input
stringlengths
1
130k
ከዚያም አንድ ግቢ ውስጥ አስገቡን ያለው ታሪኩ ኹኔታውን ያብራራል።
ግቢ ውስጥ እንደገባን ከመኪናው ላይ እየጉተቱ ካወረዱን በኋላ የያዝነውን ዕቃ ፊት ለፊት እንድናስቀምጥ ካደረጉን በኋላ በየተራ እያስቆሙ እያመናጨቁ ፈተሹን።
ወንዶችን ለብቻ ሴቶችንም ለብቻ ካደረጉን በኋላ የመጡት ወታደሮች ሁሉ ከ ጊዜ በላይ ቆጠሩን።
ወደ ፊታችን ሁለት ሰዎች መተው ቆሙ አንደኛው የእጅ ሽጉጥ የያዘ ሲሆን ሁለተኛው ሽመል ይዟል።
ባለመሣሪያው የአካባቢው የፀጥታ ክፍል ኃላፊ ሲሆን ባለሽመሉ የፖሊስ ኮሚሽን ነው።
ሁለቱ ሰዎች ወደኛ እንደቀረቡ ወታደሮቹም ዙሪያችንን ከበው እጃቸውን የመሣሪያቸው መላጭ ላይ አደረጉ በማለት ይቀጥላል የታሪኩ ጽሑፍ።
ወደ አካባቢው ዘመን ድራማን ለመሥራት ሲሄዱም ለ ኛ ጊዜያቸው እንደነበር ጽፏል።
ምክንያቱም ይላል ታሪኩ ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃ ማሪያም ደሳለኝ ስለነበሩ ነው።
እኛም ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ካሉበት ኬ ሜ እርቀት ላይ ነበርን።
ዳሩ መንግሥት የመንግስት ብቻ እንደሆነ ህዝብም ህዝብ እንደሆነ በአንድ ሀገር ሳንተያይ መኖር ከጀምርን አመት አልፎናል ሲልም ጽሑፉን አጠቃሏል።
የዳዊት ጽሑፍ፦ የዘመን ድራማ ፕሮዲውሰሮች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለምን ችግር ገጠማቸው
የቡድኑ አባላት ወደ ክልሉ ለቀረጻ የገቡት ከክልሉ መንግሥት እውቅና ውጪ በድብቅ ነው ብሏል ዳዊት።
ዳዊት ከአካባቢው የጸጥታ ኃላፊ አገኘሁት ባለው መረጃ የ ዘመን ድራማ ፕሮዲውሰሮች ውጭ ከሚገኝ ድርጅት ጋር ግንኙነት አድርገዋል ይላል።
ዳዊት በጽሑፉ ማጠቃለያ ላይ ባሰፈረው ዐረፍተ ነገር ግን ከላይ የገለጠውን የራሱን ክስ የሚቃረን ጽሑፍ ጽፏል።
ሳያስፈቅዱ ለቀረጻ መግባታቸው ብቻውን ከጥርጣሬ በዘለለ የውጭ ኃይል ተባባሪ ናቸው ብሎ ለመደምደም አያበቃም በሚል።
ድርቅ የሚያጠቃው የሽንሌ ዞን ከፊል ገጽታ የ ዘመን ድራማ ደራሲ መስፍን ጌታቸው ለዳዊት አጭር መልእክት በፌስቡክ አስፍሯል።
ስህተት በመሠራቱም በአግባቡ ይቅርታ ተጠይቀን ነው የተለቀቅነው ይላል መስፍን አክሎም ከዛ በኋላም እስካሁን ድረስ ሥራችንን በስፍራው እየሠራን እንገኛለን ብሏል።
ሽንሌ ከድሬዳዋ በ ኪ ሜ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች።
ሁሌም ቢሆን ለእውነት ዋጋ መስጠት ትልቅነት ነው ሲል አጠቃሏል።
ይኽ በ ዘመን ድራማ ሠራተኞች ላይ ደረሰ የተባለውን እንግልት የሚገልጸዉን መረጃ በርካቶች በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ተቀባብለውታል።
ጣና ሐይቅ ካለፉት አራት እና አምስት ዓመታት አንስቶ በመጤ አረም የመወረሩ ዜና በርካቶችን አስደንግጧል።
አረሙ በአፋጣኝ ካልተወገደ በዓባይ ምንጭነቱ የሚታወቀው የጣና ሐይቅን ሊያደርቀው ይችላል ተብሏል።
ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ዶይቸ ቬለ ከዘገበበት በኋላ የበለጠ ትኩረት ሊያገኝ እንደቻለ አንዳንድ አድማጮቻችን ገልጠውልናል።
የሀገራችን ህዝብ ተቆርቋሪነቱን በተለያየ ማኅበራዊ ድረ ገፅ እየገለፀ ይገኛል በማለት ይጀምርና መፍትኄ የሚለውንም ሐሳብ አስፍሯል።
ጣናን የወረረው እምቦጭ የተሰኘው መጤ አረም በኔ አስተሳሰብ ይህን አረም ለማጥፋት የክልሉ መንግሥት ከአቅሙ በላይ የሚሆን አይመስለኝም።
አረሙን ለማጥፋት ይረዳል በሚል የመፍትኄ ሐሳብ የሰጠን ሌላው የፌስቡክ ተከታታያችን የዑራኤል ልጅ ነኝ የሚል የፌስቡክ መጠሪያ አለው።
እንዲህ ይላል፦ ይህን አረም ለማጥፋት እንደ ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች በቴሌ በኩል ገንዘብ የሚሠበሠብበት መንገድ ቢመቻች መልካም ነዉ።
ይሄነው ላቀው በበኩሉ፦ ጣናን ሐይቅ ፌደራሉ መንግሥት አይመለከተውም እንዴ
ሕዳሴ ግድብ መለመኛ ሆኗል በጣናም ይለመና ሲል ጣና ሐይቅ እንደ ሕዳሴው ግድብ በመንግሥት በኩል ትኩረት አልተሰጠዉም የሚል አስተያየቱን ሰጥቷል።
ኧረ ያገሬ ሕዝብ እንነሳ እንነጋገርበት ሌላ ሀገር አለን ወይ
ጣና ከሌለ ባሕር ዳር እሚባል ነገር ተረት ይሆናል ብሏል።
ታደሰ ወልደአብ በአጭር አረፍተ ነገር ያሰፈረው መልእክቱ፦ ይህን ያኽል ጊዜ ለምን ዝም ተባለ
ገበሬዎች በሐይቁ ዙሪያ እምቦጭ የተባለውን አረም ሲነቅሉ የሚያሳዩ ፎቶዎችም በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ይገኛሉ።
ከፎቶዉ ጋር አረሙን ለማጥፋት አስቸኳይ መፍትኄ እንደሚያሻው የሚጠቁሙ መልእክቶችም ይነበባሉ።
ስፖርት ስፖርት መጋቢት ቀን ዓ ም የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለጃፓኑ የኦሎምፒክ ውድድር ለመሳተፍ በድል ጎዳና እየገሰገሱ ነው።
ዩጋንዳን በደርሶ መልስ ለ የረቱት ሉሲዎቹ ከምዕራብ አፍሪቃዊቷ ካሜሩን ጠንካራ ተፎካካሪዎች ጋር ይፋለማሉ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለጃፓኑ የኦሎምፒክ ውድድር ለመሳተፍ በድል ጎዳና እየገሰገሱ ነው።
የእንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ በኤፍ ኤ ካፕ ድሉ ማግስት ለሻምፒዮንስ ሊግ ወሳኝ ፍልሚያ ራሱን እያዘጋጀ ነው።
በፕሬሚየር ሊጉ ዋነኛ ተፎካካሪው ሊቨርፑልም ነገ ምሽት በተመሳሳይ ሰአት ለሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ወሳኝ ጨዋታውን ያከናውናል።
በጁጂትሱ የትግል ስፖርት ኢትዮጵያውያን ተፋላሚዎች ለመጀመሪያ ጊዜ አራት ሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል።
በአፍሪቃ የመረብ ኳስ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ሁለት ቡድኖች ተካፋይ ኾነውዋል።
ሌላኛው የእንግሊዝ ቡድን ሊቨርፑል ከፖርቹጋሉ ፖርቶ ቡድን ጋር ነገ ምሽት በተመሳሳይ ሰአት ለሩብ ፍጻሜ ይጫወታል።
በፕሬሚየር ሊጉ ሊቨርፑል አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ማንቸስተር ሲቲን በኹለት ነጥብ በልጦ ይገኛል ነጥብ ሰብስቧል።
ባየር ሙይንሽን ዶርትሙንድን የጎል ጎተራ ባደረገበት ጨዋታ ያሸነፈው ለ ነበር።
ባለፉት ተከታታይ አምስት ጨዋታዎች ኹለት ጊዜ ሽንፈት የገጠመው ቦሩስያ ዶርትሙንድ ነጥብ አለው።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከአንድ ዓመት በኋላ በጃፓን በሚካሄደው የበጋ ኦሎምፒክ ውድድር ተካፋይ ለመኾን የመጀመሪያ ደረጃ ማጣሪያውን አልፏል።
ቡድኑ አሁን በኹለተኛው ዙር የማጣሪያ ውድድር የሚገጥመው የካሜሩንን ቡድን ነው።
በካምፓላ ከተማ ፊሊፕ ኦሞንዲ ስታዲየም ውስጥ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረችው ለብሔራዊ ቡድኑ በአጥቂ መስመር ተሰላፊዋ የኾነችው ሎዛ አበራን በስልክ አነጋግረናታል።
ብሔራዊ ቡድኑ ለድል የበቃው ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች በመላ ተቋቁሞ እንደኾነ ተናግራለች።
ሌላው ባሳለፍነው ሳምንት ለኢትዮጵያውያን ስፖርተኞች ደማቅ ድል ኾኖ የተመዘገበው ኢትዮጵያውያን ተፋላሚዎች በአፍሪቃ የጁጂትሱ ትግል ስፖርት አራት ሜዳሊያዎችን ማስመዝገባቸው ነው።
ያሬድ ቪዬና ኦስትሪያ ፖላንድ እንዲሁም ዱስልዶርፍ ጀርመንን በመሳሰሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ልምድ ያካበተ አትሌት ነው።
በሴት ተወዳዳሪዎች ዘርፍ ደግሞ መስከረም ዓለማየሁ ነጋሽ በኹለት የውድድር ዘርፎች የብር እና የነሐስ ሜዳሊያዎች አስገኝታለች።
የወርቁም ኾነ የብር ሜዳሊያው በኢትዮጵያ የጁጂትሱ ስፖርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ መኾኑ ተገልጧል።
የሞሮኮ ፌዴሬሽን እና ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያውያኑን አትሌቶች የመጓጓዣ የመኝታ እና ሌሎች ወጪዎችን እንደሸፈኑ ተገልጧል።
ላለፉት ሁለት ሳምንታት በመቐለ ሲካሄድ የሰነበተው ኛው የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች የስፖርት ሻምፒዮና ባሳለፍነው ቅዳሜ ተጠናቋል።
የውድድሩ አዘጋጆች እንደገለፁት በተለይም በኦሎምፒክና እግርኳስ ስፖርቶች በርካታ ተስፋ የሚጣልባቸው ተማሪ ስፖርተኞች በውድድሩ መታየታቸው ተገልጧል።
በኦሎምፒክ ውድድሮች ኦሮምያ ክልል የወርቅ ሜዳልያዎች በማግኘት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ አማራ ክልል ትግራይ ወርቅ ሜዳልያዎች በማግኘት ተከታታይ ደረጃዎች ይዘዋል።
በፓራ ኦሎምፒክ ስፖርቶች ኦሮምያ በአጠቃላይ ሜዳልያዎች በማግኘት የበላይ ሲሆን አማራ ትግራይ ሜዳልያዎች በማስመዝገብ ተከታትለው ውድድሩ ጨርሰዋል።
ሌላው ስፖርተኛ ተማሪዎቹ የተሳተፉበት ውድድር የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ናቸው።
በዚሁ ውድድር የአማራ ክልል ባህል ስፖርት ተወዳዳሪዎች ወርቅ ሜዳልያ በማስመዝገብ ቀዳሚ ሆነው ያጠናቀቁ ሲሆን ትግራይና አዲስ አበባ ተከታዮቹ ደረጃዎች ይዘዋል።
በመዝግያው ዕለት በተካሄደው የወንዶች እግርኳስ ፍፃሜ ኦሮምያ ደቡብ ክልልን አንድ ለባዶ በመርታት አሸናፊ ኾኗል።
በአጠቃላይ ኦሮምያ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሲሆን አማራ ሁለተኛ ትግራይ ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸው አጠናቀዋል።
በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች የስፖርት ሻምፒዮና በርካታ ተተኪ ስፖርተኞች የሚፈሩበት መኾኑን አዘጋጆቹ ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል።
ትናንት ይፋ የሆነዉ ፕሮጄክት ከሁለቱ ዞኖች ተፈናቅለዉ ለነበሩ ከ ሺሕ የሚበልጡ ነዋሪዎችን ይረዳል።
ታድያ የወጣትነት ጊዜ ሲደርስ ለዚህ መሰረት የሆነውን የትምህርት ዘርፍ ለመከታተል ወይም ጨርሶ በሌላ መስክ ለመሰማራት እንወስናለን።
ወደሚፈልጉት የሙያ ዘርፍ ለመግባት የተለያዩ ነገሮች ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ።
አንዳንዶች የበፊቱ ምኞታቸው አሁን ካለው ጋር ፍፁም ተቃራኒ ሆኖ ሲያገኙ ሌሎች ደግሞ በዚሁ የሙያ መስክ ገፍተው የስራውን ዓለም ይቀላቀላሉ።
የ አመቷ መክሊት መርሻ ከሁለት ዓመት በፊት በማህበራዊ ሳይንስ ወይም ሶሲዮሎጂ በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት አጠናቃለች።
መክሊት ዛሬ ለሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር መፅሄቶች ለማስተዋወቂያ የሚሆኑ ፎቶዎች እያነሳች ትሸጣለች።
ወጣቷ መሆን የምትፈልገውን ወይንም አቅጣጫዋን አስቀድማ ብታውቅም በወቅቱ በምርጫዋ ብዙዎች እንደማይረኩ ታውቅ ነበር።
የስራ ቦታ ሆኖ ስለ ዕረፍት ወይም ሌላ ስራ ማለም ሌላው ያነጋገርነው በንቲ እጄታን ነው።
ይሁንና በንቲ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ድርጅት እየሰራ አይደለም መስሪያ ቤት ቀይሯል።
በዚህም ፍላጎት ላይ ተመርኩዟ ይህንን ዕውን ለማድረግ እየሰራች ትገኛለች።
እነዚህ ነገሮች ምርጫዬ ትክክል እንደነበርና ነኝ ያልኩትን ለመሆኔ ማሳያ ሆነውኛል ትላለች ምስራቅ እዚህ እስክትደርስ የነበረውን ውጣ ውረድ እያስታወሰች።
ወጣቶች በተመኙት የስራ መስክ ለመሰማራት ስለሚያደርጉት ትግል በዛሬው የወጣቶች ዓለም የቃኘነው ርዕስ ነው።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ ጥቅምት አምስት ቀን ዓም ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ቢስማርክ የጉባኤዉ መሐንዲስ ብዙ ጊዜ በታሪክ ለሚፈፀሙ በደሎች የገንዘብ ካሳ ይከፈላል።
ዝክሩ መነሻ ጉባኤ ዉጤቱ ማጣቃሻ የዛሬ አስተጋብቶ መድረሻችን ነዉ ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።
አፄ ምኒሊክ የመሩት ኢትዮጵያዊ ሐገር ነፃነቱን ለማስከበር የከፈለዉ መስዋዕትነት፥
በኢጣሊያ ቅኝ ገዢዎች ላይ የተቀዳጃዉ ድል ለኢትዮጵያዊዉ ክብር አኩሪ ታሪክነቱ፥
ለድፍን ጥቁር ሕዝብ የነፃነት እኩልነቱ አብነት አለኝታነቱ በርግጥ የዘመን ሒደት ሊሽረዉ አይችልም።
ትግሉ ፀረ ቅኝ አገዛዝ አላማ ግቡ ነፃነት እኩልነት መሆኑ አያነጋግርም።
አክራ ዳሬ ሰላም ወይም ሌላ ከመሆን ይልቅ በርሊን መሆኑ ነዉ የዛሬዉ ዚቅ።
ከሕዳር አስራ አምስት እስከ እስከ የካቲት አጋማሽ የዘለቀዉ ጉባኤ ከተሰየመበት አዳራሽ አጠገብ አንዲት የመታሰቢያ ሰሌዳ ቆማለች።
ሰሌዳዉን ያቆመዉ የቶጎዉ ተወላጅ ቪክቶር ድሲድሶኑ የያኔዉን ታሪክ አፍሪቃዉን የመዘንጋት የለባቸዉም ባይ ነዉ።
ዛሬ እዚያ ያለዉን ችግር ያኔ ከተፈፀመዉ ጋር ማገናኘት ሥለምሻ ነዉ።
ይሕ ሰሌዳ በቅኝ አገዛዝ ዘመን የተፈፀመዉ በደል እንዳይረሳ ማስታወሻ እንዲሆን እፈልጋለሁ።
ለዚሕም ነዉ ያኔ አፍሪቃ በተቀራመቱባት ሥፍራ መቆም አለበት ብዬ ያሰብኩት።
ኢጣሊያ ከኦስትሪያ ሐንጋሪ እና ከጀርመን ጋር የጦር ቃል ኪዳን ስትፈራረም፥
በተለይ ፈረንሳይ የሊዮፖልድን እርምጃ ደግፋለች መባሉ በጣሙን የፖርቱጋልና የብሪታንያን ቁጣ ቀስቅሶ ነበር።
ኮንጎ በሊዮፖልድ ዳግማዊ እጅ መዉደቋና በዚያ በኩል የሚደረገዉ የሸቀጥ ዝዉዉር መታገዱ ለቢስማርክና ለሌሎቹ አሳሳቢ ነበር።
ሌሎች ሐያል መንግሥታትም ወደ ኮንጎ የመግባት መብታቸዉ መጠበቅ አለበት የሚል ነበር።
የእርስበራሳቸዉ መፈራራት ምክንያት ከሁሉም በላይ አፍሪቃን የመቀራመቱ ፍላጎት መሠረት ሆኖ ቢስማርክ ያን ጉባኤ ጠሩ።
ሐያሉ የአፍሪቃን ካርታ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠዉ አፍሪቃን ሲቀራመቱ ሴለር እንደሚሉት አንድም አፍሪቃዊ አልተወከለም ነበር።
በግልፅ መታወቅ ያለበት አንድም አፍሪቃዊ በዚያ ጉባኤ እንዲገኝ አልተጋበዘም ነበር።
ያኔ አይደለም ዛሬም የዚያን ዘመኑን ታሪክ የሚያስብ አፍሪቃዊ መሪ የለም ካለም አይታወቅም።
ዉሉ ኢትዮጵያ የምፅዋን የመሳሰሉ ወደቦች ጉባኤዉ ሪታንያ እዉቅና የሰጠችበት ነዉ።
የሐይል ሚዛንን አሰላለፍ እልፍ ሲልም የዘር ወገን ቅርበት በሚዘዉረዉ የፖለቲካ ጨዋታ ሐቅ እዉነት፥
የበርሊኑ ጉባኤ ልዩነት ድብልቅልቁ ወጥቶ አንደኛና ሁለተኛ በሚባሉት ጦርነቶች አለም እስክትነድ ድረስ የድፍን አፍሪቃ ሕዝብ በቅኝ ገዢዎች ሐይላት ተጨፍጭፏል።
ዉይይት ላይ ከሚካአሉት አፍሪቃዉያን አንዱ ስቬን ሜካሪደስ እንደሚለዉ በቅኝ አገዛዝ ዘመን በአፍሪቃዉያን ላይ ለተፈፀመዉ በደል ካሳ የማይከፈልበት ምክንያት አይገባዉም።