gem_id
stringlengths
21
24
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
target
stringlengths
6
506
references
list
text
stringlengths
136
19.6k
xlsum_amharic-train-201
https://www.bbc.com/amharic/news-43551835
ሴቶች በሰሜን ኮሪያ ሠራዊት ውስጥ
የቀድሞ ወታደሯ እንደተምትናገረው በዓለማችን ትልቁ ወታደራዊ ኃይል ውስጥ መሆን ለሴት በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ብዙዎች የወር አበባቸው ማየት ያቆሙ ነበር። መደፈር ደግሞ አበረዋት ካገለገሉት መካከል ለብዙዎቹ እውነታ ነበር።
[ "የቀድሞ ወታደሯ እንደተምትናገረው በዓለማችን ትልቁ ወታደራዊ ኃይል ውስጥ መሆን ለሴት በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ብዙዎች የወር አበባቸው ማየት ያቆሙ ነበር። መደፈር ደግሞ አበረዋት ካገለገሉት መካከል ለብዙዎቹ እውነታ ነበር።" ]
በያሉ ወንዝ ዳርቻ አነድ የሰሜን ኮሪያ ወታደር ለ10 ዓመታት ሊ ሶ ዬዎን ከ20 በላይ ከሚሆኑ ሴቶች ጋር በምትጋራው መኝታ ቤት ተደራራቢ ከሆነው አልጋ ታችኛው ላይ ነበር የተምትተኛው። እያንዳንዳቸውም ዩኒፎረማቸውን የሚያስቀምጡበት መሳቢያ ነበራቸው። ከወታደር ቤት ከወጣች ከአሥር ዓመት በላይ ቢሆናትም የነበረውን ሁኔታ ከኮንክሪቱ ሽታ አንስቶ ታስታውሳለች። ''ያልበናል። የምንተኛበት ፍራሽ ከጥጥ የተሰራ ስላልሆነ የላብና ሌሎች ሽታዎች ይፈጠራሉ። ደስ አይልም'' ትላለች። ለዚህም የዳረጋቸው የማጠቢያ ቦታው ችግር ነው። ''ሴት እንደመሆኔ በጣም ከባድ ሆኖ ያገኘሁት እንደፈለግን ገላችንን መታጠብ አለመቻላችን ነው'' ትላለች ሊ ሶ ዬዎን ። ሊ ሶ ዬዎን አሁን 41 ዓመቷ ሲሆን ያደገችው በሃገሪቱ ሰሜን አካባቢ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ልጅ ናት። የቤተሰቧ ወንድ አባላት ብዙዎቹ ወታደር ነበሩ። እ.አ.አ በ1990 በሃገሪቱ ረሃብ ሲከሰት ቢያንስ በቀን አንዴ መብላት እንደሚቻል በማሰብ ነበር ወታደራዊ ኃይሉን ለመቀለቀል የወሰነችው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችም በተመሳሳይ ምክንያት ወታደር ሆነዋል። ''ረሃቡ በተለይ ለሴቶች ጊዜውን በጣም ከባድ አድርጎት ነበር'' ይላል የ'ኖርዝ ኮሪያ ሂድን ሬቮሉሽን' ደራሲ የሆነው ጂውን ቤክ። በመቀጠልም ''ብዙ ሴቶች የሠራተኛውን ኃይል መቀላቀል ነበረባችውና በዚህም ወቅት ለፆታዊ ጥቃትና ለሌሎችም ችግሮች ተጋልጠዋል'' ብሏል። የሸሹትን ማመን ጁሊዬት ሞሪሎ እና ጀኢውን ቤክ የሊ ሶ ዬዎን ትውስታዎች ከብዙዎች ትውስታ ጋር እንደሚመሳሰል ቢያረጋግጡም የሸሹትን ግን ማመን በጥንቃቄ ነው ይላሉ። ቤክ እንደሚሉት ''ስለ ሰሜን ኮሪያ ማወቅ በጣም ይፈለጋል። በተለይ የገንዘብ ድጋፍ ካለው ሰዎች የተጋነኑና ከእውነታው የራቁ ታሪኮችን ለሚድያ ለመዘገብ ይገፋፋሉ። ሸሽተው በሚድያ መታየት የማይፈለጉትን መጠንቀቅ ያስፈልጋል።'' ከሰሜን ኮሪያ ምንጮች የሚመጣው መረጃ ደግሞ ፕሮፖጋንዳ ነው። ሊ ሶ ዬዎን ግን ከቢቢሲ ጋር ላደረገችው ቆይታ ምንም ዓይነት ክፍያ አልተሰጣትም። በመጀመሪያ ሊ ሶ ዎን ያኔ የ17 ዓመት ወጣት የነበረች ሲሆን በሃገር ፍቅርና በአብሮ መሥራት ስሜት እየተገፋፋች በጣም ደስተኛ ነበረች። ብዙም ባትጠቀምበትም የፀጉር ማድረቂያ ሳይቀር መኖሩ በጣም እንደትገረም አድርጓት ነበር። የዕለተለት እንቅስቃሴዎች ለወንድም ለሴትም አንድ ዓይነት ነበሩ። ሴቶች ከወንዶች ይልቅ አጠር ያለ የሰውነት እንቅስቃሴ ቢኖራቸውም እንደ ፅዳት፣ ልብስ አጠባ፣ ምግብ ማብሰልና ሌሎች ሥራዎችን እንዲሠሩ ይጠበቅባቸው ነበር። ''ሰሜን ኮሪያ በባህሉ በወንድ የሚመራ ማህበረሰብ በመሆኑ ባህላዊ የፆታ ክፍፍል አለ'' ትላለች በፈረንሳይኛ የተጻፈው የ'ኖርዝ ኮሪያ 100 ክዌስችንስ' ደራሲ ጁሊዬት ሞሪሎ። ቀጥላም '' ሴቶች እስካሁን እንደ 'ቱኮንግ ኡንጄዎንግሱ' ነው የሚታዩት ይህ ደግሞ ቃል በቃል 'የድስት ክዳን መሪ' ማለት ሲሆን ሴቶች ምንጊዜም በማዕድ ቤት መቅረት እንዳለባቸው መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው። ከባዱ ሥልጠናና ምግብ ማከፋፈሉ የሊ ሶ ዬዎንና የአጋሮቿን ሰውነት ጎድቶት ነበር። ''በገባን ከ6 ወር እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በምግቡ አለመመጣጠንና በጭንቀት ምክንያት የወር አበባችን መምጣት አቆመ'' ትላለች። ''ብዙ ሴት ወታደሮች የወር አበባቸው ባለመምጣቱ ደስተኛ ነበሩ። ምክንያቱም ሁኔታዎች በጣም አስቸጋሪ በመሆናቸው በዚያ ላይ ወር የአበባ ቢጨመርበት ይበልጥ ከባድ ይሆንብን ነበር'' ብላለች። ሊ ሶ ዬዎን ለወር አበባ መጠበቂያ ምንም ነገር እንደማይሰጣቸውና ብዙዎቹ የተጠቀሙባቸውን ፓዶች በድጋሚ ለመጠቀም ይገደዱ እንደነበር አስረድታለች። ''ሴቶች እስከ ዛሬ ባህላዊውን ነጭ የጥጥ ፓድ ነው የሚጠቀሙት'' የምትለው ጁሊዬት ቀጥላም ''ማታ ማታ ወንዶች በማያዩበት ጊዜ ነው መታጠብ ያለባቸው። ለዚህም በሌሊት እየተነሱ ያጥቡ ነበር።'' ጁሊዬት ያነጋገረቻቸው ሴት ወታደሮች የወር አበባቸው እንደማይመጣ ነግረዋታል። ሊ ሶ ዬዎን ወታደራዊ ኃይሉን በፈቃደኝነት ትቀላቀል እንጂ በ2015 ከ18 ዓመት በላይ ያሉ ሴቶች በሙሉ 7 ዓመት የወታደራዊ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ተደንግጓል። በዚያን ጊዜም የሰሜን ኮሪያ መንግሥት ያልተለመደ እርምጃ በመውሰድ ለሴት ወታደሮቻቸው 'ዳይዶንግ' የሚባለውን አንደኛ ደረጃ የወር አበባ መጠበቂያ ፓድ እንደሚያከፋፍል አሳወቋል። ''ይህን እርምጃ የወሰዱት የቀድሞ ስተታቸውን ለማረም ይሆናል'' ይላል ጂውን ቤክ። ቀጥሎም ''ይህ መግለጫ የተሰጠው በጊዜው የነበረው የሴት ወታደሮች ሁኔታ መጥፎ እንደነበር በመታወቁ ሞራላቸውን ለመጠበቅና ለሴቶች 'ካሁን በኋላ እንክብካቤ ይኖረናል' ብለው እንዲያስቡ ለማድረግ ነው'' ብሏል። 'ፒዮንግ ያንግ ፕሮዳክትስ' የተሰኙም የውበት ዕቃዎች በቅርቡ ለአየር ኃይል ሴት አብራሪዎች ተከፋፍሏል። ይህም በ2016 ኪም ጆንግ ኡን የሰሜን ኮሪያ የውበት ዕቃዎች አንደ ሻኔል፣ ዲዮር እና ከሌሎችም ዓለም አቀፍ ስመጥር ዕቃዎች ጋር መዳደር መቻል አለባቸው ካለ በኋላ ነበር። ይህም ሆኖ ግን በክፍለ ሃገር የተመደቡ ሴት ወታደሮች አብዛኞቹ የተለየ መፀዳጃ ቤት እንኳን የላቸውም። ለጁሊዬት እንደነገሯት አንዳንዴ ከወንዶች ጋር መፀዳጃ ቤት መጠቀም እንደሚገደዱ ይህም አደጋ ላይ ሊጥላቸው እንደሚችል ይናገራሉ። ጂውንና ጁሊዬት እንደሚናገሩት የፆታ ትንኮሳ በጣም የተለመደ ነው። ጁሊዬት ሴት ወታደሮቹን ስለ መደፈር በጠየቀችበት ጊዜ ሁሉም ''ሌሎችን ያጋጥማል'' እንጂ ማናቸውም አጋጥሞናል ብለው እንዳልነገሯት ገልፃለች። ''የቡድኑ ኮማንደር በቡድኑ ክፍል ውስጥ ባለው መኝታ ቤቱ ከሰዓት እላፊ በኋላ በመቆየት በእርሱ ሥር ያሉት ሴት ወታደሮች ይደፍራል። ይህም በተደጋጋሚ ያለማለቂያ ነበር የሚፈጸመው'' ትላለች። የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ኃይል የፆታ ጥቃትን እንደማይቀበሉና ለደፈረ ወታደር ደግሞ እሰከ 7 ዓመት እስራት እንደሚቀጡ ይናገራል። ''ብዙ ጊዜ ግን ማንም ሰው ቃሉን ለመስጠት ፈቃደኛ አይደልም። ስለዚህ ወንዶቹ ሳይቀጡ ያልፋል'' ትላለች ጁሊዬት። አክላም በወታደራዊ ኃይል ውስጥ የፆታ ጥቃትን በተመለከተ ያለው ዝምታ በሰሜን ኮሪያ ከሰፈነው ጥልቅ አባዊነት አመለካከት የመጣ ነው። ይህም ነው ሴት ወታደሮች የፅዳትና ምግብ ማብሰልን እንደሠሩ የሚያደርገው ትላለች። ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚመጡ ሴቶች በተለይ የምህንድስና ብሪጌድ ውስጥ የሚቀጠሩ ሲሆን፤ መደበኛ ባልሆኑ ጎጆ ቤቶች ውስጥ ስለሚያስቀምጧቸው አደጋ ላይ ይወድቃሉ። ''በቤት ውሰጥ የሚፈፀሙ ጥቃቶች አይወገዙም ስለዚህም ይፋ አይወጡም፤ በወታደራዊ ሥርዓት ውስጥም ያው ነው። አጥብቄ ግን መናገር የምፈልገው በደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ኃይል ውስጥም ተመሳሳይ የሆነ ባህል ነው ያለው'' ትላለች። ሊ ሶ ዬዎን ሳጂን ሆና ያገለገለችው በደቡብ ኮሪያ ጠረፍ ላይ የነበረ ሲሆን፤ 28 ዓመት ሲሞላት ነበር ለቃ የወጣችው። ከቤተሰቧ ጋር ተጨማሪ ጊዜ ማግኘት በመቻሏ ደስ ቢላትም ከውትድርና ውጪ ላለው ሕይወት ግን ዝግጁ የነበረች አልመሰላትም። ምክንያቱም የገንዘብ ችግር ገጥሟት ስለነበረ ነው። እንደ አውሮፓዊያኑ በ2008 ነበር ወደ ደቡብ ኮሪያ ለማምለጥ የወሰነችው። በመጀመሪያ ሙከራዋ በቻይና ጠረፍ ላይ ተይዛ ለአንድ ዓመት ታስራለች። ከእስር ቤት እንደተለቀቀችም በሁለተኛ ሙከራዋ ቱሜን የሚባለውን ወንዝ በዋና አቋርጣ በቻይና በኩል ወደ በደቡብ ኮሪያ ለመግባት ችላለች።
xlsum_amharic-train-202
https://www.bbc.com/amharic/news-44304527
ኢንዶኔዥያዊቷ ድዛይነር አኔይሳ በማጨበርበር ለእስር ተዳረገች
በቅርቡ በኒውዮርክ በተካሄደው የፋሽን ዲዛይን ሞዶሎቿን ስካርፍ እንዲጠመጥሙ በማድረግ ታሪክ የሰራችው የፋሽን ዲዛይነር በማጭበርበር ወንጀል የ18 ዓመት እስር ተፈረደባት።
[ "በቅርቡ በኒውዮርክ በተካሄደው የፋሽን ዲዛይን ሞዶሎቿን ስካርፍ እንዲጠመጥሙ በማድረግ ታሪክ የሰራችው የፋሽን ዲዛይነር በማጭበርበር ወንጀል የ18 ዓመት እስር ተፈረደባት።" ]
አኔይሳ ሃሲቡአን ከፋሽን ዲዛይን ስራዋ በተጨማሪ የጉዞ ወኪልንም ታስተዳድራለች። ኢንዶኔዥያዊቷ ዲዛይነር አኔይሳ ሃሲቡአንና ባለቤቷ አንዲካ ሱራችማን በጉዞ ወኪላቸው አማካኝነት ገንዘብ በማጭበርበራቸው ጥፋተኛ ተብለዋል። አቃቤ ህጉ እንደገለፁት ወደ መካ ለሚደረገው መንፈሳዊ ጉዞ ለማስተባበር ከ 60 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ከፍለዋል። ይሁን እንጂ ጥንዶቹ ጥፋተኛ የተባሉት ገንዘቡን በማጭበርበራቸውና መንፈሳዊው ጉዞው እንዳይካሄድ እንቅፋት በመሆናቸው ነው። ዲዛይነሯ በምትሰራቸው ዘመነኛ ድዛይኖቿ የእስልምና ፋሽን መሪ ብለው ይገልጿታል። በእንግሊዝ፣ በቱርክ፣ በፈረንሳይና አሜሪካ በተካሄዱ የፋሽን ዝግጅቶች ላይ ሥራዎቿን አቅርባለች።
xlsum_amharic-train-203
https://www.bbc.com/amharic/news-48287053
የዛሬ 30 ዓመት... የኮ/ል መንግሥቱ አውሮፕላን ለምን አልጋየም?
የዛሬ 30 ዓመት፣ ማክሰኞ'ለታ የወጣችው ጨረቃ "ጤፍ ታስለቅም ነበር"። ሌ/ኮ ካሳዬ ታደሰ ናቸው እንዲያ የሚሉት። እንደ ትናንት ያስታውሷታል፤ የነፍስ ውጭ-ነፍስ ግቢ ሌሊት። እርሳቸው ያኔ የ102ኛው አየር ወለድ ኢታማዦር ሹም ነበሩ።
[ "የዛሬ 30 ዓመት፣ ማክሰኞ'ለታ የወጣችው ጨረቃ \"ጤፍ ታስለቅም ነበር\"። ሌ/ኮ ካሳዬ ታደሰ ናቸው እንዲያ የሚሉት። እንደ ትናንት ያስታውሷታል፤ የነፍስ ውጭ-ነፍስ ግቢ ሌሊት። እርሳቸው ያኔ የ102ኛው አየር ወለድ ኢታማዦር ሹም ነበሩ።" ]
30 ዓመት ብዙ ነው። ግንቦት 8 የኾነው ግን ዛሬም ድረስ እንቆቅልሽ ነው። እንደው በደፈናው "ተምኔታዊም ተውኔታዊም" ነበር ማለቱ ይቀል ይሆን? የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹሙ ጄኔራል መርዕድ ንጉሤ 'የኢትዮጵያን ባንዲራ ራሳቸው ላይ ጠምጥመው' ምናልባትም እንደ 'መይሳው ካሣ' ሽጉጣቸውን የጠጡባት ምሽት። እርግጥ ነው በጄኔራል መርዕድ ዙርያ ብዙ የሚጣረስ ታሪክ አለ። ባንዲራ ለብሰው ነበር ከሚለው ሰነድ አልባ ተረክ ጀምሮ እስከ አሟሟታቸው ድረስ ይኸው 30 ዓመት እንኳ ያልፈታው ምሥጢር...። • ''ኢትዮጵያን ወደተሻለ ስፍራ ሊወስዳት የሚችል ሌላ መሪ የለም'' የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሻምበል እዮብ አባተን እዚህ ጋ እናምጣቸው። ያኔ የወታደራዊ ደኅንነት ባልደረባ ነበሩ። ከዚያ በኋላም ስለ መፈንቅለ መንግሥቱ ጥናት አድርገዋል። ስለ ጄኔራል መርዕድ አሟሟት በስፋት ከሚታመነው በመጠኑም ቢኾን ያፈነገጠ ታሪክ ጽፈው አስነብበዋል። ጄኔራል መርዕድ ራሳቸውን ባጠፉ አፍታ እዚያ ደረስኩ ያለ አንድ የልዩ ብርጌድ ወታደር ነገረኝ ብለው ለቢቢሲ እደተናገሩት ከሆነ ጄ/ል መርዕድ ያን ምሽት ራሳቸው ላይ ቢተኩሱም ነፍሳቸው ወዲያውኑ አልወጣችም። ሺህ ወታደር ሲያዝዙ ኖረው ሞት አልታዘዝ አላቸው። አምቡላንስ ተጠርቶ ቢመጣም አምቡላንሷ ወደ ሆስፒታል አልወሰደቻቸውም፤ ወደ ቤተመንግሥት እንጂ። አምቡላንሷ ውስጥ እስከ ንጋት ድረስ እያጣጣሩ ነበር። ቢያንስ ለ6 ሰዓታት፤ በሁለት ወታደሮች እየተጠበቁ ጣር...። • የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች? ነገሩ ሆን ተብሎ የተፈጸመ የጭካኔ ተግባር ይመስላል፤ አልያም ደግሞ ዘመኑ የወለደው የበዛ ፍርሃት። በዚያች የነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ቅጽበት ማን ደፍሮ የመፈንቅለ መንግሥትን አውራ አቀናባሪና ጎንጓኝ "ሕክምና ያግኙ!" ብሎ ይጮኻል? 'አንተን የነዚህ ከሐዲዎች ጠበቃ ማን አደረገህ? ብባልስ' ይላል የዐይን እማኙ ዝምታን ለምን እንደመረጠ ሲተርክ። ...በሥራ ስንዋከብ ቆይተን ወደ አምቡላንሷ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ስንመለስ 'የጄኔራሉ ህሊና የሚረብሸውና አንጀት የሚያላውሰው የጣርና የሲቃ ድምጻቸው ከበፊቱ ቀንሶ ይሰማ ነበር።' ብ/ጄኔራል መርዕድ ንጉሤ 1975-1979 የኤርትራ አስተዳዳሪ እና የሁለተኛው አብዮታዊ ሠራዊት አዛዥ ሳሉ። በዚህ ረገድ የአየር ኃይሉ አዛዥ ጄኔራል አምሐ ዕድለኛ ነበሩ ማለት ይቻላል። የሟችና የአሟሟት ዕድለኛ ካለው...። ጄ/ል አምሐ ሽጉጣቸውን መኪናቸው ውስጥ ረስተውት ነበር ወደ ስብሰባ የገቡት። ሽጉጥ ፍለጋ ተሯሯጡ። መከላከያ አንድ ቢሮ ዘው ብለው ሲገቡ ግድግዳ ተደግፎ የቆመ ክላሽ አገኙ። እስከ ወዲያኛው አሸለቡ። ጄ/ል መርዕድ እያጣጣሩ ከሚገኙበት አምቡላንስ ውስጥ፣ በሁለት የልዩ ብርጌድ ወታደሮች እየተጠበቀ ከነበረው አምቡላንስ ውስጥ የእርሳቸውም ሬሳ ተጠቅልሎ እንደነገሩ ተጋድሞ ነበር፤ እንደ ሻምበል እዮብ 'የማያወላዳ' የዐይን እማኝ ከሆነ። • ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች ቢቢሲ፡- ሻምበል! ግን እኮ ይሄ ጄ/ል መርዕድን አሟሟት በተመለከተ የሚሉን ነገር እስከ ዛሬ ያልተሰማ ታሪክ ነው። ነገረኝ የሚሉትን ወታደር ያምኑታል? ሻምበል እዮብ፦ የልዩ ጥበቃ ብርጌድ የመምሪያ ረ/መኮንን የነበረ ሰው ነው። ይህ መኮንን ጄኔራሎቹ በእስር ላይ እያሉ የአስተዳደራዊ ጉዳያቸውን እንዲፈጽሙ ከተመደቡት መኮንኖቸ አንዱ ነው። ያን ምሽት ያየው ነገር እስከዛሬም ይረብሸዋል። ታሪክ ተዛብቶ ሲነገር ተበሳጭቶ ነው እኔን ያገኘኝ። 'እውነታውን አስተካክለህ ጻፍ፤ እኔ እዚያው የነበርኩ ወታደር ነኝ' ነው ያለኝ። በዚያ ምሽት እሱ እዚያ ስለመኖሩ ከሌሎች አረጋግጫለሁ። ግንቦት 8፣ የነፍስ ውጭ፣ ነፍስ ግቢ ዕለት አየር ወለዱ ጄኔራል አበራ አበበ የገዛ አለቃቸውን የመከላከያ ሚኒስትሩን ጄኔራል ኃይለጊዮርጊስን በሽጉጥ ገድለው፣ የዘበኛ ልብስ አስወልቀው፣ የወታደር ዩኒፎርማቸውን ቀይረው፣ ሲኒማዊ ኩነት በሚመስል አኳኋን አጥር ዘለው ከመከላከያ ግቢ ያመለጡበት ቀትር! ይህም ታሪክ አሻሚ ነው። ለምን አመለጡ? ለምን ሚኒስትሩን ገደሉ? እንዴት መፈንቅለ መንግሥት የሚያህልን ነገር እየመሩ አንድ ሚኒስትር ስለገደሉ ብቻ እንደ ተራ ነፍሰ ገዳይ ሊያመልጡ ይችላሉ? 30 ዓመት ያልመለሳቸው ጥያቄዎች። • በረመዳን ፆም ምግብ የበሉ 80 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ግንቦት 8፤ የነፍስ ውጭ፣ ነፍስ ግቢ ዕለት ጄኔራል ፋንታ በላይ ለሦስት ቀን-ሦስት ሌሊት ኮንቴይነር ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ በሌለበት የተደበቁበት ምሽት…። ጄኔራል ፋንታ የትምህርት ዝግጅታቸውና የአመራር ብቃታቸው ለርዕሰ ብሔርነት አሳጭቷቸዋል። ምናልባትም ስዒረ መንግሥቱ ተሳክቶ ቢኾን ኖሮ ኢትዮጵያን የሚመሯት "ፕሬዝዳንት" ፋንታ በላይ ነበሩ። ይህን የጄኔራል ፋንታ በላይን ድርጊት ተከትሎ 'ማሽሟጠጥ የሚቀናው' ሰፊው ሕዝብ ተቀኘ ተባለ… _"ፔፕሲ ኮካ ኮላው ከከተማ ጠፍቶ_ _ፋንታ ተገኘ አሉ በኮንቴይነር ሞልቶ"_ • በኤርትራ የማህበራዊ ድረ ገጾች አገልግሎት ተቋረጠ ግንቦት 8፤ የነፍስ ውጭ፣ ነፍስ ግቢ ምሽት… ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ በብዙ ጽናት፣ በብዙ ትጋት አምጣ ያዋለደቻቸው፣ ለወግ ማዕረግ ያበቃቻቸውን እጅግ ውድና ምትክ የለሽ የሚባሉ ጄኔራሎቿን በአንድ ጀንበር ያጣችበት…ምሽት። አይደለም አገረ ኢትዮጵያ፣ አህጉር-አፍሪካ ሳትቀር ከተቀረው ዓለም ወራሪ ጦር ቢገጥማት ከፊት ልታሰልፋቸው የምትችላቸው ምርጥ ጄኔራሎቿ ነበሩ…። በእርሻ መሣሪያ የተያዘው አርሶ አደር እግሩን ቆረጠ ግንቦት 8 የኾነው በትክክል ምንድነው? ጓድ ሊቀመንበር ምሥራቅ ጀርመንን ለመጎብኘት ክብርት ወ/ሮ ውባንቺንና ልጃቸውን ትዕግስትን (ወይም ትምህርትን) አስከትለው፣ በትረ መኮንናቸውን እየወዘወዙ ቦሌ ተገኙ። ረፋድ ላይ። መንጌ ቆቅ ናቸው። ሆን ብለው ሰዓት ያዛባሉ። ጠላትን ለማወናበድ ወይ ረፈድ ወይ ቀደም ይላሉ። እርሳቸው ላይ የሚዶልተው ብዙ ነዋ። ያን ለታም እንዲሁ አደረጉ። ማልጄ ነው 'ምሳፈረው ብለው ለደኅንነት ሚኒስትራቸው ተናገሩ። ሚኒስትሮቻቸው እውነት መስሏቸው ቦሌ ማልደው ደረሱ። እርሳቸው ግን ረፋድ ላይ ግንባራቸውን ቅጭም አድርገው ከቸች…። ብዙዎቹ ጄኔራሎች እስከዚያች ሰዓት ድረስ ይቁነጠነጡ ነበር። ቶሎ ወደ ቢሮ መመለስ አለባቸዋ። አጣዳፊ ሥራ ነው የሚጠብቃቸው። መንጌን ወደ 'መንግሥተ ሰማይ' ልኮ መሬት ላይ አዲስ መንግሥት የማቆም ብርቱ ሥራ አለባቸው። ጄኔራሎቹ ጦርነት ታክቷቸዋል። በመንጌ "ቆራጥ" አብዮታዊ አመራር ሺህ የድሀ ልጆችን መማገድ አንገሽግሿቸዋል፤ በአፋቤቴ፣ በቀይ ኮከብ፣ በባሕረነጋሽ ዘመቻ…አሥር ሺህዎች እንደቅጠል ረግፈዋል። 'ጦርነትን እንደ ሥራ የያዘ መንግሥት ሕዝብ ሊመራ እንዴት ይቻለዋል?' ሲሉ ነበር ድምጻቸውን ዝግ አድርገው የሚያጉረመርሙት። • ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? መንግሥቱ ይሄን ማጉረምረም ከሰሙ ጄኔራሎቹን አይምሯቸውም። ማዕረጋቸውን በመቀስ፤ ግንባራቸውን በሽጉጥ ሊነድሉት ይችላሉ፤ አድርገውታልም። የናደው ዕዝ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ታሪኩ ዓይኔን፣ አሳዛኝ ፍጻሜን የሰማ ከመንጌ ጋር አይቀልድም።፡ የአገሪቱ ምጣኔ ሐብት ደቋል፣ ሕዝብ ተርቧል፤ ወታደሩ ኮቾሮ እየበላ ነው የሚዋጋው። የገዛ ልጁንና ሚስቱን እንኳ ማየት አይፈቀድለትም። ጄኔራሎቹ 'የገዛ ወገናችንን ትርጉም በሌለው ጦርነት ለምን እናስጨርሳለን?'፣ 'ደግሞስ የሰሜኑ ችግር በፖለቲካ እንጂ በአፈሙዝ ይፈታል እንዴ?'…እያሉ ያጉረመርሙ ነበር፤…መንጌ ሳይሰሙ። ኮ/ል መንግሥቱ ግን ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር እያሉ ጦርነቱን ገፉበት። በዚያ ላይ ከጦር አዛዦቻቸው ይልቅ ካድሬዎቻቸውን ማመን አበዙ። "ይሄ ሰውዬ እኛን የማይሰማ ከሆነ ለምን አናስወግደውም?" አሉ…ጄኔራሎቹ፤ ማንም ሳይሰማቸው። መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ ዝግጅት ተጧጧፈ። ለዚያ ነው ያን ቀን፣ ግንቦት 8 መንጌን ቶሎ መሸኘት የነበረባቸው…፤ ከሻዕቢያ ጋር ቶሎ ለድርድር መቀመጥ ያሻል። ይሄን የውጭውን ሽርጉድ፣ ገና ድሮ መንጌን የከዱት ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ አሰናድተውታል። ጄኔራሎቹ የመንጌን ወደ ምሥራቅ ጀርመን መሸኘት…ይቅርታ የመንጌን እስከወዲያኛው መሸኘት በጉጉት እየጠበቁ ያሉት ለዚሁ ነው። የዛሬ 30 ዓመት፤ ግንቦት 8፤ ረፋድ ላይ ሰዓቱ አልገፋ አለ… ወግ ነውና…መሪን መሸኘት… "ጓድ ሊቀመንበር በሰላም (አ)ይመልስዎ" እያሉ ቀኝ-ወ-ግራ ተሰይመው ተሰናበቷቸው፤ የገዛ ጄኔራሎቻቸው። መንጌ ያቺን ተወርዋሪ ኮከብ የመሰለች ፈገግታቸውን ቦግ እልም እያደረጉ አጸፋውን መለሱ። ለምን ይሆን ግን ፈጣሪ ለአምባገነኖች ችምችም ያለ፣ የተፈለፈለ በቆሎ የሚመስል ጥርስና ረዥም ዕድሜን የሚቸረው? • 63 ሚሊዮን ብር ገደማ የሚያወጣ መኪና የሰረቀው አልተያዘም የሚደንቀው ታዲያ…በዚያች ዕለት የቦሌ ሽኝት ጄኔራል መርዕድ ንጉሤ አልተገኙም። ይሄ ቀላል ፕሮቶኮሏዊ ህጸጽ ተብሎ ሊታለፍ ይችላል። ጊዜ አጥተው ነው ሊባልላቸውም ይችላል…። ምክንያቱም ዘመኑ የጥድፊያ ነዋ…የጦርነት። በየግንባሩ ‹‹ገንጣይ-አስገንጣይን›› ለመፋለም የወገን ጦር ከሺህ "የወንበዴው ጦር" ጋር ተናንቆ እየተዋደቀ ነው። ፈንጂ እየረገጠ ነው…በእንዲህ ያለ ቀውጢ ጊዜ ለሽኝት መኳኳል ቅንጦት ሊሆን ይችላል። ቢኾንም…ጄኔራሉ ደግ አልሠሩም። "መርዕድ ምነው ቀረ? ምንስ ብርቱ ጉዳይ ቢገጥመው፣ ቆራጡን መሪያችንን መሸኘት አልነበረበትም?" የምትል የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ ሳይገባቸው አልቀረም፤ የደኅንነቱን ሹሙን፤ ኮ/ል ተስፋዬ ወልደሥላሴን…። ኢታማዦር ሹሙ ደግ አልሠሩም፤ እንደምንም ብለው አለቃቸውን መሸኘት ነበረባቸው። እርሳቸው በተቃራኒው መከላከያ ሚኒስትር ውስጥ፣ ከኢትዮጵያ ሆቴል ፊት ለፊት፣ ከአምባሳደር ሲኒማ ጎን፣ ከቢሯቸው ቁጭ ብለው የክፍለ ዘመኑን አስገራሚ የስዒረ መንግሥት 'ተውኔት' እየጻፉ ነበር። የመንጌ አውሮፕላን ለምን አልጋየም? ጓድ መንግሥቱ ለምሳ ያሰቧቸውን ለቁርስ ማድረግን ተክነውበት ሊሆን ይችላል። በዚያች ዕለት ግን ቁርስም ምሳም እራትም ሊደረጉ የነበሩት እርሳቸው ናቸው። ይህን ፈጽሞ አያውቁም። አውሮፕላኑን የተሳፈሩትም የእሳትራት ኾነው ነው። የተሳፈሩባትን አውሮፕላናቸው ሰማይ ላይ እንዳለ የማጋየቱ ነገር ያበቃለት፣ ተቦክቶ ያለቀ፣ የደቀቀ ጉዳይ ነው። ይህን ያጸደቁት ደግሞ ከሞላ ጎደል ሁሉም የጦር አዛዦች ነበሩ። ድንገት መንጌን ሸኝተው ሲመለሱ ቆፍጣና ወታደራዊ መንፈሳቸው በ'ኖና ተ'ኖ የባህታዊ ሐሳብ በልባቸው አደረ። "…ጓዶች! ለምን እናጋየዋለን ግን?" "እንዴት ማለት…" "...እሱን ለመግደል ብለን የ70 ንጹሐን ነፍስን ከምናጠፋ…." "ኖኖኖኖ…ወደ ኋላ ባንመለስ ነው የሚሻለው በዚህ ጉዳይ…ተስማምተን የጨረስነውን? '' "አደለም!ተስማምተን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ወ/ሮ ውባንቺስ፣ ልጃቸውስ? አብራሪዎቹስ? ወገኖቻችን አይደሉም? ምን አጠፉና ነው በዚህ ሰውዬ ጦስ የሚጠፉት…" ይሄ ሐሳብ ምናልባትም ከአየር ኃይል አዛዡ ጄኔራል አመሃ የመጣ ሳይሆን አይቀርም። "…እና ምን በጀ ጓዶች?" ምናልባት እርጋታ የማይለያቸው ሰብሳቢው ጄኔራል መርእድ እንዲያ ጠይቀው ይሆናል። "…ባይሆን በጦር አውሮፕላን አስገድደን አሥመራ ብናሳርፈው አይሻልም?" ይሄ ከጄኔራል አመሃ የመጣ መፍትሄ ሊሆን ይችላል። " አሥመራ የማይሆን ነው፤ በሙሉ መንጌ መንጌ የሚል አየር ወለድ ነው ያለው" • የታሪክ መማሪያ መጻሕፍት ለምን ይከለሳሉ? በዚህ ጊዜ ምናልባትም የዘመቻ አዛዡ ጄኔራል አበራ እምር ብለው እንዲህ ተናግረው ይሆናል፤ "ምንድነው ይሄ ውልውል? ተስማምተን? ተግባብተን በአንድ ያጸደቅነውን? የምን መንሸራተት ነው? ይሄኮ ፌዝ አይደለም! መፈንቅለ መንግሥት ነው እያካሄድን ያለነው። የሊቀመንበሩን አውሮፕላን ካላጋየን ኋላ የምንጋየው እኛው ነን…ውርድ ከራሴ…" ጄኔራሎቹ መግባባት ተሳናቸው። ይህ ጉዳይ የመጨረሻቸው መጀመርያ ኾነ። ጄኔራሎቹ በመከላከያ ሚኒስትር ግቢ፣ አንደኛ ፎቅ ላይ፣ ፊቷን ወደ ክቡ የብሔራዊ ባንክ ሕንጻ ባዞረች አንዲት የስብሰባ አዳራሽ ታድመው በኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ላይ እንዲህ ጉንጭ አልፋ ክርክር እያደረጉ ሳለ ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱን የያዘው አውሮፕላን በሰማይ ላይ ሳይጋይ፣ አሥመራም ተገዶ ሳያርፍ የኢትዮጵያን የአየር ክልል እየቀዘፈ ራቀ። ደብረዘይት አየር ኃይል ግቢ አውሮፕላኑን ለመምታት በተጠንቀቅ የነበሩት ጄቶችም ሞተር አጠፉ። ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ በአሥመራ ግን 'መንጌ ተገድለዋል' በአሥመራ የግዙፉ 2ኛው አብዮታዊ ሠራዊት አድራጊ ፈጣሪ፣ ሥመ ጥሩው ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ናቸው። እንዲያውም የስዒረ መንግሥቱ ሁነኛው ጠንሳሽ ሳይሆኑ አይቀሩም። ምክትላቸውን ጠርተው ነገሩ ሁሉ መልክ መልክ መያዙን አረጋገጡ። ጄኔራል ቁምላቸው በአራት አንቶኖቭ የታጨቁ 433 ልዩ ኮማንዶዎችን አሳፍረው ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እንዲጀምሩ አዘዟቸው። • "በጥሩ ጤንነት ላይ አይደለችም" የስምረት ካህሳይ ቤተሰቦች ጄኔራል ቁምላቸው አገሪቱ አለኝ የምትላቸውን የአየር ወለድ አባላት "ዳይ! ተንቀሳቀስ" አሏቸው። በወታደር ቤት አለቃ ሲያዝ "አቤት ጌታዬ!" እንጂ "ለምን ጌታዬ?" አይባልም። ሶቭየት ሠራሽ አንቶኖቭ ውስጥ እንዳሉ ድንገት ጄ/ል ቁምላቸው እመር ብለው ተነሱ። የሃሎ ሃሎ መነጋገሪያውን ረዳታቸው አቀበሏቸው። አንድ በራሪ ወረቀት ከኪሳቸው አውጥተው ማንበብ ጀመሩ። እዚያ አንቶኖቭ ውስጥ ያለው ወታደር በሙሉ በታላቅ ፌሽታ አጨበጨበ። በዚያ አንቶኖቭ ውስጥ የነበሩትና ዛሬም በሕይወት የሚገኙት ሌ/ኮ/ል ካሳዬ ታደሰ ለቢቢሲ አማርኛ እንደተናገሩት… "መንግስቱ ተገድሏል ሲባል መጀመርያ ደነገጥኩ፤ ከዚያ ሁሉም ሲያጨበጭብ እኔም ማጨብጨብ ጀመርኩ" ሲሉ የወቅቱን ድራማ ገልጸዋል፡፡ ሰማይ ላይ አንቶኖቩ ውስጥ ይህ ሲሆን የአሥመራ ሬዲዮ በበኩሉ መንግሥቱ መገደሉን አወጀ። ከአንድ ሰዓት ተኩል በረራ በኋላ ጄኔራል ቁምላቸው ኮማንዷቸውን ይዘው አዲስ አበባ ጦር ኋይሎች ልደታ አርሚ አቪየሽን ገብተዋል። ግማሾቹን ኮማንዶዎች ደግሞ እዚያው ቦሌ አየር መንገድን እንዲቆጣጠሩ አድርገዋል። የዚህ ልዩ ኮማንዶ ተግባር ሬዲዮ ጣቢያውን መቆጣጠር፣ መከላከያ ሚኒስትር ለሚገኙት መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎች ደግሞ ከለላ መስጠት፤ ድንገት ‹‹ለመንጌ አንገቴን እሰጣለሁ›› የሚል ኃይል ካለ አንገቱን እንደ ዶሮ መቀንጠስ ነው። • ወመዘክር፡ ከንጉሡ ዘመን እስከዛሬ የሚገርመው የአሥመራ ሬዲዮ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እስከወዲያኛው እንደተሰናበቱ ያወጀው ገና ረፋድ ላይ ነበር። በመሆኑም ጄኔራል ቁምላቸውም እስከመጨረሻው የሚያውቁት መንግሥቱ መገደሉን ነው። ሌ/ኮ/ል ካሳዬም ይህንኑ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከጦላይ የመጣው ሠራዊት መፈንቅለ መንግሥቱን ለማቅናት ከአሥመራ በጄ/ል ቁምላቸው እየተመራ አዲስ አበባ ከገባው ኃይል ሌላ ከጦላይም አንድ ሻለቃ ተንቀሳቅሷል። ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ ከሴረኞቹ ጋር በስሱም ቢሆን ሳይመሳጠሩ አልቀሩም። አሁንም ድረስ በሕይወት አሉ፤ አሜሪካን አገር። ወደ አዲስ አበባ የሚላከውን ጦር አዘጋጅተው እሳቸው ከሰሜን ኮሪያ የመጣ ልኡካን ቡድንን ተቀብለው እያነጋገሩ ነበር። ጦላይ ያለው ልዩ ኮማንዶ የቁልምጫ ስሙ ''ስፖርታ'' ይባላል። ሰሜን ኮሪያዎች ለከተማ ውጊያ፣ ለጨበጣ ፍልሚያ በልዩ ጥንቃቄ ያሰለጠኑት ጦር ነው። ጄ/ል ውበቱ ጥርት ያለ መመርያ ባይደርሳቸውም 150 የሚሆኑትን ምርጥ ምልምሎች በወታደራዊ ሄሊኮፕተር ወደ አዲስ አበባ ላኳቸው። ፖስታ ቤት መገናኛ ሚኒስትር አካባቢ በሚገኝ ሜዳ ላይ ሆነው ትዕዛዝ እንዲጠባበቁ ተደረጉ። ኋላ ላይ 4ኛ ክፍለ ጦር... አምባሳደር ጋ፣ ኢትዮጵያ ሆቴል ጎን፣ መከላከያ ሚኒስትር ውስጥ … ከኢትዮጵያ ሆቴል ትይዩ በዋናው የመከላከያ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ የጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይገኛል። ይህ አዳራሽ ፊቱን ወደ ወርቃማው የብሔራዊ ባንክ የሰጠ ነው። በዚህ አዳራሽ 18 መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎች ሴራ እየጎነጎኑ ነው። ቁጥራቸው ይጨምራል ይቀንሳል። ሆኖም በአገሪቱ አንድም የቀረ ቱባ ጄኔራል የለም። • ያለ እናት የመጀመሪያው የእናቶች ቀን በኢትዮጵያ የመጀመርያው አብዮታዊ ጄኔራል፣ ተወዳጁ፥ ደርባባው፣ አንደበታቸው የረጋው ጄ/ል መርዕድን ጨምሮ የባሕር ኃይል አዛዡ ሪር አድሚራል ተስፋዬ ብርሃኑ፣ የአየር ኃይል አዛዡ ጄኔራል አምሐ፣ የምድር ጦር አዛዡ ጄኔራል ኃይሉ፣ የፖሊስ ሠራዊት አዛዡ ጄኔራል ወርቁ ይገኙበታል። ስለ ጀግንነታቸው ሳር ቅጠሉ የመሰከረላቸው እነ ጄኔራል ፋንታ በላይ፣ እነ ጄኔራል አበራ አበበ፣ እነ ጄ/ል ደምሴ ቡልቶም አሉበት። ስለነዚህ ጄኔራሎች የጦር ጀብድ እንኳን ወታደሮቻቸው አንዳንድ የሰሜን ተራሮችም አፍ አውጥተው ባይናገሩ...ማን ቀረ ታዲያ? እርግጥ ነው ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ በአካል አምባሳደር-ብሔራዊ አካባቢ አይሁኑ እንጂ በመንፈስ አብረዋቸው ናቸው። እርሳቸው አሥመራ ትልቁን የቤት ሥራ ሠርተው ጨርሰዋል። የአገሪቱ ሁለት ሦስተኛ ጦር በርሳቸው ሥር ነው ያለው። አሁንም ድረስ አስገራሚው ነገር ታዲያ የአሥመራ ጦር መጀመሪያ በታቀደው መሠረት የመንጌ አውሮፕላን መመታቷን ነው የሚያውቀው። ይህንኑም በሬዲዮ አስነግሯል። • የሥራ ቃለመጠይቅ ማድረግ ያስፈራዎታል? እነዚህ 18 የጦር አበጋዞች ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋውን የአገሪቱን ሠራዊት ያዛሉ። ሁሉም በመፈንቅለ መንግሥቱ ጉዳይ ላይ መግባባት ደርሰዋል። ሆኖም እዚያው መከላከያ ሚኒስትር ስብሰባ ላይ ናቸው። ይህ ይሆን መዘናጋትን የፈጠረባቸው? ምን ዓይነት ምድራዊ ኃይል መጥቶ ይህን 'ኩዴታ' ሊያከሽፍ ይችላል? ስክነት የራቃቸው ጄኔራል አበራ ብቻ ናቸው። እስራኤል ነው የተማሩት። የዘመቻ አዛዡ ጄኔራል አበራ ወትሮም ችኩል ናቸው ይባላል። ቀልባቸው የሆነ ነገር ሳይነግራቸው አልቀረም። በስብሰባው መካከል ወጣ እያሉ ግቢውን ይቃኛሉ። በዚህ መሀል የታንክ ቃቃታ የሰሙ መሰላቸው። የመከላከያ አስተዳደር መምሪያ አዛዡን ጄኔራል ዑመርን አስከትለው የመከላከያ ግቢ የባንዲራ መስቀያው ጋ ቆመው መከላከያ ቢሮ ውስጥ ያለውን ሰው በሙሉ ወደ ግቢው እንዲሰለፍ አዘው ንግግር ማድረግ ጀመሩ፤ የመንጌን ፍጻሜም አበሰሩ። ተጨበጨበ…ቪቫ ኩዴታ ተባለ. . . መከላከያ ሚንስትሩ ጄ/ል ኃይለጊዮርጊስ ለጄ/ል ደምሴ ቡልቶ ዕውቅና እየሰጡ። ከመከላከያ ሚንስትሩ ጎን ቆመው የሚታዩት ጄ/ል አበራ ናቸው-ሟች እና ገዳይ። የመከላከያ ሚኒስትሩ መገደል የደኅንነት ሚኒስትሩ ተስፋዬ ወ/ሥላሴ ሴራ ሸትቷቸዋል፤ ባምቢስ ከሚገኘው የደኅንነት ቢሯቸው እየበረሩ ወደ ምኒሊክ ቤተ መንግሥት ነዱ። የመንጌን ልዩ ረዳት መንግሥቱ ገመቹን ጠርተው አስቸኳይ ስብሰባ ጀመሩ። እነ ፍቅረሥላሴ ወግደረስም አሉበት። እንዲያውም ሰብሳቢው እርሳቸው ናቸው። ምንድነው እየሆነ ያለው? እነ መርእድ ምንድነው እየዶለቱ ያሉት? ‹‹እረ በፍጹም›› አሉ ሚኒስትሩ። ሄደው እንዲያጣሩ ሐሳብ ቀረበ። በሄዱበት ይቀራሉ ያለ አልነበረም። • "ልዩ ነዳጅ መኖሩን አልደረስንበትም" የማዕድን፣ የፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ቁልቁል ወደ አምባሳደር በረሩ። ወደ ቢሯቸው ገብተው ወጡ። ጄ/ል ኃብተጊዮርጊስ ወትሮም ከጄ/ል አበራ ጋር እስተዚህም ናቸው። እረ እንዲያውም ዐይንና ናጫ...። ጄ/ል አበራ የሆነ የቀፈፋቸው ነገር ያለ ይመስላል። ጄ/ል መርዕድ ከሚመሩት ስብሰባ በየመሀሉ እየወጡ ኮሪደሩን፣ አካባቢውን ይቃኙና ይመለሳሉ። ድንገት ለቅኝት ደረጃውን ሲወርዱ፣ መከላከያ ሚኒስትሩ ደግሞ ደረጃውን ሲወጡ ተገጣጠሙ። "አበራ! ምንድነው እኔ የማላውቀው ስብሰባ?" ሳይሉ አልቀሩም። አንዱ ሁለት ተባብለውም ሊሆን ይችላል። ብቻ ጄኔራል አበራ በቅልጥፍና ሽጉጣቸውን አውጥተው መከላከያ ሚኒስትሩ ላይ አከታትለው ተኮሱ። ጦር ኃይሎች ቢወሰዱም አልተረፉም። ጄኔራል አበራ እንዴት አመለጡ? ለምን አመለጡ ? ይህ ሁሉ ሲሆን ከአሥመራ የመጣው የጄኔራል ቁምላቸው ሠራዊት ጦር ኃይሎች ግቢ ሆኖ በተጠንቀቅ ትእዛዝ ይጠባበቃል። እንዲያውም ስልክ ወደ ጄ/ል አበራ ደውሎ አልተነሳለትም። ከጦላይ የመጣውና በሰሜን ኮሪያዎች የሰለጠነው የስፓርታ ጦርም ፖስታ ቤት አካባቢ ሥራ ፈትቶ ሜዳ ላይ ተቀምጧል። ። ሁሉም ታዲያ ሪፖርት የሚያደርጉትም ትእዛዝ የሚቀበሉትም ከጄኔራል አበራ ብቻ ነው። የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ እሳቸው ናቸዋ። ጄ/ል አበራ ግን ያልተጠበቀ ነገር ፈጽመው ችግር ውስጥ ገብተዋል። መከላከያ ሚኒስትሩን ከገደሉ በኋላ ወደ ቢሮ አልተመለሱም። ልዩ ኮማንዶነት የሰለጠኑት ጄ/ሉ በአጥር ዘለው አምልጠዋል። • ሶማሊያ በሀገር አቀፍ ፈተና ወቅት ማህበረዊ ሚዲያዎችን ልትዘጋ ነው አንዳንዶች ከጎን የሚገኘው ቡና ገበያ ግቢ ገብተው ዘበኛ ማርከው የወታደር ልብሳቸውን አውልቀው የዘበኛ ልብስ ለብሰው ተሰወሩ ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ የለም ከመከላከያ የወጡት በአጥር ሳይሆን በበር ነው፤ የአንድ ሠራተኛ ልብስ ቀይረው ነው ይላሉ። የጄ/ል አበራ ከመከላከያ መሰወር ነገሮችን አመሰቃቀለ። ከጦላይና ከአሥመራ የመጣው ኃይል ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገብቶት እርሳቸውን ይፈልጋል። እርሳቸው ግን ስልክ አያነሱም። ቢሮም የሉም። በዚያ ዘመን ሞባይል የሚባል ነገር አይታወቅ ነገር… • "የሚያክሙን ሙዚቃዎች እንዳሉ ሁሉ የሚያውኩንም አሉ" ዶ/ር መልካሙ ጄኔራሎቹ ራሳቸውን ለምን አጠፉ? ግንቦት ስምንት ቀትር ስምንት ሰዓት ግድም የጀመረው መፈንቅለ መንግሥት ራሱን በራሱ እየተበተበ አንድም ፋይዳ ያለው ነገር ሳያከናውን መሸበት። ደኅንነቱ ተስፋዬ ወ/ሥላሴ ሻምበል መንግሥቱ ገመቹን ይዘው መከላከያን አስከበቡ፤ ለዚያውም በታንክና በብረት ለበስ። ከዚያ በፊት ግን ነገሩን በሰላም እንጨርሰው በሚል ሽማግሌ ተልኳል፤ ሌ/ኮ አዲስ ተድላና ኮ/ል ደበላ ዲንሳ ነበሩ አደራዳሪዎቹ። ‹‹መፈንቅለ መንግሥቱ ያበቃለት ጉዳይ ነው፤ ምንም ድርድር ብሎ ነገር የለም። ባይሆን አግዙን›› ሳይሏቸው አይቀርም፣ እነ ጄ/ል መርዕድ። • ቴምር በረመዳን ለምን ይዘወተራል? ዞሮ ዞሮ ሰዓቱ ነጎደ። ማስታወቂያ ሚኒስትር አልተያዘ፣ ሬዲዮ ጣቢያ አልተያዘ፣ ቴሌ አልተያዘ…ሰዓቱ ነጎደ። የሳር ቅጠሉ አዛዦች በሙሉ እዚያ መሆናቸው ሳያዘናጋቸው አልቀረም። የጄ/ል አበራ ድንገት ሰው ገድሎ መሰወር ግን ነገሮችን አወሳሰበ። የመንጌ ቀኝ እጅ ሞክሼያቸው መንግሥቱ ገመቹ የልዩ ብርጌድ ኃይላቸውን ከ4ኪሎ አንቀሳቀሱ። በሂልተን አድርገው አምባሳደር ጋ ሲደርሱ 'መከላከያ ሚኒስትሩን ክበብ' አሉ። ውስጥ እነ ጄ/ል ፋንታ በላይ፣ አነ ጄ/ል አመሃ፣ እነ ጄ/ል መርዕድ…ምን እያደረጉ እንዳሉ የሚያውቅ ምድራዊ ኃይል የለም። ሆኖም በዚያ ሰዓት መከበባቸውን እንደተረዱ ከአሥመራ ይመጣል የተባለው ኃይል ባለመድረሱ ተስፋ ቆርጠው ሊሆን ይችላል። ብቻ ጄ/ር መርዕድና ጄ/ል አመሐ ዛሬም ድረስ ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ እዚያው ራሳቸውን አጠፉ። ድኅረ ታሪክ ግንቦት 9 ማታ ኮ/ል መንግሥቱ ከምሥራቅ ጀርመን ጉብኝታቸውን አቋርጠው ኮሽታ ሳያሰሙ ተመለሱ። ግንቦት 10፣ ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ በገዛ ወታደሮቻቸው ተገደሉ፤ ከእርሳቸው ጋር በድምሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች ተመሳሳይ ክፉ እጣ ገጠማቸው። በሟቾቹ ሬሳ ላይ እጅግ የሚቀፍ፣ ታሪክ የሚጸየፈው የሰይጣን ድርጊት ተፈጸመ። ከሦስት ቀን በኋላ ጄኔራል ፋንታ በላይ ከተደበቁበት ኮንቴይነር ወጡ። ለጥቂት ወራት ማዕከላዊ ለብቻቸው ተነጥለው ታስረው ሳሉ እስከዛሬም ይፋ ባልሆነ ሁኔታ "ጠባቂያቸውን ገድለው ሊያመልጡ ሲሉ ተገደሉ" ተባለ። • እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ''ደካማ ነው'' ተባለ በሦስተኛው ሳምንት መከላከያ ሚኒስትሩን ገድለው ያመለጡት ጄ/ል አበራ ጉለሌ አካባቢ ከተደበቁበት ዘመድ ቤት ተከበቡ። በመስኮት ዘለው ጣሪያ ላይ ወጥተው ሊያመልጡ ሲሉ በአንድ ወጣት ፖሊስ ግንባራቸውን ተመትተው ወደቁ። አንዳንድ የሰው መረጃዎች ጄ/ል አበራን አሳልፎ የሰጣቸው ዘመድ ዛሬም ድረስ በጸጸት ይኖራል ይላሉ። ከሆኑ ወራት በኋላ የአሥመራውን አየር ወለድ ጦር አዲስ አበባ ይዘው የመጡት ጄኔራል ቁምላቸው በአንዳች ተአምር አምልጠው አሜሪካ ገቡ ተባለ። ሲአይኤ እንዳሾለካቸው ተጠረጠረ። • የስኳር ፋብሪካዎችን ለግል ባለሃብቶች የመስጠት ፋይዳና ፈተናዎቹ ከዓመት በኋላ ግንቦት 13፣ 1981 መፈንቅለ መንግሥቱ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 12 ጄኔራሎች ድንገት ለውሳኔ ተጠሩ። የወታደራዊ ፍርድ ቤት የመሀል ዳኛው ጄ/ል አሥራት ብሩ በብጣሽ ወረቀት የተጻፈችና ከኮ/ል መንግሥቱ እንደተላከች የምትገመት አንዲት ወረቀት እንባ እየተናነቃቸው አነበቧት ተባለ። በ12ቱ ላይ ሞት ተፈረደ። ፍርደኞቹም እንዲህ እያሉ ይጮኹ ነበር፤ ‹‹ቤተሰባችንን ሳንሰናበት አትግደሉን…››፣ ‹‹ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ዕድሜ የለውም››፣ ‹‹ልጆቻችንን አደራ››። ያንኑ ምሽት ተረሸኑ። ከስዒረ መንግሥት ሙከራው ከ2 ዓመት በኋላ ግንቦት 13 ቀን ኮ/ል መንግሥቱ ከአገር ሸሹ። የኮ/ሉን ሽሽት ተከትሎ ለአንድ ሳምንት ርዕሰ ብሔር የሆኑት ጄ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳን ሞታቸውን እየተጠባበቁ ለነበሩ ጥቂት የመፈንቅለ መንግሥቱ ተከሳሾች ምሕረትን አወጁ።
xlsum_amharic-train-204
https://www.bbc.com/amharic/news-55219617
ቴክኖሎጂ ፡ ከጉግል ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው ኢትዮጵያዊት ትምኒት ገብሩ ማናት?
የአዲስ አበባ ልጅ ናት። ትምኒት ገብሩ (ዶ/ር)።
[ "የአዲስ አበባ ልጅ ናት። ትምኒት ገብሩ (ዶ/ር)።" ]
ትምኒት ገብሩ ዓለምን በፍጥነት እየለወጠ ያለው ሰው ሠራሽ ልህቀት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ኤአይ) ውስጥ አሉ ከሚባሉ ጥቁር ሴት ባለሙያዎች መካከል አንዷ ነች። ትምኒት፤ ጉግል ውስጥ የኤአይ የሥነ ምግባር ዘርፍ ባልደረባ ነበረች። ቴክኖሎጂው አካታች እና ፍትሐዊ እንዲሆን ከሚጥሩ መካከል በግንባር ቀደምነት ትጠቀሳለች። ባለፈው ሳምንት ከጉግል አመራሮች ጋር በተፈጠረ ውዝግብ ከሥራዋ መባረሯ በርካታ የዘርፉ ሙያተኞችን አስቆጥቷል። ትምኒት አዲስ አበባ ሳለች. . . የናዝሬት ስኩል ተማሪ ነበረች። አስረኛ ክፍል ስትደርስ ወደ አየርላንድ አቀናች። የሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ትምህርቷን ያጠናቀቀችው አሜሪካ ነው። ለቤተሰቧ የመጨረሻ ልጅ ናት። ከሁለት ዓመት በፊት ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ፤ ልጅነቷን ስታስታውስ "ሕጻን ሳለሁ ትምህርት እወድ ነበር። ስታመም ራሱ ከትምህርት ቤት መቅረት አልወድም ነበር" በማለት ነው። በተለይም ለሒሳብ እና ፊዚክስ ልዩ ፍቅር ነበራት። አባቷ ኤሌክትሪካል መሀንዲስ መሆናቸው ወደ ሳይንስ እንድታዘነብል እንዳደረጋት ትናገራለች። ሁለት ታላላቅ እህቶቿም በዚሁ የሙያ ዘርፍ ነው የተሰማሩት። ትምኒት በአሜሪካ. . . ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን አጠናቃ ስታንፈርድ ዩኒቨርስቲ ገባች። የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪዋን የሠራችው በኤሌክትሪካል ምህንድስና ነው። በዓለማችን ስመጥር ከሆኑት መካከል በሚጠቀሱት አፕል፣ ከዚያም ጉግል ውስጥ ሠርታለች። ትምኒት በግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ውስጥ ፍትሐዊነት፣ ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና ሥነ ምግባር ላይ ያተኮረ ቡድን ውስጥ ሠርታለች። በሰው ሠራሽ ልህቀት ዘርፍ የጥቁር ሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ 'ብላክ ኢን ኤአይ' የተባለ ተቋምን ከመሠረቱ መካከል አንዷ ናት። የፈጠራ ሥራዎችን አካታችነት በሚፈትሹ ጥናቶቿ እንዲሁም ቴክኖሎጂና የሰብአዊ መብት ጥያቄን በማስተሳሰርም ትታወቃለች። ብላክ ኢን ኤአይ፤ ጥቁር ሴቶች ወደ ሰው ሠራሽ ልህቀት ዘርፍ እንዲገቡ፣ በሙያው የተሰማሩ እርስ በእርስ እንዲደጋገፉና ተደማጭነት እንዲያገኙ ለማስቻል ነው የተቋቋመው። ትምኒት እንደምትለው፤ ስብስቡ ጥቁር ሴቶችን የሚያበረታታ፣ ወደላቀ ደረጃ እንዲደርሱ የሚያስችልም ነው። ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ፤ "ከዚህ ሙያ ልወጣ ነበር፤ ወደ እናንተ ተቋም ከመጣሁ በኋላ ግን ጥናት መስራት ጀምሬያለሁ ብለው ኢሜል ያደርጉልናል። ሥራ ያገኙ፤ ማስተርስና ፒኤችዲ ማጥናት የጀመሩም አሉ። በእኛ ወርክሾፕ ተገናኝተው በጥምረት መስራት የጀመሩም አሉ" ስትል ነበር ብላክ ኢን ኤአይ ያለውን ሚና የገለጸችው። ለብላክ ኢን ኤአይ መመሥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካበረከቱ መካከል ኢትዮጵያዊቷ ረድኤት አበበ ትገኝበታለች። የኮምፒውተር ሳይንቲስቷ ረድኤት፤ በአልጎሪዝም እና ኤአይ ዙርያ ትሠራለች። ከኮርኔል ዩኒቨርስቲ በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ [ዶክትሬት] በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ናት። በዘርፉ ያሉ ጥቁሮች፣ በተለይም ደግሞ ጥቁር ሴቶች ውስን እንደሆኑ የምታስረዳው ትምኒት፤ አብዛኞቹ ጥናቶቿ የፆታና የዘር አካታችነት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ትምኒት ገብሩ የትምኒት ጥናቶች ከትምኒት ታዋቂ ጥናቶች መካከል ፌሻል ሪኮግኒሽን ሲስተም ወይም የሰዎችን ፊት ገጽታ በማየት ማንነታቸውን የሚያሳውቅ መተግበሪያን በተመለከተ የሠራችው ይጠቀሳል። መተግበሪያው የጥቁር ሰዎችን በተለይም ደግሞ የጥቁር ሴቶች ገጽታ አይቶ ማንነታቸውን ለመለየት እንዲችል ተደርጎ አለመሠራቱን ጥናቱ ይጠቁማል። ትምኒት እንደምትናገረው፤ ጥናቱን የጀመረችው ኤምአይቲ ከምትሰራ ጓደኛዋ ጋር ነው። "ጓደኛዬ ጥቁር ሴት ነች። ለአንድ ፕሮጀክት 'ፌስ ሪኮግኒሽን' ስትጠቀም ፊቷን 'ዲቴክት' ማድረግ [ማንበብ] አልቻለም። እንደሌለች ነው የሚቆጥራት። ነጭ 'ማስክ' [ጭንብል] ፊቷ ላይ ስታደርግ ግን ያነባል" በማለት የጥናቱን መነሻ አጋጣሚን ታስታውሳለች። 'ፌስ ሪኮግኒሽን' ነጮችና ጥቁሮች ላይ እኩል እንደማይሠራና በተለይ ደግሞ ጠቆር ያሉ ሴቶች በአግባቡ ማንበብ ወይም ማወቅ እንደሚሳነው ጥናታቸው ያመለክታል። እንዲህ አይነት ዘረኛ እና ፆተኛ መድልዎ በብዙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ እንደሚስተዋል የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ትምኒት ከምታደንቃቸው መጽሐፎች አንዱ በሆነው 'ዌፐንስ ኦፍ ማት ዲስታራክሽን' ላይ ስለመድልዎ በዝርዝር ተጽፏል። ጸሐፊዋ ካቲ ኦኒል ሰው ሠራሽ ልህቀት አካታች አይደለም ስትል ትተቻለች። ዘር፣ ፆታ፣ ቀለምና መደብን መሠረት ያደረገ መድልዎን ማስወገድ ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ ዘርፉን የበለጠ አካታች ማድረግ እንደሆነ ካቲ ትጠቁማለች። ሰዎች እነሱን የሚመስል ሰው የሚያካትት ወይም እነሱን ለሚመስል ሰው ጥቅም የሚሰጥ ቴክኖሎጂ መፍጠር የሚችሉት በዘርፉ ሲሰማሩ መሆኑን ትምኒት፣ ካቲና ሌሎችም ባለሙያዎች ይስማሙበታል። 'ዳታ አክቲቪዝም' ትምኒት፤ ከበይነ መረብ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙርያ ንቅናቄ ከሚያደርጉ የመብት ተሟጋቾች (ዳታ አክቲቪስትስ) አንዷ ነች። እነዚህ የመብት ተሟጋቾች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ምን ያህል አካታች ናቸው? ሲሉ ይጠይቃሉ። ክፍተት ሲያገኙም ከግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር ሳይቀር ይፋለማሉ። ለትምኒት ቴክኖሎጂ ከመብት ሙግት ጋር የተያያዘ ነው። "ለአብዛኛው ሰው የማይሠራ ቴክኖሎጂ ከተሠራ ለሰው የማይሆን ነገር እየተሠራ ነው ማለት ነው" የምትለው ባለሙያዋ፤ አፍሪካውያን ሴቶች ለራሳቸው የሚሆን ነገር እንዲሠራ ቴክኖሎጂ ውስጥ መግባት እንዳለባቸው ታሳስባለች። እንደ ምሳሌ የምትጠቅሰው የዘረ መል ቅንጣት ላይ የተሠሩ እንዲሁም ለተለያዩ ህመሞች የሚቀመሙ መድኃኒቶችን ነው። አብዛኛውን ጊዜ ከአፍሪካውያን ወይም ከጥቁሮች ናሙና እንደማይወሰድ፣ ቢወሰድም የናሙናው መጠን ውስን እንደሚሆን በማስረጃነት ትጠቅሳለች። ለዚህም ነው ትምኒት ቴክኖሎጂ ከሰብአዊ መብት ትገል ጋር ጎን ለጎን እንደሚሄድ የምትናገረው። ትምኒት፤ ቴክኖሎጂ አካታችና ፍትሐዊ እስከሆነና ለበጎ አላማ እስከዋለ ድረስ መጪው ዓለም ብሩህ የመሆን እድሉ ሰፊ እንደሆነ ከሚያምኑ ባለሙያዎች አንዷ ናት። በእሷ ዕይታ፤ አፍሪካ ውስጥ የድሮን ጥናት የሚሠሩ ጀማሪዎች በመኖራቸው መንገድ ሳያስፈልግ በድሮን መድኃኒት ማዳረስ ይቻል ይሆናል። ትልልቅ ሆስፒታል መሥራት ሊቀር፣ ምናልባትም በትንንሽ መሣሪያ ሕክምና መስጠት ይቻል ይሆናል። ራሳቸውን የሚያሽከረክሩ መኪኖች ሲበራከቱ አይነ ስውራን በራሳቸው ይንቀሳቀሱም ይሆናል። ትምኒት፤ "ጥያቄው ግን እንዴት አድርገን ነው ቴክኖሎጂን የምንጠቀመው የሚል ነው? ብዙ ጦርነት ይኖራል? ኢ-ፍትሐዊነት ይኖራል? ምን አይነት ፖለቲካዊ ሁኔታ ይኖረናል? በጣም ጥቂት ሰዎች ብዙ ገንዘብ ኖሯቸው ብዙዎች ገንዘብ ከሌላቸው 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ' ነገሩን ያባብሰዋል" ትላለች። የትምኒት የኢትዮጵያ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ውስጥ ለወጣቶችን የኮዲንግ ሥልጠና የተሰጠበት 'አዲስ ኮደር' የተሰኘ ፕሮጀክት ነበራት። ከዚህ በፊትም በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደ የአይሲቲ ኮንፈረንስም ተሳትፋለች። ከኢትዮጵያ የወጡ የሰው ሠራሽ ልህቀት ባለሙያዎችን በብላክ ኢን ኤአይ እንዳካተተችም ትናገራለች። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ሠራሽ ልህቀት እየታወቀ መምጣቱን የምታምነው ትምኒት "ዘርፉ መታወቅ እየጀመረ ነው። ግን የተዋቀረ አካሄድ መኖር አለበት። ሁሉም ሰው የሚሳተፍበት እቅድም መኖር አለበት። ሰዎች ወደ ቴክኖሎጂው እንዲገቡ እድል መስጠትም አለብን" ትላለች። በተጨማሪም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የግል የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እንዲገቡ መንገዶች መመቻቸት እንዳለባቸው ትጠቁማለች። "ሰዎች የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ድርጅት እንዲጀምሩ ወይም ትልልቅ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዲመጡ መደረግ አለበት። በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ የሚሆኑ ተቋማት ቢበራክቱ ጥሩ ነው። መንግሥት ገንዘብ የሚሰጠው የጥናት ተቋም ያስፈልጋል። የዩኒቨርስቲ አስተማሪዎች በደንብ እየተከፈላቸው በትኩረት ጥናት እንዲሰሩ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል" ስትልም አስተያየቷን ሰጥታለች። ጉግል ውስጥ የተፈጠረው ምንድን ነው? በጉግል የሰው ሠራሽ ልህቀት የሥነ ምግባር ቡድን አጋር መሪ የነበረችው ትምኒት፤ ከጉግል እንደተባረረች ያስታወቀችው በትዊተር ገጿ ነበር። ትምኒት እንዳለችው፤ በሰው ሠራሽ ልህቀት ዘርፍ ላለው መድልዎ ትኩረት እንዲሰጥና በዘርፉ እምብዛም ውክልና ያላገኙ ሰዎች እንዲቀጠሩ የሚያሳስብ ኢሜል ከላከች በኋላ ነው እንደተባረረች የተነገራት። ዜናውን እንደ ዋሽንግተን ፖስት፣ ብሉምበርግ እና ኒው ዮርክ ታይምስ ያሉት ግዙፍ የአሜሪካ የሚዲያ ተቋማት ይዘውት ወጥተዋል። በሰው ሠራሽ ልህቀትና ተያያዥ የቴክኖሎጂ ዘርፎች የሚሠሩ እውቅ ባለሙያዎች የትምኒትን መባረር በመቃወም ትዊተር ላይ ድምጻቸውን አሰምተዋል። #ISupportTimnit እና #BelieveBlackWomen በሚሉ ሁለት ሀሽታጎች የጉግል ሠራተኞችን ጨምሮ በርካቶች ከትምኒት ጋር አጋርነታቸውን አሳይተዋል። በሰው ሠራሽ ልህቀት ውስጥ ካሉ ጥቂት ጥቁር ሴቶች አንዷ የሆነችው ትምኒት መባረሯ በጉግል አመራሮችና መድልዎን የሚቃወሙ ሠራተኞች መካከል የተፈጠረው ውጥረት አንድ ማሳያ ነው ተብሏል። ከቀናት በፊት ኤምአይቲ ባወጣው ዘገባ መሠረት ለትምኒት መባረር ምክንያት የሆነው ጥናት "On the Dangers of Stochastic Parrots: Can Language Models Be Too Big?" ይሰኛል። አራት የጉግል ሠራተኞችን ጨምሮ በስድስት ባለሙያዎች የተጻፈ ነው። ጥናቱን የተመለከተ ውይይት ላይ እንድትሳተፍ ከተጋበዘች በኋላ ጽሑፍ ውድቅ እንድታደርገው ትዕዛዝ እንደተሰጣት ትምኒት ተናግራለች። የጉግልን ውሳኔ ያልተቀበለችው ትምኒት፤ ከጥናቱ ላይ ስሟን ለማውጣት ለድርጅቱ ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጧን እና ጉግል ግን በምላሹ በገዛ ፍቃዷ ሥራዋን መልቀቋን እንደሚቀበል በመግለጽ እንዳባረራት ተናግራለች። ሥራዋን በገዛ ፈቃዷ አለመልቀቋንና የጉግል የሰው ሠራሽ ልህቀት ምርምሮች ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊ ጄፍ ዲን እንዲሁም ሌሎችም የተቋሙ አመራሮች እንዳባረሯት አስረድታለች። ከቀድሞውም በተቀጣሪዎቹና በሌሎችም የሰው ሠራሽ ልህቀት ባለሙያዎች ትችት የሚሰነዘርበት ጉግል፤ ትምኒትን ማባረሩ ወቀሳውን አብዝቶበታል። የጉግል ሠራተኞች፤ ለፍትሐዊ ቴክኖሎጂና አካታችነት የቆመችው ትምኒት መባረሯ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋሞች ውስጥ ያለውን መድልዎና ጭቆና አደባባይ ያወጣ ነው ብለዋል። ትምኒት ገብሩ ትምኒት ከሥራ ውጪ. . . ትምኒት ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ እንደተናገረችው፤ ፒያኖ መጫወት ታዘወትራለች። ትምህርት ቤት ሳለችም ፒያኖ ተምራለች። "የምወደው ምግብ ሽሮ በጥቅል ጎመን ነው። ጣፋጭ ነገር በተለይም ቸኮሌት እወዳለሁ። ቡና በወተት እወዳለሁ። ሁሌ ጠዋት ስነሳ ቡና በወተት እጠጣለሁ" ትላለች። 'ብሮድ ሲቲ' የተባለውን ተከታታይ ፊልምና 'ደይሊ ሾው ዊዝ ትሬቨር ኖሀ' እንደምትከታተልም ለቢቢሲ ተናግራ ነበር። ትምኒት ከፌስቡክ እና ትዊተር ውጪ፤ 'ስታክ ኦቨር ፍሎ'፣ 'ሬድዮ ላቭ ፖድካስት' እና 'አፍሪካ ኢዝ ኤ ካንትሪ' የተባሉ ድረ ገጾችን ትከታተላለች። የምታደንቃት ሳይንቲስት የሁለት ጊዜ ኖቤል ተሸላሚዋ ሜሪ ኪዩሪ (ማዳም ኪዩሪ) ናት። 'just do it!' እጅግ የምታምንበት አባባል ነው። "ሰዎች በተደጋጋሚ እንዲህ ባደርግ ከማለት ማድረግ አለባቸው። ሰዎች አቅማቸውን አያውቁም። የይቻላል መንፈስ ካላቸው ግን ያደርጉታል" ትላለች ትምኒት።
xlsum_amharic-train-205
https://www.bbc.com/amharic/news-56726061
የኮቪድ-19 ጫና በረመዳን ወቅት እንዳይበረታ የሙስሊም ወጣቶች ጥረት
ሳላሃዲን ሰኢድ ይባላል። የምሥራቋ ፈርጥ ድሬዳዋ ነዋሪ ሲሆን በንግድ ሥራ ይተዳደራል። ሳላሃዲን ባለፈው ዓመት የድሬዳዋ የወጣቶች ጀማ (ማኅበር) ሰብሳቢ ነበር።
[ "ሳላሃዲን ሰኢድ ይባላል። የምሥራቋ ፈርጥ ድሬዳዋ ነዋሪ ሲሆን በንግድ ሥራ ይተዳደራል። ሳላሃዲን ባለፈው ዓመት የድሬዳዋ የወጣቶች ጀማ (ማኅበር) ሰብሳቢ ነበር።" ]
በ2012 የኮሮናቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ በተነገረ በጥቂት ወራት ውስጥ ረመዳን መግባቱን ተከትሎ የድሬደዋ ሙስሊም ወጣቶች ማኅበር ልዩ ልዩ ሥራዎችን ሲሰራ ነበር። በወቅቱ ታውጆ በነበረው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ምክንያት የሐይማኖት ተቋማት በአብዛኛው ተዘግተው ከርመዋል። ሳላሃዲን "መስጊድ በመዘጋቱ ልቡ ያላዘነ ማን ነበር?" ሲል አንድ ዓመት ወደ ኋላ ተጉዞ ያስታውሳል። "መስጊድ መሄድ ለአንድ ሙስሊም የዘወትር ተግባር ቢሆንም፣ በረመዳን መስጊድ ተዘግቶ ስናይ ግን ድጋሚ የሚከፍትም አይመስልም ነበር" ሲል እርሱን ጨምሮ ሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ተፈጥሮ የነበረውን ሐዘን ያስታውሳል። በድሬዳዋ ብቻ ሳይሆን ኮቪድ-19 ዓለምን የሚያሰጋ ወረረሽኝ ተብሎ ከታወጀ ገና በሦስተኛ ወሩ ነበር በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የረመዳን ፆም የገባው። በሚያዚያ 2012 ዓ.ም የዓለም የጤና ድርጅት በአንድ ወር ውስጥ በአምስት አህጉራት ቫይረሱ መግባቱ ሪፖርት ተደርጎልኛል በማለት ነበር ወረርሽኙን ዓለም አቀፍ ሲል ያወጀው። ታዲያ በወቅቱ ከሚታወቀው ባህሪይው የማይታወቀው የሚበልጠው ኮሮናቫይረስ በመላው ዓለም ያሉ 1.8 ቢሊዮን ሙስሊሞች ታላቁ የረመዳን ጾምን በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እንዲያሳልፉ ተገድደው ነበር። አገራት ይህ ገና ማንነቱ በቅጡ ያልተለየ በሽታ የዜጎቻቸውን ህይወት እንዳይቀጥፍ የሐይማኖት ቦታዎችን ጨምሮ የመሰባሰቢያ መንገዶችን አግደውም ነበር። በእስላማዊ የቀን መቁጠሪያ ሂጅራ መሰረት፣ ዘጠነኛ ወር ላይ የሚውለው ረመዳን በኢትዮጵያ እና በሌላው የዓለም ክፍል ብቻ ሳይሆን በእስልምና ቅዱስ በሆነው የመካ ከተማም እንደቀደመው ተሰብስቦ መስገድ ቀርቶ ወደ ሳዑዲ አረቢያ መግባትም ክልክል ነበር። ዓለም ከኮሮናቫይረስ ጋር የተሻለ ተላምዳ እና ከትባቱም በመላው ዓለም መዳረስ በጀመረበት ዓመት የረመዳን ወር ተጀምሯል። ድሬዳዋ ሸምሰዲን ባለፈው ዓመት ረመዳን በድሬዳዋ ከተማ ብቻ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ያክል ተዋጥቶ በከተማዋ ባሉ ቀበሌዎች በሙሉ ያሉ አቅመ ደካሞችን ማገዛቸው እንደሚያስደስተው ይናገራል። "ድሬዳዋ ከአንድ ቤት ሁለት ሦስት ልጅ በውጭ አገር የሌለው የለም። በውጭ ያሉትም በከተማ ካሉት ብዙ ገንዘብ ሰብስበን ድጋፍ አድርገን ነበር" ሲል ያስታውሳል። አክሎም በከተማዋ የኮሮናቫይረስ ያመጣው ድንጋጤ ከፍተኛ እንደነበር እና ይህም በተለይ በንግድ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ከፍተኛ ጫና አስከትሎ እንደነበርም ይገልጻል። ነገር ግን ያኔ መስጊዶቹ መዘጋቱ እና የነበረው ጥንቃቄ ዋጋ ቢስ አልነበረም የሚለው ሸምሰዲን፤ በዚህ ዓመት የኮሮናቫይረስ ከፍተኛ ስርጭት ላይ እንደሚገኝ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥንቃቄው መቀነሱ ያሳስበዋል። በመስጊዶች ውስጥ "ሰው ለራሱ ሲል እንዲጠነቀቅ ትምህርት እየተሰጠ ቢሆንም ቸልተኝነቱ ያሳስበኛል" ሲል ይናገራል። "በአሁኑ ዓመት እርዳታ የማሰባሰብ ተግባራት አምብዛም አይታዩም" የሚለው ሳላሃዲን፤ ምን አልባት ጾሙ ሲገባ እርዳታዎች (ዘካ) ይደረጋል ብሎ እንደሚጠብቅ ይናገራል። ነገር ግን አሁንም ወጣቶቹ እየተወያዩ እንደሚገኙ አና በተቻለ መጠን በዚህኛውም ረመዳን ድጋፎችን ለማጠናከር እና ወደ መስጊድ የሚመጡ ሰዎችን በማስተባባር ስርጭቱ እንዳይጨምር ለማድረግ ሥራ መጀመራቸውን ይናገራል። ከአንድ ዓመት በፊት የኮሮናቫይረስ ከፍተኛ ስርጭት አይሎባት የነበረችው ድሬዳዋ አሁን ላይ በመላው አገሪቱ የተስፋፋው ኮሮናቫይረስ በሁሉም ከተሞች ተስፋፍቶ ስጋቱን ከከተማዋ ጋር ሌሎችም እንዲጋሩት አድርጓል። አዲስ አበባ ልክ እንደ ሰላሃዲን ሁሉ ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ እርዳታ ሲያሰባስቡ ከነበሩ ወጣቶች መካከል ነው አዱኛው ሙጬ። ባለፈው ዓመት 10 ሺህ አባወራዎችን ለአንድ ወር የሚሆን ቀለብ በማሰባሰብ ካከፋፈሉት ወጣቶች አንዱ የሆነው አዱኛው በተያዘው ዓመት ይቀዝቅዝ እንጂ ድጋፉ አልቀረም ሲል ያስረዳል። በተያዘው ዓመትም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደቀጠሉ የሚናገረው አዱኛው፣ ከአንድ ሳምንት በፊት አፋር ክልል ሄደው ከነጃሺ በጎ አድራጎት ማኅበር ጋር ድጋፍ አድርገው መመለሳቸውን ይናገራል። ባለፈው ዓመት በአፋር ክልል በጎርፍ የተጎዱ ሰዎችን በዕለት ደራሽ ድጋፍ ሲያግዙ መቆየታቸውን ያስታውሳል። የረመዳን ጾምን አስመልክቶም ለ150 አርብቶ አደሮች መልሰው እንደቋቋሙ አምስት አምስት ፍየል ለግሰው መመለሳቸውን ያስረዳል። "ሁሌ ዱቄት ይዞ መሄድ ሳይሆን መልሶ ለማቋቋም ነው ፍየሎቹን የሰጠናቸው። በአንድ ኣመት አምስት ፍየል 15 ይሆናል ተብሎ ይታመናል፤ ይህም በዘላቂነት መልሰው እንዲቋቋሙ ያግዛል" ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። ነገር ግን እንዳለፈው ዓመት ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራውን ማስተባባር በተለይም የማኅበራዊ ሚዲያውን የያዙት አጀንዳዎች ትኩረት አለማግኘቱን ያስረዳል። ወጣቶቹም የማስተባባር ሥራውን ማካሄድ የሚችሉበት ሌሎች አማራጮች እንዳልነበሯቸውም ይገልጻል። አዱኛው ያለፈውን ዓመት ሲያስታውስም ምንም እንኳን ድጋፍን በማሰባሰብ እና መሰል ሥራዎች በመስጊድ ውስጥ ቢያሳልፍም ህዝበ ሙስሊሙ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን ሐዘን ያስታውሳል። "ብዙዎች መስጊድ ተዘግቶ ሲያዩ አልቅሰዋል፣ ረመዳን ታላቅ የሰደቃ ወቅት በመሆኑ ብዙ የተቸገሩ ሰዎች መስጊድ ደጅ ተቀምጠው የሚረዱበት ወር ነው። እነዚህ ሰዎች የዓመት ወጪ ጭምር የሚያገኙበት ወር ነው። በአጠቃላይ ለኔም በግሌ ከባዱ የረመዳን ወር ነበር" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። በ2013 ግን መስጊዶች ተከፍተው ረመዳን ጾም ተጀምሯል። ለአዱኛው ይህ መልካም ዜና ቢሆንም "ያለው መዘናጋት እጅግ ያሳስበኛል" ሲል ይነጋራል። በአዲስ አበባ ሰዎች ማስክ የሚያደርጉት ፖሊስ እንዳይቀጣቸው ብቻ ይመስላል የሚለው ወጣቱ፤ ከአዲስ አበባ ውጪ ሲንቀሳቀስ ደግሞ ማስክ የሚለብስ ሰው እንደውም ኮሮናቫይረስ ያለበት ተደርጎ እንደሚታሰብ ይናገራል። በመስጊድ ውስጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ምክንያት በሙስሊም መቃብር አካባቢ ያለውን ነገር እንደሚመለከት የሚያስረዳው አዱኛው ሁኔታውን አሳሳቢ ሲል ይገልጻል። "በቀን ሦስት አራት ሰው ኮሮና ነው እየተባለ በጥንቃቄ ሲቀበር አያለሁ" በማለት ይህ በረመዳን ጾም ወቅት የሚደረጉ የማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች በአግባቡ ካልተደረጉ "እልቂት እንዳያመጡ እሰጋለሁ ይላል። ታዲያ ከሐይማኖታዊ ስብስቦች ውጪም "መርካቶም፣ አውቶብስ ውስጥም ሆነ ሌላ ቦታም ጥንቃቄዎች ያለመኖራቸው በአጠቃላይ ገና ብዙ ማሻሻል ያስፈልጋል" ሲልም የግል ምልከታውን ያስቀምጣል። መውጫ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች አሁንም መስጊዶችን ጨምሮ የእምነት ቤቶች ተዘግተዋል አልያም በአነስተኛ ቁጥር ማኅበራዊ ርቀቶች ተጠብቀው ሐይማኖታዊ ሥርዓቶችን በመከወን ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ከኮሮናቫይረስ መከሰት በፊት ወደ ነበረው አገልገሎት ከገቡ ሰነባብተዋል። ብዙዎች ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ የመሳሰሉ ተግባራት ተረስተዋል ሲሉም ይደመጣል። ታዲያ የተያዘው የረመዳን ጾምን ተከትሎ የሚካሄዱ የጋራ ሐይምኖታዊ ክንውኖች በጥንቃቄ ካልተከወኑ ብዙዎችን ሊጎዳ እንደሚችል እነዚሁ ወጣቶች ይናገራሉ። "እኛ ወጣቶች የራሳችንን ሚና ተስፋ ሳንቆርጥ እንጫወታለን" የሚለው አዱኛው "አንድ ህይወት ማዳን ዓለምን ማዳን ነው፤ አንድ ነፍስ ማጥፋት ዓለምን ማጥፋት ነው" ሲል ቁርአንን በመጥቀስ የበጎ ፈቃድ ተግባራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ይናገራል። ይህም የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በረመዳን ወቅት ጥንቃቄዎች እንዲካሄዱ እየጣሩ እንደሆነ ይገልጻል። ያለፈው ዓመት የመስጊድ መዘጋት ትርጉሙ ትልቅ እንደሆነ እና ይህ በሽታ ሥጋዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ህይወታችንን እንዳይጎዳ ቀድመን እንድንጠነቀቅ ሊያሳስበን ይገባል ይላል። በተያዘው ዓመትም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማከፋፈል፣ ሰዎች ሲሰግዱ እንዲራራቁ እና እጅ መታጠብን ጨምሮ ማታ ማታ መስጊድ ላይ በማስተባባር ሕዝበ ሙስሊሙን በቫይረሱ እንዳይጎዳ ለማንቃት ማሰባቸውን ገለጿል። "እነዚህ ነገሮች ዋጋ እንዳያስከፍሉን እና እንደቅጠል እንዳንረግፍ የሐይማኖት አባቶች ከማንም በላይ ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው" የሚለው አዱኛው "ይሄ ግን ለእነሱ ብቻ የሚተው ሳይሆን እኛ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ደግሞ ማታ ማታ በቡድን በቡድን ሆነን እናስተባብራል" ሲል ለቢቢሲ ገልጿል።
xlsum_amharic-train-206
https://www.bbc.com/amharic/43800239
የሚበሉ ነፍሳት
ጣዕማቸው ምን ሊመስል ይችላል? ጥሩ ሊሆን ይችላል?
[ "ጣዕማቸው ምን ሊመስል ይችላል? ጥሩ ሊሆን ይችላል?" ]
ከአካባቢ ደህንነት አንፃር እንዲሁም ለእንስሳት ሥጋ እንደ አማራጭ ከመሆን አንፃር የነፍሳት ምግብ ተመራጭ ነው። ግን ማን ነው ነፍሳትን በምግብነት እየተጠቀመ ያለው? ዓለም በበርካታ ነፍሳት የተሞላች ነች። ብዙዎችም እነዚህን ነፍሳት ምግባቸው ያደርጋሉ። ይህን የሚያደርጉት ምግብ ተቸግረው ሳይሆን በጣዕሙ መርጠውት ነው። በሜክሲኮ በጣዕማቸው ተወዳጅ የሆኑ የነፍሳት አይነቶች አሉ። በተለይም ቀይ ትሎች ዋጋቸውም ውድ ነው። እነዚህ ቀይ ትሎች በጥሬ ሁሉ ለምግብነት ይውላሉ። የተለያዩ ነፍሳትን ለምግብነት ለማግኘት ነፍሳቱ ወደ ሚገኙበት የተለዩ ገበያዎች መሄድ ሊያስፈልግ ይችላል። አንዳንድ ነፍሳት በጣም ተፈላጊ ከመሆናቸው የተነሳ ነፍሳቱን ለማራባት የመሞከር ነገርም አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ነፍሳት ማራባት በጥብቅ የሚከለከልበት ሁኔታ አለ። ለምግብነት የሚውሉ አብዛኞቹ ነፍሳት እንዲሁ በቀላሉ የሚገኙ ናቸው። ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገራት ለምግብነት የሚውሉ ነፍሳትን በምሳሌነት ማንሳት ይቻላል። አብዛኛውን ጊዜ በዝናብ ወቅት የመጀመሪያው ዝናብ እንደጣለ ነፍሳት በብዛት ካሉበት ይወጣሉ ወይም ይፈለፈላሉ። በቀጣዩ ቀን መሬት ያለብሳሉ በሚባል ደረጃ ይበዛሉ። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ነፍሳት በብዛት የሚበሉት በገጠራማ አካባቢዎች ሲሆን በከተማ ደግሞ ገቢያ ላይ ይገኛሉ። ሳይንስ እንደሚለው አብዛኞቹ ነፍሳት ሙሉ በሙሉ ለምግብነት መዋል ይችላሉ። በዚህ ንፅፅር 40 በመቶ የሚሆኑ የከብቶች ሥጋ ግን ለምግብነት መዋል አይችልም። ለምግብነት መዋል የሚችሉ ሌሎች ነፍሳት ደግሞ በብዛት ዛፍ ላይ ይገኛሉ። ለምሳሌ በዝናብ ወቅት ወደ ቡርኪና ፋሶ ቢኬድ የዛፎች ስር በአባጨጓሬ ተሸፍኖ ይገኛል። በዚህ ወቅት ኗሪዎችም ንጋት ላይ ተነስተው ነፍሳቱን ይለቅማሉ። ነፍሳቱ የፍራፍሬ ያህል ጣም ያላቸው መሆናቸውንም ይናገራሉ። በዛፎች ግንድ ውስጥ የሚፈጠሩ ነፍሳትም አሉ። በዚህ መልኩ ከሚፈጠሩት የተወሰኑት በዲሞክራቲክ ኮንጎ በጣም የተለመዱ ናቸው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዛት ለምግብነት የሚውሉት ፌንጣና አምበጣና ናቸው። በእስያ ገበሬዎች የሩዝ እርሻ ላይ መረብ ወጥረው ለምግብነት የሚውሉ ነፍሳትን ይይዛሉ። በሜክሲኮም ከበቆሎ እርሻ በተመሳሳይ መልኩ ነፍሳትን ለመያዝ ይሞከራል። እንደ ሰብል ሁሉ ለምግብነት የሚውሉ ብዙ ነፍሳት የሚገኙት ወይም የሚፈጠሩት በተለያየ ወቅት ነው። ነፍሳቱ የሚገኙባቸውን ወቅት ተከትሎም የተለያዩ በአላት በተለያዩ አገራት ይካሄዳሉ። ለምሳሌ የጃፓኑን የተርብ፤ በቡርኪና ፋሶና በዲሞክራቲክ ኮንጎ የሚካሄደውን የአባጨጓሬ በአል መጥቀስ ይቻላል። በአሁኑ ወቅት ነፍሳትን በብዛት አምርቶ ለምግብነት የማዋል ፍላጎት ቢኖርም እዚያ ደረጃ ላይ አልተደረሰም። ነፍሳትን ለምግብነት የማዋሉ ነገር በብዛት እየታየ ያለው የምግብ አማራጭን ከማስፋት እንዲሁም ይዘትን ከማሻሻል አንፃር ነው። በሌላ በኩል ደግሞ አካባቢን ከብክለት ከመጠበቅ አንፃር ነው።
xlsum_amharic-train-207
https://www.bbc.com/amharic/news-50450022
ታይሮን ሚንግስ፡ ከመጠጥ ቀጅነት ወደ እንግሊዝ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን
መጠጥ ቀጅነት፤ ቤት አሻሻጭ፤ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን።
[ "መጠጥ ቀጅነት፤ ቤት አሻሻጭ፤ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን።" ]
ከ10 ዓመት በፊት ሳውዝሃምፕተኖች ቀጫጫ ነው በማለት ያሰናበቱት ወጣት ዛሬ [እሁድ ኅዳር 7] ደግሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ወክሎ ይጫወታል፤ ታይሮን ሚንግስ። ታድያ በእነዚህ 10 ዓመታት ብዙ አሳልፏል። ለጠጪዎች መጠጥ ቀድቷል። የ100 ፓውንድ መኪናውን እያሽከረከረ ሰዎች ከባንክ የቤት መሥሪያ ብድር እንዲወስዱ አስማምቷል። ኢፕስዊች ታውን ለተሰኘው ክለብ መጫወት ፈልጎ ሳይታመም አሞኞል ብሎ ከሥራ ቀርቷል በሚል ቅጣት ድርሶበታል። ከአየርላንድ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ጋር ቡጢ ቀረሽ ቁርሾ ነበረው። ጉዞ ወደ ኮሶቮ ሚንግስ አሁን ለሚጫወትበት አስቶን ቪላ የፈረመው በውሰት ከመጣበት ቦርንመዝ ነው። የ26 ዓመቱ ተከላካይ ዘንድሮ የተቀላቀለው ፕሪሚዬር ሊግ ብዙ የከበደው አይመስልም። 195 ሴንቲሜትር የሚረዝመው ተከላካዩ ሚንግስ በፕሪሚዬር ሊግ ብዙ ኳሶችን ከግብ ክልሉ በማራቅ [ክሊራንስ] ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የአካዳሚ ጓደኛው አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይን ነገሮች ተመቻችተውለት ታላላቅ ክለቦችን እየቀያየረ አሁን ሊቨርፑል ሲደርስ ሚንግስ ግን ብዙ ክለቦች አንፈልግህም እያሉ አባረውታል። ብሪስቶል ሮቨርስ አታዋጣንም ብለው ያባረሩት ሚንግስ ወደ ተማረበት ት/ቤት ተመልሶ መጫወት ጀመረ። በወቅቱ አንድ ባር ውስጥ መጠጥ ቀጅ ነበር። ቀን ቀን ደግሞ ለባንክ ቤት በኮሚሽን ተቀጥሮ የቤት ኪራይ ብድር ያስማማ ነበር። ታድያ በዚህ ጊዜ ያልተለየችው በደጉ ዘመን የሸመታት የ100 ፓውንድ [በአሁኑ ገበያ 3,700 ብር ገደማ] መኪናው ነች። ከዚያ ኢፕስዊች ታውን ለሙከራ ጊዜ ብሎ ወሰደው። ነገር ግን የወቅቱ የቡድኑ አሠልጣኝ ከነበሩት ሚክ ማካርቲ ጋር ሊስማማ አልቻለም። ቢሆንም ችሎታውን ያስተዋሉት አሠልጣኝ ለ18 ወራት አስፈረሙት። ይህ የሆነው ከዛሬ ስድስት ዓመታት በፊት ነበር። ፊርማውን ካኖረ ከስድስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢፕስዊች ተሰለፈ። ከዚያ በኋላ ባሉት 18 ጨዋታዎችም ይህን ያህል የመሰለፍ ዕድል አላገኘም። የወቅቱ የክለብ ጓደኞቹ 'ለምን አልተሰልፍኩም?' ብሎ ከአሠልጣኞች ጋር ይጋጭ ነበር ይሉታል። 2015 ላይ ለቦርንመዝ ፈረመ፤ በ8 ሚሊዮን ፓውንድ። ነገር ግን የመጀመሪያ ጨዋታውን ለማድረግ በገባ በ6 ደቂቃ ውስጥ ተጎድቶ ወጣ። ለ17 ወራትም ምንም ዓይነት ጨዋታ ማድረግ አልቻለም ነበር። ይሄኔ ነው ቦርንመዝ ለአስቶን ቪላ አሳልፈው በውሰት የሰጠው። ቪላ ፕሪሚዬር ሊጉን እንዲቀላቀል ሚንግስ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ክለቡ በቋሚነት እንዲያስፈርመውም ሆነ። ሚንግስ ለአንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን መጫወት እንደሚፈልግ እና ህልሙ እውን እንደሚሆንም በዙሪያው ላሉ ሰዎች ይነግራቸው ነበር። እነሆ ህልሙ እውን ሆኖ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተመርጧል። እንግሊዝ ዛሬ ምሽት ከኮሶቮ ጋር በምታደርገው ጨዋታም ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል። አልፈልግህም ያለው ሳውዝሃምፕተን በዚህ ዓመት በጣም ብዙ ጎል ተቆጥሮበታል። በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ 19ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት። ብዙዎች እንደው ሳውዝሃምፕተኖች ታይሮን ሚንግስን ቀጫጫ ነው ብለው ማሰናበታቸው ይቆጫቸው ይሆን? ሲሉ ይጠየቃሉ። ሚንግስ ግን ምንም ዓይነት ቁጭትም ቂምም የለበትም።
xlsum_amharic-train-208
https://www.bbc.com/amharic/news-53973611
ፍርድ ቤት የአቶ ልደቱን መዝገብ ቢዘጋም አሁንም እስር ላይ ናቸው
ሁከት በማስተባበርና በመደገፍ ተጠርጥረው በፖሊስ ተይዘው የቆዩትን የአቶ ልደቱ አያሌውን ጉዳይ ሲመለከት የነበረው ፍርድ ቤት ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የምርመራ መዝገቡን ቢዘጋውም እስር ላይ መሆናቸውን የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለቢቢሲ ገለጹ።
[ "ሁከት በማስተባበርና በመደገፍ ተጠርጥረው በፖሊስ ተይዘው የቆዩትን የአቶ ልደቱ አያሌውን ጉዳይ ሲመለከት የነበረው ፍርድ ቤት ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የምርመራ መዝገቡን ቢዘጋውም እስር ላይ መሆናቸውን የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለቢቢሲ ገለጹ።" ]
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ ጠዋት ነበር በቀጠሯቸው ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የቀረቡት። በዛሬው ችሎት አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ፖሊስ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን ገልጾ ዐቃቤ ህግ ክስ እስከመሰርት ድረስ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ የፖሊስን ጥያቄ የህግ አግባብነት እንደሌለው ጠቅሶ ሳይቀበለው መቅረቱን አቶ አዳነ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ፍርድ ቤቱ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ መዘጋቱን ገልጾ አቶ ልደቱ አያሌው በሌላ መዝገብ የዋስትና ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ ማዘዙን ጠቅሰዋል። አቶ አዳነ እንዳሉት፤ ችሎቱ ፖሊስ እስካሁን አለኝ ያለውን የምርመራ ውጤትን ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ የቀረበው ማስረጃ አቶ ልደቱን አያስከስስም ብሎ መዝገቡን ዘግቷል ብለዋል። ችሎቱ አቶ ልደቱን የሚያስከስስ ማስረጃ አለማገኘቱን ገልጾ ጉዳዩን ቢቋጨውም፣ አቶ ልደቱ እስካሁን [እስከ ዛሬ ቀትር ድረስ] እንዳልተለቀቁ ተናግረው፤ ስለዚህም አባላቸው ከእስር እንዲወጡ ነገ ሁለት ማመልከቻዎችን ሊያስገቡ እንዳሰቡ አቶ አዳነ አክለዋል። "አንደኛው የዋስ መብት የሚጠየቅበት ማመልከቻ ነው። ሌላኛው ደግሞ አካልን ነጻ የማውጣት ክስም እንመሰርታለን” ብለዋል። አቶ ልደቱ በፍርደ ቤት ነፃ ከተባሉ በኋላ ለምን ከእስር እንደማይለቀቁ ጠይቀው፤ ከፍርድ ቤት እንዲሁም ከፖሊስ ያገኙት ምላሽ፤ “አሠራራችን ነው። የዋስትና ማመልከቻ አስገቡ” መባላቸውንም አቶ አዳነ ለቢቢሲ አስረድተዋል። "የፍትሕ ሥርዓቱ የምናውቀው ስለሆነ ነገ ከነገ ወዲያ ምን እንደሚከሰት አናውቅም። በፍርድ ቤት ይህ አይነት ውሳኔ ቢወሰንም ፖሊስ አልለቀቃቸውም። የዋስትና ማመልከቻ ካልቀረበ እንደማይለቃቸውም ገልጿል። ይሄ አስፈጻሚው ከፍርድ ቤት የበለጠ ጡንቻ እንዳለው ያሳያል” ብለዋል የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ። የልብ ህመም ያለባቸው አቶ ልደቱ "ደህና ነኝ ልል አልችልም። እርግጠኛ የሚሆነው ቀዶ ሕክምና ያደረግኩበትን ዓመታዊ ክትትል ሳደርግ ነው" ብለው ስለ ጤና ሁኔታቸው እንደነገሯቸውም አያይዘው ገልጸዋል። አቶ ልደቱ ከአንድ ወር በፊት በፌደራል ፖሊስ ተይዘው ለኦሮሚያ ፖሊስ ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ መኖሪያ ቤታቸው በሚገኝበት የቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ በእስር ላይ ይገኛሉ። አቶ ልደቱ ለእስር የተዳረጉት ከሁለት ወራት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ የተከሰተውን የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተከሰተው ሁከት ጋር በተያያዘ ቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ ሁከቱን በማነሳሳትና በመደገፍ ተጠርጥረው እንደተያዙ ተገልጾ ነበር።
xlsum_amharic-train-209
https://www.bbc.com/amharic/news-52913928
በኮሮናቫይረስ ሰበብ ትኩረት የተነፈጉት የዓለማችን ገዳይ ችግሮች
ጊኒ ውስጥ፤ የሁለት ዓመቱ ኤሚሊ ኦሞኑዎ ቤቱ አቅራቢያ የሚገኝ የተቦረቦረ ዛፍ ውስጥ ገብቶ መጫወት ያዘወትራል። ዛፉ የሌሊት ወፎች መኖሪያ ነው።
[ "ጊኒ ውስጥ፤ የሁለት ዓመቱ ኤሚሊ ኦሞኑዎ ቤቱ አቅራቢያ የሚገኝ የተቦረቦረ ዛፍ ውስጥ ገብቶ መጫወት ያዘወትራል። ዛፉ የሌሊት ወፎች መኖሪያ ነው።" ]
የአካባቢው ታዳጊዎች የሌሊት ወፎቹን ጠብሶ የመብላት ልማድ አዳብረው ነበር። ታዲያ አንድ ቀን ኤሚሊ በጠና ታመመ። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2013 ላይ እሱ ብቻ ሳይሆን እናቱ፣ እህቱና አያቱ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ተያዙ። ሕይወታቸውም ተቀጠፈ። ከቀብራቸው በኋላ በሽታው ይስፋፋ ጀመር። ይህ በተከሰተ በዓመቱ 49 ሰዎች በበሽታው ተይዘው፣ 29 ሰዎች ሞቱ። ተመራማሪዎች በሽታው ኢቦላ መሆኑን አረጋግጠዋል። በቀጣይ ሦስት ዓመታት በበሽታው ሳቢያ በዓለም ከ11,325 በላይ ሰዎች ሞተዋል። የወቅቱ የዓለም ጭንቅ ይህ በሽታ ብቻ አልነበረም። በሽታው የጤና ሥርዓትን አቃውሷል። ሠራተኞች ሞተዋል። ብዙ ሆስፒታሎች ተዘግተዋል። ክፍት የነበሩትም ከአቅማቸው በላይ ህሙማን እያስተናገዱ ነበር። በበሽታው ክፉኛ በተጠቁት ሴራሊዮን፣ ላይቤርያ እና ጊኒ ውስጥ ሰዎች ወደ ህክምና መስጫ መሄድ አቁመው ነበር። በሽታው አስፈርቷቸው ነበር። በሽታውን ብቻ ሳይሆን የጤና ባለሙያዎችንም ፈርተዋቸው ነበር። ባለሙያዎቹን ማንም ሊጠጋቸው አልደፈረም። 2017 ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳው፤ በወረርሽኙ ምክንያት ለህክምና ሙያ የሚሰጠው ዋጋ ቀንሷል። ሐኪም ቤት መውለድ የሚፈልጉ ነፍሰ ጡሮች ቁጥር 80 በመቶ ቀንሷል። ወባ የያዛቸው ልጆችን ወደ ሆስፒታል የሚወስዱ ቤተሰቦች ደግሞ 40 በመቶ አሽቆልቁሏል። ለክትባት ወደ ጤና ተቋም የሚሄድ ሰውም ዝቅ ብሎ ነበር። በዓለም አቀፍ ርብርብ ወረርሽኙ ቢገታም፤ ከበሽታው በላይ ጉዳት ያስከተሉት ከወረርሽኙ ጋር ተያይዘው የመጡ ችግሮች ነበሩ። ከዘንድሮው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞም መሰል ስጋት አለ። ሌሎች በሽታዎች ችላ መባል አገራት ኮቪድ-19ኝን መዋጋት ቅድሚያ እንደሚሰጠው ተናግረዋል። ለህሙማን አልጋ፣ ቬንትሌተርም ተዘጋጅቷል። በተለያየ ዘርፍ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ወረርሽኙን ወደመከላከል ተዘዋውረዋል። የሥነ ተዋልዶ ጤና፣ የአዕምሮ ጤና፣ ካንሰር እንዲሁም መደበኛ የህክምና ክትትሎችም ችላ ተብለዋል። በመላው ዓለም ያሉ የካንሰር ህሙማን፣ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው፣ አስቸኳይ ቀዶ ህክምና የሚሹ ሰዎችም ሰሚ አጥተናል እያሉ ነው። በባልካን አገራት ውስጥ አደገኛ በሆነ ቦታ ለማስወረድ የተገደዱ፣ በዩናይትድ ኪንግደም ደግሞ ለራሳቸው የጥርስ ህክምና ለመስጠት ከመሞከር ውጪ አማራጭ ያጡም አሉ። ለወባ ህክምና የሚውለው ሀይድሮክሎሮኪን በብዛት ያከማቹም አልታጡም። በተለይ በድሀ አገራት ከወረርሽኙ አኩል ኤችአይቪ፣ ቲቢና ወባ ያሰጋሉ። ሌላው ችግር በተገቢው ጊዜ ክትባት አለማግኘት ነው። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፤ ወረርሽኙ ቢያንስ የ68 አገሮችን የጤና ዘርፍ ስለሚያቃውስ፤ 80 ሚሊዮን ጨቅላዎች ክትባት ባለማግኘት ለኩፍኝ፣ ፖሊዮና ሌሎችም በሽታዎች ይጋለጣሉ። በብዙ ሚሊዮን ዶላር ወጪ የጠፋው ፖሊዮ ዳግመኛ ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋትም አለ። የዓለም አቀፉ የምግብ ተቋም ዋና ኃላፊ ዴቪድ ቢስሊ፤ ዓለም ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው አይነት ቸነፈር ይጠብቃታል። 130 ሚሊዮን ሰዎች ለዚህ ተጋላጭ ናቸው። አሁን ላይ 135 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል። በእንቅርት ላይ. . . እንዲሉ አገራት እንቅስቃሴ መገደባቸውም ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። የሚፈጠረው የምጣኔ ሀብት ቀውስ ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ አልያም ጠጪ እንዲሆኑም ሊገፋፋ ይችላል። የኮቪድ-19 ጉዳት ምን ያህል ጥልቅ ነው? የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲው የበሽታዎች ጥናት ባለሙያ የሆኑት ኢፒዲሞሎጂስቱ ቲሞቲ ሮበርተን ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ወረርሽኙ ስለሚያሳድረው ተጽዕኖ ተወያይተዋል። “በ2014 በምዕራብ አፍሪካ ኢቦላ ሲቀሰቀስ ምን እንደተፈጠረ ስላየን አሁንም ምን እንደሚከሰት አውቀናል” ይላሉ። ኮቪድ-19 ከሰሀራ በታች ባሉ ድሀ አገሮች በዋነኛነት በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚያሳድረው ጉዳት የነቲሞቲን ትኩረት አግኝቷል። ሁለት ጉልህ ነጥቦችም አስቀምጠዋል። አንደኛው በጤና ሥርዓት ላይ የሚፈጠረው ቀውስ ነው። “ሰዎች እርዳታ ለመጠየቅ ሊፈሩ ይችላሉ። በሌላ በኩል የጤና ባለሙያዎች ሊታመሙ፣ ሙሉ ትኩረታቸውን ወረርሽኙ ላይ ሊያደርጉ፣ የመድኃኒት እጥረት ሊገጥማቸውም ይችላል” ሲሉ ያስረዳሉ። ሁለተኛው ችግር በቂ ምግብ ባለማግኘት ለሌሎች ተላላፊ በሽታዎች መጋለጥ ነው። በተመራማሪዎች ትንበያ መሠረት፤ የጤና አገልግሎት የማግኘት እድል 50 በመቶ ሲቀንስ፤ ምግብ ማጣት ደግሞ በዚያው መጠን ይጨምራል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ልጆች፣ 56,700 እናቶች ሊሞቱ ይችላሉ። የልጆች ሞት ከሚከሰትባቸው ምክንያቶች መካከል ኒሞንያ [የሳንባ ምጭ] እና በተቅማጥ ሳቢያ የሚከሰት የፈሳሽ እጥረት ይጠቀሳሉ። ሴቶች ከእርግዝናና ወሊድ ጋር በተያያዙ ችግሮች ሕይወታቸው ሊያልፍም ይችላል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በየቀኑ ለ100 ሚሊዮን ሰዎች ምግብ እያደለ ሲሆን፤ ወደ 30 ሚሊዮን የሚጠጉት ሕይወታቸው የተመረኮዘው በዚህ እርዳታ ላይ ነው። በተቋሙ አሃዝ መሠረት፤ እርዳታው ከተቋረጠ፤ በቀጣይ ወራት በየቀኑ 300 ሺህ ሰዎች በረሀብ ሊሞቱ ይችላሉ። የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጄን ሀዋርድ እንደምትለው፤ በመላው ዓለም የተራቡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ተችሎ ነበር። ባለፉት አምስት ዓመታት በግጭትና በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ይህ ለውጥ ተቀልብሷል። “ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት ክፉኛ ለረሀብ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ አስደንግጦን ነበር” ትላለች። ወረርሽኙ 130 ሚሊዮን ሰዎችን ብቻ አይደለም ምግብ የሚያሳጣው። ድርጅቱ እርዳታ እንዳይሰበስብም እንቅፋት ይሆናል። ጄን እንደምትለው፤ የምግብ እጥረት የከተማ ነዋሪዎችም ችግር ነው። የከተማ ነዋሪዎች ደግሞ በዋነኛነት በወረርሽኙ ይጠቃሉ። “ገጠር የአትክልት እርሻ፣ ወይም ላም ያላት አክስት ያለው ሰው አለ። በመጠኑም ቢሆን ድጋፍ ይገኛል። ከተማ ውስጥ ግን ከመደብር ውጪ መሄጃ የለም” ስትል ታስረዳለች። የጉልበት ሠራተኞች፣ የግንባታ ሠራተኞችና ሹፌሮች ደግሞ በቀዳሚነት ተጋላጭ ናቸው። የጡት ካንሰር ምርመራ ከቫይረሱ በላይ ምን ይገድላል? ኮቪድ-19 አረጋውያንን በይበልጥ ይጎዳል። ከኒው ዮርክ በተገኘ መረጃ መሠረት፤ 75 እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው ሰዎች ከ811 ጊዜ በላይ በወረርሽኙ ሞተዋል። ይህም ወደ 17 ዓመት ገደማ ካሉ ወጣቶች ጋር ሲነጻጸሩ ነው። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች አብዛኛው ዜጎቻቸው ወጣቶች ናቸው። ለምሳሌ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ኒጀር የሕዝቡ አማካይ እድሜ 15.2 ነው። በበሽታው እስካሁን የሞቱት 254 ሰዎች ናቸው። በተቃራኒው በጣልያን አማካይ እድሜ 45 ነው። በበሽታው የሞቱ ሰዎች 33,000 ደርሰዋል። በእርግጥ ከሞቱት ሰዎች መካከል ምን ያህሉ በወርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸውን አጡ? የሚለው አከራካሪ ነው። ምክንያቱም አረጋውያን የሚጋለጡት ለኮቪድ-19 ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ወቅት ጠብቀው ለሚመጡ የመተንፈሻ አካላት ህመሞችም ነው። በኮሮናቫይረስ በቀጥታ ባይሞቱም በተዘዋዋሪ ለህልፈት የሚጋለጡት ያደጉ አገራት ነዋሪዎች ጭምርም ናቸው። ለምሳሌ ካንሰርን ለመከላከልና ለማከም የሚደረገው ጥረት ቀንሷል። በዩናይትድ ኪንግደም የካንሰር ማዕከል ዳይሬክተር ሣራ ሂሎም፤ “ካንሰር ጊዜ አይሰጥም። በሽታው ቶሎ ከተገኘ ለማከምም ይቀላል” ይላሉ። ሆኖም ግን አገሪቱ እንቅስቃሴን ስትገታ የካንሰር ምርመራ ቆሟል። ያ ማለት ደግሞ ቀድሞ በየወሩ ይገኙ የነበሩት 1,600 የካንሰር ህሙማን አሁን ግን በሽታቸው አይታወቅላቸውም ማለት ነው። ህሙማን ከቤታቸው እየወጡ ስላልሆነ መደበኛ ምርመራ ማቆማቸው ሌላው ስጋት ነው። አንድ የካንሰር ሐኪም እንደሚሉት፤ ሕክምና በመጓተቱ ሳቢያ በዩናይትድ ኪንግደም ብቻ ወደ 60 ሺህ ሰዎች ይሞታሉ። ሌላው የዚህ ወረርሽኝ ጉዳት የሚያስከትለው የምጣኔ ሀብት መላሸቅ ነው። ለዚህም ጀርመንን መጥቀስ ይቻላል። በዋናነት ድጎማ ላይ የሚመሠረቱ የካንሰር ጥናቶች አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውም አይቀሬ ነው። ሣራ፤ የካንሰር ምርመራና ሕክምና በአፋጣኝ መጀመር አለበት ትላለች። የዓለም ምግብ ፕሮግራሟ ጄን ደግሞ አገራት ለዜጎቻቸው የአደጋ ጊዜ መዘጋጃ የሚያደርጉበትን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ትናገራለች። አንደኛው መንገድ ትምህርት ቤቶች ቢዘጉም ታዳጊዎችን መመገብ መቀጠል ነው። የንግድ ሰንሰለት እንዳይበጣጠስ ጥረት መደረግ እንዳለበትም ትመክራለች።
xlsum_amharic-train-210
https://www.bbc.com/amharic/news-55677506
ትግራይ ፡ የመብራትና የስልክ አገልግሎት መቼ ይጀምራል?
በትግራይ ክልል መብራት፣ ስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት እስካሁን መልሶ ሥራ ባልጀመረባቸው አካባቢዎች ውስጥ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ አብዛኞቹ አገልግሎቶቹን እንደሚያገኙ የመብራት ኃይልና የኢትዮቴሌኮም ኃላፊዎች ለቢቢሲ ገለፁ።
[ "በትግራይ ክልል መብራት፣ ስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት እስካሁን መልሶ ሥራ ባልጀመረባቸው አካባቢዎች ውስጥ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ አብዛኞቹ አገልግሎቶቹን እንደሚያገኙ የመብራት ኃይልና የኢትዮቴሌኮም ኃላፊዎች ለቢቢሲ ገለፁ።" ]
ከሁለት ወራት በፊት በክልሉ በተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ተቋርጠው የነበሩት የመብራት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በከፊል የተመለሱባቸው አካባቢዎች ቢኖሩም፤ በበርካታ ከተሞች ውስጥ እስካሁን አለመመለሳቸውን ኃላፊዎቹ ተናግረዋል። አገልግሎቶቹን መልሶ በቶሎ ለማስጀመር ያልተቻለው በመሠረተ ልማቶቹ ላይ "የደረሰው ውድመት በጣም ከፍተኛ" የሚባል በመሆኑ እንደሆነ አስረድተዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያዎች መስመሮች በመቆረጣቸውና ኢንሱሌተሮች [የኃይል ተሸካሚዎቹ እንዳይነካኩ የሚያደርጉ ስኒዎች] በመሰባበራቸው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የኤሌትሪክ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል። የስልክና ኢንተርኔት አቅርቦትን በተመለከተም የኢትዮቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩም በክልሉ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ላይ የደረሱ ከፍተኛ ጉዳቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ አስካሁንም ጥገና እየተካሄደ መሆኑንና "ባለው ነባራዊ ሁኔታ እንደልብ ተንቀሳቅሶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥገናዎችን ማድረግ ያስቸጋሪ ስለነበር" በቶሎ ሥራ ማስጀመር አለመቻሉን ተናግረዋል። እየተጠናቀቀ ባለው ሳምንት በበርካታ አካካቢዎች ከፍተኛ የጥገና ሥራዎች ተከናውነዋል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ አገልግሎት ለመጀመር መደበኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መብራት የሚያስፈልግ ቢሆንም በአማራጭነት ግን ጄኔሬተርና የፀሐይ ኃይልን እየተጠቀሙ መሆኑን አስረድተዋል። ጥገና በተጠናቀቀባቸው አካባቢዎች አገልግሎት ለመስጠት ተቃርበናል ያሉት ኃላፊዋ፣ መቀለ የስልክና የብሮድ ባንድ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አመልክተው በዚህም ምክንያት የባንክ አገልግሎት በከተማዋ ማስጀመር መቻሉን ገልፀዋል። በተጨማሪም በማይጨው፣ ዳንሻና በሁመራ የስልክ አገለግሎት መጀመሩን አስታውሰዋል። ከአላማጣ ጀምሮ በሁመራ በኩል እስከ ሽሬ አካባቢዎች በነበሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን የሚናገሩት አቶ ሞገስ በበኩላቸው፣ በዚህ ምክንያት የተቋረጠውን የኃይል አቅርቦት ለመመለስ ከፍተኛ የሆነ መስመር የመጠገን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት የሚያስተዳድራቸው የስርጭት መስመሮች፣ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት "አገልግሎት በፍጥነት መስጠት እንዳይችሉ" በሚያደርግ ሁኔታ ጉዳትና ዘረፋ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ከፍተኛ የኃይል መስመሮችን እንዲሁም የስርጭት መስመሮቹን ጠግኖ ሥራ ለማስጀመር የጥገና ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ያስረዱት ዳይሬክተሩ፤ በአላማጣ፣ በማይጨው፣ በመሆኒ፣ በአሸጎዳ እና በመቀለ እና በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ ትንንሽ ከተሞች የኤሌትሪክ አገልግሎት አግኝተዋል ብለዋል። ነገር ግን እስካሁን አክሱም፣ አድዋ፣ ሽሬ፣ ሽራሮ እና ወልቃይት አካባቢዎች ባሉ መሠረተ ልማቶች ላይ "የደረሰው የጉዳት መጠን ከፍተኛ በመሆኑ" የኤሌትሪክ ኃይል አለማግኘታቸውን ተናግረዋል። ጥገናው ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች መካከል አክሱም፣ ሽሬ፣ አድዋ፣ አካባቢዎች የተወሰኑ ሥራዎች እንደሚቀር እና እርሱን ለማተናቀቅ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም "የተለየ ነገር የማይኖር ከሆነ በአጭር ቀናት ውስጥ፣ . . . በሳምንታት እድሜ ውስጥ" የአክሱምና የአድዋ አካባቢዎች ኃይል የሚያገኙበት ሁኔታ ይፈጠራል ሲሉ ገልፀው፣ ቀኑን ግን ከማስቀመጥ ተቆጥበዋል። የኢትዮቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በበኩላቸው የትግራይን ክልል የሚያገለግሉት ዋነኛው ማዕከላት (ኮር ሳይት) የሚገኙት መቀለና ሽሬ ውስጥ እንደሆነ አመልክተው፤ ከመቀሌ አቢይ አዲ ያለው ኦፕቲካል መስመር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር አስታውሰዋል። ይህንን ለመጠገን ረዥም ጊዜ መውሰዱን የተናገሩት ኃላፊዋ በአሁኑ ጊዜ 98 ኪሎ ሜትር ያህል የመስመር ጥገናው ተከናውኖ መጠናቀቁን ገልፀው፤ ሽሬ ላይ ያለውን ማዕከል (ኮር ሳይት) ሥራ ለማስጀመር ከአብይ አዲ ወደ ሽሬ ያለውን መስመር መጠገን እንደሚጠበቅ ጨምረው ተናግረዋል። ወደ አደዋ ባለው መስመር ላይ ደግሞ ጥገናው ቢካሄድም ውቅሮ በአንዳንድ አካባቢዎች ባሉ የቴሌኮም ማማዎች [ታወሮች] ላይ የሚገኙ እቃዎች በመዘረፋቸው እነዚህ እቃዎች የማሟላት ሥራን ማከናወናቸውን ጠቅሰዋል። ውቅሮ፣ አዲግራት፣ ነጃሺ አካባቢ በጣም አነስተኛ ሥራዎች ብቻ መቅረታቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልፀው በቅርቡ አገልግሎት ይጀምራሉ ብለዋል። አቶ ሞገስ መኮንን በበኩላቸው መሥሪያ ቤታቸው በክልሉ ያለው የኃይል አቅርቦትን ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ የሚካሄደው ጥገና በኃይል ተሸካሚዎችና በስርጭት መስመሮች ላይ በመሆኑ ሥራው ጎን ለጎን እየተገናኘ እንዲሄድ ማድረግ ካልተቻለ የአንዱ ሥራ መጠናቀቅ ብቻውን ለከተሞቹ የኃይል አቅርቦት ማግኘት ወሳኝ አለመሆኑን አስረድተዋል። በደኅንነት ስጋት ውስጥ ሆነው የሚሰሩ ባለሙያዎች የመስመር ጥገናው በሚካሄድባቸው አካባቢዎች አሁንም ጥቃት ፈጽመው የሚሸሹ ቡድኖች መኖራቸውን የገለፁት ኃላፊዎቹ፣ እስካሁን በድርጅቱ ሠራተኞች ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም እንደዚህ አይነት ክስተቶች ሥራቸውን እንደሚያስተጓጉሉ ጨምረው ገልፀዋል። በተጨማሪም የእንቅስቃሴ ገደብ መኖሩ፣ በመሠረተ ልምቶቹ ላይ የደረሱት ውድመቶች ከፍተኛ የሚባሉ መሆናቸው ተደማምረው አሁን የሚያከነውኑትን ጥገና ከባድ እንዳደረገውና ለነዋሪው በፍጥነት የኤሌትሪክ እና የስልክ አገልግሎቶችን ማቅረብ እንዳይችሉ ማድረጉን ተናግረዋል። ሥራው "ኃላፊነት እና አደጋ ያለበት" ያሉት አቶ ሞገስ፣ በተረጋጉት አካባቢዎች ሥራዎች ቢጠናቀቁም አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ መስተጓጎሎች ደግሞ ሥራው መቼ ተጠናቅቆ አገልግሎት ማቅረብ እንደሚቻል ቁርጥ ያለ ቀን ለማስቀመጥ አስቸጋሪ ማድረጉን ተናግረዋል። አሁንም የጥገና ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለፁት አቶ ሞገስ ከመቀለ ተነስቶ ወደ አክሱምና አደዋ በየዕለቱ በመሄድ ባለሙያዎቻቸው በአስቸጋሪ የመልከ አምድር አቀማመጥ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል። የቴሌኮም አገልግሎትን መልሶ ለማስጀመር የሚደረገውን ጥረት በተመለከተ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወትም ሲናገሩ በአካባቢው የቴሌኮም መስመሮች ላይ "ከፍተኛ ጉዳት ነው የደረሰው፣ በርካታ እቃዎች ጎድለዋል ተዘዋውሮ ለመስራት የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ አመቺ አይደለም" በማለት እስካሁን ግን ከፍተኛ ሥራዎችን መከናወናቸውን ገልጸዋል። ባለሙያዎቻቸው በክልሉ ያለውን አገልግሎት ለማስጀመር ቀን ተሌት እየሰሩ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊዋ፣ ጥገና የተደረገባቸውና አስፈላጊ ነገሮች የተሟሉላቸው አካባቢዎች ሥራው እንደተጠናቀቀ የተወሰኑ ቦታዎች አገልግሎት ይጀምራሉ ብለዋል። ጨምረውም እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ የተወሰኑ ስፍራዎችን ፈጥኖ ለማስጀመር እየሰሩ መሆኑን ገልፀው፣ በርካታ ስፍራዎች በወር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ብለዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ሪጅን ቅርንጫፍ 746 ሠራተኞች ያሉት ሲሆን እስካሁን ድረስ 699 ሠራተኞቹ ወደ ሥራ ገበታቸው መመለሳቸውን ኃላፊዋ አስታውሰዋል። የደረሰው የጉዳት መጠን ይታወቃል? አቶ ሞገስ ስለደረሱት ጉዳቶች ለቢቢሲ ሲያስረዱ ከአላማጣ ወደ ማይጨው፣ መሆኒ፣ መቀለ እንዲሁም ከአሸጎዳ ወደ አክሱም እና ሌሎች የክልሉ ከተሞች የሚሄዱት አብዛኞቹ የ230 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ መስመሮች መሆናቸውን ይናገራሉ። እነዚህ መስመሮች በዋናነት 230 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ ቢሆኑም ክልሉ ላይ የተለያዩ አካባቢዎችን የሚያዳርሱ 11 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ገቢና ወጪ መስመሮች አሉ። ከኃይል ማከፋፈያዎቹ ውጪ የድርጅቱ ሠራተኞች ተዘዋውረው በተመለከቷቸው መስመሮች ላይ "ከፍተኛ ጉዳት" መድረሱን አቶ ሞገስ ገልፀዋል። መስመሮቹ በተለያየ ስፍራ የተለያየ የጉዳት መጠን ስለደረሰባቸው፣ የደረሰውን የጉዳት መጠንን አስልቶ ለመናገር እንደሚያስቸግር ገልፀው "የጉዳቱ መጠን ግን ከፍተኛ ነው" ሲሉ ገልፀውታል። ሁሉም ውድመት የደረሰባቸው አካባቢዎች ለጥገና አለመድረሳቸውን በመግለጽም በገንዘብ የደረሰው ኪሳራ መጠንን እንዲሁም ለጥገና ያስወጣውን አጠቃላይ ወጪ አሁን ለመናገር እንደሚያስቸግራቸው ተናግረዋል። በትግራይ ክልል ጥቅምት መጨረሻ ላይ የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የኤልክትሪክ ኃይልና የቴሌኮም አገልግሎቶች ተቋርጠው ቆይተዋል። ምንም እንኳን የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ ከተቆጣጠረ በኋላ በመቀሌና በአንዳንድ አካባቢዎች ግን አሁን ድረስ አገልግሎቶቹ እንደተቋረጡ መሆናቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የኤልክትሪክና የስልክ አገልግሎቶችን በመላው አገሪቱ የሚያቀርቡት ሁለቱ ተቋማትም በክልሉ ውስጥ አገልግሎታቸውን መልሰው ለማስጀመር እጣሩ መሆናቸውን እየገለጹ ነው።
xlsum_amharic-train-211
https://www.bbc.com/amharic/news-53041157
በሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ የተሳተፉ ሴቶች የተዘነጋ ታሪክ
በአሰቃቂው የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደ ቅጠል ረግፈዋል። በርካቶች ተደፍረዋል፣ አካል ጉዳተኛ ሆነዋል።
[ "በአሰቃቂው የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደ ቅጠል ረግፈዋል። በርካቶች ተደፍረዋል፣ አካል ጉዳተኛ ሆነዋል።" ]
ፎርቹኔት ሙካንኩራንጋቨ የማያቋርጥ ዋይታ፣ ለቅሶ የተሰሙባቸው መራር መቶ ቀናት። የዘር እልቂቱ ሁለት አስርት ዓመታትን ቢያስቆጥርም ከመራር ሃዘን ጋር ለመኖር የተገደዱ፣ ከማይሽር ጠባሳ ጋር እየተጋፈጡ የሚኖሩ ጥቂት አይደሉም። ያው ህይወት መቀጠል አለባት። ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት በሩዋንዳው የዘር እልቂት ተሳትፈዋል የሚባሉት ታዋቂ ስሞች በተደጋጋሚ ይነሳሉ። ብዙዎቹም ወንዶች ናቸው። ከእልቂቱ ጀርባ ግን በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ቢሳተፉም ታሪክ ዘንግቷቸዋል። ጋዜጠኛዋ ናታሊያ ኦጄውስካ በጭፍጨፋው ተሳታፊ ከነበሩት መካከል በእስር ላይ የሚገኙትን የተወሰኑትን አናግራቸዋለች። ቀኑ ምንም የተለየ ነገር አልነበረውም። ፎርቹኔት ሙካንኩራንጋ ሌላ ጊዜ እንደምታደርገው ከቤቷ የወጣችው ቁርስ ለማዘጋጀት በሚል ውሃ ልትቀዳ ነበር። ነገር ግን በዚያኑ ዕለት ውሃ ብቻ አይደለም የቀዳችው፤ የሰው ህይወትም ነበር ያጠፋችው። እንዴት? የእስር ቤቱን ብርቱካናማ ቀለም ያለው መለያ ልብስ ለብሳ፣ ረጋ ባለ ድምጿ ከሃያ ስድስት ዓመት በፊት የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ታስታውሰዋለች። ጊዜው ሚያዝያ 2/1986 ዓ.ም (በጎርጎሳውያኑ ሚያዝያ 10/1994)፤ እለቱም እሁድ ነበር። ቁርስ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጋትን ውሃ ልትቀዳ ከቤቷ ወጣች። በመንገዷ ላይም በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ሁለት ወንዶችን ክፉኛ ሲደበድቧቸው አየች። በጥላቻ የተሞላ ጊዜ፤ ርህራሄም ሆነ ሃዘን በመጀመሪያ አልተሰማትም። "ግለሰቦቹ ድብደባው ሲበዛባቸው መሬት ላይ ተዝለፍልፈው ሲወድቁ እንጨት አነሳሁና ቱትሲዎች መሞት አለባቸው እያልኩ አብሬ መደብደብ ጀመርኩ . . . ሰዎቹ በድብደባውም ሞቱ። ከገዳዮቻቸውም መካከል አንዷ እኔ ነኝ" ትላለች የ70 ዓመቷ እስረኛ። የሞቱት ድምፅ ይጣራል እነዚህ በጭካኔ መንገድ ላይ የተገደሉት ሁለቱ ሰዎች በመቶ ቀናት ውስጥ ከተገደሉት 800 ሺህ ቱትሲዎችና፣ ለዘብተኛ ከተባሉ ሁቱዎች መካከል ናቸው። ከሁቱ ጎሳ የሆነችው ፎርቹኔት በግድያው ከተሳተፈች በኋላ ለሰባት ልጆቿ ቁርስ ልትሰራ ወደቤቷ፣ ወደኑሮዋ ተመለሰች። ወደ ቤቷ ስትመለስ ግን ሌላ ሰው ሆና ነው የተመለሰችው። ቤት ስትደርስ ተሸማቀቀች። ውስጧ ተፀፀተ። የተገደሉት ሁለት ሰዎች ተማፅኖ፣ አሰቃቂ ድብደባም ፊቷ ላይ ድቅን ይልባታል። እረፍትም ነሳት። "እናት ነኝ። የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ" ብላለች። ከጥቂት ቀናትም በኋላ ወላጆቻቸው በቆንጨራ የተገደሉባቸው ሁለት የቱትሲ ህፃናት እየተንቀጠቀጡ ቤቷ መጡ። የሚደበቁበት የጠፋቸው፤ የሚሄዱበት የጨነቃቸው ልጆች መጠለያን ፈልገው ነበር ደጃፏ የደረሱት። ከምትጠላው ጎሳ ቢሆኑም የእናትነት አንጀቷ አላስቻላትም። አስገብታ ደበቀቻቸው። ከጭፍጨፋውም ሊተርፉ ቻሉ። "ሁለቱን ልጆች ባድናቸውም በሁለት ሰዎች ግድያ ተሳትፌያለሁ። ምንም ቢሆን ካደረስኩት ጥፋት ነፃ ሊያወጣኝ አይችልም" ብላለች ፎርቹኔት። በዘር ጭፍጨፋው ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል ክስ ከተመሰረተባቸው 96 ሺህ ሴቶች መካከል ፎርቹኔት አንዷ ናት። እንደ ፎርቹኔት በርካታ ሰዎችን በመግደል እስር ቤት የገቡ እንዳሉ፤ ብዙዎችም ቱትሲ ሴት ህፃናትን ጨፍጭፈዋል እንዲሁም ቱትሲ ሴቶች እንዲደፈሩ ተባብረዋል። ከምሽቱ ሚያዝያ 2/ 1986 ዓ.ም በጊዜው ፕሬዚዳንት የነበሩት ጁቬናል ሃብያሪማና ተሳፍረውበት የነበረው አውሮፕላን መዲናዋ ኪጋሊ በሚገኘው አየር ማረፊያ አካባቢ ተመትቶ ወደቀ። ከሁቱ ጎሳ የሆኑት ፕሬዚዳንት ጁቬናልም ህይወታቸው አለፈ። ፕሬዚዳንቱን የገደላቸው ማን እንደሆነ ባይታወቅም የሁቱ ፅንፈኞች ግን የቱትሲ አማፂ ቡድን ነው ጥቃቱን የፈፀመው በሚል ወሬ መንዛት ጀመሩ። ምንም እንኳን ይሄ የፕሬዚዳንቱ ሞት የቅርብ መንስኤ ቢሆንም ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲዘራ የነበረው የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ፍሬ አፍርቶ ለበርካታ ቱትሲዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነ። ደም የጠማቸው በጥላቻ የናወዙ ጽንፈኛ ሁቱዎች ተደራጅተው ወጡ፤ ያገኙትንም በአሰቃቂ ሁኔታም ጨፈጨፉ። ምንም እንኳን በዚህ ጭፍጨፋ ላይ ብዙ ጊዜ ስማቸው የሚነሳው ወንዶች ቢሆኑም በርካታ ሴቶች ተሳትፈዋል። ልክ እንደ ሌሎቹ አገራት በሩዋንዳም ሴቶች እንደ አዛኝ፣ ጠባቂና ርህራሄ የተሞሉ ናቸው ተብለው የተሳሉ ከመሆናቸው አንፃር ሴቶች በግድያዎቹ ተሳትፈዋል የሚለው በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ፎርቹኔት ትናገራለች። "ልጆቿን የምትወድ እናት እንዴት የጎረቤቶቿን ልጆች ትገድላለች የሚለውን እሳቤ መቀበል አስቸጋሪ ነው" በማለት የምትናገረው በሰላምና እርቅ ላይ የሚሰራ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሠራተኛዋ ሬጂን አባንዩዙ ናት። ጭፍጨፋዎቹ ከተቀጣጠሉ በኋላ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሴቶቸ ከወንዶች ጋር አብረው ተሳትፈዋል። በእስር ቤት የሚገኙ ታራሚዎች ፓውሊን ኒይራማሹኮ በወቅቱ የቤተሰብ ደኅንነትና የሴቶች ልማት ሚኒስትር ነበሩ። በወንድ ፖለቲከኞች ተሞልቶ በነበረው የሩዋንዳ መንግሥት ውስጥ የመሪነት ቦታን ከተቆናጠጡ ሚኒስትሮች መካከል አንዷ ናቸው። በዘር እልቂቱም ከፍተኛ ሚናን እንደተጫወቱ ይነገርላቸዋል። በጎርጎሳውያኑ 2011ም የሩዋንዳን ጭፍጨፋ ሲያይ የነበረው የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤትም ጥፋተኛ ብሏቸዋል። በታሪክም ውስጥ በሰብአዊነት ላይ በሚፈፀም ወንጀል በመድፈር የተከሰሱ ብቸኛዋ ሴት ናቸው። የቀድሞ ሚኒስትሯ ቡታሬ በተሰኘ የመንግሥት ቢሮ ውስጥ የቱትሲ ሴቶች በታጣቂዎች እንዲደፈሩ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ተብሏል። ሚኒስትሯ በኃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው ትዕዛዝ በማስተላለፍ ሲሳተፉ በርካቶች ደግሞ ባገኙት መሳሪያ ጎረቤቶቻቸውን ከመጨፍጨፍ ወደ ኋላ አላሉም። ከሩዋንዳ እርቅ ጋር ተያይዞ በእልቂቱ እጃቸው ያለበት ወንዶች በተሃድሶ ፕሮግራም ቢሳተፉም ሴቶች በማኅበረሰቡ በሚሰጣቸው ሚና ከእርቅ ፕሮግራሞቹ ተገለዋል፤ እንዲሁም ተገፍተዋል። ማርታ ሙካሙሺንዚማና የጭፍጨፋው ሁለት ወግ የአምስት ልጆች እናት ማርታ ሙካሙሺንዚማና ለአስራ አምስት ዓመታት ያህል ወንጀሏን ደብቃ ነበር። ሸክሙን ጫንቃዋ መቻል ሲከብደው፣ ከህሊናዋ ጋር መኖር ሲያዳግታት በእራሷ ጊዜ ወንጀሏን ለመናዘዝ ወሰነች። በርካቶቹ ካላቸው የእናትነት ሚናም ጋር ተያይዞ በጭፍጨፋዎቹ ላይ መሳተፋቸውን ለቅርብ ወዳጅ ዘመዶች ለመንገርም ያሳፍራቸዋል። ልጆች ያሏት እናት እንዴት ልጆችን ትገላለች? "በጊዜ ሂደት ብዙ ህመሞች ያገግማሉ። የተሃድሶውም ዋነኛ ትኩረት ጊዜን መስጠት ነው። የተቻለውን ያህል ጊዜ እንሰጣቸዋለን፤ እናደምጣቸዋለን። በራሳቸው ጊዜም የፈጸሙትን ጥፋት እንዲናዘዙ እናደርጋቸዋለን" ይላሉ ንጎማ የተባለው የሴቶች ማረሚያ ቤት ዳይሬክተር ግሬስ ንዳዋንይ። "ቤቴ መንገድ ዳር ነበር። ፉጭት ይሰማኛል፤ እሱንም ተከትሎ በርካታ ጎረቤቴ የሆኑ ቱትሲዎችም ወደ ቤተክርስቲያን ሲወሰዱ ትዝ ይለኛል" ትላለች ፓውሊን ሳግ በሚቆራርጠው ድምጿ። በሺህዎች የሚቆጠሩ ቱትሲዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ ለሳምንት ያህልም ተደብቀው ነበር። የሃምሳ ሦስት ዓመቱ ስታኒስለስ ካይቴራ በህይወት ከተረፉት እድለኞች መካከል አንዱ ነው። በክርኑ ላይ የሚታየው ትልቅ ጠባሳ ያንን የጨለማ ጊዜ ማስታወሻ ነው። ቦምቡ ባያገኘውም፤ ፍንጣሪው አቁስሎታል። "ሴቶቹ ድንጋይ ለወንዶች ሲያቀብሉ ትዝ ይለኛል። ወንዶቹም ድንጋይ እየወረወሩብን ነበር። ከዚያም አለፍ ሲል ወንዶቹ ሽጉጥ ይተኩሳሉ፤ ቦምብ ይወረውራሉ። በእሳትም ለማቃጠል ሞክረዋል" ይላል ። "ቤተ ክርስቲያኑንም በርግደው ገብተው በቆንጨራ ጨፈጨፉን" የሚለው ስታኒስለስ የተረፈውም ከተደራረቡ አስከሬኖች በታች ሆኖ ነው፤ የሞተ መስሏቸው ዳነ። ፓውሊን አሁን ብትፀፀትም በወቅቱ ግን "ትዕዛዝ ተቀባይ ነበርኩ" ትላለች። "ልጄን አዝዬ በቤተክርስቲያኑ ተደብቀው የነበሩት ላይ ድንጋይ የሚወረውሩትን ተቀላቀልኩ። ብዙዎችንም ገድለናል" የምትለው ፓውሊን በወቅቱ ከወለደች ሁለት ሳምንቷ ነበር። ከአስራ አምስት ዓመታት በኋላ የፈፀመችውን ወንጀል ለመናዘዝ ስትወስንም ዘመዶቿ ልጆቿን ለመያዝ ፈቃደኛ አልነበሩም። "የዘር ጭፍጨፋ እልቂት ብቻ አይደለም የሚያስከትለው። ማኅበረሰቡን ሽባ ያደርገዋል። ተጠቂዎችን ብቻ ሳይሆን የአጥቂዎቹንም ቀሪ ህይወት ይነጥቃል። አጥቂዎቹም ቢሆኑ ካደረሱት ጉዳትና ፀፀት ሊድኑ ይገባል" በማለት የሩዋንዳ ብሔራዊ ትብብር የእርቅ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ፊደሌ ንዳይሳባ ይናገራሉ። ወንጀላቸውን የተናዘዙ ሴት ጥቃት አድራሾች ለገደሏቸው ሰዎች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች ደብዳቤ እንዲፅፉ ይበረታታሉ። ከእስር ሲለቀቁ ማኅበረሰቡን ለመቀላቀልና ቀሪ ህይወታቸውንም በሰላም እንዲኖሩ ያለመ ቢሆንም ለበርካታ ሴቶች ቀላል አይደለም። የቀድሞ ባለቤቶቻቸው ሌላ ሴት አግብተው ከውርሳቸውም እንዲሁ ይነጠቃሉ። ከወንዶቹ ጥቃት አድራሾች ጋር ሲነፃፀር በዘር ጭፍጨፋ የተሳተፉ ሴቶች ማኅበረሰቡ አይቀበላቸውም። ቤተሰቦቻቸውም እንዲሁ አይናቸውን ማየት አይፈልጉም። ምንም እንኳን በርካቶች በፈፀሙት ወንጀል ተፀፅተው ይቅርታ ቢጠይቁም አሁንም ቢሆን የጎሳ ጥላቻ ውስጣቸው የዘለቀና ዝንብ የገደሉ የማይመስላቸውም አሉ። "ምንም ወንጀል እንዳልፈፀሙ የሚሰማቸው አንዳንዶች አሉ። ቁጥራቸው ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው" ይላሉ ፊደሌ። እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ፎርቹኔትም ቢሆን ከታሰረች ከአራት ዓመታት በኋላ ነው ወንጀሏን የተናዘዘችው። በግድያው ከተሳተፈችበት የአንደኛውን ልጅ ይቅርታ ስትጠይቅም ልቧ እንዴት እንደተሸበረ ታስታውሳለች። ከምትጠብቀውም ውጪ ልጁ ተረጋግቶና በሰላም ነው ያናገራት "ደስ ብሎት አናገረኝ፤ እምባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም። አቅፌው አለቅስ ነበር" ብላለች። ፎርቹኔትም እሱ ይቅር ካላት በኋላም የወደፊቱ ህይወቷ ብሩህ ሆኖ ታይቷታል። ምናልባትም ቀሪ ህይወቷን ከቤተሰቧ ጋር በሰላም ልትኖር እንደምትችል ተስፋ ሰንቃለች። "ከእስር ቤት ወጥቼ ቤቱ ስመለስ ከቤተሰቦቼ ጋር በሰላም እኖራለሁ። የበለጠ ሰው ወዳጅና በደንብ ተንከባካቢ እሆናለሁ። ለፈፀምኩት ወንጀል እየከፈልኩ ቢሆንም እናት እንደ መሆኔ መጠን እስር ቤት መቆየት አልነበረብኝም" በማለት ሃሳቧን አጠናቃለች።
xlsum_amharic-train-212
https://www.bbc.com/amharic/news-57035752
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ስለትግራይ እንዳልናገር "ድምጼ ታፍኗል" አሉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርስትያን ፓትርያርክ የሆኑት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ግጭት "የአረመኔነት ሥራ" በማለት ጠርተው ብዙ ጊዜ በጉዳዮ ላይ የሰጡት አስተያየት ፈቃድ ባለመሰጠቱ ምክንያት መታገዱን ተናገሩ።
[ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርስትያን ፓትርያርክ የሆኑት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ግጭት \"የአረመኔነት ሥራ\" በማለት ጠርተው ብዙ ጊዜ በጉዳዮ ላይ የሰጡት አስተያየት ፈቃድ ባለመሰጠቱ ምክንያት መታገዱን ተናገሩ።" ]
የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ባለፈው ወር ነው የተቀረፀው ባለው በዚህ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቪዲዮ ላይ በትግራይ ክልል ስላለው ግጭት እና ስለሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተናግረዋል። በትናንትናው ዕለት በትግራይ ሚዲያ ሀውስ ላይ በተለቀቀው በዚህ ቪዲዮ ላይ አቡነ ማቲያስ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ጦርነትን "የአረመኔነት ተግባር" ሲሉ የጠሩት ሲሆን እንዲቆም ብዙ ጊዜ መመኮራቸውን ነገር ግን አለመሳካቱን ገልፀዋል። የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር የነበረው ሕወሓት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ወደ ግጭት ከገባ በኋላ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መሰደዳቸው እና የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈፀማቸውን የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ሲገልፁ ቆይተዋል። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የትግራይን ግጭት በሚመለከት እስካሁን ድረስ ይፋዊ መግለጫ ሳትሰጥ ቆይታለች። የኢትዮጵያ መንግሥት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቪዲዮ ላይ እስካሁን ድረስ የሰጠው ምላሽ የለም። የፓትሪያርኩ ጽህፈት ቤትም በአቡነ ማቲያስ የቪዲዮ መልዕክትም ሆነ በትግራይ ግጭት ላይ እስካሁን ድረስ ያለው ነገር የለም። በኢትዮጵያ ከሚገኘው አጠቃላይ ሕዝብ መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ነው። ስድስተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ ከዚህ ቀደም የደርግ መንግሥትን ተቃውመው በመናገራቸው የተነሳ በስደት ከሰላሳ ዓመት በላይ በውጪ አገር ለመኖር ተገድደዋል። ቪዲዮውን ማን ቀረፀው? ከዚህ ቀደም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስም ሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በይፋ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው ግጭት ሲናገሩ አልተሰማም። እንደ የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ዘገባ ከሆነ ይህ የአቡነ ማቲያስ ቪዲዮ የተቀረፀው ከቤተክርስትያኒቱ ጋር በቅርበት የሚሠራው እና መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የ'ብሪጅስ ኦፍ ሆፕ' ባልደረባ፣ ዴኒስ ዌድሊ ነው። ቪዲዮው በአዲስ አበባ በፓትርያሪኩ ጽህፈት ቤት መቀረፁን የተናገረው ዴኒስ ፓትሪያሪኩን በጽህፈት ቤታቸው በጎበኘበት ወቅት ስልኩን በማውታት ". . . መናገር የሚፈልጉ ከሆነ አሁን መቅረጽ እንችላለን" እንዳላቸው ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ገልጿል። እንደ ኤኤፍፒ ዘገባ የቤተክርስትያኒቱ ተወካዮች አቡነ ማቲያስ መልዕክታቸው ለሕዝብ እንዲደርስ እንደፈቀዱ አረጋግጠዋል። "ድምፄ ታፍኗል" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በተደጋጋሚ በትግራይ ክልል ስላለው ግጭት የሰጡት አስተያየት ፈቃድ ባለመሰጠቱ ምክንያት መመለሱን በዚህ ቪዲዮ ላይ ተናግረዋል። መልዕክታቸው ለሕዝብ እንዳይደርስ "እየታፈነ" እንደሚቀር ተናግረው እነማን ፈቃድ እንደሚሰጡ እና እንደሚከለክሉ የተናገሩት ነገር የለም። "እኔ የምናገረው ዓለም የሚያውቀውን ነው" ያሉት ፓትሪያርኩ፣ እስካሁን ድረስ የባሰ ጉዳት እንዳይደርስ "በፍርሃት አፋቸው ተለጉሞ፣ በተጽዕኖ አለመናገራቸውን" ገልፀዋል። በትግራይ ሚዲያ ሐውስ በትናንትናው ዕለት በተለቀቀው በዚህ ቪዲዮ ላይ ሚያዚያ 7/2013 ዓ.ም ለቤተክርስትያኑ ቴሌቪዥን ቃለምልልስ መስጠታቸውን አስታውሰው መታገዱን ጨምረው ተናግረዋል። በዓለም አቀፍ ሚዲያ የሚነገረውን እኛ እንዳንናገር ተከልክለናል ያሉት አቡነ ማቲያስ፣ በትግራይ የሚደርሰው "የንፁኀን ዜጎች ግድያ እና ስቃይ" ሁሌም አእምሯቸውን እንደሚያውከው በመግለጽ ያሉበትን ሁኔታ አስረድተዋል። "በትግራይ ያለው ግጭት ከሁሉም ይብሳል" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በዚህ የቪዲዮ መልዕክታቸው ላይ በትግራይ ክልል የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አንስተዋል። በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ችግር መኖሩን የተናገሩት አቡነ ማቲያስ ነገር ግን "የትግራይን ያክል አይደለም" ሲሉ የጉዳዩን ግዝፈት ተናግረዋል። የትግራይ ችግር "እጅግ የከፋ፣ ጭካኔ የተሞላበት" ነው በማለት እርሳቸውም ሆኑ አለም ይህንን እንደሚያውቅ አብራርተዋል። አቡነ ማቲያስ በዚሁ መልዕክታቸው ላይ በማህበረ ዴጎ የተፈፀመውን ግድያ በማንሳት ንፁኀን ዜጎች ተገድለው ገደል መጣላቸውን በሥርዓት አለመቀበራቸውን ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም የቢቢሲ 'አፍሪካ አይ' ፕሮግራም ባደረገው ምርመራ በማህበረ ዴጎ ከተማ አቅራብያ 15 ወንዶች የተገደሉበት አንድ ጭፍጨፋ በኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት መፈጸሙን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች ማግኘቱን ገልፆ ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ግን ውንጀላውን አስተባብሎ ነበር። አቡነ ማቲያስ አክለውም በትግራይ ሴቶች እንደሚደፈሩና እንደሚሰቃዩ ገልፀው፣ "በሴቶች ላይ የደረሰው ዘላለም በአእምሯቸው የሚቀር ጠባሳ ነው እያስቀመጡባቸው ያሉት" ብለዋል። ድርጊቱንም "ቆሻሻ" በማለት የኮነኑት ፓትርያርኩ እጅግ በጣም ማዘናቸውንም አክለው ተናግረዋል። በትግራይ የተቀሰቀሰው ግጭት ስድስት ወር መያዙን ያስረዱት ፓትሪያርኩ መፍትሔ አለማግኘቱን ጨምረው አስረድተዋል። "ይህን ግፍ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚመልሰው የራሱ ዳኝነት ይኖረዋል" በማለት ሕዝብ ክፉኛ እያለቀ ነው ብለዋል። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተሟጋች ቡድን፣ አምንስቲ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ለስድስት ወራት በዘለቀው የትግራይ ጦርነት በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተካሂደዋል ብሏል። ከዚህ ቀደም አምንሲቲ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአክሱም በሰብዓዊ ዜጎች ላይ በኤርትራ ወታደሮች ስለደረሰው ጭፍጨፋ ሪፖርት ማውጣታቸው ይታወሳል። አምንስቲ በትግራይ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤ መቶ ሺዎች ክልል ውስጥ ተፈናቅለዋል፤ እንዲሁም 63 ሺህ ሰዎች ወደ ሱዳን ተሰድደዋል ብሏል። አምነስቲ በተለያ ጊዜ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች በጋራ መድፈርን ጨምሮ ታዳጊና አዋቂ ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንደፈፀሙ ማስረጃዎች አሉ ይላል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በትግራዩ ግጭት ተፈጽመዋል የተባሉ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተመርምረው ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙ የሠራዊቱ አባላት ለሕግ ይቀርባሉ ብለው ነበር። ከዚህ በተጨማሪም፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት ሰብዓዊ አጥኒ ኮሚሽን ጋር የተፈጸሙ የመብት ጥሰተኞችን በጋራ እንደሚመረምሩ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። በሌላ በኩል ከመብት ጥሰቶቹ ጋር ተያይዞ ሰሙ በተደጋጋሚ ለሚነሳው የኤርትራ ጦር በተመለከተ አገሪቱ መንግሥት ከሶቹ መሠረተ ቢስ ናቸው ሲል አጣጥሎ ነበር። ንብረት ዘረፋ "የትግራይ ሕዝብ ንብረቱ ተዘርፏል፣ መብቱ ተገፏል ሕይወቱን ተነጥቋል" ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ "ካላጠፋንህ ብለው እስካሁን ድረስ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ" ብለዋል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ለአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሰጡት ማብራሪያ ወቅት ትግራይ ውስጥ "የዘር ማፅዳት ወንጀል" ተፈጽሟል ያሉ ሲሆን ድርጊቱን ከማውገዝ በተጨማሪ "ሙሉ ተጠያቂነት" እንዲኖር ጥሪ አቅርበው ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥትም በትግራይ ክልል 'የዘር ማጽዳት' ድርጊት ተፈጽሟል የሚለው ክስ በፍጹም "ተጨባጭ ያልሆነና ሐሰተኛ" ነው ሲል በወቅቱ አስተባብሏል። ለዚሁ ክስ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ምላሽ ሲሰጥ "በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተሰነዘረ ተጨባጭነት የሌለውና ሐሰተኛ ክስ ነው" ብሎታል። መግለጫው ጨምሮም መንግሥት በትግራይ ክልል ውስጥ ያካሄደው ዋነኛው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅትና ከተጠናቀቀ በኋላ ሆን ተብሎ በክልሉ ውስጥ ማንንም ኢላማ ያደረገ "ዘር ማጽዳት" ተብሎ የሚጠቀስ ድርጊት አልተጸመም በማለት ክሱን የኢትዮጵያ መንግሥት አጥብቆ እንደሚቃወመው ገልጿል። አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ክልል ተከሰተ ስላሏቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ግድያዎች ተአማኒ መረጃዎች እንዳሉ አመልክተው የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን እንዲያስቆም ጠይቀዋል። አቡነ ማቲያስ በቪዲዮ መልዕክታቸው ላይ ገበሬዎች እርሻቸውን እንዳያርሱ ተከልክለዋል ያሉት ፓትርያርኩ፣ "በአብያተ ክርስትያናት ላይ ይተኩሳሉ፣ በገዳማት ላይ ይተኩሳሉ" በማለት በተለየዩ አብያተ ክርስትያናት ደርሷል ያሉትን ጥቃት ዘርዝረዋል። በደብረ ዳሞ በተተኮሰ መድፍ የመነኮሳቱ ቤት መፍረሱን፣ አንድ የእምነቱ አባት መገደላቸውንም ተናግረዋል። በዋልድባ ገዳም የሚገኙ መነኮሳት ከሚኖሩበት ገዳም እንዲወጡ መደረጋቸውን፣ አዛውንቶች ጎዳና መውደቃቸውን፣ በአሲምባ ባህታዊ ዘወንጌል መመታቱን፣ በማርያም ደናግላት ደግሞ ክብረ ዓል ላይ የነበሩ ንፁኀን መገደላቸውን ተናግረዋል። የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ እርምጃ ይውሰድ ዓለም አቀፍ መንግሥታት የንፁኀን ግድያ የሚቆምበትን መንገድ እንዲፈልጉ ሲሉ ተማጽኖአቸውን አቅርበዋል። አቡነ ማትያስ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። የዓለም ቤተክያርስትያናት ይህንን ጉዳይ አይተው የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርባል። ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ጉዳዮች ተቋማት በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች በአፋጣኝ ዕርዳታ ማቅረብ ካልተቻለ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ሲያሳስቡ መቆየታቸው ይታወሳል። በተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በክልሉ ለተፈናቀሉ እና ለተጎዱ ዜጎች የሚቀርበውን ሰብዓዊ እርዳታ ከ70 በመቶ በላይ እያቀረበ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።
xlsum_amharic-train-213
https://www.bbc.com/amharic/46755784
አቶ ጌታቸው አሰፋ በሚያውቋቸው አንደበት
ስለ የቀድሞ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ የሚታወቀው ነገር እጅግ በጣም ጥቂት ነው። ስለግለሰቡ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ የቀድሞ የትግል አጋሮቻቸውን እና የሥራ ባልደረቦቻቸውን ጠይቋል። በተጨማሪም ከቢቢሲ ዜና ክትትልና ክምችት ክፍል (ሞኒተሪንግ) እንዲሁም ዊኪሊክስ ላይ የወጡ መረጃዎች ዋቢ ተደርገዋል።
[ "ስለ የቀድሞ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ የሚታወቀው ነገር እጅግ በጣም ጥቂት ነው። ስለግለሰቡ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ የቀድሞ የትግል አጋሮቻቸውን እና የሥራ ባልደረቦቻቸውን ጠይቋል። በተጨማሪም ከቢቢሲ ዜና ክትትልና ክምችት ክፍል (ሞኒተሪንግ) እንዲሁም ዊኪሊክስ ላይ የወጡ መረጃዎች ዋቢ ተደርገዋል።" ]
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መረጃዎች የተሰበሰቡት ከቢቢሲ ሞኒተሪንግ ነው። ቢቢሲ ሞኒተሪንግ የብሪቲሽ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን /ቢቢሲ/ አካል ሲሆን ከ1931 ጀምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃንን ዘገባዎች በመከታተል መዝግቦ ያስቀምጣል። የት ተወለዱ? አቶ ጌታቸው አሰፋ 1940ዎቹ መጨረሻ ላይ በመቀሌ ከተማ፤ ቀበሌ 14 በተለምዶ 'እንዳ አቦይ ፍቐዱ' የሚባል ሰፈር ነው የተወለዱት። • አቶ ጌታቸው አሰፋ በየትኛው የሕግ አግባብ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ? • የአቶ ጌታቸው አሰፋ ጉዳይ፡ ፖለቲካዊ ወይስ ሕጋዊ መፍትሄ? እስከ 8ኛ ክፍል እዚያው መቀሌ ከተማሩ በኋላ 9ኛ ክፍል ወደ አዲስ አበባ ሄዱ። ትምህርታቸውን በዊንጌት ትምህርት ቤት መከታተል ጀመሩ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማቋረጥ 1969 ላይ የትጥቅ ትግሉን ተቀላቀሉ። ትጥቅ ትግሉን ከተቀላቀሉ በኋላ በመሪዎቻቸው አማካኝነት በመንግሥት ላይ ድንገተኛ ጥቃቶችን የሚሰነዝር ቡድንን እንዲቀላቀሉ ተደረጉ። ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት አቶ ጌታቸው በአልታዘዝም ባይነታቸው እና ግትር አቋማቸው ሦስት ጊዜ ከደረጃቸው ዝቅ ተደረገው እንዲሠሩ ተደርገው ነበር። 1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው መመረጥም ችለው ነበር። የደርግ መንግሥት ከተገረሰሰ በኋላ፤ 1983 ላይ አቶ ጌታቸው በአገር መከላከያ ኃይል ውስጥ የኦፕሬሽን ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። ከአምስት ዓመታት በኋላ ደግሞ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው አገልግለዋል። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ለሚሰበስቡት የመከላከያ ማእከላዊ እዝ አዛዥ ሆነው ተሹመውም ነበር። ግንቦት 1993 ላይ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ክንፈ ገብረመድህን መገደልን ተከትሎ አቶ ጌታቸው አሰፋ የደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ። ይህ ሹመታቸውም የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ አድርጓቸዋል ተብሎ ይታመናል። አቶ ጌታቸው አሰፋ በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከሥልጣናቸው እንዲነሱ እስከተደረጉበት ዕለት ድረስ የደኅንነት መሥሪያ ቤቱን ለ17 ዓመታት ያህል አስተዳድረዋል። • የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ከሥልጣናቸው ተነሱ አቶ ጌታቸው ለረዥም ዓመታት የመሩትን ተቋም ለጄኔራል አደም መሐመድ ካስረከቡ በኋላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የክልሉ የደኅንነት አማካሪ አድርጎ ሹመት ሰጥቷቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጌታቸው በአሁኑ ሰዓት የሕወሃት እና የኢህዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ናቸው። አቶ ጌታቸው የሁለት ሴት ልጆች አባት ናቸው። አቶ ጌታቸው አሰፋ በህወሓት የትግል አጋሮቻቸው እና የሥራ ባልደረቦቻቸው አንደበት ወላጅ አባታቸው ሻለቃ አሰፋ በንጉሡ እና በደርግ ዘመን የትግራይ ክፍለ አገር የስለላና ምርመራ ፖሊስ ምክትል አዛዥ ነበሩ። ሻለቃ አሰፋ በደረግ አደረጃጀቶች ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት በመቀሌ ከተማ ውስጥ ተገድለዋል። የአቶ ጌታቸው የትግል አጋሮች እንደሚሉት ከሆነ አቶ ጌታቸው በልጅነት ዘመናቸው ጠንካራ ተማሪ ነበሩ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማቋረጥ 1969 ላይ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር የትጥቅ ትግል ከተቀላቀሉ በኋላ አፋር ክልል ውስጥ ካዳሓራ በተሰኘ ሥፍራ ነበር ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱት። 1970 ላይ ህወሓት ውስጥ የተከሰተው 'ሕንፍሽፍሽ' እየተባለ የሚጠራው የመከፋፈል ክስተት ላይ አቶ ጌታቸው 'ተሳትፈሃል' ተብለው ለእስር ተዳርገው ነበር። በምሕረት ከድርጅቱ እስር ነጻ የወጡት አቶ ጌታቸው፤ ከደርግ ሠራዊት ጋር በተለያዩ የጦር ሜዳዎች ላይ መፋለማቸውን የትግል አጋሮቻቸው ይናገራሉ። በትግል ወቅት አቶ ጌታቸው በብዛት ይሰጣቸው የነበረው ተልዕኮ መረጃ ማሰባሰብ፣ ማደራጀትና መተንተን እንደነበርም ይናገራሉ። በግትር አቋማቸው የሚታወቁት አቶ ጌታቸው በህወሓት ፖለቲካዊ ፕሮግራሞች ላይ ጠንካራ አቋም በመያዝ በተለያዩ ጊዜያት ከፓርቲው ለመገለል ቢቃረቡም፤ በቅርብ ጓደኛቸው አቶ መለስ ዜናዊ አማካኝነት በትግሉ እንዲቀጥሉ ይደረጉ ነበር። ለምሳሌ እነ ዶክተር አረጋዊ በርሀ ከድርጅቱ ጋር የተቆራረጡበት የማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ (ማሌሊት) ምስረታ መድረክ ላይ እሳቸውም 'ኣላመንኩበትም' ብለው አቋም ይዘው እንደነበር ይነገራል። በአቶ መለስ አግባቢነት ነበር በአባልነት ሊቀጥሉ የቻሉት። አቶ ጌታቸውም የደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ከሆኑ በኋላ፤ ወደመጨረሻ አካባቢ ከጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጋር የነበራቸው መልካም ግንኙነት ባልታወቀ ምክንያት ሻክሮ እንደነበረ ባልደረቦቻቸው ይናገራሉ። ከአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ሕይወት በኋላም አቶ ጌታቸው በህወሓት ስብሰባዎች ላይ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ጠንካራ አስተያየቶችን ይሰነዝሩ እንደነበረ ይነገራል። የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ሆነው የተመረጡበት 12ኛው የህወሓት ጉባኤ ላይ በድርጅቱ አመራር የሰፈነውን ሥርዓተ አልበኝነትና ሙስና ጠቅሰው አመራሩን በድፍረት ወርፈዋል ተብሎ ይነግርላቸዋል። ከወራት በፊት ኢህአዴግ አካሄድኩ ባለው ''ጥልቅ ተሃድሶ'' ላይ ከግንባሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበረ እርሳቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው የሥራ ባልደረቦቻቸው ይናገራሉ። አቶ ጌታቸው በሌሎች አንደበት ሕዳር 3 ቀን 2011 ዓ. ም የሰኔ 16ቱ የቦንብ ፍንዳታን በማስመልከት የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ፤ ''ወንጀሉን በዋናነት የመሩትና በገንዘብ የደገፉት የብሔራዊ ደኅንነት እና መረጃ ኤጀንሲ የቀድሞው ኃላፊ [አቶ ጌታቸው አሰፋ] ናቸው'' ብለዋል። • ሜጀር ጄኔራል ክንፈ: ‘‘ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም፤ ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው’’ አቶ አብዲ ሞሃመድ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ሳሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን የመጀመሪያዎቹን 100 ቀናት አስመልክቶ ሐምሌ 5 ቀን 2010 በሰጡት መግለጫ ላይ ስለ አቶ ጌታቸው አሰፋ ሲናገሩ ''ጌታቸው ሙሰኛ፣ ሌባ እና ራሰ ወዳድ ነው። አዲስ አበባ ላይ ተቀምጦ የክልል መስተዳድሮችን ይሾማል።'' ሲሉም ተደምጠዋል። • አቶ አብዲ ስለተናገሩት ጉዳይ እንደማያውቅ ኢህአዴግ ገለፀ ''አቶ ጌታቸው አሰፋ በርካታ ነጹሐን እንዲገደሉ፣ እንዲጠለፉ፣ እንዲሰቃዩ፣ እንዲጉላሉ፣ እንዲታሰሩ እና ከአገር ተሰደው እንዲሄዱ አድርጓል። በየትኛውም መስፈርት አቶ ጌታቸው ወንጀለኛ እና የሰብዓዊ መብት ጣሽ ነው''፤ ይህን ያሉት የቀድሞ የኮንግረስ አባል ማይክ ኮፍማን ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ማይክ ፖምፔዮ እና ለግምዣ ቤት ኃላፊው ስቲአ ሙንሽን ጥቅምት 13፣ ቀን 2010 በጻፉት ደብዳቤ ነው። አቶ ጌታቸው በራሳቸው አንደበት ''የኤርትራ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የተጣለበትን ማዕቀብ ተከትሎ፤ የኢትዮጵያ እና ሱዳን አዋሳኝ ደንበርን የአሸባሪዎች መፈንጫ ለማድረግ እየጣረ ነው'' ይህን ያሉት አቶ ጌታቸው አሰፋ ናቸው በማለት የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ድረ-ገጽ ታህሳስ 2002 ላይ ጠቅሷቸው ነበር። አቶ ጌታቸው በወርሃ ሰኔ አዲስ አበባ ላይ ከአሜሪካው ልዩ መልእክተኛ ዶናልድ ያማማቶ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው ተወያይተው ነበር። አቶ ጌታቸው ''እንደ ኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር የመሰሉ ሰርጎ ገብ አማጺያን ዙሪያ አሜሪካ ያላትን አቋም ኢትዮጵያ ማወቅ ትሻለች'' ብለዋቸው ነበር። አቶ ጌታቸው አሰፋ በዊኪሊክስ ሰኔ 1፣ ቀን 2001 ዓ.ም አቶ ጌታቸው አሰፋ በወቅቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ከነበሩት ኢረቭ ሂክስ ጋር ለአራት ሰዓታት የቆየ ውይይት አድርገው ነበር። በውይይታቸው ወቅት የኦነግ እና ኦብነግ እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ውስጣዊ ደኅንነት አስጊ ስለመሆኑ፤ የአሜሪካ ድምጽ ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ፣ የቀድሞ የህወሓት አባል እና የመከላከያ ሚንስትር የነበሩት የአቶ ስዬ አብረሃ በተቃዋሚነታቸው ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪነታቸው እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው ለአምባሳደሩ መግለጫቸው ዊኪሊክስ አሳውቋል። በተጨማሪም አቶ ጌታቸው ምርጫ 97ን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመው የነበሩትን ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ''ጽንፈኛ'' ብለው መጥቀሳቸውን ዊኪሊክስ አጋልጧል። አፈትልከው የወጡ የዊኪሊኪስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አቶ ጌታቸው አሰፋ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት አይዋጥላቸውም ነበር። ጥቅምት 26፣ ቀን 2002 አቶ ጌታቸው አሰፋን የያዘ በወቅቱ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር በነበሩት በአቶ ስዩም መስፍን የሚመራ የልዑክ ቡድን ወደ አሜሪካ አቅንቶ ከውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ሂላሪ ክሊንተን ጋር ተወያይቶም ነበር። በውይይቱ ላይ የጸጥታ ትብብር፣ ዲሞክራሲዊ አስተዳደር እና የምጣኔ ሐብት ሪፎርም ጉዳዮች ለውይይት ቀርበው የነበረ ሲሆን፤ ሂላሪ ክሊንተን የአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋት ለኢትዮጵያ ሌላ ጫና እንደሆነ በመጥቀስ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የጸጥታ ትብብር አድንቀዋል ይላል፣ ዊኪሊክስ። ሂላሪ ክሊንተን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ላቀናው የኢትዮጵያ ልዑክ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሶማሊያ ጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች ስልጠናዎችን እንዲሰጥ እና ለሶማሊያ የሽግግር መንግሥት የማይቋረጥ ድጋፍ እንድትሰጥ አሳስበዋል ይላል ዊኪሊክስ።
xlsum_amharic-train-214
https://www.bbc.com/amharic/news-54348248
ኮሮናቫይረስ፡ ትምህርት ሊጀመር ስለመሆኑ ትምህርት ማኀበረሰቡ ምን ይላል?
አኮቴት የሻው የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጀ ሳለ ነው የኮሮቫይረስ ወረርሽኝ ኢትዮጵያ መግባቱ የተነገረው። ስለ መጀመሪያዎቹ ሳምንታት ሲናገር ሞዴል ሊፈተን እየተዘጋጀ እንደነበርና ቅድሚያ ትምህርት ሲዘጋ ለሁለት ሳምንት ብቻ መባላቸውን ያስታውሳል።
[ "አኮቴት የሻው የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጀ ሳለ ነው የኮሮቫይረስ ወረርሽኝ ኢትዮጵያ መግባቱ የተነገረው። ስለ መጀመሪያዎቹ ሳምንታት ሲናገር ሞዴል ሊፈተን እየተዘጋጀ እንደነበርና ቅድሚያ ትምህርት ሲዘጋ ለሁለት ሳምንት ብቻ መባላቸውን ያስታውሳል።" ]
"ሰኞ ሞዴል ልንፈተን እየተዘጋጀን እያለ ነው ትምህርት የለም ተብሎ የተነገረን" በማለት በጊዜው በእሱና በጓደኖቹ ዘንድ የፈጠረውን ደስታ አይረሳም። ነገር ግን ትምህርት ለ15 ቀን ብቻ ሳይሆን ለተራዘመ ጊዜ እንደሚዘጋ ሲታወቅ እቅዱ ሁሉ ተስተጓጎለ። እርሱን ጨምሮ አብዛኞቹ ተማሪዎች በተለያዩ አገራት የትምህርት እድል ለማግኘት እየሞከሩ ስለነበር የወረርሽኙ መከሰት እና የትምህርት መቋረጥ እቅዳቸውን ዳግም እንዲከልሱ አድርጓቸዋል። ለሰባት ወራት ከትምህርት ገበታ ውጪ የነበሩት እነ አኮቴት የትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ለፈተና እየተዘጋጁ ነው። ዝግጅታችሁ ምን ይመስላል ተብሎ ሲጠየቅም "ዝግጅቱ እንደመጀመሪያው አይሆንም" ይላል። ትምህርት ሚኒስቴር ለተፈታኝ ተማሪዎች የ45 ቀን የዝግጅት ጊዜ እንዳዘጋጀ ይፋ ሲያደርግ ተማሪዎች ራሳቸውን ከቴክኖሎጂ እና ከትምህርት ቤት ድባብ ጋር ዳግም ማስተዋወቅ ራሱን የቻለ ጊዜ እንደሚጠይቅ በማንሳት ጊዜው በቂ አለመሆኑን ይናገራል። ትምህርት ቤት ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ በርካታ ሞዴል ፈተናዎችን እንደሚወስዱ የሚጠቅሰው አኮቴት በጊዜው እጥረት "ብዙዎቻችን ደስተኞች አይደለንም" ይላል። ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ምንም ቢሆን ፈተናውን ተፈትኖ ለመገላገል ያስባል። ለዚህ የሚጠቅሰው ምክንያት ደግሞ እየሞከራቸው ያሉት የትምህርት ዕድሎችን ለመቀጠል የመልቀቂያ ፈተና ውጤት ማስፈለጉን ነው። "መከፈቱ ደስተኛ አላደረገኝም" ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በደረጃ ለመክፈት ውሳኔ ያሳለፈው ትምህርት ሚኒስቴር፣ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ዝግጁነታቸውን ለማጣራት ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጣው ኮሚቴ ሲያረጋግጥ ብቻ እንደሚሆን አስታወቋል። የትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ይሁንታ የሚሰጠው ኮሚቴ በአብላጫው ወላጆች የሚሳተፉበት ሆኖ ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከአስተዳደር ዘርፍና ከወላጆች የተሰባሰበ እንደሆነ ገልጿ።፡ የትምህርት ቤቶች መከፈት የፈጠረባቸውን ስሜት የጠየቅናቸው መምህር ተስፋሚካኤል ክፍሌ 'የለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት' ርዕሰ መምህር ናቸው። ትምህርት ቤታቸው ለ2013 የትምህርት ዘመን 2000 ያህል ተማሪዎችን መመዝገቡን የሚናገሩት አቶ ተስፋሚካኤል፣ በምዝገባ ወቅት ያስተዋሉት የተማሪዎቹ ቸልተኝነት አስደንግጧቸዋል። በዚህ ዓይነት ትምህርት በሚሰጥበት ወቅት በእረፍት ሰዓት በሽታውን በምን መልክ መከላከል ይቻላል የሚለው ስጋት ፈጥሮባቸዋል። "ተማሪዎቹ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸው ብቻ ከቫይረሱ የሚያስጥላቸው ነው የሚመስላቸው" በማለት የአካል ርቀትን ማስጠበቅ ግን ፈተና መሆኑን ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። እርሳቸው በግላቸው ትምህርት እንዲከፈት መወሰኑ የፈጠረባቸውን ስሜት ሲጠየቁም "መከፈቱ ደስተኛ አላደረገኝም" ሲሉ መልሰዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው ትምህርት በተዘጋበት ወቅት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ነው። ተማሪዎቹ የኮሮናቫይረሰ ስርጭትን ለመከላከል ስለተቀመጡት መንገዶች ተገንዝበው ንቁ ሲሆኑ አይታዩም የሚሉት መምህሩ ጥግግታቸው በጣም የተቀራረበ መሆኑን በምዝገባ ወቅት ማስተዋላቸውን ያነሳሉ። እንደ እርሳቸው ከሆነ ትምህርት ቤታቸው የትምህርት ሚኒስቴርን መመሪያ ተከትሎ በአንድ ክፍል ውስጥ 25 ተማሪዎችን ብቻ ለማስተማር ይቸገራል። "በሦስት ፈረቃ ከሆነ ብቻ በ25 ልናስተናግድ እንችላለን። እንጂ በሁለት ፈረቃ 35 ነው [ማስተናገድ የምንችለው]" ይላሉ። ለዚህም ምከክንያታቸው በአሁኑ ወቅት በአንድ ክፍል እስከ 70 የሚደርሱ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ነው። እነዚህን ተማሪዎች በሁለት ፈረቃ ይማሩ ቢባል እንኳ 35 ተማሪዎችን ብቻ በአንድ ክፍል ውስጥ ማስተናገድ እንደሚችሉ ይገልፃሉ። ትምህርት ተዘግቶ በነበረበት ወቅት የተለያዩ ሥራዎች ማከናወናቸውን የሚገልፁት መምህሩ፤ የንጽህና ቤቶች ቁጥርን ከፍ ማድረግና በንጽህና ቤቶቹ አካባቢ የውሃ መስመር ዝርጋታ መከናወኑ ይናገራሉ። መማሪያ ክፍሎች በአጠቃላይ የፀረ ተዋህሲያን ርጭት እንደተደረገላቸው፣ በትምህርት ቤቱ ውስጥም ስለበሽታው ግንዛቤን የሚፈጥሩ የተለያዩ ማስታወቂያዎች መለጠፋቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። በመጪዎቹ ሦስት ሳምንታት ውስጥም ትምህርት ቤቶች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከላክሎ ለማስተማር የሚያስችል ደረጃ ላይ መሆናቸውንና አስፈላጊ ግብዓቶች ተሟልተው ትምህርት መጀመር መቻላቸውን ኮሚቴው ገምግሞ ውሳኔ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል። የተማሪ ወላጆች ትምህርት ሊጀመር በመሆኑ ደስተኛ ናቸው ያሉት መምህሩ፤ ልጆቻቸው ቤት ውስጥ ተቀምጠው የኮሮናቫይረስ መከላከያዎችን በአግባቡ እየተገበሩ ስላልሆነ አንደኛውኑ ትምህርት ቤት ሄደው ቢውሉ ይሻላል የሚል አስተያየት መስማታቸውን ይናገራሉ። የወላጆች ኮሚቴ፣ ኅብረተሰቡም ተማሪዎቹ ትምህርት መጀመር እንዳለባቸው ሙሉ እምነት እንዳለው በማከልም "ከነችግሩም ቢሆን ወደ ትምህርት መግባት አለብን" የሚል አመለካከት እንዳላቸው ይናገራል። ሁለት ልብ አቶ ኤፍሬም ታዬ ሁለት ልጆች ያሏቸው ሲሆን ሁለቱም በእዲስ አበባ በሚገኝ የግል ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አስመዝግበዋቸዋል። ልጆቹን በአካል ትምህርት ቤት ልኮ ለማስተማር ስጋትና ፍራቻ ቢኖርባቸውም እንዳስመዘገቧቸው ግን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ልጆችን በአንድ አካባቢ ሰብስቦ አትነካኩ ማለት ፈታኝ መሆኑን የሚያነሱት አቶ ኤፍሬም፤ እስከ መቼ ድረስ ከትምህርት ቤት ርቀው በዚህ ሁኔታ ይቆያሉ የሚለው ሌላው መንታ ስሜት ውስጥ የከተታቸው ጉዳይ ነው። የአቶ ኤፍሬምና የባለቤታቸውን ልብ የከፈለው ነገር ትምህርት ቤቶቹ ተማሪዎችን ሲቀበሉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ማሟላት ስላለባቸው ነገሮች ተዘርዝሮ አለመስማታቸው እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ መከላከል ሥራውንና ቫይረሱ ያለበትን የስርጭት ሁኔታ ሲመለከቱ "የግድ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው መማር አለባቸውን?" ሲሉ እንደሚጠይቁ ይናገራሉ። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የግል ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው በቆዩባቸው ወቅት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ልጆቹ እየተማሩ ዓመቱን መጨረሳቸውን ያስታውሳሉ። ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት በሚልኩበት ወቅት ትምህርት ቤቱ ያሟላቸውን ነገሮች ለመገምገምና ከትምህርት ቤቱም ጋር ለመነጋገር የሚያስችላቸውን መከታተያ መስፈርት ከትምህርት ሚኒስቴር አለመስማታቸው ውሳኔያቸውን አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚጥለው ይገልጻሉ። አቶ ኤፍሬም ልጆቻቸው ከሚማሩበት ትምህርት ቤት አስተዳደር ጋር መነጋገራቸውን ቢገልጹም ወረርሽኙን በሚመለከት ማሻሻያ ሲያደርጉ አለመመልከታቸውን ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገር ደግሞ ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር የሰሙት ተማሪዎቹን ግምሽ ቀን ለማስተማር እቅድ መኖሩን እንደሆነ አስታውሰው፤ ነገር ግን የተማሪዎቹን ንክኪ ለመቀነስ እንዲሁም ንጽህናቸውን በመጠበቅ ስርጭቱን ለመከላከል ምን እንዳሰቡ አለማወቃቸውን ተናግረዋል። የግል ንጽህና መጠበቂያ፣ የመምህራኑ ዝግጅት እንዲሁም ሌሎች ዝግጅቶችን ለወላጆች ማሳወቅ እንደሚገባ በመጥቀስ "ጥቅምት 30 ትምህርት እንደሚጀመር ተገልጿል፤ ከዚያ በፊት በአካል ሄጄ ዝግጅታቸውን አይቼ ነው ልጆቼን ለመላክ የምወስነው?" ሲሉ ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ። አቶ ኤፍሬም ልጆቸቸውን በሚያስተምሩባቸው ትምህርት ቤቶች የመምህራን እና የወላጆች ሕብረት መኖር አለመኖሩን እንደማያውቁ ተናግረው ሁሉም በግሉ አስተያየት ሲሰጥ ማስተዋላቸውን ገልፀዋል። ነገር ግን ኮሮናን ለመከላከል ወላጆች ሰብሰብ ብለው መስራት እና ትምህርት ቤቱ ማሟላት ያለበትን ነገር እንዲያሟላ ግፊት ማድረግ እንዳለባቸው ይናገራሉ። በሚገባ ተዘጋጅተናል ቆንጂት ሞገስ የማልድ ትምህርት ቤት ሥራ አስኪያጅ ናቸው። ስለ ትምህርት ቤታቸው ዝግጁነት ቢቢሲ ጠይቋቸው ሲያስረዱ በመዋዕለ ሕጻናቱና በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤታቸው ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመከላከል ያደረጉት ዝግጅት እንደሚለያይ ገልፀዋል። ወላጆች ልጆቻቸውን ከማስመዝገባቸው በፊት መጠይቅ መበተናቸውን የሚገልፁት ቆንጂት፤ በዚህም ወላጆች ምን ምን መሟላት እንዳለበት ሃሳባቸውን መስጠታቸውን ይናገራሉ። ትምህርት ቤታቸውን በፈረቃ መስራት እንደማያስፈልገው በመግለጽ፤ አዲስ ባለ ስድስት ፎቅ ሕንጻ ዘንድሮ በመከራየታቸው ከሌሎች የተሻለ እድል እንዳላቸው እና አንድ ተማሪ አንድ ወንበርና ጠረጴዛ እንዲኖረው በማድረግ እንዳዘጋጁ ለቢቢሲ አብራርተዋል። በተጨማሪም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቱ ሲገቡ እጃቸውን የሚታጠቡባቸው መታጠቢያዎች መዘጋጀታቸውን እንዲሁም ሠራተኞች በትምህርት ቤቱ ውስጥ ንክኪን ለማስወገድ በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚጠቀሙባቸው አልባሳትና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ በትምህርት ቤቱ እንደተዘጋጀላቸው አመልክተዋል። ይህም በተለይ የመዋዕለ ሕጻናት ተማሪዎች ከመምህራኖቻቸው ጋር እጅጉን የቀረበ ንክኪ ስላላቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ ለማድረግ መምህራኖች ከትምህርት ቤቱ ውጪ የለበሷቸውን ልብሶች በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ ላለመልበስ መወሰናቸውንም ገልፀዋል። የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛም እንዲሁ እያንዳንዱ መምህር እንዲኖረው ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ተማሪዎቹ የእጅ ንጽህናቸውን የሚጠብቁበት መታጠቢያም ቢሆን ከእጅ ንክኪ ነጻ እንዲሆን ማድረጋቸውንም ለቢቢሲ አብራርተዋል። በአንድ ክፍል 15 ተማሪዎችን ብቻ እንደሚያስተምሩ የሚናገሩት ሥራ አስኪያጇ ክፍሎቹም ሰፋፊ መሆናቸውና እንደልብ አየር መዘዋወር እንደሚችል ገልፀዋል። በትምህርት ቤቱ ውስጥ ተማሪዎች የሚጋሯቸው መማሪያዎችና መጫወቻዎችን ለመቀነስ ለእያንዳንዱ ተማሪ መማሪያ ቁሳቁሶቹን ማስቀመጫ የሚዘጋ ላስቲክ መዘጋጀቱን እንዲሁም መምህራኖቻቸው ንጽህና ማጽጃ በመጠቀም እንዲያፀዱ መመሪያ መስጠታቸውን ይናገራሉ። ትምህርት ቤቱ የኮሮናቫይረስ ምልክት የሚያሳዩ ተማሪዎች ካሉ በሚል ለልጆቹ የተለየ ለይቶ ማቆያ ክፍል ማዘጋጀቱን ጨምረው ገልፀዋል። የማልድ ትምህርት ቤት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ቆንጂት እንደሚሉት ከሆነ ትምህርት ቢሮ ከሚያደርገው ክትትል ባሻገር ወላጆች በየጊዜው ልጆቻቸው የሚማሩባቸውን ትምህርት ቤቶች እንዲከታተሉ ይጠይቃሉ። ለዚህም እርሳቸው የበጎ ፈቃደኞች ወላጆችን እየመለመሉ መሆኑን ገልፀው፣ ይህ በየዕለቱ የትምህርት ቤቱን የኮቪድ-19 የመከላከል እንቅስቃሴን ለመከታተልና ክፍተት ካለም ለማረም እንደሚረዳቸው ገልፀዋል።
xlsum_amharic-train-215
https://www.bbc.com/amharic/55876981
የህወሃት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ከሁለት ወራት በኋላ ምን አሉ?
የህወሃት ሊቀመንበር የሆኑት ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በትናትናው ዕለት፣ ጥር 22፣ 2013 ዓ.ም በድምፂ ወያነ ትግራይ ፌስቡክ ገፅ ለትግራይ ህዝብ ያሉትን መልዕክት አስተላልፈዋል።
[ "የህወሃት ሊቀመንበር የሆኑት ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በትናትናው ዕለት፣ ጥር 22፣ 2013 ዓ.ም በድምፂ ወያነ ትግራይ ፌስቡክ ገፅ ለትግራይ ህዝብ ያሉትን መልዕክት አስተላልፈዋል።" ]
ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በትግራይ ላይ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በተቋረጠው ድምፂ ወያነ ትግራይ የፌስቡክ ገፅ በድምፅ ባስተላለፉት መልዕከት ክልሉ ላይ ደርሷል ስለተባሉ ውድመቶች፣ ቀጥሏል ስላሉት የትግል ሁኔታ እንዲሁም ለትግራይ ህዝብና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ያሉትን ጥሪ አስተላልፈዋል። መንግሥት በበኩሉ ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል ያቀረቧቸው ክሶች "መሰረተ የሌላቸው" እና ዓላማቸውም "የህወሓትን አጸያፊ ወንጀሎች ለመሸፋፈን ነው" ይላል። ከአሜሪካ እየተላለፈ እንደሆነ በተገለፀው የድምፂ ወያነ ገጽ ላይ የተሰራጨው ድምጽ በትክክልም የደብረጺዮን (ዶ/ር) ስለመሆኑ እና መቼ እንደተቀረፀ ቢቢሲ ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም። ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በትግራይ ላይ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት አስመልክቶ "ህዝቡ ራሱን በራሱን የማስተዳደር መብቱን በተግባር ለማረጋገጥ በፅናት ስለታገለ የተቃጣበት ጦርነት" ያሉት ሲሆን አራት መንግሥታትና የክልሎች ልዩ ኃይሎች ተሳትፈውበታል ብለዋል። አራቱ ብለው የጠሯቸው መንግሥታት እነማን እንደሆነ ባይዘረዝሩም "በዚህም ምክንያት የኃይል አለመመጣጠን አጋጥሟል" በማለት አስረድተዋል። በተለያዩ ሪፖርቶች የኤርትራ ወታደሮች መሳተፋቸው የተጠቀሰ ሲሆን በቅርቡ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል በአስቸኳይ እንዲወጡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) መጠየቁ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በተደጋጋሚ ይህ ህግ የማስከበር ዘመቻ እንደሆነና በትግራዩ ግጭት የኤርትራ ጦር አለመሳተፉን ማሳወቁ የሚታወስ ነው። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን መግለጹ ይታወሳል። መቀለ በፌደራል መንግሥቱ ሰራዊት በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ የህወሃት ሊቀ መንበር ለሮይተርስ ትግሉ እንደሚቀጥልና "ትግሉ የራስን መብት በራስ የመወሰን እንደሆነ" ገልጸው ነበር። በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸው ደብረ ፅዮን ገ/ሚካኤል በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ በግልጽ ባይታወቅም የአገሪቱ የመከላከያ አዛዦች ግን ተፈላጊዎቹ የህውሓት አመራሮች በትግራይ ተራራማ ቦታዎች ተደብቀው እንደሚገኙ ሲገልጹ ተሰምተዋል። ለእስር ማዘዣው ዋነኛ ምክንያቶቹ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል በመፈፀም፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል በጠቀሱት ትግል "ከፍተኛ ዋጋ ጠይቋል" ያሉ ሲሆን። "የህወሃት መስራች አባላት ከሚባሉት ላለፉት 45 ዓመታት ከያዙት ህዝባዊ መስመር ፈቀቅ ሳይሉ የታገሉና የመሩ፣ ያታገሉና ብዙ ድል ያስመዘገቡ አዛውንት ነባር ታጋዮች በዚህ የወረራ ጦርነት፣ በጠላት እጅ ተጎድተውብናል። ከባድ መስዋዕትነት ከፍለዋል። አሁንም እየከፈሉ ይገኛሉ። የነዚህ ጀግኖቻችን መስዋዕትነት የበለጠ ቁጭትና እልህ ያስንቀናል እንጂ ፈፅሞ ከትግላችን የሚያቆመን አይሆንም።" ብለዋል ዶ/ር ደብረፅዮን መስዋዕት ሆነዋል ያሏቸውን ግለሰቦች በስም ባይጠቅሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና አምባሳደር የነበሩት አቶ ስዩም መስፍን፣ በተለያዩ የሥልጣን ቦታ ላይ የነበሩት አቶ አባይ ጸሐዬ፣ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ እንዲሁም ከመከላከያ ሠራዊቱ ከድተዋል የተባሉት ኮሎኔል ኪሮስ ሐጎስ በግጭቱ ወቅት እጅ አልሰጥም በማለታቸው መገደላቸው ተነግሯል። በትግራይ ክልል ደርሷል ስለተባለው ውድመት ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል በክልሉ ላይ ደረሱ ስላሏቸው ጥቃቶችና ዘርፈ ብዙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል ሲሉ ከሰዋል። "የትግራይ ሴቶች በተናጠልና በደቦ ይደፈራሉ። የትግራይ መንደሮችና ዓብያተ እምነቶች፣ የትግራይ ሰራዊት ይኑርበት አይኑርበት ሳይገዳቸው የቦምቦችና የመድፎ ዒላማ ይደረጋሉ። ውድና መተኪያ የሌላቸው ቅርሶችም ይወድማሉ፣ ይዘረፋሉ። በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ እንዳለ ከቀየው ወጥቶና ተፈናቅሎ የመከራ ኑሮ ይኖራል።" ብለዋል። ደብረ ፅዮን ህዝቡ ላይ እየተፈፀመ ነው ያሉትን ወንጀል በግልፅ እንዲቃወምና እንዲያወግዝ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ ተፈፀመ ያሉት ወንጀል በገለልተኛ አካል እንዲጣራና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀው ለዚህ ተጠያቂ ናቸው ብለው የጠሯቸውን የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ወደ አለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። ስለቀጠለው ትግል የፌደራል መንግሥቱ መቀለን ከተቆጣጣረ በኋላ ውጊያዎች እንደቆሙና በክልሉ ያለውን የመሰረተ ልማት ግንባታ እንደተጀመረ በተለያዩ ሚዲያዎች ገልጿል። ደብረ ፅዮን ግን በንግግራቸው በአሁኑ ወቅት በርካቶች ትግላቸውን እየተቀላቀሉ እንደሆነ ገልጸው ህዝቡም "ጠላት" ብለው የጠሩትን ኃይል እንዲታገሉ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ደብረ ፅዮን በንግግራቸው በትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክረተሪ ቢለኔ ስዩም ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ለተቀዣበረ የወንጀለኛ ቡድን የፌስቡክ መልእክት›› ምላሽ መስጠት እንደማይፈቅዱ ገልጠዋል፡፡ ሆኖም ሕግን የማስከበር እርምጃን በተመለከተ የወንጀለኛው ቡድን እና የነሱ ዓለም አቀፍ ጋሻ አጃግሬዎች የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማደናገር ሲሞክሩ እንደቆዩና የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደተጸፈመ በማስመሰል የሚያደርጉት ይህ ማደናገር ተግባርም ከኅዳር ወር የጀመረ መሆኑን ገልጠው፣ "ይህን የሚያደርጉትም በዋናነት የህወሓትን አጸያፊ ወንጀሎች ለመሸፋፈን እንደሆነ" ተናግረዋል፡፡ ብለኔ ስዩም ‹የሕወሓትን ወንጀል ለመሸፋፈን ከመሞከር ይልቅ› የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ዓለም አቀፍ ሚዲያው እነዚህን የህወሓት ወንጀለኞች ለህግ የማቅረቡን የመንግሥት ጥረት እንዲደግፍ እንሻለን" ብለዋል፡፡ የህወሃት አመራሮች እስር በቅርቡ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል እና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ዘላለም መንግስቴ የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸው ሰዎች ብዛት 349 መሆናቸውን ከነዚህ ውስጥ 96 የሚሆኑት የህወሓት ቁልፍ አመራሮች እንደሆኑ አሳውቀዋል፡፡ ተፈላጊ ከሆኑት አጠቃላይ ተጠርጣሪዎች መካከል 124 የሚሆኑት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነም ገልጸዋል። ከሰሞኑም አቶ ስብሐት ነጋ፣ አቶ አባይ ወልዱ እና ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ በሶስት መዝገብ የተካተቱ 21 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ በሃገር ክህደት ወንጀል፣ በክልሉ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በማድረስና፣ በመሳሪያ በታገዘ አመፅና ሁከት በማነሳሳት በሚሉ ወንጀሎች ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት። በተጨማሪም የቀድሞው የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አመራሮችም በአገር ክህደትና በሠራዊት አባላት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ተጠርጥረው የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው መቃቃርና አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ "የከፋ" ሲል ገልጾታል። በተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰውና የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል እንደሚለው በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል። የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ የተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶች ህዝቡን መደረስ እንዳልቻሉም ሲናገሩና መንግሥት እንዲያመቻች ሲጠይቁም ተሰምተዋል። በክልሉ ውስጥ ያለው ሁኔታ አስከፊ እንደሆነና "በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ" አንድ የመንግሥት ባለስልጣን መናገራቸውን ከእርዳታ ሠራተኞች ጋር ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ የሰፈረ ጽሁፍ ማመልከቱ የሚታወስ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ጦርነት በተካሄደባቸው የትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ደኅንነትና ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሰብአዊ ቀውስን ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል። ከሰሞኑም እንዲሁ በክልሉ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችና የሕክም አቅርቦቶች የሰብዓዊ ድጋፍ ለ1.8 ሚሊዮን ሰዎች መድረሱን የሠላም ሚኒስቴር ገልጿል። ሚኒስቴሩ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች እየቀረበ ያለውን እርዳታ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ ከተጠቀሱት ሰዎች በተጨማሪ በክልሉ 2.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን አመልክቷል።
xlsum_amharic-train-216
https://www.bbc.com/amharic/news-57095316
ተንቀሳቃሽ ስልክን አነስተኛ ባንክ የሚያደርገው ‘ቴሌ ብር’
ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ አስቤዛ ሸምተው አልያም ዕቃ ገዝተው ወይም የአገልግሎት ክፍያ ለመፈጸም ፈልገው 'ቱ ቱ' ብለው ገንዘብ መቁጠር ላይጠበቅብዎት ይችላል።
[ "ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ አስቤዛ ሸምተው አልያም ዕቃ ገዝተው ወይም የአገልግሎት ክፍያ ለመፈጸም ፈልገው 'ቱ ቱ' ብለው ገንዘብ መቁጠር ላይጠበቅብዎት ይችላል።" ]
ከግብይትዎ በኋላ "እስኪ ስልክህን/ሽን ንገረኝ/ንገሪኝ" ብለው በተንቀሳቃሽ ስልክዎ አማካኝነት ክፍያ ሊፈጸሙ ይችላሉ። በአጭሩ ስልከዎ አንድ የባንክ መስኮት የሚሰጠውን አገልገሎት ማቅረብ ይችላል። እንዴት? ይህ በእጅ ስልክ ገንዘብ የማንቀሳቀስ አስራር በበርካታ አገራት የተለመደ ሆኗል። ጎረቤት ኬንያ ከ14 ዓመታት በፊት የጀመረችው 'ኤምፔሳ' የተሰኘውን የሞባይል ገንዘብ ስርዓት አሁን ላይ 72 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ነዋሪ እየተጠቀመው ይገኛል ይላል ቮክስ ከተባል ድህረ ገጽ የተገኘ መረጃ። በሰባት አገራት የሚሰራው ኤምፔሳ 42 ሚሊዮን ንቁ ደንበኞችና 400 ሺህ ወኪሎች አሉት። 50 በመቶ የሚሆነው የኬንያ ዓመታዊ ጥቅል ምርት [GDP] በዚሁ ስርዓት በኩል ይንቀሳቀሳል። በኡጋንዳ ከጠቅላላ ህዝቡ የባንክ አካውንት ያለው 11 በመቶ ሲሆን ኤምፔሳን የሚጠቀመው ሰው ግን 42 በመቶ ተሸጋግሯል። እናም እነዚህ አገራት ከግብይት በኋላ ቁጥርህ/ሽን ንገረኝ ማለት የተለመደ ነው። ከትናንት በስትያ [ማክሰኞ ግንቦት 3 - 2013] ይፋ የሆነው ቴሌብር መሰል አገልግሎትን በኢትዮጵያ የማቅረብ አላማ ይዟል። የኢትዮጵያ ሞባይል ገንዘብ አገልግሎት - ቴሌብር ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበራቸው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ኩባንያቸው ያሉትን መሰረተ ልማቶች ለድምጽ፣ ለጽሁፍ መልዕክትና ለኢንተርኔት አገልግሎት ብቻ ሲያውለው መቆየቱን አውስተዋል። ታድያ ቴሌብር የተሰኘው አዲሱ አገልግሎት መሰረተ ልማቱን ገንዘብ ለመቀበል፣ ለመላክ፣ የግብይትና የአገልግሎት ክፍያን ለመፈጸምም እንዲውልና "ክፍያን ለማሳልጥ" እንዲያግዝም ያስችላል ሲሉ ያስረዳሉ። በተጨማሪም የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ከውጪ ሀገራት ገንዘብ መቀበል ይችላሉ ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚዋ። በኢትዮጵያ የፋይናንስ አገልግሎቶች በባንክና መሰል ተቋማት ብቻ እየተሰጠ የቆየ መሆኑን የሚገልጹት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ኢትዮ ቴሌኮም ደግሞ ከቴሌኮም አገልግሎት በተጨማሪ የፋይናንስ ስርዓት ላይ መሳተፍ የሚችልበት የህግ ማዕቀፍ አልነበረም ብለዋል። "አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ስርአቱን ቢዘረጋም ከባድ ያደረገው ግን ኢትዮቴለኮም ይህንን አገልግሎት መስጠት እንዲችል የሚያደርገው የህግ ማዕቀፍ ለማሻሻል የሄድንበት ርቀት ግን ረጅምም አስቸጋሪም እንዲሁም ፈተናም የነበረበትም ነው ሲሉ" ተናግረዋል። ሁለት ዓመት ከፈጀ "ውጣ ውረድ" በኋላ ግን ይህንን አገልግሎት መስጠት እንዲችል ኩባንያው የተቋቋመበት ደንብ ማሻሻያ ከተደረገበትና ከብሄራዊ ባንክ ፍቃድ ካገኘ በኋላ አገልግሎቱ በ10 ቀናት ውስጥ ይፋ መሆኑን ገልጸዋል። መሰል ስርዓቶችን ለመዘርጋት ከ ሁለት እስከ ሶስት ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል ያነሱት ፍሬህይወት 'ሆኖም ፍቃድ እንደምናገኝ ተስፍ በማደረግ በአምስት ወራት ዝግጁ አድርገናል' ብለዋል። ከባንኮች ወደ ቴሌብር የገንዘብ ዝውውር ለመፍጠር ለሁሉም ባንኮች ግብዣ ልከናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ባንኮቹን ለማስተናገድ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋቱን ተናግረዋል። ንግድ ባንክ በሁለት ሳምንት ውስጥ 'ሲስተሙን ከኛ ጋር እንደሚያቀናጅ አሳውቆናል'ም ብለዋል። ይህ ማለት ቀድሞ ያሉ የሞባይል ባንክ ስርዓቶች የአንድ ባንክ ደንበኛ መሆንን ይጠይቃሉ። በአንፃሩ ቴሌብር የየትኛውም ባንክ ደንበኛ መሆን ሳይሆን ሲምካርድን ብቻ ይጠይቃል። አገልግሎቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል? ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ 53 ሚሊዮን ደንበኞች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ 25 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ናቸው። 23 ሚሊዮን ደንበኞች ደግሞ ስማርት ስልክ አላቸው። እናም እንደዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገለጻ 23 ሚሊዮኑ ደንበኞች ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጀውን መተግበሪያ በማውረድ መጠቀም ይችላሉ። ሌላኛው አማራጭ ደግሞ ኮከብና [*]መሰላልን [#] በመጫን በሚቀርቡ አገልግሎቶች ወይም USSD እና በአጭር የጽሁፍ መልዕክት መሆኑን አስረድተዋል። የስልክ ቁጥርዎ ልክ እንደ ባንክ አካውንት ቁጥር ያገለግላል። በእጅዎ ያለውን ጥሬ ገንዘብ ለኢትዮ ቴሌኮም ወኪል ይሰጣሉ ወኪሉ ደግሞ በእጅዎ ያለውን የገንዘብ መጠን ወደ እጅ ስልክዎ ይልከዋል። ወይም በተቃራኒው ከእጅ ስልክዎ ገንዘብ ወደ ወኪሉ ልከው ወኪሉ ደግሞ የላኩትን መጠን በጥሬ ገንዘብ ይሰጥዎታል። ሞባይል በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በስፍት መገኘቱ ከፋይናንስ ተቋም በበለጠ የገንዘብ ዝውውርን ለማስፋፋት ያግዛል የሚሉት ስራ አስፈጻሚዋ "በርካታ አገራት በቀላሉ ዜጎች ለግንኙነትና መረጃ ለመለዋወጥ የሚጠቀሙበትን ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በመጠቀም ገንዘብ መላክና መቀበል እንዲሁም ክፍያ እንዲፈጽሙ በማድረግ የፋይናንስ ተደራሽነትን ከፍ ማድረግ ችለዋል" ብለዋል። በኢትዮጵያ 35 በመቶ የሚሆነው ዜጋ የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑን የጠቀሱት ስራ አስፈጻሚዋ "የቀረው ሰፊው በሚሊዮን የሚቆጠር ማህበረሰብ ሊሳተፍ ያልቻለ ነው ማለት ነው። .....ስለዚህ በሞባይል ቴክኖሎጂ ታግዘን ሰፊውን ማህበረሰብ በፋይናንስ አግልግሎት ተደራሽ ብናደርገው ጤነኛ የሆነ የፋይናንስ ፍሰትና ዘለቄታዊነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ያግዛል" ሲሉ ይገልጻሉ። እናም የቴሌ ብር ዋነኛው ዓለማ ባንክን የመሰሉ የፋይናንስ ተቋም ያላገኘውን ሰፊውን የኅብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ማድረግ ነው። አገልግሎቱን ለማግኘት ተጠቃሚዎች በራሳቸው መተግበሪያውን በማውረድ ወይም #127* በመደወል አልያም 127 የጽሁፍ መልዕክት በመላክ መመዝገብ እንደሚችሉም ተናግረዋል። እናም ኢትዮ ቴሌኮም በአምስት ዓመታት ውስጥ ከ40 እስከ 50 የሚሆነውን የኢትዮጵያ የገንዘብ ዝውውር በቴሌብር በኩል እንዲሆን አቅዷል። አሁን ላይ ገንዘብ ወደቴሌ ብር ገቢ ወይም ወጪ ለማድረግ በመጀመሪያ ዙር 1ሺህ 500 ወኪሎች መዘጋጀታቸውን ጠቁመው ይህንንም ቁጥር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ 15 ሺህ ለማሳደግ መታቀዱን ገልጸዋል። ቴሌ ብርና የባንኮች የሞባይል አገልግሎት በኢትዮጵያ የተለያዩ ባንኮች የእጅ ስልኮችን በመጠቀም ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንደሚቻል ሲያስተዋውቁ ይደመጣል። ታዲያ ቴሌ ብር ከእነዚህ በምን ይለያል የሚል ጥያቄ ለዋና ስራ አስፈጻሚዋ አቅርበንላቸው ሲመልሱ "አንደኛ ደበኞቻችን 53 ሚሊዮን ደርሰዋል፤ የባንክ ተጠቃሚዎችችን ግን እዚያ ላይ አልደረሱም። ስለዚህ ሰፊ ያልደረስናቸውን ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ የተሻለ ያገለግለናል" ሲሉ ያብራራሉ። በሁለኛ ደረጃ ደግሞ "ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ የሞባይል ቴክኖሎጂ ባንኮች ከደረሱት በላይ ለመድረስ ያስችላል" ብለዋል። አገራት ይህንን ስርዓት በመዘርጋታቸው ጥሬ ገንዘብ ለማሳተምና ደህንነቱን ለመጠበቅ የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስ አግዟልም ብለዋል። ከዚህም ባሻገር ኢትዮቴሌኮሞ ልክ የአየር ሰአትን በብድር እንደሚሸጠው ሁሉ ገንዘብን በቴሌ ብር በኩል የማበደር እቅድም አለው። መሰል አገልግሎቶች የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ ለሚቀላቀሉ የውጪ ኩባንያዎች አለመፈቀዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቴሌ ብር ይፋ በሆነበት ስርዓት ላይ ተናግረዋል። ይህም በመሆኑ ምክንያት የዲፕሎማሲ ጫና እየተደረገብን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የውሳኔውን አስፈላጊነት ሲያስረዱ "በቀጥታ ከብሄራዊ ጥቅም ጋር ስለሚያያዝ ነው። ለውድድር የሚያመች ልምድ ስላልነበረን ተጠቃሚ ስለማያደርገን ነው" ብለዋል። ሆኖም ይህንን አገልግሎት ኢትዮ ቴሌኮም ብቻውን የሚሰጠው ቢበዛ ለአንድ ዓመት ነው ሲሉም ገልጸዋል። በዚህ አንድ ዓመት ደግሞ ኢትዮ ቴሌኮም ከ20 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን እንደሚመዘግብና ከዚህ ውስጥ ከ12 ሚሊዩን በላይ የሚሆኑት ንቁ ደንበኛ ሆነው 710 ሚሊዮን ብር ይዘዋወራል ተብሎ እቅድ ተይዟል።
xlsum_amharic-train-217
https://www.bbc.com/amharic/55447030
ቤንሻንጉል ጉሙዝ፡ በመተከል ዞን ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ200 በላይ ሆነ
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ታኅሳስ 13/2013 ዓ. ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መድረሱን አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ለቢቢሲ አረጋገጡ።
[ "በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ታኅሳስ 13/2013 ዓ. ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መድረሱን አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ለቢቢሲ አረጋገጡ።" ]
በጥቃት ፈጻሚዎቹ በሰዓት ውስጥ በተፈጸመው ጭፍጨፋ በቀበሌው ውስጥ ነዋሪ ከሆኑት ሰዎች መካከል 207ቱ በጥቃቱ መገደላቸውንና 171ዱ ሥርዓተ ቀብራቸው ሐሙስ መፈፀሙን የቡለን ወረዳ ኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ ካሳሁን አዲሱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም በአካባቢው ከሚገኙ ነዋሪዎች፣ ከበጎ ፈቃድ ድጋፍ ሰጪዎችና ከጸጥታ አካላት በማጣራት ባገኘው መረጃ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 207 መድረሱን እንዳረጋገጠ አሳውቋል። ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ ላይ በጥቃቱ ስለተገደሉት ዝርዝር እንዳመለከተው ከሟቾቹ መካከል አዋቂዎቹ 133 ወንዶችና 35 ሴቶች ሲሆኑ፤ አንድ የስድስት ወር ሕጻንን ጨምሮ 17 ሕጻናት ተገድለዋል። የቀሩት 20 ሰዎች ደግሞ አዛውንቶች መሆናቸው ኢሰመኮ አረጋግጧል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎችና የአካባቢው ኃላፊዎች የሟቾቹ ቁጥር ከ207 በላይ ሊሆን እንደሚችል ስጋት እንዳለቸው ገልጸዋል። ኢሰመኮ በመግለጫው ላይ እንዳለው ፖሊስ እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ጨምሮ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካላት የተወጣጡ አባላት ያሉበት የምርመራ ኮሚቴ የሟቾቹን ማንነት የማጣራቱን፣ የመመዝገብና አስከሬኖችን የመቅበር ተግባራትን እየተከታተለ ይገኛል። የወረዳው ኮሙኒኬሽን ኃላፊው አቶ ካሳሁን ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት በተፈጸመው የጅምላ ጥቃት የተገደሉት የሦስት የተለያዩ እምነት ተከታዮች ቢሆኑም ለይቶ የተናጠል ቀብር ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ ሐሙስ ዕለት በጅምላ እንዲቀበሩ መወሰኑን አስረድተዋል። በርካታ አስከሬኖች የሚያሳዩና ለጅምላ ቀብር የተዘጋጁ የቀብር ቦታዎችን የሚያሳዩ ምስሎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ሲዘዋወሩ ታይተዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሟቾቹ ቁጥር ከፍ ማለቱንና በአካባቢው ስላለው ሁኔታ በገለጸበት መግለጫው ላይ የሟቾችን አያያዝ በተመለከተም "የአስከሬን ፍለጋና የመቅበር ሥነ ሥርዓቱ ሰብአዊ ክብርን በጠበቀ መልኩ እንዲሆን" ጥሪ አቅርቧል። ጥቃቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና አምንስቲ ኢንተርናሽናል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ማክሰኞ ሌሊት ለረቡዕ አጥቢያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገልፀው ነበር። የክልሉ ኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ በወቅቱ ለቢቢሲ በጥቃቱ በትክክል ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ ለመግለጽ ባይችሉም ቁጥሩ "በጣም ከፍተኛ" ነው ብለው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም ይህንን ጥቃት "ጭፍጨፋ" መሆኑን ገልጸው "በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ" በማለት ሐዘናቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ታኅሣስ 14/2013 ባወጣው መግለጫ በበኩጂ ቀበሌ የሚኖሩ የሽናሻ፣ የኦሮሞ እና የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች በጥቃቱ ዒላማ ተደርገዋል ብሏል። ይህ ጥቃት በቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከመ መሄዱን እንደሚያሳይም ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። የአምንስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተገደሉትን ሰዎች አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ "እጅግ አሰቃቂው ግድያ በክልሉ የሚኖሩ አማራዎች፣ ኦሮሞዎችና ሺናሻዎች ላይ ያነጣጠረ ነው። ይህ መንግሥት ብሔር ተኮር የሆነ ግድያን ለማስቆም በፍጥነት ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ የሚያሳይ ነው" ማለቱ ይታወሳል። አቶ ካሳሁን አዲሱ እንደገለፁትም በአካባቢው የደረሰውን ጥቃት ለማጣራት የተሰማራው የመከላከያ፣ የክልል እና የመገናኛ ብዙሃን ቡድን ከወረዳ እና ከዞን ኃላፊዎች ጋር ሆኖ ባደረገው ማጣራት የተገደሉት 207 ሰዎች ከአማራ፣ ከኦሮሞ፣ ከሽናሻ እንዲሁም ከአገው ብሔር መሆናቸውን አረጋግጧል። ኃላፊው በጥቃቱ የተገደሉ ዜጎች በስለት፣ በጥይትና በቀስት መሞታቸውን ተናግረው አንድ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው የተቃጠሉ መኖራቸውንም አክለዋል። ከእነዚህ ውጪ እስካሁን ድረስ የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎች እንዳሉ እና በየጫካው አስከሬናቸው በመርማሪ ቡድኑ እየተፈለገ መሆኑን አስታውቀዋል። አስከሬኑን በጅምላ ለመቅበር ከአካባቢው ሽማግሌዎች ጋር በመነጋገር መፈፀሙን ያስረዱት አቶ ካሳሁን፤ የተናጠል ቀብር ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ እንዲሁም የቀበሌው አስተዳደር በአካባቢው የጋራ መታሰቢያ ለማቆም እንዲቻልም በሚል በአንድ ላይ መቀበራቸውን አብራርተዋል። የቀብር ቦታውን በመምረጥ የወረዳው አስተዳዳሪዎች ከአገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን መሳተፋቸውንም አክለው ገልፀዋል። በበኩጂ ቀበሌ ጥቃት ከተፈፀመ በኋላም ስጋት የገባቸው ዜጎች ከተለያዩ የወረዳው ቀበሌዎች ወደ ወረዳው ከተማ ቡለን እየመጡ መሆኑንም አቶ ካሳሁን ገልፀዋል። "በኩጂ ቀበሌ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላ፣ በጭላንቆ፣ በአዲስ ዓለም፣ በዶቢ እና ጎንጎ ቀበሌዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦች በስጋት ምክንያት ወደ ወረዳዋ ከተማዋ ቡለን እየመጡ ነው" ብለዋል። በአካባቢው ቀያቸውን ጥለው እየመጡ ላሉ ሰዎች ከዚህ በፊት ከፌደራል መንግሥት መጥቶ የነበረ የተለያየ ድጋፍ እየተሰጣቸው ቢሆንም በቂ አለመሆን ኃላፊው ይናገራሉ። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ከሰባት ቀበሌ ነዋሪ በላይ ቀዬውን ለቅቆ ወደ ቡለን ከተማ እየመጣ በመሆኑ እርዳታው በቂ አለመሆኑን አቶ ካሳሁን ተናግረዋል። ወደ ቡለን ከተማ ከሚመጡት ነዋሪዎች ውጪ በአቅራቢያው ወደሚገኝ የአማራ ክልል ከተማ የሚሄዱ ሰዎች መኖራቸውንም አክለው ገልፀዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ጥቃቱን ተከትሎ በግድያው ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ የክልልና የፌደራል አመራሮች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ፤ 42 የታጠቁ ሽፍቶች በጸጥታ በተካሄደ አሰሳ መገደላቸውን ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት በመተከል ዞን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አመራሮችን በሕግ ቁጥጥር ሥር እያዋለ መሆኑን ተናግሯል። የክልሉ የኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ እስካሁን ድረስ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው ያለበትና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮች በሚል በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ውስጥ መካከል አቶ ቶማስ ኩዊ የኢፌዴሪ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ፣ አቶ አድጎ አምሳያ የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ይጘኙበታል። በተጨማሪም አቶ ሽፈራው ጨሊቦ የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር፣ አቶ ባንዲንግ ማራ የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ አረጋ ባልቢድ የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር፣ አቶ ገመቹ አመንቲ የክልሉ የግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም አቶ አድማሱ መልካ የገጠር መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር መሆናቸውን ገልፀዋል። እነዚህ አመራሮች ከመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር እጃቸው እንዳለበት በመረጋገጡ በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ይባል እንጂ ከዚህ ቀደምም በዚሁ ዞን ኅዳር 5 ቀን 2013 ዓ. ም በተከሰተ የጸጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣት የተጠረጠሩ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ላይ ፖለቲካዊ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ አብዱልቃድር ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።
xlsum_amharic-train-218
https://www.bbc.com/amharic/news-47038371
ፍርድ ቤት የቀረበው የጤፍ ባለቤትነት ጉዳይ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከጤፍ ባለቤትነት ጋር በተያያዘ የሆላንድ ድርጀትን በዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ሊከስ ነው። ድርጅቱና የኢትዮጵያ መንግሥት ከአስር ዓመታት በላይ የባለቤትነት ይገባኛል ንትርክ ውስጥ የቆዩ ሲሆን የዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ውሳኔ የኢትዮጵያን ጥያቄ የሚመልስ እንዲሆን በመንግሥት በኩል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው።
[ "የኢትዮጵያ መንግሥት ከጤፍ ባለቤትነት ጋር በተያያዘ የሆላንድ ድርጀትን በዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ሊከስ ነው። ድርጅቱና የኢትዮጵያ መንግሥት ከአስር ዓመታት በላይ የባለቤትነት ይገባኛል ንትርክ ውስጥ የቆዩ ሲሆን የዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ውሳኔ የኢትዮጵያን ጥያቄ የሚመልስ እንዲሆን በመንግሥት በኩል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው።" ]
ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በጤፍ ጉዳይ ፍርድ ቤት የሚሟገተው 'ሄልዝ ኤንድ ፐርፎርማንስ ፉድ ኢንተርናሽናል' የተባለው የሆላንድ ድርጅት እንግሊዝ፣ ጣልያን፣ ቤልጂየም፣ ኦስትሪያና ሆላንድ ውስጥ የጤፍ ባለቤትነት ፈቃድ አለው። • ጤፍን ሰዳ የምታሳድደው ኢትዮጵያ ፈይሳ ቲክሴና ወንድ ልጁ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የጤፍ ማሳቸውን እየተንከባከቡ ነበር ያገኘናቸው። ጤፍ ለእነሱ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ከመሆኑ ባለፈ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ቋሚ ምግብ ነው። ይህ ተክል ከአምላክ የተሰጠን ገጸ በረከት ነው ይላል ፈይሳ። "በክረምት ወራት መሬቱን በደንብ እናርሰውና ጤፍ እንዘራበታለን። ከሽያጩ የምናገኘው ገቢ ለእኔና ለቤተሰቤ ከበቂ በላይ ነው። ሥራዬን እየሰራሁ ልጆቼን አስተምርበታለሁ። ጤፍ ታላቅ ተክል ነው።" ለብዙ ዘመናት እንደ ፈይሳ ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጤፍን በማመረት ላይ ህይወታቸውን መስርተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከጤፍ የሚዘጋጀውን እንጀራ ጋግረው በማቅረብ ሥራ ላይ ተሰማሩ በርካቶች ናቸው። አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የእንጀራ መጋገሪያ ምርቶቹን ወደ አሜሪካ ይልካል። ትልልቅ ማሽኖች የጤፍ ዱቄትና ውሃን ቀላቅለው መጋገሪያዎች ላይ ያዘጋጃሉ። ይሄ ሁሉ ሂደት ሰባት ደቂቃ ብቻ ነው የሚፈጀው። • ጤፍ ሃገሩ የት ነው? ደቡብ አፍሪካ? አውስትራሊያ? . . . በዚህ ድርጅት ጤፍ ለእንጀራነት ብቻ ሳይሆን ዳቦ፣ፓስታ፣ ብስኩትና ፒዛ ለማምረት አገልግሎት ላይ ይውላል። ታዲያ የዚህ አይነት ምርቶችም ጭምር ናቸው በኢትዮጵያ መንግሥትና በሆላንዱ ድርጅት የይገባኛል ፍጥጫ መካከል ተጎጂ የሚሆኑት። በብዙ የአውሮፓ ሃገራት እውቅና የተሰጠውን የሆላንድ ድርጅት የጤፍ ባለቤትነትና ምርቶችን የማከፋፈል መብትን ለማስነሳት የኢትዮጵያ መንግሥት ለአስራ አራት ዓመታት ሲታገል ቆይቷል። በፈረንጆቹ 2000 አካባቢ ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ጋር ስምምነት ስትፈራረም የጤፍ ምርትን ማሳደግና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነበር። ነገር ግን ለድርጅቱ የተሰጠው ፈቃድ ኢትዮጵያ የጤፍ ምርትን ወደ ውጪ ከመላክ ያግዳታል። ይህን በተመለከተ አቶ ኤርሚያስ የማነብርሃን የኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ናቸው። "በኔዘርላንድስ ኤምባሲ በኩል ከድርጅቱ ጋር ለመደራደር ሞክረናል። ነገር ግን አንድ ግለሰብ በመሆኑ ተቀባይነት ሳይገኝ ቀርቷል። እስካሁን ስንሰራው የቆየነው የባለቤትነት ፈቃዱ መጥፎ እንደሆነ ማሳየት ነው" ይላሉ። • የከተሜን ህይወት ቀላል ለማድረግ ጤፍን ፈጭቶ መሸጥ! ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለውን ጥረት ከባድ የሚያደርገው ደግሞ 'ሄልዝ ኤንድ ፐርፎርማንስ ፉድ ኢንተርናሽናል' የተባለው የሆላንድ ድርጅት ከፈረሰ መቆየቱ ነው። በወቅቱ የድርጅቱ ባለቤት ነበር የተባለው ግለሰብ ጃንስ ሩዝጀን በአሁኑ ሰዓት የሌላ ድርጅት ዋና ሃለፊ እንደሆነ ነው የሚታወቀው። ቢቢሲ ድርጅቱን ለማነጋገር ቢሞክርም ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። የጤፍ ባለቤትነትን በተመለከተ ኢትዮጵያ መንግሥትና የእኔ ነው በሚለው ድርጅት መካከል ያለው ውዝግብ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ይናገራሉ። • እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል? በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ ያናገርናቸው ኢትዮጵያዊያንም ይህንኑ ነው አስረግጠው የሚናሩት። አንደኛው አስተያየት ሰጪ "ጤፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንደሚገኝ አውቃለው። ምናልባት ወደ ውጪ ተልኮ ካልሆነ ሌላ ቦታ አታገኘውም። በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝና ህይወቴን ሙሉ ሳጣጥመው የነበር ምግብን አንድ የሆላንድ ድርጅት መጥቶ ባለቤቱ እኔ ነኝ ቢለኝ ተቀባይነት የለውም'' ብለዋል። ሌላኛው ደግሞ "ጤፍ በቅድመ አያቶቻችን ዘመንም ነበር። ከጥቂት ዓመታት በፊት የውጪ ተመራማሪዎች ጤፍ ምንም ፕሮቲን የለውም ሲሉ አስታውሳለው። አሁን ደግሞ ጥቅሙን ስላወቁ ተመልሰው አስፈላጊ ተክል ነው እያሉ ነው። የሆላንዱ ድርጅት የባለቤትነት መብቱን ማግኘቱ ትልቅ ችግር ነው። በፍጹም ልቀበለው አልችልም" ሲሉ ተናግረዋል። እነዚህን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ከመንግሥታቸው ጎን ቢቆሙ አስገራሚ አይደለም። ምንም እንኳን ጉዳዩን በተመለከተ ብዙ የተወሳሰቡ ሕጋዊ ጉዳዮች ቢኖሩም ኢትዮጵያ በቀላሉ ተስፋ ቆርጣ የምትተወው አይመስልም።
xlsum_amharic-train-219
https://www.bbc.com/amharic/news-41697075
ካለሁበት 6፡ ''ከሀገር ቤት የስደት ኑሮዬ ይሻለኛል''
ፋና ተክላይ እባላለሁ፤ በሊባኖስ ቤይሩት መኖር ከጀመርኩኝ ሁለት ዓመት ሆኖኛል፤ እንዴት ወደ ስደት እንደመጣሁኝ ላጫውታችሁ ነው ።
[ "ፋና ተክላይ እባላለሁ፤ በሊባኖስ ቤይሩት መኖር ከጀመርኩኝ ሁለት ዓመት ሆኖኛል፤ እንዴት ወደ ስደት እንደመጣሁኝ ላጫውታችሁ ነው ።" ]
በትግራይ በሰሜናዊ ምዕራብ ዞን፡ በታሕታይ ቆራሮ ወረዳ፡ ሰቀላ-ቆየጻ በሚባለ አካባቢ ነው የተወለድኩት። እሰከ ዘጠነኛ ክፍል ድረስ ከቤቴ ለሁለት ሰዓታት በእግር እየተመላለስኩኝ ተማርኩኝ። 11 ዓመት ሲሞላኝ ግን ወላጆቼ በእድሜ በጣም ከሚበልጠኝ ሰው ጋር ዳሩኝ። ከጥቂት ጊዜ በኃላ ግን ባለቤቴ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ውትድርና ዘመተ። እኔም ትምህርቴን ብቀጥልም ቤተሰቦቼ ግን ትምህርት ቤት ሳይሆን የትም ስዞር የምውል ስለሚመስላቸው እንድማር አልፈቀዱልኝም። በዚህም የተነሳ በሁለታችን ቤተሰቦች መካከል አለመግባባት ስለተፈጠረ እኔ መቋቋም አልቻልኩም። በመጨረሻም በ1994 ወደ መቐለ ጠፍቼ ዘመዶቼ ጋር ባርፍም እዚህም ማረፍ አልቻልኩም ፤ ነጋ ጠባ ትዳርሽን ትተሽ መጣሽ እያሉ ያሳቅቁኝ ነበር። ግን አማራጭ ስላልነበረኝ ሁሉንም ችዬ እኖር ነበር። ከ3 ዓመት በኋላ ግን ፍሬአብዮት በሚባል ትምህርት ቤት ያቋረጥኩትን የዘጠነኛ ክፍል ትምህርቴን ጀመርኩኝ። በዚህ ጊዜ ሞራሌ በተሰበረበት፤ አይዞሽ የሚል ሰው ባጣሁበት ጊዜ ከሌላ ወንድ ጋር ተዋወቅኩኝና ትዳር መሰረትኩ። በጣም ያስብልኝ፣ እንድማርም ያበረታታኝ ነበር። እኔም ከ10ኛ ክፍል በኋላ የኮሌጅ ትምህርት ጀመርኩኝ። ሆኖም ባለቤቴ በስራ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ሲቀይር እኔም ተከትየው ሄድኩኝ ። በመሀከላችን ግን አለመግባባት ተፈጠረ ፤ልጅ መውለድ በጣም ብፈልግም ሊፈቅድልኝ አልቻለም። ያኔ በውጪ የሚኖሩ ብዙ ጓደኞቼ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለተሻለ ህይወት እንድቀላቀላቸው ጫና ያሳድሩብኝ ነበር። በኋላ ቪዛ ሲልኩልኝ በ2001 ዓ.ም ወደ ኩዌት ተሰደድኩ። ኩዌት መጀመሪያ ላይ እንደጠበቅኳት ኣላገኝኋትም፤ ምክንያቱም በሌሎች ሰዎች አማካኝነት ድጋፍ ካልተገኘ በተሻለ የስራ ቦታ መስራት አይቻልም። እኔም በሰው ቤት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩኝ። እዚህ እንድመጣ ያበረታቱኝ ጓደኞቼ እንኳን አልተቀበሉኝም። ለኔ ደግሞ የመጀመርያ የስደት ኑሮዬ ስለነበረ ከቤተሰብ ተለይቶ መኖር በጣም ከበደኝ። አሰሪዎቼን አላውቃቸውም፤ በዛ ላይ በማይገባኝ ቋንቋ ሲጯጯሁ የሚበሉኝ ይመስለኝ ነበር። ሁሉም ነገር ጨለመብኝ። በመምጣቴ ብጸጸትም ወደ ኃላ መመለስ ስለማልችል ለሰባት ወራት በለቅሶ አሳለፍኩኝ። "የኔ ህይወት ውስብስብ ነው" ኩዌት በሄድኩበት ግዜ፤ ባለቤቴ የፈለገ ቦታ ቢሆንም ሳይደውልልኝ አይውልም ነበር። ከሶስት ዓመታት በኋላ በኩዌት የነበረኝን የስደት ቆይታ ጨርሸ፤ ወደ ሀገር ቤት ስመለስም ባለቤቴን ለማግኘት ትልቅ ጉጉት ነበረኝ። እርሱም ደስ ብሎት ከአየር መንገድ ተቀብሎ ወደ ቤት ወሰደኝ፤ ቤቴ ግን እንደተውኩት አልጠበቀኝም። ወደ ቤት ስገባ አንዲት ሴት አግኝቼ ሰራተኛው እንደሆነች ነገረኝ። አመሻሽ ላይ ግን በመካከላቸው ጭቅጭቅ ተፈጠረ። ለካ ሁለተኛ ሚስት አስቀምጦልኝ ኖሯል። ከዛ በኋላ መስራት እንዳለብኝ ወሰንኩና እና የፀጉር ስራ ትምህርት ተምሬ፣ የሚያስፈልጉ እቃዎቼንም ገዝቼ ለመስራት ብሞክርም መረጋጋት አልቻልኩም። ውስጤ ሰላም አጣ፤ ሰዎችም ከአሁን በፊት የነበረኝን ህይወት በማነፃፀር ከንፈር ይመጡልኝ ጀመር። ይህንኑ መቋቋም ቢያቅተኝ፤ በድጋሚ ፊቴን ወደስደት አዞርኩና ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጓዝኩኝ። ለሁለት ዓመታት በቤት ሰራተኝነት እና ፀጉር ቤት በፈረቃ እሰራ ነበር። ሀገር ቤት እያለው የደረሰብኝ በደልና ከማህበረሰቡ ይደርስብኝ የነበረው ስነልቦናዊ ስብራት የስደት ኑሮየ አሜን ብየ እንድቀበለው አድርጎኛል። እናም አሁንም ለተሻለ ኑሮ ለሶስተኛ ጊዜ እግሮቼ ወደሌላ ስደት ወደ ሊባኖስ መሩኝ። በሊባኖስም የምሰራው የሰው ቤት ተቀጥሬ ቢሆንም የተሻለ የስራ ሰዓትና ክፍያ አለኝ። በሕይወቴ ሶስት የአረብ አገራት፤ሶስት ስደት አይቻለሁ። መጀመሪያ ላይ እንደመጣሁ ምግባቸው በጣም ያስጠላኝ ነበር። ሌሎቹን ቀሰ በቀስ መላመድ ብችልም አባጨጓሬ የሚመስል " ሽሪምፕ" የሚባል ከባህር የሚወጣ ምግባቸውን ግን አሁንም እንደጠላሁት ነው። " እኛን አማክራችሁ ነበር እንዴ የመጣችሁት ?" በቤይሩት ብዙ ኢትዮጵያውያን አሉ፤ብዙ ችግርም ያጋጥማቸዋል። ታመውና አብደው በየጎዳናው ሲሄዱ አያለሁ። አንዳንዶቹ በደላላ መጥተው በአሰሪዎቻቸው ይበደላሉ። ይህንን አይተን በሊባኖስ ወደሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ስንደውል የሚሰማን የለም። እህቶቻችን ችግር አጋጠማቸው ስንላቸው "ለኛ አማክራችሁ ነበር እንዴ የመጣችሁት?" ይሉናል። የሌሎች ሀገራት ዜጎች ኤምባሲዎቻቸው ስለሚተባበሯቸው ጥሩ ክፍያ እና እረፍት ያገኛሉ። ለኛ ግን እንደ ዜጋ የሚተባበረን የለም። እርሰ በርሳችን ግን እንተሳሰባለንን። በበዓላት የምንገናኛባቸው አጋጣሚዎች አሉ። እዚህ ካለው ስደተኛ ጋር መልካም ጊዜ የምናሳልፍባቸው የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶችም አሉ። '' ከሀገር ቤት የስደት ኖሮዬ ይሻለኛል'' ወደሀገሬ ብገባ የሰዎች አሽሙር ብሰደድ የስደተኛ በደል ነው የሚጠብቀኝ። ሁሉም በደል ነው። ባወዳድር ግን ተሰድጄ የምኖረው ኑሮ ይሻላል። እኔ አብዛኛውን ጊዜ ትርፍ መፅሃፍ በማንበብ ነው የማሳልፈው፣ ቤተክርስትያንም እሄዳለሁ። የአሰሪዎቼ ቤተሰቦችም ትንሽ ስለሆኑ ነፃነት ይሰጡኛል። ጥዋት ከመኝታ ቤቴ ተነስቼ የበረንዳ መሰኮት ስከፍት፡ ከፊት ለፊቴ የሚታየኝ ባህር አለ። ራሴ የምንከባከባቸው አትክልትም አሉኝ። ይህ ለመንፈሴ እርካታ ይፈጥርብኛል። ትናንት ያሳለፍኩት ሕይወት ጠንካራ አድርጎኛል። ስለነገ ሳልጨነቅ ደስተኛ ሁኜ ለመኖር እጥራለሁ። የተለያዩ ጉዳዮችን በፌስቡክ አጋራለሁ። በፌስቡክ ያገኝኋቸው ጥሩ ጓደኞች አሉኝ። በተቻለኝ ሁሉ ከማገኘው ደሞዝ መፅሃፍትን በመግዛት ለትምህርት ቤቶች መለገስ ያስደስተኛል። ባለፈው ዓመት በትግርኛ ቋንቀ የተፃፉ 350 መጻህፍትን ለትምህርት ቤቶች ለግሻለሁ። የስምንተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ በሌሎች የትምህርት አይነቶች ጎበዝ ብሆንም፤ በአማርኛ ግን ሰነፍ ስለነበርኩ በዚህ የተበሳጨ አንድ ዘመዴ ዶሮ ሽጦ መፅሃፍ ገዛልኝ። ያቺ የመፅሃፍ ስጦታ ለሱ ትንሽ ብትሆንም ለኔ ግን በሀይወቴ የማልረሳት እና ለሌሎች ሰዎች መፅሃፍ እንዳበረክት ምክንያት የሆነችኝ ስጦታ ናት። በስደት ሕይወቴ አጋጠመኝ የምለው ከባድ ነገር ቢኖር ሳዑዲ አረቢያ በነበርኩበት ጊዜ በጣም ታመምኩኝ። ወደ ሊባኖስ እንደመጣሁ ደግሞ ሶሪያ እና እስራኤልን በሚያዋስን ድንበር አካባቢ ስሰራ አካባቢው በጣም የሚያስፈራ ሁልጊዜም ወታደሮች የሚታዩበት ነበር። ያኔ አሰሪዎቼ ለሶስት ወራት ቤታቸውን ትተው ወደ ሌላ አገር ሲጓዙ በማላውቀው ሀገር ለብቻዬ መኖር በጣም እንደከበደኝ አስታውሳለሁ ተመልሰው ከመጡ በኋላም በተመሳሳይ ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ ሲዘጋጁ ዳግመኛ ለብቻየ በተዘጋ ቤት መቆየት አልፈለግኩም። እናም አንድ ነገር ማድረግ እንደለብኝ ወሰንኩኝ። ከዛ ቤት ጠፍቼ ለሶስት ሰዓታት ያክል በማላውቀው መንገድ በሌሊት የእግር ጉዞ ጀመርኩኝ። በሌሊት በዛ ላይ የዝናብ ዶፍ እየወረደብኝ ወደ ከተማ ገባሁኝ። ይህ አጋጣሚ በስደት ሕይወቴ የማልረሳው ከባድ አጋጣሚ ነው። ድንገት አሁን ካለሁበት ራሴን ወደ ሌላ አካባቢ መላክ ብችል ራሴን በትግራይ ክልል በሽረ እንዳስላሴ ከዛም በመቐለ ከተማ አገኛት ነበር። ለላይን ጽጋብ እንደነገረቻት ካለሁበት 7፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ካምቦዲያ መኖር እፈልግ ነበር ካለሁበት 8፡ ኢትዮጵያዊው የበረዶ ሸርተቴ ተወዳዳሪውና አስተማሪው በጃፓን
xlsum_amharic-train-220
https://www.bbc.com/amharic/news-47689735
የገጠር አስተማሪው አንድ ሚሊዮን ዶላር አሸነፉ
በኬንያ በአንድ ገጠር ውስጥ ሳይንስ አስተማሪ የሆኑት ፒተር ታፒቺ የዓለም ምርጡ አስተማሪ ተብለው ወደ 30 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የገንዘብ ሽልማት አሸንፈዋል። መምህሩ ድሀ ተማሪዎችን ከደመወዛቸው በመቀነስ ጭምር ያግዙ ነበር።
[ "በኬንያ በአንድ ገጠር ውስጥ ሳይንስ አስተማሪ የሆኑት ፒተር ታፒቺ የዓለም ምርጡ አስተማሪ ተብለው ወደ 30 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የገንዘብ ሽልማት አሸንፈዋል። መምህሩ ድሀ ተማሪዎችን ከደመወዛቸው በመቀነስ ጭምር ያግዙ ነበር።" ]
መምህር ፒተር ታፒቺ የ2019 የዓለም የምርጥ አስተማሪነት ውድድርን ነው ያሸነፉት። ጥቂት መጻሕፍት ባሉበትና በተማሪዎች በተጨናነቁ ክፍሎች እያስተማሩ ተማሪዎቻቸው ለመርዳት ያሳዩት ትጋት ብልጫን አስገኝቶላቸዋል። እኚህ መምህር ልዩ የሚያደርጋቸው ታዲያ የደመወዛቸውን 80 እጅ ለተቸገሩ በተለይም ወላጅ አልባ ለሆኑ ተማሪዎቻቸው የደንብ ልብስና መጽሐፍ መግዣ መስጠታቸው ነው። • ሴት ተመራቂዎች ለምን ሥራ አያገኙም? መምህሩ ፕዋኒ መንደር፣ ናኩሩ አውራጃ በሚገኘው ከሪኮ ሚክስድ ዴይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር የሚያስተምሩት። ተማሪዎቻቸውንም «የወደፊቱ ተስፋ በሳይንስ ነው፤ ጊዜው የአፍሪካ ነው» በሚል ያበረታቱ ነበር። የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የተካሄደው በዱባይ ሲሆን ለዚህ ሽልማት ከ179 አገራት አስር ሺ የሚሆኑ መምህራን እጩ ነበሩ። የመምህሩን ያልተጠበቀ ድል ተከትሎ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ኡሁሩ ኬንያታ የእንኳን ደስ ያለዎት መልእክትን አስተላልፈዋል። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? • በእርግጥ የአብራሪዎቹ ስልጠና ከአደጋው ጋር ይያያዛል?
xlsum_amharic-train-221
https://www.bbc.com/amharic/news-41696873
"የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረትን እናጠፋለን ብለን አልሸባብን ፈጠርን"
በሶማሊያ አሰቃቂ የሚባለውን የቦምብ ፍንዳታ፤ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ለሶማሊያ የሚሰጠው ድጋፍ መቀነሱ እንደ አንድ ምክንያትነት ያነሱት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ-ማርያም ደሳለኝ ናቸው።
[ "በሶማሊያ አሰቃቂ የሚባለውን የቦምብ ፍንዳታ፤ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ለሶማሊያ የሚሰጠው ድጋፍ መቀነሱ እንደ አንድ ምክንያትነት ያነሱት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ-ማርያም ደሳለኝ ናቸው።" ]
በሞቃዲሾ በቅርቡ የደረሰው ፍንዳታ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከፓርላማው የተነሱ ጥያቄዎችን በመለሱበት ወቅት ነው የተናገሩት። የኢትዮጵያ መንግስት በሶማሊያ የነበረው ጣልቃ ገብነት ቢተችም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አልሻባብን በመዋጋትና መንግስት አልባ በነበረቸው ሶማሊያም መንግስት እንዲመሰረት ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተችም ተናግረዋል። "ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ለሶማሊያ የሚሰጠውን ድጋፍ ነፍጎናል፤ ሰላምንና እርጋታን ለመፍጠር የተሰማራውን የአፍሪካ ህብረት ሰላማዊ አስከባሪ ኃይል ሰራዊት ቁጥሩ እንዲቀንስ ቢደረግም እኛ በራሳችን በጀት እየሰራን ነበር አሁንም አጠናክረን እንቀጥላለን። "ብለዋል። የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት የፈረሰው አማፂያን የሲያድ ባሬን መንግሥት ሠራዊት አሸንፈው የበላይ ሆኖ ሃያል ሆኖ የወጣ ኃይል በጠፋበት ጊዜ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሃገሪቱ መንግሥት ኣልባም ሆና ከ20 ዓመታት በላይ ዘልቃለች። በሶማሊያ መንግሥት ለመመስረት በተለያዩ ሃገራት አደራዳሪነት በርካታ የሰላም ሂደት ሙከራዎች ተደረገው ነበር። የተባበሩት መንግሥታት፣ አውሮፓ ኅብረትና የአፍሪካ ኅብረት ከሰላም ሂደቶቹ ጀርባ ነበሩ። የዕርቅ ሂደቶቹ የተለያየ መልክ የነበራቸው ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ የአደራዳሪዎቹን ሃገራት ብሔራዊ ጥቅም መሰረት ያደረጉ እንደነበሩ የፖሊቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። በኢትዮጵያ የተደረገው ተደጋጋሚ የሰላም ሂደት በንፅፅር የተሳካ እነደነበር ይነገራል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕውቅና ያለው ፌደራላዊ የሽግግር መንግስት ለማቋቋምም ተችሏል። ባለፈው ዓመት በምርጫ ለመጣው መደበኛ መንግሥትም መሰረት ሆኗል። አሁንም ሶማሊያ የጦር ቀጠና እንደሆነች ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መረጋጋትን እየፈጠርን ነው በሚሏት ሶማሊያ የሃገሪቱን የደህንንት ችግር በዘላቂነት ከመፍታት አንፃር ግን የኢትዮጵያ ሚና እንዴት ይታያል? ታሪካዊ ቁርሾ ኢትዮጵያ የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረትን ለመቆጣጠር ብቸኛው አማራጭ ሠራዊቷን ወደ ሶማሊያ ማስገባት ነበር ወይ? ለሚለው ጥያቄ የአፍሪካ ቀንድ የታሪክ፣ የግጭቶችና የደህንነት ተንታኝ የሆኑት ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሰ ሲመልሱ በቀጥታ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መፈፀም አደገኛነቱን ያስረዳሉ። በተለይም ኢትዮጵያና ሶማሊያ ካላቸው የታሪክ ቁርሾ አንፃር የኢትዮጵያ ሠራዊት ሶማሊያ ውስጥ ገብቶ በቋሚነት መንቀሳቀሱ ለእስላማዊ አክራሪ ቡድኖች ከፍተኛ መነቃቃትን እንዲሁም ትልቅ ካርድ የመዘዙበት ጉዳይ ነው። "የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረትን እንደ ሃገር እናጠፋለን ብለን ገብተን አልሻባብን ነው የፈጠርነው" የሚሉት ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሰ፤ ታሪኩ ተቀይሮ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር፤ ክርስትና ከእስልምና ጋር የሚያደርጉት ጦርነት ተደርጎ መልኩ ተቀይሯል ይላሉ ። የኢትዮጵያ ሰራዊት በሶማሊያ በተለያዩ ጊዜያት ሶማሊያን እንደ መነሻ አድርገው አካባቢውን ለማተራመስ የሞከሩ እስላማዊ ቡድኖች እንደነበሩ የሚናገሩት ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሰ አል ኢትሃድ አል ኢስላሚያ የተባለውን ቡድን ያስታውሳሉ። "የእስልምና ፍርድ ቤቶች ኅብረት ወይም አልሸባብ ከመምጣታቸው በፊት ሶማሊያ ውስጥ የፀጥታ ስጋት በነበረባት ወቅት ኢትዮጵያ ሠራዊቷን ማስገባቷ አዲስ ነገር አይደለም" ይላሉ ፕሮፌሰር መድሃኔ። ከዚያም ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ሶማሊያን በተመለከተ፤ የተረጋጋች ሶማሊያ መኖሯ ለኢትዮጵያ ደህንነት እንደሚጠቅም ቢታመንም የአክራሪ እስላማዊ መንግሥት ወይም ቡድን ቁጥጥር እንዲኖር ግን አትሻም። በተቃራኒው የሶማሊያ ፖለቲካ ተንታኞች "ኢትዮጵያም ትሁን ኬንያ የተረጋጋች ሶማሊያን ማየት አይፈልጉም" ቢሉም ፕሮፌሰር መድሃኔ፤ ይህን ካለው ታሪካዊ ቁርሾ ጋር የተያያዘ ነው ይላሉ። "ይሄ አስተሳሰብ በሶማሌ ብሄርተኞች በኩል በከፍተኛ ሁኔታ ነው የሚንፀባረቀው፤ እያደገ ከመጣው የደህንነት ትንተና ጋር በፍፁም አይገናኝም" ይላሉ። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት በቀድሞ ጊዜ ድንበርን ብቻ ማስጠበቅ የነበረው ተቀይሮ በሃገሮች መካከል የህዝብና የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ በመኖሩ ሁኔታውን ሊለውጠው ችሏል። ከዚህም በተጨማሪ አካባቢው በቀላሉ ለግጭት ተጋላጭ በመሆኑ ነገሩ በቸልታ እንደማይታይም ይናገራሉ። ፕሮፌሰር መድሃኔ "የተዳከመች ሶማሊያ ለኢትዮጵያ ትጠቅማለች የሚል አስተሳሰብ የለም፤ ይህ ጊዜ ያለፈበት አመለካከት ነው" ይላሉ። የአፍሪካ ህብረት ሰላማዊ አስከባሪ ኃይል ሰራዊት በሶማሊያ አቅመ ቢሱ የሽግግር መንግሥት የሽግግር መንግሥቱ በዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ከማግኘቱ ውጪ ራሱንና መላውን የሶማልያ ግዛት ለመከላከል የሚያስችል የፖለቲካ ብቃትም ወታደራዊ አቅምም አልነበረውም። በመሆኑም በዳሂር አዌይስ የሚመራው የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረት የሃገሪቱ ደቡባዊ ክፍልን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በኢትዮጵያም ላይ ጅሃድን ማወጁ ይታወሳል። ኅብረቱ "ታላቋ ሶማሊያ" የሚለውን የቆየ አስተሳሰብ ማቀንቀን ጀምሮ የነበረ ሲሆን፤ በተለይ በኢትዮጵያ የሚገኘውን አዋሳኝ የኦጋዴን አካባቢን ለማስመለስም ዝቶ ነበር። በዚህም ምክንያት፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ በወቅቱ ከሽግግር መንግሥት በቀረበው ግብዣ መሰረት፤ ወደ ሶማልያ ጣልቃ ለመግባት በፓርላማ ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት ከተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በኩል ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በሶማሊያ ላይ ብዙ ጥናቶችን ያደረገችው ቅድስት ሙሉጌታ "ዘ ሮል ኦፍ ሪጂናል ፓወርስ ኢን ዘ ፊልድ ኦፍ ፒስ ኤንድ ሴኩሪቲ ዘ ኬዝ ኦፍ ኢትዮጵያ" በሚለው ፅሁፏ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግሮች፣በአገሪቷ ውስጥ ፖለቲካዊ መስማማቶች ቢጎሉዋትም ከድንበሯ አልፋ \ በሌሎች አገራት በምታደርገው ተፅእኖ የኃያል አገርነትን ሚና ትጫወታለች። ኢትዮጵያ ያላት ጠንካራ የሰራዊት ሃይል፣ከፍተኛ የህዝብ ቁጥሯ፣ በአንፃራዊነት ያላት የአገሪቱ መረጋጋትና የዲፕሎማሲያዊ ጥንካሬ አገሪቷ በክልሉ ላይ የምትጫወተውን ሚናና ቦታ እንዲሁም የክልሉን ሰላምና የደህንነት ጅማሮዎችን እንድትመራ አስችሏታል በማለት ፅሁፉ ያትታል። ከእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረት በኩል "ግልፅና ወቅታዊ ስጋት" ተደቅኖብናል በማለት ለማሳመን ቢሞክሩም፤ በተለይ በወቅቱ የምክር ቤቱ አባል የነበሩት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ጣልቃ ገብነቱ በኢትዮጵያ ላይ 'ዘላቂ ጥላቻን' ሊያስከትል እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀው ነበር። ከኅብረቱ ጀርባም በርካታ ሃብታም የአረብ ሃገራት እንደነበሩ በመተንተን፤ ኢትዮጵያ የማትወጣው ጦርነት ውስጥ እየገባች እንደነበርም የተለያዩ ስጋቶች ሲቀርቡ ነበር። አሜሪካም ከጣልቃ ገብነቱ ጀርባ እንደነበረች ቢነገርም፤ በወቅቱ ሾልኮ የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው አሜሪካ ስጋቷን ለኢትዮጵያ መንግሥት ገልፃ ነበር። በተለይ አፍሪካ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር (አፍሪኮም) የሚመሩት ጀነራል ጆን አቢዛይድ "የቸኮለ ውሳኔ" በማለት የጣልቃ-ገብነቱን አላስፈላጊነት ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ መምከራቸው ይነገራል። በተቃራኒው የኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነት የአሜሪካ ፖሊሲ ቅጥያ ተደርጎ እንደታየ የሚያስረዳው የቅድስት ፅሁፍ የአሜሪካ መንግስት ራሱ በኢትዮጵያ ደህንነት መረጃዎች ጥገኛ እንደሆነም ይጠቁማል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከውጭም ውስጥም ከባድ ተቃውሞ ይግጠማቸው እንጂ በድምፅ ብልጫ ሃሳባቸውን በምክር ቤቱ አስፀድቀው ወታደራዊ ኃይል ወደ ሶማሊያ መላክ ችለዋል። ከኅብረቱ ጀርባ ከኢትዮጵያ ግብፅንና ኳታርን ጨምሮ በርካታ ሃገሮች እንደበሩበት ሲታሙ፤ የኤርትራ መንግሥትም ኢትዮጵያን ለማጥቃት ከህብረቱ ጀርባ አለ የሚል ክስም ቀርቦ ነበር። ኤርትራ ብታስተባብልም የተባበሩት መንግሥታት ኮሚቴ ባደረገው ማጣራት የኤርትራ መንግሥትን ጣልቃ ገብነትን ማረጋገጥ መቻሉን ባቀረበው ሪፖርት መግለፁ ይታወሳል። ወታደራዊው ዘመቻና መዘዙ በ2001 ዓ.ም የሁለት ዓመት ቆይታውን አጠናቆ ወደ ሃገሩ የተመለሰው የኢትዮጵያ ሠራዊት፤ የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረትን በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ማፈራረስ ችሎ ነበር። ነገር ግን የኅብረቱ የወጣቶች ክንፍ እንደሆነ የሚነገርለት አልሸባብ በመባል የሚታወቀው አክራሪ ቡድን ማንሰራራቱ ይታወቃል። ኢትዮጵያም ለሁለተኛ ጊዜ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ አዝምታ አልሸባብን መውጋት ከጀመረች በኋላ ሌሎች ሃገራትም በአፍሪካ ኅብረት በኩል ወደ ሶማሊያ ገብተዋል። አልሸባብ ከቀደመው እስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅበረት ቡድን የባሰ ፅንፈኛ እንደሆነ ይነገርለታል። ፕሮፌሰር መድሃኔም የቡድኑ አፈጣጠር በቀጥታ ከኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነት ጋር ያገናኙታል። ዛሬ ከሃገሪቱ ጠፍቷል ሲባል፤ ነገ በዋና ከተማዋ ሶማልያ ከባድ ጥቃት ሲፈፅም ይስተዋላል። ጨርሶ ማጥፋት ይቅርና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መጥቶ በቅርቡ በሞቃዲሾ የተፈፀመውን ዓይነት የሽብር ድርጊት በጎረቤት ሃገራት ጭምር ለመፈፀም በቅቷል። ሶማሊያውያን ከሁሉም አቅጣጫ በሚካሄዱ ዘመቻዎች እና በሚሰነዘሩ ጥቃቶች ከባዱን ዋጋ ሲከፍሉ ኖረዋል። የሂውማን ራይትስ ዋች ሪፖርት በሚሊየን የሚቆጠር ህዝብ መፈናቀሉን እንዲሁም የኢትዮጵያ ሠራዊትን ከሽግግሩ መንግስት ጋር በመተባበር በተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይከሳል። የወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መዘዙ ሰፊ ነው የሚሉት ፕሮፌሰር መድሃኔ "ሶማሊያዊያን እራሳቸው የማያደርጉትን በጎረቤት አገር በተለይም ደግሞ ታሪካዊ ቁርሾ ባለበት ሁኔታ የሚደረግ ሃገር የመገንባትና የሰላም ግንባታ ጥረት ብዙ ኪሳራዎች አሉት" ይላሉ። የቅድስት ፅሁፍ እንደሚያትተውም ኢትዮጵያ ራሴን ለመከላከል ነው ብትልም እንደ "ወራሪ" ነው የታየችው፤ ጣልቃ መግባቷ ስህተት እንደነበረና ከዚህ በፊት አልኢትሀድ ላይ እንዳደረገችው የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት የያዛችውን ቦታዎች ለይታ መምታት ሰራዊቱንም ማዳከም ትችል ነበር። የተለያዩ የሶማሊያ የፖለቲካ ተንታኞችም የአውሮፓ ኅብረት፣ አሜሪካ እንዲሁም ሌሎች ሃገራት በየዓመቱ ለአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል የሚያደርጉትን በቢሊየኖች ዶላር የሚቆጠር መዋዕለ-ንዋይ ድጋፍ የሶማሊያን ሰራዊት ለመገንባት ቢፈስ ለውጥ ይመጣል ይላሉ። ''የጦር ሠራዊቱን ለማሰልጠን የተለያዩ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም መፍትሄ አላመጡም ባጠቃላይ ችግሩ ጣልቃ ከመግባቱ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው።" ይላሉ። የሶማሊያ ምርጫ "ሁሉም በውጭ ጣልቃ ገብነት የመጡ የሰላምም ይሁኑ የመንግሥት አወቃቀር አማራጮች የሶማሊያን ባህላዊና ታሪካዊ እውነታዎችን ያገናዘቡ አይደሉም" የሚሉት ፕሮፌሰር መድሃኔ፤ በተጨማሪም "እነዚህ መንግሥታትም ይሁኑ ተቋማት እነሱ የሚያዉቁትን ምዕራባዊ የመንግሥት አወቃቀር በፍጥነት ለመጫን ተሞክሯል" ይላሉ። በሶማሊያውያን ተነሳሽነት ቀስ በቀስ እያደገ ሳይሆን በአቋራጭ ማዕከላዊ መንግሥት ለመመስረት ቢሞከርም መድሃኔ እንደሚሉት የትኛውም የሶማሊያ የፖለቲካ ቡድንም ሆነ ሃይል ማዕከላዊ መንግሥት ለመመስረት አቅም እንደሚያጥረው ያስረዳሉ። እንደ መፍትሔ የሚያስቀምጡትም በየአካባቢው የተፈጠሩ የሰላም ዞኖችና አካባቢዎችን በማጠናከር ዘላቂ የፌደራል መንግሥትን ማምጣት አለመቻሉን እንደ እክል ያዩታል። የሶማሊያ አለመረጋጋት እንዲቀጥል የሚፈልግ አካላት ይኖሩ ይሆን? ሶማሊያን ተረጋግታ እንደሃገር እንድትቆም ብዙ መንግሥታዊ፣ አህጉራዊና ሌሎች ተቋማት በቢሊዮን የሚቆጠር መዋዕለ-ነዋይ እያፈሰሱበት ቢሆንም ችግሩ ሊፈታ አልቻለም። "በሶማሊያ ግጭት የተነሳ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ፍላጎቶች ተፈጥረዋል። የተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶችም በግጭቱ ተጠቅመዋል። በዚህም የተነሳ የተለያዩ ኃይሎች ግጭቱና ጦርነቱ እንዲቀጥል ይፈልጋሉ"ፕሮፌሰር መድሃኔ ይላሉ። የኢትዮጵያ ሠራዊት በሃገሪቷ ባሉ አለመረጋጋቶችም ይሁን በተለያዩ ምክንያቶች ከሶማሊያ ወጥቶ ኢትዮጵያ ያላት ሚና ቢቀንስም የኬንያ፣ ኡጋንዳና ቱርክ የመሳሰሉት ሃገራት ሚና በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በሶማሊያ ላይ ያላት ሚና እንደ ሃገር ከፍተኛ ባይሆንም፤ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ወታደራዊ ዘመቻዎች ሳቢያ ሶማሊያውያን ለኢትዮጵያ አሉታዊ ዕይታ እንዲኖራቸው አድርጓል። ለዚህም ማሳያ በቅርቡ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ተፎካካሪዎች ለቅስቀሳቸው ፀረ-ኢትዮጵያ እንዲሁም ጣልቃ የገቡ ኃይሎችን ማዕከል አድርገው ነበር። ፕሮፌሰር መድሃኔም እንደ መፍትሔ የሚያስቀምጡት ሶማሊያውያን በራሳቸው ተነሳሽነት ወደ እራሳቸው ባህል በመመልከት በድርድር ባህላቸው፤ ከማዕከላዊ መንግሥት ወደታች ያተኮረ ሳይሆን ከታች ወደ ማዕከላዊ መንግሥት የሚመጣ ማዋቀር መገንባት ያስፈልጋቸዋል ይላሉ።
xlsum_amharic-train-222
https://www.bbc.com/amharic/news-48735439
ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ
የኢፌዲሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን በትናንትናው ጥቃት መገደላቸውን ተነገረ።
[ "የኢፌዲሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን በትናንትናው ጥቃት መገደላቸውን ተነገረ።" ]
መቀሌ የሚገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር ድምፂ ወያነና የትግራይ ቴሌቪዥን የጄኔራል ሰዓረን መገደል ዘግበው የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሃዘን መግለጫ መልእክትንም አቅርበዋል። •የመፈንቅለ መንግሥቱና የግድያ ሙከራዎች •የከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት ሥዕላዊ መግለጫ •ጓድ መንግሥቱ እንባ የተናነቃቸው 'ለት ከጄኔራል ሰዓረ በተጨማሪ ጄኔራል ገዛኢ አበራም ህይወታቸው ማለፉን በተጨማሪ ዘግበዋል። በአማራ ክልል በተሞከረው መፈንቅለ መንግሥትም ሁለት የክልሉ ባለስልጣናት መሞታቸው የተገለፀ ሲሆን ማንነታቸው እስካሁን አልታወቀም።
xlsum_amharic-train-223
https://www.bbc.com/amharic/news-53237140
የሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በአዳማ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ አምስት ሰዎች ሞቱ
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በአዳማ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ አምስት ሰዎች በጥይት ተመትተው መሞታቸውን የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር መኮንን ፈይሳ ለቢቢሲ አረጋገጡ።
[ "የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በአዳማ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ አምስት ሰዎች በጥይት ተመትተው መሞታቸውን የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር መኮንን ፈይሳ ለቢቢሲ አረጋገጡ።" ]
የአዳማ ከተማ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ግለሰቦቹ ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት መሞታቸውን ተናግረዋል። ዶ/ር መኮንን አክለውም 75 ሰዎች ቆስለው በሆስፒታሉ እንደሚገኙ የገለፁ ሲሆን ከአርሲ ዴራ ደግሞ 19 ሰዎች ተጎድተው ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸውንና የተወሰኑት በእሳት ቃጠሎ መጎዳታቸውን አስረድተዋል። በአዳማ በነበረ ተቃውሞ የመንግሥት ህንጻዎች መቃጠላውን የቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተያያዘ ዜና በጭሮ በነበረ ተቃውሞ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን የከተማዋ ሆስፒታል ምንጮች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በአዳማ ከተማ ከምሳ ሰዓት በፊት የነበረው አለመረጋጋት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ወዲህ ጋብ ማለቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢበሲ ገልፀዋል። የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ መገደልን ተከትሎ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በኦሮሚያ አንዳንድ ከተሞች ተቃውሞ የተቀሰቀሰ ሲሆን በዚህም የተነሳ የተለያዩ ጉዳቶች በሰውና በንብረት ላይ መድረሱ እየተሰማ ነው።
xlsum_amharic-train-224
https://www.bbc.com/amharic/news-55968845
አስተያየት፡ ከኢትዮጵያ እስከ የመን፡ ረሃብ ተከስቷል ብሎ የማወጅ ፈታኝነት
በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በክልሉ ረሃብ ተከስቷል የሚሉ በርካታ ሪፖርቶች ሲወጡ ቆይተዋል።
[ "በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በክልሉ ረሃብ ተከስቷል የሚሉ በርካታ ሪፖርቶች ሲወጡ ቆይተዋል።" ]
በባለፈው ሳምንት ረቡዕ በተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በክልሉ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ እየከፋ እንደሆነና በአሁንም ወቅት በግጭቱ ለተጎዱ ነዋሪዎች እርዳታ ማድረስ እንዳልተቻለ ገልፀዋል። በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ እንዲሁ ይህንኑ ድርጅት ይመሩ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የኖርዌይ ስደተኞች ካውንስል ዋና ፀሃፊ የሆኑት ጃን ኢግላንድ "በረድዔት ድርጅቶች በሰራሁባቸው አመታት እንዲህ ያለ የተንጓተተ አሰራር አይቼ አላውቅም። በአፋጣኝ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታውን ማድረስ አስቸጋሪ ሆኗል፤ ረዥም ጊዜ እየወሰደ ነው" በማለት አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል። ጃን ኢግላንድ አክለውም "አጠቃላይ የረድዔት ድርጅቶች የችግሩን ክብደት አጉልተው አለማሳየቻው ውድቀት ነው" ብለዋል። በሌላ ቋንቋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ያለውን ሁኔታ "ረሃብ ተከስቷል" ይለዋል፤ ከሆነስ ወቅቱ መቼ ይሆን? በግጭት በተጎዳችው ትግራይ፣ ያለው የግብርና ሁኔታ ከዚህ ቀደምም ከእጅ ወደ አፍ ቢሆንም በባለፈው አመት ደግሞ የተከሰተው የአንበጣ ወረርሽኝ ሁኔታውን አክፍቶታል። በመስከረም ወር ላይ በነበረው አለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ግምገማ መሰረት ከክልሉ 7 ሚሊዮን ነዋሪዎች 1.6 ሚሊዮኑ ያህሉ በረድዔት እርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ ነበሩ ተብሏል። በፌደራል መንግሥቱና በህወሃት መካከል የነበረው የግንኙነት መሻከር ወደማይታረቅ ደረጃ ላይ ደርሶ በክልሉ የነበረው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈፅሟል በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወታደራዊ ዘመቻ ማወጃቸው የሚታወስ ነው። ግጭቱም የተነሳው ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም ነው። 60 ሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ተፈናቃዮች በስደት ሱዳን ውስጥ ይገኛሉ ለአመታት ገዢ የነበረውን ኢህአዴግን በማፍረስ ውህድ ፓርቲ መፈጠሩን ህወሃት ተቃውሞ ነበር። በፌደራሉ መንግሥት እና በህወሃት መካከል የነበረውን ቅራኔ አስፍቶታል። ቅራኔውም ወደ ወታደራዊ ግጭት አምርቶ አሁን ያለውን መልክ ይዟል። በዚህ ጦርነት ላይ የኤርትራ ሰራዊት ተሳትፈዋል የሚሉ ሪፖርቶች ወጥተዋል። በቅርቡም አሜሪካን ጨምሮ የተባበሩት መንግሥታት ለሳምንታት ሲባል የነበረውንና የኤርትራ ጦር በክልሉን መኖሩን አምነዋል። የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል በአስቸኳይ እንዲወጡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) መጠየቁ ይታወሳል። የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት በተደጋጋሚ የኤርትራ ጦር አልተሳተፉም በማለት ይናገራሉ። በክልሉ አብዛኛው ክፍል አሁንም ቢሆን የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት አለመኖሩን ተከትሎ ከአለም ጋር ተቆራርጦ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የረድዔት ድርጅቶች ሰራተኞቻቸውን እየላኩ ሲሆን በክልሉ የሆነውና እየሆነ ያለውን ነገር ይረብሻል እያሉ ነው። ሆሰፒታሎች ተዘርፈዋል፣ መዳን በሚችሉ በሽታዎችና ረሃብ ምክንያት ነዋሪዎች መሞታቸው፣ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ምግብም ሆነ ገንዘብ ለማግኘት አለመቻላቸው በፍራቻ እንዲዋጡ አድርጓቸዋል የሚሉ ዜናዎች እየተሰሙ ነው። ስልክ ማግኘት የቻሉ የትግራይ ነዋሪዎች መጠነ ሰፊ የሆነ ዘረፋ፣ የእህል መቃጠልና መውደም እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እርዳታ ሊደርሳቸው አለመቻሉን ይናገራሉ። ሁለት ሚሊዮን አካባቢ የሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል ከሰሞኑም በክልሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሊሞቱ እንደሚችሉ አንድ የመንግሥት ባለስልጣን ማስጠንቀቃቸውን ከረድዔት ድርጅቶችና ከተባበሩት መንግሥታት ሰራተኞች ጋር ታህሳስ 30፣ 2013 ዓ.ም ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ የሰፈረ ፅሁፍ አመላክቷል። በዚሁ ሪፖርት መሰረት በችግሩ ተጠቂ ከሆኑት መካከል 99 በመቶ መድረስ አልተቻለም ተብሏል። በረድዔት ድርጅቶች መረጃ መስረት በክልሉ 4.5 ሚሊዮን ህዝብ፣ 60 በመቶ የሚሸፍነው ህዝብ በግጭቱ ተጎድቷል፤ እርዳታም ያስፈልገዋል ይላሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ አኃዙ የተጋነነ ነው በማለት ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ በቁጥጥር እንዳዋለው ይናገራል። እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ነዋሪዎች 2.5 ሚሊዮን እንደሆኑና ሁሉንም በሚባል ሁኔታ መድረስ እንደተቻለም አስታውቋል። የኢትዮጵያ ረሃብ የመካድ ታሪክ በዚህ ረሃብ ሊከሰት ይችላል በሚሉ ሪፖርቶች በተጥለቀለቁበት መካከል የኢትዮጵያ መንግሥት ዋነኛ ለጋሹን የአውሮፓ ህብረትን ለትግራይ ድንገተኛ እርዳታ ማድረስ ችግር ጊዜያዊ ነው፤ ህብረቱ ለአገሪቷ የሚሰጠውን የልማት እርዳታ ሊቀጥልበት ይገባል ይላል። ህብረቱ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የ107 ሚሊዮን ዶላር የበጀት ድጋፍን የሰብዓዊ ርዳታ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች ያለ አንዳች ገደብ ዕርዳታ ማቅረብ እስኪችሉ ድረስ አግዷል። ከዚህ ቀደም ህብረቱ ለኢትዮጵያ ከመደበው የበጀት ድጋፍ ውስጥ 90 ሚሊዮን ዩሮ (110 ሚሊዮን ዶላር) እንዲዘገይ ያሳለፈው ውሳኔ በተመለከተ እርምጃው በተሳሳተ ግምገማ ላይ የተመሰረተ ነው ሲል ቅሬታውን መግለፁ የሚታወስ ነው። ሆኖም የኢትዮጵያ መሪዎች ረሃብን የመደበቅ ታሪክ አላቸው። በአውሮፓውያኑ 1973 የጆናታን ዲምቢልቢ ፊልም አገሪቷ ያጋጠማትን መጠነ ሰፊ ረሃብ ከማጋለጥ በተጨማሪ በወቅቱ መሪ በነበሩት አፄ ኃይለ ስላሴ የረሃቡ አስከፊነት ከአለም እንዴት እንደተደበቀ አሳየ። በረሃቡም 200 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሞተዋል። ያ ሁሉ ህዝብ በተራበበት ወቅት ንጉሱ ያሳዩት ቸልተኝነት እንዲሁም ቅንጡ ህይወት መቀጠል በርካቶችን ወደ ጎዳና አውጥቷል። መዘዙ ስማቸውን ከማጉደፍ በላይ በቀጣዩ አመት ለውድቀታቸውና የስልጣን ማክተሚያቸው ምክንያት ሆነ። በ1977 ትግራይና ወሎ የሌላ ረሃብ ማዕከል ነበሩ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በየጊዜው የሚከሰተው ድርቅና በተጨማሪ ጦርነት ነበር። በዚህ ዘግናኝ ረሃብም ከ600 ሺህ- 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን አጥተዋል። በወቅቱ ኢትዮጵያን ይመራ የነበረው የደርግ መንግሥት ረሃብ አልተከሰተም በማለት ቢፀናም በሚካኤል በርክና መሃመድ አሚን ይመራ የነበረው የቢቢሲ ፊልም ቡድን ያለውን አሰቃቂ ሁኔታ አጋልጦታል። የረሃቡ ዜና ታዋቂው ሙዚቀኛ ቦብ ጌልዶፍ 'ዱ ዜይ ኖው ኢትስ ክሪስማስ' የሚለውን ዘፈኑን እንዲሰራ መነሻ ነበር። አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለእርዳታ እንዲነሳ በከፍተኛ ሁኔታ ቀስቅሷል። ረሃቡ የወታደራዊውን መንግሥት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በአገር ውስጥ እንዲሁም ከአገር ውጭ ስማቸው እንዲጎድፍ አድርጎታል። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ የረሃብና የችጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ሆና መሳሏ ኢትጵያውን በሌላው አለም ዘንድ ለማኝ ሆነው መታየታቸው አስከፋቸው። በአውሮፓውያኑ 2001 እንዲሁ በህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ዘመን በአገሪቱ ደቡባዊ ምስራቅ ክፍል ረሃብ ተከስቷል የሚለው አወዛጋቢ ጉዳይ ነበር። በአካባቢው አማፂ ቡድን ጋር መንግሥት እየተፋለመ የነበረበት ወቅት ሲሆን ከ20 ሺህ-25 ሺህ ሰዎች መንግሥት " አፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታ" ብሎ በጠራው ችግር ጋር በተያያዘ ህይወታቸው አልፏል። በባለፉት አስርት አመታት የአለም አቀፉ ረድዔትና የሰብዓዊው ስርዓት መጠነ ሰፊ ሆኗል፤ በበለጠ የተደራጀ መልክ ይዟል። በአህጉሪቷ ከህፃናት የተመጣጠነ (አልሚ) ምግብ ቁጥጥርና፣ ምግብ አቅርቦት ጋር በተያያዘ የተራቀቀ ስርዓት የተዘረጋ ሲሆን ይሄም የምግብ እጥረት ሲያጋጥም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እንዲኖረውና ረሃብ እንዳይከሰት ለመከላከል በወጠነ መልኩ ነው እየተሰራበት ያለው። ከአምስት አመታት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥትና የውጭ ለጋሾች በአገሪቷ ላጋጠመው ብሄራዊ ድርቅ ምላሽ በመስጠት 10.2 ሚሊዮን ህዝብ አስፈላጊው እርዳታ እንዲደርሳቸው አድርገዋል። እንደ ቀድሞው ረሃብ ሲከሰት ምግብ ማደል ሳይሆን ነዋሪዎች ያላቸውን ከብት፣ በግና ሌሎች እንስሳቶች ከመሸጣቸው በፊት እርዳታው በየመንደራቸው እንዲደርስ ሆኖ ስርዓቱ ተዋቅሯል። አርሶ አደሮቹ ችግራቸው ተቀርፎ በቀጣዩ አመት መሬታቸው ላይ እህል እንዲዘሩና እንዳይሰደዱ አስችሏል። ነገር ግን በ2015-2016 የተከሰተው አፋጣኝ እርዳታና በአሁኑ ወቅት ያለውን የሚለዩዋቸው ሁለት አንኳር ነጥቦች አሉ፤ መረጃና ፖለቲካ። በአሁኑ ወቅት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ረሃብ ተከስቷል ብሎ ለማወጅ በቂ መረጃ የለም። ከ15 አመታት በፊት የረድዔትና የሰብዓዊ ጉዳይ ሰራተኞች የምግብ ደህንነት መጓደልን ለመለካት በተባበሩት መንግሥታት የተደገፈ ደረጃውን የጠበቀ መለኪያን ሰርተዋል። የተቀናጀ የምግብ ደህንንትን ለመለካት በደረጃ የሚከፋፍለው 'integrated food security phase classification' (IPC) የተሰኘ ስርዓት ነው ያመጡት። ይህ ስርዓት አምስት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን ከዝቅተኛው የምግብ ደህንነት መጓደል ወደ ከፋው ረሃብ መከሰት ያለውን የሚለካ ነው። አይፒሲ መደበኛ የሚባሉ ጠቋሚዎችን ለምሳሌ የምግብ ፍጆታ፣ በምግብ እጦት የተሰቃዩ ህፃናትና የተከሰተውን ሞት በማጥናት ደረጃውን ይለካል። መረጃ የለም፤ ረሃብ የለም ረሃብ ተከስቷል ወይ ለሚለው የተሰጠው ይፋዊ ትርጉም በየቀኑ ከምንጠቀምበት በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን አደጋ ላይ በሚጥል የምግብ እጦት ተቸግረዋል ከሚለው የበለጠ ግልፅ ነው። ነገር ግን ይህንን ችግር ለመቅረፍ የአይፒሲ ስርዓት ሌላ መዋቅር ዘርግቷል። በአሁኑ ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ረሃብ ተከስቷል ለማለት የተጠናቀረ ግልፅ መረጃ ያስፈልገዋል። መንግሥታት ረሃብ ተከስቷል የሚለው ሁኔታ ስማቸውን እንዳያጠለሸው መረጃዎችን በመደበቅ ወይም በማጭበርበር እቅዳቸውን የሚያሳኩ ሲሆን በዚህም የረሃቡን አስከፊነት ዝቅ ያደርጉታል። ከረሃብ ዝቅ ባለው ደረጃ ያሉት "ቀውስ" ፣ "አፋጣኝ እርዳታ" ተብለው በሚመደቡትም ውስጥ የሰዎች ህይወት ይቀጠፋል፤ ምንም እንኳን ሂደቱ ዝግ ያለ ቢሆንም። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ቀውሶች በተከሰተባቸው ቦታዎች እንዲህ አይነት ፈተናዎች ተጋርጠውበታል። በየመን፤ የሳዑዲ ጥምር ኃይል፣ መንግሥትና የሁቲ ባለስልጣናት ረሃብ ተከስቷል በተባሉ አካባቢዎች እንዳይደርሱ የረድዔት ድርጅቶችን ከልክለዋል። በዚህም ምክንያት ድርጅቶቹ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ አልቻሉም። በግጭቱ የተጎዱት የየመን ትምህርት ቤቶች የተመጣጠነ (አልሚ) ምግብ እጥረት፣ የህፃናት ሞት፣ የምግብ ፍጆታ ጋር የተያያዘ መረጃ ከሌለ የምግብ ደህንነት መጓደል ስርዓትን የሚለካው የአይፒሲ ኮሚቴ ለጥንቃቄ ሲባል "አፋጣኝ እርዳታ" የሚያስፈልጋቸው በማለት ይመድባል። ረሃብ ተከስቷል ማለት አይችልም ምክንያቱም በአባሪነት መሪጃ ማቅረብ ስለማይቻል። በደቡብ ሱዳን መንግሥት የመረጃ ስብስብን ማቆም አልቻለም። ነገር ግን ታህሳስ ላይ በነበረው የአይፒሲ የምግግብ ግምገማ "ረሃብ ተከስቷል" የሚለውን ዝቅ ለማድረግ ጣልቃ ገብቷል። ሆኖም ረሃብ ተከስቷል የሚለው ትርጉም ሊያጨቃጭቀን አይገባም። በለንደን ስኩል ኦፍ ሃይጂን ኤንድ ትሮፒካል ሜዲሲን መረጃ መሰረት በደቡብ ሱዳን ከምግብ እጥረትና ግጭት ጋር በተያያዘ 380 ሺህ ሰዎች በባለፉት አምስት አመታት ሞተዋል። ነገር ግን ከዚህ ውስጥ 1 በመቶ የሚሆኑት የሞቱት ረሃብ ተከስቷል በተባለበት በዩኒቲ ስቴት ግዛት በ2017 ነው። የረድዔት ድርጅቶች የገቡበት አጣብቂኝ ሌላኛው ዋነኛው ችግር ፖለቲካ ነው። ለተከሰተው ከፍተኛ የምግብ እጥረትና ረሃብ ወታደራዊ ፖሊሲ ምክንያት ሲሆን የረድኤት ድርጅት ሰራተኞች መውጣት የሚቸገሩበት አጣብቂኝ ውስጥ ይገባሉ። እየደረሰ ያለውን ጥሰት ማውገዝና ከአገር ውጭ መባረር ወይስ በረሃቡ ወንጀል ተባባሪ ሆኖ ዝምታን መምረጥ። የኢትዮጵያ መንግሥት አሁንም አልፎ አልፎ ውጊያ መኖሩን አምኗል። ነገር ግን ግጭቱ ካለባቸው አካባቢዎች የሚወጡ ሪፖርቶች አንደሚያሳዩት ከፍተኛ የሆነው የትግራይ ገጠራማ ክፍል አሁንም ቢሆን የጦር ሜዳ እንደሆነ ወይም በህወሃት ቁጥጥር ስር መሆኑን ነው። በአለም አቀፉ የሰብዓዊ ህግ መሰረት ይህ ወታደራዊ ግጭት ነው እናም ወደ ሽምቅ ውጊያ የተመለሰው ህወሃት ከማጥቃት ወደ ኋላ አይልም። በግጭቱ የምግብ እጥረት ላጋጠመውና ለተራበው ህዝብ እርዳታ ለማድረስ ከህወሃት ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ድርድር ያስፈልጋል። በአንደኛው ወገን ተባባሪነት ብቻ በጭራሽ የሚሳካ አይሆንም። እስካሁን ድረስ ባለው ህወሃትም ቢሆን ተኩስ ለማቆምም ሆነ የረድዔት ድርጅቶች እንዲገቡ አልጠየቀም። ከዚህ ጋር ተያይዞ አማፂ ቡድኖች እርዳታውን አላግባብ በመጠቀም የራሳቸውን ሰራዊት ሊመግቡ ይችላሉ የሚለው ፍራቻ አለ። ለዚያም ነው አለም አቀፍ ተቆጣጣሪዎች አስፈላጊ የሚሆኑት። በትግራይ ያለው የምግብ እጥረትና ረሃብ ለረድዔት ድርጅቶቹ አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ከቷቸዋል። ስለ ቀውሱ ከባለስልጣናቱ የሚሰጠውን ይፋዊ መረጃ በመገዳደር በክልሉ ያላቸውን ውስንና መሰረታዊ ስራዎች አደጋ ውስጥ አለመክተት ይችላሉ ወይ? የሚለው ጥያቄ ሆኖባቸዋል። በረድዔት ሰራተኞች መካከል የተለመደ አባባል አለ፤ ለሰብዓዊ ቀውሶች ሰብዓዊ እርዳታ መፍትሄ አይደለም። በዋናነት የሚያስፈልገው የከፍተኛ አመራር ፖለቲከኞች ተግባርና ቁርጠኝነት ነው። በሁሉ ነገር በሚለያዩ ሶሪያና ኮንጎ በመሳሰሉ አገራት በተከሰቱ ቀውሶችና እንዲሁም በተለያዩ አገራት በተደጋጋሚ የሚከሰት ችግር በመሆኑ የተባበበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ወታደራዊ ግጭትና ረሃብን በተመለከተ ሪዞሉሽን 2417 የተባለ ሰነድን ከሶስት አመታት በፊት አፅድቋል። ሪዞሉሽን እስካሁን ድረስ በተግባር ላይ ባይውልም፣ ድርጅቱ በተደጋጋሚ እንደሚለው ረሃብን እንደ መሳሪያ መጠቀም እንደ ጦር ወንጀል ይቆጠራል። ከዚህም በተጨማሪ በሪዞሉሽኑ መሰረት ወታደራዊ ግጭቶች መጠነ ሰፊ የምግብ ደህንነት መጓደል ወይም ረሃብ የሚያስከስት ከሆነ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ የፀጥታው ምክር ቤትን ማሳወቅና ማስጠንቀቅ አለበት። ይሄንን ሪዞሉሽን አስተውሎ ላየው እንደ ትግራይ ክልል ባሉ የተከሰቱ ቀውሶችን እሳቤ ውስጥ በመክተት የፀደቀ ነው። ነገር ግን ለረድዔት ድርጅቶች ይህንን ሪዞሉሽን እንዳይጠቅሱም መደናገጥ አለ፤ ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ የኢትዮጵያን መንግሥት ማስቀየም አይፈልጉም። በትግራይ ክልል ባለው የረሃብተኞች፣ ህመምተኞችና ሞት ቁጥር አስተማማኝ ቁጥር ባይኖርም ነገር ግን እስካሁን በተረዳነው መሰረት ክፉኛ የሆነ ቀውስ እየተፈጠረ ለመሆኑ ማሳያ ነው። ፀሃፊው አሌክስ ዲዋል በአሜሪካ በሚገኘው በተፍትስ የፍሌቸር ስኩል ኦፍ ሎው ኤንድ ዲፕሎማሲ ዩኒቨርስቲ ፣ የዓለም አቀፉ የሰላም ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው።
xlsum_amharic-train-225
https://www.bbc.com/amharic/news-50231131
ቦይንግ ከተሳፋሪዎች ደህንነት ትርፉን አስቀድሟል ተባለ
የአሜሪካ ሴናተሮች ኩባንያው የተሳፋሪዎችን ደህንነት ከማረጋገጥ ይልቅ ትርፉን አስቀድሟል ሲሉ ቦይንግን የወነጀሉት የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሙ ዴኒስ ሙለንበርግ ከሴኔቱ የንግድ ቋማ ኮሚቲ ፊት ቀርበው ነገሮቸን ባብራሩበት ወቅት ነው።
[ "የአሜሪካ ሴናተሮች ኩባንያው የተሳፋሪዎችን ደህንነት ከማረጋገጥ ይልቅ ትርፉን አስቀድሟል ሲሉ ቦይንግን የወነጀሉት የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሙ ዴኒስ ሙለንበርግ ከሴኔቱ የንግድ ቋማ ኮሚቲ ፊት ቀርበው ነገሮቸን ባብራሩበት ወቅት ነው።" ]
ሴናተሮቹ ኩባንያው ትርፉን ብቻ በማስላት ቦይንግን ቶሎ ወደ ስራ ለማስገባት መጣደፉ ከባድ ችግር ነበር ሲሉ ወቅሰዋል። በአምስት ወር ልዩነት በደረሰው በላየን አየር መንገድና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ ማክስ 8 አውሮፕላኖች አደጋ በጥቅሉ 346 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ሴናተሮቹም ለሁለቱም አደጋዎች ምክንያት የሆነውን የአውሮፕላኑን ችግር ቦይንግ ቀደም ሲልም ያውቅ ነበር የሚለው ላይም በግልፅ ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል። • ቦይንግ የአደጋውን የምርመራ ውጤት ተቀበለ ሴናተር ሪቻርድ ብሉሜንዛል እንዳሉት ቦይንግ ይሁንታን አግኝቶ ቶሎ ወደ በረራ እንዲገባ ኩባንያው ነገሮችን በጥድፊያ አድርጓል ሲሉ ደምድመዋል። ከአደጋው ምርመራ ጋር በተያያዘም ቦይንግ በተደጋጋሚ ሆን ብሎ መረጃዎችን ሲያሳስትና ሲዋሽ እንደነበርም ገልፀዋል። • ቦይንግ የ737 ማክስ ሶፍትዌርን አሻሽያለሁ አለ
xlsum_amharic-train-226
https://www.bbc.com/amharic/news-50901886
የኢትዮጵያን አፈር ለማከም የሚመራመረው ዶ/ር መሐመድ አባኦሊ
በአሁን ወቅት በአሜሪካ፣ አትላንታ የሚገኘው ዶ/ር መሐመድ አባኦሊ በእጽዋትና በአፈር ላይ ይመራመራል፤ ስለ አየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም ስለብዝሀ ሕይወት ጥበቃም ያጠናል።
[ "በአሁን ወቅት በአሜሪካ፣ አትላንታ የሚገኘው ዶ/ር መሐመድ አባኦሊ በእጽዋትና በአፈር ላይ ይመራመራል፤ ስለ አየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም ስለብዝሀ ሕይወት ጥበቃም ያጠናል።" ]
ዶ/ር መሐመድ በቅርቡ 'ኢንተርናሽናል ኤጀንሲ ፎር ስታንዳርድስ ኤንድ ሬቲንግ' በተባለ ተቋም እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2019፣ በባዮማስ ዴንሲቲ የዓለም ተሸላሚ ሆኗል። ተመራማሪው በዚህ ዓመት ዓለም አቀፍ ሽልማት ሲያገኝ ይህ ሦስተኛው ነው። በ2019 በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በሠራው ሌላ ጥናትም እውቅና ተሰጥቶታል። 'ግሎባል ጆርናል'ን ጨምሮ በተለያዩ የሳይንስ መጽሔቶች በቦርድ አባልነት የሚሠራው ተመራማሪው፤ በባዮማስ ዴንሲቲ ዙርያ የሠራው ጥናት፤ የኢትዮጵያን አፈር ማከም እንዲሁም አርሶ አደሩ ለዘለቄታው ከመሬቱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ ያመላከተ ነው። • የኢትዮጵያን በቆሎ እያጠቃ ያለው ተምች • ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት ባዮማስ ዴንሲቲ (እጽዋት በምን ፍጥነትና እንዴት እንደሚያድጉ የሚጠናበት ዘርፍ ነው) ከዶ/ር መሐመድ የምርምር ትኩረቶች አንዱ ነው። ለሽልማት ያበቃው ጥናት፤ እጽዋት ሥራቸው ምን ያህል አፈርን ሸፍኖታል? በሚል በትውልድ ቀዬው በጅማ ዞን በሚገኘው ጊራ የተሠራ ነው። በአካባቢው ኬሚካል ማዳበሪያ ጥቅም ላይ በዋለበትና ባልዋለበት መሬት መካከል ያለው የአፈር ምርታማነት ልዩነት ላይ እንዳተኮረ የሚናገረው ዶ/ር መሐመድ እንደሚያስረዳው፤ ኬሚካል ማዳበሪያ አፈር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል። አፈር ውስጥ የሚኖሩ ሕይወት ያላቸውና ለአፈር ጤናማነት እንዲሁም ምርታማነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ነገሮች በኬሚካል ማዳበሪያ ሳቢያ ጉዳት ይደርስባቸዋል። ጥናቱም በኬሚካል ማዳበሪያ የተበላሸ መሬት እንዴት ማገገም ይችላል? የሚለውን የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያመላክት ነው። "የኛ ሕዝብ መሬቱን ውጤታማ ለማድረግ ብሎ ኬሚካል ማዳበሪያ ሲጨምር እነዚህ ጠቃሚ ነገሮች ከአፈሩ ይጠፋሉ፤ እነሱ ሲጠፉ ደግሞ ምርታማነት ይቀንሳል፤ እኔ ያጠናሁት በዚህ አይነት የተጎዳ አፈር እንዴት እንዲያገግም ማድረግ ይቻላል? የሚለውን ነው" አፈር እንዴት ያገግማል? ዶ/ር መሐመድ ጥናቱን የሠራው በተለያዩ እጽዋት ላይ ሲሆን፤ ምርምሩን ለማገባደድ ወደ አንድ ዓመት ተኩል ወስዶበታል። አንድ ተክል የሆነ አካባቢ ከተተከለ ምን ያህል ወደ ውስጥ ገብቶ ያን አፈር ሊያገግመው ይችላል? ወደ ጎን እስከ ስንት ሜትር ድረስ ሊያገግም ይችላል? በሚለው ተመርኩዞ ያ ተክል እንዲበቅል ይመከራል ወይስ አይመከርም? የሚለውን በጥናቱ መመልከቱን ያስረዳል። ጥናቱን በሠራበት አካባቢ፤ ቀደም ባለው ጊዜ አርሶ አደሮች ኬሚካል ማዳበሪያ እንደማይጠቀሙ፣ መሬቱም ምርታማ እንደነበር ያስታውሳል። ዩሪያ እና ዳፕ ማዳበሪያ ሲጠቀሙ ግን የአፈር ምርታማነት በጣም እየቀነሰ፣ አንዳንዱ አካባቢ ሳር እንኳን ማብቀል እንዳልቻለም አርሶ አደሮቹ ነግረውታል። "ኬሚካል ማዳበሪያ በግብርና ምርት ጥቅም እያመጣ ቢሆንም፤ መሬቱ ሁለት ሦስቴ አምርቶ ከዚያ በኋላ እንዲጠፋ ያደርጋል። በእኛ አገር ደግሞ ጥናት ሳይደረግ ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ተመሳሳይ ዩሪያ እና ዳፕ ለአርሶ አደሩ ስለሚከፋፈል በጣም ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።" • ዓለምን ሊመግብ የሚችለው የስንዴ ዘር • አዲስ አበባ፡ የፈጠራ ማዕከል ለመሆን እየጣረች ያለች ከተማ በአገሪቱ በአራቱም አቅጣጫ ያለው የግብርና መሬት የተለያየ ቢሆንም ለሁሉም በደምሳሳው ተመሳሳይ አይነት የኬሚካል ማዳበርያ ጥቅም ላይ መዋሉ ምርት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን ዶ/ር መሐመድ ይገልጻል። በሌሎች አገሮች በአግባቡ መሬት ተለክቶ፣ በባህሪው መሠረት ቢሠራም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታ ከዚህ በተቃራኒው እንደሆነ ያክላል። "አርሶ አደሮችን ኬሚካል ማዳበርያ ካልወሰዳችሁ ተብለው ይገደዳሉ። ቢወስዱም ባይወስዱም ገንዘብ ስለሚከፍሉ ወስደው የሚጥሉትም አሉ" የሚለው ተመራማሪው፤ ኬሚካል ማዳበሪያ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከግምት ሳይገባ ንግድ ተኮር ንቅናቄ መደረጉን "አገራዊ ኪሳራ" ሲል ይገልጸዋል። አርሶ አደሩ ምን ይጠቀም? ተመራማሪው ከሁሉም ቅድሚያ የሚሰጠው መሬት ምን ባህሪ እንዳለው ለማጥናት ነው። ከዚያ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፣ በተጠና መንገድ ኬሚካል ማዳበሪያ ጥቅም ላይ ይውላል እንጂ ለሁሉም አይነት መሬት መዋል የለበትም ይላል። "ለምሳሌ ደጋ አካባቢ ብንሄድ. . . አብዛኞቹ የአገሪቱ ማዳበሪያዎች ኤንፒኬ (ከናይትሮጅን፣ ፎስፈረስ፣ ፖታሽየም) የተሠሩ ናቸው። ደጋ አካባቢ ደግሞ ናይትሮጅን ሙሉ ነው። አንቺም የምትጨምሪበት ናይትሮጅን ይሆናል። ናይትሮጅን ደግሞ የሚያበዛው ባዮማሱን ነው። (ቅጠል እና ግንድ ነው የሚያበዛው) ግንዱ የማይበላበት አካባቢ ከሆነ ፍሬ አይሰጥም። እንዲያውም ቶክሲክ [መርዛማ] እየሆነበት ይሄዳል።" ዶ/ር መሐመድ ይህን ምሳሌ ማሳያ አድርጎ፤ ምርታማንትን ለማሳደግ የመሬት አይነትን ማወቅ፣ ከዚያም ኬሚካል ያስፈልጋል? የሚለውን መገንዘብ የግድ ነው ይላል። አፈር እንዲያገግምና የመሬት ምርታማነት እንዲጨምር ለማድረግ ሌላው አማራጭ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን መጠቀም ነው። ለምሳሌ እህል ከተሰበሰበ በኋላ ገለባውን ከመጣል፣ መልሶ ለማዳበሪያነት መጠቀም ይቻላል። አርሶ አደሩ ለምን ኬሚካል ማዳበሪያ እንዲጠቀም ይገደዳል? ዶ/ር መሐመድ አርሶ አደሮች የኬሚካል ማዳበሪያ ለመጠቀም የሚገደዱት ማዳበሪያውን ከመሸጥ የሚገኘው ትርፍ ብቻ ስለሚታሰብ መሆኑን ያስረዳል። "የግብርና ፖሊሲው መሬት ተኮር ሳይሆን ሰው ተኮር ነው፤ የሚታሰበው ስለ አገር ሳይሆን አሁን ላይ ተሽጦ ስለሚገኘው ገንዘብ ብቻ ነው።" • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቋ ለምን ይጠቅማታል? • የዋግ ኽምራ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው የኬሚካል ማዳበሪያ ሲገዛ አምራቹን አገር ለመጥቀም የሚታሰበውን ያህል ቀጣይነት ስላለው ምርት አለመወጠኑን ይተቻል። ለየትኛው አካባቢ ያስፈልጋል? የተጎዳው መሬት የትኛው ነው? የሚለው ተጠንቶና አርሶ አደሩ ከግምት ገብቶ መካሄድ እንዳለበትም ይመክራል። "መሬት ከትውልድ ወደ ትውልድ ምርታማነቱን ይዞ መሸጋገር አለበት። መሬት ላይ መጋደል ሳይሆን መሬቱን አለመግደል የተሻለ ነው። የእከሌ መሬት. . . የእኔ፣ ያንቺ እየተባለ ሰው ይጋደላል። መሬቱንም እየገደልን እርስ በእርስም እየተጋደልን ነው። ይህንን ያመጣው ደግሞ የአገሪቱ ፖሊሲ ነው።" ፈተና የበዛበት ዘርፍ ኬሚካል ማዳበሪያ የግብርናውን ዘርፍ ከሚፈትኑ አንዱ ቢሆንም ብቸኛው ችግር ግን አይደለም። አብዛኛው ማኅበረሰብ በግብርና በሚተዳደርበት አገር ግብርናው አለመዘመኑ፣ የምርትን ቀጣይነት ማረጋገጥ አለመቻሉም ይነገራል። ለዶ/ር መሐመድ ቀዳሚው ችግር ሠሪና መሠራት ያለበት አለመገናኘታቸው ነው። በግብርና ዘርፍ ቁልፍ ቦታ የሚሰጣቸው ግብርና ያጠኑ፣ በዘርፉ ልምድ ያካበቱ አለመሆናቸው ዋነኛው ችግር ሆኖ ይታየዋል። "መሬቱ ምን እንደሚፈልግ፣ አርሶ አደሩ ምን እንደሚፈልግም አይታወቅም፤ እኛ አገር የራሳቸው ፖለቲካ እንዴት ይዘው መሄድ እንዳለባቸው የሚያዩ እንጂ መሬት ላይ ምን እየተከናወነ እንደሆነ አያውቁም።" ሌላው ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ አለመጠቀም ነው። ለምሳሌ አሜሪካ ውስጥ ካለው ሕዝብ ወደ አንድ በመቶው ብቻ ግብርና ላይ ቢሰማራም፤ ከበቂ በላይ አምርተው ከአገራቸው አልፈው ለሌላ አገርም ይተርፋሉ። አገራቸውን በምጣኔ ኃብት ጠቅመው ለሌላ አገር እርዳታም ይሰጣሉ። በተቃራኒው ከ80 በመቶ በላይ ዜጋ በግብርና በተሰማራባት ኢትዮጵያ፤ አርሶ አደሩ ራሱን መመገብ ሳይችል በድጎማ ቀለብ ሲኖር ይታያል። ይህን ችግር ለመቅረፍም ቴክኖሎጂን ከግብርና ማስታረቅ የግድ እንደሆነ ተመራማሪው ያምናል። በሌላ በኩል የግብርና ምርምር ተቋሞች በሚያስፈልገው መጠን፣ ሙከራ [ሳምፕል] ሠርተው ለአርሶ አደሩ የሚጠቅመውን ዘርፍ ማመላከት አለመቻላቸውን ያነሳል። "እኔ በማውቀው በምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ጅማ ውስጥ ያለ የምርምር ማዕከል ከድሮም ጀምሮ ቡና እና አቮካዶ ላይ ብቻ ይሠራሉ። ነገር ግን ግብ ተቀምጦ ሌላ ነገርም መሠራት አለበት።" ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰው ኃይል (አብዛኛው ወጣት)፣ የጊዜ እና የተፈጥሮ ኃብት (መሬትና ብዙ አይነት ምርት ማፍራት የሚቻልበት መልከዓ ምድር) ውጤታማ ሊሆን የሚችለው፤ መንግሥት ምቹ ሁኔታ ሲፈጥር ቢሆንም የግብርና ፖሊሲው ማነቆ መሆኑን ይጠቅሳል። ሮቦት ገበሬዎች የሰዎችን ስራ ሊነጥቁ ነው። "ሥልጣን ላይ እንዲቆይ ብቻ ፖሊሲ አዘጋጅቶ ሕዝቡ ላይ የሚጮህ መንግሥት ሳይሆን፤ አገሪቱን መለወጥ የሚችል ፖሊሲ ለሕዝቡ አቅርቦ ወደ ሥራ መገባት አለበት። አቅጣጫ ሊኖረንም ይገባል።" በግብርና ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ መስኮች ጥናትና ምርምሮች ቢካሄዱም ከመደርደሪያ አልፈው፣ ምክረ ሀሳቦቻቸው እንደማይተገበሩ የሚተቹ ባለሙያዎች አሉ። ግብርናን ስለማሻሻል፣ ቀጣይነት ስላለው ምርታማነት የሚሠሩ ጥናቶች ምን ያህል ተግባራዊ ይደረጋሉ? የሚለው ላይም ጥያቄ ይነሳል። ስለ አፈር ለምነት፣ ስለ ኬሚካል ማዳበረያ አሉታዊ ተጽዕኖም በተደጋጋሚ በተለያዩ ባለሙያዎች ቢነገርም፤ ጥናቶቻቸውን በመጠቀም ችግሩን ምን ያህል መቅረፍ ተችሏል? የሚለውን ዶ/ር መሐመድን ጠይቀን ነበር። እሱ እንደሚለው፤ መንግሥት ፖሊሲ ሲረቀቅ እንደ ግብዓት የሚሆኑና የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያመላክቱ ጥናቶችን ለመተግበር ዝግጁ መሆን አለበት። አርሶ አደሩ በኬሚካል ማዳበሪያ ሳቢያ የገጠመው ችግር ለመፍትሔ ሀሳቦች ዝግጁ ቢያደርገውም፤ መንግሥት መፍትሔዎቹን በፖሊሲው ካላካተተ ውጤታማ መሆን አይቻልም። "ባለሙያዎችን እና ተመራማሪዎችን መጋበዝ፣ ማማከር ያስፈልጋል። በእውቀት ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ ቢወጣ ለአገርም ይጠቅማል" ሲል ዶ/ር መሐመድ ሀሳቡን ያስቀምጣል።
xlsum_amharic-train-227
https://www.bbc.com/amharic/45505752
ቄሮ፣ ሴታዊት፣ ፋኖ…የትውልዱ ድምጾች
እያንዳንዱ ትውልድ የራሱ ድምፅ አለው እንደሚባለው በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይም ይሁን መሬት ላይ ተፅእኖ እየፈጠሩ ያሉ እንቅስቃሴዎች አሉ። የመንግሥታዊ ሥርዓት ለውጥን ከማምጣት ጀምሮ በማህበረሰቡ የማይደፈሩ ሃሳቦችን የሚያነሱ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተፈጥረዋል። ከነዚህም ውስጥ ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ፣ ሴታዊትና የሎው ሙቭመንት ይገኙበታል።
[ "እያንዳንዱ ትውልድ የራሱ ድምፅ አለው እንደሚባለው በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይም ይሁን መሬት ላይ ተፅእኖ እየፈጠሩ ያሉ እንቅስቃሴዎች አሉ። የመንግሥታዊ ሥርዓት ለውጥን ከማምጣት ጀምሮ በማህበረሰቡ የማይደፈሩ ሃሳቦችን የሚያነሱ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተፈጥረዋል። ከነዚህም ውስጥ ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ፣ ሴታዊትና የሎው ሙቭመንት ይገኙበታል።" ]
ሴታዊት "አልነካም ባይ ሴት" በዓመቱ መጨረሻ በጳጉሜን ወር #የጳጉሜ ንቅናቄ በሚል በአምስቱ ቀናት ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ ብዙዎችን ያሳትፈ ዘመቻ ነበር። እህትማማችነት፣ አሪፍ ወንድ፣ የሴቶች የሥነ-ተዋልዶና ወሲባዊ ጤንነት፣ ሴቶችና የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲሁም በቅርቡ ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞባት ህይወቷን ያጣችው ጫልቱን የሚዝክር 'ለጫልቱ የምንገባላት ቃል' በሚሉ ርዕሶች ላይ ብዙዎች ተሳታፊ ሆነዋል። • 'ጫልቱን በመድፈር የተጠረጠረው ክስ አልተመሠረተበትም' ከእነዚህ ዘመቻዎች ጀርባ የፆታ እኩልነት ጥያቄዎችን፣ አባታዊ ሥርዓትን እና የፆታ አስላለፍ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ሙግቶችን በማንሳትና ውይይቶችን በመፍጠር የምትታወቀው ሴታዊት ናት። እንቅስቃሴዋ የተጀመረችው ከአራት ዓመታት በፊት 'ፌሚኒስት' የሆኑና በፆታ እኩልነት በሚያምኑ ሴቶች በወር አንድ ጊዜ በመገናኝት ነበር። ከወንዶችና ከሴቶችም እንቅስቃሴውን የመቀላቀል ጥያቄ ሲነሳ "ኦፕን ሴሺን" ተብሎ የሚጠራውና ለሁሉም ክፍት የሆነውን ዝግጅት በሦስት ወር አንድ ጊዜ ማዘጋጀት ጀመሩ። በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ የህትመት ውጤቶችን ያበረከቱ ፀሀፍት ወይም ተመራማሪዎች ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ። • ' በ70 እና 17 ዓመት ሴት መካከል ልዩነት አለ ብለህ ነው?' • 'መኝታ ቤት ስልክ ይዘን አንገባም' በሚቀጥለው ዓመትም በቅርቡ ተደፍራ ህይወቷን ያጣችው ጫልቱን ማን ገደላት? በሚል ርዕስ ዘመቻ ለማካሄድ አቅደዋል። ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የፍልስፍና ጥናት፣ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ጥያቄ፣ በተለያዩ ባህሎችና የትግል እንቅስቃሴ የሴቶች ጥያቄ የተነሳበትን መንገድ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፌሚኒዝም እንዴት ይታያል? በሚልም ዘለግ ያለ ጥናት በማካሄድ ላይ ናቸው። የሎው ሙቭመንት "እንደማመጥ፤ እንወያይ፤ እርስ በርስ ደግ መሆንን እናበረታታ" ከጥቂት አመታት በፊት የበረራ አስተናጋጅ የነበረችው አበራሽ ሃይላይ በቀድሞ የህይወት አጋሯ በደረሰባት ጥቃት አይኗን ማጣት ብዙዎችን ያስደነገጠ ዜና ሲሆን አጋጣሚው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለነበሩ ጥቂት ተማሪዎች የፆታ እኩልነት ጥያቄ ያነገበውን የየሎው ሙቭመንት እንቅስቃሴ እንዲጀምሩ ምክንያት ሆነ። መለያቸው ቢጫ ቀለም ነው። በየዓመቱ ብር እያሰባሰቡ ችግረኛ ለሆኑ ሴት ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግ፣ በወሊድ ጊዜ ለሚቸገሩ እናቶች የደም ልግሳንና ሌሎች እርዳታዎቸንም ያስተባብራሉ። ቄሮ "የራስን ዕድል በራስ የመወስን መብት" ከጥቂት ዓመታት በፊት በኦሮሚያ ክልል ከተካሄዱት ተቃውሞዎች ጋር ተያይዞ የቄሮ ስም በተደጋጋሚ ይነሳል። ምንም እንኳን ቄሮ በቅርብ ዓመታት ቢታወቅም ቄሮ የሚለውን ስም ከመያዙ በፊት የኦሮሞ ወጣቶች በተለያየ መንገድ ይንቀሳቀሱ እንደነበር ገመቹ ከፈና ይናገራል። የትግሉም አላማ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጭቆና ማስወገድና ፍትሐዊ ሥርዓትን ለመገንባት አቅጣጫ የያዘ ትግል እንደነበረም ገመቹ ያወሳል። በዚህ ወቅት ከመንግሥትም ሆነ ከተለያዩ የፀጥታ ኃይሎች ለትግሉ የተሰጠው ምላሽ እስርና ግድያ በመሆኑ ትግሉ አቅጣጫውን እንዲቀይር እንዳደረገው ገመቹ ያመለክታል። ቄሮ በአንድ ጊዜ የመጣ ሳይሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ የመጣ አደረጃጀት ሲሆን መነሻውም የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር ነው። ቄሮ የፍልስፍና አደረጃጀቱን ከገዳ ሥርዓት የተወሰደ ሲሆን ይህም ያላገባ ወጣትን ሁሉ እንደሚያጠቃልል ገመቹ ይናገራል። የትግሉ አላማም የራስን ዕድል በራስ የመወስን መብት፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን እና የመሬት መቀራመትን መቃወም ላይ ያተኮረ ነው። ምንም እንኳ ስለ ቄሮ አመሰራረትም ሆነ ስለ መሪዎቹ የተለያየ ህሳብ ቢኖርም ቄሮ መሪ አልባ ድርጅት ነው በሚለው ሀሳብ ገመቹ በፍፁም አይስማማም። ይልቁንም የድርጅት መልክ አወቃቀርና ተቋማዊ መልክ አለው ይላል። እንደ ማሳያነት የሚጠቅሰውም ከሦስትና ከአራት ዓመታት በፊት የነበረው ትግልን በስትራቴጂ የተነደፈ መሆኑን፣ በግልፅ የሚታወቁና የህቡዕ መሪዎች ያሉት መሆኑን ነው። "የህዝቦችን ጥያቄ በመነጋገርና በሰላም መፍታት የሚቻልበት ደረጃ የደረሰው በቄሮ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ወጣቶች ትግልም ነው" ይላል። ይህ ሁሉ ሲሆን ብዙ መስዋእትነት የተከፈለ ሲሆን ገመቹም ለስድስት ዓመት ከስምንት ወራት ያህል በእስር ቤት ቆይቷል። ፋኖ፡ መገፋት የወለደው «የለውጥ ኃይል» በበደል ተገፍቶ ዱርን የመረጠ፣ መጨቆንን ጠልቶ ጠመንጃ የጨበጠ ሰው «ፋኖ» ይባላል። ከሦስት ዓመታት ወዲህ አብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል በህዝባዊ ተቃውሞ በተናጠበት ወቅት በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች የነበሩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን በህቡዕ ሲያስተባብር የነበረው ቡድን ስያሜም ይሄን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ከመስራቾቹ መካከል አንዱ የሆነው የለውጥ አራማጅ ሙሉቀን ተስፋው ይናገራል። ሙሉቀን ጋዜጠኛ ነበር። በስራ ምክንያት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚዘዋወርበት ወቅት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን በደል ሲታዘብ መቆየቱን፣ የበደል እና ጭቆና ምንጭ የሆነው አገዛዝ መወገድ አለበት በሚል እምነት ከሌሎች ጓዶቹ ጋር የአማራ ወጣቶችን ለማደራጀት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ያወሳል። «ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምረን በአማራ ተወላጆች ላይ ችግር ደርሷል በተባለበት ቦታ ሁሉ እንገኝ ነበር። ለምሳሌ የዋልድባ ገዳም ሲታረስ፣ አማራዎች ከጋምቤላ እና ከጉራ ፈርዳ ሲፈናቀሉ በክስተቶቹ ላይ በርካታ ስራዎችን ሰርተናል» ይላል። «(ሥርዓቱ) ሁሉም ዜጎች እኩል ያልነበሩበት ስለነበር እሱን ማፈራረስ ዋና ዓላማችን ነበር።» የሚለው ሙሉቀን፤ ይሄ ይሳካ ዘንድ ስለ አመፅ የሚያሳውቁ ጽሑፎችን ከማከፋፈል ጀምሮ፣ በተለያዩ የገጠር እና የከተማ አካባቢዎች ህቡዕ ቡድኖችን ማደራጀትን እንደተከተሉ ያስረዳል። ከዚህ በተጨማሪ በየፈርጁ ነፍጥ ከጨበጡ ወገኖች ጋር የሚደረግ የመረጃ ልውውጥ፣ በማህበራዊ ገፆች የሚደረግ ቅስቀሳ የእንቅሰቃሴው አካል እንደነበር ያስገነዝባል። «ፋኖ» እንዲደረጅ አስፈላጊውን ጫና እንዲያመጣ ያደረገው ፆታ እና ዕድሜ ባልለየ መልኩ በሁሉም የክልሉ አቅጣጫዎች የነበረው «መናበብ» እንደሆነ ሙሉቀን ያምናል። ህዝባዊ ተቃውሞው አይሎ መንግሥት የተለያዩ ለውጦችን ተግባራዊ አድርጓል። ይሄ ለውጥ ብቻውን የፋኖ ትግል ማብቂያ እንደማይሆን ሙሉቀን ያስረዳል። «የመጣው ለውጥ መቀልበስ የማይችልበት ደረጃ ላይ እስኪደርስ ፣ተመልሰን ወደ ነበርንበት አለመግባታችንን እስክናረጋግጥ ድረስ የፋኖ ተጋድሎ ይቀጥላል !» በማለትም ያክላል። ዘርማ "ሁሉን አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት" የ1997 ምርጫ ብዙ የፖለቲካ መነቃቃትን የፈጠረ ቢሆንም ምርጫውን ተከትሎ የደረሱ ማዋከቦች፣ እስሮችና የሰው ህይወት መጥፋት በጉራጌ ማህበረሰብ ውስጥ የወጣቶች እንቅስቃሴ የሆነው 'ዘርማ' ትግል መጠንሰስ ምክንያት ሆኗል። ዘርማ በጉራጌ ማህበረሰብ ወጣት ማለት ሲሆን ከተመሰረተም አስር ዓመታት መድፈኑን ከመሪዎቹ አንዱ አሸናፊ አየለ ይናገራል። አሸናፊ እንደሚለው በአሜሪካ የተቋቋመው ዘርማ በአሁኑ ወቅት ከ30ሺ በላይ አባላት አሉት። በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉትን ለማታገል ፌስቡክን ይጠቀማሉ። ዋናው አላማቸው መብቱን የሚጠይቅ ማህበረሰብ መፍጠር፤ በህዝቡ ላይ የሚደርሱ ግፎችን ማጋለጥና ህዝቡ መብቱንም በአደባባይ እንዲጠይቅ ማድረግ እንደቻሉ ይናገራል። ምንም እንኳ በአገሪቱ ውስጥ እንዳሉ የወጣት እንቅስቃሴዎች መሪ የለውም ቢባልም፤ አሽናፊ እንቅስቃሴው በተደራጀ መልኩ እንደሚመራ ይናገራል። በተለያዩ የእንቅስቃሴዎች ህዝቡ አስተዳደሩ ላይ ተፅእኖ መፍጠር እንዲችል አድርገናል ብሎም ያምናል። በአሁኑ ወቅት መንግሥት እስከሚቀጥለው ምርጫ ድረስ የህዝቡን ድምፅ እንዲሰማና፣ ሁሉን ያካተተ ህገ-መንግሥት እንዲረቅና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረትም የትግሉ ቀጣይ ሥራዎች እንደሆኑም አመልክቷል።
xlsum_amharic-train-228
https://www.bbc.com/amharic/news-56344363
ከአደገኛ የወረርሽኝ መቅሰፍት የሰው ልጅን የታደጉት ክትባቶች የትኞቹ ናቸው?
በዓለም ላይ በተለያዩ ጊዜያት ወረርሽኞች ተከስተው የሰው ልጅን ሕይወትና ደኅንነት ለአደጋ አጋልጠውት ነበር።
[ "በዓለም ላይ በተለያዩ ጊዜያት ወረርሽኞች ተከስተው የሰው ልጅን ሕይወትና ደኅንነት ለአደጋ አጋልጠውት ነበር። \n\n" ]
ወረርሽኞች ብዙዎችን ገድለዋል፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉትን ደግሞ አካል ጉዳተኛ አድርገዋል። ነገር ግን እነዚህን ወረርሽኞች ለመግታት የተቻለው በክትባት ነው። ለመሆኑ በክትባት ምክንያት የሰው ልጅ ከስቃይ እና ከሞት ተረፈባቸው በሽታዎች የትኞቹ ናቸው?
xlsum_amharic-train-229
https://www.bbc.com/amharic/news-52838474
በአፍሪካ ስላለው የኮሮናቫይረስ ዘገምተኛ አካሄድ ምን ማለት ይቻላል?
የኮሮናቫይረስ በቻይናዋ ዉሃን ከተነሰባት እለት ጀምሮ የአፍሪካ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚሉ በርካታ መላምቶች ስለ አህጉሪቷ እናውቃለን ከሚሉ አካላት ተሰምቷል።
[ "የኮሮናቫይረስ በቻይናዋ ዉሃን ከተነሰባት እለት ጀምሮ የአፍሪካ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚሉ በርካታ መላምቶች ስለ አህጉሪቷ እናውቃለን ከሚሉ አካላት ተሰምቷል።" ]
በአህጉሪቷ ቫይረሱ በግብጽ ከተመዘገበበት የካቲት 6/2012 ዓ.ም በፊትም ለምን አህጉሪቷ ውስጥ ለመግባት ዘገየ? ብለው ከሚጠይቁ ወረርሽኙ በአህጉሪቷ ውስጥ ከተዛመተ የአፍሪካውያን መጥፊያ እንደሆነም ተተንብይዋል። ወረርሸኙ በተለያዩ አገራት መዛመት ሲጀምሩ 'አፍሪካውያን ሊያልቁ ነው' የሚሉ ቃለ መጠይቆችም ተሰምተዋል። በሚያዝያ ወር ላይ ሜሊንዳ ጌትስ ከሲኤንኤን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የአፍሪካውያን አስከሬኖች በጎዳናዎች ላይ እንደሚረፈረፉም ታይቷቸው ነበር። ምንም እንኳን በኮሮናቫይረስ በሚያዙ ሰዎች ሆነ በሟቾች ቁጥር አሜሪካ እንዲሁ አውሮፓውያን ቢመሩም፤ የምዕራቡ ዓለም ተቋማትም ሆነ የጤና ልኂቃን ትንበያ መስጠትም አልደፈሩም። በአስር ሺህዎች እያለቁ ላሉት አውሮፓውያን መላምቶች ሳያስቀምጡ መቶዎች ባልሞቱባት አህጉር ሚሊዮኖች ሊያልቁ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ ኮሚሽንም ሆነ ሌሎች ሪፖርቶች ሲያወጡ ታይተዋል። የጤና ልኂቃኑ የሃምሳ አራት አገራትን ሁኔታ እንደ አንድ አገር እንዲሁም መንደር አድርገው የጤና ሥርዓት የላሸቀ መሆኑንም አስተያየታቸውን ሲሰጡ፤ አፍሪካውያን በራሳቸው ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ተደርገው የእርዳታ ጥሪ ሲጎሰምላቸው፤ የኮሮናቫይረስን መዛመት ለመግታት የጤና ሥርዓታቸውም ሆነ ማዕከላቱ ብቁ ናቸው ብለው በሚያሞካሿቸው አውሮፓ አገራት ወረርሽኙን መቆጣጠር ተስኗቸዋል። በርካታ የአፍሪካ ምሁራንም ሃምሳ አራት አገራት ታሪክ፣ ባህል፣ ኢኮኖሚ የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን የሁሉም በተናጠል ሊታይ ይገባል። እንደዚህ አይነት ሪፖርቶች ማውጣት ፖለቲካዊ ትርጉም እንዳለውና መላው የአፍሪካ አገራትን እንደ አንድ መንደር አድርጎ ማየት ከቅኝ ግዛት እሳቤም ጋር የተመሳሰለና "አፍሪካውያንን ኋላ ቀርና እርባና የሌላቸው" የሚለውን አስተሳሰባቸውን ያንፀባረቁበት ነውም በማለትም ተችተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በመጀመሪያው ዓመት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከ83ሺህ አስከ 190 ሺህ ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉና፤ ከ29 እስከ 44 ሚሊዮን ሰዎችም ሊጠቁ እንደሚችሉ ቢገምትም፤ በአፍሪካ ውስጥ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በርካታ የምዕራባውያን ተቋማትና የጤና ባለሙያዎች ከሰጧቸው መላ ምቶች ተቃራኒ መሆኑ ብዙዎች ላይ ተስፋን አጭሯል። በአህጉሪቷ ውስጥ እስካሁን ባለው መረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 125 ሺህ 640 ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 51 ሺህ 462ቱ አገግመዋል፤ 3 ሺህ 709 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል። ከአንድ ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ላላት አህጉር ቁጥሩ በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ትንሽ ነው የተባለ ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅትም ሆነ ሌሎች የአህጉሪቷን ሁኔታ የሚተነብዩ ባለሙያዎች በአፍሪካ እንደተፈራው ላይሆን ይችላል እያሉ ነው። በአፍሪካ የተመዘገበው ቁጥር ለምን አነሰ ለሚለው የተለያዩ ምክንያቶች እየተሰጠ ሲሆን፤ ለዚህም በርካታ የአፍሪካ አገራት የጉዞ እገዳን ጨምሮ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ማገድ፣ የሰዓት እላፊ መመሪያ እንዲሁም ድንበሮቻቸውን መዝጋት፣ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ማስገባት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ጠቅሟቸዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ የአህጉሪቱ የሕዝብ ቁጥር አብዛኛው ወጣት መሆኑ እንደ ምክንያትነት የተገለፀ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ በርካታ ቁጥር ያላስመዘገበችው የምርመራ ቁጥሯ ትንሽ በመሆኑ እንደሆነም ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የምርመራ ቁጥር ትንሽ መሆን በቫይረሱ ለተያዙት ቁጥር ላለመጨመር እንደ ምክንያትነት ቢገለጽም በሆስፒታሎች የሚመዘገበው የህሙማን ቁጥር አለመጨመሩ፣ እንዲሁም ከሆስፒታሎች ውጪ ሞቶች አለመመዝገባቸውም አገራቱ ወረርሽኙን ተቆጣጥረውታልም እየተባለ ነው። የአፍሪካ ቀንድ አገራት እንዴት ናቸው? በአፍሪካ ቀንድ ካሉ አገራት መካከል አንድ ሚሊዮን የማይሞላ ሕዝብ ባላት ጂቡቲ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ ሦስት ሺህ ደርሷል። አገሪቱም ከ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎቿ ምርመራ ያደረገች ሲሆን፤ ይህም ከሕዝብ ቁጥሯ ጋር ሲነፃፀር እንደነ ፈረንሳይ ካሉ አገራት በልጣ አቅሟ 25 ሺህ 600 በሚሊዮን አድርሷታል። ጂቡቲ 20 ዜጎቿንም በኮሮናቫይረስ አጥታለች። የኮሮናቫይረስ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረባት ካለችው ጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ድንበር አቋራጭ አሽከርካሪዎችም በቫይረሱ እየተያዙ እንደሆነ ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዪት የወጡ መረጃዎችም ያሳያሉ። የኮሮናቫይረስ የመርመር አቅሟን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረች ያለችው ኢትዮጵያም ቫይረሱ ከተገኘበት እለት ጀምሮ በመቶዎች ከመርመር ጀምራ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎችን በቀን መመርመር ችላለች። ኢትዮጵያ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎችን ብትመረምርም ከመቶ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ባለቤት ከመሆኗ አንፃር በሚሊዮን ሲሰላ 842 ነው። ኢትዮጵያ የመርመር አቅሟን በመጨመር በቀን ከአስር ሺህ በላይ ሰዎችን የመርመር እቅድ እንዳላት ተገለጿል። በተጨማሪም አገሪቷ አርባ ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች የሙቀት ልኬት በማድረግ አመርቂ ሥራ እየሰራች እንደሆነ ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል። ከዚህም በተጨማሪ ለሃምሳ ሺህ ሰዎች የሚሆን የለይቶ ማቆያ ማዘጋጀቷን ዘገባው አክሎ ገልጿል። በርካታ የአፍሪካ አገራት በዘፈቀደ የማይመረምሩ ሲሆን ለመርመር የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። ለምሳሌ ኢትዮጵያ የላብራቶሪ ናሙናዎች የምትመረምረው ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች በመውሰድ ነው። በሶማሊያ 1 ሺህ 741 ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን፤ 67 ዜጎቿንም በበሽታው አጥታለች። አገሪቱ ምን ያህል ሰዎችን እንደመረመረች ግን መረጃ የለም። በኤርትራም እንዲሁ በቫይረሱ የተያዙት 39 ሰዎች ሙሉ በሙሉ ማገገማቸው ተገልጿል። አዳዲስ የሚመዘገቡ ሰዎችም እንደሌሉ ቢገለፅም እስካሁን ምን ያህል ሰዎች እንደተመረመሩ የተገኘ መረጃ የለም። ማኅበረሰቡ ማዕከል የሆነበት የመከላከል ሥራ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት መከላከሉ ላይ ማተኮራቸው የተገለፀ ሲሆን በኢትዮጵያም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የሙቀት ልኬት መደረጉ፣ ከመንግሥት በተጨማሪ ማኅበረሰቡ ማዕከል የተደረገበት የመከላከል ሥራም እየተከናወነ ይገኛል። ማኅበረሰቡ በራሱ ፈቃደኝነት እርዳታ የማሰባሰብ ሥራ፣ ግንዛቤ የማስጨበጥ እንዲሁም መመሪያዎችንም በማስከበር ረገድ ከፍተኛ ሥራ እየሰራ ይገኛል። በኢትዮጵያም ሆነ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ፀረ-ተህዋሲያንንና የፊት ጭምብሎችን በነፃ ማደል እንዲሁም የቬንትሌተርም ሆነ ሌሎች ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁሶች ፈጠራ የተሞላባቸው አስተዋፅኦዎች ተስተውለዋል። ማኅበረሰቡ ራሱን አስተባብሮ ወረርሽኙን ለመግታት የሚያደርገው ጥረት፣ ከዚህ ቀደም የነበሩ ልምዶችንም በመተግበር እያደረገ ያለውን አስተዋፅኦ በርካታ በአፍሪካ ላይ ጨለምተኛ አቋም ያላቸው ተቋማት እያዩት አይደለምም ተብሎ ይተቻል። በዚህም አፍሪካ ለሌሎች አህጉራት ማስተማር የምትችለውም ልምድ አለ እየተባለ ነው። እነዚህም ተግባራት ወረርሽኙን በመቆጣጠር ምን ያህል እያገዙ እንደሆነም ከግምት ውስጥ ሊገቡ እንደሚገባም አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ። በተለያዩ የአፍሪካ አገራት እንደ ኤችአይቪ፣ ቲቢና የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር የተዘረጉ ዘዴዎችንም እየተጠቀሙ ሲሆን፤ ተጋላጭ የሆነውን ማኅበረሰብ መለየት እንዲሁም ህዝቡን የማስተባበር ሥራም እየተሰራ ይገኛል ተብሏል። ሆኖም በተለያዩ አገራት ውስጥ የተስተዋለው የውሃ፣ መብራት፣ የመፀዳጃ ቤቶችና የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶችም እጥረት ችግር ደቅነዋል። ማኅበረሰቡ አካላዊ ርቀትንም ለመጠበቅም ሆነ ንፅህናውን ለመጠበቅ በተጨናነቁ ሰፈሮችስ ውስጥ እንዴት ይቻላል? የሚሉ ጥያቄዎች በርክተዋል። መንግሥታት አካላዊ ርቀትን እንዲጠበቁ እንዲሁም እንቅስቃሴ የሚገድቡ መመሪያዎችን ሲያወጡ የሕዝቡን የአኗኗር ሁኔታ፣ በየቀኑ የዕለት ጉሮሮውን ለመድፈን የሚያደርገውን ሩጫ ከግምት ውስጥ ያስገባም አይደለም ተብለውም ተተችተዋል። ምንም እንኳን በአብዛኛው በሕዝቡ ውስጥ ቸልተኝነት እንዳለ ሆኖ መንግሥታት ለሚያወጧቸው መመሪያዎች ከሕዝቡ ጋር መጣጣሙን ሊያጤኑት ይገባልም ተብሏል። በተለያዩ አገራት ችግሮች ቢስተዋሉም ቫይረሱን ለመቆጣጠር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውም ልብ ሊባል እንደሚገባ ተንታኞች ይናገራሉ። በተለያዩ አገራት ያለው የመርመር አቅም በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር በመመርመር ደቡብ አፍሪካ የአንበሳውን ድርሻ የያዘች ሲሆን ከዊንዶ ሜትር በተገኘ መረጃ ከ634 ሺ በላይ ሰዎችን መርምራለች። በዚህም መሰረት የመመርመር አቅሟ ከፍተኛ ከሚባሉት 10 ሺህ 720 በሚሊዮን እንደሆነም መረጃዎች ያሳያሉ። ጋናም ከ200 ሺህ በላይ ሰዎችን የመረመረች ሲሆን፣ ሴኔጋልና ሞሪሽየስም ከፍተኛ ቁጥርን አስመዝግበዋል። አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ብቻ ባለባት ሞሪሺየስ አስር በመቶ ሕዝቧን መርምራ 334 ሰዎችን ያገኘች ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ አስሩ ሞተዋል፤ 322ቱ አገግመዋል። በአገሪቱ ውስጥ አዲስ ህሙማን መመዝገብ ካቆመች ከወር በላይ ቢያስቆጥርም ከሰሞኑ ከህንድ የመጡና በለይቶ ማቆያ ያሉ ሁለት ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ደቡብ አፍሪካ፣ ካሜሮን፣ ሞሪታንያ፣ ኢትዮጵያና ናይጄሪያ የቤት ለቤት ቅኝቶችን በማድረግ፤ የሙቀት ልኬት ሥራዎች ሰርተዋል። በበርካታ ትንንሽ የአፍሪካ አገራትም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ጥቂት ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውንም ዜጎቻቸውን ለመመርመር ችለዋል። ለምሳሌ በሲሽየልስ ቫይረሱ የተገኘበት ሰው የመዘበችበት የመጨረሻው ቀን ሚያዝያ 3/2012 ዓ.ም ሲሆን ሁሉም አገግመዋል። በናሚቢያም እንዲሁ ለመጨረሻ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች የተገኙት ከወር በፊት ሲሆን፤ በለይቶ ማቆያ የነበሩ ከጎረቤት አገር ደቡብ አፍሪካ የመጡ ሁለት ሴቶች ካገገሙ በኋላ የተመዘገበ ቁጥር የለም። የአፍሪካ በሽታዎች ቁጥጥርና ክትትል ዳይሬክተር ዶክተር ጆን ንኬንጋሶንግ ከሁለት ሳምንት በፊት የነበረን መረጃ ጠቅሰው 1.3 ሚሊዮን ሕዝብ በአህጉሪቱ ተመርምረዋል ብለዋል። ምንም እንኳን ለሁሉም አገራት ተመሳሳይ አይነት ማጠቃለያ መስጠት ቢያዳግትም በጦርነትና ግጭት የተናጡ አገራት የመርመር አቅም ዝቅተኛ መሆኑ አሳሳቢ ነው ተብሏል። ከኢንተርናሽናል ሬስኩዩ ኮሚቴ የተገኘ መረጃ እንደሚያስረዳው በአፍሪካ ውስጥ ዝቅተኛ ከመረመሩ አገራት መካከል ቻድና ማሊ የሚጠቀሱ ሲሆን በአፍሪካ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ናይጄሪያ እስካሁን የመረመረችው ሰው ቁጥር 44 ሺህ 458 ነው። ከስምንት ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ በተያዙባት ናይጄሪያ የመርመር አቅምምም 216 በሚሊዮን ነው ተብሏል። ናይጄሪያ ዋነኛ ትኩረቷ በከፍተኛ ቁጥር መመርመር ሳይሆን ከወረርሽኙ ጋር ንክኪ ያላቸውን እንዲሁም የተነሳባቸውን አካባቢዎች በማተኮር እየመረመረች መሆኑን አስረድታለች። እንደ ታንዛንያ የመሰሳሰሉ አገራት ምን ያህል ሰዎችን እንደመረመሩ ይፋ ከማድረግ የተቆጠቡ ሲሆን ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ በተደጋጋሚ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው ብለዋል። ሆኖም ወደ ኬንያና ዛምቢያ የሚሻገሩ የታንዛንያ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ በቫይረሱ መያዝ እሳቸው ከሚሉት ተቃራኒ ነው። ይህንንም ተከትሎ ኬንያን የመሳሰሉ ጉረቤት አገራት ከታንዛንያ ጋር የሚያዋስናቸውን ድንበር ዘግተዋል። ምንም እንኳን አንዳንዶች በተለያዩ አገራት ያለው የምርመራ ቁጥር ትንሽ መሆኑ በማህኅረሰቡ ውስጥ መዛመቱን አያሳይም፤ እንዲሁም በሽታው የመሰራጨት ሁኔታው ተደብቆ ሊሆን ይችላል ቢሉም ዶክተር ጆን ንኬንጋሶንግ በዚህ አይስማሙም። ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚሰጡት በበርካታ አገራት በማኅበረሰቡ ውስጥ ሞቶች አለመጨመራቸው፤ ምክንያት የሌላቸው ሞቶች አለመመዝገባቸው፤ እንዲሁም ድንገተኛ ወረርሽኝ አለመከሰቱን እንደ ምክንያትነት ይጠቅሳሉ። "በአህጉሪቱ ውስጥ ያለውን ሁኔታን ስንገመግም በከሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ሆስፒታሎች አልተጨናነቀቁም" ብለዋል። ቢሆንም አሁን ያለውን ሁኔታ በማየት ሁሉ ነገር አዎንታዊ ነው ማለት ባይቻልም፤ አገራት የመርመር አቅማቸውን እንዲጨምሩም በርካታ የጤና ባለሙያዎች እየመከሩ ነው። ምንም እንኳን የመመርመሪያ መሳሪያዎች እጥረት በአንዳንድ አገራት ቢያጋጥምም አማራጭ የፈጠራ ዘዴዎችን እያጎለበቱ የሚገኙ አገራት አሉ። ለምሳሌ በሴኔጋል በፓስተር የምርመራ ተቋም እየተሰራ ያለው በፈጣን ሁኔታ መመርመር የሚያስችሉ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ከአርባ ብር ባነሰ ዋጋ እየሰሩ ነው። የአፍሪካ በሽታዎች ቁጥጥርና ክትትል ማዕከልም የመርመሪያ መሳሪያዎችን አቅም ለመጨመር የተለያዩ ጅምሮችን ጠንስሷል። ቫይረሱ በማኅበረሰቡ ውስጥ መዛመቱን ሪፖርት ባደረጉ አገራት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በመረመሩ ቁጥር በበሽታው የተያዙ ሰዎችመጠንም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሊመጣ እንደሚችል እየተነገረ ሲሆን፤ አገራቱ እስካሁን በወሰዷቸው እርምጃዎች የቫይረሱን ሁኔታ መቆጣጠር ቢችሉም ከዚህ በኋላ በቀጣዮቹ ወራት ሊወስዷቸው የሚችሉ እርምጃዎች የወረርሽኙን ስርጭት የሚወስኑት ይሆናል ተብሏል።
xlsum_amharic-train-230
https://www.bbc.com/amharic/52498998
ኮሮናቫይረስ፡ በምዕራብ ሐረርጌ ጉባ ኮሪቻ በኮቪድ-19 የተያዘው ግለሰብ ማን ነው?
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ረቡዕ ዕለት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው አራት ግለሰቦች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ገልጾ ሦስቱ ከፑንትላንድ መምጣታቸውን፤ አንዱ በምዕራብ ሐረርጌ ጉባ ኮሪቻ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ ግን ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ንክኪም ሆነ የጉዞ ታሪክ እንደሌለው በመግለጽ ቫይረሱ እንደተገኘበት ካስታወቀ በኋላ ጉዳዩ እየተጣራ ነው ተብሎ ነበር።
[ "ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ረቡዕ ዕለት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው አራት ግለሰቦች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ገልጾ ሦስቱ ከፑንትላንድ መምጣታቸውን፤ አንዱ በምዕራብ ሐረርጌ ጉባ ኮሪቻ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ ግን ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ንክኪም ሆነ የጉዞ ታሪክ እንደሌለው በመግለጽ ቫይረሱ እንደተገኘበት ካስታወቀ በኋላ ጉዳዩ እየተጣራ ነው ተብሎ ነበር።" ]
በምዕራብ ሐረርጌ በጉባ ኮሪቻ በኮቪድ-19 እንደተያዘ የተነገረው ወጣት፣ ካሊፍ ጃሚር [ስሙ የተቀየረ] እንዴት በቫይረሱ ሊያዝ ቻለ በማለት ተኝቶ ወደሚታከብት ሂርና ሆስፒታል በመደወል አነጋግረነዋል። በአሁኑ ሰዓት በሂርና ሆስፒታል ለይቶ ማከሚያ ውስጥ የሚገኘ ካሊፍ፤ በሆስፒታሉ ውስጥ ከእርሱ ውጪ ሌላ የኮቪድ-19 ታማሚ እንደሌለ ለቢቢሲ ገልጾ የጤና ባለሙያዎችም አስፈላጊውን እንክብካቤ በሙሉ እያደረጉለት መሆኑን ይናገራል። • ኒው ደልሂ ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ታካሚዎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ • የልጄን ገዳይ ልቀቁልኝ ያሉት እናት • ትራምፕ ቻይና በምርጫው እንድሸነፍ ትፈልጋለች አሉ አሁን ስላበት ጤንነት ሁኔታ ሲጠየቅም "ይህ በሽታ እንዴት እንደያዘኝ አላውቅም፤ ምንም የሚያመኝ ነገር ስለሌ ተይዣለሁ ብዬም አላስብም" ብሏል። በምዕራብ ሐረርጌ ነዋሪ የሆነው ካሊፍ ጤና ሚኒስቴር የጉዞ ታሪክ የለውም ይበል እንጂ እርሱ ግን በጅቡቲ በኩል ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሄድ ሲሞክር ጅቡቲ ላይ በቁጥጥር ስር ውሎ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሰ ነግሮናል። "ጅቡቲ ደሂል የምትባል ቦታ 11 ቀን ነው የቆየነው። ከዚያ ፖሊስ [የጅቡቲ] ይዞን ወደ ኢትዮጵያ መለሰን" ካለ በኋላ፣ እርሱና ጓደኞቹ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ለ12 ቀናት በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ለይቶ ማቆያ ውስጥ መቀመጣቸውን ለቢቢሲ አስረድቷል። የ14 ቀን የለይቶ ማቆያ ቆይታ በኋላ ወደ ጭሮ ከዚያም ቤተሰቦቹ ወዳሉበት ስፍራ እንዳቀና እና እዚያም ለ14 ቀናት እንደቆየ ነግሮናል። የካሊፍ እድሜ በጤና ሚኒስቴር መግለጫ ላይ 23 እንደሆነ ቢገለጽም እርሱ ግን "19 እንኳ አልሞላኝም" ብሏል። "ድሬዳዋ እንዳለን አትጨባበጡ፣ የምግብ እቃዎችን በጋራ አትጠቀሙ፤ ከቤተሰቦቻችሁ ጋር አትቀላቀሉ ተብሎ ምክር ተሰጥቶን ነበር በዚህም ምክንያት ከቤተሰቦቼ ጋር አልተቀላቀልኩም፤ ሰላምም ያልኳቸው በሩቁ ነው" ይላል። ነገር ግን በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠ በኋላ ቤተሰቦቹን ጨምሮ ከእርሱ ጋር ንክኪ አላቸው ተባለው የተጠረጠሩ ከ70 በላይ ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው። እንዴት የኮቪድ-19 ምርመራ እንደተደረገለት የተጠየቀው ካሊፍ፣ በጉባ ኮሪቻ 12 ቀናት ከቆየ በኋላ ከእርሱ ጋር አብሮ የነበረ ጓደኛው ስለታመመ ወደ ጭሮ እንዲመጣ በጤና ጽህፈት ቤት ሰዎች እንደተደወለለትና እንደተመለሰ ይናገራል። ጭሮ ከደረሰ በኋላ ናሙና ተወስዶ ሲመረመር ቫይረሱ እንዳለበት እንደተነገረው ገልጿል። በምዕረራብ ሐረርጌ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው የሂርና ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አሊይ አደም፤ ወጣቱ በጥሩ ሁኔታ እንዳለ ገልፀው ከእርሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 75 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም አመልክተዋል። "ምንም ህመም የለውም፤ የኮቪድ-19 ምልክቶች የሉትም፤ አልፎ አልፎ ሳል ብቻ ይታይበታል" ሲሉ ገልፀዋል። የሂርና ሆስፒታል የኮቪድ 19 ህክምና ማዕከል ሆኖ እየተደራጀ ሲሆን 100 አልጋዎችና ሁለት መካኒካል ቬንትሌተሮች አሉት። ሆስፒታሉ በአጠቃላይ 110 ሠራተኞች ሲኖሩት 67 የጤና ባለሙያዎች፣ 43 ደግሞ ተጨማሪ ህክምና ድጋፍ የሚሰጡ ናቸው። ሆስፒታሉ በአንዴ እስከ 100 ሰው ማስተናገድ ሚችል ቢሆንም ያሉት ግን 60 አልጋዎች ናቸው። ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ለ18 ሺህ 754 ሰዎች ምርመራ ያደረገች ሲሆን 66 ሰዎች ከወረርሽኙ አገግመዋል።
xlsum_amharic-train-231
https://www.bbc.com/amharic/news-57140215
የኤርትራ ምጣኔ ሃብት ባለፉት 30 ዓመታት
ኤርትራ በ1992 ዓ.ም 52ኛ አፍሪካዊት አገር ስትሆን ዜጎቿና የነጻነት ጉዞዋን ሲከታተሉ የነበሩ ተንታኞች 'ኤርትራ በአጭር ጊዜ ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ የአካባቢዋ ሞዴል ትሆናለች' የሚል ተስፋ ነበራቸው።
[ "ኤርትራ በ1992 ዓ.ም 52ኛ አፍሪካዊት አገር ስትሆን ዜጎቿና የነጻነት ጉዞዋን ሲከታተሉ የነበሩ ተንታኞች 'ኤርትራ በአጭር ጊዜ ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ የአካባቢዋ ሞዴል ትሆናለች' የሚል ተስፋ ነበራቸው።" ]
ከነጻነት በኋላ የነበሩ የጊዝያዊ አስተዳደሩ ስራ አስፈጻሚዎችም "ኤርትራን ሲንጋፑር እናደርጋታለን" ሲሉ ተናግረው ነበር። አገሪቷ በ1994 ያጸደቀችው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ በግብርና ኢንዳስትሪ፣ አሳና ጨው፣ የመሰረተ ልማቶች ግንባታ፣ ኤሌክትሪክና ውሃ ማስፋፋት፣ ትምህርት፣ ጤናና ሌሎች የማስፈጸም ተልእኮ ተሰጥቶት ስራ ተጀመረ። ሰነዱ መግቢያ ላይ "ኤርትራ ከጦርነትና ግጭት፣ ከጭቆና አገዛዝ nጻ ወጥታ ወደ አዲስ ብልጽግናና ሰላም እየገባች ነው። ይህ በመስዋእትነት የተገኘው ሰላምና መረጋጋት ፈጣን ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እያሳየ ነው። በጦርነት የወደመው ምጣኔ ሃብትን ለመገንባትም ጥረት እየተደረገ ይገኛል" ይላል። የአፍሪካ ፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር መንግስትአብ ኪዳነ የኤርትራ መንግሥት በግል ባለሃብቶች የሚመራ የኢንቨስትመንትና ወደ ውጪ የሚላክ ምርት ትኩረት ያደረገ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ እንደነደፈ ያስታውሳሉ። "መንግሥት የህግደፍ ኢኮኖሚ፣ የመንግሥት ኢኮኖሚ፣ የግል ኢንቨስትመንት ኢኮኖሚ በሚል ሦስት መንገድ የተገበረውን ፖሊሲ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለበት መንገድ እጁ ማስገባት ስለጀመረ ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ነው የተደናቀፈው" ይላል። በተዘበራረቀ አሰራር ምክንያት ህዝብ የመንግሥት የሆነው ንብረት ከፓርቲ ሃብት ለይቶ ማየት እንዳልቻለ የሚናገረው ፕሮፌሰር መንግስትአብ፤ "ለምሳሌ ህዝብ ማዕድን በመንግሥት ነው ወይስ በፓርቲ የሚተዳደረው የሚያውቀው ነገር አልነበረም" በማለት የአገሪቷ የምጣኔ ሃብት ስርአት የተዘበራረቀ መሆኑ ይናገራል። በሳውዝ ባንክ ዩኒቨርሲቲ ለንደን ፕሮፌሰር የሆነው ጋይም ክብረአብ በበኩሉ፤ ህዝቡ፣ በመንግስት በኩል የነበረበትን አስተዳደራዊ ችግር "ልምድ እስኪያገኙ ድረስ ነው" እያለ ጊዜ ቢሰጠውም በጊዜ ማስተካከል ባለመቻሉ የአገሪቷ ምጣኔ ሃብትና ፖለቲካ ወደ ኋላ ቀርቷል ይላል። በዚህ ምክንያት ብዙ በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ፍላጎት የነበራቸው ዜጎች እውቀታቸውና ገንዘባቸው ይዘው ከስደት ወደ አገራቸው ቢመለሱም፤ የግል ኢኮኖሚው ህጋዊ ግብር የማይከፍለው የፓርቲ ኢኮኖሚ ጋር መወዳደር ባለመቻሉ ቀስ በቀስ እንደከሰረ ያስረዳል። ይህ አሰራር ማን ምን እንደሚያስተዳድር ስለማይታወቅ ለሙስና የተጋለጠ እንደሆነ የሚያነሳው ፕሮፌሰር መንግስትአብ፣ በፓርቲ የሚመራው የኢኮኖሚ ተቋም በኢንዳስትሪ፣ ግንባታ፣ ትራንስፖርት፣ መሰረታዊ ሸቀጦች ሳይቀር ስለሚሳተፍ የኢኮኖሚው መተላለፊያ በመቆጣጠር ነጋዴዎች እድል ስለነፈጋቸው ኢኮኖሚው በአግባቡ መራመድ አልቻለም ይላል። "መንግሥትና ፓርቲ የውጭ ምንዛሪና ብድር ተቆጣጥረው የግል ኢንቨስትመንቱን አዳከሙት። በዚህ ላይ ወጣቱ በአገራዊ ግዳጅ ስለተጠመደ በግብርና እና የቀን ስራ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች ሰራተኛ አጥተው ኢኮኖሚው እንዲወድቅ ሆኗል" በማለት ያስረዳል። እንዲህም ሆኖ ዜጎች በንግድና ኢንቨስትመንት ተሳትፎ ያደርጉ ስለለነበረ በ1996 የአገሪቷ ኢኮኖሚ እስከ 6.7 በመቶ እድገት እንዳስመዘገበ ፕሮፌሰር ጋይም ይናገራል። በፋይናንስ ሚኒስትር የኢኮኖሚ ኃላፊ የነበረው አቶ ክብሮም ዳፍላ በወቅቱ ከኤርትራ መገናኛ ብዙሃን ባደረገው ቆይታ እሱ ኃላፊነት ላይ በነበረበት ወቅት ያስተዳድረው የነበረው ተቋም 'ሂምቦል የውጭ ምንዛሪና ሃዋላ' ብቻ በአመት እስከ 80 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ይመነዘር ነበር ብሏል። በተጨማሪም በተመሳሳይ ንግድ ተሰማርተው የነበሩ ሌሎች የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃድ የተሰጣቸው 29 ተቋማት እንደነበሩ ገልጿል። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትና ለ20 ዓመታት የዘለቀው ውዝግብ በአስተዳደራዊ ችግርና ጫና ለህግደፍ የንግድት ተቋማት ይሰጥ በነበረው ኢፍትሃዊ የግብርና ቀረጥ እፎይታ ሲያዘግም የነበረው ብቸኛ ኢኮኖሚ፣ ለሁለት አመታት በዘለቀው የኢትዮ ኤርትራ ግጭት ምክንያት ተንኮታኮተ። ጦርነቱ ተከትሎ ላለፉት 18 አመታት በቀጠለው ውዝግብም አብዛኛው ዜጋ በብሄራዊ አገልግሎት እንዲጠመድ ስለሆነ እንደምንም ሲንቀሳቀስ የነበረው ኢኮኖሚ በጦርነት ታግቶ እንደቆመ ፕሮፌሰር ጋይም ይናገራል። "የኤርትራ ብሄራዊ በጀት የሚመለከት ሆነ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ሪፖርት ስለሌለ በጦርነቱ ምክንያት ምን ያክል ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እንደደረሰ ባይገለጽም የነበረውን መባከኑን ግን ግልጽ ነው" ይላል። የኤርትራ መንግሥት ባለስልጣናት ግን "በቅድሚያ የአገር ሉአላዊነት መረጋገጥ ስላለበት አገር ሳናስጠብቅ የውስጥ ጉዳዮቻችን ላይ መነጋገር ጊዜው አይደለም" ሲሉ ቆይተዋል። የመንግሥት ኢኮኖሚያዊ ቅርጽ ሁሉንም የኢኮኖሚ አማራጮች በመቆጣጠሩ ዲሞክራሲያዊ አሰራር እንዳይኖር አድርጓል የሚለው ፕሮፌሰር መንግስተአብ በበኩሉ፤ "ፓርቲው የራሱ ኢኮኖሚ ስለገነባ ከህዝብ ጋር የሚያስተሳስረው መንገድ አይኖረውም። ለዚህም እስከ ዛሬ ለህዝብ ጥያቄ ጆሮ አልሰጠም። ህዝቡም ድምጹን የሚሰጥበት እድል ስለሌለ በድምጹ ተቃውሞ ማሰማት አልቻለም" ይላል። በዲሞክራሲያዊ አገር ፓርቲ ከአባላቶቹ በሚሰበስበው መዋጮ ነው የሚተዳደረው። በኤርትራ ግን ህገ መንግሥታዊ ስርአት ስሌለለ አገሪቷን የሚያስተዳድር ፓርቲም አንድና አንድ ብቻ ስለሆነ፤ ህግደፍ የአገሪቷን ንብረት በሙሉ እያስተዳደረ ይገኛል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ ያላደገበት አንድ ምክንያትም ዴሞክራሲያዊ የሆነ አሰራር አለመኖሩ ነው ሲል ፕሮፌሰር ጋይም ያስረዳል። የቢሻ ማዕድን ማውጫ ማዕቀብ ኤርትራ እኤአ በ2009 ከሶማልያ ጋር በተያያዘ፣ በ2011 ከጅቡቲ ጋር በነበራት አለመግባባት የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክርቤት የመሳሪያ ግዢና የተወሰኑ ሰዎች ባንክ እንዳይንቀሳቀስ በማለት ማዕቀብ ጥሎባት ነበር። መንግሥት 'መሬት ላይ የሌለ ነገር በመጠቀም ኤርትራን ለማዳከም የተወሰደ ተከታታይ የአሜሪካ መንግሥታት ሴራ ነው፤ ከኢትዮጵያ ጋር በነበረው ግጭት ምክንያት በማድረግ የአፍሪካን ቀንድ ለመቆጣጠር ያሴሩት ነው' ሲል ቅሬታው ይገልጽ ነበር። በመጨረሻም ኤርትራና ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ሲፈርሙ ህዳር 14 2019 ላይ ማእቀቡ ተነሳ። ሁለቱም አገራት ስምምነት ከፈረሙ በኋላ የተዘጉ ድንበሮች ሲከፈቱ የአገሪቷ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አሳይቶ ነበር። ይሁን እንጂ ድንበሮቹ ምክንያቱ በውል ባይታወቅም ተመልሰው በመዘጋታቸው የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ዳግም ማሻቀቡን የኤርትራ ምንጮች ይገልጻሉ። ፕሮፌሰር ጋይም ግን ከዚህ በፊት ኤርትራ ላይ የተደነገጉ ማዕቀቦች በአገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ ጫና አሳድሯል የሚለው እምነት እንዳለው ተናግሯል። በሌላ በኩል መንግሥት በ2015 ህገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ ጭማሪ ለመቆጣጠር፤ የአገሪቷን ገንዘብ በመቀየር ሁሉንም በህዝብና ነጋዴዎች እጅ የነበረው ገንዘብ ባንክ እንዲገባ ካደረገ በኋላ ታላላቅ የንግድ ልውውጥ በባንክ እንዲከናወን ትእዛዝ አስተላለፈ። ዜጎችም ከ5 ሺ ናቅፋ በላይ ከባንክ ማውጣት እንደማይችሉ የሚቆጣጠር ህግ ተግባራዊ ሆኖ እየተሰራበት ይገኛል። ይህም ምታኔ ሃብቱ እንዲዳከም ማድረጉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳል። የኤርትራ ህዝብ ለነጻነት ሲታገሉ የነበሩ ድርጅቶች በቻለው ሁሉ እርዳታ በማድረጉ ለድል በቅቷል የሚለው ፕሮፌሰር መንግስትአብ በጣልያን እና ሌሎች አገሮች በስደት የነበሩ እናቶች ከፍተኛ የሞራልና የኢኮኖሚ ድጋፍ አድርገዋል ይላል። ከ1998 እስከ 2000 በነበረው የድንበር ግጭት ብዙ ህዝብ የአገሩን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ቦንድ በመግዛትና በጥሬ ገንዘብ በመለገስ ማገዙን የሚያነሳው ፕሮፌሰር መንግስትአብ 'አገሬ ሽልማቴ' በማለት እናቶች ሽልማታቸውን አበርክተዋል ሲል ያስታውሳል። በተጨማሪም ከጦርነቱ በኋላም ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሳይመጣ በአንጻሩ ለውጥ ሲጠይቁ የነበሩት ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችና ጋዜጠኞች ያለ አግባብ ታስረው ይገኛሉ፤ እነዚህ እና ሌሎች ተያየዓዥ ምክንያቶች ተደማምረው የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት እንዲጎዳ አድርጓል ይላል። በመሆኑም "ፖለቲካዊ ለውጥ ካልመጣ ኢኮኖሚያዊ እድገት የማይታሰብ ነው" ሲል ፕሮፌሰር ጋይም መሰረታዊ ማሻሻያ ለማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚ መርሆዎችን ተመልሶ ማየት አስፈላጊ ነው ሲል ይመክራል።
xlsum_amharic-train-232
https://www.bbc.com/amharic/42562515
ኡጋንዳ ስደተኞችን ከእስራኤል ለመቀበል ስምምነት ማድረጓን አስተባበለች
የምታስወጣቸውን ስደተኞች ለመቀበል ከእስራኤል ጋር ያደረገችው ምንም አይነት ስምምነት እንደሌለ የኡጋንዳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄንሪ ኦሪም ኦኬሎ መግለፃቸውን ዴይሊ ሞኒተር ዘግቧል።
[ "የምታስወጣቸውን ስደተኞች ለመቀበል ከእስራኤል ጋር ያደረገችው ምንም አይነት ስምምነት እንደሌለ የኡጋንዳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄንሪ ኦሪም ኦኬሎ መግለፃቸውን ዴይሊ ሞኒተር ዘግቧል።" ]
ሚኒስትሩ ኡጋንዳ እስራኤል የምታስወጣቸውን በሺህ የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞች ልትቀበል እንደሆነ የሚገልፀው ሪፖርት ከየት እንደመጣ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል። እስራኤል የገቡት በህገወጥ መንገድ ነው ያለቻቸውን ስደተኞች ለመቀበል የተደረገ ምንም አይነት ስምምነት አለመኖሩንም አረጋግጠዋል። "በእስራኤል የሚገኙ የሌላ አገር ስደተኞችን ለመቀበል ከእስራኤል ጋር ያደረግነው ስምምነት የለም።ሪፖርቱም ግራ አጋብቶናል።በዚህ ረገድ ከአገሪቱ ጋር ምንም ዓይነት አጋርነት የለንም።ስለጉዳዩ ዝርዝር ነገር ከፈለጋችሁ እነሱን ጠይቋቸው።"ብለዋል። ከእስራኤል ይውጡ የተባሉት ስደተኞች አብዛኞቹ የኤርትራና የሱዳን ዜጎች ሲሆኑ ወደ አገራቸው መመለስ ለህይወታቸው እንደሚያሰጋቻው ይናገራሉ።
xlsum_amharic-train-233
https://www.bbc.com/amharic/news-49143337
ኦሳ ማዕከሉን በአዲስ አበባ እንዲከፍት ምክትል ከንቲባው ጠየቁ
ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የኦሮሞ ጥናት ማህበር ጉባኤ ላይ (ኦሳ) ዛሬ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ማህበሩ ማዕከሉን አዲስ አበባ ላይ እንዲያደርግና ከዚህ በኋላ ዝግጅቱን ለማካሄድ ወደ ባዕድ ሃገር መመልከት የለበትም ብለዋል።
[ "ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የኦሮሞ ጥናት ማህበር ጉባኤ ላይ (ኦሳ) ዛሬ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ማህበሩ ማዕከሉን አዲስ አበባ ላይ እንዲያደርግና ከዚህ በኋላ ዝግጅቱን ለማካሄድ ወደ ባዕድ ሃገር መመልከት የለበትም ብለዋል።" ]
ከአርብ ጀምሮ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ በቆየው የማህበሩ ጉባኤ የመጨረሻ ቀን ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባው፤ ማህበሩ ላለፉት 33 ዓመታት ሥራውን ለማከናወን ሲል መስዋዕትነት ሲከፍል መቆየቱን ተናግረው፤ አሁን ግን ወደ ሃገር ቤት በመምጣቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። ምክትል ከንቲባው አክለውም ማህበሩ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸውን ጥናቶች የፖሊሲና መመሪያዎች መሰረት መሆን ስላለባቸው በተቀናጀ መልክ በማዘጋጀት ለትውልድና ለሃገር በሚጠቅም መልኩ ሥራ ላይ እንዲውሉ መድረግ አለበት ብለዋል። • የኦሳ 33ኛ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀመረ "መስዕትነት ስትከፍሉላቸው የነበሩ ጥናቶቻችሁን ወደ ኋላ መለስ ብላችሁ በማየት ትውልድ፣ ሃገርና ሃብታችን ላይ ልዩነትን እንዲያማጣ ማድረግ ይጠበቅባችሏል" ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ በኋላም የኦሮሞ ጥናት ማህበር ሥራውን ለማከናወን ወደ ሌሎች ሃገራት ማየት እንደሌለበት የጠቆሙት ምክትል ከንቲባው በአዲስ አበባ ከተማ ማዕከሉን ከፍቶ እንዲሰራ ጥሪም አቅርበዋል። ማህበሩ ከዚህ በፊት ጥናቶቹን ያካሂድባቸው የነበሩትን መንገዶችን በአግባቡ ቀርጾና መዝግቦ የሚቀጥለው ትውልድ ውጤታማ ምርምር እንዲያደርግ መርዳት አለበት ሲሉ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ተናግረዋል። ለዚህ ደግሞ እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ እንደ ሃገርና እንደ ግለሰብም ማህበሩ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸዋል። • በባርነት ከመሸጥ የተረፉት 64 ኢትዮጵያዊያን ምክትል ከንቲባው በተጨማሪም ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ በገዳ ሥርዓት ጥናት ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በሌላ በኩል ደግሞ "ቤተሰቦቻችን ዋጋ ከፍለው ባያስተምሩን ኖሮ ዛሬ በዚህ መልኩ አንወያይም ነበር" ያሉት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የትምህርትንና የምርምርን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በጉባኤው የማብቂያ ዕለት ተገኝው ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባው የኦሮሞ ጥናት ማህበር ጉባኤ ተሳታፊዎች እየተካሄደ ባለው የችግኝ መትከል ዘመቻ ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ችግኝ የመትከያ ቦታዎች መዘጋጀታቸውን ገልጸው፤ ጉባኤተኞቹም በችግኝ ተከላው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
xlsum_amharic-train-234
https://www.bbc.com/amharic/news-41401393
ስለ ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ ማወቅ የሚገባዎትን በስድስት ሰንጠረዦች እነሆ
ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር በቃላት ጦርነት በተጠመደችበት በዚህ ወቅት፤ ሰሜን ኮሪያውያን የሃገራቸው ከምዕራባዊያን ጋር ስለገባችበት ውዝግብ ያላቸው ግንዛቤ ምን እንደሚመስል ማወቅ አስቸጋሪ ነው። በዚህ ክፍለ ዘመን ሃገሪቷ ከተቀረው ዓለም እጅጉን ተነጥላለች። የህዝቡን የአኗኗር ሁኔታ ሊያሳዩ የሚችሉ አሃዞችን ማግኘት አስቸጋሪ ቢሆንም ኑሮ በሰሜን ኮሪያ ውስጥ ምን እንደሚመስል ሊያሳዩን የሚችሉ መረጃዎች አሉ።
[ "ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር በቃላት ጦርነት በተጠመደችበት በዚህ ወቅት፤ ሰሜን ኮሪያውያን የሃገራቸው ከምዕራባዊያን ጋር ስለገባችበት ውዝግብ ያላቸው ግንዛቤ ምን እንደሚመስል ማወቅ አስቸጋሪ ነው። በዚህ ክፍለ ዘመን ሃገሪቷ ከተቀረው ዓለም እጅጉን ተነጥላለች። የህዝቡን የአኗኗር ሁኔታ ሊያሳዩ የሚችሉ አሃዞችን ማግኘት አስቸጋሪ ቢሆንም ኑሮ በሰሜን ኮሪያ ውስጥ ምን እንደሚመስል ሊያሳዩን የሚችሉ መረጃዎች አሉ። \n\n" ]
ኪም ኢል-ሱንግ እአአ በ1948 ዓ.ም ሰሜን ኮሪያን ከመሠረቱ በኋላ ከአባት ወደ ልጅ በሚያልፍ የስልጣን ርክክብ ሃገሪቷን ከተመሰረተች አንስቶ እስካሁን እያስተዳደሯት ይገኛሉ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ደቡብ ኮሪያ ስድስት የሪፐብሊክ መንግሥታት ተቀያይረውባታል። አብዮትን አስተናግዳለች። ሁለት መፈንቅለ-መንግሥት ተካሂደውባታል። እንዲሁም ነጻና ገለልተኛ የሆኑ ምርጫዎችን አስተናግዳለች። በአጠቃላይ 12 ፕሬዝዳንቶች ለ19 ዙር ሃገሪቷን አስተዳድረዋል። ሦስት ሚሊዮን ተንቀሳቃሽ ስልክ ብዙ ሊመስል ይችላል። 25 ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርባት ሃገር ውስጥ ግን 3 ሚሊዮን ማለት አንድ አስረኛው ነዋሪ ብቻ ነው ተንቀሳቃሽ ስልክ ያለው። አብዛኛው የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች በዋና ከተማዋ ፕዮንግያንግ አካባቢ የሚኖሩ ናቸው። በተቃራኒው በደቡብ ኮሪያ የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ቁጥር 51 ሚሊዮን ገደማ ሲሆን ይህም ከሰሜን ኮሪያ ህዝብ ቁጥር በላይ ነው። ለረጅም ዓመታት ከግብጽ ኩባንያ ጋር በመተባበር የሰሜን ኮሪያው ኮሮሊንክ የተባለው የቴሌኮምዩኒኬሽን ድርጅት በብቸኝነት አገልግሎት ሰጪ ሆኖ ቆይቷል። የግብጹ ኩባንያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለው ግንኙነት ሲሻክር ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደንበኞቹ መረጃ ከቁጥጥሩ ውጪ እንደሆነ ይፋ አድርጎ ነበር። የአሜሪካ-ደቡብ ኮሪያ የጥናት ተቋም አደረኩት ባለው ጥናት መሠረት አዲስ የአየር ሰዓት ከመግዛት ይልቅ አዲስ መስመር ማውጣት ይረክሳል። በሃገሪቷ ውስጥም ከፍተኛ የሆነ የተንቀሳቃሽ ስልክ እጥረት አለ። አብዛኛው የሰሜን ኮሪያ ህዝብ በሃገር ደረጃ ብቻ የሚሰራውን የኢንተርኔት አገልግሎት ይጠቀማል። እአአ በ2016 የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው በሃገሪቷ ውስጥ 28 የኢንተርኔት አድራሻዎች ብቻ ይገኛሉ። የሰሜን ኮሪያ ወንዶች ከደቡብ ኮሪያዎች በቁመት እንደሚያጥሩ ጥናቶች አመላክተዋል። በሁለቱ ሃገራት ወንዶች መካከል በአማካይ ከ3 እስከ 8 ሴ.ሜ ልዩነት አለ። ጥናቱን ያካሄዱት ፕሮፌሰር በሁለቱ ሃገራት ወንዶች መካከል የተፈጠረው የቁመት ልዩነት፤ የዘረ መል ልዩነት አይደለም። ምክንያቱም የሁለቱም ሃገር ዜጎች አንድ ህዝብ ናቸው። ልዩነቱ የተፈጠረው በምግብ እጥረት ሳቢያ ነው ብለዋል። ከሰሜን ኮሪያ ዋና ከተማ ፕዮንግያንግ የሚገኙ ምስሎች ሰፋፊ እና ብዙ የትራፊክ እንቅስቃሴ የማይታይባቸውን ጎዳናዎች ያሳያሉ። ገጠራማው የሃገሪቷ ክፍል ደግሞ የተለየ መልክ ነው ያለው። እአአ 2006 ዓ.ም የነበረ አሃዝ እንደሚያሳየው ሰሜን ኮሪያ 25554 ኪ.ሜ መንገድ ቢኖራትም ከዚህ ውስጥ 3 በመቶው ብቻ ነው አስፋልት። ከዚህ በተጨማሪም ከ1000 የሃገሪቱ ዜጎች 11 በመቶው ብቻ ናቸው መኪና ያላቸው። በሰሜን ኮሪያ የሕዝብ መጓጓዣ እጥረት አለ ሰሜን ኮሪያ ወደ ውጭ በምትለከው የድንጋይ ከሰል ምርት ምጣኔ ሃብቷን ትደግፋለች። አብዛኛው የሰሜን ኮሪያ የድንጋይ ከሰል ወደ ቻይና ነው የሚላከው። እአአ እስከ 1973 ዓ.ም ድረስ የሁለቱ ኮሪያዎች የሃብት መጠን ተመጣጣኝ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ደቡብ ኮሪያ እንደ ሳምሰንግ እና ሃዩንዳይን የመሳሰሉ ግዙፍ ኩባንያዎችን በመያዝ ከዓለማችን ቀዳሚዎቹ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች አንዷ ስትሆን፤ ሰሜን ኮሪያ ግን በአምባገነናዊ ሥርዓት ውስጥ ሆና እንደ 1980ዎቹ እየኖረች ትገኛለች። በህዝብ ቁጥር ብዛት ሰሜን ኮሪያ ከዓለማችን 52ኛ ደረጃን ስትይዝ በሠራዊት ብዛት ግን ከዓለም 4ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ይገመታል። ከሃገሪቷ አጠቃላይ ምርት ውስጥ 25 በመቶ የሚሆነው ለሃገሪቷ ጦር ኃይል የሚውል ነው። በአጠቃላይ ሁሉም የሰሜን ኮሪያ ወንድ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የጦር ልምምድ ያደርጋል። እ.አ.አ በ1990 በተከሰቱት ተደጋጋሚ ድርቆች ምክንያት የሰሜን ኮሪያ የእድሜ ጣሪያ ዝቅ ብሏል። እአአ 2017 የደቡብ ኮሪያ የወሊድ መጠን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሃገሪቷ ላለፉት አስር ዓመታት ያክል የወሊድ መጠንን ከፍ ለማድረግ እየጣረች ትገኛለች። የደቡብ ኮሪያ መንግሥት ወሊድን ለማበረታታት ለወላጆች በስጦታ መልክ ገንዘብ በመስጠት፣ በወሊድ ጊዜ ለአባቶች ረዥም የዕረፍት ጊዜን በመፍቀድና የመሃንነት ህክምና በማድረግ ከ70 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጓል።
xlsum_amharic-train-235
https://www.bbc.com/amharic/news-55421939
ጃፓኖች ትዳርን እንደተውት አብሮ መብላትንም እርግፍ አርገው እየተውት ይሆን?።
የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት እየጀመርን ነው ጊዜ ይለወጣል። ጊዜ የማይለውጠው ምን አለ? ጃፓኖችም ቢሆን።
[ "የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት እየጀመርን ነው ጊዜ ይለወጣል። ጊዜ የማይለውጠው ምን አለ? ጃፓኖችም ቢሆን።" ]
ለምሳሌ የዛሬ 10 እና 20 ዓመት አንዲት ሴት ጃፓናዊት ብቻዋን ምግብ ቤት ገብታ፣ መዘርዝረ ምግብ ቃኝታ፣ ምግብ ጥርግርግ አድርጋ በልታ ብትወጣ አገር ጉድ ነበር የሚባለው። አንዲት የጃፓን ሴት ካፌ ገብታ በርገር ስትገምጥ ብትታይ ተስተናጋጆች ለእሷ ይሸማቀቁ ነበር። ምን ይህ ብቻ፣ ቢሮ በምሳ ዕቃ ምግብ አምጥቶ ለብቻ መብላት እንኳ ያሳፍር ነበር። ከዚህ ሀፍረት ለመዳን አማራጩ ሁለት ነበር። ወይ ከሰው ጋር ተጠግቶ አብሮ መብላት፣ ወይ ሆድን እያከኩ መዋል። ይቅርታ ሦስተኛ አማራጭ አለ። ዘንግቼው ነው። መታጠቢያ ቤት ገብቶ በር ቆልፎ ጥርግርግ አድርጎ መብላት. . .። ይህ በጃፓን በጣም የተለመደ ተግባር ነበር። እዚያ ይህ ተግባር እጅግ የተለመደ ከመሆኑ የተነሳ የራሱ መጠሪያ ስም አለው። "ቤንጆ ሜሺ" ይባላል። የመታጠቢያ ቤት ምሣ ማለት ነው። ዛሬ ጃፓን ያን ዘመን እየረሳችው ነው። ብቸኝነት ነውር መሆኑ እያበቃለት ነው። ስለዚህ ጉዳይ በደንብ የምታጫውተነን ሚኪ ታተይሽን ተዋወቋት። በቶክዮ አንድ ቡና ቤት ውስጥ አስተናጋጅ ናት። ቡና ቤቱ 'ሂቶሪ' ይባላል። በቶክዮ ታዋቂ ቡና ቤት ነው። ሰዎች እዚህ ቡና ቤት የሚመጡት ታዲያ ለብቻቸው ነው። ሴቶች 'ባለጌ ወንበር' ላይ ፊጥ ብለው፣ ያሻቸውን ኮክቴይል መጠጥ አዝዘው፣ ደንቅ የግል ጊዜን አሳልፈው እየተንገዳገዱ ቤታቸው መግባት ይችላሉ። ይህ የዛሬ 10 ዓመት በጃፓን የሚሞከር አልነበረም። እረ በጭራሽ! ይህ 'የብቸኞች' ቡና ቤት የተከፈተው በ2018 ነበር። እንዴት ሊከፈት ቻለ? ምክንያቱም የጃፓን የሕይወት ዘይቤና ባሕል ቀስ በቀስ እየተቀየረ ስለመጣ። ላጤ ጃፓናዊያን እና ፈት ጃፓናዊያን ቁጥራቸው እየተምዘገዘገ ነው፤ ሽቅብ! ስለዚህ ብቻቸውን እንደሚኖሩት ሁሉ ብቻቸውን ሽር ብትን ማለትን ይፈልጋሉ። የብቸኝነት ኑሮ ተበራክቷል፤ እዚያም እዚህም። መታጠቢያ ቤት ቆልፎ ምሣ መብላት የቀረው ከዚህ በኋላ ነው። አስተናጋጇ ታተይሺ ደንበኞቿ እየበዙ እንደሆነ በየምሽቱ ታስተውላለች። "እዚህ የሚመጡት ብዙዎቹ ብቸኝነትን ፈልገው ነው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ከሌላ በቸኛ ሰው ጋር መዳበል ሽተው" ትላለች ታተይሺ። በዚህ ቡና ቤት ግን ሰብሰብ ብሎ መምጣት አይቻልም። ክልክል ነው። የብቸኞች ቡና ቤት ነው። ቡና ቤቱ አሰራሩ ራሱ ለቡድን አይመችም። አብሮነትን አያበረታታም። ጠበብ ያለና ባለ አንድ-አንድ ወንበር ነው። የጃፓን ባሕል የደቦ ነው። የሚበላው በጋራ፣ የሚሰራው በጋራ፣ መዝናናት በጋራ…። አሁን ግን ይህ ቶሎ ቶሎ እየተቀየረ ነው። በጃፓን አዲሱ ብቸኝነት 'ሂቶሪ' ተብሎ ይጠራል። 'አንድዬ' እንደማለት ነው። ቡና ቤቱም ስሙን የወሰደው ከዚሁ ነው። ይህን የብቸኝነት፣ ነጠል የማለት አዲስ ባሕል የተረዱ ቢዝነሶች እየጎመሩ ነው። የጉዞ ወኪሎች በፊት ለአንድ ሰው የሚሆን ፓኬጅ አልነበራቸውም። አሁን አሁን የነጠላ ተጓዦች በዝተዋል። ምግብ ቤቶች ለአንድ ሰው ጠረጴዛና ወንበር አልነበራቸውም። አሁን እየበዙ ነው። ካፌዎችም እንደዚያው፣ መዝናኛዎችም እንደዚያው። ይህ በእጅጉ ብቸኝነትን የመውደድ አባዜ ጃፓኖቹ 'ኦሂቶሪዛማ' ብለው እየጠሩት ነው። አሁን ማኅበረሰባዊ እንቅስቃሴ እየሆነ ነው። ጽንሰ ሐሳቡ ሰዎች ብቸኝነትን እንዲወዱ ማድረግ ነው። ሐሳቡ በደቦ ባሕል የተቆላለፈውን የጃፓን አኗኗር መበጣጠስ ነው። የነጠላ ጉልበት ኦሂቶሪሳማ በደምሳሳው ሲተረጎም 'የላጤ ድግስ' እንደማለት ነው። የላጤ ፌሽታ። ላጤነት ከትዳር ገሸሽ ማለት ብቻ አይደለም። በሁሉም የአኗኗር ዘይቤ ነገሮችን ለብቻ ማድረግንም ያካትታል። ለምሳሌ በኢንስታግራም ይህንን የጃፓን ቃል አስገብታችሁ ኢንተርኔቱን ብታስሱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፎቶዎችን ታገኛላችሁ። ሁሉም የብቸኛ የሕይወት ዘይቤን የሚያንቆለጳጵሱ ናቸው። ባለፉት ሁለት ዓመታት የጃንፓ ኢንተርኔት መድረኮች ይህንን የብቸኛ ሕይወትን ውበት በሚያሞግሱ መረጃዎች ታጭቀዋል። ጃፓኖች እየተቀየሩ ይሆን? ለምሳሌ መስክ ላይ የሚጠበስ ሥጋ አብስሎ በጋራ መብላት አዲስ ፋሽን ሆኗል፤ በጃፓን። 'ሒቶሪ ያኪኒኩ' ይሉታል። ያኪኒኩ እንደኛ ጥሬ ሥጋ ሰብሰብ ብሎ ከመብላት ጋር ይመሳሰላል። እነሱ ሥጋውን ቢጠብሱትም። የሚገርመው ታዲያ ይህ የመሥክ ላይ ሥጋን በደቦ አርዶ፣ በቅርጫ መልክ ተካፍሎ ጠብሶ በጋራ የመብላቱ ባሕል በአዲስ እየተቀረ መምጣቱ ነው። አሁን በርካታ ጃፓናዊያን ይህን ለብቻቸው እያደረጉት ነው። አንድ ሰው ለብቻው መስክ ሄዶ፣ ክምር ሙዳ ሥጋ ብረት ምጣድ ላይ ጠብሶ፣ ተመግቦ፣ ተምነሽንሾ ይመጣል። ይሄ ሴቶችንም ይጨምራል። ይህ ለጃፓን ባሕል ባዕድ ነው። ሆኖም አሁን እየለመደ መጥቷል። ካሪዮኪን ለብቻ ምን ይህ ብቻ፣ ካራዮኪ የሚሉት የጃፓን መዝናኛ አለ። ይህ በሩቅ ምሥራቅ አገሮች በጣም የሚዘወተር ነው። ቡና ቤቶች፣ ላውንጆች፣ ምሽት ክበቦች ካራዮኪ ከሌላቸው ምኑን መዝናኛ ሆኑ? ካሪዮኪ በመሰረቱ በሞቅታ ውስጥ ዘፋኝ መሆን ማለት ነው። የሚዝናኑ ሰዎች መድረክ ላይ ወጥተው፣ ማይክራፎን ጨብጠው ከተቀናበረ ሙዚቃ ውስጥ፣ ከሚወዱት ዘፋኝ፣ የወደዱትን ዜማ ወስደው መዝፈን። 'ሩቅ ምሥራቅ ሳለሁ፣ ጃፓኗን ወድጄ' የሚለውን የጥላሁን ገሠሠ ዜማን እየተጫወተ ከሙዚቃው የጥላሁን ድምጽ ይወጣና የሚዝናናው ሰው ድምጽ ይገባል። ይህ ነው ካሪዮኪ። ካሪዮኪ ሲታሰብ ታዲያ በደቡ የሚሆን ነገር ነው። በርካታ ወዳጆች በየተራ መድረክ እየወጡ የሚወዱትን ዜማ ማንጎራጎር። አሁን ግን ጃፓኖች ለብቻቸው ካሪዮኪ አስከፍተው መዝፈን ጀምረዋል። ቡና ቤቶች ውስጥ የካሪዮኬ ስቱዲዮዎች አሉ፤ የስልክ ማነጋገርያ ክፍሎች የመሰሉ። በቃ ብቸኛው ሰው እዚያች ክፍል ገብቶ ለብቻውን አንጎራጉሮ ሲወጣለት ይወጣል። ጃፓን፣ አብሮ መብላትን ትታ፣ አብሮ መጠጣትን ትታ፣ አብሮ መደነስን ትታ፣ ትዳርን ትታ አሁን ምን ቀራት? ምናልባት አብሮ መሥራት? እርግጥ ነው በብዙ አገሮች ብቸኝነት እየተስፋፋ ነው። በምዕራቡ ዓለም ነጠል ብሎ መኖር የተለመደ ነገር ነው። አስገራሚም አይሆንም። በቤተሰብ ሕይወትና በአብሮነት አኗኗር የሚታወቁት ጃፓኖች ብቸኝነት እየወደዱ መምጣታቸው ነው አስገራሚው። 125 ሚሊዮን የደረሰው የጃፓን ሕዝብ እንደ ፍንጭት ጥርስ ዝርዝር ብለው በተፈጠሩ በርከት ባሉ ትንንሽ ደሴቶች ተጠጋግቶ ነው የሚኖረው። "ጃፓን ትንሽዬ አገር ናት፤ ሰዎች ባይፈልጉም ይቀራረባሉ፤ ተጠጋግተው ነው የሚኖሩት" ይላሉ ሞቶኮ ማቱሺታ። ማቱሺታ በምጣኔ ሀብት የምርምር ማዕከል ውስጥ ተመራማሪ ናቸው። ኦሒቶሪሳማ ላይ ምርምር አድርገዋል። ይህ ብቸኝነትን እየሻቱ የመምጣቱ ነገር ጃፓን ብቻ ሳይሆን ቀሪው ዓለምም ወደዚያው እያቀና ነው ይላሉ። ማቱሺታ እንደሚሉት ለዚህ አዲስ ባሕል መፈጠር የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ምክንያት ናቸው። እንዴት ለሚለው እንዲህ ያብራራሉ። "አሁን አሁን ዋጋ የምንሰጣቸው ነገሮች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙ መወደድ (ላይክ) የሚያስገኙ ነገሮችን ነው። ብዙ የጃፓን ሴቶች ራሳቸውን በማኅበራዊ ገጽ ላይ ማውጣት ጀመሩ። ሕይወታቸውን አደባባይ አሰጡት። ብዙ ሰዎች ተከተሏቸው እንጂ አላሸማቀቋቸውም።" ስለዚህ ብቻ መኖርን የኅብረተሰቡን ሳይሆን የራስን የሕይወት አኗኗር ዘይቤ መከተል ችግር ሲፈጥር አልታየም። እንዲያውም ተወዳጅና ዝነኛ መሆን ጀመረ። ወጣቶች ይህን እያዩ በድፍረት ወደ ምግብ ቤት፣ መዝናኛ፣ እየሄዱ ዓለማቸውን መቅጨት ጀመሩ። ቀደም ብሎ ሴት ጃፓናዊ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ውስጥ እንኳ ምሳቸውን ተደብቀው ይበሉ የነበረው ወደው አልነበረም። ጓደኛ አልባ መሆን አሳፋሪ ስለነበረ ነው። አለመወደድን፣ መገፋትን፣ ቆንጆ አለመሆንን ያመላክት ነበር። አሁን ያ ስሜት ጠፋ። ይህ ብቻ አይደለም፤ ሴቶች ማግባት አለባቸው፤ መውለድ አለባቸው የሚለው ጠንካራ ማኅበራዊ አስተሳሰብ በፍጥነት እየተሸረሸረ ነው። 10 ሺህ ጃፓናዊያን ላይ በተደረገ ጥናት ብዙዎቹ ብቻ መኖር የተሻለ ነው ብለው እንዳመኑ አሳይቷል። ብዙዎቹ ከትዳር መፋታት የነጻነት መቀዳጀት እንደሆነ እንደሚያስቡ አመላክቷል። ጃፓን የአዛውንቶች አገር ናት። የወሊድ መጠን አሽቆልቁሎ መሬት ሊነካ ምን ቀረው። ባለፈው ዓመት በጃፓን የተወለዱ ልጆች ብዛት 864ሺህ ብቻ ነበር። ከ1899 (እአአ) ጀምሮ ጃፓን የወሊድ ቁጥር መመዝገብ ጀምራለች። በመቶ ዓመት የታየ አነስተኛ የወሊድ ቁጥር ነው ይህ አሀዝ። ሌላው የላጤ ቁጥር መመንደግ ነው። ከ2015 ወዲህ የላጤዎች ቁጥር ከ25 በመቶ ወደ 35 በመቶ ተመንድጓል። በትዳር ያልተጣመረው ሕዝብ ቁጥር መጨመር የመጣው ካለማግባት ብቻ ሳይሆን አግብቶ መፍታት በጣም እየተለመደ በመምጣቱም ጭምር ነው። ካዙሒሳ አራካዋ በዚህ ጉዳይ ተመራማሪ ነው። መጽሐፍም ጽፏል። እሱ በሰራው ጥናት 50 ከመቶ የሚሆነው ጃፓናዊ በ2040 ብቻውን ይኖራል። የጃፓን ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሔዋን የደረሰ ግማሽ በግማሽ ሕዝብ ላጤ ሆኖ ይቀራል። በብዙ አገራትም ይኸው ነው እየሆነ ያለው። ሰዎች የሕይወትን ጥያቄ ለመጠየቅ ብቻቸውን መሆንን ይመርጣሉ። ሕይወት የከበዳቸው ሰዎች ወደዚህ ከባድ ዓለም ሌላ ፍጡር መጋበዝ አይፈልጉም። ራሳቸው ላይ የልጅ ጫና ማምጣትን አይሹም። ብዙ ነገር አይበቃም። ጊዜ አይበቃም። ሌላ ሰውን ባሕሪ መሸከም ማባበል ይሰለቻል። ማኅበራዊ ሕይወት ደስ የሚሉ ብዙ ትሩፋቶች ቢኖሩትም አዲሱ ትውልድ ግን ለእነሱ ጊዜም ታጋሽነትም እያጣ ይመስላል። ዓለማችን በሚቀጥሉት 50 ዓመታት የላጤዎች ወይም የፈቶች ዓለም ትሆናለች ይላል ካዙሒሳ አራካዋ። ጃፓን ግን ይህን መንገድ ቀድማ የተያያዘችው ይመስላል። በ10 ዓመቱ ውስጥ ከደቦ ወዳድ ማኅበረሰብነት ወደ ላጤና ነጠላነት የተጓዘችበት ፍጥነት እንደ ባቡሮቿ ነው።
xlsum_amharic-train-236
https://www.bbc.com/amharic/50542245
ቢሊየነሩ ማይክል ብሉምበርግ በመጭው የአሜሪካ ምርጫ እወዳደራለሁ አሉ
የኒውዮርክ ከንቲባ የነበሩት ቢሊየነሩ ማይክል ብሉምበርግ እንደ አውሮፓውያኑ በ2020 በአሜሪካ በሚካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩ በመሆን እንደሚወዳደሩ አስታወቁ።
[ "የኒውዮርክ ከንቲባ የነበሩት ቢሊየነሩ ማይክል ብሉምበርግ እንደ አውሮፓውያኑ በ2020 በአሜሪካ በሚካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩ በመሆን እንደሚወዳደሩ አስታወቁ።" ]
የ77 ዓመቱ ማይክል ብሉምበርግ "ዶናልድ ትራምፕን አሸንፌ አሜሪካን ዳግም ለመገንባት ነው የምወዳደረው። ይህን ምርጫ የግድ ማሸነፍ አለብን " ብለዋል። ማክይል ብሉምበርግ በውሳኔያቸው ትራምፕን ለመፎካከር የተዘጋጁ 17 ዴሞክራት ተወዳዳሪዎችን ተቀላቅለዋል። እስካሁን ባለው የኦባማ ቀኝ እጅ የነበሩት የቀድሞ ምክትል ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን፣ ሴናተር ኤሊዛቤት ዋረን እና በርኒ ሳንደርስ የዴሞክራቲክ ፓርቲ የፊት መስመር አጥቂዎች ናቸው። ቢሊየነሩ ብሉምበርግ ግን አሁንም የዴሞክራቶች ቡድን በሚገባ ትራምፕን የሚገዳደር አይደለም የሚል ስጋት አላቸው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ዶናልድ ትራምፕ "ትንሹ ማይክልን እንደ መወዳደር የምፈልገው ነገር የለም" በማለት ቢሊየነሩ ማይክል ብሉምበርግን ነቁረዋቸው ነበር። • "አሜሪካ ምኞቷ ሞላላት"፡ ዶናልድ ትራምፕ • ሂላሪ ክሊንተን በሚቀጥለው ምርጫ ይወዳደሩ ይሆን?
xlsum_amharic-train-237
https://www.bbc.com/amharic/news-49207200
ሮዝ መስቲካ፡ 'ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ ለእናቶች' ስትል የምትወተውተዋ እናት
ዓለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት በኢትዮጵያ ለ11ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው። የእናት ጡት ወተት ለልጆች ጤናማ አካላዊና አዕምሯዊ እድገት ወሳኝና መተኪያ የሌለው ነው። ለዚህም ነው እናቶች ልጆቻቸውን ያለ ተጨማሪ ምግብ እስከ ስድስት ወር ድረስ ከዚያም ከተጨማሪ ምግብ ጋር እስከ ሁለት ዓመት ድረስ እንዲያጠቡ የሚመከረው።
[ "ዓለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት በኢትዮጵያ ለ11ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው። የእናት ጡት ወተት ለልጆች ጤናማ አካላዊና አዕምሯዊ እድገት ወሳኝና መተኪያ የሌለው ነው። ለዚህም ነው እናቶች ልጆቻቸውን ያለ ተጨማሪ ምግብ እስከ ስድስት ወር ድረስ ከዚያም ከተጨማሪ ምግብ ጋር እስከ ሁለት ዓመት ድረስ እንዲያጠቡ የሚመከረው።" ]
ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ይህንን መተግበር አዳጋች ሲሆን ይስተዋላል። • የዱቄት ወተት እና የእናት ጡት ወተት ምንና ምን ናቸው? • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና ልጆችን ጡት ማጥባት ሳይንስ ነው። ከእናትየዋ አመጋገብ ጀምሮ (የምግብ አሠራር በሉት) ቀላል አይደለም። አቀማመጡ፣ የልጅ አስተቃቀፉ፣ የጡት አጎራረሱ በዘፈቀደ የሚደረግ አይደለም። መራመድ ቢፈልጉም ለረዥም ሰዓት ለመቀመጥ ይገደዳሉ። እጅ ይዝላል። ፍላጎት ባይኖርም መመገብ ይጠይቃል፤ ያገኙትን አሊያም ያሻዎትን ሳይሆን የተመጣጠነ ምግብ። አጣደፊ ጉዳይ ቢገጥመዎት ጡትዎን ከልጅዎ አፍ መንጠቅ ያሳሳል። ግራኝ ሆኑም ቀኝ በሁለቱም ክንድዎ ልጅዎን ማቀፍ ግድ ይላል- ሁለቱንም ጡቶች ማጥባት ስላለብዎ። ያስርባል፤ ልብ ያዝላል። ያጠቡትን የጡት ወተት መጠንን የመስፈሪያ መንገድ ስለሌለ ልጅዎ ምን ያህል የጡት ወተት እንዳገኘ በቀላሉ ለማወቅ ስለማይቻል ያስጨንቃል። ለእናት ከባዱ ነገር ደግሞ ልጀ አልጠገበም ብሎ ማሰብ ነው። አንዳንዴም የጠቡት ይወጣና ለንዴት ይዳርግዎት ይሆናል። ወተት አግቷል አላጋተም ጡትዎን የሚዳብሱበት ቁጥር ይበረክታል። ጠብተው ሲጨርሱም ቆሞ ማስገሳት አለ። በተለይ ለጀማሪ እናቶች አሳሩ ብዙ ነው። በዚህ ላይ ደግሞ የትዳር አጋሮች ድርሻቸውን ካልተወጡ ፈተናው ያይላል- ጡት ወደ ማስጣል ውሳኔም ሊያደርስ ይችላል። ይህን ያለችን ሮዝ መስቲካ ናት። በማስ ኮሚዩኒኬሽን የመጀመሪያ ድግሪ አላት። በተለያዩ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግላለች። በሚዲያው ዘርፍም በጋዜጦችና በራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ ሠርታለች። 'ሁለት ሦስት መልክ - ልጅ ወልዶ ማሳደግ' የሚል መፅሐፍ አላት። መጽሐፉ ከእርግዝና ጀምሮ ልጆችን በማሳደግ ሂደት የገጠሟትን ፈተናዎች እና የሌሎች እናቶች ተሞክሮ ተካቶበታል። ሮዝ መስቲካ 'ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ ለእናቶች' በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች በምታደርገው ዘመቻዎቿና ቅስቀሳዎቿ ትታወቃለች። ባለትዳርና የአራት ልጆች እናት ናት። • በየቀኑ አንድ ሚሊየን ሰው በአባላዘር በሽታ ይያዛል ከመጀመሪያ ልጇ በስተቀር ሦስቱን ልጆቿን ለተከታታይ ስድስት ወራት ያለተጨማሪ ምግብ አጥብታለች። የመጀመሪያ ልጇን ስትወልድ በልምድ ከምታውቀው ውጪ የተሻለ ግንዛቤ ስላልነበራት እና የወለደችበት የጤና ተቋም ልጇ እንደተወለደ እንገር በመስጠት ፋንታ የዱቄት ወተት ስለሰጡት ጡት መጥባት አሻፈረኝ ብሎ እንደቀረ ምክንያቱን ትናገራለች። እግረ መንገዷን ኃላፊነታቸውን በሚገባ የማይወጡ የጤና ተቋማትን በመኮነን ነው ታዲያ። በዚህ ጡት ባልጠባው ልጇና በሌሎቹ መካከል በሽታን በመቋቋም ረገድ ልዩነቱ ከፍተኛ መሆኑን አስተውላለች። እርሱ በቀላሉ በጉንፋንም ሆነ በትንሽ በሽታ ይዳከማል፤ ሌሎቹ ግን በሽታን የመቋቋም አቅማቸው የተሻለ ነው። በወሬ መሃል ሳይጠባ ማደጉን ሲሰማም 'ለምን?' ብሎ ይጠይቃታል፤ ይናደዳል። እርሷም በእርሱ ፊት እንዲህ ብላ ማውራት ትታለች። ሮዝ፤ ልጆቿን እንደ እርሷ ሆኖ የሚንከባከብ ሰው ስለሌለ የመጀመሪያ ልጇን እንደወለደች ከባለቤቷ ጋር ተማክራ ሥራዋን ትታ ልጆቿን በማሳደግ ተጠምዳ ትውላለች። ምን አልባት አማራጮች ቢኖሩ፣ የወሊድ ፈቃድ ጊዜው ቢጨመር፣ ሥራ ቦታዎች የሕፃናት ማቆያ ቢኖር ወደ ሥራዋ ተመልሳ መድረስ የምትፈልግበት ቦታ ልትደርስ ትችል እንደነበር ታስባለች። ልክ እንደሷ ሁሉ አገራቸው የምትፈልጋቸው፣ ችሎታና አቅም ያላቸው ሴቶች እየተቆጩ በየቤታቸው ቀርተዋል ትላለች። ሩቅ ሳትሄድ እናቷ እርሷን ለማሳደግ ሲሉ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን ዋቢ ታደርጋለች። "ከልጅነቴ ጀምሮ የሴቶች ኑሮ በጣም ያሳዝነኛል፤ ያሳስበኛል። እናቴ መምህር ስለነበረች የከፈለችውን ዋጋ አውቃለሁ። ቀኑን ሙሉ ታስተምራለች፤ ቤት ውስጥ ደግሞ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ ኃላፊነቶች ተወጥራ ትውላለች። በዚህም ሴቶች ያሉባቸውን ችግሮች እያየሁ ነው ያደኩት" ትላለች። በዚህም ተነሳስታ በ1996 ዓ.ም የሴቶች ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያተኩር 'አብነት' የተባለ መጽሔት ጀምራ ነበር። እርሷ እንደምትለው በቂ ዝግጅት ሳታደርግ በመጀመሯና ገበያ ላይ የሚፈለገው ይዘት ታዋቂ ሰዎች ላይ ያተኮረ፣ ስሜታዊነት የሚንፀባረቅበት፣ የሴቶች ሕይወት ላይ ሳይሆን አካላዊ ቁንጅና ላይ ያተኮረ ስለነበር ገበያ ላይ እምብዛም አልቆየም። ሴቶች ላይ የሚሰሩ ተቋማትም እንደዚህ ዓይነት ሥራዎችን የማበረታታትና የመደገፍ ልምዱ የላቸውም። ያኔ ነው ስለሴቶች አብዝታ መቆርቆር የጀመረችው። • ልጁን ጡት ያጠባው አባት • ላጤ እናት መሆን የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች "ከባለቤቴ ድጋፍ በማግኘቴና ሥራዬን ለቅቄ ልጆቼን ማጥባት የቻልኩት እድለኛ ሆኜ ነው፤ ይህ እድል የሌላቸው እናቶችስ?" ጥያቄዋ ነው። "ትዳር መያዝና ልጅ መውለድ ስኬታማነት እንደሆነ በማሰብ፤ ወግ ማዕረጉን እንጂ በውስጡ ያለውን ተግዳሮት በቀናነት የሚያካፍል የለም" ትላለች። ሮዝ እንደምትለው የትዳር አጋር ጥሩ የገቢ ምንጭ ኖሮት ሥራ ትቶ ልጅ ማሳደግን መታደልና ደስታ ብቻ እንደሆነ ይቆጠራል። ይሁን እንጂ ሥራ ትቶ ልጆችን ማሳደግ ቀላል አይደለም። በአንድ ወቅት ድብርት ውስጥ ገብታ እንደነበር ታስታውሳለች - ሮዝ። ምንም እንኳን ባለቤቷ ድርሻውን በመወጣቱ ፈተናዎቹን ማለፍ ብትችልም፤ ሥራ ትቶ ቤት ውስጥ መዋል በራሱ የሚያመጣውን ተፅእኖ እንዳለ በተግባር ተመልክታዋለች። ይህ በሌለበት ግን ቤተሰባዊና ማህበራዊ ቀውሶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ትናገራለች። እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ዘመቻ ወደ ማካሄዱ እንዳዘነበለች ትናገራለች - ሮዝ መስቲካ። እንዲህ ዓይነት ዘመቻዎችን ማካሄድ ከጀመረች አራት ዓመታትን አስቆጥራለች። በባለቤቷ ሥራ ምክንያት ወደ ህንድ አገር ተዛውረው ሳለ እዚያው ሆና ነው የጀመረችው። በማህበራዊ ሚዲያዎች በምታካሂዳቸው ዘመቻዎች እናቶች ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ እንዲያገኙና ያለ ተጨማሪ ምግብ ልጆቻቸውን ጡት እንዲያጠቡ ቅስቀሳዎችን ታደርጋለች። ሮዝ ሐምሌ 27/2011 ዓ.ም የጡት ማጥባት ሳምንትን በማስመልከት በጁፒተር ሆቴል መሰናዶ አዘጋጅታለች። በዝግጅቱ ላይ ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ፤ ለስድስት ወር ያህል ያለተጨማሪ ምግብ፤ ከስድስት ወር በኋላ ለሁለት ዓመታት ልጆቻቸውን ያጠቡ እናቶችን ይበረታታሉ። የሕፃናት ማቆያ ያላቸው መሥሪያ ቤቶች ይመሰገናሉ። የግል ድርጅቶች ሆነው መንግሥት ከሚፈቅደው ውጪ የወሊድ ፈቃድ የጨመሩ ድርጅቶችም ምስጋና እንደሚቀርብላቸው ገልጻልናለች። የሮዝ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ሴቶችንና ሕፃናትን የተመለከቱ ሕጎችን በዝርዝር ባትመለከተም የሚከተሉት ግን አሁንም ጥያቄዎቿ ናቸው። • የወንዶች አጋርነት • የወሊድ ፈቃድ የተከለከሉ እናቶች፤ እረፍት ወስደው ሲመለሱ ሥራቸውን ያጡ እናቶች ጉዳይ • የህፃናት ማቆያ በየመሥሪያ ቤቱ እንዲቋቋም የሚያዘውን አዋጅ ትግበራ ክትትል • እናቶች ልጆቻቸውን እስከ ስድስት ወር እንዲያጠቡ ለማድረግ ተጨማሪ የወሊድ ፈቃድ እንዲሰጣቸው የሚሉ "ሁሉም ያሉት ፖሊሲዎች የሚተገበሩት ጤናማ ትውልድ ሲኖር ነው" የምትለው ሮዝ እናቶችና ሕፃናትን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች ጠንካራ መሆን እንዳለባቸው ታሳስባለች።
xlsum_amharic-train-238
https://www.bbc.com/amharic/news-53680615
ኮሮናቫይረስ ፡ 'በጦርነት አድጌ በወረርሽኝ አልሞትም"
"በጦርነት ነው ያደግኩት፤ በወረርሸኙ አልሞትም።"
[ "\"በጦርነት ነው ያደግኩት፤ በወረርሸኙ አልሞትም።\"" ]
ማርጋሬት አልኮክ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ጀርመን በእንግሊዝ ላይ ያደረሰችው "ዘ ብሊትዝ" ተብሎ የሚጠራው የቦምብ ጥቃት በመጠለያ ውስጥ ሆነው ያን ፈታኝ ጊዜ አልፈውታል ። ከዚያም ባሕር፣ ውቅያኖስ ተሻግረው ወደ አውስትራሊያ ተወሰዱ። ላኪ ማርቲን እባላለሁ፤ የ89 ዓመቷ ማርጋሬት አያቴ (ናና) ናት ያንን የጦርነት ጊዜ በጨለምተኝነት አታወሳውም፤ በተቻለ መጠን ሳቅና ቀልድ በተሞላበት መልኩ ነው ጦርነትን የመሰለ አስከፊ ነገር የምታወራው። ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝም እንዲሁ በቀልድ ነው የምታወራው። "አንዳንዴ በምን ተአምር ነው እንዲያው እዚህ ወረርሽኝ ላይ የጣለኝ፤ እንዴት በህይወት እያለሁ ይሄን አየሁ" ትለኛለች ስደውልላት። ከዚያም ትቀጥልና "የከፋ ነገር ስላየሁ ወረርሽኙ ብዙም አያስጨንቀኝም" ትለኛለች። በጥር ወር ላይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአውስትራሊያ ሲያጋጥም አያቶቼ የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል በመሆናቸው ወላጆቼም ሆነ እኔ ከበሽታው እንደሚጠበቁና ምንም እንደማይነካቸው እርግጠኛ ነበርን። ነገር ግን ግምታችን የተሳሳተ ነበር በአምስት ወራት ውስጥ በአውስትራሊያ ከተከሰተው 247 ሞቶች መካከል 156ቱ በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በርካታ አረጋውያንም ሊያልቁ የቻሉበት ምክንያትም የጤና ሥርዓቱ እነዚህን ተጋላጭ የኅብረተሰቡ ክፍሎችን ችላ በማለቱ ነው ተብሎ እየተተቸ ነው። በተለያየ የስልጣን እርከን ደረጃ ላይ የሚገኙ ኃላፊዎችም ለዚህ ክፍተት መፈጠር ጥያቄዎች እየቀረቡላቸው ነው። ፀሃፊዋ ከአያቷ ማርጋሬት አልኮክ "ናና" ጋር በአውስትራሊያ ውስጥ 180 ሺህ ያህል አረጋውያን በእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ይኖራሉ። እነዚህ ማዕከላት በእርዳታ ድርጅቶች፣ በግል ኩባንያዎችና በመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሚተዳደሩ ናቸው። የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ እነዚህም ማዕከላት በፍጥነት ነው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያስገቧቸው። አንዳንዶቹም መንግሥት ካስተላለፈው መመሪያም በማፈንገጥ እንግዶች እንዳይጎበኙ አረጋውያኑም በክፍላቸው ብቻ እንዲቆዩና ሌሎች እንቅስቃሴዎችንም እንዳያደርጉ ሲከለክሉ ቆይተዋል። ማርጋሬት ያሉበት ማዕከል ለተወሰነ ጊዜ ጎብኚዎችን ቢከለክሉም በግቢው ውስጥ እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱና መውጣትም ስለፈቀዱላቸው እድለኛ ናቸው። ሌላኛዋ የ87 ዓመቷ አያቴ፤ የእሷም ስም በሚገርም ሁኔታ ማርጋሬት ነው፤ ከመጋቢት ጀምሮ በክፍሏ ውስጥ ናት። ማዕከሉ በሜልቦርን የሚገኝ ሲሆን፤ ይህች ከተማም የወረርሽኙ ማዕከል ሆናለች። አያቴ በክፍሏ ተወስና ነው ያለችው፤ የሚፈቀድላት በኮሪደሩ ላይ እንድትራመድ ብቻ ነው። ለወራትም ያለ ጎብኚ ብቻዋን ትበላለች፤ ወንበሯ ላይ ቁጭ ብላ ነው የምታሳልፈው። እንዲያም ሆኖ በዚህ አስጨናቂ ሰዓት በማዕከሉ እያገለገሉ ላሉ ሠራተኞች ምስጋናዋ ከፍ ያለ ነው። "እንዲህ ተዘግቶ መቀመጥ ከባድ ቢሆንም ተቀብየዋለሁ፤ ከሁሉ በላይ ለእኔ ደኅንነትም ነው" ትለናለች። "ብዙም አልጨነቅም። ቤተሰቦቼን አለማየቴ ከባድ ቢሆንም እዚህ አይደሉም ማለት ግን አይወዱኝም ማለት አይደለምም" በማለት ስሜታችንን ትነካዋለች። ፀሃፊዋ ከሌላኛዋ አያቷ ማርጋሬት ማርቲን ጋር በቪዲዮ ሲያወሩ እሷ ያለችበትን ማዕከል የሚያስተዳድረው ኩባንያ በሁሉም ነገር ዝግጁ እንደሆነ አሳውቆናል። ጥብቅ የሆነ የጽዳት ቁጥጥርን ጨምሮ፣ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በከፍተኛ መጠን አከማችቷል። ነገር ግን በተለያዩ ሁለት ግዛቶች የሚገኙ ማዕከላት የቫይረሱን መዛመት መቆጣጠር አቅቷቸው በርካታ አረጋውያን ረግፈዋል፤ ይህም ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው ልብ ሰባሪ ሆኗል። እነዚህ አረጋውያን በቫይረሱ በቀላሉ እንደሚጠቁና፣ ተጋላጭም እንደሆኑ ማወቅ የሮኬት ሳይንስ አይደለም። በርካታዎቹ አረጋውያን ሌላ ተደራራቢ ህመሞች ያሉባቸው ሲሆኑ በማዕከላቱም ውስጥ ያለው የህክምና አገልግሎት የተወሰነ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የማዕከሉ ሠራተኞችም በተለያዩ ቦታዎች ከመስራታቸውም አንፃር ቫይረሱን በቀላሉ ያዛምታሉ። በየካቲት ወር ላይ በአውሮፓ በሚገኙ ማዕከላት ውስጥ ያሉ አረጋውያን በሚያሰቅቅ ሁኔታ እንደ ቅጠል እየረገፉ እንደሆነ ታሪኮች መውጣት ጀመሩ። ይህም ሁኔታ በአውስትራሊያ ሊያጋጥም እንደሚችል አገሪቷ ማወቅ ነበረባት የሚሉት በሞናሽ ዩኒቨርስቲ የጤና ሕግ ክፍል ኃላፊ ጆ ኢብራሂም ናቸው። "የአውስትራሊያ ምላሽ በቂ አልነበረም። ለሚመጣው ነገር በሙሉ ዝግጁ አልነበረችም እናም አሁን የተፈጠረው ክስተት ሊያስደንቀን አይገባም" ይላሉ ። "ብዙ ሰዎች ይህ መሆኑ አይቀሬ ነበር ሲሉ ይሰማል። ይሄ ግን ትክክለኛ አይደለም፤ ምክንያቱም ምንም ማድረግ አንችልም ነበር የሚለውን ትርጉም ስለሚሰጥ ነው። የኮሮናቫይረስ በአረጋውያን ላይ ምን ያህል አደጋ እንደደቀነ ከግምት ውስጥም አላስገባነውም። በሌሎች አገሮች ላይ እያለቁ የነበሩትንም አረጋውያን መረጃዎች አላጤንነውም" ይላሉ። በመጋቢት ወር ላይ በሲድኒ የሚገኝ ዶሮቲ ሄንደርሰን ሎጅ የተባለ የአረጋውያን ማዕከል ሠራተኛ በኮሮናቫይረስ መያዟ ተረጋገጠ፤ በግንቦት ወርም 21 በማዕከሉ የሚኖሩ አረጋውያንና ሠራተኞችም ተያዙ። ከእነዚህም ውስጥ ስድስቱ ሞቱ። ሌላ እንዲሁ በሲድኒ ውስጥ የሚገኝ ኒውማርች የተባለ ማዕከልም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ህሙማንን ወደ ጤና ማዕከል ከመላክ ይልቅ ክፍላቸው ውስጥ እንዲዘጉ አደረገ። ማዕከሉ የሠራተኞች ዕጥረት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችም በበቂ ሁኔታ አልነበሩትም። ይህንንም ተከትሎ 19 አረጋውያን ሲሞቱ በርካቶችም በቫይረሱ ተያዙ። በኒውማርች አረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ቤተሰቦቻቸው የሞቱባቸው ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ የአረጋውያኑ መሞት በርካታ ጥያቄዎችን ቢያጭርም ይህ ለምን እንደተከሰተ አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጥ አካል አልተገኘም። አሁንም ከክስተቱ ያልተማረችው አውስትራሊያ አረጋውያኗን በኮሮናቫይረስ እያጣች ነው። የቪክቶሪያ ግዛት እንደ አዲስ ወረርሽኙ እያገረሸባት ሲሆን ከማህበረሰቡ ስርጭት በተጨማሪ የአረጋውያኑ የእንክብካቤ ማዕከላት በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቁ ነው። በአሁኑ ወቅትም 1 ሺህ 200 የሚሆኑ አረጋውያን በ97 ማዕከላት ውስጥ መያዛቸው ተረጋግጧል። ፕሮፌሰር ኢብራሂም እንደሚሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ብቻቸውን ቫይረሱን መግታት አይችሉም። "በሽታው ቢያጋጥም ምን ማድረግ አለብን የሚለው ላይ የተቀመጠ ግልጽ ያለ ፖሊሲም ሆነ ይህንንም መቆጣጠር የሚችል መዋቅር አልተዘረጋም" ይላሉ። የአረጋውያኑን የእንክብካቤ ማዕከላት በቀጥታ የሚመለከተው የፌደራል መንግሥቱን ቢሆንም ወረርሽኙን ደግሞ በየግዛቱ ያሉ የኅብረተሰብ ጤና ኃላፊዎች በበላይነት ይቆጣጠሩታል። "በዚህም ምክንያቱ ኃላፊነቱ የማን ነው በሚል መወዛገብ ተፈጠረ። ይሄ ብቻ አይደለም የኮሮናቫይረስ ህሙማን ህክምናው መሰጠት ያለበት ሆስፒታል ወይስ ቤታቸው ውስጥ የሚለውም ላይ ውሳኔ ሳያገኝ እንዲሁ እያወዛገበ ነበርም" በማለት ያስረዳሉ። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንቶኒ አልባኔዝ በዚህ ሳምንት ሰፋ ያለ ምርመራና ኃላፊነት ሊወስዱ የሚባቸውም አካላት እንዲጠየቁ ተናግረዋል። "በኒውማርች እንክብካቤ ማዕከል ካጋጠመን ክስተት ለምን አልተማርንም? ይህ የተከሰተው ከወራት በፊት ነበር" በማለትም ይጠይቃሉ። በሜልቦርን የግዛቲቷና የፌደራል ኤጀንሲዎች ተጣምረውም በቪክቶሪያ የተከሰተውን የወረርሽኝ ቀውስ ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው። ለፕሮፌሰር ኢብራሂም ግን ዋናው ነገር ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በአውስትራሊያ የሚገኙ የእንክብካቤ ማዕከላት ሁኔታ ሊገመገም እንዲሁም ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል ይላሉ። "በዚህም መንገድ ነው የትኞቹ ማዕከላት አደጋ ውስጥ እንዳሉ የምንረዳው" የሚሉት ፕሮፌሰሩ አክለውም "ከዚያ በመቀጠልም ያለምንም ማንገራገር ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ ሊወሰድ ይገባል" በማለትም ምክራቸውን ለግሰዋል። በእንክብካቤ ማዕከላቱ የተፈጠረውንም ሁኔታ የሚያጣራ የመንግሥት ቡድንም ተቋቁሟል። ከተለያዩ ቦታዎች የተገኙ መረጃዎች እንደሚያስረዱትም ለእነዚህ አረጋውያን መሞት ዋነኛ ምክንያቶች በማዕከላቱ የሚገኙ ሠራተኞች እጥረት እና በቂ ስልጠና አለማግኘት የሚጠቀሱ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ ቁሳቁሶች እጥረትና የጤና ኃላፊዎች ምላሽ መዘግየት ይገኙበታል። የአውስትራሊያ ህክምና ማኅበር በበኩሉ መንግሥትን ተጠያቂ አድርጓል፤ ጥብቅ ምርመራም ያስፈልጋል እያለ ነው። በቪክቶሪያ የሚገኘው ቅርንጫፉ ፕሬዚዳንት ጁሊያን ራይት ለናይን ጋዜጣ እንደተናገሩት ቀውሱ "የተገመተውን አሳዛኝ ክስተት ጥሎ አልፏል" እንዳሉ አስነብቧል። በቪክቶሪያ የሚገኙ በርካታ አረጋውያን በኮሮናቫይረስ መሞታቸው አይቀሬ እንደሆነ የአውስትራሊያ ጤና ቢሮ ፀሐፊ ብሬንዳን መርፊ ከሰሞኑ ተናግረዋል። ውድ አያቶቼ በእነዚህ ማዕከላት አለመገኘታቸው እድለኛ ነኝ። አሁንም የሚገኙባቸው የእንክብካቤ ማዕከላት ከኮሮናቫይረስ ነፃ ናቸው። አንደኛዋ አያቴ ማርጋሬት ጎብኚም አያያትም፤ ሌላኛዋ አያቴ ማርጋሬትን ግን በሳምንት አንዴ እንድናያት ተፈቅዶልናል፤ እናቴም ቅዳሜ እለት ሄዳ ነበር። ለረዥም ጊዜያት ሳቁ፣ ተቃቀፉ፣ ቀልድም ጣል እያደረጉ ኮሮናቫይረስ እንዳለ ዘነጉት። አያቴ ናና ቫይረሱ ከያዛት መሞቻዬ ነው ብትልም እንዲህ በቀላሉ እጅ አልሰጥም ትላለች። "ህፃን እያለሁ ዳክዬዎች አባረሩኝ ግን አልደረሱብኝም፤ አሁንም ኮሮናቫይረስ ይይዘኛል የሚል ግምት የለኝም" ብላ አስቃናለች።
xlsum_amharic-train-239
https://www.bbc.com/amharic/news-43174899
ፍቅርና ጋብቻ በቀይ ሽብር ዘመን
ፍቅር ተስፋ በሌለባቸው ቦታዎችም ያብባል
[ "ፍቅር ተስፋ በሌለባቸው ቦታዎችም ያብባል" ]
ለአይናለምና ለገነትም ይህ ነበር የሆነው። እ.አ.አ በ1978 በኢትዯጵያ ታሪክ ከባድ የቀይ ሽበር ወቅት ተጋቡ። የደም መፋሰሱ ከጋብቻቸው ከዓመት በፊተ የጀመረ ሲሆን፤ እሱም መንግሥቱ ኃይለማሪያም ሥልጣን ይዞ ጠላቶቹን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳበት ጊዜ ነበር። . ሥልጣን በተቆጣጠረበትም ጊዜ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞቱ ደግሞም በሺህ የሚቆጠሩ ለመፈናቀል ተገደው ነበር። ይህ ግን አይናለምንና ገነትን ከአዲስ አበባ ወጣ ብላ በምትገኘው በሰንዳፋ የጋብቻ ቃላቸውን ከመቀያየር አላገዳቸውም ነበር። ለዚህ ታስበው የተወሰዱት ፎቶግራፎች ከ Vintage Addis Ababa ሲሆን በልዩ ሁኔታዎች ላይ ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ማሳያ እንዲሆን ታስቦ በቤተ-መዛግብት የተቀመጡ ነበሩ። ረዥሙ የመጠናናት ጊዜ እ.አ.አ በ1973 ነበር፤ ወጣቶቹ የተዋወቁት በአንድ ሰፈር ይኖሩ ስለነበር ነው። በዓመቱ ደርግ መንግሥት ወደ ሥልጣን ሲመጣ ለመንግሥቱ ኃይለማሪያም የሥልጣን ጥርጊያ መንገድ አመቻቸ። እ.አ.አ በ2008 በሌለበት መነግሥቱ ኃይለማሪያም ሞት ተፈርዶበታል። እሱ በዚምባብዌ ነው የሚኖረው። ይህን ተከትሎ የተከሰተው ግርግር ሳያስቡት ሕይወታቸውን አንጠልጥሎ አስቀረው። አይናለም ገነትን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንደጨረሰች ለማግባት አቅዶ ነበር። ሆኖም ግን እ.አ.አ በ1978 የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተይዛ ለሦስት ወራት ታሰረች። "በደርግ ስር መኖር ቀላል አልነበረም" ትላለች ገነት። በመቀጠልም "ያለው ፍራቻ ሙሉ ሰው ከመሆን ያደናቅፈን ነበር" ብላለች። የደርግ ሥርዓት የታሰረን ሰው ቤተሰብ እንዲጠይቅ ባይፈቅድም፤ አይናለም ግን በየተወሰነ ቀናት ገነትን ያያት ነበር። የአብዮቱ ጠባቂ ስለነበር ሌሎች ተቃዋሚዎች ስለግንኙነታቸው ቢያውቁ ለሕይወቷ ያሰጋ ስለበር በጣም ይጠነቀቅ ነበር። "ሰላም መባባልም ሆነ መነጋገር አንችልም ነበር። ጥበቃዎቹ እንደምንተዋወቅ ሊያውቁብን ይችሉ ነበር። ሆኖም ግን ግቢው ውስጥ ባየሁት ቁጥር ደስ ይለኝ ነበር" ትላለች። ገነት ታስራ የነበረ ቢሆንም የጋብቻቸው ፎቶግራፎች ግን የጉስቁልና አንዳች ምልክት የላቸውም። ጉልበት ተሳመ የሠርጋቸውን ዕለት በኢትዮጵያ ባህል መሠረት ጀመሩት። አይናለም ገነትን ከቤተሰቦቿ ቤት ወደ እራሱ ቤት ለመውሰድ ከመሄዱ በፊት የእናቱን ጉልበት ስሞ ነበር ከቤቱ የወጣው። በቤቱ ደጃፍ ላይም ጎረቤትና ጓደኞቹ ሊሸኙት ተሰብስበው ነበር። ጥቁር ሱፍ አንገትን በሚሸፍን ነጭ ሹራብ የለበሰው አይናለም ገነትን ለማምጣት ወደ ተዘጋጀችው ቼቭሮሌት አቀና ። ቀለበቶቻቸውን ፒያሳ ከሚገኘው አፍሪካ ወርቅ ቤት የገዙት ሙሽሮች ከሰዓት በኋላ በገነት አባት ቤት ቄስ ፊት ቃል ገቡ። ከተጋበዙት 300 ሰዎችም ራቅ ብለው ሙሽሮቹ ፎቶግራፍም ለመነሳት ችለው ነበር። ለገነት በሚያሳዝን ሁኔታ ግን አይናለም እ.አ.አ በ2008 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። እሷ ግን አብረው ያሳለፉትን ጊዜያት በጣም እንደምትወድና እንደምትናፍቅ ትናገራለች። "ያፈቀርኩትን ሰው ነበር ያገባሁት፣ ያሳደግሁትም ከልቤ የምወዳቸውን ልጆች ነው" ትላለች። የፎቶግራፎቹ መብት ሙሉ በሙሉ የVintage Addis Ababa ነው።
xlsum_amharic-train-240
https://www.bbc.com/amharic/news-54478773
ተፈጥሮ ፡ እውቅና ሳያገኝ ለአደጋ የተጋለጠው የሃላይ ደጌ አሰቦት ጥብቅ ደን
የሃላይደጌ አሰቦት "ብሔራዊ እጩ ፓርክ" በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ ብርቅዬ የሆኑ እንስሳትን በውስጡ የያዘ ነው። ከ1960ዎቹ ጀምሮ በጥብቅ ደንነት የኖረው ፓርኩ፣ በብሔራዊ ፓርክ ደረጃ አለማደጉ ግን በበጀትና በአስተዳደር የተደረጃ እንዳይሆንና ለሕገ ወጥ ድርጊት ተጋላጭ አድርጎታል።
[ "የሃላይደጌ አሰቦት \"ብሔራዊ እጩ ፓርክ\" በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ ብርቅዬ የሆኑ እንስሳትን በውስጡ የያዘ ነው። ከ1960ዎቹ ጀምሮ በጥብቅ ደንነት የኖረው ፓርኩ፣ በብሔራዊ ፓርክ ደረጃ አለማደጉ ግን በበጀትና በአስተዳደር የተደረጃ እንዳይሆንና ለሕገ ወጥ ድርጊት ተጋላጭ አድርጎታል።" ]
በአፋርና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኘው ሃላይደጌ አሰቦት ፓርክ፣ 1 ሺህ 90 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት እንደሚሸፍንና በርካታ እንስሳትንና የእጽዋት ዝርያዎችን ያቀፈ መሆኑን የፓርኩ ኃላፊ አቶ መቆያ ማሞ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንደሃላፊው ገለጻ በፓርኩ ውስጥ 42 አጥቢ የዱር እንስሳት፣ ከ240 በላይ አዕዋፋት እና ከ260 በላይ ደግሞ የዕጸዋት ዝርያዎች ይገኙበታል። አብዛኞቹ እንስሳት ጎብኚዎች ሊያይዋቸው የሚፈልገጨውና ምናልባትም በአፍሪካ ደረጃ በብዛት በዚሁ ፓርክ የሚገኙ መሆናቸውን አቶ መቆያ ይገልጻሉ። ፓርኩ ከአዲስ አበባ ወደ ሐረር በሚወስደው መንገድ 280 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝ፣ ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ብዙም ያልራቀ ምቹ የጉብኝት አካባቢ መሆኑን ኃላፊው ያብራራሉ። ፓርኩ በብሔራዊ ፓርክ ደረጃ ተመዝግቦ አስፈላጊው የአስተዳደርና የጥበቃ ሁኔታ እንዲሟላላት ጥያቄ ማቅረብ የተጀመረው ከስድስት ዓመታት በፊት በ2006 ዓ.ም ነበር። ነገር ግን እስካሁን ጥያቄው ምላሽ አላገኘም። በወቅቱ ሁሉንም መስፈርቶች በማሟላት የአካባቢውን ማኅበረሰብ ይሁንታን በማግኘት እውቅናውን ለማሰጠት ሂደቱ መጀመሩን አቶ መቆያ ያስታውሳሉ። ከሃላይደጌ አሰቦት ጋር ሰባት ፓርኮች ወደ ብሔራዊ ፓርክነት ለማደግ ጥያቄ ቢያቀርቡም እነሱ ግን እስካሁን እውቅና አላገኙም። "ሰነድ በማዘጋጀት ረገድ የሚጠበቅብንን ሁሉ አጠናቀናል" የሚሉት አቶ መቆያ፣ "ሰነዱ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስፈላጊው ምርመራና ማሻሻያ ተደርጎበት አስተያየት እንድንሰጥ ተመልሶልናል" ይላሉ። የያንጉድራሳ ብሔራዊ ፓርክ ከሃላይ ደጌ አሰቦት ፓርክ በቅርብ ርቀት ስለሚገኝ፣ የሃይላደጌ አሰቦት ፓርክን በሞግዚትነት ያስተዳድረው ነበር። የያንጉድራሳ ብሔራዊ ፓርክ ቀደም ሲል በፌደራል መንግሥት ሥር ይተዳደር የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን የአፋር ክልል በራሱ ሊያስተዳደረው ሂደቶች እየተጠናቀቁ ነው። ይህ ሲሆን ደግሞ የሃላይ ደጌ አሰቦት ብሔራዊ ፓርክ ብቻውን ያለ ጠባቂ ይቀራል የሚል ስጋትን ፈጥሯል። በዚህ ምክንያትም ጥበቃው ያልተጠናከረ ከመሆኑ አንጻር የዱር እንስሳቱ ለሕገ ወጥ አደን ይጋለጣሉ፣ ሌሎች ሕገ ወጥ ተግባራትም ሊስፋፉ ይችላሉ የሚለው ስጋትም አለ። አብዛኞቹ የአካባቢው የዱር እንስሳት አነስተኛ ዝርያ ያላቸውና በመጥፋት ላይ ያሉ በመሆናቸው እነዚህ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ከነጭራሹ የመጥፋት አደጋ ሊገጥማቸው ይችላል የሚለውም ሌላኛው ስጋት ነው። በአፋር በኩል የዱር እንስሳትን የመጠበቅ ጥሩ ልምድ መኖሩ ለፓርኩ ሕልውና አንዱ እድል ቢሆንም፤ በሌላ በኩል ግን እነዚህን እንስሳት አንዳንድ ሰዎች ለመድኃኒትነትና ለሌሎች ጉዳዮች ስለሚፈልጓቸው በሕገ ወጥ አደን ሊያጠፏቸው ይችላሉ ይላሉ አቶ መቆያ። በፓርኩ ላይ የተጋረጠው አደጋ ፈጣን ምላሽ የሚያስፈልገው መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጂራ ይናገራሉ። ፓርኩን ወደ ብሔራዊ ፓርክነት የማሳደጉ ሂደት በተለያዩ ምክንያቶች ከሚገባው በላይ መጓተቱን የሚያምኑት አቶ ኩመራ፤ በአሁኑ ወቅት ግን ተስፋ ሰጭ ደረጃ ላይ ነው ያለው ይላሉ። ፓርኩ በሁለት ክልሎች ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኝ መዋቅርን ማሳተፍ እንደሚጠይቅ ጠቅሰው፤ እስካሁን ሂደቱ በሚፈለገው መጠን ባይፈጥንም ነገር ግን በሚንስትሮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ አስፈላጊው መረጃ ተሰባስቦ በዝግጅት ላይ መሆኑን ይገልጻሉ። በርካታ አደረጃጀቶችና የለውጥ ሥራዎች ስለሚሰሩ ከእነሱ ጋር ማጣጣሙ ጊዜ እንደወሰደ ተናግረዋል። ፓርኩ ለረጅም ጊዜ 'ጥብቅ ክልል' ተብሎ ነበር የሚታወቀው። በዚህ ምክንያትም ፓርኩ ተገቢው ጥበቃና አስተዳደር ሳያገኝ ቆይቷል። ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ግን ፓርኩ ያለውን ጥቅም በመገንዘብ በያንጉድራሳ ፓርክ ጥላ ስር ሆኖ ሲተዳደር ነበር። ፓርኩ ለቱሪዝም ዘርፍ እምቅ ሃብት ያለው ሲሆን፤ ሳላ የሚባለው እንስሳ በአፍሪካ ደረጃ በብዛት የሚገኝበትም ነው። ይህ እንስሳ በብዛት የሚገኘው ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን ከኢትዮጵያ ደግሞ በብዛት የሚገኘው ሃላይ ደጌ አሰቦት መሆኑን አቶ ኩመራ ተናግረዋል። ሌላኛው ለጥፋት የተጋለጠው የሜዳ አህያ ዝርያም በዚሁ ፓርክ ውስጥ ይገኛል። የዚህ ዝርያ ትልቁ መንጋ የሚገኘው እዚሁ ፓርክ ውስጥ መሆኑን አቶ ኩመራ ዋቅጂራ ይገልጻሉ። በመሆኑም እነዚህ እንስሳትን በዘላቂነት በፓርኩ ውስጥ ህልውናቸውን ለማስጠበቅና ፓርኩ የሚሰጠውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማሳደግ ጥረቶች ቀደም ብለው ቢጀመሩም እስካሁን መቋጫ እንዳላገኙ ይገልጻሉ። ከ40 ዓመታት በላይ በጥብቅ ደንነት ብቻ በመቆየቱ በ2002 ዓ.ም ጥብቅ ደኑ ያሉት ጸጋዎች ተለይተው በያንጉድራሳ ፓርክ ጥላ ሥር ሆኖ ጥበቃ እንዲደረግለት መደረጉም ተነግሯል። ከአራት ዓመታት በኋላ ደግሞ የባለሙያ ቡድን ተዋቅሮ በ2006 ዓ.ም ወደ እጩ ብሔራዊ ፓርክነት እንዲያድግ ሥራዎች ተሰርተው መነሻ ሐሳቡ ለሚመለከተው አካል ጥያቄው ቀርቧል። በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች ምክክር ተደርጎ ስምምነት ላይም ተደርሶ እንደነበር አቶ ኩመራ ያስታውሳሉ። በወቅቱ ቀሪው ሂደት የነበረው የብሔራዊ ፓርክነት እውቅና እንዲያገኝ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚንስትሮች ምክር ቤት እንዲቀርብ ማድረግ ነበር። ነገር ግን እዚህ ደረጃ ከተደረሰ በኋላ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በኩል የተወሰኑ ቢሮዎች ጉዳዩን እንደማያውቁትና አካሄዱም ትክክል አለመሆኑን መግለጽ በመጀመራቸው ሂደቱን ማስቀጠል አለመቻሉን አቶ ኩመራ ይገልጻሉ። ፓርኩ አሰቦት ገዳምንም የሚያካትት ስለነበረ 'ሃላይደጌ አሰቦት' የሚል ስም በመያዙ ከስያሜ ጋር የተያያዘ ቅሬታ አጋጥሞ ነበር። በዚህ መካከል ደግሞ አመራሮች በፍጥነት ስለሚቀያየሩ መጀመሪያ ጉዳዩን ያንቀሳቀሱት አካላት በመቀየራቸው ጉዳዩ እንደገና ተመልሶ ወደ ኋላ ተጎተተ ይላሉ አቶ ኩመራ። በዚህ ምክንያት ፓርኩን ወደ ብሔራዊ ፓርክነት የማሳደጉ ሂደት ተስተጓጎለ። የሚንስትሮች ምክር ቤት ደግሞ ሁሉም በየደረጃው የሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት የተስማሙበትን ሰነድ ካረጋገጠ በኋላ ነው እውቅና የሚሰጠው። በሁለቱ ክልሎች በኩል በተነሱ ቅሬታዎች ምክንያትም እነዚህ ሂደቶች እንዲሟሉ ወደ ኋላ ተመልሶ የሁለቱንም ክልል የየደረጃው አመራሮችና ነዋሪዎችን ማወያየት ማስፈለጉም ተነግሯል። ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኩመራ እንደሚሉትም እነዚህን ጉዳዮች ታሳቢ በማድረግ በአሁኑ ወቅት አንድ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ፣ ዝርዝር እቅድ ተዘጋጅቶለት፣ ለእውቅና ሚያበቁት ሂደቶችና የክልሎች ይሁንታ ተጠናቆ የእውቅና ጥያቄው እስከመቼ መቅረብ እንዳለበት በእቅድ መቀመጡን ጠቅሰዋል። በዚሁ መሰረትም በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ቀሪ ሥራዎች ተጠናቀው ለሚንስትሮች ምክር ቤት የእውቅና ጥያቄ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
xlsum_amharic-train-241
https://www.bbc.com/amharic/news-56924983
ምርጫ 2013፡ "በራሱ መሬት ላይ እንግዳ የሆነ ሕዝብ ቢኖር የአፋር ሕዝብ ነው"
በአሸባሪነት ተፈርጇል። እንደ ግንቦት 7 እና ኦብነግ ነፍጥ አንስቶ በኤርትራ በረሃ ኳትኗል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር ሥልጣን ከያዘ በኋላ ወደ አገር ቤት ገብቷል።
[ "በአሸባሪነት ተፈርጇል። እንደ ግንቦት 7 እና ኦብነግ ነፍጥ አንስቶ በኤርትራ በረሃ ኳትኗል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር ሥልጣን ከያዘ በኋላ ወደ አገር ቤት ገብቷል።" ]
አሁን በአፋር ከፍተኛ ተሰሚነት ካላቸው ፓርቲዎች አንዱ ነው። "የአፋር ሕዝብ ፓርቲ" ወይም በእንግሊዝኛ ምሕጻሩ ኤፒፒ (APP) ተብሎ ይጠራል። ከፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ሙሳ አደም ጋር በቁልፍ የአፋር ሕዝብ ጉዳዮች ዙርያ ዘለግ ያለ ቆይታ አድርገናል። ፓርቲ ስለበዛ እስኪ የእርስዎን ፓርቲ በአጭሩ ያስተዋውቁን? በፈረንጆች 2010 ላይ ነው የተመሠረትነው። ከዚያ በኋላ ግን ሕጋዊነት አልነበረውም። እዚህ የነበረው ነገር ፈረሰና ከዚያ ፓርቲው በአሸባሪነት ተፈረጀ። አባላቱ ተበተኑ። ህቡዕ ገባን። ተሰደድን። ምን ያህል ወታደሮች ነበሯችሁ? ወደ 3ሺህ ታጣቂ ወታደሮች ነበሩን። ኤርትራ ነው የነበሩት። ወታደሮቻችሁ አሁን የት ነው ያሉት? ከለውጡ በኋላ በምዕራፍ፣ በምዕራፍ አስገብተናቸዋል። አጠቃላይ ወታደሮቻችን መልሰው ተቋቁመዋል። የወታደራዊ ክንፋችን ዜሮ ፐርሰንት ነው፤ በዚህ ሰዓት። ምን ያህል አባላት አሏችሁ? በቋሚነት ወርሃዊ ክፍያ የሚከፍሉ አባላት 250ሺህ ሰዎች ይሆናሉ። ለምንድነው "የአፋር ግንቦት 7" የሚሏችሁ? ዛሬም አንድ ጋዜጠኛ ይህንኑ ሲጠይቀኝ ነበር። 'ከግንቦት 7 ጋር ግንኘነት አላችሁ ይባላል' አለኝ። 'ግንቦት 7 አለ እንዴ?' አልኩት። ምናልባት መንፈሱን ኢዜማ ወርሶት ከሆነ ብለን በዚያ እንያዘውና ጥያቄውን እንቀጥል። ለምን ይህ ቅጽል መጣ? የግንቦት 7 ተላላኪዎችም' የሚሏችሁ አሉ። የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ሲፈጠርም አግላይ አስተሳሰብ የለውም። ጽንፈኛም አይደለም። አማካይ (Moderate) የፖለቲካ አካሄድን ነው የሚመርጠው። ግንቦት 7 በትግል ወቅት አብረን የተባረርን የትግል አጋር ፓርቲ ነበር። ኤርትራም ሳለን ሰፊ ግንኙነት ነበረን፣ ውጭ እያለንም 'ኢትዮጵያን ናሽናል ሞቭመንት' የሚባል እንቅስቃሴ ነበረን። እዚያ ውስጥ እነ ሌንጮ ባቲ የነበሩበት ድርጅት፣ የሲዳማ አርነት ንቅናቄና እኛም፣ ግንቦት 7ም ነበረ። አሁን ግንቦት 7ም ፈርሶ እኛም እንደ አዲስ ተደራጅተን ነው ያለነው። አሁን ኢዜማ አለ። ኢዜማና ፓርቲያችን ጥሩ ግንኙነት ነው ያለን። ይሄ ምንም የሚሸፋፈን ነገር የለውም። በፖለቲካ አስተሳሰብ ደረጃ ግን አንድ ነን ማለት አይደለም። መሠረታዊው ልዩነታችሁ ምንድነው? ለምሳሌ በመንግሥት አወቃቀር ላይ እኛ አሁን ያለው የፌዴራል አወቃቀር መቀጠል አለበት፣ ችግር የለበትም ነው የምንለው። ቋንቋ ላይ መሠረት ያደረግ ዘውጌ የፌዴራል አወቃቀር ትክክለኛ ነው ብላችሁ ነው የምታምኑት? አዎ! ፌዴራል አወቃቀር ችግር አለበት ብለን አናምንም። የፌዴራሊዝሙ አፈጻጸም፣ የተተገበረበት መንገድና 'ማኒፑሌት' የተደረገበት መንገድ (የተጠመዘዘበት ሁኔታ) ግን መርዘኛ ነው ብለን እናምናለን። መርዘኛ ብቻ ሳይሆን ሕዝቦች ማንነታቸውን ይዘው አብረው እንዳይኖሩ የሚያደርግ መጥፎ አተገባበር ነበረ ብለን ነው የምናስበው። ኢዜማ ደግሞ መልከአምድራዊ (Geographic) ፌዴራሊዝም ነው መኖር ያለበት ይላል። ከእኛ ጋር በጣም ይራራቃል። የአፋር ሕዝብ መንፈሳዊ አባት ከነበሩት ሡልጣን ሐንፍሬይ አሊሚራህ ጋር የናንተ ፓርቲ የተለየ ግንኙነት ነበረው ልበል? ስትገቡም አብራችሁ ነው የገባችሁት። ሡልጣን አሊሚራህ በጣም ቅርብ ወዳጃችንም መካሪችንም ነበሩ። በወንድማቸው የሚመራ የአፋር ነጻ አውጪ ፓርቲ አለ። እኩል ነበር የሚያዩን። በተለይ ከእኛ ፓርቲ መሪ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ጋር ልባዊ ግንኙነት ነበራቸው። የተሰደዱ ጊዜ ከፍተኛ አቀባበል አድርገንላቸዋል። በብዙ ነገር ይደግፉን ነበር። ከሚጠበቅባቸው አባታዊ ድጋፍም በላይ መካሪያችን ነበሩ። ይሄን ጥያቄ ያለምክንያት አላነሳሁም፣ አቶ ሙሳ። ሡልጣኑ ከእናንነተ ጋር መወገን የጨዋታውን ሕግ ስለሚቀይር ነው። እርሳቸው በአፋር ክልል "አያቶላህ" ማለት ናቸው። በፖለቲካ ባረኳችሁ (Endorse ) ማለት ትልቅ የፖለቲካ ድል ነው። የድጋፍ መሠረታችሁንም ያደላድላል። ልክ ነህ። ይሄ እንግዲህ እንደ ሰው ዕይታ ነው የሚወሰነው። እኛ በፕሮግራም ደረጃ ለአገር ሽማግሌዎች፣ ለነባር ታጋዮች እና ለመንፈሳዊ አባቶች ፕሮግራም ቀርጸን ነው የምንቀሳቀሰው። ለአገር ሽማግሌዎች የተለየ ስፍራ አለን። ራሱን የቻለ ፓርላማ (ቼምበር) አዘጋጅተናል...። እሱን ወደኋላ እንመለስበታለን። ሌላ ጥያቄ ላንሳ። ፓርቲያችሁ ስለሴቶች ግድ ይለዋል? ለምሳሌ ስንት አባላት በአመራር ደረጃ አሏችሁ? እኛ የሴቶችን ተሳትፎ በዋዛ አንመለከተውም። ሴቶች ያለገደብ የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ነው የምንታገለው። የአፋር ሴት እንደሌሎች አካባቢዎች ሁኔታዎች የተመቻቹላት ሴት አይደለችም። የአፋር ሴቶችን ወደ ፖለቲካ ሜዳ ማምጣት በራሱ ቀላል ሥራ አይምሰልህ። ያም ሆኖ በጣም ብዙ ሴት አባልና ደጋፊዎች አሉን። ወጣት ሴቶች በስፋት ገብተው ፖለቲካ እንዲሠሩ እናደርጋለን። በአሐዝ አስደግፈው ይገሩኝ፤ ስንት አባላት በሥራ አስፈጻሚ ደረጃ አሉ? ከአሥራ አንድ ሥራ አስፈጻሚ መሀል አራቱ ሴቶች ናቸው። ቁልፍ ኃላፊነቶችን የያዙም ናቸው። በማዕከላዊ ኮሚቴ ደረጃ 45 አባላት አሉ። 15ቱ ሴቶች ናቸው። ትንሽ ቁጥር ነው፤ እናውቃለን። ግን በስፋት እየሠራንበት ነው። በነገርህ ላይ፣ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከብዙዎቹ እኛ በሴቶች አሳታፊነት የላቅን ነን። ምርጫ ቦርድ በዚህ ረገድ ያወጣው ጥናት አለ። እኛ ጋ በአባላት ደረጃ 34 ከመቶ ሴቶች ናቸው። ይሄ ትንሽ ቁጥር ቢመስልም በአገር ደረጃ ትልቁ 38 ከመቶ ነው። እውነት ለመናገር እኛ ሴቶችን ወደፊት ለማምጣት ቁርጠኛ ነን፤ ግን ሥራው ቀላል አይደለም። የአፋር ሴት ሌሊት ወጥታ ማታ ነው የምትገባው። እንጨት ለቅማ፥ እረኝነቱ፤ ውሃ መቅዳት በሴቷ ጫንቃ ላይ ነው ያለው። የአፋር ሴት ፖለቲካን ለመሥራት ምን የተመቻቸላት ነገር አለ? ይቺ አሐዝ ላይ የደረስነውም በከፍተኛ ትኩረት ስለሠራንበት ነው። ከተመረጣችሁ የአፋር ፓርላማን ባለ ሁለት ቼምበር ለማድረግ አስባችኋል። የባሕላዊ ሽማግሌዎች የሚወከሉበት ሸንጎ ይኖረዋል። ይሄ ለምን አስፈለገ? ከጀርባው ያለው ፖለቲካዊ አመክንዮ ምንድነው? ጥሩ! በክልልም በአገርም ደረጃ እያወዛገበን ያለ ነገር አለ። ወይ ዘመናዊ አልሆንም ወይም በራሳችን ባሕል ውስጥ ዘመናዊ ፖለቲካን አልፈጠርንም። በመሀል እየዋለለን ያለን ሕዝቦች ነን። ተጭበርብረናል። አመክንዮው ወደራስ መመለስ ነው። እኛ በምክር ቤት ደረጃ ሁለቱ ምክር ቤቶች (ቼምበርስ) ይኖሩናል። ሦስተኛ ደግሞ አማካሪ ምክር ቤት ይባላል። የመጀመርያው ምክር ቤት በሕዝብ በሚመረጡ እንደራሴዎች የሚሞላ ነው። ሁለተኛው ከተለያዩ ባሕላዊ ተቋማት በተለይም ሃይማኖታዊና ባሕላዊ አባቶች፣ ነባር ታጋዮች የሚወከሉበት ነው። የአፋር ሽማግሌዎች በማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ታግለው ይምጡ፣ ለሕዝባችን ለአገራችን ዋጋ ከፍለዋል፣ ወድቀው ተነስተዋል፤ ብዙ አይተዋል። እነዚህ ሽማግሌዎች ወደድንም ጠላንም የካበተና የደረጀ ዕውቀት አላቸው። ለዚህ ተገቢውን ቦታ መስጠት አለብን። መንግሥት "ፈንክሽን" ሲያደርግ ባሕላዊውንም ዘመናዊውምን አስተዳደር አጣምሮና አስታርቆ መሄድ አለበት ብለን እናምናለን። ሁለቱ ቼምበር ያስፈለገው ለዚህ ነው። በመሀል የአማካሪ ምክር ቤት አለ። አማካሪ ምክር ቤቱ ደግሞ በየትኛውም ዓለም የሚገኙ የአፋር ተወላጆች የሆኑ ምሁራንን ያቀፈ ነው የሚሆነው። ይህ አማካሪ ምክር ቤት የባሕላዊ ሸንጎውንና የላይኛውን የክልል ምክር ቤት እንደ ድልድይ ያገናኛል። የአፋር ሕዝብ በማይናወጽ ብሔራዊ ስሜቱ ይነሳል። መንፈሳዊ መሪው "እንኳን እኛ ግመሎቻችን ባንዲራውን ያውቋታል" ብለዋል ይባላል። በታሪክም ውስጥ በግዛት አንድነት ጉዳይ ላይ ከቱርክ፣ ከግብጽ፣ ከፖርቹጋል የመጡ ወራሪዎችን በመመከት ይነሳል። የአፋር ሕዝብ ለዚህ ተግባሩ በኢትዮጵያ ታሪክ ተገቢው ቦታ ተሰጥቶታል ብለው ያምናሉ? ወይስ ተገድፏል? የአፋር ሕዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ በተለይ ሉዓላዊነትና አገራዊ አንድነት ላይ ሰፊ ገድል የፈጸመ ሕዝብ ነው። እንደ አገር ያልተዋጋናቸው፣ እንደ ሕዝብ ብቻ የመለስናቸው ትልልቅ ውጊያዎች አሉ። አፋር ብትመጣ ዕውቅ የጦርነት አውድማዎች አሉ። የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይዘምት አፋሮች ብቻ የመከቷቸው ብዙ ጦርነቶች አሉ። አልተጻፉም እንጂ። የተለያዩ ወራሪዎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ በመጡበት ጊዜ ትላልቅ ውጊያ አፋሮች አድርገው ውጊያ በተጀመረበት መሬት እንዲያልቅ አድርገዋል። በታሪክ ደረጃ አፋር ተወርቶለታል ወይ ላልከኝ የሚያውቀው ያውቀዋል። ነገር ግን ሌላው እንደሚንቆለጳጰሰው አልተንቆለጳጰሰም። ሕዝቡም ያን የሚፈልግ አይደለም። በአገሩ ጉዳይ ከማንም ምስጋና እንዲቸረው አይፈልግም። በነገርህ ላይ ጣሊያንን የወጉ አርበኛ አባቶች ዛሬም አፋር አሉ። ሜዳሊያ ያጠለቀላቸው ግን የለም። ባንዲራ ያለበሳቸው የለም። ታሪካችሁን እንጻፍ ያላቸው ግን የለም። የፖለቲካ ታሪክ (Political History)ን የሚጽፉ ሰዎች አፋር ቢመጡ ቱባ ታሪክ ያገኛሉ። አፋሮች ሌላውን "ይሄ ክልልህ አይደለም፣ ውጣ" ሲሉ አይሰማም። በሌላ አካባቢ ይህ ነገር ትልቅ ቀውስ ፈጥሯል። ምንድነው እናንተ ጋር ያለው ነገር? የኛ የባሕላዊ ፍልስፍና መነሻ አንድነት ነው። አንድ ብለህ ነው ሁለት የምትለው። ሁለት ከአንድ በኋላ ነው የሚመጣው። ይቺን አገር አንድ ሆና ስትቆይ ትከበራለች። ደግሞም ተከብረን ቆይተናል። በአንድነታችን ተከብረንበታል። የተከፋፈሉ ሕዝቦች በቅኝ ግዢ ወድቀው ነው የሚገኙት። የተከፋፈሉ ሕዝቦች የባሪያ ቀንበርን ተሸክመው ዛሬም ድረስ ከዚያ ዳፋ አልተላቀቁም። ባሕላቸውም ማንነታቸውን እምነታቸውን አጥተዋል። አንድነታችን ነው ከዚህ ያዳነን። ማንነታችን እንዳናጣ ያደረገን እሱ ነው።አፋር ይህን አሳምሮ ስለሚያውቅ ይመስለኛል። የመገፋቱ፣ የመገለሉ ነገር እንዳለ ነግረውኛል። ያም ሆኖ ነው ስለ አገር አንድነት የጸና አቋም አለን የሚሉኝ? ይሄ እኛን የመግፋቱ፣ የማግለሉ ነገር አስተዳደራዊ ጉዳይ ነው። ወደፊት ታግለህ የምታስቀይራቸው ነገሮች ናቸው። በአገርህ የሚያደራድሩህ ነገሮች አይደሉም። በፌዴራል ደረጃ አፋር ያለውን ውክልና እንዴት ይገመግሙታል? በፌዴራል ደረጃ ያለን ውክልና ዜሮ ሊባል የሚችል ነው። አንዲት ሚኒስትር ናት ያለችው። ከዚያ ባለፈ ሃያ የሚኒስቴር ኤጀንሲና ተቋማት ውስጥ በዳይሬክተርነት ደረጃ እንኳን አፋሮች የሉም። ለምን ይመስልዎታል? ድሮ የተማረ የሰው ኃይል የላችሁም ይሉን ነበር። ካልተማርክ የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ ልትሆን አትችልም፤ ልክ ነበሩ። አሁንስ? አሁን በጤና፣ በምህንድስና፣ በሳይንስ፣ በአስተዳደር የአፋር ሕዝብ በዚህ ሰዓት ከማንም አያንስም። ነገሩ መዋቅራዊ ግፉእነት (Structural marginalization) ነው በአፋር ሕዝብ ላይ ላለፉት 50 ዓመታት የተደረገው። የኃይለ ሥላሴ ሕገ መንግሥት "ዘላን ርስት የለውም" ይለን ነበር። ደርግም ከመጣ በኋላ፣ ወያኔም በአፋር ሕዝብ ብዝበዛና ጭፍጨፋ ነው ያካሄዱት። የአፋር ሕዝብ በአገሩ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ሥርዓቶቹ ዕድል ሰጥተውት አያውቁም። "ገዢ መደቦች የተፈጥሮ ሃብቱን እንጂ የአፋርን ሕዝብን አይፈልጉትም፤ ጉዳያቸው ኾኖም አያውቅም" ትላላችሁ በማኒፌስቷችሁ ላይ። ምን ማለታችሁ ነው? ይሄኮ በተጨባጭ ያየነው ነው። የኖርነው ነው። ሩቅ ሳንሄድ ወያኔ ምንድነው ያደረገው። ሰፊውን የጨው መሬት ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ በእጁ አስገባ። አንድ በል። አፋሮችን ያኔ ምን ያሠራቸው እንደነበር ታውቃለህ? መጥረቢያ ይዘው፤ ጨው መቅረጽ (እንደ ብሎኬት ቅርጽ ማውጣት) ነበር የሚሠሩት። አፋሮች "የቀን ጆርናታ" ነበር የሚከፈላቸው። በዚያ በረሃ፣ ቁምጣ ለብሰው የጨው ቅርጽ ማውጣት ነበር ሥራቸው። የመሬት ባለቤትነት መብት የላቸውም፤ የአምራችነት መብት የላቸውም። የነበራቸው ተሳትፎ የጉልበት ሠራተኝነት ብቻ ነው። በዚያ በበረሃ። አፍዴራ ብትሄድ ይህን ታያለህ። እንቀጥል፤ አብአላ ሂድ። ከፍተኛ የወርቅ ክምችት አለ። ብሔራዊ ባንክ ቅርንጫፍ ከከፈተባቸው ቦታዎች አንዱ እዚያ ነው። ፖታሽ አለ። ከፍተኛ ምዝበራ ነበር የሚደረገው። አፋር ግን ተጠቃሚ ሆኖ አያውቅም። በራሱ መሬት ላይ እንግዳ የሆነ ሕዝብ ቢኖር የአፋር ሕዝብ ነው። በተጠቃሚነት ደረጃ ተገለን ቆይተናል ነው የሚሉኝ? ግን'ኮ ያው ሁሉም ክልል ይህንን ነው የሚለው ... ምን መሰለህ! እኛ ቅድሚያ የምንሰጠው የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነትን ነው። በኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ ላይ አንደራደርም፤ በፍጹም። ይሁንና እንደ አፋር በትልቋ ኢትዮጵያ ውስጥ መከበርንም፣ መክበርም እንፈልጋለን። ሀብት ማፍራት ማደግ እንፈልጋለን። መልማት እንፈልጋለን። የኛ ሴቶች ምጥ ሲመጣባቸው ሌላ ክልል እንዲሄዱ አንፈልግም። ሌላው "እኔ አውቅልሃለው" እንዲለን አንፈልግም። ራሳችንን ችለን መቆም እንፈልጋለን። ኤርታሌ ቱሪስት የሚያስደነግጥ ቦታ ነው። አፋር የቱሪስት ገነት ሆና ለምንድነው "ቱሪስት አንድ ቀን የማያድርባት ከተማ የተባለችው? ብትመረጡ በዚህ ረገድ ምን አስባችኋል? ዳሎል የዓለማችን ዝቅተኛ ቦታ ነው። ኤርታሌ የዓለማችን ሞቃታማው ቦታ ነው። ሉሲ አዳኣር ላይ ነው የተገኘችው። ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመነጋገር ሉሲ የተገኘችበት ቦታ ላይ ትልቅ ሙዝየም በመገንባት እዚህ አፋር እንድትመጣና እንድትጎበኝ እንፈልጋለን። የአገር ውስጥ ቱሪስቱም የውጭ ቱሪስቱም እኛ ጋር መጥቶ እንዲጎበኛት ነው ፍላጎታችን። የደኅንነት የምቾት የትራንሰፖርትና የሆቴል አገልግሎቶችን ማዘመን አስበናል። ቱሪስቶች ተመችቷቸው ሄደው ስለኛ መልካም ትዝታቸውን እንዲያጋሩ ማድረግ አለብን። የአርብቶ አደር የግጦሽ መሬት ባለቤትነቱ እንዲረጋገጥ እንሠራለን ትላላችሁ። አልተረጋገጠም እንዴ? አልተረጋገጠም። የግጭቶች መነሻም ከዚህ የተነሳ ነው። አሁን ትላልቅ ፋብሪካዎች ይከፈታሉ። ተንዳሆ፣ የከሰም ስኳር ፋብሪካ እርሻ ልማቶችም አሉ። ማኀበረሱ በአንድ ቦታ ረግቶ የማይኖር፣ ተንቀሳቃሽ ስለሆነ ብቻ ባዶ መሬት ሲያዩ ተንሰፍስፈው ይወስዱታል። ይሄ መሬት ባለቤት እንዳለው ይረሳሉ። አርብቶ አደሩ ተንቀሳቃሽ ነው ማለት የመሬት ይዞታው አይረጋገጥለት ማለት አይደለም። የአርብቶ አደሩን ጉዳይ እንመለስበታለን። በአፋር ከተሞች ውስጥ ነጋዴዎች በሙሰኛ ባለሥልጣናት ፍዳቸውን ነው የሚበሉት ይባላል። የአፋር ሕዝብ ጉዳት ተናግረናል፤ በክልላችን ያሉ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ወንድሞቻችን ጉዳትም መናገር አለብን። በትውልድ አፋር ያልሆኑ ሰዎች የሚሠሯዋቸው ሥራዎች አሉ። በብዛት ነጋዴዎች ናቸው። ነጻ ሆነው እንዳይሠሩ ሥርዓት የለም። በግብር ያሠቃይዋቸዋል። ማንኛውም የክልሉ ባለሥልጣን ብር ባስፈለገው ሰዓት ብር አምጣ ይልሃል። ሾፌሩን ነው የሚልክብህ። የሚገርም ነገር ልንገርህ፤ በአፋር ሾፌሮች ዕቁብ አላቸው። ዕቁብ የገቡት በየሳምንቱ ለደንብና ሥርዓት አስከባሪዎች ለመስጠት ነው። የሚያሳዝን ነው። በብዛት አፋር ተወልደው አፋር ያደጉ ነጋዴዎችን ነው የሚያሰቃዩት። የመለወጥ መብታቸውን ነው የነፈጉት። ወንድሞቻችን እዛ መኖራቸው አልቀረ፣ ለፍቶ ማደራቸው አልቀረ፣ በዚያ በረሃ ላባቸውን ጠብ አድርገው መኖራቸው አልቀረ። አንድ ባለሥልጣን መጥቶ ሀብትህን ይቀማዋል። የዜጎችን እኩል ተጠቃሚነት የሚጻረር ነው። ዱብቲን ብታያት የምትገርም ከተማ ናት። ትልቅ የገበያ ቦታ ናት። ከፍተኛ የገንዘብ ልውውጥ ያለባት ከተማ ናት። አንድ ደህና ቤት የለም። ገብተህ ምግብ በልተህ ረክተህ አትወጣም። እንዳሉ የቆርቆሮ ቤቶች ናቸው። የጦር ካምፕ ነው የሚመስሉት። እዛ ውስጥ እየሠሩ ያሉት ለምንድን ነው ዘመናዊ ሱቅ የማይከፍቱት ስትል ያለተተመነና መጠኑ የማይታወቅ ግብር ይዘውብን ይመጣሉ ይሉሃል። ይሄ ያሳፍራል። ባለሥልጣኖቹ ሾፌራቸውን እየላኩ ነጋዴን "ብር ላክ" እያሉ ማሰቃየት ማቆም ይኖርባቸዋል። በክልላችሁ ከለውጡ በኋላ ለውጥ አለ? እውነት ለመናገር በክልል ደረጃ ያለው አመራር በጣም የሚደነቅ ነው። ትልቅ አክብሮትም አለን፤ ለሰዎቹ። በደፈናው መጨፍለቅ አካሄዳችን አይደለም። የክልሉ ፕሬዝዳንትም ሌሎቹም ከፓርቲያችን ጋር መልካም ግንኙነት ነው ያላቸው። በብዙ ነገሮች ላይ አብሮ መሥራቱ አለ። ሌሎች ክልሎች ጋር ባልተለመደ ሁኔታ አብሮ የመሥራቱ ነገር እኛ ጋር አለ። ነገሩ የሚበላሸው ወደታች ሲወርድ ነው። ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ይህንኑ ነግርያቸዋለሁ። ከአዲስ አበባ ወጥተህ ክልል ስትሄድና ወደታች ስትወርድ የብልጽግና ለውጥ እየጠፋ ይሄዳል። የታችኛው መዋቅር ለውጡን አያውቀውም ብያቸዋለሁ። ለምሳሌ ዕጩዎቻችንን ከሥራ ያባርሩብናል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ዘመቻ ስናደርግ ሕዝቡ ግልብጥ ብሎ ሲወጣ ወረዳ ላይ ያሉ ካድሬዎች ይደነግጣሉ። በኛ ክልል እንዲህ ዓይነት ቅስቀሳ ኖሮ አያውቅም። ያስደነግጣቸዋል። በቃ እነዚህ ሰዎች ሊያጠፉን ነው ብለው ስለሚሰጉ ወከባ ይፈጥሩብናል። አንዳንድ ቦታ ደግሞ አዳራሽ መጥተው መክፈቻ ንግግር አድርገው አይዟችሁ፣ አገራችሁ ነው ብለው አበረታተውን የሚሄዱ ካድሬዎች አሉን። "ይህን ትግል እናንተ ናችሁ ያመጣችሁት። በምርጫና በምርጫ ብቻ እንሸናነፋለን፤ አብሽሩ" ብለው የሚያሰናብቱንም አሉ። ነገሮች የማይስተካከሉ ከሆነ ከምርጫው እንዳንወጣ ስጋት አለን። አርብቶ አደር የምንወክል ፓርቲ ነን ትላላችሁ። አርብቶ አደሩ ማኅበራዊ ፍትሕን ይናፍቃል። የአርብቶ አደሩን አጀንዳ ብሔራዊ አጀንዳ የምታደርጉት እንዴት ነው? በኢትዮጵያ ደረጃ የሚወጡ ማናቸውም ፖሊሲዎች አርብቶ አደሩን ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑ ታግለናል። ትግላችን ይቀጥላል። ለምሳሌ የምርጫ ሕጉ ሲወጣ ፓርላማ ላይ 6 አንቀጾች እንዲስተካከሉ ያደረግነው እኛው ነን። የምርጫ ሕጉ አንድ ሰው መራጭ ለመሆን ሁለት ዓመት መኖር አለበት የሚል ነበር። ይሄ የአርብቶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤ ያላገናዘበ ነው በሚል አንስተን ተስተካክሏል። ሌሎችም ብዙ አሉ። የቤት ቁጥር የግድ ነው ይላል መራጭ ለመሆን። የኛ ሕዝብ የቤት ቁጥር የለውም። ተንቀሳቃሽ ነው። ይህን አስተካክለናል። የአርብቶ አደር ፖሊስ እንዲቀረጽ ከፍተኛ ጫና ያደረገው የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ነው። አሁን በሚኒስተሮች ምክር ቤት ፖሊሲው ጸድቆ ወደ ትግበራ ሊገባ ደርሷል። እንግዲህ አስበው፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የእንሰሳት ሃብት ደረጃ በአንደኝነት ተቀምጣ እስከዛሬ ድረስ የአርብቶ አደር ፖሊሲ የሚባል ነገር አልነበራትም። አርብቶ አደሩ ከሕዝቡ በመቶኛ ምን ያህል ነው? በቁጥር ደረጃ ከ12 እስከ 15 ሚሊዮን ሕዝብ ይሆናል። በመሬት ስፋት የአገሪቱን 62 ከመቶ ይሸፍናል። በውጭ ምንዛሬ ረገድ ከቡና ቀጥሎ በ2ኛ ደረጃ ነው የሚጠቀሰው፤ የእንሰሳት ተዋጽኦ። የእርሻ ጠቅላላ አገራዊ ጥቅል ምርት (GDP) አርብቶ አደሩ 43 በመቶ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ይህ ዘርፍ በፖሊሲ ካልተደገፈ እንዴት ነው አገር ወደፊት የምትሄደው? እኛ በፖሊሲ ደረጃ ነው የምንታገለው። በእስክሪብቶ ነው የምንዋጋው፤ በፌዴራል ደረጃ ጀምረናል ለውጡን እናስቀጥላለን። በአፋርና በሶማሌ አዋሳኝ ቦታዎች በቅርቡ ግጭት ነበር። አቶ ሙስጠፌና አቶ አወል ተገናኝተው እንፈተዋለን ሲሉ ነበር። በእርግጥ እንፈተዋለን ስላሉ የሚፈታ ነው? የአፋርና የኢሳ ግጭት ድሮም የነበረ ነው። ለምን አልተፈታም? በአጭሩ ልመልስልህ። የመንግሥት ክፍተት ነው የችግሩ ምንጭ። ምን ማለቴ መሰለህ? አቶ ሙስጠፌና አቶ አወል ተገናኝተው፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ጋር ተወያይተው ውሎ ሳያድር በነገታው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፋጅተዋል። ስለዚህ በወሬ ችግሩ አይፈታም። ትክክለኛ የመፍትሄ ፍላጎትና ፍለጋ አልነበረም። የሦስቱ ቀበሌዎች ጉዳይ ብዙም ውስብስብ አይደለም። የአፋር ክልል አስፈላጊውን ሁሉ ለእነዚህ ቀበሌ ነዋሪዎች በማድረግ የሚፈታ ነው። አፋር ክልል ትምህርት ጤና መሰረተ ልማት ሊያቀርብላቸው ግዴታ አለበት። ነዋሪዎቹ ሶማሌዎች ናቸው አይደል፤ በሦስቱ አወዛጋቢ ቀበሌዎች? እና ሶማሌ ቢሆኑስ መሠረት ልማት መነፈግ አለባቸው? እንደዛ ማለቴ ሳይሆን ጥያቄያቸው የቦታ ይገባኛል ሳይሆን የልማት ነው ወይ ማለቴ ነው? አዎ በአፋር ክልል የሚገኙ ልዩ ቀበሌዎች ናቸው። ሶማሌዎች ናቸው የሚኖሩበት። በዚያ በኩል ደግሞ ይሄን እንወስዳለን ይህን እንመልሳለን ማለት ሳይሆን፤ ሕግና ሥርዓትን መከተል አለበት። በመንግሥት ደረጃ ድንበር ማካለል መሠራት አለበት። "ያ የኔ ነው፤ ይሄ የኔ ነው" መባባል ሳይሆን እንደ ዘመናዊ ሰው ተነጋግሮ መፍታት ያስፈልጋል። ወሰን ማበጀት ያስፈልጋል። ሁለቱ ሕዝቦች ከሚያለያያቸው ይልቅ የሚያቀራርባቸው ነገር ይበዛል። እንዴት ነው ወደ ግጭት የሚገቡት? ሁለቱ ሕዝቦች ተፈጥሮ ያጎራበተቻቸው አንድ ዓይነት የጉስቁልና ሕይወት የሚመሩ ወንድማማች ሕዝቦች ናቸው። በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ገሸሽ የተደረጉ ግፉኣን ናቸው። በዚህ ችግር ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ አያስፈልግም። እኛ መንግሥት ስንሆን ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ይህ ነው። አፋር የኢትዮጵያ ጉሮሮ ነው የምትባለው። አፋር ሰላም ከሌለ የመሐል አገር ሰው ጋር በነገታው ነው ሕመሙ የሚደርሰው። ይህ በቅርቡ በነዳጅም እጥረትም ታይቷል። የክልላችሁን በአስተማማኝ ሰላም ለማስጠበቅ የትኛውን መንገድ ትከተላላችሁ? የልዩ ኃይል ማደራጀትን ታምኑበታላችሁ? ልዩ ኃይልን በተመለከተ አንድ ወጥ አገራዊ አቅጣጫ መቀመጥ አለበት ብለን ነው የምናምነው። መደበኛ ፖሊስ አለ፣ ፌዴራል ፖሊስ አለ፣ መከላከያ አለ። ወደ ታች ስትወርድ ሚሊሻ አለ። እነዚህ በቂ ናቸው ብለን እናምናለን። ዘመናዊ ዓላማ ያለው የሰለጠነ የፖሊስ ኃይል መገንባት ያስፈልጋል። ምን እያደረጉ እንደሆኑ የሚያውቁ። ለዜጎች ከለላ መስጠት እንጂ ደኅንነት መንሳት ሥራቸው እንዳልሆነ የሚያወቁ የጸጥታ ኃይሎች ያስፈልጋሉ። የክልሎች የልዩ ኃይል ፉክክር ያሳስበናል። ከሁለቱ አንዱ መሆን አለበት። ወይ በአገር ደረጃ ወደ ተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች መበተን አለባቸው። ወይ ደግሞ ሥርዓት ያለው ፊትና ኋላው የሚታወቅ የተለየ ተልእኮ ያለው ኃይል መገንባት አለበት። ምን ማለቴ ነው? ለምሳሌ በፊት ፊናንስ የሚባሉ ነበሩ። ከኮንትሮባንድ ጋር የተያያዙ ቁጥጥሮችን የሚከታተሉ። የጸረ ሽብር ግብረ ኃይል አለ። ተልዕኮው ተለይቶ የተቀመጠለት። እንደዚህ ለተለየ ተልዕኮ ጸጥታ መዋቅር ሊያስፈልግ ይችላል እንጂ ልዩ ኃይል መልካም ነገር ይዞ ይመጣል ብለን አናስብም። ይሄ የመንግሥት ትልቅ የቤት ሥራ ነው የሚሆነው። ከጂቡቲ ጋር በተያያዘ ስለ ጂቡቲ ከአፋር የተሻለ ሊናገር የሚችል የለም። ቤተሰብ ሕዝብ ነው። አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ላንሳ...። እንደው በረዥም ዘመን ጂቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር ኅብረት ፈጥራ ሉአላዊነቷ እንደተጠበቀም ቢኾን ለኢትዮጵያ ነጻ የንግድና እንቅስቃሴ ቀጠና ሆና በአንድ አገራዊ ስሜት ከኢትዮጵያ ጋር የምትቀርብ ይመስልዎታል? በቅድሚያ የእነርሱን ሉዓላዊነት መንካት አልፈልግም። ከጠየቅከኝ አይቀር አንድ ነገር ልንገርህ። የጂቡቲ ጉዳይ የኛ ጥንካሬ ላይ የሚመሠረት ጉዳይ ነው፡፡ ጂቡቲና ኢትዮጵያ ፈቅደው አንድ ለመሆን የሚቸገሩ አገሮች አይደሉም። የሩቅ ነገርም አይደለም። ይገባኛል! እንዴት ፖለቲከኛ እንዲህ ይላል ልትለኝ ትችላለህ። በአጭሩ ላስረዳህ። ጂቡቲ ላይ ያሉት ኢሳና አፋሮች ናቸው። የነሱ ትልቁ የቤተሰብ ግንድ ያለው እዚህ አፋር ኢትዮጵያ ነው። ከዚህ ጂቡቲ የሄደ እንጂ ከጂቡቲ እዚህ የሰፈረ ሕዝብ የለም። አፋር እኮ እዚያ አጎት፤ እዚህ አክስት አለው። አባት እዛ ነው ልጅ እዚህ ነው። እናት እዛ ልጂቱ እዚህ። በቃ ምን ልበልህ ቤተሰብ ነው። ኢሳውም በተመሳሳይ ማለቴ ነው። ስለዚህ እኛ ከጠነከርን በተለይ አንድ የኢኮኖሚ አገር ከጂቡቲ ጋር ለመፍጠር የሩቅ ዕቅድ ኾኖም አይደለም የሚታየን። ለምሳሌ ሱዳንን በቤኒሻንጉል እንጎራበታለን። ወደ አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመምጣት ግን አስቸጋሪ ነው። ትልቅ አገር ነው። ብዙ ብሔር ያለበት አገር ነው፤ ሱዳን። ጂቡቲ ግን ኢሳና አፋር ነው። የኔ ወንድምና እህቶች ናቸው። ቤተሰብ ነን። ስለዚህ እንደ ቤተሰብ ልንይዛቸው ነው የሚገባው። ውሃ ማቅረብ። ኤሌክትሪክ ማቅረብ፣ መሠረተ ልማት ማቅረብ፤ ንግዱን ማሰባጠር ነው። ቀስ በቀስ በምጣኔ ሀብት "ኢንተግሬትድ" መሆን ቀላል ነው። ይህ በተለይም በሶማሌ ክልልና በአፋር ክልል በኩል መሆን የሚችል ነገር ነው። ይህ በኢትዮጵያ መረጋጋት፣ አንድነትና ጥንካሬ መሳካት የሚችል ነገር ነው። ጂቡቲን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣትና አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መፍጠር ለእኛ ለአፋሮች ከባድ ሥራ አይደለም። በአፋር በኩል መሳለጥ የሚችል ነገር ነው። እኔ አሁንም ቢሆን የጂቡቲን ሉአላዊነት ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት አይደለም። በመፈቃቀድ ግን አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት የሩቅ ነገር ተደርጎ መታሰብ የለበትም። ጎጠኝነትን እየተውን ከመጣን ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ከባድ አይደለም። ኢስማኤል ኡማር ጊሌ ባለፈው አዋሽ ወንዝን መጠቀማችንን እናረጋግጣለን የሚል ይዘት ያለው ትዊት አድርገው ነበር። አይተኸዋል? አዎ አይቼዋለሁ። እሳቸው ራሱ የኛ ስለሆኑ ነው አዋሽን 'የኛ ነው' የሚሉት ብለን ነው የወሰድነው። ለዚያ ነው ያልተገረምነው። ያልተናደድነው።
xlsum_amharic-train-242
https://www.bbc.com/amharic/48159695
ቦይንግ 737 ተንሸራቶ ወንዝ ውስጥ ገባ
አሜሪካ ቴክሳስ ውስጥ አንድ የቦይንግ አውሮፕላን ካረፈ በኋላ ተንሸራቶ ወንዝ ውስጥ ገብቷል። አውሮፕላኑ ያረፈው መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ እየዘነበ ሳለ ነበር።
[ "አሜሪካ ቴክሳስ ውስጥ አንድ የቦይንግ አውሮፕላን ካረፈ በኋላ ተንሸራቶ ወንዝ ውስጥ ገብቷል። አውሮፕላኑ ያረፈው መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ እየዘነበ ሳለ ነበር።" ]
በቦይንግ 737 ተሳፍረው የነበሩት 143 ሰዎች የከፋ ጉዳት አልደረሰባቸውም። ሆኖም ከተሳፋሪዎቹ መካከል ወደ 20 የሚሆኑት ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና መስጫ ተወስደዋል። • ቦይንግ ትርፋማነቴ ቀንሷል አለ በሚያሚ ኤር ኢንተርናሽናል ስር የሚተዳደረው አውሮፕላኑ ጉዞውን የጀመረው ከኩባ ጓንታናሞ ቤይ ነበር። ተሳፋሪዎቹ እንዳሉት በዝናብ ወቅት ያረፈው አውሮፕላኑ ሴንት ጆን የተባለ ወንዝ ውስጥ ተንሸራቶ ገብቷል። ከተሳፋሪዎቹ አንዱ ቼሪል ቦርማን ለሲኤንኤን "አውሮፕላኑ መሬቱን ነክቶ ነጠረ። አብራሪው መቆጣጠር እንዳቃተው ያስታውቅ ነበር" ብለዋል። • ቦይንግ የአደጋውን የምርመራ ውጤት ተቀበለ ተሳፋሪዋ እንደገለጹት፤ አውሮፕላኑ የገባው ወንዝ ውስጥ ይሁን ባህር ውስጥ አላወቁም ነበር፤ "ሁኔታው አስፈሪ ነበር" ብለዋል።
xlsum_amharic-train-243
https://www.bbc.com/amharic/news-48715607
"እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" ኢንስትራክተር መሠረት ማኒ
ውልደቷ ድሬዳዋ ነው፤ ልዩ ስሙ አንደኛ መንገድ ከሚባል ሥፍራ፤ ደቻቱ ግድም ማለት ነው። ይህ ሠፈር ደግሞ ለአሸዋው ቅርብ ነው። ኳስ እያንቀረቀቡ ለማደግ የሰጠ ነው።
[ "ውልደቷ ድሬዳዋ ነው፤ ልዩ ስሙ አንደኛ መንገድ ከሚባል ሥፍራ፤ ደቻቱ ግድም ማለት ነው። ይህ ሠፈር ደግሞ ለአሸዋው ቅርብ ነው። ኳስ እያንቀረቀቡ ለማደግ የሰጠ ነው።" ]
አንደኛ ደረጃ ትምህርቷን በለገሃሬ፤ ሁለተኛውን ደግሞ በድሬዳዋ አጠቃላይ ትምህርት ቤት ተስተምራለች። ፊፋ በ1983 የዓለም የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫን በይፋ ከማካሄዱ በፊት ሴቶቹ በይፋ እግር ኳስ እንዲጫወቱ አይፈቀድም [አይፈለግምም] ነበር። ነገር ግን ይህ ኳስ ከመጫወት አላገዳትም [በፕሮፌሽናል ደረጃ ባይሆንም]። ማንም ከተጫዋችነት ወደ አሠልጣኝነት ወደ መምጣት የከለከላት አልነበረም፤ በኢትዮጵያ [በአፍሪካም] ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ ከመሆን ሊመልሳት የቻለም አልተገኘም. . . እርሷም ማንም ወደኋላ እንዲጎትታት አልፈቀደችም. . . መሠረት ማኒ። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ የአሠልጣኝነት ሕይወት «አሠልጣኝነትን የጀመርኩት ገና በልጅነቴ ነው ። ልጅ እያለሁ ራሱ 'የሊደርሺፕ' ተሰጥዖ ነበረኝ። ከዚያ ጓደኞቼን ሰብስቤ 'ድል በትግል' የሚባል ቡድን መሠረትኩ። ከዚያ የሕንፃ ቡድን፤ ቀጥሎ የመድህን ድርጅት የተወሰነ ድጋፍ እያደረገልኝ ማሠልጠን ጀምርኩ። ከዚያ የ'ሴቭ ዘ ቺልድረን' የሴቶች እና ወንዶች ቡድንን መሥርቼ ማሠልጠን ያዝኩ።» መሠረት የምታሠለጥነው የእግር ኳስ ቡድኖችን ብቻ አልነበረም። የቴኒስ እና መረብ ኳስ ቡድኖችንም ታሠለጥን ነበር። 'ማቴሪያል' ስለነበር ፍላጎቱ ያላቸው የድሬዳዋ ልጆች እንዲሠለጥኑ አደርግ ነበር። 1970 ዎቹ ላይ እነ ማክዳ፣ ታጠቅ፣ አየር ኃይል እና መሰል የሴት እግር ኳስ ቡድኖች፤ የሴቶች እግር ኳስ ሲቋረጥ በዚያ ከሰሙ። ከዚያ 1986 ላይ የመጀመሪያውን የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በማቋቋም በታሪክ መዝገብ ስሟን አሰፈረች። 2004 ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ሲጀመር መሠረት የከተማዋን ሴቶች ቡድን ይዛ ተቀላቀለች። መሠረት ማኒ ታሠለጥነው የነበረው የድሬዳዋ ከነማ መረብ ኳስ ቡድን [1977] ድሬዳዋ ከነማ 2007 ላይ ድሬዳዋ ከነማ የፕሪሚዬር ሊጉ ታናሽ በሆነው የሊግ ውድድር ላይ ተሳታፊ ነበር። ይሄኔ ነው መሠረት ማኒ የወንዶቹን ቡድን ተረክባ ለፕሪሚዬር ሊግ ለማሰለፍ ቃል በመግባት ሥራ የጀመረችው። «እርግጥ በጣም 'ቻሌንጂንግ' ነበር። ቢሆንም ለእኔ ብዙ ያልከበደኝ፤ ከልጅነቴም ጀምሮ ወንዶችን እያሠለጠንኩ ማደጌ ነው። ትላልቆቹም ሳሰለጥናቸው የሚሠጡኝ አክብሮትና ፍቅር እንዲሁም ኃላፊነታቸውን የሚወጡበት መንገድ አቅም ሆኖኝ ነበር። በፆታ መለካቴ ግን አልቀረም። 'እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል? ቀልድ ነው እንዴ የያዙት?' ያሉ አልጠፉም ነበር። አንዳንዶቹም እንደውም ይሄ ለፖለቲካ 'ኮንሳምፕሽን' ነው ብለው ከንቲባው [የድሬዳዋ] ድረስ ይሄዱ ነበር። ነገር ግን ለኔ የበለጠ አቅም ነበር የሆነኝ። ምክንያቱም ይህንን መቀየር አለብኝ አልኩኝ፤ በምን? በውጤት።» ከውጭ ብዙ ፈተና የገጠማት መሠረት ከውስጥም መንገዱ አልጋ 'ባልጋ አልሆነላትም። በዚያ ላይ የመጀመሪያው ዙር ለመሠረት ቀላል የሚባል አልነበረም፤ ሦስት ነጥብ ማግኘት። «ተጨዋቾቼን ማሳመን አንዱ ፈተና ነበር። በሴት ሠልጥነው አያውቁም፤ ትልልቅ ተጨዋቾች ናቸው። 'እንዴት ነው አሁን እሷ እኛን የምትመራን?' የሚል ጥያቄ ነበራቸው። አንዳንዶቹ የመሥራት ፍላጎታቸው ውርድ ያለም ነበር። ነገር ግን ልጆቼን በሥራ ማሳመን ቻልኩኝ። በተለይ ሁለተኛው ዙር ላይ በውጤት በጣም አሪፍ ነበርን። እንደውም ከ12 ጨዋታ 11 አሸንፈን በአንዱ ብቻ ነው አቻ የተለያየነው።» ጉዞ ወደፕሪሚዬር ሊግ ድሬዳዋ ከነማ በአሠልጣኝ መሠረት ማኒ እየተመራ ፕሪሚዬር ሊግ ገባ። ሁሉም 'ሴት የወንዶች አሠልጣኝ?' ሲል መጠየቅ ጀመረ። አድኖቆት ጎረፈላት። ተጫዋቾች፣ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይ ደግሞ ድሬዎች ቆመው አጨበጨቡላት። ፕሪሚዬር ሊግ ከብሔራዊ ሊግ ሲነፃፀር ከበድ [በጥራት] ያለ ቢሆንም መሠረትን የሚያቆም ግን አልተገኘም። ክለቧ ትልቁ ዓላማው የነበረው ከፕሪሚዬር ሊጉ ተመልሶ አለመውረድ ነበር። መሠረት ግን አለመውረድ አላስጨነቃትም፤ ውጤቱ የበለጠ እንዲያምር ጣረች። «ስንጀምረው አራት ጨዋታ ማሸነፍ አልቻልንም ነበር። ከአምስተኛው ጨዋታ በኋላ ግን ሁሉንም እያስተካከልን መጣን። እንደውም በአንደኛው ዙር አምስተኛ ሆነን ጨረስን፤ ይሄ ደግሞ ትልቅ ድል ነው። በተለይ ከብሔራዊ ሊግ ለመጣ ቡድን ሊያውም በሴት አሠልጣኝ ለሚሠለጥን።» ፍቺ ከድሬዳዋ ጋር ቢሆንም ሁለተኛው ዙር የድሬዳዋ ውጤት ዕለት ተ'ለት ያሽቆለቁል ያዘ። በመጀመሪያዎቹ አምስት ጨዋታዎች ጥሩ ውጤታ ማምጣት የቻለው ድሬዳዋ ከነማ ሦስት ነጥብ ብርቁ ሆነ። ምን ተፈጠረ? «እኔ እስከዛሬም ድረስ ሳስበው ግራ ይገባኛል። ምንድን ነው ነገሩ ብዬ ልጆቼን ጠየቅኩ፤ ግን አጥጋቢ ምላሽ አላገኘሁም። አንድ የማላውቀው እና ውጤታችንን እንዲያሽቆለቁል ያደረገ ነገር እንዳለ አሁንም ድረስ ይሰማኛል። አሁን ራሱ አንዳድንድ ተጨዋቾችን ሳገኝ እጠይቃለሁ፤ ግን ብዙም አይነግሩኝም። የሆነ ነገር እንዳለ ግን ይሰማኛል፤ ከውጭም ከውስጥም። ወደፊትም መጠየቄን አላቆምም።» • ሴት እግር ኳሰኞች ስንት ይከፈላቸው ይሆን? ከዚያ «በዚህ መንገድ መቀጠል አልቻልኩም ትላለች» መሠረት። «ገንዘብ ፈልጌ አይደለም የመጣሁት እኔ። እኔ መሥራት ነው የምፈልገው። በዚህ መንገድ መቀጠል ደግሞ አልፈልግም። ጫናዎች በዝተዋል። እግር ኳስ ደግሞ ነፃነት ይፈልጋል። እኔ በቃኝ 'ቴንኪው' ብዬ፤ ልጆቼን እና 'ስታፉን' ተሰናብቼ ቡደኑን ለቅቄ ወጣሁ።» ይህ የሆነው እንግዲህ 2008 ላይ ነው። መሠረት 2002 ላይ ሉሲዎችን ተረክባ ታሪክ ፅፋለች፤ ታሪኩ ምንድን ነው? ብሎ ለሚጠይቅ 'ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴት አሠልጣኝ የተመራበት ወቅት በመሆኑ [የተሰጣት ኮንትራት የ3 ወራት ብቻ ቢሆንም]' መልሷ ነው። መሠረት ከዚያ በኋላ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በቀረበላት ግብዣ ወደ አሜሪካ አቀናች። ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ከአሜሪካ ኤምባሲ በቀረባለት ግብዣ አሜሪካ ደርሳ ተመልሳለች። ወደ አሜሪካ ከማቅናቷ በፊት ሉሲዎችን እንደገና ተረክባ ነበር [2009]። ስትመለስ ግን የአሠልጣኝነት ቦታው በሌላ ሰው ተይዞ ጠበቃት። እንደገና ሉሲዎችን ተረክባ ወደ ኡጋንዳ አቀናች፤ በሴካፋ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ። ኳስ ይዞ በማጥቃት የአጨዋወት ስልት የምትታወቀው መሠረት ውድድሩን ሦስተኛ ሆና በማጠናቀቅ የነሃስ ሜዳሊያ ይዛ ተመለሰች [የራሳችን ድክመት ነው እንጂ ዋንጫ ማምጣት ይገባን ነበር ትላለች]። ቢሆንም ኮንትራቷ ከመጠናቀቁ በፊት ሉሲዎች ሌላ አሠልጣኝ ተሾመላቸው። መሠረት አዲሱን መፅሐፏን ለማስመረቅ ጉድ ጉድ በማለት ላይ ትገኛለች። 'የስኬት ተምሳሌት' የተሰኘ ርዕስ ሰጥታዋለች። ያለፈችበትን ውጣ ውረድ የሚያትት 198 ገፆች ያሉት መፅሐፍ ነው። «ይሄኔ ነው ጀምሬው የነበረውን መፅሐፍ ልጨርስ ብዬ ትኩረቴን ወደዚያ ያደርግኩት» ብላናለች። ክፍያ መሠረት ድሬዳዋ ከነማ እያለሽ ምን ያህል ነበር የሚከፈልሽ? እንደው ፈቃደኛ ከሆንሽ ብትነግሪን? «ኧረ በደንብ ነው ምነግርህ [ፈገግታ]. . . እንግዲህ እኔ ፕሪሚዬር ሊግ እያለሁ 14 ክለቦች ነበሩ። በወቅቱ ዝቅተኛው የአሠልጣኝ ክፍያ የኔ ነበር። ተቆራርጦ እጄ ላይ 'ሚደርሰኝ 13ሺህ 500 ብር ነበር። ያኔ የወረዱት ዳሸንና የሆሳዕና ቡድን አሠልጣኞች ከኔ የተሻለ ክፍያ ያገኙ እንደነበር አውቃለሁ። ምክንያቱም እኔ ብዙ ጊዜ በፆታዬ ነው 'ምለካው። እንጂ ባለኝ አቅም አልነበረም። ይሄን ሳስብ ያመኛል ግን በቃ ፍቅር ነው፤ ኳሱን እወደዋለሁ፤ እሠራዋለሁ። ስፖርታዊ ጨዋነት አሠልጣኞች እና ተጨዋቾች በድህረ-ጨዋታ መጨባበጥና ማልያ መቀያየር የተለመደ ነው። እርግጥ አሁን አሁን በሰላም ጨዋታን መጨረስ በራሱ ትልቅ ድል እየሆነ ቢመጣም። እንደው በመሠረት እንዴት እንሸነፋለን ያሉ አሠልጣኞች እና ተጫዋቾች እጅ ነስተዋት ያውቁ ይሆን? «የነፈጉኝን እንኳ ብዙም አላስታውስም፤ ግን እኔ አንድ ጊዜ በደስታ ውስጥ ሆኜ ሳልጨባበጥ በመቅረቴ ተከስሻለሁ። እዚሁ ድሬዳዋ ላይ ነው። ከሙገር ሲሚንቶ ጋር እየተጫወትን ነበር። ደርቢ በመሆናችን ጨዋታው ደመቅ ያለ ነበር። 0-0 ነበርንና ባለቀ ሰዓት አገባንና አሸነፍን። በቃ በጣም ደስተኛ ስለነበርኩ የሙገር አሠልጣኝን ሳልጨብጠው ቀረሁ። ከዚያ እስከ ክስ ደረጃ ደርሶ ነበር።» እንዴት ይረሣል? ሰዎች አሠልጣኝ መሠረትን ሲያስቡ ቀድሞ ትዝ የሚለቸው ከድሬዳዋ ከነማ ጋር የተጎናፀፈችው ስኬት ነው። እርሷም ከማትረሳቸው ድሎች መካከል አንዱ እርሱ ነው። ግን ከዚያም በላይ የማልረሳው ትላለች መሠረት. . . «የማልረሳቸው ሁለት ቀናት አሉ። አንደኛው ከአዲስ አበባ ከነማ ጋር አራት ውስጥ ለመግባት የተጫወትነው ነው። 1 ለ 0 እየመራን ነበር፤ ከዚያ አቻ ሆንን። አንድ ጨምረን መምራት ያዝን፤ ግን መልሶ ተቆጠረብን። በስመዓብ አሁን በቃ 2 ለ 2 ሆነን ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ልንሄድ ነው። ከምክትሌ ጋር ተነጋገርኩና 'ቤንቹ' በረኛ 'ፔናሊቲ' ጎበዝ ስለሆነ ብለን አስገባነው። በረኛችን ሦስት ጎል አዳነልንና አሸነፍን።» «ሁለተኛው ቅዱስ ጊዮርጊስን የረታንበትን ነው። እንግዲህ ጊዮርጊስ በጣም ትልቅ ቡድን ነው። እኔ ደግሞ ፕሪሚዬር ሊጉ አዲሴ ነው። እና በሜዳዬ ሊያውም በጨዋታ ብልጫ ማሸነፌ ፍፁም አልረሳውም። በጣም ልዩ ነበር። 2012. . .? መሠረት አሁን ላይ የአዲስ አበባ ሴቶች እግር ኳስ ቡድንን በማሠልጠን ላይ ትገኛለች። አንደኛ ዲቪዚዮን ላይ እየተጫወተ የሚገኘው አ.አ. ስድስተኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዘመኑን አጠናቋል። መሠረት ስለወደፊቱ ዕቅዷ እጅጉን እያሰበችበት እንደሆነ አልደበቀችንም። «ብዙ ዕቅዶች አሉኝ። የሕፃናት አካዳሚም አለኝ [120 ሕፃናት ያሉት]። እሱን ከፍ ማድረግም ሕልሜ ነው። የአሠልጣኝነት ጥያቄዎችም ይመጣሉ። እውነት ለመናገር ብዙ 'ፍራስትሬት' የሚያደርጉ አጋጣሚዎች ገጥመውኛል። ሙያውን ለመተው ሁላ አስቤ አውቃለሁ፤ ግን ደግሞ ብዙ ሰዎች ይህን ውሳኔዬን ሲቃወሙ አያለሁ። በተለይ ያሠለጠንኳቸው ልጆች 'ኖ መቀጠል አለብሽ' የሚል አስተያየት ይሰጡኛል። ስለዚህ ቁጭ ብዬ ማሰብ አለብኝ ብያለሁ።» ኢንስትራክተር መሠረት ማኒ ሉሲዎችን በተደጋጋሚ አሠልጥናለች ምክር ለተተኪዎች በኢትዮጵያም ሆነ በአህጉረ አፍሪካ ከመሠረት ሌላ ሴት የወንዶች እግር ኳስ ክለብ አሠልጣኝ እንዳለች አልሰማንም፤ አላየንም። ይህንን ክብር መጎናፀፍ ምን ዓይነት ስሜት ይሰጥ ይሆን? «በጣም ነው ደስ የሚለኝ። ሌላ ሴት አለመኖሯ ሳይሆን፤ ስኬታማ መሆን መቻሌ ደስ ያሰኘኛል። ሴት ልጅ ይህንን ማድረግ እንደምትችል ደግሞ ማሳየት መቻሌ እጅግ ያኮራኛል። እንጂ ብቸኛ ስለሆንኩኝ አይደለም፤ በቃ ይቻላል የሚለውን መንፈስ ማንገስ መቻሌ ነው። ሁሌም የምለው ሴቶች በፆታቸው ሳይሆን በአቅማቸው ቢለኩ ነው።» «አንዲት ሴት አናጢም መሆን ትፈልግ፣ ኢንጅነር ወይም ኤሌክትሪሺያን ለዚያ ሙያ የሚሆን ዕውቀት ያስፈልጋታል። ይህ ደግሞ እንዲሁ አይገኝም፤ ልፋት ይጠይቃል፤ ጥረት ያስፈልጋል፤ ድካም ያስፈልጋል፤ በቀላሉ የሚገኝ ነገር የለም። እኔ ሴት ስለሆንኩ እንደው እንደ ገፀ-በረከት እንዲሰጠኝ አልፈልግም። በራሴ ልክ፤ ባለኝ አቅም እንጂ። የማይቻል ምንም ነገር የለም። ሕልም ይኑረን።» እኛም ምክር ያፅና ብለናል፤ ለመሠረትም መልካም ዕድል! • "የናንዬ ሕይወት" የአይዳ ዕደማርያም ምስል ከሳች መፀሐፍ
xlsum_amharic-train-244
https://www.bbc.com/amharic/news-54018572
2012፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከጅማሬ እስከ ውሃ ሙሌት
በ2012 ዓ.ም ከፍተኛ ትኩረትን ከሳቡ ክስተቶች መካከል አንዱ የሆነው የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት በአጭር ጊዜ ውስጥ መከናወኑ በበርካታ ኢትኦጵያውኣን ዘንድ ደስታንና ተስፋን ፈጥሯል።
[ "በ2012 ዓ.ም ከፍተኛ ትኩረትን ከሳቡ ክስተቶች መካከል አንዱ የሆነው የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት በአጭር ጊዜ ውስጥ መከናወኑ በበርካታ ኢትኦጵያውኣን ዘንድ ደስታንና ተስፋን ፈጥሯል።" ]
አስር ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በግንባታ ላይ የቆየው ውሃ መያዝ መጀመሩ ሱዳንና ግብጽን ቅር አሰኝቷል። የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ የውሃ ሙሌቱ ደረጃ በደረጃ ተካሂዶ ኃይል ማመንጨት ሲጀምር በአፍሪካ ግዙፉ ይሆናል። ግብጽ አሁንም ቢሆን የአባይን ውሃ በጋራ መጠቀም በሚለው ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ሙሉ በሙሉ መስማማት ያቃታት ሲሆን ሁሉን አቀፍ ስምምነት መደረግ አለበት በማለት ስትከራከር ቆይታለች። በ2003 ዓ.ም ላይ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን መገንባት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በተለይ ግብጽ ተቃውሞዋንና ስጋቷን በተለያዩ መንገዶች ስትገልጽ እስከ ዛሬ ደርሳለች። በዚህ ጊዜው ግብጽና ኢትዮጵያ ሱዳንን ጨምሮ ላለፉት አስር ዓመታት ያህል በአባይ ወንዝ ጉዳይ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ሲደራደሩ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ሦስቱንም አገራት የሚያስማማ ሁሉን አቀፍ መግባባት ላይ መድረስ አልተቻለም። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወሳኝ ክስተቶች የጊዜ ሰሌዳ 2003 መጋቢት፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በአባይ ወንዝ ላይ በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላሮች በማውጣት ሊገነባው ያሰበውንና በአፍሪካ ትልቁ እንደሚሆን የተነገረለትን የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ይፋ አደረገ። ሚያዝያ ላይ የግድቡ ግንባታ ተጀመረ። ግንቦት ወር ላይ ግብጽ ሱዳንና ኢትዮጵያ በግድቡ ግንባታ ዙሪያ የቴክኒክ ኮሚቴ አዋቅረው ጥናት ማካሄድ ጀመሩ። መስከረም ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ግድቡ የግብጽን የውሃ ድርሻ የሚጎዳ አይደለም አለ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በግብጽ ጉብኝት ለማድረግ ካይሮ በገቡበት ወቅት ደግሞ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድቡ ሁለቱንም አገራት ሊጠቅም እንደሚችል ተናገሩ። 2004 ግንቦት፡ ከሦስቱ አገራት የተወጣጣ የኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሌሎች አራት የውጭ አካላትን ያካተተው ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን የግድቡን ተጽእኖ ማጥናት ጀመረ። በጥቅምት 2005 ላይ ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ግድቡ የሚገነባበትን ቦታ ሄዶ ጎበኘ። ከዚህ በኋላም ስፍራውን አራት ጊዜ ሄደው ጎብኝተዋል። 2005 ግንቦት፡ ኢትዮጵያ የአባይን ወንዝ አቅጣጫን ቀየረች። ሰኔ ላይ ደግሞ የባለሙያዎቹ ቡድን የመጨረሻ ሪፖርቱን አቀረበ። ኢትዮጵያና ግብጽም በሪፖርቱ አተረጓጎም ላይ መስማማት አልቻሉም። የግብጹ ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ሙርሲ በግድቡ ዙሪያ ጠንከር ያሉ ሀሳቦችን ማራመድ ጀመሩ። በተለያዩ አጋጣሚዎችም በቴሌቪዥን በሚያደርጓቸው ንግግሮችና ውይይቶች ላይ ኃይል መጠቀም የሚለውን ሀሳብ በተደጋጋሚ ያነሱ ነበር። ግብጽ በተደጋጋሚ ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንደምትወስደው ብትናገርም ብዙም ሳይቀይ አገራቱ የባለሙያዎቹ ቡድን ያቀረበውን ሀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ፖለቲካዊና ቴክኒካዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስማሙ። በ2006 መስከረም ወር ላይ የተባበሩት መንግሥታት አጠቃላይ ስብሰባ በኒውዮርክ ሲካሄድ ሁለቱ አገራት ባደረጉት የጎንዮሽ ስብሰባ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ድርድሩን ለማስቀጠል ተስማሙ። በኅዳር እና በታህሳስ ወር ላይ የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች ካርቱም ላይ ተሰባስበው የባለሙያዎቹ ያቀረቡት ሀሳቦችን ተግባራዊ ለማድረግ ውይይት አካሄዱ። ነገር ግን ስብሰባው ያለምንም ስምምነት ተጠናቀቀ። 2006 ጥር፡ የኢትዮጵያ፣ የግብጽና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች ለሦስተኛ ጊዜ በካርቱም ተሰበሰቡ። በስብሰባውም በቀሪ ጉዳዮች ላይ መስማማት ስላልቻሉ ከዚህ በኋላ ስብሰባ ላለማድረግ ተስማሙ። የካቲት ወር ላይ ደግሞ የኢትዮጵያና የግብጽ የውሃ ሚኒስትሮች ብቻ በአዲስ አበባ ቢሰበሰቡም ምንም አይነት ስምምነት ላይ መድረስ ሳይችሉ ቀርተዋል። መጋቢት ወር ላይ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የግብጽን አቋም ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅና በጎኑ ለማሰለፍ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። ሚያዝያ ወር ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ ግብጽ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የጀመረቸውን ዘመቻ እንድታቆምና ወደ ሦስትዮሹ ድርድር እንድትመለስ ጥያቄዋን አቀረበች። ሰኔ ወር ላይ የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር በኢኳቶሪያል ጊኒ በተካሄደው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ላይ በተጓዳኝ ውይይት በማድረግ የሦስትዮሽ ኮሚቴው በድጋሚ ሥራውን እንዲጀምር ተስማሙ። በነሐሴ ወር ላይ ደግሞ የሦስቱ አገራት የውሃ ሚኒስትሮች በካርቱም ድርድራቸውን በድጋሚ ጀመሩ። በዚያውም በባለሙያዎቹ ቡድን ምክረ ሀሳብ መሰረት አገራቱ በገልተኛ ዓለም አቀፍ ድርጅት የሚመራና ከሦስቱ አገራት የተወጣጡ አባላት ያሉት ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማሙ። 2007 መስከረም ፡ የግብጽና የሱዳን ውሃ ሚኒስትሮች የግድቡን የግንባታ ሂደት ከጎበኙ በኋላ የሦስትዮሽ ኮሚቴው አባላት በአዲስ አበባ ውይይት አደረጉ። ጥቅምት ወር ላይ ደግሞ የግድቡን አጠቃላይ ጥናት የሚያካሂድ ገለልተኛ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅትን ለመምረጥ በካይሮ ስብሰባ አደረጉ። 2007 ጥር፡ ግብጽ የግድቡን 74 ቢሊየን ኪዪቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅምና የግድቡን ከፍታ አልቀበለውም አለች። መጋቢት ላይ ደግሞ ሦስተኛው ዙር የሦስትዮሽ ኮሚቴ ስብሰባ በሱዳኗ መዲና ካርቱም ተካሄደ። በዚያውም ሦስቱ አገራት በመርህ ደረጃ በሚያስማሟቸው ጉዳዮች ላይ ተፈራረሙ። በተመሳሳይ ወርም የግብጹ ፕሬዝደንት በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ንግግር አደረጉ። 2007 ሚያዝያ፡ የሦስትዮሽ ኮሚቴው በአዲስ አበባ በመገናኘት የግድቡን አጠቃላይ ጥናት የሚያከናውኑ ሁለት የአውሮፓ አማካሪዎችን መረጡ። ሐምሌ ወር ላይ ደግሞ የኮሚቴው አባላት በካይሮ ባደረጉት ስብሰባ የሁለቱ አማካሪዎች የመጀመሪያ ዙር ምክረ ሀሳብን ገመገሙ። 2008 ኅዳር፡ የሦስትዮሽ ኮሚቴው በካይሮ ተሰበሰበ። በዚህ ስብሰባ ላይም ሁለቱ የአውሮፓ አማካሪ ቢሮዎች መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተገለጸ። ታህሳስ ወር ደግሞ ኮሚቴው ካርቱም ላይ ተሰብስቦ የካርቱሙን ስምምነት ተፈራረመ። በስምምነቱ መሰረትም የግድቡን አጠቃላይ የጥናት ሥራ በአንድ ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅና ከማማመከሩ እራሱን ባገለለው ድርጅት ፈንታ አዲስ አማካሪ ለመምረጥ ተግባቡ። 2008 ጥር፡ የግብጽ ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ውስጥ በመገናኘት የካርቱሙን ስምምነት ለማክበርና ከመግባባት ላይ ለመድረስ ተስማሙ። የካቲት ወር ላይ ደግሞ የሦስትዮሽ ኮሚቴው በካርቱም በመሰብሰብ ግድቡ በግብጽና በሱዳን ላይ ስለሚኖረው ተጽእኖ በፈረንሳይ አማካሪ ድርጅት በተሰራው ጥናት ላይ በመወያየት ግምገማ አካሄደ። 2009 መስከረም፡ ሦስቱም አገራት በዓለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ለማስፈጸም 'ቢአርኤልአይ' ከተባለው የፈረንሳይ ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራረሙ። 2009 የካቲት፡ ሁለቱ የፈረንሳይ አማካሪ ድርጅቶች የመጀመሪያ ዙር ሪፖርታቸውን በግድቡ ዙሪያ አቀረቡ። ሪፖርቱን ግብጽ ስትቀበለው ኢትዮጵያና ሱዳን ግን ውድቅ አደረጉት። ሚያዝያ ወር ላይ ደግሞ የግብጽ ፕሬዝዳንትና ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካይሮ ውስጥ ተገናኙ። በዚያውም የግብጹ ፕሬዝዳንት ካርቱም ላይ የተፈረመውን ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ የግድቡ ሙሌት ላይ ከስምምነት መድረስ እንደሚገባ ገለጹ። 2010 ጥቅምት፡ የሦስትዮሽ ኮሚቴው ካይሮ ውስጥ በመሰብሰብ በሁለቱ የፈረንሳይ አማካሪ ድርጅቶች በቀረበው ምክረ ሀሳብ ላይ በተፈጠሩ አለመግባባቶች ዙሪያ ምክክር አደረገ። ሕዳር ወር ላይ ደግሞ በድጋሚ ኮሚቴው በካይሮ ቢሰበሰብም ምንም ስምምነት ላይ መድረስ ሳይቻል ቀረ። በዚያው ወር ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግብጽ ችግር እየፈጠረች ነው በማለት ከሰሰ። 2010 ጥር፡ የግብጹ ፕሬዝደንት ድርድሩ ተስፋ ሰጪ ነገር እየታየበት አለመሆኑ እንዳሳባቸው በመግለጽ የዓለም ባንክን በጉዳዩ ለማስገባት ሀሳባቸውን አቀረቡ። ነገር ግን ኢትዮጵያ የግብጽን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አደረገችው። በዚያው ወር ላይ ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ዓመታዊ የሦስትዮሽ ስብሰባ ለማካሄድና በአንድ ወር ውስጥ ከግድቡ ጋር በተያያዘ የመሰረት ልማት ፈንድ በማቋቋም የሦስቱንም አገራት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቶችን ያካተተ ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማሙ። ሚያዝያ ወር ላይ ደግሞ የሦስቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የውሃ ሚኒስትሮችና የደኅንንት ኃላፊዎች በካርቱም ተሰበሰቡ። ነገር ግን ስብሰባው ፍሬያማ ስምምነት ላይ መድረስ ሳይችል ተበተነ። ግንቦት ወር ላይ የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን የውጭ ጉዳይ፣ የደህንንትና የውሃ ሚኒስትሮች በድጋሚ ስብሰባቸውን በአዲስ አበባ ላይ አደረጉ። ግብጽም ስብሰባው ስኬታማ እንደነበረ ገለጸች። ሰኔ ወር ላይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብጽን ሲጎበኙ በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ግድብ የግብጽን የውሃ ድርሻ እንደማይጎዳ ተናገሩ። 2011 መስከረም ፡ ከግድቡ ሙሌት ጋር በተያያዘ ግብጽ ስምምነቱን አልፈርምም አለች። 2011 ጥር፡ በሱዳን እየተካሄደ በነበረው ከፍተኛ ሕዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ምክንያት የግድቡ ድርድር መቋረጡን ግብጽ አስታወቀች። ሐምሌ ወር ላይ የግብጹ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካይሮ ውስጥ ተገናኙ። በዚያውም የሦስትዮሽ ድርድሩን ለማስቀጠል ተስማሙ። 2012 መስከረም ፡ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የድርድሩ መጓተት እንዳላስደሰተው አስታወቀ። ኢትዮጵያ ደግሞ ግብጽ ከግድቡ አሞላል ጋር በተያያዘ ያቀረበችውን ሀሳብ በድጋሚ ውድቅ አደረገችው። ግብጽ በበኩሏ ኢትዮጵያ ግድቡን ወደ ሥራ እንዳታስገባ አስጠነቀቀች። ጥቅምት ወር ላይ ደግሞ ዋይት ሐውስ ለመጀመሪያ ጊዜ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ መግለጫ አወጣ። ግብጽም በግድቡ ድርድር ላይ አሜሪካ እጇን እንድታስገባ ጥያቄዋን አቀረበች። ኢትዮጵያ ደግሞ የግብጽን ጥሪ ተቃወመች። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር ማንኛውም አይነት ኃይል ኢትዮጵያን ግድቡን ከመገንባት እንደማያስቆማት ተናገሩ። ግብጽ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር በመተቸት በአሜሪካ ዋሽንግተን ለመነጋገር የቀረበውን ሀሳብ እንደምትቀበለው ተናገረች። ሁለቱ አገራት በሶቺ በተካሄደው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ ላይ በመገናኘት የሦስትዮሽ ድርድሩን ለማስቀጠል ተስማሙ። ኅዳር ላይ ደግሞ በአሜሪካ አደራዳሪነት አዲስ ውይይት ተጀመረ። የሦስቱ አገራት የውሃ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችም በበዋሽንግተን ድርድራቸውን ካደረጉ በኋላ በአሜሪካና በዓለም ባንክ ታዛቢነት ሁለተኛ ድርድራቸውን በአዲስ አበባ አካሄዱ። ታህሳስ ወር ላይ የሦስትዮሽ ኮሚቴው በካይሮ፣ ዋሽንግተን እና ካርቱም በአሜሪካና በዓለም ባንክ ታዛቢነት ሦስት ስብሰባዎችን አካሄደ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ስብሰባው ውጤታማ እንደነበረና ግብጽም ከግድቡ ሙሌት ጋር በተያያዘ ያቀረበችውን ሀሳብ እንደተወችው አስታወቀ። ነገር ግን ግብጽ አልተውኩትም በማለት አስተባበለች። 2012 ጥር፡ የአገራቱ የውጭ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች ዋሽንግተን ሁለት ጊዜ ሲገናኙ የውሃ ሚኒስትሮች ብቻ ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ተገናኝተዋል። ሕጋዊና ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰራው ቡድን ደግሞ ካርቱም ውስጥ ተገናኘ። በዚህ ወቅት ከተደረሱ ስምምነቶች ዙሪያ ግብጽና ኢትዮጵያ እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ መግለጫዎችን አወጡ። ሕጋዊና ቴክኒካዊ ቡድኑ እንዲሁም የውሃና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በአሜሪካ ዋሽንግተን በተደጋጋሚ ተወያዩ። ነገር ግን የመጨረሻዎቹን ሁለት ስብሰባዎች ኢትዮጵያ አልተካፈለችም። ግብጽ ደግሞ ከግድቡ ሙሌት ጋር በተያያዘ በአሜሪካ አሸማጋይነት የቀረበውን ሀሳብ ተቀብላ ስምምነቱን ፈረመች። መጋቢት ወር ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃላፊዎች በግድቡ ላይ የሚፈጸም ማንኛውም አይነት ጥቃትን ለመመከት ዝግጁ መሆናቸው አስታወቁ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም አሜሪካ በድርድሩ ላይ ወደ አንድ ቡድን ያጋደለ አቋም እንዳረመደች በመግለጽ ቅሬታውን አቀረበ። ግብጽ በበኩሏ ወደ አረብ አገራት በመሄድ አቋሟን እንዲረዱና እንዲደግፏት ዘመቻ አደረገች። ኢትዮጵያም በአረብ ሊግ የቀረበውን ሀሳብ አልቀበለውም አለች። ግንቦት ላይ ደግሞ የግድቡን ሙሌት የተመለከተውን በኢትዮጵያ የቀረበውን ሀሳብ ግብጽ አልቀበለውም እንደማትቀበለው አሳወቀች። ኢትዮጵያ ደግሞ የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅና የውሃ ሙሌት ሥራውን በተገቢው መንገድ ለማከናወን የግብጽን ይሁንታ እንደማትፈል በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ጻፈች። ግብጽ ደግሞ ቀደም ብላ ሁለቱ አገራት ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ኢትዮጵያ ግድቡን የመሙላት ሥራውን እንዳትጀምር ለጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ደብዳቤ አስገብታ ነበር። የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ ሁለቱ አገራት አለመግባባታቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱት ሀሳቡን አቅርቧል። ሰኔ ወር ላይ ሱዳን ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ሁለቱ አገራት ውይይት ሳይካሄድ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳያስተላልፉ ስትል ጠየቀች። በጉዳዩ ላይ የማሸማገል ሥራ ለመስራት ሩሲያ ሀሳብ አቅርባ ነበር። የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን አምስት ተከታታይ ድርድሮችን አካሄዱ። ግብጽ ድርድሩ ተስፋ ሰጪ አይደለም ስትል ኢትዮጵያ በበኩሏ ድርድሩ ውጤታማ የማይሆነው በግብጽ ምክንያት ነው ስትል ከሳለች። ሰኔ 26 ላይ ደግሞ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሰብሳቢ ሲሪል ራማፎሳ ከሦስቱ አገራት መሪዎች ጋር በቨዲዮ ኮንፈረንስ ተገናኘተው ተወያዩ። በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታትም ስምምነት ላይ ለመድረስ የተስማሙ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ግን የግድቡ የመጀመሪያ ዙር ሙሌት በተከታይነት በነበሩት ሳምንታት እንደምትጀምር በመግለጽ የግድቡን ሥራ ለማከናወን አገራትን መለመን እንደበቃት አስታወቀች። ሐምሌ ላይ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ወታደራዊ አማራጭ እንደማከተሉ ገለጸ። በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት ሦስቱንም አገራት በማሳተፍ የተካሄደውም ድርድር ያለምንም ስምምነት ተጠናቀቀ። ተከትሎም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሙሌት መጀመሩን ይፋ ማድረግ ጀመሩ። የአረብ አገራት ሚዲያዎችም ዜናውን ተቀባበሉት። ግብጽ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጣት የኢትዮጵያን መንግሥት ጠየቀች። ከጥቂት ሰዓታት በኋላ መረጃውን ቀድሞ ይፋ ያደረገው የአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዜናውን ከገጹ ላይ አነሳ። ሱዳን በበኩሏ የሙሌት ስራው ተጀመረ ከተባለ በኋላ የ90 ኪዩቢክ ሜትር ቅናሽ ማየቷን አስታወቀች።
xlsum_amharic-train-245
https://www.bbc.com/amharic/news-52604645
"በፋና ከትግራይ የሚወጡ መረጃዎች ተለቅመው እንዲለዩ ይደረጋል" የመቀለ ፋና ኤፍ ኤም ሥራ አስኪያጅ
መቀለ በሚገኘው የፋና ኤፍ ኤም ቅርንጫፍ ሬዲዮ ጣቢያ የሚሰሩ ጋዜጠኞችና አመራር አዲስ አበባ የሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በሥራችን ላይ ጫና እየደረሰብን ነው አሉ።
[ "መቀለ በሚገኘው የፋና ኤፍ ኤም ቅርንጫፍ ሬዲዮ ጣቢያ የሚሰሩ ጋዜጠኞችና አመራር አዲስ አበባ የሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በሥራችን ላይ ጫና እየደረሰብን ነው አሉ።" ]
የመቀለ ፋና ኤፍኤም 94.8 ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ መሰረት ታደሰ "ፋና ሁለት ዓይነት ፋና ሆኗል" ሲል በመቀለው ቅርንጫፍና በአዲስ አበባው ዋና መሥሪያ ቤት መካከል ስለተፈጠረው መለያየት ያስረዳል። "በመቀለና አዲስ አበባ ያሉ አጀንዳዎች ተለያይተዋል። በሁለቱም የሚሰራጩ ዜናዎችና ዝግጅቶችም የማይገናኙ ሆነዋል" የሚለው ሥራ አስከያጁ፤ በክልሉ ስላሉ ጉዳዮች ሳይሆን ከመሃል አገር ለሚመጡ አጀንዳዎች የቅድሚያ ትኩረትን መስጠት አለባችሁ በሚል ጫና እንደተደረገባቸው መሆኑን ይገልጻል። ይህንን በመቃወም በተደጋጋሚ ለማስረዳት ቢሞክሩም ከዋናው መሥሪያ ቤቱ በኩል ሰሚ እንዳጡና የድርጅቱን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ በማይጥስ መልኩ ለክልላዊና አገራዊ ጉዳዮች ሽፋን መስጠት እንደቀጠሉ ሥራ አስኪያጁ ተናግሯል። "ድርጅቱ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ፤ እንዲሁም ሌሎች ማንዋሎችና የኢትዮጵያ ብሮድካስት አዋጅ እንደሚለው ከሆነ ሚድያው 60 ከመቶ ለአገራዊ ጉዳዮች ወይም መረጃዎች ሽፋን መስጠት አለበት። ፋና ግን ላለፉት ሁለት ዓመታት አገራዊ አጀንዳዎችን ወደጎን ትቷል" ሲል ይገልጻል- ጋዜጠኛ መሰረት። ምክንያቱን ሲያስረዳም "ተቋሙ በአዲስ አበባና በከተማዋ ለሚገኘው የፌደራል መንግሥትን የሚመለከቱ አጀንዳዎች ሽፋን በመስጠት ክልላዊ ጉዳዮችን ረስቷል፤ ይህም የመንግሥት ቃል-አቀባይ ሆኖ እንደማገልገል እንቆጥረዋለን" ብሏል። "በደብዳቤ አሳውቀናል. . . " ችግሩ ማስተካከያ እንዲደረግበት ከዋናው መሥሪያ ቤት አመራሮች ጋር እንደተነጋገሩና ከአመራሩ የያገኙት መልስ ግን "ከዚህ ለሚሰጣችሁ አጀንዳ ትኩረት ሰጥታችሁ መሥራት አለባችሁ" የሚል እንዶነ አስታውሷል። የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ መሰረት እንደሚለው፤ በየክልሉ የተከፈቱት የፋና ኤፍኤሞች በየአካባቢያቸው ላሉ ጉዳዮች ሽፋን መስጠት ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ለሚገኘው ዋናው ማሰራጫም ክልላዊ በዜናም ይሁን በፕሮግራም በመልክ እንዲያቀርቡ በኤዲቶሪያል ፖሊሲውም እንዲሆንም በማንዋሎቹ ሰፍሮ ይገኛል። "ይሁን እንጂ" ይላል ጋዜጠኛ መሰረት "በመቀለም ይሁን በትግራይ ክልል የሚኖሩ ሁነቶች በዜናና በፕሮግራም መልክ ስንልክላቸው አብዛኞቹ እንዲታገዱ፣ ሌሎቹ በተዛባ መልኩ እንዲቀርቡ፣ አልፎ አልፎም እኛ የዘገብነውን ትተው ሌላ ምንጭ የመጠቀም ሁኔታ አለ" ሲል ስለሁኔታው ይገልፃል። ይህ ክስተት እየተደጋገመ በመሄዱም በህዳር ወር 2012 ላይ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት ደብዳቤ በመጻፍ "እኛ የምንልካቸው መረጃዎች ሲታገዱና በተዛባ መልኩ ሲቀርቡ እዚህ ካሉት አድማጮቻችን ጋር ስለሚያራርቁን መሻሻል አለበት። 'ይህ መሆን ካልቻለ ግን ከዚህ ወዲህ የምንልክላችሁ ዘገባ አይኖርም' የሚል መልዕክት አስተላልፈናል" በማለት ይናገራል። ይሁን እንጂ በህዳር ወር ላይ ለተጻፈ ደብዳቤ እስከ ዛሬ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው የሚናገረው ሥራ አስኪያጁ፤ በእነርሱ በኩልም ወደ ዋናው ማሰራጫ የተላኩ ዘገባዎች እንዳልነበሩ አስታውሷል። ይህ ዋናው መስሪያ ቤትና በቅርንጫፍ ጣቢያው መካከል ያለው አለመግባባትም ከሁለት ዓመት በፊት እንደጀመረ ሥራ አስኪያጁ ይገልጻል። "የመንግሥት ለውጥ ከተደረገ ወዲህ ፋና በአካባቢያችን የነበረው ተቀባይነትና ተደማጭነት እየቀነሰ መጥቷል። በዚህ ሁኔታ ውስጥም ሆነን ግን ለአካባቢያችን ይመጥናል የምንላቸውን ይዘቶችና አጀንዳዎችን ማቅረብ ስንጀምር ጉዳዩ እየከረረ ሄደ" መሄዱን ጋዜጠኛ መሰረትአመለክቷል። ጨምሮም የመቀለው ቅርንጫፍ ከአዲስ አበባ ለሚሰራጩ ፕሮግራሞች በተመደበው የአየር ጊዜ አንዳችም መሸራረፍ ሳያደርግ ሙሉ ሽፋን መስጠቱን አስረድቷል። እሱ እንደሚለው፤ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ግን በዋናው ማሰራጫ ትግራይን ለሚመለከቱ ዘገባዎች የሚሰጠው ሽፋን ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ሆኗል። የታገዱ ይዘቶች ምን ምን ናቸው? መቀለ ፋና ኤፍ ኤም ከአዲስ አበባ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች በሊንክ እየተቀበለ በመቀለና አካባቢዋ ለሚገኙ አድማጮች የሚያደርስ ሆኖ በቀን ካለው የሥርጭት ሰዓትም ስምንቱን በራሱ ጋዜጠኞች ለሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ያውላል። ክልሉን የሚመለከቱ ጉዳዮችም በነዚህ ሰዓታት ሽፋን ያገኛሉ። አለመግባባቱ የተፈጠረውም በእነዚ ሰዓታት ላይ በሚቀርቡት ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ቁጥጥር መደረግ በመጀመሩ እንደሆነ የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ መሰረት ይናገራል። "እንዳንሰራቸው ወይም ሽፋን እንዳንሰጣቸው የተከለከልነው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። ከትግራይ የሚወጡ መረጃዎች ተለቅመው እንዲለዩ ይደረጋል። አብዛኞቹም እንዳይተላለፉ ይደረጋል" ይላል። በማስከተልም "ለምሳሌ የክልሉ ምክር ቤት ውሳኔዎች፣ የክልሉ ፓርቲዎች በተለይም የህወሓት መግለጫዎች፣ የክልሉ ሥራ አስፈጻሚዎች የሚሰጧቸው መግለጫዎች፣ የምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ መግለጫዎችና ቃለ-መጠይቆችን በተደጋጋሚ ልከን እንዳይተላለፉ ታግደዋል" ሲል በዝርዘር ያስቀምጣል። ሌላው ቀርቶ በክልሉ የተካሄዱ ታላላቅ ሕዝባዊ ሰልፎችም በቀጥታና ከተካሄዱ በኋላ የአየር ሽፋን እንዳይሰጣቸው መደረጉንም ገልጿል። "ሽፋን የተሰጣቸውም ካሉ በተሸራረፈና ባልተባለ መልኩ ሲቀርቡ ታዝበናል። እዚያ ያሉ ጋዜጠኞችም 'የፌደራል መንግሥት በሚመለከት የሚሰጡ አስተያየቶች እንዳትልኩልን' ይሉናል" በማለትም ይናገራል። ማስጠንቀቂያው! ጋዜጠኛ መሰረት እንደሚለው ጉዳዩ እየጠነከረ በመምጣቱ በሚያዝያ 30/2012 ዓ.ም ከዋና መሥሪያ ቤቱ የተጻፈ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ በግንቦት 1/2012 ደርሷቸዋል። ደብዳቤው ግን በግልጽ ያሰፈረው መልዕክት እንደሌለ ይናገራል። "ደብዳቤው የሚድያ ተቋሙ 'ኤዲቶሪያል ፖሊሲና መመሪያዎችን አለማክበርና እንዲከበሩ አለማድረግ' ይላል። በዝርዝር ያሰፈረው ነገር የለም፤ ጥቅል ነው። የተጣሰው ነገር ምንድነው? ያልተከበረውስ? የሥራ ዲሲፕሊን ጥሰትም ይላል፤ በማንና መቼ ነው የተጣሰው? የሚሉት በግልጽ አልሰፈሩም" ብሏል። ደብዳቤው ተፈጽመዋል የተባሉት ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲስተካከሉ ስለሚጠይቅ መታረም ያለባቸው ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ በግልጽ ባለመቀመጣቸው "ግልጽ ያልሆነ ደብዳቤ" ሲል ገልጾታል። የተነሱት ጉዳዮች በግልጽና በዝርዝር እንዲቀመጡም ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት ደብዳቤ መላካቸውንም አስታውሷል። ኤፍቢሲስ ምን ይላል? ደብዳቤው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አክሲዮን ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ በቀለ ሙለታ ቶላ እንደተጻፈ በስም፣ ፊርማና ማህተም መረዳት ችለናል። ቢሆንም በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን በስልክ ጥያቄ ያቀረብንላቸው ዋና ሥራ አስኪያጁ "ጉዳዩን በደንብ ስለማላውቀው መልስ መስጠት አልችልም" ብለውናል። በማስከተልም "ጉዳዩም የውስጥ ጉዳይ ስለሆነ በውስጥ ነው የምንፈታው እንጂ አሁን መናገር አልችልም" በማለት ለተጨማሪ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የመቀለ ፋና ኤፍ ኤም ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ መሰረት ታደሰ እንደሚለው ከሆነ "የድርጅቱ ስም እየተበላሸ በመምጣቱ ምክንያት ብዙ ጋዜጠኞች ሥራቸውን ለቀዋል። የተቀሩት ደግሞ እነዚህን ፈተናዎች በመቋቋም አሁንም ኤዲቶርያል ፖሊሲውን በመጠበቅና 'ለወራት ስናካሂደው የነበረውን ትግል እናስቀጥላለን' በማለት ሥራቸውን እንደቀጠሉ" ገልጿል። "አሁን እየመጣ ስላለው ቁጣና ማስጠንቀቂያ ቀድሞውንም እናውቀው ነበር፤ ሙያዊ አቅማችንን በመጠቀምም ትግራይንና የትግራይን ሕዝብ እናገለግላለን። ምናልባት ቅጣት ከመጣም ተዘጋጅተናታል" ብሏል ሥራ አስኪያጁ። በአገሪቱ ከሚገኙ ጥቂት ግዙፍ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት አንዱ የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በተለያዩ ስፍራዎች ካሉት የኤፍኤም ጣቢያዎች አንዱ የሆነው መቀለው ቅርንጫፍ ጣቢያ ከተከፈተ 10 ዓመት እንደሆነው ለማወቅ ተችሏል።
xlsum_amharic-train-246
https://www.bbc.com/amharic/news-49619074
ህንዳዊቷ በ73 ዓመታቸው መንታ ተገላገሉ
በሕንድ ደቡባዊ ግዛት አንድህራ ፕራደሽ የ73 ዓመቷ አዛውንት የመንታ ሴት ልጆች እናት ሆነዋል። አዛውንቷ ባሳለፍነው ሐሙስ በሐኪሞች እገዛ የሴትን እንቁላልና የወንድ ዘር ፈሳሽ (ስፐርም) በቤተ ሙከራ በማዋሃድ [IVF treatment] መንትዮች ጸንሰው ዐይናቸውን በዐይናቸው ማየት ችለዋል።
[ "በሕንድ ደቡባዊ ግዛት አንድህራ ፕራደሽ የ73 ዓመቷ አዛውንት የመንታ ሴት ልጆች እናት ሆነዋል። አዛውንቷ ባሳለፍነው ሐሙስ በሐኪሞች እገዛ የሴትን እንቁላልና የወንድ ዘር ፈሳሽ (ስፐርም) በቤተ ሙከራ በማዋሃድ [IVF treatment] መንትዮች ጸንሰው ዐይናቸውን በዐይናቸው ማየት ችለዋል።" ]
የ73 ዓመቷ ማንጋያማ ያራማቲ • በሕይወት ከሌለች እናት የተወለደችው ሕፃን • መንታ ጠብቃ አምስት የተገላገለችው እናት የ73 ዓመቷ ማንጋያማያ ማርቲ እንዳሉት፤ እሳቸውና የ82 ዓመቱ ባለቤታቸው ልጅ መውለድ ቢፈልጉም እስካሁን ድረስ ሳይሳካላቸው ቆይቶ ነበር። ማንጋያማያ ሁለቱን መንታ ሴት ልጆች የወለዷቸው በቀዶ ሕክምና ነው። ሀኪማቸው የነበሩት ዶ/ር ኡማ ሳንካራም፤ እኝህ እናት ከነልጆቻቸው በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። ልጆቹ ከተወለዱ ከሰዓታት በኋላ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አባት ሲታራማ ራጃሮ በበኩላቸው " በጣም ተደስተናል" ብለዋል። ይሁን እንጂ ይህንን በተናገሩ ማግስት ድንገተኛ ስትሮክ ስላጋጠማቸው በሆስፒታል ውስጥ የሕክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ። • አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው? እድሜያቸው በመግፋቱ ምክንያት በባለቤታቸውና በእሳቸው ላይ አንድ ነገር ቢፈጠር ልጆቹን ማን ሊያሳድጋቸው ይችላል? ተብለው የተጠየቁት የ82 ዓመቱ አዛውንት ሮጀር፤ "በእጃችን ላይ ምንም ነገር የለም፤ መሆን ያለበት ይሆናል፤ ሁሉም ነገር በፈጣሪ እጅ ነው ያለው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በመንደራቸው ልጅ ባለመውለዳቸው መገለል ይደርስባቸው እንደነበር የሚናገሩት ጥንዶቹ፤ ልጆች መውለድ ለነሱ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያስረዳሉ። እናት ማንጋያማያ፤ "ልጅ አልባዋ ሴት እያሉ ይጠሩኝ ነበር" ሲሉ ይደርስባቸው የነበረውን የሥነ ልቦና ጫና ያስታውሳሉ። "ብዙ ጊዜ ሞክረናል፤ በርካታ የሕክምና ተቋማትንም ጎብኝተናል" በማለት አሁን ግን በሕይወት ዘመናቸው ደስታን የተጎናፀፉበት ጊዜ እንደሆነ ይገልፃሉ። ከሦስት ዓመታት በፊትም እዚያው ሕንድ ውስጥ በ70ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ዳለጂንደር ካዩር የተባሉ አዛውንት ወንድ ልጅ መውለዳቸው ይታወሳል።
xlsum_amharic-train-247
https://www.bbc.com/amharic/news-49354761
"በክልል ደረጃ ቅሬታ ሲቀርብ የመጀመሪያው ነው" የምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ
የሃገር አቀፉ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ከተደረገ አንስቶ የተለያዩ ቅሬታዎች እየተሰሙ ነው። ቅሬታው የጀመረው በፈተናው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሳይቀሩ ስኮላስቲክ አፕቲቱዩድ በሚባል የፈተና ዓይነት ዝቅተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው ነው።
[ "የሃገር አቀፉ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ከተደረገ አንስቶ የተለያዩ ቅሬታዎች እየተሰሙ ነው። ቅሬታው የጀመረው በፈተናው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሳይቀሩ ስኮላስቲክ አፕቲቱዩድ በሚባል የፈተና ዓይነት ዝቅተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው ነው።" ]
ይህንንም ተከትሎ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ የፈተናው ውጤት ላይ ቅሬታ እንዳለው አስታውቋል። የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮም በፈተናው ውጤት ላይ ቅሬታ እንዳለው ለቢቢሲ ገልጿል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በበኩሉ የአፕቲቲዩድ ፈተና ውጤትን የሚያጣራ ኮሚቴ ማዋቀሩን ተናግሯል። • የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ላይ ቅሬታ አቀረበ • የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተና ውጤትን የሚያጣራ ኮሚቴ ተዋቀረ ያነጋገርናቸው በአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሺፋ ዛሬ እንደገለፁልን "በክልል ደረጃ ቅሬታዎች ሲሰሙ ይህ የመጀመሪያው ነው" ብለዋል። አቶ ረዲ ሺፋ እንደሚሉት የፈተና ማረሚያ ሶፍትዌሩና የማረሚያ ማሽኑ ከእንግሊዝ አገር የመጣ ሲሆን አገልግሎት መስጠት ከጀመረም ዓመታት እንደተቆጠሩ ያስረዳሉ። ይህ ማሽን ሥራ ላይ ከመዋሉ አስቀድሞ 'ኮብል' የሚባል ሶፍትዌር ለፈተና ማረም አገልግሎት ይውል እንደነበር ያስታውሳሉ። ኤጀንሲው የሚዘጋጀው የ10ኛ ክፍልን አገር አቀፍ ፈተና እንደሆነ የሚገልፁት አቶ ረዲ፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ስለሆነ የሚዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ተቋም ውስጥ ባሉ ባለሙያዎችም የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ፈተና ይዘጋጃል። ይሁን እንጂ ኤጀንሲው ፈተናውን የመረከብ፣ የማሰራጨት፣ የማረም እና ውጤት የመግለፅ በአጠቃላይ የማስተዳደር ኃላፊነት አለው። እርሳቸው እንደገለፁልን የ12ኛ ክፍል የፈተና የመልስ ቁልፍም የሚመጣው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው። ለመሆኑ ከፈተና ዝግጅት እስከ ውጤት የሚከናወኑ ተግባራት ምንድን ናቸው? 1.ቅድመ ጥንቃቄ የፈተና ዝግጅቱ ቅድመ ጥንቃቄና ሚስጢራዊነቱ የሚጀምረው እያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ማን እንደሚያዘጋጀው ባለማሳወቅና ሚስጢራዊነቱን በመጠበቅ ነው ይላሉ- አቶ ረዲ። ፈተናው በሚዘጋጅባቸው ጊዜያትም አገልግሎት ላይ ከሚውሉት ኮምፒዩተሮች መረጃ አፈትልኮ እንዳይወጣ ታስቦ ኔትወርክ አልባ ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው። ፈተናው ከተዘጋጀ በኋላም የሚቀመጥባቸው የፈተና ካዝናዎች አሉ። በሕትመት ወቅትም የሚታተምበት ተቋም በደህንነት ካሜራ 24 ሰዓት ጥበቃ ይደረግለታል። በመማተሚያ ቤቱ ሥራውን የሚያከናውኑት ባለሙያዎች በሥነ ምግባራቸውና በሥራ ብቃታቸው ለፈተና ሥራ ብቻ የተመረጡ ናቸው። እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚደረገው ከኤጀንሲው የተመረጡ ባለሙያዎችና የፌደራል ፖሊሶች ባሉበት ነው። • ''ውጤቱ ለእኔ ደመወዜ ነው" ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ብሩክ እናት ፈተናው ወደ 'ሚታተምበት ክፍል ምንም ዓይነት ነገር ይዞ መግባት የማይፈቀድ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ፍተሻና ቁጥጥር ይደረጋል። ከዚህም ባሻገር ፈተና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በሚጓጓዝበት ወቅት በምርጫ ቦርድ ቁልፍ ታሽገው ነው። ተረካቢው አካልም ቃለ ጉባኤ ተፈራርሞ፤ ወደ ክልል ሲሄድም በፌደራል ፖሊስ ጥበቃ ተደርጎ ነው። ፈተናው በወጣው መረሃ ግብር መሰረት ለተማሪዎች እስከሚሰጥ ድረስም እንዲቆይ የሚደረገው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ነው። 2.ግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ከፈተናው ቀደም ብሎና በፈተናው ወቅት ተማሪዎች አስፈላጊ መረጃዎችንና የመልስ ምርጫቸውን በጥንቃቄ እንዲሞሉ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማብራሪያ ይሰጣቸዋል። ይሁን እንጂ በልጅነት ምክንያት ትኩረት ባለመስጠትም ሆነ በመደናገጥ ስህተት ሲሰሩ ግን ያጋጥማል። ፈተናው ሲሰጥም ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል። 3.ከየፈተና ጣቢያው የመልስ ወረቀቶችን መሰብሰብ በዚህ ሂደት የፈተና ወረቀቶቹ ተሰብስበው በየትምህርት ዓይነቱ፣ በየክልሉና ዞኑ ይደራጃሉ። ከተደራጁ በኋላ ከእርማት በፊት በወረቀት (Hard copy) የተሰበሰቡት የመልስ ወረቀቶች ስካን ተደርገው ወደ ሶፍት ኮፒ (Soft copy) ይለወጣሉ። ከዚያም በተቋሙ ዳታ ቤዝ (የመረጃ ቋት) ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል። 4.ቁልፍ ማስተካከያ (Key correction) ተፈታኞች ስም ሲፅፉ ወይም በራሳቸው በተማሪዎቹ መሞላት የሚገባቸው ኮዶችን ሲፅፉ የሚሳሳቱ ካሉ ቁልፍ ማስተካከያ ይደረጋል። በዚህ ሂደት ነው የፈተና ወረቀቶቹ ከአራሚዎቹ እጅ ጋር የሚነካኩት። ይህ ስህተት ከየመፈተኛ ጣቢያዎቹ የሚመጣ የተፈታኞች ስም ዝርዝር (Master List) ጋር ተመሳክሮ ይስተካከላል። "እንደዚህ ዓይነት ስህተት የሚፈጥሩ ተማሪዎች በርካታ ናቸው" የሚሉት ዳይሬክተሩ "የራሳቸው ጉዳይ ብለሽ ብትተያቸው ዜጎች ናቸው" ሲሉ በዚህ ምክንያት ማስተካከያ እንደሚደረግ ገልፀውልናል። ለተቋሙ ጊዜ የሚወስድበትም ይህን የማስተካከል ሥራ ነው። መልሱን ለማስተካከል ግን የሶፍት ዌሩም ስሪት አይፈቅድም። ለማስተካከል ቢታሰብ እንኳን የሚቻል አይደለም። 5.የእያንዳንዱ ፈተና የመልስ ቁልፍ የመልስ ቁልፉ ሶፍት ዌሩ ውስጥ ከገባ በኋላ እያንዳንዱን ፈተና የማረም ሥራ ይጀመራል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ከሆነ የፈተና ማረሚያ ማሽኑ ፈተናውን ለማረም የሚወስድበት ጊዜ ብዙ አይደለም። ሂደቱ በፍጥነት ነው የሚከናወነው። ይህንን የፈተና ማረሚያ ማሽን ያቀረበው ድርጅት ማሽኑ ያለዕክል የሚጠበቅበትን ተግባር እንዲያከናውን በየጊዜው ፍተሻ ያደርግለታል። አገልግሎት የማይሰጡና ያረጁ ማሽኖች እየተወገዱ በአዳዲስ ይተካሉ። በየወቅቱም በባለሙያዎች ክትትል ይደረግለታል። ስለዚህ "የሚያሰጋ ነገር የለም" ብለዋል- ዳይሬክተሩ። ቅሬታዎች ... በዘንድሮው ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተና በሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሳይቀሩ በርካታ ተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው ቅሬታዎች ቀርበዋል። በዚህ የትምህርት ዓይነት ላይ ከዚህ ቀደም ቅሬታ ቀርቦ እንደማያውቅ የሚናገሩት ባለሙያው በ2007 ዓ.ም ግን [ጊዜውን እርግጠኛ አይደሉም] በአስረኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በታሪክ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ቅሬታ ተነስቶ እንደነበር ያስታውሳሉ። በወቅቱም ቅሬታዎች ቀርበው በባለሙያዎች ሲፈተሽ የመልስ ቁልፉ ወደ ማረሚያ ማሽኑ ሲገባ ስህተት መፈጠሩ ታውቆ፤ ከዚያ በኋላ ትክክለኛው የመልስ ቁልፍ ገብቶ እንዲታረም መደረጉንና ውጤቱ በድጋሚ እንደተገለፀ ይናገራሉ። • 28 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች በፈተና ወቅት ወለዱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ሾልኮ መውጣት እንዲሁም ውጤት ላይ ቅሬታ መሰማታቸው የተለመደ ሆኗል። በዚህም ምክንያት በፈተና ወቅት በመላ ሃገሪቱ ኢንተርኔት እስከ ማዘጋትም ደርሷል። ፈተና በድጋሚ የተሰጠበት አጋጣሚም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህንኑ ያነሳንላቸው ዳይሬክተሩ "ያኔ በአገሪቱ ውስጥ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ነበር፤ ፈተናው እያንዳንዱ የአገሪቱ ጫፍ እስከሚደርስ ድረስ የተለያዩ የፀጥታ ችግሮች ነበሩ" ይላሉ። ነገር ግን በትክክል በወቅቱ ተከስቶ የነበረው ጉዳይ በሕግ የተያዘ ስለሆነ እርሱ ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ታዲያ አሁን ያለው ሁኔታ እንዲህ ዓይነት ችግር እንዲፈጠር የሚያደርግ አይደለም ነው የሚሉን? ስንል ለዳይሬክተሩ ጥያቄያችንን አስከተልን። "ከቀደመው ጋር ሲነፃፀር ሰላማዊ ነው ማለት ይቻላል፤ ይሁን እንጂ ችግሮች የሉም ማለት አይደለም" ሲሉ መልሰዋል። በፈተና ውጤት ዙሪያ በክልሎች ደረጃ ቅሬታ ሲቀርብ ይህ የመጀመሪያው ሲሆን እንደ ግለሰብ ግን በየዓመቱ ቅሬታዎች እንደሚቀርቡና እንደሚታይላቸው ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። ቢቢሲ ረቡዕ እለት ያነጋገራቸው የሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ገ/እግዚአብሄር በበኩላቸው፤ በውጤቱ ላይ ለሚነሱ ቅሬታዎች በሙሉ አስፈላጊው ማጣራት ከተካሄደ በኋላ ምላሽ ይሰጠዋል ብለዋል።
xlsum_amharic-train-248
https://www.bbc.com/amharic/news-52586475
ያልተነገረላቸው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀግና ሴቶች
እስቲ ለአፍታ የጦርነት ጀግኖችን ያስቡ። በጀግንነት ሲፋለሙ ያሰቧቸው ወንዶች ናቸው ሴቶች? በብዙዎች አእምሮ ጀብድ የፈጸሙ ሴቶች አይታወሱም። አርብ ዕለት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአውሮፓ ያበቃበት 75ኛ ዓመት ዕለት ነበር። እኛም በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ጀብድ የፈጸሙ 8 ሴቶችን ልናስተዋውቃችሁ ፈቅደናል።
[ "እስቲ ለአፍታ የጦርነት ጀግኖችን ያስቡ። በጀግንነት ሲፋለሙ ያሰቧቸው ወንዶች ናቸው ሴቶች? በብዙዎች አእምሮ ጀብድ የፈጸሙ ሴቶች አይታወሱም። አርብ ዕለት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአውሮፓ ያበቃበት 75ኛ ዓመት ዕለት ነበር። እኛም በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ጀብድ የፈጸሙ 8 ሴቶችን ልናስተዋውቃችሁ ፈቅደናል።" ]
ቼንግ ቤንሁ፡ ሞትን በፈገግታ የተቀበለችው ቼንግ ቤንሁ ቻይናዊ ጀግና ነበረች። ጃፓን እ.አ.አ. 1937 ላይ አገሯን ስትወር ቼንግ ከሌሎች ጋር ሆና ወራሪውን ጠላት ከአገሯ ለማባረር ታግላለች። ቼንግ በስለት ተወግታ ከመገደሏ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት የተነሳችው ፎቶግራፍ ሰዎች ያለፍርሃት የትጥቅ ትግል እንዲያደርጉ መነሳሳትን የፈጠረ ነበር። ፎቶግራፉን ያነሳው ጃፓናዊ ፎቶግራፍ አንሺ የቼንግን የመጨረሻ ሰዓታት መዝግቦ አስቀምጧል። • የኮሮናቫይረስ ተመራማሪው ዶ/ር ቢንግ ሊው ለምን ተገደሉ? በጃፓን ጦር በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ ድብደባ ተፈጽሞባታል፤ በበርካቶች በተመሳሳይ ጊዜ ተገዳ ተደፍራለች፤ ለጠላቶቿ ግን አልተንበረከከችም። ምንም እንኳ የቼንግ ሕይወት ቢያልፍም ከመሞቷ በፊት በተነሳችው ፎቶ ላይ በፈገግታ ተሞልታ እና እጆቿን ደረቷ ላይ አጣምራ አይኖቿ ካሜራውን እያዩ ነበር። ቼንግን ለመዘከረም በጃፓን ወታደሮች ከ300 ሺህ በላይ ቻይናውያን በተገደሉበት ናንጂንግ ከተማ 5 ሜትር የሚረዝም ሃውልት ቆሞላታል። ቼንግ በ24 ዓመቷ ነበር እ.አ.አ. በ1938 የተገደለችው። ኖራ ኢናያት ካሃን፡ ሰላይዋ ልዕልት ኖራ ኢናያት ካሃን የህንድ ልዕልት እና የብሪታኒያ ሰላይ ነበረች። ኖራ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የሕንዷን ማይሱሩ ከተማ ሲያስተዳድር ከነበረው ቲፑ ሱልታን የዘር ግንድ ትመዘዛለች። ከሕንዳዊ የእስልምና እምነት አስተማሪ እና ከአሜሪካዊቷ ተዋናይት የተወለደችው ኖራ፤ ትውልድ እና እድገቷ ሩሲያ፣ ሞስኮ እንዲሁም ትምህርቷን የተከታተለችው ደግሞ ፈረንሳይ፣ፓሪስ ነው። የቋንቋ ችሎታዋ የብሪታኒያ የደህንነት ኃላፊዎችን ቀልብ ገዛ። ኖራ ከብሪታኒያ ተነስታ በናዚ ጀርመን ቁጥጥር ሥር ወደሚገኘው ፈረንሳይ በፓራሹት አማካኝነት ገብታ የናዚ ጀመርን ወታደሮችን እንቅስቃሴ በተመለከተ ለእንግሊዝ መረጃ አቀብላለች፣ አጋር የነበሩትን ፈረንሳይ እና እንግሊዝ መካከል ግንኙነት እንዲፈጠር ረድታለች። ኖራ አደገኛ የሚባለውን የሬዲዮ ኦፕሬተርነት ኃላፊነትን በብቃት ተወጥታለች። በጠላት ክልል ውስጥ ላለመያዝ በተደጋጋሚ መቀመጫዋን ትቀያይር ነበር። በመጨረሻ ግን በናዚ ጀርመን ደህንነት ኃይል ተያዘች። ኖራ ለእስር በተዳረገችበት ወቅት በተደጋጋሚ ከእስር ለማምለጥ ሙከራ አድርጋለች። • "ስለምንወዳችሁ ሠርጋችን ላይ አትምጡ" የአዲስ አበባዎቹ ሙሽሮች ለማምለጥ በሞከረች ቁጥር የሚደርስባት ስቃይ እና እስር በከፋ ሁኔታ ይባባስ ነበር። ናዚ ጀርመኖች የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ኖራ መረጃዎችን እንድታወጣ በርካታ ጥረቶችን ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ጀርመኖች 'ሜድላይን' ከሚባለው የሚስጥር ስሟ ውጪ ሕንዳዊ ስለመሆኗ እንኳ ማወቅ አልቻሉም። እ.አ.አ. መስከረም 1944 ላይ ኖራን ጨምሮ ሌሎች ሶስት ሴቶች፣ ጀርመን ወደሚገኝ ማሰቃያ ካምፕ ከተወሰዱ ከቀናት በኋላ ተረሽነዋል። ኖራ ለጀብዱ ስራዎቿ የፈረንሳይ እና ብሪታኒያ መንግሥታት ሽልማት አበርክተውላታል። እርሷን የሚዘክር ሃውልትም በለንደን ከተማ ቆሟል። ሊዩድሚል ፓቨሊቼንኮ፡ የሞት ሴት ሊዩድሚል ፓቨሊቼንኮ ባሪክ እጅግ ውጤታማ ከነበሩ አልሞ ተኳሾች መካከል አንዷ ነበረች። ናዚ ጀርመን እ.አ.አ. 1941 የተባበሩት ሶቬት ህብረትን በወረረበት ወቅት 306 ጠላቶቿን ከርቀት መትታ ጥላለች። ከእነዚህም መካከል ቀላል የማይባሉት እንደ እርሷ አልሞ ተኳሾች ነበሩ። ከአልሞ ተኳሾች ጋር የነበራት ግብግብ 'ሌዲ ዴዝ' የሞት ሴት፣ የሚል ስም አሰጥቷታል። የናዚ አልሞ ተኳሾች ሊያገኟት አልቻሉም፤ ይሁን እንጂ በሞርታር ጥይት ተመትታ በደረሰባት ጉዳት አልሞ ተኳሽ ሆና መቀጠል አልቻለችም። ይህ ግን አገሯ ከጠላት ጋር የምታደርገውን ፍልሚያ ከማገዝ አልገደባትም። • ከኮሮናቫይረስ ለማገገም ምን ያክል ጊዜ ይወስዳል? የተለያዩ ተልዕኮችን በመውሰድ በመላው ዓለም የተጓዘችው ሊዩድሚል በሥራዋ አማካኝነት ከወቅቱ ፕሬዝደንት ፍራንክሊን ሩዝቬልት ጋር ተገናኝታለች። ሊዩድሚል ለጀብድ ሥራዋ የወርቅ ኮከብ ተሸላሚ ብትሆንም ሕይወቷ ካለፈ በኋላ ከሩሲያ የታሪክ መዝገብ ላይ ስሟ እንዲሰረዝ ተደርጓል። "የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሶቬት ታሪክ ውስጥ ጀግና ተብለው በታሪክ መዝገብ ላይ የሰፈሩት ወንዶች ብቻ ናቸው። ሴቶች የዛኔ የታሪክ አካል አይደሉም" ስትል የጾታ እኩልነት ተሟጋቿ ኢራይና ስላቪስካ ለቢቢሲ ተናግራለች። ናንሲ ዌክ፡ ነጯ አይጥ የተወለደችው ኒው ዚላንድ ያደገችው ደግሞ አውስትራሊያ ነው። ናንሲ አደገኛ ተዋጊ እና አማላይ፣ ጠጪ እና ለጠላቷ ናዚ የራስ ምታት ነበረች። ናንሲ ገና የ16 ዓመት ታዳጊ ሳለች ከትውልድ አገሯ በመጥፋት ወደ ፈረንሳይ አቀናች። በዚያም የጥንታዊ ግብጽ ቋንቋ እችላለሁ ብላ በመዋሸት በአንድ የፈረንሳይ ጋዜጣ ላይ ጋዜጠኛ ሆና ተቀጠረች። ከአንድ ፈረንሳይ ዜጋ ጋር በፍቅር የወደቀችው ናንሲ በፍቅር ተጣምራ ትዳር ለመመስረት ብዙ ጊዜ አልወሰደባትም። በማርሴ ከተማ ሳለች ጀርመኖች ፈረንሳይን እ.አ.አ. 1939 ላይ ወረሩ። ናንሲ የፈረንሳይ አርበኞችን ተቀላቀለች። በተለያየ አጋጣሚ በጀርመን ጦር ተከበው የነበሩ ፈረንሳውያን ታጋዮችን እያስመለጠች ወደ ስፔን አሽሽታለች። • በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ ከብሪታኒያ በመነሳት በፓራሹት ከአውሮፕላን እዘየለለች በፈረንሳይ በርካታ ተልዕኮችን በድል ተወጥታለች። ከአንድ የጀርመን ካምፕ ጠባቂ ጋር በጨበጣ ውጊያ ድል ነስተዋለች። እስከ 500 ኪ.ሜትር ድረስ ወደ ጠላት ድንበር ዘልቃ በመግባት በማይታመኑ አጫጭር ጊዜያት ውስጥ የተለያዩ ተልዕኮችን በስኬት ተወጥታለች። ድምጽ ሳታሰማ ጠላት መንደር ገብታ በመውጣት ክህሎቷ የተነሳ "ነጯ አይጥ" የሚል ስያሜን በጀርመን ጦር አሰጥቷታል። በ98 ዓመቷ እ.አ.አ. 2011 ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ናንሲ፤ ለጀብድ ሥራዋ የተለያዩ ሽልማቶችን ተቀብላለች። ጄን ቫያል፡ ዘጋቢ፣ ሰላይ፣ ፖለቲከኛ ጄን ቫያል ትውልዷ በአፍሪካዊቷ ኮንጎ ሪፐብሊክ ቢሆንም በልጅነቷ ወደ ፈረንሳይ አቅንታለች። ጋዜጠኛ ሆና እየሰራች ሳለች ነበር ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተቀሰቀሰው። መኖሪያዋ የነበረችው ፓሪስን ጥላ በመሰደድ በደቡባዊ ፈረንሳይ ተደራጅተው የነበሩትን የፈረንሳይ ነጻነት ታጋዮችን ተቀላቀለች። ጄን የምትልካቸው መልዕክቶች በኮድ የተቆለፉ ስለነበሩ ጠላት እጅ ሲደርሱ ከተራ አህዝ እና የቃላት ድርዳራ ውጪ ትርጉም የሚሰጡ አልነበሩም። ጄን የናዚ ወታደሮችን እንቅስቃሴ እየሰለለች ለአጋር አገሮች እና ለነጻነት ታጋዮቹ ትልክ ነበር። እ.አ.አ. 1943 ላይ በጠላቶቿ እጅ ወደቀች። ከዚያም የአገር ክህደት የሚል ክስ ተመሰረተባት። በናዚ ጀመርን ከተያዘች በኋላ ወደ ማርሴ የሴቶች እስር ቤት ተልካ የጉልበት ሥራ ስትሰራ ነበር። ከእስር ቤት አምልጣ ይሆን በምህረት ተለቃ ግልፅ ባይሆንም ጄን ሁለተኛው ዓለም ጦርነት ህይወቷን አልነጠቃትም። እ.አ.አ. 1947 ላይ የፈረንሳይ ሴኔት አባል ሆና ተመርጣ ነበር። ሄዲ ላማር : የሆሊውዷ በውበቷ ገዳይ ትውልደ ኦስትሪያዋ ሄዲይ ላማር በትወና ስራዋ ዝናዋ የናኘ መልከ መልካም ሴት ነበረች። የሆሊውዷ እንቁ 6 ባሎች ነበሯት። ሄዲ የመጀመሪያ ትዳሯ ባይጥማት ከቬይና ተነስታ ወደ ፓሪስ ከዛም ወደ ለንደን አቀናች። በለንደንም ዝነኛ የነበረውን የጥበብ ሰው ሉዊስ ሜይር ጋር ተዋወቀች። በሆሊውድ መስራት እንድትችል የሚያስችላትን ኮንትራትም አስፈረማት። "የዓለማችን ውቧ ሴት" በማለት ያስተዋውቃት ጀመር። የተሳተፈችባቸው 30 ፊልሞች ዝነኛ አድርጓታል። የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀግና ያስባላት ግን የፊልም ስራዎቿ አልነበሩም። የፈጠራ ሥራዋ እንጂ። • የኮሮናቫይረስ ክትባትን በማግኘት ህንድ የዓለምን ሕዝብ ትታደግ ይሆን? የፈጠራ ሥራዋ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ እና ብሪታኒያ የጠላቶቻቸውን መርከቦች ለማጥቃት ጥቅም ላይ የሚያውሏቸው ተተኳሾች (ቶርፒዶ) ፍሪክዌንሲዎች በጠላት እንዳይጠለፉ የሚያስችል ስርዓት ነበር። ቶርፒዶዎቹ ፍሪኩዌንሲያቸውን በመቀያየር በጠላት እንዳይታፈኑ ወይም እንዳይጠለፉ አስችላለች። ምንም እንኳ ለፈጠራ ስራዋ እውቅና ባይቸራትም፤ የፈጠራዋ ግብዓት የሆኑ ሃሳቦች በብሉቱዝ እና ዋይፋይ ቴክኖሎጂዎች ላይ ተንጸባርቀዋል። ማይ ዪ: በጎራዴ እና መርዝ የማይ ዪ ትግል የጀመረው ጃፓኖች በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት በርማን ከመውረራቸው በፊት ነበር። ለአገሯ በርማ ነጻነት ድምጿን ከፍ አድርጋ ትናገር ነበር። የእንግሊዝን ቅኝ ገዢነት ተቃውማለች። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅትም በእግሯ በጠላት የተያዙ ስፍራዎችን እያቆራረጠች ጎራዴ እና መርዝ በበልቃጥ ይዛ ትጓዝ ነበር። በሕንድ ጃፓኖች ምን ያህል በበዛ ጭካኔ ሕዝቡን እያሰቃዩ እንደሆነ የሚገልፅ በራሪ ወረቀቶችን በርማዎች በሚገኙበት ስፍራ ትበትን ነበር። በፓራሹት መውረድ ስልጠና የወሰደችው ዩ ምንም እንኳ የመጀመሪያ ልጇን ከወለደች በኋላ ከትዳር አጋሯ ጋር ወደ በርማ ለመመለስ ብታቅድም፣ የመጣላትን እድል ለሌላ ተዋጊ አሳልፋ በመስጠት ጦርነቱ ካለቀ በኋላ እ.አ.አ. በጥቅምት 1945 ተመልሳለች። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ቢሆን ለነፃነት እና ከዚያም በኋላ ወታደራዊ መንግሥትን ታግላለች። ራሱና ሰይድ፡ ሴቷ አንበሳ ኢንዶኔዢያዊቷ ራሱና ሰይድ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ካሉት ጀግኖች ለየት ያለች ነበረች። በኢንዶኔዢያ የነጻነት ትግል ውስጥ ትልቅ ቦታ እንደነበራት ይነገርላታል። ለእሷ ዋነኛ ጠላቷ ወራሪው የጃፓን ኃይል ሳይሆን የደች ቀኝ ገዢዎች ነበሩ። ገና በወጣትነቷ ነበር ወደ ፖለቲካ በመግባት የራሷን ፓርቲ የመሰረተችው። ፓርቲውም የኢንዶኔዢያ ሙስሊም ማህበር የሚባል ሲሆን ኃይማኖትና ህብረ ብሄራዊነትን የሚሰብክ ነበር። • አቅመ ደካሞችን እያማለለ የሚገኘው የማፊያዎች ገንዘብ በአንድ ወቅት የቅኝ ገዢው የደች ባለስልጣናትና ወታደራዊ ኃላፊዎችን የሚወርፍ ንግግር በማድረጓ ደግሞ ብዙዎች አይረሷትም። በዚህም ሴቷ አንበሳ የሚል ስያሜ ማግኘት ትችላለች። ይህንን ንግግር ባደረገችበት ወቅት ወዲያው በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን ለ 14 ወራትም ታስራ ነበር። ጃፓኖች በጦርነቱ ተሸንፈው ከኢንዶኔዢያ ከወጡ በኋላም አገሪቱ ነጻነቷን ማግኘት አልቻለችም። የደች ቅን ገዢዎች ተመልሰው መጥተው ነበር። በዚህም ምክንያት ለአራት ዓመታት የዘለቅና ብዙ ደም ያፈሰሰ ጦርነት ተደርጓል። ታዲያ ራሱና ሰይድ በዚህ ጦርነት ላይ ቁልፍ ሚና እንደነበራት ይነገራል። በዋና ከተማዋ ጃካርታም አንድ መንገድ በእሷ ስም ተሰይሟል።
xlsum_amharic-train-249
https://www.bbc.com/amharic/54769255
የአማራ ክልል መንግሥት በድንበር አካባቢ ስላለው ግጭት ምን አለ?
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ትናንት ምሽት 4፡30 ጀምሮ በአጠቃላይ በሰሜን እዝ የመከላከያ ሠራዊት ካምፖች፣ ዴፖዎች፣ እና የተለያዩ መሰረተ ልማት ባሉባቸው አካባቢዎች ላይ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ፣ የተቀናጀ ጥቃት ማድረስ መጀመሩን በዛሬው ዕለት ለአማራ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
[ "የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ትናንት ምሽት 4፡30 ጀምሮ በአጠቃላይ በሰሜን እዝ የመከላከያ ሠራዊት ካምፖች፣ ዴፖዎች፣ እና የተለያዩ መሰረተ ልማት ባሉባቸው አካባቢዎች ላይ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ፣ የተቀናጀ ጥቃት ማድረስ መጀመሩን በዛሬው ዕለት ለአማራ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።" ]
የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል በክልሉ የሚገኘው የመከላከያ ኃይል አዛዦች እንዳይንቀሳቀስ ከማድረግ ጀምሮ አሁን ደግሞ ወደጥቃት መሸጋገሩን ተናግረዋል። ሠራዊቱ ያለውን ትጥቅ ወደ መቀማት ሄዶ እንደነበርም አቶ ተመስገን አስታውቀዋል። አቶ ተመስገን አክለውም በአማራ ክልልም ሶሮቃ እና ቅራቅር በሚባሉ አካባቢዎች የጥቃት ሙከራ ማድረጉንና በክልሉ ልዩ ኃይል መመከቱን ተናግረዋል። እንደ አቶ ተመስገን ገለጻ ከሆነ በሌሎች የክልሉ አካባቢዎችም ሊገመት የሚችል ጥቃት ያለ ሲሆን፣ የክልሉ ልዩ ኃይል አንዳንድ በትግራይ ልዩ ኃይልና ሚኒሻ አባላት ከበባ ውስጥ የነበሩ የመከላከያ አባላትንም ማዳንና ማውጣት ችሏል ብለዋል። ልዩ ኃይሉ ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ የከባድ መሳሪያዎችንም ከስፍራው በማውጣት ተመልሰው ለውጊያ እንዲዘጋጁ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የኮማንድ ፖስቱን ከመከላከያ ጋር በመሆን በቅንጅት እየመሩና እየሰሩ መሆኑን የተናገሩት አቶ ተመስገን "የአማራ ሕዝብ ስትራቴጂካዊ ጠላቱን እስካላጠፋ ድረስ በየጊዜው የሸረሪት ድር ስናፀዳ አንኖርም" ብለዋል። በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች በሕወሓት የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የሥልጠና ድጋፍ የሚደረግለት ነው በማለትም በአልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ውስጥ የኤርትራ ወታደርን አይነት ልብሶችን በመስፋትና የትግራይን ልዩ ሀይል በማልበስ ለትግራይ ህዝብ ኤርትራ ወረረችህ በማለት ህዝቡን ሊያደናግር ነው በማለት ገልፀዋል። ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይህንን ኃይል ሥርዓት የማስያዝ ስራ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በመሆን የክልሉ መንግሥት እንደሚሰራም ተናግረዋል። ሁሉም የፀጥታ ኃይል የሚሰጠውን ትዕዛዝ ተቀብሎ የሚመጣውን ጥቃት ለመከላከል ዝግጁ እንዲሆን ተናግረዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ከክልሉ መንግሥት እና ከፌደራል መንግሥቱ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ከሰራዊቱ በተለያዩ ምክንያት ወጥተው የነበሩ አባላትም የክልሉ መንግሥት ጥሪ ማቅረቡን ተናግረዋል።
xlsum_amharic-train-250
https://www.bbc.com/amharic/news-55438474
"ባለቤቴን እና ዘጠኝ ልጆቼን አጠገቤ ገደሏቸው" ከበኩጂ ነዋሪዎች አንዱ
ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ. ም. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ይፋ ተደርጓል።
[ "ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ. ም. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ይፋ ተደርጓል።" ]
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ይህንን ጥቃት "ጭፍጨፋ" መሆኑን ገልጸው "በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ" በማለት ሐዘናቸውን ገልጸዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ በጥቃቱ እጃቸው አለበት የተባሉ የክልልና የፌደራልም አመራሮች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ፤ 42 የታጠቁ ሽፍቶች እ እደተደመሰሱ፤ ስለትን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ተናግረዋል። ባለቤታቸውንና 9 ልጆቻቸውን ያጡት አርሶ አደር የ41 ዓመቱ አርሶ አደር አቶ በላይ ዋቅጅራ ነዋሪነታቸው ታጣቂዎች በድንገት ጥቃት ፈጽመው ከ120 በላይ ሰዎች በተገደሉባት የበኩጂ ቀበሌ ውስጥ ነው። በጥቃቱ በሰዓታት ውስጥ ባለቤታቸውና 9 ልጆቻቸው ተገድለዋል። አቶ በላይ "ባለቤቴ፣ 5 ሴት ልጆቼ እና 4 ወንድ ልጆቼ ናቸው የተገደሉት" ይላሉ በሐዘን በተሰበረ ድምጽ። ቤተሰቡ በእንቅልፍ ላይ እንዳለ ቤታቸው ላይ በተከፈተው ተኩስ መላው ቤተሰባቸውን ያጡት አቶ በላይ ወገባቸው ላይ በጥይት ተመትተው አሁን ቡለን ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ። "ረቡዕ ሌሊት 12 ሰዓት አካባቢ መጥተው ከበቡን። ከዚያም በር ሰብረው ገቡና ተኩስ ከፈቱብን። አስሩንም የቤተሰቤን አባላት አጠገቤ ነው የገደሏቸው" ይላሉ። ለ27 ዓመት በትዳር አብረው በመኖር አስር ልጆች ያፈሩት የባለቤታቸው ስም ኦብሴ ፉፋ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ በላይ ጥቃት ፈጻሚዎቹ "ከገደሏት በኋላ አንገቷ ላይ የነበረውን ወርቅ ወስደው ሄዱ" በማለት ገልጸዋል። አርሶ አደሩ አቶ በላይ ሐዘናቸው ከባድ ነው። በግፍ የተጨፈጨፉትን የልጆቻቸውን ስም ደጋግመው ይጠራሉ። ቢቢሲ ሲያናግራቸውም "ከትልቋ ጀምሬ የልጆቼን ስም ልዘርዝርህ. . . ሹመቴ በላይ የጀመሪያ ሴት ልጄ ናት። ከዚያ በኋላ ደራርቱ በላይ፣ ቀጥላ ሲዲቄ በላይ፣ ቀጥላ ጸሃይነሽ በላይ . . ." እያሉ ሳግ ቢተናነቃቸውም አላቋረጡም። ከእንባቸው ጋር እታገሉ "የወንዶቹ ታላቅ መገርሳ ይባላል። ቀጥሎ አያና በላይ እና ደረጄ በላይ። ኤሊያስ የመጨረሻው ልጄ ነው" እያሉ እንባቸው ገነፈለ። ብቻቸውን የቀሩት አባት ቆስለው ሆስፒታል ናቸው። በጭካኔ የተገደሉት ባለቤታቸውና ልጆቻቸውን ማን እንደሚቀብራቸው ያሳስባቸዋል። "ሰው ሁሉ ከአካባቢው ሸሽቶ ወጥቷል። ማን ይቅርበራቸው? በሸራ ተጠቅልለው ነው ያሉት" ብለዋል። የአስር ልጆች አባት የነበሩት አቶ በላይ አንዲት ልጃቸው ተርፋለች "እንደ አጋጣሚ አጎቷ ጋር ወንበራ ከተማ ሄዳ ነው የዳነችው። ከቤተሰቡ እሷ ብቻ ናት የተረፈችው።" ረቡዕ ጎህ ከመቅደዱ በፊት የተኩስ ድምጽ በአካባቢያቸው መስማታቸውን የሚገልጹት አርሶ አደሩ "ባለቤቴን በጥይት ሲመቱ እሷን እከላከላለሁ ብዬ ስሄድ እኔንም መቱኝ። ከዚያ ሮጥኩ። እኔን ፍለጋ ሲመጡ ዝም ብዬ ተኛሁ። ሳያገኙ አለፉ" ይላሉ ከጥቃቱ እንዴት እንደተረፉ ሲያስረዱ። ጥቃት አድራሾቹ ከሁኔታቸው ወታደር እንደሚመስሉና ጥይት በሻንጣ መያዛቸውን የሚናገሩት አቶ በላይ "በዓይን የምናቃቸው ሰዎች አሉበት። አንዳንዶቹን መልካቸውንም አይተን አናውቅም" ይላሉ። ከጥቃቱ ለማምለጥ የሮጡ ሰዎችን በጥይት ተኩሰው እንደገደሏቸውና ከጎረቤታቸው ከሚገኝ አንድ ቤት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን "ከጎረቤቴ አንድ ጎጃሜ ቤት 13 ሰው ታርዷል" ብለዋል። "ይሄ ይከሰታል ብለን አልጠበቅንም። መንግሥት አካባቢያችን 'ሰላም ነው'፣ 'የልማትና የእድገት ቦታ ነው'፣ 'እናንተን የሚነካ የለም፤ ሥራችሁን ሥሩ' ብለው አታለው ጨረሱን።" በጥቃቱ ከአቶ በላይ ቤተሰብ በተጨማሪ በርካታ ሰው ተገድሏል። ቤቶች ተቃትለዋል። እሳቸው እንደሚሉት "መከላከያ ገባ እንጂ አንድም ሰው አይርፍም ነበር"። "እኔ አካባቢ 80 አስክሬን ተቆጥሯል። ሜዳ ውስጥ ገና ያልተቆጠረ አስክሬንም አለ። እንዲህ አይነት ነገር አይተን አናውቅም። እኔ እንኳን የጦር መሳሪያ ጦር የለኝም። መንግሥት ሰላም ነው እያለ አታለለን። እኛ ምንም የምናወቀው ነገር የለም" ሲሉ በምሬት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለቤታቸውንና ዘጠኝ ልጆቻቸውን በግፍ የተነጠቁት አቶ በላይ ተስፋ የቆረጡ ይመስላሉ። "ከዚህ በኋላ ሰው እዚያ ይኖራል ብዬ አልገምትም። አንዳንዶች ንብረትም ሰብስበው ወጥተዋል። ሰው ተስፋ ቆርጧል። ከእንግዲህ ሰው እዚያ ሰፍሮ የሚኖር አይመስለኝም።" "መአት ነው የወረደብን" በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ የሚኖረው ሌላው የዓይን እማኝ አቶ ተስፋ [ስሙ የተቀየረ] ጥቃቱ ያልታሰበ ነው ይላል። "መአት ነው የወረደብን" ያለው ጥቃት ይሆናል ብለው ባልጠረጠሩት ሰዓት ሊነጋ ሲቃረብ መፈጸሙን ይገልጻል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ የእሱንና የሌሎችንም ቤት ከበው "የጥይት በረዶ አዘነቡብን" በማለት መትረፋቸውን ተአምር ይለዋል። "ነገር ግን ብዙዎችም ሞተዋል። ከአንድ ቤተሰብ 12 ሰው የተጨፈጨፈበት ሁሉ አለ" ሲል የነበረውን ሁኔታ ይገልጸል። ለሱና ለቤተሰቡ ይህ ጥቃት የመጀመሪያው አይደለም። ከጥቂት ሳምንታት በፊት እናትና አባቱ ለሠርግ በሚጓዙበት ወቅት ድባጤ አካባቢ በተሳፈሩበት ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አሁን ደግሞ በኩጂ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ሌሎች ዘመዶቻቸው ተገድለዋል። በሐዘናቸው ላይ ሌላ ሐዘን መጨመሩን ይናገራል። "በዚህ ጥቃት ዘመዶቼንና ጓደኞቼን አጥቻለሁ። ዓይኔ እያየ አጠገቤ እንኳን ብዙ ናቸው ተመተው የሞቱት።" በተከታታይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ቤተሰቦቹን ያጣው አቶ ተስፋ፤ ለግድያው ምክንያቱ ምን እንደሆነ ምላሽ ያላገኙለት ጉዳይ መሆኑን በማንሳት "አላጠፋን። ምንም አላደረግን። በምን እንደሆነ እንጃ። እንግዲህ ይሄ ሁሉ ነገር የሚደርስብን ምን ባደረግነው ነው?" ይላል። በሚኖርበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ጨምሮ የክልሉን ልዩ ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ይዘው ጥቃት ሲያደርሱና የሳር ቤቶችን በውስጡ ካሉ ሰዎች ጋር ሲያቃጥሉ እንደነበር ይገልጻል። "ጉልበት ያላቸውን በጥይት ሲገድሉ፤ ሌሎቹን ደግሞ ሳር ቤት ላይ በለኮሱት እሳት ጨርሰዋቸዋል" በማለት ከእንዲህ አይነቱ ጥቃት መትረፋቸውን ለቢቢሲ ተናግሯል። አቶ ተስፋ፤ በቀበሌው ከተወሰኑት በስተቀር በአካባቢው ያሉ አብዛኞቹ የሳር ቤት በእሳት መውደሙን፣ ጥቃቱም ለሊት 11 ሰዓት ጀምሮ የመከላከያ ሠራዊት እስኪደርስ መቀጠሉን ይገልጻል። "መከላከያ ብዙ ሰው ከተገደለና ቤቶች በእሳት ከወደሙ በኋላ ነው የደረሰው። እኛን የረዳን ከአዲስ ዓለምና ከአካባቢው የመጣው ሕዝብ ነው" ሲል በአቅራቢያው ያሉ ነዋሪዎች በቻሉት የተወሰኑትን እንዳተረፉ ይናገራል። ከጥቃት ፈጻሚዎቹ መካከል የሚያውቋቸው እንዲሁም የማያውቋቸው ታጣቂዎች በአንድ ላይ በቡድን በቡድን ሆነው "ግማሹ ቤት ያቃጥላል፣ ሌላው ያገኘውን በጥይትና በስለት ይገድል ነበር" ብሏል። በድርጊቱ ውስጥ የመንግሥት አካላት እጅ አለበት ብሎ እንደሚያስብ ለቢቢሲ ገልጿል። "በአካባቢው መንግሥትም አለ ብዬ አላስብም። ምንም ያላደረገ ሰው በማንነቱ ተለይቶ ሲጨፈጨፍ በጣም ያሳዝናል። ከአንድ ቤተሰብ 12 ሰው የታረደው ከጎረቤቴ ነው። ግድያው በጣም በጣም ነው የሚዘገንነው። በጣም ብዙ አስከሬን ነው የቆጠርኩት፤ ከ120 በላይ የተሰበሰበ አስከሬን ነበር። በእርግጠኝነት የማውቀው ቁጥር ግን የለም።" "አሁን ግን [ሐሙስ] አካባቢው ተረጋግቷል። የመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ ተሰማርቷል። ጭላንቆ ከሚባለው ቦታ ግን የተኩስ ድምጽ ይሰማል" ብሏል። "የሚታወቁ ሰዎችም አሉበት" ሌላው ቢቢሲ ያናገራቸው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ በቡለን ወረዳ 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ግለሰብ፤ በጥቃቱ ተገደሉ የሚባሉ ሰዎችን አስከ 150 ሊደርስ እንደሚችል ይናገራሉ። እኚህ ነዋሪ እንደሚያረጋግጡት ጥቃት ፈጻሚዎቹ በየቦታው ቤት እያቃጠሉ ሰዎችን ገድለዋል። "በኩጂ ላይ የእኔ ቤተሰብ በአጠቃላይ፤ አባትና ልጅ፣ የእኔ እህትና የአጎቶቼ ቤተሰብ እዚያው አልቀዋል። ከነልጁ እነሱን የሚያስተምራቸው መምህር አጎቴ [ስም ጠቅሰዋል] ጭምር ነው የተገደለው" ሲሉ ገልጸዋል። "ጥቃት አድራሾቹ የልዩ ኃይል ልብስ ያላቸው ናቸው። ሽፍታ ናቸው ይባል እንጂ የሚታወቁ የአካባቢው ሰዎችም አብረው አሉ" ሲሉ ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች እንደነገሯቸው የዓይን እማኙ ተናግረዋል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ "ማንንም ከማንም አይለዩም። ህጻንን በቀስት ከመምታት ጀምሮ አዋቂዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ነው የጨፈጨፉት። ሆስፒታል ያለው ነገር ከባድ ነው። ሆስፒታሉም ከአቅሙ በላይ ነው አሁን። ቁስለኛው የት እንደሚታከም ከባድ ሁኔታ ላይ ነው።" ረቡዕ ማለዳ በርካታ ሰዎች ከተገደሉበት ከበኩጂ ወጣ ብሎ በሚገኝ ዶሊ በሚባል ቦታ ረቡዕ ማታ ጥቃት ተፈጽሞ 5 ሰው መገደላቸውን ነዋሪዎችና የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል። ከተገደሉትና ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ነፍሳቸውን ለማትረፍ በአቅራቢያ ወደሚገኙ ቀበሌዎች መሸሻቸውን የሚገልጹት የዓይን እማኙ፤ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በተጨማሪ በሌሎች ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች ጥቃት ሊፈጸም ይችላል በሚል ስጋትና ጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ አመልክተዋል። በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በሚገኘው የመተከል ዞን ውስጥ በታጣቂዎች እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ወራትን አስቆጥሮ፤ አሁንም ድረስ በተለያዩ ጊዜያት በሚፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል። አሁን ያጋጠመው ጥቃት ደግሞ ከዚህ በፊት ከተፈጸሙት ጥቃቶች አንጻር እጅግ የከፋውና በርካታ ሰዎች የተገደሉበት ሲሆን፤ ነዋሪዎች በቅርበት የሚያውቋቸው ሰዎች ጥቃት በመፈጸሙ መሳተፋቸውን በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ጥቃቱን ተከትሎም ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሰባት ከፍተኛ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ የጸጥታ ኃይሎች በአካባቢው ባደረጉት አሰሳ ከ40 በላይ ታጣቂዎችን መግደላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሳውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ ስለሚፈጸሙ ጥቃቶች አስመልክተው በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ እንዳሉት "ችግሩን በተለያየ መንገድ ለመፍታት ያደረግነው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት አላመጣም" በማለት መንግሥታቸው ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት "አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ አድርጓል" በማለት ገልጸዋል። ካለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ በርካታ ሰዎች የተገደሉበት የመተከል ዞን፤ ሠላምና መረጋጋት ለማስከበር የፌደራል መንግሥት ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና የክልሉ የጸጥታ ኃይል በጋራ በሚመሩት ኮማንድ ፖስት ከሚተዳደሩ አካባቢዎች አንዱ እንዲሆን ቢደረግም ጥቃቱ ሳይገታ ቆይቷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚገኘውና ተደጋጋሚ ጥቃቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸምበት የመተከል ዞን ሰባት ወረዳዎች ያሉት ሲሆን በዋናነት የጉሙዝ፣ የሽናሻ፣ የአማራ፣ የአገው፣ የኦሮሞና የበርታ ብሔሮች የሚኖሩበት አካባቢ ነው።
xlsum_amharic-train-251
https://www.bbc.com/amharic/51225314
የጀነራሉ ጦር የመንገደኞች አውሮፕላንን ኢላማ አደርጋለሁ ሲል አስፈራራ
በጀነራል ካሊፋ ሃፍታር የሚመራው ጦር የትሪፖሊን አየር ማረፊያ የሚጠቀሙ የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ኢላማ እንደሚያደርጉ ተናገሩ።
[ "በጀነራል ካሊፋ ሃፍታር የሚመራው ጦር የትሪፖሊን አየር ማረፊያ የሚጠቀሙ የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ኢላማ እንደሚያደርጉ ተናገሩ።" ]
የጦሩ ቃል አቀባይ በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ የሚየያርፉ የጦርም ሆነ የመንገደኞች አውሮፕላኖች መትተው ከመጣላቸው በፊት የመጨረሻ ያሉትን ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። በአሁኑ ሰዓት በሊቢያ ሁለት ዋነኛ ተቀናቃኝ ኃይሎች ይገኛሉ። በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተሰጠው በጠቅላይ ሚንስትር ፋዬዝ አል-ሴራጅ የሚመራው መንግሥት እና በጀነራል ካሊፋ ሃፍታር የሚመራው አማጺ ኃይል ናቸው። በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተሰጠው መንግሥት ትሪፖሊን ተቆጣጥሮ ይገኛል። • ''ኢትዮጵያዊያንን የባሕር ላይ አደጋ መሞከሪያ ያደርጉ ነበር'' • በሊቢያ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ላይ በደረሰ ጥቃት በርካቶች ሞቱ ታዲያ ከሳምንታት በፊት በተባበሩት መንግስታት እውቅና የተሰጠውን መንግሥት ለመደገፍ ቱርክ ወታድሮቿን ወደ ሊቢያ መላኳ የጀነራል ሃፍታር ጦርን አበሳጭቷል። የጦሩ ቃል አቀባይ ቱርክ የትሪፖሊን አየር ማረፊያ የጦር ካምፕ በማድረግ ጥቃት እየሰነዘረችብን ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም 'ሚተጋ' የተባለው ከትሪፖሊ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኝ የነበረ አየር ማረፊያ ሮኬት ከተተኮሰበት በኋላ ሥራውን ለማቋረጥ ተገዷል። ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ እውቅና ባለው መንግሥት እና በአማጺያኑ መካከል በነበረ ግጭት ቢያንስ 2 ሺህ ሊቢያውያን ሕይወታቸውን አጥተዋል። 146 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ የመኖሪያ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። የጀነራል ሃፍታር ጦር ትሪፖሊን ለመቆጣጠር ክፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። የሊቢያውን የእርስ በእርስ ጦርነት እና የሌሎች አገራት ጣልቃ ገብነት አሁንም የዓለም ትኩረትን እንደሳበ ነው። ለመሆኑ ሊቢያውያን እዚህ አጣብቂኝና ውስብስ ነገር ውስጥ እንዴት ገቡ? ልክ እንደ ሶሪያ ሁሉ፤ የሊቢያውያን ሰቆቃ የጀመረው የአረብ አብዮትን ተከትሎ ነው። እ.አ.አ. 2011 ላይ በምዕራባውያኑ ኔቶ (የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት) ድጋፍ የረዥም ጊዜ የሊቢያ መሪ የነበሩት ሙዓመር ጋዳፊ ከሥልጣን ተባረሩ። አምባገነኑ ሙዓመር ጋዳፊ በሊቢያውያን ለውጥ ናፋቂ ወጣቶች መንገድ ላይ ተጎተቱ፤ አይደፈሬው ተዋረዱ፤ ከዚያም በጥይት ተመትተው ተገደሉ። በሊቢያ አዲስ ለውጥ መጣ ተባለ። ሊቢያውያን ግን አምባገነናዊ ሥርዓቱን በሕዝባዊ አብዮት ሲገረስሱት፤ ነጻነትን እና የተሻለ ሥርዓትን አልመው ነበር። የሙዓመር ጋዳፊ ሞት ግን ሊቢያውያን የተመኙትን ለውጥ ሳይሆን፤ መግቢያ መውጫ ያሳጣቸውን የእርስ በእርስ ጦርነት ነው ያስከተለው። የተባበሩት መንግሥታት በጠቅላይ ሚንስትር ሰርጀ የሚመራ መንግሥት መቀመጫውን በትሪፖሊ እንዲያደርግ አመቻቸ። ሁሉም በዚህ አልተስማማም፤ ጀነራል ሃፍታር ሥልጣን ፈለጉ። ጀነራሉ በምስራቅ ሊቢያ በሚገኙ 'ቶበሩክ' እና 'ቤንጋዚ' ከተሞች መቀመጫቸውን አድርገው የራሳቸውን ጦር አደራጁ። ተጽእኖ ፈጣሪው ጀነራል፤ የሊቢያ ብሔራዊ ጦር የተሰኘ ኃይል አቋቁመው ካለ እኔ ለሊቢያ የሚፈይድ የለም፤ እኔ እንጂ ማንም "እስላማዊ አሸባሪዎችን" አያስወግድም አሉ። ከዚያም በተመድ እውቅና ያለውን መንግሥት መውጋት ተያያዙት። ትሪፖሊን ለመቆጣጠር የጦር እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ 9 ወራት ተቆጠሩ። ከጀነራሉ ጦር በተጨማሪ በሊቢያ ''ነጻ'' አውጪ ነን የሚሉ ኃይሎች በርካቶች ናቸው። ከየመሸጉበት እየወጡ፤ አንዱ አንዱን ይወጋል። በሊቢያ ''እስላማዊ መንግሥት'' መመሠረት አለበት ብለው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችም ብዙ ናቸው። ተጽዕኖ ፈጣሪው ጀነራል ካሊፋ ሃፍታር የእጅ አዙር ጦርነት በሊቢያ የሚንቀሳቀሱት ኃይሎች የራሳቸውን ብቻ ሳይሆን የሌሎች የውጪ ሃገራት ፍላጎትን ለማሳካት ነፍጥ አንግበዋል። በቀጠናው የሚገኙ ሃገራት በተለያየ አሰላለፍ የእጅ አዙር ጦርነት ወይም የውክልና ጦርነት ያካሂዳሉ። ጀነራል ሃፍታር "እስላማዊ አሸባሪዎችን" እዋጋለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች እና ጆርዳን ጽንፈኞች ከቀጠናው መጽዳት አለባቸው በማለት አጋርነታቸውን ከጀነራሉ ጋር አድርገዋል። ጆርዳን እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ከድጋፍም አልፈው የጀነራሉን ጦር አስታጥቀዋል፤ በተመድ እውቅና ባለው መንግሥት ላይ ጥቃት ሲሰነዘር የአየር ላይ ድጋፍ ያደርጋሉ። በግጭቱ ወቅት የተገደሉት ንጹሃን ዜጎች ለሞት ያበቃቸው የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ጦር መሳሪያ ነው ሲል የተባበሩት መንግሥታት ይከሳል። ከእነዚህ ሃገራት በተጨማሪ፤ ጎረቤት ሃገር ግብጽም የጀነራሉ አጋር ነች። አል ሲሲ ለጀነራል ሃፍታር ጦር የሎጂስቲክ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ። ከአካባቢው ሃገራት በተጨማሪም ሞስኮ በሊቢያ እጇን እያስገባች እንደሆነ እየተነገረ ነው። ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት በሩሲያ መንግሥት ተከፋይ የሆኑ የሌሎች ሃገራት ወታደሮች ከጀነራሉ ጎን ሆነው እየተዋጉ ይገኛሉ። የክሬምሊን መንግሥት ግን ቀጥተኛ ተሳትፎ የለኝም ይላል። በሌላኛው በኩል ደግሞ ቱርክ የተመድ እውቅና የተሰጠውን መንግሥት ትደግፋለች። ከጥቂት ቀናት በፊትም ቱርክ ወደ ሊቢያ የትሪፖሊን መንግሥት ለመደገፍ ጦሯን ልካለች። የቱርክ መንግሥት ጦሩን ወደ ሊቢያ የላከው "የሥልጠና እና የምክር አገልግሎት" ለመስጠት ታስቦ ነው ብሏል። በሊቢያ መንግሥት ውስጥ የሚገኝ የቢቢሲ ውስጥ አዋቂ ግን በቱርክ በኩል ወደ ሊቢያ ከመጡ ወታደሮች መካከል በቱርክ የሚደገፉ የሶሪያ አማጺያን ይገኙበታል ብሏል። በመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ውስጥ ብዙውን ግዜ ተገልላ የምትገኘው ኳታር፤ በሊቢያ ጉዳይ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከቱርክ ጎን ተሰልፋለች። የምዕራባውያን ሃገራት ፍላጎቶች ሌላ የሊቢያ ጉዳይ ያገባኛል የምትለው ፈረንሳይ፤ የቱርክን አሰላለፍ ተቀላቅላለች። ፈረንሳይ የተባበሩት መንግሥታት እውቅና ያለውን መንግሥት እደግፋለሁ ትበል እንጂ ልቧ ያለው ከጀነራሉ ጦር ጋር ነው ተብሎ ይታመናል። የቀድሞ የሊቢያ ቅኝ ገዢ የሆነችው ጣሊያን፤ ፓሪስ ለጀነራሉ ጦር የምታደርገውን ድጋፍ አጥብቃ ካወገዘች በኋላ፤ ሮም ሁልጊዜም ተመድ እውቅና ለሰጠው መንግሥት ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። • በሊቢያ የተፈፀመው የጦር ወንጀል ሊሆን ይችላል ተባለ በርካታ አፍሪካውያን ስደተኞች በሊቢያ በኩል አድርገው ሜዲትራኒያን ካቋረጡ በኋላ የመጀመሪያው መዳረሻቸው ጣሊያን ነች። በዚህም ጣሊያን የስደተኞችን ፍሰት ለማስቆም በሊቢያ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አለብኝ ባይ ነች። ኃያሏ ሃገር አሜሪካም በሊቢያ በቀጥታ እጇን አስገብታለች። በደቡብ ምዕራብ ሊቢያ የሚገኙ የአይኤስ ሚሊሻዎች ላይም እርምጃ ትወስዳለች። ይህ ሁሉ ሃገር በሊቢያ ጉዳይ እጁን የሚያስገባው ለምን ይሆን? በሊቢያ የእርስ በእርስ ጦርነት እጃቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያስገቡት ሃገራት ቁጥር ከፍተኛ ነው። ለዚህም የመጀመሪያው ምክንያት ሰሜን አፍሪካዊቷ ሊቢያ ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያላት ሃገር ነች። በተፈጥሯዊ ጋዝ ገበያ ላይም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሃገር መሆን ትችላለች። ሌላኛው ምክንያት መዳረሻቸውን አውሮፓ ለማድረግ ከአፍሪካ የሚሰደዱ ወጣቶች መነሻቸውን የሚያደርጉት ከሊቢያ ነው። ሊቢያ ከ 2 ሺህ ኪ.ሜትር በላይ ከሜድትራኒያን ባህር ጋር እንደምትዋሰን እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። ከኢራቅ እና ሶሪያ ድል የተመታው ጽንፈኛው አይኤስ በሊቢያ በረሃዎች ላይ እግሩን እየከተተ መሆምኑ ተነግሯል። ይህ ለሊቢያ እና ጎረቤት አገሮች ብቻ ሳይሆን ለዓለም ደህንነት ስጋት ነው።
xlsum_amharic-train-252
https://www.bbc.com/amharic/news-46465118
በሳተላይቶች ዙርያ ማወቅ የሚገባዎ ሰባት አስደናቂ እውነታዎች
በመሬት ዙርያ የሚሾሩ ሳተላይቶች ቁጥራቸው ስንት ይደርስ ይሆን? ደግሞስ እርስ በርስ እንዴት አይጋጩም? ደግሞስ እንዴት ወደ መሬት አይፈጠፈጡም?
[ "በመሬት ዙርያ የሚሾሩ ሳተላይቶች ቁጥራቸው ስንት ይደርስ ይሆን? ደግሞስ እርስ በርስ እንዴት አይጋጩም? ደግሞስ እንዴት ወደ መሬት አይፈጠፈጡም?" ]
ከሰሞኑ በአንድ ጊዜ 64 ሳተላይቶችን የማምጠቅ ሐሳብ ተወጥኗል። ይህ የተወጠነው በደቡብ አፍሪካዊው ባለጸጋ ኢለን ማስከ አማካኝነት ሲሆን «ስፔስ ኤክስ ኤሮስፔስ» ደግሞ ኩባንያው ነው። በቅርቡ የሚመጥቀው ፋልከን 9 ሮኬት ታሪካዊ የሆነውም ለዚሁ ነው። ከአሜሪካ ምድር የሚነሳው ይህ ሮኬት በአንድ ጉዞ ብቻ 64 ሳተላይቶችን ያመጥቃል። እነዚህ በኅብረት እንዲመጥቁ የሚደረጉት 64 ሳተላይቶች ከ34 ድርጅቶችና ከ17 አገራት የተሰበሰቡ ናቸው። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? ሳተላይቶቹ የተለያየ መጠንና አገልግሎት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። ለስልክ ግንኙነቶች፣ ለኢንተርኔትና በመርከቦች ላይ የሚፈጸሙ የባሕር ላይ ወንጀሎችን ለመከታተል እንዲያገለግሉ የታሰቡም ይገኙበታል። ለመሆኑ ስንት ሳተላይቶች ሕዋ ላይ እንዳሉ ይታወቃል? ደግሞስ ማንም ተነስቶ ወደ ሕዋ ሊያመጥቃቸው ይችላል? ወይስ ፍቃድ ያሻል? ፍቃድ ካስፈለገ ፍቃድ ሰጪው ማን ነው? ሳተላይቶች እርስበርስ ሊላተሙ የሚችሉበት አጋጣሚስ ይኖር ይሆን? ለመኾኑ በመሬት ምህዋር የሚዘዋወሩ ሰው ሰራሽ ሳተላይቶች ስንት ይሆናሉ ብለው ይገምታሉ? መቶ? ሺህ? 10ሺህ? በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአውተር ስፔስ ጉዳዮች ቢሮ UNOOSA እንደተገለጸው ዛሬ ላይ ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ሳተላይቶች ይገኛሉ። ቁጥሩን በትክክል ለማስቀመጥ ያህል 4921 ሳተላይቶች ምድርን እየተሽከረከሩ ነው። ነገር ግን ሁሉም በሥራ ላይ ናቸው ማለት አይደለም። • ኬንያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው ከሥራ ውጭ የሆኑት 2600 ሲሆኑ በሕዋ ላይ እነዚህን ሳተላይቶች ጨምሮ 17ሺህ የሚጠጉ የተለያዩ ሳተላይት ያልሆኑ መሣሪያዎች ይገኛሉ ይላል በደቡብ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሕዋ ተመራማሪው ዴቪድ ባርን ሀት። እነዚህ ቁሳቁሶች በድምሩ 7600 ቶን ይመዝናሉ። ሁሉም የሚገኙት ታዲያ ከመሬት እስከ 35 ሺህ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው። 1. የሳተላይቶቹ መጠን ምን ያህል ነው? ሳተላይትን ስናስብ መጀመርያ ወደ አእምሯችን የሚመጣው እጅግ ግዙፍና እጅግ ከባድ ከሆኑ ቁሳቁሶች የተሠራ በጣም ትልቅ ቁስ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሁሉም ሳተላይቶች እንደዚያ አይደሉም። መጠናቸውም ቢሆን ይለያያል። ትንሽ የዳቦ ቅርጫት ከሚያክሉት አንስቶ የከተማ አውቶቡስ እስከሚያህሉት ድረስ አሉ። አንድ መለስተኛ የእግር ኳስ ሜዳ የሚያክሉ ሳተላይቶችም ይገኛሉ። 2. ሳተላይት አገልግሎቱ ምንድነው? ሁሉም ሳተላይቶች ወደ ምድር አጎንብሰው የመሬት አካልን ፎቶ የሚያነሱ አይደሉም። ዘርፈ ብዙ አገልግሎትን ይሰጣሉ። የኮሚኒኬሽን ሥራ አንዱ ነው። የስልክ ግንኙነትን፣ የዳታ ስርጭትን የምናገኘው በሳተላይቶች አማካኝነት ነው። የመሬት ቅኝትና ምልከታን (የጂፒኤስ ሥርዓትን ይጨምራል) የምናውቀው ሳተላይቶች ስላሉ ነው። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ የሕዋ ጥናትን እንዲሁም የፕላኔት ጥናትን የሚያካሄዱ መልከ ብዙ ሳተላይቶችም ይገኛሉ። ነገ አዲስ አበባ ይዘንብ ይሆን ወይስ ደመናማ ይሆናል ለማለት የሳተላይት ምስሎች ያስፈልጉናል። የባህር ወጀብን ሳይቀር ምስል አንስቶ የሚልከው ሳተላይት ነው። የዓለማችን ሳንባ የሚባለው አማዞን ጫካ ውስጥ ምን ያህል ምንጣሮ እየተካሄደ እንደሆነ፣ ቻይና በረሃ ውስጥ አፈናና ግድያ የሚፈጸምበት ማጎርያ እየተገነባ ይሁን አይሁን ሳተላይቶች ፍንጭ ያቀብሉናል። በቤታችን ቁጭ ብለን የምንኮመኩማቸው የቴሌቪዥን ስርጭቶችና የራዲዮ ሞገዶች የሳተላይት እገዛን የሚሹ ሊሆኑ ይችላሉ። 3. እንዴት ነው ሳተላይት በምህዋሩ መቆየት የሚችለው? ሳተላይቶች በምድር ዙርያ ሊሾሩ የሚችሉት የመሬት ስበትን ለመቋቋም በሚያስችል ፍጥነት ላይ እንዲሆኑ ስለተደረጉ ነው። አለበለዚያ ወደ መሬት ይወድቁ ነበር። ይህን ለመረዳት ትንሽ ውስብስብ ቢሆንም በቀላሉ አንድ መድፍ በከፍተኛ ጉልበት በ180 ዲግሪ ቢተኮስ መሬት ላይ ከመውደቁ በፊት በሆነ አቅጣጫ የተወሰኑ ርቀቶችን ይጓዛል። ወደ መሬት የመውደቅ ርቀቱ የሚወሰነው በሚኖረው የፍጥነት ጉልበት ነው። ሳተላይቶችም ለመሬት ስበት እጅ የማይሰጡበት ምክንያት ፍጥነታቸው ነው። 4. የሳተላይቶችን ዕድሜ ምን ያህል ነው? ሮኬቶች ሳተላይትን ጭነው ወደ ሕዋ ያመጥቁና ለሳተላይቱ ከተሰናዳለት ቦታ ያኖሩታል። የተስተካከለ ርቀቱን እስኪያገኝ ወራትን ሊወስድ ይችላል። በመጨረሻም ሳተላይቱን በምህዋሩ ላይ ይቀመጣል። ሳተላይቱ ተሸክሞት ከሄደው ሮኬት ቀስ በቀስ በሚለያይበት ወቅት የሚኖረው ፍጥነት በመሬት ዙርያ ለመቶ ዓመት መሽከርከር ያስችለዋል ይላሉ ባለሞያዎች። ዋናው ሳተላይት በሕዋ ላይ እንዲቆይ የሚያደርገው ምስጢር የመሳሳብ ፊዚክስ ሲሆን በመሬት ስበት እንዳይወድቅ የሚያግደው ብቸኛው ጉዳይ የእሽክርክሪት ፍጥነቱ ነው። ለዚያም ነው ከመሬት በቅርብ ርቀት የሚገኙት ሳተላይቶች የሚሾሩበት ፍጥነት ከመሬት ራቅ ብለው ከሚገኙት ይልቅ ፈጣን የሆነው። • በዓይነ ስውሯ የተሠራው የሚያይ ሻንጣ ሳተላይቶች የእሽክርክሪት ምህዋራቸውን መለወጥ ቢያስፈልግ እና እርስበርስም እንዳይጋጩ እንዲረዳ የየራሳቸውን ነዳጅ ተጭኖላቸዋል። ሳተላይቶች ከ5 እስከ 15 ዓመታት አገልግሎት ላይ ሊቆዩ ይችላሉ። ዕድሜያቸው ግን በሚሰጡት አገልግሎትና በሚታጠቁት የነዳጅ መጠን ይለያያል። 5. ሳተላይቶች ሊጋጩ ይችላሉ? ሊጋጩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ የሚሆን ነገር አይደለም። ምክንያቱም የሚሾሩበት መስመር ከመለያየቱም ባሻገር ሕዋ እጅግ ሰፊ አካል መሆኑ ግጭት እንዳይኖር ያደርጋል። ይህ ማለት ግን ግጭት በፍጹም አይከሰትም ማለት አይደለም። በአሁኑ ጊዜ እጅግ በርካታ ሳተላይቶችን የማምጠቅ ዕቅድ መኖሩ ሲታይ ግጭት የመከሰቱ ዕድል ዜሮ ነው ማለት አይቻልም። በየካቲት፣ 2009 አንድ የአሜሪካና አንድ የራሺያ ሳተላይቶች ተላትመው ያውቃሉ። ይህ በታሪክ የተመዘገበ የመጀመርያው የሳተላይቶች ግጭት ነው። 6. ሳተላይቶችን ማን ነው የሚቆጣጠራቸው? ሳተላይቶች በድርጅቶች ወይም በኩባንያዎች ወይም በመንግሥት አንዳንድ ጊዜም በግለሰቦች ባለቤትነት ሊያዙ ይችላሉ። በ1967 በተደረገው የአውተር ስፔስ ስምምነት መሠረት እያንዳንዱ ሳተላይት ያመጠቀ አገር የተወሰነ የመቆጣጠር ሥልጣን እንዲኖረው የተደረገው የሬዲዮ ልውውጥ መጠላለፍን ለማስቀረት ጭምር ነው። በአሜሪካ ለምሳሌ የግል ኩባንያዎች በስፔስ አገልግሎት ላይ ለመሰማራት መጀመርያ ከፌዴራል መንግሥት ፍቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል። ለኮሚኒኬሽንና ቴሌኮም ሳተላይት ግንኙነት ለማድረግ ከፌዴራል ኮሚኒኬሽን ኮሚሽን ፍቃድ መውሰድ ግድ ነው። ሳተላይትን ወደ ሕዋ ለማምጠቅ ደግሞ የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደርን ፍቃድ ማግኘት ያሻል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ የተባበሩት መነግሥታት ድርጅት የአውተር ስፔስ ጉዳዮች በእንግሊዝኛ ምህጻሩ UNOOSA የሚባለው ኃላፊ መሥሪያ ቤት ነው። በሕዋ ጉዳዮች ዙርያ ሕግ ያረቃል ይቆጣጠራል። 7. ማንም ሳተላይት ወደ ሕዋ ማምጠቅ ይችላል? አዎ! ዛሬ ማንኛውም ሰው ሳተላይትን ወደ ሕዋ ማምጠቅ የሚችለበት ደረጃ ተደርሷል። የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሳይቀሩ ሳተላይት ገንብተው በማምጠቅ ፕሮግራማቸውን ከሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት ጋር ይጋራሉ። ከመቼውም ጊዜ በላይ የንግድ ኩባንያዎች ሳተላይት የሚያመጥቁበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። ኾኖም ከፍ ያለ በጀት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ይህ የሳተላይት ኢንዱስትሪም በቢሊዮን ዶላር ይገመታል።
xlsum_amharic-train-253
https://www.bbc.com/amharic/44722155
‹‹እኛ ላይ ከደረሰው ጉዳት ይልቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የደረሰው ይበልጣል!›› የዘ-ሀበሻ ድረ-ገፅ ባለቤት
የኢትዮጵያ መንግሥት ስም እና ረቂቅ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተገዳዳሪ የዜና ተቋማት ድረ-ገጾችን የማፈን ልማድ ለዓመታት በቁርኝት ተራምደዋል፡፡ በዓመታት ውስጥ Deep Packet Inspection (DPI) በተሰኘው ልዩ ማጥለያ ዘዴ እየተጠለፉ ለጎብኝዎች ከመድረስ የታገዱ ድረ-ገፆች ብዛት ከፍተኛ ነው፡፡
[ "የኢትዮጵያ መንግሥት ስም እና ረቂቅ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተገዳዳሪ የዜና ተቋማት ድረ-ገጾችን የማፈን ልማድ ለዓመታት በቁርኝት ተራምደዋል፡፡ በዓመታት ውስጥ Deep Packet Inspection (DPI) በተሰኘው ልዩ ማጥለያ ዘዴ እየተጠለፉ ለጎብኝዎች ከመድረስ የታገዱ ድረ-ገፆች ብዛት ከፍተኛ ነው፡፡" ]
ቀዳሚ ዓመታትን ትተን ከሦስት ዓመታት በፊት በመላው ሀገሪቱ የተነሳውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ 16 የዜና ተቋማት በሀገር ውስጥ እንዳይታዩ መታፈናቸውን በወቅቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘ ተቋም አጋልጧል፡፡ በመሰል ርምጃዎቹ በመብት ተሟጋቾች ዘንድ ሲብጠለጠል የሰነበተው የኢትዮጵያ መንግሥት ‹ታሪክ ቀያሪ› ስለመሆኑ የተጠቀሰ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻዎች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይፋ እንዳደረጉት ሀገር ውስጥ እንዳይጎበኙ ታፍነው የነበሩ ከ250 በላይ ድረ-ገጾች ክልከላው ተነስቶላቸዋል፡፡ መታፈን ማንን ጎዳ? ሄኖክ ዓለማየሁ ደገፉ አሜሪካን የስደት ዘመን መጠለያ ካደረጉ ጋዜጠኞች እና አሳታሚዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት በፖለቲካ፣ መዝናኛ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ድረ-ገጽ አስተዋወቀ፡፡ መጠሪያው "ዘ-ሀበሻ" የሆነው ይሄ ድረ-ገጽ በመንግሥት እጅ ውስጥ በነበሩ የዜና ተቋማት ተመሳሳይ ዘገባ ተሰላችቶ ለነበረው ‹‹ዲያስፖራ›› እንደ አንድ የመረጃ ምንጭ ሆነ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግን "ዘ-ሀበሻ" ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይነበብ እግድ እንደተጣለበት አዘጋጆቹ አወቁ፡፡ ‹‹እኛ ላይ ከደረሰው ጉዳት ይልቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የደረሰው ይበልጣል!›› ይላል ሄኖክ፣አንባቢያን ከእገዳው ሾልከው ድረ-ገጹን ለመጎብኘት የተለያዩ መተላለፊያ ሶፍትዌሮችን ለማግኘት ለወጪ እና ለሰዓት ብክነት መዳረጋቸውን በማስታወስ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ 100 ቀናት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ፕሮጀክት መሥራች ሶሊያና ሽመልስ በሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ላይ ደረሱ የምትላቸውን ጥቃቶች በየመድረኩ ስታሰማ ባጅታለች፡፡ ለእርሷ የኢትዮጵያ መንግሥት ድረ-ገጾችን የማፈን ርምጃ የመጀመሪያ ጉዳቱ አማራጭ ሐሳቦች የሚደመጡበትን ቀዳዳ መድፈኑ ነው፡፡ "(ርምጃው) የመረጃ ፍሰቱ የተገደበ እንዲሆን፣ ሀገሪቱ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ትርክት መንግሥት በሚፈልገው አንድ መንገድ ብቻ ቅርፅ እንዲይዝ አድርጎታል፤ ዓላማውም ይሄ ነበር፡፡" በማለት የምታብራራው ሶሊያና መንግሥት ድረ-ገጾችን በመዝጋቱ፣ የሐሳብ ውድድርን በማጥፋት ሕዝቡ ሕይወት ቀያሪ መረጃዎችን የማግኘት መብቱ እንዴት እንደተነፈገ ታወሳለች፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እርምጃዎች የት ድረስ? መንግሥት ድረ-ገጾች በሀገር ቤት አንባቢያን ወይንም ተመልካቾች እንዳይታዩ ያደርግ እንደነበር በተዘዋዋሪ መንገድ ማመኑን እንደ አንድ ልዩ ነገር የምታነሳው ሶሊያና የአሁኑ ርምጃ ያለውን ዐብይ ፋይዳ ታነሳሳለች፡፡ ጦማሪ እና የመብት ተሟጋች ሶሊያና ሽመልስ የኢትዮጵያ መንግሥት በድረገጾች ላይ አድርጎት የነበረውን ክልከላ ማንሳቱ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ሕዝቡ እንደሆነ ትጠቁማለች፡፡ ሕዝቡ አንድን ርእሰ ጉዳይ በተለያየ አቅጣጫ የሚተረጉሙ የመገናኛ ብዙኃንን ካለ ገርጋሪ ለመታደም፣ የሚበጀውን ሐሳብ የመምረጥ ዕድሉን እንደሚፈጥርለት ታሰምራለች፡፡ የ"ዘ ሀበሻ" ድረ-ገጽ ባለቤት ሄኖክ አለማየሁ በበኩሉ ከእገዳው መነሳት በተጨማሪ የመንግሥት ባለሥልጣናት መቀመጫቸውን በውጭ ሀገራት ላደረጉ ድረ-ገፆች ምላሽ ያለመስጠት እና መረጃን የመንፈግ አሠራራቸውን እንዲያርሙ ይመክራል። "የመንግሥት ኃላፊዎች በራቸውን ክፍት ካደረጉ ዘገባዎቻችንን ሚዛናዊ ለማድረግ እንሞክራለን፡፡ እስከ አሁንም ሚዛናዊ አይደሉም ተብለን የምንተችባቸው ምክንያቶች ለ27ዓመታት ለነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች ደፍሮ መረጃ የሚሰጥ የመንግሥት ኃላፊ አለመኖሩ ነው፡፡" ይላል ሄኖክ፡፡ የኢትዮጵያን አንገት የሚያስደፋ የፕሬስ ነጻነት እና የጋዜጠኞች ደኅንነት ደረጃ ሲያጋልጡ ከከረሙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መካካል "ሲፒጄ" አንዱ ነው፡፡ ድርጅቱ ከሰሞኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር የተወሰዱ ርምጃዎችን በአውንታ እንደሚያይ ለቢቢሲ ተናግሯል፡፡ የድርጅቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ አንጄላ ኩዊንታል አክለው መንግሥት ከዚህ ርምጃ በተጨማሪ ሊወስዳቸው ይገባል ያሏቸውን ርምጃዎች አጋርተዋል፡፡ "በ2009 እ.ኤ.አ የወጣው የጸረ-ሽብር ሕግ ፕሬሱን ድምጽ አልባ ለማድረግ በሥራ ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ ይህ ሕግ መከለስ እንዳለበት ከዚህ በፊት በደብዳቤ አሳውቀናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራሮች በጉዳዩ ላይ እየተወያዩበት መሆኑን ተረድተናል፤ ይሄም አስደስቶናል፡፡" ያሉት የሲፔጃ ባልደረባ፣ በተመሳሳይ የሀገሪቱ የወንጀል ሕግ የተወሰኑ የስም ማጥፋትን የሚመለከቱ አንቀጾች ጋዜጠኞችን ለመጨቆን በሥራ ላይ እንደዋሉ በመግለጽ፣ "በግልጽ አንቀጾች መሻር አለባቸው፡፡" ብለዋል አንጄላ፡፡ 'ለአደጋ የተጋለጠው' የኢትዮጵያ ህትመት ሚድያ
xlsum_amharic-train-254
https://www.bbc.com/amharic/49027425
ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው?
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች የሚለውን ጨፍልቆም ቢሆን ይበይነዋል፤ የተናጥል ትርጉም ግን ፈልጎ ማግኘት አይቻልም። በመካከላቸው ስላለው ልዩነትም የተብራራ ነገርም የለም።
[ "የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች የሚለውን ጨፍልቆም ቢሆን ይበይነዋል፤ የተናጥል ትርጉም ግን ፈልጎ ማግኘት አይቻልም። በመካከላቸው ስላለው ልዩነትም የተብራራ ነገርም የለም።" ]
ለብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ የሰጠው የወል ትርጉም በአንቀጽ 39፤ 5 ተቀምጧል። "...ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባሕል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡት የሚችልሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልውና አለን ብለው የሚያምኑ...." እያለ ባሕርያቸውን ይተነትናል። ተባባሪ ፕሮፌሰር ዮናታን ተስፋዬ ፍሰሀ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ዌስተርን ኬፕ የሕግ መምህር ሲሆኑ፤ በፌደራሊዝም ጉዳዮች ላይ በተለያዩ የምርምር ሥራዎች ይሳተፋሉ። እንደ እሳቸው አባባል በሕገ መንግሥቱ ዙሪያ የተደረጉ ውይይቶችም ቢሆኑ ማነው ሕዝብ?፣ ማነው ብሔረሰብ?፣ ማነው ብሔር? ለሚለው እቅጩን መልስ አያስቀምጡም። በሕገ መንግሥቱም ቢሆን ይህ የተናጥል ትርጉም አልተቀመጠም፤ ቢሆንም ግን... ይላሉ ዮናታን (ዶ/ር) "ቢሆንም ግን ይህ አለመሆኑ ከሕገ መንግሥቱ አንፃር ብዙም ለውጥ አያመጣም።" ይህንን ሐሳብ ሲያፍታቱት፤ ብሔር ስለሆንክ ይህን ታገኛለህ፤ ብሔረሰብ ስለሆንክ ያንን ታጣለህ ብሎ የሚያስቀምጠው ነገር የለም ይላሉ። ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደህንነት ጥናት ተቋም መምህር ናቸው። ብሔር ማነው? ብሔረሰብስ? ሕዝብስ? ለሚለው መልሳቸው "የመጣው ከጆሴፍ ስታሊን ነው፤ ሶሻሊስታዊ አስተሳሰብ ነው ነው" ይላሉ። ለሳቸው ይህ አብዛኛውን ጊዜ አምባገነኖች ሕዝቡን ከፋፍሎ ለማስተዳደር የሚጠቀምበት መሣሪያ ነው። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች • "ነገ ክልል መሆናችንን እናውጃለን" የኤጀቶ አስተባባሪ ለዶ/ር ዮናስ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ብሎ ነገር ራሱ እምብዛም ስሜት የሚሰጥ ነገር አይመስልም። "ብሔርን ከፍ አድርገው፣ ብሔረሰብን መካከለኛ አድርገው ሕዝብን ዝቅተኛ አድርገው፤ አንዳንዴም አስደንጋጭ ቅጥያዎችን ሁሉ ጨማምረው ሕዳጣን፤ አናሳ ብሔረሰብ የሚሉ ስሞችም ይሰጣሉ፤ ሁሉም ግን ሕዝብን ለመከፋፈል የተደረጉ ናቸው" ይላሉ። በሕገ መንግሥቱም ላይ አንድ ብሔር፣ ብሔር ስለሆነ ይህ ይገባዋል፣ ብሔረሰብ ደግሞ ስለሆነ ያ ይገባዋል የሚል የተቀመጠ ነገር የለም የሚሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዮናታን፤ ሕገ መንግሥቱ መብትና ጥቅም ሲሰጥ በእነዚህ መካከል ምንም ልዩነት እንዳላስቀመጠ ያትታሉ። ታዲያ ልዩነት ከሌለ የክልልነት ጥያቄ ገፍቶ የሚመጣው ለምንድን ነው? የሕግ ምሁሩ ዮናታን (ዶ/ር) መልስ አላቸው፤ ክልል እንሁን የሚሉ ወገኖች ራሳቸውን ብሔር ነን ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ሕገ መንግሥቱ ክልልነት የምታገኘው ብሔር ስለሆንክ ነው፣ ወይንም ደግሞ ብሔረሰብ ስለሆንክ ክልልነት አይገባህም የሚል ነገር የለውም። የትኛውስ ነው አቃፊ? ብሔር ውስጥ ነው ብሔረሰቦች ያሉት? ሕዝቦችስ ብሔር ውስጥ ናቸው? ወይስ ብሔረሰቦች ውስጥ ናቸው? ለሚለው ጥያቄም ሕገ መንግሥቱ ልዩነት እንደሌለው ዮናታን (ዶ/ር) ይናገሩና "የሕገ መንግሥቱ ትልቁ ግርታ ያለው እዚያ ላይ ነው" ይላሉ። በርግጥ ይላሉ፣ አንዳንዶቹ የመብት ጥያቄ ሲያቀርቡ ራሳቸውን ብሔር አድርገው ይወስዳሉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ብሔረሰብ አድርገው ይወስዳሉ። በማለት እንደ ሲዳማ ያሉ ትላልቅ ማህበረሰቦች ራሳቸውን እንደ ብሔር አድርገው ነው የሚወስዱት፤ እንደ ስልጤ ያሉት ደግሞ ባለፈው መብታቸውን ሲጠይቁ እንዳስቀመጡት ራሳቸውን እንደ ብሔረሰብ አድርገው ነው የቆጠሩት ይላሉ። ታዲያ በምን መስፈርት ነው እነዚህ ወገኖች አንደኛው ራሱን ብሔር ሌላኛው ብሔረሰብ ያለው? ቢባል ግልፅ ያለ ነገር የለም ባይ ናቸው የሕግ ምሁሩ። • በሲዳማ ክልልነት ጉዳይ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የምርጫ ቦርድ ወሰነ የብሔረሰቡ ሊቃውንትም ራሳቸውን በአንደኛው ሥር ያካተቱበት መስፈርት የማህበረሱ ቁጥር ይሁን ሌላ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም። ሕገ መንግሥቱ ግን ክልል የመሆን መብትን የሚሰጠው ለሁሉም ነው ይላሉ ዶ/ር ዮናታን። ለብሔርም፣ ለብሔረሰብም፣ ለሕዝብም። ስለዚህ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ክልል ለመሆን ቁጥር መስፈርት አይደለም። ታዲያ ሕገመንግሥቱ ለማንኛውም አካል ክልል የመሆን ጥያቄን በዚህ መልክ አቅልሎ ከነበር እንዴት እስከዛሬ ድረስ ጥያቄዎች ሳይቀርቡ ቀሩ? ለዶ/ር ዩናታን እስከዛሬ አልቀረቡም ብሎ በሙሉ አፍ መናገር ከባድ ነው። ምክንያቱም የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ከበፊት ጀምሮ የነበረ ነው ይላሉ። እንደውም በማለት፤ የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ተገንጥዬ የራሴን ክልል እመሰርታለሁ ብሎ ወስኖ ጥያቄ ለፌደራል መንግሥቱም አቅርቦ ነበር። ነገር ግን የፌደራል መንግሥቱ ያስገቡትን ጥያቄ እንዲተዉት እንዳደረጋቸው ያስታውሳሉ። "ራሳቸው ያስገቡትን ጥያቄ ድጋሚ ደብዳቤ በመጻፍ ጥያቄያችንን አንስተናል። ጥያቄው በዚህ ጊዜ መቅረብ የነበረበት አልነበረም በማለት ደብዳቤ አስገብተዋል።" ስለዚህ ከዚህ በፊት ጥያቄዎቹ ይነሱ የነበረ ቢሆንም፣ ጥያቄዎቹን ለማስተናገድና ለመመለስ ግን ፍቃደኝነት አልነበረም ሲሉ የድሮና ዘንድሮን ፖለቲካዊ ድባብ ልዩነት ያብራራሉ። አሁን ለምን? ለዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) በአሁኑ ሰዓት የክልልነት ጥያቄ ከተለያዩ አቅጣጫ እየተሰማ ያለው በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት የብሔር አክራሪነት ስለገነነ ነው። የኢትዮጵያ አገረ መንግሥትም ይላሉ ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)፤ መሰረቱን በብሔር ማንነት ላይ ማድረጉ የመጨረሻው ውጤት ይህ እንዲሆን አድርጎታል። "በማንነት ላይ የተመሰረተው ፌደራሊዝም መጨረሻው ይኸው ነው። በምሥራቅ አውሮጳ የታየውም ይኸው ነው።" • ኢህአዴግን ያጣበቀው ሙጫ እየለቀቀ ይሆን? ነገሩን ከፖለቲካው ምኅዳር መስፋትና መጥበብ ጋ የሚያያይዙት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዮናታን፤ ቀደም ሲል ቡድኖቹ ጥያቄውን ለመግፋት የሚችሉበት የፖለቲካ ሁኔታ አልነበረም ይላሉ። "ፖለቲካው ከፈትፈት ብሏል። ጠንካራ የነበረው የፓርቲው ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አሁን ብዙም የለም፤ ስለዚህ እነዚህ ቡድኖች ጥያቄያቸውን ማንሳት እንደሚችሉ፣ ገፍተው ቢሄዱ የሚያስፈራራቸው፣ የሚጫናቸው ኃይል ብዙም እንደሌለ ስለሚሰማቸው በአሁኑ ሰዓት ክልል እንሁን የሚል ጥያቄ ሊበራከት ችሏል" ይላሉ። ክልል በመሆን የሚገኘው ትርፍ ምንድነው? የሚታጣውስ? "ክልልነት ለማህበረሰቡ የተሻለ ሥልጣን ይሰጣል" ይላሉ ዶ/ር ዮናታን። አብዛኛው ክልል የበጀት ድጎማ የሚያገኘው ከፌደራል መንግሥቱ ነው። ክልሎች ከፌደራል መንግሥቱ ያገኙትን ገንዘብ እነርሱ ደግሞ ለዞኖች ያከፋፍላሉ። አሁን ባለው ሁኔታ ሲዳማ ክልል ስላልሆነ በቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ አያገኝም። ክልል ሲሆን ግን ዞን ሲሆን ከሚያገኘው የተሻለና ከፌደራል መንግሥቱም በቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛል። ከበጀት ባሻገርም ራስን የማስተዳደሩን ሥልጣን የመጠቀም መብቱ ከፍ ያለ ይሆናል። የዞን ስልጣን የነበረው ወደ ክልልነት ከፍ ሲል ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣኑም አብሮ ያድጋል። ሕገ መንግሥቱ የሚሰጣቸውን ሥልጣኖች በቀጥታ የመጠቀም፣ ፍርድ ቤቶች፣ የጸጥታና የፖሊስ ተቋማትን ማቋቋም ይቻላል። ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢታደል ምንድነው ችግሩ? ዶ/ር ዮናታን ነገር ግን ክልልነት ማደል ከጀመርን ጥያቄው መቆሚያ አይኖረውም ሲሉ ፍርሀታቸውን ይገልፃሉ። ኢትዮጵያ ከሰማኒያ በላይ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያሉባት ሀገር ናት የሚሉት ምሁራኑ፤ የክልልነት ጥያቄ ላነሳው ሁሉ የፌደራል መንግሥት እያነሳ ቢሰጥ ክልል ለመሆን ኢኮኖሚያዊ ብቃት የሌላቸው ቦታዎች ክልል እንዲሆኑ ማድረግ ይሆናል ይላሉ። ይህ ደግሞ ክልል ቢሆኑ እንኳ ሙሉ በሙሉ በፌደራል መንግሥት ድጋፍ ላይ የሚንጠለጠሉ አካባቢዎችን ይፈጥራል። ስለዚህ ካሉን ከ80 በላይ ብሔረሰቦች፣ ብሔሮችና ሕዝቦች መካከል በፖለቲካ፣ በምጣኔ ሀብት፣ በሰው ኃይልም ለክልልነት ብቁ የማይሆኑ እንዳሉ ግልፅ ነው። • ኢህአዴግ ከአባል ፓርቲዎቹ መግለጫ በኋላ ወዴት ያመራል? ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ሕገ መንግሥታዊ ነው ያሉት ዶ/ር ዮናታን፤ ያ መብት ግን በተለያየ መልኩ ወደ ሥራ ሊገባ ይችላል ሲሉ ያስረዳሉ። ክልል በመሆን ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊ መብት ማረጋገጥ ይቻላል። ነገር ግን ያ ብቸኛ መንገድ አይደለም። ከክልል በታች ዝቅ ያሉ ዞንም ሆኑ ወረዳዎች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል ሲሉ ይናገራሉ። "ስለዚህ ሰማኒያ ብሔር ባለበት አገር ሁሉም ክልል ይሆናል ብሎ ማለት አስቸጋሪ ነው። ያ እንዳይሆን ግን የሚያግድ ሕጋዊ መሰረት የለም።" አሁን ባለውም ሕገ መንግሥት ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የመሆን መብት አላቸው ሲሉ ይደመድማሉ ዶ/ር ዮናታን። ሌላ የተቀመጠ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የጂኦግራፊ መስፈርት ወይንም ቅድመ ሁኔታ የለም። መብት አለ፤ ግዴታ የለም ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 47 የክልልነት ጥያቄ ለሚያነሱ መብት ይሰጣል። ይህንንም ይዘረዝራል፤ ነገር ግን የፌደራል መንግሥቱም ሆኑ፣ ክልሉ ይህንን ጥያቄ መቀበል አለባቸው ብሎ አያስቀምጥም። ስለዚህ እዚህኛው አንቀጽ ላይ መብት አለ፤ መብቱ ግን የተቀመጠው ሌሎቹ መቀበል አለባቸው ከሚል ግዴታ ጋር እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ሁለተኛ ነጥብ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ባደረጉት ንግግር ላይ የጠቀሱት የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሐሳብ ነው። በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 47፣3 መሠረት ክልሎች የክልልነት ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት እንዳገኙና ሕዝበ ውሳኔው በአብላጫ ድምፅ ከተጠናቀቀ ወዲያውኑ የፌደሬሽኑ አካል ይሆናሉ። ነገር ግን እዛው አንቀፅ ላይ 47፣1 በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ክልሎች በአጠቃላይ ይዘረዝራል። እነዚህ ክልሎች ዘጠኝ ሲሆኑ አዲስ የሚመጣ ክልል እዚህ ዝርዝር ውስጥ የግድ መግባት አለበት። እዚያ ውስጥ ለመግባት ደግሞ አንቀፁ መሻሻል ወይንም መቀየር አለበት ይላሉ የሕግ ምሁሩ። • “የመከላከያው በአደባባይ ሚዲዎችን እከሳለሁ ማለት አስፈሪ ነው” ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ ዶ/ር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸውም ሕገ መንግሥቱን ሳያሻሽሉ አዳዲስ ክልል መመስረት ያለውን ጦስ ያስረዳሉ። በቅድሚያ ሕገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጡት ዘጠኝ ክልሎች ጉዳይ መሻሻል አለበት ሲሉም ይመክራል። አዲስ የሚመጡ ክልሎች ከሌሎቹ እኩል ሆነው የፌደራል መንግሥቱን ሥልጣን እንዲካፈሉ ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ ደግሞ የሕገ መንግሥት እውቅና እንዲኖራቸው ይገባል የሚሉት ዮናታን (ዶ/ር) ያ እንዲሆን ደግሞ አንቀፅ 47፣1 መሻሻል አለበት። የሕገ መንግስት ማሻሻያ ለማድረግ ደግሞ የራሱ ሂደት አለው። ሕገ መንግሥት እንዲቀየር የክልሎቹን ሁለት ሦስተኛ ድጋፍ ማግኘት፣ የፌደሬሽን ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድምፅ መስጠትና መደገፍ አለባቸው። ስለዚህ ይህ ክልል ሙሉ በሙሉ ክልል ተብሎ ሕገ መንግሥታዊ እውቅና እንዲሰጠው ሕገ መንግሥቱ መቀየር አለበት ማለት ነው። ሕገ መንግሥቱ እንዲቀየር ደግሞ የሌሎቹ ድጋፍ ያስፈልጋል። በሁለቱ ምሁራን አመለካከት ይህ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሂደት ግምት ውስጥ ሲገባ አሁን ባለው ሁኔታ ጥያቄ ስለቀረበና ድጋፍ ስለተገኘ ብቻ ክልል መሆን ይቻላል ብሎ መደምደም አስቸጋሪ ይሆናል። የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ ሲፀድቅ የሌሎቹስ? በሕጉ መሰረት ካየን፤ የሲዳማ ዞን ማሟላት ያለበትን አሟልቶ ሕዝበ ውሳኔ (ሪፈረንደም) ተካሂዶ የሚያስፈልገው ድምፅ ቢገኝም እንኳ ሕገ መንግሥቱ እስካልተሻሻለ እና ሲዳማ አንዱ ክልል መሆኑ ሕገ መንግሥቱ ላይ እስካልሰፈረ ድረስ ክልል ነው ማለት ያስቸግራል ይላሉ ዮናታን (ዶ/ር)። ከዚያ በፊት ያለውን ሂደት ማቆም አይቻልም የሚሉት ዶ/ሩ፤ ለዚህ ነው የራሳቸውን ክልል እንዲኖራቸው በሚጠይቁት የሲዳማ ማህበረሰብ ተወካዮች መካከል፣ በፌደራል መንግስቱና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል መካከል ውይይት የሚያስፈልገው ይላሉ። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ ውይይቱ አሁን የክልልነት ጥያቄ ተነስቶ ሙሉ ድጋፍ ካገኘ በዲሞክራሲያዊ፣ መንገድ የቀረበውን እና የተገለጠውን ሀሳብ ማክበር ያስፈልጋል። ነገር ግን ሌሎች ከሲዳማ ክልል መሆን ጋር የሚያያዙ ጥያቄዎች ካሉ እነርሱን በተመለከተ፣ በተለይ ደግሞ የሌሎቹን ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ ፣ የአገሪቱን ሁኔታ ጥቅምና ጉዳት ግምት ውስጥ ያስገባ ውይይት ተደርጎ፣ ማመቻመች እና ስምምነት ላይ መድረስ አለበት ሲሉ ይመክራሉ። የሲዳማ ማህበረሰብ ተወካዮችም ከክልሉ እና ከፌደራል መንግሥቱ የሚመጡ ስጋቶችን መጋራትና ለድርድር ዝግጁና ክፍት መሆን አለባቸው ሲሉም ይመክራሉ። ከአንድ ክልል ጋር አብሮ በሚኖርበት ጊዜ የሚያገገናኝ ብዙ ነገር እንዳለ ሁሉ ሲለያዩም የሚያነጋግር ነገር ይኖራሉ በማለት ሲዳማ ውስጥ ስላሉ የሀብት ክፍፍሎች፣ ሲዳማ ውስጥ ስለሚኖሩ ሌሎች ማህበረሰቦች፣ ስለ ሲዳማ ክልል ድንበር፣ ውይይት ብቻ ሳይሆን ስምምነትም ላይ ሊደረስባቸው ይገባል ሲሉ ያስቀምጣሉ። ቀጣይ ፈተናዎች ምንድናው? የሕግ ምሁሩ ዮናታን (ዶ/ር) ክልል የመሆን ጥያቄ እና የሚሰጡ መልሶች ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎች እንዲነሱ በሩን ወለል አድርጎ እንዳይከፍተው ስጋት አላቸው። የሚነሱ ቀጣይ ጥያቄዎች ቀጣይ የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው የሚሉት ዶ/ር ዮናታን፤ እነዛን ጥያቄዎች እንዴት መፍታት ይቻላል? የሚለው መታየት አለበት ሲሉ ይመክራሉ። "የሲዳማን ጉዳይ የምንመልስበበት መንገድ የሌሎችን ጥያቄዎችን የምናስተናግድበትን መንገድ ይበይናል" በማለትም የሌሎቸንም አገራት ልምድ ማየት መልካም መሆኑን ይመክራሉ። • "ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?" "ሕንድ እንዲህ ዓይነት በርካታ ጥያቄዎች አስተናግዳ ታውቃለች። ነገር ግን ሕንድ ማዕከላዊ መንግሥቱ ነው ለጥያቄው መብት መስጠትየሚችለው" በማለት በሕንድ በዚህ መንገድ ከአንድ ክልል ብቻ ስድስት አዳዲስ ክልሎች መፈጠራቸውን በመጥቀስ ከሌሎች አገራት ልምድ መቅሰም አስፈላጊነቱን ያሰምሩበታል።
xlsum_amharic-train-255
https://www.bbc.com/amharic/49220661
በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ..
በጋ ፈረንጆቹን ያፈካቸዋል። ኮምጫጫ አውሮፓዊ ለማያውቀው መንገደኛ ሳይቀር ፈገግታ የሚመጸውትበት ጊዜ ነው። ለሀበሾችስ ቢሆን? በጋው የፌሽታ ነው። በረዶ ያቆፈነው በጓንት የተጀቦነ እጅ እንጀራ ለመጠቅለል የሚፍታታበት ወቅት ነው። ካፖርታና ጋቢ ወዲያ የሚሽቀነጠርበት ወቅት ነው። በከፊል ዕርቃን መዘነጥ የሚያስችል በቂ ንዳድ አለ።
[ "በጋ ፈረንጆቹን ያፈካቸዋል። ኮምጫጫ አውሮፓዊ ለማያውቀው መንገደኛ ሳይቀር ፈገግታ የሚመጸውትበት ጊዜ ነው። ለሀበሾችስ ቢሆን? በጋው የፌሽታ ነው። በረዶ ያቆፈነው በጓንት የተጀቦነ እጅ እንጀራ ለመጠቅለል የሚፍታታበት ወቅት ነው። ካፖርታና ጋቢ ወዲያ የሚሽቀነጠርበት ወቅት ነው። በከፊል ዕርቃን መዘነጥ የሚያስችል በቂ ንዳድ አለ።" ]
ከሁሉ በላይ ዓመታዊው የባህልና ስፖርት አውደፌሽታ አለ። ቁርጥ አለ፤ በቂቤ ያበደ ሽሮ አለ፤ ጎረድ ጎረድ አለ። ቡናው ይንከሸከሻል…እጣኑ ይንቦለቦላል…፤ የአገር ሰው ከዚህ በላይ ምን ይሻል? ይህ አገር ቤት እየኖረ እንግሊዝኛ ለሚቀናው ሰው ‹‹ሶ ዋት?›› የሚያስብል ሊሆን ይችላል። ከአገር ለራቀ ሰው ግን ትርጉሙ ራስ ዳሽን ነው። ለዚህም ነው ለዓመታዊው የሐበሾች ‹‹መካ›› በየዓመቱ በሺዎች የሚተሙት፡፡ ዘንድሮ ተረኛዋ ዙሪክ ነበረች። እጅግ አምሮባት ተኩላ ነበር እንግዶቿን የጠበቀችው። እርግጥ ነው በነዚህ መድረኮች ላይ ሀበሾቹ የሚገናኙት ለሳቅ ለጨዋታ ነው። የሚጠራሩት ለእስክስታና ፌሽታ ነው። ሆኖም ክትፎና ቁርጥ ቀማምሰው ሲጨርሱ ቡጢ ይቀማመሳሉ። መነሻው ምንም ሊሆን ይችላል። በሐበሾች መንደር ግን ጸብ ጠፍቶ አያውቅም። በዙሪክ ይህ ባይሰተዋልም በስቱትጋርት ሆኗል። •"እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ እንዴት እጅግ የተነፋፈቀ የአገር ልጅ ለያውም በሰው አገር፣ ለያውም ለሳቅ ለጨዋታ ተጠራርቶ ቡጢ እንደሚሰነዛዘር መተንተን የቻለ ሊቅ ለጊዜው አልተገኘም። ብቻ የአገር ልጆች በየዓመቱ ተሰባስበው የ‹‹ፍቅር ቡጢ››ን እንካ ቅመስ-እንቺ ቅመሽ ሲባባሉ ዓመታት አስቆጥረዋል። ለምሳሌ የዛሬ ዓመት የፌሽታው አስተናጅ ስቱትጋርት ነበረች። ቴዲ አፍሮ መጥቶ አፍሮ ተመልሷል፤ ሳይዘፍን። ንብረት ወድሟል። የአዳራሽ መስታወት እንዳልነበር ሆኗል። የጀመርን ፖሊስ ‹‹ኤሎሄ! ዘንድሮ ምን ጉድ ላ'ክብን›› ብሏል። ጸቡ ከእኛም አልፎ ወንድም ኤርትራዊያንን ያሳተፈ ነበር። የቢራ ጠርሙስ ከአንድ ኢትዮጵያዊ እጅ ተምዘግዝጎ ሌላ ኢትዮጵያ የራስ ቅል ላይ አርፏል። ሀበሾች ሲገናኙ ‹‹አብሿቸው›› ይነሳል መሰለኝ ፍቅራቸው በጸብ ካልደመቀ…። ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ዙሪክ የከተሙት ይህንኑ የጸብ ትዝታ ይዘው ነበር። ዙሪክ አላሳፈረቻቸውም። ለሰላሙ ቅድሚያ ሰጥታ አጫውታ፣ አዝናንታ አፋቅራ ሸኝታቸዋለች። በአሉታዊነቱ ስቱትጋርት እንደ ምሳሌ ተነሳ እንጂ፣ ሮም በ2012 ‹‹የፌዴሬሽኑን ገንዘብ ይዘው ተሰውረዋል›› በሚሉና ‹‹እንዲያውም አዘጋጅተን ከሰርን›› በሚሉት መሀል መራር ጸብ ነበር። ደግነቱ የሮም ጸበኞች ዘንድሮ በዙሪክ ይቅር ለእግዛብሔር ተባብለዋል። በ2014 ሙኒክ ላይም ምክንያቱ መናኛ የሆነ ዱላ መማዘዝ ነበር። ‹‹ሐበሻ ድሮም አብሮ መብላት እንጂ…አብሮ መሥራት…›› የሚል ተረት የሚያስተርቱ አጋጣሚዎች በርካታ ነበሩ። ሆኖም ይህን ሁሉ ዓመት ከጸብና መወነጃጀል መራቅ ለምን አልተቻለም? የሚለው ጥያቄ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ምላሽ አላገኘም። አንድ ሁለት ምክንያቶችን መዘርዘር ግን ይቻላል። አንዱ በየዝግጅቶቹ ውስጥ የአገር ቤቱ ፖለቲካ የሚያጠላው ጥላ ሰፊ መሆኑ ነው። ሌላው በጎ ፈቃድ እንጂ የአመራር ክህሎት በሌላቸው ሰዎች ትልቅ ድግስ መሰናዳቱ የሚፈጥረው ትርምስ ነው። ሦስተኛው ለጥቅም መንሰፍሰፍ ነው። •የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ ‹‹እንዲህ ዓይነቱን ሺህዎች የሚታደሙበት አውደ ፌሽታ ለማሰናዳት ከመቶ እስከ ሁለት መቶ ሺህ ዩሮ ፈሰስ መደረጉ አይቀርም›› ይላሉ ወጪውን የሚያውቁት። ይህንን ወጪ ለመመለስ፣ ብሎም በትርፍ ለመንበሽበሽ አድብቶ የሚጠብቀው ብዙ ነው፤ በዚህ መሀል ትርምስ ይፈጠራል። ከፍተኛ የጥቅም ግጭት ይነሳል። ‹‹ስልጡን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሰለጠነ መንገድ መነጋገር ይሳናቸዋል። በሰለጠነ መንገድ ሂሳብ ኦዲት አያስደርጉም። በሰለጠነ መንገድ ወጪና ገቢ አያሰሉም። መጨረሻው የማያምረው ለዚህ ይመስለኛል›› ይላል በዓመታት ውስጥ ባየው ነገር ተስፋ ቆርጦ ራሱን ከአዘጋጅነት ተሳትፎ ያገለለ ወጣት ለቢቢሲ። የዙሪኩ መሰናዶ ግን በሁሉም መለኪያ የተሻለና የተዋጣለት መሆኑ ለብዙዎች መልካም ስሜትን ፈጥሯል። ለሌሎች ቀጣይ አዘጋጅ ቡድኖችና ከተሞችም ምሳሌ መሆን የሚችል ነበር። ኢትዮጵያ መግባት የማይችሉ ኢትዮጵያዊያን ከደርግ ጀምሮ ከዚያም ቀደም ብሎ ከአገር የወጡ ኢትዮጵያዊያን አሉ። በአውሮፓ የሚኖሩ የድሮ የብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ብዛታቸው ለጉድ ነው። ይህ ዓመታዊ አውደ ፌሽታ ታዲያ ለአንዳንዶች የፌሽታ ያህል ፌዝ አይደለም። የምር ጉዳይ ነው። የአገር ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያን ናፍቀው ኢትዮጵያ መግባት የማይችሉ በርካታ ዜጎች ነበሩ። በፖለቲካም ይሁን በያዙት የስደተኛ ወረቀት ምክንያት። ስለዚህ ኢትዮጵያዊን ባይረግጡም ‹‹የኢትዮጵያን ኮፒ›› መርገጥ ይፈልጋሉ። በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኮፒ ደግሞ ይህ ዓመታዊ አውደ ፌሽታ ብቻ ነው። በዚህ ምክንያት ዝግጅቱን እንደዋዛ አያዩትም። በማንከሽከሻ የሚቆላ ቡና…እጅ የሚያስቆረጥም ቁርጥ…ምራቅ የሚያስውጥ ክትፎ፣ ከሸክላ የሚንቆረቆር አገርኛ ሙዚቃ…ከኢትዮጵያ ብዙ ሚሊየን ማይሎች ርቆ ለሚኖር ሰው ቀልድ አይደለም፡፡ መዝናኛ ብቻ አይደለም። አገር የመግባት ያህል ነው። ለነዚህ ኢትዮጵያዊያ የአገርን፣ የአገር ልጅን ናፍቆትም ለመወጣት ሁነኛ ሥፍራ ይኸው መድረክ የሆነውም ለዚሁ ነው። ጎረቤታሞች ቡና ሊጠራሩ ቀርቶ በማይተያዩበት፣ በሁለት ሦስት ሥራ ደፋ ቀና ካላሉ ሕይወት በማይገፋበት፣ ጥሬ ሥጋ መጉረስ ዜና በሚሆንበት አውሮፓ ኢትዮጵያዊያንን የሚያገናኘው ፌስቲቫል ከተጀመረ ዘንድሮ 17ኛ ዓመቱን ይዟል። አውሮፓ ውስጥ ኢትዮጵያውያን የሚገናኙበት ምናልባትም ብቸኛው ፌስቲቫል ነው። ለዚህም ነው ጁላይ 31 እስከ ኦገስት 2! ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን በቀን መቁጠሪያቸው ላይ በደማቅ ቀለም ያከበቡት። ቀኑ ሲደርስ ራቅ ካሉቱ እንደ ኖርዌይ እና ስዊዲን በጢያራ በረሩ። ቀረብ ካሉቱ ከጀርመን፣ ከፈረንሳይ፣ ከእንግሊዝ…በአውቶቡስ ተሳፈሩ፣ የባቡር ትኬት ቆረጡ፣ የመኪናቸውን ሞተር ቀሰቀሱ። ሆኖም ድንበር ሲደርሱ ስዊዘርላንድ ‹‹የማይደረገውን!?›› አለች። ስዊዘርላንድ ከተቀሩት የአውሮፓ አገሮች የድንበሯን ነገር በዋዛ ባለመመልከት ትታወቃለች። በቂ የጉዞ ሰነድ የላቸውም ያለቻቸውን ኢትዮጵያዊያንን ወደመጡበት መልሳቸዋለች። ከእነዚህ መካከል በዙሪክ ለመጫወት የተንቀሳቀሱት የፈረንሳዩ ኢትዮ-ማርሴይ የእግር ኳስ ቡድን እና ከኢትዮ-ፍራንክፈርት ሁለት ቡድኖች አንዱ፣ እንዲሁም የጀመርኑ ዳርምሽታት የእግር ኳስ ቡድን አባላት በከፊል ይገኙበታል። አብዛኞቹ በሚኖሩበት አገር ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ተሰጥቷቸው የዜግነት ማረጋገጫ ወረቀት የሚጠብቁ ወይም የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ወይም ጭርሱኑ ያላገኙ ናቸው። የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ አሳየኸኝ ጥላሁን ለቢቢሲ እንደተናገሩት እንግሊዝ ከ40ሺ የሚልቁ ኢትዮጵያዊያን የሚገኙባት አገር ሆኖ ነገር ግን ይህ ፌስቲቫል እንግሊዝ የማይዘጋጅበት አንዱ ምክንያት እንዲህ ዓይነቱ ችግር እንዳያጋጥምና ኢትዮጵያዊያኑ እንዳይንገላቱ በመስጋት እንደነበር ያስረዳሉ። ‹‹ይህ ዝግጅት ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ዓመታዊ የሥነ ልቦና ቴራፒ የሚያገኙበት ነው። በጉጉት የሚጠብቁት ነው፤ ከድንበር መመለሳቸው ያሳዘነን ጉዳይ ነው›› ይላሉ አቶ አሳየኸኝ። በዙሪክ የፍጻሜ ጨዋታ በሁለት ወጣት ደጋፊዎች መጠነኛ ጠብ ከመፈጠሩ ውጭ ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቋል ፌስቲቫሉ ሲጠነሰስና ዛሬ ፌስቲቫሉ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2001 ላይ ሲጀመር ከአንድ ቀን የእግር ኳስ ግጥሚያ የዘለለ አልነበረም። 2003 ላይ ግን የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማለትም ግርማ ሳህሌ፣ ዩሀንስ መሰለ፣ ከበደ ኃይሌና ሌሎችም፤ በተዋቀረ ሁኔታ የሚንቀሳቀስ ፌደሬሽን መመሥረታቸውን በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የባህልና የስፓርት ፌደሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ብስራት ይናገራል። ፌስቲቫሉ በተጀመረበት ወቅት አውሮፓ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንደዛሬው አልተበራከቱም ነበር። የእግር ኳስ ቡድኖቹ በቂ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ስለማያገኙ አውሮፓውያንን ያካትታሉ። ያኔ ፌስቲቫሉ እንደዛሬው ብዙ ኢትዮጵያውያን ታዳሚዎችም አልነበሩትም። "ከ2007 ወዲህ የሊቢያ መንገድ ሲከፈት ወጣቱ ግልብጥ ብሎ ወደ አውሮፓ መጣ። እዚያ የሚኖሩ ህጻናትም እያደጉ የእግር ኳስ ቡድኖችን መቀላቀል ጀመሩ። በጣም ጠንካራ ኳስ መጫወት የተጀመረው ከዚያ ወዲህ ነው" ይላል ዳንኤል። ባለፈው ዓመት ፌስቲቫሉ የተካሄደው በጀርመኗ ስቱትጋርት ነበር። ከዚያ በፊት ሮም፣ ጄኔቭ፣ ስቶኮልም፣ አምስተርዳምና ሌሎችም የአውሮፓ ከተሞች ፌስቲቫሉን አስተናግደዋል። አውሮፓ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ባቋቋሟቸው ቡድኖች መካከል የሚካሄድ የእግር ኳስ ግጥሚያ ፌስቲቫሉን ደማቅ ያደርገዋል። ዘንድሮ አበበ ቢቂላ፣ ሻላ እና ቡና የተባሉ የጤና ቡድኖች መቀመጫቸውን አውሮፓ ካደረጉት ቡድኖች ጋር ለመፋለም ከኢትዮጵያ ወደ ዙሪክ አቅንተዋል። በስም ከሚታወቁት የቀድሞ ተጨዋቾች መካከል ሳሙኤል ደምሴ (ኩኩሻ)፣ ስንታየሁ ጌታቸው (ቆጬ)፣ ተክሌ ብርሃኔ፣ ቴዎድሮስ ቦካንዴ፣ ሃብቶም ብርሃኔ፣ ሰይፈ ውብሸት፣ ጌታቸው ካሳ (ቡቡ)፣ ኃይሉ አድማሱ (ቻይና)፣ግርማ ሳህሌ ይጠቀሳሉ። በነዚህ ጨዋታዎች በየዓመቱ ይገኛሉ። በዘንድሮው የሦስት ቀን ፌስቲቫል ከአምስት ሺህ እስከ አስር ሺህ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ የሆነው ኢትዮ-ዙሪክ ቡድን ፕሬዘዳንት ሙሉጌታ በየነ በመክፈቻው ዕለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በፌስቲቫሉ ላይ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያን ባህል የሚወዱ የሌሎች አገሮች ዜጎችም ይገኛሉ። ኢትዮጵያዊያንን ያገቡ ዜጎች ይህ ዝግጅት ነፍሳቸው ነው። ከሰሜን አሜሪካው ፌስቲቫል ቀጥሎ ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገናኙበት ፌስቲቫል እንደመሆኑ ፍቅርና አንድነትን የሚያስተጋቡ ሙዚቀኞች መጋበዛቸውን ሙሉጌታ ይገልጻል። ዘንድሮ ጋሽ ማሕሙድና ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላን) ጨምሮ በርካታ ስመ ገናና ድምጻዊያን ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። ፌስቲቫሉና የዳያስፖራ ፖለቲካ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ራስ ምታት ከኢትዮጵያ ውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵዊያን ትኩሳት ይለቅባቸዋል።አሰላለፋቸው ያሸብራል። ልዩነታቸው የሀበሻ ሬስቶራንት ድረስ ይዘልቃል። የእንቶኔ ብሔር በቀነጠሰው በርበሬ የተሰራ ዶሮ ወጥ በአፌም አይዞር እስከማለት… በፖለቲካ አሰላለፍ ጎራ ተለይቶ መራኮት ዕለታዊ በሆነበት አውሮፓ 'አንዲት ኢትዮጵያ' በሚል ፌስቲቫል ማዘጋጀት ምን ይመስል ይሆን? የየወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታስ ፌስቲቫሉ ላይ ጥላውን አላጠላም? ብለን አቶ ዳንኤልን ጠይቀነው ነበር። "…ፖለቲካው ፌስቲቫሉን ሊያፈርስ የደረሰበት ወቅትም ነበር" ሲል መልሷል። የእግር ኳስ ቡድኖች የመንግሥት ተቃዋሚና ደጋፊ በሚል እንደሚከፋፈሉ ካስታወሰ በኋላ በተለይ በምርጫ 97 ሰሞን የተካሄደውን የእግር ኳስ ግጥሚያ ያሸነፈው ቡድን አባላት በፖለቲካ አቋም ልዩነት ምክንያት አኩርፈው ዋንጫ ሳይቀበሉ ወደ መጡበት አገር መመለሳቸውን እንደ አብነት ያነሳል። "ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት ያላቸው መገናኛ ብዙኃን ሲመጡ እንደ ፌደሬሽን የማስተናገድ ግዴታ አለብን ስንል የሚቃወሙ አካላት አሉ። ሜዳ ላይ ያለውን መንፈስ ይረብሻል። እነ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ ታማኝ በየነ፣ ተስፋዬ ገብረአብ ይመጡ ነበር። ያ አንዳንዶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊፈጥር ይችላል። ግን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የመምጣት መብት አለው። አትምጡ ልንላቸው አንችልም›› ይላል፤ ያም ሆኖ መድረኩ ከፖለቲካ የጸዳ የባህልና የስፖርት ፌስቲቫል ብቻ እንዲሆን አዘጋጆቹ ይተጋሉ። የ17ኛው በአውሮፓ የኢትዮጵያን የስፖርት እና ባህል ፌስቲቫል ሻምፒዮና- ኢትዮ ቡና ፍራንስ ፌስቲቫሉን በየዓመቱ ማን ያዘጋጀው በሚለው ላይ ሁለት ተሞክሮዎች እንዳሉ አቶ ዳንኤል ያብራራል። እንደ ሰሜን አሜሪካው ውድድር ፌዴሬሽኑ ያሰናዳው ወይስ አዘጋጅ አገር? 2017 ላይ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ፌደሬሽኑ እንዲሆን ተወስኖ ጣልያን ውስጥ ፌስቲቫሉን ለማካሄድ መሰናዶ ተጀምሮ ነበር። ሆኖም የፌደሬሽኑ አመራሮች ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ እሰጣ ገባ መፈጠሩን ይናገራል። ከዚህ የሮሙ ክስተት በኋላ ፌስቲቫሉ በየዓመቱ በተለያዩ የእግር ኳስ ቡድኖች እንዲዘጋጅ ውሳኔ ተላለፈ። በዚህም መሠረት የዘንድሮውን ፌስቲቫል ያዘጋጀው ኢትዮ-ዙሪክ ቡድን ነው። የኢትዮ ዙሪክ ቡድኑ ፕሬዝዳንት ሙሉጌታ፤ ፖለቲካው ለጊዜው እንዲቆይ ይማጸናል። ወደ ፌስቲቫሉ የሚሄዱ ሰዎች "ፖለቲካን ማሰብ የለባቸውም። እንዲያውም እዚያ ሜዳ ላይ ፌስቡክን አጥፍቶ፤ ሰላም ተባብሎ መጫወት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መሳቅን ነው ማየት የምንፈልገው" ሲል በበዓሉ መክፈቻ ዕለት ለቢቢሲ ምኞቹን አጋርቷል። አማርኛ የሚኮላተፉ ሕጻናት በአውሮፓ የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል አውሮፓ ውስጥ የተወለዱ የኢትዮጵያ ልጆች እነሱን ከሚመስሉ ልጆች ጋር የሚገናኙበትም መድረክ ነው። ብዙዎቹ ታዲያ በግማሽ ኢትዮጵያዊ ካልሆኑ ወላጆች የተገኙ ናቸው። በተለይ ኢትዮጵያን ረግጠው የማያውቁ የኢትዮጵያዊያን ልጆች በእናት በአባታቸው ቋንቋ እየተኮላተፉ ሲያወሩ መስማት አንዳች ልዩ ስሜት ያጭራል። በየዓመቱ የሚጋበዙት ኢትዮጵያዊያን ሙዚቀኞች ታዳጊዎቹን ከአገሪቱ ባህል ጋር በመጠኑም ቢሆን ያስተዋውቋቸዋል። ‹‹ፌስቲቫሉ የአዋቂዎች ብቻ መሆን የለበትም፤ ለነዚህ ሕጻናት በቂ ትኩረት መሰጠት አለበት›› ይላል ለዚሁ መሰናዶ ዙሪክ የሚገኘው ጋሽ አበራ ሞላ። የእግር ኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊዎች ዕድለኛ ከሆኑ ለተለያዩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖችና ክለቦች ሊታጩ የሚችሉትም በዚሁ ፌስቲቫል ላይ ነው። በደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድናችን ላይ የተሰለፈው ዩሱፍ ሳሊህ ከዚሁ መድረክ የተገኘ ነው። ፌስቲቫሉን ለመታደም በዙሪክ፣ ክሎተን ስቴድየም ከተገኙ ኢትዮጵያዊያን አንዷ የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ቅድስት በላይ ናት። በልጆች ክፍለ ጊዜ መርሀ ግብር የምትታወቀው ቅድስት የምትኖረው ስዊዘርላንድ ሲሆን፤ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል ላይ ስትሳተፍ የዘንድሮው የመጀመሪያዋ ነው። ፌስቲቫሉ፤ አውሮፓ ውስጥ ተወልደው በምዕራባውያን ባህል የሚያድጉ ልጆች ስለ ኢትዮጵያ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ትናገራለች። "ስብስቡ ማኅበራዊ ትስስሩን ያጠነክራል። ልጆችም በጣም ደስተኛ ይሆናሉ። ለምሳሌ የጓደኛዬ ቤተሰቦች ከኖርዌይ መጥተው ከሌሎች ልጆች ጋር ስለ ስዊዝና ኖርዌይ ባህል ሲያወሩ ነበር።" ኢትዮጵያዊያን በብዛት በሌሉበት አካባቢ ለሚኖሩ ልጆች፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በሚውለበለብበት፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በሚነገሩበት፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች በሚበሉበት ቦታ መገኘትን የሚተካ ነገር እንደሌለም ቅድስት ታስረዳለች። ትናንት ምሽት የትዝታው ንጉስ ማህሙድ አሕመድን ጨምሮ ታዋቂ ድምጻውያን ሊያዜሙበት የነበረው ኮንሰርት በርካታ ኢትዮጵያውያን በትኬት ሽያጭ የቅንጅት ጉድለት የተንገላቱበት ነበር ፌስቲቫሉን ማን ያስቀጥለው? አውሮፓ በሮቿን ለስደተኞች ባትዘጋም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሽንቁሩ እየጠበበ ይመስላል። ምናልባትም ለወደፊት ወደ አውሮፓ የሚሄዱ ኢትዮጵዊያን ቁጥር ያሽቆለቁል ይሆናል። ይህ መላ ምት፤ አሁን በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የጀመሩትን ፌስቲቫል ለወደፊት የሚረከባቸው ይኖራልን? የሚል ጥያቄ ማጫሩ አይቀርም። ከኢትዮጵያዊያን እና ከሌሎች አገሮች ዜጎች የሚወለዱ ህጻናት እየተበራከቱ መጥተዋል። እነዚህ በከፊል ብቻ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ልጆች ከኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ጋር የሚያስተሳስራቸው ፌስቲቫል አስፈላጊነት የሚታያቸው እስከ መቼ ነው? ሌላው ጥያቄ ነው። ዳንኤል የፌስቲቫሉ ቀጣይነት አያጠራጥርም ይላል። አንድም "በቀጣይ ለሚመጣው ትውልድ ብቸኛ መገናኛው ይህ ፌስቲቫል ነው" ሲል ያስረዳል። በልጅነታቸው ወደ አውሮፓ ቢሄዱም የእግር ኳስ ፌደሬሽኑን ለዓመታት ያገለገሉ ወጣቶች መኖራቸውም ተስፋ ይሰጠዋል። ዳንኤል፤ አውሮፓ ተወልደው ያደጉ ልጆች በፌስቲቫሉ ድምቀት በመማረክ ከዓመት ዓመት ቀጠሮ ሲይዙ አስተውሏል። ለነጭ ጓደኞቻቸው 'የኢትዮጵያ ፌስቲቫል ሄጄ ነበር' ብለው በኩራት እንደሚያወሩም ሰምቷል። እነዚህ ልጆች አሁን ያለውን ሥርዓት እንዲረከቡ ከተደረገ የፌስቲቫሉ ዕድሜ እንደሚረዝም ያምናል።የቡናው መዓዛ ሳይጠፋ…እስክስታው ሳይለዝዝ፣ ቁርጡ ሳይወደር፣ ሙዚቃው ሳይጎትት የዛሬ ዐሥር፣ ሀያ፣ ሠላሳ ዓመት ኢትዮጵያዊያኑ ይገናኙ ይሆን? ከብዙ ፍቅርና ከትንሽ ቡጢ ጋ'ም ቢሆን…
xlsum_amharic-train-256
https://www.bbc.com/amharic/51867056
ኬንያ በኮሮናቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች
ኬንያ የመጀመሪያውን በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች። የኬንያው ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሙታይ ካግዌ እንደገለፁት በኮሮና ቫይረስ መያዟ የተረጋገጠው ሴት ከሳምንት በፊት ከአሜሪካ ወደ ኬንያ የመጣች ነች።
[ "ኬንያ የመጀመሪያውን በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች። የኬንያው ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሙታይ ካግዌ እንደገለፁት በኮሮና ቫይረስ መያዟ የተረጋገጠው ሴት ከሳምንት በፊት ከአሜሪካ ወደ ኬንያ የመጣች ነች።" ]
ግለሰቧ ከአሜሪካ ወደ ኬንያ የመጡት በለንደን አድርገው ሲሆን መጀመሪያ ኬንያ ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ ምርመራ ተደርጎላቸው ነበር። • በየደቂቃው በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ • • ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ከወንዶች ያነሰ ክፍያ ይገባቸዋል-አሜሪካ • ኬኒያ ሕገወጥ የደም አዘዋዋሪዎች ላይ ምርመራ ጀመረች ሚኒስትሩ እንደገለፁት በወቅቱ የተገኘባቸው ነገር ያልነበረ ቢሆንም አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በሚገኝ የለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ተደርጎ ከቀናት በኋላ በትናንትናው እለት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል። ሚኒስትሩ እንዳሉት ህመምተኛዋ ያሉበት ሁኔታ ደህና የሚባል ሲሆን ምግብም ይበላሉ፤ ትኩሳታቸውም እየወረደ ነው ብለዋል። በሽተኛዋ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው በኬንያ ብሄራዊ የኢንፈሉዬንዛ ላብራቶሪ እስኪረጋገጥ ድረስም በለይቶ ማከሚያው ተገልለው እንደሚቆዩ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። የኬንያ መንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት ሲሪስ ኦጉና በትናንትናው ዕለት እንዳስታወቁት የመንግሥት ሰራተኞች ወደ ውጭ አገራት ጉዞ እንዳያደርጉ እገዳ ተላልፏል። ሚስተር ኦጉና አክለውም ቫይረሱ ከተገኘባቸው አገራት ሚመጡ ኬነንያውያን ራሳቸውን ለተወሰነ ጊዜ ከማንኛውም ንክኪ አግልለው እንዲቀመጡ መክረዋል።
xlsum_amharic-train-257
https://www.bbc.com/amharic/47810950
ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ የተከሰከሰበት ምክንያት ቅድመ-ሪፖርት ዛሬ ይወጣል
ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ከተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰከሰውና የሁሉንም ተሳፋሪዎች ህይወት የቀጠፈው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ሞዴል አውሮፕላን የተከሰከሰበት ምክንያት ቅድመ-ሪፖርት ዛሬ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።
[ "ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ከተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰከሰውና የሁሉንም ተሳፋሪዎች ህይወት የቀጠፈው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ሞዴል አውሮፕላን የተከሰከሰበት ምክንያት ቅድመ-ሪፖርት ዛሬ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።" ]
በአደጋው ህይወታቸውን ከጡት መካከል በትራንስፖርት ሚንስትር የኮሚኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሴ ይሄይስ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ዛሬ የአደጋውን ምክንያት ሲያጣራ የነበረው ቡድን ቅድመ-ሪፖርቱን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ያቀርባል። • አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 የገጠመው ምን ነበር ? • "የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ • "በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል" እናት የትራንስፖርት ሚንስቴር ትናንት አመሻሽ ላይ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት አደጋው ከደረሰበት በመጀመሪያዎቹ 30 ቀናት ውስጥ ቅድመ ሪፖርት እንዲቀርብ በሚጠይቀው መሠረት ቅድመ ሪፖርቱ ዛሬ ይፋ ይሆናል። ዛሬ ከረፋዱ 4፡30 ጀምሮ የትራንስፖርት ሚንስትር የሚያቀርበውን ቅድመ-ሪፖርት እንዲሁም ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚወጡ መረጃዎችን በቀጥታ ወደ እናንተ እናደርሳለን።
xlsum_amharic-train-258
https://www.bbc.com/amharic/news-48774190
የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ
ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ተፈፀመ በተባለው 'መፈንቅለ መንግሥት' የተገደሉት የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የአስክሬን ሽኝት ሥነ ስርዓት በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተደርጎላቸዋል።
[ "ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ተፈፀመ በተባለው 'መፈንቅለ መንግሥት' የተገደሉት የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የአስክሬን ሽኝት ሥነ ስርዓት በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተደርጎላቸዋል።" ]
ሥርዓተ ቀብራቸውም በበባህር ዳር አባይ ማዶ ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመድ፣ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች በተገኙበት ተፈፅሟል። • ዶ/ር አምባቸው በሚያውቋቸው አንደበት • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን ለክብራቸው ሲባልም በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው 17 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል። በአስክሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንንና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልልና የፌደራል ባለሥልጣናት ተገኝተዋል። በሥነ ሥርዓቱ የሱዳንና የኤርትራ የልዑክ ቡድን አባላትም መገኘታቸው ተገልጿል። ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የአዴፓ ሊቀመንበር ደመቀ መኮንን ከእምባ ሳጋቸው ጋር እየተጋሉ ንግግር አድርገዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግራቸውን የጀመሩት "በሰኔ ወር አጋማሽ ለሥራ ወደ ውጭ አገር ከመድረሴ በመጀመሪያ የተቀበልኩት የስልክ ጥሪ ለማመን የሚከብድ፤ ሰውነትን በድንጋጤ የሚያርድ፤ ልብን የሚሰብር መጥፎ መልዕክት የያዘ ነበር" በማለት ነበር። ለሥራ ወደ ውጭ አገር ከመሄዳቸው ከሰዓታት በፊት ከሦስቱም አመራሮች ጋር በተከታታይ ደውለው በውጭ ቆይታቸው ስለሚሰሯቸው ጉዳዮችና ምክር ሃሳቦቻቸውን አውርተው እንደነበር አስታውሰዋል። "ልጅነታቸውን ሳይጨርሱ ለህዝብ አገልግሎት ራሳቸውን የሰጡ፤ ለለውጡ ዋጋ ከፍለው፤ ለመጭው ዘመን ብርቱ ክንድ ሆነው በተሰለፉ፤ እንዲህ ዓይነት መርዶ እጅግ ልብ ሚነካ ነው" ሲሉ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልፀዋል። ክስተቱ ከሥልጣን ጋር በተያያዘ የነበረውን መጠፋፋት ወደኋላ የመለሰ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ከስሜታዊነት፣ ከጀብደኝነት፣ ከግለኝነት በፀዳ መልኩ መስራት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል። በባህርዳርና በክልሉ ሌላ የባሰ ችግር እንዳይከሰት የክልሉ ህዝብ፣ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ባለሥልጣናት ያደረጉትን አስተዋፅኦ አመስግነዋል። በአገርና በክልል የተያዘውን የለውጥ አጀንዳ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተሰውትን አመራሮች ሕልምና ትግልም ለማስቀጠል ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። በመጨረሻም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ " እነዚህ አመራሮች ለቤተሰቦቻቸው በቂ ጊዜ ሳይሰጡ ለህዝብ ሲሉ ተሰውተዋል፤ በመሆኑም የእነርሱ ልጆችና ቤተሰቦች ሊጨልምባቸው አይገባም፤ መንግሥት ከእነርሱ ጎን ይቆማል" ሲሉም ተደምጠዋል። "የሥራ ባልደረቦቹን 'ወንድም ዓለም' እያለ ነበር የሚጠራቸው" መዓዛ አምባቸው በአስክሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሦስቱ አመራሮች ልጆች ስለ አባቶቻቸው ንግግር አድርገዋል። የዶክተር አምባቸው ልጅ መዓዛ አምባቸው "አባቴ የዋህና ቅን አሳቢ፤ ሰው ሲጣራ ወንድም ዓለም እያለ ነው የሚጠራቸው፣ መከፋፈል አያውቅ፣ ሁሉንም በአንድ የሚያይ፤ የሚፈራው እግዚያብሔርን ብቻ ነው፤ ደሙ ውስጥ ያለው ኢትዮጵያ ብቻ ነው" ብላለች። • ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ "ደሙን ብታዩት ኢትዮጵያ ብቻ ናት፤ ኢትዮጵያን ነው ያፈሰሷት። እኛ ውስጥ ያለውን የሞቀውንና የደመቀውን ቤትህን ትተህ አትሂድ፤ ተው ይቅርብህ ስንለው ለህዝቤ ልኑር፤ አገሬን እስከ እድሜ ልኬ አገለግላለሁ ብሎ ነው... ጥይት በግንባሬ እንዳለ ይሄው አሁን ልንቀብረው ነው" ስትል በለቅሶ ለአባቷ ያላትን ስሜት ተናግራለች። የአቶ እዘዝ ዋሴ ልጅ ፍቅሬ እዘዝም "ለእነርሱ ይሄ አይገባም ነበር፤ አንድ ቀን እንደ ልጅ ሳያጫውቱን ነው ያለፉት፤ ሙሉ ጊዜያቸውን ለድርጅታቸውና ለአገራቸው ሲሰሩ ነው ያለፉት፤ ጀግና ናቸው፤ እንደሞቱ አንቆጥረውም" ሲል ስለአባቱ የሥራ ባልደረቦች ምስክርነቱን ሰጥቷል። "አባቴ ለእኔ መስተዋቴ ነው። የእኔ ብቻ አይደለም የሁሉም ኢትዮጵያ ነው" ስትል የተናገረችው ደግሞ የአቶ ምግባሩ ከበደ ልጅ ሥነ ምግባሩ ናት። እርሷም እንዲሁ በለቅሶ ነበር ስሜቷን የገለፀችው። ዶ/ር አምባቸው መኮንን ደቡብ ጎንደር ጋይንት ያደጉት ዶ/ር አምባቸው መኮነን ሲሳይ የ48 ዓመት ጎልማሳ ነበሩ። በልጅነታቸው የፊዚክስና የሒሳብ ትምህርቶችን አብልጠው ይወዱ እንደነበር የሚነገርላቸው ዶ/ር አምባቸው ሕልማቸው መምህር መሆን ነበር። የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወቅቱ በነበረው ጦርነት ምክንያት ለማቋረጥ ተገደዋል። ከዚያም ትግሉን ከተቀላቀሉ ከ5 ዓመታት በኋላ ያቋረጡትን ትምህርት በርቀት አጠናቀዋል። የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ነው። የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን ደግሞ ደቡብ ኮሪያ በሚገኘው ኬዲአይ የፐብሊክ ፖሊሲና አስተዳደር ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። በቅድመ ምረቃም ሆነ በድኅረ ምረቃ ያጠኑት የትምህርት ዘርፍ ምጣኔ ሐብትን ነው። ከኮሪያ ተመልሰው ለ11 ዓመታት በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ካገለገሉ በኋላ ለሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ወደ እንግሊዝ አቅንተዋል። ሦስተኛ ዲግሪያቸውንም እንዲሁ በምጣኔ ሐብት ዙርያ ከእንግሊዙ ኬንት ዩኒቨርስቲ ነው ያገኙት። በበጀት እጥረት ምክንያት ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ለማቋረጥ ጫና እንደነበረባቸው፤ ጓደኞቻቸው ገንዘብ በማዋጣት ጭምር ያግዟቸው እንደነበር ከዚህ ቀደም ካፒታል ለተሰኘው ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ዶ/ር አምባቸው ከትጥቅ ትግሉ በኋላ ከወረዳ ጀምሮ አስተዳደራዊ አገልግሎት ሰጥተዋል። በዋናነት ከሚጠቀሱት መካከል በአማራ ክልል የሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር፣ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊነቶች ይገኙባቸዋል። በፌዴራል ደረጃ ደግሞ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚንስትር ኾነው ለአንድ ዓመት ያህል አገልግለዋል። ከዚያ በኋላም የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር በመሆን ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል ጊዜ ሰርተዋል። • “የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ነበር” ከግንቦት 2010 ዓ.ም ጀምሮ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ለአጭር ጊዜ ያገለገሉ ሲሆን፣ ከሕዳር 2011 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው እስከ ተሾሙበት የካቲት 29/2011 ዓ.ም ድረስም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የመሠረተ ልማት አማካሪ ሚንስትር ኾነው አገልግለዋል። ዶ/ር አምባቸው ከለውጡ በኋላ ለርዕሰ ብሔርነት ታጭተው እንደነበርና ሕዝቡም ሆነ ፓርቲያቸው በፖለቲካው ተሳትፏቸው እንዲቀጥሉ በመፈለጋቸው ሐሳባቸውን መቀየራቸው ሲነገር ነበር። አቶ ምግባሩ ከበደ አቶ ምግባሩ ከበደ በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ በ1966 ዓ.ም የተወለዱ ሲሆን ሥራ የጀመሩት የወረዳና ዞን ዐቃቢ ሕግ በመሆን ነበር። የምስራቅ ጎጃም ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ፣ የደብረ ማርቆስ ከንቲባ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ፣ የአዴፓ የገጠር ፖለቲካና አደረጃጃት አማካሪ፣ የአደፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደረጃ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ኃላፊ በመሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ አገልግለዋል። አቶ ምግባሩ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ተፈፀመ በተባለው መፈንቅለ መንግሥት ጥቃት ደርሶባቸው ጉዳት ካጋጠማቸው በኋላ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሰኔ 17/2011 ዓ.ም ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። አቶ እዘዝ ዋሴ አቶ እዘዝ ዋሴ በ1957 ዓ.ም በደቡብ ጎንደር አስቴ ወረዳ ዲስጎ አበርጎት አካባቢ ተወለዱ። አቶ እዘዝ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሥራ አመራር፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል። በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ የአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድሩ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ በመሆን ሲያገልግሉ ነበር።
xlsum_amharic-train-259
https://www.bbc.com/amharic/news-46017609
ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን?
በቅኝ ግዛት ወቅት በምዕራባዊያን ሃገራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ቅርሶች ከአፍሪካ ተዘርፈዋል። ናይጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 2021 ሙዚየም ለመገንባት ማቀዷን ተከትሎ በጣም አስገራሚ በሆነ ሁኔታ የአውሮፓ ታላላቅ ሙዚየሞች ዋና ዋና ቅርሶችን በውሰት ሊሰጧት ተስማምተዋል።
[ "በቅኝ ግዛት ወቅት በምዕራባዊያን ሃገራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ቅርሶች ከአፍሪካ ተዘርፈዋል። ናይጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 2021 ሙዚየም ለመገንባት ማቀዷን ተከትሎ በጣም አስገራሚ በሆነ ሁኔታ የአውሮፓ ታላላቅ ሙዚየሞች ዋና ዋና ቅርሶችን በውሰት ሊሰጧት ተስማምተዋል። \n\n" ]
ስለተዘረፉ የአፍሪካ ቅርሶች ምን ያውቃሉ? ጥያቄ 1/6 ሮሴታ ስቶን የግብጽን ጥንታዊ ጽሁፍ ለመረዳት ዋነኛ ቁልፍ ነው። በብሪታኒያ ሙዚየም ውስጥ የሚገኘውን 750 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን ዝርግ ድንጋይ በ1799 ያገኘው ማነው? ጥያቄ 1/6 በስፋት ተቀባይነት ያገኘው ታሪክ የፈረንሳይ ወታደሮች በአባይ ወንዝ ዳርቻ ምሽግ ሲቆፍሩ ድንጋዩን እንዳገኙ የሚያወሳው ነው። ጥያቄ 2/6 በ1868 የብሪታኒያ ወታደሮች ከመቅደላ ውጊያ በኋላ ከኢትዮጵያ ቅርሶችን ዘርፈዋል። ቅርሶቹን ለመውሰድ ስንት ዝሆኖችን ተጠቀሙ? ጥያቄ 2/6 ከመቅደላ የተዘረፉትን ቅርሶች ለማጓጓዝ 15 ዝሆኖችና 200 በቅሎዎችን ተጠቅመዋል። የሃይኖት መጻህፍት፣ የወርቅ ዘውድና ጽዋዎች ተዘርፈዋል። ጥያቄ 3/6 ሰው በላዎቹ ፃቮ የሚባሉት እነማን ናቸው? ጥያቄ 3/6 በ1899 በብሪታኒያ ወታደሮች ከመገደላቸው በፊት ከሞምባሳ እስከ ቪክቶሪያ ሃይቅ የሚደርሰው የባቡር መስመር በሚገነባበት ጊዜ ፃቮ በሚባል ቦታ 140 ሰራተኞችን የበሉ ሁለት አንበሶች ናቸው። ጥያቄ 4/6 ከድንጋይ የተቀረጸችው የዚምባብዌ ወፍ የሃገሪቱ መለያ አርማ ናት። ቅርሶቹ በቅኝ ገዢዎች ከተዘረፉ በኋላ ከስምንቱ ጥንታዊ የድንጋይ ቅርጾች ስንቶቹ ወደ ዚምባብዌ ተመለሱ? ጥያቄ 4/6 ሰባቱ የድንጋይ ቅርጾች ዚምባብዌ ውስጥ ይገኛሉ። ከ15 ዓመታት በፊት ጀርመን በእጇ ያሉትን የመለሰች ሲሆን ስምንት የሚሆኑት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ውስጥ ይገኛሉ። ጥያቄ 5/6 የባንግዋ ንግሥት በመባል የምትታወቀው የእንጨት ቅርጽ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ከካሜሩን የተወሰደች ናት። ሃገሬው የሴት ገጽ ያላትን ቅርጽ "ጁዊንዴም" ይላታል። ስያሜው ምን ማለት ነው? ጥያቄ 5/6 በባንግዋ ህዝብ ቋንቋ "ጁዊንዴም" "የእግዜር ሴት" ማለት ነው። ይህ ቅርስ በ1899 እንዴት ጀርመናዊው የቅኝ ግዛት መልዕክተኛ እጅ ውስጥ እንደገባ እስካሁን አልታወቀም። ጥያቄ 6/6 የቤኒን የነሃስ ቅርሶች ከምንድን ነው የተሰሩት? ጥያቄ 6/6 በ1897 በብሪታኒያ ወታደሮች የተዘረፉት የቤኒን ብሮንዝ የተሰሩት ከብራስ ነው። ብዙዎቹ በእንግሊዝ፣ ጀርመንና አሜሪካ ውስጥ ይገኛሉ። ያገኙትን ውጤት ለሌሎች ያሳውቁ ያዘጋጁት፡ ዊሊያም ሙሊ፣ ሚልሰንት ዋቺራ፣ ጆርጅ ዋፉላ፣ አሽሊ ሊም፣ ሁጎ ዊሊያምስና ሙቶኒ ሙቺራ ስለተዘረፉ የአፍሪካ ቅርሶች ምን ያውቃሉ? ጥያቄ 1/6 ሃገር: ግብጽ ሮሴታ ስቶን የግብጽን ጥንታዊ ጽሁፍ ለመረዳት ዋነኛ ቁልፍ ነው። በብሪታኒያ ሙዚየም ውስጥ የሚገኘውን 750 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን ዝርግ ድንጋይ በ1799 ያገኘው ማነው? ትክክለኛ መልስ በስፋት ተቀባይነት ያገኘው ታሪክ የፈረንሳይ ወታደሮች በአባይ ወንዝ ዳርቻ ምሽግ ሲቆፍሩ ድንጋዩን እንዳገኙ የሚያወሳው ነው። ጥያቄ 2/6 ሃገር: ኢትዮጵያ በ1868 የብሪታኒያ ወታደሮች ከመቅደላ ውጊያ በኋላ ከኢትዮጵያ ቅርሶችን ዘርፈዋል። ቅርሶቹን ለመውሰድ ስንት ዝሆኖችን ተጠቀሙ? ትክክለኛ መልስ ከመቅደላ የተዘረፉትን ቅርሶች ለማጓጓዝ 15 ዝሆኖችና 200 በቅሎዎችን ተጠቅመዋል። የሃይኖት መጻህፍት፣ የወርቅ ዘውድና ጽዋዎች ተዘርፈዋል። ጥያቄ 3/6 ሃገር: ኬንያ ሰው በላዎቹ ፃቮ የሚባሉት እነማን ናቸው? ትክክለኛ መልስ በ1899 በብሪታኒያ ወታደሮች ከመገደላቸው በፊት ከሞምባሳ እስከ ቪክቶሪያ ሃይቅ የሚደርሰው የባቡር መስመር በሚገነባበት ጊዜ ፃቮ በሚባል ቦታ 140 ሰራተኞችን የበሉ ሁለት አንበሶች ናቸው። ጥያቄ 4/6 ሃገር: ዚምባብዌ ከድንጋይ የተቀረጸችው የዚምባብዌ ወፍ የሃገሪቱ መለያ አርማ ናት። ቅርሶቹ በቅኝ ገዢዎች ከተዘረፉ በኋላ ከስምንቱ ጥንታዊ የድንጋይ ቅርጾች ስንቶቹ ወደ ዚምባብዌ ተመለሱ? ትክክለኛ መልስ ሰባቱ የድንጋይ ቅርጾች ዚምባብዌ ውስጥ ይገኛሉ። ከ15 ዓመታት በፊት ጀርመን በእጇ ያሉትን የመለሰች ሲሆን ስምንት የሚሆኑት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ውስጥ ይገኛሉ። ጥያቄ 5/6 ሃገር: ካሜሩን የባንግዋ ንግሥት በመባል የምትታወቀው የእንጨት ቅርጽ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ከካሜሩን የተወሰደች ናት። ሃገሬው የሴት ገጽ ያላትን ቅርጽ "ጁዊንዴም" ይላታል። ስያሜው ምን ማለት ነው? ትክክለኛ መልስ በባንግዋ ህዝብ ቋንቋ "ጁዊንዴም" "የእግዜር ሴት" ማለት ነው። ይህ ቅርስ በ1899 እንዴት ጀርመናዊው የቅኝ ግዛት መልዕክተኛ እጅ ውስጥ እንደገባ እስካሁን አልታወቀም። ጥያቄ 6/6 ሃገር: ቤኒን የቤኒን የነሃስ ቅርሶች ከምንድን ነው የተሰሩት? ትክክለኛ መልስ በ1897 በብሪታኒያ ወታደሮች የተዘረፉት የቤኒን ብሮንዝ የተሰሩት ከብራስ ነው። ብዙዎቹ በእንግሊዝ፣ ጀርመንና አሜሪካ ውስጥ ይገኛሉ። የበለጠ ይወቁ የመቅደላ ቅርሶች የመቅደላ ቅርሶች የ18ኛው ክፍለ ዘመን የወርቅ አክሊል እና የንጉሣዊያን የሠርግ ልብስን ያካትታል። ከ185 ዓመታት በፊት በአውሮፓዊያኑ 1868 ከኢትዮጵያ (አቢሲኒያ) በብሪታንያ ወታደሮች አማካይነት የተወሰዱ ናቸው። የቪክቶሪያ እና አልበርት ሙዚየም የዘውድ አክሊል፤ ብር እና መዳብን ጨምሮ በተለያዩ ጌጦች የተሠራ ነው። አክሊሉ እና ንጉሣዊ የጋብቻ ልብሶቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምልክቶች ናቸው። • ከኢትዯጵያ የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት ሊመለሱ ነው • የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት መመለሳቸውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ምላሽ ምንድን ነው? ተመራማሪዎች አንደሚሉት አክሊሉ በ1740ዎቹ በእቴጌ ምንተዋብ እና ልጃቸው ንጉሥ እያሱ ወጪ የተሠራ እና ጐንደር ውስጥ ለሚገኝ ቤተክርስቲያን በስጦታ መልክ ከወርቅ ጽዋ ጋር እንደተሰጠ ያምናሉ። እነዚህ ቅርሶች ለ146 ዓመታት በቪ ኤንድ ኤ ውስጥ ለዕይታ በቅተዋል። በ1868 እንግሊዞች ባደረጉት ውጊያ ወቅት የተወሰዱ ሲሆን ውስብስብ ታሪክም አላቸው። በኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ 2ኛ እስር ቤት የታሰሩትን የእንግሊዝን ወታደሮች ለማስፈታት በሌተናንት ጄኔራል ሰር ሮበርት ናፒየር የሚመራ ከፍተኛ መጠን ያለው ጦር ተሰማርቶ ነበር። የታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚሉት ከመቅደላ ቅርሶቹን ለመውሰድ በጠቅላላው 15 ዝሆኖች እና 200 ፈረሶች አስፈልገው ነበር። ከመቅደላ ተወሰዱ ተለያዩ ቅርሶች በአሁኑ ጊዜ ለበርካታ የእንግሊዝ ሙዚየሞች ተከፋፍለዋል። • የመቅደላ 150ኛ ዓመት ኢትዮጵያ በ2007 ብዙዎቹ ቅርሶች ሊሰጧት እንደሚገቡ ጥያቄ አቅርባለች። በሚያዝያ ወርም ቪ ኤንድ ኤ ከ150 ዓመት በፊት በእንግሊዝ ወታደሮች የተወሰዱ ቅርሶችን በውሰት ለኢትዮጰያ ለመስጠት ተስማምቷል። ከእነዚህ ውስጥም አክሊል፣ የንጉሣዊያን የሠርግ ልብሶችና የወርቅ ጽዋ ይገኙበታል። የቤኒን ነሐሶች የቤኒን ነሐሶች የተለያዩ ቅርጻ ቅርጾች ስብስብ ሲሆን መገኛውም በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው ቤኒን የሚገኘውን የኦባ (ንጉሥ) ኦቮንራምዌንን ቤተ መንግሥትን ያስዋቡ ነበሩ። ቅርጻ ቅርጾቹ ከዝሆን ጥርስ፣ ከነሐስ፣ ሴራሚክ እና እንጨት የተሠራ ነው። ከ15ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ኦባውን ያገለግሉ በነበሩ ባለሙያዎች የተሠሩ ናቸው። ብዙዎቹም ለቀደምት ኦባዎች እና ንግሥት እናቶች የተሠሩ ናቸው። ከ15ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ቤኒን በምዕራብ አፍሪካ ከሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሃገራት መካከል አንዷ ነበረች። በአውሮፓዊያኑ 1897 ቤኒን በእንግሊዝ ዲፕሎማቶችን ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ በብሪታንያ ጥቃት ደርሶባታል። በዚህም ከተማዋ ሙሉ ለሙሉ ተቃጥላለች። የንጉሣዊያን ቤተ መንግሥቱ ካለመትረፉም በተጨማሪ ህይወታቸው በአውሮፓዊያኑ 1917 እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ኦባ ኦቮንራምዌን ወደ ካላባር ሸሽተው ይኖሩ ነበር። ይህ ደግሞ የነጻይቱ የቤኒን መንግሥት መጨረሻ ምልክት ነበር። • አሜሪካ ለላሊበላ ቤተክርስትያን ጥበቃ ፕሮጀክት 13.7 ሚሊዮን ብር ሰጠች ከዚህ ተልዕኮ መጠናቀቅ በኋላ ከነሐስ ቅርጻ ቅርጾች በተጨማሪ ሌሎችም የንጉሳዊ ቤተሰቡ ቅርሶች ተዘርፈዋል። አንዳንዶቹ የተዘረፉት ቅርሶች በወታደሮች እጅ ሲገቡ ሌሎቹ ደግሞ ተሽጠው ወታደራዊው ተልዕኮን ለማስፈፀም የወጣውን ወጪ እንዲሸፍን ተደርጓል። የነሐስ ቅርሶቹ በመላው ዓለም ተበትነው ይገኛሉ። የብሪቲሽ ሙዚየም በተለያዩ ሙዚየሞች በተለይም በጀርመን ሙዚየም የሚገኙ እና ከቤኒን የተዘረፉ ቅርሶችን እንዲገዙ ወኪል በመሆን መሥራቱን አስታውቋል። በብሪቲሽ ሙዚየም የሚገኙ አብዛኛዎቹ ከቤኒን የመጡ ቅርሶች ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና ከሎርድስ ኮሚሽነርስ በአውሮፓዊያኑ 1898 የተሰጡት እንደሆነ ሙዚየሙ አስታውቋል። ናይጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 2021 አዲስ ሙዚየም ለመክፈት መዘጋጀቷን ተከትሎ ጥቅምት ወር ላይ የአውሮፓ ታላላቅ ሙዚየሞች ዋና ዋና ቅርሶችን በውሰት ወደ ናይጄሪያ ለመላክ ተስማምተዋል። የናይጄሪያው ሙዚየም ነሐሶቹን ጨምሮ ሌሎች ቅርሶችን ለማሳየት ተዘጋጅቷል። ከጀርመን፣ ኔዘርላንድ፣ ስዊድን እና እንግሊዝ ተወጣጡ የሙዚየም አስተዳዳሪዎች ቅርሶቹን በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማሳየት ተስማምተዋል። የፃቮ ሰው በሊታዎቹ እነዚህ በኬንያው ፃቮ አካባቢ የሚገኙ ታዋቂ ሁለት አንበሶች ናቸው። አንበሶቹ በብሪትሽ ኬንያ-ዩጋንዳ የባቡር መስመር ዝርጋታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞችን በልተዋል። አንበሶቹ በሞምባሳ እና ቪክቶሪያ ሃይቅ መካከል ሚገነባውን የባቡር መስመር የሚሰሩ ህንዳዊያን ላይ ለዘጠኝ ወራት ስጋት ከመፍጠር ባለፈ ግንባታው እንዲቋረጥም አስገድደው ነበር። የፃቮ አንበሶች ከሌሎች የፃቫና አካባቢ አንበሶች ይለያሉ። ምክንያቱም ከተለመዱት አንበሶች በላይ ትልቅ ከመሆናቸውም በላይ ወንዶቹ ጎፈር አልነበራቸውም። ባህሪያቸውም ቢሆን ለየት ያለ ነው። በአካባቢው ሚሰራውን የባቡር መስመር ተከትሎ ሠራተኞች ሲሞቱ በየቦታው ይጣሉ ስለነበር ሰዎችን በቀላሉ ለአደናቸው ይመርጧቸው ጀመር። ሁለቱ አንበሶች በባቡር ፕሮጀክቱ በኃላፊነት ይሠራ የነበረውን የአዳኝ እና የሲቪል መሐንዲስ በነበረው እንግሊዛዊው ሌፍተናንት ኮሎኔል ጆን ፓተርሰን ተገድለዋል። ሁለተኛው አንበሳ የሞተው በፒተርሰን 10 ጥይቶች ከተመታ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ነው። በኋላም ግለሰቡ የአደን ቦታ የጥበቃ ሠራተኛ በመሆን ማገልገል ችሏል። አንበሶቹ ታክሲደርሚ በሚባለው ዘዴ ህይወት ያላቸው መስለው እንዲቀመጡ ቢደረግም ፓተርሰን በመጽሀፉ ከገለጸው በመጠን አነስ ብለው ነው ያሉት። 'ዘ ጎስት ኤንድ ዘ ዳርክነስ' የተባለው እና ስሙን ከሁለቱ አንበሶች ያገኘው ፊልም በአውሮፓዊያኑ 1996 ተሠርቷል። ፓተርሰን አንበሶቹን እንደሽልማት በመውሰድ በቤቱ ለ25 ዓመታት አኑሯል። አንበሶቹ ለሌሎች ሁለት ሆሊውድ ፊልሞች፣ የምርምር እና የጋዜጣ ጽሑፎች መነሻም ሆነዋል። ቺካጎ ኢሊዮንስ ውስጥ የሚገኘው ፊልድ ሙዚየም ኦፍ ናቹራል ሂስትሪ አንበሶቹን ከፓተርሰን በአውሮፓዊያኑ 1925 በመግዛት ከሙዚየሙ ቋሚ ስብስቦች መካከል አደረጋቸው። ፓተርሰን አንበሶቹ የ135 የባቡር ፕሮጀክቱን ሠራተኞች እና አካበቢውን ነዋሪዎች እንደበሉ ገልጾ ነበር። ሆኖም ሙዚየሙ በኋላ ላይ በሳይንቲስቶች አደረኩት ባለው ጥናት ቁጥሩን ወደ 35 ዝቅ አድርጎታል። ኬንያ ብሔራዊ ሙዚየም አንበሶቹ እንዲመለሱ ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል። የሮዜታ ድንጋይ በእንግሊዝ ሙዚየም የሚገኘው ሮዜታ ድንጋይ መነሻው ግብጽ ሲሆን ለየት ካለ የድንጋይ ዓይነት የተሠራ እና 1.06 ሜትር ቁመት ያለው ነው። ድንጋዩ ከትልቅ አለት ላይ የተከፈለ ሲሆን ላዩ ላይ የተጻፈው ነገር ተመራማሪዎች የግብጻዊያንን ሄሮግላፊስ እንዲያነቡ ያስተማረ ነው። የእንግሊዝ ሙዚም እንደሚለው ናፖሊዮን ቦናፓርት ግብጽ ውስጥ ከአውሮፓዊያኑ 1798 እስከ 1801 ድረስ ተሰማርቶ ነበር። ምሥራቃዊ ሜድትራኒያን ከመቆጣጠር ባለፈ በህንድ ላይ የበላይ በነበረችው እንግሊዝ ላይ ይዝት ነበር። በአውሮፓዊያኑ 1799 ድንጋዩ እንዴት እንደተገኘ ባይታወቅም በናፖሊዮን ወታደሮች እንደተገኘ ግን ከፍተኛ እምነት አለ። በናይል ዴልታ በምትገኘው ራሺድ (ሮዜታ) አካባቢ ምሽግ ለመሥራት ሲቆፍሩ ነው ድንጋዩን ያገኙት። የወታደሮቹ ኃላፊ የነበረው ፒየር-ፍራንኮስ ቡቻርድ ነው ድንጋዩ ትልቅ ቁም ነገር ያለው መሆኑን ያወቀው። ናፖሊዮን ሲሸነፍ በአሌክሳንደሪያ ስምምነት መሠረት ድንጋዩን ጨምሮ ሌሎች በፈረንሳይ ሥር የነበሩ ቅርሶች በእንግሊዝ ቁጥጥር ስር ዋሉ። ድንጋዩ ወደ እንግሊዝ በማጓጓዝ በአውሮፓዊያኑ 1802 ፖርትስማውዝ ደረሰ። በዚያው ዓመት በጆርጅ ሦስተኛ ለእንግሊዝ ሙዚየም ተሰጠ። ሙዚየሙ የሮዝታ ድንጋይን ለማስቀመጥ የሚሆን ጥንካሬ ስለሌለው ለዚህ የሚሆን ጊዜያዊ ቦታ ተዘጋጀ። ሌሎቹንም ቅርሶች እንዲይዝ ሌላ ማሳያ ተዘጋጀ። ድንጋዩ በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝ ሙዚየም ይገኛል። የባንግዋ ንግሥት የባንግዋ ንግሥት 0.82 የምትረዝም ከእንጨት የተሰራች የካሜሮን ቅርስ ናት። ንግሥቷ የባንግዋን ህዝብ ስልጣንና ጤንነትን የሚገልጽ አቋም አላት። ንግሥቷን ቅርስ በመላው ዓለም ከሚደነቁ የአፍሪካ ቅርሶች አንዷ ስትሆን ለካሜሮን ህዝቦች ደግሞ የጽድቅ ተመሳሌት ናት። በቀድሞዋ ባንግዋ በአሁኗ ሌቢያልም ዲቪዥን ተምሳሌታዊ የሆኑ ምስሎች ተሠርተው ባንግዋ ንግሥት የሚል ስም ይሰጣቸዋል። በንጉሳዊው ዘውድ ውስጥ ያላቸው ስልጣን በአንገት ጌጣቸው ላይ የሚመሠረት ነው። የባንግዋ ንግሥት ያላት ዋጋ በሚሊዮን ዶላሮች ይገመታል። በኒውዮርክ በሚገኘው የሜትሮፖሊታን ሙዚም ካለው የባንግዋ ንጉሥ ጋር ከአፍሪካ ከተገኙ ምርጥ ቅርሶች መካከል ይጠቀሳል። የባንግዋ ንግሥት እንዴት እንደተሰረቀች አሁንም ድረስ አይታወቅም። የእንጨት ቅርሱ በጀርመን የቅኝ ግዛት መልዕክተኛ ጉስታቭ ኮንራው ተሰርቋል ወይም በስጦታ መልክ አግኝቶታል ተብሎ ይገመታል። ይህ የሆነው በአሁኗ ካሜሮን ውስጥ የምትገኘውን የቀድሞዋን ባንግዋን ጀርመኖች ቅኝ ከመግዛታቸው በፊት ነው። ቅርሱ በበርሊን ለሚገኘው ፈር ቮልከኩንድ ሙዚም ተሰጠ። በኋላ ላይ ለጨረታ ቀርቦ አሜሪካዊው የቅርስ ሰብሳቢ በአውሮፓዊያኑ 1966 ገዛው። ልጁ ደግሞ በ1990 ለዳፐር ፋውንዴሽን በጨረታ አሳልፋ ሰጠችው። የባንግዋ ንግሥት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከካሜሮን ከወጣች በኋላ በታዋቂ የቅርስ ሰብሳቢዎች እጅ እንደገባች ታሪክ ይገልጻል። እንደ ካሜሮናዊያኑ የባንግዋ ህዝቦች ጠበቃ ከሆነ በሃገሪቱ መንግሥትና በዳፐር ፋውንዴሽን መካከል የነበረው ድርድር ተቋርጧል። ጠበቃው እንደሚሉት የባንግዋ ህዝቦች ዋነኛ ስጋት ፋውንዴሽኑ ቅርሱን በጨረታ ለግለሰብ በማስተላለፍ እንዳይታወቅ ሊያደርግ ይችላል። ሆኖም የአካባቢው ሰዎች ጥያቄ ከተቀረው ዓለም ትኩረት አልተሰጠውም። ዳፐር ፋውንዴሽን እንደሚለው ከሆነ ንግሥት ባንግዋ በ1990ዎቹ በጨረታ ያገኛት ንብረቱ ናት። ከዚህ ቀደም በሄሌና ሩቢንስቴይንና ሃሪ ፍራንክሊን እጅ ነበረች። የዚምባብዌ ወፍ የዚምባብዌ ወፍ የተቀረጸ ወፍ ሲሆን ከታላቋ ዚምባብዌ ፍርስራሽ ቦታዎች ተገኘ ነው። ምስሉ በሃገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ገንዘቦች እና ሳንቲሞች ላይ የሚታይ አርማ ነው። ተወዳጅ የሆኑት የወፍ ምስሎች በ12ኛውና በ15 ኛው ክፍለ ዘመን የተገነቡ ሲሆን በጥንታዊቷ ከተማ በቀደምት ሾናዎች የተሠሩ ናቸው። ዘመናዊ ዚምባብዌ 1,800 ሄክታር ከሚሸፍነው ፍርስራሽ ነው ስያሜዋን የያገኘችው። ፍርስራሹም ከሰሃራ በስተደቡብ ከሚገኙት ትላልቅ የድንጋይ ሕንፃዎች አንዱ እንደሆነ ይገለጻል። ቅርሱ ከጀርመን ሙዝየም በ2003 ከተላለፈ በኋላ አሁን በዚምባብዌ እጅ ይገኛል። ሴሲል ሮሄድስ የሚባሉት የዚምባብዌ ቅኝ ገዢ እንግሊዛዊያን በ1906 የተወሰኑ ወፎች ከታላቋ ዚምባብዌ ወደ ደቡብ አፍሪካ ወስደዋል። ደቡብ አፍሪካ በ1961 ዞምባብዌ ነጻነቷን ካወጀች በኋላ አራት ቅርሶችን መልሳለች። ይሁን እንጂ በአንድ ጀርመናዊ ሚስዮናዊ ተይዞ የነበረ አንድ ቅርስ በ1907 በበርሊን ለሚገኝ ሙዚየም ሸጦታል። ከዚያም የሩሲያ ወታደሮች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ጀርመንን ሲይዙ ወፉ ከበርሊን ወደ ሌኒንግራድ ተወስዶ ከቆ በኋላ የቀዝቃዛው ጦርነት ሲያበቃድረስ ወደ ጀርመን ተመለሰ። ተወሰኑት ደግሞ በኬፕታውን በሚገኘው የሲሲል ሮዴስ መኖሪያ ቤት ይገኛሉ።
xlsum_amharic-train-260
https://www.bbc.com/amharic/56539799
ያልተሰማው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ድምጽ እና መፍትሄው
ረቡዕ ታኅሣሥ 14/2013 ዓ.ም ንጋት የ41 ዓመቱን አርሶ አደር በላይ ዋቅጅራን ሕይወት እስከወዲያኛው የቀየረ ክስተት ተከሰተ።
[ "ረቡዕ ታኅሣሥ 14/2013 ዓ.ም ንጋት የ41 ዓመቱን አርሶ አደር በላይ ዋቅጅራን ሕይወት እስከወዲያኛው የቀየረ ክስተት ተከሰተ።" ]
የመተከል ዞን ነዋሪ የነበረው አለሙ በየነ፣ ቤተሰቡን ለመታደግ በአውቶብስ ወደ ቻግኒ ከተማ በታኅሣሥ 3 2013 ዓ.ም ይልካቸዋል። ታጣቂዎች ግን ባለቤቱን እና ሦስት ልጆቹን ጨምሮ 44 ተሳፋሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኩጂ ተብላ በምትጠራው ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት በላይ ዋቅጅራ ባለቤታቸው እና 9 ልጆቻቸው አይናቸው እያየ በግፍ ተገደሉ። ታዳጊ ልጆቻቸው በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ከተለቀቀው እሳት ራሳቸውን ለማዳን ከቤት ሲወጡ፤ የጦር መሳሪያ ደግነው በሚጠብቋቸው ታጣቂዎች ሰላባ ሆነዋል። "አጠገቤ ገደሏቸው" ይላሉ። "ባለቤቴ፣ 5 ሴት ልጆቼ እና 4 ወንድ ልጆቼ ናቸው የተገደሉት" ይላሉ የልጆቻቸውን እና የባለቤታቸውን ስም በሐዘን በተሰበረ ድምጽ እያስታወሱ። ሌላኛው ነዋሪ አቶ ተስፋ [በጥያቄው መሠረት ስሙ የተቀየረ] እናትና አባቱ ሠርግ ለመታደም በወጡበት እንደቀሩ ይናገራል። ታጣቂዎች በተለያየ ወቅት ባደረሱት ጥቃት ወላጆቹን ጨምሮ በርካታ ዘመዶቹን አጥቷል። በተለያየ ጊዜ የመንግሥት ጦር የሚወስደውን ጥቃት በመሽሽ ወደ ሱዳን ድንበር ሲሽሽ እንደቆየ የሚናገረው የጉሙዝ ተወላጁም፤ ንሑሃን የጉሙዝ ተወላጆች ሲገደሉ አይቻለሁ ይላል። የመተከል ዞንን ችግር ውሰብስብ እንደሆነ የሚያሳየው ደግሞ የኢንስፔክተር ነጋሽ ኩቲል ታሪክ ነው። ኢንስፔክተር ነጋሽ የክልሉ የፖሊስ አባል እና የጉሙዝ ተወላጅ ናቸው። ኢንስፔክተሩ በተሰጣቸው ግዳጅ ላይ ተሰማርተው ሳለ ከታጣቂዎች ጋር ውጊያ መግጠማቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ጉሙዝ ነኝ። ሚስቴም ጉሙዝ ናት። ግዳጅ ተልኬ ከጉሙዝ ጋር ውጊያ አጋጠመን። 'ነጋሽ ነው መከላከያን መርቶ ያመጣው' ብለው ጠቆሙብኝ። ከዚያ እኔን ለመግደል ሲመጡ አጡኝ። እዚያው ሚስቴን እና ልጆቼን በጥይት ጨረሷቸው" ሲል ኢንስፔክተር ነጋሽ ይናገራል። ይህን መሰል የሰቆቃ ታሪክ በቤኒሻንጉል ክልል የሚኖሩ የተለያዩ ብሔር ተወላጆች የሚጋሩት ሃቅ ነው። ከቅርብ ወራት ወዲህ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኘው መተከል ዞን በሚፈጸሙት ጥቃቶች እና በሚያጋጥሙት ግጭቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሺናሻ እና ጉሙዝ ብሔር ተወላጆች በግፍ ተገድለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል። መሰል ጥቃቶች ለምን ይፈጸማሉ? ይህ እልቂትስ ሊቆም የሚችለው እንዴት ነው? ትኩረታችንን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በማድረግ፤ በስፍራው የሚኖሩ የተለያዩ ብሔር ተወላጆችን፣ የአካባቢውን ባለስልጣናት እና ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ፖለቲከኞችን ጠይቀናል። ከዚያ በፊት ግን ጥቂት ስለክልሉ እና የአከባቢውን በአጭሩ እንመልከት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን በጨረፍታ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕጻናት አድን ድርጅት እአአ 2019 ባወጣው የሁኔታ መግለጫ ሪፖርት (ሲቹዌሽን ሪፖርት) ላይ የክልሉ ነዋሪ ቁጥር ወደ 1.1 ሚሊዮን እንደሚጠጋ አስቀምጦ ነበር። ከእነዚህ የክልሉ ነዋሪዎች መካከልም 44 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ነው። በክልሉ ከሚኖሩ የተለያዩ ብሔር ተወላጆች መካከል የጉሙዝ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሺናሽ እና አገው ብሔር ተወላጆች ደግሞ ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ። በክልሉ ሶስት ዞኖች የሚገኙ ሲሆን መተከል፣ ካማሺ እና አሶሳ በመባል ይታወቃሉ። ትኩረት የምናደርግበት መተከል ዞን ከኦሮሚያ፣ አማራ እና ሱዳን ጋር ይዋሰናል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የክልሉ ነዋሪ ኑሮውን መሠረት ያደረገው በእርሻ ሥራ ላይ ነው። የክልሉ ነዋሪ ቁጥር ወደ 1.1 ሚሊዮን የሚጠጋ ሲሆን ከዚህም መካከል 44 በመቶ የሚሆነው እድሜው ከ18 ዓመት በታች ነው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መሬት ለም ነው። በርካታ አልሚዎች ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን የኢንቨስትመንት ፈቃድ በመውሰድ ያለማሉ። የግጦሽ መሬትም ሠፊ ነው። ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ይሁን እንጂ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በተለያዩ ጊዜያት ከሌሎች ስፍራዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሰፍሩ ተደርጓል። የሕጻናት አድን ድርጅቱ በሁኔታ መግለጫ ሪፖርቱ ክልሉ ከተቀረው የአገሪቱ ክልሎች በተነጻጻሪነት ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ቁጥር ጭማሪ እንደሚያሳይ ይገልጻል። ከከፍተኛ የወሊድ መጠን በተጨማሪ የእርሻ እና የግጦሽ መሬት መኖሩ እና በክልሉ ያሉት ሰፋፊ የእርሻ ኢንተርፕራይዞች ሰዎች ወደ አካባቢው እንዲፈልሱ እና የክልሉ ሕዝብ ቁጥር በፍጥነት እንዲጨምር ምክንያት ናቸው ይላል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወቅታዊ ሁኔታ የፌደራሉ መንግሥት እና የአካባቢው ባለስልጣናት የመተከል ዞን ከዚህ ቀደም ከነበረበት የደህንነት ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር አንጻራዊ ሰላም አለ ይላሉ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ግን አሁንም ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ስጋት እንዳላቸው ይናገራሉ። የመተከል ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አብዲ ጎረና ዞኑ በፌደራል ኮማንድ ፖስት ስር እንደሚገኝ በማስታወስ "የጸጥታው ሁኔታ ጥሩ ደረጃ ላይ ነው ያለው። ኮማንድ ፖስቱ ወደ ሥራ ከገባ በኋላ አንጻራዊ ሰላም አለ" ከማለት ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ተደጋጋሚ ጥቃት ከሚፈጸምባቸው በመተከል ዞን ውስጥ ከሚገኙት ወረዳዎች አንዷ የሆነችው የድባጤ ወረዳ ፖሊስ አዛዥም፤ በተመሳሳይ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ መስጠት ባይሹም፤ "ምን ሰላም አለ?" በማለት የፀጥታ ስጋት እንዳለ ተናግረዋል። ታኅሣሥ ወር ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡባት ቡለን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በበኩላቸው በወረዳዋ የተሻለ መረጋጋት ቢኖርም፤ በዙሪያዋ በሚገኙ አካባቢዎች ግን አሁንም የጸጥታ ስጋት እንዳለ ገልፀዋል። ኮማንደር ቢራቱ ተሰማ፤ "በወረዳው የተሻለ ቢሆንም፤ በወረዳው ዙሪያ ግን አሁንም ስጋት አለ" በማለት ታጣቂዎች የጸጥታ ስጋት ሆነው መቀጠላቸውን ይናገራሉ። ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ የተጠለሉ ሰዎች ቁጥርም 65000 መድረሱን የቻግኒ ከተማ አስተዳዳር የሰላምና ደህንነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ማስረሻ ይትባለ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥት የስደተኞች ከፍተኛ ድርጅት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሸሽተው ወደ ሱዳኗ ናይል ስቴት እየተሰደዱ እንደሆነ ገልጿል። ድርጅቱ ለቢቢሲ እንደገለጸው፤ 7ሺህ 393 ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው በሱዳን በአምስት የተለያዩ ስፍራዎች ሰፍረው ይገኛሉ። ስፍራዎቹ ሩቅ እና መሠረታዊ አገልግሎቶች የሌሉባቸው ቦታዎች መሆናቸውንም ድርጅቱ ገልጿል። የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን መጋቢት 14 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ስደተኞቹ ክልሉን በመሸሽ ወደ ሱዳን መግባት የጀመሩት ከኅዳር 7 2013 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑን አስታውሶ፤ በቅርቡም መጋቢት 8 2013 ዓ.ም. ላይ ተጨማሪ 370 ሰዎች ሱዳን ደርሰው እንደስደተኛ መመዝገባቸውን አስታውቋል። የተመድ የስደተኞች ድርጅት የሱዳን ተወካይ ሶፊያ ጄሰን ስደተኞቹ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተሰድደው ወደ ሱዳን የሚሸሹት በደህንነት ስጋት እና በግጭቶች ምክንያት መሆኑን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካርታ ጥቃቶች/ግጭቶች ለምን ይፈጸማሉ? የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ የተለያዩ ብሔር አባላት እና ጉዳዩ ይመለከተናል የሚሉ ፖለቲከኞች በተደጋጋሚ ለሚከሰቱት ግጭቶች እና ጥቃቶች ምክያቶቹ ከማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ባሻገር ፖለቲካዊ ይዘቶች እንዳላቸው ያስረዳሉ። ስሜ አይጠቀስ ያለው የጉሙዝ ብሔር ተወላጅ የሆነ ወጣት፤ የጉሙዝ ብሔር ተወላጆች ባለፉት ዓመታት "ደሃ እንዲሆኑ ተደርገዋል" ይላል። ይህ ወጣት እንደሚለው ከሆነ የጉሙዝ የእርሻ እና የግጦሽ መሬቱን እንዲነጠቅ ተደርጓል፤ "ስለዚህ ጉዳይ ማንም ማውራት አይፈልግም" ሲል ሁኔታውን ያስረዳል። ወጣቱ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ትክክል ናቸው ብሎ እንደማያምን ገልጾ፤ የጉሙዝ ሕዝብ "ሲጎዳ ዝም መባል የለበትም" ብሏል። የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆነው እና ስሜ አይጠቀስ ያለ ሌላ ወጣት ደግሞ፤ መተከል መወለዱን እና ማደጉን በመግለጽ "አባቴ ከሌላ ስፍራ ይመጣ እንጂ፤ አገሬ እዚሁ ነው። ሠርቶ የተለወጠ ሰው ነው እንደ ጠላት የሚታየው እንጂ ሌላ ነገር የለም" በማለት ይናገራል። ነዋሪነታቸው የክልሉ መዲና በሆነችው አሶሳ ከተማ የሆነው ፖለቲከኛው አብዱልሰላም ሸንገል በበኩላቸው፤ የግጭቶቹ መነሻዎች ምላሽ ሳይሰጥባቸው የቀሩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እንደሆኑ ያስረዳሉ። ፖለቲከኛው እንደሚሉት በመተከል ዞን ማንነትን መሠረት ያደረገ መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘር ከመጀመራቸው በፊትም በግለሰቦች ደረጃ በግጦሽ መሬት እና በውሃ ይገባኛል ግጭቶች ይከሰቱ እንደነበረ ያስታውሳሉ። "መጠነ ሰፊ ብሔር ተኮር የሆነው ግጭት የጀመረው ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ ነው። ከመተከል ዞን ጋር በሚዋሰነው ጃዊ ወረዳ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉሙዞች ተገድለው ነበር። ስለ ግድያው ምንም ሳይባል ቀረ። ማንም ተጠያቂ ሳይሆን ቀረ። ከዚያ በኋላ እዚህ ያለው ጉሙዝ ስሜት ውስጥ ገባ። ከዚያም እዚህ ካለው አማራ ጋር ግጭት ፈጠረ" ይላሉ። አቶ አብዱልሰላም እንደሚሉት የተለያዩ ማህበራዊ አንቂዎች መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም "መተከል የእኛ ነው። የጉሙዝ አይደለም። እናስመልሳለን የሚሉ ዛቻዎች" ማሰራጨታቸውን ተከትሎ፤ "እዚህ ያሉ ፖለቲከኞች 'መሬትህ ሊወሰድ ነው'፣ 'ራስህን አድን' የሚሉ ፕሮፖጋንዳዎችን በጉሙዙ ውስጥ ረጩ" ይላሉ። በተለይ በገጠር ያለው የጉሙዝ ማህበረሰብ በትምህርት ያልገፋ መሆኑን ጠቅሰው፤ በመሰል ቅስቀሳዎች ተገፋፍተው "ስሜት ውስጥ የመግባት ነገር አለ" ብለዋል። አቶ አብዱልሰላም እንደሚሉት በክልሉ የተለየዩ ለውጦች ቢኖሩም፤ የጉሙዝ ሕዝብ ከዚህ ተጠቃሚ ሳይሆን እንደቀረ ይናገራሉ። "መተከል ስትመሠረት በከተማዋ በስፋት የነበሩት የጉሙዝ እና የሺናሻ ብሔር ተወላጆች ናቸው። አሁን ላይ ከተማዋ ሰፍታ ትልቅ ሆናለች። በከተማዋ ያለው ሁኔታ ተቀይሯል። ጉሙዝ ግን በጊዜ ሂደት ከከተማው ወጥቷል" ሲሉ ያስረዳሉ። ይህንንም ሲያብራሩ "ባለሆቴሉ እና ባለሱቁ ከሌላ ማህብረሰብ የመጡ ናቸው። ንብረት ያፈሩት ጉሙዞች በቁጥር በጣም ጥቂት ናቸው። አርሶ አደሩ ከቀዬው እየተፈናቀለ መሬቱ ለኢንቨስተር የሚሰጥበት ሁኔታ አለ።" አቶ አብዱልሰላም ፍትሃዊ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት አለመኖሩ በሕዝቦች መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር አንዱ ምክንያት አንደሆነ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለችው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ይገኛል "በግጭቱ ባስልጣናት፣ ባለሃብቶች እና የውጪ ኃይሎች እጅ አለበት" መብራቱ አለሙ (ዶ/ር) የሺናሻ ብሔር ተወላጅ ናቸው። የክልሉን ሁናቴ በቅርብ ስከታተል ቆይቻለሁ ይላሉ። መብራቱ (ዶ/ር) በክልሉ በተለያዩ የስልጣን ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎችም ግጭት በመቀስቀስ ተሳትፎ ሲያደርጉ ቆይተዋል ሲሉ ይከስሳሉ። ከዚህ በተጨማሪም በስፍራው በኢንቨስትመንት ፍቃድ መሬት የወሰዱ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ባለሃብቶች የጉሙዝ ወጣቶችን ዳንጉር ወረዳ ጠረፍ እና ወደ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ ወስደው ስልጠና ስለመስጠታቸው እና ስለማስታጠቃቸው ይናገራሉ። "እውነት ለመናገር ጉባ፣ ዳንጉር እና ወንበራ አካባቢ ያሉ ሰፊ መሬቶች ለኢንቨስትመንት ተብለው ተሰጥተዋል። ግን ስጋት ካልሆነ በቀር አሁን ያለው መሬት ለእነርሱ [ጉሙዝ] በቂ አይደለም ማለት ይከብደኛል። ለግላቸው የሚሆን የእርሻ መሬት አላቸው። ሰፊ መሬት አርሰው የመጠቀም ልምድ የለም። በእጅ ነው የሚቆፍሩት" ይላሉ። የግጭቱ አንዱ መንስኤ እውነታው ከፖለቲካው ፍላጎት ጋር ተደማምሮ ነው ተመስገን ገመቹ የሕግ ባለሙያው ሲሆን ትውልድ እና እድገቱ መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ እንደሆነ ይናገራል። ተመስገን አሁናዊ የሆኑ ይፋዊ አህዞች ባይኖሩም በመተከል ዞን ላይ በብዛት ያለው የጉሙዝ ተወላጅ እንደሆነ መገመት ይቻላል ይላል። ባለፉት ዓመታት ወደ አካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በሰፈራ ምክንያት መምጣቱን አስታውሶ፤ የኦሮሞ እና አገው ሕዝብ ግን የአካባቢው ቀደምት ነዋሪዎች ናቸው ይላል። ተመስገን በስፍራው የሚስተዋለውን "ግጭት" የተለያዩ ምክንያቶች ድምር መሆኑን ተናግሮ ዋነኛው ምክንያት ግን በሕዝቡ ውስጥ ያለው እውነታ ከፖለቲካ ፍላጎት ጋር ተደማምሮ የሚከሰት ነው ብሏል። "በጉሙዝ ሕዝብ ዘንድ ከዚህ ቀደም ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ወይም በጥርጣሬ የሚመለከታቸው ነገሮች አሉ። በክልሉ በሚደረግ የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ የጉሙዝ ሕዝብ በስፋት ተሳታፊ አይደለም። ከተማ ሲስፋፋ ሁሉ ጉሙዞች በብዙ ኪሎ ሜትሮች እንዲርቁ እየተደረገ ነው። በዚህ መካከል 'ቀዩ መሬትህን ሊውስድ ነው፣ ህዝበ ውሳኔ ተብሎ አገርህን ልትነጠቅ ነው' የሚል ቅስቀሳ ፖለቲከኞቹ ይመግቧቸዋል። ፖለቲከኞቹ ብሶትን ነው ለህዝባቸውን የሚናገሩት። ህዝቡ እውነታው አለው። ይህ እውነት ግን ለዚህ መሰል ግጭት ብቻውን ምክንያት ሊሆን አይችልም" በማለት ጠበቃው አቶ ተመስገን ይናገራል። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ 'መተከል ርስት ነው። እናስመልሳለን' የሚሉ ቅስቀሳዎችም በሕዝቡ ዘንድ መረጋጋት እንዳይፈጠር ምክንያት መሆኑን ያስረዳል። ከዚህ በተጨማሪም የአንድ ብሔረሰብ ተወላጅ በሚበዛበት አካባቢ የአመራር ስብጥር አለመኖሩ ሌላው የግጭት መንስዔ አንደሆነ ጠበቃው ተመስገን ይናገራል። "ውክልና የለም። አማራው፣ ኦሮሞ፣ አገው ባሉበት ቦታ ውክልና የላቸውም ማለት ይቻላል። 'የክልል ባለቤት' የሚባሉት ብቻ ናቸው ስልጣን ላይ ያሉት" ይላል። መፍትሄው ምንድነው? ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጥር 15 2013 ዓ.ም. በመተከል የተከሰተውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት የአካባቢውን ነዋሪዎች አሰልጥኖ በማስታጠቅ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ያደርጋል ስለማለታቸው ኢዜአ ዘግቦ ነበር። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በበኩሉ መተከል ዞን የአመራር ስብጥር በዞኑ የሚኖሩ የሌሎች ብሄር ተወላጆችን ታሳቢ ያላደረገ መሆኑ በዞኑ የጸጥታ ችግር እንዲባባስ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ መሆኑን በአካባቢው የተሰማራው የተቀናጀ ግብረ ኃይል አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። የካቲት 14 በተላለፈው ዘገባ ላይ የግብረ ኃይሉ አባል እና የሰላም ሚንስቴር ዲኤታ ፍሬዓለም ሽባባው፤ "ይህን ዞን ፈተና ውስጥ ያስገባው አንዱ ማዳላት ነው። ፊት አይቶ ማዳላት የመሪ ባህሪ አይደለም" ሲሉ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተደምጠዋል። ፖለቲከኛው አቶ አብዱልሰላምም የጠፋ ያለ አድልኦ ቢነገር እና ፍትሃዊነት ቢኖር ሰላም ማምጣት ይቻላል ባይ ናቸው። "አማራው እና ኦሮሞ ሲገደል ነው የሚነገረው እና ጉሙዝ ብዙ ሞቷል። ከዚህ በላይ ሞቷል። ተሰድዷል። ለጉሙዙ ድምጽ ሆኖ የደረሰበትን የሚናገርለት የለም። ስንት እንደሞተ፣ እንደቆሰለ፣ እንደተሰደደ መንግሥት እንኳን በአግባባቱ ለይቶ ያደረገው ነገር የለም። በግጭት ይሞታሉ። በረሃብም ይሞታሉ። የታሰሩትም ለሕግ አልቀረቡም" ይላሉ። እንድ አቶ አብዱልሰላም ከሆነ፤ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መፍትሄውን ማምጣት ችግር ይሆናል። "ሁሉም እኩል ካልታየ ችግሩ በቀላሉ ይቀረፋል የሚል እምነት የለኝም። ፍትሃዊነት ከሌላ ሰዎችን ወደመጥፎ ነገር ይገፋፋል" ይላሉ። "ችግሩ የፖለቲካ ችግር ነው። መፍትሄውም ፖለቲካ ነው" የሚሉት ደግሞ መብራቱ አለሙ (ዶ/ር) ናቸው። "ለአንዲት ዞን ተብሎ ኮማንድ ፖስት የተቋቋመው መስከረም 11 2013 ዓ.ም ነው። ችግሩ ግን በጭራሽ አልተፈታም። ሰዎች አሁንም እየተገደሉ ነው። ቤቶች እየተቃጠሉ ነው። ከብት እየተዘረፈ" ነው። የችግሩ መንስዔዎች ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ባለሃብቶች እንደመሆናቸው፤ መፍትሄው የሚሆነውም ፖለቲካ ነው ይላሉ። "ከሁሉም ብሄረሰብ የተውጣጡ ምሁራን እና የአገር ሽማግሌዎች ቁጭ ብለው ችግራቸውን መፍታት አለባቸው። በተናጠል በየሚዲያው የሚባለው የባሰ ያቀቅረናል" ይላሉ። ጠበቃው ተመስገን በበኩላቸው የችግሩ ዋነኛ ምክንያቶች ፖለቲከኞች እንደመሆናቸው መጠን ''ፖለቲከኞች እጃቸውን ካልሰበሰቡ" ሰላም አይወርድም ይላል። "ለማይደርሱላቸው ሕዝብ የርስት ስሜት እየቀሰቀሱ ችግር ውስጥ ከሚከቷቸው እጃቸውን ቢሰበሰቡ ይሻላቸዋል። በጉሙዝ በኩል ያሉትም ፖለቲከኞች ሕዝቡን ለአመጻ ከመቀስቀስ ካልተቆጠቡ ግጭቱ ሊቆም አይችልም" ይላል። ሌላኛው መፍትሄ የሚሆነው ይላል ተመስገን፣ ጉሙዞች በአገራቸው የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ ነው። "አሁን ላይ እኮ ገበያ ወጥተው ከሌላ ማህብረሰብ ጋር እየተገበያዩ አይደለም። በደህንነት ስጋት አገር ጥለው ወደ ሱዳን ተሰድደዋል። የእነሱን 'ኮንፊደንስ' መመለስ አስፈላጊ ነው" በማለት ሃሳቡን ያብራራል።
xlsum_amharic-train-261
https://www.bbc.com/amharic/51582957
ኮሮናቫይረስ፡ "ቻይና፣ ዉሃን በመሆኔ ደህንነቴ የተጠበቀ ነው"
ሄኖክ አምደማሪያም ኪዳኔ በቻይና ዉሃን ግዛት የምህንድስና ትምህርቱን መከታተል ከጀመረ አምስት ዓመት እንደሞላው ይናገራል። ወደ ዉሃን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቴክኖሎጂ የሄደው የመጀመሪያ ዲግሪውን ለመሥራት የነበረ ቢሆንም በዚያው ሁለተኛ ዲግሪውን ቀጥሎ መቆየቱን ለቢቢሲ ገልጿል።
[ "ሄኖክ አምደማሪያም ኪዳኔ በቻይና ዉሃን ግዛት የምህንድስና ትምህርቱን መከታተል ከጀመረ አምስት ዓመት እንደሞላው ይናገራል። ወደ ዉሃን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቴክኖሎጂ የሄደው የመጀመሪያ ዲግሪውን ለመሥራት የነበረ ቢሆንም በዚያው ሁለተኛ ዲግሪውን ቀጥሎ መቆየቱን ለቢቢሲ ገልጿል።" ]
ሄኖክ አምደማሪያም በቻይና ዉሃን ግዛት የምህንድስና ተማሪ ነው ሄኖክ በዉሃን ብቻ ወደ 300 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እንደሚገኙ ገልጾ፣ እርሱ በሚማርበት ዉሃን ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቴክኖሎጂ አርባ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ይናገራል። ሄኖክ የሚማርበት ተቋም በግዛቲቱ ከሚገኘው ዉሃን ዩኒቨርስቲ ቀጥሎ ሁለተኛው ነው። • ኮሮና ቫይረስ መጠሪያ ስሙን አገኘ • በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ህመምተኛ ተገኘ የቫይረሱ ወረርሽኝ ከመከሰቱ አስቀድሞ ከኢትዮጵያውያኑ ጋር በተለያዩ በዓሎች አከባበር ላይ ይገናኙ እንደነበር የሚያስታውሰው ሄኖክ፤ ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ ግን በስልክ ደህንነትን ከመጠያየቅ ባለፈ አብሮ ጊዜ ለማሳለፍ ምቹ አለመሆኑን ይገልፃል። የኮሮናቫይረስና ዉሃን ውሃን በየቀኑ ትለያያለች ይላል ሄኖክ፤ በፍጥነት የምታድግ ከተማ ናት። እንደርሱ አገላለጽ ዛሬ የታየ ባዶ ስፍራ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ህንፃ አልያም አትክልት ተተክሎበት የሚገኝባት፣ ሕይወት እስከነሙሉ ጣዕሟ የምትገማሸርባት ከተማ ነበረች። በከተማዋ የሚኖሩ ሰዎች ተግባቢ፣ ማኅበራዊ ሕይወቱ የሞቀ፣ ሁሉም በመልክም በልክም በዝቶና ሰፍቶ የሚገኝባት ነበረች። በሚማርበት ዩኒቨርስቲም ቢሆን ከቻይናውያን ውጪ ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ በላይ ከተለያዩ አገራት የሄዱ ተማሪዎች የሚገኙበት፣ የመልከ ብዙ ተማሪዎች መሰባሰቢያ መሆኗን ይገልፃል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽን ከመከሰቱ ጥቂት ቀደም ብሎ፤ ውሃን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ወታደራዊ መኮንኖች አውደ ርዕይን አዘጋጅታ፤ ለቻይናውያን አዲስ ዓመት ሽር ብትን እያለች ነበር። እንደድሮው ቢሆን ኖሮ ሰባት ቀን ፌሽታና ደስታ በመሆኑ ሁሉም በዚህ መንፈስ ውስጥ ይሆን ነበረ ይላል ሄኖክ። ሄኖክም ወደ ታይላንድ ሄዶ ለማሳለፍ ሻንጣውን አዘገጃጅቶ፣ የአውሮፕላን ቲኬት ቆርጦ እየተጠባበቀ እንደነበር ያስታውሳል። • የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና የአየር መንገዶች የገቢ ማሽቆለቆል ስጋት አንድ ቀን የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለመሸማመት ወደ ገበያ አዳራሽ ሲሄድ፤ ከኢትዮጵያውያን ጓደኞቹ በተጨማሪ ሌሎች ሰዎችም የመተንፈሻ አካላቸውን ሸፍነው ተመለከተ። ኮሮናቫይረስ፡ በዉሃን ተማሪ የሆነው ሄኖክ ህይወት በከተማይቱ ምን እንደሚመስል አስቃኝቶናል እርሱም ግራ ስለተጋባ "ከሰው ላለመለየት ብዬ የመተንፈሻ አካል መሸፈኛ ገዝቼ መጠቀም ጀመርኩ" ይላል። በኋላ ላይም ቤቱ ሳለ የታይላንድ ጉዞህ ተሰርዟል የሚል ኢሜልና ገንዘቡ መመለሱን የሚገልጽ መልዕክት ደረሰው። በዉሃን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ጎዳናዎቿ የሰው ጠኔ ያዛጋቸዋል። የገበያ አዳራሾቹ ሠው አልባ ሆነዋል። ወረርሽኙ እንደተከሰተ በሳምንት አንዴ ወይንም ሁለቴ ወጥቶ የሚያስፈልጉ ነገሮችን መሸማመት የሚቻል የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ እንቅስቃሴ ተከልክሏል ይላል። ስለ ኮሮናቫይረስ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ይለቀቃሉ የሚለው ሄኖክ፤ የሚማርበት ዩኒቨርስቲ ስለበሽታውም ሆነ ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ በማኅበራዊ ሚዲያ የቡድን መወያያቸው (ዊቻት) በኩል መረጃ እንደሚሰጣቸው ይገልፃል። ቤተሰቡም ቢሆን በየዕለቱ ከኢትዮጵያ እየደወለ ይጠይቃል። ዘወትር በየዜና አውታሩ የሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ሲገለጽ ሲሰሙ ስጋት እንደሚገባቸው ይናገራል። በየዕለቱ የእርሱ በሕይወት መኖርና በጤና መቆየት የእነርሱ ጭንቀት ነው። በቻይና የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደህንነታቸውን ለማወቅ መልዕክት እንደሚልክላቸው የሚናገረው ሄኖክ፤ መመለስ የሚፈልጉ ካሉ በሚል ቅጽ ልኮ ማስሞላቱን ይናገራል። "የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዜጎቹን ከዉሃን ለማውጣት የሚፈልግ ከሆነ የማልሄድበት ምክንያት የለም" ቢልም እዚያው ቻይና ውስጥ መቆየት ደግሞ ፍላጎቱ መሆኑን ይናገራል። "ቻይና በመሆኔ ደህንነቴ የተጠበቀ (ሴፍ) ነው ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም በሽታው እዚህ ስለተነሳ ከሌላው አገር የተሻለ ትንሽም ቢሆን እውቀቱም ሆነ ቴክኖሎጂው አላቸው ብዬ አስባለሁ" • ወደቻይና የተጓዙና የኮሮናቫይረስ ምልክቶች የታዩባቸው ሰዎች ተገኝተው ነበር ተባለ አገር ቤት ቢሄድ ቫይረሱ ያለበት እንደሆነ ለማወቅ ከአስራ አራት ቀን እስከ ሃያ ቀን ለይቶ ማቆያ ውስጥ ማስቀመጥ፣ ናሙናውን ወደ ደቡብ አፍሪካ ወስዶ ማስመርመር እንደሚያስፈልግም ይገልጻል። ሄኖክ እንደሚለው ባይታመምም የጥንቃቄ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። "እዚህ ያለው ነገር ቢታክተኝም ማንንም መውቀስ አልፈልግም" በማለትም ስሜቱን ይገልጻል። ቻይና ዉሃን ግን ቢያንስ ምርመራውና ሕክምናው አለ በማለት "ያልፋል ብዬም አምናለሁ፤ ይህ ሁሉ ያልፋል" ሲል ለቢቢሲ ተስፋውን ተናግሯል። እኛ እዚህ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እናደርጋለን ብሎም "ፈጣሪ ከእኛ ጋር ነው" ሲል ያክላል። ሄኖክ በዉሃን የተማሪነት ሕይወቱ ከትምህርት ባሻገር የተለያዩ ስፖርቶች ላይ ይሳተፋል ኑሮ በሰው ድርቅ በተመታች ከተማ ሄኖክ በዉሃን የተማሪነት ሕይወቱ ከትምህርት ባሻገር የተለያዩ ስፖርቶች ላይ ይሳተፍ እንደነበር ይገልፃል። አሁን ግን በአንድ ክፍል ውስጥ ከዩኒቨርስቲ ጓደኛው ጋር ቀኑን ሙሉ በር ዘግቶ ማሳለፉ ድብርትና እንቅልፍ እንደለቀቀበት ይገልፃል። "ከዚህ በፊት ስፖርት እሠራ ነበር። እዋኝ ነበር። ቅርጫት ኳስ ከጓደኞቼ ጋር እጫወት ነበር። አሁን ይህ ሁሉ ናፍቆኛል። ከጓደኞቼ ጋር ሻይ ቡና ማለት፣ ትምህርት ሁሉ ናፍቆኛል። እዚህ ባለው ነገር ደስተኛ ነበርኩ፤ አሁን ግን ሁሉም ነገር ጨለማ ውጦታል።" • ቀጣሪዎች ሠራተኞቻቸውን መሰለል ይፈቀድላቸዋል? አሁን በማደሪያ ክፍላቸው ውስጥ ቀኑን ሙሉ ምግብ በማብሰል፣ መጻሕፍት በማንበብ እና ፊልም በማየት እንደሚያሳልፉ ይናገራል። "አገር ቤት በጣም ናፍቆኛል" የሚለው ሄኖክ፤ ሙሉ ቀን አልጋ ላይ መዋሉ ይጨንቃል ሲልም የሚሰማውን ለቢቢሲ አጋርቷል።
xlsum_amharic-train-262
https://www.bbc.com/amharic/news-54744135
በኮቪድ-19 ማዕከላት የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች የተገባልን ቃል አልተፈጸመም አሉ
በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር በሚተዳደሩ እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በተቋቋሙ የሕክምና መስጫዎች ውስጥ የሰሩ እና የሚሰሩ የሕክምና ባለሙያዎች በተለያየ ጊዜ የተገባላቸው ቃል እንዳልተፈጸመ በመግለጽ ቅሬታቸውን አቀረቡ።
[ "በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር በሚተዳደሩ እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በተቋቋሙ የሕክምና መስጫዎች ውስጥ የሰሩ እና የሚሰሩ የሕክምና ባለሙያዎች በተለያየ ጊዜ የተገባላቸው ቃል እንዳልተፈጸመ በመግለጽ ቅሬታቸውን አቀረቡ።" ]
የጤና ባለሙያ ቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ኮሮናቫይረስ ወረርሽን በኢትዮጵያ መገኘቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ መንግሥት በሕክምና ባለሙያዎችን ላይ የሚኖረውን ጫና ከግምት በማስገባት ከባለሙያዎቹ ጎን እንደሚቆም አስታውቆ ነበር። በዚህ መሠረትም የሚንስትሮች ምክር ቤት ግንቦት 14/2012 ዓ. ም ባካሄደው 83ኛ መደበኛ ስብሰባ የኮቪድ-19 ወረርሽንን በመከላከል እና የህክምና አገልግሎት በመስጠት በቀጥታ ለሚሳተፉ የጤና ባለሙያዎች ልዩ አበል እንዲከፈላቸው ውሳኔ ማሳለፉን ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ምክር ቤቱ እንደሙያቸው እና ሥራቸው ሁኔታ ከ1ሺህ150 ብር ጀምሮ እስከ 300 ብር በየቀኑ እንዲከፈላቸው ነው የወሰነው። በዚህ መሠረትም በፌደራል ደረጃ የሚተዳደሩት እንደ ኤካ ኮተቤ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል እና ሚሊኒየም ሆስፒታል ያሉት የጤና ተቋማት እና አንዳንድ ክልሎች ወሳኔውን መሠረት በማድረግ ለባለሙያዎቻቸው ልዩ አበል እንደከፈሉ ባለሙያዎቹ አስታውቀዋል። ሆኖም በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር ከሚተዳደሩ ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች መከካከል የተወሰኑት የኮሮናቫይረስ ህክምና መስጫ ማዕከል ሆነው እያገለገሉ ቢሆንም ለባለሙያዎች እስካሁን ምንም ዓይነት ከፍያ እንዳልተፈጸመ የጤና ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ግንቦት አጋማሽ መመሪያው ከወጣ በኋላ የባለሙያ እና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች የአበል ዝርዝር በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ደረጃ አልወጣ ሲል ጠብቀን መታገል ጀመርን" ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት በጉለሌ ክፍለ ከተማ የጉቶ ሜዳ ኮቪድ -19 ማዕከል ሠራተኛ የሆኑት አቶ ዲኖ ጀማል ናቸው። ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ከእያንዳንዱ የኮቪድ -19 ህክምና ማዕከል 3 ተወካይ በመምረጥ አቤቱታቸውን ለተለያዩ የመንግሥት ተቋማት አስገብተዋል። ወኪሎቻቸውን ያላሳወቁትን ሳይጨምር 1158 ሠራተኞች ወኪሎቻቸውን መርጠው ልዩ አበሉ ለምን እንዳልተከፈላቸው መጠየቃቸውን ገልጸዋል። ኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ ተብሎ ሰዉ በሚሸሽበት ወቅት ጭምር ሙያዊ ግዴታ በሚል ወደ ሥራ መግባታቸውን የገለጹት የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ባልደረባ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሰሩ ጤና ባለሙያዎች ተወካይ የሆኑት አቶ ከድር ሳሊህ ናቸው። . ኮቪድ-19 ያስተጓጎለው የኢትዮጵያ የካንሰር ህክምና . በኢትዮጵያ በአስክሬን ምርመራ ኮቪድ-19 መገኘቱ ምን ያመላክታል? "ሁሉም እኛን ማሞካሸት ጀመረ። በመሃል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኮቪድ -19 ላይ ለሚሰሩ ልዩ አበል ይከፈል አለ። እኛ ሙያዊ እና ሰብዓዊነት ነው ያስገባን። ክፍያ አይተን አይደለም። አንዳንድ ቦታ ይከፈላል ሌላ ቦታ አይከፈልም" ብለዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ጠቅላላ ሐኪም በበኩላቸው በኮሮናቫይረስ ማዕከል ከአምስት ወር በላይ እንደሠሩ እና አሁን ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን አስታውቀዋል። መጀመሪያ ላይ ህብረተሰቡ በነበረው ፍራቻ እና በተለያየ ምክንያት ብዙዎች ከቤት እና ለተወሰነ ቀን ብቻ ከሥራ ቦታቸው እንዲሠሩ በተደረገበት እና ትርፍ ክፍያ ባልነበረበት ወቅት ጭምር መሥራት መጀመራቸውን ገልጸዋል። ሆኖም ሥራ ጀምረው ከሁለት ወራት በኋላ ተግባራዊ እንዲሆን የወጣው መመሪያ ተባግባራዊ አለመሆኑ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው አስታውቀዋል። "ማህበረሰቡ ባለሙያው ብዙ ክፍያ እንዳለው ነው የሚያውቀው። የማይከፍሉ ከሆነ ማህበረሰቡ ማወቅ አለበት። ቢከፍሉን ጥሩ ነው። የማይለከፍሉ ከሆነ ግን አንከፍልም ግን እናመሰግናለን የሚል ደብዳቤ ቢሰጠን። ከህክምና ጣቢያው ስወጣ በግሌ የሚያስጠሉ ፈተናዎች ነበሩት። 'የት ነበርሽ?' ምናምን የሚሉት ነገሮች ትንሽ ቅስም ይሰብራል" ብለዋል ሐኪሟ። እንደ አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ልዩ አበሉ ባይከፈልም በፌደራል ስር በሚገኙ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከላት እና በአንዳንድ ክልሎች ተግባራዊ መደረጉን ግን እነዚህ ባለሙያዎች ገልጸዋል። "አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሄደው ያነጋገሩ ባልደረቦች አሉ። እነሱ ግን በቃ እንደማይገባን ነገሩን ያሉት። በጀት የለንም አሉ። በጀት ከሌለ መጀመሪያም ውሳኔው (የሚንስተሮች ምክር ቤት) አይፈቅድም" ብለዋል። ውሳኔውን መሠረት በማድረግ ጤና ቢሮው ክፍያውን እንዲፈጽምላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ተገቢውን ምላሽ አላገኙም። ክፍያው ሁለት ቢሊዮን ብር ገደማ ስለሚሆን እንደሚክብዳቸው፤ ከኮቪድ-19 ማዕከላት ውጭ ያሉት ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ጭምር በመግለጽ እነሱን ስለማያካትት ለአፈጻጸም አመቺ አይደለም ተብሎ ከጤና ቢሮው እንደተመለሰላቸው አቶ ዲኖ አስታውቀዋል። የጤና ጥበቃ ሚንስትር ደግሞ ጉዳዩ እንደማይመለከተው እንዳስታወቃቸው እና ለከተማው ካቢኔ ደብዳቤ አስገብተው ምላሽ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የሚንስትሮች ምክር ቤት በመመሪያው ያወጣው በኮሮናቫይረስ የተያዙን የሚያክሙ፣ በለይቶ ማቆያ ህክምና በመስጠት ላይ የሚገኙ፣ ቀጥታ ተጋላጭ ሆኑ ባለሙያዎች በሚል በዝርዝር ለይቶ ማስቀመጡን ገልጸዋል። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ግን አሠራሩን በመቀየር ቢሮ የሚሠሩትን ተጠቃሚ በማድረግ ሌላ ውሳኔ ተግባራዊ መደረጉን ኮንነዋል። 'የወጣው ውሳኔ ሁሉንም ባያካትትም ሁሉም የህክምና ባለሙያ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ነው' በሚል ቢሮ ውስጥ ያሉትንም ለመጥቀም የሚመስል ሁሉንም የሚያካትት አሠራር ለመፍጠር መሞከሩን አቶ ከድር አስታውቀዋል። ስለ ጉዳዩ ለሲቪል ሰርቪስ ያቀረቡት ቅሬታ ደግሞ 'ካልተስማማችሁ መልቀቅ ትችላላችሁ ብዙ ሥራ የሚፈልግ ባለሙያ አለ' በሚል ምላሽ አንደተሰጣቸውም ገልጿል። የቤት ጉዳይ የጤና ባለሙያዎቹ ሌላ ቅሬታ ደግሞ የቤት ጉዳይ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ተገንብተው የተጠናቀቁና በግንባታ ላይ ያሉ በርካታ ቤቶች መኖራቸውን ጠቅሶ፤ በራሳቸውም ሆነ በባለቤቶቻቸው ስም ቤት እንደሌላቸው የሚገልጽ ማስረጃ እንዲያቀርቡ መጠየቁን አስታውሰዋል። መረጃውን ለሟሟላትም ውጣ ውረድ በማሳለፍ በተሰጣቸው ጥቂት ቀናት መረጃውን ማስገባታቸውን ገልጸዋል። ዕጣ እንደሚወጣላቸው በተነገራቸው ሰሞን የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረው ችግር ምክንያት መደናቀፉን አስታውቀዋል። ምላሽ እንገኛለን በሚል ቢጠብቁም የቀድሞው ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከቦታቸው ተነስተው ወደ ሌላ ቦታ ተቀይረዋል። . የያዘዎት ጉንፋን ወይስ ኮሮናቫይረስ መሆኑን እንዴት መለየት ይችላሉ? . በለይቶ ማቆያ ያሉ የጤና ባለሙያዎች መሠረታዊ ፍላጎታችን እየተሟላ አይደለም አሉ . በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኋላ የተሰጣቸው ምላሽ 'ዳታ' ለመስብሰብ ነው የሚል ነበር። ቤት እናገኛለን በሚል መረጃ ለማቅረብ ተሯሩጠው 'ለዳታ ነው' መባላቸው ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ጠቅሰዋል። መጀመሪያ ተስፋ ስለተሰጣቸው እንጂ ያሰቡት ባይሆንም ቃል ከተገባ ደግሞ ሊፈጸም ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል። ሰኔ 2012 ዓ. ም የጤና ባለሙያው በሦስት ቀን ውስጥ በራሳቸው እና በትዳር አጋራቸው ስም ቤት እንደሌላቸው የሚገልጽ ማስረጃ አምጡ መባላቸውን አቶ ዲኖ ገልጸው "አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ለህክምና ባለሙያዎች ቤት ሊሰጥ ነው ሁሉ ብለዋል" ሲሉ ተናግረዋል። "አንዳንድ ታካሚዎች ቤት ተሰጣችሁ ደስ ብሎናል እስከሚሉ ድረስ። እኛ ላይ የማታለል ሠራ ነው የሰረቡን" ብለዋል። በራሳቸውም ሆነ በትዳር አጋሮቻቸው ስም ቤት እንደሌላቸው የሚያሳይ ማስረጃ አስገብተው ዕጣው ሊወጣ አካባቢ በአርቲስት ሃጫሉ ሞት ምክንያት ዘገየ ሲሉ ያስታወሱት አቶ ከድር ናቸው። ከህክምና ቦታቸው ወጥተው ሰዎች ከኮቪድ-19 ማዕከላት በመምጣታቸው ብቻ እያገለሏቸው እና በአጭር ቀናት ውስጥ ያስገቡትን ማስረጃ "ለዳታ ነው። ምን ያህል ቤት እንደሌላችሁ ለማወቅ ነው እንጂ ቤት ይሰጣችኋል አልተባለም" መባሉ እንዳሳዘናቸውም አስታውቀዋል። የህክምና ዶክተሯ በበኩላቸው "ቤት እንሰጣለን ብለው ወከባ ፈጠሩ። እንደ ግለሰብ ሳይሆን እንደ ጤና ባለሙያ ግን ከቤት ውጣ የተባለ ሃኪም አለ። በኮቪድ-19 ጊዜ ቤት ልንሰጥ ነው ብለው የኑሮ ውድነት እንዲመጣ፤ ጤና ባለሙያዎች የሚከራየውን ቤት በእጥፍ እንዲጨመረበት ነው ያደረጉት። ይከፈላቸዋል በሚል ብቻ የኑሮ ውድነት እንዲጨምርበት ተደርጓል" ብለዋል። የገቢ ግብር ቅነሳ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት ጠቅላላ ሐኪም የገቢ ግብር እስካሁን እንዳልተነሳ እና በየትኛውም ህክምና ተቋም የሚከፈለው 'ዲዩቲ' (የሥራ) አበል አንኳን በአግባቡ እንዳልተከፈላቸው አስታውቀዋል። "ሁሉም የህክምና ባለሙያዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ናቸው ከተባለም ይህ መሸፈን ያለበት በጤና መድህን ነው። ቤተሰቦቻችን እየተከፈላችሁ ነው። ቤተሰብ እና ጓደኞቻችን የት አደረጋችሁት እያሉ ነው። እነሱ ባወጡት ህግ ነው የጠየቀውነው። ለምን ይሸራርፉታል በሚል። ህዝቡ በአዋጁ እየተጠቀማችሁ ነው እያለ ነው። ቤተሰብም ጓደኛም ግብርም ቀርቶላችኋል ይላል" ብለዋል አቶ ከድር። ይህም ሆኖ ግን እስካሁን የገቢ ግብር ቅነሳውም ቢሆን ተግባራዊ አለመደረጉን ጠቁመዋል። ቢቢሲ በመጨረሻም ለባለሙያዎቹ ምላሽ ካላገኛችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል? በሚል ላቀረበላቸው ጥያቄ የሚከተለውን መልሰዋል። "ሥራ ለማቆም አላሰብንም። ባለሙያው ሥራ እንዳያቆም ነው ተወካይ የተላከው። ተወካዮች ኮሚቴ መረጡ። እነሱ ናቸው የሚንቀሳቀሱት። ኮሚቴዎቹ ሥራም እየሠሩ ነው። በሚዲያ እያሳወቅን ነው ህዝቡ እንዲያውቅልን። በኮሚቴም በአባላትም ደረጃ ወደፊት ወደ ፍርድ ቤት ልናመራ እንችላለን የሚል ሃሳብ ነው ያለው" ያሉት አቶ ዲኖ ናቸው። "አገራዊ እና ሙያዊ ግዴታ ነው። እኔ ሥራ ባቆም የሚሞቱ ሰዎች አሉ። ይሄ ባለሙያው ምሎ የወጣበት ስለሆነ ሥራ ማቆም አይችልም። አመጽም አይኖርም። እየተረገጥክ ጥቅመህን አሳልፈን እንድትኖር ነው የሚያደርጉት" ያሉት ደግሞ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሐኪም ናቸው። የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምላሽ ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ናቸው። እንደ ዶ/ር ሙሉጌታ ከሆነ ልዩ አበሉን ለማስፈጸም መመሪያ ከወጣ በኋላ አፈጻጸም ላይ ችግር ገጥሟቸዋል። በመጀመሪያው የልዩ አበሉ የተፈቀደው የኮቪድ -19 ማዕከላት ውስጥ ለሚሠሩ እና በመከላከል ላይ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች በሚል ነው። እንደ ምክትል ኃላፊው ከሆነ ግን በዚህ ውስጥ ሁሉም የጤና ሠራተኞች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየተሳተፉ ነበር አሁንም በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። በዚህ ምክንያት ለማስፈጸም አስቸግሮናል ይላሉ። በተጨማሪም ደግሞ ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በራሳቸው አውድ እንዲጠቀሙበት መመሪያው እንደሚፈቅድ ገልጸው የተለያዩ አማራጮችን በመውሰድ ለመተግበር ሙከራ መደረጉን አስታውቀዋል። ሆኖም ሙከራዎቹ ጥቂት ሠራተኞችን ብቻ የሚጠቅሙ ሆነው ተገኝተዋል ይላሉ። "መሬት ላይ ስናወርደው ጽዳቱም፣ ሹፌሩም ድንገተኛ ክፍል የሚሠራው ይገባዋል። ተመላላሽ ህክምና፣ ቀዶ ጥገና ክፍል፣ ማዋለጃ የሚሠሩና ሁሉም ላይ ያሉ ሠራተኞቻችን ከኮቪድ -19 ጋር ተጋፍጠው እየተከላከሉ እየሠሩ ነው። እንተግብረው ካልን ደግሞ ለሁሉም ነው መተግበር ያለብን" ሲሉ ያስረዳሉ። ሌላው ደግሞ ለትግበራ ያስቸገረው የበጀት ጥያቄ ነው። "የከተማ አስተዳድሩ ላይ ትልቅ ወጪ አለ። ከተማ አስተዳደሩ ያንን መሸከም የሚችል አይደለም" ብለዋል። ከዚህ በተሻለ አማራጭ ተደርጎ የተወሰደው ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ከገባበት ወቅት አንስቶ በከተማ መስተዳድሩ በጤና ዘርፍ ለሚሠሩ ባለሙያዎች በሙሉ የግብር ቅነሳ ማድረግ ነው። "ሁሉም የጤና ዘርፍ ሰራተኞች ራሳቸውም አደጋ ላይ ጥለው ነው እየሠሩ ያሉት። ኮቪድ-19 ላይ ቅዳሜ እና እሁድ ገብተው የሚሠሩ አሉ። ገብተው የሚያድሩ አሉ። ይሄንን የትርፍ ሰዓት ክፍያቸውን እንሰጣለን" ሲሉ ተናግረዋል ። አክለውም "ከተማ መስተዳድሩ ታክስ ቅነሳ ወይም ራሱ መስተዳድሩ ታክሱን ይከፍላል ማለት ነው። ስለዚህ ኮቪድ-19 ከጀመረበት ከመጋቢት ጀምሮ ኮቪድ-19 ከስጋትነት እስከሚወጣበት ድረስ ሁሉም የጤና ሠራተኞቻችን ያንን ከግብር ተቀንሶላቸው መስተዳድሩ ራሱ እየሸፈነ በዚያ መንገድ እናስተናግድ ተብሎ ተወሰነ" ብለዋል። መመሪያው ሲወጣ መጀመሪያ ድንገተኛ የአደጋ መቆጣጠር ዘርፍ ላይ የሚሠሩ የተወሰኑ ሠራተኞችን ብቻ ታሳቢ አድርጎ እንደነበር ዶ/ር ሙሉጌታ አስታውቀው፤ የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ ሲሄድ ብዙ ባለሙያዎችን ከማሳተፉም በላይ መመሪያዎችም መቀያየራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ኮሮናቫይረስ ላይ የሚሠሩ ሠራተኞች ቁጥር መጨመርም ሌላው ምክንያት ነው። ቸግሩን ለመቅረፍ ከሠራተኞች ጋር በተደጋጋሚ መወያየታቸውን አንስተው "ብዙ የጤናው ዘርፍ ሠራተኛ በውሳኔው ላይ ጥሩ እይታ እንዳለው ነው ያየነው" ብለዋል። ሆኖም ቅሬታዎች መኖራቸውን ጠቁመው ጤና ቢሮው የወሰደውን እርምጃ ሌሎችም (ክልሎች እና ጤና ጥበቃ) የመከተል ነገር እንዳለ መመልከታቸውን ጠቁመዋል። ከዚህ በተቃራኒ ሁላችንም ለአደጋ ተጋልጠን በምንሠራበት ለጥቂቶች ብቻ መከፈል የለበትም የሚሉ ጥያቄዎች መነሳታቸውን በተመለከተ፤ "እኛም አደጋ ላይ ወድቀን እየሠራን ለጥቂቶች ብቻ እየተከፈለ ታሳቢ አለመደረጉ ተገቢ አይደለም ብለው ደግሞ በተቃራኒው የሚጠይቁ አሉ። የግድ ኮቪድ-19 ማከሚያ ቦታ ብቻ ነው ወይ እኛም እየተጋፈጥን ነው የሚሉ አሉ" ሲሉ አስረድተዋል። ገቢ ግብርን በተመለከተ ደግሞ በከተማ መስተዳድሩ ሥር በሚገኙ ሁሉም ጤና ተቋማት መረጃ የማሰባሰብ ሥራ መከናወኑን አስታውቀው በጥቂት ቀናት ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል። ህክምና ባለሙያዎቹ ቤት ይሰጣችኋል ተብለን በተገባልን ቃል መሠረት አልተፈጸመልንም ለሚለው ቅሬታቸውም ምላሻውን እንደሚከተለው ሰጥተዋል። "ቤት ይሰጣል የሚል እንደ መስተዳደርም እንደ ቢሮም የለም። መረጃ ሊሰበሰብ ቤት ያለውን እና የሌለው የጤና ባለሙያ መረጃ እንዲያዝ ከተማ መስተዳደሩ መጠየቁን ነው እኔ የማውቀው። መረጃውን ጠይቁ አለ መረጃውን ሰብስበን ልከናል። ቤት ይሰጣቸዋል የሚል ነገር ግን የለም" ብለዋል።
xlsum_amharic-train-263
https://www.bbc.com/amharic/44123096
"የናንዬ ሕይወት" የአይዳ ዕደማርያም ምስል ከሳች መፀሐፍ
ማንደጃው ላይ የተጣዱ አራት ፍሬ ከሰሎች ወርቃማ ቀለም ያለው እሣት ይተፋሉ፤ አያቴ ከዕጣኑ ቆንጠር በማድረግ እፍሙ ላይ ብታኖረው ጊዜ ደስ የሚል ሽታ አካባቢውን ያውደው ጀመር። መቁያው ላይ እሣት እየመታው ካለው ቡና ጋር ሲቀላቀል ደግሞ መዐዛው እንደው ልብ የሚሰውር ሆነ፤ ቤቱ በሽታ ቀለማት ተውቦ ሞቅ ብሎ ሳለ ውጭው ግና በጳጉሜ ዝናብ እና ብርድ ይንቀጠቀጥ ነበር. . .
[ "ማንደጃው ላይ የተጣዱ አራት ፍሬ ከሰሎች ወርቃማ ቀለም ያለው እሣት ይተፋሉ፤ አያቴ ከዕጣኑ ቆንጠር በማድረግ እፍሙ ላይ ብታኖረው ጊዜ ደስ የሚል ሽታ አካባቢውን ያውደው ጀመር። መቁያው ላይ እሣት እየመታው ካለው ቡና ጋር ሲቀላቀል ደግሞ መዐዛው እንደው ልብ የሚሰውር ሆነ፤ ቤቱ በሽታ ቀለማት ተውቦ ሞቅ ብሎ ሳለ ውጭው ግና በጳጉሜ ዝናብ እና ብርድ ይንቀጠቀጥ ነበር. . ." ]
«በዕለተ ሩፋኤል ዝናብ ከጣለ ውሃው የተቀደሰ ነው» ትል ነበር አያቴ። «ልጅ እያለን የቅዱስ ውሃው በረከት ያገኘን ዘንድ ልብሳችንን አውልቀን በዝማሬ በመታጀብ ጭቃው ላይ እንቦርቅ ነበር። ቀስተ ደመናው ተሩቅ የሚታየን ተሆነ ደግሞ ማርያም መቀነቷን ሰማዩ ወገብ ላይ አስራለችና ይበልጥ ደስ ይለን ነበር. . .» የናንዬ ሕይወት. . . ከአንድ ክፍለ ዘመን ቀደም ብሎ አንዲት ልጅ በሰሜን ኢትዮጵያዊቷ የጎንደር ከተማ ተወለደች። ገና 8 ዓመቷ ሳለ በሁለት አስርት ዓመታት ከሚበልጣት ሰው ጋር ትዳር እንድትመሠርት ሆነ። በርካታ ልጆችንም አፈራች። የጣልያን ዳግም ወረራ፣ የቦምብ ናዳ፣ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አልፋ እና ኦሜጋ፣ አብዮት እና የእርስ በርስ ጦርነት ይህች ሴት በዚህች ምድር በቆየችባቸው 95 ዓመታት ውስጥ ያስተናገደቻቸው ክስተቶች ናቸው። 'The Wife's Tale' ወይንም በግርድፍ ትርጉሙ 'የሚስት ትረካ' በሚል ደራሲና ጋዜጠኛ አይዳ ዕደማርያም የፃፈችው መፅሐፍ በእነዚህ 95 ዓመታት አያቷ የተመኙ ያሳለፉትን አስደናቂ የሕይወት ውጣ ውረዶች የሚዳስስ ጠርቃ ያለ ጥራዝ ነው። ኮራ ጀነን ያሉ ቀሳውስት፣ ሃገር ወዳድ ወታደሮች፣ የባለቤቷ እሥርና እንግልት፣ ፍትህን ፍለጋ፣ እመበለትነት. . .ብቻ ከልጅነት እስከ እውቀት የተመኙ ያየችውን ቆጥሮ መዝለቅ ውሃ እንደ መፍጨት ነው። አፄውና እቴጌይቱ፣ ምሁራንና መነኩሳት፣ የማርክስ አብዮተኝነት አቀንቃኞች እንዲሁም ባንዳዎች አይዳ 'ናንዬ' ብላ በምትጠራት አያቷ ሕይወት መስኮት የሚቃኙ የእውነተኛው ዓለም ገፀ-ባህርያት ናቸው። 'ዘ ዋይፍስ ቴል' የአንዲት አትዮጵያዊት ሴት የክፍለ ዘመን ትረካ ብቻ ሳይሆን የሃገሯ ታሪክ የክፈለ ዘመን ትውስታም ነው" ትላለች አይዳ ስለመፅሃፉ መናገር ስትጀምር። "ትዝ ይለኛል የዛሬ 20 ዓመት ገደማ ነበር የናንዬን ሕይወት መመዝገብ የጀመረኩት፤ ቢሆንም እንዲህ ወደ ታሪክ ገላጭ ጥራዝ እቀይረዋለሁ የሚል እሣቤ አልነበረኝም" በማለት የመፅሐፉን መፀነስ ታወሳለች አይዳ። "ብዙ ጊዜ ታሪክ ነጋሪ ሆነው የምናያቸው በጦርነት አውድማ የተሳተፉ አሊያም ሥልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች ናቸው። ነገር ግን ታሪክ ሊታይ የሚገባው በተለምዶ ተራ ሰው ብለን ከምንጠራው ግለሰብ ዓይን ነው" ስትል ትከራከራለች። "የናንዬ ሕይወት የሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሕይወት ነው፤ ለዚህም ነው ታሪክ ያለው ብዙም እውቅና ካለገኙ ግለሰቦች ጓዳ ነው ብዬ የምለው። መነገርም ያለበት በእነዚህ ሰዎች አንደበት ነው።" ጎንደር ስለኢትዮጵያ ታሪክ በተወሳ ቁጥር ስሟ ይነሳል፤ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ አንድ መዘክር ሆናም ትጠቀሳለች። የሃገሪቱ ርዕሰ-መዲና ሆናም አገልግላለች፣ በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነትም ትልቅ ሥፍራ የሚሰጣት ቦታ ናት፤ ጎንደር። የየተመኙ ውልደት ጎንደር እንደመሆኑ 'ዘ ዋይፍስ ቴል' ጉምቱውን የታሪክ መቼት ያደረገው በዚህች ታሪካዊ ከተማ ነው። በተፈጥሮ ፀጋ የታደለችው ጎንደር የጥራዙ ትልቅ አካል መሆኗ መፅሐፉ በታሪክ፣ እምነት እንዲሁም ቀለማት ድምቆ የተዋበ እንዲሆን ረድተውታል ትላለች አይዳ። "እርግጥ ነው አዲስ አበባም የናንዬ ሕይወት ትልቅ አካል ናት፤ ቢሆንም ግማሽ ያህል ሕይወቷን ያሳለፈችው ጎንደር ነው። እትብቷ የተቀበረውም እዚያው ጎንደር ነው" የምትለው አይዳ መፅሐፉ በታሪክ የበለፀገ ሆኖ አገኘው ዘንድ ጥናት ለማድረግ ጎንደር ብዙ ጊዜ አሳልፌያለሁ ስትልም ትዘክራለች። ጉዞ ወደ አዲስ አበባ «እኔ ምለውን ትደግሚያለሽ» ቄሱ ተናገሩ። «ቢታመም»...ቢታመም፤ «ቢጎሳቆል»...ቢጎሳቆል፤ «ክፉ ቢገጥመው፣ ቢደኸይ፣ ቢሞት እንኳ...አልክደውም»...አልክደውም። የተመኙ በ20 ዓመታት ከሚበልጣት፤ ከገጣሚና መንፈሰ ብርቱ የቤተስኪያን ሰው ሊቀ ካህናት አለቃ ፀጋ ተሻለ ጋር ጎጆ ትቅለስ ዘንድ ሆነ። ከፍርግርጉ በስተጀርባ ያለ ባሏን ለመጠየቅ በሄደች ጊዜ እጅግ ከፍቶት አገኘችው፤ «ወይኔ ልቤን፤ አይዞህ...እሽ እኔ ምን ላድርግ? ወይ አዲሳባ ተሚሉት ሃገር ልሂድ እንዴ?» አለቃ ፀጋ ሃሳቡን አላወገዘውም። «ወደ አዲሳባ ሂጂ፤ እከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ እንጉሱ ጋር ሄደሽ መበደሌን ንገርሊኝ፤ ነፃ አውጭኝ።» የሕይወት ምዕራፍ ወዳላሰቡት ሆነና የተመኙ ለእሥር የተዳረገ ባልተቤቷን ነፃ ለማውጣት አዲሳባ ከሚሉት የማታውቀው ዓለም መሄድ ግድ የሆነባት። ሰው በሰው ላይ የሚሄድበት ምድር. . .. መኪና ከየት መጣ ሳይሉት ጥሩንባውን እየነፋ የሚክለፈልፍበት ሃገር. . .አዲስ አበባ። የየተመኙ ወደ አዲሳባ ማቅናት ጉዳይ ስለባሏ ፍትህ ለመጮህ ቢሆንም ተቆጥሮ የማያልቅ ጉድ አይታበታለች። የገበያው ግርግር፣ የተማሪ ጥድፍያ፣ የዘመድ ዓይን. . .ኧረ የቱ ተነግሮ የቱ ይተዋል? ማርያም ማርያም. . . 1930 ዓ.ም ጎንደር ከተማ፤ የተመኙ ምጡ ቢጠናባት ጊዜ እንደ ሃገሬ እና ሃገሯ እናቶች ማርያምን አጥብቃ ትለማመን ጀመር። ባለቤቷ ሊቀ ካህናት አለቃ ፀጋ ተሻለ ልጃቸውንም የልጃቸውንም እናት እንዳያጡ ስጋት ቢገባቸው ወደአምላካቸው ቀና ብለው አጥብቀው ይጸልዩ ነበር። የአካባቢው ሰው የአለቃን ቤት ሞልቶታል፤ ሁሉም ተጨንቋል። በቤቱ የተገኙ ቀሳውስትም ከድርሳነ ሩፋኤልና ተዓምረ ማርያም ላይ ጸሎት ያሰሙ ይዘዋል። የተመኙ እንዲህ የምጥ ጭንቅ ውስጥ ሆና ሁለት ቀናት አለፉ። ሦስተኛም ቀን ሆነ፤ የተመኙ እንቅልፍ ወሰድ መለስ ያደርጋት ይዟል። ሦስተኛውም ቀን እንዲሁ ባለ ስሜት ካለፈ በኋላ ሌሊት ላይ ወንድ ልጅ ተገላገለች። መጀመሪያ ጨቅላው አልንቀሳቀስ አልላወስ ይልና የሁሉም ልብ በድንጋጤና ጭንቀት ይዋጣል፤ አዋቂዋ አዋልጅ ግን አልደነገጡም። በንጡህ ጨርቅ አርገው ጨቅላውን በውሃ ሲያብሱት አንቀላፍቶ የነበረው እንደው ንቅት ይልና ጣቱን መጥባት ተያያዘው፤ ቤቱም በደስታ ተሞላ። ልጁም እደማርያም ተብሎ ይጠራ ተባለ፤ የማርያም እድ (እጅ) እንዳማለት። ፕሮፌሰር እደማርያም ፀጋ በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሕክምና ታሪክ ሉዓላዊ ሥፍራ ከሚሰጣቸው ጠበብት ሐኪሞች አንዱ ነበሩ። እርሣቸው ደግሞ አይዳን ወለዱ። 'ዘ ጋርዲያን' ለተሰኘው ጋዜጣ የምትሰራው አይዳ ስለ አያቷ አውርታ የምትጠግብም አትመስል። "ምንም እንኳ አብዛኛውን የሕይወቴን ክፍል የኖርኩት በምዕራባዊው ምድር ቢሆንም ከአያቴ ጉያ መጥፋት አልሻም ነበር" ትላለች። "ቢያንስ ደውዬ ሳናግራት ደስታ ይወረኛል። ኢትዮጵያ እያለሁ ቤታችን ስትመጣ እንደው አካባቢው አንዳች ኃይል ይላበሳል። በቡና መዓዛ የታወደ መሳጭ ታሪክ መስማትን የመሰለ ነገር የለም።" "ምንም እንኳ የናንዬ ታሪክ ልብ በሚሰብሩ ኹነቶች የተሞላ ቢሆንም ውጣ ውረዱን አልፋ አስደናቂ ሕይወት መምራት ችላለች፤ የልቧን ደስታም ሳትሸሽገው ኖራለች። ይገርምሃል ልብ በጣም ንፁህ ነው፤ ባህርይዋ ደግሞ በአስደናቂ ድርጊቶች የተሞላ። ደግሞ መደነስ ትወድም ትችልም ነበር። በሚያስለቅሰው ታለቅሳለች፤ በሚያስቀው ትፈነድቃለች። ሕይወት በሙሉ ለመኖር ሰስታ፤ ስሜቷን ለመግለፅ ፈርታ አታውቅም።" 'ዘ ዋይፍስ ቴል' በበርካቶች ዘንድ የሚነበብ ብቻ ሳይሆን የሚታይ ታሪክ ያዘለ ተብሎ ተደንቋል። እኔም መፅሓፉን አነበብኩት፤ ኧረ እንድያውም ተመለከትኩት። እንደው ቃላቶችሽ እንዴት ቢካኑ ነው እንዲህ ውብ ቀለም የተላበሱት ስልም ጠየቅኳት አይዳን። ''ዕድሜ ለአያቴ'' አለችኝ። ''ታሪክ ስትነግረኝ እንደምትስልልኝ ሁሉ እመለከተው ነበር፤ እኖረውም ነበር። መንገዱ፣ ገበያው፣ ልዩ ምልክቱ፣ ሳሩ ቅጠሉ ጤዛው. . .ብርት ብሎ ይታየኛል። እኔም ቁጭ ብዬ እሷን በመመሰጥ ማድመጥና በመቅረፀ-ድምፄ ማስቀረት የዕለተለት ሥራዬ ሆነ።'' "ናንዬ እኮ ታሪክን በመናገር ብቻ የተካነች አይደለችም፤ በመኖርም ጭምር እንጂ። ነገሮችን ሁሉ በአግባቡ ስታከናውን አያት ነበር። ምንም እንኳ የእኔም ቃላትን ገላጭ አድርጎ የመግለፅ ክህሎት ቢኖርበትም የእርሷ አገላለፅ ግን ከድርጊት እኩል ነበር።" "አያቴ የከወነቻቸውን ነገሮች ለመከወን ሞክሬያለሁ፤ በሄደችበት መንገድ ሄጃለሁ፣ የሳመችውን ቤተስኪያን ስምያለሁ፣ የገበየችውን ገብይቻለሁ፣ እኒህን ነገሮች ያደረግኩት ከአያቴ ሕይወት ጋር በምናብ ለመገናኘት ነው" ትላለች አይዳ። 'ዘ ዋይፍስ ቴል' የአይዳ አያት ድንቅ ሕይወት፤ የኢትዮጵያ ታሪክ የአንድ ምዕተ ዓመት ነፀብራቅ፤ የገጠሩና የከተማው ትዕይንተ-ሕይወት ማሳያ አቡጀዲ ጨርቅ፤ ኃይማኖታዊና ዓለማዊ ትርክት ነው።
xlsum_amharic-train-264
https://www.bbc.com/amharic/news-50597486
በምዕራብ ኦሮሚያ ባለፉት 12 ወራት ቢያንስ 8 የአካባቢው ባለስልጣናት ተገድለዋል
ባለፈው አንድ ዓመት በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በመንግሥት እና በተቋማት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች እየተጠናከሩ መጥተዋል።
[ "ባለፈው አንድ ዓመት በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በመንግሥት እና በተቋማት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች እየተጠናከሩ መጥተዋል።" ]
የመንግሥት ኃላፊዎች የጥቃቱ ዋነኛ ዒላማ ይደረጉ እንጂ፤ የተለያዩ የግልና የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች፣ የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች፣ ሰላማዊ ሰዎችና የውጪ አገራት ዜጎች ጭምር የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው ሲዘገብ ቆይቷል። • "በኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊ ግድያ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም" የነቀምቴ ፖሊስ አዛዥ የክልሉም ሆነ የየአካባቢዎቹ የመንግሥት ባለስልጣናት ለግድያዎቹ ተጠያቂ የሚያደርጉት "ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂ ኃይሎችን" ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ ከኦነግ ተነጥሎ የወጣውን 'ኦነግ ሸኔ' የተባለውን ቡድን ተጠያቂ ያደርጋሉ። በምዕራብ ኦሮሚያ ከኅዳር 2011 እስከ ኅዳር 2012 ባሉት 12 ወራት ውስጥ በተለያዩ አጋጣሚዎች በጥቃቶቹ ሰለባ የሆኑትን ሰላማዊ ሰዎችን ሳይጨምር በመንግሥት ሥራ ላይ ተሰማርተው በታጣቂዎች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ10 በላይ እንደሚሆን የተለያዩ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ኅዳር 2012 ዓ.ም ባለንበት ዓመት በዚህ የኅዳር ወር ብቻ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 5 የመንግሥት ባለስልጣናት ተገድለዋል። ከእነዚህም መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ የጀልዱ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ረጋኔ ከበበ እና የጎጆ ከተማ የፖለቲካ ዘረፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ገረመው በተመሳሰይ ቀን ተገድለዋል። ሁለቱ የአካባቢው ባለስልጣናት በጎጆ ከተማ ማክሰኞ ህዳር 16 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት 12 ሰዓት ገደማ ላይ ነበር በጥይት ተመትተው የተገደሉት። የሁለቱን ባለስልጣናት መገደል ለቢቢሲ ያረጋገጡት የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ ሲሆኑ፤ የመንግሥት ኃላፊዎቹ የተገደሉት "ባልታወቁ ታጣቂዎች" ነው ብለዋል። በተመሳሳይ መልኩ ባለፈው ሳምንት አንድ የምዕራብ ሸዋ ዞን ባለስልጣን በጥይት ሲገደሉ፣ በዚህ ሳምንት መጀመሪያም ማንነታቸው በውል ያልተገለፀ ታጣቂዎች ደግሞ የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ጫላ ደጋጋ መግደላቸውም ተነግሯል። ቀደም ብሎ ረቡዕ ኅዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጠዋት ላይ የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር የመንገዶች ባለስልጣን ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ቶላ ገዳ ለሥራ ወደ ምዕራብ ወለጋ ቄለም ወለጋ ዞን እየተጓዙ ሳሉ ላሎ አሳቢ ተብሎ በሚታወቀው ወረዳ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ኡመታ በወቅቱ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ጥቅምት 2012 ዓ.ም ጥቅምት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ዕሁድ አመሻሽ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም የምዕራብ ዞን ኃላፊ የነበሩት አቶ ገመቺስ ታደሰ በታጠቂዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸው ይታወሳል። የነቀምቴ ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ዳምጠው አቶ ገመቺስ ቢያንስ በአራት ጥይት መመታታቸውን እና አንድ ጊዜ በስለት መወጋታቸውን ለቢቢሲ ገልፀው ነበር። ግለሰቡ ቀደም ሲልም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ዛቻ ይሰነዘርባቸው እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን በወቅቱ ፖሊስ በአቶ ገመቺስ ግድያ ተጠርጣሪ እንዳልያዘ የነቀምቴ ፖሊስን በመጥቀስ ዘግበን ነበር። መስከረም 2012 ዓ.ም የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ አበበ ተካልኝ በመኖሪያ ቤታቸው ደጃፍ ላይ የተገደሉት መስከረም 7 ቀን 2012 ነበር። አቶ አበበ በታጣቂዎች መገደላቸውን የጉሊሶ ወረዳ የአስተዳደር እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋ ሊካሳ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። "ደጃፋቸው ላይ በሁለት ጥይት ግንባራቸውን ተመትተው ነው የተገደሉት" ሲሉ የጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊው ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ ከንቲባውን ቤታቸው በር ላይ ከገደሉ በኋላ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ዘልቀው በመግባት "ለስብሰባ የተዘጋጀ ጽሑፍ እና የአካባቢውን ባለስልጣናት ስም ዝርዝርን የያዘ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ይዘው ሄዱ'' ሲሉ አቶ ተስፋ ጨምረው ተናግረዋል። ከንቲባውን ገድለው ላፕቶፕ ዘርፈው ሄዱ የተባሉት ታጣቂዎች በቁጥር ወደ ስድስት እንደሚጠጉ የሟች የቤተሰብ አባላት ለመንግሥት የጸጥታ አካል መናገራቸውም ተገልጿል። በተመሳሳይ በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ በሚገኝ የሃገር መከላከያ ሠራዊት ካምፕ ላይ ቦምብ ተወርውሮ አንድ ሰው የተገደለው እና በርካቶች የቆሰሉት መስከረም 2012 ነበር። የመንዲ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለሙ ጉዲና ለቢቢሲ እንደተናገሩት የተወረወረው ቦምብ የአንድ ሰው ህይወት ከመቅጠፉም በላይ በርካቶችን አቁስሏል። ሰኔ 2011 ዓ.ም ሰኔ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ሌላኛው የታጣቂዎች ኢላማ የነበሩት ባለስልጣን ደግሞ የደምቢዶሎ ከተማ ከንቲባ አቶ ታደለ ገመቹ ነበሩ። ከንቲባው በጥቃቱ በጥይት ተመትተው ቆስለው በህይወት ተርፈዋል። ከንቲባው አቶ ታደለ በጥይት ተመትተው የቆሰሉት ከቢሯቸው ወጥተው መኪናቸው ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ነበር። "ከንቲባው ከሥራ በሚወጡበት ሰዓት ነበር በር ላይ ጥቃቱን ያደረሱባቸው" ሲሉ የአካባቢው ባለስልጣን ለቢቢሲ አረጋግጠው ነበር። • የደምቢ ዶሎ ከንቲባ በጥይት ተመትተው ቆሰሉ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከንቲባውን በሁለት ጥይት እንደመቷቸውና አንደኛው ጥይት እጃቸውን ሌላኛው ደግሞ በጎን በኩል ኩላሊታቸው አካባቢ እንደመታቸውም ለማወቅ ተችሏል። ታኅሳስ 2011 ዓ.ም ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ መነ ቤኛ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ላይ በጥይት ተመተው የተገደሉት ታኅሳስ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ነበር። የዞኑ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ተረፈ፤ ሁለቱ የፌደራል ፖሊስ አባላት የፊንጫአ ኃይል ማመንጫ እና ጌዶ ከተማ ላይ የሚገኝ የኃይል ማከማቻ ጣቢያዎችን የሚጠብቁ የጸጥታ ኃይል አባላት ነበሩ ብለዋል። ''መኪና ላይ ሆነው ወደ ፊንጫአ እየተጓዙ ሳሉ ባልታወቁ ታጣቂዎች ተኩስ ተከፈተባቸው'' በማለት አቶ ደሳለኝ የነበረውን ሁኔታ ተናግረው ነበር። መጋቢት 2011 ዓ.ም የውጪ አገር ዜጎችን ጭምር ዒላማ ያደረገው እና ለአምስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ጥቃት የተሰነዘረው ሌላኛው ጥቃት መጋቢት 11 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር የተፈጸመው። በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ሁምነ ዋቀዮ በተባለ ቀበሌ ሦስት ኢትዮጵያዊያን፣ አንድ ጃፓናዊ እና አንድ የህንድ ዜግነት ያላቸው ሰንራይዝ ለሚባል የማዕድን አውጪ ተቋም ይሰሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው በጥቃቱ የተገደሉት። ክስተቱን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰዎቹ የተገደሉት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ነው ብሎ ነበር። ከተገደሉት ሰዎች አራቱ ወንዶች ሲሆኑ አንንደኛዋ የውጪ ዜጋ ሴት ናት። እነዚህ የጥቃቱ ሰለባዎች ከማዕድን ኩባንያው ጋር ይሰሩ የነበሩ ሲሆን አቶ አለማየሁ በቀለ የተባሉት ግለሰብ የኩባንያው ባለቤት እንደነበሩም ለማወቅ ተችሏል። አቶ አለማየሁ ይህንን የማዕድን ማውጣት ሥራ ለመጀመር ሦስት ዓመታትን የፈጀ ጥናት ማከናወናቸውንና የምርት ሥራውን ለመጀመር በተቃረበበት ወቅት ከአራት ባልደረቦቻቸው ጋር በታጣቂዎቹ መገደላቸውን የቅርብ ጓደኛው በወቅቱ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ተጠያቂ ያልተገኘላቸው ጥቃቶች በምዕራባዊው የአገሪቱ ክፍል ውስጥ በተለይ የመንግሥት ባለስልጣናትንና የጸጥታ አካላትን ኢላማ በመድረግ ሲፈጸም የቆየው የታጣቂዎች ጥቃትን በተመለከተ ከግምት ባለፈ ተጠያቂ የሆነ አካል አልተገኘም። በተለያዩ ጊዜያት በታጣቂዎች በተፈጸሙት በእነዚህ ጥቃቶች በመንግሥት ሥራ ላይ ከተሰማሩት ሰዎች በተጨማሪ ሰላማዊ ነዋሪዎችም ሰለባ ሆነዋል። እስካሁን በተለይ የመንግሥት ኃላፊዎችንና የጸጥታ አካላትን ኢላማ አድርገው የተፈጸሙት የታጣቂዎች ጥቃቶች ምክንያቱ ምን እንደሆነና ለድርጊቱም ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም። ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ በአካባቢው በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት የጸጥታና ከተለያዩ የመንግሥት አካላትን ያካተተ የዕዝ ማዕከል (ኮማንድ ፖስት) ተቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ እንደነበር ይታወሳል።
xlsum_amharic-train-265
https://www.bbc.com/amharic/news-53578012
"እቅዴ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አሁን ያለኝን 3 ሺህ ሰራተኛ 6 ሺህ ማድረስ ነበር፤ ግን ቀነሱብኝ"
ከሳምንታት በፊት በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት ከ167 በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። ከዚህ ባሻገርም በርካታ ተቋማትና መኖሪያ ቤቶች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተገልጿል።
[ "ከሳምንታት በፊት በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት ከ167 በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። ከዚህ ባሻገርም በርካታ ተቋማትና መኖሪያ ቤቶች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተገልጿል። \n\n" ]
በሻሸመኔና በባቱ ከተሞች ውስጥ በተፈጸመው ጥቃት፤ በንብረት ላይ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ መሆኑን ቢቢሲ ያናገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎችና ባለንብረቶች እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። በእነዚህ ከተሞች ከወደሙ ንብረቶች መካከል በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለማችን የሩጫ ታሪክ ውስጥ ስማቸው ከሚጠቀሱ ጥቂት ብርቅዬ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው የአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ሁለት ትልልቅ ሆቴሎች ይገኙበታል። "ትክክለኛ ቁጥሩን አላወቅንም፤ እስከ 290 ሚሊዮን [ሊደርስ ይችላል]። እንዲሁ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ብለን ነው የያዝነው" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።
xlsum_amharic-train-266
https://www.bbc.com/amharic/news-55287481
እግር ኳስ፡ ህይወቱ በሱስ ምክንያት የተመሳቀለው የፕሪምየር ሊግ ቡድን አምበል
"በጣም ብዙ እርዳታ አስፈልጎኝ ነበር። ወደ ሌላ አይነት ሕይወት ለመሸጋገር ከብዶኝ ነበር፤ ምክንያቱም ህይወቴን በሙሉ እግር ኳስን ብቻ ነበር የማውቀው። ከእንደዚያ አይነት ቦታ መውደቅ ከባድ ነው።"
[ "\"በጣም ብዙ እርዳታ አስፈልጎኝ ነበር። ወደ ሌላ አይነት ሕይወት ለመሸጋገር ከብዶኝ ነበር፤ ምክንያቱም ህይወቴን በሙሉ እግር ኳስን ብቻ ነበር የማውቀው። ከእንደዚያ አይነት ቦታ መውደቅ ከባድ ነው።\"" ]
ክላውስ ሉንደክቫም ክላውስ ሉንደክቫም ቁርጭምጭሚቱ ላይ ባጋጠመው ተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት በአውሮፓውያኑ 2008 ከእግር ኳስ እራሱን እንዲያገል መገደዱን በተመለከተ የተናገረው ነው። ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ደግሞ የአልኮልና የአደንዛኝ እጽ ሱሰኛ ሆነ። ክላውስ በወቅቱ የ35 ዓመት እግር ኳስ ተጫዋች የነበረ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በሚጫወተው ሳውዝሃምፕተን ውስጥ እጅግ የላቀ ብቃት አላቸው ከሚባሉት ተጫዋቾች መካከል ነበር። ለቡድኑ ከ400 በላይ ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1996 ነበር ከኤስኬ በርገን ሳውዝህምፕተንን የተቀላቀለው። በሳውዝህምፕተን ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ክብርና መወደድን ማግኘት ችሏል። ክልጅነቱ ጀምሮ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መጫወት ህልሙ እንደነበር በተደጋጋሚ ይገልጻል። "የመጀመሪያም የመጨረሻም ፍላጎቴ በእንግሊዝ እግር ኳስ መጫወት ነበር" ይላል። "የልጅነት ህልሜ ነው እውን የሆነው። እውነቱን ለመናገር ያንን ያክል ጊዜ ተፎካካሪ ሆኜ እቆያለሁ ብዬ አላስብኩም ነበር" ይላል የኖርዌይ ዜግነት ያለው ክላውስ። ከኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመሆንም 40 ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችሏል። ''ለእኔ ከሌላ አገር መጥቶ ለሳውዝህምፕተን ለ12 ዓመታት መጫወትና የቡድኑ አምበል ለመሆን መቻል ልዩ እና ትልቅ ቦታ ያለው ነገር ነው" ይላል። በ2008 (እአአ) 18 ሺህ የሳውዝሀምፕተን ደጋፊዎች በተገኙበት ቡድኑ ሴልቲክን ገጥሞ ነበር። በወቅቱ ክላውስ ከነጉዳቱ ነበር ወደ ሜዳ ገባው። ነገር ግን የመጀመሪያዎቹን ጥቂት ደቂቃዎች ከተጫወተ በኋላ ተቀይሮ ሲወጣ በከፍተኛ ጭብጨባ ነበር የተሸኘው። ያቺ ዕለት ለክላውስ የእግር ኳስ ሕይወቱ ማብቂያ የመጀመሪያዋ ነበረች። ከ1996-2007 (እአአ) ለሳውዝሀምፕተን ተጫወተው ክላውስ ሉንደክቫም ከመጨረሻው ጨዋታ አንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ክላውስ ሉንደክቫም ሙሉ በሙሉ ሌላ ዓለም ውስጥ ገብቶ በሱስ የተጠመደ ሰው ሆኖ ነበር። የቀን ተቀን ሕይወቱን ይመራበት የነበረው የታቀደና በስልጠና የታገዘ የኑሮ ዘይቤው ሲቀየር እግር ኳስ ከህይወቱ ወጣ። ለበርካታ ዓመታት የሚያውቀው ስልጠና ማድረግ፣ ለጨዋታ መጓዝ፣ እግር ኳስ መጫወት፣ ከጉዳት ማገገም የሚባሉት ነገሮች ታሪክ ሆነው ቀሩ። ከእግር ኳስ በኋላ በሳውዝሃምፕተን የነበረው ቆይታ በተስፋ መቁረጥና በጭንቀት የተሞላ ነበር። ይህንን አስጨናቂ ጊዜ ለማለፍም ፊቱን ወደ አልኮልና ወደ አደንዛዥ እጽ አዞረ። "በሕይወቴ በርካታ ስህተቶችን ሰርቻለሁ። አሁን መለስ ብዬ ሳስበው በጣም ከባድ ጊዜ ነበር። በተለይ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጠዋት ከእንቅልፋቸው ሲነሱ ተስፋና ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር ሊኖር ይገባል። ከእግር ኳስ በኋላም ቢሆን የሚሰሩት ነገር መኖር አለበት።" ''እኔ በወቅቱ ሁሉም ነገር ነበረኝ። በጣም ብዙ ገንዘብ ነበረኝ፣ በጣም ምርጥ ቤተሰብ እና መኖሪያ ቤት ነበረኝ። ኖርዌይ ውስጥም የራሴ መኖሪያ ቤት ነበረኝ። ጀልባዎች፣ መኪናዎች፤ ሁሉም ነገር ነበረኝ። ነገር ግን በደግንገት ድብርት ውስጥ ገባሁና ብቸኝነት ተሰማኝ። የሚፈልገኝ ሰው እንደሌለ ተሰማኝ።" "የእግር ኳስ መልበሻ ክፍሉን ናፈቅኩት። በየሳምንቱ ከቡድን ጓደኞቼ ጋር መሰልጠንና መጫወት አማረኝ። ይሄ ሁሉ ነገር በድንገት ከህይወቴ ሲጠፋ በጣም ከባድ ጊዜን እንዳሳልፍ አደረገኝ።" በርካታ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጫማቸውን ከሰቀሉ በኋላ በተመሳሳይ የህይወት መስመር ውስጥ ሲገቡ ይታያሉ። እጅግ በተራቀቀውና ትንሿ ስህተት እንኳን ትልቅ ዋጋ በምታስከፍልበት የእግር ኳስ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን በየቀኑ መጣርና መልፋት ግድ ይላል። ይሄ ሁሉ ልፋትና የዕለት ተዕለት ስልጠና በአንድ ጊዜ ሲቋረጥ ተጨዋቾች ከፍተኛ ድብርትና የህይወት መመሰቃቀልና ትርጉም ማጣት ውስጥ ይገባሉ። ምንም እንኳን ልክ እንደ ክላውስ አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች የሚፈልጉት ነገር በሙሉ የተሟላላቸው ቢሆንም ከድብርት ግን ማምለጥ አይችሉም። "በየቀኑ ስኬታማ ለመሆን መጣር፣ የውስጥ አቅምን አሟጥጦ መጠቀም፣ በየቀኑ እና በየሳምንቱ ምርጥ ሆኖ ለመገኘትና በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎችን ለማስደስት የሚደረገው ትግል በጣም አስደሳችና ሰውነትን የሚያነቃቃ ነው" ይላል ክላውስ። ክላውስ ሉንደክቫም ከኖርዌዩ ኤስኬ ብራን ወደ ሳውዝሃምፕተን የተቀላቀለው በ350 ሺህ ፓውንድ ነበር። ክላውስ ሉንደክቫም ለሳውዝሀምፕተን ለረጅም ጊዜ ተጫውቷል በነበረው የእግር ኳስ ህይወትም ሁሉም ተጫዋት ሊተማመንበት የሚችል አይነት ሰው ነበር። ምርጥና ቀጣይነት ያለው አቋም የሚያሳይ ተጫዋች ነበር። ነገር ግን ከእግር በኋላ የነበረው ማንነት ከመጀመሪያው በፍጹም የተለየ ነበር። በአንድ ወቅት እንደውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር እስከመዋልና በሱሱ ምክንያት ሆስፒታል እስከመግባት ደርሶ ነበር። "እግር ኳስ ካቆምኩኝ በኋላ ምናልባት ለትንሽ ዓመታት ቀለል ያለ ሕይወት መኖር አለብኝ ብዬ ለእራሴ ነገርኩት። በወቅቱ በርካታ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ እሳተፍ ነበር። በሄድኩበት ቦታ ሁሉ መጠጥ ነበር። በዚያውም ለመዝናናት እየተባለ መጠጥ ቤት መሄድ ተጀመረ።" "ወዲያው እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ። ከባድ ድብርት ውስጥም ገባሁ። ሳላስበው ከዚህ በፊት አይቼው በማላውቀው ሁኔታ እራሴን ተስፋ ቆርጬ አገኘሁት። ፊቴንም ወደ መጠጥና ኮኬይን አዞርኩኝ። ነገር ግን የአልኮልና የኮኬይን ጥገኛ ስሆን ነገሮች እንደውም እየከፉ መጡ።" "በየቀኑ መጠጣትና አደንዛዥ እጽ መጠቀም ጀመርኩ። ባለቤቴ እና ሁለት ሴት ልጆቼ ወደ ኖርዌይ ተመለሱ።" "ከአንዴም ሁለት ጊዜ እራሴን ለማጥፋት ሞክሬያለው። በጣም ከባድ ጭንቀት ውስጥ ገባሁና ሁሉም ነገር ትርጉም አጣብኝ። ድሮ የማውቀው ማንነቴ ጠፋብኝ። በወቅቱ የመረጥኩት ሁሉንም ለመርሳት አልኮል መጠጣት ነበር። ጥፋተኝነቴንና ሃፍረቴን ለመደበቅ ሁሌም መስከር ነበረብኝ።" ምንም እንኳን ክላውስ ሉንደክቫም በጣም አስቸጋሪ የህይወት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ቢፈጅበትም እርዳታ ለመጠየቅ ግን አልቦዘነም ነበር። የቀድሞው የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ፒተር ኬይ ወዳቋቋመው የስፖርተኞች ክሊኒክ ገባ። "የቀድሞው ሳውዝሀምፕተን አምበል እና በርካቶች እንደ ጀግናቸው የሚቆጥሩት የነበረው ሰው እንደዚህ ተሰብሮ ማየት ከባድ ነው። በወቅቱ በጣም ከባድ ቢሆንም አብረውኝ ለነበሩ ሰዎች ስሜንና ያለብኝን ችግር ስናገር ብዙዎቹ ይደነግጡ ነበር።" ረጅም ጊዜ የፈጀው የማገገም ሂደት ቀላል አልነበረም። ተመልሶ አልኮል መጠጣትና ኮኬይን መጠቀምን ጨምሮ ሌሎች አስቸጋሪ ፈተናዎች ነበሩ በመሀል ላይ። ነገር ግን ቆራጥ መሆንና ሕይወትን ለመቀየር እራስን ማሳመን ወሳኝ መሆኑን ክላውስ ይናራል። "በጣም ብዙ ውጣ ውረዶች ነበሩ። ሁለት ጊዜ ወደ ሱሴ ተመልሼ ነበር። አሁን ጥቂት ዓመታት አልፎታል ግን ሱሰኛ መሆኔን አምኜ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ፈጅቶብኝ ነበር።" "በነበረኛ ቆይታ ያለ አልኮልና አደንዛኝ እጽ ጥሩ ሕይወት መኖር እንደሚቻል እየገባኝ መጣ። በጣም ደስተኛ ሆንኩኝ፤ በእራሴም ኮራሁ። ምንም እንኳን ያሳለፍኩት ጊዜ ቀላል ባይሆንም አሁን ካለሁበት ሁኔታ ላይ በመገኘቴ በጣም እድለኛ ነኝ።" ምንም እንኳን ክላውስ ሉንደክቫም እና ባለቤቱ በአውሮፓውያኑ 2014 ላይ ትዳራቸውን አፍርሰው ፍቺ ቢፈጽሙም አሁን ጥሩ የሚባል ግንኙነት ያላቸው። ከሁለቱ ሴት ልጆቹ ጋር ያለውም ግንኙነት ከምን ጊዜውም በበለጠ ጥሩ የሚባል ነው። ክላውስ ለሳውዝሀምፕተን በሚጫወትበት ወቅት ስለ አእምሮ ጤና እና ጭንቀት ማውራት ብዙም የተለመደ ነገር አልነበረም። ነገር ግን አሁን ነገሮች በፍጥነት እየተቀየሩ ይመስላል። ሰዎች በህይወታቸው የሚገጥማቸውን ጭንቀትና አስቸጋሪ ነገር ማጋራት ጀምረዋል። ክላውስ በአሁኑ ጊዜ አደንዛዥ እጽ የሚጠቀሙና ሱሰኛ የሆኑ ሰዎችን በመርዳት ላይ ተሰማርቶ ይገኛል። ከቀድሞ ክለቡ ሳውዝሀምፕተን ጋር በተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ ለመስራትም ፍላጎት አለው። ከቀድሞ ቡድኑም ጋር ግንኙነት የፈጠረ ሲሆን በቡድኑ ታሪክ ስማቸው ከሚጠቀስ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደመሆኑ፤ ተጫዋቾች ሊያጋጥሟችው ስለሚችሉ ፈተናዎች ግንዛቤ ማስጨጥ ደግሞ ህልሙ ነው።
xlsum_amharic-train-267
https://www.bbc.com/amharic/news-56791486
በትግራይ የወሲባዊ ጥቃት ተጎጂዎችን የሚያክሙ ባለሙያዎች ትግል
ከጥቅምት 24/2013 ጀምሮ ወታደራዊ ግጭቶች በተካሄደባት በትግራይ ክልል ዕዳጋ ሓሙስ አንዲት ሴት ልጅ ረዘም ለቀናት ወሲባዊ ጥቃት ከተፈፀመባት በኋላ ማህጸንዋ ባእድ ነገሮች ገብቶበት ተጥላ መገኘቷ ተሰማ።
[ "ከጥቅምት 24/2013 ጀምሮ ወታደራዊ ግጭቶች በተካሄደባት በትግራይ ክልል ዕዳጋ ሓሙስ አንዲት ሴት ልጅ ረዘም ለቀናት ወሲባዊ ጥቃት ከተፈፀመባት በኋላ ማህጸንዋ ባእድ ነገሮች ገብቶበት ተጥላ መገኘቷ ተሰማ።" ]
ይህች ተጠቂ ቁጥራቸው በርከት ያለ የኤርትራ ወታደሮች አካባቢው ወደሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ በመውሰድ ለቀናት እንደደፈሯት በአዲግራት ሆስፒታል የሚገኘው የህክምና ታሪኳ ያስረዳል። በመጋቢት ወር ወደ አዲግራት ሆስፒታል ስትመጣ "ማህጸንዋ ውስጥ የነበሩ ባእድ ነገሮች ለማስወጣት ስሞክር ከአቅሜ በላይ ሆነ" የሚለው መጀመሪያ ያያት ዶክተር አታኽልቲ ስዩም ነው። በመሆኑም ሌላ ሐኪም እንዲያያት ግድ ሆነ፤ አንድ የማህፀንና ጽንስ ሐኪም ተጠርቶም በቀዶ ጥገና እንዲወገዱ አደረገ። ዶክተር አታኽልቲ "ይህ አሰቃቂ ክስተት መቼ ከአእምሮዬ እንደሚወጣ አላውቅም" በማለት እያለፈበት ያለውን ሥነ ልቦናዊ ጫና ያስረዳል። እሷም የነርቭ ችግር አጋጥሟት በመቀለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል የጤና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል። "...ብዙ ተደራራቢ ወሲባዊ ጥቃት የደረሳቸው ሴቶች ታሪክ ስሰማ ውዬ ወደ ቤት ስሄድ፤ ምን እንደምረግጥና ምን እንደምናገር አላውቅም" ትላለች በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ስር በሚገኘው የዋንስቶፕ ሴንተር የምትሰራው ነርስ ሙሉ። እነዚህ የህክምና ባለሙያዎች በየቀኑ የሚያስተናግዷቸው ተደፍረው የመጡ ሴቶች ተመሳሳይ ታሪክ አላቸው። የተመድ ሰብዓዊ ዕርዳታ ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ ለፀጥታው ምክር ቤት ወሲባዊ ጥቃት በትግራዩ ግጭት እንደ ጦርነት መሳሪያ አገልግሏል ብለዋል። በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካው አምባሳደር ዋሺንግተን "በመድፈር እና ጭካኔ በተመላባቸው ወሲባዊ ጥቃቶች ደንግጣለች" ሲሉ ተናግረው ነበር። የደረሰባቸው ስቃይ ከብዶባቸው መፈጠራቸውን የጠሉ፣ ጥቃቱ ባሳደረባቸው ሥነ ልቦናዊ ጫና ተረብሸው "ሰው አይፈልገኝም፣ በህይወት መኖር የለብኝም፣ ሞት ይሻለኛል" የሚሉ ተጠቂዎች ቁጥራቸው ቀላል አለመሆኑን የሕክምና ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። የታካሚዎቻቸው ቀልብ አረጋግተው፣ ታካሚዎቻቸው አዲስ ህይወት እንዳለ ተስፋ እንዲያደርጉ ጥረት ማድረግ የሐኪሞቹ ኃላፊነት ከሆነ ወራቶች መቆጠር ጀመረዋል። እነዚህ የሕክምና ባለሙያዎች በቂ የህክምና መሳሪያና መድኃኒት በሌለበት፣ የሰው ኃይል እጥረት ባለበት ሁኔታ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተደፈሩ ሴቶችና እናቶች ሲያስተናግዱ ይውላሉ። በአዲግራት ሆስፒታል ከአንድ ዓመት በላይ ሲያገለግል የቆየው ዶክተር አታኽልቲ እስከ አሁን ድረስ ከ140 በላይ ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ማከሙን ይናገራል። ይሁን እንጂ ይህ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ስለሚመጣ በዚያው ልክ ሥነ ልቦናዊና ማኅበራዊ ጫናውን እየበረታበት እንደመጣ ያስረዳል። "በየቀኑ የምሰማውና የማየው ጉዳይ ስለሆነ፣ በየቀኑ ራሴን ያመኛል፣ ጭንቀት አለብኝ፣ ምግብ አልበላም፣ ራስን የመጣልና በሆነ ነገር ያለመደሰት ሁኔታ ይታይብኛል" ይላል። እንደ ዶክተር አታኽልቲ ከሆነ እስከ አሁን ድረስ ከ258 በላይ ሴቶች ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው በመግለጽ አዲግራት ሆስፒታል ለሕክምና መጥተዋል። ዶ/ር አታኽልቲ ካስተናገዳቸው ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች መካከል በእድሜ ትንሿ 12 ዓመት ሲሆናት፣ ትልቋ እድሜ ደግሞ የ89 ዓመት አዛውንት ይገኙባቸዋል ይላል። "አብዛኛዎቹ እናቶች ናቸው፤ የ70 ዓመት የካህናት ባለቤቶች፣ ቆራቢ እናቶች አሉ። የደረሰባቸው ሲናገሩ እንባቸው ይቀድማቸዋል። ይህን ሳይ ሁሉም ነገር ያስጠላኛል" ሲል ይናገራል። በትግራይ ካሉ ከተሞች ሁሉ መቀለ ከተለያዩ አካባቢዎች በተሻለ የህክምና አገልግሎት የሚገኝባት ከተማ ናት። በአይደር ሪፈራል ሆስፒታልና በመቀለ ሆስፒታል የሚታከሙ ከመቀለና ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች የመጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጠቂዎች ይገኛሉ። እስከ አሁን በአይደር ሆስፒታል ወደሚገኘው የጾታዊ ጥቃት ሰለባ ማዕከል (ዋን ስቶፕ ሴንተር) ከ335 በላይ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች መምጣታቸውን የምትናገረው ነርስ ሙሉ፣ ከእነዚህ መካከል ከ140 በላይ ሴቶች በመደፈራቸው ያረገዙትን ጽንስ እንዲቋረጥ የሚፈልጉ ናቸው ትላለች። በተጨማሪም ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች የተጠቁ፣ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት የደረሰባቸው፣ ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ የማይችሉ ሆነው ሲመጡ የዚህ ማዕከል ነርስ ሙሉ፣ ቀድሞ የማግኘት ኃላፊነቱ በእሷ ጀርባ ላይ ወድቋል። "ሰው መቅረብ አይፈልጉም፤ በደረሰባቸው ጥቃት ምክንያት ራሳቸውን ከመጥላታቸው የተነሳ የአእምሮ መድኃኒት መውሰድ የጀመሩ አሉ" የምትለው ነርሷ፤ በዚህ ሁኔታ የተሳካ ሥራ መስራት ከባድ እንደሆነ ትናገራለች። "በቀን እስከ 15 ታካሚ የምናይበት ሁኔታ አለ። በርካታ የጤና ተቋማት ስለ ተዘረፉና ስለወደሙ ፅንስ የሚያቋርጡበት አልያም መድኃኒት የሚያገኙበት ሁኔታ የለም። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ሕዝቡም እኛም በጣሙን ተቸግረናል" ትላለች። በትግራይ ክልል ውስጥ ወታደራዊ ግችቱ ከተከሰተ በኋላ የሚያጋጥሙ ጾታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሪፖርት ማውጣታቸው ይታወሳል። በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ በግጭት ወቅት የሚከሰት ወሲባዊ ጥቃት ላይ አተኩሮ የሚሠራው ቡድን ልዩ ተወካይ ፕራምሊያ ፓተን በትግራይ የሚስተዋለው ጾታዊ ጥቃት እንዲገታ ቀደም ሲል ጥሪ አቅርበው ነበር። ባለፉት ሁለት ዓመታት በማዕከላዊው መንግሥትና በህወሓት በሚመራው የትግራይ ክልላዊ መስተዳደር መካከል የነበሩ ፖለቲካዊ ልዩነቶች እየተካረሩ መጥተው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ላይ ወደ ወታደራዊ ግጭት መከሰቱ አይዘነጋም። በዚህ ምክንያት በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ሱዳን ሲሰደዱ፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ወደ ተለያዩ የክልሉ ከተሞች ተፈናቅለዋል። የዓለም የምግብ ድርጅት 91 በመቶ የክልሉ ሕዝብ አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ሲገልጽ፤ መንግሥትና ሌሎች ድርጅቶች የተለያዩ የእርዳታ ቁሳቁሶች እያቀረቡ መሆናቸውን አስታውቋል። ትግራይ ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ኃይሎች ፈጽመዋቸዋል ከተባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል ጾታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው እንደተናገሩት በክልሉ ውስጥ የመብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙና ምርመራ ተደርጎ ጥፋተኛ ሆነው በተገኙት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል። "በትግራይ ወሲባዊ ጥቃትና ዘረፋ እንደተፈጸመ የሚያሳዩ ሪፖርቶች አሉ። የመከላከያ ሠራዊት አባል ሆኖ የትግራይ ሴቶች የደፈረና ንብረት የዘረፈ ወታደር በሕግ ይጠየቃል" ብለዋል። የኤርትራ መንግሥትም የሚቀርብበትን ክስ ውድቅ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፤ በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት ሶፊያ ተስፋማሪያም ለድርጅትቱ የጸጥታው ምክር ቤት በጻፉት ደብዳቤ የኤርትራ ወታደሮች አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ፈጽመዋል መባሉ "የሚያስቆጣ ብቻ ሳይሆን በሕዝባችን ባህልና ታሪክ ላይ የተሰነዘረ የከፋ ጥቃት ነው" ሲሉ ተቃውመውታል። "ትንሽ መድሃኒት እንቁ ሆናብናለች" የጤና ተቋማት በትግራይ ከባድ ውድመት ከደረሰባቸው ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቦታዎች አንዱ ናቸው። ከታህሳስ ወር አጋማሽ እስከ መጀመርያ የመጋቢት ወር ባለው ጊዜ ድንበር የለሹ የሐኪሞች ማኅበር በ106 የጤና ተቋማት ላይ ባካሄደው ዳሰሳ፤ 70 በመቶ የሚጠጉ ተዘርፈዋል፤ 30 በመቶ ደግሞ ወድመዋል ብሏል። እነዚህ "ሆን ተብሎ የወደሙና የተዘረፉ" ናቸው ሲል የክልሉ ሕዝብ ጥቂት የህክምና አማራጮች ብቻ እንደቀሩት ገልጿል። "የሽንትና ደም መርመራ ማድረግ የምንችልበት ሆነ መድኃኒት የምናገኝበት ደረጃ ላይ አይደለንም። ታካሚዎች ለተከታታይ አራት ቀናት ወረፋ ይዘው ይውላሉ። ትንሽ መድኃኒት እንቁ ሆናብናለች" የሚለው ዶክተር አታኽልቲ የባለሞያ እጥረት ባለበት ሁኔታ የጾታዊ ጥቃት ታካሚዎች ቁጥር መብዛቱ ሥራውን እንዳከበደው ይናገራል። ተጎጂዎቹ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ፣ በጦርነቱ ምክንያት አባት ወይም ወንድማቸው የተገደሉባቸው ሲሆኑ፣ ሌሎች የቆዳና የሥነ አእምሮ ችግሮች ይታይባቸዋል። "አብዛኛውን ጊዜ ጠዋት ገብተን ምግብ ሳንበላ የምናድርበት ሁኔታ ስላለ ውሎ አዳሬ ሆስፒታል ውስጥ ሆኗል። ከሩቅ አካባቢ ስለሚመጡ ትተናቸው መሄድ ይከብደናል፤ ደግሞም ያለቅሳሉ። ወደ ቤት ስገባ ሁሉም ነገር ስለሚረብሸኝ አልተኛም" ይላል። የመቀለ ዋን ስቶፕ ሴንተር ማኅበራዊ ሠራጠኛ፣ ዐቃቢ ሕግ፣ ሐኪምና ፖሊስ ያለው የተደራጀ አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል በመሆኑ የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ የሆኑት ሴቶች ከመጠቋቆም ገለል ብለው እንዲታከሙ ረድቷቸዋል። ይሁን እንጂ አብዛኛዎቹ ሴቶች የኅብረሰተቡ አመለካከትና ባህል ጫና ስለሚያሳድርባቸው ወደ ህክምና ለመምጣት አይደፍሩም፤ የደረሰባቸውን ጉዳት የሚናገሩትም ጥቂት ናቸው። ነርስ ሙሉ ማዕከሉ ከአቅሙ በላይ የሆነ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ትናገራለች። "በህይወቴ ሙሉ እንደዚህ ሥነ ልቦናዬን የገደለው አጋጣሚ የለም። ድንጋጤውን ቤታችን ድረስ ይዘነው እንሄዳለን፣ ምግብ አይበላልንም። ሰው ስለሚበዛም ሰዓት እላፊውን አናከብርም። ህይወትን ሽጦ ነው እየተሰራ ያለው" ብላለች። በተጨማሪም "ወደ ቤት ስሄድ እያንዳንዱ ሳክማቸው የዋልኳቸውን ሴቶች ስም፣ የሰውነታቸው ሁኔታና ስቃያቸው በፍጹም አይረሳኝም። ቀንና ሌሊት ከእኔ ጋር ናቸው። ስቃያቸው የእነሱ ቢብስም ሁላችንንም የጎዳ ሆኗል" በማለት ቤተሰቦችዋ ፊት ስለ ሥራዋ እንደማታወራ ገልጻለች። "ድሮ በትንሽ ነገር እደሰት የነበርኩ ሰው አሁን ቤተሰቦቼም ሆነ ጓደኞቼን ሳገኝ እንኳ አልደሰትም" የሚለው ዶክተር አታኽልቲ በበኩሉ "ሁሌም ለመጪው ትውልድ ምንድን ነው የምንነግረው? በሚል እጨነቃለሁ" ይላል። "ከዚህ በፊት ሻይ እየጠጣሁ ስለ አንድ የዳነልኝ ታካሚዬ ሳወራ እውል ነበር፤ አሁን ግን ስደክም ባድርም ለሰው አላወራውም። የተስፋ መቁረጥ ስሜት ነው የሚሰማኝ። በዚህ ወቅት አገልግሎት መስጠት ስላለብኝ እንጂ፤ ዘወትር ዛሬም ላያቸው ነው? እያልኩ እየተጨነቅኩ ነው የምሄደው" በማለት ያለበት ሁኔታ አስቸጋሪ እንደሆነ ይናገራል። "ሁሉም ህልም ይመስለኛል" የህክምና ባለሞያዎች ስለ ግል ስሜታቸውና ድካማቸው ለማሰብም ሆነ ለማዘን ብዙም ጊዜ የላቸውም። ነርስ ሙሉ እንደምትለው "አሁን እንደልብ ተናግሮ መሄድም አይቻልም። ብንናገርም የሚያግዘን የለም፤ እየሆነ ያለውን ነገር ከሆነ በኋላ ላግዝህ የሚለው ደግሞ ስቃይን ነው የሚጨምረው" ትላለች። የአዲግራት ሆስፒታል ዶክተር አታኽልቲ በበኩሉ የመብራትና ስልክ አገልግሎት በተደጋጋሚ እንደሚቋረጥና ከሁሉም በላይ ውሃ አለመኖሩ ትልቅ ችግር እንደሆነባቸው ያነሳል። "ሕዝቤና አገሬ ነው በሚል ወኔ ነው የምንሰራው እንጂ፤ ሰርተን እጃችን የምንታጠብበት ውሃ እንኳ የለም። መብራት ስለሚጠፋ ዳቦና እንጀራ የማይገኝበት ቀን ብዙ ነው። ለስላሳ ጠጥተን የምንሰራበት ሁኔታ ነው ያለው" ሲል ያስረዳል። ከሁሉም በላይ ግን "ህይወታችን ሁሉ ህልም ሆኗል። ትንሽ መድኃኒት ማግኘት፣ መብራትና ሌሎች ነገሮች እንደልብ ማግኘት ህልም ነው" ብሏል። ከ10 ዓመታት በላይ በነርስነት ያገለገለችው ሲስተር ሙሉ በዚህ ሁሉ አስቸጋሪ ሁኔታ አንድ ተስፋ የሚሰጣት ነገር አለ። እሱም "ጥቃቱ የደረሰባቸው ሴቶች እዚህ በመምጣት አእምሯቸውን ሰቅዞ ይዞት የነበረው ችግር በትንሽ ቃላት ቀለል ሲልልቸው ደስ ይለኛል። ቀልባቸውን ስተው መጥተው አሁን በእግራቸው ሲሄዱ ሳይ እደሰታለሁ" ትላለች። ይህች መቅለል ግን ጊዜያዊ ናት። ሐኪሞቹ ትንሽ ቀለል ያላቸው ሸክም መልሶ የሚቆለልባቸው እንደገና አዲስ የጥቃት ሰለባዎች ሲመጡ ወደነበረው የጭንቀት አዙሪት መልሰው እንደሚገቡ ይናገራሉ።
xlsum_amharic-train-268
https://www.bbc.com/amharic/news-45215114
በምስራቅ ጎጃም መሬት መንሸራተት አደጋ የስምንት የሰዎችን ህይወት ቀጠፈ
በምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ፣ እነገት ቀበሌ፣ ወይን ውሃ ጎጥ ነሃሴ 8፣2010 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡30 ገደማ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በአንድ ቤት ውስጥ የነበሩ ስምንት ግለሰቦች ህይወት አልፏል።
[ "በምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ፣ እነገት ቀበሌ፣ ወይን ውሃ ጎጥ ነሃሴ 8፣2010 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡30 ገደማ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በአንድ ቤት ውስጥ የነበሩ ስምንት ግለሰቦች ህይወት አልፏል።" ]
ከሟቾቹ መካከል ስድስቱ የአንድ ቤተሰብ አባል ሲሆኑ፤ አምስት ልጆች እና እናታቸው እንዲሁም ከሌላ አካባቢ በእንግድነት የመጣ የእርሷን ወንድም ጨምሮ ስራ ለማገዝ ሲል በቤቱ የተገኘ ጎረቤት ህይወታቸው እንዳለፈ የምስራቅ ጎጃም ዞን ኮሚዩኒኬሽን ፅ/ቤት ባለሙያ አቶ ጋሻዬ ጌታሁን ለቢቢሲ ገልፀዋል። •በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው •የመገንጠል መብት ለማን? መቼ? •ልዩ ፖሊስ ማነው? የወደፊት ዕጣውስ? የሟቿ ባለቤት ካህን በመሆናቸው በወቅቱ ቤተ ክርስቲያን በመሄዳቸው ከአደጋው ሊተርፉ ችለዋል። የሟቾቹ የቀብር ስነ ስርዓትም በትናንትናው ዕለት ተፈፅሟል። በነሃሴ 3፣2010 ዓ.ም በደጀን ወረዳ፣ ቆቅ ውሃ ቀበሌ ላይ ተመሳሳይ አደጋ ደርሶ በእንስሳት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ባለሙያው ይናገራሉ። በተለይ የክረምት ዝናብ እየጨመረ በመሄዱ ተራራ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ቢሮው አስተላልፏል። በተለይ ወደ ተራራ ጫፍ የሚወጣ ጎርፍ መቀየሻ ቦዮች አቅጣጫቸው እንዲቀየር እየተደረገ መሆኑን አቶ ጋሻዬ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
xlsum_amharic-train-269
https://www.bbc.com/amharic/50135333
"መንገድ መዝጋት የኋላ ቀር ፖለቲካ ውጤት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ
ዛሬ ጥቅምት 11፣ 2012 ዓ. ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
[ "ዛሬ ጥቅምት 11፣ 2012 ዓ. ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።" ]
ስለ ምርጫ፣ ስለ ፌዴራል ሥርዓቱ፣ ሙስና፣ ሚዲያ፣ ፀጥታና ደህንነት፣ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እና ሌሎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላቱ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "መደመር" መጽሐፍ ተመረቀ • የጠቅላይ ሚኒስትሩ መጽሐፍ ምን ይዟል? • "ውስኪ ጠጪ ኢህአዴጎች እባካችሁ ውሃ የናፈቀው ሕዝብ እንዳለ አትርሱ" ጠ/ሚ ዐብይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምርጫን በሚመለከት ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ "በዘንድሮም ምርጫ ይሁን በሚቀጥለው ምርጫ ተግዳሮት የሌለው ምርጫ ማድረግ አይቻልም" በማለት ምርጫው ይራዘም የሚለው እንደማያስኬድ ተናግረዋል። መንግሥት በቂ በጀት ለምርጫ ቦርድ መመደቡን እንዲሁም የቦርዱ አባላትም ከማንኛውም ጊዜ የተሻለ ነፃ ነው የሚያስብል እንደሆነም በመጥቀስ ካለፉት ጊዜያት የተሻለ ምርጫ ማድረግ ይቻላል ብለዋል። "የመንግሥት ፍላጎትም ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲካሄድ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግሥት ዝግጁነትም ከዚህ በፊት ከነበረው የተሻለ እንደሆነ አረጋግጠዋል። መንግሥት፣ ሕዝብ እና ምርጫ ቦርድ ተባብረው የተሻለ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል እምነት እንዳላቸው አስረድተዋል። በምርጫ ሕጉ ላይ ቅሬታ ያላቸው ፓርቲዎች ያቀረቡት ቅሬታ አግባብ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ሰብሰብ ማለት ለሁላችንም ያስፈልጋል" ብለዋል። "ምርጫውን ማድረግ በብዙ መልኩ ይጠቅመናል፤ ፈተና አልባ ምርጫ ባይሆንም የተሳካ ምርጫ ማድረግ ይቻላል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ኢህአዴግ በውስጡ ያለውን ቅሬታ በሚመለከትም ሲናገሩ "ኢትዮጵያ የኢህአዴግ አባት እንጂ፤ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ አባት አይደለም" በማለት እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትበተናለች የሚል አስተሳሰብ ትክክል ያልሆነ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢህአዴግ ውስጥ ላለፉት 5 እና 10 ዓመታት ውህደቱ ውይይት ሲደረግበት መቆየቱን አስታውሰው፤ ውህደት እንዲፈፀም በሀዋሳው ጉባኤ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን አስታውሰን "እየተወያየን ነው" ብለዋል። • "ተጨማሪ የፌደራል የሥራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ እየተሠራ ነው" ጠ/ሚኒስትር ዐብይ • "ለእናንተ ደህንነት ነው በሚል እንዳሰሩን ተገልፆልናል" የባላደራ ምክር ቤት አስተባባሪ ውህደቱ ጊዜው አሁን አይደለም የሚሉ ፓርቲዎችና አባላት ቢኖሩም እስካሁን ግን ውህደቱ አያስፈልግም ያለ አካል ሰምተው እንደማያውቁ ተናግረዋል። በክልሎች መካከል ያለውን ፀጥታ በተመለከተም፤ የትጥቅና የቃላት ፉክክር እንደሚታይ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "የውጊያ ቀስቃሾች ሁል ጊዜም አንድ ዓይነት ናቸው" በማለት በየጊዜው ግጭት እየቀሰቀሱ በዚያ ውስጥ መኖር የሚፈልጉ አሉ በማለት ወጣቶች እንዲነቁ መክረዋል። የትግራይ ክልልን እየመሩ ያሉ አመራሮች የክልሉን ችግር መፍታት እንጂ ከአማራ ክልል ጋር መዋጋት አይፈልጉም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በመካከል የድራማው አካል የሆኑትን የመለየት ችግር ነው ያለው" ብለዋል። የክልሎች ትጥቅ በሀገር ደረጃ የሚያሰጋ አይደለም በማለት ክልሎች መዘጋጀት ያለባቸው የራሳቸውን የክልል ውስጥ ደህንነት ለመጠበቅ እንጂ ከሌሎች ክልሎች ጋር ለመጋጨት መሆን እንደሌለበት ተናግረዋል። የፌደራል መንግሥት የሚችለውን እያደረገ እንደሚሄድ ጠቅሰው በአማራና ቅማንት፣ በሶማሌና በአፋር መካከል የሦስት ቀበሌ ችግር ነው ያለው በማለት ችግሩን የፈጠሩት ሌሎች ናቸው ማለት የሚለው ስለማያዋጣ ኃላፊነት ወስዶ መሥራት ይጠይቃል ሲሉ አሳስበዋል። "መንገድ መዝጋት የኋላ ቀር ፖለቲካ ውጤት ነው።" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፈጠረው ነገር የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልፀዋል። "የሚያባሉን እድሜ ጠገብ ሰዎች ናቸው" በማለት ባይሎጂም [ሥነ ሕይወትም] ከዚህ አንጻር የራሱ መፍትሔ ስላለው ሰላም ማደፍረሱ እንደማይቀጥል አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ሥፍራዎች በግላቸው በመንቀሳቀስ በርካቶችን ያነጋገሩት ሰላም ለኢትዮጵያ ቀዳሚ ስለሆነ ነው በሚል መርህን በመከተል እንደሆነና በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ፣ በብሔሮች መካከል እርቅ እንዲፈጠር የእርቅ ኮሚሽን እንዲቋቋም የተሠራው የውስጥ ሰላም ወሳኝ ስለሆነ መሆኑን ተናግረዋል። መፈናቀል ቁጥሩን ማጋነን ብቻ ሳይሆን በማለት "50 ሺህ ተፈናቃይ አለብን ያሉ 1ሺህ ተፈናቃይ ማቅረብ አልቻሉም በማለት ማፈናቀልና ተፈናቃይ መቀበል ንግድ ነው የሆነው" ብለዋል። "በጌዲዮ የተፈናቀለው በሚሊየን ተጠርቶ ስንመልስ ግን አነስተኛ ቁጥር ብቻ እንዳላቸው ተረድተናል" ሲሉም ተናግረዋል። መንግሥታቸው ለውስጥ ሰላም አበክሮ እየሰራ መሆኑን ገልፀው "የምንታገሰው የነበረውን ነገር ላለመድገም ነው" ሲሉ አስረድተዋል። የሕዳሴው ግድብን በተመለከተ ጠንከር ያለውን የግብፅ አቋም አስመልክቶ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የማንንም ፍላጎት ለመጉዳት የጀመርነው ፕሮጀክት አይደለም" በማለት በመግባባትና የግብፅን ስጋት ከግምት ውስጥ በማስገባት እንቀጥላለን ብለዋል። በሚቀጥሉት ቀናት ከግብፅ ፕሬዝዳንት አልሲሲ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም አስረድተዋል። " ቁጭ ብለን እናወራለን፤ ማንም ይህንን ግንባታ ማስቆም አይችልም። ይህ ሊሰመርበት ይገባል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጦርነት እንከፍታለን የሚሉ አስተያየቶቸን አስመልክተው ሲናገሩ "ማንንም አይጠቅምም ብለን እናምናለን" ብለዋል። "ጦርነትም ከሆነ ኢትዮጵያ ብዙ ሕዝብ አላት፤ በሚሊዮን ማሰለፍ እንችላለን" ብለዋል። አክለውም "በቀድሞ መሪዎች የተፈጠሩ ስህተቶችን እናስተካክላለን እንጂ የተጀመሩ ምርጥ ስራዎችን አናቋርጥም፤ እንዲህ አይነት ምርጥ ስራዎችን በማቋረጥ አገር አትገነባም" ብለዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ሰራሽ የሆነም መዋቅራዊም የሆነ የዋጋ ንረት አለ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ 'ሆም ግሮውን' ኢኮኖሚ ማሻሸያ የተነሳው ነገር በማለት ማክሮ ኢኮኖሚ አለመመጣጠን ለማስተካከል መዋቅራዊና ዘርፋዊ (ሴክቶራል) ማሻሻያ ይካሄዳል ብለዋል። በእነዚህ ውስጥ የኑሮ ውድነቱን ካመጡ ነገሮች መካከል አንዱ የቤት ኪራይ ውድነት መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለተኛው የምግብ ዋጋ መናር እንዲሁም ስራ አጥነትና የሚመረተው ምርት በገበያ ከሚፈለገው ያነሰ መሆን ነው ብለዋል። አንደኛውን ነጥሎ በመፍታት ለሁሉም መፍትሄ አይሆንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤት በሚመለከት እስካሁን ከተገነቡት ቤቶች በእጥፍ የሚልቅ በመንግሥትም በግል ባለሃብቶችም ለመገንባት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። ይህ ግንባታ በአዲስ አበባም ከአዲስ አበባ ውጪም የሚካሄድ እንደሆነ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባታው በጥምረት ወይንም በሙሉ ኢንቨስትመንት እንደሚሆን አብራርተዋል። ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣውን የለገሃሩን ፕሮጀክትንም በማስታወስ ሌላ ጎተራ አካባቢ በተመሳሳይ ለባለሃብቶና ዲፕሎማቶች የቤት ፍላጎት የሚሆን አዲስ ቱሞሮ የተሰኘ አዲስ ፕሮጀክት አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከቻይና መንግሥት ኩባንያ ጋር ሊፈራረሙ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገረዋል። ሌላው የግል ባለሀብቶች መካከለኛ ገቢ ላላቸው ግለሰቦች የሚሰሯቸው ቤቶች ችግሩን እንደሚያስተነፍሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ እንደራሴዎቹ አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪም በሁለት ወር ውስጥ እስከ 4ሺህ የጎዳና ተዳዳሪዎችን የሚሆን የቤቶች ግንባታ እየተካሄደ ነው ብለዋል። እነዚህ የጎዳና ተዳዳሪዎችን መጠለያ በመስጠት የተለያዩ ስራዎች ላይ ለማሰማራት ሁሉንም ታሳቢ ያደረገ ስራ መንግሥታቸው እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላው ምግብ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለት ወር ውስጥ የሚጠናቀቀው በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርተው ከግለሰቦች ጋር በመነጋገር እየተገነባ ያለው ፋብሪካ ቢያንስ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ሰዎች በቅናሽ ዳቦ ለማቅረብ እንደሚያስችል ገልፀዋል። በዚህ ዓመት የበጀት ዓመት መጠናቀቂያ ድረስ የሚጠናቀቀውና ግዙፍ የሆነው ሌላ የዳቦ ፋብሪካ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ንጉስ በሰጡት ርዳታ በቀን ከ10 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካ መሆኑንም ገልፀዋል። ይህ ፋብሪካ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ ላሉ ዜጎችም የዳቦ አቅርቦት ይኖረዋል ብለዋል። የከተማ እርሻ ላይ በመሰማራት የስራ ፈጠራና የኑሮ ውድነቱን ለመቆጣጠር ይሰራል ሲሉም አክለዋል። የመገናኛ ብዙኃንን አስመልክቶ ጠቅላዩ በተናገሩት ንግግር ሚዲያው ላይ ያሉ ባለ ድርሻ አካላት ሚዲያ ነፃ እንዲሆን በተደጋጋሚ መጠያቃቸውን አውስተዋል። "መቻል ላይ ግን ችግር አለ፤ ሚዲያ የዘር፣ የብሔር፣ የነጋዴዎች መቀለጃ ሆኗል።" በማለት ኢትዮጵያዊያን መረጃዎችን እያጣሩ እንዲሰሙና ኃላፊነት እንዲወስዱ ጠይቀዋል። የሌላ አገር ፓስፖርት ኖሯቸው የሚዲያ ባለቤት የሆኑ ሰዎችን በሚመለከትም "ትዕግሥት እያደረግን ያለነው አውዱን ለማስፋት ነው... እርምጃዎችን መውሰዳችን አይቀርም" በማለት "ሁለት ቤት መጫወት አይቻልም" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በነጻነት ልማትን የሚያግዙ ከሆነ እንደሚበረታቱ፤ ካልሆነ ግን ዲሞክራሲን ለማደናቀፍ የሚሠሩትን መንግሥታቸው እንደማይታገስ በአፅንኦት አስጠንቅቀዋል።
xlsum_amharic-train-270
https://www.bbc.com/amharic/50805232
መንግሥት አደገኛ የሆነውን የትግራይን መገለል መለስ ብሎ ሊያጤነው ይገባል- ክራይስስ ግሩፕ
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሽግግር ሃዲዱን እንዳይስት መንግሥት፣ የፖለቲካ አመራሮችና ዓለም አቀፍ አጋሮች አስፈላጊ ነገሮችን እንዲያደርጉ ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ጠየቀ።
[ "በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሽግግር ሃዲዱን እንዳይስት መንግሥት፣ የፖለቲካ አመራሮችና ዓለም አቀፍ አጋሮች አስፈላጊ ነገሮችን እንዲያደርጉ ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ጠየቀ።" ]
በዓለም ዙሪያ የሚከሰቱና ሊከሰቱ የሚችሉ ቀውሶችን የሚከታተለው ይህ ቡድን ኢትዮጵያን በተመለከተ ባወጣው ዘገባ ላይ በተለይ ከመጪው ምርጫ በፊት ሊደረጉ ይገባሉ ያላቸውን ነገሮች በዝርዝር አመልክቷል። ሪፖርቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ በአገር ውስጥና በውጪ ተስፋን የፈነጠቀ ቢሆንም አደገኛና ከፋፋይ ሁኔታንም ደቅኗል ይላል። ቡድኑ እንዳለው በቅርቡ ጥቅምት ወር ላይ ኦሮሚያ ውስጥ የተቀሰቀስው ተቃውሞ የደም መፋሰስን ማስከተሉን ጠቅሶ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የተከሰቱ ግጭቶች በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞትና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩት ደግሞ መፈናቀል ምክንያት መሆናቸውን አመልክቷል። • ሲዳማ: 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል ሪፖርቱ አክሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በብቸኝነት አገሪቱን ሲመራ የነበረውን ኢህአዴግን ለመለወጥ የወሰዱት እርምጃ ያለውን መከፋፈል የበለጠ ሊያሰፋው እንደሚችል አመልክቷል። ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩና አጋሮቻቸው እያካሄዱ ካለው የለውጥ እርምጃ አንጻር በኦሮሞ ቡድኖች መካከል እንዲሁም በአማራና በትግራይ ክልል አመራሮች መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ጥረት ማድርግ እንዳለባቸው በመምከር፤ "ነገር ግን ውጥረቶቹ እየተባባሱ የሚሄዱ ከሆነ ይደረጋል የተባለው ምርጫ ማዘግየት ሊያስፈልግ እንደሚችል" ጠቁሟል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ የወሰዷቸው ተከታታይ የለውጥ እርምጃዎች በአገር ውስጥና በውጪ ትልቅ ተቀባይነትን እንዳስገኘላቸው የጠቀሰው የክራይስስ ግሩፕ ሪፖርት፣ ነገር ግን እርምጃዎቹ የነበረውን ሥርዓት በማስወገድ የመንግሥትን አቅም እንዳዳከመው ጠቅሷል። ይህም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ስልጣን ያመጣው ሕዝባዊ ተቃውሞን ያንቀሳቀሰው የብሔርተኝነት እንቅስቃሴ "አዲስ ጉልበት እንዲያገኝ አድርጎታል" ይላል። አክሎም በግንቦት ወር እንደሚካሄድ በሚጠበቀው ምርጫ እጩዎች ከየመጡበት የብሔር ቡድን ድምጽ ለማግኘት ፉክክር ስለሚያደርጉ ግጭቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ስጋቱን ገልጿል። ክራይስስ ግሩፕ በሪፖርቱ በአገሪቱ ውስጥ በተለይ ስጋትን የሚፈጥሩ ያላቸውን አራት ሁኔታዎችን አመልክቷል። • የደቡብ ክልል፡ ውስብስቡ የዐብይ ፈተና የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጡበትን የኦሮሚያ ክልልን የሚመለከት ሲሆን ተቀናቃኞቻቸው እንዲሁም አንዳንድ የቀድሞ አጋሮቻቸው ሳይቀሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የክልሉን ጥቅም በማስከበር በኩል የበለጠ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ያምናሉ። ሁለተኛው ተግዳሮት ደግሞ በኦሮሞና በአማራ ፖለቲከኞች መካከል በአዲስ አበባና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያለው የተጽእኖ ፉክክር ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ ተካልለዋል በሚባሉ የድንበር አካባቢዎች ያለው የመረረ ውዝግብ እንዲሁም አራተኛው ያቋቋሙትና በበላይነት ሲመሩት የነበረው ሥርዓት እየፈረሰ ነው በማለት ቅሬታቸውን የሚያቀርቡት የትግራይ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያላቸው ተቃውሞ ዋነኛ ፈተናዎች እንደሆኑ በሪፖርቱ ተመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪም በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ እየጨመረ የመጣው በአብያተ ክርስቲያናትና በመስጊዶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በእምነቶች መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ መምጣቱን ከመጠቆሙ ባሻገር አገሪቱ ባለባት ችግር ላይ ሌላ ፈተናን የሚጨምር ነው ብሏል ሪፖርቱ። ሌላኛው የውጥረት ምንጭ ብሎ ሪፖርቱ ያስቀመጠው ጉዳይ ደግሞ አገሪቱ የምትከተለው የብሔር ፌደራላዊ ሥርዓት ጉዳይ ነው። ይህንን በሚደግፉና በሚቃወሙ ወገኖች መካከል ያለው ክርክር በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ "ዋነኛ የመፋለሚያ ምክንያት" መሆኑን ጠቅሷል። • የህወሓት አመራሮች ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጋር ስለምን ጉዳይ ተወያዩ? በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት ግንባር ሌሎች አጋር ድርጅቶችን አካትቶ አንድ ወጥ አገር አቀፍ ፓርቲ ለመሆን ከወሰነ በኋላ ድጋፍና ተቃውሞ እንዳጋጠመው ሪፖርቱ ጠቅሶ፣ ውህደቱ ከላይ በኢህአዴግ የተያዘው የመንግሥት ቢሮክራሲ ውስጥ ተጨማሪ ውጥረት ሊፈጥር እንደሚችል ሪፖርቱ አመልክቷል። እርምጃው የብሔር ፌደራሊዝምን ሊያስቀር ይችላል በሚል የትግራይ አመራሮችና የኦሮሞ ቡድኖች መቃወማቸው የሚታወስ ሲሆን ህወሓትም አዲሱን ፖርቲ እስካሁን ድረስ አልተቀላቀለም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉንም የሚያቀራርብ አስማሚ እርምጃዎች በመውሰድ አገሪቱን አንድ ለማድረግ ጥረት ቢያደርጉም ከባድ ተግዳሮቶች እንደገጠማቸው የክራይስስ ግሩፕ ሪፖርት ያመለክታል። ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥታቸውና ዓለም አቀፍ አጋሮች ሊወስዷቸው ይገባል ያላቸውን እርምጃዎች ሪፖርቱ ጠቁሟል። በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የአማራና የትግራይ አመራሮች ግንኙነታቸውን የሚያሻሸል ውይይት እንዲያደርጉ ግፊት ማድርግና በኦዲፒ ውስጥም ሆነ ከሌሎች የኦሮሞ ተቃዋሚ አባላት ጋር በመነጋገር ልዩነቶች ከኃይል ይልቅ በምርጫ ውጤት መፍትሄ እንደሚያገኙ መተማመን ላይ መድረስ ይጠበቅባቸዋል ሲል ይመክራል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራና በኦሮሞ አመራሮች መካከል የሚካሄዱ ውይይቶች እንዲቀጥሉ በማድረግ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የሚስተዋሉ ውጥረቶችን ማርገብ ይጠበቅባቸዋል ይላል ሪፖርቱ። • ከ20 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? መንግሥት ከትግራይ አንጻር እርቅ የሚያወርድ እርምጃን በመውሰድ ከቀድሞ ባለስልጣናት አንጻር የሚነሱ ክሶችን ተመልሰው እንዲያጤኑ ሊያደርግ ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም ሽግግሩን ተከትሎ የተፈጠረውን አደገኛ የሆነውን የትግራይ መገለል መንግሥት ሊያጤነው ይገባል። የትግራይ አመራሮችም በበኩላቸው እንደማይቀበሉት ያሳወቁትን ከአማራ ክልል ጋር የሚወዛገቡበትን የይገባኛል ጥያቄዎች ለመመለስ የተቋቋመውን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን በተመለከተ ውሳኔያቸውን መለስ ብለው ማስተካከል ይኖርባቸዋል ይላል ሪፖርቱ:: በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩና አጋሮቻቸው ውህድ ፓርቲ በሚመስርቱበት ሂደት ውስጥ የብሔር ፌደራሊዝሙ ሊቀር ይችላል በሚል የተፈጠረውን ስጋት በጥንቃቄ ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል የሚለው ክራይስስ ግሩፕ፣ በሕገ መንግሥቱ ላይ ማንኛውም አይነት ማሻሻያ የሚደረግ ከሆነ የሚመለከታቸው ወገኖች በሙሉ የሚሳተፉበት እንደሚሆን በግልጽ ማስቀመጥ ያስፈልጋል ብሏል። ሪፖርቱ እንደሚለው ምርጫው በተያዘለት ጊዜ የሚካሄድ ከሆነ ቀደም ብሎ ቁልፍ ተቃዋሚ ኃይሎችንና ሲቪል ማህበራትን በማሳተፍ ከምርጫው በፊትና በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን ለማስወገድ ተከታታይ ውይይቶችን ማድረግ ያስፈልጋል። ነገር ግን መከፋፈልና ግጭትን የሚያስከትል የምርጫ ዘመቻ የሚያይል ከሆነ መንግሥት ከዋነኛ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ድጋፍ በመጠየቅ ምርጫው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍና ብሔራዊ ውይይት እንዲካሄድ ሊጠይቅ ይችላል። ሪፖርቱ ለኢትዮጵያ መንግሥት ካቀረበው ሃሳብ በተጨማሪ ለአገሪቱ ዓለም አቀፍ አጋሮችም ጥሪ አቅርቧል። በዚህም መሰረት አጋሮች የሚይዙት አቋም በመሬት ላይ ያለውን አሳሳቢ ሁኔታን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት ብሏል። ስለዚህም ለሽግግሩ በይፋ ድጋፋቸውን በመግለጽ በዝግ ደግሞ ሁሉም ወገኖች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማግባባት ይጥበቅባቸዋል ብሏል። ከዚህ ባሻገርም በመጪዎቹ ወራት የፖለቲካውና የደህንነቱ ሁኔታ የማይረጋጋ ከሆነ ምርጫው እንዲዘገይ ሃሳብ ሊያቀርቡ ይችላሉ። የውጪ አጋሮች የሚሰጡት ተከታታይ የገንዘብ ድጋፍ እስፈላጊነትን የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ የተዳከሙ ተቋማትን ለማጠናከር፣ የኢኮኖሚ መዋቅር ለውጥ ለማምጣት እንዲሁም በለውጡ ወቅት የሚከሰትን የወጣቱን ቅሬታና ተቃውሞ ለመቀነስ ይረዳል። • የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ? ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ለብዙዎች ተስፋን የሰጠ እንደሆነ የጠቀሰው ሪፖርቱ የሚታዩ ምልክቶች ግን ለቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት አሳሳቢ ናቸው ብሏል። የእንዳንዶች ስጋት የተጋነነ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጀመሩት የለውጥ ሂደት ላይ ጥንቃቄን በማከል ወሳኝ የሆኑ ደጋፊዎችን አሳትፈው መጓዝ እንደሚያስፈልጋቸው አመልክቷል። በተጨማሪም ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለማሳተፍ የሚያደርጉትን ጥረት በማጠናከር፣ በሚወዛገቡ የክልል ልሂቃን መካከል ውይይቶች እንዲቀጥሉ በማድረግ፣ የገዢው ግንባር ውህደት አገሪቱን እንደማያናጋ የሚያረጋግጡ እርምጃዎችን መውሰድና ለአሁን በሕገ መንግሥቱና በብሔር ፌደራሊዝም ላይ የሚደረጉ መደበኛ ድርድሮችን ለሌላ ጊዜ ማቆየት እንደሚያስፈልግ የክራይስስ ግሩፕ ሪፖርት ይመክራል።
xlsum_amharic-train-271
https://www.bbc.com/amharic/news-49792728
'ሶሪያውያን' ስደተኞች የስፖርት ቡድን አባላት በመምሰል ድንበር ሲሻገሩ ግሪክ ውስጥ ተያዙ
የሶሪያ ዜጎች ሳይሆኑ እንዳልቀረ የተገመቱ 10 ሰደተኞች የመረብ ኳስ ተጫዋች መስለው ወደ ስዊዘርላንድ በሕገ-ወጥ መንገድ ለመጓዝ ሲሞክሩ በግሪክ ፖሊስ አቴንስ አየር ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
[ "የሶሪያ ዜጎች ሳይሆኑ እንዳልቀረ የተገመቱ 10 ሰደተኞች የመረብ ኳስ ተጫዋች መስለው ወደ ስዊዘርላንድ በሕገ-ወጥ መንገድ ለመጓዝ ሲሞክሩ በግሪክ ፖሊስ አቴንስ አየር ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።" ]
ስደተኞቹ ሶሪያውያን ሳይሆኑ አይቀርም ተብሏል። የቡድኑ አባላት ተመሳሳይ የስፖርት ትጥቅ የለበሱ ሲሆን ሁለት የመረብ ኳሶችም በእጆቻቸው ይዘው ነበር። ፖሊስ እንደሚለው ሶሪያውያን እንደሆኑ የተገመቱት 10ሩ ስደተኞች የእራሳቸው ባልሆነ ፓስፖርት ለመጓዝ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። • ሚሊዮን ዶላር አጭበርባሪው ስደተኛ • «ሳሸንፍ ጀርመናዊ ስሸነፍ ስደተኛ» ኦዚል • ካለሁበት፡ ''በሜዲትራንያን ባህር ከመስመጥ መትረፌ ሁሌም ይደንቀኛል" ስደተኞቹ መዳረሻቸውን ወደ የስዊዘርላንዷ ዙሪክ ማድረግ ነበር ህልማቸው። ግሪክ ወደ ተቀሩት የአውሮፓ ሃገራት መሄድ ለሚፈልጉ ስደተኞች ቅድሚያ መሻገሪያ ሃገር ናት። ሌስቦስ እና ሳሞስ የሚባሉ ታዋቂ የግሪክ ደሴቶችን ጨምሮ ብዙ ደሴቶች ከአቅማቸው በላይ ስደተኞችን በማስተናገዳቸው ማህብራዊ ቀውስ እየተፈጠረባቸው ነው።
xlsum_amharic-train-272
https://www.bbc.com/amharic/news-42514461
"ለሴት ምሁራን የተከለከለ ኃላፊነት?"
በአገሪቱ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር 45 እንደሚደርስ እየተገለፀ ነው። ከእዚህ ሁሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱም በሴቶች ተመርቶ አያውቅም ቢባል ያለጥርጥር በአገሪቱ ለእዚህ ሃለፊነት የሚበቁ ሴቶች የሉም ወይ? የሚል ጥያቄ ይከተላል።
[ "በአገሪቱ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር 45 እንደሚደርስ እየተገለፀ ነው። ከእዚህ ሁሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱም በሴቶች ተመርቶ አያውቅም ቢባል ያለጥርጥር በአገሪቱ ለእዚህ ሃለፊነት የሚበቁ ሴቶች የሉም ወይ? የሚል ጥያቄ ይከተላል።" ]
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል በተለያየ መንገድ ባስነገረው ማስታወቂያ መሰረት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ለመሆን የውጭ ሃገር ዜጎችን ጨምሮ 22 ምሁራን አመልክተዋል። ከመካከላቸውም 13ቱ ለቀጣዩ ውድድር ቀርበዋል። የውጭ ሃገር ዜጎች እንኳ ለውድድር ራሳቸውን ሲያቀርቡ አንድም ሴት ተወዳዳሪ ኢትዮጵያዊት ምሁር የለችም። ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ 11 ፕሬዝዳንቶች መርተውታል። አሁን ካመለከቱት ምሁራን የሚያሸንፈው 12ኛው ፕሬዝዳንት ይሆናል። በዩኒቨርሲቲው የፕሬዝዳንትነት መንበር የወንዶች ብቻ መሆኑ ይቀጥላል ማለት ነው። በተለያየ ዘርፍ ምርምር በማድረግ ለአገሪቱ አስተዋፆ ያበረከቱ፤ በተመሳሳይም በተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩና ብዙ ጥናቶችን ያደረጉ ሴት ምሁራን አሉ። ነገር ግን ከዚህ ቀደምም ሴት ምሁራን የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆኑ ሲባል ብዙ አልተሰማም። ለምን? በአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የመሆን ውድድርስ ለምን ሴት አመልካቾች የሉም? የሚል ጥያቄ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አቅርበን ነበር። የዩኒቨርሲቲው ህዝብ ግንኙነት አቶ አሰማኸኝ አስረስ ብቃት ያላቸውና የትም ያሉ ምሁራን መረጃው ይደርሳቸው ዘንድ እንዲወዳደሩ ማስታወቂያው በተለያየ መንገድ እንዲነገር መደረጉንና ብቃት ያላቸው ሴቶች እንደሚበረታቱም ጭምር መገለፁን ይናገራል። ቢሆንም ግን አንድም ሴት አላመለከተችም። በአሁኑ ወቅት ከዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ሠራተኞች (መምህራን) 15 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ፤ ዩኒቨርሲቲው በታሪኩ ሴት ፕሬዝዳንት ግን ኖሮት አያውቅም። ባለፉት ዓመታት ዩኒቨርሲቲውን በምክትል ፕሬዝዳንትነት ያገለገሉ ሴቶችም ሁለት ብቻ ናቸው። እነርሱም በፕሮፌሰር አንድርያስና በፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ የፕሬዘዳንትነት ዘመን የነበሩ ናቸው። ዩኒቨርሲቲው ሴት ምሁራንን በብዛት ለማፍራት የተለያዩ ጥረቶች እንደሚያደርግ የሚናገሩት አቶ አሰማኸኝ፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸው ላይ ከፍተኛ ውጤት ባያመጡም ጥሩ ውጤት ያላቸው ሴት ተማሪዎች ተባባሪ ምሩቃን ሆነው እንዲቀጠሩ ያደርጋል። በተጨማሪም በዩኒቨርሲቲው ሥርዓተ-ፆታ ቢሮ አማካኝነት ሴት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርቶችን እንዲከታተሉ ማድረግም ሌላው ሴቶችን የመደገፍ እርምጃ እንደሆነ ባለሙያው ይናገራል ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን 11 ፕሬዝዳንቶች ነበሩት ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ በቅርቡ ፕሬዝዳንቱን በመረጠው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለውድድር ቀርበው ከነበሩት ሰባት ተወዳዳሪዎች መካከል ብቸኛዋ ሴት ነበሩ። በመጨረሻም በውድድሩ ሦስተኛ ሆነዋል። ዶ/ር ሙሉነሽ በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲውን በምክትል ፕሬዝዳንትነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ከዓመት ከስምንት ወር በፊት ለምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ከነበሩት ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ሴቶች ሁለት ብቻ እንደነበሩ ያስታውሳሉ። የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትነት በውድድር ከመሆኑ በፊት ዩኒቨርሲቲውን ለሁለት ዓመት በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉ ዶ/ር የሺመብራት ካሳ የተባሉ ሌላ ሴት ነበሩ። ባለን መረጃ መሰረት ዶ/ር የሺመብራት በአገሪቱ አንድ ዩኒቨርሲቲን በፕሬዝዳንትነት የመሩ ብቸኛዋ ሴት ኢትዮጵያዊ ምሁር ናቸው። በአገሪቱ የዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንትነት መንበር ሁሌም በወንዶች የተያዘ እንደሆነ፤ ምንም እንኳ ብቃት ያላቸው ሴቶች ቢኖሩም በዚህ ቦታ ላይ ሴቶችን ለመቀበል የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዝግጁ እንዳልሆነ ዶ/ር ሙሉነሽ ይናገራሉ። በዩኒቨርሲቲዎች ያለው እውነታ ሴቶች ወደ አመራር እንዲወጡ የሚያመች እንዳልሆነም ያምናሉ። ሴቶች ይበረታታሉ፤ ለሴቶች ማበረታቻ አለ ቢባልም ይህ ግን በተግባር የሚታይ እንዳልሆነ ዶ/ር ሙሉነሽ ያስረዳሉ። "እንኳን ድጋፍ ለማድረግ ድጋፍ የማያስፈልጋቸውንና ብቃት ያላቸውን ሴቶች እንኳን ለመቀበል ማህበረሰቡ ዝግጁ አይደለም። የሚፈልገው የተለመደውን ነገር ማስቀጠል ነው"ይላሉ። ዛሬ ላይ ብቃት ያላቸውን ሴቶች በአመራር ደረጃ መቀበል ካልተቻለ በአዎንታዊ ድጋፍ ሴቶችን ማብቃት ብዙ አስርታትን እንደሚፈጅም ያምናሉ። የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባል የነበሩና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ድህረ-ዶክትሬታቸውን በመስራት ላይ የሚገኙ ሌላ ሴት ምሁርም በአጠቃላይ በዶ/ር ሙሉነሽ ሃሳብ ይስማማሉ። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ አመራር ደረጃ ለመውጣት ለሴቶች የተመቹ እንዳልሆኑና ፈተናውም ለሴቶች ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር እጥፍ ድርብ እንደሆነ ይናገራሉ። "መካከለኛ የሚባሉ የአመራር ደረጃዎች በሙሉ በወንዶች የተያዙ ናቸው" በማለት አጠቃላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መዋቅሮች ምቹ አለመሆናቸውን ይገልፃሉ። ብቃት ስላላቸው ብቻ ሴቶች እነዚህን መዋቅሮች አልፈው ወደ ላይ መውጣት አዳጋች እንደሆነም ይጨምራሉ። ደቡብ ክልል ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ያስተምሩ በነበረበት ወቅት ያጋጠማቸውን ነገር እንደ ቀላል ማሳያ ያስታውሳሉ። "ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ኮንፍረንስ ነበር እኔም ፅሁፍ አቅራቢ ነበርኩ። ዩኒቨርሲቲው በር ላይ ቀሚስሽ ጉልበትሽን አይሸፍንም አትገቢም ተባልኩ። ይሄ መቼ ማን ያወጣው ህግ ነው? ብዬ ስጠይቅ ከዲን በላይ ያሉ ሰዎች ተባልኩ። ከዲን በላይ ያሉት ሁሉ ወንዶች ነበሩ። በመጨረሻ ስልክ ደዋውዬ ገባሁኝ። ኋላ ላይ ዩኒቨርሲቲው እውነትም እንደዚያ ያለ ህግ ማውጣቱን ተረዳሁ"ይላሉ። በዚያ አጋጣሚ ፅሁፋቸውን ማቅረብ ባይችሉ ኖሮ የእሳቸው ድክመት ነበር? ጉዳዩ እንደራሳቸው ድክመት እንጂ የዩኒቨርሲቲው አሰራር ያደረሰባቸው ተፅእኖ ውጤት ተደርጎ ሊታይ እንዳልነበር በርግጠኝነት ይናገራሉ። ከእንደዚህ አይነቱ የበር ላይ አጋጣሚ ጀምሮ እስከ ላይ የሴት መምህራን መንገድ አስቸጋሪ እንደሆነና በዚህ መልኩ ወደ አመራር መውጣት ደግሞ በጣም ከባድ እንደሆነ ያስረዳሉ። አሉ የሚሏቸው የመዋቅር ችግሮች ትልቅ አይደሉም። ይልቁንም "አመራር ላይና መካከለኛ ደረጃ ላይ ላሉ ሴቶች ፈተና የሚሆኑ ትንንሽ እንቅፋቶች ናቸው። ስለዚህ ወደ ላይ ልውጣ የምትል ሴት ብዙ ትንንሽ እንቅፋቶችን ማለፍ ይጠበቅበታል"ይላሉ። ለሴቶች አዎንታዊ ድጋፍ ይደረጋል የሚባለውም በወሬ እንጂ በተግባር የሚታይ እንዳልሆነ ይገልፃሉ። እንደሳቸው እምነት ወደ ላይ መውጣት የቻሉ ጥቂት ምሁራን ሴቶችም ብዙ እንቅፋቶችን ማለፍ የቻሉ እንጂ ከሚባለው አዎንታዊ ድጋፍ የተጠቀሙ አይደሉም። በአሁኑ ወቅት የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ሴት ሲሆኑ ይህም በውድድር የሆነ ነው። ከአጠቃላይ አካዳሚክ ሰራተኛው ደግሞ 14 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ ሃይለስላሴ ይናገራሉ። ከአንጋፋዎቹ አንዱ የሆነው ጅማ ዩኒቨርሲቲም ሴት ፕሬዝዳንት ኖሮት አያውቅም። አወዳድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት የሾመውም ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት ነው። በውድድሩ ያሸነፉት ዶ/ር ፀጋ ከተማ በመማር ማስተማር ሥራ ረዥም ጊዜን ያሳለፉት በዚሁ ዩኒቨርሲቲ ስለሆነ ሁሌም በወንዶች ይያዝ ወደ ነበረው ወንበር ሲመጡ የተቀባይነት ችግር እንዳላጋጠማቸው ይናገራሉ። ሴቶች ወደ አመራር ሲወጡ የተለያዩ ችግሮች አያጋጥሟቸውም ግን አይሉም። "በየዩኒቨርሲቲው ብቃት ያላትን ሴት ማህበረሰቡ ሳይወድ በግድ ይቀበላል"ይላሉ። የአመራር ልምድ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለመመረጥ ዋነኛ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ምንም እንኳ በትምህርት ደረጃቸው የላቁ ቢሆኑ በየዩኒቨርሲቲው ለአመራርነት፤ ለምሳሌም ለዲፓርትመንት ሃላፊ ወይም ተባባሪ ዲንነት ማስታወቂያ ሲወጣ ሴት ምሁራን እንደማያመለክቱ አስተያየት የሚሰጡ አሉ። በዚህ ምክንያት የአመራር ልምድ አለማዳበራቸው ደግሞ ለፕሬዘዳንትነት እንወዳደር ቢሉ እንኳን ከመንገድ ያስቀራቸዋል ሲሉም ያክላሉ። እነዚህ አስተያየት ሰጭዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሴቶች ወደ ፕሬዝዳንትነት ያልመጡት ሁኔታዎች ምቹ ስላልሆኑ ብቻ ሳይሆን እራሳቸውም ወደ ኋላ በማለታቸው ነው ሲሉ የሚከራከሩም አሉ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደነገሩን ሴት ምሁራን ለፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ ግፊት መደረጉን ነገር ግን ሴት ምሁራኑ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምክንያታቸውም ምን እንደሆነ ግን አልታወቀም። ከአዲስ አባባና መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ በጅማ ዩኒቨርሲቲም በመማር ማስተማር ውስጥ ያሉ ሴቶች ቁጥር ከአጠቃላዩ 15 በመቶ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ሴት ተማሪዎችንም ሆነ መምህራንን ለማብቃት አዎንታዊ ድጋፎች እንደሚደረጉ ያነጋገርናቸው ዩኒቨርሲቲዎች ይገልፃሉ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን 11 ፕሬዝዳንቶች ነበሩት። 1. ዶ/ር ሉሲን ማት (1945-1954) 2. ደጃዝማች ካሳ ወ/ማርያም (1954-61) 3. ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ (1961-1966) 4. ዶ/ር ታየ ጉልላት (1966-1969) 5. ዶ/ር ዱሪ ሞሃመድ (1969-1977) (1985-1987) 6. ዶ/ር አብይ ክፍሌ (1977-1983) 7. ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ (1984-1985) 8. ፕሮፌሰር ሞገሴ አሸናፊ (1988-1993) 9. ፕሮፌሰር እሸቱ ወንጨቆ (1993-1995) 10. ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ (1995-2003) 11. ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ (2003-2010)
xlsum_amharic-train-273
https://www.bbc.com/amharic/news-46519016
አባይ ፀሐዬ፡ መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው
ከህወሓት መስራቾች አንዱና የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት እንዲሁም በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሠሩት አቶ አባይ ፀሐዬ ከወራት በፊት ተጀምሮ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ፖለቲካዊ ለውጥና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
[ "ከህወሓት መስራቾች አንዱና የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት እንዲሁም በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሠሩት አቶ አባይ ፀሐዬ ከወራት በፊት ተጀምሮ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ፖለቲካዊ ለውጥና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።" ]
ቢቢሲ፡ አሁን በኢትዮጵያ ባለው ለውጥ ላይ ህወሓት እንደ እንቅፋት ተደርጎ ይቀርባል። ለውጡን እንዴት ያዩታል ? አቶ አባይ ፀሐዬ፡ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ለውጥ ኢህአዴግ 'ብዙ በድያለሁ፤ አጥፍቻለሁ' ብለው አራቱ አባል ድርጅቶች ገምግመው ሕዝብን ይቅርታ ጠይቀው የተጀመረ ነው። ኢህአዴግ በዚህ ደረጃ እራሱን እንዲፈትሽ፣ መፈትሄ እንዲያሰቀምጥና ሕዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ ህወሓት የጎላ ድርሻ ተጫውቷል። የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ግምገማ በጣም ጥልቀትና ስፋት ነበረው። ሌሎችም እንደ ፈር ቀዳጅና እንደ ማሳያ ነው የወሰዱት። ስለዚህ ህወሓት የለውጥ ጀማሪ፣ በለውጡ የነቃ ተሳትፎና አብነታዊ ሚና ተጫውቷል። ከዚያ በፊት ህወሓት በትግራይ ሕዝብ ተዓማኒነት እስኪያጣ ድረስ የከፋ ችግር ነበረበት፤ በአገር ደረጃም የኢህአዴግ አካል ሆኖ ብዙ ስህተት የፈፀመ ድርጅት ነው። ስለዚህ ስህተት አልፈፀምኩም፣ ጉድለት የለኝም፣ ያልተገባ ነገር አልሠራሁም አላለም። ይሄን ሁሉ ዘርዝሮ ለኢህአዴግ አቅርቧል፤ ለሕዝቡም ይፋ አድርጓል። ከዚያ በኋላም ህወሓት የኢህአዴግ አካል ሆኖ ለተሠሩ ስህተቶችም ከግምገማና ከሂስ አልፎ ዶክተር ዐብይ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ሲመረጥ፤ በጋራ የመረጥነውን መሪ በፀጋ ተቀብሎ ደግፏል። በፓርላማም ድምፁን ሰጥቶ 'የጋራ መሪያችን ነው፤ የጋራ ለውጥ ነው' ብሎ በቅንነት በሕግ አክባሪነት ለውጡን ደግፏል። • አቶ ጌታቸው አሰፋ የት ናቸው? የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል? • በሱዳን ሄሊኮፕተር ተከስክሶ አራት ባለሥልጣናትን ገደለ በተሠሩ መልካም ሥራዎች ላይም ህወሓት ጉልህ ሚና ነበረው። ለምሳሌ ከኤርተራ ጋር የተደረገው የሰላም ስምምነት፣ በውጭ የነበሩ ተቃዋሚዎች እንዲመጡ፣ በነፍጥ ሲፋለሙ የነበሩ ወደ ሰላም እንዲመጡ የተደረገው ጥረት መነሻው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚና የኢህኣዴግ ምክር-ቤት ውሳኔ ነው። አፈፃፀሙ ላይ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶክተር ዐብይ ላቅ ያለ ጥረት አድርገው ውጤታማ እንዲሆን ሠርተዋል። ይህንንም ህወሓት አድንቆና አመስግኖ ተቀብሎታል። ከዚያም አልፎ የእሰረኞችን መፍታት አድንቆና ተቀብሎ ነው የሄደው። እንዲሁም የባለስልጣናት ሽግሽግ ሲደረግ፤ በርካታ ከስልጣንና ከሚኒስትርነትም የተነሱ ሰዎች ፣ ከዚያ በታች ባሉ የሲቪል ኃላፊነት ቦታዎችም፣ ከሠራዊትም በርካቶች ከህወሓት ነው የተነሱት። ይሄንንም በፀጋ ነው የተቀበለው። ዲሞክራሲያዊ ነን በሚሉ ሃገራት አንድ ፓርቲና አንድ ግለሰብ ከሠራዊት ወይም ከድህንነት ኃላፊነት ሲነሳ ስንት ኩርፍያና ግርግር ይፈጠራል። ህወሓት ግን አካሄዱ ላይ ይስተካከል ብሎ አስተያየት ሰጥቷል፤ ነገር ግን ተግባራዊ አድርጎታል። የቱ ጋር ነው ለውጡን የተቃወመው? አፈፃፀም ላይ የታዩ ጉድለቶች ነበሩ እነርሱም ደግሞ ይታረሙ ብሏል። ያለፉትን 27 ዓመታት ምንም እንዳልተሠራ ይነገራል "ይሄ ትክክል አይደለም፤ አብረን ነው የሠራነው" በሎ ሃሳብ አቅረቧል። እንዴ ህወሓት ነው እንዴ የሰራው? ህወሓት ብቻ ነው እንዴ የሚከፋው? ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብም'ኮ የለፋበት ነው። ይሄ ሲነቋሸሽ ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ ልዩ ቅሬታ፣ ልዩ መከፋት የሚሰማቸው መስሎ የሚታያቸው ካሉ ትክክል አይደሉም። ይሄ ሚዛኑን ይጠብቅ ማለት ለውጥ መቃወም አይደለም። ቢቢሲ፡ ለምሳሌ የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ላይ ህወሓት ተቃውሞ አሰምቶ ነበር ... አቶ አባይ ፀሐዬ፡ የኢትዮ-ኤርትራ ሰላም አፈፃፀሙ ላይ የተወሰኑ ጉድለቶች ነበሩ። ሕዝብን ብናማክር ይጠቅም ነበር። በትግራይ በኩል ያለው በር ይከፈት፤ ግንኙነቱ ከአዲስ አበባ ብቻ አይሁን፤ አሰብ ብቻ ሳይሆን ምፅዋም ይከፈት። የትግራይ ድንበሮች ክፍት ይሁኑ የሚል ነው። ይህንን ሃሳብ ማቅረብ ለውጡን መቃወም አይደለም። ቢቢሲ፡ በውጭ የነበሩ የታጠቁ ኃይሎች ሃገር ቤት ሲገቡስ ደስተኞች ነበራችሁ? አቶ አባይ ፀሐዬ፡ ውጭ የነበሩት ተቃዋሚ ኃይሎች በአጭር ጊዜ እንዲገቡ መደረጉ ህወሓትም የትግራይ ሕዝብም አድንቋል። አብዛኛው በይቅርታና በፍቅር መንፈስ፤ አንድነትን በመፍጠርና ዲሞክራሲን በማስፋት መንፈስ ነው የመጣው። ጥቂቶቹ ግን ከእነ ቂም በቀላቸው ነው ያሉት። ኢህአዴግ ላይ በጠቅላላ ቂምና በቀል ሊወጡ የሚፈልጉ አሉ። ይሄ ደግሞ የለውጡ መፈክር በፍቅርና በይቅርታ እንዲሄድ የሚለውን ሃሳብ ይፃረራል። ስለዚህ ይሄም ትክክል አይደለም 'ተው' መባል አለባቸው። ጥቂቶች ናቸው። ስለዚህ ይሄ ይታረም ማለቱ ምንድን ነው ክፋቱ? ቢቢሲ፡ ህወሓት ለውጡን እንዴት ነው የሚረዳው? በተደጋገሚ የሕግ የበላይነት ይከበር ስትሉስ ምን ለማለት ነው? አቶ አባይ ፀሐዬ፡ ለውጥ ሲባል እናጨብጭብ ማለት አይደለም። ጥሩ ፈር ይዞ የሄደውን እናጨብጭብለት። ዳር እናድርሰው። በስመ ለውጥ ያልሆነ ነገር ተደባልቆ የሚደረግ ከሆነ፤ ተቀላቅሎ የሚፈፀም ሌላ ጤነኛ ያልሆነ ነገር ካለ ደግሞ "ይሄ እንከን አለው፤ ይሄ ለውጡን ያኮላሸዋል። ይሄ አይደለም የለውጡ መንፈስና ይዘት" ብሎ ማረም ለውጡን ከጉድለት የፀዳ እንዲሆን ማድረግና ይሄን በይፋ እንዲታረም መጠየቅ ለውጡን ያጎለብታል እንጂ ለውጡን የሚያደናቀፍ አይደለም። ስለዚህ ላለፈውም ዋነኛው ተጠያቂ ህወሓት፤ የሕግ የበላይነት ሲባልም የትግራይ ተወላጆች ላይ የሚያነጣጥር ከሆነ የትም አያደርሰንም። የሕግ የበላይነት በሁሉም ክልል፣ በሁሉም ድርጅቶች፣ በሁሉም ፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ በእኩል ዓይን በሕግና በጠራ መረጃ ብቻ ፖለቲካዊ ዓላማ በሌለው፤ አድልዎ በሌለው መንገድ ይፈፀም ነው እያለ ያለው የትግራይ ሕዝብና መስተዳደር። • ከስም ፊት የሚቀመጡ መለያዎና አንድምታቸው • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ይሄ ለውጡን መቃወም ነው? አይደለም። ህወሓት ላይና የትግራይ ተወላጆች ላይ አነጣጥሮ ሌላውን ነፃ አድርጎ ሸፍኖና ከልሎ ከሆነ ይሄ የሕግ የበላይነት አይደለም። ሕግ የማስፈን ጉዳይ አይደለም። ሕዝብ እንዲያኮርፍና እንዲያገል የሚያደርግ ካልሆነ የትም አያደርስም። አንድን ሕዝብ ማግለልና ማስከፋት የጀመረ መንግሥት ሌላውንም ማስከፋቱና ማግለሉ አይቀርም። የጊዜ ጉዳይ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ እንዲከፋ እንዲተራመስ ማንም አይፈልግም። ያን ሁላ መስዋዕትነት የከፈለው የትግራይ ሕዝብ፤ ያን ሁላ ትግል ያካሄደው ህወሓት፤ ለኦሮሞ ሕዝብ ለአማራ ሕዝብ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት ነበር። በምን ተዓምር ነው አሁን በየቦታው ለሚፈጠረው ችግር ወያኔ/ህወሓት ምክንያት ተደርጎ የሚነሳው? እንደዚህ ዓይነት አንድ ብሔር የሁሉም ችግር ምክንያት አድርጎ መመልከት አደገኛ ነው፤ ሃገርም ያፈርሳል። ጣት የምንቀስርበት ብሔር ወይም ደግሞ የሕብረተሰብ ክፍል መኖር የለበትም። እንቀፈው፣ እናድምጠው፤ ምን አጎደልን ብለን እንጠይቀው። እንመካከርና እናርም። አለበለዝያ በየቦታው ግጭት፣ በየቦታው ጥርጣሬና ስጋት እየሰፋ የሚሄድበት ሁኔታ በጣም ያሰጋል። ቢቢሲ፡ ትግሉን በመምራት፣ ፌደራላዊ ሥርዓቱን ተግባራዊ በማድረግና አጠቃላይ ሥረዓቱን (በኢህአዴግም ቢሆን) በበላይነት ይመራ የነበረው ህወሓት ነው። በተሰሠራው ስህተት ላይ ተጠያቂነቱ ከፍ ቢል የሚጠበቅ ነገር አይደለም ይላሉ? አቶ አባይ ፀሐዬ፡ ፈረንጆች 'ዳብል ስታንዳርድ' የሚሉት አለ። አንደኛ አረመኔው የደርግ መንግሥት ተወግዷል፣ ልማት መጥቷል፣ ሰላም መጥቷል፣ ሃገራችን አንገቷን ቀና አድርጋ በዓለም እውቅና አግኝታ አካባቢዋን አረጋግታ እራሷን ማልማትና ማረጋጋት ጀምራለች ይላል ብዙ ሰው። በዚህ መንግሥት ውስጥ ህወሓት ከሆነ የአንበሳው ድረሻ የነበረው መመስገን አለበት። ጉድለት ላይ ሲሆን ህወሓት ነው ዋናው ተጠያቂ፤ ስኬቱ ላይ ደግሞ 'እኛ'ኮ ነን የሠራነው፤ አለንበት' የሚል ይመጣል። የህወሓት መዳከምና ወደ ብልሽት መግባቱ፤ እንደ ትጥቅ ትግሉ ጊዜ፣ እንደ ሽግግሩ ጊዜ ሕዝብ አመኔታ የሚያሳድርበት መሆኑ እየቀረና እያሽቆለቆለ መሄዱ ትግራይን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን በአጠቃላይ ደግሞ ሥርዓቱንም መጉዳቱን ገምግሞታል። የእኛ መዳከም ለሥርዓቱ መዳከም ትልቅ ድርሻ አለው ብሎ ነው የገመገመው። ይሄ ማለት ግን ህወሓት አድራጊ ፈጣሪ ነበረ ማለት አይደለም። ስልጣንን ሰብስቦ የያዘው ህወሓት ነው ማለት አይደለም። በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውስጥ ሦስት አራት ሚኒስትሮች፣ ፓርላማ ውስጥ ስድስት ወይም ሰባት በመቶ ናቸው። እኚህ አካላት ናቸው ፖሊሲ የሚያፀድቁት ሕግም የሚያወጡት። እዚያ ላይ ደግሞ አብላጫ ድምፅ ያላቸው ብዙ ወንበር፣ ብዙ ሚኒስትር ያላቸው ትልቁ ድርሻ አላቸው። ፍትህ አካላት ላይም ደግሞ እንደዚሁ። ብዙም የትግራይ ሰዎች አልነበሩበትም። በፖሊስና በሠራዊት አመራር ላይ አዎ ነበሩ። ደህንነትም ላይ እንደዚሁ። ባለፉት ሰባት ስምንት ዓመታት ግን በአበዛኛው የሌላ ብሔር ተወላጆች ናቸው ያሉት። ኤታማዦር ሹምና የደህንነት ኃላፊ የትግራይ ሰው ከሆነ በቃ! ሁሉም ነገር በዚያ ይመዘናል። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? • ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ስለዚህ ሃገሪቱ ለገባችበት ችግር፣ ኢህአዴግ ላጋጠመው ቀውስ፣ የህወሓት አስተዋፀዖ ትልቅ ነበረ፤ ትክክል። ነገር ግን ለሁሉም ነገር ህወሓት ተጠያቂ መሆን ነበረበት የሚል ትክክል አይደለም። ምክንያቱም ህወሓት አናሳ ነው ድምፁ። የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲወስኑ አንድ አራተኛው ነው ድምፁ። ፓርላማም ውስጥ ከአስር በታች ነው ድምፁ። የሚኒስትሮች ምክር-ቤት ውስጥም እንደዚሁ። ስለዚህ ዋናው ተጠያቂ ኢህአዴግ የእራሱ ሥራ አስፈፃሚ ነው ብሎ ነው የገመገመው። ህወሓት ነው ብሎ አልገመገመም። ምክንያቱም ፌዴራል መንግሥቱን ሲመራ የነበረው፤ ሠራዊቱንም ደህንነቱንም ሲመራ የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚያ ቀጥሎ መከላከያ ሚኒስትሩና ኤታማዦር ሹሙ ናቸው። ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው ከህወሓት ከሆነ፡ እሱ በነበረበት ጊዜ ተጠያቂ ይሆናል። ሌላው በነበረበት ጊዜ ድግሞ ሌላው ይጠየቃል። ቀደም ብለን ማድረግ ይገቡን የነበሩብን አሁን የተደረጉ ለውጦች አሉ፤ የሚል ከሆነ እቀበላለሁ። ለምሳሌ እስረኞችን መፍታት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጥ እስኪደረግ ድረስ ለምን አላደረግነውም? እዚህ ላይ ሁላችንም ድርሻ አለን እቀበላለሁ። ህወሓት ብቻ ለሁሉም ነገር ተጠያቂ ነው የሚል፣ መነሻው የህወሓትና የትግራይ የበላይነት ነበረ ከሚል ነው የሚነሳው። ነገር ግን ከመረጃና ከሃቅ አይደለም የሚነሳው። እንደርሱ ቢሆን ለምን የትግራይ ሕዝብ የተለየ ነገር አላገኘም? አንድ ሚሊዮን ሕዝብ በየዓመቱ በረሃብ የሚጠቃ ነው። ህወሓት እራሱን በማያዳግምና ያለምህረት ሂስ አድርጓል። ለማስተካከል ልባዊ ጥረት አድርጓል። አሁንም ለውጡን ደግፎ በሙሉ ልብ እየሄደ ነው። አንዳንድ ጉድለቶችና ዝንፈቶች ደግሞ እንዲስተካከሉ በይፋ በኢህአዴግ መድረክ ላይ እያረመ ነው እየሄደ ያለው። ከዚያ በተረፈ ስለግለሰቦች ከሆነ የሚነገረው ስለሌሎች ግለሰቦችም ይነሳ። እያንዳንዱ ክልሉን ሲያስተዳደር የነበረ ይጠየቅ። ክልሉን ካላለማ፣ ካተራመሰ ህወሓት ነው የሚጠየቅለት? ለምን? ህወሓት ሲያስተዳድረው የነበረው ክልል አለ ከትግራይ ውጭ? ስለዚህ 'የጎደለ ነገር ካለ በዋናነት የሚጠየቀው እዚያ ያለው ፓርቲ ነው' ብለን ነው በኢህአዴግ ውስጥ የገመገምነው። ለምንድነው ወደ ህወሓት ጣት የሚቀሰረው? አንቀበልም፤ ድርጅቱም እንደዚያ ብሎ አልገመገመም። በፌደራል ደረጃ ላለው ችግር ደግሞ የምንጠየቀው በጋራ ነው። ለዚያውም ዋናው ተጠያቂ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ነው። ከዚያ በመቀጠል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ብለን ነው የገመገምነው።
xlsum_amharic-train-274
https://www.bbc.com/amharic/news-45677196
«ማስተር ፕላኑ ተመልሶ ይመጣል» አቶ ኩማ ደመቅሳ
በኦሮሚያ ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞን ቀስቅሶ የነበረው አዲስ አበባን በዙሪያዋ ካሉ የኦሮሚያ ከተሞች ጋር ያስተሳስራል የተባለው ማስተር ፕላን ተራማጅና አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል ብለው እንደሚያስቡ ኦህዴድ ሊቀ መንበር እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ ለቢቢሲ ተናገሩ።
[ "በኦሮሚያ ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞን ቀስቅሶ የነበረው አዲስ አበባን በዙሪያዋ ካሉ የኦሮሚያ ከተሞች ጋር ያስተሳስራል የተባለው ማስተር ፕላን ተራማጅና አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል ብለው እንደሚያስቡ ኦህዴድ ሊቀ መንበር እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ ለቢቢሲ ተናገሩ።" ]
ባለፈው ሳምንት ኦዴፓ (የቀድሞው ኦህዴድ) በጅማ ከተማ ድርጅታዊ ጉባኤውን ባደረገበት ወቅት ተሳታፊ የነበሩት አቶ ኩማ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ አወዛጋቢ ስለነበሩና እርሳቸው በከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት ላይ በነበሩበት ጊዜ ስለታቀዱና ተግባራዊ ስለተደረጉ ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል። «ኦሮሞ እና አማራን የሚነጣጥሉ አይሳካላቸውም» በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትና ከ2006 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላንን በተመለከተ የተሳሳተ አመለካከት እንዳለ ተናግረዋል። ጉዳዩ ከመፈናቀል ጋር አብሮ ስለመጣ እንጂ «ተራማጅ አስተሳሰብ ነው ብዬ አስባለሁ» በማለት የሚናገሩት አቶ ኩማ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ማስተር ፕላኑ አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል ብለው እንደሚያስቡ ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪም በተመሳሳይ ኦሮሚያ ውስጥ ለጠንካራ ጥያቄና ተቃውሞ ምክያት የነበረው የአዳማ ከተማን የኦሮሚያ ክልል መዲና እንድትሆንና የክልሉ መስሪያ ቤቶች ወደዚያው እንዲዘዋወሩ መደረጋቸው ይጠቀሳል። • ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን? ስለዚህ ጉዳይ የተጠየቁት አቶ ኩማ ውሳኔው ስህተት እነደሌለበት ያምናሉ። አሁንም ወደኋላ መለስ ብለው ሲመለከቱ «አሁንም ያኔ የነበረኝ አቋም ስህተት ነው ብዬ አላምንም» ካሉ በኋላ፤ «አዳማ የክልሉ ዋና ከተማ ሆና እንደተቀየረች ብትዘልቅ ኖሮ ከተማዋ ታድግ እንደነበር» ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም ዋና ከተማን በመምረጥ ረገድ ሁሉንም እንቅስቃሴ ተቆጣጥሮ ሥራ ለማከናወን የተሻለው እንደሚመረጥ ጠቁመዋል። በውሳኔው ውስጥም ግፊት እንዳልተደረገባቸው ሲያስረዱም «ያኔ ይህንን ያደረገው ሌላ ኃይል ነው የተባለው ውሸት ነው። ውሳኔውን የወሰነው እኔና ከእኔ ጎን የነበሩት ናቸው» ብለዋል። ይህም ሆኖ የኦሮሞ ህዝብን መብት የሚነካ ውሳኔ አስተላልፈው እንደማያውቁ «በግሌ የኦሮሞ ህዝብ ፋይዳና መብት ላይ ተደራድሬ አላውቅም» በማለት አስረግጠዋል ተናግረዋል። ከሰው የሚያገኙትን የድጋፍ ወይም የነቀፋ ምላሽ እንደማያስቡ ተናግረው «የኦሮሞን ህዝብ የሚጠቅም ሀሳብ ሁሌም አራምዳለሁ» ብለዋል። • የካማሼ ዞን አመራሮች በታጣቂዎች ተገደሉ አቶ ኩማ ደመቅሳ የቀድሞው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ያሁኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በክብር ካሰናበታቸው መስራችና ነባር አባላቱ መካከል አንዱ ሲሆኑ፤ በእሳቸው እይታ ትግል የሚካሄደው ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ሆኖ ብቻ ስላልሆነ፤ ከኮሚቴው መሸኘታቸው ከትግል እንደማያግዳቸው «ትግል በተለያየ ደረጃ ይካሄዳል» በማለት ገልጸዋል። የስንብት ሥነ ሥርዓቱ ሲካሄድ ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው የሚናገሩት አቶ ኩማ፤ ለረዥም ጊዜ የቆዩበትን የትግል ጊዜ በማስታወስ «ከእኛ ጎን የነበሩና የተሰዉ ሰዎች ይህንን እድል አላገኙም። እኔ ይህንን እድል ስላገኘሁ ደስታዬ ወሰን የለውም» ብለዋል። አቶ ኩማ ደመቅሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እንዲሁም በተለያዩ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ለረጅም ጊዜ ሰርተዋል።
xlsum_amharic-train-275
https://www.bbc.com/amharic/news-56890645
በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ለመሳተፍ ስለተጫረቱት ኩባንያዎች ምን ይታወቃል?
የኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ከአንድ መቶ ሃያ ዓመት በላይ በመንግሥት ስር በሚተዳደረው ኢትዮቴሌኮም ብቸኛ የበላይነት በብቸኝነት ተይዞ ቆይቶ አሁን ተፎካካሪ እንዲገባበት ተፈቅዷል።
[ "የኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ከአንድ መቶ ሃያ ዓመት በላይ በመንግሥት ስር በሚተዳደረው ኢትዮቴሌኮም ብቸኛ የበላይነት በብቸኝነት ተይዞ ቆይቶ አሁን ተፎካካሪ እንዲገባበት ተፈቅዷል።" ]
በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ለሁለት የቴሌኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሰጪ የውጭ ኩባንያዎች ፈቃድ ለመስጠት ጨረታ ካወጣ ከወራት በኋላ በተለያዩ አገራት ውስጥ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት ፍላጎት ማሳየታቸው ተገልጿል። መንግሥት በእጁ የሚገኙትን የተለያዩ ተቋማት ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር ከወሰነ በኋላ ካቀረበው ሁለት የቴሌኮም ዘርፍ ፈቃዶች በተጨማሪ የኢትዮ ቴሌኮምን የተወሰነ ድርሻ ለግልና ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ለመሸጥ መወሰኑ ይታወሳል። ይህንን ዘርፍ ለውድድር ክፍት ማድረግ ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ሲሰነዘሩ የነበሩ ሲሆን፤ በተለይ በስልክና በኢንተርኔት የአገልግሎት ጥራት ላይ የሚያስከትለው ለውጥና የዋጋ ቅናሽ በተለያዩ ዘርፎች ላይ አውንታዊ እድገትን ያመጣል የሚሉት ይበረክታሉ። የምጣኔ ሀብት ባለሙያውና ፌርፋክስ አፍሪካ ግሎባል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ እንደሚሉት፤ በየዓመቱ ከፍተኛ እድገት ለማስመዝገብ ዘርፉን ክፍት ማድረግ አስፈላጊ ነው ይላሉ። ወደ ገበያው ለመግባት ያመለከቱት ኩባንያዎች ትልልቅ መሆናቸውን በመግለጽም "ዘርፉን ለማዘመን የውጭ ዕውቀትና ካፒታል ያስፈልጋል። ኩባንያዎቹ ይህንን ይዘው ይመጣሉ ብዬ አስባለሁ" ሲሉ አስረድተዋል። የእነዚህ ተቋሞች ወደ ገበያው መምጣት ምጣኔ ሀብቱ ላይ አወንታዊ ሚና እንዳለው የሚያሰምሩበት አቶ ዘመዴነህ፤ እንደ ባንክ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት፣ አምራቾችና በሌሎችም ዘርፎች ያሉ ተቋማት በተሻለ ቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲሠሩ እንደሚረዳም ያክላሉ። በውጭ ኩባንያዎች ከሚያዙት ሁለቱ የቴሌኮም ፈቃዶች በተጨማሪ ዋነኛው የአገሪቱ አገልግሎት ሰጪ ኢትዮቴሌኮምም በሩን ለባለሃብቶች ይከፍታል። በዚህም በመንግሥት ብቸኛ ባላቤትነት ስር የቇየው ተቋሙ በቅርቡ 40 በመቶን ድርሻ ለውጪ ባለሃብቶች፣ 5 በመቶን ለኢትዮጵያውያን እና 55 በመቶውን መንግሥት እንደሚይዘው ይጠበቃል። የቴሌኮም ዘርፍ ለውድድር ክፍት መሆኑ ጥራት ያለው አገልግሎት በርካሽ ዋጋን ከማስገኘቱ ባሻገር "ለሥራ ፈጠራና ለውድድር በር ይከፍታል" ይላሉ አቶ ዘመዴነህ። እንደ ቴሌኮም ያሉ የመሠረታዊ አገልግሎት ዘርፎች ክፍት ሲሆኑ ከሥራ ፈጠራ በተጨማሪ ምጣኔ ሀብትን እንደሚያሳድጉ የሚናገሩት አቶ ዘመዴነህ፤ "ኢትዮጵያ ዘርፉን ለገበያ ክፍት ማድረጓ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ እርምጃ ነው" ይላሉ። ዘርፉን ለውድድር ክፍት ለማድረግ መንግሥት ከወሰነ ጥቂት ዓመታት የተቆጠሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለሥልጣን ያዘጋጃቸውን ሁለት ፈቃዶች ለመስጠት የጨረታ ጥሪ ያቀረበው ኅዳር 18/2013 ዓ.ም ነበረ። በዚህም 12 ያህል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎት ያሳዩ ቢሆንም በመጨረሻ ላይ የጨረታ ሰነድ ያቀረቡት የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን እና የአራት ድርጅቶች ጥምረት የሆነው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተባሉት ኩባንያዎች ናቸው። በዚህም መሰረት የኬንያው ሳፋሪኮም፣ የብሪታኒያው ቮዳፎን፣ የደቡብ አፍሪካው ቮዳኮም እና ኤምቲኤን ግሩፕ፣ የብሪታኒያው ሲዲሲ ግሩፕ እና የጃፓኑ ሱሙቲሞ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ውስጥ ለመስራት የጨረታ ሰነዳቸውን አስገብተዋል። በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ለመሳተፍ በጋራና በተናጠል ፍላጎት ስላሳዩት ኩባንያዎች ምን ይታወቃል? ተቋሞቹ ከዚህ ቀደም በየትኞቹ አገራት ሠርተዋል? በቴሌኮም ዘርፍ ያላቸው እንቅስቃሴስ እንዴት ይገለጻል? ሳፋሪኮም ዋና መሥሪያ ቤቱ ናይሮቢ የሚገኘው ሳፋሪኮም የኬንያ የቴሌኮም ድርጅት ሲሆን፤ ኬንያ ውስጥ ትልቁ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢና በምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ትርፋማ ከሆኑ ድርጅቶች አንዱ ነው። ሳፋሪኮም የተንቀሳቃሽ ስልክ መስመር፣ የኢንተርኔት፣ የስልክ ግብይት እንዲሁም ሌሎችም አገልግሎቶች ይሰጣል። እአአ በ1997 ገደማ የተቋቋመው ሳፋሪኮም፤ በተለይም ኤምፔሳ በተባለው የሞባይል ገንዘብ መለዋወጫ አገልግሎቱ በስፋት ይታወቃል። ሌላው ኤምሽዋሪ የሚባለው አገልግሎት ሳፋሪኮም ከባንክ ጋር በጥምረት የጀመረው ሲሆን፤ ተገልጋዮች በሞባይል ገንዘብ እንዲቆጥቡና እንዲበደሩ ያስችላል። ሳፋሪኮም በሌሎች አገራት ከሚሠሩ የቴሌኮም ድርጅቶች ጋር በመጣመር አገልግሎቱን ማስፋፋት ጀምሯል። ከእነዚህ መካከል ታንዛንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሕንድ ይጠቀሳሉ። የሳፋሪኮም ድረ ገጽ እንደሚያሳየው፤ ከኬንያ የቴሌኮም ገበያ 64.5 በመቶ ድርሻን ይወስዳል። ወደ 35.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎችም አሉት። የዩናይትድ ኪንግደሙ ቮዳፎን ከሳፋሪኮም 40 በመቶ ድርሻን ገዝቷል። ሳፋሪኮም ኬንያ ውስጥ ከሚገኙ የቴሌኮም ድርጅቶች ቀድሞ የ3ጂ ኢንተርኔት አስገብቷል። በቅርቡ ደግሞ ዋና ዋና በሚባሉ የኬንያ ከተሞች የ4ጂ አገልግሎት መዘርጋት ጀምሯል። የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ጥሪ ማድረግ ሳይችሉ ሲቀሩ፤ ሰዎች እንዲደውሉላቸው የሚጠይቅ የጽሁፍ መልዕክት በነጻ እንዲልኩ የሚያስችል አሠራር ዘርግቷል። ቮዳኮም በአፍሪካ ውስጥ ሰፊ የቴሌኮም አገልግሎት ከሚሰጡት ኩባንያዎች መካከል ቮዳኮም ይጠቀሳል። የኢንተርኔት፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ ጥሪ እንዲሁም ከፋይናንስ ጋር የተያያዙ ዘርፎችም አሉት። መነሻውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገው ቮዳኮም፤ በታንዛንያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሞዛምቢክ፣ ሌሶቶ እና ኬንያ ውስጥ አገልግሎት ይሰጣል። የሞባይል ኔትወርክ ዝርጋታው ከ296 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ እንዳደረገ የድርጅቱ ድረ ገጽ ይጠቁማል። ቮዳኮም ቢዝነስ አፍሪካ በሚል በ29 አገራት ንግድ ነክ አገልግሎቶች ይሰጣል። ከቮዳኮም 60.5 በመቶ የሚሆነው የባለቤትንት ድርሻ የብሪታኒያው ቮዳፎን ነው። የ3ጂ እና 4ጂ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጠው ቮዳኮም፤ በአፍሪካ በግንባር ቀደምነት የቀጥታ 5ጂ ኔትወርክ እንደዘረጋ ይነገርለታል። ቮዳፎን የብሪታኒያው ቮዳፎን አገልግሎት የሚሰጠው በአውሮፓ፣ እስያ እና አፍሪካ ውስጥ ሲሆን፤ በ21 አገራት ውስጥ ኔትወርክ ዘርግቷል። አውሮፓ ውስጥ በኔትወርክ ዝርጋታ የአንበሳውን ድርሻ እንደያዘ የሚነገርለት ቮዳፎን፤ አፍሪካ ውስጥ ከ42 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የሞባይል ገንዘብ መለዋወጫ አገልግሎትን እንዲጠቀሙ እንዳስቻለ በድረ ገጹ የሰፈረው መረጃ ይጠቁማል። ቮዳፎን የተንቀሳቃሽ ስልክ ጥሪ፣ ኢንተርኔትና ሌሎችም ተያያዥ አገልግሎቶች ይሰጣል። በኢንተርኔት አማካይነት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ነክ መገልገያዎችን በማስተሳሰር የሚታወቀውና ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ የሚባለውን አገልግሎት በተለይም ለንግድ ተቋማት ያቀርባል። እንደ አውሮፓውያኑ ከ1980ዎቹ ወዲህ የተስፋፋው ቮዳፎን የስልክ ጥሪ፣ የጽሁፍ መልዕክትና ኢንተርኔት የሚያቀርብ ሲሆን፤ አውሮፓ ውስጥ የ5ጂ ዝርጋታ ላይ በስፋት ይሠራል። በአፍሪካ በጋና፣ በሊቢያና በካሜሩን፤ በመካከለኛው ምሥራቅ ደግሞ በኳታር፣ በባህሬንና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፤ በእስያ ደግሞ በጃፓን እና በሕንድ የሚሰጠውን አገልግሎት መጥቀስ ይቻላል። ኤምቲኤን ግሩፕ ኤምቲኤን ግሩፕ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገ የቴሌኮም ተቋም ነው። በተለያዩ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እንዲሁም የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት አገልግሎት ይሰጣል። ዋና መሥሪያ ቤቱን ደቡብ አፍረካ ጆሀንስበርግ ያደረገው ተቋም ወደ 273 ሚሊዮን የሚጠጉ ተገልጋዮች እንዳሉት በድረ ገጹ ያሰፈረው መግለጫ ይጠቁማል። በ20 አገሮች የሚሠራው ኤምቲኤን ግሩፕ ከፍተኛውን ገቢ የሚያገኘው ከናይጄሪያ ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በ1994 ገደማ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት በተገኘ ድጋፍ ነበር የተቋቋመው። የተንቀሳቃሽ ስልክ ጥሪ እና የሞባይል ገንዘብ ልውውጥ የሚሰጠው ኤምቲኤን ግሩፕ፤ በዋትስአፕ መተግበሪያ ተጠቃሚዎቹ የአየር ሰዓት እና የስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት (ዳታ) እንዲያገኙ በማስቻል ስሙ ይነሳል። ከማስተርካርድ ጋር በመጣመር ለተጠቃሚዎቹ የድረ ገጽ ግብይት (ኢ-ኮሜርስ) ከመዘርጋቱ ባሻገር፤ በሞባይል ገንዘብ መለዋወጥ የሚቻልበት መንገድም አለው። ሱሙቲሞ ኮርፖሬሽን ሱሙቲሞ ኮርፖሬሽን የጃፓን ተቋም ሲሆን ቴሌኮምን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማራ ነው። በብረት ምርት፣ በትራንስፖርትና ምህንድስና፣ በማዕድን፣ በሪልስቴት እና ሌሎችም ዘርፎች ለረዥም ዓመታት ሠርቷል። ከእነዚህ በተጨማሪ በመገናኛ ብዙሃን እና በቴሌኮምዩኒኬሽን ዘርፍ የሚሰጠው አገልግሎት የኬብል ቴሌቭዥን እና 5ጂ የሞባይል ኢንተርኔትን ያካትታል። ቲ-ጋያ የሚባል የሞባይል አከፋፋይ ያለው ሱሙቲሞ ኮርፖሬሽን አጠቃላይ አገልግሎቶቹን በ66 አገራት እንደሚሰጥ ከድረ ገጹ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። ከተሰማራባቸው ዘርፎች መካከል የመገናኛ ብዙሃን እና ቴሌኮምዩኒኬሽን ቅርንጫፉ 11.9 በመቶ ድርሻ ይይዛል። እንደ አውሮፓውያኑ በ1919 ኦሳካ ኖርዝ ሀርበር በሚል ስያሜ ከተቋቋመ በኋላ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማራው ድርጅቱ፤ በምሥራቅ እስያ፣ በአውሮፓ፣ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና ሌሎችም የዓለም ክፍሎች ውስጥ ይንቀሳቀሳል። ሲዲሲ ግሩፕ የብሪታንያው ሲዲሲ ግሩፕ እንደ አውሮፓውያኑ በ1948 ከተመሠረተ ወዲህ ላለፉት 70 ዓመታት በፋይናንስ ዘርፍ ሲሠራ ቆይቷል። በተመሠረተበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በዛምቢያ የሲሚንቶ ዘርፍ፣ በቦትስዋና የከብር እርባታ ዘርፍና በሌሎችም የአፍሪካ እና እስያ አገሮች ሠርቷል። 1998 ላይ ሴልቴል በተባለ የአፍሪካ የሞባይል ስልክ ድርጅት ኢንቨስት ማድረጉ ከቴሌኮም ዘርፍ እንቅስቃሴው አንዱ ነው። በድረ ገጹ ላይ በሚገኘው መረጃ መሠረት፤ በተለያዩ አገሮች በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ፣ በጤና እና ሌሎችም ዘርፎች ኢንቨስት ማድረግ ይቻላል። ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የተደረገባቸው አገራት ሕንድ፣ ናይጄሪያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኮትዲቯር ናቸው።
xlsum_amharic-train-276
https://www.bbc.com/amharic/news-56272130
የኢትዮጵያ ምርጫ 2013፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ያልተመለሰው የሴቶች አካታችነት ጥያቄ
በአስርት አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲ ጉባኤዎችን፣ ክርክሮችን፣ ቅስቀሳዎችን ለተከታተለ አንድ ጎልቶ የሚንፀባረቅ ጉዳይ አለ።
[ "በአስርት አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲ ጉባኤዎችን፣ ክርክሮችን፣ ቅስቀሳዎችን ለተከታተለ አንድ ጎልቶ የሚንፀባረቅ ጉዳይ አለ።" ]
የአንበሳ ድርሻውን የሚይዙት ወንዶች ከመሆናቸው በተጨማሪ በማዕከላዊ እና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነታቸው የሴቶች ቁጥር የተመናመነ ወይም በአንዳንድ ፓርቲዎች እንደሚታየው የሉም ማለት ይቻላል። በኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ ቦርድ እውቅና ያገኙ ከ60 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢኖሩም ሁሉም በሚባል ሁኔታ አመራሮች ወንዶች መሆናቸው በአገሪቱ ውስጥ ግማሽ የህዝብ ቁጥር የሚወክሉት ሴቶች ለምን በነዚህ ፓርቲዎች ውስጥ የውሳኔ ሰጭነት ቦታ አላገኙም የሚለውን ጥያቄ ያጭራል። በእነዚህ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በአመራር ደረጃ ቀርቶ ከወረዳ ጀምሮ ባለው መዋቅሮች ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ይሄን ያህል እንዳልሆነ ተንታኞች ይናገራሉ። በተለይም አገሪቱ ምርጫ በምታካሂድበት ወቅት የሚስተዋለው ክፍተት በከፍተኛ ሁኔታ ጎልቶ ይወጣል፤ ፓርቲዎቹ የሚያቀርቧቸው ዕጩ ተወዳዳሪ ሴቶች አናሳ መሆኑንም ማስተዋል ይቻላል። የሴቶች ውክልና በምክር ቤት እስቲ ወደኋላ 26 አመታትን ተመልሰን የ1987 ዓ.ም ምርጫን እንመልከት። በዚህ አመት በተደረገው አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ 536 ወንዶች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫን ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን የሴቶች ቁጥር ደግሞ 10 ነበር። በዚሁ ወቅት የነበረውን የክልል ምክር ቤቶችን አሸናፊዎች ስንመለከት ደግሞ 1 ሺህ 355 ወንዶች በዘጠኙ ክልለ ባሉ የክልል ምክር ቤት ውስጥ መቀመጫ ማግኘት መቻላቸውን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በዚሁ አመት በዘጠኙ ክልሎች መቀመጫ ያገኙ የሴቶች ቁጥር 77 ነው። አስርት አመታትን ወደኋላ ሄደን በንጉሱ አገዛዝ ዘመን የነበረውን ቁጥር በምንመለከትበት ወቅት ከ240 የፓርላማ አባላት መካከል 2ቱ ሴቶች የነበሩ ሲሆን በደርግ ጊዜ ደግሞ ከ835 የሸንጎ አባላት መካከል 14 ሴቶች ይገኙበታል። ከአስር አመታት በኋላ ወይም ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ ባደረገችው ምርጫ በምክር ቤቱ መቀመጫን ማሸነፍ ያገኙ ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ መሻሻልን አሳይቷል። በ2007 ወይም በአሁኑ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች ሴቶች ያላቸው ቁጥር 212 ወይም በመቶኛ ሲሰላ 38.8 በመቶ ነው። የክልል ምክር ቤቶችን ስንመለከት ደግሞ በወቅቱ አገሪቷን ያስተዳድር የነበረው ኢህአዴግ እና የተለያዩ አጋር ድርጅቶች ሁሉንም መቀመጫዎችን ያገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል 800 ወይም በመቶኛ 40.3 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። ምንም እንኳን በምክር ቤቶች ያለው የሴቶች ውክልና ቁጥር መሻሻል ቢያሳይም በወሳኝ ቦታዎች አለመቀመጥ፣ የይስሙላ ተሳትፎና ቁጥር ማሟያ መሆናቸው የሚነሳ ጉዳይ ሆኗል። በርካቶቹ የፓርቲዎቻቸውን ፕሮግራም ከማስፈፀም በዘለለ አጀንዳዎችን በመቅረፅም ሆነ ፖሊሲዎችን በማርቀቅ ደረጃ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንደሌላቸው ይናገራሉ። በተለይም የስርዓተ ፆታ የኃይል ሚዛን ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት መዋቅራዊ የሆኑ የፖሊሲ ለውጦች ያስፈልጋሉ በሚባልበት ወቅት ሴቶች የራሳቸውን ዕጣ ፈንታ፣ በራሳቸው መወሰን አልቻሉም ይባላል። በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ስድስተኛና አገር አቀፍ ብሔራዊ ምርጫን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ናት፤ ምርጫው የተቆረጠበት ቀን ሊደርስም 13 ሳምንታት ያህል ቀርቶታል። በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረትም የፖለቲካ ፖርቲዎች እጩዎቻቸውን እያስመዘገቡ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም እስከ የካቲት 30፣ 2013 ዓ.ም እንደሚቀጥል ተገልጿል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባላቶቹ በታሰሩበት ሁኔታ፣ ቢሮዎቹ ተዘርፈውና ተዘግተው እንዲሁም የምርጫ መርሃ ግብሩ ባልተሻሻለበት በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ አልሳተፍም ሲል አሳውቋል። ከፓርቲው16 የስራ አስፈፃሚዎች መካከል ብቸኛ ሴት የሆኑት ዶ/ር በላይነሽ ይስሃቅም በዘንድሮው ምርጫ ለመወዳደር ፓርቲያቸውና መንግሥት እያደረገ የነበረውን ውይይት በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። ነገር ግን ፓርቲው ባሉት ሁኔታዎች "ተገፍቼ ወጥቻለሁ" ማለቱን ተከትሎ እርሳቸውም በዘንድሮው ምርጫ አይወዳደሩም። ሆኖም መለስ ብለን ከዚህ በፊት የተሳተፉባቸውን ምርጫዎች እንዲሁም የሴቶች በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ተሳትፎ ማነስ ምክንያቶችን ቢቢሲ ጠይቋቸዋል። "ሴቶች በፖለቲካዊ ተሳትፏቸው ምክንያት ወሲባዊ ጥቃቶችንና የስም ማጥፋት ዘመቻን አስተናግደዋል" ዶክተር በላይነሽ የፖለቲካ ህይወታቸው የሚጀምረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዲን)ን በተቀላቀሉበት በ1997 ዓ.ም ነበር። በዚያኑ አመት በትውልድ ቦታቸው በቄለም ወለጋ በምትገኘው አንፊሎ ወረዳን ወክለው ተወዳደሩ፤ ማሸነፍም ቻሉ። ምንም እንኳን ምርጫውን ማሸነፍ ቢችሉም ለሴቶች ምርጫ ውድድር ውስጥ እጩ ሆኖ መቅረብ ሳይሆን ሴት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ይገጥማቸው የነበሩ ፈተናዎች "ተዘርዝረው አያልቁም" ይላሉ። የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ይገጥማቸው የነበሩት ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታዎች ተደራርበው ይጨምራሉ ይላሉ። በተለያዩ ምርጫዎች በተሳተፉበት ወቅት፣ በተለይም በቅስቀሳ ወቅት የሚያጋጥማቸው ከሆቴል መባረር እንደሆነም ያስታውሳሉ። በአንድ ወቅት አንድ ሆቴል ገንዘባቸውን መልሶላቸው ሌላ ማደሪያ ባለማግኘታቸው መኪና ውስጥ ለማደር መገደዳቸውንም ያስታውሱታል። አንዳንድ ጊዜም ለምርጫ ቅስቀሳ ይዘዋቸው የሄዱት መኪኖችም በፍራቻ ባዶ ሜዳ ላይ ውረዱልን ብለዋቸው ያውቃሉ። ሆቴሎቹም ሆነ የትራንስፖርት መጓጓዣዎች በፍራቻ እንደሚያባርሩዋቸው በተደጋጋሚ ነግረዋቸዋል። እርሳቸው ፓርቲውን በተቀላቀሉበት ወቅት በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ይሳተፉ የነበሩ የሴቶች ቁጥር በጣም አናሳ የነበረና ብዙ መስዋዕትነትም ስለሚያስከፍል በርካቶች መገፋታቸውን ይጠቅሳሉ። "ተቃዋሚ መሆን በራሱ ከባድ ነው" የሚሉት ዶክተር በላይነሽ በተለይ ሴት ተቃዋሚ መሆን ደግሞ በርካቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ዋጋ እንዳስከፈላቸውም በአመታት ታዝበዋል። በወንድ ተቃዋሚዎች ከሚደርሱት ማስፈራሪያ፣ ዛቻዎችና እስሮች በተጨማሪ ዘርዘር አድርገው ባይናገሩትም በፖለቲካ ተሳትፏቸው ምክንያት የመደፈር (ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸው) መኖራቸውን ይጠቅሳሉ። "ተቃዋሚ መሆን እንኳን ለሴት ለወንድ ከባድ ነው። እኔ የማልናገራቸው በርካታ ነገሮች የደረሰባቸው አሉ። ደረሰብን ብለው የሚናገሩት በጣም አስፈሪ ነው። ለሴት በጣም ፈታኝ ነው" ይላሉ። ከዚህም በተጨማሪ ከስራ መባረር፣ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች እንዲሁ በተቃዋሚ ፓርቲ ሴት አባላት ውስጥ የሚደርሱ በመሆናቸው በርካቶችን እንዲፈሩ ማድረጉንም ያስረዳሉ። የእንስሳት ሃኪም የሆኑት ዶክተር በላይነሽ ራሳቸው በፖለቲካ ተሳትፏቸው ምክንያት ከስራ በመባረራቸው ኑሯቸውን በአንድ ወቅት ፈታኝ አድርጎት እንደነበር ያወሳሉ። በተለይም ሴት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ የሚደርሰው የሚከፋው በክፍለ ሀገር ከተሞች በመሆኑ በወረዳዎች ላይ የሚገኙ ሴቶች በፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎም ሆነ በእጩ ተወዳዳሪነት ለመቅረብ ከፍተኛ ፍራቻ እንዳላቸውም ያስረዳሉ። የስርዓተ-ፆታ የኃይል ሚዛን መዛባት የፈጠረው ክፍተት ከፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብ በተጨማሪ የወንዶችንና የሴቶችን ግንኙነት ወይም ሴቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ሊኖራቸው የሚችለውን ቦታ አስመልክቶ በሚወስነው አባዊ ስርዓት (ፓትሪያርኪ) ምክንያት ሴቶች በፖለቲካው፣ በትምህርት እና በኢኮኖሚው ዘርፍ ተሳታፊነታቸውን ወደ ኋላ እንዲቀሩ አድርጓቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በሰፈነው ኢ-ፍትሃዊ የስርዓተ-ፆታ የኃይል ሚዛን ለተለያዩ መድልዎችና ፆታዊ ጥቃቶችም እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል። የስርዓተ-ፆታ ሚዛን ኃይል አለመመጣጠን በተለይም የሚገለፅበት አንዱ ሁኔታ በሴቶች ላይ ያለው ተደራራቢ የስራ ጫና ሲሆን ይህም ሁኔታ ለሴቶች እፎይታ አግኝተው በሌሎች መድረኮች እንዳይሳተፉ አድርጓቸዋል። በተለይም ዶክተር በላይነሽ እንደሚናገሩት በገጠሪቷ ክፍል የማገዶ እንጨት ለቀማ፣ ውሃ መቅዳት፣ ልጆች ማሳደግና ሌሎች ፋታ የማይሰጡ ስራዎች ወስኗቸው ይገኛሉ ይላሉ። ከዚህ በተጨማሪ በከተሞች ዘንድም ቢሆን በፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸው ሴቶች ልጆችን ከመንከባበብ ጀምሮ የማይከፈልባቸው የቤት ውስጥ የስራ ጫናዎች ድርብር ኃላፊነትን ተሸክመው ይገኛሉ። ምንም እንኳን ሴቶች በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ይህ ነው ባይባልም ፓርቲዎች በሚያደርጓቸው የድጋፍ ሰልፎች፣ የምረጡኝ ቅስቀሳም ሆነ ሌሎች ተሳትፎዎች ላይ የሚመዘገበው ቁጥር ከፍተኛ ነው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንደ አንድ ትልቅ ምዕራፍ የሚታየውን የ1997 የመራጭ ሴቶች ቁጥር እንመልከት እስቲ- ግንቦት 07 ቀን 1997 ዓ.ም በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ላይ 27 ሚሊዮን 372 ሺህ 888 ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የሴቶች ቁጥር 13 ሚሊዮን 087 ሺህ 594 ነው። ከተመዘገቡትም ውስጥ በአጠቃላይ 22 ሚሊዮን 610 ሺህ 690 መራጮች ድምፅ ሰጥተዋል፤ ከነዚህም ውስጥ 12 ሚሊዮን 058 ሺህ 511 ወንዶች ሲሆኑ የሴቶች ቁጥር ደግሞ 10 ሚሊዮን 552 ሺህ 179 መሆኑን ከምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። በአመታት ውስጥ መራጩ ህዝብ (ሴቶችም ይሁኑ ወንዶች) ሴት እጩ ተወዳዳሪዎች ካሉ ለመምረጥ ወደኋላ እንደማይሉም ወይዘሮ በላይነሽ በራሳቸው ልምድ አይተውታል። ምንም እንኳን ሴት መራጮች በከፍተኛ ሁኔታ በአመታት ቢጨምሩም የሴት ፖለቲከኞችም ሆነ ተመራጮች ቁጥር አሁንም ይህን ያህል አልተራመደም። በቅርቡ የተመሰረቱት ፓርቲዎች ለዘመናት ወጣቶችን አግልሎ የነበረውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በተወሰነ መልኩ ቢቀይሩም የሴቶች ተሳትፎ ብዙ መራመድ እንዳልቻለም የፓርቲዎቹን የሴቶች ቁጥርና የስልጣን ተዋረድ በማየት መረዳት ይቻላል። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) መስራች ከሆኑት መካከል የ29 አመቷ እመቤት ከበደ አንዷ ናት። በሙያዋ የፕሮጀክት አስተባባሪ የሆነችው እመቤት፣ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ስትገባ የመጀመሪያዋ ሲሆን ይህም በ2010 ዓ.ም ነው። ፓርቲውን ስትመስርት ለእርሷ ዋነኛ ጉዳይ የነበረው "አማራ በባለፉት አስርት አመታት ተወካይ አላገኘም" የሚል እንደሆነ ትናገራለች። ፓርቲያቸውም "የአማራ ውክልናን ማዕከል" አድርጎ ከመነሳቱ አንፃር እመቤት የስርዓተ ፆታ ጥያቄዎችም በዚያው ሊመለሱ እንደሚችሉ ትናገራለች። ሆኖም በፓርቲያቸው ውስጥ ያሉ የሴቶች ቁጥር አነስተኛ መሆኑንም እሷም ቢሆን አትክደውም። ለምሳሌ ያህል ከ45 ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መካከል ሴቶች ሶስት ብቻ ናቸው። ከዘጠኝ ስራ አስፈፃሚዎች መካከል አንዲት ሴት የለችም። ሴቶች ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን በፓርቲያቸው ውስጥ ውሳኔ ሰጭዎች እንዲሆኑ አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርጉ ብትናገርም "ያን ያህል አጥጋቢ አይደለም" ትላለች። ምንም እንኳን በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የሴቶች ቁጥር ዝቅተኛ ቢሆንም በወረዳዎች ደረጃ ባለው አወቃቀር ግን በርካታ ሴቶች ቁልፍ ሚናን እንደያዙም ትናገራለች። እመቤት ለአንድ አመት ያህል የፓርቲው የባህርዳር ፅህፈት ቤት ኃላፊ የነበረች ሲሆን፣ ሴቶች በፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ ለመሆኑ የተለያዩ ምክንያቶች ትሰጣለች። በራሷ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ሴቶች ቁጥር ማሟያ ተደርገው መታየታቸውና (የይስሙላ ሴቶችን አሳትፈናል) ለማለት ብቻ የሚገቡ ሲሆን ሴቶች በወሳኝ ቦታዎች እንደማይቀመጡና አብዛኛውን ጊዜም የስራ ድርሻቸውም ይህን ያህል የረባ አለመሆኑንም ታዝባለች። እንደ ዶክተር በላይነሽ እሷም ቢሆን "ለአመታት በአገሪቱ የሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ተደጋጋሚ እስር፣ እንግልት፣ ዛቻና ማስፈራሪያዎች ሴቶችን በፓርቲዎች እንዳይሳተፉ አድርጓቸዋል" ትላለች። ከዚህም ጋር ተያይዞ "በፖለቲካ ፓርቲዎች መሳተፍም ሆነ የአመራር ቦታውን ይፈሩታል" ትላለች። በተለይም ከፖለቲካ ምህዳሩ ጋር ተያይዞ ቤተሰቦች ስለሚሰጉ ሴቶች የቤተሰብ አባላትን በፖለቲካው እንዳይሳተፉ ተፅእኖ ማድረጋቸውን ትጠቅሳለች። "ለስብሰባዎች በምንሄድበት ወቅት ከፍተኛ ፍራቻ አለ። ሴቶች ራሳችንም እንፈራለን፤ እንዲሁም ቤተሰብም ስለሚሰጋ ከፍተኛ ተፅእኖ ያደርጋል። የተቃውሞ ፖለቲካ ከባድ ነው" ትላለች እመቤት በአብን ፓርቲ ውስጥ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሴቶች ጉዳይ ዴስክ ኃላፊ የሆነችው እመቤት እሷም ቢሆን ቤተሰቦቿ መጀመሪያ አካባቢ ፍራቻ እንደነበራቸው አትደብቅም። ሆኖም በፖለቲካ ፓርቲ ተሳትፎዋ ቀጥላ ኢትዮጵያ በምታደርገው ስድስተኛ ብሔራዊ ምርጫ በባህርዳር ከተማ ዕጩ ተወዳዳሪ ሆና ትቀርባለች። እመቤትን ጨምሮ አብን በአገር ውስጥ ከሚያቀርባቸው እጩ ተወዳዳሪዎች መካከል 30 በመቶዎቹ ሴቶች እንደሆኑም ፓርቲዋን ወክላ ለቢቢሲ ተናግራለች። የዘንድሮ የአገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ሲነሳ በከፍተኛ ደረጃ እየቀሰቀሱ ካሉትና የዜግነት ፖለቲካን አካሂዳለሁ ከሚለው ፓርቲዎች መካከል ኢዜማ ይገኝበታል። ኢዜማም በኢትዮጵያ ደረጃ ከሚያቀርባቸው እጩ ተወዳዳሪዎች መካከል 30 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸውን የኢዜማ የወጣቶች ተጠሪ ፅዮን እንግዳዬ ለቢቢሲ ተናግራለች። ፅዮን እሷን ጨምሮ ከ21 የስራ አስፈፃሚዎች መካከል ስድስቱ ሴቶች እንደሆኑ ትናገራለች። የፅዮን የፖለቲካ ፓርቲ ተሳትፎዋ በኢዜማ ቢጀምርም በአገሪቱ ውስጥ የሰፈነውን የስርዓተ-ፆታ ኃይል አለመመጣጠን እንዲሁም ያሉትን በሴቶች ላይ ጭቆና የሚያሳርፉ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ሌሎች መዋቅሮችን ለመቅረፍ የሚሰራው የሎው ሙቭመንት አካል ናት። በምስረታው ወቅት ባየችው ተስፋ ሰጭ ነገርም ፖለቲካ ፓርቲው ይወክለኛል በሚል እንዳመነች ትናገራለች። ለዚህም እንደ ዋነኝነት የምታነሳው ለስርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጭ ስርአት (Gender responsive system) በመዘርጋት በማህበራዊ ፍትህ የተቃኙ ፖሊሲዎች መኖራቸውን ትጠቅሳለች። ፓርቲዋ በምጣኔ ኃብት፣ ትምህርት፣ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ያወጣቸው 42 ፖሊሲዎችም እንዲሁ በስርዓተ-ፆታ አይን እንዲታይና እንዲፈተሽ ማድረጉንም ታስረዳለች። ከዚህም ጋር ተያይዞ የስርዓተ-ፆታ የኃይል ሚዛን እንዲመጣጠን የምትሰራው ሴታዊት እንቅስቃሴን ማሳተፉ ያለውን ቦታ አሳይ እንደሆነም ትጠቁማለች። ከዚህም በተጨማሪ ከታችኛው መዋቅር ጀምሮ የሴቶች ጉዳይ ተጠሪዎች መኖሩ ፓርቲው የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማስፈን እየሰራ መሆኑ ማሳያ ነው ትላለች። በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ሴቶች እንደ ተቀጥላ መታየት በኢትዮጵያ ታሪክ የተደራጀ ተቃውሞ ከሚነሱት መካከል የፊውዳላዊውን አገዛዝ ለመገርስስና የተቀሰቀው የተማሪዎች ጥያቄ ይጠቀሳል። ስር ነቀል ለውጥን በማቀንቀንና መሬት ለአራሹ በሚል እንቅስቃሴያቸው የአብዮቱ ጠባቂ (ጋርዲያን ኦፍ ዘ ሪቮሉሽን) የሚል ስያሜም ተሰጥቷቸዋል። ተማሪዎቹ የኢትዮጵያ ትግል ለብቻው እንዳልሆነና በተለይም ከዓለም አቀፉ ፀረ-ኢምፔሪያሊዝም፣ ፀረ ቅኝ ግዛት እንዲሁም ዘረኝነትን ከመታገል ጋር ተያይዞ ትብብር ሊኖር እንደሚገባና ትንታኔም በዚያ መልክ ይሰጥ ነበር። በዚያን ወቅት ተሳትፏቸው የሚጠሩት ጥቂት ሴቶች ሲሆኑ በርካቶች የእንቅስቃሴዎቹ መሪዎችም አልነበሩም። ቁጥራቸው ትንሽ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ጥቂቶቹም ቡና በማፍላት፣ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ መያዝ፣ ወረቀት መበተን፣ መፈክር መያዝ የመሳሰሉ ሚናዎች እንደነበሩ የታሪክ ድርሳናት ይዘክራሉ። ቀስ እያሉ ሁኔታዎች የተቀየሩት የሴቶች መብትን እንደ ሰው መብት ወይም ደግሞ እንደ ፖለቲካዊ ጥያቄ ባዩ አንዳንድ የፖለቲካ ንቃተ ህሊናቸው ከፍ ባሉ አመራሮች ምክንያት እንደሆነም የታሪክ ተንታኞች ያስረዳሉ። ከአስርት አመታት በኋላ ይኸው ሴቶችን ከቤት ስራዎች ድርሻ ጋር የመያያዙ ባህሉም ሆነ ልምዱ አልቀረም ። በርካታ የሴት ፖለቲከኞችም ሆነ ፅዮን የታዘበችው ቢኖር በተለያዩ ስብሰባዎች ሴቶች እንዲያስተናብሩ፣ ቡና እንዲያፈሉ፣ ቆሎ ማቀበል፣ አስተናግዱ እና ሌሎች ባለው የስራ ክፍፍል ውስጥ የሴቶች ተብለው የሚሰሩ ስራዎች እንዲያከናውኑ እንደሚጠየቁ ትናገራለች። አንዳንድ ጊዜም የሴቶች ውጫዊ እይታቸውንም ከፖለቲካዊ ህይወታቸው ጋር በማስተሳሰር የሚሰጡ አስተያየቶችንም ሰምታለች "አንቺማ በመልክሽ ትመረጫለሽ" የሚል አስተያዬት እንዲሁም የፓርቲውን ፕሮግራሞች ለማስተዋወቅ "ቆንጆ ሴቶች ለምን አንመርጥም" የሚል ጉዳይ ሰምታለች። የማህበረሰቡን አስተያየት ሙሉ በሙሉ መቅረፍ አስቸጋሪ ቢሆንም ፓርቲው መዋቅራዊ የሆነ መገለልን እንደማይቀበልና ይህንንም ለመፍታት ከደንብ በተጨማሪ የዲሲፒሊን ኮሚቴም አዋቅሯል ትላለች። ከዚህም በተጨማሪም የስርዓተ-ፆታንም በተመለከተ ስልጠናዎች እንደሚሰጡም ታስረዳለች። በላይኛው አመራር ያሉ የፓርቲው አባላት በስርዓተ-ፆታ ጉዳይ ላይ ያላቸው እይታ መልካም ቢሆንም በወረዳ ደረጃ አንድም ሴት ሊቀ መንበር አለመኖሩ የሴቶችን ተሳትፎ ጥያቄ ገና ለመሆኑ ማሳያ ነው ትላለች። ነገር ግን ኢዜማ በዘንድሮው ምርጫ ሴቶች በዕጩ ተወዳዳሪነት እንዲሳተፉ በዕጩ መመልመያ መስፈርት ውስጥ ከፍተኛ ማበረታቻ በማድረጋቸው ምክንያት በርካታ ሴት ዕጩዎችን ማግኘት መቻላቸውን ትናገራለች። "ኢዜማ ስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማስፈን የሚሰራ ፓርቲ ነው" ብላ ፅዮን ሙሉ በሙሉ የምታምን ሲሆን ለዚህም በዋነኝነት "ሴቶች ራሳቸውን ወክለው ራሳቸው መጥተው የራሳቸውን ችግሮች የሚያነሱበትን መድረክ መፍጠር ችሏል" ትላለች። የሴቶች ተሳትፎ ለምን? እንዴትስ ፍሬያማ ይሁን? ኢትዮጵያ በነበሯት ህጎችም ሆነ የተለያዩ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ መዋቅሮች ሴቶችን በልዩነትና በበታችነት ለዘመናት ስታይ ቆይታለች። ለአመታትም የነበረው ሁኔታ ሲታይ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በመንግሥት ደረጃ የፖለቲካውን ስፍራ የተቆጣጠሩት ወንዶች ናቸው። ማህበረሰቡን ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ሴቶችን የሚመለከቱ ህጎችን የሚያረቁትም ሆነ የሚያስፈፅሙት ወንዶች መሆናቸውም የህግ አውጭ ምክር ቤቱ በወንዶች ለመያዙ አስረጅ ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ለምን አስፈለገ የሚለው የፍትህ ጥያቄ አንደሆነና ግማሹን የህብረተሰብ ክፍል እንደ መያዛቸው መጠን በውክልና ዲሞክራሲ ሴቶች በራሳቸው ለምን አይወከሉም የሚል ነው። ሌላኛው ደግሞ የሴቶችና የወንዶች የህይወት ልምድ በተለይም ከታሪካዊ ፆታዊ ኢ-ፍትሀዊነት ጋር ተያይዞ መስተካከል ያለባቸው ህግጋትንና አፈፃፀማቸውን ከሴቶች በላይ የሚያውቅ ስለሌለ እንደሆነም ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሴቶችን በፖለቲካውም ሆነ በምርጫ እንዲሳተፉ ምርጫ ለማድረግ መዋቅራዊና ተቋማዊ ለውጦችን ማምጣት እንደሚያስፈልግ በርካቶች ይናገራሉ። የሴቶችን ድርብርቦሽ የስራ ጫና ከመቀነስ ጀምሮ፣ በማህበረሰቡ ላይ ግንዛቤን መፍጠር እንዲሁም ፓርቲዎች አቃፊ እንዲሆኑ ማስቻል ከሴት ፖለቲከኞች የሚነሱ ሃሳቦች ናቸው።
xlsum_amharic-train-277
https://www.bbc.com/amharic/news-56206404
ጉቱ አበራ-"እወድሻለሁ ብሎ መንገር ሳይሆን ልክ እንደ ዓመት በዓል ያለ የደስታ ስሜት ነው መፍጠር የፈለኩት"
ሀዋነዋ (Hawanawa) ለወራት መልካም ዜና ለራቀው የኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ የተወሰነም ቢሆን እስትፋስ የሰጠ ሙዚቃ ነበር። የሙዚቃው ቪዲዮ በተለቀቀ በሰአታት ውስጥ ነበር የብዙዎችን ቀልብ የገዛው። እንዲህ ያሉ አስተያየቶችን መቀበሉን ሙዚቀኛውም ይናገራል።
[ "ሀዋነዋ (Hawanawa) ለወራት መልካም ዜና ለራቀው የኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ የተወሰነም ቢሆን እስትፋስ የሰጠ ሙዚቃ ነበር። የሙዚቃው ቪዲዮ በተለቀቀ በሰአታት ውስጥ ነበር የብዙዎችን ቀልብ የገዛው። እንዲህ ያሉ አስተያየቶችን መቀበሉን ሙዚቀኛውም ይናገራል።" ]
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው ነገር ጥሩ እንዳልሆነ እናውቃለን። አንዳንዴ ግን እረፍት ያስፈልጋል። አንዳንዶቹ በዚህ ሙዚቃ እረፍት እናደርጋለን፤ ከዛ ተመልሰን ወደ ጭንቀታችን እንመለሳለን ይሉኛል (ሳቅ)›› ይላል ጉቱ። ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በአዲስ ስራው ብቅ ያለው ጉቱ አበራ በኦሮምኛ ያቀነቀነው ሙዚቃ ቋንቋውን በማይናገሩ አድማጮች ዘንድም ከፍተኛ ተቀባይነትን አትርፎለታል። ሀዋነዋ (Hawanawa) ለህይወት ዘመኔ እፈለግሻለሁ እንደማለት ነው። ግጥሙም ዜማውንም ራሱ ጉቱ ጽፎታል። ነገር ግን ሙዚቃውን ያቀናበረችው ሚራ ቲሩቼልቫም (Mira Thiruchelvam) ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራት። ጉቱ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ ለሚራ እውቅናውን ሰጥቷል። ጉቱ ማነው? የተወለደው በኦሮሚያ ምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ ውስጥ ነው። የ16 አመት ታዳጊ ሆኖ ነበር ቤተሰቦቹ በስደት ወደ ሚኖሩባት ኖርዌይ ከ 12 አመት በፊት የሄደው። ከልጅነቱ ጀምሮ ከፍተኛ የሙዚቃ ፍላጎት እንደነበረው የሚናገረው ጉቱ ኖርዌይ ከሄደ በኋላ ወደ ጥሩ ሙዚቀኞች እየሄደ ሙዚቃን በመማር አዲስ ነገር ለመፍጠር እና በተለይም የፊውዥን ሙዚቃዎች ላይ አተኩሮ መስራት ጀመረ። በሶሻል ወርክ እና አንትሮፖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪውን የያዘው ጉቱ በሞያው ሶሻል ወርከር ነው። የትምርት ዝግጅቱም ለሙዚቃ ስራው እገዛ እንዳደረገለት ይናገራል፡፡ ‹‹ስራዬ እኮ እሱ ነው፤ ወደ ሙዚቃ ግን ጠቅልዬ መግባቴ ነው መሰለኝ አሁንስ (ሳቅ)። ከሆነልኝማ ሙዚቃውን እመርጣለሁ። ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ፤ እስከመጨረሻው ሙዚቃን እሰራለሁ›. ሲል ይናገራል። "በኖርዌይ የኦሮሞን ሙዚቃ ወደ ዓለም መድረክ ለማምጣት ጥረት ማድረግ ጀመርኩኝ፤ በዚህም ምክንያት የተለያዩ አገር ሙዚቃዎችን በመጨማመር የሚሰራ ፋርገስ ፒል (Fargespill) የተሰኘ የሙዚቃ ባንድ አባል ሆንኩኝ።" የሚለው ጉቱ ከዚህ በኋላ የኦሮምኛ እና የምዕራብውያን ሙዚቃ በመቀላቀል መድረክ ላይ ማቅረብ መጀመሩን ይናገራል። ኦሮሚያ በሎ (ሰፊዋ ኦሮሚያ) የሚለው ሙዚቃ ከበርካታ ሰዎች ጋር እንዳስተዋወቀውም ለቢቢሲ ገልጿል። ከዚህም የተነሳ በኖርዌይ ንጉስና ንግሥቱቷ ፊት ለፊት ተጋብዞ መጫወቱንም ይናገራል። ኦሮሚያ በሎ የሚለው ሙዚቃ ቅድሚያ የተጫወተው ሌላ ድምጻዊ ሲሆን፣ ኦሮምኛ የማይችሉ የባንዱ አባላትን በማሰልጠን በተለያዩ መድረኮች ላይ በጋራ ስራውን አቅርቧል። ጉቱ አበራ የተሰኘ የሙዚቃ ባንድንም ማቋቋሙን ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ወቅት ተናግሯል። ጉቱ ስለ አዲሱ ሙዚቃው አጠር ያለ ቆይታ ከበቢሲ ጋር አድርጎ ነበር፡፡ ቢቢሲ- ሀዋነዋ የተሰኘው ነጠላ ቪዲዮህ ከወጣ ገና አንድ ሳምንት አለሞላውም፣ ነግር ግን በኢትዮጵያ ማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች እጅግ ተወዶልሃል። ጠብቀህው ነበር? ጉቱ አበራ- ይህ ስራዬ ለየት ብሎ የተሰራ ነው። ሀዋናዋም ለመያዝ የሚቀል እና ሳቢ መጠሪያ ነው። ሙዚቃው አዲስ ስለሆነ ነው መሰለኝ ብዙ ሰዎች መልዕክቶችን እየላኩልኝ ነው። በርታ ጥሩ ነው እያሉኝ ነው። ይህ ሙዚቃ የተወሰነ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ ስለመጣ ሰዎች ዝግጁ አይሆኑም በሚል ምናልባት ተደማጭነቱ ላይ ጫና ያመጣ ይሆን ብዬ ሰግቼ ነበር። ግን ደግሞ ሙዚቃው በጥሩ ጥራት መሰራቱን ደግሞ አውቃለሁ። በቀጥታ መሳሪያዎች ነው የተቀረፀው። ስኬሉም ትንሽ ይለያል። የእኛ አገር ሙዚቃ ፔንታ ቶኒክ ነው፣ ይሄ ደግሞ በተለይ ኳየሮቹ በሌላ ስኬል ነው የገቡት። ስለዚህ በተለይ ከወጣቱ ትውልድ አድማጭ አገኛለሁ ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን እንደዚህ ቶሎ ብዙ ተቀባይ አገኛለሁ ብዬ ግን አልጠበኩም። ስለዚህ ይሄንን ያህል ባልጠብቅም የተወሰነ ግምት ግን ነበረኝ። በዚህ ሙዚቃ ደስ ያለኝ ነገር ቢኖር እስከዛሬ መልክት ከሚልኩልኝ አድናቂዎች ውጪ አዳዲስ አድናቂዎች አፍርቻለሁ። ይህ ሙዚቃ በኦሮምኛም ሆነ በአማርኛ ከሚዘፈኑ ዘፈኖች ለየት ያለ መልክ በመያዙ ምክንያት ይመስለኛል። ከመላው ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ መልክቶች እየደረሱኝ ነው። ጥሩ ነው ብለውኛል። ቢቢሲ- በኦሮምኛ ሙዚቃዎች ውስጥ የፍቅር ዘፈኖች ብዙ ግዜ በውስጣቸው ሰም እና ወርቅ አላቸው፤ አንዳንዴ ስለ አገር ወይም ፖለቲካዊ መልክት ይይዛሉ። ሃዋነዋ ሰምና ወርቅ ይኖረው ይሆን? ጉቱ አበራ-ይህ ሙዚቃ በውስጡ የተለየ መልክት አልያዘም፣ በግልፅ ከሚገልፀው የፍቅር መልክት ውጪ። እኔ ተወልጄ ያደኩት ወለጋ ውስጥ ነው። ይሄን ዘፈን ደግሞ ለሸዋ ልጅ ነው የዘፈንኩት። የጥበብ ስራው ላይ ትኩረት አድርጌአለሁ። ሁሉም ሰው የኦሮምኛ ሙዚቃን እንዲያዳምጥ እና ጥበባችን ከፍ እንዲል የፈለኩት እንጂ ምንም ፖለቲካዊ መልዕክት የለውም። ቢቢሲ- የሙዚቃ ቪዲዮውም ሆነ ሙዚቃው ከኦሮሞ እና ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በተጨማሪ የአፍሪካ መልክ የሚሰጡ ነገሮች አሉት። በተጨማሪም ወደ ኋላ አስርተ አመታትን ሄደህ ከባህል ባሻገርም የዘመን ህብር ፈጥረሃል። እንዴት ይህንን ለመፍጠር አሰብክ? ጉቱ አበራ- ሙዚቃው እንደሰማሽው ተለዋዋጭ (ዳይናሚክ) ነው። መጀመሪያ ሲገባ በቤዝ ጌታር እና በፕርኪሽን እጀምራለሁ፤ መጨረሻ ላይ ደግሞ በጣም ሞቅ ብሎ ያልቃል። ቪዲዮውም እሱን ነው የሚመስለው። መጀመሪያ እኔ እና እሷ ቀስ ብለን ሳይክል እየነዳን እንሄዳለን ከዛ ጭፈራውም ከሙዚቃው ጋር ከፍ ይላል። ስለዚህ የሙዚቃ ቪዲዮው ታስቦበት ነው የተሰራው። ሌላው በቀጥታ የሙዚቃ መሳሪያ ስለተሰራ ድምጹ ተፈጥሮአዊ ነው። ስለዘመን ስናወራ ደግሞ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ከ 1970 እና 1980 ዎቹ በጣም ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ ነበር። እኔ በተለይም የዚያን ግዜ የኢትዮጵያን ሙዚቃዎች በበለጠ እወዳለሁ፤ አዳምጣለሁ። እናም ወደዚያ መመለስ እና ከዚያ መጀመር ነው የፈለኩት። አሁን ያለው ዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ያኔ እንደነበረው ብቃት ላይ አይደለም። በአሊ ቢራ እና አለማየሁ እሸቴ ጊዜ ኢትዮ ጃዝ በጣም ያደገበት ወቅት ነበር። አሁንም እነርሱ ትልቅ ናቸው፤ አከብራቸዋለሁ። እኔ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ገና ያልተነካ ነው ብዬ ነው የማምነው። በተለይ ከጥሩ ባለሞያዎች ጋር ቢሰራበት አዲስ ነገር መስራት ይቻላል። ስለዚህ ነው በኔም ስራ በዚህ መልኩ አዲስ ነገር መስራት የፈለግነው፣ ደግሞም አድርገነዋል። በተጨማሪም አቀናባሪዋ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ታጠናለች እና ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ያላት እውቀት በጣም ጥልቅ ነው። ስለዚህ ለእርሷ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከሌሎች አይነት ሙዚቃዎች ጋር ማቀናበር አልከበዳትም። ሀዋነዋ ሙዚቃው ጃዝ፣ ብሉዝ፣ ራያ/ወሎ፣ አፍሮ፣ ኢቺሳ፣ ጌሎ፣ ሸጎዬ ምቶች የተቀላቀለበት ነው። ይሄ ብቻ ሳይሆን ችክችካ እና አፍሮ ቢትስም አሉበት። ስለዚህ አንዱን ሪትም የማይወድ ቢያንስ ሌላውን እንዲወድ አድርገን ነው የቀረጽነው። እርሷ እንደ ባለሞያ ስታቀናብር እኔ አብሬያት ስለበርኩ በምፈልገው መልኩ ለመቅረፅ ችያለሁ። ስለዚህ ያ ለሙዚቃው ጣዕም የራሱ አበርክቶ እንዲኖረው አድርጓል። ቢቢሲ- የሙዚቃ ቪዲዮህ የመብራት አጠቃቀሙ በጣም ፈካ ያለ ነው። ቅድም አንተም እንዳለከው የዘፈንህን ግጥም የማይሰሙ ሰዎችም ሙዚቃህን ወደውልሃል። የሃዋነዋ ግጥም ክሊፑ ላይ ከተጠቀምከው የመብራት ሴቲንግ ጋር ይገናኛል? ጉቱ አበራ- የኔ ፍላጎት ታሪኩን መንገር ብቻ አይደለም። ስሜቱን መፍጠር ላይ ነበር ትኩረት ያደረኩት። ሰዎች ሙዚቃውን ሲሰሙ ደስተኛ ይሆናሉ፣ ቀለማቱን እንዲሁም የተቀረፀበት ቦታ የሚፈጥረው ስሜት አለ። የሙዚቃ ቪዲዮ ሲሰራ ልክ እንደ ፊልም ታሪኩን መንገር አይደለም ዋና አላማው፣ ሰዎች ስሜቱ እንዲሰማቸው አድርጎ መፍጠር ነው። እኔም ልክ እንደ አመት በዓል ያለ የደስታ ስሜት ነው መፍጠር የፈለግኩት። በአጠቃላይ ግጥሙ የፍቅር ነው፤ ነገር ግን አንድ ሰው እወድሻለሁ ብሎ መንገር ሳይሆን ልክ እንደ አመት በዓል ያለ የደስታ ስሜት ነው መፍጠር የፈለኩት። አድማጮቼ ስሜቱን ወድደውታል ብዬ አስባለሁ። እንደ መሰናበቻ ጉቱ አድናቂዎቹን ‹‹በጣም አመሰግናለሁ። አዳዲስ ሙዚቃ በቅርቡ ሰርቼ ለመመለስ እሞክራለሁ። ያላችሁኝን መልካም ነግሮች በሙሉ አከብራለሁ። እናም ታትሬ እንደምሰራ ቃል እገባላችኋለሁ። በቅርቡ ደግሞ በመድረክ ላይ እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ›› ሲል አመስግኗችኋል። አክሎም ‹‹አልበሜ በ ያዝነው የፈረንጆች አመት መጨረሻ፤ ካልሆነ ደግሞ 2022 መጀመሪያ ይወጣል ብዬ አስባለሁ። ከዛ በፊት አንድ ነጠላ ዜማ መስራቴ ግን አይቀርም›› ብሏል።
xlsum_amharic-train-278
https://www.bbc.com/amharic/news-54783379
የአፍሪካ ሕብረት፡ "ሁሉም አካል ግጭትን ከሚያባብስ ትርክት ይቆጠብ"
የኦሮሚያ ፖሊስ ከትናንት በስቲያ በምዕራብ ወለጋ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 32 ነው ሲል የዓይን እማኞች እና አምነስቲ የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 54 ነው ብለዋል።
[ "የኦሮሚያ ፖሊስ ከትናንት በስቲያ በምዕራብ ወለጋ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 32 ነው ሲል የዓይን እማኞች እና አምነስቲ የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 54 ነው ብለዋል።" ]
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እሁድ ዕለት በደረሰው ጥቃት የተገደሉት ንጹሃን ዜጎች ቁጥር 32 ነው ብለዋል። የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 32 እንደሆነ ቢጠቀስም ኮሚሽኑ ያገኛቸው መረጃዎች አሃዙ ከዛ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ ብሏል። በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሰዎች ሕይወት ማለፉን ይታወሳል። የክልሉ ቃል አቀባይ ጥቃቱ የተፈጸመው በስብሰባ ስም በአንድ ቦታ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ነው ብሏል። የክልሉ መንግሥት ትናንት ባወጣው መግለጫ ምን ያክል ሰዎች በጥቃቱ እንደተገደሉ ያለው ነገር የለም። የአፍሪካ ሕብረት፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናልና ሌሎችም ድርጅቶች ጥቃቱን በማውገዝ መግለጫ አውጥተዋል። "የ54 ሰው አስክሬን ተመልክቻለሁ" ቢቢሲ ያነጋገራቸው የዓይን እማኞች ከ50 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ይናገራሉ። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ጥቃቱ የተፈጸመበት ቀበሌ ነዋሪ ጥቃቱ የተጀመረው ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ ነው ይላሉ። "ልክ መከላከለያ እንደወጣ ኦነግ ሸኔ ገባ። ከዚያ ወረራ ጀመረ፤ ዘረፋ ጀመረ። ቅዳሜ ዕለት እንደዛ እያደረጉ አደሩ። ሞባይል ስልክ፣ ገንዘብ እንዲሁም የቤት እቃ ሲዘርፉ ነበር። ከዚያ ትላንት [እሁድ] 11 ሰዓት አካባቢ ስብሰባ አለ ብለው አዛውንት፣ ሴቶችና ሕፃናት ሳይለዩ ሰብስበው አንድ ትምህርት ቤት አስገቡ። ከዚያ ጥቃት ፈፀሙ።" ይላሉ። የዓይኑ እማኙ ስብሰባውን የጠራው ጥቃት ያደረሰብን ኦነግ ሸኔ ነው ይላሉ። "ሰዉ በፍርሃት ተገዶ ነው ወደ ስብሰባው የገባው። ሕይወቱ የሚተርፍ መስሎት ነው የሄደው። ከዚያ በመትረየስና በቦንብ ነው ጥቃት የፈፀሙት።" የዓይኑ እማኙ ጥቃቱ ሲፈፀም ከሌሎች ሰዎች ጋር ሸሽተው ጫካ ውስጥ ተደብቀው እንደነበር ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የሚፈልጉት ወንዶችን ነበር። እኛ ሸሽተን ጫካ ውስጥ ነበርን። ሴቶች፣ ሽማግሌዎች ቤት ቀርተው ነበር። ገንዘብ ቢውስዱ እንጂ እነሱን አይነኩም ብለን ነበር ያሰብነው። ከዚያ የፍንዳታ ድምፅ ስንሰማ ቀስ ብለን ከተደበቅንበት ጫካ ወጥተን ስናይ አመድ ሆነዋል።" ለደህንነታቸው በመስጋት ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈቀዱት እኒህ የዓይን እማኝ ከሌሎች ሰዎች ጋር ጫካ ውስጥ አድረው ዛሬ [ሰኞ] ረፋዱን መውጣታቸውን ይናገራሉ። ሰኞ ከረፈደ በኋላ ነው መከላከያና ልዩ ኃይል የገባልን ይላሉ። ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡት የዓይን እማኝ በስፋራው የነበረው የመከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ጠዋት አካባቢውን ለቆ እንደወጣ ይናገራሉ። መከላከያ ሠራዊት ሥፍራውን ለቆ በወጣ በሰዓታት ልዩነት ታጣቂዎች አከባቢውን እንደተቆጣጠሩ አስረድተዋል። የምዕራብ ወለጋ ኮማንድ ፖስት ከታወጀ ወዲህ መከላከያ በሥፍራው እንደነበርም ያወሳሉ። "አንድ ወንድሜ ሞቷል። የአጎቴ ልጅና አባቱ ሞተዋል። ወንድሜ ሚስትና ልጆች አሉት። አጎቴ ደግሞ ሽማግሌ ነበር። ወንድሜ ስብሰባ ሲጠራ ልጆቼን ልይ ብሎ ከጫካ ወጥቶ ሄዶ ነው የሞተው። ሚስትና ልጆቹም አብረው አለቁ።" አሁን መከላከያ ከገባ ወዲህ በሥፍራው መረጋጋት እንዳለ የዓይን እማኙ ያስረዳሉ። መከላከያ ሠራዊት የሸሹትን እየጠራ እንደሆነና የሞቱ ሰዎችን ሬሳ እየሰበሰበ እንዳለ ይናገራሉ። የዓይኑ እማኙ እስካሁን ድረስ 54 ሰዎች መሞታቸውን ማረጋገጣቸውን ይናገራሉ። ሌላ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የዓይን እማኝም ጥቃቱ የደረሰው ሰዎች በተሰበሰቡበት እንደሆነ ይናገራሉ። "ጥሩ ነገር እንነግራችኋለን ብለው ከሰበሰቧቸው በኋላ ቦምብ ሲጥሉባቸው 60 ሰው ሕይወቱ አለፈ። 20 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። የሰዎች አስክሬን አሁን እየተሰበሰበ ነው" ብለዋል። እኚሁ የዓይን እማኝ ወደ አከባቢው የመንግሥት ጸጥታ ኃይል መሰማራቱን ተከትሎ ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት ምላሽ የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ኦነግ ሸኔ የተባለው ቡድን ንሑሃን ዜጎችን ስብሰባ ብሎ ከጠራ በኋላ ሰዎች ላይ በተወረወረ ቦምብ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ጌታቸው፤ "ቦምቡን የወረወሩት ሐሰተኛ ስበሰባ የጠሩት ናቸው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ እየተጠቀሰ ነው። ነገር ግን ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ በአካባቢው ያለው አካል አጣርቶ እስኪልክልን እየተጠባበቅን ነው" ይላሉ። በተመሳሳይ የኦሮሚያ ክልል ዛሬ ንጋት ላይ መግለጫ አውጥቷል። ክልሉ "ጭካኔ በተሞላበት መንገድ የሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ ባደረገው የኦነግ ሸኔ ቡድን ላይ እርምጃ ይወሰዳል" ብሏል። የክልሉ ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳም በዜጎች ላይ ለደረሰው ጥቃት "ጥልቅ ሃዘኔን እገልጽለሁ" ያሉ ሲሆን "በኦነግ ሸኔ አሸባሪ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለው ውጤታማ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ላረጋግጥ እወዳለሁ" ብለዋል። የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ትላንት ምሽት የተፈጸመው ጥቃት መጠን እና ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ጋር በመተባበር እየተጠራ ነው ብሏል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ማንነትን መሠረት ባደረጉ ጥቃቶች ማዘናቸው በፌስቡክ ገፃቸው ገልፀዋል። "የኢትዮጵያ ጠላቶች፤ "ወይ እኛ እንገዛለን፤ ወይ ሀገር አትኖርም" ብለው ተነሥተዋል። ለዚህም የጥፋት ዐቅማቸውን ሁሉ እየተጠቀሙ ነው። አንደኛው ዒላማቸውም የሕዝባችንን ቅስም መስበር ነው" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። "ግራ ቀኝ የሚያውቁ ሰዎችን እየሰበሰቡ በማሠልጠንና በማስታጠቅ በየአካባቢው ማንነትን መሠረት ያደረገ አረመኔያዊ ጥቃት ማድረስ" ጠላቶች ያሏቸው ሰዎች አላማ ነው ሲሉ በመግለጫቸው አትተዋል። "መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ያላቸውን ጥፋቶች በቅድሚያ መረጃ ሰብስቦ ርምጃ በመውሰድ ሲያከሽፍ ቆይቷል። ነገር ግን ያለፈው ሥርዓት ያወረሰንን ቀዳዳዎች ሁሉ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ደፍኖ መጨረስ አልተቻለም" ይላል የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኦፊሴላዊ ገፅ ላይ የሰፈረው መልዕክት። አክለውም "የጸጥታ አካላት ጥቃቱ ወደተፈጸመበት አካባቢ ተሠማርተዋል። ርምጃም እየወሰዱ ነው። በቀጣይም የሕዝባችንን ደኅንነት ለማስጠበቅ መንግሥት የመንግሥትነቱን ሥራ በቁርጥና በጽናት ይሠራል" ብለዋል። የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሞሳ ፋኪ ማሕማት፤ ንጹሀን ዜጎች መገደላቸውን አጥብቀው እንደሚያወግዙ ገልጸዋል። ሕብረቱ ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት ጥቃቱን የፈጸሙ ቡድኖችን ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበት አሳስቧል። በማኅበረሰቡ መካከል የሚከሰት ግጭት እየተባባሰ መምጣቱን በመጥቀስ፤ ሁሉም አካል ግጭትን ከሚያባብስ ትርክት እንዲቆጠብ ሊቀ መንበሩ ጠይቀዋል። በአገሪቱ ግጭትን ለማርገብ ጥረት መደረግ እንዳለበት፣ ሁሉን አቀፍና ወደ ብሔራዊ መግባባት የሚወስድ የፖለቲከኞች ውይይት መካሄድ እንደሚገባውም መግለጫው ይጠቁማል። ይህ ካልሆነ ግን አለመረጋጋቱ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጠናውም ይተርፋል ያሉት ሊቀ መንበሩ፤ የአፍሪካ ሕብረት በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን እንዲሰፍን እንደሚያግዝም ገልጸዋል። አምነስቲ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከ54 የማያንሱ ብሄራቸው አማራ የሆኑ ሰዎች ተገድለዋል ብሏል ትናንት ባወጣው መግለጫ። አምነስቲ የአገር መከላከያ አከባቢውን ጥሎ መውጣቱን ተከትሎ የኦሮሞ ነጻነት ጦር አባላት ሳይሆኑ እንደማይቀሩ የተጠረጠሩ ጥቃቱን መፈጸማቸውን ገልጿል። መከላከያ ሠራዊት አከባቢውን ለምንና አንዴት ጥሎ መውጣት እንዳስፈለገው መጣራት ይገባዋል ብሏል አምነስቲ። በጥቃቱ ሴቶች እና ሕጻናት ጭምር መገደላቸውን አምነስቲ በሪፖርቱ አመልክቷል። የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በምዕራብ ወለጋ የተፈጸመውን ጥቃት አውግዟል። ኮሚሽኑ ወደ 60 የሚጠጉ ታጣቂዎች በሶስት ቀበሌዎች በሚኖሩ ብሄራቸው አማራ የሆኑ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በጥቃቱ ሴቶች እና ህጻናት መገደላቸውንም ገልጾ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 32 እንደሆነ ቢጠቀስም፤ ኮሚሽኑ ያገኛቸው መረጃዎች አሃዙ ከዛ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ ብሏል።
xlsum_amharic-train-279
https://www.bbc.com/amharic/news-52446447
ሰዎች እጃቸውን የማይታጠቡበትን ሥነ ልቦናዊ ምክንያት ያውቃሉ?
የፎክስ ኒውስ ዜና አንባቢ ፒት ሄግሴት “እጄን ለአስር ዓመታት አልታጠብኩም” ማለቱን ተከትሎ የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።
[ "የፎክስ ኒውስ ዜና አንባቢ ፒት ሄግሴት “እጄን ለአስር ዓመታት አልታጠብኩም” ማለቱን ተከትሎ የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።" ]
ለ10 ዓመታት እጁን ታጥቤ አላውቅም ያለው ዜና አንባቢ ፒት ሄግሴት፤ በኋላ ግን ቀልዴን ነው ብሏል ከአምስት ዓመት በፊት ተዋናይት ጄኔፈር ሎውረንስ ከመጸዳጃ ቤት ስትወጣ እጇን የመታጠብ ልምድ እንደሌላት መናገሯም ይታወሳል። ፒት እና ጄኔፈር “እጃችንን አንታጠብም” ካሉ በኋላ መልሰው ደግሞ “ስንቀልድ ነው” ያሉትን አስተባብለዋል። ሆኖም ግን እጅ መታጠብን አምርረው የሚቃወሙ ሰዎች እንዳሉ ያውቃሉ? • በሊባኖስ ለሽያጭ የቀረበችው ናይጄሪያዊት ተረፈች የኖርዝ ኬሮላይናው ሪፐብሊካን የሕዝብ እንደራሴ ቶም ቲልትስ፤ የሬስቶራንት ተቀጣሪዎች እጃቸውን ይታጠቡ መባሉ አላስፈላጊ ድንጋጌ ነው ያሉት ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር። ከመጸዳጃ ቤት ሲወጡ እጃቸውን የማይታጠቡ ሰዎች እንዳሉ ሳትታዘቡ አልቀራችሁም። እአአ 2015 ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ በመላው ዓለም መጸዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ እጃቸውን የሚታጠቡት 26.2 በመቶ ሰዎች ብቻ ናቸው። ቀላል ግን በቀላሉ የሚረሳ ልማድ በለንደን የኅብረተሰብ ጤና ምሁሩ ሮበርት አውገር፤ እጅ መታጠብ “ቀላል ልማድ ይመስላል” ይላሉ። “እጅ መታጠብ በቀላሉ የሚለመድ ቢመስልም፤ ለ25 ዓመታት ያህል ሰዎች እጃቸውን መታጠብ እንዲያዘወትሩ ለማድረግ ብንሞክርም፤ እጃቸውን የሚታጠቡ ጥቂቶች ናቸው።” ድህነት በተንሰራፋባቸው አገራት ሳሙናና እጅ መታጠቢያም በስፋት ስለማይገኝ፤ ብዙሃኑ እጃቸውን አለመታጠባቸው ላያስገርም ይችላል። • የቻይናና የአፍሪካ ግንኙነት በኮሮና ዘመን ምን ድረስ ይዘልቃል? በታዳጊ አገራት 27 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ብቻ እጅ መታጠቢያ ያገኛል። በተቃራኒው እጅ መታጠቢያ እንደልብ በሚገኝባቸው ያደጉ አገራት፤ ከመጸዳጃ ቤት ሲወጡ እጃቸውን የሚታጠቡ 50 በመቶ ብቻ ናቸው። ሕይወት አዳኙ እጅ መታጠብ በሰው ልጅ ታሪክ ከተፈጠሩ ሕይወት አዳኝ ተግባሮች አንዱ እጅ መታጠብ ነው። እጅ መታጠብ በ1850ዎቹ እውቅናው እየጨመረ ከመጣ ወዲህ፤ ሰዎች ዘለግ ላለ ጊዜ ምድር ላይ መኖር ችለዋል። ወረርሽኞችን ለመከላከልም እጅ መታጠብ አንዱ መንገድ ነው። እአአ 2006 ላይ የወጣ ጥናት፤ አዘውትሮ እጅ መታጠብ በመተንፈሻ አካላት በሽታ የመያዝ እድልን ከ6 እስከ 44 በመቶ እንደሚቀንስ ያሳያል። • የኮሮናቫይረስ ክትባትን በማግኘት ህንድ የዓለምን ሕዝብ ትታደግ ይሆን? የኮቪድ-19 ስርጭት ከሰዎች እጅ የመታጠብ ልማድ ጋር ግንኙነት እንዳለው ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ታዲያ ለምን አንዳንድ ሰዎች እጃቸውን አይታጠቡም? እጅ መታጠብ አለመፈለግ ከሰዎች ሥነ ልቦና ጋር ይተሳሰራል። ቀጣዮቹ ነጥቦች ማብራሪያ ይሰጧችኋል። እጅን በተደጋጋሚ በደንብ መታጠብ ኮሮናቫይረስን የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎችን ከመከላከል ይረዳል 1. የ‘ክፉ አይነካኝም’ ተስፋ መጥፎ ነገር አይደርስብንም የሚል እምነት ያላቸው በርካቶች ናቸው። በብዙ ማኅበረሰቦች ዘንድ ክፉ ነገር የሚመጣው በሌላ ሰው እንጂ በእኔ ላይ አይደለም የሚል እምነት ይስተዋላል። ይህ አይነቱ አመለካከት ሲጋራ በሚያጨሱ ሰዎች ዘንድም ይታያል። የእኔ ትዳር አይፈርሰም፣ እኔን ካንሰር አይዘኝም የሚሉም ጥቂት አይደሉም። እጅ አለመታጠብም ከዚሁ ጋር ይገናኛል። ይህ አመለካከት ያላቸው የህክምና ተማሪዎች እና ምግብ አዘጋጆችም እጃቸውን ከመታጠብ ይቆጠባሉ። 2. ባህል እጅ መታጠብ ከባህል ጋር የተቆራኘ ነው። በተለያዩ ማኅበረሰቦች ዘንድ እጅ መታጠብ የሚሰጠው ዋጋ ሰዎች እጃቸውን ለመታጠባቸው ወይም ላለመታጠባቸው ምክንያት ይሆናል። 64,002 ሰዎችን ከ63 አገሮች ያሳተፈ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ከቻይና፣ ከጃፓን፣ ከደቡብ ኮርያ እና ከኔዘርላንድስ የተጠየቁ ሰዎች መጸዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ እጃቸውን በሳሙና የመታጠብ ልማድ እንዳላቸው የተናገሩት ከግማሽ በታች ናቸው። በተቃራኒው 97 በመቶ የሚሆኑ የሳኡዲ አረቢያ ዜጎች እጃቸውን መታጠብ እንደሚያዘወትሩ ተናግረዋል። • ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች የሕብረተሰብ ጤና ምሁሩ ሮበርት እንደሚሉት፤ በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ሴቶች ከወንዶች በበለጠ እጃቸውን መታጠብ ያዘወትራሉ። ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተሠራ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው፤ 65 በመቶ ሴቶች እና 52 በመቶ ወንዶች እጃቸውን ይታጠባሉ። “እጅ መታጠብ ከሥነ ልቦና እና ከባህል ጋር ይተሳሰራል። እንድ ነገር የምናከናውነው ሌሎች የሚያደርጉትን እና እኛ እንድናደርግ የሚጠብቁትን በማየት ነው” ይላሉ ተመራማሪው። ጥናቶች ሴቶች ከወንዶች ይልቅ እጃቸውን ይታጠባሉ 3. ቀልብ እና ሙከራ እጅ መታጠብን ሀኪሞችም ቸል የሚሉበት ጊዜ አለ። እአአ 2007 ላይ አውስትራሊያ ውስጥ የተሠራ ጥናት፤ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ህክምና ከመስጠታቸው በፊት እጃቸውን የታጠቡት 10 በመቶ ጊዜ ብቻ እንደሆነና ከህክምና በኋላ እጃቸውን የታጠቡት ደግሞ 30 በመቶ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ያመለክታል። በቅርቡ የተሠሩ ጥናቶችም ተመሳሳይ ውጤት አሳይተዋል። በኩቤክ የህክምና ባለሙያዎች እጃቸውን የሚታጠቡት 33 በመቶ ጊዜ ብቻ መሆኑን ባለፈው ዓመት የተሠራ ጥናት ይጠቁማል። እጅ መታጠብ በስፋት በተለመደበት ሳኡዲ አረቢያ ሳይቀር የህክምና ባለሙያዎች ብዙ ጊዜ እጃቸውን አይታጠቡም። • ኮሮናቫይረስንና የፀሐይ ብርሃንን ምን አገናኛቸው? 2008 ላይ የተሠራ አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው፤ እጃችንን አንታጠብም ካሉት ሀኪሞች አብዛኞቹ በሙከራ የሚያምኑ ናቸው። በተቃራኒው ቀልባችንን እናምነዋለን ያሉ ሀኪሞች በብዛት እጃቸውን እንደሚታጠቡም ተስተውሏል። ይህ የሚያሳው አንድ ሰው እጁን እንዲታጠብ ለማሳመን መከራከሪያ ነጥቦች መደርደር እንደማያዋጣ ነው። ባለፈው ወር ብራዚል ውስጥ የተሠራ ጥናት ይህንን መላ ምት ያጠናክራል። በቀልብ የሚመሩ ወይም ልባም የተባሉ ሰዎች አብዝተው እጃቸውን እንደሚታጠቡና ማኅበራዊ ርቀታቸውን እንደሚጠብቁ ታይቷል። 4. መጠየፍ አውስትራሊያዊው የሥነ ልቦና ተመራማሪ ዲክ ስቲቨንሰን እንደሚሉት፤ ሰዎች አንድ ነገር ሲቀፋቸው፤ ከዚያ ነገር ጋር ንክኪ ላለማረጋቸው ጥሩ ምክንያት ይሆናል። ለምሳሌ አንድ ሰው ምግብ ውስጥ ነፍሳት ቢያይ ስለሚቀፈው አይመገበውም። እንደ ማንኛውም ስሜት አንድን ነገር መጠየፍ ከሰው ሰው ይለያያል። ጥዩፍ የሆኑ ሰዎች በፖለቲካው መስክ ወግ አጥባቂ የመሆን አዝማሚያ አላቸው። • ኮሮናቫይረስ ሁለቴ ሊይዘን ይችላል? ብዙም የማይጠየፉ ሰዎች፤ እጃቸውን መታጠብ እንደማያዘወትሩ፣ ቢታጠቡም በቅጡ እጃቸውን እንደማያጸዱ ጥናቶች ያመለክታሉ። በሄይቲ እና በኢትዮጵያ የተሠራ ጥናት እንደሚጠቁመው፤ ሰዎች እጃቸውን ለመታጠብ ምክንያት የሚሆናቸው የጤና ጉዳይ ሳይሆን አንድን ነገር የመጠየፍ ወይም ያለመጠየፋቸው ጉዳይ ነው። ሰዎች እጃቸውን እንዲታጠቡ ምን ይደረግ? ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የጤና ባለሙያዎች፣ በጎ አድራጊዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እጅ የመታጠብ ዘመቻን ሲያበረታተቱ ነበር። እጅ አለመታጠብ ከሥነ ልቦና ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያለው ተግባር እንደመሆኑ እነዚህ ንቅናቄዎች ምን ያህል ውጤታማ ይሆናሉ? ከአስራ አንድ ዓመታት በፊት የተሠራ ጥናት እንደሚጠቁመው፤ ሰዎች እጃቸውን እንዲታጠቡ ለማድረግ፤ እጅ መታጠብን ውብ ተግባር አድርጎ ማቅረብ ብዙ አያዋጣም። እንዲያውም ሰዎች እጃቸውን አለመታጠባቸው አስጸያፊ እንደሆነ ማሳየት ውጤታማ ነው። በጥናቱ ወቅት፤ አስጸያፊ ትምህርታዊ ቪድዮ እንዲመለከቱ የተደረጉ ተማሪዎች ከሳምንት ጊዜ በኋላ፤ ቆሻሻ ነገር ነክተው ምግብ እንዲበሉ ሲጠየቁ፤ ከመመገባቸው በፊት እጃቸውን ለማጽዳት ተነሳሽነት አሳይተዋል። በጥናቱ ወቅት አስጸያፊውን ቪድዮ ያላዩ ተማሪዎች ግን ቆሻሻ ነገር ከነኩ በኋላ መታጠብ እንፈልጋለን አላሉም። የሥነ ልቦና ተመራማሪው ዲክ፤ ሰዎች እጃቸውን እንዲታጠቡ የሚያነሳሱ ማስታወቂያዎች መሥራትን ያበረታታሉ። አንድ ሰው እጁን መታጠን ሲያዘወትር ከልምዶቹ አንዱ ይሆናል። የኅብረተሰብ ጤና ምሁሩ ሮበርት በበኩላቸው፤ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ብዙዎች እጅ መታጠብ እያዘወተሩ ቢሆንም ምን ያህል ቀጣይነት ይኖረዋል? የሚል ጥያቄ አላቸው። ምናልባትም ለተወሰነ ጊዜ፤ እንደ ዜና እንባቢው ፒት እና ተዋናይቷ ጄኔፈር፤ እጃችንን አንታጠብም ብለው የሚኩራሩ ታዋቂ ሰዎች አናይ ይሆናል።
xlsum_amharic-train-280
https://www.bbc.com/amharic/news-54245292
ኢትዮጵያ፡ ለአንድ ሳምንት 'የዲጂታል ጦር አውርድ' ያወጁት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን
የዛሬ ዓመት ግድም ነው። ዶ/ር ዓለማየሁ አስፋው ገብረየስ ከወዳጃቸው አንድ የስልክ ጥሪ ይደርሳቸዋል። ወዳጃቸውም ዶ/ር ዮናስ ይባላል። እንደሳቸው ሐኪም ናቸው።
[ "የዛሬ ዓመት ግድም ነው። ዶ/ር ዓለማየሁ አስፋው ገብረየስ ከወዳጃቸው አንድ የስልክ ጥሪ ይደርሳቸዋል። ወዳጃቸውም ዶ/ር ዮናስ ይባላል። እንደሳቸው ሐኪም ናቸው።" ]
"እረ ባክህ አንተ ሰው፣ ይሄን የሐኪሞች ማኅበርን መስመር እናሲዘው፣ ምነው ዝም አልክ?" የሚል የወዳጅ ጥሪና ወቀሳ ያደርሷቸዋል። ዶ/ር ዓለማየሁ በስኮትላንድ ከፍተኛ የካንሰር ስፔሻሊስት ናቸው። በታላቋ ብሪታኒያ የኢትዮጵያዊያን ሐኪሞች ማኅበር አባልም ናቸው። ወቀሳውም ከዚሁ ማኅበር ጋር የተያያዘ መሆኑ ነበር። ያ ወቅት ግን ዶ/ር ዓለማየሁ ስለሙያ ማኅበር የሚያስቡበት ጊዜ አልነበረም። ቆዝመዋል። አዝነዋል። ተረብሸዋል። ግራ ገብቷቸዋል። እትብታቸው ከተቀበረባት ከአገራቸው ኢትዮጵያ የሚመጡ ዜናዎች በሙሉ የሚረብሹ ነበሩ። ልክ የዛሬ ዓመት ኦክቶበር ወር አካባቢ መሆኑ ነው ይሄ። እርግጥ ነው በዚያን ጊዜ ከኢትዮጵያ በተለይም ከኦሮሚያ አካባቢ የሚወጡ ዜናዎች ልብ የሚሰብሩ ነበሩ። "ምን የሐኪም ማኅበር እናጠናክር ትለኛለህ፣ አገር እንዲህ እየታመሰች..." ይሉታል፣ ወዳጃቸውን፣ ዶ/ር ዮናስን፣ ከቁዘማው ሳይወጡ። ዶ/ር ዮናስም ሐዘን ገባቸው። ሐሳብ አወጡ አወረዱ። "ታዲያ የኛ ማዘን ምን ሊፈይድ ነው፤ አንድ ነገር እናድርግ፣ ሐሳብ እናዋጣ። ነገ ምን ይመጣ ይሆን በሚል ዳር ቆሞ የሚያይ በቂ ሕዝብ አለ። እኛ እዚያ ሕዝብ ላይ መጨመር የለብንም" ተባባሉ። ኢትዮጵያ ውላ ካደረች በኋላ የህክምና ማኅበሩ ይደርሳል። መጀመርያ አገር ትኑረን ሲሉ ተማከሩ። ለተግባር ተነሱ፤ የአገር ልጅ ለሚሉት ሁሉ ጥሪ አቀረቡ፣ ደወሉ፣ጻፉ። ይህ ማኅበር ያን ቀን በቁጭት ተወለደ። ስሙም የኢትዮጵያ እርቅና የሰላም ኅብረት ተባለ። ዩናይትድ ኪንግደም ተቀምጦ ኢትዮጵያ ሰላም ማምጣት ይቻላል? ይህ ማኅበር አሁን 50 የሚሆኑ በትምህርታቸው እጅግ የገፉ ምሁራንን አሰባስቧል። ሐኪሞች ብቻ አይደሉም ታዲያ። ሳይንቲስቶች፣ መምህራን፣ የሰርጓጅ መርከብ መሐንዲስ፣ የግጭት አፈታት ከፍተኛ አማካሪዎችን፣የአእምሮ ጤና ባለሙያዎችን፣ የሕጻናት ጤና ስፔሻሊስቶች፣ የቀዶ ጥገናና ንቅለ ተከላ ሐኪሞች ወዘተ. ያቀፈ ማኅበር ነው። የኢትዮጵያ እርቅና የሰላም ኅብረት። በቅርብ በሎንዶን ደመቅ ያለ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር፤ ስለ ኢትዯጵያዊነት የሚል። ብዙዎቹ በአካል የተገናኙት ያኔ ነው። ማኅበሩን ሲመሰርቱ ዓላማ እንጂ ሌላ ጉዳይ አላገናኛቸውም። ኢትዯጵያዊነት ብለው ሲጮኹ ሌላ ማንነትን ደፍጥጠው አልነበረምና ኋላ ላይ የትውልድ ስፍራን እንደነገሩ ሲጠያየቁ ግማሾቹ የትግራይ ልጆች ሆነው ተገኙ፣ ሌሎች ከወለጋ፣ ሌሎች ከሆሳእና፣ ሌሎች ከጎጃም፣ ከወሎ፣ ከአዲስ አበባ... መሆናቸው አስደሰታቸው። አስበውበት ባይሆንም ኅብረ ቀለማምነቱ፣ ጌጥ ሆናቸው እንጂ አላቃቃራቸውም። አገር ምን ማለት እንደሆነ በተግባር አዩት። ብዙዎቹ አባላት ታዲያ ከ15 እና ከ20 ዓመታት በላይ ከአገራቸው ርቀው ይቆዩ እንጂ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ስለ ኢትዮጵያ መጨነቃቸው አልቀረም፤ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ነገሩ እያሰጋቸው የመጣ ይመስላል። "የትኛውም ኢትዮጵያዊ እኮ እንደው በአካል ከአገሬ ወጣሁ ይበል እንጂ በመንፈስ ኢትዮጵያን ተለይቶ ማደር አይችልም። ይቻለዋል ብለህስ ነው?" ይላሉ ዶ/ር ዓለማየሁ። እነዚህ በታላቋ ብሪታኒያ የሚኖሩ ምሁራን ብዙዎች ጭንቀታቸውን ውጠው ከዛሬ ነገ ምን ሊመጣ ይሆን በሚል ውጥረት ዝም ባሉበት ወቅት ዝም አንልም ያሉ መሆናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል። ብዙ የድርጊት መርሐ ገብሮችን ነድፈዋል። ስለ ሰላም መስበክ ብቻ ሳይሆን በህዳሴው ግድብ ዙርያ ተሰሚነታቸውን በመጠቀም ለ4 ቀናት የሚዲያ ዘመቻ አድርገው ነበር። በሰላም ዙርያ በየጊዜው የዲጂታል ጉባኤዎችን ያዘጋጃሉ። ኮቪድ ወረርሽኝ ብዙ የመስክ ሥራ ውስጥ እንዳይገቡ ቢያግዳቸውም ለወገናቸው የሕክምና ቁሳቁስ አሰባስበው አገር ቤት ልከዋል። የዓለም ሰላም ቀንን አስመልክተው በዌቢናር ትምህርተ ጉባኤ ካቀረቡት ምሁራን መካከል ዶ/ር ፀሐይ አጥላው ይገኙበታል። ዶ/ር ፀሐይ ሥመ ጥር ሳይንቲስት ናቸው። ሴቶች በሰላም ዙርያ ያላቸውን ሚና ያጎሉት ዶ/ር ጸሐይ ለእርቅና ሰላም የሴቶችና እናቶችን ሚና ጉልህ እንደሆነና ይህንኑ ለመልካም ተግባር መጠቀም አስፈላጊነት ላይ አተኩረዋል። በዚህ ማኅበር ውስጥ ከሚገኙ አመራሮች አንዱ አቶ ወንድሙ ነጋሽ ናቸው። በሙያ ኢንጂነር ይሁኑ እንጂ ይበልጥ የሚታወቁት በአእምሮ ሳይንስ ዘርፍ ተመራማሪነታቸው ነው። "ሁሉም ጦርነቶች የተወለዱት ከሰዎች አእምሮ ነው፣ አእምሮን ካከምን ሌላው ሁሉ ቀላል ነው።" ይላሉ። አቶ ወንድሙ በተደጋጋሚ ለማኅበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች በሚያቀርቧቸው ሴሚናሮች ውስጥ ከጥላቻ ንግግር ለመራቅ፣ "እኛና እነሱ" ከሚለው ትርክትና ክፉ አባዜ ለመውጣት፣ የሰውን ክብሩነት በሰውነቱ ብቻ ለመመተር፣ በአጠቃላይ አእምሮን እንዴት ወደ ሰላም መግራት እንደሚቻል ትምህርተ ጉባኤ ያቀርባሉ። "ሰላም ስለፈለግነው ብቻ አይመጣም፣ ይህን እንረዳለን፣ ፖለቲካ ውስብስብ ነው፣ ይህንንም እንረዳለን። ግን ደግሞ አገር ስትታመም የበይ ተመልካች መሆን አንሻም" ይላሉ የካንሰር ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ዓለማየሁ። ቢቢሲ አንድ ጥያቄ አንስቶላቸው ነበር ለማኅበሩ ጸሐፊ። "ከባሕር ማዶ ቁጭ ብሎ በአገር ቤት ሰላም ማምጣት የሚመስል ነገር ነው? የሚል። በእርግጥ በኢንተርኔት ሰላም ማምጣት ይቻላል?" ዶ/ር ዓለማየሁ ለዚህ ምላሻቸው ፈጣን ነው። መጀመርያውኑስ ሰላም የደፈረሰው በኢንተርኔት በመሸጉ የዲጂታል ጦር አበጋዞች አይደለምን? ሲሉ ችግሩም፣ የችግሩ መፍትሄም ከዲጂታሉ ዓለም ጎራ እንደሆነ ያሰምሩበታል። "ኢትዮጵያ ብዙ አበሳ ያለባት አገር ናት። ለጊዜው ግን ትልቁ ህመሟ ከዲጂታል ዓለም የሚመነጨው የጥላቻ ንግግር ነው።" ይላሉ፣ ደጋግመው። ምሁራኑ ከትናንትና በስቲያ ዕለት ጀምሮ፣ የዓለም የሰላም ቀንን በሚመለከት የተለያዩ የዌቢናር ውይይቶች እያካሄዱ ሲሆን ለአንድ ሳምንት "የዲጂታል የጦር አውርድ" (Digital ceasefire) ጥሪ አቅርበዋል። ይህ እምብዛምም ያልተሰማ ነገር ነው። ለምን አስፈለገ? ምንስ ማለት ነው? ጉባኤያተኞችን ለ15 ደቂቃ ሰላማዊና ግጭት አልባ ኢትዮጵያን በሕሊናቸው እንዲያስቡ የጠየቁት የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ይህን መልካም ስሜት ለማቆየት ቢያንስ ለአንድ ሳምንት ኢትዮጵያዊያን የጥላቻ ንግግሮችን በፌስቡክ ከመጻፍ ብቻ ሳይሆን ከማንበብ፣ ከማየትና አስተያየት ከመስጠት እንዲታቀቡ ተማጽነዋል። ይህም የዓለም የሰላም ቀንን አስመልቶ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ አዲስ ዘመቻ ነው። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከጥላቻ ንግግሮች ለአንድ ሳምንት በመራቅ እንዴት ጥሩ ስሜት ለራሳቸው መፍጠር እንደሚችሉ እንዲያዩት ይፈልጋሉ፣ ዶ/ር ዓለማየሁ። በማህበራዊ ሚዲያ የደፈረሰ ሰላምን በማህበራዊ ሚዲያም መመለስ ይቻላል? ዶ/ር ልዑል ሰገድ አበበ የእርቅና የሰላም ጉዳዮች አማካሪ ምሁር ናቸው። የተለያዩ የምርምር ሥራዎቻቸውንም የሰሩት በዚሁ የግጭት አፈታትና እርቀ ሰላም ዙርያ ነው። በታላቋ ብሪታኒያ ብቻም ሳይሆን በምዕራብ አፍሪካ የተለያዩ አገራት ላይ በዚሁ መስክ አገልግለዋል። ዶ/ር ልዑልሰገድ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን "በሬን የሚያዋልዱ ሰዎች" ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ለማድረግ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ከዚህ በተቃራኒ ለሰላምና ሕዝቦችን ለማቀራረብ ሊያገለግል እንደሚችል ይናገራሉ። የግጭት አንዱ መንስዔ ያልተረጋገጠ መረጃን ማስተላለፍ ነው የሚሉት ምሁሩ፣ ሁላችንም ከእንዲህ ዓይነት ተግባር መቆጠብ እንደሚያስፈልገን ይመክራሉ። በርግጥ በማህበራዊ ሚዲያ ብቻ ሰላምን ማምጣት ይቻላል የሚለው ላይ መጠነኛ ጥርጣሬ ቢኖራቸውም፣ ሐሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች ግን እንዲቆሙ ማድረግ ይቻላል ሲሉ ገልፀዋል። እነዚያ መረጃዎችና ንግግሮች ቆሙ ማለት ደግሞ ለሰላም የመጀመሪያው በር ተከፈተ ማለት ሊሆን ይችላል ሲሉ ያላቸውን ተስፋ ይገልፃሉ። በተጨማሪም ማህበራዊ ሚዲያ አያያዙን ካወቅንበት ሃሳብን ገንቢ በሆነ መልኩ የማቅረብ፣ የመከራከር ባህልን እንድናዳብር ለማድረግ አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላልም ብለው ያምናሉ። ዶ/ር አለማየሁ ይህን የዶ/ር ልኡልሰገድን ሐሳብ ያጠናክራሉ። "ኢትዮጵያ ብዙ አበሳ ያለባት አገር ናት" ካሉ በኋላ፣ ከዚህ ሁሉ "ክፉኛ ያመማት" ደግሞ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና ጥላቻ ንግግሮች ናቸው" ይላሉ። እንደ እርሳቸው እምነት በዲጂታል ቴክኖሎጂን የተዘራን ክፉ ሃሳብ ማከም የሚቻለው በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ብቻ ነው። ሰላም በአንድ ቀን ወርክሾፕ የሚገኝ አይደለም የሚሉት ዶ/ር ልኡልሰገድ በበኩላቸው "ሰላም ሂደት" መሆኑን ያሰምሩበታል። ሂደቱን ለማገዝም የሰዎችን አስተሳሰብና አመለካከት መለወጥ እንደሚያስፈልግ፣ ሰዎች እንዲናገሩ፣ ሃሳባቸውን እንዲገልፁ ቦታና ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚገባ ይናገራሉ። ግጭትን እንደመቅሰፍት አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች መኖራቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ልኡልሰገድ፤ ግጭት መቅሰፍት ሳይሆን የሃሳብ አለመግባባት ወይንም የመረጃዎች አለመጣጣም ነው በማለት እንደነዚህ አይነት ነገሮችን ቁጭ ብሎ በመወያየት መፍታት እንደሚቻል ያስረዳሉ። ይህ ግጭትን በውይይት የመፍታት ባህል በአገሪቱ በሚገኙ በተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ዘንድ መኖሩን ገልፀው፣ እነዚያን ግጭት መፍቻ ነባር ባህሎች አምጥቶ ለሰላም መጠቀም እንደሚገባ ያስረዳሉ። "መሣሪያ ዘላቂ ሰላምን አያሰፍንም" ከአገር በብዙ ማይሎች ርቀው የወገንን ዜና በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን በኩል ሲሰሙ በአካል ተገኝተው ምንም ማድረግ ባይችሉም ፣ ምንም ማድረግ አንችልም ብለው እንደማያስቡ የሚናገሩት ደግሞ ዶ/ር አለማየሁ ናቸው። " የምንችለውን ያክል እናድርግ" ብለው ለሰላም መምጣት እየሰሩ መሆኑን ይናገራሉ። ሰላምን በአንድ ሰው የሚመጣ ጉዳይ አይደለም የሚሉት ዶ/ር ልኡልሰገድ፣ "ሰላምን መንግሥት ብቻውን፣ ሊያመጣው የሚችል ጉዳይ አይደለም። ሰላምን ፖሊስ፣ ጦር ሰራዊት ሊያመጣው አይችልም፤ ሁሉም በጋራ ኃላፊነት መስራት ሲችል ነው ሰላም የሚመጣው" ይላሉ። የኢትዮጵያ ሰላም ማጣት በየደቂቃው፣ በየሰዓቱ በየእለቱ ያሳስበኛል የሚሉት ዶ/ር አለማየሁ፣ ሰላም ከእጃችን አምልጦ ወደ ቀውስ ውስጥ ከተገባ "ማጣፊያው ከባድ ነው" ሲሉ ይገልፃሉ። ይህንን ጎረቤት አገራትን መመልከት ብቻ ሳይሆን፣ ከዚህ ቀደም በአገር ውስጥ የተከሰቱ የሰላም መደፍረሶችን በማየት ብቻ እንዴት በቀላሉ ወደ ብጥብጥና አለመረጋጋት መግባት እንደሚቻል ማስተዋል ተገቢ መሆኑን ዶ/ር አለማየሁ ይመክራሉ። ለዚህም እያንዳንዱ ግለሰብ ዛሬ የሚሰራው ስራ የነገ ሰላም ላይ የሚኖረውን አስተዋጽኦን በማየት በጥንቃቄ መራመድ እንዳለበት ያሳስባሉ። ዶ/ር ልኡልሰገድ በበኩላቸው እያንዳንዱ ኀብረተሰብ "ግጭት በቃኝ፣ በፍርሃት መቀመጥ በቃኝ፣ ቤተሰቦቼን ለጥይት እዳ አልዳርግም፥ እርሻዬን አርሼ መኖር መቻል እፈልጋለሁ" ማለት አለበት ይላሉ። ያኔ ወታደሩም፣ መንግሥትም ሊረዳ ይችላል በማለት እዚያ ደረጃ እስካልተደረሰ ድረስ ዘላቂ ሰላም ማስፈን እንደማይቻል ያስረግጣሉ። መሳሪያ ሰላምን አያሰፍንም የሚሉት ምሁሩ፣ የታጠቀ ኃይል ያነገተው መሳሪያ "ዛሬ ላይ ቢያሳልፈው ነገ ላይ ሊያቆመው አይችልም" ብለዋል። ሰዎች የሰላም ባለቤት እነርሱ መሆናቸውን ማወቅ እንደሚገባቸውና፣ "ግጭት በቃን" ማለት እንደሚያስፈልጋቸው ይናገራሉ። የአካባቢ ሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ አዛውንቶች፣ የሃይማኖት አባቶች በአካባቢያቸው የሚገኝ የሕገ ወጥ መሳሪያ ዝውውር እንዲቆም ለማድረግ "ከራስ ወዳድነት ወጥቶ ለሌሎች ደህንነት መቆም እንደሚያስፈልጋቸው" ይመክራሉ። አገራችን ለፖለቲከኞች ወይንም ለአክቲቪስቶች ብቻ መተው ኃላፊነት የጎደለው ነገር ነው የሚሉት ዶ/ር አለማየሁ ደግሞ፣ "አይመለከተኝም ብሎ ለእነዚህ ወገኖች አገርን መተው በአንድ ቀን ከተማ አመድ እንደሚሆን አይተናል" ይላሉ። ዶ/ር ልኡልሰገድ ሕዝቡ ግጭት በቃኝ ካለ "ሰላምን ማስፈን ረዥም ጊዜ ይወስዳል ብዬ አላምን" በማለት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ለማስፈን በአገር ውስጥ ሆነ ከአገር ውጪ ያሉ ሰዎች ኃላፊነት መውሰድ እንደሚገባቸውና ይህንንም መወጣት ተገቢ መሆኑን ይናገራሉ። ዶ/ር አለማየሁ በበኩላቸው ሰላምን ለማምጣት ለወጣቶች የመነጋገርንና የመከራከርን መድረክ ማሳየት፣ የኢትዮጵያዊነትን እሴት በማስተማር በመግራት መስራት ይገባል ይላሉ። ዶ/ር ልዑል ሰገድም ለልጆቻችን የምንናገራቸው ነገሮች ማስተዋል እንደሚገባ ገልፀው፣ "ከማንነት ባሻገር እኛነታችን እየነገሩ ማስተማር ያስፈልጋል" ብለዋል። አክለውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ቢሆኑ፣ ሃሳብን በሃሳብ መመከትን፣ ተማሪዎቻቸው እንዲያጎለብቱ መስራት እንደሚገባቸው ይመክራሉ። የማኅበሩ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ነገር አሁንም ያባንናቸዋል። ሰላም ቢደፈርስስ? ወደ እርስ በርስ ቀውስ ብንገባስ? ብለው ያስባሉ። ሰላም በእጃችን ላይ ሳለች ብዙም አታስታውቅም የሚሉት ዶ/ር ዓለማየሁ፣ ከእጅ ላይ ሸርተት ብላ እንደ ብርጭቆ ብትወድቅስ? ብለው ይጨነቃሉ። ዙሪያዋን በቀበሮ እንደተከበበች በአንዲት አጋዘን የሚመስሏት የዛሬዋን ኢትዮጵያን ሁኔታ እያየን እንዴት ዝም እንላለን ይላሉ። "ለምን የመን ሊቢያና ሶሪያ እንላለን? አየነው እኮ በኛው፤ ያላየነው ምን አለ? ያልሆነው ምን አለ?" ይላሉ። ያቺ ክፉ ቀን እንዳትመጣ ይጨነቃሉ። ነገር ግን ዳር ሆኜ አልጨነቅም፥ የምችለው እያደረኩ እጨነቃለሁ ነው የሚሉት። "አገርን ለፖለቲከኛና ለአክቲቪስቶች ጥሎ እንዴት ይታደራል?"
xlsum_amharic-train-281
https://www.bbc.com/amharic/news-46671870
ሳይንስ እንዲህ ይላል፦ «ስጦታ ከመቀበል፤ መስጠት ያዋጣል»
የፈረንጆቹ ገና ዛሬ ነው፤ የኛ ደግሞ ዳር ዳር እያለ ነው።
[ "የፈረንጆቹ ገና ዛሬ ነው፤ የኛ ደግሞ ዳር ዳር እያለ ነው።" ]
ታድያ በዓል ሲመጣ ስጦታ መሰጣጣቱ የተለመደ ነው። ስጦታ መስጠት የሆነ ደስ የሚያሰኝ ነገር አለው፤ «መቀበልን የመሰለ ነገር ደግሞ የለም» የሚሉም አይጠፉም። አጥኚዎች ስጦታ ከመቀበል ይልቅ መስጠት የተሻለ የመንፈስ እርካታ እንደሚሰጥ መርምረን ደርሰንበታለን ይላሉ። ለዘመድ፣ ለጓደኛ፣ ለቤተሰብ፣ ለፍቅረኛ ስጦታ ምን ልሸምት የሚለው ጭንቀት የበዓል ትሩፋት ነው። ታድያ እርስዎ በመጪው ገና ለወደዱት ሰው ምን ዓይነት ስጦታ ለመስጠት አሰቡ? «እራሴን» እንዳይሉን ብቻ!?!?! ኤድ ኦብራያን የተሰኙ የአዕምሮ ጤና ባለሙያ «ደጋግሞ መስጠት ለመንፈስ እርካታ ነው፤ ሰላማዊ መኝታ ነው» ባይ ናቸው። • ለጎረቤት ልጅ ለወደፊቱ 14 ዓመታት የገና ስጦታ አስቀምጦ የሞተው ግለሰብ 100 ተማሪዎች ተመረጡ፤ ለእያንዳንዳቸው አምስት አምስት አምስት ዶላር በየቀኑ እንዲሰጣቸው ሆነ። ታድያ ያንን አምስት ዶላር ማጥፋት ያለባቸው በተመሳሳይ ነገር ላይ ነው፤ አሊያም በስጦታ መልክ ማበርከት። ግማሾቹ ገንዘቡን ለቀረበላቸው አገልግሎት ማመሰገኛ 'ቲፕ' አደረጉት፣ ግማሾቹ ደግሞ ለእርዳታ ድርጅት ለገሱት፣ የተቀሩቱ ደግሞ ያሻቸውን ሸመቱበት። ተማሪዎች በየቀኑ ያንን በማድረጋቸው ምን ያክል እርካታ እንዳገኙ ያሳውቁ ዘንድ መጠይቅ ቀረበላቸው፤ ያለማንገራገርም ሞሉት። ውጤቱም እንደተጠበቀው ሆነ፤ ሁሉም ተማሪዎች ባደረጉት ነገር እጅግ መደስታቸውን የሚለገልፅ ቅፅ ሞሉ። ነገር ግን ገንዘቡን በመጠቀም ያሻቸውን ነገር የሸመቱት ተማሪዎች ደስታቸው ከቀን ቀን እየቀነሰ እንደመጣ በሞሉት ቅፅ ላይ መስተዋል ተቻለ። እርግጥ ነው፤ ከመቀበል መስጠት ለምን የተሻለ ደስታ ሊያጎናፅፍ እንደቻለ ግልፅ አድርጎ የሚያስቀምጥ ጥናት አልተገኘም። ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች ይነሳሉ፤ ለምሳሌ ምን ዓይነት ስጦታ መስጠት ነው ደስታን የሚያጎንፅፈው? መጠኑ ምን ያክል መሆን አለበት? እና መሰል። ሱዛን ሪቻርድስ የበጎ አድራጎት ሥራ ለሰጪው ምን ዓይነት የአዕምሮ ሰላም ይስጥ ይሆን? የሚለውን ጥያቄ ይዛ ጥናት አካሄደች፤ ውጤቱም በጎ ሆኖ ነው ያገኘችው። • የኢትዮጵያ ገና ለምን ታህሳስ 29 ይከበራል? በፈቃዳቸው የበጎ አድራጎት ሥራ የሚያከናውኑ የጭንቀት በሽታ ያለባቸው ሰዎች የተሻለ የአዕምሮ ደስታ እንደሚያገኙ የአጥኚዋ ሥራ ያሳያል። የሱዛንም ሆነ የኦብራያን ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች ስጦታ በየቀኑ ቢሰጣቸው ፊታቸው ላይ የሚነበበው የደስታ ስሜት ከቀን ቀን እየቀነሰ እንደሚመጣ ነው። ጥናቶቹ ላይ የተሳተፉ ሰዎችም ይህንኑ ነው በግልፅ ያሳዩት፤ በየቀኑ ስጦታ ለሌሎች ሰዎች መስጠት የቻሉቱ ተማሪዎች በየቀኑ ደስታቸው እየላቀ ነው የመጣው። በቅርቡ ያረፈችው የኮምፒውተር ባለሙያ ኤቬሊን ቤሬዚን እንዲህ ትላለች «አንድ ግብ መምታት ጊዜያዊ ደስታ ሊሰጥ ይችል ይሆናል፤ ዋነኛው ደስታ ያለው ግን ያንን ግብ ለማሳካት በሚደረገው ትግል ውስጥ ያለው ሂደት ነው።» • ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ የሚመጡ የሙያ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው?
xlsum_amharic-train-282
https://www.bbc.com/amharic/news-56439792
ኮሮናቫይረስ፡ ከአሜሪካ ለእረፍት የመጡትን ጨምሮ 10 አባላቱ በኮቪድ-19 የተያዙበት ቤተሰብ
በኢትዮጵያ ያለው የኮሮናቫይረስ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል። በበሽታው የሚያዙ፣ በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሌላው ጊዜ በተለየ በከፍተኛ መጠን ጨምሯል።
[ "በኢትዮጵያ ያለው የኮሮናቫይረስ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል። በበሽታው የሚያዙ፣ በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሌላው ጊዜ በተለየ በከፍተኛ መጠን ጨምሯል።" ]
የጥንቃቄ ጉድለት ብዙዎችን ለወረርሽኙ በማጋለጥ ዋጋ እያስከፈለ ነው። ከአሜሪካ ቤተሰብ ጥየቃ የመጡ ሁለት ግለሰቦችን ጨምሮ አስር የአንድ ቤተሰብ አባላት በጥንቃቄ ጉድለት ሳቢያ እንዴት ለበሽታው እንደተጋለጡ ታሪካቸውን ለቢቢሲ ነግረዋል። አቶ ሰለሞን ድረስ በቅርቡ ነው ከሚኖሩበት አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት። እንደማንኛውም ዓለም አቀፍ መንገደኛ ከበረራቸው ዕለት ቀደም ብሎ የኮሮናቫይረስ ምርመራ አድርገዋል። ውጤቱ ነጋቲቭ በመሆኑ ነው ጉዟቸውን ማድረግ የቻሉት። አዲስ አበባ በደረሱ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ዘመዶቻቸውን እና ጓኞቻቸውን አግኝተዋል። "ኮሮናቫይረስ የሌለባት የምትመስለው አዲስ አበባ ጥቂት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የሚያደርጉ ሰዎች ባይታዩ የተለመደው የኑሮ ሂደት የቀጠል ይመስላል" ይላሉ። የአቶ ሰለሞንም በሚኖሩበት አሜሪካ አስገዳጅ ስለሆነ የሚያደርጉትን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጥለው አገሬውን ለመምሰል ጊዜ አልፈጀባቸውም። በጥቂት ቀናት ውስጥ ግን ነገሮች በፍጥነት መቀያየር ጀመሩ። "መጀመሪያ ላይ ከባድ ድካም ነበር ይሰማኝ የነበረው" ሲሉ የህመማቸውን ጅማሬ ይገልጻሉ። በመጀመሪያው ቀን ጉዞው እና ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ያደረጉት እንቅስቃሴ ያደከማቸው ቢመስላቸውም ሁለተኛው ቀን ላይ ድካሙ "ከሚገለጸው በላይ ሆነ።" "መጀመሪያ ከነበረኝ ድካም እጅግ የከበደ ነበር። ከአልጋ ወርጄ መጸዳጃ ቤት መሄድ ራሱ ፈታኝ ሆነብኝ" ሲሉ ሁኔታውን ይገለጻሉ። በተመሳሳይ ዘመድ ጥየቃ ከውጭ የመጡት አጎታቸውም "ከፍተኛ ድካም" ይሰማቸው ይጀምራል። ሁኔታው ስጋት ያሳደረባቸው አቶ ሰለሞን ከአጎታቸው ጋር በመሆን ወደ ህክምና ማዕከል በማቅናት ምርመራ ያደርጋሉ። ውጤቱ ግን ፍጹም ያልጠበቁት ነበር - ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው። ህመምና ጭንቀት "ከድካም በስተቀር ምንም የተለየ ምልክት ስላልነበረን ኮሮናቫይረስ ይሆናል የሚል ግምት አልነበረንም። ምርመራም ያደረግነውም በአጋጣሚ ነበር። ድካሙ እጅግ ከባድ ሲሆን ለተከታታይ ቀናትም የቀጠለ ነበር። አቶ ሰለሞንም ሆኑ አጎታቸው ራሳቸውን በመለየት የጤናቸውን ሁኔታ መከታተል ጀመሩ። ውጤቱ ከታወቀ በኋላ ከእርሳቸው በላይ ያስጨነቃቸው የአጎታቸው ሁኔታ ነበር። የአጎታቸው ሁኔታ ያሳሰባቸው ከዕድሜያቸው እና ባለባቸው ተጓዳኝ ህመም ምክንያት ነው። "የተለያየ ክፍል በመሆናችን ያለኝን አቅም ሰብሰብ አድርጌ እሱ [አጎቴ] ያለበትን ሁኔታ እጠይቃለሁ።" ይላሉ። ድካሙ እየጨመረ የሚወስዱት ምግብ እየቀነሰ ሄዶ ምግብም ሆነ ውሃ መውሰድ የማይችሉበት ደረጃ ደረሱ። ይህ ደግሞ ሌላ ችግር ሆነ። "የምንበላውም ሆነ የምንጠጣው ነገር በሙሉ ይወጣ ነበር" ሲሉ ሁኔታውን ያስታውሳሉ። "የምንወስደው ነገር በሙሉ ስለሚወጣ በሽታውን ለመቋቋም እንዲረዳን ምግብም ሆነ ማስታገሻ መድኃኒቶችን ለመውሰድ ባለመቻላችን ከቀን ወደ ቀን እየተዳከምን ሄድን" ይላሉ አቶ ሰለሞን። "እኔም ሆንኩኝን አጎቴ ከመዳከማችን የተነሳ መቃዠት ጀምረን ነበር።. . . አንዳንዴ በእውን የማይመስሉ ነገሮችን እንመለከታለን። ከመተኛት ውጪ ምንም የማድረግ ጉልበት አልነበረንም።" ሲሉ ረዥሙን ሰዓት በእንቅልፍ ያሳልፉ እንደነበር ይናገራሉ። ከህክምና ባለሙያዎች በተነገራቸው መሠረት ቤት ውስጥ ሆነው በምግብ ምትክ ጉልኮስ እንዲሰጣቸው ተደረገ። በዚህ መልኩ ከቫይረሱ ጋር ትንቅንቁ ቀጠለ። ተጨማሪ ታማሚዎች ብዙም ሳይቆይ ግን ታናሽ ወንድማቸውም የማያቋርጥ ሳል እንዳለበት በማወቃቸው እንዲመረመር ይጠይቁታል። "ወንድሜን እኔም አጎታችንም ኮሮናቫይረስ እንዳለብን ከማወቃችን ከሁለት ቀናት በፊት አግኝተነው ነበር። ሳል ስለጀመረው ምርመራ እንዲያደርግ ብንመክረውም 'ጉንፋ ነው' የሚል ምላሽ በመስጠት ሳይመረመር ይቀራል።" የወንድማቸው ሳል ግን እንደዚህ ቀደሙ ቀላል የሚባል ባለመሆኑ እና የድካም ስሜት በማሳየቱ ምርመራ አደረገ። በውጤቱ ቫይረሱ ተገኘበት። በቀናት ልዩነት ሦስተኛው የቤተሰቡ አባል በኮሮናቫይረስ ተያዘ። በዚህ ወቅት እነአቶ ሰለሞን ጤናቸው መሻሻል የጀመረበት እና "አሁን እንደማንሞት እርግጠኛ ሆንን" ያሉበት ጊዜ ነው። ምግብ በመጠኑም ቢሆን ይመገባሉ። ውሃ ይጠጣሉ። ማስታገሻ መድኃኒቶችንም መውሰድ ጀምረዋል። ከአምስት ቀናት በፊት አብዛኛዎቹ የቤተሰባቸው አባላት ተሰባስበው ስለነበር ሁሉም እንዲመረመሩ ይደረጋል። ቤተሰቡ በነበረው ስጋትና ንክኪ ምክንያት ሁሉም ቢመረመር ለጥንቃቄ እንደሚረዳ በማሰብ "ወደ ሃያ የሚጠጉ የቤተሰቦቼ አባላትና ከእኛ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች በሙሉ በተለያዩ ቀናት ተመረመሩ" ይላሉ አቶ ሰለሞን። ነገር ግን ከአቶ ሰለሞን እና አጎታቸው ጋር ግንኙነት ኖሯቸው ለምርመራው ፈቃደኛ ያልሆኑም ነበሩ። "'እስካላመመኝ ወይም ምልክት እስካላሳየሁ ለምን እመረመራለሁ?' የሚል ነበር ምክንያታቸው" ሲሉ ይገልጻሉ። በዚህ መካከል የአንደኛዋ እህታቸው ውጤት ኮቪድ-19 እንዳለባት የሚያመለክት ሆነ። በዚህም ወረርሽኙ የተገኘባት አራተኛ የቤተሰቡ አባል ሆነች። "ምንም ምልክት ያላሳየች የመጀመሪያዋ የቤተሰባችን አባል ነች" ይላሉ። እህታቸው ተጓዳኝ በሽታ ስላለባት ስጋት ቢፈጠርም ምንም ህመምም ሆነ ምልክት ሳታሳይ ቀጠለች። የተመረመሩት የቤተሰባቸው አባላት ቀስ በቀስ ሲመጣ ቫይረሱ ያልተገኘባቸው እንዳሉ ስንረዳ በትንሹም ቢሆን ጭንቀታችንን ቀለል አድርጎት ነበር። ከቀናት በኋላ ግን ያልተጠበቀ ውጤት መጣ። "እኔና አጎቴ ተመርምረን ውጤት ባወቅን በሳምንቱ ሌላኛው ወንድሜ በኮሮናቫይረስ መያዙ ተነገረው። ከወንድሜ በተጨማሪ ሚስቱ እና ልጆቹም መያዛቸው አስደንጋጭ ነበር" ይላሉ አቶ ሰለሞን። ይህም በቤተሰቡ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ ዘጠኝ ከፍ አደረገው። ውጤት ጥበቃ አስደንጋጩ ነገር ናሙና ከሰጡ በኋላ ለአራት ቀናት ያህል ውጤት ባለመድረሱ የተለመደውን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር የሰነበቱት። "ውጤቱ ሲዘገይ የተለመደውን እንቅስቃሴዬን ቀጥዬ ነበር" ይላሉ የአቶ ሰለሞን ወንድም የሆኑት አቶ ሲሳይ። "ቤተሰቦቼን በተደጋጋሚ አግኝቻለሁ። ሥራ ቦታዬ ላይ ለአንድም ቀን ሳላዛንፍ ተገኝቻለሁ። ባለቤቴም እየሠራች ነበር። ሦስቱም ልጆቼ አንድም ቀን ከትምህርታቸው አልቀሩም ነበር" ብለዋል። በዚህ ምክንያትም የኮሮናቫይረስ ምርመራ ያደረጉ ቤተሰቦቻቸው በሦስት ቀን ልዩነት በድጋሚ ናሙና ለመስጠት ተገደዱ። "የምርመራው ውጤት መዘግየት ቤተሰቡ ድጋሚ እንዲመረመር ከማስገደዱም በተጨማሪ አገርንም ዋጋ የሚያስከፍል ነው" ይላሉ አቶ ሲሳይ ሁኔታው ለቫይረሱ መስፋፋት ያለውን ሚና በመግለጽ። ውጤቱ ከታወቀ በኋላ የአቶ ሲሳይ ቤተሰብ አባላት ምንም ምልክትም ሆነ ህመም ሳይኖራቸው ራሳቸውን ለይተው ቆዩ። "የመጀመሪያዎቹ ቀናት አካባቢ ስጋት ነበረብን። 'ልጆቼን ቢያማቸውስ? ባለቤቴስ ብትታመም?' እያልኩ እጨነቅ ነበር። ከራሴ በላይ የእነሱ ሁኔታ ያሳስበን ነበር" ይላሉ። "የህክምና ባለሙያዎች በየጊዜው እየደወሉ ያለንበትን ሁኔታ ይጠይቁን ነበር። ለሁለት ሳምንት ራሳችንን ለይተን ከቆየን በኋላ ወደ መደበኛው ህይወታችን መመለስ እንደምንችል ተነገረን" ብለዋል። መዘናጋት ያስከተለው ጥንቃቄ ጉድለት ህይወት በተለመደው መንገድ ቢቀጥልም ኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ መግባቱ በተገለጸ በመጀመሪያዎቹ ወራት የነበረው ጥንቃቄ ቀርቶ ሁሉም በተለመደው አኗኗር መቀጠሉ ምክንያት እንደሆነም ጨምረው ገልጸዋል። እሳቸውም ሆኑ ዘመዶቻቸው ለወራት ያደረጉትን ጥንቃቄ በማላላት የተለያዩ ዝግጅቶች ላይ ተገኝተዋል። "ከቤት ውጭ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያደረገውም ያለደረገውም ቤት ሲደርስ አውልቆ ይቀላቀላል" ይህም ሲጠነቀቅ የዋለውን የቤተሰብ አባል ተጋላጭ እንደሚያደርግ በመጠቆም። የአቶ ሲሳይ ቤተሰቦች ራሳቸውን ለይተው በቆዩበት ጊዜ ሌላ የቤተሰባቸው አባልም በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ። ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ አስረኛው የቤተሰቡ አባል ሆኑ። 'መልካም' የሚባለው ነገር ከአስሩ የቤተሰቡ አባላት መካከል ሰባቱ ምንም ምልክትም ሆነ ህመም ያልነበራቸው መሆናቸው ነበር። ሦስቱም ቢሆኑ መካከለኛ የሚባል ነበር ህመማቸው። ወደ ጤና ተቋም የማያስኬድ እና ቤት ውስጥ የሚደረግ ጥንቃቄና እንክብካቤ ብቻ የሚያስፈልገው አይነት ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ለሦስት ሳምንት የመጡት አቶ ሰለሞን እና አጎታቸው በኮሮናቫይረስ ምክንያት አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ክፍል ተለይተው እንዲቀመጡ ተገደዋል። "ቫይረሱ እንዴት ቤተሰቡ ውስጥ እንደገባ እና እንደተሰራጨ የምናውቀው ነገር የለም" የሚሉት አቶ ሰለሞን "የተለያየ ግምት ቢኖረንም እርግጠኞች ግን አይደለንም" ብለዋል። እርግጠኛ የሆኑት "ወረርሽኙ በሰዎች ቸልተኝነት እና የጥንቃቄ ጉድለት በፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑን እና ብዙዎች ህይወታቸውን እስከማጣት መድረሳቸውን ነው።" "ያለማስክ መንቀሳቀስ ተለምዷል። የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ትርፍ ጭነው ሲሄዱ እየተመለከትኩ ነው። የንግድ ቦታዎች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው ተመልሰዋል። ተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል አድርገው በፈረቃ እየተማሩ ቢሆንም ከትምህርት ቤት ውጭ ያለው ጥንቃቄ አነስተኛ ነው" ብለዋል። አንዳንዶችም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በአግባቡ ከመጠቀም "እጃቸው ላይ ሰክተው ሲንቀሳቀሱ ላየ 'ቫይረሱ በምንድነው የሚተላለፈው?' የሚል ጥያቄን ይጭራል" ሲሉ ትዝብታቸውን ያስቀምጣሉ። ለሁለት ሳምንት ያህል በኮሮናቫይረስ ተይዘው የነበሩት የአቶ ሰለሞንና አስር የቤተሰባቸው አባላት አሁን አገግመው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል። አንዲት እህታቸው ግን አሁንም የጀመራት 'ሳል' አልፎ አልፎም ቢሆን ሄድ መለስ ይላል። አቶ ሰለሞን ዘመድ ለመጠየቅ፣ ላለባቸው የግል ጉዳይ እና ለእረፍት በሚል ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉት ጉዞ በቫይረሱ ምክንያት ብዙ መስተጓጎል ገጥሞታል። "ከዕቅዴ ብስተጓጎልም የከፋ ጉዳት ሳይገጥመን ከቫይረሱ ነጻ በመሆናችን ዕድለኛነት ይሰማኛል። በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ አሳሳቢ ሆኖብኛል። ሕዝቡ ጥንቃቄውን ትቶ ወደ መደበኛ ህይወቱ መመለሱ ይበልጥ ችግሩን ያስፋፋዋል። . . .ስለዚህ ሕዝቡ ቸልተኝነቱን ትቶ መጠንቀቅ አለበት" ይላሉ። በመጨረሻም አቶ ሰለሞን እና አጎታቸው እንዳመጣጣቸው ወደ አሜሪካ ለመመለስ የኮሮናቫይረስ ምርመራ አድርገው ውጤቱን ተቀብለዋል። ኔጋቲቭ።
xlsum_amharic-train-283
https://www.bbc.com/amharic/54351582
ኢትዮጵያ፡ ፖለቲከኛ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ደራሲው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
ታዋቂው ምሁር፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰማ።
[ "ታዋቂው ምሁር፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰማ።" ]
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ከሳምንት በፊት ታምመው ሆስፒታል መግባታቸው ተነግሮ የነበረ ሲሆን ህክምና እየተከታተሉ በነበረበት ጊዜ የጤናቸው ሁኔታ መሻሻሉን የቅርብ ሰዎቻቸው ገልጸው ነበር። ነገር ግን ማክሰኞ መስከረም 19/2013 ዓ.ም ለረቡዕ አጥቢያ ከቤተሰቦቻቸው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አዛውንቱ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በዘጠና ዓመታቸው ማረፋቸው ተገልጿል። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከአጼ ኃይለሥላሴ አስተዳደር ጊዜ አንስቶ የነበሩትን የኢትዮጵያ መንግሥታት በግልጽ በመተቸትና የሚያውቁትን፣ ያዩትን እንዲሁም የሚሰማቸውን በጽሁፍና በተለያዩ መንገዶች በመግለጽ የሚጠቀሱ ምሁር ናቸው። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በ1922 ዓ.ም የተወለዱት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ወደ ዘመናዊው ትምህርት ከመግባታቸው በፊት በልጅነታቸው በቤተክርስትያን የሚሰጠውን ሐይማኖታዊ ትምህርት በመከታተል ድቁናን እንዳገኙ የህይወት ታሪካቸው ያመለክታል። ከዚያም በኋላ በአሁኑ የእንጦጦ አጠቃላይ፣ በቀድሞው የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ገብተው የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ጥሩ ውጤት ከሚያስመዘግቡ ተማሪዎች መካከል ለመሆን ችለዋል። "የሐሳብ ልዕልና ምልክት፤ የሰላማዊ ትግል አርአያ፣ ላመኑበት ነገር እስከ መጨረሻቸው ሞጋች፣ ላመኑበት እውነት ብቻ የሚቆሙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በማረፋቸው ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዚህም በወቅቱ ኮከብ ከሚባሉት የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች መካከል ልቀው የተገኙት መስፍን ወልደማሪያም፣ በወቅቱ ለጎበዝ ተማሪዎች ይሰጥ የነበረው የውጪ አገር የትምህርት እድል አግኝተዋል። ፕሮፌሰር መስፍን በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ውስጥ ባሳዩት ብቃት ከፍ ያለ ትምህርት እንዲከታተሉ ወደ ህንድ አገር በማቅናት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከፑንጃብ ዩኒቨርሲቲ ከተቀበሉ በኋላ፣ በማስከተል ደግሞ አሜሪካን አገር ከሚገኘው ክላርክ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። ፕሬፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ አብዛኛውን የሥራ እድሜያቸውን ወዳሳለፉበት የመምህርነት ሥራ በመሰማራት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አገልግለዋል። ፕሮፌሰር መስፍን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በቆዩባቸው ዓመታት ውስጥ በጂኦግራፊ የትምህርት ክፍል ውስጥ በመምህርነት እንዲሁም በትምህርት ክፍሉ ኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን፣ ለክፍሉ ማስተማሪያ የሚሆኑ መጽሐፍትን በማዘጋጀትም ታላቅ ባለውለታ መሆናቸው ይነገርላቸዋል። ከዚህ በተጨማሪም ፕሮፌሰር መስፍን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመምህርነት ባገለገሉባቸውና ከዚያም ውጪ በነበሩት ጊዜያት በርካታ የጥናታዊ ጽሑፎችንና ሌሎች መጽሐፍትን አዘጋጀተው አሳትመዋል። እንዲሁም የተለያዩ ይዘት ያላቸውን ጽሑፎች በማዘጋጀት በጋዜጦች፣ በመጽሔቶችና ፌስቡክን በመሰሉ የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ጭምር ሲያካፍሉ ቆይተዋል። በተለይ በተደጋጋሚ እየተከሰተ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈተና ሆኖ የቆየውን እሳቸው "ጠኔ" የሚሉትን ረሃብ በተመለከተ ተጠቃሽ መጽሐፍትን አዘጋጅተው አሁን ድረስ ጉዳዩን በተመለከተ እንደማጣቀሻ ከሚቀርቡ ሥራዎች መካከል በቀዳሚነት የሚነሳ ነው። ፕሮፌሰር መስፍን የአገሪቱ ተደጋጋሚ ፈተና የሆነውን ረሃብን በምሁር ዓይን በማየት ትኩረት እንዲያገኝ ምርምርና ጽሑፍ ከማዘጋጀት ባሻገር፣ በተለይም በንጉሡ ጊዜ የተከሰተውን ረሃብ ወደተለያዩ ቦታዎች በመሄድ በቅርበት ለመመልከት ከመቻላቸው ባሻገር የተቸገሩትን ለመርዳት ከባልደረቦቻቸው ጋር ጥረት እንዳደረጉ ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል። ፕሮፌሰር መስፍን ከትምህርታዊ የምርምር ሥራዎቻቸው በተጨማሪም ፖለቲካውን ጨምሮ በአጠቃላዩ የዕለት ከዕለት ህይወታቸው የተመለከቷቸውን ጉዳዮች በማንሳትም ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ትችትን እንዲሁም ምክሮችንም በጽሑፎቻቸው ያለፍርሃትና ይሉኝታ የሚያንጸባርቁ ምሁር ነበሩ። ሃሳባቸውን በረጅሙ በመጽሐፍ፣ በመካከለኛ መጣጥፎች በመጽሔትና በጋዜጣ እንዲሁም በጣፈጠና በአጭሩ ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚያቀርቡት ፕሮፌሰር መስፍን በግጥምም ጠንካራ ሃሳባቸውን የሚገልጹ ምሁር ነበሩ። ለዚህም ማሳያዋና አሁን ድረስ መነጋገሪያ እንደሆች ያለችው የፕሮፌሰሩ የሥነ ግጥም ስብስብ መድብል የሆነችው "እንጉርጉሮ" ማሳያ ናት። 'እንጉርጉሮ' የተለያዩ ጉዳዮችን በማንሳት በተመረጡ ቃላት ጥልቅ መልዕክትን የያዘች የግጥም መጽሐፍ እንደሆነች በርካታ አንባቢያን አስካሁን ድረስ ይመሰክራሉ። አስካሁንም በእንግሊዝኛ ከዘጋጇቸው መጽሐፍት ባሻገር በአማርኛ ኢትዮጵያ ከየት ወዴት፣ አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ፣ሥልጣን ባሕልና አገዛዝ፣ ፖለቲካና ምርጫ፣ የክህደት ቁልቁለት፣ አገቱኒ፣ መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ አድማጭ ያጣ ጩኸት፣ እንዘጭ! እምቦጭ! የኢትዮጵያ ጉዞ፣ አዳፍኔ፣ ፍርሃትና መክሸፍ፣ ዛሬም እንደ ትናንት እና ሌሎችም መጽሐፍትን አሳትመዋል። የፖለቲካ ህይወት ፕሮፌሰር መስፍን በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ ማድረግ ጀመሩት ከንጉሡ ጊዜ ጀምሮ ነበር። የሕዝቡ የመብትና የኑሮ ጥያቄዎች እንዲሁም በየዘመኑ ይነሱ የነበሩ የለውጥ ፍላጎቶችን በመደገፍ በተለያየ መንገድ ተሳትፈዋል። በዩኒቨርስቲው ውስጥ ይነሱ የነበሩ የተማሪዎችን የለውጥ ጥያቄዎች ይደግፉ ስለነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን በንጉሡ ባለስልጣናት በኩል በጎ አመለካከት አልነበረም። ስለዚህም በሹመት ስም ከአዲስ አበባ እንዲወጡ ለማድረግ ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጊምቢ አስተዳዳሪ ሆነው መሾማቸው ቢነገራቸውም ሹመቱን ተቃውመውት ነበር። ከዚያም በወቅቱ በወሎ ክፍለ አገር በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ለችግር ተጋልጠው የነበሩት ሰዎች ቀያቸውን እየተዉ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት በሚሞክሩበት ወቅት ባለስልጣናት ረሃቡ እንዳይታወቅ ጥረት ማድረጋቸውን የተመለከቱት ፕሮፌሰር መስፍን ችግሩን ለሕዝቡ ለማሳወቅ የቻሉትን አድርገዋል። በዚህም ረሃቡ ያስከተለውን ጉዳትና ለችግር የተዳረጉትን ሰዎች የሚያሳይ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን በዩኒቨርስቲው ውስጥ ላለው የመምህራን ማኅበር አቀረቡ። በዚህም ሳያበቁ ከተለያዩ ሰዎች እርዳታን በማሰባሰብ በረሃብ ለተጎሳቆሉት ሰዎች ለማድረስ ጥረት ማድረጋቸው በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይመሰክራሉ። አንዳንዶች እንደሚሉትም ፕሮፌሰር መስፍን ድርቁንና የተከተለውን ረሃብ በተመለከተ ሌሎች እንዲያውቁት በማድረግ በኩል ቀዳሚ ከመሆናቸው ባሻገር፤ የንጉሡ አስተዳደርን ኋላ ላይ ለውድቀት የዳረገው የተማሪዎች ጥያቄና እንቅስቃሴ ተጨማሪ ምክንያት ለመሆን በቅቷል ይላሉ። ወታደራዊው ደርግ የንጉሡን አስተዳደር አስወግዶ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ለበርካታ ሰዎች ዕልቂት ምክንያት የሆነውን የወሎ ክፍለ አገር ረሃብን በተመለከተ የሚያጣራው መርማሪ ኮሚሽን ውስጥም አባል ሆነው ሰርተዋል። በደርግ ዘመን አብዛኘውን ጊዜያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በማስተማር ያሳለፉ ሲሆን፤ በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የነበረው የእርስ በርስ ጦርነት እየበረታ በሄደበት ጊዜ የነበረው መንግሥት ችግሮች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው በፊት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር። ከዚያም ወታደራዊው መንግሥት በአማጺያኑ ኃይሎች ተሸንፎ ከስልጣን ሲወገድና ኢህአዴግ አገሪቱን በተቆጣጠረ በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የተባለ ድርጅት በማቋቋም በአገሪቱ ስለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ክትትል ማድረግና ሪፖርቶችን ማውጣት ጀመሩ። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለረጅም ዓመታት ኢሰመጉን በሊቀመንበርነት በመሩባቸው ጊዜያት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለይ የመንግሥት ኃይሎችና ባለስልጣናት የሚፈጸሙ ሪፖርቶችን ሲያወጡ ቆይተዋል። ብዙ የተባለለትና ከባድ ቀውስን አስከትሎ የነበረው የ1997ቱ ምርጫ ሊካሄድ በተቃረበበት ጊዜም የቀስተ ዳመና ንቅናቄ ለማኅበራዊ ፍትህ (ቀስተ ዳመና) የተባለ የፖለቲካ ፓርቲ ከእነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ከሌሎችም ጋር እንዲመሰረት አድርገዋል። ይህም ፓርቲ በኋላ ላይ በምርጫው ላይ ግዙፉን ኢህአዴግን በመገዳደር በኩል ትልቅ ሚና የነበረውን ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ (ቅንጅት) የተባለውን ጥምረት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ለመመስረት ችሏል። በዚህ ሂደት ውስጥም ፕሮፌሰር መስፍን የጎላ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል። ምንም እንኳን ፕሮፌሰር በምርጫው ላይ ተወዳዳሪ ሆነው ባይቀርቡም በሚደረጉ የምርጫ ክርክሮች ላይ ቀርበው የፓርቲያቸውን ዓላማ በማብራራት ተሳታፊ ነበሩ። በኋላም ከምርጫው ውጤት ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ውዝግብና ሳቢያ መንግሥት የቅንጅት አመራሮችን ሲያስር ፕሮፈሰር መስፍንም ለእስር ተዳርገው ነበር። ይህ እስር ግን የመጀመሪያቸው አልነበረም ቀደም ሲልም በተለያዩ ጊዜያት ታስረው ነበር።
xlsum_amharic-train-284
https://www.bbc.com/amharic/news-56027522
የኢትዮጵያ ምርጫ 2013፡ የትኞቹ ፓርቲዎች ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆኑ ይችላሉ?
በግንቦት ወር መጨረሻና በሰኔ ወር መጀመሪያ ከትግራይ ክልል ውጪ በመላው ኢትዮጵያ ለማካሄድ በታቀደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
[ "በግንቦት ወር መጨረሻና በሰኔ ወር መጀመሪያ ከትግራይ ክልል ውጪ በመላው ኢትዮጵያ ለማካሄድ በታቀደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።" ]
ቢቢሲ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የኋላ ታሪክ፣ የመሪዎቻቸውን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና አሁናዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን መነሻ በማድረግ በፌዴራሉና በክልሎች እንዲሁም በከተማ መስተዳድሮች ምክር ቤቶች ድምጽ የማግኘት እድል ሊኖራቸው እንደሚችል የሚገመቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንደሚከተለው ዘርዝሯል። ፓርቲዎቹ የተዘረዘሩት በእንግሊዘኛ መጠሪያቸው ሆሄያት ቅደም ተከተል መሠረት ነው። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ አብን ረዥም የፖለቲካ የትግል ታሪክ ባይኖረውም በወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ውስጥ ተጽዕኖው ቀላል የሚባል አይደለም። በብሔር ተኮር የፓለቲካ እንቅስቃሴ የአማራ ብሔርተኝነትን በመወከል የሚንቀሳቀሰው አብን የተመሠረተው በ2010 ዓ.ም ነው። ንቅናቄው ዋነኛ ዓላማዬ "የአማራ ህዝብን ጥቅምና መብት ማስከበር ነው" የሚል ሲሆን ከምስረታው በኋላ ባሉት ሦስት ዓመታት ጎልቶ መምጣት ችሏል። ፓርቲው በአማራ ክልል በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው ይታመናል። በክልሉ በርካታ ስፍራዎችም ቢሮዎችን ከፍቶ ይንቀሳቀሳል። ከአምስት ወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ከሚቀርቡ ፓርቲዎች መካከል አብን አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል። በቅርቡ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ የነበራቸው የንቅናቄው ሊቀ መንበር አቶ በለጠ ሞላ፤ ለምርጫው ሰፊ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናውን ገልጸዋል። "በሕዝብ ለመዳኘትና ውጤቱን በጸጋ ለመቀበል" ዝግጁ ስለመሆናቸውም ተናገረዋል። አብን ከአማራ ክልል ውጪም የአማራ ተወላጆች በብዛት በሚኖሩባቸው በተለያዩ የኢትዮጰያ ክፍሎች ጽህፈት ቤቶችን እያደራጀ ሲሆን ይህም በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሊያደርገው እንደሚችል ይታመናል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ባልደራስ በቀድሞው ጉምቱ ጋዜጠኛ እና የመብት ተሟጋች በዛሬው ፖለቲከኛ አቶ እስክንድር ነገ የሚመራ ፓርቲ ነው። አቶ እስክንድር በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስና ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ተሳትፎ አለው። ባልደራስ "የአዲስ አበባን ጥቅም ለማስከበር" ያስጀመረው እንቅስቃሴ ሲሆን፤ እንቅስቃሴው አድጎ አዲስ አበባን መሠረት በማድረግ ወደ ፓለቲካ ፓርቲነት አድጓል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ መሪው አቶ እስክንድር የታሰርበት ባልደራስ፤ በከተማ አስተዳደሩ ይሰራሉ ያላቸውን 'ሕገ ወጥ' ተግባራት እንደሚታገል ሲገልጽ ቆይቷል። ባልደራስ በተለያዩ ወቅቶች የሚጠራቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎችና ሰልፎች ግልጽ ባልሆኑ ምክንያቶች ሲሰረዙ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ፓርቲው በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ በፈጠረው ተጽዕኖ እና አቶ እስክንድር በፖለቲካው ውስጥ ባለው 'የገዘፈ' ስም ምክንያት፤ ባልደራስ በመጪው ምርጫ አዲስ አበባ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። የኢትዮጰያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ ኢዜማ በምርጫ 97 ተሳትፏቸው የታወቁ እውቅ ፖለቲከኞችን ያቀፈ ነው። በመላው አገሪቱ ሊባል በሚያስችል መልኩ ከ400 በላይ የምርጫ ወረዳ ጽህፈት ቤቶችን ከፍቷል። ከብሔር ፖለቲካ በተለየ "ዜግነትን መሰረት ያደረገ" ፖለቲካን እንደሚያራምድ የሚገልጸው ፓርቲው፤ በኢትዮጵያ ማህበራዊ ፍትህን ማረጋገጥ ቀዳሚ ግቤ ነው ይላል። ፓርቲው ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለየ መልኩ፤ በአገሪቱ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና የውጪ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ 40 የፖሊሲ ሰነዶችን እንዳዘጋጀም ገልጿል። ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ሕገ ወጥ ነው ያለውን የመሬትና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ወረራ በተመለከተ ያወጣው የጥናት ሪፖርት የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በ97ቱ ምርጫ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከነበሩ ፖለቲከኞች መካከል ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የፓርቲው መሪ፤ አቶ አንዱአለም አራጌ ደግሞ የፓርቲው ምክት መሪ ናቸው። ከጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን መምጣት ቀደም ብሎ የጎላ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የነበረውን ሰማያዊ ፓርቲ ሲመሩ የነበሩት አቶ የሺዋስ አሰፋን ሊቀ መንበር ያደረገው ኢዜማ፤ 6 ፓርቲዎች ከስመው የመሰረቱት ነው። ከእነዚህ ውስጥ ነፍጥ አንግቦ ሲታገል የነበረው አርበኞች ግንቦት 7 ተጠቃሽ ነው። ይህ ድርጅት በውጪና በአገር ውስጥ ቀላል የማይባል ደጋፊዎች እንዳሉት ይገለጻል። ታዲያ የዚህ ሁሉ ድምር ኢዜማን በምርጫ 2013 ለውጤት ከሚጠበቁ ፓርቲዎች አንዱ አድርጎታል። የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግ/ ኦብነግ በፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ረዥም እድሜ ያስቆጠረ ድርጅት ነው። ከ37 ዓመታት በፊት የተመሠረተው ኦብነግ መሰረቱን በሶማሌ ክልል ያደረገ ነው። ከ1986 እሰከ 2010 ዓ. ም በትጥቅ ትግል የቆየው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፤ ከ1983-87 የነበረው የሽግግር መንግሥት አካል ነበር። በ1984 በተከናወነው የአካባቢ ምርጫ 87 በመቶ የሚሆነውን ድምጽ በማሸነፍ የሶማሌ ክልልን ለሁለት ዓመታት አስተዳድሯል። ሆኖም በኦብነግና ማዕከላዊ መንግሥቱ መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ግንባሩ ወደ ትጥቅ ትግል እንዲገባ አድርጎታል። በዚህም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 'አሸባሪ' ተብሎ ተፈርጆ ነበር። በ2010 የጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከተሎ ከሽብር መዝገብ ተሰርዞ በሕጋዊ ፓርቲነት ተመዝግቧል። የሶማሌ ክልል ሕዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ማረጋገጥ ዋነኛ ዓላማዬ ነው የሚለው ፓርቲው፤ በቀጣዩ ምርጫ በሶማሌ ክልል ብርቱ ተፎካካሪ እንደሚሆን ይጠበቃል። የፓርቲው አመራሮች በ2011 ወደ አገር ቤት በገቡበት ወቅት የተደረገላቸው 'ሞቅ' ያለ አቀባበል ግንባሩ አሁንም ያለውን ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ምርጫ ያለውንም ተስፋ የሚያመላክት ይመስላል። የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ /ኦፌኮ/ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የረዥም ዘመን ተሳትፎ ያላቸው መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) የሚመሩት ኦፌኮ፤ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ተሳታፊ ነበር። ሊቀ መንበሩ መረራ (ፕሮፌሰር) በፌዴራሉ የፓርላማ አባል ሆነው በቆዩባቸው ዓመታት በፓርላማ ውስጥ በሚሰጧቸው አስተያየቶች በበርካቶች ዘንድ ይታወሳሉ። በተደጋጋሚ የታሰሩ ሲሆን ለመጫረሻ ጊዜ ከእስር ሲፈቱ በርካታ ደጋፊዎቻቸው አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን ገልጸዋል። በተመሳሳይ አሁን እስር ቤት የሚገኙት ምክትል ሊቀ መንበሩ አቶ በቀለ ገርባ የዳበረ የፖለቲካ ልምድ ያላቸው ናቸው። በኦሮሚያ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አቶ ጀዋር መሐመድ ፓርቲውን መቀላቀሉ የኦፌኮን ተጽዕኖ ከፍ እንዳደረገው ይታመናል። መረራ (ፕሮፌሰር)፣ አቶ በቀለ እና አቶ ጀዋር ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት በኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች በተጓዙበት ወቅት የተደረገላቸው አቀባል ኦፌኮ በምርጫ 2013 ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንደሚቀርብ ያመላከተ ነበር። በኢትዮጵያ የምርጫ ስርዓት ልምድ ያካበቱ ጉምቱ ፖለቲከኞችን መያዙ [ምንም እንኳን በእስር ላይ የሚገኙ ቢኖሩም] ኦፌኮን በቀጣዩ ምርጫ ለውጤት የሚጠበቅ ፓርቲ አድርጎታል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/ ከተመሠረቱ ብዙ ዓመታት ካስቆጠሩት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አንዱ ኦነግ ነው። በበርካታ የኦሮሚያ አከባቢዎች የነጻነት አርማ ተደርጎ የሚቆጠረው ኦነግ በ1965 ዓ. ም ነበር የተመሠረተው። ግንባሩ የ1983ቱ የሽግግር መንግሥት አካል የነበረ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ ግን አማጺ ቡድን ሆኖ ጫካ ገባ። እናም ለዓመታት በትጥቅ ትግል ቆይቶ ከ3 ዓመታት በፊት የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ ወደ አገር ቤት ተመልሷል። ከበርካታ ዓመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ለመወዳደር የተዘጋጀው ፓርቲው፤ በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ ነው። ፓርቲው በውስጣዊ ችግሮቹ እና በፓርቲ አመራሮች እስር ታጅቦ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ያለውን የገዘፈ ስምና የትጥቅ ትግል ታሪክ ይዞ ምርጫው እየተጠባበቀ ነው። ፓርቲው በመንግሥት ይደርስብኛል በሚለው ጫናና በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ቅራኔ በምርጫ ተሳትፎው ላይ ተጽዕኖ ካላደረገበት በስተቀር በኦሮሚያ ክልል ብርቱ ተፎካካሪ መሆኑ የሚቀር አይመስልም። ብልጽግና ፓርቲ ብልጽግና፤ ያለፉትን 5 አገራዊ ምርጫዎች 'አሸንፊያለሁ' ያለውና አገሪቱን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሲያስተዳድር የቆየው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ውጤት ነው። ብልጽግና ከኢሕአዴግ መክሰም በኋላ አንዳንድ ለውጦችን እንዳደረገ ቢነገርም፤ ህወሓት ብቻ የተቀነሰበት የቀድሞው ኢሕአዴግ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከህወሓት ውጪ ግንባሩን ከ 'አጋሮቹ' ጋር በመዋሃድ ብልጽግና የተሰኘ አዲስ ፓርቲ ፈጥረዋል። የቀድሞውን ኢሕአዴግ ሀብት እና ንብረቶች ጠቅልሏል። አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብን ሽሮ መደመር በተሰኘ የፓርቲው ፕሬዝዳንትና በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እሳቤ ተክቷል። ፓርቲው በመላው ሀገሪቱ አለኝ ከሚለው በሚሊዮን የሚቆጠር አባላት እንዲሆም ረጅም አመታት ያሰቆጠር ጠንካራ መዋቅር በቀጣዩ ምርጫ ተጠባቂ እንዲሆን አርጎታል። የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ (ዶ/ር) አምጥተውታል የሚባለው ለውጥና በአገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ያላቸው ድጋፍ እንዲሁም ፓርቲው በክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ተጽዕኖ ፈጣሪ አመራሮችን መያዙ በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንዲገመት አድርጎታል። ከላይ የተጠቀሱት አንዳንድ ፓርቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች በቀጣዩ ምርጫ ላይሳተፉ እንደሚችሉ እየገለጹ ቢሆንም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ይኖራቸዋል ተብሎ የሚጠበቀው ፍክክር ምርጫ 2013 ከባለፉት በተሻለ ዓይን የሚጣልበት እንዲሆን አድርጎታል።
xlsum_amharic-train-285
https://www.bbc.com/amharic/news-52789443
በኮሮናቫይረስ ምክንያት በማያቋርጥ የጫጉላ ሽርሽር ላይ ያሉት ሙሽሮች
ትውውቃቸው ከስምንት ዓመታት በፊት ነበር፤ የ36 ዓመቱ ካሊድና የ35 አመቷ ፔሪ።
[ "ትውውቃቸው ከስምንት ዓመታት በፊት ነበር፤ የ36 ዓመቱ ካሊድና የ35 አመቷ ፔሪ።" ]
ካሊድና ፔሪ የጫጉላ ጊዜያቸውን ለማሳለፍ ወደ ሜክሲኮ ያቀኑት መጋቢት ላይ ነበር ለስምንት ዓመታት በጓደኝነት ከቆዩ በኋላ ቤተሰብ ዘመድ ወዳጅ በተሰበሰበት፣ በግብጿ መዲና ካይሮ ድል ባለ ድግስ ተጋቡ። ሠርጋቸው የካቲት 27/2012 ዓ.ም የነበረ ሲሆን ከጥቂት ቀናት በኋላም ለጫጉላ ሽርሽራቸው ወደ ሜክሲኮዋ ከተማ አቀኑ። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ገና እየጀመረ የነበረበት ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መቀመጫቸውን ዱባይ ያደረጉት ሙሽሮች ልክ እንደ በርካቶች ስጋትም አልገባቸውም። ምንም እንኳን ሙሽሮቹ የተጨናነቁ ስፍራዎችን ቢያስወግዱም ቫይረሱ በሌሎች አገራት ላይ ባለመዛመቱ ጉዞዎች ሊሰረዙ ይችላሉ የሚለው ሃሳብ በጭራሽ ያላለሙት ጉዳይ ነው። የጫጉላ ጊዜያቸውን አጠናቀው ወደ ቤታቸው ለመመለስም መጋቢት አስር ቀን በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ አየር መንገድ ቲኬታቸውን ቆረጡ። የገዙትም ቲኬት መሸጋገሪያቸው በቱርክ፣ ኢስታንቡል ነበር። "አውሮፕላን ውስጥ ሆነን ኢንተርኔት ማግኘት ችለን ነበር። ከቤተሰቦቻችንም መልዕከት ማግኘት ቻልን። ዱባይ እንዴት ልትደርሱ ነው? የውጭ አገር ዜጎች ወደ ዱባይ እንዳይገቡ መመሪያ ወጥቷል" የሚሉ ዜናዎችን ፔሪ ማንበቧን ታስታውሳለች። ሆኖም በአውሮፕላን ውስጥ እያሉ ወደ ዱባይ መግባት እንደሚችሉ አስበው ነበር። ነገር ግን ኢስታንቡል ላይ ወደ ዱባይ ለመሳፈር ሲሞክሩ፤ መሳፈር እንደማይችሉ ተነገራቸው። ልክ ከሜክሲኮ እንደተነሱ ነው ዱባይ መመሪያውን መተግበር የጀመረችው። በቱርክ ያለው የጉዞ ክልከላ ሁሉንም ዕቅድ አጨናገፈባቸው። በአየር ማረፊያውም ለሁለት ቀናት ያህል ለማደር ተገደዱ። ቱርክ ያረፉት ለመሸጋገሪያ በመሆኑም ህጋዊ የሆነ የይለፍ ወረቀት (ቦርዲንግ ባስ) አልነበራቸውም። የመፀዳጃ ቤት ወረቀቶች፣ ልብሶችን መሸመት እንዲሁም ሻንጣቸውንም ማግኘት አልቻሉም። ከዱባይ በተጨማሪ አማራጭ ብለው ያሰቧትም ግብጽም ማንኛውንም ጉዞ ማገዷን ተከትሎ፤ ሌላ እቅድ ማሰብ ነበረባቸው። ስለዚህም ግብጻውያንን ያለ ቪዛ የሚያስገቡ አገራትን በጉግል በኩል መፈለግ፤ ይሄ ብቻ አይደለም በረራስ አላቸው ወይ የሚለውንም ማጣራት እንደነበረባቸው ፔሪ ታስረዳለች። አማራጩም አንድ ብቻ ነበር! የማልዴቪስ ደሴት። በህንድ ውቅያኖስ ተከበበው፣ በነጭ አሸዋና፣ አይንን በሚስብ የመሬት አቀማመጣቸው የማልዴቪስ ደሴቶች በዓለም ላይ ከሚያስደንቁና ልብን ከሚሰርቁ ውብ የተፈጥሮ ቦታዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ካሊድና ፔሪ የጫጉላ ጊዜያቸውን ለማሳለፍ ሜክሲኮን ከመምረጣቸው በፊት የማልዴቪስ ደሴቶችምም አስበዋቸው ነበር። በዚህ ወቅት ግን የተፈጥሮ ውበትን የታደለው የውቅያኖስ ዳርቻ ወይም ደሴቶቹ ላይ መዝናናት መቻላቸው አይደለም የፈለጉት ትንሽ ምቾትን ብቻ ነው። ለሁለት ቀናትም ያህል በአየር ማረፊያ ወንበሮች ላይ ሲያድሩ ስለነበርም ትንሽ እፎይታን ፈጠረላቸው። "ማልዴቪስ እንደደረስን ደስታችንን መቆጣጠር አልቻልንም። በደስታም ተያየን ቢያንስ ከአየር ማረፊያ ወንበሮች ላይ መተኛትን ተገላግለን በአልጋ ላይ መተኛት መቻላችን ትልቅ ነገር ነው" በማለት የቴሌኮም ኢንጅነር የሆነው ካሊድ ይናገራል። ከዚህም በተጨማሪ ሻንጣቸውን ማግኘታቸው ጭንቀታቸውን ቀለል አደረገላቸው። ሆኖም ችግሮቻቸው በሙሉ አልተቀረፉም። "ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ጫና ሊደርስብን እንደሚችልም ማሰቡ በራሱ የራስ ምታት ነው የሆነብን፤ እዚህ ሆነን ሥራችንን መስራት አንችልም። ላፕቶፕም አላመጣንም" ትላለች ሚዲያ ውስጥ የምትሰራው ፔሪ "በጫጉላ ሽርሽር ላይስ ማን እሰራለሁ ብሎ አስቦ ላፕቶፕ ይይዛል?" በማለት ትጠይቃለች ባልና ሚስቱ ደሴቶቹ ላይ የሚያርፉበት ሪዞርትም ሲደርሱ የተወሰኑ እንግዶች ብቻ የነበሩ ሲሆን፤ እነሱም ወደ የአገራቸው ሊመለሱ ጥቂት ቀናት ብቻ የቀራቸው ነበሩ። በርካታዎቹ እንግዶች በጥቂት ቀናት ውስጥ ሆቴሉን ለቀው ወደየአገራቸው ሲመለሱ፤ ሪዞርቱ ሊዘጋ እንደሆነ ለባልና ሚስቱ ተነገራቸው። እንደገና ወደ ሌላ ደሴት፣ ሌላ ሆቴል ቢይዙም በተመሳሳይ ይሄኛውም ሆቴል ተዘጋ። ችግራቸውንም የተረዳው የማልዴቪስ መንግሥት ተባብሯቸው ኦልሁቬሊ በምትባል ደሴት ላይ በምትገኝ ሪዞርት ውስጥ ነው ያሉት። ባለስልጣናቱ ሪዞርቱ እንዲከፈት ከማድረግ በተጨማሪ የሚያርፉበትንም ዋጋ ስለቀነሰላቸው ሙሽሮቹ ባለስልጣናቱ እያደረጉላቸው ያለውን ትብብር ከልብም አመስግነዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሆቴሉ ሠራተኞችም እየተንከባከቧቸው መሆኑንም አስረድተዋል። "በተቻለ መጠን ሁሉም የሆቴሉ ሠራተኞች የተሻለ ጊዜ እንዲኖረን ይጥራሉ። ማታ ማታም ሙዚቃ ያጫውቱልናል፤ ሁልጊዜም ዲጄ አለ። አንዳንድ ጊዜም ሙዚቃ እየተጫወተ ማንም የሚደንስ ስለሌለ ትንሽ እንሳቀቃለን" በማለት ካሊድ ይናገራል። በሪዞርቱ ሰባ ያህል የጫጉላ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ እንግዶች ቢኖሩም ልዩነቱ ፔሪ እንደምትለው " እነሱ የማልዴቪስ ደሴትን ለጫጉላ ሽርሽራቸው መርጠውት ነው። እኛ ግን አልመረጥነውም" ብላለች። በአጠቃላይ በማልዴቪስ 300 ቱሪስቶች የሚገኙ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ደሴቷ አዳዲስ እንግዶች እንዳይገቡ ከልክላለች። ምንም እንኳን የማልዴቪስ ደሴት ውብ ቦታ ቢሆንም፤ ተገደው ቢመጡበትም ከዚህ በባሰ ሁኔታ ሰዎች አማራጭ አጥተው የከፋ ቦታም ማሳለፍ እንዳለ ይረዱታል። ሆኖም ማር ሲበዛም ይመራል እንደሚባለው በአሁኑ ወቅት ዋነኛው ምኞታቸው የጫጉላ ሽርሽራቸው ተጠናቆ ወደ ዱባይ መመለስ ነው። በማልዴቪስ የውቅያኖስ ዳርቻው የተዝናኑት ለጥቂት ቀናት ብቻ ነው። ምክንያቱም ወቅቱ የሞንሱን አውሎ ንፋስ የሚነፍስበት በመሆኑ ኃይለኛ ዝናብ ይዘንባል። ከዚህም በተጨማሪ የረመዳን ፆምንም ለአንድ ወር ያህል እየፆሙ ነበር። በተቻለ መጠን ወደ ሥራም ለመመለስ ቢሞክሩም የኢንተርኔቱ ደካማ መሆን ስብሰባዎችን እንዳይታደሙ አግዷቸዋል ። ወደ መኖሪያ ቤታቸው መመለስም ቀላል አይደለም። ዱባይ መኖሪያቸውም ብትሆንም የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ዜጎች አይደሉም። ወደ ሌሎች የባሕረ ሰላጤው አገራትም መመለስ አልቻሉም። ምናልባት ማድረግ ይችሉ የነበረው ግብጽ ዜጎቿን ተመለሱ በምትልበት ወቅት ተመልሰው አስራ አራት ቀናትን በመንግሥት ለይቶ ማቆያ አሳልፈው አገራቸው መቀመጥ ነው። ነገር ግን ቤታቸው ዱባይ በመሆኑ ግብጽስ ረዥም ጊዜ የሚያስቆያቸው ጉዳይ የለም። የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ባለስልጣናት ጋር በመደወልና እንደእነሱና መሰል አጣብቂኝ ውስጥ የገቡ ነዋሪዎችን ችግር እንዲፈቱም እየተማፀኑ ነው። በረራዎች የማይገኙም ከሆነ በመንግሥታዊ መመላለሻዎችም እንዲጓዙ ፈቃድ የጠየቁ ሲሆን ምላሽም በመጠበቅ ላይ ናቸው። "አየር መንገዱ ሥራ የሚጀምርበትን ቀን ማራዘሙን ዜና ስንሰማ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንገባለን። የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን፣ ሆቴልም ይሁን ቤታችን ለይቶ ማቆያ ውስጥ ግቡ ካሉን እንገባለን" በማለት ፔሪ ተናግራለች። ለሁለት ወራት ያህል በሆቴል ውስጥ ያሉት ሙሽሮች ወጪያቸው እየናረ እንደሆነ ቢገባቸውም "ቤታችን እስከምንመለስ ድረስ ወጪያችንን ላንደምር ተስማምተናል። መቼ እንደምንመለስም አናውቅም" ብላለች። ምንም እንኳን ከእነሱ በከፋ ሁኔታ አጣብቂኝ ውስጥ የገቡ ሰዎች እንዳሉ ቢረዱም፤ ነገር ግን ጠብቀውት የነበረው አጠር ያለው የጫጉላ ጊዜ መራዘሙ እንዳሰላቻቸው አልደበቁም። "በሪዞርቱ ውስጥ ያሉ እንግዶች በሙሉ ሄደው እኛ ሁልጊዜም የመጨረሻ ነን። ሠራተኞቹም ቻው በማለት እጃቸውን እንዳውለበለቡልን ነው። እነሱም ያሳዝናሉ። ሁለት ጊዜ እንዲህ አይነት አጋጣሚ አጋጥሞናል" የሚለው ካሊድ "እንደዚህ አይነት ቦታዎች በበርካታ ሰዎች እና በደስታ ሊሞላ ይገባ ነበር ሁኔታው ግን እንደዛ አይደለም" ብሏል። አክሎም "ማልዴቪስ ደሴቶች ላይ መውጪያ እንዳጣን ለምናውቃቸው ሰዎች ስንናገር ብዙዎች ከት ብለው ይስቃሉ። 'ምናለበት እንደናንተ በሆንኩ ደስ የሚል ቦታ ነው' የሚሉም ብዙዎች ናቸው" የምትለው ፔሪ " እንደሚታሰበው ቀላልም አይደለም። ደስተኞችም አይደለንም። በጣም የሚያስጨንቅ ሁኔታ ላይ ነን፤ ከቤተሰባችን ጋር መሆን ያስደስተናል። በአሁኑ ሰዓት እሱን ለማግኘት የማልከፍለው ነገር የለም" ብላለች ፔሪ።
xlsum_amharic-train-286
https://www.bbc.com/amharic/news-51388871
ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠሩት ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተገለጸ
ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠሩት አራት ግለሰቦች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን የጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታወቀ።
[ "ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠሩት አራት ግለሰቦች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን የጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታወቀ።" ]
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሁለት ቀናት በፊት በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም የተባሉ ሌሎች አዲስ አራት ሰዎች መገኘታቸውን አስታውቆ ነበር። ከቀናት በፊት በቫይረሱ የተጠረጠሩት ሶስቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዱ ደግሞ ቻይናዊ ነበር። የጤና ጥበቃ ሚንስትር ከበፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳስታወቀው የአራቱ ግለሰቦች የደም ናሙና ወደ ደቡብ አፍሪካ ለምረመራ ተልኮ ውጤቱ ከኮሮናቫይረስ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል ብሏል። ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ መልኩ በቫይረሱ ሳይያዙ አይቀሩም የተባሉ አራት ሰዎች ተገኝተው የደም ናሙናቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኮ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው መነገሩ ይታወሳል።
xlsum_amharic-train-287
https://www.bbc.com/amharic/51626233
ከ68 ሺህ በላይ ጥንዶች በጳውሎስ ሆስፒታል የመካንነት ሕክምና እየተከታተሉ ነው
በትዳር ውስጥ ከመካንነት ጋር በተያያዘ በርካታ አሳዛኝ ታሪኮች በየአካባቢያችን ይሰማሉ። ረጅሙን ታሪኳን በአጭሩ ያቀረብንላት ሴት ልጅ ፍለጋ ያስከፈላትን ዋጋ እንደሚከተለው አጫውታናለች . . .
[ "በትዳር ውስጥ ከመካንነት ጋር በተያያዘ በርካታ አሳዛኝ ታሪኮች በየአካባቢያችን ይሰማሉ። ረጅሙን ታሪኳን በአጭሩ ያቀረብንላት ሴት ልጅ ፍለጋ ያስከፈላትን ዋጋ እንደሚከተለው አጫውታናለች . . ." ]
በቴክኖሎጂ በታገዘ ሕክምና የተወለደ ሕፃን "ሌላ እንዲያገባ ፈቀድኩለት. . . " "ከምወደው አብሮ አደጌ ጋር ድል ባለ ሠርግ ወዳጅ ዘመድ መርቆን ትዳር መሠረትን። ደስተኞች ነበርን። ዓለማችን ጎጇችን ሆነ። በርካታ ዓመታትን አብረን አሳለፍን። ፍቅራችን በዙሪያችን ያሉትን ሁሉ የሚያስቀና ነበር። ኑሯችንም የተሳካና የተደላደለ። ይሁን እንጂ ዓይናችንን በዓይናችን ማየት አልቻልንም። በመጀመሪያ አካባቢ የመደናገጥና ግራ የመጋባት ስሜት ውስጥ ገባን። በኋላ ላይ የተለያዩ ሕክምናዎችን ሞከርን። በእምነታችንም የዘወትር ፀሎታችን "በልጅ ባርከን" ሆነ። ሆኖም ሊሆን አልቻለም። ፈልገነው የሆነ ይመስል ከቤተሰብና በዙሪያችን ካሉ ሰዎች "ውለዱ እንጅ" የሚለው ምክር የሰላምታ ያህል ተደጋገመ። መሸማቀቅ ጀመርን። ጫናው እንደሚወራው ቀላል አልነበረም። በዚህ ሁኔታ ዓመታትን ገፋን። በጤና ምርመራው ችግሩ ያለው ከእኔ እንደሆነ ስረዳ ደግሞ እጄ በሌለበት ነገር የባሰ ጥፋተኝነት ይሰማኝ ያዘ። እሱ ግን እኔን ከማበረታታት ባለፈ ምንም ትንፍሽ አይልም "ፈጣሪ የፈቀደው ነው የሚሆነው" ነበር የሚለኝ። እኔ ግን "እኔን ብለህ ያለ ልጅ መቅረት የለብህም፤ ሌላ አግባና ውለድ" ስል ሃሳብ አቀረብኩለት፤ ከልቤ ነበር። እሱ ግን "የልጅነት ፍቅረኛዬን ለልጅ ብዬ ጥዬ ለመሄድ ህሊናዬ አይፈቅድልኝም" በማለት በሃሳቤ አልተስማማም። በመካከላችን ውዝግብ ተነሳ። የኋላ ኋላ አግብቶ ልጅ እንዲወልድና ልጁን ይዞ ወደ እኔ እንዲመጣ አግባብቼው ተስማማ። እርሱም ሌላ አገባ። እኔም ብቻዬን እርሱን መጠባበቅ ጀመርኩ። ሁለት ዓመት ሳይሞላ የሴት ልጅ አባት ሆነ። ደስ አለኝ። እርሱ ልቡ እኔ ጋ ነበርና ልጅቷ ልክ ከአራስ ቤት ስትወጣ "ካንች ጋር ይበቃናል፤ ልጄን ስጭኝና ልሂድ" የሚል ጥያቄ ያቀርብላታል ለእናትየው። እርሷም እናት ናትና "ከፈለክ አንተ ትሄዳለህ እንጂ፤ ልጄን እንዴትም ብዬ አሳድጋለሁ" የሚል መልስ እንደሰጠችው ነገረኝ። ይህንን እንዴት እንዳላሰብነው ይገርመኛል። ራስ ወዳዶች ሆነን ነበር። አንዱን በድሎ አንዱን ማስደሰት አይቻልምና ያሰብነው ሳይሆን ቀረ። እርሱም ልጅ ነበርና ያሰደደው፤ እኔን ትቶ ከልጁ እናት ጋር ትዳሩን አፀና። አልፈርድበትም። እኔም ቤት ንብረታችንን ይዤ ብቻዬን ቀረሁ። የምወደውን ባሌን በልጅ ምክንያት አጣሁ . . . " ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ ታዲያ ይህንን የሥነ ተዋልዶ ጤና ችግር ለመፍታት በሚያዚያ ወር 2011 ዓ. ም የመካንነት ሕክምና ማዕከል አስመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። አገልግሎት መስጠት በጀመረ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ60 ሺህ በላይ ጥንዶች የመካንነት ሕክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን በሆስፒታሉ የሥነ ተዋልዶ ማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቶማስ መኩሪያ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከእነዚህ መካከል 1400ዎቹ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመካንነት ሕክምና ለማግኘት ተመዝግበዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ ወደዚህ ሕክምና ከመግባታቸው በፊት ሌሎች ሕክምናዎችን በመከታተል ሂደት ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ጥንዶች በተለያየ ኑሮና የትምህርት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ከተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የመጡ ናቸው። በቴክኖሎጂ በታገዘው በዚህ የመካንነት ሕክምና ከ70 በላይ እናቶች ነፍሰጡር ሆነው በተለያየ የእርግዝና ወራት ላይ ይገኛሉ። 6 ወላጆች ወልደው ስመዋል። 8 ልጆች ተወልደዋል። አንዲት እናት ሦስት የወለደች ሲሆን አንዱ ሞቶባታል፤ መንታዎቹ ግን በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ሰምተናል። ጥንዶቹ ከ18 እስከ 4 ዓመታት በትዳር ውስጥ ቢቆዩም፤ ልጅ ሳያፈሩ ቆይተው አሁን ልጅ ያገኙ ናቸው። "በዚህ መንገድ እናቶች ልጃቸውን ሲያቅፉ በደስታ ያለቅሳሉ። በጋብቻ መሃል ልጅ አላዩም ነበር። ልጅ ይናፍቁ ነበር። ልጅ ለማግኘት በዕምነት ቦታዎችና የባህል መድሃኒት ፍለጋ ሲንከራተቱ፤ ከማኅበረሰቡ የሚደርስባቸው ጫና ቀላል አይደለም። ይህን ሁሉ አልፈው ልጅ ሲያቅፉ የተሰማቸው ሊቆጣጠሩት የማይችሉት የደስታ ስሜት ነው። በደስታ ሲፈነጥዙ ነው ያየነው" ይላሉ የሆስፒታሉ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ንዋይ ፀጋዬ። ሕክምናው የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ባስተማራቸው የአገር ውስጥ የሕክምና ባለሙያዎች ይሰጣል። ይህ የሕክምና አገልግሎት መሰጠት ከመጀመሩ በፊት የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጉንም ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል። ሕክምናውን ከሚሰጡ የባለሙያዎች ቡድን የተወሰኑ አባላት መካንነት ምንድን ነው? ጥንዶች ለአንድ ዓመት የወሊድ መከላከያ ሳይጠቀሙ ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እየፈፀሙ ፅንስ መፈጠር ካልቻለ መካንነት እንደሚባል ዶ/ር ቶማስ ይናገራሉ። የሴቷ ዕድሜ ደግሞ ከ35 ዓመት በላይ ከሆነ እና በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ያለ ወሊድ መከላከያ በሳምንት ሁለት ጊዜ እና ከዚያ በላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽመው እርግዝና መፈጠር ካልቻለ የመካንነት ችግር ሊኖር ይችላል ተብሎም ይታሰባል። ሳይለያዩ ለአንድ ዓመት የቆዩ ጥንዶች ያለምንም መከላከያ ግንኙነት እያደረጉ ማርገዝ ካልቻሉም እንዲሁ። መካንነት በሴቶችና በወንዶች ላይ ሊከሰት ይችላል። በሴቶች ላይ ከዕድሜ ጋር ተያይዞም ሆነ ያለዕድሜ የዘር እንቁላል ማለቅ፣ የቱቦ መዘጋት እና በአባላዘር በሽታዎች በተደጋጋሚ መጠቃት እንዲሁም በሌሎች ችግሮች ሊከሰት ይችላል። የችግሮቹን መንስዔ በምርመራ በዝርዝር መረዳት እንደሚቻል ዶ/ር ቶማስ ያስረዳሉ- የችግሩ መንስዔ እንደ ግለሰቦቹ ስለሚለያይ። አንዳንዴ ሁሉም ነገር ጤናማ ሆኖ እርግዝና ላይፈጠር ይችላል፤ ይህ የማይገለፅ መካንነት [Unexplained Infertility] ይባላል። ይህ ማለት ቴክኖሎጂ ያልደረሰባቸው ችግሮች አሉ ማለት ነው። 20 በመቶ የሚሆኑ ጥንዶችም ይህ ችግር ያጋጥማቸዋል። እነዚህ ጥንዶች በቴክኖሎጂ የታገዘ ሕክምና ሊደረግላቸውም ይችላል። መካንነት በተለይ አፍሪካ ውስጥ የተለመደ ችግር ነው የሚሉት ዶ/ር ቶማስ፤ በተለይ በአባላዘር በሽታዎችና በሌሎች ኢንፌክሽኖች የመካንነት ችግር እንደተንሰራፋ ይናገራሉ። ዶ/ር ቶማስ የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርትን ጠቅሰው እንደነገሩን፤ በኢትዮጵያ ከ15-20 በመቶ ጥንዶች የዚህ ችግር ተጠቂ ናቸው። ሴቷም ሆነ ወንዱ በእኩል ደረጃ በመካንነት ሊጠቁ ይችላሉ፤ በመሆኑም በማኅበረሰቡ ሴቷ ላይ ብቻ ጣት የሚቀሰረው በተሳሳተ አመለካከት መሆኑንም ሳይጠቅሱ አላለፉም። በአውሮፓዊያኑ 2016 የወጣው የኢትዮጵያ ሥነ ሕዝብና ጤና ዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው በተለያዩ ምክንያቶች በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የውልደት መጠን እየቀነሰ መሆኑን ያመለክታል። በገጠር የሚኖሩ ሴቶች በ2000 ከነበረው 6.0 የውልደት መጠን በ2016 ወደ 5.2 ወርዷል። በከተሞች ደግሞ በ2000 ከነበረው 3.0 በ2016 ወደ 2.3 ዝቅ ብሏል። በአጠቃላይ አንዲት ሴት መውለድ ካለባት አማካይ የውልደት መጠን በ2000 ከነበረው 5.5 በ2016 ወደ 4.6 መቀነሱን የዳሰሳ ጥናቱ ያመለክታል። በቴክኖሎጂ የታገዘ የመካንነት ሕክምና [IVF] ምንድን ነው? ዶ/ር ቶማስ እንደገለፁልን ይህ የሕክምና ዘዴ ከሴቷ እንቁላል ከወንዱ ደግሞ የዘረ ፈሳሽ በመውሰድ በቤተ ሙከራ እንዲገናኙ ተደርጎ ፅንስ ከተፈጠረ በኋላ ያ ፅንስ ተመልሶ ማህፀን ውስጥ ሲገባ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመካንነት ሕክምና [IVF] ይባላል። ይህ ሕክምና እንደየ ሰዉ ቢለያይም ከ40-50 በመቶ ሊሳካ የሚችል ሂደት ነው። እስካሁን ይህን አገልግሎት ለማግኘት ወደ ሆስፒታሉ ከሄዱት ውስጥ 200 ለሚሆኑ ጥንዶች አገልግሎቱ ተሰጥቷል። ከእነዚህ መካከል 95ቱ ነፍሰጡር ሆነዋል። መጀመሪያ አገልግሎቱን ካገኙት 8 ሴቶች 5ቱ ነፍሰ ጡር የነበሩ ሲሆን 3ቱ ወልደዋል። ሁለቱ ግን በመካከል ውርጃ አጋጥሟቸዋል። ይህም የሕክምናው ውጤታማነት ከ50 በመቶ በላይ መሆኑን ያሳያል። ከተፈጥሯዊው መንገድ በምን ይለያል? የእርግዝናው ወራቶች ግን ተመሳሳይ ሲሆን እንደ ሁኔታው አሊያም እንደ እናትየውና ፅንሱ የጤና ሁኔታ በቀዶ ሕክምናም ሆነ በምጥ ሊወልዱም ይችላሉ። ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ይህንን በቴክኖሎጂ የታገዘ ሕክምና ሲሰጥ በአገር ውስጥ የመጀመሪያው የመንግሥት ተቋም ሲሆን አሊክማ የተሰኘ አንድ የግል ተቋም አገልግሎቱን ሲሰጥ መቆቱን ዶ/ር ቶማስ ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ምንም እንኳን ማኅበረሰቡ ከእምነትና ከባህል ጋር ጥብቅ ቁርኝት ቢኖረውም፤ ሰዎች አሁን አሁን ለመረጃ ቅርብ በመሆናቸው በቴክኖሎጂው ለመደገፍ ፈቃደኛ ናቸው። ይሁን እንጂ በሌሎች አገራት እየተሠራበት ያለው እና ከጥንዶቹ ውጭ ከሌላ ሴት እንቁላል አሊያም ከሌላ ወንድ የዘረ ፈሳሽ ወስዶ፤ ልጅ ከተፈጠረ በኋላ እንደገና ወደ ማህፀን የመመለሱ ሕክምና የእንቁላል ወይም የዘር ፈሳሽ ልገሳ [Egg or Sperm donation] የተለመደ አይደለም። አንዳንዴም ደግሞ የእናት ማህፀን ጽንስ መያዝ አልችል ሲል የማህፀን ኪራይ ይኖራል። እነዚህ ሕክምናዎች የሕግ ማዕቀፍ ስለሚያስፈልጋቸውና ግንዛቤ መፍጠር ስለሚያስፈልግ አሁን ላይ እየተሠራበት አለመሆኑን ዶ/ር ቶማስ ገልፀውልናል። ውጭ አገር በመሄድ በከፍተኛ ወጪ ሕክምናውን የሚያደርጉ እንዳሉ የሚገልፁት ዶ/ር ቶማስ፤ ለወደፊቱ ሕክምናውን ለመስጠት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ነግረውናል። እንዲህ ዓይነቱን የሕክምና አገልግሎት ለመጀመር ግን ማኅበረሰቡ ላይ ግንዛቤ መፍጠር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑንም አስምረውበታል። "በማኅበረሰቡ ልጅ መውለድ፣ ቤተሰብ መመሥረት አንደ ሕይወት ግብ ተደርጎ የሚወሰድ በመሆኑ፤ መካንነት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ያስከትላል" የሚሉት ዶ/ር ቶማስ፤ "በዚህ ቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩም ሆነ በሌላ መልኩ መፍትሔ ሲያገኙ ጥንዶች ደስተኛ ይሆናሉ" ይላሉ። ይህ የሕክምና አገልግሎት መጀመሩም መልካም ጅምር መሆኑን ይጠቅሳሉ። ቢሆንም ባለው የባለሞያና ተቋማዊ አቅም ውስንነት መድረስ የሚቻሉትን ጥንዶች ያህል መድረስ አለመቻሉንም ሳያነሱ አላለፉም። በአንድ ዓመት ከ1500 በላይ ለሆኑ ጥንዶች አገልግሎቱን መስጠት የሚያስችል አቅም አለመኖሩንም ያክላሉ። ዶ/ር ቶማስ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ68 ሺህ በላይ ጥንዶች ወደ አንድ ሆስፒታል ብቻ መምጣቱ የሚያስደነግጥ ቁጥር መሆኑን በመግለጽ፤ ቀጠሮዬ ረዘመ የሚሉ ቅሬታዎችን የሚያቀርቡ ሰዎች በርካቶች መሆናቸውን ሳይገልፁ አላለፉም።
xlsum_amharic-train-288
https://www.bbc.com/amharic/48754495
"በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን
ቢቢሲ፦ በሃገሪቱ ከፍተኛ ስልጣን ላይ ያሉና፤ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠበቁ እንደ ጄነራል ሰዓረ መኮንን እንዲሁም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና የሌሎቹም ግድያ ስለ ኃገሪቱ የፀጥታና ደህንነት ጉዳይ የሚናገረው አለ። እርስዎ ይህንን እንዴት ነው የሚረዱት ?
[ "ቢቢሲ፦ በሃገሪቱ ከፍተኛ ስልጣን ላይ ያሉና፤ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠበቁ እንደ ጄነራል ሰዓረ መኮንን እንዲሁም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና የሌሎቹም ግድያ ስለ ኃገሪቱ የፀጥታና ደህንነት ጉዳይ የሚናገረው አለ። እርስዎ ይህንን እንዴት ነው የሚረዱት ?" ]
ጄነራል ፃድቃን ጄኔራል ፃድቃን፦ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን፣ ጄኔራል ገዛኢ አበራና ዶ/ር አምባቸው መኮንን ሌሎቹም በስራ ቦታቸው ላይ እያሉ መገደል በጣም ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ችግር እንዳለ ያሳያል። ኢንተለጀንስ አሰባሰብ ላይ ከፍተኛ ችግር እንዳለ ነው የሚያሳየው፤ ከዚህ ቀደም እኔ የማውቀው እንኳን ይሄን ያህል ሴራ እየተሸረበ አይደለም በግለሰብ ደረጃ የሚደረጉ ትንንሽ ነገሮች ፈጥኖ ይታወቅ ነበር። ቀላል ያልሆነ የፀጥታ ችግር መኖሩን፣ በፀጥታ መዋቅሩ ውስጥ መታየት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ ነው የሚያሳየው። ጄኔራል ሰዓረን የገደለው የራሱ የጥበቃ ኃይል ነው። መከላከያ ውስጥ የመከላከያን ተቋም የሚጠብቅ ፀረ-መረጃ የሚሉት ኃይል አለ። ለእንደነዚህ አይነት ትልልቅ ባለስልጣናት የሚመደብ ሰው የሚመደበው በዚህ አካል ከተጣራ በኋላ ነው። ይህ አለመሆኑ ቀላል ያልሆነ የፀጥታ ችግር እንዳለ ያሳያል። የፀጥታ ችግሩ ከፖለቲካዊ ሁኔታም ጋር ይያያዛል። ቢቢሲ፦ክልላዊ "መፈንቅለ መንግሥት" አይደለም ፤ በከፍተኛ አመራሮች ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው የሚለው አከራካሪ ሆኖ እንዳለ፤ በአንድ ክልል ፤ በአንድ ፓርቲ ውስጥ በአመራሮች መካከል የልዩነት መካረር ነው ነገሮችን ወደዚህ ያመራው የሚለው ሃሳብ ጎልቶ እየወጣ ነው። የፖለቲካ ልዩነቶች መጨረሻቸው እንዲህ የሚሆን ከሆነ፤ ስለ ፖለቲካውም የሚለው ነገር አለ። እዚህስ ላይ ምን ይላሉ? ጄኔራል ፃድቃን፦ "መፈንቅለ መንግሥት" ነው አይደለም የሚለው ክርክር ውስጥ መግባት አልፈልግም። ጉዳዩ በጣም አስቀያሚ ነው። ከህግ ውጭ ነው። ግን አንድ ግልፅ መሆን ያለበት ነገር አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የፌደራል ስርዓት አንድ ክልል እንኳን ሙሉ በሙሉ ቢቆጣጠሩ ኖሮ፤ አንደኛ አንድን ክልል የመቆጣጠር አቅማቸው አነስተኛ ነበር ብዬ ነው የምወስደው፤ ሁለተኛ ያ እንኳን ቢሳካ በሃገር አቀፍ ደረጃ ሊኖር የሚችለው ተፅኖ የተወሰነ ነበር ብዬ ነው የምወስደው። ብጥብጥ አይፈጥርም፤ ችግር አይፈጥርም ማለት ሳይሆን የአገር የፖለቲካ ስልጣንን ከመያዝ አንፃር ግን በእኩል ደረጃ የነሱን ያህል አቅም ያላቸው ክልሎች አሉ። እነዛ ክልሎች ደግሞ የራሳቸው የፀጥታ መዋቅርም አላቸው። የራሳቸው ህገ መንግሥታዊ አወቃቀር አላቸው። ከዛ በላይ ፣ አንድ ክልል ውስጥ ከሚፈጠር ችግር በላይ የሚያልፍ አይሆንም ነበር ብዬ ነው የማስበው። ያም ሆነ ይህ ግን ከህገ መንግሥቱ ውጭ የሆነ በጣም አረመኔያዊ እርምጃ ነው። ከዚህ በመለስ ያለው "መፈንቅለ መንግሥት" ነው አይደለም የሚለው ክርክር አሁን ለተፈጠረው ነገር ብዙ ጠቀሜታ ያለው መስሎ አይሰማኝም። ቢቢሲ፦አገሪቷ ለውጥ ላይ ነች እየተባለ ቢሆንም ከፍተኛ የብሔር ውጥረቶችና ጥቃቶችንም እየተመለከትን ነው። አሁን እያየነው ያለውን የፖለቲካ ባህል እንዴት ያዩታል? • መፈንቅለ መንግሥቱና የግድያ ሙከራዎች • ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ ጄኔራል ፃድቃን፦ አገራችን ውስጥ የፖለቲካ ችግር እንዳለ ይታወቃል። በተደጋጋሚም የሚነገር ጉዳይ ነው። በተለይም አማራ ክልል ውስጥ ፅንፍ የያዙ አንዳንድ ችግሮች ያጋጥሙ እንደነበር ይታወቃል። እነዚህ ችግሮች በእኔ አመለካከት የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ፈንድተው መውጣታቸው አይቀርም የሚል አመለካከት ነበረኝ። አሁን የሆነው የሚመስለኝ ይሄ ነው። በጣም ፅንፈኛ የሆነው በኃይል ፍላጎቱን ለመጫን ሲሞክር የነበረው በአማራ ክልል ላይ ብቻ ሳይሆን በሃገር አቀፍ ደረጃ ይህንን ለማድረግ ሲያስብ የነበረው ግልፅ ሆኖ ወንጀል በመፈፀም ደረጃ ወጥቷል። አሁን የሚጠረጠሩት ፤ ተይዘዋል የሚባሉት፤ ተገድለዋል የሚባሉት ላይ ማተኮር ብቻ ሳይሆን መንግሥት ይሄን ሁኔታ እንደ 'ኦፖርቹኒቲ' እንደ እንደ እድል አይቶ ችግሮችን ለመፍታት አመቺ ሁኔታ ተፈጥሮለታል ብየ አስባለሁ። በብልሃትና በብቃት ከተመራ ችግሩን ለመፍታት ጥሩ መነሻ ይሆነዋል ብየ አስባለሁ። በሌላ በኩል ደግሞ በደንብ ካልተያዘ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ሊሄዱ የሚችሉበት እድልም መኖሩን የሚያሳይ ምልክትም አለ። ይሄንን ተግባር የፈፀሙ የተወነሱ ስብስቦች ፣ በአንድ የፀጥታ መዋቅር ብቻ የሰራ አይደለም። ከዛ በላይም ሌላ ስብስብ ይኖራል። ይህ ነገር በተፈጠረበት ክልልም ሌሎች የመንግሥት ተቋማትም አደጋው እስከምን ድረስ ሊሄድ እንደሚችል ያሳየ ነው። የተከፈለው ዋጋ በጣም ከፍተኛ ነው። ይህንን ዋጋ ከፍለን፤ መከፈል ያልነበረበት ዋጋ ነው። ግን ደግሞ የመጣውን አጋጣሚ ለጥሩ ነገር ተጠቅመን ችግሮቹን አንዴ ለመፍታት ጥሩ መነሻ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ። ይህ ግን ዝም ብሎ የሚመጣ አይደለም። ብልሃት ያለው ሰከን ብሎ ከጥላቻ ፖለቲካ ወጥቶ በአማራጭ የፖለቲካ ሃሳቦች በማመን የአመራር ፖለቲካ ይጠይቃል። ይህ ጠንከር ያለ ስራ ይጠይቃል። ያ ካልሆነ የቀደመውን የጥላቻ ፖለቲካን እያራገቡ የሚኬድ ከሆነ ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል። ቢቢሲ፦የፌደራሉ መንግሥት በአማራ ክልል የተፈጠረውን "መፈንቅለ መንግሥት" ብሎታል። "መፈንቅለ መንግሥት" በክልል ደረጃ ይደረጋል ወይ? ግቡስ ምን ሊሆን ይችላል? ጄኔራል ፃድቃን፦ አሁን ባለው የኢትዮጵያ አወቃቀር በክልል ደረጃ እንዲህ አይነት ነገር ሲፈፀም አላውቅም። አልነበረም ማለት አይደለም፤ ኖሮ ሊሆን ይችላል እኔ ግን አላውቅም። በኢትዮጵያ አሁን ባለው የመንግሥት አወቃቀር ደረጃ አንድ ክልል ውስጥ ስልጣን እንኳን ቢያዝ አንደኛ ክልሉ ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ አጥፍቶ ስልጣን የመያዝ እድሉ አነስተኛ ነው። ነገር ግን ስልጣን ቢያዝና የክልሉን ኃይል ቢቆጣጠሩ በሃገር አቀፍ ደረጃ አበቃለት የሚባል አይደለም። ዋናው ኃይል የፌደራል ስርአቱ ነው። የፌደራል ስርአቱ ደግሞ የህዝብን ምርጫ ምንም ግምት ውስጥ ሳያስገባ በጉልበት የክልሉን ስልጣን ይዞ አስተዳድራለሁ ሊል አይችልም።ይህ ለክልሉ ህዝብ ስድብ ነው የሚመስለኝ። የክልሉን ህዝብ ፖለቲካዊ አስተሳሰብና ባህል መናቅ ነው። የሚመስለኝ ግን ይህንን ለጊዜው ትተን ቢሳካለት እንኳን ከክልሉ ያለፈ ችግር አይሆንም። በክልሉ ላይ ያለውን ችግር ደግሞ የፌደራል መንግሥቱ ከሌሎች ክልሎች ጋር በመሆን ሊፈታው ይችል የነበረ ነው የሚመስለኝ። እኔ ምን ሊባል እንደሚችል የያዝኩት ቃል የለኝም፤ የክልል "መፈንቅለ መንግሥት" ነው የሚሆነው፤ ነገር ግን በክልል ብቻ የተቃጣ አይደለም። ከክልል በላይ አልፎ በመከላከያም ውስጥ የተቀናጀ ስራ እንዲሰራ አድርገዋል። ግን ደግሞ ይሄ ያመጣው ውጤት የሚታወቅ ነው። ስለዚህ ያም ሆነ ይህ በሃገር አቀፍ ደረጃ ስልጣን ለመያዝ አስበው ከሆነ እሱን የሚያሳይ ምልክት የለም ። በክልል ደረጃ ስልጣን ለመያዝ አስበው ነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት፤ መከላከያ ላይ የነበሩትንም ባለስልጣናት እርምጃ የወሰዱባቸው በክልላቸው ለሚደረግ ስራ እንቅፋት እንዳይፈጥሩባቸው ነገሮችን ለማዛባት አስበው የሰሩት ነው የሚመስለው። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ፤ ይሄ ደግሞ ክልሉ ላይ ለሚሰራው ስራ ማሳለጫ ነው እንጂ ስልጣን ለመያዝ የታሰበ አይመስልም። አማራ ክልል ላይ ቢሳካላቸው ኖሮ የሚሄደው ርቀት አነስተኛ ነው።አማራ ክልሉም የመሳካት አቅሙ አነስተኛ ነበር ፤ የታየውም ይሄ ነው። ፍላጎት አልነበራቸውም ማለት አይደለም፤ ስላልቻሉ ነው የወደቀው፤ የአገር ውስጥ ጉዳት በጣም ከፍተኛ ቢሆንም ከዚያ በላይ መሄድ የሚችል አልነበረም ብየዬነው የምወስደው። • የሰኔ 16ቱ ጥቃትና ብዙም ያልተነገረላቸው ክስተቶች
xlsum_amharic-train-289
https://www.bbc.com/amharic/47871211
የኢቲ 302 የመጨረሻዎቹ ስድስት ደቂቃዎች
በዓለም አቀፉ አሠራር መሰረት የተለያዩ አካላት ተሳትፈውበታል የተባለለት በአደጋው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ላይ የቦይንግ 737 ማክስ 8 የበረራ ቁጥር የኢቲ 302 የመጨረሻ ደቂቃዎች የበረራ ታሪክ ዝርዝር መረጃ ወጥቷል።
[ "በዓለም አቀፉ አሠራር መሰረት የተለያዩ አካላት ተሳትፈውበታል የተባለለት በአደጋው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ላይ የቦይንግ 737 ማክስ 8 የበረራ ቁጥር የኢቲ 302 የመጨረሻ ደቂቃዎች የበረራ ታሪክ ዝርዝር መረጃ ወጥቷል።" ]
የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር የተደረገውን ምልልስ፣ በበረራ መረጃ መመዝገቢያ ሳጥን ውስጥ የተገኘውን መረጃ እና ከአብራሪዎች ክፍል ውስጥ የተቀረጸውን ድምጽ ዋቢ አድርጓል። ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ አብራሪ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ላይ በመመስረት የኢቲ 302 የመጨረሻዎቹ ስድስት ደቂቃዎች ምን ይመስሉ እንደነበር ለቢቢሲ እንደሚከተለው አስቃኝቷል። እሁድ ጠዋት መጋቢት 1/2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንግድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የአየር መንገዱን 8 ሰራተኞችን ጨምሮ 157 መንገደኞችን በመያዝ ወደታቀደለት ናይሮቢ ኬንያ ለመብረር እየተዘጋጀ ነው። • አውሮፕላኑ 'ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ነበር' • አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 የገጠመው ምን ነበር ? ጠዋት 02፡37፡34- የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አውሮፕላኑ በረራውን እንዲያደርግ እና በ119.7 ሄርዝ ላይ በራዳር አማካኝነት ግንኙነት እንዲፈጽም ፈቃድ ሰጥተው አውሮፕላኑ ለመነሳት ዝግጅቱን ጀመረ። የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አንድ አውሮፕላን እንዲነሳ ፍቃድ (ቴክ ኦፍ ክሊራንስ) ከመስጠታቸው በፊት የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ያረጋግጣሉ።ከነዚህም መካከል በተመሳሳይ ሰዓት የሚነሱ እና የሚያርፉ አውሮፕላኖች አለመኖራቸውን፣ ለመንገደኞች የሚደረጉ የበረራ ላይ ደህንነት ገለጻዎች መጠናቀቃቸውን እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። ከዚያም አውሮፕላኑ ተንደርድሮ ወደ ሚነሳበት የመንደርደሪያ ጥርጊያ (ራንዌይ) 07R (07ቀኝ ማለት ነው) መጠጋት ጀመረ። ማብራሪያውን የሰጠን አብራሪ እንደሚለው ከሆነ አውሮፕላን ተንደርድሮ የሚነሳበት መንገድ (ራንዌይ) ስያሜውን የሚያገኘው በአቅጣጫ መጠቆሚያ መሰረት ነው። አብራሪው ጨምሮም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥሮችም አውሮፕላኑ ወዴት እንደሚበር ይጠቁማሉ። ለምሳሌ ኢቲ3xx ብለው የሚጀምሩ የበረራ ቁጥሮች መዳረሻቸው ምሥራቅ አፍሪካ ሲሆን ኢቲ5xx ብለው የሚጀምሩት ደግሞ ሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም ኢቲ6xx ብለው የሚጀመሩ የበረራ ቁጥሮች መዳረሻቸው ሩቅ ምሥራቅ ነው። 02፡37፡34 - የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ አውሮፕላኑን እያበረረ እንደሆነ ገልጿል። 02፡38፡44 - አውሮፕላኑ ከተነሳ በኋላ ወዲያውኑ ማለትም አውሮፕላኑ ለመነሳት መንቀሳቀስ ከጀመረበት ከአንድ ደቂቃ ከ10 ሰከንዶች በኋላ የአውሮፕላኑ በግራ እና በቀኝ ክንፉ በኩል አንግል ኦፍ አታክ ሴንሰር የተመዘገበው መረጃ ከተገቢው ውጪ መሆኑን ያሳያል። 02፡38፡46 - ረዳት አብራሪው ''Master Caution Anti-Ice'' ማስጠንቀቂያ መምጣቱን ለዋና አብራሪው ሲናገር ተሰምቷል። ማስተር ኮሽን (Master Caution) በአውሮፕላን ሥርዓት ላይ አንዳች ችግር ሲያጋጥም ለአብራሪዎች የሚጠቁም ሥርዓት ሲሆን በዚህ ሰዓት የደረሳቸው ''Master Caution Anti-Ice'' ማሰጠንቀቂያ የአውሮፕላኑን አካል ከከፍተኛ ቅዝቃዜ የሚጠብቀው አካል ችግር እንዳጋጠመው እንደሆነ አብራሪው ያስረዳል። 02፡38፡58 -ዋና አብራሪው ''ኮማንድ'' በማለት አውሮፕላኑን ''አውቶፓይለት'' ሥርዓት ላይ ለማድረግ ቢጥርም፤ አውሮፕላኑ አውቶፓይለት ላይ እንዳልሆነ የሚያስጠነቅቅ መልዕክት መጣ። አውቶፓይለት ማለት አውሮፕላኑ በተወሰነለት አቅጣጫ በእራሱ ሥርዓት እንዲበር የሚያደርግ ዘዴ ነው። ከሁለት ሰከንዶች በኋላ ማለትም 02፡39፡00 ላይ ዋና አብራሪው በድጋሚ ''ኮማንድ'' በማለት አውሮፕላኑን ''አውቶ ፓይለት'' ሥርዓት ላይ ለማድረግ ቢሞክርም ከአንድ ሰከንድ በኋላ (02፡39፡01) አውሮፕላኑ አውቶ ፓይለት ላይ እንዳልሆነ የሚያስጠነቅቅ መልዕክት ከአውሮፕላኑ መጣ። 02፡39፡06 - ከአምስት ሰከንዶች በኋላ ማለት ነው፤ በዋና አብራሪው ትዕዛዝ ረዳት አብራሪው ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ግንኙነት አደረገ። ረዳት አብራሪው ''SHALA 2A departure crossing 8400 ft and climbing FL 320'' በማለት ሪፖርት አደረገ። አብራሪው ይህንን ሲል 'ሻላ 2ኤ' ማለት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ የሚወስድ የተወሰነ የበረራ አቅጣጫ ሲሆን፤ 8400 ጫማ ከፍታ እያቋረጡ እንደሆነ እና 32000 ጫማ ከፍታ ይዘው እንደሚበሩ ነው ረዳት አብራሪው ሪፖርት ያደረገው። • የመደመር እሳቤ ከአንድ ዓመት በኋላ • ጨው በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ሰዎችን ይገድላል 02፡39፡45 - ዋና አብራሪው ፍላፕስ አፕ (Flaps up) በማለት ለረዳት አብራሪው ትዕዛዝ ሰጠ። ረዳት አብራሪውም ትዕዛዙን ተቀበለ። ፍላፕስ የአውሮፕላኑ አካል ሲሆኑ አውሮፕላኑ ከመሬት ለመነሳት በሚያደርገው ጥረት በቂ ፍጥነት እንዲያገኝ የሚያስችሉ ናቸው። ማብራሪያውን የሰጠን አብራሪ እንደሚለው የኢቲ 302 አብራሪዎች እንዳደረጉት ሁሉ አንድ አውሮፕላን ከተነሳ እና በቂ ከፍታን ከያዘ ፍላፕሶቹን ይሰበስባል። 02፡39፡50 - አውሮፕላኑ የበረራውን አቅጣጫ ከ072 ወደ 197 ዲግሪ መቀየር ጀመረ። በተመሳሳይ ሰዓት ዋና አብራሪው በተፈቀደው የበረራ አቅጣጫ ላይ እንዲቆይ ትዕዛዝ ሰጠ። 02፡39፡55 - አውሮፕላኑ ከአውቶ ፓይለት ተላቀቀ (ዲስኢንጌጅ አደረገ)። 02፡39፡57 - ረዳት አብራሪው በዋና አብራሪው ጥያቄ መሰረት ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አውሮፕላኑን የመቆጣጠር ችግር እንደገጠማቸው አሳወቀ። • "ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት 02፡40፡03- ''Ground Proximity Warning System (GPWS)'' የተባለው የአውሮፕላኑ ሲስተም (ስርአት) ''ቁልቁል አትመዘግዘግ'' (DON'T SINK) የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ይህ ሲስተም አውሮፕላኑ ወደሚበርበት አቅጣጫ ከመሬት ወይም ከግዑዝ ነገር ጋር የመጋጨት አደጋ እንደተደቀነበት ለማሳወቅ ለአብራሪዎች መልዕክት ለመስጠት የተቀረጸ ነው። 02፡40፡03 እስከ 02፡40፡31 ድረስ ባሉት 28 ሰከንዶች ውስጥ ሦስት (GPWS) የ''DON'T SINK'' ማስጠንቀቂያዎች ተመዝግበዋል። 02፡40፡27 - ዋና አብራሪው የአውሮፕላኑን አፍንጫ በአንድ ላይ ክፍ እንዲያደርግ ረዳት አብራሪውን ጠየቀው። 02፡40፡44 - ዋና አብራሪው ሦስት ግዜ ''ቀና አድርገው'' (ፑል-አፕ) አለ፤ ረዳት አብራሪውም እንደተባለው አደረገ። 02፡40፡50 - ረዳት አብራሪው በዋና አብራሪው ጥያቄ መሰረት ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ግነኙነት በማድረግ 14ሺህ ጫማ ላይ መቆየት እንደሚሹ እና በረራውን የመቆጣጠር ችግር እንዳጋጠማቸው አሳወቀ:: 02፡41፡30 - አሁንም በድጋሚ ዋና አብራሪው ረዳት አብራሪው አውሮፕላኑን አብሮት ከፍ እንዲያደርግ ጠየቀ። እሱም እንደተባለው አደረገ። • "አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ 02፡42፡10- ዋና አብራሪው ረዳት አብራሪው ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ግነኙነት እንዲያደርግ እና መመለስ እንደሚፈልጉ እንዲያሳውቅ ነገረው። ረዳት አብራሪውም እንደተባለው አደረገ፤ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎቹም ፍቃድ ሰጡ። 02፡42፡30 - የአየር ትራፊክ መቆጣጣሪያውም ኢቲ 302 ወደቀኝ ዞሮ 260 ዲግሪ እንዲይዝ ትዕዛዝ ተሰጠው። ረዳት አብራሪውም ትዕዛዙን ተቀበለ። 02፡43፡04 - ዋና አብራሪው ረዳቱን አሁንም በድጋሚ አውሮፕላኑን አብሮት ከፍ እንዲያደርግ ጠየቀ። ዋና አብራሪው መልሶም አውሮፕላኑ በበቂ ሁኔታ ከፍ አለማለቱን ተናገረ። አውሮፕላኑ አፍንጫውን እሰከ 40 ዲግሪ ደፈቀ። ስለክስተቱ የአደጋውን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት መሰረት አድርጎ ማብራሪያውን ለቢቢሲ የሰጠው አብራሪ እንደሚለው ከሆነ እንደየ አውሮፕላኖቹ የሚለያይ ቢሆንም አንድ አውሮፕላን ለማረፍ ሲቃረብ 3 ዲግሪ ያክል ብቻ ነው የፊተኛው አካሉ ዝቅ የሚለው። 02፡43፡43- ቀረጻው ቆመ። የአውሮፕላኑን መከስከስ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለአውሮፕላን አደጋ መርማሪ ቢሮ አስታወቁ። ከደቂቃዎች በኋላም የኢቲ302 መከስከስ ዜና ተሰማ። የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ አብራሪዎቹ በቦይንግ እና በአሜሪካ ትራንስፖርት ባለስልጣን ዘንድ ተቀባይነት ያለውን የደህንነት ቅድመ ተከተል ተግባራዊ በማድረግ በበረራው ላይ ያጋጠማቸውን አስቸጋሪ ሁኔታ በቁጥጥር ሥር ለማድረግ ጥረት ማድረጋቸውን በግልጽ አመላክቷል። አብራሪዎቹ ተገቢውን እርምጃ ቢወስዱም ያጋጠማቸውን ያልተቋረጠ አውሮፕላኑ አፍንጫውን የመድፈቅ ችግርን መቆጣጠር ተስኗቸዋል። •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማሪያምም ከመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ጋር በተያያዘ "ፓይለቶቹ እጅግ በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚጠበቅባቸውን ተገቢ እርምጃ በመውሰድ ያላቸውን ከፍ ያለ ሙያዊ ብቃት በማስመስከራቸው አየር መንገዱ እንደሚኮራባቸው ተናግረዋል። የዋና ካፒቴን ያሬድ ጌታቸው አባት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ልጃቸው ከባልደረባው ጋር ሆኖ አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር የተቻለውን ሁሉ በማድረጉ ጀግና መሆኑን በሃዘን በተሰበረ ስሜት ተናግረዋል።
xlsum_amharic-train-290
https://www.bbc.com/amharic/news-55883439
ኮሮናቫይረስ፡ ቻይና ስለሰራቻቸው የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ምን ያህል እናውቃለን?
ቻይና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ላይ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ክትባት ለማግኘት ስትመራመር ቆይታለች።
[ "ቻይና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ላይ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ክትባት ለማግኘት ስትመራመር ቆይታለች።" ]
በዓለም ላይም በ2020 የበጋ ወራት ለሕዝቦቿ ክትባቱን መስጠት በመጀመር ቀዳሚዋም ናት። በአሁኑ ሰዓት 16 የተለያዩ ዓይነት ክትባቶች ላይ ምርምር እያደረገች ሲሆን ተሳክተው ለጥቅም የዋሉት ግን ሲኖቫክ እና ሲኖፋርም የተሰኙት መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ያቀረቧቸው ናቸው። እነዚህ ሁለት ክትባቶች በቱርክ፣ በብራዚል፣ ኢንዶኔዢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፍቃድ አግኝተዋል። በኢንዶኔዢያ የሕክምና ባለሙያ የሆነቸው ዶ/ር አንጊዲታ ዲያ " ለአንድ አመት ያህል ይህንን ወረርሽኝ ለማቆም ምንም ተስፋ ሳይኖር ቆይቶ፣ አሁን ይህንን ክትባት በማግኘቴ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ" ብላለች። እነዚህ ክትባቶች የሚሰሩትልክ እንደ ሂፒታይተስ ኤ እና ሬቢስ ክትባቶች ነው ። መጀመሪያ ቫይረሱ እንዲሞት ተደርጎ በክትባት መልክ እንድንወስደው ይደረጋል። ቫይረሱ በመሞቱ ኮቪድ-19 ሊያስይዝ አይችልም። ክትባቱን የወሰደው ሰው ወደፊት ለኮሮናቫይረስ በሚጋለጥበት ወቅት በቂ የመከላከል አቅም ሊኖረው የሚያስችለው አንቲቦዲ በፍጥነት ያዳብራል። ሰውነቱመ የመከላከል አቅሙን ወዲያው ያዳብራል። ልክ እንደ ፋይዘርና ሞደርና ክትባቶች ሁሉ የቻይናዎቹ ሲኖፋርም እና ሲኖቫክ ክትባቶችንም ሁለት ጊዜ መውሰድ ያስፈልጋል። የሞደርና እና ፋይዘር ክትባቶች ግን እጅግ በጣም ቀዝቃዛ ስፍራ መቀመጥ ሲኖርባቸው የቻይና ክትባቶች ግን በማንኛውም ማቀዝቀዣ ውስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ። እነዚህ የቻይና ክትባቶች በዚህ ምክንያት የተነሳ በማጓጓዝ እና በማከማቸት ወቅት ይህ የተለየ ብልጫ ይሰጣቸዋል። በተለይ ደግሞ ሙቀት ከ30 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች የሚገኝባቸው አገራት እና የመንገድ ፍሰት በበቂ በሌለባቸው ስፍራዎች ይህ የተሻለ ብልጫ እንዲኖራቸው ያደርጋል። ሳይኖፋርም ያመረተው ክትባት የኮቪድ-19 ምልክቶችን በማቆም ረገድ 79 በመቶ ውጤታማ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሳይኖቫክ ያመረተው እና ኮሮኖቫክ የተሰኘው ክትባት ደግሞ መጀመሪያ ላይ 91 በመቶ ውጤታማ ነው ተብሎ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ተጨማሪ የተደረጉ ሙከራዎች ሌላ ውጤት አሳይተዋል። ብራዚል በዚህ ክትባት ላይ ያደረገችው ሙከራ ውጤቱን ወደ 50.4 በመቶ አውርዶታል። ይህ ደግሞ የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት አንድ ክትባት ወደ ሕብረተሰቡ ከመሰራጨቱ በፊት ማሟላት አለበት ከሚለው መስፈርት በጥቂት ብቻ ከፍ ብሎ እንዲገኝ አድርጎታል። ቻይና ለከ20 አገራት በላይ ክትባቷን ለመስጠት ስምምነት ላይ የደረሰች ሲሆን በመላው ዓለምም ለማሰራጨት አቅዳለች። የዓለም ጤና ድርጅት ግን በመጪው መጋቢት ወር ሳይኖፋርምም ሆነ ሳይኖቫክ ያመረቷቸውን ክትባቶች መጠቀም አለመጠቀም ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ለመሆኑ የትኞቹ ክትባቶች ጥቅም ላይ ውለዋል? በአሁኑ ጊዜ በርካታ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎችና አገራት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚሆን ክትባት በማበልጸግ ላይ ሲሆኑ ጥቂቶቹም በስራ ላይ መዋል ጀምረዋል። ፋይዘር/ባዮንቴክ ኮሮናቫይረስን በመከላከል 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለው ይህ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ይፋ የሆነው በፈረንጆቹ ሕዳር 9/2020 ላይ ነበር። በወቅቱ ክትባቱን ይፋ ያደረጉት ፋይዘር እና ባዮኤንቴክ ኩባንያዎች ግኝቱ ለሳይንስና ለሰው ልጅ ትልቅ እድል ነው ብለዋል። የአሜሪካ እና የጀርመን ኩባንያ የሆኑት ፋይዘር እና ባዮንቴክ በስድስት የተለያዩ ሃገራት 43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከራቸውን የገለፁ ሲሆን አንድም ጊዜ አሳሳቢ የጤና ችግር አልታየም ብለዋል። ፋይዘርና ባዮንቴክ ክትባቱን በፈረንጆቹ የህዳር ወር መጨረሻ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም ዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል በመፍቀድ ከዓለማችን ቀዳሚዋ አገር ሆናለች። ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ማክሰኞ ዕለት ለዜጎቿ መስጠት የጀመረች ሲሆን የዘጠና ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባትን በመውሰድ በዓለም የመጀመሪያዋ ሰው ሆነዋል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚገኙ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች እና ለጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተገልጿል። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር መስሪያ ቤትን (ኤፍዲኤ) የሚያማክሩ ባለሙያዎች በፋይዘር/ባዮንቴክ የበለጸገው የኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ሀሳብ ማቅረባቸውም ተገልጿል። ባለሙያዎቹ ይህን ምክረ ሃሳብ የሰጡት 23 አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ክትባቱ ሊፈጥረው የሚችለው ስጋት ከሚሰጠው ጥቅም አንጻር ምን ሊመስል እንደሚችል ምክክር ካደረጉ በኋላ ነው ተብሏል። የአሜሪካ የጤና ሚንስትር አሌክስ ረቡዕ ዕለት ''በሚቀጥሉት ቀናት ክትባቱ በእጃችን ሊገባ ይችላል፤ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን ዜጎች መከተብ ልንጀምር እንችላል'' ብለዋል። የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት እስካሁን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ባህሬን እና ሳኡዲ አረቢያ ጥቅም ላይ ለመዋል ፍቃድ አግኝቷል። ሞደርና የዩናይትድ ስቴትስ መድኃኒት አምራች ኩባንያ የሆነው 'ሞደርና' ከኮሮናቫይረስ 95 በመቶ የሚከላከል አዲስ ክትባት ማግኘቱን ይፋ ካደረገ ሰነባብቷል። በአሁኑ ሰአትም ከአውሮፓና አሜሪካ ፈቃድ ሰጪዎች ክትባቱን ለመጠቀም የሚያስችል ፈቃድ ጠይቆ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ሞደርና የምርምር ውጤቱን ይፋ ያደረገበትን ዕለት 'ታላቅ ቀን' በማለት ሐሴቱን የገለፀ ሲሆን፤ በቅርብ ሳምንታትም ክትባቱን ለመጠቀም ፈቃድ እንደሚያገኝ አስታውቋል። የቤተ ሙከራ ሂደቶች እንደሚያሳዩት ኤምአርኤንኤ የተሰኘው ክትባት 94 በመቶ ውጤታማና ሰዎችን ከኮሮናቫይረስ የሚያድን ነው። የክትባቱ ሙከራ አሜሪካ ውስጥ ያሉ 30 ሺህ ሰዎችን ያሳተፈ ሲሆን፤ ግማሾቹ በየአራት ሳምንቱ ክትባቱ ሲሰጣቸው ግማሾቹ ደግሞ ጥቅምና ጉዳት የሌለው መርፌ ተወግተው ውጤቱን ለመለየት ተሞክሯል። ከዚህ ሙከራ በተገኘ ውጤት መሠረት 94.5 በመቶ ሰዎች በክትባቱ ምክንያት ለኮሮናቫይረስ ሳይጋለጡ ቀርተዋል ተብሏል። ስለ ክትባቱ ውጤቱ የቀረበው ዘገባ ጨምሮም፤ ሙከራ ከተደረገባቸው መካከል 11 በኮቪድ-19 ክፉኛ የታመሙ ሰዎች የመከላከል አቅም አዳብረዋል ይላል። ስፑትኒክ 5 ይህ ሩሲያ ሰራሽ ክትባት ይፋ በተደረገ ጊዜ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአገር ውስጥ በተደረገ ምርምር አገር በቀል ክትባት አግኝተናል፤ ለሰዎች አገልግሎት እንዲውልም ይፋዊና ብሔራዊ ፍቃድ ሰጥተናል ብለው ነበር። በዓለም የመጀመርያው የተባለው ይህ ስፑትኒክ-5 ክትባት ሞስኮ የሚገኘው ጋማሊያ ኢንስቲትዩት ነው ያመረተው። ክትባቱ ይፋ የተደረገውም ነሀሴ ወር ላይ ነበር። ኢንስቲትዩቱ እንደሚለው ክትባቱ አስተማማኝ የመከላከል አቅም ይሰጣል። ፑቲን በበኩላቸው ገና ቀደም ብሎ "ይህ ክትባት አስተማማኝ እንደነበር አውቅ ነበር" ብለዋል። "ሁሉንም ሳይንሳዊ ሂደቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ማለፍ ችሏል" ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል። ፑቲን ከልጆቻቸው ለአንዷ ክትባቱ ተሰጥቷት ትንሽ አተኮሳት እንጂ ምንም አልሆነችም ብለዋል። ፑቲን የትኛዋ ልጃቸው ክትባቱን ወስዳ እንዳተኮሳት ግን በስም አልገለጹም። የሩሲያ ሳይንቲስቶች የመጀመሪያ ዙር ሙከራዎች ተደርገው ሁሉም ድንቅ ውጤት አስመዝግበዋል ብለዋል። ሳንቲስቶቹ ሰዎች ላይ ጉንፋንን የሚያመጣው አዲኖቫይረስ የተሰኘውን የተላመደ የተህዋስ ቅንጣት ተጠቅመው ነው ክትባት ሰራን ያሉት። ይህን ለማዳ ተህዋሲ አዳክመው ወደ ሰውነት በማስገባት ሕዋስ በማቀበል ክትባቱ ሰውነት ኮቪድ-19 ተህዋሲ ሲገባ ነቅቶ እንዲዋጋ ያደርገዋል ብለዋል። በአውሮፓውያኑ ታሕሳስ 5/2020 ላይ ደግሞ ይሄው ክትባት በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ መሰጠት ተጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን ለመውሰድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተመዝግበዋል። ሩሲያ ምን ያህል ክትባት ማምረት እንደምትችል ግልጽ ባይሆንም፤ አምራቾች እስከ ዓመቱ መገባደጃ ሁለት ሚሊዮን ጠብታ እንዲያዘጋጁ ይጠበቃል። 13 ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጌ ሶቢያን እንዳሉት፤ ክትባቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ለጤና ባለሙያዎች እና ለትምህርት ቤት ሠራተኞች ይሰጣል። ተጨማሪ ክትባቶች ሲመረቱ ለተቀረው ማኅበረሰብ እንደሚዳረስ ከንቲባው ጠቁመዋል። ከላይ በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች የተሰማሩና እድሜያቸው ከ18 እስከ 60 የሆኑ ዜጎች በድረ ገጽ ተመዝግበዋል። በሞስኮ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የክትባቱን አገልግሎት የሚሠጡ 70 ማዕከሎች ተከፍተዋል። ክትባቱ የተሰጣቸው ባለፉት 30 ቀናት የመተንፈሻ አካል ህመም የገጠማቸው፣ የከፋ የጤና እክል ያለባቸው፣ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንደሚለዩ ተገልጿል። ሲኖቫክ መላው ዓለም ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና ሲል ቻይናም እጇን አጣጥፋ አልተቀመጠችም። ሲኖቫክ የተባለ ክትባት መስራት ከጀመረች ሰነባብታለች። እንደውም በጎ ፈቃደⶉችን መከተብ ከጀመረች ቆየት ብላለች። በቻይና በሙከራ ላይ የሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት አመርቂ የሚባል ውጤት እያስገኘ ነውም ተብሏል። ሆኖም ክትባቱ አመርቂ ውጤት ያስገኘው በረዥም የሙከራ ሂደት ውስጥ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ሳይሆን፣ መካከለኛ ምዕራፍ በሚባለው ክፍል ነው። ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡት ከቻይና ሰራሽ ክትባቶች አንዱና ታዋቂ እየሆነ የመጣው በሲኖቫክ ባዮቴክ የተመረተው ሲኖቫክ ክትባት በ700 ሰዎች ላይ ተሞክሮ ይበል የሚያሰኝ ውጤት አስገኝቷል። ክትባቱ የተሞከረባቸው ሰዎች በሽታን የመከላከያ ህዋሳቸውን አንቅቶ ቫይረሱን መመከት እንደቻለ ተደርሶበታል። ላንሴት በሚባለው ሥመ ጥር የሳይንስ ጆርናል ላይ ይህንን ክትባት በተመለከተ የተዘገበው፤ ክትባቱ ለጊዜው በምዕራፍ አንድና ሁለት ያስመዘገበው ውጤት እንጂ አሁን ያለበትን ደረጃ አይገልጽም። በተጨማሪም የስኬት ምጣኔው ምን ያህል እንደሆነ ይፋ አልተደረገም። በዚህ ጆርናል ላይ ስለዚህ ቻይና ሰራሹ ክትባት ከጻፉት ተመራማሪዎች አንዱ የሆኑት ዙ ፋንቻይ እንደሚሉት፤ በምዕራፍ አንድ እና በምዕራፍ 2 ሙከራዎች 600 ሰዎች ላይ ጥናት ተደርጎ ክትባቱ ለአስቸኳይ ሕክምና አገልግሎት ላይ መዋል ይችላል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል። ነገር ግን ወሳኝ በሚባው በምዕራፍ ሦስት ሙከራ ላይ ይህ የቻይና ክትባት ስላስገኘው ውጤት በተጨባጭ ተአማኒ ሳይንሳዊ ጆርናል ላይ የተጻፈ ዘገባ የለም። በቻይና በአሁን ሰዓት ሙሉ በሙሉ ሊባል በተቃረበ ደረጃ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በቁጥጥር ሥር የዋለበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ሆኖም ቻይና ለዜጎቿ ይህንን ክትባት መስጠቷን ቀጥላበታለች። በአሁኑ ሰአት ደግሞ መቀመጫውን ቤዢንግ ያደረገው የክትባት አምራቹ ኩባንያ ያዘዛቸው በርካታ የህክምና ቁሳቁሶች ከኢንዶኔዢያ መግባት ጀምረዋል። ይህ ደግሞ አገሪቱ በቅርቡ ዜጎቿን በይፋ መከተብ ልትጀምር እንደሆነ ማሳያ ነው ተብሏል። በዓለም ላይ ኮቪድ-19 ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰባቸው አገራት ተርታ የምትመደው የደቡብ አሜሪካዋ ትልቅ አገር ብራዚል በበኩሏ ቻይና ሰራሽ ክትባት ለሕዝቤ አድላለሁ ማለቷ የሚታወስ ነው። የሳኦ ፖሎ ገዥ ጃዎ ዶሪያ እንዳሉት የፌዴራል መንግሥት 46 ሚሊዮን ጠብታዎችን ለመግዛት ስምምነት ላይ ደርሷል። የክትባት ዘመቻው መቼ ይጀመራል በሚል የተጠየቁት የሳኦ ፖሎ ገዥ በፈረንጆች አዲሱ ዓመት የመጀመርያ ወር ላይ ሊሆን ይችላል ብለዋል። አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እያበለፀጉ ያሉት ክትባት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው ክትባቶች መካከል ነው። ይሄው ክትባት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሙከራ መልክ ተሰጥቷል። ደቡብ አፍሪካ ለዚህ የክትባት ሙከራ የተመረጠችው በዘርፉ ባሏት ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ያሉባትና ወረርሽኙም በፍጥነት እየተስፋፋባት በመሆኑ ነው። ይህ የክትባት ሙከራ ኦኤክስ1ኮቪድ-19 ክትባት የሚባል ሲሆን፤ ኮሮናቫይረስን የሚያስከትለው ሳርስ-ኮቪ-2 በተባለው ቫይረስ ሰዎች እንዳይያዙ ለመከላከል የታለመ ነው። በደቡብ አፍሪካ የሚደረገው የክትባት ሙከራ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ጥልቅ ፍተሻ ተደርጎበት በደቡብ አፍሪካ መንግሥት የጤና ምርቶች ተቆጣጣሪ ተቋምና በዊትስ ዩኒቨርስቲ ፈቃድ ተሰጥቶታል ተብሏል። ይህ ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከአራት ሺህ ሰዎች በላይ የተሳተፉበት ክሊኒካል ሙከራ የተደረገበት ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካ ከሚደረገው ሙከራ ጋር ተመሳሳይና ተዛማጅ የሆነ ሙከራ ብራዚል ውስጥ ሊጀመር እንደሆነ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም ከሁሉም የላቀ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የሚሳተፉበት የዚህ ክትባት ሙከራ አሜሪካ ውስጥ በ30 ሺህ ሰዎች ላይ ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል። በሌሎች ድርጅቶች የሚሠሩ እና በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ሙከራ ተጨማሪ ውጤቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራቶች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ሰአትም የመጨረሻው የሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኙ በርካታ ተጨማሪ ክትባቶች አሉ። ከነዚህም መካከል ከታች የተዘረዘሩት የሚጠቀሱ ናቸው።
xlsum_amharic-train-291
https://www.bbc.com/amharic/news-50206434
በግጭት ውስጥ የሰነበቱት ከተሞች የዛሬ ውሎ
ባለፈው ረቡዕ በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሱ ተቃውሞዎችን ተከትሎ የተቀሰቀሱ ግጭቶች የብሔርና የሃይማኖት መልክ ይዘው ለቀናት ከቀጠሉ በኋላ ከ67 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፉ በኋላ በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጠሪዎች እየተያዙ መሆናቸው የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
[ "ባለፈው ረቡዕ በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሱ ተቃውሞዎችን ተከትሎ የተቀሰቀሱ ግጭቶች የብሔርና የሃይማኖት መልክ ይዘው ለቀናት ከቀጠሉ በኋላ ከ67 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፉ በኋላ በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጠሪዎች እየተያዙ መሆናቸው የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።" ]
አዳማ • በተለያዩ ሥፍራዎች ባጋጠሙ ግጭቶች የሟቾች ቁጥር 67 ደርሷል ትናንት በማህበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ሰልፎች እንደሚካሄዱ የሚገልጹ መልዕክቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ዛሬ ሰኞ ግጭቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተሰግቶ ነበር። ቢቢሲ እስካሁን ያለውን ሁኔታ ለማወቅ ከሰሞኑ ግጭት የተከሰተባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎችን አናግሯል። ሐረር በሐረር ከተማ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ዛሬም በከተማዋ የነበረው እንቅስቃሴ መቀዝቀዙን ቢቢሲ ያናገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት ትምህርት ቤቶች ዝግ ሲሆኑ ወደ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ተገልጋዮች ስለማይታዩ ጭር እንዳሉና አንዳንድ ሱቆችም ዝግ ናቸው። • በዶዶላ ቤተክርስቲያናት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ምዕመናን ስጋት ላይ ነን አሉ በከተማዋ ያሉ መንገዶች እምብዛም ተሽከርካሪዎች ስለማይታዩባቸው ጭር ማለታቸውን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ የጸጥታ አካላትም በከተማዋ እየተዘዋወሩ ጥበቃ እያደረጉ እንደሆነም ተገልጿል። በተጨማሪም ቀደም ካሉት ቀናት በተለየ የጸጥታ አካላት ስለትም ሆነ ዱላ ይዞ መንቀሳቀስን ከልክለዋል። እነዚህን ቁሶች ይዘው ከሚገኙ ሰዎች ላይ እንደሚቀሙ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሰልፍም ሆነ ግጭት ይህንን ዘገባ እስካጠናቀርንበት ድረስ አለመከሰቱን ለማወቅ ችለናል። ሞጆ ዛሬ ጠዋት በሞጆ ከተማ በተከሰተ ሁከት ሁለት ሰዎች በጥይት ተመተዋል። በከተማዋ ዛሬ ጠዋት 'የታሰሩ ሰዎች ከእስር ይለቀቁ' በማለት ሰልፍ የወጡ ሰዎች ከመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ተጋጭተው በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማው ከንቲባ ወ/ሮ መሰረት አሰፋ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቅዳሜ ሌሊት ላይም በከተማዋ በምሽት ሰልፍ ተካሂዶ እንደነበር ከንቲባዋ ተናግረዋል። "ቅዳሜ ሌሊት 'ቤተክርስቲያን ተቃጥለ' የሚል ወሬ ተናፍሶ ሌሊቱን ሁከት ተፈጥሮ ነበር። በንብረት ላይ ጉዳት ደርሶ ነበር" ብለዋል። • "ያለን አማራጭ ውይይት ብቻ ነው" ጀዋር መሐመድ ከንቲባዋ ጨምረው እንደተናገሩት ቅዳሜ ሌሊት ቤተ-ክርስቲያን ተቃጥሏል እየተባለ የተናፈሰው ወሬ ሃሰት መሆኑን እና ይህ የተደረገው "በከተማው ሆን ተብሎ ረብሻ ለመፍጠር" ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል። በተመሳሳይ መልኩ ዛሬም 'የታሰሩ ሰዎች ከእስር ይለቀቁ' በማለት አደባባይ እንደወጡ እና ከጸጥታ አካላት ጋር እንደተጋጩ እንዲሁም በተከፈተው ተኩስ ሁለት ሰዎች መጎዳታቸውን አስረድተዋል።እስካሁን የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ የሞከሩ 9 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የተናገሩት ከንቲባዋ፤ ዛሬ ተከስቶ የነበረው ሁከት በቁጥጥር ሥር ውሎ በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ጨምረው ተናግረዋል።አዳማ አዳማ ከሰሞኑ ሁኔታ በተሻለ መልኩ አንጻራዊ ሰላም እንደሚታይባት በስፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን ዘግቧል። • ቅዱስ ሲኖዶሱ ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ እና ከመከላከያ ሚንስትሩ ጋር ተወያየ የአዳማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ራውዳ ሁሴን በከተማዋ ዛሬ ጠዋት የታውሞ ሰልፍ ለማካሄድ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ ጥሪዎች ሲደረጉ መቆየታቸውን ጠቅሰው የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ይህን ለማስቆም ጥረት ማድረጋቸውን ተገልጸዋል። በነዋሪዎች ዘንድ ከሚስተዋለው የደህንነት ስጋት ውጪ ከተማዋ ከሞላ ጎደል ወደ ቀድሞ የንግድ እንቅስቃሴ እየተመለሰች መሆኑን ሪፖርተራችን ዘግቧል። ሰበታ ሰበታ ከተማ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች መሆኑን የከተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ታዬ ዋቅኬኔ ተናግረዋል። • "ክስተቱ 'የግድያ ሙከራ' እንደሆነ ነው የምረዳው" ጀዋር መሐመድ የንግድ ተቋሞቻቸውን ዘግተው ከነበሩት እና ከአጠቃላይ ነዋሪው ጋር ውይይት ማድረጉ እንደቀጠለ ተናግረው፤ መልካም የሚባል ለውጦች እየተመለከቱ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ባሌ እና ጎባ ከተሞች በማሕበራዊ ሚዲያዎች ዛሬ ጠዋት በባሌ ዞን በሚገኙ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ሲጠሩ ነበር። ይሁን እንጂ በከተሞቹ ዛሬ ምንም አይነት የተቃውሞ ሰልፎች አለመካሄዳቸውን ከነዋሪዎች ሰምተናል። በተመሳሳይ መልኩ በነዋሪዎች ዘንድ ካለው የደህንነት ስጋት ውጪ በከተሞቹ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
xlsum_amharic-train-292
https://www.bbc.com/amharic/news-52805122
በትግራይ ክልል የተፈጠረው ምንድን ነው?
ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ተቃውሞ በማሰማት ላይ እንደሆኑ በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ሲነገር ቆይቶ ነበር።
[ "ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ተቃውሞ በማሰማት ላይ እንደሆኑ በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ሲነገር ቆይቶ ነበር።" ]
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይም ጉዳዩን በተመለከተ በሽሬ እንደስላሴ እና በዋጅራት አካባቢዎች የመልካም አስተዳደር፣ የመሰረተ ልማት እንዲሁም ከሥራ ዕድል ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት የተቃውሞ ሰልፎች እንደተካሄዱ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያውን ጨምሮ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይህንንም ተከትሎ የትግራይ ክልል መንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በየትኛውም ቦታ "የተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ የተፈጠረ የሰላም መደፍረስና ግርግር ፈፅሞ ያልተሰማና መሬት ላይ የሌለ ነው" በማለት ዘገባዎቹን አስተብብሏል። መግለጫው ጨምሮም "በሽረ እንዳስላሰና አከባቢው እንዲሁም በዋጅራትና አከባቢው ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ፣ ፍትህ መጓደል አለ የሚባለው የተፈበረከ ሐሰተኛ፣ የበሬ ወለደ ወሬ ነው" ሲል አጣጥሎታል። በተጨማሪም "ሐሰተኛ ወሬ በማሰራጨት፣ የተጠመዱት" ባለቸው የመገናኛ ብዙሃን ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንም "በሚዲያዎቹ የተሰራጨውን ሐሰተኛ የበሬ ወለደ ወሬ አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ" የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጠይቋል። ቢቢሲ ከወጀራትና ከሽረ እንዳስላሰ 70 ኪሎሜተር እርቃ ከምትገኘው ማይሃንሰ አስተዳዳሪዎችና ከነዋሪዎች እንደተረዳው በአካባቢዎቹ ጥያቄዎችን በማንሳት ለቀናት የዘለቀ ተቃውሞዎችና የመንገድ መዝጋት ክስተቶች አጋጥመዋል። የተቃዋሚው አረና ትግራይ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አምዶም ገብረስላሰ በማይሃንሰን እና ወጀራት በተባሉ የትግራይ ክልል አካባቢዎች የተነሱ ሕዝባዊ ጥያቄዎች አሁንም አንዳልበረዱ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አቶ አንዶም ገብረስላሰ እንደሚሉት ለተቃውሞዎቹ መቀስቀስ ምክንያቶቹ ከዚህ ቀደምም ሲንከባለል የቆየ የወረዳነት ጥያቄ ሲሆን ተገቢ ምላሽ አላገኘንም ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ምዕራባዊ ዞን የሚወስደውን የዳንሻ መንገድ ከዘጉ ዘጠኝ ቀናት አስቆጥረዋል፤ አሁንም ቢሆን "ጥያቄውም አልተፈታም፤ መንገድም አልተከፈተም" ብለዋል። መነሻ ለዚህ ሁሉ እንደመነሻ የሚጠቀሰው የወረዳ ማዕከል እንሁን በሚል የሁለት ቀበሌ ነዋሪዎች ያነሱት ጥያቄ ነው። ጥያቄ የቀረበባቸው ቀበሌዎች በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሚገኘው ማይ ሓንሰ እና በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ የሚገኘው ባሕሪ ሓፀይ መሆናቸውን የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። ሽረ አካባቢ የምትገኘው የማይሃንሰን ሕዝባዊ ቅዋሜ ከወረዳነት ጥያቄ በዘለለ፥ በስፍራው በተመደቡ አስተዳዳሪዎች ቅር መሰኘትንም ያካትታል ይላሉ የተቃዋሚ ፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ። በደደቢት እና አደጋ ሕብረትም ተመሳሳይ ድርብ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ነው አቶ አንዶም የሚናገሩት። ከጥቂት ዓመታት በፊት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፤ ‘ተሃድሶ’ ባካሄደበት ወቅት፤ በትግራይ የአስተዳደር መዋቅር ለውጥ እንደሚያደርግ አስታውቆ ነበር። ይህም አስተዳደራዊ ለውጥ ያልተማከለ አስተዳደር ለመፍጠር፣ ሥልጣንን በዋናነት ወደ ወረዳዎችና ጣብያዎች ማውረድ የሚል ነበር። በዚህም መሠረት አዲስ የወረዳ እና የጣብያ አደረጃጀት እንዲኖር ተደረጓል። የአንድ ወረዳ ማዕከል የሚሆነው ቀበሌ የትኛው ይሁን? የሚለው ግን በአንዳንድ አካባቢዎች አወዛጋቢ ጥያቄን ማስከተሉንና አሁን ለተፈጠረው ነገር መነሻ እንደሆነ ይነገራል። በሰሜን ምዕራብ ትግራይና በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ የሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ጥያቄ ያቀረቡትም እኛ የወረዳችን ማዕከል መሆን አለብን ብለው ነው። በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የወረዳ ምክር ቤት የወረዳው ማዕከል ብሎ የወሰነውን ቀበሌ ያልተቀበሉ የሌላ ቀበሌ ነዋሪዎች፣ መንገድ ዘግተው መኪና አናሳልፍም ብለው ለተቃውሞ መውጣታቸውን ከዘጋቢያችን ለመረዳት ችለናል። በአካባቢው አዲስ የተዋቀረ አስገደ የሚባል ወረዳ አለ። በወረዳው ከሚገኙ ሕፃጽ፣ ዕዳጋ ሕብረት፣ ክሳድ ጋባ እና ማይ ሓንሰ የተባሉ ቀበሌዎች ለወረዳው ማዕከልነት ተወዳድረው ነበር። የወረዳው ምክር ቤት ክሳድጋባ ማዕከል እንድትሆን ውሳኔ ቢያስተላለፍም፤ የማይ ሓንሰ ነዋሪዎች ውሳኔውን አልተቀበሉም። ተቃውሞና መንገድ መዝጋት በሰሜን ምዕራብ ዞን የማይ ሓንሰ ነዋሪዎች፡መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ ማሰማት ከጀመሩ 11 ቀናት አልፎባቸዋል። ነዋሪዎቹ የዞኑ አተዳዳር እና የፀጥታ አካላት ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም የሚሉ ሲሆን ጥያቄያቸው ከክልሉ መንግሥት መልስ እስካላገኘ ድረስ ወደ ቤታቸው እንደማይመለሱ ይናገራሉ። የማይ ሓንሰ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብርሃለይ ገብረእየሱስ "የወረዳው አስተዳዳሪዎች ለራሳቸው ወደ ሽረ እንዲቀርባቸው ክሳድ ጋባ ወረዳው ትሁን አሉ። ህዝቡ ደግሞ የተሰጠንን ወረዳ የመሆን መብት ለምን እንከለከላለን በማለት ነው የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄደ ያለው" በማለት ገልፀዋል። ሌላኛዋ የማይሓንሰ ነዋሪ ወይዘሮ ለተብርሐን ደግሞ "ውሳኔው በጉቦ እና በሙስና በድብብቆሽ የተደረገ ነገር ነው" በሚል ነዋሪው ለተቃውሞ እንደተነሳ ይጠቅሳሉ። የኮሮናቫይረስ ወረረሽኝ ባለበት በዚህ ወቅት ለተቃውሞ መውጣታቸውን በሚመለከትም ሲናገሩ "ሕዝቡ ስለተቸገረ እንጂ ወዶ አይደለም። ሞትም ቢሆን እንሙት። ፍትህ ማጣትም ሞት ነው፤ በኮሮና መሞትም ሞት ነው" ብለዋል። የአስገደ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብቶም አበራ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የአካባቢው ወጣቶች ለሰባት ቀናት ያህል መንገድ ዘግተው ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል። “የወረዳው ምክር ቤት የወሰነውን የማይቀበሉ ከሆነ የክልሉን ኃላፊዎች ማነጋገር እንዳለባቸው ገልጸንላቸዋል። ቢሆንም ኃላፊዎች መጥተው ካላናገሩን እኛ ወደ ክልል አንሄድም ብለዋል” ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው አስረድተዋል። የወረዳው አስተዳደር የአገር ሽማግሌና የሐይማኖት መሪዎች በማነጋገር፤ ወጣቶቹ በሰላማዊ መንገድ እንዲግባቡ ለማድረግ እየጣሩ መሆኑንም አክለዋል። "ጥያቄያቸው በሰላማዊ እና ዲሞክራስያዊ መንገድ ለሚመለከተው አካል እንዲያቀርቡ እየሰራን ነው" የሚሉት አቶ ሃብቶም፡ መንገድ መዝጋት ግን ህጋዊ እንዳልሆነ እና ይህም ለህዝቡ በግልፅ እንዲነገረው ተደርጓል በማለት ስለሁኔታው አስረድቷል። የአክሱም ዩኒቨርሲቲው መምህር ዳንኤል ዘሚካኤል,, ዪኒቨርሰቲው በተለያዩ ዞኖች በህብረተሰብ የኮሮናቫይረስ ግንዛቤ እንዲኖር እየሰራው ባለው ስራ በቡድን ወደ ምዕራባዊ ዞን ከላካቸው አንዱ ነው። ዘጠኝ በመሆንም ወደ ምዕራባዊ ዞን በማይ ሓንሰ ሲጓዙ በዛ ማለፍ እንደማይቻል፣ በማይ ሓመንሰ ነዋሪዎች እንደተነገራቸው እና ይህን ብቻ ሳይሆን ወደ መጡበት አካባቢ እንዳይመለሱም ከቡድኑ እና መኪኖቻቸው ጋር በአካባቢው ነዋሪዎች እንዲታገቱ መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በማይ ሓንሰ ወደ 30 መኪኖች ታግተው እንደነበረ እና ሌሎቸ አምልጠው በመውጣት አሁን 18 እንደቀሩ የሚናገረው መምህር ዳንኤል፣ ህዝቡ 24 ሰዓታት ተሰባስቦ እንደሚውል እና እንደሚያድር ይናገራሉ። ለሊት በአስፋልቱ ዳር ዱንኳን ጥለው ከ 200 እስከ 300 ሰዎች አንድ ዱንኳን ላይ እንደሚያድሩ እና ይህም ለህዝቡ ጤና አደገኛ እንደሆነ ይናገራሉ። በህብተረሰብ የኮሮናቫይረስ ግንዛቤ ለመፍጠር ተጉዘው በመንገዳቸው እንዳያልፉ እና እንዳይመለሱ የተደረጉት እነ አቶ ዳንኤል እና ባለደረቦቻቸው በማይ ሓንሰ ለሶስት ቀናት እንዲቆዩ ተገደዋል። ለሶስት ቀናት በመኪናቸው እያደሩ፣ ህዝቡ ለበሽታው ያለውን ግንዛቤ እንደተረዱ ስለ ኮሮናቫይረስ የቀረፅዋቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶችን ማስደመጥ መጀመራቸውን ይናገራሉ። "ቢሆንም እንድናጠፋው ተነገረን። ለሌላ አካባቢ ይዘነው የሄድነው መፀዳጃ አልኮል ለአካባቢው የጤና ሃላፊ ብንሰጥም ተወሰነ ለህዝቡ መስጠት በቢሮው ነው የቆለፈው። ህዝቡ ቀን ላይ ሲሰበሰብ እና ሲመክር ይውልና፤ ለሊት በጋራ ሲጨፍር ነው የሚያድረው" ይህ ቦታም አስጊ ነው በማለት ፍራቻቸውን ይገልጻሉ። በማይ ሓንሰ ከታገቱት ከባባድ መኪኖች መካከል፣ ከጂቡቲ የመጡ 5 ሹፌሮች እንዳሉ እና ሙቀታችን ተለክተናል በማለት ብዙ ሰዎች ጋር መነካካት እንደነበራቸው ይናገራሉ። የማይ ሓንሰ ነዋሪዎች ባንክ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች አግልገሎት እንዳይሰጡ በግዴታ እንዲዘጉ ስለተደረጉ ቆይታቸው ከባድ እንደነበረ ይገልፃሉ። የማይ ሓንሰ ነዋሪዎች ግን የዞን አስተዳደር እና ፖሊስ ጥያቄያቸውን ከመስማት ይልቅ እኛ ያልናችሁ ስሙ በማለት መፍትሄ እንዳልሰጣቸው ይገልፃሉ። የዞኑ ፖሊስም፡ ለአካባቢው ሚሊሻዎችም መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ እያሰማ ያለውን ሕዝብ በመበተን መንገዱ እንደከፍቱ አልያም ሚልሻዎቹ ትጥቃቸው እንዲፈቱ ጫና በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ ገልፀውልናል። ወይዘሮ ለተብርሃን "ሚሊሻዎቹ፡ እኛ የህዝብ ነን፤ እናንተ አላስታጠቃችኑም። ህዝብ ያለን እንጂ እናንተ ያለቹን አንሰመማም። ከፈለጋቹ ወደ ህዝቡ ቅረቡ እና እንረዳዳ ሲሉዋቸው ግዜ፡ በሉ ፈርሙ ሲሉዋቸው ህዝቡ ይህን ስለአወቀ ውጡልን በማለት አባረርናቸው" በማለት በሚሊሻዎቹ እየተፈጠረ ያለውን ጫና ገልፀውልናል። በማይ ሓንሰ ሚሊሻ የሆነት አቶ ገብረክርስቶስ ገብረኣረጋዊም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ተሰባስቦ ተቃውሞ ማሰማት ጥሩ እንዳልሆነ ሕዝቡን ለማስረዳት እንደሞከሩ ገልጸው "የዞኑ አስተዳዳሪዎች ከኮሮና የሚብሱ እንጂ የሚሻሉ አይደሉም" በማለት ሰሚ አለማግኘታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። "የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝቡን የማትበትኑ ከሆነ ትጥቃችሁን እንድትፈቱ ብሎናል። እኛም ከእናንተ ጋር ትውውቅ የለንም ሕዝቡ ነው ያስታጠቀን፤ ሕዝብ ትጥቃች እንድትፈቱ ካለን እንፈታለን። ካልሆነ ግን ለእናንተ ብለን ትጥቅ አንፈታም ብለናቸዋል" በማለት ህዝቡ እያነሳ ያለው ጥያቄ ትክክል እንደሆነ ይናገራሉ። ወጀራት በተመሳሳይ ሁኔታ በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ወጀራትና ሕንጣሎ የተባሉ ከዚህ ቀደም አንድ የነበሩ፤ አሁን ግን ለሁለት የተከፈሉ ወረዳዎች አሉ። በወጀራት ወረዳ ከሚገኙት ባሕሪ ሓጸይ እና ዓዲ ቀይሕ የተባሉ ቦታዎች መካከል የወረዳ ማዕከል መሆን ያለበት ባህረሀፀይ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ጥያቄ አቅርበዋል። የአረናው አባል አቶ አንዶም እንደሚሉት የወረዳነት ጥያቄ የተነሳበት የወጀራት ሕዝባዊ ተቃውሞ አራተኛ ቀኑን ይዟል። እዚህም አካባቢውን የሚያስተዳድሩት 'የዞን እና የክልል መልዕክተኞች ናቸው እንጅ እኛን አይወክሉንም' በሚለው ቅሬታ የተቃውሞው አካል ሆኗል ይላሉ። "ጥያቄው [ወረዳነት] ተፈቅዶልን እያለ፤ እንደገና ተከልክለናል የሚል ነው።" የቀድሞው የወጀራት ወረዳ ማዕከል የነበረችው ጣቢያ ባሕሪ ሓፀይ ነዋሪዎቿ፤ ባሕሪ ሓፀይ የወረዳው ማዕከል ስለነበረች ከጣቢያ ዓዲ ቀይሕ ጋር መወዳደር የለባትም በማለት ይጠይቃሉ። ይሁን እንጂ የወጀራት ምክር ቤት የወረዳዋ ማዕከል ማን ትሁን? በሚል ውሳኔ እንዳላሳለፈ የወረዳው አስተዳደር አቶ ዳርጌ ፀጋይ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጣብያ ባሕሪ ሓፀይ ሰላዊ ሰልፍ ከማካሄድ ጥያቄ ከማቅረብ ውጪ በወጣቶቹ ላይ የተወሰደ እርምጃ እንደሌለ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል። "ወጣቶቹ ሥርዓት ያላቸው ናቸው። እስከአሁንም በአካባቢው የደረሰ ችግር የለም። አሁን ከእነሱ ጋር ንግግር ጀምረናል። መንግሥት ጥያቄያችንን ሰምቶ የቀድሞ ወረዳችን ይመልስልን ነው የሚሉት" ብለዋል። የወረዳው ምክር ቤት የትኛው ወረዳ ማዕከል እንደሚሆን ውሳኔውን ባያስተላልፍም፤ የባህረሀፀይ ነዋሪዎች ከዚህ በፊት የወረዳው ማዕከል ስለነበርን ከሌሎች ጋር መወዳደር አንፈልግም ብለዋል። በክልሉ መዲና መቀለ ከሳምንት በፊት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የወጣውን ደንብ ተላልፈዋል ከተባሉ ወጣቶች ጋር በተከሰተ አለመግባባት የአንድ ሰው ህይወት መጥፋቱ እታወሳል። አቶ አንዶም እንደሚሉት በጸጥታ ኃይል አባላት በተተኮሰ ጥይት ከሞተው ወጣት በተጨማሪ ሁለት ሰዎች ከቆሰሉ በኋላ "በአካካቢ ባሉት 05፣ 06 በሚባሉ ቀበሌዎችና አይደር የሚባለ ሠፈር ተቃውሞዎች ተቀስቅሰው ነበር" ብለዋል። 'መንገድ ተከፍቷል' " የክልሉ መንግስት መፍትሄ ይስጠን" በሚልም ለአንድ ሳምንት መንገድ ዘግተው የነበሩ ነዋሪዎቹ የክልሉ መንግሥት ቀርቦ እንዲያናግራቸው በጠየቁት መሰረት በነዋሪዎቹና በመንግሥት አካላት መካከል ውይይት መደረጉን ሰምተናል። መንገዱን እንዲከፍቱና ጥያቄያቸውን በህጋዊ መንገድ ለማቅረብ መስማማታቸውን የወረዳው አስተዳደር አቶ ሀብቶም አበራ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ነዋሪዎቹ ጥያቄያቸው ለክልሉ መንግስት የሚያቀርብላቸው 14 አባላት ያሉት ኮሚቴ ማቋቋማቸውን ገልፀዋል። መንገዱም ከዛሬ ከሰአት ጀምሮ መከፈቱንም ጨምረው ተናግረዋል።
xlsum_amharic-train-293
https://www.bbc.com/amharic/news-55004605
ከሬዲዮ ሞገድ አፈና እስከ ርዕሰ መስተዳድር፡ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ማናቸው?
ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ዋነኛው ተዋናይ የሆነው የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ መሪና የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የፍጥጫው ቀዳሚ ገጽታ ናቸው። ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ማናቸው?
[ "ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ዋነኛው ተዋናይ የሆነው የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ መሪና የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የፍጥጫው ቀዳሚ ገጽታ ናቸው። ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ማናቸው?" ]
ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ደርግን ለመገርሰስ የተካሄደውን ትግል የተቀላቀሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው ነበር። አብዛኛውን ሕይወታቸውን ያሳለፉት የህወሓት አባል ሆነው ነው። የቀድሞው የሽምቅ ተዋጊ ደብረጽዮን (ዶ/ር) በሬዲዮ ሞገድ አፈናና ጠለፋ (ጃሚንግ) ይታወቃሉ። የወቅቱ የህወሓት ሊቀ መንበርና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት ደብረጽዮን ባለ ትዳርና የትንሽ ልጅ አባት ናቸው። የቅርብ ጓደኛቸውና የትግል አጋራቸው ዓለማየሁ ገዛኸኝ፤ ደብረጽዮን በቴክኒክ ክፍል እንዲመደቡ ለህወሓት አመራሮች መጠቆማቸውን ያስታውሳሉ። ሁለቱም በተራራማዋ ትግራይ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ሲያጠናቅቁ፤ ደብረጽዮን ቴክሊካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የተሻለ ክህሎት እንዳላቸው ማስተዋላቸውን የትግል ጓዳቸው ይናገራሉ። ደብረጽዮንን የሚገልጿቸው "ብሩህ፣ ቁጥብ፣ ከተሜ" በማለት ነው። "ከወዳደቁ ነገሮች የራሱን አምፖል ይሠራ ነበር" ያደጉት ሽሬ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሳሉ ያረጀ ባትሪ፣ ራድዮ እና የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች እየሰበሰቡ ይጠግኑ እንደነበር አቶ ዓለማየሁ ያስታውሳሉ። "በከተማችን ማንም ሰው መብራት ሳይኖረው ከወዳደቁ ነገሮች የራሱን አምፖል ይሠራ ነበር" ይላሉ። ህወሓት የያኔውን የኢትዮጵያ ወታደራዊ ኃይል ላይ እንዲሰልል በማስቻል እንዲሁም የራድዮ ሞገድ በማቋረጥ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ ሲሆን፤ በህወሓት የቴክኒክ ክፍል ከፍተኛ ደረጃ ላይም ደርሰዋል። "የህወሓት የነፃነት ታጋዮች የጠላትን እንቅስቃሴ ቀድመው እንዲያውቁ በማስቻል እንድናሸንፍ ረድቶናል። መገናኛ መስመራቸው ስለሚቋረጥ ጥቃት ሲደርስባቸው እርስ በእርስ መነጋገር አይችሉም ነበር።" ደብረጽዮን ክህሎታቸውን ለማዳበር በወቅቱ በሐሰተኛ ፓስፖርት ወደ ጣልያን አቅንተዋል። ወደ አገር ቤት ሲመለሱ የህወሓትን የመጀመሪያ ራድዮ ጣቢያ ድምጺ ወያነ መስርተዋል። በትግርኛ መርሃ ግብር የሚያሰራጭ ጣቢያ መኖሩ የክልሉን ተወላጆች አኩርቷል። "ከተራራው ተንሸራቶ አተረፍነው" በደርግ ሰላዮች እይታ ውስጥ ላለመግባት በሌሊት ተጉዘው ተራራ ላይ አንቴና ይሰቅሉ እንደነበር ሌላው ሽምቅ ተዋጊ ማሾ ገብረኪዳን ያስታውሳሉ። "አንድ ምሽት ከተራራው ተንሸራቶ እኔና ሌሎች ጓዶቻችን አተረፍነው። ሞቶ ቢሆን ኖሮ ይሄ ራድዮ ጣቢያ ይከፈት ነበርን? ብዬ እጠይቃሉ" ይላሉ። ዋና መቀመጫውን መቀለ ያደረገው ድምጺ ወያነ አሁንም በተለያዩ ቋንቋዎች በሚያሰራጨው መርሃ ግብር፤ ጦርነቱን በተመለከተ የህወሓትን መግለጫዎች ያስተላልፋል። ጣቢያው ስለ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰሉ ትችቶች ያስተናግዳል። የፌደራል መንግሥት የስርጭት ሞገዱን ቢቆርጠውም በነጋታው መርሃ ግብር ወደማስተላለፍ ተመልሰዋል። "አልበሰልክም፤ ትክክለኛው እጩ አይደለህም ብዬዋለሁ" ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ሥልጣን የመጡ ሰሞን ከርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን (ዶ/ር) ጋር ተወዳጅተው ነበር። ዐብይ (ዶ/ር) በመቀለ አቀባበል ሲደረግላቸው፤ "ትግራይ የታሪካችን መሠረት ናት። የውጪ ወራሪዎች [ጣልያን እና ግብፅን ጨምሮ] ተሸንፈው የተዋረዱበት ቦታ ነው። በዘመናዊ የአገራችን ታሪክ ትግራይ የኢትዮጵያ ማህጸን ናት" ብለው ነበር። በወቅቱ ደብረጽዮን (ዶ/ር)፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ሰላም በማውረዳቸው አሞግሰዋቸው ነበር። የሰላም ስምምነቱ ለዓመታት የዘለቀውን ጦርነትም ሰላምም ያልነበረበትን ሁኔታ ለውጧል። ያኔ፤ "ዐብይ ወደ ኤርትራ ተጉዞ ከኢሳያስ ጋር ተገናኝቷል። ለዓመታት ይህን ማድረግ አልተቻለም ነበር። ትልቅ ነገር ነው። ለአገሪቱ የጎላ እድል ይዞ ይመጣል" ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረው ነበር። በሁለቱ መሪዎች መካከል ያለው ውጥረት በጊዜያዊነት ቢሆንም ተሸፍኖ ነበር። በኢሕአዴን ውስጥ ለመሪነት ውድድር ሲካሄድ ጠቅላይ ሚንስትሩ ያሸነፉት ደብረጽዮንን ረትተው ነበር። "አልበሰልክም፤ ትክክለኛው እጩ አይደለህም ብዬዋለሁ" ሲሉም ደብረጽዮን እአአ 2019 ላይ ለፋይናንሽያል ታይምስ ጋዜጣ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር። ድጋፍ እና ተቃውሞ ለ27 ዓመታት በኢሕአዴግ ውስጥ ህወሓት የበላይነት ሚና ሲጫወት በጭቆና እና ሙስና እንደመወንጀሉ የደብረጽዮን መሸነፍ ተጠባቂ ነበር ማለት ይቻላል። ስለ ደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚሰጡ አስያየቶች ድጋፍም ነቀፋም የቀላቀሉ ናቸው። ተቺዎቻቸው እንደሚሉት፤ የኢትዮጵያ ደኅንነት ምክትል ሳሉ ተቃዋሚዎችን ይሰልሉ፣ ተቃውሞን ያዳፍኑ ነበር። በተቃራኒው ደጋፊዎቻቸው የኢትዮጵያን የቴሌኮምንኬሽን ዘርፍን አዘምነዋል ይላሉ። በኢትዮጵያ የተንቀሳቃሽ ስልክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ፕሮጀክት ጀምረዋል። በሌላ በኩል መንግሥት በቴሌኮም ዘርፉ የበላይነት መያዙ ያስተቸዋል። ተቃውሞ ሲኖር የኢንተርኔት አገልግሎት በማቋረጥም መንግሥት ይወቀሳል። የፖሊሲ ጉዳዮች ባለሙያው ዳደ ደስታ "አብዛኞቹ የቴሌኮም ፕሮጀክቶች የሚመሩት በእሳቸው ነበር። አዲስ አበባ ያለው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ የእሳቸው ሐሳብ ነው። አሻራቸውን በብዙ የመንግሥት ድርጅቶች ላይ አሳርፈዋል" ይላሉ። "ልማት እንጂ ጦርነት አንፈልግም" ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ (ዶ/ር) ኢሕአዴግን አክስመው ብልፅግና ፓርቲን ሲመሠርቱ የህወሓትና የኢሕአዴግ ግንኙነት ተቋረጠ። ደብረጽዮን (ዶ/ር) ወደ ትግራይ ሲመለሱ እንደ ለውጥ ኃይል ይታዩ ጀመር። አራት አዳዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎች በትግራይ ክልላዊ ምርጫ እንዲሳተፉ ፈቅደዋል። በተደጋጋሚ "በሬ ለሁሉም ክፍት ነው" ሲሉም ይደመጣሉ። ሌላው የሚታወቁበት አባባል "ልማት እንጂ ጦርነት አንፈልግም" የሚለው ነው። አሁን ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱበት እና ከ30,000 በላይ ዜጎችን ለስደት የዳረገ ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። ጦርነቱ፤ መንገድና ሕንጻዎችን ጨምሮ መሠረተ ልማት ላይም ውድመት አስከትሏል። "ደብረጽዮን ይህንን ጦርነት እንደ እርግማን ነው የሚያዩት" ሰሉ ዳደ ያስረዳሉ። አያይዘውም ህወሓት በፌደራል መንግሥቱ ትግራይ ላይ የሚሾም የአስተዳደር መዋቅርን አጥብቆ እንደሚታገል ይናገራሉ። "ከኤርትራ ጋር ጦርነት ውስጥ ነበሩ። ከደርግ ጋርም ታግለዋል። ስለዚህ ልምዱ አላቸው። ጦርነት የሕዝብ ይሁንታን ይፈልጋል። ያ ደግሞ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ አለ" ሲሉም ያብራራሉ። ተንታኙ ግጭቱ ረዥም እንደሚሆን ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በበኩላቸው የህወሓት አመራሮችና ወታደራዊ ባለሥልጣኖችን ለፍርድ አቅርበው ጦርነቱን እንደሚያሸንፉ እርግጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
xlsum_amharic-train-294
https://www.bbc.com/amharic/news-55516802
[ምልከታ] ፡ ለዘመናት የዘለቀው የኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር አለመግባባት
በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ለዘመናት በቆየው ውዝግብ ምክንያት በሁለቱ አገራት ሠራዊቶች መካከል የሚደረግ ግልጽ ወታደራዊ ግጭት ከዚህ በፊት እምብዛም አጋጥሞ ባያውቅም በቅርቡ በድንበር አካባቢ የታየው ሁኔታ ግን ነገሮች እየተቀየሩ መሆናቸውን ያመለክታል።
[ "በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ለዘመናት በቆየው ውዝግብ ምክንያት በሁለቱ አገራት ሠራዊቶች መካከል የሚደረግ ግልጽ ወታደራዊ ግጭት ከዚህ በፊት እምብዛም አጋጥሞ ባያውቅም በቅርቡ በድንበር አካባቢ የታየው ሁኔታ ግን ነገሮች እየተቀየሩ መሆናቸውን ያመለክታል።" ]
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለዚህ ችግር ቀዳሚ ምክንያት የሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ ግዛት ከሆነው ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰነውና የሱዳን የዳቦ ቅርጫት ተብሎ በሚጠራው የገዳሪፍ ግዛት ውስጥ በሚገኘው አል ፋሻጋ አካባቢ የግዛት ይገባኛል ነው። ሁለቱን አገራት የሚለየው ድንበር መልክአ ምድራዊ አቀማመጦችን በመጥቀስ ከሚገለጸው ውጪ በመሬት ላይ በግልጽ ተለይቶ የተካለለ አይደለም። የቅኝ ግዛት ስምምነቶች በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ድንበሮች በጣሙን አወዛጋቢ ናቸው። ከአስርት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር በኦጋዴን የተነሳ ጦርነት አድርገዋል። እንዲሁም ከ20 ዓመታት በፊት ደግሞ በትንሿ ባድመ ይገባኝል ምክንያት ኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ውስጥ ገብተው ነበር። በጦርነቱ 80 ሺህ የሚደርሱ ወታደሮች መሞታቸው የሚነገር ሲሆን በዚህም ምክንያት በሁለቱ አገራት ፍጥጫ ውስጥ ቆይተዋል። በተለይ ደግሞ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ለኤርትራ ከወሰናቸው ግዛቶች ኢትዮጵያ ለመውጣት ፈቃደኛ ባለመሆኗ አለመግባባቱ ለዓመታት ቆይቷል። እነዚህ ቦታዎች በዚህ ዓመት በትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ውጊያ ተከትሎ የኤርትራ ወታደሮች መልሰው ተቆጠጥረዋቸዋል። ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያና ሱዳን ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረውን 744 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ድንበራቸውን ለይቶ ለማመላከት የሚያስችል ንግግርን መልሰው ጀመሩ። በዚህ መፍትሄ ለመስጠት አስቸጋሪ የሆነው አካባቢ ፋሽጋ የሚባለው ነበር። በ1902 እና በ1907 (እአአ) የነበረው የቅኝ ግዛት ስምምነት መሰረት ዓለም አቀፉ ድንበር ወደ ምሥራቅ ይዘልቃል። በዚህም ሳቢያ መሬቱ ወደ ሱዳን የሚካተት ይሆናል። ነገር ግን ቦታው ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት ሲሆን የግብርና ሥራ በማከናወንም የሚጠበቅባቸውን ግብር ለኢትዮጵያ መንግሥት ሲከፍሉ ቆይተዋል። የሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት አወዛጋቢውን ቦታ ይዘው እንደሚቆዩ አሳውቀዋል 'ድብቅ ስምምነት' ሁለቱ አገራት ሲደረጉ በነበረው የድንበር ድርድር አማካይነት በ2008 (እአአ) ላይ ከመግባባት ደረሱ። በዚህም ኢትዮጵያ ለሕጋዊው ድንበር ዕውቅና ስትሰጥ ሱዳን ደግሞ ኢትዮጵያውያኑ በስፍራው ያለችግር ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ ፈቀደች። ይህም አስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በድንበር አካባቢ ያሉ የነዋሪዎችን ህይወት ሳያደናቅፍ ኢትዮጵያ ግልጽ የድንበር መለያ እንዲኖር እስክትጠይቅ ድረስ ቀጥሎ ነበር። በሁለቱ አገራት መካከል ከስምምነት የተደረሰበትን የዚህ የድርድር ልዑክ የተመራው የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣን በሆኑት በአባይ ፀሐዬ ነበር። ህወሓት ከማዕከላዊው መንግሥት ስልጣን ሲወገድ የአማራ ብሔር መሪዎች ከሱዳን ጋር የተደረሰው ስምምነት በአግባቡ ሳያውቁት የተደረገ ድብቅ ውል ነው ሲሉ ተቃውመውታል። በአሁኑ ጊዜ በፋሽጋ አካባቢ ለተከሰተው ግጭት ሁለቱም ወገኖች የየራሳቸውን ምክንያት ያቀርባሉ። ነገር ግን የተከሰተው የሚያከራክር አይደለም፤ በዚህም የሱዳን ሠራዊት ኢትዮጵያዉያኑን ከሚኖሩባቸው መንደሮች ለቀው እንዲወጡ አድርጓል። በቅርቡ ጂቡቲ ውስጥ በተካሄደው ቀጠናዊ የኢጋድ ጉባኤ ላይ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጉዳዩን ከኢትዮጵያው አቻቸው ዐብይ አህመድ ጋር አንስተው ተወያይተዋል። ስለድንበሩ ጉዳይ ድርድር ለማድረግ ቢስማሙም ሁለቱም የየራሳቸውን ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል። ኢትዮጵያ በድንበር አካባቢ ጉዳት የደረሰባቸውን ማኅበረሰቦች ሱዳን እንደትክስ ስትጠይቅ፤ ሱዳን በበኩሏ ነገሮች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ትፈልጋለች። በበርካታ የድንበር ውዝግቦች ውስጥ እንደሚያጋጥመው ሁሉም ወገን የተለያየ የታሪክ፣ የሕግና ለዘመናት የቆዩ ስምምነቶችን እንዴት መተርጎም እንዳለባቸው የየራሱ ትንታኔ አለው። ነገር ግን ይህ የሁለት ጉዳዮች ማሳያ ምልክት ነው፤ ይህም ከጠቅላይ ሚኒስርት ዐብይ የፖሊሲ ለውጥ ጋር የሚያያዝ ነው። የአማራ ክልል ኃይሎች በሁመራ ግዛት ይገባኛል በፋሽጋ አካባቢ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን የአማራ ብሔር አባላት ናቸው። ይህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገሪቱ ትልቁ ከሆነው የኦሮሞ ብሔር በኩል የነበራቸው ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ በመቀነሱ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት ትኩረት ያደረጉበት ማኅበረሰብ ነው። አማራ በአገሪቱ ሁለተኛው ትልቁ ብሔር ሲሆን በአገሪቱ የመሪነት ስፍራም ታሪካዊ ስፍራ አለው። ከወር በፊት የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል በህወሓት ኃይሎች ላይ ድል መቀዳጀቱን ተከትሎ የአማራ ክልል የግዛት ይገባኛል ጥያቄን እያነሳ ነው። የህወሓት ኃይሎች ሽንፈት ሲገጥማቸውና የአማራ ክልል ሚሊሻ ጥያቄ የተነሳባቸውን አካባቢዎች ሲቆጣጠር የራሱን ባንዲራ በመስቀል "ወደ አማራ ክልል እንኳን ደህና መጡ" የሚሉ የመንገድ ምልክቶችን አስቀምጧል። ቦታዎቹ በአማራ ክልል ጥያቄ የሚቀርብባቸው ሲሆን ወደ ትግራይ ክልል የተጠቃለሉት ህወሓት ስልጣን በያዘበት ጊዜ ነበር። ምንም እንኳን ጉዳዩ የውስጣዊ የድንበር ጉዳይ ሳይሆን ከጎረቤት አገር ጋር ያለ የግዛት ጉዳይ ቢሆንም፤ የፋሽጋው ግጭትም ተመሳሳይ የግዛት ይገባኛል ጥያቄን የተከተለ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የውጭ ግንኙነት የፖሊሲ ለውጥ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዳይፈታ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ምክንያት ሆኗል። ለ60 ዓመታት የኢትዮጵያ ስትራተጂካዊ ዓላማ ግብጽን መግታት ላይ ያተኮረ ነበር። ነገር ግን ከዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወዳጅነት እጃቸውን ዘርግተዋል። ኢትዮጵያና ግብጽ የአባይ ወንዝን የህልውናቸው ጥያቄ አድርገው ይመለከቱታል። ግብጽ በቅኝ ግዛት ዘመን ተቀመጡ ስምምነቶችን መሠረት አድርጋ በላይኛው የተፋሰሱ አገራት ውስጥ የሚገነቡ ግድቦች በውሃ ድርሻዋ ላይ የተጋረጡ አደጋዎች እንደሆኑ ትመለከታቸዋለች። ኢትዮጵያ ደግሞ የአባይ ወንዝን ለምታደርገው የኢኮኖሚ ልማት በጣሙን አስፋላጊ ለሆነው የኤሌክትሪክ ኃይል ዋነኛ ምንጭ አድርጋ ትመለከተዋለች። በግዙፉ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ውዝግብ የተነሳውም በዚህ ሳቢያ ነው። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሚያካሂደው የውሃ ዲፕሎማሲ ዋነኛው መሰረቱ በቀሪዎቹ የአባይ ወንዝ የላይኛው ተፋሰስ የአፍሪካ አገራት መካከል ተፈጥሮ የነበረው የትብብር መዋቅር ነበር። ዓላማውም በርካታ አገራትን ያካተተ በአባይ ወንዝ የውሃ ክፍፍል ላይ አጠቃላይ ስምምነት መድረስ ነበር። በዚህ መድረክ ላይም ግብጽ በቁጥር ተበልጣ የበላይነትን ማግኘት አልቻለችም። ህዳሴው ግድብም ጎርፍን በመቆጣጠር፣ የመስኖ ልማቷን በመጨመርና ርካሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት እንደሚያስችላት በመረዳት፤ ሱዳንም ከቀሪዎቹ የአፍሪካ አገራት ወገን ተሰልፋ ነበር። ግብጽ ግን በቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነት ላይ የተቀመጠውን አብዛኛውን የአባይ ወንዝን ውሃ ለማግኘት የሚያስችላትን ጥቅም ለማስከበር ቀጥተኛ የሁለትዮሽ ድርድር ፈልጋ ነበር። በጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስርት ዐብይ በሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ሩሲያ ሶቺ በሄዱበት ጊዜ ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲሰ ጋር ተገናኝተው ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ባልተገኙበት በዚህ ውይይት ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ ላይ ከምትከተለው ስትራተጂ ውጪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፕሬዝዳንት አል ሲሲ የቀረበውን በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ አሜሪካ በአሸማጋይነት እንድትገባ የቀረበውን ሐሳብ ተቀበሉት። በዚህም ሂደት አሜሪካ ከግብጽ ጎን ቆመች። ከኤርትራ ጋር የነበረውን ውጥረት ለማስወገድ የቻሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተመሳሳይ ከግብጽ ጋርም ከስምምነት እንደሚደርሱ አስበው ነበር፤ ግን አልሆነም። እንዲያውም እራሳቸውን አጣብቂኝ ውስጥ አስገቡ። በዋሽንግተኑ ድርድር ላይ የተጋበዘችው አገር ለዓመታት በአሜሪካ ሽብርተኞችን ከሚደገፉ መንግሥታት ዝርዝር ውስጥ ገብታ የገንዘብ ማዕቀብ ስር የቆየችውና ለአሜሪካ ተጽእኖ ተጋላጭ የሆነችው ሱዳን ነበረች። በድርድሩም ሱዳን ከግብጽ ጋር ተስማምታ ቆመች። በኢትዮጵያውያን ዘንድ አሜሪካ ያቀረበችው የስምምነት ሐሳብ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን፤ በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሐሳቡን ውድቅ ለማድረፈግ ተገደዱ። ይህንንም ተከትሎ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምትሰጠው እርዳታ የተወሰነውን አገደች። የአሜሪካው ፕሬዝዳንትም ግብጽ የህዳሴውን ግድብ "ልታፈነዳው" ትችላለች ሲሉ ያስጠነቀቁ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም ግድቡ በሚገነባበት አካባቢ ማንኛውም በረራ እንዳይካሄድ አደረገች። አብዛኛው የአባይ ውሃ የሚመነጨው ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ገባር ወንዞች ነው ተቃዋሚዎችን መደገፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በትግራይ ውስጥ ከተከሰተው ግጭትና በሱዳን ድንበር ካለው ውጥረት በተጨማሪ ከግብጽ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባት አይችሉም። ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ችግር በታሪክ ለረጅም ጊዜ የቆየውን ውዝግብ መልሶ እንዲያንሰራራ አድርጎታል። ከአርባ ዓመታት በፊት ሱዳን ህወሓትን ጨምሮ የብሔር ሸማቂ ቡድኖችን ስታስታጥቅ የኢትዮጵያው ወታደራዊ መንግሥት ደግሞ የሱዳን አማጺያንን ይረዳ ነበር። በአውሮፓውያኑ በ1990ዎቹ ሱዳን ታጣቂ እስላማዊ ቡድኖችን ስትደግፍ ኢትዮጵያ ደግሞ የሱዳን ተቃዋሚዎችን ትረዳ ነበር። በትጥቅ የተደገፉ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች በብዙ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ በሚያጋጥሙበት በዚህ ጊዜ፤ ሱዳን በቅርቡ የተሟላ ባይሆንም በዳርፉርና በኑቢያ ተራሮች ካሉ አማጽያን ጋር የሰላም ስምምነት ደርሳለች። በዚህ ሁኔታም አገራቱ ወደ ቆየው አንዳቸው የአንዳቸውን ሠላም ወደ ሚያናጋ ተግባር ሊመለሱ ይችላሉ። በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ከፍተኛ ከሚባለው ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ካርቱም ሄደው አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ የዲሞክራሲ መብት ጠያቂ ተቃዋሚዎችና የአገሪቱ ጀነራሎች የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰርቱ ድጋፍ ባደረጉበት ጊዜ ነው። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክም ውለታቸውን ለመመለስ በትግራይ ግጭት በተከሰተበት ጊዜ መፍትሄ ለማምጣት ለማሸማገል ሙከራ አድርገው ነበር። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይዋን በራሷ ትወጣዋለች በሚል ሳይቀበሉት ቀርተዋል። ረሃብና አሰቃቂ ታሪክ ያላቸው ስደተኞች ከትግራይ ወደ ሱዳን እየሄዱ ባሉበት ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽምግልናውን ላለመቀበል የበለጠ አስቸጋሪ ሊሆንባቸው ይችላል። ምናልባትም በሁለቱ አገራት መካከል አዲስ ዙር ድንበር ተሻጋሪ ጠላትነት ሊቀሰቀስ የሚችልበት ስጋት ያለ ሲሆን ይህም የቀጠናውን ቀውስ ሊያባብሰው ይችላል። *አሌክስ ደ ዋል በአሜሪካው ተፍትስ ዩኒቨርስቲ በሚገኘው የፍሌቸር የሕግና ዲፕሎማሲ ትምህርት ቤት ውስጥ የወርልድ ፒስ ፋውንዴሽን ዋና ዳይሬክተር ነው።
xlsum_amharic-train-295
https://www.bbc.com/amharic/44286378
ኤርትራ ውስጥ በአጋጠመ የመኪና አደጋ 33 ሰዎች ሞቱ
ትላንትና ግንቦት 20 ረፋዱ ላይ ከአስመራ ወደ ከረን በሚወስድ መንገድ በአጋጠመ የአውቶቡስ አደጋ 33 ሰዎች እንደሞቱ መንግስታዊው የዜና ማዕከል አስታወቀ።
[ "ትላንትና ግንቦት 20 ረፋዱ ላይ ከአስመራ ወደ ከረን በሚወስድ መንገድ በአጋጠመ የአውቶቡስ አደጋ 33 ሰዎች እንደሞቱ መንግስታዊው የዜና ማዕከል አስታወቀ።" ]
ከአስመራ በስተ ሰሜናዊ ምዕራብ ሽንድዋ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በአጋጠመ የአውቶቡስ መገልበጥ አደጋ ሹፌሩን ጨምሮ 11 ሰዎች በጽኑ በመቁሰላቸው ለከፍተኛ ህክምና አስመራ በሚገኘው ሐሊበት ሆስፒታል እንደተወሰዱ ዜናው በተጨማሪ አረጋግጧል። አውቶቡሱ፣ አመታዊውን የቅድስት ማርያም ክብረ-በዓልን ለማክበር የሚጓዙ 45 ሰዎች የጫነ እንደነበርና መንገዱን ስቶ 80 ሜትር ጥልቀት ያለው ገደል ውስጥ መግባቱ ተገልጧል። አደጋው የደረሰው ከተገቢው ፍጥነት በላይ በማሽከርከር ሊሆን እንደሚችል ምርመራውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኤርትራ ትራፊክ ፖሊስ ጽሐፈት ቤት መግለጡን የመገናኛ ብዙሃኑ ዘገባ ያስረዳል።
xlsum_amharic-train-296
https://www.bbc.com/amharic/news-49494997
በፈረንጅ "ናይት ክለብ" ጉራግኛ ሲደለቅ
አንድ የሆነ የአውሮጳ ጉራንጉር ውስጥ፣ «አንድ-ሁለት» ለማለት፣ ወደ አንድ የሆነ መሸታ ቤት ጎራ ስትሉ፣ ለአመል እንኳ አንድ ሐበሻ በሌለበት አንድ የፈረንጅ ቡና ቤት፣ አንድ ቀጭን ዘለግ ያለ 'ፈረንጅ'፣ ከኢትዮጵያ ሙዚቃዎች አንዱን ከፍቶ፣ ትከሻውን ሲሰብቅና ሲያ'ሰብቅ ብታዩት ምን ይሰማችኋል? ለዚያውም የብዙዬን...
[ "አንድ የሆነ የአውሮጳ ጉራንጉር ውስጥ፣ «አንድ-ሁለት» ለማለት፣ ወደ አንድ የሆነ መሸታ ቤት ጎራ ስትሉ፣ ለአመል እንኳ አንድ ሐበሻ በሌለበት አንድ የፈረንጅ ቡና ቤት፣ አንድ ቀጭን ዘለግ ያለ 'ፈረንጅ'፣ ከኢትዮጵያ ሙዚቃዎች አንዱን ከፍቶ፣ ትከሻውን ሲሰብቅና ሲያ'ሰብቅ ብታዩት ምን ይሰማችኋል? ለዚያውም የብዙዬን..." ]
ዲጄ አሌክስ በ'ኤይልሃውስ' "ፎቅና መርቼዲስ ስሜት አይሰጡኝም፤ እኔ ፍቅር እንጂ ሐብት አያሞኘኝም፤ አያገባው ገብቶ ሰው ይዘባርቃል፤ እኔ ስሜን እንጂ ስሜቴን ማን ያውቃል..." የሚለውን...ወዝዋዥና ወስዋሽ ዜማ...። ይህ ሰው አሌክሳንደር ባውማን ይባላል። 43 ዓመቱ ነው። ዲጄ ስለሆነ አሌክስ እያልን እናቆላምጠዋለን። በስዊዘርላንድ ዙሪክ ጎታርድ እና ከርን በሚባሉ የምሽት ክለቦች ውስጥ...የሙዚቃ ሸክላ 'ያቁላላል'፤ አቁላልቶ ለጆሮ ያጎርሳል፣ አጉርሶ አቅል ያስታል፤ የ60ዎቹን የኢትዮጵያን ሙዚቃ፤ የያ የወርቃማውን ዘመን። አሌክስ እንኳን ኢትዮጵያ፣ አፍሪካንም ረግጦ ስለማወቁ እንጃ...። ቱኒዚያና ደቡብ አፍሪካ አንድ ሁለቴ ገባ ብዬ ወጥቻለሁ ያለኝ መሰለኝ። ከዚያ ውጭ 'ወላ ሃንቲ'። አማርኛም ሆነ ኦሮምኛ፣ ትግርኛም ሆነ ጉራግኛ...ጆሮውን ቢቆርጡት አይሰማም። 'ወላ ሃባ...' ኾኖም የትኞቹ የኢትዮጵያ ሸክላዎች በምን ቋንቋ ፤ በምን ዘመን፤ ከምን ባንድ ጋር እንደተቀነቀኑ ሲያስረዳ አገር ፍቅር ጓሮ ወይ እሪ በከንቱ ጀርባ ያደገ ነው የሚመስለው። የዘፋኞቻችንን ታሪክና የሙዚቃ አጀማመራቸውን ሳይቀር ለጉድ ይተነትናል...ለዚያውም ብ...ጥ...ር...ጥ..ር አድርጎ...። የቢቢሲ ዘጋቢ አሌክስን ለመጀመርያ ጊዜ ያገኘው በስዊዘርላንድ፣ ዩኒቨርሲሻትስትራሰ 23 ጎዳና፤ ከታላቁ ዙሪክ ዩኒቨርስቲ ማዶ በሚገኘው «ኤይልሀውስ» ውስጥ ነበር። • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን • አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ «ኤይልሃውስ» በዓለም ዙርያ የተጠመቁ እልፍ የቢራና የድራፍት መጠጦች የሚሸጡበት ዕውቅ መጠጥ ቤት ነው። ያን ምሽት እዚያ ግቢ ጓሮ ከድራፍቱ ፉት እያሉ እራታቸውን የሚመገቡ በርካታ ስዊሳዊያን ይታዩ ነበሩ። ዲጄ አሌክስ ታዲያ ለታዳሚው የኢትዮጵያን የወርቃማውን ዘመን ሙዚቃዎች በሸክላ እያጫወተ ሲያምነሸንሻቸው አድሯል። በዚያች ድንገተኛ ምሽት ያለቀጠሮ የተገናኙት አሌክስና የቢቢሲ ዘጋቢ "አንድ ሁለት" እያሉ ለአንድ ሰዓት ያህል ቆይተዋል። ወጋቸው በጥዑም ሙዚቃዎች ሲታጀብ የሚከተለውን መልክ ይይዛል። "ፈረንጆች የኢትዮጵያን ሙዚቃ ሲሰሙ ጆሯቸው ግር ይለዋል" ዲጄ አሌክስ ሳቂታና ተግባቢ ነው። ዲጄ ኾኖ ድሮስ ሊኮሳተር ያምረዋል እንዴ?! ከፊትለፊቱ ሸክላ ማጫወቻ ጥንድ ምጣዶች አሉት። ጆሮው 'የከባድ መኪና ጎማ' በሚያካክሉ የአፍኖ- ማድመጫ (Head Phone) ተለብዷል። ባተሌ ነው። አንድ የጋለ ምጣድ ላይ አንድ የሸክላ ድስት ጥዶ፣ሌላኛው ምጣድ ላይ በስሎ የሚንተከተክ ሸክላን ያወርዳል ። ፋታ ጠብቄ የእግዜር ሰላምታ ሰጠሁት። የቢቢሲ ጋዜጠኛ መሆኔን፣ ከባላገር መምጣቴን በትህትና ገልጬ ፍቃዱ ከሆነ በየሙዚቃ መሀል እንድናወጋ ብጠይቀው «ኽረ ምን ገዶኝ» አለኝ፤ በትከሻው፣ እንዲሁም በእንግሊዝ አፍ...። ምን ዋጋ አለው ታዲያ! አይረጋም። ወጋችን ወግ ለመሆን ገና ወግ ሳይደርሰው ተስፈንጥሮ ይነሳል፤ ሌላ ሸክላ ይጥዳል። የሙዚቃ ባተሌ ነው ብያችሁ የለ! 'ኤይልሀውስ'መጠጥ ቤት በረንዳ ላይ ነው ያለነው። በዚያ ላይ 22፡00 ሰዓት ተኩል አልፏል'ኮ። ደግነቱ በአውሮፓ የበጋ ፀሐይ በጣም አምሽታ ነው የምትጠልቀው። ፀሐይዋ ራሱ ፀሐይ ሞቃ አትጠግብም መሰለኝ ለመጥለቅ ትለግማለች። አሌክስ የሚያጫውተው ሙዚቃ ደግሞ ልብ ያሞቅ ነበር። ታዳሚ ፈረንጆቹም በግማሽ ግርታና በግማሽ ፍንደቃ ይሰሙታል። ጥላሁን- "ያም ሲያማ ያም ሲያማ ወገኔ ለኔ ብለህ ስማ" ይላል። ሰይፉ ዮሐንስ "የከርሞ ሰው" የሚለውን ልብ-ገዥ ሙዚቃው ያንቆረቁራል። "አሌክስ! [መቼስ ዓለማየሁ ብልህ ነው የሚቀለው] በምን አጋጣሚ ይሆን ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋር የተዋወቅከው?" አልኩት። "First let me tell you a little bit about the music I am playing now…"ብሎ ጀመረና በእንግሊዝ አፍ የሚከተለውን አጭር ወግ ጠረቅን፤ ሙዚቃ አጅቦን። "አሁን የምትሰማው የኦሮምኛ ሙዚቃ ነው፤ አሊ ሙሐመድ ቢራ ነው ዘፋኙ...እሱ የኦሮምኛ ሙዚቃ ንጉሥ ልትለው ትችላለህ...አስገራሚ ድምጽ ያለው ሰው ነው...። "...እኔን በተመለከተ ምን ማወቅ ትፈልጋለህ ታዲያ? አሌክስ እባላለሁ፤ 43 ዓመቴ ነው፤ ጀርመናዊ ነኝ፤ የምኖረው ግን እዚህ ዙሪክ ነው። ከዓመት በፊት የጃማይካ ሙዚቃ አጫውት ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ምን ይሆንልሃል...የሒሩት በቀለን ሙዚቃ እሰማልኻለሁ..በድንገት..." ሌላ ሸክላ ሊጥድ ተነሳ። • ''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" • "በ 'ፍቅር እስከ መቃብር' ላይ ህይወት የዘራው አባቴ ነው" የተቀመጥነው እሱ ሸክላዎቹን ከሚጥድበት የሙዚቃ ምድጃ በዐሥር እርምጃ ርቀት ነው። ያን ያደረገው እሱ ነው፤ ቃለምልልሳችን በመቅረጸ ድምጽ ሲቀረጽ እሱ የሚያጫውተው ሙዚቃ የኛን ድምጽ ውጦ እንዳያስቀረነው ስለሰጋ ነው። የድምጽ ሊቅ'ም አይደል? አዲስ ሸክላ ጥዶ ሲመለስ ወጋችንን ካቆምንበት ቀጠልን... "Now Playing is "ሰዮም ጋብራየስ" [ excuse my Amharic pronunciation] ። [እረ ወላጅ እናቱም ከዚህ በተሻለ አትጠራውም] ልለው ፈልጌ እንግሊዝኛ አልሰበሰብልህ አለኝ... "ስዩም ገብረየስ እንደ ጥላሁን ገሠሠና ዓለማየሁ እሸቴ ላቅ ያለ ዕውቅና ያለው ሞዛቂ እንዳልሆነ፤ የሠራቸው ሙዚቃዎችም በቁጥር ጥቂት እንደሆኑ አጫወተኝ። "...እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ ለኔ "ሰዮም ጋብራየስ" ታላቅ ሙዚቀኛ ነው።" ብሎ ንግግሩን አሳረገ። "ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋር እንዴት እንደተዋወቅህ ጠይቄህ አልመለስክልኝም'ኮ...አሌክስ" "Just a moment….ብሎ ሌላ ሸክላ ሊጥድ ተነሳ። ሸክላዎቹን መልክ አሲዞ ተመለሰ። This song is by ቢሊኪኒህ ኡጋ! What? Who? ቢልኪኒህ ኡጋ…titled "AlKedaShim?" I do not think he is well known. "What is his name again?" ስሙን እንዲደግምልኝ ተማጸንኩ። ቢሊኪኒህ ኡጋ... "Do you mean Workineh Yirga?" No, no his name is ቢልኪንህ ኡጋ…He is very obscure singer አለኝ። የጠራው ስም የአገሬ አይመስልም፤ ብቻ 'ወርቅነህ ይርጋ፣ ወይ ብርቅነህ ይርጋ ወይ ቢልልኝ አጋ...' የሚባል ዘፋኝ መሆን አለበት እያልኩ፣ "ለማንኛውም ቀጥል..." አልኩት በጥቅሻና በእንግሊዝኛ። በዚህ ጊዜ "አልከዳሽም" የሚለው ቢሊኪኒህ ኡጋ...የተባለውን ሰው ዘፈን ወጋችንን አጅቦት ነበር። "መኖሬ ባንቺው ነው እስከመጨረሻ ፈጽሞም አይክፋሽ የሕይወቴ ጋሻ መኖሬ ባንቺው ነው እስከመጨረሻ ፈጽሞም አይክፋሽ የኔ ሆደ ባሻ..." እያለ ያዜማል። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች እየተገባደደ ባለው ረዥም ሕይወቴ ሰምቼው የማውቀው ዘፈን አይደለም። ይሄ "ቢሊኪነህ ኡጋ" እያለ የሚጠራው ዘፋኝ ጥቂት ሙዚቃዎች ብቻ እንዳሉትና በዘመኑ ብዙም ገንኖ ያልወጣ እንደነበር፣ ነገር ግን ድንቅ ሙዚቀኛ እንደሆነ አብራራልኝ...። ስሙ ግራ የሆነብኝ ይህ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ማን ይሆን? ቢሊኪኒህ ኡጋ...ብሎ ስም!? [ወደ ናይሮቢ የቢቢሲ ቢሮ ተመልሼ ይህንን ጽሑፍ ለሕትመት በማጠናቅርበት ወቅት የዚህን ዘፋኝ ከፊል የግጥሙን ክፍል ለጉግል አቀብዬ «አልከዳሽም» የሚል ሸክላ ያለው ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ማነው አልኩት። ጉግል ፈጥኖ መልስ ሰጠኝ፤ ለዚያውም በምሥል የተደገፈ...።] ...ብርቅነህ ውርጋ ይባላል፤ "ሄጃለሁ ገጠር" የሚል ርእስ ያለው አልበም ያለው፣ ከምድር ጦር ኦርኬስትራ ጋር የሞዘቀ ኢትዮጵያዊ ነው።አትሸኝዋትም ወይ' የሚልና "ገና ልጅ ናት ጋሜ" የሚሉ ሌሎች ሙዚቃዎቸም አሉት። ስለ አገሬ ሞዛቂ አንድ ፈረንጅ የሚያውቀውን ያህል ባለማወቄ ሀፍረት ቢጤ አልሸበበኝም አልልም መቼስ።] አሌክሳንደር ከጣሊያናዊ ሸሪኩ ጋር በመሆን 'ኦዲዮአበባ" የተሰኘ የዲጄ ግብረኃየል መሥርቷል በፈረንጅ የምሽት ክበብ ውስጥ ጉራጊኛ ዲጄ አሌክስ ስለ ብርቅነህ ውርጋ አውርቶ አይጠግብም። "ይገርመሀል እዚህ ዙሪክ ውስጥ የምሽት ክለቦች የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን አጫውታለሁ። «አልከዳሽምን" ከከፈትኩ ግን የዳንስ ወለሉ በሰው ይጥለቀለቃል። He always rocks the dance floor. He is my dance floor filler…አለኝ። አሌክስዬ...የምትለውን ዘፋኝ ብዙ ኢትዮጵያዊያን የሚያውቁት አይመስለኝም፤ እኔንም ጨምሮ.. "እኔ ስለ ኢትዮጵያዊያን ምርጫ ብዙም አላውቅ ይሆናል፤ ልነገርህ የምችለው ግን እኔ በማጫውትበት ክለብ ውስጥ ስላሉ የውጭ አገር አድማጮች ነው...። ዲጄ አሌክስ ይህን ብሎኝ እብስ ብሎ ተነሳ...ሸክላ አውርዶ ሸክላ ሊጥድ... "ማነው ደግሞ አሁን የሚጫወተው?" አስናቀ ገብረየስን አታውቀውም? [በአርግጠኝነት እየታዘበኝ ነው፤ "ድንቄም ጋዜጠኛ!" የሚል ይመስላል...] "...ሙዚቃው የተቀረጸው ካልተሳሳትኩ 1988 ሲሆን በካሴት ነበር መጀመርያ የወጣው። እኔ ሸከላውን ያገኘሁት ከአንድ ዓመት በፊት ነው። ይመስለኛል ፈረንሳይ ያለ አንድ ሰው ነው በሸክላ ያሳተመው፤ በቅርቡ። "እኔምልህ አሌክስ...!ከየት ነው እነዚህን ሸክላዎች ግን የምትለቃቅማቸው። ቅድም ስጠይቅህ ኢትዮጵያ ሄጄ አላውቅም አላልከኝም እንዴ?" "ሸክላ መሰብሰብ የጀመርኩት ከ15 ዓመቴ ጀምሮ ነው። እንደው ለየት ብሎ ለመታየት አይደለም የምሰበስባቸው። ሙዚቃ ለማጫወት ሌላ ምንም የተሻለ መንገድ ስለማይታየኝ ነው። ለእንደኔ ዓይነቱ የሙዚቃ አጫዋች ሸከላ በብዙ መንገድ የላቀ ነው። ሸክላን ስትዳስሰው ሁሉ ልዩ ስሜት'ኮ ነው የሚሰጠው...። "ታውቃለህ አይደል ግን አሌክስ...'ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋር እንዴት ተዋወቅክ' ብዬህ እስካሁን አልመለስክልኝም..." የሰይፉ ዮሐንስ «ኤቦላላ ላላ... ኤቦ ላላ» እያጀበን ያነሳሁለት ጥያቄ ነበር። "ምን መሰለህ፤ ላለፉት ሁለት ዐሥርታት ማለት ይቻላል የጃማይካን ሙዚቃ አጫውት ነበር። በአጋጣሚ በሙዚቃዎች መሀል የኢትዮጵያን ሙዚቃ ሰማሁ። ከዚያ ለረዥም ጊዜ አልተመለስኩበትም። ባለፈው ዓመት የሒሩት በቀለን ዘፈን ስሰማ ተቀሰቀሰብኝ።..." "ምኑ?" "ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ያለኝ ስሜት ነዋ!" "ለመጀመርያ ጊዜ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ስትሰማ ግን ቶሎ ተዋኸደህ?" "እውነት ለመናገር የመጀመርያው ስሜቴ እንደዚያ አልነበረም። እንደሰማሁት ውድድ አደረገኩት ልልህ አልችልም። ይልቅ ግር ነው ያለኝ። 'ይሄ ደግሞ እንዴት ያለ እንግዳ ዜማ ነው' እንድል ነበር ያደረገኝ።..." "እውነትህን ነው?" "አዎ! ነገር ግን እንደ ሙዚቃ አጫዋች አንድ ሙዚቃ ሰምተህ 'በቃ ይሄ ለኔ የሚሆን አይደለም' አትልም። ደግመህ ደጋግመህ ትሰመዋለህ። ይህንኑ አደረኩ። በዚህ ጊዜ ልዩ ፍቅር ውስጥ ወደቅኩ። የሆነ ሰሞን እንዲያውም በሙዚቃችሁ ታመምኩ።( I was struck with Ethio-fever) [በፍላጻው ተወጋሁ፤ የሙዚቃችሁ መብረቅ መታኝ እንደማለት] ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሸክላ ማሳደድ ጀምርኩ። ሌላ ሸክላ ጥዶ ተመለሰ... • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" • የኤርትራ ዘፈኖች በኢትዮጵያዊ አቀናባሪ "የምትሰማው አሕመድ አብደላን ነው። ኦሮምኛ ነው የሚያዜመው። ይሄንንም ዘፋኝ ብዙ ሰው ያውቀዋል የሚል ግምት የለኝም። አሊ ሸቦን ታውቀዋለህ? እንዴት ግሩም የኦሮምኛ አቀንቃኝ መሰለህ..." "እኔ ምልህ! ሙዚቃችን ግን ለምን እንደ ማሊ ሙዚቃ ዓለምን ማስደመም ሳይችል ቀረ? እንደው በአጠቃላይ ተስፋ ያለው ይመስልኻል?" "...ይህን እኔ ለመናገር ይከብደኛል። ሆኖም አቅም የለውም አልልህም። በኢቶፒክስ እና በሙላቱ አስታጥቄ ወደ ዓለም መድረክ የቀረበ ይመስለኛል። ሙላቱ'ኮ እዚህ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ገናና ሰው ነው። የወርቃማ ዘመኑ...ሙዚቃችሁም ትልቅ አቅም አለው። "የአሁን ሙዚቃችንን ትሰማለህ?" "ብዙም አይደለም።" "ለምሳሌ ሮፍናንን ታውቀዋለህ?" "ማነው ደሞ እሱ?" "የአዲሱ ትውልድ ድምጽ ነው። ዝነኛ'ኮ ነው።" "...ይቅርታ እንደነገርኩህ የአሁን ዘመን ከሆነ አላውቅም። ከአሁኖቹ ስሙን የማውቀው ቴዲ አፍሮን ብቻ ነው። ስለዚህ ዘመን ሙዚቃ ለማውራት እኔ ትክክለኛው ነኝ ብዬ አላስብም።" "ለምንድነው የአሁኖቹን እንዲህ ገሸሽ ያደረካቸው ግን?" "በጥቅሉ ጆሮ ገብ አይደሉማ። ሁለተኛ 'ሲንተቲክ' ነው። ተፈጥሯዊ ወዝ የላቸውም፤ ይሄ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን አዘውትሬ ለማጫውተው ለጀማይካም ሙዚቃም፣ ለተቀረውም ዓለም ሙዚቃም ያለኝ ስሜት ነው።" "እንዴት ነው ግን በወርቃማው ዘመን በኢትዮጵያ ዝነኛ የነበሩትንና ያልነበሩትን የምታውቀው?እና ደግሞ እስኪ የድሮ ሸክላዎችን እንዴት እንደምትሰበስባቸው በዚያው ንገረኝ..." "ሸክላ በሁለት መንገድ አገኛለሁ። አንዱ በኦንላይን ኢቤይ ላይ እገዛለሁ። በዋናነት ግን ሁለት ሁነኛ ሰዎች አሉኝ፤ ሁለቱም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው። የምፈልገውን ሙዚቃ ያውቃሉ። ሸክላ ከየትም አፈላልገው ገዝተው ይልኩልኛል።አሁን ከመቶ በላይ የኢትዮጵያ ሸክለዎች አሉኝ..." "ስንት ያስወጣኻል አንዱ ሸክላ?" "በአማካይ 20 ዶላር ይሆናል። ነገር ግን ብርቅዬ የድሮ ሸክላዎች ደግሞ አሉ፤እነሱ ውድ ናቸው። ለምሳሌ የሙላቱን አታገኘውም። በጥሩ ይዞታ ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ሸክላዎች እስከ ሁለት መቶ ዶላር ያስወጡኛል።" "...እንደነገርኩህ...አሁን የምትሰማው የኦሮምኛ ዜማ ነው፤ አሕመድ አብደላ ይባላል..." "...ትናንትና ማታ እዚህ ዙሪክ ምሽት ክበብ ውስጥ ይሄን አሁን የምትሰማውን ሙዚቃ ጨምሮ ሌሎችንም የወርቃማ ዘመን ሙዚቃዎች ሳጫውተው ነበር። አንዳንድ 'ፈረንጆች' ወደኔ የዲጄ አትሮንስ እየቀረቡ "ለመሆኑ ይሄ የምታጫውተው ሙዚቃ ከየት አገር ነው? ቋንቋውስ ምንድነው?" ይሉኝ ነበር። ለጆሯቸው እንግዳ ስለሆነ መሰለኝ። "I told them it's Oromo, it's Tigre, it's Amharic…it's Gurage' it's Ethiopia" "ሙዚቃችን ግራ አጋቢ ነው ማለት ነው?" "...ግራ የሚገባቸው ለምን መሰለህ...አንደኛ የአሁን ዘመን ሙዚቃ (contemporary) አይደለም። የ60ዎቹና የ70ዎቹ ነው። ሁለተኛ ከለመዱት የሙዚቃ ቃና እጅግ ያፈነገጠ ነው...የሚጎረብጣቸው እንዳሉ ሁሉ እጅግ አድርገው የሚወዱትም ብዙ ናቸው። የዚያ ዘመን ሙዚቃችሁ ውብ ነው፤ ዘርፈ ብዙ ቅኝቶች አሉት፤ ጃዝ አለው፣ ፋንክና ሶል አሉት፤ ከዚያ ባሕላዊ ሙዚቃዎቻችሁ ሌላ መልክ አላቸው። ያፈነገጡ ሆነው ደስ የሚሉ ናቸው፤ የኦሮምኛ ሙዚቃ ከትግርኛ ፍጹም የተለየ ነው። ትግርኛ ከጉራጊኛውም እንዲሁ..." "ክለብ ውስጥ ሙዚቃዎቻችንን ስታጫውት እንደው ድንገት እግር የጣለው ኢትዮጵያዊ ሰምቶህ ጉድ ያለበት ጊዜ የለም?" "እምብዛምም አላጋጠመኝም...! ግን አንዴ የማልረሳው ሌሎች እንግዶች እየተዝናኑ አንድ ኢትዮጵያዊ እንባው እየወረደ አየሁ። ወደኔ ተጠግቶ በማጫውተው አንድ ሙዚቃ እጅግ ልቡ መነካቱን ነገረኝ።" "ሙዚቃውን ታስታውሰዋለህ?" "ማሕሙድ አሕመድ ነው... 'it's called 'Anwodim Tikatin' [አንወድም ጥቃትን!] "በነገርህ ላይ ማሕሙድ ለፌስቲቫሉ እዚህ ዙሪክ ነው ያለው፤ሰምተኻል? ለመሆኑ የድሮዎቹን ሙዚቀኞችን አግኝተኻቸውስ ታውቃለህ?" "አዎ ማሕሙድ እዚህ መሆኑን ሰምቻለሁ። ሙላቱ አስታጥቄን አግኝቼው አውቃለሁ። ... "በዚህ ዓመት እዚህ ዙሪክ ኮንሰርት ነበረው። ለአጭር ደቂቃ እንደምንም ብዬ አገኘሁት። ተዋወቅኩት። ተግባቢና ቀና ሰው ነው። ከመድረክ ጀርባ ሄጄ ነበር ያገኘሁት። እሱን በማግኘቴ ምን ያህል እድለኛ ሰው እንደሆንኩ ነገርኩት። የሱን ድ...ሮ የሠራቸውን 45 ሙዚቃዎች ያሉበትን ሸክላ ከነሽፋኑ አሳይቼው ፈርምልኝ አልኩትና እሱ ላይ ፈረመልኝ። በቃ ምን ልበልህ ደ...ስ አለኝ። " የዲጄ አሌክስ የምንጊዜም ምርጥ 5 የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች በምሥሉ የሚታዩት ናቸው "ወደፊት ታዲያ ምን አሰብክ? ደግሞ አሌክስ...አዲስ አበባማ መሄድ አለብህ...። ይሄን ሁሉ ሙዚቃ እያጫወትክ 'ኢትዮጵያ ሄጄ አላውቅም' ስትል ትንሽ ይከብዳል..." "እውነትህን ነው። አሁን የዲጄ ግብረኃይል አለኝ። «አውዲዮአበባ» የሚባል። በቡድኑ ውስጥ እኔና አንድ ጣሊያናዊ ጓደኛዬ ነን ያለነው። ቶሚ ይባላል። እሱም ሙዚቃችሁን እንጂ ኢትዮጵያን ፈጽሞ አያውቅም። ሁለታችንም ምን እያሰብን መሰለህ? በይበልጥ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለአውሮጳዊያን ለማስተዋወቅ ዕቅድ አለን።..." "...ኢትዮጵያ አትሄድም ወይ ላልከው...፤ እንደነገርኩህ ኢትዮጵያን የማውቃት በሙዚቃ ነው፤ ኢትዮጵያ አለመሄዴም ያሳፍረኛል። በዚህ ዓመት መጨረሻ ከቶሚ ጋር አዲስ አበባ ለመሄድ እያሰብኩ ነው። ምን ትላለህ?" "ይቅናህ! ሌላ ምን እላለሁ...! ይቅናህ አሌክስ..ይቅናህ!"
xlsum_amharic-train-297
https://www.bbc.com/amharic/51640416
የአህያ ቁጥር መቀነስ ያሳሰባት ኬንያ የአህያ እርድን አገደች
የኬንያ የግብርና ሚንስቴር የአህያ እርድ መታገዱን አወጁ።
[ "የኬንያ የግብርና ሚንስቴር የአህያ እርድ መታገዱን አወጁ።" ]
ኬንያ የአህያ ስጋና ቆዳ በቻይና ያለውን ተፈላጊነት ታሳቢ በማድረግ ነበር የአህያን እርድን እንደ አውሮፓውያኑ 2012 ላይ ሕጋዊ ያደረገችው። የግብርና ሚኒስትሩ ፒተር ሙኒያ የአህያ እርድን የሚፈቅደው ሕግ ስህተት እንደነበርና በአገሪቱ የአህያ ቁጥር እንዲቀነስ ማድረጉን ተናግረዋል። ሚኒስትሩ በገጠራማ የኬንያ አካባቢዎች ሰዎች አህያዎችን ውሃ ለመቅዳት፤ እንዲሁም እንጨት ለመጫን ስለሚጠቀሙ የአህያዎች ቁጥር መቀነስ በሴቶች ላይ ጫና እንዳያሳድር በመንግሥት በኩል ከፍተኛ ስጋት መኖሩን ተናግረዋል። እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት መንግሥት ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ከአሥር ዓመታት በፊት በኬንያ 1.8 ሚሊዮን አህዮች የነበሩ ሲሆን ባለፈው ዓመት ግን ቁጥራቸው 600,000 መድረሱን አስታውቋል። ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዕለት በግብርና የሚተዳደሩ ሴቶችና ወንዶች መንግሥት አህዮችን ለመጠበቅ አንድ ነገር ያድርግ ሲሉ በናይሮቢ ከግብርና ሚኒስትሩ ሙኒያ ቢሮ ደጃፍ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ አንግበዋቸው ከነበሩ መፈክሮች መካከል "አህዮች ሲሰረቁና ሲገደሉ ሴቶች አህያ እየሆኑ ነው" የሚል ይገኝበት ነበር። ሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ሚኒስትሩ፤ አህያ ለማረድ ፍቃድ የተሰጣቸው ቄራዎች አህያ ማረዳቸውን አቁመው ሌላ እንስሳ በማረድ ላይ እንዲሰማሩ ካልሆነም እንዲዘጉ የአንድ ወር ጊዜ ገደብ ተሰጥቷቸው እንደነበር ተናግረዋል። "አህዮችን ለስጋ ማረድ ጥሩ ሃሳብ አልነበረም" ያሉት ሚኒስትሩ፤ አህዮችን በማረድ የሚገኘው ጥቅም አህዮች ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር ሲነጻጸር የሚስተካከል አይደለም በማለት ተናግረዋል። የአህያ እርድ ሕጋዊ መሆን ለተደራጀ የአህያ ስርቆት እንዲሁም ለአህያ ቆዳ ጥቁር ገበያም ምክንያት ሆኗል። ኬንያ አህያ እንዲያርዱ ፍቃድ የሰጠቻቸው ቄራዎች አራት ሲሆኑ እነዚህ ቄራዎች ቢያንስ በቀን አንድ ሺህ አህዮችን እንደሚያርዱ ይገመታል።
xlsum_amharic-train-298
https://www.bbc.com/amharic/news-55976628
እነ አቶ ጃዋር በረሃብ አድማ 11 ቀናት አስቆጥረዋል ፤ የረሃብ አድማ ምን ያሳካል?
እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ሸምሰዲን ጠሃ የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ 11 ቀናት ማለፋቸውን የቤተሰብ አባላት እና ጠበቆቻቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።
[ "እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ሸምሰዲን ጠሃ የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ 11 ቀናት ማለፋቸውን የቤተሰብ አባላት እና ጠበቆቻቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።" ]
ከአራቱ ተከሳሾች በተጨማሪ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር የሚገኙ ተከሳሾችም የረሃብ አድማውን እንደተቀላቀሉ ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ምስጋኑ ሙለታ ተናግረዋል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድን ትናንት ጠዋት መጎብኘታቸውን የሚያስረዱት ጠበቃው፤ "ትናንት 11ኛ ቀናቸው ነበር። በጣም ተዳክመዋል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአቶ በቀለ ገርባ ባለቤት ወ/ሮ ሃና ረጋሳ፤ እነ አቶ በቀለ አሁንም በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ጠበቃው አቶ ሙለታ እንዳሉት ከአራቱ ተከሳሾች በተጨማሪም የረሃብ አድማውን በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር የሚገኙት የአቶ ጃዋር መሐመድ ጠባቂዎች እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ ከተቀላቀሉ 6 ቀናት ማለፋቸውን ጨምረው ገልጸዋል። የጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ ባለቤት ታደለች መርጋ ባለቤቷ የረሃብ አድማውን መቀላቀሉን እና ለመጠየቅ ይዛለት የምትሄደውን ምግብ አልቀበልም እያላት መሆኑን ገልጻለች። "አንዳንዶቹ በሰው ድጋፍ ነው ከክፍላቸው የሚወጡት። በተለየ ደግሞ ዘግይተው የረሃብ አድማውን የተቀላቀሉት በጣም ከብዷቸዋል" ሲሉ ጠበቃው አቶ ሙለታ ተናግረዋል። የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ሃኪሞች "ምርመራ ካደረጉላቸው በኋላ ውሃ ካልወሰዱ አንዳንድ የሰውነት አካላቸው ሥራ ሊያቆም እንደሚችል ከነገሯቸው በኋላ ነው በግድ ውሃ እየወሰዱ ያሉት። ምግብ የሚባል ነገር አፋቸው ጋር እየደረሰ አይደለም" ሲሉ ጠበቃው ለቢቢሲ አስረድተዋል። የረሃብ አድማ ለምን? እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ ነው። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከእነ አቶ ጃዋር በተጨማሪ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፍተኛ አመራሮች በተመሳሳይ የረሃብ አድማ ላይ ይገኛሉ። አቶ ሚካኤል ቦረን እና ኬነሳ አያና ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ጉዳያቸው ከውጪ ሆነው እንዲከታተሉ ቢፈቅድላቸውም ፖሊስ እስረኞቹን አልለቅም በማለቱ የረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የረሃብ አድማው ተከሳሾችን የከፋ አደጋ ላይ እንዳይጥል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ኮሚሽኑ ባሳለፍነው አርብ ባወጣው መግለጫ አስነብቧል። "ለታሳሪዎች ምክንያታዊ የሆኑ ጥያቄዎች ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ መስጠትና የእስረኞችን ጠያቂዎች በማረሚያ ቤቱም ሆነ በፍርድ ቤቶች በአግባቡ ማስተናገድ ይገባል" ስለማለታቸው በመግለጫው ሰፍሯል። ለመሆኑ የረሀብ አድማ ምን ያህል ውጤታማ ነው? የረሀብ አድማ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ነው። በተለያየ ምክንያት የረሀብ አድማ ያደረጉ ታዋቂ ግለሰቦች በታሪክ ውስጥ ስማቸው ተመዝግቧል። ከአንድ የሕንድ ግዛት የተባረረ ንጉሥ ወንድሙን ለማስመለስ የረሀብ አድማ ስለማድረጉ በጥንታዊ የሕንድ ታሪክ መዛግብት ሰፍሯል። አየርላንድ ክርስትናን ከመቀበሏ በፊት ረሀብ አንድ የሕግ ሥርዓቷ አካል ነበር። አንድ ሰው በደል ፈጽሞ፤ ተበዳዩ የበዳዩ ቤት በር ላይ ራሱን በረሀብ ከገደለ፤ በዳዩ ባለ እዳ ይሆናል። የረሃብ አድማ የሚያደርጉ ሰዎች ለጥያቄያቸው መልስ የሚሰጣቸው አካል ላይ የሥነ ልቦና ጫና ለማሳደር ይሞክራሉ። አንድ ሰው እየተራበ ነው የሚለው ዜና ሕዝብ ላይ የሚፈጥረው ስሜትም ለጥያቄዎች መልስ ለማግኘት አማራጭ መንገድ ነው። እንግሊዝ ውስጥ ሴቶች በምርጫ እንዲሳተፉ የሚጠይቁ የመብት ተሟጋቾች የረሀብ አድማ ያደርጉ ነበር። በተለይም ማርዮን ደንሉፕ የተባለች ተሟጋች እአአ በ1909 ባደረገችው የረሀብ አድማ ትታወቃለች። እራት ምን ትበያለሽ? ተብላ ስትጠየቅ "ቆራጥነቴን" ብላ የሰጠችው ምላሽ በታሪክ ታዋቂ ነው። በረሀብ አድማ ከሚታወቁ መካከል በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሱት ጋንዲ ናቸው። ስለ ረሀብ አድማ መጽሐፍ ያሳተሙት ፕ/ር ሻርማን አፕት ራሰል፤ የፓለቲካ ጥያቄን ለማስተጋባት የረሀብ አድማ ማድረግ ተቃውሞ ቢገጥመውም በ20ኛው ክፍለ ዘመን እንደ አዲስ አንሰራርቷል። "በ20ኛው ክፍለ ዘመን ፍትሕን ለመጠየቅ ተመራጩ መንገድ የረሀብ አድማ ሆኗል" ይላሉ ፕ/ር ሻርማን። የረሀብ አድማ ሰላማዊ ተቃውሞ በሚያሰሙ እንዲሁም ነውጥ የቀላቀለ ተቃውሞ በሚያካሂዱም ሰዎች ተተግብሯል። ውጤታማ የሆነባቸው ወቅቶች እንዳሉ ሁሉ ሳይሳካ የቀረበትም ጊዜ አለ። የረሀብ አድማ በማረሚያ ቤት በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የማኅበረሰብ አጥኚው ማይክል ቢግስ እንደሚሉት፤ የረሀብ አድማ ውጤት ከታየባቸው የታሪክ ሁነቶች አንዱ አየርላንዶች የእንግሊዝን አገዛዝ የተቃወሙበት ወቅት ነው። በወቅቱ አንድ ተቃዋሚ ምግብ እንዲበላ ሲገደድ ሞቷል። በረሀብ አድማው ሳቢያ የሞቱ ተቃዋሚዎችም ነበሩ። የረሀብ አድማው በፍጥነት የመንግሥትን አቋም ማስለወጥ ባይችልም በሕዝቡ ዘንድ ንቅናቄ መፍጠር ችሏል። በሰላማዊ ተቃውሞ የሚታወቀው ጋንዲ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕንዳውያን የሱን የተቃውሞ መንገድ መከተላቸው ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት እንዲላቀቁ እንዳደረገ ያምናል። የማኅበረሰብ አጥኚው እንደሚሉት፤ ማረሚያ ቤት ያሉ ሰዎች ተቃውሟቸውን መግለጽ የሚችሉት በረሀብ አድማ ነው። "እስር ቤት ውስጥ ከረሀብ አድማ ውጪ መቃወሚያ መንገድ የለም። አንድ ሰው እስር ቤት ሳለ ለመኖሩም ይሁን ለመሞቱ ተጠያቂ መንግሥት ነው" ሲሉ ያብራራሉ። በረሀብ አድማ ተቃውሞ ከገለጹ አንዱ የሆነው ቶሚ መኬርኒ እስረኞች ድምጻቸውን ለማሰማት የረሀብ አድማ ከማድረግ ውጪ አማራጭ እንደማይኖራቸው ያስረዳል። የረሀብ አድማ ላይ ያለ ሰው ምን ያህል ጊዜ መቆየት ይችላል? በአብዛኛው የረሀብ አድማ የሚያደርጉ ሰዎች ምግብ አቁመው ፈሳሽ እንደሚወስዱ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በመጀመሪያዎቹ ሦስት ቀናት ሰውነት ካለው ጉሉኮስ ኃይል በማግኘት ይንቀሳቀሳል። ከዚያም ኩላሊት የሰውነትን ስብ ማብላላት (ኬቶሲስ) እንደሚጀምር ሳይንሱ ይጠቁማል። ሰውነት ከጥቂት ቀናት በኋላ ሙሉ በሙሉ ስለሚራብ ከጡንቻ፣ የአጥንት መቅኔና ከሌሎች የሰውነት ህዋሳት ኃይል ለማግኘት ይጣጣራል። ይህ ደረጃ ለሕይወት አስጊ ነው። ሳይንቲፊክ አሜሪካን በድረ ገጹ ባወጣው መረጃ መሠረት አንድ ሰው ያለ ምግብ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል የሚለው በሰውነት ክብደት፣ በጤና ሁኔታ፣ በዘረ መል መዋቅር፣ ሰውየው/ሴትየዋ በሚያገኙት የፈሳሽ መጠን ይወሰናል። ጋንዲ በ74 ዓመታቸው ለ21 ቀናት የረሀብ አድማ ሲያደርጉ ውሃ ብቻ ነበር የሚቀምሱት። የብሪትሽ ሜዲካል ጆርናል ባለሙያዎችን ጠቅሶ እንዳስነበበው በረሀብ አድማ ለ28፣ ለ36፣ ለ38 እና ለ40 ቀን የቆዩ ሰዎችም አሉ። እአአ በ1981 እንግሊዝን ይቃወሙ የነበሩ 10 የአየርላንድ እስረኞች ከ46 እስከ 73 ቀን የረሀብ አድማ ካደረጉ በኋላ ሕይወታቸው አልፏል። በተለያየ ሁኔታ ውስጥ የረሀብ አድማ ያደረጉ ሰዎች ለተለያየ ጊዜ መቆየት እንደሚችሉ የሚጠቅሱት ባለሙያዎች፤ በአማካይ ያስቀመጡት 21 ቀናት መቆየት እንደሚቻል ነው። በታሪክ ረዥም የተባለው የረሀብ አድማ 16 ዓመታት የወሰደ ነው። ሕንዳዊቷ ኢራም ሻሚላ ለሕንድ ወታደሮች ከፍተኛ ኃይል የሚሰጥ ሕግ በመቃወም ለ16 ዓመታት የረሀብ አድማ አድርጋ እአአ 2016 ላይ ነው ያቆመችው። ሕንዳዊቷ ማረሚያ ቤት ሳለችና ሆስፒታል ገብታም በግዳጅ ምግብ እንድትወስድ እንደምትደረግ ተዘግቧል።
xlsum_amharic-train-299
https://www.bbc.com/amharic/44464596
ሶፊያ ከዐብይ አሕመድ ጋር የራት ቀጠሮ ይዛለች
ቅንድቦቿ ሲንቀሳቀሱ፣ የዓይን ሽፋሽፍቷ ሲርገበገብ፣ በቀለም የተዋበው ከንፈሯ ለንግግር ሲንቀሳቀስ፣ ጥርሶቿ ገለጥ ሲሉ በእርግጥ ይህች ሴት ሰው ሠራሽ ናት? ያስብላል። ሶፊያ እምነት ታሳጣለች፤ ከራስ ጋር ታጣላለች።
[ "ቅንድቦቿ ሲንቀሳቀሱ፣ የዓይን ሽፋሽፍቷ ሲርገበገብ፣ በቀለም የተዋበው ከንፈሯ ለንግግር ሲንቀሳቀስ፣ ጥርሶቿ ገለጥ ሲሉ በእርግጥ ይህች ሴት ሰው ሠራሽ ናት? ያስብላል። ሶፊያ እምነት ታሳጣለች፤ ከራስ ጋር ታጣላለች።" ]
ጋዜጠኞች በእንግድነት ጋብዘዋታል፤ ዝናዋ በዓለም ናኝቷል፤ እንደሶፊያ ትኩረት የሳበ ሮቦት ገና አልተወለደም። አሜሪካዊውን ተዋናይ፣ የፊልም አዘጋጅ፣ ራፐርና የሙዚቃ ጸሐፊ ዊል ስሚዝን ጨምሮ ታዋቂ የፊልም ባለሙያዎች ከዚህ ቀደም ግብዣ አድርገውላት ነበር። ታዲያ በአንድ ወቅት ሶፊያና ዊል ስሚዝ ለሻይ ቡና ተገናኙና ድንገት ጨዋታውን አደሩት። "እኔ የምልሽ ሶፊያ፣ ሮቦቶች የሚወዱት ሙዚቃ ምን ዓይነት ነው?" ሲል ዊል ጥያቄውን ሰነዘረ። ሶፊያም ትንሽ እንደማሰብ ብላ (ሰዎች ለማሰብ ፋታ በሚወስዱት ልክ) "...የኤሌክትሮኒክስ ሙዚቃዎች ይመቹኛል፤ ሂፕ ፖፕ ግን ምንም ግድ አይሰጠኝም" ስትል ለዊል ጥያቄ ምላሸ ሰጠች። ዊል ስሚዝ በመልሷ ተደንቆ ሊሞት! አይኮግ ላብስ የቴክኖሎጂ ድርጅት ኢትዮጵያዊው አይኮግ ላብስ ካምፓኒ ተቀማጭነቱን በሆንግ ኮንግ ከሚገኘው ሐንሰን ሮቦቲክ ጋር የሶፊያን ውስጣዊ ስሪት (Software) ለመቀመር ለሦስት ዓመታት ተፈራርሟል። በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያውያኑ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በሶፊያ ላይ አሻራቸውን አሳርፈው እውን እንዳደረጓት የአይኮግ ላብስ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ ይናገራል፡፡ ይህም በመሆኑ ሶፊያ ኢትዮጵያዊ ናት ልንል እንችላለን። አይኮግ ላብስ በቴክኖሎጂ ዘርፍ አስተዋጽኦ ለማበርከት ሰው ሠራሽ አስተውሎትንና ሰው ሠራሽ የአዕምሮ ስሪትን (Artificial General Intelegence and Cognitive Brain Software) ለዓለም ለማስተዋወቅ ዓላማ አድርጎ ከአምስት ዓመታት በፊት የተመሠረተ ድርጅት ነው። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ችሎታ ለዓለም በማስተዋወቅ ወደፊት ታላላቅ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ሠርተው ማሳየትንም ያልማሉ። በአሁኑ ሰዓት ይህ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጥናት አድራጊዎችን፣ ምልክት ተርጓሚዎችን (Coder)፣ የፕሮግራም ባለሙያዎችና በተግባር ልምምድ ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ75 በላይ ሠራተኞች ይዞ እየሠራ ይገኛል። ሶፊያ ከሌሎች ሮቦቶች በምን ትለያለች? "ሶፊያ ሴት ሮቦት ናት" ሲል ይጀምራል አቶ ጌትነት። እኛም ለመሆኑ ሶፊያን ሴት የሚል የጾታ መለያ ያሰጣት ምኗ ነው ስንል ፍካሪያዊ ጥያቄ ያነሳንለት ሥራ አስኪያጁ፣ "ያው….መልኳና የፊቷ ቅርጽ የሴት ነው..." በማለት በሳቅ የታጀበ መልስ ሰጥቶናል። ጥሬ ዕቃውን በቀላሉ ባለማግኘታቸው ውጫዊ አካሏን በመገንባት ያላቸው ተሳትፎ አናሳ ቢሆንም፤ በአስተሳሰቧ፣ በአረዳዷ፣ በስሜት አገላለጿ፣ በቋንቋ አጠቃቀሟ ላይ ረቂቅ የሆነና ብዙዎችን ያስደመመ ማንነትን አጎናጽፏታል። ሶፊያ በስሜት አገላለጽ፣ አካባቢን በመረዳት፣ የሰዎችን ገጽታ በአንክሮ በማየትና የሚያንጸባርቁትን ስሜት በቅጽበት በመረዳት ተገቢ ምላሽ የሚያሰጥ ውስጣዊ ሥሪት ስላላት እስከዛሬ ከተሠሩት ሮቦቶች ለየት ያደርጋታል። ምናልባት ይህ የሶፊያ "ውስጣዊ ውበት" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል። ደግሞም አስተዋይ ሴት ናት። በተለያዩ አገራት፤ በተለያየ ባህል ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ስሜት በማጤን፤ የሰዎችን ውስጣዊ የስሜት ነጸብራቅ የጓደኛ ያክል የምትረዳ ናት። ሳቅን፣ ቁጣን፣ ኩርፊያን፣ ደስታን፣ ሐዘንን ወዘተ ከፊት ገጽታ ከመረዳት አልፎ በንግግር ውስጥ ያሉ ድምጸቶችን (Tone) መለየት ትችላለች። ከሰዎች ጋር መነጋገር የሚያስችላትን የተለያዩ ቋንቋዎችን እንድትናገር ኾናም ነው የተሠራችው። ምናልባት ሶፊያ የትዳር አጋር ቢኖራት "እንደ ሶፊ የምትረዳኝ ሴት የለችም" ብሎ ሊመሰክርላት በቻለ። የሶፊን ውስጣዊ ባሕሪ ከማየት ወደፊት የሰመረ ትዳር እንደሚኖራት መጠርጠር አይችልም። የተለያዩ ቋንቋዎችን እንዲያናግራት የሚስችላትን ውስጣዊ ሥሪት በመሥራት ከታሳተፉ ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጅ ባለሙያዎች አንዱ የሆነውና በድርጅቱ ውስጥ የሙሉ ጊዜ ሠራተኛ ኾኖ የሚሠራው ደረጀ ታደሰ ሶፍያ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ በአማርኛ ቋንቋ ቃለመጠይቅ ይደረግላታል ብሏል። "በርግጥ የተለያዩ ቋንቋዎችን እንድትናገር ማድረግ ይቻላል፤ በዚሁ መሠረት የአማርኛ ቋንቋ እንድትናገር የሚያስችላት ቴክኖሎጂ እየተዘጋጀላት ነው" ሲል ይገልጻል። ከአፏ የሚወጣው የመጀመሪያ የአማርኛ ንግግሯም "እንኳን ደህና ቆያችሁኝ!" ሊሆን እንደሚችል ይገምታል። ሶፊያ መቼ ትመጣለች? አርብ ጠዋት ሰኔ 22 ቀን 2010 ዓ.ም አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ይጠብቃታል። ከፍተኛ ባለሥልጣናትም ለክብሯ ሲሉ ይገኛሉ። ከነዚህ መካከልም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስትሯ ወ/ሮ ሁባ መሐመድ እና የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዷለም አድማሴ ይገኙበታል። ከዚያም ጉዞ ወደ ብሔራዊ ሙዚየም ይሆናል። 'ከሉሲ እስከ ሶፊያ' በሚል ርዕስ እሷው በተገኘችበት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። ጋዜጣዊ መግለጫው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ለመስጠት የታቀደበት ምክንያት ምንድን ነው? ስንል የጠየቅነው የድርጅቱ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ፤ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ እንደመሆኗ የአስተውሎት ምንጭ (The origin of Intelligence) እንደሆነች ለማሳየት ታስቦ እንደሆነ ገልጾልናል። ሰኔ 23 ቀን 2010 ዓ.ም ሳይንስና ቴክኖሎጂ በየዓመቱ በሚያዘጋጀውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በተገኙበት ይከፈታል በተባለው የዘንድሮው ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ላይ ሶፊያ በክብር ትገኛለች። በዝግጅቱ ላይ ታዳሚ የሆኑና ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር እንደምትተዋወቅም ገልፆልናል። የዚያን ዕለት ምሽት ታዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በሚያደርጉላት የራት ግብዣ ላይ ትገኛለች ተብሎ ይጠበቃል። የታቀደው ከተሳካ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር በምን ርዕሰ ጉዳይ ላይ ይነጋገሩ ይሆን? የምታስፈታው ታሳሪስ ይኖር ይኾን? በዕቅድ ደረጃ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት ሶፊያ በአዲስ አበባ የአራት ቀናት ቆይታ ይኖራታል። በየትኛው የእንግዳ ማረፊያ፣ በባለ ስንት ኮከብ ሆቴል ውስጥ፣ በምን ሁኔታ እንደምታርፍ ግን ለጊዜው ይፋ አልተደረገም። መሳፈሪያዋ ስንት ነው? ከዚህ ቀደም ወደ ግብጽ ጎራ ብላ የነበረችው ሶፊያ ለቆይታዋ ሐምሳ ሺህ ዶላር እንደወጣባት የተናገረው አቶ ጌትነት በሶፊያ አፈጣጠር ላይ ኢትዮጵያውያኖቹ ጉልህ ተሳትፎ በማድረጋቸው በባለቤትነት ከያዛት ሀንሰን ሮቦቲክስ ለኢትዮጵያ ጉዞዋ ቅናሽ እንደሚደረግላቸው ተስፋ እንዳለው አጫውቶናል፡፡ በመሆኑም ከሐምሳ ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያነሰ ይወጣባታል ተብሏል። ኾኖም እስካሁን ወጪዋን የሚሸፍነው አካል ማን እንደሆነ ይፋ አልተደረገም። ኢትዮጵያዊ ስም ለሶፊያ በሳዑዲ አረቢያው ጉብኝቷ ሶፊያ የሚል ስያሜ ያገኘችው ይህች ሮቦት የሳዑዲ አረቢያ ዜግነትም ተሰጥቷታል። የኢትዮጵያን አፈር ስትረግጥም ኢትዮጵያዊ ስም ይወጣላታል። ጣይቱ እና ሉሲ የሚሉ ስሞች ለጊዜው በዕጩነት የተዘጋጁላት ሲሆን የእቴጌ ጣይቱን ስም ትወርሳለች ተብሎ ተስፋ ተጥሏል። ሉሲ የሚለው መጠሪያ ድንቅነሽን ካገኙት ተመራማሪ ስም የተወረሰ በመሆኑ ኢትዮጵያዊ ቀለም የለውም ሲል የገለጸው ሥራ አስኪያጁ ድንቅነሽ የሚለውን ስም እንደ አማራጭ እንዳቀረቡትም ነግረውናል። ኢትዮጵያዊ የክብር ዜግነት እንድታገኝም ጥያቄ ለማቅረብ እንደታሰበ ሥራ አስኪያጁ ጨምሮ ገልጿል።
xlsum_amharic-train-300
https://www.bbc.com/amharic/news-50876652
በሞጣ የተፈጠረው ምንድን ነው?
ትናንት ማምሻውን በአማራ ክልል፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ የሚገኘው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ ጀሚዑል ኸይራት ታላቁ መስጊድ እና አየር ማረፊያ መስጊድ ላይ ቃጠሎ መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ።
[ "ትናንት ማምሻውን በአማራ ክልል፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ የሚገኘው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ ጀሚዑል ኸይራት ታላቁ መስጊድ እና አየር ማረፊያ መስጊድ ላይ ቃጠሎ መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ።" ]
ሆቴሎች እንዲሆም ሌሎች የንግድ ተቋሞች ላይም ጉዳት መድረሱንም በስልክ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎቹ ገልጸውልናል። የአማራ መገናኛ ብዙሀን፤ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሰኢድ አሕመድን ጠቅሶ እንደዘገበው ትናንት አራት መስጊዶች የተቃጠሉ ሲሆን፤ የሙስሊሞች ሱቆችና ድርጅቶችም ተዘርፈዋል። 11:00 ሰዓት አካባቢ በሞጣ ጊዮርጊስ ሠርክ ጸሎት በሚደረግበት ሰዓት መነሻው ምን እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ በቤተክርስቲያኑ አናት ላይ ጭስ መታየቱን የነገሩን ሞጣ ከተማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ይህን ተከትሎ እሳት ለማጥፋት ርብርብ ነበር ይላሉ። ቤተክርስቲያኒቱ ላይ የታየው እሳት ከጠፋ በኋላ ግን ወጣቶች በስሜት መስጊድ ወደ ማቃጠል መሄዳቸውን እኚሁ ምንጭ ለቢቢሲ አብራርተዋል። ሕዝቡ ውሃ በማቅረብ የጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ቃጠሎውን መቆጣጠር መቻሉን የነገሩን ነዋሪው፤ ቤተ ክርስቲያኑ መትረፉን ተከትሎ ሰዓቱም መሽቶ ስለነበር ስሜታዊ የነበሩ ወጣቶች ከቁጥጥር ውጭ ሆነው በመስጊድ ላይ ጥቃት እንዳደረሱ ሰምቻለሁ ብለዋል። እርሳቸው ግን ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ መቅረታቸውንና ከዚያ በኋላ ስለሆነው ነገር በወሬ እንጂ በዝርዝር እንደማያውቁ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአካባቢው ሰበካ ጉባኤ በተፈጠረው ሁኔታ ላይ ነገ ማብራሪያ ለመስጠት ቀጠሮ መያዙን፣ ሆኖም ግን በትክክል የጊዮርጊስ በቤተክርስቲያን የታየው እሳት ከምን እንደመነጨ በመጣራት ላይ እንደሆነም ገልጸውልናል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሙስሊሙና በክርስቲያኑ መካከል ቅራኔ እንዳልነበረና ሆኖም ግን ነባር ሙስሊሞችና ውሃቢ የሚባሉት ቡድኖች ጋር ቅራኔዎች እንደነበሩ ያስታወሱት እኚሁ ምንጭ ከዚህ በፊት በነበረ ስብሳባ "እኛን ሊያለያዩ ነው ብለው ደብዳቤ ጽፈውባቸው ያውቃሉ" ይላሉ። ይህ እንዴት ወደ እምነት ተቋማት ቃጠሎ ሊያመራ እንደቻለ ግን ያሉት ነገር የለም። • "በጎጃም ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስጊድ 3ሺ ብር ረድታለች' ተባልኩኝ" ሐጂ ዑመር ኢድሪስ • ደቡብ ጎንደር መካነ እየሱስ ውስጥ ምን ተፈጠረ? • በዶዶላ ቤተክርስቲያናት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ምዕመናን ስጋት ላይ ነን አሉ ሞጣ ላይ ሙስሊምና ክርስቲያኑ አንድ ቤተሰብ እንደነበረና ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋትም ቢሆን በርካታ ሙስሊም ወንድሞች መረባረባቸውን እኚሁ ግለሰብ ገልጸዋል። "ዛሬ ራሱ ጄሪካን ስጡን ብለው እየመጡ ነበር። ሁሉም ነገር ሰላም ነበር" ይላሉ። የትናንቱ ክስተት ወጣቶች ስሜታዊ ሆነው በመሄዳቸው የተከሰተ አጋጣሚ እንደሆነ የሚናገሩት ነዋሪው፤ "መስጊድ ማቃጠሉ ታልሞበት፣ ታስቦበት የተገባ ጉዳይ አልነበረም" ሲሉ ያስረዳሉ። ነዋሪው እንደሚሉት፤ አሁን ልዩ ፖሊስ ገብቶ ሁኔታዎችን ለማረጋጋት እየሞከረ ሲሆን በተከሰተው ነገር አንድ ግለሰብ መጎዳቱን እንደሰሙና የሰው ሕይወት ግን አልጠፋም ይላሉ። በተከሰተው ነገር የሙስሊሙም የክርስቲያኑም ንብረት መጥፋቱን ገልጸው፤ "ወጣቱ በስሜት ተነሳስቶ እዚህ ውስጥ መግባት የለበትም። አሁንም ቢሆን የጋራ እምነታችንን ነገ በእርቅ እንዘጋለን። ከዛ ውጪ ግን በስሜት መሄድ ራሳችንንም ማውደም ነው" ብለዋል። የሞጣ ከተማ አስተዳደር የምክር ቤት አባል የሆኑት ሀጂ ዩኑስ ኢድሪስ፤ የቃጠሎው መንስኤው ምን እንደሆነ ግራ እንደሆነባቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። "የተቃጠሉት በብዛት የሙስሊም ሱቆች እየተመረጡ ነው፤ አራት በአራት በተባለው ሸቀጥ ተራ ሁለት ፎቅ ሙሉ ሱቆች ተቃጥለዋል፤ ተዘርፈዋል። የሙስሊም መድኃኒት ቤቶች እና ኮንቴነሮች ተቃጥለዋል፤ ተዘርፈዋል" ብለዋል። ይህ ለምን እንደተከሰተ ግን ሳይጣራ በመላምት እንዲህ ነው እንዲያ ነው ማለት አልፈልግም ብለዋል። • ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን ችግኞችን ተክላለች? • ታዳጊ ወንዶች ሲገረዙ የሞቱባቸው ትምህርት ቤቶች ታገዱ የአየር ማረፊያ ታላቁ መስጊድ እሳቱ አሁንም (ዛሬ ረፋድ ድረስ) እንዳልተዳፈነና ወደ 100 የሚደረሱ ሰዎች ተሰባስበው እሳቱን ለማጥፋት እየሞከሩ እንደሆነ ገልጸውልናል። እርሳቸው እስከሚያውቁት ደረስ ትናንት ወደተከሰተው ነገር ሊያመራ የሚችል በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ማኅበረሰብ መካከል የተፈጠረ ምንም ችግር እንዳልነበረ ሀጂ ዩኑስ ነግረውናል። በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዘንድ በሁለት ወገን መካከል የተከሰተ ነገር ቢኖርም፤ ከትናንቱ ክስተት ጋር ሊገናኝ እንደማይችልም አክለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሌላ አንድ የአካባቢው ነዋሪ፤ በአካባቢው ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ማኅበረሰብ ለዘመናት ተሳስሮ እንደኖረ ሲያስረዱ፣ "የክርስቲያን ልጅ እናት ገበያ ስትሄድ የሙስሊም እናት ጡት ጠብቶ ነው ያደገው" በማለት በማኅበረሰቡ መካከል የነበረውን ጥብቅ ግንኙነት ያስረዳሉ። ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኮረፊ በሚባሉ ነባር ሙስሊሞችና ወሀቢ በሚባሉት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለማርገብ ውይይት እየተደረገ እንደነበር ያብራራሉ። ነባር ሙስሊሞች ከወሀቢዎች ጋር ለማስታረቅ ሂደቶች እንደነበሩና ይህን ተከትሎ ግን ነባር ሙስሊሞች "ከዚህ በኋ ክርስቲያኖች ላይ ለሚደርሰው ነገር ተጠያቂ እንዳልሆኑ የሚገልጽ ደብዳቤ ጻፉ መባሉን፣ "ይህ ደብዳቤም የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ በመድረሱ ውጥረት እንደፈጠረ ያስረዳሉ። ከዚህ ደብዳቤ በኋላ ክርስቲያኑ ማኅበረሰብ ዘንድ "ሙስሊሞች ሊያጠቁን ይችላሉ" የሚል ስሜት ማደሩን እንደሚያውቁ ይናገራሉ። ይህ ሁኔታ፣ አሁን ካለው አገራዊ ሁኔታ ጋር ተደማምረው ወደትናንቱ ክስተት እንዳመሩም ያምናሉ። ከዚህ መላምት ባለፈ ግን በሞጣ ከተማ እስከ ትናንት 11፡00 ድረስ ከሙስሊም ወንድሞቻችን ጋር በአንድ መዓድ ስንበላ ስንጠጣ እንደነበረ ነው የማውቀው ይላሉ። "እስኪ አስበው ቀን 11፡00 ቤተ ክርስቲያን መቅደስ ገብቶ እሳት የሚለኩስ እንዴት ይኖራል?" ሲሉም ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተነሳ ስለተባለው እሳት በሰው የተነሳ ነው ብለው ለማመን እንደሚቸገሩ ተናግረዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሞጣ ምርጫ ክልል ተወካይ ለሆኑት አቶ ኃይሉ ያዩት ደውለንናለቸው እርሳቸው ለጊዜው ከአካባቢው ርቀው እንደሚገኙና ያላቸው መረጃ በወፍ በረር ያገኙት ብቻ እንደሆነ ነግረውናል። አቶ ኃይሉ እንዳሉት በስልክ ከአካባቢው ባገኙት መረጃ መሠረት እስካሁን ሁለት መስጊድና የተወሰኑ ሱቆች መቃጠላቸውን፣ አሁን ንብረት የማስመለስ ሂደት እንዳለና አንድ ትልቅ ሆቴል ላይ እሳት ተለኩሶ በርብርብ መትረፉን እንደሰሙ ነግረውናል። አሁን አካባቢው ልዩ ፖሊስ በመግባቱ ሰላማዊ ነው ብለዋል። መምህር ሲሳይ የተባለ የሞጣ ከተማ ነዋሪ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ትናንት አስተምሮ ከትምህርት ቤት ሲወጣ ተኩስ እንደሰማና ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ መባሉን ይናገራል። ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ካመራ በኋላ ቤተ ክርስቲያኑ ጉልላት ላይ ጢስ እንደነበረና በመሰላል ወጥተው ተረባርበው እንዳጠፉት ይናገራል። "እሳቱ በምን ምክንያት እንደተነሳ አልታወቀም" ሲልም መንስኤው አለመታወቁን ያስረዳል። ከዛ በኋላ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ሱቆች ወደሚገኙበት አካባቢ እንደሄዱና እነሱን ለማስቆም ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ከቁጥጥር ውጪ መውጣታቸውን ይናገራል። "የተቃጠለው የሙስሊሞች ሱቅ ብቻ አይደለም፤ ለምሳሌ የባለቤቴ ቤተሰቦች ሱቅም ተቃጥሏል" የሚለው ሲሳይ፤ ወጣቶቹ ከሱቆቹ በኋላ ወደ መስጊዶቹ እንደሄዱና ርብርብ ቢደረግም ማስቆም እንዳልተቻለ ያክላል። ከተቃጠሉት መካከል ማርዘነብ ህንጻ እንደሚገኝበት ጠቅሷል። ከሳምንታት ቀደም ብሎ "ማርዘነብ ህንጻ ውስጥ የተሰበሰቡት ሙስሊሞች ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ከፍለው ሊያቃጥሉ ነው" የሚል ወሬ በማኅበራዊ ሚዲያና በሻይ ቤቶች ጨምር ውስጥ ውስጡን ይነዛ እንደነበር ሲሳይ ይናገራል። "እንደዚህ ያሉ ወሬዎች የእርስበርስ ግጭት ለማስነሳት የሚፈልጉ ኃይሎች የሚነዙት ነው ብንልም የሚሰማን አጣን" "ወጣቶቹን ለማስቆም ከፍተኛ ጥረት አድርገን ነበር። ግን አልሆነም። የሕዝብ ማዕበሉን ማን ያቁመው። ሁሉም ነገር ከቁጥጥር ወጣ። አድማ በታኞችም 3፡00 ሰዓት አካባቢ ነው የደረሱት" ይላል። መምህር ሲሳይ፣ "ዛሬ ለሞጣ የሐዘን ቀን ነው፤ ማኅበረሰባዊ ኪሳራ ነው የደረሰብን፤ ሙስሊም ወንድሞቻችንን አሳዝነናል" ሲልም በደረሰው ነገር የተሰማውን ገልጿል። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ጀማል መኮንን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ትናንት የሞጣ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ቃጠሎ ህብረተሰቡ ተረባርቦ ካጠፋው በኋላ፤ የተሰባሰው ነዋሪ ወደ መስጊዶች በመሄድ ጥቃት አድርሰዋል። አንድ መስጊድ ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ እንደወደመና ሁለት መስጊዶች ደግሞ በከፊል እንደተቃጠሉ ኮማንደር ጀማል ተናገረዋል። ማርዘነብ የሚባል የመኝታና የሱቅ አገልግሎት የሚሰጥ የአክሲዮን ህንጻ መስታወቱ እንደተሰበረና፣ ቃጠሎ እንደደረሰበትም ጨምረው ገልጸዋል። "አሁን ኅብረተሰቡን የማወያየትና የማረጋጋት ሥራ እየተሠራ ነው፤ በኋላ ለደረሱት ጥፋቶች ምክንያት ተብሎ የሚጠቀሰው በቤተ ክርስቲያኑ ላይ የደረሰው የቃጠሎ ሙከራ ነው" ሲሉም አብራርተዋል። እስካሁን ምንም ተጠርጣሪ እንዳልተያዘ ዞኑ ሪፖርት እንዳደረገም ኮማንደር ጀማል ገልጸዋል። "በአካባቢው ያለው የጸጥታ ኃይል ባደረገው ርብርብ ነው እንጂ ከዚህ በላይም ትልቅ ስጋት እንደነበረ ነው የሰማነው" ሲሉም ተናገረዋል። በአካባቢው ስለሆነው ነገር ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን የደወልንላቸው የሞጣ ከተማ ከንቲባ፣ የከተማዋ የጸጥታ ኃላፊ እና የድርጅት ኃላፊ ሁሉም ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ልናገኛቸው አልቻልንም። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙትን ደውለንላቸው ያልተጣራ መረጃ ልሰጣችሁ አልችልም፤ አጣርተን የደረስንበትን ጊዜው ሲደር እንነግራችኋለን ብለዋል።