gem_id
stringlengths
21
24
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
target
stringlengths
6
506
references
list
text
stringlengths
136
19.6k
xlsum_amharic-train-101
https://www.bbc.com/amharic/news-56151145
ዘመናዊው የሒሳብ ቀመር ከጥንታዊው እስላማዊ ቤተ-መጽሐፍት
የጥበብ ቤት (ባይት አል-ሂክማህ) ተብሎ የሚጠራውና በ13ኛው ክፍለ ዘመን የፈረሰው የዚህ ጥንታዊ ቤተ-መጽሐፍት ምንም ቀሪ ፍርስራሽ የለም። ስለዚህም ይህ ቤተ-መጸሕፍት በትክክል የት እንደነበር ወይም ምን ይመስል እንደነበር እርግጠኛ መሆን አይቻልም።
[ "የጥበብ ቤት (ባይት አል-ሂክማህ) ተብሎ የሚጠራውና በ13ኛው ክፍለ ዘመን የፈረሰው የዚህ ጥንታዊ ቤተ-መጽሐፍት ምንም ቀሪ ፍርስራሽ የለም። ስለዚህም ይህ ቤተ-መጸሕፍት በትክክል የት እንደነበር ወይም ምን ይመስል እንደነበር እርግጠኛ መሆን አይቻልም።" ]
የሙሐመድ ኢብን ሙሳ አል-ክዋርዚም ሐውልት በኡዝቤኪስታን ይህ የጥበብ ቤት በእስላማዊው ወርቃማ ዘመን በባግዳድ ቀዳሚው የምሁራን ቤት ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ባይት አል-ሂክማ የዘመናችን "አረብኛ" ቁጥሮችን ጨምሮ የሒሳብ ፅንሰ-ሀሳቦች መነሻ ነው። በስምንተኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በሀሩን አል-ራሺድ የተቋቋመው በይት አል-ሂክማ አሁን ላይ ከአራቱም የዓለም ጫፍ ተመራማሪዎችን ወደ ባግዳድ እንዲመጡ ያስገድዳል። በለንደን የሚገኘውን የብሪታንያ ቤተ-መጻሕፍት ወይም የፓሪስ ቢብሊዮቴክ ናሽናሌን የሚያህለው የጥበብ ቤት የሒሳብ፣ የሥነ ፈለክ፣ የህክምና፣ የኬሚስትሪ፣ የጂኦግራፊ፣ የፍልስፍና፣ ሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ ጥበባትን ጨምሮ እንደ ኮከብ ቆጠራ ያሉ ተጨማሪ ትምህርቶች ይሰጡበታል። አንድ ነገር ግን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል አካዳሚው የሒሳብ ትምህርትን ሙሉ በሙሉ የሚቀይር እሳቤን አስገኝቷል። ይህ የጥበብ ቤት እአአ በ1258 ባግዳድ ውስጥ ወድሟል ይህ የጥበብ ቤት እአአ በ1258 ባግዳድ ውስጥ ወድሟል። በአፈ ታሪክ እንደሚባለው ብዙዎቹ ጽሑፎች ወደ ጤግሮስ ወንዝ በመጣላቸው የወንዙ ውሃ ቀለም ጥቁር ሆኖ ነበር ይባላል። የወንዙ ጥቁር ቀለም የያዘው መጽሐፍቱ የተጻፉበት ቀለም ጥቁር ስለነበረ ነው። በኋላ ላይ ግን እዚያ የተደረሰባቸው ግኝቶች በእስላማዊው ኢምፓየር፣ በአውሮፓ እና በመላው ዓለም ተቀባይነት ያገኘውን ረቂቅ የሒሳብ ቋንቋ ወልዷል። ወደ ቀዳሚው ጊዜ መራመድ "ዋናው ቁም ነገር የጥበብ ቤቱ የት እና መቼ እንደተጀመረ ዝርዝር ነገር ማወቅ አይደለም። ትልቁ ጉዳይ የመዳበሩ ሳይንሳዊ ሀሳቦቹ ነው" ሲሉ በሱሬይ ዩኒቨርስቲ የፊዚክስ ፕሮፌሰር የሆኑት ጂም አል-ካሊሊ ይናገራሉ። የጥበብ ቤትን የሒሳብ ትሩፋት ለመፈለግ ትንሽ ወደ ቀደመው ጊዜ መራመድን ይጠይቃል። በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት አንድ ስም በአውሮፓ ውስጥ ከሒሳብ ጋር አብሮ ይነሳ ነበር፤ ሊዮናርዶ። ህይወቱ ካለፈ በኋላ ፊቦናቺ ተብሎ ይጠራል። በጎርጎሮሳዊያኑ 1170 ፒሳ ውስጥ የተወለደው ጣሊያናዊው የሒሳብ ሊቅ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው በሰሜን አፍሪካ ባርበሪ የባህር ዳርቻ በሚገኘው የንግድ አካባቢ በሆነችው ቡጊያ ነው። በ 20ዎቹ መጀመሪያ ዕድሜው ላይ ፊቦናቺ ከሕንድ በፋርስ በኩል ወደ ምዕራብ በመጡ ሐሳቦች ተማረኮ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተጓዘ። ፊቦናቺ ወደ ጣሊያን ሲመለስም የሂንዱ-አረብኛ የቁጥር ሥርዓትን ከሚገልጹ የመጀመሪያዎቹ የምዕራባውያን ሥራዎች አንዱ የሆነውን 'ሊበር አባቺን' አሳተመ። ሊዮናርዶ ፊቦንቺ ሊበር አባቺ በ1202 ለመጀመሪያ ጊዜ ሲታተም የሂንዱ-አረብ ቁጥሮች በጥቂት ምሁራን ብቻ ይታወቁ ነበር። የአውሮፓ ነጋዴዎች እና ምሁራን የሮማውያንን ቁጥሮች የሙጥኝ ብለው ነበር። ይህም ማባዛት እና ማከፈልን በጣም ከባድ አድርጎታል (እሰቲ MXCI ን በ LVII ለማባዛት ይሞክሩ)። የፊቦናቺ መጽሐፍ በሒሳብ ሥራዎች ውስጥ የቁጥር አጠቃቀሞችን አሳይቷል። ይህም እንደ ትርፍ ልዩነት፣ የገንዘብ መለወጥ፣ ክብደት መለወጥ እና ወለድ ባሉ ተግባራዊ ጉዳዮች ላይ ሊተገበሩ የሚችሉ ቴክኒኮችን ያየዘ ነው። "የማስላት ጥበብን ለማወቅ በእጅ ጣቶች ቁጥር ማስላትን ማወቅ አለባቸው" ሲሉ ፊኖባቺ ጽፏል። በአሁኑ ወቅት ልጆች በትምህርት ቤት ሒሳብ ማስላትን ሲጀምሩ በጣቶቻቸው መማር እንዲጀምሩ ይደረጋል። "በእነዚህ ዘጠኝ ቁጥሮች እና በዜሮ (0) ማንኛውም ቁጥር መጻፍ ይቻላል" ይላል። የፊቦናቺ ብልህነት በሒሳብ ሊቅነቱ ፈጠራ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት በሙስሊም ሊቃውንቶች ዘንድ የሚታወቁትን ጥቅሞች በሚገባ መረዳቱ ነበር። ይህም የሒሳብ ቀመሮቻቸውን፣ የአስርዮሽ ቦታ ሥርዓታቸውን እና አልጀብራቸውን ያካትታል። በእርግጥ ሊበር አባቺ በዘጠነኛው ክፍለዘመን የሒሳብ ሊቅ አል-ክዋርዝሚ የቀመር ስልት ላይ ሙሉ በሙሉ የተመሠረተ ነበር። አብዮቱ ኩዋድራቲክ ኢኩዌዥንን ለመፍታት የሚያስችል ስልት ለመጀመሪያ ጊዜ አቅርቧል። በግኝቶቹ ምክንያትም አል-ክዋርዝሚ በብዛት የአልጄብራ አባት ተብሎ ይጠራ የነበረ ሲሆን በ821 ደግሞ የሥነ ፈለክ ተመራማሪ እና የጥበብ ቤት ዋና ቤተመጻሕፍት ኃላፊም ሆኖ ተሾመ። የአል-ክዋርዝሚ የህትመት ጽሑፍ የሙስሊሙን ዓለም የአስርዮሽ ቁጥር ሥርዓትን አስተዋውቋል። ሌሎች እንደ ሊዮናርዶ ያሉት ደግሞ በመላው አውሮፓ እንዲተላለፍ ረድተዋል። አል-ክሃዋሪዝሚ የአልጀብራ አባት ተብሎ ይጠራል ፊቦናቺ በዘመናዊ ሒሳብ ላይ ያለው የለውጥ ተጽዕኖ ውስጥ አል-ክዋርዝሚ ትልቅ ድርሻ ነበር። በአራት ምዕተ ዓመታት ገደማ ተለያይተው የነበሩ ሁለት ሰዎች በአንድ ጥንታዊ ቤተ-መጽሕፍት ምክንያት ተገናኙ። በመካከለኛው ዘመን የታወቀው የሒሳብ ባለሙያ በእስላማዊ ወርቃማ ዘመን ታዋቂ አስተማሪ ትከሻ ላይ መሠረቱን አድርጓል። ምናልባትም ስለ ጥበብ ቤት ብዙም ስለማይታወቅ የታሪክ ጸሐፊዎች አልፎ አልፎ ስፋቱን እና ዓላማውን ለመግለጽ ይፈተናሉ። ይህም ካለን አነስተኛ የታሪክ መዛግብት ጋር በተወሰነ መልኩ የሚፃረር ደረጃ ይሰጠዋል። "አንዳንዶች የጥበብ ቤት በብዙዎች ዘንድ እንደታየው ታላቅ ነገር አልነበረም ብለው ይከራከራሉ። ነገር ግን እንደ አል-ክዋርዝሚ ካሉ ሰዎች ጋር ያለው ቁርኝት እና የሒሳብ፣ የከዋክብት ጥናትና የጂኦግራፊ ሥራው የጥበብ ቤት የተተረጎሙ መጻሕፍት ማከማቻ ብቻ ሳይሆን ለእውነተኛ አካዳሚ የቀረበ መሆኑን እንደሚያሳይ ለእኔ ጠንካራ ማስረጃ ነው" ይላሉ አል-ካሊሊ። በቤተ-መጽሐፍት ውስጥ የነበሩ ምሁራንና ተርጓሚዎች ሥራዎቻቸው ለሕዝብ ተደራሽ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ኃላፊነት ነበራቸው። በኦፕን ዩኒቨርሲቲ የሒሳብ ታሪክ ፕሮፌሰር የሆኑት ጁን ባሮው-ግሪን "የጥበብ ቤት በመሠረቱ ወሳኝ የሆነው፤ የአረብ ምሁራን የግሪክ ሐሳቦችን ወደ ቋንቋው የተረጉመው የሒሳብ አረዳዳችን እንደመሠረትን ስላስቻሉ ነው" ብለዋል። የቤተ መንግሥቱ ቤተ-መጽሐፍት ሳይንሳዊ ፈጠራ ቦታ በመሆኑ የቀደሙት ጊዜያትን ቁጥራዊ ሐሳቦችን መመልከቻ መስኮት ያህል ነበር። ከአሁኑ የአስርዮሽ ሥርዓታችን በፊት ሰዎች ስሌቶችን ለመመዝገብ ቀደምት የቁጥር ሥርዓቶችን ይጠቀሙ ነበር። እነዚህ የተለያዩ የቁጥር ውክልናዎች ስለ መዋቅር፣ ግንኙነቶች እና ስለተነሱበት ታሪካዊ እና ባህላዊ አውዶች ሊያስተምሩን ይችላሉ። ቁጥሮች እንዴት እንደሚሠሩ በተሻለ ለመረዳት እንድንችል የቦታ እሴትንና ረቂቅነትን ሐሳብ ያጠናክራሉ። "የምዕራቡ ዓለም ብቸኛው መንገድ አልነበረም። የተለያዩ የቁጥር ሥርዓቶችን በመረዳት ረገድ እውነተኛ እሴት አለ" ይላሉ ባሮው-ግሪን። አንዲት ጥንታዊ ነጋዴ "ሁለት በጎች" ብላ ለመጻፍ ከፈለገች የሁለት በጎች ምስል በሸክላ ላይ ማስፈር ትችላለች። ይህ ግን "20 በጎች" ለመፃፍ ከፈለገች ተግባራዊነቱ አነስተኛ ነው። የምልክት አጻጻፍ አንድን እሴት ለማመልከት የቁጥር ምልክቶች አንድ ላይ የሚደመሩበት ሥርዓት ነው። በዚህ ሁኔታም ትክክለኛውን ቁጥር ለመወከል ሁለት በጎች መሳልን ይጠይቃል። ይህን መሰል የሮማውያን ቁጥር ለመጥፋት ተቃርቧል ዘንድሮ የፊቦናቺ የተወለደበት 850ኛ ዓመት ነው። የሮማን ቁጥሮችን ሥራ የሚቀለበስበት ጊዜም ሊሆን ይችላል። በዩናይትድ ኪንግደም ትምህርት ቤቶች ቀደም ሲል የነበሩት እና በሮማውያን ቁጥሮች የተዘጋጁት የግዜ ሠሌዳዎች በተማሪዎች በቀላሉ በሚነበቡ የዲጂታል ሰዓቶች ተተክተዋል። ምክንያቱ ደግሞ ተማሪዎች የአናሎግ ሰዓትን በትክክል ማወቅ አይችሉም በሚል ፍራቻ ነው። አንዳንድ አገራት ከመንገድ ምልክቶች እና ከኦፊሴላዊ ሰነዶች ያወጧቸው ሲሆን ሆሊውድ ደግሞ በፊልሞቹ ላይ የሮማውያን ቁጥሮችን ከመጠቀም ተቆጥቧል። ሱፐርቦውል የተባለው የስፖርት ውድድርም ለ50ኛ ጨዋታው ደጋፊዎችን ግራ የሚያጋቡ ናቸው በሚል አስቀርቷቸዋል። "የማንን ታሪክ ነው የምንነግራቸው፣ የማንን ባህል እንደሆነ እና ወደ መደበኛው ትምህርት የምናስገባቸው የዕውቀት ዓይነቶች በምዕራባዊያን የቅኝ ግዛት ተጽዕኖ ሥር መውደቃቸው የማይቀር ነው" ይላሉ በኬምብሪጅ የሒሳብ ሥራ አዘጋጅ የሆኑት ሉሲ ሪይክሮፍት-ስሚዝ። ቀድሞ የሒሳብ መምህር የነበሩት ሪይክሮፍት-ስሚዝ በሒሳብ ትምህርት ውስጥ ዋና ድምጽ ሲሆኑ የዓለም አቀፍ ሥርዓተ-ትምህርቶችን ልዩነቶችም ያጠናሉ። ዌልስ፣ ስኮትላንድ እና አየርላንድ በትምህርታቸው ውስጥ የሮማን ቁጥሮችን ባያካትቱም አሜሪካ ደግሞ ምንም መደበኛ መስፈርቶች የላትም። እንግሊዝ ተማሪዎቿ እስከ 100 ያሉትን የሮማን ቁጥሮችን ማንበብ መቻል እንዳለባቸው በግልፅ አስቀምጣለች። ብዙዎቻችን MMXX ላይ ምንም ልዩ ነገር አናገኝም (2020 ማለት ነው)። በእሱ ስም ለተሰየመው በአንድ የሚጀምረው እና ከዚያ በኋላ የሁለቱ ቀዳሚ ቁጥሮች ድምር በሆነው ዝነኛው ንድፍ ፊቦናቺን በጥቂቱ ልናውቀው እንችላለን። እነዚህም ብዙውን ጊዜ በሥነ-ጽሑፍ፣ በፊልም፣ በምስል ጥበባት፣ በዘፈን ግጥሞች፣ የኦርኬስትራ ውጤቶች እና በሥነ-ሕንጻ ውስጥም እናገኛቸዋለን። ሊዮናርዶ በሒሳብ ውስጥ ያደረገው አስተዋፅኦ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እምብዛም የሚነሳ ነገር ነው። ይህ ታሪክ የሚጀምረው ከአንድ ሺህ ዓመት ገደማ በፊት በቤተመንግሥት ቤተመጽሐፍት ውስጥ ሲሆን በወቅቱ አብዛኛዎቹ ምዕራባውያን በዕውቀት ጨለማ ውስጥ የነበሩበት ነው። ይህም ሒሳብን ከአውሮፓ ጋር የሚያያይዘውን ሃሳባችን ሲያፈርስ፣ በእስላማዊው ዓለም ሳይንሳዊ ግኝቶች ላይ ብርሃን የሚፈነጥቅ እና ከረጅም ጊዜ በፊት ለነበሩ የቁጥር ሀብቶች አስፈላጊነት ትኩረት እንዲሰጥ የሚከራከር ነው።
xlsum_amharic-train-102
https://www.bbc.com/amharic/news-48741589
ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ
የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንንና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ጄነራል ገዛኢ አበራን ተኩሶ ገደለ የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ራሱን ያጠፋው ወዲያው መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ይታወሳል።
[ "የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንንና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ጄነራል ገዛኢ አበራን ተኩሶ ገደለ የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ራሱን ያጠፋው ወዲያው መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ይታወሳል።" ]
ሰኞ ምሽት ፌደራል ፖሊስ በብሔራዊው ቴሌቪዥን (ኢቢሲ) ቀደም ሲል ራሱ የሰጠውን መግለጫ አስተባብሎ ጠባቂው በሕይወት እንደሚገኝ አስታውቋል። ቢቢሲ ማክሰኞ ጠዋት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት እንደሻው ጣሰው ጋር በመደወል ትናንት በሰጡት መግለጫ እና ማታ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በቀረበው መግለጫ መካከል ስለተፈጠረው ልዩነት ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቋቸው ነበር። ኮሚሽነሩ በአጭሩ "በአጭሩ ልጁ ተመትቷል። ከፍተኛ ህክምናና ክትትል የሚደረግበት ክፍል ውስጥ ነው ያለው። እኛ የወሰድነው መረጃ ሞቷል የሚል ነበር። አሁን ግን በሕይወት አለ። በመሞትና በሕይወት መካከል ነው የሚገኘው" ብለዋል። ዕሁድ ስለጥቃት ፈጻሚው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢሮ በተሰጠ መግለጫ ጠባቂያቸው ቆስሎ መያዙ ቢገለፅም ሰኞ ጠዋት በተሰጠው የፌደራል ፖሊስ መግለጫ ላይ ግን ወዲያውኑ ራሱን ማጥፋቱ ተነግሮ ነበር። ሆኖም ማምሻውን ፌዴራል ፖሊስ ይህንኑ መግለጫ በድጋሚ አስተባብሏል። • ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት እንደማይታወቅ የአማራ ክልል ገለፀ በጠዋቱ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ገለፃ መሰረት በወቅቱ ከጄኔራሎቹ ጋር የነበረው ጠባቂ ሁለቱንም ተኩሶ የገደላቸው ሲሆን፤ በቦታው የነበሩ ሌሎች ጠባቂዎች በጥቃት ፈጻሚው ላይ ቢተኩሱበትም ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበትና ግለሰቡም ወደነበረበት ክፍል ተመልሶ በመግባት ራሱን ማጥፋቱን ኮሚሽነሩ ገልፀው ነበር። "ጠባቂው በጄኔራል አሳምነው የተመለመለ ሲሆን፤ ራሱን ማጥፋቱ የሚያሳየው የተሰጠው ተልዕኮ ከፍተኛ ግዳጅን የሚጠይቅ መሆኑን ነው። ይህም የአጥፍቶ መጥፋት ተልዕኮ ነው" ብለዋል ኮሚሽነሩ በመጀመርያው መግለጫ። • ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው ኮሚሽነሩ ባህርዳር ተፈጸመ ከተባለው "የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ" በፊት ብርጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ የክልሉ ፀጥታ ኃላፊዎችን በየቢሯቸው አስረዋቸው እንደነበርም አብራርተው ነበር። ኮሚሽነሩ አክለውም በብርጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ስር ያሉ ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።
xlsum_amharic-train-103
https://www.bbc.com/amharic/news-53668653
ሊባኖስ፡ በቤይሩቱ ፍንዳታ አንድ ኢትዮጵያዊ መሞቱ ተገለፀ
በሊባኖስ መዲና ቤሩት ከትላንት ወዲያ በደረሰው ከባድ ፍንዳታ አንድ ኢትዮጵያዊ ሕይወቱ ማለፉን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል የሆኑት አቶ ተመስገን ኡመር ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
[ "በሊባኖስ መዲና ቤሩት ከትላንት ወዲያ በደረሰው ከባድ ፍንዳታ አንድ ኢትዮጵያዊ ሕይወቱ ማለፉን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል የሆኑት አቶ ተመስገን ኡመር ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።" ]
ከዚህ በተጨማሪ አንዲት በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባትና ህክምና እየተከታተለች የነበረች ኢትዮጵያዊት በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ እንደምትገኝም አቶ ተመስገን ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ አስር ኢትዮጵያዊያን ጉዳት እንደደረሰባቸው ቆንስላው በትናንትናው ዕለት ገልጿል። ቢቢሲ በቤይሩት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን በማናገር እንዳረጋገጠው በዚህ ከባድ ፍንዳታ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት ደርሷል። በከተማዋ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ስላሉበት ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ ያለው በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ እንዳሳወቀው የደረሰው ፍንዳታ ከባድ ከመሆኑ አንጻር በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ላይም ጉዳት ደርሷል። አቶ ተመስገን ለቢቢሲ በቆንስላውና በኢትዮጵያ ማህበረሰብ በኩል ጉዳት እንደደረሰባቸው የተረጋገጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር አስር መሆኑንም በትናንትናው ዕለት ገልፀዋል። ከእነዚህም መካከል ሁለቱ መካከለኛ፣ ሰባቱ ደግሞ ቀላል ጉዳት ሲደርስባቸው አንድ ግለሰብ መሞቱ ቢነገራቸውም ከሚሰራበት ተቋምም ሆነ ከሊባኖስ መንግሥት የተጣራ መረጃ እንዳልደረሳቸው ገልፀው ነበር። እንደ ቆንስላው ከሆነ መካከለኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን ያሉበትን ሁኔታ የሚታከሙበት ሆስፒታል ድረስ በመሄድ መመልከታቸውን ገልፀው፣ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ሰባቱ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ግን ህክምና አግኝተው ወዲያው ወደ መኖሪያቸው መሄዳቸውን አስረድተዋል። አቶ ተመስገን አክለው ወደ ቆንስላውም ሆነ ወደ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ያልመጡ ሌሎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሊኖሩ ይችላሉ ብለዋል። በቤይሩት ትናንት አመሻሽ ላይ ባጋጠመው ከባድ ፍንዳታ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል። የሊባኖስ ፕሬዝደንት ማይክል አኑን ፍንዳታው ባገጠመበት ቦታ ላይ 2750 ቶን የሚመዝን አልሙኒየም ናይትሬት ደኅንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለስድስት ዓመታት ተከማችቶ እንደነበር ገልፀዋል። በቤይሩት ያሉ ኢትዮጵያዊያን ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ከፍንዳታው በኋላ የቆንስላው ኃላፊና ሠራተኞች የኢትዮጵያዊያኑን ሁኔታ ለማወቅ ሌሊቱን ወደ ተለያዩ አካባቢዎችን የህክምና ቦታዎች በመሄድ ሲያጣሩ ነበር። በሊባኖስ የኢትዮጵያውያን በጎ አድራጎት ማህበር ከሆነው "የእኛ ለእኛ በስደት" አባላት ቢቢሲ በማጣራት ባጋጠመው ፍንዳታ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያዊያን ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውና ቁጥራቸው ያልታወቀ ደግሞ የት እንዳሉ አለመታወቁን አረጋግጧል። ነገር ግን እስካሁን በተገኘው መረጃ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ጥቂት ሲሆኑ አብዛኞቹ ግን ቀላል የሚባል ጉዳት አጋጥሟቸው ትናንት ከፍንዳታው በኋላ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ ወደ ህክምና መስጫ ተቋማት በመሄድ ድጋፍ አግኝተው መመለሳቸው ተገልጿል። የማኅበሩ አባላት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ባላቸው መረጃ መሰረት ሁለት ኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት ደርሶ ሆስፒታል መግባታቸውንና አንዲት ኢትዮጵያዊት ያለችበትን ለማወቅ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ማኅበሩ አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን ማግኘት ስላልቻሏቸው ጓደኞቻቸው በተደጋጋሚ እየጠየቁ ስለመሆናቸውም ተናግረዋል። የወደመው የወደብ አካባቢ የቤይሩቱ ፍንዳታ በኢትዮጵያዊቷ ዓይን በቤይሩት ነዋሪ የሆነችው ጽጌረዳ ብርሃኑ ትናንት በከተማዋ ቤይሩት ስለደረሰው ፍንዳታ ለቢቢሲ ስትናገር "ሕልም የሚመስል እውነት እና የሚያስፈራ" ነበር ብላለች። ፍንዳታው የተከሰተው ትናንት፣ ማክሰኞ እለት፣ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 12 ሰዓት አካባቢ መሆኑን አስታውሳ፣ እርሷ በወቅቱ ከጓደኞቿ ጋር ተሰብስባ አሽፈርዬ የሚባል አካባቢ እንደነበረች ትናገራለች። ፍንዳታው በደረሰበት ወቅት ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ለችግር ለተጋለጡ ኢትዮጵያዊያን የምግብ እርዳታ ለማቅረብ በሚሰባሰቡበት ስፍራ ሰዎችን እያስተናገዱ ነበር። ኢትዮጵያዊያኑ በፍንዳታው ህንፃዎች ሲንቀጠቀጡ የመሬት መንቀጥቀጥ የደረሰ መስሏቸው እንደነበር ገልጻ፣ ወደ ዋናው መንገድ በምትወጣበት ወቅት በፍንዳታው ከባድ ውድመት መድረሱን ማስተዋሏን ገልፃለች። እርሷ ያለችበት አሽረፍዬ፣ እንዲሁም የቱሪስት መስህብ የሆኑት ዋርኒኬል፣ ጅማይት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። ፍንዳታው የደረሰበት የወደብ አካባቢ ጽጌረዳ ከምትኖርበት ከአሽረፍዬ የ15 ደቂቃ የእግር ጉዞ መንገድ መሆኑንም ጠቅሳለች። ከፍንዳታው በኋላ ወደ ጎዳና ስትወጣ በደም ተነክረው የሚሮጡ፣ የሚያለቅሱ ሰዎች እንዲሁም አውራ ጎዳናዎች በተሰባበሩ መስታወቶች ተሞልተው በሰዎች ተጨናንቀው እንደነበር ትናገራለች። በወቅቱ በተለያዩ ሆቴሎች የነበሩ ኢትዮጵያውያን ቀላል ጉዳት ብቻ አጋጥሟቸው መትረፋቸውንም ማረጋገጧን ለቢቢሲ ገልፃለች። የሆስፒታሎች እርዳታ ለተጎጂ ግለሰቦች ከፍንዳታው በኋላ በቤይሩት ከተማ ውስጥ የመብራት፣ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ በከተማዋ ያሉ ሆስፒታሎች በሙሉ በአደጋው በተጎዱ ሰዎች ተሞልተው ነበር። በፍንዳታው ከ100 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት የደረሰ በመሆኑ ወደ ሆስፒታሎች የሚመጣው ሰው ማከም ከሚችሉት በላይ ስለነበረ በተቋማቱ ግቢ እና የመናፈሻ ስፍራዎች ላይ ህክምና ለመስጠት ተገደው ነበር። "በሆስፒታሉ ስደርስ በርካታ ሰዎች እየመጡ ቁስላቸው እየታሸገላቸው ወደ መጡበት ሲመለሱ ተመልክቻለሁ፤ ታሞ የሚታከም ሰው አልነበረም። ይህንን ለማድረግ የሚያስችል አቅም ያለ አይመስልም" ነበር ትላለች በሆስፒታል ውስጥ ያየችውን ጽጌረዳ ለቢቢሲ ስትናገር። "በሆስፒታሎች ውስጥ ህክምና የሚሰጠው ተጎድቶ ለመጣ ሁሉ ነበር" የምትለው ጽጌረዳ፣ እስከ ለሊቱ 9፡00 ሰዓት ድረስ በተለያዩ ሆስፒታሎች መሄዷን በማስታወስ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁስላቸው እየተጠረገና እየታሸጉ መውጣታቸውን ነገር ግን በትክክል ስንት ኢትዮጵያዊያን እንደተጎዱ እርግጠኛ መረጃ እንዳላገኘች ትናገራለች። • “የኑሮ ውድነቱ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል” "አንዲት ኢትዮጵያ መሞቷን ብሰማም ማረጋገጥ አልቻልኩም" የምትለው ጽጌረዳ፣ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በርከት ያሉ ኢትዮጵያን ቢኖሩም ቀላል ህክምና አግኝተው መሄዳቸውን ማረጋገጧን ጨምራ ትናገራለች። የኢትዮጵያ ቆንስላ እርሷ የተጎዱ ኢትዮጵያዊያንን ለማየት ወደ ሆስፒታል በምትሄድበት ወቅት በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ የሆኑት አምባሳደር ተመስገን በተለያዩ ሆስፒታሎች እየተዘዋወሩ ኢትዮጵያዊያኑ ያሉበትን ሁኔታ እየተከታተሉ መሆናቸውን በመስማቷ እንዳስደነቃት ለቢቢሲ ገልጻለች። ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ቆንስላ ኃላፊዎች በዜጎቻቸው ችግር በሚገጥማቸው ወቅት በፍጥነት ምላሽ እንደማይሰጡ በማንሳት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የቆንስላው ተግባር ተስፋ እንደሰጣት ጠቅሳለች። • ኬንያዊውንና የኦኤምኤን ጋዜጠኛን ጨምሮ 9 ሰዎች በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ ፍንዳታው አሁን ካደረሰው ጉዳት ባሻገር በኢትዮጵያዊያን ኑሮ ላይ ከባድ ጫና እንደሚኖረው የምትናገረው ጽጌረዳ፤ ፍንዳታው በርካታ የገበያ ማዕከሎችን በማውደሙ እዚያ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እንደነበሩና በዚህም ሳቢያ ከሥራ ውጪ ስለሚሆኑ ለተደራራቢ ችግር መጋለጣቸው አይቀርም ስትል ትናገራለች። እንኳን እኛ የአገሪቱ ዜጎች እያለቀሱ ነው የምትለው ጽጌረዳ በምጣኔ ሃብቱ መንኮታኮት፣ በኮሮናቨይረስ ወረርሽኝ ላይ ይህ ችግር መጨመሩ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ መሆኑን ትገልፃለች። "ባለው ችግር ላይ እጥፍ ችግር ነው የተጨመረው" በማለትም የችግሩን ግዝፈት ታስረዳለች። የደረሰ ጉዳት በከተማዋ ላይ ባጋጠመው ከባድ ፍንዳት ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል። ፕሬዝደንት ማይክል አኑን ፍንዳታው ባገጠመበት ቦታ ላይ 2750 ቶን የሚመዝን አልሙኒየም ናይትሬት ደኅንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለስድስት ዓመታት ተከማችቶ ነበር ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ለዛሬ አስቸኳይ የካቢኔ ሰብሰባ የጠሩ ሲሆን፤ ለሁለት ሳምንታት የሚዘልቅም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። ሌባኖስ ለሦስት ቀናትም የብሔራዊ የሃዘን ቀን አውጃለች። ከዚህ በተጨማሪ ፕሬዝደንቱ 66 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ እንዲመደብ አዘዋል።
xlsum_amharic-train-104
https://www.bbc.com/amharic/news-54495523
አንበጣ ፡ ኢትዮጵያ የአንበጣ መንጋን ለመቆጣጠር ምን ያህል አውሮፕላኖች አሏት?
የምሥራቅ አፍሪካ አገራትን በማዳረስ በተለይ የኢትዮጵያን ሰሜናዊና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎችን ክፉኛ እያጠቃ የሚገኘውን ግዙፍ የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከል ከአየር ላይ ጸረ ተባይ መድኃኒት የሚረጩ ጥቂት አውሮፕላኖች ተሰማርተው ጥረት እየተደረገ ነው።
[ "የምሥራቅ አፍሪካ አገራትን በማዳረስ በተለይ የኢትዮጵያን ሰሜናዊና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎችን ክፉኛ እያጠቃ የሚገኘውን ግዙፍ የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከል ከአየር ላይ ጸረ ተባይ መድኃኒት የሚረጩ ጥቂት አውሮፕላኖች ተሰማርተው ጥረት እየተደረገ ነው።" ]
የአንበጣ መንጋው ክፉኛ ባጠቃቸው አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ብዙም ውጤታ ያልሆነውን ባህላዊ አንበጣን የመከላከያ መንገድ ጥረት እያደረጉ ሲሆን፤ ከዚሁ ጎን ለጎን አውሮፕላኖችም ተሰማርተው ጸረ ተባይ መድኃኒቶችን እየረጩ ቢሆንም እክል እየገጠማቸው የመከላከሉ ሥራ ላይ እክል እያጋጠመ ነው። ባለፈው የመስከረም ወር ሁለት የጸረ ተባይ መርቻ አውሮፕላኖች በሰሜንና በምሥራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ አካበቢዎች ተሰማርተው በነበረበት ጊዜ ወድቀው ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል። የመጀመሪያው አውሮፕላን በአማራ ክልል ወረባቦ ወረዳ ፍራንጉል በሚባል ቦታ ወድቆ የተከሰከሰ ሲሆን የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአብራሪው ላይ ከደረሰው መጠነኛ ጉዳት ውጪ በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። ነገር ግን በአደጋው በአውሮፕላኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የተነገረ ሲሆን በዚህም ሳቢያ አውሮፕላኑ ከአገልግሎት ውጪ ሊሆን ይችላል ተብሏል። ሁለተኛው አውሮፕላን ደግሞ በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ኬሚካል በመርጨት ላይ በነበረበት ጊዜ ጊደያ በሃ በምትበል ቀበሌ ውስጥ ነው የመውደቅ አደጋ የገጠመው። የወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዱል ቃድር ደዚ ለቢቢሲ በአደጋው ወቅት በአውሮፕላኑ ውስጥ አብራሪው ብቻ የነበረ ሲሆን እሱም ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበትና በአውሮፕላኑ ላይም ቀላል ጉዳት እንዳጋጠመ ተናግረዋል። ስለዚህም የአንበጣው መንጋ ጥፋት የሚያደርስባቸውን አካባቢዎች እያሰፋ ባለበት በዚህ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉት የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጫ አውሮፕላኖች ሁለቱ በአንድ ወር ውስጥ ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል ማለት ነው። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ስንት አውሮፕላኖች አሏት? የአፍሪካ ቀንድንና ደቡብ እስያን እያካለለ ያገኘውን ሰብል በማውደም የአካባቢውን ሕዝብ የምግብ አቅርቦትና ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ የሚኘውን በ25 ዓመት ውስጥ ካጋጠሙት ሁሉ የከፋው ነው የተባለለትን የአንበጣ መንጋ ወረርሽን ለመከላከል ኢትዮጵያ ከምድር እና ከአየር ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። የአንበጣ መንጋው ጥቃት ሰፊ ቦታን በሚሸፍን ቦታ ላይ እንደተከሰተ የግብርና ሚኒስቴር ግብርና ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር) የገለጹ ሲሆን፤ በአፋር፣ ሶማሊ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ተከስቷል። ባለፉት ወራት በኢትዮጵያ ውስጥ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ስድስት አውሮፕላን እና ሁለት ሄሊኮፕተሮች ተሠማርተው የነበሩ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በገጠማቸው አደጋና ለጥገና ወደ ውጭ የሄዱ በመኖራቸው በሥራ ላይ የሚገኘው አንድ አውሮፕላን ብቻ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የአንበጣ መንጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከዚህ ቀደም አውሮፕላኖቹ ተሰማርተው ባከናወኑት አንበጣውን የመከላከል ሥራ "በጣም ውጤታማ ነበሩ" የሚሉት ማንደፍሮ (ዶ/ር)፤ "በሰባት ክልሎች እና በአንድ ከተማ መስተዳድር የበረሃ አንበጣው ሲከሰት በተቀናጀ መልክ ተሠማርተው በመከላከል በሁለት ክልሎች ብቻ ሲቀር የሌሎቹን መቆጣጠር ችለው ነበር" ይላሉ። ነገር ግን ከወራት በፊት የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በመቆጣጠር "የቀረውንም ተረባርበው ለማጥፋት ሲቃረቡ አዲስ የበረሃ አንበጣ መንጋ ከውጭ ገባ" የሚሉት ሚኒስትር ዲኤታው ሌላ ጫና መፈጠሩን አመልክተዋል። ስለዚህም አሁን የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ውስጥ ሁለቱ እክል ገጥሟቸው የወደቁ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በጥገና ላይ በመሆናቸው የቀረው አንድ አውሮፕላን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ካጋጠመው የአንበጣ መንጋ ወረራ አንጻር ከአቅም በላይ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚሁ ተግባር የሚውሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል። አዲሶቹ የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጫ አውሮፕላኖች ስምንት ሲሆኑ የሚመጡትም በኪራይ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ማንደፍሮ (ዶ/ር) አመልክተው፤ ተባዩን ለመቆጣጠር በግብርና ሚኒስትሩ የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ከአውሮፕላን በተጨማሪ በሰው ኃይልና በተሸከርካሪ በመታገዝ የጸረ ተባይ ርጭት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አውሮፕላኖቹ ምን አጋጠማቸው? የአንበጣ መንጋው ወረራ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ባለፈው የመስከረም ወር ላይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ጸረ አንበጣ መድኃኒት ለመርጨት ተሰማርተው የነበሩት አውሮፕኖች ላይ በተከታታይ የደረሰው አደጋ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን የጸረ ተባይ መርጫ አውሮፕላኖች ቁጥር አንድ ብቻ አድርጎታል። ለአደጋው መከሰት ምክንያቱ ምን እንደሆነ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ሚኒስትር ዲኤታው ማንደፍሮ (ዶ/ር) ግን "ከፍ ብሎ ለመብረር መቸገራቸው ምክንያት ሳይሆን አይቀርም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አደጋው የደረሰባቸው ሁለቱም አውሮፕላኖች በኪራይ የመጡና ንብረትነታቸውም የደቡብ አፍሪካ ሲሆኑ፤ አብራሪዎቹም ኢትዮጵያዊያን አለመሆናቸው ተገልጿል። አውሮፕላኖቹ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ የመጡ ሲሆን የአደጋና የኢንሹራንስ ጉዳይ የግብርና ሚኒስቴርን የሚመለከት እንዳልሆነ ተጠቅሷል። አደጋው መድረሱ እንዳሳዘናቸው ነገር ግን "እኛ በውላችን መሠረት ኪራይ መከፈል እንጂ አደጋ ሲደርስ እንከፍላለን የሚል ውል የለም" ሲሉ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ተናግረዋል። የግብርና ሚንስቴር የራሱ እንዲህ አይነቱ የተፈጥሮ ችግር በሚያጋጥምበት ጊዜ ፈጥነው በመሰማራት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ሄሊኮፕተርም ሆነ አውሮፕላን እንደሌለው የጠቆሙት ሚንስትር ዲኤታው "አውሮፕላኖች ቢኖሩን ኖሮ አንበጣውን በፍጥነት ለመከላከል ይቻል ነበር" ብለዋል። ከዚህ አንጻርም የጎረቤት አገር ሱዳን የግብርና ሚንስቴር የአንበጣ እና የወፍ መከላከያ እንዲሁም ለሌሎች ሥራዎች የሚያገለግሉ ዘጠኝ አውሮፕላኖች እንዳሉት ጠቅሰው በኢትዮጵያም "ተመሳሳይ አቅም መገንባት" አስፈላጊነትን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ምን ያህል አውሮፕላኖች ያስፈልጓታል? በተለይ በኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙ ክልሎች ላይ ተከስቶ ከባድ ውድመት እያስከተለ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ያመለከተውን የአንበጣ መንጋ ወራረ ለመከላከል ከአየር ላይ የሚደረገው የጸረ ተባይ ርጭት ወሳኝ መሆኑን ከዓለም የምግብ ፕሮግራም መረጃ ያመለክታል። በተለይ ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ተራራማ አገራት ውስጥ ከአየር ላይ የሚደረገው የጸረ አንበጣ መድኃኒት ርጭት አንበጣው የሚያደርሰውን ጉዳት በቶሎ ለመቆጣጠር ያስችላል። ነገር ግን አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር ለመግዛትም ሆነ ለመከራየት የሚያስፈልገው ገንዘብ ቀላል የሚባል አይደለም። ሚኒስትር ዲኤታው እንደሚሉት አንድ ሄሊኮፕተር ለመግዛት የሚያስፈልገው ገንዘብ ሁለት ሚሊዮን ዶላር እንደሚገመት ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ አስር ብትገዛ ወደ 20 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል። አንበጣው በአገሪቱ ግብርና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳትና ለተለያዩ ችግሮች ከሚያጋልጣቸው የአገሪቱ ዜጎች አንጻር የአውሮፕላኖቹ አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው። "በአገሪቱ ከዚህ በሚበልጥ ወጪ የሚሠሩ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን እና በተመሳሳይ ለዚህም ግዢ ትኩረት ያስፈልጋል" ብለዋል። አንድ አውሮፕላን የአንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በአንድ ጉዞ አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ኬሚካል የመርጨት አቅም ሲኖረው፤ አንድ አውሮፕላን በቀን እስከ አምስት ምልልስ በማከለናወን የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጨት ከቻለ አምስት ሺህ ሄክታር መሬትን መሸፈን ይችላል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በአንበጣ መንጋው የወረራ ስጋት ውስጥ ይሆናል ተብሎ እንደሚገመት ሚኒስትር ዲኤታው አመልከተው፤ ይህንንም ስፋት የጸረ ተባይ መድኃኒት ለመርጨት በትንሹ 10 አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ። የበረሃ አንበጣ መንጋው እስካሁን ስላደረሰው ጉዳት ጥናት ባለመደረጉ የተረጋገጠ መረጃ አለመኖሩን የተናገሩት ማንደፍሮ (ዶ/ር) አሁን ዋነኛ ትኩረት የተደረገው በመከላከል ሥራው ላይ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ሚኒስትር ዲኤታው ጨምረውም የበረሃ አንበጣውን ወረራ ለመከላከል ከአውሮፕላኖች በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ መኪኖች ጉዳቱ በከፋባቸው አካባቢዎች ተሰማርተዋል። ከ25 ዓመታት ወዲህ የከፋ ነው የተባለለት የበረሃ አንበጣ ለወራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ ያሉ አገራት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ አስካሁን በተከታታይ ለተከሰተው የአንበጣ መንጋ ምክንያቱ እንደ አውሮፓዊያኑ በ2018 እና 2019 ያጋጠመው ከባድ ነፋስና ዝናብ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንዳመለከተው ከሁለት ዓመት በፊት በደቡባዊ የአረብ ልሳነ ምድር ላይ የነበረው እርጥብና አመቺ የአየር ሁኔታ የአንበጣው ሦስት ትውልድ ሳይታወቅ እንዲራባ እድል ፈጥሮ በአካባቢው አገራት ላይ የሚታየውን የአንበጣ መንጋ ወረራ አስከትሏል።
xlsum_amharic-train-105
https://www.bbc.com/amharic/news-48605257
1 ዩኒት ደም እስከ 5 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረበት ጊዜ
ድሮ ሠው ታሞ ደም ያስፈልገዋል ከተባለ ዙሪያው ገደል ነው የሚሆነው። አስታማሚም ታማሚም ማጣፊያው ሲያጥራቸው የሚያማክሩት ወገን ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ማየት የተለመደ ነበር።
[ "ድሮ ሠው ታሞ ደም ያስፈልገዋል ከተባለ ዙሪያው ገደል ነው የሚሆነው። አስታማሚም ታማሚም ማጣፊያው ሲያጥራቸው የሚያማክሩት ወገን ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ማየት የተለመደ ነበር።" ]
ቆፍጠን ብሎ ወደ ደም ባንክ የሄደ ደግሞ ደም ሰጥቶ ሕይወት ለማትረፍ የተሰለፈ ደም ለጋሽ፣ ደም ሸጦ የእለት ጉሮሮው ላይ ቁራሽ እንጀራ ለማኖር የሚጣደፍ 'ነጋዴ'፣ ደም ደልሎ የድርሻውን ሊቦጭቅ ያሰፈሰፈ ደላላ ጋር ይፋጠጣል። ሕይወትን ለማትረፍ ደም በቀላሉ ማግኘት ዳገት የነበረት ጊዜ ነው ያዘመን። ሩቅ ይመስላል፤ ግን የትናንት ያህል የሚያስታውሱት አሉ። • ጠቅላይ ሚነስትር ዐብይ አህመድ በአክሱም ምን ተጠየቁ? • በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ ለ79 ጊዜ ደም ለግሷል። የ54 ዓመቱ ጎልማሳ አቶ ሠለሞን በየነ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን ኑሮውን የመሰረተው በግል ሥራ ላይ ተሰማርቶ ነው። በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ስር ይተዳደር የነበረው የደም ባንክ በሚገኝበት ስታዲየም ዙሪያ የደም ሽያጭ ገበያ ደርቶ በነበረበት ወቅት ደማቸውን ለመሸጥ ከተሰለፉ ጋር ተጋፍቶ ደሙን በነጻ ይለግስ እንደነበር ያስታውሳል። ደም ለጋሽ እንዲሆን ያደረጉትን አጋጣሚዎችም እንዲሁ አይረሳቸውም። ክፉ አጋጣሚ በጎ ትምህርት አንደኛው አጋጣሚ ቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኛ በመሆን አምቡላንስ ላይ ይሠራ በነበረበት ወቅት በጽንስ መቋረጥ የተጎዳች ሴት ደም አጥታ ሕይወቷ ሲያልፍ መመልከቱ ነው። ሌላው ደግሞ ሆስፒታል ውስጥ በተመሳሳይ ምክንያት ብዙ ደም ፈሷት የነበረች ሴት ደም ተሰጥቷት ሕይወቷ ሲተርፍ መመልከቱ ነበር። እነዚህ ሁለት አጋጣሚዎች ያለ ምንም ማቅማማት ለረዥም ዓመታት ደም እንዲለግስ የሁል ጊዜ የሕሊና ደወል እንደሆነለት ይናገራል። • የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ እንደ ሠለሞን ለዓመታት ከለገሱና ካነጋገርናቸው የደም ባንክ ሠራተኞች መረዳት እንደሚቻለው ደም እስከ አምስት ሺህ ብር ይሸጥ ነበር። ምንም እንኳ በሕክምና በሦስት ወር አንድ ጊዜ ብቻ ደም መስጠት የሚመከር ቢሆንም በሳምንት ሦስት ጊዜ ደማቸውን የሚሸጡ ምንዱባን እንደነበሩ ሠለሞን ያስታውሳል። ስታዲየም ዙሪያ ደም ይሸጥ በነበረበት ወቅት ደም ሻጮችና ገዥዎች ብቻ ሳይሆኑ ደላሎችም የገበያው ተዋናዮች ነበሩ። "የበሬ ንግድ ይባል ነበር" ሲል ያስታውሳል። የደም ሽያጭ ደርቶ የነበረው ደም ባንክ የምትክ ደም አሰራርን ይከተል በነበረበት ወቅት ነበር። ለአንድ ታማሚ ይህን ያህል ደም ያስፈልጋል ሲባል፤ የሚያስፈልገውን ያህል ደም ሊሰጡ የሚችሉ የቤተሰብ አባላት ወደ ደም ባንክ ሄደው ደም ይሰጣሉ። በምትኩ ደም ባንክ ለበሽተኛው የሚያስፈልገውን የደም አይነት ታማሚው ለሚገኝበት ሆስፒታል ይልካል። የደም ሽያጭ እንዴት ቆመ? በ2004 እንዲሁም በ2003 ዓ.ም የደም ባንክ ደጃፍ በደም ገዥና ሻጭ እንዲሁም ደላላ ግርግር የሞቀ ነበር። በእነዚያ ዓመታት ሆስፒታሎች ደግሞ እየተስፋፉ ነበሩ። የሆስፒታሎቹ ደም ፍላጎት ሲጨምር የደም ሽያጭ ገበያ እንዴት ሊደራ እንደሚችል የተረዳው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በቀይ መስቀል ስር የነበረውን ደም ባንክ ተጠሪነት በቀጥታ ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አድርጎ ነገሮችን ለውጦ ምትክ ደም አሠራር እንዲቀር አደረገ። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በአጠቃላይ 42 የደም ባንኮች ይገኛሉ። ከእነዚህም የሐረርና የጅግጅጋ ደም ባንኮች ዛሬም የምትክ ደም አሠራርን እንደሚከተሉ አቶ ያክጋል ባንቴ፣ የብሔራዊ ደም ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ አልሸሸጉም። አጠቃላይ ከሚሠበሠበው ደም አንድ ሦስተኛው አዲስ አበባ ላይ ሲሰበሰብ ሁለት ሶስተኛው ደግሞ በክልል ደም ባንኮች የሚሠበሰብ ነው። • ከወለደች ከ30 ደቂቃዎች በኋላ ለፈተና የተቀመጠችው እናት እንደ ሠለሞን ያሉ ለጋሾች ምስጋና ይግባቸውና ደም ባንክ ዛሬ ላይ የምትክ የደም አሠራርን ትቶ ደም ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ያለምትክ ደም እየሰጠ ይገኛል። በደም ልገሳ ላይ መሻሻሎች ቢኖሩም ስኬት ላይ ነን ማለት የሚቻልበት ደረጃ ላይ አልተደረሰም ይላሉ የብሔራዊ ደም ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ። ምክንያቱ ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት ከአንድ አገር አጠቃላይ ሕዝብ አንድ በመቶ የሚሆነው በፈቃደኝነት ደም የሚለግስ መሆን ይገባዋል ቢልም የኢትዮጵያ እውነታ ከዚህ የራቀ መሆኑን በመጥቀስ ነው። ይህ ማለት ሳይንሱ እንደሚለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ሚሊዮን የሚሆነው በበጎ ፈቃደኛነት በዓመት ሦስት ጊዜ ደም ቢለግስ ሦስት ሚሊዮን ደም ሊገኝ ይችል ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ደም ባንክ እየሰበሰበ ያለው በዓመት ሁለት መቶ ሺህ ደም ብቻ እንደሆነ ኃላፊው ይናገራሉ። "በጣም በጣም ታች ነን ያለነው፤ ይህ ምንም ነው" በማለት ሁኔታውን ይገልፃሉ። ነገር ግን 2011 ዓ.ምን በምሳሌነት በማንሳት ምንም የደም እጥረት እንዳላጋጠመ ያስረዳሉ። እጥረቱ ያልተፈጠረው ግን ሆስፒታሎች በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ ባለመሆኑ ነው። በሌላ በኩል እጥረት የለም ማለት የሆስፒታሎች የደም ፍላጎት በመጠንም በዓይነትም ደም ባንክ አሟልቷል ማለት እንዳልሆነ ይልቁኑም የኔጋቲቭ ደም አይነቶች እንዲሁም የፕላትሌት እጥረት መኖሩን ይገልፃሉ። • ስለ ግንቦት 27፤ 1983 የጎተራው ፍንዳታ ምን ያስታውሳሉ? ከኔጋቲቭ ደሞችም በይበልጥ በተለያየ ምክንያት እጥረት ያለው ለማንኛውም ህመምተኛ ሊሠጥ የሚችለው 'ኦ ኔጋቲቭ' የደም ዓይነት ነው። የዚህ የደም ዓይነት እጥረት የሚፈጠረው ደግሞ ይህ የደም አይነት ያላቸው ሠዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑና ለማንኛውም ሠው መስጠት የሚችል ደም በመሆኑ ነው። በተጨማሪም ደግሞ በአስገዳጅ ጊዜ ብቻም ሳይሆን ሆስፒታሎች ቀድመው የበሽተኞችን ደም ሳይመረምሩ በመቅረት እንዲሁ ኦ ኔጋቲቭን መስጠታቸው እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን አቶ ያረጋል ያስረዳሉ። የኦ ኔጋቲቭ የደም እጥረትን ለመፍታት በማሠብ የደም ባንክ ባለፈው ሠኔ 2 ቀን 2011 ዓ.ም የዚህ ደም በጎ ፈቃደኛ ለጋሾች ቡድን እንዲመሠረት ያደረገ ሲሆን ከ800 በላይ የሚሆኑ ኦ ኔጋቲቭ ሰዎች በእለቱ ግንዛቤ ለመፍጠር የእግር ጉዞ አድርገዋል። "ለእናታችን ደም ስጥልን እኛ እንፈራለን" ወጣት ጥበቡ ቢያድግ ከ17 ዓመታት በፊት ሰዎች ደም ሲለግሱ አብሮ በመሔድ በድንገት ነበር ደም መስጠት የጀመረው። እስከ አሁን 38 ጊዜ ለግሷል። ኦ ኔጋቲቭ ነው። ደሙ ለማንም እንደሚሆን ከተረዳበት ጊዜ ጀምሮ በፍቃደኝነት ለመለገስ ወደኋላ ብሎ አያውቅም። የደም ባንክም የኦ ኔጋቲቭ ደም እጥረት ሲያጋጥም ከሚደወልላቸው ሰዎች መካከልም አንዱ ነው። እሱና ጓደኞቹ በቡድን ሆነው ደም ለመስጠት ደም ባንክ ሲሄዱ በር ላይ ደላሎች 'ገንዘብ ማግኘት ስትችሉ ለምን በነፃ ትሰጣላችሁ' እያሉ ያዋክቧቸው እንደነበር ጥበቡ ያስታውሳል። እሱና ጓደኞቹ ግን ከገንዘብ ይልቅ ከቀይ መስቀል የተሰጣቸውን 'እኔ ደም ለጋሽ ነኝ'፣ 'ደም ለጋሽ ጀግና ነው' የሚሉ ቲሸርቶችን ለብሰው አደባባይ መውጣት ኩራታቸው ነበር። በዚህም ደም ለጋሽ እንደሆኑ ያወቁ በርካታ ሰዎች ለሕመምተኛ ቤተሰባቸውና ወዳጃቸው ደም እንዲሰጡላቸው ይጠይቋቸው ነበር። በዚህም የማይረሳው አጋጣሚም አለ። አንዲት ጎረቤቱ ቀዶ ሕክምና ሊደረግላቸው ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ገብተው ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም ደም መስጠት ይፈራሉ። ከዚያም ጥበቡን እባክህ ይሉታል። ደም መስጠት ምንም ችግር እንደሌለውና እነርሱም ሊሰጡ እንደሚችሉ ቢነግራቸውም ስለፈሩ ልጆቻቸው ለእናታቸው ደም መስጠት አልቻሉም ይላል። በመጨረሻ ለእናታቸው ደም እንደሚሰጥ ነገር ግን በቀጣይ እሱን አይተው እነርሱም ለጋሽ እንዲሆኑ ቃል አስገባቸው። • አምስት ጂ ኢንተርኔት ምን አዲስ ነገር አለው? • የወንዶች ያለዕድሜ ጋብቻ እርሱ ለታማሚዋ እናት የሚያስፈልገውን ደም ሰጠ፤ እናትም ተረፉ። ጥበቡም ከቤተሰቡ ጋር ዘመድ ሆነ። የሴትየዋ ልጆች ግን ከዛሬ ነገ አብረንህ ሄደን ደም እንለግሳለን እያሉ ቆይተው በመጨረሻ ደም መስጠት እንደማይችሉ ነገሩት። "ገርሞኝ ዝም አልኩ" ይላል ጥበቡ ሁኔታውን አስታውሶ "አንዳንዱ ደሙ የሚያልቅ ወይም የሚታመም ይመስለዋል፤ አንዳንዱ ደግሞ ደም ማነስ አለብኝ ደም አይነቴን አላውቀውም ይላል።" ከወጣትነት እስከ... የላብራቶሪ ቴክኒሻኑ ዳዊት ፍቅሩ የ37 ዓመት ወጣት ነው። ከ1995 ጀምሮ የበጎ ፈቃደኛ የደም ለጋሽ መሆኑን ይናገራል። የደም አይነቱ ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚያጥረውና ለማንኛውም ሠው የሚሰጠው ኦ ኔጋቲቭ ነው። ኦ ኔጋቲቭ መሆኑን ያወቀው ቀይ መስቀሎች በሚማርበት ትምህርት ቤት ተገኝተው በፍቃደኝነት ደም ይሰበስቡ በነበረበት ወቅት እንደነበር ያስታውሳል። ስለ ደም ልገሳ ቢያውቅም ስለ ኦ ኔጋቲቭ ደም የሚያውቀው ነገር ግን አልነበረም። ዳዊት ስለ ኦ ኔጋቲቭ ደም ካወቀ በኋላ ግን ከደም ባንክ ቢደወልለትም ባይደወልለትም እስከ አሁን 38 ጊዜ ደም ሰጥቷል። ዳዊት እርሱ በሚለግሰው ደም የሰው መርዳት በመቻሉ ደስተኛ ነው "የእኔ ደም ለማንም መሆን እንደሚችል አውቃለሁኝ። ስለዚህ ማንም ቢድንበት ደስታዬ ነው" ይላል። ምትክ ደም በሚጠየቅበት ወቅት ለዓመታት ለሚያውቃቸውና በሚያውቃቸው ሰዎች ለመጡበት በርካታ ሠዎች ደሙን ሰጥቷል። በዚህ ረገድ ብዙ አጋጣሚዎችን ያስታውሳል። እርሱ 'ተፈላጊውን' የደም ዓይነት በነፃ ሊለግስ በፈቃደኝነት በተደጋጋሚ ሲሄድ፤ ስታዲየም ዙሪያ በደም እስከ አምስት ሺህ ብር ይቸበቸብ እንደነበር እንደሚያስታውስ ይናገራል። • የበርካታ ዕፅዋት ከምድረ-ገፅ መጥፋት አሳሳቢ ሆኗል ብሩ አያጓጓም ነበር ወይ? ለዳዊት ያነሳነው ጥያቄ ነበር። ገንዘብ ተሠርቶ በማንኛውም ጊዜ ሊገኝ ስለሚችል ዳግም የማይገኝ የሠው ህይወትን ማትረፍ ትልቅ እርካታ እንዳለውና ያኔ ደም ሲሸጥ ሲያይ እጅጉን ያዝን እንደነበር ያስታውሳል። "ደም አጥተው የሚሞቱት የእኔ እናት፣ አባቴ ወይንም ጓደኛዬ ቢሆን ብሎ የሚያስብ ሰው ደም ለመሸጥም ሆነ ለመደለል አያስብም " ይላል። የበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች ጥምረት ወጣት ፀደቀ ሞገስ ለ57 ጊዜ ደም ለግሷል። ሦስት በጎ ፈቃደኛ የደም ለጋሾች ቡድንም እንዲቋቋም አስተባብሯል። እሱና ጓደኞቹ ቀደም ሲል ደም ይለግሱ የነበረ ቢሆንም በቡድን ደም መለገስ የጀመሩት የ1997ቱን ፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ በተፈጠረው ችግር በጊዜው ከፍተኛ ደም እጥረት በነበረበት ወቅት ነበር። በወቅቱ የደም እጥረት ስለነበር የደም ሽያጭ ገበያውም ደርቶ እንደነበር ፀደቀ ያስታውሳል። ሠዎችን በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ማድረግ ግድ እንደሆነ የሚናገረው ፀደቀ ብዙዎችን ማሰባሰብ የቻለው ቤተክርስቲያን አካባቢ እንደሆነ ይገልፃል። ለእናታቸው ወይም ለአባታቸው ደም አንሰጥም ያሉ ሰዎች ፀደቀንም አጋጥመውታል። በብዙ ሰዎች ዘንድ ደም ስለመስጠት ግንዛቤ አለመኖሩ ደም ለጋሽ እንዳይሆኑ አድርጓል ይላል ፀደቀ። በሌላ በኩል እንደሱ ያሉ ለዓመታት ያለማቋረጥ ደም የሚለግሱ ሰዎች በሰብዓዊነት ሳይሆን በሆነ ጥቅም እንደሆነ የሚያስቡም ብዙ መሆናቸውን ይናገራል። "በእኛ ደም እየበላ" መባሉንም ፀደቀ ያነሳል። "ባለቤቴ ከምትሞት እኔ ደም ሰጥቻት ልሙት" ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ በብሔራዊ ደም ባንክ የትምህርትና ቅስቀሳ ባለሙያ ሲሆኑ የበጎ ፈቃደኛ የደም ለጋሽም ናቸው። በግምት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ለ72 ጊዜ ደም ለግሰዋል። በመጀመሪያ ጊዜ ደም የሰጡበትን አጋጣሚ ሁሌም ያስታውሳሉ። የምትክ ደም አሠራር በነበረበት ወቅት ነው። ባለቤቱ ሆስፒታል የተኛችና የሁለት ሠው ደም እንዲያመጣ የተነገረው ከገጠር የመጣ አንድ ሰው "ባለቤቴ የልጆቼ እናት ከምትሞት እኔ ደሜን ሰጥቻት ልሙት" ይላቸዋል። ሲስተር አሠጋሽ ሠውዬው ደም መስጠት እንደሚገድል እንዳሰበ ተረድተዋል። በጣም ተጨናንቆ አዝኖ ነበር ይላሉ በወቅቱ የነበረውን መለስ ብለው ሲያስታውሱ። ሠውዬው የተፃፈለት ሁለት ዩኒት ደም እንዲያመጣ ስለነበር አንደኛውን ሲስተር አሠጋሽ በበጎ ፈቃደኝነት ሲሰጡ ሌላኛውን ሌሎች የደም ባንኩ በጎ ፈቃደኞች ከሠጡት እንደተገኘለት ያስታውሳሉ። "መነሻዬ ያ ባለቤቱን የሚወድ ሰው ነው" የሚሉት ሲስተር አሰጋሽ ለሚስቶቻቸው ደም ላለመስጠት የሚያንገራግሩ ባሎች አጋጥሟቸዋል። የምትክ ደም አሠራር ለደም ባንኩ ከባድ ጊዜ ለሰራተኞቹም አስቸጋሪ እንደነበር ይገልፃሉ። እንደ ገቢ ማግኛ በቀን ሁለት ጊዜ ደም የሚሠጡ፣ የጤናቸውን ሁኔታ ደብቀው ደማቸውን የሚሸጡም እንደነበሩ ይናገራሉ። • የሱዳንን መፃዒ ዕድል የሚወስኑት የጦር አበጋዝ አንድ ሠው ክብደቱ 45 ኪሎ፣ እድሜው ከ18 እስከ 65 ከሆነ፣ ምንም ዓይነት መድኃኒት የማይወስድ ማንኛውም ሠው በየሦስት ወሩ ደም መስጠት እንደሚችል ሲስተር አሠጋሽ ይናገራሉ። ሌላው ያነጋገርነው ደም ለጋሽ አቶ ዳዊት ተስፋዬ ነው። የስድስት ልጆች አባት የሆነው አቶ ዳዊት ደም መስጠት ከመጀመሩ በፊት ማለትም ተማሪ ሳለ የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኛ ነበር። በ25 ዓመታት ውስጥ ለ75 ጊዜ ያህል ደም ለግሷል። "እኔ በሰጠሁት ደም ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ተጠቅመዋል ብዬ አስባለሁ" ይላል። የዓለም የጤና ድርጅት ሀገራት በ2020 ወጣት ዜጎቻቸው በፈቃደኝነት ደም እንዲሰጡ በማድረግ የሀገራቸውን የደም ፍላጎት እንዲያሟሉ ጥሪ ያቀርባል። በአሁኑ ሰአት በዓለም ላይ 80 ሚሊየን ዩኒት ደም የሚሰበሰብ ቢሆንም በተለይ በታዳጊ ሀገራት ከፍተኛ እጥረት መኖሩን ይገልፀዓል
xlsum_amharic-train-106
https://www.bbc.com/amharic/53060108
በዩትዩብ የትኞቹ አፍሪካውያን ሙዚቀኞች ይመራሉ?
ዳይመንድ ፕላትነምዝ ታንዛኒያዊ ሙዚቀኛ ነው፡፡ ፕላትነምዝ የመድረክ ስሙ ሲሆን ነሲቡ አቡዱል ጁማ የሚለውን የፓስፖርት ስሙን የሚያውቀው ያለም አይመስልም፡፡
[ "ዳይመንድ ፕላትነምዝ ታንዛኒያዊ ሙዚቀኛ ነው፡፡ ፕላትነምዝ የመድረክ ስሙ ሲሆን ነሲቡ አቡዱል ጁማ የሚለውን የፓስፖርት ስሙን የሚያውቀው ያለም አይመስልም፡፡" ]
የተወለደው በዳሬ ሰላም ነው፡፡ አሁን ገና 30 ደፍኗል፡፡ ባለፈው ሳምንት ብዙዎች የሚወዱለትን ደረቱን አጋልጦ በግማሽ እርቃን ቤተ መንግሥት በመሰለ ቤቱ እየተንጎማለለ ሳለ የርሱ የሙዚቃ ኩባንያ ሰራተኞቹ ‹‹በድንገቴ የምስራች!›› አስደነገጡት፡፡ • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን • ታዋቂዎቹ ኤርትራዊያን በሙዚቃቸው ምክንያት ይቅርታ ጠየቁ ያስጋገሩት ኬክ የ‹ዩትዩብ› ልዩ የንግድ መለያ ቀይ ምልክት የተደረገበት ነበር፡፡ ለካንስ እሱ ዘንግቶት እንጂ ዳይመንድ ፕላትነምዝ በዩቲዩብ የተመልካቾቹ ቁጥር ያን ዕለት 1 ቢሊዮን ሞልቶ ነበር፡፡ ለዚህም ነበር የምሥራቹ! ባለፉት 10 ዓመታት ዳይመንድ ፕላትነምዝ በርካታ ሽልማቶች አግኝቷል፡፡ የስዋሂሊ ቋንቋን ከእንግሊዝኛ ጋር በማቀናጀት ባህላዊና ዘመናዊ የሙዚቃ ቃናዎች በማዳቀል ተወዳጅ ሥራዎችን ለአድናቂዎቹ አቅርቧል፡፡ ‹‹ፕላትነምዝ በጣም ታታሪ ሙዚቀኛ ነው›› ይላል ዲጂ ኤዱ፡፡ ዲጄ ኤዱ ሳምንታዊውን የፓን አፍሪካን የሙዚቃ ዝግጅትን በቢቢሲ ለረዥም ዘመን ሲያጫውት የኖረ የራዲዮ ሙዚቃ አሳላፊ (ዲጄ) ነው፡፡ 55 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ታንዛኒያ ዘመናዊ ስልክ ኖሮት ኢንተርኔት የሚያገኘው ሕዝብ በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱ ዳይመንድን ለመሰሉ ሙዚቀኞች ትልቅ ገበያ ነው፡፡ ለጊዜው ከታንዛኒያ ሕዝብ 43 ከመቶ ብቻ ነው ኢንተርኔትን በስልኩ ማግኘት የሚችለው፡፡ ከዳይመንድ ሌላ አዳዲስ ሙዚቀኞች በስዋሂሊ ተናጋሪ ምሥራቅ አፍሪካዊያን ዘንድ ተወዳጅ እየሆኑ ነው፤ ዕድሜ ለበይነመረብ፤ ዕድሜ ለ‹ዩትዩብ›፡፡ ቢሊዮን ተመልካች በዩቲዩብ ማግኘት ብርቅ ነው? ዳይመንድ ፕላትነምዝ ከዩትዩብ ይልቅ በኢንስታግራም በርካታ ተከታይ አለው፡፡ የዩትዩብ ታማኝ ተከታዮቹ (ሰብስክራይበርስ) 3.7 ሚሊዮን ሲሆኑ የኢንስታግራም ግን 9.7 ሚሊዮን ደርሰዋል፡፡ ዲጄ ኤዱ እንደሚለው ኢንስታግራም በዋናነት የሕይወት ዘይቤና ፋሽንን መስበኪያ መድረክ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዝነኛ የሆነው ቲክቶክ በአንጻሩ በጣም ወጣት የሆኑ አድናቂዎችን ለመመልመል ይበልጥ ተመራጭ ነው፡፡ ገና ከወዲሁ አንዳንድ ሙዚቃዎች እጅግ ዝነኛ ሆነዋል በቲክቶክ፡፡ ለምሳሌ ዳይመንድ ፕላትነምዝ በቅርቡ የለቀቀው ኳረንቲን የተሰኘ ሥራው ተወዳጅ የሆነው በቲክቶክ አማካኝነት ነው፡፡ ተወዳጅ የሆኑ ሥራዎችን ወደ ዩትዩብ መውሰድ የተለመደ የሆነው በ‹ዩትዩብ› በማስታወቂያ የሚገኘው ገንዘብ ጠርቀም ያለ ስለሆነ ነው፡፡ • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" ባለፉት ዓመታት ለአፍሪካ ሙዚቀኞች ዩትዩብ እጅግ ጠቃሚው የመታያ መድረክ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም አሁን ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ደጅ መጥናት እየቀረ መምጣቱ ነው፡፡ በጣቢያዎች ይሁንታ ለማግኘት የነበረው ዕድል አሁን በሞዛቂዎቹ በእጃቸው እንዲገባ የሆነው በዩትዩብ ምክንያት ነው፡፡ በዩትዩብ ከአፍሪካ ማን ይመራል? ዳይመንድ ፕላትነምዝ ከሰሀራ በታች ከፍተኛ የዩትዩብ አድናቂዎች ቁጥር ቢኖረውም እርሱን ከሰሜን አፍሪካ ሞዛቂዎች ጋር ካነጻጸርነው እዚህ ግባ የሚባል አይሆንም፡፡ ምክንያቱም የሰሜን አፍሪካ ሞዛቂዎች ከሰሀራ በታች ካሉት ይልቅ በቀላሉ ዝነኛ ስለሆኑ ነው፡፡ የሰሜን አፍሪካ አገራት በመካከለኛው ምሥራቅ የአረብኛ ተናጋሪዎች ዘንድ የመታየት ዕድል ስለሚኖራቸው ሰፊ መልከአምድር የመሸፈን ዕድል ያገኛሉ፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ አገራት ሙዚቀኞች ደግሞ ተቀማጭነታቸው በአፍሪካ ባይሆንም ሰፊ የዩትዩብ ተቀባይነት ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ የማሊ ተወላጇ አያ ናካሙራን ብንወስድ የምትኖረው በፈረንሳይ ቢሆንም በ2018 የለቀቀችው ጃጃ (Djadja) የተሰኘው ሥራዋ 1.7 ቢሊዮን ተመልካቾች ወደውላታል፡፡ አያ ገና 25 ዓመቷ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ሌላው ተጠቃሽ ኤኮን ነው፡፡ የሴኔጋሉ ተወላጅ ኤኮን 3.5 ቢሊዮን የዩትዩብ ተመልካች አግኝቷል፡፡ ከሰሀራ በታች በዩትዩብ ተመልካች ብዛት ከዳይመንድ ፕላትነምዝ የሚፎካከሩ ሞዛቂዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ በዚህ ዝርዝር ውስጥ የዴቪዶና የበርና ቦይ ቁጥር ልዩ የሚያደርገው ሁለቱም ዩትዩብ የከፈቱት ከ2 ዓመት በፊት ገና በ2018 ነበር፡፡ ዳይመንድ ፕላትነምዝ ግን ከ2011 ጀምሮ ዩትዩብ ላይ ነበረ፡፡ ዊዝኪድ በበኩሉ ስታርቦይ ቲቪ የሚባል የሙዚቃ ዩትዩብ መለያና ስቱዲዮ አለው፡፡ በዚያ በኩል ያለው ተመልካቹን ስንደምረው የዩትዩብ ተመልካቾቹ ብዛት 802 ሚሊዮን ያልፋል፡፡ አንዳንድ ሙዚቀኞች ሥራዎቻቸውን በሙዚቃ ስቱዲዮ በኩል እንዲለቀቅ ያደርጋሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በቀጥታ በራሳቸው ቻናል ይለቁታል፡፡ ሙዚቃ አሰናጆች ቢሮክራሲያቸው ይበዛል ብለው የሚያስቡ ናቸው በራሳቸው መንገድ በቀጥታ መልቀቅ የሚመርጡት፡፡ • አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ • በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የሚጠቀሱት አርመኖች ማጂክ ሲስተም የተሰኘው የአይቮሪኮስት የደቦ ሙዚቃ ቡድንም ቀላል ተመልካች አይደለም ያገኘው፡፡ 477 ሚሊዮን ሰዎች ተመልክተውታል፡፡ ይህ የሙዚቃ ቡድን በተለይ በምዕራብ አፍሪካ የፈረንሳይኛ ተመልካቾች ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡ ዊዝኪድ ከካናዳዊው እውቅ አቀንቃኝ ድሬክ ጋር በ2016 በጥምረት የሰራው ‹‹ዋን ዳንስ›› የተሰኘው ሥራው 1.8 ቢሊዮን ጊዜ በዩትዩብ ተሰራጭቷል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማን በርካታ ዩትዩብ ተመልካች አለው? ካናዳዊው ድሬክ 7 ቢሊዮን የዩትዩብ ተመልካች አለው፡፡ ቢዮንሴ 12 ቢሊዮን የዩትዩብ ተመልካች አግኝታለች፡፡ ቢዮንሴ ባለፈው ዓመት ከአፍሪካዊ አርቲስቶች ጋር የ‹‹ላየን ኪንግ›› አልበምን መሥራቷ ይታወሳል፡፡ ገና በአዳጊ ዕድሜው ዝናን የተቀዳጀውና አሁን የ26 ዓመት ወጣት የሆነው ካናዳዊው ጀስቲን ቢበር 21.6 ቢሊዮን ተመልካቾች አሉት፡፡ በ2016 የተመሰረተው የሴት ሞዛቂዎች ቡድን ብላክፒንክ 9 ቢሊዮን የዩትዩብ ተመልካቾች አሉት፡፡ የአፍሪካ ሴት ሞዛቂዎች ደረጃ የት ነው? በሚገርም ሁኔታ ሴት የአፍሪካ ሙዚቀኞች በርካታ የዩትዩብ ሙዚቀኛ ማግኘት አልሆነላቸውም፡፡ ለምሳሌ የሚ አላድ እና ቲዋ ሳቬጅ ከወንድ አቻዎቻቸው ጋር ሲነጻጸር እጅግ ያነሰ የዩትዩብ ተመልካች ነው ያላቸው፡፡ የሚ 434 ሚሊዮን፣ ቲዋ ደግሞ 239 ሚሊዮን ተመልካቾች አግኝተዋል፡፡ ይህ ምናልባት የአፍሪካ የሙዚቃ መድረክ በወንዶች የተያዘ መሆኑ እና ለሴቶች እምብዛምም ቦታ አለመኖሩ ያመጣው ችግር ይመስለኛል ይላል ዲጄ ኤዱ፡፡ "እንዲያውም እኮ በቅርብ ጊዜ ነው ለትልልቅ የሙዚቃ ድግሶች ሴት ሙዚቀኞችን በዋናነት ማስፈረም እየተለመደ የመጣው፡፡ ትልልቅ መድረኮች ላይ እየተጋበዙ ቢሆን ኖሮ ብዙ ተከታይ እያፈሩ መምጣታቸው ደግሞ አይቀርም" ይላል ዲጄ ኤዱ፡፡ ከሙዚቀኞች እኩል የወንጌል ዘማሪዎችም በአፍሪካ የሙዚቃ ገቤ ትልቅ የዩትዩብ ተመልካች አላቸው፡፡ ለምሳሌ ዘማሪ ሲናች 472 ሚሊዮን ተመልካቾች አሏት፡፡ ይህን ማሳካት የቻለችው ደግሞ ዓለም አቀፍ መንፈሳዊ ጉባኤዎችን ስለምትመራና በ‹‹ክራይስት ኤምባሲ›› ቤተ ክርስቲያን ስለምትሰብክ ነው፡ "ዘማሪዎች ተከታይ ለማግኘት መድከም አይጠበቅባቸውም፡፡ ለመዝሙራቸው ግጥም ሲመርጡም አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መስመር ሳብ አድርጎ ማውጣት ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው፡፡ እንዲህ ሲያደርጉ ግጥሞቻቸው ቤት የሚመቱት በራሳቸው ጊዜ ነው፡፡ ተከታይ ለማፍራት ብዙ መድከም አይጠበቅባቸውም" ይላል ዲጄ ኤዱ፡፡ የትኛው ይሻላል? በአካል ወይስ በዩትዩብ እንደ ኡጋንዳዊው ኤዲ ኬንዞ ያሉ ዘፋኞች ከመድረክ ሥራ ይልቅ የበይነ መረብ በኩል ዝናን ማጋበስ የተሻለ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ኬንዞ 388 ሚሊዮን የዩትዩብ ተመልካች አለው፡፡ ለአንጎላዊው ሲፎር ፔድሮ ግን ለመድረክ ሥራ ከአገር አገር መዞርን የመሰለ የለም፡፡ የኪዞምባ ስልት ኮከቡ ፔድሮ ብዙ አገር ሄዶ ስታዲየም ሙሉ ታዳሚ ማግኘት ይችላል፡፡ ዳይመንድ ፕላተነምዝ ግን ምንም እንኳ በዩትዩብ ዝነና ቢሆንም ዓለም አቀፍ ተጽእኖ ፈጣሪነቱ ውስን ነው፡፡ ኾኖም ግን ዝናና ገናና ስም ገና ላልገነቡ የአፍሪካ ሙዚቀኞች ዩትዩብን የመሰለ መድረክ የለም፡፡ ገና ጀማሪ ወጣቶች ዩትዩብን ይመርጣሉ፣ ገፋ ያሉት ደግሞ መድረክ ይወዳሉ፡፡ ለምሳሌ የዚምባብዌ ተወላጅ የ32 ዓመት ሙዚቀኛ ጃ ፕራይዛህ 99 ሚሊዮን የዩትዩብ ተመልካቾች አሉት፡፡ የአፍሪካ አፍሮ ጃዝ አባት እየተባለ የሚሞካሸውና የአህጉሪቱ ጥላሁን ገሠሠ የሚባለው ኦሊቨር ምቱኩዚ ግን ባለፈው ዓመት ሕይወቱ እስክታልፍ ድረስ ከመድረክ አልራቀም፤ የሚደንቀው እስኪሞት ድረስ አንድም የየትዩብ ቻናል በስሙ አልነበረም፡፡ "ኦሊቨር ምቱኩዚን ካየሽው ዕድሜ ዘመኑን ከመድረክ መድረክ ጊታሩን ይዞ ሲዞር ነው የኖረው፡፡ የሙዚቃ ጉዞው ፋታ አልነበውረም፤ ዓለምን ሲዞር ኖሮ ነው የሞተው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ መቶ ሚሊዮን የዩትዩብ ተመልካች ከመቃረም 50 ጽድት ያሉ የመድረክ ሥራዎችን አቅርቦ ማለፍ ይሻል ይሆን ያስብላል" ይላል ዲጄ ኤዱ፡፡ በገቢ ረገድም ቢሆን ዩትዩብ ሚሊዮነር አያደርግም፡፡ "አንድ ሚሊዮን ተመልካች በዩትዩብ ያገኙ 3ሺህ ዶላር ያገኛሉ፡፡ አንድ ቆንጆ መድረክ ሥራ የዚህን 10 እጥፍ አያስገኝም?"
xlsum_amharic-train-107
https://www.bbc.com/amharic/50135607
በዋግ ኽምራ ከ126ሺ ሰዎች በላይ አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለፀ
በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በተከሰተው ድርቅ 126ሺ ዘጠና ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።
[ "በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በተከሰተው ድርቅ 126ሺ ዘጠና ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።" ]
ባለፈው ዓመት በነበረው ዝቅተኛ ዝናብ ምክንያት ድርቅ በመከሰቱ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ ደስታ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች ምንም ዓይነት ዝናብ ያልጣለ ሲሆን፣ ክረምት ዘግይቶ የገባባቸው እንዲሁም የመጠን እና የሥርጭት ጉድለት የታየባቸው አካባቢዎች ለድርቅ እንደተጋለጡ ያስረዳሉ። •የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ከየት ወደ የት? •"የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ ምንም እንኳን የዝናብ እጥረቱ የዋግ ኽምራ አብዛኛው ወረዳዎች ላይ ቢከሰትም በተለየ ሁኔታ ግን ሰሃላ ሰየምት፣ ዝቋላ እንዲሁም ከፊል ሰቆጣ ዙሪያ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል ብለዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በዞኑ ከሚገኙ ስድስት መቶ ሺ ነዋሪዎች መካከል 126 ሺ ዘጠና የሚሆን ሰው አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል። የሰብል ግምገማ እየተደረገ መሆኑን የሚገልፁት አቶ መልካሙ ድርቁ ያስከተለውን ጉዳት ሙሉ በሙሉ ለማወቅ የሚያስችል ቢሆንም ምንም አይነት ዝናብ ያልጣለባቸው አካባቢዎች ግን የከፋ ችግር ከማጋጠሙ በፊት ፈጣን ምላሽ እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ። "ዝናብ ባለመጣሉ ችግር የገጠማቸው ወረዳዎች የሰብል ግምገማ ተደርጎ ምላሽ ይሰጣል ከማለት ቀድሞ ለነዚህ ሰዎች መድረስ አለብን፤ አሁን ባለው ሁኔታ 126ሺህ ሰዎች በአፋጣኝ ልንደርስላቸው ይገባል" የሚሉት አቶ መልካሙ በማኅበረሰቡ መካከል ያለው የመረዳዳት እና ያለውን የመካፈል ባህል እስካሁን ቢያቆየውም መንግሥት በአፋጣኝ ካልደረሰ ችግሩ እንደሚከፋ ይገልጻሉ። "ድርቅ ረሀብ መሆን አይገባውም" ሲሉም ድርቁ አሁን ካለበት ደረጃ የከፋ ሆኖ ወደ ረሀብ ሳይሸጋገር በፊት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ይናገራሉ። •ወመዘክር፡ ከንጉሡ ዘመን እስከዛሬ •ኮሎኔል መንግሥቱን ትግል ለመግጠም ቤተ መንግሥት የሄደው ደራሲ ሰዎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ለክልል እና ለፌደራል መንግሥት ያሳወቁት ከሐምሌ መጨረሻ ጀምሮ እንደሆነም ያስረዳሉ። መረጃ በወቅቱ ለማጥራት ባለመቻላቸው ሂደቱ ቢዘገይም ክልሉ ጉዳዩን ለፌደራል መንግሥት አሳውቋል ይላሉ። ከዛ በኋላ የጨረታ፣ የሎጂስቲክ ችግር ገጥሟቸው የነበረ ቢሆንም አሁን የከፋ ችግር ውስጥ ያሉት ተለይተው እርዳታ ማጓጓዝ ሥራው ተጀምሯል ይላሉ። 126ሺህ ለሚሆኑት ሰዎች ከፌደራል የተደረገው እርዳታ ከመንግሥት መጠባበቂያ የተገኘ ሲሆን፤ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተገኘ እርዳታ ጎን ለጎን እንደሚሰጥም ገልጸዋል። የመንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ ወደ አካባቢው ገብቶ ከተጠናቀቀ በኋላ (የፊታችን እሮብ ጥቅምት 12 ድረስ) ወደማከፋፈል እንደሚሄዱም ተናግረዋል። "አሁን የገጠመን ችግር የመንገድ ነው። እሱን ኀብረተሰቡን በማሰማራት መሠራት ያለበት ሥራ መሠራት አለበት። በዚህ ወር ውስጥ መድረስ ካልተቻለ የሰው ሕይወት ሊያልፍ ይችላል ብለን እንፈራለን" ይላሉ። እስካሁን የሞተ ሰው እንደሌለ አቶ መልካሙ ገልፀው ነገር ግን አፋጣኝ ድጋፍ ስለሚያስፈልግ በቀጣይ ዐሥር ቀናት መድረስ ባለበት ቦታ ሁሉ መድረስ እንዳለባቸውም ገልጸዋል። •"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ •በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግዕዝና ኦሮምኛ ቋንቋዎች ጥናት ፍላጎት ጨምሯል በዝቋላ ወረዳ በ01 ቀበሌ ነዋሪና የአራት ልጆች አባት አቶ በርሄ እያሱ በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከተጎዱ አርሶ አደሮች አንዱ ናቸው። "ያለንበት ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው። ድሮ ዋግ ህምራ ወይም በዝቋላ ወረዳ ችግር ሲከሰት ወደ በለሳ፣ ደንቢያ ወይም ወደ ሱዳንም ይኬድ ነበር። አሁን ግን የተረጋጋ ስላልሆነ አልተቻለም" ይላሉ። በቀበሌያቸው የክረምት ዝናብ ያገኙት ሐምሌ 29፣ 2011 ዓ.ም መሆኑን ገልፀው ከዚያ በኋላ ግን ዝናብ የሚባል ነገር በቀበሌው እንደሌለና ድርቁ ሰዎችንም ብቻ ሳይሆን እንስሳትን እያጠቃ መሆኑንም አፅንኦት በመስጠት ይናገራሉ። "ኑሮ በጣም ከብዷል። የቀን ስራ እንዳንሰራም የምንሰራው ነገር ግራ አጋብቶናል። በግልም ያው ዕቃ የሚያሸክምም የለም። ያው ከእግዚአብሔር በታች ያለው መንግሥት ነው፤ የሚያደርገንን ለማየት በጉጉት እየጠበቅን ነው" ይላሉ። ከእርሻቸው ውጭ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ እንደሌላቸው የሚናገሩት አቶ በርሄ " ከተለያዩ ከተሞች ነጋዴ የሚያመጣው ቀይ ማሽላ አለ። ያው እሱን 15፣ 20 ኪሎ በብድር ሸምተን ነው የምንበላው፤ ያው የሰው ሕይወት በረሀብ ማለቅ ስለሌለበት" ይላሉ። የእሳቸው ቀበሌ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ቀበሌዎችም በድርቁ እንደተጠቁና በአካባቢውም ስር የሰደደ ድህነት እንዳለ ይናገራሉ። ችግሩ የከፋ ከመሆኑ አንፃር ለመንግሥት ማሳወቃቸውን የሚገልፁት አቶ በርሄ "ዞሮ ዞሮ ተረጋጉ ሰው ወደ ስደት እንዳይሄድ አረጋጉት የሚል ነው ምላሽ የተሰጠን፤ ስደትስ ቢሆን የት ይሄዳል? አሁን ግን የተረጋጋ ሁኔታ ስለሌለ ወደየት እንሄዳለን?" ይላሉ። ሌላው በዝቋላ ወረዳ የሚኖሩት የሰባት ልጆች አባት የሆኑት የ40 ዓመቱ አርሶ አደር አቶ አደሩ ወልዴም አፋጣኝ ድጋፍ እንደሚሹ ይናገራሉ። ያጋጠማቸውንም ድርቅ በኢትዮጵያ ለብዙ ሰዎች እልቂት ካደረሰው ከ1977 ረኃብ ያላነሰ ድርቅ ነው ይላሉ። "ህዝቡ በጣም ተቸግሮ ነው ያለው፤ እንሰሳትም እየሞቱብን ነው ያሉት። አሰቃቂ ሁኔታ ነው የገጠመን " በማለት አክለውም "ሳለ እግዚአብሔር የሞተ ሰው የለም፤ በቀጣይም እርዳታ ካልተደረገ የሰው ህይወት ሊጠፋ ይችላል" በማለት ይናገራሉ። •አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት •ኢትዮጵያውያን ዛሬም ከአለት አብያተ-ክርስትያናትን ያንፃሉ ከፌደራል መንግሥት ተወክለው የመጡ ሰዎችም በአካባቢው ጉብኝት ማድረጋቸውን ያስረዳሉ። ከሰሞኑ እንዲሁም የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ሲያወያዩዋቸው የነበረ መሆኑን ጠቅሰው "ሕዝቡ በአጠቃላይ የሚበላው የለም። ምን እናድርግ? ምን እንብላ" ብለው እንደጠየቁና ከአደጋና መከላከልና ምግብ ዋስትና መልስ ጠብቁ የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። ወረዳው ለአቅመ ደካሞችና ለአካል ጉዳተኞች የብር እርዳታ ቢያደርግላቸውም "ለሌላው ለተቸገረው ህዝብ ምንም አይነት እርዳታ አልደረሰውም" ይላሉ። በቀድሞው ጊዜ እንዲህ አይነት ችግር በሚያጋጥምበት ወቅት አርሶ አደሩ ወደሌላ አካባቢዎች ተሰዶ አጠራቅሞ የሚያመጣበት ሁኔታ ነበር አሁን ያ ሁኔታ በመቆሙ ለተደራረበ ችግር መጋለጣቸውን ይናገራሉ። "ቀድሞ ወደ ጎንደር፣ መተማ ይሰድድ ነበር። ባለው አለመረጋጋት ሁኔታ መሰደድ አልቻልንም። አርሶ አደሩ መሔጃ አጥቶ በጣም ተቸግሮ ነው ያለው" ይላሉ የቀን ስራ በመፈለግም የዕለት ጉርስ ለማግኘትም እየታገሉ መሆናቸውን ይናገራሉ። አቶ መልካሙም በአርሶ አደሮቹ ሃሳብ ይስማማሉ "ከዚህ በኋላ ወር ወይም ሁለት ከዘገየ የከፋ ችግር ሊመጣ ይችላል" ይላሉ። •በቅዳሜው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ምግባሩ ከበደ አረፉ •አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" እንስሳትን በተመለከተ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መኖ በማቅረብና መስኖ ተከትሎ በመዝራት ለእንስሳት እንዲደርስ ማድረጋቸውንም ያክላሉ። እንስሳት ወደ አጎራባች ቀበሌና ወረዳ እንዲሄዱ ቢደረግም ሌላ ቦታም እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ስጋት አላቸው። አሁን እየተደረገ ያለው የሰብል ግምገማ ውጤት ከ10 ቀን በኋላ እንደሚታወቅና ይፋ እንደሚደረግም ይገልጻሉ። ከድርቁ ጋር በተያያዘ በሰዎች እና በእንስሳት ላይም በሽታ ሊከሰት ስለሚችል አስቀድሞ መከላከል አስፈላጊ መሆኑንም አክለዋል። ለእንስሳት መኖ ከመሰጠቱ በፊት ክትባት እንሚሰጣቸውም ይናገራሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዝናብ እጥረት ምክንያት በዞኑ አስቸኳይ ድጋፍ ጉዳይ ላይ የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ እታገኘሁ አደመ እንደተናገሩት ድጋፍ የሚያስፈልገውን ህዝብ ችግር መንግሥት ሊፈታው የሚችል ነው ብለዋል። ችግሩን መጠን ለማጥናት የተለያዩ ባለሙያዎች ወደ አካባቢው በማቅናት ጥናት ማድረጉን አስታውቀዋል። በዚህ መሠረትም "የፌደራል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ለሚኖሩ የየዕለት ቀለብ ድጋፍ እንዲቀርብ ጠይቀን እየተጓጓዘ ይገኛል" ብለዋል። "ከመስከረም ወር ጀምሮ ችግር ይኖራል በሚል እየተሠራ ነው" ያሉት ኮሚሽነሯ "ለ12 ወር የሚሆን ድጋፍ ለመጠየቅ ዕቅድ ተይዟል" ሲሉ ገልጸዋል። የተጠየቀው ድጋፍ በመጓጓዝ ላይ መሆኑን ጠቁመው የሌሎች ድጋፍ በሚያስፈልግበት ወቅት በተቀናጀ መልኩ በቀጣይ ሊሠራ እንደሚችል አስረድተዋል። በዞኑ የተሻለ ዝናብ ያገኙ አካባቢዎች በመኖራቸው ሙሉ ለሙሉ ድጋፍ የሚፈልጉ አለመሆናቸው ታውቋል።
xlsum_amharic-train-108
https://www.bbc.com/amharic/50818734
'የአልባኒያ ተቃዋሚዎች' በትግራይ
የትግራይዋን 'አልባንያ' በደቡባዊ አውሮፓ ባልካን በሚባለው አካባቢ በስተምዕራብ ከምትገኘው አልባንያ ጋር የሚያመሳስላት አንዳች ነገር የለም።
[ "የትግራይዋን 'አልባንያ' በደቡባዊ አውሮፓ ባልካን በሚባለው አካባቢ በስተምዕራብ ከምትገኘው አልባንያ ጋር የሚያመሳስላት አንዳች ነገር የለም።" ]
ምናልባትም የ'ትግራይዋ አልባንያ' ያለምንም የአቋም ለውጥ ለረዥም ዓመታት የህወሓት ተቃዋሚ መሆኗ ከቀሪው የትግራይ ክፍል የተለየች ሊያስብላት ሲችል፤ አልባንያም በአስቸጋሪ መልክዓ ምድሯ እንዲሁም በውስብስብ የታሪክ፣ የባህልና ማህበራዊ ሁኔታዎች ተለይታ የምትኖር መሆኗ ካላመሳሰላቸው በስተቀር። ከመቐለ በስተምሥራቅ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውና ቀድሞ በእንደርታ ወረዳ አስተዳደር ስር የነበረችው 'እግሪ ሃሪባ' በብዙዎች ዘንድ 'አልባንያ' በመባል ትጠራለች። • ህወሓት ከኢህአዴግ ለመፋታት ቆርጧል? • ህወሓት: "እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም" ይህ ግን በሌላ ሳይሆን፤ ይደርስብናል የሚሉትን ኢፍትሀዊነት አምርረው በመቃወማቸው፣ በደል የሚሸከም ጫንቃ የለንም በማለታቸው መሆኑን ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢዋ ነዋሪዎች ያስረዳሉ። የእግሪ ሃሪባ 'አልባኒያ' ኗሪዎችህወሓትን ለምን አምርረው ይቃወማሉ? "ስንቱን እናገረዋለሁ . . . እስር ላይ በነበርንበት ወቅት፣ ሌሊት ስድስት ሰዓት ላይ በየቀኑ በሚቀያየሩ ሰዎች እንመረመር ነበር። ራሳቸው በፈጸሙት ጥፋት የተከሰስንበት ጊዜም ነበር፤ ከባድ በደል ደርሶብናል። ህወሓት እያታለለ የሚኖር ፓርቲ ነው" ይላሉ የእግሪ ሃሪባዋ የሦስት ልጆች እናት አርሶ አደር አልጋነሽ ገብረሕይወት። ወ/ሮ አልጋነሽ ቀድሞ የህወሓት ደጋፊ የነበሩ ቢሆንም የአካባቢያቸው ነዋሪ ለሚያነሳው ጥያቄ የፓርቲው ምላሽ 'ጆሮ ዳባ ልበስ' ሲሆንባቸው "ጥያቄያችንን እና መብታችንን እናስመልሳለን" ካሉ የእግሪ ሃሪባ አርሶ አደሮች ጋር አብረው ተሰልፈዋል። አብዛኛው የአካባቢው ሰው ብዙ ችግር ማሳለፉን፤ ስብሰባ ላይ ሃሳባቸውን እንዳይገልፁ ይደረጉ እንደነበር የሚናገሩት ወ/ሮ አልጋነሽ፤ ተናገራችሁ ተብለው የታሰሩበት ጊዜም እንደነበር ያስታውሳሉ። 'አልባንያዎች'ና ህወሓት የተካረሩት በ2003 ዓ.ም የመቀሌ ከተማ አስተዳደር ትንሽዋን የገጠር ከተማ እግሪ ሃሪባ [አልባንያ] በመቀለ ከተማ አስተዳደር ስር መግባት አለባት የሚል ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ነው። በወቅቱ ነዋሪዎቿ አስፈላጊው መሰረተ ልማት ሳይሟላ እንዴት በከተማ አስተዳደር ስር እንገባለን ሲሉ አሻፈረን አሉ። ወ/ሮ አልጋነሽ እና ሌሎች ስድስት የአካባቢው ኗሪዎች የተቃውሞው መሪዎች ነበሩ። ያነጋገርናቸው የእግሪ ሃሪባ ነዋሪዎች እንደገለፁልን አካባቢው በከተማ አስተዳደር ስር እንዲሆን ሲወሰን፤ ውሃ፣ መብራት፣ መንገድና ሌሎች መሰረታዊ የልማት አቅርቦቶች አልነበሩም። የሕክምና ባለሞያዎችና የሕክምና መሳሪያ ባልተሟላበት የጤና ተቋም ልጆቻችንን አናስከትብም፣ አስተማሪ ባልተሟላበትና የትምህርት መሳሪያ እጥረት ወዳለበት ትምህርት ቤትም ልጆቻችንን አንልክም በማለት የእግሪ ሃሪባ ነዋሪዎች ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ያደርጉ ነበር። በዚህ ተቃውሟቸውም 'የአልባኒያ ተቋማዊዎች' የሚል መጠሪያ እንደተሰጣቸው ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። ወ/ሮ አልጋነሽ ከእስር ከተፈቱ በኋላ በወቅቱ ብቸኛው የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲ የነበረው አረናን እንደተቀላቀሉ ይገልጻሉ። • መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው፡ አባይ ፀሐዬ • "አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው" አቦይ ስብሃት ከአምስት ዓመት በፊት በተካሄደው አራተኛው አገራዊ ምርጫ፤ ከወ/ሮ አልጋነሽ ጋር የህዝብ ጥያቄ ይመለስ ሲሉ ድምፃቸውን ያሰሙ ተቃዋሚዎች በምርጫው ዋዜማ በሽብር ተከስሰው ታሰሩ። "እኔን ጨምሮ መሬታችንን አትቀሙንም ብለን ያልን ሰዎች ታሰርን" የሚሉት ወ/ሮ አልጋነሽ፤ ለሦስት ዓመታት ልጆቻቸው ማረሚያ ቤት እየተመላለሱ እሳቸውን በመጠየቅ እንደተንገላቱ በቁጭት ያስታውሳሉ። ወ/ሮ አልጋነሽ ከመቀለ ከተማ አፍንጫ ስር የምትገኘው መንደራቸውን በመጥቀስ "አካባቢያችን ላይ ውሃ ስለሌለ የሁለት ሰዓት መንገድ ተጉዘን ውሃ እንቀዳለን፤ መብራት የለም፤ ለአምቡላንስ የሚመችም መንገድም የለም፤ ከተማ ላይ ሆነን ሁሉም የራቀብን ሰዎች ነን። በቃ! 2003 ላይ የወደቀችው አካባቢ እንደወደቀች ናት፤ እስከ አሁን አምነን የተቀበልነው አስተዳዳሪ'ኳ የለንም፤ ቢኖርም አናውቀውም" ይላሉ። የእግሪ ሃሪባ አርሶ አደሮች ዛሬም የክልሉ መንግሥት የሚልካቸው አስተዳዳሪዎችን 'የህወሐት ካድሬ' ናቸው በሚል በሙሉ ልቡ አይቀበሏቸውም። ትግራይ ውስጥ ያለው ሰው ባለው ወቅታዊ የፖለቲካ ምክንያት ለህወሓት ልቡ የራራ ቢመስልም 'አልባንያዎች' ግን ህወሓትን ይቅር ያሉት አይመስሉም። አቶ መኮንን አብርሃ [ለዚህ ታሪክ ሲባል ስማቸው ተቀይሯል] አርሶ አደር ናቸው። "2003 ላይ መብታችን ይከበር፣ መሰረተ ልማት ይሟላልን በማለታችን፤ ለሦስት ወይም አራት ዓመት ገደማ አስተዳዳሪ አልተመደበልንም ነበር" ይላሉ። በ2008 ህዳር ወር ላይ አሸባሪዎች ተብለው በክልሉ መንግሥት ታስረው ለ14 ወራት የክስ ሂደታቸውን በውጪ ሲከታተሉ ቆይተው በመጨረሻ የተወሰኑት አራት፤ ሌሎቹ ደግሞ ሦስት ዓመት ተፈርዶባቸው መታሰራቸውን ያስረዳሉ። ልጆቻንን አናስከትብም፤ ወደ ትምህርት ቤትም አንልክም ማለትስ ምን አይነት ተቃውሞ ነው? የሚል ጥያቄ በቢቢሲ የተጠየቁት አቶ መኮንን፤ ጥያቄው ያስቆጣቸው ይመስላል፤ ለህወሓት የሚሰሩ ናቸው ያሏቸው መገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን የዘገቡት በተሳሳተ መልኩ መሆኑን በማስረዳት ነገሩ እንደዚያ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል። "ልጆቻችን አናስከትብም ሳይሆን፤ የሚከተቡት በቀደመው አስተዳደር ስር ስንሆን ነው፤ የትምህርት ቤቱ ጉዳይም ወላጆቻችሁ ወደ ከተማ አስተዳደሩ ገብተናል ብለው ሲፈርሙ ነው የምናስተምራችሁ በማለታቸው እራሳቸው የፈጠሩት ችግር ያመጣው ነው።" ወ/ሮ አልጋነሽም በበኩላቸው "የክልሉ መንግሥት ክትባት የሚለው ምን ዓይነት የጤና ተቋም ሰርቶ ነው?" የሚል ጥያቄ በማንሳት "መጀመሪያ አላስከትብ፤ ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት አልልክ አሉ ብሎ ለመውቀስ የክልሉ መንግሥት ተቋማቱን በቅጡ መች ሰርቷቸው ነው?" ሲሉ ለጉዳዩ ምላሽ ይሰጣሉ። ህወሓት ያቀረብኩለትን ጥያቄ መመለስ ስላልቻለም "ፓርቲዬን ቀየርኩ" የሚሉት ወ/ሮ አረጋሽ፤ "እውነት በመጉደሉ ከህወሓት እንድንርቅ ተገደናል" ብለዋል። የ'አልባኒያዎች' ተቃውሞ ሰላማዊ ሊባል የሚችል የነበረ ቢሆንም እነሱ እንደሚሉት ግን የህወሓት ጠንካራ እጅ ከብዶባቸው ነበር። እነርሱ እንደሚያስረዱት በወቅቱ የአካባቢው ገበሬዎች የሰበሰቡት እህል በእሳት ጋይቶ ያድር ነበር። ይህ በአካባቢው ነዋሪና በአካባቢው የመንግሥት ተሿሚዎች መካከል ውጥረትን ፈጥረ። ውጥረቱ እየተካረረ በሄደበት ወቅት እንደ ወ/ሮ አልጋነሽ ያሉ የአካባቢው ተቃውሞ መሪዎች ታሰሩ። ቤተሰባቸው እንደተበተነና ልጆች ከትምህርታቸው እንደተስተጓጎሉ ይናገራሉ። "እኔ ስታሰር፤ ልጄ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቷን አቋርጣ ጠላ እየሸጠች፣ ወንድሞችዋን ተታሳድግ ነበር። የአካባቢው ህብረተሰብም መሬት ያርስላቸው፣ እህል ያጭድላቸው ነበር። ሁላችንም ግን ፍላጎታችን ለውጥ እንጂ ሌላ አልነበረም" ይላሉ። የእግሪ ሃሪባ ገበሬዎችንና የከተማዋ አስተዳደርን ለማሸማገል የሀገር ሽማግሌዎችና ቀሳውስት በመካከል ገቡ፤ ነገር ግን አልተሳካም። የአጽቢ ወንበርታ ወረዳ የ'አልባኒያዎች'፣ የእነ ወ/ሮ አልጋነሽ እና የህወሓት ጉዳይ በዚህ አላበቃም ወደ ኋላ እንመለስበታለን። አሁን ደግሞ ከመቀለ በ50 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቃ ወደምትገኘው የአጽቢ ወንበርታ ወረዳ እንሂድ። • "ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) • "ውስኪ ጠጪ ኢህአዴጎች እባካችሁ ውሃ የናፈቀው ሕዝብ እንዳለ አትርሱ" ጠ/ሚ ዐብይ ያነጋገርነው በወረዳዋ ኗሪ የሆነው ሕድሮም ኃይለሥላሴ የተባለ አርሶ አደር፤ ህወሓት የትግራይ ህዝብ ትግልን መንገድ ላይ 'ክዶታል' ይላል። ለዚህም ማስረጃ ሲል የሚጠቅሰው ህወሓት ደርግ ከመውደቁ በፊት የነበረ ባህሪውን ከደርግ መውደቅ በኋላ ቀይሯል በማለት ነው። ሕድሮም የታጋይ ልጅ ሲሆን እርሱም በአፍላ ወጣነት እድሜው በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ሚሊሻ ነበር። በትምህርት ደግሞ 10ኛ ክፍል ደርሷል። ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ህወሓት ላይ የነበረውን እምነት እያጣ መምጣቱን የሚናገረው ሕድሮም፤ 2002 ላይ አረና ትግራይን ተቀላቅሎ ህወሓትን መቃወም ጀመረ። 'ህወሓትን የመቃወም ጉዞው' ግን ቀላል አልሆነም፤ ከባድ ዋጋ ያስከፍለው ጀመር። ተቃዋሚ መሆኑ ሲታወቅ፤ ወደ እሱ እርሻ የሚሄደው የመስኖ ውሃ 'የህወሓት ካድሬዎች' በሚላቸው ሰዎች ተዘጋ፤ ከማህበራዊ ህይወት እንዲገለል በብዙ መልኩ ጫና ደረሰበት በመጨረሻም ታሰረ። ይህን ታሪኩን ይዞ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ የመጣው ሕድሮም፤ ብዙ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጫና የተዘጋበት የመስኖ ውሃ መስመር ከዓመታት በኋላም ቢሆን ተከፈተለት። "ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነኝ፤ እናቴ ማረሚያ ቤት ተጠርታ ልጅሽ ትግራይን የካደ፣ የአማራ ተላላኪ ነው ስትባል አዝና ማየቴ ነው" ይላል። ሰው በምንም መልኩ እንዳይረዳው፣ ቀብር ላይ እንዳይገኝ፣ እስር ላይ ሳለም እንዳይጠየቅ ክልከላዎች ተደርገውበት እንደነበር ህድሮም በተሰበረ አንደበት ይገልፃል። እናቱ "በጉያሽ ጠላት እያሳደርሽ ነው" በመባላቸው ሲጨነቁ በዚሁ ምክንያት ከአማቾቹ ጋር እንዲለያይ መሆኑም ለእሱ ከባድ ስቃይ እንደነበር ይናገራል። ምንም እንኳ የተለያየ አካባቢ ነዋሪዎች ቢሆኑም የ'አልባንያዎቹ' እነ ወ/ሮ አልጋነሽና ህድሮም ህወሓትን በመቃወም የደረሰባቸው የቅጣት እጣ ተመሳሳይ ነው። በብዙ መልኩ አካላዊም ሥነ ልቦናዊም ዋጋ ከፍለዋል። "በወሬ መሃል እኛ ስንቀላቀል ዝም ይባላል፤ አሁን ሰልችቶን ትተነው ነው እንጂ ልጆቻችንንም አትናገሩ፤ ብትመቱም አንገታችሁን ደፍታችሁ ቤታችሁ ግቡ ብለናቸዋል። የሕዝብ ሁኔታ እንዲሻሻል የማደርገው ጥረት የለም፤ አርፌ ኑሮዬን እየኖርኩኝ ነው" ይላሉ ወይዘሮ አልጋነሽ። ያለፈው ነገር የአካባቢያቸውን አርሶ አደር በፍርሀት የሥነ ልቦና ጫና ውስጥ እንዲገባ ማድረጉንም ይገልጻሉ። 'የእገሌ ወንድም እኮ ነው' እየተባለ ከማህበራዊ ኑሮ ተገለናል የሚሉት አቶ መኮንን፤ ፍትህና ለውጥ እስኪገኝ የሚደረገው ትግል ዋጋ እንደሚያስከፍል ይናገራሉ። የትግራይዋ 'አልባኒያ' ህወሓትን ይቅር ብላዋለች? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያ በተለያዩ የለውጥ ሂደቶች ውስጥ ብትሆንም አለመረጋጋት በዚህም በዚያም እየናጣት ነው። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ • "ለውጡ ሐዲዱን ስቷል ብዬ ነው የማምነው" አርቲስት ታማኝ በየነ በአንድ ግንባር ስር የቆየው በኢህኢዴግ አባል ድርጅቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት፤ በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል ያለው ፍትጊያም ከጊዜ ወደ ጌዜ እየተካረረ ሄዷል። ይህ መካረር ለህወሓት በክልሉ ውስጥ ድጋፍ እያስገኘለት መምጣቱን በክልሉ የሚኖሩ ሰዎች ይናገራሉ። "ይህ ሕዝብ እኮ ትዕግስተኛ ስለሆነ ነው እንጂ፤ የተሸከመው ችግር ቀላል አይደለም" የሚሉት ወ/ሮ አልጋነሽ፤ ህወሓት በስመ ይቅርታ እየኖረ ነው ይላሉ። "አሁን ጊዜው ጨለም ስላለ ይነጋ ይሆናል ብለን ሁሉንም በሆዳችን ይዘነዋል። ሌላ ቦታ ቤትም ንብረትም ተቃጠለ ሲባል እንሰማለን፤ ይህ እኛ ጋርም እንዳይፈጠር ልጆቻችንን ረጋ ብለን እየገራን ነው። ለዚህ ድርጅት አስበን ሳይሆን ለራሳችን . . ." አክለውም "አዲሱ ትውልድ የራሱን ርዕስ ፈጥሮ እንዲሄድ እንሻለን እንጂ ህወሓትን ተቀይሞ ጠብና ግጭት እንዲያነሳ አንፈልግም" ይላሉ። በትግራይ ፍትህ የሚባል አለመኖሩ የሚናገሩት አቶ መኮንን በበኩላቸው፤ አሁን ያለንበት ጊዜ የትግራይ አስተዳደር እንዲህ አድርጎናል ብለን "ክልላችንን ለአደጋ የምናጋልጥበት አይደለም" ይላሉ። "ባለፈው የምቀየም ሰው አይደለሁም፤ በትግራይ ብዙ ደምና አጥንት ተከፍሏል። ይህ በማንም ሰው እንዲረገጥና እንዲደፈር አንፈልግም። ፍትህ ባይኖርም ትግራይን እንጠብቃለን፤ ከህወሓት ጋር ያለንን ሂሳብ ኋላ ላይ እንተሳሰባለን" ቢሉም መልሰው ደግሞ ጥያቄ ያነሳሉ። "ህወሓት አሁን ለትግራይ እሰራለሁ ካለ፤ ለምን ታድያ አሁን ዞር ብሎ አያየንም? ስለምን ችግራችንን አይፈታልንም?" የትናንቱ ህወሃት ከተመሰረተ 45 ዓመታት ያስቆጠረው ህወሓት፤ በሂደት የሚገነባው ሥርዓት ዲሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ይሆናል የሚል የብዙዎች ተስፋና የድርጅቱ ቃል ነበር። • መንግሥት አደገኛ የሆነውን የትግራይን መገለል መለስ ብሎ ሊያጤነው ይገባል- ክራይስስ ግሩፕ ይሁን እንጂ፤ ህወሓት ከበረሀ ወጥቶ "ሥልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ መርሆቹን ጥሷል" ብለው የሚተቹት የድርጅቱ አባላት የነበሩ ጭምር ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ፤ በጅግጅጋና አምቦ ከተሞች ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ወደ መቀለ በመሄድ ለነዋሪዎች ንግግር ሲያደርጉ፤ በእያንዳንዷ ንግግራቸውም ነዋሪው በድጋፍ ሲያጨበጭብ ነበር። ያኔ በህወሓት አስተዳደር የተገፉ የክልሉ ነዋሪዎች ሌላ መሪ በማግኘታቸው ሸክማችን ይቀላል ብለው፤ ተስፋ አድርገው እንደነበር ይናገራሉ። ተስፋው ግን ብዙ አላስኬደም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወሰዷቸው የለውጥ እርምጃዎች ደስተኛ አልሆኑም። የአገሪቷ አንዳንድ መገናኛ ብዙኀንም በሰሯቸው 'ሙስናና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጋልጡ ናቸው' በተባሉ ዘጋቢ ፊልሞች 'ትግርኛ ተናጋሪ' የሚለውን ማስተጋባታቸው የትግራይን ሕዝብ እንዳስኮረፈም ይጠቅሳሉ። ሕዝቡም ተቀባይነቱ እየተመናመነ መጥቶ ለነበረው ህወሓት የራራለት መሰለ። "ይህ ሁሉ፤ ሃገሪቷ ላይ ያለው ሁኔታ የፈጠረው ስጋት እንጂ፤ ህወሓት ተመችቶት አይደለም" የሚለው ስሙ ሊጠቀስ ያልፈለገ የፖለቲካ ተንታኝ፤ ህወሓት ዛሬ ትግራይ ላይ ያገኘው ድጋፍ "ዘላቂ ነው ወይ?" በሚለው እርግጠኛ መሆን አይቻልም ይላል። በትግራይ፤ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ከባድ መሆኑን የሚናገረው ሕድሮም፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለይ በክልሉ መንግሥት ላይ ትንሽ ለውጥ ቢመጣም፤ አሁንም እኛ በምንፈልገው መንገድ እየሄድን፣ ሃሳባችን እየገለጽን ግን አይደለም ይላል። "ቢሆንም፤ ቢያንስ ፖሊስ መጥቶ አያስረንም፣ ገበያ ላይም ሰው አይሸሸንም።" የህወሓት ሊቀ መንበርና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመሩት ድርጅት፤ የህዝብ ጥያቄ ለመመለስም ሆነ የተሻለ የፖለቲካ ምህዳር ለመፍጠር እንደሚሰራ በተለያዩ መድረኮች ገልጸዋል። • የ31 ዓመቱ ኢሕአዴግ ማን ነው? • "ስተዳደር የቆየሁት በዋናነት ለመለስ በሚሰጠው የጡረታ ገቢ ብቻ ነው" ወ/ሮ አዜብ መስፍን "ድርጅቱ አሁን ጠቅልሎ ቢመጣም [ወደ ትግራይ] መጨረሻው ግን የት ነው? የሚለውን ማወቅ አስቸጋሪ ነው" የሚለው ሕድሮም፤ አገሪቷ ላይ ባለው ፖለቲካዊ ሁኔታ በማመካኘት ለግል ጥቅሙ ህዝብ ላይ የፍርሀት ሥነ ልቦና እየፈጠረ ነው" ይላል። ህወሓት በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን ምላሽ ለማወቅ የታሪኩ መነሻ ወደሆነችው የእንደርታ ወረዳ ተመለስን፤ የወረዳው የህወሓት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደም ዓለም ድርጅታቸው "ህወሓትን የሚቃወም ሆነ ጥያቄ የሚያቀርብ አካል ላይ በደል አልተሰራም" ብለዋል። "ስላለፈው የአርሶ አደሮቹ ታሪክ የማውቀው ነገር የለም፤ ለአካባቢው አዲስ ብሆንም እንዲህ የሚል መረጃም ግን አላገኘሁም። በአጠቃላይ ግን፤ ከሥርዓት ውጪ የሆነ በሥርዓት ይጠየቃል እንጂ ተቃዋሚ ስለሆነ የሚያስርና የሚገርፍ ድርጅት [ሕወሓት] አይደለም።" በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት ታሪክ የሚያነሱ ሰዎችንም "በአገር ደረጃ እየደረሰ ካለው ጥላሸት የመቀባት ዘመቻ ለይቼ አላያቸውም" ያሉት ኃላፊው፤ "ህወሓት በሃሳብ የሚታገል ድርጅት" ነው በማለት ይናገራሉ። እርሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ ፓርቲው ቀደም ብሎ ባካሄደው ጥልቅ ተሃድሶ፤ ጸረ ዲሞክራሲያዊ ባህሪይ ሲያሳይ መቆየቱን ማመኑ ይታወሳል።
xlsum_amharic-train-109
https://www.bbc.com/amharic/news-56521488
ደም መለገስ፡ በኢትዮጵያ ደም በመለገስ ቀዳሚ የሆኑት ነርስ ማን ናቸው?
አንድ ሰው በጠና የታመመች ሚስቱን ሊያሳክም ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ያቀናል። ሚስቱ ህክምና ትጀምራለች።
[ "አንድ ሰው በጠና የታመመች ሚስቱን ሊያሳክም ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ያቀናል። ሚስቱ ህክምና ትጀምራለች።" ]
ሐኪሞች ግለሰቡን ጠርተው ባለቤቱ በአስቸኳይ ሁለት ዩኒት [አንድ ሰው በአንድ ጊዜ አንድ ዩኒት ደም ነው መለገስ የሚችለው] ደም እንደሚያስፈልጋት ይነግሩታል። ግለሰቡ ደም ፍለጋ ከጥቁር አንበሳ ስታዲየም ጎን ወደ ነበረው የደም ባንክ ያቀናል። ግለሰቡ እንደመጣ "ሚስቴ ከምትሞት ከእኔ ደም ወስዳችሁ ስጧት" እያለ ይማጸነን ጀመር ይላሉ የብሔራዊ ደም ባንክ ባልደረባ የሆኑት ሲስተር አሰጋሽ ጎሣ። "በጣም ተጨንቋል" ሲሉ የነበረበትን ሁኔታ ያስታውሳሉ። ". . .'ባለቤቴ የልጆቼ እናት ልትሞት ነው። እሷ ከምትሞት እኔ ልሙት' ሲል አልቻልኩም" ይላሉ። በወቅቱ ደም የሚያስፈልጋቸው ሰዎች የጠየቁትን ከማግኘታቸው በፊት ዘመዶቻቸው ወይም የሚያቋቸው ሰዎች ምትክ ደም ከሰጡ በኋላ ነው ደም የሚያገኙት። ይህም ነው ግሰለቡን ጭንቀት ላይ የጣለው። ይስጥ ቢባልም አንድ ዩኒት ደም ብቻ ነው መስጠት የሚችለው። እሱንም ቢሆን አይችልም። ግለሰቡ ጭንቀት፣ ድካምን ጨምሮ ሌሎች ደም መስጠት የማይችልባቸው ሁኔታዎች ነበሩ። "'እኔ ባንተ ቦታ ደም እለግሳለሁ' አልኩት" ሲሉ ሲስተር አሰጋሽ ያስታውሳሉ። ለግለሰቡ አንድ ዩኒት ደም ከመስጠት በተጨማሪ ከበጎ ፈቃደኞች የተገኘ ሌላ አንድ ዩኒት ደም ከደም ባንክ እንዲሰጠው ያደርጋሉ። ከዚህ በኋላ የእርሳቸው ደም የመስጠት ታሪክ መጻፍ ጀመረ ለግለሰቡ ሲሉ አንድ ብለው የጀመሩት ደም ልገሳ አሁን 80 ደርሷል። ሲስተር አሰጋሽ ጎሣ ይባላሉ። እዚህ ጋር የጤና ሚንስትር የሆኑትን የዶ/ር ሊያ ታደሠን አገላለጽ እንጠቀም- "ሲስተር አሰጋሽ ጎሣ ነርስም፣ እናትም ቀዳሚ ደም ለጋሽም" ናቸው ይላሉ። ሲሰተር አሰጋሽ ደግሞ ራሳቸውን የጤና ባለሙያ እና በብሔራዊ የደም ባንክ በደም ልገሳ ዙሪያ የተግባቦት ባለሙያ እንደሆኑ ይገልጻሉ። በብሔራዊ የደም ባንክ ከሃያ ዓመት በላይ ሠርተዋል። ዋነኛ ሥራቸው ህብረተሰቡ ደም እንዲለግስ ትምህርት መስጠት ነው። ስለ ደም ልገሳ ሲነሳ በተደጋጋሚ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አመህመድን (ዶ/ር) አባባል ይጠቀማሉ- 'ደም መለገስ የፍቅር መግለጫ ነው' የሚለውን። ለሚስቱ ህይወት ሲንሰፈሰፍ ላዩት ግለሰብ ሲሉ የጀመሩትን የደም ልገሳ በየጊዜው ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ቀደም ሲል ሴቶች በየስድስት ወሩ ደም እንዲለግሱ ይመከር ነበር ይላሉ። ይህ ግን ለእርሳቸው እንቅፋት አልነበርም። "በሁለት ወርም በሦስት ወርም ደም እለግስ ነበር" ሲሉ ያስታውሳሉ። ጊዜው ተቀየረና አሁን በየሦስት ወሩ መስጠት ተፈቀደ። "አሁን ደም ልገሳው በየሦስት ወሩ ቢደረግም ምዝገባ የሚደረገው በኮምፒውተር ስለሆነ [እንደዚህ ቀደሙ] ከሦስት ወር ቀደም ብሎ መስጠት አይቻልም" ይላሉ። በዚህ ምክንያትም ጊዜያቸውን ሳያዛንፉ ደም ይለግሳሉ። የጤና ባለሙያ መሆናቸው እና በደም ባንክ መሥራታቸው ተገቢውን ጥንቃቄ አድርገው እንዲሰጡ ረድቷቸዋል። "አስፈላጊውን ጥንቃቄ አደርጋለሁ። መሟላት ያለበትን በሙሉ አሟልቼ ስለምቀርብ 'አይ አሁን ደም መለገስ አትችይም' ተብዬ የተመለስኩበት ጊዜ የለም" ሲሉ ይገልጻሉ። ቢቢሲ፡ ለመሆኑ የሰጡት ደም ለማን እንደደረሰ ያውቃሉ? ሲሰተር አሰጋሽ፡ ደም ለማን እንደሰጠ አይታወቅወም። በበጎ ፈቃድ የምንሰጠው ደም ለማን እንደሆነ አናውቅም። [ደሙ] ተሰብስቦ ሆስፒታል ይሄዳል። ለሚይስፈልገው ሰው ይሰጣል። እኔም አልከታተልም። አይመለከተኝምም [ሳቅ]። ቢቢሲ፡ ደም ለምን ሰጠሁ ብለው ተጸጽተው ያውቃሉ? ሲሰተር አሰጋሽ፡ ደም ባልሰጠሁ ያልኩበት ጊዜ የለም። ከፈጣሪ በታች ከራስ አልፎ የአንድን ሰው ህይወት እንዲኖር መርዳት ትልቅ ነገር ነው። ታምሜ ደም ከሚሰጠኝ ብሰጥ ይሻላል። ከሁሉም በላይ የህሊና እርካታ አለኝ። መጀመሪያ ላይ የረዳሁት ግለሰብ ሁሌም ያስደስተኛል። መነሻዬም ነው። ያንን ሰው እንደዛ ተጨንቆ አይቼ በመርዳቴ በጣም ነው ደስ ያለኝ። ሌሎች ተጨንቀው እርዳታ በመስጠታችን እና ደም ባንክ በመሥራቴ ደስተኛ ነኝ። መለገስ በመቻሌ የህሊና እርካታ ነው የሚሰማኝ። ቢቢሲ፡ ለምን ደም ይሰጣሉ ያለዎትስ የለም? ሲሰተር አሰጋሽ፡ ምንም የለም። እናቴ ደም ያስፈለገው ሰው ኖሮ ሰው ሁሉ ፈርቶ 'እምቢ [ደም አልሰጥም]' ሲል ትሰጥ ነበር። እሷ ግንዛቤ ሳይኖራት ከተነሳሳች እኔ ደግሞ ምንም ጉዳት እንደሌለው ስለማውቅ በጣም ቀላል ነው። ዶ/ር ሊያ ስለ ሲስተር አሰጋሽ ወዳካፈሉት ሃሳብ እንመለስ። "ሲሰተር አሰጋሽ ጎሳ ነርስም፣ እናትም ቀዳሚ ደም ለጋሽም በመሆን ዛሬ የሴቶችን ቀንን በማስመልከት 80ኛ የደም ልገሣዋን አድርጋለች። ይህ ቁጥር በሃገራችን ሴት ደም ለጋሶች በሪከርድ [በክብረ ወሰንነት] የተመዘገበ ነው። እንኳን ደስ አለሽ። እናመሰግናለን" ብለዋል በማህበራዊ ድረገጻቸው ላይ። የሚስቱን ህይወት ለማትረፍ የተጨነቀ ባል አሳዝኗቸው አንድ ብለው የጀመሩት ደም ልግሳ ዛሬ 80 ደርሷል። ይህ ቁጥር በሴት ደም ለጋሾች ታሪክ ቀዳሚ መሆኑን በመጥቀስ ዶ/ር ሊያ መልዕክታቸውን ከምስጋና ጋር በማስፈራቸው "በጣም ነው ደስ ያለኝ" ሲሉ ሲስተር አሰጋሽ ይገልጻሉ። "ከመነሻዬ እዚህ [ቁጥር ላይ] እደርሳለሁ ብዬ አላሰብኩም። ሄዶ ሄዶ እዚህ ደርሷል" ብለዋል። ከጤና ሚንስትሯ በተጨማሪም ብሔራዊ የደም ባንክም የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጅቶላቸዋል። እሳቸውም ለተሰጣቸው ዕውቅና ምስጋናዬ ይድረሳችሁም ብለዋል። ቢቢሲ፡ የወንዶችን ክብረ ወሰን ለማሻሻል አያስቡም? ሲሰተር አሰጋሽ፡ [ሳቅ] ሴቶች ከሴቶች ጋር ነው የሚወዳደሩት። እኛ ሴቶች ዘንድ መውለድ፣ ማርገዝ እና ማጥባት አለ። በምናረግዝበት፣ በምንወልድበት እና በምናጠባበት ወቅት ደም መለገስ አንችልም። አንዲት ሴት ማጥባት ካቆመች ከአንድ ዓመት በኋላ ነው ደም መለገስ የምትችለው። ስለዚህ በትንሹ ወደ 11 ወይም 12 ጊዜ መስጠት የምትችለውን ነው የምታጣው ማለት ነው። እና ወንዶች ጋር ደርሼ እበልጣለሁ የሚል ሃሳብ የለኝም። [ከወንዶች ሳያቋርጥ] በትክክል የሚሰጥ ሰው ካለ እንደዛ ብዬ አላስብም። በራሴ ግን ማድረግ የምችለውን በሙሉ አደርጋለሁኝ። የዓለም ጤና ድርጅት ማንም ሰው በደም እጦት መሞት የለበትም የሚል መርሆ አለው። ለዚህም ደግሞ ከአንድ ሃገር አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር አንድ በመቶ የሚሆነው ደም መስጠት ይኖርበታል። በዚህ ስሌት መሠረት ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ ከሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆነው በየሦስት ወሩ ደም መለገስ አለበት ማለት ነው። በኢትዮጵያ ደም የሚለግሱ ሰዎች አሃዝ ግን ግማሽ የሚሊዮን እንኳን አልደረሰም። "አንዳንዶች ከግንዛቤ እጥረት ደም ለመለገስ ፈቃደኛ አይሆኑም" ይላሉ ሲስተር አሰጋሽ በሥራቸው ወቅት የሚመለከቱትን ህብረተሰቡን ግንዛቤ ሲገልጹ። "አንዳንዶች ከግንዛቤ እጥረት ደም ለመለገስ ፈቃደኛ አይሆኑም። ደም የሚጠራቀም የሚመስላቸው፣ ደም የሚለገሰው በውፍረት የሚመስላቸው እና ሌሎችም የተሳሳቱ ግንዛቤ ያላቸው አሉ" ይላሉ። ከዚህ ይለቅ "ሰው ደም ከመቀበል ይልቅ ቢሰጥ ጥሩ ነው" ይላሉ። ደም የሚያስፈልጋቸውን "ሁሌም 'እናቴ፣ እህቴ ወይም ዘመዴ ቢሆኑስ?' ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ከአነስተኛ መርፌ መወጋት ህመም በኋላ በሚሰጥ ደም፣ የሰው ህይወት ማዳን ቀላል አይደለም" ይላሉ። ለዚህም ነው ለሲስተር አሰጋሽ ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ የማይሆነው። 'ሰውን ለመርዳት ሰው ከመሆን በተጨማሪ ቅንነት ያሰፈልጋል' ብለው ያምናሉ። እሳቸውም ቢሆን "ወደፊት ፈጣሪ ቢፈቅድ ደም እለግሳለሁ" ሲሉ በአንድ ግለሰብ ምክንያት 80 የደረሰውን ደም ልገሳ ቁጥር ማሳደግ እንደሚፈልጉ ይገልጻሉ። ቢቢሲ፡ መጀመሪያ ላይ ደም ለመለገስ ምክንያት የሆኖትን ግለሰብም ሆነ ሚስቱን አግኝተዋቸው ያውቃሉ? ሲስተር አሰጋሽ፡ አላውቅም። ከዚያ በኋላ እንዴት እንደሆኑ አላውቅም። ከዚያ በኋላ ታሪኩን አላውቀም። [ምትክ ደም ስለተሰጠ ደም መውሰድ እንደሚችል የሚገልጽ] ደብዳቤ እኛ ጻፍንለት። ጥቁር አንበሳ ደብዳቤውን ሲያገኙ ደም ከእኛ ይወስዳሉ። ብዙም የማውቀው ነገር የለም እኔ [ኃላፊነቴ] የድርሻዬን መወጣት ነው።
xlsum_amharic-train-110
https://www.bbc.com/amharic/news-48619211
የመንግሥት ድርጅቶችን 'ፕራይቬታይዝ' ጉዳይ እጅግ አከራካሪ ሆኗል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን የመጡ ሰሞን ነበር ከኤርትራ ጋር ሰላም እንደሚያሰፍኑ፤ በመንግሥት ስር ያሉ ግዙፍ የኢኮኖሚ ተቋማት ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ወደ ግል እንዲሸጋጋሩ ለማድረግ እንደሚሰሩ ይፋ አደረጉ።
[ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን የመጡ ሰሞን ነበር ከኤርትራ ጋር ሰላም እንደሚያሰፍኑ፤ በመንግሥት ስር ያሉ ግዙፍ የኢኮኖሚ ተቋማት ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ወደ ግል እንዲሸጋጋሩ ለማድረግ እንደሚሰሩ ይፋ አደረጉ።" ]
በወቅቱ ሁለቱም አበይት ጉዳዮች አነጋጋሪ ነበሩ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀዳሚ ሥራ የነበረው ግን የኤርትራ ጉዳይ ነበር። 'የፕራይቬታይዜሽኑ' ጉዳይ በይደር ተቀምጦ ቆይቷል። ጉዳዩ ለሕዝብ ጆሮ ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ አሁን እንደ አዲስ ተነስቶ መናጋገሪያ ሆኗል። ሐሙስ እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዉጭ ኩባንያዎች በቴሌኮሙኑኬሽን ዘርፍ መዋዕለ ነዋይ እንዲያፈሱ የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ አፅድቋል። ምክር ቤቱ ገለልተኛ የኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን መስሪያ ቤትን ለማቋቋም የሚያስችል አዋጅም እንዳጸደቀ የተከበሩ ዶ/ር ሙሉጌታ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ባለስልጣኑ የቴሌኮም ዋጋ ትመናን፣ የኮምኒኬሽን ፖሊሲዎችን ማስፈጸምና የኮምኒኬሽን ድርጅቶችን፣ ኢንተርኔትንና የሬዲዮ ሞገዶችን ይቆጣጠራል ሲሉም ያብራራሉ። • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ 'ፕራይቬታይዜሽን' ወይንም የመንግሥት ድርጅቶችን ለግል ይዞታነት የማዞር ጉዳይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችንና ፖለቲከኞችን በሦስት ጎራ ከፋፍሏል። አንደኛው ጎራ 'አዎ መሸጥ አለባቸው፤ እኒህ ድርጅቶች ገበያውን በሞኖፖል ይዘውት እስከመቼ?' የሚል ሃሳብ የሚያነሱ ግለሰቦች ስብስብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ 'ይህ ሃገር ከመሸጥ አይተናነስም፤ የመወዳደር አቅም ሳይኖረን እንዴት ሃብታሞች ሃገራችን እንዲገቡ እንፈቅዳለን?' ሲሉ ይሞግታሉ። ሦስተኛው 'መሸጥ ያለባቸው እና የለሌባቸው አሉ' ሲሉ የሚመክሩ ናቸው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከሁለቱ ፅንፍ ሃሳቦች መሃል ላይ ናቸው። «ይህንን ፖሊሲ የሚያስፈፅሙ ሰዎች ሁሉም ነገር ፕራይቬታይዝ ይደረጋል ብለው ማሰብ የለባቸውም። መደረግ ያለባቸው አሉ፤ መደረግ የሌለባቸው አሉ። ለምሳሌ በምንም መሥፈርት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደረግ የለበትም። በፖለቲካም በኢኮኖሚም መሥፈርት መደረግ የለበትም። ከሃገር ጥቅምም አንፃር መደረግ የሌለበት ነው" በማለት አጥብቀው ይከራከራሉ። ነገር ግን ይላሉ ፕሮፌሰር አለማየሁ «ሌሎቹን ለምሳሌ ስኳር ፋብሪካን ፕራቬታይዝ ብታደርገው፤ ብትሸጠው አዋጭ ነው። ኢትዮ-ቴሌኮም ላይ ስትመጣ ደግሞ አብዛኛውን ድርሻ እኛ ይዘነው ለምሳሌ 70 በመቶውን ከያዝነው በኋላ ሌላውን መሸጥ አዋጭ ነው። ቀሪውን ድርሻ የሚይዘው ደግሞ አፍሪካዊ ድርጅት ቢሆን ይመረጣል፤ በዚያውም የቀጠናውን ጥምረት ለማጠናከር።» • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? መሸጡ የግድ ቢሆን እንኳ 'ሬጉላቶሪ ቦዲ' [ተቆጣጣሪ አካል] ማቋቋም ሊውል ሊያድር የሚገባው ጉዳይ እንዳልሆነ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። «ለምሳሌ መንግሥት 60 በመቶ ገቢ ያገኘው ከቴሌ ነው። ሌላው 30 በመቶ ከንግድ ባንክ ነው። ስለዚህ ንግድ ባንክን፤ ቴሌን ሸጥክ ማለት ባዶ እጅህን ነው አራት ኪሎ ቁጭ የምትለው። ስለዚህ ምጣኔ ሃብታዊ ውሳኔ ለመወሰን ምንም ዓይነት 'ኢንቨስትመንት' የለህም ማለት ነው። አሁን መንግሥት ማድረግ ያለበት፤ በተለይ እንደ ቴሌ ላሉት የተወሰነውን ሽጦ ሲያበቃ የመቆጣጠር አቅሙ ሲጎለብት ለሌሎች ክፍት ማድረግ ነው።» የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የነበሩት ፖለቲከኛው ዮናታን ተስፋዬ የመንግሥትን 'ፕራቬታይዜሽን' ዕቅድ ከሚደግፉት መካከል አንዱ ናቸው። «ፕራቬታይዝ የማድረጉ አንደኛ ጥቅም 'ሞኖፖሊ' እንዳይኖር ማድረጉ ነው። ሁለተኛ የፉክክር ገበያ ይኖራል፤ ይህ ደግሞ ሕብረተሰቡ የተሻለ ምርትና አገልግሎት እንዲያገኝ ያደርጋል።» ምጣኔ ሃብታዊውን ትንታኔ ለባለሙያዎች ልትወው፤ የሚሉት አቶ ዮናታን «የመንግሥት ድርጅቶች በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መሆን አምባገነንነትን ያበረታታል» ባይ ናቸው። «'እኔ ነኝ አሳቢ፤ እኔ የተሻለ ለማሕበረሰቡ እጨነቃለሁ' የሚል ሥነ-ልቡናን እያሳደረ ነው የሚሄደው። ይህ አስተሳሰብ ደግሞ ሥር በሰደደ ቁጥር ሌሎች ተፎካካሪ ኃይሎችን እንደ ሥልጣን ተቀናቃኝ ነው የሚያየው፤ ምክንያቱም ራሱ ነጋዴው መንግሥት እየሆነ ስለሚመጣ። ስለዚህ ፖለቲካዊ ብልሽትን ይፈጥራል፤ ነፃ ገበያ እና ፉክክር የሌለበት፤ አንድ ወገን ብቻ እሴት የሚጨምርበት በጣም ደካማ የገበያ ሥርዓት እንዲኖር ነው የሚያደርገው።» • ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ስታቋርጥ በየቀኑ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች የሕዝብ ይሁንታ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች 'ዘ ቢግ ፋይቭ' ይሏቸዋል፤ አየር መንገድ፣ ቴሌኮም፣ ባንክ፣ ባቡር እና ስኳር ፋብሪካዎች። መንግሥት እነዚህን ድርጅቶች ለግል ባለሃብቶች ሲሸጥ ሕዝብን ማማከር አለበት የሚሉ ሃሳቦች በአለፍ ገደም እያሉ ይደመጣሉ። አቶ ዮናታን «ይሄ እኮ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው. . .» ይላሉ። «ይሄ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው። የኢኮኖሚ ጉዳይ ደግሞ በባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ፤ በዚያ ጥናት ላይ ተመርኩዞ፤ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ይሄ ያዋጣል ብለን የምንወስነው ነገር ነው እንጂ ልክ እንደባንዲራ ጉዳይ ወይም የክልል እንሁን ጥያቄ ሕዝበ-ውሳኔ የሚደረግበት አይደለም። በየትኛውም ዓለም ላይ ሕዝብ በእንደዚህ ዓይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ የሆነ ውሳኔ ማሳለፍ አይችልም።» መሰል የፖሊሲ ለውጦች የሕዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ባይኖራቸው እንኳ ምርጫ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም ወይ? በርካቶች የሚያነሱት ጥያቄ ነው። እርግጥ ነው አቶ ዮናታን በዚህ ጉዳይ ይስማማል። ግን እሱ አልሆነም፤ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ለሃገሪቱ ይጠቅማል የሚለውን ፖሊሲ የማፅደቅ መብት አለው ይላል። «አሁን ባለንበት ወቅት ኢኮኖሚው እየወደቀ ነው። ለዚህ ደግሞ አንድ ትልቅ ድርሻ የሚወስዱት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ናቸው። እነዚህ የልማት ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ ስላልሆኑ አሁን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ምንም ሊቋቋመው የሚችለው አይደለም። የውጭ ባለሃብቶችን መሳብ የሚቻለው ደግሞ የኢኮኖሚ ፖሊሲውን መቀየር ሲቻል ነው።» ነዋሪነቱን እንግሊዝ ያደረገው የምጣኔ ሃብት ምሁሩ እዮብ ባልቻ፤ አዲሱ የፕራቬታይዜሽን አጀንዳ በግለሰቦች የሚመራ ነው ሲል ይሞግታል። እንደ እዮብ ትንተና አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በምጣኔ ሃብት ጉዳይ የሚያማክሩ ግለሰቦች ከዓለም ባንክና እና ዓለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት ጋር በቀጥታም ሆነ ተዘዋዋሪ ቁርኝት ያላቸው ናቸው። ምንም እንኳ የእዮብ ትንታኔ ግለሰቦቹ ላሳኩት ግብ ምስጋና ቢሰጥም በፕራቬታይዜሽን ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም አያስተማምንም ይላል። ፕሮፌሰር አለማየሁም ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሥር ጫና እንዳሉና ያንን ጫና ለመቋቋም የሚያስችል የምጣኔ ሃብት አቅም የላቸውም ባይ ናቸው። ትክክለኛው ጊዜ ላይ እንሆን? ለፕሮፌሰሩ የመንግሥት ድርጅቶችን ለገበያ የማቅረብ ጊዜው አሁን አይደለም። ትርፉ ከመንግሥት ሞኖፖሊ ወደ ግለሰብ ሞኖፖሊ መሸጋገር ነው ይላሉ። • ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት «ለምሳሌ ቴሌን በ5 ወይም 10 ቢሊዮን ዶላር ሸጥነው እንበል። ነገ ያ ድርጅት የሚያተርፈውን አትርፎ የቀረውን ይዞ ሹልክ ይላል። በኢትዮጵያ ሕግ ደግሞ ያተረፍከውን ገንዘብ 'እክስፓትረየት' [ይዘህ መውጣት] ማድረግ ትችላለህ፤ የፈለግከውን። መሰል ስትራቴጂክ ነገሮችን ስታስብ መንግሥት ለፕራቬታይዜሽን መጣደፍ የለበትም። መንግሥትም ስለጨነቀውና ዶላር ስላጠረው እንጂ ፈልጎት አይመስለኝም» ይላሉ። ታድያ ትክክለኛው ጊዜ መቼ ነው? ለአቶ ዮናታን ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው። መከራከሪያው ደግሞ ኢኮኖሚያችን እየደቀቀ ነው የሚል። ፕሮፌሰር አለማየሁ ደግሞ ጉዳዩን በሁለት ከፍለው ያዩታል። «አንደኛው ፖለቲካዊ ነው፤ ማለት አንድ መንግሥት ይህንን ፖሊሲ አስተዋውቆ የሕዝቡን ይሁንታ ካገኘ ሊያስፈፅመው ይችላል። ምክንያቱም እነዚህ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ የሚቆጣጠሩ ተቋማት ናቸው» ይላሉ። • የስኳር ፋብሪካዎችን ለግል ባለሃብቶች የመስጠት ፋይዳና ፈተናዎቹ ስለዚህ ትክክለኛው ጊዜ መንግሥት የሕዝቡን ፖለቲካዊ ውክልና ባገኘበት ጊዜ መሆን እንዳለበት የሚጠቅሱት ፕሮፌሰር አለማየሁ «በኢኮኖሚ መነፅር ስናየው ግን አሁን ባለው ሁኔታ በእኔ ግምት ትክክል አይደለም። ምክንያቱም መንግሥትም አልተረጋጋም፤ ሃገሩም አልተረጋጋም። ግን ደግሞ መንግሥት ብር የለውም። ከጀርባቸው ጠንካራ ኃይሎች ካልሸጣችሁ እይሏቸው ይሆናል። ስለዚህ ያለው አማራጭ ቅድም ያነሳሁት ሃሳብ ነው። የተወሰነውን ፕራይቬታይዝ ማድረግ።»
xlsum_amharic-train-111
https://www.bbc.com/amharic/49619046
የኢትዮጵያ ሙዚቃ- ከመስከረም እስከ መስከረም
ይህ ዓመት ቴዲ አፍሮ አድናቂዎቹን በሚሌኒየም አዳራሽ ሰብስቦ የተሳካ ሥራውን ያቀረበበት እንደሆነ ባለሙያዎች መስክረዋል።ሮፍናን በመዲናዋ ሸገርና በሌሎች የአገሪቱ ከተሞችም ምስጋና የተቸረው ኮንሰርት ያቀረበበት እንደነበርም ተነግሯል።
[ "ይህ ዓመት ቴዲ አፍሮ አድናቂዎቹን በሚሌኒየም አዳራሽ ሰብስቦ የተሳካ ሥራውን ያቀረበበት እንደሆነ ባለሙያዎች መስክረዋል።ሮፍናን በመዲናዋ ሸገርና በሌሎች የአገሪቱ ከተሞችም ምስጋና የተቸረው ኮንሰርት ያቀረበበት እንደነበርም ተነግሯል።" ]
ለዓመታት የተጠበቁት የአስቴር አወቀ እና የጎሳዬ ተስፋዬ የሙዚቃ ሰንዱቆችም አድማጭ ጆሮ የደረሱት ልንሰናበተው ሽራፊ ዕድሜ በቀረው 2011 ዓ. ም. ነው። የዓመቱን የኢትዮጵያ ሙዚቃ አክራሞት በወፍ በረር ምልከታ ቃኝተነዋል። ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት ኢትዮጵያ፤ የሙዚቀኞች ቁጥር እጅግ ውስን ነው። በየዓመቱ የሚቀርቡ የሙዚቃ ድግሶችም በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ይህ ደግሞ ካለው የሙዚቃ ሀብት አንፃር አነስተኛ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በዚህ ዓመት (2011 ዓ. ም.) የቀረቡት ሥራዎች በአገሪቱ ከሚነገሩ ቋንቋዎች መካከል በተወሰኑት ብቻ የተዘጋጁ ናቸው። ይህም ሙያተኞች በተለያዩ ቋንቋዎች ሥራቸውን እንዲያቀርቡ የቤት ሥራ የሚሰጥ ነው። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች • በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ነሺዳም ሆነ መዝሙር፣ ብሎም ዘፈን በተለያዩ ቋንቋዎች ቢቀርቡ ሰሚ ጆሮ፣ አመስጋኝ ልብ፣ ተዝናኝ መንፈስ አያጡም። ሥራዎቹ ኖረው 'የጆሮ ያለህ!' ቢሉ እንኳን በአግባቡ ሰንዶ የሚያስቀምጣቸው ባለሙያ እጥረት መኖሩ ቁጥራቸው በልው እንዳይታወቅ አድርጓል። የ 'ለዛ' የሬዲዮ መሰናዶ አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ብርሃኑ ድጋፌ፤ በአገሪቱ መንፈሳዊ ዜማዎች በአግባቡ ስላልተሰነዱ በዚህ ዓመት የወጡ ሥራዎች እነዚህ ናቸው ብሎ ለመናገር እንደሚያስቸግር ይገልፃል። "እኛም እነዚህን ሥራዎች ለማግኘት፣ ስለመውጣታቸው እንኳን ለማወቅ ተቸግረናል" በማለት ነሺዳም ሆነ መዝሙር ሲወጣ ለሬዲዮ ጣቢያዎች የሚሰጥ ባለሙያ ገጥሞት እንደማያውቅ ይናገራል። ምንም እንኳን መረጃ የመሰብሰብ ክፍተት ቢኖርም፤ በ2011 ዓ. ም. ከ17 በላይ የሙዚቃ አልበሞች ለገበያ እንደቀረቡ ብርሀኑ ተናግሯል። ይህ መረጃ ታዲያ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ታትመው ለአድማጭ ጆሮ የደረሡ የሙዚቃ ሠንዱቆችን ታሳቢ ያደረገ አይደለም። የነገረን የሙዚቃ ሰንዱቆች በአማርኛ የተቀነቀኑ፣ በትግርኛ የተዘፈኑና በኦሮምኛ የተሞዘቁ ናቸው። እነዚህም ስም ካላቸው ከእነ አስቴር አወቀና ከጎሳዬ ተስፋዬ ጀምሮ እስከ አዳዲስ ጆሮ ፈላጊዎች ያካትታሉ። በዚህ ዓመት በሙሉ አልበም የአድማጭ ጆሮን ካንኳኩ ድምፃውያን መካከል አስቴር አወቀ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ ልዑል ኃይሉ፣ ዮሐና፣ ሳሚ ዳን፣ ጃኪ ጎሲ፣ ዳግ ዳንኤል፣ ቼሊና፣ አቤል ሙሉጌታ፣ ዳዊት ነጋ፣ ኃይለየሱስ ፈይሳ፣ ጃሉድ፣ በኃይሉ ታፈሰ (ዚጊ ዛጋ)፣ ዳዊት ሰንበታ፣ ዘሩባቤል ሞላ እና አቡሽ ዘለቀ ይገኙበታል። ዘንድሮ ገበያ ላይ ከዋሉ የሙዚቃ አልበሞች ሁለቱ እንደው በዚህ ዓመት ከወጡት የሙዚቃ ሥራዎች የትኛው የአድማጭ ቀልብ ገዛ? የቱስ ጥሩ ገበያ አገኘ? ብለን ብርሀኑን ስንጠይቀው፤ መለኪያችን ምንድን ነው? በማለት ጥያቄያችንን በጥያቄ መልሷል። 'የእከሌ ሥራ በዚህ ሳምንት አንደኛ ነው፤ የእከሌ ደግሞ ይከተላል' ብሎ የሚመድብ ተቋም በሌለበት፤ ተወዳጅነትን ለመመዘን እንደሚከብድ ይናገራል። "ተደማጭነት በተለያዩ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በመጫወት ነው ብለን የምንወስድ ከሆነ፤ ዘሩባቤል ሞላና አስቴር አወቀ አየሩን ተቆጣጥረውት ይታያሉ" ሲል ይገልጻል። የትኛው የሙዚቃ ሰንዱቅ በሚገባ ተደመጠ? ብሎ ለመተንተን ጥናት ያስፈልጋል የሚለው ብርሃኑ፤ ዘንድሮ እንደ ከዚህ በፊቱ የሙዚቃ አድማጩ በአንድ አልበም ላይ ብቻ አለማተኮሩን ያስረዳል። እንደ አስቴር አወቀ ያሉ አንጋፋ ድምፃዊያንን ሥራዎች በርካቶች ተስማምተውበት የሚያደምጡ ሲሆን፤ የወጣቱን ቀልብ የሚገዙ፣ በተለያየ ዘውግ የተዘጋጁ የቸሊናን፣ የዘሩባቤልን እና የሳሚ ዳንን የመሰሉ አልበሞችም ወጥተዋል። የ 'አውታር' መምጣት የአውታር መልቲ ሚዲያ አርማ በብርሃኑ አስተያየት፤ በዚህ ዓመት ለኢትዮጵያ ሙዚቃ የተጨመረው አዲስ ነገር በኢንተርኔት ሙዚቃ መገበያየት የሚያስችለው አውታር መተግበሪያ ሥራ መጀመሩ ነው። ዓለማችን የዲጂታል ዘመን ላይ በመሆኗ፤ ሙዚቃ ሻጭም ሆነ አከፋፋይ ሳያስፈልግ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ አልበሞችን ለአድማጮች ማድረስ ይቻላል። የኢትዮጵያ ሙዚቃም በአውታር በኩል አንገቱን ወደዚህ የዲጂታል ዓለም ማስገባቱን ይመሰክራል። አውታር ከአሳታሚ፣ ከአከፋፋይና ከሻጮች ጋር ያለውን ውጣ ውረድ የሚያቀል፣ የሽያጭ ሥርዓቱን በግልፅ የሚያሳይ መተግበሪያ ከመሆኑም በላይ በባለቤትነት የተያዘው በሙዚቀኞች በመሆኑ፤ ለሙዚቀኛው የደራ ገበያ እንደሚፈጥርም ያስረዳል። • አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን "አውታር በአገር ውስጥ ሆነው የኢንተርኔት አቅርቦት ላላቸው ጥሩ የመገበያያ አማራጭ ነው" የሚለው ብርሃኑ፤ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ትልቅ ችግር ለነበረው የኮፒራይት መብት ጥሰትና የባለቤትነት ጥያቄ መፍትሔ ይሰጣል ይላል። አውታር የቀደምት ሥራዎችም ሆነ የአዳዲስ ሥራዎች መረጃ በሚገባ ተካቶበት፣ ሙያተኛውም ገቢ የሚያገኝበት እንደሆነ ያብራራል። 'ለዛ' የተሰኘውን የሙዚቃ ሽልማት ከዘጠኝ ዓመት በፊት የጀመረው ብርሀኑ፤ ያኔ ሽልማቱ ሲጀመር የሙዚቃ ኢንደስትሪው የተቀዛቀዘ እንደነበር ያስታውሳል። ካለው የኮፒራይት መብት ጥሰትና የገቢ ማነስ አንፃር እንዲህ ዓይነት የማበረታቻ ሽልማቶች ቢበራከቱ፤ ሙያተኛው ይነቃቃል በማለት ሽልማቱ እንደተጀመረ ይናገራል። በዚህ ዓመት የወጡትን ሥራዎች አወዳድረው የሚሸልሙት የሚቀጥለው ዓመት በጥቅምት ወር በስድስተኛው ቀን ሲሆን፤ ሽልማቱ ከሐምሌ 2010 ዓ. ም. እስከ ግንቦት 30፣ 2011 ዓ. ም. ድረስ የወጡትን ያካትታል። የዩቲዩብ ዓለም- ከሆፕ ኢንተርቴይመንትና ከምነው ሸዋ ዩቲዩብ ላይ የሚጫኑ ሙዚቃዎች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የኢትዮጵያ ሙዚቃ አድናቂዎችን በመድረስ ረገድ ፈጣን መሆናቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ። አንድ ሙዚቃ በዩቲዩብ ሲጫን፤ ዩቲዩብ ለጫነው አካል ክፍያ ይፈፅማል። ይህን የሚያደርገው የዩቲዩብ ቻናል በእነዚህ ገጾች ላይ ማስታወቂያ ለመልቀቅ ስለሚፈልግ ሲሆን፤ ለዚህም በማለት የሥራው አጋር ያደርጋቸዋል። ዩቲዩብ እነዚህን ቻናሎች አጋር ሲያደርግ ያላቸውን ተከታይ (ሰብስክራይበር) እንደሚመለከት በሥራው ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። በየትኛውም የዓለም ክፍል ያሉ የሙዚቃ አፍቃርያን ወደ ቻናሎቹ መጥተው ሙዚቃ ባደመጡና ባዩ ቁጥር ዩቲዮብ ማስታወቂያ የሚለቅ ሲሆን፤ ለድርጅቶቹ ደግሞ በስምምነታቸው መሰረት ክፍያ ይፈፅማል። በኢትዮጵያ ስማቸው ገኖ ከሚሰማና የተለያዩ አዳዲስ የሙዚቃ ሥራዎች በየጊዜው ከሚጫንባቸው ቻናሎች መካከል ሆፕ ኢንተርቴይመንት፣ አድማስ እና ምነው ሸዋ ይገኙበታል። የምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት አርማ ብርሃኑ እንደሚለው፤ በዩቲዩብ ከተለቀቁና በርካታ አድማጮች ካገኙ ነጠላ ዜማዎች መካከል የትግርኛ ሙዚቃዎችን የሚያክል የለም። የሆፕ ኢንተርቴይመንት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዮሴፍ ኃይሉ በበኩላቸው በዩቲዩብ ቻናላቸው በዚህ ዓመት ከተጫኑ የሙዚቃ ቪዲዮዎች መካከል ከፍተኛ ተመልካች ያገኘው ጆሲ (ዮሴፍ ገብሬ) እና ኤርትራዊቷ ድምጻዊት ሚለን ኃይሉ በጋራ ያቀነቀኑት ሙዚቃ መሆኑን ይናገራሉ። ይህ የሙዚቃ ቪዲዮ ከ7 ሚሊየን በላይ ተመልካች እንዳለው ያስታወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ የጌትሽ ማሞ 'ተቀበል'፣ የሰላማዊት ዮሐንስ 'ሰናይ' እና የወንዲ ማክ 'አባ ዳማ' የተሰኙት ሥራዎች በቅድመ ተከተል መቀመጣቸውን ይጠቅሳሉ። ሆፕ ኢንተርቴይመንት በዚህ ዓመት ብቻ ከ600 በላይ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን በቻናሉ ላይ መጫኑን የተናገሩት አቶ ዮሴፍ፤ ሥራዎቹ በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎ፣ የታዋቂና ጀማሪም ድምፃውያን መሆናቸውን ተናግረዋል። በቻናላቸው ላይ በእይታ ብዛት ቀዳሚ የሆነው የእነ ጆሲ ሙዚቃ በአንድ ቀን ስድስት መቶ ሺህ ተመልካች ያገኘ መሆኑንም አክለው ተናግረዋል። "ከፍተኛ እይታ ያላቸው በየትኛውም ወቅት ከፍተኛ ተከፋይ ናቸው" የሚሉት አቶ ዮሴፍ፤ ሙዚቃዎ በእነርሱ ስም ዩቲዩብ ቻናላቸው ላይ ከተጫኑ ባለ ሙሉ መብት ስለሆኑ የመብት ጉዳዮችንም ለማስከበር ድርጅታቸው ሙሉ ኃላፊነቱን ወስዶ እንደሚሠራ ተናግረዋል። • ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ • ''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" የምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ኮንቴንት ማናጀር የሆኑት አቶ ነብዩ ይርጋ፤ በቀን ሁለት ሙዚቃ በቻናላቸው ላይ እንደሚጭኑ ይናገራሉ። በቻናላቸው በዚህ ዓመት በብዛት የታየው የድምጻዊት ራሄል ጌቱ 'ጥሎብኝ' የተሰኘው ሙዚቃ መሆኑን በመጥቀስ እስከ 9 ሚሊየን ድረስ እንደታየ ይናገራሉ። ከራሔል ጌቱ ሥራ በተጨማሪ፤ የአሕመድ ተሾመ (2.9 ሚሊየን)፣ የጃምቦ ጆቴ (2.4 ሚሊየን)፣ የአብነት አጎናፍር (1.8 ሚሊየን)፣ የሚካኤል መላኩ (1.8 ሚሊየን)፣ የቤቲ ጂ (1.5 ሚሊየን) ተመልካች ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል። በዚህ ዓመት በምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ከ628 ሙዚቃዎች በላይ መጫናቸውን የተናገሩት አቶ ነብዩ፤ ለክፍያ ሦስት ዓይነት መስፈርት እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል። እነዚህም የሙዚቃ ሥራውን ሙሉ በሙሉ መግዛት፣ ቅድመ ክፍያ ከፍሎ መግዛት ወይንም ዩቲዩብ ቻናሉ ላይ ከተጫነ በኋላ የሚገኘውን ክፍያ ሀምሳ ሀምሳ መካፈል መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ ዓይነቱን የክፍያ ሥርዓትን ሆፕ ኢንተርቴይመንትም የሚጠቀም ሲሆን፤ ቅድመ ክፍያ የተከፈላቸው ሥራዎች፤ የቅድመ ክፍያ ገንዘቡ ከዩቲዩብ ከሚገኘው ክፍያ ከተካካሰ በኋላ ቀሪው ከዩቲዩብ ገቢው ሀምሳ ሀምሳ የሚካፈል መሆኑን አቶ ነብዩ ጨምረው አስረድተዋል። የሆፕ ኢንተርቴይመንት የዩቲዩብ ገጽ ከምነው ሸዋ ጋር ውለታ የገቡ ድምፃውያን ውለታቸው ለሁለት ዓመት እንደሚቆይ የሚናገሩት አቶ ነብዩ፤ ሙሉ በሙሉ ግዢ ካልፈፀሙ የቅድመ ክፍያ ወይንም በታየ ቁጥር እንዲከፈል ለተስማሙ ድምፃውያን በየስድስት ወሩ ከዩቲዩብ ያገኙትን ክፍያ እንደሚያካፍሉ አክለዋል። የዚህ ዓመት የሙዚቃ ድግሶች ምን መልክ ነበራቸው? "አንድ ሙዚቀኛ አልበሙን ለገበያ ካቀረበ በኋላ ተስፋ ያደርግ የነበረው" ይላል የለዛ መሰናዶ አዘጋጁ ብርሃኑ፤ "ተስፋ ያደርግ የነበረው የሰንዱቁ ሽያጭ ገቢን አይደለም።" የአልበም ሽያጭ በቂ አይደለም የሚለው ብርሃኑ፤ የሙዚቃ ድግሶች ከአድማጭ ጋር ለመገናኘትም ሆነ ገቢ ለማግኘት ሁነኛ መላ ተደርገው ይወሰዳሉ ይላል። ነገር ግን ባለፉት ሦስት ዓመታት በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የፀጥታው ሁኔታ አስተማማኝ ስላልነበር ተዘዋውሮ ኮንሰርቶች ለማቅረብ አዳጋች ሆኗል ይላል። ይህንን ዓመት ጨምሮ በአዲስ አበባም በጣት የሚቆጠሩ ኮንሰርቶች ብቻ መዘጋጀታቸውን ይናገራል። በዚህ ዓመት ከገጠመው ፈተና አንዱ የቢራ አምራቾች የሙዚቃ አልበሞችን ስፖንሰር ለማድረግ አለመቻላቸው መሆኑን የሚያስታውሰው ብርሃኑ፤ የሙዚቃ ባለሙያው ሥራዎቹ በአድማጮችና በአድናቂዎች ቢሰማለትም ጥሩ ገቢ ስለማያገኝበት የሙዚቃ ድግሶችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በማዘጋጀት ገቢውን ለማካካስ ያስብ ነበር ይላል። "የሙዚቃ ድግሶች ላይ በጣም በጣም መቀዛቀዝ አለ" ሲል ሁኔታውን የሚገልፀው ብርሃኑ፤ በዚህ ዓመት ክፍለ ሀገር የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ ሥራዎቹን ያቀረበ ሙዚቀኛ ሮፍናን ብቻ መሆኑን ይናገራል። ሮፍናን ባህርዳር፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ አዳማና አዲስ አበባ ኮንሰርት ማቅረቡን በመግለፅም፤ አዲስ አበባ ውስጥ ከቴዲ አፍሮና የጎሳዬ ተስፋዬ ኮንሰርት እንዲሁም በዓላትን በማስታከክ ከሚቀርቡ አውደ ርዕዮች ውጪ ሌሎች ትልልቅ የሙዚቃ ድግሶች እንዳልነበሩ ያስረዳል። የኤ ፕላስ ኤቨንትና ፕሮሞሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ጌታቸው፤ የሙዚቃ ድግሶችን በማዘጋጀት ከ9 ዓመት በላይ ሠርተዋል። ከ15 በላይ ትልልቅ የሙዚቃ ድግሶች ላይ ተሳትፈዋል። በዚህ ዓመት መግቢያ ላይ የተካሄደው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ላይ ከ20ሺህ በላይ ትኬት መሸጡን የተናገሩት አቶ ኤርሚያስ፤ የሮፍናንና የጎሳዬ ኮንሰርቶች የተካሄዱት ጊዮን በመሆኑ እስከ አስር ሺህ ሰዎች ታድመዋል ሲሉ ቦታው የሚይዘውን የሰው ብዛት ከግምት በማስገባት ያስረዳሉ። • የኤርትራ ዘፈኖች በኢትዮጵያዊ አቀናባሪ • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" የጆርካ ኤቨንትስ ኤንድ ፕሮሞሽንስ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አጋ አባተ፤ ከ2007 ጀምሮ በርካታ ኮንሰርቶችን በመሥራት ስማቸውን የተከሉ ናቸው። ፌስቲቫሎችን፣ የስፖርታዊ ዝግጅቶችንና የአልበም ምርቃቶችን ጨምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት ከ20 በላይ ኮንሰርቶችን ያዘጋጀው ጆርካ ኤቨንትስ ኢትዮጵያዊ ኮንሰርት፣ አዲስ ኮንሰርት ፣ ሄሎ መቀሌና ጊዜ ኮንሰርትንም አዘጋጅቷል። አቶ አጋ የድምፃውያንና ሌሎች የሙዚቃ ባለሙያዎች ክፍያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መምጣቱን በማስረዳት፤ በዚህ ዓመት ከሥራው ላለመውጣት ብቻ ከሙዚቃ ድግሶች ይልቅ ባዛር ላይ ማተኮራቸውን ይናገራሉ። ባዛሮቹ ከ15 እስከ 20 ቀን የሚቆዩ መሆናቸውን በመጥቀስም እስካሁን ድረስ ሦስት ባዛሮች ላይ መሳተፋቸውን ገልጸዋል። "ለአንድ ድምፃዊ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሚከፈልበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው" የሚሉት የጆርካ ኤቨንትስ ሥራ አስኪያጅ ለመድረክ እስከ 300 ሺህ ብር እንደሚከፈል፣ ለማስታወቂያም ከፍተኛ ወጪ እንደሚያወጡ ይናገራሉ። የኮንሰርት መግቢያ ዋጋ ዛሬም ድረስ ባለበት እንዳለ በማስረዳት፤ ከአምስት ዓመት በፊት አንድ ዶላር 18 ብር እያለ በ300 ብር ይገባ የነበረ የሙዚቃ ድግስ ዛሬም በዛው ዋጋ እንደሚታይ በመጥቀስ የኮንሰርት ሥራ ፈተናን ያሳያሉ። "በርካታ ሥራዎች ሠርተናል ነገር ግን ከትርፉ ኪሳራው ያመዝናል" የሚሉት የጆርካ ኤቨንትስ ሥራ አስኪያጅ አቶ አጋ፤ በዚያ ምክንያት ከኮንሰርቶች ይልቅ ወደ ባዛሮችና ፌስቲቫሎች ላይ ማተኮራቸውን ተናግረዋል። አቶ አጋ አክለውም በዚህ ዓመት የሙዚቃ ሥራዎች ዋነኛ አጋር የነበሩት የቢራ አምራቾች የሙዚቃ ድግሶችን መደገፍ ላይ በመቀዛቀዛቸው ሥራው አብሮ መፋዘዙን ይጠቅሳሉ። ከቢራ አምራቾች ውጪ የድርጅቱን ስምና ምርት ለማስተዋወቅ ደፍሮ ወደ ኮንሰርት አዘጋጆች የሚመጣ እንደሌለ የሚናገሩት አቶ አጋ፤ እነርሱም ሲሄዱ ተቀባይነት እንደማያገኙ ያስረዳሉ። በዚህ ዓመት ከአገሪቱ ጠቅላላ ሁኔታ አንፃር የተቀዛቀዘ ቢሆንም የተወሰኑ የሙዚቃ ድግሶች መደረጋቸውን ይናገራሉ። የኤ ፕላሱ አቶ ኤርሚያስ፤ የቢራ ፋብሪካዎች ማስታወቂያቸውን በቴሌቪዥንና በሬዲዮ የሚያቀርቡበት ሰዓት ላይ ገደብ ቢደረግም የሙዚቃ ድግሶችን ከመደገፍ ወደኋላ ያሉ አይመስለኝም ይላሉ። ከዚያ ይልቅ በተደጋጋሚ የነበሩ መሰረዞች በዚህ ዓመት የሙዚቃ ድግሶች ለመቀዛቀዛቸው አንዱ ሰበብ ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ። የአዳዲስ አልበሞች አለመውጣት ለመቀዛቀዙ ሌላ ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። አንድ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ከሚያስፈልገው የሥራ ፈቃድ ባሻገር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጸጥታና ደህንነት ሲባል መገኘት ያለበትን ፈቃድ ለማስጨረስ ያለው ውጣ ውረድ ራሱን የቻለ ራስ ምታት እንደሆነ የሚናገሩት የጆርካ ኤቨንትስ ሥራ አስኪያጅ፤ በዚህም የተነሳ በርካታ ሥራዎች ይሰረዛሉ ይላሉ። የከተማ አስተዳደሩ ለኮንሰርቶች ፈቃድ የሚሰጠው የሙዚቃ ድግሶች መተዋወቅ ከጀመሩ በኋላ ነው የሚሉት ኃላፊው፤ ቀኑ እየተቃረበ ሲመጣ የሚኖረው የፀጥታና የደህንነት ጉዳይ ተገምግሞ ስጋት ይኖራል ከተባለ እንደማይፈቀድ ያብራራሉ። ይህ ደግሞ ለተለያዩ ዝግጅቶች ቀድመው የወጡ ወጪዎች ላይ ኪሳራ እንደሚያስከትል አፅንኦት ይሰጡታል። ኮንሰርቶች ሲሰረዙ ለማስታወቂያ የወጡ ከፍተኛ ወጪዎች መና እንደሚቀሩ የሚያስረዱት አቶ ኤርሚያስ፤ ከተሰረዘ በኋላ ራሱ መሰረዙን ለታዳሚያን ለመንገር ወጪ እንደሚወጣም ያብራራሉ። የኮንሰርት አዘጋጆች በተደጋጋሚ ስለተሰረዘባቸው ዘንድሮ እጃቸውን ሰብሰብ እንዳደረጉ በማስረዳት፤ የቢራ አምራቾችም እንደ ከዚህ ቀደሙ የሚሰጡትን ገንዘብ እንደቀነሱ ይናገራሉ። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ደጋፊ አካላት በመገናኛ ብዙኀን ስማቸው አለመጠራቱና ቢልቦርዶች እንደ ከዚህ ቀደሙ አለመሰቀላቸው ነው። የሙዚቃ እቃዎች ኪራይ፣ የቦታ ኪራይ እና የባለሙያዎች ዋጋ ውድ መሆን ከእነዚህ ጉዳዮች ጋር ሲደራረብ ኮንሰርቶች በመግቢያ ትኬት ሽያጭ ብቻ አትራፊ እንዳልሆኑ ያስረዳሉ። የኤ ፕላሱ አቶ ኤርሚያስ 2012 ዓ. ም. ተስፋ ይዞ ይመጣል ይላሉ። ሮፍናን ሌሎች ድምፃውያን ያልደፈሩትን የክፍለ አገር የሙዚቃ ድግስ ጉዞ ውጤታማ ሆኖ ማጠናቀቁ እንዲሁም አዳዲስ አልበሞች መውጣታቸው ዋና ዋና ከተሞች ላይ የሙዚቃ ድግስ ለማዘጋጀት ተስፋ እንደሚሰጡ ይጠቅሳሉ። በአዲስ አበባም ቢሆን የተለያዩ ድምፃውያን አድናቂዎች በጉጉት የሚጠብቋቸው ኮንሰርቶች ሊዘጋጁ እንደሚችሉ ያላቸውን ተስፋ ይናገራሉ። በዚህ ዓመት ከፍተኛ የአማራ ክልል ባለስልጣናት እና ወታደራዊ ሹማምንት ላይ በተፈፀመ ግድያ ምክንያት ታንዛኒያዊው ዳይመንድ ይገኝበታል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት የሙዚቃ ድግስ ወደሌላ ጊዜ ተዛውሯል ሲሉ ሳይካሄድ ስለቀረው ኮንሰርት አቶ አጋም ሆኑ አቶ ኤርሚያስ ያስረዳሉ።
xlsum_amharic-train-112
https://www.bbc.com/amharic/news-54145137
3.7 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የብር ኖቶች ምን ይዘዋል?
የወረቀት የብር ኖቶች በኢትዮጵያ የግብይት ሥርዓት ውስጥ ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩ በኋላ አገሪቱ ለ7ኛ ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ማድረጓን መስከረም 04/2013 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል።
[ "የወረቀት የብር ኖቶች በኢትዮጵያ የግብይት ሥርዓት ውስጥ ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩ በኋላ አገሪቱ ለ7ኛ ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ማድረጓን መስከረም 04/2013 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል።" ]
በብዙዎች ዘንድ የባንክ ኖቶች ለውጥ ሊኖር ይችላል የሚለው ግምት መነገር ከጀመረ ጥቂት ዓመታት ተቆጥረዋል። አሁን ግን አዲሱ ዓመት በገባ በአራተኛው ቀን ምንም ነገር ሳይሰማ ይፋ የተደረገው የብር ለውጥ አገሪቱ እያካሄደችው ካለው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብር በዘመናት ሂደት ውስጥ በርካታ ለውጦችን ያስተናገደ ሲሆን፤ ከዋጋ አንጻርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና የሐሰተኛ የብር ኖት በገበያው ውስጥ በተደጋጋሚ መከሰታቸው በተለያዩ ጊዜያት ሲዘገብ ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የብር ለውጡ ለሕገ ወጥ ተግባራት የሚውለውን ገንዘብ ለማስቀረት፣ ሙስናንና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር ይረዳል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በአገሪቱ ያጋጠመውን የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባትን ለማስተካከል ባለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ ጥረቶች በመደረጋቸው ምጣኔ ሀብቱ ከነበረበት ችግር በመውጣት በማንሰራራት ላይ መሆኑን አመልክተዋል። ጨምረውም በአገሪቱ ያለውን የዋጋ ንረት የመቆጣጠሩ ተግባር በሚፈለገው መጠን ማከናወን እንዳልተቻለ ጠቅሰው፤ ለዚህ ደግሞ ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መኖሩ ደግሞ ችግሩን በማባባሱ የብር ኖት መቀየር አንድ መፍትሄ መሆኑን ተናግረዋል። ምን ተለወጠ? አዲሶቹ የብር ኖቶች ቀደም ሲል ከነበሩት በተሻለ ለአጠቃቀም ምቹና ረዥም ጊዜ እንዲያገለግሉ ተደርገው መሰራታቸ የተገለጸ ሲሆን፤ ኖቶቹን በመቀየሩ ሥራ ለህትመት ብቻ በአጠቃላይ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገ ተነግሯል። ከቀለም አንጻር አዲሱ ባለ 200 ብር ኖት ሐምራዊ፣ ባለ100 ብር ኖት ውሃ ሰማያዊ፣ ባለ50 ብር ኖት ቀይ ብርቱካናማ፣ ባለ10 ብር ኖት ደግሞ አረንጓዴ ቀለም አላቸው። ቀደም ሲል በዝውውር ውስጥ የቆየው የባለ5 ብር ኖት ለውጥ ሳይደረግበት በሥራ ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ ነገር ግን የወረቀት ገንዘቡ ቀስ በቀስ በሳንቲም እንደሚተካ ተገልጿል። በአዳዲሶቹ የብር ኖቶች ላይ ቀደም ሲል በነበሩት ላይ ያልነበሩ የአገሪቱን ገጽታ የሚያሳዩ ምስሎች የተካተቱበት ሲሆን፤ በዚህም በባለ አስር ብር ኖት ላይ ግመል፣ በባለ መቶ ብር ኖት ላይ ደግሞ የሶፍ ኡመር ዋሻና የሐረር ግንብ እንዲካተቱባቸው ተደርጓል። ከባንክ ውጪ ያለ ብር የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ እንዳመለከቱት "ከኢትዮጵያ ውጪ በጎረቤት አገራት ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያ ብር ተከማችቶ ይገኛል።" ከብር ለውጡ ጋር ተያይዞም በውጪ አገራት ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብር ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ብሔራዊ ባንክ ያወጣው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ በቤት ውስጥ ማስቀመጥ የሚከለክለው ሕግም ተግባራዊ መሆኑ የሚቀጥል ሲሆን፤ ይህንን ደንብ በመተላለፍ የሚንቀሳቀስ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ውሎ ለመንግሥት አገልግሎት ይውላል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በየጊዜው ድንገተኛ ፍተሻ እንደሚኖርም ተገልጿል። የብር ለውጥ ሂደት ላለፉት 23 ዓመታት በዝውውር ላይ የነበሩትን የብር ኖቶች ከገበያ በማስወጣት በአዲሶቹ የመተካቱ ሂደት በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወን የጊዜ ሰሌዳ ተቀምጧል። ነገር ግን አሮጌዎቹን የብር ኖቶች በአዲስ በመተካቱ ሂደት ውስጥ 100 ሺህ እና ከዚያ በላይ ብር ያላቸው ሰዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መቀየር እንዳለባቸው ተገልጿል። በዚህ ሂደት ውስጥ እስከ 10 ሺህ ብር ድረስ ለሚደረግ የብር ለውጥ ቀጥታ ገንዘቡን በመስጠት የሚከናወን ሲሆን፤ ከአስር ሺህ ብር በላይ የሚቀየር ከሆነ ደግሞ ብሩን ለመለወጥ ባመጣው ግለሰብ ስም የባንክ ደብተር ተከፍቶ እንዲቀመጥ ይደረጋል ተብሏል። የደኅንነት ገጽታዎች ይፋ የተደረጉት አዳዲሶቹ የብር ኖቶች አስመስለው የሚሰሩ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ለመከላከልና ለመለየት በሚያስችል ሁኔታ የተለያዩ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታዎች እንዲኖሯቸው ተደርጓል። በተጨማሪም ለዓይነ ስውራን አጠቃቀም እንዲያመች የመለያ ምልክት ያለው ሲሆን፤ በዚህም ዓይነ ስውራን የብሩን ዋጋ በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት ምልክትና የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታ አላቸው። ከዚህ ባሻገርም የብር ኖቱ ወደ ላይ ወይም ወደታች በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታ ያለው ሲሆን፤ የብር ኖቶቱ በእጅ ሲዳሰሱ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የብሩ ዋጋ ይታያል። አዲሶቹ ኖቶች ተጨማሪ ባለቀለም ኮከብ የደኅንነት ገጽታን ከማካተታቸው ባሻገር አብረቅራቂ የደኅንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስያሜ በምህጻረ ቃላት በአማርኛና በእንግሊዝኛ እንዲሁም የብሩ መጠን ሰፍሮ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ አዲሶቹ የብር ኖቶችን ወደ ብርሃን አቅጣጫ በማዞር ሲታዩ ከፊት ከሚታየው ምስል ትይዩ ተመሳሳይ ደብዛዛ መልክ የያዘ ምልክት ይታያል። እንዲሁም የብር ኖቶቹ በብርሃን አቅጣጫ ሲታዮ ኳስ የሚመስሉ ምልክቶች ከኖቶቹ በስተጀርባ ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ። የብር ለውጥ ታሪክ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት የብር ኖቶች ወደ ዝውውር እንዲገቡ የተደረጉት ከ23 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ እንደነበረ ይታወሳል። ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራ ላይ በነበሩ የገንዘብ የወረቀት ገንዘቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ወደ አምሳ ዓመታት በሚጠጋው የንጉሡ የሥልጣን ዘመን አራት ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ተደርጓል። ወታደራዊው መንግሥት ዘውዳዊውን ሥርዓት አስወግዶ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም የንጉሡ ምስልን የያዙትን የመገበያያ ገንዘቦች ለውጦት ቆይቷል። በተመሳሳይም ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ለሰባት ዓመታት ያህል ቀድሞ የነበረውን ገንዘብ ሲጠቀም ቆይቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶቹ እንዲቀየሩ አድርጓል። በኢትዮጵያ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የነበሩት የገንዘብ ኖቶች 1፣ 5፣ 10፣ 50 እና 100 ብር የነበሩ ሲሆን፤ ለረጀም ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የገንዘብ ኖት 100 ብር ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም ግን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከዋሉት የብር ኖቶች መካከል የ2 ብር እና የ500 ብር ኖቶች ነበሩበት። ስለዚህም በአገሪቱ የወረቀት ገንዘብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የነበረው የብር ኖት ባለ 500 ብር ኖት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ከግብይት እንዲወጣ መደረጉን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል። ስለዚህም አሁን ከወረቀት የብር ኖቶች መካከል እንዲገባ የተደረገው የባለ 200 ብር ኖት በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሲሆን ወደገበያ ሲገባም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብር ኖት ለውጥ እንደሚደረግ በተለያዩ መንገዶች ሲነገር የቆየ ሲሆን፤ ከብር ዋጋ መቀነስ ጋር ተያይዞ 500 ዋጋ ያለው የብር ኖት ወደ ገበያ እንደሚገባ አንዳንድ ሰዎች ሲገልጹ ቆይተው ነበር። በአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች መደረግ ከጀመሩባቸው ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንደሚካሄድ በጉምሩክና በፖሊስ በኩል በተደጋጋሚ የሚወጡ ሪፖርቶች የሚያመለክቱ ሲሆን፤ ይህም ለውጥ ያስፈለገው ይህንኑ ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል።
xlsum_amharic-train-113
https://www.bbc.com/amharic/news-54662213
ስደት፡ የኤርትራውያን ዋይታ የተሰማባት ላምፔዱሳ
መስከረም 23 ኤርትራውያኖቹ ዮሴፍና አድሓኖም በጣልያኖቹ ሲሲሊ፣ ላምፔዱሳ፣ ፓልርሞና ካታንያ ከተሞች ላይ የሚገኙ ህዝባዊ የመቃብር ቦታዎችን በየአመቱ ይጎበኛሉ።
[ "መስከረም 23 ኤርትራውያኖቹ ዮሴፍና አድሓኖም በጣልያኖቹ ሲሲሊ፣ ላምፔዱሳ፣ ፓልርሞና ካታንያ ከተሞች ላይ የሚገኙ ህዝባዊ የመቃብር ቦታዎችን በየአመቱ ይጎበኛሉ።" ]
መቃብሮቹ ስም የላቸውም፣ ማንነታቸውም አይታወቅም፤ አንዱን ከአንዱ ለመለየትም በኮድ ቁጥር ተቀምጦላቸዋል። ዮሴፍና አድሓኖም ፎቶ ያነሳሉ፤ ቪዲዮ ይቀርፃሉ፤ ጥልቅ ሃዘናቸውንም ይገልፃሉ። በየአመቱ ይህችን ቀን መቼም ቢሆን አያልፏትም። በዚህች ቀን ምን ተፈጠረ? ጊዜው ከሰባት አመታት በፊት ነው፣ መስከረም 23፣2006 ዓ.ም ከሊቢያ የተነሳች ጀልባ በጣልያኗ ደሴት ላምፔዱሳ ሰመጠች፤ ጥም ረሃብና መራቆት ሳይበግራቸው፣ ቀያቸውን ለቀው፣ ባህር ተሻግረው የተሻለ ህይወት እናገኛለን ብለውም የተሳፈሩም 366 ስደተኞችም ሞቱ። በወጡበት ቀሩ። ዮሴፍና አድሃኖም በተአምር ከተረፉት ስደተኞች መካከል ናቸው። ዮሴፍና አድሃኖም ሞትን ተሻግረዋታል፤ ሃዘንን በጥልቀት ያውቁታል፤ ማጣትንም እንዲሁ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ አብረዋቸው የተጓዙ ስደተኞችን በአሰቃቂ ሁኔታ ከአጠገባቸው ተነጥቀዋል። ጓደኝነታቸውም የሚጀምረው ከስደት ነው። የተወለዱበትን ቀዬ ለቆ፣ ባህልና አኗኗር ዘዬ፣ ዘመድና ቤተሰብ ትቶ መሰደድ ምን አይነት ስሜት ይኖረው ይሆን? ዮሴፍና አድሃኖም ይህንን በቅርበት ያውቁታል። አገራቸው በጦርነት ፈራርሶ፣ ቤታቸው በጦርነት ወድሞ፣ በፖለቲካ እምነታቸው ተሳዳጅ ሆነው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ነገን በማለም የነጎዱትን ታሪክ ይቁጠራቸው። ሃብቴን፣ ንብረቴን፣ ጨርቄንና ማቄን ሳይሉ ብዙዎች ተሰደዋል፤ ሜዳ ላይ ቀርተዋል፣ ጥሙ ረሃቡና መራቆቱ ሳይበግራቸው ባሕርና ተራሮችን ሲያቆራርጡ፤ ባሕር በልቷቸዋል አልያም እንደወጡ ላይመለሱ የቀሩትም በርካቶች ናቸው። ዮሴፍና አድሃኖም ስደትን የጀመሩት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በመሻገር ከዚያም በሱዳን አድርገው ወደ ሰሃራ በረሃ አቀኑ። አጥንት ያቀልጥ በሚመስልና መፈጠርን በሚያስጠላ የሰሃራ በረሃም ላይ አንዲት አንሶላ ለሁለት ለብሰው፤ ተስፋቸውን ሰንቀው ነበር ወደ ሊብያዋ ትራብሎስ ከተማ የገቡት። የሰሃራን ምድር አቆራርጦ ትራብሎስ ከተማ የገባ ስደተኛ ተስፈኛ ነው፤ ወደ አውሮፓ "የተስፋይቱ ምድር" ለመድረስ፤ የሁለት ሌሊት የባህር ጉዞ ብቻ ነው የሚቀረው። ሁለት ቀንም ብትሆን ፤ ፀሎትና እድል ካልታከለበት በባህር የተበሉትን ቤቱ ይቁጠረው። ጀልባዋም እስክትሞላ ድረስ መዝርዓ እየተባለ በሚጠራ የባህርዳር መንደሮች ተሰባስበው ነበር። ዋዜማው ላይም በርካቶች በተስፋና በጭንቀት ተሞልተው ነበር። በርከት ያለ ተሳፋሪ ከተሰባሰበ በኋላ ያቺ ተለቅ ያለች ጀልባ ወደ ባህር ዳርቻው እየተጠጋች መጣች። የሊብያ የባህር ጥበቃዎች እንዳያገኙዋቸው፤ በቲዮታ መኪና እያስጠጉ ነበር የሚያሳፍሩዋቸው። በፈታኙ የስደት ጉዞ ያልተለያዩት ዮሴፍና አድሓኖም ወደ ጀልባዋ አንድ ላይ ነበር የወጡት። ጀልባዋ ከአፍ እስከ ገደፏ በርካታ ሰዎች ጭና ትንሽ ከተንቀሳቀሰች ብኋላ ካፕቴኑ ደላሎችን ጠርቶ መርከቧ ሚዛን ስለሳተች የተወሰኑትን እንዲቀንሱ ጠየቋቸው። ደላሎቹም ባልተወለደ አንጀታቸው በዱላ እየቀጠቀጡና እየገረፉ 26 ሰዎች አውርደው በትናንሽ ጀልቦች መለሷቸው። ጨለማ ሰለነበር ኣድሓኖም የበረሃ ጓደኛው ዮሴፍ ከተመለሱት መካከል መሆኑን አላወቀም ነበር። ያቺ ሰዓት በጀልባዋ ተጭነው የነበሩት 518 ስደተኞች መጨረሻ ከሌለው ባህር ወጥተው በርቀት የደሴቷን መብራቶች ሲያዩ የስቃያቸው መጨረሻ፣ የአዲስ ህይወት ምዕራፍ መስሏቸው ነበር። በርካቶቹ እዚህ ለመድረስ የራሳቸውን ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቻቸውን ጥሪት አሟጠዋል። ከሊቢያ ብቻ ወደ ጣልያን ለመሻገር እያንዳንዳቸው 1 ሺህ 600 ዶላር ከፍለዋል። ከሰላሳ ስድስት ሰዓታት የማያቋርጥ የውሃ ጉዞ፣ የጋዝ ሽታ በኋላ መሬቱን በርቀት ሲያዩም የአውሮፓ መሬትን ሲመለከቱ በተወሰነ መልኩ የቅዠታቸው መጨረሻም መስሏቸውም ለመውረድ ዝግጅት የጀመሩም ነበሩ። ካፕቴኑ የጀልባዋ ሞተሩን አጥፍቶ የጣልያን ባህር ጥበቃዎች ገፍተው እንዲያስገቧቸው እየተጠባበቁ ነበር። በጀልባዋ በላይኛው ክፍል ላይ የነበሩት ብርድ ልብሳቸውን ለብሰው ተቀምጠው የነበረ ሲሆን የተወሰነም ንፋስ ነበረው። የታችኛው ተጨናንቋል፤ የባህሩ ሽታ እያጥወለወላቸው በርካቶችም ታጉረዋል። በዚህም ወቅት ነው የባህሩ ውሃ ወደ ጀልባዋ መግባት የጀመረው። በወቅቱ የነበሩ የአይን እማኞችም እንደሚናገሩት ካፕቴኑ ከላይኛው የጀልባ ክፍል ወደታችኛው ወርዶ ሞተሩን ሊያስነሳ ቢሞክርም እምቢ አለው። የተጨናነቀው ካፕቴን ጋዝ ብርድ ልብስ ላይ አርከፍክፎ ባህር ዳርቻው ላይ በማሳየትም አትኩሮት ለመሳብ ሞከረ። ጀልባም አጠገባቸው መጥቶ እንዲረዳቸውም ለማድረግ ነበር። ሆኖም ያ ከመሆኑ በፊት እሳቱ እጁን ስላቃጠለው ጣለው። እሳት ጀልባው ላይ መንደድ ጀመረ። ተኝተው የነበሩ ስደተኞች በጩኸትና በእሳቱ በድንጋጤ ተነሱ። በስደተኞች የታጨቀችው በረብሻ፣ በጩኸትና በዋይታ ተሞላች። በርካቶች ከእሳቱ ለማምለጥም ሲሞክሩና ሲረጋገጡ ጀልባዋም እያጋደለች መስመጥ ጀመረች። ታችኛው የጀልባ ክፍል የነበሩትም የመትረፍ እድሉም አልነበራቸውም። ከላይ የነበሩት ደግሞ ወደ ባህሩ ተወረወሩ፤ የተወሰኑት በደመነፍስ ጀልባዋን የሙጥኝ ብለው ለመትረፍ ሞከሩ። ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ በሌሊት፣ በባዕድ አገር ለሰዓታት በህይወት ለመቆየት ታገሉ። ከሰዓታት በኋላም ነው ጥዋት አስራ ሁለት ሰዓት ላይ አሳ ለማጥመድ የወጡ ሰዎች ያዩዋቸው። የሞቱት ሞተው፤ ያሉት ደግሞ በህይወትና በሞት መካከል እጃቸውን እያውለበለቡ፤ ውሃውን እየተናነቁ በድካምና በተስፋ መቁረጥ መካከል ነበሩ። በኋላም የባህር ጠባቂዎች መጥተው የተወሰኑትን ለማዳን ሞከሩ። በጀልባዋ የነበሩት ከአስራ ሁለት አመት በታች ህፃናት አልተረፉም። አለምን ባስደነገጠው በዚህ አደጋም ተቃቅፈው የተገኙ አስከሬኖችም ነበሩ ተብሏል። መለየት የተቻለውንም፣ ያልተቻለውንም፤ አስከሬናቸው የተገኘው ሲሲሊ አካባቢ በሚገኝ መካነ መቃብር አረፉ፤ አፈሩ ይቅለላቸውና። አድሓኖም ወደ ባህር ከተወረወሩትና ዋኝተው በህይወት ከተረፉት 155 ሰዎች አንዱ ነው። "እንዴት እንደወጣሁ አሁንም ድረስ ይገርመኛል። በርካታ ዋና የሚችሉ ሰዎች ሞተዋል። እንደ እኔ ዓይነት ምንም የዋና ችሎታ የሌለን ደግሞ በእግዚሄር ፍቃድ በህይወት ተርፈናል።" ይህች ዕለት ለህይወት ሁለተኛ እድል ያገኘባት ዳግም የተወለደባት ቀን አድርጎ ያከብራታል። አድሃኖም በህይወት ከተረፈም በኋላ ሲያስጨንቀው የነበረው የጓደኛው ጉዳይ ነበር። በተአምር ከሞት የተሻገረው አድሓኖም ዮሴፍ ከመነሻው ደብደብው እንዲወርዱ ከተገደዱት መካከል መሆኑን ስላላወቀ ከባህር የወጡትን ሬሳዎች መካከል ያፈላልግ ጀመር። ሆኖም አልሰመረለትም፤ ሊያገኘው አልቻለም። አለምን ያስደነገጠውን ይህንን ዜና ሚዲያዎች ሲቀባበሉት ዮሴፍ ሰምቶ ኃዘኑ ጠነከረ፤ ላጣቸው ወዳጆቹ እንባውን አፈሰሰ። ከመካከላቸው ጥቂት በህይወት የተረፉ መኖራቸውን ሲሰማ ደግሞ ምናልባት ጓደኞቹ በህይወት ተርፈው ይሆን የሚልም የተስፋ ጭንላንጭል ትታየው ነበር። አድሃኖም በህይወት ከተረፉት መካከል መሆኑን ዮሴፍ ሰማ። ደስታውን መቆጣጠር አቅቶት፤ እምባ ብቻ ነበር የገለፀለት። በመጨረሻም በስልክ ተገናኙ። ሊቆጣጠሩት በማይችሉት እንባ ታጅበው እንኳን ተረፍክ ተባባሉ፤ ተላቀሱ፤ ምስጋናቸውንም አቀረቡ። አደጋው ካጋጠመ ከሁለት ወር በኋላ ዮሴፍም አውሮፓ ለመግባት ቆርጦ በሌላ ጀልባ ተሳፈረ። ዕድለኛ ሆኖም ወደ ጣልያን አገር በሰላም ገብቶ ከአድሓኖም ጋር ለመገናኘት በቁ። የሆነውን ሁሉ በአካል አወሩ። ሁለቱም ብዙ ሳይቆዩ ጉዟቸውን ወደ ሌላ አውሮፓዊቷ አገር ስዊድን አደረጉ። የጥገኝነት ጥያቄያቸውም ተቀባይነት አገኘላቸው። ሆኖም መስከረም 23 በየዓመቱ የላምፑዴሳ አደጋ ወደደረሰባት ቦታ ያቀናሉ። ተመሳሳይ አደጋ እንዳይደርስ ግንዛቤ ያስጨብጣሉ። በዘንድሮውም፣ በአደጋውም ሰባተኛ አመት ወደ ሲሲሊ ተጉዘዋል። "ትዝታው ፊቴ ላይ ድቅን ይልብኛል። በወቅቱ የነበረውን ለቅሶና ዋይታ፣ የሰዎቹ መልክና ሬሳቸው ባህር ላይ ሲንሳፈፍ ማየት፣ማስታወስ ከባድ ነው" በማለትም ከዚህ በላይ ማውራት ባለመቻልም በዝምታ ተዋጠ። ከአሟሟታቸውና ከትዝታቸው በላይ ደግሞ እንቅልፍ የነሳው ነገር በርካቶች ቤተሰቦቻቸውን ባለመቅበራቸው ሃዘኑ እንዳልወጣላቸው ሲያስበው ነው። ባለፈው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት አጋጣሚም ልጇ በዚህ አደጋ የሞተባት እናት ዛሬም ድረስ ልጇ በህይወት ይኖራል ብላ እንደምታስብ ነገረችው። በርካታ ልጆቻቸውን ለመቅበር እንኳን ያልታደሉ እናቶች ስቃይና መከራ መስማት የሚዘገንንም ሆነበት። በዚህ አመት ግን ዮሴፍና አድሐኖም በቁጥር የተወከለውን መቃብር እየለዩ የትኛው መቃብር የማን እንደሆን በመለየት እናቶችና ቤተሰቦች አንድቀን ቦታው ድረስ ሂደው ሃዘናቸውን እንዲወጣላቸው እያመቻቹ ይገኛሉ። በእርግጥ ስራው ቀላል አልሆነላቸውም፤ የትኛው መቃብር የማን እንደሆነ ለመለየት ፈታኝ ሆኖባቸዋል። ሁኔታውም ልባቸውን ነው የሰበረው። ። ለዚህ ጉዳይ የሚቆረቆር መንግሥት ባለመኖሩ በባህሉ መሰረት አፅማቸው ወደ አገርቤት መጥተው የሚቀበሩበት ሁኔታ የኤርትራ መንግሥት ባይፈቅድም ሌሎች በስደተኞች ጉዳይ ላይ የሚሰሩት ድርጅቶች ቢተባበሩ ጥሪ አድርገዋል። ለዚህ ዓላማ ሲንቀሳቀሱ ድጋፍ ላደረጉላቸው ለኣባ ሙሴ ዘርኣ፣ ኣቦ መንበር ትረ-ኦቶብረ ታረቀ እና ለሌሎች በሟቾች ስም ምስጋናቸውን አድርሷል። በርካቶቹ ስደተኞች የሰሃራን በረሃ አቆራርጠው አደገኛ በሚባል ሁኔታ ሊቢያ ይደርሳሉ፤ ከዚያም የሜዲትራንያን ባህርንም ተሻግረው አውሮፓ ይገባሉ። በርካቶቹ ድንበር ለማቋረጥ በአዘዋዋሪዎች እጅ ድብደባን፣ መደፈርንና ሌሎች ጥቃቶች ይደርስባቸዋል። አንዳንዶችም በአዘዋዋሪዎች ታግተው በርካታ ሺህ ብሮችን ክፈሉም ተብለው፤ ቤተሰብ፣ ጥሪታቸውን አሟጠው ከፍለዋል።
xlsum_amharic-train-114
https://www.bbc.com/amharic/news-47084925
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በፓርላማው ያነሷቸው ቁልፍ ጉዳዮች
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አምስተኛ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአራተኛ ዓመት የመንፈቅ እረፍት ከመውጣቱ በፊት ሁለተኛ ልዩ ስብሰባውን አካሂዶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሕዝብ እንደራሴዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
[ "የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አምስተኛ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአራተኛ ዓመት የመንፈቅ እረፍት ከመውጣቱ በፊት ሁለተኛ ልዩ ስብሰባውን አካሂዶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሕዝብ እንደራሴዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።" ]
በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች የሚታዩ ግጭቶች እና ከዚህም ጋር ተያይዞ የሚስተዋለው የተፈናቃዮች ቁጥር ማሻቀብ፣ የታጠቁ ኃይሎች እና ከውጭ የተመለሱ የፖለቲካ ቡድኖች እንዲሁም የህግ የበላይነት የማስከበር አቅም እንደራሴዎቹ ያጠነጠኑባቸው ጉዳዮች ሲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በጉዳዮቹ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' በ2018 ጎልተው የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው የዲሞክራሲ ምጥ እና ውልደት ህመሞችን ነቅስዋል፤ የሃሳብ ልዕልናን ፈዋሽነት ደጋግመው አውስተዋል፤ የኋላ ቀርነት መገለጫ ናቸው ያሏቸውን በአንድ አካባቢ አናሳ ቁጥር ያላቸውን ማኅበረሰቦች ማጥቃትን እና ዜጎችን ማፈናቀልን አምርረው ወቅሰዋል። "የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቷል፤ ይህም ረጅም ርቀት መሮጥ የማይችሉት ትንፋሽ ያጥራቸዋል ማለት ነው" ብለዋል። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተነሱ ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ተደጋግመው ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፤ በበርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች ሲለኮሱ የሚታዩትና ለብዙዎች ሞት እና መፈናቀል ምክንያት የሆኑት ግጭቶች ይገኙበታል። ከእንደራሴዎቹ መካከል የተወሰኑት በጥያቄዎቻቸው በአንድ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ስልጣን ያመጣው እና ከዚያም በኋላ ልዩ ልዩ የመንግሥት እና የማኅበረሰብ ፈርጆችን የነካውን ለውጥ ለመቀልበስ ይጥራሉ ያሏቸውን እና በስም ለይተው ያላነሷቸውን ኃይሎች ተጠያቂ በማድረግ ይሄንን ለማስቆም መንግሥት ምን እያደረገ እንዳለ እንዲያስረዷቸው ጠይቀል። • በ2018 ጎልተው የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ደግሞ መንግሥት የምህረት አዋጅ መደንገጉን፣ መቀመጫቸውን በውጭ አገራት አድርገው የነበሩ የፖለቲካ ቡድኖች እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡንም ተከትሎ ከተመለሱ ቡድኖች መካከል ነፍጣቸውን እስካሁንም ያነገቡ መኖራቸው ለግጭቶች መፈጠር አስተዋፅዖ ማድረጉን አንስተዋል። እነዚህ ቡድኖች በትክክል የሰላማዊ ትግል ግብዣውን ተቀብለዋል ማለት ይችላል ወይ ሲሉ ጥያቄ ወርወረዋል። መፈናቀል "ሰዎችን ከአንድ አካባቢ ልቀቁ ብሎ ማፈናቀል የሥነ ምግባር ልምሻን ከማመላከቱም ባሻገር ኢሕገ-መንግሥታዊ ጭምር ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ከለውጡ በኋላ ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል ብዙዎቹ ወደቀያቸው መመለሳቸውን ተናገረዋል። ያልተመለሱትን በተመለከተ ይሄንን ጉዳይ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ በአትኩሮት እየተከታተለው እንደሚገኝም ገልፀዋል። የግጭት እርሾዎች ከመብላላታቸው በፊት ለማምከን መስራት፤ ግጭቶች ከተከሰቱ በኋላ እነርሱን ለማክሰም ከመሯሯጥ የበለጠ ተመራጭ አንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ አባላት ነግረዋቸዋል። የፖለቲካ ቡድኖች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ስለታጠቁ የፖለቲካ ቡድኖች የቀረበላቸውን ጥያቄ ለመመለስ በበዓለ ሲመታቸው ወቅት አድርገውት የነበረውን ንግግር አጣቅሰዋል። "ዲሞክራሲን ለመፍጠር መንግሥት ዋነኛው አውታር ስለሆነ ሆደ ሰፊ መሆን አለበት" ሲሉ መናገራቸውን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሃያ የሚጠጉ የታጠቁም ያልታጠቀሙም ቡድኖች መመለሳቸውን ይህም ትልቅ ድል መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። • ". . . ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል" ጠ/ሚ ዐብይ ከእነዚህ ቡድኖች መካከል የሚበዙቱ ያሉባቸውን የገንዘብ፣ የጽህፈት ቤት እና የመሳሰሉ ችግሮች ተቋቁመው በሃገሪቷ ውስጥ በዲሞክራሲ ግንባታው የድርሻቸውን ለመወጣት ሃቀኛ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም "በጉራማይሌ የፖለቲካ የተጠመዱም" አሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ስም ሳይጠቅሱ ወቀሳ ሰንዝረዋል። እነዚህን "አንድ እግራቸው አዲስ አበባ አንድ እግራቸው ውጪ" የሆነ ነው ያሏቸው ቡድኖች አካሄድ "ለድል አያበቃም" እንዲያወም የዲሞክራሲን እርምጃ "ወደኋላ ይመልሳል" ሲሉ ነቅፈዋል። ሃሳብ አጠር ናቸው ያሏቸውን ፓርቲዎች "በመቶ ሜትር ውስጥ ሩጫ የለመዱ ፓርቲዎች ማራቶን ሲሆን ትንፋሽ ያጥራቸዋል" ሲሉ ወቅሰዋል። መንግሥታቸው ለሁሉም የሚሰራ የሰላምን መርህ የተከተለ ጥሪ እንዳቀረበ ገልፀው፤ አስፈላጊ ሲሆን የትዕግስቱን ያህል መረር ያለ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችልም አስጠንቀቀዋል። በሚቀርብለት ጥሪ ወደ ተለያዩ ክልሎች ሰላም ለማስፈን የሚገባው የመከላከያ ሠራዊትን በስኬታማነቱ ያሞካሹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት የሚገዳደር እንቅስቃሴ የሚያደርግ አካልም ጦርነት እንዳወጀብን እንቆጥራለን ብለዋል። በሃገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ቡድኖች የውስጥ ዲሞክራሲያቸውን እንዲያጎለብቱ ምክር የለገሱት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ "በራሱ ፓርቲ ላይ ያልተለማመደውን ዲሞክራሲ ኢትዮጵያ ላይ መለማመድ አይችልም" ብለዋል። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት "የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን እንደጦር መናኸሪያ የመጠቀም አዝማሚያ እንደሚኖር አስቀድሞም እናውቅ ነበር" በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስለሚከሰቱት ችግሮች ምላሽ የሰጡት ጠ/ሚ ዐብይ "ይህንም ስለምናውቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አድርገናል፤ ለተማሪዎቹም በብዙሃን መገናኛ አውታሮች መልዕክት አስተላልፈናል" ብለዋል። ወጣት ተማሪዎች "ለፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀሚያ" ህይወታቸውን መገበራቸውን "አሳዛኝ" እና "አስነዋሪ" ነው ብለዋል። አክለውም "ድንጋይ እና ድንጋይ አጋጭቶ እሳት ማውጣት የጋርዮሽ ዘመን ፈጠራ ነው። የምንፈልገው ሃሳብ እና ሃሳብ የሚያጋጭ ተማሪ ነው" ብለዋል። ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝውውር በሌላ በኩል መቼም ኮንትሮባንድ ለሰላማችም ለምጣኔ ኃብትም ስጋት እንደሚሆን ታሰቦ እርምጃ መውሰድ መጀመራችን ለጉዳዩ እንደ አዲስ ትኩረት እንዲሰጥ አድርጎታል ሲሉ ተናግረዋል። እንደተበራከተ ከሚገለፀው የጦር መሣርያዎች እና የገንዘብ ዝውውር ጋር ተያይዞም ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የትርፍ ፍላጎት ሻጮችን፣ የደህንነት ስጋት ሸማቾችን ወደ መሳርያ ንግድ እንደሳበ አስረድተው "ሰላምን የማደፍረስ ፍላጎት ያላቸው" ኃይሎችም ይህን እንቅስቃሴ አባብሰውታል ብለዋል። • የአቶ ጌታቸው አሰፋ ጉዳይ፡ ፖለቲካዊ ወይስ ሕጋዊ መፍትሄ? አገሪቱ ውስጥ ሕገ-ወጥ የጦር መሣርያ መኖሩን የሚገልፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጦር መሳርያ ከህዝቡ ቁጥር በላይ ነው" ብለው፤ ህጋዊ ቢሆንም እንኳ የጦር መሣርያ መብዛት መዘዙ እንደሚከፋ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ስላልተያዙ ሰዎች ህግ የሚፈልጋቸውን ወንጀለኞችን መያዝ ለምን ከበደ? ክልሎች ወንጀለኞችን አሳልፈን አንሰጥም የማለት ስልጣናቸው ምን ያህል ነው? ተብለው የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ሰርቶ፤ መንግሥትም ይሄንን ነገር አውጆ ያልታሰረ ወንጀለኛ የለም። ልዩነቱ በእኛ እስር ቤት ውስጥ ነው ወይንስ በራሱ የሚለው ነው" ሲሉ ምላሻቸውን ጀምረዋል። • አቶ ጌታቸው አሰፋ በሚያውቋቸው አንደበት "ሁሉም ክልሎች ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው" ብለው አሁን የተያዙ ተጠርጣሪዎችን እና ተከሳሾችን በሚመለከትም "የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ድንገተኛ ቁጥጥር በእስር ቤቶች ላይ አድርጓል። በእኛ እስር ቤት ያሉ ሰዎች ስፖርት ይሰራሉ፣ ያነባሉ፣ ይፅፋሉ፣ በቤተሰብ ይጠየቃሉ። በግል እስር ቤት ውስጥ ያሉት እንደዚህ መሆናቸውን እርግጠኛ አይደለሁም" ብለዋል። ሰው ገድሎና ዘርፎ ፍርድ ሳያገኝ የሚቀር እንደማይኖር ካስረገጡ በኋላ "በግራም ሆነ በቀኝም ፍርድ አለ" ብለዋል።
xlsum_amharic-train-115
https://www.bbc.com/amharic/news-50015452
የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ከየት ወደ የት?
የቅማንት የማንነት ጥያቄ በተነሳባቸው አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶች እየተፈጠሩ የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ወድሟል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም ከመኖሪያ ቤታቸው ሲፈናቀሉ ቆይተዋል። ለመሆኑ የዚህ ሁሉ ምክንያት ምንድን ነው?
[ "የቅማንት የማንነት ጥያቄ በተነሳባቸው አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶች እየተፈጠሩ የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ወድሟል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም ከመኖሪያ ቤታቸው ሲፈናቀሉ ቆይተዋል። ለመሆኑ የዚህ ሁሉ ምክንያት ምንድን ነው?" ]
• "በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር የተከሰተው ለመላው ሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት ነው" የአማራ ክልል ደኀንነትና ጸጥታ ካውንስል የቅማንት የማንነት ጥያቄስ በምን መልኩ ተጠይቆ ምን አይነት ምላሽ ተሰጠው? የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከውልደት አሁን እስካለበት ደረጃ ድረስ ጉዞው ምን ይመስላል? ቢቢሲ ጉዳዩን በዝርዝር ተመልክቶታል። ቅድመ - ቅማንት የማንነትና አስተዳደር ጥያቄ የቅማንት ህዝብ በቀድሞው የጎንደር ክፍለ ሃገር፤ በአሁኑ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን በሚገኙ የተወሰኑ ወረዳዎች የሚኖር ህዝብ ነው። በተለይ በጎንደር ከተማ ዙሪያ በሚገኙ ላይ አርማጭሆ፣ ወገራና ጭልጋ ወረዳዎች ማህበረሰቡ በብዛት የሚኖርባቸው አካባቢዎች ናቸው። • የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ለችግር ተዳረግን አሉ ከ1983 ዓ.ም በፊት በነበረው የመንግሥት አወቃቀርም የብሔር ማንነትን መሰረት ያደረገ ስላልነበር ብሔረሰቡ የጎንደር ክፍለ ሃገር አካል ሆኖ ከአማራው ህዝብ ጋር በብዛት ተቀላቅሎ ይኖር ነበር። የራሱ የተካለለ ልዩ አካባቢና አስተዳደርም እንዳልነበረውም መረጃዎች ያሳያሉ። የቅማንት የማንነት ጥያቄ መነሻ? ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በኢትዮጵያ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የብሔር ፌደራሊዝምን መሰረት ያደረገና ስልጣን በፌደራልና በክልሎች የተከፋፈለ ሥርዓት ተመሰረተ። የቅማንት የማንነት ጥያቄ ይህ ሥርዓት ከሰፈነ በኋላ በ1984 ዓ.ም መነሳቱን በቅማንት ማንነት ዙሪያ ጥናት ያካሄዱት አቶ ቹቹ አለባቸው ያስረዳሉ። "የቅማንት ብሔረሰብ ጥያቄ ከየት ወደየት-ከማንነት ጥያቄ እስከ የራስ አስተዳደር ጥያቄና የፖለቲካ ፓርቲ ምስረታ" በሚለው ፅሁፋቸው፤ ጥያቄው በቅማንት ህዝብም ተቀባይነት ያልነበረው ሲሆን ለግለሰቦቹ የተሰጣቸውም ምላሽ "የያዛችሁት ሐሳብ ከአማራ ወንድሞቻችን ጋር የሚያጋጭ ነው፣ ስለሆነም አንቀበላችሁም" የሚል እንደነበረ ጥናቱ ያሳያል። • በጎንደር የተለያዩ ዞኖች በተከሰተ ግጭት 39ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ በሕዝቡ ተቀባይነት ካጣ በኋላም ጥያቄው ለአስራ አምስት ዓመታት ያህል ተዳፍኖ ሳይነሳ መቆየቱን ይኸው ጥናት ያመላክታል። የ1999 ዓ.ም የሕዝብና ቤት ቆጠራ ግን አዲስ ክስተት ይዞ መጣ። የማንነት ጥያቄ ባይነሳም በ1984 ዓ.ም በተካሄደው ሕዝብና ቤት ቆጠራ የቅማንት ሕዝብ በራሱ ተለይቶ 'ቅማንት' በሚል መለያ ኮድ እንደተቆጠረ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዋና የህግ አማካሪ አቶ መርሃ ጽድቅ መኮንን ይናገራሉ። ነገር ግን ለብቻው ተለይቶ መቆጠሩ አልቀጠለም፤ በቀጣዩ 1999 በተካሄደው ሕዝብና ቤት ቆጠራ ግን ኮዱ ተሰርዞ 'አማራ ወይም ሌላ' በሚል የቅማንት ሕዝብ እንዲቆጠር መደረጉን ያስረዳሉ። ይህ ሁኔታ ቅሬታን እንደፈጠረና ጥያቄዎችም መቅረብ መጀመራቸውን የሚናገሩት አቶ መርሃ ጽድቅ፣ በተለይም ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ማመልከቻ ይዘው ወደ ክልሉ መንግሥት መምጣት መጀመራቸውን ያስታውሳሉ። የቅማንት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይርሳው ቸኮልም በአቶ መርሃ ጽድቅ ሃሳብ ይስማማሉ። "ቅማንት ሆነን ሳለ ለምን 'ሌላ' ተባልን በሚል ተሰባስበን ጥያቄውን ጀመርን" ይላሉ። • የሰሜን ጎንደር ሕዝበ ውሳኔ የቅማንትን ሕዝብ አምስት በመቶ ድምጽ ማለትም 18500 ድምጽ ሰብስበው ማንነታቸው እንዲታወቅ ለክልሉ መንግሥት ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን አቶ ይርሳው ይጠቅሳሉ። የቅማንት የማንነት ጥያቄ በተደራጀ መልኩ መቅረብ የጀመረው በዚህ ወቅት ነው። የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ማንነት ጥያቄ ምላሽ የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄንም ለመመለስ የክልሉ የርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤት ጥናት እንዲጠና አድርጓል። የአቶ ቹቹ ጽሁፍ እንደሚያመለክተው በክልሉ መንግሥት አነሳሽነት በተቋቋሙ ኮሚቴዎች አማካኝነት ሁለት ጥናቶች በ2003 እና 2004 ዓ.ም ተደርገዋል። ጥናቱም ሞዴል አድርጎ የወሰደው የአርጎባ ልዩ ወረዳ የማንነት ጥያቄ የተመለሰበትን መንገድ እንደነበር አቶ መርሃ ጽድቅ ያወሳሉ። የአርጎባ ጥያቄ በ1998 ዓ.ም ልዩ ወረዳ መሆን ይችላሉ በሚል ምላሽ ተሰጥቶታል። የተጠናው ጥናትም በ2005 ዓ.ም ለክልሉ ምክር ቤት መቅረቡንም የሚናገሩት አቶ መርሃ ጽድቅ፤ ይህም በሰነድ ደረጃ የአማራ ክልል ምክር ቤት የቅማንት የማንነት ጥያቄን አስመልክቶ ውይይት ሲያደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። •"የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኞች ከሌሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው" ጄኔራል አሳምነው በሕገ መንግሥቱ መሰረት የማንነትና የራስ አስተዳደርን ጥያቄ ለመመለስ አምስት መስፈርቶች አሉ፤ እነዚህም የጋራ ባህል መኖር፣ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ መኖር፣ የአካባቢው ኩታ ገጠም መሆን፣ በሥነ ልቦናና ማንነት ለጠየቀው ብሔረሰብ አባል ነኝ ብሎ ማመንና የተዛመደ ህልውና መኖር ሲሆን፤ የአርጎባ ጥያቄም ምላሽ የተሰጠው እነዚህ መስፈርቶች በማሟላቱ እንደሆነም አቶ መርሃ ጽድቅ ያስረዳሉ። ጥናቱንም መሰረት በማድረግ የቅማንት ጥያቄ "ማህበረሰቡ እንደ ማህበረስብ መኖሩ ተረጋግጦ እውቅና ቢሰጠውም የራሱን የውስጥ አስተዳደርና ነጻነት ለመመስረት ግን ሕገ መንግሥታዊ መስፈርቶችን አያሟላም" ተብሎ አደረጃጀቱ በክልሉ ምክር ቤት ውድቅ መደረጉን ይናገራሉ። የማንነት ጥያቄው እንዲመለስ ሞዴል ከተደረገው የአርጎባ ልዩ ወረዳ ጋር ተቀራራቢነት የሌለው፤ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ የሌለው በመሆኑና ኩታ ገጠም አሰፋፈር ስላልነበረው ጥያቄውን ለመመለስ የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ አካሄድ እንዳልነበረ አቶ መርሃ ጽድቅ ያስረዳሉ። በምክር ቤቱ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ይህ ውሳኔም 174 የምክር ቤት አባላት የብሔረሰብ አስተዳደሩን መቋቋም ሲቃወሙ፣ ሰባት ደግፈውና 21 የምክር ቤቱ አባላት ድምጻቸውን በማቀባቸው ነው ውድቅ የተደረገው ይላሉ። • "የአማራ ልዩ ኃይል ከማዕከላዊ ጎንደር አይወጣም" የክልሉ የሰላምና ሕዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ "'ይህ አካባቢ ያንተ ነው ራስህን አስተዳድር ለማለት የሚያስችል ሁኔታ አልነበረም። የራስ አሰተዳደሩን ለመወሰን የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ መስፈርቶች አልተሟሉም በማለት የራስ አስተዳደር ጥያቄው በክልሉ ምክር ቤት ውድቅ ተደርጓል" ይላሉ አቶ መርሃ ጽድቅ። ከአማርኛ ጋር እየተቀላቀለና በተወሰኑ አዛውንቶች ብቻ የሚነገረውን የቅማንት ቋንቋ እንዳይጠፋ ለማበልፀግም ጥረት መደረግ እንዳለበት ምክር ቤቱ የራስ አስተዳደር ጥያቄውን ውድ ባደረገበተወ ወቅት ሃሳብ አቅርቦ እንደነበር አቶ መርሃጽድቅ ያስረዳሉ። • ጎንደር፡ የአስቸኳይ ጊዜ ወይስ የመሣሪያ እገዳ? አቶ ይርሳው በበኩላቸው ሕገ መንግሥቱ የሚጠይቀውን መስፈርት ማሟላታቸውን ይገልፃሉ። መግባቢያቸው አማርኛ ቋንቋ ቢሆንም የቅማንትኛ ቋንቋ ያልሞተ መሆኑን፣ ወጥ የሆነ የሕዝብ አሰፋፈር፣ በሥነ ልቦና ቅማንት ነኝ ብሎ የሚያምን ህዝብ መኖሩንና ከአማራው ጋር የተቀላቀለ ቢሆንም የራሳቸው ባህል እንዳላቸውም ይገልጻሉ። በዚህም መሰረት ውሳኔው የማንነት ጥያቄ ያነሱትን የኮሚቴ አባላት ያስደሰተ አልነበረም። ውሳኔውን ባለመቀበልም ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን አቶ ይርሳው ይናገራሉ። የፌደሬሽን ምክር ቤት ደግሞ ጉዳዩን የክልሉ መንግሥት ድጋሚ እንዲያየው መልሶ የላከው ሲሆን ከሁለት ዓመታት በኋላ ግን በ2007 ዓ.ም የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር መፈቀዱን አቶ ይርሳው ለቢቢሲ ገልፀዋል። የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ እንዴት ተመለሰ? ክልሉ በ2005 ባደረገው ጥናት የቅማንት ማህበረሰብ የማንነትና የራሱን አስተዳደር ለመመስረት ሕገ መንግሥታዊ መስፈርቶችን አላሟላም ከተባለ ከሁለት ዓመት በኋላ ጥያቄው እንዴት ተቀባይነት አገኘ? በምን መስፈርት የራስ አስተዳደሩ ተመለሰ? ለአቶ መርሃጽድቅ የቀረበ ጥያቄ ነው። እንደ አቶ መርሃ ጽድቅ ከሆነ በተለይ በአካባቢው ግጭቶች እየተበራከቱና ተቋማት እየተዘጉ በመምጣታቸው፤ በ2007 ዓ.ም የክልሉ የርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤት "ጉዳዩ እንደገና ይታይልኝ" በማለቱ ጥናቱ ለሁለተኛ ጊዜ ለክልሉ ምክር ቤት መቅረቡን ያስታውሳሉ። • "ችግርን ከመፍታት ይልቅ ጩኸት ማፈን ነው የሚቀናቸው" ምክር ቤቱ የቅማንትን የማንነት ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ ለማየት እንደተገደደ የሚያስረዱት አቶ መርሃ ጽድቅ "ይህም ፖለቲካዊ ጫና ነበረበት" ይላሉ። አቶ መርሃ ጽድቅ ፖለቲካዊ ጫና የሚሉትም የ2005ቱ ዓ.ም የምክር ቤት ውሳኔ በቅማንት የማንነት ኮሚቴ ቁጣን ከመቀስቀሱ ጋር የተያያዘ እንደሆነም ያስረዳሉ። "ውሳኔው በኮሚቴው ዘንድ ቁጣን ስለቀሰቀሰ እና የሰው ህይወትም እየጠፋ ሲመጣ ፖለቲከኞቹ [በተለይ በፌደራል ደረጃ የነበሩ የብአዴን ካድሬዎች ከፍተኛ ጫና በማሳደራቸው] እጃቸውን አስረዝመው ቅማንት ይኖርባቸዋል የሚባሉትን አካባቢዎች አገናኝታችሁ ወስኑላቸው፤ ሕዝባችን እስከሆኑ ድረስ የትም አይሄዱም" የሚል ትዕዛዝ እንደተሰጠ አቶ መርሃ ጽድቅ ይናገራሉ። በዚሁ መሰረትም ከላይ አርማጭሆ ወረዳ 25 እና ከጭልጋ ወረዳ 17 በድምሩ 42 ቀበሌዎችን በቅማንት የራስ አስተዳደር፤ በልዩ ወረዳ እንዲዋቀሩ ተወስኗል። ይህም ከሕገ መንግሥቱ መስፈርት ውጪ ብዙ ርቀት ተሂዶ የተወሰነ መሆኑን አቶ መርሃ ጽድቅ ይናገራሉ። ነገር ግን ውሳኔው ግጭቱን አላስቆመውም። የቅማንት የማንነት ጥያቄና የአስተዳደር ቅሬታ ክልሉ የቅማንትን አስተዳደር አርባ ሁለት ቀበሌዎች በልዩ ወረዳ እንዲዋቀር መወሰኑ በማንነት ኮሚቴው ዘንድ ተቀባይነት እንዳላገኘ የሚናገሩት አቶ ይርሳው ናቸው። "ሕዝቡን ባላሳተፈ መልኩ፤ 42 ቀበሌዎችን ሰጥቻችኋለሁ ነው የተባልነው" ይላሉ። አርባ ሁለት ቀበሌዎች ለቅማንት የራስ አስተዳደር መወሰኑንም በመቃወምና በቂ አይደለም በሚልም በጭልጋ በ2007 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ። "እነዚህ 42 ቀበሌዎች በውይይትና በፖለቲካዊ ውሳኔ የተካለሉ እንጂ ሕዝበ ውሳኔ የተካሄደባቸው አልነበሩም" ብለውም አቶ ይርሳው ያምናሉ። የአቶ ቹቹ ፅሁፍም እንደሚያስረዳው በወቅቱ በቅማንት ወረዳዎች የመንግሥት ሥራ ቆሞ ስለነበር፤ ሥራ ለማስጀመር፤ እንዲሁም ውሳኔውን ለማስፈጸም፤ የፀጥታ ኃይሎች ወደ ሮቢት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ማውራ ከተባለ አካባቢ ጥቅምት 2008 ዓ.ም ላይ ከሕዝብ ጋር ግጭት ተደርጎ የሰው ህይወት አልፏል። ግጭቱም በህዳር 2008 ዓ.ም በሽንፋ አካባቢ ቀጠለ። • ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ረቂቅ ህግ የሞት ቅጣት ተካቶበታል ውሳኔውንም ባለመቀበል የማንነት ጥያቄ አቅራቢዎቹ በድጋሜ ቅሬታቸውን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ቢያቀርቡም መልሱ ተመሳሳይ ነበር። 'የክልሉ መንግሥት እንደጀመረው ይጨርሰው' የሚል ምላሽ እንደተሰጠ ይነገራል። ለሦስት ዓመታት ጉዳዩ በውዝግብ ከቀጠለ በኋላ 2010 ዓ.ም ላይ ጥያቄው እንዴት መፈታት አለበት በሚል ከክልሉ መንግሥት ጋር መስማማታቸውን አቶ ይርሳው ይናገራሉ። በዚህም መሰረት ከቅማንት የማንነት ጥያቄና ከአማራ ክልል መንግሥት የተውጣጣ ጥምር ኮሚቴ ተዋቅሮ ጥናት ካካሄደ በኋላ ተጨማሪ 21 ቀበሌዎች ወደ ቅማንት ይካለሉ ተብለው ወደ ቅማንት የራስ አስተዳደር መካለላቸውንም አቶ ይርሳው ይጠቅሳሉ። በተመሳሳይም እነዚህ ቀበሌዎች ሲካለሉ ሕዝበ ውሳኔ አለመካሄዱንና እንዲሁ "በውይይትና በፖለቲካ ውሳኔ" የተካለሉ መሆናቸውንም አቶ መርሃ ጽድቅም ሆኑ አቶ ይርሳው ይስማማሉ። ቀበሌዎቹን ወደ ቅማንት ራስ አስተዳደር የማካለል ውሳኔ ጥምር ኮሚቴው በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር በመዘዋወር የተለያዩ ቀበሌ ነዋሪዎችን አወያይቷል። ከቀደሙት ውሳኔዎችም በተለየ መልኩ በ2010 ዓ.ም 12 ቀበሌዎች በሕዝበ ውሳኔ እንወስናለን የሚል ምላሽ መስጠታቸውንም አቶ ይርሳው ይናገራሉ። ምንም እንኳን ቀበሌዎቹ የራሳቸውን አስተዳደርን በራሳቸው ድምፅ ለመወሰን ቢያስቡም አራት የጭልጋ ቀበሌዎች ላይ ሁከት በመፈጠሩ ምርጫ ሳይካሄድ መቅረቱን አቶ ይርሳው ይገልጻሉ። • "ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ ከአስራ ሁለቱ በስምንቱ ቀበሌዎች ሕዝበ ውሳኔ ተካሂዶ ሰባቱ ወደ ነባሩ አስተዳደር እንዲካለሉ ሲወስኑ፤ አንዷ ቀበሌ ወደ ቅማንት የራስ አስተዳደር ለመካለል መወሰኗን ይናገራሉ። በቅማንት የራስ አስተዳደር ጥያቄ ሂደት ይህች አንዲት ቀበሌ የራስ አስተዳደሩን በሕዝበ ውሳኔ የተቀላቀለች ብቸኛዋ ቀበሌ ነች። በተፈጠረ ሁከት ምክንያት ሕዝበ ውሳኔ ያልተካሄደባቸው አራቱ ቀበሌዎች በጥምር ኮሚቴው አማካኝነት ከቀበሌው ነዋሪዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ ሁለት ወደ ቅማንት የራስ አስተዳደር ሁለቱ ደግሞ ወደ ነባሩ አስተዳደር እንዲካለሉ መደረጋቸውን አቶ ይርሳው ይገልጻሉ። በዚህ ሁኔታ በውይይት፤ በፖለቲካዊ ውሳኔና በሕዝበ ውሳኔ የተካተቱት የቅማንት የራስ አስተዳደር ቀበሌዎች ቁጥር ከ60 በላይ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ይርሳው ቀጣዩ ሥራ የራስ አስተዳደሩን መመስረት ነበር። የቅማንት የራስ አስተዳደርና የሦስት ቀበሌዎች ጥያቄ ቀበሌዎቹ ከተካለሉ በኋላ የራስ አስተዳደሩን ለመመስረት የሚያስችል መነሻ መዋቅር (proposal) ኮሚቴው እንዲያዘጋጅ በክልሉ መንግሥት በተጠየቁት መሰረት ሌሎች ሦስት የመተማ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ቅማንት ናቸው በሚል እሳቤ በማካተት 72 ቀበሌዎች፤ በስድስት ወረዳ ለማድረግ ወስነው ለክልሉ መንግሥት ምክረ ሃሳብ እንዳቀረቡ አቶ ይርሳው ያስረዳሉ። የኮሚቴውን ምክረ ሃሳብ በ2010 ዓ.ም የተመለከተው የክልሉ ምክር ቤት "በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆኖ የማንነት ጥያቄው በ69 ቀበሌዎች እንዲዋቀርና ከልዩ ወረዳነት ወደ ብሔረሰብ አስተዳደርነት እንዲያድግ መወሰኑን" አቶ መርሃ ጽድቅ ይጠቅሳሉ። ይሁን እንጂ ኮሚቴው ጥያቄያቸው ሙሉ በሙሉ ምላሽ እንዳላገኘና በቅማንት አስተዳደር ስር መካተት የሚገባቸው 3 ቀበሌዎች (መቃ፣ ጉባኤ ጀጀቢትና ሌንጫ) በቅማንት ራስ አስተዳደር ስላልተካተቱ ቀበሌዎቹ በቅማንት ራስ አስተዳደር ካልተካለሉ ውሳኔውን እንደማይቀበለው ይፋ ማድረጉን የአቶ ቹቹ ጽሑፍ ያስረዳል። አቶ ይርሳውም በበኩላቸው በአቶ ቹቹ ፅሁፍ ይስማማሉ "አራቱን ወረዳ ብንቀበለውም ሦስቱ ቀበሌዎች ወደ እኛ መካተት አለባቸው ብለን ስላሰብን በህግ ሊፈቱ ይገባል ብለን ቅሬታችንን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ላክን" ይላሉ። የፌደሬሽን ምክር ቤት ምላሽ ቅሬታው የደረሰው የፌደሬሽን ምክር ቤትም ጥናት አድርጎ ምላሽ እንደሰጠ የፌደሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጸሃፊ አቶ ወርቁ አዳሙ ለቢቢሲ ገልፀዋል። እሳቸው እንደሚሉት ሦስት ባለሞያዎች ከፌደሬሽን ምክር ቤት ወደ ስፍራው ተልከው፤ የተነሳውን ቅሬታ በአካል ቦታው ድረስ በመጓዝ ጥናት ማካሄዳቸውን ያስረዳሉ። "ሕገ መንግሥቱ ጋር ስለማይጣጣምና ቅሬታ የቀረበባቸው ቀበሌዎች ኩታ ገጠም ስላልሆኑ፤ የክልሉ መንግሥት የሰጠው ውሳኔ ትክክል ነው" የሚል ምላሽም መስጠታቸውን ያስታውሳሉ። እንደ ፌደሬሽን ምክር ቤት አሰራር ደግሞ እንደዚህ አይነት ቅሬታዎች ሲፈጠሩ በተለይ ቀበሌን ከቀበሌ፤ ወረዳን ከወረዳና ዞንን ከዞን የማዋቀር ውሳኔ መስጠት ያለበት ቅሬታ የተነሳበት ክልል ራሱ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ወርቁ፤ "ቅሬታው አስተዳደራዊ ጉዳይ በመሆኑ መመለስ ያለበት አስተዳደራዊ በሆነ መልኩ ነው" ይላሉ። • ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት አክለውም "ዋናው ነገር ማንነትን እውቅና መስጠት ነው፤ ይህም ምላሽ አግኝቷል" ያሉት አቶ ወርቁ በክልሉ ውስጥ የሚፈጠርን የአስተዳደር ወሰን በተመለከተ ክልሉ ራሱ እንዲፈታ ነው ህጉ የሚያዘው" ብለዋል። ኮሚቴው ግን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን አለመቀበሉን የሚገልፁት አቶ ይርሳው ለዚህ የሚያቀርቡት ምክንያት "ጥናቱን ለማከናውን የተላኩት ሰዎች ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጡ ስላልነበሩ፤ ገና ከመመለሳቸው በፊት ምን ይዘው እንደሚመለሱ ስለምናውቅ እነዚህ ሰዎች ይዘውት የሚመለሱት ውጤት ምንም ይሁን ምን አንቀበልም ብለን ለሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤ ጽፈናል" ይላሉ። ኮሜቴው ጥናቱን ለማከናወን የተላኩት ግለሰቦች ገለልተኛ አይደሉም የሚል ጥያቄ ቢያነሳም አቶ ወርቁ በበኩላቸው "የሚዛናዊነት ጥርጣሬ ካለ ከብሔር ብሔረሰብ የተወጣጡ ቢሆኑ የተሻለ ሊሆን ይችላል፤ ካልሆነ ግን መታየት ያለባቸው ሰዎቹ ሳይሆኑ ይዘውት የሚመጡት መረጃ ነው፤ ከዚህም አንጻር የመጣው መረጃ መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በትክክል የሚገልጽ ነው" ይላሉ። የማንነት ጥያቄና የራስ አስተዳደር ለምን ተፈለገ? የቅማንት የራስ አስተዳደር ጥያቄ በዋናነት ልማትን ለማፋጠን እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ይርሳው "ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር እኩል ተጠቃሚነት፣ ባህልንና እሴትን ለማሳደግ እንዲሁም የራስን አካባቢ ህዝቡ ራሱ በሚመርጣቸው ሰዎች እንዲያስተዳደርና በዚህም ከፍተኛ ልማት ለማምጣት ነው" ይላሉ። የቅማንት የራስ አስተዳደር ጥያቄና የክልሉ ውዝግብ መፍትሔ ሳያገኝ በዚህ ከቀጠለ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት፤ ኮሚቴውንና የክልሉን መንግሥት ተወካዮች ባካተተ መልኩ ውይይት ተደርጎ ጉዳዩ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲፈታ ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል። እንደ አቶ ይርሳው ገለጻ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ምክረ ሃሳብ በኋላ ኮሚቴው ነሐሴ ወር 2010 ዓ.ም ጎንደር ለስብሰባ ተቀምጧል። • "የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ "ስብሰባ ላይ እያለን በክልሉ የፀጥታ ኃይል የእገታ ሙከራ ተካሂዶብናል፤ ከዚያም በኋላ ከክልሉ መንግሥት ጋር ያለን ግንኙነት ተቋረጠ" ይላሉ። ውዝግቡ እንዳይቋጭ ምክንያቱ ይህ መሆኑንም ያነሳሉ። አቶ መርሃ ጽድቅ ግን በዚህ አይስማሙም፤ እሳቸው እንደሚሉት በተለይ የጸጥታው መደፍረስና ነገሮች መበላሽት የጀመሩት ክልሉ በ2005 ባጠናው መሰረት የመጀመሪያውና ትክክለኛው ውሳኔ በመቀልበሱ እንደሆነ አፅንኦት በመስጠት ይናገራሉ። "ክልሉ ሰለባ ሆኗል፤ በተለይ ከ2005 ዓ.ም ውሳኔ በኋላ ክልሉ ከሚገባው በላይ ባልተገባ መንገድ ተጠልፏል። በማንም አይደለም የተጠለፈው፤ በራሱ ሰዎች ነው። በተለይ በፌደራል ደረጃ ላይ በነበሩት ትልልቅ የብአዴን ሰዎች የክልሉን ምክር ቤት ወደዚህ ችግር አስገብተውት አካባቢው እንዳይረጋጋ ተደርጓል" የሚል ሃሳብ ያነሳሉ። ግጭትና መፈናቀል በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር በአካባቢው በተለያዩ ጊዜያት ችግሮች እየተነሱ የሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም በስፋት ተስተውሏል። በተለይ ባለፈው ዓመት የተነሳው ግጭት የክልሉን አጠቃላይ ተፈናቃይ አሃዝ ወደ 90 ሺህ ያሳደገና በግጭቱም ቢያንስ 560 ቤቶች መቃጠላቸውን በወቅቱ የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። ለተወሰኑ ወራት አንጻራዊ ሰላም ሰፍኖ ቢቆይም ሰሞኑን በተቀሰቀሰ ግጭት ደግሞ ሰዎች ተገድለዋል፤ ንብረት ወድሟል። ንጹሃን ዜጎችን ከተሽከርካሪ አስወርደው ማንነታቸውን መሰረት በማድረግ ቢያንስ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉና ይህም "በጽንፈኛው ኮሚቴ" የሚመራና የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ያለው መሆኑን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። • ቤይሩት፡ ባለፉት 7 ወራት 34 ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን አጥተዋል ለዚህ ክስ ምላሽ የሰጡት አቶ ይርሳው "እኛ የማንም ተላላኪ አይደለንም፤ እንደዚያም ሆነን ከሆነ የክልሉ መንግሥት ምን ይሰራ ነበር?" በማለት ይጠይቃሉ። ከሰሞኑ የተቀሰቀሰውን ግጭት በተመለከተ ደግሞ "የቅማንት ሕዝብ የትም አልሄደም፤ ሲመጡበት ግን ራሱን ተከላክሏል" ያሉት አቶ ይርሳው "መኪና ላይ ሰዎችን አስወርዶ በማንነታቸው ምክንያት መግደል ነውር ነው፤ ማን እንደፈጸመው ግን መረጃ የለኝም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። አሁን የክልሉ መንግሥትና ኮሚቴው አንዱ ሌላውን በመክሰስ ላይ ይገኛሉ። በአካባቢው ግጭቶች እየተፈጠሩ በየጊዜው የሰው ህይወት መጥፋትና የንብረት መውደም የአካባቢው መገለጫ እንደሆነ ብዙዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። መፍትሄው ምን ይሆን? አቶ መርሃ ጽድቅ ለጉዳዩ ሁለት የመፍትሔ ሃሳቦች መኖራቸውን ይገልጻሉ። እንደ እርሳቸው ገለጻ "የራስ አስተዳደሩ ሕገ መንግሥታዊ መስፈርቶችን ሳያሟላ የተወሰነ በመሆኑ ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት ውሳኔውን ውድቅ ማድረግ ይቻላል" የሚለው አንደኛው አማራጭ ነው፤ ነገር ግን ይህ አማራጭ ተግባራዊ ቢደረግ "ሰላም ሊሰፍን ይችላል ወይ?" የሚለው አጠያያቂ መሆኑን ይገልጻሉ። "ሕዝቡ በዚህ ደረጃ ከተነሳሳ በኋላና ብዙ ተስፋዎችን ካሳየነው በኋላ የራስ አስተዳደርህን አጥፌብሃለሁ ቢባል ውጤቱ መረጋጋትን የሚያሰፍን አይሆንም" ባይ ናቸው። ሌላኛው ደግሞ እንደ አማራጭ የሚያቀርቡት የተፈቀደውን የራስ አስተዳደር መመስረትና ይህንን ህጋዊ አካሄድ በሚያስተጓጉሉት አካላት ላይ ደግሞ ህጋዊ ርምጃ መውሰድ እንደሆነ አቶ መርሃ ጽድቅ ይናገራሉ። "ሂደቱ የራሱ ችግር እንዳለበት ሆኖ 69 ቀበሌዎችን ያቀፈው የራስ አስተዳደር ይደራጃል" ያሉት አቶ መርሃ ጽድቅ ይካተቱልኝ የሚባሉት ሦስት ቀበሌዎች አስፈላጊ ከሆነ ባሉበት በልዩ ቀበሌ ሊደራጁ ይችላሉ ብለዋል። አቶ ይርሳውም በበኩላቸው ሁለት የመፍትሄ አማራጮችን ያቀርባሉ። አንደኛው የብሔረሰብ አስተዳደሩ እንዲቋቋም ነገር ግን ባለፈው የፌዴሬሽን ሰዎች የሰጡት ውሳኔ ተሽሮ ሌላ አካል በተለይ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጣ አካል የሦስቱን ቀበሌዎች ጉዳይ እንዲያጠና ጠይቀዋል። ሁለተኛው ደግሞ "ብሔረሰብ አስተዳደሩ ሲመሰረት ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት አያስፈልገንም፤ ምክንያቱም አሁን ባለው ሁኔታ ከኮሚቴው ጋር የነበሩ ነገር ግን አሁን አብረውን ያልሆኑ ሰዎች እንዲሳተፉ እየተደረገ ስለሆነ ነው" ይላሉ።
xlsum_amharic-train-116
https://www.bbc.com/amharic/49137137
"ኦሮሞ እና ማዳጋስካርን የሚያገናኝ ፖለቲካ እንዳለ አላውቅም" የትነበርሽ ንጉሤ
ድሬዳዋ ተካሂዶ በነበረው የአዲስ ወግ ምክክር መድረክ ላይ የትነበርሽ ንጉሤ ያደረገችው ንግግር በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። የትነበርሽ ከቢቢሲ ጋር አጭር ቆይታ አድርጋለች። ቢቢሲ፡ ሰውን እንዲህ እንዲነጋገር ያደረገው ምን ነበር? እዛ መድረክ ላይ ማለት የፈለግሽውስ ምን ነበር?
[ "ድሬዳዋ ተካሂዶ በነበረው የአዲስ ወግ ምክክር መድረክ ላይ የትነበርሽ ንጉሤ ያደረገችው ንግግር በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። የትነበርሽ ከቢቢሲ ጋር አጭር ቆይታ አድርጋለች። \n\nቢቢሲ፡ ሰውን እንዲህ እንዲነጋገር ያደረገው ምን ነበር? እዛ መድረክ ላይ ማለት የፈለግሽውስ ምን ነበር?" ]
የትነበርሽ ንጉሤ የትነበርሽ፡ ብሔር የሚለው ቃል አገር ማለት ነው የሚለውን ፅንሰ ሐሳብ ለማስረዳት የተጠቀምኳት አንዲት አማራ፣ ኦሮሞ እንዲሁም ትግሬ የትም ይኖራል፣ ኦሮሞ የትም ይኖራል። ኦሮሞ ቋንቋ ነው እንጂ ብሔር አይደለም፣ ትግርኛም እንዲሁ። ስለ ብሔር ስናወራ ስለ አገር ነው የምናወራው። ኦሮሞ የትም ይኖራል ብየ አንድ ምሳሌ ሰጥቻለሁ፤ ያ ምሳሌ ማዳጋስካር የምትባል አገር ናት። እኔ ለማለት የፈለግኩት ደሴት ውስጥ እንኳን ሰው ይገኛል እንኳን አገር ውስጥ የሚል ነው። እውነት ለመናገር እስከ ትናንት ጥዋት ድረስ ኦሮሞና ማዳጋስካርን የሚያገናኝ ፖለቲካ እንዳለ እኔ አላውቅም፤ ባውቅ ኖሮ እንደዚህ አይነት ምሳሌ አልጠቀምም፤ ሌላም አገር መጥራት እችል ነበር። ማሳየት የፈለግኩት እንኳን ትልልቅ አገራት ውስጥ ማዳጋስካር ደሴት ውስጥ ኦሮሞ አግኝቼ አውቃለሁ ነው ያልኩት። • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" ይህቺን ቃል የመዘዙ ሰዎች በአጠቃላይ ስለተነሳው ስለኔ ሀሳብ ሳያወሩ፤ ኦሮሞ ማዳጋስካር አግኝቻለሁ የሚለው አይቻለሁ ወደሚል ተቀየረ። እሷ እንዴት ነው ያየችው ወደሚል የአይነ ስውር ክርክር ውስጥ ገቡ። ከዛ በኋላም የራሳቸውን ሐሳብ ማራመድ የሚፈልጉ ሰዎች ማራመድ ጀመሩ። ከዚህ የምንረዳው አንደኛ ቦታው ላይ የነበሩ ሰዎች ብዙ ፅፈዋል። ሙሉ ንግግሩንም አንድ አፍታ የሚባል የማኅበራዊ ሚዲያ ድረ ገፅ ይዞት ወጥቷል። ድረ ገፁ በደንብ አብራርቶ ፅፎታል። ይሄ ሃሳብ እንደሌለኝና በዚህ መልክ ለምንድንነው የተረዳነው የሚለውን ይዟል። ዋናው ነገር የኔን ሐሳብ ተጠቅመው ሰዎች የራሳቸውን መልእክት አስተላልፈዋል። ማዳጋስካር አግኝቻለሁ ብሎ ማለት ከማዳጋስካር ተሰደው ነው የመጡት ብለው መከራከሪያ የሚያቀርቡትን መደገፍ ነው ብሎ ማሰብ እንግዲህ በጣም የተራራቀ ነው። ሙሉ ንግግሩ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ተላልፏል። ኦንላይንም አለ። እነሱ የሚሉት ሐሳብ የተገለፀበት ቦታ የለም። ከንግግሩ ውስጥ ሦስት ቃላት መዘው አውጥተው ኦሮሞ ማዳጋስካር አግቻለሁ ማለት ክፋት ባይኖረውም፤ ያሳደሩት ቡኮ ስለነበራቸው ያንን ቡኮ ለመጋገር የሞከሩ ሰዎች አሉ። • የኦሳ 33ኛ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀመረ መጀመሪያ ላይ አበሳጨኝ፤ ያላልኩት ነገር አለች ሲባል የኔ እምነት ያልሆነ ነገር በኔ ጭንቅላት ሊያስቀምጡ ሲሞክሩ ያበሳጫል። እያደር ሳስበው ግን ያው የምንታገለው ለሐሳብ ነፃነት አይደል? እነሱ የኔ ሐሳብ ነው ብለው ሐሳባቸውን ቢገልፁ ሐሳባቸው ይከበራል። እነዚህ ሰዎች ኦፖርቹኒስቲክ ናቸው፤ አጋጣሚ እየጠበቁ ታዋቂ፣ ተሰሚ መሆን የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። ማኅበራዊ ሚዲያም ላይ ከኔ በላይ ሰው ነው ትክክል እንዳልሆነ እየገለፀ ያለው፤ ብሔራዊ ሎተሪ ወይም ብሔራዊ ትምባሆ እንላለን ብሔር የሚለው ቃል ለቋንቋ በተለዋጭ እየተጠቀምንበት ነው። እሱ ስህተት ነው የሚል ሐሳብ ነው ያስቀመጥኩት። ቢቢሲ፡ ሰዎች ሙሉውን ያንቺን ንግግር የያዘ ቪድዮ ቢያዩ የተሻለ ግንዛቤ ያገኛሉ ብለሽ ታስቢያለሽ? የትነበርሽ፡ ሙሉ ቪዲዮውን ራሴ ፌስቡክም ላይ አስቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ኤዲት አድርጋው ነው የሚል ሐሳብም አመጡ። አንድ አፍታዎች ናቸው በመጀመሪያ ያወጡት፤ ኤዲትም እንዳላደረግኩት አስቀምጠዋል። ሰዎች መረጃ ሲያገኙ ሙሉውን ቢያነቡ ጥሩ ነው። አልተደነቅኩም ምክንያቱም ይሄ የቆየ ተግባር ነው። እንደዚህ ሕዝብ የሚወዳቸው ሰዎች ሀሳብ እንዳይሰጡ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች ናቸው። የሚያሳዝነው ግን የሀሳብ ነፃነትን ለማስከበር የሚታገሉ ሰዎች የሌሎችን የሃሳብ ነፃነት እንዲህ ባለ ኢፍትሐዊ በሆነ መልኩ ለመርገጥ መሞከራቸው ተገቢ አይደለም። ሌላው አንድ ነገር ሲነገር የተነገረበት ኮንቴክስት (አውድ) ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ተገቢ ይሆናል። አለበለዚያ እንዳንነጋገር በር ይዘጋሉ። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ኢትዮጵያን ከችግር ሊያወጣት የሚችለው ነገር መነጋገር፣ መደማመጥ፣ መከባበርና መፈላለግ ነው። ከዚህ ነጥለው ሊያወጡን የሚሞክሩ ኃይሎችን እምቢ ማለት በሐሳባችንም በድርጊታችንም የኛ ድርሻ ነው ብየ አስባለሁ። እኔ ማኅበራዊ መሪ ነኝ ብየ ነው የማስበው፤ ፖለቲከኛም አይደለሁም። ፖለቲከኛም መሆን አልፈልግም። ለፖለቲካ አጀንዳ መጠቀም ስህተት ነው ምክንያቱም መጨረሻ ላይ ፊት አላደርግም፤ አልሆንም። • የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቀረቡ ያግባቡናል፤ ማህበረሰቡን እንደ ማህበረሰብ ወደፊት ይወስዳሉ ብየ የማስባቸውን የራሴን ሐሳቦች እናገራለሁ፤ ሌሎችም እንዲናገሩ እድሉን እሰጣለሁ። ሰዎች ሐሳባቸውን በነፃነት እንዳይናገሩ እንቅፋት በመሆን የሐሳብ ነፃነትን ማረጋገጥ አይቻልም ስህተት ነው። የምናደርገውና የምንናገረው አንድ መሆን እንኳን ባይሆን፤ ባይቃረን ጥሩ ነው ብየ አስባለሁ። እኔ የማምንበት ነገር ትክክል ነው ሰዎች ይቀበሉኝ የሚል እምነት የለኝም፤ አለማመን መብታቸው ነው። ምክንያቱም ወደፊት ለመሄድ አንድ አይነት መሆን አይጠበቅብንም፤ ነገር ግን የኔን ክብር የሚነካ ነገር በማድረግ፤ ሐሳቤን በሐሳብ ማሸነፍ ይቻላል አሁን የተያዘው ግን የካራክተር አሳሲኔሽን ጉዳይ ነው። ይሄ እንግዲህ እኔን በግልፅ ለማጥቃት እንደሆነ የምታውቀው የስልክ ቁጥሬ ድረ ገፁ ላይ ተቀምጧል። እግዚአብሔር ይስጣቸው እስካሁን የደወሉልኝ ሰዎች በጣም አስተዋይ፣ አክባሪ ለማድመጥ የሚፈልጉና መጨረሻ ላይ ተግባብተን የተለያየንና እነሱም በራሳቸው ገፅም አስተያየታቸውን የሰጡ ሰዎች ናቸው። እነሱ እንደሚያስቡት ለሚፈልጉት አላማ የስልክ ቁጥሬ የዋለ አልመሰለኝም። ስልክ ቁጥር መስጠትም ስህተት ነው። በወንጀል ከሰህ ቅጣት ማስቀጣት ይቻላል። ያንን ያህል ርቀት መሄድ አስፈላጊ ነው ወይ? ለነሱስ እንዲህ አይነት ጉልበት (ኢነርጂ) ማባከን ይጠቅማል ወይ? ያው የሥራ ዘርፋችን ይለያያል፤ አንዳንዶቹ በወሬ ይተጋሉ ሌሎቻችን በሥራ መትጋት አለብን ስለዚህ ወደ ሥራየ አተኩሬያለሁ። እኔ የማግዛቸው የበጎ አድራጎት ተቋማት አሉ። እኔ ከሕዝብ ጋር ያገናኘኝ ፌስቡክ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀኝ በፌስቡክ ፀሐፊነት አይደለም፤ ወይም በፖለቲካ ሐሳብ አራማጅነቴ አይደለም። የተፈጠርኩትም፣ የመጣሁበትም መንገድ ለዛ አይደለም ስለዚህ ወደሥራየ ተመልሻለሁ። ያው እንዲህ ሲሆን ከመደበኛ ሥራ ይረብሻል። ቢቢሲ፡ አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ፣ የብዙዎች ስሜተ ስሱ መሆን ነገሩ እንዲካረር አድርጓል ብለሽ ታስቢያለሽ? የትነበርሽ፡ እኔ ንግግሬን ብዙ ሰው ወስዶታል ብየ አላስብም። ብዙ ሰው አልተረጎመውም ያስደሰተኝም ይሄው ነው። እነዚህ ሰዎች ቢያንስ እንደማይሳካላቸው ያውቃሉ። ተስፋ ይቆርጣሉ ብየ አስባለሁ፤ የጥቂት ሰዎች ሙከራ ነው እንጂ በርካታ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ወጣቶች ደውለውልኛል፤ ከአዳማ፣ ከኤሊባቡርና ከሌሎችም አካባቢዎች፤ በጣም ተደስቻለሁ። እግዚአብሔር ያክብራቸው። እንዲህ አይነት ልጆች አሉን። ሙሉውን እንዳልሰሙትና ይህንን ቃል እንዴት ተናገርሽ? የሚል በርካታ ጥያቄዎች ጠይቀውኛል። ግብታዊ ሆነው አንድ ሰው ክፉ ቃል የተናገረኝ የለም። ተሰምቶኛል፣ አንቺ እንዴት? ያለኝ ሰው አለ እናም ሳስረዳው ጊዜው እኮ መጥፎ ነው እና ምንም ባትይ ብለውኛል። እኔም እነሱ በመደቡኝ አልንቀሳቀስም።
xlsum_amharic-train-117
https://www.bbc.com/amharic/news-47498869
ለአደጋ የተጋለጡ ሦስት የትግራይ ቅርሶች
ትግራይ በጥንታዊ ቅርሶች የታደለች ብትሆንም ከቱሪዝም ማግኘት የሚገባትን ጥቅም አላገኘችም በሚል ብዙ ቅሬታዎች ይሰማሉ። ለዚህም ምክንያቱ በአግባቡ የማስተዋወቅ ሥራ አለመሠራቱ እንደሆነ ይታመናል።
[ "ትግራይ በጥንታዊ ቅርሶች የታደለች ብትሆንም ከቱሪዝም ማግኘት የሚገባትን ጥቅም አላገኘችም በሚል ብዙ ቅሬታዎች ይሰማሉ። ለዚህም ምክንያቱ በአግባቡ የማስተዋወቅ ሥራ አለመሠራቱ እንደሆነ ይታመናል።" ]
ከዚህ ባሻገርም አንዳንድ የትግራይ ቅርሶች ተገቢ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ባለመሆኑ አደጋ ውስጥ ይገኛሉ። አደጋ ከተጋረጠባቸው ጥንታዊ ቅርሶች መካከል ውቕሮ ክልተኣውላዕሎ ያሉት በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። እንዳ አብርሃ ወአጽብሃ ከአለት ተወቅረው ከተሠሩ ጥንታዊ ውቅር አብያተ ክርስትያናት አንዱ እንዳ ኣብርሃ ወኣጽብሃ ነው። ይህ ጥንታዊ ህንፃ ከውቅሮ ከተማ በስተምዕራብ በ17 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። በአራተኛው ክፍለ ዘመን ሁለት ታዋቂ የአክሱም ነገስታት (አብርሃ እና አፅበሃ) ማስታወሻ እንዲሆን በስማቸው እንዳሠሩት የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ተዘዋውረን እንደተመለከትነው ቤተክርስትያኑ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተጋርጠውበታል። የቤተክርስትያኑ ጥንታዊ ስዕላት በተባይ ተበልተው አደጋ ውስጥ ወድቀዋል። ስዕላቱደብዝዘዋል፤ እየጠፉም ነው። በስተደቡብ የሚገኘው የህንፃው አካል በመሰነጣጠቁበሚያሰጋ ሁኔታ ይገኛል። የህንፃው ውስጣዊ ክፍልና ላይኛው ጣሪያም ተቃጥሎና ጨልሞ ይታያል። ይህ ደግሞ በዘመነ ዮዲት ጉዲት የደረሰ ጉዳት እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ለዚህም እሰከአሁን የተደረገለት ጥገና የለም። በተለይም በህንፃው መግብያ በር ላይ የሚገኝ 'ዓምደወርቅ' ተብሎ የሚጠራ እና ከአቅሙ በላይ ተሸክሞ የሚገኝ ምሰሶ አስቸኳይ ጥገና እንደሚያስፈልገው ያለበት ይዞታ ይመሰክራል። ይህ ምሰሶ በህንፃው ከሚገኙ 42 ምሰሶዎች አንዱ ሲሆን፡ በዮዲት ጉዲት ጉዳት ደርሶበት በእንጨት የተጠገነ ነው። • ዶ/ር አምባቸው ማን ናቸው? ይህ ጥንታዊ ህንፃ 'ሳንድስቶን' ከሚባል የመፈረካከስ ባህሪ ካለው አለት የተሰራ በመሆኑ ከግዜ ወደ ግዜ የማርጀት ባህሪ እየታየበት ነው፤ በተለይም አንዳንድ የህንፃው አስደናቂ ምሰሶዎች እንዳይቆረጡ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ቄስ ተኽላይ አጽበሃ የቤተክርስትያኑ ቄሰ ገበዝ ሲሆኑ ቤተክርስትያኑ ከጥዋቱ 3 ሰአት እስከ 12 ሰአት ክፍት እንደሆነና በውጭ ቱሪስቶች በብዛት የሚታይ እንደሚጎበኝ ገልፀውልናል። ቢሆንም ግን ከትልቅ እንጨት ተቀርፆ የተሰራው ጥንታዊው ትልቁ የቤተክርስትያኑ በር ጭምር ለአደጋ ተጋልጧል። ከቢቢሲ ባልደረቦች ጋር ተጉዘው ቤተ ክርስትያኑ ላይ ላይ ስለተጋረጠው አደጋ ማብራርያ የሰጡንን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቅርሶች ጥበቃ ከፍተኛ ኃላፊ አቶ ጎይተኦም ዕቡይ ቅርሶቹን መጠበቅ የማን ኃላፊነት ነው? ስንል ጠየቅናቸው ነበር። ቅርሶቹን የመጠገን ኃላፊነት የፌደራል ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን እንደሆነና ይህንንም በተደጋጋሚ እንዳሳወቁዋቸው ይገልፃሉ። በአስቸኳይ ጥገና ካልተደረገም አደጋው ወደ ከፋ ደረጃ ሊደርስ እንደሚችልም ያሳስባሉ። እንዳ ጨርቆስ ዉቕሮ ጨርቆስ ውቕሮም ከውቕሮ-ገርዓልታ አብያተክርስትያናት አንዱ ሲሆን ከውቕሮ በስተ ሰሜን አቅጣጫ ወደ ዓዲግራት ከተማ መውጫ በስተግራ ይገኛል። ይህ ቤተክርስትያንም በአብርሃ ወአፅበሃ እንደተሰራ ይነገራል። ሶስት ቤተመቅደሶች ፣ ሶስት በሮች እና ሶስት መስቀሎች እንዲኖረው ተደርጎ እንደተሰራ ሊቃውንት ይናገራሉ። ህንፃው ጥንታውያን ከሆኑ ቅርሶች አንዱ ቢሆንም እንዴት ሆንክ የሚለው ያለ አይመስልም። የቤተክርስትያኑ ዋነኛው ክፍል የሆነው ቤተመቅደስ በተለይም በክረምት ግዜ ዝናብ ስለሚገባበት ለከባድ አደጋ ተዳርጓል። በቤተክርስትያኑ ቅጥር ያገኘናቸው አባ ገብረሚካኤል በየነ ስለ ቤተክርስትያኑ ጥንታዊነት ያወጉን ሲሆን "ይሁን እንጂ በአስቸኳይ ጥገና ያስፈልገዋል። ክረምት ላይ ወደ ቤተመቅደሱ ዝናብ እየገባበት ተቸግረናል" አሉን። በቤተመቅደሱ ትልቅ በርሚል በማስቀመጥ የሚገባውን ውሃ እንደሚያቁሩት እና አንዳንድ ግዜም ታቦቱን ከቦታው ለማንቀሳቀስ እንደሚገደዱ በሃዘኔታ ገልፀዋል። ከማህሌት አልፈን ወደ ቤተመቅደሱ ውስጥ መግባት ስለማንችል አጋጠመ የተባለውን አደጋ ማየት ባንችልም ከዛ ውጪ ባለው የህንፃው አካል የደረሰውን ጉዳት በማየት ግን ስለሁኔታው መመስከር ከባድ አይደለም። ከቤተክርስትያኑ ጣርያ ላይ ወጥተን ከህንፃው በላይ የተለያዩ አለስፈላጊ ተክሎች እና አረሞች በቅለውበት የቤተከርስትያኑ አለቃ ሲያርሟቸው መመልከት ችለናል። ከፍተኛ የአባቶች ጥበብ ያረፈበት ጥንታዊ ህንፃ በእንክብካቤ እና ተገቢ ጥገና እጦት ምክንያት እንዲህ ያለ ደረጃ ላይ ደርሶ መመልከት ልብ የሚሰብር ነገር ነው። ከአሁን በፊት የባህል እና ቱረዝም ቢሮ በስስ አለት (ቃፀላ) እና ስሚንቶ በማድረግ ከላይ ክፍተቱን ለመድፈን ቢሞክሩ እንኳን ወደ ውስጥ የሚገባው ውሃ መንበረ ታቦቱን ማበላሸቱን እንዳላቆመ የቅርስ ጥበቃ ባለሞያው አቶ ጎይተኦም ዕቡይ ይናገራሉ። እሳቸው እንደሚሉት በህንፃው ጥንታዊ ጣርያም ጉዳት እየደረሰ ነው። ጉዳቱ ከአብርሃ ወኣፅብሃ ቤተክትርስትያን ሲነፃፀር ነዋሪዎች እና የቤተክርስትያኑ ተገልጋዮች በቀላሉ ሊከላከሉት የሚችሉት አደጋ የነበረ ቢሆንም ይህ ባለመደረጉ አሁን ለከፋ ደረጃ ደርሷል። "ህብረተሰቡን በማስተማር መከላከል ይቻል ነበር። ወጪው ትንሽ ነው፤ እየደረሰ ያለውን አደጋ ግን ከባድ ነው" ይላሉ። የቤተክርስትያኑ ገበዝ እና ተገልጋዮቹ ግን አሁንም የሚመለከተው አካል አስቸኳይ እና ችግሩን ከስር መሰረቱ የሚፈታ ጥገና እንዲያደርግለት ይጠይቃሉ። • የኮንዶሚኒየሙ እሰጣገባ የአፄ ዮሃንስ ቤተ መንግሥት - አጉላዕ ከምስራቃዊ ዞን ከክልተአውላዕሎ ወረዳ ሳንወጣ ብዙም ያልተነገረለት ግን ልዩ ታሪክ ያለው ስፍራ በአጉላዕ ከተማ ይገኛል። ይህችን በማደግ ላይ የምትገኝ የአጉላዕ ከተማ ከበስተደቡብ ወደ ምእራብ የሚያልፍ እና ወደ 'ገረብ ግባ' የሚገባ አንድ ወንዝ ከመሻገራችን በፊት ከርቀት ስንመለከት አንድ እንደመፈራረስ ያለ ትልቅ ህንፃ ማስተዋል ቻልን። ወደ አከባቢው ስንቀርብም የህንፃው ቅጥር ግቢ ፈራርሶ ኦና ሆኖ ይታያል። በደቡባዊ ትግራይ በአደጋ ላይ የሚገኘው በለስም በህንፃው ጣርያ ላይ በቅሎ እሱም ሌላ ችግር ሆኖ ይገኛል። የንጉሰ ነገስት አፄ ዮሃንስ አራተኛ በመቐለ ከተማ የሚገኝ እና አሁን እንደ ሙዝየም ሁኖ እያገለገለ ካለው በፌደራል መንግስት ከሚተዳደር ትልቁ ቤተመንግስት ውጪ፡ ሌላ ቤተመንግስት እንዳላቸው ትንፍሽ ያለ ሚድያም ያለ አይመስልም። በተለይም ከጥንት ጀምሮ በትግራይ እና በኤርትራ ለሚገኝ የቤት አሰራር ማሳያ የሆነው ይህ ቤተመንግሥት፡ በትግራይ መዲና መቐለ ከሚገኘው የንጉሱ ቤተመንግስት ቀድሞ እንደተሰራ የታሪክ ድርሳናት ይመሰክራሉ። ንጉሰ ነገስት አፄ ዮሃንስ ይህን ቤተመንግስት ሲሰሩ ለትግራይና ዓፋር ያማከለ ስትራተጅይካዊ ቦታ አደርገው እንደመረጡት ምሁራን ይናገራሉ። በህንፃው ቅጥር ግቢ ሰፊ ሜዳ ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት እየታረሰ መሆኑን በአይናችን አየን። በመስመር ሲያርሱ (ክሓርሱ) ያገኘናቸው አንድ ገበሬ 'ምን እየሰሩ ነው? ስንላቸው በልበ ሙሉነት "ጤፍ እየዘራው" አሉን። በቅጥር ግቢው በሬዎች ተፈትተው፣ ሞፈር እና ቀንበር አንሰራፍተው፣ ከብቶች እና የጋማ ከብቶች በግድግዳው እየተሻሹ ምግባቸውን ሲበሉም ተመለከትን። ገና ወደ ቅጥር ግቢው ስንደርስ የፈራረሰው የቤተመንግስቱ የላይኛው አካል 'አድኑኝ፤ ብሎ የሚጮህ ይመስላል። የቤተመንግስቱ ውስጣዊ ክፍልም ቢሆን የተቆፋፈረ ነው። በጣም ቢዘገይም ከአምና ጀምሮ፡ ቤተመንግስቱን ወደ ሙዝየም ለመቀየር እየተሞከረ መሆኑን የሚያሳዩ አንዳንድ መሳርያዎች ቦታው ላይ ይገኛሉ። "ቤተመንግስቱ ቀደም ሲል አንደኛውን ፈርሶ ነበር ማለት ይቻላል፤ በኋላ ግን የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጥንታዊነቱን እና ቅርስነቱን ግምት ውስጥ በማስገባት ጥገና እንዲደረግለት ተወሰነ" ይላሉ የቅርስ ጥበቃ ባለሞያ አቶ ጎይቶኦም። ከዛም በመቀጠል የከተማዋ አስተዳደር እንዲረከበው እንደተደረገና ርክክቡን ተከትሎ ግን ወደ ልማት መግባት ይገባ እንደነበር ጠቁመዋል። "እንደ አንድ የቅርስ ባለሞያ ያሳዝነኛል። አንድ ህንፃ ቶሎ ወደ ልማት እንዲገባ ካልተደረገ ለአደጋ መጋለጡ ማይቀር ነው። ትልቅ ታሪክ ያለው ቦታን በመንከባከብ ለትውልድ የማስረከብ ስራ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ያሳያል" ይላሉ አቶ ጎይቶኦም። ያናገርናቸው ሌላ የአካባቢው ነዋሪ ድግሞ ከአሁን በፊት ህንፃውን ለማፍረስ የሞከሩ አካላት እንደነበሩ ገልፀውልናል። በአጠቃላይ ይህ በተወሰኑ አካባቢዎች የታዘብነው በጥንታዊ ቅርሶች እየደረሰ ያለ አደጋ እንጂ ከአክሱም ሐወልት ጀምሮ በክልሉ አደጋ ላይ የሚገኙ እና አስቸኳይ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው በርካታ ታላላቅ ቅርሶች መሆናቸውን መረዳት ይቻላል።
xlsum_amharic-train-118
https://www.bbc.com/amharic/news-53422732
ጀርመን፡ በዓለም ለደንብና ለሥርዓት ተገዢ ዜጎች ያሏት አገር ማን ናት?
ከበርሊን ወደ ዱሱልዶፍ ከተማ በሚከንፍ ፈጣን ባቡር ውስጥ ነኝ። አጠገቤ ከተቀመጠው ወጣት ጋር ወግ ይዘናል። "እኔምልህ. . . . በጀርመንና በአሜሪካ ባሕል መካከል ምን ልዩነት አስተዋልክ?" አለኝ።
[ "ከበርሊን ወደ ዱሱልዶፍ ከተማ በሚከንፍ ፈጣን ባቡር ውስጥ ነኝ። አጠገቤ ከተቀመጠው ወጣት ጋር ወግ ይዘናል። \"እኔምልህ. . . . በጀርመንና በአሜሪካ ባሕል መካከል ምን ልዩነት አስተዋልክ?\" አለኝ።" ]
በዚህ መሀል አንዲት ሴትዮ በወንበሮች መሀል በመተላለፍያው ወደ መቀመጫ ወንበሯ እየተመለሰች ነበር። "እሽሽሽ. . . " ስትል እንደ ልጅ ተቆጣችን። ድምጻችሁን ቀንሱ ማለቷ ነው። እኛ ያለንበት የባቡሩ ፉርጎ ድምጽ አይመከርም። ምክሯን ቸል ብለን ወሬያችንን መሰልቀጥ ያዝን. . . በድጋሚ ሞባይል ማነጋገር እንደማይፈቀድ የሚያመላክተውን ባቡሩ ፉርጎ ላይ የተለጠፈ ምልክት በጣቷ ጠቆመችን። በምሥል ከገባቸው በሚል. . . አደብ አንገዛ ስንላት ደግሞ ወደኛ ጠጋ ብላ በሹክሹክታ "ድምጻችሁን መቀነስ ይኖርባችኋል" አለችን፣ በትህትና። አጠገቤ ወደተቀመጠው ወዳጄ ዞር ብዬ ቀደም ሲል ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ እንዳገኘሁ ነገርኩት። "በአሜሪካና በጀርመን ባሕል መካከል ያለው ልዩነት ይቺ ሴትዮ ናት።" ምን ማለቴ እንደሆነ ሳይገባው አልቀረም። የጀርመናዊያን ወግ አጥባቂነት፣ ደንብ አክባሪነት… አራት ዓመት በጀርመን ስኖር "እባካችሁ ዝም በሉ" ያለችን ሴትዮ የምትወክለውን ኅብረተሰብ አይቻለሁ። ፍጹም ለወግ-ባሕል፣ ለደንብ ሥርዓት ተገዢ ማኅበረሰብ ነው። በሁሉም ሁኔታና ከባቢ ሕዝቡ ሕግ አክባሪ ነው ማለት ይቻላል። በዚያ ምድር ሥርዓት የሚባለው ነገር የትም አለ። በቃ በሕይወት ውጣ ውረድ ከደንብና ሥርዓት ውልፍ የለም። ምክንያቱም በጀርመን ባሕል ዝነኛው አባባል የትኛው ይመስላችኋል? "ሰውን ሰው ያደረገው ሥራ ነው" የሚለው? አይደለም። "መማር ያስከብራል፣ አገርን ያኮራል" የሚለው? አይደለም። በጀርመን ዝነኛው አባባል. . . "Ordnung Muss Sein" (ሥርዓት ሊኖር ይገባል!) የሚለው ነው። በቃ! የመላው ጀርመናዊያን ሕይወት የሚመራው በዚህ አባባል ነው ማለት ይቻላል። ከልጅ እስከ አዋቂ ለዚህ አባባል ይገዛል። ሥርዓት ሊኖር ይገባል! ሥርዓት ሊኖር ይገባል! ሥርዓት ሊኖር ይገባል! ሥርዓት በምን ይገለጻል? በጀርመን የቆሸሹና ንጹህ ጠርሙሶች በአንድ አይጣሉም። በጀርመን ምሽት ከ4፡00 ሰዓት በኋላ የሚረብሽ ድምጽ ማሰማት የለም። በጀርመን ቀይ መብራት ከበራ ለምን ገጠር ውስጥ አይሁንም፣ ለምን እልም ያለ የገበሬ ማኅበር ያለበት አይንም. . . ለምን እግረኛ ሰው ቀርቶ እግረኛ-ወፍ መንገድ እየተሻገረች አይሆንም ትራፊክ የለም ብሎ ሕግ አይጣስም። አረንጓዴው እስኪበራ እግር ፍሬን ላይ ጠቆም ይደረጋል! ጡሩንባ ማንባረቅ የለም፤ ጸጥ ረጭ! ውልፍ ዝንፍ የለም! በዚህ አገር አንድ ነገር ለማስፈጸም ከፈለጋችሁ ቀጥተኛ አካሄድ ነው ያለው። መጀመርያ ቅጽ መሙላት፤ በቅጹ ላይ በትክክል ስምና አድራሻን መጻፍ፣ ከዚያ ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል። ቅጽ የሚሞላ ሰው መቼስ መሳሳቱ የት ይቀራል። ከተሳሳተ ተደውሎ ይጠራል። ቅጹን አስተካክሎ መሙላት ግዴታው ነው። ምክንያቱም በጀርመን "ሥርዓት ሊኖር ይገባል!" የማርቲን ሉተር ውርስ? ከላይ ከላዩ ሲታይ ጀርመን የደንብና ሥርዓት አገር ትመስላለች። ሁሉ ነገር እስትክክል ያለባት አገር ናት። ነገር ግን ጀርመን እንደሚባለው ሁሉ ነገር ደንብና ሥርዓት የያዘባት፣ በዚያ ላይ ደግሞ ለለውጥ እጅ የማትሰጥ አገር ናት ወይ? ብለን ከጠየቅን መልሱ አሉታዊ ሊሆን ይችላል። ይህን ለመመለስ ወደ ማርቲን ሉተር ዘመን መመለስ ሳይኖርብን አይቀርም። ሉተር ጀርመንም ሆነች ዓለም እንዴት ጌታ እየሱስ ክርስቶስን ማምለክ እንዳለባቸው ሥር ነቀል ለውጥ እንዳመጣ ሁሉ ባለፉት 500 ዓመታት የጀርመን "ሪፎርሚስቶች" በጀርመን ባሕል ላይ ትልቅ አሻራን አሳርፈዋል። እንዲያውም ይህ ዝነኛ የጀርመኖችን የሕይወት መመሪያ የጻፈው ማርቲን ሉተር እንደሆነ ነው የሚነገረው። Ordunug Muss Sein Unter Den Leuten (በሕዝቦች መካከል ሥርዓት ሊኖር ይገባል!) እንዲል ማርቲን ሉተር። ጀርመኖች የቢራ ፍቅራቸው (ለጠመቃም ለመጠጥም)፤ የመጽሐፍ ፍቅራቸው (ለመጻፍም ለንባብም)፣ የዳቦ ሱሳቸው (ለመጋገርም ለመግመጥም) አይጣል ነው። በዓለም የተወደዱላቸው የአውቶሞቢል ዝርዝር ዘለግ ይላል፤ መርሴዲስ ቤንዝ፣ ቮልስዋገን፣ ቢኤምደብሊው፣ አውዲ፣ ፖርሸ የትም ቢኬድ የጀርመኖችን ጥንቁቅነት ያሳብቃሉ። ከዚህ ሁሉ ልቆ የጀርመኖችን ፈጠራ መስመር ያስያዘ፣ ከጀርመኖችም አልፎ በዓለም ተጽእኖ የፈጠረ አንድ የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት አለ። ባውሐውስ (Bauhaus) ይባላል። ስለእርሱ ትንሽ ካላልን ጀርመኖችን ማወቅ አንችልም። ግንባታዎች ጭምር ጥብቅ ሥርዓትን እንዲከተሉ ይደረጋል ባውሐውስ ምንድነው? ባውሐውስ የሥነ ጥበብና ሥነ ሕንጻ ትምህርት ቤት ነው። በቫይማር ጀርመን በ1919 በእውቁ አርክቴክት ዋልተር ግሮፒየስ አማካኝነት የተመሰረተ ትምህርት ቤት ነው። ከዚያ በኋላ በወቅቱ ድንቅ የተባሉ ጥበበኞች ዋልተር ግሮፒየስ ዘንድ ተሰባሰቡ። የአንደኛው የዓለም ጦርነት ያንኮታኮተውን አገር መልሶ ለመገንባት ይህ ስብስብ ቆርጦ ተነሳ። አገር 'በአዲስ መልክ ሥራ ጀምረናል!' እንዳለች ቁጠሩት። ባውሐውስ በጀርመኖች ዘንድ በሥነ ሕንጻና ዲዛይን የፈጠረው ተጽእኖ የትየለሌ ነው። ከዚህ ትምህርት ቤት የወጡ አዲስ ጽንሰ ሐሳብ መሞከር ያዙ። ለምሳሌ ቦታ የሚይዝ ሕንጻ ሳይሆን ቦታ የሚፈጥር ሕንጻ መገንባት ያዙ። ለምሳሌ ከፈትፈት ያሉና አንድ ሰው ቤቱ ወይም ቢሮው ውስጥ ሆኖ ደጅ ያለ ስሜት የሚፈጥሩ ኪነ ሕንጻዎች ያን ዘመን ነበር እየተለመዱ የመጡት። አሁንማ አውሮፓን ያጥለቀለቁት እነዚህ የኪነ ሕንጻ አሰራሮች ናቸው። በዚያ ዘመን ግን አዲስ ነበሩ። ለምሳሌ የሕንጻ ጣሪያ ሲሚንቶ ኮንክሪት የሚሞላ ጠፍጣፋ ሜዳ እየተደረገ መሠራት ተጀመረ። ከዚያ በፊት ሾጣጣ ነበር። የሕንጻዎች የፊት ገጽታ (Façade) ቀላልና ለዓይን ማራኪ ሆነው መገንባት ያዙ። የግንባታ የውስጥ ደረጃዎች ጥምዝ (spiral) መሆን ጀመሩ። ከፈትፈት ያሉ ብርሃን እንዲዘልቅ የሚያደርጉ የመስታወት ግድግዳዎች፣ በብርሃንና በጥላ ዙርያ ውብ ገጽታ መፍጠርና መጠበብ የባውሐውስ ኪነ ሕንጻ ፍልስፍና ያመጣው ነው። እንዴት እንዲህ ዓይነት የሥነ ጥበብ አብዮት ሊመጣ ቻለ ያልን እንደሆን አባት አርክቴክት ዋልተር ግሮፒየስን ማውሳት ይኖርብናል። አርክቴክት ግሮፒየስ በጀርመን የፈጠረው ባውሀውስ የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ሁሉም ተማሪዎች የሚወስዱት የወል ስልጠና አዘጋጀ፤ ይህን የወል ኮርስ ሳይወስዱ መመረቅ ቀረ። በዚያው ትምህርት ቤት አዲስ የቅርጻ ቅርጽና የዕደ ጥበብ ስልት በስዊዛዊው አርቲስት ዮሐንስ ኢትን ተነደፈ። ተማሪዎች ፈጠራን መሠረት አድርገው እንዲሰሩ መሠረት ተጣለ። ከዚያ ዘመን በኋላ በሥነ ጥበብ፣ በዕደ ጥበብ፣ በሥነ ሕንጻና በሌሎችም ፈጠራዎች ስለ ቀለም፣ ስለ ቅርጽ፣ ስለ ውበት መጨነቅ መጠበብ፣ መፈላሰፍ ባሕል እየሆነ መጣ። ቀይ፣ ቢጫና ሰማያዊ መደበኛ ቀለሞች፣ አራት ማዕዘን፣ ክብና ሦስት ማዕዘን ቅርጾች የፈጠራ መንሸራሸሪያ የባውሃውስ መለያ ሆኑ። ባውሃውስ በ1933 በሂትለር እስኪዘጋ ድረስ በመላው አውሮፓ ኪነ ሕንጻም ሆነ ሌሎች የሥነ ጥበብ ውጤቶች ላይ አሻራውን ጥሎ አልፏል። የጀርመኖች ቤትና ደጅ፣ አስተሳሰብና ድርጊት፣ ሁለመናቸውን ያሰመረውም ይኸው ትምህርት ቤት ነው ይባላል። ጀርመኖች መጽሐፍ፣ ቢራና ዳቦ እንደሚወዱት ሁሉ የባውሀውስ ጥበብንም ይወዳሉ ይባላል። ሥርዓት ማክበር እንዲሰርጽ ከ500 ዓመት በፊት የነበረው የማርቲን ሉተር አስተዋጽኦም አለበት 'ሥነ ሥርዓት ይከበር!' ማን የጀመረው ነው? ሉተር በነገረ መለኮት ጉዳዮች በጻፋቸው ጽሑፎች ሕዝብ ለመሪዎች ይታዘዝ ይላል። 'ሥነ ሥርዓት ይከበር!' በሚል የጻፈው ግን ማኅበረሰብን በቀጥታ የሚመለከት ሳይሆን የሰው ልጅ በግሉ ሥርዓት ሊያከብር የሚገባው ፍጡር ነው ብሎ ያምን ስለነበረ ነው። ከሉተር በኋላ ይሄ ሥነ ሥርዓት የሚለውን ሐረግ ዝነኛ ያደረገው ሰው የቫይማር ሪፐብሊክ የመጨረሻው ፕሬዝዳንት ፖል ቮን ሂደንበርግ ሳይሆን አይቀርም። በ1934 ዝነኛው የታይም መጽሔት ሂደንበርግን በሽፋኑ ሲያወጣው ከእርሱ ፎቶ ስር የተጻፈው "ሥነ ሥርዓት ይከበር!" የሚለው እውቅ አባባሉ ነበር። ይህም እሱንም አባባሉንም ዝነኛ አደረጋቸው። ክርስቲና ሮጀርስ የጀርመን ባሕል አጥኚና ተመራማሪ ናት። ይሄ ሥነ ሥርዓት በጥብቅ የማክበር ነገር ገና ድሮም የፕሩሲያ (የድሮዋ ጀርመን) ባሕል ነበር ትላለች። ግዴታን መወጣት፣ ቀጠሮን አለማዛነፍ፣ ሐቀኝነት እና ጠንካራ ሠራተኝነት ድሮም የጀመርኖች ሲወርድ ሲወራረድ የመጣ ባሕል ነው። ክርስቲና ይህን ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ የመጣን ሥነ ሥርዓት በተመለከተ ከጀርመኖች ጋር የቢዝነስ ሽርክና ለሚጀምሩ የሌላ አገር ዜጎችና ትልልቅ ኩባንያዎች ታማክራለች። ምክንያቱም ጀርመኖች ስንፍናን ላይታገሱ፣ ቸልተኝነትና እንዝህላልነት ቶሎ ሊያስቆጣቸው የሚችሉ ሕዝቦች ስለሆኑ ነው። ይህ 'ሥርዓት ይከበር!' የሚለው ነገር ከየትም ይነሳ የት፣ ማንም ይጀምረው ማን፤ ዛሬ በጀርመኖች ደም ውስጥ የተቀበረ ጥብቅ ባሕል እንደሆነ ግን አያጠራጥርም። ደስ የሚለው ነገር የዛሬዎቹ ጀርመኖች ስለ ሥነ ሥርዓት ሲያወሩ አይሰሙም። ውስጥ ውስጡን ተግባብተው ጨርሰዋልና። ይኖሩታል አንጂ አያወሩትም። የጀርመን ባሕል አጥኚዋ ክርስቲን ይህ ሥርዓት አክባሪነት ለጀርመን ልጆች "በውሃ ቧንቧቸው በኩል የሚመጣላቸው የላም ወተት ነው" ስትል ትቀልዳለች። ሥነ ሥርዓት ማክበርን ሁሉም የጀመርን ሕጻናት ገና ጨቅላ እያሉ ክፍላቸውን ከማጽዳት ይጀምራሉ። እቃ እቃ መጫወቻዎቻቸውን በሥነ ሥርዓት በማስቀመጥ ይቀጥላል። በዚያው የሕይወት ዘይቤያቸው ሆኖ ያድጋሉ። ክርስቲን ነገሩን ስታጠቃልለው እንዲህ ትላለች። "አንድ ሰው ሲናገር የቋንቋ ሰዋሰውን እያሰበ እንደማይናገረው ሁሉ ጀርመኖች ደንብና ሥርዓት ያከብራሉ እንጂ ስለ ደንብና ሥርዓት አያወሩም።" ሁሉ ነገር በሥርዓት እንዲሆን ደንብ አስከባሪዎች ይቆጣጠራሉ ሁሉ ነገር ከሥርዓት መከበር ጋር ይያያዛል ጀርመናዊያን የተረበሻችሁ መስሎ ከታየው "Alles in Ordnung?" ይሏችኋል፤ በጀርመን አፍ። ምን ማለት ነው? የአባባሉ መንፈስ ወደ እኛ ሲተረጎም "አማን ነው? ሁሉ ሰላም?" እንደምንለው ዓይነት መሆኑ ነው። ነገር ግን የጀርመንኛው አባባል ቃል በቃል ስንፈታው "ሥነ ሥርዓት ተከብሯል?" እንደማለት ነው። አባባሉ አስቂኝ ይመስላል። ከአስቂኝነቱ ባሻገር ግን የሚነግረን አንድ ቁም ነገር አለ። ለዚያ ሕዝብ "ሥነ ሥርዓት" የሚለው ቃል በቋንቋው ውስጥ ጭምር በምን ያህል ጠልቆ እንደገባ ነው። ይኸው ቃል በጀርመን የደንብ ተቆጣጣሪዎች የደንብ ልብስም ላይ ተጽፏል። ኦርድኖንግስአምት (Ordnungsamt) የሚባሉት የጀርመን የማኅበረሰብ ደንብ አስከባሪ ቢሮ መኮንኖች ናቸው። የእነዚህ መኮንኖች ሥራ ሥርዓት ማስከበር ነው። ለምሳሌ አንድ የመኖሪያ ህንጻ ላይ ሙዚቃ የሚያስደልቅ ረባሽ ካለ የቅጣት ትኬት ይቆርጡለታል። እንዲሁም መኪና ማቆሚያ ውስጥ መኪናውን በአግባቡ ያላቆመውን ዋጋውን ይሰጡታል። በጀርመን ውሻ ራሱ ስንት ጊዜ መጮኸ እንዳለበት ተደንግጓል ብትባሉ ታምናላችሁ? ጸጥታ መስፈን ባለበት ሰዓት በአንድ ጊዜ የእርስዎ ውሻ ከአስር ጊዜ በላይ ከጮኸ ጉድ ፈላ! ይህ ማለት ግን ጀርመን ውስጥ ዝንፈት የለም ማለት ነው እንዴ? በፍጹም። በመንገድ ላይ የተቀመጡ የቆሻሻ ቅርጫቶችን በጠረባ የሚያጎናቸው ሰካራም ጀርመናዊ መቼም አይጠፋም። ስካሩ ሲለቀው ግን "ሥነ ሥርዓት ይከበር!" እያለ ሊጮኽ ይችላል።
xlsum_amharic-train-119
https://www.bbc.com/amharic/47493179
ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን የኃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
[ "የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን የኃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።" ]
ዘገባውም እንደሚያስረዳው ጥያቄውን ያቀረቡት እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው። •የብአዴን መግለጫ፡- ከስያሜ መቀየር እስከ ኢትዮ ሱዳን ድንበር ፓርቲያቸው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የርዕሰ መስተዳድሩን ጥያቄ የተቀበለው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ምክንያታቸውንም ፓርቲያቸው ለክልሉ ምክር ቤት ያቀርባል። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለአምስት አመታት ያህል ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል። በምትካቸውም ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾመዋል።
xlsum_amharic-train-120
https://www.bbc.com/amharic/news-47944536
በኢንተርኔት የፍቅር ጓደኛ ለማግኘት የሚረዱ ሰባት ነጥቦች
የከንፈር ወዳጅ አሊያም ውሃ አጣጫችን በተለያዩ አጋጣሚዎች አግኝተን ይሆናል። ሰዎች የሕይወታቸውን ሕይወት ለመፈለግ የተለያዩ ዘዴዎችን ሲጠቀሙ ማየቱም የተለመደ ነው። ቴክኖሎጂ በዘመነበት በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የፍቅር ጓደኞቻቸውን ለመፈለግ ኢንተርኔትን እንደሚጠቀሙ ታውቋል።
[ "የከንፈር ወዳጅ አሊያም ውሃ አጣጫችን በተለያዩ አጋጣሚዎች አግኝተን ይሆናል። ሰዎች የሕይወታቸውን ሕይወት ለመፈለግ የተለያዩ ዘዴዎችን ሲጠቀሙ ማየቱም የተለመደ ነው። ቴክኖሎጂ በዘመነበት በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የፍቅር ጓደኞቻቸውን ለመፈለግ ኢንተርኔትን እንደሚጠቀሙ ታውቋል።" ]
የፍቅር ጓደኛ ለማግኘት የሚያስችለውን መተግበሪያ መጠቀም ጥሩ ነው፤ ነገርግን የፍቅር ጓደኛ በመፈለጋችሁ ደስተኛ መሆናችሁንም እርግጠኛ መሆን አለባችሁ በኢንተርኔት የሚደረጉ የፍቅር ግንኙነት መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዓለማችን 91 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የፍቅር ጓደኛ ለመፈለግ የሚያስችሉ መተግበሪያዎችን ይጠቀማሉ፤ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ግንኙነቱ እንዲቀጥል ሲያደርጉ አይታዩም። በእንግሊዝ ዩ ጎቭ በተሰኘ የህዝብ አስተያየትና የመረጃ ካምፓኒ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት ምንም እንኳን 10 በመቶ የሚሆነው የእንግሊዝ ነዋሪ የፍቅር ጓደኛ መፈለጊያ መተግበሪያዎችን ቢጠቀምም አብረው የሚዘልቁት ከግማሽ የሚያንሱት ናቸው። • የጂግጂጋ ነዋሪ ጥንዶች ስጋት ላይ ነን እያሉ ነው • ሶሻል ሚድያ በተጠቃሚዎች ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ? • ፍቅር እና ግንኙነት ከቲንደር አብዮት በኋላ በሱሴክስ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁርና የፍቅር ጓደኝነት አማካሪ የሆኑት ዞ ሰትሪምፔል እውነተኛ የፍቅር ጓደኛችንን ለመፈለግ የሚረዱ ሰባት ነጥቦችን አስቀምጠዋል 1.ወዳችሁና ፈቅዳችሁ እንጂ ተገዳችሁ በግንኙነት ውስጥ አትቆዩ፡ የተዋወቃችሁትን የፍቅር ጓደኛ ካልወደዳችሁትና እንዳልወደዳችሁት ከተሰማችሁ መቀጠሉ አስፈላጊ አይደለም። ያንን ሰው ካልወደዳችሁት ዳግም አታግኙት። እስኪ ልየው/ልያት እያሉ መሞከር አስቸጋሪ ነው፤ አንዳንዴ ስሜታችንን ይጎዳል። ስለ ራሳችን አሊያም ለሌሎች ያለን አመለካከትንም አሉታዊ እንዲሆን ያደርጉታል። 2. ልባችንን እንከተል፡ ስሜቱን ካልተጋራችሁት አሊያም ግንኙነቱን ካልወደዳችሁት ተዉት። ግንኙነቱን ለማቆም ከወሰናችሁ ወዲያ ወለም ዘለም አትበሉ። ምንም እንኳን የእኔ ጥፋት ሊሆን ይችላል ብለን ልናስብ እንችላለን፤ ነገር ግን የዚያኛው ሰውም ስህተት ሊሆን ይችላል። 3. መልዕክቶችን ወደ መለዋወጥ ከተሻገራችሁ፤ ጥቂት መልዕክቶች ብዙ እንደሆኑ አስቡ፡ ብዙ ጊዜ በብዛትና በተደጋጋሚ መልዕክት የሚልክልን ሰው ስለ እኛ ያሰበ ሊመስለን ይችላል። ነገር ግን ስለ ብዛቱ ሳይሆን ስለ ጥራቱ ተጨነቁ። ከብዙ ያልረቡ የሃሳብ ልውውጦች ጥቂት ጥሩ የሃሳብ ልውውጦች መልካም ስሜት እንዲሰማችሁ ያደርጋል። በአንድ ጊዜ ከ100 ሰዎች ጋር ልናወራ እንችላለን፤ ነገር ግን ከመረጣችሁትና ከወደዳችሁት ሰው ጋር ብቻ አውሩ። ወደፊት አብሯችሁ ሊዘልቅ ከሚችል ሰው ጋር ማውራቱ የተሻለ ነው። 4. ፍቅረኛ መፈለግ የቁጥር ጨዋታ ነው፤ በመሆኑም በርካታ ሰዎች ያሉበትን ምረጡ፡ ብቻውን በበርሃ ውስጥ እንዳለ ሰው ከመሆን ይልቅ በብዙ ሰዎች ተከበቡ። ከዚያም አንዱን መርጣችሁ ከእርሱ ጋር በፍቅር የመውደቅ እድል ይኖራችኋል። በመሆኑም አልማዙን ለማግኘት አፈሩን ማግኘት አለባችሁ። አቋራጭ መንገድም የለም። 5.መጀመሪያ ተራ ጓደኝነትን ማሰብ፡ ስለ ፍቅር ጓደኝነት ስናስብ መጀመሪያ ስለ ጓደኝነት ማሰብ ግድ ይላል። በጓደኝነት የተጀመረ ግንኙነት መጨረሻውም ያማረ ይሆናል ፤ ወደ የህይወት አጋርነት የመቀየር አዝማሚያው ሰፊ ነው። • ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች 6. ደረቅ አትሁኑ፡ ምን እንደሚማርካችሁና እንደማይማርካችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ። ይሁን እንጂ 'ከዋክብቶችን ስትቆጥር ጨረቃውን ታጣለህ' እንደሚባለው ምርጫችሁን በጣም ካጠባባችሁት እናንተን አጥብቆ የሚፈልገውን ሰው ልታጡት ትችላላችሁ። ውሃ አጣጭን በሂሳብ ስሌት ማግኘት አይቻልምና። 7. ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባችሁ አትዘንጉ በተለይ በድረ ገፅ የሚመሰረቱ ግንኙነቶች ደስታን ሊሰጧችሁ ይችላሉ፤ ነገር ግን ምርምርና ጥንቃቄ ማድረጋችሁን ማቆም የለባችሁም። በጥርጣሬና በጥንቃቄ ነገሮችን መከታታል ያስፈልጋል። በአብዛኛው የበይነ መረብ የፍቅር ጓደኛ መተግበሪያዎች ችግር የምትመርጡትን ሰው እንጂ የእርሱን ጓደኛ አሊያም ዘመድ አዝማድ የማወቅ እድሉ አይኖርም። የጋራ ጓደኛ ስለማይኖር ስለዛ ሰው ማንነት ከሌላ ወገን ለመስማትና ለማወቅ እድል አይሰጥም።
xlsum_amharic-train-121
https://www.bbc.com/amharic/news-56474381
የአሊባባው ጃክ ማ ለሦስት ወራት ከዕይታ የጠፉት ለምንድን ነው?
ጃክ ማ በቻይና ሃብታሙ ግለሰብ ለመሆን ተቃርበው ነበር፡፡
[ "ጃክ ማ በቻይና ሃብታሙ ግለሰብ ለመሆን ተቃርበው ነበር፡፡" ]
በጎርጎሮሳዊያኑ ህዳር 2020 ለሌላ የንግድ ሥራ ስኬት ደፋ ቀና በሚሉበት ዋዜማ ሃሳባቸውን በግልጽ የሚናገሩት ቢሊየነር በድንገት ጠፉ። ኩባንያቸው አሊባባ መኖሪያ ቤት ውስጥ ከሚሠራ የድረ ገጽ መደብርነት ተነስቶ በዓለም ግዙፉ ቴክኖሎጂ ለመሆን በቅቷል፡፡ ዛሬ በድረ ገጽ ግብይት፣ ክላውድ ኮምፒውቲንግ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች ወደ 800 ሚሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎችን ደርሷል፡፡ ተጽዕኖ ፈጣሪው እና ሃብታሙ የቴክኖሎጂው ሰው በደማቅ መድረኮች በመገኘት እና በማስተዋወቅ ይታወቃሉ፡፡ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸው 'ፓርቲ' ይደግሳሉ። 'You Raise Me Up' ያሉ ሙዚቃዎችንም ይጫወታሉ፡፡ አዲሱ ኩባንያቸው አንት ግሩፕ በቻይና ያለውን የዲጂታል ክፍያን በአሊፔይ የሞባይል ፋይናንስ መተግበሪያ በኩል ይመራል፡፡ አወዛጋቢ ንግግር ኩባንያው በቻይና የሚገኙ ባንኮችን በማዘመን ያላቸውን ኃይልን ከእነዚህ ነባር ተቋማት ለማሸጋገር ዓላማ አድርጎ ተነስቷል። ጥቅምት 24 ቀን በሻንግሃይ ውስጥ አንት ግሩፕ በዓለም ላይ ትልቁን የአክሲዮን ድርሻ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ለማቅረብ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም ብሎ ግን ማ በቻይና የገንዘብ ስርዓት ላይ ትችት የሰነዘሩበትን አከራካሪ ንግግር የታወቁ ሰዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ አደረጉ፡፡ እስከ ጥር መጨረሻ ድረስም እንደገና በአደባባይ አልታዩም፡፡ ምናልባትም በቤት ውስጥ እስራት ወይም በሌላ መንገድ ተይዘው ሊሆን ይችላል የሚሉ ወሬዎች ነበሩ፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም በሕይወት ስለመኖራቸው ጠይቀዋል። ከላይ ነው ትዕዛዙ ሁለት ተከታታይ ክፍሎች ያሉት እና እውነተኛዎቹ የኢንተርኔት ኃያላን 'The Real Internet Giants' በሚል ርዕስ የማ ታሪክ በቢቢሲ ራዲዮ 4 በሥራ ፈጣሪዋ ካትሪን ፓርሰንስ ቀርቧል፡፡ የአሊባባው መስራች የቻይና ባንኮችን "በተለመደው አስተሳሰብ" የሚንቀሳቀሱ ሲሉ ይከሳሉ፡፡ በተጨማሪም ባለሥልጣኖቹ አዲሱን የዲጂታል ፋይናንስ ዓለምን ለመቆጣጠር "የአውሮፕላን ማረፊያውን ለማስተዳደር የባቡር ጣቢያውን አስተዳደር ዘዴ ለመጠቀም እየሞከሩ ነው" ብለዋል። ባንክ ሌላ ዲጂታል ፋይናንስ ሌላ እንደማለት። መግለጫዎቹ ባንኮቹን አስቆጥቷል። ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግም ሰምተውታል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ማ እና የቅርብ የሥራ ባልደረቦቻቸው ከተቆጣጣሪ አካላት ጋር ለመገናኘት ተጠሩ። የአንት ግሩፕ ወደ አክሲዮን ገበያ መግባትም ከግብ ሳይደርስ ቆመ፡፡ የማ ኩባንያዎች የአክሲዮን ዋጋም ወደቀ። ወደ 76 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጡ፡፡ ከዚያ ስብሰባ በኋላም ጃክ ማ ከዕይታ ተሰወሩ፡፡ 'ቀዩን መስመር አለፈ' "በዚያ ቀን በዢ ጂንፒንግ ቻይና ሊባል እና ሊደረግ ከሚችለው በላይ በመሄድ ቀዩ መስመር አልፏል" ሲሉ ቀደም ሲል ከማ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የቻይና ተንታኝ ክሪስቲና ቡትረፕ ገልጸዋል። "ለእሱ አስገራሚ ነገር ነው ብዬ አምናለሁ። ምን ያህል መጥፎ ሊሆን እንደሚችል ቢያውቅ ኖሮ ያንን መስመር ባልተሻገረ ነበር፡፡" ጥር 20 ቀን 2021 ማ በአንድ በጎ አድራጎት ዝግጅት ላይ አጠር ባለች የቪዲዮ መልዕክት እንደገና ታዩ፡፡ በሚቀጥለው ወርም በቻይና ሃይናን ደሴት ጎልፍ ሲጫወት ድጋሚ ታዩ፡፡ "በግልጽ እንደሚታየው በጣም ዝቅ ባለ ሁኔታ ነው የታየው። በእውነቱ ሊያደርገው ከሚችለው በጣም ጥሩው ነገር ነው" ብለዋል ቡትረፕ፡፡ ሰፊው የቴክኖሎጂ ዘርፍ የቻይና መንግስት ግዙፍ ቴክኖሎጂዎችን የመቆጣጠር አካሄድን እንደገና እያጤነ ነው፡፡ በአሊባባ በበላይነት ገበያው ስለመቆጣጠሩ (ሞኖፖል) ለማጣራት ምርመራ ጀምሯል። ባለፈው ሳምንት ቴናሴት እና ባይዱን ጨምሮ በ12 ኩባንያዎች 10 ስምምነቶች ላይ የፀረ ሞኖፖል ደንቦችን ይጥሳሉ በማለት ቅጣት አስተላልፏል፡፡ ይህም በሰፊው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ውስጥ አለመግባባቶች መባባሳቸውን ሊያመላክት ይችላል፡፡ ቻይና በሆንግ ኮንግ እና በዢንጂያንግ የሰብአዊ መብት ፖሊሲዎቿን በተመለከተ ከአሜሪካ እና ከተቀረው ዓለም ጫና እየደረሰባት ይገኛል፡፡ በቴክኖሎጂ ኃያላን የተወሰደው እርምጃ መረጋጋትን ለማስቀደም እና የንግዱን ስኬት ለመቆጣጠር የተደረገ ጥረት እንደሆነ ይታያል፡፡ "... ፓርቲው እንደ ጃክ ማ ባሉና ተሰሚነት ባላቸው ግለሰቦች ላይ እንኳን ስልጣን እንዳለው ኩባንያዎቹን ለማስታወስ የሚፈልጉ [የኮሚኒስት] ፓርቲ ኮሚቴዎች አሉ" ብለዋል በአውስትራሊያ ስትራቴጂክ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ሳማንታ ሆፍማን፡፡ ይህ ቁጥጥር እስከ ምስጢራዊነት ይደርሳልም ይላሉ፡፡ "ፓርቲው የሚጠይቀውን ለመፈፀም ኃላፊነት ያለበት ኩባንያው ብቻ ሳይሆን ከተጠየቀም ያንን ስለማድረጉ አይስማማም፡፡" ሌላ ባለሙያ እንደሚጠቁሙት ግን አሊባባ እና ሌሎች ግዙፍ የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በምዕራቡ ዓለም በፖለቲካ መነፅር ብቻ መታየት የለባቸውም፡፡ "ቻይና አሁንም ታዳጊ አገር ነች… በታዳጊ አገር ላይ ካደጉት አገራት ጋር ተመሳሳይ መመዘኛዎችንና ብቃቶችን በመውሰድ መፍረድ አግባብነት የጎደለው ይመስለኛል" ብለዋል የታዋቂው የቻይና የቴክኖሎጂ ዜና መጽሔት ቻይኒዝ ካራክተርስቲክስ ጸሐፊ ሊሊያን ሊ፡፡
xlsum_amharic-train-122
https://www.bbc.com/amharic/50832946
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሊያድኑት የነበረው ለገሰ ወጊ ማን ነበረ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከ11 ዓመት በፊት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የምዕራብ ዕዝ መሪ በነበረው ለገሰ ወጊ ላይ መንግሥት ሊፈጽም አቅዶት የነበረውን ጥቃት በተመለከተ ለግንባሩ አመራር መረጃ አቀብለው እንደነበር ከተሰማ ሰነባብቷል።
[ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከ11 ዓመት በፊት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የምዕራብ ዕዝ መሪ በነበረው ለገሰ ወጊ ላይ መንግሥት ሊፈጽም አቅዶት የነበረውን ጥቃት በተመለከተ ለግንባሩ አመራር መረጃ አቀብለው እንደነበር ከተሰማ ሰነባብቷል።" ]
ኦነግም በወቅቱ ባወጣው መግለጫ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ከጥቃቱ ቀደም ብለው በግንባሩ የጦር መሪ ላይ ሊፈጸም ስለታቀደው ጥቃት መረጃ በውጪ ለሚገኙት አመራሮች መስጠታቸውን አረጋግጧል። • ከ10 ዓመት በፊት ጠ/ሚ ዐብይ መረጃ አቀብለውት እንደነበር ኦነግ ገለጸ • በምዕራብ ኦሮሚያ በ12 ወራት ቢያንስ 8 የአካባቢው ባለስልጣናት ተገድለዋል ለገሰ ወጊ የተገደለው ከ10 ዓመት በፊት ሲሆን ግድያው እንዴት እንደተፈጸመ በጊዜው ዘጋቢ ፊልም ተዘጋጅቶ በመንግሥት መገናኛ ብዙኀን ተላልፎ እንደነበር ይታወሳል። ለመሆኑ ለገሰ ወጊ ማን ነው? ስንል ቤተሰቡን ጠይቀናል። የለገሰ ወጊ ውልደትና ዕድገት በ1960 የተወለደው ለገሰ ወጊ፤ በአሁኑ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሺኖ ወረዳ ኩዩ ጊጪ ቀበሌ ገበሬ ማህበር መወለዱን ባለቤታቱ ወ/ሮ ወይንሸትና ታላቅ ወንድሙ አቶ በቀለ ወጊ ይናገራሉ። ለገሰ ወጊ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በተወለደበት አካባቢና ኢንጪኒ ውስጥ የተማረ ሲሆን 11ኛ ክፍልን ለመማር ደግሞ ወደ አዲስ አበባ መጣ። ለገሰ የ11ኛ ክፍል ትምህርቱን በማቋረጥ በ1970ዎቹ ውስጥ በመካኒክነት ሙያ ሰልጥኖ ወደ ሥራ ተሰማርቶ ነበር። ከመካኒክነት በተጨማሪ ወደ ድሬዳዋና ሌሎች ከተሞች በመንቀሳቀስ ጨርቃ ጨርቅና ሸቀጣ ሸቀጣ በማምጣት ይሸጥ እንደነበር ወ/ሮ ወይንሸት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወደ ትጥቅ ትግል እንዴት ገባ? የለገሰ ወጊ ባለቤት ወ/ሮ ወይንሸት ጌታሁን አሁን ከልጆቻቸው ጋር ኑሯቸውን በኖርዌይ አድርገዋል። ከለገሰ ጋር ከድሬዳዋ አዲስ አበባ እየተመላለሰ በሚነግድበት ወቅት ነበር ትዳር የመሰረቱት። ወ/ሮ ወይንሸት ውልደታቸውም ሆነ እድገታቸው አዲስ አበባ፣ አዲስ ከተማ ነው። ከትዳር አጋራቸውም ሦስት ልጆችን ማፍራታቸውን ይናገራሉ። • የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በዋጋ የሚያንራቸው ምርቶች ለገሰ ወጊ ለነጻነት የነበረው ከፍተኛ ስሜት በልጆቹ መጠሪያ ስም ላይ ይንጸባረቃል። የመጀመሪያ ልጁን በኦሮምኛ 'ቢሊሱማ' ብሎ ከሰየመ በኋላ ሦስተኛ ልጃን ደግሞ በአማርኛ 'ነጻነት' ሲል ተመሳሳይ ትርጉም ያለው ስም ሰጥቷል። ለገሰና ባለቤቱ ትዳር ከመሰረቱ በኋላ ኑሯቸውን ያደረጉት እዚያው አዲስ ከተማ ነበር። ለገሰ የሚያስበውን ነገር መፈፀም የሚፈልግ ሰው እንደነበር ታላቅ ወንድሙም ሆኑ ባለቤታቱ ይናገራሉ። ለገሰ ወጊ ሁለተኛ ልጁ [ፍሬህይወት] ተወልዳ ጡት ሳትጥል ሦስተኛ ልጁ ተረግዛ እያለ ነው ወደ ትግል ያቀናው። ቤት ውስጥ አብረው ሳሉ በሀገሪቱ ውስጥ ስለሚካሄደው ጉዳይ በማንሳት ያወራ ነበር ሲሉ የሚያስታውሱት ወ/ሮ ወይንሸት፤ "አልፎ አልፎ ወደ ትግል መግባትም እንዳለበት ይነግረኝ ነበር" ብለዋል። 1982 ታህሳስ 23 ከቤት ወጣ። ያኔ ታዲያ ባለቤታቱ ወ/ሮ ወይንሸት ለገሰ ወደ ወለጋ ንግድ ጀምሮ ስለነበር ወደዚያው እንደሄደ ነበር የሚያውቁት። ከሳምንት በኋላ ለገና እመጣለሁ ስላለ ቤት ያፈራውን አዘገጃጅተው መጠበቃቸውንም ያስታውሳሉ። ለገሰ ባሉት ቀን ብቅ ሳይል ቀረ። መጥፋቱም በሚያውቁት ሰዎችና በቤተሰቡ መካከል በስፋት ተወራ። ይጓዝበት የነበረው መኪና ተመትቷል የሚሉ ወሬዎች ይሰሙም ነበር። በወላጆቹና በባለቤቱ መካከል ጭንቀት ነገሰ። እናትና አባቱ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ፎቶውን በመያዝ ወደ ወለጋ ለፍለጋ ሄዱ። ለሁለት ወር ያህል ፈለጉት፤ ሊያገኙት ግን አልቻሉም። • አል-ሲሲ በአባይ ጉዳይ ጦርነት መፍትሄ አይሆንም አሉ ወ/ሮ ወይንሸት ሦስተኛ ልጃቸውን ወልደው አራስ ቤት ሳሉ ለገሠ ለባለቤቱ በአንድ ወጣት በኩል የእጁን ሰዓትና ደብዳቤ ላከላት። ደብዳቤው ወደ ትግል መቀላቀሉን የሚገልጽ ነበር። "ወደ ትግል ገብቻለሁ፤ ፈጣሪ ፈቃዱ ከሆነ በድል እንመለሳለን። በጸሎትሽ አስቢኝ" የሚለው ይህ ደብዳቤ ስለ ቤተሰብ ደህንነት ስለልጆቻቸውና ስለራሱ ካወራ በኋላ "የሚወለደው ልጅ ወንድም ሆነ ሴት 'ነጻነት' ብለሽ ሰይሚልኝ" የሚል ተማጽኖን ያዘለም እንደነበር ባለቤታቱ ወ/ሮ ወይንሸት ያስታውሳሉ። ከዚያ በኋላ አልፎ አልፎ ደብዳቤ ይልክ ስልክም ይደውል ነበር የሚሉት ቤተሰቦቹ ለረዥም ጊዜ ድምጹ ጠፋባቸው፤ ቤተሰብም ተስፋ ቆረጠ። "የሚወለደው ልጅ ወንድም ሆነ ሴት 'ነጻነት' ብለሽ ሰይሚልኝ ከ16 ዓመት በኋላ ስልክ... ለገሰ ወጊ በትጥቅ ትግል ውስጥ በተለያዩ ደረጃዎች ውስጥ ማለፉን የድርጅቱ መረጃ ያሳያል። ከተራ አባልነት ተነስቶ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የምዕራብ ዕዝ ጦር አመራር እስከ መሆን ደርሶ ነበር። ደርግ ከስልጣን ሲወገድ ለገሰ ገና የኦነግ ካድሬ የነበረ ሲሆን ኦነግ ከሽግግር መንግሥቱ ከወጣ በኋላ በቀጥታ ወደ ትጥቅ ትግል መግባቱ ይነገራል። በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በምዕራብ ኦሮሚያ ከመንግሥት ወታደሮች ጋር ከሚካሄዱ ውጊያዎች ጋር ተያይዞ የለገሰ ስም በተደጋጋሚ ይነሳ ነበር። • የዩኒቨርስቲ መምህርቷ ሞዴል፡ "ውበት ባመኑበት ነገር ጠንክሮ መሥራት ነው" ለወ/ሮ ወይንሸት አቶ ለገሰ አሉበት ከሚባለው አካባቢ መጣን የሚሉ ሰዎች ደህንነቱን እየነገሯቸው በደብዳቤም ሆነ በስልክ ሳይገናኙ ዓመታት አለፉ። በኋላ ግን ድንገት ስልክ ደወለ። ወ/ሮ ወይንሸት "ለገሰ አዲስ አበባ ከሚገኘው ቤቱ በወጣ በ16 ዓመቱ ስልክ ደወለ" ይላሉ። ቤተሰብም ተደሰተ። ልጆቹ አድገዋል፣ ጡት የሚጠቡት ትምህርት ቤት ከገቡ ከርመዋል። የሚታዘሉት በእግራቸው መሄድ ከጀመሩ ቆይተዋል። ልጆቹ የአባታቸውን መልክ፣ ድምጽ እንዲሁም ጣዕም ፈጽሞ አያውቁም። የመጀመሪያ ልጁ ቢለሱማ "ትንሽ ትንሽ ብቻ አስታውሰው ነበር" ትላለች። "ከዚያ በኋላ በሳምንትም በ15 ቀንም ይደውል ነበር" ይላሉ ወ/ሮ ወይንሸት። በስልክ ስለቤተሰብ ስለልጆች ከማውራት ባሻገር ትግል ላይ መሆኑን ብቻ ይነግራቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ልጆች አባታቸውን ሲናፍቁ 'መቼ ነው የምትመጣው?' ብለው ሲጠይቁ የለገሰ መልስ ሁሌም ተመሳሳይ ነው፤ "እመጣለሁ ብሎ ሸንግሎን አያውቅም" ትላለች ቢሊሱማ። ልጆች እንዲመጣ ይወተውታሉ፤ በስልክ ላይ ያለቅሱ እንደነበርም ያስታውሳሉ። ለልጆቻቸው "የሕዝብ አደራ ተቀብሎ ስለወጣ መምጣት አንደማልችል ንገሪያቸው" ይል እንደነበር ያክላሉ። ወ/ሮ ወይንሸት "ልጆቼን ባህላቸውን አስተምረው እንዲያሳድጓቸው ለኦሮሞ ሕዝብ አደራ ሰጥቻለሁ፤ ለፈጣሪ አደራ ሰጥቻለሁ" ይል እንደነበር ይናገራሉ። አንድ ቀን አቶ ለገሰ ደወለ። ልጆች ስልኩን ከበው እናት ሲያዋሩ፣ ፍሬሕይወት ወረቀትና እስክቢርቶ ይዛ እንድትመጣ እንደነገሯት ቤተሰቡ ያስታውሳል። "ይህንን ቀን ወሩንና ዓመተ ምህረቱን ጽፋችሁ በሚገባ ያዙ፤ ታሪክ በጊዜው ራሱ ያወጣዋል" ብለው ቀንና ዓመተ ምህረት አጻፏቸው። ፍሬሕይወት ቀኑንም ዓመተ ምህረቱንም በሚገባ ብትጽፍም ጊዜ ጊዜን እየወለደ ሲመጣ ቀኑም ተረሳ፤ የተጻፈውም ወረቀትም ጠፋ። እናም ዛሬ ድረስ ያቺ ቀን ምን የተፈጠረባት እንደሆነች ለማወቅ እንደጓጉ አሉ። • መንግሥት አደገኛ የሆነውን የትግራይን መገለል መለስ ብሎ ሊያጤነው ይገባል- ክራይስስ ግሩፕ ይኼኔ ደግሞ ቢልሱማ ድንገት ተነስታ ሱዳን ገባች። ሱዳን እያለች ኤርትራ ያሉ የኦነግ አመራሮችን ስልክ አፈላልጋ በመደወል መልዕክት ትልክ ጀመር። በእነርሱ በኩል ያለችበትን ያወቀው ከአባቷ ጋር ከሱዳን ሊቢያ ከተሻገረችም በኋላ፣ ጣሊያን ገብታም ይደዋወሉ እንደነበር ታስታውሳለች። ለገሰ ዘወትር ተእንደሚያደርገው ለቤተሰቦቹ አዲስ አበባ ስልክ ደውሎ ከትግሉ ስፍራ እንዲወጣ እንደተነገረው ወ/ሮ ወይንሸት ያስታውሳሉ። ነገር ግን ትዕዛዙን ተቀብሎ ለመውጣት አሻፈረኝ እንዳለ ይነገራል። ለምን ሲባልም ከጠባቂዎቹ ጋር እየወጡ ሳለ በሰማይም በምድርም ጥይት እየዘነበባቸው በርካቶች መሰዋታቸውን እንደገለጸላቸው ያስታውሳሉ። ከተረፉት ጠባቂዎቹ ጋር ወደ ምሽግ ከተመለሰ በኋላም "ፈጣሪ ነፍሴን ለመቼ እንዳቆያት አላውቅም" ማለቱን የሚናገሩት ወ/ሮ ወይንሸት ይህንን ያላቸው በሐምሌ ወር ውስጥ እንደሆነ ያስታውሳሉ። ከዚህ በኋላም የስልክም ሆነ የደብዳቤ መልዕክት መቋረጡን ይናገራሉ። ቢሉሱማ ግን አባቷ ከመገደሉ ከ15 ቀን ቀደም ብሎ ማውራታቸውን ትናገራለች። ያኔ ሁሌም ሐሙስ ሐሙስ እናወራ ነበር የምትለው ቢልሱማ ለምን እንደማይመጣ በጠየቀችው ቁጥር "እናንተን ለኦሮሞ ሕዝብ ሰጥቻለሁ፤ የሕዝብ አደራ ትቼ መምጣት አልችልም" ይሉ አንደነበር ታስታውሳለች። የለገሰ ወጊ መገደል ጥቅምት 26 2001 ዓ.ም ለሊቱን ተገድሎ ጥቅምት 27 2001 ዓ.ም ማታ ዜና ላይ መገደሉ ተናገረ። እርሳቸው ቤታቸው ውስጥ ብዙ ጊዜ ቴሌቪዥን ከፍተው እንደማያዩ የተናገሩት ወ/ሮ ወይንሸት ጎረቤት የሞቱን ዜና አረዳቸው። ወዲያውም ቴሌቪዥን ሲከፍቱ የእለቱ ዜና አንባቢ የባለቤታቸው ምስል እየታየ የሞቱ ዜና ይናገራል። "ማልቀስም አልቻልንም" ይላሉ ወ/ሮ ወይንሸት። ከዚህ በኋላ የነበረው ስሜት ከባድ አንደነበር፣ ሲያስታውሱት እንኳ የሚረብሻቸው መሆንን ያስረዳሉ። "በአጭር ቃል አልቅሶ እርም ማውጣት ከባድ ሆነ" ይላሉ። በማህበራዊ ህይወትም ፈተና ውስጥ ወደቁ። አንገታቸውን ቀና አድርገው መሄድ ከበዳቸው። • ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ በወቅቱ ስለለገሰ ወጊ መገደል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተነገረውን መረጃ እውነትነት የኦነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ቦረን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በወቅቱ የመንግሥት መግለጫ ለገሰ በአካባቢው ገበሬ መገደሉን የተናገረ ቢሆንም፤ አቶ ሚካኤል ግን የተገደለው በመንግሥት ወታደሮች በተወሰደበት እርምጃ መሆኑንና "ገበሬው ከጎናችን ነበር" ሲሉ ያስተባብላሉ። "ለገሰ በተለያዩ ጊዜ በተፈጸመበት ጥቃት ብቻውን ቀርቶ ነው ሰው ቤት የገባው" ይላሉ አቶ ሚካኤል ሁኔታውን ሲያስታውሱ። አብረውት በተለያየ ጦርነት ላይ እንደተሳተፉ የሚናገሩት አቶ ሚካኤል፤ ለገሰ ጎበዝ ታጋይ እንደነበር ይመሰክራሉ። ተዋግቶ የሚያዋጋ ነበር በማለትም "እንኳን በሕዝብና በደጋፊዎቹ በጠላቶቹም በትልቅነቱ ይታወቃል" ብለዋል። ወ/ሮ ወይንሸት ባለቤታቸው ሽፍታ እየተባለ፣ እንደ አጥፊ እየታየ ልጆቻቸውን ባሳደጉበት አዲስ ከተማ መኖር ከባድ ሆነባቸው። በዚህም ምክንያት በብዛት ቤተክርስቲያን ማሳለፍና ብቸኝነት አጠቃቸው። ፖሊስ ቤታቸው ላይ ብርበራ አካሄደ። እርሳቸውንም ልጃቸውንም አቅራቢያ ፖሊስ ጣቢያ ወስዶ አሰራቸው። የቤታቸው ስልክ ተቋረጠ። ይኼኔ ልጆቻቸውን ሰብስበው ወደ ኬኒያ ተሰደዱ፤ ከዚያም ኖርዌይ ገቡ። የለገሰ መልዕክተኞች ለለገሰ መልዕክት የሚያደርሱላቸው ሁለት ሰዎች እንደነበሩ ልጃቸው ቢሉሱማና ባለቤታቸው ወ/ሮ ወይንሸት ያስታውሳሉ። በመጀመሪያ አንድ ወጣት ልጅ ነበር ይላሉ። በኋላ ላይ ግን እርሱ ዳግመኛ ቢመጣ እንኳ ምንም አይነት መልዕክት አትቀበሉት ብሎ በስልክ እንደነገራቸው ያስታውሳሉ። ከዚያ በኋላ በእድሜ ከፍ ያሉ አዛውንት መልዕክት ያመጡላቸው ጀመር። ከደብዳቤ ጋር የለገሰን ፎቶ ሲያመጡ ከእነርሱ ደግሞ የናፍቆት ደብዳቤያቸውንና የቤተሰብ ፎቶ ይወሰስዱላቸው ነበር። እኚህን ሰው አባ ፊጣ እያሉ ይጠሯቸው እንደነበር የምትናገረው ቢሊሱማ፤ ሁሌም ከአባታቸው የሚላከውን ምስል ካዩ በኋላ ለመደበቅ ወደ ቤተሰቦቻቸው ቤት ኢንጪኒ ይልኩት አንደነበር ታስታውሳለች። • "ማርታ፣ ለምን ለምን ሞተች?" ቢሉሱማ፤ አባ ፊጣ ወደ ቤታችን የሚመጡት ከመሸ ነው በማለት ለገሰ መልዕክት ከእርሳቸው ውጪ ከማንም እንዳይቀበሉ እንደነገራቸው፣ ቢጠየቁ ደግሞ ምንም እንደማያውቁ እንዲናገሩ እንዳሳሰባቸው ታስረዳለች። "እንፈራ ነበር፤ ድንገት ቤታችን በፖሊስ ተበርብሮ ቢገኝብን ብለን እንሰጋ ነበር።" በመጨረሻም አባ ፊጣ ላይም ክትትል መደረግ እንደተጀመረ ሰሙ። አባ ፊጣም "በቃ አታስቡ፤ ሰላም ነው፤ እኔ ዳግመኛ አልመጣም" ብለው ተለየአቸው።
xlsum_amharic-train-123
https://www.bbc.com/amharic/news-54884551
ትግራይ፡ ሕይወት በጦርነት ቀጣና ውስጥ በምትገኘው መቀለ
በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሉ መካከል ግጭት ከተከሰተ ዛሬ ሰባተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
[ "በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሉ መካከል ግጭት ከተከሰተ ዛሬ ሰባተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።" ]
መቀለ ከተማ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የትግራይ ልዩ ኃይል በክልሉ በሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት የሠሜን እዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን በመጥቀስ ወታደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸው ይታወሳል። የክልሉ መንግሥት በበኩሉ ጦርነቱን የከፈተብን የፌደራሉ መንግሥት ነው ይላል። ለመሆኑ ዕለታዊ ሕይወት በጦርነት ቀጠና ውስጥ ምን ይመስላል? ሪፖርተራችን ከስፍራው የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል። የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ማክሰኞ ጥቅምት 24 ምሽት ላይ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ በመቀለ ከተማ ተሰማ። ከዚያም ብዙም ሳይቆይ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች ተቋረጡ። ነዋሪዎች በክልሉ እና ከክልሉ ውጪ ካሉ ዘመድ ወዳጆቻቸው ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ይናገራሉ። መምህሯ ንግሥቲ አበራ አራት ልጆች እንዳሏት ትናገራለች። አራቱም ልጆቿ ኑሯቸው በአዲስ አበባ ነው። ስለ ልጆቿ ትጨነቃለች። "ላለፉት ሦስት ቀናት መብላትም መተኛትም አቃተኝ። ልጆቼን ድምጽ ከሰማሁ ቆየሁ" ብላለች ለቢቢሲ። ኤሌክትሪክ ጦርነቱ እንደተጀመረ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ ተቋርጦ ነበር። ይሁን እንጂ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ከሁለት ቀናት በኋላ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲመለስ ተደርጓል። ይሁን እንጂ በመቀለ ከተማ በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ እያጋጠመ እንደሆነ ሪፖርተራችን አስተውሏል። ትግራይን የሚያስተዳድረው ህወሓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲቋረጥ ያደረገው የፌደራል መንግሥቱ ነው ይላል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በበኩላቸው የአሌክትሪክ አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ያደረገው የህወሓት ኃይል መሆኑን ተናግረዋል። የውሃ ችግር ወትሮም የመጠጥ ውሃ ችግር የነበረባት የመቀለ ከተማ አሁን ችግሩ በርትቷል። ከዚህ ቀደም በተንቀሳቃሽ ቦቴ መኪናዎች እና በሌሎች ዘዴዎች ውሃ ያገኙ የነበሩ ነዋሪዎቸ አሁን ላይ የግንኙት መስመሮች በመቋረጣቸው ውሃ ለማግኘት መቸገራቸው ይናገራሉ። በመቀለ ከተማ በስልክ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ውሃ ያቀርቡ የነበሩ ድርጅቶች አሉ። በአሁኑ ወቅት ግን የስልክ ግንኙነት ባለመኖሩ ውሃ በትዕዛዝ ማግኘት ከባድ ነው ሲል ሪፖርተራችን ይናገራል። በሳምንት አንድ ጊዜ ትመጣ የነበረው የቧንቧ ውሃ ሳትመጣ መቅረቷ ችግሩን አባብሶታል ይላል ሪፖርተራችን። በመቀለ ከተማ በተለያዩ ስፍራዎች ውሃ ማከፋፈያ ስፍራዎች አሉ። ከእነዚህ ማከፋፈያ ስፍራዎች በአሌክትሪክ ኃይል ተስበው በውሃ መጫኛ ቦቴዎች ነበር የሚጓጓዙት። በአሁኑ ወቅት የአሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ የውሃ እደላ የማካሄድ ሥራውን ከባድ ማድረጉን ባልደረባችን ይናገራል። የባንኮች መዘጋት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ የግል እና የመንግሥት ባንኮች በትግራይ ሙሉ በሙሉ ዝግ ናቸው። ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በትግራይ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች የደኅንነት ስጋት ስላለባቸው በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የባንክ ቅርንጫፎች እንዲዘጉ ወስኗል። በክልሉ ነዋሪዎች ላይ አስቸጋሪው ኩነት የባንኮች አገልግሎት መቋረጥ መሆኑን ሪፖርተራችን ይናገራል። የሦስት ልጆች እናት የሆነችው ንግሥቲ መለስ በባንክ ያላትን ገንዘብ ወጪ ማድረግ ባለመቻሏ ችግር ላይ መሆኗን ትናገራለች። ወ/ት ዓለምነሽ ገብረሥላሴ በጉሊት ገበያ የችርቻሮ ንግድ ላይ ተሰማርታ ነው ህይወቷን የምትመራው። ወ/ት ዓለምነሽ ገዢ ጠፍቷል ትላለች። "ሰዎች እየገዙ አይደለም፤ እኔም ገቢ እያገኘሁ ስላልሆነ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው የምገኘው" ብላለች። ባንኮች ከመዘጋታቸው አንድ ቀን በፊት፣ የጥሬ ገንዘብ እጥረት በገበያ ውስጥ መታየቱን ሪፖርተራችን ዘግቧል። የባንኮች መዘጋት እና የጥሬ ገንዘብ እጥረት ነዋሪዎች ወደ ገበያ ወጥተው መሠረታዊ ፍጆታዎችን እንዳይሸምቱ ጋሬጣ እንደሆነባቸው ይናገራሉ። የትራንስፖርት አገልግሎት ጦርነቱ እንደተጀመረ ማክሰኞ ጥቅምት 24 የትግራይ ክልል መንግሥት ባወጣው የመጀመሪያው መግለጫ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ መወሰኑን ይፋ አድርጎ ነበር። ይህ እግድ ለሁለት ቀናት ከዘለቀ በኋላ፤ ከመኖሪያ ቀያቸው ርቀው የነበሩ ሰዎች ከትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ፍቃድ እየተቀበሉ ወደ መኖሪያቸው መመለሳቸውን ሪፖርተራችን ተመልክቷል። ይህ ልዩ ፍቃድ የሌለው ወይም ማግኘት የማይችል የክልሉ ነዋሪ ግን ወደ የትኛው የክልሉ ስፍራ መንቀሳቀስ አይችልም። ክልሉ ከሌሎች አጎራባች ክልሎች ጋር በሚዋሰንባቸው ድንበሮች ዙርያ ወታደሮች ስለሰፈሩ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባና ወደሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች መጓዝ የማይታሰብ ሆኗል። የአየር ድብደባ ስጋት ሐሙስ ጥቅምት 26 ከሰዓት ላይ አንድ ተዋጊ ጄት በመቀለ ዙርያ በራ ነበር። ይህም ነዋሪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ አስደንግጦ እንደነበረ ዘጋቢያችን ለመታዘብ ችሏል። ምሽቱን የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ይህ የጦር ጄት ቦምብ እንደጣለና ሰዎች ላይ ግን ጉዳት እንዳልደረሰ ገለጧል። ይህ ግን በሪፖርተራችንም ይሁን በገለልተኛ አካል አልተረጋገጠም። ባሳለፍነው እሑድ ወደ ቤተ-ክርስቲያን ሲሄዱ የነበሩ ሰዎች የጦር ጄት ድምጽ ሲሰሙ በፍጥነት ተሯሩጠው ሲበተኑም ተመልክቷል። በዚያው ዕለት ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለትግራይ ሕዝብ በከተሞች አከባቢ እና በተለያዩ ወታደራዊ ጥቃት ሊያጋጥማቸው በሚችሉ ስፍራዎች በብዛት ሆነው ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ጥሪ አስተላለፉ። ይህም ተጨማሪ የአየር ድብደባ እንደሚኖር ያመላከተ ነበር። ጥቅምት 29 እሑድ ምሽት ላይ የፌደራል መንግሥቱን የጦር ጄት መትተን ጥለናል ሲሉ የሕውሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገረው ነበር። የአገር መከላከያ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ ግን ይህ የሐሰት ዜና ነው ሲሉ ትናንት ጥቅምት 30 ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። የነዳጅ እጥረት በመቀለ የሚገኘው ሪፖርተራችን ግጭቱን ተከትሎ በትግራይ በተለይም በክልሉ መዲና የነበረው የንግድ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ይናገራል። የንግድ ብቻ ሳይሆን የትራፊክ እንቅሴውም ቀንሷል ይላል። ለዚህ ደግሞ ከምክንያቶች አንዱ በክልሉ የነዳጅ እጥረት በመከተሱ ነው። አቶ ሐለፎም ተክላይ መኪናቸውን ሙሉ በሙሉ ለማቆም መገደዳቸውን ይናገራሉ። ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያታቸው የነዳጅ እጥረት እንደሆነ ይናገራሉ። የክልሉ መንግሥት ምን ይላል? ከፌዴራልም ሆነ ከክልሉ መንግሥት በትግራይ እየተከሰቱ ባሉ ሁኔታዎች ዙርያ በቂ የሚባል ማብራሪያ የክልሉ ሕዝብ ማግኘት እንዳልቻለ ሪፖርተራችን ይናገራል። የክልሉ ሕዝብ ግራ መጋባትና ስጋት ውስጥ ባለበት ሁኔታ ወሳኝ የሚባሉ መረጃዎች ከመንግሥት አካላት አያገኘ ነው ለማለት አያስደፍርም ይላል ዘጋቢያችን። የትግራይ ክልል የሕዝብ ግንኙት ቢሮ አሁን ያሉት ችግሮች 'በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፈታሉ' ከሚል አጭር መልስ ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ ሊሰጥ አልቻለም። የነዋሪዎቹ ጥያቄዎቹ "ወደ የት እየተኬደ ነው? ይህ ሁሉ መጥፎ ሁኔታስ መቼ ነው የሚያበቃው?" የሚሉት ጥያቄዎችን እያነሱ መሆኑን ሪፖርተራችን ይናገራል። የከተማዋ ነዋሪም የጦርነትን አስከፊነት በተደጋጋሚ ይናገራል። ነዋሪዎች ግጭቱ በቶሎ የሚፈታበትን ሁኔታና ዕድል እንዲፈጠር በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ ይላል ባልደራባችን። አንዴት እዚህ ነገር ውስጥ ተገባ? በህወሓት እና በፌዴራል መንግሥቱ መካከል ልዩነቶች እየሰፉ የመጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ያካሄዱትን የለውጥ እርምጃ ተከትሎ ነው። ኢሕአዴግ ከስሞ ወደ ብልጽግና ፓርቲ መቀየሩ እንዲሁም የፌደራል መንግሥት በኮሮናቫይረስ ስጋት ያሸጋገረው አገራዊ ምርጫን ወደ ጎን በመተው የትግራይ ክልል ክልላዊ ምርጫ ማካሄዱ በሁለቱ አካላት መካከል ከፍተኛ መቃቃር እንዲፈጠር ምክንያት እንደሆኑ ይነገራል። የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል የተካሄደውን ምርጫ ሕገ-ወጥ ነው ሲለው ሕውሃት በበኩሉ የጠቅላይ ሚንስትሩ መንግሥት የሥራ ዘመን አብቅቶለታል ሲል ነበር። ነገሮች ተባብሰው ጥቅምት 24 ላይ የትግራይ ልዩ ኃይል፣ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን በመጥቀስ ጠቅላይ ሚንስትሩ የአገር መከላከያ ሠራዊት ሕውሃት ላይ እርምጃ እንዲወስድ ማዝመታቸውን ተናግረዋል።
xlsum_amharic-train-124
https://www.bbc.com/amharic/news-45875764
ተፈጥሯዊ መለያችን ስለሆነው ስለድምጻችን ልናውቃቸው የሚገቡ ሰባት ነጥቦች
ሁሉም ሠው የተለየ ድምጽ ይዞ ነው የሚወለደው።
[ "ሁሉም ሠው የተለየ ድምጽ ይዞ ነው የሚወለደው።" ]
የቋንቋ አስተማሪ ወይንም ዘፋኝ ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ምን ያህል ስለአስደናቂው የሰው ልጅ የተፈጥሮ ሃብት ምን ያህል ያውቃሉ? • ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ የቢቢሲ ሳይንስ ፕሮግራም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት በማድረግ አስገራሚ ውጤቶችን አግኝቷል። 1. ሁላችንም ከውልደት ጀምሮ የአነጋገር ዘዬ አለን ህጻናት ማሕጸን ውስጥ እያሉ ጀምሮ ነው የቤተሰቦቻቸውን የአነጋገር ዘዬ የሚይወርሱት። ተመራማሪዎች አዲስ የተወለዱ ፈረንሳያዊያን እና ጀርመናዊያን ላይ ባደረጉት ምርምር ለቅሷቸው የቤተሰቦቻቸውን ዘዬ የያዘ መሆኑን አረጋግጠዋል። • በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው ከዚህ በመነሳትም የህጻናትን ለቅሶ ብቻ በመስማት ሃገሮቻቸውን መናገር እንደሚቻል ገልጸዋል። 2. የድምጽ ሳጥናችን ከውስጥ ምን ዓይነት ድምጽ አለው ድምጽ የሚጀምረው አየር በተመጠነ መልኩ በድምጽ ሳጥናችን በኩል ከደረታችን ሲወጣ ነው። ሁለቱ የድምጽ አውታሮች ወይንም ቮካል ኮርዶች አየር ሲወጣ እና ሲገባ ንዝረት የሚፈጥር ሲሆን ይህም ድምጽ ይፈጥራል። • የካንሰር የደም ምርመራ "አሰደናቂ ውጤት" አስገኘ ከዚህ በተጨማሪ እንደ መንጋጋ፣ ምላስ፣ ከንፈር እና ሌሎችም የድምጽ መፍጠሪ አካላችንን በመጠቀም ድምጽ ይፈጠራል። 3. ለምን ይጎረንናል? በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ያለ ወንድምዎት ሲዘፍን. . . የወንዶች ድምጽ በጉርምስና ወቅት ይቀየራል። የድምጽ ሳጥናቸው ካለበት ቦታ ትንሽ ዝቅ በማለት ወጣ ለማለት ይሞክራል። ይህም ማንቁርጥ (የአዳም አፕል) በመባል በብዛት ይታወቃል። በዚህ ምክንያትም በድምጽ ሳጥን እና በአፍ መካከል ያለው ርቀት ይሰፋል። • በህንድ ጥቅም ላይ የዋሉ የንፅህና መጠበቂያ ጨርቆች ለምን ተፈለጉ? ርቀቱ መስፋቱ ደግሞ ዝቅ ያለ ድምጽ (ኖት) እንዲኖር እና የወንዶች ድምጽ ጎርናና እንዲሆን ያደርጋል። ሴቶች በሚያርጡበት ወቅትም አነስተኛ በሆነ ሁኔታ ግን በተመሳሳይ ሂደት ውስጥ ያልፋሉ። ይህም የድምጻቸውን ቅላጼ ዝቅ ያደርገዋል። 4. የሚወዱትን ሠው ድምጽ ያስመስላሉ አንድን ሠው ስንወድ ድምጻችን ከምንወደው ሠው ድምጽ ጋር እያመሳሰልን እንሄዳሉ። ለምሳሌ አንዲትን ሴት የወደደ ወንድ ከእሷ ጋር ሲያወራ የድምጹን ቅላጼ ከፍ አድርጎ ነው። በህንድ ጥቅም ላይ የዋሉ የንፅህና መጠበቂያ ጨርቆች ለምን ተፈለጉ? 5. እርጅና ሲጫጫን ዕድሜ ሲጨምር የድምጽ አውታሮች ወይም ቮካል ኮርዶች ስለማይጠነክሩ አየር ማስወጣት ይጀምራሉ። ይህም ድምጻችን የበለጠ ትንፋሽ ያለው ያደርጋል። በዚህም እድሜአቸው የገፋ ሰዎች የትንፋሽ እጥረት ስለሚያጋጥማቸው ረዣዥም ዓረፍተ ነገሮችን አይናገሩም። የጡንቻ መድከም ስለሚጨመርበትም ዕድሜ ሲጨምር የድምጻችን ቅላጼ ከፍ ይላል። 6. ድምጻችን ለረዥም ጊዜ ወጣት ሆኖ ይቆያል ጥሩው ዜና ዕድሜያችን እየጨመረ ሰውነታችን እያረጀ ሲሄድ በድምጻችን ላይ የሚታየው ለውጥ ግን አነስተኛ ነው። የሠዎችን ድምጽ በመስማት ዕድሜያቸውን ለመገመት ከሞከሩ በአማካይ ዕድሜያቸውን ዝቅ አድርገው ነው የሚገምቱት። 7. ድምጻችንን እንዴት መንከባከብ እንችላለን? ዕድሜያችን ሲጨምር እንደሠውነታችን ሁሉ የድምጻችን ጡንቻዎችም ተከታታይ ልምምድ ይፈልጋሉ። ይህን የድምጽ ልምምድ በማድረግ የድምጽ አውታሮችን በመለጠጥ በጥሩ ደረጃ ላይ ሊያቆዩ ይችላሉ። (ግን ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ አይደለም የሚለማመዱት) ወይንም ደግሞ የዘፈን ቡድን ውስጥ መግባትም ሌላኛው አማራጭ ነው። ይህም ድምጻችን ጤነኛ እንዲሆን ከመርዳቱም በላይ በመዝፈናችን እና ከሌሎች ጋር በመተዋወቃችን የሚያዝናናን ይሆናል።
xlsum_amharic-train-125
https://www.bbc.com/amharic/news-52703737
የ64 ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው የኮንቴነር ውስጥ ሞት የተረፈው ደጀኔ
የአስራ ስምንት ዓመቱ ደጀኔ ደገፋ በያዝነው ዓመት መባቻ በሞያሌ በኩል ኢትዮጵያን ትቶ ወደደቡብ አፍሪካ ጉዞ ሲጀምር ኪሱ ውስጥ ሦስት ሺህ ብር ገደማ ነበረው።
[ "የአስራ ስምንት ዓመቱ ደጀኔ ደገፋ በያዝነው ዓመት መባቻ በሞያሌ በኩል ኢትዮጵያን ትቶ ወደደቡብ አፍሪካ ጉዞ ሲጀምር ኪሱ ውስጥ ሦስት ሺህ ብር ገደማ ነበረው።" ]
ደጀኔ ደገፋ በሚቀጥሉት ሰባት ወራት አራት የአፍሪካ አገራትን ካቆራረጠ በኋላ ግን ካሰበበት ከመድረስ ይልቅ ስድሳ አራት የጉዞ አጋሮቹን ለሞት ገብሮ በዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት እገዛ ወደገሩ ነብሱን ብቻ ይዞ ተመልሷል። ትውልድ እና ዕድገቱ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔሮች እና ሕዝቦች ክልል ከሆሳዕና ከተማ አቅራቢያ በሻሸጎ ወረዳ በምትገኝ የገጠር ቀበሌ ነው። የእናቱን ሞት ተከትሎ አባቱ እርሱን ጨምሮ አምስት ልጆቻቸውን በግብርና ለማስተዳደር ይታትሩ ነበር። ገበታቸው ላይ ግን ለልጆቻቸው የሚበቃ ነገር አቅርበው አያውቁም ነበር። ኑሮ እንደቋጥኝ መክበዱ ነበር ደጀኔንም ትምህርቱን አምስተኛ ክፍልን ሳይሸገር እንዲተው እና ሥራ ፍለጋ እንዲባዝን ያስገደደው። የ'ጆበርግ' ጥሪ ቀየውን ለቅቆ ወደ ኦሮሚያዋ ቢሾፍቱ ከተማ በማቅናት ልዩ ልዩ የቀን ሥራዎችን እየከወነ ራሱን በመደጎም ላይ ሳለ ታዲያ የደቡብ አፍሪካዋ ጆንሃንስበርግ ታማልለው ያዘች። ከጥቂት ዓመታት በፊት ወደ ከተማዋ አቅንቶ የተደላደለ ኑሮ የመሠረተውን የቅርብ ዘመዱን ተመስላ ነበር 'ጆበርግ' አማላይ ጥሪዋን የላከችው። "ብዙ ጓደኞቼና ዘመዶቼ [ደቡብ አፍሪካ በመሄድ] ሰርተው እየተለወጡ ስለሆነ፤ እኔም ሰርቼ እለወጣለሁ በማለት ነው መስከረም ሁለት ቀን ጉዞ የጀመርኩት" ይላል ደጀኔ አዲስ አበባ ከተመለሰ እና የአስራ አራት ቀን የለይቶ ማቆያ ጊዜውን ጨርሶ ከወጣ በኋላ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። የቅርብ ዘመዱ ጥሪ ብቻ አልነበረም ያቀረበለት፤ ጉዞውንም አመቻችቶለታል- ይህም አሸጋጋሪዎችን ማገናኘትን እና ለእነርሱ የሚከፈለውን ገንዘብ መሸፈንንም ያካትታል። ጉዞ በደቡብ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ ከቢሾፍቱ ከተማ ወደ ሐዋሳ በማቅናት የተጀመረው ጉዞው፤ በሞያሌ በኩል ወደኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ማቅናትና ከዚያም በሞምበሳ በኩል ወደ ታንዛኒያ መሻገርን ያካተተ ነበር። በየአገራቱ ባሉ የፀጥታ ኃይሎች እይታ ውስጥ ላለመግባት ሲባል ጉዞዎች የሚካሄዱት በምሽት ሲሆን፤ የመጓጓዣ ዘዴውም እንደየቦታው ይለያያል። እንዳንዴ በእግር፣ ሌላ ጊዜ በሞተር ብስክሌት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በጭነት መኪና አሊያም በኮንቴይነር ውስጥ ነበር። መዐልታትን በየበረሃው እና በየጫካው ተኝቶ ማሳለፍ ግድ ሲሆን፤ አሸጋጋሪዎቹ ሩዝና ኡጋሊ የሚባለውን ከበቆሎ የሚዘጋጅ ገንፎ መሰል ምግብ ያቀርባሉ። ይሁንና የተደረጉት ጥንቃቄዎች እርሱን ጨምሮ ሃያ የሚጠጉ ተጓዦችን ታንዛኒያ ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች ከመያዝ አላዳኗቸውም። በእስር ግን ከሁለት ቀናት የዘለለ ጊዜ አላሳለፉም። "እንዴት እንደተለቀቅን አናውቅም" የሚለው ደጀኔ ስደተኛ አዘዋዋሪዎቹ ለአሳሪዎቹ ገንዘብ ከፍለው ሳያስለቅቋቸው እንዳልቀረ ይገምታል። አብረውት የሚጓዙት ሰዎች ቁጥር በየጊዜው ይለያያል፤ "አምስትም፣ አስርም፣ ሃያም፣ ሰላሳም የምንሆንበት ጊዜ አለ።" አዘዋዋሪዎቹም እንደዚሁ ይቀያየራሉ፤ አንደኛው አንድ ቦታን ያሳልፍና ሌላኛው ይተካል - እንደደጀኔ ትረካ። አብረውት ከነበሩ ኢትዮጵያውያን ተጓዦች መካከል የእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚሞክሩ መኖራቸው ከድንበር አሻጋሪዎቹ ጋር መጠነኛም ቢሆን የመግባቢያ ዕድልን ፈጥሯል። ጉዞው ማላዊን አሻግሮት ሞዛምቢክ ሲያደርሰው ግን መከራ ነው የጠበቀው። ደጀኔ አብረውት ወደ አገራቸው ከተመለሱት ወጣቶች ጋር የኮንቴነር ውስጥ ሰቆቃ በግምት ከምሽቱ ሦስት ወይንም አራት ይሆናል፤ "ያው ስንት ሰዓት እንደሆነ ስለማናውቅ" ይላል ደጀኔ፤ በሞዛምቢክ ሰሜን ምዕራባዊ ክፍል በምትገኘው ቴቴ ክፍለ ግዛት የነበረውን መዘዘኛ ቆይታ ሲያስታውስ። "ሃምሳ ሰባት ነበርን" ይላል ይቀጥልና አዘዋዋሪዎቹ "ወስደውን ፒስታ (የጠጠር ጥርጊያ) መንገድ ላይ አስቀመጡን" ቆይቶም ሃያ አንድ ተጓዦች ተጨመሩና ቁጥራቸው ወደሰባ ስምንት አደገ። ወዲያውም አዘዋዋሪዎቹ ሰባ ስምንቱን ተጓዦች ወደ ደቡብ አፍሪካ ያጓጉዛል ያሉትን ኮንቴይነር አመጡ። "ኮንቴነሩ ሲመጣ አንገባም ብለን እምቢ ብለን ነበር" ይላል ደጀኔ፤ በእምቢታ "የሮጡም ነበሩ።" ነገር ግን አዘዋዋሪዎቹ "በዱላም፣ በቆንጨራም" እየደበደቡ እና እያስፈራሩ ኮንቴነሩ ውስጥ እንዳጨቋቸው ያስታውሳል። "በግድ ነው ያስገቡን"፤ በዚህ መሃል "የተጎዱ፣ እግራቸው የቆሰለም አሉ።" ተጓዦቹ ኮንቴነተሩ ውስጥ መታጨቃቸው ያዘለውን አደጋ ገምተው ቢማፀኑም፤ ውስጡን ቢደበድቡም አዘዋዋሪዎቹ በሩን ከመጠርቀም አልተመለሱም። ጉዞው ሲጀምር ጩኸት ማሰማታቸውን ቀጠሉ። "አንዲት ሴት አብራን ነበረች፤ '[ኮንቴነሩን] አትሰብሩትም ወይ?' እያለች" የኮንቴነሩን ግድግዳ መደብደቡን ታበረታታ ነበር። "እኛም በቦክስም፣ በእግርም እየታገልን ነበር። የሚሰማ [ግን] አልነበረም።" እንስቷ "ቀድማ እንደሞተች አውቃለሁ" ይላል ደጀኔ። "እየለመነች፤ እየተናገረች ፀጥ አለች። [. . . ] እኔም እየደከምኩ መጣሁ።" ድካሙ ሲበረታበት ራሱን ስቶ ወደቀ። ኮንቴነሩ ግን መሄዱን አላቆመም። ከንጋቱ "አስራ አንድ ሰዓት የሚሆን ይመስለኛል። [ስነቃ] በሩ ተከፍቷል። ሲከፈት እግሬ ላይ ልጆች ወድቀዋል፤ ዐይኔን ስከፍት ሰማይ ነው የሚታየኝ።" በቦታው የነበሩ የአገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች 'ኢትዮጵያዊያና ናችሁ?' እያሉ ሲነጋገሩ ማዳመጡንም ያስታውሳል። ወደ አገር ቤት የስድሳ አራት ኢትዮጵያዊያንን ሕይወት ከቀጠፈው በኮንቴነር የመተፋፈን አደጋ የተረፈው ደጀኔ በተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) እገዛ ከሌሎች አስር ተራፊዎች ጋር ወደአገር ቤት ተመልሷል። ከአደጋው በኋላ ከቤተሰቡ አባላት ጋር የነበረውን የስልክ ውይይት ሲያስታውስም "'ማን ነው?' አሉ። ደጀኔ ነኝ፤ ስላቸው አላመኑም። ያው እንደሞትኩ ነው ያሰቡት" ይላል። አደጋው እና የተጓዦቹ ሞት በወርሃ መጋቢት የብዙሃንን አትኩሮት የሳበ ዜና ስለነበረ፤ መረጃውን ማግኘታቸው አልቀረም፤ ሆኖም ስለተራፊዎቹ ማንነት የሚያውቁት ነበር አልነበረምና እርሱም ሞቶ እንደሆነ ጠርጠረው ነበር። ስልኩን ያነሳችው ታላቅ እህቱ በድንጋጤ እንደዘጋችውና ከደቂቃዎች በኋላ ተረጋግታ እንዳናገረችው ለቢቢሲ ተናግሯል። አገር ቤት ውስጥ ጥሩ ገቢ የሚያስገኝለት ሥራ ማጣቱ የደቡብ አፍሪካን ጉዞ እንዲሞክር እንደገፋፋው የሚናገረው ደጀኔ "ከዚህ በኋላ ግን ለምኜ እበላለሁ እንጂ ሁለተኛ የደቡብ አፍሪካን ጉዞ አልሞክርም" ይላል። ይሁንና አደጋ የበዛባቸውን ኢ-መደበኛ የስደት መንገዶች የሚሞክሩ ወጣቶች ያሰቡበት ቦታ እስኪደርሱ ድረስ ሙከራቸውን ባንዴ እንደማያቆሙ ይዘገባል። ከደጀኔ ጋር ከነበሩ ተጓዦች መካከል እንኳ ለሁለተኛ ጊዜ ሙከራ የሚያደርጉ ነበሩበት። አንዳንዶቹ እንዲያም የምሥራቅ አፍሪካ አገራት መግባቢያ ቋንቋ የሆነውን ስዋሂሊኛ ይሞካክሩ ነበር። ኮቪድ-19 የደቀነው ፈተና ደጀኔ እና ጓደኞቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ሮጠው ከናፈቋቸው ወዳጆቻቸው እቅፍ ውስጥ እልገቡም፤ እንደማንኛውም ወደአገር ቤት እንደሚመለስ ተጓዥ አስራ አራት ቀናት በለይቶ ማቆያ መቀመጥ፣ ከዚያም መመርመር እና ዓለምን እየናጣት ከሚገኘው የኮሮናቫይረስ ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነበረባቸው። ምልሰታቸውን ያገዘው እና ያቀላጠፈው የአይኦኤም የኢትዮጵያ የበላይ የሆኑት ማውሪን አቺንግ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ባለበት ወቅት ደጀኔን ለመሳሰሉ ኢ-መደበኛ ስደተኞች እገዛ ማድረግ እጅግ ፈታኝ ሆኖብናል ይላሉ። ስደተኞቹ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ሲደረጉ ሒደቱ የስደተኞቹን ጤና በጠበቀ መልኩ መከናወን አለበት። ከዚህም በዘለለ ስደተኞቹ ሳይታወቃቸው ወረርሽኙን እንዳያስፋፉ ጥንቃቄ መደረግ ግድ ይሆናል። "ስለዚህም ለወትሮው የማናደርጋቸውን እምርጃዎች እንከውናለን" ይላሉ አቺንግ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ "አቋማችን ግልፅ ነው፤ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ባለበት ሁኔታ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች እንቅስቃሴ አይመከርም።" በመሆኑም አቺንግ አገራት በአንድ ወይንም በሌላ ምክንያት ድንበሮቻቸውን አልፈው የገቡ ስደተኞችን ለመመለስ ከመጣደፍ ይልቅ እንክብካቤ እንዲሰጧቸው ይመክራሉ።
xlsum_amharic-train-126
https://www.bbc.com/amharic/news-46395978
በአዛውንቶች የሚመራው የኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ
ማክሰኞ ኅዳር 18 ቀን ፣ 2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የምርጫ ሥርዓትን ስለ ማሻሻል የመከሩበት መድረክ ከዋናው አጀንዳ ባሻገር አንድ ጉዳይ በተለየ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል ፤ መድረኩ በአዛውንት ወንድ ፖለቲከኞች የተሞላ መሆን።
[ "ማክሰኞ ኅዳር 18 ቀን ፣ 2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የምርጫ ሥርዓትን ስለ ማሻሻል የመከሩበት መድረክ ከዋናው አጀንዳ ባሻገር አንድ ጉዳይ በተለየ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል ፤ መድረኩ በአዛውንት ወንድ ፖለቲከኞች የተሞላ መሆን።" ]
የኢትዮጵያ ተቃውሞ ፖለቲካ ፊታውራሪዎች በተለይም ለአራት ወይም አምስት ዐሥርታት በተቃውሞ የቆዩና በዕድሜ የገፉ መሆናቸው ብዙዎችን ያነጋግር ይዟል። ክስተቱ 'ወጣት ሴቶችና ወጣት ወንዶች በተቃውሞ ፖለቲካ ተሳትፎ ቦታቸው የት ነው?' የሚል መሠረታዊ ጥያቄ ሳይለኩስ አልቀረም። በሌላ በኩል ሴት በመብራት የሚፈለግበት መድረክ መሆኑን ተከትሎም "ሴቶችን የማያሳትፉ ተቃዋሚዎችን እንቃወማለን" የሚሉ አስተያየቶችም በማኅበራዊ ሚዲያ ተንፀባርቀዋል። "ሴቶችን የማያሳትፉ ተቃዋሚዎችን እንቃወማለን" የሥርዓተ ፆታና ሕግ አማካሪ የሆነችው ሕሊና ብርሃኑ "ሴቶቸን የማያሳትፉ ተቃዋሚዎችን እንቃወማለን" ሲሉ ድምፃቸውን ካሰሙት መካከል አንዷ ናት። 'ያለውን ሥርዓት ክፍተትና ጉድለት እሞላለሁ ብሎ የተነሳ ተቃዋሚ ሴቶችንና ወጣቶችን አካታች አለመሆን ተቃርኖ አለው' ትላለች ሕሊና። "አንድን ሥርዓት የተሻለ አደርጋለሁ ብሎ አካታች አለመሆን፣ ፍትህና መፍትሄ ሳይዙ መምጣት እርስ በርሱ የሚጋጭ ነገር ነው። አካታች ሳይሆኑ ተቃዋሚ መሆን አይቻልም "ትላለች። • የታገቱት ሕንዳውያን ድረሱልን እያሉ ነው • "ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ • ኢትዮጵያ በዲፕሎማቶቿ ላይ ሽግሽግና ለውጥ ልታደርግ ነው ወጣት ሴቶች በሁለት መልኩ ከፖለቲካ ተሳትፎ ውጭ እንዲሆኑ እንደሚደረግ ስታስረዳ፤ ወጣት ሲባል የሚታሰበው ወንድ ፤ ሴት ሲባልም የሚታሰበው ትልልቅ ሴት መሆኑን በምክንያትነት ታስቀምጣለች። ስለዚህም ሴቶቸን በተለይም ወጣት ሴቶችን ሳይዙ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መፍጠር የሚቻል አይደለም። "አካታች ያልሆነ፣ በቁጥር ብዙኃኑን የማይጨምር ፖለቲካ በብሔር ቢሆን ያስነውር ነበር" የምትለው ሕሊና 'ወጣቱ አገር ተረካቢ ነው ' እንዲሁም 'የሴቶች ተሳትፎና ወደ አመራርነት መምጣት ቀስ በቀስ ይስተካከላል' የሚሉ አስተያየቶችንም በበጎ አትመለከታቸውም። "ወጣት የነገ መሪ ነው" የሚባለው መደለያ ሆኖ ይሰማታል። "ወጣት የሆንኩት፣ ሰው የሆንኩትና ጉዳይ ያለኝ ዛሬ ነው። ስለዚህ የዛሬ እንጂ የወደፊት አይደለሁም።" ትላለች። በተመሳሳይ ሁኔታ የሴቶች ተሳትፎም መሆን እንደሚገባው ሳይሆን ቀስ ብሎ እንደሚመጣ ነገር መታየቱም ትክክል እንዳልሆነ ትረዳለች። ሕሊና በከፊል መፍትሄ ሊመነጭ የሚችለው ከምርጫ ቦርድ እንደሆነ ታስባለች። ይህ ሊሆን የሚችለውም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምዝገባ በሚመጡበት ጊዜ ነው። ይኸውም ተመዝጋቢ ፓርቲዎች የሴቶችና የወጣቶች ተሳትፎን በቁጥር ጭምር እንዲያስቀምጡ መስፈርት ማበጀትን ይጨምራል። በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲህ ዓይነቱ ሕግ ሲኖር ደግሞ ፓርቲዎቹ እንዲሁ መቃወም ብቻ ሳይሆን የጠራ የሥርዓተ ፆታና የወጣቶች ፖሊሲ እንዲቀርፁ እንደሚያበረታታቸው እምነት አላት። "ትግላችን ይቀጥላል" የአረና ፓርቲ መሥራች የሆኑት የቀድሞ የህወሓት ታጋይ ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ እስከ አሁን የኢትዮጵያ ተቃውሞ ፖለቲካ በጣም የተገደበ መሆን የተቃውሞ መድረኩ ዛሬም በስልሳዎቹ የፖለቲካ ትኩሳት ወጣቶች፤ (በዛሬዎቹ አዛውንቶች) እንዲመራ ምክንያት ሆኗል ይላሉ። "ምህዳሩ በጣም ገዳቢና ነፃነት የሌለው ነበር። እስከዛሬ በተቃውሞ ያሉት በስልሳዎቹ ወጥተው ደፍረው መናገር የቻሉ ናቸው።ወጣቱ ግን የሴቶች ፣ የወጣት ማኅበርና ወጣት ሊግ እየተባለ ታፍኖ የቆየ ነው።" • የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ተዋሃዱ ነገሮች ክፍት ሆነው ሰዎች በፈለጉበት መንገድ በነፃት የሚደራጁበት እድል እስካልተፈጠረ ድረስ አሁንም ለዓመታት የዘለቁት ቀደምት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መቀጠላቸው እንደማይቀር ያመለክታሉ። በተጨማሪ የፖለቲካው ሴቶችን አሳታፊ አለመሆን የአባታዊ ሥርዓት ውጤት እንደሆነ የሚናገሩት ወ/ሮ አረጋሽ ሴቶች በመደራጀት ለራሳቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጥቅም ተደራጅተው ይህን እውነታ መቀየር እንዳለባቸው ያምናሉ። ለእርሳቸው በብዙ የትግል ድምር ውጤት ዛሬ ላይ መደረሱ አንድ ነገር ነው ። የሕገ መንግሥቱ መፅደቅ ደግሞ እንደ ትልቅ ስኬት ይመለከቱታል። "ግን ይህ ሕግ ስላልተተገበረ ዛሬም ስለ ዲሞክራሲ ችግር፣ ስለ ሰብአዊ መብት ጥሰት እየሰማን ነው። ታገልን፣ የተቻለንን አደረግን፤ ግን ሂደት ነውና ምን ማድረግ ይቻላል። ለውጥ እንዲመጣ ትግላችን ይቀጥላል" ይላሉ ወ/ሮ አረጋሽ። "ቆሞ የቀረ ተቃውሞ" የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው ዮናታን ተስፋዬ በፓርቲ ደረጃ በአስተዳደር ወደ ላይ እየወጡ ያሉ ሰዎች ሲታይ ኢህአዴግ የተሻለ አቋም ላይ ነው የሚል እምነት አለው። በተቃራኒው "በ60ዎቹና 70ዎቹ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በከፍተኛ ሁኔታ የተቆጣጠሩት የተቃውሞ ፖለቲካ ቆሞ ቀርቷል" ይላል። የተቃውሞ ፖለቲካው ለምን በአንጋፋዎች ተሞላ? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ መሪዎቹ ለተለየ ሐሳብ ክፍት አለመሆናቸውን ያነሳልና፣ ወጣቱ ደግሞ በነበረው 'ዘልማዳዊ ፖለቲካ' ውስጥ ጊዜውን ከሚያጠፋ ለራሱ ሮጦ የፈለገበት መድረስ የሚፈልግ በመሆኑ እንደሆነ ይገልፃል። ከነዚህ በተጨማሪም ጥናት የሚያስፈልጋቸው ቢሆኑም ሌሎች ምክንያቶችም እንዳሉ ያምናል። እርስበርስ መጠላለፍና በወጣቶች አቅም ላይ ጥርጣሬን ማሳደር በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ናቸው። "...የሚሞክረውም በሴራና በዘልማድ በሚሠራ ሥራ ተጠልፎ ይወጣል። የእኔም ቆይታ በዚህ ውስጥ ነበር። 'እናንተ ደግሞ ትናንት መጥታችሁ ፖለቲካ ልታስተምሩን ነው?' ይባላል" ይህ በእንዲህ እያለ በርካቶቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አብዛኞቹ አባሎቻቸው ወጣቶች እንደሆኑና በአደረጃጀትም የወጣት ቡድን እንዳላቸው ይገልፃሉ።ይህ ከሆነ ወጣቶች ለምን ጎልተው አይታዩም? ዮናታን እንደሚለው ምንም እንኳ መዋቅሮቹ ቢኖሩም በዚህ 'በጣም በታፈነ ' የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ ልምድ ለሌለው ወጣት ሰብሮ መውጣት ትልቅ አቅም የሚጠይቅ ነው። "የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ደግሞ ከራሳቸው ውጭ ማንም ጎልቶ እንዲወጣ የሚፈቅዱ አይደሉም።" "ወጣቶችም አዛውንቶችም ያስፈልጋሉ" የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ድርጅታቸው በመዋቅር የተደራጀ የወጣት ሊግ እንዳለውና የወጣት ክንፉ ትግሉን በበላይነት የሚመራ እንደሆነም ይገልጻሉ፤ በግምት ሰማንያ በመቶ የሚሆነው አባላቸውም ወጣት እንደሆነ በማስገንዘብ። ወጣቱን እንዴት ወደ አመራር እናውጣ? የሚለው ላይ ካልሆነ በስተቀር ትግሉን የተሸከመውና የዛሬውን ለውጥ ያመጣው ወጣቱ እንደሆነ በጽኑ ያምናሉ። "ከሥር የወጣነው፣ ከውጭ የገባው እንዲሁም ምኒሊክ ቤተመንግሥት የገባነውም በወጣቱ ትግል እንጂ በሌላ እኮ አይደለም" ሲሉ ይህንኑ እምናታቸውን በማስረጃ ያጠናክራሉ። በተቃውሞ ፖለቲካው አመራር ደረጃ ለምን የሴቶችና የወጣቶች ተሳትፎና አመራር አልታየም ለሚለው ጥያቄ ታዲይ ዶ/ር መረራ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ይልቅ መንግሥትን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ጥያቄውን የሚመልሰውም የአገሪቱ ፖለቲካ ነውም ይላሉ። "የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዞ ላለፉት አርባና ሃምሳ ዓመታት ከቀውስ ወደ ቀውስ ነበር። በዚህ ጊዜ ውስጥ መንግሥት ወጣቱን ሲያሳድድ፣ ሲገርፍና ሲገድል ነበር። ስለዚህም ወጣቱ ወይ እስር ቤት ወይ ስደት ላይ ነበር። "ወጣቶችም አዛውንቶችም ያስፈልጋሉ" የሚሉት ዶ/ር መረራ በፓርቲያቸው በወጣቶችና በአዛውንቶች መካከል ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለና አንጋፋዎቹ ወጣቶቹ ላይ መንገድ እንዳልዘጉም ያስረዳሉ። ጠቃሚውና ቀጣዩ እርምጃ መሆን ያለበት ወጣቱም አዛውንቱም የራሱን የቤት ሥራ ቢሠራና በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማስፈን የሚታገሉ ሰዎች ትግሉን ቢገፉ የተሻለ እንደሆነ ያምናሉ።
xlsum_amharic-train-127
https://www.bbc.com/amharic/54701708
በግድቡ ጉዳይ ትራምፕ ኢትዮጵያን ከድተዋል?
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተቺዎች እንደሚሉት፤ ፕሬዚዳንቱ ለዘመናት የአሜሪካ ወዳጆች በሆኑት ኢትዮጵያ እና ግብፅ መካከል ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ውጥረት ቀስቅሰዋል።
[ "የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተቺዎች እንደሚሉት፤ ፕሬዚዳንቱ ለዘመናት የአሜሪካ ወዳጆች በሆኑት ኢትዮጵያ እና ግብፅ መካከል ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ውጥረት ቀስቅሰዋል።" ]
ይህም በአሜሪካ እና በአፍሪካ የዲፕሎማሲ ታሪክ ትልቁ የትራምፕ ስህተት ነው ይላሉ። ትራምፕ ከቀናት በፊት ግብፅ "ግድቡን ልታፈነዳው ትችላለች" ማለታቸው ይታወሳል። ጥር ላይ ፕሬዚዳንቱ "ስምምነት መፍጠር ችያለሁ፤ ከባድ ጦርነትም አስቁሜያለሁ" ብለው የኖቤል የሰላም ሽልማት እንደሚገባቸው መናገራቸው ይታወሳል። ነገር ግን ተሸላሚ የሆኑት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ነበሩ ። ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እንደሚገባቸው ሲናገሩ ጉዳዩን ግልፅ ባያደርጉትም፤ በግብፁ ፕሬዘዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ጥሪ መሠረት በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ጣልቃ ስለመግባታቸው እየተናገሩ እንደነበረ ይታመናል። ትራምፕ በአንድ ወቅት አብዱልፈታህ አል-ሲሲን "የኔ ምርጡ አምባገነን" ማለታቸው አይዘነጋም። ግብፅ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ "ለደህንነቴ ያሰጋኛል" ትላለች። ሱዳንም የግብፅን ያህል ባይሆንም ስጋቱን ትጋራለች። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የኃይል አመንጪውን ግድብ አስፈላጊነት አስረግጣ ትገልጻለች። ኢትዮጵያውያን ትራምፕን ጠልተዋል? ኬንያ የሚገኘው የአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ጉዳይ ተንታኝ ረሺድ አብዲ እንደሚለው፤ በግድቡ ዙሪያ ኢትዮጵያ እና ግብፅን ለማደራደር አሜሪካ ጣልቃ መግባቷ የሁለቱን አገሮች ውጥረት አባብሷል። "ኢትዮጵያ በግድቡ አቅራቢያ የጸጥታ ኃይሏን እያጠናከረች ነው። ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ከበረራ ውጪ ማድረጓ አንዱ ማሳያ ነው። በግድቡ ዙሪያ በረራ የሚያግድ መሣሪያም ተገጥሟል። ግብፅ የወታደራዊ ቅኝት በረራ ልታደርግ እንደምትችል ከመስጋት የመነጨ ሊሆን ይችላል" ይላል። ተንታኙ እንደሚናገረው፤ ትራምፕ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ እንዴት እንደሚሠራ የሚገነዘቡ አይመስልም። "በንግዱ ዓለም እንደሚደረገው ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል የሚል የተዛባ አመለካከት አላቸው። የውጪ ጉዳይ መያዝ ያለበትን ጉዳይ ግምዣ ቤት ድርድሩን እንዲመራ ያደረጉትም ለዚህ ነው። ከመነሻውም መጥፎ የነበረውን ሁኔታም አባብሶታል" ሲልም ረሺድ ያስረዳል። ኢትዮጵያ ከግብፅ እና ከሱዳን ጋር ያለው ድርድር ሳይቋጭ ግድቡን ለመሙላት በመወሰኗ አሜሪካ የ100 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ማጠፏ ተዘግቧል። ትራምፕና አል-ሲሲ ረሺድ "ኢትዮጵያ አሜሪካ እንደከዳቻት ይሰማታል። ብዙ ኢትዮጵያውያን ትራምፕን የጥላቻ ምልክት አድርገውታል" በማለት ሁኔታውን ይገልጻል። የዴሞክራት እጩው ጆ ባይደን እንዲያሸንፉም የበርካታ ኢትዮጵያውያን ምኞት ነው። አሜሪካ የሚገኘው ሴንተር ፎር ግሎባል ዴቨሎፕመንት ውስጥ የፖሊሲ አጥኚ ደብሊው ጉዬ ሙር እንደሚሉት፤ የትራምፕ አስተዳደር እስራኤልና የአረብ ሊግ አገራት መካከል ሰላም መፍጠር ስለሚፈልግ ከግብፅ ጎን መቆሙ የሚጠበቅ ነው። የትራምፕ ዲፕሎማሲ ግብፅ ከእስራኤል ጋር ዘመናት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ትስስር አላት። ትራምፕ የአረብ ሊግ አገራት ለእስራኤል እውቅና እንዲሰጡ ጥረት እያደረጉ ስለሆነ አብዱልፈታህ አል-ሲሲን ማስቀየም አይፈልጉም። ሙር እንደሚናገሩት፤ የትራምፕ አስተዳደር በግድቡ ዙርያ ለግብፅ የወገነውም በዚህ ምክንያት ነው። ትራምፕ ሱዳንን በተመለከተ የደረሱበት ውሳኔ የአረቡን አገራት ከእስራኤል ጋር ለማስስማት የሚያደርጉት ጥረት አንድ አካል ነው። ሱዳን ከእስራኤል ጋር ስምምነት ለማድረግ ወስናለች። በእርግጥ የአገሪቱ ተጠባባቂ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ውሳኔው ገና በሕግ አውጪ መጽደቅ እንዳለበት ቢናገሩም፤ ሱዳን እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 1967 ላይ የአረብ ሊግ አገራት ውይይት ማስተናገዷ መዘንጋት የለበትም። በውይይቱ "ከእስራኤል ጋር መቼም ሰላም አይፈጠርም። መቼም ቢሆን ለእስራኤል እውቅና አይሰጥም። ድርድርም አይካሄድም" ተብሎም ነበር። ሱዳን ከእስራኤል ጋር ለመስማማት በመፍቀዷ ትራምፕ ሽብርን ከሚድፉ አገሮች ዝርዝር እንደሚያስወጧት ተናግረዋል። ይህም ለምጣኔ ሀብቷ ማገገም የሚረዳ ድጋፍ እንድታገኝ ያግዛታል። ትራምፕ በድጋሚ ከተመረጡ ኢትዮጵያ ግድቡን በተመለከተ ሱዳን እና ግብፅ ላላቸው ስጋት አንዳች መልስ እንድትሰጥ ጫና እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። አጥኚው እንደሚሉት፤ ሱዳን ሽብርን ከሚደግፉ አገሮች ዝርዝር ከወጣች የትራምፕ አስተዳደር በምላሹ የሚጠብቀው ነገር አለ። "ከእስራኤል ጋር ስምምነት የመፍጠር ጉዳይ የሱዳን ማኅበረሰብን የከፋፈለ ነው። መንግሥት የራሱ የጸጥታ ጥያቄዎች እያሉበት ይህን ውሳኔ ማሳለፉ ችግር ሊያስከትል ይችላል" ብለዋል። ከቻይና ጋር ያለው ውጥረት ትራምፕ አፍሪካን በተመለከተ የሚያራምዱት ፖሊሲ፤ በአሜሪካ እና በቻይና መካከል የሚካሄድ 'አዲሱ ቀዝቃዛ ጦርነት' ነው ሲል ረሺድ ይገልጸዋል። ለምሳሌ ቻይና ከግዛቷ ውጪ የመጀመሪያውን ወታደራዊ መቀመጫ የከፈተችው በጅቡቲ ነው። ማዕከሉ የሚገኘው አሜሪካ የሶማሊያ ታጣቂዎች ላይ የአየር ጥቃት ለመሰንዘር ያቋቋመችው ማዕከል አቅራቢያ ነው። በቅርቡ የአሜሪካ ተዋጊ ጀቶች ለማረፍ ሲሞክሩ፤ ቻይና የአሜሪካውያን ወታደሮችን እይታ የሚጋርድ መሣሪያ መሞከሯን ረሺድ ያጣቅሳል። "የትራምፕ አስተዳደር ጸረ ቻይና ፖሊስ ያራምዳል" የሚለው ተንታኙ ሁኔታው ለአፍሪካ ቀንድ አስቸጋሪ መሆኑንም ያስረዳል። ቻይና አፍሪካ ውስጥ ያላትን የንግድ የበላይነት ለመቀልበስ፤ የትራምፕ አስተዳደር 'ፕሮስፔሪቲ አፍሪካ ኢን 2018' የተባለ ፖሊሲ ነድፏል። በአፍሪካ እና በአሜሪካ መካከል የሚካሄደውን ንግድ በእጥፍ የማሳደግ እቅድ አለ። አምና የአሜሪካ መንግሥት የንግድ ተቋሞች አፍሪካ ውስጥ እንዲሠሩ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጥበት አሠራር ዘርግቷል። ሙር እንደሚሉት፤ የአሜሪካ ድርጅቶች ከቻይና ተቋሞች ጋር መወዳደር አልቻልንም ብለው ቅሬታ ስላሰሙ የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት ተወስኗል። "የአይቲ ዘርፍ እንደ ማሳያ ቢወሰድ፤ 70 በመቶ የአፍሪካ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተመሠረተው በቻይና ድርጅቶች ላይ ነው" ሲሉ ያብራራሉ። የአፍሪካ ሕብረትን ማጣጣል የትራምፕ አስተዳደር በ2025 የሚያበቃውን ከ30 በላይ የአፍሪካ አገሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑበት ታስቦ በአሜሪካ ለአፍሪካውያን የተሰጠው ከታሪፍና ከቀረጥ ነፃ የገበያ ዕድል (አፍሪካ ግሮዝ ኤንድ ኦፖርቹኒቲ አክት-አጎዋ) የመሰረዝ እቅድ አለው። ለአፍሪካ ምርቶች የአሜሪካን ገበያ ክፍት የሚያደርገው ስምምነት የተፈረመው በቢል ክሊንተን ነበር። አሜሪካ አሁን ላይ ትኩረቷ የሁለትዮሽ የንግድ ስምምነት እንደሆነ ሙር ይናገራሉ። ለምሳሌ ከኬንያ ጋር ንግግር እየተካሄደ ነው። ኬንያ፤ የቻይና 'ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሽየቲቭ' አካል እንደሆነች ይታወቃል። ስምምነቱ ቻይናን ከአፍሪካ ጋር በንግድ የሚያስተሳስርና የቻይና ዓለም አቀፍ ተደማጭነት የሚያጎላ እንደሆነ አሜሪካ ታምናለች። ትራምፕ ከኬንያ ጋር በቀጥታ ከተስማሙ በኋላ ተመሳሳይ መንገድ ተጠቅመው ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር የመሥራት ውጥን እንዳላቸው ሙር ይናገራሉ። ይህ የትራምፕ መንገድ፤ ከአፍሪካ ሕብረት የንድግና ኢንዱስትሪ ኮሚሽነር አልበርት ሙቻንጋን ሐሳብ ጋር ይጣረሳል። እሳቸው የአፍሪካ አገራት በተናጠል ሳይሆን በአንድነት ከአሜሪካ ጋር ስምምነት እንዲያደርጉ ይፈልጋሉ። ሙር እንደሚሉት፤ የአሜሪካ ውሳኔ የአፍሪካ ሕብረት የአህጉሪቱን ምጣኔ ሀብት ለማጣመር ከሚያደርገው ጥረት ጋር ይጣረሳል። ሕብረቱ፤ አፍሪካን የዓለም ትልቋ ነጻ የንግድ ቀጠና የማድረግ አላማ አለው። ትራምፕ ግን በጥምረት ከሚሠሩ ኃይሎች ጋር በጋራ ያለመደራደር አዝማሚያ ያሳያሉ ሲሉ አጥኚው ያክላሉ። የትራምፕ ተቀናቃኝ ጆ ባይደን ካሸነፉ የአፍሪካ ፖሊሲያቸው ምን እንደሚሆን እስካሁን አልገለጹም። "የባይደን አስተዳደር በኦባማ ጊዜ ወደነበረው ሂደት ሊመለስ ይችላል" ይላሉ ሙር።
xlsum_amharic-train-128
https://www.bbc.com/amharic/news-44150665
የፕሬዝዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛን የስልጣን ዘመን እስከ 2034 ሊያራዝም የሚችለው ህዝበ-ወሳኔ ዛሬ ይካሄዳል
ውዝግብ ያልተለየው የብሩንዲ ህዝበ-ውሳኔ ዛሬ ይካሄዳል።
[ "ውዝግብ ያልተለየው የብሩንዲ ህዝበ-ውሳኔ ዛሬ ይካሄዳል።" ]
ፕሬዝዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ ከ2005 ጀምሮ የብሩንዲ በስልጣን ቆይተዋል በህገ-መንግሥቱ ላይ የሚካሄደው ህዝበ-ውሳኔ የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በስልጣን የሚቆዩበትን ጊዜ እስከአውሮፓዊያኑ 2034 ድረስ ሊያረዝመው ይችላል። በ2015 ለሶስተኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት መወዳደራቸው በሃገሪቱ ግጭት ከመቀስቀሱም በላይ ያልተሳካ መፈንቅለ መንግሥት እንዲካሄድ ምክንያት ሆኗል። በ2015 ብቻ 40 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ብሩንዲ መሸሻቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል በህዝበ-ውሳኔው የሃገሪቱን ፕሬዝዳንት የስልጣን ዘመን ከአምስት ወደ ሰባት ከማሳደግ ባለፈ ጠቅላይ ሚንስትር እንዲኖር የሚያደርግ ስርዓት እንዲዘረጋ ወይም አሁን ያለው አሰራር እንዲቀጥል ነው ድምጽ የሚሰጠው። የመብት ተከራካሪዎች ፕሬዝዳንት ንኩሩንዚዛ የሚፈልጉት ማሻሻያ ድጋፍ እንዲያገኝ ግጭት፣ ጭቆና እና ፍርሃት እንዲሰፍን ሰርተዋል በሚል ይከሷቸዋል። ታዛቢዎች ሁኔታው የ2015ቱ ዓይነት ፖለቲካዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል በሚል ስጋታቸወን ያስቀምጣሉ። ከቀናት በፊት በብሩንዲ ሰሜን-ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኝ የገጠር መንደር 25 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ህዝበ-ውሳኔው ላይ ህዝቡ እንዳይሳተፍ ጥሪ ቢቀርብም ይህን ያደረገ ሰው እስከ ሶስት ዓመት የሚደርስ እስራት ይጠብቀዋል ተብሏል። መንግሥት የሚቀርቡበትን ክሶች በሙሉ ውድቅ አድርጓል። ባለፈው ወር ብቻ 50 ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰራቸው አንድ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ከቀናት በፊት በሃገሪቱ ሰሜን-ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኝ የገጠር መንደር 25 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል። መንግሥት ቢቢሲ እና ቪኦኤ ላይ የስድስት ወራት እገዳ ጥሎባቸዋል። ቢቢሲ በስደት ላይ የሚገኙ የመብት አቀንቃኝን ሞግቶ አልጠየቀም በሚል ነው እገዳው የተጣለበት።
xlsum_amharic-train-129
https://www.bbc.com/amharic/news-54078495
ቤቶች ልማት ለተፈናቃይ አርሶ አደሮች የጋራ መኖሪያ ቤት እያስተላለፍኩ ነው አለ
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በልማት ምክንያት የእርሻ መሬታቸውን ላጡ አርሶ አደሮች የጋራ መኖሪያ ቤቶች እያስተላልፍኩ ነው አለ።
[ "የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በልማት ምክንያት የእርሻ መሬታቸውን ላጡ አርሶ አደሮች የጋራ መኖሪያ ቤቶች እያስተላልፍኩ ነው አለ።" ]
ቀደም ሲል ቢቢሲ ተፈናቃይ አርሶ አደሮች አነጋግሮ ባወጣው ዘገባ ላይ ተፈናቃይ አርሶ አደሮች የተሰጠን የጋራ መኖሪያ ቤት የለም ማለታቸውን ተከትሎ የከተማው ቤቶች ልማት ኃላፊ ሰናይት ዳምጠው በሰጡት በሰጡት ምላሽ ቤቶቹ እተላለፉ መሆኑን አመልክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ኮሚሽንም የከተማው ካቢኔ ግንቦት 2011 ላይ የእርሻ መሬታቸውን በልማት ምክንያት ላጡ አርሶ አደሮች ከ23 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤት ተላልፎ እንዲሰጥ ቢወስንም የጋራ መኖሪያ ቤቱ ተላልፎ አልተሰጣቸውም ብሎ ነበር። ዘገባው ከወጣ በኋላ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ዳምጠው በዘገባው ላይ አስተያየታቸው እንዲካተት የጠየቁ ሲሆን በዚህም ቢሮ ወደ 17 ሺህ ለሚጠጉ አርሶ አደሮች የጋራ መኖሪያ ቤት ማስተላለፉን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአርሶ አደሮች አቤቱታ በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ አርሰው ያድሩ የነበሩ ገበሬዎች፣ በከተማዋ መስፋፋት እና ለልማት በሚል ምክንያት ከእርሻ መሬታቸው የተፈናቀሉ በርካቶች መሆናቸው ይነገራል። "እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም ገበሬ ባዶ እጁን ነው ያለው። ይህ ፈጣሪ የሚያውቀው እውነት ነው" በማለት የተናገሩት ከመሬታቸው ተፈናቅለው የጋራ መኖሪያ ቤት ይሰጣቸዋል ተብለው የጋራ መኖሪያ ቤት እንዳልተሰጣቸው ለቢቢሲ ቃላቸው ከሰጡት አርሶ አደሮች መካከል አንዱ ናቸው። ከንፋስ ስልክ፣ ቦሌ እና የካ ክፍለ ከተሞች ለልማት በሚል ምክንያት ከይዞታቸው የተፈናቀሉ ገበሬዎች ጉዳያቸው መፍትሄ እንዳላገኘ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ዶሮ እንኳ የለንም" አቶ ተሾመ ፈይሳ በየካ ክፍለ ከተማ 15 ሄክታር መሬታቸው የካ ኮንዶሚኒም ሲሰራ በ2004 ዓ.ም እንተወሰደባቸው ይናገራሉ። አቶ ተሾመ እንደሚሉት ከሆነ የእርሻ መሬታቸውን ከተነጠቁ ወዲህ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ገልፀዋል። "የእኔ እና የአባቴን 15 ሄክታር መሬት ሲወስዱብን 1 ካሬ መሬትን በ15 ብር ነው ያሰሉት። እኛ ወደ 14 የቤተሰብ አባላት እንሆናለን። በዛን ወቅት ለአጨዳ የደረሰ እህል እስክናነሳ እንኳን አልጠበቁንም። እህላችንን በዶዘር ነው የጠረጉት።" ከእርሻ ውጪ ሌላ ክህሎት እንደሌላቸው የሚናገሩት አቶ ተሾመ፤ የእርሻ መሬታቸው ከተወሰደ ወዲህ ላለፉት 8 ዓመታት በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ይገልጻሉ። "መሬታችን ከተወሰደ በኋላ እርሻ የለንም፣ ከብት ለንም። ዶሮ እንኳን የለንም። እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም ገበሬ ባዶ እጁን ነው ያለው። ይህ ፈጣሪ እና ይህች ምድር የሚያውቁት ሃቅ ነው።" ይላሉ። አቶ ተሾመ ጨምረው እንደተናገሩት እርሳቸው እና ጎረቤቶቻቸው የገቢ ምንጭ ስለሌላቸው ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ እንዳልቻሉ ያስረዳሉ። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የነበሩት አቶ ታዬ ከበደም በተመሳሳይ የእርሻ መሬታቸው ለልማት በሚል ምክንያት ከተነጠቁ በኋላ ለችግር መጋለጣቸውን ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ከ1995 ጀምሮ ለልማት በሚል ምክንያት የእርሳቸው እና የጎረቤቶቻቸው መሬት ስለተወሰደባቸው፤ ከአዲስ አበባ ተሰድደው መውጣታቸውን አቶ ታዬ ይናገራሉ። "እኛ አከባቢ መፈናቀል የቆየ ነገር ነው። አያቶቻችንም ከመሃል ከተማ ተገፍተው ነው ወደ ከተማ ዙሪያ የወጡት። አገር ለቀው የተሰደዱም አሉ" በማለት ይናገራሉ። መሬታቸው የተነጠቁ ገበሬዎች እና የተወሰነ የእርሻ መሬት ያላቸው ገበሬዎች በከተማ ግብርና እንዲሰማሩ ከ2012 ጀምሮ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን አርሶ አደሮቹ ጨምረው ተናግረዋል። አርሶ አደሮቹ ግን በቀረችን መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ ትከሉበት ብለውን ትንሽ እንቅስቃሴ ተጀምሯል እንጂ ያገኘነው ነገር የለም ይላሉ። የከተማ አስተዳደሩ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ፈትያ መሐመድ በአንድ ዓመት ውስጥ ከይዞታቸው የተፈናቀሉ 67 ሺህ አርሶ አደሮች መረጃ መሰብሰቡን ይናገራሉ። ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ በ2012 ዓ.ም መሬታቸው ከተወሰደባቸው ገበሬዎች መካከል 1655 የሚሆኑት መጠለያ እና ገቢ ምንጭ በማጣታቸው በእምነት ተቋማት እና መንገድ ላይ በልመና ህይወታቸውን እየገፉ ነው። "እነዚህ አርሶ አደሮች መሬታቸው ከተወሰደ በኋላ ወዴት እንዳሉ የሚያውቅ አካል የለም፤ መረጃው ያለው ማንም የለም። የተከናወነው ነገር ገበሬዎቹን የማፈናቀል ስራ ነው የሚመስለው" ይላሉ ኮሚሽነሯ። ከይዞታቸው የተፈናቀሉት አርሶ አደሮች ተበታትነው ይኑሩ እንጂ የአንድ አካባቢ ጎረቤታሞች የነበሩት አርሶ አደሮች ማን የት እንዳለ ያውቃሉ። ኮሚሽነር ፈቲያም ስለ አርሶ አደሮቹ መረጃ መሰብሰብ የተቻለው በእነዚህ አርሶ አደሮች አማካኝነት እያጠያየቁ ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ እንደሆነ ይናገራሉ። ኮሚሽኑ መረጃ የተሰበሰበባቸው 67ሺህ አርሶ አደሮች ከቀደመ ኑሯቸው ዝቅ ያለ ደረጃ ላይ ቢገኙም 1ሺህ 655 የሚሆኑት ግን በከፍተኛ ድህነት ውስጥ እንደሚገኙ እና በልመና የሚተዳደሩም እንዳሉ ተናግረዋል። በዚህም መሠረት ለእነዚህ ለከፍተኛ ችግር ለተጋለጡት አርሶ አደሮች በየወሩ ገንዘብ እንዲያገኙ በማድረግ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ 2011 ግንቦት ወር የእርሻ መሬታቸውን የተነጠቁ ገበሬዎች ከ23ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤት እንዲተላለፍላቸው ቢወስንም ቢቢሲ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ግን የጋራ መኖሪያ ቤቱ ተላልፎ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል። የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) ወደ 20ሺህ የሚጠጉ ጋራ መኖሪያ ቤቶች በልማት ምክንያት ከእርሻ መሬታቸው ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች መሰጠቱን ተናግረው ነበር። ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በቅርቡ በኋላ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ በከተማው ካቢኔ ውሳኔ መሠረት ለ20ሺህ አርሶ አደሮች ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የጋራ መኖሪያ ቤት እንዲሰጥ መወሰኑን አስታውሰዋል። "እንዲሰጥ የተወሰነው ቤት ቁጥር ከተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ከግማሽ በታች ነው። እጣ የወጣው ጥቅምት 2012። ገበሬ እጅ የደረሰ ግን አንድም ቤት የለም። የከተማው የቤቶች ልማት ቢሮ ለምን ይዞ እንደሚቀመጥ ግልጽ አይደለም" የሚሉት ደግሞ ወ/ሮ ፈትያ ናቸው። የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ምላሽ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ዳምጠው በልማት ምክንያት ለተነሱ አርሶ አደሮች ተገቢው የማጣራት ሥራ እየተከናወነ በከተማ ካቢኔው ውሳኔ መሠረት የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን ቢሯቸው እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። የከተማው ካቢኔ ተላልፈው እንዲሰጡ ከወሰናቸው ወደ 23 ሺህ ከሚጠጉ መኖሪያ ቤቶች አብዛኛው ቤቶች ለአርሶ አደሮች ተላልፈው መሰጠታቸውን ተናግረዋል። ሰናይት ዳምጠው "በልማት የተነሱ አርሶ አደሮች መሆናቸው በኮሚሽኑ [የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ኮሚሽን] ሲረጋገጥ ይሰጣቸው ተብሎ የተወሰነላቸው ወደ 23 ሺህ የሚጠጉ አርሶ አደሮች ናቸው" ብለዋል። ጨምረውም "እስካሁንም ከተጠቀሱት መካከል ለአብዛኞቹ ቤቱን ሰጥተናል። የቀሩት ወደ 5 ሺህ የሚጠጉት ብቻ ናቸው። ለተቀሩትም ተጣርቶ ሲመጣ የከተማው ከቢኔ በወሰነው መሠረት የሚቀጥል ነው የሚሆነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቢሮ ኃላፊዋ እንዳሉት ቤቶቹን ለአርሶ አደሮች በማስተላለፍ ሂደት ላይ መዘግየት መኖሩንም ሳይጠቅሱ አላለፉም። "ቤቶቹን አስተላልፈን ከመስጠታችን በፊት የማጣራት ሥራ እንዲሰራ ተደርጓል። አርሶ አደሮቹን ፈልጎ ማግኘት፣ ማንነት ማጣራት፣ የሚገባቸው መሆኑን አለመሆኑን የመለየት በርካታ ሥራዎች በኮሚሽኑ በኩል ሲሰሩ ነበር" ሲሉ ቤቶች ከመተላለፋቸው በፊት ማጣራት እንደሚደረግ አመልክተዋል፥ በቢሮው በኩልም "ዕጣ የማውጣት ሥራ፣ የልኬት ሥራ፣ ካርታ የማጣም ሥራዎች ነበሩብን። ለሌላው የከተማ ነዋሪም የሚሰጥ ቤት ነበር ተደራራቢ ሥራ አለ" በማለት ለአርሶ አደሮች ቤቶች በፍጥነት ተላልፈው ያልተሰጡበትን ምክንያት አስረድተዋል።
xlsum_amharic-train-130
https://www.bbc.com/amharic/news-45705051
በቤንሻንጉል ጉምዝ በተፈጠረ ግጭት ከ70 ሺህ ሰዎች በላይ ሲፈናቀሉ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተሰማ
መስከረም 16/2011 ዓ.ም የካማሼ ዞን አመራሮች ከምዕራብ ኦሮሚያ አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ ጋር የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቅቀው እየተመለሱ በነበሩ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ በተከፈተው ተኩስ የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በተወሰኑ ከኦሮሚያ ጋር በሚዋሰኑ ስፍራዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞታቸውን፣ መፈናቀላቸውን ቤቶች መቃጠላቸውን የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አበራ ባይታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
[ "መስከረም 16/2011 ዓ.ም የካማሼ ዞን አመራሮች ከምዕራብ ኦሮሚያ አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ ጋር የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቅቀው እየተመለሱ በነበሩ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ በተከፈተው ተኩስ የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በተወሰኑ ከኦሮሚያ ጋር በሚዋሰኑ ስፍራዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞታቸውን፣ መፈናቀላቸውን ቤቶች መቃጠላቸውን የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አበራ ባይታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።" ]
በተለይ በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ ስር ሳይ ዳለቻ ቀበሌ ግጭት የነበረ ሲሆን በግጭቱም 75 ቤቶች ተቃጥለዋል ብለዋል። በዚሁ ወረዳ ጅጋንፎይ ቀበሌ በጭበጭ በምትባል አካባቢ ላይ ቤቶች መቃጠላቸውን ጠቅሰው ሌሎች ቀበሌዎችም ላይ ተመሳሳይ ግጭቶች መከሰሰታቸውን ተናግረዋል። • በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር ዘጠኝ ደርሷል ተባለ • ሞትና መፈናቀል በአዲስ አበባ ዙሪያ • በሰኔው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች ላይ የሽብርተኝነት ክስ ተመሰረተ • የካማሼ ዞን አመራሮች በታጣቂዎች ተገደሉ በበሎይ ጅጋንፎ ሶቤይ ከተማ ላይ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በሶጌ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ልቢጋ፣ ሳይ ዳላቻ፣ ታንካራ ቀበሌዎች በርካታ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አስረድተዋል። "በተንካራ 105 ቤቶች ተቃጥለዋል 3 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል" ያሉት መስተዳድሩ በበጭበጭ 1 ሰው መሞቱንና አንገርባጃ ቀበሌ 2 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አስረድተዋል። እንደ ክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለፃ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ እና በስጋት ምክንያት ወደ ጫካ የገቡ ሰዎች ያሉ ሲሆን ቁጥራቸው ምን ያህል ነው የሚለውን ግን የተጠናቀረ መረጃ የለኝም በማለት ሳይናገሩ ቀርተዋል። የተፈናቀሉት ሰዎች ከቤንሻንጉል ብቻ ሳይሆን ክልሉን ከሚያዋስኑት የኦሮሚያ ቀበሌዎችም እንደሆነ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ሳስጋ ወረዳ ዱራበሎ፣ ካምፕ፣ በሎበሬዳ፣ ስምንተኛ ከሚባሉት ቀበሌዎች በስጋት ምክንያት ወደ ነቀምትና በሎበሬዳ ወደሚገኙ ማዕከሎች ተፈናቅለው እንደሚገኙ ተናግረዋል። የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታከለ ቶሎሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቤንሻንጉል ክልል የኦሮሚያ አዋሳኝ ቀበሌዎች በተከሰተው ግጭት 12 ሰዎች ሲሞቱ 14 ሰዎች እንደቆሰሉ የነገሩን ቢሆንም አሁን ግን የሟቾች ቁጥር 23 መድረሱን ገልፀውልናል። ከዚህ በተጨማሪም ከ70 በላይ የሚሆኑ የቀንድ ከብቶች እንደተወሰዱባቸውም ጨምረው ተናግረዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሳስጋ ወረዳ ጤና ጣቢያና በነቀምት ሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል። እንደ ኃላፊው ገለፃ ከሆነ ቀያቸውን ጥለው ወደ ኦሮሚያ የተሰደዱ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ ደርሷል ያሉን ቢሆንም አሁን ግን የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከ70 ሺህ በላይ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እነዚህ ሰዎች የተፈናቀሉት ከበሎይ ጅጋንፎና ያሶ ሲሆን ከኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ደግሞ ሀሮ ሊሙ፣ ሶጌና ሳስጋ አካባቢዎች ነው። አቶ ታከለ ጨምረውም ከእነዚህ አካባቢዎች የሚፈናቀሉ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆችች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ መሆኑን ገልፀዋል። የተፈናቀሉት ሰዎች ሳስጋ ወረዳ፣ ነቀምት ከተማ፣ ሀሮ ሊሙ ወረዳና ጉቶ ጊዳ ወረዳ ውስጥ ኡኬ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ጨምረው አስረድተዋል። በምሥራቅ ወለጋ የሀሮ ሊሙ ወረዳ ኮሙኑኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዱጋሳ ጃለታ በበኩላቸው ከቤንሻንጉል ክልል 7 ቀበሌዎች 20 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን እስካሁን ባላቸው መረጃ በወረዳው ብቻ 5 ሰዎች ሞተዋል። 2 ነፍሰጡር እናቶች መንገድ ላይ መውለዳቸውን የተናገሩት አቶ ዱጋሳ ህፃናት፣ እናቶችና አቅመ ደካሞች የመኪና መንገድ ባለመኖሩ የተነሳ ለመሸሽ አዳጋች እንደሆነባቸውም ጨምረው አስረድተዋል። በቤንሻንጉል ክልል ግጭት በተከሰተባቸው በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ ሦስት አካባቢዎች እንዲሁም በካማሼ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሰፍረው እንደሚገኙ የተናገሩት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በተለያየ ጊዜ ምርት በሚደርስበት አካባቢ በክፍፍል ወቅት በተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚነሱ ነገር ግን እነዚህን ወስዶ ብሄር ተኮር ግጭት ነው ማለት እንደማይቻል አስረድተዋል። የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታከለ ቶሎሳ በበኩላቸው እስካሁን ድረስ 40 ሰዎች ከቤንሽንጉል 5 ሰዎች ደግሞ ከኦሮሚያ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ለተፈናቀሉ ሰዎች የአካባቢው ማህበረሰብ እርዳታ እያደረገላቸው መሆኑን ከመንግሥት ደግሞ አስፈላጊው ድጋፍ እየተጠበቀ እንደሆነ ተናግረዋል።
xlsum_amharic-train-131
https://www.bbc.com/amharic/news-44198353
ምላሹ የዘገየው የኢትዮጵያዊያን የካሳ እና ይቅርታ ጥያቄ ፣ወደ ቫቲካን ሰዎች
ከያኔው ገነተ-ልዑል ቤተመንግስት፣ከዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዝቅ ብሎ ኢትዮጵያ መቼም የማትዘነጋውን የእልቂት ቀን የሚዘክር ባለ 28 ሜትር ሃውልት አለ፡፡
[ "ከያኔው ገነተ-ልዑል ቤተመንግስት፣ከዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዝቅ ብሎ ኢትዮጵያ መቼም የማትዘነጋውን የእልቂት ቀን የሚዘክር ባለ 28 ሜትር ሃውልት አለ፡፡" ]
የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ሃውልት በያመቱ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ስፍራ የካቲት 12 ቀን ይሰበሰባሉ፡፡አባት እና እናት አርበኞች "እመ-ሰቆቃ" ግራዚያኒን በቀረርቶ ያወግዛሉ፣አምስት አመት ጣልያን ታግለው ለሀገሪቱ ዳግም ነጻነትን ያመጡትን ጀግኖች እያነሳሱ በፉከራ ያሞግሳሉ፡፡አንዳንዶቹ ደግሞ የዚህ ሁሉ በደል ፈጻሚ ሀገር መቼ ይሆን ይፋዊ ይቅርታ የምትጠይቀው? እጃቸው ያለበት አካላትስ የካሳ ከረጢታቸው መቼ ይሆን የሚፈታው ? ሲሉ ከንፈራቸውን ይነክሳሉ :: የካሳ እና ይቅርታ ዘመቻ ወደ ቫቲካን ሰዎች የሙዚቃ መሳሪያ እስከ አፍንጫው የታጠቀ የማርሽ ባንድ ሰራዊት፣ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የመጡ ብላቴናዎች ክያኔ፣ለዝክር የመጣው ሰው ስነ-ስርዓቱ ካለቀ በኋላ ቤቱ ገብቶ የሚያወራው አዲስ ነገር አሳጥተውት አያውቁም፡፡ የ2002 ዓመተ ምህረቱ የሰማዕታት ቀን ማግስት አዲስ ነገርን በተመለከተ በአያሌው ዕድለኛ ሳይሆን አልቀረም፡፡ አዲስ አበባ ጀግኖችን አሞግሳ ፤ለሰማዕታት የነፍስ ይማር ጸሎት አድርሳ በተመለሰች ማግስት፣ የካቲት 29-2002 ዓ.ም ፣ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ‹ዓለማቀፍ ህብረት ለፍትህ -ለኢትዮጵያዊያን ጉዳይ› የተሰኘ ተቋም በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ትብብር የሚጠይቅ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ ይፋ አደረገ። የዘመቻውን ይዘት ከሚያብራራው ጥራዝ ላይ ትንሽ እንቆንጥር፣ "በ1935-41(እኤአ) ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ወርራ ባደረሰችው አሰቃቂ የጦር ወንጀል፣ የቫቲካን መንግስት እጅ ከጓንት ሆና ተባባሪ ስለነበረች፤የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ ተጽዕኖ እንዲደረግባት ፣ለዓለማቀፋዊው ህብረተሰብ ፣በዓለም ላሉ መንግስታት ሁሉ ፣ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፤ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት፣….ለሌሎች ለሚመለከታቸው ድርጅቶችና ለእውነት ለቆሙ ህዝቦች ድጋፋቸውን እንዲያበረክቱ አቤቱታችንን በታላቅ ትህትና እናቀርባለን፡፡" የዘመቻው ተጽዕኖ ውጤታማ ይሆን ዘንድ፣ 100ሺ ሰዎች ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ተቋሙ በወቅቱ ጠይቋል። ስምንት ዓመታት አለፉ፣ዘመቻውን የተቀላቀሉ ሰዎች ቁጥር 7ሺ አልሞላም፣ቫቲካንም ይቅርታ አልጠየቀችም። ከፋሽስት ጣልያን የመርዝ ጭስ ራሱን ለማዳን ጭንብል ያጠለቀ ኢትዮጵያዊ የቫቲካን ዝምታ …የአረጋዊው ቁጭት ዘመቻው ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በየአደባባዩ ብቅ እያሉ የዘመቻውን አስፈላጊነት ለማስረዳት ሲለፉ የሚታዩ አረጋዊ አሉ። እኝህ ሰው "ዓለማቀፍ ህብረት ለፍትህ -ለኢትዮጵያዊያን ጉዳይ" የተሰኘው ተቋም ሀላፊ ኪዳኔ ዓለማየሁ ናቸው ፡፡ የታለመው የፈራሚ ብዛት ካለመስመሩ ጎን ለጎን፣ ቫቲካን ካለወትዋች እስከአሁን ኢትጵያዊያንን ይቅርታ አለመጠየቋ አይወጥላቸውም ፣"ናዚዎች በአይሁዶች ላይ እልቂት ሲፈጽሙ ቫቲካን ዝም በማለቷ ብቻ በክርስቲያናዊ ትህትና አይሁዶችን ይቅርታ ጠይቃለች ፣" ሲሉ የሚያነሱት አቶ ኪዳኔ ፣« እንደ ክርስቲያን ድርጅት ለፈፀሙት የወንጀል ተባባሪነት ይቅርታ መጠየቅ አይበዛባቸውም። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሀገር ስለሆነች ይሆን ወደኃላ የሚሉት?ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ነው፣›› ሲሉ ጥያቄ ይመዛሉ፡፡ የተቋማቸውን ስልክ የመታ ሰው ከሚነሳቸው ጥያቄዎች አንዱ ቫቲካን በኢትዮጵያዊያን እልቂት ውስጥ ያላት ተሳትፎ ምን ያህል ነው? የሚል ነው፡፡ ከሌላኛው ጫፍ ብዙ ጊዜ የማይጠፉት አቶ ኪዳኔ የቫቲካንን ተሳትፎ ፤ የይቅርታውን አስፈላጊነት ለማስረዳት አይታክቱም። "ፋሽስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረች ጊዜ ብዙ ወንጀሎች ተፈፅመዋል። አንድ ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ተጨፍጭፈዋል፣ከዚያ ውስጥ በአዲስ አበባ በሶስት ቀናት ብቻ 30ሺ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል፣ ከ2ሺ በላይ ቤተ-ክርስቲያኖችና 525ሺ ቤቶች ወድመዋል። ፋሽስት ጣልያኖች ብዙ ዝርፊያ፣ስደት እና እንግልት በኢትዮጵያዊያን ላይ አድርሰዋል።እንዲያ በሚሆንበት ጊዜ ቫቲካኖች ፋሽስት ጣልያኖችን ደግፈዋል፣ባርከዋል ቀድሰዋል፣" ሲሉ በቁጭት ይናገራሉ። አቶ ኪዳኔ ዓለማየሁ ከታሪክ አዋቂዎች፣ ከንጉሳዊያን ቤተሰቦች፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በመሆን ያቋቋሙት ተቋም፣ ቫቲካን ይቅርታ ትጠይቅ ዘንድ የሚለፋው -ይቅርታው ለኢትዮጵያዊያን ስነልቦናዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ካሳን ብሎም ዓለማቀፋዊ ዕውቅና እንደሚያመጣ በማመን እንደሆነ ያብራራሉ። በተቀናጀ ዘመቻ አቤቱታቸውን ያሰሙ ህዝቦች ለተገቢ ካሳ መብቃታቸውንም ለአብነት ይዘረዝራሉ፣"ጣልያኖች 30ሺ ሊቢያዊያንን በመጨፍጨፋቸው ፣ለዚህ አድራጎታቸው 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ካሳ (በልማት ስራ መልኩ) ለመክፈል ተስማምተዋል፣" በማለት ካለመናገር ደጅ አዝማችነታችን እንዴት እንደተነፈገ ያሰምራሉ፡፡ ይሄ ዘመቻ እንደ ኢትዮጵያ መንግስት እና የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ያሉትን ተቋማት ድጋፍ ቢያገኝ ኖሮ ውጤቱ ይፈጥን እንደነበረ የሚያነሳሱት አቶ ኪዳኔ ፣ዘመቻው ከታለመው የፈራሚዎች ቁጥር እስከ አሁን ድረስ አንድ አስረኛውን አለማግኘቱ የፈጠረባቸውን ቅሬታ አይሸሸጉም፡፡ የጣልያን ጦር ኢትዮጵያን ሲወር "ዲፕሎማሲን " የሚመክረው የአርበኞች ማህበር "በደም እና አጥንት ግብር " ሀገራቸውን ያቆዩ እናትና አባት አርበኞች ያቋቋሙት "የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር" በስምንት ዓመታት ውስጥ የተለያዩ ለውጦችን አስተናግዷል፡፡ ጥቂት የማይባሉት አባላቱን በሞት ተለይተዋል፣ የአስተዳደር ሽግሽግም ተፈጽሟል፡፡ የዛሬ ስምንት ዓመት ማህበሩን ይመሩ የነበሩት ሊቀ-ትጉሃን አስታጥቄ አባተ -በልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተተክተዋል፡፡እንደነበር ከቀጠሉት አንዱ ወኔ ይመስላል፣በማህበሩ መሪ ድምጸት ውስጥ እንደሚሰማው ያለ፣ "የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የኢትዮጵያ ንብረት የሆነ ሚስማር ጭምር ያለአግባብ ሄዶ እንደሆነ 'ወደ ሀገሩ መመለስ አለበት' የሚል ፅኑ የሆነ፣ የማያወላውል አቋም አለው ፣" ይላሉ ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የቫቲካን እና የይቅርታው ጉዳይ ሲነሳ፣ የጋለ ድምጸታቸው መልሶ ይሰክንና በተጀመረው አይነት መንገድ ካሳ እና ይቅርታን የመጠየቅ ሂደት ውስጥ ማህበራቸው ሊሳተፍ እንደማይችል ይናገራሉ። ለዚህ የሚሰጡት ምክንያት ማህበሩ የተመሰረተበት ህግና ደንብ ከላይ የተጠቀሰውን ዓይነት ዘመቻ ለመከወን የማያስችል መሆኑ ነው። ከሁሉም ከሁሉም ግን የማህበሩ ፕሬዚደንት በግለሰቦች አስተባባሪነት እዚህ የደረሰው የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ ውጤታማ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አላቸው።በጋርዮሽ ተፅዕኖ የመፍጠር ሙከራ ይልቅ በመንግስታት መካከል የሚደረግ ንግግር ፍቱን መፍትሄ እንደሚያመጣ ለማሳየት ባቀደ መልኩ፣ "የአክሱምን ሀውልት የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ሄዶ አላመጣውም … ዲፕሎማሲ እንጂ" ይላሉ፡፡ ቫቲካን 'አላት'የሚባለውን የግፍ ተሳትፎንም ልጅ ዳንኤል ጆቴ ይጠራጠሩታል፣ "እኛ እንደምንረዳው( የጣልያንን ጦር) ባርኮ የላከው ሚላኖ ላይ የነበረ ቄስ ነው። የአቶ ዘውዴ ረታን መፅሃፍ ላይ ራሱን የቻለ ታሪካዊ መግለጫ አለው(አቶ ዘውዴ ረታ አምባሳደር በነበሩበት ወቅት ተመራምረው እና ጥናት አድርገው የፃፉት መፅሃፍ ነው)። አንዳንድ ታሪኮችን በስሜታዊነት ተነስቶ ከማየት ርቀን፣ አንስተን እና አውርደን በደንብ ተዘጋጅተን የቀረብን ጊዜ ጣልያኖችም ሆነ እንግሊዞች ነገሮችን የማይመልሱበት ፣የተጠየቁትን የማያደርጉበት ምንም ምክንያት የለም፣"ሲሉ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር በዘመቻው ላይ ያለውን የፍሬ ነገር ጥርጣሬ ያጋራሉ፡፡ ዓለማቀፍ ህብረት ለፍትህ -ለኢትዮጵያዊያን ጉዳይ -የተሰኘው ተቋም ሀላፊ ኪዳኔ ዓለማየሁ "የኢትዮጵያ አምላክ፣ይረዳናል!" በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ‹ዓለማቀፍ ህብረት ለፍትህ -ለኢትዮጵያዊያን ጉዳይ› ሃላፊ ኪዳኔ ዓለማየሁ ድምጽ ውስጥ ሀዘን ተጠልሏል፡፡በልጅ ዳንኤል ጆቴ በኩል የተሰጠው ምላሽ እንዳልተዋጠላቸው ያሳብቃል፡፡ "ለፍትህ ጉዳይ ሁላችንም ሃላፊነት አለብን።እንኳን እኛ ኢትዮጵያዊያኑ ይቅርና ጣልያኖች ሳይቀሩ እየደገፉት ያለ ጉዳይ ነው።በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ኋላ ማለት ለአገር የሚያኮራ ጉዳይ አይደለም፣" ሲሉ ይመክታሉ፡፡ የቫቲካን ተሳትፎ ላይ ጥያቄ መነሳቱም ቢሆን ለእሳቸው እንቆቅልሽ ነው፣ "ብዙሃኑ ጳጳሳት ወርቃቸውን ሳይቀር እያወጡ ለጦርነቱ አስተዋፅኦ ያደረጉ መሆኑን፣ አንደኛው ‹ካርዲናል› ይሄ ጦርነት ቅዱስ ጦርነት ነው ሲሉ የተናገሩት መረጃ አለን፣ የጣልያን ጦር አዲስ አበባ ሲገባ የደስታ መግለጫ ካወጡት መካከል የመጀመሪያው (የቫቲካኑ) ፖፕ ሃያስ ነበሩ፡፡ ይሄንና ሌላ ማስረጃዎችን ያየ ..እንዲህ ያለ የማይሆን ነገር ለመናገር አይችልም፣" ሲሉ ይሟገታሉ፡፡ አቶ ኪዳኔና አጋሮቻቸው ከእኒህ ሁሉ ዓመታት በኃላ "ይሄ ነገር አይሰምርም" ብለው መዝገባቸውን ለማጠፍ ዝግጁ አይደሉም፡፡ ከዚህ ቀደም በቫቲካን ተባባሪነት ለደረሰ በደል፣ የነዋይ ካሳን እና ይፋዊ ይቅርታን ማግኘት እንዲሁም በወቅቱ የተዘረፉ ቁሳቁሶች እና ቅርሶች ወደሀገራቸው ተመላሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ጥረታቸው እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ዓለማቀፍ ህብረት ለፍትህ -ለኢትዮጵያዊያን ጉዳይ -የተሰኘው ተቋም ሀላፊ ኪዳኔ ዓለማየሁ በእነ አቶ ኪዳኔ አለማየሁ መንደር የተስፋ ጀምበር አልጠለቀችም ፡፡በዚህ ዓመት ህዳር ወር ላይ ከ81 ዓመት በፊት የካቲት 12 ለተፈጠረው እልቂት ሰበብ የሆነው ሩዶልፎ ግራዚያኒ መታሰቢያ ሃውልት 'አፊል' ከተሰኘችው የሮማ ጎረቤት ከተማ እንዲነሳ ተወስኗል፡፡ ሃውልቱ እንዲሰራ የገንዘብ ፈሰሱን ያጸደቁት የከተማዋ ከንቲባ እና ሁለት የአስተዳደር አባላት ‹‹ፋሽስት ይቅርተኝነት›› Apologia del Fascismo የሚሰኘው ህግ ተጠቅሶ በስምንት እና ስድስት ወራት እስር እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡ ሃውልቱ መወገድ እንዳለበት ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ሲጎተጉቱ ከነበሩ ተቋማት አንዱ ለሆነው 'ዓለማቀፍ ህብረት ለፍትህ -ለኢትዮጵያዊያን ጉዳይ'፣ውሳኔው የሌሎች ዘመቻዎች ተስፋም ፈጽሞ እንዳልከሰመ የሚያሳይ ምልክት ይመስላል፡፡ ሃላፊው የ ቫቲካን ይቅርታ መዘግየት የሚያብከነክናቸውን ያክል አንድ ቀን ይቅርታው እንደሚሰማ ያላቸውን ዕምነትም ከፍተኛ ነው፡፡ ይሄን የሚደግፈው የሚደጋግሙት ሀረግ ነው ''የፍትህ አምላክ፣የኢትዮጵያ አምላክ፣ይረዳናል!'' የሚለው፡፡
xlsum_amharic-train-132
https://www.bbc.com/amharic/news-48741852
የጄነራል ሰዓረ ቀብር አዲስ አበባ ሳይሆን መቀሌ ይፈጸማል
ቅዳሜ ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ የተገደሉት የሃገር መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የጄኔራል ሰዓረ መኮንን አዲስ አበባ ውስጥ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቀብራቸው እንደሚፈጸም የተነገረ ቢሆንም ከቤተሰቦቻቸውና ከትግራይ ክልል ባለስልጣናት እንደተነገረው ሥነ ሥርዓታቸው መቀሌ ውስጥ እንደሚፈጸም ተገለጿ።
[ "ቅዳሜ ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ የተገደሉት የሃገር መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የጄኔራል ሰዓረ መኮንን አዲስ አበባ ውስጥ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቀብራቸው እንደሚፈጸም የተነገረ ቢሆንም ከቤተሰቦቻቸውና ከትግራይ ክልል ባለስልጣናት እንደተነገረው ሥነ ሥርዓታቸው መቀሌ ውስጥ እንደሚፈጸም ተገለጿ።" ]
የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም ቀደም ብሎ እንደተናገሩት የጄነራል ሰዓረ የቀብር ሥነ ሥርዓት ማክሰኞ ዕለት እንደሚፈጸምና በዚህም የጄነራሉ አስከሬን ከቤታቸው ተነስቶ በወታደራዊ ሥርዓት ታጅቦ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ተወስዶ ከጠዋት እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ በሚሊኒየም አዳራሽ ቤተሰቦቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው በሚገኙበት የሽኝት ሥነ ሥርዓት ይደረጋል ተብሎ ነበር። • ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው • የተገደሉ ባለስልጣናትና ጄኔራሎችን ለመዘከር የሃዘን ቀን ታወጀ ነገር ግን ሰኞ ከሰዓት በኋላ የጄነራሉ ቤተሰቦችና የትግራይ የክልል ሕዝብና መንግሥት ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ሊያ ካሳ የጄነራሎቹ ቀብር መቀሌ ውስጥ እንደሚፈጸምና ይህን ሥነ ሥርዓት የሚያስተባብር ኮሚቴ መዋቀሩን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዠንም የጄነራል ሰዓረ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመቀሌ እንደሚካሄድ እና ማክሰኞ ጠዋት ቦሌ የሽኝት ሥነ ሥርዓት እንደሚደረግ ግልጸዋል። ከጄነራል ሰዓረ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ የተገደሉት የጄኔራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት አስከሬናቸው ወደ ትውልድ ስፍራቸው ተወስዶ የሚቀበር መሆኑንም ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ተናግረዋል። ሁለቱ ጄነራል ሰዓረ መኮንንና ጄነራል ገዛኢ አበራ ቅዳሜ ምሽት ሦስት ሰዓት ላይ አዲስ አበባ በሚገኘው የጄነራል ሰዓረ ቤት ውስጥ በጄነራሉ ጠባቂ መገደላቸው መገለፁ ይታወሳል።
xlsum_amharic-train-133
https://www.bbc.com/amharic/news-45057121
ከባዱ የራስ ምታት ማይግሬን መድሃኒት ሊገኝለት ነው
ማይግሬን (በጭንቅላት የተወሰነ ከፍል ላይ የሚያጋትም የራስ ምታት) ከአምስት ሴቶች አንዷን የሚያጠቃ ሲሆን፤ ሥራን ጨምሮ አጠቃላይ የእለት ከእለት ህይወትን በከፍተኛ ሁኔታ ያውካል። ሆኖም በህመሙ ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች በጣም ጥቂት ናቸው። በቂ የገንዘብ ድጋፍም አላገኙም።
[ "ማይግሬን (በጭንቅላት የተወሰነ ከፍል ላይ የሚያጋትም የራስ ምታት) ከአምስት ሴቶች አንዷን የሚያጠቃ ሲሆን፤ ሥራን ጨምሮ አጠቃላይ የእለት ከእለት ህይወትን በከፍተኛ ሁኔታ ያውካል። ሆኖም በህመሙ ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች በጣም ጥቂት ናቸው። በቂ የገንዘብ ድጋፍም አላገኙም።" ]
ለመጀመሪያ ጊዜ የማይግሬን ህመም ያጋጠመኝ ከትምህርት ቤት ስመለስ ነበር ትላለች የቢቢሲ ጋዜጠኛ ላውረን ሻርኪይ። በመጠኑ ምቾት በመንሳት የጀመረው ህመም ቀስ በቀስ ወደ ከፍተኛ የራስ ምታት ተቀይሮ መፈጠረን የሚያስጠላ ህመም እንደሆነባት ትናገራለች። • የወባ መድሃኒት ጥቅም ላይ ሊውል ነው • የወር አበባ ለምን በአንዳንድ ሴቶች ላይ ህመም ያስከትላል? • ቀዶ ህክምና በአፍሪካ ስጋት መሆኑ ከፍ ብሏል ''በማይግሬን ምክንያት ማንም ሰው ሊረዳኝ እንደማይችል እስከማሰብና እንደውም ሥራዬንም እስከመተውም ደርሼ ነበር። በዚህ ሁኔታ ለዓመታት ኖሬያለሁ" ትላለች። እስካሁን ድረስ የማይግሬን ትክክለኛ መንስኤ አልታወቀም። ሀኪሞችም የማያዳግም ህክምና መስጠት አልቻሉም። የዓለም የጤና ድርጅት ከ195 ሀገራት በሰበሰበው መረጃ መሰረት እንደ አውሮፓውያኑ ከ1990 እስከ 2016 ድረስ ማይግሬን ሰዎችን ለአካል ጉዳት ከሚያጋልጡ በሽታዎች ሁለተኛውን ቦታ ይዟል። ማይግሬን በዓለም ላይ ውስን ጥናት ከተደረገባቸው የጤና እክሎች አንዱ ሲሆን፤ ብዙ ጊዜ ሴቶችን ያጠቃል። ከአምስት ሴቶች አንዷ በማይግሬን የምትጠቃ ሲሆን በአንጻሩ ከ15 ወንዶች አንዱ ብቻ ማይግሬን ሊይዘው ይችላል። ሴቶች ላይ ለምን በብዛት የይከሰታል? ማይግሬን በሴቶች ላይ በብዛት የሚታይበት ምክንያት እስካሁን አይታወቅም። የአሪዞና ዩኒቨርሲቲ አይጦችን በመጠቀም በሰራው ጥናት መሰረት ልዩነቱ የተፈጠረው፤ ሴት አይጦች ''ኤን ኤች ኢ 1'' የተባለ ንጥረ ነገር በሰውነታቸው ውስጥ ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ ስላለና ወንድ አይጦች ደግሞ ''ኤስትሮጂን'' የተባለ ንጥረ ነገር በሰውነታቸው ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚገኝ ሳይሆን እንደማይቀር ጠቁሟል። ''ኤን ኤች ኢ 1'' የተባለው ንጥረ ነገር ሰውነታችን ውስጥ በበቂ ሁኔታ ካልተገኘ ህመምን የመቋቋም አቅማችን በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ ይችላል። • በእባብ በመነደፍ ሳቢያ በመቶ ሺዎች እንደሚሞቱ ተገለፀ • ስለ ወንዶች ፊስቱላ ምን ያህል ያውቃሉ? ማይግሬን በዋነኛነት ሴቶችን ቢያጠቃም በአሪዞና ዩኒቨርሲቲ ከተሰራው ጥናት ውጪ የተሰሩ ሌሎች ጥናቶች አብዛኛውን ናሙና የወሰዱት ከወንዶች ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 በተሰራ ጥናት ማይግሬን ካለባቸው ሰዎች ከሌለባቸው ጋር ሲነጻጸሩ በሦስት እጥፍ ለጭንቀት ይጋለጣሉ። ድብርት ያለባቸው ሰዎች ደግሞ በሦስት እጥፍ ለማይግሬን የተጋለጡ ናቸው። በጥናቱ መሰረት በማይግሬን ከተጠቁ ስድስት ሰዎች መካከል አንዱ ራሱን ለማጥፋት ያስባል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ማይግሬን ለብዙ የአእምሮ በሽታዎች የሚያጋልጥ ቢሆንም እስካሁን አስተማማኝ ህክምና ሊገኝለት አልቻለም። መፍትሄ ይገኝለት ይሆን? ስለማይግሬን ሲያጠኑ የነበሩ ተመራማሪዎች በቅርቡ ተስፋ ሰጪ መድሃኒት ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። መድሃኒቱ ''ኢረንማብ'' ይሰኛል። በመርፌ መልክ የሚወሰድ ይሆናል። መድሃኒቱ በወር አንዴ ይሰጣል። የማይግሬን በሽታ ከመከሰቱ በፊት ቀድሞ ለመከላከል ይረዳልም ተብሏል። መድሃኒቱን ለየት የሚያደርገው ከሌሎች በሽታዎች ጋር በተያያዘ ሳይሆን ለማይግሬን ብቻ ተብሎ መሰራቱ ነው። በማይግሬን የሚሰቃዩ ሰዎች በቅርቡ መፍትሄ ሊያገኙም ይመስላል።
xlsum_amharic-train-134
https://www.bbc.com/amharic/news-50915564
የኤርትራና ኳታር ቅራኔ
ኤርትራ ከመካከለኛው ምሥራቅና ከባሕረ ሰላጤው አረብ አገራት ጋር ለዓመታት የተገነባ ጥብቅ ግንኙነት አላት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቀደም ሲል ወዳጇ ከነበረችው ኳታር ጋር ያላት ግንኙነት ከመቀዛቀዝ አልፎ በግልጽ እስከ መካሰስ ደርሷል።
[ "ኤርትራ ከመካከለኛው ምሥራቅና ከባሕረ ሰላጤው አረብ አገራት ጋር ለዓመታት የተገነባ ጥብቅ ግንኙነት አላት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቀደም ሲል ወዳጇ ከነበረችው ኳታር ጋር ያላት ግንኙነት ከመቀዛቀዝ አልፎ በግልጽ እስከ መካሰስ ደርሷል።" ]
የኤርትራ መንግሥት ከኳታር ጋር የመረረ ውዝግብና ክስ ውስጥ ገብቶ ባለፉት ወራት ብቻ ኳታር የኤርትራን መንግሥት ለማዳከም የተለያዩ ጥረቶችን እንዳደረገች የሚገልጹ ጠንካራ ክሶች ስታቀርብ ኳታር ግን በተደጋጋሚ ስታስተባብል ቆይታለች። • "የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ • የኦሮሞና የሶማሌ ግጭት የወለደው የቴሌቭዥን ጣቢያ ኤርትራ ቅሬታዋን ስታቀርብ የቆየችው በኳታር ላይ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጊዜያት የኤርትራ መንግሥት ያወጣቸው ክሶች ሱዳንና ቱርክንም የሚጨምሩ ናቸው። ከእነዚህም በአንዱ ኳታር በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተፈጠረው ግንኙነት ደስተኛ አይደለችም ሲል ጎንተል አድርጓታል። ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ በኤርትራ መንግሥት የወጣው መግለጫ ሦስቱንም አገራት ያካተተ ነበር። በዚህም ኳታርና ሱዳን ያቀናጁትን "አፍራሽ" ተግባር በኅብረት እየሰሩ እንደሆነና፤ ቱርክም ተሳታፊ በመሆን የአገራቱ "ጥንስስ እያማሰለች" እንደሆነ ይጠቅሳል። በተለይም ቱርክ ሱዳንን ማዕከሉ ያደረገውን የሙስሊም ምክር ቤትን [መጅሊስ ሹራ ራቢጣ ኡላማአ ኤሪትሪያ] በመደገፍ፤ ኤርትራን ለማወክ እየሰራች መሆኑንና ሱዳንም ተባባሪ እንደሆነች መክሰሱ ይታወሳል። ባለፈው ወር የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው ጠንከር ያለ መግለጫ ደግሞ፤ "ኳታርና ሸሪኮቿ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎችንና የፖለቲካ መሪዎች እንዲሁም ወጣቶችን በመቀስቀስ የጦር መሳሪያ እንዲታጠቁና ተቃውሞ እንዲያስነሱ ተዘጋጅታለች" ሲል ከሷል። የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ይህ ክስ "ውሸት ነው" ብላ ያጥላላችው ኳታር በበኩሏ፤ ኤርትራ ውስጥ ካሉ ቡድኖች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላት አመልክታ፤ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኳታር የኤርትራ አምባሳደርን በመጥራት አገራቸው ለኤርትራ ክስ ያላትን "ተቃውሞ" የሚገልጽ ሰነድ ሰጥተዋል። ኤርትራና ኳታር የሁለትዮሽ ግኑኝነት ነበራቸው? በአንድ ወቅት፤ የኤርትራው ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ኳታር አዘውትረው ከሚጎበኟቸው አገራት መካከል ቀዳሚዋ ነበረች። የሁለቱ መንግሥታት ወዳጅነትም ጠንካራና እንደነበረም፤ የቀጠናውን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ ተንታኞች ይናገራሉ። ለዚህም ከ10 ዓመታት በፊት በድንበር ይገባኛል ምክንያት ግጭትና ውዝግብ ውስጥ ገብተው የነበሩት ኤርትራና ጂቡቲን ለማስማማት ጥረት ከማድረግ አልፋ በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ ሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን እስከማስፈር ደርሳ ነበር። ይህም ኳታር ከኤርትራ ጋር ለነበራት ወዳጅነት እንደ አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊነሳ ይችላል። ኤርትራ፤ በሱዳንና በኳታር ላይ ክስ ማቅረብ ከመጀመርዋ በፊትም፤ "የቤጃ እርቅ" ተብሎ የሚጠራውንና በምሥራቅ ሱዳን የነበረውን ችግር ለመፍታት የተደረገው ስምምነት አገሯ ላይ እንዲፈረም አድርጋለች። • መገደል፣ መደፈር፣ መዘረፍ ማብቂያ የሌለው የኢትዮጵያውያን የስደት ጉዞ • የኤምሬትስና የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ፖለቲካ? ለዚህም በወቅቱ የኤርትራ የቅርብ ወዳጅ የነበረችው የኳታር ድጋፍ እንደነበረት የአፍሪካን ፕሮግረስ ሴንተር ኃላፊና የአካባቢው የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አቶ ዓሊ ህንዲ ለቢቢሲ ይገልጻሉ። የኋላ የኋላ ግን ወዳጅነታቸው የሚያሻክር ክስተት መከሰቱን ጨምረው ይጠቅሳሉ፤ ኳታር በመካከለኛው ምሥራቅና በባሕረ ሰላጤው አካባቢ ኃያል ከሆኑት ከሳኡዲና ከኤምሬትስ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ስትገባ ጂቡቲና ኤርትራ ኳታርን ገሸሽ አድርገው ወዳጅነታቸውን ከሁለቱ አገራት ጋር አጠናከሩ። ኳታርም ወታደሮቿን አስወጣች። የፍጥጫው ጅማሬ የመካከለኛው ምሥራቅና የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንተኝ የሆኑት አቶ ዓብዱልራሕማድ ሰይድ አቡሃሽም፤ ለዚህ መነሻ የሆነውን ምክንያት ሲጠቅሱ፤ በገልፍ አረብ የሚገኙት ኤሜሬትስና ሳውዲ ኳታርን የሚቃወም አቋም በመውሰድ የየብስና የባሕር ማዕቀብ መጣላቸው ነው። ኤርትራም ከኳታር ጋር የነበራት ግንኙነት በማቋረጥ የሳኡዲና የኤምሬትስን ጎራ በመቀላቀል፤ አገራቱ በመን አማጺያን ላይ የሚያካሂዱትን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ደግፋ ቆመች። ይህም ኤርትራ ወዳጇ የነበረችውን ኳታርን ትታ በሳኡዲ ከሚመራው ጥምረት ጋር በመቆሟ የሁለቱ አገራት ግንኙነትም ሌላ መልክ ወደ መያዝ አመራ። "የኤርትራ መንግሥት ወደዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ኤምሬቶች አሰብ ውስጥ ወታደራዊ ካምፕ ስላላት ነው። በተጨማሪም ሥርዓቱ ከሁለቱ አገራት የተለያዩ ድጋፎችን ያገኛል። ስለዚህ ከኳታር ጋር ለነበረው ግንኙነት መሻከር መነሻው የኤርትራ መንግሥት ኳታርን ማንበርከክ ከሚሹ ኃይሎች ጋር በመሰለፉ ነው" ይላሉ አቶ ዓብዱልራሕማድ። • ኩዌት ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞችን እንደምትፈልግ አሳወቀች • ህገወጡ የአረብ አገራት ጉዞ በአዲሱ አዋጅ ይገታል? በመካከለኛው ምሥራቅና በባሕረ ሰላጤው አካባቢ በሚገኙ አገራት መካከል ላለው ፍጥቻ መባባስ በሳኡዲ የሚመራው ጥምረት በመን ላይ የሚያካሂደው ዘመቻ ምክንያት ሆኗል። ኳታር ዘመቻውን በመቃወሟ የተለያዩ ክሶች የቀረቡባት ሲሆን በተጨማሪም ለአካባቢው አገራት መንግሥታት ስልጣን ስጋት የሆነውን 'ሙስሊም ብራዘርሁድ' እንቅስቃሴን ትደግፋለች ብለውም ይወንጅሏታል። ኳታር በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል አገራት መገለል ሲደርስባትና ሌሎችም ከእነሱ ጎን ሲቆሙ ብቻዋን ግን አልቀረችም። ቱርክ ኳታርን በመደገፍ በአካባቢው ፖለቲካ ውስጥ ያላትን ሚና አጠናክራለች ይባላል። ለ30 ዓመታት ሱዳንን ያስተዳደሩት ኦማር አልበሽር ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት፤ ኤርትራና ሱዳን አልፎ አልፎ አለመግባባት ይገጥማቸው ነበር። ነገር ግን አልበሽር በተቃውሞ ከሥልጣናቸው ከተነሱ በኋላ የሁለቱንም አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በካርቱምና አስመራ ሲገናኙ ታይተዋል። "ሱዳኖች የራሳቸው የውስጥ ችግሮች ስላሉባቸው በዚህ ጊዜ ከኳታር ጋር በማበር ኤርትራን ለማጥቃት ፍላጎት አይኖራቸውም። በእኔ አስተያየት ሱዳን በሌላ አገር ላይ አዲስ ችግር ለመፍጠርና ራሷን ውዝግብ ውስጥ ለመክተት አትፈልግም" ይላሉ አቶ አብዱልራሕማድ አቡሃሽም። ኳታር የሳኡዲና ኤምሬቶችን ተጽእኖ ለመመከት በምሥራቅ አፍሪካ እንቅስቃሴ እንደነበራት የሚያነሱት የአፍሪካን ፕሮግረስ ሴንተር ሃላፊና የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ዓሊ ህንዲ በበኩላቸው፤ የሙሰሊም ክንፍ የሆነው 'ሙስሊም ብራዘርሁድ' በመደገፍ አቅሟን ለማጠናከር ብዙ አማራጮች ትጠቀም እንደነበር ይገልጻሉ። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሊያድኑት የነበረው ለገሰ ወጊ ማን ነበረ? • የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር መከፈትን መነሻ ያደረገው ፌስቲቫል • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? ኳታር ቀደም ሲል ከኤርትራ ጋር ግንኙነት ነበራት፤ ነገር ግን በአረቡ ዓለም የተቀሰቀሰውን አብዮት ተከትሎ 'ሙስሊም ብራዘርሁድ' በግብጽ ሥልጣን በያዘበት ጊዜ ከኤርትራ የሙስሊም ቡድኖች ጋር ግንኙነት ጀምሯል የሚሉ መረጃዎች ሲሰሙ፤ በወቅቱ ኤርትራ ደስተኛ አለመሆንዋ መግለጽዋን ያስታውሳሉ። ከዚህ በተጨማሪም "የፎርቶ ኦፕሬሽን በሚባለውና የኤርትራ የሠራዊት አባላት በታንክ ታጅበው ወደ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት በመሄድ መንግሥት ላይ ተቃውሞ ለማንሳት ያደረጉት ሙከራ ላይ የኳታር እጅ አለበት ተብሎ ስሟ ሲነሳ ነበር። በእነዚህ ምክንያቶች ጠንካራና እውነተኛ ሲባል የነበረው ግንኙነታቸው ወደ ጥላቻ አመራ" ይላሉ አቶ አሊ። የኳታሩ ኢምር ሼኽ ታሚም ቢን ሐማድ አልታኒ ኤርትራ ከነጻነት ትግሉ ጊዜ አንስቶ ከመካከለኛው ምሥራቅና ከባሕረ ሰላጤው አገራት ጋር ቅርብ የሆነ ግንኙነት ለመፍጠር ችላለች። ከኳታርም ጋር ያላት ግንኙነት ከዚሁ አንጻር የሚታይ ቢሆንም በመካከላቸው ንፋስ ከመግባቱ ቀደም ብሎ ጠንከር ያለ ነበር። ለዚህም ይሆናል ኤርትራ በአረቡ ዓለም ካሏት ኤምባሲዎች ሁሉ ኳታር ውስጥ የሚገኘው ትልቁ የሆነው። የኤርትራ መንግሥትም የአገራቱን ፖለቲካና ፍላጎት በቅርበት ስለሚያውቀው ከቀጠናው አገራት ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንደሚኖረውና ብሔራዊ ጥቅሞቹን እንዴት ማስጠበቅ እንዳለበት በቀላሉ የመረዳት ልምድ እንዳለው አቶ ዓሊ ይገልጻሉ። ኤርትራ በቅርቡ ያወጣቻቸው ኳታርን የሚከስ መግለጫ፤ የተለያዩ ድጋፎችን ለኤርትራ በምትሰጠው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና አጋሮቿ የተገፋ ሊሆን እንደሚችል አቶ አብዱልራሕማን አቡሃሽም ይናገራሉ። በሳኡዲ የሚመራው ጥምረትና ኳታር በመካከላቸው ያለው መቃቃር በዚህ ከቀጠለ ለኤርትራ መንግሥት መልካም አጋጣሚን ይፈጥርለታል የሚሉት አቶ አሊ፤ የኤርትራ መንግሥት አሁን ካለው ሁኔታ ተቃዋሚ መሆኑን በማመልከትም "ምናልባት ኳታር ከእነዚህ አገራት ጋር እርቅ ካወረደች ግን ሌላ መንገድ ለመፈለግ ይገደዳል" ይላሉ። የፖለቲካ ተንታኙ አብዱልራሕማን ሰይድ በበኩላቸው፤ ይህ በአፍሪካ ቀንድ አገራትና በባሕረ ሰላጤው መንግሥታት መካከል ያለው ፖለቲካ ለቀጠናው ትልቅ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ያምናሉ።
xlsum_amharic-train-135
https://www.bbc.com/amharic/news-51499405
የሕዝብ እንደራሴዎችን ጎራ አስለይቶ ያሟገተው የጥላቻና ሐሰተኛ መረጃ ሕግ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ አንደኛ አስቸኳይ ስብሰባ ባደረገበት ሐሙስ ዕለት ከወትሮው በርከት የሚሉ ሪፖርቶችን እና የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ አፅቋል።
[ "የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ አንደኛ አስቸኳይ ስብሰባ ባደረገበት ሐሙስ ዕለት ከወትሮው በርከት የሚሉ ሪፖርቶችን እና የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ አፅቋል።" ]
ይሁንና በሕዝብ እንደራሴዎች ዘንድ ሞቅ ያለ ሙግትን ያስተናገደው የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠር የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ነው። ረቂቁ የኋላ ኋላ በዕለቱ በምክር ቤቱ ከተገኙ 320 አባላቱ የሃያ ሦስቱን ተቃውሞ አስተናገዶ፤ ሁለቱ ደግሞ ድምጻቸውን አቅበው በአብላጫ ድምፅ አዋጅ ቁጥር 1185/2012 ሆኖ ቢፀድቅም ከአንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ዘንድ የሰላ ትችት ሲቀርብበት በሌሎች ደግሞ በብርቱው ተደግፏል። • ሥጋት ያጫረው የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ሕግ ጸደቀ • ቴክቫህ ኢትዮጵያ፡ የፀረ ጥላቻ ንግግር የወጣቶች እንቅስቃሴ በምክር ቤቱ የሕግ፣ ፍትሕ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴን በመወከል አቶ አበበ ጌዴቦ በረቂቁ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ጨምሮ ሪፖርት እና የውሳኔ ሐሳብን በንባብ ካቀረቡ በኋላ የተደረገው ክርክር አባላቱ መካከል አሽሙር መወራወርን ያካተተ ነበር። በተለይም ከአምስት ዓመታት በፊት ሁሉንም የምክር ቤቱን ወንበሮች በአባል እና አጋር ፓርቲዎቹ ከተቆጣጠረው ኢህአዴግ መፍረስ በኋላ መንገዳቸው ለየቅል በሆነው በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አባል የሕዝብ እንደራሴዎች እና በብልፅግና ፓርቲ የምክር ቤት አባላት መካከል ያለው ፍትጊያ ጎልቶ መውጣቱን ሙግቱን የታደመው የቢቢሲ ዘጋቢ ልብ ብሏል። በቅድሚያ በረቂቅ አዋጁ ዙርያ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ካሳ አዋጁ ሊያስፈፅማቸው የሚሞክራቸው ተግባራት በሌሎች የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግጋት ሊፈፀሙ የሚችሉ ናቸው አንዲሁም ሕገ መንግሥታዊ የመናገር ነፃነትን ይሸራርፋል የሚሉ ሙግቶችን አቅርበዋል። አሁን ሥራ ያሉ የተለያዩ ሕግጋት ግጭት ማነሳሳት፣ ሐይማኖቶችና ብሔር ብሔረሰቦችን ማጥላላትን የሚከለክሉ መሆናቸውን ጠቅሰው የሕጉን አስፈላጊት አጣጥለዋል። በመቀጠል ዕድሉን ያገኙት አድሓና ኃይለም (ዶ/ር) እንዲሁ የዜጎችን የመናገር መብት መገደብ አሳሳቢ ነገር ነው ሲሉ ተሟግተዋል። ሕዝብን የሚያናቁሩ ንግግሮች በአብዛኛው የሚደመጡት ከባልስልጣናት፣ ከፖለቲካ መሪዎችና ከአንዳንድ የብዙሃን መገናኛዎች መሆኑን ጠቅሰው ተራውን ዜጋ በሰበቡ ለመቀፍደድ ከመሞከር ይልቅ እነዚህ አካላት ላይ ያነጣጠረ ሕግ ሊወጣ ይገባል ሲሉ ተከራክረው ሕጉን ምክር ቤቱ እንዳያፀድቀው ጠይቀዋል። ረቂቅ አዋጁ የተቹ የምክር ቤት አባላት የአገርን እና የሕዝብን ደህንነትን ለመጠበቅ ሲባል ነው አዋጁ መረቀቅ ያስፈለገው የሚለውን የሕግ፣ ፍትሕ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሐሳብን "አዛኝ ቅቤ አንጓች" እና "አፉ ቅቤ ልቡ ጩቤ" የተሰኙ ተረቶችን ተጠቅመው ነቅፈዋል። ይሁንና የአዋጁ ደጋፊዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት እየታዩ ካሉና በተለይ በማኅበራዊ የብዙሃን መገናኛዎች ከሚሰነዘሩ ጥላቻ የታጨቀባቸው ወይንም ሐሰተኛ ከሆኑ መረጃዎች ጋር ትስስር ካላቸው ግጭቶች ጋር በተያያዘ በረቂቅ አዋጁ ዙርያ ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ "ለምን እስካሁን ዘገየ?" የሚል ሊሆን እንደሚገባ ተሟግተዋል። ከመካከላቸው አቶ ተስፋዬ ዳባ በሕገ መንግሥቱ እንዲሁም በሌሎች የሕግ መርሆዎች መሰረት የመናገር ነፃነት ፍፁማዊ ከሚባሉት መካከል እንደማይመደብ ጠቅሰው ሕጉን ያለማጽደቅ አደጋን ይጋብዛል ብለዋል። • “ኢትዮጵያ አዲስ የጥላቻ ንግግር ህግ አያስፈልጋትም” አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ አቶ ተስፋዬ ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም "ጥፍርን ለመንቀል፣ ለማኮላሸት" ምክንያት ሆኗል ያሉትን የፀረ ሽብር ሕግ እንዲሁም የቀድሞውን ፕሬዚደንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን መብት ለመከልከል "ለአንድ ሰው ሲባል" ሕግጋትን ማፅደቁን ማስታወስ ይገባል "ለዚህም ይቅርታ ጠይቀናል" ሲሉ ተናግረዋል። ይሁንና አዲሱ ሕግ ዜጎች እና አገር ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመጋፈጥ ዕድል ይሰጣል እንደርሳቸው ሙግት። ከዚያ ይልቅ ረቂቅ ሕጉ ለጥፋተኞች ይሁን ብሎ ያቀረበው ቅጣት መቅለል የክርክር መንስዔ ሊሆን ይገባው ነበር ብለዋል። "ያቀረብኩት ሐሳብ ተገቢ ባልሆነ መልኩ ተተርጉሞ ምላሽ እየተሰጠበት ነው" ያሉት አድሃና (ዶ/ር) ሁለተኛ ዕድል እንዲሰጣቸው ከጠየቁ በኋላ፤ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ጫላ ለሚ የአካሄድ ተቃውሞ ቀርቦበት ሳይሳካ ቀርቷል። በመቀጠልም በረቂቅ አዋጁ ዙርያ የሚነሰዘሩ ሐሳቦችን መበራከት ያስተዋሉት ምክትል አፈ ጉባዔዋ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ ወደ ድምፅ መስጠት መሄድ ሳይሻል እንደማይቀር ሐሳብ አቅርበው ከሕዝብ እንደራሴዎቹ "አዎ" የሚል ጎላ ያለ የወል ድመፅ በመሰማቱ የምክር ቤት አባላቱ ወደ ድምፅ መስጠቱ አምርተው በ295 ድምፅ ረቂቁን አዋጅ አድርገው አፅድቀውታል። ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ምን አሉ? ቢቢሲ በሕጉ መውጣት ላይ ያለውን አስተያየት የጠየቀው አዲስ አበባ ውስጥ በእንግሊዝኛ እየታተመ ለረጅም ዓመታት የቆው የፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረ ጊዮርጊስ "የጥላቻ ንግግርና አደገኛ ንግግር ተምታቷል" ሲል የሕጉን መውጣት ይቃወማል። የጥላቻ ንግግርን የሚቀጣ ሕግ ማውጣት ልክ አይደለም ያለው አቶ ታምራት ሐሳቡን በሦስት አንኳር ነጥቦች ለይቶ ይሞግታል። ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሕገ መንግሥታዊ ጥበቃ አለው በማለትም "ባይወጣ ይሻል ነበር" ሲል አንደኛውን ምክንያቱን ያቀርባል። ሁለተኛው ምክንያቱን ሲያስረዳም ሕግ አውጪው "እንዲህ አይነት ሕግ የማውጣት ሕገ መንግሥታዊ ስልጣን የለውም" በማለት ነው። • "ረቂቅ ሕጉ የመናገር ነጻነትን አደጋ ላይ ይጥላል" ሂይውመን ራይትስ ዎች ይህንን ሐሳቡን በዝርዝር ሲያስረዳም ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት የሚገደብባቸውን ምክንያቶች ሕገ መንግሥቱ በጠባቡ ማብራራቱን በማስታወስ ነው። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ተነጻጻሪ መብቶችን ለመጠበቅ ሲባል ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ሊታገድ ወይም ገደብ ሊጣልበት ይችላል እንደሚል ገልጾ፣ "...እርሱ ግን የሚሆነው ጦርነትን ለመቀስቀስ የሚሞክሩ ሰዎችን አደብ ለማስገዛት፣ የሰውን ሰብዓዊ ክብር ለመጠበቅ ሲባል ከዚያ ደግሞ የሕጻናትን ወይም የወጣቶችን ደህንንት ለመጠበቅ ሲባል ሊጣልበት ይችላል ይላል። ከዚህ ውጪ ግን በምንም መስፈርት ሀሳብን የመግለጽ ነጻነትን ሊገድብ የሚችል ምንም ዓይነት ምክንያት የለም ማለት ነው" ሲል አስተያየቱን ያጠናክራል። አቶ ታምራት አክሎም በሕገ መንግሥቱ ላይ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን መገደብ ቢፈቀድ ኖሮ በጣም የተብራራ ዝርዝር ሊኖር ይችል ነበር ይላል። "የጥላቻ ንግግርን ለማስቀረት ወይንም ለመከላከል ሲባል ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ላይ ገደብ ይጣላል አልተባለም። እና ሕገመንግሥታዊ መሰረት የለውም ብዬ የምከራከረውም በዚያ ምክንያት ነው።" አቶ ታምራት ሦስተኛው ሐሳቡን ሲያስረዳም ሕጉን ያረቀቁት ሰዎች መቆጣጠር የፈለጉት አደገኛ ንግግርን ነው በማለት ነው። "አደገኛ ንግግርን ለመቆጣጠር ደግሞ በሥራ ላይ ያሉ ወይም እስካሁን የወጡ በቂ ሕጎች አሉ" ሲል ያክላል። "የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ውስጥ በቂ ነገር አለ። ከዚህ በፊት የነበረው የሚዲያ ሕግ፣ የማስታወቂያ ሕግ፣ የኮምፒውተር ወንጀል ሕግ ምናምን የሚባሉ በርካታ ሕጎች አሉ።" ለአቶ ታምራት እነዚህ የጠቀሳቸው ሕጎች አደገኛ ንግግርን ለመቆጣጠርና ለመቅጣት የሚበቁ የሕግ መሳሪያዎች ናቸው። እነርሱን ሳይጠቀሙ ቀርቶ አዲስ ሕግ ማውጣም አስፈላጊ አይደለም ብሎ ያምናል። "በጽንሰ ሃሳብ አደገኛ ንግግርና የጥላቻ ንግግር የተደበላለቀ ይመስለኛል" የሚለው ታምራት የጥላቻ ንግግርን መታገስ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል። ሕብረተሰቡ ውስጥ ያሉ ቅሬታዎች፣ ሙግቶች፣ መከፋቶችና አቤቱታዎች ይፋ አይውጡ እንጂ አይቀሩም የሚለው አቶ ታምራት የጥላቻው መንስዔና ምክንያት እስካልተነካ ድረስ መናገር የሚችሉት ሰዎች ፈርተው ለጥቃት አንጋለጥም ብለው በሚያስቡበት ቦታ ላይ ያደርጉታል እንጂ ሊያስቆመው አይችልም ይላል። "የጥላቻ ንግግር ባለበት አካባቢ ላይ ብዙ ተፎካካሪና ተቃራኒ ተሟጋች ንግግሮች እንዲሰሙ፣ እንዲሰራጩ ማድረግ የሰዎች አስተሳሰቦችና ፍላጎቶች በአደባባይ እንዲፋጩ፣ እንዲፈተሹ እድል ያገኛሉ" ይላል አቶ ታምራት። "ይህ ካልሆነ ግን ግጭት የመጨረሻው እውነት ይሆናል" በማለት "ለዚያ ትልቅ ጥቅም ሲባል የጥላቻ ንግግርን መታገስ መቻል ይኖርብናል ብዬ አስባለሁ" ይላል። የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በዚህ ሕግ ረቂቅ ላይ ማሻሻያ መደረግ አለበት በማለት ሲወተውቱ ከነበሩት አካላት መካከል አንዱ ነው። የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር ) ያሳስባቸው የነበረውን ጉዳይ በማንሳት ለምክር ቤቱ አስተያየት መስጠታቸው ያስታውሳሉ። በወቅቱ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው መሻሻል አለባቸው ብለው ካነሷቸው ሐሳቦች መካከል የጥላቻ ንግግርን በሚመለከት ያነሱት ነጥብ ሙሉ በሙሉ ለማለት በሚቻል መልኩ በጸደቀው ሕግ ላይ መሻሻሉን ይናገራሉ። በዚህ ሕግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ የተወሰነ ውጤት አግኝተንበታል የሚሉት ኮሚሽነሩ ከእንግዲህ በኋላ ደግሞ ወሳኙ ነገር የሕጉን ሥራ ላይ አዋዋል መከታተል መሆኑን በማንሳት ይህንንም እንደሚያደርጉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ሕጉ ከፀደቀ በኋላ መግለጫ ያወጣው ሂይውመን ራይትስ ዎች በበኩሉ "የጥላቻና የሐሰተኛ መረጃ ሕጉ የመናገር ነጻነትን አደጋ ላይ ይጥላል" በማለት መጪውን ምርጫ ታሳቢ በማድረግ መንግሥት ሠላማዊ ውይይት የሚደረግበትን መንገድ መፈለግ አለበት ሲል አሳስቧል።
xlsum_amharic-train-136
https://www.bbc.com/amharic/48014323
የአቶ በረከት ስምዖን ባለቤት፡ «ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ስለ በረከት አናግረውናል»
በጥረት ኮርፖሬት የሃብት ብክነት የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሣ የተያዙት ከወራት በፊት ቢሆንም በአማራ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይፋ ክስ የተመሠረተባቸው ግን ሚያዝያ 14፣ 2011 ዓ. ም. ነው።
[ "በጥረት ኮርፖሬት የሃብት ብክነት የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሣ የተያዙት ከወራት በፊት ቢሆንም በአማራ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይፋ ክስ የተመሠረተባቸው ግን ሚያዝያ 14፣ 2011 ዓ. ም. ነው።" ]
በተለይ ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ጉልህ ሚና የነበራቸው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሠ ካሣ በከባድ ሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ወዲህ ስለግለሰቦቹ ብዙ ተብሏል። በተለይ አቶ በረከት ስላለፈው እና አሁን ስላሉበት ሁኔታ ምን ያስቡ ይሆን? ባለቤታቸው ወ/ሮ አሲ ፈንቴ ይናገራሉ። ቢቢሲ፦ አቶ በረከት እንዴት እንደተያዙ ሊያስታውሱን ይችላሉ? ወ/ሮ አሲ፦በረከትና አቶ ታደሰ በአንድ ቀን ነው የተያዙት። ጥር 15 ቀን ከጥዋቱ በግምት 12፡30 አካባቢ ነበር። በር ሲንኳኳ አልሰማሁም፤ ልጄን ትምህርት ቤት ለመውሰድ እየተዘጋጀሁ ነበር። ሊይዙት እንደመጡ ስሰማ እውነት አልመሰለኝም ነበር። እነሱ [አዴፓ] እሱን ለመያዝ ያሰቡበት ጊዜና በትክክልም የያዙበት ጊዜ በጣም ክፍተት ነበረው። ባላሰበውና ባልተዘጋጀበት ሁኔታ ነው መጥተው የወሰዱት። ቢቢሲ፦ አቶ በረከት ሊያዙ እንደሚችሉ መረጃ ነበራቸው ማለት ነው? ወ/ሮ አሲ፦ እንግዲህ ከዚያ በፊት በሚድያ እነሱ [አቶ በረከትና አቶ ታደሰ] ሳያውቁ ከአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ መታገዳቸው ተሰማ። ከዚያ በፊት ግን የሚመለከታቸው የፓርቲው ሰዎች ተሰብስበው ሲገመግሙ ጉዳዩ የማያስጠይቃቸው መሆኑን አስረግጠው ነበር፤ በፖለቲካ ውሳኔ ደረጃ ማለት ነው። ቢሆንም እነ በረከት ባልተገኙበት ከማዕከላዊ ኮሚቴ መወገዳቸው ተሰማ። ይህ ማንም ያልጠበቀው ነበር። በረከትም አልጠበቀውም ነበር። ምክንያቱም በግምገማው ላይ በረከት ቦርድ ሊቀመንበር [የጥረት ኮርፖሬት] እንጂ 'ኦፕሬሽናል' ሥራዎች ላይ አይሰማራም ብለው ነበር። አልፎም እሱ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የቦርድ አባላት ፊርማ ያረፈበት ሥራ ስለሆነ የአሠራር ድክመት እንጂ በከባድ ሙስና አያስወነጅልም ተብሎ ነበር። ይህንን ተከትሎ በረከት በሚድያ ነገሩን አብራርቶ መግለጫ ሰጥቷል። ያው በተለያየ ጊዜ ሊከሱ እንደሚችሉ 'ኢንፎርማሊ' እንሰማ ነበር። የመክሰስ ያለመክሰስ መብቱ ያለው በነሱ እጅ ነው። መቼ ነው የሚለውን ግን ያው አናውቅም ነበር። እና ድንገተኛ ነበር። • በረከት ስምኦን ስለራሱ ይናገራል ቢቢሲ፦ የተያዙት ቦሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነው። ወደ ባሕርዳር የተወሰዱት እንዴት ነበር? ወ/ሮ አሲ፦ መጀመሪያ ፖሊሶቹ ሲመጡ የፌዴራል ናቸው ብሎ ነው ያሰበው። ግን መጥሪያው የታዘዘው በአማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። ይሄንን እሱ አልተቀበለውም፤ ምክንያቱም የፌዴራል መሥሪያ ቤት ሠራተኛ ስለነበር። ተከሶበታል የተባለው ነጥብም ትክክል አይደለም ብሎ ተከራከረ። ወደቤቱ መመለስ አልቻለም፤ ምግብም አልበላም፤ መድሃኒትም አልወሰደም ነበር። ለሁለት ሰዓት ያህል ተከራከረ። እኔ ከጎኑ ስለነበርኩ የተለያዩ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር እየደወልኩ እርዳታ ለማግኘት ሞከርኩ። ማናቸውም ለማናገር ፍላጎትም ዝግጁነቱም አልነበራቸውም። የ13 ዓመት ልጃችን ይህ ሁሉ ሲሆን እዚያው ነበረች። መጨረሻ ላይ እነዚህ የታዘዙ ፖሊሶች ስለሆኑ መፍትሄ አይመጣም፤ እንደውም እዚያው ሄጄ እራሴን ነፃ አወጣለሁ ብሎ ወሰነ። ከዚያ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻርተር አውሮፕላን ከታደሰ ጋር ወደ ባህርዳር ተወሰዱ ማለት ነው። ከዚያ ባህርዳር ዘጠነኛ ፖሊስ ጣብያ ሄዱ። በቀጣዮቹ ቀናት በተደራጁ ወጣቶች እንዲሰደቡና እንዲዘለፉ ሆነ። ቢቢሲ፦ አሁን እንዴት ባለ ሁኔታ ነው እየተመላለሳችሁ እየጠየቃችኋቸው ያላችሁት? ወ/ሮ አሲ፦ በሚካሄደው የፍርድ ሂደት ላይ መቅረት አልፈልግም። ምክንያቱም እዚያ አካባቢ ቤተሰብ የላቸውም። ሁሉም ቤተሰብ አዲስ አበባ ነው የሚኖረው። በዚያ ላይ የእነሱን ውንጀላ እንጂ ሌላ ውሳኔ የማይጠብቅ የተደራጀ ቡድን አዳራሹን ሞልቶ ነው የሚውለው። የተከሰሱበትም 'ኬዝ' የፖለቲካ እንጂ እውነት እንደሌለው ስለምናውቅ በዚህ ሁኔታ ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው ስንል ሁሌም መገኘት አለብን። ፍርዱን እየተከታተልን ለሚድያም ማሳወቅ አለብን። በዚያ ላይ እነዚህ ሰዎች ጠበቃ የላቸውም። ጠበቃ የሚሆን ሰው ላይ እርምጃ እንወስዳለን የሚል መልዕክት 'ሶሻል ሚድያ' ላይ ስለተሠራጨ ጠበቃ ማግኘት አልቻልንም። ሁለት ጠበቆች መጥተው ነበር ሁኔታውን ለማጣራት፤ ነገር ግን ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው ጥለው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። ቢቢሲ፦ በማረሚያ ቤት የእነ አቶ በረከት አያይዝስ እንዴት ነው? ወ/ሮ አሲ፦ እሥር ቤቱ እውነት ለመናገር አዲስ ነው። ሌላ እሥር ቤት ባላውቅም ሰዎች እንደሚናገሩት የተሻለ ነው። ከባህርዳር ወጣ ያለ ነው። ለብቻቸው ገለል አድርገው ነው ያስቀመጧቸው። ለዚህ እናመሰግናለን። ይህ ማለት ግን ችግር የለም ማለት አይደለም። ቀደም ሲል ቤተሰብ ረዘም ያለ ጊዜ ተሰጥቶት ይጠይቅ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ተሰልፈን ጠብቀን ነው የምንጠይቃቸው። በዚያ ላይ የተሰጠን አጭር ጊዜ ሳያልቅ በቃችሁ እንባላለን። ይብዛም ይነስም በስልክ እንገናኝ ነበር፤ አሁን ግን ያን ማድረግ አልቻልንም። አዲስ አበባ ላይ ጠበቆችን አማክረን ያሉንን መልዕክት በአግባቡ ማስተላለፍ አልቻልንም። በዚህ በኩል ቤተሰብ እየተንገላታ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መጻሕፍት ይገቡላቸዋል ግን የሚጽፉት በኮምፒውተር ሳይሆን በእስክሪቢቶ ነው። ቢቢሲ፦ ማረሚያ ቤት ውስጥ ከአቶ በረከት ጋር ብዙ ጊዜ የምታወሩት ስለምንድነው? ወ/ሮ አሲ፦ በርካታ ጉዳዮች እናነሳለን። ስለቤተሰን እናወራለን። ብዙ ጊዜያችንን የምናጠፋው ግን ስለ ፍርድ ሂደቱ በማውራት ነው። ጠበቃ ስለሌላቸው ከጠበቆች የተሰጠንን ምክር እናደርሳለን፤ ጥያቄም ካለን ይዘን እንመለሳለን። ስለ ሀገሪቱ ፖለቲካም እናወራለን። እርግጥ ቴሌቪዥን ገብቶላቸዋል። ቢቢሲ፦ አቶ በረከት ከመታሠራቸው በፊት ከሀገር መውጣት ይፈልጋሉ ወይ ተብለው እንደማይፈልጉ ገልፀው ነበር። አሁን ላይ የተለየ ሃሳብ ይኖራቸው ይሆን? ወ/ሮ አሲ፦ እኔ እስከማውቀው ድረስ እስከ ዕለተ ሞቴ ድረስ ከኢትዮጵያ የመውጣት ፍላጎት የለኝም ነው የሚለው። ወደፊት ምን ይሆናል? አይታወቅም። ሰው ስለሆነ አስገዳጅ ነገሮች ይፈጠሩ ይሆናል። ብዙ ወዳጅ ዘመድ ይገፋፋው እንደነበር አስታውሳለሁ፤ ከኢትዮጵያ ውጣ እያለ። ግን አንድም ቀን ከሀገር የመውጣት ፍላጎት እንዳለው ሲናገር ሰምቼው አላውቅም። ቤተሰቤ ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል የሚል ፍራቻ ነበረው እንጂ እሱ ለሞትም የተዘጋጀ ሰው ነው። • በረከት ስምኦን ከየት ተነስተው እዚህ ደረሱ ቢቢሲ፦ አቶ በረከት ዛሬ ላይ የሚቆጫቸው ነገር ይኖር ይሆን? ባደርገው ወይም ባላደርገው ኖሮ የሚሉት? ወ/ሮ አሲ፦ የሚቆጨው ነገር ሊኖር ይችል ይሆናል። በዚህ ደረጃ የማውቀው ነገር የለም። በዚሁ ሁኔታ ነገሩ መደምደሙ ግን ያሳዛነዋል። እነዚህ ያሰሩትን ሰዎች ከማንም በላይ ያምናቸው ነበረ። ሥልጣንም አሳልፎ ሰጥቷቸዋል። እኔ ይበቃኛል፤ እኛ መውጣት አለብን፤ እናንተ ተረከቡ ብሎ አስተላልፏል። ይቆጨዋል ብዬ የምገምተው ነገር፤ የእነርሱ ዓይነት 'ቫልዩ' ያለው ትክክለኛ ተተኪ አለመፈጠሩ ያሳዝነዋል ብዬ እገምታለሁ። እዚህ ላይ ጉድለት እንዳለ ሲናገር እሰማዋለሁ። ከመታሠሩ ጋር በተያያዘ የሚቆጨው የማውቀው ነገር የለም። ቢቢሲ፦ አቶ በረከት የተከሰሱበት ሂደት ፖለቲካዊ ተፅዕኖ አለው ብለው ያስባሉ? ወ/ሮ አሲ፦ አዎ፤ በደንብ! ለምን? ብለህ ብትጠይቀኝ፤ አንደኛ በርካታ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሙስና ይጠረጠራሉ። ነገር ግን ብዙ ጊዜ አይጠየቁም። ከእነዚህ ሰዎች ጋር አብረው የሠሩ ሰዎች ሳይያዙ እነሱ ብቻ ተነጥለው የተያዙበት ሁኔታ በግምገማ መታየት ነበረበት። ሁለተኛ ነገር ደግሞ በረከትም ሆነ አቶ ታደሰ በሙስና አይታወቁም። እንደውም ይጠየፋሉ ተብሎ ነው የሚነገርላቸው። እንዲሁም መጽሐፉ ላይ የሙስና እና የሥነ ምግባር ችግር ያለባቸውን ሰዎች ስም እየጠቀሰ አጋልጧል። አቶ ታደሰም ቢሆን ተመሳሳይ ነው። ኑሯቸውን በዝቅተኛ ደረጃ፤ በድህነት የሚመሩ ሰዎች ናቸው። በሱም ስም ሆነ በዘመድ አዝማድ አንድም ንብረት የለውም። መሬት እንኳን የሌላቸው፤ ቤት የሌላቸው፤ መኪና ወይም ሌላ ንብረት ያላፈሩ፤ መንግሥት በሚሠጣቸው ገቢ የሚኖሩ ናቸው። ከድርጅቱም በቃኝ ብሎ የተገለለው ሙስና በመንሠራፋቱ ምክንያት ነው። ቤት ድረስ 'ያላንተ አይሆንልንም' እያሉ የሚመጡ እንደነበሩ አውቃለሁ። ዛሬ ደርሶ ሙሰኛ ነው ተብሎ ሲወቀስ ፖለቲካ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። ቢቢሲ፦ ምንም እንኳ ክሳቸው እየታየ ያለው በአማራ ክልል ሥር ቢሆንም፤ የአቶ በረከት ክስ የፌዴራል መንግሥት እጅ አለበት ብለው ያስቡ ይሆን? ወ/ሮ አሲ፦ እንግዲህ የፌዴራል መንግሥት 'በእኛ በኩል አንፈልጋቸውም' ሲል መግለጫ ሰጥቷል። እንዲህ አለም አላለም እነዚህ ሰዎች በግፍ ታሥረዋል። ሰብዓዊ መብታቸው እየተረገጠ ነው፤ በፍትህ እየተዳኙ አይደለም። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይህንን በተመለከተ ለፌዴራል መንግሥት የሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤ ብንጽፍም ምላሽ የሚሠጥ አልተገኘም። የሚሰጠን መልስ በፍርድ የተያዘ ጉዳይ ስለሆነ በዚህ ላይ ጣልቃ አንገባም የሚል ነው። ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩም አናግረውናል። ከመታሠራቸው ጋርም አያይዞ ያለብንን እክል ነግረናቸዋል። ሊተባበሩን የማይፈልጉ ሰዎች እንዳሉ ነግረናቸው ችግሩ እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥተውልናል። በፍትህ ጉዳይ መግባት እንደማይችሉ ነገር ግን ፍትህ በአፋጣኝ ይሰጥ ዘንድ እንደሚያናግሯቸው ነግረውናል። ለዚህ እናመሰግናለን። ግን በጣም ዘግይቷል፤ አሁንም እየዘገየ ነው ያለው። ቢቢሲ፦ አቶ በረከት ባህርዳር ሲገቡ በርካታ ሕዝብ ወጥቶ መያዛቸው ትክክል ነው ሲል ነበር፤ ቀደም ብሎም ደብረማርቆስ ላይ እሳቸው አሉበት የተባለ ሆቴል ጥቃት ደርሶበታል። አቶ በረከት ምንም ዓይነት ጥፋት ከሌለባቸው፤ እንዲህ ያለ መረር ያለ ተቃውሞ እንዴት ሊያጋጥማቸው ቻለ? ወ/ሮ አሲ፦ በተለይም በረከት ከመታሠሩ በፊት ከፍተኛ ዘመቻ ተደርጎበታል። ፀረ-አማራ ነው፤ ለትግራይ የሚያደላ ነው የሚሉና መሰል ዘመቻዎች ሲደረጉበት ነበር። የዋሁ ሕዝብ እውነት ሊመስለው ይችላል። ለእነዚህ ዘመቻዎች ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ በረከት መልስ አይሰጥም ነበር። ትኩረትም አይሰጣቸውም። ማሕበራዊ ሚድያ ላይም አይሳተፍም። ቀላል የማይባል ስም ማጥፋት የተደረገበትም ወጣቱን ማዕከል ባደረገ መልኩ ነበር። የጥላቻ ፖለቲካ ውጤት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። እንደውም እንደተደረገበት ዘመቻ ቢሆን ኖር በሕይወት የሚቆይም አልነበረም። ቢቢሲ፦ አቶ በረከት የተመሠረተባቸው ክስ ውድቅ ሆኖ በነፃ ይሰናበታሉ ብላችሁ ታስባላችሁ? ወ/ሮ አሲ፦ አሁን ትልቁ ፈተና ሊሆን ይችላል ብዬ የማስበው ያሠሩበት ምክንያት ውሃ የማይቋጥር መሆኑ ነው። በጥላቻ እና በመንጋ ግፊት የተመራ መሆኑ ነው፤ የለውጥ ሆይሆይታ ያመጣው ግፊት ነው። ሁለቱም [አቶ በረከትና አቶ ታደሰ] አማራ አይደሉም ተብሎ ይታሰባል። ሁለቱም ለብሔረሰቦች መብት ሲሠሩ የነበሩ ናቸው፤ የአማራ ብሔር ተወላጅ እንደመሆናቸው ግን ለአማራ ሕዝብ ሲሠሩ የነበሩ ናቸው። አሁን ክሱ ውድቅ ሆኖ በነፃ ቢለቀቁ ከመጀመሪያውስ ለምን ታሠሩ? የሚል ነገር ሊመጣባቸው ይችላልና ይሄ ነው ትልቁ ፈተና። በእኔ ግምት የክልሉ መሪዎች ከፍትህ በላይ ይህ የሚያስጨንቃቸው ይመስለኛል። • በደብረማርቆስ 'ባለስልጣኑ አርፈውበታል' የተባለው ሆቴል ጥቃት ደረሰበት
xlsum_amharic-train-137
https://www.bbc.com/amharic/49093788
በባርነት ከመሸጥ የተረፉት 64 ኢትዮጵያዊያን
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር መስከረም 1888 ሮያል የባህር ኃይልን የሚያገለግለው ኤችኤምኤስ ኦስፕሬይ መርከብ፤ መቀመጫውን የመን ኤደን አድርጎ በቀይ ባህር ላይ ባካሄደው የፀረ ባርነት ዘመቻ ከኢትዮጵያ የባህር ዳርቻ የተነሱ ሦስት ጀልባዎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል።
[ "እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር መስከረም 1888 ሮያል የባህር ኃይልን የሚያገለግለው ኤችኤምኤስ ኦስፕሬይ መርከብ፤ መቀመጫውን የመን ኤደን አድርጎ በቀይ ባህር ላይ ባካሄደው የፀረ ባርነት ዘመቻ ከኢትዮጵያ የባህር ዳርቻ የተነሱ ሦስት ጀልባዎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል።" ]
በ1888 በየመን የናህር ዳርቻ አቅራቢያ ከባሪያ ነጋዴዎች የተያዙት እና በሼክ ኦቶማን እንክብካቤ ሲደረግላቸው የነበሩ የኢትዮጵያ ሕፃናት እነዚህ ጀልባዎች ከራሃይታ እና ታጁራ የተነሱ ሲሆን፤ 204 ወንዶችና ሴቶችን በአረብ ገበያ ለባርነት ለመሸጥ እየተጓዙ ነበር። ሕጻናቱ ከኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች፤ ከአሁኑ ኦሮሚያ ክልል የተወሰዱ ነበሩ። ሕጻናቱ በርካታ መቶ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው ነበር ከባህር ዳርቻው የደረሱት። የፀረ ባርነት ዘመቻውን የሚመራው ቡድን እነዚህን ሕጻናት ከነጋዴዎች መንጋጋ ፈልቅቆ ካወጣ በኋላ በቀጥታ የወሰዳቸው ወደ ኤደን ነበር። በዚያም ሕፃናትና ታዳጊዎቹ በፍሪ ቸርች ኦፍ ስኮትላንድ ሚሲዮን አማካኝነት በሼክ ኦትማን አስፈላጊው እንክብካቤ ሁሉ ተደረገላቸው። • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው? • ከ43 ዓመት በኋላ የተገናኙት ኢትዮጵያዊ እናትና ስዊድናዊ ልጅ ጉዞው አካላቸውን አጣምኖ፣ መንፈሳቸውንም አዳክሞ ነበር። ወባና አስቸጋሪው የአየር ጠባይ እንኳን ለታዳጊ ባይተዋር ሕጻን ቀርቶ ለብርቱ የባህር ላይ ቀዛፊም ከባድ ነበር። በ1890 ከሞት አፍ የተረፉት 64ቱ ኢትዮጵያዊያን ሕጻናት ደቡብ አፍሪካ በምሥራቃዊ ኬፕ በምትገኘው አሊስ ውስጥ ወደሚገኘው ፍሪ ቸርች ኦፍ ስኮትላንድ ላቭዳሌ ተቋም ተሸጋገሩ። ከሕጻናቱ መካከል ሙስሊሞቹን የአካባቢው ማህበረሰብ በማደጎ ወሰዳቸው። በዚያው ዓመት መጨረሻ ላይ የአየር ጸባዩን ባለመቋቋምና በሌላም ምክንያት ከሕጻናቱ መካከል የ11ዱ ሕይወት አልፏል። የመን እያሉ የስኮት ሚሲዮናዊያን ከባርነት ነፃ የወጡትን ሕጻናት መጠይቅ ይዘው ማነህ? ከየት ነሽ? ሲሉ ጠየቁ። ዛሬ የእነዚህ 64 ሕፃናት ታሪክ በምሥራቃዊ ኬፕ በኮሪ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ተሰንዶ ይገኛል። ይህንን ለህትመት ብርሀን ያበቃችው የታሪክ ተመራማሪዋ ሳንድራ ሼልስ (ዶ/ር) "ዘ ችልድረን ኦፍ ሆፕ" የተሰኘውን የምርምር ሥራዋን ባሳተመችበት መጽሐፍ ውስጥ ነው። ቶሎሳ ወዬሳ በላቭዴል ቶለሳ ወዬሳ ቶለሳ ወዬሳ የወዬሳና የሀታቱ ልጅ ነው። በባርነት ተሸጦ በየመን ቃሉን ሲሰጥ እድሜው 13 ተገምቷል። እትብቱ የተቀበረው ጊቤ ወዲያ ማዶ ጅማ፣ ቲባ እንደሆነ ሰነዶች ያሳያሉ። አባቱ ብዙ ጋሻ መሬት የሚያርሱ የኮሩ ገበሬ ነበሩ። ሀያ በሬዎች፣ አስራ አምስት በጎችና ፈረሶችም ነበሯቸው። ቶሎሳ በወቅቱ ከሰጠው ቃል መረዳት እንደሚቻለው አንድ ቀን በቤቱ አቅራቢያ እየተጫወተ እያለ ሦስት ሰዎች መጥተው ፈረስ አይቶ እንደሆን ጠየቁት። እሱም በቀና ልቦና፣ በትሁት አንደበት ፈረሱ በየትኛው አቅጣጫ እንደሄደ መለሰላቸው። • "በጎጃም ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስጊድ 3ሺ ብር ረድታለች' ተባልኩኝ" ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ግን የጥርጣሬ ነፋስ ሽው አለው፤ ወዲያው የለበሰውን የቆዳ ልብስ ወርውሮ በቀጫጭን እግሮቹ ወደ ቤቱ መሮጥ ጀመረ። እግሮቹ የልቡን ያህል አልሮጡለትም፤ ሰዎቹ ደርሰው ያዙት። አፉን በእጃቸው ግጥም አድርገው አፍነው፣ ወደ ጫካ ውስጥ ገቡ። እርሱንም፣ ቶሎሳንም የጫካው ሆድ ውጦ ዝም አለ። ሰዎቹ ጎዳዋራቤሳ የሚባል አካባቢ ወስደው ለባሪያ ነጋዴ እንደሸጡት በወቅቱ በሰጠው ቃል ላይ ሰፍሮ ይገኛል። እነዚህ ነጋዴዎች ደግሞ ከሁለት ሳምንት ጉዞ በኋላ ቢሎ የሚባል ገበያ ወስደው አተረፉበት። ቢሾ ጃርሳ ቢሾ ጃርሳ- በበቆሎ የተለወጠችው ታዳጊ በ1874 እንደተወለደች ተገምቷል፤ የ16 ዓመቷ ቢሾ። አባቷ ጃርሳ እናቷ ደግሞ ዲንጋቲ ይባላሉ። እናትና አባቷ በተመሳሳይ ወቅት ነው የሞቱት። ከ1887-1892 በኢትዮጵያ ውስጥ ብርቱ ረሀብ ተከስቶ እንደነበር የታሪክ ሰነዶች መዝግበውት ይገኛሉ። ይህ ረሀብ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በበርካታ የአፍሪካ አገራት የተከሰተና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ነበር። በወቅቱ በአገሪቱ በገባው ጽኑ ርሀብ ሰውም ከብትም አልቆ ነበር። የእነ ቢሾ ከብቶችም ከዘመኑ ክፉ እጣ አልተረፉም። ቢሾ ወንድሞች አሏት፤ ሁለት። አባቷን የሞት ብርቱ ክንድ ሲነጥቃት የአባቷ ባሪያ የነበረ ግለሰብ ይንከባከባት ነበር [ያኔ ይሆን 'ቀን እስኪያልፍ የአባቴ ባሪያ ይግዛኝ' የተተረተው]። ያኔ አገሩ ሁሉ በቸነፈር በተመታበት ወቅት ቢሾ ከሰዎች ጋር ወደ ገበያ ተላከች፤ ጎቡ የሚባል፤ ያው የሚላስ የሚቀመስ ፈላልጋ እንድትመጣ ነበር የታዘዘችው። • ምግብ ወሲብን የተሻለ ያደርጋል? ገበያ ስትደርስ ታዲያ ለእነሱ እህል ለመሸመት እሷን በበቆሎ ለወጧት፤ በአካባቢው ነጋዴ የነበረ ግለሰብ ገዛት፤ በበቆሎ። ይህ ቀን የወጣለት ሲራራ ነጋዴ በየወቅቱ እዚህ አካባቢ እየተመላለሰ ልጆችን ለባርነት ይገዛል። ቢሾ ተሸጣ ወራካላ ወደሚገኝ አንቻሮ የሚባል ስፍራ ተወሰደች። ከዚያም በርካታ ሕጻናትን ለባርነት ገዝተው ላከማቹ ሌሎች ነጋዴዎች ተሸጠች። እነሱ ደግሞ አዳል ለሚገኝ ሌላ ነጋዴ ሸጧት፤ ከዚያ በታጁራህ በኩል አድርገው ወደ ዳዌ ወሰዷት። ያኔ ነው በጀልባ ጭነዋት ከሌሎች አምስት ጀልባዎች ጋር ባህሩ ላይ በመቅዘፍ ጉዞ የጀመሩት። ነገር ግን ብዙ ርቀት አልሄዱም፤ አንዲት በቅኝት ላይ የነበረችና የጠበንጃ አፈሙዝ የደገነች ጀልባ ተመለከቱ። ሁለቱ ጀልባዎች ወዲያውኑ ቀኝ ኋላ ዞረው ተመለሱ። ከዚያም ያሳፈሯቸውን ሕጻናት አውርደው ለስድስት ሳምንት ያህል ተደብቀው ቆዩ። አገር አማን ብለው ባመኑበት ሰዓት ዳግም መቅዘፍ ጀመሩ። በድጋሚ ያቺ አሳሽ ጀልባ አገኘቻቸው። ከሁለቱ በአንዱ ጀልባ ቢሾ ተሳፍራ ነበር። ከሁለቱም ጀልባ በሕይወት የተረፉት ወደ ኤደን ተወሰዱ። በኤደንም ቃላቸውን የተቀበሏቸው ሚሲዮናውያን የቢሾን ታሪክ እንዲህ አስቀሩልን። ቢሾና ቶሎሳ ከምን ደረሱ? ይህ ሁሉ የሆነበት ዘመን የሸዋው ንጉሥ፣ ንጉሥ ምንሊክ በሥልጣን ላይ የነበሩበት ዘመን ነበር። ንጉሥ ምንሊክ ከፈረንሳዮች መሣሪያ ለመግዛት እንዲያስችላቸው ገንዘብ በብርቱ ይፈልጉ ነበር። ለዚህም ግዛታቸውን አቋርጠው በባሪያ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችንም ሆነ በአገር ውስጥ ባሪያ ንግድ ላይ የሚሳተፉት ላይ ቀረጥ ጥለውባቸው ነበር። በተሰበሰበው ቀረጥም ከፈረንሳይ መሣሪያ መሸመታቸው ሳንድራ ሼልስ በመጽሐፏ ላይ ጠቅሳለች። በዚህ መካከል ታሪክ በሰነድ ያስቀመጠልን 64 ታዳጊዎች በባርነት ከመሸጥ ተረፉ። ከእነሱም ውስጥ ቢሻና ቶሎሳ ከሌሎች በመቶ ከሚቆጠሩ የእድሜ አቻዎቻቸው ጋር በመሆን በየመን የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በብሪታኒያ የጦር ኃይል ከባሪያ ንግድ ነፃ ወጡ። • "ራሴን የምፈርጀው የሀቅ ታጋይ ነኝ ብዬ ነው" አሊ ቢራ በወቅቱ እንግሊዝ የባሪያ ንግድን ለማስቀረት ወስና ይህንንም የሚያስፈፅም ጦር በኮማንደር ጊሲንግ እየተመራ የቀይ ባህር የንግድ መስመርን ይቆጣጠር ነበር። ቢሾ ጃርሳ በየመን የወደብ ከተማ በባርነት ከመሸጥ የብሪታኒያ ባህር ኃይል ከታደጋት በኋላ በቀጥታ የሄደችው ወደ ደቡብ አፍሪካ ነበር። የመን የባህር ዳርቻ ላይ በባርነት ልትሸጥ ስትል የአፍ መፍቻዋ ኦሮምኛ ነበር፤ ጆሮዋን ቢቆርጡት ሌላ ቋንቋ አትሰማም። የቢሻ ጃርሶ የልጅ ልጅ ኔቪል አሌክሳንደር (ዶ/ር ) በ2008 በኋላ ግን እንግሊዘኛን ታቀላጥፈው ገባች። በርግጥ ኦሮምኛንም አልረሳችም። ወደ ደቡብ አፍሪካ ከሄደች በኋላ በሎቬዳሌ መምህርት ሆነች። በርግጥ መጀመሪያ የቤት ውስጥ ሥራ እንድትሠራ ነበር ስልጠና ያገኘችው። ነገር ግን ብርታቷን ያዩ ከአንዲት የአገሯ ልጅ ጋር መምህርነት አሰለጠኗት። በ1911 ፍሬድሪክ ስቺፐርስ የተባለ አንድ ማኅበረ ምዕመናን ውስጥ የሚያገለግል ሰው አግብታ አራት ልጆች አፍርታለች። ከቢሻ ልጆች አንዷ ዲምቢቲ ትዳር መስርታ ኒቬል አሌክሳንደርን ወለደች። የቢሻ የልጅ ልጅ ለደቡብ አፍሪካ ነፃነት የታገለ፣ ኔልሰን ማንዴላ በታሠሩበት የሮቢን ደሴት ላይ ለአስር ዓመታት ታስሯል። ለደቡብ አፍሪካ ነፃነት ሲታገል ኢትዮጵያዊ ደም እንዳለው አያውቅም ነበር። ቆይቶም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ደም እንዳለው በተረዳ ጊዜ ደስታው ታላቅ እንደነበር በአንድ ወቅት ለቢቢሲ ገልጿል። ቶሎሳ ወዬሳ ደቡብ አፍሪካ ከሄደ በኋላ በትምህርቱ ብርቱ ነበር። በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናም ሸጋ ውጤት ነበር ያስመዘገበው። በወቅቱ ግን ትምህርቱን ከመቀጠል ይልቅ በአንግሎ ቦየር ጦርነት ወቅት (1899-1902) የብሪታኒያ ጦርን ተቀላቅሎ አገልግሏል። ነገር ግን በጦርነቱ ውስጥ ባየው ነገር አእምሮው ታወከ። በኋላም ከጦርነት ተመልሶ ከጅቡቲ ድሬዳዋ የባቡር መንገድ ሲገነባ በአስተርጓሚነት አገልግሏል። ታሪኩን የመዘገቡ ጸህፍት በወቅቱ በእንግሊዝና በፈረንሳይ መካከል የነበረውን የበላይነት ፍላጎት በማቻቻል ጥሩ የዲፕሎማሲ ሥራ መሥራቱን መስክረዋል። የቶሎሳ የልጅ ልጅ፤ ብሩክ ተረፈ ኑሮውን በካናዳ አድርጎ ይገኘኛል። አቶ ብሩክ ተረፈ በአሁኑ ሰዓት ዕድሜው 50ዎቹ ውስጥ የሚገመት ሲሆን፤ የእሱ የቅርብ ዘመዶች ደግሞ ኑሯቸውን በአዲስ አበባ አድርገው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። • የጋዜጠኛዋ መገደል ለምን የዓለም መነጋገሪያ ሆነ? የእነ ቢሾና የ64ቱ ሕጻናት ታሪክ ደቡብ አፍሪካንና ኢትዮጵያ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ለመተሳሰራቸውን ቋሚ ምስክር የሆነ የኢትዮጵያ ግዙፍ ታሪክ አካል ነው። ወደ ደቡብ አፍሪካ ከተወሰዱት 64 ኢትዮጵያዊያን ታዳጊዎች መካከልም ወደ እናት ምድራቸው የተመለሱ እንዳሉም መረጃዎች ያሳያሉ። ከባርነት ንግድ ከተረፉትና ደቡብ አፍሪካ ከነበሩት መካከል የሎቬዴል አስተዳደሮች ወደ አገራችው ለመመለስ ፍቃደኛ የነበሩትን 17 ኢትዮጵያዊያን፤ የጀርመን አማካሪዎች ከአፄ ምኒልክ ጋር ተነጋግረው በ1909 እኤአ ወደ ኢትዮጵያ መልሰዋቸዋል። ከነዚህ መካከል ጉዴ ቡልቻ፣ አማኑ ፊጎ፣ ድንቂቱ ቦኤንሳ፣ ፌእሳ ገሞ፣ ሊበን ቡልቱ ጥቂቶቹ ናቸው። 'አሰቃቂ' ተብሎ በሚጠራው አፍሪካውያንን እንደ እቃ የማጋዝ 'ባርያ ንግድ' እንግሊዝ ከፍተኛ ስፍራ ነበራት። በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ16ኛው ክፍለ ዘመን በተጀመረውና ከሁለት መቶ አመት በላይ በቆየው ንግድ ከአስር ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ተሽጠዋል፤ ብዙዎችም ሞተዋል። እንግሊዝ የባርያ ንግድን በህግ ከከለከለች በኋላም ለባርያ አሳዳሪዎቹ ሃያ ሚሊዮን ፓውንድ ካሳ ተከፍሏቸዋል። የመጽሐፉ ሽፋን ሳንድራ በአዲስ አበባ "ዘ ችልድረን ኦፍ ሆፕ" የተባለውን የእነዚህን በባርነት የተጋዙ ኢትዮጵያዊያንን ታሪክ የጻፈችው ሳንድራ ሼልስ (ዶ/ር) ተወልዳ ያደገችው ዝምባብዌ ነው። በኋላም የዩኒቨርስቲ ትምህርቷን በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ኬፕታውን ተከታትላለች። የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪዋን በታሪክ ትምህርት ተከታትላ አጠናቅቃለች። ሳንድራ ሼልስ በዚህ ዓመት አዲስ አበባ ውስጥ በሚካሄደው 33ኛው የኦሮሞ ስተዲስ አሶሲየሽን (ኦሳ) ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ተሳታፊ እንደምትሆን የተሰማ ሲሆን፤ ከዓመት በፊት ለውጪው ዓለም አንባቢ የቀረበው መጽሐፏም ኢትዮጵያ ውስጥ በቡክ ወርልድ ታትሞ ለገበያ እንደሚቀርብ ተነግሯል። የኦሳ ፕሬዝዳንት ኩለኒ ጃለታ፤ የዚህ ዓመት ጉባኤ በኦሮሚያ፣ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ያለመ መሆኑን ገልፃለች። ከቢቢሲ ጋር ቃለ ምልልስ ባደረገችበት ወቅት እንደገለፀችው፤ ለዘመናት በወንዶች የበላይነት ይታወቅ የነበረው ማኅበሩን በሴቶችና በወጣቶች ለመተካት ዓላማ እንዳላትም ገልፃ ነበር።
xlsum_amharic-train-138
https://www.bbc.com/amharic/41857305
ስሜታዊ ድራማ እና ትርዒት በሙምባይ ባቡር ጣቢያዎች ውስጥ
23 ተሣፋሪዎች ሕንድ ሙምባይ ውስጥ በሚገኝ አንድ የባቡር ጣቢያ ውስጥ በተከሰተ ግርግር ተረጋግተው ከሞቱ እነሆ አንድ ወር ደፈነ። የቢቢሲዋ ኪንጃል ፓንድያ ዋግ በሙምባይ ባቡሮች ለአስር ዓመት ያህል ተመላልሳለች። እነሆ በኪናጃል የተሳናደውና በሙምባይ ባቡር ጣቢያዎች ውስጥ ምን እየተካሄደ እንዳለ የሚያትተው ፅሑፍ።
[ "23 ተሣፋሪዎች ሕንድ ሙምባይ ውስጥ በሚገኝ አንድ የባቡር ጣቢያ ውስጥ በተከሰተ ግርግር ተረጋግተው ከሞቱ እነሆ አንድ ወር ደፈነ። የቢቢሲዋ ኪንጃል ፓንድያ ዋግ በሙምባይ ባቡሮች ለአስር ዓመት ያህል ተመላልሳለች። እነሆ በኪናጃል የተሳናደውና በሙምባይ ባቡር ጣቢያዎች ውስጥ ምን እየተካሄደ እንዳለ የሚያትተው ፅሑፍ።" ]
የሙምባይ ባቡሮች የከተማዋ እስትንፋስ ናቸው። በቀን ቢያንስ 8 ሚሊዮን ሰዎች ይመላለስባቸዋል። ሙምባይን ከባቡሮቹ በፊት እንዴት ትንቀሳቀስ እንደነበረ ማሰብ በራሱ ይከብዳል። በዘጋቢ ፊልሞች፣ በማስታወቂያዎች እንዲሁም በቦሊውድ ፊልሞች ውስጥ የሙምባይ ባቡሮችን ማየት እጅግ የተለመደ ነው። ባቡሮቹን መጠቀም ግን ሌላ ዓለም ነው፤ በሰው ብዛት የሚከሰተው መጨናነቅ ግን ከቁብም ላይቆጠር ይችላል። የሙምባይ ከተማ ባቡሮችን መጠቀም ስጀምር ገና የኮሌጅ ተማሪ ነበርኩ። ወደ ትምህርት ቤቴ ለመሄድ የሁለት ሰዓት የባቡር ጉዞ ይጠይቃል። አሁንም ሽታው፣ ግርግሩ ይታወሰኛል። በተለይ ደግሞ ባቡሩ ደቡብ ሙምባይ ባለው ፌርማታ ሲደርስ፤ እጅግ ደስ ይል ነበር። ተጠቃሚዎች ስልካቸው ላይ ተጥደው ከሚታዩበት የሌላው ዓለም የከተማ ባቡር ሕይወት በተለየ የሙምባይ ባቡር ተጠቃሚዎች እርስ በርስ እየተጫወቱ ነው የሚጓዙት። ምንም ውይይት ሳያካሂዱ ዓይን ለዓይን እየተያዩ የሚመላለሱም እንዳሉ ሆነው። በቡድን ሆነው የቦሊውድ ሙዚቃቸውን እየዘፈኑ የሚጓዙ ሰዎችን መመልከትም የተለመደ ነገር ነው። ለሴቶች ብቻ ተብሎ በተከለለው ክፍል ደግሞ ልደት የሚያከብሩ እና ኬክ የሚያድሉ ብዙ ጊዜ ይስተዋላሉ። ሃሜት የተለመደ ነገር ነው፤ የሥራ ቦታ ፖለቲካም እንዲሁ። በሃያዎቹ መጨረሻ ላይ የምትገኛ አንዲት ሴት ስለ ዘመናዊቷ የሕንድ ሴት የኑሮ ውጣ ውረድ ምን የመሰለ ትንታኔ እየሰጠች ስትጓዝ የነበረች ሴት ዛሬም ትዝ ትለኛለች። ደንገተኛ ብስጭት በሙባይ ባቡሮች ውስጥ መቀመጫ ማግኘት እጅግ አዳጋች ነው፤ በተለይ ደግሞ በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት። ብዙ ጊዜ በተሳፋሪዎች መካከል ግጭት የሚነሳው በወንበር ምክንያት ነው። አንዳንዱ ግጭት ቶሎ ይቋጫል፤ ሌላው ደግሞ ከብዙ ንትርክ እና አንዳንዴም ከድብድብ በኋላ። ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ቀድሜያቸው ስገባ ሊቀድሙን የሞከሩ ሰዎች ቲሸርቴን ቀደውብኛል። በተለይ ደግሞ ወንበር ለማግኘት የሚሯሯጡ ተጓዦች ብዙ ጉልበት ይጠቀማሉ። የሙምባይ ባቡሮች በጣም አስፈሪው ነገር በሮቹ ባቡሩ ካልተንቀሳቀሰ በቀር አለመዘጋታቸው ነው። ሌላው ደግሞ ባቡሩ ከመቆሙ በፊት ሮጦ ወደውስጥ መግባት ወንበር ስለሚያስገኝ ጊዜ ጠብቆ ዘሎ መግባት የግድ ነው። እኔም ብዙ ጊዜ ባቡሩ ሲመጣ ዘልዬ ገባና ወይ የባቡሩን ብረት እይዛለሁ ወይም ደግሞ ቀድሞኝ የገባ ሰውን እጅ። እድል ከቀናኝ ወንበር አገኛለሁ፤ ካልሆነም ለሁለት ሰዓት ያህል ቆሞ መሄድ ግድ ይላል። ቀድሞ መቀመጫ ያገኘ ሰውን መውረጃ ቦታ ጠይቆ መተካካትም ሌላው መላ ነው። የሙምባይ ባቡሮችን መጠቀም እጅግ አዳጋች ሊሆን ይችላል። እጅግ ቀላል ሊሆንም ይችላል። ዋናው ነገር ስለባቡሩ ያለዎትን አመለካከት ማስተካከል ይጠይቃል። ታጋሽና ሁሉ ነገር ቻይ እንድሆን አስተምሮኛል። የሙምባይ ባቡሮች ከተለያየ ዓለም የመጡ ሰዎች አንድ ላይ የሚሰበሰቡበት ሥፍራ ነው። ሁሉም ወደየመዳረሻው ለመሄድ የሚጠቀምባቸው መጓጓዣዎች።
xlsum_amharic-train-139
https://www.bbc.com/amharic/news-48846532
ዓንዶም ገብረጊዮርጊስ፡ የአሜሪካ ምክርቤት አባል ለመሆን ቅስቀሳ እያደረገ ያለው ኤርትራዊ
የ34 አመቱ አንዶም ከኤርትራውያን እናትና ኣባት የተወለደው አሜሪካ ውስጥ ነው። የከፍተኛ ትምህርቱን በፖለቲካል ሳይንስና በኢኮኖሚክስ የትምህርት ዘርፍ አሜሪካ ከሚገኘው የል ዩኒቨርስቲ ተከታትሏል። ለአመታትም የማህበራዊ ፍትሕ ተሟጋች ሆኖ ሰርቷል። በኒውዮርክ ውስጥ የኮንግረስ አባል ለመሆን ቅስቀሳ የጀመረው አንዶም ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።
[ "የ34 አመቱ አንዶም ከኤርትራውያን እናትና ኣባት የተወለደው አሜሪካ ውስጥ ነው። የከፍተኛ ትምህርቱን በፖለቲካል ሳይንስና በኢኮኖሚክስ የትምህርት ዘርፍ አሜሪካ ከሚገኘው የል ዩኒቨርስቲ ተከታትሏል። ለአመታትም የማህበራዊ ፍትሕ ተሟጋች ሆኖ ሰርቷል። በኒውዮርክ ውስጥ የኮንግረስ አባል ለመሆን ቅስቀሳ የጀመረው አንዶም ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።" ]
• የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? ከመምህርነት ወደ ፖለቲካ እንድትገባ ምንድን ነው የገፋፋህ? ለኤርትራ ነጻነት ከታገሉት ወላጆች በመወለዴ ከልጅነቴ ጀምሮ የፖለቲካ ግንዛቤ ነበረኝ። ስለ ኤርትራ ትግል፣ ተስፋና ተግዳሮቶች ይነግሩኝ ነበር። የአምስት ዓመት ልጅ ሆኜ ከእኩያዎቼ በተለየ መልኩ በኒውዮርክ እየሆኑ ስለነበሩ ነገሮች አውቅ ነበር። ሰለ አንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎችም እንዲሁ አውቅ ነበር። ምክንያቱም ወላጆቼ ስለእነዚህ ቦታዎች ደጋግመው ይነግሩኝ ነበር። በኢትዮጵያና ኤርትራ በተደረገው ጦርነትም አጎቴን አጥቻለሁ። ትግርኛ ቋንቋ ባልችልም፤ እነዚህ አስፈሪ የፖለቲካ ሁኔታዎች ስትሰማ ስለ ጉዳዩ ለማወቅ ፍላጎት ያድርብሃል። በርግጥ እዚሁ አሜሪካ ውስጥም የስደተኞች ጉዳይ፣ ሃይማኖት እንዲሁም የዘረኝነት የመሳሰሉ ችግሮች አሉብን። እነዚህ ናቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች እንድሆን የገፋፉኝ። •ኢሳያስን ለመጣል ያለመው'#ይበቃል' የተሰኘው የኤርትራውያን እንቅስቃሴ •ኤርትራ የደብረቢዘን ገዳም መነኮሳትን አሰረች በአሜሪካ ወስጥ የሚኖሩ ታዋቂ ኤርትራውያንስ ተጽእኖ አሳድረውብህ ይሆን? አዎ! በተለይ ጆ ንጉስ፤ ኤርትራዊ ባትሆንም ኤልሃምን ዖማርም ሌላ አርአያ የሆነችኝ ናት። ባለፈው ምርጫ በርካታ ፖለቲከኞች በየደረጃው የተለየዩ የፖለቲካ ኃላፊነቶች ሲይዙ ተመልክተናል። ጆ ንጉስ ባሸነፈበት ወቅት ለበርካታ ትውልደ-ኤርትራ አሜሪካውያን ትልቅ ዜናና መነቃቃትን የፈጠረ ጉዳይ ነበር። በርካታ የቤተሰባችን አባላትም ተራው ያንተ ነው ይሉኝ ነበር። በፖለቲካውም ተሳትፌ አስተዋፅኦየን እንዳበረክትም አስተያየቶችንም እየሰጡኝ ነው። አጎትህን ያጣኸው በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ነው፤ አሁን በሁለቱ ኃገራት መካከል የተፈጠረውን ዕርቀ ሰላም እንዴት ታያዋለህ? ላለፉት 20 ዓመታት በሁለቱ ሃገራት መካከል የነበረውን ሁኔታ ኢሳያስ እንደ ሰበብ ሲጠቀምበት ቆይቷል። ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትም ሆነ ህገ-መንግስት የለም። በሁለቱ ሃገራት ሰላም ተፈጠረ ማለት ያ ማሳበብ ይቀራል ማለት ነው። ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሊከበር ይገባል። ህገ መንግሥት አስፈላጊ ነው። ወጣቶችን በብሔራዊ ግዳጅ ወደ ሳዋ ሳይሆን ወደ ትምህርት ቤት ሊሄዱ ይገባል። ለዚያም ነው እየተባለ ያለውን ሰላም በጥራጣሬ የማየው። ኤርትራ ውስጥ እውነተኛ ዲሞክራሲ እስኪሰፍንና ሰብአዊ መብቶች እስኪከበሩ ድረስ መጠራጠሬን እቀጥላለሁ። ጋንዲም እንዳለው "ሰላም አለ የሚባለው ጦርነት ስለሌለ አይደለም። ማህበራዊ ፍትህ ሲኖር ነው" ወደ ኤርትራ ሄደህ ታውቃለህ? አዎ! የስምንት ዓመት ልጅ እያለሁ ሄጄ ነበር፤ በወቅቱ ልደቴንም ያከበርኩት እዛው ነው። በህይወቴም ደስ ያለኝ ጊዜ ነበር። ወላጆቼ በየቀኑ ስለ ኤርትራ ስለሚያወሩ፤ እኔም እንድ ልጃቸው ኤርትራን ማየት ነበረብኝ። ገና አስመራ አየር መንገዱ ላይ ወጣ እንዳልን ግራና ቀኝ ወደ ሰማይ መመልከት ጀመርኩ። በርካታ ኤርትራውያን በተለይም ሴቶች ደግሞ አበባ ይዘው ዕልል... ሲሉም ነበር። በህይወቴ እንደዚህ አይነት 'እንኳን ደህና መጣህ!' ተብዬ አቀባበል ተደርጎልኝ አያውቅም። ለእኔ ያኔ ኤርትራ የምድር ገነት ነበረች። ከ25 አመታትም በኋላ ተመልሼ ወደ ኤርትራ የሄድኩት ከሁለት አመታት በኋላ ነው። •የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? ለሁለተኛ ግዜ ተመልሰህ ስትሄድስ ኤርትራን እንዴት አገኘሃት? ትግርኛ ቋንቋ አለመቻሌ ምናልባት ትዝብቴን ጎዶሎ ሊያደርገው ይችላል። ነገር ግን ከ25 አመታት በፊት ካየኋት ኤርትራ ፈፅሞ የተለየች ነበረች። በዛን ወቅት ይህን ያህል የውኃና የመብራት ችግር አልነበረም፤ አሁን ግን በከፍተኛ ሁኔታ የውሃና የመብራት ችግር አለ። ከዚህ ሁሉ በባሰ ሁኔታ የነበረው ተስፋ ደብዛው ጠፍቷል። አብዛኞቹ ያነጋገርኩዋቸው ወጣቶች ከአገር መውጣት እንደሚፈልጉ ነግረውኛል። ማህበረሰቡ በምን አይነት ችግር እየኖሩ ሲነግሩኝ በጣም ነው ያዘንኩት። ራሴን የማየው የማህበረሰቡ አካል አድርጌ ነው። ልዩነታችን እኔ አሜሪካ መወለዴ ብቻ ነው። የኮንግረስ ውድድሩን ካሸነፍክ ለኤርትራ ምን ለመስራት ታስባለህ? ኤርትራ ለምንም አይነት ሁኔታ ከተዘጉ አገሮች መካከል ነች። መሪው ከተናገረው ውጪ አንዳች ነገር ትንፍሽ ካልክ የምትታሰርበት አገር ነው። አሜሪካ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ የተለያዩ አገሮች ላይ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ ምን መምሰል እንዳለበት ያሳስባታል። የኤርትራም ጉዳይንም የማየው በዚሁ መንገድ ነው። ነፃ ፖለቲካዊ አስተዳደር፣ ሰብአዊ መብት እንዲከበርና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ያስፈልጋል። አሜሪካ ውስጥ ያሉ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎችም የጀመሯቸው የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አሉ የነሱንም እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ እገፋበታለሁ። የምርጫ ቅስቀሳው እንዴት እየሄደ ነው ? አሸንፋለሁ ብለህ ታምናለህ? ቅስቀሳ ከጀመርኩ አንድ ሳምንቴ ነው። በጥሩ እየሄደ ነው፤ መልእክቶቻችን እያስተላለፍን ነው። በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄድ የመጀመርያ ደረጃ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ እየተንቀሳቀስን ነው። መራጮቻችን ምን ሃሳብ እንዳለን እያስተዋወቅን እንገኛለን። በሚቀጥለው ዓመት ሁለተኛ ኤርትራዊ በአሜሪካ ምክርቤት ይኖራል ብየ አምናለሁ። •ጄኔራል አብረሃ ወልደ ማርያም (ኳርተር) ማን ነበሩ? የምትወክለው አካባቢ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በብዛት የሚኖሩበት ነው? እኔ የምወክለው አካባቢ የተለያዩ ማህበረሰቦች የሚኖሩበት ነው፤ ይሁን እንጂ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚገኙበት አይደለም። ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕን እንዴት ታያቸዋለህ? ፕረዚዳንት ትራምፕ ከመመረጣቸው በፊትም ሆነ በኋላ ንግግራቸው ዘረኝነትን የሚያንፀባርቅ እንዲሁም የአንዱን ፆታ የበላይነት የሚሰብክ ነው። ይሄ አሜሪካውያንን የሚከፋፍል ነው። የትራምፕ መምጣት የፈጠረው አዎንታዊ ነገር ካለ ህዝቡን አንድ ላይ ማምጣት ችሏል። •ጄኔራል አደም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሾሙ ዲሞክራቶችን ወክለው በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተሳተፉ ካሉት የትኞቹን ነው የምትደግፈው? ዲሞክራቶችን ወክለው የሚወዳደሩ ብዙ ናቸው። የእግር ኳስ ቡድን ያክላሉ። [ሳቅ] በአንድ በኩል ጥሩ ነው። ምክንያቱም የተለያዩ ሃሳቦችን ስለሚያመነጩ አማራጭ ይሰጣል። በመጀመሪያ የምደግፈው በርኒ ሳንደርስ ነበር። አሁንም እደግፈዋለሁ። ይሁን እንጂ አሜሪካን በሚቀይሩና ትኩረት የተነፈጉ ማህበረሰቦች በሚጠቅሙ ፖሊሲዎችዋ ኤሊዛበት ዋረንም ቀልቤን እየሳበቸው ነው።
xlsum_amharic-train-140
https://www.bbc.com/amharic/50143221
የኢትዮጵያዊው ጉዞ፡ ከኬኒያ የስደተኞች ካምፕ እስከ ሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ
ኤልሻዳይ ጌትነት ይባላል፤ በሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ የጥርስ ቀዶ ጥገና የዶክትሬት ተማሪ ነው። ኤልሻዳይ ከስደተኞች ካምፕ ተነስቶ እስከ ካናዳ ያደረገውን ጉዞ አካፍሎናል።
[ "ኤልሻዳይ ጌትነት ይባላል፤ በሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ የጥርስ ቀዶ ጥገና የዶክትሬት ተማሪ ነው። ኤልሻዳይ ከስደተኞች ካምፕ ተነስቶ እስከ ካናዳ ያደረገውን ጉዞ አካፍሎናል።" ]
ኤልሻዳይ እና ቤተሰቦቹ አባቱ በደርግ ዘመን የነበረውን ወታደራዊ ግዴታ ካጠናቀቁ በኋላ ከእናቱ ጋር በመሆን ከኢትዮጵያ ለቀው ለመውጣት ተስማሙ። አገራቸውን ለቀው ወደ ኬንያ ለመሰደድ ሲያቅዱ ሁለቱም በአሥራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ ነበር የሚገኙት። ''እንደውም እናቴ እንደነገረችኝ ለሴት አያቴ ቡና ከምታፈላበት ድንገት ተነስታ 'መጣሁ' ብላ እንደወጣች ነው ኬንያ የገባችው። ከዛም ከአባቴ ጋር ተያይዘው ጉዞ ወደ ኬንያ ጀመሩ።'' በእግር እና በመኪና የተደረገው ጉዟቸው እጅግ አስቸጋሪና ፈታኝ ነበር። ጫካዎችን በሚያቋርጡበት ወቅት አንዳንዶቹ ስደተኞች በአንበሳ እንደተበሉም ወላጆቹ የነገሩትን ኤልሻዳይ ያስታውሳል። • ለ20 ዓመታት ዴንማርካዊት እህቱን የፈለገው ኢትዮጵያዊ ሀኪም • መጻሕፍትን ማንበብና መጻፍ ለአዕምሮ ጤና ቤተሰቦቹ ከአዲስ አበባ ተነስተው የኬንያ ድንበር ለመድረስ 23 ቀናት የፈጀባቸው ሲሆን፤ በመጀመሪያ መርሰቢት የሚባለው የስደተኞች ማቆያ ውስጥ ነበር የገቡት። የደርግ ሥርዓት መውደቅን ተከትሎ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ቢነገራቸውም 'አንዴ ወጥተናል አንመለስም' ብለው ሌላ አማራጭ መፈለግ ያዙ። አንድ ከብቶቹን ወደ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚወስድ ገበሬ አግኝተው፣ እነሱንም ይዟቸው እንዲሄድና በምላሹ ገንዘብ ሊከፍሉት ተስማሙ። በመጨረሻም ከከብቶች ጋር መኪና ውስጥ ተጭነው በድብቅ ናይሮቢ ገቡ። ናይሮቢ ከደረሱ በኋላም በኬንያና ሶማሊያ ድንበር ላይ ወደሚገኝ ዳዳብ ወደተባለ የስደተኞች ማቆያ ተዘዋወሩ። ከአንድ ዓመት በኋላ ኤልሻዳይ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ተወለደ። ኤልሻዳይ እና አባቱ አቶ ጌትነት "እናቴ ኤልሻዳይ የሚለውን ስም የሰጠችኝ በምክንያት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኤልሻዳይ ማለት ሁሉን ቻይ ማለት ነው። እኔ የተወለድኩት በስደተኞች ማቆያ ውስጥ ሲሆን፤ እዛ የተወለዱ ብዙ ህጻናት በወባና በምግብ እጥረት ምክንያት ሕይወታቸው ያልፍ ነበር። እናቴ በምንም አይነት ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ፈጣሪ እንደሚጠብቀኝ ተስፋ ታደርግ ነበር። ለዚህም ነው ይህንን ስም የሰጠችኝ።" ምንም እንኳን በዛ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ልጆችን ማሳደግ ከባድ ቢሆንም፤ በአካባቢው የነበሩ ሌሎች ስደተኞችም ጭምር ተባብረው ልጆችን ያሳድጉ እንደነበር ኤልሻዳይ ያስታውሳል። ''እኛ የነበርንበት የስደተኞች ማቆያ በብዛት ሶማሌዎች የሚገኙበት ነበር። የባህል እንዲሁም የሃይማኖት ልዩነት ቢኖርም ያለምንም ችግር ነበር ያደግኩት። ሁሉም ሰው ይንከባከበኝ ነበር።'' አፉን በአማርኛ የፈታው ኤልሻዳይ፤ አራት ዓመት ሲሞላው ሶማልኛ እና ስዋሂሊ በተጨማሪነት አቀላጥፎ መናገር ይችል ነበር። ''በነበረው አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ምክንያት እናቴ የራሷን ልብሶች እየቀደደች ለኔ ልብስ ትሰፋልኝ ነበር። አባቴም ቢሆን በዛ በረሃ ውስጥ ጫማ እንኳ ሳያደርግ የጉልበት ሥራ እየሠራ ለእኔ ጫማ ይገዛልኝ ነበር። በወር የሚሰጠን ቀለብም እጅጉን ትንሽ ነበር። ለአንድ ቤተሰብ በወር 2 ኪሎ ምግብ ብቻ ነበር የሚሰጠው። ነገር ግን ስደተኞቹ ተሰባስበው ህጻናቱ እንዳንራብ ይጥሩ ነበር" ሲል ያስታውሳል። የካምፑ ነዋሪዎች ከፍተኛ የምግብ እጥረት ቢገጥማቸውም፤ ሁሌም ቢሆን አዋቂዎች በቅድሚያ ለህጻናት ምግብ ይሰጡ ነበር ይላል ኤልሻዳይ። ''ሌላው ቀርቶ የወለዱ እናቶች የሌላ ሰው ልጆችን ጭምር ያጠቡ ነበር።'' በስደተኞች ማቆያው ውስጥ መኖሪያ ቤት ማግኝት ከባድ እንደነበርም ያስታውሳል። "እኔና ቤተሰቦቼ የምንኖረው በትንሽዬ ጎጆ ውስጥ ነበር። አባቴ ወታደር ስለነበር ጠንካራ እንድሆንና በቀላሉ እጅ እንዳልሰጥ አድርጎ አሳድጎኛል'' ይላል። የኤልሻዳይ አባት የኢትዮጵያን ጀግኖች ታሪክ ይተርኩለት እንደነበርም ይናገራል። ''ሁሌም ቢሆን ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ታሪክ ይነግረኝ ነበር። ስለ አፄ ቴዎድሮስ፣ ጉንደት ላይ የግብፅን ጦር ስላሸነፈው አፄ ዮሃንስ፣ ሙሉ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ቅን ገዢ ጣልያኖችን ከኢትዮጵያ ስላባረረው አፄ ምኒሊክ እንዲሁም በዲፕሎማሲ ሥራቸው ስለሚታወቁት አፄ ኃይለሥላሴ ታሪክ እየሰማሁ ነው ያደግኩት። በተጨማሪም እንደ ባልቻ ሳፎ፣ ራሥ ጎበና፣ ንግሥት ጣይቱና ሌሎችም ጀግኖች ሕይወትና አኗኗር መስማት በልጅነቴ ትልቅ ቦታ ነበራቸው።" የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ብዙ ህጻናት ስላልነበሩ ከሌሎች ህጻናት ጋር ተቀላቅሎ የማደግ እድልን አላገኘም ነበር ኤልሻዳይ። የኤልሻዳይና የወላጆቹ የህይወት ጉዞ ጉዞ ወደ ካናዳ ''በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ለአምስት ዓመታት ከቆየን በኋላ ወደ ካናዳ የምንሄድበት እድል ተፈጠረ። ሕይወታችንም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ተቀየረ። በመጀመሪያ በኖቫ ስኮሺያ ግዛት ሃሊፋክስ ከተማ ለአንድ ዓመት ቆየን።'' ''በመቀጠል ደግሞ ካልጋሪ ወደምትባል ከተማ ተዘዋውረን አዲስ ሕይወት መሰረትን። ልክ እንደማንኛውም ስደተኛ ከፍተኛ የሆነ የባህል መጣረስ ቢያጋጥመንም ቀስ በቀስ በራስ መተማመናችን እየጨመረና እየተላመድነው መጣን።'' • "በኤችአይቪ የምሞት መስሎኝ ልጄን ለጉዲፈቻ ሰጠሁ" • የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ ኤልሻዳይ የትምህርት ውጤቱ በጣም ጥሩ ስለነበር የካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስ ዲግሪ ፕሮግራም ተቀበለው። በሰዓቱ ምን አይነት ዘርፍ ላይ መሰማራት እንደሚፈልግ እርግጠኛ ባይሆንም በጤናው አካባቢ ግን ፍላጎት እንዳለው ያውቅ ነበር። ከዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዓመት ቆይታው በአንዱ ቀን፤ ወደተለያዩ አገራት በመጓዝ ነጻ የጥርስ ህክምና ይሰጥ የነበረ ዶክተር ራልፍ ዱቤኒስኪ የሚባል ግለሰብ ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያና ሩዋንዳ እንደሚጓዝ ነግሮት አብሮት እንዲሄድ ጥያቄ አቀረበለት። ኤልሻዳይ አይኑን ሳያሽ ነበር ሃሳቡን የተቀበለው። "እ.አ.አ. በ 2012 ከዶክተር ራፍ ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ አገሬን በአይኔ ለመመልከት በቃሁ። አዲስ አበባንና ቤተሰቦቼ ያደጉበት ልደታ ሰፈርንም ለማየት እድሉን አገኘሁ። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ስሄድ የመጀመሪያዬ ቢሆንም ልክ ስደርስ ቤቴ የተመለስኩ አይነት ስሜት ነበር ተሰማኝ'' ሲል ወቅቱን ያስታውሳል። ዶክተር ራልፍና ኤልሻዳይ ከወሊሶ ወጣ ብላ ወደምትገኝ ሃርቡ ጩሉሌ ወደምትባል ትንሽ መንደር ተጉዘውም ነበር። በነበራቸው ቆይታ ወላጅ አልባ ለሆኑ ህጻናት ቤት ሲገነቡ፣ የጥርስ ህመም ለነበረባቸው ሰዎች ህክምና ሲሰጡና ቀላል ቀዶ ጥገና ሲያደርጉ እንደቆዩ ይናገራል። ''እሱ የህክምና ሥራዎቹን ሲሠራ አብሬው እየሄድኩ አግዘው ስለነበር የአካባቢው ልጆች እኔም የህክምና ባለሙያ መስያቸው 'ዶክተር' እያሉ ይጠሩኝ ነበር። በዚህ ሁኔታ በጣም ነበር የተገረምኩት። የአገራቸው ሰው ህክምና ላይ ተሰማርቶ በመመልከታቸው በጣም ተደስተው ህጻናት ሲያደንቁኝ ማየት ተጨማሪ መነሳሳትና ጉጉትን ፈጥሮብኝ ነበር።" ''ጉዞዬን ጨርሼ ወደ ካናዳ ስመለስ በአገሬ ባህልና ታሪክ በእጅጉ ተነክቼና አዲስ ሰው ሆኜ ነበር የተመለስኩት። የቀደሙት አባቶቼ እንደ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደሩ ቤተ መንግሥትና አክሱም ሀውልት ያሉ ቅርሶችን በራሳቸው መገንባት ከቻሉ፤ እኔም ምንም አያቅተኝም የሚል ስሜት አደረብኝ።'' ኤልሻዳይ ጌትነት ኤልሻዳይ በካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ በነበረው ቆይታ ከትምህርቱ ጎን ለጎን ሁለት ወይም ሦስት ተጨማሪ ሥራዎች ይሠራ ነበር። ''ቀላል አልነበረም ግን መድረስ የምፈልግበትን ቦታ አውቅ ስለነበር ያለምንም ችግር ተወጥቼዋለው'' ይላል። የመጨረሻው ዓመት ላይ በጥርስ ቀዶ ህክምና በእጅጉ በሚታወቀው የአውስትራሊያው ሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ ለተጨማሪ ትምህርት አመለክቶ ነበር። እ.አ.አ. በ2018 መጨረሻ አካባቢ ደግሞ ከሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ ሙሉ በሙሉ እንደተቀበሉት የሚገልጽ ኢሜይል ደረሰው። ''እውነቱን ለመናገር በሕይወቴ እጅግ በጣም አስደሳቹ ቀን ነበር ማለት እችላለሁ። አስታውሳለሁ መልዕክቱ ሲደርሰኝ ማልቀስ ጀመርኩ፤ ቤተሰቦቼም ምን ሆነ ብለው ተደናግጠው ነበር። ምናልባት የቤተሰብ አባል ወይም ከጓደኞቼ መካከል አንዳቸው መጥፎ ነገር ያገጠማቸው ነበር የመሰላቸው።'' ''ልክ የኢሜይል መልእክቱን ሳሳያቸው እናቴ 'እግዚአብሔር ይመስገን' ብላ መሬት ላይ ወደቀች። በተደጋጋሚ 'እግዚአብሔር ይመስገን' ትል ነበር። አባቴ ደግሞ በቆመበት ከአይኖቹ እንባ እየወረደ እንደነበር አስታውሳለው። ሦስታችንም ተቃቅፈን ቆየን።'' ''ለቤተሰቦቼ በጣም ትልቅ አጋጣሚ ነበር፤ ምንያቱም ከስደተኞች ካምፕ እስከ ካናዳ ያደረጉትን የመከራ ጉዞ የሚያስረሳ ስለሆነ ነው። ልፋታቸው ሁሉ መና ባለመቅረቱ እነሱም እኔም በጣም ደስተኞች ነን።" በአሁኑ ወቅት በሜልቦርን ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ትምህርቱን ሊያጠናቅቅ እንደተቃረበ የሚናገረው ኤልሻዳይ፤ በእያንዳንዱ ቀን ከባድና አስቸጋሪ ፈተናዎችን ማለፍ ግድ እንደሆነ ያስረዳል ሆኖም ግን "ከአቅሜ በላይ የሚሆን ነገር የለውም። ማንኛውንም አይነት ፈተና ለማለፍ ዝግጁ ነኝ" ይላል። "በትምህርት ክፍሉ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ መሆኔ ደግሞ አገሬን በአግባቡ እንድወክልና ጠንክሬ እንድሠራ አድርጎኛል።" ኤልሻዳይ አንዳንዴ ለትምህርት ወደ ክፍል ሲገባ ጋቢ ይለብሳል። የክፍል ጓደኞቹና አስተማሪዎቹም በጣም እንደወደዱትና ሁሉም 'ጋቢ እንፈልጋለን' እንዳሉትም ይናገራል። ክሊኒክ ውስጥ ሲሆን ደግሞ ገዋኑ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ያደርዳል። • የጥሩ አባትነት ሚስጥሮች ምንድናቸው? • የዩኒቨርስቲ መምህርቷ ሞዴል፡ "ውበት ባመኑበት ነገር ጠንክሮ መሥራት ነው" "ለአሁኑም ለወደፊቱም ለስኬቴ ትልቁን ሚና የሚጫወተው የቤተሰቦቼ ያልተቋረጠ ድጋፍና ሁሌም ከጎኔ የሆኑ ሰዎች አበርክቶ ነው። የአገሬን ታሪክና ባህል ማወቄም እራሴን በደንብ እንዳውቅና ስኬታማ እንደሆን እንደረዳኝ አስባለው" ሲል ይገልጻል። ኤልሻዳይ ነጠላ ለብሶ ኤልሻዳይ እንደሚለው፤ አስቸጋሪና ተስፋ አስቆራጭ ነገር ሲያጋጥመው፤ ወራሪ ኃይልን ለመዋጋትና አገራቸውን ከጠላት ለመከላከል ወደ አድዋ ስለዘመቱት ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ያስባል። "እነሱ ተስፋ ቆርጠው ቢሆን ኖሮ የምናውቃት ኢትዮጵያ አትኖርም ነበር። እነሱ በዛ አስቸጋሪ ሁኔታ ተስፋ ሳይቆርጡ እኔ እንዴት ተስፋ እቆርጣለሁ?" "የአሁኑ የኢትዮጵያውያን ጦርነት አድዋ ላይ አይደለም። ጦርነቱ በትምህርት ቦታ፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢኮኖሚ፣ በሕግ እና በመሳሰሉ ዘርፎች ነው። በመላው ዓለም ብዙ ዳያስፖራዎች አሉ፤ ይህንን እንደ ትልቅ እድል ልናየውና ልንጠቀምበት ይገባል።" "ምናልባት የኔ ቤተሰቦች ከአገር በመውጣታቸው ይህንን ዕድል አግኝቼ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ስደት የሁሉም ነገር መፍትሄ ነው ብዬ አላስብም። ሁላችንም ከተባበርን ይቺን አገር ወደ ተሻለ ቦታ ማድረስ የምንችል ይመስለኛል። እኔ ባለኝ እውቀትና ልምድ የቻልኩትን ሁሉ ለማድረግና ሌሎችን ለተሻለ ነገር ለማነሳሳት ዝግጁ ነኝ።" ኤልሻዳይ "የቀድሞ አባትና እናቶቻችን ያኖሩልንን ገናና ታሪክና ባህል ወደ ቀድሞው ታላቅነቱ ለመመለስ ሁላችንም እንሥራ" ሲልም ይናገራል።
xlsum_amharic-train-141
https://www.bbc.com/amharic/50709584
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ክፍፍልና ጠብ
እኤአ ከ2005 ጀምሮ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ለሁለት መከፈሏን ተከትሎ፤ በተለያዩ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅና ሌሎች የውጭ አገር ከተሞች የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቷ ምዕመናንም ተከፋፍለው ግጭት ውስጥ ገብተዋል።
[ "እኤአ ከ2005 ጀምሮ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ለሁለት መከፈሏን ተከትሎ፤ በተለያዩ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅና ሌሎች የውጭ አገር ከተሞች የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቷ ምዕመናንም ተከፋፍለው ግጭት ውስጥ ገብተዋል።" ]
ይህ ግጭት ለበርካታ ጊዜያት በመንግሥት ደጋፊና ተቃዋሚ መካከል እየተካሄደ ያለ ነው ቢባልም፤ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሁኔታው ከመንግሥት ደጋፊነት ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ያስረዳሉ። በአንድ እምነት ስር በተለያየ መንገድ እየተጓዙ ያሉ ምዕመናን ጠብ እንደሆነም ቢቢሲ ያናገራቸው ምዕመናን ገልፀዋል። አቡነ አንጠንዮስ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው ለጥቂት አመታት ያገለገሉ ሲሆን ከመንበረ ስልጣናቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ሲኖዶሱ ለሁለት ተከፍሏል። አቡነ አንጠንዮስ ትክክለኛ የቤተክርስቲያኗ ፓትርያርክ ናቸው ያሉ በአንድ ወገን ተከፍለው፤ ሌሎቹ ደግሞ እሳቸውን በማይቀበሉና በሚያወግዙ መካከል ትገኛለች። አቡነ አንጠንዮስን የሚደግፈው ጎራ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ጳጳስ ይሾምልን ባሉት መሰረት አቡነ መቃርዮስ በስደት ያለውን የኤርትራ ቤተ ክህነትን እንዲያስተዳድሩ ተደርጓል። • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ ይህ አቡነ አንጠንዮስን ፓትሪያርኩ አድርጎ የሚወስደው አካል 'መናፍቅ'፣ 'ተሃድሶ' የሚል መጠሪያ እንደተሰጠው አገልጋዮቹ ይናገራሉ። አቡነ አንጠንዮስ ከመንበረ ፖትርያርክነታቸው ከተነሱም በኋላ በቁም እስር ላይ ይገኛሉ። ከአስር አመት በላይ ድምጻቸው ሳይሰማ የቆየው አቡነ አንጠንዮስ ባለፈው ዓመት ከቤታቸው ተቀድቶ ነው በተባለ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ፍታሄ ዲሜጥሮስ የተባለ የመንግሥት ልኡክ ቤተክርስቲያኗን ለመምራት እንደመጣና፤ እሳቸውም በምላሹ ጨዋ የሆነ [የቤተክርስቲያን ትምህርት ያልተማረ ] ቤተክርስቲያኗን አያስተዳድራትም ብለው መቃወማቸውን ሲገልፁ ታይቷል። በዚህ ምክንያት አቡነ አንጠንዮስ የቤተክርስቲያንዋን አሰራር ተከትለው "በምድር የታሰረ በሰማይ የታሰረ ነው . . ." ብለው ገዝተዋል። ግዝቱም እንዲነሳ በሳቸው ወገን ያለው ምዕመናን ለአሰርት ዓመታት ያህል ጠይቀዋል። በቴልአቪቭ የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ካህን ሰለሞን ኢዮብ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እርቅና ይቅርታን እንዲወርድ ጥረት እያደረገች ነው ይላሉ። ካህን ሰለሞን ፓትርያርኩ አቡነ አንጠንዮስ ናቸው ብሎ የሚያምነው ጎራ አካል ሲሆኑ፤ ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያን አደራ የተሰጣቸው ከመሆናቸው አንፃር ውግዘታቸውን እስኪያነሱ ድረስ ምዕመኑ ከጎናቸው ሊቆም እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። "በሁለቱ ወገኖች መካከል ዕርቅ እንዲወርድ ጥረት አድርገናል፤ ሆኖም ውጤት አልተገኘበትም። አሁን ወደ እግዚአብሄር መጸለይ እንጂ ሌላ ተስፋ የለንም" በማለት ካህን ሰለሞን ያስረዳሉ። "የቤተክርስቲያናችን ታሪክ እንዲህ አልነበረም፤ ቤተክርስቲያናችን አሳፍረናታል" ይላሉ በለንደን የልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን የአውሮፓ ሃገረስብከት አገልጋይ ቄስ ሺኖዳ እዮብ ሃይለ። ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ቴልአቪቭ በሚገኘው የኤርትራ መድሃኒያለም ቤተክርስትያን በካህናትና አገልጋዮች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ተዘግቧል። በወቅቱ በመቋሚያ የተደበደቡ፣ በስለት የተወጉ መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን የእስራኤል ፖሊስም ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። በእስራኤል ከሚገኙት አራት የኤርትራ አብያተ ክርስቲያናት መካከል በመድሃኒያለም ቤተክርስቲያን የተፈጠረው ግጭት ከቤተክርስቲያንዋ ውድቀት ጋር የሚያያይዙት ቄስ ሺኖዳ በካህናት፣ ዲያቆናትና መዘምራን የደረሰው ጉዳት "እጅግ የሚያሳዝን ፍጻሜ ነው" ሲሉ ገልጸውታል። • ኤርትራ፡ ''እናቶች ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር ታስረዋል'' ይህ በተለያዩ የአውሮፓ፣ የሰሜን አሜሪካና እስራኤል ሀገራት ሲታይ የቆየው በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈጠረው ግጭት መሰረታዊ ምክንያቱ ምንድን ነው? መፍትሄውስ? የሚለው ያነጋገርናቸውን አካላት ያሳሰበ መሆኑን ገልፀዋል። የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መከፋፈል ምክንያት የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፖትርያርክ የሥልጣን ይገባኛል ጥያቄ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሙግትና ጠብ ማስከተል ከጀመረ 10 ዓመት ተቆጥሯል። በተደጋጋሚ በውጭ አገራት በሚገኙ ቤተክርስቲያናት የሚያጋጥም ግጭት ግን 'በመንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች የሚፈጠር ችግር ነው' የሚል ሥም ተሰጥቶት ቆይቷል፤ አሁንም በዚህ መልኩ ይገለጻል። ይህ መፍትሄ ያላገኘው ሙግት ደግሞ የመከፋፈል ስሜት በመፍጠር የእምነቱን አንድነት እሴቶች የማላላት ብሎም የማጠልሸት ችግሮች እየፈጠረ መሆኑን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ካህናትና ምዕመናን ይናገራሉ። "በአንድ ፓትሪያርክ፣ በአንድ ጳጳስ እየተመራን በአንድ መንፈስ እንሄድ ነበር። ይህ የከፋፈለን ጉዳይ ግን ከ2005 ጀምሮ [የአውሮጳ አቆጣጠር] የተፈጠረ ነው" ይላሉ በአቡነ መቃርዮስ ስር የሚተዳደሩ አብያተ ክርስቲያን የአውሮጳ፣ አሜሪካና እስራኤል ሃገረስብከት መንበረ ጵጵስና ጸሃፊ ቄስ ገብረሚካኤል ዮሃንስ። • ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑ ተገለፀ "የኤርትራ መንበረ ፓትሪያርክ ህጋዊ ፓትሪያርኩ አቡነ አንጠንዮስን ማስረጃ ሳያቀርብ ከስልጣናቸው አነሳ፤ አሰሩዋቸውም። የቤተክርስቲያን አባት ያለ ወንጀል መነሳት ስለሌለባቸው በመቃወማችን በቤተክርስቲያንዋ ላይ መከፋፈል ተፈጠረ" ሲሉም ያስረዳሉ። በ2006 አቡነ አንጠንዮስን የሚቃወሙ ጳጳሳት ወደ ግብፅ በመሄድ ፓትርያርኩ ከመንበራቸው እንዲነሱ የጠየቁ ሲሆን የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጥፋት ያልተገኘበት ፓትሪያርክ ከመንበሩ የማውረድ ስልጣን የላችሁም ብላ መልሳለች። በዚህ ጉዳይም ፍርድ አንሰጣችሁምም ካለቻቸው በኋላ በ2009 ሌላ ፓትሪያርክ መሾማቸውን ቄስ ገብረሚካኤል ይናገራሉ። የአቡነ አንጠንዮስ እስርና እንግልት የተቃወሙ በውጭ አገር ያሉ የቤተክርስቲያኒትዋ ምዕመናን "ጥያቄያችንም አባታችን ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ነው" ይላሉ ቄስ ገብረሚካኤል። ቄስ ሽኖዳ "ይህች ቤተክርስቲያን እንደ ሽንኩርት እየተላጠች ነው። ይቅርታን በማይሰብኩ ሰዎች ደግሞ እንደ 'ሕልበት' እየተመታች ነው። ከኢትዮጵያ ይሁን ከሌሎች ቤተክርስቲያናት ትምህርት ወስደን ወደ አንድነት መምጣት አለብን" በማለት አሁን ያለውን መከፋፈል ያወግዛሉ። ቤተክርስቲያን ሰላምና ፍቅርን ማስተማርና በተግባር ማሳየት ነበረባት የሚሉት ቄስ ሰለሞን "አሁን ቤተክርስቲያናችን የሚያሳዝን መገዳደል የሚፈጸምባት ሆናለች፤ ይህም ሁሉንም አሳዝኗል" ብለዋል። • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . የዚህ ችግር ምክንያት በኤርትራ ያለው ሲኖዶስ አቡነ አንጠንዮስን በሚመለከት የእርቅ ሀሳብ ይዞ ከመጣ በኋላ ተመልሶ ሲተወው የተፈጠረው መከፋፈል እንዳገረሸ በመግለጽ ችግሩ ለአመታት ሲንከባለል የቆየ መሆኑን ይጠቅሳሉ። "ይህን ለዚህ ሁሉ ሊያደርሰን አይገባም ነበር" ያሉት ቄስ ሰለሞን በእስራኤል ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በሦስት እንደተከፈሉ ይናገራሉ። የመንግስት ደጋፊ ነው ተብሎ የሚነገርለት አንደኛው የቤተክርስቲያኒቱ አካል በቅርቡ ወደ አሜሪካ ባደረገው ጉዞ ወቅት "አቡነ አንጠንዮስ እስረኛ ያደረጉት ራሳቸው እንጂ የኤርትራ መንግሥት እጁ የለበትም፣ አላሰራቸውም" በማለት ለቪኦኤ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ቢቢሲ ቴልአቪቭ ከሚገኘው የዚህ ወገን ሃገረስብከትም ሆነ ከኤርትራ ቤተክህነት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል። እርቅ ታስቦ ያውቃል? ፓትሪያርክ የምትሾምና የምተቀባው የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከኤርትራ ጋር ባላት ታሪካዊ ዝምድና ምክንያት ችግሩን ለመፍታት ጥረት ማድረግዋንም ካህናቱ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ይላሉ ቄስ ሰለሞን "በኛ እምነት የቤተክርስቲያንዋ ስልጣን ከእጇ ወጥቶ ወደ ሌላ አካል ስለሄደ እርቁ ሊሳካ አልቻለም። ስልጣንዋ በቤተክርስቲያኗ ስር ቢሆን ኖሮ ይህን ያህል ባልተጨካከንን ነበር። ግን ወደ አንድ አካል እንድንመጣ አይፈለግም። " መጀመሪያ ላይ በብዙ መንገድ ይህ ችግር ለመፍታት ተሞክሮ ነበር የሚሉት ቄስ ገብረሚካኤል፣ በተባበሩት መንግሥታት የኤርትራ አምባሳደርና አሁን በህይወት የሌሉት ግርማ አስመሮም ጉዳዩ ሲጀመር ከስር መሰረቱ መፈታት እንዳለበትና ወደ እርቅ እንዲመጡ ጥረት ማድረጋቸውን ያወሳሉ። "በኛ በኩል ፈቃደኞች ብንሆንም፤ አስመራ ግን ማንኛውም አይነት ግንኙነት እንዳይኖር ተከልክሏል የሚል ወሬ እንደተሰማ ተቋረጠ" በማለት ቄስ ሰለሞን ያስረዳሉ። "ከዚህ በኋላም ምእመኑ ቢንቀሳቀስም አሁንም በአስመራ በኩል ፈቃድ አልተገኘም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የክፍፍሉ ጉዳት ይህ ሁሉ ችግር የቤተክርስቲያንዋ '"ውድቀት" ማሳያ ነው ያሉት ቄስ ሺኖዳ "ውድቀቱ የሚገባን ለይቅርታና አንድነት ዝግጁ ስንሆን ነው" ብለዋል። "ኤርትራ ባለው 'ምስለ ሲኖዶስ' የሚተዳደሩ ቤተክርስቲያናት አስር አመት ሙሉ ስም ማጥፋት ላይ ነው ያሳለፉት። 'መናፍቃን ገብተዋል፣ እነዚህ ከሲአይኤ ጋር ግንኙነት ያላቸው' እየተባለ ስጋትና ፍርሃት ሲሰበክ ኖሯል። በዚህ ፈንታ ይቅርታን አላስተማሩም። ለዚህ ነው ሰው ቤተክርስቲያን ውስጥ እየተጣላ ያለው" ይላሉ። ሌላው የቤተክርስቲያንዋ ትልቁ ችግር አገልጋዩ እንደሆነ የሚናገሩት ቄስ ሺኖዳ "በስሜት የሚነዳ፣ ፈሪሃ እንግዚአብሄር የሌለው አገልጋይ ነው ያላት። ከስጋዊ አስተሳሰብ ወጥተን ለመነጋገር የኔ ወገን መሰማት አለበት የሚለው ንትርካችን መቆም አለበት" ይላሉ። • ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ በወረርሽኝ ደረጃ ነው ያለው እስከ አሁን እየቀጠለ ባለው የቤተክርስቲያን ግጭት ግን በስደተኛው ማህበራዊ ኑሮ ውስጥ በመዝለቅ ችግሩ የከፋ እንዲሆን እያደረገው ነው ይላሉ ካህናቱ። "ተጽእኖው ይህ ነው ብሎ መግለጽ አይቻልም" የሚሉት ቄስ ሰለሞን በበኩላቸው፣ ምክንያታቸውን ሲያስረዱም "ቤተክርስቲያንዋ ላይ በፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት በመኖሩ ችግሩን አባብሶታል" ሲሉ ያስረዳሉ። "የቤተክርስቲያኒቱ ችግር ፖለቲካ ነው። በአገራችን የሃይማኖት ነጻነት ቢኖር ኖሮ ፓትሪያርኩ ስለ ተከሰሱበት ወንጀል እዛው ሆነን እንታገል ነበር። ግን በዚህ ምክንያት ተሰደናል፤ ተሰደን በምንኖርበት አገር ደግሞ ይህ እየተፈጠረ ያለው ችግር ተጽእኖ እያሳደረብን ይገኛል" ይላሉ። ቄስ ሰለሞን ችግሮቹ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እሴቶችን እየሸረሸሩ ስለ መሆናቸውም ያስረዳሉ። "ፓትሪያርኩ ላይ የተፈጠረው የህግ ጥሰት የእምነታችን አምድ የሆነውን ፍቅር ሸርሽሮታል። የአምልኮ ሥፍራዎች እንደ መጠጥ ቤቶች ሆነዋል። እርስ በእርሳችን እየተጣላን ምእመኑ እንዲጠፋ ቤተክርስቲያን ባዶዋን እንድትቀር ራሳችን ጠላቶች ሆነንባታል" ሲሉ ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝ ጠይቀዋል።
xlsum_amharic-train-142
https://www.bbc.com/amharic/news-56128110
ኮሮናቫይረስ፡ ክትባቱን ከወሰዱ በኋላ ኮቪድ-19ን ሊያስተላልፉ ይችላሉ?
እንደ አውሮፓውያኑ በ2009 አንድ የ11 ዓመት ታዳጊ ከዩናይትድ ኪንግደም ወደ አሜሪካ ተመለሰ።
[ "እንደ አውሮፓውያኑ በ2009 አንድ የ11 ዓመት ታዳጊ ከዩናይትድ ኪንግደም ወደ አሜሪካ ተመለሰ።" ]
ኒውዮርክ ውስጥ የአይሁድ ትምህርት ይማር የነበረው ታዳጊ ምንነቱ ያልታወቀ ህመም ገጥሞት ሰውነቱ ያብጥ ነበር። ወደ 400 ከሚጠጉ የእድሜ እኩዮቹ ጋር የሐይማኖት ትምህርት ይወስድ የነበረው ታዳጊ ህመሙን ለ22 ልጆችና ለሦስት ጎልማሶች አስተላልፏል። ልጆቹ ወደ ቤታቸው ሲሄዱ በሽታውን ለቤተሰቦቻቸው አስተላልፈው ህመሙ በብሩክሊን እና ሮክላንድ ተሰራጨ። ወረርሽኙ ለአንድ ዓመት ቆይቶ 3,502 ሰዎች ታመዋል። ኋላ ላይ ሳይንቲስቶች ሲመራመሩ፤ ህመሙ የተስፋፋው ታዳጊዎቹ በጣም ተቀራርበው የሃይማኖት ትምህርት ሲወስዱ መሆኑን ደረሱበት። ታዳጊው የኩፍኝና ሌሎችም በሽታዎች ክትባት ወስዷል። እናም ሰውነቱ በሽታ የመከላከል አቅም አዳብሯል። ምንነቱ ባልታወቀው በሽታ ሲያዝ እምብዛም ምልክት ያላሳየውም በክትባቶቹ እገዛ ነው። ታዳጊው ምንም እንኳን ክትባት ቢወስድም በሽታውን ወደ ሌሎች ሰዎች አጋብቷል። ብዙ ክትባቶች የህመም ምልክትን ቢያጠፉም ሙሉ በሙሉ ከበሽታ አይከላከሉም። ክትባት የወሰዱ ሰዎች ሳይታወቃቸው ቫይረስ ሊያስተላልፉ ይችላሉ ማለት ነው። በሽታን የመከላከል አቅም ከክትባት የሚገኝ በሽታን የመከላከል አቅም በሁለት ይከፈላል። አንደኛው ቫይረስ ሰውነት ውስጥ ከገባ በኋላ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያስከትል የሚከላከል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ሙሉ በሙሉ በበሽታ መያዝን የሚገታ ነው። ማጅራት ገትርን እንደ ምሳሌ እንውሰድ። የዚህን በሽታ የተለያዩ ዝርያዎች የሚከላኩ ክትባቶች አሉ። ክትባቶቹ ከ85 እስከ 90 በመቶ የበሽታውን ስርጭት ይገታሉ። ሆኖም ግን ሰዎች ክትባት ከተሰጣቸው በኋላ ባክቴርያውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ባክቴርያው አፍንጫና ጉሮሮ ውስጥ ተደብቆ ሰዎች ሲያስነጥሱ፣ ሲያስሉ ወይም ሲሳሳሙ ወደሌላ ሰው ይሸጋገራል። ክትባቶች ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅም እንዲያዳብር ይረዳሉ። የኮቪድ-19 ክትባት ቫይረሱን ለይቶ የሚያጠቃና ሰውነትን የሚከላከል አንቲቦዲ (ጸረ እንግዳ አካላት) ያመርታል። የኮሮናቫይረስ ክትባት ሰውነት ውስጥ እንዴት ይሠራል? ኒል የተባሉት ተመራማሪ እንደሚሉት፤ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች በምን መንገድ በሽታን የመከላከል አቅም እንደሚያዳብሩ ለማወቅ ጊዜው ገና ነው። አንድ ሰው ክትባቱን ከወሰደ በኋላ ቫይረሱን ሊያስተላልፍ ይችላል? የሚለው ጥያቄ በተደጋጋሚ ይነሳል። እስካሁን ገበያ ላይ የቀረቡት የኮሮናቫይረስ ክትባቶች የተፈተሹት ሰዎች በሽታውን እንዳያስተላልፉ በማድረግ አቅማቸው አይደለም። የተመራማሪዎች ዋነኛ ትኩረት ክትባቶች ቫይረሱን መከላከል ይችላሉ ወይ የሚለው ነው። ፕሮፌሰር ዳኒ አልትማን የተባሉ የኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደን ተመራማሪ፤ ሰውነት የሚያመርተው ጸረ እንግዳ አካላት ሰዎች በድጋሚ በቫይረሱ እንዳይያዙ የመከላከል አቅማቸው ደካማ እንደሆነ ያስረዳሉ። በአንድ ጥናት ላይ ክትባት ከወሰዱ ሰዎች መካከል 17 በመቶው ለሁለተኛ ጊዜ ቫይረሱ ይዟቸዋል። ከእነዚህ 66 በመቶው የበሽታውን ምልክት አላሳዩም። ሰዎች የበሽታውን ምልክት ባያሳዩም ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላለፉ የሚችሉበት እድል አለ። በሌላ በኩል አንዳንድ የክትባት አይነቶች ሰዎች በሽታውን ወደ ሌላ ሰው እንዳያስተላልፉ የማድረግ አቅም እንዳላቸው ታይቷል። ይህን ማድረግ የሚችሉት በሰውነት ውስጥ ያለውን የቫይረስ ቅንጣት መጠን በመቀነስ ነው። አሁን ገበያ ላይ የሚገኙት ክትባቶች ሰዎች ቫይረሱን ወደሌላ ሰው እንዳያስተላልፉ በማድረግ ረገድ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆኑ እንመልከት። ከኦክፎርድ-አስትራዜኒካ ክትባት እንጀምር። ኦክፎርድ-አስትራዜኒካ አምና ሐምሌ ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ክትባቱ በበሽታው የመያዝ እድልን በእጅጉ ቢቀንስም በሽታውን ወደ ሰው ባለማስተላለፍ ረገድ ሙሉ በሙሉ ውጤታማ ላይሆን ይችላል። ይህ ውጤት የተገኘው በዝንጀሮዎች ላይ በተደረገ ሙከራ ሲሆን፤ ክትባቱ በሰዎች ላይ ሲሞከር የተለየ ውጤት ታይቷል። የኦክስስፎርድና አስትራዜኒካ ክትባት ሲሞከር በሁለት ዙር ጠብታ አልነበረም። በጥናቱ የተሳተፉ ሰዎች በየሳምንቱ ከአፍንጫቸው እና ከጉሮሯቸው ናሙና ተወስዷል። የጥናቱ ውጤት በያዝነው ዓመት ሲታተም እንደጠቆመው፤ ከፊል ክትባቱን ከወሰዱ ሰዎች 59 በመቶ ያህሉ በበሽታው የመያዝ እድላቸው ቀንሷል። ከእነዚህ ሰዎች አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው። በሌላ በኩል ሙሉ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች በበሽታው የመያዝ እድላቸው 55 በመቶ ቀንሷል። አንድ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ ክትባቱ በአንድ ጠብታ ለቫይረሱ የመጋለጥ እድልን 67 በመቶ ቀንሷል። ይህም ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው እንዳያስተላልፉ የማድረግ አቅም እንዳለ ያሳያል። ፋይዘር-ባዮንቴክ ክትባቱ ሰዎች በቫይረሱ እንዳይያዙ በማድረግ ስርጭቱን ስለመግታቱ ገና ባይረጋገጥም፤ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች አሉ። ታኅሣሥ ላይ የፋይዘር ዋና ኃላፊ አልበርት ቦርላ እንዳሉት፤ በእንስሳት ላይ የተደረገ ሙከራ እንደሚያሳየው ክትባቱ በሽታውን ወደ ሌላ ሰው የማስተላለፍ መጠንን ይቀንሳል። ሆኖም በሰዎች ላይ ያለው ውጤታማነት አልተረጋገጠም። እስራኤል ውስጥ የተሠራ ጥናት የክትባቱ ሁለት ጠብታ ከተሰጣቸው 102 የሕክምና ባለሙያዎች፤ ጠንካራ በሽታ የመከላከል አቅም ያላዳበሩት ሁለቱ ብቻ ናቸው። ይህ ማለት 98 በመቶ ጸረ እንግዳ አካላት አምርተዋል ማለት ነው። አጥኚዎቹ እንዳሉት፤ ሰዎች ጠንካራ ቫይረሱን የመከላከል አቅም ሲያዳብሩ በሽታውን የማስተላለፍ እድላቸው ይቀንሳል። በእርግጥ የእስራኤሉ ጥናት የተሠራው በጥቂት ሰዎች ላይ መሆኑ ውጤቱ ላይ ጥያቄ ያስነሳል። ሞደርና ሞደርና በሽታውን ወደ ሌላ ሰው እንዳይተላለፍ ስለማድረጉ የሚፈትሽ ሙከራ አልተደረገም። የመጀመሪያውን ዙር ጠብታ ከወሰዱ ሰዎች 14ቱ በቫይረሱ ተይዘዋል። ሁለተኛውን ዙር ጠብታ ከወሰዱት አንጻር ይህ ቁጥር ዝቅ ይላል። ሙከራው የሚያሳየው ክትባቱ ከአንድ ጠብታ በኋላ የበሽታውን ምልክት የማሳየት እድልን ሦስት ሁለተኛ እንደሚቀንስ ነው። ጥናቱ ሲሠራ ሙከራ የተደረገባቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ውስን ነበር። እናም የጥናቱ ውጤት ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ላይሆን ይችላል። ኖቫክስ እስካሁን ይህ ክትባት የትም አገር ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ አላገኘም። ሰዎች በበሽታው እንዳይያዙ ወይም ቫይረሱን እንዳያስተላልፉ የማድረግ ብቃቱ ገና አልተፈተሸም። በእርግጥ ጥቅምት አካባቢ ይፋ የተደረጉ ውጤቶች ለሳይንቲስቶች ተስፋ ሰጥተዋል። ክትባቱ ለዝንጀሮዎች በከፍተኛ መጠን ከተሰጠ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ እንደሚረዳ የሚጠቁሙ ውጤቶች ታይተዋል። በተጨማሪም የበሽታውን ምልክት የማያሳዩ ሰዎችን የማስተላለፍ መጠን እንደሚቀንስ ተደርሶበታል። ክትባቱ በሰዎች ላይ ተሞክሮ ውጤታማነቱ እስከሚረጋገጥ ተመራማሪዎች እየጠበቁ ይገኛሉ። የጋርዮሽ በሽታን የመከላከል አቅም ብዙ ሰዎች በሽታውን የመከላከል አቀም ሲያዳብሩ የጋራ በሽታን የመከላከል አቅም (ኸርድ ኢምዩኒቲ) ይፈጠራል። ክትባቶች የጋራ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና አላቸው። በሳውዝሀምተን ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ማይክል ሄድ "የጋራ በሽታን የመከላከል አቅም ለማዳበር ክትባቶች የበሽታውን ስርጭት መግታት ይጠበቅባቸዋል" ይላሉ። የጋራ በሽታን የመከላከል አቅም እንዲፈጠር አብዛኛው ማኅበረሰብ ቫይረሱን መከላከል መቻል አለበት። የጋራ በሽታን የመከላከል አቅም ዳብሯል የሚባልበት ቁጥር እንደየአገሩ ቢለያይም፤ አማካዩን የሚጠቁሙ ጥናቶች ተሠርተዋል። ለምሳሌ በአንድ አገር ከ60 አስከ 72 በመቶ ያህል ሕዝብ ክትባት ሲወስድ የጋርዮሽ በሽታ የመከላከል አቅም ወደማዳበር ይሄዳል። ይህ ቁጥር አንድ ክትባት ምን ያህል ቫይረሱን መከላከል ይችላል የሚለው ላይ ይወሰናል። አሁን ላይ የዓለም ትኩረት የቫይረሱን የስርጭት መጠን መቀነስ ቢሆንም፤ የመጨረሻ ግቡ ወረርሽኙን ማስወገድ ነው።
xlsum_amharic-train-143
https://www.bbc.com/amharic/news-55421935
ኮሮናቫይረስ ፡ ባንነካካ፣ ባንተቃቀፍ፣ ባንሳሳም በጤናችን ላይ የሚጎድል ነገር ይኖር ይሆን?
ያለፈው የፈረንጆች ዓመት በጥቅሉ ካየነው መልካም ዓመት አልነበረም።
[ "ያለፈው የፈረንጆች ዓመት በጥቅሉ ካየነው መልካም ዓመት አልነበረም።" ]
አራራቀን እንጂ አላቀራረበንም። ለመሆኑ ባንተቃቀፍ ምን ይቀርብናል? ትዝ ብሎንስ ያውቃል? ለምን አልተጨባበጥኩም ብሎ የከፋውስ አለ? ለነገሩ ልጆችንን አቅፎ መሳም፣ ፍቅረኛችንን መሳም፣ ባሎቻንን ማቀፍ. . . እንዴት አንናፍቅም? በዓለም ላይ በርካታ ሰዎች የፈረንጆቹን 2020 የማኅበራዊ መራራቅ ዓመት ብቻ ሳይሆን ቤት ተከርችሞብን የታሸግንበት ዝጋታም ዓመት ሆኖ ነው እያበቃ ያለው። ከኮቪድ-19 መከሰት በፊት ማንም ሰው መቼስ ወደፊት መጨባበጥ ይከለከላል፣ መተቃቀፍ ያስቀስፋል ብሎ ያሰበ ይኖራል ተብሎ አይገመትም። ለመሆኑ አለመተቃቀፋችን አለመጨባበጣችን የራሱን ችግር ይዞ ብቅ ይል ይሆን? ተመራማሪዎች አዎ ይላሉ። መነካካት ተራ ነገር አይደለም። በፍቅር መነካት ወይም መታቀፍ ሕጻን ሳለን የመጀመርያ ቋንቋችን ነው። ፍቅርን የምንማርበት ቋንቋ። መግቢያቢያችን። ደግነትን፣ ሰው መውደድን፣ ለሆነ ፍጡር እምነታችንን መስጠትን የምንሰለጥነው በእቅፍ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። በጊዜ ሂደት ረስተነው ይሆናል እንጂ ድሮ ድሮ ካልታቀፍን ብለን አልቅሰናል። ካላመናችሁ እናታችሁ ጋር ደውሉ። ለዕድገታችንም እንደ እናት ጡት ወተት ሁሉ መታቀፍ አስተዋጽኦ ነበረው። በጊዜ ሂደት ክደውን ነው እንጂ. . . ። "የሰዎች ተቀራርቦ መነካካት የዋዛ ነገር አይደለም። ማኅበራዊ ሙጫ ማለት ነው። አስተሳስሮናል። ከምንወደው ሰው ጋር ገምዶናል። እንደ ሰው የሚያቀራርበን አንድ ነገር ቢኖር ይኸው ነው" ይላሉ ዴቪድ ሊንደን። ዴቪድ 'ዘ ኒው ሳይንስ ሂዩማን ኢንዲቪጁዋሊቲ' ደራሲ ናቸው። በዚህ የንክክኪ ሳይንስ ውስጥ ብዙ አጥንተዋል። "የመነካካት ነገር እና ፋይዳው እምብዛምም አልተጠናም። ቸል ያልነው፤ ገሸሽ ያደረግነው ጉዳይ ሳይሆን አይቀርም" ይላሉ ደራሲ ዴቪድ። ለመሆኑ ሌሎችን ሰዎችን ስንነካ አእምሯችን ውስጥ ምንድነው የሚፈጠረው? አንዳንድ ጥናቶች መነካት፣ መታቀፍ፣ ልክ ሕመም ማስታገሻን የመውሰድ ያህል ፈውስ ይሰጣል ይላሉ። ይህ የተጋነነ አረፍተ ነገር ከመሰላችሁ፣ አንድ ሕጻን ልጅ ሲነካ እንዴት እንደሚሆን ለማየት ሞክሩ። አንድ ሕጻን ልጅ በእናቱ ጭንቅላቱ ቢዳበስ የልብ ምቱ መረጋጋት ይጀምራል። ይህን ያሉት በሕጻናት አንጎል [ኒውሮሳይንስ] ላይ ተመራማሪ የሆኑት ሬቤካ ስላተር ናቸው። አንዳንድ ጥናቶች ይህንን ነገር ከዚህም በላይ ገፋ ያደርጉታል። ለምሳሌ ክብደታቸው ከአማካይ በታች ሆነው የተወለዱ ልጆች በእናቶቻቸው ሲነካኩና ሲታቀፉ መጠናቸው እየተስተካከለ እንደሚመጣ ተደርሶበታል። የዝግመተ ለውጥ ተመራማሪ ሮቢን ደንበር እንደሚሉት የሰው ልጅ ከእንሰሳት ጋር ከሚያመሳስሉት ነገሮች አንዱ ንክኪና ለዚያ የሚሰጠው ትርጉም ነው። የሰው ልጅ ያለበት የነ ዝንጀሮና ዝርያቸው ጨምሮ አጥቢዎች በሕይወት ዘመናቸው 20 ከመቶውን የሚያሳልፉት እርስ በርሳቸው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በመነካካት ነው። ከዝርያቸው ጋር ወዳጅነታቸውን የሚገልጹትም በብዛት በንክኪ ነው። ለምሳሌ አንድን ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ስንነካ በመዳፋችን ያለው የነርቭ ብልጭታ ለጭንቅላታችን 'ከአዲስ ሰው ጋር አዲስ ግንኙነት እየፈጠርክ ነው' የሚል መልዕክት ያደርስለታል። ያ ስሜት ደግሞ ብዙ እጢዎች መልካም የሰውነት ፈሳሾችን እንዲያመነጩ ያደርጋል። በንክኪ ውስጥ አእምሯችን ዘና ይላል፤ በተለይም ደግሞ አብረነው በንክኪ እየተግባባነው ያለውን ሰው የምናምነው ሲሆን እፎይታን ይመግበናል ይላሉ እኚሁ ተመራማሪ። ከመነካካት ጋር የነበረን የመጀመሪያ ቁርኝት ፈዋሽ ብቻ ሳይሆን ስሜትን ሰቅዞ የሚይዝ ነው። መጀመሪያ የሳምናትን ኮረዳ፣ መጀመሪያ የዳበስነውን መልከ መልካም ልጅ፣ የመጀመሪያ የፍቅር ግንኑነቶች ሁሌም በአእምሯችን የማይጠፉት ከንክኪ በሚያገኙት ኃያል የተነሳ ነው። ለመሆኑ መነካካት ይህን ያህል ትርጉም ካለው አለመነካካት ምን ሊያደርገን ይችላል? መነካት፣ መታቀፍ ይህን ያህል አእምሯችን ላይ በጎ ተጽእኖ አለው ብለናል። ያረጋጋናል፣ ያስደስተናል፣ ሕይወታችንን እንድንወዳት ያደርገናል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሕመማችንን ያስወግድልናል። አልተጋነነም። በንክኪ ደዌ ይፈወሳል። የንክኪ ሕክምና ያለውም ለዚህ ሳይሆን ይቀራል? አሁን እንዳትነካኩ፣ እንዳትጨባበጡ፣ እንዳትስሙ ስንባል ሳናውቀው የሆነ ነገራችን እየተጎዳ ነው። "እርግጥ ነው አትነካኩ በተባልን ማግስት ሕመም አልጀመረንም። ራሳችንን አልሳትንም፣ መፈጠራችንን አልጠናል ይሆናል. . ." ይላሉ ደራሲው ሊንደን። . . . ነገር ግን ከሰው ጋር የነበረን የቁርኝት ገመድ ለእኛ ባይታየንም ተበጥሷል፤ በስሜት ተለያይተናል። ቀስ በቀስ መጎዳታችንን ሳናውቀው ተጎድተናል።" ለምሳሌ አንዳንድ እንሰሳትን በፍጹም እንዳይነካኩ ብንከለክላቸው ወዲያውኑ ሊታመሙ ይችላሉ። ታመሙ የምንለው በመንፈስ ብቻ ሳይሆን በአካልም ጭምር ነው። በጭንቀት ይወጠራሉ፤ አዳዲስ የአውሬነት ባህሪን እያሳዩ ሊመጡ ይችላሉ። በጊዜ ሂደት ደግሞ ጤናቸው እየተቃወሰ ሊመጣ ይችላል። እስከመሞትም ሊያደርሳቸው ይችላል። ወረርሽኙ የገባ ሰሞን፣ በተለይ ደግሞ ብዙ አገሮች ማኅበራዊ መራራቅን ግዴታ ባላደረጉበት ወቅት እንኳ ብዙ ሰዎች ከሰዎች ጋር መቀራረብን፣ መነካካትን እንደናፈቁ ይናገሩ ነበር። አሁን ዓለም እንዲህ በተራራቀበት ጊዜ ይህ ሁኔታ ሲብስበት ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ነው። ምናልባት ነገሩን ትተነዋል። ቅርርቦሽንና ፋይዳውን የምናስብበት ጊዜ እንኳን አጥተን ይሆናል። ሕይወት እያራወጠን ዘንግተነው ይሆናል። ያ ማለት ግን ውስጣችን አልተጎዳም ማለት አይደለም። ጎልድስሚዝ ዩኒቨርስቲ በቢቢሲ ራዲዮ ፎር በኩል አንድ ጥናት አድርጎ ነበር። በጥናቱ በ110 አገሮች የሚኖሩ 40ሺህ ሰዎች ተጠይቀው ነበር። 20ሺህ የሚሆኑት መተቃቀፍን እጅግ አድርገው መናፈቃቸውን አምነዋል። መነካትን መናፈቅ ከባድ ናፍቆት ነው። ታዲያ ምን ተሻለ? ፕሮፌሰር ስሌተር እንደሚሉት ከሆነ ከዚህ በኋላ በሰዎች መካከል ተህዋሲው ቢጠፋ እንኳን ከተህዋሲው በፊት እንደነበረው ጊዜ ንክኪዎች አይኖሩም ይላሉ። ሰዎች በመጨባበጥ ውስጥ የሚለዋወጡት ወዳጅነት እንደነበረው አይዘልቅም ነው የሚሉት። ነገር ግን የዝግመተ ለውጥ ተመራማሪና ሳይኮሎጂስት ሮቢን ደንበር ይህ ነገር አያሳምናቸውም። እሳቸው የሚያምኑት ወዳጅነትና መነካካት ሰዋዊ ነው። ሰዋዊ ባህሪ ደግሞ እንዴትም ቢሆን ካቆመበት ይቀጥላል። መዳፋችን የውስጠኛው አካሉ ሲፈጠር ራሱ እንዲነካ፣ እንዲዳስስ ተደርጎ ነው። የነርቮቹ ብዛት የሚያመላክቱትም ያንኑ ነው። እኛ ባናውቀውም ሰውነታችን ልክ እንደ ጥልፍልፍ የኤሌክትሪክ ገመድ ያለ ነው። ንክኪ ቶሎ ብሎ ወደ አእምሮ መልዕክት ይልካል። ስለዚህ ያለ መነካካት ጤናችን ልክ አይመጣም። በሚወዱት ሰው መነካትን የመሰለ የአእምሮ ፈውስ የለም። ለረዥም ጊዜ በናፈቅነው ሰው እቅፍ ውስጥ የመግባትን ያህል ደስታ የለም። በናፈቅነውና በምንወደው ሰው እቅፍ ውስጥ ለሰከንዶች መቆየት ትንሽዬ የገነት ጎጆ ውስጥ ገብቶ የመውጣት ያህል ነው። "አንድ ሰው ስለእናንተ የሚሰማውን በትክክል ለማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ . . . የሚነግሯችሁን ከመስማት ይልቅ እንዴት እንደሚነካችሁ ስሜቱን ለመረዳት ሞክሩ" ያላሉ ባለሙያው። ብዙ ሰዎች ከልጅነታቸው ጋር በነበራቸው የእናት ፍቅር ውስጥ ምን ትዝ ይላችኋል ሲባሉ፤ እናታቸው ፀጉራቸውን ስትነካካቸው የነበራቸው ስሜትን በይበልጥ ያስታውሳሉ። ለምን? የፈረጆቹ 2021 ዳግም የምንተቃቀፍበት ዘመን ይሆን ይሆን?
xlsum_amharic-train-144
https://www.bbc.com/amharic/50232051
"በመንግሥት መዋቅር ሥር ውስጥ ሆነውም ግጭቶችን የሚያባብሱ ኃይሎች እንዳሉ እናውቃለን" ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከሰሞኑ የተፈጠሩ ግጭቶችን በተመለከተ ትናንት ጥቅምት 18 ቀን 2012 ዓ. ም. መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው በተለይ ጥቅምት 13 እና 14 ለደረሰው ጥፋት መነሻ ነው ካለው እና ለመንግስት አካል ማሳወቅ ሲገባው "ተከብቤያለሁ" ብሎ ለሕዝብ መረጃ ካሳራጨው ጀምሮ ጥፋት ያደረሱ ሰዎች በሕግ እንዲጠየቁ ይጠይቃል። ስለ መግለጫውና ተያያዥ ጉዳዮች የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀን አነጋግረናል። ት ና ንት ኢዜማ ያወጣው መግለጫ ይዘት ምንድን ነው?
[ "የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከሰሞኑ የተፈጠሩ ግጭቶችን በተመለከተ ትናንት ጥቅምት 18 ቀን 2012 ዓ. ም. መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው በተለይ ጥቅምት 13 እና 14 ለደረሰው ጥፋት መነሻ ነው ካለው እና ለመንግስት አካል ማሳወቅ ሲገባው \"ተከብቤያለሁ\" ብሎ ለሕዝብ መረጃ ካሳራጨው ጀምሮ ጥፋት ያደረሱ ሰዎች በሕግ እንዲጠየቁ ይጠይቃል። ስለ መግለጫውና ተያያዥ ጉዳዮች የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀን አነጋግረናል። \n\nት ና ንት ኢዜማ ያወጣው መግለጫ ይዘት ምንድን ነው?" ]
አቶ ናትናኤል፦ ስምንት ነጥብ ያለው የአቋም መግለጫ ነው ያወጣነው። ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል በተፈጠሩ ሁከቶች የሰው ሕይወት መጥፋቱና ንብረት መውደሙ እንዲሁም የተለያየ አካል ጉዳት መድረሱን መነሻ በማድረግ የተሰጠ መግለጫ ነው። አገራችን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚደረግ ሽግግር ውስጥ እንደሆነች ይታወቃል። ያ ሽግግር እና የአገር አንድነትን ለማረጋገጥ ዜጎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ፍርሀት የፈጠረባቸው ኃይሎች የመጨረሻ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ የገቡበት እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ተረድተናል። • "ምርጫው እንዲራዘም እንፈልጋለን" አቶ አንዷለም አራጌ • "ትግላችን ከጨቋኝ ገዥዎች ጋር እንጂ ከሕዝቡ ጋር አልነበረም" ኦዴፓ ለጠፋ ሕይወትና ለተጎዱ ሰዎች ሀዘናችንን ገልፀን፤ ይህንን ድርጊት በመፈፀም ከመነሻው ጀምሮ ምክንያት የሆኑና በተለያየ ደረጃ ወንጀሉን ሲፈፅሙ የነበሩ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀናል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በተለይ እነዚህ ግጭቶችን በማባባስ ሚና ሲጫወቱ የነበሩ የሚዲያ ተቋማት ላይ ስልጣን ያለው አካል እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀናል። በተለያየ አካባቢ የተፈፀመውን ድርጊት ተከትሎ ሰዎች ቁጭት ላይ ስለሆኑ ወደ አላስፈላጊ ድርጊት እንዲሁም የመልስ እርምጃ ለመውሰድ ፍላጎት እንዳለ የሚያሳዩ ጉዳዮች ስላሉ፤ ይህ ፍላጎት በፍፁም ተግባራዊ ሊሆን እንደማይገባውና በሰላማዊ መንገድ ችግሮቻችንን ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች አሁንም መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበናል። በአጠቃላይ በአገር ላይ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም መጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ውይይት በቶሎ መጀመር እንዳለበት ገልፀን፤ እዚህ ውይይትም ውስጥ ለመሳተፍ ያለንን ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት የገለፅንበት ነው። በመፈናቀል፣ በድርቅ እና ሰሞኑን ባጋጠመው የአንበጣ መንጋ የተመቱ አካባቢዎች እንዳሉና እነዚህ አካባቢዎች ትኩረት ማግኘት እንደሚገባቸውና ትኩረት አጥተው የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስ በመግለጫችን ጥሪ አስተላልፈናል። መግለጫው እንደዚህ አይነት ግጭቶች ለመፈጠራቸው ምክንያቱ ባለፉት ጊዜያት ተዘርተው ከነበሩ የዘረኝነትና የአግላይነት ፖለቲካ ለመላቀቅ ሰው በመንቀሳቀሱ ነው ይላል። እውን ምክንያቱ ይህ ነው? ለለውጥና ለአንድነት መንቀሳቀሳቸው ነው ይሄንን ችግር ያመጣው ብላችሁ ታምናላችሁ? አቶ ናትናኤል፦ ባለፈው ሳምንት የተፈጠረው ነገር ከሌላው የተለየ ክስተት ነው ብለን አናምንም። ተነጥሎ የሚታይ ድርጊት ነው ብለን አናምንም። በተለያየ አካባቢ የሰው ሕይወትና ንብረት ላይ አደጋ እንዲደርስ ያደረጉ ግጭቶች ሲነሱ ቆይተዋል። እነዚህ ሁሉ ተደምረው በአጠቃላይ ትልቁ ምስል፤ በዜጎች መካከል በዘውግ ወይም በሀይማኖት ልዩነት ለመፍጠር የሚደረገው ነገር፤ ዲሞክራሲያዊና ዜጎችን እኩል እድልና እኩል መብት የሚሰጥ ሥርዓት ለመፍጠር የሚደረገው ጉዞ ያስቀራቸው ኃይሎች በተደጋጋሚ እዚህ ጉዞ ላይ ችግር እየፈጠሩበት እንደሆነ ነው። ባለፈው ሳምንት የተከሰተው ነገር ለብቻው ተነጥሎ የሚታይ ሳይሆን የዚህ ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዳንሄድ የማደናቀፍ ሙከራ አንዱ አካል ነው ብለን ነው የምናምነው። • ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የኢዜማ መሪ ሆነው ተመረጡ • "ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች መግለጫውን ለማውጣት አልዘገያችሁም? አቶ ናትናኤል፦ መግለጫ ለማውጣት ዘግይተናል ብለን አናስብም። ጉዳዩ ተከስቶ ወዲያውኑ የሀዘን መግለጫችንን አስተላልፈናል። ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ የሆነ ከኛ የምርጫ ወረዳ አባላት የሚመጡ ማስረጃዎችን ማሰባሰብ ነበረብን። እንዲሁ ዝም ብሎ በጨበጣ ከሚዲያዎች ላይ በሚነሱ ነገሮች ተነስተን መግለጫ መስጠት አልፈለግንም። ከራሳችን የምርጫ ወረዳዎች የሚመጡ መረጃዎችና ማስረጃዎች ለማሰባሰብ ከወሰደብን ጊዜ ውጪ ዘግይተናል ብለን አናስብም። ኤዜማ እንዲህ አይነት ክስተቶች ሲፈጸሙ መግለጫ ለማውጣት ድፍረት ያጣል ሲባል ይሰማል። እውን ድፍረት ታጣላችሁ? አቶ ናትናኤል፦ እውነት ለመናገር ምንም የምንፈራው ነገር የለንም። የሚፈራው የሚመስለኝ እስር፣ መሞት ወይም ከአገር መሰደድ ነው። ኢዜማ ውስጥ ያለው ስብስብ እንደዚህ አይነት ነገሮች ይከሰታሉ ብሎ የሚፈራ እንዳልሆነ በተግባር የታየ ነው። ከዚህ በፊት የታሰሩ፣ የተሰደዱ፣ ሕይወታቸው ላይ ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠባቸው ሰዎች ያሉበት ነው። ለነጻነትና ለእኩልነት እንዲሁም ለዴሞክራሲያዊ ትግል ሲባል። ኢዜማ ውስጥ ያሉት በተግባር የተፈተኑ ሰዎች ናቸው። የሚነሳው ወቀሳ አግባብ ነው ብዬ አላምንም። እኛ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው የአገር ሰላም፣ አንድነትና እኩልነትን ነው። ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የምናደርገው ሽግግር ትዕግስተኛነትና የሰከነ የፖለቲካ ጉዞ ይፈልጋል ብለን በማመን፤ ግጭትን ከሚያነሳሱ እና ኃይለኝነት ከሚያሳዩ ንግግሮች እንቆጠባለን። ያ ምናልባት በስህተት ከፍርሀት ተወስዶ ከሆነ መታረም አለበት ብለን ነው የምናምነው። የኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በተደጋጋሚ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ተጋብዘው እንደሚወያዩና ከመንግሥት ጋር ያለው ቅርርብ ፓርቲውን ድፍረት እንዳሳጣው ይነገራል። አቶ ናትናኤል፦ ፕ/ር ብርሀኑ ከዚህ በፊት የፖለቲካ ታሪካቸው ምን እንደነበረ ለሚያውቅ ሰው አንድም ውሀ የሚቋጥር አይደለም። በተደጋጋሚ እንዳልነው ኢዜማ እንደ ፓርቲ ከመንግሥት ጋርም ይሁን ከየትኛውም የፖለቲካ ኃይል ጋር አገርን በማረጋጋትና ሰላም እንዲመጣ እንዲሁም ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚደረገው ሽግግር ሰላማዊ እንዲሆን ከሁሉም አካላት ጋር ይሠራል። የአገር አንድነት ላይ አደጋ ሲመጣ ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚደረገው ሽግግር አደጋ ውስጥ ሲወድቅ፤ ምንንም፣ ማንንም ፈርተን ወደ ኋላ የምንል አይደለም። የፓርቲያችን መሪ ፕ/ር ብርሀኑ ለዚህ ጉዳይ በተግባር የተፈተነ ተሞክሮ ያላቸው ሰው ናቸው። • አሳሳቢው የሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር በኢትዮጵያ • የባልደራስ፣ የአብን አባላትና የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባለቤት ተፈቱ በመግለጫው ላይ ካስቀመጣችሁት ነጥብ አንዱ "ተከብቤያለሁ" ብሎ ለሕዝብ መረጃ ካሰራጨው ጀምሮ ሌሎችም ጉዳት ያደረሱ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ነው። እነዚህ አካላት እነማን ናቸው? አቶ ናትናኤል፦ ይሄ ችግር ሲነሳ ከምን እንደተነሳ ሁሉም ሰው ያውቃል። በማኅበራዊ ድረ ገጽ አደጋ ሊደርስብኝ ነው የሚል መረጃ ያሰራጩ ሰው አሉ። ከዛ ግለሰብ አንስቶ ይህንን ጥሪ ተከትሎ በየደረጃው የወንጀል ተግባር የፈጸሙ በሙሉ ተጣርቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ ነው ጥያቄ ያቀረብነው። ይሄ ለግጭቱ መነሻ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ? አቶ ናትናኤል፦ ሌላ ምንም የተከሰተ ነገር የለም። ይሄ ነገር ከተከሰተ በኋላ ነው በቀጥታ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ግጭቶች የተነሱትና በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ አደጋ የደረሰው። ምንም ቢሆን ደህንነቴ አደጋ ውስጥ ገብቷል ብሎ የሚያስብ ሰው በየደረጃው ላሉ የመንግሥት አካላት ማሳወቅ እንጂ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ግጭትን በሚያነሳሳ ሁኔታ እንደዚህ አይነት ጥሪ ማድረግ አለባቸው ብለን አናምንም። ስህተት ነው። ለዛ ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል ብለን ነው የምናምነው። ማንን ነው የምትሉት? አቶ ናትናኤል፦ እሱ በጣም ግልጽ ነው ብለን ነው የምናምነው። ግን በተጠየቅን ጊዜ የመንግሥት አካል ማንን ነው ያላችሁት? ብሎ ካለን ከማስረጃ ጭምር ለማቅረብ ዝግጁ ነን። አሁን ላይ ስም መጥቀስ አልፈለጋችሁም? አቶ ናትናኤል፦ አዎ። ይቆየን። የኢዜማ የወጣቶች አደረጃጀት አዳማ ላይ ቄሮ የተባለውን ቡድን ለመመከት ጉዳት አድርሷል የሚል ክስ ይቀርባል። እንደዚህ አይነት አደረጃጀት አላችሁ? አቶ ናትናኤል፦ እኛ በ400 የምርጫ ወረዳዎች በሰላማዊ መንገድ ተወዳድረው የመንግሥትን ስልጣን ለመያዝ የሚሠሩ የምርጫ ወረዳ አደረጃጀቶች አሉን። አዳማ የተለየ አይደለም። በማንኛውም መልክ ከሰላማዊ መንገድ ውጪ የሚደረጉ ነገሮች እኛ አደረጃጀት ውስጥ አይሳተፉም። ይህንን ለማረጋገጥ ደግሞ ፓርቲያችን ከመመስረቱ በፊት በ312 የምርጫ ወረዳዎች በጋራ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተፈራረሙበትን የሥነ ምግባር የቃል ኪዳን ሰነድ ጭምር አሰልጥነናል። ኢዜማ በጣም ብዙ ነገር ነው የሚባለው። ግጭት አስነሳ የተባለው የቅርብ ክስ ከነዚህ አንደኛው ነው። መሰረተ ቢስ የሆነ ክስ ነው። ከዚህ በፊትም የተለያዩ ነገሮች የተባለ ፓርቲ ነው። ይህ ለምን እንደሆነ እናውቃለን። ምን ፈርተው እንደዚህ አይነት ክስ እንደሚያቀርቡ እናውቃለን። በዋነኛነት ማኅበረሰቡ እንዲረዳ የምንፈልገው እኛ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተወዳድረን ስልጣን መያዝ ነው አላማችን። ከዛ በፊት ቅድሚያ ሰጥተን የምንሠራው ለአገር መረጋጋትና ሰላም ነው። አባሎቻችን ለሰላምና መረጋጋት ይሠሩ እንደነበር በማስረጃ አስደግፈን ማቅረብ እንችላለን። • "በኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊ ግድያ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም" የነቀምቴ ፖሊስ አዛዥ • “በእግር ወይም በአውሮፕላን እያሉ ወሬ ማብዛቱ ትርጉም አልባ ነው” አምባሳደር እስቲፋኖስ ስለዚህ አልተሳተፋችሁም? አቶ ናትናኤል፦ በፍጹም እንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ ተሳትፎ አልነበረንም። ከዚህ በፊትም እንደዚህ አይነት የሰው ሕይወት ያለፈባቸው ግጭቶች በተለያዩ አካባቢዎች ነበሩ። ኢዜማ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ማነው ይላል? አቶ ናትናኤል፦ በየቦታው ለተፈጠሩ ችግሮች የየራሱ የሆነ ተጠያቂ አካል ይኖራቸዋል። በተለይ ድርጊቱን በመፈጸም የተሳተፉ አካላት የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ። በዋነኛነት ተጠያቂ የሚሆኑት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እና ዜጎችን በእኩልነት የሚያይ የፖለቲካ ሥርዓት መመስረት ሂደት ላይ እንቅፋት ለመጣል የሚፈልጉ ኃይሎች ናቸው። መንግሥትም ይሄን ከፍ ያለ ትኩረት ሰጥቶ ተጠያቂዎችን ለሕግ ማቅረብ አለበት ብለን ነው የምናምነው። በመግለጫው መንግሥት አለበት ያላችሁትን ክፍተት ስላነሳችሁ ነው ይህንን ጥያቄ ያነሳሁት። አቶ ናትናኤል፦ ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚደረገው ሽግግርና ዜጎችን በእኩልነት የሚያይ የፖለቲካ ሥርዓት እንዳይመሰረት እንቅፋት የሚሆኑት የውጪ ኃይሎች ማለት ከመንግሥት ውጪ ያሉ ኃይሎች ብቻ ሳይሆን፤ በመንግሥት መዋቅር ሥር ውስጥ ሆነውም ግጭቶችን በማባባስ ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የምናደርገውን ጉዞ ለማስተጓጎል ሙከራ እያደረጉ ያሉ ኃይሎች እንዳሉ እናውቃለን። እነዚህ ኃይሎች ደግሞ ከዚህ በፊት ማኅበተሰቡን ሲበድሉ የነበሩና እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ቢመጣ ማኅበረሰቡ ሥልጣን እንደማይሰጣቸው ያረጋገጡ ኃይሎች ናቸው። እነዚህ ኃይሎች የሚያባብሱት ግጭት ራሳቸውን ችግር ውስጥ ከመክተቱ በፊት፣ ራሳቸውን አደጋ ላይ ከመጣሉ በፊት እንዲያቆሙ ነው መልዕክት ያስተላለፍነው። እነዚህ ኃይሎች እነማን ናቸው? አቶ ናትናኤል፦ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ ሰዎችን ጨምሮ ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ኃይሎች ናቸው። በመግለጫው ለግጭት የሚያነሳሱ መልዕክቶች የሚተላለፉባቸው ማኅበራዊ ድረ ገጾችና ሚዲያዎችን የተመለከተ ሀሳብ አንስታችኋል። የለያችኋቸው ሚዲያዎች አሉ? አቶ ናትናኤል፦ በሕግ ሥልጣን የተሰጠው አካል የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ነው የጠየቅነው። ይህ አካል በጠየቀን ጊዜ አሁንም በማስረጃ አስደግፈን የምንሰጥ ይሆናል። ኢዜማ መግለጫ ከማውጣት ባሻገር በተግባር ምን እየሠራ ነው? አቶ ናትናኤል፦ በሚቀጥለው ምርጫ በሰላማዊ መንገድ ተወዳድረን አሸንፈን የመንግሥትን ስልጣን ለመያዝ አደረጃጀታችንን በማስፋትና በማጠናከር ሂደት ላይ ነው የምንገኘው። በየጊዜው በምርጫ ወረዳዎቻችን ባደራጀንባቸው ቦታዎች ላይ የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠን፤ አደረጃጀት በሌለባቸው ቦታዎች ደግሞ ተደራሽነታችንን እያሰፋን እየሄድን ነው። የፖሊሲ አማራጭ የሆኑ ዶክመንቶችን እየቀረጽን ነው የምንገኘው። ከዚህ ባለፈ ግን ከፍተኛ ትኩረት የምንሰጠው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ነው። አባላቶቻችን እና አባላቶቻችን የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ያሉ የማኅበረሰብ አካላትን ከማንኛውም ሰላምና መረጋጋትን ከሚያውክ ተግባር ራሳቸውን እንዲያቅቡና እንዲከላከሉ፤ ማኅበረሰቡንም አስተባብረው እንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ እያስተባበርን፣ እያስተማርን፣ እያደራጀን ነው። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ለማቆየት፣ ኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ ፍላጎት ያላቸው የሙያ ማኅበራት፣ የሀይማኖት ተቋሞች፣ መንግሥት እና ሌሎችም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ ውይይት ማድረግ አለብን ብለን እናስባለን። ያንን ውይይት በቅርቡ አዘጋጅተን የምናደርግ ይሆናል።
xlsum_amharic-train-145
https://www.bbc.com/amharic/50572338
ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ በወረርሽኝ ደረጃ ነው ያለው
በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ ኤችአይቪ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌደራል ኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ለቢቢሲ ገለፀ።
[ "በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ ኤችአይቪ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌደራል ኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ለቢቢሲ ገለፀ።" ]
ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ አፋር፣ ትግራይ፣ አማራና ቤንሻንጎል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ በኤችአይቪ ወረርሽኝ ውስጥ መሆናቸውን የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኑኬሽን ዳይሮክተሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዳንኤል በትረ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቫይሱ በወረርሽኝ ደረጃ የማይገኝባቸው የሶማሌ፣ የኦሮሚያና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች መሆናቸውን ያስረዳሉ። • "እናቴ ኤች አይ ቪ እንዳለብኝ ሳትነግረኝ ሞተች" በዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሕግ መሰረት ይላሉ አቶ ዳንኤል፤ ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከአንድ በመቶ በላይ በበሽታው ከተያዘ እንደ ወረርሽኝ እንደሚቆጠር በመግለጽ እነዚህ ክልሎች ወረርሽኝ ውስጥ መሆናቸውን ይናገራሉ። ነገር ግን ይላሉ አቶ ዳንኤል፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለው የስርጭት መጠን ሲታይ ወረርሽኝ ላይ ነው ማለት እንደማይቻል ያስረዳሉ። በወጣቱ ዘንድ የተዘነጋው ኤችአይቪ የፌደራል ኤች አይቪ መከላከልና መቆጠጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት አክሎም በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ መዘናጋት እንደሚታይ አስታውቋል። በየዓመቱ ከ23 ሺህ በላይ ዜጎች በቫይረሱ ይያዛሉ ያለው ጽህፈት ቤቱ፤ ከ11 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ በኤድስና ተያያዥ በሽታዎች እየሞቱ መሆናቸውን ገልጿል። ይህ ቁጥር ከባለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር እየቀነሰ ነው ያሉት አቶ ዳንኤል፤ ይህ ግን እንደ ሀገር "መዘናጋትና ቸልተኝነትን ፈጥሯል" በዚህ ምክንያት ኤችአይቪ እስከመኖሩም የረሱ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ጨምረው ይናገራሉ። ይህም በተለይ ወጣቶች ላይ በይበልጥ እንደሚስተዋል ተናግረው፤ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ፣ በልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች፣ በአበባ ልማት ላይ፣ በስኳር ፋብሪካ የአገዳ ቆረጣ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች መዘናጋቱ በስፋት ከሚታይባቸው ሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል መሆናቸውንም ይጠቅሳሉ። • እንግሊዛዊው ከኤችአይቪ 'ነጻ' ሆነ መንግሥት ይህንን በማስተዋል ቀደም ሲል ለውጥ ካመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ አደረጃጀቶች፣ የመገናኛ ብዙኀንና ታዋቂ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የተለያዩ ሥራዎችን ለመስራት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። የአገር አቀፍ ኤድስ ምክር ቤት ጉባዔ ባለፉት አምስትና ስድስት ዓመታት ትኩረት ሳይሰጠው መቆየቱን በማንሳትም ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በድጋሚ ማስጀመራቸውን ይናገራሉ። ይህንን ተከትሎም በክልሎች ምክር ቤቱ እንዲጠናከር የማድረግ ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል። የኤች አይ ቪ ስርጭት በአገር አቀፍ ደረጃ ኤች አይ ቪ በአገር አቀፍ ደረጃ የስርጭት መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መሄዱን አቶ ዳንኤል በተር ያስረዳሉ። ይህንንም በቁጥር ሲያስቀምጡ 0.91 አካባቢ ነው በማለት "በአሁኑ ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ በወረርሽኝ ደረጃ ነው" እንደማይባል ተናግረዋል። የኤች አይቪ ስርጭት በክልል ደረጃ ሲታይ ግን ከአገር አቀፉ የስርጭት መጠን ከፍ ያለ የተመዘገበባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ይጠቅሳሉ። የጋምቤላ ክልል 4.8 በመቶ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 3.4፣ የትግራይና የአማራ ክልል በበኩላቸው 1.2 የስርጭት ምጣኔ እንዳላቸው በመጥቀስ ኤች አይ ቪ በወረርሽኝ ደረጃ እንደሚገኝ ገልፀዋል። እንዲሁም የድሬዳዋ፣ የሐረር፣ የአፋርና የቤንሻንጎል ጉሙዝ ክልሎች ኤች አይ ቪ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ያስረዳሉ። ዝቅተኛ የስርጭት ምጣኔ ያለባቸው ክልሎች ደግሞ ሶማሌ (0.01) የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል (0.04) መሆናቸውን ይናገራሉ። እንደ አገር በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል ያለው የስርጭት ምጣኔም እንደሚለያይ በማንሳት በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶች ከፍተኛውን ቁጥር አንደሚይዙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህም 23 በመቶ መሆኑን በማንሳት፤ ባሎቻቸውን በሞት ካጡ ሴቶች መካከልም ያለው የስርጭት ምጣኔ 19 በመቶ መሆኑን ገልፀዋል። በረጅም ርቀት አሽከርካሪዎችና በታራሚዎች በኩል ያለው የስርጭት ምጣኔ በአንጻራዊነት ከአገራዊው አሃዝ ከፍ ብሎ እንደሚታይ አቶ ዳንኤል ጨምረው አስረድተዋል። በአዲስ አበባ ወሲብ የመጀመሪያ እድሜው ዝቅ ማለቱ ይታያል አቶ ታሪኩ ሞላ በአዲስ አበባ የኤች አይ ቪ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የክትትልና ግምገማ ባለሙያ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት በአዲስ አበባ ያለው የኤች አይ ቪ ስርጭት በአገር አቀፍ ከተጠናውና ከተገኘው ውጤት ጋር የተዛመደ ነው። በአገር አቀፍ ደረጃ የኤችአይቪ ስርጭት በከተሞች ከፍ እንደሚል በገጠሩ አካባቢ ደግሞ አነስተኛ መሆኑን ጥናቱ እንደሚያሳይ አስታውሰው፤ ከጋምቤላ ክልል በመቀጠል አዲስ አበባ የኤች አይ ቪ ስርጭት ከፍ ያለበት መሆኑን ይናገራሉ። ጽህፈት ቤታቸው በአዲስ አበባ የኤች አይ ቪ ስርጭት ሁኔታና በከተማዋ ኤች አይ ቪ እንዲስፋፉ ያደረጉ ምክንያቶች ላይ ጥናት ማድረጉንም ይጠቅሳሉ። ይህ ጥናት በአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተሞች ውስጥ ለኤች አይ ቪ መስፋፋት ይበልጥ ምቹ ሁኔታ ያለባቸው አካባቢዎችን የለየ ሲሆን እነዚህም ቡና ቤቶች በስፋት የሚገኙባች፣ ግሮሰሪዎች፣ ፔኒሲዮኖች፣ የእንግዳ ማረፊያ በሚል የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ህንጻዎች፣ ማሳጅ ቤቶች፣ ሆቴሎች፣ ሺሻ ቤቶች፣ የውጪ ቱሪስቶች የሚያዘወትሩባቸው ስፍራዎች መሆናቸውን ባለሙያው ይናገራሉ። እነዚህ ስፍራዎች በአስሩም ክፍለ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎችንና ሰፈሮች ጭምር መለየታቸውን የሚጠቅሱት አቶ ታሪኩ የመከላከል ሥራውም እነዚህ ላይ ያተኮረ ይሆናል ይላሉ። ምንም እንኳ እነዚህ ተቋማት በአስሩም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ቢሆኑም በብዛት ተስፋፍተው የሚገኙባቸው ግን አራዳ፣ አዲስ ከተማ፣ ቦሌና ቂርቆስ ናቸው። ለቫይረሱ መስፋፋት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ባህሪያትን በማንሳትም በከተማዋ ጥንቃቄ የጎደለው የወሲብ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መምጣቱን በጥናቱ ውስጥ መታየቱን ይናገራሉ። ይህም ከትዳር ውጪ እንዲሁም በወሲብ ንግድ ከተሰማሩ ሴቶች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀምን ያካትታል ይላሉ። ኮንዶም አጠቃቀም ላይም በተደረገው ጥናትም፤ የአዲስ አበባ ወጣቶች ኮንዶምን በአግባቡና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ መጠቀም ላይ ያላቸው ልምድ ዝቅተኛ መሆኑን ጥናቱ እንደሚያሳይ ባለሙያው ገልፀዋል። አደንዛዥ ዕፅና አደገኛ ዕጾችን የመጠቀም ሁኔታ በከተማዋ በስፋት ይታያል የሚሉት አቶ ታሪኩ፤ በአዲስ አበባ ወሲብ የሚጀመርበት እድሜ ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ መጥቷል ብለዋል። ቀደም ባሉ ጊዜያት ወሲብ የሚጀመረው በአማካይ በ17 እና 18 እድሜ ላይ አንደነበር በማንሳት፤ በአሁኑ ጊዜ ግን በአስራዎቹ መጀመሪያ ግፋ ሲልም ከአስር ዓመት በታችም ወሲብ ሲጀምሩ ይታያል ብለዋል። ይህም ታዳጊና ወጣት ልጃገረዶች ለኤች አይ ቪ ያላቸውን ተጋላጭነት እንደሚያባብስ ይታመናል ይላሉ። አልፎ አልፎም ድንግልናን የመሸጥ ሁኔታ በከተማዋ እንደሚታይ ገልፀዋል። በከተማዋ ካለው የወሲብ እንቅስቀሴ አንጻር ለትዳር አጋር ታማኝ የመሆን ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱን የአዲስ አበባ ኤች አይ ቪ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት ያደረገው ጥናት እንደሚያሳይ ይናገራሉ። ወጣቶች የወሲብ ጓደኞቻቸውን የመቀያየርም ሆነ የመቀያየር (መለዋወጥ) ባህሪያቶች ተስተውሎባቸዋል በማለት፤ ሰፊ ግንዛቤ በኤች አይ ቪ ላይ ተፈጥሯል ተብሎ በሚታመንበት በዚህ ወቅት አሁንም ለኤች አይ ቪ የተሳሳቱ እምነቶችና አመለካከቶች በስፋት መኖራቸውን በጥናቱ ማግኘታቸውን ይገልፃሉ። ለኤች አይ ቪ ይበልጥ በከተማዋ ከተጋለጡት መካከልም በግንባር ቀደምትነት በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶችና ደንበኞቻቸው፣ የተፋቱና የትዳር አጋሮቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች፣ ወሲብን ለገንዘብና በገንዘብ የሚጠቀሙ ሰዎች፣ የቀን ወይም ተንቀሳቃሽ ሰራተኞች፣ ረዥም ርቀት ተጓዥ መኪና አሽከርካሪዎች፣ አደገኛና አነቃቂ መድሃኒት ተጠቃሚዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችና ሌሎችም ከማህበረሰብ አንጻር በተለየ ሁኔታ ለኤች አይ ቪ ተጋላጭ መሆናቸው ተለይቷል ብለዋል። አማራ ክልል በአማራ ክልል አዲስ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሰዎችም ሆነ በዚህ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን በክልሉ ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ምላሽ ማስፋት እና ማጠናከር የማህበረሰብ ንቅናቄ አስተባባሪ የሆኑት አቶ በቃሉ ዳኜ በተለይ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክልሉ የኤች አይቪ/ኤድስ ስርጭት ጉራማይሌ ነው የሚሉት አስተባባሪው "በአጠቃላይ ህረተሰበቡ ዘንድ ያለው ስርጭት 1.2% ወይንም ከአንድ ሺህ ውስጥ 12ቱ ሰዎች ቫይረሱ ደማቸው ይኖራል ተብሎ ይታሰባል" ብለዋል። • ለመጀመሪያ ጊዜ ከኤች አይቪ በሽተኛ ኩላሊት ተለገሰ በአንዳንድ የክልሉ ከተሞች ያለው የስርጭት መጠን ከፍተኛ ነው በማለትም ከአንድ ሺህ ሰዎች እስከ 41 ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ይኖራል ተብሎ ይታሰባል ሲሉ ያብራራሉ። "የአማራ ክልል የኤች አይቪ ስርጭት ሁኔታ ከአገሪቱ የስርጭት ሁኔታ አንጻር ከ30 በመቶ በላይ ድርሻ ሲሆን አዲስ ከሚያዙት ደግሞ የ29 በመቶውን ድርሻ ይወስዳል። ከኤች አይ ቪ ጋር በተያያዘ ከሚሞቱት ደግሞ 32 በመቶ ደርሻ አለው" ብለዋል። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ የሴቶች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ 66 ከተሞች ከፍተኛ ስርጭት አለባቸው ተብለው የተለዩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ስድስት የሚሆኑት ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ ብለዋል አቶ ዳኜ። ስለኤች አይቪ/ኤድስ ያለው እውቀት ማነስ፣ አድሎ እና ማግለል፣ መከላከል ላይ የሚደረገው ሥራ መቀዛቅ እና የአመራር ቁርጠኝነት መቀነስ "ተመልሶ እንዳያገረሽ ዋስትና የሚሰጥ አይደለም" ሲሉ ገልጸዋል። ኦሮሚያ በኦሮሚያ ክልል ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ 178 ሺህ ሰዎች (0.67 በመቶ) ቫይረሱ በደማቸው እንደሚገኝ በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረገ ጥናት መረጋገጡን ለቢቢሲ የተናገሩት የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ነጋሽ ስሜ ናቸው። በኦሮሚያ ክልል የስርጭት መጠኑ ከገጠር ይልቅ በከተማ እንደሚሰፋ ገልፀው፤ ይህም በከተሞች ያለውን የስርጭት ምጣኔ 3 በመቶ እንደሚያደርሰው በማንሳት ቁጥሩ ቀላል የሚባል አለመሆኑን ያስረዳሉ። በኦሮሚያ ከተሞች የሚገኙ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶች፣ ሺሻና መጠጥ ቤት የሚሰሩ ሴቶች፣ የረዥም ርቀት መኪና አሽከርካሪዎች ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውንም ይናገራሉ። • አለማችን የኩፍኝ ወረርሽኝ እንደሚያሰጋት አለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ በክልሉ እድሜያቸው ከ15 እስከ 24 ያሉ ወጣቶች ለኤች ኤይ ቪ ተጋላጭነታቸው በስፋት ይታያል ያሉት አቶ ነጋሽ፤ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው ጥናት በኦሮሚያ የሚገኙ 76 ከተሞች የኤች አይ ቪ ስርጭት በብዛት የሚታይባቸው መሆናቸውን ይናገራሉ። ከእነዚህ 76 ከተሞች መካከልም በቀዳሚነት አዳማ፣ ሞጆ፣ አሰላ፣ ሻሸመኔ፣ ነቀምቴ፣ ጂማ፣ ባሌ ጎባ እና ሻኪሶ ይገኙባቸዋል ብለዋል። ፌስቡክን ኤች አይቪ ለመከላከል የፌደራል ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ዳንኤል በአገር አቀፍ ደረጃ ስርጭቱን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶ ካልተሰራ ከፍ ሊል የሚችልበት እድል መኖሩን ይናገራሉ። "መዘናጋቱን መቀልበስ ካልተቻለ እንደ አገር ከባድ ዋጋ ያስከፍለናል" በማለትም ይህ ደግሞ ከሚያሳድረው የሥነ ልቦና፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ተጽዕኖም አለው ብለዋል። አቶ ዳንኤል ባለፈው ዓመት እንኳ ቢታይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የስርጭት ምጣኔው 1.18 ነበር ብለው ከዓመት ወዲህ በተሰራው ሥራ መቀነስ መታየቱን በማንሳት "እንደ አገር ስጋቱን የመቀልበስ አቅም ላይ ነው ያለነው" ይላሉ። • ሲሽልስ፡ የሔሮይን ወረርሽኝ የሚያመሳቅላት ምድረ ገነት በመላ አገሪቱ ለወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ለመስራት ዘመኑ የሚጠይቀውን የተግባቦት ዘዴ መጠቀም እንደሚያስፈልግ የሚናገሩት አቶ ዳንኤል፤ ለዚህም ጽህፈት ቤታቸው ማህበራዊ መገናኛ ብዙኀንን ለመጠቀም ማቀዱን ይናገራሉ። ሬዲዮ፣ ጋዜጣና ቴሌቪዥን ዳግም የመጠቀም ፍላጎት መኖሩን አንስተው፣ ነገር ግን ወጣቶችን ለማግኘት የሚረዱ የመገናኛ ብዙኀን አይነቶችን ቅድሚያ እንደሚሰጡ ተናግረዋል። ኤች አይ ቪ በደማቸው ያያለ ግለሰቦች፣ ማህበራት፣ ጥምረቶች አሁንም መኖራቸውን በማንሳትም ከእነርሱ ጋር የሚሰሩ ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስታውሰዋል።
xlsum_amharic-train-146
https://www.bbc.com/amharic/news-48373470
"ማሰብን የሚፈራ ትውልድ ፈጥረናል"- ቢንያንቫንጋ ዋይናይና
"በህይወቴ መኖር የምፈልገው ነፃ በሆነ ምናብ(ሃሳብ) በመመላለስ ነው። በአህጉሪቷ ካሉ ሰዎች ጋር አዳዲስና፤ ሳይንሳዊ የሚያስደስቱ ስራዎችን መስራት እፈልጋለሁ፤ማሰብን የሚፈሩ ትውልድን ፈጥረናል፤ አዲሱ ትውልድ የራሱን ታሪክ የሚፅፍበት፤ አፍሪካውያን የራሳቸውን ሃሳብ የሚያሰርፁበት አህጉርን ማየት እፈልጋለሁ። በተለይም መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ለደሃው የትኛውንም ፖሊሲን የሚቀርፁት እነሱ ናቸው፤ ሃሳብንም ሆነ ፈጠራን የሚገድሉት እነሱ ናቸው"
[ "\"በህይወቴ መኖር የምፈልገው ነፃ በሆነ ምናብ(ሃሳብ) በመመላለስ ነው። በአህጉሪቷ ካሉ ሰዎች ጋር አዳዲስና፤ ሳይንሳዊ የሚያስደስቱ ስራዎችን መስራት እፈልጋለሁ፤ማሰብን የሚፈሩ ትውልድን ፈጥረናል፤ አዲሱ ትውልድ የራሱን ታሪክ የሚፅፍበት፤ አፍሪካውያን የራሳቸውን ሃሳብ የሚያሰርፁበት አህጉርን ማየት እፈልጋለሁ። በተለይም መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ለደሃው የትኛውንም ፖሊሲን የሚቀርፁት እነሱ ናቸው፤ ሃሳብንም ሆነ ፈጠራን የሚገድሉት እነሱ ናቸው\"" ]
ይህ የተወሰደው በትናንትናው ዕለት ህይወቱ ያለፈው ኬንያዊው ፀሀፊ ቢንያቫንጋ ዋይናይና 'ነፃ እሳቤ' ከሚለው ንግግሩ ነው። •"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ •"ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ በአፍሪካ ስነ-ፅሁፍ ዘርፍ ከፍተኛ ስፍራ የነበረው ቢንያቫንጋ በቋንቋው ውበት፣ በጠንካራ አቋሙ፣ በድፍረቱና አፍሪካንና ህዝቦቿን ማእከል ባደረገ ፅሁፎቹ ይታወቃል። ከነዚህም ፅሁፎቹ መካከል 'ዋን ደይ አይ ዊል ራይት አባውት ዚስ ፕሌስ'፣ 'ሃው ቱ ራይት አባውት አፍሪካ' ይገኙበታል። የምዕራቡ አለም ከአንድ ቢሊዮን በላይ ህዝቦች በላይ የሚኖሩባትን አህጉር በተለይም በፀሃፍያን ዘንድ የምትመሰልበትን መንገድ ሽሙጣዊ በሆነ መልኩ በፃፈበት "ሃው ቱ ራይት አባውት አፍሪካ (ስለ አፍሪካ እንዴት መፃፍ እንችላለን) በሚለው ፅሁፉ ቢንያቫንጋ ዋይናይና "የመፅሃፋችሁን ሽፋን በየቀኑ የምናገኛቸውን አፍሪካውያንን ፎቶ ሳይሆን ኤኬ 47 ጠመንጃን የተሸከመ፤ የሽምቅ ውጊያ የተራቆቱ ጡቶች፤ የገጠጡ አጥንቶችን አድርጉ" በማለት ምዕራባውያን ስለ አፍሪካ ሲፅፉ በተደጋጋሚ የሚያወጧቸውን ፎቶዎች በማየት በነገር ሸንቆጥ አድርጓቸዋል። •ሙዚቃ ሳይሰሙ መወዛዋዝ ይችላሉ? ከምዕራባውያን በተጨማሪ መካከለኛ ገቢ ያላቸውን አፍሪካውያን በመተቸት የሚታወቀው ቢንያቫንጋ "አፍሪካን ወደ አውሮፓ መቀየር ይፈልጋሉ፤ የልማት ሞዴላቸው አውሮፓን ሙሉ በሙሉ መኮረጅ ነው፤ ለራሳችን ችግሮች ሀሳብ፣ ፈጠራን ማስተማር አቅቶናል። እንዴት የአፍሪካን ልማት እናመጣለን' " ሀሳብን ነፃ በማድረግ፤ አህጉሪቷን እንዴት እንድትቀየር እንፈልጋለን፤ ህይወታችንስ? በራሳችን መንገድ ልናስብ ይገባል። እስካሁን የተማርናቸው ነገሮች ለአፍሪካ ምን አመጡላት? እንደገና ልናየው አይገባም?" በማለት ይጠይቃል። በዚህ ሀሳቡም ከታዋቂው ምሁር ፍራንዝ ፋኖን ጋር ይመሳሰላል፤ ፍራንዝ ፋኖን እንደሚለው የአውሮፓ የስልጣኔ እሴቶች መሰረታቸው ቅኝ ግዛት፣ ባርነት፣ ብዝበዛ ነው፤ አዲስ የሆነ የልማት ሀሳብ ሊኖራት ይገባል። በአርባ ስምንት አመቱ ህይወቱ ያለፈው ቢንያንጋ ተቃውሞን የማይሸሽ፤ ብቻውን መቆም የማይፈራ ግለሰብ ነበር። ፖለቲካውን በግል ህይወቱ እስከ መጨረሻው ድረስ የኖረ፤ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ወንጀል በሆነባት ኬንያ፣ ስለ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የፃፈ፤ እንዲሁም በተደጋጋሚ ድፍረት የተሞላባቸውን ንግግሮች ያደርግ የነበረ ነው። •"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ ፀጉሩን ደማቅ ቀለብ ቀብቶ፣ ቀሚስ ለብሶ በአደባባይ ይታይ ነበር። ለምግብ ማብሰል ከፍተኛ ፍቅር የነበረው ቢንያቫንጋ ዋይናይና የቅብ ጓደኞቹ 'አብዛኛውን ጊዜ' ቅመም ቅመም ይሸታል ይሉታል። የተለየ እሳቤን ለአፍሪካ በተለያየ ፅሁፎች ለማምጣት ከፍተኛ አላማ የነበረው ቢንያቫንጋ ክዋኒ የተባለ የፀሀፊዎች ስብስብን በመመስረት አፍሪካን ማዕከል ያደረጉ፤ የቅኝ ግዛት እሳቤን የጣሱ ፅሁፎን ማሳተም ችሏል። ቢንያቫንጋ በ2002 የኬን ተሸላሚ የነበረ ሲሆን በ2014 ደግሞ ታይም መፅሔት ከዓለማችን 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከል አንዱአድርጎ አካትቶት ነበር።
xlsum_amharic-train-147
https://www.bbc.com/amharic/news-46631471
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኩረጃን ለመከላከል የተጣለው የስም ለውጥ እግድ ተነሳ
ኩረጃ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ሥርዓቱን የሚፈታተን ማነቆ ሆኗል። ከቴክኖሎጂ መርቀቅ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ኩረጃዎችን ለማስቀረትም በብሔራዊ ፈተና ወቅት የበይነ መረብ አገልግሎት እንዲቋረጥ የተደረገበት ጊዜም ሩቅ አይደለም። ይህ ብቻም ሳይሆን የፈተና ወረቀቶች እንደገና የተፃፉበትና የተዘጋጁበት ጊዜም አይዘነጋም።
[ "ኩረጃ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ሥርዓቱን የሚፈታተን ማነቆ ሆኗል። ከቴክኖሎጂ መርቀቅ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ኩረጃዎችን ለማስቀረትም በብሔራዊ ፈተና ወቅት የበይነ መረብ አገልግሎት እንዲቋረጥ የተደረገበት ጊዜም ሩቅ አይደለም። ይህ ብቻም ሳይሆን የፈተና ወረቀቶች እንደገና የተፃፉበትና የተዘጋጁበት ጊዜም አይዘነጋም።" ]
• መረጋጋት ያልቻሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት • ትምህርት ዕድሜን እንደሚያስረዝም በጥናት ተረጋገጠ ከሰሞኑ ከወደ አማራ ክልል የተሰማው የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል። በባለፈው የትምህርት ዘመን ከናሙና ዞኖችና ትምህርት ቤቶች በተገኘ መረጃ ተማሪዎች ለኩረጃ ይመቻቸው ዘንድ ከጎበዝ ተማሪዎች ጋር በማመሳሰል ስማቸውን በፍርድ ቤት አስለውጠዋል። በተያዘው የትምህርት ዘመንም ተመሳሳይ ችግር እንዳይገጥም የክልሉ ትምህርት ቢሮ የቀየሰው አንዱ ዘዴ ተማሪዎቹ ስማቸውን እንዳይለውጡ እግድ ማስጣል ነበር። በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዓለምእሸት ምህረቴ አንዳንድ ተፈታኞች ለኩረጃ ሲሉ ስማቸውን ከጎበዝ ተማሪዎች የስም ፊደል ጋር እያመሳሳሉ በፍርድ ቤት እየቀየሩ እንደሆነ ጠቅሰው ይህን በተመለከተ ትምህርት ቢሮው ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ደብዳቤ መፃፉንም አውስተዋል። ደብዳቤው ድርጊቱ ላልተገባ ዓላማ እየዋለና በጎበዝ ተማሪዎች ሥነ ልቦና ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን ጠቅሶ ፈተናዎቹ ከኩረጃ የፀዱ ይሆኑ ዘንድ የፈተናው ምዝገባ እስኪጠናቀቅ ስም መቀየር የሚከለክል የሕግ አሠራር ተግባራዊ እንዲደረግ ይጠይቃል። ከደብዳቤውም ጋር በ2010 ዓ.ም ከተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተሰበሰቡና ከጎበዝ ተማሪዎች ስም ጋር የተመሳከሩ 1550 ተማሪዎችን ስም ዝርዝር ያለበት 37 ገፅ አያይዟል። ይሄንን መነሻ በማድረግ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጊዜያዊ መፍትሄ ይሆናል በማለት በክልሉ ለሚገኙ 13 ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ጊዜያዊ የስም ለውጥ የሚከለክል እግድ እንደፃፈ ይናገራሉ። እነዚህ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችም በሥራቸው ለሚገኙ ወረዳ ፍርድ ቤቶች ተመሳሳይ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። የተጠቀሰውን ችግር ለመፍታት ሲባልም ፍርድ ቤት የስም ለውጥ እግዱ የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል የፈተና ምዝገባ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ እንዲቆይ የሚያዝ ነው። "ፍርድ ቤቱ ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፈው ዜጎች በፈለጉት ስም የመጠራት መብታቸውን ለመገደብ ተፈልጎ ሳይሆን በክልሉ የገጠመውን የፈተና ሥርዓት ተግዳሮት ለማቃለል ነው" ይላሉ አቶ ዓለምእሸት። • በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግዕዝና ኦሮምኛ ቋንቋዎች ጥናት ፍላጎት ጨምሯል • "ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆኑት አቶ ተፈራ ፈይሳ ቢሮው የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ የሚያከናውናቸው በርካታ ተግባራት ቢኖሩም እግዱ የስም ለውጥ በማድረግ የሚደረግን ኩረጃ ለመቀነስ የተጠቀሙት አማራጭ እንደሆነ ይናገራሉ። ላለፉት 5 ዓመታት የሚጠቀሙበት የትምህርት ክትትል ሥርዓት እንዳላቸው የሚናገሩት ኃላፊው በክልሉ ኩረጃ ያን ያህል ሰፊ ባይሆንም ተማሪዎች በራሳቸው ተማምነው እንዲሰሩ ለማድረግና ችግሩን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ይህንን እግድ ጨምሮ ሌሎች መፍትሔዎችን እየወሰዱ እንደሚገኙ ይገልፃሉ። "ጉዳዩ በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎችን የማይወክል ቢሆንም በራሳቸው የማይተማመኑ ተማሪዎች የጎበዝ ተማሪዎችን ስም እየፈለጉ ስም የሚቀይሩ ግን አሉ፤ በመሆኑም ኩረጃ በትምህርት ጥራት ላይ እንቅፋት በመሆኑ እንደ አንድ ወሳኝ መፍትሔ ባይሆንም ችግሩን ለመፍታት በማሰብ ይህን አማራጭ ተጠቅመናል" ይላሉ። ተማሪዎቹ ለኩረጃ ሲሉ ስማቸውን ስለመቀየራቸው ማረጋገጫ ከየት አገኛችሁ ያልናቸው ኃላፊው በየዓመቱ ትምህርት ቢሮው ግምግማ እንደሚያካሂድ ጠቅሰው በዚህም መሠረት ቁጥራቸውን ለጊዜው በውል ባያስታውሱትም የተወሰኑ ተማሪዎች ለኩረጃ ሲሉ ስማቸውን እንደሚለውጡ ከደረሳቸው መረጃ ተረድተዋል። አቶ ተፈራ እንደሚሉት በተለይ ምዝገባ በሚካሄድባቸው ወቅት የስም ለውጦች ተበራክተው ይታያሉ፤ በመሆኑም ይህንን ለመከላከል ለ3 ወራት የሚዘልቅ (ከህዳር - የካቲት) የስም ለውጥ እግድ ለማድረግ ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጋር እንደተስማሙ ያስረዳሉ። "ትምህርት ቢሮው ይህንን መፍትሄ ትክክለኛ መፍትሄ ነው ብሎ ባያምንም ለትልቁ መፍትሄ አጋዥ ይሆናል" ይላሉ አቶ ተፈራ። ይህም ግለሰቦች በፈለጉት ስም የመጠራት መብት ለመጣስ ሳይሆን ችግሩን ለመፍታት በሚል ከፍርድ ቤቱ ጋር በተደረገ ቀና ስምምነት እንደሆነ ያሰመሩበት ጉዳይ ነው። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ • "በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው" የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ በበኩላቸው ምንም እንኳን በቅንነት ታስቦ በጊዜያዊ መልክ እግድ የተጣለ ቢሆንም እግዱ የስም ለውጥ መብትን ይጥሳል በሚል ከሕግ ባለሙያዎችና ሚዲያዎች ትችት እንደተሰነዘረባቸው ይናገራሉ። እንደ አንድ የፍትህ መሥሪያ ቤት፤ ከሌላ አካል ቅሬታና አስተያየት እስከሚመጣ ለምን ጠበቃችሁ? ቀድሞስ ጉዳዩን እንዴት አላሰባችሁበትም? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላቸው ዳይሬክተሩ "ያለውን ጊዜያዊና መሰረታዊ ችግር መነሻ በማድረግ ታስቦ የተፃፈ ሲሆን ይህም ስህተት ሆኖ ተገኝቷል" ይላሉ። "ቢሮው ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት እንጂ መታገዱ ችግሩን በዘላቂነት ሊፈታው አይችልም፤ በሕግ የተረጋገጠ የግለሰብ መብት በጊዜያዊም ቢሆን የሚገድብ በመሆኑ እንዲሁም በአስተዳደር የሚሰጥ ትዕዛዝ ለሌላ ያልተገባ ልምድ ሊሆን ይችላል በማለት ደብዳቤው ስህተት መሆኑን ፍርድ ቤቱ አምኗል" ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። በመሆኑም በትናንትናው ዕለት የእግዱ የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ የመስሪያ ቤቶቹን ተዋረድ በጠበቀ መልኩ እግዱን የሚሽር ደብዳቤ ማሰራጨታቸውን ነግረውናል። ይሁን እንጂ የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊውን ባነጋገርናቸው ወቅት እግዱ እንዲነሳ የሚጠይቀው ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው ነግረውናል። ሕጉ ምን ይላል ? የሕግ ባለሙያው አዲ ደቀቦ፤ ስም ማውጣት መብት ያለው ማነው? ስምን ለማስለወጥ የሚያስፈልጉ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? የሚሉና ከስም ጋር ተያይዘው የሚነሱ እሰጥ አገባዎችን በሚመለከት በፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 43 እንደተቀመጠ ይገልፃሉ። ሕጉን ጠቅሰው ባለሙያው እንደሚናገሩት መጠሪያ ስምን በተመለከተ የተቀመጠው ድንጋጌ ስም አስለዋጩ ግለሰብ ምክንያቱን ለፍርድ ቤት ሲያስረዳ ጥያቄው የሚስተናገድበት አግባብ ሲኖር በምን ምክንያቶች ጥያቄው ላይስተናገዱ የሚችሉበት ምንም የተቀመጠ መስፈርት የለም። በመሆኑም የስም ለውጥ በፍትሐብሔር ሕግ ላይ የተቀመጡ መብቶች ስለሆነ በሕጉ ላይ የተቀመጡ ድንጋጌዎች ሊቀየሩ የሚችሉት በተመሳሳይ ሥልጣን ባላቸው አዋጆች ብቻ መሆኑንም ባለሙያው ያስረዳሉ። "መጥፎ ተግባርን ለመከላከል ሲባል ቢሆንም እንኳን የተቀመጠን ሕግ መጣስ የለበትም" የሚሉት ባለሙያው ይህንን ተላልፈው እግድ የሚጥሉ ካሉ የክልከላ ድንጋጌ እየሰሩ እንደሆነ ይቆጠራል። ነገር ግን የስም ለውጡ ችግር ከሆነባቸው ሥልጣን ላለው አካል ጥያቄያቸውን በማቅረብ ሕጉ እንዲሻሻል ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችሉ የሕግ ባለሙያው ጠቁመዋል።
xlsum_amharic-train-148
https://www.bbc.com/amharic/news-49270155
ሶማሌ ክልል፡ የ'ጄል' ኦጋዴን የሰቆቃ ታሪኮች
'ጄል' ኦጋዴን ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ነው የሚገኘው። ለጥ ባለ ሜዳ ላይ ሰፊ ቦታን የያዘው የቀድሞ እስር ቤት ከብሎኬት በተገነባ ረዥም እና አናቱ ላይ አደገኛ ሽቦ ባለው አጥር ተከልሏል።
[ "'ጄል' ኦጋዴን ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ነው የሚገኘው። ለጥ ባለ ሜዳ ላይ ሰፊ ቦታን የያዘው የቀድሞ እስር ቤት ከብሎኬት በተገነባ ረዥም እና አናቱ ላይ አደገኛ ሽቦ ባለው አጥር ተከልሏል።" ]
አሁንም ድረስ መግቢያው በር ላይ "የጅግጅጋ ከተማ ማረሚያ ቤት" ተብሎ ይጻፍበት እንጂ ይፈጸምበት በነበረው ሰቆቃ ስሙ የገነነው እስር ቤት "ጄል ኦጋዴን" በሚል ስያሜው ነው የሚታወቀው። የቀድሞ አስተዳደር እስር ቤቱ "ጄል ኦጋዴን" ተብሎ እንዳይጠራ ብዙ ጥረቶችን ስለማድረጉ ሰምተናል። የክልሉ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽነር የሆኑት በሽር አህመድ፤ ጄል ኦጋዴን ተለይቶ ይታወቅ እንጂ ስቃይ ይፈጸምባቸው የነበሩ ሌሎች ስፍራዎች እንደነበሩ ነግረውናል። ወደ ውስጥ ተዘልቆ ሲገባ፤ በሰፊው ግቢ ውስጥ በርካታ በቅርብ ርቀት ከብሎኬት የተገነቡ ቤቶች ይታያሉ። በግቢ ውስጥ ሌላ ግቢ አለ። እንደገና በሌላኛው ግቢ ውስጥ ሌላ ግቢ ይገኛል። • አቶ አብዲ ስለተናገሩት ጉዳይ እንደማያውቅ ኢህአዴግ ገለፀ •"ከሞቱት አንለይም" የሶማሌ ክልል እስረኞች ከዚህ ቀደም በጄል ኦጋዴን ታስረው የነበሩ ሰዎች ሲናገሩ፤ እነዚህ የተለያዩ ግቢዎች ታሳሪዎች እንደየ ደረጃቸው ስቃይን የሚቀበሉባቸው ስፍራዎች እንደሆኑ ይናገራሉ። እስር ቤቶቹ በቁጥር ነው የሚለዩት። 7ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ . . . እየተባሉ። ከእነዚህ መካከል 8ኛ ተብሎ የሚጠረው እስር ቤት ጨለማ ክፍሎች የሚገኙበት ሲሆን፤ በሽብር ወንጀል ወይም የኦብነግ አባል ወይም ድጋፍ ሰጪ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበት ቤት ነው። 8ኛ ተብሎ የሚጠራው ቤት ወደ በአግድም ረዘም ያለ ሲሆን፤ አራት በሮች አሉት። በእያንዳንዱ በር ዘልቀው ወደ ውስጥ ሲገባ አስር ክፍሎች ይገኛሉ። ክፍሎቹ ሙሉ በሙሉ በድቅድቅ ጨለማ የተዋጡ ናቸው። የእያንዳንዱ ክፍል ስፋት ከ10 ካሬ የሚበልጥ አይደለም። በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ የሰቃይ ገፈትን ከቀመሱት መካከል አንዱ አሊ ሃሰን ነው። አሊ ሃሰን አሊ ሃሰን አሊ ጄል ኦጋዴን ውስጥ ከመታሰሩ በፊት፤ የእስር ቤቱ የጥበቃ ክፍል አባል በመሆን ለ17 ዓመታት ሰርቷል። "ለሊት የጥበቃ ሥራ ላይ ሳለሁ፤ አለቃዬ 'ና እስረኞቹን ቀጥቅጥ አለኝ' እኔ አልቀጠቅጥም ብዬ ተመለስኩ። ሌላ ጊዜም ቀጥቅጥ ሲለኝ እምቢ አልኩት። ከዚያ ኮሚሽነሩ ሲሰማ 'አንተ ከኦብነግ ጋር ግንኙነት አለህ' አለኝ እና ታሰርኩ" በማለት ከእስር ቤቱ ጠባቂነት እንዴት እስረኛ እንደሆነ ይናገራል። አሊ ለ20 ወራት 8ኛ ቤት በሚባለው እስር ቤት ውስጥ ጨለማ ክፍል ውስጥ መታሰሩን፣ ጉድጓድ ውስጥ ከእባብ ጋር ብዙ ጊዜ ማደሩን፣ ድበደባ እና በርካታ ስቃይ እንደደረሰበት ይናገራል። "30 ሆነን እዚህ ክፍል ውስጥ እንታሰር ነበር። ክፍሉ ጠባብ ስለሆነ እንደ ውሻ ተደራርበን ነበር የምንተኛው። ተኝተን እንዳናድር አንዳንዴ ክፍሉን በውሃ ይሞሉታል" ይላል አሊ ሃሰን። • የሶማሊያ ባለስልጣናት ከአልሸባብ ጋር በተያያዘ የጎሳ መሪዎችን አስጠነቀቁ የእስር ቤቶቹ በሮች ከላሜራ የተሰሩ ሲሆን በወለሉ እና በበሩ መካከል ክፍታት እንዳይኖር በሲሚንቶ ተደፍኗል። አሊ እንደሚለው ከሆነ ይህ የሚደረግበት ምክንያት አየር እና ብርሃን ወደ ውስጥ እንዳይገባ እንዲሁም ወደ ክፍሉ በላስቲክ ቱቦ እንዲፈስ የሚደረገው ውሃ ከክፍሉ እንዳይወጣ ለማድረግ ነው። "ክፍሉ ውሃ ብቻ ይሆናል። ውሃ ላይ እንዴት ይተኛል?" በማለት የሚጠይቀው አሊ፤ "ውሃ ላይ መተኛት ስለማንችል ግንባራችንን ግድግዳው ላይ በመለጠፍ ተደግፈን ነው የምናድረው" ይላል። አሊ ደርሶብኛል የሚለው ስቃይ ይህ ብቻ አይደለም። "ኑ ቤቴን ላሳያችሁ" ብሎ ከፊት ሆኖ እየመራን ወደ ሌላኛው ግቢ ይዞን ሄደ። አሊ "ቤቴ" ብሎ የጠራው ለሽንት ቤት ፍሳሽ ማጠራቀሚያነት ታስቦ የተሰራን ጉድጓድ ነው። አሊ በዚህ ጉድጓድ ውስጥ ከእባብ ጋር አብሮ እንደታሰረ ይናገራል። "እዚህ ውስጥ ያስገቡንና ይዘጉብናል። ከዚህ ጉድጓድ ውስጥ ስወጣ ደግሞ ምንም አይታየኝም" በማለት ይናገራል። አሊ በዚህ ጉድጓድ ውስጥ በስም ከሚጠቅሰው ጋዜጠኛ ጋር መታሰሩን ያስረዳል። ይህ ብቻም አይደለም። በጄይል ኦጋዴን ግቢ ውሰጥ የውሻ ቤት የሚያክሉ ሁለት በሽቦ የተሰሩ ቤቶች አሉ። በአንዷ ውስጥ አነር፤ በሌላኛው ቤት ውስጥ ደግሞ ጅብ ይዘው እንደነበር የጄይል ኦጋዴን ጥበቆች ነግረውናል። በእነዚህ የውሻ ቤት በሚያክሉ ቤቶች ውስጥ ሰዎች ከጅብ እና ከአነር ጋር ይታሰሩ እንደነበር አሊ ነግሮናል። ምንም እንኳ አሊ በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ ባይታሰርም፤ የእስር ቤቱ ጥበቃ ሳለ ሰዎች ከአውሬዎቹ ጋር ሲታሰሩ ማየቱን ነግሮናል። "ጅቡም ሰውዬውም ተፈራርተው ጥቅልል ብለው ጥግ ጥግ ይዘው ይቀመጣሉ" ሲል አሊ ያስታውሳል። አክሎም "ነብሩም (አነር ነው) ይፈራል። ግን አንዳንዴ በኃይል በጥፍሩ ይቧጭራቸዋል።" መርማሪዎቹ ይህን ሁሉ ስቃይ በታሳሪዎች ላይ የሚያደርሱት መረጃ ለማወጣጣት እንደሆነ አሊ ይናገራል። "ተናገር ይሉኛል። እኔ ግን ምንም አላውቅም። በጣም ስሰቃይ ዝም ብዬ የሰዎችን ስም እጠራለሁ። ከዚያ ሰዎቹ ተይዘው ሲመጡ ደግሞ ምንም የለም" ይላል አሊ። መሪየም አብዱል መሪየም አብዱል ሌላዋ የዚህ ገፈት ቀማሽ የስድስት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ መሪየም አብዱል ናቸው። ወ/ሮ መሪየም "ኦብነግ ነሽ ተብዬ በጄይል ኦጋዴን እና በቃሊቲ በጠቅላለው 10 ዓመት ከ8 ወር ታስሪያለሁ" ይላሉ። ወ/ሮ መሪየም በጄይል ኦጋዴን የደረሰባቸወን ስቃይ ሲያስቡ እምባ ይቀድማቸዋል። "ቀን እና ማታ ደብድበውኝ አሁን በዳይፐር ነው ያለሁት" ይላሉ። ወ/ሮ መሪየም በደረሰባቸው ድበዳባ እና ህክምና ማጣት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ሽንታውን መቆጣጠር ስለማይችሉ ሁል ጊዜም ዳይፐር ለመጠቀም እንደሚገደዱ ይናገራሉ። ወ/ሮ መሪየም በእርሳቸው ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ታሳሪዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ በደል ይፈጸም እንደነበር ይመሰክራሉ። "ከአንድ የእሰረኛ ክፍል ወደ ሌላኛው ለመውሰድ አንድ እጅ እና አንድ እግርን በካቴና ያስሩ ነበር። እሰቲ አስቡት አንድ እጅ እና አንድ እግር በካቴና ታስሮ መራምድ እንዴት ይቻላል?" በሴት እስረኞች ላይም ይፈጸሙ የነበሩ የጾታ ትንኮሳዎች እጅግ አስከፊ እንደነበሩ ይናገራሉ። "ለሊት ላይ እየመጡ ቆንጆ ናቸው የሚሏቸውንና ትንሽ ዕድሜ ያላቸውን ብቻ እየመረጡ 'ነይ ለኮሚሽነር ሻይ አፍይ' ይላሉ። ለምን ሌሎቹን አሮጊት አይወስዱም?" ሲሉ ይጠይቃሉ። በጄይል ኦጋዴን ህጻናት ልጆች ከእናቶቻቸው ጋር ይታሰሩ እንደነበር፤ ለአንድ እስረኛ ከበቆሎ ዱቄት የሚሰራ አንድ ቂጣ እና አንድ ብርጭቆ ሻይ ብቻ በቀን እንደሚሰጥም ያስታውሳሉ። • መንግሥት ልዩ ፖሊስን እንዲበትን አምነስቲ ጠየቀ "የሚሰጠው አንድ ቂጣ እና አንድ ብርጭቆ ሻይ ነው። እሱን እናት ትብላ ወይስ ልጅ ይብላ?" የሚሉት ወ/ሮ መሪያም ከእርሳቸው ጋር በእስር ላይ የነበሩ እናቶች እነርሱ ለቀናት ምንም ሳይመገቡ የሚሰጣቸውን ሻይ እና ቂጣ ልጆቻቸውን ይመግቡ እንደነበር ይናገራሉ። መርማሪዎች ለሚጠይቁት ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ ለማግኘት ሲሉ በባልዲ ከሽንት ቤት የሰገራ እና የሽንት ቅልቅል እየተቀዳ በአናታቸው ላይ ያፈሱባቸው እንደነበረ እንዲሁም አስረው ለሰዓታት ፀሐይ ላይ እንዲቆዩ ይደረግ እንደነበርም ወ/ሮ መሪየም እየተንገሸገሹ ነግረውናል። አሁንም ድረስ በባልዲ ተቀድቶ እና ደርቆ የሚገኝ የሽንት ቤት ፍሳሽ በቦታው ላይ ይገኛል። የቤተሰብ ሰቆቃ የጄል ኦጋዴን ሰቆቃ ለታሳሪው ብቻ ሳይሆን ለቤተሰብም ይተርፋል። በሰቆቃ በሚታወቀው በዚህ እስር ቤት የሚፈጸሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በህብረተሰቡ ዘንድ በስፋት ይታወቃሉ። ወዳጅ ዘመዱ በጄል ኦጋዴን የሚገኘበት ሰው ለደቂቃ እረፍት እንደሌለው አይሻ አህመድ ምስክር ናት። የአይሻ አህመድ ባለቤት የመንግሥት ሰራተኛ ነበር። አይሻ በማታውቀው ምክንያት ባሏ ከሥራ ቦታው ተይዞ በጄይል ኦጋዴን ታሰረ። የአምስት ልጆች እናት የሆነችው አይሻ፤ ባለቤቷን ማየት ባትችልም እሱን ብላ በየቀኑ ወደ እስር ቤቱ ምግብ እየቋጠረች ትሄድ ነበር። ሃሰን ፋራህ ባለፉት አስር ዓመታት በጄይል ኦጋዴን እና ጎዴ በሚገኙ እስር ቤቶች ውስጥ በጥበቃነት አግልግሏል። እርሱ እንደሚለው በጄይል ኦጋዴን ቤተሰብ ታሳሪዎችን እንዲጠይቁ አይፈቀድላቸውም። • ልዩ ፖሊስን ማን መሰረተው? አይሻም ባለቤቷን አንድም ቀን በአይኗ ባታየውም ለወራት በየቀኑ ምግብ አመላልሳለች። ይሁን እንጂ ባለቤቷ የሞተው ገና እስር ቤት እንደገባ በቀናት ልዩነት ውስጥ ነበር። ከጄል ኦጋዴን የተለቀቀ እስረኛ ነበር ባሏ እንደሞተ ለአይሻ ያረዳት። ባሏ በምን ምክንያት እንደሞተ፣ መቼ እንደሞተና አስእከሬኑ የት እንዳለ እንኳን እንደማታውቅ ትናገራለች። የእስር ቤቱ ጠባቂ የነበረው ሃሰን ፋራህ "እስረኛ እዚህ ታሞ ከሞተ፤ ታሟል ተብሎ አስክሬኑ ከግቢ ውጪ ወዳለ ህክምና ቦታ ይላካል፤ ከዚያ እዚያው ይቀበራል። ለቤተሰብ ግን አይነገርም። ከዚህ ተፈተው የሚወጡ ሰዎች ናቸው ለቤተሰብ ሄደው እከሌ ሞቷል ብለው የሚናገሩት" ይላል። ቤተሰብ ፍለጋ ምንም አማራጭ እንደሌለው የሚናገረው ሃሰን፤ "በተሰብ ሰው ጠፋብኝ ብሎ ቢመጣ ማን ያስገባዋል?" ሲል ይጠይቃል። ሃሰን እንደሚለው ከሆነ በእስረኞች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በመቃወሙ እርሱም ለእስር ተዳርጎ ነበር። ሐሰን ፋራህ ፍትህ የሶማሌ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽነር በሽር አህመድ በጄል ኦጋዴን እና በሌሎች ይፋዊ ባልሆኑ እስር ቤቶች ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ግፍ መፈጸሙን ይናገራሉ። "እስር ቤቱ ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ ነበር። በእንድ ወቅት ከ11 እስከ 15ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ታስረውበታል ይባል ነበር" የሚሉት ከሚሽነሩ፤ በእስር ቤቱ በርካቶች መሞታቸውን ጠቅሰው ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ የማጣራት ሥራዎች መሰራት አለበት ይላሉ። ኮሚሽነሩ የእስር ቤቱ ኃላፊ ከነበሩት መካከል ሦስቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን እና የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁን ያልተያዙ ሰዎች መኖራቸውንና እነሱንም ፍትህ ፊት ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። • "የወ/ሮ መዓዛ ንግግር ሌሎችንም [ክልሎች] የተመለከተ ነበር" የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእስር ቤት ውስጥ የአካል እና አእምሮ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመደገፍ የክልሉ መንግሥት የሚወስደው ኃላፊነት ምንድነው ፤ "ግማሽ ያክሉ የሶማሌ ህዝብ እስር ቤት ነበር። ለሁሉም ድጋፍ ማድረግ ይከብዳል" የተባሉት ኮሚሽነሩ፤ ነገር ግን የጉዳት መጠናቸው ከፍተኛ የሆነ ሰዎች ወጪ ሃገር ድረስ ሄደው እንዲታከሙ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የጄል ኦጋዴን የወደፊት እጣ ጄል ኦጋዴን ከተዘጋ ወራቶች ተቆጥረዋል። የእስር ቤቱ የወደፊት እጣውን በተመለከተ ኮሚሽነሩ "የተፈጸመውን ነገር ሁል ጊዜም ማስታወስ የሚገባን በመሆኑ ሙዚየም ለማድረግ አስበናል።" አክለውም በአሁኑ ወቅት በሶማሌ ክልል አንድም በፖለቲካ አመለካከት ምክንያት የታሰረ ሰው አለመኖሩን በልበ ሙሉነት የማረሚያ ቤቶቹ አስተዳዳሪ ይናገራሉ።
xlsum_amharic-train-149
https://www.bbc.com/amharic/44439786
ልዑል ፊሊፕ፡ የኤደንብራው መስፍን ልዑል ፊሊፕ የሕይወት ታሪክ
የኤደንብራው መስፍን ልዑል ፊሊፕ ለንግሥቱቱ በነበራቸው ያልተቋረጠ ጠንካራ ድጋፍ የተነሳ ሠፊ አክብሮትን ለማግኘት ችለው ነበር።
[ "የኤደንብራው መስፍን ልዑል ፊሊፕ ለንግሥቱቱ በነበራቸው ያልተቋረጠ ጠንካራ ድጋፍ የተነሳ ሠፊ አክብሮትን ለማግኘት ችለው ነበር።" ]
ልዑሉ የነበራቸው ሚና በባሕር ኃይል ውስጥ በመሪነት ቦታ ላይ ለቆየ እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ሠፊ ዕውቀትን ላዳበረ ሰው ቀርቶ ለሌላ ለማንም ሰው እጅግ አስቸጋሪ ነበር። ነገር ግን የነበራቸው ጠንካራ ባህሪይ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በውጤታማነት እንዲወጡት ያስቻላቸው ከመሆኑም በላይ ለባለቤታቸው የንግሥትነት ሚና ከሙሉ ልባቸው ድጋፍ አድርገውላቸዋል። የእንስት ዘውዳዊ ባለማዕረግ ወንድ አጋር እንደመሆናቸው፤ ልዑል ፊሊፕ ምንም ዓይነት ሕገ መንግሥታዊ የሥልጣን ሚና አልነበራቸውም። ነገር ግን ማንም ከእርሳቸው የበለጠ ለዘውዳዊው አስተዳደር ቅርብና ለንግሥቲቷ አስፈላጊም አልነበረም። ፊሊፕ በእናቱ ልዕልት አሊስ እቅፍ ውስጥ ቀዳሚ ዓመታት የግሪኩ ልዑል ፊሊፕ የተወለዱት እ.ኤ.አ ሰኔ 10 ቀን 1921 በኮርፉ ደሴት ነው። የልደት የምስክር ወረቀታቸው ላይ የሰፈረው ቀን ግን ግንቦት 28/1921 የሚል ነው። ለዚህም ምክንያቱ በወቅቱ ግሪክ የጎርጎሪዮሳዊያን የቀን አቆጣጠር ቀመር ትከተል ስላልነበረ ነው። አባታቸው የግሪኩ ልዑል አንድሪው ሲሆኑ እርሳቸውም የሄሌናው ንጉሥ ጆርጅ ቀዳማዊ ትንሽ ልጅ ነበሩ። እናታቸው የባተንበርጓ ልዕልት አሊስ ደግሞ የባተንብርጉ ልዑል ልዊስ የበኩር ልጅ እንዲሁም የበርማው ኧርል ሞንትባተን እህት ነበሩ። በ1922 መፈንቅለ-መንግሥት ከተካሄደ በኋላ አባታቸው በአብዮታዊው ፍርድ ቤት ከግሪክ ተባርረዋል። ሁለተኛ የአክስት ልጃቸው በነበሩት ንጉሥ ጆርጅ አምስተኛ የተላከ የብሪታንያ የጦር መርከብ ከነቤተሰባቸው ወደ ፈረንሳይ ወስዷቸዋል። ልዑሉም ቀለም መቁጠር የጀመሩት በፈረንሳይ ቢሆንም ተቀዳሚ ትምህርታቸውን የተከታተሉት የሰባት ዓመት ልጅ ሳሉ ከዘመዶቻቸው ጋር ለመኖር በመጡበት እንግሊዝ ነው። በዚህ ጊዜ እናታቸው ስኪዞፍሬኒያ በሚባለው ከባድ የአዕምሮ ህመም ተጠቅተው የአዕምሮ ህሙማን ማቆያ ውስጥ ገብተው ነበር። ወጣቱ ልዑል ከእናታቸው ጋር የነበራቸው ግንኙነትም ውስን ነበር። ፊሊፕ (የተቀመጠው) በጎርደንስታውን በአማተር ተዋናይነት ወታደራዊ ስልጠና ልዑል ፊሊፕ በወታደራዊው ዘርፍ ለመሳተፍ ወሰኑ። ዘውዳዊውን የአየር ኃይል ለመቀላቀል ፈልገው የነበረ ቢሆንም የእናታቸው ቤተሰብ የባሕር ላይ ታሪክ ስለነበራቸው፤ በእንግሊዝ ደቡባዊ ዳርቻ ባለችው ዳርትሞዝ በሚገኘው በብሪታንያ ዘውዳዊ የባሕር ኃይል ኮሌጅ ውስጥ እጩ መኮነን ሆነው ተመዘገቡ። እዚያ በነበሩበት ጊዜ ንጉሥ ጆርጅ ስድስተኛ ኮሌጁን በሚጎበኙበት ወቅት ሁለቱን ወጣት ልዕልቶች ኤልሳቤጥን እና ማርጋሬትን እንዲያጅቡ ተወክለው ነበር። ይህ መገናኘትም በ13 ዓመቷ ልዕልት ኤልሳቤጥ ልቦና ውስጥ የጠለቀ ስሜትን ፈጠረ። ፊሊፕ ወዲያውኑ ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው ማስመስከር ቻሉ፤ በ1940 ትምህርታቸውን ከክፍላቸው ቀዳሚ ሆነው ያጠናቀቁ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ወታደራዊ ተሳትፏቸውንም በህንድ ውቅያኖስ አደረጉ። በ1942 በዘውዳዊው የባሕር ኃይል ውስጥ ካሉት ወጣት መኮንኖች መካከል አንዱ የነበሩ ሲሆን፤ ኤችኤምኤስ ዋላስ በምትሰኘው የጦር መርከብ ላይ ያገለግሉ ነበር። ፊሊፕ በባሕር ኃይል ውስጥ አገልግለዋል መታጨት በዚህ ሁሉ ጊዜ እርሳቸው እና ወጣቷ ልዕልት ኤልሳቤጥ ደብዳቤ ይለዋወጡ ነበር። በበርካታ አጋጣሚዎችም ከዘውዳዊው ቤተሰብ ጋር ጊዜ እንዲያሳልፉ ይጋበዙም ነበር። ግንኙነታቸው በሰላሙ ጊዜ ይበልጡን ተጠናክሮ በ1946 የበጋ ወራት ልዑሉ ልጃቸውን ለጋብቻ ይሰጧቸው ዘንድ ለንጉሡ ጥያቄ አቅርበዋል። ይሁንና መተጫጨታቸው ይፋ ከመሆኑ አስቀድሞ ልዑሉ አዲስ ዜግነት እና የቤተሰብ ስም አስፈልጓቸዋል። የግሪክ ማዕረጋቸውን ትተው የብሪታንያ ዜግነትን ሲቀበሉ የእናታቸውን የአንግሊካን ልማድን የሚከተለውን ሞንትባተን የተሰኘ ስም ወስደዋል። ጋብቻው በዌስትሚኒስቴር አቤ በ1947 ተከናውኗል። ልዕልት ኤልሳቤጥ እና ፊሊፕ ሞንትባተን ጋብቻ ፈፀሙ የተቋረጠው የሥራ መስመር መስፍኑ ወደ ባሕር ኃይል ሥራቸው ተመልሰው ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜ ያህል ጥንዶቹ እንደማንኛውም የወታደር ቤተሰብ ወደሚኖሩበት ማልታ አቀኑ። ልጃቸው ልዑል ቻርለስ በ1948 ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ውስጥ ሲወለዱ ልዕልት አን ደግም በ1950 ወደዚህች ዓለም መጥተዋል። በ1950 ልዑሉ የማንኛውንም የባሕር ኃይል አባል ህልም አሳክተው ኤችኤምኤስ ማግፓይ የተባለችው የጦር መርከብ አዛዥ ሆነዋል። በ1951 ዘውዳዊውን የባሕር ኃይል ለቀቁ፤ ወደ መደበኛው የባህር ኃይል ሥራም አልተመለሱም። የሥራ አጋሮቻቸው እንደሚሉት በሥራቸው ብቃት ብቻ የባሕር ኃይል የበላይ አዛዥ (ፈርስት ሲ ሎርድ) መሆን ይቻላቸው ነበር። ኤልሳቤጥ ንግሥናውን ሲረከቡ ታማኝነታቸውን ከገለፁት መካከል ፊሊፕ ቀዳሚው ነበሩ የማዘመን ውጥኖች በ1952 ጥንዶቹ በመጀመሪያ በንጉሡ እና በንግሥቲቱ ታቅዶ የተከናወነውን የጋራ ብልፅግና (ኮመንዌልዝ) አገራት ጉብኝትን አደረጉ። በወርሃ የካቲት ኬንያ ውስጥ ባለ የመዝናኛ ስፍራ እንዳሉ ነበር ንጉሡ የመሞታቸው ወሬ የተሰማው። በዚህ ጊዜም ለሚስታቸው ንግሥት የመሆናቸው ዜና የማድረሱ ኃላፊነት በልዑሉ ላይ ወደቀ። በዓለ ሲመቱ ሲቃረብ በሁሉም ጉዳዮች ከንግሥቲቷ ቀጥሎ ልዑል ፊሊፕ ስልጣን እንደሚኖራቸው የሚያስረግጥ ዘውዳዊ ድንጋጌ ታወጀ። እንዲያም ቢሆን ግን ምንም ዓይነት ሕገ-መንግሥታዊ ስልጣን አልነበራቸውም። ፊሊፕ ንግሥቲቱን አጅበው መራር ቅሬታ ፊሊፕ የተነቃቃ ማኅበራዊ ሕይወት የነበራቸው ሲሆን በተደጋጋሚ ከአሽብራቂ ባልንጀሮች ጋር ፎቶ ይነሱ ነበር። የእርሳቸውን የቤተሰብ ስም ሳይሆን ዊንድሰር የተባለውን የራሳቸውን ስም ይዞ ለመቀጠል ንግሥቲቱ መወሰናቸው ልዑሉ ላይ መራር ቅሬታን ፈጥሮ ነበር። "ስሙን ለልጆቹ ማውረስ የማይፈቀድለት በአገሪቱ ውስጥ ያለው ብቸኛው ወንድ እኔ ነኝ" ሲሉ ለወዳጆቻቸው ምሬታቸውን አሰምተው ነበር። የልዑል ቻርልስን የህይወት ታሪክ የፃፈው ጆናታን ዲምቢልቢ እንደሚለው፤ በወጣትነታቸው ጊዜ በሰዎች ከአባታቸው ፊት ባጋጠማቸው ነቀፌታ የተነሳ አምርረው አለቀሰዋል። በአባት እና በልጅ መካከል ያለው ግንኙነትም መቼም ቀላል አልነበረም። ፊሊፕ ንግሥቲቱን አጅበው "ሰናይ ምግባር" ልዑል ፊሊፕን ከሚያሳስቧቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የታዳጊ ልጆች እጣ ፈንታ ነበር። ይህም በ1956 እጅግ ስኬታማ የሆነው የኤደንብራ መስፍን ሽልማት ለመጀመሩ ምክንያት ሆኗል። በቀጣይ ዓመታትም የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ እና ላልሆኑ ስድስት ሚሊዮን ያህል ከ15 እስክ 25 ዓመት ያሉ ወጣቶች የቡድን ሥራን፣ የፈጠራ ችሎታን እንዲሁም ተፈጥሮን ማክበርን ለማበረታታት በበርካታ ከቤት ውጪ እንቅስቃሴዎች ራሳቸውን እንዲፈትኑ አስችለዋል። ለዱር አራዊት እና ለአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮችም በጋለ ስሜት ይሟገቱ ነበር። በኋላ ላይ የዓለም አቀፍ ፈንድ ለተፈጥሮ ተብሎ ስሙ ለተቀየረው ለዓለም አቀፉ የዱር እንስሳት ፈንድ በከፍተኛ ደረጃ ጉልበታቸውን ያፈሰሱ እና ተፅዕኖም ያሳረፉ ሲሆኑ፤ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት መሆናቸውም የሚያስገርም አልነበረም። ቃለ መጠይቅ ላደረገላቸው የቢቢሲ ጋዜጠኛ እንዲህ ብለው ነበር "እንደማስበው እኛ ሰዎች ህይወት እና ሞትን -መጥፋት እና መትረፍን - የማምጣት አቅም ካለን፤ በአንዳች ዓይነት ምግባረ ሰናይነት ልንተገብረው ይገባናል። ማጥፋት የሌለብንን ነገር እንዴት እናጠፋለን?" ቀጥተኛ ነገሮችን ፍርጥርጥ የማድረግ እና በቀጥታ የመናገር ዝንባሌያቸው አንዳንድ ጊዜ ልዑሉን ችግር ውስጥ ይጥላቸው ነበር። በዚህም በአንዳንዶች ዘንድ ክፉኛ ቢብጠልጠሉም፤ ሌሎች በራሳቸው የሚሽከረከሩ እና በፖለቲካዊ ትክክለኛነት ያልታሰሩ ሰው ናቸው ይላሉ። ኋለኛ ዘመን የዕድሜ መግፋት የህይወታቸውን ፍጥነት ሊቀንሰው አልቻለም። በህይወታቸው ሁሉ፤ ልዑል ፊሊፕ ለስፖርት ልዩ ፍቅር ነበራቸው። ዓለም አቀፉን የዱር እንስሳት ፈንድ በመደገፍ እና ንግሥቲቱን በውጭ አገር ጉዞ በማጀብ በስፋት መጓዛቸውንም ቀጥለዋል። ግላዊ የኃይማኖት ጉዞም በ1994 ወደ እየሩሳሌም አድርገው የእናታቸውን የመቃብር ስፍራ ጎብኝተዋል። እናታቸው በጥያቄያቸው መሰረት የተቀበሩት በእየሩሳሌም ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጃፓን የተሸነፈችበት 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል እ.ኤ.አ በ1995 በተከበረበት ወቅት ሌላ ስሜታዊ ዕለትን አሳልፈዋል። ጃፓን እጇን ስትሰጥ ልዑል ፊሊፕ በቶኪዮ ሰርጥ በብሪታንያ የጦር መርከብ ውስጥ ነበሩ። በክብረ በዓሉ ዕለትም በሩቅ ምሥራቁ ዘመቻ ተሳትፈው ከነበሩ የቀድሞ የጦር መኮንኖች ጋር በመሆን ከንግሥቲቱ ፊት የሰልፍ ትርኢት አሳይተዋል። ግትርነታቸው በኋለኛ ዘመናቸው በመጠኑ ረገብ ብሏል፤ ይህም የዌልሷ ልዕልት ዳያና ከሞቱ በኋላ ሕዝቡ አንዳንዴ ለዘውዳዊው ቤተሰብ አሉታዊ አስተያየትን ከማዳበሩ የመነጨ ነው። የዳያና የመጨረሻው የፍቅር አጋር አባት መሃመድ አል ፋይድ የልዕልቲቷ ሞት በሚመረመርበት ወቅት በልዑል ፊሊፕ ትዕዛዝ ነው የተገደለችው እስከ ማለት ደርሰዋል። ይህንን ውንጀላ ግን ልዑሉ ፍርጥም ብለው አጣጥለውታል። እአአ በ2007 ከልጃቸው ሚስት ጋር ቅራኔ ነበራቸው የሚለውን ውንጀላ ለማጣጣል በመስፍኑ እና በሟቿ ልዕልት መካከል የተደረጉ የደብዳቤ ልውውጦች ታትመዋል። ደብዳቤዎቹ እንደሚያሳዩት መስፍኑ ለዳያና ታላቅ ድጋፍን ሲያደርጉ ነበር። ይህ ሃቅም ልዕልቲቷ ይፅፉ በነበረበት ሞቅ ያለ ስሜት የበለጠ ይጠናከራል። ንግሥቲቱ ባለቤታቸውን የጥንካሬያቸው ምንጭ እንደሆኑ ይገልጿቸዋል "የማይረባ አቀራረብ" የኤደንብራው መስፍን ልዑል ፊሊፕ የሥራ ኃላፊነታቸው ሁልጊዜም ሁለተኛ ስፍራን እንዲይዙ ያስገደዳቸው ተፈጥሯዊ መሪ ነበሩ። ተጋፋጭ ባህርያቸውም የተቀመጡበት ቦታ ካለው ስሱነት ጋር ደጋግሞ የሚጋጭባቸው ሰውም ነበሩ። "የሠራሁት ባለኝ አቅም ሁሉ የላቀውን ነው" ሲሊ በአንድ ወቅት ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ነገሮችን የማከናውንበተን መንገድ ሙሉ በሙሉ በድንገት መለወጠወ አልችልም፣ ፍላጎቶቼንና ለነገሮች ምልሽ የምሰጥበትን መንገድ መቀየር አልችልም። ይህም የእኔ ዘይቤ ነው።" ይህንንም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በልዑሉ 90ኛ ዓመት የልደት በዓል ዋዜማ ላይ ባደረጉት ንግግር መስክረውላቸው። "ምንጊዜም ነገሮችን የሚከውኑት በቀለል ነገር ግን የራሳቸው በሆነ ልዩ መንገድ ነው። ለብሪታኒያ ሕዝብ ለማይማርክ የማይረባ አቀራረብን ቦታ የላቸውም" ብለው ነበር። ከሕዝባዊው እንቅስቃሴ መራቅ ለበርካታ አስርት ዓመታት ንግሥቲቱን ሲያግዙና በራሳቸውና በሌሎች ድርጅቶች በሚካሄዱ የበጎ አድራጎት ዝግጅቶች ላይ ሲታደሙ የቆዩት ፊሊፕ ከዚህ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ገለል ያሉት ከአራት ዓመታት በፊት ነበር። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ባሉት ጊዜያት 22,219 የተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች ላይ ብቻቸውን እንደተሳተፉ የባኪንግሃም ቤተመንግሥት ገልጿል። ለዚህም የቀድሞዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ በዘመናቸው ላበረከቱት "ድንቅ የሕዝብ አገልግሎት" ምስጋናቸውን አቀውርበውላቸዋል። ከሰባት አስርት ዓመታት በላይ በትዳር ውስጥ የቆዩት ፊሊፕ፤ በዳሌያቸው ላይ ከፍተኛ የቀዶ ሕክምና የተደረገላቸው ቢሆንም በዊንድሰር ቤተ መንግሥት ውስጥ ንጉሣዊ ሠረገላቸውን እያሽከረከሩ ከመዘዋወር አልተቆጠቡም ነበር። ልዑሉ ከሁለት ዓመት በፊት እራሳቸው በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ካጋጠማቸው ከባድ የመኪና አደጋ የተረፉ ሲሆን፤ በሌላኛው መኪና ውስጥ የነበሩ ሁለት ሴቶች በአደጋው የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ፊሊፕ በገዛ ፈቃዳቸው የመንጃ ፈቃዳቸውን መልሰዋል። በኮሮናቫይረስ ወቅትም በጥር ወር 2021 (እአአ) ፊሊፕና ንግሥቲቱ ባለቤታቸው የወረርሽኙን መከላከያ ክትባት የእንቅስቃሴ ገደብ የተጣለበትን ጊዜ ባሳለፉበት የዊንድሰር ቤተመንግሥት ሐኪም አማካይነት ተከትበዋል። ፊሊፕ ንጉሣዊ ሥልጣናቸውን ለብሪታንያውያን ህይወት ከፍተኛ አበርክቶ ለማድረግ በመጠቀምና ዘውዳዊው ሥርዓት በኅብረተሰቡ ዘንድ በዘመናት ሂደት እየተለወጠ ከመጣው አመለካከት ጋር እንዲጣጣም በማድረጉ ረገድም ስኬታማ ነበሩ። ከሁሉም ስኬቶቻቸው የሚልቀው ለንግሥቲቷ በረጅም የንግሥና ዘመናቸው ድጋፋቸውን ያበረከቱበት ወጥነት እና ጥንካሬ እንደሆነ ይነገራል። የጥንዶቹን የጋብቻ የወርቅ እዮቤልዩ ለማክበር በተሰናዳ ዝግጅት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ንግሥቲቷ በብሪታንያ ታሪክ ለረጅም ዘመን ላገለገሉት ባለቤታቸው እንዲህ በማለት ውዳሴ አቅርበውላቸዋል፡ "ሙገሳን በቀላሉ የማይቀበል ሰው ነው። ነገር ግን በቀላሉ ጥንካሬዬ ሆኖ እነዚህን ዓመታት ሁሉ ዘልቋል። እኔም፣ ጠቅላላው ቤተሰቡም እንዲሁም ይህች እና ሌሎች አገራትም እርሱ ሊጠይቀው ከሚችለው እኛም ልናውቀው ከምንችለው በላይ ባለዕዳዎቹ ነን።"
xlsum_amharic-train-150
https://www.bbc.com/amharic/51657331
"እልም ያለ ሥርዓት አልበኝነት ሊፈጠር ይችላል" ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌ.)
ዛሬ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የሚከሰቱ አለመረጋጋቶች፣ ግጭቶችና ከዕለት ወደ ዕለት አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የሰላም ዕጦት፣ ነገ ደግሞ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን? የሚል ስጋት/ጭንቀት መኖሩን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።
[ "ዛሬ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የሚከሰቱ አለመረጋጋቶች፣ ግጭቶችና ከዕለት ወደ ዕለት አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የሰላም ዕጦት፣ ነገ ደግሞ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን? የሚል ስጋት/ጭንቀት መኖሩን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።" ]
ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የለውጡን ሂደት፣ በዚህ ዓመት ማጠናቀቂያ ላይ የሚካሄደውን ምርጫ ፋይዳ እና በኢትዮጵያ ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን በሚመለከት ባቀረቡት ግምገማና ጥሪ ላይ ነው ይህንን የተናገሩት። በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የሠላም ዕጦት ኢዜማን እንደሚያሳስበው ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል። ኢዜማ ከአባላቱና ከተለያዩ አካላት ያገኘውን መረጃ በመሰብሰብ፣ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ በመገምገም የጋራ አገራዊ ግንዛቤ ለመፍጠርና፣ ውይይት ለመክፈት በማለት በትናንትናው ዕለት አገራዊ ጥሪ ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በመሪው በኩል አቅርቧል። • "በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት አገረ መንግሥት ግንባታ ያለፈችባቸውን ለውጦች ዘርዝረው፣ በእነዚህ ለውጦች ውስጥ የታዩት ተግዳሮቶች ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ከመገንባት ይልቅ ማኅበረሰብን በጠባብ የዘውግ መለኪያ ብቻ የሚመለከት የአድሎ ሥርዓት መፍጠሩን በትንታኔያቸው ላይ ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ለሦስተኛ ጊዜ ትልቅ የለውጥ ሂደት ውስት ገብታለች ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ "ነገር ግን ይህ ለውጥ ወደምንፈልገው የተረጋጋ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ይውሰደን አይውሰደን ገና የታወቀ ነገር የለም" ሲሉ ይገልፃሉ። ለዚህም እንደምክንያት ያነሱት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች፣ መፈናቀሎችና ሥርዓት አልበኝነቶችን ሲሆን በሕዝቡ ዘንድም ቀጣዩ ምርጫ ያጫረውን ስጋት በዋቢነት ጠቅሰዋል። ለውጥና የገጠመው ተግዳሮት ፕሮፌሰር እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት ያለው ለውጥ የተጀመረው በፊት የነበረውን መዋቅር ሙሉ በሙሉ በማፈራረስ ሳይሆን ቀስ በቀስ የነበሩ ህፀጾችን እየቀነሱ ባለው መልካም ሁኔታ ላይ እየጨመሩ መሄድ በሚል መሆኑን ይጠቅሳሉ። ነገር ግን የተለያየ ዓላማ ይዘው ለለውጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች እና ለውጡን እንደግፋለን ብለው ወደ አገር ቤት የገቡ፣ በመንግሥትም ሆነ በተለያየ የሥልጣን እርከን ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ከለውጡ አላማ ውጪ መንቀሳቀስ የጀመሩት ወዲያውኑ መሆኑን ያነሳሉ። ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የኢዜማ መሪ ሆነው ተመረጡ በዚህም የተነሳ ይላሉ ፕሮፌሰሩ ማዕከላዊው መንግሥት ሰላም የማስጠበቅ አቅሙን ከመገንባቱ በፊት ማኅበረሰቡ፣ በለውጡና በለውጡ ኃይሎች ተስፋ እንዲቆርጥ "መንግሥት የለም" ብሎ ሥርዓት አልበኝነት በአገሪቱ እየነገሰ ነው ብሎ እንዲሰጋና ለደህንነቱ ሲል ሁሉም ወደ ዘውጌ ምሽግ እንዲገባ እና የጣለውን ዘውጌ ሥርዓት እንዲናፍቅ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋቸውን ይጠቅሳሉ። ይህንን እንቅስቀሳሴ ሦስት አካላት ይሳተፉበታል በማለትም ሲዘረዝሯቸው የቀድሞ ሥርዓት ዋነኛ ተጠቃሚዎች፣ ለውጡን የሚፈልግና በባለተራ ዘውጌነት ክልሉን መግዛት የሚፈልግ፣ እንዲሁም የለውጥ ኃይሉን በፍፁም የማያምን ናቸው በማለት ያስቀምጧቸዋል። እንደ ፕሮፌሰሩ ማብራሪያ ከሆነ "ይህ ሦስተኛው ኃይል የለውጥ ኃይሉ በደንብ ከመደላደሉ በፊት በመቃወም፣ የህዝብ ተቀባይነት እንዳያገኝ በማድረግና ለውጡን ለማስኬድ ብቃትም ሆነ ተአማኒነት የለውም በማለት የተጀመረውን ለውጥ ከግቡ ለማድረስ ከሁሉም የተውጣጣ የሽግግር መንግሥት ይፈጠር በሚል የራሱን አጀንዳ ለማራመድ የሚሞክር ኃይል ነው።" የሦስቱ ኃይሎች የጋራ ፍላጎት መንግሥትን ማዳከም ሲሆን በጋራ ላይሰሩ ይችላሉ ይላሉ። አስፈሪው ስጋት ፕሮፌሰሩ በዚሁ ጥሪ ባቀረቡበት ዘለግ ያለጽሑፍ ላይ እንዳስቀመጡት ሕዝቡ ይወክለኛል ያለውን ያለመሳቀቅ እና ፍርሃት መምረጥ ካልቻለ ባለፉት 18 ወራት ያየናቸውና ማኅበረሰባችንን ጭንቀት ውስጥ የከተቱት ችግሮች እጅግ በጣም በገዘፈ መልኩ የሚከሰቱበትና ወደ አጠቃላይ ቀውስ የምንገባበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀሬ ይሆናል ይላሉ። ውክልናቸው በህዝብ ያልተረጋገጠላቸው "ወኪል ነን" ባይ ድርጅቶች "ውክልናቸውን ለማረጋገጥ" ሊሄዱበት የሚችሉት ብቸኛ መንገድ ጉልበትና አመጽ ብቻ ይሆናል ሲሉም ይገልጻሉ። ይህ አመጽ ደግሞ አንድ ኃይል ወይም አንድ ወገን ብቻ የሚያካሂደው አመጽ ሳይሆን ሁሉም ሁሉንም የሚፈራበት፤ ሁሉም ከፍርሀቱ ለመውጣት ሳልቀደም ልቅደም በሚል ራሱን ለአመጽ የሚያዘጋጅበት፤ ተዘጋጅቶም "ጠላቴ" የሚለውን ኃይል ለማጥፋት የሚንቀሳቀስበት ነው። የዘውጌ ክልሎች አንዱ ካንዱ ጋር ለውጊያ የሚነሳሱበት፣ በዘውጌ ክልሎችም ውስጥ፤ በየአካባቢው ባሉ 'ጊዜው የኛ ነው' ባይ ጉልበተኞች (የጦር አበጋዞች) የሚመሩ ቡድኖች የበላይነት ለማግኘት የዕርስ በዕርስ ጦርነት ውስጥ የሚገቡበት እልም ያለ ሥርዓት አልበኝነት የሚነግስበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀሬ ነው ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። አክለውም ይህ የተያያዝነው የለውጥ ሂደት ከዚህ በፊት እንደነበሩት የለውጥ ሙከራዎች ከስሞ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሌሎች ማኅበረሰቦች የደረሱበት ስልጣኔ ሂደት አካል ከመሆን ይልቅ ከመቶዎች ዓመታት በፊት ወደነበርንበት የጨለማ ዘመን መልሶ የሚከተን ከሆነ አደጋው ወደኋላ መመለስ ብቻ ሳይሆን እንደ አገር መቀጠል አለመቻልም ሊሆን ይችላል ብለዋል። ያለተማከለ አስተዳደር ህዝብ በሚኖርበት የአስተዳደር እርከን ሁሉ እራሱን በራሱ ማስተዳደር አለበት የሚለውን መሰረተ ሃሳብ በግልጽ የሚቃወም የፖለቲካ ኃይል በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የለም የሚሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ልዩነት ያለው ያልተማከለ ፌደራላዊ አስተዳደር ሲባል በተጨባጭ ምን ማለት ነው የሚለው ጥያቄ ላይ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። አክለውም በፌደራላዊ የመንግሥት አደረጃጀት ውስጥ ከታችኛው እርከን ጀምሮ ያሉ የመንግሥት አስተዳደሮች ሁሉ በአካባቢው ነዋሪ በተመረጡ መሪዎች ይተዳደራሉ ወይም አካባቢውን የሚመለከቱ አስተዳደራዊም ሆነ የልማት ውሳኔዎችን በህዝብ በተመረጡ መሪዎች ይወሰናሉ ብለዋል። "ኢትዮጵያ ውስጥ ግን በብሔር የተደራጁ ኃይሎች ይህንን ለዘመናት "ታግለንለታል" የሚሉትን መርህ እንኳን በተግባር ለማዋል ፈቃደኞች አይደሉም" በማለት ከክልላቸው ውጪ ያሉ ዜጎች ምንም አይነት የዜግነት መብት የሌላቸው እንደሆኑ ተደርጎ የመቁጠር ሁኔታ እንዳለ ምሳሌ ጠቅሰው አስረድተዋል። በማስከተልም "እንዲህ አይነት አስተሳሰብ በነገሰበት አገር ውስጥ የተለያየ የዘውግ ማንነት ያላቸው ህዝቦች አገራዊ አንድነት ፈጥረው በሰላም አብሮ መኖር ይችላሉ?" በማለት "ዜጎች በሚኖሩበት አካባቢ ሰርተውና ያፈሩትን ሃብትና ከሚኖሩበት አካባቢ ነዋሪዎች ጋር ተጋብተው ወልደው የመሰረቱት ኑሮ ዋስትና ከሌለው እንዴት እራሳቸውን የዚህ አገር ዜጋ ነኝ ብለው ይጠራሉ?" ብለው ይጠይቃሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ። ምርጫ 2012 ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ የችግሮቻችን መፍቻ መነሻ ነው የሚሉት ፕሮፌሰሩ ምርጫው ተዓማኒ እንዲሆንና፣ የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት መገለጫ እንዲታይ መሟላት ያለባቸው ጉዳዮችን ይዘረዝራሉ። ከእነዚህም መካከል አማራጭ አለን የሚሉ ድርጅቶች በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሰው፣ ያለምንም ችግር ማኅበረሰቡን ሰብስበው ማናገር መቻል አለባቸው የሚለው ቀዳሚው ነው። መራጩም የሚፈልገውን ስለመረጠ ምንም ዓይነት የደህንንት አደጋ አይደርስብኝም ብሎ መተማመን ደረጃ ላይ መድረስ አለበት ይላሉ። በማስከተልም ሌሎች በምርጫው ወቅትና ከምርጫው በኋላ መሆን አለባቸው ያሏቸውን ከዘረዘሩ በኋላ ለምርጫው ሳንካዎች ናቸው ያሏቸውን ፓርቲያቸው በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የገጠሙትን ችግሮች በመንቀስ ያስረዳሉ። ይህ ጉዳይ ከቀጠለ ለበለጠ ግጭት ሊዳርግና ምርጫውን ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋልም ብለዋል። በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ በተለይ በታችኛው እርከን ያሉ የመንግሥት አስተዳዳሪዎችና የፀጥታ ኃይሎች ከፖለቲካ ኃይሎችና ኢ-መደበኛ ከሆኑ የወጣት አደረጃጀቶች ጋር ህዝባዊ ስብሰባዎችን የማሰናከል፣ የተፎካካሪ ድርጅት አባሎችን ማሰርና ማንገላታት በተደጋጋሚ እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ፕሮፌ. ብርሃኑ ለገዢው ፓርቲ ማስመረጫ ገንዘብ ማሰባሰብ በሚል እየተደረገ ነው በሚል በምሳሌ አስደግፈው ያቀረቡት ክስ ላይ "የመንግሥት ኃላፊነት ያለባቸው የገቢዎች ባለስልጣን ኃላፊዎች የሚቆጣጠሩትን የንግድ ማህበረሰብ ለብልጽግና ፓርቲ ገንዘብ እንዲያወጣ ሲጠይቁ፤ ባንዳንድ ቦታ የገቢዎች ባለስልጣን ማህተም ባለበት ደብዳቤ ነጋዴዎች ለብልጽግና ፓርቲ ገንዘብ እንዲያስገቡ ሲጠየቁ" እንደነበር አመልክተዋል። "ይህ እየተሄደበት ያለው መንገድ የምርጫውን የመወዳደሪያ ሜዳ እጅጉን ሚዛናዊነት የጎደለው እንዲሆን ከማድረጉም በላይ ከምርጫው በኋላ ሊመጣ የሚችለውን የሙስና አካሄድ የሚያሳይ ነውና ካሁኑ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል" በማለት የመግሥትና የፓርቲ ኃላፊነቶችን የሚያደበላልቁ ሁኔታዎች ማየታቸው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘም "የምርጫውን ተአማኒነት የሚያሳጡና ሀሳቦች በነጻነትና እንዳይንሸራሸሩ የሚያሰናክሉ ተግባራት፤ ወይም ምርጫው በፍትሃዊነት እንዳይካሄድና ወደ ገዥው ፓርቲ እንዲያደላ የመንግሥት ሃብትና መዋቅርን እራሱን ለማስመረጥ በሚል በየትኛውም መልክ ከተጠቀመበትና ምርጫው ተአማኒነት ካጣ፤ በሽግግሩ ሂደቶች ለሠራቸው ጥሩ ሥራዎች የምናመሰግነውን ያህል ዋናውን የመዳረሻ ሂደት ካበላሸው የለውጥ ኃይሉን በግልጽ ከመኮነንና ተጠያቂ ከማድረግ በፍጹም ወደኋላ እንልም!" ሲሉ በአጽኖት ተናግረዋል። በአጠቃላይ ግን ይህ ምርጫ እውነትም የህዝብ ውክልና የሚገለጥበት እንዲሆን ከተፈለገ እነኝህን በየክልሉ በተለይም በታችኛው እርከን ላይ የሚገኙ የመንግሥት ጉልበተኞች በአስቸኳይ መቆጣጠር ካልተቻለ ይህ ምርጫ ከፍተኛ የተአማኒነት ችግር ውስጥ እንደሚገባ ግልጽ ነው በማለት ጠቁመዋል። የጠቀሷቸው ችግሮች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነም የምርጫው አካሄድ ክፉኛ ሊያበላሽና "አስፈሪ" ወዳሉት ሥርዓት አልበኝነት ወይንም "አዲስ ዓይነት አምባገነናዊ ሥርዓት" አገሪቱን ሊወስድ እንደሚችል ጠቁመዋል። አክለውም "ይህ የሽግግር ሂደት የለውጥ ኃይል እየተባለ ሲሞካሽ በነበረው ኃይል አጋዥነት ከተቀለበሰ የበለጠ ወደ አሳፋሪና አስፈሪ አደጋ አገራችንን መውሰዱ አይቀሬ ነው" በማለት አስጠንቅቀዋል።
xlsum_amharic-train-151
https://www.bbc.com/amharic/news-48754533
የጄኔራሎቹና የአዴፓ አመራሮች ግድያ፡ ሙሉ እውነቱን ማን ይንገረን?
ነገሩ ሁሉ የጀመረው ቅዳሜ አመሻሽ ገደማ ነው። ከአማራ ክልል የሚወጡ ዜናዎች በርካቶች ያልጠበቁት ነበር። በአማራ መንግሥት መስተዳድር ላይ "መፈንቅለ-መንግሥት" እንደተሞከረ ተገነረ።
[ "ነገሩ ሁሉ የጀመረው ቅዳሜ አመሻሽ ገደማ ነው። ከአማራ ክልል የሚወጡ ዜናዎች በርካቶች ያልጠበቁት ነበር። በአማራ መንግሥት መስተዳድር ላይ \"መፈንቅለ-መንግሥት\" እንደተሞከረ ተገነረ።" ]
ከግራ ወደ ቀኝ፤ ጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ እና አቶ አምባቸው መኮንን [ዶ/ር] በአማራ ክልል በደረሰው በዚህ ጥቃት በቅርቡ ወደ ሥልጣን የመጡት አቶ አምባቸው መኮንን [ዶ/ር] መጎዳታቸውን ተሰማ። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴም ጥቃት እንደደረሰባቸው ወሬዎች መሠራጨት ጀመሩ። በአማራ ክልል አስተዳደር ላይ "የመፈንቅለ-መንግሥት" ሙከራ መደረጉን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ይፋ ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቃል-አቀባይ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ነበሩ። • ስለ'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች • ሳፋሪኮም የተጠቃሚዎችን መረጃ በማውጣት ተከሰሰ • በሱዳን የተቋረጠው ኢንተርኔት ለአንድ ጠበቃ ብቻ መሥራት ጀመረ ይህ በሆነ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ ሌላ አሳዛኝ ዜና ተሰማ። ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ በገዛ ጠባቂያቸው በጥይት መመታታቸው፣ እንዲሁም አብረዋቸው የነበሩት ጄነራል ገዛዒ አበራም ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገነረ። ፕሬስ ሴክሬታሪው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቀርበው ከሠጡት መግለጫ ውጭ ምንም ዓይነት ይፋዊ መግለጫ አልተሰማም። ቅዳሜ አመሻሹን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በሰጠው መግለጫ የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ "የመፈንቅለ-መንግሥ" ሙከራ ነው ከተባለለት ክስተት ጀርባ ያሉ ሰው መሆናቸውን አሳወቀ። ማሕበራዊ ሚድያ ላይ ዜናው የተዋጠላቸውም ሆኑ ያልተዋጠላቸው ሐሳባቸውን ከመሰንዘራቸው ውጭ የክልልም ሆነ የፌዴራል ባለሥልጣን ጉዳዩን አስመልክቶ ሙሉና ግልፅ መረጃ ሊሰጥ እንዳልቻለ አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ። ምሽቱን በይነ-መረብ መቋረጡን ከወደ አዲስ አበባ ሰማን። እኩለ ሌሊት ገደማ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ዥጉርጉር ወታደራዊ ሸሚዝ ለብሰው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ብቅ አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ባህር ዳር ከተማ ውስጥ "የመፈንቅለ-መንግሥት" ሙከራ የተደረገው የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ በማካሔድ ላይ በነበሩበት ጊዜ ነው ሲሉ አስታወቁ። "በመፈንቅለ መንግሥት" ሙከራው ወቅት ጥቃት ከተፈጸመባቸው መካከል "ከፊሉ መሞታቸውንና ከፊሉ መቁሰላቸውን" ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩ ሲሆን ጉዳቱ የደረሰባቸው እነማን እነደሆኑ የሰጡት ምንም ዓይነት ማብራሪያ ግን አልነበረም። አክለውም ኤታማዦር ሹማቸው አዲስ አበባ ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳወቁ። 'አዲስ አበባ ውስጥ በኤታማዦር ሹሙ ላይ የተፈጸመው የመግደል ሙከራ "ከመፈንቅለ መንግሥቱ" ሙከራ ጋር ግንኙት አለው' ሲሉም ተደመጡ። ኤታማዦር ሹሙ ፡ከመፈንቅለ መንግሥት" ሙከራው ጋር በአማራ ክልል የተከሰተውን ችግር ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እየመሩ እንደነበር የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሽት ላይ "ቅጥረኞች" ጄኔራል ሰዓረንና አጋራቸው ጄኔራል ገዛዒ አበራን እንዳጠቋቸው ተናገሩ። እሑድ እሑድ ጠዋት ላይ በርካታ መረጃዎች ተከታትለው ወጡ። ጄኔራል ሰዓረ እና ጄኔራል ገዛዒ መሞታቸውን ለማርዳት ድምጸ ወያነን የቀደመ አልነበረም። ትንሽ ቆየት ብሎ ደግሞ በብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ 'የአማራ ክልል አስተዳዳሪ አቶ አምባቸው መኮንንና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ ተሰዉ' ሲል አተተ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መግለጫ እሰጣለሁ ሲል ለመገናኛ ብዙኃን ሰዎች መልእክት አስተላለፈ። ረፋዱ ላይ በሥፍራው የተገኙት የሚድያ ሰዎች ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን አስቀምጠው ገቡ። መግለጫውን የሰጡት አቶ ንጉሱ ጥላሁን [በአማርኛ] እና ቢለኔ ስዩም [በእንግሊዝኛ] ነበሩ። ከጋዜጠኞች ጥያቄ ለመቀበል ዝግጁ ያልነበሩት ቃል አቀባዮቹ በመግለጫቸው ጄኔራል ሰዓረ፣ ጀኔራል ገዛዒ፣ አቶ አምባቸውና አቶ እዘዝ መሞታቸውን አረጋገጡ። ጄነራል ሰዓረ ላይ ጥቃት አድርሷል የተባለው ግለሰብ ቢጎዳም በቁጥጥር ሥር መዋሉን አሳወቁ። በአማራ ክልል የተደረገውን "የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ" ያካሄዱት በቅርቡ በምሕረት የተለቀቁት ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ እንደሆኑም ተገለጸ። ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ላቀ አያሌው የአማራ ክልል ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆነው እንደሚያገለግሉ የተሰማውም በዚሁ መግለጫው ላይ ነበር። እሑድ ረፋዱን ከተሰሙ ትኩስ ዜናዎች አንዱ የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ በደረሠው ጥቃት ተጎድተው ሕክምና ላይ መሆናቸው ነበር። እሑድ ከሰዓቱን ለቢቢሲ ድምፃቸውን የሰጡት የክልሉ የሰላም ግንባታና ህዝብ ደኅንነት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ 'የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ግምገማ እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ብርጋዴር ጄኔራሉ በልዩ ኃይሎች ታጅበው እንደመጡና በመጀመሪያም የርዕሰ መስተዳደሩ አጃቢዎች ላይ ተኩስ እንደከፈቱ፤ ቀጥለውም የክልሉ አመራሮች ላይ የተኮሱ ሲሆን በዚህም ሦስቱ እንደተመቱ' አስረዱ። አክለውም አለቃቸው እና "መፈንቅለ-መንግሥት ሙከራውን" በማቀነባበር የሚጠረጠሩት ብራጋዴር ጄነራል አሳምነው የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ገለፁ። ሰኞ እጅጉን የተጣረሱ መረጃዎች ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩት በዕለተ ሰኞ ነው። መጀመሪያ የተሰማው ግን የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ መሞት ነበር። ከሁሉ ልቆ የወጣው ዜና ግን የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፀጌ መገደል ነው። ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው ኢቲቪ 'ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ ተገደለ' የሚል ዜና ይዞ ብቅ አለ። ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ከባህርዳር ወጣ ብሎ ባለች ዘንለዘልማ ተብላ በምትታወቅ ሥፍራ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ እንደተገደሉ ተሰማ። ሌላኛው ዜና ደግሞ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰማ ነበር። ዜናው ደግሞ የጄነራል ሰዓረ ገዳይ መሞቱን የሚያትት ነበር። ይህ ዜና ነበር ብዙዎችን ግራ ያጋባው። ቢቆስልም በቁጥጥር ሥር ውሏል የተባለው ግለሠብ ራሱን አጥፍቷል መባሉ ግርታን ፈጠረ። እንዴት በቁጥጥር ሥር ያለ ሰው ራሱን ያጠፋል? የብዙዎች ጥያቄ ነበር። የፖሊስ መግለጫ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀተታ መጣረስ ጉዳዩን ከድጡ ወደማጡ አደረገው። ነገር ግን ዘግይቶ ደግሞ ብሐራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ግለሰቡ አልሞተም፤ በሕይወት አለ ሲል አተተ። ሥርዐተ ቀብር ቅዳሜ ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ የተገደሉት የሃገር መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የጄኔራል ሰዓረ መኮንን አዲስ አበባ ውስጥ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቀብራቸው እንደሚፈጸም ተናግሮ ነበር። የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም ቀደም ብሎ እንደተናገሩት የጄነራል ሰዓረ የቀብር ሥነ ሥርዓት ማክሰኞ ዕለት እንደሚፈጸምና በዚህም የጄነራሉ አስከሬን ከቤታቸው ተነስቶ በወታደራዊ ሥርዓት ታጅቦ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ተወስዶ ከጠዋት እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ በሚሊኒየም አዳራሽ ቤተሰቦቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው በሚገኙበት የሽኝት ሥነ ሥርዓት ይደረጋል ተብሎ ነበር። የዛኑ ዕለት የትግራይ ቴሌቪዠን ላይ ከቤተሰቦቻቸውና ከትግራይ ክልል ባለስልጣናት እንደተነገረው የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መቀሌ ውስጥ ይፈፀማል ተብሏል። በርካታ መረጃ፤ ሥፍር ጥያቄ. . . በክልል ደረጃ "መፈንቅለ-መንግሥት" አለ ወይ ከሚለው አብይ ጥያቄ አንስቶ የቅዳሜው ክስተት እና መዘዙ ብዙ ጥያቄዎች እያስተናገደ ነው። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ [አብን] ጉዳዩ ጥቃት እንጂ 'የመፈንቅለ-መንግሥት' ሙከራ አይደለም ሲል ተቃወመ፤ በተፈጠረው ነገር ማዘኑን ሳይሸሽግ። አቶ ገደቤ ጉዳዩን ሲተንትኑልን እንዲህ ብለው ነበር፤ "11፡00 ሰዓት አካባቢ የተወሰኑ የፀጥታ አመራሮች ከድርጊቱ በፊት ለስብሰባ እንደተፈለጉና ወደ ስብሰባው ቦታው እንደሄዱ፤ ከዚያም ወዲያውኑ እነርሱ መግባታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ተከታትሎ የተደራጀ ኃይል ገብቶ ከፍተኛ ተኩስ በመክፈት ግለሰቦች እንዲታፈኑና እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉን አውቃለሁ።" አቶ ገደቤ አክለው "በወቅቱ እኔ በስብሰባው ላይ አልነበርኩም፤ አልተጠራሁም። ቅዳሜ እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ ብርጋዴር አሳምነው ቢሮ ነበርኩ። 9 ሰዓት አካባቢ ሌላ ሥራ ስለነበረኝ እስከ 11፡00 ሰዓት ሥራ ላይ ነበርኩ፤ ከዚያም ከፍተኛ ተኩስ ሰማሁ" ሲሉ ክስተቱን ያወሳሉ። አቶ ገደቤ ጥቃቱ ከፕሬዝደንቱ ጽሕፈት ቤት በተጨማሪም የፀጥታ ቢሮ፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮና የአዴፓ ጽሕፈት ቤት ላይም ጥቃት መፈፀሙን ተናግረዋል። በርካታ የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን አቶ ገደቤ ይናገራሉ፤ ምንም እንኳ ቁጥሩን ይፋ ባያደርጉም። በባሕርዳር የርዕሰ መስተዳድሩ ጽሕፈት ቤት ስብሰባ ላይ የነበሩት ሰባት ሰዎች እንደነበሩ ተነግሯል። ከሞቱት አራት ባለሥልጣናት በተጨማሪ አቶ ዮሃንስ ቧያለው፣ አቶ ላቀ አያሌው፣ አቶ መላኩ አለበል እና አብርሃም አለኸኝ በሕይወት የተረፉ ናቸው። ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ከሰሞኑ ልዩ ኃይል ሲያስመርቁ የተለየ ወታደራዊ ልብስ መልበስቸውና ያስተላለፉት መልዕክትስ ከግርግሩ ጋር ምን ግንኙነት አለው? አሁንም ምላሽ ያላገኙና ጊዜ የሚጠብቁ ናቸው። የባሕርዳሩ ግርግር እና የጄኔራል ሰዓረ ግድያ ምን አገናኛቸው? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን ሲከታተሉ ነው ቢሉም፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ዝርዝር መረጃ እስኪገኝ ድረስ አጥጋቢ ሆኖ የተገኘ አይመስልም።
xlsum_amharic-train-152
https://www.bbc.com/amharic/49160706
ብሔራዊ አገልግሎት መንፈሳዊ ህይወቱን የነጠቀው ኤርትራዊው ዲያቆን
ተስፋጋብር ባህታ በወጣትነቱ ተመኝቶ ያጣው ሐይማኖታዊ እና መንፈሳዊ አገልግሎት አሁን በልጆቹ እንዲካካስ ፍላጎት አለው። ከ13 ዓመት በፊት የኤርትራ ብሔራዊ አገልግሎት አባል ሳለ ያሳለፈውን ሕይወት በማስታወስ አሁን ኤርትራ በዓለም ማሕበረሰብ የምትከሰስባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲሻሻል፣ የእምነትና ሐይማኖት ነጻነትን ሲከበሩ ማየት ይናፍቃል።
[ "ተስፋጋብር ባህታ በወጣትነቱ ተመኝቶ ያጣው ሐይማኖታዊ እና መንፈሳዊ አገልግሎት አሁን በልጆቹ እንዲካካስ ፍላጎት አለው። ከ13 ዓመት በፊት የኤርትራ ብሔራዊ አገልግሎት አባል ሳለ ያሳለፈውን ሕይወት በማስታወስ አሁን ኤርትራ በዓለም ማሕበረሰብ የምትከሰስባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲሻሻል፣ የእምነትና ሐይማኖት ነጻነትን ሲከበሩ ማየት ይናፍቃል።" ]
የኤርትራ መንግሥት በአገሪቷ የሚሰጠው ወታደራዊ አገልግሎት የተጀመረበት 25ኛ ዓመት በዚህ ሳምንት በደማቅ ሁኔታ ሲያከብር፤ የብሔራዊ አገልግሎቱ ስኬቶችና የዜጎቹን አስተዋጽኦ በብርቱ ቃላት ማሞካሸቱን በማስታወስ፤ "ባለታሪኮቹ እኛ እኮ አለን?" በማለት መንግሥትን አገልግሎቱን ያንቆለጳጰሰበትን መንገድ ይተቻል። • በፍጥነት እየመጣ ወደነበረ ባቡር በኤርትራዊው የተገፈተረው ታዳጊ ህይወቱ አለፈ በጎርጎሳውያኑ 1976 በኤርትራ ደቡባዊ ዞን ኮዓቲት በሚባል ቦታ ተወልዶ ያደገው ተስፋጋብር ይህ አገራዊ የውትድርና አገልግሎት መንፈሳዊ ህይወቱን ቀምቶ እንዴት ወደማያውቀው ዓለም እንደወሰደው በራሱ አንደበት ይናገራል። የቤተክርስትያን አገልጋዮች በውትድርና ሲያገለግሉ በጎርጎሳውያኑ 1995 መንፈሳዊ ትምህርቴን በመማር፤ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የምሯሯጥ የ19 አመት ወጣት የድቁና ተማሪ ነበርኩ። ብዙዎች እንደሚሉኝ ታዛዥ፣ እኩዮቼን የምገስፅ፣ አርዓያ አገልጋይ በመሆኔ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ይወዱኝ ነበር። በአጋጣሚ በዚሁ ዓመትም ህይወቴን የሚቀይር ነገር ተከሰተ። የብዙ ሴት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እና ወንድ ዲያቆናት ስም ዝርዝር የያዘ ወረቀት በየአውራጎዳናዎቹ፣ በየሱቆቹ ለወራት ተለጥፎ ይነበብ ነበር፤ እዚህ የስም ዝርዝር ውስጥ የእኔም ስም ተካቶ ነበር። 'የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወደ ውትድርና!?' ብየ ተደነቅኩኝ፤ ምክንያቱ ምን ይሁን ምን ይህ ለእኔ እንቆቅልሽ ነው። እርግጥ ነው ኤርትራ ባሳለፈችው ረዥም የትጥቅ ትግል ታሪክ ብዙ ዲያቆናትና አባቶች በግድ ተወስደው በረሃ ላይ ቀርተዋል። የእኔም የእዚህ ታሪክ ቀጣይ ክፍል ነበር ማለት ነው። • አምባሳደር ሬድዋን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለምን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አላቀረቡም? • "ኦሮሞ እና ማዳጋስካርን የሚያገናኝ ፖለቲካ እንዳለ አላውቅም" የትነበርሽ ንጉሤ የተጠራንበት ቀን እንደደረሰ ወታደሮች መጥተው እኔና እኩዮቼን በቁጥጥር ስር አዋሉን። በቀኝ ግዛት ጊዜ ያልተደፈሩ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት በእኔ ዘመን ሲደፈሩ ሳይ እያዘንኩኝ ተገድጄ ወደ ብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ሄድኩኝ። በወታደሮች ጥበቃ ከተወሰድኩባት ቀን ጀምሮ ለ11 ዓመታት እዛው አሳለፍኩኝ። በብሔራዊ አገልግሎቱ ላይ ፈጣን ከሆኑት መካከል አንዱ ነበርኩ። አንድም ስህተት ተገኝቶብኝ ተቀጥቼም እስር ቤት ገብቼም አላውቅም። ትንሽ ልጅ ብሆንም ያው በእኔ እድሜ ያለው ወጣት የሚያጋጥመውን "ኢ-ሥነምግባራዊ" የምለውን ሕይወት ለማሳለፍ ተገድጃለሁ። ለብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት በሄድኩበት ወቅት እድሜዬ አፍላ ስለነበር ሱሰኛ ሁኜ ባህሪዬ በሙሉ ተቀይሮ ነበር። በፈጣሪ ፊት የተወገዘ ለሰው ጆሮ የከበደ ነገር ውስጥ ገባሁ። ሳዋ ላይ ከመጥፎ ነገር የሚከላከልህ ነገር የለም። ቤትህ፣ በተለይ ደግሞ ወጣትም ሆነህ መንፈሳዊ ሰው ከሆንክ፣ ቤተሰብህ፣ ወንድሞችህ፣ ህብረተሰቡ በምክር በተግሳጽ ይጠብቁሀል። በዛም ከብዙ ክፉ ነገር ትሰወራለህ። የባድመ ጦርነት ላይ ተሰለፍኩኝ። የጥይት ድምፅ ከማያንቀላፋበት፣ አብረውን የዘመቱ እኩያ ጓደኞቼን ካጣሁበት የባድመ ጦርነት በሕይወት ተርፌ ወደቤተሰቦቼ ተመለስኩኝ። ባድመ ላይ ተማርኬ ስለነበር ደዴሳ ላይ ቆይቼ ሁለቱ አገራት ምርኮኞች ሲለዋወጡ ነበር ወደ ኤርትራ የተመለስኩት። በሕይወቴ የተቸገርኩበት ቀን እንደ ወታደር ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከሰው ጋር ሲዋጋ ያየሁት እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ሰኔ 10 1998 በትግራይ ማቲዎስ ምሽግ የነበረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ተኩስ ስንከፍት ነው። ጦርነቱ ከቀኑ 10 ሰዓት ነበር የተጀመረው። በብዙ መልኩ ስጋት ነበረኝ። እንደፈራሁትም በሕይወቴ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የወደቅኩበት ቀን ነው። ብዙ ሰው እዚያ የጦርነት አውድማ ላይ ቀረ። ያን ቀን ማታ 3፡30 ሰአት ላይ አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ዘንቦ የጦር መሳሪያዎች አንደበት ዝም አለ፤ እኛም ወደ ምሽጋችን ተመለስን። ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት ለማጥቃት በሄድንበት ጊዜ ሳይገባን እናላግጥ ነበር። ሲተረክልን የነበው ጦርነት ደርሶ በአይኔ አየሁት አልኩኝ። ፊታቸው ላይ ስንደርስ ግን ቦንብ እንደቆሎ ተወረወረብን። ጥይት እንደ ዝናብ ተርከፈከፈብን፣ ከፊት ከኋላ ጓደኞቼ ረገፉ። ኦሮማይ! አበቃ! • ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል? እውነት ነው "አገር ተወረረ ሲሉን እምቢ አይባልም ሄድን" ግን ጦርነት ኪሳራ ነው። ከመግደል ውጪ ሌላ አታስብም፤ ጠቅላላ ተቀይረህ ሌላ ሰው ትሆናለህ። እኔም ሌላ ሰው ሆንኩኝ። "ሳልሳይ ወራር" (ፀሐይ ግብዐት ዘመቻ) በምንለው የኢትዮጵያ ሰራዊት ባጠቃበት የመጨረሻው ጦርነት ተማርኬ በህይወት ከቀሩት የሻዕቢያ ሰራዊት አንዱ ነኝ። ከዚያ በኋላ ለ11 ዓመታት ብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ስሰጥ ቆየሁኝ። በደሞዝ፣ በሌላ ሌላ ነገር የሚታይ ዕድገት ባለመኖሩ ተስፋ ቆረጥኩኝ። እኔ ወታደር ነኝ? እስረኛ? የሚል ስሜት ይሰማኝ ነበር። ከኤርትራ መራቅ አለብኝ ብዬም ወሰንኩ። ከዚያም ከኤርትራ መንገድ አሳብሬ ትግራይ ገባሁ፤ ከትግራይ አዲስ አበባ፤ ከአዲስ አበባ እስራኤል። ከኤርትራ አይደለም እጅና እግሬን አየሩንም ይዤ ብወጣ ደስ ባለኝ። ኑሮ በስደት ከተማ በልጅነቴ ሳገለግላት ስለነበረችው ስላሴ ኮዓቲት ቤተክርስቲያን አሁንም እሰማለሁ፤ አባቶቻችን ሁሉም አልፈዋል፤ አገልጋዮችም የሉም። ካሉም ከመንግሥት ፍቃድ ውጪ መሄድ አይችሉም ሲባል እሰማለሁ። ያው የኤርትራ ህዝብ እያሳለፈው ያለውን ሁሉ ቤተክርስቲያኒቱም እያሳለፈች ነው። ልጆቼ አስተምሬ አገልጋዮች እንዲሆኑልኝ እመኛለሁ። መንፈሳዊ ህይወት እና ህብረተሰብ እንዲኖረኝም እፈልጋለሁ። ደግሜ መክሰር አልፈልግም። ብሔራዊ አገልግሎትን ከውጤቱ ስገመግመው ኪሳራ ነበር፤ ችግሩ አገርህን ማገልገል ሳይሆን፤ ወደ ኋላ የመለሰንና ያከሰረን ነው ለማለት እደፍራለሁ።
xlsum_amharic-train-153
https://www.bbc.com/amharic/news-50066506
የዓመቱ የቢቢሲ የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ 100 ሴቶች
ቢቢሲ በአውሮፓዊያኑ 2019 በዓለም ዙሪያ ለሌሎች መልካም ተነሳሽነት የፈጠሩና ተጽእኖ ፈጣሪ ያላቸውን የ100 ሴቶችን ስም ይፋ አድርጓል።
[ "ቢቢሲ በአውሮፓዊያኑ 2019 በዓለም ዙሪያ ለሌሎች መልካም ተነሳሽነት የፈጠሩና ተጽእኖ ፈጣሪ ያላቸውን የ100 ሴቶችን ስም ይፋ አድርጓል።" ]
የዚህ ዓመት ሴት ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ለመለየት በተደረገው ምዘና፤ ዋነኛው ጥያቄ ሆኖ የቀረበው፤ ሴቶች ከፊት ሆነው መምራት ቢችሉ መጪው ዘመን ምን ሊመስል ይችላል? የሚል ነው። በዚህ የዓመቱ የቢቢሲ የዓለማችን ሴት ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ በጦርነት የፈራረሰችውን ሶሪያን መልሶ ለመገንባት እያቀደች ካለች የሥነ ህንጻ ባለሙያ አንስቶ በናሳ ውስጥ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ እስከሆነች ባለሙያ ድረስ ተካተዋል። •"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዝርዝሩ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ በያሉበት የሙያ መስክ ከከፍተኛው ደረጃ ላይ ያሉ ሲሆኑ ከአስር ዓመታት በኋላ ህይወት በምድራችን ላይ ምን ልትመስል እንደምትችል ከሙያቸው አንጻር ትንበያ ሰጥተዋል። ሌሎቹ ደግሞ የማፍያ ቡድንን እየተጋፈጠች ያለች ፖለቲከኛና በሴቶች ላይ ያለውን የተዛባ አመለካከት እየታገለች ያለች እግር ኳስ ተጫዋች የተለየ የህይወት ልምዳቸውን ተጠቅመው ለሚከተሏቸው መንገድ የሚመሩ ሴቶች ናቸው። •የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? ከዓለም ዙሪያ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸው ተብሎ በቢቢሲ የተመረጡት ሴቶች የሚከተሉት ናቸው።. 1) ፕሪሺየስ አዳምስ፣ አሜሪካዊት፣ የባሌ ዳንሰኛ 2) ፓርቪና አሃንገር፣ በህንድ ከምትተዳደረው ካሽሚር፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ 3) ፒየራ አዬሎ፣ ጣሊያናዊት፣ ፖለቲከኛ 4) ጃስሚን አክተር፣ ዩኬ/ባንግላዲሽ፣ የክሪኬት ተጫዋች 5) ማናል አልዶዋያ፣ ሳዑዲ አረቢያዊት፣ አርቲስት 6) ኪሚያ አሊዛዴህ፣ ኢራናዊት፣ የቴክዋንዶ ስፖርተኛ 7) ማርዋ አል ሳቡኒ፣ ሶሪያዊት፣ የሥነ ህንጻ ባለሙያ 8) አላኑድ አልሻሬኪህ፣ ኩዌታዊት፣ የሴቶች መብት ተሟጋች 9) ሪዳ አል ቱቡሊ፣ ሊቢያዊት፣ የሠላም ተሟጋች 10) ታባታ አማራል፣ ብራዚላዊት፣ ፖለቲከኛ 11) ያሊትዛ አፓሪሲዮ፣ ሜክሲኳዊት፣ ተዋናይትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች 12) ዳያና አሽ፣ ሌባኖሳዊት፣ የባህላዊ መብቶች ተሟጋች 13) ዲና አሸር ስሚዝ፣ እንግሊዛዊት፣ አትሌት 14) ሚሚ አውንግ፣ አሜሪካዊት፣ የናሳ ፕሮጀክት ኃላፊ 15) ኒሻ አዩብ፣ ማሌዢያዊት፣ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ተሟጋች 16) ጁዲት ባክሪያ፣ ኡጋንዳዊት፣ አርሶ አደር 17) አያህ ብዲር፣ ሌባኖሳዊት፣ ሥራ ፈጣሪ 18) ዳማናንዳ ቢኹኒ፣ ታይላንዳዊት፣ መነኩሴ 19) ማቤል ቢያንኮ፣ አርጀንቲናዊት፣ የህክምና ዶክተር 20) ራያ ቢድሻሂር፣ ኢራናዊት፣ የትምህርት ባለሙያ 21) ካቲ ቦማን፣ አሜሪካዊት፣ ሳይንቲስት 22) ሲናድ በርክ፣ አየርላንዳዊት፣ የአካል ጉዳተኞች መብት ተከራካሪ 23) ሊሳ ካምፖ-ኢነግለስቲን፣ አሜሪካዊት፣ የሥነ ህይወትና ሥነ ምግባር ባለሙያ 24) ስካርሌት ከርትስ፣ እንግሊዛዊት፣ ጸሐፊ 25) ኤላ ዳይሽ፣ እንግሊዛዊት፣ የተፈጥሮ አካባቢ ተመራማሪ 26) ሻራን ዳሊዋል፣ እንግሊዛዊት፣ ጸሐፊና አርቲስት 27) ሳልዋ ኢድ ናስር፣ ናይጄሪያ/ባህሬን፣ አትሌት 28) ራና ኤል ካሉቢ፣ ግብጻዊት፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀነስ ባለሙያ 29) ማሪያ ፈርናንዳ ኤስፒኖሳ፣ ኤኳዶራዊት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት 30) ሉሲንዳ ኢቫንስ፣ ደቡብ አፍሪካዊት፣ የሴቶች መብት ተሟጋች 31) እህት ጄራርድ ፈርናንዴዝ፣ ሴንጋፖራዊት፣ የሮማ ካቶሊክ መነኩሴ 32) ቤታኒ ፊርዝ፣ እንግሊዛዊት፣ አካል ጉዳተኛ የዋና ስፖርተኛ 33) ኦውል ፊሸር፣ አይስላንድ፣ ጋዜጠኛና የጾታዊ መብቶች ተሟጋች 34) አሽሊ-አን ፍራዘር-ፕራይስ፣ ጃማይካዊት፣ አትሌት 35) ዛሪፋ ጋፋሪ፣ አፍጋኒስታናዊት፣ ከንቲባ 36) ጃሊላ ሃይደር፣ ፓኪስታናዊት፣ ጠበቃ 37) ታይላ ሃሪስ፣ አውስትራሊያዊት፣ እግር ኳስ ተጫዋችና ቦክሰኛ 38) ሆሊ፣ አሜሪካዊት፣ ከወሲባዊ ጥቃት ያመለጠች 39) ሁጋን ዌንሲ፣ ቻይናዊት፣ ቦክሰኛ 40) ሉቺታ ሁርታዶ፣ ቬኔዙዌላዊት፣ አርቲስት 41) ዩሚ ኢሺካዋ፣ ጃፓናዊት፣ የመብት ተሟጋች 42) አስማ ጄምስ፣ ሴራ ሊዮናዊት፣ ጋዜጠኛና የመብት ተሟጋች 43) አራንያ ጆሃር፣ ህንዳዊት፣ ገጣሚ 44) ካትሪና ጆንስተን፣ አሜሪካዊት፣ አንትሮፖሎጂስት 45) ጋዳ ካዶዳ፣ ሱዳናዊት፣ መሀንዲስ 46) ኤሚ ካርል፣ አሜሪካዊት፣ የሥነ ህይወት አርቲስት 47) አህላም ኹድር፣ ሱዳናዊት፣ የተቃውሞ መሪ 48) ፊዮና ኮልቢንገር፣ ጀርመናዊት፣ ብስክሌተኛ 49) ሂዮሪ ኮን፣ ጃፓናዊት፣ የጃፓን ነጻ ትግል ስፖርተኛ 50) አይሳታ ላም፣ ሞሪታኒያዊት፣ የጥቃቅን የገንዘብ ተቋማት ባለሙያ 51) ሱ የንግሊ፣ ደቡብ ኮሪያዊት፣ ሳይኮሎጂስት 52) ፊ ፊ ሊ፣ አሜሪካዊት፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ባለሙያ 53) ኤሪካ ለስት፣ ስዊዲናዊት፣ የፊልም ባለሙያ 54) ሎሪን ማሆ፣ እንግሊዛዊት፣ ከካንሰር የዳነች 55) ጁሊ ማካኒ፣ ታንዛኒያዊት፣ ተመራማሪና ዶክተር 56) ሊሳ ማንዲማከር፣ ኔዘርላንዳዊት፣ ዲዛይነር 57) ጄሚ ማርጎሊን፣ አሜሪካዊት፣ የአየር ጸባይ ለውጥ ተሟጋች 58) ፍራንሲያ ማርኬዝ፣ ኮሎምቢያዊት፣ የተፈጥሮ አካባቢ ባለሙያ 59) ጊና ማርቲን፣ እንግሊዛዊት፣ የመብት ተሟጋች 60) ሳራ ማርቲንስ ዳ ሲልቫ፣ እንግሊዛዊት፣ የማህጸንና ጽንስ አማካሪ 61) ራጂ ሜዚያን፣ አልጄሪያዊት፣ ድምጻዊ 62) ሱስሚታ ሞሃንቲ፣ ህንዳዊት፣ የህዋ ሥራ ፈጣሪ 63) ቤኔዲክት መንዴል፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ፣ የምግብ ባለሙያ 64) ሱባላክሽሚ ናንዲ፣ ህንዳዊት፣ የጾታ እኩልነት ባለሙያ 65) ትራንግ ንጉየን፣ ቬትናማዊት፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ 66) ቫን ታይ ንጉየን፣ ቬትናማዊት፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚና፣ የአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋች 67) ናታሻ ኖኤል፣ ህንዳዊት፣ የዮጋ ባለሙያ 68) አሌክሳንድሪያ ኦካሲዮ-ኮርቴዝ፣ አሜሪካዊት፣ የምክር ቤት አባል 69) ፋሪዳ ኦስማን፣ ግብጻዊት፣ ዋናተኛ 70) አሻሪያ ፔሪስ፣ ሲሪ ላንካዊት፣ ዲዛይነር 71) ዳኒት ፔሌግ፣ እስራኤላዊት፣ ዲዛይነር 72) ኦተም ፔልቲየር፣ ካናዳዊት፣ የንጹህ ውሃ አቅርቦት መብት ተከራካሪ 73) ስዌቲኒያ ፐስፓ ሌስታሪ፣ ኢንዶኔዢያዊት፣ የተፈጥሮ አካባቢ ባለሙያና ሾፌር 74) ሜጋን ራፒኖ፣ አሜሪካዊት፣ እግር ኳስ ተጫዋች 75) ኦንጃሊ ራኡፍ፣ እንግሊዛዊት፣ ጸሐፊ 76) ቻርሊን ሬን፣ ቻይናዊት፣ የንጹህ ውሃ አቅርቦት መብት ተከራካሪ 77) ማሪያ ሬሳ፣ ፊሊፒናዊት፣ ጋዜጠኛ 78) ጃሚላ ሪቤሮ፣ ብራዚላዊት፣ ጸሐፊና የእኩልነት ተሟጋች 79) ጃዋሂር ሮብሌ፣ እንግሊዝ/ሶማሊያዊት 80) ነጃት ሳሊባ፣ ሌባኖሳዊት፣ የኬሚስትሪ ፕሮፌሰር 81) ናንጂራ ሳምቡሊ፣ ኬንያዊት፣ የዲጂታል እኩልነት ባለሙያ 82) ዚሃራ ሳየርስ፣ ቱርካዊት፣ ሳይንቲስት 83) ሃይፋ ስዲሪ፣ ቱኒዚያዊት፣ ሥራ ፈጣሪ 84) ኑር ሼከር፣ ሶሪያዊት፣ የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያ 85) ቦኒታ ሻርማ፣ ኔፓላዊት፣ የፈጠራ ባለሙያ 86) ቫንዳና ሺቫ፣ ህንዳዊት፣ የተፈጥሮ አካባቢ ባለሙያ 87) ፕራጋቲ ሲንግ፣ ህንዳዊት፣ ዶክተር 88) ሉቦቭ ሶቦል፣ ሩሲያዊት፣ ጠበቃ 89) ሳማህ ሱቤይ፣ የመናዊት፣ ጠበቃ 90) ካሊስታ ሲ፣ ሴኔጋላዊት፣ የፊልም ጸሐፊና ፕሮዲዩሰር 91) ቤላ ቶርን፣ አሜሪካዊት፣ ተዋናይና አዘጋጅ 92) ቬሮኒክ ቱቬኖት፣ ቺሊያዊት፣ ዶክተር 93) ግሬታ ተንበርግ፣ ስዊዲናዊት፣ የአየር ጸባይ ለውጥ ተሟጋች 94) ፓውላ ቪላሪያል፣ ሜክሲኳዊት፣ የኮምፒውተር ፕሮግራም ቀማሪ 95) ኢዳ ቪታሊ፣ ኡራጓያዊት፣ ገጣሚ 96) ፒዩሪቲ ዋኮ፣ ኡጋንዳዊት፣ የህይወት ተሞክሮ አሰልጣኝ 97) ማሪሊን ዋሪንግ፣ ኒው ዚላንዳዊት፣ ኢኮኖሚስትና የተፈጥሮ አካባቢ ጥበዋ 98) ኤሚ ዌብ፣ አሜሪካዊት፣ እየተከናወኑ ባሉ ነገሮች ላይ በመመርኮዝ ስለሚጪው ዘመን የምትተነብይ 99) ሳራ ዌስሊን፣ ፊንላንዳዊት፣ ጋዜጠኛ 100) ጊና ዙርሎ፣ አሜሪካዊት፣ የሃይማኖት ምሁር
xlsum_amharic-train-154
https://www.bbc.com/amharic/news-51237836
ፖስተኛው 24 ሺህ ደብዳቤዎችን በቤቱ ደብቆ ተገኘ
የጃፓን የቀድሞ ፖስተኛ የነበረ ግለሰብ ለሰዎች መድረስ የነበረባቸው 24 ሺህ ደብዳቤዎችን ወደ ታለመላቸው አድራሻ በመላክ ፋንታ በቤቱ ደብቆ ማስቀመጡን በምርመራ እንደደረሰበት ፖሊስ አስታወቀ።
[ "የጃፓን የቀድሞ ፖስተኛ የነበረ ግለሰብ ለሰዎች መድረስ የነበረባቸው 24 ሺህ ደብዳቤዎችን ወደ ታለመላቸው አድራሻ በመላክ ፋንታ በቤቱ ደብቆ ማስቀመጡን በምርመራ እንደደረሰበት ፖሊስ አስታወቀ።" ]
ደብዳቤዎቹ የተገኙት ቶኪዮ አቅራቢያ ካናጋዋ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው የ61 ዓመቱ የቀድሞ ፖስተኛ ቤት በተፈተሸበት ወቅት ነው። ፖስታዎቹን ማድረስ አድካሚ ስለሆነበትና በእድሜ ከእሱ ከሚያንሱ ፖስተኞች ጋር ሲነፃፀር ደካማ ሆኖ ላለመታየት ሲል ፖስታዎቹን ቤቱ እንዳስቀራቸው ተናግሯል ግለሰቡ። • ጃፓናዊው ቢሊዬነር ወደ ሕዋ አብራው የምትጓዝ 'ውሃ አጣጭ' እየፈለገ ነው • ጃፓን ከቀበሌ መታወቂያ ያነሰች ሞባይል ሠራች ግለሰቡ የቅርንጫፍ ሃላፊ ሆኖ ይሰራበት የነበረው 'ኮዮዶ ኒውስ' ባለፈው ዓመት ተጠራጥሮ ነገሮችን ለማጣራት ሲሞክር ግለሰቡ ጥፋቱን በማመኑ ከሥራ አባሮታል። ይህን ተከትሎም ግለሰቡ ላይ አንድ ሺህ ፖስታዎችን በማጥፋት ክስ ተመስርቷል። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ፖስተኛው ለፉት 17 ዓመታት ፖስታዎችን በቤቱ ሲያስቀምጥ ነበር። ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ሶስት ዓመት እስር እና አራት ሺህ ስድስት መቶ ዶላር ቅጣት ይጠብቀዋል እየተባለ ነው።
xlsum_amharic-train-155
https://www.bbc.com/amharic/sport-45401974
ሞሃመድ ሳላህ በፊፋ ምርጥ የወንድ ተጫዋች የመጨረሻ ሶስት ውስጥ ገባ
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፤ ሉካ ሞድሪች እና ሞሃመድ ሳላህ የፊፋ የ2018 ምርጥ የወንድ ተጫዋች ምርጫ የመጨረሻ ሶስት ውስጥ ገብተዋል። የባርሴሎና እና የአርጀንቲና አጥቂ እንዲሁም የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻ ሶስት እጩዎች ውስጥ መግባት ሳይችል ቀርቷል።
[ "ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፤ ሉካ ሞድሪች እና ሞሃመድ ሳላህ የፊፋ የ2018 ምርጥ የወንድ ተጫዋች ምርጫ የመጨረሻ ሶስት ውስጥ ገብተዋል። የባርሴሎና እና የአርጀንቲና አጥቂ እንዲሁም የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻ ሶስት እጩዎች ውስጥ መግባት ሳይችል ቀርቷል።" ]
የአለም ዋንጫን ካነሳው የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንም ምንም አይነት ተጫዋች መግባት አልቻለም። ከሊዮን ጋር የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳት የቻሉት የኖርዌዩዋ ኣዳ ሄገርበርግ እና ጀርመናዊቷ ዜኒፈር ማሮዝሳን እንዲሁም የብራዚሏ አጥቂ ማርታ በፊፋ የሴቶች ምርጥ ተጫዋች ዘርፍ የመጨረሻ ሶስት ውስጥ መግባት ችለዋል። የፖርቹጋሉ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሮናልዶ እ.አ.አ የ2016 እና 2017 የፊፋ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠ ሲሆን፤ ከሪያል ማድሪድ ጋር ደግሞ አምስት ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ አሸንፏል። • በሳምንቱ የጋሬዝ ክሩክስ ቡድን ውስጥ እነማን ተካተዋል? • ዘጠኝ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ታሰሩ ያልተዘመረለት ጀግና የሚባለው የሪያል ማድሪዱ ድንቅ አማካይ ሉካ ሞድሪች የ2018 የአለም ዋንጫ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል። በወቅቱም ከፈርንሳይ ጋር ለፍጻሜ ቢደርሱም፤ በፈረንሳይ አራት ለሁለት ሽንፈት ደርሶባቸዋል። የግብጹ አጥቂ ሞሃመድ ሳላህ ደግሞ ቡድኑ ሊቨርፑል በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ለፍጻሜ ደርሶ በሪያል ማድሪድ በተሸነፈበት የውድድር ዓመት 44 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የአውሮፓ ምርጥ ወንድ ተጫዋች ምርጫ ሞድሪች፤ ሮናልዶ እና ሞሃመድ ሳላህን በመብለጥ አሸናፊ መሆን ችሎ ነበር። የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን ለአለም ዋንጫ ድል ያበቃው የቀድሞ ተጫዋች የአሁኑ አሰልጣኝ ዲዲዬር ዴሾ፤ ክሮሺያን በአለም ዋንጫው ለፍጻሜ ያደረሰው አሰልጣኝ ዝላትኮ ዳሊች እና የቀድሞው የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን በምርጥ አሰልጣኝነት እጩ ውስጥ ተካተዋል። እ.አ.አ በ2016 ፊፋ ከባሎንዶር ሽልማት ጋር ያለውን ግንኙነት ካቋረጠ በኋላ ሽልማቱ ለብቻው መካሄድ ጀምሯል። • ቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ማን ይሆን? • የሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ለመሆን የሚያስችለው ሥነ-ልቦና በፊፋ የተወከሉ ታዋቂ ተጫዋቾችና ባለሙያዎች በእያንዳንዱ የሽልማት ዘርፍ በመጀመሪያው ዙር አስር ተጫዋቾችን በእጩነት ያቀርባሉ። በመቀጠል እያንዳንዳቸው 25 በመቶ ድምጽ ያላቸው ከብሄራዊ ቡድን አምበሎች፤ አሰልጠኞች፤ ስፖርት ጋዜጠኞች እና ደጋፊዎች የተውጣጣ የዳኞች ስብስብ አሸናፊውን ይመርጣል። ከዚህ በተጨማሪ ሮናልዶ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ጁቬንቱሳ ላይ በመቀስ ምት ያስቆጠራት ግብ እና የማድሪዱ አጥቂ ጋሬዝ ቤል በፍጻሜው ጨዋታ ሊቨርፑል ላይ ያስቆጠራት ተመሳሳይ የመቀስ ምት ግብ በምርጥ ጎል ዘርፍ ከታጩት አስር ግቦች መካከል መሆን ችለዋል። አሸናፊዎቹ እ.አ.አ በመስከረም 24 ለንደን ውስጥ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል።
xlsum_amharic-train-156
https://www.bbc.com/amharic/news-50094859
እሷ ማናት? #1: ፈቲያ መሐመድ ከዐረብ ሃገር ኑሮ ወደ ስኬታማ የግብርና ሥራ
በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ጫናዎች ምክንያት ሴቶች ውጣ ውረዶች ይገጥሟቸውና ከሚዘፈቁባቸው ችግሮች ደግሞ ሳይወጡ የሚዘልቁም ይኖራሉ። የፈቲያ መሐመድ ተሞክሮ ግን ከብዙዎች ለየት ያለ ነው። ፈቲያ በምሥራቅ ሐረርጌ በባቢሌ ወረዳ፤ በየረር ወንዝ ዙሪያ በግብርና ሥራ ላይ ተሰማርታ ትገኛለች. . .
[ "በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ጫናዎች ምክንያት ሴቶች ውጣ ውረዶች ይገጥሟቸውና ከሚዘፈቁባቸው ችግሮች ደግሞ ሳይወጡ የሚዘልቁም ይኖራሉ። የፈቲያ መሐመድ ተሞክሮ ግን ከብዙዎች ለየት ያለ ነው። ፈቲያ በምሥራቅ ሐረርጌ በባቢሌ ወረዳ፤ በየረር ወንዝ ዙሪያ በግብርና ሥራ ላይ ተሰማርታ ትገኛለች. . ." ]
እሷ ማናት? #1: ፈቲያ መሐመድ ከዐረብ ሃገር ኑሮ ወደ ስኬታማ የግብርና ሥራ ሰሜ ፈቲያ መሐመድ ነው፤ የተወለድኩትም በምሥራቅ ሐረርጌ በባቢሌ ወረዳ ሲሆን በ12 ዓመቴ ቤተሰቦቼ ለአንድ ዐረብ ዳሩኝ። ይህ ከሳዑዲ ዐረብያ የመጣው ሰው ብዙ ገንዘብ ነበረው። እዚያም ለ28 ዓመታት ኖርኩኝ። በ28 ዓመታት ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ የተመለስኩት ሁለት ጊዜ ብቻ ነበር። ያንን ሁሉ ጊዜ ዐረብ ሃገር ስኖር ስለ ኢትዮጵያ ጥሩ ነገር ሰምቼ አላውቅም። ኢትዮጵያን በረሃብና በስቃይ ነው የሚገልጿት። እኔንም 'ከረሃብ ሃገር ነው የመጣሽው' ሲሉኝ ውስጤ በጣም የይታመም ነበር። እኔ ግን ሃገሬን የማውቃት በተፈጥሮ ሃብት የተሸለመች በመሆኗ ነው። ስለ ድህነቴ በሚሰድቡኝ ጊዜ በዓይኔ የሚሄድብኝ ዙሪያው ለምለም የሆነው ቀዬ ነው። ሃገራቸው አሸዋ እንጂ ለሰብል የሚሆን መሬት እንኳን የለም። ከአሸዋው ውስጥ የሞቀ ውሃ አውጥተው አቀዝቅዘው እና አፈር ደግሞ ከሌላ ሃገር እያሰመጡ ነው የሚጠቀሙት። ሃገሬ ግን በተሄደበት ቦታ ሁሉ የተሰጣትን የምታፈራ ሃገር ናት። ይህም ነው ለሁሉም ነገር መነሻ የሆነኝ። የቅንጦት ኑሮ ትቼ ገንዘቤን መቋጠር ጀመርኩኝ። እጄ የሚገባውን ገንዘብ በሙሉ እቀብረው ነበር። በዚህ መልኩ ብሬን ሰብስቤ ወደ 20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ሲጠጋልኝ ቀልቤ ወደ 'ሃገርሽ ተመልሽ' አለኝ። ብሬን ቋጥሬ ወደዚህ ለመምጣት በቆረጥኩበት ሰዓት የኢትዮጵያ መንግሥት ሰው በሃገሩ ሠርቶ እንዲበለጽግ ጥሪ እያቀረበ ነበር። እኔም ያንን ዕድል በመጠቀም ማድረግ ስለምፈልገው ኢንቨስትመንት ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በደብዳቤ ጥያቄዬን አቀረብኩኝ። በኢትዮጵያ መንግሥት ጋባዥነት በ1998 ዓ.ም ወደ ሃገር ቤት ተምልሼ ለሥራዬ ሁኔታዎችን አመቻቸሁኝ። በ1999 ወደ ኢትዯጵያ ስመለስ መንግሥት አዲስ አበባ አካባቢ ኢንቨስት እንዳደርግ መሬት ሰጥቶኝ ነበር። እኔ ግን በተወለድኩበት አካባቢ ነበር ለውጥ ማምጣት የምፈልገው። የተቸገረን መርዳት፣ የተጠማን ማጠጣትና የተራበን ማብላት ትልቁ ሕልሜ ነበር። መንግሥት ግን 'አንቺ ሴት ነሽ፣ ብዙ ገንዘብም ይዘሻል። መሬት ሰጥተንሽ እዚሁ አዲስ አካባቢ ብትሆኚ ነው የሚሻለው' አለኝ። "ወይ እንደ እኔ ትሆናላችሁ ወይ እንደ እናንተ እሆናለሁ" የተወለድኩበት አገር ህዝብ ውሃ ላይ ተኝቶ ይጠማል፣ ለም አፈር ላይ ተቀምጦ ይራባል። ለዚህ ነው ይህንን ሕዝብ መጥቀም እንደምፈልግ ለመንግሥት ያሳወቅኩት። ሆዴን በጣም የሚበላው ነገር የባቢሌና የሐረርጌ ሕዝብ ወንዝ በመንደሩ እያቋረጠ መጠማቱ ነው። እንደ እነ ግብፅ፣ ሱዳንና ሳዑዲ ዐረብያ ያሉ አገራትን አይቼም እውቀት ቀስምያለሁ። ባገኘሁትም ልምድ የአገሬን ሕዝብ ኑሮ መቀየር እንደምችል አምን ነበር። መጀመሪያ ወደ ባቢሌ ስመጣ ምድሩ አቀቅበትና ቁልቁለት እንዲሁም ጋራና ገደል የበዛበት ነበር። ሰዎች በቆሎ ከሚያበቅሉባቸው ትንንሽ ማሳዎች ውጪ ምንም አልነበረም። በወቅቱ ከፌዴራል እስከ ወረዳ ያሉ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮች ድጋፍ አድርገውልኛል። ከመጣሁ ጊዜ አንስቶ የመንግሥት ልማት ቢሮ የሞራል ድጋፍ በማድረግ ለስኬቴ ምክንያት ሆኗል። የኤረር ወንዝ ባለበት አካባቢ መሬት ከተፈቀደልኝ ወዲህ ከውጪ ሃገር ትራክተሮችንና የእርሻ መሣሪያዎችን በማስመጣት ሥራውን አንድ ብዬ ተያያዝኩት። ያንን ጋራና ገደል ደልድሎ የእርሻ መሬት ማድረግ በጣም ከባድ ነበር። ዶዘርና ግሬደር በ2 ሚሊዮን ብር ተከራይቼ ቦታውን ሜዳ አደረግኩት። መሬቱን ካደላደልኩኝ በኋላ እንዴት ዉሃ ከከርሰ ምድሩ ማውጣት እንደምችል ማሰብ ጀመርኩኝ። ይህንን ያስበኩት ደግሞ ለእራሴ ብቻ ሳይሆን ለሕዝቡም ብዬ ነበር። ውሃ በማውጣት ልምድ ያላቸውን ሰዎች ከሱዳን በማምጣት ማሠራት ጀምረኩ። ይህን ሳደርግ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፍቃድ አውጥቼ እና እነርሱን በዶላር ከፍዬ ነበር። እነርሱም በአንድ ቀን ውስጥ ከጉድጓድ ውሃ ማውጣት ይችሉበታል። እግረ መንገዳቸውን 50 ወጣቶችን እንዲያሰለጥኑ አደረግኩኝ። ሥልጠናውን የወሰዱት ወጣቶችም በአካባቢው ላሉ ብዙ ሰዎች ዉሃ አውጥተዋል። በዚህ አጋጣሚ የባቢሌ አካባቢ ሰዎች ይገጥማቸው የነበረው የውሃ ችግር ተፈቷል ለማለት ይቻላል። ለእኔ ሕዝቤን ውሃ ማጠጣት ትልቅ ደስታ ነው። ውሃ በማግኘቴ እኔም ማሳዬን አስፍቼ እያለማሁ ነው። እስካሁን 5ሺህ ማንጎ፣ 5ሺህ ብርቱካን፣ 30 ሺህ ፓፓዬ፣ 1ሺህ ዜይቱን፣ 2200 ቡና እና 2 ሺህ ሽፈራው (ሞሪናጋ) የሚባል ዘር ተክያለሁ። የዚህ አካባቢ ሰው ንፁህ የመጠጥ ውሃ በማግኘቱ ተጠቅሟል። ደግሞም በማሳዬ መሥራት መተዳደሪያቸው የሆነላቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የተወጣጡ ሰዎች ይሠሩበታል። እስካሁን 100 የሚሆኑ ሰዎች ይሰራሉ፤ በቋሚነት ደግሞ ከ60 እስከ 70 የሚሆኑ ሰዎች በዚህ ማሳ ይሠራሉ። ቤተሰብ አፍርተው እዚሁ የሚኖሩም ብዙ ናቸው። በአጠቃላይ የአካባቢው ሕዝብ ማሳውን እንደራሱ ንብረት ነው የሚጠቀምበት። በተለይ ሴቶች እንደፈለጉ አምርተውና ሽጠው እንዲጠቀሙ ፈቅጄላቸዋለሁ። እስካሁንም በሠራኋቸው ሥራዎች ዋንጫና ሜዳልያ ጨምሮ ብዙ ሽልማቶች ተሰጥተውኛል። ሕዝብ በተፈናቀለበት ጊዜ ረብሻ ስለነበረ ሥራችን ላይ እንቅፋት ገጥሞን የነበረ ቢሆንም ሥራችንን ግን አላቋረጥንም ነበር። አሁን ሕዝብ የሚጠቀምበት አንድ የጭነት ፒክ አፕ እና አንድ አይሱዙ አለኝ። እኔ ደግሞ የእራሴ የቤት መኪና እና ደረጃውን የጠበቀ ቤት በዚሁ በማሳዬ መካከል ሠርቼ እየኖርኩኝ ነው። ልጆቼ በሙሉ በሳዑዲ ዐረብያ የእራሳቸውን ቤተሰብ መሥርተው እየኖሩ ነው። ባለቤቴ ሞቷል። ልጆቼና የባለቤቴ ዘመዶች መጥተው ማሳዬን በጎበኙ ጊዜ በኢትዮጵያ እንደዚህ ዓይነት ቦታ አለ ብሎ ለማመን ከብዷቸው በጣም ተደንቀው ነበር። የያዝኩት ማሳ ሰፊ ነው። ስለዚህ ዓላማዬ ይህንን ሰፊ ማሳ መሙላት፣ እያለሙ መንከባከብ እና በብዛት ለገበያ ማቅረብ ነው። ቀጥዬም ፋብሪካ አቋቁሜ ከፍራፍሬዎቹ የተለያዩ ምርቶች ማውጣት ነው። እዚያው ማሳዬም ላይ ለፋብሪካው የሚሆን ቦታ አስቀምጫለሁ። ለሴቶች አስረግጬ መንገር የምፈልገው ሁሉን ነገር የመሥራት ችሎታ እንዳላቸው ነው። ቆርጠው ከተነሱ ደግሞ ማንኛውንም ነገር ከግብ ማድረስ እንደሚችሉ አምናለሁ። አብዛኛዎቹ ግን ብከስርስ ብለው በመስጋት ያመነታሉ። አንድን ሥራ ሳትጅምሪው ለፍርሃት እጅ ከሰጠሽ በጭራሽ ስኬታማ መሆን አይቻልም። ስለዚህ ሴቶች ቆራጥ፣ በእራሳቸው የሚተማመኑ እና ጠንካራ አቋም ካላቸው የሚፈልጉበት ቦታ ይደርሳሉ። የምንሠራውንና ወደ ስኬታችን የሚያሻግሩንን ነገሮች ለይተን ማወቅ አለብን። በተለይ ዐረብ ሃገር የሚኖሩ ሴቶች እዚያ መዝናናቱን ትተው ለወደፊታቸውና ለሃገራቸው የሚጠቅማቸውን ነገር ለመሥራት ማቅድ ይኖርባቸዋል፤ ለነገ ማሰብ አለባቸው። እሷ ማናት? የሚለው ጥንቅራችን ያሰቡበትን ዓላማ ለማሳካት ብዙ ውጣውረዶችን ያሳለፉ ሴቶችን ታሪክ የምናስቃኝበት ነው።
xlsum_amharic-train-157
https://www.bbc.com/amharic/news-49725751
እንደ ግለሰብ የኢትዮጵያዊነት ግዴታን እንዴት መወጣት ይቻላል?
ይህ ጥያቄ ምናልባት እ.አ.አ በ1961 የዚያን ጊዜው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩትን የጆን ኤፍ ኬኔዲን የመጀመሪያ ንግግር ያስታውስ ይሆናል። እሱም "ስለዚህ ውድ [የሃገሬ] ሰዎች ሃገሬ ለእኔ ምን ታደርግልኛለች ብላችሁ ሳይሆን ለሃገሬ ምን ላድርግላት ብላችሁ ጠይቁ" ያሉትን ነው።
[ "ይህ ጥያቄ ምናልባት እ.አ.አ በ1961 የዚያን ጊዜው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩትን የጆን ኤፍ ኬኔዲን የመጀመሪያ ንግግር ያስታውስ ይሆናል። እሱም \"ስለዚህ ውድ [የሃገሬ] ሰዎች ሃገሬ ለእኔ ምን ታደርግልኛለች ብላችሁ ሳይሆን ለሃገሬ ምን ላድርግላት ብላችሁ ጠይቁ\" ያሉትን ነው።" ]
የ'ሳውዝ ሳውዝ ዊሜን' ውይይት መድረክ ላይ ከተለያዩ የዓለም ደቡብ ክፍሎች የተወጣጡ 8 ሴቶች መካከል ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። እንደ ግለሰብ የዜግነት ግዴታን እንዴት መወጣት ይችላል? ቀለል ባለ መልኩ 'ሳውዝ ሳውዝ ዊሜን' በሚል ስያሜ በናይሮቢ ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ከተለያዩ የዓለማችን ደቡባዊ ክፍል ከተወጣጡ 8 ሴቶች መካከል ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። • ከነፍስ የተጠለሉ የዘሪቱ ከበደ ዜማዎች ሃና ፀጋዬ ለሃገሯ አልፎም ለአካባቢዋ የተሻሉ ነገሮችን ለመሥራት እየጣረች ያለች ጠንካራ ሴት ነሽ ተብላ ወደ ኬንያ ተጋብዛ ነበር። ሃገሯን ወክላ የ'ሳውዝ ሳውዝ ዊሜን ሌጋሲ ቶክስ' የተባለው የውይይት መድረክ መክፈቻ ላይ ተገኝታ በአሁን ሰዓት እየሠራች ያለቻቸውንና ወደፊት ደግሞ ለመሥራት የምታቅዳቸውንም አካፍላለች። "መንግሥት ምን ይሥራ ብቻ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ምን ዓይነት አስተዋጽዖ ማድረግ አለብን ብለን ማሰብ ያስፈልጋል" የምትለው ሃና ወደፊት በኢትዮጵያ የገጠር ክፍሎች ውስጥ የሚሰጠውን የትምህርት ደረጃ ከፍ የማድረግ ሕልም እንዳላት ትናገራለች። አክላም "በግለሰብ ደረጃ በተለያየ ዘርፍ እየተሰማራን የዜግነት ግዴታችንን የምንወጣበትንና የሃገራችንን የተለያዩ ችግሮች የምንቀርፍበትን መንገድ መወያየትና መፍትሔ የማምጣት ግደታ አለብን" ትላለች። • ከባህላዊ ጃንጥላ እስከ እንጀራ ማቀነባበሪያ፡ የ2011 አበይት ፈጠራዎች በአሁን ሰዓት ጠንክራ እየሠራች ያለችው የኢትዮጵያን የመድሃኒት ዘርፍ ለማሻሻል ሲሆን ቢኒፋርማ ፒ.ኤል.ሲ የተሰኘ የመድሃኒት ማምረቻ አቋቁማ በዓመት ጊዜ ውስጥ ሥራ ለመጀመር ከመንግሥት ጋር ንግግር ላይ እንደሆነች ትናገራለች። ሃና የቢኒ ፒ.ኤል.ሲ የሥራ ሂደት ኃላፊ ስትሆን ያላትን ልምድ ተመርኩዛ "ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት መድሃኒቶች አብዛኛውን ጊዜ ደረጃቸውን የጠበቁ አይደሉም። ጥሩ መድሃኒት ለማግኘት ደግሞ ገንዘብ ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ ትክክል ነው ብዬ አላምንም ምክንያቱም ሁሉም ግለሰብ ደረጃውን የጠበቀ መድሃኒት የማግኘት መብት አለው" ትላለች። ሃና ፀጋዬ ሌላኛዋ ተሳታፊ ሳምራዊት ሞገስ የአስጎብኚ ድርጅት ባለቤት ናት። ከዚህ በተጨማሪ በእርሻ ተሰማርታለች። አበቦችና የአተር ዓይነቶችን በማምረት ወደ ሆላንድ በመላክ ትተዳደራለች። ሳምራዊት በ'ሳውዝ ሳውዝ ዊሜን' ተገኝታ ተሞክሮዋን እንድታካፍል የተደረገው ተቀጣሪ ሆነው በእርሷ ሥር የሚሠሩት አብዛኛዎቹ ሴቶች በመሆናቸው ነው። ሳምራዊት ከምታስተዳድራቸው 600 ሠራተኞች 90 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው። ለምን ስትባል "ለሴቶች ያለነው ሴቶች ነን" ብላ እንደምታምን ትናገራለች። • "ስተዳደር የቆየሁት በዋናነት ለመለስ በሚሰጠው የጡረታ ገቢ ብቻ ነው" ወ/ሮ አዜብ መስፍን ሠራተኞቿ በሚወልዱበት ጊዜ የነበራቸውን ሥራ እንዲያቆሙ ወይም ደግሞ ወልደው ሲመለሱ እንደ አዲስ እንዲጀመሩ መገደዳቸውን ተመልክታ ይህንን እውነታ ለመቀየር ስትል እያጠቡ ወደ ሥራ ገበታቸው እንደሚላለሱ በመፍቀድ ኑሯቸው ሳይጎሳቆል መቀጠል የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸቷን ትገልጻለች። "በአካባቢያችን ያሉትን ክፍተቶች ለይቶ በማወቅ ለመሸፈን መጣራችን አስፈላጊ ነው። እኔ ኢትዮጵያን ከልብሴ በተጨማሪ በሥራዬም ማስጠራት እፈልጋለሁ" የምትለው ሳምራዊት በማንኛውም ዘርፍ የተሰማራ ሰው የአቅሙን የመሥራቱን ጠቀሜታ ታጎላለች። ሳምራዊት አክላም "ሴቶች ስንደጋገፍ ብዙ ነገሮችን ማሳካት እንደምንችል አምናለሁ። ሴት ፕሬዚዳንቷን ኢትዮጵያ ስትሾም ውጪ የምትማረው ልጄ ማመን አቅቷት ደስታዋን ገልፃልኝ ነበር። ሆኖም ግን ሴት ብቻ ስለሆንን መሆን የለበትም፤ የሥራ ዕድል የሚሰጠን ለሥራው መሆን አለበት" በማለት ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች እኩል ዕድል የመስጠቱን አስፈላጊነት ታጠብቃለች። • “ጭኮ እወዳለሁ” ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የዚህ 'ሳውዝ ሳውዝ ዊሜን' የውይይት መድረክ መስራች ዛይና 'አፍሪካ' ከኬንያ ስትወጣ የነበራት ሕልም ከዓለም የተለያዩ ክፍል የተወጣጡ ሴቶችን በአንድ ላይ በማገናኘት ሁሉም የሚማማርበትን መድረክ መፍጠር ነበር። ዛይናም ሃሳቡ ከተጠነሰስም ከዓመታት በኋላ መጀመሪያውን የውይይት መድረክ ሁለት ኢትጵያውያንን በመጋበዝ ለማስጀመር ችላለች። • “በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማርን ዛሬም፣ ነገም፣ ወደፊትም የምከራከርበት ነው” ገነት ዘውዴ [ዶ/ር] ትኩረቱን ለምን ከደቡባዊ የዓለማችን ክፍል በመጡ ሴቶች ላይ አተኮረ? ብለን ስንጠይቃት ዛይና "የሌላው ዓለም ክፍል ብዙ ዕድሎችና አማራጮች፣ የመማሪያና የመማማሪያ መድረኮችም በነፃም ሆነ ተከፍሎበት አሏቸው። ከዓለም የተለያዩ የደቡብ ክፍሎች የሚወጡ ሴቶች ግን የሚገናኙበትም ሆነ የሚተዋወቁበት አጋጣሚ ለማግኘት ከባድም አናሳም ነው። ለዚህ ነው 'ሳውዝ ሳውዝ ዊሜን' አስፈላጊ የሚሆነው" ትላለች።
xlsum_amharic-train-158
https://www.bbc.com/amharic/50258996
የኬንያው ሳፋሪኮምና የደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም በጋራ ወደ የኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ የመግባት ፍላጎት አላቸው
የኬንያ ትልቁ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያ ሳፋሪኮም፤ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ቮዳኮም ጋር በመሆን ኢትዮጵያ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ልትሰጥ ካሰበቻቸው ሁለት የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃዶች ውስጥ አንዱን ለማግኘት እየሠራ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ።
[ "የኬንያ ትልቁ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያ ሳፋሪኮም፤ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ቮዳኮም ጋር በመሆን ኢትዮጵያ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ልትሰጥ ካሰበቻቸው ሁለት የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃዶች ውስጥ አንዱን ለማግኘት እየሠራ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ።" ]
የሳፋሪኮም ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚው ማይክል ጆሴፍ እንዳሉት፤ በቮዳኮምና በብሪታኒያው ቮዳፎን በከፊል ባለቤትነት ሥር ያለው ኩባንያ፤ በመንግሥት የሚተዳደረው ኢትዮ-ቴሌኮምን በከፊል በመግዛት፤ ከፍተኛ ትርፍ ወደሚያስገኘው የኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ለመቀላቀል ከውሳኔ አልደረሰም። • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? • የኢትዮ ቴሌኮም 49 በመቶ ድርሻ ለሽያጭ ይቀርባል ተባለ • የውጪ ሀገር ጥሪዎች ለምን በኢትዮጵያ ቁጥር ይወጣሉ? የቴሌኮም ሞገዱን ለማግኘት ከፍተኛ ወጪ እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ጆሴፍ፤ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ፈቃዱን ለማግኘት የሚፈልጉ ተቋማት የደለበ የገንዘብ ምንጭ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል። "ለአየር ሞገዱ በጨረታ መወዳደር ያስፈልጋል። ፈቃዱን ለማግኘት በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ወጪ እንደሚጠየቅ እየተነገረ ነው" ሲሉ ተቋሙ ያገኘውን የመጀመሪያውን ግማሽ ውጤት ይፋ ካደረጉ በኋላ ተናግረዋል።
xlsum_amharic-train-159
https://www.bbc.com/amharic/news-42007398
ኢትዮጵያ ውስጥ የጠፉት ጀርመናዊ ፕሮፌሰር ዱካ አልተገኘም
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ኢንስቲትዩት ኦፍ አርክቴክቸር ኮንስትራክሽን ኤንድ ሲቲ ዴቨሎፕመንት ወይም በቀድሞ አጠራሩ የህንፃ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪው ጀርመናዊው ፕሮፌሰር ደርክ ዶናዝ ከጠፉ አንድ ወር ከ17 ቀናቸውን ይዘዋል። አጠፋፋቸው እስካሁን ምስጢራዊ ሲሆን ስላሉበት ሁኔታም ምንም አይነት ፍንጭ አልተገኘም።
[ "በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ኢንስቲትዩት ኦፍ አርክቴክቸር ኮንስትራክሽን ኤንድ ሲቲ ዴቨሎፕመንት ወይም በቀድሞ አጠራሩ የህንፃ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪው ጀርመናዊው ፕሮፌሰር ደርክ ዶናዝ ከጠፉ አንድ ወር ከ17 ቀናቸውን ይዘዋል። አጠፋፋቸው እስካሁን ምስጢራዊ ሲሆን ስላሉበት ሁኔታም ምንም አይነት ፍንጭ አልተገኘም።" ]
ልጃቸው ሞሪትዝ ሉስ ለቢቢሲ እንደገለፁት ከስራ ባልደረቦቻቸውና ከጓደኞቻቸው ጋር ወደ ኦሞና ማጎ ብሔራዊ ፓርክ በማቅናት ሀገር በቀል የሆነውን የኪነ-ህንፃ ለመመራመር እንዲሁም አካባቢውን ለመጎብኘት እንደሄዱ ይናገራሉ። በጠፉበት ወቅት በመኪናው ውስጥ አብረዋቸው የነበሩት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የስራ ባልደረባቸውና ጓደኛቸውም በአካባቢው ከስራ በተጨማሪ ለጉብኝትም በተደጋጋሚ አብረው እንደሚሄዱ ይናገራሉ። መነሻቸውን ያደረጉት በኦሞ ወንዝ አከባቢ ሲሆን በምስራቅ በኩል ኛንጋቶም ቀጥሎም ምጉሉ ወደሚባለው አካባቢ ከዚያም ወደ ደቡባዊ ማጎ ፓርክ በመጓዝ ላይ ነበሩ። "ማጎ ፖርክ ብዙ ቱሪስቶች የሚጎበኙት ስፍራ ሲሆን የሚመጡትም በሰሜን በኩል ነው" በማለት እኚህ ጓደኛቸው ይናገራሉ። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚገኘው ይህ ፓርክ ከአዲስ አበባ 782 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ምንም እንኳን በደቡባዊ የፓርኩ በኩል መግባት ያልተለመደ ቢሆንም ከምጉሉም ወደ ማጎ ፓርክ የሚመጡት በዛው አቅጣጫ ነበር። በመንገዳቸውም ላይ ጥቅጥቅ ወዳለ የደን ቦታ ላይ ደረሱ። ጓደኛቸው እንደሚናገሩት በዚያው አካባቢ ከሰባት ዓመታት በፊት አልፈው የሚያውቁ ቢሆንም በባለፉት ሶስት ዓመታት ግን መኪና ተነድቶበት እንደማያውቅ ይናገራሉ። ሞሪትዝ እንደሚሉትም የመኪና ቅያስ መንገድም አልነበረውም። እናም አማራጭ መንገድም ስላልነበር በዚሁ ባልተጠረገ መንገድ ይዘው ጉዟቸውን ቀጠሉ። በተለይም በጠፉበት ቀን የነበረው የአየር ፀባይ ጭጋጋማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የአካባቢውን ሁኔታ ከባድ እንዳደረገውም ጓደኛቸው ይናገራሉ። መንገዱም ጥቅጥቅ ወዳለ ጫካ ሲጠጋም ያሉበትን ቦታ ማወቅ ስላልቻሉ ፕሮፌሰር ደርክ ከመኪናው በመውረድ አካባቢያቸውን ማሰስ እንደጀመሩ ይኼው ጓደኛቸው ይናገራሉ። ለአስር ደቂቃዎችም ጥቅጥቅ ወዳለው ጫካ በእግራቸው ገብተው አቅጣጫ ለማመላከት እየሞከሩ ነበር። ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ ግን ባለመመለሳቸው በሁኔታው የተደናገጡት ጓደኞቻቸው የእግር ዱካቸውን በመከተል አሰሳ ጀመሩ። በአሳዛኝ ሁኔታ ተንቀሳቃሽ ስልክም ሆነ የአቅጣጫ ማመላከቻ (ጂፒኤስ) መኪና ውስጥ ትተው በመሄዳቸው የመኪናቸውን ጥሩንባ በማስጮህ፣ በመጮህ ቢፈልጓቸውም ውጤታማ አልነበሩም። "ደኑ ጥቅጥቅ ያለ በመሆኑ ከሃምሳ ሜትር በላይ ድምፃችን ደኑን ማለፍ እንዲሁም መሰማት አልተቻለም" በማለት ጓደኛቸው ይናገራሉ። ይመለሳሉ በሚልም መብራቶቻቸውን አብርተው፤ ዛፎቹም ላይ መብራቶችን ሰቅለው እየጠበቁ አደሩ። ድንገት ቢመለሱ እንዳያጡዋቸውም በሚል ዛፍ ላይም ተሰቅለው አደሩ። ከዚህም በተጨማሪ የድንገተኛ ሳተላይት ጥሪዎች ለጀርመኑ ድርጅት ጂአይዜድ ተላከ። የአካባቢው ባለስልጣናት በፍለጋው ላይ የተሳተፉ ሲሆን በቀጣዮቹም ቀናት በቀጣይነትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰራዊት በፍለጋው እንደተሳተፉ ሞሪትዝና ጓደኛቸው ይገልፃሉ። ከ50-70 የሚሆኑ የሰራዊቱ አካላት የተሳተፉ ሲሆን ለአስር ቀናትም በተጠናከረ መልኩ አሰሳቸውን ቢቀጥሉም ምንም ፍንጭ እንዳልተገኘ ሞሪትዝና ጓደኛቸው ይናገራሉ። ሞሪትዝ እንደሚናገሩትም በውሻና በሄሊኮፕተር ለመፈለግ ሙከራ ቢያደርጉም እንዳልተሳካላቸው ይናገራሉ። ልጆቻቸውና እህታቸውም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲሁም ወደ አካባቢው በመሄድ ፈልገዋቸዋል። "በእያንዳንዱ ጫካና ሰርጥ ብንገፈልግም ልናገኛቸው አልቻልንም" በማለት አቶ ሞሪትዝ ስለ እልህ አስጨራሹ ፍለጋ ይናገራሉ። አካባቢውን በደንብ እንደሚያውቁት እንዲሁም ለዓመታትም ብዙ አገራትን የመጓጓዝ ልምድ እንዳላቸውም የሚናገሩት ሞሪትዝ በህይወት እንዳሉ ከፍተኛ ተስፋ አላቸው። "ምናልባት ውሃ ጠምቶት ቅርብ ወደሚገኘው ማጎ ወንዝ ሄዶ ይሆናል፤ በአካባቢው ትንሽ መንደርም አግኝቶ እየኖረ ይሆናል" በማለት ተስፋቸውን ሞሪትዝ ተናግረዋል። ምንም እንኳን እያንዳንዷን መንደር መሸፈን ባይችሉም ጠፉበት ከተባለው ቦታ ጀምረው ፎቷቸውን ያሰራጩ ሲሆን ያሉበትን ለሚያውቅም ሆነ ለሚያገኛቸው ሰው 25 ሺ ብር ሽልማት አዘጋጅተዋል። ጓደኛቸው በበኩላቸው በቀላሉ ኑሮን እንዲሁም አካባቢዎችን መለማመድ የሚችሉ ሰው ስለሆኑ አንድ መንደር ውስጥ እየኖሩ እንደሆኑ ተስፋ ያደርጋሉ። ፕሮፌሰር ደርክ ማን ናቸው? የ56 ዓመቱ ዕድሜ ባለፀጋ ፕሮፌሰር ደርክ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ ዘጠኝ ዓመታትን አስቆጥረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ኢንስቲትዩት ኦፍ አርክቴክቸር ኮንስትራክሽን ኤንድ ሲቲ ዴቨሎፕመንት ያስተምሩ ነበር። ለብዙ ዓመታትም ጀርመን በሚገኘው ባውሃውስ ዩኒቨርስቲም አስተምረዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከባውሃስ ዩኒቨርስቲና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር 8000 ያህል አዳዲስ ለሚወጡ የገጠር ከተሞችም ላይ "ኢንተግሬትድ ኢንፍራስትራክቸር" በሚባል ፕሮጀክት ስር የከተማ እንዲሁም የቤቶችን ዕቅድም እየሰሩ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ቴክኖሎጂን በመጠቀም በቀላሉ የሚሰሩ፣ ውድ ያልሆኑ፣ አካባቢን የማይበክሉ የመገንቢያ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የህንፃ አሰራርን በመመራመርና በመስራትም ላይ ነበሩ። ይሄም በአዲስ አበባ እየተወደደ ለመጣውና በቤት እጥረት ለሚሰቃየው ህዝብ መፍትሄ ይሰጣል ተብሎ ታምኖበታል። በሙያቸውም በኪነ-ሕንፃ (አርክቴክቸር)ና በኮምፒውተር ሳይንስ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ አላቸው።
xlsum_amharic-train-160
https://www.bbc.com/amharic/49027647
ከ43 ዓመት በኋላ የተገናኙት ኢትዮጵያዊ እናትና ስዊድናዊ ልጅ
[የዛሬ 43 ዓመት ገደማ ነው። ሀሊማ ሀሰን በ20ዎቹ እድሜ ክልል የምትገኝ ወጣት ሳለች ከአጋሯ ጋር ልጅ ወለዱ። ሀሰን የሚባል። ጥንዶቹ ብዙም ባይጣጣሙም ሁለተኛ ልጅ ወለዱ። ኑኑ ተባለ። ኑኑ አሁን የሚጠራው ማንስ ክላውዘን ተብሎ ነው። ሀሊማ ታሪኳን እንዲህ አካፍላናለች።]
[ "[የዛሬ 43 ዓመት ገደማ ነው። ሀሊማ ሀሰን በ20ዎቹ እድሜ ክልል የምትገኝ ወጣት ሳለች ከአጋሯ ጋር ልጅ ወለዱ። ሀሰን የሚባል። ጥንዶቹ ብዙም ባይጣጣሙም ሁለተኛ ልጅ ወለዱ። ኑኑ ተባለ። ኑኑ አሁን የሚጠራው ማንስ ክላውዘን ተብሎ ነው። ሀሊማ ታሪኳን እንዲህ አካፍላናለች።]" ]
ሀሊማ ሀሰን እና ማንስ ክላውዘን ከ43 ዓመት በኋላ ሲገናኙ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ፣ ስድስት ኪሎ አካባቢ ማንስ የልጅነት ልጄ ነው። በእኔና በአባቱ መካከል ችግር ነበር። ሥራ ፈቶ የሚረዱት አባቱ ነበሩ። ቤተሰቦቼ የልጆቼን አባት ስላልወደዱት ተጣልተን ነበር። ሲቸግረኝም ወደ ቤተሰቦቼ ለመመለስ አፍሬ ብቻዬን ተጋፈጥኩ። ማንስን አርግዤ የእለት ጉርስና አንገት ማስገቢያ አጣሁ። ሀሰንን አዝዬ ማንስን በሆዴ ይዤ በጣም የምቀርባቸው ጓደኞቼ ቤት አድር ጀመር። ዛሬ አንዷ ጋር፤ ትንሽ ቀን ሌላዋ ጋር አሳልፍ ነበር። ከነችግሩ እርግዝናዬ እየገፋ መጣ. . . ሁለት ወር፣ አምስት ወር. . . ስምንት ወር. . . እንደቸገረኝ መውለጃዬ ደረሰ። ምጤ የመጣው እንኳን ለሰው ለእንስሳም የማይመች ቦታ ነበር። ሰው ከማጣቴ የተነሳ ሆስፒታል የሚወስደኝ አልነበረም። ጠዋት 12 ሰዓት ምጥ የጀመረኝ እስከ ምሽት 12 ሰዓት ብቻዬን አምጬ ቤት ውስጥ ወለድኩ። • የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ ስወልድ እትብት የሚያትብ ሰው እንኳን ጠፋ። ልጄን በልብሴ ታቅፌ ደሜ ላይ ቁጭ አልኩ። የገዛ ደሜን በእጄ አፈስኩ። ምን ልብላ? ምን ልጠጣ? ለእግዚአብሔር ያሉ ሰዎች ቡና አፍልተው ባዶ ቡና ቁርስ ሰጡኝ። የነበርኩበት ቦታ ከራስጌዬ እሳት ይነድ ነበር። ለመኖር አይመችም። የልጆቼን አባት እህት 'እባክሽ ከዚህ ቦታ አንሽኝ፤ ወይ ውጪ ልውደቅና ዘመድም ይስማኝ' ብዬ ሳለቅስባት ቀበና አካባቢ ያለ ቤታቸው ውስጥ አንድ ክፍል ይሰጣት ብላ አዘዘች። ወቅቱ ዝናብ ነበር። የሦስት ቀን አራስ ሆኜ በታክሲ ወደቤታቸው ወሰዱኝ። የልጆቼ አባት፣ አባቱ ብር ሲሰጡት ወይ ያመጣዋል ወይ ይጠጣበታል። አንዳንዴ እንደ እብድ ሆኖ ይመጣል። ሦስት ዓመት ከእሱ ጋር ስቀመጥ የነበረኝ የሦስት ወር ፍቅር ብቻ እንጂ ስለ ሕይወት የማውቀው ነገር የለም። እህቱ ቤት እያለሁ ሲሰጡኝ መብላት ካጣሁኝም መተው. . . አቤት የልጆቼ ስቃይ. . . እንደ ውሻ ደረቅ ጡቴን ጎትቼ ልጄን አጠባ ነበር። የልጆቼ አባት ከእህቶቹ ጋር አልተስማማም፤ ከእኔጋም ተለያየን። ከዚያ አንድ የወታደር ጊቢ ውስጥ ተከራየሁ። አንድ ቀን ልጆቼን በጣም ሲያምብኝ የካቲት 12 ሆስፒታል ወሰድኳቸው። በሰው በሰው የማውቀው ጆንሰን የሚባል ዶክተርን አገኘሁ። ልጆቼን ሳሳክም 'መንታ ናቸው?' አለኝ። በተቀራራቢ ጊዜ ስለተወለዱ ነው እንጂ መንታ አይደሉም አልኩት። በዚያው እንዲህ ሆኜ፣ እንዲህ ሆኜ እያልኩ ችግሬን ነገርኩት። 'ልጆችሽ በምንም አይነት አያድጉም፤ ከሚሞቱብሽ ጥሩ ቦታ [በማደጎ] ይሂዱ' ብሎ አምስት ኪሎ ማርኪ የምትባል ስዊድናዊት ጋር እንድሄድ መከረኝ። ቢሮዋ ሄድኩ። ባለቤቷ ኢትዮጵያዊ ነበር። ተቀበለችኝና ለህጻናቱ የታሸገ ጡጦ፣ ወተትና ለታክሲ ብላ 20 ብር ሰጠችኝ። በዚያ ጊዜ 20 ብር ትልቅ ነው። 'ልጆቹ የጤና ምርመራ ያስፈልጋቸዋል' ስላለችኝ ለሁለቱም ምርመራውን ጀመርኩ። ትልቁ ልጄ ቶሎ በእግሩ አልሄደም ነበር። ራጅ ላይ 'ልቡ ትልቅ ሆኗል፤ ሌላ ሆስፒታል ይታይ' ተባለ። ሌላ ሆስፒታል ሲታይ ደግሞ ጤናማ ነው አሉ። የማንስ ምርመራ ግን ፈጠኖ አለቀለት። ማንስ 'ጡትሽን እንዲተው የህጻናት ማቆያ ይግባ' ተባለ። ከዚያ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ቀጠሮ ተሰጠኝ። አንድ የማርኪ ተወካይ 'ሁለቱም እኮ አይሄዱም' አለኝ። ተናድጄ 'ሁለቱም እኮ እቃ አይደሉም! ስለቸገረኝ ነው እንጂ ሁለቱም እንዲሄዱ ፍቃደኛ አይደለሁም' አልኩ። ፍርድ ቤት ወሰደኝና 'ለ18 ዓመት' ብለው አስፈረሙኝ። በወቅቱ አባቴ በጣም ታመው ሆስፒታል ነበሩ። ትንሽ ቆይተው አረፉ። ልጄ 'ጡት እንዲተው' ሰባ ደረጃ አካባቢ ያለ ማቆያ ያስገባሁት አባቴ ከማረፋቸው ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር። የአባቴን ለቅሶ ሦስት ቀን ተቀምጬ ልጄን ልይ ብዬ ወደ ማቆያው ሄድኩ። ማቆያው ውስጥ የሚሠሩት ሞግዚቶች 'ታቀፊው' ብለውኝ ልጄን ሳቅፈው የአልጋ ብረት መቶት ክፉኛ ማልቀሱን መቼም አልረሳውም። በጣም አዝኜ አብሬው አለቀስኩ። አባብዬው፣ ጡጦ ሰጥቼው ወደ ለቅሶ ቤት ተመለስኩ። • ዓለም አቀፍ ጉዲፈቻን ማገድ አዋጭ ነው? በስንተኛ ቀን ወደ ማቆያው ስሄድ 'ልጅሽ ሄዷል' አሉኝ። እህህህ! ምድር ልሁን ሰማይ ልሁን አላውቅም። በጣም ሀዘን ውስጥ ገባሁ፤ ጭንቅላቴ ተረበሸ። ከአባቴ ሀዘን ጋር ተደራረበብኝ። ትልቁን ልጄን ይዤ ቀረሁ። በሦስተኛው ወር የልጄ ፎቶግራፍ ተላከልኝ። ልጄን ይዛ የሄደችው ሚስስ ኢንግሪንድ የምትባል ሴት ናት ተባለ። ኢንግሪንድ ትኖር የነበረው አፍንጮ በር ነበር። ባለቤቷ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ነበር የሚሠራው። በሌላ ወር ቤቷ ስሄድ ባዶ ነው። ደነገጥኩ። እንደኔ ከየአቅጣጫው የመጡ ሌሎች ወላጆችም ነበሩ። እሷ ግን የለችም። ከዚያ በኋላ በቃ! የልጄ አድራሻው ጠፋኝ! ጠፋኝ! ጠፋኝ! የማይበጅሽ ይጥፋ. . . ከዚያማ ማልቀስ ነው. . . መሰቃየት ነው. . . ማልቀስ ነው. . . መሰቃየት ነው! ሀሊማ ሀሰን ከልጆቿ ጋር ስዊድን፤ ጎተንበርግ [የሀሊማ ልጅ በማደጎ ስዊድን ሄዶ ማንስ ክላውዘን ተብሎ ከአሳዳጊ ቤተሰቦቹ ጋር መኖር ጀመረ። ልጅነቱን፣ ወጣትነቱን እንዲህ ያወሳል።] ያደኩት ከእናቴ፣ ከአባቴ፣ ከወንድምና እህቴ ጋር ነው። የማደጎ ልጅ እኔ ብቻ ነበርኩ። ቤተሰቦቼ ይወዱኛል። አያቶቼም ተቀብለውኝ ነበር። የማደጎ ልጅነቴ እምብዛም ተሰምቶኝ አያውቅም። በቃ አንድ የቤተሰቡ አካል ነበርኩ። በአካባቢው ብዙ ጥቁር ልጆች አልበሩም። ክፍል ውስጥ፣ የእግር ኳስ ቡድናችን ውስጥም ብቸኛው ጥቁር ነበርኩ። ብዙ ጥቃት ባይደርስብኝም በነጮች ተቀባይነት ለማግኘት 'ስዊድሽ' አቀላጥፌ እናገር ነበር። ገና በዘጠኝ ዓመቴ ነጮችን 'ምቾት ላለመንሳት' ምን አይነት ልጅ መሆን እንዳለብኝ ተማርኩ። እያደግኩ ስሄድ ጓደኞቼ ስለ ትውልድ ቤተሰቦቼ ይጠይቁኝ ነበር። 'ቤተሰቤ ይህ ነው፤ ወንድሜና እህቴም እነዚህ ናቸው' መልሴ ነበር። ብዙ ሰዎች ግን ስለ እኔ መጠየቅ አላቆሙም። አይኔን፣ ፀጉሬን፣ ቆዳዬን ያደንቃሉ። 'ከየት መጣህ?' እባላለሁ። 'ከኢትዮጵያ' ስላቸው፤ 'ኦ ኢትዮጵያ!' ይላሉ በመገረም። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ ኢትዮጵያ ሰው ሁሉ የሚራብበት አገር ነው የሚመስላቸው። የአባቴ እናት ስለ ኢትዮጵያ አንዳንድ መጻሕፍት ብታነብልኝም ስለ አገሪቱ ብዙ አላውቅም ነበር። አድጌ ቤተሰቦቼን ስለ ወላጆቼ ስጠይቅ ብዙ መረጃ እንደሌላቸው ነገሩኝ። እርግጠኛ ባይሆኑም እናቴ ተቸግራ እንደነበር ያውቃሉ። በየወሩ በባንክ ገንዘብ ይልኩላት ነበር። ከስድስት ወይም ከሰባት ወር በኋላ ገንዘቡን ማንም እንዳልወሰደው ባንኩ ለአባቴ ነገረው። ቤተሰቦቼ እናቴን የት ያግኟት? ምናልባት ከአዲስ አበባ ወጥታለች ወይም ሞታለች ብለው እንዳሰቡ ነገሩኝ። ከዚያ በኋላ መጠየቅ አቆምኩ። ስለእሷና ስለተቀረው ቤተሰብም አላሰብኩም። ለብዙ ዓመታት ስዊድናዊ መሆኔን አምኜ ኖርኩ። ጓደኞቼ 'ወደ ኢትዮጵያ መሄድ አትፈልግም?'፣ 'እናትና አባትህን ማግኘት፣ እህት፣ ወንድም ካለህ ማወቅ አትፈልግም?' ቢሉም ያን ማድረግ እንዳለብኝ አልተሰማኝም። ቤተሰቦቼ ኢቫና እና የንስ ናቸው! ጥሩ ልጅነት ነበረኝ። የተለየ የቆዳ ቀለም ስላለኝ ብቻ 'ወላጆቼን' መፈለግ አለብኝ የሚለው ሀሳብ ትርጉም አልሰጠኝም። አንዳንዴ ግን ለምን ቤተሰቤን መፈለግ እንዳለብኝ አልተሰማኝም? እልና ሀፍረት ይሰማኛል። አዲስ አበባ ባድግ ምን ይፈጠር ነበር? ብዬ ማሰቤም አልቀረም። የማንነት ጥያቄ የሚረብሻቸው በማደጎ ያደጉ ጓደኞች ነበሩኝ። በጣም ይከፉ ነበር። እንደ ጓደኞቼ ያልተወዛገብኩት ምናልባትም በፍቅር ስላደኩ ይሆናል። ማንስ ክላውዘን ወጣት ሳለ ከጥቁር ጓደኞቼ ጋር ሂፕ ሀፕ እና ሬጌ እሰማለሁ፤ ቅርጫት ኳስ እጫወታለሁ. . . ከነጭ ጓደኞቼ ጋር ሻምፓኝ ወይም ወይን እየጠጣሁ እራት እበላና ማታ ደግሞ ከጥቁር ጓደኞቼ ጋር ሬጌ ክለብ እሄዳለሁ። ሁለቱንም ሳደርግ ምንም ችግር አልነበረብኝም። ጎን ለጎን አስኬዳቸዋለሁ። አጣጥማቸዋለሁ። 18 ዓመቴ አካባቢ ጠበቃ መሆን እፈልግ ነበር። ለምን እንደሆነ እንጃ። ግን የሕግ ትምህርት ቤት አልገባሁም። አንድ ጓደኛዬ እስኪ የትወና ትምህርት ቤት እንሞክር ሲለኝ ተስማማሁ። ትምህርቱ ደስ አለኝ። አስከትዬም ዩኒቨርስቲ ገብቼ ቴአትር አጠናሁ። አሁን ተዋናይ ነኝ። በብዛት የመድረክ ቴአትር እሠራለሁ። አልፎ አልፎ ደግሞ የራድዮ ድራማ። • አራት ህጻናትን በአንዴ ያገኘው ቤተሰብ ተጨንቋል በአባቷ ኢትዮጵያዊት በእናቷ ስዊድናዊት የሆነች ጓደኛ ነበረችኝ። ኢትዮጵያዊ ልጅ በማደጎ ታሳድግም ነበር። ወደ 30 ዓመቴ አካባቢ ቴአትር ቤቷ ውስጥ ቀጠረችኝ። ስዊደን ውስጥ ጥቁር ሆኖ መኖር ምን ማለት እንደሆነ፣ ስለ ኢትዮጵያም ብዙ እናወራ ነበር። ከእሷ ጋር ለ12 ዓመት መሥራቴ ስለ ታሪኬና ባህሌ አበክሬ እንድጠይቅ አደረገኝ። ጨዋታችንን ተመርኩዤ የማንነት ጥያቄዎቼን የሚያንጸባርቅ መነባንብ ሠርቻለሁ። ያዘጋጀችው እሷ ነበረች። 'ብለድ ኢዝ ቲከር ዛን ወተር' [ትንሽ ሥጋ እንደ መርፌ ትወጋ] ይባል የለ? ቴአትሩ የሚያሳየውም ይህንን ነው። አሁን የምኖረው ስቶኮልም ውስጥ ከልጆቼ ኦሊቪያና ቻርሊ ጋር ነው። ያው የትወና ሥራ ማግኘት ቢከብድም አለሁ. . . የእውነት ኢትዮጵያዊነት ተሰምቶኝ አያውቅም. . . ይህን ስልሽ ትንሽ አፍራለሁ. . . ስለ ኢትዮጵያ ማንበብ የጀመርኩትም በቅርቡ ነው። አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያዊ እንደሆንኩ አይሰማኝም። እንዲህ ማሰቤ ችግር አለው ብዬም አላስብም። ኢትዮጵያ፤ አዲስ አበባ [ሃሊማ ልጇን ካጣችበት ጊዜ አንስቶ መፈለግ አላቆመችም። ከሁለቱ ልጆቿ አባት ጋር ከተለያዩ በኋላ ሞተ። እሷም ከሌላ ሰው ጋር ትዳር መሰረተች። አራት ልጆችም አፈሩ።] ከአራቱ ልጆቼ አባት ጋር ጅጅጋ እንተዋወቅ ነበር። 'እድገት በሕብረት ዘመቻ ጨርሼ ከመጣሁ አብረን እንኖራለን' ይለኝ ነበር። ጌታ ምስጋና ይግባውና ዘመቻውን ጨርሶ መጣ። ከእሱ ጋር ኑሮ ቀጠልኩ። በጣም ጥሩ ሰው ነው። ልጄን ስናፍቅ ያጽናናኝ ነበር። ወዳጅ ዘመዶቼ ሲመክሩኝ፤ እኔ ሳለቅስ፤ አስከመቼ ነው እንዲህ የምኖረው? ስል ዓመታት ተቆጠሩ። 'የ40 ቀን ልጅ እንኳን ውጪ ሄዶ ይመለሳል' እያሉኝ እንዳይኖሩት የለም መቼም፤ ኖርኩ። የማንስ ጉዳይ በጭንቅላቴ ስላለ ቶሎ አልወለድኩም። ወሊድ መከላከያ ለሁለትና ለሦስት ዓመት ብቻ መውሰድ ሲገባኝ ለሰባት ዓመት ወሰድኩ። መድሀኒቱን ሳቆም አረገዝኩና አራት ልጆች አከታትዬ ወለድኩ። መሀል ላይ መንታ ልጆች አስወርዶኛል። • የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች የዘወትር ሥራዬ ስዊደን ኤምባሲ መመላለስ ሆነ። ቤታችን ስዊድን ኤምባሲ አጠገብ ነበር። 'የወሰደው ድርጀት ስም ማን ነው?' ይሉኛል። ስነግራቸው 'አናውቀውም' ይላሉ። ማኅበራዊ ጉዳይ ስመላለስም 'የምናውቀው ነገር የለም' አሉኝ። አንድ ወቅት ላይ ስዊድን ኤምባሲ የምትሠራ የሩቅ ዘመድ አገኘሁ። አያቷ የአክስቴ ልጅ ናቸው። የማርኪን ኢትዮጵያዊ ባል አድራሻ አገኘችልኝ። እሱ 'ከሚስቴ ከተለየሁ 23 ዓመት ሆነኝ እኮ' አለን። እኔና ዘመዴ አድራሻዋን ስጠን እያልነው ሳንገናኝ ሦስት ዓመት አለፈ። ከዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ህጻናት ድርጅት ስሄድ ማኅበራዊ ጉዳይ ላኩኝ። ፋይል ክፍል ገብተን አገላበጥን። የአደራ የተባሉት ሰዎች እንኳን ፋይላቸውን ሲያገኙ እኔ ግን የልጄን ፋይል ላገኝ አልቻልኩም። ጭንቅላቴን አዙሬ፣ አልቅሼ የማታ ማታ ቤት ገባሁ። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች ሲነሳብኝ እንደ ጉድ አለቅሳለሁ። እቃ እሰብራለሁ። ወይ ሞተ ብዬ አልተወው። አንዳንዴ ስናደድ 'ይሄ ሰው 18 ዓመት ከሞላው፤ ኢትዮጵያ መጥቶ በጋዜጣ አያሳውጅም? በሬድዮ አይናገርም?' እላለሁ። እኔም ዘመዶቼም እያንዳንዱን ሚድያ እንከታተል ነበር። በእሱ ምክንያት ሳልማር፣ ደረጃዬንም ሳላሻሽል ቀረሁ። ሀሊማ ሀሰን ወጣት ሳለች ማንስን ፍለጋ የምወጣው ከልጆቼ ጋር ነበር። የመጨረሻ ልጄ ሁሴንን ከትምህርት ቤት ይዤው እወጣና ፍለጋ እንሄዳለን። ሁሴን አድጎ ስልክ መያዝ ከጀመረበት እድሜ አንስቶም ወንድሙን መፈለግ ቀጠለ። ልጄን ፍለጋ ያልሄድኩበት ድርጅት የለም። በሬድዮ 'አንድ ሰው ልጁን ከ40 ዓመት በኋላ ስዊድን አገኘ' ሲሉ እሱ ጋር ሄድኩ። 'ልጁ የስዩም ቻቻ ነው፤ ስሙ ኑኑ አይደለም' አሉኝ። ከጉጉቴ የተነሳ የውጪ አገር ኳስ ጨዋታ ከባለቤቴ ጋር ቁጭ ብዬ አያለሁ። ከጭንቀቴ የተነሳ ነው እንጂ የዘጠኝ ወር ልጅ ውጪ ሄዶ ኳስ ይጫወት፣ ንጉሥ ይሁን አላውቅም። በሕይወት መኖሩንም አላውቅም። እንዲሁ ጠይም ሰው ሳይ ሆዴ ይባባል። በልጅነቱ ፀጉሩ ረዥም መሆኑን አስታውሳለሁ። ፀጉረ ረዥም ኳስ ተጫዋች ሳይ እሱ ይሆን? እላለሁ። የእናት ነገር፤ ሆዴ እየዋለለ። ማነው እሱ. . . ሮናልዲንሆ. . . ልጄ ይመስለኝ ነበር. . . እንዲያውም ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ መጥቶ ነበር. . . • በስዊድን ያሉ የስደተኛ ልጆች ሚስጥራዊ ህመም ልጆቼን እንኳን ወለድኳቸው እላለሁ። ግን ማንንም ከማንስ በላይ አላደርግም። ማንስ ታሪኬ ነው። ልጅነቴን የሰበርኩበት ልጄ ነው። በሕጋዊ መንገድ ፍርድ ቤትን ተገን አድርጌ ነበር የላኩት። ነገር ግን ፍርድ ቤት ምላሽ አልሰጠኝም። ያጽናናኝ የነበረው ባሌ ከ28 ዓመት ትዳር በኋላ በሞተ በሦስት ዓመቱ የመጀመሪያ ልጄ [ሀሰን] በሁለት ቀን ህመም ሞተ። ሀሰን ሞተብኝ፤ ማንስም ከአገሩ ወጥቶ ይሙት ይኑር ሳላውቅ. . . ስቃዬ በረታ። ሆኖም እግዚአብሔር የሰጠኝን ነፍስ በእጄ አላጠፋም ብዬ ትምህርት ቤት ውስጥ የህጻናት ክፍል እየሠራሁ በማገኘው ብር ሌሎቹን ልጆቼን ለብቻዬ ማሳደግ ቀጠልኩ። ኢትዮጵያ፤ አዲስ አበባ [የሀሊማ የመጨረሻ ልጅ ሁሴን ፈይሰል ከልጅነቱ ጀምሮ ወንድሙ ማንስን መፈለግ ጀመረ። ፍለጋውን እንዲህ ይተርካል።] በጣም ልጅ ሆኜ እናቴ ማንስን ስትፈልገው አስታውሳለሁ። ቤታችን ስዊድን ኤምባሲ አካባቢ ነበርና ሁሌ አርብ አርብ ቪዛ ከሚጠብቁ መንገደኞች ጋር ትሰለፋለች። ተራ ሲደርሳት ስለልጇ ትጠይቃለች። ጥሩ መልስ አይሰጧትም። ያጉላሏታል። 'ምንም መረጃ የለንም?' 'አንቺስ ምን መረጃ ይዘሽ ነው?' ይሏታል። እሷ ግን ሳትታክት ተመልሳ ትሄዳለች። ለእናቴ ቅርብ ነኝ። ብዙ ችግር ስታይም ከጎኗ ነበርኩ። በየሄደችበት የምትጠይቃቸው ሰዎች ሲያመናጭቋት፣ ሲሰድቧት ጭምርም አይቻለሁ። ሁሌም ወሬዋ ስለሱ ነው። ትልቁ ምኞቷ እሱን አይታ አፈር መቅመስ ነበር። ላገኘችው ሰው፣ ላገኘችው 'ኤንጂኦ' ፎቶውን ትሰጣለች። ከጭንቀቷ ብዛት ፎቶውን ለአንድ መንገደኛ መስጠቷን አልረሳውም። ሴትየዋ ፎቶውን ይዛባት ሄደች. . . አቤት እናቴ ያኔ የተሰማት ሀዘን. . . በልጅነቴ 'ፍለጋ እንሂድ' ስትለኝ ትዝ ይለኛል። ለተወሰነ ሰዓት እናፈላልግና ቤት እንገባለን። 'ውጪ ዘመድ አለኝ' ያላትን ሁሉ ፈልጉልን ትላለች። የእናቴ ጭንቀት እኔንም ያስጨንቀኝ ነበር። በሞባይል 'ዳታ' ካገኘሁ ጊዜ ጀምሮ ኢንተርኔት መጎርጎር አላቆምኩም። 'አፍሮ ስዊድሽ' ድረ ገጾች ላይ የጉዲፈቻ ልጆች እፈልጋለሁ። ጥቁር ስዊድናዊያን ሁሉ ወንድሜ ይመስሉኛል። ድንገት ኢትዮጵያ ከመጣ እንዲያገኘን 'ስዊድናዊ ኢትዮጵያዊያን' የሚል ገጽ አውጥቼም ነበር። • በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ እስኪ 'ቤተሰብ ፍለጋ' [Ethiopian Adoption Connection] ላይ ፎርም ሙላ አሉኝ። ሞላሁ። አንድርያ [መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገና የተጠፋፉ ቤተሰቦችን የሚያገናኘው ድርጅት መስራች] እና ብሌን የምትባልን ልጅ አገኘሁ። ስለተወለደበት፣ ስለታከመበት አካባቢ ብዙ ይጠይቁኝ ነበር። ሲያዋሩኝ ወንድሜን በነጋታው እንደማገኘው ይሰማኝ ነበር። በአምላኬ እተማመናለኋ! ቤት ውስጥ የነበሩ የማንስ ፎቶዎች ጠፍተው ያገኘሁት አንድ ብቻ ነበር። እሱን ለማንም አልሰጠሁም። [ይህ የማንስ የልጅነት ፎቶ ቅጂ ማንስም ነበረው]። እናቴ ማንስ የሚገኝ ስላልመሰላት ብዙ ጥያቄ ስጠይቃት ትሰላች ነበር። እነ ብሌን የሚደውሉልኝ ማታ ማታ ነበር። 'ኧረ አንተ ልጅ ለምን አተኛም?' ትለኛለች። እናቴ በዚያ ወቅት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ነበረች። ከግራ ማንስ ክላውዘን፣ ሀሊማ ሀሰንና ሁሴን ፈይሰል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዝየም ስለ ወንድሜ መረጃ እየሰጠኋቸው ሲያፈላልጉ ወራት ተቆጠረ። የሆነ ቀን ደወሉና ጥሩም መጥፎም ዜና ነገሩኝ። 'ጥሩው ዜና ወንድምህ ተገኝቷል። መጥፎው ዜና ነገሩን እንደሰማ ድንጋጤ ውስጥ ስለገባ ትንሽ ይረጋጋና እናገናኝሀለን' አሉኝ። ተርበተበትኩ፤ እግሬ ተያያዘ፤ ፈራሁም። እናቴን የሚያስከፋ አይነት ሰው ቢሆንስ? ደስታ ስናስብ ሀዘን ቢጠብቀንስ? ከእኛ ጋር ስላላደገ አናውቀውም። እናቴን ቢያስከፋብኝ ሌላ ህመም ነው የሚሆንብኝ። ለቤተሰባችንም ሌላ ተጨማሪ ህመም! በድጋሚ መጸለይ ጀመርኳ. . . አምላኬ እዚህ እድርሰኸናልና መጨረሻውን አሳምርልን ብዬ። ስዊድን፤ ስቶኮልም [ማንስ ወላጅ እናቱ እየፈለገችው እንደሆነ ያወቀው 'ቤተሰብ ፍለጋ' የተባለው የተጠፋፉ ቤተሰቦች አገናኝ ድርጅት ኢ-ሜል ሲልክለት ነው። ወቅቱንም እንዲህ ያስታውሳል።] 'ጤና ይስጥልን ሚስተር ማንስ ክላውስ፤ በዚህ ጽሁፍ ላይ የተገለጸው ሰው አንተ ልትሆን ትችላለህ' የሚል ኢሜል ደረሰኝ። ኢሜሉን ከፍቼው በ10 ሰከንድ ውስጥ ልቤ በፍጥነት ይመታ ጀመር። 'ከ1970ዎቹ እስከ 75 ባለው ጊዜ የተወለደ ልጅ እየፈለግን ነው' ይላል። የተወለድኩበትን ዓመተ ምሕረት በትክክከል ካላወቁማ የሚፈልጉት ሰው እኔ አይደለሁም አልኩ። ምንም እንኳ በተባለው ዓመት ገደማ ብወለድም ማመን አልፈለኩም። ልቤ ግን መምታቱን ቀጠለ። ድው ድው ድው. . . እኔ ልሆን እችላለሁ. . . • በኢትዮጵያ ካምፕ ውስጥ ባለ2 ፎቅ መኖሪያ የገነባው ስደተኛ የተጻፈውን ስም አነበብኩ። የእኔ ነው! በመጨረሻ የሀሊማን ፎቶ አየሁ። ቤት አንድ ፎቶዋ ነበረኝ። የተላከልኝ ሌላ ፎቶ ቢሆንም ፎቶዎቹ ላይ ያለችው ሴት አንድ ናት። የልጆቼ እናት እውነት ሊሆን ይችላል አለችኝ። ከዚያ ለእናቴ ደወልኩ። [አሳዳጊ] እናቴ [ወላጅ] እናቴ እንደሞተች ነበር የምታስበው። አንድ ሰው ገንዘብ ፈልጎ ያደረገው ቢሆንስ? ብዬ አሰብኩ። ይሄንን ሁሉ ዓመት እየፈለጉኝ ከነበረ እንዴት አላገኙኝም? እኔን ማግኘት ያን ያህል ከባድ ሊሆን አይችልም። ስዊድን ኤምባሲ ወይም በማደጎ የሰጠኝ ድርጅት መደወል ይችሉ ነበር እያልኩ አወጣሁ አወረድኩ. . . እየተፈለገ ያለው ሰው እኔ መሆኔን ልቤ ቢያውቅም ተጨማሪ ማስረጃ ላኩልኝ አልኩ። ተጨማሪ የሀሊማ ፎቶዎች ደረሱኝ። ከተላኩት ፎቶዎች አንዱ እኔ ከድሮም ጀምሮ ከነበረኝ ፎቶ ጋር ተመሳሳይ ነበር። ግራ ገባኝ. . . ትንሽ ቆይቼ በኤጀንሲው [ቤተሰብ ፍለጋ] በኩል ለቤተሰቡ መልዕክት ላኩ። ሀሊማ ብዙም እንግሊዘኛ ስለማትችል በቀጥታ ለእሷ መጻፍ አልቻልኩም። ከሥራ እረፍት ሳገኝ የአውሮፕላን ትኬት ገዛሁ። ከመሄዴ ከአንድ ሳምንት በፊት የአክስቴ ልጅ ሙና ደወለችልኝ። እንግሊዘኛ ስለምትችል የሚጠብቀኝን ነገር አስረዳችኝ። ቀለል አለኝ። ቤተሰቦቼ ለብቻዬ አዲስ አበባ እንድሄድ አልፈለጉም ነበር። ፈሩ፣ ተጨነቁ፣ ተጠራጠሩ። አብረውኝ ለመሄድም ፈልገው ነበር። እኔ በተቃራኒው የተሰማኝ ፍርሀት ሳይሆን ጉጉት ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ብቻዬን እንደምሄድ ለቤተሰቦቼ ነገርኳቸው። ጉዞው የእኔና የእኔ ብቻ ነበር. . . ማንስ ክላውዘን ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቹ ጋር የተነሳው ፎቶ ኢትዮጵያ፤ አዲስ አበባ፤ ሀያት አካባቢ [የዛሬ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ገደማ ላይ ሀሊማ ከ43 ዓመታት ፍለጋ በኋላ ልጇ እንደተገኘ የሰማችበት ቀን ምን ይመስል ነበር?] ጥቅምት 18 ለ19 አጥቢያ ሌሊት 11 ሰዓት ለፀሎት ተነስቼ ነበር። ፀሎት አድርጌ ለልጄ ልጆች ሻይ ጣድኩ። 'ኪችን' ውስጥ ቆሜ ስልክ ተደወለ። 'እናት፣ እናት፣ እናት' እያለ ሁሴን ጠራኝ። ምንድነው? ስለው 'ወንድምህ ተገኝቷል አሉኝ' አለ። ከዚያማ. . . ምን ልበልሽ ኡኡታ. . . እልልታ ቀለጠ። በዚያች ሌሊት ልጆቼ አቅፈውኝ ጮህን! ሰላት ከመስገዳችን በፊት ሽንት ቤት ለመግባት 'እኔ ልቅደም፤ እኔ ልቅደም' እያልን ከሁሴን ጋር ተጣላን። አንድ ልጅ አምስት ሰዓት ላይ ደብዳቤ ይዛ ትመጣለች ተባልኩ። ሰዓቱ እንዴት ይድረስልኝ። እንደገና ተደውሎ የምትመጣው ዘጠኝ ሰዓት ነው ተባለ። ይሁን አልኩ። ልጅቷን ለመጋበዝ ምግብ ሠራን፤ ወጣሁ ወረድኩ. . . መጣች። የልጄን ፎቶ ከደብዳቤ ጋር ሰጠችኝ። አቤት ደስታዬ! ከዚያም ፎቶ አነሳችኝ። 'የቤተሰብ ፎቶ አዘጋጂ' አለችኝ። ወንድም እህቶቹን ሰብስቤ ፎቶ ተነስተን ለማንስ ተላከ። ወዲያው ወደየዘመዱ ተደወለ። አንዱ ከአንዱ ተቀባበለ። ድህነቴን ልትቀርፍ ሪያድ የሄደች ልጅ አለችኝ፤ ወደእሷ ተደወለ። አንድ ከርታታ ወንድምም ካናዳ አለኝ። ተደወለለት። የማንስ ፎቶ ወደ እንግሊዝ፣ ወደ አሜሪካ ተበተነ። • ኮሎኔል መንግሥቱ ለህፃናት አምባ ልጆች ደብዳቤ ላኩ አንዷ ዘመዴ ትራፊክ እስከሚከሳት መሀል መንገድ ላይ መኪና አቁማ ኡኡኡ ነው ያለችው። እልል አይደለም። ኡኡ! 'ምን ሆነሻል ሙና?' ስትባል 'የአክስቴ ልጅ ተገኘ' ብላ ለቅሶና ሳቋ ድብልቅልቁ ወጣ። ደስታችን ወደር አልነበረውም፤ ዛሬም የለውም። ፎቶ ከላኩለት በኋላ በአስተርጓሚ 'አቅም አጥቼ ነው እንጂ ወዲያው መጥቼ አይህ ነበር' አልኩት። 'እናቴ ፈቃደኛ ከሆነች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት እፈልጋለሁ' ብሎ መልስ ሰጠ። ደስታውን አልቻኩትም። ወንዝ እንዳይገባብኝ በሰላም ይምጣ ስል ልጆቼ ይስቁ ነበር። ኢትዮጵያ፤ አዲስ አበባ፤ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ሀያት [ማንስ] አዲስ አበባ ደረስኩ። የሆነ የእውነት የእውነት የማይመስል ነገር ነው። አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ሀሊማ፣ ሁሴን፣ ሙናና እስክንድርን ሳገኛቸው እየጮሁ፣ እያለቀሱ ነበር፤ ግራ ገባኝ። ምን ይሰማኝ? እነዚህን ሰዎች አላውቃቸውም እኮ! በእርግጥ ሀሊማን አውቃትለሁ። ግን አላስታውሳትም። እየፈለኳትም አልነበረም። ሀሊማ በጣም ተደስታ ነበር። እኔም ልጄ ቢጠፋብኝ መላ ሕይወቴን ስለምፈልገው ስሜቷ ገባኝ። ሀሊማ አስሩንም ቀን ስታቅፈኝ፣ ስትስመኝ፤ እኔ እንዴት ይህ አልተሰማኝም? ብዬ ተጨንቄ ነበር። ጥፋተኛነትም ተሰምቶኝ ነበር። ምን እንደተሰማኝ፣ ምን አይነት ስሜት ሊሰማኝ እንደሚገባ ማወቅ አልቻልኩም። አዲስ አበባ አንድ ኢትዮጵያዊ አግኝቼ ነበር። ምን አለኝ መሰለሽ? 'ለራስህ ጊዜ ስጠው!' ወንድሙና እህቱ በማደጎ ስዊድን ውስጥ 30 ዓመት ኖረው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ነበር። ወንድሙ ኢትዮጵያ ግራ አጋባችው። 'እኔ ስዊድናዊ ነኝ' ብሎ ወደ ኢትዮጵያ ሳይመለስ ቀረ። እህቱ ኢትዮጵያን ወዳት እዛው መማር ጀመረች። የኢትዮጵያና የስዊድኑ ቤተሰብ በቅጡ ለመተዋወቅና ለመግባባት 25 ዓመት እንደወሰደባቸው ነገረኝ። 'በተለያየ ዓለም ነው የምንኖረው፤ እንዲህ ይሰማኝ! ብለህ አትጣደፍ' አለኝ። ይህንን ስሰማ ጫናው ቀለለልኝ። ሁሉም ነገር ቀስ በቀስ እንደሚሆን ተረዳሁ። ወደ 40 ዓመት ምናምን ተጠፋፍተን ነበር እኮ! ለሀሊማም ጊዜ እንደሚወስድብኝ ነግሬያታለሁ። ትረዳኛለች ብዬ አስባለሁ። የሆነ ሰው ለዓመታት ሲፈልግሽ፣ ሲናፍቅሽ እንደነበረ ማሰብ የተለየ ስሜት ይሰጣል። ምናልባትም ቤተሰቤን መፈለግ ነበረብኝ እንዴ? ስሜቴን ደብቄ ነበር የኖርኩት? እንጃ. . . አሁን 'ቴራፒስት' [የሥነ ልቦና አማካሪ] ጋር እየሄድኩ ነው። • "ራሴን የምፈርጀው የሀቅ ታጋይ ነኝ ብዬ ነው" አሊ ቢራ ጎድሎኝ እንደነበረ ያላወኩት ክፍተት እንደተሞላ አስባለሁ። በመጠኑም ቢሆን ሁለት አገር እንዳለኝ ተሰምቶኛል። ቢያንስ ለልጆቼ ስለ ታሪኬና ባህሌ አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ። ከሀሊማ ጋር ደብዳቤ እንጻጻፋለን። በቋንቋ ችግር ምክንያት ትስስራችን እንዳይላላ እሰጋለሁ። ግን ደግሞ ሁለት ቤተሰብ አግኝቻለሁ። አንድ ቀን ስዊድንዊ እና ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቼን አገናኛቸው ይሆናል. . . እናያለን. . . ሀሊማ ሀሰን ለልጇ ማንስ ክላውዘን አቀባበል ስታደርግ [ሀሊማ] ጥር 6 ኢትዮጵያ ገባ። ፈረንጅ፣ መንገደኛ፣ ሕዝብ ሁሉ እስከሚያለቅስ በእልልታ ልጄን ተቀብዬው ቤቴ ይዤው መጣሁ። እናትና ልጅ ጠበቃ የለውም። ዳኝነት የለውም። በቃ ችግራችን አበቃ። አላህ ልጄን ጉያዬ ስር ከተተልኝ። እሱን ካረፈበት ሆቴል እኔ ቤት የሚያመጣ እኔንም የሚወስድ መኪና ተከራየልኝ። 'ከቤተሰብ ርቀው የሚኖሩ ልጆች ብር ሲጠይቋቸው ይበረግጋሉ' ብለው መከሩኝ። አሄሄ. . . እኔ ግን ብር የምል ሰው አይደለሁም። የመጀመሪያ ቀን 'ኢንተርቪው አደርግሻለሁ' ብሎ ታሪኬ በአስተርጓሚ ሲነገረው ብድግ ብሎ እያለቀሰ ጉልበቴ ላይ ተደፍቶ 'ይቅርታ እናቴ፤ እኔን ብለሽ ነው። የትም አልተጣልኩም። ጥሩ ቦታ፣ በጣም ጥሩ ቤተሰብ ውስጥ ነው ያደኩት። በጣም አመሰግንሻለሁ እናቴ' አለኝ። ልጄ ሽቁጥቁጥ ነው። ውስጤን አንብቧል። እሱን ያሳደገ ቤተሰብ ለዘለዓለም ይኑር። ላሳደገው ቤተሰብ በአንድ እግሬ ቆሜ ነው የምጸልየው። መቼም እንግሊዘኛዬን ተይው. . . እሰባብረዋለሁ። ግን እንኳን እናትና ልጅ አንደበቱ የተዘጋም ይግባባል። እናትና ልጅ መካከል ጌታ ከባድ ስልጣን አለው። አብሮኝ የቆየበትን አስር ቀን እንደ አስር ሰዓት ነው የቆጠርኩት። አጠረብኝ። ናፍቆቱ አልወጣልኝም። ልጄ ሳይለየኝ ቤተ ዘመድ መጥቶ አየልኝ። የታከመበት የካቲት 12 ሆስፒታል ወሰድነው። የማርኪ ቢሮ የነበረውንም አሳየነው። ሙዝየምም አብረን ገባን። አዲስ አበባን እንደ ልቡ ዞራት። እራት አከሌ ጋር. . . ምሳ. . . ምናምን ስንል ቀኗ ሄደችብን። አለቀች። ሻንጣውን ጎትቶ ቤቱ ሳይገባ 'ደርሻለሁ' ብሎ ደወለልን። አላህ ምስጋና ይግባውና አሁን ከልጄ ጋር እጅና ጓንት ሆነን አለን። ደብዳቤ እንጻጻፋለን። ፖስታ ሲልክልኝ ከፖስታ ቤት ደብዳቤውን እየሳምኩ ነው የምወጣው። እግሬን ስለሚያመኝ ዳገትና ፎቅ አትውጪ እባላለሁ። የእሱን ፖስታ ሳገኝ ግን ያ ያመመኝ እግር ይፈወሳል። ኃይል አገኛለሁ!
xlsum_amharic-train-161
https://www.bbc.com/amharic/news-56549405
ልጅን አቅፎ መተኛት ወይስ ለብቻ በተዘጋጀ አልጋ ላይ ማስተኛት?
ወላጆች ስለ ልጆቻቸው የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። ይህ ግን ከአገር አገር፣ ከባህል ባህል፣ ከኑሮ ደረጃ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊለያይ ይችላል።
[ "ወላጆች ስለ ልጆቻቸው የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። ይህ ግን ከአገር አገር፣ ከባህል ባህል፣ ከኑሮ ደረጃ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊለያይ ይችላል።" ]
"ልጄ ክፍሉ ውስጥ ይሆን?" የሚለው ጥያቄ በበርካታ የምዕራቡ ዓለም ወላጆች ጭንቅላት ውስጥ የሚመላለስ ሃሳብ ነው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ይህ እየተለወጠ የመጣ ይመስላል። የህጻናት አስተዳደግና ሁኔታም እየተቀያየረ ነው። ይህ ደግሞ በምዕራባውያኑ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለማችን ከፍል እየሆነ ያለ ነው። በአንዳንድ ባህሎች ከልጆች ጋር አንድ ክፍል መጋራት አንዳንዴም አንድ አልጋ ላይ መተኛት የተለመደ ቢሆንም የምዕራቡ ዓለም ወላጆች ግን ልጆቻቸውን የሚያሳድጉበት የራሳቸው የሆነ መንገድ አላቸው። በእቅድ የሚመራ የእንቅልፍ ሥርዓትና የእንቅልፍ ልምምድ ስልጠና እስከመስጠትም ተደርሷል። ምናልባት እነዚህ ነገሮች ዘመናዊና አዲስ ዓይነት ልጆችን የማሳደጊያ መንገዶች መስለው ሊታዩ ይችላሉ። በአሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ወላጆች ልጆቻቸው ከተወለዱ በኋላ ቢያንስ ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት አብረዋቸው አንድ ክፍል ውስጥ እንዲያስተኟቸው ይመከራሉ። በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ ማሕበረሰቦች፤ ልጆች ከዚህ ረዘም ላለ ጊዜ ከወላጆቻቸው ጋር ያሳልፋሉ። በአውሮፓውያኑ 2016 ላይ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት በተለይ የእስያ አገራት የሚገኙ ወላጆች ረዘም ላለ ጊዜ ከልጆቻቸው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ አልያም በአንድ አልጋ ላይ ይተኛሉ። ለምሳሌ እንደ ሕንድ እና ኢንዶኔዢያ ባሉ አገራት 70 በመቶ የሚሆኑት ወላጆች እንዲሁም በስሪላንካ እና ቪዬትናም 80 በመቶ የሚሆኑት ወላጆች ረዘም ላለ ጊዜ ከልጆቻቸው ጋር በአንድ አልጋ ላይ ይተኛሉ። በአፍሪካ ደግሞ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ረዘም ላለ ጊዜ በአንድ ክፍል ውስጥ አልያም በተመሳሳይ አልጋ መተኛት ብዙም የተለመደ አይደለም ይላል ጥናቱ። ከዚህ መረዳት የሚቻለው ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ቢያንስ በመጀመሪያዎቹ ወራት በአንድ አልጋ ላይ መተኛት የተለመደ ነገር መሆኑን ነው። ዴብሚታ ዱታ በሕንዷ ባንጋሎር ዶክተር እና የልጆች አስተዳደግ አማካሪ ሲሆኑ ምንም እንኳን የምዕራባውያን ተጽዕኖዎች ቢኖሩም የአልጋ መጋራት አሁንም ሕንድ ውስጥ ጠንካራ ባህል ነው ይላሉ። ሌላው ቀርቶ በርካታ ልጆች ያሉበት ቤት ቢሆንም አልያም ልጆቹ ሲያድጉ የራሳቸው ክፍል የሚሰጣቸው ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ ወራት (እስከ 12 ወራት) ግን ከወላጆቻቸው ጋር በአንድ አልጋ ላይ እንዲተኙ ይደረጋሉ። ''በአንድ አልጋ ላይ መተኛት ዋነኛው ጥቅሙ ልጆች ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው እንዳይነሱ እና ወላጆቻቸውን እንዳይረብሹ ነው'' ይላሉ ዶክተር ዴብሚታ። አክለውም ''ሴት ልጄ ሰባት ዓመት እስከሚሞላት ድረስ ከእኛ ጋር ነበር አልጋ የምትጋራው። ጡት መጥባት ካቆመች በኋላ እንኳን ከእኛ ጋር መተኛት ትወድ ነበር'' ይላሉ። ልጆች ከልጅነታቸው ጀምሮ ነጻነታቸውን አውጀው እንዲያድጉ ማድረግ የምዕራቡ ዓለም ፍልስፍና ተደርጎ ይቆጠራል። በዚህ ምክንያት ከወላጆች ጋር አልጋ መጋራት ልጆች በራሳቸው ነገሮችን ማድረግ የማይችሉ እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸው ይታመናል። በተጨማሪም ልጆች ከወላጆች ጋር አብረው የሚተኙ ከሆነ ሁሉም ፍላጎታቸው ያለገደብ ይሟላል ተብሎ ይታሰባል። ይህ ደግሞ የልጆች አስተዳደግ ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል ይላሉ ምዕራባውያኑ። እንደ ዶክተር ዴብሚታ ያሉ ወላጆች ግን በዚህ ሀሳብ አይስማሙም። '' ትንሽ በራስ መተማመን እንዲኖራቸውና መጠኑን ያላለፈ ነጻነት ከሰጠናቸው ልጆች በራሳቸው ጊዜ ከወላጆቻቸው መለየት ይጀምራሉ። ለዘለአለም ከወላጆቻቸው ጋር መቆየት አይፈልጉም'' ይላሉ ዶክተር ዴብሚታ። በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ በርካታ ወላጆች ግን ልጆችን እንቅልፍ ማለማመድ ላይ ተጠምደዋል። ልጆች ቢያለቅሱ እንኳን እዚያው ትንሿ አልጋቸው ላይ ሆነው ለቅሷቸውን እስኪጨርሱ እስከመጠበቅ ደርሰዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ ልጆች ለረጅም ጊዜ እንቅልፋቸውን መተኛት እንደሚማሩ ይታሰባል። በዚህ መካከልም ወላጆች በቂ የሆነ እረፈት ያገኛሉ ማለት ነው። በአውስትራሊያ በመንግሥት ድጋፍ የሚደረግላቸው እንቅልፍ ማስተማሪያ ማዕከላት ጭምር አሉ። ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ እነዚህ ማዕከላት ይዘው በመሄድ ልጆቻቸው ረዘም ላለ ጊዜ እንቅልፍ መተኛት እንዲማሩ ማድረግ ይችላሉ። በመሆኑም በተለያዩ አገራት ያለው የባህል ልዩነት ልጆች የት መተኛት አለባቸው የሚለውን ብቻ ሳይሆን መቼ እና እንዴት መተኛት አለባቸው የሚለውን ይወስናል ማለት ነው። በቶክዮ ቤይ ኡራያሱ ኢቺካዋ ሜዲካል ማዕከል ውስጥ በተሰራ ጥናት መሰረት፤ ጃፓን ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ሦስተኛ ወራቸው ላይ ሲደርሱ ከሌሎች የእስያ አገራት ያነሰ እንቅልፍ እንደሚተኙ ተገልጿል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ጃፓን ውስጥ እንቅልፍ የስንፍና ምልክት ተደርጎ ስለሚቆጠር ሊሆን እንደሚችል ይነገራል። በእስያ አገራት የሚገኙ ህጻናት ለምሳሌ ከምዕራቡ ዓለም ህጻናት ጋር ሲነጻጸር እንቅልፍ ሳይተኙ ረዘም ላለ ጊዜ ይቆያሉ። ይህ ደግሞ የሚሆነው ወላጆች ከሥራ ሲመለሱም ይሁን በየትኛውም አጋጣሚ ከልጆቻቸው ጋር እንደ ልብ መጫወትና ጊዜ ማሳለፍ ስለሚፈልጉ ነው ይላል ጥናቱ። በዩናይትድ ኪንግደም ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲተኙ ይመከራል። ልክ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም በአሜሪካም የዘርፉ ባለሙያዎች ተመሳሳይ ምክር ይሰጣሉ። ምክንያቱ ደግሞ ልጆች ብቻቸውን ሆነው የሆነ እክል ቢያጋጥማቸው ሊከሰት የሚችለውን የሞት ቁጥር ለመቀነስ ብቻ ነው። ይሁን እንጅ ባለሙያዎቹ ከልጆች ጋር አንድ ላይ መተኛትን አጥብቀው ይቃወማሉ። ለዚህ በምክንያትነት የተቀመጠው ደግሞ ልጆች ታፍነው ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ነው። ነገር ግን በጉዳዩ ላይ በቂና ጥልቅ የሆነ ምርምር ባለመካሄዱ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አልጋ መጋራታቸው ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ የሚለው ላይ ጥርት ያለ አቋም መያዝ ከባድ ነው ይላሉ- የህጻናት ህክምና ባለሙያው ዶክተር ራሽሚ ዲያዝ። በዚህ ጉዳይ የተሰሩት ጥናቶችም ቢሆኑ አብዛኛዎቹ ካደጉት አገራት በተሰበሰበ መረጃ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በእነዚህ አገራት ደግሞ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አልጋ የመጋራት ባህላቸው ዝቅተኛ ነው። በሌላ በኩል ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ከልጆች ጋር አልጋ መጋራት የተለመደ ባህል ሲሆን በእነዚህ አገራት በእንቅልፍ ላይ እያሉ የሚሞቱ ህጻናት ቁጥር በእጅጉ ዝቅተኛ ነው። ልክ ከልጆች ጋር አልጋ መጋራት ሌሊት ላይ ቅርብ ለመሆን እንደሚያስችለው ሁሉ፤ ልጆች ቀን ላይ እንዳይተኙ ማድረግ ደግሞ ወላጆች ሥራቸውን እየሰሩ ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ ሊረዳቸው ይችላል። ሌላኛው ከልጆች አስተዳደግ ጋር የሚነሳው ነጥብ ልጆችን አቅፎ መንቀሳቀስ ብዙ እንዳያለቅሱ ያደርጋቸዋል ወይ የሚለው ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ ምርምር የሰራችው ኩሮዳ እንደምትለው ወላጆች ልጆቻቸውን አቀፏቸው፣ አዘሏቸው ወይም አላዘሏቸው ማልቀሳቸው አይቀርም። ''ልጆችን ማቀፍ እና እንዳያለቅሱ ማድረግ ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም። በዚህ ላይ ልስማማ አልችልም'' ትላለች። በኩሮዳ ጥናት መሰረት ልጆችን ማቀፍ የልብ ምታቸውና እንቅስቃሴያቸው እንዲቀንስ እንደሚያደረግ የተስተዋለ ሲሆን ከለቅሷቸው ጋር ግን የሚገናኘው ነገር የለም። ነገር ግን ልጆችን አቅፎ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ትኩረታቸው በሌላ ነገር ላይ እንዲሆን ሲደረግ የማልቀሳቸው መጠን የሚቀንስ ሲሆን እያለቀሱም ከሆነ የማቆም እድላቸው ከፍተኛ ነው። ከልጆች ጋር ዐይን ለዐይን መተያየት ሁሌም ቢሆን ከህጻናቱ በኩል የሚጠበቅ ነገር ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለመጀመሪያዎቹ ወራት ህጻናት ያለማቋረጥ ምግብ መመገብ አለባቸው። ሌላው ቀርቶ ከአዋቂዎች የእንቅልፍ ሥርዓት ጋር መላመድ በሚጀምሩበት ወቅት እንኳን እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው ሊነቁ ይችላሉ። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው። ነገር ግን ምዕራባውያን ወላጆች ከጓደኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸው የሚነገራቸው ነገር ለየት ያለ ነው። ልጆች ሌሊት ላይ የሚነቁ ከሆነ ችግር ውስጥ እንደሆኑ ነው የሚነገራቸው። ይህ ደግሞ ከባህል ጋር የሚገናኝ ነገር ነው። ልጆች ሌሊት መነሳታቸው የተለመደና ጤናማ ነገር ቢሆንም፤ ቀን ላይ ረዥም ሰዓት የማይተኙ ከሆነ ግን ሌሊት ላይ ሳይነቁ ሊተኙ ይችላሉ። ልጆች ሌሊት ላይ ለጥ ብለው መተኛት አለባቸው የሚለው ብሂል የመጣው በአውሮፓውያኑ 1950ዎቹ አካባቢ በተሰራ አንድ ጥናት ላይ ተመስርቶ ነው። በጥናቱ መሰረት ከእንግሊዟ ለንደን ከተማ ከተውጣጡ ከ160 ህጻናት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት በሦስተኛ ወራቸው ላይ ሌሊቱን ሙሉ ነበር የሚተኙት። ነገር ግን ተመራማሪዎቹ ሌሊቱን ሙሉ መተኛት ብለው የገለጹት ህጻናቱ ሌሊት ላይ ወላጆቻቸውን አለመረበሻቸውንና ድምጻቸው አለመሰማቱን ብቻ ነው። ምናልባት ህጻናቱ ወላጆቻቸውን አይረብሹ እንጂ ቢያንስ አንድ ጊዜ እንኳን መንቃታቸው አይቀርም። አሁንም ቢሆን ከህጻናት እንቅልፍና አስተዳደግ ጋር በተያያዘ የሚሰሩት ጥናቶች በጣም ጥቂት የሚባል የዓለማችንን ማህበረሰብ ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው። አብዛኛዎቹ ጥናቶች የተሰሩት 'ባደጉት' በሚባሉት ምዕራባውያን አገራት ውስጥ በሚገኙ ህጻናት ላይ ብቻ ነው። ምንም እንኳን በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ያለው የልጆች አስተዳደግ በተለያዩ ባህሎች ላይ የተመሰረተ ቢሆንም፤ ልጆች ሁልጊዜም ከወላጆቻቸው ተገቢውን ጊዜና እንክብካቤ ማግኘት አለባቸው የሚለው ግን አጠያያቂ ጉዳይ አይደለም።
xlsum_amharic-train-162
https://www.bbc.com/amharic/news-43028351
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ፈተና እና ተስፋ
መንግስት ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት የተጠመደ ሲሆን ይህም የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ መናኸሪያ ለመሆን የሚደረገውን ጥረት ማቀላጠፍ እንዲሁም የሥራ አጥነት ችግርን በመቅረፍም ላቅ ያለ ሚና ይጫወታል ሲል ይሟገታል።
[ "መንግስት ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት የተጠመደ ሲሆን ይህም የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ መናኸሪያ ለመሆን የሚደረገውን ጥረት ማቀላጠፍ እንዲሁም የሥራ አጥነት ችግርን በመቅረፍም ላቅ ያለ ሚና ይጫወታል ሲል ይሟገታል።" ]
አንዳንድ ባለሞያዎች ግን ውጥኑ እንደብዙ ዕቅዶቹ ሁሉ የተለጠጠ ነው ሲሉ ይተቹታል። በሌላ በኩል በፓርኮቹ በሚገኙ ፋብሪካዎች የሠራተኞች ደመወዝ አነስተኛ ከመሆን ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ፍልሰት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና የፖለቲካ ያለመረጋጋት ፈተናዎችን ደቅነዋል። በአውሮፓውያኑ እስከ 2025 በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ውጤቶችን ማቀነባበር እስከ አልባሳትን ማምረት ድረስ ትኩረታቸውን አድርገው እንደሚከፈቱና ከፍተኛ የምጣኔ ኃብት ጠቀሜታን ማስገኘትን ዓላማቸው እንዳደረጉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኃለላፊዎች ሲገልፁም ነበር። ያስገኙታል ተብሎ ከሚታመነው ምጣኔ ኃብታዊ ጠቀሜታ መካከል አንደኛው ቁጥሩ እየገዘፈ ለሄደው ወጣት የሥራ ዕድልን መፍጠር ነው። ዕድሉን ለመጠቀም ተስፋ ከሚያደርጉት ወጣቶች መካከል የ19 ዓመቷ ቅድስት ደምሴ አንዷ ናት። በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ውስጥ ሥራ ለመቀጠር ወደሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ እያመራች በነበረችበት ወቅት ቢቢሲ ያናገራት ቅድስት ከምትፈልገው ሥራ ጋር የሚገናኝ ምንም ዓይነት የቀደመ ልምድ ባይኖራትም ፤ ቀጣሪዋ ስልጠና እንደሚሰጣት ግምት ይዛለች። ሥራውን የምታገኘው በመቶዎች ከሚቆጠሩ በየዕለቱ ወደፓርኩ ከሚመጡ ሌሎች መሰል ሥራ ፈላጊዎች ጋር ተወዳድራ ነው። ፈተናውን አልፋ ሥራውን ማግኘቱ ከተሳካላት በአነስተኛ ካፊቴሪያ ውስጥ ከነበራት የአስተናጋጅነት ሥራ በመጠኑ የተሻለ ገቢ እንደምታገኝ ትጠብቃለች። ከዚህ ቀደም በፓርኩ ሥራ የጀመሩ ጓደኞቿ በወር 750 ብር እንደሚከፈላቸው ታውቃለች። "ይች ብር ግን ምን አላት? ለኪራይና ለምግብ ስትባል ታልቃለች። መቼም እስከጊዜው ድረስ ነው" ትላለች። እርሷም ሆነች ጓደኞቿ በፓርኩ ውስጥ ለመስራት የሚያስቡት ሌላ የተሻለ ሥራን እስኪያገኙ ድረስ ብቻ ነው። "በዚያ ላይ ሥራው አድካሚ ነው።"ይላሉ። ከክፍያ ማነስ ጋር የሚያያዝ የሠራተኞች ፍልሰት የሃዋሳ ሳይሆን የሌሎች የተገነቡም ሆነ በመገንባት ላይ ያሉ የኢንዱስትሪያል ፓርኮች አንድ ችግር እንደሆነ የሚያወሱት የመዋዕለ ነዋይ ባለሞያው አብዱልመናን መሃመድ ፓርኮቹ ከፍተኛ የሥራ ዕድልን መፍጠራቸው አይቀሬ ነው ይላሉ። ሆኖም በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የወጣቶች የሥራ አጥነት ዕድል በኢንዱስትሪ ፓርኮች ብቻ መፍታት የማይታሰብ ነው ባይም ናቸው። "የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ እየተከፈቱ ያሉበት ሂደት ቀርፋፋ መሆን እንዲሁም ፓርኮቹ ከተከፈቱ በኋላ ተከራይተው ሥራ የሚጀምሩ ፋብሪካዎች ቁጥር አነስተኛ መሆን የወጣት ሥራ አጥነት ቁጥርን የመቀነሱን ውጥን የሚያደናቅፍ ሆኗል።" የሚሉት አብዱልመናን "ስለዚህም ተመጋጋቢ ዕቅዶች ሊመተሩ ይገባል።" ይላሉ። የተጋነነ ዕቅድ ፤ ቀርፋፋ አተገባበር በሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ ሥራቸውን የጀመሩ አምራቾች ርካሽ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ ነፃ ውሃ እና የአስተዳደር አገልግሎት ያገኛሉ። ጠቀም ያለ የግብር ፋታ የሚሰጣቸው ከመሆኑም በላይ ኪራዩም ረከስ ያለ መሆኑ ይነገራል። የፓርኩ ግንባታ 250 ሚሊዮን ዶላር ያስወጣ ሲሆን ከዚህ ቀደም ባልተለመደ ፍጥነት ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ተሰርቶ መጠናቀቁን በበላይነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ይገልፃል። እስካሁን ድረስ ሥራ የጀመሩት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በመገንባት ላይ ካሉት እና ይገነባሉ ተብለው ከታሰቡት አንፃር ዝቅተኛ ቁጥር ያለው እንደሆነ ልብ ማለት ይቻላል። ተገንብተው የተጠናቀቁ የመንግስት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በበላይነት በሚያስተዳድረው የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሥር ያሉት ፓርኮች ሁለት ብቻ ናቸው። ግንባታቸው ተጠናቅቆ ሥራ በጀመሩት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ፋብሪካዎቻቸውን ያቋቋሙ በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ቢኖሩም የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያስወጡትን ገንዘብ ከጠቀሜታቸው ጋር አነፃፅሮ ብያኔ ለማስቀመጥ ብሎም መፃኢ መልካቸውን ለመተንበይ የሚያስችል አጠቃላይ ጥናት ለማድረግ ዘለግ ያለ ጊዜ ወስዶ ፤ ውስብስብ የመዋዕለ ነዋይ መስፈሪያዎችን መመልከትን እንደመጠየቁ ያንን የማድረጊያ ጊዜው ገና እንደሆነ አቶ አብዱልመናን ይናገራሉ። እንደዚያም ቢሆን የታሰቡት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሁሉ ይገነባሉ ብሎ ማመን ግን እንደሚከብዳቸው አይሸሽጉም። "እጅግ የገዘፈ የገንዘብ እና የቴክኒክ ዕውቀት የሚያስፈልግ በመሆኑ ይህንን በተተለመው የጊዜ ክልል ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ የማይቻል ነው።"ይላሉ። ባለሞያው ኃሳባቸውን ለማጠናከር በአስረጅነት በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ላይ አተኩረው በአውሮፓውያኑ እስከ 2025 ይሰራሉ የተባሉትን 17 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ያነሳሉ። ፓርኮቹን ለመገንባት 2.5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያስፈልግ ሲሆን ይህ ገንዘብ በሌሎች ዘርፎችም እንዲሁ ይገነባሉ ከተባሉት ሌሎች በርካታ ፓርኮች ጋር ሲደመር ፤ በየጊዜው የሚኖረው ግሽበት ከግምት ውስጥ ሲገባ ከመቶ ቢሊዮን የሚልቅ ብር የሚፈልግ ይሆናል። የማኑፋክቸሪንግ መናኸሪያ? በከፍተኛ ደረጃ የማኑፋክቸርኒንግ ዘርፍን ሲስብ የቆየው የእስያ ገበያ ርካሽ የሰራተኛ ጉልበት አምራቾችን የሚስብበት ገፅታው ሆኖ ቢቆይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጉልበት ዋጋ እየጨመረ መምጣቱን ተከተሎ አምራቾች ፊታቸውን ወደአፍሪካ ማዞር ይዘዋል። ኢትዮጵያ ይህንን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የአህጉሪቱ የማኑፋክቸሪንግ መናኸሪያ ለመሆን ጠንከር ያለ ፍላጎት አላት። የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ይህንን ፍላጎት ወደተግባር የመመንዘሪያ አንድ መንገድ ተደርገው ይጠቀሳሉ። የሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ባለፈው ዓመት በተመረቀበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ለማሳካት መሰረቱን የጣለ መሆኑን አስረግጠው አሞካሽተውት ነበር። የሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ 35 የፋብሪካ ማረፊያ አዳራሾች በተጨማሪ 15 አዳራሾችን መገንባት ያስፈለገው ኢንቨስተሮች ባሳዩት ፍላጎት መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ይገልፃል። የኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስሪ ልማት ኢንስቲቲዩት በበኩሉ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ በሐዋሳ ኢንዱስሪያል ፓርክ የሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻዎች ምርቶቻቸውን ወደውጭ በመላክ በየወሩ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ እየተገኘ መሆኑን ገልፆ ነበር። በወቅቱም ኢትዮጵያ በዘርፉ አገኘዋለሁ ብላ ተስፋ ካደረገችው ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሩብ ያህሉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ያመነጩታል ተብሎ እንደሚጠብቅ አብሮ ተገልጿል። ሁሉም ፋብሪካዎች ሥራ ሲጀምሩ ከ60000 በላይ ሠራተኞችን ይቀጥራል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል። ፓርኩ በሙሉ አቅሙ ሥራውን እንዲሠራ በማድረግ በየዓመቱ አንድ ቢሊየን ዶላር እንዲያመነጭም የማድረግ ዕቅድ አለ። ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፋብሪካዎቻቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከፍቱ ለመሳብ ተደጋግመው ከሚሰጡ ቃል ኪዳኖች መካከል መካከል ርካሽ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ ማሽኖችን ከቀረጥ ነፃ ማስገባትን የመሳሰሉ ልዩ ልዩ የማትጊያ እርምጃዎች፣ የልማት ብድሮች እንዲሁም የባቡር መንገድን ጨምሮ እየተስፋፋ ያለ የመሰረተ ልማት ግንባታ ይገኙበታል። ርካሽ የሠራተኛ ጉልበትም አንደኛው ኢትዮጵያን ተመራጭ ያስደርጓታል ከሚባሉ እውነታዎች መካከል ይጠቀሳል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች በርካታ አገልግሎቶችን አንድ ሥፍራ ላይ ሰብሰብ አድርገው የሚያቀርቡ መሆናቸው ተገቢ መሰረተ ልማት የሚገነባላቸው መሆኑ እና ከሌሎች አምራቾች ጋርም የሚያገናኙ መሆናቸው በተለየ ተመራጭ የሚያደርጓቸው ምክንያቶች ናቸው። እነዚህ እርምጃዎች ወደፓርኮቹ ገብቶ ሥራ መጀመርን ቀላል እና ጊዜንም የሚቆጥብ ሒደት ያደርጉታል ተብሎ ከመታመኑ የሚወሰዱ ናቸው። ሆኖም ኢትዮጵያ በዕቅድ የያዘቻቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች በውጥኑ መሰረት ገንብታ ወደሥራ ማስገባት ብቸኛው የተደቀነባት ተግዳሮት አይደለም። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ስኬት በግቢያቸው ውስጥ የሚገነቧቸው እና ፋብሪካዎችን የሚያስጠልሉ አዳራሾችን በሙሉ በማከራየት እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሚመጣ ምጣኔ ኃብታዊ ጠቀሜታ ላይ የሚመሰረት ነው። ሥራ የጀመሩና በግንባታ ላይ ያሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ የገንዘብ እና የቴክኒካዊ ዕውቀት እጥረት ቢኖርባቸውም ተቀዳሚው ፈተና ግን ፖለቲካዊ እንደሆነ አብዱልመናን ይገልፃሉ። "በአሁኑ ሰዓት አገሪቱን ፖለቲካዊ ያለመረጋጋት እየወረራት ሲሆን ይህም ኢንቨስተሮች ስጋት እንዲገባቸው እና ከመምጣት እንዲቆጠቡ ሊያደርጋቸው ይችላል።" ይላሉ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሌላኛው ሥራን የሚያስተጓጉል ምክንያት እንደሆነ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይገልፃሉ። ሥራ አጥነት እና የስደተኞች ጉዳይ አብዱልመናን ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ አፍስሶ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በገፍ ለመገንባት ከመቻኮል በፊት አሁን የተገነቡት ፓርኮች የሥራ ሂደት እና የስኬት መጠን እንደአመላካች መውሰድን ይመክራሉ። "በርካታ ፓርኮችን ከመገንባት በፊት፤ ባሉት ላይ ማተኮርና ለቀጣይ እርምጃዎች አጠቃላይ የሆነ ጥናትን ማከናወን ይሻላል።" የሚሉት አብዱልመናን ይህ ግን ሲከናወን እየተመለከቱ እንዳልሆነ አይሸሽጉም። "እያየን ያለነው ለፈርጀ-ብዙው የምጣኔ ኃብት ችግራችን ሁሉንም ፈዋሽ መድኃኒት ናቸው በሚል እምነት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የማከታተል ትኩሳት ነው።" ይላሉ። የኢትዮጵያ መንግስት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በተለይ ለወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ሊጠቀምበት እንደሚፈልግ ይናገራል። በሌላ በኩል የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ኢትዮጵያ ውስጥ ለስደተኞች የሥራ ዕድልን መፍጠር ወደአውሮፓ የሚደረግን ስደት ይቀንሳል በሚል እምነት 90000 ሰዎችን ይቀጥራሉ ብሎ ላመነባቸው ሁለት ፓርኮች ግንባታ 500 ሚሊዮን ዶላር ለመለግስ ቃል ገብቷል። የአውሮፓ ኅብረት ያለበትን ከስደት ጋር የሚያያዝ ችግር ለመቅረፍ ሲል ለኢትዮጵያ የለገሰው ገንዘብ ኢትዮጵያ በሽህዎች ለሚቆጠሩ ስደተኞች ሥራን እንድትፈጥር የሚጠይቃት ነው። አብዱልመናን ግን ይህን ውሳኔ በጥልቅ ልትፈትሸው ይገባል ባይ ናቸው። "ኢትዮጵያ ጠናን የሆነ የራሷ የወጣቶች ሥራ አጥነት ችግር አለባት።"ይላሉ።
xlsum_amharic-train-163
https://www.bbc.com/amharic/news-54040199
2012፡ የኢህአዴግ መክሰም፣ የተማሪዎች እገታ፣ የምርጫ መራዘም፣ ግድያና እስር
በ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያውያንን ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊና ማኅበራዊ ሕይወት በበጎም ሆነ በአሉታዊ ሁኔታ የሚነኩ ነገሮች ተከስተዋል።
[ "በ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያውያንን ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊና ማኅበራዊ ሕይወት በበጎም ሆነ በአሉታዊ ሁኔታ የሚነኩ ነገሮች ተከስተዋል።" ]
ከእነዚህ ክስተቶች የትኞቹ ጉልህና ወሳኝ ናቸው የሚለውን ለመለየት እንደምንጠቀምበት መመዘኛ የተለያየ ቢሆንም፣ ቢቢሲ በተለይ በለውጥ ሂደት ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው አንድምታ ከፍ ያለ ነው ያላቸውን ጥቂት ክስተቶችን መርጦ ቃኝቷል። ኢህአዴግ መክሰምና የብልጽግና ውልደት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አገሪቱን ሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በብቸኝነት የአገሪቱን ሁለንተናዊ ህልውና የመራውና መሠረታዊ ለውጥ በማምጣት ረገድ የአራት የብሔር ድርጅቶች ግንባር የሆነው ኢህአዴግን ያህል የሚጠቀስ ቡድን የለም። ነገር ግን ከሦስት ዓመት በፊት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተቀሰቀሰበት ተቃውሞ ግንባሩ ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ስላላስቻለው የለውጥ እርምጃዎችን ወስዶ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰይሞ፤ በ27 ዓመታት ሂደት ውስጥ የቆየበትን ገጽታውን ለመቀየር ሥራውን የጀመረው በዚህ ዓመት ነበር። ግንባሩ ለዓመታት ሲንከባለል የነበረው አንድ ውህድ ፓርቲ የመሆን እቅዱን በፍጥነት ለማከናወን ወስኖ ከህወሓት ውጪ ያሉት ኦዲፒ፣ አዴፓ እና ደኢህዴን ስምምነት ላይ ደርሰው "ብልጽግና" የተሰኘውን አንድ ወጥ ፓርቲ መሰረቱ። ሂደቱም ከዚህ በፊት የኢህአዴግ አጋር ፓርቲዎች የሚባሉትን ክልላዊ ፓርቲዎችን አንድ በአንድ በማካተት አገራዊ ቅርጽ ያዘ። የኢህአዴግ መስራችና በግንባሩ ውስጥ ጉልህ ሚና የነበረው ህወሓት በአዲሱ ውህድ ፓርቲ ውስጥ ላለመሳተፍ ከወሰነ በኋላ በማዕከላዊው መንግሥት ውስጥ የነበረው ተሳትፎ ቀስ በቀስ እየተዳከመ ከብልጽግና ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ፍጥጫ ውስጥ ገባ። በዚህም ሳቢያ ህወሓት በገዢ ፓርቲነት በሚያስተዳድረው ትግራይ ውስጥ እንቅስቃሴውን በማጠናከር የብልጽግና ፓርቲ ተቀናቃኝ ሆነ። በቀሪው የአገሪቱ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ቡድኖችንም በማስተባበር "የፌደራሊስት ኃይሎች" የተሰኘ ስብስብን ፈጥሮ በሥልጣን ላይ ካለው ፓርቲ በተቃራኒ ቆመ። በዚህም በብልጽግናና በህወሓት መካከል በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ያለው አለመግባባት እየሰፋ መጥቶ፣ በግልጽ አስከ መወነጃጀል የደረሰ ሲሆን፤ ይኸው ፍጥጫ ተካሮ ትግራይ ክልል በተናጠል ምርጫ ለማካሄድ እስከመወሰን ደርሷል። የጃዋር መከበብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የተከፈተባቸው ክስና የተጣለባቸው እገዳ ተነስቶ ወደ አገር ቤት ከገቡ የፖለቲካ ቡድኖች መሪዎችና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነው ጃዋር መሐመድ በቤቱ አካካቢ ለደኅንነቱ ስጋት ነው ያለውን እንቅስቃሴ ተከትሎ የፈጠረው አለመጋጋት ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኖ ነበር። ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ገደማ መሃል አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ አካባቢው የጸጥታ ኃይሎች ያልተለመደ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሶ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት፣ ደጋፊዎቹ በቤቱ ዙሪያ ከመሰባሰባቸው ባሻገር በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተቃውሞ ተቀስቅሷል። አለመረጋጋቱን ተከትሎም በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ80 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት ሲጠፋ በንብረትም ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሶ ውጥረቱም ለቀናት ዘልቆ ነበር። ደስታውን የሚገልጽ የሲዳማ ወጣት የሲዳማና ክልልነት ጥያቄ በደቡብ ለዓመታት የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማዕከል ከሆነው የደቡብ ክልል በመውጣት ራሱን የቻለ ክልል ለመመስረት ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የሲዳማ ዞን፣ ቀደም ሲል ካጋጠመ ውዝግብ እንዲሁም ደም ካፋሰሰ ግጭትና ጥቃት በኋላ ኅዳር 10/2012 ዓ.ም በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ መቋጫ አግኝቷል። ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በመራው በሲዳማ ዞን ውስጥ በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ድምጻቸውን ከሰጡ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች፤ ማለትም 98.51 በመቶው፤ ዞኑ ክልል እንዲሆን የሚያስችለውን ድምጽ መስጠታቸውን ይፋ ሆኖ ሲዳማ 10ኛው የአገሪቱ ክልል መሆን ችሏል። ከሌሎቹ የአገሪቱ ክልሎች በተለየ ከ50 በላይ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን የያዘው የደቡብ ክልል ለሲዳማ ጥያቄ ምላሽ ቢሰጥም ከአስር የማያንሱ ሌሎች ዞኖችም የክልልነት ጥያቄ አቅርበዋል። በተለይ የሲዳማ ክልልነት በይፋ ከደቡብ ክልል መውጣቱ ሰኔ ወር ላይ ከተገለጸ በኋላ፣ የክልልነት ጥያቄ ያቀረቡት ዞኖች ውስጥ እንቅስቃሴዎች በጉልህ ከመታየታቸው ባሻገር አንዳንዶች መለያችን ነው የሚሉትን ባንዲራ የሚያሳዩ ምስሎችን በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በስፋት ሲያሰራጩ ነበር። ዓመቱ በተለይ የወላይታ ዞን ተወካዮቹ ከደቡብ ምክር ቤት መውጣታቸውንና ዞኑ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠው ግፊት ማድረጉን አጠናክሮ በመቀጠሉ ውጥረት ተከስቶ ነበር። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአካባቢው አመራሮች ሌሎችም በስብሰባ ላይ እንዳሉ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር በመዋላቸው አለመረጋጋት ተቀስቅሶ ከ20 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል። የተማሪዎች እገታ በ2012 ዓ.ም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በተከሰቱ ግጭቶች ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዚህ ሳቢያ በተፈጠረው ስጋት በዩኒቨርስቲዎቹ ይካሄድ የነበረው ትምህርት በተደጋጋሚ ተስተጓጉሏል። በዓመቱ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኖ ብዙ የተባለለትና እስካሁንም መቋጫ ያላገኘው የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እገታ ጉዳይ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው። በዩኒቨርስቲው ባጋጠመ የጸጥታ መደፍረስ ሳቢያ ትምህርት በማቋረጡ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የነበሩ 18 የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መታገታቸው ከተነገረና በኋላ ለወራት የት እንደደረሱ ሳይታወቅ እስካሁን ደብዛቸው እንደጠፋ ይገኛሉ። የተማሪዎቹ ወላጆች ከራሳቸው ከልጆቻቸው ተደውሎላቸው ችግር እንደገጠማቸው የሰሙት ኅዳር 24/2012 ዓ.ም ቢሆንም ክስተቱ ተገቢውን ትኩረት ለማግኘት ሳምንታትን ወስዷል። ቢቢሲ ስለተማሪዎቹ እገታ የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ ዘገባዎችን የሰራ ቢሆንም ከክልልና ከፌደራል የመንግሥት አካላት መረጃ ለማግኝት ሳይችል ቆይቷል። በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚወጡት መረጃዎችም አንዳንዶቹ ዕገታው እንዳልተፈጸመ ሲያስተባብሉ ሌሎቹ ደግሞ እርስ በርስ የሚጣረሱ ሆነው ቆይተዋል። በመጨረሻም መንግሥት የተማሪዎቹን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን በመጥቀስ በአጭር ጊዜ ውስጥ መቋጫ እንደሚያገኝ ገልጾ የነበረ ሲሆን፣ ከወራት በኋላ ከተማሪዎቹ እገታ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የተባሉ አስራ ሰባት ሰዎች ላይ ሐምሌ 10/2012 ዓ.ም የሽብር ወንጀል ክስ እንደተመሰረተባቸው ብሔራዊው ቴሌቪዥን ዘግቧል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፤ በዚህም ያሉበት ያልታወቁና አብዛኞቹ ሴት ተማሪዎችን በማገት፣ በመጥለፍና በሽብር ወንጀል ተከስሰዋል። በክሱ ላይ ተማሪዎቹ በተጠርጣሪዎቹ አማካይነት በምዕራብ ኢትዮጵያ ይንቀሳቀሳል ለሚባለው አማጺ የኦነግ-ሸኔ ቡድን ተላልፈው እንደተሰጡ ቢጠቀስም እስካሁን ግን የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አይታወቅም። ከታገቱ ተማሪዎች መካከል የአንዷ አባት ምርጫ መራዘም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በተለያዩ አጋጣሚዎች ምርጫ ቦርድን ነጻና ገለልተኛ በሆነ ሁኔታ እንዲዋቀር በማድረግ በ2012 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ሁሉ የተለየ እንዲሆን እንደሚፈልጉ በተደጋጋሚ ተናግረው ነበር። በዚህም መሠረት የቀድሞዋ ፖለቲከኛ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ኃላፊነቱን ይዘው ቦርዱ የሚተዳደርባቸው የሕግና የመዋቅር መሻሻያዎች ተደርገው፤ ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶ፣ በመጀመሪያ ነሐሴ 10 ከዚያም ማሻሻያ ተደርጎ ነሐሴ 23/ 2012 ዓ.ም የድምጽ መስጫ ቀን እንዲሆን ቀን ተቆርጦ ነበር። የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰቱን ተከትሎ ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ምርጫውን ማካሄድ የማይችል መሆኑን በመግለጽ ለምርጫው መከናወን ያለባቸው ሥራዎች ለጊዜው እንዲቆሙ መወሰኑን መጋቢት 22/2012 አስታወቀ። በዚህም መሠረት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ተወግዶ የሚኖረውን ተጨባጭ ሁኔታ እንደገና ገምግሞ አዲስ የምርጫ ሥራ ዝግጅት ዕቅድና የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት እንቅስቃሴውን እንደሚያስጀምር አሳውቋል።፡ ይህንንም በማስመለከት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ጠቅሶ ምርጫውን ማካሄድ እንደማይችል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቨማቅረብ፣ ምክር ቤቱ የቦርዱን የውሳኔ ሐሳብ በመቀበል በጉዳዩ ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲካሄድ መጠየቁ ይታወሳል። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በወረርሽኙ ምክንያት ምርጫ በወቅቱ ማካሄድ ባለመቻሉ እንዲሁም የምክር ቤቶችንና የአስፈፃሚ አካላትን የሥራ ዘመን አስመልክቶ በቀረበለት የሕገ መንግሥት ትርጉም መሰረት የበሽታው ስጋት እስካለ ድረስ የፌደራልና ክልል ምክር ቤቶች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ወሰነ። ምርጫውም ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት ወረርሽኙን አስመልክተው የሚያወጡትን መረጃ መሰረት በማድረግ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ተቋም በሽታው የሕዝብ ጤና ስጋት አለመሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ምርጫው እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ እንዲካሄድ ተወሰነ። ከዚህ በተቃራኒ ግን በምንም ምክንያት ምርጫው ሊራዘም አይገባም ያለው የትግራይ ክልል ግን በዚህ ዓመት በተናጠል ምርጫ ለማካሄድ ሲዘጋጅ ቆይቶ ረቡዕ ጳጉሜ 04 መራጮች ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ምርጫው ሕግን የጣሰ በመሆኑ ተቀባይነት ስለሌለው እንዳልተካሄደ ይቆጠራል ሲል ለምርጫው እውቅና እንደማይሰጥ ገልጿል። እንደተባለው ምርጫው በትግራይ ክልል ውስጥ የሚካሄድ ከሆነ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሚኖረው ግንኙነትን የበለጠ ስለሚያበላሸው ውዝግቡ ወደ 2013 መሸጋገሩ አይቀርም። የሃጫሉ መገደልና እስር ዓመቱ ሊጠናቀቅ ሁለት ወራት ሲቀሩት የተፈጸመው የታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በአገሪቱ አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ካመጡት ክስተቶች መካከል ቀዳሚው ነው። አንዳንዶች የሃጫሉ ግድያና እሱን ተከትሎ የተከሰተው ውጥረትና አለመረጋጋት ውጤቱ ለወራት ሊቆይ እንደሚችል ይገምታሉ። ሰኞ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም ምሽት የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እንደተሰማ ወዲያው ነበር በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሁከትና ተቃውሞ የተቀሰቀሰው። ከድምጻዊው ግድያ በተጨማሪ የአስከሬን ሽኝትና ቀብሩ የሚፈጸምበት ቦታ ያስከተለው ውዝግብ የተፈጠረውን ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ አጡዞታል። በሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ሰበብነት በተለያዩ ስፍራዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ150 በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። በአንዳንድ ከተሞች ላይ ደግሞ ሆቴሎች፣ የንግድ ተቋማት፣ የመንግሥት ቢሮዎች፣ የግለሰቦች መኖሪያ ቤቶችና ሌሎችም በተፈጸመባቸው ጥቃት ወድመዋል። ከሰኔ 23 2012 ከሰዓት በኋላ ጀምሮም በርካታ ፖለቲከኞችና በሺህዎች የሚቆጠሩ በሁከቱ ተሳትፈዋል የተባሉ ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋል ጀመሩ። በዚህም መሠረት ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ለእስር የተዳረጉ ሲሆን፤ ሁከቱን በማባባስ በኩል አስተዋጽኦ አድርገዋል የተባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በጸጥታ ኃይሎች እንደተዘጉ የተነገረ ሲሆን ጋዜጠኞችም ከታሰሩት መካከል ይገኙባቸዋል። የሃጫሉ መገደልን ተከትሎ የተፈጠሩት ነገሮች አገሪቱ የጀመረችውን ነገሮች ወደኋላ ሊመልሱት ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች የተበራከቱ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞና አለመረጋጋት እየተከሰተ ነው። የቀናት ዕድሜ በቀረው በዚህ ዓመት በርካታ ጉልህ ነገሮች በተለያዩ መስኮች በኢትዮጵያ ውስጥ መከሰታቸው ይታወቃል። ነገር ግን በቢቢሲ ምርጫ ከብዙ በጥቂቱ በ2012 ዓ.ም ከተከሰቱት ዋነኛ ናቸው ያልናቸውን እነዚህን መለስ ብለን ቃኝተናል። እናንተስ በዓመቱ ከተከሰቱት ውስጥ የትኞቹን በጉልህነት ትመለከቷቸዋላችሁ?
xlsum_amharic-train-164
https://www.bbc.com/amharic/news-55214419
ትግራይ ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ለምን መከላከያውን ወደ ትግራይ አዘመቱ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ላይ ጦርነት ምን ያክል አስከፊ እንደሆነና ምን ያክል እንደሚያጨካክን በስሜት ተናግረው ነበር።
[ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ላይ ጦርነት ምን ያክል አስከፊ እንደሆነና ምን ያክል እንደሚያጨካክን በስሜት ተናግረው ነበር።" ]
ላለፉት ሦስት ሳምንታት የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የህወሓት አመራሮችን በሕገ ወጥነት በመፈረጅ ጦርነት ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚንስት ዐብይ ተመርጠው ብዙም ሳይቆዩ መገናኛ ብዙሃንን በሰበር ዜና ያጥለቀለቁ ውሳኔዎች ማስተላለፋቸው ይታወሳል ሞት ተፈርዶባቸው የነበሩ እሰረኞች ነጻ ወጡ፣ አሸባሪ ተብለው በነበሩ አካላት ምትክ መንግሥት "አሸባሪዎቹስ እኛ ነን" በማለት ብዙዎችን ከእስር ለቀቀ። ከኤርትራ ጋር እርቀ ሰላም የማውረድ ጅማሮ ታየ። ወቅታዊ ዜናዎችን ያደመጡ ኢትዮጵያን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችም "እንዲህ ከሆነማ ወደአገራችን እንመለሰላን" ብለው ሻንጣቸውን አነሱ። መንግሥት አላስነካ ብሏቸው የነበሩት የኃይል፣ ቴሌኮሚዩኒኬሽን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ መንግሥታዊ ተቋማትን ለአገር ውስጥና ለውጪ ባለሀብቶች ድርሻ እሰጣለሁ አለ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ጥቅምት 24/2013 ዓ. ም የትግራይ ኃይሎች በትግራይ የሚገኘው ትልቁንና በትጥቅ የተደራጀው የመከላከያ ሠሜን ዕዝ ካምፕ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልፀው ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ይታወሳል። ውጥረቱ ወደ ወታደራዊ ግጭት ከማምራቱ በፊት በፌደራል መንግሥትና የትግራይን ክልልን ይመራ በነበረው ህወሓት መካከል የቆየው መቃቃር የተባባሰው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሆነ ፓርላማው በአገሪቱ ታቅዶ የነበረው ምርጫ እንዲራዘም የሰጡትን ውሳኔ ባለመቀበል የትግራይ ክልል የተናጠል ምርጫ ማድረጉን ተከትሎ ነው። የእስር ማዘዣ በሌላ በኩል በኬል ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የሕግ መምህር የሆኑት አወል አሎ (ዶ/ር)፤ 'ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም አገሪቱን ለመበታተን በመስራት' በሚል በፌደራል ፖሊስ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል። የፌደራል ፖሊስ አወልን (ዶ/ር) ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም አገር አፍራሽ መረጃ ያሰራጫሉ ባላቸው ሰባት ግለሰቦች እና በ27 ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱን ማስታወቁ የሚታወስ ነው። ''በዚህ ሰዓት በቁጥጥር ስር እንድውል ማዘዣ ስለመውጣቱ አላውቅም፤ ነገር ግን ወደ ኢትዮጵያ መሄድ ከፍተኛ ስጋት እንደሚፈጥር አውቃለው'' ብለዋል አወል (ዶ/ር) ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ። ''ተቃዋሚዎችን ዝም ከማሰኘት አንጻር በቀድሞው መንግሥትና በአሁኑ መካካል ምንም ልዩነት የለም። የሕግ ሥርዓቱን ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል፣ ተቃዋሚዎችንና የተለየ አመለካከት ያላቸውን ጸጥ ለማድረግ ነው እየተጠቀሙበት ያሉት።'' ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ጦርነቱ በተወሰኑ የህወሓት አባላት ላይ ያነጣጠረ ሕገ መንግሥትን ለማስከበር እየተወሰደ ያለ እርምጃ መሆኑን ገልፀው በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ መግለፃቸው ይታወሳል። የትግራይ ክልል በበኩሉ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጦርነት እንደተከፈተበትና ሕዝቡ ላይ ያነጣጠረ ነው ይላል። መቀመጫውን ጄኔቫ ያደረገው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊው ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖምም ቢሆኑ ስማቸው ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተነስቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስን በተመለከተ ቅሬታ እንዳለውና ደስተኛ አለመሆኑን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መግለጻቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም ዶ/ር ቴድሮስ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው ህወሓትን የሚደግፍ የማግባባት ሥራ አከናውነዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ከሰዋል። ዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም በበኩላቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት በኩል ከመንግሥት ሠራዊት ጋር ግጭት ውስጥ የገባውን ህወሓትን ለመደገፍ ጥረት አድርገዋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አድርገዋል። ዶ/ር ቴድሮስ ለቀረበባቸው ክስ በትዊተር ገጻቸው ላይ በሰጡት ምላሽ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ባለው ነገር ልባቸው እንደተሰበረ ገልጸው "በዚህ ውስጥ አንድ ወገንን እንደደገፍኩ የሚገልጹ ዘገባዎች ሲወጡ ቆይተዋል። ነገር ግን ይህ እውነት አይደለም" ብለዋል። ጨምረውም "እኔ የምደግፈው አንድ ወገን ቢኖር ሠላም የሚመጣበትን መንገድ ብቻ ነው" ሲሉ ለሠላም ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል። በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ምንይችል መሰረት በበኩላቸው፤ ኢላማ የተደረጉት ሰዎች በሙሉ ከሕወሓት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ናቸው በማለት የመንግሥትን እርምጃ ደግፈዋል። ''ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከዚህ በፊት ተዘግተው የነበሩ 264 ድረ ገጾች ተከፍተዋል። አሁን እየሆነ ያለው አጠቃላይ የአገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ የሚገልጽ አይደለም። አገሪቱ ትልቅ አደጋ ላይ ነበረች። ህወሓት በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል የሚገኝ ወታደራዊ ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽሟል። የትኛውም አገር ይህንን አይታገስም'' ብለዋል። አወል (ዶ/ር) ግን ''ዋናው ጥያቄ የመጀመሪያውን ጥይት ማን ተኮሰ አልያም ማነው ጥፋተኛው የሚለው አይደለም፤ ዋናው ነገር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መቀመጫውን አዲስ አበባ ካደረገው የአፍሪካ ሕብረት እንኳን የቀረበላቸውን የድርድር ሀሳብ ውድቅ ማድረጋቸው ነው'' ይላሉ። ''እንደ አንድ መንግሥት የሚያስፈልገው ትዕግስት፣ መቻቻልና ለሰላምና እርቅ ቅድሚያ መስጥት ነው። የሚያሳዝነው ግን ሁለቱም ወገኖች ለጦርነት ሲዘጋጁ ነበሩ።'' የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በነሐሴ ወር ሊካሄድ ታስቦ የነበረው አገር አቀፍ ምርጫ እንዲራዘም መደረጉን ተከትሎ ህወሓት፤ የ2012 አገራዊ ምርጫ በማንኛውም ሁኔታ መካሄድ አለበት፤ ምርጫ የማይካሄድ ከሆነ በክልል ደረጃ ምርጫ እናካሂዳለን የሚል አቋም አንጸባርቆ ነበር። በወቅቱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ስድስተኛው ዙር ምርጫን እንዲያስፈጽምለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል። ምንም እንኳ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትግራይ ክልል ለማካሄድ የጠየቀውን የክልላዊ ምርጫ ለማስፈጸም የሚያስችለው ሁኔታ የለም ቢልም፤ የትግራይ ክልል የሚያቋቁመው አካል ምርጫውን እንደሚያስፈጽም የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ ለቢቢሲ አስታውቀው ነበር። በትግራይ ክልል ጳጉሜ 4/2012 ዓ. ም በተደረገው ክልላዊ ምርጫም ህወሓት በበላይነት ማሸነፉ እንደተገለጸ ይታወሳል። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይና በህወሓት አመራሮች መካከል ከፍተኛ መቃቃር የተጀመረውም በዚህ ወቅት እንደሆነ አወል (ዶ/ር) ያስታውሳሉ። ''ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህወሓት አመራሮች እውቅና አይሰጡም፤ የሕወሓት አመራሮችም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገ ወጥ ናቸው በማለት እንደማይቀበሉ ገልጸው ነበር። ለጦርነቱ መቀስቀስ ይሄ ትልቅ ምክንያት ነው።'' በሰሜን ዕዝ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት ተከትሎም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የአገር መከላከያ ሠራዊት በህወሓት ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ መሰጠቱን በወቅቱ ይፋ አድረገዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው "ይህንን ጡት ነካሽ ኃይል ለማሳፈር እና ለመደምሰስ አስፈላጊውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን እገልጻለሁ" ብለው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሩ መከላከያ ሠራዊት አገር የማዳን ግዳጅ እንደተሰጠውም አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ "ህወሓት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል" ብለዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ "ብዙ ጊዜ የሠላም ስምምነቶች እንደተፈረሙ የሚጣሱ በመሆናቸው ጥፋተኞችን ለፍርድ ከማቅረብ ይልቅ የኃይል ድርጊትን የሚያበረታታ ነው" በማለት የውጭ ሽምግልና አስፈላጊነትን ጥያቄ ውስጥ ከተውታል። ለውጡና ፌደራሊዝም "በአገሪቱ ፍትሕ የለም" የሚሉት ዶ/ር አወል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ባለፈው ሐምሌ ወር ብቻ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች በእስር ቤት ይገኛሉ ይላሉ። ''ምናልባት በትግራይ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ደግሞ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ ሊጨምር ይችላል'' ሲሉ ያስረዳሉ። ተመሳሳይ አስተያየት የሚሰጡት በአሜሪካው ፒስ ኢንስቲቲዩት ውስጥ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ፓይተን ኖፍም "የፖለቲካው መድረክ በድጋሚ ተዘግቷል። ታዋቂ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ታስረዋል፤ ለዐብይ ወደ ስልጣን መምጣት ጉልህ ሚና የነበራቸው ለማ መገርሳ በቤታቸው ውስጥ በቁም እስር ላይ ናቸው" ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ምንይችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በፊት የነበረውን "ጨቋኝ'' ሥርዓት አስወግደዋል ብለው ይከራከራሉ። ''ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታግደው የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዲመለሱ አድርገዋል። የማረሚያ ቤት ሥርዓቱ እንዲሻሻል አድርገዋል። በርካቶች ከስደት ወደ አገራቸው እንዲገቡ አድርገዋል። ችግሩ የተፈጠረው በብሔር ፖለቲካ የሚጠቀሙ ፖለቲከኞች እዚም እዚያም ግጭት እንዲቀሰቀስ በማድረጋቸው ነው'' ይላሉ። አቶ ምንይችል አክለውም ህወሓት ከአውሮፓውያኑ 1991 ጀምሮ ክልሎችን በፌደራላዊ ሥርዓት ስም በብሔር በመከፋፈል አገሪቱን ለዚህ ችግር እንደዳረጋት ይገልጻሉ። ''የብሔር ፌደራሊዝም ለአገሪቱ መከራን ነው ያሸከማት። አንዳንድ ብሔሮች የሆነ አካካባቢ የእነሱ ብቻ እንደሆነና ሌሎች ሰዎች መኖር እንደማይችሉበት እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። በዚህ ፌደራሊዝም ምክንያት ሰዎች ከመኖሪያቸው ተባርረዋል፤ ተገድለዋል፤ ተቃጥለዋል'' ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚተቹ ሰዎች እንደሚሉት፤ አሁን ያለው ብሔርን መሰረት ያደረገ ፌደራላዊ ሥርዓት የሚወገድ ከሆነ በአጼ ሚኒሊክና በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመን ወደነበረው ንጉሣዊ ሥርዓት ይመለሳል። ይህም ሌሎች ማኅበረሰቦች በግድ ተጨፍልቀው የአማራውን ባህል እንዲቀበሉ የሚያደርግ ነው ብለው ቢከሱም፤ በርካቶች ይህ ሐሰት ነው ሲሉ ያስተባብላሉ። "የጠቅላይ ሚኒስትሩ ራዕይ ቀደም ሲል የነበረውን የኢትዮጵያ ባሕላዊ የሥልጣን መዋቅርን የሚመስል ነው" የሚሉት ከአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ተቋም የሆኑት ፋይሰል ሮብሌ "ይህም በአማራ ባህል ዙሪያ የሚያጠነጥንና ልክ እንደራሳቸው ከዚሁ ጋር መመሳሰልን የሚቀበል ሥርዓት ነው" ይላል። ለዚህም ምሳሌ ሲያስቀምጥ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምኒልክን ያወድሳሉ። ቤተ መንግሥታቸውንም መልሰው ገንብተውታል። ኢትዮጵያን መልሰው ታላቅ ለማድረግ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። ነገር ግን የሚያልሟት ኢትዮጵያ ብሔሮች ችላ የተባሉባት ናት። የሚያደንቋቸውን ንጉሥ ሌሎች ወራሪና በባርነት የፈነገሏቸው እንደሆኑ ነው የሚያስቧቸው" ሲል ፋይሰል ይናገራል። አዲስ አቅጣጫ ፈይሰል ባለፈው ዓመት ኢህአዴግን ተክቶ የተመሰረተውን አዲሱን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፓርቲ በተመለከተም ሲናገር፤ ቀደም ሲል ኢህአዴግ ከ10ሩ የአገሪቱ ክልሎች የሚያስተዳድረው አራቱን ነበር። አዲሱ ብልጽግና ፓርቲ ሲፈጠር የፓርቲው የተጽዕኖ ክልል ሰፍቶ ከትግራይ ክልል ውጪ ሁሉንም ክልሎች ማቀፍ ቻለ "በዚህ ጦርነትም ትግራይን ለመቆጣጠር ችሏል" ሲል ፈይሰል ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን እንደመጡ ሕዝቡ "የጠበቀው የፖለቲካ ብዝሃነት፣ በአገሪቱ ያሉ ብሔር ብሔረሰቦች ሰፋ ያለ የባህልና የቋንቋ እውቅና ማግኘት ነበር። ነገር ግን አሃዳዊ ሥርዓትን መርጠዋል" ብሏል። ምንይችል ግን ከፈይሰል በተለየ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፖለቲካዊ ብዝሃነትና ለየትኛውም ብሔር ስጋት አይደሉም ይላል። "አንድነት ማለት ለብዙ ሺህ ዘመናት የያዝከውን የብሔር ማንነት ደብቅ ወይም አጥፋው ማለት አይደለም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያሉት ያለው 'እያንዳንዱ ፖለቲከኛ ስለእራሱ ብሔር ከሚያስበው በመውጣት ወደ ፊት እንደሂድ። ግድያዎችን እናስቁም። በአንድነት በወንድማማችነትና በእህትማማችነት ስለምንኖርባት ኢትዮጵያ እናስብ' ነው።" "ብልጽግና ይህንኑ እያደረገ ነው ያለው። በኢህአዴግ ወደጎን ተገፍተው የነበሩትን ሶማሊዎችን የመሰሉ ማህበረሰቦች ወደ አንድነት አምጥተዋል" ሲል ምንይችል ገልጿል። በከፍተኛ ደረጃ ጽንፍ የወጡ አመለካከቶች ባሉባት ኢትዮጵያ "መንግሥት ፖለቲካዊ ቁርሾዎችንና ቅሬታዎችን የሚያስተነፍስበት መንገድ ማመቻቸት አለበት" የሚሉት ኖፍ ናቸው። "አገሪቱን ወደ አዲስ አቅጣጫ የሚወስድ አማራጭ የለም። ከዚያ ይልቅ በተደራጀ መልኩ ውይይቶች ያስፈልጋሉ፤ ነገር ግን የፖለቲካ መሪዎች እስር ቤት ሆነው ይህንን ማድረግ አይቻልም" ሲሉም ኖፍ ያክላሉ። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት ዶ/ር አወልም "ሽግግሮች በአንድ ፓርቲ የሚመሩ ሳይሆኑ ሁሉን አቀፍ መሆን አለባቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣኑን በማዕከል ይዘውታል። ሁሉም ነገር እሳቸው እንዲመነጭ ይፈልጋሉ" ይላሉ። የኖቤል ሽልማት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ያለፈው ዓመት የሠላም የኖቤል ሽልማትን ያገኙት በቀዳሚነት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለሁለት አስርታት የቆየውን የድንበር ፍጥጫ እንዲያበቃ በማስቻላቸው ቢሆንም በተጨማሪም በአገራቸው ውስጥ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ እርምጃ በመውሰዳቸው ነው። ሽልማቱ በጥድፊያ የተሰጠ ነው የሚሉት ኖፍ "የድንበር መተላላፊያዎች ለአጭር ጊዜ ተከፍተው ተዘጉ። ስለ ሰላም ስምምነቱ በጽሁፍ የሰፈረ ነገር የለም። በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል የተደረሰ መግባባት ነው። በዚህ መልኩ አይደለም ሰላም ማስፈን የሚቻላው" ይላሉ። በአሜሪካ የሚገኙት ሌላኛው ተንታኝ አሌክስ ደ ዋል በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ህወሓትን ለማሸነፍ የተደረገ "የደኅንንት ስምምነት" ነው የሚመስለው ይላሉ። "ኤርትራ በጦርነቱ ከፍ ያለ ሚና ነበራት። በትግራይ ውስጥ 20 ያህል ብርጌዶች እንደነበሩ የሚያመለክቱ ሪፖርቶች ወጥተዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮችም ወደ ኤርትራ ገብተው ነበር" ቢሉም ሁለቱም አገራት ይህንን ሐሰት ሲሉ ያስተባብላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለኖቤል ሽልማት ካጩት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር አወል፤ "አሁን የሆነውን ባውቅ ኖሮ አላደርገውም ነበር። የኖቤል ሽልማት ማግኘት ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ጦርነት ውስጥ የሚገባ ከሆነ ደግሞ ኃላፊነትን ያስከትላል" በማለት ባለሁለት መልክ መሆኑን ይገልጻሉ።
xlsum_amharic-train-165
https://www.bbc.com/amharic/news-53972196
"እንደተወለድኩ ሊገድሉኝ ነበር፤ ዛሬ ገጣሚ ሆኛለሁ"
የተወለደችው በሕንድ ገጠራማ አካባቢ ነው። ኩሊ ኮሂል ትባላለች። ሰረብራል ፓላሲ ከተባለ ህመም ጋር የተወለደችው ኩሊ በሕይወት መትረፏ እድለኛ ያስብላታል።
[ "የተወለደችው በሕንድ ገጠራማ አካባቢ ነው። ኩሊ ኮሂል ትባላለች። ሰረብራል ፓላሲ ከተባለ ህመም ጋር የተወለደችው ኩሊ በሕይወት መትረፏ እድለኛ ያስብላታል።" ]
ህመሙ ሰውነት እንዳይንቀሳቀስ ያደርጋል። የኩሊ ቤተሰብ ጎረቤቶች ልጅቷ ህመምተኛ ስለሆነች ወንዝ ውስጥ ትጣል ብለው ነበር። ቤተሰቦቿ ግን ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ወሰዷት። ወንዝ ውስጥ ትጣል የተባለችው ጨቅላ ዛሬ አድጋ ገጣሚ ሆናለች። ያደገችበት ውልቨርሀምተን ውስጥ ግጥም ለማቅረብ መድረክ ላይ እስክትወጣ የጠበቀችበትን ቀን ታስታውሳለች። በጣም ፈርታ ነበር። ቃላት ከአፏ የሚወጡ አልመሰላትም። አስተዋዋቂው ሲጋብዛት የመድረኩ መብራት እሷ ላይ አነጣጠረ። ታዳሚው አጨበጨበ። ኩሊ እየተንቀጠቀጠች ድምጽ ማጉያውን አነሳች። ለመጀመሪያ ጊዜ ግጥሟን በአድማጭ ፊት ያነበበችው ያን ዕለት ነበር። ህመሟ ንግግሯን፣ እንቅስቃሴዋን፣ የሰውነቷን ሚዛን ያውካል። መድረክ ላይ ወጥታ ግጥሟን ማንበቧ፤ አካል ጉዳተኛ በመሆኗ ሕይወቷ ዋጋ እንደሌለው የነገሯትን ሰዎች ድል የምትነሳበት መንገድ ነበር። “እናቴእንድትጥለኝይነግሯትነበር” ኩቲ በአውሮፓውያኑ 1970 ኡታር ፕራደሽ የተባለ መንደር ውስጥ ነው የተወለደችው። እናቷ እሷን ሲወልዱ 15 ዓመታቸው ነበር። ኩሊ የበኩር ልጅ ናት። በእሷ ምትክ ወንድ ባለመወለዱ ማኅበረሰቡ ተበሳጭቶ ነበር። ሰውን ያስቆጣው ሴት መሆኗ ብቻ እንዳልነበረ ትናገራለች። “ልዩ ስለሆንኩ እንደ እንግዳ ፍጥረት ያዩኝ ነበር። ማንም እንደኔ አይነት ሴት ሊያገባ ስለማይችል እናቴ እንድትጥለኝ ይነግሯት ነበር። በመንደሩ ስለ አካል ጉዳት ግንዛቤ አልነበረም። ችግሬ ምን እንደሆነ የተረዳ አልነበረም። ለቤተሰቦቼ የቀደመ ሕይወት ቅጣት እንደሆንኩ ይነገራቸው ነበር።” የመንደሩ ነዋሪዎች ወንዝ ውስጥ ተጥላ እንድትሰጥም ይፈልጉ ነበር። ሕይወቷን ያተረፉት አባቷ ናቸው። "ወስደው እንደ እቃ ሊጥሉኝ ሲሉ አባቴ አዳነኝ" ትላለች ኩቲ። በዚያ መንደር ውስጥ ልጃቸው ልትኖር እንደማትችል የተረዱት ቤተሰቦች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ተሰደዱ። ያኔ ሁለት ዓመት ተኩል ነበረች። አባቷ የአውቶብስ ሹፌር ሆኑ። ኩሊ ዩናይትድ ኪንግደም ሄዳም ሕይወት አልጋ ባልጋ አልሆነላትም። በዙርያዋ ያሉ ሰዎች "እርግማን ናት" ብለው ማሰባቸው ነገሮችን አክብዶባታል። "ብዙዎች አካል ጉዳተኞች እንደ ማንኛውም ሰው መውጣት፣ መማር፣ ማግባት ወዘተ የሚችሉ አይመስላቸውም" ስትል መድልዎውን ትገልጻለች። በዩናይትድ ኪንግደም የእስያ ተወላጅ አካል ጉዳተኞችን የሚደግፈው ተቋም፤ አካል ጉዳት ለቀደመ ሕይወት ቅጣት ነው ተብሎ መታሰቡ፤ አካል ጉዳተኞች እንዲገለሉ ምክንያት ሆኗል ይላል። ኩሊ የተማረችው በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ከትምርት ቤቱ ውጪ መገለል ይሰማት እንደነበር ታስታውሳለች። "አካል ጉዳተኛ ብለው ሌሎች ልጆች ይጠሩኛል። ቃሉን እጠላዋለሁ። ይጠቋቆሙብኛል፣ ያፈጡብኛል። ቤተ አምልኮ ስንሄድ ራሱ ሰዎች ያዩኛል። ምንም የማልረባ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ያደርጉኛል። ልጆች ለምን እንደዛ ትራመጃለሽ? ለምን እንደዛ ታወሪያለሽ? ይሉኛል።" እድሜዋ እጨመረ ሲመጣ ከሰው ጋር ለመግባባት ትቸገር ጀመር። በንግግር መግባባት ሲያቅታት ወደ ጽሑፍ ተሸጋገረች። አስተማሪዎች ግጥም ሲያነቡ ደስ ይላት እንደነበር ታስታውሳለች። “ከዚያ እፎይታ ለማግኘት ግጥም መጻፍ ጀመርኩ። ስለ ስሜቴ መጻፍ፣ ቃላት ማገጣጠም ደስ ይለኝ ጀመር።" "የምጽፈውእፎይታለማግኘትናለመዝናናትምነው" በ13 ዓመቷ ወደ መደበኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገባች። ከክፍል ጓደኞቿ ጋር ስትግባባ፣ በሥነ ጽሑፍ ስትገባም ነገሮች መሻሻል አሳዩ። "የምጽፈው እፎይታ ለማግኘትና ለመዝናናትም ነው። አካሌ ላይ ጉዳት ቢኖርም አዕምሮዬ ይሠራል። ይሰማኛል፣ አስባለሁ። መጻፍ ኃይል ሰጠኝ።" ኩሊ ትምህርት ቤቷን ወዳው ነበር። ግን ፈተና ትወድቅ ስለነበር አዘነች። በ16 ዓመቷም ከትምህርት ቤት ስለወጣች ዩኒቨርስቲ ላልገባ እችላለሁ ብላ ቅር ተሰኘች። ያኔ ቤተሰቦቿ ሊድሯት መዘጋጀት ጀመሩ። "ቤተሰቦች ለልጃቸው እንደምመጥን ለማየት ይመጡ ነበር። ባህላዊ ልብስ ለብሼ እጠብቃቸዋለሁ። ሲያዩኝ ‘ልጃችን እሷን እንዲያገባ ነው የምትፈልጉት’ ይሉና ወጥተው ይሄዳሉ።" “አካል ጉዳተኛ አይደለም። የእኔ ጉዳትም ግድ አልሰጠውም" ግጥም እንደምትጽፍ ማንም አያውቅም ነበር። አንድ ቀን ግን ሰዎች እንደሚያነቡት ተስፋ ታደርግ ነበር። ሰዎች ስለ ህመሟ እንዲረዱ ማድረግ እንጂ ከንፈር እንዲመጡ አትፈልግም። የትዳር አጋሯን ያገኘችው በዚያ ወቅት ነበር። "መጀመሪያ ብዙ አልወደድኩትም ነበር። ኋላ ላይ ግን ፍቅር ያዘኝ። እሱም ወደደኝ። አካል ጉዳተኛ አይደለም። የእኔ ጉዳትም ግድ አልሰጠውም። ኩሊ የወጣቶች ሥልጠና ዘርፍ ላይ ሥራ ጀምራ፤ ወደ ውልቨርሀምተን የከተማ ምክር ቤት ገብታለች። ከ30 ዓመታት በላይም ሠርታለች። አሁን በአርባዎቹ እድሜ ክልል ትገኛለች። ጥሩ ትዳርና ሦስት ልጆች አሏት። "እንደ እናት፣ ሚስት፣ አማች፣ ሠራተኛ የሚጠበቅብኝ ነገር አለ። አካል ጉዳት ከሌለባቸው እናቶች የሚጠበቀው አይነት ሥራ ላከናውን አልችልም። ገበያ አለመውጣቴ፣ የልጆቼን ጫማ ማስር አለመቻሌም ያበሳጨኛል።" "በጽሑፍ ስሜታቸውን የሚገልጹ. . .ሴቶች ጊዜ አባካኝ ተደርገው ይቆጠራሉ" በከተማ ምክር ቤት ስትሠራ ከሥነ ጽሑፍ ክፍል ሠራተኛው ሳይመን ፍሌቸር ጋር ተገናኘች። ግጥሞቿና አጭር ልብ ወለዷ ላይ አስተያየት እንዲሰጣትም ጠየቀችው። በጽሑፎቿ ውስጥ በሚነበበው ስሜት፣ ስብራት እና እውነተኛነት የተማረከው ሳይመን ጽሑፎቿን ለህትመት እንድታዘጋጅ አበረታታት። ለብዙ ድምጽ አልባ ሴቶች ድምጽ እንደምትሆን ያምናል። እሷም ስሜታቸውን ለመግለጽ የሚከብዳቸው ሴቶችን ለማነሳሳት ቆረጠች። “ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ እንደኔ ያሉ የፑንጃብ [ህንድ ውስጥ ያለች ግዛት] ሴቶችን አውቃለሁ። ያንዳንዶቹ ሴቶች ህልም ሚስት፣ እናት፣ አያት፣ የልጅ ልጅ፣ አማች በመሆን ከስሟል። በጽሑፍ ስሜታቸውን የሚገልጹ የፑንጃብ ሴቶች ጊዜ አባካኝ ተደርገው ይቆጠራሉ። ልጅ መንከባከብ፣ ማብሰል ላይ እንድናተኩር ይፈለጋል። እኔ እድለኛ ሆኜ ከዚህ ቀንበር አምልጫለሁ።" የፑንጃብ ሴት ጸሐፊዎች ማኅበር መስርታ፤ በየወሩ ይገናኛሉ። ራሳቸውን በነፃነትም ይገልጻሉ። ስለ ጠጪ ባሎች፣ የቤት ውስጥ ጥቃት እንዲሁም ስለ ሕይወት ውብ ነገሮችም ያወራሉ። ለመጀመሪያ ጊዜ ግጥሟን መድረክ ላይ ያነበበችው ከሦስት ዓመት በፊት ነው። "ህልም አለኝ" ስትል ነበር ንባቧን የጀመረችው። "ለ15 ደቂቃ ያህል ወደ 40 ሰዎች በተሰበሰቡበት ግጥሜን አነበብኩ። ትንሽ ቃላት ብገድፍም በቻልኩት መጠን በግልጽ ለማናገር ሞክሬያለሁ። አድማጩ ግጥሜት በትዕግስትና በጉጉት ነበር የተቀበለው። አካሌ ላይ ጉዳት ቢኖርም አዕምሮዬ፣ ልቤና ነፍሴ ያገለግላሉ። መድረክ ላይ የተዋጣላት አንባቢ ላልሆን እችላለሁ። ግን እሻሻላለሁ።" የኩሊ በራስ መተማመን ለፑንጃብ ሴቶች ስብስብም መነሳሳት ፈጥሯል። አምና የቡድኑ አባላት ሥራዎቻቸውን በአንድ ፌስቲቫል ላይ አቅርበዋል። የ49 ዓመቷ ኩሊ፤ ብዙ አሳልፋ እዚህ ደርሳለች። የደረሰችበትን ድምዳሜ እንዲህ ትገልጻለች፦ "የደረስኩበት ድምዳሜ አካል ጉዳት የመላው ማኅበረሰቡ ችግር እንደሆነ ነው። ማኅበረሰባችን አካል ጉዳተኞችን አይደግፍም። የግል ጉዳዮቻቸው እንዲሁም ችግሮቻቸውን በቁም ነገር የሚወስድ የለም። ጉዳዮቻቸውና ችግሮቻቸው ይድበሰበሳሉ። ሁላችንም በተወሰነ ደረጃ የአካል ጉዳት አለብን። ይህም ስለ አካል ጉዳት ያለን የተዛባ አመለካከት ነው። ይህን አመለካከት ለመቅረፍ በርካታ ትውልዶች ማለፍ አለብን።"
xlsum_amharic-train-166
https://www.bbc.com/amharic/news-54483065
የሴቶች መብት፡ "ወሲባዊ ጥቃቶችና ግድያ ማስፈራሪያዎች፣ አፀያፊ ስድቦች..."- በኢንተርኔት የሴቶች ጥቃት
ሜይትሬይ ራማክሪሽናን በኔትፍሊክስ ላይ ለዕይታ በበቃው 'ኔቨር ሃፍ አይ ኤቨር' የኮሜዲ ፊልም ላይ በመሪ ተዋናይነት ከፍተኛ እውቅናን አትርፋለች።
[ "ሜይትሬይ ራማክሪሽናን በኔትፍሊክስ ላይ ለዕይታ በበቃው 'ኔቨር ሃፍ አይ ኤቨር' የኮሜዲ ፊልም ላይ በመሪ ተዋናይነት ከፍተኛ እውቅናን አትርፋለች።" ]
የ18 ዓመቷ ተዋናይት የመሪ ተዋናይነቱን ቦታ ያገኘችው ከአስራ አምስት ሺህ ተወዳዳሪዎች መካከል ነው። በኔትፍሊክስ ላይ ከፍተኛ ተመልካች ካገኙ ፊልሞች መካከል በሆነው በዚህ ፊልም ላይ ከስደተኛ የሕንድ ቤተሰቦች በአሜሪካ የተወለደችና ስደተኝነትን፣ ባህልና አሜሪካዊ ታዳጊ መሆንን ለማጣጣም የምትጥር ገፀ-ባህርይን ወክላም ተጫውታለች። በፊልሙም ላይ ባሳየችው የትወና ችሎታም ከፍተኛ አድናቆትን ማትረፍ ችላለች። ያገኘችው ድንገተኛ ዝናም በተወሰነ መልኩም ቢሆን ተወዳጅ ብቻ የምትሆን መስሏት ነበር። "ለሥራውም ቢሆን እንደዚህ አይነት ቃለ መጠይቆች ራሴን አዘጋጅቻለሁ። በጭራሽ ያልጠበቅኩትና መቼም ቢሆን ላዘጋጅ የማልችለው በኢንተርኔት ላይ ለገጠመኝ ጥላቻ ነው" ትላለች። ሜይትሬይ የኢንተርኔት ጥላቻ የምትለው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የገጠማትን ትንኮሳ ነው። "እንዲህ አይነት ትንኮሳ እንደሚያጋጥም መጠበቅ አለብኝ፤ ምክንያቱም የምንኖርባት ዓለም ይህቺ ናትና" በማለትም ታስረዳለች። አክላም "አፀያፊና ዘግናኝ የሚባሉ አስተያየቶች ይፃፉብኛል። የሞት ማስፈራሪያዎችም ይደርሱኛል። እንዲህ አይነት ነገር ያው በእውነታ ሲያጋጥም ሌላ መልክ ይኖረዋል" ትላለች። ካናዳዊቷ ተዋናይት በማኅበራዊ ሚዲያ የሚገጥማት የሞት ማስፈራሪያም ሆነ ትንኮሳና ስድብ ግራ ስላጋባትም ለተወሰነ ጊዜም አካውንቶቿን ሁሉ ዘግታለች። "የተወሰነ ወቅት ላይ ሁሉንም የማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች እኔ ነበርኩ የምቆጣጠራቸው። የራሴን ድምፅ በትክክለኛ መልኩ ማሰማት ስለምፈልግ ነበር ያንን የማድርገው" የምትለው ተዋናይቷ "በአሁኑ ጊዜ ግን አካውንቶቼን ዘግቼ እረፍት እየወሰድኩኝ ነው" ትላለች። 'በርካታ ታዳጊዎችና ሴቶች ትንኮሳና ጥቃት በኢንተርኔት ይደርስባቸዋል' ሜይትሬይ ታዋቂ ተዋናይት ስለሆነች ነው እንዲህ አይነት ትንኮሳዎችን፣ ዘግናኝና አፀያፊ ስድቦችን የምታስተናግደው ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል። ከ15 አስከ 22 እድሜ ያሉ 14 ሺህ ታዳጊዎችና ሴቶች ተመሳሳይ ትንኮሳ እንደሚደርስባቸውም በቅርቡ የተሰራ የዳሰሳ ጥናት ይፋ አድርጓል። እነዚህም ታዳጊዎችና ሴቶች በሃያ አገራት ነዋሪዎች ናቸው። ለዚያም ነው ተዋናይቷ በሥርዓተ-ፆታ እኩልነትና፣ ትንኮሳዎችን ለመከላከል በሚሰራው ፕላን ኢንተርናሽናል ለተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አምባሳደር የሆነችው። በዳሰሳ ጥናቱ ላይ ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው 58 በመቶ ያህሉ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ትንኮሳ ወይም ጥቃትን አስተናግደዋል። ከአስሩ ስምንቱ ደግሞ አፀያፊና፣ ዘግናኝ፣ ዘረኛ ስድቦችን እንዲሁም የወሲባዊ ጥቃት ማስፈራሪያዎቸ እንደገጠማቸው ተናግረዋል። "ይሄ መቼም ቢሆን ዝም ሊባል የሚገባው ጉዳይ አይደለም። ኢንተርኔት በርካታ ዕውቀቶችን የምንማርበት መድረክ ነው። ሆኖም በዚህ ፋንታ ታዳጊዎችና ሴቶች የየቀኑ ህይወታቸው አልበቃ ብሎ በኢንተርኔትም ላይ ተመሳሳይ ትንኮሳ ማጋጠሙ አሳዛኝ ነው" ትላላች ሜይትሬይ። በኢንተርኔት ላይ የሚደርስ ጥቃት ሴቶች ከማኅበራዊ ሚዲያ እንዲወጡ እየገፋቸው ነው። ፕላን ኢንተርናሽናል በሰራው የዳሰሳ ጥናት መሰረት ከአምስት ታዳጊና ሴቶች መካከል አንዷ በኢንተርኔት ላይ በሚፈጸመው ትንኮሳና ጥቃት ምክንያት የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንታቸውን ይዘጋሉ ወይም የሚያሳልፉትን ጊዜ ይቀንሳሉ። እነዚህ ጥቃቶች በአብዛኛውን የሚያጋጥሙት በፌስቡክና በኢንስታግራም ላይ መሆኑንም ጥናቱ አመልክቷል። ሴቶች በዚህ መንገድ ከማኅበራዊ ሚዲያ መገለላቸው በተለይም በዚህ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት በርካቶች ኢንተርኔትን ሙጥኝ ባሉበት ጊዜ መሆኑ አሳዛኝ እንደሚያደርገው የፕላን ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አን ብሪጂት አልብሬክትሰን ተናግረዋል። "ታዳጊዎችንና ሴቶችን ከኢንተርኔቱ መድረክ በዚህ መንገድ ማባረር በጣም አሳፋሪ ነው። በተለይም በዚህ ዲጂታል ዓለም ላይ ሴቶች የሚሰሙበትና መሪ የሚሆኑበትን አቅም ማሳጣትም ነው" ብለዋል ሥራ አስፈፃሚዋ። "እነዚህ ጥቃቶች አካላዊ ላይሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ማስፈራሪያ፣ ስድብና ትንኮሳው ራሳቸውን በነፃነት እንዳይገልፁ ይገድባቸዋል፤ ያሳስራቸዋል" ብለዋል። የሰብዓዊ መብት ታጋይዋ ወሲባዊና የዘረኝነት ጥቃት ማስፈራሪያዎች ደርሰውባታል የአስራ ዘጠኝ ዓመቷ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ፌሚኒስት ናዱስካ በአገሯ ኒካራጓ በተወሰነ መልኩ ትንኮሳን ብታስተናግድም በከፍተኛ ሁኔታ ያስደነገጣት ግን ስፔን በሄደችበት ወቅት መሆኑን ትናገራለች። በባለፈው ዓመት የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ በተደረገው ዘመቻ ወደ ስፔን ያቀናችው ናዱስካ፤ ማስፈራሪያዎችን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማስተናገዷን ታስታውሳለች። የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ፌሚኒስት ናዱስካ በርካታ የጥላቻ መልዕክቶች እንደደረሷት የምትናገረው ናዱስካ አንዳንዶቹም "መጤ ነሽ ከአገር እናባርርሻለን፤ እንደበድብሻለን" የሚሉም ነበሩ። "በጣም ነው ያስፈራኝ። በእውነቱ በኢንተርኔት ላይ ደኅንነት አይሰማኝም" ትላለች። በተደጋጋሚ ትንኮሳና ጥቃቶችን ያስተናገደችው ናዱስካ ሁኔታው በጣምም ስለረበሻት የአዕምሮ ጤንቷንም በተወሰነ መልኩ ነክቶት ነበር። የሥነ ልቦና አማካሪዎችን ማየት እንዲሁም መድኃኒትም መውሰድ ጀምራለች። በተለያዩ አገራት መሬት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በተመሳሳይ በኢንተርኔት ላይ የሚያጋጥሙ ሲሆን በተለይም አናሳ ማኅበረሰብ ተብለው በሚታሰቡና የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ላይ ጥቃቱ እንደሚበረታም የዳሰሳ ጥናቱ ይፋ አድርጓል። "እንደ ሚቱ (እኔም) እና የጥቁር ህይወት ዋጋ አለው (ብላክ ላይቭስ ማተር) የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ማኅበራዊ ሚዲያው ምን ያህል ለትግሉ ጠቃሚ መድረክ እንደሆኑ አሳይተዋል" ይላሉ አን ብሪጀት። ጥናቱ ይፋ ያደረገው እውነታ የሚረብሽ እንደሆነ የሚናገሩት ሥራ አስፈፃሚዋ፤ ከፍተኛ ትንኮሳ ያለበት አህጉር አውሮፓ ሲሆን ይህም 63 በመቶ የሚሆኑ ታዳጊዎች በኢንተርኔት ላይ የሚደርስባቸውን ትንኮሳ ሪፖርት አድርገዋል። ዝቅተኛው ደግሞ ሰሜን አሜሪካ ሲሆን ቁጥሩም 52 በመቶ ነው። "በአካል ከሚደርስባቸው ትንኮሳ በላይ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በታዳጊዎች ላይ የሚደርስው ትንኮሳ ከፍተኛ ነው" ይላሉ ሥራ አስፈፃሚዋ። በሥርዓተ ፆታ እኩልነት ላይ የሚሰሩ ግለሰቦችም እንዲህ አይነት ትንኮሳዎች ሙሉ በሙሉ ሴቶችን ከኢንተርኔቱ መድረክ እንዳያርቃቸውም ይፈራሉ። "ወንዶች የብልታቸውን ፎቶ በተደጋጋሚ መላካቸው አስድንጋጭ ነው" ለማኅበራዊ ሚዲያ አዲስ የሆኑ ሴቶች በኢንተርኔት ላይ የሚከናወኑ ትንኮሳዎችም ሆነ አንዳንድ ያልተገቡ ድርጊቶች ተስፋ አስቆራጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ኡጋንዳዊቷ፣ የ20 ዓመቷ ካቲ ትናገራለች። ከሦስት ዓመት በፊት የማኅበራዊ ሚዲያ ገጿን ስትከፍት የተሰማትም ስሜት ይሄው ነው። በልብስ ሰፊነት እናቷን፣ እህቷንና ወንድሟን የምታስተዳድረው ካቲ ማኅበራዊ ሚዲያን የተቀላቀለችው ካለባት የሥራ ጫና እፎይታና እረፍት አገኝበታለሁ በሚል እሳቤ ነበር። ነገር ግን በፌስቡክ የተዋወቀችው ሰው ራቁቱን እንዲሁም የብልቱን ፎቶ እየላከ ያስጨንቃት ጀመር። የ 20 አመቷ ካቲ "አንድ ግለሰብ በፌስቡክ ላይ 'ሃይ' የሚል መልዕክት ላከልኝ፤ እኔም በምላሹ 'ሃይ' አልኩት"፤ ቀጥሎም "እንዴት ነሽ ሲለኝ ምላሽ ሰጠሁኝ" ትላለች። "በነገታው ስነቃ ሌሊቱን ሙሉ ራቁቱንና ብልቱን የሚያሳዩ በርካታ ፎቶዎች ልኮልኛል። በጣም ነው የደነገጥኩት" ትላለች። ካቲ ብቻ ሳትሆን በርካታ ታዳጊዎችና ሴቶች ይህ ሁኔታ በተደጋጋሚ እንደሚያጋጥማቸው ይናገራሉ። በጥናቱም ላይ ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸውም መካከል 40 በመቶ የሚሆኑት ታዳጊዎች እንዲህ አይነት ጥቃቶች የየቀኑ ገጠመኛቸው እንደሆነ ተናግረዋል። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችንም ለመከላከል በርካታ ጥሪዎች እየቀረቡ ሲሆን አንዳንድ ኩባንያዎችም ፕሮግራሞችን ዘርግተዋል። የኢንስታግራምና የዋትስአፕ ባለቤት የሆነው ፌስቡክ፤ ትንኮሳ ይደርስብናል የሚሉ ሪፖርቶችን በጥንቃቄ እንደሚከታተልና የመድፈር ማስፈራሪያዎች ደግሞ ሲሆኑ ወዲያው እንደሚያስወግድ አስታውቋል። የታዳጊዎችንና የሴቶችን ደኅንነት በኢንተርኔት ላይ ለመጠበቅም ቁርጠኝነት እንዳለው የሚናገሩት የፌስቡክ የሴቶች ደኅንነት የበላይ ኃላፊ ሲንዲ ሳውዝወርዝ በዓለም ላይ ካሉ 200 የደኅንነት ተቋማትም ጋር በመተባበር በኢንተርኔት ላይ የሚደረገውን ጥቃት ለመከላከል እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ትዊተርም እንዲሁ በሴቶች ላይ በኢንተርኔት የሚደርሱ ጥቃቶችን ሴቶቹ ሪፖርት የሚያደርጉትን ከመከታተል በተጨማሪ የሚቆጣጠር ቴክኖሎጂም እየተጠቀመ እንደሆነም ገልጿል። ሌላኛው ማኅበራዊ ሚዲያ ስናፕቻት ቃለ አቀባይም ለትንኮሳዎች፣ ማስፈራሪያዎችና ጥቃቶች ምንም አይነት ቦታ እንደሌለውና የማያውቋቸውን ግለሰቦች መልዕክት መላክ በማይቻልበት መንገድም ለመቆጣጠርም እንደሚሞከር አስታውቋል። ቲክቶክ ይህ ዘገባ በሚዘጋጅበት ወቅት ምላሽ እንዲሰጠው ቢጠይቅም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። በሥርዓት ፆታና ዲጂታል መብቶች ላይ የሚሰሩት ቼናይ ቼይር በአሁኑ ወቅት በኢንተርኔት ላይ ጥቃት የደረሰባቸውን በማገዝ አብረው እንደሚገኙ ገልፀው ማኅበራዊ ሚዲያዎች በእነዚህ ጥቃቶች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። ተዋናይቷ ሜይትሬይ በበኩሏ ታዳጊዎችና ሴቶች ሪፖርት የሚያደርጉበትን መንገድ ከማጠናከር በተጨማሪ እነዚህ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ከመጀመሪያው ጥቃት እንዲፈጸም መፍቀድ የለባቸውም ትላለች።
xlsum_amharic-train-167
https://www.bbc.com/amharic/news-44622938
የትናንትናዋ እለት- በኢትዮ ኤርትራ ግጭት ቤተሰባቸው ለተለያየ?
እርሱ ኢትዮጵያ ፤ ወንድሙም ኤርትራ ውስጥ ጋዜጠኛ ነበር።
[ "እርሱ ኢትዮጵያ ፤ ወንድሙም ኤርትራ ውስጥ ጋዜጠኛ ነበር።" ]
ሁለቱ ወንድማማቾች ጋዜጠኛ ዮናስ አብርሃምና ጋዜጠኛ በረከት አብርሃም ለተለያየ አገር የመንግስት ስርዓት ጋዜጠኛ ሆነውአንዳቸው ሻእቢያ ፤ሌላኛቸው ደግሞ ወያኔ እያሉ ፅንፍ ለፅንፍ ሆነው ሲዘግቡ ዓመታት ተቆጥረዋል። ጋዜጠኛና ደራሲ ዮናስ አብርሃም ተውልዶ ያደገው ኢትዮጵያ ነው። በሁለቱ አገራት ጦርነት ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዜጠኝነት ተቀጥሮ ይሰራ ስለነበር ከርሱ ውጭ ያሉ የቤተሰቡ አባላት ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ እርሱ ኢትዮጵያ ተነጥሎ ኢትዮጵያ ቀርቷል ። "እናቴ በአውቶብስ ተሳፍራ ስትሄድ ተደብቄ አያት ነበር" ሲል ከቤተሰቡ ጋር የተለያየበትን ጊዜ ያስታውሳል። ላለፉት ሃያ ዓመታት ከቤተሰቦቹ ጋር በዓይነ ስጋ እንዳልተገናኘ የሚናገረው ዮናስ በቅርቡ በረከትን ጨምሮ ሌሎች ወንድሞቹ በድንበር አካባቢ ጠፍተው ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።ይሁን እንጂ በተወለዱበት አገር ስደተኛ እንደሆኑ ይናገራል። "የአገራቱ ድንበር ያለው ዛላምበሳ፣ ባድመና የመሳሳሉት የድንበር መስመሮች ላይ ብቻ አይደለም ፤ የእናታችን ማህፀን ውስጥም ድንበሩ አለ ማለት ነው" ሲል የሁለቱ አገራት ቁርሾ ያስከተለውን ጣጣ ይናገራል። አሁን ሁለቱ አገራት የጀመሩት የሰላም ግንኙነት ሃዘን የሚያበቃበት፣ አዲስ ተስፋ የሚመጣበትና አገራቱንና ህዝቡን የሚጠቅም እንደሚሆን ተስፋ አለው። "ተስፋ ቆርጨ ስለነበር ግንኙነቱ ይበልጥ አስደናቂ ሆኖብኛል" ብሏል። ሳሚያ እዮብ የተወለደችው አስመራ ነው። ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ገና የስድስት ዓመት ልጅ እያለች ነው። ኢትዮጵያዊቷ ሳሚያን የሁለቱ አገራት ጠብ ከአባቷ ጋር ለያይቷታል። ከ 1993 ዓ.ም ጀምሮ በምንም ዓይነት አጋጣሚ ከአባቷና ቤተሰቦቹ ጋር ተገናኝታ አታውቅም። አሁን ሁለቱ አገራት የጀመሩት የሰላም ግንኙነት አባቷን ለማየት ተስፋ እንደሰጣት ትናገራለች፤ ትንሿ ሮማ የምትባለውን ኤርትራን መጎብኘትም ትሻለች። ከኤርትራ ለመጣው ከፍተኛ ልዑካን አቀባበል ለማድረግ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተገኘችው ድምፃዊት ፀደኒያ ገብረ ማርቆስም ሁለቱ አገራት የጀመሩት የዕርቅ ጉዞ ታሪካዊ አጋጣሚ እንደሆነ ትገልፃለች። "ከዚህ በኋላ ምን እንደሚሆን ባላውቅም፤ ጥሩ ነገር ይፈጠራል ብየ አስባለሁ፤ ግንኙነቱም መልካም ይሆናል" ትላለች። ቀኑን በጉጉት ሲጠባበቅ የነበረው አትሌት ስለሺ ስህን ዛሬ በሁለቱ አገራት መካከል የነበረው ነገር በጣም ደስ የሚል እንደነበር ይገልፃል። "አንድ ቀን ጠንካራ መሪ ሲፈጠር ሁለቱን አገራት አንድ ያደርጋል" ሚል ተስፋ እንደነበረውም ይናገራል። "ይህ ቀን የሰላም ቀን ብዬ አሰብኩት" ያለን ደግሞ አትሌት ገብረ እግዚያብሔር ገ/ማሪያም ነው። አቀባበል ለማድረግ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ረጅም ሰዓት እንደቆየ የሚናገረው አትሌቱ መዘግየታቸው ስጋት ፈጥሮበት እንደነበርና ልዑካኑን የያዘው አውሮፕላን ሲያርፍ ግን ሰላም ከዛሬ ጀምሮ እውን ሆኗል ማለት ነው የሚል ስሜት እንደተሰማው ገልፆልናል። ሌሎች ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጭዎችም ሰላም እንደሚፈጠር ይጠብቃሉ። ከዚህ በፊት በነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር ስምምነት አለመደረጉን ገልፀው አሁን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር የጀመሯቸው መልካም ግንኙነቶች ዕርቅ ላይ እንደሚያደርስ ተስፋቸውን የገለፁም አሉ። "ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያንን እንወዳለን፤ እነሱም እንደሚወዱን ተስፋ አደርጋለሁ። ህዝብ ለህዝብ ቅርርብን ለመፍጠር መንግስታቱ ጠንክረው ቢሰሩ ደስ ይለኛል፤ እኔም ወደ አስመራ መሄድ እፈልጋለሁ" ብላች አንድ አስተያየት ሰጭም። የአገራቱ ስምምነት ኢትዮጵያን ወደብ ተጠቃሚ ያደርጋታል፤ ይህ ደግሞ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል የሚል ጉልህ ተስፋ እንዳላቸውም ገልፀውልናል።
xlsum_amharic-train-168
https://www.bbc.com/amharic/news-55945193
"ለምን ስሜን ለ20 ዓመታት ደበቅኩ?"
ለእኛ ስም ማለት ቁልፍ ነገር ነው። ስማችን ከታወቀ አዲስ ያልተነገረ ታሪክ ሊያጋልጥ ይችላል። ታዲያ ሌሎቹን ለማስደሰት ሲባል ስንቀይረው የሚያደርሰው ተጽዕኖ እንዴት ይገለጻል? ' የእኔነቴን ትልቅ ነገር ደብቄያለሁ '
[ "ለእኛ ስም ማለት ቁልፍ ነገር ነው። ስማችን ከታወቀ አዲስ ያልተነገረ ታሪክ ሊያጋልጥ ይችላል። ታዲያ ሌሎቹን ለማስደሰት ሲባል ስንቀይረው የሚያደርሰው ተጽዕኖ እንዴት ይገለጻል? \n\n' የእኔነቴን ትልቅ ነገር ደብቄያለሁ '" ]
አፒያህ-ዳንጓህ ስሟን ለማስመለስ 20 ዓመት ፈጅቶባታል "በ1980ዎቹ አጋማሽ እና በ1990ዎቹ መጀመሪያ ምስራቅ ለንደን ውስጥ ማደግ አሁን እንዳለው አልነበረም" ትላለች ሚሪያም አፒያህ-ዳንቋህ። "አንደኛ ደረጃ ስንማር እኔ ከአምስት ጥቁሮች መካከል አንዷ ስሆን በተጨማሪ አንዲት ህንዳዊት ነበረች። ቀሪዎቹ ግን ሁሉም ነጮች ነበሩ" በማለት ታስታውሳለች። "አንዱ የቆየው ትዝታዬ መዋዕለ ሕጻናት እያለሁ እናቴ 'ትዊ' ብላ የጠራችኝ ነው [ጋና ውስጥ የሚነገር ቋንቋ ነው]። ያኔ ሦስት ወይም አራት ዓመት ቢሆነኝ ነው። እናም "ይህንን ቋንቋ እዚህ አንናገርም" ነበር ያልኳት። "በእርግጠኝነት በአፍሪካዊነቴ እንዳፍር እና በዚያ እድሜዬ እንደዚያ መናገር ማለት የሆነ አካል እኔነቴ ትክክል አለመሆኑን ይነግረኛል የሚል እሳቤ የነበረኝ ይመስለኛል" "አስታውሳለሁ፣ ከጥቁር አፍሪካዊ ጋር በመጣመሬ እና የተለየ የጸጉር አሰራር ስለነበረኝ ብቻ ከተማሪ እስከ ተማሪ መዘባበቻቸው ነበርኩ። ሚሪያም በ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' ወቅት በኢንስታግራም ድምጽ ለመሆን ተነሳስታ ነበር የአንደኛ ደረጃ ትምህርቷን ስትጀምር ሚሪያም ዳንቋህ የሚለውን ስም በትምህርት ቤት ውስጥም ሆነ የመማሪያ ደብተሯ ላይ መጻፏን አቆመች። ይህ የሆነው ደግሞ አስተማሪዎቿ ስሙን መጠቀም እንደሌለባት ትዕዛዝ በመስጠታቸው ነበር። ከዚያም ቀደም ብላ ያገኘቻቸው የምስክር ወረቀቶች ሁሉ ላይ ሳይቀር እየለቃቀመች ስሟን ማጽዳት ዋነኛ ሥራዋ ሆነ። "ሁሉም ብራውን፣ ስሚዝ፣ ዋይት ወይም ጆንስ እየተባለ ሲጠራ የእኔው ስም ግን ረጅም እና የተለየ ሆነ። እናም ያ አፍሪካዊነቴን ስለሚያስባንን የትኛውም ሰነድ ላይ ስሜ እንደይገኝ ማድረግን ቀዳሚ ሥራዬ አደረግኩ። "ዩኒቨርሲቲ ገብቼ ከዚያ ሥራ ጀመርኩ። ዳንቋህ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል፤ ማንም አያውቀውም ነበር። ምክንያቱም ከማንኛውም ሕጋዊ ሰነድ ላይ ስላስወገድኩት ማንም አላወቀውም ነበር።" ባለፈው ሰኔ ዓለም አቀፉ የብላክ ላይቭስ ማተር አመጽ ሲቀጣጠል ከ20 ዓመታት በኋላ ሚሪያም ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ስሟን በኢንስታግራም ጻፈች። "የጆርጅ ፍሎይድ መገደል እና ቀጥሎ የመጣው ተቃውሞ ለእኔ ትልቅ የማንቂያ ደወል ነበር። ትልቁን አኔነቴን ደብቄው መቆየቴ ተገለጸልኝ። ይህ ደግሞ የእራሴን ማንነት እና ጥቁርነቴን የሚያካትት ነው" ትላለች የ34 ዓመቷ አካውንታት። "የእርሱ ሞት የመጨረሻ ደወል እና ብዙዎቹን ወደፊት ያመጣ፣ ምናልባትም ለብዙዎቻችን ወደ ትክክለኛ ማንነታችን [ጥቁር ማንነት] የመለሰ ነው። ጥቁር በመሆናችን ራሳችንን ጨቁነን ነበር፤ ሰላም ማስፈን መርጠን ጥቁር በመሆን ተቀባይነት የማያስገኙ ብለን የደበቅናቸው ነገሮች ነበሩ። "የመጣልኝ ሃሳብ ለዓመታት የኖርኩት ኑሮ የውሸት እንደነበር ነው፤ ንዑስ ማንነቴን መኖር ስለማይገባኝ እንደ ጥቁር ሴት ሙሉ ሆኜ የምኖርበትን ሁናቴ መፈተሽ ግድ ይለኛል።" ሙሉ ስሟን የሚገልጽ ጽሑፍ ካጋራች በኋላ ሚሪያም ነጻነት ተሰምቶኛል ትላለች። ይህ ጽሁፏም እስከዛሬ ካጋራቻቸው ጽሁፎች ሁሉ ላቅ ያለ ተወዳጅነትን ያተረፈ እና "በርቺ" አይነት በርካታ ኮመንቶችንም አስተናግዷል። "ስሜት የሚነካ ነበር፤ እናም አልቅሻለሁ" ትላለች። "ልክ ሰዎች እና ማህበረሰቡ እኔን በእኔነቴ እንዲገልጸኝ ለማድረግ ራሴን ይቅር እንደማለት ያክል ነበር። "አፒያህ ማለት ልዑል ማለት ሲሆን ዳንቋህ ደግሞ ዘላለማዊ ሕይወት ማለት ነው። ታዲያ ይህ ለምን ይደበቃል? ይህ ስሜ ነው፤ እኔ ማለት እንደዚህ ነኝ።" 'የማንነት ቀውስ ነበረብኝ' ራኪሻና ካንዋል ኢጃዝ ስሟን በመደበቅ ሮክሲ ብለው እንዲጠሯት አድርጋ እንደነበር ተናግራለች ራኪሻና ካንዋል ኢጃዝ ተወልዳ ያደገችው በእንግሊዝ በርሚንግሃም ሲሆን ከፓኪስታን ተሰደው ከመጡ ቤተሰቦች የተገኘች ነች። እንደሚሪያም ሁሉ ራኪሻና ከስሟ ጋር ትግል የጀመረችው ከትምህርት ቤት ነው። ሌሎች ሲጠሩትም ሆነ ሲያነቡት ቀላል ይሆንላቸዋል ባለችው ስም ቀይራ ተመዘገበች። ምክንያቱም አንዳንድ አስተማሪዎች ራኪሻና የሚለውን ስሟን ፊደላት በናጉደል ራክሻና ወይም ራክሳና ይሉታል። "አይ! መጻፍ ያለበት እንደዚህ ነው ስል በተወሰነ ደረጃ ቁጣ ይሆንባቸዋል፤ ነገር ግን የተወሰነ ነገር ካልኩ ድርቅና ተደርጎ ይቆጠራል" ትላለች። ይመስለኛል ያ ስሜን እንድጠላው አድርጎኛል፤ እናም ሳድግ ስሜን እቀይራለሁ እያልኩ ለቤተሰቦቸ እቀልድላቸው ነበር።" የ27 ዓመቷ ወጣት በአባቷም በማህበረሰቡም ስም ቢወጣላትም ችግሮች ገጥመዋታል። "ስሜ የተለመደ አይደለም፤ ምክንያቱም መነሻው ፐርሽያ ስለሆነ- ፋርሲ እና ኡዱ ይባላል። እናም ፓኪስታኖች እና ሌሎች ሙስሊሞች ሳይቀሩ ስምሽ ከየት የመጣ ነው ብለው ይጠይቁኛል። "እናም ለተወሰነ ጊዜ ከየት እንደሆንኩ ስለማላውቅ የማንነት ቀውስ ውስጥ ገብቼ ነበር፤ የማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ለመጥራት ስለሚቸገሩ ለእኔ ከባድ ነበር።" ራኪሻና እንደምትለው በእዚህ ምክንያት ያዳበረችው የዝቅተኝነት ስሜት ዩኒቨርስቲ ስትማር ከዚያም ሥራ እስክትጀምር ድረስ አብሯት ቆይቷል። "ስሜን አልጠላሁትም፣ ግን ደግሞ ማካካስ ነበረብኝ" የምትለው ራኪሻና "ጓደኞቼን 'ሮክሲ ብላችሁ ጥሩኝ' እላቸዋለሁ። እናም ከተወሰኑ ሥራዎች በኋላ ሮክሲ ወይም ሮክሳኔ በሚል ታወቅኩ፤ ማንም ግን እውነተኛ ስሜን አያውቀውም። "ወደኋላ ስመለከት፣ ሳያውቁኝ መኖራቸው ምን ያክል የሚያናድድ መሆኑን አስባለሁ።" ራኪሻና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፊት ስሟን ቀይራ እንደነበር ማሳወቅ ጀምራለች። ከዚያም ባል ስታገባ የባሏን ስም ደርባ መያዝ እንዳለባት ወስና በዚያው ቀጥላለች። "አባቴ ያወጣልኝን ስም ማጣት አልፈልግም። ካንዋል ማለት የውሃ ላይ አበባ ወይም ጣፋጭ ፍሬ ማለት ነው። ሁልጊዜ እንደዚያ ነው የሚጠራኝ። "ስሜን ትቼ በባሌ ስም ብቻ መወሰን አልፈለግኩም። ምክንያቱም ከባሌ በፊት የነበረው እኔነቴ አሁን ላለኝ ማንነቴ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል። ወደፊትም ይሆናል። እናም ያንን የህይወቴን ክፍል ማስወገድ አልችልም። ስም ብዙ ኃይል ይሸከማል።" የራኪሻና አባት ባለፈው ዓመት አርፈዋል። እናም እራሷ ቤተሰብ በመመስረቷ ሰዎች ትክክለኛ ስሟን እንድትይዝ እየጎተጎቷት ነው። "አባቴ በስሜ ሁሌ እነደኮራ ነበር፤ ነገር ግን ወጣት እስክሆን ድረስ ስሙ ለምን እንደተሰጠኝ አልገባንም ነበር" ብላለች የሁለት ልጆች እናቷ ራኪሻና። "አሁን በእሱ ምክንያት በእኔነቴ ኮርቼው የማላውቀው ኩራት እየተሰማኝ ነው። ሁሉም ለእኔ ያደረገው ነገር ሁሉ ያኮራኛል።" "አሁን ተመልሼ ወደኋላ ስመለከት፣ ሌሎቹን ለማስደሰት ሲባል የራሴን ስም ለ20 ዓመታት ማሳሳቴ ምን ያክል እብደት እንደሆነ ነው የገባኝ" ትላለች። "ለሰዎች ሲባል ማንነታቸውን መቀየር እንደሌለባቸው ነው ለሰዎች የምናገረው። ለሌሎች ሰዎች ድክመት ሲባል የእኔን ስም ማሳሳቴን አቁሜያለሁ። "ዳዕነሪስ ታርጋሪየን [ጌም ኦፍ ትሮንስ] የሚለውን መጥራት ከቻልን ብዙ ልንጠራቸው የምንችላቸው ስሞች አሉ። ዋናው መሞከሩ ነው" 'ስምሙ ለመሆን እፈልግ ነበር' ግሪጎሪጂ ሪቸርስ ለሥራው ያመቸው እንደሁ በሚል ስም መቀየሩን ያስታውሳል ገሪጎሪጂ ሪቸርስ የተወለደው ጀርመን ቢሆንም የቼክ ዜግነት ያላት እናቱ ያወጡለት ስም ግን የሩሲያ ነው። ስምሙ ለመሆን ሲባል የ15 ዓመት ታዳጊ እያለ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለአዳሪ ትምህርት ቤት ሲላክ ስም መቀየሩን ይናገራል። "ስሜ ግሪ-ጎ-ሪጅ ተብሎ ነው የሚነበበው፤ በእንግሊዝኛ ሲሆን ግን ክራይግ-ሪጅ ይሆናል። ስለዚህ እንደ አንድ ደኅንነቱ እንደሚያሰጋው ታዳጊ ስሜን ቀይሬ ስምሙ መሆንን መረጥኩ ይላል የ33 ዓመቱ ጎልማሳ። "በትምህርት ቤቱ ውስጥ በእኔ የሚያላግጡ እና የሚዝናኑ ብዙ ተማሪዎች ነበሩ፤ አንዳቸውም ስሜን በትክክል አይጠሩትም። እናም ሰላማዊ ነው ብዬ አላስብም ነበር። "ከዚያ ግሬግ ተባልኩ ከዚያ ደግሞ ግሪጎሪ" ግሪጎሪጅ በሕጻንነቱ የፊልም ተዋንያን ለመሆን ያልም ነበር፤ ለእዚህ ኢንዱስትሪ ደግሞ ለአፍ የሚቀል ስም ያስፈልጋል ብሎ በማመኑ አንደኛው ስሙን የመቀየሪያው ምከንያት ሆኗል። "ለእኔ ያን ያክል አስፈሪ ነገር አልነበረም፣ እንዲሁ ለሰዎች ነገሮችን ቀላል ላድርግላቸው ከሚል እሳቤ የተነሳ ነው።" ወጣት ሲሆን ስሙን በመቀየሩ ተጸጽቷል፤ ነገር ግን ገና ታዳጊ እያለ ደስ ይሰኝ ነበር። "ነጭ ነኝ፣ እከበራለሁ፣ አውሮፓ ውስጥ ነው የምኖረው- እና እነዚህን ሁኔታዎች ሚዛን ላይ አስቀምጠናቸው የእኔን ስም አስቸጋሪነት ስንመዝነው ብዙም ውሃ የሚያነሳ ጉዳይ አይደለም። "ሁላችንም ቅድሚያ የምንሰጣቸው ጉዳዮች አሉ፤ በዚያ ወቅት ለእኔ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ስሜን የሚመች አድርጎ ከቡድኑ ጋር ስምሙ መሆን ነበር፤ ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ ነው። "ለእኔ እውነት ለመናገር ስምን መቀየር በ15 እና 16 ዓመት እድሜዬ ወቅት ትልቅ ጉዳይ እንደነበር ተመልሶ ማሰብ በራሱ አስቂኝ ጉዳይ ነው።"
xlsum_amharic-train-169
https://www.bbc.com/amharic/news-47154111
እያነጋገረ ያለው የአማራ ክልል የቤተሰብ ዕቅድ ደብዳቤ
ባለፉት ጥቂት ቀናት ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ስለ ወጣ አንድ ደብዳቤ ብዙዎች ብዙ ነገር እያሉ ነው።ደብዳቤው በአማራ ክልል የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት አሰጣጥን የሚመለከት ሲሆን ከደብዳቤው ሃሳብ በመነሳት በክልሉ ሴቶች በተለያየ መንገድ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲጠቀሙ ግፊት እየተደረገባቸው ነው የሚሉ ሃሳቦች አይለዋል።
[ "ባለፉት ጥቂት ቀናት ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ስለ ወጣ አንድ ደብዳቤ ብዙዎች ብዙ ነገር እያሉ ነው።ደብዳቤው በአማራ ክልል የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት አሰጣጥን የሚመለከት ሲሆን ከደብዳቤው ሃሳብ በመነሳት በክልሉ ሴቶች በተለያየ መንገድ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲጠቀሙ ግፊት እየተደረገባቸው ነው የሚሉ ሃሳቦች አይለዋል።" ]
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ታሪኩ በላቸው ደብዳቤው ሁሌም ከቢሯቸው ከሚወጡ ደብዳቤዎች የተለየ ነገር እንደሌለው ፤ ይልቁንም የደብዳቤውን ሃሳብ በተሳሳተ መንገድ የመረዳት ችግር እንደገጠመ ይናገራሉ። ከሁሉም በላይ በክልሉ አንዳንድ የጤና ፕሮግራሞችን በጥርጣሬ የማየት ነገር እንዳለ ይህም ከፍተኛ ችግር እስከመፍጠር እንደደረሰ የሚናገሩት ሃላፊው ባለፈው ዓመት በክልሉ ጥናት ለማድረግ ወደ ክልሉ የሄዱ ሁለት ምሁራን መገደልን በዋቢነት ይጠቅሳሉ። • ኢትዮጵያ ዳግም ጤፍን በእጇ ለማስገባት ገና በዝግጅት ላይ ናት "ይህን ሁሉ ያመጣው የክልሉ ጤና አገልግሎት ላይ ጥርጣሬ መኖሩ ነው። ክትባት፣ የህናቶች ጤና አገልግሎትንና ሌሎችንም አገልግሎቶች ያለመጠቀም ችግርም አለ " በማለት ጥርጣሬው በጣም በሚያሰጋ ደረጃ ያለ እንደሆነ ያመለክታሉ። በጤና አገልግሎት አሰጣጡ ጉድለቶች ካሉ ለማስተካከል፣ አገልግሎቱን በሚመለከት አለመረዳትና የግንዛቤ ችግር ካለም ማስተማር ማስረዳት አስፈላጊ ነው ብሎ በማመን ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ተደርጎ እንደነበር አቶ ታሪኩ ይናገራሉ። በተጨማሪም በዚህ አመት የማህፀን በር ካንሰር መከላከያና የኩፍኝ ሁለተኛ ዶዝ ክትባቶች ለመስጠት ታስቦ ስለነበር ለዚህም ከማህበረሰቡ ጋር የተደረው ውይይት በእጅጉ አስፈላጊ ነበር ይላሉ። እናም በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ የተባለበት ደብዳቤ ከማህበረሰቡ ጋር የተደረገውን ውይይት ተከትሎ የተፃፈ ነው ይላሉ አቶ ታሪኩ። እሳቸው እንደሚሉት በውይይት መድረኮቹ የሃይማኖት አባቶች፣ አክቲቪስትና የሚዲያ ባለሙያዎች ስለ ስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ብዙ ያነሷቸው ጥያቄዎች ነበሩ። "ስምንቱ ነጥቦች ብቻ ሳይሆኑ የተነሱ ሌሎች ጉዳዮች ነበሩ።እኛ በጥናት ያገኘነው እና የታመነበት ባይሆንም ማስተካከያ መስጠት አስፈላጊ ነበር" የሚሉት አቶ ታሪኩ የተባሉት ችግሮች እውነትም ካሉ ማስተካከያ ሊደረግ ይገባል በሚል መንፈስ አቅጣጫ ለመስጠት ደብዳቤው መጿፉን ያስረዳሉ። • በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ • በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? ደብዳቤው ለሁሉም የዞን ጤና መምሪያዎች የተፃፈ ሲሆን መምሪያዎቹ ደግሞ ለወረዳዎች እንዲያወርዷቸው ተደርጓል። በጥቅሉ በክልሉ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አሉ የሚባሉ ችግሮች ካሉ እንዲስተካከሉ አቅጫ የሚሰጥ ደብዳቤ እንደሆነና ምንም የተለየ ነገር እንደሌለው አቶ ታሪኩ ያስረግጣሉ። በደብዳቤው ላይ የተነሳ ሌላው ጉዳይ ደግሞ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑ ሴቶች ቁጥርን የሚመለከት ሲሆን በቁጥር ደረጃ ይህን ያህል ሴቶችን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተብሎ ሲቀመጥ ለእቅድና አማራጮችን ለማስቀመጥ እንጂ የግድ ይህን ያህል ሴት ተጠቃሚ ይሆናል በሚል እንዳልሆነም አቶ ታሪኩ ያስረዳሉ።
xlsum_amharic-train-170
https://www.bbc.com/amharic/news-56841522
በጣሊያን ለ15 ዓመታት በሥራ ገበታው ሳይገኝ ደመወዝ 'ሲበላ' የነበረ ግለሰብ ተያዘ
በጣሊያን በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ተቀጥሮ በ15 ዓመታት ውስጥ አንድም ቀን ወደ ሥራው 'ዝር ሳይል' ደመወዝ 'ሲበላ' የነበረው ተቀጣሪ ላይ ክስ ሊመሰረት እንደሆነ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
[ "በጣሊያን በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ተቀጥሮ በ15 ዓመታት ውስጥ አንድም ቀን ወደ ሥራው 'ዝር ሳይል' ደመወዝ 'ሲበላ' የነበረው ተቀጣሪ ላይ ክስ ሊመሰረት እንደሆነ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።" ]
ሰውየው ሥራ ባልተገኘባቸው አመታት የተከፈለው ጠቅላላ ገንዘብ 538 ሺህ ዩሮ ወይም በወቅታዊ ምንዛሬ ከ26 ሚሊዩን ብር በላይ እንደሆነ ተነግሯል። ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ የሆስፒታሉ ስድስት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። የሕዝብ ሀብት ላይ የሚደረጉ ማጭበርበሮችን በተመለከተ ፓሊስ በደረገው ዘለግ ያለ ምርመራ ነው ተጠርጣሪዎቹ ተደርሶባቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት። በመንግሥት ሆስፒታል ተቀጥሮ የነበረው ግለሰቡ በሥራው ላይ የተመደበው እንደ አውሮፓውያኑ በ2005 ነው። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ወደ ስራ መሄድ አቆመ። ከዛ በኃላ ለቀጣዩቹ 15 አመታት ከሥራ ቦታው ጋር አልተያየም። የተቀጣሪው አለቃ የሥነ ምግባር ጥሰት እንደፈፀመ ሪፓርት እንዳታደርግ ሲያስፈራራት እንደነበረም ተጠቁሟል። እሷ ጡረታ ስትወጣ የእሷ ተተኪም ይሁን የሆስፒታሉ የሰው ሀብት ክፍል ጉዳዩ ላይ ምንም መረጃ እንዳልመበራቸው ተዘግቧል።
xlsum_amharic-train-171
https://www.bbc.com/amharic/news-49619044
በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ
ኢትዮጵያ 2011 ዓ. ም. ን አገባዳ 2012ን ልትቀበል የቀሯት ጥቂት ቀናቶች ናቸው። በ2011 ዓ. ም. በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ አነጋጋሪ፣ አወዛጋቢ፣ አሳዛኝ እንዲሁም የሰውን ስሜት ሰቅዘው ይዘው ከነበሩት ጉዳዮች መካከል ጥቂቶቹ እነሆ. . .
[ "ኢትዮጵያ 2011 ዓ. ም. ን አገባዳ 2012ን ልትቀበል የቀሯት ጥቂት ቀናቶች ናቸው። በ2011 ዓ. ም. በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ አነጋጋሪ፣ አወዛጋቢ፣ አሳዛኝ እንዲሁም የሰውን ስሜት ሰቅዘው ይዘው ከነበሩት ጉዳዮች መካከል ጥቂቶቹ እነሆ. . ." ]
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ችግኝ ሲተክሉ የውጤት ግሽበት በቅርቡ የዘንድሮ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት በተሰጡት አራት የትምህርት አይነቶች ብቻ እንደሚወሰን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። ከ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ትምህርቶች ሒሳብ፣ እንግሊዝኛ፣ አፕትቲዩድ፣ ጂኦግራፊና (ለማኅበራዊ ሳይንስ) ፊዚክስ (ለተፈጥሮ ሳይንስ) ተመርጧል። የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት በተሰጡት አራት የትምህርት አይነቶች ብቻ መወሰኑ አነጋጋሪ ነበር እንደ ምክንያት የተቀመጠው ደግሞ ሌሎቹ የትምህርት አይነቶች ከፍተኛ የውጤት ግሽበት ስለታየባቸው መሆኑም ተገልጿል። ጉዳዩ በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን፤ በፈተና አሰጣጡ ላይ ችግሮች ከነበሩ መስተካከል የሚችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው ወይ? በተመረጡት ትምህርቶች ውጤት ብቻ መዳኘት ተማሪዎችን ማዕከል ያላደረገ እንዲሁም እድል የሚነፍጋቸው ነው ብለው የተቹትም አልታጡም። • ብሔራዊ ፈተናዎች ምን ያህል ከስርቆትና ከስህተት የተጠበቁ ናቸው? 350 ሚሊዮን ችግኞች ሐምሌ 22፣ 2011 ዓ. ም. ኢትዮጵያ በ12 ሰዓታት ውስጥ 200 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ቆርጣ ተነሳች። በቀኑ መገባደጃ ላይ የፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ፤ አገሪቱ 350 ሚሊዮን ችግኞችን መትከሏን አሳወቁ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፤ የደን መመናመንን ለመከላከል አርባ ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ችግኝ የመትከል ዕቅድ ይዘው የተነሱት በቅርቡ ነው። መንግሥት እንደሚለው፤ የሚተከሉት ዛፎች ለበጎ ፈቃደኞች መታደል የጀመሩት ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ ነበር። በርካታ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዕለተ ሰኞ ሐምሌ 22፣ 2011 ዓ. ም. መደበኛ ሥራቸውን በመተው ዛፍ በመትከል እንዲውሉ ተደረገ። • ችግኝን በዘመቻ መትከል መቼ ተጀመረ? በአንድ ቀን 350 ሚሊዮን ዛፎች መትከል ይቻላል ወይ? የሚለው ብዙዎችን ሰቅዞ የያዘ ጉዳይ ነበር። እንደተለመደው ጉዳዩ የማኅበራዊ ድር አምባ መነጋገሪያ ከመሆን አልተቆጠበም። ይቻላል ብለው የተነሱና ችግኝ የተከሉ፤ ከዛፉ ጋር ፎቶ የተነሱ ባይጠፉም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያጋጠማቸውን የፖለቲካ ፈተና በችግኝ ተከላ ሽፋን እያደባበሱት ነው ብለው የወቀሱም አልጠፉም። ሰኞ ሐምሌ 22፣ 2011 ዓ. ም. የመንግሥት ሠራተኞች እንዲሁም የግል ተቀጣሪዎችም መደበኛ ሥራቸውን በመተው ዛፍ ተክለዋል የመረጃ ትክክለኛነትን የሚያረጋግጠው ክፍላችን ቢቢሲ ሪያሊቲ ቼክ፤ በቀን 350 ሚሊዮን ዛፎች መትከል ባያዳግትም፤ እጅግ ከባድ ዝግጅት ይጠይቃል ይላል። ባለሙያዎችም ይህንን ነው የሚሉት። አልፎም ክብረ ወሰን የሚመዝግበው 'ጊነስ ወርልድ ሬከርድስ' ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም ማለቱ መነጋገሪያ ርዕስ ነበር። ስለጉዳዩ በቢቢሲ አማርኛ የተሠራ ዘገባ፦ ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን ማስረጃ የለም» ቶቶ ቱርስ ቶቶ ቱርስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ አስጎብኝ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ሊያደርግ የነበረው ጉዞ በዓመቱ መነጋገሪያ ከነበሩ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነበር። ድርጅቱ ወደ ላሊበላ ይዟቸው ሊመጣ ያሰባቸው ጎብኝዎች የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን መሆናቸው ነው ጉዳዩ እንዲጦዝ ያደረገው። ቶቶ ቱርስ በኢትዮጵያ ለ14 ቀናት የሚዘልቅ የጉብኝት መርኃ ግብር አውጥቶ ጎብኚዎችን እየመዘገበ ሳለ ነበር ተቃውሞ እየተበረታበት የመጣው። በአንድ ሰው 7 ሺህ 900 የአሜሪካን ዶላር የሚጠየቅበት ይህ የጉብኝት ፕሮግራም በሁለት ሳምንት ቆይታው አርባ ምንጭ፣ ደቡብ ኦሞ፣ የጣና ገዳማት፣ ጎንደር፣ ላሊበላ፣ አክሱምን እና ሌሎች የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ለማስጎብኘት መርሃ ግብር ቀርፆ ነበር። ጫናው የበረታበት ቶቶ ቱርስ ለጎብኝዎቹ ደህንነት በመስጋት ጉዞውን ሰርዟል መጀመሪያ ላይ ድርጅቱ ምንም እንኳ ተቃውሞ ቢረታበትም ጎብኝዎች ይዞ ወደ ላሊበላ ከመጓዝ እንደማይቆጠብ አስታውቆ ነበር። የቶቶ አስጎብኚ ድርጅት መስራች እና ባለቤት ዳን ዌር በበኩላቸው ''በተፈጠረው ነገር በጣም አዝኛለሁ። ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ ግን አንሰርዝም'' ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠው ነበር። ይህ ጉዳይ ማኅበራዊ ድር አምባ እንዲሁም መገናኛ ብዙሃን ላይ በርካቶች በተመሳሳይ ፆታ ፍቅር ላይ ያላቸውን እይታ ጎራ ለይተው የተወያዩበት ሆኗል። ብዙዎችም ጥቃት እንደሚያደርሱ የዛቱ ሲሆን፤ የኋላ ኋላ ግን ጫናው የበረታበት ቶቶ ቱርስ ለጎብኝዎቹ ደህንነት በመስጋት ጉዞውን ሰርዟል። ስለጉዳዩ በቢቢሲ አማርኛ የተሠራ ዘገባ፦ ''ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም'' የምክትል ከንቲባው ጫማ እና ቪላ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ከመገናኛ ብዙሃን እና ከማኅበራዊ ድር አምባ አፍ ጠፍተው አያውቁም። ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ አንድ ወቅት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ያለን አንድ የግንባታ ሥፍራን ሲጎበኙ የተጫሙት ጫማ የሰውን ቀልብ ስቦ ነበር። 'ባሌንሲያጋ' የተሰኘው ይህ አሜሪካ ውስጥ የሚመረት ጫማ ዋጋው ውድ መሆኑ ነው ሰዎች ፎቶዉን እንዲጋሩትና እንዲነጋገሩበት ያደረጋቸው። • "አዲስ አበባ የምንወዛገብባት ሳትሆን በጋራ የምንኖርባት ከተማ ናት" ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በበይነ መረብ መሻሻጫ መስኮቶች ላይ ይህ ጫማ በወቅቱ ገበያ በትንሹ 780 ዶላር [22 ሺህ ብር ገደማ] ያወጣል። ይህ ለአንድ ጫማ የተሰጠ ዋጋ መናር ብዙዎችን አደናግሮ ነበር። ከንቲባው የፈለጉትን መጫማት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ነው ሲሉ የሞገቱም አልጠፉም። ከዚህ በተጨማሪ የምክትል ከንቲባው ነው የተባለ ቤት በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን፤ በተለይም ለኪራይ የሚከፍሉት 140ሺ ነው መባሉ ደግሞ የበለጠ ጉዳዩን ወደ ሌላ መስመር ወስዶት ነበር። ቀጥሎም ከንቲባው ለኪራይ የሚከፍሉት በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ብር ሳይሆን 680 ብር ብቻ ነው መባሉ የአንድ ሰሞን የማኅበራዊ ሚዲያ ወሬ ማድመቂያ ሆኗል። የ "መፈንቅለመንግሥት" ሙከራ ኢትዮጵያ ስድስት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮችን ያጣችው በጥቂት ቀናት ልዩነት ውስጥ ነበር። ቅዳሜ አመሻሽ፤ ሰኔ 15፣ 2011 ዓ. ም. ። ባህር ዳር በተኩስ ተናወጠች፤ አዲስ አበባም የቀለሃ ድምፅ ተሰማ። መንግሥት የመንበር ፍንቀላ ሙከራ ነው ባለው በዚህ ጥቃት፤ ባህር ዳር ከተማ ላይ የክልሉ አስተዳዳሪ የነበሩት አምባቸው መኮንን [ዶ/ር] እና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉ ታወቀ። አልፎም አዲስ አበባ ላይ ደረሰ በተባለው ጥቃት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮነን ጄኔራል ገዛኢ አበራ መገደላቸው ታወቀ። ክስተቱ ከተሰማበት አልፎ ባለው ሰኞ ደግሞ በቅዳሜው አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩት የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ ማለፋቸው ተነገረ። ከግራ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን፣ ጄነራል አሳምነው ፅጌ እና አምባቸው መኮንን [ዶ/ር] የባህር ዳሩ እና የአዲስ አበባው ጥቃት ግንኙነት አላቸው ሲል መንግሥት አስታወቀ። ዋነኛ ተጠርጣሪ ደግሞ የአማራ ክልል የፀጥታ ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩት ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ መሆናቸው ተነግሮ ግለሰቡን ፍለጋ መጠናከሩ ተነገረ። ሰኞ ሰኔ 17፣ 2011 ዓ. ም. ዘንዘልማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ብሔራዊው የቴሌሊቪዥን ጣቢያ አስታወቀ። ከቅዳሜ እስከ ሰኞ ድረስ የተሰሙት ዜናዎች ለበርካታ ኢትዮጵያውያን አስደንጋጭ የነበሩ ናቸው። ከ "መፈንቅለ መንግሥቱ" ጋር ተያይዞ የጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሰአረ መኮንን እና ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ ገዳይ ተብሎ የተጠረጠረው ጠባቂያቸው ጉዳይ ውዥንብር መፍጠራቸውንም ብዙዎች በማኅበራዊ ሚዲያቸው አጋርተዋል። ጄነራል ሰዓረ ላይ ጥቃት አድርሷል የተባለው ግለሰብ ቢጎዳም በቁጥጥር ሥር መዋሉ መጀመሪያ ተገለፀ። ትንሽ ቆይቶ ግለሰቡ ቢቆስልም በቁጥጥር ሥር ውሏል የተባለው ግለሠብ ራሱን አጥፍቷል መባሉ ግርታን ፈጠረ። እንዴት በቁጥጥር ሥር ያለ ሰው ራሱን ያጠፋል? የብዙዎች ጥያቄ ነበር። ነገር ግን ዘግይቶ ደግሞ ብሐራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ግለሰቡ አልሞተም፤ በሕይወት አለ ሲል አተተ። በብዙ ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ውዝግብና መነጋገሪያ ሆኖም አልፏል። ስለጉዳዩ በቢቢሲ አማርኛ የተሠራ ዘገባ፦ ስለ'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች ዶላር የዶላር የውጭ ምንዛሬ የጥቁር ገበያ ዋጋ በ2011 ዓ. ም. በጣም በርካታ ጊዜ ማሻቀብ እና ማሽቆልቆል አሳይቷል። በቅርቡ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያ ያለው ዋጋ ከ40 ብር በላይ መድረሱ ተዘግቦ ነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፤ የዶላር የጥቁር ገበያ ሰዎች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ባሉት መሠረት፤ አንድ ሰሞን የጥቁር ገበያ ሱቆች ተዘግተዋል፤ ሲያሻሽጡ ነበሩ ያተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም የሚዘነጋ አይደለም። ቢሆንም በቂ ዶላር ባንኮች የላቸውም የሚል ቅሬታ በተለይም ከነጋዴዎች መሰማቱ አልቀረም። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችም በቂ ዶላር ባንኮች ውስጥ ሳይከማች ጥቁር ገበያውን ማሸግ አዋጭ አይደለም ሲሉ የመንግሥትን ውሳኔ የመጨረሻው መፍትሄ አይደለም ብለው ኮንነውት ነበር። በቅርቡ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያ ያለው ዋጋ ከ40 ብር በላይ መድረሱ ተዘግቦ ነበር። የጥቁር ገበያ ሱቆቹ ግን ከድንገተኛ የፖሊስ ፍተሻ አልዳኑም። እንደሌሎቹ አንገብጋቢ ርዕሶች ሁሉ የዶላር ዋጋ ማሻቀብ ጉዳይ ኢትዮጵያን እንዲወያዩበት ሆኗል። ስለጉዳዩ በቢቢሲ አማርኛ የተሠራ ዘገባ፦ ጥቁር ገበያውን ማሸግ መፍትሄ ይሆን? ኢቲ 302 አደጋ መጋቢት 1፣ 2011 ዓ. ም. ቀኑ ደግሞ እሁድ። በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተሳፈሩ 157 ተጓዦች እንደወጡ ቀሩ። ረፋድ ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያን የለቀቀው መዘዘኛ አውሮፕላን በተነሳ በስድስተኛው ደቂቃ እንደተከሰከሰ ተሰማ። አውሮፕላኑ ውስጥ የ33 አገራት ዜጎች መኖራቸው ታወቀ። ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አፍሪቃ ደነገጠች፤ ዜጎቻቸው በአደጋው እንዳለፉ የሰሙት አውሮፓ እና አሜሪካም ዜናው ዱብ ዕዳ ሆነባቸው። • የኢቲ 302 የመጨረሻዎቹ ስድስት ደቂቃዎች ከወራት በፊት በኢንዶኔዥያው ላይን ኤር የሚመራ ተመሳሳይ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መከሰከሱ ሰዎች አደጋውን ከቦይንግ ጋር እንዲያይዙት አደረጋቸው። በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተሳፈሩ 157 ተጓዦች ሕይወታቸውን አጥተዋል የኢቲ 302 አደጋ የመጀመሪያ ውጤት እንደጠቆመውም የአውሮፕላን አብራሪያው የተቻለውን ሁሉ ቢያደርግም አደጋውን መከላከል አለመቻሉን ነው። በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በቦይንግ መካከል ለወራት ጣት መቀሳሰር እና መወነጃጀል ሆነ። በስተመጨረሻም ቦይንግ የአደጋውን ሙሉ ኃላፊነት መውሰዱን አመነ። ለሟች ቤተሰቦች የሚሆን ካሳ በማለትም 100 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስታወቀ። ይህ ካሳ ግን የሟች ቤተሰቦችን እጅግ ያስቆጣ ነበር። በቦይንግ እና በሟች ቤተሰቦች መካከል ያለው እሰጥ አገባ አሁንም አልተቋጨም። የሟች ቤተሰቦች በጋራ በመሆን ቦይንግን ለመክሰስ እና ለመርታት አልመዋል። በዚሁ ሁሉ መካከል ግን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች አስፈላጊው ጥገና እስኪደርግላቸው ድረስ ከአገልግሎት ውጭ ይሁኑ ተብለው ታግደዋል። የሴቶች ሹመት ሚያዚያ 9፣ 2011 ዓ. ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቧቸው የካቢኔ አባላት እጩዎች በሙሉ ድምጽ ነበር የፀደቀላቸው። አዳዲስ ሚንስትሮችን ወደፊት ያመጡ ሲሆን፤ ስድስት ሚንስትሮችን ደግሞ ከነበሩበት ሥፍራ ወደሌላ ሚንስትር መሥሪያ ቤት እንዲዘዋወሩ አድርገዋል። ከካቢኔው ተሿሚዎች መካከል 50 በመቶው ሴቶች መሆናቸው በወቅቱ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ እንደማስረገጫ ''የሴቶችን ተሳትፎ በሁሉም የአመራር እርከን ማረጋገጥ ስለሚያስፈልግ ነው'' ሲሉ ተናግረው ነበር። • ሃምሳ በመቶ የሚኒስትሮች ሹመት ለሴቶች ከካቢኔው ተሿሚዎች መካከል 50 በመቶው ሴቶች መሆናቸው በወቅቱ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር በተለይ ሴቶችን በተመለከተ፤ በእሳቸው ካቢኔ ውስጥ የፆታ ተዋጽዖ እና ለሴቶች የተሰጠው የሥልጣን እርከን የሚጠበቀውን ያህል እንዳልሆነ የሚሞግቱ አልጠፉም። ሴቶች እንደሁልጊዜው የተለመዱ ቦታዎች ናቸው የተሰጧቸው፤ ቁጥሩ ብቻ ነው ከፍ ያለው የሚለው መከራከሪያ አቅርበውም ነበር። ከዚህ ባለፈ ማኅበራዊ ሚዲያው የተለያዩ አስተያየቶችን አስተናግዷል። ሴቶች ሹመት የተሰጣቸው በሴትነታቸው ብቻ እንደሆነ ተደርጎ፤ ሌሎች ወንዶች ሲሾሙ የማይጠየቁ የብቃት ጥያቄዎች መንሸራሸራቸውንም አንዳንድ ነቃሾች እየተቹ ፅፈዋል። ከካቢኔ ሹመት ባለፈ ሳህለወርቅ ዘውዴ የአገሪቱ ፕሬዝደንት፤ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት 2011 ዓ. ም. ላይ ነው። እግር ኳስ እና የብሔር ፖለቲካ እንከን የማያጣው የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ እንደ 2011 ዓ. ም. የውድድር ዘመን የተፈተነ አይመስልም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፖለቲካው ወደ እግር ኳስ ሜዳ መግባቱ ለአድማጭ ለተመልካች በግልፅ የሚታይ እውነታ ነው። ክልላቸውን ወክለው የሚጫወቱ ክለቦች ደጋፊዎች ሜዳ ድረስ ዘልቀው ተጫዋቾችና ዳኞችን እስከመምታት ደርሰዋል። የከነማ ክለቦችም ከዚህ የፀዱ አልነበሩም። ትግራይ ስታዲየም ውድድሩ ሊጠናቀቅ ጥቂት ጨዋታዎች ሲቀሩት ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የኢትዮጵያ ቡና እና የመቀሌ 70 እንደርታ ጨዋታ ፌዴሬሽኑ በወሰነው መሠረት እንዲሰረዝ መደረጉ ነገሮች እንዲጦዙ ምክንያት ሆኖ ነበር። ፌዴሬሽኑ ጨዋታው በገለልተኛ ሜዳ [አዳማ] በዝግ እንዲካሄድ መወሰኑ ያልተወጠላቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች ጨዋታውን እንደማያከናውኑ አስታውቀው ነበር። በዚህም ምክንያት ውድድሩ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ ቆይቷል። በስተመጨረሻም ፌዴሬሽኑ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ፤ የፀጥታ ኃይልም እንዲጠናከር አደርጋለሁ ብሎ የሁለቱም ቡድኖች ደጋፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታድየም ጨዋታው እንዲከናወን ሆኗል። ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁም አይዘነጋም። የኋላ ኋላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የነበረው መቀሌ 70 እንደርታ የመሪው ፋሲል ከነማ ነጥብ መጣልን ተከትሎ የ2011 ዓ. ም. የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ መሆን ችሏል። ስለጉዳዩ በቢቢሲ አማርኛ የተሠራ ዘገባ፦ ፌዴሬሽኑ፡ «የቡና እና መቀለ ደጋፊዎች ባሉበት ጨዋታ ሊካሄድ አይችልም»
xlsum_amharic-train-172
https://www.bbc.com/amharic/news-54627458
ኢትዮጵያ- በርካቶች ጋር መድረስ የቻለው የትዊተር ዘመቻ
ከትናንት በስቲያ ኢትዮጵያን የተመለከተ እና ለ24 ሰዓታት የዘለቀ የትዊተር ዘመቻ ተካሂዷል።
[ "ከትናንት በስቲያ ኢትዮጵያን የተመለከተ እና ለ24 ሰዓታት የዘለቀ የትዊተር ዘመቻ ተካሂዷል።" ]
በዚህ ዘመቻ ጥቅም ላይ የዋሉት ሃሽታጎች (የዘመቻ ሐረጎች) ከ40 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ጋር መድረሳቸውን የትዊተር አናሊቲክስ ድረ-ገጾች ያመላክታሉ። ከትናንት በስትያ (ሐሙስ) በተካሄደው የትዊተር ዘመቻ ላይ ሁለት ዋነኛ ሃሽታጎች ጥቅም ላይ ውለው ነበር። #300Lives3Months (300 መቶ ህይወቶች በ3 ወር ውስጥ) እና #ProblmeIsTyrannyNotEthnicity (ችግሩ የብሄር ሳይሆን አምባገነንነት ነው) የሚል ይዘት ያላቸው መሪ መፈክሮች ተጋርተዋል። ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመዳሰስ የሚታወቀው ቶክዎከር (Talkwalker) ድረ-ገጽ ላይ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ጥቅምት 12 እና 13 ላይ #300Lives3Months የተሰኘው ሃሽታግ 44.5 ሚሊዮን ትዊተር ተጠቃሚ ሰዎች ጋር ደርሷል። 239 ሺህ ሰዎች ደግሞ #300Lives3Months የሚለውን ሃሽታግ የያዘን ትዊት ክሊክ አድርገዋል፣ አጋርተዋል፣ መውደዳቸውን አሳይተዋል (ላይክ አድርገዋል)፣ ተከትለዋል፤ አልያም አስተያየት ሰጥተውበታል። ጥቅምት 12 እና 13 ላይ #300Lives3Months የተሰኘው ሃሽታግ 44.5 ሚሊዮን ትዊተር ተጠቃሚ ሰዎች ጋር ደርሷል። ከዘመቻው አስተባባሪዎቹ አንዱ የሆነው ኣየስፔድ ተስፋዬ ከሁለቱ ሃሽታጎች በተጨማሪ ተመሳሳይ መልዕክት የሚያስተላልፉ 'ሶማሌ'፣ 'ምስራቅ ሃረርጌ' እና 'ምዕራብ ሃረርጌ' የሚሉ ሃሽታጎች ጨምሮ ከትዊተር አናሊቲክስ መረዳት እንደቻልነው 1.1 ሚሊየን ጊዜ ትዊት እና ሪትዊት ተደርጓል ይላል። ዓለማው ምንድነው? የዘመቻው አስተባባሪ ከሆኑት መካከል ሌላኛው ሳሙኤል በቀለ፣ የትዊተር ዘመቻው ዋነኛ ግብ "በኢትዮጵያ እየሆነ ስላለው ሁኔታ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ ነው" ይላል። ሳሙኤል "መንግሥት ከውጪ የሚገኘውን ድጋፍ ከተፈቀደለት ዓላማ ውጪ እየተጠቀመ ነው። ይህንንም የውጪው ማህብረሰብ እንዲያውቅ ዘመቻውን አስፈልገወል" ይላል። #300Lives3Months የትዊተር ዘመቻው አስተባባሪዎች ባለፉት ሦስት ወራት 300 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል ይላሉ። እያስፔድ ተስፋዬ በትዊተር ዘመቻ ላይ ከሦስት መቶ በላይ የሚሆኑ ሟቾችን ማንነት በሥም፣ የተገደሉበትን ስፍራ እና በቀን ለይተን አስቀምጠናል ይላል። "በነገራችን ላይ ባለፉት 3 ወራት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ300 በላይ ነው። 'ሴንሰቲቭ' ያልናቸውን መርጠን ነው እንጂ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዚያ በላይ ነው" ሲል አክሏል። ከ300ዎቹ ሰዎች ከፍተኛ ድርሻውን የሚይዙት በመንግሥት የጸጥታ ኃይል የተገደሉ ናቸው የሚለው እያስፔድ፤ "ከተገደሉት መካከል የ8 እና የ9 ዓመት ልጆች እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው ሳለ የተገደሉ የሃይማኖት አባቶች አሉ" ሲል ለቢቢሲ አስረድቷል። #ProblmeIsTyrannyNotEthnicity እያስፔድ በኢትዮጵያ ዋነኛው ችግር አምባገነንነት ነው እንጂ የብሔር ጉዳይ አይደለም ይላል። "መንግሥት እየወሰዳቸው ላሉት ያልተመጣጠኑ የኃይል እርምጃዎች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች 'የብሔር ግጭት' የሚል ምክንያትን እንደ መሸፈኛ እየተጠቀመበት ይገኛል" ሲልም ያብራራል። ሕይወታቸውን ካጡት እና በዘመቻው ከተጠቀሱት ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሰዎች ምንም አይነት የብሔር ግጭት ባልተከሰተባቸው አካባቢዎች፣ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ መሆናቸውንም ይገልጻል። ለዚህም እንደ ምሳሌ የወላይታን ጉዳይ በማንሳት፣ መንግሥት "ሕገ-መንግሥታዊ የሆነውን የክልልነት ጥያቄ በመመለስ ስልጣንን ያልተማከለ ማድረግ ስላልፈለገ ብቻ በርካቶች ተገድለዋል። ይህንን በዘመቻችን ውስጥ አካትተነዋል" ብሏል። ሰኔ 3 2012 ዓ.ም. ከወላይታ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በጸጥታ ኃይሎች በተያዙ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሰበብ በተከሰተ አለመረጋጋት ቢያንስ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል። ዞኑን በክልልነት ለማደራጀት ከተቋቋመው ሴክሬታሪያት ጋር ስብሰባ ተቀምጠው የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የህግ ባለሙያዎችና የአገር ሽማግሌዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነበር ችግሩ የተከሰተው። በወቅቱ የደቡብ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች "የክልል እንሁን ጥያቄ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እንዳይፈታ ለማድረግ ሲጥሩ የነበሩ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው" ሲሉ ለአገር ውስጥ መገናኛ ተናግረዋል። "ለሰብዓዊ መብት ጥሰት መንስዔው የፖለቲካ ቀውስ ነው" የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ሚዲያዎች የሚነሱት ሁሉ በሚገለጸው ልክ ትክክል ናቸው ማለት ባይቻልም፣ በኢትዮጵያ አሳሳቢ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳዮች መኖራቸውን ይናገራሉ። "በእኛ በኩል ማለት የምችለው ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ፤ ሰፊ የሆነ የሰብዓዊ መብት ችግር አለ" ለቢቢሲ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። ኮሚሽነሩ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሪፎርም ሥራ እያከናወን መሆኑን አስታውሰው፣ ባለው አቅም የሚደርሱትን ጥቆማዎች መርምሮ መፍትሄ እና ምክረ ሃሳብ እየሰጠ መሆኑንም ገልፀዋል። ኮሚሽነር ዳንኤል "አብዛኛው የሰብዓዊ መብት ችግር የሚመነጨው ከፖለቲካ ቀውሳችን ነው" ካሉ በኋላ፣ የፖለቲካ ቀውሱ በሚፈጥረው ግጭት የበርካቶች ሕይወት መጥፋቱን፤ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው መፈናቀላቸውን እና ያለ አግባብ መታሰራቸውን ይናገራሉ። "የጸጥታ ኃይሎችም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚሰሩ እናውቃለን። ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ፍልሚያ ያደርጋሉ። በዚህ መካከል የጸጥታ ኃይሎች እንደሚገደሉ እናውቃለን። ይህ የውስብስብ ፖለቲካችን መገለጫ ነው" ብለዋል። ይህ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ችግር መፍትሄ የሚያገኘው "የፖለቲካ ቀውሱ መፍትሄ ሲያገኝ ነው" የሚሉት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነሩ፤ "በመንግሥት በኩል ለፖለቲካ ችግሩ የፖለቲካ መፍትሄ እንዲፈለግለት እናሳስባለን፤ ምክረ ሃሳብ እንሰጣለን" ብለዋል። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ ወስደዋል አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚፈጸሙት የሰብዓዊ መብት ጥስቶች እየተበራከቱ መጥተዋል ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። የአምነስቲ የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ተክሌ በኦሮሚያ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሰላም ለማስፈን የተሰማሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ ወስደዋል ይላሉ። በዚህም የበርካቶች ሕይወት ማለፉን ይናገራሉ። እንደ ምሳሌም በኦሮሚያ ክልል፣ ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የተገደለውን ወጣት ያነሳሉ። እሑድ ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ. ም. ሮቤ ከተማ አንድ ወጣት ከፖሊስ በተተኮስ ጠይት መገደሉ ይታወሳል። የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ ወጣቱ መገደሉን አረጋግጠዋል፤ ክስተቱ ሰልፍ ሳይሆን በከተማው ረብሻ ለመፍጠር የተደረገ ሙከራ ነው ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሰልፉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከ15-20 የሚጠጉ ወጣቶች "ጀዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ይፈቱ የሚል" መፈክር እያሰሙ ሳለ ፖሊስ ተኩስ ከፍቶ እንደበተናቸው እና በዚያ መካከል ወጣቱ መገደሉን ተናግረዋል። አምነስቲ ባለፉት ጥቂት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለተገደሉት ሰዎች ያለው መረጃ ምን እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ፍሰሃ፤ በሐረርጌ ተካሂዶ በነበረው ተቃውሞ ቢያንስ 20 ሰዎች ተገድለዋል፤ በወላይታ ዞን ደግሞ ቢያንስ 16 ሰዎች በመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ ኃይል ተገድለዋል በማለት ለቢቢሲ አስረድተዋል። በጉጂ፣ ቦረና እና ምዕራብ ወለጋ በተመሳሳይ ግድያዎች እየተፈጸሙ እንደነበረ መረጃው አለን ሲሉም አቶ ፍሰሃ ያብራራሉ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ደግሞ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካቶች ስለመገደላቸው መረጃው እንዳላቸው እና ተጨማሪ ጥናቶችን እያካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል። ቢያንስ ወደ 60 የሚጠጉ ሰዎች በታጣቂዎች በማለትም፣ በደቡብ ክልል ደግሞ በቤንች ማጂ ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል። በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ እንደተባለው 300 ሰዎች ስለመገደላቸው ግን የተጣራ መረጃ እንደሌላቸው እና አሁንም ምርመራ እያደረጉ መሆናቸው ይናገራሉ። አቶ ፍሰሃ መንግሥት የሰብዓዊ መብት እንዲከበር ቁርጠኝነት ካለው ከተመጣጣኝ በላይ የሆነ እርምጃ የወሰዱ ኃይሎችን ለሕግ ማቅረብ ይኖርበታል ሲሉም ሃሳባቸውን ይቋጫሉ። የአንድም ሰው ሕይወት ማለፍ የለበትም የብልጽግና ፓርቲ ዓለም አቀፍ እና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ጉዳዩን በሚመለከት ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ባለፉት ዓመታት ሁለት ችግር ማጋጠሙን ተናግረዋል። በእነዚህ ችግሮች ድምጻቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ፣ " ችግር ለመፍጠር" የተንቀሳቀሱ፣ እንዲሁም የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መሆናቸውንም አብራርተዋል። መንግሥት የአንድም ሰው ሕይወት ማለፍ የለበትም ብሎ አንደሚያምን የተናገሩት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ቢቀለ ሁሪሳ (ዶ/ር)፣ "አላስፈላጊ እርምጃ በመውሰድ የሰው ሕይወት እንዲያልፍ ያደረገ በሕግ መጠየቅ አለበት" ብለዋል። እንደ ዶ/ር ቢቀለ ከሆነ ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ በመውሰድ የሰው ሕይወት እንዲያልፍ ያደረጉ አካላት እየተጠየቁ ሲሆን "መንግሥት እያጣራ የሕግ እርምጃ መውደሱን ይቀጥላል" ሲሉም ተናግረዋል። ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አክለውም በየትኛውም ቦታ በግጭቶች መካከል የሰው ሕይወት ሲያልፍ የሚኖርበት ዞን፣ወረዳ እንዲሁም ቀበሌ እና ሕይወቱ ያለፈበት ምክንያት ከአስከሬን ምርመራው ከተረጋገጠ በኋላ ይመዘገባል። "በዚህ ውስጥ ኃይል እርምጃ የወሰደ አካል ይጠየቃል። ሌሎች አካላትም ወንጀል ሊፈጽሙ ይችላሉ። ይህም መጣራት አለበት ብዬ አምናለሁ" ሲሉም አክለዋል። በመጨረሻም በተለያዩ ጉዳዮች 'መጓተቶች ቢኖሩም' የማጣራት ስራው ይቀጥላል ብዬ አምናለሁ ብለዋል ዶ/ር ቢቂላ።
xlsum_amharic-train-173
https://www.bbc.com/amharic/news-55621030
ትግራይ ፡ አቦይ ስብሐት ነጋ ማን ናቸው?
ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አገሪቱን በመራው ኢህአዴግ ውስጥ አድራጊ ፈጣሪ የነበረው የህወሓት ቀደምት ታጋይና መሪ እንዲሁም ቁልፍ ሰው የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ በፌደራል መንግሥቱ ሲፈለጉ ከቆዩት ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ።
[ "ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አገሪቱን በመራው ኢህአዴግ ውስጥ አድራጊ ፈጣሪ የነበረው የህወሓት ቀደምት ታጋይና መሪ እንዲሁም ቁልፍ ሰው የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ በፌደራል መንግሥቱ ሲፈለጉ ከቆዩት ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ።" ]
በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ መንግሥት ለግጭቱና ለቀውሱ ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮችን ለመያዝ የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው ሰዎች መካከል አቦይ ስብሐት ይገኙበት ነበር። ከባላባት ቤተሰብ የወጡት የ86 ዓመቱ አዛውንት አቦይ ስብሐት ነጋ መምህር፣ የመንግሥት ሠራተኛ፣ ታጋይ፣ የህወሓት ሊቀመንበር፣ እንዲሁም በኢህአዴግና በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ ተደማጭና ተጽእኖ ፈጣሪ ሆነው ለአስርታት ቆይተው ነበር። አቦይ ስብሐት ከዚህ ሁሉ ባሻገር በአገሪቱ ኢኮኖሚና የውጭ ጉዳይ ላይ ጉልህ ተጽዕኖ ያላቸውን ተቋማትን ለመምራትም ችለዋል። ከእነዚህም መካከል ብዙ ሲባልላቸው የነበሩትንና ህወሓት የትግራይ ሕዝብ ንብረት ናቸው ይላቸው የነበሩትን ግዙፎቹን የኤፈርት ድርጅቶችን ለዓመታት አስተዳድረዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራተጂያዊ ጥናት ተቋምን ጡረታ እስከ ወጡበት ጊዜ ድረስ በዋና ዳይሬክተርነት መርተውት ነበር። አቦይ ስብሐት በአገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች ሲፈለጉ ቆይተው ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ትግራይ ውስጥ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በሆነ ገደላማ አካባቢ ከባለቤታቸውና ከእህታቸው ጋር ተይዘው ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸው ተዘግቧል። ከአርባ ስድስት ዓመታት በፊት የካቲት 1967 ዓ.ም የህወሓትን የትጥቅ ትግል ከጠነሰሱት ታጋዮች መካከል አንዱ ናቸው፤ አንጋፋው ታጋይ አቶ ስብሐት ነጋ። አቦይ በሚል ቅጽልም ይበልጥ ይታወቃሉ። አብዛኛዎቹ የህወሓት መስራቾች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች ሲሆኑ፤ ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲው የትግራይ ብሔረ ተራመጆች ማኅበር (ማገብት) የሚል ስብስብ ነበር። አቦይ ስብሐት የዚሁ ማኅበር ጠንሳሽ አባል ሆነው በቀጣይ ስለሚካሄደው የትጥቅ ትግልን በተመለከተ በሚደረግ ውይይት ላይ ከይርጋለም ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ንቁ ተሳትፎ ያደርጉ እንደነበር ከማኅበሩ አባላት አንዱ ለቢቢሲ ገልጿል። የደጃዝማች ነጋ ልጅ ስብሐት በጣልያን ወረራ ወቅት በ1928 ዓ.ም በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ከታሪካዊቷ የዓድዋ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ዓዲ አቤቶ በምትባል ስፈራ ከባላባት ቤተሰብ ነው የተወለዱት። አባታቸው ደጃዝማች ነጋ የወረዳ አስተዳደሪ/ገዢ የነበሩ ሲሆን ከእሳቸው ጋር ወደ ተለያዩ ቦታዎች እየተዘወሩ የጸሐፊነት ሥራ ይሰሩ እንደነበር በ1989 ዓ.ም 'እፎይታ' ከተባለው መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል። አቦይ ስብሐት ትምህርታቸው እዚያው በተወለዱባት በዓድዋ ከተማ ነበር የጀመሩት። መጀመርያ የቄስ ተማሪ እንደነበሩም ይናገራሉ። በዚያው በቤተ ክህነት ስር በነበረው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ቀጣዩን ትምህርታቸውን ጀመሩ። በወቅቱ አባታቸው 'ዛና ወዲ' ወደ ሚባለው አከባቢ ሲዘዋወሩ እሳቸውም አብረው ተጉዘዋል። አባተቸው 'አንተ ነህ የእኔ ወራሽ' ይሏቸው እንደነበርና በልጅነታቸው በግብርና ሥራ ተሰማርተውም እንደነበር ያስታውሳሉ። ሆኖም በወንድሞቻቸው ውትወታ ወደ ትምህርት ቤት ተመልሰው እስከ 8ኛ ክፍል እዚያው ዓድዋ ውስጥ ተምረዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመቀለ ከተማ በአንጋፋው የአጼ ዮሐንስ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው የተከታተሉት። ከሪፖርተር መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ትምህርት ዘግይተው መጀመራቸው "ያኔ [የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳሉ] ታናሽ ወንድሜ በድግሪ ተመርቋል" ሲሉ ተናግረው ነበር። አብሯቸው የተማረ ታጋይ አቦይ ስብሐት በ1955 ዓ.ም የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሆነው ፀረ ፊውዳሊዝም በነበረው የተማሪዎች ተቃውሞ ወቅት በትምህርት ቤቱ አንዱ ቀሳቃሽና የእንቅስቃሴው መሪ እንደነበሩ ለቢቢሲ ተናግሯል። በኋላ ላይ ወደ ትጥቅ ትግል ገብተው የህወሓት አመራር ሆነው ያገኛቸው ይሄው ታጋይ በነበራቸው ንቁ እንቅስቃሴያቸው ያስታውሳቸዋል። አቦይ ስብሐት ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት በስለሌና ጎሃ ጽዮን፣ በፍቼና በደብረ ብርሐን ከተሞች ተዘዋውረው አስታማሪ ሆነው ሰርተዋል። ወደ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል የመጀመርያ ድግሪ ተመርቀዋል። በኢኮኖሚ ሚኒስቴር ውስጥም የኢኮኖሚ ባለሙያ ሆነው ለአንድ ዓመት ሰርተዋል። "በዚህ ወቅት የብሔር ጥያቄ ይነሳ ስለነበር ወደ ትግራይ ዝውውር ጠየቅሁ" ሲሉ ከዓመታት በፊት ለእፎይታ መጽሔት የተናገሩት አቦይ ስብሐት፤ የዝውውር ጥያቄያቸው ተቀባይነት ስላለገኘ ወደ ትግሉ ለመቅረብ ሥራቸውን ለቀው ወደ መምህርነት ተመለሱ። ከዚያም ወደ ዓድዋ ተመልሰው የንግሥተ ሳባ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሆነው የሰሩ ሲሆን፤ እዚያም ብዙ ሳይቆዩ ወደ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ይርጋለም ከተማ ተዘዋውረው አስተምረዋል። "እዚያ አስተማሪ ሆኜ ሳለ ደርግ ወደ ስልጣን ወጣ" ሲሉም ለእፎይታ መጽሔት ተናግረዋል። አቦይ ስብሐት በቁጥጥር ስር ውለው አዲስ አበባ ሲገቡ 'አቦይ' የሚለውን ቅጽል እንዴት አገኙ? አቦይ የሚል አጠራር በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው አገላለጽ ነው። ቃሉ ዕድሜን ብቻ አመላካች ሳይሆን 'ዋናው' የሚል ትርጓሜም ሊሰጠው ይችላል። ብዙ ጊዜም የአገር አባት ሆኖ በሽምግልናና በዕርቅ ላይ ለሚሳተፍና ትልቅ አክብሮት ለሚሰጠው ሰው የሚሰጥ መጠርያ ነው። የአጼ ኃይለሥላሴ ሥርዓት የሸንጎ እንደራሴ አባል የነበሩትና ሥርዓቱን ተቃውመው ወጣቶችን መርተው ወደ ደደቢት በርሃ የወረዱት በትግል ስማቸው ስሑል ተብለው የሚታወቁት አቶ ገሰሰ አየለ አቦይ ስብሐትን በዕድሜ በ10 ዓመታት ይበልጡዋቸዋል። ስሑል በ1968 ዓ.ም ነበር ሲሞቱ ከእሳቸው በኋላ በታጋዮቹ መካከል በዕድሜ የበለጡ ስብሐት ነበሩ። ታጋዮቹን የሚደግፉ አርሶ አደሮች ጺማሙን ታጋይ ስብሐት ነጋን ሲያዩ 'አቦይ' እያሉ ይተሯቸው ነበር። ይህንንም ተከትለው የትግል ጓዶቻቸው ቀልደኛና ተጫዋች የነበሩትን ስብሐትን 'አቦይ' እያሉ መጥራት ጀመሩ። ቀልደኛው ስብሐት በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ ታሞ ጓዶቹ በቃሬዛ ተሸክመው እየወሰዱት ሳለ መንገድ ላይ ያገኟቸው አርሶ አደሮች 'ማን ነው የተሸከማችሁት?' ተብለው ሲጠየቁ፤ አቦይ ስብሐትም 'ምላስ ነው' በማለት በቀልድ የታመመው ተናጋሪው መለስ እንደሆነ ምላሽ ሰጡ ተብሎ ይነገራል። ስብሐት ብቻ ሳይሆኑ ብዙዎቹ የህወሓት ታጋዮች በትጥቅ ትግሉ ወቅት በተሰጣቸው ቅጽል ይጠራሉ። 'አቦይ'ም በቁጥጥር ስር እስከዋሉበት እስካሁን ድረስ መጠርያቸው ሆኖ ቀጥሏል። አቦይ ስብሐት በትግሉ ወቅት በህወሓት የትጥቅ ትግል ወቅት በከተማ አደረጃጀት ተመድበው የነበረ ሲሆን፤ በትግሉ መጀመሪያ ዓመታት ከሰባቱ አመራሮች መካል አንዱ አቦይ ስብሐት ነበሩ። በወቅቱ የድርጅቱ ጊዜያዊ ሊቀመንበር የነበሩት አረጋዊ በርሀ (ዶ/ር) ሲሆኑ፤ በ1971 ዓ.ም የድርጅቱ የመጀመሪያ ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ አቦይ ስብሐት የመጀመሪያው ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ። የሊቀመንበርነቱን ቦታ መለስ ዜናዊ በ1981 ዓ.ም እስከተረከባቸው ጊዜ ድረስም ህሓትን ለአስር ዓመታት መርተዋል። በመጀመርያዎቹ የትጥቅ ትግል ዓመታት አቦይ ስብሐት ቆራጥ ታጋይ እንደነበሩ ጓዶቻቸው ይመሰክራሉ። ሆኖም ግን በድርጅቱ ከፍተኛ አመራር ውስጥ የእርስ በርስ ትስስር (ኔትወርኪንግ) እንዲሰፍንና ክፍፍል እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል በሚል በተደጋገሚ ይወቀሳሉ። በ1968 ዓ.ም በድርጅቱ ውስጥ የተከሰተው 'ሕንፍሽፍሽ' በሚል የሚታወቀው መከፋፈልና በ1977 ዓ.ም እነ አረጋዊ በርሀ (ዶ/ር) እና አቶ ግደይ ዘርአጽዮን ከድርጅቱ እንዲገለሉ አንዱ ምክንያት እሳቸው እንደሆኑ ይነገራል። ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኋላ በ1993 ዓ.ም በተከሰተው ክፍፍል ወቅት ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ 'አንጃ' ተብለው ለእስርና ለስቃይ የተዳረጉ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ነበሩ። አቦይ ስብሐት የአገሪቱ የደኅንት ተቋም፣ መከላከያ ሠራዊቱና የድርጅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን እንዲቆሙ ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋቸው ይነገራል። ሆኖም ግን በአቶ መለስ የስልጣን ዘመን መጨረሻ አካባቢ በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት ለረዥም ጊዜ የበላይ ሆነው ሲመሩት ከነበረው ታላላቅ የምርትና የአገልግሎት ተቋማትን ከሚያንቀሳቅሰው ኤፈርት ኃላፊነት በመነሳታቸው ደስተኛ እንዳልነበሩ ይነገራል። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስም በአቦይ ስብሐት ምትክ መጀመሪያ ለተወሰነ ጊዜ በአምባሳደር አባዲ ዘሞ፣ ቀጥሎ ደግሞ ባለቤታቸውን ወይዘሮ አዜብ መስፍንን ሾመው ግዙፉን ተቋም እንዲመሩ ማድረጋቸው ይታወሳል። ህወሓት የከፍተኛ ካፒታል ባለቤት የሆኑ ተቋማትን በውስጡ የያዘው ኤፈርት የትግራይ ሕዝብ ንብረት መሆኑን ሲገልጽ የቆየ ቢሆንም፤ ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በድርጅቱ በሚመደቡ የፖለቲካ ሹመኞች ነበር ሲተዳደር የቆየው። አቦይ ስብሐት ምን ብለው ነበር ? የህወሓት አመራሮች በመርህ ደረጃ ማዕከላዊነትን የተከተለ የጋራ አመራር የሚከተሉ በመሆናቸው ከድርጅቱ ውጪ በነጻነት የራሳቸው ሐሳብ የመግለጽ ዝንባሌ የላቸውም። አቦይ ስብሐት ይህንን ቢያውቁም ከሌሎቹ በተለየ የመሰላቸው በነጻነት ከመናገር አይቆጠቡም። ባለፈው ዓመት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ "በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ መሰረት ያደረገ ትግል አይሳካም" ማለታቸው ይታወሳል። ከኤርትራ ጉዳይ ጋር በተያዘ "ህወሓት ከሻዕቢያ በላይ ለኤርትራ ነጻነት መስዋዕት ከፍሏል" ብለው በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆነው ነበር። ለዚህም እንደ ምክንያት "ሻዕቢያ በመጨረሻው ሰዓታት ከደርግ ሥርዓት ጋር ድርድር ጀምሮ ነበር" በሚል ይከሳሉ። አቦይ ስብሐት ኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ ሙስና እንደተንሰራፋ በግልጽ ሲናገሩ ይታወቃሉ። "ሙስና እየተንፏቀቀ የሚመጣ በሽታ ነው" የሚሉት አቦይ ስብሐት፤ ከሙስና ጋር የእርሳቸውም ስም እንደሚነሳ ጠቅሶ ቢቢሲ ጥያቄ አቀርቦላቸው ነበር። "መጣራት አለባት። ማን ነው ሙሰኛ? ንጹህስ ማን ነው? ብሎ የሚያጣራ ጀግና አልተገኘም። ቆራጥነት የለም" በማለት ባልተጣራ ሁኔታ "እኔ እንዲህ ነኝ ማለት አልችልም" ብለው ነበር። ከሁለት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ሥልጣን የመጡበት መንገድ ውስጥ የአሜሪካን እጅ አለበት ብለው የሚያምኑት አቦይ ስብሐት "ካዘዙን በላይ ኢህአዴግ ፈርሷል። ሕገ መንግሥቱም ፈርሷል፤ የፌዴራል ሥርዓቱም ፈርሷል" ሲሉ በአደባባይ ይወቅሱ ነበር።
xlsum_amharic-train-174
https://www.bbc.com/amharic/news-52697081
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ኢትዮጵያውያን እየተፈተኑባት ያለችው ኢስሊ
ቡና ለኢትዮጵያውያን የምታነቃቃ መጠጥ ብቻ አይደለችም። ጎረቤት፣ ዘመድ፣ ወዳጅና ቤተሰብ ተሰባስቦ የሚወያይባት፤ የአብሮነት መገለጫ፣ እንዲሁም ከዘመን ወደ ዘመን ስትተላለፍ የመጣች የትውልድ አሻራ ናት።
[ "ቡና ለኢትዮጵያውያን የምታነቃቃ መጠጥ ብቻ አይደለችም። ጎረቤት፣ ዘመድ፣ ወዳጅና ቤተሰብ ተሰባስቦ የሚወያይባት፤ የአብሮነት መገለጫ፣ እንዲሁም ከዘመን ወደ ዘመን ስትተላለፍ የመጣች የትውልድ አሻራ ናት።" ]
ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች በየሄዱበት ቡናን ይዘዋት ተጉዘዋል፤ 'በባዕድ አገር' አገራቸውን ለመፍጠር ሞክረዋል። በተለያየ እድሜ ላይ ለሚገኙ ሴቶች ምስጋና ይግባቸውና በውጭ አገራትም ቢሆን ቡና ይቆላል፣ ፈንዲሻው ይፈካል፣ ዕጣኑ ይጨሳል የተገኘውም የቡና ቁርስ ይቀርባል። ኢትዮጵያውያኑ ባህር አቋርጠው፣ በሺዎች ኪሎ ሜትር ርቀትም ባሉበት ሁሉ እንጀራ፣ ቅቤው፣ የወጡ ሽታ የመኖሪያ ህንጻዎችን ያውዳል፤ ዓመት በአል አከባበራቸው አገርን፣ ባህልን፣ ቤተሰብንና ትውልድን ተሸክሞ መምጣት ምን ማለት እንደሆነ ያሳያል። ከአገር ውጭ አገርን፤ ከቤት ውጭ ቤትን መፍጠር ያውቁበታል። በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ውስጥ በምሥራቅ ሲቢዲ የምትገኘው ኢስሊም በፔርሙስ ቡና ከሚያዞሩ፣ ልክ እንደ ኢትዮጵያ የእማማ ቤቶች ተብለው በሚጠሩ ትንንሽ ምግብ ቤቶች ውስጥ ቡናው ይቆላል፣ ጭሱም ይጨሳል፣ አድባሯንም ይለማመኗታል። ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ኢስሊ መሸጋገሪያ ናት፤ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ለሚደረጉ ጉዞዎች ለሌላ ስደት ጊዜን የሚጠብቁባት እንዲሁም የሚዘጋጁበት ቦታ ናት። ጉዳያቸው ተጠናቆ ምን ያህል ዓመታት እንደሚጨርስ ባይታወቅም ባሉበት በተለያዩ ንግዶች ተሰማርተው ይኖራሉ። በተለይም ኢስሊ 10ኛ ተብላ የምትጠራው ሰፈር የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን ስደተኞች መናኸሪያ ናት፤ የህልሞች መሰሪያ ስፍራ። በኢስሊ ቅናሽ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመጋረጃ ጨርቆች፣ ታዋቂ የዲዛይነር ምርቶች ከሚሸጡባቸው ትልልቅ ሞሎች በተቃራኒው የፕላስቲክ እና የማዳበሪያ ጣሪያ የለበሱ ሱቆች፤ የጡት ማስያዣ ሳይቀር ሰልባጅ ልብስ የሚሸጥባቸው ቦታዎች፣ ጉንጫቸው በጫት የተወጠረ ቃሚዎችና ጫት ሻጮች ሁሉ በየአይነቱ የተሞላባት ናት። በኢስሊ አዳዲስ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ይሰማሉ፣ ልክ ኢትዮጵያ ያሉ ይመስል በአማርኛ የተሰሩ ፊልሞች ድራማዎች በሲዲዎችም ኮፒ እየተደረጉ ይሸጣሉ። ምግብ ቢሆን የፍም ጥብስ፣ ቁርጥ፣ ክትፎ፣ በየአይነቱ፣ ሽሮ የሌለ የለም፤ ሬስቶራንቶቹ ውስጥ ውሃም ከሌለ እንደ ኢትዮጵያም በጆግ ሊታጠቡ ይችላሉ። ኢስሊ፤ በርካታ ቋንቋዎች፣ ቀለሞች፣ ድምፆች፣ ማታቱና 'ጀብሎው' የሚነታረኩባት፣ መንገዶቿ ከመጨናነቃቸው የተነሳ የታክሲ አሽከርካሪዎች ከገቡ ለመውጣት እንደሚቸገሩ ስለሚያውቁ እንደ 'ቤርሙዳ ትሪያንግል የሚፈሯት' አዛኑ ቀጥታ ወደ ፈጣሪ የሚደርስ ይመስል ጎላ ብሎ የሚሰማባት ያች ደማቅ ስፍራ በአሁኑ ሰዓት ፀጥ ረጭ ብላለች። ኬንያ እንደ ሌሎች አገራት አስገዳጅ የቤት መቀመጥ መመሪያ ባታስተላልፍም የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው በርካታ ህሙማን በመዲናዋ ናይሮቢ ኢስሊና በባህር ዳርቻዋ ከተማ ሞምባሰ ኦልድ ታውን መገኘታቸውን ተከትሎ ሰፈሮቹ ከምንም አይነት እንቅስቃሴ ተገድበዋል። በተለይም በኢስሊ በአንድ ቀን ውስጥ 29 የኮሮናቫይረስ ማግኘታቸውን ተከትሎ ነበር የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት ወደ ኢስሊ መግባትም ሆነ መውጣት የከለከሉት። ባለስልጣናቱ አስፈላጊ የሚባሉት እንደ መድኃኒትና ምግብ ለማድረስ ካልሆነ በስተቀር በአቅራቢያው መድረስ አይቻልም ብለው መወሰናቸውን ተከትሎም ፖሊሶችና ፀጥታ አስከባሪዎች አካባቢውን ወረውታል። ይህ የዋና ከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ዋነኛ ስፍራ ከእንቅስቃሴ ውጪ መሆኑ አስከዛሬ [ግንቦት 12/2012 ዓ.ም] የሚቆይ እንደሆነ የተነገረ ቢሆንም ሁኔታዎች ካልተቀየሩ ግን ሊቀጥል ይችላል። "የባሰ አያምጣ" ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የእንቅስቃሴ ገደቡን በተወሰነ መልኩ ላልቶ የንግድ ቦታቸውን እንዲከፍቱ ቢወሰንም፤ አሁንም ቢሆን ከኢስሊ ውጪ ያሉ ደንበኞች ወደ አካባቢው አለመግባታቸው መክፈታቸውን ትርጉም አልባ እንዳደረገው በኤምፔሳ ንግድ የሚተዳደረው ኢትዮጵያዊው ዮናስ ይናገራል። ኢስሊ ሙሉ በሙሉ ከመዘጋቱ በፊት በተቻለ መጠን ኦካላዊ ርቀታቸውን እየጠበቁ ይሰሩ የነበረ ሲሆን በመሆኑ እንደነ ዮናስ ላሉት ጉሮሮ መድፈኛቸውን አላሳጣቸውም ነበር። በአሁኑ ሰዓት ግን የሚከፍለው የቤት ኪራይ 12 ሺህ ሺልንግ፣ ለሱቅ ኪራይ ደግሞ የሚከፍለው 20 ሺህ ሺልንግ በየወሩ አለበት። ከዚያ በተጨማሪ ምግብ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎች ሲደማመሩ ገቢው ለተቋረጠበት ሰው እንዴት ፈታኝ እንደሆነ ለማሰብ አያዳግትም። ዮናስ ምንም እንኳን "ማማረር አልወድም" ቢልም በጣም ከባድ ወቅት እያሳለፉ እንደሆነም ይገልፃል። በአካባቢው የሚሰሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚበሉት አጥተዋል፤ ትንሽ ሻል ያሉትም ቁርስ በልተው ምሳ መድገም ከብዷቸዋል። የቤት ኪራይ ሳይከፍሉ ትንሽ አቅም ካላቸው ጋር ተጠግተው የሚኖሩም አሉ። ዮናስም የቤት ኪራዩ በርካታ ቀናት ቢያልፍም የንግድ እንቅስቃሴው ቀጥ በማለቱ የሚከፍለው የለውም፤ ነገም እንዴት እንደሚከፍል አያውቅም። "አሁንም መስሪያዬን ነው እየበላሁት፤ ግን ቢሆንም አላማርርም። እናቴ እንደምትለው "የባሰ አያምጣ ነው" የሚባለው" ይላል። ሁኔታዎች ደህና በነበሩበት ወቅት በቀን ከአርባ እስከ አምሳ ሰው ያስተናግድ ነበር እሱም ሆኖ ለኑሮው በቂ አልነበረም። የሚኖርበትም ቦታ በኢስሊ 11ኛ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ሲሆን ከሚሰራበትም ቦታ የጥቂት ደቂቃዎች መንገድ መሆኑ ቢያንስ የትራንስፖርት ወጪን ቀንሷል። ሆኖም እነ ዮናስ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ራሳቸውን ከአዲሱ ሁኔታ ጋር ማለማመድ ግዴታቸው ሆኗል። "በኢስሊ ኑሮን ቀለል ታደርጊዋለሽ። የተገኘውን ነገር አበሳስሎ መብላት ይቻላል። 'እግዚአብሔር አይነ ስውር አሞራን ይቀልባል' አይደል የሚባለው። ሆኖም ከእኔ የባሱ ጓደኞቼም፣ ወንድሞቼም አሉ" ይላል ዮናስ። በተለይም ወደ ሞያሌ የሚጓዙ መንገደኞች መናኸሪያ የሆነችው ኢስሊ ገንዘብ የሚቀይሩት፣ የሚያስፈልጓቸውን እቃዎች የሚሸምቱባት ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በአሁኑ ወቅት የአውቶብሶቹ እንቅስቃሴ መቆሙ ሰፈሯን ሽባ አድርጓታል። የአውቶብሶቹ መከልከል የተጀመረው ዮናስ እንደሚለው አሁን ሳይሆን ኢስሊ የመዘጋት ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት ነው። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት "ሰብአዊነት ቢኖር" የሚለው ዮናስ ለተቸገሩት የቤት ኪራይ ቢቀንስ፣ የቻሉት ደግሞ የቤት ኪራይ ሙሉ በሙሉ መተው ቢችሉ በተቻለ መጠን ችግሩን እንደሚያቀለው ያምናል። በአሁኑ ወቅት በርካቶች ያላቸውን ገንዘብ አሟጠው እየተጠቀሙ ሲሆን ይህም ሁኔታ ለወደፊቱ የሚፈጥረውን ጫና ማሰብ ለዮናስ ከባድ ነው። "ሰርተሽ ሳይሞላልሽ የምትከፍይው የቤት ኪራይ ያናድዳል። ምንም ሳትሰሪ ሲሆን ደግሞ በጣም ያበሳጫልም" ይላል። ሆኖም ወቅቱን ተረዳድተው ለማለፍ ምግብ ቤቶች ባይከፈቱም ያልተከፈተ አንድ ሱቅ አለ። እዚያች ገባ ብለው፣ ሽሮውንም፣ አቮካዶና ድንችም ቀላቅለው ያገኙትን ምሳ ይቀማምሳሉ። ። እዚያች ገባ ብለው፣ ሽሮውንም፣ አቮካዶና ድንችም ቀላቅለው ያገኙትን ምሳ ይቀማምሳሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በእለት ገቢያቸው የሚተዳደሩባቸውን አካባቢዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በመዘጋታቸው በርካታ ሰዎች ለረሃብና ለእንግልት መዳረጋቸውን ተከትሎ አገራት የወሰዷቸውን እርምጃዎች ከኢኮኖሚያዊ ፍትህና፣ የማኅበረሰብን ደኅንነትን ከመጠበቅ አንፃር በርካቶች ተችተውታል። አስገዳጅ ቤት ውስጥ የመቀመጥ ውሳኔ አብዛኛውን ደሃ ሕዝብ ያላማከለ፣ በተለይ በኢ-መደበኛ ዘርፎች ተሰማርተው የሚኖሩ አፍሪካውያንን የዘነጋ፣ ለጥቂቶች የተሰጠ ቅንጦት ብለውታል። በኢስሊ በተለይም ክፉኛ የተጎዱት በምግብ ቤቶች፣ በሱቆች እንዲሁም በተለያዩ የንግድ ቦታዎች ተቀጥረው በቀን ሥራ የሚተዳደሩት ናቸው። በቀን ለፍተው የሚያገኙት ገቢ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ እንደመሆኑ መጠን እንኳን መቆጠብ የእለት ጉርስና ማደሪያም መሸፈን በትግል ነው። አሰሪዎቻቸውም ባለው የኮሮናቫይረስ ቀውስ እንኳን ለመክፈል ለራሳቸውም ኪሳራ ላይ ናቸው። በኢስሊ ውስጥ ምጣድ፣ ሽሮ፣ በረበሬ፣ ቅቤ፣ ጤፍ፣ ባቄላ በአጠቃላይ ማንኛውንም የኢትዮጵያ ምርቶችን የሚቸረችረው ተስፋዬ በስሩ የሚያስተዳድራቸው ሠራተኞች በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሆኑ ይናገራል። ምንም እንኳን ከሰሞኑ ሱቁ ቢከፈትም ዝር የሚል ደንበኛ የለም፤ ለዚህም በርካታ ደንበኞቹ ከኢስሊ ውጭ በመሆናቸው ነው። በመኪናም ሆነ በሞተር እንኳን እንዳይልክ መንገዶች በመዘጋታቸው መውጫ የለም። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ በርካታዎቹ ሸቀጦች የሚበላሹ ከመሆናቸው አንፃር በቅርብ ጊዜ መሸጥ ካልቻለ ለበለጠ ኪሳራ እንደሚጋለጥ ይናገራል። ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያና በኬንያ ያለው ድንበርን መዘጋትን ተከትሎም ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ያመጣቸው የነበሩ ምርቶችንም ማስመጣት አይችልም። ለወደፊቱም መቼ እንደሚከፈት ግልፅ ካለመሆኑም ጋር ተያይዞ የወደፊቱን ሁኔታ አጨልሞበታል። ምንም እንኳን የንግድ እንቅስቃሴው ቀጥ ቢልም ለሱቁ 40 ሺህ ሺልንግ፣ ለመጋዘኑ 30 ሺህ ሺልንግ፣ የቤት ኪራይ 50 ሺህ በአጠቃላይ 120 ሺህ ሺልንግ [ከ1100 ዶላር በላይ] ወጪ አለበት። ከዚህም በተጨማሪ የአራት ልጆቹ እንዲሁም በአጠቃላይ የቤተሰቡ ወጪ ሲደማመር ወጪውን ያንረዋል። ገቢ በሌለበት ሁኔታ ደግሞ ይሄ ሁሉ ወጪ "ኪሳራ ነው" ይላል። ከዛሬ አስራ አንድ ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የመጣው ተስፋዬ በኢስሊ በንግድ ለ10 ዓመታት ያህል ሰርቷል። በሕግ ትምህርት የተመረቀው ተስፋዬ ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ወቅት በአቃቤ ሕግነትም ሰርቷል። ከነበረበት የሥራ ዘርፍ ወደ ስደት ስለመጣበት ሁኔታም መናገር የሚፈልገው ታሪክ አይደለም። "ከበሽታው በላይ ድህነት ነው የሚገድለን" ለአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ኢስሊ ከመዘጋቷ በፊት ንግዳቸው ቀጥ ብሏል። ከእነዚህም መካከል በኢስሊ 10ኛ ሰፈር የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ባለቤት የሆነው በረከት አንደኛው ነው። ኬንያ የኮሮናቫይረስን መዛመት ለመግታት ስትል ሬስቶራንቶችን መዝጋቷን ተከትሎ እሱም ከሥራ ውጪ ከሆነ ሁለት ወራትን ያህል አስቆጥሯል። በየወሩ ለሬስቶራንቱ ኪራይ የሚከፍለውን 66 ሺህ 300 ሺልንግ ሥራ ባቆመበት ሁኔታ መክፈል የማይቻል ትግል ሆኖበታል። ለሁለት ወራት ያህልም የሱቅ ኪራይ እንዳልከፈለ አልደበቀም። እንዲያው ይኼ ቀውስ እስኪያልፍ ድረስ ሌላ ቦታ ተቀጥሮ ለመስራትም አስቦ የነበረ ቢሆንም የብዙ ንግድ እንቅስቃሴዎች በመዳከሙ ተስፋዬ ያገኘው ነገር የለም። ምንም እንኳን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሬስቶራንቶች ይከፈቱ የሚል ፍቃድ ቢኖርም የእሱ ብዙዎቹ ደንበኞች ከሌላ ቦታ የሚመጡ በመሆናቸው እንዲሁም እሱ የሚሸጥበት የምግብ ዋጋ በአማካኝ 400 ሺልንግ በመሆኑ፤ እንኳን አሁን ከዚህ ቀደምም ለመብላት አቅሙ እንደሌላቸው በረከት ይገልፃል። ለብዙዎች በአሁኑ ወቅት እንጀራ በወጥ መብላት የማይታሰብ በመሆኑ፣ በቀን ሶስት ጊዜ መብላት እንደ ቅንጦት እንደሚታይ የሚገልፀው ተስፋዬ፤ በርካቶች በቀን የሚያገኟትን ዳቦ በአቮካዶ ይበላሉ። "ከበሽታው በላይ ድህነት ነው የሚገድለን" ይላል። ሆኖም "በህይወት መኖር ደግ ነው። ያው የተሻለ ጊዜ እግዚአብሔር ያምጣልን" ይላል። ምንም እንኳን በኢስሊ በርካታ ሶማሌዎች ቢኖሩም ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከታንዛንያና ከኮንጎ የመጡ ስደተኞች አንድ ላይ የሚኖሩባት፣ የቀጠናውን ባህል፣ ሕዝብ እና እምነት አንድ ላይ የሚመጣባት ስፍራ ናት። ዮናስም ለዚህ ምስክር ነው። "ቦታው ከብዙ ሰው ያገናኛል። ኬንያውም፣ ኢትዮጵያዊውም፣ ኤርትራዊውም እዚህ አለ። ደስ ይላል። አንዳንዴም 'ስደተኛ' በማለት ዝቅ ሊያረግሽ የሚሞክርም ይመጣል" በማለት ዮናስ መልካሙንና መጥፎውን ያወሳል። መርካቶ ያደገው ዮናስ ወደ ናይሮቢ ከመጣ በኋላ አሁን የሚሰራውን የኤምፔሳ ንግዱን ከመጀመሩ በፊት ለስምንት ዓመታት ያህል ፎቶ ቤት ውስጥ ተቀጥሮ ተሰርቷል። ኢስሊ በተወሰነ መልኩ መርካቶን ያስታውሰዋል። ግርግሩንም የሚያውቀው ነው። "ኢስሊ ጥሩ ሰፈር ነው። እንደ ወንድም እህት ተፈቃቅረን፤ እንደ ቤተሰብ ቡና አፍልቶ በአብሮነት የምናሳልፍበት ነው" በኢትዮጵያ ያደርጉት የነበረውን ሁሉ በኢስሊም ያደርጉታል። የማርያምም ማኅበር አላቸው። በተለይም ልክ እንደ አዲስ አበባ 'የእነ እማማ ቤቶች' ተብለው የሚጠሩ ምግብ ቤቶችም በኢስሊ አሉ። "ምግቡ ብቻ አይደለም። የእናትንም ፍቅር ታገኚበታለሽ" ቢልም ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ አይደለም። የኢስሊ ነጋዴዎች እንዲሁም ሚዲያዎችና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንዳሳወቁት፤ ስፍራው በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች በፖሊስ ከፍተኛ እንግልት፣ ያለምንም ጥፋት መታሰር እንዲሁም ገንዘብ የሚጠየቁበት ቦታ ነው። ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል እንደሚሉት ኢስሊ የፍራቻ ቦታ ነው፤ ለስላሳ ፀጉር፣ ፈካ ያለ የቆዳ ቀለም ማለት የተለየ ማንነት ካለ የፖሊስ ኢላማ እንደሚኮን ይሰማሉ። ከሰሞኑም ዮናስ ከቤቱ በር ወጥቶ ማስክ ሊያደርግ እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት ፖሊስ ለምን ማስክ አላደረግክም በሚልም አስጠንቅቆታል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሰለሞን ምንም እንኳን ስለ ንግዱም ሆነ ስለ ራሱ ህይወት መናገር ባይፈልግም በኮሮናቫይረስ ምክንያት የፖሊስ ዛቻና ማስፈራሪያ፣ የሙስናው ሁኔታ መንሰራፋቱን ይናገራል። ከዚህ ቀደምም የነበሩት ሙስናዎች በአሁኑ ሰዓት መልኩን ቀይሮ ሕዝቡ እየተንገላታ ነው ይላል። በዚህም ኢስሊ በተለየ መንገድ ኢላማ ተደርጋለች ይላል። ይህ ግን የሰለሞን ሃሳብ ብቻ ሳይሆን ኢስሊ መዘጋቷን ተከትሎ በርካቶች ሰፈሯ የሶማሌዎች መኖሪያ በመሆኗ እነሱ ላይ ያነጣጠረ ነው የሚሉ ትችቶችም ተሰምተዋል። በዚህም ምክንያት ባለፈው ሳምንት የኬንያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፍሬድ ማቲያንግ የኢስሊ ማኅበረሰብና የሙስሊም ማኅበረሰብ አመራሮችን ባናገሩበት ወቅት "ሰፈሩ መዘጋቱ ሕዝቡን ለመጠበቅ እንደሆነ ተናግረው፤ ብዙዎች ኢስሊ የተዘጋው አብዛኛው ማኅበረሰብ ሶማሌ ስለሆነ ነው የሚለውን ውንጀላ ነው" ብለው አጣጥለውታል። "ይህ የሁላችንም ችግር ነው። ተባብረን ከሰራን እንወጣዋለን። እንዲህ አይነት አስተሳሰቦች መኖራቸው የሚያሳዝን ነው። እመኑኝ መንግሥት በብሔር እንዲሁም በእምነት ላይ አያነጣጥርም" ብለዋል። ቅድመ ታሪክ በቅኝ ግዛት ወቅት እንግሊዞች በዘር እንዲሁም በብሔር የተለያዩ ማኅበረሰቦች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ሲወሰን፤ የኢስሊ ሰፈር አመሰራረት ግን በመደብ ላይ ያተኮረ ነበር። ቀደምት ነዋሪዎቹም እስያውያንና የተማሩ አፍሪካውያን ፀሐፊዎች፣ የግንባታ ሠራተኞችና ጫማ ሰሪዎች የሚኖሩበት ነበር። የኬንያውያንና እስያውያን መኖሪያ መሆኗ አስከ ጎርጎሳውያኑ 1963 ቢቀጥልም በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው ሶማሌና ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ ስደተኞች መኖሪያ ናት። በአሁኑ ሰዓት የሶማሌዎች አሻራ ጎልቶ በሚታይባት ኢስሊ የግመል ሥጋ ወጥ፣ በግመል ሥጋ የተሰራ ፖስታ፣ የተለያዩ ቅመሞች የተቀላለቀሉበት የግመል ወተት፣ ሂና፣ ቀሲልና መፋቂያዋ ለየት ያደርጋታል። የኢስሊው ኬኤፍሲ (የኬንተኪው ፍራይድ ቺክን አይደለም) ኪሊማንጃሮ ፉድ ኮርት ለፍየል ጥብስና ለግመል ጥብስ ተመራጭ ያደርገዋል። ከተለያዩ ቦታዎች የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየውም ኢስሊ ለናይሮቢ የከተማ ግብር ከ25 በመቶ በላይ አስተዋፅኦ የሚደረግባት ሰፈር ናት። ማስታወሻ፦ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ስም ተቀይሯል
xlsum_amharic-train-175
https://www.bbc.com/amharic/news-41036951
''ለብዙ ሰዎች ቦክስ ድብድብ ነው ፤ ለእኔ ግን ሳይንስ ነው''
በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ ተወልዳ ያደገችው መስከረም ጩሩ ገና በልጅነቷ ኑሮን ለማሸነፍ ብዙ ታግላለች፤ የሶስተኛ ክፍል ተማሪ እያለች ለእርሷ እንደክፍል ጓደኞቿ የመጫወቻ ጊዜ አልነበራትም ።
[ "በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ ተወልዳ ያደገችው መስከረም ጩሩ ገና በልጅነቷ ኑሮን ለማሸነፍ ብዙ ታግላለች፤ የሶስተኛ ክፍል ተማሪ እያለች ለእርሷ እንደክፍል ጓደኞቿ የመጫወቻ ጊዜ አልነበራትም ።" ]
መስከረም ሴት ቦክሰኞችን በሳምንት ለሶስት ቀናት ታሰለጥናለች ከትምህርት ቤት ስትመለስ እዛው በአካባቢዋ መንገድ ዳር ሊስትሮ ሆና ትሰራ ነበር። መሸትሸት ሲል ደግሞ ቤቷ ገብታ ሽመና የሚሰሩትን አባቷን በድውር ታግዛለች። አሁን መስከረም 26 ዓመቷ ነው፤ ዛሬም ቢሆን በትግል ውስጥ ናት ፤ ውድድሯ ግን ከኑሮ ጋር ብቻ ሳይሆን እሷ ሳይንስ ነው ከምትለው ቦክስ ጋር ነው። በእንጦጦ አምባ ትምህርት ቤት ገና የአምስተኛ ክፍል ተማሪ እያለች ነበር ወንድ ተማሪዎች ቦክሰ ሲለማመዱ አይታ ምን እያደረጉ እንዳሉ ብዙ ባይገባትም ቀረብ ብላ መላላክ የጀመረቸው። ''ያኔ ስለስፖርቱ ምንም አላውቅም ነበር፤ በኋላ ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ውድድር ወደሚደረግበት ስታዲየም ይዘውኝ ሲሄዱ በቃ ልቤ እዛው ቀረ፤ በጣም ወደድኩት ፤ እኔም መሰልጠን እንዳለብኝ ወሰንኩና ከ 20 ወንዶች ብቸኛዋ ሴት ሆኜ ተቀላቀልኳቸው'' ትላለች መስከረም። ወንዶቹም ብዙም ስላልተለመደ በውሳኔዋ ቢገረሙም በደስታ ተቀብለው የቡድናቸው አባል አደረጓት፤ ውጤታማ ለመሆንም ቢሆን ብዙ ጊዜ አልፈጀባትም፤ በየጊዜው ባለድል መሆኗን ተያያዘችው። መስከረም ለተከታታይ አስር ዓመታትም ሻምፒዮን ሆናለች። ያኔ ሀገርን ወክሎ የመወዳደሩ እድል ብዙም አልነበረምና ነገን ተስፋ በማድረግ ገና ቦክስን የሚቀላቀሉ ልጆችን ማገዝ እንዳለባት ወስና ለዚህ የሚያበቃትን ዓለማቀፍ ስልጠና በመውሰድ ፊቷን ወደአሰልጣኝነት አዞረች። ታዲያ እርሷ በውሳኔዋ እርግጠኛ ብትሆንም ስለስፖርቱ ያውም ስለሴቶች ቦክስ የብዙ ሰዎች አመለካከት ጥሩ አልነበረምና አረ ተይ የሚላት ብዙ ነበር። '' ለብዙ ሰዎች ቦክስ ማለት ድብድብ ነው፤ ለእኔ ግን ሳይንስም ጥበብም ነው፤ ቴክኒኩንና ታክቲኩን ለማወቅ በጣም ድካም አለው፤ በትክክል ለመረዳትም ብዙ የመማሪያ ጊዜ ያስፈልጋል'' ባይ ናት መስከረም። ይህ የሌሎች ኃሳብ ሰልጣኞችም ጋር ሊኖር እንደሚችል በመገመት ሁልጊዜም የሚቀላቀሏትን ልጆች በመጀመሪያ ቦክስን እንደጥበብ እንዲቀበሉና የስነልቦና ዝግጁነት እንዲኖራቸው ታስተምራቸዋለች። ከመስከረም ሰልጣኞች ብዙዎቹ ሴቶች ናቸው ከዚህ በኋላም ቢሆን በቀጥታ ወደስንዘራ አይገቡም ፤ ለቦክሱ የሚያስፈልገውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ይሰራሉ። ሰውነታቸው በስፖርት መዳበሩን ወይም መጠንከሩን ካረጋገጠች በኋላ መሰረታዊ የቦክስ አቋቋምና የእጅ እንቅስቃሴዎች ስልጠና ይቀጥላል። ይህን ሲጨርሱ ደግሞ የቦክስ አሰነዛዘር ቴክኒክ ፣ታክቲክና ትንፋሽ አወሳሰድ ተምረው አቅማቸው ሲያድግ በፕሮጀክት ውስጥ መወዳደር ይጀምራሉ ። ከፍ ሲሉ ደግሞ የውድድር ሂደቶችን ተከትለው እስከሃገር አቀፍ ውድድሮች ድረስ ተሳትፎ ይኖራቸዋል ። መስከረም 30 የሚሆኑ ወንድና ሴት ቦክሰኞችን በሳምንት ለሶስት ቀናት በዚህ ሂደት መሰረት ታሰለጥናለች ። ከሰልጣኞችም አራት ሴቶች በአዲስ አበባ ፖሊስ ክለብ ሲታቀፉ የኒያላና ማረሚያ ቤቶችን የቦክስ ክለቦች የተቀላቀሉ ወንዶችም አሉ። በኦሎምፒክ ወደማሳተፍ ህልሟ የተጠጉላትን ሁለት ሴቶችና አንድ ወንድ ቦክሰኛም ለብሄራዊ ቡድን አስመርጣለች። ሴት ቦክሰኞች ብዙም ባልተለመደባት ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ጉለሌና ኮልፌ አካባቢ ብዙ ሴቶች እነመስከረምን እያዩ ቤተሰቦቻቸውን እንድታግባባላቸው ይለምኗታል ። እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች እርሷንም በኃሳብ ወደ ኋላ ይመልሷታል። ''የኔ ቤተሰቦችም ገና ስጀምር አካባቢ በጣም ተቃውመውኝ ነበር። በኋላ ግን በኔ ተገርመው ሳይጨርሱ ሁለት እህቶቼም ቦክሰⶉች ሲሆኑ ሃሳባቸውን ከማንሳት ውጪ አማራጭ አልነበራቸውም'' ትላለች። መስከረም በሽሮ ሜዳ አካባቢ በሚገኘው የወጣቶች ማሰልጠኛ ውስጥ በአንድ ጊዜ እስከ 50 የሚደርሱ ወጣቶችን በፕሮጀክት ስታሰለጥን የምታገኘው ገቢ ለሳሙና በሚል በወር የሚከፈላትን 1000 ብር ብቻ ነው። ቤተሰቧንም ለመደጎም ይሕ ገንዘብ በቂ አይደለምና ከዚህ ሁሉ ልፋት በኋላም ቤቷ ደግሞ ሌላ አድካሚ ስራ ይጠብቃታል። በሽመና ስራ ባህላዊ አልባሳትን እያመረተች ለገበያ ታቀርባለች፤ ግን ሁለቱን ማወዳደር አይታሰብም ትላለች ። ''የምሰራው ለገንዘብ ቢሆን ቦክሱን ድሮ ነበር የምተወው ፤ ግን ብሞክርም አይሆንልኝም፤ ምክንያቱም ያለቦክስ መኖር አልችልም'' በማለት ትናገራለች። የ18 ዓመቷ ገነት በ54 ኪሎ ግራም የቀላል ሚዛን ተወዳዳሪ ናት ገነት ጸጋዬ ሴቶች የሚበዙበትን የመስከረም የቦክስ ማሰልጠኛ ፕሮጀክት ከተቀላቀለች ሶስት ዓመት ሆኗታል። አብሮ አደጎቿ የሚያውቋት 'ወንደወሰን' በሚለው ቅጽል ስሟ ነው፤ ልጅ እያለች ጸጉሯ መቆረጡን እግርኳስንም ማዘውተሯን የተመለከተ ጎረቤቷ ነበር ይህን ስያሜ የሰጣት። ገና የ15 ዓመት ልጅ እያለች እንደወትሮ ሁሉ በአካባቢዋ ስትጫወት ያየ አንድ ሰው ለምን ቦክስ አትሞክሪም? ብሎ መስከረም ወደምታሰለጥንበት ቦታ ይዟት መጣ። ያኔ ገነት ቦክስ ምን እንደሆነ እንኳን አታውቀውም ነበር፤ ሆኖም ገና በ 15 ዓመቷ ከፕሮጀክቱ የመጀመሪያው ማሊያ ሲሰጣት የልጅነት ሞቅታ ተሰማት፤ ቦክሱንም ትምህርቷንም ጎን ለጎን ማሰኬድ ፈለገች። ''መስከረም ስታሰራ አቋሟ ይመቸኛል፤ በጣም ትስበኛለች'' የምትለው ገነት ቀሰ በቀስ እርሷም ከቦክስ ጋር ተወዳጀች ። ጠዋትና ማታ ቢያንስ ለአራት ሰዓታት በትጋት መሰልጠን ጀመረች። ከአንድ ዓመት በኋላ ስትፈልገው የነበረውን እድል አገኘች፤መስከረም ጋር ስትለሰለጥን አቋሟን ያዩ አስልጣኞች በክለብ ከታቀፉ ቦክሰⶉች ጋር እንድትወዳደር ጠየቋት። ''ያኔ ብዙ አቅም እንዳለኝ የተሻለም መስራት እንደምችል አውቅኩ፤ ምክንያቱም ከብዙዎቹ የተሻልኩ ነበርኩኝ'' ትላለች። በ2008 በአዲስ አበባ ፖሊስ ክለብ ታቅፋለች ፤ ትጥቆች ጓንቶችና የ 3000 ሺህ ብር ወርሃዊ ደሞዝ ታጘኛለች። የወደፊት ህልሟ ደግሞ በብሄራዊ ቡድን ሃገሯን ወክሎ መወዳደር ነው። በክለብ ብትትቃፍም አሁንም መሰከረም ጋር መሰልጠኗን አላቋረጠችም። በሳምንት ለሶስት ቀናት ትሰለጥናለች፤ ከእርሷ ያነሱትን በማሰልጠንም ታግዛለች ። ''ለቦክሰኛ አመጋገቡ አቋሙንም ክብደቱንም በጣም ይወስነዋል ፤እኔ ኪሎዬ ጥሩ ከሆነ እንዳይጨምርም እንዳይቀንስም ፓስታ እበላለሁ፤ ኪሎዬ ከቀነሰ ግን በቃ ያገኘሁትን ሁሉ ነው የምበላው ፤ይሄኔ ካሽካ የሚባለውን በበቆሎ የሚሰራ የዶርዜ ባህላዊ ምግብ እመርጣለሁ"ትላለች ገነት። ገነት በራሷ ትጋት እዚህ ደረሰች እንጂ ቤተሰቦቿ ቦክሰኛ የመሆን ሃሷቧን እንድትቀይር ስልጠናውንም እንድታቆም ጫና ያደርጉባት ነበር። '' በተለይ ደግሞ አባቴ የሆነ ጊዜ ላይ ጫወታውን ሊያይ መጥቶ በውድድሩ ላይ ስደባደብ ሲያየኝ ሆዱ ባብቶ አረ ተይ ይለኝ ነበር ግን የኋላ ኃላ ሳሸንፍ ሜዳሊያም ሳመጣ ግፊቱ እየቀነሰ መጣ" ሴት ቦክሰኞችን ለመቀበል ሌሎች ሰዎችም ይቸገራሉ ትላለች ገነት። '' ብዙዎች ለሴቶች ቦክስ ምን ያደርጋል እያሉ ያንቋሽሹናል ፤እኔ ደግሞ ለምን እንዲህ ትላላችሁ ከወንዶቹ በምን እንለያለን እላቸዋለሁ?'' በማለት ትጠይቃለች። ከንግግርም አልፎ እሷንም ሆኑ ሴት ጓደኞቿን የሚፈታተናቸው ወንድ አልጠፋም ፤ያኔ ስፖርቱም እንደሚጠይቀው ትዕግስትን መላበስ ግድ ይላታል ፤ ግን ይሄ ሁልጊዜ በቂ ላይሆን ይችላል። ''አንድ ቀን አንዱ ጎረምሳ ጓደኛዬን ተተናኮላት፤ አረ ተው ብንለው እምቢ አለ፤ እኔም እባክህን በናትህ ተዋት እያልኩ ልመና ገባሁ፤ ቢሳደብ ቢቆጣ ዝም አልኩት፤ ድንገት መጥቶ በጥፊ ሲመታኝ ግን ትእግስቴ አልቆ አንድ ጊዜ አቀመስኩት፤ ከውድድር ውጪ ለቦክስ እጄን ዘረጋሁት ያን ጊዜ ብቻ ነው'' በማለት ትናገራለች።
xlsum_amharic-train-176
https://www.bbc.com/amharic/news-56442846
አብደላ ሸሪፍ፡ በዩኔስኮ በቅርስነት በተመዘገበችው ከተማ በሐረር የግል ሙዚየም ያቋቋሙት ግለሰብ
መጋቢት 04/2013 ዓ,ም ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ለሁለት ሰዎች የክብር ዶክተሬት ሰጥቶ ነበር። አንደኛው አቶ አብደላ ሸሪፍ ሲሆኑ ሌላኛው ደግሞ የቀድሞው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን አቶ አባዱላ ገመዳ ናቸው።
[ "መጋቢት 04/2013 ዓ,ም ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ለሁለት ሰዎች የክብር ዶክተሬት ሰጥቶ ነበር። አንደኛው አቶ አብደላ ሸሪፍ ሲሆኑ ሌላኛው ደግሞ የቀድሞው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን አቶ አባዱላ ገመዳ ናቸው።" ]
የዛሬ ጉዳያችን ታድያ አቶ አብደላ ሸሪፍ ናቸው። የክብር ዶ/ር አብደላ አሊ ሸሪፍ ሙሉ ስማቸው አቶ አብዱላሂ አሊ ሸሪፍ እንደሚባል ነግረውናል። በአብዛኛው የሚታወቁት ግን አብደላ ሸሪፍ በመባል ነው። ተወልደው ያደጉባት፣ ክፉ ደግ አይተው አግብተው የወለዱባት፣ ታሪኳንና ባህሏን የሚሰንዱላት ሐረር መኖሪያቸውም ጭምር ናት። የሐረር ከተማ፣ በ2006 ዓ.ም በዩኔስኮ ቅርስነት ተመዝግባለች። የ69 ዓመት አዛውንት የሆኑት እኚህ ግለሰብ፣ የግላቸውን ቅርሳ ቅርስ የሚሰበስቡበት ማዕከል በታሪካዊቷ ሐረር ከተማ አላቸው። ይህንን ሥራ ለመጀመር ምክንያት የሆናቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ አብሯቸው ያደገው "ራስን የመፈለግ ዝንባሌ" ነው ይላሉ። በተለይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሚከታተሉበት ወቅት ስለ ቤተሰባቸው ታሪክ መጠየቅ መጀመራቸውን የሚያስታውሱት አቶ አብደላ "ታሪክ አዋቂ የሆኑ የአገር ሽማግሌዎችን መጠየቅሁ" ይላሉ። በወቅቱ ታዲያ ለአቶ አብደላ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የተሰየሙት የአገር ሽማግሌዎች "ታሪክ ድሮ ነበረን አሁን ግን የለንም" ስላሏቸው ያለፈውን ታሪካቸውን ያለማወቅ ችግር ገጠማቸው። ከዚህ በኋላም የራሳቸውንና የማኅበረሰባቸው ታሪክ ለማወቅ ፍለጋ ጀመሩ። አቶ አብዱላሂ፣ በወቅቱ ለተፈጠረባቸው የማንነት ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ባህላቸውን የሚያንፀባርቅ ቅርስ ለማሰባሰብ ቆርጠው ተነሱ። ከልጅነታቸው ጀምሮ ቅርስን የመጠበቅና የመንከባከብ ዝንባሌ የነበራቸው አብደላ አሊ ሸሪፍ፣ ህልማቸውን ለማሳካት ቀደምት የሐረሪ ሙዚቃዎችንና ጥንታዊ የእጅ ፅሁፎችን በማሰባሰብ ሥራቸውን 'ሀ' ብለው ጀመሩ። በዚህም ታሪክን መመርመር ማጥናት ጀምረው ከ1982 ዓ.ም ጀምሮ መጻህፍትን የሐረሪ ዘፈኖችን፣ ጥናታዊ ጽሑፎችን፣ አልባሳትን እና የተለያዩ ባህላዊ እቃዎችን መሰብሰብ ጀመሩ። በዚህም ሂደት ወቅት በምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙትን የኦሮሞን፣ የሐረሪን፣ የሶማሌ፣ የአፋርን እና የአርጎባን ባሕሎች የሚያስተዋውቁ ቅርሶችን እንደሰበሰቡ ይናገራሉ። የሰበሰቧቸው እነዚህ የአገሪቱን የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ባህልና ታሪክን የሚያሳዩ እቃዎችን ከቤተሰባቸው ጋር ለ17 ዓመታት ቤታቸው ውስጥ መቆየቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በርካታ መጠን ያላቸውን እነዚህን እቃዎች በቤታቸው ውስጥ በጠባብ ስፍራ ለረጅም ጊዜ በማስቀመጣቸው የተነሳ "ለአስም በሽታ ልጋለጥ ችያለሁ" ይላሉ። 'ሸሪፍ ሙዚየም'' ከዓመታት ጥረት በኋላም በ1991 ዓ.ም ''ሸሪፍ ሙዚየም'' በማለት በኢትዮጵያ ብቸኛውን "የግል ሙዝየም" ለመመስረት በቁ። ይህ የቅርስ ማዕከል አቶ አብደላ ባህላዊ እቃዎችን መሰብሰብ ከጀመሩ ከ17 ዓመት በኋላ የተቋቋመ ነው። ሙዚየሙ በሐረር ከተማ መኪና ግርግር በሚባለው ስፍራ ላይ ይገኛል። ሙዚየሙ የሚገኝበት ቤት እራሱ ከ110 ዓመት በፊት የተሰራ በመሆኑ ታሪካዊ እንደሆነ ይናገራሉ። በ1999 ዓ.ም የሐረሪ ክልል መስተዳደርም የአቶ አብደላ ሸሪፍን ጥረት ለመደገፍ፣ የተፈሪ መኮንን ጫጉላ ቤት የሚባለውና የ21 አባወራዎች መኖሪያ ሆኖ የቆየውን ታሪካዊ ቤት ለሙዚየምነት እንዲውል በመስጠት ከፍተኛ ድጋፍ እንዳደረገላቸው ገልጸዋል። ይህ ቤት ራስ መኮንን ልጅ የነበሩት ተፈሪ መኮንን በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩት አጼ ኃይለሥላሴ የሐረር አስተዳዳሪ በነበሩት ጊዜ በ1903 ዓ.ም የተሰራ እንደነበር አቶ አብደላ ይናገራሉ። እንዲህ አይነት የባህል እና የታሪክ ቅርሶችን በአንድ ስፍራ ሸክፎ ያዘ ሙዚየም ወይንም የግል የቅርስ ማዕከል በግል ማደራጀት በኢትዮጵያ የተለመደ አይደለም። አቶ አብደላ ግን በዘርፉ በግል የተሰማራ እንደሌለ ሲተቅሱ ከኢትዮጵያ አልፈው የአካባቢውን አገራትን ይጠቅሳሉ። "በግል እኔ ብቻ ነኝ ያለኝ። በምሥራቅ አፍሪካም እኔ ብቻ ነኝ ያለሁት" ይላሉ። በእርግጥ በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ካሉ በርካታ አገራት ውስጥ እርሳቸው ብቸኛ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ ባይቻልም፣ በግል ተነሳሽነት ይህንን የሚያክል ሙዚየም ማደራጀት ቀላል እንዳልሆነ መረዳት ይቻላል። በሙዚየሙ ውስጥ የሚገኙ ቅርሶች እንዴት እንደሰበሰቡ ሲናገሩ፤ የተወሰኑትን ሰዎች በስጦታ እያመጡላቸው፣ የተወሰኑትን ደግሞ በራሳቸው ገንዘብ በመግዛት እንደዚሁም ደግሞ ለሰዎች በአደራ በማስቀመጥ መሆኑን መሆኑን ይናገራሉ። እንደዚህም ሆኖ ጥንታዊ እቃዎችን መሰብሰብ ቀላል አለመሆኑን አቶ አብዱላሂ ሸሪፍ ለቢቢሲ ይናገራሉ። "መጀመሪያ ሰዎች አያምኑኝም ነበር። ምክንያቱም ይሸጠዋል ብለው ስለሚያስቡ ነበር። መሰብሰብ ጀምሬ ሰው መጥቶ ማየት ከጀመረ በኋላ ግን እምነት እያገኘሁ መጣሁ" ይላሉ። የበዚህም ሳቢያ በሕዝቡ ዘንድ በተፈጠረው መተማመን ጥንታዊ መጽሐፍት በሙዝየማቸው ውስጥ ለመገኘት እንዲገኝ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። "ከሰበሰብኳቸው ታሪካዊና ባህላዊ እቃዎች መካከል 60 በመቶ ያህሉ ሕዝቡ ነው የሰጠኝ" በማለት የተለያዩ ሰዎች ቅርሶቹን እንደሚያመጡላቸውም ይገልጻሉ። "ቅርሶቹን የማሰባስበው ለታሪክ እንጂ ለሽያጭ አይደለም" የሚሉት አቶ አብደላ፣ በሙዚየሙ የሚገኙት የተለያዩ ቅርሳ ቅርሶች "የሕዝብ ታሪክ ነው፤ ለመሸጥ እና ነጋዴ መሆን አይደለም የሰበሰብኳቸው። ታሪክን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ እንጂ እኔ ለመሸጥ አልገዛሁም አንድም አልሸጥኩም።" በሙዚየሙ ውስጥ ምን ምን አለ? እንደ አቶ አብደላ አገላለጽ ሙዚየሙ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ጌጣጌጦችን በሚያሳዩ ቅርሶች የተሞላ ነው። በዚህ ማዕከል ውስጥ የሐረሪና የአክሱም እንደዚሁም ከ120 አገራት በላይ ገንዘቦች ይገኛሉ። በአብዛኛው በእጅ የተጻፉ ቅዱስ ቁርዓንን ጨምሮ ከ1000 ዓመት በላይ እድሜ ያላቸው የአረብኛና በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉ መጻህፍት በሙዚየሙ ውስጥ በአግባቡ ተደራጅተው እንደሚገኙ ይናገራሉ። አቶ አብደላ አሊ ሸሪፍ እንደሚሉት በዚህ የግል ሙዝየማቸው ውስጥ ከ13 ሺህ በላይ ውድና እድሜ ጠገብ የአገር ሀብት የሆኑ ቅርሶችን በማሰባሰብና በመጠበቅ ለትውልድ ለማቆየት ችለዋል። "13 ሺህ በላይ የሚሆኑ ቅርሱች ይገኛሉ፤ አልባሳት፣ የጦር እቃዎች፣ ጎራዴ፣ ማህተሞች፣ የጌጣ ጌጥ እቃዎች ሁሉ በስብስቡ ውስጥ አሉ።" በዚህ የግል ሙዚየም ቅርሶችን ከመሰብሰብ ባለፈም ቅርሶችን የመመዝገብና የመንከባከብ እንዲሁም የተጎዱ ቅርሶች የመጠገንና የማደስ ሥራዎችም እንደሚከናወኑ ገልጸዋል። ከዚህ ባለፈም ከተለያዩ ዓለማት ለሚመጡ የውጭ አገር ጎብኚዎች እንዲሁም በተለያየ ደረጃ ለሚገኝ ኢትዮጵያዊያንም ሙዚየማቸውን በማስጎብኘት ታሪክን እና ማንነትን እንዲያውቁ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ያምናሉ። አቶ አብዱላሂ ሸሪፍ ቀደም ሲል ይህንን ሙዚየም ለመጎብኘት ከሚመጡ ቱሪስቶች "በወር ከ25 ሺህ እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ" እናገኝ ነበር ብለዋል። አሁን ግን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በመላው ዓለም በመከሰቱ ምክንያት የጎብኚዎች ቁጥር ቀንሶ "እየከሰርን ነው ያለነው" ይላሉ። የክልሉ መንግሥት ቀድሞ የተፈሪ መኮንን ቤተ መንግሥት የነበረውን ቤት ለቅርስ ማዕከልነት እንዲውል በማለት ለአቶ አብደላ ከመስጠት ባሻገር ሙዚየሙን የጥበቃ ሠራተኞች ደሞዝ በመክፈል ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ተናግረዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት ከኤምባሲ እና ከተለያዩ ድርጅቶች እንዲሁም ከሼህ አላሙዲን ጭምር ለሙዚየሙ ማጠናከሪያ ድጋፍ አግኝተዋል። አቶ አብደላ ሸሪፍ ለሥራቸው የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ማግኘት የቻሉ ሲሆን በአገር ወስጥም የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማትን ጨምሮ በርካታ እውቅናዎችን አግኝተዋል። መጋቢት 04/2013 ዓ.ም ደግሞ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ "የአገራችንን ጥንታዊና ዘመናዊ ስልጣኔዎችን በዓለም ሕዝቦች እንዲታወቁ የላቀ አስተዋፅኦ አበርክተዋል" በማለት የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል።
xlsum_amharic-train-177
https://www.bbc.com/amharic/49699399
ከባህላዊ ጃንጥላ እስከ እንጀራ ማቀነባበሪያ፡ የ2011 ዓ.ም አበይት ፈጠራዎች
በ2011 ዓ. ም. በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ከተመዘገቡ የግብርና ምርቶች መካከል የጅሩ ሰንጋ፣ የይፋት ደብረሲና ቆሎ፣ የምንጃር ጤፍ፣ የአረርቲ ሽምብራ፣ የመንዝ በግ፣ የአንጎለላና ጠራ ወተት የሚገኙ ሲሆን፤ የወሎ ጋቢና የደሴ ሳፋ በምዝገባ ሂደት ላይ እንደሚገኙ የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለቢቢሲ አረጋግጧል።
[ "በ2011 ዓ. ም. በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ከተመዘገቡ የግብርና ምርቶች መካከል የጅሩ ሰንጋ፣ የይፋት ደብረሲና ቆሎ፣ የምንጃር ጤፍ፣ የአረርቲ ሽምብራ፣ የመንዝ በግ፣ የአንጎለላና ጠራ ወተት የሚገኙ ሲሆን፤ የወሎ ጋቢና የደሴ ሳፋ በምዝገባ ሂደት ላይ እንደሚገኙ የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለቢቢሲ አረጋግጧል።" ]
ሰብለወንጌል ብርቁና ሔዋን መርሀ በተጨማሪም በርካታ የሥነ ጽሑፍ፣ ሥነ ጥበብና ሌሎችም የጥበብ ውጤቶች እንዲሁም የንግድ ምልክቶችም ተመዝግበዋል። ባህላዊ ጃንጥላ እና እንጀራ 'ፕሮሰሰር' [እንጀራን አቡክቶ የሚጋግር መሣሪያ]፤ ባሳለፍነው ዓመት በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ከተመዘገቡ የፈጠራ ሥራዎች መካከል ይገኙበታል። እኛም የፈጠራዎቹን ባለቤቶች እንግዳችን አድርገናል። • የወንድሙን ገዳይ ለመበቀል ወደ ፈጠራ ሥራ የገባው ኢትዮጵያዊ • የኢትዮጵያ ተረት ገፀ-ባህሪን በአኒሜሽን • የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች "ድሮ ነጠላቸውን ቆልፈውበት ይሄዱ ነበር" ሔዋን መርሀ 24 ዓመቷ ነው። ያጠናቸው 'ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ' ሲሆን፤ 'ዳታ ኢንኮደር' ናት። ሔዋን "እጇ የማይቦዝን" የምትባል አይነት ሰው ናት። የረዘመ ልብስ ታሳጥራለች፣ ጨሌ ሰብስባ የእጅ ጌጥ ትሠራለች ወዘተ. . . "ባህላዊ ነገር ደስ ይለኛል" የምትለው ሔዋን፤ በተለይ ነጠላ ካገኘች ደስታዋ ወደር የለውም። ትቀደዋለች፣ ትሰፋዋለች፣ አንዱን ዘርፍ ከሌላ ጋር ታስተሳስራለች። "ከልጅነቴ ጀምሮ በጣም ልብስ እቀዳለሁ። [የገዛሁትን ልብስ ቀድጄ] በራሴ 'ሙድ' አደርገዋለሁ። ከሰፋኝ አጠባለሁ፤ ከጠበበኝ አሰፋለሁ። እጁ ካልተመቸኝ ቆርጬ ሌላ ቦታ አደርገዋለሁ" ታዲያ ይህን ልማዷን ቤተሰቦቿ እምብዛም አይደግፉትም ነበር። በተለይ እናቷ "እሷ ነጠላ ካገኘች አትቻልም" እያሉ ከቤት ሲወጡ ነጠላቸውን ቆልፈውበት ይሄዱ እንደነበር ታስታውሳለች። የዛሬ ዓመት ከስድስት ወር ገደማ ጥበብ ልብስ አድርጋ ከቤት ልትወጣ እየተሰናዳች ሳለ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለላት። ከጥበብ ልብስ ጋር አብሮ እንዲያዝ የተሠራው ጃንጥላ "የገዛሁት ሐበሻ ቀሚስ ሁለት ነጠላ ነበረው። ከቤት ልወጣ ስል ጸሐይ ነበር። ከዛ አንዱን ነጠላ ለምን ጥላ አላደርገውም አልኩ? እናቴ 'ይቺ ልጅ ቀሚስም መቅደዷ አይቀርም' ብላኝ ነበር. . . " ሀሳቧ ሀሳብ ሆኖ አልቀረም። ከጥበብ ጃንጥላ ሠራች። የጃንጥላው መደብ ጥበብ ነው። ሰዎች ሐበሻ ልብስ አድርገው ሲወጡ ከልብሳቸው ጋር በሚመሳሰል ጥብበ በተሠራ ጃንጥላ እንዲዘንጡ፣ ራሳቸውን ከጸሐይ እንዲከላከሉም አስባ እንደሠራችው ትናገራለች። "ጥለቱን ሽሮ ሜዳ ሸማኔዎች ጋር ሄጄ አሠራዋለሁ። ሰው ሐበሻ ልብስ ሲገዛ ከልብሱ ጋር 'ማች' የሚያደርግ [የሚመሳሰል] ጃንጥላ እኔን ማሠራት ይችላል።" ጃንጣላው እንደሚሠራበት ጥበብ አይነት፤ ከ1000 ብር እስከ 2000 ብር ድረስ ትሸጠዋለች። ጃንጥላው በተጠቃሚው ፍላጎት መሰረት በክብ ወይም በዚግ ዛግ ይሠራል። ሔዋን ጃንጥላውን ለልጆችና ለአዋቂዎችም ታዘጋጃለች። የጥበብ ኮፍያም ትሠራለች። ባህላዊ ጃንጥላውን በአዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ብታስመዘግበውም፤ የሙሉ ጊዜ ሥራዋ አይደለም። ለወደፊት አቅሟን አደራጅታ፣ ሱቅ ከፍታ፣ ንግዱን ማጧጧፍ እንደምትፈልግ ነግራናለች። "ድሮ ነጠላቸውን ቆልፈውበት የሚሄዱት ቤተሰቦቼ፤ ሥራዬ ገንዘብ እንደሚያመጣ ሲያውቁ እኔን መደገፍ ጀምረዋል" ትላለች። "በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንጀራ የሚጋገርበት መንገድ መለወጥ አለበት" የ21 ዓመቷ ሰብለወንጌል ብርቁ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህክምና ተማሪ ናት። እንጀራ 'ፕሮሰሰር' የተሰኘ ማሽን ለመሥራት የወጠነችው የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ነበር። ለቤተሰቦቿ የመጀመሪያ ልጅ ናት። ከአንድ ጓደኛዋ ጋር ስለ ቤት ውስጥ ሥራ ጫና ሲያወሩ፤ 'በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንጀራ መጋገር የሚወስደውን ጊዜ እንዴት መቀነስ አይቻልም?' ትለዋለች። እንጀራ ተቦክቶ ሲጋገር የሚወስደውን ጊዜና ጉልበት መቀነስ እንደሚቻል የነገረችው ጓደኛዋ፤ ሀሳቧ አልዋጥልህ አለው። እሷ ግን 'እንደውም ሀሳቤን እውን አድርጌ አሳይሀለሁ' ብላ ዛተች። በትምህርት ቤቷ በሚገኝ 'ወርክሾፕ' ውስጥ ረዥም ጊዜ ታሳልፍ ጀመር። ሀሳቧን ያካፈለቻቸው ጓደኞቿም ከጎኗ ነበሩ። በስተመጨረሻም ለሙከራ የሚሆን እንጀራ አቡክቶ፣ የሚጋግር ከዛም በሰፌድ አውጥቶ የሚያስቀምጥ መሣሪያ ሠራች። ሰብለወንጌልና ጓደኞቿ እንጀራ 'ፕሮሰሰር' ሲሠሩ በፈጠራው በትምህር ቤቷ ተሸላሚ እንደነበረች ታስታውሳለች። ሰብለወንጌል የፈጠራውን ሀሳብና ዲዛይን በአዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ለማስመዝገብ የወሰነችው ዩኒቨርስቲ ስትገባ ነበር። "የሰውን ሕይወት እንዴት ማቅለል ይቻላል? የሚለው ጥያቄ ሁሌም ያቃጭልብኛል። ሕልሜ ችግርን በቀላሉ መፍታት ነው" ትላለች። መሣሪያው ጥቅም ላይ ሊውል በሚችልበት መንገድ ማምረት አልጀመረችም። ሆኖም አገልግሎት እንደሚሰጥ ስለተረጋገጠ ለወደፊት እንደምትተገብረው ትናገራለች። ሰብለወንጌል እንደምትለው፤ እንጀራ 'ፕሮሰሰር' ጤፍ አቡክቶ፣ አብሲት ጨምሮ፣ ሊጡ ኩፍ ሲል ይጋግራል፤ እንጀራውን ከምጣድ ላይ አውጥቶም ያከማቻል። "እንጀራ አቡክቶ፣ ጋግሮ ለማውጣት የሚወስድበት ጊዜ እንጀራ በሰው ጉልበት ሲጋገር ከሚወስደው መደበኛ ሰዓት ጋር እኩል ነው። አንድ ሰው ሊጥ ቦክቶ መቼ እንደሚጋገር ወስኖ ማሽኑን 'ሴት አፕ' ማድረግ [ማስተካከል] ይችላል። ምን ያህል እንጀራ፣ በምን አይነት የውፍረት መጠን እንደሚጋገር አስቦ ማሽኑን ማስተካከልም ይቻላል።" ሌሎች የ2011 ፈጠራዎች ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባገኘነው መረጃ መሰረት ባለፈው ዓመት ከተመዘገቡ ፈጠራዎች መካከል በቆሎ የሚዘራ ማሽን እና በዶሮ ኩስ እና በተረፈ ምርቶች የሚሠራ ማብሰያ ይገኙበታል። የልብ ህመምን ለመከላከል የሚሆን ተጨማሪ ምግብ አዘገጃጀት ዘዬ እንዲሁም ቀላልና ጣፋጭ ምግቦች የሚሠሩበት መንገድ ዝርዝርም በፈጠራነት ተመዝግበዋል።
xlsum_amharic-train-178
https://www.bbc.com/amharic/news-47493185
በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም የተቀሰቀሰው ውዝግብ
የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ ተላልፎ መሰጠት ከፍተኛ ተቃውሞ የቀሰቀሰውን የአዲስ አበባና የኦሮሚያ የተቀናጀ ማስተር ፕላንን ማስቀጠል ነው የሚል ሀሳብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንፀባረቀ ሲሆን፤ ይህም ሁኔታ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞን አስነስቷል። በትናንትናው ዕለት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በዛሬው ዕለትም እንደቀጠለ ነው።
[ "የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ ተላልፎ መሰጠት ከፍተኛ ተቃውሞ የቀሰቀሰውን የአዲስ አበባና የኦሮሚያ የተቀናጀ ማስተር ፕላንን ማስቀጠል ነው የሚል ሀሳብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንፀባረቀ ሲሆን፤ ይህም ሁኔታ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞን አስነስቷል። በትናንትናው ዕለት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በዛሬው ዕለትም እንደቀጠለ ነው።" ]
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የተገነቡት በኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ፤ ለአርሶ አደሮችም በቂ ካሳ ሳይከፈል ነው የሚሉ ሃሳቦች እየተነሱ ነው። ከሻሸመኔ ቢቢሲ ያናገረው አንድ ተቃዋሚም ይህንኑ ሀሳብ ያጠናክራል። •የጋራ መኖርያ ቤቶቹ በዕጣ መተላለፋቸውን የኦሮሚያ ክልል ተቃወመ "ኮንደሚኒየሞቹ የተሰሩት ከአዲስ አበባ ዙሪያ ወጥቶ ነው። እንዴት ነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲህ አይነት ውሳኔ የሚያስተላልፈው?። ቤቶቹ በኦሮሚያ ክልል ስር ተመልሰው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ሊቋቋሙባቸው ይገባል" ይላል። ከሰሞኑ 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ የተላለፉ ሲሆን፤ ከአካካቢው ለተነሱ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ያለ እጣ እንዲሰጣቸው በከተማው አስተዳደር ካቢኔና በቤቶች አስተዳደር ውሳኔ መሰረት እንዲተላለፍ መወሰኑን ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ገልፀዋል። •ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኦሮሚያ ተቃውሞን ቀሰቀሱ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ሲገነቡ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ የተናገሩት ምክትል ከንቲባው "በተለይም የእርሻ መሬታቸውን ለነዚህ ተግባራት ሲሉ የለቀቁና ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ቀውስ የተዳረጉ የአርሶ አደር ቤተሰቦችና ልጆቻቸው ህመማችሁ የእኛም መሆኑን እንድታውቁ" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። ምክትል ከንቲባው ይህንን ቢሉም ውሳኔውን የተቃወሙት ብዙዎች ናቸው። በተለይም ለአመታት ተቸግረውና ካለቻቸው ቆጥበው ለከፈሉ ሰዎች እርምጃው ተቀባይነት ያለው አይመስልመ። አንድ ስሟ እንዲገለፅ ያልፈለገች የአዲስ አበባ ኗሪ "ከደመወዛችን ላይ የቤት ኪራይ ከፍለን፤ ቆጥበን እንግዲህ ያልፍልናል፤ ነገ የቤት ባለቤት እሆናለን በሚል ተስፋ ነው። በጣም ከፍተኛ ተስፋ ነበረኝ፤ ቤቶቹንም አይቻቸዋለሁ። አሁን ይሄንን ስሰማ ደግሞ የባሰ ነው የተበሳጨሁት፤ እኛ እየቆጠብን ሰው አመፅ ስላስነሳ ያለ ዕቅድ እንደዚህ መደረግ የለበትም።መንግስት የራሱን ነገር ማድረግ አለበት" ብላለች የኮንዶሚኒየሙ ለአዲስ አበባ ኗሪ መተላለፍ ፤ ኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትና ከ2006 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው ከሚሉት አንዱ ጃዋር መሀመድ ነው። የጋራ ቤቶቹ በዕጣ መተላለፍ ፍፁም ኢ ፍትሀዊ ነው ይላል። ቤቶቹ ከዚህ ቀደም የነበረው የማስተር ፕላኑ አካል እንደሆነ የሚናገረው ጃዋር፤ ማስተር ፕላኑ ከህግ ውጪ በመሆኑ እንዲቆም ከተደረገ በኋላ ይህንን ለመተግበር መንቀሳቀስ ትክክል እንዳልሆነና፤ የህዝቡም ተቃውሞ ምንጭ ይሄ መሆኑን ይናገራል። "አሁንም ቢሆን ፊንፊኔ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነች። ክልል አይደለችም። የሁለት ክልሎች ግጭትም አይደለም። ማንኛውም ከተማ ድንበር አለው።ለምሳሌ አዳማ ከተማ ድንበር አለው፤ ወለንጪት ሄዶ ቤት ሠርቶ ማስተላላፍ አይቻልም። አርሶ አደሮችን የማፈናቀል ሂደት ደግሞ ፊንፊኔን ከሌላ ክልል ጋር የማገናኘት የማስተር ፕላኑ እቅድ ነበር። ሕግን አፍርሶ የተገነባና አሁንም ሕግን አፍርሶ ለማስተላለፍ እየተደረገ ያለ ጥረት ነው።" ይላል። የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ድንበር ወሰንን ለማስመር ከዓመታት በፊት የተጀመረው ጥረት ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ ኮንዶሚኒየሞቹ ኦሮሚያ ክልል ናቸው በሚል እጣው እንዴት ይቆማል የሚል መከራከሪያ የሚያነሱም ጥቂት አይደሉም። •ሃምሳ በመቶ የሚኒስትሮች ሹመት ለሴቶች የሰብአዊ መብት አቀንቃኙና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በበኩሉ ተቃውሞው የጥቂቶች እንቅስቃሴ ነው ይላል። ትርጉም የሌለው ጥያቄም ነው ብሎ ያጣጥለዋል። ህዝቡን ለመከፋፈል እየተሰራ ያለ ሴራም ነው ብሎ ያምናል። "አሁን ይሄንን ግርግር እየፈጠሩ ያሉ ጥቂቶች ናቸው። እዚህ ላይ መሰመር ያለበት እነዚህ ጥቂቶች ምንን ነው የሚወክሉት? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። ፀረ ዲሞክራሲያዊ፤ ፀረ-አንድነት የሆኑ እንቅስቃሴዎች ናቸው። ሁላችንም የዲሞክራሲ ሃይሎችና ወዳጆች፣ የኢትዮጵያ አንድነት ወዳጆች አጥብቀን ልንታገለው ይገባል።" ይላል የእስክንድርን ሃሳብ የሚጋሩት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ መተላለፍ የለባቸውም የሚለው ተቃውሞ ትክክል አይደለም ሲሉ የግል አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። ፍትሃዊ አይደለም የሚሉበት ምክንያት ለአመታት ገንዘብ ሲያጠራቅሙ የነበሩና በጉጉት ሲጠብቅ የነበረን ህዝብ አይገባውም ማለት ኢዲሞክራሲያዊ ነው ብለው ማመናቸው ነው። "በአዲስ አበባ አካባቢ የተገነቡ ቤቶች በተለይ ደሃው ወይም መካከለኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ ለብዙ አመታት ገንዘብ እየቆጠበ፤ በገንዘቡ እየተሰሩ ያሉ አፓርትመንቶች ናቸው። በነፃ የሚታደል አፓርትመንት አይደለም። እነዚህ ግለሰቦች ለአመታት ጠብቀው፤ደረሰኝ ፤ አልደረሰኝ እያሉ በጉጉት በሚጠብቁበት ጊዜ ይሄ የእጣው ሂደት መቆም አለበት የሚለውን አስተያየት በጭራሽ አልተቀበልኩትም፤ ፍትሃዊም አይደለም።"ብለዋል
xlsum_amharic-train-179
https://www.bbc.com/amharic/news-50038627
የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል?
ሃኪም ገብረወልድ ማን ነው? ሆሊውድስ ምን ያደርጋል? ስለ ሃኪም ገብረወልድ ለማወቅ ከቀድሞው የኒውዮርክ ምክር ቤት አባል ጋር ካደረገው ጭውውት እስቲ እንጀምር።
[ "ሃኪም ገብረወልድ ማን ነው? ሆሊውድስ ምን ያደርጋል? ስለ ሃኪም ገብረወልድ ለማወቅ ከቀድሞው የኒውዮርክ ምክር ቤት አባል ጋር ካደረገው ጭውውት እስቲ እንጀምር።" ]
የቀድሞ የኒውዮርክ ምክር ቤት አባል የሆነው ጋሬት ኢትዮጵያዊውን ሃኪም ገብረወልድን የኡበር ታክሲ ሲያሽከረክር አግኝቶት መጀመሪያ የጠየቀው ''ይሄ መቼም ከፍተኛ ለውጥ ነው፤ ከኢትዮጵያ ወደ ኒውዮርክ መምጣት'' አለው። •"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ ሃኪም፡ አዎ ይሆናል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የማገኘውን ገንዘብ ያህል አላገኝም፤ ግን ይሁን እስቲ። ጋሬት፡ ቆይ፣ ቆይ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ነበር የምትሰራው? ሃኪም፡ የልብ ቀዶ ህክምና ሐኪም ነበርኩ፤ እናም ዲቪ ሎተሪ አሸንፌ ነው አሜሪካ የመምጣት እድል ያገኘሁት። ጋሬት፡ ዶክተር ከሆንክ ታዲያ ለምን ታክሲ ትነዳለህ? ሃኪም፡ ያው ፈቃድ ማግኘት አልቻልኩም፤ እንግዲህ ወረቀቴን ሳገኝ ይረዳኝ ይሆናል። ቢሆንም ያው ዓመታት መውሰዱ አይቀርም፤ ጋሬት፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ጥሩ ህይወት ነበረህ። ለምን ወደዚህ መጣህ? ሃኪም፡ ምክንያቱም አሜሪካ ከሁሉም የበለጠች ስለሆነች፤ ሁሉ ነገር የሚቻልባት ስለሆነ፤ ሃኪም፡ ይሄን ያህል ምንድነው ያው ታክሲ ብነዳም፣ ፎርም ብሞላም ጄትስኪየን (በውሃ ላይ የሚነዳ ሞተር) ትቼ ብመጣም ፤ ምንም ማለት አይደለም። አሜሪካን በጣም እወዳታለሁ፤ የዚህችም አገር አካል መሆን እፈልጋለሁ። ጋሬት፡ [በመደነቅ] እንዴ ጄትስኪ አለህ? እኔም እኮ አለኝ። ይህ በቅርቡ በአሜሪካ ቴሌቪዥን ጣቢያ ኤንቢሲ ለዕይታ ከበቃው ሰኒ ሳይድ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም ውስጥ ዋነኛ ገፀባህርይ የሆነው ሃኪም ገብረወልድና የቀድሞው የኒውዮርክ የምክር ቤት አባል ጋሬት ሞዲ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ ነው። ኒውዮርክ ውስጥ መቼቱን ያደረገው ይህ ፊልም በስደተኞች ህይወት ላይ ያጠነጠነ ሲሆን አንደኛው ዋና ገፀባህርይ ኢትዮጵያዊው ሃኪም ገብረወልድ ነው። ሃኪም ገብረወልድ የተሳለበት መንገድ እስከዛሬ በሆሊውድ ውስጥ ከተሰሩና ኢትዮጵያን ከረሃብና ከችግር ጋር ከሚያይዙ ፊልሞች ለየት እንደሚል በፊልሙ ዘርፍ ካሉ አስተያየት ሰጪዎች እየተሰማ ነው። በፖለቲካው ዓለም ዝናው እየገነነ የነበረው ጋሬት አሳፋሪ ሥራ በመስራቱ ከምክር ቤት አባልነቱ ይባረራል። ለህይወቱም ትርጉም ሲፈልግ የአሜሪካ ዜግነታቸውን ለማግኘት የአሜሪካን ፖለቲካ ከስር መስረቱና ህገ መንግሥት የሚያጠኑ ስደተኞች ያገኛል። ከስደተኞቹም አንዱ የህክምና ሙያውን፣ ቅንጡ መኪናውንና ቤቱን ጥሎ አሜሪካ የተሰደደው ሃኪም ገብረወልድ ነው። ምንም እንኳን ሃኪም ገብረወልድ የቴሌቪዥን ገፀ ባህርይ ቢሆን ሥራቸውን፣ ቤታቸውን ትተው አሜሪካ ወይም አውሮፓ የከተሙ ዶክተሮች፣ መምህራን፣ ጋዜጠኞችን ቤቱ ይቁጠረው። በዚህ ፊልም ላይ ስደተኛውን ዶክተር ወክሎ የሚጫወተው የሞሪሽየስ ዜግነት ያለው ሳምባ ሹት ነው። ሳምባ ሞሪሽየስ ቢወለድም ከሁለት ዓመቱ ጀምሮ አስራ ስምንት ዓመት እስኪሆነው ድረስ ያደገው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፤ የተማረውም እንዲሁ። •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም በዚህ ፊልም ላይ ሆሊውድ አፍሪካ ከምትሳልበት የርስ በርስ ጦርነት፣ እልቂት፣ ችግር፣ ሰቆቃ ከተሞላበት የታሪክ ንግርት ወጥተው የተማሩ ስደተኞችም ይመጣሉ፤ ስደተኞችም ሕይወት አላቸው፤ የሚለውን በቀልድ መልኩ እያዋዛ ይነግራል። የአሜሪካ ህልምንም በተለይም ለስደተኞች ምን ማለት እንደሆነ በነገር ሸንቆጥ በማድረግ ይነግራል። ምንም እንኳን ከአሜሪካም ሆነ ከአውሮፓ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎች ስደተኞች የኢኮኖሚ ዋልታ መሆናቸውን ቢያሳይም ከሚከፈላቸው ዝቅተኛ ገንዘብ አንስቶ እስከ ስደተኞች ወደ ሃገራቸው ይመለሱ የሚሉ ጉዳዮች የብዙ ሃገራት ፖለቲከኞች የፖሊሲ ክርክሮችን የሚያስነሳ ነው። ለዚያም ነው ሃኪም ገብረወልድ ረዘም ያለ ጭውውት ከተጨዋወተውና የታክሲ አገልግሎት ከሰጠው ግለሰብ፤ 'አመሰግናለሁ' ብሎ ሊወርድ ሲል ይህንን የሚለው "አሜሪካ ታላቅ እንዲሁም ሌላ ሌላ ብትሆንም ዋናው ነገር ለሰሩበት ስትከፍላቸው ነው" የሚለው። •"የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ የስደተኞችን ህይወት የተወሰሳበ መልኩን በማሳየት፤ ገፀ ባህርዮቹ ህይወት እንዲኖራቸው፤ ባህል፣ አለባበስ፣ ፍቅርና ሌሎች መስተጋብሮችንም ማሳየትም እንደቻለ የፊልም ልሂቃን እየመሰከሩለት ነው። ታዋቂዋ ፀሀፊ ኤድዊጅ ዳንቲካት ሁሉም ስደተኛ አርቲስት (ጥበበኛ) ነው ትላለች። ለዚህም የምታጣቅሰው ስደተኞች ከተፈናቀሉበት አገር መጥተው ህይወታቸውን ከዜሮ ለመጀመር ሳይፈሩ፤ ራሳቸውን ትልቅ ቦታ ላይ አድርሰው፤ ልጆቻቸውን ለትልቅ ቦታ በማብቃት ህይወትን ይመሰርታሉ። ሃኪም ገብረወልድም ታዋቂ ዶክተር ቢሆንም እሱን ወደ ጎን በመተው ታክሲ እያሽከረከረ የህክምና ፈቃዱን ሲያገኝ ዶክተር እንደሚሆን ያስባል። በሃኪም ገብረወልድ ታክሲ ውስጥ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አለ። አገሩም ሆነ የህክምና ሙያው በጣም የሚናፍቀው ይመስላል። በስሜትም ስለ ህክምና ሂደት ለማያቀው ሰው ያወራል። ለዚያም ነው ጋሬት ስለ ሃኪም ገብረወልድ ሲያወራ ይህንን ያለው፡ "ሃኪም ገብረወልድ ኢትዮጵያ ውስጥ እኮ ዶክተር ነበር፤ አንድ ጊዜ እንዳውም መንገድ ላይ በመኪና የተገጨች አይጥ አግኝቶ ደረቷን በመጫን እርዳታ ሲሰጣት ዳነች" በማለትም በግነት ለሙያው ስላለው ፍቅር ምስክርነት የሚሰጠው። ስደተኛ ጓደኞቹ ባያውቋቸውም የኢትዮጵያን ከተሞች ይጠራል፤ የመቀሌንና አለታ ወንዶን ቤት ኪራይ በማወዳደር ይናገራል። በአብዛኛው የሆሊውድ ፊልሞች ላይ የሚሳሉት አፍሪካዊያን ምንም የማያውቁ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የሚናገሩት ቃላቶች የተመጠኑ፤ ማንነት የሌላቸው፣ በችግርና እጦት የተደቆሱ፣ እምነትም ሆነ የራሳቸው የዓለም ዕይታ የሌላቸው ተደርገው ነው። ለፊልሙ ማጣፈጫ (ፕሮብስ) ከመሆን በስተቀር ሌላ አላማንም ሲያሟሉና በአብዛኛው ሲያሳኩ አይታይም። በዚህ ፊልም ለየት ባለ መልኩ ስለ ኢትዮጵያ የሚያውቅ ገፀባህርይ ተካቶበታል። ሃኪም ገብረወልድ መልካም ስብዕና ያለው፤ አዋቂ እንዲሁም የቡድናቸው ማዕከልም እንዲሆን ተደርጎ ገፀባህርዩ ቢሳልም አንዳንድ ጊዜም የ"መሽቁቅነት" ባሕርይ ያሳያል። እህትህን ወደ አሜሪካ ለማምጣት እረዳሃለሁ ብሎ ያጭበረበረውን ግለሰብ "በአገራችን 'ይቅርታን የሚሰብክ ክፉ ነህ' የሚል ፅንሰ ሃሳብ አለ፤ ዓለማችንም መልካም የምትሆነው ይቅርታ ስናደርግ ነው። እናም ይቅርታ አድርጌልሃለሁ" ይለዋል ግለሰቡ ክፉ ነህ እያለም አልመሰለውም፤ ይቅርታ ያደረገለት መስሎት ነበር። ሳምባ ይህንንም በማለት ከሸወደው በኋላም ድምፁን በመቅዳት ገንዘቡን ያስመልሳል። በአስራ ስምንት ዓመቱ ወደ አሜሪካ የሄደው ሳምባ ቲያትር ለማጥናት ሲሆን፤ የፊልሙ ታሪክ ከእርሱ ጋር እንደሚመሳሳል በተለያየ ጊዜ ባደረጋቸው ቃለ መጠይቆች ተናግሯል። "ታሪኩ ከእኔ ታሪክ ጋር ይመሳሰላል፤ ከስምንት ዓመት በፊት አሜሪካ ስመጣ፤ ህልሜንም ለማሳካት መስዋዕትነት ከፍያለሁ፤ በአሜሪካ የቴሌቪዥን ጣብያም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ኢትዮጵያዊ ገፀ ባህርይ በፊልም (ሲት ኮም) ላይ ሲታይ። ለእኔ ትልቅ ቦታ ያላትን ሃገርና ባህል መወከሌም ትልቅ ኩራት ይሰማኛል" ብሏል። ኢትዮጵያ፣ አፍሪካ በሆሊውድ ፊልሞች አፍሪካ ላይ ያጠነጠኑ የሆሊውድ ፊልሞችን ብናይ አንደኛ አፍሪካ መንደር ተደርጋ የምትሳልበት፤ ረሃብ፣ ችግር፣ ጦርነትና እርስ በርስ መጨፋጨፊያ ጨለማ ቦታ ተደርጋ ነው የምትሳለው፤ የኢትዮጵያም ከዚህ የተለየ አይደለም። በአፍሪካ ላይ የሚያጠነጥኑ አንዳንድ ፊልሞችን ወደኋላ ሄደት ብለን ለምሳሌ "queen of the jungle" ብናነሳ ትንቢት የተነገረላትና ወርቃማ ፀጉር ያላት አንዲት ነጭ አፍሪካን ስታድን የሚያሳይ ነው። የምዕራቡ ዓለም ከአንድ ቢሊዮን ህዝቦች በላይ የሚኖሩባትን አህጉር በተለይም በፀሀፊያን ዘንድ የምትመሰልበትን መንገድ ሽሙጣዊ በሆነ መልኩ በፃፈበት "ሃው ቱ ራይት አባውት አፍሪካ'' (ስለ አፍሪካ እንዴት መፃፍ እንችላለን) በሚለው ፅሁፉ ቢንያቫንጋ ዋይናይና፡ "የመፅሃፋችሁን ሽፋን በየቀኑ የምናገኛቸውን አፍሪካዊያንን ፎቶ ሳይሆን ኤኬ 47 ጠመንጃን የተሸከመ፤ የሽምቅ ውጊያ፣ የተራቆቱ ጡቶች፤ የገጠጡ አጥንቶችን አድርጉ" በማለት ምዕራባዊያን ስለአፍሪካ ሲፅፉ በተደጋጋሚ የሚያወጧቸውን ፎቶዎች በማየት በነገር ሸንቆጥ አድርጓቸዋል። በረሃብ፣ በችግር፣ በጦርነት፣ በእርስ በርስ ግጭት ብቻ በተሞላችው በሆሊውዷ አፍሪካ ላይ ይህንን ሲቀርፉ የሚታዩትና ሲያድኑ የሚታዩትም ነጭ ሰዎች ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ ብዙዎች የሚጠቅሷቸው "ብለድ ዳይመንድ" ዘረኛ ነጭን ወክሎ የሚጫወተው ቅጥረኛው ነፍሰ ገዳይ ሊዮናርድ ዲካፕሪዮ ጥቁሩን ሴራሊዮናዊና ልጁን ከጥቁር ነፍሰ ገዳዮች ሲያድንም ይታያል። የፊልም ልሂቃን ቆጥረው ከማይዘልቋቸው መካከልም አምስቴድ፣ ቲርስ ኦፍ ዘ ሰን፣ ክራይ ፍሪደምና ሌሎችም ይገኙበታል። ኢትዮጵያን ማዕከል አድርገው የተሰሩ ጥቂት የሆሊውድ ፊልሞችን ብናይ ከረሃብና ከድርቅ ጋር የተገናኘ ነው። ከነዚህም ውስጥ 'ቢዮንድ ቦርደርስ' እንዲሁም ታዋቂው ተከታታይ የካርቱን ፊልም 'ሳውዝ ፓርክ' ውስጥ አንደኛውን ክፍል 'ስታርቪንግ ማርቪን (የተራበው ማርቪንን) ማስታወስ ይቻላል። በዚህ ፊልም ላይ ረሃብን በቴሌቪዥን ሲከታተሉ የነበሩ ታዳጊዎች ታይኮ የስፖርት ሰዓት ሽልማት እናገኛለን በሚል ገንዘብ ቢረዱም በስህተት የተራበ ኢትዮጵያዊ ልጅ ይላክላቸዋል። የገረጣ፣ የከሰለ ልጁንም በየተራ ለማሳደግ ይወስናሉ። ስሙንም ስታርቪን ማርቪን ብለው ይሰይሙታል፤ ትምህርት ቤትም ይወስዱታል። በኋላም ስህተት መሰራቱ ይታወቅና እንደ እቃ አፍሪካ ለመላክ ይወስናሉ። በቅርቡ ኔትፍሊክስ ላይ ለዕይታ የበቃው 'ዘ ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት' ኢትዮጵያዊያንን አለማሳተፉ፣ አማርኛ እየተኮላተፉ የሚያወሩበት እንዲሁም የታሪክ ግድፈቶች አሉበት በሚልና የነጭ አዳኝነት (ዋይት ሴቪየር)ን በማቀንቀን ትችቶች ቀርበውበታል። በዚህም ፊልም ላይ ነጮች ኢትዮጵያዊያንን ማዳን ብቻ ሳይሆን ሱዳን ውስጥ ያለን አንድ ማህበረሰብ የሰው ስጋ እንደሚበሉ የሚነገርበት፤ የፀጥታ ኃይሉ ምንም ርህራሄ የሌለውና (ያልተፈጠረ ታሪክ በመጨመር) ሱዳናዊያን ኢትዮጵያዊያንን ሲጨፈጭፉ የሚያሳየው ዝም ብሎ የሚወሰድ ሳይሆን ለዘመናት የተካኑበት የታሪክ አነጋገር ዘያቸው እንደሆነ ተችዎች ፅፈዋል። የባርነትን ታሪክ እንደገና ከመፃፍ ጀምሮ፣ ቀደምት አሜሪካዊያንን ሰው በላ አድርጎ መሳል፣ አፍሪካዊያንን ነፃ በማውጣትና በመርዳት ነጮችን የአዳኝነት ታሪክ ስፍራ ሆሊውድ እንደፈጠራላቸው ተችዎች ይተነትናሉ። ጥቁርም ሆኑ ግሎባል ሳውዝ (ከነጩ ዓለም ውጪ) ታሪክን እንነግራለን የሚሉ ፊልም ሰሪዎችም ዋነኛ ፈተናቸው በተለይም ከበጀት ጋር ተያይዞ፤ የታሪኩን ማዕከል ወይም ዋነኛ ገፀ ባህርዩን ነጮችን (የነጮችን አዳኝነት) ታሪክ እንዲያስገቡ መገደዳቸው እንደሆነ ይናገራሉ። በዚህም ኃይሌ ገሪማ አድዋን ለመስራት ከፍተኛ በጀት ጠይቀው በነበረበትም ወቅት የሚኒልክን አማካሪ ነጭ ሰው እንዲያደርግ መጠየቁ እንደ ምሳሌ የሚነሳ ነው። "የእኔ እናት ወይም አያት በፊልሞች ላይ እንድትኖር ለማድረግ አንድ ነጭ ሰው ሊኖር ይገባል" በማለትም በአንድ ወቅት ተናግረዋል። ምዕራባዊያን ወይም ነጭ የፊልም ጸሀፊዎችና አዘጋጆች ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካን ታሪክ የሚያዩት በራሳቸው መነጽር (ዋይት ጌዝ) ነው ተብለው ይተቻሉ። የአፍሪካዊያን ታሪክ በነጮች ሲፃፍ ወይም ሲዘጋጅ ባህሉን ካለማወቅ በደንብ መንገር አይችሉም ይባላል። በአንድ ወቅትም የድፍረት ዳይሬክተር ዘረሰናይ መሐሪ ለቢቢሲ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ይህንን ብሏል ''ለምሳሌ የማልረሳውና ያስደነገጠኝ ትልቅ ነገር አለ። "ድፍረት" ሰን ዳንስ እንዳሸነፈ ስርጭት እየተስማማን እያለ አንድ ጣልያናዊት አሰራጭ በጣም ፊልሙን ስለወደደችው ተደራደረች። ፊልሙን በዓለም ለማሳየትም የ "ወርልድ ዋይድ ራይትስ'' መብቱንም መውሰድ ፈለገች። ድርጅቷ ያለው ጣልያን ቢሆንም ጣልያን ሀገር ማሳየት አልፈለገችም። ለምን? ስላት፣ ፊልሙ ውስጥ ምንም ነጭ ገፀባህርይ ስለሌለ ፊልሙን ጣልያን ሀገር ለማሳየትና ለመሸጥ በጣም ይከብዳል አለች። ያላቸው አስተሳሰብ ወይም አንድን ነገር ለመገንዘብ እነሱን የሚመስል ሰው እዚያ ውስጥ መኖር አለበት የሚለው ነገር ነው። በጣም አስደነገጠኝ። ከዚያ በተጨማሪ ጃፓን ሀገር "ድፍረት" በየቴአትር ቤቱ ለማሳየት የስርጭቱን መብት ከወሰዱ በኋላ ፖስተሩን መቀየር ፈለጉ። ፖስተሩ ላይ የ13 ዓመት ኢትዮጵያዊት ታዳጊ ነው ያለችው። ተመልካች እሱን ካየ አያይልንም ብለው የአንጀሊና ጆሊን ፎቶ እናድርግበት ወይ? ብለው ጠይቀውናል''ብሏል። አፍሪካ ጦርነት፣ ረሃብ፣ ችግር ብቻ ሳይሆን፤ ከሃምሳ በላይ አገራት፣ ከ2000 በላይ ቋንቋዎች፤ ባህል፣ ጥበብ፣ ታሪክ ያላት በመሆኑ የራስን ታሪክ ራስ መንገር በሚልም ብዙ እንቅስቃሴዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ አፍሪካዊያንና ከነጩ ዓለም ውጭ ያለውን የደቡቡ ዓለም (ግሎባል ሳውዝ)ን ታሪክ በሲኒማ ለመንገር ያጠነጠነው ሰርድ ሲኒማን መጥቀስ ይቻላል። ገና ሁለት ክፍል በወጣው በዚህ ፊልም ላይ ኢትዮጵያን በትንሽ ለማየት ያስቻለ ሲሆን በሚቀጥሉትም ክፍሎች በዋነኛው ገፀ ባህርይ ሳምባ በኩል ስለኢትዮጵያን ብዙ ልናይ እንችላለን። ሳምባ ሹት ከዚህ ቀደምም በኔት ፍሊክስ የወጣው ታይገር ሃንተር፤ እንዲሁም ታዋቂውን የቪዲዮ ጌም ባትል ፊልድ ፅፏል። ከፊልሞችም በተጨማሪ ሽልማትን በተንበሸበሹ የቪዲዮ ጌሞች ላይ 'ስታር ዋርስ ጄዲ፡ ፎለን ኦርደር'፤ ኮል ኦፍ ዲዩቲ፡ ብላክ ኦብስ ተውኗል።
xlsum_amharic-train-180
https://www.bbc.com/amharic/news-48876042
በደቡብ ወሎ 'የህፃናት ስርቆት' ስጋት መነሻ ምንድን ነው?
ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን፣ ለጋምቦ ወረዳ 'ህፃናት አፍነው ሊወስዱ ነው' በሚል አምስት ግለሰቦች በአካባቢው ነዋሪዎች በደቦ መገደላቸው ይታወሳል። ይህ ግለሰቦችን በደቦ እስከመግደል የሚያደርስ የህፃናት ስርቆት ስጋት መነሻው ምንድን ነው?
[ "ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን፣ ለጋምቦ ወረዳ 'ህፃናት አፍነው ሊወስዱ ነው' በሚል አምስት ግለሰቦች በአካባቢው ነዋሪዎች በደቦ መገደላቸው ይታወሳል። ይህ ግለሰቦችን በደቦ እስከመግደል የሚያደርስ የህፃናት ስርቆት ስጋት መነሻው ምንድን ነው?" ]
• አምስት ሰዎች ደቡብ ወሎ ውስጥ በደቦ ጥቃት ተገደሉ የደሴ ከተማና የለጋምቦ ወረዳ ነዋሪዎች በተለይ ካለፉት ሁለት ወራት አንስቶ 'ልጆቻችን ይሰረቁብናል' በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደወደቁ ይናገራሉ። ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ልጆቻቸው ለጨዋታም ቢሆን ለአፍታ ከዓይናቸው ሥር ሲሰወሩ ወዲያው ወደ አዕምሯቸው የሚመጣው መሰረቃቸው እንደሆነ ነው የሚገልፁት። ለጋምቦ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አንዲት ወላጅ "ልጆችን መቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም ከወትሮው በተለየ ከዓይናችን ሥር እንዳይጠፉ ክትትል ለማድረግ ተገደናል" ሲሉ ስጋታቸውን ያካፍላሉ። የደሴ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ አባት ደግሞ ልጆቹ ከሚማሩበት ትምህርት ቤትም 'ልጆቻችሁን በጊዜ ከትምህርት ቤት ውሰዱ፤ በእረፍት ጊዜያቸው ሲጫወቱም ክትትል አድርጉላቸው' የሚል ማስታወሻ እንደሚላክላቸው ነው የሚናገሩት። ነዋሪዎቹ በተለይ በየአካባቢው የሚናፈሰው የህፃናት ስርቆት ወሬ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ገልፀውልናል። ስጋቱ እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ጊዜውን በውል ባያስታውሱትም ከአንድ ወር በፊት የሆነ ነው። የደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ ላይ አንዲት እናት ልጇን ለማሳከም ወደ ጤና ተቋም ታመራለች። እዚያም ከአንዲት ነጭ ገዋን ከለበሰች ሴት ጋር ይገናኛሉ። ሴትዮዋም 'ልጅሽ በጣም ታማለች ለተሻለ ህክምና ደሴ መሄድ አለባት' ትላታለች - የህክምና ባለሙያ በመምሰል። እናትም የህክምና ባለሙያ ከመሰለቻት ሴት ጋር ህጻኗን ይዘው ወደ ደሴ ያመራሉ። በሁኔታው የተደናገጠችው እናት ለባለቤቷ እንኳን ስልክ ለመደወል ፋታ አላገኘችም ነበር። ወደ ደሴ ጉዞ ከጀመሩ በኋላ ደውላ ገንዘብ ይዞ እንዲከተላት ለባለቤቷ መልዕክት አስተላለፈች። ከዚያም ደሴ ከተማ 'ምስጋናው' የተባለ የግል ክሊኒክ ይዘዋት ይገባሉ። በመሃል 'ባልሽን ተቀበይ እኔ ልጅሽን እይዛለሁ' ትላታለች። ሴትዮዋ የህክምና ባለሙያ ናት ብላ እምነት ለጣለችባት ሴት ልጇን ትታ ዞር ስትል ነበር ሴትዮዋ የተሰወረችው። ከዚያም ለደሴ ከተማ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት ተደርጎ ክትትል ይጀመራል። በአጋጣሚ ተጠርጣሪዋ ተቀምጣበት የነበረው ወንበር ላይ ትንሽ ቦርሳ ያገኛሉ። ቦርሳውን ሲከፍቱት ግን የተፋቀ የሞባይል ካርድ እንጅ ሌላ ቁስ የለውም። ካርዱ በማን ስልክ እንደተሞላ በማጣራትና ከአጎራባች ከተሞች ፖሊስ ጋር በመነጋገር ኬላዎች እንዲዘጉና ፍተሻ እንዲደረግ ተደረገ። በመጨረሻም 'ነጭ ገዋን ለባሿ ሴት' አፋር ክልል አዋሽ አርባ ኬላ ላይ በቁጥጥር ሥር ዋለች። ህጻኗም በማግስቱ በሰላም ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀላቀለች። ድርጊቱን አቀነባብራለች ተብላ የተጠረጠረችው ሴት እና አሽከርካሪውን ጨምሮ ሦስት ወንዶች በቁጥጥር ሥር ውለው በደሴ ማረሚያ ቤት ይገኛሉ። ይህንን ልብ-ወለድ የመሰለ እውነተኛ ታሪክ ያጫወቱን የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደረጀ አሰፋ፤ ከዚህ ቀደም በደሴ ከተማ ከሚገኝ 'አሊፍ' ከተባለ የግል ትምህርት ቤት ሁለት ዕድሜያቸው ሰባት ዓመት ገደማ የሆኑ ህጻናት ጠፍተው በክትትል ከከተማ ወጣ በሚል ቦታ መገኘታቸውን ያነሳሉ። በጉዳዩ የተጠረጠሩት ግለሰቦችም ተመሳሳይ ሆነው ተገኝተዋል። ተጠርጣሪዋ "ባለቤቴ ወደ ውጭ አገር ሲሄድ ነፍሰ-ጡር ነኝ ብየው ስለነበር፤ ያን የዋሸሁትን ነገር ለመሸፈን ብየ ነው ያደረግኩት" የሚል መልስ እንደሰጠች ኮማንደሩ ያክላሉ። እውነተኛ ምክንያቱን ለማጣራትም ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ነው የሚያስረዱን። ይህ ክስተት ከተፈጠረ አንስቶ በከተማውና በተለያዩ ወረዳዎች ወሬው በስፋት መራገብ ጀመረ። ሕብረተሰቡም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወደቀ። • 360 ብር ለአንድ ሕጻን • "በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ተወካይ ግን ከሐይቅ ከተማው ስርቆት ሌላ ሕፃን ጠፋብኝ ብሎ ሪፖርት ያደረገ ሰው እንደሌለ ይገልፃሉ። የተናፈሰው ወሬ ምን አስከተለ? በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ ህፃናትን አፍነው ለመውሰድ የመጡ ሰዎች ናቸው በሚል አምስት ሰዎች በደቦ ጥቃት መገደላቸውን፤ የሰማነው ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር። ግለሰቦቹ በአንድ የአካባቢው ነዋሪ ቤት አርፈው ነበር፤ ካረፉበት ቤት ወጣ ብለው በአካባቢው እየተንቀሳቀሱ ሳለ ነው በሕብረተሰቡ በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸው ያለፈው። የወረዳው አስተዳዳርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ከበደ ይማም አምስቱ ግለሰቦች በተገደሉበት ሥፍራ ወደ 300 ሰዎች ገደማ እንደነበሩና ፖሊሶች ሁኔታውን መቆጣጠር ስላልቻሉ መሸሻቸውንም ነግረውናል። ኃላፊው አክለውም በወረዳው ከዚህ ቀደም ሕፃን ስለመሰረቁ የደረሳቸው ሪፖርት እንደሌለና በስጋት ተነሳስተው ድርጊቱን እንደፈፀሙት ነው የሚያስረዱት። ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉ 8 ተጠርጣሪዎችም የተለዩ ሲሆን አምስቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ የፀጥታ ኃላፊው ነግረውናል። የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ተወካይ ኮማንደር ለማ ተስፋየ በለጋምቦ ወረዳ የደቦ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላ በቦረና ወረዳም 'ህፃን ሊሰርቅ ነው' በሚል አንድ ግለሰብ ታግቶ እንደነበር ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ በግለሰቡ ላይ ምንም ጥቃት ሳይደርስ በፖሊስ ክትትል ሊለቀቅ እንደቻለ ይገልፃሉ። • "ደላላው ወደ ቤቱ ወሰደኝ፤ በዚያው ቀን አስገድዶ ደፈረኝ" 'በሕብረተሰቡ ክፍተኛ ስጋት የፈጠረ አሉቧልታ አለ' የሚሉት ኮማንደር ደረጀ በከተማው ጢጣ በሚባል አካባቢ አንድ ጥቆማ ደርሶ በጅምላ አንድን ግለሰብ ለመግደል ተሞክሮ በከፍተኛ ጥረት ሊተርፍ ችሏል ብለዋል። እንዲሁም በደሴ ከተማ አራዳ አካባቢ ሌላ ግለሰብ በህብረተሰቡ ድብደባ ደርሶባታል። ይሁን እንጂ ኮማንደሩ እንዳሉት የፖሊስ ምርመራ ውጤቱ ጉዳዩ ከህፃናት ስርቆት ጋር እንደማይገናኝ ያሳያል። "በደሴ፤ በጢጣ እና በአራዳ የሆነው ከህፃናት ስርቆት ጋር ባይገናኝም፤ እንዲህ ዓይነት ወንጀሎች የሉም ማለት ግን አይደለም" የኮማንደር ደረጀ አስተያየት ነው። በለጋምቦ ወረዳ በደቦ የተገደሉት ግለሰቦች እነማን ናቸው? አምስቱ ግለሰቦች ከአዲስ አበባ፣ ከከሚሴ፣ ከሳይንትና ከደሴ የመጡ ሲሆን፤ አንደኛው ግለሰብ ከየት አካባቢ እንደመጣ አለመታወቁን የለጋምቦ ወረዳ አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ከበደ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ወደ አካባቢው ያመሩት በቁጥር ስድስት መሆናቸውን የሚገልፁት ኃላፊው እስካሁን አንደኛው ማምለጡንና እየተፈለገ መሆኑን አክለዋል። ግለሰቦቹ ወደ አካባቢው 'ዘመድ ለመጠየቅ' እንዳቀኑ መግለፃቸውን፤ አሁን ግን ወንጀል ለመፈፀም በአካባቢው የተሰማሩ ሰዎች እንደነበሩ አንዳንድ ማስረጃዎች እየወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል- አቶ ከበደ። ምን ዓይነት ወንጀል? ለምን ዓላማ? የሚለውን ፖሊስ እያጣራ ነው ብለዋል። ለጊዜው አሳርፏቸው የነበረው ግለሰብም በወቅቱ ድብደባ ስለደረሰበት በሕክምና ላይ እንደሚገኝ ገልፀው የተገደሉት ግለሰቦች መታወቂያቸው ላይ ባለው መረጃ መሰረት አስክሬናቸው ወደ የቤተሰቦቻቸው መላኩንና የአራቱ ሥርዓተ-ቀብር መፈጸሙን ሰምተናል። የአንደኛው ግለሰብ መታወቂያ ላይ ያለው አድራሻ ግን ሀሰተኛ በመሆኑና ቤተሰብ ጋር ማገናኘት ባለመቻሉ ሥርዓተ ቀብራቸው በወረዳው መፈፀሙን አቶ ከበደ ነግረውናል። ምን እየተሰራ ነው? ሕብረተሰቡ ልጆቹን የመከታተልና፣ የማስተማር፣ አካባቢውን የመጠበቅ፣ ልጆችን የሚያታልሉ እንኳን ቢኖሩ ልጆች በጨዋታ ቦታ፣ መንገድ ላይም ሆነ በትምህርት ቤት እንዳይታለሉ ማስተማርና ክትትል ማድረግ እንዳለበት ኮማንደር ደረጀ ያሳስባሉ። "ከሌላ ቦታ ለሌላ ጉዳይ የሚመጣንና የሚንቀሳቀስን ሰው፤ 'ህጻናት ሊያፍኑ ነው' በማለት በተሳሳተ ስጋት አላስፈላጊ ጉዳት ከማድረስ መቆጠብ አለበት፤ ከተጠራጠረም ለህግ መጠቆም አለበት" የኮማንደሩ መልዕክት ነው። የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ተወካይም "ማንኛውም ሰው ህፃን ሊሰርቅ እንደማይመጣ፤ የሚሞክርም ቢኖር ተባብረው ለህግ ማቅረብ እንዳለባቸው ከህዝቡ ጋር ውይይት እየተካሄደ እንደሆነና ህብረተሰቡም 'ድርጊቱን እንዳወገዘው' ያስረዳሉ።
xlsum_amharic-train-181
https://www.bbc.com/amharic/news-52913209
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የመስፋፋት ስጋት ያጠላበት የኢትዮ-ሱዳን ድንበር
የምዕራብ ጎንደር ዞን ሦስት ወረዳዎች 17 ቀበሌዎችና አንድ ከተማ አስተዳደር ከሱዳን ጋር የሚዋሰኑ ሲሆን በየዕለቱም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድንበሩን በማቋረጥ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ። በዚህ ምክንያትም አካባቢው ከኮሮና መስፋፋት ጋር በተያያዘ የስጋት ቀጠና ሆኗል።
[ "የምዕራብ ጎንደር ዞን ሦስት ወረዳዎች 17 ቀበሌዎችና አንድ ከተማ አስተዳደር ከሱዳን ጋር የሚዋሰኑ ሲሆን በየዕለቱም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድንበሩን በማቋረጥ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ። በዚህ ምክንያትም አካባቢው ከኮሮና መስፋፋት ጋር በተያያዘ የስጋት ቀጠና ሆኗል።" ]
እንደአማራ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሆነ ማክሰኞ (ግንቦት 25/2012) በክልሉ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተገለጹት ሰባት ሰዎች በሙሉ ከዚሁ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ነው። ኢንስቲትዩቱ እንዳለው ከሆነ ግለሰቦቹ ከ25 እስከ 53 ዓመት የሆናቸው ወንዶች ናቸው። በአማራ ክልል እስከ ማክሰኞ ድረስ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 83 ሰዎች መካከል 62ቱ በዚሁ ዞን የሚገኙ ናቸው። ወደ አካባቢው ከሚገባው ሰው አንጻር የተለያዩ ችግሮች እየተከሰቱ ነው። በአካባቢው በለይቶ ማቆያ ማዕከል እጥረት እየተሰቃየን ነው ያሉት የመተማ ወረዳ የጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በቃሉ እውነቱ ናቸው። • ደቡብ ሱዳን በግዛቷ ግብጽ የጦር ሰፈር እንድታቋቁም ፈቅዳለች? • በምዕራብ ትግራይ በመሬት ካሳ ጉዳይ ለተቃውሞ የወጡ '45 ሰዎች ታሰሩ' • "በጣም እርግጠኛ ሆነን ያወጣነው ሪፖርት ነው" አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደ አቶ በቃሉ ከሆነ ኮኪት ለይቶ ማቆያ ማዕከል ላይ ስፍራ በመጥፋቱ ብዙ ሰው ማስገባታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህንንም ሲያብራሩ "የኮኪት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መጀመሪያ ጥናት ተደርጎበት ስንሠራ ለ80 ሰዎች ብቻ ነው የሚሆነው ብንልም ስላልቻልን 400 ሰዎችን አስገባን። መጀመሪያ ቀን 2 ሰዎች ፖዘቲቭ ሆኑ [ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል]፤ በሚቀጥለው ጊዜ 8 ሰዎች [ቫይረሱ] ተገኝቶባቸዋል። ይህ ደግሞ መጨመሩ አይቀርም" ብለዋል። በአካባቢው ከሱዳን ከ200 እስከ 300 የሚሆኑ ሰዎች በየዕለቱ ይገባሉ። "በመተማ ዮሃንስ ብቻ ኳራንቲን ከተጀመረ በኋላ ከ1300 የሚበልጡ ሰዎች ሙቀት ለክተን መርምረን ወደ መኖሪያቸው ልከናል" ሲሉ ገልጸዋል። ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ በሚረዝመው የኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ህጋዊ እና ህገ ወጥ በሆነ መንገድ የሚገባባቸው ብዙ በሮች መኖራቸው ሌላው አሳሳቢ ነገር ነው። "በደሎሎ፣ በቲያ፣ በቱመት እና በሌሎችም በሮች አንዴ ዘግተን ብንሰራ ጥሩ ነበር" ይላሉ አቶ በቃሉ። እንደ የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊው ከሆነ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡ ብዙ መግቢያ ቦታዎች አሉ። መጀመሪያ በሽታውን ለመከላከል ከቋራ እስከ ምዕራብ አርማጭሆ ድረስ መስመሩ መዘጋት አለበት የሚሉት ኃላፊው፣ ከዚያም በዚህ ይውጡ በዚህ ይግቡ በማለት መለየት እና ከሱዳን የሚመጡትን ሰዎች ይዞ ማከም ይቻል ነበር ሲሉ ለበቢሲ ተናግረዋል። " ከዚያ ኳራንታይን በማመቻቸት ሰዎችን 14 ቀን አቆይቶ ናሙና በመውሰድ ቫይረሱ ያለባቸውን ማከም ሌሎችን ደግሞ ወደ ቀዬአቸው መላክ ነው ያለበት። በክፍል እና በቦታ ጥበት ምክንያት ግን አልሆነም " ሲሉም ያስረዳሉ። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት የምዕራብ ጎንደር ዞን የማህበራዊ ልማት ኃላፊ ሲስተር ክሽን ወልዴ " ያለው የኮሮና ስርጭት አስደንጋጭ ነው። የዞኑ አቅም ትንሽ፣ ቀዳዳው ብዙ ነው። ሰፊ ድንበር ስለሚጋራ እና ብዙ በሮች ስላሉት የስርጭቱ ሁኔታ አስደንጋጭና አሳሳቢ ችግር ላይ ነን ማለት ይቻላል።" "ዞኑ ካለው ስፋት አኳያ በተለይ ተደጋግፍን ሰዎቹ ሲገቡ መያዝ ካልቻልን ከዞኑ አቅም በላይ ነው" ይላሉ። እንደ ኃላፊዋ ከሆነ ከ700 በላይ ናሙናዎች ከዞኑ ለምርመራ ተልኳል። እስካሁን 62 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ለማረጋገጥም ተችሏል። "61 በለይቶ ማቆያ ያሉ ናቸው። አንድ ሰው ግን ኮኪት ከተማ ላይ የግል ፋርማሲ ያለው ሰው በሥራ ላይ እያለ ምልክት አሳየ። ወደ ለይቶ ማቆያ አስገባነው። ሲመረመር ፖዘቲቭ ሆነ" ብለዋል ሲስተር ክሽን። ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ የማስገባት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። አንዳንዶቹ ደግሞ በፈቃድ ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል ብለውናል። ሲስተር ክሽን አክለውም ከግለሰቡ ጋር ንክኪ ካላቸው ሰዎች መካከል ከሱዳን ከመጣ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው መኖራቸውን ይናገራሉ። "በሆነ አጋጣሚ [ከሱዳን] ሾልኮ ገብቷል ማለት ነው። እንዲህ አይነት ችግር ነው ያለው። አሁን ባለው ሁኔታ ዞኑ ተጋላጭነት ትንሽ ሰፋ ያለ ነው።" ወደ አካባቢው የሚገቡ ሰዎች የዞኑ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ከመላው አገሪቱ የሚመጡ ናቸው ያሉት ኃላፊዋ እነዚህ ሰዎችን ለማቆየት የሚያገለግሉት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ለይቶ ማቆያዎቹ ምቹ አለመሆናቸውን የሚናገሩት ሲስተር ክሽን ከማዕከሎቹ የሚጠፉ ሰዎችም እንደነበሩ ለቢቢሲ ገልፀዋል። "[ከለይቶ ማቆያ] የጠፉ ሰዎች ነበሩ። ሥራውን ከጀመርነው ቆይተናል። 575 ለይቶ ማቆያ አቆይተን ተመርምረው ወጥተዋል። ከለይቶ ማቆያው መጀመሪያ ላይ የሾለኩ አሉ። አንዳንዶቹ ጎንደር፣ ማዕከላዊ ጎንደር እና ደቡባዊ ጎንደር እኛ ጥቆማ ሰጥተን ተይዘዋል። አንዳንዶች ከእኛ አካባቢ የያዝናቸው አሉ። አንዳንዶች የጠፉንም አሉ። ከዚያ በኋላ ግን ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን ከሚሊሻ በተጨማሪ በልዩ ሃይል ጥበቃ እየተደረገ ነው" ሲሉ አሁን ስላለው ሁኔታ አስረድተውናል። በሱዳን አዋሳኝ ቦታዎች ላይ 19 ዋና ዋና በሮች እንዳሉ ለቢቢሲ የገለጹት የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ፣ በዞኑ 7 የሚደርሱ የለይቶ ማቆያ ማዕከሎች መኖራቸውን ይናገራሉ። ኃላፊው አክለውም በእነዚህ በሮች የሚገቡት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ብለዋል። ለዚህም ተጨማሪ ማዕከሎች እንደሚያስፈልጉ አስምረውበታል። "በረሃ ውስጥ ማሽላ ቆረጣ እና ጥጥ ለቀማ ላይ የቆየ ኃይል ነው። ስለዚህ ወደ ዞኑ በየትኛውም አቅጣጫ የመግባት ዕድል አለው። በዚህ ረገድ 19 ዋና ዋና የሚባሉ በሮችን ለይተን እነሱ ላይ ርብርብ ለማድረግ እየሞከርን ነው" ይላሉ። ከሱዳን የሚዋሰኑ 17 ቀበሌዎችን ተለይተው ስልጠና ተሰጥቷል። ክትትል በማድረግ እየተሠራ ቢሆንም የሚገባው ሰው ቁጥሩ ሰፊ ነው። በመተማ ዮሃንስ በኩል ብቻ ከዘጠኝ ሺህ በላይ ሰው የሙቀት ልኬት ተደርጓል ያሉት አቶ አደባባይ ከዚያ ውስጥ ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገባ የተደረገው 1400 እንደሚደርስ ያስረዳሉ። "መጀመሪያ የሙቀት ልኬት በማድረግ ብቻ ነበር የምናሳልፈው፤ በኋላ ላይ ግን ነገሩ ሲጠብቅ እና ሱዳን አካባቢ ኮሮና ሲከሰት እኛም ጠበቅ ብለናል። አሁን 14 ቀን አቆይተን ምርመራ በማድረግ ነጋቲቭ የሚሆኑት ብቻ ናቸው እየሄዱ ያሉት። አሁን 700 በላይ ሰዎች በተለያዩ ስፍራዎች ኳራንቲን ላይ ይገኛሉ" ብለዋል። • ቢል ጌትስ በክትባት ስም ክንዳችን ውስጥ ሊቀብሩት ያሰቡት ነገር አለ? • በአማራ ክልል ሁለት አመራሮች እና አንድ የፖሊስ አባል ተገደሉ • ሐኪሞችን ግራ ያጋባው የኮሮናቫይረስ ወረርሽንና የሚያስከትለው ጉዳት በአካባቢው ሦስት መሠረታዊ ችግሮች መኖራቸውን አቶ አደባባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከሚገባው የሰው ቁጥር አንጻር ያሉት የለይቶ ማቆያ ማዕከሎች አነስተኛ ናቸው። በተጨማሪም " ያሉትም ጥቂት ናቸው። እነዚህም ከመመዘኛው በታች ናቸው። ትምህርት ቤቶችን ነው እየተጠቀምን ያለነው" ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል። "ሁለተኛ አካባቢው ላይ በለይቶ ማቆያ ማዕከሎቹ ልክ የማግለያ ማዕከሎች (Isolation center) ያስፈልጋል። በለይቶ ማቆያ የተለየ ምልክት የሚያሳዩትን ብቻቸውን ለይቶ ማቆየት ያስፈልጋል። ገንደውሃ ከተማ ላይ ካለው አንድ ገስት ሃውስ ውጭ ለዚህ የሚረዳ የማግለያ ማዕከል የለንም። ። ሌላው አሁን ላይ የማግለያ ማዕከልነት እያገለገለ ያለው መተማ ሆስፒታል ነው።" በሦስተኛነት ያነሱት የኮቪድ ላብራቶሪ እና ህክምና መስጫ ጉዳይ ነው። "ምርመራው እና ህክምና መስጫውም ጎንደር እና ባህርዳር ላይ ነው" ብለውናል። ዞኑ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለምርመራ የሚያገለግለውን ማሽን ማግኘት የቻለ ሲሆን አስፈላጊ ግብዓቶች ተሟልተው በቅርቡ ሥራ እንደሚጀመር ዋና አስተዳዳሪው ያስረዳሉ። "ክልሉ በተለይ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር የተመራ የክልል ቡድን መጥቶ አካባቢውን በአካል ካየ በኋላ በበጀትም በቁሳቁስም የሚደረገው ድጋፍ ተጠናቅሮ እየቀጠለ ነው። በፌደራል መንግስት በኩል አሁንም የተጠናከረ ድጋፍ ያስፈልጋል። በዞን በክልል ወይም በወረዳ ብቻ የሚፈታ አይደለም። የአቅማችንን እየሠራን ነው። የፌደራል መንግስት ማድረግ ያለበትን ማድረግ አለበት" ብለዋል። ሲስተር ክሽንም ምርመራ ለመጀመር ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ላደረገላቸው ምስጋና አቅርበው ህክምና መስጫውም በአካባቢው የህክምና ማዕከላት አስፈላጊ ቁሳቁሶች ተሟልተው እንዲጀመሩ ጠይቀዋል። ከለይቶ ማቆያ ማዕከል አንጻር ብዙ ሰዎችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችሉ ተገጣጣሚ ማቆያዎችን ወይንም ድንኳኖችንም ቢሆን የፌደራል መንግሥት እገዛ ቢያደርግልን ብለዋል። ካልሆነ ግን አሁን ባሉት ማዕከላት ብዙ ሰዎች በአንድ ሰፊ ክፍል ስለሚቆዩ "እኛ ካስገባናቸው በኋላም ሊተላለፍባቸው ይችላል " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸውልናል።
xlsum_amharic-train-182
https://www.bbc.com/amharic/news-55217765
የራሴን 'አገር' ካልሠራሁ ብሎ ከመንግሥት የተጣለው ግለሰብ ታሪክ ፊልም ሆኖ መጥቷል
ጊዜው በፈረንጆቹ 1960ዎቹ። ቦታው ደግሞ አገረ ጣልያን።
[ "ጊዜው በፈረንጆቹ 1960ዎቹ። ቦታው ደግሞ አገረ ጣልያን።" ]
አንድ ወጣት መኃንዲስ በአድሪያቲክ ባሕር ላይ የራሱን ደሴት ይገነባል። 'ምግብ ጀምረናል' የሚል ታፔላ የሰቀሉ ሬስቶራንቶች ይከፍታል፤ መጠጥ ቤት ያስመርቃል፤ አልፎም ፖስታ ቤት ይገነባል። ይህን ልብ ወለድ የሚመስልን ታሪክ ብዙዎች አያውቁትም። አሁን ግን ይህ አስደናቂ ታሪክ ኔትፍሊክስ በተሰኘው ፊልም አከፋፋይ ድርጅት ቤትዎ ድረስ ሊመጣ ነው። 'የራስ ወዳዶች ልዑል' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ፊልም የጆርጂዮ ሮዛን ታሪክ ይዳስሳል። ታሪኩ የተፈፀመው በጣሊያኗ ሪሚኒ ከተማ ነው። ከዚህች ከተማ ባህር ዳርቻ ላይ ነው ጆርጂዮ የራሱን ደሴት አቋቁሞ አገር ካልመሰርትኩ ያለው። ጆርጂዮ ይህችን ዓለም የተሰናበተው በፈረንጆቹ 2017 ነው። በ92 ዓመቱ። ነገር ግን ከመሞቱ በፊት የኔትፍሊክስ ሰዎች ወደ መኖሪያ ቤቱ ብቅ ብለው እባክህ ፈቃድህ ከሆነ ያንተን ታሪክ በፊልም ልንሰንደው አስበናል አሉት። ጆርጂዮ ይህ ጥያቄ ሲቀርብለት ትንሽ አንገራገረ። ከጥቂት ልመና በኋላ ግን ፈቃደኝቱን አሰማ። ፊልሙ ጆርጂዮ እንዴት ደሴት እንደቀለሰ፤ ይደምሰስ የሚለውን የመንግሥት ውሳኔ እንደቀለበሰ የሚያሳይ ነው። ጆርጂዮ የራሴን ብዙ እሳት የማትፈጅ አገር ካልመሰርትኩ ያለው በ9167 ነው። ደሴቷ የነፃነት አርማ እንድትሆንም አቅዶ ነበር ሰውዬው። በወቅቱ ብዙዎች ገላመጡት፤ አብደህ መሆን አለበት የሚልም አስተያየት ሰጡት። ነገር ግን የጆርጂዮ ልጅ አባቴ 'አይሶላ ዴሌ ሮዛን' ለመቀለስ የተነሳው እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ አይደለም ይላል። "አባቴን ብታውቁት ኖሮ. . . በጣም ጥንቁቅ እና የተደራጀ መኃንዲስ ነበር። እርግጥ ነው ትንሽ ወጣ ያለ ባህሪ ነበረው። ነገር ግን የራሱን መድረክ መገንባት ይፈልግ ነበር። ይህ ነው የራስ ወዳዶች ልዑል ያስባለው" ይላል ሎሬንዞ ሮዛ። ደሴቷ በ400 ስኩዌር ሜትር ላይ የተገነባች ናት። ከባህር ጠለል 26 ኪሎ ሜትር ከፍ ብላ ነው የተገነባችው። ከሪሚኒ ጠረፍ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ገባ ብላ ትገኛለች። ይህ ማለት ከጣልያን ግዛት ውጭ ናት ማለት ነው። ጆርጂዮ ሮዛ ራሱን የደሴቲቱ ፕሬዝደንት አድርጎ ሾመ። የሮዝ ደሴት ሪፐብሊክ ሲልም 'ነፃ አገር' አወጀ። ይህ ግን ለጣልያን መንግሥት አልተዋጠም። እንዴት ፈቃድ ሳይጠይቅ አገር ይገነባል? በዚያ ላይ ከቱሪዝም ቤሳ ይሰበስባል ሲሉ ተቆጡ። አንዳንድ ባለሥልጣናት ደሴቲቱ የቁማርና የስካር መንደር ሆናለች። ምን እሱ ብቻ ለሶቪዬት ሕብረት የባህር ጠላቂ ዋናተኞች መደበቂያ ሆናለች ሲሉ ከሰሱ። ጆርጂዮ ነፃ ደሴት ባወጀ በ55ኛ ቀኑ የጣልያን መንግሥት ወደ ደሴቷ ወታደር ላከ። ጆርጂዮ ላቡን ጠብ ያደረገባትን ደሴት በዳይናማይት ድብልቅልቋን አወጡት። ጆርጂዮ ደሴቷን ሲገነባ የብዙዎችን ትኩረት ስቦ ነበር። የጣልያን ጋዜጦች ከቪዬትናም ጦርነት ይልቅ የደሴቷን ብርቅርቅነት የፊት ገፃቸው ማጀቢያ አደረጓት። ወጣቶች ከአራቱም የዓለም አቅጣጫዎች ወደ አዲሷ የነፃነት ደሴት ይጎርፉ ጀመር። ጆርጂዮ ከቱሪዝም የሚያገኘውን ገቢ ልቁረጥ የሚል መንግሥት አልነበረውም። መንግሥት እሱ ራሱ ነበር። ብዙዎች ይህ ድርጊቱ ነው የጣልያን ባለሥልጣናትን ያስቆጣው ብለው ይገምታሉ። ሰውዬው ከጣልያን መንግሥት ጋር የገባው እሰጥ-አገባ ጭራሽ ትኩረት ሳበለት። መኃንዲሱ ጆርጂዮ ደሴቷን ለመግንባት ብዙ ላብና ገንዘብ አፍስሷል። የዴሴቷ ዲዛይን ልዩ ነው እየተባለም ይሞካሽ ነበር። ነገር ግን ጆርጂዮ ስንት የለፋባት ምድር ስትወድም ከተመለከተ በኋላ ቅስሙ ተሰበረ። ስለ ደሴቲቱ ማውራትም ሆነ ማሰብ አይሻም ነበር ይላል ልጁ ሎሬንዞ። በጣልያን መከላከያ ሠራዊቷ የወደመችው ደሴት አፅም ግን አሁንም ከባህር በላይ ተንሳፎ ይታያል።
xlsum_amharic-train-183
https://www.bbc.com/amharic/news-53985493
ሳዑዲ አረቢያ፡ የዓለም መነጋገሪያ የሆነው የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ በሳዑዲ እስር ቤቶች
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሁለት ዓመታት በሹፌርነት ሲሰራ የነበረው *አብዱ በርካታ ልጆች ካሉበት ቤተሰብ እንደመጣ ይናገራል። የተሻለ ገቢ በማግኘት እናትና አባቱን እንዲሁም እህት ወንድሞቹን ለመደገፍ ነበር ከጓደኞቹ ጋር በጂቡቲ በኩል ባሕር አቋርጦ ወደ የመን ከወራት በፊት ያቀናው።
[ "ኢትዮጵያ ውስጥ ለሁለት ዓመታት በሹፌርነት ሲሰራ የነበረው *አብዱ በርካታ ልጆች ካሉበት ቤተሰብ እንደመጣ ይናገራል። የተሻለ ገቢ በማግኘት እናትና አባቱን እንዲሁም እህት ወንድሞቹን ለመደገፍ ነበር ከጓደኞቹ ጋር በጂቡቲ በኩል ባሕር አቋርጦ ወደ የመን ከወራት በፊት ያቀናው።" ]
ጠባብ ቦታ ላይ የሚገኙት ስደተኞች በእንዲህ ያለ ሁኔታ እንዲቆዩ መደረጋቸውን ይናገራሉ አብዱ ከጂቡቲ ተነስቶ ባሕሩን ለማቋረጥ 25 ሺህ ብር ሲከፍል፤ የመን ከደረሱ በኋላ ደግሞ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሻገር ሦስት ሺህ አምስት መቶ ሪያል [35 ሺህ ብር ገደማ] ከፍሏል። በአንዲት ጀልባ 180 ሰዎች ታጭቀው በአደጋ መካከል ለ9 ሰዓታት፣ በአደገኛው ባሕር ላይ ተጉዘው ወደ የመን መግባት ችለው ነበር። በጭንቅ ውስጥ ሆነው ባሕሩን እንዳቋረጡ የሚናገረው አብዱ ለአስራ አምስት ቀናት የመን ተቀምጠው በጦርነቱና በበሽታው መካከል መንቀሳቀስ ሳይችሉ ቆይተዋል። እቅዳቸው ወደ የመን ተሻግረው ከዚያም ወደ ሳዑዲ አረቢያ በማቋረጥ ሥራ አግኝቶ ያሰቡትን ማሳካት የነበረ ቢሆንም፣ በመካከል ላይ ኮሮናቫይረስ ተከስቶ የሁሉም ስጋት ሆነ። በዚህም እንኳን ከአገር ወደ አገር ማቋረጥ ቀርቶ በቆዩበት ጦርነት በሚካሄድባት የመን አማጺያኑ ወረርሽኙን ታስፋፋላችሁ በሚል እንዳሳደዷቸው ይናገራል። የሁቲ አማጺያን አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ጫና ሲያሳድሩባቸው እንዲሁም በሚካሄደው ጦርነት ምክንያት እዚያው የመን ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንዳሉም ነግሮናል። ለጥቂት ጊዜ ባሉበት ከቆዩ በኋላ አማጺው የሁቲ ሠራዊትና በሳዑዲ የሚመራው ጥምረት በሚያደርጉት ውጊያ ሳቢያ ተጠልለውበት ከነበረው ስፍራ ለቅቀው ወጡ። በእስር ቤቱ የሚገኙት አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን የኮሮናቫይረስን ሰበብ አድርጎ የየመኑ ሁቲ አማጺ ቡድን በጦርነት ከሚታመሰው ግዛቱ በኃይል ያሳደዳቸው ናቸው። ሁቲዎች ከየመን እንዲወጡ ሳዑዲዎች ደግሞ ወደ ግዛታቸው እንዳይገቡ በሚያደርሱት ጫና በርካታ የሞቱ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ይናገራል። ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ባወጣው መግለጫ ላይም የየመን ሁቲ ታጣቂዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከሰሜናዊ የመን ማስወጣታቸውንና በፈጸሙባቸው ጥቃት መግደላቸውን አስታውቆ ነበር። ድርጅቱ የተለያዩ ኢትዮጵያዊያንን በማናገር አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ጥቂት የማይባሉ ስደተኞች ተገድለዋል። ጨምሮም ከየመን "ወደ ሳዑዲ አረቢያ ድንበር የተባረሩት ስደተኞች በድንበሩ ጠባቂዎች ሌላ ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ በዚህም የተወሰኑ ሲሞቱ በመቶዎች የሚቆጠሩት ወደ ተራራማ አካባቢ ሸሽተዋል" ብሏል። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ከየመን ወጥተው ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንደገቡ የኮሮናቫይረስ ክስተትን ተከትሎ አሁን ባሉበት እስር ቤት ውስጥ ስድስት ወር ሊሆናቸው ነው። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑት እነዚህ ስደተኞች ያሉበትን ሁኔታ እስር ቤት ሳይሆን "የምድር ላይ ሲኦል ነው" ሲሉ ካሉበት ሆነው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በድብደባ የተጎዱ ስደተኞች ከየመን በድንበር በኩል ወደ ሳዑዲ አረቢያ ከገቡ በኋላ ግን ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ተስፋ ቢያደርጉም የገጠማቸው ግን "ሲኦል" ወዳሉትና በችግርና በተለያዩ በሽታዎች ወደሚሰቃዩበት እስር ቤት "መወርወር" ነበር። በዚህ እስር ቤት ውስጥ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሁኔታ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ የሚናገረው ቢቢሲ ያነጋገረው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ፣ በርካቶቹ በተለያዩ ህመሞች እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብሏል። እስር ቤቱ ከ20 የሚበልጡ ግቢዎች እንዳሉት ይነገራል። በየአንዳንዱ ግቢ ውስጥም 400 ያህል ስደተኞች በተጨናነቀና ንጽህናው ባልተጠበቀ ሁኔታ ታስረው እንደሚገኙ በአንደኛው ጊቢ ያሉት ስደተኞች ጠቅሰዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንዳሉት እነሱ ባሉበት ቦታ ለወራት በር ተዘግቶባቸው ውጪውን እንዳላዩና፣ ካሉበት አስጨናቂ ሁኔታ የተነሳም ከኢትዮጵያዊያን መካከል ብዙዎቹ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ችግር እየገጠማቸው ነው። ከመካከላቸውም "ሁለቱ ካሉበት የስቃይ ህይወት የተነሳ ራሳቸውን አጥፍተዋል" ብለዋል። በእስር ቤቱ የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን ቁጥርን በትክክል ባያውቁትም አስከ አራት ሺህ እንደሚደርስ ይገምታሉ። ከእነዚህም ውስጥ ሴቶች የሚገኙበት ሲሆን፤ ነገር ግን በተለየ እስር ቤት ውስጥ ስላሉ ያሉበትን ሁኔታ እንደማያውቁ ይናገራሉ። ሴቶች ታስረው ከሚገኙበት በአንዱ እስር ቤት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ቢቢሲ ለማግኘት ችሎ ነበር፤ ምንም እንኳን በአንድ ግቢ ውስጥ እንደ ወንዶቹ በመቶዎቹ ሆነው በተጨናነቀ ሁኔታ ባይታሰሩም ሙቀቱና የንጽህናው ሁኔታ ተመሳሳይ እንደሆነ ይናገራሉ። ለወራት በእስር ቤቱ ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ በመቆየታቸው ልብሳቸው ላያቸው ላይ አልቆ መራቆታቸውን የምትናገረው ለቢቢሲ ቃለወን ሰጠችው ግለሰብ፣ የንጽህና ችግርና እሱን ተከትሎ የሚጣው የቆዳ በሽታ እያሰቃያቸው መሆኑን ገልጻለች። በሴቶቹ እስር ቤት ውስጥ ጥቂት ህጻናትና ነፍሰጡር እናቶች መኖራቸው ገልፀው፣ እነዚህ ሴቶችና ህጻናት ጤናና ሕይወት አደጋ ላይ እንደሆነ ይናገራሉ። ቢሆንም ግን አልፎ አልፎ ህክምና እንዲያገኙ እንደሚደረግ ቢገልጹም የሚሰጣቸው መድኃኒት ለፈውስ የሚሆን ሳይሆን የተለመደ የህመም ማስታገሻ ነው ብለዋል። ሴቶቹ ለእስር ቤቱ ኃላፊዎች ወደ አገራቸው እንዲመለሷቸው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የእስር ቤቱን ተጠሪዎች ቢወተውቱም "ይህ የሚመለከተው የአገራችሁን መንግሥት ነው" የሚል ምላሽ እንዳገኙ በመግለጽ የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያደርግላቸው የሚችለውን ነገር በጉጉት ሲጠብቁ ወራት እንዳለፋቸው አንደኛዋ ስደተኛ ለቢቢሲ ተናግራለች። በእስር ቤቱ በተስፋፋው የቆዳ በሽታ ብዙዎቹ ተጠቅተዋል ከዚህ ቀደም አንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካይ ወደ እስር ቤቱ መጥቶ እንዳናገራቸውና መንግሥት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥረት እያደረገ መሆኑን ቢገልጽላቸውም ምንም ነገር ሳይሰሙ "የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል" በማለት ከዚያ በኋላ ስላሉበት ሁኔታ መጥቶ የተመለከተም ሆነ ያየ እንደሌለ ጠቅሳለች። ሁሉም ኢትዮጵውያን ወጣቶች በሞትና በሕይወት መካከል በአደገኛ ሁኔታ በመጓዝ ወደ ሳኡዲ አረቢያ የገቡት ጉልበታቸውን አፍስሰው ሥራ በመስራት የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ሕይወት ለመለወጥ በማለም ነበር። በሴቶቹ እስር ቤት ካሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል አንዷ የሆነችው *መሰረት ልጆቿን ለማስተማርና ለማሳደግ እንዲሁም በእድሜ የገፉ ወላጆቿን ሳዑዲ ውስጥ ሰርታ ለመጦር "ብዙ ብር ከስክሳ" ብትመጣም ከወራት በፊት ተይዛ ወደ እስር ቤት በመግባቷ ግራ መጋባት ውስጥ እንዳለች ትናገራለች። ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች መጥተው አብረዋት ያሉት ሴቶችም ተመሳሳይ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፣ ያቀዱት ባለመሳካቱና ለቤተሰቦቻቸው ድጋፍ ከመሆን ይልቅ እንዲሁ በእስር ቤት ባክነው መቅረታቸው ህሊናቸውን እየረበሸው በመሆኑ ብዙዎቹ በጭንቀት ላይ ናቸው ትላለች። ነገር ግን በጦርነትና በበሽታ መካከል አልፈው የተረፉት ሳዑዲ አረቢያ ቢገቡም ለወራት የታሰሩበት እስር ቤት ውስጥ ከሞት ጋር እንዲፋጠጡ እንዳደረጋቸው ይናገራሉ። በከፍተኛ ሙቀትና ከንጽህና ጉድለት ተነሳ ለተለያዩ በሽታውች በመጋለጣቸው ሕይወታቸውን ለአደጋ ማጋለጡን ይናገራሉ። "እስር ቤቱ ጽዳት የለውም፣ ሽንት ቤቶች ሞልተው ፍሳሹ ወደ ክፍሎቹ ይገባል፣ ከእከክ ጋር የሚመሳሰል የቆዳ በሽታ ሁሉንም እሰረኞች ይዟል" በዚህም ሳቢያ በርካቶቹ እንቅልፍ እንደማይወስዳቸውና ፊታቸው ሳይቀር እያበጠ መቸገራቸውን ከእስረኞቹ አንዱ ለቢቢሲ ገልጿል። በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ሆነው ህክምና ቢጠይቁም ማግኘት አዳጋች ነው ይላሉ። ሲበረታባቸውም ምግብ በሚቀርብበት ወቅት ስለንጽህናቸውና ስለህክምና ጥያቄ በሚቀርቡበት ጊዜ በጥበቃዎቹ ድብደባ እንደሚፈጸምባቸው ይናገራሉ። ከእስር ቤቶቹ የወጡ ፎቶዎችም ይህንኑ የሚያረጋግጡ ናቸው። ኢትዮጵያዊያኑ ወደእዚህ እስር ቤት የገቡት ወንጀል ሰርተው እንዳልሆነ የሚናገረው አብዱ "ሰርተን ለእኛም ለቤተሰቦቻችንም የተሻለ ነገር እናደርጋለን ብለን ነበር ከአገር የወጣነው። ግን ኮሮና መጥቶ ያሰብነው ሳይሳካ ወደ እስር ቤት ገብተናል" በማለት የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ገልጿል። ሳኡዲ ውስጥ ወደ ሚገኙት እነዚህ እስር ቤቶች ውስጥ ሲገቡ በአጭር ጊዜ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እንደሚደረግ እንደተነገራቸው የሚያስታውሱት ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች፣ አሁን ግን ካሉበት ሁኔታ አንጻር በህይወት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ስለመቀላቀላቸው እርግጠኛ አይደሉም። "የሳዑዲም ሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት ዘንግቶናል፤ ለዚህም ነው በምድር ላይ ባለ አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ በሕይወት የምንቆይበትን ቀን እየቆጠርን ያለው" ሲል አብዱ በምሬት ይናገራል። መሰረትና አብዱ አሁንም ተስፋ አልቆረጡም የመጨረሻ ተስፋቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ መሆኑን ይናገራሉ። ከዛሬ ነገ "ከዚህ ሲኦል ወጥተን ቢርበንም ቢጠማንም በችግር ወደ ምንኖርበት አገራችን ተመልሰን፣ የቤተሰቦቻችን አይን ማየት ነው ተስፋችን" ይላሉ። አብዱ እናትና አባቱ ሁሉንም ትቶ እንዲመለስ ይፈልጋሉ፤ እሱ እንደሚለውም "እነሱን እደግፋለሁ ብዬ ወጥቼ በተቃራኒው በደካማ ጎናቸው እነሱ ስለእኔ በመጨነቅ እየተጎዱ ነው" ይላል። የታዳጊ ልጆቿን ሕይወት የሰመረ ለማድረግ የተሰደደችው መሰረትም "ከሁሉ በላይ የናፈቀኝ የልጆቼን አይን ማየት ነው" ትላለች በእስር ቤቱ ያለው ሁኔታ ስላላስተማመናት። በሳዑዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ያላቸውን አስተያየት ለማግኘት በስልክ በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው ሳይሳካልን ቀርቷል። ይህንን የስደተኞቹን ስቃይና ሰቆቃ በተመለከተ 'ዘ ቴሌግራፍ' የእንግሊዝ ጋዜጣ በዝርዝር መዘገቡን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በሳዑዲ መንግሥት የስደተኞቹ አያያዝ ላይ ጥያቄ በማንሳት ድርጊቱን አውግዘውታል። ይህንንም ተከትሎ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ለንደን በሚገኘው ኤምባሲው በኩል ለጋዜጣው በሰጠው ምላሽ "ከቀረበው ክስ አንጻር በመንግሥት በሚተዳደሩት እስር ቤቶች ውስጥ በሙሉ ስላለው ሁኔታ ምርመራ" እያደረገ መሆኑን ገልጾ "በእርግጥም አስፈላጊው ነገሮች የተጓደለ ሆኖ ከተገኘ የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል" ሲል ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ [ሐሙስ] ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ ላይ ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ እየሰራ መሆኑንና የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻር በሪያድ የሚገኘው ኤምባሲው እንዲሁም በጅዳ ያለው ቆንስላ ሙሉ ትኩረቱን ለዚሁ ጉዳይ መስጠቱን አስታውቋል። ከሚያዚያ እስከ ሐምሌ 2012 ባሉት ወራት 3500 ዜጎች ከሳዑዲ እንዲመለሱ መደረጉም ሚኒስቴሩ ተጠቅሷል። አሁንም ከጰጉሜ 3/ 2012 እስከ መስከረም 28/2013 ባሉት ቀናት ቅድሚያ የተሰጣቸው 2ሺህ ስደተኞችን ወደ አገር እንደሚመለሱም ተጠቁሟል። ስደተኞችን ወደ አገር ቤት የመመለሱ ሥራው የተለያዩ የፌደራል ሚንስቴር መስሪያ ቤቶችን፣ ኤምባሲዎችን እና የክልል ቢሮዎችን በቅንጅት የሚሰሩት ነው ብሏል። በዚህም መሰረት አገሪቱ በውጭ አገራት በስደት ላይ ያሉ ዜጎቿን አልቀበልም ብላ እንደማታውቅ ገልጾ በተቻለ አቅም ስደተኞቹ ወደ አገራቸው እንዲመረሱ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልከቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ወደ ሳዑዲ አረቢያ እየገቡ ያሉ ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል። * ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው ተቀይሯል የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሰቆቃ በሳኡዲ አረቢያ እስርእ ቤቶች
xlsum_amharic-train-184
https://www.bbc.com/amharic/42985381
የቦረናን የዘመን አቆጣጠር ከሌሎች አቆጣጠሮች ምን ይለየዋል?
የቦረና የዘመን አቆጣጠር ከኦሮሞ ህዝብ የዕለት ተዕለት ኑሮ ወይም የገዳ ሥርዓት መሰረት ነው።
[ "የቦረና የዘመን አቆጣጠር ከኦሮሞ ህዝብ የዕለት ተዕለት ኑሮ ወይም የገዳ ሥርዓት መሰረት ነው።" ]
የባህልና የታሪክ አጥኚ የሆኑት ጃተኒ ዲዳ የዘመን አቆጣጠሩ ቀንና ወራትን ከመቁጠር ባለፈ የዓለምን አፈጣጠር ቅደም ተከተል በውስጡ ያካተተ እንደሆነም ይናገራሉ። ከዋክብትንም ስለሚያጠና ከሥነ-ፈለግ ጋር ከፍተኛ ትስስር አለው። የዘመን አቆጣጠሩ እንደ ሌሎቹ አቆጣጠሮች ሃይማኖትን ሳይሆን ተፈጥሮን መሰረት ያደረገ ነው። ሥለ ዘመን አቆጣጠሩ ማወቅ ያለባችሁ 11 ነጥቦች ይህ የዘመን አቆጣጠር የገዳ ስርዓት እስካሁን የሚተገበርባቸው አካባቢዎች እንደ ቦረናና ጉጂ ያሉ አካባቢዎች ይጠቀሙበታል።
xlsum_amharic-train-185
https://www.bbc.com/amharic/sport-46257731
የ2018 የቢቢሲ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች፡ አምስት ዕጩዎች
የ2018 የቢቢሲ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ዕጩዎች ይፋ ሆነዋል።
[ "የ2018 የቢቢሲ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ዕጩዎች ይፋ ሆነዋል።" ]
ከግራ ወደ ቀኝ፤ መህዲ ቤናቲያ፣ ካሊዶ ኩሊባሊ፣ ሳድዮ ማኔ፣ ቶማስ ፓርቴይ እና ሞሐማድ ሳላህ የዘንድሮው ዕጩዎች መህዲ ቤናቲያ ከሞሮኮ፤ ካሊድ ኩሊባሊ ከሴኔጋል፤ ሳድዮ ማኔ ከሴኔጋል፤ ቶማስ ፓርቴይ ከጋና እንዲሁም ሞሐመድ ሳላህ ከግብፅ ናቸው። ቅዳሜ ዕለት ይፋ የሆነው ውድድሩ፤ ለሁለት ሳምንታት ያህል ከቆየ በኋላ ኅዳር 23/2011 አሸናፊው ታውቆ ይጠናቀቃል። አሸናፊው በቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ጣቢያዎች ዓርብ ታኅሳስ 5/2011 ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። • ለመምረጥ ይህንን ይጫኑ • በሃሰተኛ ዜናዎች "የሞቱ" የኪነጥበብ ሰዎች አምስቱ ዕጩዎች የተመረጡት በአፍሪካውያን የእግር ኳስ አዋቂዎች ስብስብ በተሞላ ቡድን ነው። የሊቨርፑሉ አጥቂ ሞሐመድ ሳላህ የአምናውን ውድድር ማሸነፉ አይዘነጋም፤ ጄይ ጄይ ኦካቻ፣ ማይክል ኢሴይን፣ ዲዲየር ድርግባ፣ ያያ ቱሬ አና ሪያድ ማህሬዝም ከአሸናፊ ተጫዋቾች የሚጠቀሱ ናቸው። ዕጩዎች የ31 ዓመቱ የጁቬንቱስ መሃል ተከላካይ ቤናቲያ ባለፈው ዓመት ለአራተኛ ተከታታይ ጊዜ የሊግ ዋንጫ ማግኘት ችሏል፤ ሁለት ከባየር ሙኒክ እና ሁለት ከጁቬንቱስ ጋር። የናፖሊው ተከላካይ ኩሊባሊ 27 ዓመቱ ሲሆን አምና ቡድኑ ዋንጫ ለማግኘት ከጁቬንቱስ ጋር ባደረገው ትንቅንቅ የበኩሉን አስተዋፅኦ ሲወጣ ነበር፤ በዓለም ዋንጫው ከሃገሩ ሴኔጋል ጋርም ተሳትፎ አድርጓል። የ26 ዓመቱ የሊቨርፑል አጥቂ ማኔ፤ ለሴኔጋል በዓለም ዋንጫ ተፋልሟል። በዓምናው ቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ መጨረስም ችሏል። • እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው የአትሌቲኮ ማድሪዱ የ25 ዓመት አማካይ ቶማስ ፓርቴይ በዲዬጎ ሲሞኒ ቡድን ውስጥ የቋሚነት ሥፍራውን ማስከበር የቻለ ተጫዋች ነው። በዓምናው የአውሮፓ ሊግ ፍፃሜም ተቀይሮ በመግባት ተጫዋቷል። ለሃገሩ ጋናም በቋሚነት እየተጫወተ የሚገኝ አማካይ ነው። የዚህ ውድድር የአምናው አሸናፊ የሊቨርፑሉ የ26 ዓመት አጥቂ ሞሃመድ ሳላህ የፕሪሚየር ሊጉን ወርቃማ ዋንጫ ማግኘት ችሏል፤ 32 ጎሎችን በማስቆጠር። በ10 ጎሎች ደግሞ ከቡድን አጋሩ ሳዲዮ ማኔ ጋር የቻምፒየንስ ሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ማዕረግ በሁለተኛነት መጨረስ ችሏል። • ለመምረጥ ይህንን እዚህ ይጫኑ
xlsum_amharic-train-186
https://www.bbc.com/amharic/45675617
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ካማሼ ዞን አመራሮች በታጣቂዎች ተገደሉ
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት 4 የካማሼ ዞን አመራሮች ሲገደሉ የተወሰኑ መቁሰላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርን ጠቅሰው የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያው አቶ በፍቃዱ አዳነ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
[ "በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት 4 የካማሼ ዞን አመራሮች ሲገደሉ የተወሰኑ መቁሰላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርን ጠቅሰው የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያው አቶ በፍቃዱ አዳነ ለቢቢሲ ተናግረዋል።" ]
ከቤንሻንጉል ጉምዝና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ አመራር አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ መስከረም 15 በአሶሳ ላይ ስብሰባ አካሂደው ነበር። •ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው •በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር ዘጠኝ ደርሷል ተባለ •የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች ስብሰባውንም ጨርሰው የካማሼ ዞንና የአምስት ወረዳ አመራሮች በሚመለሱበት ወቅት በካማሼና ነዶ መካከል በምትገኝ ቦታ በተከፈተ ተኩስ አራት የካማሼ ዞን አመራሮች እንደተገደሉ አቶ በፍቃዱ ገልፀዋል። አቶ በፍቃዱ ጥቃት አድራሾቹን ማንነት "ፀረ ሰላም ኃይሎች" ከማለት ውጭ ያሉት የለም። ከአመራሮቹም በተጨማሪ የፀጥታ ኃይል አባላት በዚህ ተኩስ እንደቆሰሉ ገልፀው፤ በህይወት ያሉት የት እንዳሉ እንደማይታወቁ ና አቶ በፍቃዱ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ሰይፈዲን ሃሮን እንዳስታወቁ ገልፀዋል። ሁኔታውን ለማረጋጋት የመከላከያ ኃይል ወደ ቦታው የገባ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።
xlsum_amharic-train-187
https://www.bbc.com/amharic/news-50909822
"የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ
በኢትዮጵያ እየተደረጉ ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከምዕራቡና ከአረቡ ዓለም የገንዘብ ድጋፍና ብድር እያገኘች ነው። እየተደረገ ካለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ 'አገር በቀል ኢኮኖሚ' የሚል አካሄድን እየተከተለ መሆኑንም መንግሥት እየገለፀ ነው።
[ "በኢትዮጵያ እየተደረጉ ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከምዕራቡና ከአረቡ ዓለም የገንዘብ ድጋፍና ብድር እያገኘች ነው። እየተደረገ ካለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ 'አገር በቀል ኢኮኖሚ' የሚል አካሄድን እየተከተለ መሆኑንም መንግሥት እየገለፀ ነው።" ]
በቅርቡም የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ የ2.9 ቢሊዮን ዶላር የብድር ድጋፍ ለማድረግ ተስማምቷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ነመራ ገበየሁ ማሞን በአገሪቱ እየተደረገ ስላለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም ስለ አይኤምኤፍ ብድር ጠይቀናቸዋል። ቢቢሲ፡ አይኤምኤፍ ብዙ ጊዜ የሚያበድረውም ሆነ የእርዳታ ድጋፍ የሚያደርገው ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ ነው። ኢትዮጵያስ የ2.9 ቢሊዮን ዶላሩን ብድር በምን አግባብ አገኘች? ዶ/ር ነመራ፡ እውነት ነው እነ አይኤምኤፍ ከአሁን በፊት ብድር የሚሰጡት ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ነው። ቅድመ ሁኔታው ደግሞ ከማክሮ ኢኮኖሚ እስከ ታች ያሉ ነገሮችን የሚነካ ነው። አሁን የኢትዮጵያን ለየት የሚያደርገው፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ከአንድ ዓመት በላይ ባሉት ጊዜያት ብዙ የፖለቲካ ማሻሻያዎችን እያካሄደች፤ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት ሃገር በቀል የሆነ የለውጥ መንገድ ስትተገብር ነበር። አይኤምኤፍ ደግሞ ለእንደዚህ ያሉ ነገሮች እርዳታ የማድረግ አካሄድ አለው። በዚህ መንገድ መጥተው ነው ኢትዮጵያን እንረዳለን ያሉት። • የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በዋጋ የሚያንራቸው ምርቶች ስለዚህ እነሱ ያስቀመጡት ቅድመ ሁኔታ የለም። ኢትዮጵያ በመንግሥት እጅ ያሉ ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዛወር እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ እጥረት ችግርን ለመፍታት የወሰነቸው አይኤምኤፍ ከመምጣቱ በፊት ነው። አሁን ያለው መንግሥት ማሻሻውን የጀመረው ቀድሞ ነው። ከዚያ እነሱ ይሄንን ሀሳብ እንደግፋለን ብለው ነው ብድሩን ሊሰጡ የቻሉት። ቢቢሲ፡ ለአይኤምኤፍ ተብሎ ባይሆንም ቅድመ ሁኔታዎቹ በኢትዮጵያ በኩል ተሟልተው ነበር ማለት እንችላለን? ዶ/ር ነመራ፡ በትክክል፤ በእርግጥ በአይኤምኤፍም በዓለም ባንክም እነዚያ በ1980 እና 90 ዎቹ የነበሩት የመዋቅር ማስተካከያ ፕሮግራሞች Structural Adjustment Policy) የሉም፤ እየላሉ መጥተዋል። ከነበሩ ልምዶች ተነስተው ነገሮችን ለቀቅ እያደረጉ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ደግሞ ከግብር መሰብሰብ ጀምሮ እስከ የውጭ ምንዛሪ ያሉ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ችግር ውስጥ ስለሆነ ያንን መቅረፍ ግዴታ ነበር። እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የተወሰደውን ተነሳሽነት ለመደገፍ ነው እነ አይኤምኤፍ የመጡት። ስለዚህ በሚቀጥሉት ከ3 እስከ 5 ዓመት የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ፍጥነት የሚወስነው የኢትዮጵያ መንግሥት እንጂ ማንም አደለም። ኢትዮጵያ ባላት የሰው ኃይል እና ሌሎች ሁኔታዎች ፍጥነቱን ጠብቃ መሄድ አለባት የሚለው ጠንካራ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠውም በኢትዮጵያ መንግሥት ነው። በሌላ በኩል አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ደግሞ እርዳታ ሲሰጡ ግልጽነት ይፈልጋሉ፤ እውነት ይሄ ለውጥ በሚፈለገው አቅጣጫ እየሄደ ነው ወይ? የሚለውን ማወቅ ይፈልጋሉ። እዚህ ላይ ከእነሱ ጋር የሚሰራበት ሁኔታ ይኖራል ግን ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ እንደሚባለው እጅ ለመጠምዘዝ ኢትዮጵያ ላይ አቅም የሚኖራቸው አይመስለኝም። ቢቢሲ፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአይኤምኤፍ የሚያገኘውን ብድር በሚፈልገው ሁኔታ ወጪ የማድረግ ነጻነት ይኖረዋል? ዶ/ር ነመራ፡ አዎ፤ ግን እንደፈለገ ሲባል መንግሥት የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት ስላለበት፤ የራሱን ቀዳሚ ሥራዎችን በመለየት ግልጽነት ባለው መንገድ ለሚፈለገው አላማ ገንዘቡን የማዋል ሙሉ ስልጣን አለው። ለምሳሌ ፕራይቬታይዜሽን ላይ የተለያዩ ሥራዎች ይኖራሉ። ድርጅቶቹ ላይ ለውጥ የማድረግ፣ አቅም መገንባት የመሳሰሉ ሥራዎች የፋይናንስ ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው። • ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ? ወደ በጀትም ከሄድን፤ ባለፉት 50 ዓመታት ሲያከራክር የነበረው ጉዳይ መንግሥት ወጪዎችን መቀነስ አለበት የሚለው ነው። አሁን ያለው የኢኮኖሚ ለውጥ ትኩረት ያደረገው የመንግሥትን ግብር የመሰብሰብ አቅም ማሳደግ ላይ አንጂ ወጪ መቀነስ ላይ አይደለም። የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ ለውጥ ማድረግ፣ ከመንግሥት ወደ ግል ማዞርም ላይ የሚሰሩ ብዙ ሥራዎች አሉ። ለዚህም የገንዘብ ድጋፍ ስለሚያስፈልግ እዚህ ላይ ይውላል እርዳታው። ሌሎች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል የተባሉ እንደ ግብርናና ቱሪዝም ያሉ ዘርፎችም አሉ፤ ገንዘቡ እዚህ እዚህ ላይ ነው የሚውለው። መጨረሻ ላይ ግን ይህ ብር የኢትዮጵያ ተወዳዳሪነትን በማጎልበት ወደ ውጭ ሃገር የምትልከውን ምርት በማሳደግ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት መቅርፍ አለበት፣ ሃገር ውስጥ ያለውን የሥራ ፈጠራና የገቢ እድገት ማረጋገጥ አለበት፤ ምክንያቱም ድህነትን ለመቀነስ ሁለቱም ቀዳሚ ጉዳዮች ናቸውና። ቢቢሲ፡ መንግሥት እየተከተለ ያለው አካሄድ ወጪውን ለመቀነስ የሚያደርጋቸውን ድጎማዎች ማንሳት ሳይሆን የታክስ ገቢውን ማስፋት እንደሆነ ገልፀውልኛል። ሰሞኑን ለፓርላማ የቀረበው ኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ የዚህ ውጤት ነው? ዶ/ር ነመራ፡ አዎ፤ መንግሥት ድህነት ለመቀነስና መሰረት ልማት ለማስፋፋት የሚያርገው የገንዘብ ወጪ ላይ ትልቅ ለውጥ አይኖርም፤ ግን ኢትዮጵያን የሚያስቸግሯት እንደ ሙስናና የሃብት ብክነትን የመሳሰሉ ነገሮች ላይ ትልቅ ለውጥ እየተካሄደ ነው። ኢትዮጵያ ላይ እንደ ትልቅ አጀንዳ ተወስዶ እየተሰራ ያለው ነገር ግን፤ ከተቋም ጀምሮ እስከ ፖሊሲ ግብር መሰብሰብ ላይ ነው፤ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን አቅም ማሳደግ ላይም ብዙ ሥራ እየተሰራ ነው። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥም ግብር የመሰብሰብ አቅም እያደገ መጥቷል። ታክስን በተመለከተ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚታዩ የፖሊሲ ክፍተቶች አሉ፤ እዚህ ላይም ማሻሻያ እየተደረገ ነው። ወደ ፓርላማ የተላከው የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅም ከዚህ አንፃር የሚታይ ነው። አገር ውስጥ የሚመረቱና ከውጭ የሚገቡ አንዳንድ ምርቶች ላይ የንግድ ምህዳሩን በማይጎዳ መልኩ የመንግሥትን ግብር የመሰብሰብ አቅም ለማሳደግ የሚደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች አሉ። • ከ20 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? ኢትዮጵያ የምትታወቀው በአፍሪካ ደረጃ ጭምር ዝቅተኛ ግብር በመሰብሰብ ነው። ስለዚህ እዚህ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ትልቅ ሥራ እየተሰራ ሲሆን እርምጃው ኤይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ከሚያተኩሩባቸው ነገሮች ጋር አብሮ የሚሄድ ነው። ቢቢሲ፡ እየወጡ ባሉት መረጃዎች መሰረት ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ እንዳለ ከፀደቀ የብዙ ነገሮችን ዋጋ የማናር አዝማሚያ ይኖረዋል የሚል ትልቅ ስጋት አለ። እርሶ እንዴት ነው አዋጁን የሚያዩት? ዶ/ር ነመራ፡ ምን አይነት ጫና ይኖረዋል የሚለውን አሁን መናገር ትንሽ ይከብደኛል። ረቂቅ አዋጁ ገና ብዙ መንገድ ያልፋል፤ ብዙ የሚቀየሩ ነገሮችም ይኖራሉ። ለምን አስፈለገ የሚለው ላይ ግን፤ ከምንልከውና ከምናስገባው ምርት ጋር በተያያዘም መንግሥት በጣም ዝቅተኛ ገቢ እየሰበሰበ ስላለ መሞላት ያለባቸው ክፍተቶች ስላሉ ነው ፖሊሲው የመጣው። ጫናው ግን ደሃው የህብረተሰብ ክፍል ላይ እንዳይሆን ጥንቃቄ ይደረጋል። ቢቢሲ፡ በአጠቃላይ አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ ብድር የሰጠው ፕራይቬታይዜሽንን ለማሳለጥ ነው ብለን መውሰድ እንችላለን? ዶ/ር ነመራ፡ የአይኤምኤፍ ብድር ፕራይቬታይዜሽን ላይ፣ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ እንዲሁም በብሔራዊ ባንክ የሚደረጉ አንዳንድ የፋይናንስ ፖሊሲ ማሻሻያዎች ገንዘብ ስለሚጠይቁ እዚያ ላይ ይውላል። ነገር ግን ይህ ዋነኛው ምክንያት ነው፤ ይሄኛው ሁለተኛ ነው የምልበት መመዘኛ ስለሌለኝ፤ ፕራይቬታይዜሽን ዋነኛው አጀንዳ ነው ማለት ይከብደኛል። ግን ሁለት ነገሮች ላይ ማለትም የመንግሥት የልማት ተቋማትን ማሻሻል እንዲሁም ወደ ግል ይዞታ ማዞር ላይ ትልቅ ሥራ እየተሰራ ነው። ቢቢሲ፡ ኢትዮጵያ ትልቅ የእዳ ጫና ያለባት አገር ናት፤ ከዚህ አንፃር የተጨማሪ ብድር አስፈላጊነት እንዴት ይታያል ? ዶ/ር ነመራ፡ የብድር ጫና የሚባለው መጠኑ አይደለም። ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ምጣኔ አንጻር ሲታይ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ብድሩ 60 በመቶ ጠቅላላይ የሀገር ውስጥ ምርት አይሆንም፤ ስለዚህ ይህ በራሱ ችግር አደለም። አሁን ኢትዮጵያ ላይ ትልቅ ችግር እየፈጠረ ያለው ብዙዎቹ የውጭ ብድሮች፤ በትልቅ የወለድ መጠን በአጭር ጊዜ የሚከፈሉ ሆነው መምጣታቸው ነው። የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ካየን ግን ዶላር የማግኘት አቅሙ በጣም ዝቅተኛ ነው። ችግሩ እዚህ ጋር ነው ያለው። • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከአይኤምኤፍ፣ ከአለም ባንክ፣ ከአውሮፓ ሕብረትና ሌሎች አገራት እየተደረጉ ያሉትን የብድር ድጋፎች በዝቅተኛ ወይም በዜሮ የወለድ መጠን የሚወሰኑ ናቸው። የምንመልስበት ጊዜም በረጅም ጊዜ ነው። የውጭ ምንዛሪ ላይ ጫና ሳይፈጥር ነው የሚከፍለው፤ ስለሆነም ከዚህ በፊት በከፍተኛ ወለድ ከቻይና የወሰድናቸውን ብድሮችም ወደ ዝቅተኛ ወይም ዜሮ ወለድ እንዲቀየሩ እያደረግን ነው። ይህ ኢትዮጵያ ላይ ያለውን ጫና እየቀነሰ ይሄዳል ከዚህ ወዲህም አካሄዱ በዚህ አንፃር ይሆናል። ቢቢሲ፡ መንግሥት እያደረገው ያለውን ማሻሻያ ተከትሎ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ብድርና ድጋፍ እየተገኘ ነው። ብድሩና እርዳታው የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት እና ሌሎች የኅብረተሰቡን ችግሮች ለመቅረፍ የሚረዱት እንዴት ነው? ዶ/ር ነመራ፡ የዚህ ሁሉ ማሻሻያ ዋና አላማ የግል ዘርፉን ምርታማነት ማሳደግ ነው። የዚህ ዘርፍ ምርታማነት ካላደገ ኢኮኖሚው ውስጥ የሥራ ፈጠራ እድሎችን ማስፋት አይቻልም። ኢትዮጵያን አንቆ የያዛት ትልቅ ነገር የግል ዘርፉ ምርታማነት ዝቅተኛ መሆን ነው። የጠቀስናቸው አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መጨረሻ ግብ የግሉን ዘርፍ ምርታማነት ማሳደግ ነው። በግብርና፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግ፤ በተለይ ደግሞ በአግሮ ኢንዳስትሪ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል። ለእነዚህ ዘርፎች ቅድሚያ መስጠት ያስፈለገው የሥራ መፍጠር አቅማቸው ታይቶ ነው። ጊዜ ሊወስድ ቢችልም በአጭርና መካከለኛ ጊዜ የሚደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ኅብረተሰቡን እንዲያግዙ የተቀመጡ ግቦች አሉ። ቢቢሲ፡ አገር በቀል ኢኮኖሚ ምንድን ነው? ዶ/ር ነመራ፡ የተለየ የኢኮኖሚ እሳቤ አይደለም ይልቁንም አሁን የምንከተለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ በመደመር እሳቤ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብን በመጠቀም ያለብንን የፖለቲካል-ኢኮኖሚ ችግሮች መፍታት አለብን የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ እሳቤ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፈው ሃያ ወራት እየተደረገ ያለው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ለውጥ መነሳሳት እና እሳቤው የመጣው ከዚሁ አንፃር ከአገር ውስጥ ነው። ለውጡ የውጭ ግፊት የወለደው ሳይሆን ከራስ የመጣ ስለሆነ ነው አጠቃላይ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተባለው። ቢቢሲ፡ ዋና ዋና ተብለው ሊገለፁ የሚችሉ የአገር በቀል ኢኮኖሚ እሳቤ መገለጫዎች አሉ? ዶ/ር ነመራ፡ ዋናው ነገር እሳቤው፣ ፍቃደኝነትና ተነሳሽነቱ የመንግሥት መሆኑ ነው። የኢኮኖሚ ጎኑን ብቻ ካየን ግን ሦስት ዋና ነገሮችን ይዞ ነው የተነሳው። የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር በጣም በሚያስፈራ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። የብድር ጫናው፣ የወጪ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ፣ የወጪ እና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን የፈጠረው መዛባት ትልቅ መሆን፣ በአገሪቱ የገንዘብ ፖሊሲ ምክንያት የገንዘብ ሥርዓቱ በጣም የቀጨጨ እንዲሁም ቁጠባና ኢንቨስትመንት መካከል ያለው ሚዛንም አስፈሪ ነበር፤ የሥራ አጥነትና የዋጋ ግሽበትን ካየን ነገሮች በጣም ከባድ ነበሩ። • ዝነኞቹ ቮልስዋገኖችና ድንቅ ታሪኮቻቸው የግል ዘርፉም በብዙ ማነቆዎች የተያዘ ነው የሚያበረታታው ነገር የለም። ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ከግንዛቤ ገብተው አገር በቀል ኢኮኖሚው ትኩረት ያደረገባቸው ዋንኛ ነገሮች ማክሮ ኢኮኖሚ ማኔጅመንቱ፣ የቢዝነስ ተነሳሽነቶችን ማምጣትና የኃይል እንዲሁም የሎጀስትክ ዘርፍ ላይ ማሻሻያ ማድረግ ናቸው። በዚህ ረገድ የማዕድን እና የቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ ትኩረት የሚደረግባቸው ናቸው። ቢቢሲ፡ ትልልቅ የውጭ ብድሮች በተቋማት የማስፈፀም አቅም ማነስና በሙስና የታለመላቸውን ዓላማ ሳያሳኩ ሲቀሩ ታይቷል። አሁን ኢትዮጵያ እያገኘች ካለችው ብድር ጋር በተያያዘ ይህ እንዳይሆን የሚያስችል ሥርዓት አለ? ዶ/ር ነመራ፡ እውነት ነው ይህ ትልቅ ስጋት ነው። የኢትዮጵያ ተቋማዊ ሥርዓት ጥራትና አቅም ማነስ በሙስናም ይሁን በሌላ ለሕዝብ ሃብት ብክነት ምክንያት ናቸው። አሁን ብዙ እየተባለ ያለው ስለ ፕራይቬታይዜሽን ብቻ ሆነ እንጂ በለውጡ እየተሰራ ያለው ትልቅ ነገር በመንግሥት እጅ ያሉና ትልቅ ሙስና እየተሰራባቸው ያሉ ድርጅቶች አስተዳደር ላይ ማሻሻያ ማድረግ ነው። [የማሻሻውን ውጤት ማየት ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም።] ቢቢሲ፡ በመሰረተ ልማት ግንባታ በብድርም ሆነ በንግድ ኢትዮጵያ ጠንካራ ትስስር የነበራት ከቻይና ጋር ነው። በአሁኑ ወቅት በተለይም ከለውጡ ወዲህ ኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ምዕራቡና አረቡ ዓለም አዙራለች። የቻይና አጋርነት እያበቃ ነው? ዶ/ር ነመራ፡ አንድ አገር ያላት የብድር፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ሁለት መልክ አለው። አንዱ በማስፋት፤ ሁለተኛው በጥልቀት መሄድ ነው። ከቻይና ጋር ባለፉት 15 ዓመታት በጣም በጥልቀት ነው የሄድንበት፤ አሁንም ኢትዮጵያ ይህንን ትታ ሌላ መፈለግ ላይ አይደለም ያለችው። ያለው ነገር ላይ መጨመር ማስፋት ነው እየተደረገ ያለው። አዲስ ምንጭ፣ አዲስ የንግድ አጋር የማፈላለግ ሥራ ነው እየተሰራ ያለው። እርግጥ ነው ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ ከምዕራቡና ከአረቡ ዓለምም ጋር ጥሩ ትስስር እየፈጠረች ነው። ቻይና አሁንም ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት አላት።
xlsum_amharic-train-188
https://www.bbc.com/amharic/news-50054045
'አይስታንድ ዊዝ አዲስ' እንቅስቃሴ
በአዲስ አበባ የባለ አደራ ምክር ቤት ለጥቅምት 2/2012 ዓ. ም ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መከልከሉን ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፉ ተሰርዟል።
[ "በአዲስ አበባ የባለ አደራ ምክር ቤት ለጥቅምት 2/2012 ዓ. ም ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መከልከሉን ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፉ ተሰርዟል።" ]
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ድጋፍ ሰኔ 16/2010 መስቀል አደባባይ የተደረገ ሰልፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን "በአዲስ አበባ ከተማ የተፈቀደም ሰልፍ ይሁን በሰልፉ የሚዘጉ መንገዶች የሉም" የሚለውን መግለጫ ተከትሎም ምክር ቤቱ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ "ለሃገሪቱ ሰላምና ለህዝቧ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሰልፉን ሰርዟል" ብሏል። ይህንንም ተከትሎ በትዊተር ላይ ""IStandWithAddis" በሚል ሃሽታግ ብዙዎች ተቃውሟቸውን አስፍረዋል። • "ለእናንተ ደህንነት ነው በሚል እንዳሰሩን ተገልፆልናል" የባላደራ ምክር ቤት አስተባባሪ • ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ ምንም እንኳን ትዊተር ላይ የሰፈሩት ሃሳቦች ከሰልፍ ክልከላው አልፎ ሌሎች ከአዲስ አበባ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ቢያንሸራሽርም ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ሃሽታጉን ተጠቅሞ ሲፅፍ በዋናነት ከሰልፉ መከልከል ጋር እንደሆነ ይናገራል። "አዲስ አበባ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ መደረግ አለበት። ይህ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው። መንግሥት መፍቀድ ብቻ ሳይሆን እንዲህ አይነት ሰልፍ ለሚጠሩ ቡድኖችም ሆነ ግለሰቦች ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት" ይላል። ለዚህም ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ህጎችም ሆነ ህገመንግሥቱን ዋቢ በማድረግ እነዚህ መብቶች እንዲከበሩ እንደሚያስገድድም ያስረዳል። የሃገሪቱ ህግ ሊከበር ይገባል የሚለው መስፍን፤ በህጉ መሰረት ሰላማዊ ሰልፍን እንዲከለክሉ መብት አይሰጣቸውም። "ግዴታ አለባቸው፤ በቸርነት የሚሰጡት መብት አይደለም፤ ይሄ የተጠራው ሰልፍ ሊያስደስተን ወይም ላያስደስተን ይችላል ቁም ነገሩ እሱ አይደለም" ይላል። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የመጡ መሻሻሎች እንዳሉ ሆነው፤ ሁሉም ነገር በአንድ ጊዜ ይስተካከላል የሚል እምነት እንደሌለው ይናገራል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የሰልፉ መከልከል ለመስፍን ባያስደነግጠውም እንዲህ አይነት ጥያቄዎችና ትችቶች የሚቀርቡበት ዋናው አላማ ያለው ነገር የበለጠ እንዲሻሻል ከመፈለግ ነው ይላል። "የዚህ ዋና አላማ ዜጎች የበለጠ መብት እያገኙ፤ የበለጠ ጥበቃ እየተደረገላቸው፤ መብቶቻቸውን መተግበር የሚችሉበት ሁኔታ እየሰፋ እንዲሄድ ነው" በማለት ያስረዳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመጡ በኋላ የተደረጉ ጥሩ መሻሻሎች የሚያሻሙ እንዳልሆኑ የሚናገረው መስፍን "እነዚህ ነገሮች ወደ ኋላ ሊመለሱ ይችላሉ። ወደ ኋላ መመለስ የለም የሚል በጣም አሳሳች ሃሳብ ውስጥ መገባት የለበትም" ይላል። •የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? •በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው በተለይም የሃገሪቱ ዋና ከተማ እንዲሁም የሃገር ውስጥም ሆነ ዓለም አቀፍ አትኩሮት ያለባት ከተማ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ አለመቻሉ በጣም ትልቅ ትርጉም እንዳለውም ይናገራል። የከተማ መስተዳድሩም ሆነ የፌደራል መንግሥት ወደፊት የሚመጡ የተቃውሞ ሰልፎችንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመፍቀድ ግዴታ እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥቶ ይናገራል። "ምንም አይነት ማብራሪያም ሆነ ምክንያት ብዙ ርቀት አያስኬድም። ለዚህኛው ሰልፍ መከልከል አንድ ምክንያት ሊሰጥ ይችላል። ከዚህኛው በኋላ ሌሎች የተቃውሞ ሰልፎች ሊመጡ ይችላሉ። ለሁሉም እንደዛ አይነት አንካሳ መልስ የሚሰጥ ከሆነ ወደነበርንበት ነው የምንመለሰው" ይላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊትም የተቃውሞ ሰልፍ እንጂ የድጋፍ ሰልፍ ይፈቀድ እንዳልነበር አስረድቷል። "መለኪያውም የተቃውሞ የፍቃድ ሰልፍ መፍቀድ ነው እንጂ ድጋፍ መፍቀድ አይደለም። ድጋፍማ የሚጠይቀው ነገር የለም" የሚለው መስፍን በተለይም በቀጣዩ ምርጫን ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ ባለችው ኢትዮጵያ የተለያዩ የተቃውሞ ድምፆች መድረክ ያስፈልጋቸዋል ይላል። "እየተደረገ ያለው ነገር በጣም አሳዛኝ ነው፤ ጥሩ ምልክትም አይደለም። በተለይም ከፊታችን ምርጫ ይመጣል እያልን የተቃውሞ ድምፆችን መታገስ፤ እነሱ እንዲደሰሙ እድል መስጠት ነው የሚያስፈልገው። በእንደዚህ አይነት ከቀጠልን ትንሽ መጥፎ ምልክት ሊሆን እንደሚችል እሰጋለሁ" ብሏል። • ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ የ "IStandWithAddis" ሀሽታግን በመጠቀም ተቃውሞውን የገለፀው ሌላኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ ዘላለም አባተ ነው። የሰልፉ መከልከል ሕገ መንግሥቱን እንደሚጻረር የሚናገረው ዘላለም፤ ተቃውሞውን ለመግለጽ የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄውን መቀላለቀሉን ያስረዳል። "ከተማዋ ላይ የነዋሪዎች መሰረታዊ መብቶች አይከበሩም" የሚለው ዘላለም ሰልፉ መከልከሉ በነጻነት የመናገር መብትን እንደሚገፍ ይገልጻል። የከተማዋ ነዋሪዎች ጥያቄ ሲኖራቸው ከማድመጥ ይልቅ የማዳፈን አዝማሚያ እንደሚስተዋልም ያክላል። "በአንጻራዊነት ሌሎች አካባቢዎች ላይ የሚታየው ነጻነት በአዲስ አበባ የለም። ሌሎች ቦታዎች ላይ የተፈቀዱና በሆደ ሰፊነት የሚታዩ ነገሮች አዲስ አበባ ላይ ግን መንግሥት አይታገሳቸውም" ሲል ይናገራል። የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በስፋት የተጋሩት ሀሽታግ በተለይም ካለፈው ዓመት ወዲህ የከተማዋ ነዋሪዎች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዳይገልጹ የተደረጉባቸው አጋጣሚዎች እየተደጋገሙ መምጣታቸው ነዋሪው የመገፋት ስሜት እንዲያድርበት ማድረጉን ይናገራል። በተለይም ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2012 ዓ. ም ከሰዓት እንዲሁም በነጋታው እሁድ እለትም ሀሽታጉን የትዊተር ተጠቃሚዎች በስፋት ሲጋሩት ነበር። በተለይም ከባላደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) ሕዝባዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ጋር በተያያዘ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለመቃወም ብዙዎች ሀሽታጉን ተጠቅመዋል። ግለሰቦቹ ከእሥር ከተፈቱ በኋላም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይከበር የሚል ጥያቄ በሀሽታጉ ተስተጋብቷል። ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንም በ "IstandWithAddis" ሀሳባቸውን ገልጸዋል። ከነዚህ አንዷ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው ኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርስቲ ፒኤችዲዋን እየሠራች ያለችው እየሩሳሌም አማረ ናት። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸው ይፋ በተደረገበት ማግስት አዲስ አበባ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ መከልከሉ "አሳፋሪ ነው" ትላለች። በርካቶች የኢትዮጵያ ስም በዓለም አቀፍ መድረክ በበጎ በመጠራቱ እና ጠቅላይ ሚንስትሩ ተሸላሚ በመሆናቸው ደስታቸውን ገልጸው ሳይጨርሱ፤ ሕዝባዊ ሰልፍ የመከልከሉ ዜና መሰማቱን እየሩሳሌም ትነቅፋለች። • "ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች • "የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ "ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ቅንጦት አይደለም። ተቃውሞ ሸሽቶ፣ ትችት ፈርቶ፣ ጥሩ ጥሩውን ብቻ አውሩ፣ አባብሉኝ አይነት መንግሥት ለጀመርነው እና ለምናራምደው ጥሩ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ ጉዞ አይጠቅምም" ስትል ታስረዳለች። አንጻራዊ ለውጥ አለ በሚባልበት በዚህ ወቅት ሕዝባዊ ሰልፍን መከልከል ተገቢ እንዳልሆነም ትናገራለች። የኖቤል ሽልማቱን በማስታከክ የተጠራ ሰልፍ እንዲካሄድ ተፈቅዶ፤ በተቃራኒው ከጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ. ም አስቀድሞ የታቀደ ሰላማዊ ሰልፍ መከልከሉ ትክክለኛ ውሳኔ አለመሆኑንም ታክላለች። የባልደራስ ምክር ቤት ከሰልፉ ቀን ቀደም ብሎ ለሚመለከተው አካል ሰልፍ እንደሚያካሂድ ማሳወቁን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ሲገልጽ ቢቆይም፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ ከታቀደው ሰልፍ አንድ ቀን ቀደም ብለው ቅዳሜ ዕለት ለቢቢሲ እንደገለፁት በከተማዋ ውስጥ የሚደረግ ሰልፍ እንደሌለ ተናግረው ነበር። እስካሁንም ሰልፉ በምን ምክንያት እንዳይደረግ እንደተከለከለ የተገለጸ ነገር የለም። ሰልፉ የተከለከለበትን ምክንያት ለመጠየቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በተደጋጋሚ ብንደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።
xlsum_amharic-train-189
https://www.bbc.com/amharic/news-56616311
የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ፍጥጫ ወዴት እያመራ ነው?
ሱዳን እና ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ለም በሆነው ለእርሻ ተስማሚው አልፋሽቃ የድንበር አካባቢ ይገባኛል በሚል ወታደራዊ ፍጥጫ ውስጥ ከገቡ ወራት ተቆጥረዋል።
[ "ሱዳን እና ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ለም በሆነው ለእርሻ ተስማሚው አልፋሽቃ የድንበር አካባቢ ይገባኛል በሚል ወታደራዊ ፍጥጫ ውስጥ ከገቡ ወራት ተቆጥረዋል።" ]
ሁለቱ አገራት ተፋጥጠው በሚገኙበት በዚህ የድንበር ይገባኛል ምክንያት ወደ ጦርነት መግባት እንደማይፈልጉ ቢገልፁም የሁለቱ አገራት ሠራዊት ግን በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ መግባታቸው ይሰማል። ሱዳን በትግራይ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ በአካባቢው ያለው የኢትዮጵያ ጦር ለቅቆ ሲወጣ ስፍራውን መቆጣጠሯ በወቅቱ ተዘግቧል። በፈረንጆቹ መጋቢት 20/2013 ሱዳን ትሪቢውን እንደዘገበው የሱዳንን አካባቢ ጥሰው ለመግባት የሞከሩ 200 ያህል የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ከሱዳን ጦር ጋር ተኩስ ገጥመው ሁለት ሰዎች ሞተዋል። ቀደም ብሎም በመጋቢት 14/2013 ደግሞ ይኸው መገናኛ ብዙሃን የሱዳን ወታደሮች ኢትዮጵያውያን ታጣቂዎችን በማጥቃት መሳሪያ መማረካቸውንና የግብርና መሳሪያዎች መውሰዳቸውን ዘግቧል። እነዚህ ግጭቶች እንዳሉ ሆነው ሁለቱ አገራት የድንበሩን ፍጥጫ በንግግርና ውይይት ለመፍታት ፈቃደኛ መሆናቸውን ይገልጻሉ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሱዳን ጋር ጦርነት እንዳማይፈልጉ ሲናገሩ ሱዳን በበኩሏ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የቀረበውን የማሸማገል ጥያቄ ተቀብለዋለች። የሱዳን ኢትዮጵያን ድንበር ግጭት የሚያቀጣጥለው ምንድን ነው? ሱዳን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1902 የተፈረመው የአንግሎ-ኢትዮጵያ የካርታ ላይ ምልከታ ስምምነት አልፋሽቃ የእኔ መሆኑን በእርግጠኝነት ያሳያል ስትል ትገልጻለች። አክላም በርካታ ኪሎ ሜትሮች የሚረዝመው የሁለቱ አገራት የድንበር አካባቢ በአግባቡ ባለመካለሉ ከ1980ዎቹ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ድንበሩን ዘልቀው ይገባሉ ስትል ትከስሳለች። የሱዳን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ድንበሩን ጥሰው ሲያልፉ እና ሰዎች ሲገደሉ፣ የአርሶ አደሮች እንስሳት ሲዘረፍ እና ሰዎች ሲታገቱ ችላ ብለዋል ተብለው ይወቀሳሉ። በዚህም የተነሳ በርካታ ሱዳናውያን አርሶ አደሮች አልፋሽቃ አካባቢን ጥለው ለመሄድ መገደዳቸው ይነገራል። ሁለቱ አገራት ለምን አሁን ጦራቸውን ወደ ድንበር አስጠጉ? በታኅሣሥ 06/2013 የኢትዮጵያውያን ታጣቂዎች አልፋሽቃን እየጠበቁ የነበሩ የሱዳን ወታደሮች ላይ የደፈጣ ጥቃት አድርሰው አራት ሱዳናውያን ወታደሮች መሞታቸው ካርቱም በድንበሩ አካባቢ በርካታ ጦሯን እንድታሰፍር አድርጓታል። ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ታኅሣሥ 21/2013 ደግሞ ሱዳን አጨቃጫቂውን የድንበር አካባቢ ሙሉ በሙሉ መቆጣጣሯን ገለፀች። ኢትዮጵያ የጦር ኃይሏ በትግራይ ክልል ውስጥ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ላይ በነበረበት ወቅት ሱዳን በአልፋሽቃ አካባቢ ላይ ወረራ በመፈፀም የበርካታ ገበሬዎች ንብረት እንዲወድም ማድረጓን ዜጎችም መፈናቀላቸውን በመጥቀስ ትከስሳለች። እንዲሁም ኢትዮጵያ በድንበር ፍጥጫው ውስጥ የሦስተኛ ወገን እጅ አለበት ስትል ትወነጅላለች። በመጋቢት 07/2013 የሱዳን ጦር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄነራል አብድል ፈታህ አል ቡርሐን ኢትዮጵያ አልፋሽቃ የሱዳን መሆኑን እስካልተቀበለች ድረስ ምንም ዓይነት ንግግር አይኖርም ብለው ነበር። ቡርሐን "በኢትዮጵያ ወገን ይህ የሱዳን ግዛት መሆኑ ተቀባይነት አግኝቶ ድንበሩ እስካልተሰመረ ድረስ ከማንም ጋር አንደራደርም" ማለታቸው ተሰምቷል። የሱዳን ሚዲያዎች ግጭቱን እንዴት ዘገቡት? የሱዳን የአገር ውስጥ ጣቢያዎች፣ የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና)፣ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣብያው፣ የሱዳን መከላከያ ኃይል ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግጭት ብዙ ጊዜ ባይዘግቡትም በግል የሱዳን መገናኛ ብዙሃን በኩል በሰፊው የሚዘገቡትን ደግሞ አያስተባብሉም። የሱዳን መከላከያ ኃይል የፌስቡክ ገጽ የአገሪቱ ወታደሮች መሳሪያቸውን እያወዛወዙ የጀግንነት ሙዚቃ ተከፍቶ ሲጨፍሩ ያሳያል። በየካቲት 04/2013 ሌተናል ጄነራል ያሲር አል አታ አልፋሽቃን በጎበኙበት ወቅት በአካባቢው የሚገኙትን ወታደሮች "ስንዝር የሱዳን መሬትን እንዳትሰጡ" ሲሉ ተናግረዋል። የሱዳን ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ኢትዮጵያ በአልፋሽቃ "ወረራ" ፈፀመች፤ እንዲሁም ግብጽ በማዕድን የበለፀገውን ሃላዬብ ትርያንግልን "ያዘች" ሲሉ ይጽፋሉ። የኢትዮጵያና የኤርትራ መገናኛ ብዙሃንስ እንዴት ዘገቡት? ኢትዮጵያውያን የድንበሩን ፍጥጫ እንደ ሱዳናውያን በሰፊው አይዘግቡትም። አብዛኛውን ጊዜ ስለአለመግባበቱ የሚጽፉ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚጠቅሱት የሱዳን ሚዲያዎችን ነው። ብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣብያም ሆነ የመንግሥት ደጋፊ የሆኑ መገናኛ ብዙሃን በድንበር ይገባኛሉ ላይ ለመነጋገር በቅድሚያ "ሱዳን ወደነበረችበት ትመለስ" የሚሉ የመንግሥት ባለስልጣናትን ብቻ ሲጠቅሱ ይስተዋላል። የኤርትራ ብሔራዊ ሚዲያ ፕሬዝዳንት ኢሳያስን ጠቅሶ ኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን "በእርጋታ እና በማስተዋል" እንዲፈቱ መጠየቃቸውን ዘግቧል። ሱዳን ኤርትራ የኢትዮጵያን ጦር ለመርዳት በድንበሩ አካባቢ ጦሯ ሰፍሯል ስትል ወንጅላለች። የድንበር ይገባኛል ግጭት የመቀስቀስ እድሉ ምን ያህል ነው? በአሁኑ ወቅት ሱዳን እና ኢትዮጵያ በድንበር ይገባኛሉ የተነሳ ወደ ጦርነት የመግባት እድላቸው አነስተኛ ነው። ሁለቱም አገራት በውስጣዊ አለመረጋጋት እየታመሱ ነው። የኢትዮጵያ ጦር ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ በተቀሰቀሰው ግጭት የተወጠረ ሲሆን በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችም ያሉ የበርካታ ንፁሃንን ሕይወት የቀጠፉ ብሔር ተኮር ጥቃቶችን ለመቆጣጠር እየታገለ ይገኛል። ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በሚደረግ ጦርነት ካርቱም ዳግም የህወሓትን ቅሪቶችን እንዳታስታጥቅ እና መጠጊያ እንዳትሰጣቸው ትሰጋለች። ሱዳን በአሁኑ ጊዜ የትግራይን ግጭት ሸሽተው ወደ ግዛቷ የገቡ ከ70 ሺህ በላይ ስደተኞችን ታስተናግዳለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መጋቢት 14/2013 በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙበት ወቅት "በአሁኑ ጊዜ ሱዳን ከጎረቤት አገር ጋር ጦርነት የምትገጥምበት ሁኔታ ላይ አይደለችም፤ የከፋ ችግር አለው። ኢትዮጵያም ብትሆን ከሱዳን ጋር ጦርነት ለመግጠም በርካታ [ውስጣዊ] ችግር አለባት" ብለው ነበር። ሱዳን አልበሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ በሁለት እግሯ ጠንክራ አልቆመችም። አገሪቱ አሁንም ከፍተኛ የሆነ የምጣኔ ሀብት ድቀት ላይ ትገኛለች። በቅርብ ጊዜ እንኳ የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች ውድነት፣ በዳርፉር የተከሰተው አለመረጋጋት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሱዳንን ፈትረው ከያዟት ጉዳዮች መካከል ናቸው። ቀጠናዊ ተፅዕኖው ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ከሱዳን እና ከግብጽ ጋር በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት ላይ እስካሁን ይህ ነው የሚባል መቋጫ ላይ አልደረሰችም። ሦስቱ አገራት ላለፉት አስር ዓመታት በግድቡ ላይ ሙሉ በሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም። ሱዳን በሕዳሴ ግድቡ ላይ ገለልተኛ ሆና የቆየች ቢሆንም የድንበር አለመግባባቱ ከተከሰተ በኋላ ግን አቋሟን ቀይራለች። ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወንዙን ተከትለው ለሚኖሩ 20 ሚሊዮን ሱዳናውያን የሕዳሴ ግድብ "ስጋት" መሆኑን ተናግረዋል። ግብጽ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት፣ አውሮፓ ሕብረት፣ አሜሪካ እና የአፍሪካ ሕብረት እንዲያደራድሩ ያቀረበችውን ጥያቄ ስትደግፈው ኢትዮጵያ ደግሞ ተቃውማዋለች። የካቲት 23/2013 ሱዳንና ግብጽ ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ይህም ሁለቱ አገራት ከማንኛውም ጊዜ በላይ ወዳጅነታቸውን እያጠናከሩ ለመሆኑ ማሳያ ሆኖ ይጠቀሳል።
xlsum_amharic-train-190
https://www.bbc.com/amharic/news-49418691
ባለማዕረግ ተመራቂው እና በ3ዲ ፕሪንተሩ የፈጠራ ሥራ ያሸነፈው መልካሙ
"በእውነቱ የተወለድኩበት ቦታ የመኪና ድምፅ ብቻ ነበር የሚሰማው፤ ያውም ትላልቅ መኪና ሲያልፍ" ይላል። የተወለደው በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ልዩ ቦታው ከላቻ የተባለ ሥፍራ ነው- የማዕረግ ተመራቂውና የዘንድሮው ሶልቭ አይቲ የፈጠራ ሥራ ውድድር አሸናፊ መልካሙ ታደሰ።
[ "\"በእውነቱ የተወለድኩበት ቦታ የመኪና ድምፅ ብቻ ነበር የሚሰማው፤ ያውም ትላልቅ መኪና ሲያልፍ\" ይላል። የተወለደው በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ልዩ ቦታው ከላቻ የተባለ ሥፍራ ነው- የማዕረግ ተመራቂውና የዘንድሮው ሶልቭ አይቲ የፈጠራ ሥራ ውድድር አሸናፊ መልካሙ ታደሰ።" ]
የመልካሙ ቤተሰቦች አርሶ አደሮች ናቸው። ያሉበት ነባራዊ ሕይወት ሳይበግራቸው እርሱም ሆነ ወንድሞቹ ማንኛውም የገጠር ተማሪ በሚያሳልፈው የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ አልፈው ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። እርሱ እንደሚለው የሚማሩበት ትምህርት ቤት የ40 ወይም 50 ደቂቃ መንገድ በእግር ያስጉዛል። ተራራና ሸለቆውን አቆራርጠው ነበር ትምህርት ቤት የሚደርሱት። የመንገዱ ርቀት ብቻ ሳይሆን በጠዋት ተነስቶ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ሥራዎችን (ላም ማለብ፣ ከብቶችን ማሰማራት) ማከናወንም ይጠበቅበታል። ይህን ማድረጉ ግን መልካሙን ከዓላማው አልገታውም። • የወንድሙን ገዳይ ለመበቀል ወደ ፈጠራ ሥራ የገባው ኢትዮጵያዊ በዚህ ሁኔታ እየተማረ ከክፍል ክፍል ሲዘዋወር የአንደኝነትን ደረጃ የሚወስድበት አልነበረም። ከዚያም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ መካኒካል ምህንድስና አጠና። በዚህ ዓመት በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብም በማዕረግ ተመርቋል። እውቀቱንና ችሎታውን ለማሳደግ ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች መካከል ሌሎችን ማስጠናት፣ ማስተማርና ማለማመድ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛሉ። ያወቀውን ለሌሎች ለማካፈል በሚያደርገው ጥረት ውስጥ እርሱ እንደሚማር ይገልፃል። "አባቴ በኢኮኖሚ አቅም ማጣት ምክንያት ነው ያልተማረው" የሚለው መልካሙ ቁጭታቸውን እርሱ እንዲወጣላቸው ግን አደራ ይሉት እንደነበር ይናገራል። በዚህም ምክንያት ወንድሞቹም ሆኑ አባቱ ባላቸው አቅም ሁሉ ድጋፍ ያደርጉለት ነበር። "አባቴ ውጤታማ ሆኜ በማየቱ እጅግ ደስተኛ ነው፤ ደስታውን ከወዳጆቹ ጋር ለመጋራት ድግስ ለመደገስ እየተዘጋጀ ነው" ይላል። አሁን ደግሞ ሶልቭ አይቲ ባዘጋጀው የፈጠራ ሥራ ውድድር አሸናፊ በመሆን ደስታቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎታል። የፈጠራ ሥራው ባለ ሦስት አውታር ማተሚያ (3ዲ ፕሪንተር) ነው። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ይህ ለዩኒቨርሲቲ መመረቂያ ፅሁፉ የወጠነው የፕሮጀክት ሃሳብ ነው። የሚሰሩ የፈጠራ ሥራዎች የማህበረሰቡን ችግሮች መፍታት አለባቸው ብሎ የሚያምነው መልካሙ በተማረበት ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ባለ ሦስት አውታር ፕሪንተር ባለመኖሩ ተማሪዎች ፕሮጀክቶቻቸውን ለመሥራት ሲቸገሩ ያስተውላል። በእርግጥ ይህ የማተሚያ ማሽን ገበያ ላይ አለ። መልካሙ እንደሚለው ግን ዋጋው ውድ በመሆኑ በቀላሉና እንደልብ በአገልግሎት መስጫ ተቋማት አይገኝም። ይህንን ችግር ለመፍታት የእርሱ የፕሮጀክት ሃሳብ አስፈላጊ እንደሆነ ያስረዳል። በተለይ የህንፃ ዲዛይነሮች እንዲሁም ሌሎችም ንድፋቸውን በእርሳስ ከመሳል ባሻገር የህንፃውን ምስል በሦስቱም ማዕዘን ቁልጭ ብሎ እንዲወጣ የሚያትሙበት ማሽን ነው። ሃሳቡ የመጣለትም ከዚሁ ችግር በመነሳት ነው። ከዚያም ከሁለት የዩኒቨርሲቲ ጓደኞቹ መንበሩ ዘለቀ እና መልካሙ ፈቃዱ ጋር በጋራ በመሆን የፈጠራ ሥራውን ማጎልበት ጀመሩ። በውድድሩ ለመጨረሻው ዙር ከቀረቡት 63 ሥራዎች መካከልም አንዱ ለመሆን በቃ። በሶልቭ አይቲ ፋውንዴሽን ሥልጠናዎችንና ልምዶችን ለመቅሰም እድል አገኙ። ይህም የፈጠራ ሥራቸውን በድል ለማጠናቀቅ መንገድ ከፈተላቸው። በመሆኑም የመልካሙና ጓደኞቹ የ3ዲ ፕሪንተር ፕሮጀክት በአንደኝነትን ደረጃ አጠናቋል። ፕሪንተሩ የተሰራው በአካባቢያቸው በቀላሉ ከሚገኙ ቁሳቁሶች ሲሆን ቤተሰቦቹና ዩኒቨርሲቲ በሚማርበት ጊዜ አማካሪው የነበሩት አቶ ሔኖክ እገዛ እንዳደረጉላቸው ሳይጠቅስ ግን አላለፈም። 3ዲ ፕሪንተር የዚህ ፕሮጀክት የቡድን መሪ የሆነው መልካሙ እንደሚለው ፕሪንተሩ አዲስ ግኝት አይደለም። ከውጭ አገር በአርባ ሺህ ብር መግዛት እንደሚቻል መረጃው ያለው ይሁን እንጂ የእነርሱ የፈጠራ ሥራ ጠቅላላ ወጪ በጥሬ ገንዘብ ሲገመት 6 ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ ነው የወሰደው። ማተሚያ ማሽኑ ባለሦስት አውታር ማተሚያው [3ዲ ፕሪንቲንግ]፤ የታዘዘውን ምስል በብዕር መሳይ ነገር የሚስል [CNC Plotting]፣ ሌዘሪንግ (በጨረር መሳይ ዘዴ) በአንድ ጊዜ ማከናወን የሚችል ነው። ከዚህም ባሻገር ማሽኑ ሦስት የኮምፒዩተር ቋንቋዎችን [C++C፣ Language and Machine language] በአንድ ጊዜ ማንበብ የሚችል ነው። "ፕሮጀክቱ ከባድ ነው፤ የተለያዩ የሙያ ዘርፎችን እውቀት የሚጠይቅ ነው" የሚለው መልካሙ የመካኒካል ምህንድስና፣ የኤሌክትሪካል ምህንድስና፣ የኤሌክትሮኒክ እውቀት፣ የሶፍትዌር፣ የኮምፒዩተር ኮዲንግ እውቀት ይጠይቅ እንደነበር ያስረዳል። • ሀና እና ጓደኞቿ የሠሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ ይህንን ጥምረት በእነዚህ ዘርፎች ላይ ከተሰማሩ ጓደኞቹ ጋር በመተባበር በመፍጠርና በኢንተርኔት ላይ ያሉ ሥልጠናዎችን በመከታተል ከግባቸው መድረስ እንዲችሉ አስተዋፅኦ አድርጎላቸዋል። "የአሜሪካ እና የጃፓን ኤምባሲ አምባሳደሮችም ይህንን በቀላሉ ከሚገኙ ቁሳቁሶች የተሰራውን ፕሪንተር ጎብኝተው መሥራቱን አረጋግጠዋል" ይላል መልካሙ። በዘንድሮው ውድድር ወደ 2800 የሚጠጉ ተወዳዳሪዎች ተመዝግበው 160 ወጣቶች ለመጨረሻው ዙር ውድድር የደረሱ ሲሆን ተወዳዳሪዎቹ በቡድንም በግልም እየሆኑ በአጠቃላይ 63 የፈጠራ ሥራዎችን አቅርበዋል። 3ዲ ፕሪንተር የፈጠራ ሥራም በአንደኝነት ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል። በአይኮግ ላብ ድርጅት የ100 ሺህ ብር ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ወደፊት ከሃገር ውስጥና ከውጭ አገር ያሉ ባለሃብቶች ጋር በመገናኘት የፈጠራ ሥራቸውን ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሚሰሩ መልካሙ ታደሰ ገልፆልናል። የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የአሜሪካና የጃፓን ኤምባሲ አምባሳደሮች፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና እንግዶች በተገኙበት በቃና አዳራሽ መካሄዱ ይታወሳል።
xlsum_amharic-train-191
https://www.bbc.com/amharic/news-55162971
የሕንድ አርሶ አደሮችን አመፅ ያጎላው የዕድሜ ባለፀጋው ፎቶ
በሕንድ ከሰሞኑ አንድ ልዩ ፖሊስ በያዘው ቆመጥ በዕድሜ የጠኑ አንድ አርሶ አደርን ሲደበድብ የሚያሳይ ምስል ህንዳውያንን አስደንግጧል።
[ "በሕንድ ከሰሞኑ አንድ ልዩ ፖሊስ በያዘው ቆመጥ በዕድሜ የጠኑ አንድ አርሶ አደርን ሲደበድብ የሚያሳይ ምስል ህንዳውያንን አስደንግጧል።" ]
አርሶ አደሩ ሲክ ተብሎ የሚጠራው እምነት ተከታይ ሲሆን ጭንቅላታቸውም ላይ ጥምጣማቸውን ሸብ አድርገዋል። ፎቶው የተነሳው ለፕሬስ ትረስት ኦፍ ኢንዲያ በሚሰራው የፎቶ ጋዜጠኛ ራቪ ቾድሃሪ ሲሆን በማኅበራዊ ሚዲያዎችም ላይ በርካቶች ተጋርተውታል። ከዚህም በተጨማሪ ፎቶው ለፖለቲካዊ አተካሮዎች ምክንያት ሆኗል። በአገሪቱ ያሉት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ምስሉን እንደ አባሪ በመጠቀም መንግሥት ተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት ያደርሳልም በማለት ለመተቸት ተጠቅመውበታል። በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ በኩሉ አርሶ አደሩ አልተደበደቡም፤ ወቀሳው ሐሰት ነው ይላል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች የሕንድን መዲና ዴልሂ መግቢያና መውጫዋን ተቆጣጥረውታል። ባለፉት ቀናትም የአርሶ አደሮቹ አመፅ ሕንድን በተቃውሞ አንቀጥቅጧታል። አርሶ አደሮቹ አገሪቷ በቅርቡ የተሻሻለው ሕግ ከጥቅማችን የሚቃረን ነው ይሉታል። በሕንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ኑሮና በድህነት ከሚኖሩ መካከል አርሶ አደሮች ዋነኞቹ ናቸው። ከዚህ ቀደም የመንግሥት ፖሊሲዎች በነፃ ገበያ እንዳይጎዱም ሲጠብቃቸው ነበር። ያ ግን አሁን ተቀይሯል። አዲሱ ሕግ ኮርፖሬሽኖችንና ከፍተኛ ገንዘብ ያላቸውን የሚጠቅምና ደሃ አርሶ አደሮችን አዘቅት ውስጥ የሚከት ነው ይላሉ። ከዚህ ቀደም መንግሥት የግብርና ዘርፉን ገበያውን ይቆጣጠረው የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ጊዜ ግን እሱ ቀርቶ አርሶ አደሮቹ በቀጥታ ከግል ሻጮች ጋር ዋጋ መደራደር ይችላሉ። አዲሱ ሕግ ከዚህ ቀደም ነጋዴዎች እህል ማከማቸት በወንጀል ይቀጣ የነበረውን በማሻሻል ማከማቸት ይችላሉ ይላል። በዚህም በወረርሽኝ ወቅት ነጋዴዎች ዋጋ እንዲጨምሩ የሚያስችል ዕድል ሰጥቷል። በሕንድ ከ86 በመቶ በላይ የሚሆኑት አርሶ አደሮች አነስተኛ መሬት ወይም ከሁለት ሄክታር በታች ያላቸው ናቸው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ በሆነበት ሁኔታ ጠቀም ባለና ለኑሯቸው በሚሆን ዋጋ ምርታቸውን ለትልልቅ ኩባንያዎች ለመሸጥ የመደራደሪያ አቅሙ የለንም ይላሉ። የግሉ ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ የዘርና የማዳበሪያን ዋጋ በመጨመር ኑሯቸውን ከባድ አድርጎታል። ከዚህ ቀደም መንግሥት ዝቅተኛ የዋጋ ድጋፍ የሚል ፖሊሲ የነበረው ሲሆን መንግሥት ሩዝና ስንዴ ለሚያመርቱ አምራቾች የሚሰጠው የዋጋ ነበረው። በአዲሱም ሕግ ይህንንም ድጋፍ ያጣሉ ተብሏል። መንግሥት በበኩሉ የግል ተቋማትን በግብርና ዘርፉ እንዲሳተፉ የፈቀደው ይህ ማሻሻያ አርሶ አደሮችን አይጎዳም በማለት ይከራከራል። ይህ ግን ከአርሶ አደሮቹ ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም። አርሶ አደሮቹን ሳያሳትፍ የወጣ ሕግ ነው በሚል አመፁን አቀጣጥሎታል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችም ወደ መዲናዋ ዴልሂ ያቀኑ ሲሆን በከተማዋ መግቢያ በኩልም እንዳይገቡ ለማድረግ መሰናክልም ተደርጎባቸዋል። አርሶ አደሮቹ በትራክተሮቻቸው ተጭነው እንዲሁም በእግራቸው ወደ መዲናወም ሲያቀኑ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶችና ልዩ የሠራዊቱ አባላትም ለማስቆም ሞክረዋል። በዚህም ከፖሊስ ጋር ከፍተኛ ግጭት ተፈጥሯል። በበርካታ አካባቢዎችም ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ በመርጨትና በውሃ በመበተን ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ለማድረግም ሞክሯል። ነጭ ፂማቸውን ያንዠረገጉት የሲክ እምነት ተከታዩ አርሶ አደርና የፖሊስ ቆመጥ ይዞ ሊመታቸው ሲሰነዝር የሚታየው የልዩ ፖሊስ አባል ፎቶ የተነሳውም በባለፈው ሳምንት አርብ ነው። ተቃዋሚ አርሶ አደሮቹ በሰሜናዊ ምዕራብ ደልሂ በኩል በሲንኩ ድንበር በኩልም የተቀመጠውን መሰናክልም በማለፍ ወደ ከተማዋ ገብተዋል። "ከፍተኛ የሆነ የድንጋይ መወራወር ነበር፤ ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ የተቀመጡ መሰናክሎች ተሰብረዋል። አውቶብስ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በፖሊስና በተቃዋሚ አርሶ አደሮችም መካከል ከፍተኛ ግጭት ነበር" በማለት የአርሶ አደሩን ፎቶ ያነሳው የፎቶ ጋዜጠኛው ራቪ ቾድሃሪ ቡም ላይቭ ለተባለ ድረ ገፅ ተናግሯል። ፎቶ አንሺው ፖሊሶች አርሶ አደር ተቃዋሚዎችን መደብደብ መጀመራቸውንና በፎቶው ላይ ያሉት የዕድሜ ባለፀጋ አርሶ አደርም ተደብድበዋል ይላል። ፎቶው በትዊተር፣ ፌስቡክና ኢንስታግራም ማኅበራዊ ድረገፆች አማካኝነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አጋርተውታል። በርካቶችም በፎቶው ስር እንደ የጽሁፍ መግለጫ ያስቀመጡት "ጃይ ጃዋን፣ ጃ ኪሳን" የሚል ሲሆን ትርጉሙም "ክብር ለወታደሩ፤ ክብር ለአርሶ አደሩ" የሚል ነው። ይህ መፈክር በጎሮጎሳውያኑ 1965 በሕንድና በፓኪስታን በተደረገው ጦርነት ላይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ላል ባሃዱር ሻስትሪ የተጠቀሙበት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በወቅቱ በአገር ግንባታ ላይ ወታደሮችና አርሶ አደሮች ያላቸውን አስተዋፅኦም አፅንኦት ለመስጠት ነው። በምክር ቤቱ የተቃዋሚዎች ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑት ራውል ጋንዲም ፎቶውን በትዊተር ገፃቸው ለጥፈዋል። "በጣም አሳዛኝ ፎቶ ነው። መፈክራችን ክብር ለወታደሩ፣ ክብር ለአርሶ አደሩ ነበር። ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ እብሪተኝነት አርሶ አደሩ ከወታደሩ ጋር እንዲፋጠጥና እንዲጋጭ አድርጎታል። ይህ አደገኛ ነው" በማለትም የምክር ቤት አባሉ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። የገዢው ፓርቲ ቢጄፒ አመራር የሆኑት አሚት ማልቪያ በበኩላቸው ተቃዋሚውን ራውል ጋንዲን ለማሳጣት በሚል አርሶ አደሩ አልተመቱም፤ ፕሮፖጋንዳም ነው ብለውም የሶስት ሰኮንዶች ቪዲዮ በትዊተር ገፃቸው አጋርተው ነበር። ሆኖም በመጨረሻ የእሳቸው ትዊት ፕሮፖጋንዳ እንደሆነ ታወቀ። ትዊተር በኩሉ ቪዲዮው ተጨማሪ ነገሮች ገብተውት ለማስመሰል የተሰራ ነው ብሏል። እውነተኛ መረጃዎችን በማደን የሚታወቀው ቡምላይቭ የተሰኘው ድረገፅ የክስተቱን ረዘም ያለ ቪዲዮና በፎቶው ላይ ያሉትን አርሶ አደር ሱክዴቭ ሲንግን ፈልጎም በማግኘት ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል። አርሶ አደሩ በአንድ ፖሊስ ብቻ ሳይሆን በሁለት ፀጥታ ኃይሎች እንደተደበደቡና በዚህም ምክንያት ግንባራቸው፣ ክርናቸው፣ ጀርባቸው፣ እግራቸውና የባታቸው ጡንቻ መጎዳቱን እንደተናገሩም ቡምላይቭ ዘግቧል። በሺዎች የሚቆጠሩ የዕድሜ ባለፀጋ አርሶ አደሮች የምግብ ማዕከል በሚባሉት ፑንጃብና ሃርያና ግዛቶች ለተቃውሞ ወደ መዲናዋ መጥተዋል። እነዚህ የዕድሜ ባለፀጎች አስለቃሽ ጋዝ ሲረጭባቸው፣ አገሪቱ ውስጥ ያለው አጥንት ሰብሮ የሚገባ ብርድ ባለበት ወቅትም ውሃ ሲርከፈክፋባቸው ማየት በርካቶቸን አሳዝኗል። በሕንድ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ አገራት ያሉ ሕንዳውያንንም ልብ ሰብሯል። በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ፣ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሕንድ ለተቃዋሚ ሰልፈኞቹ የሰጠችው ምላሽ ስጋት እንዳሳደረባቸው ተናግረዋል። አገራቸው "ሁልጊዜም ቢሆን ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን መብት ለመደገፍም ትቆማለች" ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተያየት ግን የሕንድን መንግሥት አላስደሰተም። የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የመረጃ እጥረት ያለበትና "መሰረተ ቢስ" ሲሉም አጣጥለውታል። ሚኒስትሩ ይህንን ይበሉ እንጂ የአርሶ አደሮቹ ተቃውሞ ዓለም አቀፍ ድጋፍን አግኝቷል። ይህንንም ተከትሎ ባለስልጣናቱ አርሶ አደሮቹ ከመንግሥት ሚኒስትሮች ጋር ውይይት እንዲያደርጉ በሚል በጋበዙዋቸው መሰረት ማክሰኞ እለት የተደረገውም ውይይት ፍሬ አልባ ሆኗል። ሁለተኛ ውይይትም ሐሙስ እለት ይካሄዳል ተብሏል። አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው በከተማዋ ድንበር በተለያዩ አካባቢዎች መጠለያ የሰሩ ሲሆን ባለስልጣናቱ ይህንን "መጥፎ ሕግ" እስከሚያስቀሩት ድረስ እንቆያለን ብለዋል። አርሶ አደሮቹ እንደሚሉት "ለረዥሙ ትግል" ተዘጋጅተው መጥተዋል። ሩዝ ጨምሮ በርካታ የእህል ክምችታቸውን ጭነው እንዲሁም ምግብ ማብሰያ ብረት ድስትም ሆነ መጥበሻ ይዘን ነው የመጣነው ተብሏል። አርሶ አደሮቹ እንዳሉት ትግሉ ረዥም ይሆን አይቀርም።
xlsum_amharic-train-192
https://www.bbc.com/amharic/news-53121216
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ያስተጓጎለው የኢትዮጵያ የካንሰር ህክምና
የ33 ዓመቷ ሸምስያ ጀበል ተወልዳ ያደገችው ደሴ ነው። ወሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ምግብ ቤት ትሠራ ነበር። አምና የመጀመሪያ ልጇ ሲታመምባት ለህክምና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ተላከች። የአራት ዓመት ልጇ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተደረገለት ምርመራ የደም ካንሰር እንዳለበት ተነገራት።
[ "የ33 ዓመቷ ሸምስያ ጀበል ተወልዳ ያደገችው ደሴ ነው። ወሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ምግብ ቤት ትሠራ ነበር። አምና የመጀመሪያ ልጇ ሲታመምባት ለህክምና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ተላከች። የአራት ዓመት ልጇ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተደረገለት ምርመራ የደም ካንሰር እንዳለበት ተነገራት።" ]
በኮሮናቫይረስ ምክንያት በተለያዩ የህክምና አገልግሎቶች ላይ ጫና ተፈጥሯል ሸምሲያ ይህን ስትሰማ ዙሪያው ገደል እንደሆነባት ታስታውሳለች። ልጇን የምታሳክምበት ገንዘብ አልነበራትም። የሚደግፋትም ሰው አልነበረም። የካንሰር ህክምና ደግሞ እጅግ ውድ ነው። ልጇ የደም ካንሰር እንዳለበት በተነገራት በአንድ ወሩ፤ የልጇ አባት ‘አቅሜ አይችልም’ ብሎ ጥሏት እንደሄደ ትናገራለች። በወቅቱ የወር ከ15 ቀን ነፍሰ ጡር ነበረች። “ልጄ ደም በየጊዜው [ኬሞ ቴራፒ] ይወስዳል። ታዲያ የማሳክምበት ብር ጨርሼ ህክምናውን አቋርጬ ልሄድ ነበር። ጥቁር አንበሳ ያሉ ሀኪሞች ግን የካንሰር ህሙማንን የሚደግፍ ማኅበር አገናኙኝ። እዚህ ማኅበር ባልገባ ልጄ በሕይወት አይኖርም ነበር።” ሸምሲያ ማረፊያ ካገኘች በኋላ ለልጇ ህክምና መከታተል ከቀጠለች ሰባት ወራትን አስቆጥራለች። አሁን ግን መላው ዓለምን ያመሰቃቀለው ኮቪድ-19 የሸምስያም ስጋት ሆኗል። ልጇን ለማሳከም ወደ ሆስፒታል በሄደች ቁጥር በበሽታ ይያዝብኝ ይሆን ብላ ትሳቀቃለች። ሁለተኛ ልጇን ከወለደች አራት ወር ሆኗታል። የካንሰር ታማሚ ልጇን ይዛ ወደ ጥቁር አንበሳ ስትሄድ ሁለተኛ ልጇንም አስከትላ ነው። “. . . ህጻኑን የአራት ወር ልጄን ይዤ ነው የምሄደው። እና እንዴት እንደምጠነቀቅ ራሱ ግራ ይገባኛል። ካንሰር የሚታመመው ልጄ ደግሞ ቀልቃላ ነው። እሱን መከታተል እንዴት ከባድ መሰለሽ። እሱን አሳክሜ እስክመለስ ይጨንቀኛል። እዚ [ማኅበሩ ውስጥ] አልኮል አለ፤ እጃችንንም ስለምንታጠብና አጠቃላይ ጥንቃቄውም የተሟላ ስለሆነ ይቀለኛል። ስወጣ ግን ከማኅበረሰቡ ጋር መቀላቀል ራሱ በጣም ያስፈራል።” እንደ ሸምስያ የካንሰር ታማሚ ልጅ የሚያስታምሙ እንዲሁም የተለያየ አይነት የካንሰር ህመም ያለባቸው ሰዎችም ስጋቷን ይጋራሉ። በተለይም ካንሰር፣ ስኳር፣ አስም፣ ደም ግፊትና ሌላም ህመም ያለባቸው ሰዎች ለኮቪድ-19 ተጋላጭ መሆናቸው ፍርሀታቸውን ያባብሰዋል። ሸምስያ ልጇን በየ15 ቀኑ ወደ ጥቁር አንበሳ ትወስዳለች። ኮሮናቫይረስ ያለበት ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደተገኘ ከተገለጸ ወዲህ እያንዳንዱ የሐኪም ቤት ቀጠሮ ለሸምስያ ጭንቅ ነው። “ካንሰር ጊዜ የሚሰጥ በሽታ አይደለም። ቀጠሮ አይዘለልም። በመመላለሴ ደስተኛ አይደለሁም። ግን ደግሞ መመላለስ ግዴታዬ ነው። ለምን ብትይ ካልሄድኩ ልጄ ይሞታል። ከዚህ በፊት አብረውኝ የኖሩ ሰዎች የልጆቻቸውን ሕይወት ሲያጡ አይቻለሁ. . . በተቻለኝ አቅም ራሴን እየጠበቅኩ ልጄን እያሳካምኩ እመጣለሁ። እንግዲህ ፈጣሪ ከጎኔ ይሁን።” በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል ምልክት የማያሳዩ መኖራቸውን ስታስብ ፍርሀቷ ይጨምራል። ሆስፒታል ውስጥ የምታሳልፈው እያንዳንዱ ሰዓት ያሳስባታል። “ወረፋ አለ፣ ደም ሊያስፈልገው ይችላል። ለምሳሌ ቀይ ደም ስድስት ሰዓት ከተሰጠው እስከ ዘጠኝ ሰዓት መቆየት አለበት። መቼም ሐኪም ቤት በጣም ብዙ ሰው ነው ያለውና በጣም ነው የምፈራው።” ሸምስያ ከሁለቱ ልጆቿ ጋር የምትኖርበት ማቲዎስ ወንዱ የካንሰር ማዕከል ውስጥ የማህጸንና የጡት ካንሰር እንዲሁም ሌላ አይነት የካንሰር ህመም ላለባቸው ድጋፍ ይደረጋል። የማዕከሉ የፕሮግራም ኃላፊ አቶ ዘላለም መንግሥቱ እንደሚሉት፤ ኮቪድ-19 ለካንሰር ህሙማንና ቤተሰቦቻቸው ተደራቢ ፈተና ሆኗል። የካንሰር ህሙማን በሽታ የመከላከል አቅማቸው አነስተኛ በመሆኑ ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው። በበሽታው ከተያዙም ተቋቁሞ ለመዳን ይቸገራሉ። በሌላ በኩል አዲስ አበባ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። የካንሰር ህሙማን ደግሞ ጥቁር አንበሳ ለሚያደርጉት ህክምና ወደ አዲስ አበባ መምጣት ግድ ስለሚላቸው አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ ይናገራሉ። ሌላው ፈተና የህክምና ተቋማትና ባለሙያዎች አብዛኛውን ትኩረታቸውን ወደ ኮቪድ-19 ማድረጋቸው ነው። “ጥቁር አንበሳ መጀመሪያ ላይ ቀጠሮ በማራዘም፣ ታካሚዎች ባሉበት ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ጀምረው ነበር። ቀጠሮ ሲራዘም ቶሎ መድኃኒትና ህክምና ማግኘት ያለበት ታካሚ ይጎዳል። በሽታውን ከፍ ወዳለ ደረጃም ይወስደዋል። ወረርሽኙ ከሌሎች ህሙማን በበለጠ የካንሰር ህሙማን ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍ ያለ ነው” ይላሉ አቶ ዘላለም። ካንሰር ዘላቂ የሐኪም ክትትል (ቼክአፕ) እንዲሁም ህክምና የሚያስፈልገው ህመም ነው። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ከቤት መውጣት መቀነስ፣ አካላዊ ርቀት መጠበቅም አስፈላጊ መሆኑ እሙን ነው። የካንሰር ታማሚዎች ወደ ህክምና መስጫ መሄድ ግዴታቸው ስለሆነ ከቤት በወጡ ቁጥር መጨነቃቸው አይቀርም። • ዴክሳሜታሶን ምን ያህል አስተማማኝ ነው? ኢትዮጵያ ውስጥስ ይገኛል? አቶ ዘላለም እንደሚሉት፤ በአንድ ክፍል ውስጥ የሚሰበሰቡ ሰዎችን መቀነስ ስለሚያስፈልግ ማዕከላቸው የሚቀበለውን የህሙማን ቁጥር ቀንሷል። ቀድሞ በአንድ ክፍል እስከ ስድስት ሰው ይይዝ የነበረን ክፍል ወደ አንድ ታካሚና አስታማሚ ለመቀነስ ተገደዋል። “ሌላው ችግር የትራንስፖርት ዋጋ መጨመሩ ነው። ይሄ ከባድ ጫና ፈጥሮባቸዋል። ካንሰር ረዥም ጊዜ የሚወስድ ህክምና በመሆኑ ታካሚና ቤተሰብም ከባድ ሥነ ልቦናዊ ጫና ውስጥ ይገባል። አሁን ያለው ሁኔታ ደግሞ ነገሮችን አባብሷል” ሲሉ ያስረዳሉ። ተደራራቢ ጫና ካንሰር ሥነ ልቦናዊና ማኅበራዊ ጫና የሚያሳድር የገንዘብ አቅምን የሚፈትንም ህመም ነው። በዚህ ላይ ኮቪድ-19 ሲጨመር ደግሞ ችግሩ ይባባሳል። ፈተናው እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ብቻ አይደለም። የተሻለ የምጣኔ ኃብት ደረጃ ላይ መድረሳቸው የሚነገርላቸው አገሮችም እየተፈተኑ ነው። በተለያዩ አገሮች የተሠሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ኮሮናቫይረስ ከሚያሳድረው ተጽዕኖ ባልተናነሰ ሁኔታ በወረርሽኙ ሳቢያ የሚመጡ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሕይወት ያሳጣሉ። ለምሳሌ በቫይረሱ ሥርጭት ሳቢያ አገራት በረራ ላይ እገዳ በመጣላቸው፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት የሚያስፈልጋቸውን ክትባት ማግኘት አልቻሉም። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፤ ወረርሽኙ ቢያንስ የ68 አገሮችን የጤና ዘርፍ ስለሚያቃውስ፤ 80 ሚሊዮን ጨቅላዎች ክትባት ባለማግኘት ለኩፍኝ፣ ፖሊዮና ሌሎችም በሽታዎች ይጋለጣሉ። የምግብ እርዳታ ወደሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ማድረስ ባለመቻሉም ለምግብ እጥረት ተጋላጭ የሆኑ አሉ። የዓለም አቀፉ የምግብ ተቋም ዋና ኃላፊ ዴቪድ ቢስሊ፤ ዓለም ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው አይነት ቸነፈር ይጠብቃታል ብለዋል። 130 ሚሊዮን ሰዎች ለዚህ ተጋላጭ ናቸው። አሁን ላይ 135 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል። በሌላ በኩል የሥነ ተዋልዶ ጤና፣ የአዕምሮ ጤና፣ ካንሰር እንዲሁም ሌሎችም መደበኛ የህክምና ክትትሎችም ችላ ተብለዋል። በመላው ዓለም ያሉ የካንሰር ህሙማን፣ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው፣ አስቸኳይ ቀዶ ህክምና የሚሹ ሰዎችም ሰሚ አጥተናል እያሉ ነው። አቶ ዘላለም እንደሚሉት፤ አሁን ላይ አጠቃላይ የህክምና ዘርፉ ወደ ኮቪድ-19 መዞሩ የካንስር ህክምና ላይ ጫና አሳድሯል። “በፊትም እንደ ካንሰር ያሉ ህመሞች ጫና አለባቸው። አሁን ደግሞ የበለጠ ተጽዕኖው እየተሰማን ነው” ይላሉ። • የኮሮናቫይረስ ዘመኗ እመጫት ኢትዮጵያዊት የአራስ ቤት ማስታወሻ • ከባድ የጤና ችግር ኖሮባቸው ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ታሪክ ያለው ተደራራቢ ጫና ታማሚዎች ህክምና እንዲያቋርጡ እንዳያረጋቸው አቶ ዘላለም ይሰጋሉ። “ካንሰር ከጊዜ ጋር የሚሄድ በሽታ ነው። ቶሎ ታክሞ ውጤቱን ማሻሻል ካልተቻለ ወደከፋ ደረጃ ይደርሳል። በዛ ላይ ለ100 ሚሊዮን ሕዝብ ያለው ማዕከል አንድ ጥቁር አንበሳ ነው። የቅዱስ ጳውሎስ እና የዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎቹ (ጎንደር፣ ጅማ፣ ዓለማያ፣ሐዋሳ፣ ሀሮማያ) ማስፋፊያ ሲጠናቀቅ ነገሮች ይሻሻሉ ብለን እንጠብቃለን” ሲሉ ያስረዳሉ። በኮቪድ-19 ምክንያት እስካሁን የካንሰር መድኃኒቶች እጥረት ባይፈጠርም፤ ለዓመታት ሲነሱ የነበሩት የመድኃኒቶች ውድነትና እንደልብ ያለመገኘት ጥያቄዎች አሁንም እንዳልተመለሱ አቶ ዘላለም ይናገራሉ። ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት አለመቻሉ ካንሰር የተባባሰ ደረጃ ላይ ሲደርስ ህክምናው የበለጠ አስቸጋሪ ስለሚሆን፤ ሰዎች በጊዜ ህክምና እንዲጀምሩ ይመከራል። ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ የጡትና የማህጸን ጫፍ ካንሰር የመሰሉትን ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። ለዚህም ካንሰር ላይ የሚሠሩ ተቋሞችና ማኅበራት በየጊዜው የግንዛቤ ማስጨበጫ ያዘጋጃሉ። አሁን ግን መሰል መድረኮችን ለማሰናት አስቸጋሪ ነው። ይህም ካንሰር የሚመረመሩ ሰዎችን ቁጥር እንደሚቀንሰው አቶ ዘላለም ይናገራሉ። “የጤና ባለሙያዎች አሁን ከቤት ቤት እየተዘዋወሩ ሙቀት እየለኩ፣ ስለ ኮሮናቫይረስ ግንዛቤ እየሰጡ ነው ያሉት። እና በዚህ ወቅት ስለ ጡት ካንሰር ባወራ የሚሰማኝ የለም።” በዚህ ምክንያት ቶሎ ተገኝተው ህክምናቸው ሊጀመር የሚገባ በሽታዎች እንደሚባባሱ አቶ ዘላለም ያስረዳሉ። ዩናይትድ ኪንግደምን እንደምሳሌ ብንወስድ አገሪቱ በኮቪድ-19 ምክንያት እንቅስቃሴን ስትገታ የካንሰር ምርመራ ቆሟል። የአገሪቱ የካንሰር ማዕከል እንዳለው ይህ ማለት ቀድሞ በየወሩ ይገኙ የነበሩት 1,600 የካንሰር ህሙማን አሁን በሽታቸው አይታወቅላቸውም ማለት ነው። በዩኬ ህሙማን ከቤታቸው እየወጡ ስላልሆነ መደበኛ ምርመራ ማቆማቸው ሌላው ስጋት ነው። አንድ የአገሪቱ የካንሰር ሐኪም እንደሚሉት፤ ሕክምና በመጓተቱ ሳቢያ ወደ 60 ሺህ ሰዎች ይሞታሉ። አቶ ዘላለም እንደሚሉት፤ አሁን ላይ ሰዎች የካንሰር ምልክት ቢያዩ ወደ ህክምና መስጫ ላይሄዱ፣ ሄደውም አፋጣኝ ምላሽ ላያገኙ ይችላሉ። ይህ ደግሞ ለበሽታው ህክምና መሰጠት ያለበትን ጊዜ ያዘገየዋል። “በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ መድኃኒትና ኬሞቴራፒ ውድ በሆነበት አገር፣ ራድዮቴራፒ በአንድ ማዕከል ብቻ ስለሚሰጥ ወረፋ ለሚጠበቅበት አገር በአፋጣኝ ህመሙ ተገኝቶ ህክምና መገኘት አለበት። ደረጃው በጨመረ ቁጥር አክሞ ለማዳን ከባድ ይሆናል።” መፍትሔው ምንድን ነው? ካንሰር በግለሰቦች ብቻ ሳይሆን በአገር ማኅበራዊ መዋቅርና ምጣኔ ኃብት ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚያሳድር አቶ ዘላለም ይናገራሉ። የካንሰር ህክምና በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሚደርስበት ተጽዕኖ መፍትሔው ምንድን ነው? የሚለውን በቀላሉ መመለስ አይቻልም ይላሉ። ችግሩ ውስስብ መሆኑ ግልጽ መፍትሔ ማስቀመጥን አስቸጋሪ ቢያደርገውም፤ በጤናው ዘርፍ የሚተላለፉ ውሳኔዎች የካንሰር ህክምናን ታሳቢ ማድረግ አለባቸው ይላሉ። “የሆነ ተዓምራዊ መፍትሔ የለውም። ከማኅበረሰቡ ጀምሮ ብዙ ሥራ ያለበት ጉዳይ ነው። ሆኖም የጤና ውሳኔዎችና ፕሮግራሞች ካንሰርን ከግምት ማስገባት አለባቸው” ሲሉም ያስረዳሉ።
xlsum_amharic-train-193
https://www.bbc.com/amharic/news-55056386
"ጌም፣ ስልክና ቲቪ የልጆችን የአእምሮ ዕድገት እያቀጨጩ ነው"-ተመራማሪዎች
የኮምፒዩተር እና ሞባይል ስልክ ላይ የሚጫኑ ጌምዎች እና ቴሌቪዥን የልጆችን የአእምሮ ዕድገት እያቀጨጩ ነው ሲሉ ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ።
[ "የኮምፒዩተር እና ሞባይል ስልክ ላይ የሚጫኑ ጌምዎች እና ቴሌቪዥን የልጆችን የአእምሮ ዕድገት እያቀጨጩ ነው ሲሉ ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ።" ]
"በልጆቻችን ላይ እየፈጸምነው ያለው ግፍ ይቅር የማይባል ነው" ይላሉ ሚሸል ደስመርጌት። እኚህ ሰው ፈረንሳዊ ሳይንቲስት ናቸው። ከሰሞኑ ዓለምን እያነጋገሩ ነው። በተለይም በትውልዶች የአእምሮ ምጥቀት ዙርያ በጻፉት መጽሐፍ ነው እያነጋገሩ ያሉት። "በዚህ ዘመን የሚወለዱ ልጆችን ድንዙዝ እያደረግናቸው ነው፤ ይህም የሚሆነው ብዙ ጌሞችን፣ ብዙ የስክሪን ሰዓቶችን ስለፈቀድልናቸው ነው፤ ሳናውቀው ስንፍናን እያወረስናቸው ነው" ይላሉ። ፕሮፌሰር ሚሸል የኒውሮሳይንስ ሊቅ ናቸው። ዘለግ ላሉ ዓመታት በጉዳዩ ዙርያ ጥናት አድርገው የደረሱበት ሐቅ አንድ ነው። ይህም በዲጂታል ዘመን የተወለዱ ልጆች የአእምሮ ምጥቀት ልኬታቸው (IQ) በሚያስደነግጥ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መሆኑን። ብዙ ወላጆች በተቃራኒው ያስባሉ። ለልጆቻቸው ጌምና ስልክ በገፍ ያቀርቡላቸዋል። ልጆቻቸው ስልክ ነካክተው በራሳቸው መክፈታቸው የአእምሮ እድገት ልቀት መስሎ ይታያቸዋል። "ልጄን እኮ…" ብለው ማዳነቅ የሚወዱ ወላጆች ብዙ ናቸው። ልጆቻቸው ፊልም ተመልከተው መሳቃቸው በራሱ የብልህነታቸው ማሳያ ያደርጉታል። በመላው ዓለም ልጆች ረዥም ሰዓት በዲጂታል ዓለም ውስጥ ቀልባቸው ይሰወራል። ይህ እንዲሆን የፈቀደው ትውልድ በልጆቹ ላይ ይቅር የማይባል ግፍ ነው እየፈጸመ ያለው ይላሉ ፕሮፌሰር ሚሸል። የዲጂታል ቁሶች (ስልክ፣ ጌም፣ ቴሌቪዥንና የመሳሰሉት) የልጆችን የአእምሮ ዕድገት እያቀጨጩ ነው ባይ ናቸው ፕሮፌሰሩ። እኚህ ጎምቱ ሳይንቲስት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት ልጆችን ዲጂታል በማድረግ ሳናውቀው "መጪ ዘመናቸውን እያጨለምነው ነው" ብለዋል። አሁን የእሳቸው ሐሳብ በሳይንስ ማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ክርክር ቀስቅሷል። በቅርብ ለንባብ ባበቁትና ከፍተኛ ሽያጭ ባስመዘገበው መጽሐፋቸው በዲጂታል ቁስና በልጆች ዙርያ የነበረውን ሙግት ሌላ ደረጃ አድርሰውታል። የመጽሐፋቸው ርዕስ በራሱ የፕሮፌሰሩን ቁጣ ያዘለ ነው። "The Digital Cretin (or Idiot) Factory" ይላል። "ዲጂታሉ ዓለም፡ የድድብና ፋብሪካ" ብለን ወደ አማርኛ ልንመልሰው እንችላለን። ርዕሱ ለገበያ የተቃኘ ቢመስልም ሳይንቲስቱ ሙግታቸውን በደረቅ የሳይንስ ሐቆች አስደግፈው፣ ሳይንሳዊ ቅቡልነቱን ጨምረው ነው ያቀረቡት። ፕሮፌሰሩ በፈረንሳይ የጤና ምርምራና ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ናቸው። በዓለም ላይ ስመ ጥር በሆኑ ዩኒቨርስቲዎች አስተምረዋል። ለምሳሌ ኤምአይቲ ነበሩ፣ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲም አስተምረዋል። አሁን እሳቸው የጻፉት መጽሐፍ ልጆችን እንዴት ማሳደግ አለብን በሚለው ጉዳይ ላይ ዓለም አቀፍ ትኩስ ክርክር የፈጠረውም ሳይንቲስቱ ካላቸው ገናና ቦታ የተነሳ ነው። ቸል የሚባሉ ሰው አይደሉም። የጻፉት መጽሐፍ በፈረንሳይ ቁጥር አንድ ተነባቢ ከመሆኑም ባሻገር ወደ ጣሊያንኛ፣ ስፓኒሽና ሌሎች ቋንቋዎች ተመልሶ በስፋት እየተነበበ ነው። መጽሐፉ ምን ይላል? የመጽሐፉ ዋንኛ ማጠንጠኛ ኢንተርኔት ከተፈጠረ በኋላ የመጣው ትውልድ ከወላጆቹ ያነሰ ምጥቀተ አእምሮ (IQ) አለው የሚል ነው። የአእምሮ ምጥቀት ምዘናዎች፣ እንቆቅልሾችን መጨረስ፣ ነገሮችን አዙሮ ማየት፣ ተግባራትን በፍጥነት መከወን መለኪያዎች ናቸው። አንድ ሰው እነዚህን እንቆቅልሾችም ሆኑ ተግባራት ለማከናወን የሚፈጅበት ጊዜ አልያም አለመቻሉ ተመዝኖ ነጥብ ይሰጣል። ነገሩ በተወሰነ መጠን የአንድን ግለሰብ ብልህነት መለኪያ ነው ማለት ይቻላል። እኚህ ሳይንቲስት ባደረጉት ጥናት ዓለም በኢንተርኔት መጥለቅለቅ ከጀመረች ጀምሮ አዲሱ ትውልድ የብልህነት ደረጃቸው አሽቆልቁሏል። ከአባት ከእናቱ ያነሰ የአእምሮ ምጥቀት ልኬት ነው እያስመዘገበ ያለው። ከዚህም ባሻገር ጥናቶች በተደጋጋሚ ያረጋገጡት ነገር ቢኖር በሁሉም የሰው ልጅ ታሪክ ትውልድ የሚፈጥራቸው ልጆች ከራሱ እየተሻሉ ነበር የመጡት። ኢንተርኔት ከተፈጠረ በኋላ ግን ይህ ሐቅ እንቅፋት ገጥሞታል። በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ትውልድ ከቀደምት ትውልድ ያነሰ የአእምሮ ምጥቀት እያስመዘገበ ነው። ቢቢሲ ለኚህ ሳይንቲስት አንድ ጥያቄ አንስቶላቸው ነበር። በእርግጥ ይህ ትውልድ ከወላጆቹ ያነሰ አነስተኛ ንቃትና ብልሀት በማሳየት የመጀሪያው ትወልድ ነው? የሳይንቲስቱ ሚሸል ምላሽ ፈጣን ነው። "አዎ!" የሚል ነበር። አንድ ትውልድ ወደሚቀጥለው ትውልድ ሲሸጋገር የሚኖረው የአእምሮ ብርታትና መሻሻል "ፍሊን ኢፌክት" ('Flynn effect') ተብሎ ይጠራል። ይህ ስም የተሰጠው ይህን ሐቅ ለመጀመርያ ጊዜ ከደረሰበት ሳይንቲስት ስም በመነሳት ነው። ግኝቱም በእሱ ስም ይጠራል። የጽንሰ ሐሳቡ ፍሬ ነገር አዲስ ትውልድ ምንጊዜም ካለፈው ትውልድ የተሻለ ጭንቅላት ይኖረዋል የሚል ነው። በአመዛኙ ይህ ሐቅ በሳይንሱ ማኅበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ነው። የሚደንቀው ታዲያ በብዙ አገራት በተደረጉ ሰፋፊ ጥናቶች ይህ 'ፍሊን ኢፌክት' ለአዲሱ ትውልድ አልሰራም። ያልሰራው ደግሞ ኢንተርኔት የዓለም ልዩ ክስተት ሆኖ አእምሮንና ጊዜን መቆጣጠር ከጀመረ በኋላ ነው። ይህ የትውልድ ልቀት ሰንሰለት የተበጠሰው ለኢንተርኔት በተንበረከከው ትውልድ ነው። እርግጥ ነው የምጡቅ አእምሮ ልኬት (IQ) በብዙ ሁኔታዎች ተጽእኖ ሥር ሊወድቅ ይችላል። የጤና ሁኔታ፣ የትምህርት ፖሊሲና አተገባበር፣ የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት አለማግኘት ወዘተ የጠቀሳሉ። ሆኖም ተቀራራቢ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ባለባቸው አገራት በተደረገ ጥናት የአእምሮ ምጥቀት ልኬት (IQ) ለመጀመርያ ጊዜ በአዲሱ ትውልድ ማሽቆልቆል አሳይቷል። ልጆች ከወላጆቻቸው በእጅጉ ያነሰ የብልህነትና የምጡቅነት ውጤት አሳይተዋል። ይህ ሐቅ ቢያንስ በብልጹጎቹ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ኔዘርላንድና ፈረንሳይ ታይቷል። ሌላው አንኳር ጥያቄ የአእምሮ ምጡቅነት ልኬት መውረድን ያመጣው የኢንተርኔት መምጣት ነው ብለን እርግጠኛ ለመሆን የሚያበቃን ምንድነው? የሚለው ነው። እርግጥ ነው መቶ በመቶ ኢንተርኔት ነው ትውልዱን ያደናቀፈው ብሎ መናገር ይከብዳል። ለምሳሌ ማዳበርያ ያበለጸገው ምግም መመገብ፣ ወይም ለተበከለ አየር መጋለጥ ወዘተ ሌሎች ምክንያቶች ሊባሉ ይችሉ ይሆናል። ሆኖም በፕሮፌሰር ሚሸል ጥናት የተደረሰበት አንድ ሐቅ ልጆች ስክሪን ላይ ረዥም ጊዜያቸውን ማጥፋታቸው ለድንዛዜ እያበቃቸው መሆኑ ነው። ተደጋጋሚና ሰፊ ጥናቶች መልሰው መላልሰው ያረጋገጡት ሐቅ ቢኖር ቴሌቪዥን፣ ኢንተርኔት፣ ስልክና ጌም ላይ መጣድ የአእምሮ ምጡቅነትን ይቀንሳል። ይህም የሚሆነው የብልህነታችን መገለጫ የሆኑት ቋንቋ፣ ትኩረት ማድረግ፣ ነገሮችን ማስተዋል እና ባሕል በስክሪኖች ምክንያት ይሸረሸራሉ። እንዴት ነው ስክሪን የአእምሮ ብቃትን የሚያዳክመው? ምክንያቶቹ ተለይተዋል። አንዱ ከሰዎች ጋር የሚኖረን የተግባቦት ጊዜ መውረድ ነው። ሌላው ትኩረት መስጠት የምንችልበት ጊዜ በእጅጉ ማነሱ ነው። የትኩረት ርዝማኔ ለሰከንዶች አልያም ለአጭር ደቂቃዎች ብቻ የሚዘልቅ ሆኗል። ብዙ የዚህ ትውልድ አባላት አንድን ነገር ዘለግ ላለ ሰዓት በጥሞና መስማት ወይም ማስተዋል አይችሉም። ልባቸው ይባትታል። የቋንቋ እድገትና የስሜት እድገታችን በስክሪን ድጋፍ የቆመ ይሆናል። ስክሪን ይህን ትውልድ ብዙ ስሜቶቹን ሸርሽሮበታል። የማዘን፣ የማጤን፣ የመደሰት ስሜቶች አርቴፊሻል ሆነዋል። የመጽሐፍ ንባብ አእምሮ እንዲያሰላስል ያግዛል። የሥዕል ጥበብ፣ ሙዚቃና ሌሎችም እውናዊ ጥበቦች የአእምሮን ሙሉ ትኩረት ይወስዳሉ። የአእምሮ ጤናማ ዕድገትን ያሳልጣሉ። ስክሪኖች ግን ከዚህ በተቃራኒው ናቸው። ግልብነት፣ የእውነተኛ ስሜት ማጣት፣ ስለምንም ግድ አለመስጠት የስክሪን አመሎች በዚህ ትውልድ ላይ ያመጡበት ጣጣ ነው። በአጠቃላይ ጌሞች፣ ስልኮች፣ ቲቪና ኢንተርኔት አእምሮ አቅሙን እንዳያውቅ እያታለሉ እድገቱ እንዲገታ የሚያደርጉ ሆነው ተገኝተዋል። የአእምሮ መለጠጥ ለእድገቱ እጅግ አስፈላጊ ነው። ስክሪን አእምሮ እንዳይለጠጥ ያደርገዋል። ይህን እድገቱን ያቀጭጫል። በሌላ ቀላል ምሳሌ ነገሩን ማስቀመጥ ይቻላል። ጡንቻ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ይጎለብታል። ስክሪን የሚያይ ሰው ግን አንድን የስፖርት ውድድር ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ፈንዲሻ እየቃመ ብቻ በተደጋጋሚ በመመልከት ጡንቻው እንዲጎለብት የመሻት ያህል ነው። ፕሮፌሰር ሚሸል በመጽሐፋቸው ወላጆችን "ድድብና አታውርሱ" የሚሉት ለዚሁ ነው።
xlsum_amharic-train-194
https://www.bbc.com/amharic/44722156
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጎ አንደበትና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር
ኢትዮጵያ የተለየ የፖለቲካ ማዕበል ውስጥ ናት። አበይት ፖለቲካዊ እርምጃ በተወሰደባቸው ሦስት ወራት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማመስገን በተዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ያጋጠመው የቦንብ ፍንዳታ፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታዩ ግጭቶች፣ ያልተረጋጉ የፖለቲካ ጥያቄና እስከ አሁን አገራዊ መግባባት ሊደረስበት ያልቻለው የሰንደቅ አላማ ጥያቄ በተለያየ አጋጣሚ እየተንጸባረቁ ናቸው።
[ "ኢትዮጵያ የተለየ የፖለቲካ ማዕበል ውስጥ ናት። አበይት ፖለቲካዊ እርምጃ በተወሰደባቸው ሦስት ወራት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማመስገን በተዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ያጋጠመው የቦንብ ፍንዳታ፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታዩ ግጭቶች፣ ያልተረጋጉ የፖለቲካ ጥያቄና እስከ አሁን አገራዊ መግባባት ሊደረስበት ያልቻለው የሰንደቅ አላማ ጥያቄ በተለያየ አጋጣሚ እየተንጸባረቁ ናቸው።" ]
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ በእስር የነበሩ ሰዎች ማስፈታት፣ የተዘጉ የህትመትና ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙኃንን መክፈት፣ የአገሪቷን ወሳኝ ቦታዎች ተቆጣጥረዋል የተባሉትን የደህንነትና የመከላከያ አመራሮች በሌሎች መተካት፣ ለ20 ዓመታት የተቋረጠውን የኢትዮ- ኤርትራ ግንኙነት ለውይይት ክፍት ማድረግ የመሳሰሉትን አበይት ፖለቲካዊ እርምጃዎች በመውሰድ አገር የማረጋጋት ስራውን የጀመሩባቸው 100 ቀናት ተቆጠሩ። ታዲያ እነዚህ እርምጃዎች ፖለቲካዊ ምህዳሩ አሰፉ ወይስ እጅግ ፈጠኑ? ያኮረፉትን አባብለዉ አዲስ አኩራፊ ሃይል ፈጠሩ ወይስ የተጣመመውን ማቅናት ቻሉ? "መንግሥት የሚደግፈው የሙስሊሙን ሕብረተሠብ ነው" ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጠ/ሚ ዐብይ አልበሽርን የድንበር ግጭቱን አብረን እንፍታ አሉ በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ "በትግራይ ስም እንደራጅ እንጂ የኛ አመለካከት ቀድሞውንም ኢትዮጵያዊ ነው" ዶክተር አረጋዊ በርሔ "እየነጋ ያለ ይመስለኛል" በሽብርተኝነት ተከሶ 2011 ላይ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት በእስር የቆየዉ አንዱዓለም አራጌ በይቅርታ ከተፈቱ እስረኞች መካከል አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያደረጓቸው ያሉት በጎ ንግግሮች የሚመሰገኑ ናቸዉ የሚለው አንዱዓለም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለውን ፖለቲካዊ ለውጥ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ደረጃ በደረጃ እየተፈጸሙ እንዳሉ የሚያሳዩ ለውጦች ናቸዉ ሲል ይገልፀዋል። "አሁን ላይ ንጋት ነው የማየዉ" የሚለው አንዱዓለም በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተወሰዱ ያሉትን እርምጃዎችና የገቡትን ቃል የሚመሰገን ነው ይላል። "ምናልባት እየነጋ ይመስለኛል። የኢትዮጵያ ህዝብ መቃወም ብቻ ሳይሆን የሚደገፍ ሃሳብና ሰው ሲገኝ መደገፍ እንደሚችል ደግሞ እያሳየ ነዉ። ተቃዋሚው ሁሉ ሲቃወም፣ ሲታሰር ሲፈታ የነበረው የሚደገፍ ሃሳብ በማጣቱ እንደሆነና ኢትዮጵያውያን ምክንያታዊ እንደሆንን የሚያሳይ ነው" ሲል ይገልጸዋል። እየተካሄደ ያለው ለውጥ መጀመሪያም ህገ መንግሥቱ ላይ የነበሩና በረጅም ሂደት በመመሪያ፣ በደንብ፣ በፖሊሲ አንዳንዴም በጉልበትና በውሳኔ እየተጨፈለቁና እየተደመሰሱ የመጡ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር የነበረው አቶ ሙሼ ሰሙ ይናገራል። "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈሩ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ያለ ፍርድ ቤት መታሰርና ያለ ጠያቂ መቅረት፣ መገረፍና አካል መጉደል የመሳሰሉት ህገ መንግስቱ የማይደግፋቸው ድርጊቶችና ሃሳቦች እንዲቀለበሱ ነው ያደረገው" ይላል። በኢትዮጵያ በስርዓት ውስጥ ለውጥ መምጣቱን የሚናገረዉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ በበኩሉ የፖለቲካ ምህዳሩ እየሰፋ እንዳለ ለቢቢሲ ተናግሯል። "ወደ ዲሞክራሲ የምናደርገው ሽግግር በፍጥነት እየተካሄደ ነው። በተለይ ደግሞ እየተደረገ ላለው ሽግግር ምሁራዊ እርዳታ ማድረግ ያስፈልጋል። ገዢው ፓርቲ ላይም ጫና በመፍጠር ሽግግሩ በፍጥነት እንዲሄድና የተቃውሞ ኃይሉም በፍጥነት እየተዘጋጀ ለሽግግሩ አቅሙ እየጎለበተ እንዲሄድ ማድረግ አስፈላጊ ነው" ሲል የአገሪቷን የፖለቲካ ምህዳር የሚሰፋበት መንገድ አመላክቷል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጣፋጭ አንደበት ባሻገር በሃሳብም ነፍጥ በማንሳትም ለመታገል ከአገር ተሰደው በጎረቤት አገሮች፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ከትመው የነበሩ ኃይሎች ወደ አገር ቤት ገቡ። በርካቶችም ከእስር ተፈቱ። "ሽብርተኛ" የተባሉትም ጥላሸት የተቀባው ስማቸዉ ተገፎ በነጻነት መታገል እንደሚችሉ ጥሪ ቀረበላቸው። ሆኖም ግን አሁን ያለው የፖለቲካ ምህዳር ዝብርቅርቅ ያለ ነው የሚለው አቶ አንዱዓለም ነገሮች መልክ ይዘው እየሄዱ አይደለም ሲል ይናገራል። "በአንድ በኩል ሀሳቦች እንዲንሸራሸሩ ሰው ነጻ ሆኖ እንዲናገር የሚል ይፋዊ የሆኑ መግለጫዎች አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ ጊዜ ሲታገል የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ መብቱ እንዲከበር ከፍተኛ ፍላጎት አለ። እነዚህ ነገሮች ግን መልክ በያዘ መንገድ ሳይሆን አየር ላይ ሲንሳፈፉ ነው የሚታየኝ" ይላል። "መንግሥት በዚህ ጉዳይ ያለው ቁርጠኝነት በጽሁፍ፣ በአዋጅ ተደግፎ የጸደቀ አይደለም። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎ አንደበት ውጪ መልክና ቅርጽ የያዘ ነገር የለም። በሁለቱም አቅጣጫ አየሩ ገና የነጻነት አየር እየሞቀ ያለ ነው። ያ ግን ምን ድረስ ይሄዳል፣ የሚገድቡ ነገሮችስ ይኖሩ ይሆን የሚለው ግልጽ አይደለም፤ ውዥንብር አለው" ሲል ይገልጸዋል። የክርስቲያን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትና ህብረት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሸሻ ሸዋረጋ ደግሞ "በዚህ የፖለቲካ ምህዳር የማስፋት ጉዞ የወጣቶች፣ ሴቶች፣ ህጻናትና አካል ጉዳተኞች መብት ማስከበር፣ ግጭቶች መፍታት፣ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በተያያዘ የተቀመጡ ድንጋጌዎች ይሻሻላሉ ብለን እናስባለን" ይላሉ። "በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ዙርያ፣ ዜጎች እንዲጠይቁ ስለሚያስችሉ የዲሞክራሲ ግንባታን የሚያፋጥኑ ብቻ ሳይሆን ዜጎች መንግሥትን እንዲጠይቁ ስለሚሰሩ የዲሞክራሲ ምህዳሩን ያሰፋዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈ ይላሉ ዶክተር መሸሻ "የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ዜጎች ህገ መንግስቱ የሰጣቸውን መብት እንዲጠቀሙ የተለያዩ ስልጠናዎች ሲሰጡ፣ ምርጫ ላይም ሲሳተፉ ነበር። አዋጁ ከወጣ በኋላ ከተከለከሉ ነገሮች አንዱ ግን ይህ ነው፤ ይህ ከተሻሻለ ያለመሸማቀቅ መብታቸው ስለሚያረጋግጥላቸው ወደ ፊት በዲሞክራሲያዊ ምህዳር ማስፋት ትልቅ ስራ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል" ሲሉ ያክላሉ። ያዋከቡት ነገር ምዕራፍ አያገኝም... የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔዎች ፈጠኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ ይሰማል። ከውሳኔያቸው መፍጠን የተነሳ የራሳቸው እርምጃ እንቅፋት እንዳይሆኑባቸው ስጋታቸውን የሚያስቀምጡም አሉ። "ለረዝም ጊዜ ሲወድቁ ሲነሱ የነበሩ አጀንዳዎች ስለሆኑ ፈጠኑ የሚባሉ አይመስለኝም" የሚሉት ዶክተር መሸሻ ከፍተኛ ጥያቄ ሲነሳባቸው የነበሩ አዋጆችና ሲገፉ የነበሩ ጉዳዮች ስለሆኑ የተወሰደው እርምጃ የሚደነቅ ነው ይላሉ። "ሆኖም ግን ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም። የእነዚህ አዋጆች ለውጥ እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለው ገና ነው። አካራካሪና ሲያነታርኩ የነበሩ ነገሮች በምን ያክል አድማስ ይለወጣሉ? የሚል በተስፋ ከመጠበቅ ይልቅ ጮቤ የሚያስረግጥ አይደለም" ሲሉ ይናገራሉ። "የተቻኮለ ነገር የለም" የሚለው አቶ ሙሼ በበኩሉ የነበረዉ ስርአት ኣልበኝነት ወደ ስርአት እንዲመጣ አስደናቂ ሥራዎች መሥራት ግድ ይል ስለነበር የተሰራዉ ስራ ትክክል ነው ይላል። እዚህ ሂደት ላይ ያለው ፍጥነት ያሰጋኛል የሚለው የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትዎርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀምድ መሰረት መያዝ እንዳለበት ይመክራል። "ከስር ከስር መሰረት እየያዘ፣ እየተጠናከረ ስላልሄደ ለውጡ እየሄደበት ያለው ፍጥነት ያሳስበኛል። ፍጥነት ጥቅም እንዳለው ሁሉ ስጋትም አለው። በቀጣይነት የምሁራንና የተለያዩ ሰዎች ተሳትፎ ያስፈልጋል።" "እየሄድንበት ያለዉ መንገድ ለመለወጥ ጥረት እያደረግንበት ስለሆነ ከዚህ ሃሳብ ተቃራኒ ቆመናል የሚሉ ሃይሎች መድረክ ላይ በመቅረብ የማሸነፍና የመሸነፍ ልምድ መዳበር አለበት፤ መድረክ አለ ማለት ብቻ ግን በቂ አይደለም" ይላል አቶ ሙሼ ሰሙ። ጃዋር መሀመድም አሁን አገሪቷ ውስጥ እዚህም እዛም የሚታዩ አለመረጋጋቶችና ግጭቶች ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን ያሰምርበታል።
xlsum_amharic-train-195
https://www.bbc.com/amharic/49289970
ለ20 ዓመታት ዴንማርካዊት እህቱን የፈለገው ኢትዮጵያዊ ሀኪም
ስትወለድ ቤተሰቦቿ ያወጡላት ስም ትዕግስት ነበር፤ ትዕግስት አስማማው።
[ "ስትወለድ ቤተሰቦቿ ያወጡላት ስም ትዕግስት ነበር፤ ትዕግስት አስማማው።" ]
ሙሉጌታ እና እህቱ ከ20 ዓመት በኋላ ሲገናኙ ትዕግስት የአንድ ዓመት ህጻን እያለች እናቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። አባቷ እሷንና የተቀሩትን ሦስት ልጆቻቸውን ማሳደግ ስላልቻሉ ትዕግስትን ለጉዲፈቻ ሰጧት። በጉዲፈቻ የት አገር እንደተወሰደች፣ ማን እንደወሰዳት ግን የሚያውቁት ነገር አልነበረም። የትዕግስት ታላቅ ወንድም ሙሉጌታ አስማማው ነፍስ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ እህቱን ከመፈለግ አልቦዘነም። ሙሉጌታ አሁን ባለትዳርና የአንዲት ልጅ አባት ሲሆን፤ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የውስጥ ደዌ ስፔሻላይዜሽን ይማራል። ታሪኩን እንዲህ አጫውቶናል. . . የአሶሳው ልጅ- ሙሉጌታ ለቤተሰቤ ሁለተኛ ልጅ ነኝ። ከእኔ በላይ ታላቅ እህቴ አለች። ከእኔ በታች ወንድሜና ትዕግስት አሉ። ሁላችንም የተወለድነው በሦስት ዓመት ልዩነት፤ አሶሳ ውስጥ ነው። የአባቴ ወንድሞች አዲስ አበባ ይኖሩ ስለነበረ ከአሶሳ ወደ አዲስ አበባ ሄድን። አዲስ አበባ ገብተን ብዙም ሳንቆይ እናቴ ታመመች። ታናሽ እህታችን አንድ ዓመት ሊሞላት አካባቢ ነው እናታችን ያረፈችው። እናቴ ከሞተች በኋላ አባቴ እኛን ማሳደግ ከበደው። አባቴ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ቄስ ነበር። ቋሚ ቤት ስላልነበረን አራታችንንም ይዞ ከቦታ ቦታ መዘዋወር አልቻለም። • ለዓመታት የተጠፋፉት የወላይታ ሶዶዋ እናትና የኖርዝ ኬሮላይናዋ ልጃቸው ያኔ እህቴ በጣም ታማበት ነበር፤ ኩፍኝ መሰለኝ። አባቴ አማራጭ ሲያጣ እህቴን ስድስት ኪሎ አካባቢ ለሚገኙ ሚሽነሪዎች ሰጣት። እኔ ስድስት ዓመቴ ነበር። ብዙ ነገር አላስታውስም. . . ትንሽ ትንሽ ትውስ የሚለኝ እህቴ ስታለቅስ ነው። በጣም የማዝነው የእናቴ ምስል ራሱ ብዙ ትዝ አይለኝም። እህቴ ህጻን እያለች ስታለቅስ ግን የተወሰነ ትዝ ይለኛል. . . አባቴ ስለ ሚሽነሪዎቹ የነገረኝ ካደግኩ በኋላ ነው። ቀጨኔ መድኃኔዓለም አካባቢ ሳለ፤ ሰዎች ሚሽነሪዎቹ የት እንዳሉ ጠቆሙት። እህቴን ከሞት ሊያተርፋት የሚችለው ለእነርሱ በመስጠት ብቻ እንደሆነ ተሰምቶት ነበር። አድጌ ላቀረብኩለት ጥያቄ መልሱ 'ልጄ እጄ ላይ ከምትሞት. . . ሁላችሁም ከምትሞቱብኝ. . . ያለኝ አማራጭ እሷን መስጠት ብቻ ነው' የሚል ነበር። ሚሽነሪዎቹ ልጁን ተመልሶ መጠየቅ እንደማይችል ሲያስጠነቅቁት ተስማማ። እህቴን ሰጥቷት ሲመለስ ግን ታላቅ እህቴ ተቆጣች፤ መጨቃጨቅ ጀመሩ። በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ሳምንት ወደ ሚሽነሪው ሄዶ 'ልጄን መልሱልኝ' ሲል ውጪ አገር እንደሄደች ነገሩት። ባዶ እጁን ወደ ቤት ተመለሰ! በወቅቱ እህቴ ከአባቴ ጋር ትጣላ እንደነበር ነግራኛለች። 'ካላመጣሀት' እያለችው ትግል ውስጥ ገቡ። አባቴ እናታችንን ሲያጣ ብዙ ነገሮች ድብልቅልቅ ብለውበት ነበር። የልጁ መሄድ ሲጨመርበት ደግሞ የሚያደርገው ጠፋው። ልጁ ወዴት አገር እንደሄደች፣ ማን እንደወሰዳት የሚያውቀው ነገር አልነበረም። • "በኤችአይቪ የምሞት መስሎኝ ልጄን ለጉዲፈቻ ሰጠሁ" እህቴ እንደነገረችኝ ከሆነ፤ አባቴ ሚሽነሪዎቹን ተመላልሶ ቢጠይቃቸውም ስለ ልጁ ምንም ፍንጭ አላገኘም። ለጉዲፈቻ ሲሰጣት በጣም ታምማ ስለነበረ በሕይወት የምትቆይም አልመሰለውም። እኔ ግን ከፍ እያልኩ ስመጣ እህቴ አንዳለች ቀልቤ ይነግረኝ ነበር። የሆነ 'ሴንስ' የምታደርጊው ነገር አለ አይደል?. . . የሙሉጌታ እህት ሙሉጌታ- የመርካቶው አትክልት ነጋዴ አባቴ ለእኛ ባይነግረንም በእህቴ ምክንያት ሰላሙን አጥቷል። በጣም ይጨነቅ ነበር። ሁሌም የሚፀፀትበት ነገር የእርሷ መሰጠት ጉዳይ ነበር። ነገሮች የተበለሻሹበት ከዛ በኋላ ይመስለኛል። አዕምሮውን ማረጋጋት አልቻለም። መጠጥም ስለሚወስድ በቤተሰቡ መካከል ትንሽ አለመግባባት ነበር። አባቴ የቀረነውን ልጆችም አንድ ላይ ማሳደግ ከበደው።... በቃ ተበታተንን። መጀመሪያ ላይ ከአባቴ ታላቅ ወንድም ጋር መኖር ጀመርኩ። ግን ብዙ አልቆየሁም። መርካቶ ጀላቲ [በረዶ] ከሚሸጡ ሴት ጋር እኖር ጀመር። እኔም ጀላቲ እየሸጥኩ ማለት ነው። ሴትየዋ የቀጠሩኝ በሠላሳ ብር ነበር. . . ጀላቲ ለመሸጥ በወር 30 ብር. . . ከዚያ አንዲት ትልቅ ሴት 'እኔ አሳድገዋለሁ' ብለው ወሰዱኝ። አትክልት ነጋዴ ነበሩ። እኔም ካሳደጉኝ እናቴ ጋር አትክልት እየሸጥኩ የማታ ትምህርት ቤት ገባሁ። የምሠራው እንደ ልጅ አልነበረም። ጫናው ከባድ ነበር። ማለዳ 12 ሰዓት ተነስቼ ወደ ሥራ እሄዳለሁ። እስከ 11 ሰዓት ሠርቼ ወደ ትምህርት ቤት፤ ማታ 2፡30 ላይ ወጥቼ ደግሞ ወደ ቤት. . . የእለት ከእለት ሕይወቴ ይህ ነበር። እስከ ሰባተኛ ክፍል ድረስ እየነገድኩ ተማርኩ። ስምንተኛ ክፍል ስገባ በመምህራኖቼ ግፊት ወደ ቀን ተማሪነት ተዘዋወርኩ። የቀን እየተማርኩ ክረምት ላይ እሠራ ነበር። የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ በትርፍ ጊዜዬ አስጠና ነበር። • ከ43 ዓመት በኋላ የተገናኙት ኢትዮጵያዊ እናትና ስዊድናዊ ልጅ ያሳደጉኝ እናቴ በዛሽ ኃይሌ አሁን በሕይወት የሉም። እዚህ ለመድረሴ ትልቅ አስተዋጽኦ ካበረከቱ ቤተሰቦቼ መካከል ናቸው። አብረውኝ ያደጉት እህቶቼ ሙሉ ዳኜ፣ ዝናቧ ዓለማየሁ፣ መሰረት ካሳና ትዕግስት ዓለማየሁ ይባላሉ። እነሱና ሌሎችም ቤተሰቦቼ አሁን ያለሁበት ለመድረሴ ምክንያት ናቸውና አመሰግናቸዋለሁ። እህቴ ትኖር የነበረው ደግሞ ከአንዲት ነጋዴ ጋር ነበር። ለስድስት ወር እኔ ጋር መጥታ ኖራ ነበር. . . ከዚያ በኋላ ቶሎ ወደ ትዳር ገባች። የመጀመሪያ ልጇን ስትወልድ 17 ዓመት የሚያልፋት አይመስለኝም። ታናሽ ወንድሜ ለተወሰነ ጊዜ ከአባቴ ጋር ኖሯል። ግን አልተስማሙም። ወንድሜ አፈንግጦ ወጣና ብቻውን መኖር ጀመረ። የወንድሜ አስተዳደግ ከባድ ነበር። አዋዋሉ ጥሩ አልነበረም። አሁንም ያለበት ሁኔታም ጥሩ አይደለም። እኔ ደህና ኑሮ እየኖርኩ፣ ጥሩ አልጋ ላይ እየተኛሁ ወንድሜ ውጪ እያደረ እንደሆነ ማሰብ ለእኔ ከባድ ነበር። መርካቶ እየሠራሁ ታናሼን በገንዘብ ለመደገፍ እሞክር ነበር። እኔም፣ እህቴም፣ ወንድሜም መርካቶ ስንሠራ እንገናኝ ነበር። ግን አንድ ቤት አልኖርንም። አብረን አላደግንም። የቤተሰቡ መበታተን፣ እኔም ከእህትና ወንድሜ ተነጥዬ ማደጌ ከባድ ተጽዕኖ አሳድሮብኛል። ታላቅ እህቴና እኔ እህታችንን እንዴት መፈለግ እንደምንችል ባናውቅም ስለእርሷ እናወራ ነበር። ያኔ እህታችንን ስለምንፈልግበት ቴክኖሎጂ የምናውቀው ነገር የለንም። ጥያቄው አንድና አንድ ነበር፤ በሕይወት አለች? እህቴም አባቴም በሕይወት ትኖራለች ብለው አያስቡም ነበር። እኔ ግን እንዲሁ መኖሯ ይሰማኝ ነበር። ሙሉጌታ- የዩኒቨርስቲ ተማሪው ነፍስ ካወቅኩበት ጊዜ ጀምሮ እህቴን መፈለግ እንዳለብኝ አስባለሁ። በእርግጥ ቤተሰባችን እድለኛ አይደለም። ተበታትነን ነው ያደግነው። ቢሆንም እኔ፣ እህቴና ወንድሜ መገናኘት እንችል ነበር። እሷ ግን ማንነቷን አታውቅም. . . ቤተሰብ ይኑራት አይኑራት አታውቅም. . . ይህንን ሳስብ ሰላም አጣለሁ። አባቴ ሊያገኛት እንደማይችል ነበር የሚነግረን። እሱ ተስፋ ቢቆርጥም እኔ ግን ተስፋ ነበረኝ። ሁሌም የማስበው፣ የምፀልየውም እሷን ከእኛ ጋር ስለመቀላቀል ነበር። ህልሜን የማሳካበትን መንገድ አስባለሁ. . . የሆነ አገር ሄዶ እሷን መፈለግ ቢኖርብኝም፤ ይሁን. . . • ዓለም አቀፍ ጉዲፈቻን ማገድ አዋጭ ነው? በተለይ ዩኒቨርስቲ ስገባ እህቴን መፈለግ ብቻ ሳይሆን ቤተሰባችንንም መሰብሰብ እንዳለብኝ ይሰማኝ ነበር። ግቢ ስገባ እንዴት ቴክኖሎጂን መጠቀም እንደምችል አወቅኩ። እናም ጎንደር ዩኒቨርስቲ ህክምና እያጠናሁ ጎን ለጎን እህቴን መፈለግ ጀመርኩ። የጓደኛዬ አባት ጠበቃ ስለሆኑ ስለ እህቴ በምን አይነት መንገድ መጠየቅ እንዳለብኝ [ለጉዲፈቻ የሰጣትን ድርጅት] እሳቸውን አማክር ነበር። ለጉዲፈቻ የተሰጠችበትን ቀን በትክክል ስለማላውቀው ፋይል አገላብጬ መፈለግ አልቻልኩም። በዚያ መንገድ ብዙ መቀጠል እንደማልችል ሲገባኝ ኢንተርኔት ላይ ማፈላለግ ጀመርኩ። ብዙ መረጃዎችን ማሰስ ጀመርኩ። ከኢትዮጵያ በማደጎ የተወሰዱ ልጆች የሚገኙባቸው 'ሳይቶች' ላይ በስም ዝርዝር ፈለኳት። ምንም የለም። የህክምና ትምህርት ትኩረት ይሻል። ፍለጋውም ጊዜ ይጠይቃል። ሁለቱን ማመጣጠን በጣም ከባድ ቢሆንም ያለኝን የእረፍት ጊዜ ሁሉ እጠቀምበት ነበር። ሙሉጌታ እና እህቱ ኡጋንዳ ሲገናኙ ታላቅ እህቴ የእህታችን ነገር ሁሌም ያሳዝናታል። ግን በትምህርት ስላልገፋች እንዴት እንደምትፈልጋት አታውቅም። ከቤተሰቡ የተማርኩት፣ ዩኒቨርሲቲ የገባሁትም እኔ ብቻ ነኝ። ስለዚህ ኃላፊነቱ የእኔ ነበር። ያ ኃላፊነት ፍለጋውን በደንብ አጠንክሬ እንድይዘው አደረገኝ። ሁሌም እህቴን አግኝቼ ቤተሰቦቼ ሲደሰቱ ማየትን አልማለሁ። የት አገር እንደሄደች ስለማላውቅ፤ በአንድ አገር ሳልወሰን 'ዳታቤዞች' ላይ እፈልጋት ነበር። በጣም በጣም አድካሚ ነበር። ያው ግን ላያስችል አይሰጥም። አንዳንዶቹ ሳይቶች በጉዲፈቻ ስለተሰጠው ልጅ 'ፕሮፋይል' ይጠይቃሉ። አንዳንዶቹ የስም ዝርዝር ይሰጣሉ። ትዕግስት የልጅነት ፎቶ አልነበራትም። የእኛ ቤተሰብ ጸጉር ሉጫ የሚባል ነው። የሁላችንም ይመሳሰላል። እና ፎቶዋን ባይ በጸጉሯ እንደምለያት አስብ ነበር። እውነት ነው የሰው ገጽታ እድሜ ሲጨምር፣ የአኗኗር ሁኔታ ሲቀየርም ይለወጣል። ግን ባያት አውቃታለሁ። ስድስት ዓመት ፈልጌ... ፈልጌ ሳላገኛት ከዩኒቨርስቲ ተመረቅኩ። ሙሉጌታ - ሐኪሙ ከተመረቅኩ በኋላም ፍለጋውን ቀጠልኩበት። ኢንተርኔት ላይ በጉዲፈቻ የተወሰዱ ልጆችን ስፈልግ ከመጡልኝ ገጾች አንዱ 'ቤተሰብ ፍለጋ' የሚል ነበር። በቀረበልኝ ፎርም ላይ ስለ እህቴ ያለኝን መረጃ ሞላሁ። ፎርሙ ላይ ካሉት ጥያቄዎች መካከል እህቴ የተወለደችበት እና በጉዲፈቻ የተሰጠችበት ቀን ይገኝበታል። እኔ ስለማላውቀው አባቴን ጠየቅኩት። ሊያስታውስ አልቻለም። የማስታውሳቸውን ዓመተ ምህረቶች እያጠጋጋሁ ሞላሁ። • "እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ ከአንድ ወር በኋላ 'ቤተሰብ ፍለጋ' ከሚሠሩ ሰዎች ስልክ ተደወለልኝ። 'አንተ በምትፈልገው [ፕሮፋይል] አንተን የሚፈልግ ሰው አለ' ተባልኩ። እህቴን በምፈልግበት ገጽ ላይ እሷም ፎርም ሞልታ እኛን እየፈለገች እንደሆነ ነገሩኝ። እህቴ ብትሆንም ባትሆንም እኔ በምፈልገው [ፕሮፋይል] ሰው በመገኘቱ በጣም ደስ አለኝ። ደመ ነፍሴ እህቴ እንደሆነች ቢነግረኝም መጠራጠሬ አልቀረም። ግን ደግሞ ከጥርጣሬ ጋር አብሮ ደስ የሚል ነገር ተሰማኝ። የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ. . . አንድ ቀን ሥራ ጨርሼ፣ ከሆስፒታል ወጥቼ ወደ ቤት እየሄድኩ ፌስቡክ ላይ 'ፍሬንድ ሪኩዌስት' (የጓደኝነት ጥያቄ) ደረሰኝ። ዴንማርክ ከሚኖር ሰው። በዚያ ወቅት ከውጪ አገር የሚደርሰኝ መልዕክት ከእህቴ ጋር የተያያዘ እንደሚሆን ስለማውቅ 'ሪኩዌስቱን' ተቀበልኩት። የእህቴ ፍቅረኛ ነበር። ከዚያ እሷም 'ፍሬንድ ሪኩዌስት' ላከችልኝ። መጀመሪያ ምን ብላ እንደጻፈችልኝ አላስታውስም ግን "Hello" ያለችኝ ይመስለኛል። ማውራት ጀመርን. . . የምትኖረው ዴንማርክ ነው. . . ስለ ቤተሰቡ ብዙ ጥያቄዎች ታቀርብልኝ ነበር። እርግጠኛ ለመሆን 'ዲኤንኤ' ማስመርመር እንደምትፈልግም ነግራኛለች። እህቴ ትዕግስት በሚለው ስሟ አትጠራም። ስሙን አሁን ከምትጠራበት ስም አስከትላ ነው መሰለኝ የምትጠቀምበት። ልጅ እያለች ያማት የነበረው፣ ያ ኩፍኝ የመሰለኝ በሽታ ጠባሳ እንደጣለባት ነግራኛለች። በ'ኢሞ' እየደወለቸልች ከሁለት ሰዓት በላይ እናወራ ነበር። ቤተሰባችን ምስቅልቅል ያለ መሆኑን ነግሬ ላስጨንቃት ስለማልፈልግ 'ሁሉም ደህና ናቸው፤ ሥራ ይሠራሉ' እላታለሁ። ጊዜው ሲደርስ ራሷ መጥታ ብታየው ይሻላል ብዬ አስባለሁ። አባቴ ያደረገው ነገር አይዋጥላትም። መቀበል አትፈልግም። የነበረበትን ሁኔታ እየነገርኩ፤ ለማስረዳት፣ ለማሳመን እሞክራለሁ። 'እሺ' ትልና. . . መልሳ ደግሞ አይዋጥላትም። ለመቀበል ይከብዳታል። ሙሉጌታ እና እህቱ እህቴ እንደነገረችኝ ከሆነ፤ ቤተሰቦቿ እንደሞቱ ቢነገራትም ልንኖር እንደምንችል ታስብ ነበር። የማንነት ጥያቄዎቿ እንዳሉ ሆነው ያደገችው ጥሩ ቤተሰብ ውስጥ ነው። በጣም የሚያሳዝነኝ እህቴ 'ኢዲኤስ' [Ehlers-Danlos syndromes] አለባት። ቆዳ እና የአጥንት መገጣጠሚያ የሚያጠቃ የጤና ችግር ነው። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ እህቴ 23 ዓመቷ ነው። ዩኒቨርስቲ ገብታ ህክምና መማር ፈልጋ ነበር። ግን በበሽታው ምክንያት አልቻለችም። አሁን በሌላ ዘርፍ የሁለተኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ናት። እስካሁን ድረስ ከእኔ ውጪ ከሌሎቹ ቤተሰቦቼ ጋር አላወራችም። ፎቶዎች ልኬላታለሁ። እንዳገኘኋት ለአባቴ ስነግረው 'ከአሁን በኋላስ ብሞትም አይቆጨኝም' አለ። ለታላቅ እህቴ ስነግራት 'እውነት ግን እህታችን ናት?' ብላ ጠየቀችኝ። ለማመን ተቸግራ ነበር። በሕይወቴ ካደረኳቸው ነገሮች ሁሉ ትላቁ ስኬቴ እህቴን ማግኘቴ ነው። የውስጥ ሰላም አግኝቼበታለሁ። ሁሉንም ቤተሰብ የመሰብሰብ ህልሜ ገና አልተሳካም። ያው ቤተሰቡን ለመሰብሰብ ቤት ያስፈልጋል። በእኛ አገር ሁኔታ ይህን ማሳካት በጣም ከባድ ነው። የእህቴ ፍቅረኛ ኡጋንዳዊ ነው። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ ለእረፍት ወደ ኡጋንዳ ሲሄዱ ጋበዙኝና ወደ ካምፓላ አቀናሁ። ልክ ካምፓላ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ስንተያይ 'ዲኤንኤ ማስመርመር አልፈልግም' አለችኝ። በቃ! አንድ ቤተሰብ እንደሆንን አወቅን. . . ተቃቅፈን እያለቀስን ከሠላሳ ደቂቃ በላይ ቆየን። አንድ ቀን ኢትዮጵያ መጥታ ከተቀረው ቤተሰብ ጋር አገናኛት ይሆናል. . .
xlsum_amharic-train-196
https://www.bbc.com/amharic/news-56343933
ኮሮናቫይረስ፡ "ኮሮና ቤቴን አፈረሰው" ከወለደች በኋላ በኮቪድ-19 ሚስቱን ያጣው ባል
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መከሰቱ ከተረጋገጠ ከወራት በኋላ የጤና ሚኒስቴር አንዲት በኮቪድ-19 የተያዘች እናት ከቫይረሱ ነጸ የሆነ ልጅ በቀዶ ህክምና መውለዷን ሲገልጽ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ከ15 ቀናት በኋላ ግን የጨቅላው እናት በቫይረሱ ምክንያት ህይወቷ ማለፉ በርካቶችን አሳዝኗል።
[ "በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መከሰቱ ከተረጋገጠ ከወራት በኋላ የጤና ሚኒስቴር አንዲት በኮቪድ-19 የተያዘች እናት ከቫይረሱ ነጸ የሆነ ልጅ በቀዶ ህክምና መውለዷን ሲገልጽ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ከ15 ቀናት በኋላ ግን የጨቅላው እናት በቫይረሱ ምክንያት ህይወቷ ማለፉ በርካቶችን አሳዝኗል።" ]
ወረርሽኙ በኢትዮጵያ መገኘቱ የተገለጸበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የሟች ባለቤትና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል የሆነው መቶ አለቃ ካሳሁን አበራ ስለጨቅላው፣ ስለቤተሰቡ፣ ስለራሱና አሁን ስላሉበት ለቢቢሲ ታሪኩን አጋርቷል። መቶ አለቃ ካሳሁንና ባለቤቱ እስከዳር ክፍሌ የተዋወቁት በ1995 ዓ.ም ነበር። ለሰባት ዓመታት በጓደኝነት ከቆየን በኋላ በ2002 የትዳር ህይወትን ጀመሩ። ለአስር ዓመታት በዘለቀው ትዳራቸው ሁለት ሴት ልጆች ያፈሩ ሲሆን በመጨረሻም በቀዶ ህክምና የተወለደው ልጃቸው ወንድ ነው። ሁለቱን ጥንዶች የኮሮናቫይረስ ተከስቶ እከወዲያኛው እስኪለያያቸው ድረስ በፍቅር እንደኖሩ መቶ አለቃ ካሳሁን ይናገራል። "ፖሊስ በመሆኔ ከብዙ ሰዎች ጋር እገናኛለሁ፤ እሷም መውለጃዋ አስኪደርስ ድረስ በአንድ ክሊኒክ ውስጥ ትሰራ ስለነበረ ሁለታኛንም ለበሽታው ተጋላጭ ነበርን" ይላል። በጓደኝነትም በትዳርም ውስጥ በቆዩባቸው ዓመታት ሁለቱ ጥንዶች ቤታቸው ሰላምና ፍቅር የሞላበት ነበር። ሁለቱም ጥረው በሚያገኙት ገቢ ልጆቻቸውን ተጋግዘው ያሳድጉ ነበር። "በተለይ ልጆቻችን ከእሷ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ነበራቸው" ይላል ካሳሁን። ባለፈው ዓመት መጋቢት ላይ የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ በታወቀበት ጊዜ ነፍሰጡር የነበረችው አስከዳር መደበኛ የህክምና ክትትል በምታደርግበት ጊዜ ድካምና የምግብ ፍላጎቷ ቢቀንስም ሐኪሞች ጽንሱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሆነ ተነግረዋት ነበር። ነገር ግን በወቅቱ ከሚነገረው የበሽታው ምልክት አንጻር ስጋት የነበራት አስከዳር ለቤተሰቧና ለጽንሷ ደኅንነት ስትል የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ ወስና ናሙና በመስጠት ወደ ቤቷ ከተመለሰች ከሁለት ቀን በኋላ ቫይረሱ እንደተገኘባት ተነገራት። አዲሱ በሽታ የተገኘባት ነፍሰጡሯ አስከዳር ሁኔታውን እንደሰማች እራሷን አዘጋጅታ የጤና ባለሙያዎች መጥተው እስኪወስዷት ተዘጋጅታ ስጥጠብቅ "እኛ በጣም ነበር የተረበሽነው" ይላል ባለቤቷ። የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት የጤና ባለሙያዎች አስከዳርን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ቆይታ ህክምና እንድታገኝ ለማድረግ በምሽት መጥተው ከቤቷ ሲወስዷት ባለቤቷ መቶ አለቃ ካሳሁንና ሁለት ልጆቹ ብቻቸውን ከቤት ቀሩ። በወቅቱ ምንነቱ በደንብ ባልታወቀው ገዳይ በሽታ የተያዘች ባለቤቱ ብቻዋን ወደ ለይቶ ማቆያ የተወሰደችበት ካሳሁን በድንጋጤ ውስጥ ሆኖ ምን እንደሚያደርግ አያውቅም ነበር። በአንድ በኩል ልጆቹን ብቻቸውን ትቶ ሚስቱ ወደተወሰደችበት የጤና ተቋም ተከትሎ በመሄድ ከጎኗ በመሆን ጭንቀቷን ለመጋራት ቢፈልግም የልጆቹ ነገር አሳሰበው። በሌላ ወገን ደግሞ ነፍሰጡሯ ባለቤቱ በገዳዩ የኮሮናቫይረስ ተይዛ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ብቻዋን ትሆናለች በሚል ጭንቅ ውስጥ ገባ። በመጨረሻ ግን ቢያንስ ተወሰደች ወደተባለበት ቦታ ሄዶ ማድረግ የሚችለውን ለመሞከር ወስኖ ወደ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ቢሄድም ከህሙማን በስተቀር ማንም መግባት እንደማይችል ተነግሮት በተሰበራ ስሜት ከበር ተመለሰ። ደስታና ሐዘን ከታመመችው ባለቤቱ ጎን ሆኖ ሊያበረታት ባይችልም በስልክ መገናኘት ዕድልን አግኝቶ ነበር። በአንዱ ቀንም ባለቤቱ እስከዳር ስልክ ደወለችለት። በዚሁ ጊዜም "መውለድ አለብሽ ብለው ኦፕሬሽን ሊያደርጉኝ ነው" ብላ ነገረችው። ካሳሁን የሚሆነውን ከርቀት ሆኖ ከመስማማት ውጪ ምንም አማራጭ ስላልነበረው ሐኪሞቹ የደረሱበት ውሳኔን ውጤት መጠበቅ ጀመረ። ባለቤቱ የዚያኑ ዕለት አመሻሽ 12 ሰዓት አካባቢ ቀዶ ህክምና ተደርጎላት ወንድ ልጅ ወለደች። "በቀጣይ ቀናት ቅዳሜ እንዲሁም ዕሁድ ዕለት ለምታውቀው ሰው ሁሉ ስልክ እየደወለች 'እግዚያብሔር ይመስገን በሰላም ተገላገልኩ' እየለች ደስታዋን ስትገልጽ ነበረች" ይላል። ካሳሁን ባለቤቱ መውለዷን ካወቀ በኋላ የእራሱና የልጆቹ የጤና ሁኔታ ጥያቄ ሆነበት። ተከትሎም በተደረገላቸው ምርመራ አሱና ትንሿ ልጁ ላይ ቫይረሱ በመገኘቱ ባለቤቱ ህክምና እየተከታተለች ወደለበት ሆስፒታል እንዲገቡ ተደረገ። የባለቤቱ ወንድምም በኮሮናቫይረስ ተይዞ ወደሆስፒታሉ መጥቶ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ባለቤቱን የማየት እድል አገኘ። ከቤት ከወጣች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆስፒታል ውስጥ ሲያገኛት "ኦክስጅን ተደርጎላት ደርስኩ። እሷም 'እንዳትወጣ' ብላኝ እዚያው አብሪያት እስከ ሌሊቱ ሰባት ሰዓት ቆየሁ" ይላል። ዶክተሮች "'ከዚህ በኋላ በዚህ ሁኔታ ልትቀጥል አትችልም' አሉና ቬንትሌተር [የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ] ወዳለበት ክፍል አስገቧት። ያቺ ጊዜ ዓይን ለዓይን ለመጨረሻ ጊዜ የምነተያይበት ጊዜ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበር" ሲል በሐዘን በተሰበረ ድምጽ ያስታውሳል። ከዚያ በኋላ መቶ አለቃ ካሳሁን ባለቤቱን ከተኛችበት ክፍል እየሄደ ለማየት ቢጠይቅም ሐኪሞቹ እንዲታገስ እየነገሩት ለቀናት ቆየ። መጨረሻ ላይ ህይወቷ ከማለፉ በፊት ቅዳሜ [ግንቦት 29/2012 ዓ.ም] "የናፈቀችኝን ባለቤቴን ዛሬ ማየት አለብኝ ብዬ አጥብቄ ስለጠየቅኳቸው ፈቀዱልኝ።" "ስገባ አስከዳር የለችም፤ አታየኝም። በጣም ደክማለች ከዚያ በኋላ እኔም እራሴን ሳትኩ [ሳግ እየተናነቀው]" አሱ ቢያየትም ባለቤቱ አታየውም ነበር። ያቺ ዕለትም የመጨረሻቸው ሆነች። የካሳሁን ቤተሰብ ሐዘን በዚህ አላበቃም ነበር። ከቀናት በኋላ ከሕበረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት ተደውሎ የትልቋን ልጁን የጤና ሁኔታ ለማወቅ በድጋሚ ምርመራ ማድረግ እንዳለባት ተነግሮት ውጤቷ ፖዘቲቭ ሆነ፤ ሌላ ጭንቀት ተጨመረበት። ካሳሁን የልጆቹ እናት የቀናት ዕድሜ ብቻ ያለውን ጨቅላ ልጇን ትታ በኮሮናቫይረስ ሰበብ ለሞት ስትዳረግ። ሰማይ እላዩ ላይ የተደፋበት ያህል ነበር የተሰማው። ዙሪያ ገባው ጨለማ ሆነበት። በዚያ ላይ እሱም ሆነ ሁለቱ ሴት ልጆቹ በቫይረሱ ተይዘው ነበር። የእናት፣ የአባትና የሁለት እህቶቹ እንክብካቤና ፍቅር የሚያስፈልገው ጨቅላው ልጅ ከእነሱ ተነጥሎ በሐኪሞች እንክብካቤ እየተደረገለት ነው። "አብይስማክ" ሦስት ልጆቹን እናት የኮሮናቫይረስ የነጠቀው ካሳሁን የባለቤቱ ያለመኖር የፈጠረበት ሐዘን ከወራት በኋላ አሁንም ድረስ ትኩስ ነው። የባለቤቱ ሞት በህይወቱ ላይ የፈጠረው ክፈተት በምንም የሚሞላ አልሆነለትም "እንቅልፍ የለኝም። አልተኛም። እንደገና....[ለቅሶ]...እና ያው ሳልወድ በግዴ ከልጆቼ ጋር ተለያይቻለሁ። አሁን ትልቋ በተለይ በጣም እየተረበሸች ነው። እና በጣም ከባድ ነው....[ሳግ እየተናነቀው]" ሁለት ሴት ልጆች ያሏት አስከዳር ሦስተኛውን እርግዝና ካወቀች በኋላ ወንድ መሆኑን ስታውቅ በእጅጉ ተደስታ እንደነበር ካሳሁን ያስታውሳል። እናቱን በኮሮናቫይረስ ከመሞቷ በፊት "አብይስማክ" ብላ ስም ያወጣችለትና የጓጓችለት ልጇ ካለእሷ አሁን ዘጠኝ ወር ሆኖታል። በወረርሽኙ ምክንያት የቤተሰቡ ራስ የሆነችውን እስከዳርን የተነጠቀው ቤተሰብ፤ እድለኛ ሆነው ለክፉ ባይሰጣቸውም ቫይረሱ የቤተሰቡን አባላት በሙሉ አዳርሶ ነበር። በዚህም ሳቢያ ቤተሰቡን ገጥሞት የነበረው ማግለል በጣም ከባድ እንደነበር ካሳሁን ያስታውሰዋል። በሽታው በተከሰተበት የመጀመሪያዎቹ ወራት የነበረው ፍርሃት ሁሉንም ተጠራጣሪና ፈሪ አድርጎት ስለነበር በርካታ ሰዎች እሱንና ልጆቹን ይርቁ ነበር። ቤት ለመከራየትም አስቸጋሪ እንደሆነበት ይናገራል። "በቃ ቀብር አትሄድም" የኮሮናቫይረስ የታመመ ወዳጅ ዘመድን ማስታመምና መጠየቅ ብቻ ሳይሆን በርካታ ነገሮችን አመሰቃቅሏል። በሞት የተለየን የቅርብ ሰው አልቅሶ መቅበርና የመጨረሻ ስንብት ማድረግን የማይቻል ነገር አድርጎታል። ካሳሁንም እንደፍላጎቱ ሳያስታምማት ወረርሽኙ የነጠቀውን ባለቤቱን ከአስከሬኗ ጎን ሆኖ እንባውን አፍስሶ፣ ሐዘኑን በመግለጽ የመጨረሻ ስንብት ለማድረግ ከማይቻልበት ሁኔታ ላይ እንደነበረ ያስታውሳል። "በጣም ከባድ ነበር። የሆነ ቀን ጠሩኝና 'ተሰናበታት' አሉኝ። 'ምንድን ነው መሰናበት' ስላቸው አይ 'በቃ ቀብር አትሄድም' አሉኝ። 'ለምን' ስላቸው 'ከዚህ [ከሆስፒታሉ] አይወጣም' አሉኝ።" ይህ ለካሳሁን ፈጽሞ የሚዋጥለት ሐሳብ አልነበረም። አብረውት ደግሞ የባለቤቱ እናት ነበሩ። "'አይ እኔና እናቷማ እንቀብራለን' በሚል ጭቅጭቅ ተፈጠረ። እነሱም ተረዱን መሰለኝ እኔና እናቷ ቀብሯ ላይ እንድንገኝ ተደረገ።" ይህም ቢሆን ግን ካሳሁን ለውድ ባለቤቱ እሱ የሚፈልገውን አይነት የቀብር ሥነ ሥርዓት ስላልተፈጸመላት አሁን ድረስ ይቆጫል። "በቃ ይህ በህይወት እካለሁ ድረስ የእግር እሳት እንደሆነብኝ ይኖራል" ሲል በሐዘን በተሰበረ ድምጽ ይናገራል። ያልበረደ ሐዘን "ክረምት ነበር። በቀብሩ ቦታ የነበረው ሁኔታ በጣም ከባድ ነበር። በወቅቱ አስክሬኗና እኛ ታጅበን የሄድነው በፖሊስ ነው። ወደ ቀብር ቦታ ከአምስት ሰው በላይ አልገባም። እኔም እናቷም ወደ መቃብር ቦታው አልሄድንም ያመጣን መኪና ጋር ቆመን ነበር የተሰናበትናት።" አሁን ድረስ የባለቤቱን ሞት ለመቀበል የተቸገረው ካሳሁን "በእንደዚህ አይነት መልኩ እሷን ማጣት ከባድ ነው። ከባድ ህይወት ነው እየመራሁ ያለሁት። አሁንም ግራ ነው የሚገባኝ የሆነ ቦታ.......[ለቅሶ]........ደርሼ ስመጣ. . . የማገኛት ነው የሚመስለኝ። እና አሁንም ማመን አቅቶኛል" ይላል ሐዘኑ እንደ አዲስ እያገረሸበት። መቶ አለቃ ካሳሁን በደረሰበት መሪር ሐዘን ምክንያት አስካሁን አልተረጋጋም ልጆቹን የባለቤቱ እናት እየተንከባከቡለት ነው። ትልቆቹ ሴት ልጆቹ ጎበዞችና ጠንካሮች እንደሆኑ ይናገራል። ከዚህም በላይ እንዲበረቱለት ቢፈልግም ካለበት ጭንቀት የተነሳ የእሱ አለመረጋጋት ተጽእኖ እንዳይፈጥርባቸው ይሰጋል። በተጨማሪም የባለቤቱ ምትክ የሆነውን የመጨረሻውን ልጁን በልዩ ሁኔታ እንደሚመለከተው የሚናገረው ካሳሁን "ልጄን ሳየው በጣም ነው ደስ የሚለኝ። ባለቤቴ እራሷን አሳልፍ የሰጠችበት ልጄ ነው። በጣም ስትጓጓለት የነበረ ልጅ ነው። በቃ እሱን ሳየው እሷን የማይ ነው የሚመስለኝ።" ባለቤቱን ነጥቆ ፍቅር የሞላበትን የሞቀ ቤቱን ያቀዘቀዘበት የኮሮናቫይረስ ለመቶ አለቃ ካሳሁን ደመኛ ጠላቱ ነው። "ኮሮና ቤቴን ነው ያፈረሰው። ከምወዳት ባለቤቴ ተለይቻለው። ልጆቼን እያየኋቸው በብዙ ችግር ምክንያት አብሬያቸው አይደለሁም። በአንድ ጎጆ ተሰብሰበን የነበርን ሰዎችን በትኖናል።"
xlsum_amharic-train-197
https://www.bbc.com/amharic/48455959
አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ
የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከሚፈታተኑ በርካታ ነገሮች መካከል አንዱ ቴክኖሎጂ ነው። በመጀመሪያ በሸክላ ይደመጥ የነበረው ሙዚቃ ወደካሴት ከዚያም ወደሲዲ ፈቅ እያለም በሶፍት ኮፒ መሸጥ ጀመረ።
[ "የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከሚፈታተኑ በርካታ ነገሮች መካከል አንዱ ቴክኖሎጂ ነው። በመጀመሪያ በሸክላ ይደመጥ የነበረው ሙዚቃ ወደካሴት ከዚያም ወደሲዲ ፈቅ እያለም በሶፍት ኮፒ መሸጥ ጀመረ።" ]
ሁላችንም የስልካችን ምርኮኛ፤ የስልካችን እስረኛ እየሆንን መምጣታችን ለኢትዮጵያ ሙዚቀኞች የሲዲ ገበያ ቸር ወሬ አልነበረም። ለበርካታ ጊዜያት ጎምቱ ድምጻውያንም ሆኑ አዳዲስ ሙዚቀኞች ሥራዎችን ጨርሰው ለገበያ ለማውጣት እግር ተወርች ከሚያስራቸው ጉዳይ አንዱ የላባቸውን ዋጋ በአግባቡ የሚያገኙበት መሸጫ አለመኖሩ ነበር። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች ሙዚቃ አቀናባሪው ኤሊያስ መልካ "እኔ ጋር እንኳ የበርካታ ድምፃውያን ሥራ አልቆ ቁጭ ብሏል" በማለት እማኝነቱን ይሰጣል። ለኤሊያስ የሲዲ ቴክኖሎጂ እየቀረ መምጣቱም ሌላው የሙዚቃ ገበያውን አደጋ ላይ የጣለ ጉዳይ ነው። ሲዲ የሚወስዱ ቴፕ ሪከርደሮች እየቀሩ፣ ጂፓስ በየቤታችን እየገባ፣ መኪኖች ሳይቀር ፍላሽ ብቻ እንዲያጫውቱ እየሆኑ መምጣታቸውን ያስተዋለው ኤልያስ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር የሚሄድ መፍትሔ ከመሞከር አልቦዘነም። የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዳዊት ይፍሩም የኤልያስን ስጋት ይጋራሉ። "በኛ አገር ሙዚቀኞች ሥራቸውን ይሠሩና መርካቶ ላሉ አሳታሚዎች በመስጠት ይሸጣሉ" በማለት የሙዚቃ ገበያውን አሠራር ያስረዳሉ። • "በ 'ፍቅር እስከ መቃብር' ላይ ህይወት የዘራው አባቴ ነው" አሳታሚው ካሳተመ በኋላ ደግሞ በመላው አገሪቱ በማሰራጨት ሽያጭ ይካሄድ ነበር፤ በማለት የድሮውን የሙዚቃ የገበያ ሥርዓት ያብራራሉ። በዚህ መካከል ድምፃውያን አንዴ በተነጋገሩበት ዋጋ ይሸጣሉ፤ ከዚያ በኋላ ምን ያህል ያወጣል? ምን ያህል ያተርፋል? የሚለው ላይ እጃቸውን አያስገቡም በማለትም ያክላሉ። ዓመት ዓመትን ሲወልድ አሠራሩ እየተቀየረ መጥትቷል። ካሴት የሚያሳትም የለም። ሲዲ የሚያሳትመውም ቁጥሩ ቀንሷል። ላሳትም ብሎ ደፍሮ ሥራውን ለገበያ የሚያቀርብ ባለሙያም ፈተናው ብዙ ነው። በቀላሉ ኮፒ ተደርገው የሚሸጡበት በመሆኑ ከአጠቃላይ ከሽያጩ እጠቀማለሁ ማለት አይችልም ይላሉ። • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን "ለዚህም ነው በዚህ ዘመን አሳታሚ የሌለው" ይላሉ አቶ ዳዊት። አሁን ያለው ድምፃዊ ተበድሮም ይሁን ተለቅቶ አንድ ነጠላ ዜማ ካወጣ በኋላ ድምፃዊው ስራው ከተወደደለት ሰርግ ወይንም ግብዣዎች ላይ ሲቀናም ከሀገር ውጪ እየተጋበዘ ይሰራል በማለት ያለውን ውጣ ውረድ ይገልጣሉ። ይህም ከሲዲ ሽያጭ አተርፋለሁ የሚል ድምፃዊ እንዳይኖር አድርጓል። ታዲያ ምን ተሻለ? የሙዚቃ አቀናባሪው ኤልያስም ሆነ የሙዚቀኞች ማኅበር ፕሬዝዳንቱ ዳዊት ስጋት ይቀረፍ ዘንድ መፍትሔ ይሆናል በማለት፤ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሰብሰብ ብለው ሀሳብ ያወጡ ያወርዱ ከጀመሩ አምስት ዓመት አልፏቸዋል። በኋላም የኢትዮጵያ የሙዚቃ ባለሙያዎች ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጁት አውታር የሙዚቃ መሸጫ መተግበሪያና ድረ ገጽ ሥራወን በማጠናቀቅ ዓርብ ግንቦት 23 ቀን 2011 ዓ .ም. በይፋ ሥራ ይጀምራል ተባለ። "አዲሱ አመተግበሪያ ኢትዮጵያውያን የፈለጉትን ሙዚቃ በፈለጉት ጊዜና ቦታ በእጅ ስልኮቻቸው በኢንተርኔት አማካይነት ለመግዛት ያስችላቸዋል" ይላል ኤልያስ። አውታር መልቲ ሚዲያ የተመሰረተው በኤልያስ መልካ፣ ጆኒ ራጋ፣ ዳዊት ንጉሡና ኃይሌ ሩትስ ሲሆን፤ በመተግበሪያው ከሚሸጡት ሙዚቃዎች ኢትዮ-ቴሌኮም ድርሻ ይኖረዋል። • ''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" ድምፃዊት ፀደኒያ ገብረማርቆስ ይህን የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ ከሚደግፉት አንዷ ነች። "ስልጡን አማራጭ" ስትልም ትጠራዋለች። የኢንተርኔት አቅምና ተደራሽነት ከፈቀደ በርካታ ሙዚቃ መሸጥ ይቻላል በማለት ተስፋዋን ትገልጻለች። ሰዎች ዘመናዊ ስልክ መያዝ በመጀመራቸው፣ ኢንተርኔት አጠቃቀማችንም ከፍ እያለ በመምጣቱ እንደዚህ አይነት የመሸጫ መንገድ ማስለመዱ መልካም መሆኑን ትገልፃለች። ድምጻዊት ፀደኒያ እስካሁን ስራዎቿን ወደ አውታር ወስዳ በእናንተ በኩል ይሸጥልኝ ብላ ባትሰጥም፤ አገልግሎቱ ከተጀመረ ግን ይህንን ለማድረግ አይኗን እንደማታሽ ትናገራለች። • ታዋቂዎቹ ኤርትራዊያን በሙዚቃቸው ምክንያት ይቅርታ ጠየቁ ብዙ ሰዎች በአንድ ሲዲ ውስጥ ያሉ ሥራዎችን በአጠቃላይ ስለማይወዱት "እያለፉ ነው የሚያደምጡት" የምትለው ፀደኒያ፤ ግዴታ አስራ ምናምን ዘፈኖች መግዛት አይጠበቅባቸውም ትላለች። ይህ አዲስ መተግበሪያ አንድ ሰው የሚፈልጋቸውንና የሚመርጣቸውን ዘፈኖች ብቻ መርጦ የመግዛት እድል ስለሚሰጥ ተመራጭ መገበያያ መንገድ ነው ስትል ሀሳቧን ታጠናክራለች። አውታር፡- ችግር የወለደው መፍትሔ ኤልያስና ጓደኞቹ ኢትዮ-ቴሌኮም ለተጠቃሚዎቹ አጫጭር መልእክቶችን በጅምላ ሲልክ ሲመለከቱ፤ እኛስ በዚህ መንገድ ለምን ሙዚቃ አንሸጥም የሚል ሀሳብ እንዳፈለቁ ያስታውሳል። ኢትዮ-ቴሌኮም ዘንድ ቀርበው ሀሳባቸውን ሲያስረዱ ግን በአጫጭር መልእክት ጽሑፍ እንጂ ድምፅ መላክ እንደማይቻል ተነገራቸው። እነኤልያስ በሙዚቃ ሥራ ውስጥ በየእለቱ ቴክኖሎጂ ሲቀየር ተመልክተዋል። "ከካሴት ወደ ሲዲ በሄድንበት ፍጥነት የሲዲ ቴክኖሎጂም ሲቀየር ተመልክተናል" ይላል። ስለዚህ በድረገጽ የሚሸጡበት መንገድ ያስቡ ጀመር። • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" ይህ ሀሳብ ግን ከዝሆን የገዘፈ ችግር ከፊቱ አለ። ሰዎች ሙዚቃውን መግዛት ቢፈልጉ በምን ሥርዓት መክፈል እንደሚችሉ አይታወቅም። ምክንያቱ ደግሞ የባንክ የክፍያ ስርዓትን በኦን ላየን ግብይት ማድረግ ስለማያስችል ነው። ስለዚህ ያለው አማራጭ ቴሌ ብቻ ነው። ቴሌ ከእሱ ፈቃድ ወስደው አጫጭር መልዕክቶችን ለሚልኩ ድርጅቶች ከተጠቃሚዎች ገንዘብ ቆርጦ የድርሻውን በመውሰድ ለድርጅቱ ደግሞ የድርሻውን ይሰጣል። "ቴክኖሎጂው ለጽሑፍ ብቻ ስለሆነ ሙዚቃ መላክ አያስችልም" ቢባሉም እነድምፃዊ ኃይሌ ሩትስ ተስፋ ሳይቆርጡ ተመላልሰው ከቴሌ ጋር ተነጋገሩ። ለዚህ ምክንያት የሆናቸው ቴሌ ፓኬጅ ዳታ መሸጥ መጀመሩ ነው። በፓኬጅ ዳታው ከፍ ያለ ሜጋ ባይት ኢንተርኔት ስለሚሸጥ፤ ምናልባት አሁን ሳይቻል አይቀርም የሚል ተስፋ አደረባቸው። የኢትዮ-ቴሌኮም ኃላፊ የነበሩት አቶ አንዱዓለም አድማሴም ይቻላል አሏቸው። • መነሻ ሀሳብ ወይስ የሙዚቃ ቅጂ መብት ጥሰት? ኤልያስ አሁንም ግን ቴሌ ራሱ ከጽሑፍ ውጪ ሌላ መልእክት ለመላክ ዝግጁ ስላልነበር ወደሥራ ለመግባት ፈተና እንደሆነባቸው ይናገራል። የሙዚቃ ባለሙያዎቹ ኤልያስ፣ ጆኒ ራጋ፣ ኃይሌ ሩትስና ዳዊት ንጉሡ ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በጋራ የሚሠሩት ይህ የሙዚቃ መሸጫ መተግበሪያ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የተሠሩ፤ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን ያቀርባል ተብሏል። እነዚህ ሙዚቀኞች ሥራውን ለመሥራት ከቴሌ ጋር Value Added Service (VAS) ለመሥራት ፈቃድ ማውጣት ያስፈልግ ስለነበር የንግድ ፈቃድ ማውጣት አስፈልጓቸዋል። በዚህ ምክንያት አውታር መልቲ ሚዲያን አቋቋሙ። ድርጀቱ ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በጋራ መሥራት የቫስ (VAS) ፈቃድ ማውጣታቸውንም ገልጠዋል። ሦስቱ የሙዚቃ ባለሙያዎች በመጪው ዓርብ ማታ በሸራተን ይፋ የሚደረገውን የሙዚቃ ሽያጭ ሥርዓት፤ የአገሪቱ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ የገጠሙትን ፈተናዎች ለመወጣት ኹነኛ መንገድ ነው የሚል ዕምነት አላቸው። በዚሁ የሽያጭ ሥርዓት ድምፃዊ፣ የግጥም ጸሐፊ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማ ደራሲና ፕሮዲውሰር ትርፍ እንዲከፋፈሉ ይደረጋል። ሙዚቃው በአውታር መተግበሪያ ተጭኖ እንዲሸጥ አምስቱ ባለሙያዎች ተስማምተው መፈረም ይኖርባቸዋል ይላል ኤልያስ። አሁን ሰዎች በአንድ ጊዜ አገልግሎቱን ፈልገው ቢመጡ ሊከሰቱ የሚችሉ መዝረክረኮችን ለማስቀረት እየሞከርን ነው የሚለው ኤልያስ፤ ከአርብ ማታ ጀምሮ መተግበሪያው በጎግል ፕሌይ ስቶር ይገኛል ይላል። • በዝማሬ የተካኑት ዓሳ ነባሪዎች ይህንን መተግበሪያ በሞባይሉ ላይ የጫነና በአገር ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሙዚቃውን መጫን የሚችል ሲሆን፤ ካልሆነ ደግሞ ኢትዮ-ቴሌኮም ሊንክ የሚልክ ይሆናል በማለት አፕሊኬሽኑን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙበትን መንገድ ያብራራል። ኢትዮ-ቴሌኮም ለተጠቃሚዎቹ በአጠቃላይ የሚልከው ጥቅል መልእክት ላይ ማስፈንጠሪያውን አብሮ እንደሚልክ የሚናገረው ኤልያስ፤ ስማርት ስልክ ያላቸው ማስፈንጠሪያውን ሲጫኑ ወዲያውኑ በስልካቸው ላይ መተግበሪያው የሚጫን ሲሆን፤ ስማርት ስልክ የሌላቸው ግን በቁጥር እያስመረጠ እንዲጠቀሙ የሚያስችለው ዩ ኤስ ኤስ ዲ የሚባለው ቴክኖሎጂ ለመጨረስ በሥራ ላይ መሆናቸውን ይገልጣል። የአውታር ትሩፋቶች ምን ምን ናቸው? መተግበሪያው ምስሎች፣ ስለዘፋኙና ሌሎች ሙዚቀኞች መረጃ እንዲሁም የዘፈኑን ግጥም የያዘ መሆኑን የሚናገረው ኤልያስ "ሙዚቃውም ጥራት አለው" ይላል። ይህ የሙዚቃ መሸጫ መተግበሪያ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው ያሉት አቶ ዳዊት፤ አውታር የተባለው መተግበሪያ ሰዎች የገዙትን ሙዚቃ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ለሌላ ሰው ከማስተላለፍ የሚከለክል ሥርዓት አለው ሲሉ ለሙዚቀኞች ያለውን ጥቅም ያብራራሉ። ሙዚቃ አቀናባሪው ኤልያስ በበኩሉ፤ መተግበሪያው ላይ የተጫነ አንድ ሙዚቃ በአራት ብር ከአምሳ ሳንቲም እንደሚሸጥ ይናገራል። ይህ በአንጋፋዎቹ የሙዚቃ ባለሙያዎች እና በአዳዲስ ድምፃውያን የተሠሩትን ይጨምራል። መተግበሪያው የኢትዮጵያን ሙዚቃ በውጭ አገራት ስንት ለመሸጥ እንደታቀደ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም ብሏል ኤልያስ። ይህ ጉዳይ የድምፃዊት ፀደኒያም ስጋት ሲሆን፤ እንደሀገር በዚህ ዘርፍ ወደኋላ ቀርተናል በማለት ቁጭቷን ትገልጣለች። መተግበሪያው በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አገልግሎት ይሰጣል የሚለው ኤልያስ በኦሮምኛ፣ በትግሪኛ፣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ እንዲሠራ ሆኖ የተዘጋጀ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ እምነት ተከታዮችም፤ የሙስሊም፣ የኦርቶዶክስ፣ የፕሮቴስታንት፤ የሚፈልጉትን መንፈሳዊ መዝሙር ወይንም መንዙማ ማግኘት እንዲችሉ ተደርጎ መደራጀቱን ያስረዳል። • ፊቼ ጨምበላላ፦ የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመት መተግበሪያው በዓመተ ምሕረት፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በስልት ተከፋፍሎ የተቀመጠ መሆኑን አብራርቷል። "የኢትዮጵያ ሙዚቃ አብዛኛው ገበያ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው" የሚለው ኤልያስ፤ ይህ መተግበሪያ ለጊዜው የሚሠራው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ያስረዳል። ነገር ግን ከአገር ውጪ ያሉ አድማጮች ገዝተው መጠቀም እንዲችሉ ከባንክ ጋር እየተነጋገሩ ነው። በአንድ ሙዚቃ ላይ አምስት ሥራዎች አሉ የሚለው ኤልያስ፤ እነዚህም ማቀናበር፣ መዝፈን፣ ግጥም መፃፍ፣ ዜማ መድረስ እንዲሁም ፕሮዲውስ ማድረግ መሆናቸውን ያስረዳል። በአንድ የሙዚቃ ሥራ ውስጥ እነዚህን ሥራዎች አንድ ወይም ሁለት ሰው ደርቦ የሚሠራቸው ሊሆኑ ቢችሉም፤ ክፍያ ሲቀመጥ ግን ለሥራዎቹ እንደሆነ ያስረዳል። ስለዚህ ከአንድ የሙዚቃ ሥራ ላይ እነዚህ አምስት ሥራዎች እያንዳንዳቸው 20 በመቶ ክፍያ ያገኛሉ። ይህ የሙዚቃ መሸጫ መተግበሪያ አርብ ማታ ሥራ ሲጀምር፤ 24 ሰዓት፣ በየትኛውም የአገሪቱ ስፍራ፤ ሰባቱንም ቀን መሸጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው። በተለይ አዲስ ድምፃውያን ወረፋ ሳይጠብቁ በፈለጉበት ወቅት የሙዚቃ ገበያውንና አድማጮቻቸውን ማግኘት ይችላሉ። ዝግጅት በሸክላ የተቀረፁ የድሮ ዘፈኖች፣ በካሴት የተቀዱ የስድሳዎቹና የሰባዎቹ ሥራዎች፣ በሲዲ የነበሩ ሁሉ ተሰብስበው ወደኮምፒውተር ተገልብጠዋል የሚለው ኤሊያስ፤ አንዳንዶቹ ባለቤቶቻቸው በሕይወት ስለሌሉ ከሕጋዊ ወራሾቻቸው ጋር በመነጋገርና በመፈራረም እንዲጫኑ ይደረጋል ብሏል። ሁለት ዘፈኖች ብቻ ከሚይዘው ሸክላና ከሰዎች ላይ ሙዚቃ በማሰባሰብና በመግዛት ወደኮምፒውተር መገልበጥ ዋናው ሥራ እንደነበር የሚያስታውሰው ኤልያስ፤ "ሁሉም ሙዚቃ እኛ ጋር ባይኖርም በተቻለ መጠን ሁሉንም ለማሟላት እየሠራን ነው" ብሏል። አንድ ድምፃዊ ሥራው አውታር ላይ እንዲጫን፤ ፎርማቱን ወደ ኤም ፒ 3 በመቀየር 224 ኬቢ ወይንም 160 ኬቢ በማድረግ የዘፈኑን ግጥምና ፎቶውን በሶፍት ኮፒ ማስቀመጥ ብቻ በቂ ነው ይላል። ከዚያ የገዙትን ሰዎችና ምን ያህል እንደተሸጠ ለማወቅ የሚረዳውን ኮድ ከማግኘቱ በፊት መፈራረም ይጠበቅበታል። አንድ ነጠላ ዘፈን አራት ብር ከሀምሳ፤ አምስት ዓመት ያልሞላው ሙሉ አልበም አስራ አምስት ብር ይሸጣል። በአንድ ሲዲ ላይ የሚኖረው ዘፈን ምንም ያህል ቁጥር ቢኖረው ሙሉ አልበም 15 ብር እንደሚሸጥ ያሰምርበታል። • በታሪካዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን አለ? አቀናባሪው ተከፍሎት ስለሆነ የሚያቀናብረው እስከአምስት ዓመት ድረስ ሌላ ገንዘብ አይጠይቅም የሚለው ኤልያስ፤ ይህ የድምፃዊው መብት በቅጂና ተዛማጅ መብቶች በኩልም የተጠበቀ ነው በማለት "በአምስት ዓመት ውስጥ ወጪውን ሸፍኖ ትርፍ ያገኛል ተብሎ ይታሰባል" በማለት ያስረዳል። በዚህ ጊዜ ውስጥ አብዛኛው መብት የዘፋኙ ነው በማለት ያክላል። ከአምስት ዓመት በኋላ ግን ድጋሚ መክፈል ስላለበት ሙዚቃው ተነጥሎ ነው የሚሸጠው የሚለው ኤልያስ፤ ይህ የሆነው በአንድ ካሴት ውስጥ ያሉ ዘፈኖችን የተለያዩ ሰዎች ስለሚያቀናብሯቸው፣ ግጥምና ዜማቸውንም ስለሚደርሱ ለመክፈል በጅምላ መሸጥ ስለማያዋጣ ነው በማለት አሠራራቸውን ያብራራል።
xlsum_amharic-train-198
https://www.bbc.com/amharic/news-42022230
ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን ለቀቁ
የዚምባቡዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን መልቀቃቸውን የሀገሪቱ ፓርላማ አፈጉባኤ አስታውቀዋል።
[ "የዚምባቡዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን መልቀቃቸውን የሀገሪቱ ፓርላማ አፈጉባኤ አስታውቀዋል።" ]
ይህ ያልተጠበቀ ውሳኔ የተሰማው የሀገሪቱ ህግ አውጪዎች በሁለቱ ምክር ቤቶች ጥምር ስብሰባ እርሳቸውን ለመክሰስ በሚያስችል ሁኔታ ዙሪያ እየተወያዩ ባለበት ጊዜ ነው። ሙጋቤ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በፈቃዳቸው እንዲለቁ የቀረበላቸውን ጥያቄና ግፊት አልተቀበሉም ነበር። ዛሬ ግን ለ37 ዓመታት ከነበሩበት ሥልጣን ለመልቀቅ መፍቀዳቸው ተዘግቧል። በመልቀቂያ ደብዳቤያቸው ውሳኔያቸውን የቀየሩት በፈቃዳቸው እንደሆነና ጤናማ የሥልጣን ሽግግር እንዲካሄድ በማሰብ እንዳደረጉት ገልጸዋል። ዚምባቡዌያውያንም ዜናውን ከሰሙ በኋላ አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን እየገለጹ ነው።
xlsum_amharic-train-199
https://www.bbc.com/amharic/news-56795580
"ፖለቲከኞች የሶማሌን ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ አያስቡትም" የኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ መሐመድ
ከሦስት ዓመታት በፊት ለውጡን ተከትሎ ለሰላማዊ ትግል ወደ አገር ውስጥ ከገቡ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። ቢቢሲ ስለ ምርጫና ስለ ፓርቲው እንቅስቃሴ ከኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የፌደራል መንግሥት ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ መሐመድ ጋር ቆይታ አድርጓል።
[ "ከሦስት ዓመታት በፊት ለውጡን ተከትሎ ለሰላማዊ ትግል ወደ አገር ውስጥ ከገቡ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። ቢቢሲ ስለ ምርጫና ስለ ፓርቲው እንቅስቃሴ ከኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የፌደራል መንግሥት ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ መሐመድ ጋር ቆይታ አድርጓል።" ]
ስለኦብነግ እምብዛምም ከማይታወቁ ነገሮች እንጀምር። አፈጣጠሩ ከዚያድባሬ ወረራ ጋር የሚያያዝ ታሪክ አለው። በሽግግሩ ጊዜ ተሳትፋችኋል። ከምዕራብ ሶማሊያ ነጻነት ግንባር ወጣት ሊግ ነው ኦብነግ የተፈጠረው ይባላል። ክልሉን ለሁለት ዓመት ያህል አስተዳድራኋል። ልክ ነኝ? የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) የተመሰረተው (እአአ) ነሐሴ 15 ቀን 1984 ነው። በወቅቱ የነበረው የምዕራብ ሶማሌ ነጻ አውጭ ግንባር (WSLF) በኢትዮጵያ ውስጥ በነበረችው ሶማሌዎች በሚኖሩበት አገር ከተዳከመ በኋላ የግንባሩ ወጣቶች ዘርፍ የነበሩ አባሎች ተሰባስበው የመሠረቱት ግንባር ነው። የምዕራብ ሶማሌ ነጻ አውጭ ግንባር በኢትዮጵያ ሶማሌዎች የተቋቋመው ነው። ሆኖም በሶማሊያ መንግሥት ይደገፍ የነበረ ድርጅት ነበር። ወጣቶቹ ተሰባስበው፣ ተጠያይቀው ትግላችን እየተዳከመ ስለሆነ ምን እናድርግ በማለት የመሠረቱት ድርጅት ነው- ኦብነግ። እነዚህ ወጣቶች ትግላቸው ከሶማሊያ መንግሥት ነጻ አለመሆኑንና ጣልቃ ገብነት እንዳለው ተረድተው የመሠረቱት ነው። ኦብነግ በሶማሊያም በኢትዮጵያም ክልክል ስለነበርና ተቀባይነት ስላልነበራቸው በድብቅ ለዓመታት ሲሠሩ ቆይተዋል። ድርጅቱ ሲመሠረት አቶ አብዱረህማን መህዲ ነበሩ ሊቀመንበር። ከዚያም መሐመድ አብዲ መገኒ ለሁለት ወር ያህል ሊቀመንበር ሆነዋል። ከዚያም አቶ ሼህ ኢብራሂም አብደላህ ቋሚ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠው ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ መርተዋል። እርሳቸው አሁን በሕይወት የሉም። የኦብነግ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሶማሌዎች ኦጋዴን ተብሎ የሚጠራውን አገር ነጻ ማውጣት ነበር። የደርግ መንግሥት ከወደቀ በኋላ የኦብነግ መሪዎች እና ኃላፊዎች አገር ውስጥ ገብተው በመጎብ ዞን፣ ገርቦ በምትባል ወረዳ ሕዝብ ሰብስበው፤ ብሔራዊ ውይይት አድርገው ሸህ ኢብራሂም አብደላ እንደገና ተመርጠው በሽግግር መንግሥቱ ተሳትፏል። በመጀመሪያው ምርጫም ተሳትፎ በ84 በመቶ ድምፅ አብላጫ ድምጽ አግኝተው በክልሉ መንግሥት መሥርተዋል። ኢህአዴግ/ሕወሓት ምን ዓይነት የሕዝብ ድጋፍ፣ ዓለማና አቋም እንዳለን ካየ በኋላ ግን ወረረን። በዚህ ምክንያት ለትጥቅ ትግል ጫካ ተገባ፡፡ ፍላጎታችን በዲሞክራሲ መሳተፍ ነበር፤ ተገደን፣ ተገፍተን ጫካ ገባን። ለምን ያህል ጊዜ ነው ክልሉን? ለተወሰነ ጊዜ ነበር። አንድ ዓመት ከአሥር ወር ገደማ አስተዳድረናል። አሁን ያለው የክልሉ ሰንደቅ ዓላማ እንዲሁም እስካሁን ያለው በሶማሊኛ የተጻፈ መርሐ ሥርዓተ ትምህርት [ካሪኩለም] በኦብነግ በተመራው ክልላዊ መንግሥት ነበር የተጀመረው። መሠረታዊ የሆኑ ሥራዎችን ከጀመርን በኋላ የሕዝብ ድጋፋችን በጣም ከፍተኛ ስለነበር ጦርነት ተከፈተብን። ኃላፊዎችን መግደል ጀመሩ በዚህ ምክንያት ወደ ጫካ ገባን። ላለፉት 36 ዓመታት የቆየ አንጋፋ ድርጅት ነው። በዋናነት ለራስ ገዝ [self determination] ሲዋጋ የኖረ የፖለቲካ ድርጅት ነው። ለውጡን ተከትሎ በተደረሰ ስምምነት ወደ አገር ቤት መጥታችኋል። ነገር ግን አሁንም ስማችሁ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ነው። እንዴት ይህን ስም ይዛችሁ ትቀጥላላችሁ? በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ስሜት ይሰጣል? ጥሩ ጥያቄ ነው። በለውጥ ስማችን አይለወጥም። በሕዝብ ፍላጎት ነው ይህ ስም የተሰየመው። አቋም የያዘውም በሕዝብ ፍላጎት ነው። ዝም ብሎ በመሪዎች፣ በሁለት. . . በሦስት. . . በሃምሳ በመቶ ሰዎች የሚወሰን አይደለም። የመገንጠልም ሆነ ወደ ኢትዮጵያ ለመሳተፍ የሚወሰነው በሕዝብ ድምፅ ነው። ይህ ሕዝብ ምን ዓይነት ድርጅት እንደሚፈልግና ምን ዓይነት አቋም እንደሚይዝ ድርጅቱ የሚወሰነው በሕዝብ ድምፅ ነው። እኛ ከለውጡ ሰዎች ጋራ ስለተግባባን የድርጅቱን ስም፣ አቋምና ዓላማ መለወጥ አንችልም። እንደዚህ ዓይነት ባህርይም የለንም። በሕዝብ የተቋቋመ ድርጅት፣ ለሕዝብ የተቋቋመ ዓላማ ስለሆነ፤ አንቀይርም። መቀየርም አንችልም። ሕዝብ ተጠይቆ፣ ተሰብስቦ፣ ብሔራዊ ስብሰባ ተካሂዶ ነው ዓላማችን የሚቀየረው። የኢትዮጵያ መሪዎች ደግሞ ሕዝብን የመሳብ ጠባይ ካላሳዩ ዝም ብሎ በቀላል የሚቀየር ነገር አይደለም። ታዲያ ኮንፈረንሱን የማታደርጉት ለምንድን ነው? የመቀየር ጊዜው አሁን አይደለም ብላችሁ ስለምታምኑ ነው? ነጻ አውጭ ግንባር ብሎ ራሱን ከማዕከላዊ መንግሥት ለመገንጠል የሚያስብን ድርጅት ስም ይዞ ከሌሎች ፓርቲዎችስ ጋር እንዴት ነው የምትሠሩት? እኔ ግራ የገባኝ፣ እኔ ግራ የሚገባኝ ይሄ ጥያቄያችሁ ነው። ብዙ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ይሄን ጥያቄ ሲጠይቁኝ ቆይተዋል። የመገንጠል [self determination] ጉዳይ ብዙ ጋዜጠኞች …፤ ምንድነው ችግራችሁ? ከዚህ ነጥብ ማለፍ ያቃታችሁስ ለምንድነው? እንዴ! የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ራሱ እስከ መገንጠል ይፈቅዳል። ለምን ይሄ ነገር ለጋዜጠኞች ራስ ምታት (stress) ሆነባችሁ? ለምን የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይዋጥላችሁ ቻለ? ለምን ይሄ ነገር ጉሮሯችሁ ውስጥ ተቀርቅሮ እንደቀረ እኔ ግራ ገባኝ። ሕጋዊ የሆነ ነገር ነው፤ ሕዝብ ይሆንልኛል ባለው መሄድ አለበት። ኢትዮጵያ ከሆነችላቸው በኢትዮጵያዊነት መቆየት ይችላሉ፤ ካልሆነችላቸው ደግሞ የራሳቸውን መንግሥት መፍጠር ይችላሉ። ይህ በዓለም ሕግጋትም ያለ ነው። በኢትዮጵያም ሕገ መንግሥት ያለ ነው። ለምን ደግማችሁ ደጋግማችሁ የእኛን ድርጅት ይሄን ጥያቄ እንደምትጠይቁ ግራ ይሆንብኛል። ጋዜጠኞች ግን ከዚህ ጥያቄ ማለፍ ለምን አቃታችሁ? ከዓመታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ዋና ፀሐፊያችሁ አቶ አብዱራህማን መህዲ በአንድ ቃለ ምልልሳቸው ላይ "ሶማሌ በማዕከላዊ መንግሥቱ የተናቀና የተረሳ ክልል ነው። እኛ ኢትዮጵያዊነት አይሰማንም፤ በቅኝ ነው ማዕከላዊ መንግሥቱ የያዘን" ሲሉ ተደምጠዋል። ይህ ቀደም ሲል ያለ ስሜት ነው። ከለውጡ በኋላ ይህ ስሜታችሁ በምን ያህል መጠን ተፈውሷል? በእርግጥ ይህ የመሪዎች ስሜት ሳይሆን የሕዝብ ስሜት ነው። እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ የእኛ ሕዝብ፣ የሶማሌው ሕዝብ፣ የኦጋዴኑ ሕዝብ የእኔ መንግሥት የሚል ስሜት አሁንም ያለው አይመስለኝም። ምክንያቱም መንግሥት የራስ የሚሆነው ስለ ራስህ ሲያስብ ነው። ከአጤ ቴዎድሮስ፣ ከአጤ ምንሊክ፣ ከአጤ ኃይለ ሥላሴ፣ ከኮሎኔል መንግሥቱ እና አቶ መለስ ዜናዊ እስከ ዛሬ ድረስ የሶማሌ ሕዝብ ምን ተደረገለት? ምንስ ይደረግ ነበር? የሶማሌ ሕዝብ በፌደራል መንግሥት ምን ያህል ተሳትፎ ተሰጣቸው? ወይም ምን ያህል ጥቅም አገኙ? እንዴትስ ነው የሚታዩት? ዛሬ እኮ የኢትዮጵያን ብር እና የኢትዮጵያን መንግሥት የማያውቁ ሰዎች በክልላችን ውስጥ አሉ። ይሄ ምን ይነግርሃል? ለምን? በምንድን ነው የሚገበያዩት ታዲያ? ለምን? መንግሥት ስላልደረሳቸው ነዋ። የሶማሌ ሕዝብ ወታደር ተልኮ፣ ወታደር ሲጨፈጭፋቸውና ሲገድላቸው ነው የሚያውቁት። ይህን ነገር መቀየር ያለብን እኛ ሳንሆን የኢትዮጵያ መንግሥትና መሪዎች ናቸው። እኔ ልንገርህ ለምሳሌ…በቅርቡ በፌደራል የተዘጋጀ ውይይት ላይ በቢሾፍቱ ተሳትፌ አንድ ሰው ምን ብሎ ጠራኝ መሰለህ። በውይይት ላይ ነው የምልህ…አንድ ሰው "ወንድሜ ሶማሌው እንደገለፀው" ይለኛል። ተመልከት እንግዲህ! ምንድነው ችግሩ ታዲያ፣ አልገባኝም? እኔ በማንነቴ እኮራለሁ ችግር የለብኝም። ግን ለምሳሌ ሌላው ተሳታፊ የኦሮሞው ወንድሜ፣ የሃዲያው፣ የጉራጌው እየተባለ በብሔሩ ተሰይሞ ስሙን ከብሔሩ ጋር አያይዞ አልተነሳም። ወንድሜ ኦሮሞው፣ ወንድሜ ሃዲያው አልተባለም። እኔ ለምን ልዩ ሆንኩ? ይህ ምን ያሳይኻል? ይህንን መቀየር ያለብን ደግሞ ፖለቲከኞች፣ ምሁራንና መሪዎች ናቸው። ይህ ልዩነት ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ ያለ ነው። እንደ ሁለተኛ ዜጋ ነው የሚያዩን። ፖለቲከኞች የሶማሌን ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ አያስቡትም። ይህንን አለ የምትሉትን የተንሸዋረረ አመለካከት ለማቃናት እናንተስ እንደ አንድ ፓርቲ ምን ያህል ጥረት አድርጋችኋል ብዬ ለጥይቅዎ? ከጥንት እስከ ዛሬ ኢትዮጵያዊ መሆናችን አልቀረም። በድርጅት ብቻ ሳይሆን በሶማሌ ባለሥልጣናት እንደ ሶማሌ ብሔረሰብ ተወያይተው በመሆኑም ድርሻችን ምን ያህል መሆን እንዳለበት መወያየት አለብን። ትልቁ ሚና መጫወት የነበረባቸው በሥልጣን ላይ ያሉ የሶማሌ ባለሥልጣናት ነበሩ። ምን እንዳጡ፣ ምን እንደሚያንሳቸው መጠየቅ ነበረባቸው። እኛ እንደዚህ ብለን ስንጠይቃቸው እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ ነው የሚያዩን። በመሆኑም ለዚህ ከፍ ያለ ሚና መጫወት ያለባቸው በሶማሌ ክልል ያሉ ባለሥልጣናት ነበሩ። እኛ ተወያይተን ምን ማድረግ እንዳለብን ለመወሰን እንደ የቤት ሥራ እናስብበታለን። ድርጅታችንም ያስብበታል። በዚች አገር ኢትዮጵያ ውስጥ እስካለን ድረስ የድርሻችንን ማግኘት አለብን። የድርሻችንን መጫዎች እና የድርሻችንን መካፈል አለብን የሚል እምነት ነው ያለን። በአሁኗ ኢትዮጵያ ውስጥ አፋሩም፣ ሐረሪውም ፣ ሶማሌውም፣ ደቡቡም . . . እኔ ተገፍቻለሁ፤ እኔ እንደ ኢትዮጵያ አልቆጠርም እኔ ሁለተኛ ዜጋ ነኝ እያለ ነው። ይህ የስሜት መጎዳት ሁሉም ሕዝብ ላይ እንደሆነ ይታወቃል። ሁሉም አኩራፊ ከሆነ እንዴት ነው ኢትዮጵያን መጠበቅና ወደፊት ማራመድ የሚቻለው? እኔ ተጎድቻለሁ የሚለው ሕዝብስ ወደ መሀል መምጣትና የድርሻውን መወጣት የለበትም ወይ? ይህ ስሜት የማይሰማውስ ብሔር አለ ወይ ኦሮሞው፣ ወላይታው፣ አማራው፣ ሲዳማው . . . በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳኸው። በዓለም ላይ እኔ ነኝ ጎጂው፣ እኔ ነኝ በዳዩ፣ እኔ ነኝ አጥፊው የሚል ሰው የለም። ጎጂውም ተጎጂውም እንደዛ ነው የሚቀጥሉት። ባለፉት ሥርዓቶች ምን ዓይነት ችግሮች ነበሩ ብለን እንደ አንድ አገር ዜጋ ተወያይተን፣ ስህተታችንን ተጠያይቀን፤ እርቅ ተቀብለን፤ ወደፊት ምን ይሻለናል? ማለት አለብን ብዬ አንስቻለሁ። ነገሩ የአዞ እንባ እንዳይሆን፤ ማን ነው ይህን የሚያመጣው? ሥርዓቶቹ ናቸው። በመለስ ዜናዊ አስተዳደር የህወሓት፣ የትግራይ ጊዜ ይባላል። በደርግም ጊዜ የአማራው ጊዜ ይባላል። እነርሱም ግን ተበድለናል እያሉ ነው። ስለዚህ ቆሻሻችንን ከመቆፈር አሁን ምን ማድረግ አለብን? የሚለው ላይ መምጣት ያስፈልጋል። መጀመሪያ ይቅርታ መጠያየቅ፣ ሕዝብን ማስተማር፣ መቻቻልና፥ አንድ ሰው ተበድያለሁ ካለ ይቅርታ ማለት ያስፈልጋል። አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና ሥነ ሥርዓት ተከባብረን እየተጓዝን፤ ጥያቄዎች ካሉ በሕጋዊ መሠረት እንዲፈቱ፣ ማንኛውም የወደፊት ዕጣ በሕጋዊ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ነው የማስበው። እኛም እንደዛ ዓይነት አቋም ነው ያለን። ይቅርታ መጠያየቅ ላይ ብዙዎች ጥያቄ የላቸውም። ጥያቄው ይቅርታ የሚጠይቀው ማን ነው? የሚጠየቀውስ ማን ነው? አጥፊው ማነው? ተጎጂው ማነው? የሚለው ነው። የደርግ መንግሥት ብለዋል ደርግ የትኛውን ብሔር ነው የሚወክለው? ከዚያ በፊት ያሉ አስተዳደርና መንግሥታትን ስንቆጥር የትኛውን ብሔር ነው የምናነሳው? የመሪውን ብሔር ነው የምናነሳው? የወከሉት ሕዝብስ ራሱ ሲበደል አልነበር ወይ? እውነት ብለሃል። በተወሰነ መልኩ ካነሳኸው ነጥብ ጋር እስማማለሁ። ምክንያቱም በሥልጣን ላይ የነበረ ሰው ወይም ሰዎች ናቸው ሥርዓቱን ያጠፉት ይባላል። እውነት ነው የአማራ ሕዝብ ተሰብስቦ የሶማሌን ሕዝብ እንበድል አላለም። የትግራይም ሕዝብ እንደዚያው ተነስቶ የሶማሌ ሕዝብ ወይም ሌላውን እንበድል ብሎ አልተነሳም። ግን በመለስ ዜናዊ ጊዜ አራት ድርጅቶች ነበሩ። በኢህአዴግ ሥር የተሰበሰቡ ድርጅቶች። ነገረ ግን ብዙ ጊዜ ሰው ሲናገር በህወሓት የተመራው መንግሥት ነው የሚለው? በህወሓት እነማን ነበሩ ሲባል ትግራዮች ነበሩ እንላለን። በደርግ ጊዜም እነማን ነበሩ ሲባል የአማራው ነበሩ ይባላል። ያው በተወሰነ ደረጃ ካንተ ጋር እስማማለሁ ምክንያቱም ሥርዓቱ ነበር አጥፊው። በተወሰነ ደረጃ ደግሞ ከሥርዓቱ በስተጀርባ የትኛው ብሔር ነበረ? አፍሪካዊያን እኮ ብሔርተኞች ነን ሁላችንም። ይህንን መካድ አንችልም። ኬንያ ብትሄድ ተመሳሳይ ነገር ነው ያለው። ኬንያ ብታነሳ የኪኩዩ መንግሥት ነው የምትለው። እዚህም እንደዛ ዓይነት ነገር አለ። እና መካድ የለብንም፡፡ ይህን መቀበል አለብን ብዬ አስባለሁ። ከአራት ዓመታት በፊት ሊቀመንበራች አቶ አብዱራህማን መኽዲ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "በመቶ ዓመት ውስጥ ኦጋዴን ውስጥ አንድ ሃይስኩልና አንድ ሆስፒታል ነው ያለን። ሴቶቻችን ሊወልዱ ሲሉ ወይም ሲታመሙ ሞቃዲሹ ነበር የሚሄዱት" ብለዋል። በአንጻሩ ሶማሌ በተለይም ሰፊ ድጋፍ ባላችሁ ኦጋዴን በጋዝ ሃብት ትልቅ ተስፋ የተጣለበትና ትልቅ ሃብት ያለው አካባቢ ነው። አሁን ሕዝባችሁ በልማት እየተጠቀመ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? በዚያ አካባቢ ባለው እንቅስቃሴ ተስፋ ይታያችኋል? ተስፋ አለን። እንደ እንድ ሙስሊም በቁርዓን ላይ (ላ ታቅናጡ ቢራሕማቲላህ) "በፈጣሪ ፀጋና ሲሳይ ተስፋ አትቁረጡ" የሚል አንቀጽ አለ። ሁልጊዜም ተስፋ አለን። ምንም እንኳ ብንተችም አሁን ያለው የሶማሌ አስተዳደር በመጠኑ እያደረገ ነው። ጥሩ ነው። ትምህርት ቤቶች በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም በመጠኑ እየተሠሩ ነው፤ ከዚህ በላይ መሆን ነበረበት ማለታችን ባይቀርም ማለቴ ነው። ይህ ማለት ግን እንዳትሳሳት። አሁንም በእሳት ብርሃን (በኩራዝ ብርሃን) የሚወልዱ የሶማሌ እናቶች አሉ። ከ60 በመቶ በላይ የሶማሌ ሴቶች አሁንም እንደዚያው እየወለዱ ነው ያሉት። ጥራታቸው ዝቅተኛ ቢሆንም ትምህርት ቤቶች አሉ። ጥራታቸው በጣም ዝቅተኛ ቢሆኑም ሆስፒታሎችም ክሊኒኮችም በመጠኑ አሉ። እየተሠሩም ነው። ወደፊትም እንዲሠራ፣ እኛም ካሸነፍን ቅድሚያ ሰጥተን የምንሠራው ይህንን ነው። ሌላም ቢያሸንፍ መሠረታዊ የሆኑት እነዚህ ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለበት እናምናለን። የጋዝ ሃብቱ ላይ የምታነሱት የተለየ ጥያቄ አለ? አንድ የሶማሌ ተረት አለ። "Dhariba ninkii u dhow baa dhuunigiisa leh" ጭብጡ ምንድነው? "ምግብ ሲበስል ለቀረበው ሰው ነው ቅድሚያ መሰጠት ያለበት" የሚል አባባል ነው። የሶማሌው ሕዝብ ከጋዝና ነዳጅ ንብረቱ እንደዚህ ሩቅ መሆን የለበትም። የተሰጠው ድርሻም በቂ አይደለም ብለን እናምናለን። ከዚያ በላይ ነው ማግኘት ያለባቸው ብለን እናምናለን። በፌደራል መንግሥት ያላቸው ድርሻም በቂ አይደለም እንላለን። የፌደራል ሃብትም የሚደርሳቸው ከዚያ በላይ ማግኘት አለባቸው ብለን እናምናለን። አቶ አብዱራሕማን እንዳሉት ሕዝባችን ድሮም በጫካ ያለ ሐኪምና መድኃኒት ሲሞት እንደነበረው አሁንም እየሞተ ነው ያለው። ይህ ግን በእኛም ይሁን በሌላ እንደዚህ ሆኖ መቀጠል የለበትም ብለን እናምናለን። እናንተ ጫካ በነበራችሁበት ዘመን የሶማሌ ሕዝብ በቀድሞ የሶማሌ አስተዳዳሪ አቶ አብዲ ኢሌ ቁም ስቅሉን ሲያይ እንደነበረው እናንተም ፍዳውን ስታበሉት ነበር። አሁን አቶ ሙስጠፌ ከመጡ ወዲህ ግን ክልሉ ከሌሎች ክልሎች አንጻር ብዙም ኮሽታ የሌለበት፣ ሰላም ያለበት እንደሆነ ነው የምናየው፤ ፕሬዝዳንት ሙስጠፌም በዚህ የሚሞካሹ ናቸው። እናንተ እንዴት ነው የምትገመግሙት? አቶ ሙስጠፌ ከመጣ ሰላም መጣ ከማለት እናንተ ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ከፈረማችሁ በኋላ ሰላም መጣ ብትሉ ይመረጣል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም አቶ ሙስጠፌ እኛ አዲስ አበባ እያለን፤ እኛ የሰላም አቅጣጫ ከመንግሥት ጋር ከተስማማን በኋላ ነው የተሾሙት። ሰላም በአቶ ሙስጠፌ አሊያም በብልጽግና ፓርቲ ሳይሆን፤ በእኛና በኢህአዴግ ነው የተፈፀመው። ሰላም በኦብነግ ነው የመጣው፤ ሰላም በእኛ ውሳኔ ነው የመጣው ብለን እናምናለን። ምክንያቱም ከመንግሥት ጋር ስንፋለም ነበር። እኛ እስከተፋለምን ድረስ 'እነሱን ሕዝብ ይደግፋቸዋል' በሚል ሕዝብ ሲጨፈጭፉ ከእኛም ጋር ሲዋጉ ነበር። አቶ ሙስጠፌ በመሀል ገብቶ ነው እንጂ በእርሱ ሰላም አልመጣም። በእኛ ነው ሰላም የመጣው። አሁንም በእኛ ካልሆነ በሰላም አይቆይም ነበር። ምክንያቱም ድርጊታቸው፣ ጸባያቸው፣ አነጋገራቸው እና ሁሉ ነገራቸው ወደ ሰላማዊ የሚወስደን አይደለም ብዬ አምናለሁ። ሰላም በእኛ ነው የመጣው፤ በእኛ ነው የተመሠረተው። አሁንም በእኛ ነው ያለው። ነገር ግን ሰላም ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነጻጸር ጥሩ ነው። የሕዝባችን ውሳኔ ነው። ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁለተኛ ዜጋ ሆነው በያሉበት ቦታ እየተገደሉ ነው። ሶማሌው የሰላምንም የጦርነትንም ዋጋ ስለሚያውቅ፤ እኛ ስለወሰንን ነው ዛሬ ሰላም የሆነው። ዛሬ የሰላም ቀን ነው። የፈለግነውን በሰላም እንፈልግ ከሌሎች ጋር በሰላም እንወያይ፣ በሰላም እንሂድ ብለን የኦብነግ ውሳኔ ስለሆነ ነው በዚያ እየሄድን ያለው። አሁንም እንቀጥላለን። ሰላም ለሕዝባችን ለአፍሪካ ቀንድም እንዲወርድ አላህን እንጠይቃለን። እናንተ ጫካ በነበራችሁ ጊዜ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ፤ አንዳንድ የፈጸማችኋቸው ጥቃቶች አሉ። ግንቦት 2007 እአአ 65 ኢትዮጵያያዊ የጉልበት ሠራተኞች እና ዘጠኝ ቻይናዊያን በማዕድን ቁፋሮ ላይ ሳሉ አቦሌ ላይ ጥቃት አድርሳችሁ ገድላችኋቸዋል። ንጹሃን ሞተዋል። ጅግጅጋም ላይ እንደዚሁ የሰዎች ሕይወት አልፏል። ይህም በእናንተ የሆነ ነው። አሁን ለሰላም ትግል ከመጣችሁ በኋላ ይቅርታ መጠየቅ ያለባችሁ አይመስላችሁም? ሁለት ዝሆኖች ሲጣሉ ብዙ ሳር ይወድማል ይባላል። የትኛውም አገር ጦርነት ሲከሰት የሰላማዊ ሰው ሕይወት ያልፋል። ያለ ነገር ነው። እኛ ዓላማችን ሰላማዊ ሰዎችን እናጥቃ ብለን አልነበረም። ቻይናውያን በማን ጥቃት ነው የሞቱት? ማንን ጠይቀው ነው የኦጋዴን ግዛት የገቡት? ከመግባታቸው በፊትና ከገቡም በኋላ አስጠንቅቀናቸው ሰላም አለመሆኑን እየነገርናቸው 'እምቢ' ብለው ስለገቡ እኛ የመንግሥት ሠራዊትን ዒላማ ስናደርግ ቻይናውያኑ ስለሞቱ መንግሥት ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። አምጪው ነው ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። ግን ገዳዮቹ እናንተ ናችሁ እኮ? የተገደሉት በእናንንተ አይደለም እንዴ? በሁለቱም በኩል ጥይት ተተኩሷል። በማን ጥይት እንደሞቱ አይታወቅም። በማን ጥይት እንደተገደሉ ማን ይናገራል? በእኛ ብቻ የሚላከክ አይደለም። የእኛ እጅ የለበትም ብለን አንክድም። ነገር ግን ማን ነው ያመጣቸው? ሁለተኛ ደግሞ በማን ኃላፊነት ነው የመጡት? በእኛ ኃላፊነት አልመጡም። እኛ እንደውም ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነበር 'እምቢ' አሉ። በመሆኑም እኛ ይቅርታ የምንጠይቅበት ሰበብ የለም። በእኛ ፍቃድና ኃላፊነት አልመጡም፡፡ ጽፈንላቸው ይቅርባችሁ ብለን ነው እምቢ ያሉት። አገራችንና ሃብታችንን ሊወስዱ ነበር የገቡት። ስለቻይናውያኑን ይህን ካሉ ኢትዮጵያውያን የጉልበት ሠራተኞች ደም ፈሶ ይቅርታ ለመጠየቅ ለምን ጉልበት ያንሳችኋል? በዚህ ጦርነት ስንት ኢትዮጵያዊያን ሞተዋል? በዚህ ጦርነት ኃላፊው ማን ነበር? እኛ በሰላም ሕዝባችንን እየመራን በነበረበት ሰዓት አመጹን ቀስቅሶ ሕዝብ የጨረሰ ማን ነው? ጦርነቱን ያነሳሳ አካል ነው ለሁሉም ይቅርታ መጠየቅ ያለበት። ከእኛ ጦር ለሞቱት፣ ከመንግሥት ጦር ለሞቱት፣ ለንፁሃን ዜጎች ሁሉ ኃላፊነቱን መወሰድ ያለበት የኢትዮጵያ መንግሥት፤ የኢትዮጵያ መሪዎች ናቸው። ምክንያቱም በሰላም እንዲያወያየንና ችግራችን በሰላም እንዲፈታ ያልሄድንበት የለም። ኢትዮጵያውያንን ከዚህም ከዚያም የሚያዋጉት ኃላፊነት የሚወስዱት አነሱ ናቸው ብለን እናምናለን። ፓርቲያችሁ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ለብቻው ተገናኝቶ ያውቃል? ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኛችሁት መቼ ነበር? ምን ተወያያችሁ? ይህን ቀን ነው ብዬ ልነግርህ አልችልም። ግን ከስድስት ወር በፊት አንዴ በቤተ መንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ከአቶ አብዱራህማን ጋር ነበር የተወያዩት፤ እስከማውቀው ድረስ። ስለ አገራዊ ሁኔታ፣ ስለመጪው ምርጫ፣ ስለሠላም፣ ስለ ዲሞክራሲ እና ስለተለያዩ ጉዳዮች ነበር ያነሱት። በጥሩ ሁኔታ ነበር የተወያዩት። ይህን ያህል ነው የማውቀው። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ግንቦት ወር ላይ ይካሄዳል። እናንተም ትሳተፋላችሁ። በቅርቡ ጥቃት እየፈፀመብን ነው።አባላት ታስረውብኛል። ዶሎ፣ ቸረረ፣ ሸበሌና ቆራሄ ዞኖች ሰብዓዊ ጥሰት አለ። እየተንገላቱብኝ ነው ብላችኋል። አሁንም ችግር አለ ማለት ነው? ይህ ችግርስ ከምርጫ እንድትወጡ ሊያደርጋችሁ ይችላል? በዚህ ላይ ትኩረት ማድረግ እፈልጋለሁ። ዛሬ ከሚደርሱን መረጃዎችና ከምናያቸው ነገሮች በምርጫው እንደምንሳተፍ ሙሉ ቃል መስጠት አልችልም። ጫፍ ላይ የደረስን ይመስለኛል። ነገሮች እየተደማመሩ ነው። ለምሳሌ አሁን ላይ የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ነው። የመራጮች ምዝገባ ጊዜው ተራዝሟል። በቴክኒካል ችግር ሊሆን ይችላል። ሆነ ተብሎም ሊሆን ይችላል። ዛሬ ከሚደርሱን መረጃዎች ነገሮች እየተባባሱ ነው። ለምሳሌ ለመራጮች የሚሰጠው ካርድ ለሶማሌ ክልል ምን ያህል ካርድ እንደሚላክ የምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎቹ ማሳወቅ አለበት። ወደ ምርጫ ጣቢያዎቹ የሚላከውን ካርድ ተወዳዳሪዎች ማወቅ አለባቸው። በምርጫው ምዝገባ ጊዜም ፓርቲዎቹ ወይም ተወዳዳሪዎቹ ታዛቢ ወይም ወኪል መስጠት አለባቸው፤ ነገር ግን ዝም ብለው በተለያዩ ቦታዎች ሳጥኖችን አራገፉ። ሳጥኑ ደግሞ ክፍት ነው። እስካሁን ለእኛ የተሰጠን ካርድ ቁጥር የለም። እና የተያያዘ ነገር እየመጣ ነው። ብዙ ምልክቶች እየታዩ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት ድርጅቱ ተሰብስቦ ይወያይበታል። ሠራተኞቹም መጀመሪያ ሲቀጠሩ ከዘመድ፣ ከመንግሥት ሠራተኛ ሲሆኑ መቶ በመቶ በሶማሌ ክልል ሠራተኞች የብልጽግና ተከፋይ ናቸው። 99 በመቶ የመንግሥት ተከፋይ ናቸው። በመሆኑም በቀላሉ ለመንግሥት ሊገዙ ይችላሉ። በመሆኑም ምንም በሌለን መረጃ መቀጠል የምንችል አይመስለኝም። ሆን ተብሎ የተደረገ ነገርም ይመስላል። በተጨማሪም ብልጽግና በመንግሥት ሃብትና ንብረት እየተጠቀመ ነው ያለው። ሥልጣኑንም እየተጠቀመ ነው። ተወዳዳሪ ልናስመዘግብ አልቻልንም። እዚህ አዲስ አበባ ነው እያስመዘገብናቸው ያለው። ይህንን ስናመለክት እናስተካክላለን ሲሉን ነበር። ምንም የተስተካከለ ነገር የለም። የእኛ ተወዳዳሪዎች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው። በመንግሥት መኪና ዘመቻ እያደረጉ ነው። ለምን ስንላቸው ደግሞ ታርጋ መፍታት ጀምረዋል። ስለዚህ ሁኔታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ በምርጫው የምንሳተፍ አይመስለኝም። ምን ያህል ዕጩዎችን የት አስመዝግባችኋል? በሶማሌ ክልልም በሌላ የሶማሌ ማኅበረሰብ ባለባቸው አጎራባች ክልሎች እና አዲስ አበባ ለመወዳደር አስበን ነበር። ግን በተሳሳተ በዕጩዎቻችን የተሳሳተ አረዳድ እና ቴክኒካል ችግር ምክንያት አዲስ አበባ መመዝገብ አልቻሉም። ድሬዳዋ እንዳናስመዘግብ ደግሞ በብልፅግና ተከልክለናል። ተከልክለናል ሲሉ ምንድን ነው ማስረጃዎት? የእኛ ዕጩዎች እንዳይመዘገቡ ተከልክለዋል። በምርጫ ቢሮ ኃላፊዎች አትመዘገቡም ተብለዋል። በገርባ ኢሴ፣ በፊቲ፣ ሃደጋላ ያሉ ዕጩዎችም እንደዚሁ ተብለው አስፈርመዋቸው ከሦስት ቀን እስራት በኋላ ተባረዋል። በሞያሌ፣ በካሱርቱ፣ በዞላአጦ ምርጫ ኮሚሽን ተገናኝተን ለምን አታስመዘግቡም ሲሉ፤ ኦብነግን እንዳናስመዘገብ በመንግሥት ታዘናል የሚል ምላሽ የሰጡ ነበሩ። ብዙ የተከለከልንባቸው ቦታዎች አሉ። እስካሁን 237 የክልል እና 15 ድሬዳዋ ላይ ከዚህ ላይ አምስቱ ዛቻና ማስፈራሪያ ስለደረሰባቸው ወጥተዋል። ከምርጫ ቦርድ ጋር በክልል ሆነ በፌደራል ደረጃ ይህን ያህል ለማስተጋባት ምን ያህል ርቀት ሄዳችኋል? የምርጫ ቦርድ አቅማቸው እስከሚፈቅድ ችግሩን ለመፍታት ሞክረው ነበር። መፍታት ያልቻሉትን ደግሞ አዲስ አበባ መጥተን እንድናስመዘገብ አድርገዋል። ለዚህም እናመሰግናቸዋለን። ይህንን ችግር እንዲፈታ ወ/ሪት ብርቱካን ከክልል መንግሥት ጋር እናገናኛችኋለን ጂግጅጋ እመጣለሁ ብላን ነበር እስካሁን እየጠበቅናት ነው። ችግሩ ይፈታል ብለን እናምናለን። አሁንም ከምርጫ እንቀራለን ማለት አይደለም። ችግሩ ከተፈታ ምርጫ እንካፈላለን፤ ካልተፈታ ግን ውጤቱ መጥፎ ነው። ምርጫ ትሳተፋላችሁ ብለን ተስፋ እናድርግና እናንተ በክልላችሁ አብላጫ ድምፅ የማግኘት ዕድላችሁ ምን ያህል ነው? የሕዝብ ድጋፋችሁን ስትገመግሙት? ከፍተኛ ድጋፍ ያላችሁ በኦጋዴን ጎሳ ነው። የምትወክሉትም ኦጋዴን ጎሳን ብቻ ነው ይሏችኋል። ከኦጋዴን ጎሳ ውጭ ያሉትንስ ትወክላላችሁ? ይቀበሏችኋል? [ሳቅ] እኛ እንደ ጎሳ አይደለንም። እንደዚያ ዓይነት ቃላት የሚናገሩ አስተሳሰባቸው ጠባብ ነው ብለን ነው የምናምነው። እኛ የታገልነው፤ አሁንም የምንታገልለት ለሶማሌው ሕዝብ ነው። በሞያሌ፣ ነገሌ፣ ፊልቱ፣ በጎዱ ኡኩር፣ በጂግጅጋ፣ በድሬዳዋ ባለው የሶማሌ ሕዝበ ተወዳድረናል፤ ደግሞም እንወዳደራለን። ከፍተኛ የማሸነፍ ተስፋ ነው ያለን፤ ነገሩ የምርም በሕዝብ ድምፅ የሚወሰን ከሆነ። እንደዚያ ግን አይመስልም። ለምን በለኝ። ነገሩ በሕዝብ ድምጽ የሚወሰን ከሆነ ለምንድነው ዕጩ እንዳናመዘግብ የሚከለክሉን። ነገሩ በሕዝብ ድምጽ የሚወሰን ከሆነ ለምንድነው አባሎቻችን የሚታሰሩት? እኛ በሕዝብ ልብ ውስጥ ያለን ፓርቲ ነን ብለን እናምናለን። አንድ ሰውም አላሰርንም፤ አንድም ሰውም አላባረርንም በሕዝብ ምርጫ ስለምናምን። ስለዚህ ምርጫው ካልተጭበረበረ 89 በመቶ በላይ ድምፅ እናገኛለን ብለን እናስባለን። ከተጭበረበረ ግን መቶ በመቶ አሸንፈናል ሲል ነበር አቶ መለስ፤ አሁንም እንደዚያ ሊሉን ይችላሉ። እንደው በምርጫው ብትሸነፉ የምርጫውን ውጤት ተቀብሎ ወደፊት ደግሞ ለተሻለ ውጤት ለመሄድ ያላችሁ ዝግጁነት ምን ያህል ነው? መቶ በመቶ ዝግጁ ነን! ምክንያቱም እኛ ከጫካ ትግል መጥተን እንደ ጋዜጠኛ ምን ያህል ሕዝብ አቀባባል እንዳደረገልን ብታይ ጥሩ ነበር፤ አሁንም በቀብሪደሃር፣ በዋርዴር፣ በነገሌ ያለው እንቅስቃሴ ብታይ ጥሩ ነበር። ሕዝባችን እንደሚመርጠን እናምናለን። እንደ ፓርቲ ከተሸነፍንም እንቀበላለን። ከአሸናፊው ጋር አብረን እንሠራለን። ለሕዝብ ልማት ትግላችንን እንቀጥላለን። ለመጪው ምርጫ እንዘጋጃለን። ይህ የሚሆነው ግን ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ሲካሄድ ብቻ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን "አሸንፈናል ኑ ፈርሙልን" ቢሉ ግን "አጭበርብራችኋል እንጂ አላሸነፋችሁም" ነው የምንላቸው። ዘ ጋርዲያን በሶማሌ ክልል ጋዝ በማውጣት ላይ የተሰማሩ እንደ ፖሊ እና ሲጂኤል ያሉ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ሳቢያ የተፈጠረ አካባቢያዊ ብክለትን ተከትሎ በርካቶች እየሞቱ እንደሆነ ዘግቧል። እአአ በ2014 እስከ 2ሺህ 400 ሰዎች ሞተዋል ብሏል። ይህንን የሚመለከተው የፌደራል መንግሥትን ቢሆንም ስለዚህ ጉዳይ ፓርቲያችሁ ያውቃል? ፌደራል መንግሥቱ ትኩረት እንዲሰጥ ያደረጋችሁት እንቅስቃሴ አለ? ድርጅታችን ይህንን ያውቃል። ችግር እንዳለ እናውቃለን። እኔ ከቆራሂ ዞን ነኝ። ዞኔ ስለሆነ ነገሩን በጥልቀት አውቃለሁ። ዶዶይን፣ ሽላቦ እና ሌሎች ቦታዎች ሄጃለሁ። ሰው በማይታወቅ በሽታ እየሞተ ነው። ሆዳቸው አብጦ በአፍንጫቸው ደም ፈሶ ይሞታሉ። ሐኪም ቤት ሲሄዱም 'ምንም ያገኘነው ነገር የለም ነው' የሚሉት ሐኪሞቹ። እንስሳትም እየሞቱ ነው። የፌደራል መንግሥት መፍትሔ ማድረግ አለበት። ኩባንያዎቹ ምን ዓይነት እንቅስቀሴ እያደረጉ እንደሆነ ማወቅ አለበት። ምን ተበላሽቶ እንደሄደ ማወቅ አለበት። በዓለም ነዳጅ ይወጣል፣ ናፍጣ ይወጣል፣ ቤንዚል ይወጣል። ነገር ግን አካባቢን እንዳይበከል የሚያስችሉ መደረግ ያለባቸው ቅድመ ዝግጅቶች አሟልቷል ወይ የሚለውን ፌደራል መንግሥት የራሱን ኃላፊነት መወጣት አለበት። በተጨማሪም የሶማሌ ክልል መንግሥት ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለን እናምናለን። ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተናል፤ ግን ምንም ግብረ መልስ አላገኘንም። አሁንም እንጽፋለን። ሕዝብ ምንም ማድረግ አይችልም። አንድ ግመል እየጠበቀ ያለ እረኛ ግመሉ ስትሞት ቤተሰቡ ሲሞት ምን ማድረግ ይችላል? ይህ ኃላፊነት የፌደራል መንግሥትና የክልሉ መንግሥት ነው። አሁንም ጥያቄያችንን እንቀጥላል። በቀድሞው አስተዳደር አብዲ ኢሌ ብዙ ጥፋቶች ተፈፅመዋል ከእናንተ ጋር በተያያዘ። የአቶ አብዲ ኢሌን የፍርድ ሂደት ተከታትላችሁ ታውቃለችሁ? ለደረሰባችሁ ጥቃት፣ በደልና ሕዝባችሁ ላይ ለደረሰ ጥፋት ራሳችሁን ችላችሁ ክስ የመመስረት ሐሳብስ አላችሁ? እኛ በአብዲ ኢሌም ሆነ ከእሱ በፊት በነበሩት፣ ከእርሱ ጋር የነበሩትን ጠቅላይ ሚኒስትሮችና የኢህአዴግ መሪዎች በአፍሪካም በዓለም ፍርድ ቤትም ከሰናል። በሶማሌም በሌሎችም ሕዝቦች ላይ ባደረሱት በደል ተጠያቂ እንዲሆኑ ከሰናል። አሁንም እንከታተላለን። ነገር ግን ከሚያሳዝኑን እና ከሚያናድዱን ነገሮች አብዱ ኢሌ እና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በፍርድ ቤት የሚጠየቁት በሶማሌ ሕዝብ ላይ ባደረሱት በደል እና ግፍ ሳይሆን እአአ በነሐሴ 4 በጂግጅጋ የሶማሌ ተወላጅ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ባደረሱት በደል እና በቤተክርስቲያን መቃጠል ብቻ ነው። ይህ ትክክል አይደለም ማለቴ ሳይሆን ከዚያ በፊት ሲያደርግ በነበረውም ጭምር ሊጠየቅ ይገባል። አሁንም የታሰሩትና ያሉት የህወሓት አመራሮች በሶማሌ ሕዝብ ላይ ባደረሱት ግፍና በደል መጠየቅ አለባቸው ብለን እናምናለን። እንከታተላለን። ፍትሕ እስከምናገኝ ድረስ አይደክመንም፤ አይሰለቸንም። የመጨረሻው ጥያቄ የሚሆነው፣ አሁኗን ኢትዮጵያን ድርጅታችሁ እንዴት ነው የሚገመግማት? አገሪቷ ለመፍረስ ቋፍ ላይ ነው ያላችው ከሚለው ጀምሮ አገሪቷ የተሻለ የአንድነት ተስፋ የሚጣልበት ጊዜ ነው የሚሉም አሉ። በብዙ ክልሎች የሚሰማው ዜና ደግሞ የሚረብሽ ነው። እናንተ ደግሞ ድምጻችሁም አይሰማም። ሌላ ቦታ በሚታዩት ነገሮች አይመለከተንም ብላችሁ ነው? በአገር ጉዳይ ለምን ዳር ያዛችሁ? ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው ያለችው። በዚህ ወቅት ገዥው ፓርቲ የሚጫወተው ሚና እጅግ ወሳኝ ነው ብዬ አምናለሁ። እናምናለን። የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ደግሞ እንዲሁ ከፍተኛ ሚና አለው። ይህች አገር እኛ እንደሚመስለን ለምርጫ ከመሮጥ ብሔራዊ መግባባት ያስፈልጋታል ብለን እናምናለን። ለምን? ትላልቅ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ አይሳተፉም ማለት ይቻላል። ለምን? አሁን አዲስ አበባ ነው ያለሁት። ለምርጫው ጥቂት ጊዜ ነው የሚቀረው። ግን ይህን አታይም። ዛሬ እንደከዚህ ቀደሙ የምርጫ ፖስተሮችና ምልክቶች አይታዩም። ሕዝብ ደንታ አይሰጥም ለምርጫ ማለት ነው። ለምን? ብለን መጠየቅ አለብን። በሶማሌና በአፋር ጦርነት አለ። በአማራና በኦሮሞ ሽኩቻ አለ። በትግራይም ያለው ይኸው ነው። ይህ ሁሉ ነገር እያለ፤ ብሔራዊ ውይይት ተደርጎ ሳንስማማ ወደ ምርጫ መሮጣችን ወደ ከፋ ሁኔታ ይወስደናል ብለን እናምናለን። በሁሉም ነገር ባንስማማ በአንድ ነገር ቢያንስ በምርጫ ሂደትና ተሳታፊነት እንኳን ብንስማማ ይመረጣል ብዬ አምናለሁ። እኔ በግሌ አገሪቷ በከፋ፣ በከፋ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው ብዬ አምናለሁ። ስለ ነገ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ እርግጠኛ አይደሉም? አይደለሁም። እኔንጃ ወደየት እየሄድን እንደሆነ?
xlsum_amharic-train-200
https://www.bbc.com/amharic/news-55391888
ፊሊፒንስ፡ ሳይፈለጉ የተረገዙ 200ሺህ ልጆች በኮቪድ ቤት መዋል ምክንያት የተጸነሱ ይሆን?
ፊሊፒንስ ጎዳናዎች ነፍሰጡር ይበዛቸዋል። ሆስፒታል የአዋላጅ እጥረት አጋጥሞ ይሆናል፤ የዳይፐርና ጡጦ ገበያው ደርቷል። ለምን?
[ "ፊሊፒንስ ጎዳናዎች ነፍሰጡር ይበዛቸዋል። ሆስፒታል የአዋላጅ እጥረት አጋጥሞ ይሆናል፤ የዳይፐርና ጡጦ ገበያው ደርቷል። ለምን?" ]
ዛባላ ከተወሰኑት ልጆቿ ጋር ብዙ ምክንያቶች አሉ። አንዱ ግን ኮቪድ-19 ነው። የእንቅስቃሴ ገደቡ ሰዎች ቤት እንዲውሉ አስገደዳቸው። ቤት ከዋሉ ደግሞ በድንገት የሚፈጥጠሩ ውልብታዎችና ብልጭታዎች ወደ አልጋ የሚያመሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚያ እርግዝና ይከተላል። ሌላው ትልቁ ችግር የእንቅስቃሴ ገደቡ ሴቶች የእርግዝና መከላከያ አቅርቦት እንዳያገኙ ማድረጉ ነው። ይሄን ነገር ለማሳየት ለምን የአጌዋን ተወላጅ የሮቬሊ ዛባላን ታሪክ አንጋራም? ዛባላ ወፍራለች፤ ነፍሰጡር ናት። አሁን እንዲያውም ደርሳለች። የመጀመርያዋ እንዳይመስላችሁ። ይህ 10ኛ እርግዛናዋ ነው። አሁን 41 ዓመት ሆናት። ስታወራን ወገቧን ማዞር እንኳ አይሆንላትም። እርግዝናዋ ገፍቷል። 10ኛ ልጇ ሆዷ ውስጥ ሆኖ ይራገጣል። 9ኛው እቅፏ ላይ ይንፈራገጣል። እግሮቿ ሥር የሚርመሰመሱ "ለቁጥር የሚከብዱ" በሚል የሚጋነኑ ልጆች አሉ። ልጅ አይቆጠርም ይባላል። እውነት ነው፤ አንዳንዱ ግን ብዙ ስለሆነ ነው የማይቆጠረው። ዛባላን ባገኛናት ጊዜ ከእግሯ ሥር "ምድርን የሞሉትን" የአብራኳን ክፋዮች ልታስተዋውቀን ሞከረች። "…ይሄኛው ካርል፣ ያኛው ጄውል፣ ይቺ ጆይሲ…" ልጆቿን ቆጥራ ሳትጨርስ ደከማት። በመሀሉ 6 ዓመት የሞላው ልጇ ጎሸም አደረጋት። ስሙን ተሳስታ ነው ለካስ። ማኩረፉ ነው። ተቃውሞውን መግለጹ ነው በሱ ቤት። እናቴ ሆነሽ ስሜን እንኳ በትክክል አታውቂውም እንደማለት… "ውይ የኔ ነገር፣ ይሄ ጄዌል ሳይሆን ቻርሊ ነው። ተምታቱብኝ እኮ" ብላ ፈገግ አለች፤ በእናትነት፤ በቅንነት፣ እንዲሁም በቀናነት። ዛባላ ስለቤተሰብ ምጣኔ የሰማቸው 7 ከወለደች በኋላ ነው። 10ኛ ልጅ የመውለድ ሐሳብ በጭራሽ አልነበራትም። ድንገት ላልተፈለገ እርግዝና ተጋለጠች። ኮቪድ-19 ነው ጉድ የሰራት። በዚህ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ወቅት ፖሊሶች መንገድ ላይ ያገኙትን ሰው ተኩሰው እስከመምታት ደርሰው ነበር። ምግብ ለመግዛት ከቤት መውጣት የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው። በዚህ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የእርግዝና መቆጣጠርያ እንክብልም ሆነ ሌላ ዘዴን ለማግኘት ሳይቻላቸው ቀረ። በዚህ ሁኔታ 200 ሺህ ልጆች ፊሊፒንስን ሊቀላቀሉ ተዘጋጅተዋል ይላሉ ጥናቶች። የፊሊፒንስ የሥነ ሕዝብ ጥናት ኢንስቲትዩት በሠራው አንድ የዳሰሳ ጥናት 214 ሺህ ያልተፈለጉ ሕጻናት ተረግዘዋል። ይሄ ጥናት በተባበሩት መንግሥታት የሥነ ሕዝብ ተቋም የተደገፈ ነው። ፊሊፒንስ ከኮቪድ-19 በፊትም ብዙ ልጆች እየተወለዱባት መፈናፈኛ እያጣች ያለች አገር ናት። ሆስፒታሎች ሁልጊዜም በደረሱ ሴቶች የተሞሉ ናቸው። የጨቅላ ሕጻናት ለቅሶ ብሔራዊ መዝሙሯ የሆነ ይመስላል። በየዓመቱ ለ2 ሚሊዮን 300 ሺህ ብቻ የጎደላቸው ሕጻናት በፊሊፒንስ ምድር ይወለዳሉ። የሚገርመው አብዛኞቹ ልጆችን ለመውለድ የሚገደዱት የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው ቤተሰቦች መሆናቸው ነው። በዋና ከተማዋ ማኒላ ከሚገኙ የተጨናነቁ እስር ቤቶች አንዱ ሕዝብ ሞልቶ የተትረፈባት ማኒላ የፊሊፒንስ ዋና ከተማ ማኒላ ሕዝብ አሸዋ ነው። 13 ሚሊዮን ሰዎች ይርመሰመሳሉ። በእያንዳንዱ ስኩዌር ኪሎ ሜትር 70 ሺህ ዜጎች ታጭቀዋል። አየሩ የተበከለ ነው። መንገዶች በእግረኛና በተሸከርካሪ ጭንቅ ቁና ቁና ይተነፍሳሉ። ሰዎች ማደርያ ሞልቶባቸው ጎዳና ተጋድመዋል። እስር ቤቶች እንኳ ሞልተው በሰው ላይ ሰው ይጋደማል። የአንዱ እስረኛ ጭንቅላት ለሌላው መከዳ ነው። የፊሊፒንስ እስር ቤቶች ከሚችሉት በላይ በ300 እጥፍ ታሳሪ ታጉሮባቸዋል። የአገሪቱ አወዛጋቢው መሪ ዱቴርቴ የሚገድሉትን ገድለው የተረፈውን እስር ቤት ነው የሚወረውሩት። በአደገኛ እጽ አዘዋዋሪዎች ጉዳይ ላይ ቀልድ አያውቁም። ለፖሊሶቻቸው 'ድፏቸው' ብለው በይፋ እስከመናገር የደረሱ ሰውዬ ናቸው። ጭንቅ ጥብብ በሚሉት ሰፈሮች ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው ዜጎች ናቸው የሚኖሩት። በእነዚህ ሰፈሮች ብዙ ነዋሪዎች ከቆሻሻ ገንዳ የተገኘ የተጣለ ሥጋ ሳይቀር ለቅመው ይመገባሉ። በዚህ ሁሉ ድህነት ውስጥ ደግሞ ልጅ በላይ በላዩ ይወልዳሉ፤ ይዋለዳሉ። አንዳንድ አጥኚዎች ድህነቱ የልቅ ሕዝብ ብዛት ውጤት ነው ብለው ያምናሉ። የወሊድ ምጣኔው ከፍተኛ ነው። ከ1960ዎቹ ጀምሮ መንግሥት የወሊድ ምጣኔን ለመቀነስ ሞክሯል። አልተሳካለትም እንጂ። ያን ጊዜ 35 ሚሊዮን ብቻ የነበረው የፊሊፒንስ ሕዝብ አሁን ከ110 ሚሊዮን አልፎ ፈሷል። ይህ ለምን ሆነ? አንዱ ምክንያት አብዛኛው ሕዝብ ከሚከተለው እምነት ጋር ይተሳሰራል። ፊሊፒንሶች በብዛት የጥብቅ ካቶሊክ እምነት ተከታዮች ናቸው። ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በእርግዝና መከላከያ አጠቃቀም ዙርያ ያላት አቋም ነገሩን እምብዛምም የሚያበረታታ አይደለም። እንክብል ወስዶ ከማደር ይልቅ "ብዙ ተባዙ፣ ምድርንም ሙሏት" የሚለውን መንፈሳዊ መርህ አንብቦ የሚተኛ ዜጋ ይበልጣል። "እውነት ነው፤ የእርግዝና መቆጣጠሪያን አንደግፈውም" ይላሉ ቄስ ጀሮሜ ሲላኖ። ቄስ ጀሮሜ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አባት ናቸው። ለመውለድ የደረሱ እናቶች ሆስፒታል ውስጥ 'የልጅ መፈልፈያ ፋብሪካ" የዶ/ር ጆስ ፋቤላ መታሰቢያ ሆስፒታል ሠራተኞች እረፍት የላቸውም። ለነገሩ በቀን 120 እናቶችን እያዋለዱ እንዴት እረፍት ይኖራቸዋል? ያውም ይህ አሐዝ የ2012 ነው። ይህ ልዩ የእናቶችና ሕጻናት ሆስፒታል ብዙ ልጆች ከማዋለዱ የተነሳ "የልጆች መፈልፈያ ፋብሪካ" የሚል ቅጽል ተሰጥቶታል። በዚህ ሆስፒታል ማዋለጃ ክፍሎች ውስጥ በተዘዋወርን ጊዜ በአራስ ልጆች ወጀብ የተመታን ያህል ነበር የተሰማን። ክፍሉ ግማሽ የእግር ኳስ ሜዳ ያክላል። ከብረት የተሰሩ አልጋዎች ተደርድረዋል። በአልጋና አልጋ መሀል ክፍተት እንኳን የለም። ሁለት አልጋ ተጋጥሟል። መሀሉ አንድ ተጨማሪ ሰው እንዲያስተኛ። ጣሪያው ላይ የተንጠለጠሉት የሙቀት ማስተንፈሻ እርግብግቢቶች አርጅተው ሥራ አቁመዋል። ክፍሉ የሰው ትንፋሽ ተጨንቋል። በጣም ብዙ እናቶች የማዋለጃ ቀሚስ ለብሰው ባለፉት ጥቂት ደቂቃዎች ወደዚህ ዓለም ያመጧቸውን ሕጻናት ታቅፈው ተቀምጠዋል። ደግነቱ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብላቸው እንዳጠለቁ ናቸው። "አልጋ እንዲጋሩ እያደረግን ነው፤ ቦታ የለንም። ገና ብዙ በሽተኞች ይመጣሉ። ሆስፒታሉ ከሚችለው በላይ ነው እየተሠራ ያለው። አንዳንድ ጊዜ ጥቂት አልጋዎችን ለ7 ሰዎች እንዲጋሩ ሁሉ እናደርጋለን" ይላሉ ዶ/ር ዲያና ካጂፔ። ይህ ወረርሽኝ ደግሞ ነገሮችን አባብሷቸዋል። በቅርቡ ሰባት ሐኪሞችና ነርሶች በኮሮናቫይረስ ተይዘው ሆስፒታሉ ለመዘጋት ተቃርቦ ነበር። ዞሮ ዞሮ ፊሊፒንስ ልጆችን ወደ ምድር በስፋት እያመጣች ነው። የቤተሰብ ምጣኔ አዋቂዎች እንደሚሉት የዚህ ልጆችን በላይ በላዩ የመውለድ ጣጣ ለዚህ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥለው ትውልድም ድህነትን የማውረስ ተግባር ነው። እርግጥ ነው ፕሬዝዳንት ዶቴርቴ የቤተሰብ ምጣኔ አቀንቃኝ ናቸው። ነገር ግን አሁን በአደገኛ እጽና በጸረ ሙስና ዘመቻዎች ተጠምደዋል። አራስ እናቶች ሆስፒታል ውስጥ ፊሊፒንስ በደቡብ ምሥራቅ እሲያ አገሮች ሁሉ በወጣት ሴቶች እርግዝና መጠን የሚያህላት የለም። አሁን ደግሞ የእንቅስቃሴ ገደቡ ቤት መዋልን በማስከተሉና የወሊድ መቆጣጠርያ ማግኘትን ከባድ በማድረጉ የፊሊፒንስ ወጣት ሴቶች የእርግዝና መጠን በ20 እጅ ተመንድጓል። እስኪ በዛባላ ታሪክ እንደጀመርነው በእሷው ታሪክ እንጨርስ። የ10 ልጆች እናት ዛባላ የምትኖረው በባሴኮ፣ ቶንዶ ውስጥ ነው። ባሴኮ፣ ቶንዶ በዓለም ላይ እጅግ ከተጨናነቁ ጭርንቁስ ሰፈሮች አንዱ ነው። ዛባላ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በእርግዝና መከላከያ ዙሪያ ያለውን አቋም አሳምራ ታውቃለች። "ገና የአንድ ወር እርጉዝ እንደነበርኩ ሳውቅ ባሌን ጽንሱን ማቋረጥ እንደምፈልግ ነገርኩት። ምክንያቱም ሕይወት ከብዶን ነበር። እሱ ግን ግዴለሽም እንወጣዋለን አለኝ። እኔም ሐጥያት ከምሠራ በቃ ይቅር ብዬ ጽንሱን ሳላቋርጥ ቀረሁ" ትላለች። አሁን እሷና ባሏን ድህነት አለያይቷቸዋል። ዛባላ እንባዎቿ ዱብ ዱብ እያሉ በሐዘንና በጭንቀት ስለ ነገ ታስባለች። የልጆቿ ነገር ያሳስባታል። ምን ላበላቸው ነው ግን እያለች ትቆዝማለች። ይህን ታሪክ እየነገረችን በነበረበት ጊዜ ትንሽ ከሕዝብ ጭንቅንቅ ወጣ ባለ አካባቢ ድንገት ፖሊስ መጣ። ሰዎች መሸሽ ጀመሩ። ሁሉም እግሬ አውጪኝ… ፖሊሶቹ አደገኛ እጽ ቸርቻሪዎችን እያደኑ ነበር። ዛባላ ስትናገር አሁን አደገኛ እጽ ከመሸጥ የተሻለ አማራጭ በአገሪቱ የለም። አሁን ኮቪድ-19 ወረርሽኝ የፊሊፒንስን ምጣኔ ሀብት አሽመድምዶታል። አንዳንድ ጊዜ ግራ ሲገባኝ ለልጆቼ፣ "ለምን ለሆኑ ሀብታሞች አልሸጣችሁም። በጉደፈቻ ያሳድጓችኋል" እላቸዋለሁ። "ከዚያ ግን በሐሳቡ እጸጸታለው። ነገም ሌላ ቀን ነው ብዬ ተስፋ ማድረግን እመርጣለሁ" ትላለች። አሁን በፊሊፒንስ የዛባላ ዓይነት ጭንቀት ውስጥ ያሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እናቶች አሉ። ምናልባትም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ። ዓለም ፊቷን ያዞረችባቸው። አደገኛ እጽ ለመቸርቸር የሚገደዱ። በችግር ምክንያት ልጃቸውን ለሀብታም 'በመሸጥ' የተሻለ ህይወት ይገጥማቸዋል ብለው የሚያስቡ ደጋግ እናቶች። በዚህ ሁኔታ ደግሞ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጉድ አፈላ። ሌላ የወሊድ ወረርሽኝ አስከተለ። ፊሊፒንስ እንዴት አድርጋ ነው የኮቪድ-19 እቀባ በፈጠረው ቤት የመዋል ግዴታ ውስጥ ሳይፈለጉ ወደ ምድር ያመጣቻቸውን ተጨማሪ 200 ሺህ ልጆቿን የምታሳድገው?