሥት እየወሰደ ባለው እርምጃ የታጣቂዎቹ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ይላሉ። "ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሄዷል። ባለፉት ሶስት ሳምንታት ሰላም ሆኗል። ለምለም በረሃ በሚባለው ቦታ እንጂ ሌላው አካባቢ ሠላም ነው። ሁሉም አካባቢ እሰኪጸዳ የሰላም ማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ ይካሄዳል። አሁን የቀሩት ስፖንሰር ያላቸው ህይወታቸውን በዚህ መልክ ለመምራት የፈለጉት ዋነኛዎቹ ብቻ ናቸው። እነሱም ተደብቀው ነው የሚገኙት። መሮ ራሱ ተደብቆ ነው የሚገኘው። ሠራዊት እሱ ያለበት ቦታ መድረሱን ሲሰማ ቦታ ይቀይራል። እሱ አንድም ቀን መሳሪያ ሳይተኩስ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ፤ ታዳጊዎችን ከቀያቸው ሰብስቦ እያስጨረሳቸው ነው" ይላሉ። "ስልክ ማቋረጡ ኦፕሬሽኑን ስኬታማ አድርጎታል" በምዕራብ ኦሮሚያ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ከተቋረጠ ሳምንታት ተቆጥረዋል። ምክትል ኢታማዦር ሹሙ የስልክ አገልግሎት የተቋረጠው በአካባቢው የአገር መከላከያ ሠራዊት እየወሰደው ካለው ኦፕሬሽን ጋር የተያያዘ መሆኑን ተናግረዋል። • የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀንና የመንግሥት ዝምታ • ከተገደሉት አንዱ የማዕድን ኩባንያው ባለቤት ነበር የስልክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ በአካባቢው በታጣቂዎቹ ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ስኬታማ ማድረጉን ተናግረዋል። የስልክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ "በጣም ነው የጠቀመን" የሚሉት ጀነራል ብርሃኑ፤ "እኚህ ሰዎች እኮ የመገናኛ ሬዲዮ እንኳን የላቸውም፤ ሞባይል ስልክ በመጠቀም ነው የመንግሥትን እንቅስቃሴ ለሁለት ዓመት ሲያከሽፉ የቆዩት" ብለዋል። ደቡብ ኦሮሚያ ከምዕራብ ኦሮሚያ በተጨማሪ በደቡብ ኦሮሚያ ጉጂ እና ቦረና አካባቢዎች ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል እንዳለ ይታመናል። ጄነራል ብርሃኑ እንደሚሉት በቅርቡ መንግሥት የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በአካባቢ የነበሩ ኃይሎች ላይ እርምጃ ተወስዷል። "በምዕራብ እና ምስራቅ ጉጂ ህዝቡን እያስገደዱ ቡና እያስመጡ ወደ ኬንያ አሻግረው ይሸጡ ነበር። ሕዝብ ሲንገላታ ቆይቷል። ይህ የሆነው ደግሞ መንግሥት ጉዳዩን በሰላም ለመፍታት የኃይል እርምጃ ሳይወስድ በመቅረቱ ነበር። ኦፕሬሽን ካካሄድን በኋላ ሁለቱም ጉጂዎች ነጻ ወጥተዋል። አሁን መደበቂያ ሲያጡ ወደ ሶሎሎ [ኬንያ እና ኢትዮጵያ ድንበር አዋሳኝ] ሸሽተዋል።" በማለት እያካሄዱት የሚገኘው ወታደራዊ እርምጃ ውጤት ማምጣቱን ይናገራሉ።
news-57139949
https://www.bbc.com/amharic/news-57139949
አንዳንድ ሴቶች ከወሊድ በኋላ ባሕሪ ይቀይሩ ይሆን?
ማሕደር አካሉ ትባላለች። ከሁለት ዓመት በፊት መንታ ልጆችን በቀዶ ጥገና ነው የተገላገለችው። ነፍሰጡር እያለች ክብደቷ በጣም ስለጨመረ ከ30 ሳምንት በኋላ መተኛት አልቻለችም ነበር።
"ቁጭ ብዬ ነበር የማድረው" ትላለች። ስትወልድ ከዚህ ሁሉ ችግር እንደምትላቀቅ ብታስብም፣ እንደፍላጎቷ ግን አልሆነላትም ነበር። መንታ ልጆቿን በየሁለት ሰዓት ልዩነት ማጥባት እና እንደልብ መንቀሳቀስ አለመቻል ችግር ሆነውባት ነበር። በዚህ አላበቃም ማሕደር "እኔ በምክንያት እና በውጤት የማምን ነበርኩ፤ በትንሽ ነገር ስሜታዊ አልሆንም ነበር፣ ከወልድኩ በኋላ ግን ማልቀስ እና ሰዎች ለምን አይረዱኝም በማለት ማኩረፍ ጀመርኩ። በተለይም በእናቴ እና በባለቤቴ እናደድ ነበር" ትላለች። ማህደር አንዲት ሴት ስትወልድ፣ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ስለምትጀምር የተለየ ልምድ ውስጥ ነው የምትገባው በማለት የነበረውን ሁኔታ ትገልፀዋለች። ለዚህ ደግሞ ቤተሰብም ሆነ ሐኪሞች ቀድመው አያዘጋጁንም ስትል የራሰወን ልምድ በመጥቅ ታስረዳለች። እንቅልፍ ማጣት፣ ስራ ሳይሰሩ ለረዥም ጊዜ መቆየት፣ ከራስ በላይ ለጨቅላዎቹ ትኩረት መስጠት፣ ውጥረቱን ያብሰዋል ትላለች። ማሕደር ያሳለፈችውን ከባድ ጊዜ ስትገልጽም፣ "ራሴን እጠላ ነበር። በሕይወቴ ተስፋ እቆርጥ ነበር፣ እንዲሁም ልጆቼ ሲያለቅሱ በጣም ስለምናደድ እናቴን 'ነይ ውሰጃቸው' ስል እጠራት ነበር።" ይኹን እንጂ እንዲህ ባሕሪዋን የቀየረው ነገር ሴቶች ከወሊድ በኋላ ሊገጥማቸው የሚችል የአእምሮ ድባቴ እንደሆነ ያወቀችው ከሶስት ወር በኋላ ነው። "ይህ ነገር ምንድን ነው ብዬ ጉግል ሳደርግ ፖስት ማርተም ዲፕረሺን የሚባል ሕመም እንደሆነ ተረዳሁ። እኔም የዚያ ተጠቂ መሆኔን አወቅሁ" ስትል ታብራራለች። ይህ ጉዳይ የባህሪ መቀየር ጉዳይ እንዳልሆነ እና እንደ ማንኛውም ዓይነት በሽታ መሆኑን ስታውቅ መጀመሪያ የወሰደችው እርምጃ ራሷን መቀበል እና ከራሷ ጋር ለመታረቅ መሞከር ነበር። ከዚያ በመቀጠል ደግሞ በአካበባቢዋ ለሚገኙ ሰዎች ማስረዳት ነበር። እንደ ማህደር ገለጻ ይህ ቀላል አልነበረም። ምክንያቱም ትላለች "በከፍተኛ የስሜት መለዋወጥ ውስጥ ስለነበርኩኝ ችግሬን በአግባቡ ማስረዳት እንኳ አልቻልኩም ነበር።" ኋላ ላይ ወደ መደበኛ ስራዋ ስትመለስ ከሰዎች ጋር መገናኛት ስትጀምር እና ችግሯን መግለጽ ስትጀምር እየቀለላት መጣ። ከዚህ በኋላ ለትምህርት ከአገር ርቃ ሄደች። "ለትምህርት ወደ ውጪ አገር እስከ ምሄድበት ለብቻዬ ጊዜ እስካገኝ ድረስ ተስፋ የመቁረጥ እና ስሜታዊ የመሆን ነገር ቢቀንስም አልጠፋም ነበር።" ቤተሰቦቿ በአራስነት ጊዜዋ በጣም ተጎድታ ስለነበር ትልቁ ትኩረታቸው እርሷን በምግብ መጠገን ነበር። "ስለዚህ ያመጣሁት የባህሪ ለውጥ ብዙም አልታያቸውም። ብዙ ጊዚያቸውን ልጆቹን በመንከባከብ ነበር የሚያሳልፉት።" ስትል ሁኔታውን ታስታውሳለች። በተጨማሪ " ብቻዬን ሆኜ አለቅሳለሁ። ወይ ደግሞ አመመኝ የሚል ምክንያት እሰጣለሁ።" ያለምክንያት ስታለቅስ ማንም ሊረዳ ት እንደማይቸል የምትናገረው ማሕደር ከባድ ወቅት ማሳለፈን ለቢቢሲ አካፍላለች። ከራስ አልፎ ለሌላ መትረፍ ማሕደር ይህን ያሳለፈችውን ጊዜ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ካሉ ጓደኞቿ ጋር ቡድን በመፍጠር ማካፈል ጀመረች። ያኔ ሰዎች ስልክሽን ስጪን። ስለዚህ ጉዳይ ልናዋራሽ እንፈልጋለን በማለት አጭር መልዕክት ይሉኩላት ጀመር። ከእነዚህ ጓደኞቿ ጋር በማህበራዊ ሚዲያ በምታደርገው ውይይት ብዙዎቸ ወንዶች ይህንን ጉዳይ ከእነ አካቴው ሰምተውት እንደማያውቁት፣ ገሚሶቹ ሴቶችም እውቀቱ እንደሌላቸው፣ ሌሎቹ ደግሞ ጉዳዩ ቢገጥማቸው እንኳ የችግሩ ምንነት እንደማይረዱት ግንዛቤውን አገኘች። "በአጭር መልዕክት ካዋሩኝ ሰዎች አንዷ 'ባለቤቴን ላየው አልፈልግም።' ሌላዋ ደግሞ 'ልጄን እጠላዋለሁ' ስትለኝ ከወለድሽ ስንት ጊዜሽ ነው ብዬ ጠየኳት። ከዚያም 'ሰላይ ነሽ እንዴ? ልጄን እጠላዋለሁ ስልሽ እብድ ነሽ እንዴ ያላልሽኝ ለምንድን ነው?' አለችኝ። አንድ ሁለት ሶስት የሚሆኑ ሴቶች ደግሞ ራሳችንን ልናጠፋ ስንል ቤተሰብ ነው ያዳነን የሚል ነገር ነግረውኛል።" በማለት ያጋጠሟትን ታሪኮች ታካፍላለች። ከዚያም ይህ ነገር ቀላል አለመሆኑን ተረዳሁ የምትለው ማሕደር፣ "እኔ ራሴ በዚህ ጉዳይ ውስጥ ስላለፍኩኝ ጉዳታቸው ይሰማኛል" ስትል የፈጠረባትን ስሜት ታስረዳለች። የአእምሮ ጤና ጉዳይ ሌሎች ሰዎች ስለማይረዱት እና ችግሩ የደረሰባቸው ደግሞ ፍርድን ወይንም መፈረጅን ስለሚፈሩ አያወሩትም። ስለዚህ እኔ እንደዚህ አይነት ሰዎችን ቀረብ ብዬ ልምዴን አካፍዬ አንድ ሰው እንኳ ብረዳ ብዬ ነው ታሪኬን ማካፈል የጀመርኩት ትላለች። ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ ይህንን ጉዳይ አካፍላለሁ ስትልም ነግራናለች። ይህ ጉዳይ የበረታባቸውን ሴቶች ደግሞ የስነ አእምሮ ባለሙያ እንዲያያቸው ለማገናኘት እንደምትሞክር እና አድራሻ እንደምትጠቁማቸው አክላ ታስረዳለች። አስቀድሞ ማወቅ ይረዳል ሴቶች የእርግዝና ክትትል ሲያደርጉ በሐኪሞች በኩል አንዲት ሴት ከወሊድ በኋላ የድህረ ወሊድ ድባቴ ሊገጥማት እንደሚችል ሊነገራት ይገባል። ይሀንን ጉዳይ ከታወቀ በኋላ ደግሞ ቤተሰብ ልክ ሰውነቷን እንዲጠገን እንደሚረዳት ሁሉ ለአእምሮ ጤናዋም ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል። ይህ ሕመም አንዳንድ ሴቶች ቶሎ ቢለቅም ሌሎች ላይ ግን ረዥም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል "የወለደች ሴት ለተወሰነ ጊዜ ብቻዋን መተው የለባትም። ምክንየቱም በዚያ ጊዜ ውስጥ በስሜት የምትወስናቸው ውሳኔዎች ስለማይታወቅ ትላለች" ማሕደር። የተለየ ምልክት ከታየ ደግሞ ወደ ሕክምና ባለሙያ መሄድ ወሳኝ መሆኑን ታስረዳለች። የሕክምና ባለሙያዎች ምን ይላሉ? በጅማ ዩኒቨረስቲ መምህር የሆኑት የማሕፀንና ጽንስ ባለሙያው ዶ/ር ደምሰው አመኑ እንደሚሉት ይህ የድባቴ ሕመም በእርግዝና ጊዜም ሊያጋጥም ይችላል። እነዚህ ሴቶች ቀድሞውኑ ሐኪም ያላወቀው የድባቴ ሕመም ሊኖርባቸውም ይችላል ይላሉ። ይኹን እንጂ ብዙ ሴቶች በእርግዝና ጊዜ ሰውነታቸው ውስጥ የሆርሞን መለዋወጥ ስለሚፈጠር ከወሊድ በኋላ ሰውነታቸው ወደ ቀድሞ ስፍራው ለመመለስ በሚያደርገው ትግል ይህ ሕመም ሊመጣ ይችላል። በተጨማሪም ሴቶች በሚወልዱ ጊዜ ልጃቸው ችግር ያለበት ከሆነ ሕመሙ ሊብስ ይችላል። ያደጉ አገራት መረጃ እንደሚያሳየው በአጠቃላይ 50 በመቶ የሚሆኑ ወላድ ሴቶች ይህ 'ፖስት ፓርተም ዲፕረሽን' ያጋጥማቸዋል። በቀላሉ ሊለይ የሚችል ምልክት የሚያዩት ግን ጥቂቶቹ ናቸው ይላሉ ሐኪሙ። እነዚህ ሴቶች ከሚያሳዩት የሕመም ምልከቶች ውስጥ ቀድሞውኑ የደም ግፊት፣ ስኳር እንዲሁም ድባቴ የሚያማቸው ሰዎች ለዚህ ሕመም ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው። ለዚህ ሕመም የተጋለጡ ሴቶች ሌሎች ሰዎች በድባቴ ሲያዙ ከሚያሳዩት ምልክት የተለየ ላያሳዩ ይችላሉ። ይህ ሕመም ከተወሰኑ ቀናት እስከ ስድስት ሳምንት ሊቆይ ይችላል። አንዴ ምልክቱ ከተለየ መድሃኒት የሚሰጥ ሲሆን፣ የስነልቦና ባለሙያዎች ደግሞ የምክር ድጋፍ ይሰጣሉ። ይህ ከወሊድ በኋላ የሚመጣ ሕመም ለልጃቸው እንክብካቤ ለመስጠት ካለመፈለግ አልፎ የራሳቸውን ሕይወት እስከማሳለፍ ድረስ ሊደርስ ይችላል ብለዋል ዶ/ር ደምሰው። ይኹን እንጂ ሴቶች ሲወልዱ ወዲያው ሊያጋጥማቸው የሚችለው ድባቴ እዚያው የሕክምና ማዕከል ውስጥ እያሉ በቀላል ሁኔታ ድጋፍ ሊያገኙበት የሚችሉት ነው። ከሕክምና መስጫ ከወጡ እና ከዚህ ካለፈ ግን ሊረዳቸው የሚችለው የማህፀንና ጽንስ ባለሙያ ሳይሆን የስነ አእምሮና የስነልቦና አማካሪ ድጋፍ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
51081642
https://www.bbc.com/amharic/51081642
''ማን ይለቀቅ ፤ ማን አይለቀቅ እስካሁን አላወቅንም'' የታጋች ቤተሰቦች
በጸጥታ ስጋት ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲያመሩ በታጣቂዎች የታገቱ 21 የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መለቀቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ትናንት አስታውቋል።
ተማሪዎቹ የታገቱት ከደምቢ ዶሎ ጋምቤላ በሚወስደው መንገድ ላይ ነው በደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጫካ ውስጥ ታግተው መቆየታቸውን የፅ/ቤቱ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግረዋል። ታግተው ከነበሩ ተማሪዎች ውስጥ 13 ሴትና 8 ወንድ በድምሩ 21 ተማሪዎች የተለቀቁ ሲሆን አሁንም ቀሪ 5 ተማሪዎችና አንድ የአካባቢው ተወላጅ ታግተው እንደሚገኙና በአካባቢው የፀጥታ ኃይል መሰማራቱን ኃላፊው አክለዋል። • የታገቱት 17ቱ ተማሪዎች፡ "ከታገቱት መካከል አንዷ ነበርኩ፤ በሦስተኛ ቀኔ አምልጫለሁ" • በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ የታገቱት ስድስት ታዳጊዎች ለምን ተገደሉ? ኃላፊው ይህንን ይበሉ እንጅ፤ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገና እህቱ እንደታገተችበት የነገረን አንድ ግለሰብ ግን አሁንም ድረስ እህቱም ሆነች ሌሎቹ ተማሪዎች በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ መረጃው እንደሌለው ነግሮናል። ''እህቴ እስካሁን አልደወለችልኝም፤ ማንም የደወለልኝም ሰው የለም። ተማሪዎች ተለቅቀዋል የሚለውን ዜና ከሰማሁ በኋላም ሌሎች ልጆቻቸው የታገቱባቸው ቤተሰቦች ጋር በስልክ ተገናንኝተን ነበር፤ እነሱም እስካሁን ምንም መረጃ የላቸውም'' ብሏል። አክሎም ''እኔም ደወልኩላቸው፤ እነሱም ደወሉልኝ። ነገር ግን ማንኛችንም ተማሪዎቹ ስላሉበት ሁኔታ ከመንግሥትም ሆነ ከተማሪዎቹ ራሳቸው የተነገረን ነገር የለም'' ብሏል። ''ትናንት ተማሪዎች ተለቅቀዋል የሚለውን ዜና ስንሰማ በጣም ደስ ብሎናል። ነገር ግን የተለቀቁ ተማሪዎች ዝርዝር ስላልታወቀ ግራ ገብቶናል። በጣም ደስ ቢለንም ማን ይለቀቅ ማን ይቅር ስላላወቅን አስቸጋሪ ሆኖብናል።'' ለሁለት ሳምንታት ከእህቱ ጋር በስልክ ሲገናኙ ስለአወሩት ነገር ጠይቀነው ''በደወሉ ቁጥር ቦታው ምን ይመስላል? ንገሩን ወይ እራሳችን ወይ ፖሊስ እንዲመጣ ስንላቸው ማውራት አንችልም፤ አጠገባችን አሉ ይሉን ነበር። በተጨማሪ ደግሞ ማታ ላይ ለሁለት ወይም ለሶስት ሰዓታት ያክል በጫካ ውስጥ እንድንጓዝ ያደርጉናል ብላኝ ነበር'' ብሎናል። ''ከዋልንበት አናድርም፤ ካደርንበት አንውልም። ሁሌም ማታ ማታ እንጓዛለን'' የሚል ምለሽ ትሰጠው እንደነበር ያስታውሳል። ሌላኛዋ ያነጋገርናትና ወንድሟ ከታጋች ተማሪዎች መካካል አንዱ እንደሆነ የነገረችን ወጣትም እስካሁን ተለቀቁ የተባሉት ተማሪዎች ስላሉበት ሁኔታ የሰማችው ነገር እንደሌለ ትናገራለች። ''ትናንት ዜናውን ከሰማንበት ሰዓት ጀምሮ በጉጉት እየተጠባበቅን ነበር፤ ነገር ግን እስካሁን ወንድሜም አልደወለም፤ ሌላ የደወለልኝም አካል የለም'' ብላለች። ''ሌሎች የቤተሰብ አባሎቻቸው ከታገቱባቸው ጋር እንገናኛለን፤ እነሱም ቢሆኑ እስካሁን የሰሙት ነገር እንደሌለ ነግረውኛል። ማን እንደተለቀቀና ማን እንዳልተለቀቀ ይነግሩናል ብለን ብንጠብቅም እስካሁን ምንም ነገር የለም'' የታጋች እህት የሰጠችው ምላሽ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታገቱት ተማሪዎች ስለተለቀቁበት ሁኔታ እና አሁን የት እንደሚገኙ የጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። "ከታገቱት መካከል አንዷ ነበርኩ፤ በሦስተኛ ቀኔ አምልጫለሁ" ተማሪ አስምራ ሹሜ ተማሪ አስምራ ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንዷ ነበረች። የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ታስረዳለች። "በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት የኢንጅነሪንግ ተማሪ ነበርኩ። አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው በመዘጋቱ ወደ ትውልድ አካባቢዬ ተመልሼ አዲስ ዘመን ከተማ ነው ያለሁት። ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንዷ ነኝ። መጀመሪያ በአጋቾቹ የተያዝነው 18 ተማሪዎች ነበርን። እኔ ማምለጥ ስለቻልኩ አሁን ታግተው ያሉት ተማሪዎች ቁጥር 17 ነው። ከእነዚህ መካከል 4ቱ ወንዶች ሲሆኑ 13ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው። አሁን ታግተው ያሉት ተመራቂ ተማሪዎች እና የኢንጅነሪንግ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ናቸው። በወቅቱ በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ስለነበር ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጥተው ነበር። እኛም መውጣት አሰብን ወደ አዲስ አበባ በቀጥታ የሚያስመጣው ዋና መንገድ በመዘጋቱ ከደምቢ ዶሎ በጋምቤላ በኩል አድርገን አዲስ አበባ ለመግባት ወሰንን። ሁላችንም ከአማራ ክልል አካባቢዎች የመጣን ተማሪዎች ነን። ከደምቢ ዶሎ ጋምቤላ የ30 ብር ትራንስፖርት ሲሆን እቅዳችን ጋምቤላ አድረን ወደ አዲስ አበባ ነበር። ነገር ግን ያሰብነው ቦታ ሳንደርስ ደምቢ ዶሎ እና ጋምቤላ መካከል 'ሱድ' የምትባል ቦታ ላይ ስንደርስ መኪናውን አስቁመው፤ ወጠምሻ ወጣቶች መጥተው አፈኑን። የአፋኞቹ ቁጥር ከእኛ ቁጥር በላይ ነበር። አካባቢው ጥቅጥቅ ያለ ጫካ በመሆኑ በእርሱ ውስጥ ይዘውን ገቡ። ይዘውን ሲሄዱ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ከማየት ውጭ ለማስጣል የሞከረ አልነበረም። እየጮህን ነው ይዘውን የሄዱት። የጫካውን ግማሽ እንደተራመድን የተወሰኑት ሴቶች መራመድ አቃታቸውና ወደቁ። ታዲያ እነርሱን 'ተነሱ፤ አትነሱ' እያሉ ለማንሳት ሲሞክሩ ነበር እኔ ከአይናቸው የተሰወርኩት። በጫካው ውስጥ ለሁለት ቀናት ያህል ካደርኩ በኋላ፤ በሦስተኛው ቀን ወደ ዋናው የመኪና መስመር መውጣት ቻልኩ። ግራ ተጋባሁ፤ ስልኬን ስለወሰዱት ስልክ መደወል አልቻልኩም፤ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር። እንደምንም ብዬ ወደ መስመር ስወጣ አንድ አማርኛ በትንሹም ቢሆን መናገር የሚችሉ አባት አገኘሁ። እርሳቸው እንዳዩኝ 'የእኔስ ልጆች እንዲህ አይደል የሚሆኑት' ብለው በማዘን ኮታቸውን አለበሱኝ። 'ከታየሁ እኔም እገደላለሁ' ብለው ደብቀው አስቀመጡኝ። 'የት ነው መሄድ የምትፈልጊው' አሉኝ። 'ደምቢ ዶሎ ለፌደራል ፖሊሶች ስጡኝ' አልኳቸው። ከዚያም መኪና ለምነው አሳፍረው ላኩኝ። መረጃውንም ለፌደራል ፖሊሶቹ ተናግሬያለሁ። ፌደራል ፖሊሶቹ 'ቦታው እንኳን ለተማሪ ለወታደርም አስጊ ነው፤ እንከታተላለን' አሉኝ። ከታገቱት መካከል አንዷ ጓደኛዬ መጀመሪያ አካባቢ ስልክ እየሰጧት ትደውልልኝ ነበር። ለማውራት ብዙም ነፃነት ባይኖራትም 'በጣም እያሰቃዩን ነው፤ ምግብም ሲያሻቸው ይሰጡናል፤ ሲፈልጉ ደግሞ ይከልክሉናል' ስትል ነግራኛለች። የምትደውልበትን ስልክ 'የእነርሱ ነው ያዥው' ብላኝ ነበር። ከዛን ቀን በኋላ ግን አይሰራም፤ እነርሱም ደውለው አያውቁም፤ እኛም አግኝተናቸው አናውቅም። ይመለከታቸዋል ለተባሉ አካላት፤ ለአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት፣ ለፀጥታ እና ደህንነት መረጃውን ሰጥቻለሁ፤ ጠይቄያለሁ። 'እንከታተላለን' ነው ያሉኝ። ከዚያ መምጣቴን የሚያውቁ የተማሪዎቹ ወላጆችም ያለሁበት ድረስ እየመጡ ያለቅሳሉ፤ እኔ ግን 'መንግሥት ይዟቸዋል፤ አሁን ይመጣሉ' እያልኩ ከማረጋጋት ውጭ የማደርገው ጠፍቶኛል።" የታጋች ተማሪዎች ቤተሰቦች ምን ይላሉ? ተማሪዎቹ ተለቀዋል የሚለው ዜና ከመሰማቱ በፊት ቢቢሲ ያነጋገራቸው እና ስማቸውን ለልጆቹ ደህንነት ስንል ያልጠቀስናቸው የታገቱት ተማሪ ቤተሰቦች፤ ተማሪዎቹ ከታገቱ አንድ ወር እንዳለፋቸው ይናገራሉ። "በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ስልክ ይደውሉ ነበር፤ አሁን ግን ድምፃቸውን ከሰማን ሦስት ሳምንታት አልፈዋል" ይላሉ። እህቱ እንደታገተችበት የነገረን አንድ ግለሰብ፤ በዩኒቨርሲቲው ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ሌሎች ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ሲወጡ፤ እርሱም እህቱን ጨምሮ ሌሎች ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ቢነግራቸውም እነርሱ ግን ከአሁን አሁን ይረጋጋል እያሉ መቆየታቸውን ያስረዳል። ይህ ግለሰብ እንደሚለው ስልክ ተደውሎለት እህቱን ጨምሮ ሌሎች ተማሪዎች ስለመታፈናቸው የሰሙት ሕዳር 24፣ 2012 ዓ.ም ነው። ተማሪዎቹ ከታገቱ በኋላ በነበሩት ሁለት ሳምንታት በተማሪዎቹ ስልክ ከዚያ በኋላ 'የአጋቾቹ ነው' ባሏቸው ስልክ ይደውሉላቸው ነበር። ቦታውን ሲጠይቋቸው ግን እንደማያውቁት ነበር ሲነግሯቸው የቆዩት። "የሆነ ሰዓት ላይ ስልክ ተሰጥቷት የፅሁፍ መልዕክት ላከችልኝ፤ ''አሻና አፋን ገደራ' የሚባል ቦታ ነው ያለነው፤ ለመከላከያ ደውሉና እዚህ አካባቢ ይፈልጉን' ብላ ፃፈችልኝ" ይላል። በመጨረሻው የስልክ ልውውጣቸው፤ "አሁንም እዚያው ቦታ ነሽ ወይ?" ብሎ ሲጠይቃት "በፊት ቢሆን ጥሩ ነበር፤ አሁን ቦታ ቀይረናል፤ ሌሊት ሌሊት ደግሞ የሁለት የሦስት ሰዓት መንገድ በጫካ እንጓዛለን፤ አታገኙንም፤ አሁንም ልትንቀሳቀሱ ነው ተብለናል፤ እስካሁን ባለው ደህና ነን'' ስትል ስልኩን ከዘጋች ወዲህ እህቱን በስልክ ማግኘት እንዳልቻለ ይናገራል። ከታጋች ተማሪዎች ወላጆች መካከል ሁለት ሰዎች፤ ስለ ልጆቻቸው መረጃ ፍለጋ ወደ ደምቢ ዶሎ ተጉዘው እንደነበረ ይሄው እህቱ የታገተችበት ወንድም ይናገራል። እሱ እንደሚለው ወደ ሥፍራው የሄዱት ሰዎች ከዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከሚመለከታቸው የክልሉ መንግሥት ምላሽ ማግኘት አልቻሉም። ሌላኛዋ የታጋች ተማሪ እህት እንደነገረችን፤ ቀደም ብሎ በዩኒቨርሲቲው አንድ የአማራ ተወላጅ ተማሪ መገደሉን ተከትሎ ወንድሟ ከፍተኛ ስጋት አድሮበት እርሷ ጋር ደውሎ ገንዘብ እንድትልክለት መጠየቁን ታስታውሳለች። • በምዕራብ ኦሮሚያ የስልክና ኢንተርኔት ከተቋረጠ ቀናቶች ተቆጠሩ "የደወለው ቅዳሜ ቀን ስለነበር እስከ ሰኞ እንዲታገስ ነገርኩት፤ ሰኞ ዕለት ብር ልልክለት ስደውል ስልኩ አይሰራም። በማግስቱ ደውሎ መያዛቸውን ነገረኝ። ከተያዙ ጀምሮ ሁለት ሳምንታት ድረስ ይደውሉ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ድምፃቸው አልተሰማም" ትላለች። እስካሁን የምንችለውን ነገር ሁሉ እያደረግን ነው የምትለው የተማሪው እህት፤ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የምታገኛቸው የታጋች ወላጆች በከፍተኛ ሃዘንና ጭንቀት ላይ እንደሚገኙ ትናገራለች። "አንጀታቸውን በገመድ አስረው መሬት ላይ ተኝተው ይፀልያሉ፤ 'ሞተው ከሆነ አስክሬናቸው ይምጣልን'" እያሉ ነጋ ጠባ እያለቀሱ ነው" ትላለች። ተማሪዎቹ ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንደሚፈፀምባቸውና እየተሰቃዩ እንደሚገኙ መስማታቸውንም አክላለች። የአጋቾቹ ፍላጎት ምንድነው? ወንድሟ የታገተባት እህት ከወንድሟ ባገኘችው መረጃ መሠረት አጋቾቹ ገንዘብ አይፈልጉም። ከአጋቾቹ እጅ ያመለጠችው አስምራ እንደምትናገረው፤ አጋቾቹ በተደጋጋሚ "ከእናንተ ጋር ጸብ የለንም። ጸባችን ከመንግሥት ጋር ነው" እንደሚሉ ትናገራለች። አጋቾቹ "የአማራ ሕዝብ ልጆቻችን ታግተዋል ብሎ ሰልፍ ሲወጣ፤ መንግሥት እኛን ያነጋግራል። የዛኔ እኛ ጥያቄያችንን ለመንግሥት እናቀርባለን፤ ጥያቄያችንም ይመለሳል" እንዳሉ አስምራ ገልፃልናለች። የመንግሥት አካላት ምላሽ? ኦሮሚያ ቅዳሜ ጥር 2/2012 ዓ.ም. ያነጋገርናቸው የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ "ምንም አይነት መረጃ የለኝም። እኔ የሰማሁት ነገር የለም" ይላሉ። ጉዳዩ እርሳቸው የሚመሩትን ቢሮ በቀጥታ የሚመለከት መሆኑን በመጥቀስ ስለጉዳይ እንዴት መረጃ ሳይኖራቸው እንደቀረ የተጠየቁት ኮሎኔል አበበ ገረሱ፤ "እኔ ምንም አልሰማሁም ነው የምልህ። ለምድን ነው የምትጠይቀኝ?" በማለት መልሰዋል። የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በበኩላቸው ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎች የሉም ብለዋል። ኃላፊው "ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ የለም" ከማለት ውጪ ማብራሪያ መስጠት አልፈለጉም። አማራ በዕለቱ ያነጋገርናቸው የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገርም፤ "አሁን ማውራት የማልችልበት ቦታ ነው ያለሁት" በማለት የእጅ ስልካቸውን ዘግተውታል። አቶ አገኘው ተሻገርን መልሰን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከአምስት ቀናት በፊት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ "አራት ተማሪዎች ታግተው እንደሚገኙ መረጃው አለኝ" ማለታቸው ይታወሳል። ርዕሰ መስተዳደሩ ተማሪዎቹ ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ከአባ ገዳዎች፣ ከአካባቢው ማኅበረሰብ እና ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር ውይይት እያደረግንም ነው ብለው ነበር።
news-50184731
https://www.bbc.com/amharic/news-50184731
በተለያዩ ሥፍራዎች ባጋጠሙ ግጭቶች የሟቾች ቁጥር 67 ደርሷል
ከሰሞኑ በተከሰቱ ግጭቶች የሟቾች ቁጥር ስልሳ ሰባት መድረሱን ሮይተርስ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነርን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ግጭቶቹ በተከሰተባቸው ኦሮሚያ ክልል፣ ድሬዳዋ እና ሐረር ከተሞች ስልሳ ሁለት ንፁኃን ዜጎች እንዲሁም አምስት የፖሊስ አባላት መገደላቸውን ኮሚሽነር ከፍያለው ተፈራ ለሮይተርስ ተናግረዋል። ስለ አሟሟታቸውም ተጠይቀው እንደተናገሩት አስራ ሶስቱ በጥይት ሲሆን ቀሪዎቹ 54ቱ ደግሞ በድንጋይ ተደብድበው መሆኑን ዘገባው አስነብቧል። ኒውዮርክ ታይምስ በበኩሉ አስራ ሦስቱ የሞቱት በፀጥታ ኃይሎች እንደሆነና ቀሪዎቹ የግድያ መንስዔ ደግሞ የእርስ በእርስ ግጭት መሆኑን ኮሚሽነር ከፍያለው ተፈራን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ከዚህም በተጨማሪ 213 ሰዎች መቁሰላቸውንም ይኸው ዘገባ አትቷል። ከግማሽ በላይ ለሆነው የግድያ መንስዔ ደግሞ የእርስ በእርስ ግጭት መሆኑን የየአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት፣ የሆስፒታል ምንጮች እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ትናንት ቢቢሲ ከተለያዩ አካባቢዎች ባለሥልጣናት፣ ከሆስፒታል ምንጮችና ነዋሪዎች ባገኘው መረጃ የሟቾች ቁጥር 44 መድረሱን ዘግቦ ነበር። • ወደ ኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለፀ • የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር ሊወያዩ ነው አዳማ ዶ/ር ደሳለኝ ፍቃዱ በአዳማ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው። ከረቡዕ እስከ ዛሬ (ዓርብ) ድረስ ወደ አዳማ ሆስፒታል ህይወታቸው አልፎ አስክሬናቸው የመጣ ሰዎች እና የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይቶ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር በጠቅላላው 16 መሆኑን ያስረዳሉ። ዶ/ር ደሳለኝ እንደሚሉት ረቡዕ ዕለት የ3 ሰዎች አስክሬን ወደ ሆስፒታል መጥቷል። ከእነዚህም መካከል ሁለቱ አፍሪካ ዱቄት ፋብሪካ ዘበኛ ጥይት ተኩሶ የገደላቸው ሰዎች ይገኙበታል። የአዳማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ራውዳ ሁሴን የዱቄት ፋብሪካው ጥበቃ ጥይት ተኩሶ ሁለት ሰዎችን መግደሉን እና በዚህ የተበሳጩ ሰልፈኞች በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ 15 መኪኖች ማቃጠላቸውን ረቡዕ ዕለት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ዶ/ር ደሳለኝ ትናንት ሐሙስ ሆስፒታሉ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ተጎጂዎችን ያስተናገደበት ቀን እንደሆነ ያስረዳሉ። "ትናንት ጉዳት ደርሶባቸው የመጡት ሰዎች ቁጥር ከ100 በላይ ይሆናል" ያሉ ሲሆን የጉዳቱ መጠን ከከባድ እስከ ቀላል የሚባል እንደሆነ ያሰረዳሉ። "በዱላ የተደበደቡ፣ በስለት ጭንቅላታቸው ላይ የተመቱ፣ በጥይት የተመቱ ሰዎችም አሉበት" የሚሉት ዶ/ር ደሳለኝ፤ ትናንት ብቻ ህይወታቸው አልፎ አስክሬናቸው የመጣ እና በህክምና ላይ እያሉ ህይወታቸው የያለፈ ሰዎች ቁጥር 12 ነው ይላሉ። ረቡዕ ዕለት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ከፍተኛ የህክምና ክትትል ክፍል (አይሲዩ) ውስጥ የነበረ ወጣት ዛሬ ጠዋት ህይወቱ አልፏል ብለዋል። "አሁንም በሆስፒታሉ በአደጋኛ የጤና ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች አሉ። የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል። አይኑ የጠፋ፣ አጥንቱ የተሰበረ ብዙ ነው" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዶ/ር ደሳለኝ እንደሚሉት በከተማው ውስጥ ያለው ግጭት ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ዘልቆ ስለመግባቱም ይናገራሉ። "ወንድሙ የሞተበት አንድ ልጅ አስክሬን ክፍል አቅራቢያ አምርሮ እያለቀሰ ሳለ፤ የተደራጁ ሰዎች የሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ከገቡ በኋላ ሲያለቅ የነበረውን ልጅ ላይ ጉዳት አድረሰዋል" ይላሉ። ይህ ወጣት የቀዶ ህክምና ከተደረገለት በኋላ የጤናው ሁኔታ መሻሻል እያሳየ እንደሚገኝ በመግለጽ፤ የሆስፒታሉ ባልደረቦች ከታካሚ ብዛት እያጋጠማቸው ካለው የሥራ ጫና በተጨማሪ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የደህንነት ስጋት መኖሩን ጠቁመው አልፈዋል። • "ያለን አማራጭ ውይይት ብቻ ነው" ጀዋር መሐመድ በአዳማ ያለው ሁኔታ እየተረጋጋ ያለ ቢመስልም በግጭት ሳቢያ ጉዳት አጋጥሟቸው ወደ ሆስፒታል የመጡ ሰዎች ስለመኖራቸው ዶ/ር ደሳለኝ ተናግረዋል። በተያያዘ ዜና የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ (ቪኦኤ) የአፋን ኦሮሞ ክፍል ሪፖርተር የሆነው ጋዜጠኛ ሙክታር ጀማል በአዳማ ከተማ 'ጀማል መጋዘን' ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በመንገድ ላይ ቃለ-መጠይቅ እያደረገ ሳለ ድብደባ እና ዘረፋ ተፈጽሞበታል። ጭንቅላቱ እና ወገቡ ላይ ጉዳት ያጋጠመው ጋዜጠኛ ሙክታር ሆስፒታል ተኝቶ የህክምና አገልግሎት እየተከታተለ ነው። ሙክታር ቃለ-መጠይቅ እያደረገ ሳለ የተደራጁ ወጣቶች መጥተው ድብደባ እንደፈጸሙበት ያስረዳ ሲሆን፤ "ቦርሳዬን ሲበረብሩ የኢቮኤ መታወቂያ ካርድ ካዩ በኋላ ትተውኝ ሄዱ" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ጋዜጠኛ ሙክታ ሆስፒታል ተኝቶ የህክምና አገልግሎት እየተከታተለ ይገኛል። ኮፈሌ አብነት አክሊሉ በምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ከተማ ነዋሪ የነበሩ 2 ዘመዶቹ እና አንድ በዘመዶቹ ቤት ስላደገው ወጣት አሟሟት ለቢቢሲ ተናግሯል። አቶ ታምራት ጸጋዬ የአብነት አክሊሉ አጎት (የእናቱ ወንድም) ናቸው። ረቡዕ ዕለት በተፈጠረው ግርግር አቶ ታምራት ጸጋዬ፣ ልጃቸው አቶ ሄኖክ ታምራት ጸጋዬ እና በአቶ ታምራት ቤት ሱቅ ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ሌላ ወጣት ልጅ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ መገደላቸውን አብነት አክሊሉ ይናገራል። "ተሰብስበው ወደ አጎቴ ቤት መጡ። ከዚያ በመጀመሪያ አጎቴን (አቶ ታምራት ጸጋዬ) ገደሉት። ከዚያ በተመሳሳይ ሁኔታ ልጁን ገደሉት። ከዚያ ቤት ውስጥ ያደገ ሱቅ ውስጥ ይሰራ የነበረ ልጅ ገደሉ" ይላል። አብነት የሟች አስክሬን ላይም አስነዋሪ ድርጊት መፈጸሙን ለቢቢሲ ተናግሯል። የአቶ ታምራት ልጅ፤ ሄኖክ ታምራት ጸጋዬ በቅርቡ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ በምጣኔ ሃብት ዘረፍ እንደተመረቀ የሚናገረው አብነት፤ አቶ ታምራት በኮፈሌ ከተማ ወፍጮ ቤት፣ ሆቴል እና መኪኖች እንዳሏቸው ይናገራል። የቤተሰብ አባላቱን ከተገደሉ በኋላ የአቶ ታምራት መኖሪያ ቤት አና መኪና እንደተቃጠለም አብነት ጨምሮ ይናገራል። የአቶ ታምራት እና የልጃቸው ትውልድ እና እድገት እዛው ኮፈሌ መሆኑን የሚናገረው አብነት "ተወልደው ባደጉበት ኮፈሌ እንኳ መቅበር አልቻልንም። በስንት መከራ ዛሬ በናዝሬት ከተማ 10 ሰዓት ላይ ቀብራቸው ተፈጽሟል" በማለት አብነት ያስረዳል። አምቦ የነበረው ገጽታ አምቦ ረቡዕ እና ሐሙስ ዝግ ሆነው የነበሩት መንገዶች ከዛሬ ጠዋት(ዓርብ) ጀምሮ ክፍት ተደርገዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት በነበሩት ግጭቶ 5 ሰዎች ተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አንድ የፖሊስ አባል ይገኝበታል። ይህ የፖሊስ አባል የተገደለው ሐሙስ ዕለት ሲሆን ረቡዕ ዕለት በነበረው ግጭት 'ሰው ገድለሃል' ተብሎ በበቀል እርምጃ እንደተገለ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዶዶላ በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ረቡዕና ሐሙስ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው 6 ሰዎች መገደላቸውም ታውቋል። ሐሙስ በነበረ ግጭት 4 ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል። ረቡዕ ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር። • የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ አወጀ ምስራቅ ሐረርጌ ረቡዕ እና ሐሙስ በምስራቅ ሃረርጌ በነበሩ ግጭቶች የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 6 መድረሱን ሰምተናል። በዞኑ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ አየለ ዴሬሳ፤ በጉሮ ጉቱ 5 እንዲሁም በሃማሬሳ 1 ሰው መገደሉን ተናግረዋል። አቶ አየለ፤ ትናንት 5ቱ ሰዎች የተገደሉት ጉሮ ጉቱ በምትባል ከተማ ወደ ብሄር በተቀየር ግጭት ስለመሆኑ ይናገራሉ። "አንድ ባለሃብት የደህንነት ስጋት ተሰምቶት ሁለት ሰዎችን በጥይት ተኩሶ ገደለ። ከዚያም በቂም በቀል ግለሰቡ እና ሁለት የቤተሰብ አባላቱ ተገደሉ" ሲሉ ሁኔታውን ለቢቢሲ አስረድተው ነበር። የአወዳይ ከተማ ነዋሪ የሆነ ወጣት ከመከላከያ ሠራዊት በተተኮሰ ጥይት ስለመገደሉ የአወዳይ ከተማ ከንቲባ ጃፋር ሙሐመድ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ሐረር በሐረር ከተማ ረቡዕ ዕለት 3 ሰዎች መገደላቸውን ከነዋሪዎች ሰምተናል። ድሬ ዳዋ በድሬዳዋ ከተማም ረቡዕ 1 ሰው የተገደለ ሲሆን ዛሬ ደግሞ 4 ሰዎች ተገድለዋል። የድል ጮራ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አብዱራሃማን አቡበከር ለህክምና ከመጡት ሰዎች መካከል 4ቱ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል። ባሌ ሮቤ በባሌ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ሮቤ ከተማም ባለፉት ሁለት ቀናት ግጭት ተከስቶ በሰው እና በአካል ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል። ቢቢሲ በዞኑ በተከሰቱት ግጭቶች በሰው እና በአካል ላይ የደረሰውን ጉዳት ከገለልተኛ አካል ለማጣራት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ይህ የሟቾች አሃዝ ከሆስፒታል ምንጮች፣ ከመንግሥት አካላትና ከሟች ቤተሰቦች የተገኘ ሲሆን ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ስጋት አለ። መንግሥት በግጭቱ ምክንያት የደረሰው የጉዳት መጠን ምን ያክል እንደሆነ ግልጽ ባያደርግም፤ ግጭት በተከሰተባቸው ስፍራዎች የመከላከያ ሠራዊት እንዲሰማራ መደረጉን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ ዛሬ ከሰዓት አስታውቀዋል። የተቃውሞ ሠልፍ በተካሄደባቸው የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች በክልሎችና በአስተዳደሩ ጥያቄ መሰረት በአምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ባሌ ሮቤ፣ አዳማ፣ ሞጆ እንዲሁም በድሬ ዳዋ እና ሐረር የመከላከያ ሠራዊት እንዲሰማራ መደረጉን ተናግረዋል።
49306146
https://www.bbc.com/amharic/49306146
“በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር
አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል በቀድሞዋ ሐውዜን፣ በአሁኗ ሳዕሲዕ ጻዕዳ እምባ ወረዳ ነው፤ ልዩ ስሟ ጻንቃኔት በተባለች አካባቢ ነው።
በ1976 ዓ.ም. የተወለደው ገብረእግዚኣብሄር፤ ገና ታዳጊ እያለ በ16 ዓመቱ ጊዜውም በ1992 ዓ.ም ሩጫን ሀ ብሎ የጀመረው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጀመርያ ጊዜ 2003 ኒው ዮርክ በተካሄደው ማራቶን ላይ ተሳትፎ የወርቅ ሜዳልያ አገኘ። •"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ ለቁጥር በሚያዳግቱ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ውድድሮች በግሉም እንዲሁም በሃገርም ደረጃ ተሳትፎ ብዙ ወርቆችን ያስገኘ አትሌት ነው። በአሁኑ ወቅት ከሩጫው ባሻገር በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኦሎምፒክ ኮሚቴ ምክትል ኃላፊነት እያገለገለ ሲሆን፤በይፋ ጫማ ባይሰቅልም እምብዛም በሩጫ መድረክ ላይ ሲሳተፍ እየታየ አይደለም። ለዚህም ገብረእግዚአብሔር ምላሽ አለው "ሩጫ እንደሚታውቀው ብዙ ትኩረት የሚጠይቅ ነው። ቢዝነስን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እሳተፋለሁ። ከዚህ በተጨማሪም በዕድሜም እየገፋሁ ነው። በይፋ ጫማ ባልሰቅልም አሁን ወደዛው ነኝ።" በዚህና ወቅታዊ ስፖርታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ቢቢሲ ከገብረእግዚአብሄር ጋር ቆይታ አድርጓል። ለመሆኑ እንዴት ነበር ወደ ሩጫው የገባው? አትሌት ገብረእግዚአብሄር ሩጫ በጀመረበት ወቅት ሩጫ በአለም አቀፍ ደረጃ በውድድር ደረጃ ስላለው ስፍራ የጠለቀ እውቀት አልነበረውም። ትምህርቱን የተማረው እንደ ብዙው የኢትዮጵያ የገጠር ልጅ በእግሩ እየሄደ ነበር፤ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ርቀቷን በሩጫ ፉት ይላታል። •ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን? "እኔ የአርሶ አደር ልጅ ነኝ። ወላጆቼ ያዘዙኝን በሙሉ ሰርቼ በሰዓቱ ትምህርት ቤት ለመድረስ ስለማልችል እየሮጥኩ ነበር የምሄደው። ከትምህርት ቤት ስመለስም እንዲሁ በሩጫ ነበር።" ይላል ይሄ የአብዛኛው የአርሶ አደር ልጆች ታሪክ ቢሆንም ለገብረ እግዚአብሄር ግን የተለየ ዕድል እንደፈጠረለት ይናገራል። "አጋጣሚው ተፈጥሯዊ አቅምን ፈጥሮልኛል።" ሩጫን ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ በፍጥነት ለመድረስ እንጂ በስፖርቱ አለም ያለውን ስፍራም አልተረዳውም ነበር። "በስፖርት ይሄን ያህል ታዋቂነት እንደሚገኝም አላውቅም ነበር" ይላል። ውድድር ማካሄድ የጀመረው በትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት ሲሆን፤ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ በትምህርት ቤቱ በተጀመረው ውድድር ለመጀመርያ ጊዜ አንደኛ ወጥቶ የምስክር ወረቀትም አግኝቷል። •ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም» ከትምህርት ቤቱ በተጨማሪ ሌሎችን ውድድሮችን ማካሄድ የጀመረው ገብረእግዚአብሔር በ1993 ዓ.ም. የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖም አዲግራት አቅራብያ በምትገኘው ዕዳጋ ሐሙስ ከተማ ትምህርት ቤቱን ቀጢን ቃላይ' ወክሎ ነበር የተወዳደረው፤ አንደኛም ወጣ። ቀጥሎም ወረዳውን ወክሎ 1500 ኪሜ ተወዳደሮ ማሸነፉን ያስታውሳል። ለመጀመርያ ግዜ ከምስክር ወረቀት በተጨማሪ ሽልማት ያገኘበት መሆኑም ልዩ ያደርገዋል። አትሌት ገብረእግዚአብሄር አትሌት ገብረ እግዚአብሄር በተለይ ለእነዚህ ሶስቱ ድሎች [የአየርላንድ፣ የኒው ዮርክና አፍሪካ ሻምፒዮን] የተለየ ቦታ አለው። በተለይ ደግሞ የአፍሪካ ሻምፕዮን በኢትዮጵያ የተካሄደ በመሆኑና ከፍተኛ ዝናብ የጣለበት ፈታኝ ውድድርም ስለነበር ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠዋል። •"የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!" ጋሽ አበራ ሞላ "በኢትዮጵያ የመጀመርያ ውድድርም ስለ ነበር ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወርቅ እንዲያመጡ ጉልበት የሆናቸው ይመስለኛል" የሚል እምነት አለው። የአትሌት ገብረ እግዚአብሄር አርአያ ማን ነው? ገብረእግዚአብሄር ሩጫን በአጋጣሚ ቢጀምርም በትምህርት ቤት ስለ እነ አትሌት ምሩጽ ይፍጠርና አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ የሩጫ ገድል ሲሰማ በሩጫ ላይ የተለየ ፍላጎት እንዳደረበት ይናገራል። አበበ ቢቂላም ሌላኛው የገብረእግዚአብሄር አርአያ ነው። ለሶስቱ አትሌቶች የተለየ ክብርና አድናቆት እንዳለው ነው የሚናገረው ገብረእግዚአብሄር፤ "ሩጫን ለዓለም በደንብ ያስተዋወቅነው እኛ ኢትዮጵያውያን ነን" የሚል አቋም አለው። ገብረእግዚአብሄር ከሁሉም በላይ ለኃይሌ ገብረ ስላሴ ያለው ቦታ ከፍ ያለ እንደሆነ ይናገራል። በሩጫ ማሸነፉ ብቻ ሳይሆን በሩጫው ለረዥም ግዜ የቆየበት ፅናቱን እንደ ምሳሌ ይቆጥረዋል። እንዲሁም ደግሞ ከሩጫው በተጨማሪ በቢዝነስ የሚያደርገው እንቅስቃሴና ስኬትም ሌላ የሚያደንቅበት ጉዳይ ነው። "አትሌት ምሩጽ ይፍጠር አባቴ ነበር" አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በአንድ ኦሎምፒክ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆኑን ከፍተኛ ስፍራ ከመስጠቱ በተጨማሪ ለመጀመርያ ጊዜ ሩጫን በውድድርነት ሲሰማ የአትሌት ምሩጽ ይፍጠርን ድል ነበር የሰማው። የስድስተኛ ክፍል የሳይንስ መምህሩ ስለ አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ማርሽ ቀያሪነት በሚነግሯቸው ወቅት መጀመርያ የሚያወሩት ስለመኪና ማርሽ ይመስለው እንደነደበር በፈገግታ ያስታውሰዋል። "ምሩጽ ስሙም ምርጥ ማለት ነው፤ ተግባሩም ምርጥ ነበር። በአካል ሳላውቀው ለረዥም ግዜ በውስጤ ይመላለስ ነበር፤ ምን ዓይነት ሰው ይሆን ብዬ ሁሌ አስብ ነበር" ይላል። በኋላም በአካል ተገናኝተው ከተዋወቁ በኋላ ያላቸው ግንኙነት ጠንክሮ እንደ ልጅና አባት ይተያዩ እንደነበር ይናገራል። • ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ "በህይወት ሳለ እንደ አብሮ አደጎችም ነበር የምንቀራረበው። እንደ አባቴ ነበር የማየው። የሃገሪቱም ሆነ ዓለም ክብር ነበር" በማለት በኃዘኔታ ያስታውሳል። ለተወሰኑ ዓመታት አሰልጣኙ እንደነበርም ይናገራል። በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮችም ያማክረው እንደነበር ገብረእግዚአብሄር ያስታወሳል። ወቅታዊ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተተኪ አትሌቶችን ከማፍራት ባለፈ የመቀሌ ከተማና ሌሎች በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅ አላማ ያለው 'ናትና ስፖት' በሚል ከባለቤቱ ከአትሌት ወርቅነሽ ኪዳነ ጋር ባቋቋሙት ተቋም አማካኝነት ሶስተኛው 'ናትና' የጎዳና ሩጫ ባለፈው ወር መቀሌ ላይ ተከናውኗል። "ትግራይ ክልል በደንብ ከተሰራበት ለስፖርት አመቺ የሆነ ሁኔታ አለ" የሚለው ገብረእግዚአብሄር ከሩጫው በሚገኘው ገቢ ሶስት የአትሌቲክስ መንደሮች ለማቋቋም አስቧል። የመቀሌ ሰብዓ እንደርታ እግር ኳስ ቡድን ዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ በክልሉ የታየው መነቃቃትና መነሳሳት ደግሞ ስፖርት ምን ያህል ጉልበት እንዳለው የሚያሳይ እንደሆነም ያስረዳል። የስፖርት መርህ ሰላምና ፍቅር መሆኑን የሚናገረው አትሌት ገብሬ በተለያዩ ምክንያቶች የሚነሱ ግጭቶችና አለመግባቶች ስለስፖርት ምንነት ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ እንዳሆነ ይገልጻል። ኢንቨስትመንትና ማህበራዊ ኃላፊነት ከአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አገኘኋት በሚለው ተሞክሮ ባገኛት "ሳንቲም" ኢንቨስት ማድረጉን ይናገራል። አዲስ አበባ ውስጥ ሁለት ሕንጻዎች ሲኖሩት መቀሌ ከተማ ውስጥ ደግሞ ለሆቴል የሚሆን ሕንፃ እያስገነባ እንደሆነ ነግሮናል። ከዚህም በተጨማሪ የስፖርት አልባሳትን ከውጭ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት የተሰማራው ገብረእግዚአብሄር የመቀሌ ሰብዓ እንደርታ ማልያ በእርሱ ኩባንያ በኩል እንደሚመጣ ይናገራል። አትሌት ገብረ እግዚአብሄር በተለያዩ ሃገራዊ ኃላፊነቶችም በማገልገል ላይ ይገኛል። በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኦሎምፒክ ኮሚቴ ውስጥ በአመራርነት ይሳተፋል። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ቢሆንም "በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መሳተፌ ውጤታማነቴ ላይ ድክመት እንዳያስከትልብኝ እፈራለሁ" ይላል። "ሆኖም በምሰራቸው ስራዎች ደስተኛ ነኝ። ሃገራዊ ግዴታዬን መወጣቴ ደስ ያሰኘኛል። የአንድ ሰው ህይወትም ቢሆን ከቀየርኩ ደስተኛ ነኝ።" ፖለቲካ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ጥያቄ የቀረበለት ገብረእግዚአብሄር ምላሹ አጠር እና ፈርጠም ያለ ነበር፤ "በፍጹም ፍላጎት የለኝም" የሚል። "ሆኖም" ይላል ገብረእግዚአብሄር "ሰዎች ለውጥ ያመጣል ብለው ካመኑብኝ እሠራለሁ። የወከለኝን ሰው አላሳፍርም። አቅም አለኝ ብየ ግን አይደለም።" "መስዋእትነት ነበር የምንከፍለው።" 'ወርቄ' እያለ አቆላምጦ የሚጠራት ባለቤቱ ወርቅነሽ ኪዳኔም ከሩጫውም ከሚድያውም ርቃለች። "ወርቄ ለሀገሯ ብዙ ሠርታለች። ለዛውም ከፍተኛ መስዋዕትነትን እየከፈለች። አሁን ግን እኔም እሷም ወደ መተው ደረጃ ደርሰናል። የምንችለውን አድርገናል ብየ ነው የማስበው።" በተለያዩ የአትሌቲክስና ኦሎምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን በቡድን ስራ የተዋጣ ስራ ሲሰሩ እንደነበር አትሌት ገብረ እግአዚአብሄር ይናገራል። ሆኖም ወርቅ ላመጣ ብቻ የሚሰጠው እውቅናና ክብር ግን ያንን የቡድን ስራ ዋጋ እንዳይቀንሰው ይሰጋል። "እኛ፤ እኔም ሆነ ቀነኒሳ፤ ጥሩነሽ ሆነች ወርቅነሽ ሁላችንም የምንሰራው ኢትዮጵያ ወርቅ እንድታገኝ ነው። በእኛ ምክንያት ሃገር ማፈር የለባትም ብለን ነው። ስለሆነም ቀነኒሳ ወርቅ አምጥቶ ባንዲራ አንስቶ ሲሮጥ፤ ሁላችንም ተነስተን በደስታ እንጨፍራለን።"ይላል። ነገር ግን ወርቅ ያመጣው ላይ ብቻ ከፍተኛ ትኩረት ስለሚሰጥም በመንግሥትና በሚድያዎች ላይ መጠነኛ ቅሬታ እንዳለው ግን አልደበቀም። "ወደ አገር ስትመጣ ለእንዲህ ዓይነት የቡድን ስራ ክብር ሲሰጥ አይታይም። ወርቅ ላመጣ ብቻ ክብር መስጠት ራሱን የቻለ ችግር አለበት። ይህንን ደጋግመን ነግረናቸዋል" ይላል። አክሎም "በእርግጥ እኛ ተሰምቶን አያውቅም። የምንችለውን አድርገናል። መስዋዕትነት ነበር የምንከፍለው። ይሄ ከየት የመጣ ነው - ካልከኝ ከወከለን ህዝብ አደራ ነው።" "በአምስት የአለም ዋንጫዎች ተሳትፌያለሁ። በአምስቱም ወርቅ አላመጣሁም። ወርቅ እንዲመጣ ግን ምክንያት ነኝ። በሁለት ኦሎምፒክ ተሳትፌያለሁኝ። በሁለቱም ወርቅ እንዲገኝ ምክንያት ነኝ። ወርቄ [ወርቅነሽ] ደግሞ በተመሰሳይ በስድስት የዓለም ዋንጫና በሶስት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ተሳትፋለች። እሷም እንደዚሁ። ወርቅ እንዲመጣ የመጀመርያ ተጠሪ እሷ ነች። 'ዘ ካንትሪ ዉማን' ይሉዋታል። ወደፊት ወጥታ ለሁለትና ለሶስት ቆርጣ ደረጃ ታወጣባቸዋለች። ከተሸላሚዎቹ በላይ ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነች። እነሱም ያምናሉ። ወደ መንግሥት ስትመጣ ግን ሌላ ነው፤ ይሄ የአስተሳሰብ ጠባብነት ነው የሚመስለኝ።" ይላል በሩጫ ውድድር ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሌሎች አገራዊ ዘርፎችም እንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ችግር እንዳለና መስተካከል እንዳለበት ያሳስባል ገብረእግዚአብሄር "ለሁሉም በተለይ ደግሞ መስዋዕትነት ለሚከፍለው ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ ነው። ጥቅም አይፈልግም" በማለት ሃሳቡን ይቋጫል።
news-54451120
https://www.bbc.com/amharic/news-54451120
የትግራይ ክልል፡ የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔና ተግባራዊነቱ
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ የመጣው የፌደራልና የትግራይ ክልል መንግሥት ግንኙነት የማይታረቅ ደረጃ የደረሰ ይመስላል።
በተለይም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሆነ ፓርላማው ምርጫው በሕገ መንግሥት ትርጓሜ እንዲራዘም ያፀደቀ ቢሆንም የትግራይ ክልል ምርጫ ማድረጉ የበለጠ ነገሩን አክርሮታል። ምክር ቤቱ ስልጣኑን የሕገ መንግሥት ትርጉም በመስጠት ማራዘሙ ሕገ መንግሥታዊ መሰረት እንደሌለውም የትግራይ ክልል ይጠቅሳል። የፌደራል መንግሥቱ ደግሞ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ነው ባለው ምርጫም ህወሓት አብላጫ ድምፅ አግኝቶ ሕጋዊ መንግሥት መስርቻለሁ፤ እንዲሁም ዶክተር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤልንም የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጌ ሰይሜያለሁ ብሏል። ሆኖም በትግራይ ክልል የተካሄደው ስድስተኛ ክልላዊ ምርጫ እንዳልተደረገ የሚቆጠርና ተፈፃሚ የሌለው ነው በማለትም የፌዴሬሽን ምክርቤት ውሳኔ አሳልፏል። በዚህ ሳምንት ደግሞ ህወሓት መስከረም 25/2013 ዓ.ም የፌደራል መንግሥቱ ስልጣን ማብቂያ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ፓርላማው ሕጋዊ ስልጣን የላቸውም በማለት፤ አባላቱ በፌዴሬሽንና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ያላቸውን ውክልናና ኃላፊነት እንዲለቁ ጥሪ አቅርቧል። በምላሹም መስከረም 26/2013 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ አስተላልፏል። ምክር ቤቴ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈውም ነሐሴ 30/2012 ዓ.ም አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባኤ የትግራይ ክልል ያደረገው ምርጫ እንዳልተደረገና እንደማይፀና ያስተላለፈውን ውሳኔንም በመጣሱ ነው። ይህንን ውሳኔ በበላይነት ሲከታተል የነበረው የሕገ መንግሥቶች ጉዳዮችና የማንነት ጉዳዮች አጣሪ ኮሚቴ ክልሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አላከበረም ማለቱም ተገልጿል። "የፌደራል መንግሥት የክልሉ ከተማ፣ ወረዳና ቀበሌ አስተዳደሮች ጋር ግንኙነት ማድረግ ያስፈለገው ህጋዊ ናቸው ብሎ ስለሚያምን ነው" የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ ያራዘመውን ውሳኔ በመተላለፍና "ሕገወጥ" ያለውን ምርጫ በማካሄዱም የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚ አካላት ጋር ምንም ግንኙነት ላለማድረግም ውሳኔ ላይ ደርሷል። በዚህም ውሳኔ መሰረት የፌደራል መንግሥት የትግራይ ሕዝብን የልማትና መሰረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎትን ማዕከል በማድረግ የከተማና፣ ወረዳና ቀበሌ አስተዳደሮችና በክልሉ ከሚገኙ ሕጋዊ ተቋማት ጋር የሥራ ግንኙነት እንደሚያደርግም አስታውቋል። ይህ ውሳኔ ሲተላለፍ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ያካሄደው ምርጫ "ሕገወጥ" በመሆኑ፤ ምክር ቤቱ የፌደራል መንግሥቱ ተፈፃሚነት የለውም ባለው ምርጫ የክልሉ ምክር ቤትም ሆነ ከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚዎች በመዋቀራቸው ምክንያት ምንም ግንኙነት እንዳይኖረው ውሳኔ ተላልፏል፤ ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቃለ አቀባይ አቶ ካሳሁን በቀለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ማዕከላዊው መንግሥት ከዚህ በኋላም በቀጣይነት ግንኙነት የሚኖረው ሕዝቡን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መሆኑንም ይጠቅሳሉ። የትግራይ ሕዝብን የሰላምና የልማት መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማዕከልም በማድረግ በክልሉ ከተሞች፣ ወረዳዎችና ቀበሌ አስተዳደሮች ወይም ቃለ አቀባዩ "ሕጋዊ" ካሏቸው ተቋማት ጋር የፌደራል መንግሥቱ በቀጥታ ግንኙነት ያደርጋል ብለዋል። የፌደራል መንግሥቱ ከነዚህ ተቋማት ጋር በቀጥታ ለመስራትም የመረጠበት ምክንያት የአካባቢ ምርጫ ባለመደረጉና አስተዳደሮቹ በነበሩበት በመቀጠላቸው መሆኑንም አቶ ካሳሁን ያስረዳሉ። የከተማ አስተዳደሮችም ሆነ ወረዳዎች የሚመሩት በክልሉ አስተዳደር ወይም እውቅና የሚያገኙት በክልሉ ሕገ መንግሥት መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌደራሊዝም መምህር የሆኑት ዶክተር ሲሳይ መንግሥቴ ይናገራሉ። ከዚህም አልፎ እነዚህ አስተዳደሮች በክልሉ ማስፈፀሚያ አዋጅም የተደገፉ ናቸው። ከዚህም አንፃር የከተማው፣ የወረዳውም ሆነ የቀበሌ አስተዳደሮችም ሆነ የሚመረጡትም ሆነ ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግሥት ከመሆኑም ጋር ተያይዞም የፌደራል መንግሥቱ ከክልሉ ሕግ አውጪና ሥራ አስፈፃሚ ጋር ግንኙነት የለኝም ብሎ ተጠሪነታቸው ለክልሉ ከሆኑ አካላት ጋር እሰራለሁ የሚለው ለምንድን ነው? የሚል ጥያቄም መነሳቱ አልቀረም። ይህንንም ጥያቄ ቢቢሲ ለአቶ ካሳሁን ያቀረበላቸው ሲሆን እሳቸውም ቢሆን በዋነኝነት የሚያነሱት የትግራይ ክልል ያካሄደው የክልል ምክር ቤት ምርጫ "ሕገ መንግሥቱን የጣሰ" መሆኑንና እሱን ተንተርሶ የከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚ አካላት መዋቀሩን ነው። በአሁኑ ወቅት ክልሉ ያካሄደው ምርጫ ወረዳዎችን፣ ከተማ አስተዳደሮችን ወይም ቀበሌዎችን ባለማካተቱም የፌደራል መንግሥቱ እነዚህን አካላት "ሕገ ወጥ" አይደሉም ብሎ ያምናል ይላሉ። "ምክር ቤቱ ውሳኔውን ሲወስን ከክልሉ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና መሰረታዊ የአገልግሎት ፍላጎት ማዕከል በማድረግ ሕዝቡ እንዳይጎዳ የሚል ቀጥታ ግንኙነት በተለያየ መንገድ ሊያረግ ይችላል ማለት ነው። የአካባቢና የወረዳ ምርጫ ስላልተደረገ በነበሩበትረ የቀጠሉ ስለሆነ ከእነሱ ጋር የተጀመረው የሰላምና የልማት ሥራዎች ከሕዝቡ ጋር ይካሄዳሉ" ብለዋል። የትግራይ ክልል፤ ምክር ቤቱ ምርጫውን ያራዘመው ከሕገ መንግሥቱ ውጪ በሆነ ትርጓሜ ነው በማለት ትችት የሚያቀርብ ሲሆን፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የወሰነውንም ውሳኔ ተከትሎ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ሩፋኤል ሽፈረ ከ2.7 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የተሳተፈበትን ምርጫ ለሕዝቡ ያለውን ንቀት ያሳየ ብለውታል። ሚሊዮኖች የተሳተፉበትን ምርጫ ተቀባይነት የለውም ማለት? እንዲሁም የአሁኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ሕዝቡን የመግፋትና ክልሉንም የኢትዮጵያ አካል ሆኖ እንዳይታይ ማድረግ አይሆንም ወይ? የሚሉ አስተያየቶች መሰማታቸውን ጠቅሰን ለአቶ ካሳሁን በጠየቅናቸው ወቅትም ውሳኔው ሕገ መንግሥቱን የማክበር ጉዳይ እንደሆነ ይናገራሉ። ክልሎች የሚያወጧቸው መመሪያዎች፣ ደንቦችና ሕጎች ከሕገ መንግሥቱ በላይ ሊሆኑ እንደማይችሉ በመጥቀስም ምክር ቤቱ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ምርጫው እንዲራዘም የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ሰጥቷል። የሕገ መንግሥቱ ትርጓሜም ተፈፃሚነቱ በሁሉም ምክር ቤቶችና በሁሉም ክልሎች መከበር አለበት በማለት አፅንኦት ይሰጣሉ። "እኛ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ነው የምንሰራው፤ ሕገ መንግሥት የአንድ ፓርቲ አይደለም፤ የሕዝብ ስለሆነ መከበር አለበት። ጥያቄዎች ካሉ በተለየ አውድ መፈታት ይችላሉ። ሁላችንም ቢሆን ከሕግ በላይ ልንሆን አንችልም፤ አገሪቷ የምትመራበት ሕገ መንግሥት አላት። ይሄንን ደግሞ ሁሉም የማክበር ግዴታ አለበት" ብለዋል አቶ ካሳሁን። የፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልል ቀጣይ ግንኙነት እንዴት ይከወናል? ምክር ቤቱ የወሰነው የውሳኔ አፈፃፀምም በፌዴሬሽን ምክር ቤቱ የበላይ አመራሮችና በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ክትትል ይደረጋልም የሚል ውሳኔም ተላልፏል። አፈፃፀሙን የሚወስነው ከፌዴሬሽን ምክር ቤት በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮም መሆኑን ሲሳይ መንግስቴ (ዶ/ር) ይጠቅሳሉ። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት ባለው የስልጣን አወቃቀርና ተዋረድ መሰረት የፌደራል መንግሥቱ ቀጥታ ግንኙነት የሚያደርገው ከክልሎች ወይም ከክልል መንግሥታት ሕግ አውጪና አስፈፃሚ ጋር ነው። የአሁኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ይህንን ግንኙነት የቀየረ እንደሆነ ሲሳይ (ዶ/ር) ያስረዳሉ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነሐሴ 30/2012 ዓ.ም ባደረገው የአስቸኳይ ጉባኤ ክልሉ ያደረገው ስድስተኛ ክልላዊ ምርጫ እንዳልተደረገ የሚቆጠርና ተፈፃሚ የማይሆን ነው በማለትም ውሳኔ አስተላልፏል። በወቅቱም ግንኙነታቸው ሊቋረጥ የሚችል መሆኑንም ያመላከተበት ውሳኔም መሆኑን የሚገልፁት ሲሳይ (ዶ/ር) ከክልሉ የሕግ አውጭው ምክር ቤትና አስፈፃሚው ጋር ግንኙነት እንዲቋረጥ የወሰነበትም የዚያ ቀጣይ ተግባራዊ ውሳኔ ነው። በዚህም መሰረት የአሁኑ ውሳኔ በተለያየ ደረጃ ያሉት የፌደራል የመንግሥት አካላት ከትግራይ ክልል የሕግ አውጪው ምክር ቤትና አስፈፃሚው ጋር ግንኙነት እንዳያደርግ የደነገገ መሆኑንም ያስረዳሉ። ከዚህ በኋላ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ውስጥ በትምህርት፣ በጤናና በሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ የሚሰራቸውን መሰረተ ልማት ተግባራት ከከተማ አስተዳደሮች፣ ከወረዳና ከቀበሌዎች ጋር በቀጥታ ይሰራል ማለትም መሆኑን የውሳኔውን አንድምታ ሲሳይ (ዶ/ር) ይገልፃሉ። "ከዚህ ቀደም እንደነበረው ከክልሉ መንግሥት አመራር፣ በክልሉ በኩል አድርጎ ወደ ከተማና ወረዳ አስተዳደሮች እንዲወርድ ማድረጉን ትቶ በቀጥታ ራሱ የሚገናኝበት፣ ራሱ አቅርቦቱን የሚሰራበትና ግንኙነቱም ከእነሱ ጋር የሚሆንበት ነው" ይላሉ። ሆኖም የፌደራል መንግሥቱ በዚህ መንገድ እሰራለሁ ማለቱ ፈታኝ እንደሆነ የሚያስረዱት ሲሳይ (ዶ/ር)፤ ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚጠቅሱት ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የሚመሩትም በክልሉ አስተዳደር፣ የሚደገፉት በክልሉ ማስፈፀሚያ አዋጅ እንዲሁም እውቅና የሚያገኙት በክልሉ ሕገ መንግሥት በመሆኑ ነው። የፌደራል መንግሥት ግንኙነቴ ከክልሉ የከተማ አስተዳደሮች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ነው ብሎ ሲወስን እነዚህን ተቋማት ለሁለት አካላት ተጠሪ ያደርጋቸዋል ማለትም እንደሆነ ይናገራሉ። ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት ይቋረጣል ሲባልም የበጀት ድጋፉን ጭምር ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑንም ሲሳይ (ዶ/ር) ያስረዳሉ። በትናንትናው ዕለትም የትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚው አካል ሕጋዊ ሰውነት የላቸውም በሚል የፌደራል መንግሥት የበጀት ድጎማ እንደማይደረግ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል። ከዚህ ቀደም የፌደራል መንግሥት ለክልሉ መንግሥት ሲሳይ (ዶ/ር) እንደሚሉት "ፍሎው ግራንት" (ጥቅል ድጋፍ) የሚባል አይነት ነበር የሚሰጠው። ከዚህ በኋላ ግን እያንዳንዱ በጀት ተከፋፍሎ ለከተማ አስተዳደሮችና ለወረዳዎች ለተለያዩ የልማት ሥራዎች በሚሆን መልኩ የሚደርስበት አሰራር ውኔው ታሳቢ እንዳደረገም ይጠቅሳሉ። ይህም ማለት ለክልሉ መንግሥት ይላክ የነበረው በጀት በቀጥታ አይላክም ማለትም ነው። ሲሳይ (ዶ/ር) ይህንን ለማብራራት እንደ ምሳሌ የሚጠቅሱት ፍርድ ቤቶችን ነው። ፍርድ ቤቶች በምርጫ ስለማይደራጁና ቀጣይነት ያለው ሥራ ስለሚሰሩ የፌደራሉ መንግሥት ግንኙነት ከክልሉ ጋር ይሆናል። በዚህም ወቅት የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር ግንኙነት ይኖረዋል። የበጀት ድጋፍ የሚደረግም ከሆነ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሊደረግ የሚችል ቢሆንም፤ ከዚያ ውጭ ግን ከክልሉ ምክር ቤትና ከክልሉ አስፈፃሚ ጋር የሚኖር የበጀትም ይሁን የሥራ ግንኙነት ይቋረጣል። ከዚህም በተጨማሪ ሲሳይ (ዶ/ር) እንደሚሉት በፌደራሉና በክልሉ ምክር ቤት የስብሰባም ይሁን የስልጠና ግንኙነት አይደረግም። "የፌደራልና የትግራይ ክልል መንግሥት ተነጋግረውና ተወያይተው መፍትሄ ሊያመጡ ይገባል" የፌደራሉና የክልሉ መንግሥት እንዲህ ግንኙነት በማይኖርበት ሁኔታ የወደፊቱ የክልሉ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ጥያቄ ውስጥ መግባቱንም በርካቶች ይናገራሉ። የሁለቱ መንግሥታት እንዲህ ሆድና ጀርባ ሆኖ መሻከር የክልሉ ነዋሪስ እንዴት ይመለከተዋል? የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ውሳኔስ እንዴት ይታያል? በመቀሌ ከተማ ነዋሪ የሆነውና የሕግ ባለሙያው ሃብቶም ግርማይ የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ውሳኔ የሕግ መሰረት የለውም በማለት ይናገራል። ከዚህም ባለፈም "ከትግራይ መንግሥት (ባለስልጣናት) ግንኙነት የለኝም ማለቱ በጣም የሚያስቅ ነው። ምክንያቱም ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ነች። ለኢትዮጵያ አንድ ፌዴሬሽን ነች። ብሔርና ብሔረሰቦችን የያዘ ክልል ነው፤ ሦስት ቋንቋዎች የሚናገሩባትን ክልል ጠቅልሎ ከክልሉ መንግሥት ጋር ግንኙነት የለኝም ማለት የሚገርምና ኢ-ሕገ መንግሥታዊ የሆነ ይመስለኛል" ብሏል። እንዲህ አይነት ውሳኔ መተላለፉም ሕዝቡን የበለጠ ሌላ ስሜት ውስጥ የሚያስገባ ነውም ሲል ስጋቱን ይገልጻል። የእድሜ ባለፀጋ የሆኑት አቶ ገብረ እግዚአብሔር በበኩላቸው ነገሩ ከቁጭትና ከንዴት ጋር ተያይዞ የሚነገር እንደሆነና ሁለቱም ወገኖች ሰከን ብለው እንደሚያስቡም ተስፋ አድርገዋል። "አንዳንድ ጊዜ ከቁጭት ከንዴት የሚነገር ነገር አለ። ግን ሲውል ሲያድር ደግሞ ረጋ ብሎ ማሰብ ስላለ ምናልባት ዛሬ የተነገረው ነገር ወደኋላ መለስ ብለው ያስባሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል። አገርም ሆነ ሕዝብ መምራት ቀላል እንዳልሆነ በማስታወስም "አገር እየተመራ እንደዚህ አይነት ውሳኔ ማስተላለፍ አይገባም። አገር የሚመራው በመቻቻል፣ በመረዳዳት፣ በመተጋገዝ ነው። ግጭትና ጦርነት ለሁሉም አይበጅም፤ ለሁሉም አያዋጣም፤ ለአገሪቱም ለሕዝቡም አያዋጣምና መለስ ብሎና ረጋ ብለው እንዲያስቡ ነው ማሳሰብ የምወደው" ብለዋል። ከዚህ ቀደም አገሪቷ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያደረገቻቸውን ጦርነቶችም ሆነ እንዲሁ በአገር ውስጥ የነበሩ ግጭቶችን በመጥቀስ ትምህርት መውሰድ ይገባል ይላሉ የመቀለው ነዋሪ አቶ ገብረ እግዚአብሔር። "ይሄ ሁሉ አልፎ ወደ ድርድር መጥተን ሰላም ማምጣት ነው እንጂ እኔ እበልጣለሁ የሚል ፉክክር ጥሩ ስለማይሆን ረጋ ብለው ያስቡ የሚል መልዕክት አስተላልፋለሁ" ብለዋል። የኤሌክትሪክ መሃንዲሱም አብዱ መሃመድ በበኩሉ የክልሉ መንግሥት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለውና በምርጫ ማሸነፉን ይናገራል። እንዲህም በሆነበት ሁኔታ የፌደራል መንግሥትና የትግራይ ክልል አመራሮች ተነጋግረውና ተወያይተው መፍትሄ ቢያመጡ፣ የፖለቲካ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ አማራጭም መፍትሄን ያቀርባል። በዚሁ ከቀጠለ አገሪቱ ወዳልተገባ ትርምስ ልትገባ ትችላለች በማለትም እነ ሶርያና ሌሎች አገሮችን በምሳሌነት በመጥቀስ ከእነሱ መማር እንደሚገባና ሕዝብ ሳይጎዳ የመቀራረብ አስፈላጊነትን ይናገራል።
53299854
https://www.bbc.com/amharic/53299854
የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያና ያለፈው ሳምንት ክስተት
የዛሬ ሳምንት ሰኞ ምሽት በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሚጠቀሙት ፌስቡክ ላይ ታዋቂው የኦሮምኛ ድማጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ አንዳች ችግር እንደተከሰተ የሚገልጹ መልዕክቶች በስፋት መዘዋወር ሲጀምር፤ አብዛኛው ሰው በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እንዲህ አይነቱ በታዋቂ ሰዎች ላይ የሚነዛ ሐሰተኛ ወሬ ነው ብሎ ትኩረት አልሰጠውም ነበር።
ነገር ግን ሰዓቱ እየገፋ ሲሄድ ለድምጻዊው ቅርብ የሆኑና የሚታወቁ ሰዎችም ሃጫሉ ጉዳት እንደደረሰበት ከታማኝ ሰው መስማታቸውን ሌሎች ደግሞ ማረጋገጣቸውን መግለጽ ጀመሩ። ወዲያው ተከትሎም የድምጻዊው ህይወት ማለፉን የሚገልጹ መረጃዎች ከፎቶው ጋር ማኅበራዊ ሚዲያውን አጨናነቁት። ክስተቱ ለእውነት የቀረበ እንደሆነ ሲታወቅ ብዙዎችን ከባድ ድንጋጤና ሐዘን ውስጥ በመክተት ከመደበኛዎቹ መገናኛ ብዙሃንና ከመንግሥት የመጨረሻውን ሐቅ ለመረዳት ከአንዱ ቴሌቪዥን ወይም ሬዲዮ ወደ ሌላው በመቀየር ማመን ከባድ የሆነውን እውነታ ለማረጋገጥ በመሞከር ምሽቱ ተጋመሰ። በመጨረሻም እኩለ ሌሊት አልፎ ሰባት ሰዓት ከሩብ አካባቢ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ጌቱ አርጋው በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በእርግጥም ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት ተመትቶ ለህልፈት የመዳረጉን መርዶ ተናገሩ። ኮሚሽነሩ ጨምረውም ከግድያው ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸው፤ ፖሊስ በተፈጸመው የግድያ ወንጀል ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አመልክተው ሕዝቡም እንዲረጋጋ ጠይቀው ነበር። በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመው ግድያ በተሰማበት ጊዜ ጀምሮ እከሌ ከእከሌ ሳይባል ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ነበር ያስደነገጠው። ክስተቱ ቀድሞ የተሰማበት የማኅበራዊ ሚዲያው መድረክም ከግድያው ጋር በተያያዙ ጥያቄዎችና በድምጻዊው ምስል እንዲሁም የሐዘን መግለጫ መልዕክቶች ተጥለቀለቀ። ዜናው ይፋ እንደተደረገ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ድንቅና አንፀባራቂ በማለት የገለጹትን ሃጫሉን "ውድ ህይወት አጥተናል" ሲሉ የተሰማቸውን ሐዘን የገለጹት ሌሊቱ ከመንጋቱ በፊት ነበረ። ጨምረውም የግድያውን ሙሉ የፖሊስ የምርመራ ሪፖርት እየተጠበቀ እንደሆነ ጠቁመው "የድርጊቱን መጠን በመረዳት በአገራችን ውስጥ ስለሚደረጉ ነገሮች ትኩረት ሰጥተን የምንከታተልበት ወቅት ላይ እንገኛለን" ብለዋል። • 'ጀግናዬ' የሚለውን የወዳጁን ቀብር በቴሌቪዥን የተከታተለው የሃጫሉ ጓደኛ • ከታሰሩ ፖለቲከኞች ውስጥ ‘የተደበደበ’ እና ‘በረሃብ አድማ’ ላይ ያሉ መኖራቸው ተነገረ • "አገሪቷ ስለተረጋጋች ኢንተርኔቱ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚከፈት ተስፋ አደርጋለሁ"-ቢልለኔ ስዩም ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ተከትለው በድምጻዊው ግድያ ሐዘናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጓ ወይዘሮ አዳነች አቤቤም ግድያውን የፈጸመው ማንም ይሁን ማን ከሕግ ማምለጥ እንደማይችል ገልጸው "ለዚህ እኩይና አስነዋሪ ሥራም ዋጋቸውን በሕግ ያገኛሉ" ሲሉ ለቤተሰቡና ለሕዝቡ ትዕግስት፣ ብርታትና መጽናናትን ተመኝተዋል። በሃጫሉን እንደ አንድ አብሮ አደግና እንደ ትግል ጓዳቸው የገለጹት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸው "ግድያው ተራ አይደለም ታስቦበት የተፈፀመ ነው፤ በዚህ ምንም ጥርጥር የለኝም" በማለት እንደተራ ነገር የሚታለፍ ክስተት እንዳልሆነ አመልክተዋል። አክለውም ሕዝቡ ክስተቱን በሰከነ ሁኔታ መገንዘብ ተጠርጣሪዎቹን ለፍርድ ማቅረብና የተጀመረው ለውጥ እንዲሳካ "እጅ ለእጅ ተያይዘን በመረጋጋትና በመናበብ ይህን አስቸጋሪ ጊዜ እንድንሻገር ጥሪዬን አቀርባለሁ" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ክልሎችና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በድምጻዊው ግድያ የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው በሕዝቡ ውስጥ መረጋጋት እንዳይጠፋ ጠይቀው ነበር። የአስከሬን ሽኝት የሃጫሉ ሞት ከተነገረ በኋላ በመዲናዋ እና በዙሪያዋ ካሉ አካባቢዎች የሚኖሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ ሌሊቱን በሙሉ ተጉዘው አስከሬኑ ወዳረፈበት ሆስፒታል በመጓዝ ሐዘናቸውን ከመግለጽ ባሻገር፤ ወደ ትውልድ መንደሩ ለመሸኘት ተሰባስበው ነበር። ረፋድ ላይም የድምጻዊው አስከሬን በታላቅ አጀብ ከአዲስ አበባ በመነሳት በስተ ምዕራብ 100 ኪሎ ሜትሮች ርቃ ወደምትገኘው የትውልድ ከተማው አምቦ እየተወሰደ ሳለ መንገድ ላይ ቀብሩ አዲስ አበባ መፈጸም አለበት በሚሉ ወገኖች አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ተደረገ። በአንድ በኩል ቤተሰቡ ልጃቸው በሚኖሩበት ከተማ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እንዲፈጸም እንደሚፈልጉ ሲነገር ሌሎች ደግሞ በኖረባትና በተገደለባት አዲስ አበባ ውስጥ እንዲያርፍ የሚጠይቁ ወገኖች ነበሩ። በዚህም ቁርጥ ያለ መደምደሚያ ላይ ሳይደረስ አስከሬኑ ወደ ከተማዋ እንዲመለስ ተደረገ። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሃጫሉ የቀብር ዕለት በቴሌቪዥን ቀርበው እንደተናገሩት "አስከሬኑ ወደ ቤተሰቦቹ እየተሸኘ ሳለ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች አስከሬኑን ነጥቀው ወደ አዲስ አበባ መለሱት" ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል። በተመሳሳይም የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ወደ ቤተሰቦቹ እየተወሰደ ሳለ "መንገድ በማስቀየርና በመቀማት አመጽን አዲስ አበባ ተጀምሮ አዲስ አበባ እንዲያልቅ ሲቀሰቀስ" ነበር በማለት ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ ጋር የነበረውን ክስተት ገልጸዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳም "አስከሬኑ በቤተሰቡ ጥያቄ መሰረት ከጳውሎስ ሆስፒታል ወጥቶ ወደ አምቦ እየተሸኘ ሳለ፤ ከቤተሰቡ ፍቃድ ውጪ ቡራዩ ሲደርስ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደርጓል" ሲሉም ተናግረዋል። ቢቢሲን ጨምሮ የድምጻዊው ቤተሰቦች ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃል የሃጫሉ ቀብር አምቦ ከተማ ውስጥ እንዲፈጸም እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። በዚህም ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደረገው አስከሬን በኦሮሞ ባህል ማዕከል ውስጥ እንዲያርፍ ከተደረገ በኋላ በቤተሰቡ ጥያቄ መሰረት አስከሬኑ በሄሊኮፕተር ወደ አምቦ እንዲወሰድ መደረጉን ለቤተሰቡ ቅርብ የሆኑ ግለሰብ ለቢቢሲ በወቅቱ ተናግረዋል። የኢንተርኔት መቋረጥ ለግጭቶቹ መስፋፋትና ለጥቃቶቹ መዛመት በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ የሚሰራጩት ሐሰተኛና አባባሽ መልዕክቶችን ለመቆጣጠር ሲባል የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠው ማክሰኞ ረፋዱ ላይ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት የተለመደ ድርጊት ነው በማለት የተለያዩ ወገኖች እርምጃውን ቢቃወሙትም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ግን የኢንተርኔት አገልግሎት የብሔር ጥላቻን ለማስፋፋት ጥቅም ላይ በመዋሉ መንግሥት አገሪቱንና ሕዝቡን የመጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት ለማቋረጥ መገደዱን ተናግረዋል። ባለፈው አርብ ለቢቢሲ እንደገለጹት የነበረው አለመረጋጋት በመወገዱና ተስተጓጉሎ የነበረው መደበኛ እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት በመመለሱ በዚህ ሳምንት ውስጥ ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ይመለሳል ብለው እንደሚያስቡ ገልጸዋል። ሞት እና ውድመት የሃጫሉ ሞት ከተሰማ በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በርካታ ሰዎች በሐዘንና በቁጣ አደባባይ ወጥተው ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ከመጋጨታቸው በተጨማሪ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሻሸመኔ፣ በአርሲ ነገሌና በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከጸጥታ አካላት ጋር በተፈጠረ ግጭትና በተፈጸመ ጥቃት የበርካታ ሰዎች ህይወት ለህልፈት ተዳርጓል። በመንግሥትና በግለሰቦች ንብረትም ላይ ካባድ ውድመት እንደተፈጸመ ከየአካባቢዎቹ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ ከማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በተለያዩ ከተሞች የተፈጠረው አለመረጋጋት መልኩን ቀይሮ ማንነትን መሰረት ወዳደረጉ ጥቃቶችና ወደ ዘረፋ መሸጋገሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከፍተኛ ውድመት ያጋጠማት የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት ጥቃት ፈጻሚዎቹ ክሰተቱን ለራሳቸው አላማ መጠቀሚያ ለማድረግ በተለይ ኢላማ ያደረጓቸው ሰዎች መኖራቸውን ተናግረዋል። በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ ከማክሰኞ ጀምሮ በነበሩ ጥቂት ቀናት ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች ሁለት ፖሊሶችን ጨምሮ ቢያንስ አስር ሰዎች ህይወታቸው የጠፋ መሆኑን ፖሊስ የገለጸ ሲሆን በተመሳሳይ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ውስጥም 11 የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ 156 ሰዎች ሞተዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነት ግርማ ገላን እንደተናገሩት ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ በ167 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። የተፈጸሙትን ጥቃቶች "ዘግናኝና አሳፋሪ የግድያ ወንጀሎች" መሆናቸውን ያመለከቱት ምክትል ኮሚሽነሩ አላማውም በማኅበረሰቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ታስበው የተፈጸመ ነው ሲሉ ተናግረዋል። እስር የሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረው ሁከት ምክንያት በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት በተለያዩ ስፍራዎች ለውድመት ተዳርጓል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ፖሊስ በተለያዩ ድርጊቶች ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን ግለሰቦች መያዝ የጀመረው ከማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ ነበር። በዚህም መሰረት ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የአስከሬን ሽኝት መስተጓጎልና ከአንድ የፖሊስ አባል ግድያ ጋር በተያያዘ አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 35 ሰዎችን በቁጥጥር መዋላቸውን የፌደራልና እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖች አስታወቀዋል። በተጨማሪም አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልና ሌሎችም የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት በፖሊስ መያዛቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባና እስክንድር ነጋ ፍርድ ቤት ቀርበው ሌላ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ከዚህ ባሻገርም በነበሩት ተከታታይ ቀናት በተፈጸሙ ግድያዎችና የንብረት ውድመቶች ተጠረጠሩ 1084 ሰዎችን መያዙን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሲያስታውቀ፣ በአዲስ አበባና በድሬዳዋም በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
news-51135691
https://www.bbc.com/amharic/news-51135691
"ልዩነቶች ተፈትተዋል. . . አቶ ለማ በሥራ ላይ ናቸው" አቶ ሳዳት
አቶ ለማ መገርሳ ከዚህ ቀደም ከብልጽግና ፓርቲ አመሠራረት ጋር ተያይዞ የነበራቸውን ልዩነት በፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ በኩል በተደረገው ውይይት ተፈቷል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ የከተሞች ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ ሳዳት ናሻ ለቢቢሲ ተናገሩ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትርና የቀድሞው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ፤ በኢሕአዴግ ውህደት እና በጠቅላይ ሚንስትሩ የመደመር ፍልስፍና እንደማያምኑ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ መግለጻቸው ይታወሳል። በወቅቱ "መዋሀዱ ትክክል አይደለም። ከሆነም በችኮላ መሆን የለበትም፤ ወቅቱም አይደለም" ያሉት አቶ ለማ፤ በመደመር ፍልስፍናም እንደማይስማሙ ከራድዮ ጣቢያው ጋር ባደረጉት ቆይታ መናገራቸው ይታወቃል። መከላከያ ሚንስትሩ ለአሜሪካ ድምጽ ይህን ካሉ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ አቶ ለማ፤ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር አብረው ለውጡን እንደሚያስቀጥሉ ተነግሯል። ጠቅላይ ሚንስትሩ እና መከላከያ ሚንስትሩ በተፈጠረው ልዩነት ዙሪያ ቁጭ ብለው መወያየታቸውንና ተፈጥሮ የነበረው የሐሳብ ልዩነት ላይ መግባባት እንደቻሉና አብረው ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል። ሁለቱ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የነበሯቸው ልዩነት በምን መልኩ ፈቱት? የሚለው ጥያቄ ምላሽ ባያገኝም፤ አቶ ሳዳት ግን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ባደረገው ውይይት ልዩነቶችን ቀርፏል ብለዋል። አቶ ሳዳት መከላከያ ሚንስትሩ በሥራ ላይ ነው የሚገኙት ያሉ ሲሆን፤ ልዩነት ተፈጥሮ የነበረው ካለመግባባት እንጂ መሠረታዊ የፖለቲካ አቋም ልዩነት ኖሮ አይደለም ብለዋል። አቶ ለማ ለምን ዝምታን መረጡ? አቶ ለማ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በጉዳዩ ላይ የአቋም ለውጦች ሲኖራቸው ለመገናኛ ብዙኃን ወጥተው እንደሚናገሩ ማስታወቃቸውን ተከትሎ፤ ተፈጥሮ የነበረው ልዩነት በውይይት መፍትሄ አግኝቷል ሲባል፤ አቶ ለማ ወደ ሚዲያ ወጥተው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ብለው የጠበቁ በርካቶች ነበሩ። አቶ ሳዳት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አቶ ለማ ለመገናኛ ብዙኃን እንዳይናገሩ ክልከላ ተደርጎባቸዋል የሚባለው ከጥርጣሬ የመነጨ ነው ይላሉ። "ልዩነቱ በውይይት ተፈትቷል። ይሄ እውነት ነው። ውይይቱ ከተካሄደ በኋላ በመግባባት እየተሰራ ይገኛል። አሁንም በኃላፊነት ላይ ነው ያሉት" ይላሉ አቶ ሳዳት። "አቶ ለማ ካልተናገሩ በቀር የፓርቲው መግለጫ ስህተት ነው ብሎ ማሰቡ ትክክል አይደለም። በፓርቲው የተሰጠው መግለጫ፤ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እና የጓድ ለማ አቋም ሆኖ መታየት አለበት" ብለዋል አቶ ሳዳት። የመካከለኛ እና ዝቅተኛ ደረጃ ባለሥልጣናት ሹም ሽር በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ ከመካከለኛ እስከ ዝቅተኛ ደረጃ ባሉ ባለሥልጣናት ላይ ሹም ሽር እየተካሄደ ይገኛል። ቀላል የማይባሉ የክልሉን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ ግለሰቦች ከሥራ እንዲነሱ እየተደረጉ ያሉት፤ የአቶ ለማ ሃሳብ ደጋፊዎች ናቸው የሚሉ መላምቶችን የሚሰነዝሩም አልጠፉም። አቶ ሳዳት ግን፤ "ፓርቲው በራሱ ምዛኔ ባለሥልጣናትን ከቦታ ቦታ ያሸጋሽጋል። ምደባም ይሰጣል። እንዲህ አይነት ሹም ሽሮች የሚካሄዱት በአመለካከት ልዩነት ላይ ተመስረቶ አይደለም" "በአሁኑ ሰዓት 'የፓርቲ አስተሳሰብ' እንጂ 'የአቶ ለማ ሃሳብ' የሚባል ነገር የለም" በማለት የነበሩ ልዩነቶች መፈታታቸውን አቶ ሳዳት አስረግጠው ይናገራሉ። አቶ ለማ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጎልተው የወጡባቸው አጋጣሚዎች በወቅቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በተለይ ደግሞ በክልላቸው ፖለቲካ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው የማይካደው አቶ ለማ፤ ከፍ ሲል "ለመውደቅና ለመበታተን ከጫፍ ደርሳ የነበረችውን ኢትዮጵያ በአንድነቷ እንድትቀጥል ያደረጉ ሰው ናቸው" ተብለው እስከ መወደስ ይደርሳሉ። ለመሆኑ አቶ ለማ በኢትዮጵያ እና በክልሉ ፖለቲካ ውስጥ ጎልተው እንዲወጡ ያስቻሏቸው አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው? "ማስተር ፕላን" 2008 ዓ.ም የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተሰኘውን እቅድ በመቃወም በኦሮሚያ ሕዝባዊ ተቃውሞ የተቀጣጠለበት ዓመት ነበር። ታዲያ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ማስተር ፕላኑ መተግበሩ እንደማይቀር በሚናገሩበት ወቅት፤ አቶ ለማ የሕዝቡን ተቃውሞ ለማርገብ ከቡራዩ እና አካባቢው ነዋሪዎቸ ጋር ውይይት ሲያደርጉ "ማስተር ፕላኑ ሕዝብ ካልፈለገው ይቀራል፤ ከሰማይ የሚወርድ ነገር የለም" የሚል ይዘት ያለው ንግግር አድርገው ነበር። ይህ ንግግራቸው ከፍተኛ ድጋፍ ያስገኘላቸው ሲሆን፤ ብዙም ሳይቆይ የክልሉ ፕሬዝደንት ሆነው ተሾሙ። የለማ ቡድን "ቲም ለማ" አቶ ለማ የኦህዴድ ሊቀ መንበር እና የክልሉ ፕሬዝደንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ እርሳቸው የመረጧቸውን አባላት በመመልመል 'ቲም ለማ' የተሰኘ ቡድን እንዳቋቋሙ ይነገራል። ይህ ቡድን ሕዝቡ በወቅቱ ያነሳቸው ለነበሩ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ጥረት ያደርግ ነበረ። በዚያን ወቅትም የክልሉ ገዥ ፓርቲ ኦህዴድ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 'ኦሮምኛ የፌደራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆን እታገላለሁ" ያለው። ተከትሎም በሺህዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ከእስር መልቀቁ ፓርቲው በኦሮሚያ ያለው ድጋፍ እንዲጨምር አድርጎለት ነበር። 'ጌታችን ሕዝባችን' ጥር 4/2008 የኦህዴድ 27ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓልን በማስመልከት በአዳማ ከተማ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ አቶ ለማ ለፓርቲያቸው አባላት ". . . ጌታችን ሕዝባችን ነው። የክልላችን ሕዝብ ነው። ለሌላ ጌታ መስገድ የለብንም" በማለት ተናግረው ነበር። ይህ የአቶ ለማ ንግግር ህውሓት በኦህዴድ ላይ የነበረውን የበላይነት የሰበረ ነው በማለት አንዳንድ ድርጅቱንና የአገሪቱን ፖለቲካ በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ። "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው" ከለውጡ ማግስት ጀምሮና በተከታይ በነበሩት ጊዜያት አቶ ለማ በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙበት ወቅት ነበር። ከዚህ ቀጥሎ ያደረጉት ንግግር ከክልላቸው አልፎ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የኦሮሞ እና የአማራ ሕዝብ ወንድማማችነትን ለማጠናከር ባለመው መድረክ ላይ "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው" በማለት ያደረጉት ንግግር በበርካቶች ተወዳጅነትን አስገኝቶላቸዋል።
news-51479249
https://www.bbc.com/amharic/news-51479249
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለስምምነት ተበተነ
ባለፈው ወር ላይ ለቀናት ሲካሄድ በነበረው ውይይት ላይ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሦስቱ አገራት ስብሰባ ያለስምምነት ተጠናቀቀ።
የሦስቱ አገራት የውሃ ሚንስትሮች በግድቡ ዙሪያ በካርቱም ሱዳን ታህሳስ 11 በተገናኙበት ወቅት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የካቲት 4 እና 5 2012 ዋሽንግተን ረቂቅ ሰነድ ለማዘጋጀት ሲካሄድ የነበረው ውይይት "በዚህኛውም ዙር ሳይቋጭ" ተጠናቋል። የአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ በታዛቢነት ይሳተፉበታል የተባለውን ይህን ድርድር ያለውጤት እንዲያበቃ ያደረገው ምክንያት ምን እንደሆነ አምባሳደር ፍጹም ያሉት ነገር የለም። ውይይቱ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማዘጀት ሲካሄድ የነበረ ነው። ቢቢሲ ለውይይቱ ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች እንደተረዳው ምንም እንኳን የሚካሄደው ውይይት በግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ እንዲሆን ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች ቢሆንም በግብጽ በኩል ድርድሩ የውሃ ድርሻ ላይ እንዲያተኩር ግፊት እያደረገች ነው ብለዋል። በሱዳን በግብጽና በኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የቆየው የህዳሴ ግድብ ድርድር ትኩረቱን ስቶ ወደ ውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ መሄዱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ለቢቢሲ ተናገሩ። እኚህ ምንጫችን ሱዳን የአቋም ለውጥ አድርጋ ከግብጽ ጋር መወገኗን እንዲሁም አሜሪካ እና የዓለም ባንክ ለግብጽ መወገናቸውን በመጠቆም አሁን ላይ ጉዳዩ "4 ለ 1" ሆኗል በማለት ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። አሜሪካ እና ዓለም ባንክ በግድቡ ዙሪያ እጃቸውን እንዲያስገቡ መፈቀዱ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ እንድትከፍል እያደረጋት እንደሆነ እኚህ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ውስጥ አዋቂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ በጋራ ማዘጋጀት እንዳልተቻለ ተገለፀ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ከሁለት ቀናት በፊት ተደራዳሪ ቡድኑ ''በብዙ ጉዳዮች ላይ የመከረ ቢሆንም ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ ማዘጋጀት አለመቻሉ ታይቷል'' ብለው ነበር። ስምምነት ላይ ያልተደረሰበት የሰነዱ አብዛኛው ክፍል የቀረበው በአሜሪካ በመሆኑ፤ ትኩረቱም ስለ ግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ በመሆን ፈንታ፤ "ማን ምን ያህል የውሃ ድርሻ ይኑረው? የሚለው ላይ የሚያተኩር በመሆኑ" ከስምምነት መድረስ እንዳልተቻለ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉት እኚህ ባለሙያ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አክለውም በግድቡ ጉዳይ የኢትዮጵያ የህግ አርቃቂ ቡድን አሁንም አሜሪካ እንደሚገኝ በማስታወስ፤ በውሃ ክፍፍል ላይ ለመነጋገር እንደ አገር ዝግጁ አይደለንም፤ የድርድሩ አላማም ይህ አይደለም ብለውናል። እሳቸው እንደሚሉት ከግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ በድርቅ፣ በረዥም ጊዜ ድርቅ እና በተከታታይ ድርቅ በሚሉት ሰነዱ ላይ በሰፈሩት ቃላቶች ትርጓሜ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድጋፍ ሠልፍ እና የኦፌኮ ስብሰባ መከልከል በጅማ ስለዚህም የኢትዮጵያ የህግ አርቃቂች በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ሰነዱ ላይ የሰፈሩ በርካታ ነጥቦችን በጥያቄ ምልክት ውስጥ ለማስቀመጥ ተገድደዋል። "ትልቁ ነገር ሰነዱ የውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ ሊያተኩር አይገባም ነበር። ወደ አሜሪካ የሄደው የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ቡድንም በዚህ ላይ [የውሃ ድርሻ ክፍፍል] ለመነጋገር ስልጣን አልተሰጠውም። ስለ ውሃ ድርሻ ክፍፍል ኢትዮጵያ ከግብጽና ከሱዳን ጋር ብቻ ሳይሆን ከአስሩም የተፋሰሱ አገራት ጋር ነው መነጋገር ያለባት" ይላሉ። ኢትዮጵያ የናይል ተፋሰስ ትብብር ማዕቀፍን ፈርማ ያፀደቀች አገር መሆኗን እና ይህ ስምምነት ሳይጣስ ሁሉም የተፋሰሱ አገራት ባሉበት መነጋገር እንደሚገባት ያስታውሳሉ። ታዛቢ ወደ አደራዳሪ ሶስቱ አገራት በሚያደርጉት ድርድር ላይ የሶስተኛ አካል ጣልቃ መግባት ይኖርበታል ብላ ሃሳብ ያቀረበችው ግብጽ መሆኗ ይታወቃል። ፕሬዝደንት አብዱል ፈታ አል ሲሲ አሜሪካ በጉዳዩ ላይ ታሸማግለን ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውም የሚታወስ ነው። በወቅቱ ኢትዮጵያ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትን እንደማትቀበል ገልጻ ነበር። ለዚህም እንደምክንያት ያስቀመጠችው በሶስቱ አገራት የተደረሱ ''አበረታች'' ስምምነቶችን ያፈርሳል እንዲሁም ሶስቱ አገራት እአአ 2015 ላይ የፈረሙት የመርህ ስምምነትንም ይጥሳል የሚል ነበር። • አፍሪካ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል አቅሙ አላት? የኋላ ኋላ ግን ዓለም ባንክ እና አሜሪካ በሶስቱ አገራት መካከል በሚደረጉ ውይይቶች ላይ የታዛቢነት ሚና ኖሯቸው ይሳተፋሉ ሲባል ቆየ። የኢትዮጵያ መንግሥትም አሜሪካና አለም ባንክ በድርድሩ ታዛቢዎች እንጂ አደራዳሪ አይደሉም ብሎ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ላይ አደራዳሪነታቸው አጠያያቂ አይመስልም። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ጥር 25 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት፤ የአሜሪካ መንግሥት እና ዓለም ባንክ 'ለማደራደር' ጥያቄ አቅርበው 'ሲያደራድሩ' ቆይተዋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ "ለአሜሪካ እና ዓለም ባንክ ምስጋና ማቅረብ የሚያስፈልገው፤ በሚያውቁን እና አቅም ባላቸው ፊት ስንነጋገር መስማማት ጀምረናል" ሲሉም ተደምጠዋል። እኚህ የቢቢሲ ምንጭ እንደሚሉትም የአዲስ አበባ የመጀመሪያው ስብሰባ ላይ በታዛቢነት ተቀመጡ፣ ካይሮ ላይ በታዛቢነት ቀጥለው ሱዳን ካርቱም ላይ ግን አደራዳሪ ሆኑ። ከዚያም ተመልሰው አዲስ አበባ ላይ አደራዳሪ መሆናቸውን ቀጠሉ። "አሁን እኮ ዋሽንግተን ላይ የሕግ እና የቴክኒክ ቡድኑ ተገኝቶ፤ ሰነድ ቀርቦ ግልፅ ድርድር ነው እየተካሄደ ያለው" በማለት ያስረግጣሉ። እነዚህ አካላት ከታዛቢነት ራሳቸውን ወደ አደራዳሪነት ከማሸጋገራቸውም በላይ ኢትዮጵያ ላይ "ከፍተኛ ጫና ማሳደርና ማስፈራራትም ደረጃ ደርሰዋል" ይላሉ ባለሙያው። እርሳቸው እንደሚሉት አሜሪካና አለም ባንክ በኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች በኩል የሚነሱ ሃሳቦችን ለመቀበል በፍጽም ፍላጎት አያሳዩም። ይልቁንም እየተቀበሉ ያለው የግብፅና የሱዳንን ሃሳብ ብቻ ነው። በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ከመጀመሪያ ጀምሮ ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለራሷ ጥቅም ስትል ከኢትዮጵያ ጎን ቆማ የነበረችው ሱዳን አቋሟን ቀይራ ከግብፅ ጎን መሰለፏንም ያረጋግጣሉ። እሳቸው እንደሚያብራሩት በአሜሪካ የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት የምትፈልገው ሱዳን ይህን ፍላጎቷን ይዛ ስትመጣ አሜሪካ በበኩሏ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጣለች። • ‘በአስራ አራት ዓመቴ ስደፈር የሚያሳይ ቪዲዮ በወሲብ ፊልም ድረገፅ ላይ ነበር' ምናልባትም የሚሉት እኚህ ምንጭ ከትናንት በስቲያ እንደተሰማው የቀድሞውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አል-በሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፎ መሰጠት ሱዳን ያሟላችው አንድ ቅድመ ሁኔታ ሊሆን ይችላል። ከግብፅ ጎን መቆም ሁለተኛው ቅድመ ሁኔታ ሲሆን ይህንንም ሱዳን እየፈፀመች ነው። "ሶስተኛ ወገን ማስገባት ካስከፈለው ከባድ ዋጋ አንዱ ይሄ ነው" በማለት ድርድሩ ለኢትዮጵያ አጣብቂኝ መንገድ ላይ እንዳለ ይገልፃሉ። አሜሪካ ለግብጽ ለምን ወገነች? ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ሰላም ለብልጽግና [ፒስ ቱ ፕሮስፔሪቲ] የተሰኘውን የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅዳቸውን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይህ የትራምፕ እቅድ እየሩሳሌም ያልተከፋፈለች የእስራኤል መዲና ትሆናለች ከማለቱም ባሻገር ፍሌስጤማውያን እና የተቀረው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሕገ-ወጥ የሚለውን የእስራኤልን የዌስት ባንክ ሰፈራ እውቅና ይሰጣል። ይህ የትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ በፍልስጤማውያን ወዲያው ውድቅ የተደረገ ሲሆን እንደ ኢራቅ እና ሶሪያ ያሉ የሰላም እቅዱን በይፋ ከተቃወሙት አገራት መካከል ይገኙበታል። • ''የአሰብና ምፅዋ ወደቦችን አገልግሎት ለማሻሻል እየሰራን ነው'' ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቀላል የማይባሉ የአረቡ ዓለም አገራትም የትራምፕን የሰላም እቅድ በጥርጣሬ ዕይን መመልከታቸው አልቀረም። ታዲያ በአረቡ ዓለም ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነችው ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ግብጽ፤ የትራምፕ ዕቅድ በአረቡ አገራት ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፍተኛ የሆነ የራሷን አስተዋጽኦ ልታበረክት ትችላለች። እኚህ የቢቢሲ ምንጭ እንደሚሉት፤ የፕሬዝደንት ትራምፕ እቅድ እንዲሰምር ግብጽ የበኩሏን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ልታበረክት ትችላለች። ሱዳን እና እስራኤል ለእስራኤል እውቅና ከማይሰጡ የአረብ ሊግ አባል አገራት መካከል ሱዳን አንዷ እና ተጠቃሽ ነች። ሁለቱ አገራት ይህ ነው የሚባል ፖለቲካዊ ሆነ ኢኮኖሚያዊ ግነኙነት የላቸውም። እአአ 1967 የአረብ አገራት ያካሄዱት ታሪካዊ ስብሰባ ይታወሳል። በሱዳን ካርቱም በተካሄደው በዚህ ስብሰባ የአረብ አገራቱ 'ሶስቱ እምቢታዎች' ["Three No's"] ተብሎ የሚታወቀውን በእስራኤል ላይ ያላቸውን አቋም አንጸባርቀው ነበር። ለእስራኤል እውቅና አለመስጠት፣ ከእስራኤል ጋር ከስምምነት አለመድረስ እና ከእስራኤል ጋር አለመደራደር። ዛሬም ድረስ በርካታ የአረብ ሊግ አባል አገራት ለእስራኤል እውቅና አልሰጡም። ከእነዚህም መካከል ሱዳን አንዷ ነች። ከአንድ ሳምንት በፊት ግን ታሪካዊ በተባለ ሁኔታ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር መንግሥት ካውንስል ሰብሳቢ አብድል ፈታህ አል-ቡረሃን በኡጋንዳ ኢንቲቤ ተገናኝተው ነበር። • "የኤርትራ መሬት ያልተመለሰው በህወሓት እምቢታ ነው" ፕ/ት ኢሳያስ ሁለቱ መሪዎች ለሰዓታት ከተነጋገሩ በኋላ ግንኙነት ለመጀመር መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ኔታኒያሁ ከውይይቱ በኋላ ሱዳን አዲስ እና አዎንታዊ ወደሆነ አቅጣጫ እያመራች ነው ማለታቸውን የእስራኤል መንግሥት ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የእስራኤል ወዳጅ የሆኑት ትራምፕ፤ የኔታኒያሁ አገር በመካከለኛው ምስራቅ እና በአረብ ሊግ አባል አገራት ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖራት ይሻሉ። ሱዳን ይህንን የአሜሪካንን ፍላጎትን ማሳካት የምትችል ከሆነ በግድቡ ድርድር ዙሪያ ያላት ፍላጎት ሊጠበቅላት እንደሚችል ይታመናል። ለቢቢሲ ምልከታቸውን የሰጡት ባለሙያ እንደሚሉት ደግሞ፤ በግድቡ ድርድር ዙሪያ ሱዳን ከግብጽ ጋር አብራ የምትቆም ከሆነ፤ ተጥሎባት የሚገኘውን ማዕቀብ ሊነሳላት እንደሚችል ይጠቁማሉ። የሱዳን ከግብጽ ጎን መቆም ማለት፤ የትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ እንዲተገበር፣ የአረብ ሊግ አባላት በእስራኤል ላይ ያላቸውን አቋም ማለሳለስ ማለት ሊሆን ይችላል ይላሉ። አሜሪካ ዋና ዓላማዋ ሶሰቱን አገራት ማስማማትም ሳይሆን የራሷን እና የእስራኤልን ፍላጎት ማሳካት ዋነኛ ግቧ መሆኑን ይጠቁማሉ። በዚህ ከባድ ድርድር ውስጥ በኢትዮጵያ በኩል መታለፍ የሌለበት መስመር የቱ ነው? ለባለሙያው ያቀረብነው ጥያቄ ነበር። "እየተሄደበት ያለው መንገድ በሙሉ አደገኛ ነው" በማለት ድሮም ስለ ውሃ ክፍፍል ኢትዮጵያ ለብቻዋ ከግብፅና ሱዳን ጋር ድርድር አላደርግም ያለችው ለሁለት ጫና ያሳድሩብኛል በሚል ፍራቻ እንደነበር ያስታውሳሉ። "አሁን ግን ብሶ አራት ለአንድ ሆኗል" በማለት ግብፅ፣ ሱዳን፣ አሜሪካና አለም ባንክ በአንድ በኩል ኢትዮጵያ ደግሞ በሌላ ወገን አጣብቂኝ ውስጥ መውደቋን ያስረዳሉ። በጫና ውስጥ የሚደረግ ስምምነት አለም አቀፍ ተቀባይነት እንደማይኖረው፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስምምነት ላይ መድረስ ቢቻል እንኳ በኢትዮጵያ በኩል በቀጣይ የሚመጡ መንግሥታትና ትውልድ የሚቀበሉት ነገር ስለማይሆን ነገሩ ወደ ፊት አገራቱን የባሰ ግጭት ውስጥ የሚከት ሊሆን እንደሚችልም ምልከታቸውን ያስቀምጣሉ ባለሙያው። • የኮሮናቫይረስ ስጋትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ በኩል አሁን መወሰድ ያለበት እርምጃ ምን መሆን አለበት? ለሚለው ጥያቄያችን "አሁን ያለውን ሂደት መቆም ያለበት ይመስለኛል። ወደ ኋላ ተመልሶ ተመካክሮና ነገሮችን አጢኖ ሁሉንም ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል ነገር ላይ መስራት [የተሻለ] ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ነገሮች በ2015 አገራቱ በተፈረሙት 'ዲክላሬሽን ኦፍ ፕሪንስፕልስ' ስምምነት መሰረት መቀጠል አለባቸው ይላሉ። ስምምነቱ አገራቱ መመሪያ አዘጋጅተው በግድቡ ውሃ አያያዝና አለቃቅ ላይ ከስምምነት መድረስ እንደሚያዋጣ ያትታል። ከዚያ አንፃር አሁን እየተደረገ ያለው ድርድር ትኩረቱን ስቶ ከግድቡ ውሃ አያያዝና አለቃቀቅ ወደ የውሃ ድርሻ ክፍፍል የሄደ እንደሆነ ያስረግጣሉ ባለሙያው። የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በግድቡ ዙሪያ ለመራደር በካርቱም ሱዳን ታህሳስ 11 በተከናኙበት ወቅት የኢትዮጵያ መሪዎች ምን ይላሉ? ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙበት ወቅት ሶስቱ አገራት የመጨረሻ የተባለለትን ስምምነት ለመፈረም ከተዘጋጁ በኋላ፤ ስምምነቱ ከመፈረሙ በፊት ዝርዝር ዕይታ እና ውይይት ስለሚያስፈልገው እንዳይፈረም የሚል አቅጣጫ በመስጠታቸው ፊርማው እንዲዘገይ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በዚህም ፕሬዝደንት ትራምፕ፣ የዓለም ባንክ እና የአሜሪካ ፋይናንስ ሚንስትሩ ጋር በስልክ ተገናኝተው ረዘም ላለ ጊዜ መነጋገራቸውን ተናግረዋል። • ግብጻዊቷ ዘፋኝ አባይ ላይ ቀልደሻል ተብላ እስር ተፈረደባት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከእርሳቸው በፊት አገሪቱን ይመሩ የነበሩ መሪዎች ጋርም ተመሳሳይ አቋም እንደነበራቸው በማስታወስ፤ የድርድሩ ውጤት ኢትዮጵያን የሚጎዳ እንዳይሆን እንደሚሰሩ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያን ወክለው የሚደራደሩት የውሃ መስኖ እና ኢንርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለም ከሁለት ቀናት በፊት "የኢትዮጵያን ብሔራዊ ፍላጎት ባማከለ መልኩ ጠንክረን እንሰራለን" ብለዋል። በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋም፤ ኢትዮጵያ "በአባይ የመጠቀም መብቷን አሳልፎ የሚሰጥ ምንም ዓይነት ስምምነት አትፈጽምም!" ብለዋል። የግብጹ አህራም ኦንላይን በበኩሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ እንዳይፈረም አድርጌያለሁ ያሉትን ስምምነት ግብጽ መፈረሟን በወቅቱ ዘግቦ ነበር። አህራም የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ፊርማቸውን ከማኖራቸው በፊት ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው ውይይት ማድረግን መርጠዋል ያለ ሲሆን፤ ሱዳንም በተመሳሳይ መልኩ ስምምነቱን እንዳልፈረመች ዘግቧል። "በግድቡ አሞላል እና ውሃ አለቃቀቅ ላይ በካርቱም እና በካይሮ መካከል ጉልህ ልዩነት የለም" ሲል አህራም ጨምሮ ዘግቧል።
news-52649225
https://www.bbc.com/amharic/news-52649225
አፍሪካዊቷ ቢሊየነርና የብሩስሊ ፊርማ?
ከሰሞኑ የሃገሯን ሃብት አራቁታለች የምትባለው የቀድሞው የአንጎላ ፕሬዚዳንት ልጅና ቢሊየነር ኢዛቤል ዶስ ሳንቶስና የቻይናው ዕውቅ የኩንግፉ ስፖርተኛ፣ ፊልም ሰሪና የማርሻል ጥበብ ፈላስፋ ብሩስሊ በአንድ ላይ ስማቸው እየተነሳ ነው።
እንዴት ነው ጄት ኩንዱን የፈጠረ፣ እንዲሁም የአልበገር ባይ ምሳሌ የሆነው ብሩስሊና አንጎላዊቷ ቢሊዮነር ዶስ ሳንቶስ ምን አገናኛቸው? አንጎላዊቷ ቢሊዮነር ዶስ ሳንቶስ ከሰሞኑ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሃገር ውስጥም ሆነ በፖርቹጋል ያለው ንብረቷ የታገደው ይነሳልኝ ብላለች። ለዚህም የሉዋንዳ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመመሳጠር ሃሰተኛ ማስረጃዎችን አቅርበውብኛል ብላለች። •በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው •የቀድሞው የአንጎላ መሪ ልጅ የ15 ሚሊዮን ዶላር ቤቷን ልታፈርስ ነው ቢሊየነሯ እንደምትለው የሷ ያልሆነ ፓስፖርት አመሳስለው በመስራት የተፈበረኩ ማስረጃዎችን አቅርበውብኛል በሚል ፍርድ ቤቶቹን ወንጅላቸዋለች። ለዚህም ማስረጃ እንዳላት የተናገረችው ኤዛቤል ዶስ ሳንቶስ ፓስፖርቱ ላይ የተቀመጠው ፊርማ የሷ ሳይሆን እንዲያውም የኩንግፉው ንጉስ ብሩስሊ ነው ብላለች። ፓስፖርቱ ላይ የተቀመጠው ፊርማ የብሩስሊ መሆኑን ማረጋገጧን በፅሁፍ ለፍርድ ቤቱ ብታስገባም ፍርድ ቤቶቹ ያሉት ነገር የለም። በአፍሪካ ውስጥ አሉ ከሚባሉ የናጠጡ ቱጃሮች አንዷ የሆነችው ዶስ ሳንቶስ የተጣራ አንጡራ ሃብቷም ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል። አባቷ ጆሴ ኤድዋርድ ዶስ ሳንቶስ አንጎላን ለ38 አመታት ያህል ቀጥ ለጥ አድር በመግዛት፣ በጨቋኝ ክንዳቸው እንዲሁም የሃገሪቷን ሃብት በመመዝበር ይተቻሉ። ልጃቸውምን በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2016 የሃገሪቱ የነዳጅ ማጣሪያ ድርጅት ሃላፊ አድርገው ሾመዋት ነበር። በአመቱ አባቷ ከስልጣን መውረዳቸውንም ተከትሎ ተተኪያቸው ጆዋ ሎውሬንሶ ዝም አሏሏትም። ከነበራት ድርጀቱ ሃላፊነት ከማንሳት በተጨማሪ የሃገሪቱን አንድ ቢሊዮን ዶላር ሃብት ከተባባሪዎቿ ጋር በመመዝበር ወንጀል ከሰሷት። በፍርድ ቤት ውሳኔም በአንጎላ እንዲሁም በፖርቹጋል ያለው ሃብት እንዲታገድ ተወሰነ። በአፍሪካ ሴት ቢሊየነሮች ደረጃ ቀዳሚ የሆነችው ዶስ ሳንቶስ ይህን ሁሉ ውንጀላ በማጣጣል አልፈፀምኩም ብላ ክዳለች። ከሰሞኑም ያቀረበችው ማስረጃ "ንፁህነቴን" የሚያረጋግጥ ነው በማለት የተፈበረከ የተባለውንም ፓስፖርት በህዝብ ግንኙነቷ በኩል ይፋ እንዲሆን አድርጋለች። በትዊተር ገጿም አጋርታለች። ዶስ ሳንቶስ እንዴት ልትከሰስ ቻለች? ከነዳጅ ማጣሪያ ሃላፊነቷ መነሳቷን ተከትሎ እሷን ተክቶ የመጣው ካርሎስ ሳቱሪኖ የተባለው ግለሰብ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዳለ ባለስልጣናቱን ማሳወቁን ተከትሎ ነው ምርመራ የተከፈተባት። በጎርጎሳውያኑ 2019ም የአንጎላ ፍርድ ቤት በአንጎላ የሚገኘውን ባንኳ ውስጥ ያለው ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ እግድ ከመጣል በተጨማሪ የተለያዩ ኩባንያዎቿንም እንዳታንቀሳቅስ አድርጓታል። በሷ ላይ ብቻ ሳይሆን በባለቤቷና ሲንዲቃ ዶኮሎና በስራ አስኪያጇም ላይ ተመሳሳይ ውሳኔ ተላለፈ። በወቅቱም ዶስ ሳንቶስ ሁኔታውን ከማውገዝ አልፋ "ፖለቲካዊ ብቀላ" ነውም ብላለች። ምንም እንኳን ቢሊየነሯ ፖለቲካዊ ኢላማ ተደርጌያለሁ ብትልም ከ700 ሺህ በላይ የሆኑ ሾልከው የወጡ መረጃዎች እሷም ሆነ የኮንጎ ዜግነት ያለው ባለቤቷ የሃገሪቷን ንብረት አግባብ በሌለው ሁኔታ ጥርጣሬ የተሞላባቸው ስምምነቶች ወጥተዋል። •ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያን ሃሳብ አልቀበልም አለች ከነዳጅ ጋር በተያያዘ አንድ የለንደን የነዳጅ አውጭ ኩባንያ በአገሯ እንዲሰራ በተጭበረበረ መንገድ ሲገባ ዶስ ሳንቶስ የትወናው አካል ነበረች። በኋላ አባቷ ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ ኩባንያው ሲታገድ 58 ሚሊዮን ዶላር የከፈለችበት ደረሰኝ ተገኝቷል። ይህ ለምን እንደተፈጸመና ድርሻዋስ ምን ነበር የሚለው ያልተመለሰ ጥያቄ ነው። የኢዛቤል ዶ ሳንቶስ ጉዳይ በዚህ አያበቃም። አንድ ዱባይ ከሚገኝ ኩባንያ ጋርም በተመሳሳይ ተመሳጥራ ሁለት የክፍያ ሰነዶች እንደተላኩላት ማግኘት ተችሏል። ይህ ሕጋዊነት ይጎድለዋል የተባለው የክፍያ ሰነድም ለምን ክፍያው እንደተፈፀመ የሚያትተው ነገር የለም። በዚህ የሂሳብ መጠየቂያም በአንደኛው 472,196 ዩሮ ሁለተኛው ደግሞ 928,517 የአሜሪካን ዶላር ተጠይቆበታል። ይህም ሰነድ ህጋዊነቱ ያልተረጋገጠ ቢሆንም ቢሊየነሯ ግን ሕጋዊ መንገድን ተከትዬ የፈጸምኩት ነው ብላለች። ሌላኛው ከነዳጅና ኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ለኢዛቤል የቀረበው ክስ በጎርጎሮሳውያኑ 2006 የአንጎላ የኃይል አቅርቦት ለመሥራት ስትስማማ በወቅቱ 15% ብቻ ከፍላ ቀሪው ዝቅተኛ ወለድ ተደርጎላት በተራዘመ ጊዜ እንድትከፍል ነበር። ላለፉት 11 ዓመታት ግን መክፈል የነበረባትን 70 ሚሊዮን ዶላር አልከፈለችም። አሁን ኢዛቤል በባለድርሻነት የምትመራው ኩባንያ አጠቃላይ ዋጋው 750 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። ተቋሟ እዳውን በ2017 ለመክፈል ተስማምቶ ነበር፤ ነገር ግን ቢያንስ ወለድ ተብሎ የታሰበውን 9% ማካተት ስላልቻለ ክፍያው እንዳይፈጸም ተደርጓል። ከአልማዝ ጋር በተያያዘ በሙስና ሥራው ኢዛቤል ብቻዋን እንዳልተሳተፈች መረጃ የቀረበባት ሲሆን የሃገሪቷ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባሏም በአሻጥሩ ተሳትፏል ይላል። በጎርጎሳውያኑ 2012 ባለቤቷ መንግሥት ከሚቆጣጠረው ሶዳየም ከሚባለው የአልማዝ ኩባንያ ጋር የአንድ ወገን ፊርማ ፈርሟል። በፊርማው መሰረት ሁለቱ ፈራሚዎች የፕሮጀክቱን ወጪ ግማሽ ግማሽ መቻል ነበረባቸው። ነገር ግን ሙሉ ወጭው የተሸፈነው በመንግሥት ነው። ሰሞኑን የሚዲያዎች እጅ ላይ የገባው ዶክመንት እንደሚያሳየው ከ18 ወራት በኋላ ባለቤቷ 79 ሚሊዮን ዶላር መክፈል ሲገባው የከፈለው የገንዘብ መጠን ግን 4 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ይባስ ብሎ ደግሞ ጉዳዩን ስለደለልኩ ሽልማት ይገባኛል ብሎ ከዚሁ ፕሮጀክት ውስጥ የኢዛቤል ባለቤት ዶኮሎ ተጨማሪ 5 ሚሊዮን ዶላር ራሱን ሸልሟልም ተብሏል። ከዚህ ስምምነት የአንጎላ ሕዝብ የሚያገኘው ጥቅም ምንም ሲሆን በአንጻሩ ለኩባንያው መሥሪያ ተብሎ ከግል ባንክ ለተበደሩት 200 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ይከፍላሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የአንጎላ መንግሥት አልማዝ በዝቅተኛ ዋጋ መሽጡን ቢያምንም ምንጮች እንደሚሉት ግን እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ከስሯል። ከመሬት ጋር በተያያዘ ዶሰስ ሳንቶስ መሬት ላይም ሁነኛ ተሳታፊ ናት። መረጃው እንደሚያሳየው ቢሊየነሯ ዶ ሳንቶስ በ2017 በዝቅተኛ ዋጋ መሬት እንድትገዛ መንግሥት አመቻችቶላታል። ይህንን በመዲናዋ ሉዋንዳ የባህር ዳርቻ የሚገኘውን ጋሻ መሬት የገዛችውም በአባቷ ረጅም እጅ በመታገዝ ነበር። ኮንትራቱ የሚለው መሬቱ 96 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ነው።ዶስ ሳንቶስ ያወጣችው ግን 5 በመቶ ብቻ ነው። ቦታው ላይ የነበሩ አንጎላዊያን ግን ይዞታቸው ለዶስ ሳንቶስ በመሰጠቱ ከነበሩበት ዋና ከተማዋ ሉዋንዳ 50 ኪሎ ሜተር ርቀው ሄደዋል። ከመሬት ጋር በተያያዘ በሌላ የኢዛቤል ዶ ሳንቶስ ፕሮጀክት ከ500 በላይ ቤተሰብ በእርሷ ምክንያት ተፈናቅሏል። ከቴሌኮም ዘርፍ ጋር በተያያዘ ቢሊየነሯ ከቴሌኮም ዘርፍም አንጎላ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ አግበስብሳለች፤ በአገሪቱ ከፍተኛው የሞባይል ስልክ አቅራቢ ኩባንያ ውስጥ 25 በመቶ ድርሻ አላት። ዩኒቴል የተባለው ይህ ኩባንያ በቀቅርቡ ለኢዛቤል 1 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ የሰጣት ሲሆን ቀሪ ኃብቷም ሌላ 1 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ተብሏል። ይሁንና ሴትዮዋ ከዘርፉ ገንዘብ የምታገኝበት ይህ ብቸኛ መንገድ አይደለምም ተብሏል። በእንግሊዝ ተቀማጭነቷን ያደረገችው ቢሊየነሯ በነዳጅ፣ ቴሌኮምና ባንክ ዘርፎች በመሰማራት በሃገሯ አንጎላና በፖርቹጋል የተትረፈረፈ ሃብትን ማትረፍ ችላለች።
news-57117546
https://www.bbc.com/amharic/news-57117546
ከእስራኤል ጦር ጋር የሚፋለመው ሃማስ ማነው?
ሃማስ ጋዛን የሚያስተዳድር የፍልስጥኤም የሚሊሻ ቡድን ነው። ከበርካታ የፍልስጥኤም ሚሊሻ ቡድንም ትልቁ ሃማስ ነው።
መጠሪያውን ያገኘው ከመጀመሪያ 'ኢንቲፋዳ' በኋላ ነው። እአአ 1987 ላይ ፍልስጥኤማውያን የእስራኤልን በዌስት ባንክና ጋዛ ሰርጥ ሰፈራ ተቃውመው የመጀመሪያውን ኢንቲፋዳ ቀሰቀሱ። ሃማስ በመቋቋሚያው ቻርተር ላይ "ለእስራኤል መውደም ሳልታክት እሰራለሁ" የሚል አንቀፅ አስፍሯል። ሃማስ ሲመሰርት ሁለት ዓላማዎች ነበሩት። አንደኛው በጦር ክንፉ እስራኤል መውጋት ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ኢዘዲን አል-ቃስም በሚሰኘው ማዕቀፉ ለፍልስጤማውን ማህበራዊ አገልግሎት መስጠት ነው። እአአ 2005 ላይ እስራኤል ጦሯን እና ሰፋሪዎቿን ከጋዛ ስታስወጣ፤ ሃማስ በፍልስጤም ፖለቲካ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ጀመረ። ከአንድ ዓመት በኋላ በተካሄደ ምርጫም ሰፊ ድምጽ ማግኘት ችሎ ነበር። የሃማስ ተዋጊዎች ከእስራኤል ጋር ሦስት ጦርነቶችን ተዋግተዋል። የሃማስ የጦር ክንፍ በእስራኤል፣ በአሜሪካ፣ የአውሮፓ ሕብረት እና በዩናይትድ ኪንግደም አሸባሪ ቡድን ተብሎ ተፈርጇል። የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃቶች እአአ 1990 መጀመሪያዎች ላይ በርካታ ፍልስጥኤማውያንን በሚወክለው የፍልስጥኤማውያን ነጻነት ድርጅት (ፒኤልኦ) እና በእስራኤል መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አልቀበልም ካለ በኋላ ሃማስ ተጽእኖ ፈጣሪነቱ እየጨመረ መጣ። ሃማስ በሚያደርሳቸው የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶች በርካታ እስራኤላውያንን ገድሏል። እአአ 1995 የሃማስ ቦምብ ሰሪ የነበረው ያሃያ አይሻ መገደልን ተከትሎ ሃማስ በወሰደው የአጸፋ እርምጃ አጥፍቶ ጠፊዎች ከ60 በላይ እስራኤላውያንን ገድለው ነበር። በእስራኤል እና በፍልስጤማውያን መካከል ሰላም ለማውረድ ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል። በኦስሎ ሁለቱ አካላት የደረሱት ስምምነት፤ ሃማስ በሚያደርሳቸው ተደጋጋሚ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶች እስራኤል በስምምነቱ እንዳትገዛ ሲያደርጓት ቆይተዋል። የወቅቱ ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተንም የሁለቱን ኃይሎች መሪዎች አሜሪካ አስጠርተው ቢመክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ሃማስና የእስራኤል ጦር ሁለተኛው ኢንቲፋዳ ተብሎ ወደ ሚጠራው ግጭት ገቡ። ይህ ግጭት እአአ ከ2000 እስከ 2005 የዘለቀ ነው። በዚህ የግጭት ወቅት ሃማስ ዝነኝነቱ እየጨመረ ሄደ። ውጤታማ ያልሆነው የፍልስጤም አስተዳደር ለሕዝቡ ማድረስ ያቀታውን መሠረተ ልማት ሃማስ ለሕዝቡን ማድረግ ቻለ። እአአ 2004 ላይ የሃማስ መሪ ሼክ አሕመድ ያሲን እና መሪውን ይተካሉ ተብለው የነሩት አብዱል አዚዝ በእስራኤል የሚሳኤል ጥቃት ጋዛ ውስጥ ተገደሉ። በተመሳሳይ ዓመት የፒኤልኦ መሪ ያሲር አረፋት አረፉ። በዚህ መካከል የአሁኑ ሞሐሙድ አባስ የፍልስጤም መሪ ሆነው ብቅ አሉ። የሃማስ ቻርተር የሃማስ የ1988 ቻርተር የፍልስጤም ግዛት አሁን እስራኤል ያለችበት ቦታን እንደሚያጠቃልል ያትታል። መሬቱ የእስላም ምድር ነው ከአይሁድ አገር ጋርም ምንም አይነት ሰላም ሊኖር አይችልም ይላል። በእስራኤል ወታደሮችና በፍልስጤም ታጣቂዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት በሁለቱም ወገኖች በኩል ሞትና በርካታ ጉዳቶችን ያስከተለ ሲሆን በቀላሉ ላይበርድ የሚችልበትም ዕድል ከፍተኛ ነው። እስራኤል በጣም ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ አቅም ያላት አገር ናት፤ የአየር ኃይሏም ቢሆን በዓለም ተወዳዳሪ ነው። ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና የተለያዩ መረጃ መሰብሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም እስራኤል ቀላል የማይባሉ የጋዛ አካባቢዎችን አጥቅታለች። ነገር ግን ጥቃቱን የፈጸምኩባቸው አካባቢዎችና ህንጻዎች ሃማስ እና እስላማዊ አክራሪዎች የሚጠቀሙባቸው ስለሆኑ ነው እንጂ ንጹሀን ዜጎችን ኢላማ አላደረኩም ትላለች እስራኤል። ምንም እንኳን ሃማስ እና ኢስላማዊ ጂሃድ ቡድኖች ከእስራኤል ወታደራዊ አቅም አንጻር ዝቅተኛ ግምት የሚሰጣቸውቢሆንም እስራኤልን ለማጥቃት ግን በቂ መሳሪያዎች አሏቸው። እስካሁንም የተለያዩ ጥቃቶች ሰንዝረዋል። የእስራኤል ወታደሮች በቅርቡ መሳሪያ የታጠቀ ሰው አልባ አውሮፕላን ከጋዛ ወደ እስራኤል ለመግባት ሲሞክር ተኩሰው ጥለዋል። አንድ የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ደግሞ ‘’ከፍተኛ ስልጠና የወሰዱ የሀማስ አባላት የውስጥ ለውስጥ ቱቦዎችን በመጠቀም ወደ ደቡባዊ እስራኤል ለመግባት መሞከራቸውን ገልጸዋል። ቀድሞ መረጃ የደረሰው የእስራኤል መከላከያም ወደ እስራኤል ከመድረሳቸው በፊት መንገዳቸውን አፈንድተውባቸዋል። ነገር ግን ፍልስጤማውያን ከታጠቋቸው መሳሪያዎች መካከል በርካታ ዓይነቶች ያሉት ከመሬት ወደ መሬት የሚተኮስ ሚሳኤል በጣም ወሳኙ ነው። አብዛኛዎቹም በግብጽ በኩል በሲናይ በረሃ በተቆፈሩ ጉድጓዶች በኩል በድብቅ የገቡ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኛዎቹ ሀማስ እና ኢስላማዊ ጂሃዲስቶች የሚጠቀሟቸው ዘመናዊና ረቀቅ ያሉ መሳሪያዎች የሚመረቱት እዛው የጋዛ ሰርጥ ውስጥ በሚገኙ ሚስጥራዊ ቦታዎች ነው። እስራኤልና ሌሎች የውጭ ምንጮች ደግሞ እነዚህ መሳሪያዎች የሚመረቱት በኢራን ድጋፍ እንደሆነ ያምናሉ። በዚህም ምክንያት ነው እስራኤል መሳሪያዎቹ ይመረቱበታል ብላ የምታስባቸውን አካባቢዎች በአየር ድብደባ ጥቃት እየፈጸመች የምትገኘው። በሀማስ በኩል ያለው የመሳሪያ ክምችት ምን ያክል እንደሆነ እስካሁን አይታወቅም። ነገር ግን ሃማስ የተለያየ አይነት ጥቅምና አቅም ያላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የጦር መሳሪያዎች እንዳሉት ይታመናል። እስራኤል እነዚህ መሳሪያዎች ምን ያክል እንደሆኑና የጉዳት መጠናቸውን ምን ያክል እንደሆን መረጃ እንዳላት ቢታመንም በይፋ ግን ለመግለጽ ፈቃደኛ አይደለችም። የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይም ቢሆኑ ቁጥሩ ምን ያክል እንደሆነ ባይገልጹም ሀማስ ለረጅም ጊዜ መሰል መሳሪያዎችን በመጠቀም ጥቃቶችን የመሰንዘር አቅም እንዳለውገልጸዋል። ፍልስጤማውያን በአሁኑ ሰአት የተለያዩ አይነት ሚሳኤሎችን ጥቅም ላይ እያዋሉ ነው። ነገር ግን እስካሁን ድረስ በጣም በተራቀቀ መንገድ የተሰሩ መሳሪያዎችን መጠቀም አልቻሉም። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሚሳኤሎቹ ረጅም ርቀት እንዲጓዙና ከፍተኛ ፍንዳታ መፍጠር የሚችሉበት አሰራር ላይ ትኩረት አድርገዋል። ምንም እንኳን የእያንዳንዱ ሮኬትና ሚሳኤል አሰራር የተለያየና ግራ የሚያጋባ ቢሆንም ሃማስ በርካታ መሳሪያዎች ግን አሉት። ለምሳሌም የአጭር ርቀት ተምዘግዛጊው ‘ቃሳም’ አንዱ ሲሆን እስከ 10 ኪሎሜትር ድረስ ብቻ ነው መጓዝ የሚችለው። ‘ቁድስ 101’ የሚባለው 16 ኪሎሜትር ድረስ ተጉዞ ጉዳት ማድረስ የሚችል ሲሆን ‘ሴጂል 55’ የሚባለውደግሞ እስከ 55 ኪሎሜትሮች መጓዝ ይችላል። ነገር ግን ሀማስ ከዚህም በላይ ርቀት መጓዝ የሚችሉና ዘመናዊ ሚሳኤሎችን ይጠቀማል። ከነዚህ መካከል እስከ 75 ኪሎሜትር ድረስ መጓዝ የሚችለው ‘ኤም-75 አንደኛው ሲሆን ‘ፋጂር’ ደግሞ እስከ 100 ኪሎሜትሮች ተምዘግዝጎ መሄድ ይችላል። ሌላኛው ‘አር-160’ እስከ 120 ኪሎሜትር መጓዝ የሚችል ሲሆን ‘ኤም-320’ የሚባለው ደግሞ እስከ 200 ኪሎሜትር ድረስ ተጉዞ ጉዳት ማድረስ የሚችል ዘመናዊ መሳሪያ ነው። የእስራኤል መከላከያ እንደሚለው ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ ከ1 ሺ በላይ ሮኬቶች ከፍልስጤም ወደ እስራኤል የተተኮሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል ደግሞ 200 የሚሆኑት ያረፉት እዛው ጋዛ ውስጥ ነው። ምናልባትም እዛው ፍልስጤም ውስጥ የሚሰሩት ሮኬቶችና ሚሳኤሎች ውጤታማነታቸው ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። መከላከያ ኃይሉ አክሎም ከፍልስጤም በኩል ከተተኮሱት ሚሳኤሎች መካካል 90 በመቶ የሚሆኑት በእስራኤል ጸረ-ሚሳኤል መሳሪያዎች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል ብሏል። በአውሮፓውያኑ 2014 ላይ ባጋጠመ ተመሳሳይ ግጭት እስራኤል በወሰደችው እርምጃ እስከ 2251 ፍልስጤማውያን ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከነዚህ መካከል 1462 ንጹሀን ዜጎች ናቸው። በእስራኤል በኩል ደግሞ 67 ወታደሮች የተገዱ ሲሆን ስድስት ንጹሀን ዜጎችም ሕይወታቸው አልፏል።
41440927
https://www.bbc.com/amharic/41440927
የሳዑዲ ሴቶች አሁንም በርካታ ማድረግ የማይፈቅድላቸው ነገሮች አሉ
በምድራችን ሴቶች እንዳያሽከረክሩ በመከልከል ብቸኛዋ ሃገር የነበረችው ሳዑዲ አረቢያ ከንጉሱ በመጣ ትዕዛዝ ዕገዳው በዚህ ሳምንት እንዲነሳ እና ከሚመጣው ሰኔ ጀምሮ እንዲተገበር አድርጋለች። ምንም እንኳ ሃገሪቱ ይህን ውሳኔ ብታስተላልፍም አሁንም የሳዑዲ ሴቶች በርካታ ነገሮችን በራሳቸው ከማድረግ የታገዱ ናቸው።
የሳዑዲ ሴቶች ከታች የተጠቀሱትን ነገሮች ለመፈፀም የወንዶችን ይሁንታ መጠየቅ ይጠብቅባቸዋል። • ለፓስፖርት ማመልከት • ከሳዑዲ ውጭ ለመጓዝ • ትዳር ለመያዝ • የባንክ ሒሳብ ለመክፈት • ንግድ ለመጀመር • አስቸኳይ ያልሆነ ቀዶ-ጥገና. . . ከመመስረቷ ጀምሮ ሳዑዲ አረቢያ 'ዋሃቢዝም' በተባለው የእስለምና ሕግ የምትመራ ሃገር ናት። በሃገሪቱ እ.አ.አ. በ1979 ከተከሰተው ብጥብጥ በኋላ ሳዑዲ ይህን ሕግ አጥብቃ መተግበር ጀመራለች። በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሃገራት ሳዑዲ እኩልነት የማይትባት ሃገር ተብላ እንድትፈረጅም ሆኗል። በ2016 የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ባወጣው ደረጃ ከየመን እና ሶሪያ በመለጠቅ ሳዑዲን በመካከለኛው ምስራቅ እኩልነት ያልሰፈነባት ሃገር አድርጎ አስቀምጧታል። 'አንድ ወንድ እኩል ይሆናል ሁለት ሴት' ሳዑዲ የምታራምደው የሞግዚትነት ስርዓት እጅጉን ትችት እየደረሰበት ይገኛል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ 'ሂዩማን ራይትስ ዋች' ሳዑዲ "ሴቶቿን የራሳቸውን ውሳኔ መወሰን የማይችሉ ሕጋዊ አናሳዎች አድርጋለች" ሲል ይወቅሳል። እንዲህም ሆኖ ይህንን ጭቆና በመቃወም ድምፃቸውን ያሰሙ ሳዑዲያውያን ሴቶች ግን አልጠፉም። ሴቶች በግላጭ በወንድ ሳይታጀቡ በማያራመዱበት ሃገር ይህንን ማድረግ ቀላል እንዳልሆነ መገመት አያዳግትም። የሳዑዲ ፍትህ ስርዓት በይፋ ሴቶች ላይ መድልዎ ያሳያል። በዚህ ጉዳይ እስላማዊ ሕግን የሚከተሉ ሃገራት ስርዓቱ 'አንድ ወንድ እኩል ይሆናል ሁለት ሴት' ነው ሲሉ ተቺዎች ይወቅሳሉ። ለሳዑዲ ሴቶች ከትዳር አጋሮቻቸው ያፈሩትን ልጅ በፍቺ ወቅት የማሳደግ መብት ለማግኘትም እጅግ አዳጋች ነው። በተለይ ደግሞ ሴት ልጅ ከሆነች ዘጠኝ ዓመት ለወንዶች ሰባት ዓመት ካለፋቸው እና እናት የሌላ ሃገር ዜጋ ከሆነች የአሳዳጊነት መብት ማግኘት የማይታሰብ ነው። እንዲህም ሆኖ በሳዑዲ ከሴቶች ጋር በተያያዘ የሚያስገርሙ ነገሮች ልንሰማ እንችላለን። ከ2015 ጀምሮ ሴቶች መምረጥ እንዲችሉ ሆኗል። ማንኛውም የሳዑዲ ዜጋ፤ ሴትም ሆነ ወንድ፤ እስከ 15 ዓመታቸው ትምህርት የመማር ግዴታ አለባቸው። ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቁ ሴቶች ቁጥርም ከወንዶች የላቀ ነው። ከጠቅላላው የሳዑዲ የሥራ ሃይል 16 በመቶው ሴቶች ናቸው። ሆኖም በሥራ ቦታ ምን መልበስ እንዳለባቸው መወሰን ግን አይችሉም። 'አባያ' የተባለውን ልብስ በመልበስ የሳዑዲ ሴቶች መላ አካላቸውን መሸፈን አለባቸው። በሳዑዲ ለሴቶች ብቻ ተብለው የተዘጋጁ ቦታዎችን ማየት የተለመደ ነው። በመገበያያ ቦታዎች ለምሳሌ አባያ ለሚለብሱ ሴቶች ብቻ የተዘጋጁ ክፍሎች ውስጥ አባያ የማይለብሱ ሴቶች ከተገኙ በሃይማኖታዊ ፖሊሶች ተይዘው ሊታሰሩ ይችላሉ። የሳዑዲ ዜጋ ያልሆኑ ዜጎች አባያ መልበስ አይጠበቅባቸውም። ሙስሊም ካልሆኑም ራሳቸውን የሚሸፍን ነገር ባይደርቡም ችግር የለውም። በሌላው የዓለም ክፍልስ. . . ? ጥቂት የዓለማችን ሃገራት ሴቶችን በተመለከተ መሰል ስርዓቶችን በመዘርጋት ይታወቃሉ። ከዛም አለፍ ሲል አንዳንድ ሃገራት ሴቶች በጣም አስገራሚ ነገሮችን እንዳያደርጉ ያግዳሉ። እስቲ ጥቂቶቹን እንመልከት። ቻይና፦ የቻይና ትምህርት ሚኒስቴር ሴቶች ማዕድን ጥናት፣ የምድር ውስጥ መተላለፊያ ምህንድስና እንዲሁም የዳሰሳ ጥናት እንዲማሩ አይፈቀድም። ሚኒስትሩ መሰል የትምህርት ዓይነቶች ለሴት ክብር የላቸውም ሲሉ ይደመጣሉ። እስራኤል፦ በእስራኤል ባል ካልፈቀደ ሚስት የፍቺ ጥያቄ ማቅረብ አትችልም። ምክንያቱም ፍርድ ቤቶች በሃይማኖታዊ ስርዓት ስለሚተዳደሩ። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ጊዜ እንግሊዛዊው ዳኛ "ባልሽ በትዳር መቆየት ስለፈለገ ፍቺውን ውድቅ አድርገነዋል" ብሎ መበየኑ አይረሴ ነው። ሩስያ፦ አናፂነት፣ እሳት አደጋ ሰራተኛ መሆን፣ ባቡር ማሽከርከር እንዲሁም መርከብ መንዳት በሩስያ ለሴቶች የተፈቀዱ አይደሉም። ቀጣሪዎች ለሴቶች የሚሆን ምቹ ሁኔታ አመቻችተናል ካሉ በመሰል ድርጊቶች ሴቶችን ማሰማራት ይችላሉ። በኢንዶኔዥያ ከወንዶች ኋላ ተቀምጠው በሞተር ብስክሌት የሚሄዱ ሴቶች እግሮቻቸውን በአንድ በኩል ብቻ አድርገው መጓዝ አለባቸው። በሌላ አነጋገር እግሮቻቸውን በሁለቱም የሞተር ብስክሌቱ አቅጣጫ ዘርግተው መሄድ አይችሉም። በሱዳን ደግሞ ሱሪ አድርገው የተገኙ ሴቶች ለግርፊያ ቅጣት የተጋለጡ ናቸው።
news-53719600
https://www.bbc.com/amharic/news-53719600
ሊባኖስ፡ ለቤይሩቱ ፍንዳታ ምክንያት የሆነችው የምስጢራዊዋ አሮጌ መርከብ ታሪክ
ሰዎች የሸጎሌን ወይም የበቅሎ ቤት ፍንዳታን ያስባሉ። ይህ ነገሩን በእጅጉ ማቅለል ነው የሚሆነው። በቅሎ ቤት ሲፈነዳ አዳማ ድረስ ንቅናቄ አልተሰማም።
የሊባኖሱ ፍንዳታ ጎረቤት ቆጵሮስ ደሴት ድረስ ተሰምቷል። 240 ኪሎ ሜትር። አሁን ጥያቄው ፍንዳታው መሬት-አርድ ነበር ወይስ አልነበረም አይደለም። የፈነዳው ምንድነው? ያፈነዳውስ ማን ነው? ለምን አሁን? እንደሚፈነዳ የሚያውቁ ሰዎች ነበሩ? እነዚህን ወሳኝ ጥያቄዎች ለመመለስ የአንዲት ከርካሳ አሮጊት መርከብን ታሪክ ማወቅ ያስፈልጋል። ማክሰኞ ዕለት ሊባኖሳዊያን ከሥራ ወደ ቤት የሚገቡበት ሰዓት ተቃርቧል። መጀመርያ የሊባኖስ መሬት በስሱ ተነቃነቀ። ቀጥሎ ሸብረክ ነገር አለ፤ አሁንም በስሱ። ሰዎች እርስበርስ 'ምንድነው መሬቱ የተነቃነቀ አልመሰለህም?' ተባባሉ። "አይደለ? አዎ! እኔም…" 3-2-1….ቡምምምምምም! ሊባኖሳዊያን በሕይወት ዘመናቸው ሰምተውት የማያውቁት ፍንዳታ ተሰማ። ልብ በሉ፤ ሊባኖሳዊያን ለፍንዳታ አዲስ አይደሉም። ፍንዳታ ሰምተው የምን ስሪት ቦምብ እንደሆነ ሊነግሯችሁ የሚችሉ አዛውንቶች ያሉበት አገር ነው። ይህ ግን ይለያል። ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። አንድ ነዋሪ ለሲኤንኤን ቴሌቪዥን "እኔ 'የውማል-ቂያማ' መስሎኝ ነበር" ብሏል። 'የውመል-ቂያማ' የአረብኛ ቃል ነው፤ የምጽአት ቀን ማለት ነው። አቶሚክ ቦምብ ይሆን የፈነዳው? እስካሁን ባለው መረጃ አሞኒየም ናይትሬት ክምችት ነው የፈነዳው። ድምጹ ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ላይ ከተጣለው አውቶሚክ ቦምብ ላይተናነስ ይችላል። በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ እንደ ውሃ ፈሷል። ይህ ማለት ቦሌ ፍንዳታው ተከስቶ ቢሆን ሸጎሌ መኪና እየነዳ ያለ ሰው ቆስሏል ማለት ነው። ስለፍንዳታው ማን ያውቅ ነበር? ማንስ ተጠያቂ ነው? ለሚለው ጥያቄ ግን ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም ሆኗል። የከርካሳዋ አሮጌ መርከብ ታሪክ ግን ፍንጭ ይሰጣል። ማክሰኞ ማታ ማክሰኞ ዕለት በሊባኖስ ቤይሩት ነገሩ ሁሉ ሲተረማመስ ነው ያመሸው። ሰዎች ድምጽ እንደሰሙ እግራቸው ወደመራቸው ቦታ መሮጥ ጀመሩ። መኪና ያለው በመኪናው፣ እግር ያለው በእግሩ. . . እግሬ አውጪኝ. . . ያን ድምጽ ሰምቶ ማን ይቆማል? ማንም፤ ግን ወዴት እንደሚሸሽ እርግጠኛ አይደለም። ለምን እንደሚሸሽም የሚያውቅ የለም! ከማን እንደሚሸሽ የተረዳ የለም. . . መሮጥ፣ ማምለጥ. . . መራቅ. . . ፍንዳታው አንድ ጊዜ ወደ ላይ ከጎነ በኋላ የሆነ መስጊዶች አናት ላይ የሚቀመጥ ጉልላት ዓይነት ቅርጽ ሰራ። ከዚያም መንኮሮኮር ሲመነጠቅ ያለ የስብቀት እሳት ፈጠረ. . . ከዚያ ንዳድ. . . ሰማዩ በእሳት የሚያያዝ መሰለ። ከአፍታ በኋላ አውራ ጎዳናዎች በሰዎችና በመኪኖች ተሞሉ። አምቡላንስ ማለፊያ አጣ። ሰዎች አደጋው ወደደረሰት አቅጣጫ ሩጫ ጀመሩ። ልጆቻቸውን፣ ባሎቻቸውን ሚስቶቻቸውን ፍለጋ. . . ። አደጋው ደረሰበት ከተባለው አቅጣጫ ደግሞ ነፍስ ውጪ፣ ነፍስ ግቢ ላይ ያሉ ሰዎች እየሸሹ ነው። እንዴት ይተላለፉ። የቤይሩት ሰሜናዊ አውራ ጎዳና ተጨነቀ። በዚህ መሀል ታዲያ አንዳንድ ሰዎች በደም ባሕር የዋኙ ይመስል ድንገት ከፍርስራሽ ስር እያቃሰቱ ይወጣሉ። ጣዕረ ሞት መስለው የሚንፏቀቁም ነበሩ። ነገሩ ፊልም ይመስል ነበር። "ያ አላህ ልጄን!" እያሉ የሚያለቅሱ እናቶች. . . አንዳንዶቹ ልጆቻቸውን አግኝተዋቸዋል። አንዳንዶቹ ዛሬም ድረስ እየፈለጉ ነው። ይህ አሰቃቂ ፍንዳታ ዛሬ ማክሰኞ ሳምንት ሆነው። ብዙ ሊባኖሳዊያን በቃ ጠፍተው ቀርተዋል ማለት ነው። ምናልባት እሳት በልቷቸዋል. . . ። ምናልባት ፍንዳታው ሰማይ አድርሶ መልሶ ቀብሯቸዋል። ይህ ሁሉ ትርምስ በምን እንደተፈጠረ የሚያውቅ አልነበረም። የዓለም መገናኛ ብዙሃን ስለ ፍንዳታው በደቂቃዎች ውስጥ የቀጥታ ሥርጭት ማስተላልፍ ቢጀምሩም ፈነዳ ይላሉ እንጂ ምን እንደፈነዳ አያውቁም ነበር። እንኳን ያኔ፣ አሁንስ ማን እርግጡን አወቀ? በሞባይል የተቀረጹ ምስሎች 11፡54 ላይ የሎስአንጀለስ ታይምስ ዘጋቢ በትዊተር ሰሌዳው ላይ ከደቂቃዎች በፊት በስልኩ ያስቀረውን ቪዲዮ አጋራ። ነገሩ እሳት አደጋ ነው። እሳቱ የነካው ንጥረ ነገር ግን እጅግ አደገኛና ተቀጣጣይ ነበር። ርችት መጋዘኑ ውስጥ ሳይከማች አልቀረም። የመጀመሪያው ፍንዳታን ተከትሎ ከ35 ሰከንዶች በኋላ ሌላ ፍንዳታ ተከስቷል። የሁለተኛው ፍንዳታ ቀይ ፍም እሳትና ቡኒ ጭስ የያዘ ነበር። በመቶዎች ሞተው ሺህዎች የቆሰሉትም በዚህ በሁለተኛው ፍንዳታ ሳይሆን አይቀርም። የሁለተኛው ፍንዳታ ለቦምብ መቀመሚያነት የሚውለው የአሞኒየም ናይትሬት ክምችት ነበር ተብሎ ይገመታል። በዚያ የወደብ መጋዘን ውስጥ ወደ 3ሺህ ቶን አሞኒየም ናይትሬት ተከማችቶ ነበር። አሁንም ምን እንደፈነዳ? ምን እንደሆነ የሊባኖስ ርዕሰ ብሔርም ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን ዳያብ እርግጡን አያውቁም። ሁሉም ግን የአሮጌዋን መርከብ ታሪክ ያውቃሉ። ለቆራሌ ያልተሸጠችው ከርካሳ መርከብ። ለቆራሌው ያልተሸጠችው መርከብ ሮሰስ (Rhosus) ትባላለች፤ ግዙፍ መርከብ ናት። ማንም ግን አይፈልጋትም፣ ከቆራሌው በስተቀር። ለምን? እዚህ ፎቶ ላይ የሚታዩት ሁለቱ ሰዎች ይህን ፎቶ የተነሱት በፈረንጆቹ 2014 በጋ ላይ ነበር። ከጀርባቸው በነጭ ጆንያ የታጨቀው ነገር ይታያችኋል? የእርዳታ በቆሎ የሚመስለው? እሱ 3ሺህ ቶን የሚዝን አሞኒየም ናይትሬት ነው። በጣም አደገኛ ኬሚካል። በግማሽ ፈገግ ብሎ ስልክ እያወራ የምታዩት ሰውዬ ባለ ብዙ ሐሳብ ነው። የዚች ከርካሳ መርከብ ካፒቴን እሱ ነው። ከዩክሬን ነው የመጣው። በዚያን ጊዜ እሱም ሆነ የመርከቧ ሠራተኞች በቤይሩት ታግተው ነበር። ስልክ የሚደዋውለው ጨንቆት ነው። ለምን? ታሪኩን ትንሽ ወደ ኋላ ሸርተት ብለን ካልጀመርን ግልጽ አይሆንም። መርከቧ ከጆርጂያ ነው የተነሳቸው። ይቺ ጦሰኛ መርከብ በመስከረም 2013 ነበር ከጆርጂያ፣ ባቱሚ ወደብ የተነሳችው። ወዴት ለመሄድ ካላችሁ ወደ ሞዛምቢክ። ወደ አፍሪካዊቷ አገር ደግሞ ምን ልትሰራበት ነው የምትሄደው? ካላችሁ እቃ ተልካ። ይህን አሞኒየም ናይትሬት ጭነሽ ነይ ተብላ። መርከቧ ከርካሳ ናት ብለናል። ይህን በፎቶ አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል። አሮጊቷ መርከብ በ1986 ነው የተሠራችው። እድሳት ብሎ ነገር አታውቅም ታዲያ። ዓመታዊ ቦሎ የምታስለጥፈው አጭበርብራ ነው እንጂ ወላልቃለች። መኪና ብትሆን የምትነሳው በግፊ ነው ማለት ይቻላል። የመርከቢቱ ባለቤት ቆጵሮስ የሚኖር ሩሲያዊ ነጋዴ ነው። ስሙም ኢጎር ግሪኩሽኪን ይባላል። ይቺ ከርካሳ መርከብ ከጆርጂያ፣ ባቱሚ ወደብ የተነሳችው ምን ጭና ነው አልን? ቢቢሲ እጅ የገባ አንድ መርከብ ላይ የሚጫን እቃ ዝርዝር የሚጻፍበት ሰነድ (ቢል ኦፍ ሎዲንግ) እንደሚያስረዳው መርከቧ አሞኒየም ናይትሬት ነበር የተጫነባት። ኬሚካሉን የጫነው ድርጅት ሩስታቪ አዞት (Rustavi Azot LLC) የተባለ አሞኒየም ናይትሬት አቅራቢ ነው። ይህ ኩባንያ አሞኒየም ናይትሬቱን ለማን ነው የሚያቀርበው? ከተባለ ለኢንተርናሽናል ባንክ ኦፍ ሞዛምቢክ ነው። ተቀባይ ሆኖ የተመዘገበውም ይህ ባንክ ነው። ባንክ ደግሞ ከመቼ ወዲህ ነው ፈንጂ መቀመሚያ አሞኒየም ናይትሬት የሚያዘው? ደግሞስ ምን ይሠራለታል? ካላችሁ ነገሩ ወዲህ ነው። ዕቃ ወደ አንድ አገር በመርከብ ሲጫን ዋስ ሆነው የሚመዘገቡት ባንኮች ናቸው። ስለዚህ የሞዛምቢክ ባንክ ወኪል ሆኖ ዕቃውን የሚቀበልለት ድርጅት አንድ ትንሽ የሞዛምቢክ ፈንጂ አምራች ኩባንያ ነው። የዚህ ኩባንያ ሥራ ሌላ ሳይሆን ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን ማምረት ነው። ይህቺን ከርካሳ መርከብ ይሾፍሯት የነበሩት ካፒቴን ፕሮኮቼቭ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እርሳቸው መርከቧን የተረከቡት ከቱርክ ወደብ ነው። የመርከቧ ባለቤት ለመርከበኞቹ ደመወዝ መክፈል ስላልቻለ ሁሉም ጥለውት ሄደው ነበር። ካፒቴኑ አቴንስ መልህቃቸውን ጥለው አዳዲስ መርከበኞችን ሰብስበው ተቀመጡ። ጉዞ ለምን አይጀምሩም ታዲያ ወደ ሞዛምቢክ? ምክምያቱም የመርከቧ ባለቤት ብር አልነበረውም። ስዊዝ ካናል ሲደርስ ለወደብ የሚከፍለው ብር የለውም። "እንሂድ? ሞልታለች እኮ መርከቧ" ሲባል "ቆይ ብር የለኝም፤ ተረጋጉ" ይላል። ታዲያ ምን ይሻላል? ሲባል፣ "በቃ ቆይ ትንሽ እንታገስና መንገድ ላይ ሌላ ትርፍ የሚጫን ካርጎ እስክናገኝ እንጠብቅ።" በዚህ ሁኔታ አራት ወራት አለፉ። ከጆርጂያ ወደ ሞዛምቢክ ወደብ ልትጓዝ የነበረችው መርከብ በአቴንስ አራት ወር አንቀላፋች። እንዴት ወደ ቤይሩት ወደብ ሄደች ታዲያ? ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ 'ሽቀላ' ተገኘ ተባለ። የት? ሲባል፣ ቤይሩት ወደብ ላይ። አስቡት እንግዲህ፣ ወደ ሞዛምቢክ እቃ የጫነ መርከብ ሌላ ትርፍ ዕቃ ለመጫን አራት ወር ቆሞ ወደ ቤይሩት ሲያመራ። የመርከቧ ባለቤት ከቆጵሮስ ሆኖ ባስተላለፈው ትዕዛዝ ጉዞ ወደ ቤይሩት ሆነ። በቤይሩት ጥሩ የወደብ መክፈያ ገንዘብ ያስገባል የተባለው ካርጎ የታጨቀው የግንባታ መሣሪያዎችን ነበር። እሱን በከርካሳዋ መርከብ ጭኖ ወደ ሞዛምቢክ ለመሄድ ነው የሁሉም ሐሳብ። በስንት መከራ ቤይሩት ወደብ ደረሱ። ይህ ሁሉ የሚሆነው የዛሬ ስድስት ዓመት በኅዳር ወር ላይ ነው። "ቤይሩት ደርሰን ጭነቱን ስናየው ግዙፍ ነው። መርከቧ ላይ ስንጭነው ከርካሳዋ መርከብ መንጣጣት ጀመረች። ከአቅሟ በላይ ነበረ። ትርፍ ካርጎ ለመጫን የሚሆን ጫንቃ አልነበራትም" ይላሉ የመርከቧ ካፒቴን፤ ወደ ኋላ በትዝታ ተመልሰው። "በቃ እኔ ይሄ በፍጹም አይሆንም፤ ሁላችንም እናልቃለን። መርከቡ ካርጎውን አይችለውም አልኩኝ፤ ወሰንኩኝ" ይላሉ ካፒቴኑ። ለመርከቧ ባለቤት ተደወለ። እና ምን ይሻላል. . . ? ዝም አለ። በቃ የመርከቧ ባለቤት የወደኖርባት ቆጵሮስ ሄደን እሱኑ እናማክረው ይሉና መርከቧን ማንቀሳቀስ ሲጀምሩ የሊባኖስ ባለሥልጣናት መጥተው "ወዴት. . . ወዴት?" ይሏቸዋል። "አይ እዚህ ካርጎ ልንጭን መጥተን ካርጎው ትልቅ ሆነብንና ይቺ ከርካሳ መርከብ አልቻለችውም፤ እና ተውነው" ይላሉ። "እና የኮቴ ክፈሏ፤ የመርከብ ኮቴ፤ የገባችሁበትን ክፈሉ" በማለት የወደቧ ፖሊሶች አፈጠጡባቸው። "ምንም ሳንጭን? ካርጎውን አልጫንም እኮ. . . " ካፒቴኑ ተከራከሩ። የተራ አስከባሪና የረዳት ጭቅጭቅ ተጀመረ። ለካንስ መርከቧ ለሊባኖስ ያልከፈለችው መቶ ሺህ ዶላር እዳ ነበረባት። "እኛ ሠራተኞች ነን፤ ምን እናድርግ ብንላቸውም የቤይሩት ባለሥልጣናት አሻፈረኝ አሉ። እዳ አለባቸሁ ክፈሉ።" ነገሩ ሽማግሌ ገባበት መሰለኝ በኋላ ላይ አብዛኞቹ መርከበኞች ተለቀቁና ካፒቴኑን ጨምሮ አራት የመርከቢቷ ኢንጂነሮች ብቻ ታገቱ። በአጋጣሚ ሁሉም የዩክሬን ዜጎች ናቸው። የታገቱት ካፒቴን እንዴት ተለቀቁ? "ሌባኖሶች እኛን እንደ መያዣ አድርገው አገቱን፤ እዳ ካልተከፈለ አንለቃችሁም አሉ።" ካፒቴን ፕሮኮቼቭ ግራ ገባቸው። ቢጨንቃቸው ለቭላድሚር ፑቲን ደብዳቤ ጻፉ። መልስ የለም። በቤይሩት ለሩሲያ ቁንስላ ጉዳዩን አመለከቱ። ተሳለቁባቸው። "ፑቲን ልዩ ኃይል አስልኮ እንዲያስፈታህ ነው የምትፈልገው?" ካፒቴኑ ዩክሬናዊ ሆነው ለፑቲን ደብዳቤ የሚጽፉት፤ የመርከቧ ባለቤት ሩሲያዊ ስለሆነ ነው። ወይም ደግሞ ከፑቲን ሌላ ይህን ችግር የሚፈታ ጉልበተኛ የለም ብለው አስበውም ይሆናል። ነገሩ እየተካረረ መጥቶ የአራቱ ታጋቾች ጉዳይ የዓለም የትራንስፖርት ሠራተኞች ፌዴሬሽን ጋር ደረሰ። ጉዳዩን የመረመረችው የፌዴሬሽኑ አለቃ በመጋቢት 18/2014 በጻፈችው ደብዳቤ እንዳረጋገጠችው የመርከቧ ባለቤት ሩሲያዊው ኢጎር ግሪኮሽኪን እዳውን ለመክፈል ቤሳቤስቲን የለውም፤ ከስሯል። . . . ከዚህ በላይ ደግሞ አሳሳቢው ከርካሳዋ መርከብ የጫነችው አደገኛው አሞኒየም ናይትሬት የተባለው ኬሚካል ነው። የቤይሩት ወደብ ኃላፊዎች ይህ ንጥረ ነገር የተጫነውን ካርጎ ወደየትም እንዳይንቀሳቀስ አግደዋል። ይህ አደገኛ ነው" ስትል ጻፈች። ከአራት ወራት በኋላ ደግሞ ፍሊትሞን በተባለ አንድ የንግድ ጉዳዮች መጽሔት ላይ እንዲህ የሚል ዜና ወጣ። "ቦምብ እየተንሳፈፈባት ባለች መርከብ ውስጥ የታገቱ መርከበኞች" ይህ ሁሉ የሆነው ታዲያ የዛሬ ስድስት ዓመት በሐምሌ መጨረሻ ሳምነት ላይ ነበር። እንደሚፈነዳ ነግረናቸው ነበር… እነ ካፒቴን ፕሮኮቼቭ ከቤይሩት ራሳቸውን እንዴት ነጻ ያውጡ? አራት ሆነው ሰልፍ ቢወጡ፣ እገታውን ለሚዲያ ቢናገሩ. . . ጠብ የሚል ነገር የለም። ቢጨንቃቸው የመርከቢቱን ነዳጅ እየቀዱ መሸጥ ጀመሩ። ነዳጁን ቀሽበው በሚያገኙት ገንዘብ ጠበቃ ቀጠሩ። ከ10 ወራት የፍርድ ቤት ክርክር በኋላ ነጻ ወጡ። ጭንቀታችን የነበረው ከርካሳዋን መርከብ ውስጧ ውሃ እንዳይነካትና ደረቅ ሆና እንድትቆይ ማድረግ ነበር። ምክንያቱም የጫነችው አደገኛ ኬሚካል ነዋ። ይህ ግን የቤይሩት ሰዎችን በዚያን ጊዜ ብዙም አላስጨነቃቸውም። እነሱን ያስጨነቃቸው የመርከቢቱ እዳ አለመከፈሉ ብቻ ነው። "ነግረናቸው ነበር. . . "ይላሉ ካፒቴኑ። "ግን አልሰሙንም።" ካፒቴኑ ከቢቢሲዋ ጋዜጠኛ ጋር አደጋው በደረሰ ማግስት ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት "ቤይሩቶች ያን ጊዜ እዳችንን ክፈሉ ብለው እኛን ከሚያግቱን የመርከቧን እዳ ራሳቸው ከፍለው ያቺን መርከብ ከወደባቸው ቶሎ አስወጥተው የሰላም እንቅልፍ ቢተኙ ይሻላቸው ነበር።" ካፒቴን ፕሮኮቼቭ ፍርድ ቤት ነጻ ሲያደርጋቸው መርከቢቱን ቆላልፈው፣ የብረት መዝጊያውን ገጥመው ቁልፍ ለቤይሩት የወደብ ባለሥልጣናት አስረክበው ነው የሄዱት። ይህም በመስከረም 2014 ነው የሆነው። ያቺ ከርካሳ መርከብ ታዲያ ከዚያን ወዲያ ቆራሌውም ሳይወስዳት፣ ባለቤቷም የት ነሽ ሳይላት፣ መርከበኞቿም ረስተዋት ሰምጣ ቀረች። ዛሬም ድረስ የት እንዳለች የሚያውቅ የለም። ኬሚካሉ ለሊባኖስ ገበሬ ቢሰጥ ኖሮ ከአደጋው በኋላ ካፒቴን ከራዲዮ ሊበርቲ ጋር ባደረጉት ቆይታ የቤይሩት ባለሥልጣናት ለፍንዳታው ብቸኛዎቹ ተጠያቂዎች ናቸው ብለዋል። "አንድ መርከብ ባለቤት ከሌለው፣ በቃ የለውም ነው። ካርጎውን ማስወገድ ነበረባቸው፣ ወይም ደግሞ ለሊባኖስ ገበሬ ኬሚካሉን ቢያድሉት ኖሮ ይሄ አደጋ ባልደረሰ ነበር።" ለመርከበኞቹ ያኔ በታገቱ ጊዜ ጥብቅና ቆመውላቸው ከነበሩ ነገረ ፈጆች አንዱ እንደተናገረው፤ ደንበኞቻችን በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ካቀረብናቸው ምክንያቶች አንዱ የጫኑት ነገር ለሕይወታቸው አደጋ ሊፈጥር እንደሚችል በመጥቀስ ነው። ያን ጊዜ ለፍርድ ቤት ከጻፉት ማስታወሻ የተቀነጨበው እንዲህ ይላል. . . "መርከቡን ካርጎው አሞኒየም ናይትሬት ኬሚካል መጫናቸው ከግምት ውስጥ ገብቶ ይህ ኬሚካል ወደ ወደቡ መጋዘን እንዲገባ መርከቡም ሆነ ካርጎው በጨረታ አልያም በጥንቃቄ እንዲወገድ. . ." ዋናው ተጠያቂ ማነው? አሞኒየም ናይትሬት የናይትሮጂን ማዳበርያ ሆኖ በስፋት ለገበሬዎች አገልግሏል። ነገር ግን ይህ ኬሚካል ለሚቀበር ፈንጂ መሥሪያነት በስፋት ይውላል። ለዚያም ነው መጀመሪያ ፍንዳታውን በአንጻራዊ ቅርበት የሰሙ ኑክሌር ቦምብ የመሰላቸው። የማክሰኞው ፍንዳታ መጠነ ንዝረት ሲለካ እስከ 2 ኪሎ ቶን ይሆናል። ሂሮሺማና ናጋሳኪ ላይ አሜሪካ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ዋዜማ የጣለችው ቦምብ መጠነ-ንዝረቱ 12 ኪሎ ቶን ይሆናል። ኬሚካሉ ሲፈነዳ ቀይ ነገር በጭስ መልክ ሲተን ታይቷል። ቀዩ ትነት መርዛማው ናይትሮጂንዳይኦክሳይድ ነው። የፍንዳታው የንዝረት ፍጥነት ደግሞ ሱፐርሶኒክ ነው። 'ሱፐርሶኒክ' ፍጥነት ማለት ከድምጽ የሚፈጥን ማለት ነው። እንዴት ሊፈነዳ ቻለ? ማን አፈነዳው? ወደሚለው ወደተነሳንበት ነጥብ እንመለስ። አሞኒየም ናይትሬት ወትሮም መከማቸት ካለበት ከተማ ውስጥ አይቀመጥም። ሰው ከማይደርስበት ተራራ እንጂ። ሆኖም ግን በራሱ ጊዜ ፈንድቶ የሚጎን ኬሚካል ነው ማለት ደግሞ አይደለም። አንድ ነገር ሊያቀጣጥለው ይገባል። የቤይሩቱን ፍንዳታ ምን ቆሰቀሰው ለሚለው ግን አሁንም መልስ አልተገኘም። የቤይሩቱ ፍንዳታ ሁለት ምዕራፍ ነበረው። የዓይን እማኞች እንደሚሉት የመጀመሪያው ልክ እንደ ርችት ያለ ነበር። ሁለተኛው ግን ምድር-አርድ ነበር። የወደቡ የጉምሩክ ኃላፊ በድሪ ዳሃር በሊባኖስ መገናኛ ብዙሃን ላይ "በወደቡ መጋዘን ውስጥ የርችት ክምችት ነበረ ወይ?" ተብለው ሲጠየቁ፤ "ይመስለኛል" ብለዋል። ሌሎች ምንጮች ደግሞ በወደቡ ብረት እያቀለጡ መገጣጠሚያ የመሥራት ሂደት (ብየዳ) ሲከናወን ነበር ብለዋል። እሳቱ ምናልባት ከብደየዳ ፍንጣሪ መንጭቶ ይሆናል። የወደቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐሰን ኮራይተም ለሚዲያ እንዳመኑት "የአገሪቱ የደኅንነት ሰዎች የመጋዘኑን በር እንድንሰራው አዘውን፤ ሥራውን ቀትር ላይ ጨርሰን ሄድን፤ ከሰዓት ምን እንደተፈጠረ አላውቅም" ብለዋል። እሳቱ በምንም ይነሳ በምን ብቻ ወዲያውኑ 10 የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞች ወደ ቦታው አቅንተው ነበር። መጋዘን ቁጥር-12 ደርሰውም ነበር። ከእነዚህ መካከል ዘጠኙ ወንዶች ሲሆኑ አንዷ ሴት ነበረች። አሁን አስሩም የት እንዳሉ የሚያውቅ የለም። ከዚያ ፍንዳታ ይተርፋሉ ማለት ተአምር ነው መቼስ። የወደቡ ኃላፊዎች ቦምብ በመጋዘናቸው እንዳለ ካወቁ 6 ዓመት ሆኗቸዋል፤ ተራ ዜጎች ይህን የሰሙት ግን ማክሰኞ ማምሻውን ነው። አሁን እየወጡ ባሉ መረጃዎች የወደቡ ኃላፊዎች ከ2014 እስከ 2017 ድረስ አራት ደብዳቤዎችን ለአስቸኳይ ጉዳይ የዳኞች ሸንጎ ጽፈዋል። ደብዳቤዎቹ የሚሉት "ይሄ ኬሚካል ተቀጣጣይ ስለሆነ ወይ ውጭ አገር ወስደን እንሽጠው ወይ እናስወግደው፤ ፍቀዱልን" ነው። አንዳንድ ሊባኖሳዊያን እነዚህን ደብዳቤዎች ከተመለከቱ በኋላ የወደቡ ኃላፊዎች የሚችሉትን እንዳደረጉ ያስባሉ። ነገሩ ግን ውስብስብ ነው። ሪያድ ቆባሲስ በሊባኖስ ሙስና በማጋለጥ ስመጥር ጋዜጠኛ ነው። አደጋው ከደረሰ በኋላ በቴሌቪዥን ቀርቦ እንደተናገረው አራቱም ደብዳቤዎች ሕጋዊ የሥልጣን ተዋረድን ጠብቀው የተጻፉ አልነበሩም። ዳኞችም ደብዳቤዎቹ ሁሉንም መረጃ አሟልተው እንዲጻፉ በተደጋጋሚ ጠይቀው ነበር። የቤይሩት ወደብ ኃላፊዎች ግን የጻፉትን ደብዳቤ መልሰው ቀኑን እየቀያየሩ ይልኩታል። ሊባኖስ በሐይማኖት መስመር ነው ሥልጣን የምታደላድለው፤ በአንዳንድ አገሮች ሙሰኞች ወንጀል ሰርተው ወደ ጎሳቸው ጉያ እንደሚደበቁት በሊባኖስ ፖለቲከኞች ቶሎ ወደ ሐይማኖት ቀፏቸው ይሸሸጋሉ። የሊባኖስ ገንዘብ 80 ከመቶ ጋሽቧል። ሥራ የለም፤ ኑሮ እንደ ወደቡ ፍንዳታ ተተኩሷል። አንዳንድ ሊባኖሳዊያን ታዲያ ምርር ብሏቸዋል። እንኳንም ፈነዳን ያሉ "ጨካኞችም" አልጠፉም። "ምነው! ምነው! እንዲህ ይባላል?" ሲባሉ "ካልደፈረሰ አይጠራም" ብለው ይመልሳሉ። ከዚህ በላይ ምሬት ከየት ይመጣል?
46232661
https://www.bbc.com/amharic/46232661
በታላቁ ሩጫ ላይ ተሳትፈው ለሚያሸንፉ ተወዳዳሪዎች ላይ የአበረታች መድኃኒት ምርመራ ሊካሄድ ነው
እሁድ ሕዳር 9 2011 ዓ.ም በሚካሄደው የታላቁ ሩጫ ውድድር አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች የአበረታች መድሀኒት ምርመራ ሊካሄድባቸው መሆኑን የሩጫው አዘጋጆች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ አስታወቁ።
በሩጫው ላይ 44 ሺህ ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን 400 የሚሆኑት ከሌሎች ሀገራት የመጡ ሲሆን 5 አትሌቶች ደግሞ ኤርትራን በመወከል ይሳተፋሉ። • በሃሰተኛ ዜናዎች "የሞቱ" የኪነጥበብ ሰዎች • በካማሼ ዞን የመንግሥት ስራ ተቋርጧል • ኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተነሳ በ10 ሺህ ሜትርና በግማሽ ማራቶን ዝነኛ የሆነው አትሌት ዘረሰናይ ታደሰ ውድድሩ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ተገኝቷል። "ኢትዮጵያ በመምጣቴ በጣም ደስ ብሎኛል። የውድድሩ አዘጋጆችንም ስለጋበዙኝም አመሰግናለሁ" ብሏል። እኤአ የ2012 ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነው ዩጋንዳዊው ስቴፈን ኪፕሮቲች ውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ አትሌቶች መካከል አንዱ ነው። የኬኒያ፣ኡጋንዳ፣ ቦትስዋና ሀገራት የመጡ አትሌቶች በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ። የውድድሩ መነሻና መድረሻውን ያደረገው ስድስት ኪሎ መሆኑን በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። የታላቁ ሩጫ የቦርድ ሰብሳቢ የሆነው አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ውድድሩ በሰላማዊ መንገድ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ጥሪ አቅርቧል።
news-45722430
https://www.bbc.com/amharic/news-45722430
በጎሳ ታጣቂዎች እና በአልሸባብ ወታደሮች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ
ሶማሊያ ውስጥ በጎሳ ታጣቂዎች እና በአልሸባብ ወታደሮች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ። ግጭቱ የተፈጠረው የአልሸባብ እስላማዊ ቡድን ነዋሪዎች የገንዘብ መዋጮ እንዲያደርጉ እና ልጆቻቸውም ቡድኑን እንዲቀላቀሉ እንዲያደርጉ መጠየቁን ተከትሎ ነው።
አንዳንድ የሶማሊያ ቦታዎች አሁንም በአልሸባብ ቁጥጥር ውስጥ ናቸው። የጎሳ ታጣቂዎች የአልሸባብ ወታደሮችን ከሰፈራቸው ጠራርገው ለማስወጣት እያጣሩ መሆኑን፤ በትንሹ አራት የቡድኑን ወታደሮች እንደገደሉ ተናግረዋል። የጎሳ ታጣቂዎቹ መሪ በተኩስ ልውውጡ መገደሉም ተወስቷል። ታጣቂዎቹ የሶማሊያ መንግስት የሥራዊትና የትጥቅ ርዳታ እንዲያደርግላቸው የጠየቁ ሲሆን ለአሁኑ ግን በራሳቸው ሃቅም መታገልን መርጠዋል። • የአይኤስ ታጣቂዎች ኢትዮጵያዊያንን ገደሉ • ህገወጥ ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ ቻይናውያን ታሰሩ • በቤንሻንጉል ጉምዝ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተሰማ የተኩስ ልውወጡ የተጀመረው ያለፈው ሳምንት ማክተሚያ ላይ አልሸባብ ነዋሪዎችን ዓመታዊ ሃይማኖታዊ ክፍያ (ዛካት) እንዲከፍሉ እንዲሁም ልጆቻቸውን ለምልምል ወታደርነት አሳልፈው እንዲሰጡ ከጠየቁ በኋላ ነው። ይሄ ርምጃ በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ባሉ ስፍራዎች ያሉ ነዋሪዎች ከፍርሃት ባሻገር መልሰው ማጥቃት መጀመራቸውን የሚያሳይ አብነት ተደርጎ ተቆጥሯል። አልሸባብ የሶማሊያ መንግሥት በእጁ ሊያስገባቸው ያልቻላቸውን በደቡብ እና ማዕከላዊ ሶማሊያ የሚገኙ አንዳንድ ቦታዎችን የያዘ ሲሆን፣ ነዋሪዎች የቡድኑን ህግጋት እንዲያከብሩ ሲያስገድድም ባጅቷል።
44315974
https://www.bbc.com/amharic/44315974
ኡጋንዳ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ቀረጥ ልታስከፍል ነው
የኡጋንዳ ፓርላማ አጨቃጫቂውን አዲስ ህግ ትናንት ካፀደቀ በኋላ የበይነ-መረብ የመልዕክት መለዋወጫ የሆነውን የዋትስአፕ አገልግሎትን የሚጠቀሙ ዜጎች 200 ሽልንግ ዕለታዊ ቀረጥ እንዲከፍሉ ተወስኗል።
በዚህም ከእያንዳንዱ ተጠቃሚ በቀን 0.05 ዶላር ያህል የሚሰበሰብ ሲሆን አዲሱ ህግ ተግባራዊ የሚሆነው ከፈረንጆቹ ሐምሌ ወር ጀምሮ እንደሆነም ታውቋል። በተጨማሪም ሃገሪቱ በሞባይል ስልክ አማካይነት የሚተላለፍ ገንዘብም ላይ ቀረጥ ጥላለች። በዚህም መሰረት በእያንዳንዱ የገንዘብ ዝውውር ላይ ከአጠቃላዩ ገንዘብ አንድ በመቶ ቀረጥ እንዲከፈል ተወስኗል። የግል ጋዜጣ የሆነው ዴይሊ ሞኒተር እንደዘገበው ይህ ውሳኔ "ተደራራቢ ቀረጥ ነው" ሲሉ ቢያንስ ሦስት የፓርላማ አባላት አዲሱን ደንብ ተችተውታል። የፓርላማ አባላቱ እንዳሉት ዜጎች ዋትስአፕን የሚገለገሉት ቀድመው በሚገዙት የበይነ-መረብ አየር ሰዓት በመሆኑ ድጋሚ ቀረጥ እንዲከፍሉ ማድረግ የተጠቃሚዎችን መብት የሚጋፋ ነው። ሌላው ሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲ አባል ደግሞ "አንድ በመቶ ቀረጥ ለፓርላማ አባላት ትንሽ ገንዘብ ነው። ነገር ግን በቀን ከአንድ ዶላር በታች ለሚያገኙ ሰዎች ግን ከባድ ነው" ሲሉ ተቃውመውታል።
43028301
https://www.bbc.com/amharic/43028301
ዶክተር ሰገነት ቀለሙ፡ ከዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ሳይንቲስቶች መካከል አንዷ የሆኑት ኢትዮጵያዊት
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፍ የሆነው ዩ ኤን ውሜን ሰሞኑን የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ሰባት ሴት ተመራማሪዎችን ይፋ አድርጓል።
ከእነዚህ ሰባት ስመጥር ተመራማሪዎች መካከል ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ ተካትተውበታል። ዶ/ር ሰገነት የሥራና የሕይወት ተሞክሯቸውን ለቢቢሲ ከዚህ ቀደም አካፍለው ነበር። ተቀማጭነቱ ናይሮቢ - ኬንያ የሆነው የነፍሣት አካላት እና አካባቢ ጥናት ዓለምአቀፍ ማዕከል (ኢሲፔ) ዋና ዳይሬክተር ናት። ከክብር ዶክተሬት ጀምሮ በርካታ አለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘችው ዶክተር ሰገነት ስለህይወትና ሥራዋ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጋለች። ዶክተር ሰገነት ቀለሙ ተወልዳ ያደገችው ፍኖተ ሰላም ነው። ፍኖተ ሰላም ያኔ በጣም ትንሽ የገጠር መንደር እንደነበረች ታስታውሳለች። በፍኖተ ሰላም ያኔ መብራት አልነበረም፣ የቧንቧ ውሃ አልነበረም፣ ምንም ነገር አልነበረም፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አልነበረም። ስለዚህ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለመከታተል የ13 ዓመቷ ሰገነት ደብረ ማርቆስ ሔደች። እንደ ዶ/ር ሰገነት ገለፃ ደብረማርቆስ ያኔ መብራት የነበራት ቢሆንም ሌላው ነገሯ ከፍኖተ ሰላም ጋር ተመሳሳይ ነበር። • እሷ ማናት?፡ ፈቲያ መሐመድ ከዐረብ ሃገር ኑሮ ወደ ሚሊየነርነት ከቤተሰብ ማንም አብሯት አልነበረም "ወላጆቼ በእኔ ላይ እምነት ነበራቸው ። የትም ብሄድ ራሴን ተንከባክቤ እንደማስተዳደር ያውቃሉ" ስትል ቤተሰቦቿ በእርሷ ላይ ያላቸውን መተማመን ትናገራለች። እንጨት ለቅማ፣ እህል በእጇ ፈጭታ፣ ብቅል አብቅላ፣ ደረቆት ለጠላ አዘጋጅታ ቤተሰቦቿን እያገዘች ነው የተማረችው። "ያኔ የፊደል ዘር እለያለሁ ብሎ የትምህርት ቤት ደጃፍ የረገጠ ፈተና የሚሆንበት ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ እርሳስ ማሟላት ነው። ትምህርት ቤቱም ቢሆን በቁሰቁስ እና በመጻህፍት የተሟላ አይደለም" ትላለች ዶ/ር ሰገነት። ይህ ልምዷ ዛሬም በቢሮዋ እርሳስና እስክርቢቶ እንድትሰበስብ አድርጓታል። በልጅነቴ አስቸጋሪ ነበርኩ የምትለው ዶ/ር ሰገነት ዛፍ ላይ መውጣት፣ አህያ መጋለብ፣ ሴት አትሰራውም የተባለውን በሙሉ ለመስራት ትሞክር ነበር። በልጅነቷ ቤታቸው እህቶቿን ለማጨት ሽማግሌ ሲላክ ለእሷ የመጣ አንድም ጠያቂ ግን አልነበረም። ምክንያቱ ደግሞ ማህበረሰቡ ሴት ልጅ መሆን አለባት ከሚለው ውጭ መሆኗ ነበር። • እሷ ማናት?፡ ማየትና መስማት የተሳናት የመብት ተሟጋችና የሕግ ባለሞያዋ ሃበን ግርማ ስለዚህ እንደሌሎቹ በልጅነቷ ሳትዳር በትምህርቷ ገፋች። የዶ/ር ሰገነት ቤተሰቦች ማንበብ እና መፃፍ ባይችሉም በትምህርት ያምኑ ነበር። ስለዚህ ልጆቻቸውን ባጠቃላይ አስተምረዋል። "ሰባት እህት እና ወንድማማቾች ባጠቃላይ ነበርን ሁላችንም ትምህርት ቤት ሄደናል።" በርግጥ እህቶቿ ቀደም ብለው ያገቡ ቢሆንም ተምረዋል። ሕይወት በዩኒቨርስቲ ዶክተር ሰገነት ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ውጤት ስታመጣ ጎረቤቶቿ ጠላ፣ አረቄ፣ ምግብ እየያዙ መጥተው ቤተሰቦቿን 'እንኳን ደስ አላችሁ' እያሉ ቀኑን ሙሉ እንዳሳለፉ አትረሳውም። ከአንዲት ገጠር መንደር ወጥታ ሰፊ ወደሆነችው አዲስ አበባ ስትመጣ ግራ ተጋብታ ነበር። "መፀዳጃ ቤት እኛ ሜዳ ላይ ነው የለመድነው እዛ ሄደክ ቤት ውስጥ ነው፤ እንዴት ውሃ እንደሚለቀቅ አታውቅም። ሻወር ቤት ውስጥ ነው የምትታጠበው፤ ...ፍኖተ ሰላም ሆነን ወንዝ ውስጥ ሄደን ነው ገላችንን እንታጠብ ነበረው። ትልቅ ልዩነት ነው" ትላለች ስለነበረው ሁኔታ ስታስረዳ። ቴሌቪዥን እና ስልክ አጠቃቀምም ሌላ እንግዳ ነገር ነበር። ዶክተር ሰገነት የመጀመሪያ ዲግሪዋን ካጠናቀቀች በኋላ ለሁለተኛ ዲግሪዋ አሜሪካሄደች። ሁለተኛ ዲግሪዋን ከመጨረሷ በፊት ለሶስተኛ ዲግሪዋ የነፃ ትምህርት እድል አገኘች። ያንን ስትጨርስ ደግሞ ብዙ ቦታ የስራ በር ተከፈተላት። ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ኮርኔል ዩኒቨርስቲን መርጣ ሄደች። • እሷ ማናት፡ "አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ"- ሐና ተክሌ አባቴ የህክምና ዶክተር እንድሆን ነበር የሚፈልገው የምትለዋ ዶክተር ሰገነት "አለማያ ልገባ እርሻ ላጠና ስላቸው አንቺ በቃ ይሄ ውንብድናሽ አሁንም አለቀቀሽ ብሎ 'ገበሬ ለመሆን ዲግሪ ያስፈልግሻል?' አለኝ" ስትል ታስታውሳለች። በኋላ ግን ስለስራዋ እና ስኬቷ እየተረዱ ሲመጡ የኩራታቸው ምንጭ ሆነች። ፈተና ፈተና የሕይወታችን አንዱ ክፍል ነው ብላ የምታምነው ዶክተር ሰገነት ፈተናዎችን እንዴት እወጠቸዋለሁ ብሎ ማሰብ እንጂ ተስፋ መቁረጥን አስባው አታውቅም። ደቡብ አሜሪካ ኮሎምቢያ ከፍተኛ ተመራማሪ ሆና ለአንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት የምርምር ስራ ለመስራት በአለም ላይ ካሉ ተመራማሪዎች ጋር ተወዳድራ አለፈች። በኮሎምቢያ ጥቁር ሳይንቲስት እርሷ ብቻ ነበረች፤ እናም ጎብኚዎች ሲያዩዋት የፅዳት ሰራተኛ ወይንም ሌላ ዝቅተኛ ስራ ላይ የተሰማራች ይመስላቸው ነበር። "ዶ/ር ቀለሙን እንፈልጋለን ይላሉ እና ግቡ ካልኳቸው እሷን ጥሪልን ይላሉ።" ሌላው በኮሎምቢያ የምታስታውሰው ተቀጥራ እንደሄደች የተፈጠረውን ነው። • እሷ ማናት?፡ ከሒሳብ ጋር በአጋጣሚ ተዋደድን ስራ ስትጀምር 17 የቤተ-ሙከራው ሰዎች ነጮች ነበሩ። ትልቅ ብር ተመድቦ በርካታ ቁሳቁስ ተሟልቶ ነው ሃላፊነቱ የተሰጣት። ሴት፣ ጥቁር እንዲሁም ቀጫጫ መሆኗ ከተሰጣት ሃላፊነት ጋር ያልተዋጠለት አንድ ሰራተኛ ማስቸገር ጀመረ። በዛ ላይ ስፓኒሽኛ አለመቻሏ ፈተናውን የበለጠ አከበደው። የሙከራ ጊዜ የተሰጣት ደግሞ ለስድስት ወር ነው። በስድስት ወር ውስጥ መልክ መያዝ ያለበት ነገር መልክ ይዞ ውጤት ይጠበቃል። በአንድ እለት በስሯ የነበሩ ሰራተኞችን ሰብስባ በፀሀፊዋ አማካኝነት እያስተረጎመች ስታወያያቸውና የስራ አመራር ስትሰጥ ዳተኛ የሆነ አንድ ባለሙያ ያልተገባ ነገር ተናገራት። 'ባንሰራ ምን ታደርጊናለሽ?' በማለት የሀገሪቱን የሰራተኛ ህግ እና የቀድሞ አለቃቸውን ጠቅሶ እንቢተኝነቱን አሳየ። 'ከየት እንደመጣሽ እናውቃለን እኮ' ብሎ የኢትዮጵያን ረሃብ አነሳ። "እኔን አልፎ 80 ሚሊየን ሕዝብ ስለሰደበ ከስራ መባረሩን ነገርኩት።" "ከዛም ድርጅቱ በርካታ ገንዘብ ከፍሎ አሰናበተው። የእርሱ መሰናበት በመስሪያ ቤቱ ባጠቃለይ ተሰማ። ሌሎች ስራቸውን ሰጥ ለጥ ብለው እንዲሰሩ ምክንያት ሆነ። ያኔ ያንን ጠንካራ ውሳኔ መወሰኔ እኔንም ውጤታማ አደረገኝ" ትላለች። • እሷ ማናት፡ ከሊስትሮነት እስከ ከተማ አውቶቡስ አሽከርካሪነት በእንዲህ አይነት ጉዳዮች ተበሳጭታ እንደማታውቅ የምትናገረው ዶክተር ሰገነት ዋናው የረዳት ነገር በማንነቷ መኩራትን ተምራ ማደጓ እንደሆነ ትገልፃለች። "በትምህርት ቤትም በቤትም ቆንጆ ነን፤ ጎበዝ ነን፤ ማንም ሰው ሊያሸንፈን አይችልም፤ ቅኝ አልተገዛንም፤ የሚኒልክ ሰዎች ነን፤ እየተባልን መማራችን በማንነቴ እንድኮራ እና በትንንሽ ነገሮች እንዳልናወፅ ጠቅሞኛል።" ይህ የኢትዮጵያ ረሃብ ጉዳይ በስራ ቦታ ብቻም ሳይሆን በመንገድ ላይም ገጥሟት ያውቃል። ያኔ ግን " ኢትዮጵያ ረሃብተኛዋ አገር ሳትሆን ቡናን ለአለም ያስተዋወቀችው ናት እላቸዋለሁ። ኮሎምቢያውያን በቡናቸው ስለሚኮሩ ዝም ይላሉ" ዶክተር ሰገነት ቀለሙ የትም ሃገር ብትሆን የስራን እና የቤተሰብ ሚዛንን መጠበቅ ለሴት ልጅ ከባድ ነው የምትለው ዶ/ር ሰገነት "ለእኔ ጥሩነቱ ጥሩ ባል አለኝ እሱም ሳይንቲስት ነው። የቤቱን ስራ አብረን ነው የምንሰራው። እንደውም ብዙውን ይሰራ ነበረው እሱ ነው" በማለት ስለትዳር አጋሯ ለስኬቷ ስለሚያደርገው አስተዋፅኦ ትመሰክራለች። ጥናትና ምርምር በአሁኑ ወቅት ነፍሳት ላይ የምርምር ስራዋን እያካሄደች የምትገኘዋ ዶ/ር ሰገነት በአለም ላይ ከ1 ሚሊዮን በላይ የነፍሳት ዝርያ እንዳለ ታስረዳለች። አብዛኞቹ ነፍሳት ሰራተኛ ናቸው የምትለው ዶ/ር ሰገነት እነዚህን ነፍሳት ተጠቅሞ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት ለማሻሻል እየሰራች ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሐር ትልን ለማስለመድ የምትሰራዋ ዶ/ር ሰገነት በምግብም ረገድ ነፍሳት አማራጭ እንደሚሆኑ ታስባለች። በአፍሪካ፣ ኤስያ፣ ላቲን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ ሁለት ሚሊዮን ህዝብ ነፍሳት እንደሚበላ፤ እንደ ጀርመን ያሉ ያደጉ ሀገራትም ለሕዝባቸው ይህንኑ ለማስለመድ እየሰሩ መሆኑን ትጠቁማለች። አሁን የምትሰራበት መስሪያ ቤት ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱ ይህንን ማስተዋወቅ እና ምግብ ይዘቱንና ጥቅሙን መተንተን ነው። "የሚጎዱ እንዲሁም የሚጠቅሙ ነፍሳት አሉ። ሁለቱንም አመጣጥነን መኖር እንችላለን" ትላለች። • የዩኒቨርስቲ መምህርቷ ሞዴል፡ "ውበት ባመኑበት ነገር ጠንክሮ መሥራት ነው" ሌላው የምርምር ስራዋ የሚያተኩረው የከብት መኖ ላይ ነው። ደቡብ አሜሪካ እያለች ትሰራ የነበረው እዚህ ላይ ነው። ይህ የምርምር ስራዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ገበሬዎችን ተጠቃሚ ማድረጉንም ትናገራለች። "የበርካታ ገበሬ ሕይወት ተሻሽሏል። ከላሞቻቸው የሚያገኙት የወተት ምርት ጨምሯል ይህንንም በማየቴ ደስተኛ ነኝ" ትላለች። ይህንን የከብት መኖ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ሆኖ በአመት ለ20 ሺህ ገበሬ ለመድረስ እቅድ አላት። በቀሪው ህይወቴ ገበሬውን መርዳት እፈልጋለሁ የምትለው ዶ/ር ሰገነት በመስሪያ ቤቷ ከአፍሪካ እና ከአፍሪካ ውጭ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ለመስራት የሚመጡትን ተመራማሪዎች ማገዝ ማሳደግ ትፈልጋለች። የሕይወትሽ ደስታ ለዶክተር ሰገነት ጊዜዋን ማሳለፍ የሚያስደስታት ከቤሰተቧ ጋር ነው። "ባለቤቴ አይሰራም አሁን ታሟል። ... ደስ የሚለኝ እሱን መንከባከብ እና ልጄን ለስኬት ማብቃት ነው" ትላለች። ሌላ ደስ የሚላት ጎበዝ የሆኑ እና ዕድል ያጡ ሰዎችን ዕድል ሰጥቶ ማብቃት ነው። የራሷን ህይወት መለስ ብላ በማስታወስና ባትማር ምን ልትሆን እንደምትችል በማጤን ግለሰቦችም ሆኑ መንግስት ትምህርት ላይ ማተኮር አለበት ትላለች። በመጨረሻም ከተለያዩ አካላት ገንዘብ በማሰባሰብ የተወለደችበት አካባቢ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ብትከፍትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ብትሰራ ምኞቷ ነው።
54160718
https://www.bbc.com/amharic/54160718
እስራኤልና አረቦቹ ሰላም ማውረዳቸው ለአካባቢው የሚያመጣው 5 ስጋትና በረከት
የዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከእስራኤል አቻዎቹ ጋር ታሪካዊ የተባለ ስምምነት ይፈርማሉ፤ ዛሬ ማክሰኞ በዋይት ሐውስ፡፡
ቀጥለው ደግሞ ባሕሬኖች ተመሳሳይ ፊርማ ያኖራሉ፤ አሁንም ከእስራኤል ጋር፡፡ ይህ በአካባቢው አገራት ዘንድ የሚያመጣው ለውጥ ምንድነው፡፡ 5ቱን ብቻ እንደሚከተለው ቃኝተናል፡፡ 1. የጦር መሣሪያ ንግድ ይጦፋል ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ራሷን የአካባቢው አለቃ ማድረግ ትሻለች፡፡ ለዚህ ተፈሪነት የሚያበቃትን የጦር ጡንቻ ግን ገላ አላወጣችም፡፡ ጡንቻውን ለማፈርጠም የሚሆን ገንዘብ አላት፣ ቴክኖሎጂ የላትም፡፡ ኢማራቶች ቴክኖሎጂ ለመግዛት እንጂ ለመፍጠር አልበቁም፡፡ አሜሪካ ኢምራቶችን ከእስራኤል ጋር ስታፈራርም፣ ኢምሬቶች ጭራሽ እጃችን ይገባሉ ብለው አስበዋቸው የማያውቁ ውስብስብ የጦር መሣሪያዎችን ከእስራኤል መሸመት ያስችላቸዋል፡፡ ኤፍ-35 (F-35 )ተዋጊ ጄት፣ ኢኤ-18ጂ (EA-18G) የተራቀቁ የጦር መሣሪያዎችን የራሳቸው ለማድረግ ቋምጠዋል፡፡፡፡ ኢምራቶች በሊቢያና በየመን እጅግ የተራቀቁ የጦር መሣሪያዎችን ሞክረዋቸዋል፡፡ ሊቢያና የመን ግን እንኳን ተዋጊ ጄት ተወርዋሪ ቀስትም ለመመከት በሚችሉበት ቁመና ላይ አይደሉም፡፡ ውስብስብና ረቂቅ የጦር መሣሪያ የምትቋቋም አገር ኢራን ናት፡፡ ዋናዋ ጠላት አገርም ኢራን ናት፡፡ ለሷ የሚመጥን መሣሪያ ማግኘት የሚፈልጉት ደግሞ ከእስራኤል ነው፡፡ ኢምራቶችንና እስራኤልን የሚያፋቅራቸው የጋራ አጀንዳ እምብዛምም የላቸውም፡፡ የጋራ ጠላት ኢራን ግን ታቀራርባቸዋለች፡፡ የባህሬንም ጉዳይ ከዚህ ተለይቶ አይታይም፡፡ በ1969 ኢራን ባህሬንን አንቺ እኮ ሉአላዊት አገር ሳትሆኚ አንድ ግዛቴ ነሽ ብላት ታውቃለች፡፡ ይህ ለባህሬኖች እስከዛሬም እንቅልፍ የሚነሳ ጉዳይ ነው፡፡ ባሕሬንን የሚመሯት ሱኒዎች ናቸው፡፡ ከ60 ከመቶ በላይ ሕዝቧ ግን የሺአ ኢስላም ተከታይ ነው፡፡ የኢራን በአካባቢው ጎልቶ መውጣት ሁልጊዜም የባሕሬን ገዢዎችን እንቅልፍ ይነሳል፡፡ ገልፍ አገሮች ከኢራን ጋር ንግድ ለማጧጧፍ እንደቋመጡ ነው የኖሩት፡፡ በአካባቢው ብቻም ሳይሆን በዓለም ደረጃም ካየን ውስብስብ ቴክኖሎጂ ፈጠራ እስራኤልን የሚያህል የለም፡፡ ገንዘብ ገልፎች አላቸው፣ ቴክኖሎጂ እስራኤሎች አላቸው፡፡ ከዚህ በላይ ንግድ ከየት አለ? ከዚህ ሌላ እስራኤሎች በአረብ አገራት በረሃዎች ግመል እየጋለቡ "ሽር-ብትን" ማለት ይፈልጋሉ፡፡ ዱባይ መጥተው የነዳጅ ገንዘብ ምን ተአምር እንደሚሰራ ማየትና መዝናናት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ከጦር መሣሪያ ንግድ ሌላ ሁለቱን አገራት ሊያቀራርብ የሚችል የቱሪዝም ንግድ ነው፡፡ 2. እስራኤል ጎረቤት ጠላቶቿን ትቀንሳለች እስራኤል በአካባቢው ከጎረቤት የተኳረፈች፣ የተገለለች ሆኖ መታየትን አትፈልግም፡፡ ከተወለደች ጀምሮ በጠላት አኩራፊዎች ተከባ ነው የኖረችው፡፡ የቴክኖሎጂና ሳይንስ ምጥቀቷ ረድቷት እንጂ ጎረቤቶቿ ሰልቅጠው ሊጎርሷት በቻሉ ነበር፡፡ ለሕልውናዋም አደጋ ይሆን ነበር፡፡ የኢራን አንዳንድ መሪዎች አልፎ አልፎ እንደሚናገሩት ዓይነት ‹መካከለኛው ምሥራቅ ሰላም የሚሆነው እስራኤል ከዓለም ካርታ ስትጠፋ ነው›› የሚል እይታ ያላቸው በርከት ያሉ የአረብ አገራት ዜጎች አልጠፉም፡፡ ይህን በጠላት ተከቦ ጥሩ እንቅልፍ ለረዥም ዘመን መተኛት እንደማይቻል እስራኤሎች ገና ድሮ ነው ያወቁት፡፡ ገና አገር ሳይሆኑ፡፡ ገና በዛዮኒስት እንቅስቃሴ ጊዜ፡፡ ቤንያሚን ናታንያሁ ‹‹አይረን ዎል›› በሚባለውና በ1920ዎቹ በቪ አልሽላይም ለተጻፈው ፖሊሲ ይገዛሉ፡፡ ‹‹እኛና አረቦች›› የሚለው ይህ የውጭ ፖሊሲ ሰነድ እስራኤል በአረቦች ተከባ በእኩል ታፍራና ተከብራ መኖር የምትችለው በጦር ጥንካሬዋ ብቻ ነው ይላል፡፡ ‹‹አይረን ዎል›› ፖሊሲ እስራኤሎች እንደ ብረት የማይበገሩ ሲሆኑ ብቻ የአካባቢው አገራት እውቅና ለመስጠት እንደሚገደዱ የሚተነትን ሐሳብ ነው፡፡ እስራኤል በፈረጠመች ቁጥር አረቦች ልእልናዋን ከመቀበል የተሻለ አማራጭ አይኖራቸውም፡፡ እስራኤሎች በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ እንደ እብድ መታየት አይፈልጉም፡፡ መገለል አይፈልጉም፡፡ ታፍቶና ተከብሮ መኖርን ነው የሚፈልጉት፡፡ በዚህ ረገድ ከኃያሉ ጦርነት በኋላ ከዮርዳኖስና ከግብጽ ጋር ወዳጅነትን አሳክተዋል፡፡ ባህሬንና ኢምራቶችን ደግሞ አሁን አሳምነዋል፤ ዕድሜ ለወዳጃቸው ዶናልድ ትራምፕ፡፡ አሁን የሚቀሯቸው አገራት ብዙም አይደሉም፤ ሳኡዲ አረቢያ ደጅ ላይ ናት፤ ኦማንና ኳታር መከተላቸው አይቀርም ይላሉ ፖለቲካ አዋቂዎች፡፡ ሌላው የእስራኤሎች ደስታ ከጠላት ጋር የውዴታ ግዴታ እርቅ መፈጸማቸው ብቻ ሳይሆን አረቦቹን ከኢራኖች መነጠል መቻላቸው ነው፡፡ ናታንያሁ በምድር ላይ እንደ ኢራን ጠላት የለንም ብለው ያምናሉ፡፡ የኢራን ባለሥልጣናትን የሚያወዳድሯቸው ከነ ሂትለርና የናዚ ባለሥልጣናት ጋር መሆኑ የጠላትነት ስሜታቸው የት እንዳለ በራሱ የሚናገር ነው፡፡ 3. ትራምፕ ኖቤልን ሊመኙ ይችላሉ እነዚህ ይሆናሉ ተብለው ያልታሰቡ ስምምነቶች በሙሉ ያለ ዶናልድ ትራምፕ የሚታሰቡ አልነበሩም፡፡ ትራምፕ ዋናው ግባቸው ኢራንን ትንፋሽ ማሳጠር ነው፡፡ ቀጥሎ ለወዳጅ አገር እስራኤል ውለታ መዋል፡፡ በዚህም በኅዳር ወር ምርጫ ደጋፊዎቻቸውን ማኩራትና ዳግም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆን፡፡ ዶናልድ ትራምፕ አሁን በከፍተኛ ሩጫ ላይ ናቸው፡፡ ስምምነቶቹን እያጣደፏቸው ያሉትም ከምርጫው በፊት በዓለም መድረክ ሰላም ፈጣሪ ሆነው ለመታየት ካላቸው ፍላጎት ነው፡፡ ትራምፕ ለቤንያሚን ናታንያሁና ለእስራኤል መልካም ውለታ በዋሉ ቁጥር በአሜሪካ ክርስቲያን ኢቫንጀሊካኖች ዘንድ ይጨበጨብላቸዋል፡፡ የትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊዎችና አስተማማኝ ድምጽ ሰጪዎች ደግሞ ክርስቲያን ኢቫንጀሊካን ነጭ አሜሪካዊያን ናቸው፡፡ እነሱ ተደሰቱ ማለት ትራምፕ ዋይት ሐውስን ለሌላ አራት ዓመት ተከራዩት ማለት ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ አገራትን ዋሺንግተን እየጠሩ እያስታረቁ ነው፡፡ እጅግ የሚመኙትን ኖቤል ሽልማት ይዛችሁልኝ ኑ ማለታቸው የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ 4. ፍልስጥኤሞች ተክደዋል ኢምሬቶች ውስብስብ የዘመኑን የቢሊዮን ዶላር መሣሪያ ሲሸምቱ ፍልስጥኤሞች መድኃኒት በልመና፣ መብራት በፈረቃ ነው የሚያገኙት፡፡ ውሃ በቧንቧ ስትፈስላቸው የሚደሰቱበት ደረጃ ደርሰዋል፡፡ የድህነት አዘቅት እየነካካቸው ነው፡፡ ሆዳቸውን እያከኩም ቢሆን የኢምሬቶችን ‹‹የአብረሃም ስምምነት›› በፍልስጤም ልጆች ላይ የተፈጸመ ክህደት ሲሉ ጠርተውታል፡፡ የትኛውም አረብ አገር በፍልስጥኤሞች ነጻነት ዙርያ ላለመደራደር ቃል ተገባብቶ ነበር፡፡ ይህ ግን አሁን ያረጀ ያፈጀ ቃል ይመስላል፡፡ ቃል የሚያረጅ ከሆነ ማለት ነው፡፡ አሁን ፍልስጥኤሞች በሀብታም አረብ አገሮች ዘንድ የእርዳታ ስንዴ የሚሰፈርላቸው እንጂ የውጭ ፖሊሲ የሚታጠፍላቸው ሕዝቦች አልሆኑም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጋዛ ትልቅ እስር ቤት ሆናለች፡፡ ምሥራቅ እየሩሳሌምና ዌስት ባንክ በጉልበት የተያዙ የፍልስጤም ግዛቶች ናቸው፡፡ ዓለም እንኳን ይህን አይክድም፡፡ እስራኤልም ይህን አትክድም፡፡ የአቡዳቢው ልዑል ቢሊየነሩ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የኢምሬቶች ቅቡል መሪ ነው፡፡ እሱ ፍልስጤሞችን አልረሳችሁም ይላል፡፡ እንዴት ሲባል በዚህ ስምምነታችን ውስጥ እስራኤል ከእንግዲህ የዌስት ባንክን ሰፊ ክልል እንዳትጠቀልል ነግረናት እሺ ብላናለች ብሏል፡፡ ናታንያሁ የዓለም አቀፍ ግፊት ተጭኗቸው በዌስት ባንክ ጉዳይ ዝምታን ቢመርጡም በእርግጥ የዌስት ባንክን የእስራኤል ግዛት አካል አድርጎ ለመጠቅለል የታሰበው ነገር ቀርቷል ማለት ግን አይደለም፡፡ ለጊዜው ስለሱ ባናነሳስ የተባባሉ ይመስላል፡፡ ሳኡዲ የፍልስጥኤሞች ጠበቃ ሆና ኖራለች፡፡ አሁን ግን የበቃት ይመስላል፡፡ ኢምሬቶች ያለ ሳኡዲ እንዲህ ያለ ስምምነትን በፍልስጥኤሞች አናት ላይ እየደነሱ ሊፈጽሙ አይችሉም ነበር ይላሉ ተንታኞች፡፡ ይህ የሚያሳየው ሳኡዲ አረቢያ እንኳን ለፍልስጥኤሞች ጀርባዋን መስጠቷን ነው፡፡ የሳኡዲው ንጉሥ፣ ከዛሬ ነገ ይቺን ምድር ይሰናበታሉ የሚባሉት ንጉሥ ሳልማን ናቸው፡፡ የሁለቱ ቅዱስ የኢስላም ቦታዎች የበላይ ጠባቂ ናቸው፡፡ በድፍረትና በይፋ እስራኤልን ወዳጅ አገር ብለው የሚጠሩበት ዕድሜ ላይ አይደሉም፡፡ ወራሻቸው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ግን ስለ ፍልስጥኤሞች የሚያሳስበው ሰው አይመስልም፡፡ የአባቱን ሞት ተከትሎ ከእስራኤል ጋር ይሻረካል ይህ በጭራሽ አያጠራጥርም ይላሉ አካባቢውንና ፖለቲካውን በቅርብ የሚከታተሉ፡፡ 5. ኢራን አዲስ ራስ ምታት ጀምሯታል ኢምራቶችና ባሕሬን ይህን ስምምነት በዶናልድ ትራምፕ አሰናጅነት ለመፈጸም መስማማታቸው እንደተሰማ ከፍልስጤሞች ቀጥሎ ጨጓራቸው የተላጡት ዜጎች የሚገኙት በቴህራን ነበር፡፡ ‹‹የኢስላም ከሐዲዎች›› ብለዋቸዋል ሁለቱን አረብ አገራት፡፡ የ‹‹አብርሃም ስምምነት›› ተብሎ የሚጠራውን የኢምራቶችና የእስራኤል የዛሬ ስምምነት ሲፈረም ኢራኖች ሌላ ራስ ምታት ይጀምራቸዋል፡፡ የመጀመርያው ራስ ምታት የትራምፕ ጨካኝ ማዕቀብ ነው፡፡ ማይግሪን ቢባል ይቀላል፡፡ አላላውስ ብሏቸዋል፡፡ አሁን ደግሞ የስትራቴጂክ ራስ ምታት ጀምሯቸዋል፡፡ ይህ ከዛሬ ከሰዓት የሚጀምር ራስ ምታት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የኢራን ጠላቶቿ ቢያንስ ተከፋፍለው ነበር የቆሙት፤ አሁን በአንድ ሊቆሙ ነው፡፡ የአካባቢው የተገለለችው አገር እስራኤል ነበረች፤ ቀጣይዋ ግን ራሷ ኢራን ሆናለች፡፡
news-42479916
https://www.bbc.com/amharic/news-42479916
መረጋጋት ያልቻሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተማሪዎች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶች የትምህርት መቋረጥን በተደጋጋሚ ከማስከተላቸው በተጨማሪ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ሥጋት ፈጥረዋል።
በተለይም በተማሪዎች መካከል ማንነትን መሰረት አድርገው የሚነሱ ግጭቶችን ተከትሎ በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአካል ጉዳት ከመድረሱም በተጨማሪ ንብረትም ወድሟል። ይህ ክስተትም የመማር ማስተማር ሂደቱን ከማስተጓጎሉም ባሻገር ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች ለደህንነታቸው በመስጋት ወደየመጡበት ለመመለስ ሲገደዱ፤ ሌሎች ደግሞ ስጋት ዉስጥ ሆነው በየዩኒቨርሲቲዎቹ ባለተረጋጋ መንፈስ ይገኛሉ። መንግሥት ነገሩን ለማረጋጋት በትምህርት ተቋማቱ ውስጥ የፀጥታ ኃይሎችን ከማሰማራቱ በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲዎቹ የሰዓት እላፊ ገደብ ለመጣልም ተገዷል። በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎች ከመንግሥት ተጠሪዎች ጋር በመሆን ከተማሪዎች ጋር ውይይት እያደረጉ መሆናቸዉንና የተማሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን ነገር እያደረጉ መሆኑን ቢገልፁም ተማሪዎች፣ መምህራንምና ወላጆች አሁንም ስጋታቸው አልተቀረፈም። "ሰግተናል" በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች በየተቋሞቻቸው ባጋጠሙ ግጭቶች ሳቢያ ለደህንነታቸው በመስጋት የጀመሩትን ትምህርት አቋርጠው ወደየመጡበት አካባቢ ለመመለስ እንደተገደዱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፉት ሳምንታት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸዉ ሲከታተሉ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች በአዲስ አበባ ማደሪያ አጥተዉ ሲንገላቱ ቆይተው ብዙዎቹ ወደ ትዉልድ ቦታቸዉ መመለሳቸውን አብረዋቸው የነበሩ ተማሪዎች ተናግረዋል። እነዚህን ተማሪዎች የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ያናገሯቸዉ ቢሆንም ተገቢውን ምላሽ እንዳላገኙ ተማሪዎቹ ይናገራሉ። ከተማሪዎቹ መካከልም አንዱ "አሁን ባለዉ ሁኔታ ወደመጣንበት ዩኒቨርሲቲ ተመልሰን መሄድ ስለማንችል፤ በአካባቢያችን ወደ ሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲመድቡን ጠይቀን ነበር። ትምህርት ሚኒስቴር ግን አግባብ ያለው ምላሽ አልሰጠንም" ብሏል። "የዓመቱ ትምህርት ሲጀመር አንስቶ የተረጋጋ ሁኔታ አልነበረም" የሚለውና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪው ''ሁሌ አንድ የሚረብሽ ነገር አይታጣም። ወደ ግጭት ደረጃ ሲደርስ ደግሞ እራሴን ማትረፍ ስለነበረብኝ ከግቢ ወጥቻለዉ" ሲል ይናገራል። የተለያዩ ተማሪዎች እንደሚሉት በዩኒቨሲቲዎቹ የሚነሱት ግጭቶችና ጥቃቶች በቀላል አጋጣሚ የሚጀመሩ ቢሆንም እንኳን የሚያስከትሉት ጉዳት ቀላል የሚባል አይደለም። የሚደርሰውን ጉዳትም ለመከላከል ተቀናጅቶ በአንድነት የሚሰራ አካል ባለመኖሩ የከፋ ሁኔታ እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑንም ይጠቅሳሉ። እንዴት ተጀመረ? በምንማርባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሚከሰቱ ግጭቶችና ጥቃቶች ሳቢያ ደህንነት ተሰምቶን ትምህርታችንን መከታተል አልቻልንም ያሉ ተማሪዎች በሩን ያንኳኩበት የትምህርት ሚኒስቴር፤ ችግሩ የሃገሪቷን ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች የፈጠሩት እንጂ የህዝቡም ሆነ የተማሪዎቹ ችግር አይደለም ብሎ ያምናል። ነገር ግን ባጋጠሙት ነገሮች ምክንያት ተማሪዎቹን በየክልላቸዉ መመደብ ግን እንደማይቻል፤ ዩኒቨርሲቲዎችም የፌደራል መንግሥት ተቋማት እንጂ የክልሎች አይደሉም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በሁሉም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች፤ ጥያቄያቸዉን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማቅረብ ይገባቸዋል የሚሉት የትምህርት ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ሃረጓ ማሞ፤ አሁን ያለውን ችግር ለመፍታት ጉዳዩን በተለይ የሚከታተል ክፍል እንደተደራጀ ገልጸዋል። ከዚህ ባለፈ ግን ችግሩ የአስተሳሰብ ክፍተት የፈጠረዉ በመሆኑ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ የተማሪዎቹ ስሜት ከዚህ የተለየ ነዉ። መንግሥት የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ስለሚሰራቸዉ ሥራዎች እርግጠኞች ስላልሆኑ አሁንም ስጋታቸውን የሚቀርፍ እርምጃ አላየንም ባይ ናቸዉ። ከዚህ በተቃራኒ ሌሎች ደግሞ በየዩኒቨርስቲዎች የተፈጠሩ ግጭቶችን ለማብረድና ለማረጋጋት የተሰማሩ የፀጥታ ኃይሎች ስጋት እንደሆኑባቸው የሚናገሩ ተማሪዎችም አሉ። ካለመረጋጋቱ በኋላ ወደሚማርበት የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመለሰው ሌላኛው ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ተማሪ እንደሚለው እርሱና ጓደኞቹ ወደ ትምህርታቸው የተመለሱት ጥያቄያቸው ተመልሶ ሳይሆን በሁኔታዎች ተገደን ነው ይላል። ተማሪዎቹ አሁንም ቢሆን በግቢው የጦር መሳሪያ የያዙ ሃይሎች መገኘት ፍርሃት እንደፈጠረባቸው ይናገራሉ። ከሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ያናገርናቸው ተማሪዎችም ግቢዉ በጸጥታ ኃይሎች መወረሩን ይናገራሉ። ወደ ትምህርት የተመለሱ ቢሆንም ያለው ሁኔታ መረጋጋትን የሚያመለክት ስላልሆነ ትምህርታቸው ላይ ማተኮር በሚችሉበት የሥነ-ልቦና ሁኔታ ላይ አለመሆናቸውን የገለፁ ተማሪዎችም አሉ። የወላጆች ጭንቀት ልጆቻቸውን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለይም ግጭቶች ወደ ጎሉባቸው የላኩ ቤተሰቦች ከባድ ችግር ውስጥ እንደሚሆኑ አያጠራጥርም። የልጆቻቸው በተቋማቱ መገኘት ለደህንነታቸው እንዲሰጉ ያደርጋቸዋል። በሌላ በኩል ልጆቻቸውን ከቤት እንዲቀሩ ማድረግ ደግሞ በቀጣይ ትምህርታቸው እንዴት ይሆናል በማለት ያስጨንቃቸዋል። ሴት ልጃቸውን ከአዲስ አበባ ባለፈው ዓመት ወደ ዩኒቨርሰቲ የላኩት አቶ መኮንን በየጊዜው በፍርሃት የተዋጠ ድምጿንና የብሄር ግጭቶችን ወሬ መስማት ጭንቀት ውስጥ እንደከተታቸው ይናገራሉ። "አምኜ የላኳት አንድ ፍሬ ልጄ መማሩ ቀርቶ በሰላም ስለመኖር ስትጨነቅ ስሰማ በጣም ያሳዝነኛል፤ ሁሉ ቀርቶብኝ እንድትመለስልኝ ብፈልግም መግባት መውጣት አይቻልም ብላኝ ይኸው በጭንቀት ውስጥ ነኝ" ይላሉ። ልጆቻቸው ያሉበትን ሁኔታ በትክክል የሚያስረዳና መረጃ የሚሰጥ አካል አለመኖሩ ደግሞ ስጋታቸውን እንደጨመረው ይናገራሉ አቶ መኮንን። "ምነው እንደምንም ተቸግሬ እዚሁ ባስተምራትስ? በምን ክፉ ቀን ነው የላኳት እያልኩ እጸጸታለሁ፤ ብቻ ይሄ ቀን አልፎ በሰላም ትመለስልኝ እንጂ ዋስትና ሳላገኝ ልጄን አልካትም።'' ልጃቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት እያስተማሩ ያሉ ሌላኛው አባትም ነገሩ ለወላጆች እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን ይናገራሉ። የእርሳቸው ልጅ በሚማርበት የትምህርት ተቋም እስካሁን ምንም ዓይነት ግጭት ባለመፈጠሩ ልጃቸው ትምህርቱን እየተከታተለ ቢሆንም፤ የቅርብ ዘመዶችና ጎረቤቶቻቸው ልጆቻቸውን በተለያዩ ክልሎች ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እያስመጡ እንደሆነ ይናገራሉ። "የማውቃቸው ወላጆች ከተለያዩ ክልሎች ልጆቻቸውን እያስመጡ ነው። የእኔ ልጅ ባለበት ነገሮች ደህና ቢሆኑም የሌሎች ወላጆች ችግር በጣም ይሰማኛል "ይላሉ። ባለፍው ዓመት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የነበረውን አለመረጋጋት በማሰብ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ጨርሶ ልጆቻቸውን ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች ያልላኩ ቤተሰቦችንም ያውቃሉ። እነዚህ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን አዲስ አባባ ውስጥ በተለያዩ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለማስተማር የወሰኑ ናቸው። ነገሮች ተስተካክለው ዩኒቨርሲቲዎችም ወደ መደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት እንዲመለሱም "በዩኒቨርሲቲዎች የሚታየው ነገር በማህበረሰቡ ያለው ፖለቲካ ትኩሳት ነፀብራቅ ነው። ስለዚህ በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን ነገር ለመፍታት መጀመሪያ የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ ማግኘት አለበት" በማለት እኚህ አባት ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ። ''በዚህ ወቅት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ስለሚከሰቱ ነገሮች እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ዛሬ ሰላም ቢሆን ነገ ሌላ ይሆናል። ለዚህም ነው ከእኔ ርቆ የሚገኘው ልጄ ደህንነት ዘወትር የሚያሳስበኝ። መረጋጋት አልቻልኩም'' ይላሉ ሌላ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ እናት። ላለፉት ሳምንታት ካለበት ዩኒቨርሲቲ ተመልሶ ነገሮች እስኪረጋጉ ልጃቸው ከእርሳቸው ጋር እንዲቆይ እንዳደረጉ የሚናገሩት እናት በየዕለቱ የልጃቸውን ውሎ ይከታተላሉ። ''ምንም እንኳን ያለበት ቦታ እሩቅ ቢሆንም ዘወትር እደውልለታለሁ፤ ስልክ አልሰራ ሲለኝ በጣም እጨነቃለሁ''ይላሉ። እኚህ እናት ስለልጃቸው ደህንነት መጨነቃቸው የሚያበቃበትን ጊዜ ይናፍቃሉ፤ ''መንግሥት ሕዝቡ የሚለውን መስማት አለበት። ካልሆነ ግን ነገሮች ከቁጥጥር እየወጡ ነው። ወደከፋ አቅጣጫ እያመራን እንደሆነ መገመት አይከብድም'' በማለት ያክላሉ። የባህር ዳር ነዋሪ የሆኑትና ልጃቸው የሁለተኛ ዓመት የኢኮኖሚክስ ተማሪ እንደሆነች የሚናገሩት አቶ ይላቅም መፍትሄው በመንግሥት እጅ መሆኑን ጠቅሰው፤ እርሳቸውም የልጃቸው ደህንነት እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል። ''ይህ አሁን የምናየው ችግር ፖለቲካው ለዓመታት ሃገሪቱን የወሰደበት መንገድ ውጤት በመሆኑ አዝናለሁ። በቀደመው ዘመን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለጭቁኑ ሲጮሁና ሲንገላቱ ነበር የምናውቀው፤ አሁን ግን እርስ በርስ የጎሪጥ መተያየታቸው የተጓዝንበት መንገድን አደገኝነት የሚያሳይ ነው'' በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል። ልጃቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እያጠና ያለው አባትም የአቶ ይላቅን ሃሳብ ይጋራሉ። በዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ እየታየ ያለው ነገር ኢህአዴግ ላለፉት ዓመታት ያራመደው ፖለቲካ ውጤት እንደሆነ ያስረዳሉ። ተኽላይ ገብረንስአ የተሰኘው ወላጅ ከስድስተኛ ክፍል ጀምሮ ከገጠር አምጥቶ ያስተማረው ወንድሙ ይማርበት ከነበረው ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ኣቋርጦ እንዲመለስ አድርጓል። ትምህርቱ ቢቋረጥም ወንድሙ በህይወት በመመለሱ ብቻ ደስተኛ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሯል። "ጎበዝ ተማሪ ስለነበር ትምህርቱን ጨርሶ ታናናሾቹን ይጠቅማል የሚል እምነት ነበረኝ። ይሁን እንጂ አሁን ወንድሜ ሥነ-ልቦናው እጅግ ተጎድቷል። ከመጣ ጀምሮም ከቤት አይወጣም። ነገሩ ለታናሽ ወንደሞቹም ተስፋ አስቆራጭ ነው" ይላል። ትምህርት ጥያቄ ውስጥ ሲወድቅ እየተስተዋሉ ባሉት ክስተቶች ተጨንቀው የሚገኙት ተማሪዎችና ወላጆች ብቻ ሳይሆኑ ሁኔታው በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራንም ስጋት አላቸው። ስማቸውና የሚያስተምሩበት ተቋም እንዳይጠቀስ የጠየቁት መምህር እንደሚሉት አሁን እየታዩ ያሉት ግጭቶችና ጥቃቶች ድንገት የተከሰቱ ነገሮች አይደሉም። ''ትምህርት ከፖለቲካ ሥርዓቱ ጋር ተጣብቆ ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ ለዓመታት ሲዘራ የነበረው የጥላቻ ፖለቲካ ውጤት ነው'' ይላሉ። ይህ ደግሞ በተለያዩ አጋጣሚዎች በክፍል ውስጥ ሲያጋጥም እንደታዘቡ የሚናገሩት መምህር ''አሁን ገንፍሎ ይፋ የወጣው ሃገሪቱ ውስጥ ያለውን ፖለቲካዊ ውጥረት ተከትሎ ነው።'' በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አቶ እስራኤል ተሰማ ደግሞ ክስተቶቹ በትምህርት ሂደቱ ላይ ከባድ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ ይናገራሉ። በተማሪዎች ላይ የሚፈጠረው ስጋት የትምህርት ፍላጎታቸውንና ዝግጁነታቸውን ይቀንሰዋል። ትምህርት የተቋረጠባቸውን ጊዜያት ለማካካስ የሚደረገው ጥረትም በተማሪዎችና በመምህራን ውጤታማነት ላይ ተፅዕኖ አለው ይላሉ። አቶ እስራኤል ''እንዲህ አይነት የእቅድ መዛባቶች በትምህርት ተቋማቱ ፕሮግራም ላይ መስተጓጎልን ከማስከተል በተጨማሪ በትምህርት ጥራት ላይ ችግር ያስከትላሉ'' ይላሉ። ነገሮች ተረጋግተው ተማሪዎችም ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እየተመለሱ እንደሆነ ሲገለፅ የነበረ ቢሆንም የተለያዩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ከቀናት በፊት በመቱ እንዲሁም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት መቋረጡን ዘግበዋል።
news-47579853
https://www.bbc.com/amharic/news-47579853
"አሁን ፍርድ ቤቶቻችን ላይ በተፅዕኖ የሚሆን ምንም ነገር የለም" መዓዛ አሸናፊ
የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት የቤተሰብ፣ የወንጀል፣ የጡረታና የዜግነት ህጎችን በተመለከተ ሴቶችን አግላይ በመሆኑ ሊሻሻል ይገባል በሚሉ ዘመቻዎች፤ የሴቶችን መዋቅራዊ ጥያቄ ወደፊት በማምጣትና ሀገራዊ አጀንዳ እንዲሆን ብዙ የሰሩት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትነት ሆነው ከተሾሙ አምስት ወራትን አስቆጥረዋል። በነዚህ ወራት ምን አከናወኑ? ምን አይነት ተግዳሮቶችስ ገጠሟቸው? ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ቢቢሲ፦ ከአምስት ወር ገደማ በፊት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትነት ሆነው ሲሾሙ የገቧቸው የተለያዩ ቃል ኪዳኖች ነበሩ። በእነዚህ ወራት ምን ማሳካት ችለዋል? በዚህ ረገድስ ምን ያህል ተራምደዋል?
መዓዛ አሸናፊ፦ እንግዲህ እኔ ስሾም ያልኩት አንድ ነገር በፍትሕ ስርዓቱ ላይ የሕዝብ አመኔታን መመለስ የሚል ነው። ምክንያቱም በተለያየ ምክንያት በተለይም በፍርድ ቤት ስርዓት ላይ ሕዝቡ አመኔታው ቀንሶ ነበር። •የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? ፍርድ ቤት ስንል ዋናው ማዕከላዊ ሚና ያላቸው ዳኞች ናቸው፤ ከዳኞች ጋር እንዲሁም ደግሞ ከፍርድ ቤቱ ጋር ባለሞያዎች፥ ደጋፊ ሠራተኞች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች እያደረግን፥ ስልጠናዎችንም [እየሰጠን] ነው። ይህንን በተመለከተ ዋናው መልዕክታችን ዳኞች በነፃነት፥ ሕጉን ብቻ ማዕከል አድርገው እንዲሰሩ ነው። ይሄንን ምናልባት እናንተም ዳኞችን ብትጠይቁ የምታገኙት መልስ በከፍተኛ ሁኔታ መነቃቃት እና በራስ መተማመን ፈጥሮብናል፤ እና በራሳችን ተማምነን እንድንሰራ ይሄ የተሰጠን አቅጣጫ ይጠቅመናል [የሚል ነው።] ይሄ ትልቅ እርምጃ ይመስለኛል። በሁለተኛ ደረጃ የተጠራቀሙ ጉዳዮች እየተለዩ እልባት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው። በዚህ ረገድ በትጋት እየተሰራ ነው ያለው። የቆዩ መዝገቦች፥ የተከፈቱ መዝገቦች እያጠራን ነው ያለነው። ከዚያ ውጭ በዘላቂነት ለምንሰራቸው ደግሞ የማሻሻያ ለውጥ ስራ ጀምረናል። እርሱን ለመስራት ከፍተኛ ባለሞያዎች ያሉበት ጉባዔ ተቋቁሞ እነርሱም ደግሞ በሦስት ቡድን ራሳቸውን ከፍለው ስራ በመሰራት ላይ ነው የሚገኘው። •"እስካሁን ሙሉ የሰውነት ክፍል ማግኘት እንደተቸገርን ለቤተሰብ እያስረዳን ነው" አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ለምሳሌ የዚያ የቡድኑ ሥራ ውጤት በሚመጣው መጋቢት 23 ለሕዝቡ ይፋ ይሆናል። ዳኞችን የሚያስተዳድረው አካል፥ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ እንዲሻሻል፥ የማሻሻያ ኃሳብ ይዞ ቀርቧል ይሄ አማካሪ ቡድን። በዚያ ላይ ሕዝቡን እናወያያለን። ከፍርድ ቤት ውጭም እኛ የፍትሕ አካላት መሪ በመሆናችን፥ በዚያ ረገድም የፍትሕ ዘርፍ የማሻሻያ ለውጥ ፍኖተ ካርታ ረቂቁ ተዘጋጅቶ እርሱም ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ ዝግጅት ላይ ነን። •የተከሰከሰው አውሮፕላን የመረጃ ሳጥን ወደ ፈረንሳይ ተወሰደ ቢቢሲ፦ብዙ ተግዳሮቶች እንደሚሩ መገመት ይቻላል። እርስዎን ያጋጠሙዎት ዋነኞቹ ማነቆዎች ምንድን ነበሩ? መዓዛ አሸናፊ፦ዋና ችግር. . . . ዳኞችን የማጥራት (የቬቲንግ) ሥራ አስፈላጊ ነው፤ እንሰራለን። እስካሁን የነበሩት ዳኞች ሃቀኝነታቸው ምን ይመስላል? ችሎታቸው ምን ይመስላል? የሚለውን እንደገና የመፈተሽ ሥራ ይሰራል። ከዚያም በላይ ግን በጣም ከፍተኛ ችግር ሆኖ ያገኘሁት እኔ. . . ተቋሙ መሠረተ ልማት የለውም። ተረስቶ፥ በጣም ተዘንግቶ ወደ ጎን ተገፍቶ የቆየ ተቋም ነው ፍርድ ቤት። በዚያ ምክንያት ሰው ከሚገምተው በላይ ነው ችግር ያለው። ሌላው ቢቀር ዳኞች ችሎት የማስቻያ ቦታ የላቸውም፤ ዳኞች ቢሮ መቀመጫ የላቸውም። ከፍተኛ የግብዓት ችግር አለ። እና ከምንም በላይ እነዚህ የስርዓት እና የመሠረት ልማት ችግሮች እንደትልቅ ተግዳሮት ሆኖ ነው የማየው። ቢቢሲ፦በሹመትዎ ዋዜማ ምን ጠብቀው ነበር? ሥራው ውስጥ ከገቡ በኋላስ ምን አጋጠመዎት? ከጥበቃዎ የተለየ ሆኖ የፈተነዎት ጉዳይ አለ? መዓዛ አሸናፊ፦እኔ በከፍተኛ ጉጉት እና በከፍተኛ ቁርጠኛነት ነው ወደዚህ ቦታ ኃላፊነቱን ወስጄ የመጣሁት፤ በሄድኩበት ቦታ ሁሉ ለውጥ እንደማመጣ ስለማውቅ። እና አንድ ቦታ ኃላፊነት ሲሰጠኝ ደግሞ መቶ ፐርሰንት ሳይሆን መቶ ሃያ ፐርሰንት ነው ራሴን ሰጥቼ የምሠራው። በዚያ ጉዳይ ላይ ጥርጣሬ አልነበረኝም። ነገር ግን ምንድን ነው. . . ቅድም እንዳልኩት የፍርድ ቤት ችግሮችን [ለመፍታት] ተቋሙ ብዙ ግብዓቶችን ይጠይቃል፤ እየሰራን ነው። እኔ በዚህ በስድስት ወር ብዙ ሰርተናል ብየ ነው የማስበው። ምናልባት ጊዜ ስለሌለን ወደዝርዝሩ አልሄድኩም እንጅ ዝርዝሮቹ ብዙ ናቸው። የሚፈለጉት ነገሮች ብዙ ናቸው፤ ከመዝገብ ብዛት ጀምሮ፥ የመዋቅር ችግር፥ የዳኞች ችሎታ ጉዳይ፥ የደጋፊ ሠራተኞች አቅም ጉዳይ፥ የሥራ አሰላለፍ ጉዳይ.. . . ብዙ ጉዳዮች ናቸው። ነገር ግን የትኛው ነው ቶሎ ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው? የትኛው ላይ ብናተኩር ነው ቶሎ ለውጥ ማምጣት የምንችለው? የሚለውን ቅደም ተከተል አስቀምጠን እየሠራን ነው። እና በሚመጣው አንድ ዓመት ጥሩ ውጤት እና ለውጥ በፍርድ ቤቶቻችን ላይ እንደሚታይ ምንም ጥርጣሬ የለኝም። ከዚህ ጋር አያይዤ መናገር የምፈልገው፥ ከመንግስት ተቋማት ሌላ ብዙ አጋሮቻችን ሊረዱን ይፈልጋሉ። የመንግስት ተቋማት ነፃነታችንን በመጠበቅ፥ ነፃነታችንን በማክበር የሚያስደንቅ ዓይነት አካሄድ እያሳዩን ነው። ከዚህም ውጭ የልማት አጋሮች የእኛን ስራ ለማገዝ ይመጣሉ። ከተለያዩ ኤምባሲዎችና ከተለያየ ቦታ ሥራችንን ለመደገፍ ዝግጁ ናቸው። በተወሰነ ደረጃም ደግሞ እኛም ፕሮጄክት እየቀረፅን በማስገባት እና በማስፀደቅ፥ በእነርሱ ድጋፍ የማሻሻያ ለውጥ ሥራችንን ለማንቀሳቀስ ትብብር ጀምረናል። በጥቂቱ እንዳነሱልኝ ፍርድ ቤቶች ላይ ሲቀርብ የነበረው ትችት እና ነቀፌታ ከገለልተኛነት እና ከነፃነት ጋር የተገናኘ ነው። የፍርድ ቤቶችን ነፃነት በማስጠበቅ ረገድ ሥራ እየሠራችሁ እንደሆነ ነግረውኛል። ምን ያህል ተጉዛችኋል? ምን ያህልስ ይቀራችኋል? •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ የሚገርመው ነገር የፍርድ ቤት ነፃነት እኔ እዚህ ከተሾምኩ ቀን ጀምሮ የተጠበቀ ይመስለኛል። መምሰል ብቻ አይደለም። በተለያየ መንገድ. . . ኢመደበኛ የሆነ ውይይት ከዳኞች ጋር አደርጋለሁ፤ 'ከበላይ ኃላፊዎቻችን ይሄ መልዕክት መተላለፉ ለእኛ ትልቅ ጉልበት ሰጥቶናል፥ ሥራ ይበዛብናል፥ መዝገብ ይበዛብናል፥ ሁኔታዎቻችን አልተሟሉልንም፤ ነገር ግን አሁን፥ ከበላይ አመራሮቻችን ነፃ ሆናችሁ ሥሩ፥ ምንም ጣልቃ ገብነት የለም መባሉ ለእኛ እንደ ትልቅ ኃይል ተጠቅመንበታል። ሌሎች ነገሮች እንዲሟሉ እየጠበቅን ነው፤ ነፃነታችንን በተመለከተ ግን በጣም ውስጣዊ ነፃነት ይሰማናል" የሚል መልስ ነው ከዳኞች የማገኘው። ቢቢሲ፦በፍርድ ቤት ላይ የተያዙና ከፍተኛ አትኩሮትን የሳቡ ጉዳዮችን ላንሳልዎት፤ ከሙስና እና ከሰብዓዊ መብት ረገጣ ጋር በተያያዘ በታሰሩ ተጠርጣሪዎችን በተመለከተ። እነዚህን የፍርድ ቤት ጉዳዮች ፖለቲካዊ አንድምታ አላቸው የሚሉ ተችዎች አሉ። የቀጠሮዎችም መብዛት አብሮ ይተቻል። ለእነዚህ ትችቶች ምን ምላሽ አለዎት? ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፦የቀጠሮ መንዛዛት ሊኖር ይችላል። ሐኪም ስህተት ይሰራል። መሃንዲስ ስህትት ይሰራል። ዳኛም ስህተት ሊሠራ ይችላል። ነገር ግን ይሄ የቀጠሮ መራዘም ቢኖር፥ የተሳሳተ ውሳኔ ተሰጥቶብኛል የሚል ቡድን ሊኖር ይችላል፤ እነዚህ ሁሉ ግን [የሚሆኑት] ፍርድ ቤቱ ነፃነት ስለሌለው አይደለም። •"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ ይሄንን ነው ለሕዝቡ መልዕክት ማስተላለፍ የምፈልገው። የፍርድ ቤቶች፥ የዳኞች ነፃነት በምንም መልኩ ስለሚነካ አይደለም። በአሁኑ ሰዓት ፍርድ ቤቶቻችን ላይ በተፅዕኖ ምክንያት የሚሆን ምንም ነገር የለም። በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡም ግንዛቤ ሊኖረው የሚገባው ምንድን ነው. . . ተከራካሪ ሁለት ነው። እና የእነዚህ ሁለት ወገኖች ጥያቄ አቻችሎ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ ሁለቱን አያስደስትም። ስለዚህ አንደኛው ቅሬታውን ይዞ አንደኛው አደባባይ ይወጣል፤ ሊናገር ይችላል። ነገር ግን እንዲያውም ከማንኛውም ሙያ በላይ የዳኞች ሥራ ነው ሊስተካከል የሚችለው። ያም በምንድን ነው? በይግባኝ። ሁልጊዜም ይግባኝ አለ። ይግባኙ ለተከራካሪ ወገኖች እስከሰበር ድረስ ዕድል የሚሰጥ ነው። ስለዚህ ከነፃነት ጋር ወይ ከፖለቲካ ጋር በሚገናኝ ሁኔታ አይደለም። •"እናቱ ስታየኝ 'ልጄ ያሬድ ይመጣል' እያለች ታለቅስ ነበር"- በናይሮቢ የካፒቴኑ ጸጉር አስተካካይ ቢቢሲ፦አንዴ ላቋርጥዎትና. . . እነዚህ ጉዳዮች ግን ገና ውሳኔ አልተሰጠባቸውም። ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፦የጊዜ ቀጠሮን በተመለከተ እያንዳንዱ ዳኛ የራሱ አስተያየት አለው። አንድ መርማሪ ፖሊስ በጊዜ ምርምራ ጨርሶ፥ ለአቃቤ ሕግ ሰጥቶ፥ ፍርድ ካልተሰጠ ያ ጊዜ . . . ለምሳሌ በተባለው. . . የጉዳዩ ክብደት እና ቅለት ምን ይመስላል? ያ ሰው ቢለቀቅ ሊገኝ ይችላል ወይ? ብዙ ጉዳዮች አሉ እያንዳንዱ ዳኛ የሚመዝናቸው ከህጉ ውጭ። ያንን ከግምት ውስጥ አስገብቶ፥ 'የፖሊሶቻችን አቅም እኮ ደካማ ነው፤ የባለሞያዎቻችን ችሎታም ውሱን ነው፤ ስለዚህ ጊዜ ልስጣቸው' ብሎ አንዱ ዳኛ ተለዋጭ ቀጠሮ ሊሰጥ ይችላል። ባሉት የጊዜ ቀጠሮ ካላቀረቡ መለቀቅ አለበት ብሎ የሚወስንም ሊኖር ይችላል። ይሄ ከዳኛ ዳኛ የሚለይ ነው። ዞሮ ዞሮ እንዳልኩት ግን ይግባኝ ደግሞ መብት ስለሆነ፥ ይህ እየተስተካለለ ሊሄድ ይችላል። ስራችን ፍፁም ነው ለማለት አልችልም። ከዳኝነት ሥራ ውስብስብነት የተነሳ፥ ካለንበት የሽግግር ሁኔታ የተነሳ፥ ካለንበት አቅም የተነሳ አሁንም የምንፈልገው ቦታ ላይ አልደረስንም።
news-45175284
https://www.bbc.com/amharic/news-45175284
ኢትዮጵያ-በምስራቅ ሐረርጌ 37 ሰዎች ሲገደሉ 44 ሰዎች ጉዳት ደረሰባቸው
ትናንት ምስራቅ ሃረርጌ ውስጥ በምትገኘው ሙዩ ሙሉቄ በምትባል ወረዳ ውስጥ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ፈጽሞታል በተባለው ጥቃት የ37 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና 44 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የወረዳው የኮሙኑኬሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ትዝታ አባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል 36 የሚሆኑት ሰዎች በሙዩ ሙሉቄ ወረዳ ጤና ጣቢያ ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ እና የተቀሩት ደግሞ ወደ ጋራ ሙለታ ሆስፒታል እንደተወሰዱ የወረዳው የጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱላሂ አህመድ ካዎ ነግረውናል። • «ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር) • በምሥራቅ ወለጋ ሁለት ሰዎች ተገደሉ • በምሥራቅ ወለጋ የአራት ቀን ሬሳ አስነሳለሁ ብሎ መቃብር ያስቆፈረው 'ነብይ' በቁጥጥር ሥር ዋለ የወረዳዋ ነዋሪ የሆኑት እና በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸው በሙዩ ሙሉቄ ጤና ጣቢያ ውስጥ የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገኙት አቶ ሞሃመድ ሲራጅ ''በቤት ውስጥ ተቀምጠን ባለንበት ወቅት የሶማሌ ልዩ ፖሊሶች በር ገንጠለው ገቡብን። ባለቤቴን፣ ልጄንና የሁለት ዓመት የጎረቤት ልጅ አጠገቤ ገደሉ'' ሲሉ የደረሰባቸውን ጉዳት ተናግረዋል። ''ልቤ ላይ መቱኝ፣ ቀኝ ጆሮዬን ቆርጠው የሞትኩ መስሏቸው ትተውኝ ሄዱ'' ይላሉ አቶ ሞሃመድ። እሳቸው በጤና ጣቢያው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ፤ የልጃቸውና የባለቤታቸው አስክሬን መኖሪያ ቤታቸው እንዳለ ጨምረው ተናግረዋል። ሌላው በጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸው የሚገኙት የወረዳዋ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብዲ አብዱላሂ ''በትልልቅ የጦር መሳሪያዎች ተኩስ ከፈቱብን። እኔም እጄን ተመትቻለሁ'' ይላሉ። • "መንግሥት እየተባባሰ ካለው ብሔርን መሰረት ካደረገ ጥቃት ዜጎቹን ይጠብቅ" አምነስቲ • ሬሳን ከሞት አስነሳለሁ ያለው 'ነብይ' የሟች ቤተሰብን እንዴት አሳመነ? የልዩ ፖሊስ አባላቱ መኖሪያ ቤቶች እንዳጋዩ እና ንብረት ዘርፈው እንደሄዱ ጨምረው ተናግረዋል። ሙዩ ሙሉቄን ጨምሮ ቡርቃ እና ሮጌ በተባሉ ሶስት ወረዳዎች ውስጥ ተኩስ መከፈቱን ነግረውናል። ''ሴቶች፣ ዓይነ ስውር አዛውንቶች እና ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በጥቃቱ ተገድለዋል'' በማለት የደረሰውን ጉዳት የሙዬ ሙሉቄ ወረዳ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ትዝታ ነግረውናል። አክለውም ''ወረዳዎቹን የሚያገናኙ መንገዶች በልዩ ሃይሉ በመዘጋታችው እርዳታ መስጠት አልተቻለም፣ አስከሬን ያልተሰበሰበባቸው ቦታዎች ሁሉ አሉ'' ብለዋል። እንደ ወ/ሮ ትዝታ ከሆነ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ጥቃቱ ሲፈጸም በቅርብ ርቀት ላይ የነበረ ቢሆንም ጥቃቱን ግን ማስቆም አለመቻሉን ተናግረዋል። ይህን ጉዳይ በተመለከት የሶማሌ ክልል መንግሥትን አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
news-55465062
https://www.bbc.com/amharic/news-55465062
ትግራይ ፡ በኢትዮጵያ የትግራይ ግጭት የኤርትራ ሚና ምን ነበር?
በተለዋዋጩ የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ አንድ ሰሞን ከኢትዮጵያ ጋር ሰላማዊ ያልሆነ ግንኙነት የነበራቸው የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አጋር ሆነዋል። ከህወሓት ጋር በነበረው ግጭት ለፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
በቅርቡ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርበው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ኤርትራ፤ ከህወሓት ጥቃት በማፈግፈግ ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮችን አብልታለች፣ አልብሳለች እንዲሁም አስታጥቃለች ሲሉ ተናግረው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ እርዳታ የኢትዮጵያ ወታደር ተመልሶ 250 ሺህ ወታደሮች ያለውን ሕወሓት እንዲወጋ አስችሎታል ብለው ነበር። አሁን በፌዴራል መንግሥቱ ከሥልጣን የተወገደው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ትግል ላይ ሳለ በሽምቅ ውጊያ ይታወቅ ነበር። "የኤርትራ ሕዝብ ከእኛ ጎን የቆሙ ወገኖቻችን እንደሆኑ በአስቸጋሪ ወቅት አሳይተውናል" ብለው ነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ምንም እንኳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፕሬዝደንት ኢሳያሳ የኤርትራ ወታደሮች ለአስርታት በኢትዮጵያ መንግሥት የሥልጣን መንበር ላይ የቆውን ህወሓትን እንዲዋጉ ልከዋል የሚለውን ባያምኑም ኤርትራ ላደረገችው ድጋፍ የሰጡት እውቅና ግን ትልቅ ነበር። የኤርትራ ሆስፒታል ተደብድቧል ስለመባሉ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጎን አብረው እየተዋጉ ነው የሚለው ክስ መጀመሪያ የተሰማው ከህወሓት በኩል ነበር። አልፎም ግጭቱን ሸሽተው የተሰደዱ ነዋሪዎችና አገር ውስጥ እንዲሁም ከአገር ውጭ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ይህንን ደግመውት ነበር። "ኢሳያስ ወጣት ኤርትራዊያንን ወደ ትግራይ ልኮ ለሞት እየማገደ ነው። ጦርነቱ የአገሪቱን ምጣኔ ሃብት የበለጠ ይጎዳል። ነገር ግን ኢሳያስ ሥልጣን ላይ ለረዥም ጊዜ መቆየቱ አይቀሬ ነው። ሰዎች ለነፃነታቸው ሳይሆን ለመኖር እንዲፋለሙ እያደረገ ነው" ይላል አገሩን ጥሎ የተሰደደው ኤርትራዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጳውሎስ ተስፋጊዮርጊስ። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ኤርትራ በትግራይ ክልል በሚደረግ ውጊያ ስለመሳተፏ የሚያስረግጥ "አስተማማኝ መረጃ" አለ ብሎ "ስጋቱን" ገልፆ ነበር። ነገር ግን ሁለቱም መንግሥታት ይህንን ያስተባብላሉ። የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ "ይህ ፕሮፖጋንዳ" ነው ይላሉ። የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በፈረንጆቹ 2018 ኢትዮጵያ የገባችውን ታሪካዊ ስምምነት ተከትሎ ለኤርትራ ከሰጠችው መሬት ላይ ውጭ ምንም ዓይነት ኤርትራዊያን ወታደሮች ትግራይ ውስጥ የሉም ሲሉ አረጋግጠውልኛል ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ከኤርትራ ጋር የደረሱት ስምምነት ለ20 ዓመታት "ጦርነትም-ሰላምም የራቀው" የተባለው ግንኙነት ማብቂያ ሆኗል። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ቢያንስ 100 ሺህ ያክል ሰዎች ሞተዋል። ይህ ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። የትግራይ ክልል የቀድሞ አስተዳዳሪ ህወሓትና በፌዴራል መንግሥቱ መካከል ባለፈው ጥቅምት ወር ማብቂያ ጦርነቱ እስከሚጀመርበት ጊዜ ድረስ ግን ኢትዮጵያ ጦርነት ያስከተለውን መሬት ለኤርትራ አሳልፋ አልሰጠችም። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር መገናኛ ብዙሃን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶችና የሰብዓዊ መብት ተቋማት ወደ ትግራይ ክልል መግባት እንዳይችሉ ከባድ አድርጎታል። ይህም ገለልተኛ አካላት በሁሉም ወገን ተፈፀሙ የተባሉ ጥፋቶችን ገብተው እንዳያጣሩ አድርጓል። ተፈፅመዋል ከተባሉ ጥፋቶች መካከል ከኤርትራ በኩል በተፈጸመ የከባድ መሣሪያ ድብደባ የአንድ ሆስፒታል መመታት አንዱ ነው። ኤርትራ ተደብድቧል ስለተባለው ሆስፒታል ምንም ዓይነት አስተያየት አልሰጠችም። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ተቋም ግን በዚህ አይስማማም። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ በትግራይ ክልል አንድም ሰላማዊ ዜጋ አልሞተም ብሏል። "ይህ ጦርነት የተካሄደው እጅግ በጣም ድቅድቅ በሆነ ጨለማ ውስጥ ነው። ጦርነቱ ስላስከተለው ጉዳት ማንም ምንም አያውቅም" ይላሉ ነዋሪነታቸው ኬንያ የሆነው የአፍሪካ ቀንድ ተንታኝ ራሺድ አብዲ። በግጭቱ ከተጎዱ ስፍራዎች አንዱ ኤርትራዊያን ወታደሮች ንብረት ዘርፈዋል ስለመባሉ ተቀማጭነቱ አሜሪካ የሆነው ተንታኝ አሌክስ ደ ዋል የተባበሩት መንግሥታት ምንጮች ነገሩኝ እንደሚለው ከሆነ አምስት ሚሊየን ሕዝብ የሚኖርባትና ከኢትዮጵያ ክልሎች ደሃ የሆነችው "ትግራይ ክልል ውስጥ በርካታ ሰዎች ተፈናቅዋል።" "ይህ የሚቀጥል ከሆነ በክልሉ የጅምላ ረሃብ ሊከሰት ይችላል። ሕዝቡ ግፍ ስለተፈፀመበት ቁጣ ሊቀስቀስ ይችላል" ይላል ደ ዋል። ደ ዋል፤ የሐይማኖት አባቶችን ጨምሮ ታማኝ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ እንደሚለው የኤርትራ ወታደሮች ቤት ንብረት በመዝረፍ ተሳትፈዋል። "እንደምንሰማው ከሆነ በርና የመታጠቢያ ቤት ዕቃዎችን ሳይቀር ዘርፈዋል" ይላል ደ ዋል። ሌሎች ኤርትራዊያን እንደሚሉት ዘመዶቻቸውን ጨምሮ ኤርትራዊያን ወደታሮች ከህወሓት ኃይሎች ጋር በርካታ አምባዎች ላይ ጦርነት ገጥመዋል። አክለው አንዳንዶቹ ኤርትራዊያን ወታደሮች የኢትዮጵያ ወታደር መለዮ ለብሰው ነው ሲዋጉ የነበረው ይላሉ። ኤርትራ፤ ትግራይ ክልል ውስጥ ምንም ዓይነት ወታደሮች የሉኝም ትላለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም "እኛ አልተሳተፍንም" ይላሉ። አሁን ከአገር ውጭ በስደት የሚኖሩት የቀድሞው የኤርትራ ዲፕሎማት አብደላ አደም እንደሚሉት እሳቸው በአካላ የሚያውቋቸው ወታደሮች ሳይቀሩ በነበረው ግጭት ቆስለዋል። በደቡብ ኤርትራ የምትገኘው ሰንአፈ ውስጥ ካለ ሆስፒታል ቢቢሲ መስማት እንደቻለው ኤርትራዊያንና ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች ቆስለው ሲታከሙ ነበር። 'ኢሳያስ ህወሓት እንዲከስም ይፈልጋሉ' ከኤርትራ የተገኙ ምንጮች አንደሚሉት ከሆነ በማዕከላዊ ኤርትራ ሃጋዝ ከተማ የኢትዮጵያን ወታደሮች ተሰባስበው ነበር፤ የቆሰሉ ወታደሮች ደግሞ በአቅራቢያው በሚገኘው ጊላስ ወታደራዊ ሆስፒታል ሲታከሙ ነበር። ዩናይትድ ኪንግደም የሚኖረው ኤርትራዊው ምሁር ጋይም ክብረዓብ ኢሳያስ ወታደሮቻቸውን ወደ ትግራይ የላኩት "ህወሓት እንዲጠፋ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ነው" ይላል። ይህ ከ1990 የኢትየ-ኤርትራ ጦርነት ጀምሮ አንስቶ የኤርትራው መሪ ዋነኛ አላማ ሆኖ ቆይቷል ይላል ጋይም። ኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት በገጠሙ ጊዜ ህወሓት የትግራይ ክልልን ከማስተዳደር ባለፈው የኢትዮጵያ መንግሥት የሚመራው ግንባር የበላይ ነበር። "ከ1990-92 (እአአ) በነበረው ጦርነት ህወሓት ባድመን በመውሰድ የኤርትራውን መሪ አሳፍሯል። ምንም እንኳ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት መሬቱን ለኤርትራ ቢወስንም ህወሓት ግን ለ18 ዓመታት ወታደሮቹን ከሥፍራው ለማስወጣት ፈቃደኛ አልነበረም ነበር።" "ፕሬዝደንቱ [ኢሳያስ] ይህን ዕድል ለማግኘት ዓመታት ጠብቀዋል። ነገር ግን ህወሓት የፕሬዝደንቱን ትዕግስ ንቆት ነበር" ሲል ይተነትናል ምሁሩ። ከሁለት ዓመት በፊት የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር ሲከፈት የነበረው ደስታ ከሰላም ወደ ግጭት የኢሳያስ ደጋፊዎች የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ ክልል አልገቡም ይላሉ። ነገር ግን ባድመና አካባቢዋን በመያዝ የኤርትራን መሬት መልሰዋል ባይ ናቸው። በዚህ ሐሳብ ጳውሎስ አይስማማም። "ባድመ በኤርትራ እጅ ገብታ ነበር። ነገር ግን ይህ ለሕዝብ ይፋ አልተደረገም። ምክንያቱም የኢሳያስ ዋና ዓላማ ይህ አልነበረም። የእሱ ዓላማ የነበረው ህወሓትን ማድቀቅ ነው።" "ዐብይ ሰላም መላሽና ለውጥ አምጪ ሆኖ ነው ሥልጣን የያዘው። ነገር ግን ህወሓትን መበቀል ለሚለው ዓላማ እጁን ሰጠ። ይህ ደግሞ ኢሳያስ የሚፈልገው ነው" ይላል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከህወሓት ጋር ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሞክረናል ይላሉ። ነገር ግን ወደ ግጭት ለመግባት የተገደድነው ህወሓት የሰሜን ዕዝን ተቆጣጥሮ መንግሥት ለመገልበጥ በመሞከሩ እንደሆነ ያክላሉ። ምንም እንኳ ኢሳያስ ለእርዳታ እጃቸውን ቢዘረጉም የኤርትራ መገናኛ ብዙሃን ግን ስለ ግጭቱ አንድም ዘገባ አልሠሩም። ሌላው ቀርቶ ህወሓት ግጭቱ የተጀመረ ሰሞን ወደ አሥመራ ስላወሰነጨፋቸው ሚሳዔሎችና ስለተሰማው ከባድ ፍንዳታ ምንም ነገር አልተባለም። "የኤርትራ ቲቪ ሶሪያ ውስጥ ስለፈነዱ ቦምቦች ዜና እየሠራ አሥመራ ላይ ሚሳዔል ሲተኮስ ምንም አላለም" ይላሉ የቀድሞ የኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣን ዳዊት ፍሰሐዬ። የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ መስቀል በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት "የህወሓትን የመጨረሻና ተገማች ነገር ግን እርባና ቢስ እርምጃ ማስተጋባት ምንም ጥቅም የለውም" ብለው ነበር። ታፍነዋል ስተለባሉ ስደተኞች ኤርትራ ውስጥ የበይነ መረብ አገልግሎት እጅግ የተገደበ ነው። አልፎም ምንም ዓይነት ነፃ ሚድያም ሆነ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የለም። ኤርትራ ውስጥ ከ20 ዓመታት በፊት ለእሥር የተዳረጉት 11 ፖለቲከኞችና 17 ጋዜጠኞች የት እንዳሉ የሚታወቅ ነገር የለም። በብሔራዊ አገልግሎት አማካይነት በወታደራዊ ስልጠና መውሰድ ግዳጅ የሆነባት ኤርትራ ለዜጎቿ በቂ የሆነ የሥራ ዕድል የላትም። ይህም በርካታ ወጣቶች አገር ጥለው እንዲወጡ አድርጓል። በትግራይ ክልል ብቻ 100 ሺህ ያህል ኤርትራዊያን ስደተኞች በተባበሩት መንግሥታት መጠለያዎች ውስጥ ይኖራሉ። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ወኪል፤ ስደተኞች ስለመገደላቸው እንዲሁም ታፍነው በአንድ ፓርቲ ወደ ምትተዳደረው አገር ስለመወሰዳቸው "ከብዙ ታማኝ ምንጮች አረጋግጫለሁ" ይላል። ድርጅቱ ስደተኞቹን ማን አፍኖ እንደወሰዳቸው ያለው ነገር ባይኖርም፤ አንድ ስደተኛ ለቢቢሲ እንደተናገረው ኤርትራዊያን ወታደሮች ስደተኞችን በከባድ መኪና እየጫኑ ከአዲግራት ከተማ ወደ አዲ ቋላ ወስደዋቸዋል። ኤርትራ በዚህም ጉዳይ ምንም ዓይነት አስተያት አልሰጠችም። ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የስደተኞች ኮሚሽኑ የኤርትራን ሕዝብ ለማራቆት "ሰፊ ዘመቻ" ጀምሯል ስትል ከሳ ነበር። ዳዊት፤ የኤርትራ አገዛዝ በፍፁም ይለወጣል ብሎ አያስብም። "ኤርትራ ውስጥ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ለውጥ የለም። ምክንያቱም አገዛዙ ይህን አይፈልግም። የህወሓት መጥፋትም ምንም ዓይነት ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም። ለውጥ መጠበቅ የማይፈታ ህልም ነው" ይላል።
52627584
https://www.bbc.com/amharic/52627584
የኮሮናቫይረስ ክራሞት በኢትዮጵያ፡ ከመጋቢት እስከ ግንቦት
ኢትዮጵያ ውስጥ ኮሮናቫይረስ ያለበት ሰው ከተገኘ ዛሬ ሁለት ወር ሞላው፤ በዚህ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ በአጠቃለይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 261 ደርሷል።
እስካሁን ድረስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አዲስ አበባ ከፍተኛ ሲሆን በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ 14፣ በአፋር ክልል በሚገኝ ለይቶ ማቆያ 13፣ በትግራይ ክልል ስድስት እንዲሁም በደቡብ ክልል አራት ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ ተረጋግጧል። በተጨማሪም 106 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ለ39 ሺህ 48 ናሙናዎች ምርመራ መደረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚያወጡት የዕለት ሁኔታ መግለጫ ያሳያል። የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ዶ/ር ሊያ እንዳሉት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው በርካታ ግለሰቦች የኮሮናቫይረስ እየተገኘባቸው ነው። ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ሳይኖራቸው ኮቪድ-19 የሚገኝባቸውም ሰዎች ቁጥር እንዲሁ ጨምሯል። ቢቢሲ ላለፉት ሁለት ወራት የወጡትን ዕለታዊ መግለጫዎችን መለስ ብሎ ሲቃኝ በግንቦት ወር ሦስት ቀናት ብቻ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተመልክቷል። መጋቢት- አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ የመድኃኒት ምርምርና የጃክ ማ ድጋፍ ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ በግዛቷ ከማግኘቷ በፊት ከጥር 20/2012 ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅትና የጥንቃቄዎች ስታደርግ እንደነበር በወቅቱ ለመገናኛ ብዙኅን ይፋ ሆኖ ነበር። በወቅቱ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የማኅበረሰብ ጤና የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት መስጫዎችን እያቋቋሙ ነበር። ይህ ወር ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ እግሩን ማስገባቱ የታወቀበት ወር ብቻ አይደለም፤ ከአዲስ አበባ ባሻገር አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ አዲስ ቅዳምም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው መጋቢት 4/2012 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ በኮቪድ-19 እንደተያዘ የተረጋገጠው ግለሰብ ጃፓናዊ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ለሥራ የመጣ መሆኑንና ከኢትዮጵያ በፊት ቡርኪናፋሶ እንደነበር ተገልጿል። • የ‘ኅዳር በሽታ’ እና ኮሮናቫይረስን ምን ያመሳስላቸዋል? ግለሰቡ በኢትዮጵያ ቆይታው ወደ ተለያዩ ከተሞች በመጓዙ ከእርሱ ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 117 ሰዎች ተለይተው የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልፀው ነበር። ከዚህ በኋላ መጋቢት ስድስት ከእኚህ ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሁለት ጃፓናውያንና አንድ ኢትዮጵያዊ በቫይረሱ መያዛቸው ተገለፀ። መጋቢት ሰባት ከዱባይ የመጣ አንድ ግለሰብ በቫይረሱ መያዙ ተጠርጥሮ ምርመራ ሲደረግለት በቫይረሱ መያዙ ስለተረጋገጠ ለይቶ ማቆያ መግባቱ የተነገረው በዕለቱ ነበር። ከዚህ በኋላ ከተለያዩ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ እየተረጋገጠ ወደ ለይቶ ማቆያ ይላኩ ጀመር። የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች አንዱ በንክኪ ምክንያት የተጋለጠው ሲሆን ሌላኛው ከዱባይ የመጣ ግለሰብ ናቸው። ከዚህ በኋላ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ከተውጣጡ አካላት ጋር በመሰብሰብ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታት ይረዳል የተባሉ መመሪያዎችን ያስተላልፈዋል። በጽህፈት ቤታቸው በኩል መጋቢት 7 2012 በዋጡት መግለጫ ትላልቅ ሕዝባዊ ስብሰባዎች መከልከላቸው፣ አነስተኛ ስብሰባዎችም ቢሆኑ ያለ ጤና ሚኒስቴር እውቅና እንዳይካሄዱ፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም በስተቀር ሁሉም ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፣ የኃይማኖት ተቋማት ለአምልኮ የሚታደመውን ሰው ቁጥር እንዲቀንሱ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ መመሪያዎች የተላለፉ ሲሆን በዚሁ መግለጫ ላይ መገናኛ ብዙኀን ትክክለኛ መረጃ ለማኅበረሰቡ እንዲያደርሱ ተጠይቀዋል። በወቅቱ ዜጎች አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ፣ በጎ ፈቃደኞች የግንዛቤ ማስጨበጥ እንዲሰሩ ጥሪ ተላልፎ ነበር። የመጀመሪያው በእድሜ የገፉ ሴት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው መጋቢት 10 ነበር። እኚህ የ85 ዓመት ሴት ከባህር ማዶ የመጡና ራሳቸውን ለይተው ጤናቸውን ሲከታተሉ የነበረ መሆኑ በወቅቱ የተገለፀ ሲሆን፤ የበሽታውን ምልክት በማሳየታቸው የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ አንድ የኮቪድ-19 መመርመሪያ ላቦራቶሪ ብቻ የነበራት ሲሆን በስድስት ቀን ውስጥ መመርመር የቻለችውም 342 ናሙናዎችን ብቻ ነበር። የኮቪድ 19 መከላከል ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በመገናኘት መጋቢት ሰባት ካሳለፏቸው ዋና ዋና ውሳኔዎች በተጨማሪ ሌሎች ውሳኔዎችን አሳለፉ። በዚህ ውሳኔያቸውም መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ማናቸውም መንገደኞች በራሳቸው ወጪ በተመረጡ ሆቴሎች ለአስራ አራት ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ተወሰነ። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ወደ ሰላሳ አገራት የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት ማቆሙ የተገለፀው በዚሁ መግለጫ ላይ ነበር። • በአፍሪካ ከ63 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ቢያዙም የተጣለው ገደብ እየላላ ነው የጭፈራ እና የመጠጥ ቤቶች ቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ሲባል በጊዜያዊነት እንዲዘጉ ሲወሰን፣ የተለያዩ ክልሎች ወደ ክልላቸው የሚገቡ ሆነ የሚወጡ ተሽከርካሪዎች ላይ ክልከላ አስቀመጡ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚል ከመጋቢት 16 ጀምሮ ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚተላለፍ ድረስ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ሥራቸውን በቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ ወስኗል። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12 ለመድረስ የፈጀበት ጊዜ 10 ቀናት ብቻ ነው። በወቅቱም ለ480 ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎ ነበር። መጋቢት 18/2012 ዓ.ም ባህላዊ ህክምናን እና ሳይንሳዊ ምርምርን በማጣመር ከእጽዋት የኮሮና ቫይረስ መድኃኒት ለማግኘት ባለሙያዎች እያደረጉ ያለው ሙከራ የመጀመሪያ የቤተ ሙከራ ሂደት ማለፉ ተገለፀ። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ከተያዙ ሰዎች መካከል ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገመ አንድ ግለሰብ መኖሩ የተገለፀው መጋቢት 19/2012 ነው። መጋቢት 20/2012 ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጪ በኮቪድ-19 የተገኘበት ዕለት ነበር። በወቅቱ የአንድ የቤተሰብ አባል የሆኑ ሁለት የአዳማ ነዋሪዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው መረጋገጡ ተሰምቷል። ከዚህ በኋላ በአማራ ክልል ባህርዳርና አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዲስ ቅዳም ከተማ ውስጥ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መገኘታቸውን የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ የመጋቢት 21 መግለጫ ያሳያል። በማግስቱም፣ መጋቢት 22/2012 ዓ.ም፣ በድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነና ከአውስትራሊያ የመጣ ግለሰብ በቫይረሱ መያዙ ተገለፀ። በመጋቢት ወር የአገር አቀፍ የኮሮናቫይረስ ምረመራ የሚደረገው በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የነበረ ሲሆን በዚያው በኢንስቲትዩቱ ውስጥ ሁለተኛ መመርመሪያ ላብራቶር መደራጀቱ የተገለፀው ደግሞ መጋቢት 24 ነው። በተለያዩ ቦታዎችም የሚገኙ ላብራቶሪዎች ሥራ ጀመሩ። • "ስለምንወዳችሁ ሠርጋችን ላይ አትምጡ" የአዲስ አበባዎቹ ሙሽሮች በኮሮናቫይረስ ከተያዙ ሰዎች መካከል የመጀመሪያው ሞት የተመዘገበው መጋቢት 27/2012 ዓ.ም ነው። ግለሰቧ የስድሳ ዓመት አዛውንት ሲሆኑ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለይቶ ማቆያ ህክምና ሲደረግላቸው ነበር። በዚያው ዕለት የ56 ዓመት ጎልማሳ የነበሩ ሁለተኛው ግለሰብ መሞታቸው ተሰምቷል። በመጋቢት ወር ከፍተኛ ቁጥር ያለው በቫይረሱ የተያዘ ሰው የተመዘገበው ስምንት ሲሆን እርሱም መጋቢት 29/2012 ነበር። በመጋቢት ወር ብቻ ኢትዮጵያ 2496 ናሙናዎችን የመረመረች ሲሆን 55 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል። ሚያዚያ ፦ አፋር፣ ጅግጅጋ፣ ትግራይ በዚህ ወር ብቻ ወደ 28000 የሚጠጉ ናሙናዎች በተለያዩ ክልሎችና ተቋማት ውስጥ የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸዋል። በሚያዚያ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ዘጠኝ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል፤ በዚሁ የመጀመሪያ ሳምንት ነው ሦስተኛ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው መሞቱ የተገለፀው። ግለሰቧ የ65 ዓመት አዛውንት የዱከም ከተማ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን በወቅቱ ወደ ሆስፒታል የሄዱት ለሌላ ሕክምና ነበር። ከጃክ ማ ለአፍሪካ አገራት የተሰጠው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም ቻይናውያን የጤና ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለጤና ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ ያደረጉትም በዚሁ ወር ነው። የሚያዚያ ወር ከመጋቢት በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተመዘገበበት ሲሆን በመላው አገሪቱ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ለመድረስ ጥቂት ቀናት ብቻ ነበር የፈጀው። የመጋቢት ወር ሲጠናቀቅ 55 የነበረው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ አድጎ ወደ 105 ለመድረስ አስር ቀናት ብቻ ናቸው የፈጁበት። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ናሙናዎች መመርመራቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚያዚያ ወር እንደ ሚሌኒየም አዳራሽ የመሳሰሉ ሰፋፊ ስፍራዎች ለለይቶ ማከሚያነት የተዘጋጁ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በርካታ ግለሰቦች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ባለሃብቶች መኖሪያ ቤታቸውን፣ ሕንፃቸውን ለለይቶ ማቆያነት ሲሰጡም ተስተውሏል። በዚህ በሚያዚያ ወር በርከት ያሉ ከጅቡቲ የተመለሱ እና በድሬዳዋ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ፣ ከፑንትላንድ በመምጣት በጅግጅግ ለይቶ ማቆያ የነበሩ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተገለፀ ሲሆን ሚያዝያ 14 ደግሞ አፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ አንድ ግለሰብ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡ ተገለጿል። በቫይረሱ የተያዘ አንድም ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይገኝ የቀረው ሚያዚያ 15/2012 ነው። በዕለቱ ለ965 ናሙናዎች ምርመራ ቢደረግም በቫይረሱ የተያዘ ግለሰብ አልተገኘም። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ወስጥ መከሰቱ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዚ ከአንድ ሺህ በላይ (1019) ናሙናዎች መመርመራቸው የተገለፀው ሚያዚያ 17/2012 ሲሆን በወቅቱም 22 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ናሙናዎችን የመመርመር አቋሟን በማሳደግ በ24 ሰዓት ውስጥ 2016 ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረጓ የተገለፀው በዚሁ ወር (ሚያዚያ 24 2012) ነበር። ከፑንትላንድ በመምጣት በጅግጅግ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ ግለሰብ በቫይረሱ መያዙ የታወቀውም ሚያዚያ 18/2012 ዓ.ም ነው። በዚህ ወር (ሚያዚያ 24/2012) ኢትዮጵያ በቀን 2016 ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረጓ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከሁለት ሺህ በላይ ናሙናዎች ላይ ምርመራ ባደረገችበት ዕለት (ሚያዚያ 24/2012) በቫይረሱ የተያዘ አንድም ሰው ያልተገኘ ሲሆን፣ በዚሁ ዕለት በአጠቃላይ በአገር ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133 ደርሶ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ከአዲስ አበባ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ አድማሱን በማስፋት ሚያዚያ 25/2012 ዓ.ም በደቡብ ክልል ስልጤ ዘን ስልጢ ወረዳ አንዲት የ45 ሴት የቤት ለቤት ቅኝትና አሰሳ ሲደረግ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡ ተነግሯል። • ከኮሮናቫይረስ ለማገገም ምን ያክል ጊዜ ይወስዳል? በወቅቱ ግለሰቧ ቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳልነበራቸውና ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክም የሌላቸው መሆኑ ተገልጿል። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ከተያዙ ሰዎች መካከል አራተኛዋ ግለሰብ መሞታቸው የታወቀው ሚያዚያ 27/2012 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ ግለሰቧ እድሜያቸው 75 መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሆስፒታል ተኝተው ሲታከሙ የነበሩት በተጓዳኝ ሕመም ታመው መሆኑ ተገልጿል። ነገር ግን ግለሰቧ የመተንፈስ ችግር አጋጥሟቸው የነበረ ሲሆን ናሙና ተወስዶ ምርመራ እየተደረገላቸው እያለ ሕይወታቸው ማለፉ በወቅቱ በወጠዓው መግለጫ ላይ ተመልክቷል። ግለሰቧ በቫይረሱ መያዛቸው የታወቀው ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ነው። በዚህ ወር ለመጀመሪያ ጊዜ 17 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጾ ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበው ሚያዚያ 28/2012 ዓ.ም ሲሆን አብዛኛዎቹ ከጅቡቲ የመጡ እና በአፋር ለይቶ ማቆያ የነበሩ፣ እንዲሁም ከፑንትላንድ የመጡ እና በጅግጅግ ዩኒቨርስቲ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በማግስቱም 29 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲገለፅ ከእነዚህ መካከል 19 ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ እንዲሁም ቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪም የሌላቸው ነበሩ። በዚህ ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ በትግራይ ክልል አራት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎችን የመረመረች ሲሆን ቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 191 ደርሶ ነበር። በኢትዮጵያ እስከ ሚያዚያ 30 ድረስ 194 ሰዎች ባቫይረሱ ሲያዙ ለ30306 ናሙናዎች ምርመራ ተደርጓል። የአንድ ሰው ሕይወት ያለፈው በዚህ ወር መጨረሻ ሲሆን የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጋር በኮቪድ-19 መከላከል ላይ ለተሰማሩ የጤና ባለሙያዎቸ የመድን ዋስትና እንዲገባላቸው የሚያስችል ፊርማ አከናውኗል። ግንቦት- ወልዲያ፣ ወላይታ፣ ቡታጅራ በግንቦት ወር ሦስት ቀናት ብቻ 56 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ሲረጋገጥ፣ ከስድስት ሺህ በላይ ናሙናዎች መመርመራቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መግለጫዎች ያሳያሉ። በግንቦት የመጀመሪያው ቀን ብቻ 2 ሺህ 383 ሰዎች በመመርመር በአገሪቱ በአጠቃላይ የተመረመሩ ናሙናዎችን ቁጥር 32 ሺህ 689 ደርሷል። በዚሁ ዕለት በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 16 ሲሆን በወቅቱ እንደተገለፀው አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 210 ደርሷል። በዚሁ ዕለት በጽኑ የሕሙማን ክፍል የነበሩ አንድ የ65 አመት አዛውንት ሞተው በኢትዮጵያ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር አምስት የደረሰ ሲሆን በዚህ ዕለት በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ ሰዎች መካከል 13 የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ አንድ ከወልዲያ የለይቶ ማቆያ፣ አንድ በወላይታ ሶዶ ለይቶ ማቆያ ሌላኛው ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ መሆናቸው ተገልጿል። በዚህ ወር በአንድ ቀን ብቻ 29 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው የተገኘው ግንቦት 2/2012 ዓ.ም ነበር። ይሀም በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 239 አድርሶታል። አንድ ግለሰብ አዳማ ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት አሰሳ ቅኝት የተለዩ መሆናቸው ሲገለፅ፣ ሰባቱ ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 21 ደግሞ ከአዲስ አበባ ናቸው ተብሏል። በዚህ ወር ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ከትግራይ ክልል የተገኙ ሲሆን በአጠቃለይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 250 ደርሷል። እስካሁን ድረስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አዲስ አበባ የሚመራ ሲሆን የሶማሌ ክልል በሁለተኛነት ይከተላል። እስካሁን ድረስ 105 ሰዎች ሲያገግሙ፣ በመላው አገሪቱ ለ36 ሺህ 624 ሰዎች ምርመራ ተደርጓል። የኮሮና ዘመን ተጋቢዎች፦ ሠርጋቸው ቀረ ወይስ ተራዘመ?
news-49175130
https://www.bbc.com/amharic/news-49175130
የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤቶች ምርጫ ተራዘመ
የአዲስ አበባና እና የድሬዳዋ ምክር ቤቶች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫ ከቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባደረገው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው ወስኗል።
ወደ 2011 ዓ.ም እንዲራዘም የተደረገውን የሁለቱን ምክር ቤቶች ምርጫ በተያዘለት ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማካሄድ እንደማይችል ምርጫ ቦርድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስታወቁ ይታወሳል። • "አዲስ አበባ የምንወዛገብባት ሳትሆን በጋራ የምንኖርባት ከተማ ናት" ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ • የአዲስ አበባ መስተዳደርና የባላደራው ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ሐምሌ 4/2011ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፃፈው ደብዳቤ የሁለቱን ምክር ቤት ምርጫ እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ማካሄድ እንደማይቻል ጠቅሷል። ለዚህም እንደ ምክንያትነት ያቀረበው ምርጫ አስፈፃሚዎችን ለመመልመል፣ ለማደራጀት እና ለስልጠና የቀረው የዓመቱ ጊዜ አጭር በመሆኑ ነው። በውሳኔውም መሰረት በሥራ ላይ ያሉት ምክር ቤቶች ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ሥራቸውን እያከናወኑ ይቀጥላሉ። በ2010 መካሄድ የነበረበት የሁለቱ ምክር ቤቶች ምርጫ ሃገሪቱ ውስጥ በነበረው አለመረጋጋትን ተከትሎ በዚህ ዓመት እንዲካሄድ መራዘሙ የሚታወስ ነው። ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ በሃገሪቱ ከሚካሄዱ ብሔራዊ ምርጫዎች ጋር የሚካሄድ የነበረ ሲሆን፤ አወዛጋቢውን የ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎ ከተማዋ በባለአደራ አስተዳደር ስር ቆይታ ምርጫ በመደረጉ የምርጫው ጊዜ ከሌሎቹ ክልሎች የተለየ እንዲሆን ምክንያት ሆኗል።
41627682
https://www.bbc.com/amharic/41627682
ጣና ሐይቅ የተጋረጡበት ፈተናዎች
የጣና ሐይቅ በእምቦጭ አረም መወረሩን ተከትሎ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች አረሙን በእጅ በመንቀል ለማስወገድ ሲረባረቡ ቢስተዋልም ባለሞያዎች የዚህ መሰሉን እንቅስቃሴ ውጤታማነት እንዲሁም በማሽን የመንቀልን ዘመቻ ተግባራዊነት ይጠራጠራሉ፤ ሐይቁ ላይ የተጋረጠው አደጋ ግን ይህ ብቻ አይደለም።
ከአገሪቱ ጨው አልባ የተፈጥሮ ውሃ ውስጥ ሃምሳ በመቶ ያህሉን የያዘው የጣና ሐይቅ ለመጀመሪያ ጊዜ በእምቦጭ አረም መወረሩ የተስተዋለው እ.አ.አ በ2011 ነው። አራት ሺህ ሄክታር ያህል የውሃ ክልልን በመሸፈን የጀመረው የአረሙ ወረራ፤ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 20ሺህ ሄክታርን ወደማካለል አድጓል። በወቅቱ የክልሉ የአካባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት እምቦጭን "ጣናን የወረረው እጅግ አስከፊው አረም" ሲል የፈረጀው ሲሆን፤ በሐይቁ ዙርያ የሚኖሩ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባብር አረሙን በእጅ በመንቀል ለማስወገድ ተጥሯል። በዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት እንዲሁም ከመንግሥታዊ ቢሮዎች ጋር በትብብር የተሰናዳው "የጣና ሐይቅ የእምቦጭ አረም መከላከያ ቁጥጥር ስትራቴጅ" እ.ኤ.አ ከጥቅምት 2011 አንስቶ እስከ ታህሳስ 2013 ድረስ እምቦጭን በእጅ መንቀል ላይ የፈሰሰው ጉልበት በትንሹ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ይገመታል። ይሁን እንጅ በጥቂት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አረሙ መጠኑን ከእጥፍ በላይ ጨምሮ በመመለስ ሐይቁን ወሯል። በአሁኑ ሰዓት 50ሺህ ሄክታር የሐይቁ ክፍል በአረሙ እንደተወረረ የሚገመት ሲሆን፤ ይህም ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት በአራት ሺህ ሄክታር ብቻ የሚያንስ ነው። 128 ኪሎሜትር ያህል የሐይቁ ዳርቻ በእምቦጭ መሸፈኑም ይገመታል። በአረሙ እና በሐይቁ ላይ ምርምሮችን ያደረጉት በካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሥነ-ሕይወት ባለሞያው ዶክተር ሰለሞን ክብረት ለእምቦጭ ዳግም ምፅዓት አንደኛው ምክንያት አረሙን በእጅ ነቅሎ ለማጥፋት በተሞከረበት ወቅት ንቃዩን በአግባቡ ለማስወገድ ትኩረት ባለመሰጠቱ ነው ይላሉ። "የተነቀለው አረም በሙሉ ለሐይቁ ዳርቻ ቅርብ የሆነ ቦታ ላይ ተትቶ ስለነበር፤ ብዙም ሳይቆይ በዝናብ አማካይነት ከዚያ ቀደም ደርሶባቸው ወደማያውቅባቸው ሰፊ ቦታዎች ሁሉ ሊወሰድ በቅቷል" ሲሉ ዶክተር ሰለሞን ለቢቢሲ ያስረዳሉ። "መጥፎው ዜና [እምቦጭን] ሙሉ በሙሉ ማጥፋት እምብዛም የማይቻል መሆኑ ነው" ይላሉ ዶክተር ሰለሞን አክለው። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ "ዘሩ እስከሰላሳ ዓመት ድረስ መቆየት የሚችል መሆኑ ነው።" መጤው አጥፊ እምቦጭ መነሻውን ላቲን አሜሪካ ያደረገ፤ እንዳሻው በውሃ ላይ የሚንሳፈፍና የሚዋልል ወራሪ አረም ሲሆን በተለያዩ መንገዶች ወደአፍሪካና እስያ እንደተሰራጨ ይነገራል። ይህ ተክል የተለያዩ ጉዳቶችን የሚያስከትል ሲሆን፤ ጉዳቶቹን የሚያደርስበት መንገድም የውሃ ፍሰትን በመከልከል፣ ውሃው ውስጥ ያሉ ተክሎች እና እንስሳት የፀሐይ ብርሃን እንዳይደርሳቸው በመከልከል፣ አሳን የመሰሉ እንስሳት ኦክስጅን እንዳያገኙ በማፈን ጭምር ነው። ከዚህም በዘለለ በእርከን ሥራ፣ በኃይል ማመንጨት እንዲሁም በዓሳ ማጥመድ ላይ ተፅዕኖ አለው። የእምቦጭ አረም ከጠቅላላ አካሉ ውስጥ 90 በመቶ ያህሉ ውሃ እንደመሆኑ ብዙ ውሃን ይመጣል። እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ አጋማሽ የአዋሽ ወንዝን በመገደብ በተሰራው የቆቃ ሐይቅ ላይ ለመታየቱ ማስረጃዎች አሉ። በተለያዩ ጊዜያት የጫሞና የአባያ ሐይቆችን ጨምሮ በሌሎች የአገሪቱ የውሃ አካላት ላይ የእምቦጭ ወረራ ተስተውሏል። "የጣና ሐይቅ የእምቦጭ አረም መከላከያ ቁጥጥር ስትራቴጂ" ሐይቁ እንዴት በዚህ መጤ አረም ሊወረር እንደቻለ በትክክል ማወቅ እንዳልተቻለ ይገልፅና ከውጭ ሀገራት የገቡ ያገለገሉ የዓሳ ማጥመጃ መሳሪያዎች፣ ጀልባዎች አሊያም በእርሻ ግብዓቶች አማካይነት ሊሆን እንደሚችል ግምቶች መኖራቸውን ይጠቅሳል። አረሙ ጣናን ከመውረሩ አስቀድሞ ሱዳን ውስጥ መታየቱንም "ስትራቴጅው" ያስታውሳል። የጣና አስፈላጊነት ጣና ለዓለም ሥነ-ምኅዳራዊ ብዝሃነት ያስፈልጋሉ ከተባሉ 250 ሐይቆች መካከል አንዱ ሆኖ ተመርጧል። በውስጡ 28 የዓሳ ዝርያዎችን የያዘ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም 21 ያህሉ በሌላ ቦታ አይገኙም። በዙሪያው የሚኖሩ ከ3 -4 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሐይቁ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አላቸው። ከእነዚህም መካከል ሐይቁ በያዛቸው 37 ደሴቶች የሚገኙ ከ15ሺህ በላይ የኅብረተሰብ አካላት ይገኙባችዋል። ከጣና ሐይቅ የሚገኝ ዓመታዊ የዓሳ ምርት የገንዘብ ተመን 1.1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሆነ የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ያሳውቃል። ጣና በየዓመቱ 13ሺህ ቶን የሚደርስ ዓሳ የማምረት አቅም ቢኖረውም፤ ከ1000 ቶን የሚበልጥ ዓሳ ሲያመርት አይስተዋልም። የእምቦጭ ወረራ የሐይቁን ብዝሃ ህይወት አደጋ ላይ የጣለ መሆኑን ጥናቶች ያመላክታሉ። ተመራማሪው ዶክተር ሰለሞን እንደሚሉት ከሆነ በቅርብ ዓመታት ውስጥ የሐይቁ የዓሳ መጠን በ75 በመቶ ያህል እንደቀነሱ ጥናቶች ይጠቁማሉ። የሐይቁን ሰሜናዊ ዳርቻ ታከው የሚገኙ ሩዝ አምራቾች እስከ 500 ሄክታር የሚደርስ መሬትን በአረሙ ምክንያት አጥተዋል ይለዋል። "የአረሙ ተፅዕኖዎች በአካባቢው ኗሪዎች ላይ አሻራቸውን ማሳረፍ ጀምረዋል። ተገቢ የቁጥጥር እርምጃዎች በአፋጣኝ ተግባራዊ የማይሆኑ ከሆነ ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ህልውና አደጋ ይጋረጥበታል" ሲሉ ዶክተር ሰለሞን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ተገቢ እርምጃዎች" ዶክተር ሰለሞን ከአማራ ክልል ባለስልጣናት እና ከዩኒቨርስቲ አካላት ጋር ባደረግኩት ውይይት አረሙን በማሽን ለማጥፋት የመሞከር አማራጭ ከፍ ያለ ተቀባይነት እንዳለው ተገንዝቤያለሁ ይላሉ። ማሽኖችን መጠቀም አረሙን በፍጥነት ለማስወገድ የሚያስችል አማራጭ አንደመሆኑ የብዙሃንን ድጋፍ ሲያገኝ ይስተዋላል። የክልሉ የአካባቢ፣ ደን እና የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በላይነህ አየለ የባህርዳር እና ጎንደር ዩኒቨርስቲዎችን በማስተባበር የተሻለ ውጤት ያላቸው አማራጮችን ለመጠቀም፤ እንዲሁም አረሙን ከነቀለ በኋላ ፈጭቶ ወደባዮጋዝ ምንጭነት የሚቀይር ማሽንንም ሥራ ለማስጀመር እየተጣረ መሆኑን በቅርቡ ገልፀዋል። እ.ኤ.አ ከ2014 እስከ 2018 ላሉት ዓመታት የተቀረፀው "የጣና ሐይቅ የእምቦጭ አረም መከላከያ ቁጥጥር ስትራቴጂ" በበኩሉ የተቀናጁ እርምጃዎችን መውሰድን ይመክራል። በቅንጅት ቢተገበሩ ይበጃሉ ከተባሉት እርምጃዎች መካከልም የእጅ ነቀላ፣ የማሽን ነቀላ እና ሥነ-ህይወታዊ የቁጥጥር መንገድ ይገኙባቸዋል። ዶክተር ሰለሞን የማሽንን አማራጭ ከአገሪቱ የገንዘብ አቅም አንፃር አዋጭ አይደለም ይሉታል። "ማሽኖቹን ለማንቀሳቀስ ከሚያስፈልገው ገንዘብ በተጨማሪ ማሽኖቹ የሚንቀሳቀሱባቸው ወደቦች እንዲሁም የሚታጨደውን አረም የማጓጓዣ መንገዶች አስፈላጊ ናቸው። እነዚህ ደግሞ አሁን የሉም" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ችግሩ በነካቸው አስራ ስምንት ቀበሌዎች መንገዶችን፣ ወደቦችን እንዲሁም የማራገፊያ ስፍራዎችን መስራት ግድ ሊሆን ነው ይላሉ ዶክተር ሰለሞን ጨመረው። ተመራማሪው ይህንን ሙግታቸውን ባተቱበት ጽሁፋቸው እንደሚሉት ደግሞ፤ አንድ አረም የመንቀያ ማሽን በቀን ውስጥ ማካለል የሚችለው ስፍራ ከአስር ሄክታር አይበልጥም። በመሆኑም 10 ማሽኖች ጣናን የወረረውን እምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ ላይ ቢሳተፉ እንኳ አረሙን አስወግዶ ለመጨረስ አምስት መቶ ቀናት ወይንም ከአንድ ዓመት ተኩል የሚልቅ ጊዜ ያስፈልጋል። ከሌሎች አረሙን የማስወገጃ መንገዶች መካከል ኬሚካሎችን መርጨት አንዱ ሲሆን ይህ መንገድ ግን ሐይቁ ለያዛቸው እንስሳትና ተክሎች አደገኛ መሆኑ አያጠያይቅም። ለዶክተር ሰለሞን ሥነ-ሕይወታዊ የቁጥጥር መንገድ ካሉት አማራጮች ሁሉ ከወጭ አንፃር አዋጭ የሆነው እንዲሁም በውጤታማነቱ የተሻለው ነው። ይህ መንገድ ሥነ-አካባቢያዊ ጉዳት በማያደርስ ዘዴ ተፈጥሯዊ ጠላቶችን መጠቀምን የሚከተል መንገድ ሲሆን ሁለት የጢንዚዛ ዝርያዎች አረሙን በማስወገድና ስርጭቱንም በመቆጣጠር ውጤታማ ሆነው ተገኝተዋል። ስለዚህም ከሰላሳ በላይ አገራት ይህንን ስልት ተግባራዊ በማድረግ ውጤት አስመዝግበዋል። የሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎች እምቦጭ የበርካታ ሀገራት የውሃ አካላት ላይ አደጋን የሚጋርጥ ሲሆን ለምሳሌ ያህል ጎረቤት ሱዳን ለእምቦጭ ቁጥጥር በየዓመቱ 1 ሚሊዮን ፓውንድ እንደምታወጣ ይዘገባል። ኡጋንዳ በበኩሏ የቪክቶሪያ ሐይቅን የወረረውን አረም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መቆጣጠር የቻለች ሲሆን ከተከተለቻቸው መንገዶች ውስጥ ሥነ-ሕይወታዊ የቁጥጥር መንገድ አንዱ ነው። ይህን የቁጥጥር ስልት ሙሉ በሙሉ በተግባር ላይ አውሎ ውጤትን ለማግኘት ዘለግ ያለ ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑ ግን አረሙን በአፋጣኝ ከማስወገድ ግብ ጋር የሚቃረን ነው። ዶክተር ሰለሞን ግን ሁለቱን የጢንዚዛ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንዲራቡ እና ይህንን ሥራ እንዲያከናውኑ ማድረግ እንደሚቻል የምርምር ውጤቶች እንደሚጠቁሙና በዓመት አራት ጊዜ እንዲራቡ ማድረግ እንደሚቻል ይገልጻሉ። ሌሎች ፈተናዎች የአካባቢው ወንዞች አፈርና ዝቃጭ የሚይዙ መሆናቸው አረሙ በጣና ሐይቅ እንዲፋፋና እንዲስፋፋ አግዟል። የሐይቁን የሥነ-ሕይወት ኅልውና የሚፈታተነው አደጋ ግን እምቦጭ ብቻ አይደለም። በሐይቁ ዙርያ ያሉ ፋብሪካዎች የሚለቁት የውሃ ፍሳሽ ለውሃው ጥራት መጓደል ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። በሐይቁ ዙርያ ያለው የሕዝብ ብዛት እየጨመረ መሄድ የሐይቁን ተፈጥሯዊ ሃብት እያመናመነው እንደሆነ የሚያስረዱ ጥናቶችም አሉ። በጣና ሐይቅ ላይ የዓሳ ማጥመድ እንቅስቃሴ 400ሺህ ያህል የሚሆኑ የማኅበረሰብ አካላት የህልውና ምንጭ ነው።ከእነዚህ አካላት መካከል ከሐይቁ ዓሳ በማጥመድ የሚተዳደረው ቢተው ካሰኝ ይገኝበታል። ቢተው የዓሳው ቁጥር መመናመን የውሃው በእምቦጭ ከመሸፈን ጋር ተደማምሮ ለኅልውናው ስጋት እንዲገባው እንዳደረገው ይናገራል። "ወትሮ በአንድ ሳምንት የምናገኘው አሁን ወር ያለፋናል" ይላል። በጣና ሐይቅ የዓሳ ሃብት መመናመን ዙርያ እሸት ደጀን እና አጋሮቻቸው ያደረጉት ጥናት እንደሚያመላክተው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በሐይቁ የሚጥመድ ዓሳ መጠን ክፉኛ አሽቆልቁሏል። እ.ኤ.አ በ1993 በአንድ ጉዞ 177 ኪሎ ዓሳ ይጠምድ የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር ግን በ2010 ወደ56 ኪሎ አሽቆልቁሏል። ከዚህም በተጨማሪ የጣና ሐይቅ ኃብት አስተዳደር ምርምር ማዕከል ሐይቁ የአፈር መሸርሸር፣ የአካባቢ ብክለት፣ የአሸዋ ቁፋሮ፣ የሐይቁን ዳርቻ ታክከው ያሉ በተለይም ሩዝ አምራች ገበሬዎች ደካማ የመሬት አጠቃቀም ልማዶች እና የመሳሰሉ ተግዳሮቶችን ተጋፍጧል ይላል። በእነዚህ ሁሉ ፈተናዎች የተከበበው ጣና ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አትኩሮትን የሚሻበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ክፍል 1 ፡በፅኑ የታመመው የዓባይ ወንዝ ክፍል 2 ፡የህዝብ ብዛት መጨመርና የአካባቢ ብክለት ሌሎቹ የዓባይ ስጋቶች ክፍል 3 ፡የዓለማችን ረጅሙ ወንዝ መፃኢ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን?
45405013
https://www.bbc.com/amharic/45405013
የ2010 የጥበብ ክራሞት
2010ን ለመቀበል መስከረም ላይ ሽር ጉዱ የተጀመረው በሙዚቃ ኮንሰርቶች ነበር። የታዋቂ ሙዚቀኞች ፎቶ ከአዲስ ዓመት አብሳሪ አደይ አበባ ጋር ተጣምሮ የሚታይባቸው የኮንሰርት ማስታወቂያዎች እዚህም እዚያም ይታዩ ነበር።
ከመስከረም ጥቅምት፣ ህዳር፣ ታህሳስ . . . እያለ ዓመቱ ሲገፋ ሙዚቃው ብቻ ሳይሆን ፊልሙ፣ ሥነ ጽሑፉ፣ ሥነ ጥበቡም ተሟሙቋል። ከዓብይ አህመድ እስከ ቴዲ አፍሮ በዓመቱ አበይት ከነበሩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች መካከል የቴዲ አፍሮ "ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር" የተሰኘው ይገኝበታል። "ኢትዮጵያ" የተሰኘው አልበም መለቀቁን ተከትሎ፤ ጥር 12፣ 2010 ዓ. ም. በባህር ዳር ስቴድየም ውስጥ ነበር የተካሄደው። የጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩን የሚያሞጋግሱ ነጠላ ዜማዎች የተለበቁበት ዓመትም ነው። በኦሮምኛ ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው የአቡሽ ዘለቀ "አነቃን" የተሰኘው ዘፈን ተጠቃሽ ነው። • ቴዲ አፍሮን ለምን? አዲስ ሙላት ያወጣው "ሃገሬን" የተሰኘው ነጠላ ዜማ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሰኔ 16፣ 2010 ዓ. ም. በመስቀል አደባባይ ያደረጉትን ንግግርን መነሻ በማድረግ ጀምሮ፤ ድምጻዊው የኦሮምያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ለማ መገርሳን ያመሰግናል። የአብዲ ያሲን "ተደምረናል"፣ የፋሲል ደሞዝ "ሰላም ነው ድግሱ"፣ የሲሳይ ደሞዝ "አማረብሽ ዛሬ" በርካታ አድማጭ ካገኙ ሙዚቃዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ለዓመታት አልበም ያላወጣችው ማሪቱ ለገሰ "ይገማሸራል" የተሰኘ አልበሟን የለቀቀችው በዚሁ ዓመት ነው። 'የአምባሰሏ ንግስት' የምትባለው ድምጻዊቷ አልበም ሐምሌ 6፣ 2010 ዓ. ም. ተመርቋል። ዓመቱ የመጀመሪያ አልበማቸውን ለአድማጭ እነሆ ካሉ ድምጻውያን፤ አልበም እስከደጋገሙት ድረስም የተደመጠበት ነው። የጃኖ ባንድ "ለራስህ ነው"፣ የሮፍናን "ነጸብራቅ"፣ የጃሉድ "ንጉስ"፣ የቤቲ ጂ "ወገግታ"፣ የእሱባለው ይታየው "ትርታዬ" እና የብስራት ሱራፌልን "ቃል በቃል" መጥቀስ ይቻላል። • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን ዓመቱን ካደመቁ ኮንሰርቶች መካከል መባቻው ላይ የተካሄደው "እንቁጣጣሽ" ይገኝበታል። በካፒታል ሆቴል በተካሄደው ኮንሰርት ሚካኤል ለማ፣ ሳሚ ዳን፣ ዳዊት ጽጌ እና ሌሎችም ድምጻውያን አቀንቅነዋል። ድምጻውያኑ አልበም ከለቀቁ በኋላ ለአልበም ምርቃት ያዘጋጇቸው ኮንሰርቶችም አድማጮችን የሳቡ ነበሩ። ለአብነት የጃኖ ባንድ "ለራስህ ነው" ኮንሰርት ይገኝበታል። በሙዚቃ አድማጮች የተወደዱ፣ ሙዚቀኞች የሚሸለሙባቸው "ለዛ"ን የመሰሉ ዓመታዊ የሙዚቃ ውድድሮችም ሳይጠቀሱ አይታለፉም። ጥቅምት 11፣ 2010 ዓ. ም. በግዮን ሆቴል የተካሄደው "ቢራቢሮ" ኮንሰርት ከባህር ማዶ የኤሌክትሮኒክ ሙዚቀኞች መካከል ቶም ስዎንና ኢትዮጵያዊው ሮፍናን የተጣመሩበት ነበር። አንጋፋው መሀሙድ አህመድና አብዱ ኪያር በአንድ መድረክ ያቀነቀኑበት "ኢትዮጵያዊ ኮንሰርት 2" ሰኔ 23፣ 2010 ዓ. ም. በቃና ስቱድዮ አዳራሽ ተካሂዷል። ከባለፉት ዓመታት በተለዩ ኮንሰርቶችና ፌስቲቫሎች ከአዲስ አበባ ውጪ የተካሄዱበት ዓመት ነው። በቢሾፍቱ የተከናወነው "ኮረንቲ"ን ጨምሮ በአርባ ምንጭና ሌሎችም ከተሞች ሙዚቃና ፌስቲቫል ቀርቧል። ባለፈው ዓመት "ጊዜ 1" በሚል የተጀመረው ኮንሰርት "ጊዜ 2" በሚልም ቀጥሏል። "ጊዜ 2" ጥቅምት 18፣ 2010 ዓ. ም. በሚሊንየም አዳራሽ ሲካሄድ፣ ናይጄሪያዊው ዊዝኪድ አንዲሁም አሊ ቢራ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ አብነት አጎናፍር፣ አብርሀም ገብረመድህንና ሌሎችም ድምጻውያን ዘፍነዋል። ኃይሉ መርጊያ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙዚቃ ይጫወት በነበረበት ወቅት የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። አሁን በአሜሪካ እየኖረም ቢሆን ግን ሙዚቃ ማቀናበሩን አልተውም። ባለፉት ዓመታት የባህር ማዶ ሙዚቀኞች በተለይም ዐውደ ዓመት አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ ይጋበዙ ነበር። በዚህ ዓመት ብዙ ሙዚቀኞች ባይመጡም፤ የልደት በአልን (ገና) አስታከው ወደ አዲስ አበባ ብቅ ያሉት የሞርጋን ሄሪቴጅ ወንድማማቾች፤ በኤቪ ክለብ ለልደት በአል ዋዜማ ማቀንቀናቸው ይታወሳል። "ሚውዚክ ፎር ፒስ" ወይም "ሙዚቃ ለሰላም " በሚል ጥር 16፣ 2010 ዓ. ም. በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ (የፈረንሳይ ባህል ማዕከል) የተካሄደው ኮንሰርት ኢትዮጵያውያኑን ፀደንያ ገብረማርቆስና ሔኖክ መሀሪን ጨምሮ የኬንያ፣ የብሩንዲና የደቡብ ሱዳን ሙዚቀኞችም የተሳተፉበት ነበር። ዩቲዩብ ላይ በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ተቀባይነት ካገኙ የሙዚቃ ቪድዮዎች የወንዲ ማክ "አባ ገዳ" (9.6 ሚሊየን ተመልካች)፣ የሰላማዊት ዩሀንስ "ሀነን" (8.3 ሚሊየን ተመልካች)፣ የያሬድ ነጉ "ዘለላዬ"(7.6 ሚሊየን ተመልካች) ይገኙበታል። "ሆሄ" እና "ኢትዮጵያ ሆይ" የሥነ ጽሑፉ ዘርፍ እንዳለፉት ዓመታት በርካታ የወግና የግጥም እንዲሁም ኢ-ልቦለድ መጻሕፍት ለህትመት የበቁበት ነው። ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ ተከትሎ የወጡ መጻሕፍት ገበያውን አጨናንቀው ከርመዋል። በሌላ በኩል የሳይንስና የጤና መጻሕፍት በስፋት ተነባቢነት ያገኙበትም ዓመት ነው። በጤናው ዘርፍ በአእምሮ ዝግመት ዙሪያ የሚያጠነጥነው የዶ/ር ዮናስ ባህረ ጥበብ "አይኔን ተመልከተኝ"፤ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ "ግርምተ ሳይቴክ" ተነበዋል። ዓመታዊ የመጻሕፍት ዐውደ ርዕዮች፤ የመጻሕፍ ሽያጭና ሥነ ጽሑፋዊ ውይይት አስተናግደዋል። በሥነ ጽሑፉ ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱም በመድረኮቹ ተመስግነዋል። "ፍቅር እስከ መቃብር"ን በአይፎን 7?'' የክረምት መምጣትን አስመልክተው ከተሰናዱ የመጻሕፍት ዐውደ ርዕዮች ውስጥ በኤግዚብሽን ማዕከል ከሐምሌ 26 እስከ 30፣ 2010 ዓ. ም. የተከናወነው ንባብ ለሕይወትና የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር የሰኔ 1 የንባብ ቀንን ተከትሎ ለስምንት ቀናት በአራት ኪሎ ጎዳና ያካሄደው ዐውደ ርዕይ ይጠቀሳሉ። በርካታ መጻሕፍት አሳታሚዎች፣ አከፋፋዮችና ሻጮች የተገኙበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዐውደ ርዕይ፤ እንዲሁም እንደ እነሆ መጻሕፍት ቤት ባሉ የግል ተቋሞች ተነሳሽነት በየወሩ ማገባደጃ የተከናወኑ ዐውደ ርዕዮችም አይዘነጉም። ዘንድሮ እንደ "ሰምና ወርቅ" ያሉ አዳዲስ የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች የተጠናከሩበት፤ እንደ "ግጥምን በጃዝ" ያሉ የጥበብ መድረኮች ደግሞ ቀጣይነታቸውን ያረጋረጡበት ነበር። የመጽሐፍ ሻጩ ተስፋዬ አዳልን እድሜ ጠገብ የጽድ መጻሕፍት ቤት ለመታደግ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የተከናወነው የሥነ ጽሑፍ መሰናዶ ከዓመቱ ክንውኖችም አንዱ ነው። • ዕድሜ ጠገቧ የጥድ መፃሕፍት ቤት መደብር ትውስታ በእናት ማስታወቂያ እና በጎተ ኢንስቲትዩት (የጀርመን ባሕል ማዕከል) እንዲሁም በሚውዚክ ሜይ ዴይ የሚዘጋጁት ወርሀዊ የሥነ ጽሑፍ ውይይቶች የመጻሕፍት ይዘት የተፈተሸባቸው ናቸው። ከመስከረም አንስቶ በየወሩ በተካሄዱት መሰናዶዎች ዲስኩር፣ ወግ፣ ተውኔትና ግጥም ቀርቧል። ነቢይ መኮንን፣ ይታገሱ ጌትነት እና አለማየሁ ታደሰ ከተጋባዦቹ መካካል ነበሩ። በዓመቱ ከወጡ መጻሕፍት የአለማየሁ ገላጋይ "መለያየት ሞት ነው"፣ የክፍሉ ታደሰ "ኢትዮጵያ ሆይ"፣ የቆንጂት ብርሃን "ያላረፉ ነፍሶች"፣ የአበበ ካብትይመር "ንውዘት" እና የሰናይት ፍቃዴ "ማራ" ይጠቀሳሉ። "ፍቅፋቂ" የተሰኘው የሕይወት እምሻው የወጎችና ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ የታተመውም በዚሁ ዓመት ነበር። የአዳም ረታ "አፍ" መጋቢት 11፣ 2010 ዓ. ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም "የትውልድ አደራ" መጋቢት 7፣ 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ተመርቀው ለንባብ በቅተዋል። • በእውቀቱ ስዩም፣ አለማየሁ ገላጋይና ዳንኤል ወርቁ ተሸለሙ በሥነ ጽሑፉ ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ጸሐፍት የተሸለሙበት 'ሆሄ' የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ከዓመቱ መርሀ ግብሮች ይጠቀሳል። በወርሀ ሐምሌ የተከናወነው ሽልማቱ በቀጣይ ዓመታትም ይዘልቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከ"አብዮት እንደ በረከት" ወደ "ጥበብ በአደባባይ" ዓመታት ባስቆጠሩ ጋለሪዎች እንዲሁም በቅርቡ ብቅ ብቅ ባሉትም የሥዕልና የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕዮች የታዩበት ዓመት ነው። በአለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምሕርት ቤት የተካሄደው የቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ዓመታዊ ዐውደ ርዕይ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በሥነ ጥበብ ትምህርት ቤቱ በወርሀ የካቲት "ሊቶግራፊ፤ ፕሪንቲንግ ዊዝ ስቶን" የተሰኘና በህትመት ጥበብ ላይ ያተኮረ ዐውደ ርዕይ መከናወኑ አይዘነጋም። ዓመቱ የአንጋፋዎቹ ሠዓሊያን ታደሰ መስፍን "ፒላርስ ኦፍ ላይፍ፤ ዘ ፓወር ኤንድ ግሬስ ኦፍ ማርኬት ላይፍ"፣ የጥበበ ተርፋ "ኢንዱሪንግ ስፒሪት" እና የበቀለ መኮንን (ተባባሪ ፕሮፌሰር) "ባሩድና ብርጉድ" ዐውደ ርዕዮች የታዩበት ነበር። • "ሀገሬ ራሱ በድንቅ ተቃርኖ ውስጥ ተዛንቃ ስላለች ሥራዎቼም እንደዛ ናቸው" ዓመቱ የነቢላ አብዱልመሊክ "አፍሮ ትሮተር ዳየሪስ አዲስ- ካርቱም - ማዳጋስካር" የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ እና የስናፍቅሽ ዘለቀ "ራስን ፍለጋ" የሥዕል ዐውደ ርዕይ የተስተናገደበትም ነበር። በፈረንሳይ ባህል ማዕከል ለዕይታ ከበቁ ዐውደ ርዕዮች መካከል ከግንቦት 13 እስከ ሰኔ 2፣ 2010 ዓ. ም. የዘለቀው የለይኩን ናሁሰናይ "ነጭ መስመር" አንዱ ነው። በቅርቡ በተከፈተው ፈንድቃ ጋለሪ የሮቤል ተመስገን "ተንሳፋፊ ጀበናዎች" ዐውደ ርዕይ ታይቷል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨረ የመጣው የግል ጋለሪዎች ለሥነ ጥበቡ ቦታ በመስጠት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ማሳያም ይሆናል። ሠዓሊ ቸርነት ወልደገብርኤል በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ለአንድ ወር እየሰራ እንዲኖር (በእንግሊዘኛ ሬዚደንሲ) ተሰጥቶት ነበር። ሲጠናቀቅም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ ያተኮረ "አብዮት እንደ በረከት" የተሰኘ ዐውደ ርዕይ አዘጋጅቶ ነበር። ከህዳር 22፣ 2010 ዓ. ም. ጀምሮም በአካዳሚው ታይቷል። • ከ'ሶፍትዌር' ቀማሪነት ወደ ሥነ-ጥበብ ባለሟልነት በዘመናዊ የሥነ ጥበባት ሙዝየም የገብረክርስቶስ ደስታ ማዕከል፤ የሥነ ጥበብ ዐውደ ርዕዮች ብቻ ሳይሆን ውይቶቶችም ተካሂደዋል። የጥበብ አፍቃሪዎች ከሙያተኞች ጋር የተገናኙባቸው መድረኮች ነበሩ። በማዕከሉ ከተካሄዱ ውይይቶች ግንቦት 14፣ 2010 ዓ. ም. የተካሄደው "ምን ነበረ?" ይጠቀሳል። ኤልሳቤጥ ወልደጊዎርጊስ (ዶ/ር)፣ ሮቤል ተመስገን እና ሔኖክ መልካምዘር አወያዮች ነበሩ። ሔኖክ መልካምዘር ከመጋቢት 1፣ 2010 ዓ. ም. ጀምሮ በጠልሰም ላይ ያተኮረውን "ጠልሰማዊ ጥበብ" ዐውደ ርዕይም አቅርቧል። "ጥበብ በአደባባይ" የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው መርሀ ግብር ሙዚቃና ሥነ ጥበብ የተጣመሩበት ነበር። ሀሳቡ የጥበብን ስራዎችን ከጋለሪ አውጥቶ ማህበረሰቡ ባለበት ማድረስ ነው። የጎዳና ላይ ጥበብ ብዙም ባልተለመደበት ኢትዮጵያ መካሄዱ የሚበረታታ ጅማሮ ነው። "ጥበብ በአደባባይ" የተጀመረው ሚያዝያ 27 ሲሆን እስከ ግንቦት 19፣ 2010 ዓ. ም. በስድስት ኪሎ፣ በመገናኛ፣ በቦሌ መድሀኔአለም፣ በመስቀል አደባባይና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አካባቢ ጠቢባን እየተዘዋወሩ ለማህበረሰቡ ስራቸውን አሳይዋል። አዲስ የቪድዮ ስነ ጥበብ ፌስቲቫል በኢትዮጵያ ብዙም እውቅና ያላገኘውን የቪድዮ ስነ ጥበብ ለማሳወቅ ከጋለሪዎች እስከ ጎዳናና ጠጅ ቤት ድረስም ዘልቋል። በኢትዮጵያውያንና በሌሎችም ሀገሮች የቪድዮ ስነ ጥበብ ባለሙያዎች የተዘጋጁ ቪድዮዎች በፈንድቃ ጋለሪ፣ በአዲስ አበባ ሙዚየም፣ በብሔራዊ ቴአትር ጋለሪና በጅማ ጠጅ ቤት ታይተዋል። "ኮንቴምፕረሪ ናይትስ" በሚል ዘንድሮ የተጀመረው ወርሀዊ መሰናዶ፤ ዘመናዊ ሥነ ጥበብን ያማከለ ሲሆን፣ በዓመቱ ውስጥ በአዲስ ፋይን አርት ጋለሪና በፈረንሳይ ባህል ማዕከል ተካሂዷል። • ስዕልን በኮምፒውተር ወጣት የዲጂታል ሥነ ጥበብ ሙያተኞች ተሰባስበው ስራዎቻቸውን ያሳዩበት "የሃ" የዲጂታል ሥነ ጥበብ ዐውደ ርዕይ ዓመቱ በአዳዲስ የጥበብ ክንውኖች እንዲታወስ ካደረጉ አንዱ ነው። በሸራተን አዲስ በየዓመቱ የሚካሄደው "የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ" የተሰኘው ዐውደ ርዕይ 10ኛ ዓመቱን ያከበረው በዚሁ ዓመት ነው። ከህዳር 26 እስከ 30፣ 2010 ዓ. ም. በተካሄደው ዐውደ ርዕይ 60 ጠቢባን ስራዎቻቸውን አሳይተዋል። የሥነ ጥበብ ውጤቶች የሚሸጡበት ዓመታዊው "ዘ ቢግ አርት ሴል" ዘንድሮም ቀጥሎ ከ1,000 በላይ ስራዎች ለገበያ ቀርበዋል። "አንቺ ሆዬ" እንዲሁም "እርቅ ይሁን" በ2010 ዓ. ም. ወደ 70 ፊልሞች ወጥተዋል። ቁጥሩ ካለፉት ዓመታት አንጻር አነስተኛ የሚባል ነው። በሌላ በኩል መርካቶ አካባቢ አዲስ ሲኒማ ቤትም መከፈቱ ይጠቀሳል። የግል ሲኒማ ቤቶች በተለያዩ አካባቢዎች መከፈታቸው ከፊልም በተጨማሪ አዳዲስ የፊልም ፌስቲቫሎች ተደራሽነታቸው እንዲሰፋ አግዟል። እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው በሐምሌ ወር ቫድማስ ሲኒማ ቤት "ብላክ ብራዚሊያን ፊልም" የተሰኘ የሁለት ቀን መሰናዶ መዘጋጀቱ ነው። "ስፒሪት ኢን ዘ አይ"፣ "ካሮሊና" እና ሌሎችም ፊልሞች ታይተዋል። በዛው ሲኒማ ቤት "አዲስ ፎቶ ኤንድ ፊልም ፌስት" የተሰኘ የፎቶግራፍና ፊልም ፌስቲቫል ተካሂዷል። ፊልሞች ታይተዋል። ውይይትም ተደርጓል። ግንቦት ውስጥ የተካሄደው "አንቺ ሆዬ" የፌሚኒስት ፊልም ፌስቲቫል ሴታዊትና የሎ ሙቭመንት በጥምረት ያዘጋጁት ሲሆን፣ ለሶስት ቀናት የተምሳሌት ሴቶችን ህይወት የሚያስቃኙ ፊልሞች ታይተዋል። በስንዱ ገብሩና አስናቀች ወርቁ ህይወት ላይ ያተኮሩን ፊልሞች ታይተዋል። • “አንቺሆዬ”፡ የኢትዮጵያዊያት ታሪክን መናገር በዘጋቢ ፊልሞች ላይ ያተኮረው ዓመታዊው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ከኢትዮጵያና ከተቀረው አለም የተውጣጡ ዘጋቢ ፊልሞች በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፣ በጣልያን ባህል ማዕከልና በሀገር ፍቅር ቴአትር የታዩበት ነበር። ከፊልም ሰሪዎች ጋርም ውይይት ተደርጓል። "እርቅ ይሁን" በዓመቱ ውስጥ ለተመልካቾች ከቀረቡ ፊልሞች አንዱ ነው። "ለፍቅር ስል"፣ "አላበድኩም"፣ "ሚስቴን ዳርኳት"፣ "ወደ ኃላ"፣ "እንደ ባልና ሚስት"፣ "አብሳላት"፣ "ባንተ መንገድ" እና "ዘናጭ" በዓመቱ ከወጡ ፊልሞች መካከል ይጠቀሳሉ። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ ፊልም ለፊልም ሰሪዎች እውቅና ከሚሰጡ የሽልማት መሰናዶዎች አንዱ "ጉማ" አምስተኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል "ሰንኮፋ፤ ዘ አርት ኦፍ ስቶሪ ቴሊንግ" በሚል አርዕስት ተካሂዷል። በታሪክ ነገራ ላይ ያተኮረው ፌስቲቫሉ በፊልም ሰሪዎች መካከል ውይይት በማድረግና ባለፈው ዓመት ከወጡ ፊልሞች የተመረጡትን በመሸለም ተጠናቋል። በተጨማሪም የሀገር ውስጥና የውጪ ፊልሞች በቫድማስ ሲኒማ፣ በፈረንሳይ ባህል ማዕከልና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ታይተዋል። በማንተጋፍቶት ስለሺ ተፅፎ የተሰናዳው ግርታ ፊልም በቅርቡ በቤልጂየም በተዘጋጀ የአፍሪካ ፊልም ፌስቲቫል ላይ አሸናፊ ሆኗል። በዋነኛነት የፈረንሳይ፣ የጣልያንና የጀርመን ባህል ማዕከሎች የተለያዩ ሀገራት ፊልሞችን በማምጣት ያሳዩበትም ዓመት ነው። ዓመታዊው የአውሮፓ ፊልም ፌስቲቫል እንዳለ ሆኖ፤ ሌሎችም የምዕራቡና የምስራቁ አለም ፊልሞች የታዩባቸው ፌስቲቫሎች ተከናውነዋል። ዓመቱ ሲጠቃለል. . . በዓመቱ ውስጥ ከተከናወኑ የጥበብ መሰናዶዎች በተጨማሪ ማህበራዊ ጉዳዮችን በጥበብ የዳሰሱም ይገኙበታል። ሜላት የተባለች የኩላሊት ህመም የገጠማት ወጣትን ለመታደግ መጋቢት 20፣ 2010 ዓ. ም. "ለሜላት እኔም አለሁላት" የተባለ ኮንሰርት ተካሂዶ ነበር። ከኮንሰርቱ የተገኘውን ገቢ ለህክምና ወጪ እንድታውለው ያለመ ነበር። መጋቢት ወር ላይ ከኢትዮጵያና ሌሎችም የአፍሪካ ሀገሮች የተውጣጡ የሰርከስ ሙያተኞች የሰርከስ ትርኢት ያሳዩበት "አፍሪካን ሰርከስ አርትስ ፌስቲቫል" በመኮንኖች ክበብ ተካሂዷል። የህጻናት መዝናኛ እንዲሁም ምግብና መጠጥም ቀርቦ ነበር። "ዲዛይን ዊክ አዲስ" የሥነ ህንጻ ዲዛይን፣ የልብስ ዲዛይን፣ ምግብ፣ መጠጥና መዋቢያ ምርቶችም የቀረቡበት ነበር። በተያያዥ በፋሽን ዘርፍ ተጠቃሽ ከሆኑ ትርኢቶች መካከል "ዘ ባግ ሾው"፣ "ሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ" እና "አፍሪካን ሞዛይክ" ይገኙበታል። ታላቁ ሩጫን በማስመልከት የተሰናዳው "ግሬት ኢትዮጵያን ኮንሰርት" ህዳር ወር ላይ ተካሂዷል። ከኢትዮጵያ ንዋይ ደበበና ማዲንጎ አፈወርቅ ከውጪ ሀገር ሉችያኖ፣ ካሊ ፒ እና ቲዎኒ በግዮን ሆቴል ያቀነቀኑበት ነበር። ወቅት ተኮር ከሆኑ ሁነቶች በዓመቱ መግቢያ ላይ የነበረውና ብርዳማውን ጥቅምት ያማከለው "በጥቅምት አንድ አጥንት" የስጋና ቢራ ፌስቲቫል ተጠቃሽ ነው። በዓመቱ ማገባደጃ ደግሞ የትምህርት መጀመርን ያስታከከው "አንድ እሽግ ለአንድ ልጅ" ተካሂዷል። የትምህርት መሳሪያ ለማሟላት አቅማቸው ያልፈቀደላቸው ታዳጊዎችን መርዳት ላይ ያተኮረ ነበር።
news-49846261
https://www.bbc.com/amharic/news-49846261
የትራምፕን መረጃ ያሾለከው 'የሲአይኤ መኮንን' ነው ተባለ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ብዙ መሰናክል አልፈዋል። ይህኛው ፈተና ግን ከስከዛሬዎቹ ሁሉ የከፋ ነው ይላሉ ተንታኞች።
የቅድመ ክስ ምርመራ ፋይሉ የተከፈተባቸው ከዩክሬኑ አቻቸው ጋር አደረጉት የተባለውን 'ያልተገባ' የስልክ ውይይት ተከትሎ ነው። የድራማው አጭር የጊዜ ሰሌዳ የሚከተለውን ይመስላል፦ ጁላይ 18፡ ትራምፕ የዋይት ሃውስ ረዳታቸውን 400 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋን የወታደራዊ እርዳታ ለጊዜው ለዩክሬን እንዳይሰጥ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ትዕዛዝ ሰጡ። ጁላይ 25፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የዩክሬኑን አቻቸውን ለ30 ደቂቃ ያህል በስልክ አነጋገሩ። ሴፕቴምበር 9፡ ኮንግረሱ አንድ የተጠናቀረ መረጃ ደረሰው፤ መረጃው ትራምፕ ባደረጉት የስልክ ልውውጥ አገርን አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት መፈጸማቸውን የሚያትትና አስደንጋጭ ነበር። የስልክ ልውውጡ መሐል ትራምፕ በመጪው ምርጫ ተቀናቃኛቸው እንደሚሆኑ የሚጠበቁትን ጆ ባይደንን አንዳች ጠልፎ የሚጥልላቸውን የወንጀል ቅንጣት እንዲያፈላልጉላቸው ለዩክሬኑ አቻቸው በውለታ መልክ ሲጠይቋቸው ይሰማል። •ትራምፕ የሕንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር አሞካሹ የኮንግረስ ኢንተለጀንስ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር አዳም ሺፍ የደህንነት መሥሪያ ቤቱን ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጆሴፍ ማጓርን በጥያቄ ማጣደፍ ከመጀመራቸው በፊት በትራምፕና በዩክሬኑ ዜለንስኪ መካከል የተደረገው ቃለ ምልልስ የሚከተለውን ይመስል ነበር ብለዋል፡- ትራምፕ፦ "ከኛ ምን እንደምትፈልግ ሰማሁ። እኔ ደግሞ በምላሹ ካንተ ትንሽ ውለታ ቢጤ እሻለሁ። በዋናነት ተቀናቃኜን ጭቃ እንድትቀባልኝ ነው የምፈልገው፤ መቼስ ይገባሃል ማንን ማለቴ እንደሆነ....። ዜለንስኪ፦ "...የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" •ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በእንግሊዝ የክብር ማስታወሻ ምልክቶች ተቀመጠላቸው የትራምፕን ስልክ ማን 'ጠለፈው'? በእርግጥ የትራምፕ ስልክ አልተጠለፈም። ሆኖም ከቅርብ ሰዎቻቸው አንዱ የድምጽ ልውውጡን ይዘት ሳያሾልክ አልቀረም። አልያም በርካታ የዋይት ሃወስ ሠራተኞች መረጃ ያቀበሉት ባልደረባ ሳይኖር አልቀረም። በመሪዎች መካከል የስልክ ልውውጥ ሲኖር የተለመደው ሥርዓት የሚከተለውን ይመስላል። የፕሬዝዳንቱ ረዳቶች እና የዋይት ሃውስ ባልደረቦች እንዲሁም የደህንነት መኮንኖች አብረው ይቀመጣሉ። አብረው ባይቀመጡ እንኳ ባሉበት ክፍል ሆነው ልውውጡን ሊያዳምጡ ይችላሉ። የሥራ መደባቸው ይህንን ለማድረግ የሚያስችላቸው ብቻ ናቸው ታዲያ። በዋይት ሃውስ የስልክ ልውውጦችን የመቅዳት ባሕል የለም። ሆኖም በአጭር በአጭሩ ማስታወሻ የሚይዙ ረዳቶች ሁልጊዜም በተጠንቀቅ ይኖራሉ። የስልክ ልውውጦች የጽሑፍ ቅጂና ዋንኛ ጨመቅ በኮምፒውተር ውስጥ ይቀመጣል። የዋይት ሐውስ ምሥጢረኛው ክፍል 'ሲቺዌሽን ሩም' ፕሬዝዳንቱ ስልክ የሚደውሉት ከዝነኛው "ሲቺዌሽን ሩም" ነው። • “በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማርን ዛሬም፣ ነገም፣ ወደፊትም የምከራከርበት ነው” ገነት ዘውዴ [ዶ/ር] የዋይት ሃውሱ "ሲቺዌሽን ሩም" እንደ ጎርጎሳውያኑ በ1961 የተሠራ ቢሮ ነው። እጅግ ምሥጢራዊ ውይይቶች የሚካሄዱበት የምድር ቤት ሲሆን ከተፈቀደላቸው ባለሥልጣናት ውጭ በየትኛው ደረጃ ያሉ ሹመኞች እንኳ ቢሆኑ እንዲሁ ዘው የሚሉበት ክፍል አይደለም። ብዙዎቹ እጅግ ቁልፍ የሚባሉ የስልክ ጥሪዎች መነሻም ከዚሁ ክፍል ነው። ለምሳሌ አገሪቱ እጅግ ወሳኝ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ስታካሄድ መሪዎቹና ከፍተኛ ወታደራዊ የደህንነት መኮንኖች ክትትልና መመሪያ የሚሰጡት ከዚሁ ክፍል ነው። ለምሳሌ ባራክ ኦባማ የኦሳማ ቢንላደንን ግድያና የመጨረሻ ሰዓት ልብ አንጠልጣይ ድራማን በቀጥታ በተጠንቀቅ የተከታተሉበት ክፍል ይኸው "ሲቺዌሽን ሩም" ነው። አሁን ጥያቄው ትራምፕ ያደረጉት የስልክ ልውውጥ እንዴት ከዚህ ክፍል ሾለከ የሚል ነው። ለጊዜው ምሥጢር አውጪው ከየት ሆኖ ይህንን መረጃ አሾለከ የሚለው አልተመለሰም። ከበርካታ የዋይት ሐውስ ሰዎች የተባለውን መረጃ እንዳጠናቀረ ግን ተገምቷል። ይህ በሁለቱ መሪዎች መሀከል የተደረገውን የድምጽ ልውውጥ ይዘትን አሳልፈው የሰጠው ሰው ማንነት እስካሁን አልተገለጸም። አንድ ሰው ይሁን በርካቶች ምንም የተባለ ነገር የለም። "ምሥጢሩ ያፈተለከው ከሲአይኤ መኮንን ነው" ዛሬ ጠዋት (አርብ) እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደዘገቡት የትራምፕን ያልተገባ የስልክ ልውውጥ አጠናቅሮ ለሚመለከተው አካል እንዲሾልክ ያደረገው አንድ የሲአይኤ መኮንን ነው። መኮንኑ በስም ባይጠቀስም በአንድ ወቅት በዋይት ሐውስ ውስጥ ይሠራ እንደነበር ተመላክቷል። ይህ በትራምፕ ተግባር ላይ ቅሬታ ያጠናቀረው ግለሰብ የዋይት ሐውስ ሰዎች የትራምፕን ድርጊት ለመሸፋፈን ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም ይላል። ትራምፕ በበኩላቸው ምሥጢራቸውን አሳልፎ ለዚህ ግለሰብ የሰጠውን የዋይት ሀውስ ባልደረባ ማን እንደሆነ ለማወቅ ጓጉተዋል። "ይህ ሰው ለሰላዮች ቅርብ የሆነ መሆን አለበት" ሲሉም ተደምጠዋል። "ማነው የሰጠው ግን? ማወቅ እፈልጋለሁ። መረጃውን ማን እንዳሾለከለት ማወቅ እፈልጋለሁ፤ ምክንያቱም ያ ሰው ሰላይ ነው ሊሆን የሚችለው" ሲሉ ትራምፕ የተናገሩትን ድምጽ ሎሳንጀለስ ታይመስ እጄ ገብቷል ብሏል ዛሬ። በዚህም ንግግራቸው ሌላ የትችት መአት ዘንቦባቸዋል ትራምፕ። ይህ ቅሬታ አጠናቃሪ እንደጠቆመው የሁለቱ መሪዎች የስልክ ልውውጥ የጽሑፍ ቅጂ በተለመደው የኮምፒውተር ቋት እንዲቀመጥ አልተደረገም። ከዚያ ይልቅ እጅግ ከፍተኛ ምሥጢር በሚጠራቀምበት ሌላ ኮምፒውተር እንዲቆይ ነው የተመረጠው። ይህም ነገሩን ለመደበቅ የተደረገ ነው ይላል። ዛሬ የወጣው መረጃ እንደሚያሳያው ከሆነ ይህ የሲአይኤ መኮንን የስልክ ልውውጡን በቀጥታ የሰማ ሰው አለመሆኑን ነው። ሆኖም ከተለያዩ ምንጮች የደረሰውን መረጃ ማጠናቀሩንና የደረሱትን መረጃዎች በተለያየ መንገዱን ማመሳከሩን በቅሬታ ዶሴው አብራርቷል። ስለ ትራምፕ ማን ምን አለ? የታችኛው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ናንሲ ፒሎሲ "ዶናልድ ትራምፕ አገራቸውን በሀቅ ለማገልገል የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ እምነት የሚጣልባቸው ሰው አይደሉም" ብለዋል። ጆ ባይደን በበኩላቸው "ለጊዜው አገሬ ያላት ፕሬዝዳንት ለሥልጣኔ ለከት የለውም ብሎ የሚያምን ነው" ብለዋል በትዊተር ሰሌዳቸው። ኤልዛቤት ዋረን በበኩላቸው " ትራምፕ በዋሺንግተን የተጨማለቀው አስተዳደር አንድ ገጽታ ብቻ ናቸው"ሲሉ ጽፈዋል። ጆ ባይደን እዚህ ጉዳይ ውስጥ እንዴት ገቡ? የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንትና ቀጣዩ የትራምፕ ተቀናቃኝ ጆ ባይደን በልጃቸው ምክንያት ነው ከዩክሬን ጉዳዩ ጋር የተያያዙት። ልጃቸው ሀንተር ባይደን ለአንድ የዩክሬን የጋዝ ኩባንያ የቦርድ ሊቀመንበር ነበር። ትራምፕና ጠበቃቸው ሩዲ ጊሊያኒ ጆ ባይደን በአንዳች የሙስና ተግባር እጃቸውን አስገብተዋል ብለው ያምናሉ። •ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ስእል በአንዲት አዛውንት ማእድ ቤት ተገኘ ባይደን ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሉ ለዩክሬን መሰጠት ያለበትን እርዳታ በመያዝ ልጃቸው በቦርድ አባልነት የሚመራውን የጋዝ ኩባንያ ጫና ውስጥ በመክተት እንዲሁም ምርመራ እንዳይደረግበት በማድረግ ለልጃቸው ውለታ ውለውለታል ብለው ይከሳሉ። ለዚህ ክስ ግን ተጨባጭ መረጃ ቀርቦ አያውቅም። አሜሪካ ከሳ ከሥልጣን ያሰናበተችው ፐሬዝዳንት አላት? አሜሪካ በታሪኳ ሁለት መሪዎቿን ከ'ሳ ታውቃለች። ቢል ክሊንተንና አንድሩ ጆንሰን። ቢል ክሊንትን በጎርጎሳውያኑ 1998 በታችኛው ምክር ቤት ክስ ተከፍቶባቸው በ1999 በሴኔት ውድቅ ሆኖላቸዋል። ይህ ክስ የፍርድ ሂደትን በማደናቀፍ እና ያን ጊዜ የዋይት ሀውስ ተለማማጅ መኮንን የነበረችውን ሞኒካ ልውኒስኪ ጋር የነበራቸውን ጾታዊ ግንኙነት በተመለከተ ዋሽተዋል በሚል ነው። አንድሩ ጆንሰን በጎርጎሳውያኑ 1968 የጦር ሚኒስትራቸውን አግባብ ባልሆነ መንገድ አባረዋል በሚል ነው ክስ የተከፈተባቸው፤ እሳቸውም የታችኛው ምክር ቤት ክሱን ወደ ላይኛው ምክር ቤት መርቶባቸው ሴኔት ግን 2/3ኛ ድምጽ ሳያገኝባቸው ቀርቷል። ሪቻርድ ኒክሰን በ1974 በዋተርጌት ቅሌት ክስ ቢመሰረትባቸውም ቀድመው ሥልጣን ለቀዋል። አወዛጋቢው ትራምፕ ይህንን ረዥም ሂደት ያለውን የክስ ሂደት ምናልባት በሪፐብሊካኖች በተሞላው ሴኔት የ2/3ኛ የአብላጫ ድምጽ ማጣት ቢያልፉት እንጂ እጅግ ጥልቅ ወደሆነ ቅርቃር ውስጥ ስለመግባታቸው ግን ተንታኞች ከወዲሁ እየተናገሩ ነው። የትራምፕ መጨረሻ ተቃርቦ ይሆን?
43695355
https://www.bbc.com/amharic/43695355
የአንዱ እርግማን ለአንዱ ምርቃን፡ ኢትዮጵያን መጠጊያ ያደረጉ ስደተኞች ታሪክ
ብዙ ኢትዮጵያውያን የተሻለ ህይወትን ፍለጋ ረሀብ፣ ቁር ሳይበግራቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ለቀናት ይባስ ሲልም ለወራት በእግራቸው ተጉዘው ወደ ሌላ አገር ይሻገራሉ።
በዚህ እልህ አስጨራሽና ፈታኝ ጉዞም በአሰቃቂ ሁኔታ ብዙዎች ባህር ውስጥ ሰምጠዋል፤ የሰውነት አካላቸው ተሽጧል፤ ተስፋቸው ሳይሞላ ሞተዋል፤ ሌሎችም ለማይሽር አካላዊና ህሊናዊ ጠባሳ ተዳርገዋል። እዛም ከደረሱ በኋላ የከፋ ህይወት የሚያጋጥማቸው ብዙ ናቸው። በተለይም ወደ አረብ አገር የሚሄዱት በአሰሪዎች መደብደብ፣ መደፈር፣የጉልበት ብዝበዛ ፣ክፍያ መከልከልና ሌሎችም አስከፊ ስቃዮች የበርካታ ኢትዮጵያዊያን እጣ ነው። የአንዱ ምርቃን ለአንዱ እርግማን ነው እንዲሉ ባለው ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ሁኔታ ተማረው ከኢትዮጵያ እየተገፉ ሚሊዮኖች ወደ ተለያዩ ሀገሮች ይሰደዳሉ ፤ በተቃራኒው ኢትዮጵያ ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ ወደ ሃያ የሚሆኑ ሀገራት ስደተኞች መጠጊያ ናት። ስደተኞቹ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል ስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የህክምና ችግር ፣ በተለያዩ ጦርነቶች አልፈው ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸው ለአዕምሮ ህመም የተጋለጡ እንዲሁም ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውም በከተማ ስደተኝነት ተመዝግበው አዲስ አበባ ይኖራሉ። የከተማ ስደተኛ ማን ሊሆን ይችላል የሚለውን የሚወስነው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሲሆን በስደተኞች ዙሪያም ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር አብረው ይሰራሉ። አስረሳሽ ስራው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ልማትና ተራድኦ ኮሚሽን የስደተኞችና ተመላሾች መምሪያ የማህበራዊ አገልግሎትና የፆታዊ ጥቃት መከላከል ኃላፊ ስትሆን በሙያዋም ነርስና የሳይኮሎጂም ባለሙያ ናት። በዚህ መምሪያ የሚረዱ ወደ 4500 ስደተኞች ሲኖሩ ከህክምና ድጋፍ በተጨማሪ ገንዘብም በቤተሰባቸው መጠን መሰረት በየወሩ እንደሚሰጣቸውም ትናገራለች። ብዙዎች በጦርነት ከፈራረሱ ኃገሮች ከመምጣታቸው አንፃር ስደተኞቹ ከፍተኛ የሆነ አካላዊ እንዲሁም አዕምሯዊ ጉዳት ደርሶባቸው እንደሚመጡ አስረሳሽ ትናገራለች። አንዳንድ ታሪኮች ለመስማት የሚዘገንኑና ሰብዓዊነትን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ናቸው። ከነዚህም ውስጥ የሲናይ በረሃን ስታቋርጥ በወታደሮች ተይዛ ለስድስት ወራት ያህል በእሳት መጠበስ፣ በኤሌክትሪክ መቃጠልና መደፈር የደረሰባት 18 ዓመት ያልሆናት ልጅ በደረሰባት በደልና ስቃይ የአዕምሮ ችግር እንዲሁም አካላዊ መናጋቶች እንደደረሱባት አስረሳሽ ትናገራለች። ባዕድ ነገር ማህፀኗ ውስጥ ተጨምሮባት ማህፀኗ በቀዶ ጥገና የወጣላት ሴት፤ ሌላኛው ህፃን ወንድ ደግሞ አባቱን፣ እናቱንና ወንድሙን ከገደሉ በኋላ እሱን ወታደሮች ደፍረውት ለማያገግም የአካል እንዲሁም የአእምሮ ጠባሳ ጥሎበት እንዳለፈ አስረሳሽ ትናገራለች። "አንዳንዴ ይህንን የሚያደርጉት ሰዎች ናቸው ወይስ አውሬ ናቸው?" በማለት ትጠይቃለች። ልማትና ተራድኦ ኮሚሽን የስደተኞችና ተመላሾች መምሪያ ግቢ ውስጥ ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኮንጎ፣ ሩዋንዳና ከየመንና ከተለያዩ አገራት የመጡ ስደተኞች በየጥጉ ተቀምጠዋል። ከነዚህም ውስጥ ከኮንጎ ማሲሲ ከተባለች አካባቢ የመጣችው የ32ዓመት ዕድሜ ያላት ፌይዛ ባይንጋና ሳይመን አንዷ ናት። ከነበረችበት መንደርና ከሞቀ ቤቷ የአማፅያን ቡድን ከባሏ ጋር እንደወሰዷትና ጫካ ውስጥ እንደደፈሯት ትናገራለች። በተሰባበረ እንግሊዝኛዋም ልጇ እንዴት እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንደደቡት ትናገራለች። "ባየውም ስቃይ ለስድስት ወራት መናገር አልቻለም ነበር" ትላለች። አሁንም ከአንዳንድ ቃላት በላይ መናገር እንደማይችል የምትገልፀው ፌይዛ ራሱንም መቆጣጠር አይችልም። የደረሰባት ጉዳት ሳያገግም ከሁለት ዓመታት በኋላ አባቷ፣ ወንድሟና ሌሎች ቤተሰቦቿ እንደተገደሉ የሷም ሆነ አካባቢው የነበሩ ቤቶችም እንደተቃጠሉ ትተርካለች። ህይወቷንም ለማትረፍ ሾፌሮችን በመለመን ወደ ዩጋንዳ ተሰደደች። ስደቷ በዚህ አላበቃም፤ አቆራርጣም ወደ ኬንያ ከዚያም በአውቶብስ ተሳፍራ ወደ ኢትዮጵያ ገብታለች ይህ ሁሉ ጥፋት ከመምጣቱ በፊት ጥሩ ህይወት ትኖር እንደነበር የምትናገው ፌይዛ ኢትዮጵያ እስከምትደርስ ድረስ የደረሰባት ግፍ ተነግሮ እንደማያልቅ ትገልፃለች። መጀመሪያ ኢትዮጵያ ስትደርስ አሶሳ አካባቢ የሚገኘውና ሸንኮሌ ተብሎ የሚጠራው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ለጥቂት ጊዜ ከቆየች በኋላ ህመሟ ሲጠና ወደ አዲስ አበባ እንደተላከች ትናገራለች። የከተማ ስደተኛ በመሆኗ 3ሺብር በወር የሚሰጣት ሲሆን ባለው ኑሮ ውድነት አንፃር ምንም በቂ እንዳልሆነ ትናገራለች። " የቤት ኪራይ አዲስ አበባ አይቀመስም፣ ለትራንስፖርት መክፈል አለብኝ። በዚያ ላይ ልጆች አሉኝ እንዲሁም ከፍተኛ ህመም አለብኝ" ትላለች። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የኤድስም በሽተኛ ስትሆን በመደፈሯ ጊዜ የደረሰባት ኢንፌከክሽን ወደ ካንሰር እንደተቀየረም ተነግሯታል። ሌላኛዋ ከኮንጎ የመጣችው ስደተኛ ኩዊን መለስም ታሪክ ተመሳሳይ ነው። ከኮንጎ ከመጣች አስር ዓመት የሆናት ኩዊን የተወለደችው ኢትዮጵያ ነው። ኮንጎ ያደገቸው ኩዊን አባቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ለስራ ለጥቂት አመታት በመኖራቸው ኢትዮጵያ የመወለዷ ምክንያት ሆነ። በተለያዩ ታጣቂዎች የተከፋፈለችውን ኮንጎን አምልጣ አዲስ አበባ የመምጣቷን ታሪክ የምታወራው በለቅሶና በምሬት ነው። "ሰው አልነበርኩም፤ አሁንም በደረሰብኝ ነገር ሰው የሆንኩ አይመስለኝም። ቤተሰቦቼ ተገድለዋል፤ በሚያሳዝን መልኩ ሲገደሉ አይቻለሁ። በሰውነቴ ላይ ያደረሱትን ነገር ዘርዝሬ አልገልፀውም" ትላለች ታጣቂዎች ቤተሰቦቿን ከገደሉ በኋላ እሷንም ደፍረዋት ሞታለች ብለው ጥለዋት እንደሄዱ ትናገራለች። በጊዜው የሜዲሲን ተማሪ የነበረቸው ኩዊን ንግግሯ በሳግና በለቅሶ ይቆራረጣል። "በህይወቴ ማንም የለኝም፤ መንገድ ላይ ወንድሜን የሚመስል ሰው ሳይ መፈጠሬን እጠላለሁ" የምትለው ኩዊን "ኮንጎን ማየት የምፈልገው ካርታ ላይ ብቻ ነው። የኮንጎ መሪ የነበረው ሞቡቱ ሴሴኮ አምባገነን ነው ይላሉ፤ ግን ሰላም ነበርን። ማንም ሊገድለን አይመጣም ነበር" ትላለች። በጉዞዋ ላይ የደረሰባት መከራና ስቃይ ተዘርዝሮ እንደማያልቅ የምትናገረው ኩዊን እሷም በመጀመሪያ የደረሰችው አሶሳ የሚገኘው የቸርኮሌ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ነው። የደም ግፊት፣ አስም እንዲሁም የአዕምሮ መረበሽ ያለባት ኩዊን አብዛኛውን ጊዜ በህይወት የመኖር ተስፋዋ ይሟጠጣል። "አንዳንድ ጊዜ የተለያዩ ጥናታዊ ፊልሞችን ሳይና የኔን ሚመሰል ታሪክ ሳገኝ ብቻየን እንዳልሆንኩ ስረዳ ትንሽ እረጋጋለሁ" ትላለች። በሰው ልጅ ያላት ተስፋ በከፍተኛ ሁኔታ የተሸረሸረ ሲሆን ነገን በጥርጣሬ ብታይም ከ10 ዓመት በኋላ እንደገና ህልሟን ለመኖር የትምህርት እድል አግኝታ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የነርሲንግ ትምህርቷን እየተማረች ነው። ስቃዩ ቢዘረዘር ተወርቶ አያልቅም የምትለው አስረሳሽ ምንም እንኳን ችግሩ የጠለቀና አለም አቀፍ ችግር ቢሆንም ሰዎች ስለ ሰብዓዊነት ቢያስቡ ችግሩን መቀነስ ይቻላል ብላ ታምናለች። ከጊዜ በኋላ አንዳንዶቹ ሴቶች ተስፋቸው አንሰራርቶ የመኖር ተስፋቸው እንዲፈነጥቁ ብዙ ስራ እንደሚያስፈልገውም ትገልፃለች። "ጠንክረው ራሳቸውን ከዚያ ሁኔታ የሚያወጡበትን መንገድ እንሰራለን። የተለያዩ ማማከሮችን ስለሚያገኙ የጤናቸው ሁኔታ ይሻሻላል"ትላለች። ከተለያዩ ድርጅቶችም ጋር በመተባበር የፀጉር ስራ፣ የልብስ ስፌት እንዲሁም የኮምፒውተር ስልጠና በመስጠት ህይወታቸውን ዳግም የሚያስቀጥሉበትን መንገድ እንደሚመቻችም አስረሳሽ ትናገራለች። "ሁሌም የምፀልየው ጥንካሬ እንዲሰጠኝ ነው። ለልጆቼ ትንሽ ጊዜ እንኳን በህይወት ብቆይላቸው ደስ ይለኛል። ሁልጊዜም ቢሆን እግዚአብሄርን አመሰግነዋለሁ" የምትለው ፌይዛህይወቷ አሁን የተረጋጋ እንደሆነም ትገልፃለች። "ኢትዮጵያ የአዕምሮ ዕረፍት አግኝቻለሁ፤ የመሳሪያ ተኩስ አልሰማም፤" ትላለች ፌይዛ ለኩዊንም ከምሬትም ጋር ቢሆን ኢትዮጵያ የመኖር ተስፋን የምታልመው ቦታ ሆኖላታል።
news-53646926
https://www.bbc.com/amharic/news-53646926
የቤት ውስጥ ጥቃት፡ "ባለቤቴ ቢላ ከኪሱ አውጥቶ አፍንጫዬን ቆረጠው"
ከአስር ሳምንታት የማያባራ ስቃይ በኋላ ዛርካ የተስፋ ጭላንጭል ታያት።
"ደስ ብሎኛል። አፍንጫዬ ተመለሰ፣ ጥሩ ነው፣ በጣም ጥሩ ነው" ትላለች ዛርካ የታሸገውን አፍንጫዋን ለሚያክሟትና የቁስሉን ፋሻ እየቀየሩ ላሉት ዶክተሮች። የተሰፋው አፍንጫዋ በፋሻ ቢሸንፍም የረጋ ደም ይታያል። ዛርካም ይህንኑ ፊቷን በእጅ መስታወቷ ትኩር ብላ ትመለከታለች። በአፍጋኒስታን የቤት ውስጥ ጥቃት የተለመደ ነው፤ በከፍተኛ ሁኔታም ይፈፀማል። የተባበሩት መንግሥታት የሥነ ሕዝብ ፈንድ የአገሪቱን መረጃ በመጥቀስ እንዳሰፈረው 87 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ቢያንስ አካላዊ፣ ወሲባዊ እንዲሁም ሥነ ልቦናዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል። ሲከፋም በትዳር አጋሮቻቸው ወይም በወንድ ዘመዶቻቸው አሲድ ይደፋባቸዋል፤ በቢላም ይወጋሉ። የዛርካም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም ባላቤቷ ከኪሱ ቢላ አውጥቶ አፍንጫዋን ቆርጦታል። "ባለቤቴ ሁሉንም ይጠራጠር ነበር" ትላለች ዛርካ። በመጠርጠር ብቻ አያቆምም፤ በሚወነጅላት ሰው እያመካኘም ይደበድባት ነበር። ድበደባ የየቀን ኑሮዋ ነበር። "ሁልጊዜም ሥነ ምግባር የጎደለኝ ሴት እንደሆንኩ ይነግረኝ ነበር። 'ፍፁም ሐሰት ነው' እለው ነበር" ትላለች። የ28 ዓመቷ ዛርካ መደብደቧን ብትለምደውም ይህን ያህል ወደከፋ ደረጃ ይደርሳል ብላ አላሰበችም። ማገገም "ፈቴን በመስታወት ስመለከተው አፍንጫዬ እያገገመ ነው" በማለት ዛርካ ለቢቢሲ ተናግራለች። በማደንዘዣም ለሦስት ሰዓታት ያህል ቀዶ ህክምና አድርጋለች። "ከቀዶ ጥገና በፊት ፊቴ ደስ የማይል ሁኔታ ነበር" ትላለች በሐዘን። በአገሪቱ ካሉ የፕላስቲክ ቀዶ ህክምናና ፊትን እንዲህ መልሶ ማስተካከል ከሚችሉ ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶክተር ዛልማይ ካሃን አህማድዛይም ዛርካ እያሳየችው ባለችው ለውጥ መገረማቸውን ተናግረዋል። "የቀዶ ህክምናው በጥሩ ሁኔታ ተካሂዷል። ምንም ያመረቀዘ ነገርም የለም፤ ሁሉ ጥሩ ነው" በማለት ዶክተር ዛልማይ ተናግረዋል። ለዶክተሩ በባለቤቷ የፊቷ አካል ጎድሎ ለህክምና ስትመጣ ዛርካ የመጀመሪያዋ አይደለችም፤ በርካታ ሴቶች በትዳር አጋሮቻቸው፣ በአባቶቻቸውና በወንድሞቻቸው የፊታቸው ክፍል ተቆርጦ ይመጣሉ። የእስልምና እምነት ሕግጋት የፊት ክፍልን መቆራረጥን በፅኑ ቢቃወምም ይህ ጭካኔ የተሞላው ተግባር በቅድመ እስልምና አፍጋኒስታን ውስጥ ይፈፀም እንደነበር ድርሳናት ያስረዳሉ። ረዥሙ ጉዞ ዛርካ ትውልዷ ከመዲናዋ ካቡል 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ካሪኮት ግዛት ነው። ቤተሰቦቿ ድሆች በመሆናቸው የትምህርት ዕድል አላገኘችም። አካባቢው በታሊባን ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር በመሆኑም ጥቃት በደረሰባት ወቅት በቀላሉ ቀየዋን ለቃ መውጣት አልቻለችም። የግዛቷ ፖለቲከኞችና ታጣቂዎች ተደራድረው ነው ወደ ካቡል ለህክምና መምጣት የቻለችው። በዚያ ወቅትም ዶክተር ዛልማይ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ነበር፤ በሚያሳዝንም ሁኔታ ባለቤታቸውን በኮቪድ-19 አጡ። የ49 ዓመቱ ዶክተር ባለቤታቸውን ጃላላባድ ግዛት ቀብረው ዛርካን ለማከም ወደ ካቡል ተመለሱ። "ለህክምና መጀመሪያ በመጣችበት ወቅት በመጥፎ ሁኔታ ላይ ነበረች። አፍንጫዋ ከመቆረጡ በተጨማሪ ቁስሉም አመርቅዞ ነበር" ይላሉ ዶክተር ዛልማይ። ከሁለት ወራት በፊትም ማመርቀዙን እንዲቆምም የመከላከያ መድኃኒት ሰጧት። ከዚያም በወሩ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ተመለሰች። ዛርካ ቢቢሲ የማገገሟን ሂደት እንዲቀርጽ እንዲሁም ስለደረሰባት ጥቃት በዝርዝርም ለመናገር ፈቃደኛ ነበረች። ባለቤቷም በእሷ እድሜ እንደሆነ የምትናገረው ዛርካ ይተዳደሩም የነበረው በእረኝነት ከሚያገኘው ገቢው ነበር። ለአስር ዓመት ያህል በትዳር ኖረዋል፤ የስድስት ዓመት ልጅም አላቸው። "አጎቴ ነው ለእሱ በልጅነቴ የዳረኝ። በወቅቱ ህፃን ስለነበርኩም ስለ ህይወትም ሆነ ስለ ትዳር የማውቀው ነገር አልነበረም። እድሜዬም በትክክል ምን ያህል እንደሆነ አላውቅም" ትላለች። ስለ ፈቃደኝነቷም ማንም እንዳልጠየቃት ታስታውሳለች። ከዓመታት በኋላም አጎቷ የባለቤቷን እህት ለማግባት በመስማማት ለመለዋወጥ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተገነዘበች። "አጎቴ ለሚስቱ ጥሎሽ መክፈል ስላልቻለ እኔን እንደ ስጦታ እንደሰጠኝ ሰማሁ" ትላለች። በአፍጋኒስታን አንዳንድ ቤተሰቦች ሴት ልጆቻቸውን ለመዳር ከሙሽራው ገንዘብ ይቀበላሉ ቢባልም ይህ ተግባር ህጋዊነት የለውም። ከሠርጋቸውም በኋላ ዛርካ ባለቤቷ እህቶቹን እንደሚደበድብ ተረዳች፤ ነገር ግን ለምን እንደሆነ ብዙ አልገባትም። "አደንዛዥ እፅ አይጠቀምም፤ የአዕምሮ ህመምም የለበትም" ትላለች። "ለህይወቴ ፈራሁ" በዓመታት የትዳር ህይወታቸው ውስጥ ባለቤቷ ሌላ ሚስት ለመጨመር አቅዶ ነበር። ለአንድ ወንድ በርካታ ሚስቶች ማግባት አዲስ ነገር አይደለም። "እንደማይወደኝና ሌላ ሚስት ማግባት እንደሚፈልግ ነገረኝ" በማለት ዛርካ ታስታውሳለች። ነገር ግን ባለቤቷ ለጥሎሽ መከፈል የሚገባውን ገንዘብ ማጠራቀም ባለመቻሉ ተስፋ መቁረጥና ንዴት ተጨምረውበት በየቀኑ የሚፈጽምባት ድብደባ እየከፋ ሄደ። "ያለማቋረጥ ሲደበድበኝ ለህይወቴ እየፈራሁ መጣሁ" ትላለች። አፍንጫዋ ከመቆረጡ በፊትም ድብደባው ሲከፋባት ግንቦት ወር ላይ ወደ አባቷ ዘንድ በመሄድ ነፃ እንዲያወጣት ተማፀነችው። ነገር ግን ያለ እሱ ፈቃድ ወደ አባቷ ጋር በመሄዷ ባለቤቷ ፍለጋ መጣ። "አንድ ምሽት ቤተሰቦቼ ጋር ካሳለፍኩ በኋላ በጠዋት ትልቅ ቢላ ይዞ መጣ። አባቴንም በቢላ እያስፈራራ እንዲሰጠኝ ጠየቀው። አባቴና የአጎቴ ልጅ ምስክሮች ካላመጣ አሳልፈው እንደማይሰጡት ነገሩት" ትላለች ዛርካ። ባለቤቷም ምንም እንደማያደርጋት ቃል ገብቶ ምስክሮች ይዞ መጣ። ነገር ግን ስትመለስ የበለጠ ሁኔታዎች እየከፉ ሄዱ። "ከቤተሰቦቼ ቤት በተመለስኩባት ዕለት ክፉኛ ደበደበኝ፤ ቢላም እያሳየኝ አስፈራራኝ" የምትለው ዛርካ "አፍንጫሽን እቆርጠዋለሁ" ብሎ ስላስፈራራትም ወደጎረቤት ሄዳ ተደበቀች። ጎረቤቶቿ ጣልቃ ገብተው ቢያስጥሏትም ለጊዜው ነበር። ከዚያም ተለማምጦ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት እንደሚወስዳት ቃል ገብቶ ወደ ቤቷ መለሳት። ነገር ግን ጠመንጃ ይዞ የነበረው ባለቤቷ ዛርካን ከቤት ይዞ በመውጣት እየጎተተ ወደ አትክልት ቦታ ወሰዳት። "እየጎተተኝም፤ 'ወደየት ነው የምትሸሺው?' ይለኝ ጀመር። አትክልት ቦታውም አነስ ያለ ነው። ከኪሱም ቢላ አውጥቶ አፍንጫዬን ቆረጠው" ትላለች። የዛርካ ባላቤት አፍንጫዋን የሚቆርጠውም ያለእሱ ፈቃድ ቤተሰቦቿ ቤት በመሄዷ አዋርዳኛለች በሚል ስሜት ነው። አፍንጫዋን ቆርጦም በደም ፊቷና ሰውነቷ በደም እንደተሸፈነ ጥሏት ሄደ። "የተሰማኝን ህመም በቃላት መናገር አልችልም፤ በከፍተኛ ሁኔታም ደም እየፈሰሰኝ ነበር። መተንፈስም አልቻልኩም ነበር" ትላለች ህመሟን በማስታወስ። ጩኸቷን በመስማት በአቅራቢያው የነበሩ ሰዎች ደረሱላት። የተቆረጠው የአፍንጫዋክፍል ተገኝቶ በአካባቢው ወደሚገኝ ጤና ማዕከልም ብትወሰድም ዶክተሩ አፍንጫዋን መልሶ ማያያዝ እንደማይችል ነገራት። ዛክራ ልቧ ተሰበረ፤ ከደረሰባትም አካላዊ ጥቃትም ለማገገምም ሆነ አስቀያሚ ነኝ ከሚለው ስሜት መውጣት አልቻለችም። አባቷና ወንድ ዘመዶቿ ተሰባስበውም የደረሰባትን ጥቃት ለመበቀልም ቢፈልጉትም ባለቤቷን ሊያገኙት አልቻሉም። "'እንዴት እንዲህ አካልሽን ያጎድላል?' ብለው በጣም ተናደዱ። ቢያገኙትም እንደሚገሉት እየነገሩኝ ነበር" የምትለው ዛርካ አባቷና አጎቶቿም ምስክሮች የተባሉት ጋር ሄደው ቁጣቸውን በመግለጽ ጥይት ወደ ሰማይ ተኮሱ። ቤሰቦቿ ባሏን አግኝተው ከመበቀላቸው በፊትም ፖሊስ ባለቤቷን በቁጥጥር ስር አዋለው። ዛርካ በአካባቢው በሚገኘው ሆስፒታል ያደረገችው ህክምና በቂ አልነበረም። ፊቷን በተወሰነ መልኩ የሚያስተካክልላትንም እድል እየተመኘች ነበር። "ምንም አይነት ቀዶ ህክምና እንዲደረግልኝና አፍንጫዬ እንዲመለስ ብቻ ነበር ምኞቴ" ትላለች። ፊቷ በደም ተጨማልቆ የተነሳችው ፎቶም ብዙዎች መጋራታቸውን ተከትሎ የዶክተር ዛልማይን ትኩረት በማግኘቷ በነፃ ሊያክሟት እንደሚችሉ ቃል ገቡ። የምትኖርበት አካባቢ አስተዳደርም ወደ ዋና ከተማዋ ካቡል እንድትሄድ አደረገ። ከዚያም የዶክተር ዛልማይ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ቀዶ ጥገናውን አከናወኑ። ለቀዶ ህክምናው 2 ሺህ ዶላር ያህል ያስወጣት የነበረ ከመሆኑ በተጨማሪ ለመድኃኒት እስከ 500 ዶላር መክፈል ይኖርባት ነበር። በነጻ ባገኘችው ህክምና አካላዊ ገፅታዋን ማስተካከል ቢቻልም ከደረሰባት የሥነ ልቦና ጉዳት በማገገም በራስ መተማመኗን መመለስ ጊዜ የሚጠይቅ ነገር ነው። ልጄስ? አሁን በዚህ ሰዓት በከፍተኛ ሁኔታ እያስጨነቃት ያለው ከባለቤቷ ቤተሰቦች ጋር ያለው የልጇ ሁኔታ ነው። "ልጄ ማሹቅን ለሦስት ወራት ያህል አይኑን አላየሁትም። በጣም ነው የምወደው። ልጄ ከእኔ ጋር እንዲሆን እፈልጋለሁ" ትላለች። የባለቤቷን ጨካኝነትም አለማየቱ ባንድ በኩል አስደስቷታል። ምንም እንኳን ልጇ ከባለቤቷ ቤተሰቦች ጋር እንዳለ ብትሰማም ትክክለኛ አድራሻውን አታውቅም። የእራሷ የሆነ ገቢ ስለሌላትም የአገሪቱ ሕግ የማሳደጉን ኃላፊነት ለባለቤቷ ሰጥቶታል። አሁን ከልጇ ጋር ተለያይቶ መኖሯ ቀን ተሌት እንቅልፍ የሚያሳጣት ጉዳይ ሆኗል። "በጣም ነው የሚናፍቀኝ። ስበላ፣ ስጠጣ፣ ምንም ነገር ሳደርግ በአይኔ ላይ ይመላለስብኛል" ትላለች። የዛርካ አባትና አጎቶቿ ልጁን ለማስመለስም ምንም እቅድ የላቸውም፤ ምክንያቱም ባለቤቷ ልጁን እጠይቃለሁ ብሎ በእሷ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ነገር ሲያስቡ ከፍተኛ ፍራቻ አላቸው። ዛርካ ልጇ አብሯት እንዲኖር ብትፈልግም ነገር ግን ምንም ነገር ቢፈጠር ከባለቤቷ ጋር ድጋሚ በአንድ ቤት መኖር እንደማትፈልግ ታስረዳለች። "ከእሱ ነፃ መሆን ነው የምፈልገው። አብሬው መኖርም ሆነ ስለሱ ማሰብ አልፈልግም። እሱን ስፈታውም ልጄን እንደማይሰጠኝ ሳስብ ጭንቅ፣ ጥብብ ይለኛል" ብላለች በሐዘን በሞላው ድምጽ።
news-51602801
https://www.bbc.com/amharic/news-51602801
መክሊት ሐደሮና ከለላ ሚዛነ ክርስቶስ፡ እያንፀባረቁ ያሉት ኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞች
የተወለዱበትን ቀዬ ለቆ፣ ባህልና አኗኗር ዘዬ፣ ዘመድና ቤተሰብ ትቶ መሰደድ ምን አይነት ስሜት ይኖረው ይሆን?
መክሊት ሐደሮና ከለላ ሚዛነክርስቶስ አገራቸው በጦርነት ፈራርሶ፣ ቤታቸው በጦርነት ወድሞ፣ በፖለቲካ እምነታቸው ተሳዳጅ ሆነው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ነገን በማለም የነጎዱትን ታሪክ ይቁጠራቸው። ሃብቴን፣ ንብረቴን፣ ጨርቄንና ማቄን ሳይሉ ብዙዎች ተሰደዋል፤ ሜዳ ላይ ቀርተዋል፣ ጥሙ ረሃቡና መራቆቱ ሳይበግራቸው ባሕርና ተራሮችን ሲያቆራርጡ፤ ባሕር በልቷቸዋል አልያም እንደወጡ ላይመለሱ የቀሩትም በርካቶች ናቸው። •''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" •"ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ ኢትዮጵያውያን ወደ ሌላ አገራት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ያጠኑ ሰዎች እንደሚሉት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሕዝብ ስደት የተጀመረው በደርግ ወቅት ነው ይላሉ። የተለያዩ አፍሪካ አገራት በተለይም ሱዳን የብዙዎች መቀመጫ ነበረች፤ ከዚያም ነገን ተስፋ ወደ ፈነጠቁላቸው የምዕራቡ አገራት አቅንተዋል። ምንም እንኳን ካደጉበት አገር ባህል መነቀል ቀላል ባይሆንም በህይወት የተረፉ ስደተኞች ከዜሮ ጀምረው ኑሮን መስርተዋል፤ ልጆቻቸውን አሳድገዋል፣ ለቁም ነገርም አብቅተዋል። ይህ ሁኔታ የጃማይካዊቷ ፀሀፊ ኤድዊጅ ዳንቲካትን "ሁሉም ስደተኞች አርቲስቶች ናቸው" የሚለውን አባባል ያስታውሳል። ፀሃፊዋ ይህንን የምትልበት ምክንያት አላት ይህም ስደተኞች ከስር መሰረታቸው ተነቅለው፣ ከዜሮ ጀምረው፣ አዲስ ህይወት መስርተው ቤትና አገርን በሚመስላቸው መልኩ ስለሚቀርፁት ነው። ይህ ግን የኢትዮጵያውን ስደተኞች ብቻ እውነታ ሳይሆን የብዙ አገራት ስደተኞችም ጭምር ነው። የእነዚህ ስደተኞች ልጆችስ ኑሮ ምን ይመስላል፤ እስቲ በሌላው ዓለም እያንፀባረቁ ያሉ መኖሪያቸውን በምዕራቡ ዓለም ያደረጉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሙዚቀኞችን ታሪክ በትንሹ እናጋራችሁ። መክሊት ሐደሮ መክሊት ሐደሮ- ሁለገቧ ሙዚቀኛ ከበሮው የሚደለቅበት፣ እልልታው የሚቀልጥበት፣ የደስታው ስሜት ሌሎችም ላይ የሚጋባበት የሠርግ ዘፈኖች በሕዝብ ዘፈንነታቸው ከትውልድ ትውልድ ቀጥለው የዘመንን አሻራ መወራረስን ያሳያሉ። የባህል የሙዚቃ ዘፈኖች ባለቤትነታቸው የህዝብ እንደመሆኑ መጠን በተለያዩ ዘመናት የመጡ ሙዚቀኞችም የጊዜውን፣ የትውልዱን ድምፅ እየጨመሩ የዘመኑ ያደርጓቸዋል። ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊቷ መክሊት ሐደሮም ሌላ ቀለም በመስጠት ታላላቆቹን ማይክል ጃክሰን እና አስቴር፣ ፕሪንስና ማህሙድ አህመድ፣ የጃዙን ፈጣሪ ኮልትሬን፣ ሜሪ አርምዴ፣ ሙላቱ አስታጥቄን በማንሳት ሁሉም በእሷ ማንነትና ሙዚቃ ውስጥ ቦታ እንዳለቸው በሙዚቃዋ ትናገራለች። 'አይ ዋንት ቱ ሲንግ ፎር ዜም ኦል' በሚለው ዘፈኗም የጣሉትን አሻራ በግጥሞቿ ውስጥ በማካተት በዜማው ለየት ያለ ተሰጥኦ ያለውን የሙሉቀን መለሰ አሻራንም አካታለች። የሙዚቃ ቪዲዮውም እስክስታ፣ ኦሮምኛ፣ ጉራጊኛ፣ ትግርኛ ጭፈራ፤ ሂፕሆፕ ዳንስ፣ እልልታ፣ በአገር ልብስ ያሸበረቁ፣ አብስትራክት ስዕሎች፣ ስፌቶች ተካተውበታል፤ የመክሊት ማንነት መገለጫዎች። •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም መክሊት ሐደሮ ሁለገብ ሙዚቀኛ ናት። በሳንፍራሲስኮ፣ ካሊፎርኒያ መቀመጫዋን ያደረገችው መክሊት ከተለያዩ የሙዚቃ ስልቶች ሶውል፣ ጃዝ፣ ፎክና ኢትዮጵያ ሙዚቃ አይነትን ስልቶችም አቀላቅላ የአስቴርን ሙዚቃ "ዩ አር ማይ ላክ' በጉራጊኛና ጃዝ፣ ምን ሊመስል እንደሚችል፤ 'ከመከም' በጃዝ፣ የአርሶ አደሩ ህይወትን የሚነካውን አባይ ማዶን በጃዝ ቅላፄ ስትጫወተው ዘመንን ታሻግረዋለች፤ ሌላ ድምፅም ትሰጠዋለች። መክሊት የተወለደችው ኢትዮጵያ ቢሆንም ቤተሰቦቿ ወደ አሜሪካ ያቀኑት በህፃንነቷ ነው፤ ያደገችውም አሜሪካ ነው። በያሌ ኮሌጅም ፖለቲካል ሳይንስ አጥንታለች። ከተመረቀችም በኋላ ወደ ሳንፍራንሲስኮ በመሄድ የከተማዋ የጥበብ ማዕከል ላይ ራሷን አገኘቸው። ወደ ሙዚቃው ዓለም የገባችው ዘግየት ብላ ነው። በ24 ዓመቷ ወደ ሙዚቃ መምጣቷን በማስመልከት ራሷን 'ሌት ብሉመር' (ዘግይታ ያበበችው) ብላ ትጠራለች። ዘግየት ብላ ወደ ሙዚቃው ዓለም ለመግባት ምክንት የሆኗትም ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቿ ናቸው። ከሙዚቃ በፊት ትምህርት ይቅደም በሚለው! ምን አይነት መልዕክት ነው በሙዚቃ መተላለፍ ያለበት? ምናልባት ይሄንን ጥያቄ ናይጄሪያዊው ሙዚቀኛ ፌላ ኩቲ ቢጠየቅ 'አብዮትን ለማምጣት' ይላል። ለመክሊት ግን ማንኛውም ነገር በሙዚቃ መተላለፍ ይችላል፤ ገደብ ሊኖረው አይገባም ትላለች። ሙዚቃ የህይወት ነፀብራቅ እንደ መሆኑ መጠን! ሙዚቃ ማንኛውንም መልዕክት ሊያስተላልፍ ይገባል የሚል ጠንካራ እምነት አላት። አንዳንድ ቀላል የሚመስሉ ሃሳቦች ደግሞ ትልቁን ፖለቲካዊ መዋቅር ያነቃንቁታል። ለምሳሌ የመክሊት ዘፈን ከመከምን ብንወስድ የኢትዮጵያ የፀጉር ስታይል ብቻ ከመሆን አልፎ በብራዚል፣በ ደቡብ አፍሪካና ሌሎችም የአፍሪካና የዓለም አገራት ውስጥ ያሉ ጥቁር ሴቶች ከተፈጥሮ ፀጉራቸው ጋር የሚያደርጉትን ትግል ይገልጻል። ለዚያም ነው ከተለያዩ አገራት መክሊት ሙገሳንም፣ ውደሳንም የምታገኘው። በአንድ ወቅትም ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረገችው ቆይታ ከመከም ስላለው ተፅዕኖ ስትናገር "በሳንፍራንሲስኮ ቤይ አካባቢ የብላክ ላይቭ ማተርስ እንቅስቃሴ የሚያደራጁ ሴቶችን ባናገርኩበት ወቅት ከመከምን እንደ ብሔራዊ መዝሙር እንደሚያዩት ነገሩኝ። ሁልጊዜም ቢሯቸው ውስጥ እንደሚያጫወቱትና የሕዝባችን ማንነትና ፍቅርን የሚገልፅ ነው፤ ዘፈኑም ይህን እንዲያደርግ ነው የፈለግኩት፤ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ እንዲሁም ጥቁር ህዝቦች ጋር እንዲያገናኝ ነው ሐሳቤ" ብላለች። •"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ ከባርነትና ቅኝ ግዛት ጋር ተያይዞ ሃብት መዝረፍ፣ አገራትን መቀራመትና ግድያ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ጥቁርነትን ሊወክል የሚችል ነገር ከቆዳ ቀለም ጀምሮ የፀጉር፣ የባህል ማንነት፣ ታሪክን የማስጠላት ሥራ ተሰርቷል፤ የነጭነትን የበላይነትንም ለማስረፅ በተሰራው ሥራ ብዙዎች ይሰቃያሉ። በመላው ዓለም ቆዳን የማንጣት ሥራ በቢሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ የሚያንቀሳቅስ ዘርፍ ነው። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በነበረው የአፓርታይድ አገዛዝ የዘር ደረጃን ለማውጣት እርሳስን ፀጉር ውስጥ በማስገባት ፀጉሩ ከተዘናፈለ ነጭ፣ እርሳሱ እዛው ከቀረ ጥቁር እያሉ ለጭቆና ለመከፋፈል ተጠቅመውበታል። ለዚያ ነው የመክሊት ሐደሮ "ከመከም" የተሰኘ ዘፈን ያንን ታሪካዊ ጭቆና፣ ማንነቱን የተቀማ ሕዝብ እንደገና የመመለስና ፖለቲካዊና የኃይል አሰላለፍን የሚነካ የሆነው። መክሊት ሐደሮ መክሊት ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ቁርኝት ጠንካራ ነው። ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣው አባይ ማዶ በመጀመሪያ አልበሟ "ኦን ኤ ደይ ላይክ ዚስ" ውስጥ የተካተተው። ምንም እንኳን ሌላ አገር ውስጥ ኑሯቸውን ያደረጉ ዲያስፖራ ሙዚቀኞች ወደ ኢትዮጵያ በየወቅቱ መመላለስ ባይችሉም አገራችን፣ መሰረታችን፣ መነሻችን የሚሏት ኢትዮጵያ፣ በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ተፅእኖ ከፈጠረችባቸው ኢትዮጵያ ጋር የሚገናኙበትን ዘዴን ለመቀየስ አርባ ምንጭ ኮሌክቲቭ (የአርባ ምንጭ ስብስብ) የሚል ቡድንም መስራች ናት መክሊት። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያዊነትን ከቤተሰቦቻቸው ከተረዱት ሳይሆን በራሳችን መንገድ እንዴት ነው የምንረዳው በሚል 'ሆም አዌይ ፍሮም ሆም ' ከቤት ርቆ ቤት'- በሚል ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን በጥበብ ያገናኘ ፕሮጀክትም ጀምረው ነበር። •ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን መክሊት ሙዚቃ የተለያዩ ሕዝቦችን አንድ ላይ ያመጣል የሚል እምነት አላት። ለምሳሌ ለዓመታት የሰራችውን የናይል ፕሮጀክት ብንጠቅስ- በናይል ላይ ያለውን ፖለቲካ ወደጎን አድርገን በናይል ተፋሰስ ዙሪያ የሚኖሩ ሕዝቦችን ብናይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕዝቦች ይኖራሉ - የአባይን ፀጋ እየተቃመሱ። እነዚህን ሕዝቦችስ አንድ ላይ በሙዚቃ ብናመጣቸው ምን ይመስላል? በአባይ የላይኛውና የታችኛው ተፋሰስ የሚኖሩ አገራትንም ሙዚቀኞች በማሰባሰብ በግብፅ፣ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እንዲሁም በአባይ አገራት ዙሪያ ዘፍነዋል፤ አንድነትን ሰብከዋል። መክሊት "ዊ አር አላይቭ" የሚል ዘፈን አላት ምንም ቢሆን በህይወት መኖር ሐዘንም፣ ደስታም፣ የህይወት ትግል ውስጥ ብንሆን፤ በህይወት መኖር፣ ነገን ማየት ተስፋ ነው። ከለላ ሚዛነ ክርስቶስ- የወደፊቱን የምታልመው ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች በአሜሪካ የተወለደችው ከለላ ሚዛነ ክርስቶስ በሁለት ዓለማት ውስጥ መመላለስ ምን ይመስላል የሚለውን በሙዚቃዎቿ ውስጥ ታሳያለች። የማንነትን ብዙ ገጽታ በጥቁርነት፣ በሴትነት፣ የስደተኛ ልጅ በመሆን፣ በኢትዮጵያዊነት፣ በአፍሪካዊነት እንዲሁም በሌሎች የተደራረቡ ማንነቶች በሙዚቃዋ ውስጥ ይገለፃሉ። 'ሪትም ኤንድ ብሉዝ'፣ 'ሶውል'፣ ኤሌክትሮኒክ እንዲሁም ሌሎች ስልቶችን በማጣመር የራሷን ለየት ያለ የምትታወቅበትን ስልትም ማምጣት ችላለች። "ሙዚቃዬ ካሉት ስልቶች ውስጥ አንዱ ነው እንዲባል አልፈልግም፤ ዋነኛው እቅዴ አዲስ መፍጠር ነው" ትላለች በአንድ ወቅት 'ለፒች ፎርክ' በሰጠችው ቃለ መጠይቅ። እንዳው እድሉ ኖሯችሁ በከለላ ላይ የተፃፉ የተለያዩ ድረገፆችን ማየት ከቻላችሁ የሙዚቃ ጥልቀትን፣ መጠበብን እንዲሁም በሰው ልጅ የሚፈራረቁ ስሜቶች እናንተ እያለፋችሁበት እስኪመስል ድረስ ጎትቶ የማስገባት ኃይል አላት ይሏታል። ከለላ ሚዛነክርስቶስ ሙዚቀኛ፣ የሙዚቃ ደራሲ የሆነችው ከለላ ስትፅፍ ዋናነት ከግምት ውስጥ የምታስገባው ጉዳይ ቢኖር " ከሁሉም ነገር በላይ ስለምን ማውራት ያስፈራኛል?" የሚለውን ነው። ከዚያ በኋላም ሃሳቦቿን ሳትገድብ በነፃነት እንዲፈሱ ታደርጋቸዋለች፤ ከልቧ ጋር የምታደርጋቸውን ውይይቶች፣ ብዙዎች የግሌ ብለው የሚያስቡትን ታሪክ ከሰው ጋር ለመወያየት የሚያስፈሯቸውን ሃሳቦች፣ ለራሳቸው መድገም የማይፈልጉትን የልብ ስብራት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ለማካፈል ወደኋላ አትልም። በተለይም ከቀድሞ ጓደኛዋና ሙዚቀኛ (ቶሲን አባሲ) የነበራትን የፍቅር ግንኙነት ለአድማጮቿ "አንድ ሰው እየወደደሽም ሊጎዳሽ ይችላል፤ ብዙ ሰው ሊያልፍበት የሚችል ነገር እንደሆነ ይሰማኛል" በማለት አልበሟ ውስጥ አካታዋለች። በሎስ አንጀለስ መቀመጫዋን ያደረገችው ከለላ በጎርጎሳውያኑ 1970ዎቹ ወደአሜሪካ ከተሰደዱት ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ነው የተደወለችው፤ ያደገችውም በሜሪላንድ ነው። ለቤተሰቧ ብቸኛ ልጅ ናት፤ ከትምህርት ውጭ ያለውን አብዛኛውን ጊዜዋን ከአጎቶቿ ልጆች ጋር ታሳልፍ ነበር። መኪና ውስጥም ሆነው የትሬሲ ቻፕማንን ሙዚቃ ከፍ አድርገው ያጫውቱ ነበር፤ በተለይም "ፎር ዩ" የሚለው የትሬሲ ዘፈን ወደ ሙዚቃው ዓለም ከገባች በኋላ 'ከት ፎር ሚ' ለሚለው ዘፈን መነሻ ሆኗታል። ከእሷ በፊትም ሆነ አሁን ላሉት ጥቁር አርቲስቶች ከፍተኛ ቦታ የምትሰጠው ከለላ ዊትኒ ሂውስተን፣ ጃኔት ጃክሰን ለሙዚቃዎቿ የጀርባ አጥንት ሆነዋታል። አባቷ ሚዛነ ክርስቶስ ዮሐንስ ይሰሟቸው የነበሩት ሚሪያ ማኬባ፣ ሃሪ ቤላፎንቴን፣ አስቴር አወቀ እንዲሁም ሌሎችም የሙዚቃውንም ሆነ የሌላውን ዓለም ዕይታዋን አስፍተውላታል። ከለላ ሚዛነክርስቶስ በተለያዩ ማንነቶች ያደገችው ከለላ አስተዳደጓን እንዲህ ትገልፀዋለች፡ "እንደ አሜሪካዊ ሆኜ ነው ያደግኩት ቢሆንም ግን የመገለል ስሜት አለው፤ የሰረፀ ዘረኝነት አለ እንዲሁም ለብዙ ስደተኛ ቤተሰቦች ከውጭም ሆነ ከውስጥ የመሆን ስሜት አለው" ትላለች። በአሜሪካ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የዘር ክፍፍል የተረዳቸውም ገና በታዳጊነቷ ነበር። ትምህርት ቤት ውስጥ በነበረ አቀማመጥ፤ ባትቀበለውም ሁሉም የመጣበትን አካባቢ መርጦ፣ ዘሩን ለይቶ ይቀመጥ ነበር። የሙዚቃ ህይወቷም የጀመረው በህፃንነቷ ነው፤ ቫዮሊን ትጫወት ነበር፤ በትምህርት ቤቱ ባንድ ውስጥም ትጫወት ነበር። የሙዚቃ ህይወቷ በዚያው ቀጥሎ ዩኒቨርስቲም ከተቀላቀለች በኋላ በተለያዩ መድረኮች መዝፈን ጀመረች። ሙዚቃዋን በአንድ አይነት የማትወስነው ከለላ በአንድ ወቅት 'ዲዚ ስፔልስ' የተባለ ባንድም አባል ሆና ሜታል ሮክም ትጫወት ነበር። ከለላ ሙሉ አልበሞች ባይሆኑም የተለያዩ ሙዚቃዎች ስብስቧን በጎርጎሳውያኑ 2013 'ከት ፎር ሚ' በሚል ርዕስ ፣ በ2015 እንዲሁ 'ሃሉሲኖንን' በሚል ያወጣች ሲሆን፣ የመጀመሪያ አልበሟ 'ቴክ ሚ አፓርት' የተለቀቀው ከሦስት ዓመታት በፊት ነው። አልበሟም ከመውጣቱ በፊት 'ፍሮንት ላይን'፣ 'ዌይቲን' እና 'ብሉ ላይት' የሚሉ ሙዚቃዎቿ የወጡ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ አድናቆትንም አትርፋበታለች። አልበሟም ከወጣ በኋላ ከፍተኛ ተሰሚነት አግኝቷል፤ በሙዚቃው ዘርፍ ባሉ ባለሙያዎችም ከፍተኛ ሙገሳን አግኝቷል። ከሁለት ዓመት በፊት በወጣው 'ከመሞታችሁ በፊት ልትሰሟቸው የሚገባችሁ 1001 አልበሞች' (1001 Albums You Must Hear Before You Die) መፅሀፍ ውስጥ የከለላ አልበም ተካቷል። ገበያውን በማሰብ ሙዚቃ የማይሰሩ ተብለው ከሚነገርላቸው ሙዚቀኞች መካከል አንዷ የሆነቸው ከለላ ሶላንጅን ከመሳሰሉ ዘፋኞችም ጋር ተጣምራለች።
news-56431850
https://www.bbc.com/amharic/news-56431850
አሜሪካና ቻይና አዲስ 'ቀዝቃዛ ጦርነት' ላይ ናቸው?
የአሜሪካን መንበረ ሥልጣን ከወራት በፊት የተረከበው የባይደን አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የቻይና አቻዎቻቸው በቅርቡ ሊገናኙ ቀጠሮ ይዘዋል።
በዓለም አቀፉ መድረክ የሚፎካከሩት ሁለቱ ኃያላን አገራት ግንኙነት ምን መልክ ይኖረዋል የሚለውም የበርካቶች ጥያቄ ሆኗል። ተንታኞች አገራቱ ሰላምና ጦርነት በሌለበት ሁኔታ የሚፋጠጡበት ሁኔታ ይጨምራል በማለት እየተነበዩ ነው። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንና የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ከቻይናው ከፍተኛ ዲፕሎማትና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ይ ሃሙስ በአላስካ ይገናኛሉ። በባይደን አስተዳደር በኩል ይኼንን ግንኙነት አስመልክቶ ምንም አይነት ብዥታ የለም ተብሏል። ከስብሰባው ቀደም ብሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን "ስትራቴጂያዊ ውይይት አይደለም" ብለው ጠንከር ያሉ ጉዳዮች የሚነሱበት እንደማይሆን ጠቆም አድርገዋል። አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከቻይና ጋር ባላት ግንኙነት ተጨባጭ የሆኑ ሂደቶችና ውጤቶች የሚገኙበት መሆን አለበት ብለዋል። በዓመታት ውስጥ ግንኙነታቸው እየሻከረ የመጣው ሁለቱ አገራት ከዚህ በኋላም ቢሆን ወደ ወዳጅ ሳይሆን ወደ ባላንጣነት ያመራሉ እየተባለ ነው። የብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ጄክ ሱሊቫን ከሹመታቸው በፊት ከባይደን የእስያ ጉዳዮች አማካሪ ከርት ካምቤል ጋር ፎሬይን አፌይርስ ላይ በፃፉት ፅሁፍ በድፍረት "አሜሪካ ከቻይና ጋር የሚኖራት ግንኙነት ወደ ባላንጣነት ተቃርቧል" ብለዋል። የሁለቱ አገራት ግንኙነትንም በተመለከተ ተንታኞች 'ቀዝቃዛው ጦርነት" ይሉት ጀምረዋል። እንደሚታወሰው ቀዝቃዛው ጦርነት በአሜሪካና በሶቭየት ሕብረት መካከል 20ኛው ክፍለ ዘመንን ያጋመሰ፣ በትውልዶች የቀጠለ ከፍተኛ ፉክክር ነበር። የዋሽንግተንና የቤጂንግ ግንኙነት በምን መንገድ ነው የሚታየው የሚለው ከፍተኛ ስፍራ ሊሰጠው ይገባል። ምክንያቱም የሁለቱን አገራት ግንኙነት አስመልክቶ መጠየቅ የሚገባንን ጥያቄዎችና የምናገኛቸውን መልሶች ዐውድ ስለሚወስኑት ነው። የሚወጡ ፖሊሲዎችን ቀድሞ ለመጠቆምና አገራቱ ምን አይነት መንገዶችን ሊያዩ ይገባል የሚለውንም ያሳየናል። ምንም እንኳን ታሪካዊ ትንታኔዎችን መጠቀም የአሁኑን ዐውድ፣ ውዝግብና ሁኔታዎችን ግልፅ አድርጎ ያሳያል የሚሉ ቢኖሩም፤ በተፃራሪው ታሪክ ራሱን በዚያው መንገድ ስለማይደግም የታሪክ ትንታኔዎች ልዩነትን በማጉላት የበለጠ ግንኙነትን ሊያሻክሩ ይችላሉ የሚሉም አሉ። 'ቀዝቃዛው ጦርነት' ስንል በሁለት የፖለቲካ ሥርዓታቸው የጎላና ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለመጠበቅ የትኛውንም ኃይል ለመጠቀም ወደኋላ የማይሉና ትንቅንቅ የገቡ በሚል የምንረዳው ከሆነ፤ እውነት ነው የአሜሪካና የቻይና ግብግብ የአሜሪካና የሶቭየት ሕብረት ውጥረት ሌላኛው የሳንቲም ገፅታ ነው። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆን ኦፍ ኬኔዲና የሶቭየት ሕብረት መሪ ኒኪታ ክሩስቼቭ የባይደን አስተዳደር ጊዜያዊ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ስትራቴጂን ስናይ፤ ቻይና ብቸኛ ተወዳዳሪዋ እንዲሁም ምጣኔ ኃብታዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ወታደራዊና የቴክኖሎጂ ሃይሏን በማጣመር የተረጋጋና ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዳይኖር ልትገዳዳር የምትችል ኃይል ናት ይላል። እናም በባይደን አስተዳደር ውስጥ የሚታመነው ነገር በሚያስፈልግበት ወቅት ቻይናን መጋፈጥ ሲያስፈልግ ደግሞ መተባበር በሚል መርህ ነው። ቻይናም ቢሆን ተመሳሳይ አቋም ይዛለች። ገንቢ የሆነ ግንኙነት እንደምትፈልግ ጠቆም አድርጋ የአገሯን ብሔራዊ ጥቅም ቅድሚያ መስጠትን ተያይዛዋለች። በሆንግ ኮንግ ፀረ ዲሞክራሲ አፈናዎች፣ እንዲሁም በብሊንከን የዘር ጭፍጨፋ ነው ተብሎ የተጠራውን የሙስሊም ዜጎቿን አይን ያወጣ ስቃይን በተመለከተ ትችት ለሚሰጥ ሰው ጆሮ ዳባ ልበስ ብላለች። ቻይና በአሜሪካ ሥርዓት ላይ ያሉ ኢ-ፍትሐዊ ሁኔታዎችን ለማጋለጥ ጊዜዋን ብዙም አታቃጥልም። በዝምታ ነው የምታልፋቸው። በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወቅት አሜሪካ የኮቪድ-19 ቀውስ ውስጥ መግባቷ እንዲሁም በካፒቶል የተነሳው ነውጥ አሜሪካ በማህበራዊና በምጣኔ ኃብት ዘርፍ አርዓያ ነኝ ብላ የምታስበውን የበላይነት ጥያቄ ውስጥ የከተተ ነው። እንዲሁ ከላይ ስናየው ሁለቱ አገራት ቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ ገብተዋል የሚለው ስያሜ ተገቢ ይመስላል። ነገር ግን ይህንን ማለቱ ጠቃሚ ይሆን? በዋነኛው ቀዝቃዛ ጦርነት ወቅት ሶቭየት ሕብረትና አጋሮቿ ከዓለም ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ የተነጠሉ ነበሩ። እንዲሁም የወጪ ንግዳቸውም ከምዕራባውያኑ በኩል ከፍተኛ ቁጥጥር ነበረበት። አሁን ቻይና ያላትን አቋም ስናይ በዓለም አቀፉ ኢኮኖሚ አድራጊና ፈጣሪ ናት። የራሷም ምጣኔ ኃብት ከአሜሪካ ጋር በጥብቅ የተጋመደና የተሳሰረ ነው። የመጀመሪያው የቀዝቃዛ ጦርነት በጦር መሳሪያና በጠፈር ምርምሮች ዙሪያ በቴክኖሎጂ ማን ይበልጣል የሚል እሽቅድምድሞሽና ፉክክሮች ነበሩት። በአሁኑም ወቅት ያለው የአሜሪካ-ቻይና ፉክክር የሰውን ልጅን መፃኢ ዕድል ይወስናሉ የሚባሉት የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንደ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስና 5ጂ ጋር ተሳስሯል። የአሁኑ ዓለም አቀፍ ሁኔታም የተለየ ነው። በዚያን ቀዝቃዛ ጦርነት ወቅት ዓለም በሁለት ጎራዎች የተከፈለች ነበረች። ከየትኛውም ጎራ ያልተሰለፉት መሃል ገቦቹ ደግሞ በምዕራባውያኑ ዘንድ ከሶቭየት ሕብረት ወገን ተደርገው ነው የሚታዩት። በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በብዙ ጎራዎችን ዘንድ ተከፋፍላለች። ሆኖም ራሱን ሊበራል ብሎ የሚጠራው የዓለም ሥርዓትና ተቋማት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አደጋ ላይ ናቸው። ይህም ሁኔታ ቻይና የራሷን የዓለም እይታ እንድትጭን ቦታ ሰጥቷታል። ሆነም ቀረም ቀዝቃዛ ጦርነት የሚባለው እይታ በመሰረታዊነት ጥልቅ አደጋን ያዘለ ነው። በአሜሪካና በሶቭየት ሕብረት መካከል የነበረው የፖለቲካ ፍትጊያና፤ በሁለቱም በኩል ከሕጋዊነትንና ተቀባይነት ጋር ተያይዞ የነበረው መካካድ የዜሮ ድምር ነበር። ሁለቱ አገራት ፊት ለፊት ጦርነት ባይገጥሙም አሜሪካም ሆነ ሶቭየት ሕብረት በተለያዩ አገራት ያደርጓቸው የነበሩ የውክልና ጦርነቶች የበርካታ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። በመጨረሻም የሶቭየት ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ጠፋ፤ ተሸናፊም ሆነ። የቻይናና የአሜሪካን ፉክክርና የርዕዮተ ዓለም ብሽሽቅ ያላጤኑት ጉዳይ ውሰጥ ይከታቸዋል የሚሉ አሉ። በተለይም ከመሸነፍ ለመዳን ስትል ቤጂንግ የማትሄድበት መንገድ ሊኖር እንደማይችል ጠቋሚ ነገሮች አሉ። ነገር ግን ቻይና ሶቭየት ሕብረትን አይደለችም፤ ኃያል አገር ናት። የሶቭየት ሕብረት ያልተጣራ ብሔራዊ ገቢ (ጂዲፒ) ጣሪያ በነካበት ወቅት የአሜሪካን 40 በመቶ ነበር። የቻይና ያልተጣራ ብሔራዊ ገቢ በአስር ዓመት ውስጥ ከአሜሪካ እኩል ይስተካከላል። ቻይና፣ አሜሪካ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ አይታው የማታውቀው ኃያል ተፎካካሪዋ ናት። በሚቀጥሉት አስርት ዓመታትም ግንኙነታቸው ክትትል ያስፈልገዋል። የዘመናችን ኃያላን ተፎካካሪዎች ናቸው። ታሪካዊ ትንታኔዎችንና ነገሮችን ከአሁን ጋር ለማዛመድ የምንሞክርበትን ሁኔታ ወደ ጎን ብንተወው ይህ ሁለተኛው ቀዝቃዛ ጦርነት አይደለም። አይተነው የማናውቀውና የበለጠ አደገኛም ነው። በብዙ ዘርፎች ቻይና የአሜሪካ አቻ ተፎካካሪ ናት። ምንም እንኳን ብቸኛ የዓለም ኃያል አገር ባትሆንም ቻይና የደህንነቴ ጉዳይ ይመለከተኛል በምትለው ወታደራዊ ዘርፍም የአሜሪካ ተፎካካሪም ናት። ለፕሬዚዳንት ባይደን የቻይና ሁኔታ ውስብስብና እንዲህ በቀላል የሚፈታ አይደለም። የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸውም ለቤጂንግ እርስ በርስ የሚጋጩ ሆነው ታይተዋል። በእስያ-ፓስፊክ ቀጠናዎች ላይ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ አብሮ ለመስራት፣ ፍትሐዊ የሆነ የንግድ ሥርዓትን ለማስፈን እንዴት ቻይና ላይ ጫና ማድረግ ይቻላል? ዲሞክራሲ ላይ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮችስ? ሆኖም እነዚህ ፉክክሮች ስትራቴጂና ጥንቃቄ ያሻቸዋል። ፉክክሮቹ ተጋነው መወራትም ሆነ እንደዚሁ በቀላሉ መታለፍ የለባቸውም። ቻይና እያንሰራራች አሜሪካ እየወደቀች ነው የሚለው የተለመደ አባባል እውነታ ቢኖረውም ሙሉ ገፅታውን አያሳይም። አሜሪካ ከትራምፕ ቀውስ ወጥታ ማገገምና ዲሞክራሲያዊ አስተዳደሯ እንዲያንሰራራ ማድረግ ትችላለች? የቀድሞ አጋሮቿንስ በዓለም መድረክ ላይ እምነት የሚጣልባትና ቋሚ ኃይል መሆኗን ማሳመን ትችላለች? አሜሪካ የትምህርትና የቴክኖሎጂ መሰረቷን ማስፋትስ ትችላለች። ቤጂንግ በብዙ መንገድ የዋሽንግተንን ደወል ነጥቃለች። ነገር ግን ፈላጭ ቆራጭ አካሄዷ ምጣኔ ኃብቷ ላይ እክል ይፈጥር ይሆን? የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲስ ለዘለቄታው የሕዝቡን ድጋፍና ታማኝነት ይዞ ይዘልቅ ይሆን? ቻይና በርካታ ጠንካራ ጎኖች ቢኖራትም ደካማም በዚያው ልክ አላት። አሜሪካም ትልቅ የሚባል ደካማ ጎኖች ቢኖራትም ራሷን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ቦታው አላት። ልክ የኮቪድ-19 በአንድ አገር ተወስኖ እንዳልቀረ እነዚህ ቁልፍ የዓለማችን አገራት የሚያከናውኗቸው ነገሮችም ሆነ ውሳኔዎች በሕይወታችን ላይ ትልቅ ለውጥን ያመጣሉ። ረዥም ጎዳና ይመስላል፤ አሁን ጅማሮ ላይ ነው።
news-52793069
https://www.bbc.com/amharic/news-52793069
በአዲስ አበባ ኮሮናቫይረስን የመቆጣጠር እድል አምልጦ ይሆን?
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በየዕለቱ ኮሮናቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ፍጥነት እየጨመረ መሆኑን ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ከሕብረተሰብ ጤና ተቋም የሚወጣው ዕለታዊ መረጃ ያመለክታል።
የጤና ሚኒስትሯ፣ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩትም በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ ከስድሳ በመቶ በላይ የሚሆኑት ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው። በተለይ ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ በአገሪቱ ውስጥ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር በተከታታይ እየጨመረ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም አብዛኞቹ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተገኙ ናቸው። አርብ ግንቦት 14 ቀን 34 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ሲረጋገጥ፣ ቅዳሜ 61 ሰዎች፣ ዕሁድ ግንቦት 16 ደግሞ ሰማንያ ስምንት ሰዎች በወረርሽኙ መጠቃታቸው ሲነገር ከእነዚህም መካከል 73ቱ የተገኙት አዲስ አበባ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ባለሙያዎችን ያሳሰበው አብዛኞቹ በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች የውጭ አገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው መሆኑ ነው። ለ40 ዓመታት በሕብረተሰብ ጤና ዘርፍ የሰሩት አቶ ኃይሌ ውብነህ፤ "አሁን እየተመዘገቡ ያሉት ህሙማን የጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው መሆናቸው ያለጥርጥር ወረርሽኙ ሕብረተሰቡ ውስጥ መግባቱን የሚያሳይ በመሆኑ እየጨመረ መሄዱ አይቀርም" ይላሉ። ሕብረተሰቡ ውስጥ ገብቷል ሲባል የሚያዘው ሰው በሽታው የተላለፈበት ዋነኛው ምንጭ በአገር ወይም በዙሪያው ካለ ሰው ነው ማለት እንደሆነ በማብራራት፤ ይህም ወረርሽኙ በሕብረተሰቡ ውስጥ እየተዛመተ መሆኑን እንደሚያመለክት ይጠቁማሉ። በኒው ዮርክ ዩኒቨርስቲ በማስተማር ላይ የሚገኙትና የማይክሮባዮሎጂና የዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ ጤና ባለሙያው ዶክተር አበባየሁ ንጉሤም "ወረርሽኙ ሕብረተሰቡ ውስጥ ወደ ጎን በቀላሉ የመስፋፋት ዕድል ከመፍጠሩ በተጨማሪ ፍጥነቱም ይጨምራል" ብለዋል። በበሽታው የተያዙ ሰዎች በምርመራ እስኪታወቁ ወይም ጎልቶ ወጥቶ እስኪደረስበት ድረስም በርካታ ንክኪ ስለሚኖረው የበሽታው መስፋፋት አሳሳቢ ከመሆኑ በተጨማሪ ለመቆጣጠርም አስቸጋሪ እንደሆነ ዶክተር አበባየሁ ጨምረው ያስረዳሉ። አቶ ኃይሌ እንደሚሉት በሽታው በአገሪቱ ውስጥ መከሰቱ ከታወቀ በኋላ መንግሥት ከወሰዳቸው እርምጃዎች ጎን ለጎን ከአምስት ሳምንታት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ ሕብረተሰቡ በፍላጎቱ በየቦታው ያደርጋቸው የነበሩት የጥንቃቄ እርምጃዎች ከፍ ያለ ነበር። ነገር ግን ይህ ሁኔታ ቀስ በቀስ እየላላ በተለይ በፋሲካ በዓል ሰሞን መዘናጋቱ ጎልቶ ይታይ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ኃይሌ፤ ከዚያ በኋላ የትራንስፖርት ገደቡ መላላት፣ እንቅስቃሴዎች እንዳበበረታታቸው ጠቅሰው "ያኔ የላላው የመከላከያ ዘዴ ነው አሁን ዋጋ እያስከፈለን ያለው" ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል። ዶክተር አበባየሁም እንደሚሉት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥሩ ለሳምንታት ዝቅ ብሎ መቆየቱ በሕብረተሰቡ ውስጥ መዘናጋትን ፈጥሯል። ጨምረውም እሳቸው በሚኖሩበት ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥም በተመሳሳይ ቀስ በቀስ መስፋፋቱን ያስታውሳሉ፤ "የአንድ ሳምንት መዘናጋት ከብዙ አገራት ተሞክሮ እንደታየው ብዙ ዋጋ ያስከፍላል።" በሽታው በሕብረተሰቡ ውስጥ በመግባቱ ቁጥሩ ከዚህም እየጨመረ እንደሚሄድ የሚናገሩት ዶክተር አበባየሁ፤ በሽታው ያለባቸው ሰዎች ሳይታወቅ ወደ ሌሎች ስለሚያስተላልፉ ከፍተኛ መጠን ላይ ሊደርስ ይችላል ብለው ይሰጋሉ። ስለዚህም "መጀመሪያ ላይ ይገኝ የነበረው ቁጥር ትንሽ መሆኑና አሁን እየጨመረ መምጣቱ፤ ከፍ እያለ ሊሄድ እንደሚችል ስለሚያመለክት አሁኑኑ መወሰድ ያለባቸው እርምጃ መውሰድ ይገባል" ሲሉ ሳይረፍድ ሁሉም የሚችለውን እንዲያደርግ ይመክራሉ። አቶ ኃይሌም በህሙማን ቁጥሩ እየጨመረ መሄድ ላይ ጥርጣሬ ያላቸው አይመስሉም። በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ ባለፉት ሳምንታት ከታየው አጠቃላይ የሕዝብ እንቅስቃሴ አንጻር በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሄድ "የሚጠበቅ እንደሆነና በቅርብ ጊዜም ይቀንሳል የሚል ግምት የለኝም" ይላሉ። የጤና ባለስልጣናት በአገሪቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 582 ሰዎች ውስጥ 377ቱ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን አመልክተው፤ በተለይ በልደታና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከሌሎች ቦታዎች ከፍ ባለሁኔታ መስፋፋቱን ገልጸዋል። አቶ ኃይሌ እነዚህ የከተማዋ ከፍሎች ጎልተው ለመታየት የበቁት "ምርመራ የሚደረግባቸው ቦታዎች የበሽታው ክስተት በታየባቸውና በሚጠረጠሩ አካባቢዎች ላይ ትኩረት ስለሚያደርግ ነው፤ ሁለቱ አካባቢዎች በተለይ ጎልተው የታዩት" ብለው ያስባሉ። አክለውም በከተማዋ ከእነዚህ አካባቢዎች ውጪ ያሉ ቦታዎች ነጻ ናቸው ማለት እንዳልሆነ ጠቅሰው፤ የምርመራው ቦታ እየሰፋ ሲሄድ በሌሎችም አካባቢዎች ተመሳሳይ ወይም የከፋ ውጤት ሊገኝ ይችላል ይላሉ ብለው ይሰጋሉ። በብዙ ቦታዎችም ከተጠቀሱት ክፍለ ከተሞች በበሽታው የተያዙ ብዙ ሰዎች ባይገኙ እንኳን፤ ተመሳሳይ መጠን ያለው ቁጥር ሊኖሩ እንደሚችል ያምናሉ። • ኮቪድ ያወጣቸው የቤተልሔም አበበ ገፀ ባህሪያት • በጥሬ ገንዘብ ዝውውር ላይ የተጣለው ገደብ ለምን አስፈለገ? በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ጎልቶ በታየባቸው አካባቢዎች የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ እርምጃዎች ለመውሰድ መንግሥት እያሰበ መሆኑን እየተነገረ ነው። የጤና ሚኒስትሯ ዶክትር ሊያ ታደሰ እንዳሉት ቫይረሱ እየተስፋፋ መሆኑን በምርመራ እየተገኙ ያሉ ውጤቶች እንደሚያመለክቱ ጠቅሰው፣ በሽታውን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴን በመገደብ የልየታ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሚኒስትሯ ጨምረው እንዳሉት ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪም በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪም ሆነ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ይህም ሁለቱ የህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች ዶክተር አበባየሁና አቶ ኃይሌ እንዳሉት ወረርሽኙ በሕብረተሰቡ ውስጥ መግባቱንና የመዛመት እድሉ ከፍ እንደሚል የሚያመለክት ነው። በክፍለ ከተማም ሆነ በሌላ መልኩ ለይቶ እንቅስቃሴን መገደብ ብዙም እንደማይዋጥላቸው የሚናገሩት ዶክተር አበባየሁ "በከተማዋም ሆነ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች ቦታዎችን መለየት ሳያስፈልግ መወሰድ ያላበቸው የመከላከል እርምጃዎች በቶሎ መወሰድ አለባቸው" ይላሉ። ነገር ግን እርምጃው የራሱ የሆነ ችግር ቢኖረውም "በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመሩ ከሄደ ሌሎችን ለመጠበቅ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣልና ሌሎች ጠንከር ያሉ እርምጃዎች መውሰድ ያስፈልጋል" ብለው ይመክራሉ። "አሁን እንደሚታየው የበሽተኞች ቁጥር ከመጨመር ወደኋላ ስለማይል የበለጠ የጥንቃቄ እርመጃዎች በመንግሥት በኩል ይወሰዳሉ ብዬ እጠብቃለሁ" የሚሉት ደግሞ አቶ ኃይሌ ውብነህ ናቸው። በተለይ ደግሞ የበሽታው ክስተት በስፋት በታየባቸው አካባቢዎች ለየት ያለ እርምጃ በመውሰድ የአካባቢውን ሕዝብ የሚጠቅምና የበሽታውን በከተማዋ መስፋፋት ለመግታት የሚያስችል ይሆናልም ይላሉ። በሽታው ወደ ሌሎች የአዲስ አበባ አካባቢና ከከተማዋ ውጪ ወዳሉ የገጠር ክፍሎች እንዳይዛመት ጥብቅ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ የሚናገሩት አቶ ኃይሌ "የእንቅስቃሴ ገደብን በተመለከተ ያለውን የበሽታ መስፋፋት በመከታተልና ጥናት ላይ በመመርኮዝ መሆን አለበት" ይላሉ። በተጨማሪም "አማራጭ ወደሌለው አቅጣጫ እየሄድን ነው። በየቀበሌው የቅኝት ቡድን በማሰማራት በየቀኑ ያለውን የጤና ችግርን በማሰባሰብና መረጃውን እየተከተሉ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።" ዶክተር አበባየሁ ንጉሤም በሽታውን ለመቆጣጠር መጀመሪያ ላይ በሁሉም በኩል ሲወሰዱ የነበሩት የጥንቃቄ እርምጃዎች አሁንም ተጠናክረው በስፋት ተግባራዊ መደረግ እንዳለባቸው አጽንኦት ይሰጣሉ። እያንዳንዱ ሰውም "መረበሽ ሳይሆን ጥንቃቄ ላይ ትኩረት በማድረግ ራሱንና በዙሪያው ያሉ ሰዎችን ከበሽታው መጠበቅ ይኖርበታል" የሚሉት ዶክተር አበባየሁ፤ ወጪ የሌለባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በመውስድ የበሽታውን ስጋት መቀነስ ይቻላል ይላሉ። "በሸታውን ለመቆጣጠር የሚያስችለንን እድል ከእጃችን እየወጣ ነው" የሚሉት አቶ ኃይሌ "ነገር ግን አሁንም የበሽታውን መስፋፋት ማዘግየት ይቻላል" ብለው ያምናሉ። ለዚህ ደግሞ በጤና ባለስልጣናት በተደጋጋሚ የተመከሩትን በሽታውን የመከላከያ የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል የሚሉት አቶ ኃይሌ "እያስተማሩ ካልሆነ ደግሞ በሕግም ቢሆን ተግባራዊ እንዲሆኑ ማደረግ" በቀጣይ ሊመጣ የሚችለውን አደገኛ ሁኔታ ሊያቀለው ይችላል ይላሉ።
51529732
https://www.bbc.com/amharic/51529732
የህዳሴ ግድብ ድርድሮች ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ውይይት ተካሄደ
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ በዋሽንግተን ለቀናት ሲካሄድ የነበረው የሶስቱ አገራት ስብሰባ ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ስላሉት ድርድሮች አካሄድ እና አቅጣጫ ውይይት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ተካሂዷል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በፌስቡክ ገፁ እንዳስታወቀው ሚኒስትሮች፣ የተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ሌሎችም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ግለሰቦችን በውይይቱ ተሳትፈዋል። • የህዳሴው ግድብ ድርድር ትኩረቱን ስቶ የውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ ሆኗል ተባለ • በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ በጋራ ማዘጋጀት እንዳልተቻለ ተገለፀ ከሰሞኑ የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሕግና ቴክኒክ ባለሙያዎች በዋሽንግተን ረቂቅ ሰነድ ለማዘጋጀት ሲካሄድ የነበረው ውይይት ያለምንም ስምምነት መጠናቀቁን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ማስፈራቸው የሚታወስ ነው። የአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ በታዛቢነት ይሳተፉበታል የተባለውን ይህን ድርድር ያለውጤት እንዲያበቃ ያደረገው ምክንያት ምን እንደሆነ አምባሳደር ፍጹም ያሉት ነገር የለም። ቢቢሲ ለውይይቱ ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች እንደተረዳው ምንም እንኳን የሚካሄደው ውይይት በግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ እንዲሆን ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች ቢሆንም በግብጽ በኩል ድርድሩ የውሃ ድርሻ ላይ እንዲያተኩር ግፊት እያደረገች ነው ብለዋል። በሱዳን በግብጽና በኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የቆየው የህዳሴ ግድብ ድርድር ትኩረቱን ስቶ ወደ ውሃ ድርሻ ክፍፍል ላይ መሄዱን እኚሁ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሱዳን የአቋም ለውጥ አድርጋ ከግብጽ ጋር መወገኗን እንዲሁም አሜሪካ እና የዓለም ባንክ ለግብጽ መወገናቸውን በመጠቆም አሁን ላይ ጉዳዩ "4 ለ 1" ሆኗል በማለት ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ መሆኑንም ምንጫችን ተናግረዋል። • አል-ሲሲ በአባይ ጉዳይ ጦርነት መፍትሄ አይሆንም አሉ • ግብጽ በአባይ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና የድርቅ ማካካሻ ላይ የተዘጋጀውን ረቂቅ ሰነድም ኢትዮጵያ እንድትፈርም አሜሪካና የአለም ባንክ ጫና እያደረጉ መሆናቸውን እየተነገረ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፓምፒዮ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በዚህም ወቅት ጠቅላይ ሚነስትር ዐብይ አህመድ ጋር በረቂቅ ሰነዱ ላይ እንደሚወያዩ አንዳንድ መረጃዎች እየወጡ ነው።
51116492
https://www.bbc.com/amharic/51116492
"ከእነርሱም ሆነ ከመንግሥት የሰማነው ድምፅ የለም" የታጋች ቤተሰቦች
17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጸጥታ ስጋት ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲያመሩ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከታገቱ ሳምንታት ተቆጥረዋል።
ተማሪዎቹ የታገቱት ከደምቢ ዶሎ ጋምቤላ በሚወስደው መንገድ ላይ ነው ምንም እንኳ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ ታግተው ከነበሩ አብዛኞቹ ተለቀዋል ቢሉም፤ ቢቢሲ ተማሪዎቹ ስለመለቀቃቸው ምንም አይነት ማረጋገጫ ማግኘት አልቻለም። የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት፤ ተማሪዎቹን ያገታቸው ማነው? ከተለቀቁ የት ነው የሚገኙት? ከወላጆቻቸው ጋር ለምን እንዲገናኙ አልተደረገም? ለሚሉ እና ለሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ ስላልሰጡ፤ የጉዳዩ አወዛጋቢነት እንደቀጠለ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ከቀናት በፊት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ታግተዋል ያሉት የተማሪዎች ቁጥር እና የፌደራል መንግሥት ከእገታው አስልቅቄያለሁ የሚለው ቁጥር ልዩነት፤ በመንግሥት መካከል በራሱ የመረጃ መጣረስ መኖሩን ያሳያል የሚሉ በርካቶች ናቸው። የመለቀቃቸው ዜና ከመሰማቱ በፊት ትናንት ያነጋገርነው እህቱ የታገተችበት ወንድም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በገና ዋዜማ ላይ በሰጡት መግለጫ፤ የታገቱ ተማሪዎች ቁጥር አራት ናቸው ማለታቸውን ተከትሎ፤ መረጃው ስህተት መሆኑን ስለተረዳ ወደ ቢሯቸው አቅንቶ እንደነበር ያስታውሳል። ወደ ቢሯቸው አቅንቶ እርሳቸውን ባያገኝም "አማካሪያቸው" ላሉት ግለሰብ የተማሪዎቹን ስምና የሚማሩበትን የትምህርት ክፍል ዝርዝር የሚያሳይ ማስረጃ መስጠቱን ይናገራል። "የሰጠናቸው መረጃ ይድረሳቸው፤ አይድረሳቸው ግን አላወኩም" ብሏል። መረጃውን ለሚመለከታቸው ሌሎች አካላትም እንደሰጡ ይናገራል። • ጃል መሮ ከህወሃት ጋር እየሠራ ነው? ልጃቸው የታገተችባቸው አባት ደግሞ ከታገቱት 17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አንዷ የበኩር ልጃቸው እንደሆነች ይናገራሉ። ድምጿ ከጆሯቸው ከራቃቸው ሳምንታት አልፈዋል። ልጃቸው በዩኒቨርሲቲው የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነበረች። በትምህርት ምክንያት ከእነርሱ ከራቀች ጀምሮ ያሉበት አካባቢ የስልክ ኔትወርክ ችግር ቢኖርም፤ ቢያንስ በየሦስት ቀኑ በስልክ ይገናኛሉ፤ ቢበዛ በሳምንት ደህንነታቸውን ይጠያየቃሉ። ትንሽ ሰንበት ካለች ይጨንቃቸዋል። አሁን ግን ድምጿን ከሰሙ ሳምንታት አልፈዋል። የገባችበትን፣ የደረሰችበትን አለማወቃቸውም ግራ አጋብቷቸዋል። ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተመድባ ስትሄድ አላደረሷትም። ከጓደኞቿ ጋር ነበር የሄደችው። ይሁን እንጅ መታገታቸውን ኅዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰሙ በኋላ በማግስቱ የተሰወረችባቸውን ልጃቸውን ለመፈለግ ከተማ አቆራርጠው ደምቢ ዶሎ ሄደው ነበር። እዚያ እንደደረሱ የሚያደርጉት ግራ ቢገባቸውም በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲው ማምራታቸውን ይናገራሉ። ከዚያም ወደ ኮማንድ ፖስት በመሄድ እንዳነጋገሯቸው ያስረዳሉ። "ችግር የለም፤ 'ልጆቹን በድርድር እናስለቅቅላችኋለን' እያሉን ሁለት ሦስት ቀን እዚያው ደንቢ ዶሎ ከተማ አደርን" ይላሉ። በኋላ ላይ "እናንተንም ከባድ እርምጃ እንዳይወስዱባችሁ አገራችሁ ግቡ፤ እኛ ልጆቹን አፈላልገን እናመጣለን" እንዳሏቸውና የስልክ ቁጥራቸውን ተቀብለው እንደተመለሱ ያስታውሳሉ። ምን ላይ እንደደረሱ ስልክ እየደወሉ ቢጠይቋቸውም የሚነግሯቸው አዲስ ነገር አልነበረም። የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ልጃቸውም በራሷ ስልክ እንዲሁም "የአጋቾቹ" ነው ባለችው ስልክ ትደውልላቸው ነበር። እኚህ አባት " ዩኒቨርሲቲውን ሳየው ጫካ ውስጥ ነው፤ አጥር የለውም፤ መንግሥት ራሱ እንዴት አድርጎ ልጆቻችንን እንደሚያስተምራቸው ተገርሜ ነው የመጣሁት" በማለት ቀድመው ቢያውቁ ኖሮ ወደ ዩኒቨርሲቲው እንደማይልኳት በቁጭት ይናገራሉ። የመለቀቃቸው ዜና ከተሰማ በኋላ ቢቢሲ ያነጋገረው የታጋች ወንድም ቅዳሜ ዕለት የተላለፈው የተማሪዎቹን መለቀቅ ዜና ከሰማ በኋላ ገጠር ለሚኖሩት ቤተሰቦቻቸው ደውሎ ነግሯቸዋል። "አትጨነቁ ተለቀዋል እየተባለ ነው፤ በእርግጥ ያልተለቀቀም አለ እያሉ ነው፤ ግን አትጨነቁ" ሲል ነበር ደውሎ ያበሰራቸው። እርሱ እንደሚለው አለመደወሉ ብቻ እንጅ እስካሁን እንደተገኙ ነው የሚያስቡት፤ በዜናውም እጅግ ተደስተው ነበር። እርሱም በበኩሉ ዜናውን የሰማ ቀን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶት ነበር። ወደ ስልኳም ደውሏል፤ ግን ስልኳ አይሰራም። በተደጋጋሚ ቢደውልም እስካሁን ድምጿን መስማት አልቻለም። • ኦባማ፡ ሴቶች ከወንዶች የተሻሉ ናቸው • በቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ባለሙያ በታጣቂዎች ተገደሉ የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ኃላፊ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ከታገቱት መካከል አብዛኞቹ መለቀቃቸውን ከተናገሩ በኋላ "በደስታ ፈነጠዝኩ! ቤተሰቡ ሁሉ ተደሰተ።" ያሉን ደግሞ ልጃቸው የታገተችባቸው አባት ናቸው። እንዲህ ነበር ያወጉን፦ እኛ ገጠር ነው የምንኖረው ቴሌቪዥንም የለን፤ ባህር ዳርና ሌሎች ከተሞች የሚኖሩ የታጋች ቤተሰቦች ናቸው እየደወሉ የነገሩን። መልዕክቱ ከተላለፈ በኋላ ልጆቻችን በእጃችን ሊገቡ ነው ብለን ተደስተን ነበር። ሰሞኑን ግን መንግሥት ድምጻቸውን ስላላሰማን እየተጨናነቅን ነው። አርሶ አደሮች ነን፤ በጭንቀት ሥራ መሥራት አልቻልንም፤ ወደ ቤት ስሄድም ሆነ አንዳንድ ቦታም ወጣ ስል የሰማው ሰው በሙሉ ለቅሶ ነው። "እንዴት ነው? ድምጿን አልሰማችሁም ወይ? መቼ ነው የሚመጡት?" እያሉ ይጠይቃሉ። እኛ ግን ምንም መልስ የለንም። ቁርጡን ስላላወቅነው ሁልጊዜ ለቅሶ ላይ ነው ያለነው። እስካሁን ምንም የሰማነው ድምፅ የለም። ከቤተሰብ ባገኘነው መረጃ መሠረት ታግተው ያሉ ተማሪዎች ስምና ይማሩበት የነበረው ትምህርት ክፍል ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የመንግሥት አካላት ምላሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ቢቢሲ የተማሪዎቹን መታገት ከሰማበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎችን ለማግኘት ጥረት እያደረገ ነው። ይሁን እንጅ የተሰጠው ምላሽ የለም። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን፤ ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን በተደጋጋሚ ብንደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ ልናገኛቸው አልቻልንም። አማራ ክልል የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌትነት ይርሳውን፣ የሰላምና ሕዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ ምላሽ አላገኘም። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከሳምንት በፊት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ "አራት ተማሪዎች ታግተው እንደሚገኙ መረጃው አለኝ" ማለታቸው ይታወሳል። ታግተው የሚገኙት ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ጋር በስልክ አልፎ አልፎ እንደሚገናኙ ጭምር ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳደሩ ተማሪዎቹ ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ከአባ ገዳዎች፣ ከአካባቢው ማኅበረሰብ እና ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር ውይይት እያደረግን ነው ብለው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ያሉት ነገር የለም። ኦሮሚያ ክልል ስለታገቱት ተማሪዎች በድጋሜ የጠየቅናቸው የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ጋር ያደረግነው የስልክ ልውውጥ የሚከተለው ነው፦ ታግተው የነበሩና አሁን ተለቀቁ ስለተባሉ ተማሪዎች ለመጠየቅ ነው ደወልኩት ኮሎኔል አበበ፡ "አላውቅም፤ እኔ የሰማሁት ነገር የለም" የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሰጠው መግለጫ አብዛኞቹ መለቀቃቸውን ሰምተናል። በእናንተ በኩል የምታውቁት ምንድን ነው ? ኮሎኔል አበበ፡ ለምን እነርሱን አትጠይቋቸውም ? እርስዎም ለአንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ተማሪዎቹ በመንግሥት እጅ እንደሚገኙ ገልፀዋል። ምንድን ነው ያለው እውነት? ኮሎኔል አበበ፡ታዲያ እርሱን ለምን አትጠቀሚም ተጨማሪ ጥያቄዎች ስላሉኝ ነው. . . ኮሎኔል አበበ፡ እሽ 8፡00 ሰዓት ደውይ፤ አሁን ሥራ ላይ ነኝ። ከዚያ በኋላ በተደጋጋሚ ብንደውልም የእጅ ስልካቸውን ሳያነሱልን ቀርተዋል። የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በበኩላቸው ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎች የሉም፤ "ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ የለም" ከማለት ውጪ ማብራሪያ መስጠት አለመፈለጋቸውን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል። ማን ምን አለ? ተማሪዎቹ ከታገቱ በኋላ መንግሥት ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ የወሰደው እርምጃ የለም በማለት በርካቶች የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። ከእነዚህ መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ባወጣው መግለጫ የታገቱ ተማሪዎች እንዲለቀቁ እና ጥቃት አድራሾቹ ለሕግ እንዲቀርቡ መጠየቁ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ዛሬ በገፁ ላይ ባወጣው መግለጫም፤ የታገቱት ተማሪዎች ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው እንዲለቀቁ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአስቸኳይ እንዲወጣ መጠየቁ ይታወቃል። የአማራ ክልል ሴቶች ፌደሬሽን በተማሪዎቹ ላይ እየተፈፀመ ያለውና ኢ-ሰብዓዊ ተግባራት እንዲቆሙ፤ ጥፋተኞችም ለሕግ እንዲቀርቡ ጠይቋል። የአማራ ሴቶች ፌደሬሽንና እና የአማራ ሴቶች ማህበር ዛሬ በሰጡት መግለጫም የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ያለውን አቋም መንግሥት ግልፅ ማድረግ እንዳለበት ጠይቀዋል። የአማራ ዴሞክራሲ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) በተማሪዎቹ ላይ የተፈፀመውን ድርጊት አውግዞ፤ ይህ የመንግሥት ችግር እንደሆነ እንደሚያምን ገልጿል። 'የታገቱት ተማሪዎች ይለቀቁ' የሚል ዘመቻም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተካሄዱ ነው፤ መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጥም እየተጠየቀ ነው። የጠቅላይ ሚንስትሩን ካቢኔዎች 50 በመቶው ሴቶች መሆናቸውን በማስታወስ፤ በደህንነት ስጋት የዩኒቨርሲቲ ግቢ ለቀው ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲያመሩ የታገቱ ሴት ተማሪዎች ትኩረት አለማግኘት በመጥቀስ ብስጭት አዘል አስተያየቶች አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው።
54067733
https://www.bbc.com/amharic/54067733
ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዯጵያ በኮቪድ-19 መከላከል ባለፉት ስድስት ወራትና ወደፊት የሚጠብቋት ሥራዎች
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በኮቪድ-19 የተያዘ ግለሰብ የተገኘው መጋቢት 4/2012 ነበር። ይህም እነሆ ዛሬ ስድስት ወራትን ደፈነ።
ከዚያ ጊዜ ወዲህ የወረርሽኙ መጠን እየጨመረ መጥቶ በአሁኑ ሰዓት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ60 ሺህ አልፏል። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 60 ሺህ 784 ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 22 ሺህ 977 ሲያገግሙ፣ 949 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ በትናንትናው ዕለት የጤና ሚኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያወጡት ሪፖርት አመልክቷል። በኢትዮጵያ፣ ወረርሽኙ በመጋቢት ወር ከተከሰተ በኋላ፣ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት አስታውቋል። ካለፈው ወር ወዲህም ኢትዮጵያ በቀን 20 ሺህ ያህል ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ ጀምራለች። ይህም በአጠቃላይ በአገሪቱ የተደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎችን ከአንድ ሚሊየን በላይ እንዲሆን አድርጎታል። በአገሪቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ተብሎ ተደንግጎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ነሐሴ 30 ላይ አብቅቷል። የተወሰዱ እርምጃዎችና የተገኙ ውጤቶች በአዲስ አበባ የኮሮናቫይረስ የተያዙ እና ሕክምና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ተቀብለው ከሚያስተናግዱ የሕክምና ተቋማት መካከል ኤካ ኮተቤ እና ሚሌኒየም አዳራሽ ተጠቃሽ ናቸው። ወደ እነዚህ የሕክምና ማዕከላት የሚገቡ ህሙማን ቁጥር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመሩ መሆኑን ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሁለቱም ተቋማት ኃላፊዎች ገልፀዋል። ኤካ ሆስፒታል 500 ለኮሮናቫይረስ ህሙማን የተዘጋጁ አልጋዎች ሲኖሩት፣ ከእነዚህ መካከል 20ዎቹ ለጽኑ ህሙማን የተለዩ መሆናቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ናትናኤል በኩረ ጽዮን ይናገራሉ። ተቋሙ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታምመው የሚመጡትን ኮተቤ በሚገኘው ሆስፒታል ተቀብሎ የሚያስተናግድ ሲሆን፤ ቀለል ያለ ምልክት ያላቸውና ራሳቸውን ማግለል ለሚፈልጉ ደግሞ ገርጂ በሚገኘው የስፖርት አካዳሚ 200 አልጋዎች እንደተዘጋጁ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። በአገሪቱ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ህሙማን ተቀብሎ የሚያስተናግደው የሚሌኒየም አዳራሽ ከ800 በላይ አልጋዎች እንዳሉት መረጃዎች ያሳያሉ። ዶ/ር ናትናኤል ባለፉት ሁለት ወራት ወደ ሆስፒታላቸው ከሚመጡ የኮቪድ-19 ህሙማን መካከል በጽኑ ታመው የሚመጡ ግለሰቦች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የክፍሉን አልጋዎች እና የቬንቲሌተሮች ቁጥር ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። በቀጣዮቹ ሳምንታትም በርካታ የቬንትሌተር ድጋፍ የሚፈልጉ ህሙማን እንደሚመጡ ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ። አቶ ኃይሌ ውብነህ እንዲሁም ዶ/ር አበባየሁ ንጉሴ የኀብረተሰብ ጤና ባለሙያ ናቸው። ለሁለቱም ባለሙያዎች ኢትዮጵያ የመጀመሪያው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በተገኙበት ወቅት ያደረገችው ዝግጅትም ሆነ የሕብረተሰቡ ጥንቃቄ "እጅግ በጣም ከፍተኛ ነበር።" አቶ ኃይሌ የኮሮናቫይረሰ ስርጭትን ለመግታት በዋና ከተማዋ አዲስ አበባም ሆነ በክልል ከተሞች የተለያዩ እርምጃዎች በፍጥነት መወሰዳቸውን ያስታውሳሉ። በእርግጥ ይላሉ አቶ ኃይሌ፣ በከተማም በገጠርም ትምህርት ቤቶች እኩል መዘጋታቸው "ስህተት ቢኖረውም" በሽታውን ለመቆጣጠር አመርቂ ሥራ ተሰርቷል። እንደ አቶ ኃይሌ ከሆነ ትምህርት ቤቶችን በአንዴ ዘግቶ ሁሉንም ህጻናት ከትምህርት ውጪ ከማድረግ ቀስ በቀስ ከተሞች አካባቢ እርምጃዎች እየተወሰዱ ወደ ገጠሩ አካባቢ ማስፋት ይቻል ነበር። የፋሲካ ሰሞን የነበረው የበዓል ግርግር እንደ አቶ ኃይሌ ከሆነ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት መስፋፋት የጀመረው የፋሲካ ሰሞን ከነበረው የበዓል ገበያ እና እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ነው። ዶ/ር አበባየሁ በበኩላቸው ቁጥሮችም የሚያሳዩን ይህንኑ ነው በማለት "በርግጥ በትክክል በዚያ ሰሞን የነበረው ለስርጭቱ መስፋፋት አስተዋጽኦ ማድረጉን ለመናገር ጥናት ቢጠይቅም" በማለት፣ ስብሰባዎች እንደልብ መደረጋቸው፣ የበዓል ሰሞን ባሉ እንቅስቃሴዎች ላይ የታዩ መዘናጋቶች ለስርጭቱ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ጠቅሰዋል። የፋሲካ በዓል ካለፈ በኋላ በቫይረሱ ስርጭት የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደመጣም ያስታውሳሉ። በተቃራኒው ደግሞ ሕብረተሰቡ የሚያደርገው ጥንቃቄ ላይ መላላት መታየቱን በማንሳት ለቫይረሱ መስፋፋት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልፀዋል። ከዚህ በኋላ ሕብረተሰቡ የሚሰባሰብባቸው የተለያዩ አጋጣሚዎች መፈጠራቸውን በመግለጽ፣ ስብሰባዎች በቂ አየር በማይዘዋወርባቸው ስፍራዎች መካሄዳቸው፣ ሰልፎች መደረጋቸው እንዲሁም በዓላት መደራረባቸው ለስርጭቱ መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን ይጠቅሳሉ። ለአቶ ኃይሌ ኢትዮጵያ የምታደርገው የኮሮናቫይረስ ምርመራ መጠንን በከፍተኛ ቁጥር ብታሳድግ፤በቫይረሱ መያዛቸው የሚረጋገጥ ሰዎች ቁጥር ከፍ እንደሚል ጥርጥር የላቸውም። ኢትዮጵያ እየመረመረች ያለችው ንክኪ ያላቸው፣ የተጠረጠሩ እንዲሁም ምልክት የታየባቸው እንደሚሆኑ በማንሳት ሰፊውን ሕዝብ ለመመርመር ቢሞከር አቅምን እንደሚፈትን ተናግረዋል። ለዶ/ር አበባየሁ የምርመራ አቅምን ማሳደግ ጥሩ ቢሆንም፣ የሚመረመሩ ሰዎች በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን በመለየት በኩል ጉልህ አስተዋጾኦ እንዳለው ይናገራሉ። ልክ አቶ ኃይሌ እንዳሉት ንክኪ ያላቸውንና ምልክት ያሳዩትን ብቻ መመርመር፣ እንዲሁም በጎ ፈቃደኞችን አልያም አጠቃላይ ማኅበረሰቡን መመርመር በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ማግኘት ላይ ለውጥ ያመጣል ሲሉም ገልፀዋል። የቫይረሱ ስርጭት የት ነው የጎላው? የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ያወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው በከተማዋ በነሐሴ ወር በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች፣ ከሐምሌ ወር ጋር ሲነፃፀር በ9,384 ወይም 99.6 በመቶ ከፍ ብሏል። በአዲስ አበባ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተከሰተው የሞት መጠንም በሐምሌ ወር 191 የነበረ ሲሆን፤ በነሐሴ ወር ደግሞ 446 ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው አጥተዋል። ከዚህም ከሁለት እጥፍ በላይ የነሐሴ ወር የሞት መጠን ጭማሪ ማሳየቱን መረዳት ይቻላል። በአዲስ አበባ ከሽታው ጋር በተያያዘ በነሐሴ ወር ብቻ የነበረው የሞት ምጣኔ ባለፉት 5 ወራት ከሞቱት በሦስት ሳምንት ውስጥ ብቻ በእጥፍ ማደጉን መገንዘብ ይቻላል። አቶ ኃይሌ አዲስ አበባ የቫይረሱ ስርጭት በስፋት የተከማቸባት ከተማ ብትሆንም፣ የተሰሩት ሥራዎችም ስርጭቱን ለመግታት የሚያስችሉ መሆናቸው ላይ ጥርጣሬ አላቸው። የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ያለው የቫይረሱ የስርጭት መጠን እንደሚለያይ በመጥቀስም፣ እንደ ልዩነቱ የሚሰራው ሥራና ትኩረት የሚደረግበት አካባቢ መለያየት እንደነበረበት ይገልጻሉ። ነገር ግን ይላሉ አቶ ኃይሌ፤ የመከላከል ሥራው እየተሰራ ቢሆንም እንኳ "አይታይም።" ዶ/ር አበባየሁ በአዲስ አበባም ሆነ በክልሎች የመከላከል አቅሙ የተሻለ የነበረው የተወሰነ ጊዜ እንደነበር በመጥቀስ አሁን የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አቅም "ወርዷል" ሲሉ ይናገራሉ። በአዲስ አበባና በክልሎች መካከል ግን ያለው የነዋሪዎች ጥግግት መጠን እንደሚለያይ በመግለጽ፣ በአዲስ አበባ የስርጭቱ መብዛት ከዚህ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ይገልጻሉ። በአዲስ አበባ ያለው እንቅስቃሴ የትራንስፖርት አገልግሎት መጠቀም የሚያስገድድ መሆን፣ የእንቀስቃሴ ፍሰት ፈጣን መሆን የራሳቸው አስተዋጽኦ እንዳላቸውም አብራርተዋል። የኤካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ናትናኤል ወደ ሆስፒታል በጽኑ ታምመው የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረው ለዚህ ምክንያቱ ያሉትን ሲጠቅሱ "ቸልተኝነት አንዱ ነው።" በሕብረተሰቡ ዘንድ በሽታውን የመናቅ፣ ይያዘኝና ይለይልኝ የሚል ቸልተኝነት እንደሚስተዋል የሚጠቅሱት አቶ ኃይሌ "ይህ አደገኛ ውሳኔ ነው፣ ከሞቱ በኋላ መመለስ የለም፤ የሙከራ ሞት የሚባል ነገር የለም" ይላሉ። አሁን በርካታ ከንክኪ ነጻ የሆኑ ሰዎች ቫይረሱ ያልደረሰባቸው አካባቢዎች በመኖራቸው የመከላከል ሥራውን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አቶ ኃይሌ ጨምረው ተናግረዋል። የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እንቅስቃሴ ገደብ መጣል ፈታኝ በመሆኑ ዘዴዎችን መቀያየር፣ ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር ያገናዘበ የመከላከል እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑንም ይመክራሉ። ክልሎች አካባቢ ያለው የቫይረሱ ስርጭት አነስተኛ መሆኑን የሚገልፁት አቶ ኃይሌ፤ ይህ ከክልሎችና ከባለሙያ አቅም ጋር አንደሚያያዝ ይገልፃሉ። ክልሎች ማድረግ የሚችሉትን እያደረጉ ነው ያሉት አቶ ኃይሌ፤ በሽታው ወደ ክልሎች እንደሚዛመት በመግለጽ፤ የመመርመር አቅም እስካላደገ ድረስ ትክክለኛ የስርጭቱን መጠን ማወቅ እንደማይቻልም ይናገራሉ። ወደፊት ምን ይደረግ? በአሁኑ ጊዜ በርካታ ሕዝባዊ በዓላት እየመጡ ነው። አዲስ ዓመት ከቀናት በኋላ ይከበራል። የትግራይ ምርጫ ዛሬ እየተካሄደ ነው። እሬቻ እንዲሁም መስቀልን የመሳሰሉ የአደባባይ በዓላትም መኖራቸው ለቫይረሱ ስርጭት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከዚህ ሁሉ ደግሞ ተማሪዎች የ2013 ትምህርታቸውን ለመጀመር ምዝገባ ማድረጋቸው ለአቶ ኃይሌ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። ሁለቱም ባለሙያዎች ሕዝባዊ በዓላት ከአሸንዳ አከባበር ትምህርት በመውሰድ በውስን ሰው ቢደረጉ መልካም መሆኑን ይመክራሉ። እንደ አቶ ኃይሌ የቫይረሱ ስርጭት በሚጨምርበት ወቅት ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎችን መግታት፣ ትምህርት ቤቶችን መዝጋት፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ማገድ እንደሚያስፈልግ ገልፀው፤ በዚህ ወቅት ትምህርት ቤት መክፈት ወደ ባሰ ማጥ ውስጥ እንደሚከት ገልፀዋል። ዶ/ር አበባየሁ የኮሮናቫይረስን መከላከልን የሚመሩ ሰዎች በአዲስ ዓመት ያሉ በዓላትን ከግንዛቤ በማስገባት የመከላከል ሥራውን ከዚያ አንጻር መቃኘት እንደሚያስፈልጋቸው ይመክራሉ። የበሽታው ስርጭት አሁን እየጨመረ መሆኑን በማንሳትም፣ በዚህ ወቅት ትምህርት ቤቶችን መክፈት የበለጠ አደጋ መጋበዝ መሆኑን አቶ ኃይሌ ቢገልፁም ዶ/ር አበባየሁ ግን በዚህ አይስማሙም። አቶ ኃይሌ ትምህርት ቤቶች የሚከፈትበት ጊዜ ቢዘገይ እንዲሁም እንደ አካባቢውና ሁኔታዎች በሚፈቅዱት መንገድ ቢሆን ሲሉ ይመክራሉ። ዶ/ር አበባየሁ ደግሞ ትምህርት ሲከፈት ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት፣ በአንድ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን ቁጥር መቀነስ፣ ንጽህና አጠባበቅን፣ እንዲሁም የክፍሎቹን የአየር ዝውውር አስቀድሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ይላሉ። ተማሪዎች አፍና አፍንጫ መሸፈኛ የሚጠቀሙበትን ሁኔታም ታሳቢ ማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ወሳኝ መሆኑን በማንሳት አስቀድሞ እነዚህን ሁሉ መስራት እንዳሚያስፈልግ ይናገራሉ። ሁለቱ ባለሙያዎች በርግጥ ህጻናትና ወጣቶች በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው ላይ ተጨባጭ የሆነ ጥናት ባይኖርም ቫይረሱን ወደ ቤተሰቦቻቸው ማዛመታቸው ግን አይቀርም ሲሉ ገልፀዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭት በአንድ ወቅት ተከስቶ የሚጠፋ ባለመሆኑ ትምህርት አሰጣጡ ቀጣይ እና አሰልቺ ባልሆነ መልኩ መካሄድ እንዳለበትም ይመክራሉ። በአሁኑ ወቅት "ምክንያት አልሆንም" የሚው ዘመቻ መካሄዱ መልካም መሆኑን የሚያነሱት ዶ/ር አበባየሁ፤ ምን ያህል ታች ድረስ ዘልቋል የሚለው ላይ ግን ጥያቄ አላቸው። የኢትዮጵያውያን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አጠቃቀም በጣም አነስተኛ መሆኑን የሚናገሩት ዶ/ር አበባየሁ ይህንን ወደ 90 በመቶ ከፍ ማድረግ ቢቻል የቫይረሱን ስርጭት " በ40 እና በ50 በመቶ መቀነስ ይቻላል" ሲሉ ይመክራሉ።
47256789
https://www.bbc.com/amharic/47256789
ድምፃዊ ተፈራ ነጋሽ፡ "ታንክ ቢመጣ ወደኋላ አልመለስም"
5 አልበሞች ለአድማጭ አድርሷል፤ ከእነ አረጋኸኝ ወራሽና ሌሎች ድምፃውያን ጋር የሠራቸው ስብስብ ሥራዎችም አሉት። "ደህና ሁኝ ልበልሽ በእንባ እየታጠብኩኝ"፣ "ምነው ቀዘቀዘ ፍቅራችን"፣ ከሥራዎቹ መካከል ጎልተው የሚጠቀሱት ናቸው። ሰሞኑን በታክሲ ሾፌርነት መታየቱ ተሰምቶ አነጋግረነዋል። ዘፈንን ትተህ መንፈሳዊ ዓ ለምን ከተቀላለልክ ስንት ዓመት ሆነህ?
ተፈራ ነጋሽ፦ አሁን 13 ዓመት ጨርሼ 14 ዓመት ሊሞላኝ አንድ ወር ይቀረኛል። ያኔ ይህንን ውሳኔ ስትወስን አድናቂዎችህ ምን ይሉ ነበር? ተፈራ ነጋሽ፡-የተለያየ ዓይነት አስተያየት ነበር። የሚደግፉ አሉ። እንደገና ደግሞ በዛው ብቀጥል የሚፈልጉና የራሳቸውን ሐሳብ የሚሰጡም አሉ። እንዲሁ ደግሞ የሚቃወሙም ነበሩ። ዞሮ ዞሮ ውሳኔው ግን የራስ ስለሆነና ሕይወት ስለሆነ፣ መንፈሳዊ ነገር አንተ ለራስህ የሚገለጥልህ ነገር ስለሆነ፣ አንተ የተሰማህን ወይንም ደግሞ የተገለጠልህን ነገር ነው የምትኖረው። ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ከገባህ በኋላ የቀድሞ ሥራዎችህን ስትሰማ የሚፈጠርብህ ስሜት ምንድን ነው? ተፈራ ነጋሽ፡- እውነቱን ለመናገር ከሆነ የውሳኔህ ሁኔታ ነው የሚወስነው። እኔ ስወስን ምንም ነገር ሳልጨብጥ አይደለም የወሰንኩት። የሆነ ነገር ገብቶኝ በትክክል መንፈሴ ላይ የተረዳሁት ነገር ስለነበረ፣ ያ የተረዳሁት ነገር ደግሞ ከአእምሮ በላይ የሆነ ትልቅ ስለሆነ፣ ከምንም ነገር ጋር አላነፃፅረውም። እና በቀጥታ ወደዚህ ወደ መንፈሳዊው ዓለም ስመጣ በፊት የነበሩኝ ልምዶች እንዴት እንደሆነ ሳላውቅ ከኔ ተለይተው ነው ያገኘኋቸው። እና ሙዚቃውም ዘፈኑም አብሮ ወዴት አንደሄደም አላውቅም። ፍላጎቱ ጠፍቷል። አሁን የድሮ ሥራዎቼን በምሰማበት ጊዜ እውነቱን ለመናገር ከሆነ ምንም ስሜት አይሰጠኝም።የኔ እስከማይመስሉኝ ድረስ ነው ውስጤ የተለወጠው ልልህ ፈልጌ ነው። • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን • ኦሮምኛ ዘፋኙ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን አጣ ያንን ድምፅ ስትሰማ፣ ሙዚቃውን ስትሰማ እንደሌላ ሰው ነው የምታስበው? ተፈራ ነጋሽ፡- እውነት ነው፤ ምክንያቱም ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ከሄድን ምን ይላል፣ "ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው" ይላል። አዲስ ፍጥረት የሚለው ነገር እውነት ነው። ወደዚህ አዲስ ማንነት ስመጣ ውስጤ ለውጥ ተካሄዷል። በዐይን የማይታይ ግን መለኮት የሚሠራው ውስጣዊ ለውጥ ተከስቷል። ያ ለውጥ ዘፈንን ብቻ አይደለም፤ ሌሎች ማንኛቸውንም ነገሮች በተለይ ኀጥያት ተኮር የሆኑ ነገሮች ወዴት እንደሄዱ አላወቅሁም። ራሴ ነፃ ሆኜ፣ ፍላጎቴ ተቀይሮ፣ ሌላ ሰው ሆኜ ነው ራሴን ያገኘሁት። ለምሳሌ አንድ ነገር ልንገርህ፤ ጫት እቅም፣ መጠጥም እጠጣ ነበር። ግን ይህንን ውሳኔ በወሰንኩ በማግሥቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ነው ትዝ ያለኝ። ውስጤን ሳዳምጠው የለም። ልክ እንደዚህ ዘፈኑም አብሮ ሄዷል። ስለዚህ ይህ ውስጣዊ ለውጥ ነው፤ ይሄ የማንነት ለውጥ ነው። ሥራዎችህ ከውሳኔህ በኋላ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ተከፍተው ሲደመጡ ቅር ይልሃል? ተፈራ ነጋሽ፡- እንደዛ አላስብም፤ ተቃውሞም አላሰማም። ምክንያቱም ሥራዎቹ የብቻዬ አይደሉም። የሙዚቃ ባንዱ፣ ገጣሚያን፣ ዜማ ደራሲያን አሉ። ብቻዬን የሠራሁት ሥራ ስላልሆነ እነኛም ሰዎች መብት አላቸው። ሌላው ቢሰሙም ላለፈው ነገር እኔ አልጠየቅም። የዛን ጊዜ ትክክል ነበርኩ፤ አሁን ደግሞ የበለጠ ትክክል ነኝ። በዛን ወቅት ጥፋት አጥፍቼ ቢሆን አሁን በምሕረት ወጥቼያለሁኝና ያንን ነገር እግዚአብሔር ረስቶልኛል። ወደ ኋላ ተመልሼ ይህ ለምን ሆነ? ለምን ዘፈንኩ? ብዬ አልፀፀትም። በሌላ መንገድ ካየነው ሥራዎቹ ሲሰሙ አንድም ሰዎች መነጋገሪያ ሊያደርጉትና ሰዎች ራሳቸውን ውሳኔ መምረጫ እንዲያደርጉት መንገድ ሊፈጥር ስለሚችል ለምን የኔ ሥራ ተከፈተ፣ በሚዲያ ላይ መደመጥ የለበትም የሚል አቋም የለኝም። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች • አክሱምና ላሊበላ ለስራዎቹ መስፈርት የሆኑት ዲዛይነር ሰሞኑን ከራይድ ጋር መሥራት መጀመርህን ሰማን፤ እንዴት ወደዚህ ሥራ ልትገባ ቻልክ? ተፈራ ነጋሽ፡- ከዛ በፊትም የተለያየ ሥራ እሠራ ነበር። ለመኖር መሥራት አለብኝ። አሁን ራይድ ሲመጣ መኪናው እጄ ላይ ስላለ በቀጥታ ሰሌዳውን ወደ 3 ቁጥር አዙሬ፣ የንግድ ፍቃድ አውጥቼ፣ ከድርጅቱ ጋር ተስማምቼ መስራት ጀምሬያለሁ። ሥራው ጥሩ ነው። በጣም ተመችቶኛል። ይህንን ውሳኔ የወሰንኩበት ምክንያት ደግሞ ምንም አይነት ሥራ ስትሠራ በቀዳሚነት የአእምሮ እረፍት ታገኛለህ። ሌላው ደግሞ የሚያስፈልግህን ነገር ታሟላለህ። ሌላ ሰውንም የምትደግፍበት የምታግዝበት አቅም ታገኛለህ። ለመንግሥትም ግብር ትከፍላለህ። ስለዚህ ይህንን ሥራ ሳገኝ ምንም አላቅማማሁም፤ አላመቻመችኩም። ራይዶች እነርሱ ጋር ልትሠራ ስትሄድ ምን ዓይነት ስሜት ነበራቸው? ተፈራ ነጋሽ፡- የሚመዘግቡት ልጆች የሚያውቁኝ አይመስለኝም። ያን ጊዜ የነበረኝን የታዋቂነት መንፈስ ትቼዋለሁ። ነገር ግን የራይድ ሥራ አስኪያጅ ስታገኘኝ ደስ የሚል ነገር አይቼባታለሁ። ጥሩ አድርጋ አስተናግዳኛለች። እኔ ራሴን እንደ ማንኛውም ተራ ሰው ነው የምቆጥረው። የድሮው ስሜት የለኝም። ደንበኞችህስ? አንተ መሆንህን ሲያውቁ ምን ይላሉ? ተፈራ ነጋሽ፡- እስካሁን በጎ ምላሽ ነው ያለው። አንዳንድ ከልብ አድናቂዎች ደንገጥ የማለት ነገር ታይባቸዋለህ። ብዙ ሰዎች ውሳኔዬን ያከብራሉ ያደንቃሉም። ምክንያቱም የተሻለ እንደሆነ ያስታውቃል። እንዴት ያስታውቃል ካልከኝ ዝም ብለህ ሰውን ፊቱን ስታየው ሰላሙን ታይበታለህ። እኔ ደግሞ አሁን ያለኝ አቋም ከዕድሜዬ ጋር እንኳ አይገናኝም። 56 ዓመቴ ነው ግን የ40 ዓመት ጎልማሳ ነው የምመስለው። እንደውም አንዳንድ ሰዎች 'እሸት መሰልክ'፣ 'ገለፈፍክ'፣ 'ለመለምክ' የሚሉኝ አሉ። በውስጤ የሚታየው ሰላም ፊቴ ላይ ስለሚታይ፣ ከማንም ጋር የመግባባቱን ፀጋ ደግሞ እግዚአብሔር ስለሰጠኝ፣ ከብዙ ሰዎች ጋር እናወራለን። የሚፈልጉትን ይጠይቁኛል፤ እኔም እንደሚገባው ከዚህኛውም ከዛኛውም እያጣቀስኩ መልስ እሰጣቸዋለሁ። በአንተ ታክሲ በመገልገላቸው የተለየ ደስታ የተሰማቸው ወይንም የተከፉ አሉ? ተፈራ ነጋሽ፡- ደስ እንዳላቸው የሚነግሩኝ አሉ። እንደውም ስልኬን ወስደው እንደዘመድ የምንጠያየቅም አሉ። ከጀመርኩ ሦስት ወር ከአስራ አምስት ቀን ቢሆነኝም በዚህ አጭር ጊዜ በርካታ ሰው አግኝቻለሁ። የተለያየ ዕውቀት፣ ልምድ ያላቸው ሰዎች አግኝቻለሁና በጣም ደስ ይላል። አዲሱ የሥራ መስክ ተመቸህ? ተፈራ ነጋሽ፡- ወድጄዋለሁ። ጭቅጭቅ የለውም። ድካም የለውም። ሥራው አንተ ያለህበት ድረስ ነው የሚመጣልህ። የምታገኛቸው ሰዎችም አሪፎች ናቸው። ወድጄዋለሁ። የተለያዩ ሥራዎችን መሞከርህን ነግረኸን ነበርና ምን ምን ሥራዎችን ነው የሞከርከው? ተፈራ ነጋሽ፡- የኮሚሽን ሥራዎችን ሞክሬያለሁ። ቤት ሠርቶ ለመሸጥም ሞክሬያለሁ። ኮሚሽን ስትል ድለላ ማለትህ ነው? ተፈራ ነጋሽ፡- አዎ። ግን አጭር ጊዜ ነው የሠራሁት። መሬት ስለነበረኝ ቤት ሠርቼ ነው የሸጥኩት፤ እሱ ሁለት ሦስት ነገር ወጣው። አሁን ሌላ ቤት ጀምሬ ቆሟል። ያው የሕንፃ መሣሪያ ውድነት አለ፤ በዚህ ሰዓት ላይ። እሱ ሥራ ውስጥ ለመግባት ሐሳብ አለኝ። ሌላው ደግሞ አገልግሎት ላይ ነኝ። በነገራችን ላይ ሙዚቃውን አልተውኩም። የመንፈሳዊ ሙዚቃ ላይ በዝማሬ አገለግላለሁ። አንዳንድ ሰዎች ወደ ታክሲ ሹፌርነት የገባው ተቸግሮ ነው የሚሉ አሉ። አንተ ኑሮህ ዝቅ ብሎ ነው ወደ እዚህ ሥራ የገባኸው? ተፈራ ነጋሽ፡- እኔ ይህኛውን አባባል አልደግፈውም። ይህንን ሥራ እኔ የምሠራው ምንም ነገር አጥቼ አይደለም። በቤተ እምነት ውስጥ አገልግሎት አገለግላለሁ፤ እርሱ ለኑሮ አያንስም። በዛ ላይ የሚከራይ ቤትም አለኝ። አሁን በጣም ድሃ የመሆን ጉዳይ ሳይሆን ወደ ዚህ ያመጣኝ የጊዜ መኖር ጉዳይ ነው። እኔ የማገለግለው በሰንበት ወይንም በአዘቦት ቀናት ማታ ማታ ነው። ስለዚህ ቀን ቀን በከንቱ የሚያልፈውን ጊዜ ብጠቀምበት ጥሩ ነው። በተጨማሪም ሰው አገኝበታለሁ፤ ከዚህ ሁሉ ባሻገር ደግሞ ገንዘብ አገኝበታለሁ። የሚገኝበት ገንዘብ ቀላል አይደለም። በወር ውስጥ 30 ሺህ ሊያገኝ የሚችል ብዙ ሰው አለ ብዬ አላምንም። ከዚህ ሥራ በቀን ከሺህ ብር በላይ ታገኝበታለህ። እና ገቢው ራሱ በጣም ዝቅተኛ የሚባል አይደለም። እና ትልቁ ነገር ጤና ኖሮህ ሠርተህ የምታገኘው ነገር ነው። ይህንን ነገር እንድሠራ ያደረገኝ የዝቅታና የከፍታ ነገር አይደለም። እግዚአብሔር ይመስገን በከፍታ ውስጥ ነኝ፤ ከክርስቶስ ጋር። ወደ ዓለማዊ ሙዚቃ የምትመለስበት አጋጣሚ ይኖራል? ተፈራ ነጋሽ፡- ሐዋሪያው ጳውሎስን ታውቀዋለህ?... እነ ጴጥሮስን ታውቃቸዋለህ?... አልተመለሱም ።ለምን እንዳልተመለሱ ታውቃለህ? ...ያዩት ምድራዊ ነገር አይደለም። ሰማያዊ ነገር ነው ያዩት።... ታንክ ቢመጣ ወደኋላ አልመለስም። ወደኋላ ከምመለስ ሞት ይሻለኛል።
46458364
https://www.bbc.com/amharic/46458364
የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች
መድፈር፣ ብልት ላይ የውሃ መያዣ ፕላስቲክ ማንጠልጠል፣ በፒንሳ የብልት ቆዳን መሳብ፣ ዛፍ ላይ ሰቅሎ መግረፍ፣ በኮረንቲ መጥበስ፣ በአፍንጫ እስክሪብቶ ማስገባት፣ በአፍ እና በአፍንጫ እርጥብ ፎጣ መወተፍ፣ ሙቀታማ ስፍራዎች ላይ ለረዥም ጊዜ ማስቀመጥ፣ ጥፍር መንቀል. . .
ከአለማየሁ ወቅታዊ ካርቲኖች አንዱ እነዚህ አሰቃቂ ማሰቃያ መንገዶች በሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ፈጽመውታል የተባሉ ናቸው። • ስዕልን በኮምፒውተር • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሀኑ ጸጋዬ በሙስናና በሰብአዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ካሳወቁ በኋላ፤ ጉዳዩን መገናኛ ብዙሃን ለቀናት ዘግበውታል፣ በማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኖም ነበር። ነዋሪነቱን በእንግሊዝ ያደረገው ካርቱኒስቱ አለማየሁ ተፈራ፤ በትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ የበርካቶች መነጋገሪያ የሆነውን ርዕሰ ጉዳይ የሥራው ግብአት አድርጎታል። ሆዱ ከመላ ሰውነቱ በላይ የገዘፈና ወታደራዊ ልብስ የለበሰ ግለሰብ ፒንሳ ይዞ እጅግ የኮሰሱና ግድግዳ ላይ ወደተንጠለጠሉ ሰዎች ሲጠጋ በካርቱኑ ላይ ይታያል። • በእውቀቱ ስዩም፣ አለማየሁ ገላጋይና ዳንኤል ወርቁ ተሸለሙ • 'ደራሲ ያደረገኝ ማኅበራዊ ሚዲያው ነው' አለማየሁ መሰል ካርቱኖችን መሥራት ከጀመረ ከሁለት አሰርታት በላይ ተቆጥረዋል። የየወቅቱን የፖለቲካ ትኩሳት የሚገልጹ ካርቱኖች ሰርቷል። ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ዳሷል። ካርቱኖቹ ፈገግታ የሚያጭሩ፣ የሚተቹ፣ ሁነቶችን ከተለያየ አቅጣጫ የሚያሳዩም ናቸው። የ97 ምርጫ እንደ መነሻ. . . የአለማየሁ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ካርቱኖች ጎልተው መውጣት የጀመሩት ከ97 ምርጫ ወዲህ ነው። ያኔ ከሚኖርበት እንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ በሀገሪቱ ያስተዋለው ውጥንቅጥ ለበርካታ ሥራዎቹ መነሻ ሆኗል። የያኔውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተመርኩዞ ሥራዎቹን በፌስቡክ ማቅረብ የጀመረው፤ ካርቱን ስሜቱን የሚገልጽበት መሳሪያ በመሆኑ እንደነበረ ያወሳል። በወቅታዊ ፖለቲካ ላይ በሚያተኩሩ ሥራዎቹ ይታወቃል "የሀገሪቱን ውስጣዊ ጣጣዎች ሳያቸው ወደ ፖለቲካ የሚያዘነብሉ ካርቱኖች መሥራት ጀመርኩ። የሰፈሬ ልጆች ሞተዋል። በተገደሉት ሰዎች አዝኜ ነበር። ጊዜው ከባድና አስጨናቂ ነበር" • ዘርፈ ብዙዋ ወጣት ጥበበኛ • ካለሁበት 15፡ "ራሴንና ልጆቼን የሰሜን ተራሮች ላይ ባገኝ በጣም ደስ ይለኝ ነበር" ሀሳብን እንደልብ በአደባባይ መግለጽ ያስገድል፣ ያሳስር፣ አካል ያስጎድል፣ ያሰድድ፣ የነበረበት ወቅት እንደነበረ አይዘነጋም። "ካርቱን መልዕክት ማስተላፍ የሚቻልበት መሳሪያ ነው። ግን አደጋ ነበረው" ካርቱኖቹን እንግሊዝ ሆኖ መስራቱ በተወሰነ ደረጃ ስጋቱን ቢያቀልለትም፤ ከሀገር ርቆም ከጫና አላመለጠም። የሚሠራቸውን ካርቱኖች ተከትሎ ማስፈራሪያ ይደርሰው ነበር። የጥቃት ሙከራ እንደተደረገበትም ይናገራል። ካርቶኖቹን የሚያሰራጭበት ፌስቡክ የበርካቶች መንደር ነው። ሥነ ጥበብ የሚወዱ፣ የሚያደንቁ፣ የፖለቲካ ግንዛቤ ያላቸው፣ እንዲሁም ለጥበቡ ግድ የሌላቸው፣ ፖለቲካውም ከአንድ አቅጣጫ ብቻ እንዲታይ የሚፈልጉም ሀሳባቸውን ያለ ገደብ በፌስቡክ ይገልጻሉ። በወቅታዊ ፖለቲካ ላይ በሚያተኩሩ ሥራዎቹ ይታወቃል። ከዓመታት ስደት በኋላ ወደሀራቸው የተመለሱ የጥበብ ሰዎችን ያሳየበት ሥራ "ሰዎች ጉዳት ሊያደርሱብኝ የሞከሩበት ጊዜ ነበር። ሦስት አራት ጊዜ ጥቃት ተሞክሮብኛል። ለፖሊስ ሪፖርት አድርጌ ሰዎቹ በአካባቢዬ እንዳይደርሱም ተደርጓል" እንግሊዝ በመሆኑ ሊሠራቸው የቻላቸው ካርቱኖች ኢትዮጵያ ቢሆን እንደማይሞከሩ ይናገራል። "ኢትዮጵያ ብሆን እሞት ወይም አንዱ ጆሮዬን፣ አንዱ ጥፍሬን ነቅሎት ነበር። 'እጁን መቁረጥ ነው' የሚሉ ሰዎች እዛ [ኢትዮጵያ] ብሆን ይሳካላቸው ነበር" ሥራው የግል ህይወቱን ማደነቃቀፉም አልቀረም። አለማየሁ እንደሚለው፣ የሀበሻ ሬስቶራንት፣ ጭፈራ ቤት የማይሄድባቸው ወቅቶች ነበሩ። ዓመት በዓመት ላይ ሲደረብ፣ ሀገሪቱ በሕዝባዊ ተቃውሞ ተንጣ፣ ዛሬ ላይ ደግሞ አንጻራዊ ለውጥ ይስተዋላል እየተባለ ነው። ካርቱን ለአለማየሁ የሂደቱ ነጸብራቅ ነው። ሆኖም የአንጻራዊ ለውጥ መኖር ካርቱንን ክፍተቶችን ነቅሶ ከማውጣት ሚናው እንደማይገታው ይናገራል። ዘመናት በአለማየሁ ካርቱኖች ሲገለጹ. . . ካርቱን የመንቀፍ፣ የማሳቅ፣ ለለውጥ የማነሳሳት፣ ለሀሳብ ወይም ለክርክር የመጋበዝ ባህሪ አለው። አለማየሁ ሥራዎቹ ሙገሳም ወቀሳም ቢያስከትሉበትም ከሙያው ሕግጋት ዝንፍ የሚል አይመስልም። "ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያን ካርታ ይዘው ሲሮጡ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዘራፊዎች የሰረቁትን ይዘው ሲሸሹ" ከአንድ ወገን ምስጋና ከሌላ ወገን ኩነኔ ካመጡበት ሥራዎቹ መካከል የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የሰራውን አይዘነጋም። "መለስ በህይወት ሳለ ከአየር መንገድ ወደ ቤተ መንግሥት በሚሄድበት ሰዓት ህጻን፣ አዋቂ ሳይባል የመንገድ ጥግ ይዘው ፊታቸውን ያዞራሉ። 'ደህንነት የለም' በሚል እሱና ሕዝቡ ፊትና ኋላ ይሆኑ ነበር። ከሞተ በኋላ፤ ሬሳው በመኪና ተደርጎ ሲሄድ ሰዎች ከየአካባቢው እየመጡ መኪናው ላይ እየተንጠለጠሉ፣ እየተደፉ ያለቅሱ ነበር. . ." ሥራው የሁለት ዘመናትን ተቃርኖ የሚያሳይ ነው። ኑሮ ሲወደድ፣ ሚዲያ ለፕሮፖጋንዳ መንዣ ሲውል መመልከት እርሳሱን እንዲያነሳ ይስገድደዋል። "የዓመቱ ኮከብ ሆዶች" እና "ወያኔ ስትቆነጠጥ" የተሰኙ ካርቱኖቹን ሲገልጽ፤ "ዛሬ ዘርፈዋል ተብለው የተከሰሱ ሰዎችን እኔ ድሮ ራቁታቸውን ሰርቻቸዋለሁ።" "በእስልምናና ክርስትና መካከል ግጭት ለመፍጠር ተብሎ የተሰራ ዘጋቢ ፊልም ነበር። "ወያኔ ስትቆነጠጥ" በሚል የሰራሁት ካርቱን የእስልምናና ክርስትና ሀይማኖት መሪዎችን ሲቆነጥጡ ያሳያል።" እነዚህ ካርቱኖች ዛሬ ላይ በሀገሪቱ ላይ ለሚስተዋለው አንጻራዊ ለውጥ የድርሻቸውን አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ያምናል። "ያለፉት ዓመታት ልፋቴ ከንቱ አልቀረም" የሚለውም ያለ ምክንያት አይደለም። አንድ ሀገር ከአንድ አስተዳደር ወይም ከአንድ የፖለቲካ ሥርዓት ወደሌላው ብትሸጋገርም፤ ሁሌም መሰናክሎች ስለማይጠፉ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት የለውጥ ድምጽ መሆን ያስፈልጋል። "ካርቱን [ሁሌም] ይተቻል" "ለውጥ ሰው የሚያስፈልገውን ነገር [በአጠቃላይ] አያሟላም። ወደፊትም አያሟላም። ስለዚህ ካርቱን [ሁሌም] ይተቻል።" አለማየሁ እንደሚለው፤ ካርቱኒስት በሥራዎቹ እይታውን ይገልጻል። የሚዝናናበት፣ የሚበሳጭበት፣ የሚቆረቆርበትን ለሕዝብ ያካፍላል። "እንደ ካርቱኒስ በመደመርም በመቀነስም ውስጥ መኖር የለብኝም። ምክንያቱም እንደ ካርቱኒስት በችግሮች ዙሪያ 'ሂውመር' [ፈገግታ] ለመፍጠር ነው የምሞክረው። የሙያው ግዴታ ነው። ጎራ ተይዞ የሚሰራ አይደለም። ሁሌም ውጪ ሆኖ ነው የሚሠራው። መሠራት ያለበት በሕዝብ ወገን ነው። የሕዝብ ድምጽ ነው። ነጻነታቸውን ያጡ፣ ሀሳባቸውን በነጻነት መግለጽ የማይችሉትን ለመግለጽ [ለመወከል] ነው የምንሞክረው።" ዛሬም ችግሮች እንዳሉ ለማሰየት ከሠራቸው አንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ የኢትዮጵያን ካርታ ይዘው ሲሮጡ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዘራፊዎች የሰረቁትን ይዘው ሲሸሹ፣ በየክልሉ ያለውን ሽኩቻም ያሳያል። ካርቱን 'የትግል መሳሪያ'? ካርቱኖች መንግሥት ትኩረት እንዲሰጣቸው የተፈለጉ ነገሮች ማሳያ ሆነው ያገለግላሉ። በፖለቲካ ካርቱኖች ሙሰኞች፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የፈጠሩ ግለሰቦችና፣ ሰብአዊ መብት የጣሱ ሰዎች በጥበባዊ መንገድ ይገለጻሉ። "ካርቱንን ለነጻነት ትግል ቁልፍ መሳሪያ ነው" ተምሳሌታዊ በሆነ መንገድ ሙሰኛው ሆዱ ተቆንዝሮ፣ ጠብ አጫሪው ተንኮል በአእምሮው ሲመላለስ፣ ገዳይ በደም ተነክሮ ይሳላል። ሸረኛ በእባብ እንዲሁም ሌሎች ሰዎችንም እንደየባህሪያቸው በተለያዩ እንስሳት መመሰል ሌላው መንገድ ነው። አለማየሁ ካርቱንን "ለነጻነት ትግል ቁልፍ መሳሪያ ነው" ይለዋል። ከተቀረው ዓለም አንጻር ኢትዮጵያ ውስጥ ካርቱንን የማየት፤ እንደ ሀሳብ ማስተላለፊያ የመጠቀም ልምድ ባይዳብርም፤ የማኅበረሰቡን ድምጽ ለማስተጋባት የዋለባቸው ጊዜያት ይጠቀሳሉ። አሁን ላይ ካለው በላቀ ካርቱን በነጻነት የሚሰራበት ወቅት እንደሚመጣ ያምናል። ካርቱኒስቶችን የሸበቧቸው ስጋቶች እየተቀረፉ እንደሚሄዱም ተስፋ ያደርጋል። "ካርቱን ሲሠራ የግል ወይም የቡድን ጨዋታ ሳይሆን ሀሳብ ላይ ያተኮረ ትችት መኖር አለበት።" በእርግጥ በቂ የካርቱን ሙያተኛ የለም። ያሉትም ጎልተው መውጣት አልቻሉም። ሙያተኞቹ ሀሳባቸውን በነጻነት ለመግለጽ ከመቸገራቸው ባሻገር ለሥራቸው ተመጣጣኝ ክፍያ አለማግኘታቸውም ሌላ ጫና ይፈጥራል። አለማየሁ ወደኋላ እና ወደፊት. . . ያደገው አዲስ ከተማ አካባቢ፣ ለሥነ ጥበብ በተመቸ ቤተሰብ ውስጥ ነው። እናቱ ወረቀት፣ ቀለም. . . ያቀርቡለታል። የፋሽን ዘርፍ ይማርከው ስለነበረም የፋሽን ዲዛይን መጽሔት ይሰጠው ነበር። በልጅነቱ 'ስኬች' ከማድረግ ተነስቶ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለም በሥነ ጥበቡ ገፋበት። አለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ሳለ ዓመታዊ መጽሄት እንዲሠራ ተሰጠው። ያ የመጀመሪያው የኅትመት ውጤቱ ነው። ካርቱን ከተማሪነት ዘመኑ አንስቶ ይስበዋል። ለካርቱን ዝንባሌ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊ ስጦታ እንዳለውም ያምናል። ከኢትዮጵያ ወደ እንግሊዝ ሲሄድ ነበር ካርቱን የተከበረ ጥበብ መሆኑን የተገነዘበው። እዛው እንግሊዝ ውስጥ "ሀበሻኒ" የሚል አስቂኝ የፖለቲካ ኮሚክ መጽሐፍ አሳተሟል። የተለያዩ ዘመናት ነጸብራቅ የሆኑ ሥራዎቹን አሰባስቦ ለማሳተምም ከፀሀይ ፐብሊሸርስ ጋር ተስማምቷል። ከካርቱኖቹ ጎን ለጎን ዋነኛ የገቢ ምንጩ የአኒሜሽን ፕሮዳክሽን፣ የኢሉስትሬሽን መጽሐፍና ስቶሪ ቦርድ ሥራ ነው። ካርቱኖች ሲሠራ ፖለቲካውን እንዲሁም ፈገግታ ለማጫር የፈለገበትን መንገድ የሚረዱ ወዳጆቹን ያማክራል። ሆኖም ካርቱን በስቱድዮ፣ በሙያተኞች በውይይት ቢሰራ ይመርጣል። "ካርቱን እንደ ሀገር ትልቅ ሀላፊነት የሚጠይቅ ነው። ጠንካራ የፖለቲካና ኤድቶሪያል ብቃት ያለው ተቋም ያስፈልጋል። በስቱዲዮና በባለሙያ ታግዞ ሙሉ ሰዓት የሚሰራም ነው።" ፖለቲካዊ እውነታዎች በአለማየሁ ተፈራ እርሳስ
news-54271233
https://www.bbc.com/amharic/news-54271233
ልደቱ አያሌው ፡ "እኛ አቶ ልደቱን አላሰርንም በአደራ ነው እዚህ የተቀመጡት አሉን" የኢዴፓ ፕሬዝደንት አቶ አዳነ ታደሰ
በትናንትናው ዕለት [ማክሰኞ] የምሥራቅ ሸዋ ዞን ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በአንድ መቶ ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ ቢወስንም እንዳልተፈቱና ፖሊስ ሊፈታቸው ፈቃደኛ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለቢቢሲ አመሻሹን ተናግረዋል።
"ፖሊስ ሊፈታ ፈቃደኛ አይደለም። እስከነጭራሹ ሊያናግሩን ፈቃደኛ አይደሉም። ቢሯቸውን ጥለው ጠፉ። ማንም የሚያናግረን አጣን" ያሉት አቶ አዳነ ከቢሾፍቱ ተመልሰውም ወደ አዲስ አበባ እየመጡ እንደሆነ አስረድተዋል። የምሥራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሁለት ወር ያህል በእስር ላይ ያሉት አቶ ልደቱ በዋስ እንዲለቀቁ ለቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የፃፈ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰዋል። ደብዳቤውንም በአባሪነት በመያዝ የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ኃላፊዎችን ቢያናግሩም "እኛ አቶ ልደቱን አላሰርንም በአደራ ነው እዚህ የተቀመጡት ስለዚህ ይህንን የሚመራ ግብረ ኃይል አዳማ ላይ አለ፤ እዚያ ሄዳችሁ ጠይቁ" የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። አቶ ልደቱ የት እንዳሉም በሚጠይቁበት ወቅትም ዐቃቤ ሕግ የሚመለከት ጉዳይ ነው የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸውም አቶ አዳነ ይናገራሉ። ይህንንም ተከትሎ ወደ ምሥራቅ ሸዋ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ በማቅናት ሲጠይቁም "እንደዚህ ብሎ ነገር የለም እንዲፈቱ የታዘዘው የከተማው ፖሊስ መምሪያ ነው፤ ስለዚህ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መከበር አለበት። እኛ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም የምንለው ነገር የለም ሄዳችሁ ንገሩ አሉን" ብለው እንደመለሷቸውም አቶ አዳነ ያስረዳሉ። ወደ ቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተመልሰው የመምሪያውን አዛዥ ኮማንደር ደረጀን ቢጠይቁም በተመሳሳይ መልኩ እነሱ አቶ ልደቱን እንዳላሰሩ እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። "አቶ ልደቱን እኛ አላሰርንም፤ እዚህ የተቀመጡት በአደራ ነው። ስለዚህ ከሚመለከታቸው አካል ጋር ተነጋግረን መልስ እንሰጣችኋለን" ያሏቸው ሲሆን ከሰዓት በኋላ ወደ 7፡30 እንዲመለሱም ቀጠሮ ሰጥተዋቸው እንደነበር ተናግረዋል። በቀጠሯቸው መሰረትም ከ7፡30 እስከ 11 ሰዓት ድረስ ቢቆዩም አዛዡንም ሆነ ሌሎች አመራሮችን ማግኘት አለመቻላቸውንና ጥሩ ምላሽ እንዳልሰጣቸው ይናገራሉ። "የአቶ ልደቱ መርማሪ የነበረውን ኮማንደር አግኝተን ልናናግረው ሞክርን። እኔ አይመለከተኝም ብሎ አመናጭቆን ሄደ" ብለዋል አቶ አዳነ ። ፕሬዚዳንቱ በነገ [ሐሙስ] አዳማ ከተማ ላይ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተፈፃሚ አለመሆኑንም አስመልክቶ አቤቱታቸውንም ለማቅረብ ማቀዳቸውን ገልፀዋል። የሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በቢሾፍቱ ከተማ የተፈጠረውን ሁከት በማነሳሳት፣ መምራትና በገንዘብ መደገፍ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ልደቱ አያሌው ጉዳያቸውን ሲያይ የነበረው ፍርድ ቤት ክሳቸውን ቢዘጋም እንገደና ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ በመያዝ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል። ክሱ ከዚህ በፊት ሲታይ ከነበረበት የቢሾፍቱ ከተማ በመውጣት በአዳማ ከተማ በሚገኝ ፍርድ ቤት እየታየ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።
news-52913458
https://www.bbc.com/amharic/news-52913458
ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛን አቀላጥፎ መናገር የቻለው የማንችስተር ተጫዋች
የሮሪ ከርትስ ጉዳይ ትንግርት ካልተባለ ምን ሊባል ይችላል?
ሮሪ ከርትስ ታሪኩን በአንድ አንቀጽ የሚከተለውን ይመስላል። ሮሪ በ22 ዓመቱ ዘግናኝ የመኪና አደጋ ደረሰበት። ከሳምንታት በኋላ ከሰመመን ነቃ። በቅጡ ተናግሮት የማያውቀውን ፈረንሳይኛ እንደ ልሳን ያንበለብለው ጀመር። ሰው የማያውቀውን ቋንቋ እንዴት ሊናገር ይችላል? ሮሪ ለማንችስተር ታዳጊ ቡድን ተጫዋች ነበር። በሕይወቱ ከኳስ ሌላ ሕልም አልነበረውም። በአንድ ክፉ አጋጣሚ መኪናውን በእንግሊዝ አውራ ጎዳና በፍጥነት ሲያሽከረክር ተገለበጠ። ያን ቀትር ዶፍ እየዘነበ ነበር። መንገዱ ያንሸራትት ነበር። እሱ ከከባድ መኪና ጋር ሲጋጭ ከኋላው በፍጥነት እየተነዱ የነበሩ ስድስት ሌሎች የቤት መኪናዎች ተገጫጭተው እላዩ ላይ ወጡበት። የእርሱ መኪና ጭምድድድ. . . አለች፤ እንደ ካርቶን። እንኳን ሰው ዝንብ ከዚያ አደጋ ይተርፋል ያለ ማንም አልነበረም። ሮሪ ግን ሲፈጥረው በቀላሉ አትሙት ተብሏል መሰለኝ. . .፡፡ ራሱን ሳተ እንጂ ነፍሱ አልወጣችም ነበር። አምቡላንስ መጣ፤ ሆስፒታል ተወሰደ። ለሳምንታት አልነቃም። ሐኪሞቹ የዚህ ወጣት ነፍስ የመትረፍ ዕድሏ የተመናመነ እንደሆነ ለቤተሰቦቹ በይፋ ተናገሩ። ኾኖም ግን አንድ በሙከራ ላይ ያለ መድኃኒት እንዳለና ፍቃዳቸው ከሆነ እሱን መድኃኒት ሊወጉት እንደሚችሉ ጠየቁ። ቤተሰቡ ምን አማራጭ ነበረው? እሺ ከማለት ሌላ። የሮሪ ወላጆች ተስማሙ። አዲሱን መድኃኒት ተወጋ። ሆኖም ከሰመመኑ አልተመለሰም። በግማሽ ሞት፣ በግማሽ ሕይወት መሀል ሆኖ ለሳምንታት ራሱን እንደሳተ ቆየ። እውነት ለመናገር ቤተሰቦቹ እርም ለማውጣት በዝግጅት ላይ ነበሩ። ሁሉም ነገር ተስፋ አስቆራጭ በሚመስልበት በዚያ ሰዓት አንድ ማለዳ ሮሪ ዓይኑን ገለጠ። እሱ ሲነቃ አጠገቡ አንዲት ጥቁር ነርስ ነበረች። አንዳች ነገር ማጉረምረም ጀመረ። ቀጥሎ የሆነው ግን ለሳይንስም ግራ ነው የሆነው። ፈረንሳይኛ ቋንቋን ያንበለብለው ነበር። በአጋጣሚ አጠገቡ የነበረችው ጥቁር ነርስ ፈረንሳያዊት ስለነበረች ልጁ የፈረንሳይ ዜጋ እንደሆነ እርግጠኛ ነበረች። ኋላ ላይ አባትየውን ፈረንሳይ የት አካባቢ እንደሚኖሩ የጠየቀቻቸውም ለዚሁ ነበር። እርሳቸው ግን "ኧረ እኛ ከእግሊዝ ነን፤ የምን ፈረንሳይ አመጣሽብኝ?" አሉ። "ታዲያ እንዴት ልጆዎ ፈረንሳያዊ ሊሆን ቻለ? በእናቱ ወገን ይሆን?" ነርሷ ጠየቀች። በፍጹም ጥርጣሬ አልገባትም ነበር። ሆኖም ሮሪ አይሪሽ እንጂ ፍሬንች አልነበረም። እርግጥ ልጅ እያለ ድሮ በትምህርት ቤት መጠነኛ ፈረንሳይኛ ተምሯል። አለ አይደል? ለመግባባት ያህል የምትሆን ፈረንሳይኛ። ያን ከመማሩ ውጪ በዚህ ደረጃ ቋንቋውን አቀላጥፎ ተናግሮት አያውቅም። አይችልምም። እንዲያውም ልጅ እያለ ከተማረው በኋላ ቋንቋውን ተናግሮ ስለማያውቅ ጭራሽ ፈረንሳይኛን እንደማያስታውሰው ነበር የሚታወቀው። ነገር ግን ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛውን አንበለበለው። ይህ ትንግርት ነበር፤ ለሐኪሞቹም፣ ለወላጆቹም፣ ለሳይንስም። ሮሪ ከርትስ በታዳጊነቱ ተስፋ የተጣለበት ተጫዋች ነበር የራሱን ማንነት የረሳው የማንችስተር ተጫዋች ሮሪ ከሳምንታት ሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛ ይናገር እንጂ ማን እንደነበረ በጭራሽ አያውቅም ነበር። ለማንችስተር ታዳጊ ቡድን ይጫወት እንደነበረ ቢነገረው ሊገባው አልቻለም። ኳስ ይወድ እንደነበረ እንኳ ረስቷል። ስላለፈ ሕይወቱ በጭራሽ የሚያስታውሰው ነገር የለም። አንዳችም ነገር! ለምሳሌ ምን ሆኖ ወደ ሆስፒታል እደገባ፣ ጭኑ አካባቢ እንደተሰነጠቀ፣ ክርኑ እንደተሰበረ፣ ጭንቅላቱ እንደተፈለጠ ሁሉ አያውቅም። ፈረንሳይኛ ብቻ ያውቃል። ፈረንሳይኛው እንደ ልሳን. . . እንደ ማር. . . ከአፉ ጠብ ይል ነበር። ሆኖም ብዙ አልዘለቀም። በድንገት ዝም አለ። ፈረንሳይኛው በድንገት እንደ ጉም በነነ። በቃ አቃተው። ተናገር ሲባል ኧረ እኔ ፈረንሳይኛ አልችልም ነበር ያለው። እንዴት ይህ ሊሆን ቻለ? ቅደም አያቶቹ ከፈረንሳይ መሆናቸው ይሆን? "አባቴ ነገሩ አስገርሞት መመራመር ያዘ። የደረሰበት ነገር ቢኖር የእርሱ ቅድመ አያቶች ከሰሜን ምዕራብ ፈረንሳይ ኖርማንዲ ግዛት የሚመዘዙ መሆናቸው ነበር" ይላል ሮሪ። ይህ ዘመን ግን በ1800 አካባቢ መሆኑ ነው። ይህ ታዲያ እንዴት ከሮሪ ፈረንሳይኛ መናገር ጋር ሊገናኝ ይችላል? ቋንቋ እንደ ስኳርና ደም ግፊት በደም አይተላለፍ ነገር! ይተላለፍ ይሆን እንዴ? ሮሪ በእርሱ ላይ የደረሰው ትንግርት እንዴት ዓለምን ሲያነጋግር እንደቆየ ለቢቢሲ ሲናገር "ዩቲዩብ ላይ ስሜን ጉግል ብታደርገው ከእኔ መላምቶች ጋር በተያያዘ ብዙ ቪደዮዎችን ታገኛለህ። አንዳንዱ ቋንቋ በትምህርት ብቻ ሳይሆን በዘር የሚተላለፍና አእምሯችን ጓዳ ሊቀበር እንደሚችል የሚገልጽ ነው" ይላል። ሮሪ የሆሊውድ ተዋናይ መሆኑን ነበር የሚያውቀው ሮሪ ላይ ይህ አደጋ የደረሰው በ2012 ላይ ነበር። ያን ጊዜ ሮሪ 22 ዓመቱ ነበር። ዛሬ 30 ዓመት ደፍኗል። ሮሪ ያን ጊዜ ለማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ ቡደን እየተጫወተ በትርፍ ሰዓቱ ለአንድ ተቋራጭ ኩባንያ በተላላኪነት ይሰራ ነበር። የሚገርመው ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ ዛሬም ድረስ ያ አደጋ እንዴት እንደተፈጠረ ምንም ትዝ አይለውም። ያ አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከትዝታ ቋቱ የተፋቀ ጉዳይ ነው። ሆኖም የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ሮሪ በዚያ ዝናብ በከፍተኛ ፍጥነት እየነዳ በፍጥነት መስመር ሲቀይር ነበር ከፊት ለፊቱ ከሚገኝ ከባድ ተሸከርካሪ ጋር ሄዶ የተላተመው። ከዚያም ከኋላው የነበሩ መኪናዎች እላዩ ላይ ወጡበት። የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች ሮሪን ከተጫኑት ስድስት መኪናዎች ውስጥ ፈልፍለው ለማውጣት ከግማሽ ሰዓት በላይ ወስዶባቸዋል። ያን ጊዜ ትንፋሽ አልነበረውም። ሆኖም አምቡላንስ ውስጥ የመተንፈሻ መሣሪያዎች ተገጥመውለት በርሚንግሀም ወደሚገኘው ቅድስት ኤልዛቤጥ ሆስፒታል ተወሰደ። ሐኪሞች ምን አሉ? ሮሪ የኋላ ታሪኩ ሲጠና 7 ዓመቱ ላይ ሳለ የማጅራት ገትር የመሰለ ሕመም ታሞ እንደነበር ታውቋል። ያን ጊዜም ቢሆን የመትረፍ እድሉ 50 በመቶ ብቻ ነበር። ለ6 ሳምንት በበርሚንግሀም የሕጻናት ሆስፒታል ውስጥ ክትትል ተደረገለት። ከዚያ በኋላ በተወነ ደረጃ ዕይታው ስለተጋረደ መነጽር ማድረግ ጀምሮ ነበር። "ያን ጊዜ ሆስፒታል ከነበርነው ሕጻናት እኔ ብቻ ነኝ የልጅነት ልምሻ ያልያዘኝ። ያለምንም ጉዳት ድኜ ስወጣ ሰው ሁሉ ገርሞት ነበር" ይላል። ይኸው ነው ቅድመ ታሪኩ። ሮሪ ከዚህ በኋላ ምንም የጤና እክል አላጋጠመውም። እንዲያውም ንቁና ቀልጣፋ በመሆኑ እግር ኳስ አካዳሚ ተመዘገበ። ቤተሰቡ የለየለት የበርሚንግሀም ቀንደኛ ደጋፊዎች ናቸው። በ11 ዓመቱ ለበርሚንግሀም የታዳጊ ቡድን እንዲጫወት ተፈቅዶለት ነበር። በ13 ዓመቱ ለሴንትራል አያክስ ቡድን አጥቂ ቦታ ሲጫወት የማንችስተር ዩናይትድ መልማዮች አይተውት ወደዱት፤ ወሰዱት። ከዚህ በኋላ ነበር አሰቃቂው አደጋ የደረሰበት። ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛ መናገሩ ብቻ አይደለም የሮሪ አስገራሚው ነገር። እድሜውንም ረስቶ ነበር። ያኔ 22 ዓመቱ የነበረ ቢሆንም እርሱ ግን የ10 ዓመት ልጅ እንደሆነ ነበር የሚያውቀው። "ውሻዬ የት ሄዳ ነው?" ይላል። "እማዬ ውሻዬን አምጪልኝ" ይለኝ ነበር ትላለች እናቱ። ውሻዋ እኮ ድሮ እሱ ልጅ እያለ ነው እኮ የሞተችው። እርሱ ግን ረስቶታል። ሮሪ በበኩሉ "ቀስ እያልኩ እድሜዬ 10 ሳይሆን 12 እንደነበር ትዝ አለኝ" ይላል። የሚደንቀው ይህ አይደለም። ከሰመመን ከነቃ ከጊዜ በኋላ ደግሞ ሮሪ ራሱን የሆሊውድ ዝነኛ ተዋናይ ማቲው መካነሄይ እንደሆነ ነበር የሚያስበው። ቅዠት ሳይሆን በእውን እርሱ የሆሊውዱ ማቲው ማካነሄይ እንደሆነ በትክክል ያምን ነበር። መጀመርያ እንዲያ ያስብ የነበረው ሆስፒታል አልጋ ላይ ሳለ ነበር። ያስጨንቀው የነበረውም ቶሎ ተነስቶ ቀጣዩን ዝነኛ ፊልሙን መቅረጽ ነበር። እርሱ የኦስካር አሸናፊ ማቲው መካነሄይ እንደነበረ እቺን ታህል ጥርጣሬ አልበረውም። "ክንዴና ጭኔ አካባቢ ተሰብሬ ስለነበር እናቴ ነበረች ሽንት ቤት የምታደርሰኝ። የመጀመሪያ ከሰመመን ነቅቼ ሽንት ቤት ሳለሁ በመስታወት የማየው ልጅ ማን ነው? ስል ግራ ተጋባሁ። አላውቀውም ነበር። ራሴን አላውቀውም። የራሴን መልክ አላውቀውም። እኔ የማውቀው ማቲው መካነሄይን መሆኔን ነበር" ይላል ሮሪ። ምናልባት ሮሪ ያን ጊዜ መስታወቱ የዋሸው ያህል ሳይሰማው አልቀረም። እሱ ቆሞ እንዴት የሌላ ሰው ፊት ያሳየዋል? ሮሪ ከርትስ በቀኝ በኩል ከዳር እና ከግራ ሁለተኛ ህክምናውን ከተከታተሉ ነርሶች አንዷ ሮሪ በየ15 ደቂቃው ይረሳ ጀመር ሮሪ በኅዳር 2012 ከሆስፒታል ሲወጣ አብዛኛውን ነገር ዘንግቶ ነበር። እንኳንስ የድሮውን ይቅርና ከ15 ደቂቃዎች በፊት ያደረገውን ይረሳል። ስለዚህ ማስታወሻ ደብተር ተገዛለት። ምሳ ሲበላ ምሳ በልቻለሁ ብሎ ይጽፋል። ገላውን ታጥቦ እንደወጣ ገላዬን ታጥቢያለሁ ብሎ ይጽፋል። "በዚህ መንገድ የጨረስኩት የማስታወሻ ደብተር ብዛቱ!" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ሮሪ በዚህ መንገድ ማንነቱን መልሶ ለማግኘት ብርቱ ጥረት አደረገ። በመጨረሻም አንድ ዓመት ካገገመ በኋላ ራሱ ልብሱን መቀየር ቻለ። ከዚያ ሙሉ በሙሉ ድኖ ወደሚወደው እግር ኳስ ለመመለስ ሞከረ። ከስድስት ዓመት በፊት ለስቶርፖርት ክለብ መጫወት ጀመረ። ሐኪሞች ማመን አቃታቸው። እንዴት በዚያ ደረጃ የተጎዳ ልጅ ድኖ ኳስ ሊጫወት እንደሚችል ትንግርት ሆነባቸው። "በእርግጥ መገረም ብቻ ሳይሆን እንዳልጫወት መክረውኛል። ምክንያቱም በጭንቅላቴ ኳስ መግጨት ስለማይኖርብኝ ነው። ጭንቅላቴ በአደጋው ተጎድቶ ነበር" ይላል። ምናልባት ሮሪ ቋንቋ ማስታወስ የቻለው የጭንቅላቱ የቋንቋ ቋት በድንገት በሩ ተከፍቶ ይሆን? አንዳንዶች ጭንቅላታችን ከተወለድን ጀምሮ የሚሰማውንና የሚያየውን ነገር ሁሉ ይመዘግባል። እኛ ማስታወስ ስላቃተን ባዶ ይመስለናል እንጂ አእምሮ እጅግ ውስብስብ ተፈጥሮ ነው ይላሉ። ምናልባት ሮሪ ፈረንሳይኛው ከጭንቅላቱ የቋንቋ ቋት ተዘርግፎበት ቢሆንስ? ሮሪ ከርትስ ጸጉር እያስተካከለ ሮሪና አዲሱ መድኃኒት ሮሪ የመኪና አደጋው ከደረሰበት በኋላ በሙከራ ላይ የነበረ የሆርሞን መድኃኒት ወስዷል። ያ መድኃኒት የሰው ልጅ ላይ ሲሞከር ሮሪ በዓለም ሁለተኛው ሰው ነበር። መድኃኒቱ ጭንቅላታቸው አካባቢ ከፍተኛ አደጋ ደርሶባቸው ለተጎዱ ሰዎች እንዲያገግሙ የሚረዳ ነበር። በአሜሪካ ሐኪሞች የተመራው ይህ የመድኃኒት ሙከራ ሲናፕሴ (Synapse) ይባላል። በከፊል ፕሮግሬስትሮን የተሰኘ የሴቶችን ሆርሞን ነበር የተወጋው። ሐኪሞቹ በየሦስት ወራት ሮሪን ይመለከቱት ነበር። ቤተሰቡ ለእሱ በተአምር መትረፍ ይህ መድኃኒት ዋናው እንደሆነ ያስባል። እሱን ይከታተሉት ከነበሩት ሀኪሞች አንዱ የሆኑት ኒውሮሎጂስቱ ዶ/ር አንቶኒ ቤሊ ግን መድኃኒቱ ለእርሱ እንዳልሰራለት ነው የሚናገሩት። ከዚያ ይልቅ የልጁ ጥንካሬና ዘረመሉ ሊሆን ይችላል ለተአምሩ መፈጠር ምክንያት የሆነው። ሮሪ ሙሉ በሙሉ ይዳን እንጂ አሁንም ድረስ ራሱን አግንኖ የማየት ነገር አለበት። "ፍጹም ነኝ ብዬ የማመን ስሜት ይሰማኛል" ይላል። ሮሪ በእግር ኳሱ ብዙ ተስፋ እንደሌለው ሲያስብ ወደ አስተማሪነት ከዚያም ወደ ጸጉር አስተካካይነት ገባ። "እናቴ 6 እህቶች አሏት። ሁሉም አስተማሪዎች ናቸው። እኔም ለምን በጸጉር ሙያ አስተማሪነት አልሞክርም ብዬ ተነሳሁ። አባቴ ዘርማንዘሮቹ ሁሉ ጸጉር አስተካካዮች ነበሩ። ለምን እሱን አልሞክረውም አልኩኝ" ይላል። የአባቱ ድርጅት ቻርሊ ፓርከር ጸጉር ቤት ይባላል። ከ1980ዎቹ ጀምሮ ቤተሰቤ በጸጉር ሥራ ነው ሲተዳደር የኖረው። "ስለዚህ ከእናቴ ቤተሰቦች አስተማሪነትን ከአባቴ ደግሞ ጸጉር አስተካካይነትን ወሰድኩ።" ሮሪ በኋላ ላይ ተምሮ ከተመረቀ በኋላ በበርሚንግሀም ሳውዝ ኤንድ ሲቲ ኮሌጅ ሌክቸረር ሆኖ ተቀጠረ። ጥቂት እንደሰራ ግን የልቡ አልደርስ አለ። ስለዚህ ለምን የራሴን ጸጉር ቤት አልከፍትም ብሎ "ቻርሊ ፓርከርስ ከት ትሮት ኤንድ ኮፊ" የሚባል የውበት ሳሎን ባለፈው ዓመት ከፈተ። መጀመርያ በ11 ዓመቱ፣ በኋላ ደግሞ በ22 ዓመቱ ሞትን በቆረጣ ጎብኝቶ የመጣው ሮሪ ጭንቅላቱ ላይ በደረሰው አደጋ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። እሱ ደግሞ ከጭንቅላት በላይ በሚበቅል ጸጉር መተዳደር ጀምሯል። ስለመጪው እሱም፣ ሐኪሞቹም የሚያውቁት ነገር የለም። እንኳን ስለመጪው ስላለፈውስ መቼ በቅጡ አወቁና. . .
news-55097999
https://www.bbc.com/amharic/news-55097999
ትግራይ፡ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕመድ ማን ናቸው?
"በእኔ እምነት፤ ኢትዮጵያ ጦርት ያስፈልጋታል ብዬ አላስብም። የጦር አማራጭን ከሚመርጡ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መካተት አልፈልግም። ወደ ትግራይ ጥይት ሳይሆን መላክ የምፈልገው ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ነው።"
ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ይህን ያሉት ትግራይን የሚያስተዳድረው ህወሓት አገራዊ ምርጫ እንዲራዘም የተወሰነውን ውሳኔ ወደ ጎን በማለት ክልላዊ ምርጫ ለማድረግ ከወሰነ በኋላ ነበር። በወቅቱ አገራዊ ምርጫው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መራዘሙ ይራወሳል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዳደራቸው ከትግራይ ክልል ጋር የተገባውን እሰጣ እገ በወታደራዊ አማራጭ እንደማይፈታው አስታውቀው ነበር። ዛሬ ላይ ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ ሦስተኛ እና የመጨረሻ ምዕራፍ ያሉትን ዘመቻ የአገር መከላከያ ሠራዊት እንዲፈጽም መታዘዙን አስታውቀዋል። በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት ኃይሎች መካከል የተከሰተው ግጭት ሦስተኛ ሳምንቱን የደፈነ ሲሆን እስካሁን ግጭቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ሳያጡ እንደማይቀር ይገመታል። ተራድኦ ድርጅቶች በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ግጭቱን ሽሽት ከቀያቸው መፈናቀላቸውን እንዲሁም ከ40ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን መሸሻቸው ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ቀውስ ሊከስት ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ስልጣን የመጡት ከሦስት ዓመታት ገደማ በፊት በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ነበር። በወቅቱ ኢትዮጵያ ወደ የእርስ በእርስ ግጭት ለመግባት ከጫ ደርሳለች ተብሎ ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣናቸውን እንደተረከቡ ታሪካዊ የሚባሉ የለውጥ እርምጃዎችን ወስደዋል፤ አንዳንዶቹ ለውጦችም በኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ይሆናሉ ተብለው የማይታሰቡ ነበሩ። ኢትዮጵያ ዘወትር ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻናት እንዳይገልጹ ታደርጋለች፣ ተቃዋሚዎች የሚታሰሩባት እና ለተቃውሞ አደባባይ በሚወጡ ዜጎች ላይ የማያዳግም እርምጃ የምትወስድ አገር ናት እየተባለች በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ የምትተች አገር ነበረች። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ሲመጡ ግን ይህ ሁሉ ተቀየረ። ከኤርትራ ጋራም ሰላም ወረደ። ለዚህ ጥረታቸውን ጠቅላይ ሚንስትሩ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከእርሳቸው በፊት ስልጣን ላይ ከነበሩት እና "ጠላት" ከሚባሉት ጋር ለመገናኘት እንዲሁም ስላም ላማውረድ ቁርጠኛ መሆናቸው ተስተውሏል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አባት ሐምሌ 2011 ላይ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ "ከሁሉም ጋር ጓደኛ የሆነ ልጅ ነው" ሲሉ ልጃቸውን ገልጸው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ማን ናቸው? ጠቅላይ ሚንስትሩ ከኦሮሞ ሕዝብ የተገኙ የኢትዮጵያ መሪ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ያመጣቸው ለሦስት ዓመታት የዘለቀው ተቃውሞ በኦሮሚያ ውስጥ መሠረት ያደረገ ነበር። ለዓመታት በዘለቀው ታውሞ በርካቶች ተገድለዋል በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል። ተቃዋሚዎች ከሚያነሷቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው የኦሮሞ ሕዝብ የኢትዮጵያ ትልቁ ብሔር ሆኖ ሳለ ሕዝቡ ከአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ለዓመታት ተገሎ ቆይቷል የሚል ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩም ወደ ስልጣን ሲመጡ ይህ መቀየር ጀመረ። ዐብይ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) አካል የሆነው የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኢህዴድ) ሊቀመንበር ተደርገው ተሹመው ነበር። ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ለሦስት አስርት ዓመታት ገደማ የኢትዮጵያ ፖለቲካን ተቆጣጥሮ የቆየውን ኢሕአዴግ በማክሰም ብልጽግና የተሰኘና ከቀድሞው ገዢ ፓርቲ ሰፋ ያለ መሰረት ያለውን ፓርቲ መስርተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት በኢሕአዴግ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኖ የቆየው ህወሓት ብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል አልፈለገም። የ44 ዓመቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ክርስቲያን እና ሙስሊም ከሆኑ ወላጆች የተገኙ ሲሆን የተወለዱት ደግሞ በአሉአባቦራ ኦሮሚያ ነው። ዐብይ አህመድ በውትድርና ሕይወታቸው አስከ ሌፍተናንት ኮሎኔል ማዕረግ ለመድረስ ችለዋል። ከዚያም የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ የተባለው ተቋምን መስርተው ይመሩም ነበር። በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ያደርግ በነበረው መንግሥት ውስጥ፤ ይህ ተቋም በአገሪቱ የሚደፈጸሙ የሳይብር - ሴኩሪቲ ጥቃቶችን መከላከል ዋና ዓላማው ነበር። በተከታይነት ደግሞ ዐብይ የአገሪቱ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚንሰትር ሆነው ከተሾሙም በኋላ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሚገኘው የቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ሌሌች እንዲሰማሩ በመፍቀድ ዘርፉን ለማዘመን ቃል ገብተዋል። ቁልፍ እውነታዎች፡ ዐብይ አህመድ ኦሮሞ ከሆኑት ሙስሊም አባላታቸው እና አማራ ከሆኑት ክርስቲያን እናታቸው በአጋሮ ከተማ ተወለዱ። ዐብይ ገና በአስራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ እያሉ ደርግን መታገል ጀምሩ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በሰላም እና ደህኅነት ጥናት የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብለዋል። የማስተርስ ዲግሪያቸውን ደግሞ 'በትራንስፎርሜሽናል ሊደርሺፕ' ከለንደኑ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ግሪንዊች አግኝተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎችን ይናገራሉ። እአአ 1995 ላይ በሩዋንዳ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል ሆነ አገልግለዋል። 1999 ላይ የኢትዮጵያን የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲን አቋቁመዋል። የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቦርድ አባል ሆነውም አገልገለዋል። 2002 ላይ የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅትን (ኦህዴድ) በአባልነት ተቀላቅለው 2007 ላይ የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል መሆን ችለዋል። 2008 ላይ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል። 2010 ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። 2011 ላይ ኢሕአዲግ አንዲከስም ተደርጎ የልጽግና ፓርቲን መሠረቱ። 2012 ላይ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ሰላም እንዲሰፍን ላደረጉት ጥረት የኖቤል የሰላም ሽልማትን ተሸለሙ። 2013 ላይ በትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ መገደዳቸውን አስታወቁ። የኖቤል የሰላም ሽልማት ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ ከኤርትራ ጋር የደረሱት የሰላም ስምምነት በሁለቱ አገራት መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነትም ሰላምም የሌለበት ሁኔታን የቀየረ ነበር። ይህ ተግባራቸውም የ100ኛው የኖቤል ሽልማት አሸናፊ እንዲሆኑ አደርጓቸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በኦስሎ የኖቤል ሽልማታቸውን ሲቀበሉ የሚከተውን ንግግር አድርገው ነበር። "ጦርነት ለመቀስቀስ የሚያስፈልገው የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ነው። ሰላም ለመገንባት ግን መንድር እና ሕዝብ ያስፈልጋል። "ለእኔ ሰላምን መንከባከብ ማለት ዛፍ እንደመትከል እና ማሳደግ ነው። ዛፎች ለማደግ ጥሩ አፍር እና ውሃ እንደሚፈልጉት ሁሉ፤ ሰላምም ያልተቋረጠ ትጋት፣ ያልተቆጠበ ትዕግስት እና ቁርጠኝነትን ይጠይቃል።" ጠቅላይ ሚንሰትሩ ሽልማታቸውን ከተረከቡ በኋላ በአገሪቱ የተከሰተውን "ሞት እና መፈናቀል" ምክንያት በማድረግ የኖቤል ኮሚቴው የሰጠውን ሽልማት እንዲሰርዝ ጥያቄ ያቀረቡ ነበሩ። ይህን ተከትሎም የኖርዌይ ኖቤል ኮሚቴው መግለጫ ለማውጣት ተገዶ ነበር። ኮሚቴው በመግለጫው ለጠቅላይ ሚንስትሩ የኖቤል ሽልማት መስጠቱ ትክክል አልነበረም ብሎ እንደማያስብ አስታውቋል። መደመር ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ 'መደመር' የሚለው ቃል በበርካቶች ዘንድ ጥቅም ላይ ሲውል የቆየ ቃል ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ የመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን ችግር መፍታት የሚያስችል አካሄድ እንደሆነ ይናገራሉ። መደመር የተሰኘው የጠቅላይ ሚንስትሩ መጽሐፍም በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ከታተመ በኋላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ኮፒ መሸጡ ተነግሯል። 280 ገጽ እና 16 ምዕራፎች ያሉት መጽሐፉ የጠቅላይ ሚንስትሩን ፍልስፍና ያትታል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በዘር የተከፋፈለችው ኢትዮጵያን በአንድነት ስሜት እንድትቆም ይሻሉ፤ በተመሳሳይ ብዝሃነት እንዲከበር ይሻሉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ፍልስፍና የተለያዩ ወይም የሚቃረኑ ሃሳቦችን አንድ ላይ በማምጣት መግባባት ላይ መድረስ ይቻላል የሚል መሠረት አለው። ጠቅላይ ሚንሰትሩ እአአ 2017 ላይ በደኢህዴን ስበሰባ ላይ "አንድ አማራጭ ነው ያለን። ይህም አንድ መሆን ነው፤ መተባበር እና እርስ በእርስ መተጋገዝ ብቻ ሳይሆን መኖር እንዲቻለን አንድ መሆን አለብን። ሌላኛው አማራጭ መገዳደል ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የትግራይ ቀውስ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በትግራይ ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ መገደዳቸውን ያስታወቁት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ላይ ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሩን ከዚህ ውሳኔ እንዲደርሱ ያደረገው ምክንያት የህወሓት ኃይሎች የአገር መከላከያ ሠራዊት አንድ አካል በሆነው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል። "ስለዚህ የፌደራሉ መንግሥት ወታደራሚ አማራጭ እንዲወስድ ተገዷል" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ። በጠቅላይ ሚንሰትሩ አስተዳደር እና በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ከለውጡ በኋላ ለርካታ ወራት ቆይቷል። የስልጣን ሽኩቻ፣ ምርጫ እና የተወሰዱ ፖለቲካዊ የለውጥ እርምጃዎች በሁለቱ ወገን መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። ለሦስት አስርት ዓመታት ገደማ ህወሓት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አድራጊ ፈጣሪ ኃይል ሆኖ ቆይቷል። የህወሓት አመራሮች ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግን ከስልጣን ተገፍተናል ሲሉ ይከሳሉ። ጠቅላይ ሚንሰትሩ ለውጥና ማሻሻያዎችን ሲያደርጉ የህወሓት ኃይሎች ግን ደስተኛ አልነበሩም፤ ይህም ፖለቲካዊ ቀውስ አስከተለ። የህወሓት አመራሮች የጠቅላይ ሚንስትሩን ፈጣን የለውጥ እርምጃ ስልጣንን ለማማከል የሚደረግ ጥረት እንደሆነ እና የኢትዮጵያን የፌደራል ሥርዓት ለማፍረስ የሚደረግ ጥረት እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል። ቀጠናዊ ተጽእኖ ጠቅላይ ሚንሰትሩ በአጭር የስልጣን ዘመናቸውን አለመግባባት በተፈጠረባቸው ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በማሸማገል ተልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። በሱዳን ከአል-በሽር መወገድ በኋላ የአገሪቱ ሠራዊትና ተቃዋሚዎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ይህም ድርድር በሱዳን ሠራዊቱና እና ሲቪሎች ስልጣን ተጋርተው አገሪቷ በሽግግር መንግሥት እንድትመራ አስችሏል። ጂቡቲ እና ኤርትራም ዲፕሎማሲያዊ ግነኙነታቸውን እንዲሰያሻሽሉ ጥረት አድርገዋል። ሶማሊያ እና ኬንያም በሚጋጩበት የባሕር ጠረፍ ዙሪያ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሁለቱን አገራት አሸማግለዋል። ይህን ብቻም ሳይሆን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር እና የአማጺያኑ መሪ ሬክ ማቻር ከስምምነት እንዲደርሱ የተቻላቸውን አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በትግራይ እየተወሰደ ያለውን ወታደራዊ እርምጃ "ሕግ የማስከበር እርምጃ ነው" ይሉታል። ከህወሓት ጋር ድርድር እንደማይደረግ እና ዓለም አቀፉ ማኅብሰብም በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ በተደጋጋሚ አሳስበዋል። ትናንት "ሦስተኛ እና የመጨሻ ያሉትን" ወታደራዊ እርምጃ በህወሓት ኃይሎች ላይ እንዲወስድ ለአገር መከላከያ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን አስታውቀዋል። ይህም ወታደራዊ እርምጃም የትግራይ መዲናን መቀለን እና የህወሓት አመራሮችን መቆጣጠር ያለመ ነው። የዚህ ወታደራዊ እርምጃ ውጤት ጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዳደር ኢትዮጵያ እየተጋፈጠቻቸው ያሉትን ውስብስብ ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተለው መንገድ ላይ ለውጥን ሊያስከትል ይችላል። በተጨማሪም ከወታደራዊው ዘመቻ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጀመሩት የለውጥ እርምጃ ይገፉበታል ወይስ በሚከተሉት ዘዴ ላይ ለውጥን ያስከትል እንደሆነ ወደ ፊት የሚታይ ነው።
news-56849412
https://www.bbc.com/amharic/news-56849412
በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ አቅራብያ የኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ ሊከፈት ነው
ከስድስት ወራት በፊት በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ የነበሩ ሁለት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ከአገልገሎት ውጪ መሆናቸውን ተከትሎ በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ አቅራብያ የስደተኞች መጠለያ ሊገነባ መሆኑን የተመድ የስደተኞች ተቋም አስታወቀ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከስደተኞች እና የስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ጋር በመሆን በትግራይ ክልል እንዲዘጉ በተደረጉት ሁለት መጠለያ ጣብያዎች ምትክ በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ አቅራብያ ለመገንባት ቦታ የመለየት ስራ መከናወኑን ለቢቢሲ ገልጿል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በስፍራው ላይ ለኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ ለመገንባት ሕጋዊ ሰነዶች እስኪሟሉ እየጠበቀ መሆኑን ለቢቢሲ በኢሜል በሰጠው ምላሽ ላይ ጨምሮ ገልጿል። እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ የክረምቱ ወራት ከመጀመሩ በፊት ግንባታውን ለማካሄድ እና ስደተኞቹን በቦታው ለማስፈር እቅድ ተይዟል፟። በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤርትራውያን ስደተኞች ጉዳይ ጥቅምት 23 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ የነበሩ ሁለት ትልልቅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች፣ ሕጻጽ እና ሽመልባ፣ ከአገልገሎት ውጪ መሆናቸው ተከትሎ በርካታ ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተበታትነዋል። በወቅቱ በመጠለያ ጣብያዎቹ ተጠልለው የነበሩ ከ 19 ሺህ 200 ኤርትራዊያን ስደተኞች ወደተለያዩ ቦታዎች መሸሻቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል። አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ አዲ ሃሩሽ እና ማይ አይኒ መጠለያዎች ገብተዋል ሲል ኮሚሽኑ አክሎ ገልጾ ነበር። ከእነዚህ ውስጥም እስከ አሁን 2ሺህ 500 የሚሆኑት በአዲስ አበባ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም እያካሄደ ባለው የምዝገባ ስራ መረዳቱን የስደተኞች እና የስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ ተስፋሁን ጎበዛይ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አቶ ተስፋሁን እንደሚሉት ወደ ሁለቱ ካምፖች ከተመለሱት ውጪ ያሉት ስደተኞች የት እንዳሉ ለማወቅ ተፈልጎ ምዝገባ ተደርጓል። አክለውም ፖሊስን ጨምሮ ከተለያዩ የመንግሥት አካላት በተሰበሰበ መረጃ መሰረት ከ 6000 በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች ከመጠለያ ጣብያዎቹ ወጥተው ወደ አዲስ አበባ መጥተዋል ተብሎ እንደሚገመት ተናግረዋል። ምዝገባውንም መጠለያዎቹን ሲያስተዳድር የቆየው የተመድ የስደተኞች ተቋም እና የስደተኞች እና ስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ጋር በጋራ እንዲያካሂድ በተጠየቀው መሰረት እያከናወኑ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከ45,000 በላይ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በአዲስ አበባ መመዝገቡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ ቃል አቀባይ ኤልሳቤጥ አርስንዶርፍ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኃላፊዋ አክለውም ከእነዚህም መካከል 25,255 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ኃላፊዋ በኢሜል በሰጡት ምላሽ ላይ ገልፀዋል። እስከ ሚያዚያ ወር አጋማሽ ድረስ ብቻ 2500 ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የመጡ ኤርትራውያን ስደተኞችን መመዝገባቸውን አክለው ገልፀዋል። ስደተኞቹ ምን ይላሉ? ቢቢሲ ያነጋገራቸው በአዲስ አበባ ያሉ ሶስት ኤርትራዊያን ስደተኞችም እነርሱን ጨምሮ በርካቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል። ነገር ግን አሁን በስራ ላይ ወዳሉት ካምፖች መመለስ እንደማይፈልጉ ግን አልሸሸጉም። ከእነዚህ መካከልም ተከስተ (ስሙ የተቀየረ) ይገኝበታል። በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳሉ የሚገልፀው ወጣቱ በጋራ መኖሪያ ውስጥ በርከት ካሉ ጓደኞቹ ጋር እንደሚኖር ይናገራል። ውጪ ካሉ ዘመዶቹ በሚላክ አነስተኛ ድጎማ እንደሚኖር የሚናገረው ተከስተ፣ ይህ የአብዛኛው ኤርትራዊ ስደተኛ የገቢ አማራጭ መሆኑን ያስረዳል። ምንም እንኳን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ ቢገቡም እሱ እና ጓደኞቹ በትግራይ ክልል ወዳሉ የስደተኛ መጠለያዎች መግባት እንደማይፈልጉ ገልጿል። ይህም ጥቃት ይደርስብናል ከሚል ስጋት የመነጨ እንደሆነ "የኤርትራ ወታደር ነው የሚገድለን በሚል ቁጭት እኛን እንዳያጠቁን ስንል ነው የምንፈራው" በማለት ያስረዳል። የስደተኞች እና የስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ኃላፊው አቶ ተስፋሁን፣ ከዚህ በፊት የሰራነው ስህተት መደገም የለበትም ሲሉ ያብራራሉ። በዚህም የተነሳ መጠለያ ጣብያው፣ ስደተኞቹ ሸሽተው ከመጡበት የስጋት አካባቢ ራቅ ብሎ መቋቋም ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑንም ይገልፃሉ። አዲስ የስደተኛ መጠለያ ጣብያዎችን ለማቋቋም ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው፤ የቦታ መረጣ እና አለማቀፍ መስፈርቶቹን የሚያሟላ ቦታ ማግኘት ግን ገና ብዙ የሚቀረው ስራ መሆኑን ገልፀዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይም ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ የመጡ ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ ነበሩበት የመጠለያ ጣብያ ለመመለስ ያሉባቸውን የደህንነት ስጋቶች ተቋሙ እንደሚረዳ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ኤርትራውያን ስደተኞች እንደሚሉት በጦርነቱ ወቅት በካምፖቹ ውስጥም ጭምር ግጭቶችን ተመለክተዋል፡፡ ከመጠለያ ጣብያዎቻቸው ወጥተው ወደ አቅራቢያ ከተሞች ከዛም ወደ አዲስ አበባ እስከሚደርሱ በነበራቸው ጉዞም እጅግ አሰቃቂ ጥቃቶች እንዳጋጠሟቸውም ይገልፃሉ። ወደ አዲስ አበባ ከመጡ እንዲሁም የተመድ የስደተኞች ተቋም ምዝገባውን ካካሄደ በኋላም እንደ ህክምና ያሉ አገልግሎቶች ሳያገኙ መቆየታቸውን ይናገራሉ። አቶ ተስፋሁን ይህ ችግር መቃለሉን ቢገልፁም፣ ስደተኞቹ ወደ ኤርትራ እንመለሳለን በሚል ስጋት ለወራት ተደብቀው በመቆየታቸው አገልግሎቶች ለመስጠት እንዳላስቻለ አብራርተዋል። በተጨማሪም የሕክምና ወጪዎችን ለመሸፈን ከተመድ የስደተኞች ተቋም ጋር ምክክር እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል። ከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉት ስደተኞች ቢኖሩም ከካምፕ ውጪ ሆነው መኖር የሚፈልጉ ስደተኞችን ቢቢሲ አነጋገራል። አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ወጣት "እኔ ፕሮሰስ አለኝ። ወደ ሌላ አገር እሄደላሁ። ተከራይቼ ነው የምኖረው። ስራም አለኝ። እና ወደ ካምፕ መመለስ አልፈልግም፤ ግን ደሞ ፕሮሰሴ እንዳይቋረጥ ስጋት አለኝ" ሲል ያስረዳል። አቶ ተስፋሁን እንደዚህ ያሉ ከመጠለያ ውጪ መኖር የሚችሉ ስደተኞችን ሁኔታ የሚፈቅድ ህግ ኢትዮጵያ እንዳላት ያስረዳሉ። ነገር ግን ለጋሽ አገራት ከካምፕ ውጪ ስደተኞችን ለማቋቋም የገቡትን የድጋፍ ቃል አላከበሩም አሁንም ያንን እንዲያከብሩ ጥሪ እያደረግንላቸው ነው ብለዋል። በተጨማሪም በአዲስ አበባ የኤርትራዊያን ስደተኞች ቁጥር በድንገት በመጨመሩ ብዙዎች የቤት ኪራይን ጨምሮ ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች መሰማታቸውንም ለዋና ዳይሬክተሩ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ባሉ ሶስት ወራት ብቻ 156 ኤርትውያንን በተለያዩ ምክንያቶች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስተውቆ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን ከካምፕ ውጪ ስደተኞች የሚስተናገዱበት ፖሊሲ የራሱ መርሆች አሉት የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በአዲስ አበባ ብቻ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ ከካምፕ ውጪ መገኘቱ እንዳለ ሆኖ፣ በድንገት ከፍተኛ ጭማሪ መታየቱ የሚያመጣውን ጫና እያጠኑ መሆኑን ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም በአዲስ አበባ ተመዝግበው እየኖሩ ለሚገኙ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች አብረውት ከሚሰሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመሆን ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን እንደሚሰራ ለቢቢሲ ገልጿል። ይህ ከለላ የመስጠት አገልግሎት የተለያዩ ነገሮችን የሚያቅፍ ነው ያሉት የድርጅቱ ቃል አቀባይ፣ ውስን የሆነ የጤና አገልግሎት እና የትምህርት እንዲሁም መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርበውን መሠረታዊ ግልጋሎት የማግኘት መብት ስደተኞቹ እንዳላቸው ጨምረው ይገልፃሉ። ተመድ በአሁኑ ሰዓት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በአዲስ አበባ የገጽ ለገጽ አገልግሎት መስጠት ባይችልም በስልክ እና በኦንላየን አገልግሎቱን እያቀረበ መሆኑን ጨምረው አስታውሰዋል። አዲስ አበባ በግላቸው የመጡ የኤርትራ ተፈናቃዮችን በሚመለከት ሲናገሩ ድርጅቱ ስደተኞቹ ተገቢውን ሰነድ እንዲይዙ እና አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የመለየት ሥራ እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።
46314537
https://www.bbc.com/amharic/46314537
በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ "ተስፋይቱ ምድር" ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ
ሰሞኑን በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ላምበረት በሚገኘው ምኩራባቸው የእስራኤል መንግሥት የገባልን ቃል አላከበረም በሚል የፀሎት አድማ አካሂደዋል።
ወደ እስራኤል እንዲመለሱ ከሶስት አመት በፊት የእስራኤል መንግሥት ቃል ቢገባም ቃሉ እንደታጠፈ ይናገራሉ። ተቃውሞው በኢትዮጵያ ብቻ ውስጥ ሳይሆን በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ የእስራኤል መንግሥት ቃሉን እንዲያከብር እንደጠየቁ በአዲስ አበባ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አንዱአለም ውብ ምህረት ለቢቢሲ ገልጿል። ከጥቂት ዓመታት በፊት በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ላይ የዘር ማምከን ወንጀል ተፈፅሟል በሚል አስተዳደሩ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበታል። ዘርንም በመጨፍጨፍ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ወንጅለውታል። በተደጋጋሚም በቤተ እስራኤላዊያን ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ የዘረኝነት ጥቃትን በመቃወም ከፍተኛ ተቃውሞዎችም ተካሂደዋል። ምንም እንኳን እስራኤል እንደ ሁለተኛ ዜጋ ብታያቸውም አሁንም ሀገራችን እስራኤል ነው የሚሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ፅዮንን ሙጥኝ እንዳሉ ነው። "በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ፅዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን" እንደሚለው ጥቅስ የፅዮን ማዕከልነትን መቼም እንደማይዘነጉ ይናገራሉ። ለአስርት ዓመታትም ወደ እሥራኤል ለመሔድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ 9146 ቤተ እስራኤላውያን ከሶስት ዓመታት በፊት የእስራኤል መንግሥት ሁሉንም እንደሚወስድ ቃል ቢገባም ቃሉን እንዳላከበረ ኢትዮጵያ ላሉ ቤተ እስራኤላውያን የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ኃላፊ አቶ ንጉሴ ዘመነ አለሙ ይናገራል። እንዲህ የተጓጓተተበት ዋነኛው ምክንያት የእስራኤል መንግሥት በተደጋጋሚ የበጀት እጥረትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎች እያስተላለፉ እንደሆነ ገልጿል። ከመጀመሪያው ውሳኔ በተቃርኖም የተቀሩትን ዘጠኝ ሺ ሰዎች አንድ ላይ ሳይሆን በተለያየ ጊዜ 1300ና አንድ ሺ ሰዎች እንደወሰዱ ተናግሯል። "ይህ ውሳኔ ደግሞ ቤተሰብን ከሁለት የሚከፋፍል በመሆኑ መጀመሪያ የተወሰነውን ውሳኔ እንዲከበር እየጠየቅን ነው ያለነው" ይላል። ከተለያየ ሀገር ለሚመጡ ይሁዲዎች የበረራ ወጪያቸውን የእስራኤል መንግሥት የሚሸፍን ሲሆን ከዚያም በተጨማሪ የቤት መግዣና ለአንድ አመት ያህል ሀገሪቱን እስኪለምዱ ድረስ የሚሰጥ ወርሃዊ የኪስ ገንዘብ ይሰጣቸዋል። ለአቶ ንጉሴ ግን የበጀት እጥረት ነው ቢባልም አሳማኝ እንዳልሆነ ይናገራል። ለዚህም እንደ ምሳሌ የሚያነሳው ከሶስት አመታት በፊት የእስራኤል አዲስ ገቢዎች ሚኒስትር የተናገሩትን ነው። የእስራኤል አዲስ ገቢዎች ቢሮ ትርፍ ብር በየዓመቱ በጀት እየተረፈ ሲመልስ እንጂ ተቸግሮ እንደማያውቅ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። "በጀት የሚለው ጉዳይ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ኃላፊዎች ያመጡት ችግር እንጂ እውነት የበጀት እጥረት ነው ብየ አላምንም" ይላል። በእስራኤል ታሪክም በተደጋጋሚ ከመቶ በላይ ኃገራት አዲስ ገቢዎች ሲመጡ የበጀት ችግር አጋጥሞኛል ብላ እስራኤል እንደማታውቅ ይናገራል። ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች እንዲመለሱ በተወሰነበት ሰዓት ነው የበጀት ጥያቄ መነሳት የጀመረው አሁን እንደሆነ ጠቅሶ የዘረኝነትና የፖለቲካ ምክንያቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቅሳል። አቶ አንዱአለም በበኩሉ እንደ ምክንያትነት የሚያቀርበው እስራኤል በአፍሪካውያን ላይ ያላትን እይታ ነው። "የቤንያሚን ኔታንያሁ መንግሥት አቅም አንሶት ሳይሆን ዘረኝነት ነው። ኢትዮጵያዊ እንዲሁም አፍሪካዊ በመሆናችን እንጂ ሀገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም ችግር አላት ብለን አናምንም" ይላል። ለዚህም ምላሽ በእስራኤል የሚገኙ ከ150 ሺ በላይ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያንም እያቀረቡት ያለውም ሀሳብ "ስንመርጥህ ቤተሰቦቻችንን ከኢትዮጵያ እንደምታመጣልን ቃል ስለገባህልን ነው" እንዳሉም አቶ አንዱአለም ለቢቢሲ ገልጿል። ብዙዎች ለአስርት ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ተነጣጥለው እንደሚገኙ የሚናገሩት አቶ አንዱአለም እንደ ምሳሌም የሚያነሱት የራሳቸውን ቤተሰቦች ነው። ከሰባ አመት በላይ ዕድሜ ያላቸው አባትና እናቱ ወደ እስራኤል የሄዱ ከ16 ዓመታት በፊት ሲሆን ሶስት ታናናሽ ወንድሞቹም አብረው ሄደዋል። "ከቤተሰቦቻችን ጋር ኢሰብዓዊና ፍትሀዊ በሆነ ሁኔታ ተለያይተናል። ለምን እንደለያዩን አላውቅም፤ ለመኖር በሚከብድ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው" ይላል አባቱን በሰባት ዓመት ውስጥ አናግሯቸው የማያውቅ ሲሆን የተሰማውንም ለመግለፅ ቃላት ያንሰዋል "ህልውናውን ስቶ ሰው እያነሳ እየጣለው ድምፁን እንኳን ሰምቼ አላውቅም። ይህም በስነ ልቦናየ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አሳድሮብኛል። ጥዋት ማታ ላየው የምፈልገው አባቴን ድምፁን እንኳን መስማት ሲያቅተኝ የሚሰማውን ስሜት መገመት ይቻላል" ይላል። ከዚህም በተጨማሪ እናቱም በለቅሶና በሐዘን ላይ መሆናቸውም የአቶ አንዱአለም የሌት ተቀን ራስ ምታት የሆነበት ጉዳይ ነው። " እናቴ ሌት ተቀን በማልቀስ አይኗ ሁሉ ጎድጉዶ እንደ ሉሲ በአፅም አለች ማለት ይቻላል።" በማለት እናታቸው የደረሰባቸውን ጥልቅ ሀዘንም ይገልፃል። በዚህም ምክንያትም በእስራኤል መንግሥት ላይ ምንም አይነት ተስፋ የለውም "ለእስራኤል መንግሥት ጥሩ አመለካከት የለኝም። በኛ ላይ ያደረሰው ጭካኔ ነው" ይላል ከዚህም በተጨማሪ ቤተ እስራኤላውያን የእስራኤል ባለስልጣናት የፖለቲካ ፍጆታ ማስፈፀሚያ እንደሆኑም አቶ አንዱአለም ይሰማዋል። ለዚህም እንደምሳሌ የሚያነሳው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር ነው። "ከአፍሪካ የወሰድናቸውን ኢትዮጵያውያንን ከፍተኛ ስልጣን በመስጠት ላይ ነን፤ ከኛ ተማሩ" ማለታቸውን ገልፆ ይህ አባባል ግን ፍፁም ከእውነት የራቀ እንደሆነ ይናገራል። በተቃራኒው አቶ አንዱአለም " " እኛ ሰው መስለን አንታያቸውም" ይላሉ። ለአስርት ዓመታትም እስራኤል እንሄዳለን በሚል ጥበቃ ብዙዎች ከገጠር ተሰደው አዲስ አበባ ላይ ኑሮን መቋቋም እንደከበዳቸው አቶ ንጉሴና አቶ አንዱአለም ይናገራሉ። "ኑሮው በጣም ከባድ ነው፤ በእንግልትም ላይ ነው ያሉት ግን ወደ ፅዮን እንሔዳለን ብለው ነው ይህን ያህል መከራ እየከፈሉ ያሉት" ይላል አቶ ንጉስ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መልስ ይሰጡናል የሚል ተስፋ ቢኖራቸውም ጥያቄያቸው መልስ ካላገኘ ምን አይነት እርምጃ ይወስዱ ይሆን? አቶ ንጉሴ የሚለው አለው። " ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ፅዮናዊ ናቸው፤ እንዲሁም በመላው አለም የሚገኙ ይሁዲዎችን ለመመለስ በጣም ከፍተኛ ጥረትም ያደርጋሉ" በሚል አቶ ንጉሴ ተስፋውን ገልጿል። ምላሽ ካልተሰጣቸው በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን በሚሰጡት መመሪያ እንደሚቀጥሉ ይናገራል። የረሀብ አድማ አንዱ የተቃውሞ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሞ ከዚህም በተጨማሪ በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን መፍትሔ ለማግኘት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ወስደውታል። አቶ አንዱአለም በበኩሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን አቅም ስለሌላቸው ይህ እንደሚፈፀምባቸው ጠቁሞ " ወደ አምላክ ከመጮህ ውጭ ምንም ነገር የለም። የኛ ዋስትና እስራኤል ውስጥ ያሉ ቤተ እስራኤላውያን የሚያደርጉት ጫና ይወሰናል" ይላል። የቤተ እስራኤላውያን አመጣጥ የንግሥት ሳባ ልጅ የሆነውን ሚኒልክን አጅቦ ከመምጣት ጋር የሚያይዙት እንዳሉ ሁሉ የእስራኤል በባቢሎናውያን መወረርን ተከትሎ ከተሰደዱት መካከልም እንደሆኑ ታሪክን አጣቅሰው ይናገራሉ። በታሪክ ውስጥም የተለያዩ ስያሜ የተሰጣቸው ሲሆን ቤተ እስራኤል የተባሉትም በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትናን አልቀበልም በማለታቸው እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ይጠቅሳሉ። በተለያዩ አመታትም ቤተ እስራኤላውያንን የመመለስ ስራ የተሰራ ሲሆን ከነዚሀም ውስጥ ኦፐሬሽን ሙሴና ኦፐሬሽን ሰለሞን ይጠቀሳሉ። በነዚህም ጉዞዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን ሄደዋል።
news-47437631
https://www.bbc.com/amharic/news-47437631
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአንድ አመት ውስጥ ምን አከናወኑ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ጥናት ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ይማሩ በነበረበት ወቅት ዮናስ አዳዬ( ፒ ኤች ዲ) የትምህርት ክፍሉ የአካዳሚክ ዳይሬክተር ነበሩ፤ የመመረቂያ ጽሁፋቸውንም በቅርበት ተከታትለዋል፡፡
ለሶሰት ዓመታት በነበራቸው ቆይታ እያንዳንዱን ጊዜና ሰዓት በአግባቡ የመጠቀም መርህን ይከተሉ እንደነበር ያወሳሉ፡፡ •ሃምሳ በመቶ የሚኒስትሮች ሹመት ለሴቶች "ሰዓት በማክበር አንደኛ ናቸው፤ ሁልጊዜም መጀመሪያ የሚገኙት እሳቸው ነበሩ፤ ያኔ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ነበሩ፡፡ ብዙ ጊዜ ፒ ኤች ዲ አራት ዓመት ይፈጃል፤ እርሳቸው ግን በዓለማቀፍ ደረጃ በተቀመጠው የሶስት ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው ያጠናቀቁት፤ብስለታቸውን ያየሁት መጀመሪያ የጥናት መነሻ ሀሳባቸውን ሰያቀርቡ ነው፤ በእስልምናና ክርስትና ኃይማኖቶች ፍልስፍና ላይ ተመስርተው በአጋሮ አካባቢ የነበረውን ልምድ ነበር ያጠኑት፤ የመደመር ፍልስፍናን ያኔም ያንጸባርቁ ነበር " ይላሉ፡፡ አሁን ደግሞ ዐቢይ አህመድ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ከመጡ ዓመት ሊደፍን የተቃረበበት ጊዜ ነው፡፡ እስካሁን ያሳለፏቸው ዓበይት ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች እያሳረፉት ባለው ተጽዕኖ ዙሪያ ዮናስ አዳዬን ጨምሮ የየዘርፉ ምሁራን ኃሳባቸውን አካፍለውናል፡፡ ፖለቲካ በሰላምና ደህንነት ተቋም ጥናት መምህርና ተመራመማሪው ዮናስ አዳዬ(ፒ ኤች ዲ) እንደሚሉት የዐብይ ትልቁ ስኬት ብዙ ሰው በተስፋ እንዲኖር ማድረጋቸው ነው፡፡ "ያለጥፋታቸው ኃሳባቸው ስለተለየ ብቻ ጥፋተኛ፣ ወንጀለኛ፣ ነውጠኛ ተብለው የታሰሩ፣ ብሎም ለማመን የሚከብድ ግፍና መከራ ሲደርስባቸው የቆዩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከእስር እንዲፈቱ ከማድረጋቸውም በላይ ካሁን በኋላም ይህ መሰል በደል እንደማይፈጸም የሚያሳዩ ማሻሻያዎችን ለማድረግ መነሳታቸው ትልቅ መልዕክት አለው፡፡" ዜጎቸ በጎሳቸው፤ በማንነታቸውም ሆነ በቋንቋቸው ምክንያት እንዲሰደዱ መደረጉ ስህተት መሆኑን ማመናቸው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፈለገበት ቦታ እንዲኖር መንገድ እንደከፈተም ይናገራሉ -ተመራማሪው፡፡ ለዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበርና ያንን የሚያግዙ ተቋማትን ለማጠናከር በሚል በብሄራዊ ምርጫ ቦርድና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሹመት አሰጣጥ ያሳዩትን ቁርጠኝነትም ማጣቀሻ ያደርጋሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጎሳ ፖለቲካ ይልቅ ሃገራዊ ሲልም ክፍለ አህጉራዊ ፖለቲካ ማሰብ እንዲሚቻልም በተግባር አሳይተዋል ይላሉ፡፡ "በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን የጠላትነት ስሜት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ አስገራሚ የወዳጅነት መንፈስ መለወጣቸው ከፍተኛ ፖለቲካዊም ሆነ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማስገኘቱ የማይቀር ነው " ነገር ግን አሁንም ቢሆን ከፊታቸው የተጋረጡና በቶሎ ሊፈቱ የሚገባቸው ትላልቅ ፈተናዎች እንዳሉ ነው የሰላምና ደህንነት ጥናት መምህሩ ዮናስ አዳዬ(ፒ ኤች ዲ) የሚናገሩት፡፡ "በየቦታው እያቆጠቆጠ ያለው የጎሳ ነውጠኝነት፣ ራሱ ኢህአዴግ ውስጥ ያለው መከፋፈል እንዲሁም በክልሎች እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ያለው ግልጽ ያልሆነ ግንኙነት አፋጣኝ ምላሽ የሚፈልጉ የወቅቱ አንገብጋቢ ችግሮች ናቸው፡፡" •የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲስ ምዕራፍ ተመራማሪው ዮናስ አዳዬ ችግሮቹን ለመቅረፍ ያግዛሉ ያሏቸውን የግል የመፍትሄ አቅጣጫዎችም አስቀምጠዋል፡፡ " ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ማምጣት በሚባለው የፖለቲካ መርህ መሰረት ፣ ከመገንጠል ይልቅ መደራደርን መሰረት ያደረገ ውይይት ማድረግ፤ ኢሕአዴግን እንደአዲስ የማዋቀሩ ሂደትም በጣም ጥሩ ጅምር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡" ብለዋል። "እንደአዲስአበባ፣ ሃዋሳ፤ ባህርዳርና መቀለ ያሉ ትልልቅ ከተሞች በፌደራል አስተዳደር ሥር ሆነው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በነጻነት እንዲኖር ከዓመታት በፊት ታስቦ የነበረው ዕቅድ ሥራ ላይ መዋል አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡" በማለት የመፍትሔ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ። • በ2018 ጎልተው የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ምጣኔ ኃብት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ በአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር ሲሆኑ በኢትየጵያና በአፍሪካ ኢኮኖሚ ዙሪያ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን አካሂደዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገና ከጅምሩ ሌብነት የበዛበትን ስርዓት ለመታገል መነሳታቸው ከፍተኛ መጠን ያለውን ሃብትን ከምዝበራ በመታደግ የኢኮኖሚው ዕድገት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ማሳረፍ እንደሚችል ይገልጻሉ፡፡ ‹‹ሌብነት ቀላል ከሆነ አምርቶ ከማደግ ይልቅ ሁሉም ያን አጭር መንገድ እየተከተለ በአቋራጭ ይሄዳል ፤የሚሰርቅ እንጂ የሚያምርት አይኖርም፤ ይህ ሂደት ደግሞ የሀገርን ኢኮኖሚ የማውደም አቅም ስለሚኖረው ከሌብነት ይልቅ ሰርቶ የመለወጥን ስሜት ለመፍጠር ይህ ውሳኔያቸው በጣም የሚደገፍ ነው፡፡›› ይላሉ በከባድ ብድር አዋጭነታቸው በአግባቡ ሳይጠና በየቦታው በግዙፍ ፕሮጀክቶችና ግንባታዎች ያለቅጥ የተለጠጠው ኢኮኖሚ ‹ድንገት አዘቅት ውስጥ ሊከተን ይችላል› የሚል ስጋት ለዓመታት እንደነበራቸውና በየመድረኩ ሲናገሩ እንደነበር ያወሳሉ ፕሮፌሰር አለማየሁ፡፡ በምክንያትነት የሚያሰቀምጡት ደግሞ ከጠቅላላ የሃገሪቱ ምርት 10 በመቶ የነበረው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ድርሻ በቅርቡ 20 በመቶ ደረሰ ቢባልም አብላጫውን ቦታ የያዙት የግንባታ ሥራዎች እንጂ የፋብሪካዎች መስፋፋት አለመሆኑን ነው:: ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን የመጡት ሃገሪቱ በብድር ዕዳ ተዘፍቃ ግራ በተጋባችበት ወቅት በመሆኑ ካሁን በኋላ በከፍተኛ ብድር እየተለጠጡ የሚሰሩ ነገሮችን ለማቆም ወሰኑ፤ ከእርሳቸው በፊት የተጀመሩት ፕሮጀክቶች ደግሞ አዋጭነታቸው በአግባቡ ሳይጠና በሌብነት ዕቅድ ውስጥ ገብተው፤ ባልተቀናጀም የሥራ አካሄድ የሚመሩ ስለነበሩ ገና ተገንብተው እንኳን ሳይጠናቀቁ የመክፈያ ጊዜያቸው ይመጣ ነበር፡፡ ስለዚህ ብድሩን በረጅም ጊዜ ለመክፈል የማግባባት ሥራ ሰርተው ተቀባይነት አግኝተዋል›› ይላሉ። እንደ ባለሙያው ኢትዮጵያ በየዓመቱ 17 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ የሚያወጣ ምርት ስታስገባ ወደ ውጪ ከምትልከው የምታገኘው ገቢ ግን 3 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው፡፡ ይህን ክፍተት መሙላት በጣም አስቸጋሪ በመሆኑ ሳቢያ የውጭ ምንዛሬ የመጠባበቂያ ክምችቷ ብዙ ጊዜ የተመናመነ ነው፡፡ " ዐቢይ ሲመጡም የነበራት መጠባበቂያ ከአንድ ወር በላይ ምርት ማስገባት የማትችልበት፤ ከዚያ እየቀነሰ በሄደ ቁጥር ደግሞ እንደመድሃኒት፤ ነዳጅ ያሉ አቅርቦቶችን አደጋ ውስጥ የሚከት በመሆኑ ቢያንስ የሁለት ወራት ክምችት አስገኝተዋል፡፡ " የውጭ ኢንቨስትመንትንም አዲስ ዕይታ ፈጥረውታል፤ ልማት ማለት ለባሃብቶች ቦታ እንዲያለሙ ከመስጠት በዘለለ ሰዉንም ማልማት እንደሆነ ለማሳየት እንደቻሉ ይገልፃሉ፡፡ እንደማሳያም ከ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ነገር ግን ነዋሪዎችን እንደማያፈናቅል የተነገረለትን የለገሃሩን ፕሮጀክት ከሚጠቅሷቸው አንዱ ናቸው፡፡ በፕሮጀክቱ ኢትዮጵያም የ27 በመቶ ድርሻ መውሰዷ ስለውጭ ኢንቨስትመንት የነበረውን አመለካከት መዋቅራዊ በሆነ መንገድ እንደሚለውጥ እምነት አላቸው፡፡ •የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? " ድክመት " ዓለማቀፍ ተቋማትም ሆነ የውጭ ሃገራት ለብድር ሲጠየቁ ከዓለም ባንክና ከዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም ጋር በትብብር የሚሰራ መርሃግብር መኖሩን እንደሚጠይቁ ነው የኢኮኖሚክስ መምህሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ የሚገልጹት እነርሱ ደግሞ የመንግሥትን ግዙፍ ኩባንዎች ወደግል ማዞርን እንደቅድመ ሁኔታም እንደግዴታም ያስቀምጣሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በመንግሥት ይዞታ ሥር የነበሩ የልማት ድርጅቶችን ለግል ኩባንያዎች ክፍት እንዲሆን መወሰናቸው ከዚህ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ቢናገሩም ከዚያ መቅደም የነበረባቸው መደላድሎች ነበሩ ይላሉ፡፡ ‹‹የውጭ ኦኮኖሚ በዋናነት በግል ዘርፍ የሚመራ ነው ፤ እኛ ጋር ግን የተጠናከረ አይደለም ፤ ስለዚህ መጀመሪያ መንግሥት ራሱ ከሃገር ውስጥ የግል ተቋማት ጋር በጥምረት መስራት አለበት፤ ከዚያ በተጨማሪ ደግሞ ወደ ግል የሚዛወሩበት መሰረታዊ መርህ ፍትሃዊ የውድድር ሜዳን ፈጥሮ የተሳለጠ አካሄድ ማበጀት ስለሆነ ፍትሃዊነቱን የሚዳኝ አካል መቋቋም አለበት ካለበለዚያ ከመንግስት የበላይነት(ሞኖፖሊ) ወደ ግለሰቦች የበላይነት( ሞኖፖሊ) ነው የሚሄደው፤ የግለሰብ ኢኮኖሚ ደግሞ በየትኛውም ዓለም ተጠያቂ አያደርግም፡፡›› የሚሉት ባለሙያው አክለውም ‹‹ለምሳሌ ኢትዮ ቴሌኮምን ብንወስድ ገዢው ድርጅት አገልግሎቱን የሚሰጠው በብር ስለሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱንም ቢሆን ለአጭር ጊዜ እንጂ በዘላቂነት አይቀርፈውም፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድም ቢሆን አሁን በመቶኛ የሚያገኘው ትርፍ ከአሜሪካ ሰባት ግንባር ቀደም አየር መንገዶችም በላይ ነው›› ይላሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ የዐቢይና የመንግሥታቸው መሰረታዊ ድክመት ነው የሚሉት ደግሞ በህግና በፖለቲካው ዘርፉ ያደረጓቸውን ዓይነት ማሻሻያዎችም ሆነ ምክረ ሃሳቦችን በኢኮኖሚው አለማካሄዳቸውን ነው፡፡ •የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲስ ምዕራፍ " ኢኮኖሚውን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለማደራጃት ነጻ የሆኑ ባለሙያዎችን ሰብስበው የኢኮኖሚው ፍኖተ ካርታ እንዴት መሆን አለበት ብለው አላማከሩም፤ዕቅዱን የሚነድፈውና የሚያስፈጽመው ባለሞያው እንዲሆን የምጣኔ ሃብት ጉዳይ የአማካሪ ቡድን መቋቋም አለበት፤ የእስካሁኑን አፈጻጸም ቢባል የሚለካው በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማሳካት ከተያዘው እቅድ አንጻር እንደመሆኑ እርሳቸውን ከዚህ አንጻር ለመግምገም የሚያስችል የሰማነው ዕቅድ የለም፡፡" በማለት ይገልፃሉ እናም ሥልጣን ላይ ከመጡ እጭር ጊዜ ቢሆንም ስራ አጥነትን ለመቀነስ፤ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግና ብዙ ጉልበት የሚፈልጉ የተፈበረኩ ምርቶችን በማምጣት ብዙሃኑን ተጠቃሚ ያደረገ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ለኢኮኖሚው ካለፈው የተሻለ ጊዜ እንዲሠጡ ይመክራሉ፡፡
44672024
https://www.bbc.com/amharic/44672024
ዕድሜ ጠገቧ የጥድ መፃሕፍት ቤት መደብር ባለቤት አቶ ተስፋዬ አዳል
በአሁኑ ወቅት መጽሐፍ የሚፈልግ ቢያሻው ወደ ብሔራዊ ቲያትር ካልሆነም ፒያሳ ጊዮርጊስ ማቅናት የተለመደ ነው። የጠፉ መጻሕፍትን የሚፈልግ ደግሞ ሜክሲኮ ሊወርድ ወይም መርካቶ ሊወጣ ይችላል።
የአጋጣሚ ነገር ሆኖ የመጻሕፍት ጉልቶች እጅብ ብለው ነው የሚገኙት። ከአቶ ተስፋዬ በቀር። አቶ ተስፋዬ ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን አጥር ጥግ በፅድ ተከርክሞ በተሠራ መጽሐፍ መሸጫ ውስጥ ተቀምጠው ለደንበኞቻቸው መጻሕፍትን ሲያከራዩና ሲሸጡ ለዘመናት ኖረዋል። ክረምትና ንባብ “ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግሥት ሥራ ሲጀምሩ ጋዜጣ በመሸጥ ነበር። በወቅቱ የነበሩትን እነ ታይም፣ አዲስ ዘመን፣ ኒውስ ዊክ፣ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ሪደርስ ዳይጀስት፣ አፍሪካ ጆርናል፣ ሄራልድ ትሪቢዩን፣ የኤርትራ ድምፅ፣ የድሮዋን ቁም ነገር መጽሔት፣ ጎህን እያዞሩ ይሸጡ ነበር። በንጉሱ ስርዓት መውደቂያ አካባቢ ከመፅሔቶቹ ይልቅ የማኦ ሴቱንግ መፃህፍቶች እየበዙ እንደመጡ ይናገራሉ። እነዚህን መጻሕፍት ከአከፋፋዮች አንዱን በ10 ሳንቲም ዋጋ ተረክበው ሲቀና መቶ ሳይሆን ሀምሳውን በአንድ ቀን ሸጠው ያድራሉ። በወቅቱም ለነዚህ መፃህፍት ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበር ያስታውሳሉ። በዚህም የተነሳ አንዳንድ የሀገር ውስጥ አሳታሚዎች የማኦ ጥቅስን የያዙ፣ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ሥራዎችን፣ አራቱ ድርሰቶች፣ የቦልሼቪክ ፓርቲ፣ የሴቶች ጥያቄ፣ የቬትናም አብዮት የሚሉ የወቅቱን እንቅስቃሴ የሚያንፀባርቁ መጽሐፎች ብቅ ብቅ ማለት እንደጀመሩ ይናገራሉ። እነዚህ መጻሕፍት ሲመጡ በከተማው ፈላጊያቸው ብዙ እንደነበር ከትዝታ ከረጢታቸው ፈትተው አጫውተውናል። አቶ ተስፋዬ እና ባልደረቦቻቸው እነዚህን መጻሕፍት እያመጡ ይቸበችቡት ያዙ። ከዚህ በኋላ ደግሞ በሀገር ውስጥ የነበሩ መፃህፍት የቀድሞ ታላላቅ የሀገራችን ሰዎች የተማሩባቸው፣ ታሪክን የሚነግሩ፣ ከየትምህርት ቤቱ እና ከየድርጅቱ እየወጡ መጣል ጀመሩ። "እነዚህ መጽሐፎች የሚጣሉና የሚወድቁ አልነበሩም" ይላሉ አቶ ተስፋዬ። "ፍቅር እስከ መቃብር"ን በአይፎን 7? በወቅቱ የነበረው መንግሥት ግን መጻሕፍቱ እንዲጣሉ አልያም ተሰብስበው እንዲቃጠሉ ያደርግ እንደነበር አቶ ተስፋየ ያስታውሳሉ። የየትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን ግን እነ አቶ ተስፋዬን እየጠሯቸው ሳይቃጠል ከተጣለበት እንዲወስዱ ያደርጉ ነበር። ስለዚህም እነዚህን መጻሕፍት በትንሽ ዋጋ እየገዙ መሸጥ ጀመሩ። ያኔ እነዚህን መጻሕፍት እያዞሩ መሸጥ መዘዝ ነበረው። መጻሕፍቱ ውስጥ የጃንሆይ ምስል ከተገኘበት ያለምንም ጥያቄ አምስት ወራትን ያሳስር ነበር። ስለዚህ የጃንሆይን ምሥሎች እየፈለጉ መገንጠልና ማስወገድ የግድ ነበር። "በመጻሕፍት የተነሳ ታስሬ አውቃለሁ" የታሰሩበትንም ምክንያት ሲያስረዱም በደርግ ሥርዓት ውስጥ "የሹራብ ነጋዴውም፣ የካልሲ ነጋዴውም አፈሳ ተብሎ ልቅምቅም ተደርጎ ታፈሰ" በማለት ይጀምራሉ። "መጽሐፍት ነጋዴውም ሕገ ወጥ ነው ብለው ያዙን። ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እስከ መጽሐፎቻችን ታሰርን።" አቶ ተስፋዩ እና ሌሎች መፃሕፍት ሻጮች ለ15 ቀን ያህል በእስር ሳሉ ደራሲ ማሞ ውድነህ ለግል ጉዳያቸው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይመጣሉ። በሩ ላይ መጽሐፍ ተደርድሮም ያያሉ። ቀዩን ረዥሙን ደራሲ ማሞ ውድነህን ፖሊሱ አላወቃቸውም ነበር። ጋሽ ማሞ 4 ሰዓት ላይ በእጃቸው ላይ የሆነች ወረቀት ይዘው ነው ወደ ስድስተኛ የገቡት። ቀና ብለው ሲያዩ መጽሐፍ ተደርድሯል። አቶ ማሞ ለካ መጀመርያ መጽሐፉን ሲያዩ ለእስረኞች እንዲያነቡት የመጣላቸው ነው የመሰላቸው። "ዛሬስ ለእስረኞቻችሁ መጽሐፍ ቤት ከፈታችሁ እንዴ?" በማለት እንዳደነቁ አቶ ተስፋዬ ይናገራሉ። የጥበቃ ጓዱ ከመጻሕፍት ነጋዴዎች ጋር አብረው የታሰሩ መጻሕፍት እንደሆኑ አስረዳቸው። ማሞ ውድነህ ሐዘን ገባቸው። በተለይም የኢትዮጵያ ታላላቅ ደራሲያን መፃሕፍትን፣ እነ ፍቅር እስከ መቃብር፣ እነ ከአድማስ ባሻገር፣ የከበደ ሚካኤል፣ የራሳቸው የማሞ ውድነህ...እነዚህ ሁሉ መጻሕፍት ታስረውና ያለፍርድ እዛ ተቀምጠው ሲመለከቱ ማሞ ውድነህ ከፋቸው። በዚህን ጊዜ አቶ ማሞ ከጥበቃ ጓዱ ጋር እሰጥ አገባ ገጠሙ። የጣቢያውን አዛዥም ቢሮው ገብተው ጎትተው በማምጣት ከመፃሕፍቱ ክምር ጋር አፋጠጡት። አዛዡ አላወቅኩም ብሎ ካደ። "ወቅቱ በራሪ ወረቀት የሚበተንበት ስለነበር..." ይላሉ አቶ ተስፋዬ፣ ማሞ ውድነህ በራሪ ወረቀት በእጃቸው እንዳይገኝ መክረው በሌላ ጉዳይ ግን ከጎናቸው መሆናቸውን ጠቅሰው የጣብያው አዛዡንም የመጻሕፍት ሻጮቹን ዳግመኛ እንዳይታሰሩ አደራ ብለው አስፈቷቸው። አቶ ተስፋዬም መጻሕፎቻቸውን ይዘው ወደ መሸጫቸው አመሩ። መጽሐፍን እንደ ጉቦ ከዚያ በኋላም ቢሆን አቶ ተስፋዬ መጽሐፍ ሲሸጡ ከአብዮት ጥበቃ ጋር እየታገሉ እንደነበር አይዘነጉም። ልክ እንደዛሬዎቹ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች ሁሉ ያኔም አብዮት ጥበቃ ሲመጣ መጽሐፎቻቸውን ሰብስበው እየሮጡ፣ ዞር ሲል ደግሞ እየዘረጉ በዚሁ ንግድ ላለፉት 30 ዓመታት ኖረዋል። አቶ ተስፋዬ መጽሐፍን እንደጉቦ ለአብዮት ጥበቃዎቹ ይከፍሉ እንደነበር አይዘነጉትም። "ለልጆቻቸው እንዲያነቡ እያልን እንሰጣቸው ነበር።" ይላሉ። አቶ ተስፋዬ አብረዋቸው ይሸጡ የነበሩ ሰዎች በተለያየ ምክንያት እየተንጠባጠቡ እርሳቸው ብቻ እንደቀሩ ያወሳሉ። እርሳቸው ብቻቸውን ሲቀሩ ደግሞ የአብዮት መጽሐፍ ተፈላጊነት እየቀነሰ መጣ። የነማኦ ሴቱንግ፣ የነካርል ማርክስ መጻሕፍት አንባቢ አጥተው ማዛጋት ጀመሩ። መንግስትም አድሃሪያን ኢምፔሪያሊስቶች ሲል አወገዘ። አንዳንድ ወጣቶች ግን ሹልክ እያሉ እየመጡ ይገዟቸውም ይሸጡላቸው ነበር። ፖስታ ቤት አንድ ግሪካዊ ሚስተር ጃኖቡለስ የሚባል አከፋፋይ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ተስፋየ እርሱ መጽሐፍትን እያሾለከ ይሸጣቸው ነበር። የሶሻሊስት መጻሕፍት እየከሰሙ ሲመጡ በፊት ገዝተው ያነቡ የነበሩ ሰዎች እርሳቸው ጋር እያመጡ ይሸጡላቸዋል። አንባቢም የጠፋ መጽሐፍ ሲፈልግ እርሳቸው ጋር መምጣት ጀመረ። እንዲህ እንዲህ እያሉ አቶ ተስፋዬ ያኛውን ትውልድ ከዚህኛው ጋር በንባብ ያጋመዱ ሆነው እስካሁን ዘለቁ። በተከረከመ ጥድ የተሸፈነው መደብራቸው ለልማት በሚል የፈረሰ ሲሆን ይህ የአቶ ተስፋዬ መፈናቀል በርካታ መፃህፍት አፍቃሪን ያሳዘነ ጉዳይ ነው። የዘመናት ደንበኞቻቸው በተለይም ወጣቶች ጉዳዩን ወደ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በመውሰድ ትኩረት እንዲያገኝ አድርገዋል። አብይ ታደሰ ከነዚህ መካከል አንዱ ነው። እርሱ እንደሚለው የአቶ ተስፋዬ ታሪካዊዋ የጽድ መደብር እንድትፈርስ የሆነው በመንገድ ሥራ ምክንያት ነው። አቶ ተስፋዬን ከድሮ ጀምሮ ያውቃቸው እንደነበር የሚናገረው አብይ፣ ወዳጆቻቸው ባደረጉት ርብርብ መንግሥት በዚያው አቅራቢያ የቆርቆሮ መደብር እንዲያዋቅሩ ፈቅዶላቸዋል። እነ አብይም ይህንኑ በማስተባበር ላይ ናቸው። "እርሳቸው ከሰጡት አገልግሎት አንፃር ይህ ሲያንሳቸው ነው" ይላል አብይ። "ለምሁሩ፣ ወጣቱ እንዲሁም ለከተማው አንባቢ ዕድሜያቸውን የሰጡ እኚህን ሰው እንዴት መጽሐፍ መሸጫ ሥፍራ ያጣሉ" ሲልም ይጠይቃል። እንደ አብይ ሁሉ ሃወኒ ደበበም ከልጅነቷ ጀምሮ የማንበብ ሱሷን ያስታገሰችው ወደ እርሳቸው ጋር በመምጣት ነበር። በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተፃፉ መጻሕፍት ማንበብ ስትፈልግ ጓደኞቼና መምህሮቿ በጠቋሟት መሰረት አቶ ተስፋዬ ጋር እየመጣች ትከራይ ነበር። "ያኔ የእንግሊዘኛ መጽሐፍ አይሸጡም ነበር" ትላለች። አሁን የአቶ ተስፋዬን የዘመን ውለታ ለመመለስ ከሚጣጣሩ ወጣቶች መሐል አንዷ ሆናለች። ዓውደ ርዕይ በማዘጋጀትና በልዩ ልዩ ዘዴዎች ገቢ በማሰባሰብ ያቺን ታሪካዊ መጻሕፍት መደብር ወደ ሥፍራዋ ለመመለስ እየሞከረች ነው። በጽድ እንኳ ባይሆንም በቆርቆሮ!
news-45370912
https://www.bbc.com/amharic/news-45370912
"ዝም አልልም፤ ለምን ዝም እላለሁ"፡ አና ጎሜዝ
ጥያቄ፡- ሰሞኑን አቶ በረከትን ቃለ መጠይቅ አድርገንላቸው ነበር። 'ወ/ሮ አና፣ 'እባክዎ አርፈው ይቀመጡ' ብለዎታል፡፡ እንዲያውም እኚህ ሴትዮ ‹‹የፖርቹጋል ቅኝ ግዛት አስተሳስብ አልለቀቃቸውም››፤ ሲሉ ነው አስተያየት የሰጡት።
ወይዘሮ አና ጎሜዝ፡- ለእንዲህ ዓይነት የወረደ ሐሳብ መልስ መስጠት አልሻም ነበር። አገሬን መስደባቸው ግን ትክክል አይደለም። እኔን እና አገሬን ከቅኝ ግዛት ጋር ማያያዛቸውም አሳፋሪ ነው። በፖርቹጋል እኔ የምታወቀው በጸረ ቅኝ አገዛዝ ተጋድሎዬ ነው። ያውም ቅኝ ግዛትን መጻረር ፈታኝ በሆነበት ዘመን ነው የምልህ። ሕይወቴንም አደጋ ላይ ጥዬ ነው ይሄን ያደረገኩት። ተማሪ እያለሁ ጀምሮ ነው ይሄን ተጋድሎ የፈጸምኩት። ታሪኬ የሚያስረዳውም ይህንን ነው። •«ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» •አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" •ያለመከሰስ መብት ለማን? እስከምን ድረስ? ጥያቄ፡- ሁለታችሁን እንዲህ የቃላት ጦርነት ውስጥ የሚከታችሁ እኛ የማናውቀው ነገር አለ? አና ጎሜዝ፡- ነገሩ በ2005 እኔ የአውሮፓ ምርጫ ታዛቢ ቡድንን መምራት በጀመርኩበት ጊዜ የሆነ ነው። እሱ ያኔ የመንግሥት ተወካይ ነበር። ከእኔና እኔ ከምመራው የምርጫ ታዛቢ ቡድን ጋር እሱ ነበር በየጊዜው የሚገናኘው። የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትርም ነበር። በዚያ የታዛቢ ቡድን አማካኝነት እኔና የቡድኔ አባላት የተደረገውን ማጭበርበር ስላጋለጥን ነው በእኔ ላይ ቂም ይዞ የቆየው። ከበረከት ስምኦን ጋር በጁን 8፣ 2005 የነበረንን ንግግር መቼም አልረሳውም። በመሐል አዲስ አበባ የተደረገውን ግድያ ሰምቼና ሆስፒታሎችን ጎብኝቼ ወዲያውኑ አገኘሁት። የጎበኘኋቸው ሐኪሞችና ነርሶች እያለቀሱ ነበር [በጥይት የተመቱትን] የሚያክሙት፡፡ ሁኔታው አስቆጥቷቸው ነበር። ባየሁት ጉዳይ ላይ መግለጫ እንደምሰጥ በረከትን ነገርኩት። እርሱ በዚህ ውሳኔዬ ተበሳጨ፡፡ ይባስ ብሎ ለተፈጠረው ግድያ ተጠያቂው የአውሮፓ ኅብረት ነው አለኝ። ይህ ብሽቅ የኾነ ሐሳብ ነው። ጥያቄ፡- በቀደም ለታ የትዊተር ገጽዎ አቶ በረከትን ‹‹ርህራሔ የሌለው፣ ዋሾና፣ ጨካኝ›› ብለውታል። አልበዛም? የተጠቀሟቸው ቃላቶች የዲፕሎማት ቋንቋ አይመስልም። አና ጎሜዝ፦ እውነት ስለሆነ ነዋ፣ እውነት ስለሆነ ነው፥ እርሱ ጨካኝና ውሸታም ነው። በ2005 በደንብ አውቀዋለሁ ሰውዬውን። ባህሪው እንደዚያ ነው። እኔ ከአገሪቱ ጋር ምንም ችግር የለብኝም። የኔ ችግር ሁልጊዜም ከአምባገነኖች ጋር ነው። ጥያቄ፡- አሁን ነገሩ ረዥም ጊዜ ሆነው እኮ፤ ለምን አይረሱትም ግን እርስዎ? አና ጎሜዝ፡- ለምን እረሳለሁ?! በ2005ቱ ምርጫ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሞተዋል። የነርሱ ቤተሰቦች ይህን የሚረሱ ይመስልኻል? ስለዚህ እኔም አልረሳም። የሰው ሕይወት ነው የጠፋው፤ ለግድያው ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው ሰዎች አሉ፤ አንዱ አቶ በረከት ነው። ይህን ጉዳይ የግለሰቦች ጉዳይ ለምን ታደርገዋለህ። እኔ በግል ከሰውየው ጋር ምንም ችግር የለብኝም እኮ። ፖለቲካዊ ነው ጉዳዩ። በርካታ ሰዎችን የጨፈጨፈውን ሥርዓት ሲያገለግል የነበረ ሰው ነው። እኔ ለማወቀውና ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ ይሁን ነው እያልኩ ያለሁት። ብቸኛው ተጠያቂ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ሆኖም አንዱና ዋንኛው ነው። ጥያቄ፡- ለማለት የፈለኩት ከእርስዎ ጋር ምርጫውን የታዘቡ፣ የኾነውን የተመለከቱ ብዙ ዲፕሎማቶች ነበሩ፤ አንዳቸውም በእርስዎ መጠን መንግሥት ላይ ትችት ሲሰነዝሩ አልሰማንም። እርስዎ ለምንድነው አንዲህ ነገሩን ለዓመታት የሙጥኝ ያሉት? አና ጎሜዝ፡- ዲፕሎማቶች የተፈጠሩት እንዲዋሹ አይመስለኝም። ዝም አልልም፤ ለምን ዝም እላለሁ፤ በመለስና በአቶ በረከት ትእዛዝ የተገደሉ ሰዎችን አይቻለሁ፤ ስለምን ዝም እላለሁ? አሁንም ላረጋግጥልህ የምፈልገው፤ አሁንም ወደፊትም ዝም አልልም። ሌሎች ዝም ብለዋል ላልከው እኔ ያኔም ያስተጋባሁት የ200 የቡድኔን አባላት በመላው ኢትዮጵያ ተዘዋውረው ያዩትን ነው። ያወጣነው ሪፖርት ደግሞ ከካርተር ሴንተር ካወጣው ሪፖርት ጋር የሚመሳሰል ነው። ነገር ግን ሁሉም ሰው ለአንድ ጉዳይ የሚሰጠው ምላሽ ተመሳሳይ ላይሆን ይችላል። እኔ ባየሁት ነገር እጅግ ተቆጥቻለሁ። የመለስና የበረከት መንግሥት የሕዝብን ድምጽ ያጭበረበረበት መንገድ አናዶኛል። የአውሮፓ አገራት ይህንን መንግሥት እሹሩሩ ያሉበት መንገድ አበሳጭቶኛል። አሁንም ዝም አልልም፤ ወደፊትም ዝም አልልም፤ በእጃቸው የሰው ደም ያለባቸውን እንደ አቶ በረከት ያሉ ሰዎችን በዝምታ አላልፋቸውም። ጥያቄ፡- አቶ በረከት ወንጀለኛ ናቸው ለፍርድ ይቅረቡ እያሉ ነው? አና ጎሜዝ፡- ይሄ ምን ጥያቄ አለው፤ አቶ በረከት ለፍርድ ነው መቅረብ ያለበት። እርግጥ ነው ብቻውን አይደለም፤ ግን ዋናው ሰው ነው፤ ለፍርድ የማይቀርበው ለምንድነው? አሁን ለውጥ ላይ ያለው መንግሥት ወደዚህ ድምዳሜ ላይ ይመጣል የሚል ተስፋ አለኝ። ጥያቄ፡- የአቶ በረከት ስምኦንን ጉዳይ ለጊዜው ገሸሽ እናድርገውና፤ ሌላ ጥያቄ ላንሳ፤ በ2012 አቶ መለስ ዜናዊ በብራስልስ መሞታቸውን ለኢሳት መረጃ ያቀበሉት እርስዎ ኖት እንዴ? አና ጎሜዝ፡- ሊሆን ይችላል። መረጃው ነበረኝ። ያኔ ማንም መለስ ዜናዊ መታመሙን ቀርቶ አገር ውስጥ አለመኖሩንም የሚያውቅ ብዙ ሰው አልነበረም። መሞቱንም ብዙ ሰው አያውቅም ነበር። የነበረኝ መረጃ እጅግ አስተማማኝ የሚባል ነበር። ያን መረጃ ኢሳት የተጠቀመበት ይመስለኛል። ቀደም ብሎ መሞቱን የነገረኝ ምንጭ እጅግ የምተማመንበትና አስተማማኝ ነበር። ጥያቄ፡- ስለዚህ አቶ መለስ የሞቱት በመንግሥት ከተገለጸው ቀን ቀደም ብሎ ነው ብለው በእርግጠኝነት መናገር ይችላሉ? አና ጎሜዝ፡- ያለምንም ጥርጥር። መጀመርያ ብራዚል ለሕክምና ተወስዶ ነበር። ከሐኪሞቹ ጋር በብራዚል ተገናኝቷል። የሕመሙ ሁኔታ የተገመገመው ብራዚል በሚገኙ ስፔሻሊስቶች ነበር። ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ተነገረው። ከዚያ በኋላ ነው ብራስልስ እንዲመጣ የተደረገው። እኔ መረጃውን ባገኘሁበት ቅጽበት ራሱ ከቀናት በፊት መሞቱ ነው የተነገረኝ። ሆኖም በምሥጢር ተይዞ ነበር። ጥያቄ፡- ትክክለኛ ቀኑን ያስታውሱታል? አና ጎሜዝ፡- አላስታውስም ጥያቄ፡- የትኛው በሽታ ለሞት እንደዳረጋቸውስ ያስታውሳሉ? አና ጎሜዝ፡- እ…አንዳች የካንሰር ዓይነት ሕመም ሳይሆን አይቀርም፤ በትክክል ምን እንደነበር እርግጠኛ አይደለሁም። ጥያቄ፡- መንግሥት ለምን መሞታቸውን ዘለግ ላለ ጊዜ መደበቅ የፈለገ ይመስልዎታል? አና ጎሜዝ፡- እነርሱን ነው መጠየቅ ያለብህ። ነገር ግን በአምባገነን መንግሥታት ውስጥ የጠንካራ መሪ ሞት መደበቅ የተለመደ ነው፤ የመለስን ሞት ቀደም ብዬ አውቅ ነበር እያልኩህ አይደለም። እንደሰማሁት መረጃውን ሰጠሁ። ብዙም ሳይቆይ መንግሥትም መሞታቸውን አረጋገጠ። ከዚያ በፊት ግን ስለመታመማቸው እንኳን ለኢትዯጵያ ሕዝብ አልተነገረም ነበር። ጥያቄ፡- እርስዎ መች ነው ግን ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም የሰሙት? አና ጎሜዝ፡- በልጅነቴ ነው። በቅኝ ግዛትና ከቅኝ ግዛትም በፊት በነበረው የአገሬ ታሪክ ወስጥ የኢትዮጵያ ስም ገናና ነው። ፖርቹጋሎች ለረዥም ዓመት ኢትዮጵያ በእግር ተጉዘው ለመድረስ ይሞክሩ ነበር። የፕሪስት ጆን አገር ተብላ ትታወቅ ነበር። የፖርቹጋል አሳሾች ትልቅ ጉጉት ነበራቸው፤ ይቺን አገር ለማየት። እኔ አገሪቱን የረገጥኩት በ97 ምርጫ ጊዜ ነው። የያኔዋ ኮሚሽነር እኔን ወደዚያ እንድሄድ የመረጡኝ ከዚያ በፊት ምንም ዓይነት ግንኙነት ከአገሪቱ ጋር ስላልነበረኝና ገለልተኛ ስለነበርኩ ነበር፤ በቆይታዬ አገሪቱን ተዘዋውሬ ሕዝቡንና ታሪኩን ስረዳ ይህ ሕዝብ ዲሞክራሲ ይገባዋል የሚል እምነት አድሮብኛል። እኔ በአገሬ በጭቆና መኖሬ በጭቆና የሚኖር ሕዝብን እንድረዳ ረድቶኛል። ጨቋኞች ቋንቋቸው ይገባኛል። ዲሞክራሲ የሚል ቃል ያበዛሉ፤ ሽግግር ላይ ነን ይላሉ። በዚህ ጉዳይ ከመለስ ጋር ረዥም ውይይትን አድርገናል። ጥያቄ፡- ዘለግ ያለ ቆይታ ከአቶ መለስ ጋር ከነበርዎ አቶ መለስን ያውቋቸዋል ማለት ነው፤ አቶ መለስን እንዴት ይገልጿቸዋል? አና ጎሜዝ፡- ብልህ አጭበርባሪ (Deviously smart) ነበር፡፡ ጥያቄ፡- ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዳልዎ ይታማሉ፡፡ አና ጎሜዝ፡- (ዘለግ ካለ ሳቅ በኋላ) ይሄ ፌዝ መሆን አለበት። ብርሃኑን አውቀዋለሁ። ባለቤቱን ዶክተር ናርዶስም አውቃታለሁ። ኢትዮጵያ እያለሁ ነው የማውቃት። እሷም ታውቃለች። አሁን የምነግርህን ታሪክ እሷ ራሱ ልትነግርህ ትችላለች። በ2005፣ ጁን 7 ሌሊት ጁን 8 ሊነጋ የኾነ ታሪክ ነው፡፡ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር የነበሩት ቲም ክላርክና ባለቤቱ ቤት ነው ያደርኩት። ያኔ የኔን የሸራተን መኝታ ለብርሃኑ ነጋ ለቅቄ ነው የሄድኩት። ለርሱ ብቻ አይደለም። ባለቤቱም ጭምር። ምክንያቱም ይህን ያደረኩት አደጋ ላይ ስለነበሩ ነው። ሌላ ቦታ ተደብቀው ነበር። የት እንደነበር አሁን አልነግርህም። የተሸሸጉበት ቦታ በመለስ ወታደሮች ሊታሰስ እንደሆነ መረጃ ለአምባሳደር ቲም ደርሶት ነበር። በአምባሳደር ቲም ክላርክና ባለቤቱ ጥያቄ መሠረት የሸራተን ክፍሌን ለብርሃኑና ባለቤቱ ለቅቄላቸዋለሁ። ጥያቄ፡- ይህ ደርጊትዎ በራሱ በወቅቱ እርስዎ ገለልተኛ እንዳልነበሩ የሚያሳይ አይመስልዎትም? በፍጹም! በፍጹም! ሕይወቱ በአምባገነኖች አደጋ ላይ ላለ ለማንኛወም ሰው ላደርገው የምችለውን ነገር ነው ያደረኩት። የዶ/ር ብርሃኑና ባለቤቱ ሕይወት እኮ አደጋ ላይ ነበር። ለዚያም ነው አምባሳደር ቲም ክላርክ እኔ ክፍል እንዲቆዩ የፈለገው። ጥያቄ፡- ብርሃኑን ካነሳን ዘንዳ ወደ ኤርትራ በረሃ መውረዱን ያደንቁለታል? አና ጎሜዝ፡- ለኔ ሊታገል አይደለም እኮ እዚያ የሄደው፤ ሰዎች ሲገፉ የት ድረስ ሊሄዱ እንደሚችሉ እረዳለሁ። አንዳንድ ጊዜ አምባገነኖች ላይ ነፍጥ ማንሳት ሊያስፈልግ ይችላል። ማንዴላም አሸባሪ ሲባሉ ነበር። በሰላማዊ ትግል ነው የማምነው፤ ኾኖም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች፥ ምንም አማራጭ በሌለበት ሁኔታ ይህ ሊሆን እንደሚችልም እረዳለሁ። ጥያቄ፡- ኢትዮጵያዊ ስም እንዳልዎ ያውቁ ይኾን? አና ጎሜዝ፡- አዎ ብዙ ሰዎች ብዙ ስም እንዳወጡልኝ አውቃለሁ። በዋናነት «ጎቤዜ» የሚባለውን ሰምቻለሁ (ሳቅ) ጥያቄ፡- ምን ይሰማዎታል ? አና ጎሜዝ፡- የሚያኮራ ነው። ሆኖም እኔ ከኢትዮጵያ ጋር የምጋራው ህልምና የሚያኮራኝ ነገር ካለ አንድ ነገር ነው፤ እሱም አገሪቱ ወደ እውነተኛ ዲሞክራሲ ተሸጋግራ ማየት። ጥያቄ፡- አንዳንድ ቦታ ሰዎች የተቃውሞና የድጋፍ ሰልፍ ሲወጡ የርስዎን ምሥል መያዝ ጀምረዋል። አና ጎሜዝ፡- ምን ልበልህ …አመሰግናለሁ ስለ እውቅናው፤ ግን በሆነ መልኩ ደግሞ ኃላፊነትም ጭምር ይሰጣል። ስለ ዲሞራሲ ከሚታገሉ ሰዎች ጋር የኔን ምሥል ማየቴ ኢትዮጵያዊያንን በማገዝ እንድገፋበት ነው የሚያደርገኝ፤ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጥሩ ጅምር ላይ ያለ ይመስላል፤ ነገር ግን አስተማማኝ መሠረት ላይ ገና አልተቀመጠም። ጥያቄ፡- ኢትዮጵያዊ ዜግነት የመጠየቅ እቅድ ይኖርዎ ይሆን? ወይም ደግሞ የጡረታ ዘመንዎ በኢትዮጵያ የማድረግ ሐሳብ… ሳቅ- የኢትዮጵያ ወዳጅ ነኝ። ኾኖም የምትለው ዕቅድ የለኝም፤ ራሴን የማየው እንደዚያ ነው። እኔ ራሴን አንድ የዓለም ዜጋ አድርጌ ነው የምቆጥረው ጥያቄ፡- በግልዎ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ጀግና እንደሆኑ ይሰማዎት ይሆን? አና ጎሜዝ፡- እንደዚያ እንደማላስብ ነግሬሀለሁ፤ አሁን የታየውን ተስፋ እንዲለመልም በጣም ተስፋ በማድረግ ላይ ነው ያለሁት። ጥያቄ፡- ሳስበው ቤትዎ በኢትዮጵያዊ ቁሳቁሶች የተሞላ ይመስለኛል። እውነትህን ነው፤ አሁን የማወራህ በብራስልስ ቢሮዬ ሆኜ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ባንዲራ አለ። በአንድ አርቲስት የተሳለ ቆንጆ የአዲስ አበባ ሥዕልም ይታየኛል፡፡ ቤቴም ቢሆን ኢትዮጵያዊያን ወዳጆቼ የሰጡኝ ማስታወሻዎች ይገኛሉ። በ97 ምርጫ የለበስኩት የምርጫ ታዛቢነት የደንብ ልብስም በማስታወሻነት አለ። በርካታ መስቀሎችም አሉኝ፡፡ ከመርካቶ የገዛኋቸው። ጥያቄ፡- ወደ አቶ በረከት ጉዳይ አንድ አፍታ ልመስልዎ። ሰሞኑን በአማርኛ መጽሐፍ ጽፈዋል። የሚተርጉምልዎ በጎ ፈቃደኛ ቢያገኙ የማንበብ ፍላጎት አለዎ? አና ጎሜዝ፡- ብዙ የምሰራቸው ቁምነገሮች አሉ። ብዙ ማንበብ ያለብኝ መጽሐፍት አሉኝ። ለምን ብዬ ነው ዋሾ ነው ብዬ የማምነው ሰው የጻፈውን መጽሐፍ የማነበው። የፕሮፓጋንዳ ፋብሪካ ነው እኮ እሱ። ምናልባት ወደፊት ሥራ ፈት ብሆን ላነበው እችል ይሆናል። ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በሚያደርጉት የበዛ ተሳትፎ… አና ጎሜዝ፡- የበዛ አትበል። የበዛ ነው ብዬ አላምንም። ጥያቄ፡- …… በዚህ ተሳትፎዎ የሚበሳጩ ሰዎች የሉም? አና ጎሜዝ፡- ኦ! ብዙ ስድቦችንና ማንቋሸሾች በማኅበራዊ ሚዲያ በኩል ይደርሱኛል። ከመንግስት ሰዎች ግን እንዲያ ያለ ነገር ዐይቼ አላውቅም። እዚህ ብራሰልስ የማገኛቸው ዲፕሎማቶች በመከባበር ነው የሚያወሩኝ። በ2013 አዲስ አበባ ሄጄ ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለምሳ ጋብዘውኛል። ሌሎችንም አግኝቻለሁ። የተለየ ነገር አላየሁም። ግለሰቦች ግን ይሳደባሉ። መለስ ዜናዊም ‹‹በኢትዮጵያን ሄራልድ›› ጋዜጣ ያን ሁሉ ገጽ ከተቃዋሚ ብር ትቀበላለች ብሎ ሰድቦኛል፡፡ ጥያቄ፡- ወደ አዲስ አበባ የመምጣት ፍላጎት አለዎት? ብዙ ወዳጆቼ ለውጡን ተከትሎ እንድመጣ ይጠይቁኛል። ለመሔድ ብዬ አልሄድም። የማግዘው ነገር ሲኖር ያን አደርጋለሁ፤ ሰሞኑን ለምሳሌ ስቶክሆልም ባሉ ኢትዮጵያዊያን ለውይይት ተጋብዣለሁ። እሄዳለሁ። ጥያቄ፡- ዐብይ አህመድን አግኝተዋቸዋል? አና ጎሜዝ፡- አላገኘሁትም። እስክንድር ነጋን ግን አግኝቼዋለሁ። በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ ጥያቄ፦ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ይገመግሙታል? አና ጎሜዝ፡- መገምገም የምችለው በማገኛቸው ሰዎች ዐይን ነው። ለምሳሌ አንዳርጋቸው ጽጌ እዚህ አውሮፓ ኅብረት ምስክርነት ለመስጠት መጥቶ አግኝቼዋለሁ። ከዐብይ አሕመድ ጋር ቆይታ እንዳደረገ ነግሮኛል። አሱ በዐብይ ላይ ባሳደረው ተስፋ ተደንቂያለሁ። ለዲሞክራሲ ሕይወታቸውን የሰጡ ሰዎች ዐብይ ላይ ተስፋ ካሳደሩ እኔ ተስፋ የማላደርግበት ምክንያት የለም። ጥያቄ፡- ተቃዋሚዎች ሥልጣን ቢይዙም ድምጾትን ማሰማቱን ይቀጥሉበታል? አና ጎሜዝ፦ አዳምጠኝ፤ እኔ በኢትዮጵያ ጉዳይ ኤክስፐርት አይደለሁም። ባየሁት በደል ነው የተነሳሳሁት፥ የዓለማቀፉ ማኀበረሰብ ለኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ጉጉት ያሳየውን ንቀት ነው እዚህ ውሰጥ የከተተኝ። ያ ነው አጋርነቴን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳደርግ የሚያደርገኝ፡፡እኔ ማንም ይሁን ማን ለኢትዮጵያ ደሞክራሲን የሚያመጣ ልቤን ያሸንፈዋል፡፡ በ97 ያየሁትን የማውቀው እኔ ነኝ። ጥያቄ፦ከኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እጅግ የሚያደንቁትን አንድ ሰው ይጥቀሱ ቢባሉ ያ ሰው ማን ነው? ብዙ አሉ እኮ! ለምሳሌ የኦሮሞ ወጣቶች ይሄን አመጽ የጀመሩት ጀግኖች ናቸው። ብዙ ድንቅ ኢትዮጵያዊያን አጋጥመውኛል፤ እነ መረራ፣ እነ እስክንድር… ጥያቄ፡- አንድ ነበር ያልኩዎት? አና ጎሜዝ፦ አንድ ጀግና የለም። ዲሞክራሲ በአንድ ሰው አይገነባም። ብዙ ሰዎች ናቸው የሚገነቡት። እነ አንዳርጋቸው፣ ደግሞ ብርቱካን ሚደቅሳ ድንቅ ሴት ናት። የማይታወቁ ስንት ወጣቶች አሉ። ዐብይ የሚባለውን ሰው መቼ አውቀው ነበር? ሥልጣን ከያዘ በኋላ ነው ስለርሱ የሰማሁት፡፡ ጥያቄ፦ከፖርቱጋል ውጭ በዓለም ላይ ካሉ አገሮች በአንዱ የመኖር ዕድል ቢሰጥዎ የት ይመርጣሉ? አና ጎሜዝ፦ ተመልከት! አሜሪካ እንደ ዲፕሎማት ስኖር ይህ ዓይነቱ ነገር (ግሪንካርድ) ይቀርብልኝ ነበር። እኔ እንዲህ ዓይነት ነገር ደስ አይለኝም። ፖርቹጋላዊት ሆኜ ኖሬ መሞት ነው የምፈልገው። ያ ግን ለሌሎችን አገሮች ከመቆርቆር አይከለክለኝም።
news-45625125
https://www.bbc.com/amharic/news-45625125
ለመብረር የተዘጋጁት የደቡብ አፍሪካ ልጃገረዶች
የ14 ዓመቷ ፓባሎ (ፓቢ) ሌቅሆትሳ አራት መቀመጫ ካለው ትንሽ አውሮፕላን በደስታ ፈንድቃ ዘላ ወጣች።
ፓቢ ሌቅሆትሳ "በጣም አስደናቂ ነበር። ተቆጣጥሬዋለሁ ብዬ አስቤ ነበር ገባህ?" ትላለች በደስታ እየተሽከረከረች። አውሮፕላንን መቆጣጠር ከጆሃንስበርግ ወጣ ብላ ከምትገኘው ሶዌቶ ከተማ ለመጣችው ታዳጊ ከህጻንነቷ ጀምሮ ስታልመው የነበረው ጉዳይ ነበር። በግራንድ ሴንትራል አውሮፕላን ጣቢያ የአየር ማረፊያው ላይ ቆማ በደስታ ትጮሃለች፤ የደስታ ቃላትም ከአንደበቷ እየጎረፉ ነው። • ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ • የምግብ ብክነትን ለማስወገድ አዲስ ፈጠራ "አውሮፕላኗ በጣም የምትግርም ናት። በጣም ደስ ይል ነበር።" ከዚህ ደስታ ጀርባ ያለችው ለደቡብ አፍሪካ የፖሊስ አገልግሎት አብራሪ በመሆን የመጀመሪያዋ የደቡብ አፍሪካዊት ጥቁር ሴት ሬፊልዌ ሌዳብዌ ናት። በተጨማሪም የሀገሪቱ የመጀመሪያ ጥቁር ሴት ሄሊኮፕተር አብራሪ ናት። ይህም የስኬቷን ግማሽ እንኳን አይሆንም። ሬሊፍዌ ገርል ፍላይ ፕሮግራም ኢን አፍሪካ ፋውንዴሽን (ጅኤፍፒኤ) የተባለው እና ወጣት ሴቶችን በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ እንዲሳተፉ አቅማቸውን ለማጎልበት ለተቋቋመው ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት መስራችም ናት። ሬፊልዌ ሌዳብዌ በየዓመቱ ልጃገረዶች ስለ ሮቦቲክስ ኮዲንግ እና አቬዬሽን የሚማሩበት የበረራ ካምፕ ታዘጋጃለች። በዚህም እያንዳንዳቸው ልጃገረዶች በዓመቱ ውሰጥ የሆነ ጊዜ ነጻ የበረራ ትምህርት ያገኛሉ። የአብራሪነት የደንብ ልብሷን ለብሳ የአብራሪነት ተራውን የሚረከቡትን ታዳጊ ልጃገረዶች እየተመለከተች "ልጃገረዶቹ ውጤታማ እንዲሆኑ እፈልጋለሁ። የግድ አብራሪ ለመሆን እንዲመርጡ አይደለም፤ ነገር ግን በራሳቸው የሚተማመኑ ለማህበረሰቡ እና ለምጣኔ ሀብታችን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ብሎም ለህብረተሰባችን መልሰው የሚሰጡ በራሳቸው የሚተማመኑ ወጣት ሴቶች እንዲሆኑ ነው" ትላለች። • አንበሶችን ያባረረው ወጣት ምን አጋጠመው? • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ ለበረራ ያላት ፍቅር ወደ ሌሎች እንዲጋባ ማድረግ ትችላለች። ያም ነው የደቡብ አፍሪካ የሴት አቪዬሽን ባለሙያዎች እና የአፍሪካ የወደፊት የሳይንስ መሪዎችን የማፍራት ህልሟን ለማሳካት ጉልበት የሆናት። በአውሮፕላን ማረፊያው ላይ ቆማ እያለ ሌሎች አብራሪዎች ይጠሯታል፣ እጃቸውን ያውለበልቡላታል፣ ይቀላለዷታል እንዲሁም በረራን የተመለከቱ የተለያዩ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ምክር ይጠይቋታል። ጥያቄያቸውን በፈገግታ ተሞልታ እየመለሰች ለሳምንት የሚዘልቀውን እና 100 ለሚሆኑ ከ14 እስከ 18 ዓመት እድሜ ላላቸው ከደቡብ አፍሪካ እና ቦትስዋና ለመጡ ልጃገረዶች በማጋሊየስበርግ ተራሮች ውስጥ ካምፕ ታዘጋጃለች። ታዳጊ ልጃገረዶች በስልጠናው ካምፕ ውስጥ ይሁንና አንድ ወላጅ ብቻ ባለበት ቤት ከስድስት እህት እና ወንድሞች ጋር በሊምፖፖ ያደገችው ሬፊልዌ 17 ዓመት እስኪሞላት ድረስ አውሮፕላን አጠገብ እንኳን ደርሳ አታውቅም ነበር። ከጆሃንስበርግ ወደ ኬፕታውን እስክትበር እና አውሮፕላኑ በሴት እየበረረ መሆኑን እስካወቀችበት ጊዜ ድረስ በዩንቨርስቲ ቆይታዋ የነበራት እቅድ ሀኪም መሆን ነበር። የደቡብ አፈሪካ አየር መንገድ የበረራ ቡድን አባል ሆና መስራት እስክትጀምር ድረስም ህልሟ ባለበት ተገትቶ ነበር። የግል የበረራ ትምህርት መከታተልም ጀምራ ነበር። ወዲያው ግን አማራጭ የገንዘብ ማግኛ መንገድ እንደሚያስፈልጋት ተገነዘበች። • የ15 ዓመቷ ታዳጊ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ቀልብ እየገዛች ነው • የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች "በደቡብ አፍሪካ ይመለከተዋል ብዬ ለማስበው ኩባንያ ሁሉ ወደ 200 ያህል ደብዳቤዎች ጻፍኩ" ትላለች። በመጨረሻም ሦስቱ መልስ የሰጧት ሲሆን ከእነዚህም መካከል ለሄሊኮፕተር አብራሪነት ስልጠና ገንዘብ እንደሚከፍልላት እና የንግድ አየር መንገድ አብራሪነት ፈቃድ ለማግኘት ያላትን አቅድ እንደሚደግፉላት የገለጸው የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አገልግሎት ይገኝበታል። ሬፊልዌ አሁን ፖሊስን ለቃ ጊዜዋን በአሰልጣኝነት እያሳለፈች ሲሆን፤ ትኩረቷንም በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ሴቶች ፍላጎት እንዲያድርባቸው መስራት ላይ አድርጋለች። ከጆሃንስበርግ የሁለት ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ በሚገኘው አቧራማ እና ደረቅ ተራሮች ውስጥ በሬልፊዌ አራተኛው እና ከእስከዛሬው ሁሉ ትልቁ በሆነው የበረራ ካምፕ ለመሳተፍ ሴቶች በቦታው መድረስ ጀምረዋል። ፓቢ ሌቅሆትሳ (ከመሃል) ከጓደኞቿ ጋር በሙያቸው ስልጡን ናቸው። ሁሉም በሂሳብ እና ሳይንስ ትምህርቶች ከፍተኛ ውጤት ያገኙ ናቸው። ይሁን እንጂ ተመሳሳይነታቸው የሚያበቃው እዚህ ላይ ነው። በቀላሉ ከተለያየ ቤተሰብ እና የኋላ ታሪክ የመጡ ስለሆኑ ከከተሞች የመጡ ልጃገረዶች ሲኖሩ፤ ከግል ትምህርት ቤት የመጡ ልጃገረዶች ከዚህ በፊት ምንም አይነት ጥቁር ወይም ነጭ ጓደኛ ያለነበራቸው አሉ። የካምፕ ቆይታቸው በበረራ ልምምዶች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ከባዶ ተነስቶ በመስራት እንዲሁም ለአነቃቂ ተናጋሪ እንግዶች ምርጥ ምርጥ ጥያቄዎችን በማቅረብ የተሞሉ ናቸው። በጁሃንስበርግ ዩንቨርስቲ የሳይንስ ዲን ፕሮፌሰር ሜየር እንደሚሉት በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ላይ በመላው አፍሪካ በተለይም ልጃገረዶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፈሰስ ወሳኝ ነው። • ከጋና የፈጠራ ሥራዎች ጀርባ ያለው ሥራ ፈጣሪ "ወጣት ሴቶችን ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲያጠኑ ብቻ ሳይሆን በዘርፉ እንዲቆዩ ማበረታታት ጠቃሚ ነው። በቂ ወጣት ሴቶች እና ልጃገረዶች በሳይንስ ስኬታማ ሲሆኑ እያየን አይደለም ይህ መቀየር አለበት" ትላለች። "በተለይ ጥቁር ሴቶች ወደ ዳር ተገፍተዋል። እናም እኛ በዘርፉ ያለን ትንሽ ቁጥር ያለን በመሆኑ ሌሎች እንዲያመለክቱ ማበረታታት እና ስኬታማነታቸውን ለማረጋገጥም ማገዝ አለብን" ትላለች። የቦትስዋና የመጀመሪያዋ ሴት አብራሪ እና በቦትስዋና አየር መንገድ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ሲቪል አቭዬሽን ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው ካፒቴን ሳክሂሌ ንዮኒ ሬይሊንግም ሀሳቡን ይጋራሉ። እሳቸው እንደሚሉት በተለምዶ አቭዬሽን ሴቶች የማይሰሙበት የኢንዱስትሪ ዘርፍ ነበር። ልጃገረዶችም ከፊታቸው ስላላው አስቸጋሪ የሥራ ዘርፍ በካምፕ ቆይታቸው የሚያስፈልገውን በመገንዘብ መዘጋጀታቸው አስፈላጊ ነው ሲሉ ያክላሉ። ታዳጊ ልጃገረዶቹ ከፈጠራቸው ጋር ዝግጅት በኢንተርናሽናል ሶሳይቲ ኦፍ ዊሜን ኤርላይን ፓይለትስ የተጠናከረ መረጃ እንደሚጠቁመው በዓለም ላይ ካሉ አብራሪዎች መካከል ሴቶች 5 በመቶው ብቻ ናቸው። እናም ምንም እንኳ ሬፊልዌ ለእነዚህ ልጃገረዶች መነቃቂያ ብትሆንም ከስኬቷ ጀርባ የገዛ እናቷን ታስቀምጣለች። የሆነው ሆኖ ምን ጽናቱን ከየት አገኘችው? "ሴቶች የዓለማችንን የሕዝብ ብዛት 50 በመቶው ይሸፍናሉ። ሴቶችን ለእነዚያ ሥራዎች ካላዘጋጃችሁ እንጠፋለን።" በአቪዬሽን እና ህዋ ብቻ ሳይሆን በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና ሒሳብ ላይ ማተኮራችን ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም ይህ ልጃገረዶችን "ለወደፊቱ ሥራቸው ተወዳዳሪ ያደርጋቸዋልና። ምንአልባትም ወደማህበረሰባቸው ሊመለሱ ወይም የድህነት እሽክርክሪቱን ሰብረው እንዲወጡ ሊያግዟቸው ይችላሉ።" "በጊዜ ሂደትም ያለመመጣጠኑ ክፍተት ምንአልባትም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን መጥበብ ሊጀመር ይችላል።" "ለዚህ ነው የምንሰራውን የምንሰራው።" ይህ የቢቢሲ ተከታታይ ታሪክ የተዘጋጀው ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው። #bbcinnovators
news-48619242
https://www.bbc.com/amharic/news-48619242
ኢሳያስን ከሥልጣን ለማውረድ ያቀደው'#ይአክል' (ይበቃል) የተሰኘው የኤርትራውያን እንቅስቃሴ
በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለአስርት አመታት በስልጣን ላይ የቆዩትን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ለመጣል ዘመቻ ጀምረዋል።
ለሰላሳ አመታት በስልጣን ላይ የቆዩት የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን መውረድ ተከትሎ ለብዙዎች ተስፋን ሰንቋል። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በትግርኛ፣ አረብኛ፣ ቢለንና ሌሎችም የኤርትራ ቋንቋዎችን በመጠቀም 'ይአክል' (ይበቃል)ን ሃሽታግ በመጠቀም ዳያስፖራ ኤርትራውያን እንቅስቃሴውን ጀምረዋል። • የኢንተርኔቱን ባልቦላ ማን አጠፋው? በተለያዩ ህይወት ላይ ያሉ ኤርትራውያንን አንድ ላይ ማስተባበር የቻለው የትግል ጥሪ ለኤርትራ ነፃነት የታገሉትንና እንዲሁም ታዋቂ ሙዚቀኞችን ሮቤል ሚካኤል፣ ዮሐንስ ቲካቦ ወይም በቅፅል ስሙ 'ወዲ ተካቦ'ን የመሳሰሉ ግለሰቦችን አካቷል። ከስድስት አመታት በፊት ከአገሩ ለመሰደድ የተገደደው ቲካቦ ከሰሞኑ በትግርኛ ባወጣው ቪዲዮ ላይ "መከፋፈል፣ ስደትና አሰቃቂ ጉዞ ይቁም" የሚል መልእክት አስተላልፏል። " ሃገሪቷ ከገባችበት የቀውስ አረንቋ ልትወጣ ይገባል፣ ይበቃታል። ሰዎችን ያለ ምንም ሂደት ወደ ዘብጥያ መወርወር ይበቃል፤ ያለ ህገ መንግሥት መኖር ይበቃል" ብሏል። 'መደበቅ እናቁም!' ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖረው አማኑኤል ዳዋ ዘመቻውን ከጀመሩት ሰዎች መካከል አንዱ ነው፤ መፍራት ማቆም ይበቃል፤ በማለት ሰዎች በአፍሪካ ብቸኛዋ ስለሆነችው የአንድ ፓርቲ ሀገር ኤርትራ እንዲናገሩ ጥሪ አቅርቧል። • በንቅለ ተከላ ዕይታው የተመለሰለት ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ኢሳያስ የስልጣን መንበሩን የተቆጣጠሩት ኤርትራ ነፃነቷን ካገኘች በኋላ በ1985 ዓ.ም ነበር። ከዚያ በኋላ ኤርትራ ምርጫ አድርጋ አታውቅም፤ አንዳንድ ዲሞክራት ነን እንደሚሉ አምባገነን ሀገራት እንኳ የይስሙላ ምርጫ አይካሄድባትም። የኢሳያስ አስተዳደር ተቃዋሚዎች እንዳይንቀሳቀሱ፣ ነፃ መገናኛ ብዙኀን እንዳይኖር ከልክሎ፤ የስርዐቱን ተቺዎች ወደ ዘብጥያ እየወረወረ ወታደራዊ አገልግሎትን በግድ አስፍኖ የስልጣን እድሜውን አርዝሟል ይላሉ ስርአቱን በቅርብ የሚከታተሉ። ይህም በርካታ ኤርትራውያን ሀገራቸውን ጥለው ወደ አውሮጳ ለመሰደድ እንዲወስኑ ያደረገ ሲሆን በርካቶችም በሰሃራ በረሃ እንዲሁም በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ያሰቡበት ሳይደርሱ ቀርተዋል። አንዳንዶች በትዊተር ላይ ሳዋ በግዳጅ ብሔራዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የነበራቸውን ቆይታ በማስታወስ ጽፈዋል።ሳዋ ወጣቶችና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ወታደራዊ ስልጠና የሚያገኙበት ሲሆን የስልጠናው ማብቂያው መቼ እንደሆነ አይታወቅም። • የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ "ይህንን ዘመቻ የጀመርኩት በዚህ ትግል ውስጥ እስከመቼ ድረስ ማንነታችንን ደብቀን እንቆያለን በሚል ነው። ዋነኛ አላማው ራሳችንን በይፋ በመግለጥ ለኤርትራ ሕዝብና መንግሥት መልእክታችንን በግልፅ ማስተላለፍ ነው" በማለት ለቢቢሲ ትግርኛ የተናገረው አማኑኤል ነው። ይህንን የነአማኑኤልን የማህበራዊ ድረገፅ ዘመቻ በእንግሊዝ የገዢው ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ መሪ የሆኑት ሲራክ ባሕሊቢ "በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ላይ ከተጀመሩ ዘመቻዎች ሁሉ መጥፎው" ሲሉት የኤርትራ መንግሥት ደጋፊ የሆነው ተስፋ ኒውስ ድረገፅ ደግሞ "ይህ ዘመቻ የሕወሀት እጅ አለበት" ሲል ይከስሳል። "በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ ያሉ ኤርትራውያን፣ ኤርትራን ለማፈራረስ በሕወሀት እየተነዛብን ያለውን ፕሮፓጋንዳ ሊያምኑ አይገባም" ሲል አስነብቧል ተስፋ የዜና ድረገፅ። አማኑኤል ግን #ይበቃል የሚለው ዘመቻ ላይ የሚቀርቡትን ክሶች ሁሉ ያጣጥላል። • 'የማለዳ ወፍ' ነዎት ወይስ 'የሌሊት'? 'በስውር የሚበተኑ በራሪ ቅጠሎች' በፌስ ቡክና በትዊተር የተጀመረው ዘመቻ አንድ ወዳጅን ወይንም ዝነኛ ሰውን በመምረጥ በኤርትራ ውስጥ ያለው ጭቆናን እንዲናገሩ ያደርጋል። የዚህ ሀሳብ የተወሰደው ከቡኬት ቻሌንጅ ነው። አማኑኤል ይህንን ዘመቻ እንደ ፈር ቀዳጅ ተመልክቶታል። "ከሀገር ውጪ የሚኖሩ ኤርትራውያን የኤርትራ መንግሥትን ብተች ቤተሰቦቼ ላይ ስቃይና እንግልት ይደርሳል መሰረታዊ አገልግሎቶችንም ይነፈጋሉ ብለው መፍራት የለባቸውም" ይላል። የኤርትራ መንግሥት አሁንም በኢንተርኔት እቀባ ላይ ጠንካራ እጆቹን እንዳሳረፈ ነው። አለም አቀፉ የሀገራትን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ይፋ የሚያደርገው ተቋም በኤርትራ ከአጠቃላይ ህዝቡ 1.3 በመቶው ብቻ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው ሲል ይፋ አድርጓል። በሀገር ውስጥ ያሉ አክቲቪስቶች ሀሞታቸውን ኮስተር አድርገው የመንግሥትን ሥራ የሚቃወሙና #ይበቃል የሚል በራሪ ወረቀትን በድብቅ በመበተን ዘመቻው በሀገር ቤት ውስጥ እንዲታወቅና ስር እንዲሰድ የአቅማቸውን ጥረት እያደረጉ ነው። "በሀገር ውስጥ በህቡዕ የሚንቀሳቀስ የወጣቶች ቡድን አለ፤ እርሱ ነው #ይበቃል የሚለውን በራሪ ወረቀት በሀገር ውስጥ እንዲበተን የአንበሳውን ድርሻ የተወጣው" ብሏል አማኑኤል። ይህ ዘመቻ ይላል ጉዳዩን ሲያብራራ "ይህ ዘመቻ የመንግሥት ተቃዋሚዎችንም ወደ አንድነት ለማምጣት ያለመ ነው።" • ኤርትራ በቤተ ክርስቲያን ስር ያሉ የጤና ተቋማትን ወሰደች "ዜጎች በሚኖሩበት ማህበረሰብ፣ በተወለዱበት ቦታ፣ በሀይማኖታቸው፣ እና በሌሎች የሕይወት ትንንሽ ቡድኖች ተከፋፍለዋል። ይህንን መከፋፈል በማቆም ኃይላችንን ሁሉ በማስተባበር የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዲመጣ መስራት አለብን" ይላል አማኑኤል። በርካታ ኤርትራውያን ባለፈው ዓመት ሀምሌ ወር ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ስምምነት ሲፈፅሙ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውንና ለሁለት አስርታት የዘለቀውን የድንበር ግጭት መቆም ተከትሎ በኤርትራ የፖለቲካው ምህዳር ሰፋ ይላል ብለው ተስፋ አድርገው ነበር። ነገር ግን የጠበቁት ተስፋ እንደ ጉም በኖ ጠፋ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስም ሁሌም በሚታወቁበት አምባገነነን አስተዳደራቸው ቀጠሉ። ከኢትዮጵያ ጋር የሰላም ስምምነቱ ከተደረገ በኋላ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አንዴ ብቻ ነው የካቢኔ ስብሰባ ያደረጉት። ኤርትራ የ26ኛ አመት የነፃነት በዓሏን ስታከብር ባደረጉት ንግግርም ምንም አይነት የስርአት ማሻሻያም ሆነ የለውጥ ፍንጭ አልሰጡም። ይህም ተቃዋሚዎችን ሀገሪቱ በአንድ ፓርቲ አመራር ስር ብቻ ሳትሆን በአንድ ሰው አገዛዝ ስር ወድቃለች እንዲሉ አድርጓቸዋል። በዚህ መካከል ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከኢትዮጵያ ጋር የመሰረቱትን አዲስ ወዳጅነት ተገን አድርገው በስደት ያሉ ተቃዋሚ ቡድኖችን እያፈኑ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ። ከእነዚህም መካከል በአዲስ አበባ ቢሮውን ከፍቶ ይንቀሳቀስ የነበረው የተቃዋሚ ቡድን የኤርትራ ኢምባሲ ከ20 ዓመት በኋላ መከፈቱን በመከተል የእርሱ ቢሮ ተዘግቷል። "ተግዳሮቶችና ተስፋዎች" የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ጥሎት የነበረውን ማእቀብ አንስቷል። ማእቀቡ መሳሪያ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እና ወደታደራዊ መኮንኖች የሚያደርጉት ጉዞንም ያካትት ነበር። አክቲቪስተች በሀገር ውስጥ ያለው የተቃውሞ ማእበል ቀስ በቀስ ማደጉ አይቀርም ሲሉ ተስፋ አድርገዋል። ለዚህም ምሳሌ ብለው የጠቀሱት በቅርቡ በኤርትራ የሚኖሩ የካቶሊክ ጳጰስ የፃፉትን ደብዳቤ ነው። ደብዳቤው በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ ከመሻሻል ይልቅ እየባሰበት በመሄዱ በርካቶች እየፈለሱ መሆኑን የሚጠቅስ ነው። ጳጳሱ "በሀገር ውስጥ ያለው ብልሹ ሁኔታ እስካልተቀየረ ድረስ ወደ ሰው ሀገር መሰደዱ ቀጣይ ነው የሚሆነው" ብለዋል። ከአንድ መቶ በላይ አፍሪካውያን ደራሲዎችና አክቲቪስቶች በጋራ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ በጻፉት ግልፅ ደብዳቤ "ኤርትራ በአህጉራችን በጣም ዝግ ከሆኑ ሀገራት መካከል ነች" ስለዚህም ፕሬዝዳንቱ "ኤርትራ ከሌሎች አፍሪካ ሀገራት ጎን" እንደትቆም ተገቢውን ማሻሻያ መውሰድ አለባቸው ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ በደራሲያኑና ታዋቂ ሰዎቹ ሀሳብ ይስማሙ ወይንም በሱዳን እንደታየው ህዝባዊ እንቢተኝነት ተከስቶ ከስልጣን መወገድን ይስጉ ምን አይነት ፍንጭ የለም። • የአክሱም ሙስሊሞች ጥያቄ መቼ ምላሽ ያገኝ ይሆን? በሱዳን የተቀሰቀሰው ህዝባዊ እንቢተኝነት ከወታደራዊ ኃይሉ ጥቃት ቢደርስበትም ኤርትራውያን አክቲቪስቶች ግን ከተቃውሞው በጎ ነገር ለመቅሰም አሰፍስፈዋል። " በሱዳን ውስጥ የተከናወነው ያሳዝናል የደረሰውን በቃላት ማስቀመጥ ይቸግረኛል። ነገር ግን የሱዳን ህዝቦች በአንድነት በመሆን አምባገነኑን ስርዓት ተጋፍጠውታል። ያ ለእኔ እና በመላ ዓለም ለምንገኘው ኤርትራውያን አነሳሽ ነው" ብላለች ስውዲን ውስጥ ነዋሪነቷን ያደረገችው ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ሜሮን እስጢፋኖስ። "የሱዳን ሕዝቦች ሰላማዊ ትግል መርጠዋል ያ ደግሞ ለኛም ሕዝብ ይሰራል ብዬ አምናለሁ። ሱዳኖች ያለባቸውን ጭቆና ተቋቁመው ካደረጉት እኛ የማናደርግበት ምክንያት የለም።" በማለት ሃሳቧን ትቋጫለች