text
stringlengths
140
24k
summary
stringlengths
13
164
ወደ ህዋ የሚመጥቁ መንኮራኩሮች የሚያመርተው ቨርጅን ጋላክቲክ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ቱሪስት ይዞ የሚጓዝ በሮኬት የሚወነጨፍ አውሮፕላን ሊሞክር ነው። በእንግሊዛዊው የንግድ ሰው ሰር ሪቻርድ ብራንሰን የተቋቋመው ቨርጅን ጋላክቲክ በቀጣዩ አመት እአአ ሁለት ሺህ ሀያ አንድ ላይ ወደ ህዋ ቱሪስቶችን መውሰድ እንደሚጀምርም ተገልጿል። እስካሁን ከተመዘገቡት ስድስት መቶ ተጓዦች መካከል ጀስቲን ቢበር እና ሊዎናርዶ ዲካፕሪዮ ይጠቀሳሉ። ለዚህም ወደ ህዋ ቱሪስቶችን ማመላለስ ከመጀመሩ በፊት የሙከራ በረራው ይካሄዳል። ሁለት ተጨማሪ የሙከራ በረራዎች የሚደረጉም ሲሆን፤ በሶስተኛውና የመጨረሻው የሙከራ ደረጃ ሰር ሪቻርድ ብራንሰንም ይሳፈራሉ። ላለፉት አመታት ብዙ ሲባልለት የነበረው የህዋ የቱሪስቶች ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ቨርጅን ጋላክቲክ ዝግጅቱን ለማጠናቀቅ እየሞከረ ነው። የመጀመሪያው ሙከራ የሚካሄደው በሁለት አብራሪዎች ብቻ ነው። አብራሪዎቹ የቀድሞው የናሳ ጠፈርተኛ ሲጄ ስታርኮው እና የቨርጅን ጋላክቲክ ዋነኛ የሙከራ ፓይለት ዴቭ ማኬይ ናቸው። በረራው የሚነሳው ከአሜሪካዋ ኒው ሜክሲኮ ነው። የአውሮፕላኑን ዝግጁነት አብራሪዎቹ የሚፈትሹም ይሆናል። የድርጅቱ መሀንዲሶች ቴክኖሎጂውን አሁን ከሚገኝበት ለማድረስ ብዙ ርቀት ተጉዘዋል። ሂደቱ በኮቪድ ምክንያት ቢስተጓጎልም፤ ሰራተኞች ኒው ሜክሲኮ እና ካሊፎርንያ ውስጥ ሲሰሩ ነበር። የዩናይትድ ኪንግደም የህዋ ቡድን ፕሬዘዳንት ዊል ዋይትሆርን በረራው ትልቅ እርምጃ ነው። አስተማማኝና ርካሽ ይሆናል። ሂደቱ ቀላል አልነበረም ብለዋል። እአአ በሁለት ሺህ ላይ ከባድ አደጋ ተከስቶ የህዋ ጉዞ ሂደቱ እንዲመረመር ተወስኖ ነበር። ፕሬዘዳንቱ የህዋ ጉዞ እሽቅድድም አይደለም። ቅድሚያ የሚሰጠው ለደሀንት ነው ብለዋል። አውሮፕላኑ ጠፈርተኞችን ለማሰልጠንም ይውላል። ዋናን ጨምሮ በተለየ ከባቢ አየር ውስጥ መንቀሰቀስና ሌላም ስልጠና ይሰጣል። የህዋ ቱሪዝም እና የህዋ ሳይንስት ውስጥ ስልጠናው ጉልህ ቦታ አለው ሲሉ ተናግረዋል። ቨርጅን ጋላክቲክ በቅርቡ ቱሪስቶችን ወደ ህዋ የሚወስድበትን ዲዛይን ይፋ አድርጓል። ይህም ከምድር ወደ ህዋ ተወንጭፈው ወደ ምድር የሚመለሱበትን መቀመጫ ያካትታል። ከእያንዳንዱ ተጓዥ ፊት ለፊት በሚገኝ ስክሪን ላይ በረራው በቀጥታ ይታያል። ዲዛይኑ ላይ መስኮቶች አሉ። ይህም እስካሁን ከተሰሩ የህዋ መንኮራኩሮች የበለጠ ነው። መስኮቶቹ ተጓዦች ህዋን በደንብ እንዲመለከቱ ለማስቻል ነው የተሰሩት። በጉዞ ወቅት የመቀመጫቸውን ቀበቶ ፈትተው መንሳፈፍም ይችላሉ። ስበት ስለማይኖር ተጓዦች ሲንሳፈፉ ራሳቸውን እንዲያዩ በሚል ትልቅ መስታወትም ተገጥሟል።
ቱሪስቶችን ወደ ህዋ ለሽርሽር የሚወስደው መንኮራኩር ሊሞከር ነው
አሁን ያለው ህወሀት ቆዳ ነው እነ ስብሀትየህወሀት ወራሾች እኛ ነን እነ አባይና አዜብከኢየሩሳሌም አርአያሁለት ቦታ የተከፈለው የህወሀት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሀት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሀት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም መለስ ህወሀትን ገድሎ ነው የሄደው አሁን ያለው ህወሀት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው ህወሀት መቀጠል አለበት ወይስ የለበትም ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ህልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ የህወሀት ወራሾች እኛ ነን ሲል ለነስብሀት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በአም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች ይመለሱ አይመለሱም የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት አደገኛ የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሀኖምና ብርሀነ ገክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።የህወሀት ህልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ህወሀት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።በተያያዘም ጉባኤ ይጠራ በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም ሀድሽ ዘነበ አለም ገዋህድ በየነ ምክሩ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሀት በኩል ከፍተኛ ሀይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሀት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም አዲስአለም ባሌማ አርከበ እቁባይ ቅዱሳን ነጋ ፈትለወርቅ ፀጋዬ በርሄ አባዲ ዘሙ ሀኪሮስ ገሰሰ ተብርሀንበዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።
የህወሀት ፍጥጫ ቀጥሏል ከኢየሩሳሌም አርአያ
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት ዩኤስ አይዲ በኢትዮጵያ የረሀብ ስጋት መኖሩን ገለፀ። ዶሚኒክ ራብ እና ሳማንታ ፓዎር የዩናይትድ ስቴትስ የአለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ ዩኤስአይዲ መሪ እና የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በነበራቸው የጋራ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ የረሀብ ስጋት አለ ስለማለታቸው ድርጅቱ በድረገፁ ላይ አስፍሯል። የዩኤስአይዲ መሪ ሳማንታ ፓወር ከዩኬው የውጭ፣ የኮመን ዌልዝና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶሜኔክ ራብ ጋር በበይነ መረብ አማካይነት ሲወያዩ በኢትዮጵያና በየመን እየጨመረ ነው ስላሉት የረሀብ ስጋት መወያየታቸውን ዩኤስአይዲ አስታውቋል። ባለስልጣናቱ ስለ አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም ግንኙነት መጠናከርን፣ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን፣ የሴቶች ትምህርት፣ የሰብአዊ እርዳታ በጀትና የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ መወያየታቸውንም ድረ ገፁ አትቷል። ጨምሮም እንደ በኢትዮጵያና የመን ባሉ አገራት እየጨመረ ስለመጣው የረሀብ ስጋት መክረዋል ከማለት ውጪ በየትኛው የአገሪቱ ክፍል የረሀብ አደጋ ስጋት እንዳለ ያለው ነገር የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በትግራይ ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊ ነው ብለዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ሰዎች በትግራይ ክልል በረሀብ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ ነው፤ የምግብ እጥረትም እየተስፋፋ ነው ብለዋል። የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሀኖም በጄኔቭ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በትግራይ ያለው ሁኔታ ምናልባት ቃሉ ከገለፀው አስከፊ የሚባል ነው። እጅግ አስከፊ ነው ብለው አራት ሚሊዮን ተኩል ወይም አምስት ሚሊዮን ህዝብ የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚፈልግ ገልፀዋል። ዘጠና አንድ ከመቶ የሚሆነው ህዝብ የምግብ እርዳታን የሚጠባበቅ ነው። በርካታ ሰዎች በእርግጥም በረሀብ እየሞቱ ነው። አሳሳቢ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትም በስፋት አጋጥሟል ብለዋል። በትግራይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያሻቸው ሲገለፅ ቆይቷል። በትግራይ ክልል በርካቶች በረሀብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ ባለፈው ጥር አንድ የመንግስት ባለስልጣን መናገራቸውን ከእርዳታ ሰራተኞች ጋር ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ ሰፍሮ መገኘቱ መዘገቡ ይታወሳል። በፌዴራልና በክልሉ መንግስት መካከል በተፈጠረ ግጭት ከገበያዎች የምግብ አቅርቦት መመናመን፣ በክልሉ ተከስቶ በነበረው የአንበጣ ወረርሽኝና በተያያዥ ምክንያቶች በርካቶችን ለአስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንዳጋለጣቸው የተለያዩ ሪፖርቶች ጠቁመዋል። የተባበሩት መንግስታት ደርጅት ደግሞ በትግራይ አራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ያስፈልገዋል ብሎ ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የሰብአዊ እርዳታ ለዜጎች ለማቅረብ የተቻለውን ሁሉ ሲያደርግ መቆየቱን በተደጋጋሚ ገልጿል። መንግስት አለም አቀፍ የሰብአዊ ርዳታ አቅራቢ ድርጅቶ በመላው ትግራይ ገብተው እንዲሰሩም ከመፍቀዱም በላይ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት በኢትዮጵያ የረሀብ አደጋ ስጋት መኖሩን አመለከተ
በፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስና ክስ ተመስርቶባቸው ጥፋተኛ ከተባሉ በኋላ የዘጠኝ አመት ከስድስት ወራት በላይ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተወስኖባቸው የነበሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ተስፋዬ ብሩ የካቲት ቀን አመተ ምህረት በአመክሮ ከእስር ተፈቱ።ኮርፖሬሽኑ በ አመተ ምህረት አውጥቶት የነበረውን የሞባይል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ጨረታና የተለያዩ እቃዎች ግዥ ያላግባብ የስዊድን ቴሌኮም ኩባንያ ኤሪክሰን እንዲያሸንፍ አድርገዋል ተብለው ዶክተር ተስፋዬን ጨምሮ ከፍተኛ የኮርፖሬሽኑ ሀላፊዎችና ግለሰቦች ላይ በሰኔ ወር አመተ ምህረት የኮሚሽኑ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶ ነበር። በሌላ ፋይል የብሮድባንድ አገልግሎት ላይ ሙስና ፈፅመዋል በሚል ሁለተኛ ክስም ቀርቦባቸው ነበር።ከ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ለኤሪክሰን ከተሰጠው ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ፕሮጀክት ሚሊዮን ብር ግዥ መፈፀሙ በክሱ ተገልፆ ነበር። ግዥው ከመፈፀሙም በተጨማሪ ፕሮጀክቱ በመጓተቱ ምክንያት መንግስት ከ ቢሊዮን ብር በላይ ማጣቱን ኮሚሽኑ በወቅቱ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱ ይታወሳል።በሙስና ተከሰው ከታሰሩት ሰዎች መካከል ዶክተር ተስፋዬን ጨምሮ ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብለው በእስራትና በገንዘብ ተቀጥተዋል። ዶክተር ተስፋዬ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው የተሾሙት በጥር ወር አመተ ምህረት ሲሆን በግንቦት ወር አመተ ምህረት ከሀላፊነታቸው ተነስተው የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ አማካሪ ሆነው ተሹመው ነበር። ለዶክትሬት ዲግሪ ትምህርት ወደ ጀርመን አገር ሄደው የነበሩት ዶክተር ተስፋዬ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካይነት ተጠርተው ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ ለእስር መዳረጋቸው ይታወቃል። በእስር ላይ እያሉ የዶክትሬት ዲግሪያቸውንም አግኝተዋል።ዶክተር ተስፋዬ በ አመተ ምህረት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በ አመተ ምህረት ጥፋተኛ መባላቸው ይታወሳል። ዶክተር ተስፋዬ የእስር ጊዜያቸውን አጠናቀው የካቲት ቀን አመተ ምህረት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
የቀድሞው ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ከእስር ተፈቱ
የግብፅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የራሳቸውን የኢንዱስትሪ ፓርክ ገንብተው ማምረት የሚችሉባቸውን ፋብሪካዎች ለመትከል፣ አንድ መቶ ሀያ ሚሊዮን ዶላር መመደባቸውን የግብፅ ኤምባሲ አስታወቀ። በግብፅ ኤምባሲ የንግድ አገልግሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ዋሊድ አልዛውመር ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ትልልቅ የግብፅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዞን ለማቋቋም የሁለት መቶ ሄክታር መሬት ጥያቄ ለመንግስት አቅርበዋል። ከዚህ ቀደም የኢንዱስትሪ ፓርኩን ለመገንባት ግብፆቹ የመረጡት ቦታ ዱከም ከተማ ላይ እንደነበር ያስታወሱት አልዛውመር፣ መንግስት በበኩሉ ከዱከም ይልቅ በሌሎች አካባቢዎች ፓርኩን እንዲገነቡ በመጠየቁ እንቅስቃሴው ሲጓተት ቆይቷል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት መንግስት በኢንዱስትሪ ቀጣናነት በተመረጡ አካባቢዎች ግንባታ እንዲካሄዱም እድሉን ሰጥቷቸዋል። ግብፆች በሀዋሳ፣ በድሬዳዋ፣ በመቐለና በሌሎች ለኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ በተመረጡና መንግስት እየገነባባቸው በሚገኙ አካባቢዎች የራሳቸውን ፓርክ እንዲያቋቁሙ አማራጭ ሀሳብ መንግስት ማቅረቡን አልዛውመር ጠቅሰዋል። በዚህም ምክንያት የኩባንያዎቹ ልኡካን ቡድን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ጉብኝት ካካሄደ በኋላ ውሳኔውን እንደሚያሳውቅ ሀላፊው ጠቁመዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማሀበራት ምክር ቤት ባልደረባ አቶ መላኩ ጁሀር የኢትዮጵያና የግብፅ ንግድ ምክር ቤት ዳይሬክተር ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። አቶ መላኩ ለሪፖርተር እንዳብራሩት፣ ትልልቅ የግብፅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኙና በተለይ በመድሀኒትና በህክምና መስክ ሶስት ትልልቅ የግብፅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ተዘጋጅተዋል። መንግስት የግብፆችን ጥያቄ ተቀብሎ የኢንዱስትሪ ፓርኩ ከተገነባ፣ በዱከም የሚገኘውን የቻይናውያንን ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን በመከተል ሁለተኛው የውጭ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። በተመሳሳይ ከህንድና ከቱርክም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት የመሬት ጥያቄዎች ለመንግስት ሲቀርቡ መቆየታቸው አይዘነጋም።
የግብፅ ኩባንያዎች በአንድ መቶ ሀያ ሚሊዮን ዶላር የኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት ቦታ እያማረጡ ነው
ኢሳት ግንቦት ፥ ሁለት ሺህ ስምንት በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ በምትገኘው የጊንጪ ከተማ ዳግም ተቃውሞ መቀስቀሱንና የትራንስፖርትና የትምህርት አገልግሎት ከማክሰኞ ጀምሮ መቋረጡን ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ። ተቃውሞ ጨርሶ አልተቋረጠም ሲሉ የገለፁት ነዋሪዎች የፀጥታ ሀይሎች አሁንም ድረስ በከተማዋ ዙሪያ በመሰማራት በህብረተሰቡ ላይ ፍርሀትን አሳድረው እንደሚገኙ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው መናገር ያልፈለጉ እማኞች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። በነዋሪዎች ሲነሱ የነበሩ የተለያዩ የአስተዳደርና የመብት ጥያቄዎች በግባቡ ምላሽ አለማግኘታቸው ተቃውሞው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረጉንም ከነዋሪዎቹ ለመረዳት ተችሏል። ከማክሰኞ ጀምሮ በከተማዋና በዙሪያው ባሉ የገጠር መንደሮች የተቀሰቀሰው ይኸው ተቃውሞ በነዋሪዎቹ ዘንድ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን እያስነሳ እንደሚገኝም ታውቋል። በከተማዋ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎም የፀጥታ ሀይሎች በነዋሪዎች ላይ የሀይል እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውና በርካታ መኖሪያ ቤቶችንም ብርበራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ እማኞች ገልፀዋል። በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች አሁንም ድረስ ግድያና እስራት ቀጥሎ እንደሚገኝ የተናገሩት ነዋሪዎች በፀጥታ ሀይሎች እየተወሰደ ያለው የሀይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል። የገቡበት ያልታወቀ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ሁኔታ መጣራት አለበት ሲሉ ቅሬታቸውን በመግለፅ ላይ ያሉት ነዋሪዎች በጊንጪ ከተማ የተቀሰቀሰው ዳግም ተቃውሞ ወደ አምቦ መዛመቱንና የፀጥታ ሀይሎች ወደ አካባቢው እየተሰማሩ መሆኑንንም አስታውቀዋል። በወታደራዊ አስተዳደር ስር ነው የምንገኘው በማለት በጊንጪና አካባቢዋ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ለኢሳት ያስረዱት እማኞች በባለስልጣናት የተሰጡ መግለጫዎችና ውይይቶች ህብረተሰቡን ሊያሳምኑ እንዳልቻሉም ገልፀዋል። በተያዘው ሳምንት በሀረማያ ዩኒቨርስቲ ተመሳሳይ ተቃውሞ ዳግም አገርሽቶ የሚገኝ ሲሆን አንድ የዩኒቨርስቲ ተማሪም በዚሁ ተቃውሞ በፀጥታ ሀይሎች መገደሉን ማክሰኞ መዘገባችን ይታወሳል። በክልሉ ድጋሚ ተቀስቅሶ የሚገኘው ይኸው የነዋሪዎች ተቃውሞ ከምእራብ ሸዋ በተጨማሪ በወለጋና ምስራቅ ሀረርጌ አካባቢዎች በመዛመት ላይ መሆኑንም ከሀገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
በምእራብ ሸዋ ጊንጪ ተቃውሞ ተቀሰቀሶ የትራንስፖርትና የትምህርት አገልግሎት ተቋረጠ
አዲስ አበባ ፣ጥቅምት ሀያ አምስት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት በህወሀት ላይ በሚወሰደው እርምጃ ከፌዴራል መንግስት ጎን መሆናቸውን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ገለፁ። ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ በሰጡት መግለጫ ህወሀት ኋላ ቀር፣ ከፋፋይ እና ዘረኛ ስርአት በሀገሪቱ ላይ ዘርግቶ መቆየቱን ገልፀዋል። በዚህም በሶማሌ ክልል ህዝብ እና በሀገር ሽማግሌዎች ላይ በተለያዩ ወቅቶች የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈፀም እንደነበረ በመግለጫው አንስተዋል። ህወሀት ከለውጡ በኋላም በሶማሌ ክልል በተለያዩ ብሄሮች እና የሀይማኖት ተከታዮች መካከል ግጭት በመፍጠር አካባቢው እንዳይረጋጋ ቢሰራም፤ በህዝቡና በክልሉ መንግስት ጥረት መክሸፉን ነው የተናገሩት። ዛሬም ቢሆንም ትንኮሳው አይቀርም ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ይህን በመከላከል ለሀገር አንድነት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። አሁን ላይ ፋሽስታዊ አጀንዳው መቋጫ የሚያገኝበት እና ፍትህ የሚሰጥበት ጊዜ ላይ ተደርሷል ብለዋል።
የሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት በህወሀት ላይ በሚወሰደው እርምጃ ከፌዴራል መንግስት ጎን ናቸው አቶ ሙስጠፌ
ሰማያዊ ፓርቲ ከተቋረጠው የድርድር ሂደት እንደገና እንዲመለስ ኢህአዴግ ጥሪ አቀረበ። የኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ለድርጅቱ በፃፉት ደብዳቤ ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ድርድር ለመመለስ የመነሻ ሀሳብ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል። ሰማያዊ ፓርቲ በሰጠው ምላሽ ግን ገለልተኛ አደራዳሪ በሌለበት ውይይት ለመጀመር እንደማይፈልግ ገልጿል። የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ሚያዚያ ስላሳ ሁለት ሺህ አስር ለሰማያዊ ፓርቲ በፃፈው ደብዳቤ የፖለቲካ ድርጅቱ ወደ ድርድር ተመልሶ እንዲገባና የመነሻ ሀሳቦችን እንዲያቀርብ ጠይቋል። በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚእብሄር የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ገዥው ፓርቲ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ይፈልጋል። እናም ሰማያዊ ፓርቲ ምላሹን በ ስምንት ቀናት ውስጥ ለኢህአዴግ እንዲሰጥ ጠይቋል። ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ለኢህአዴግ በሰጠው ምላሽ በኢትዮጵያ እውነተኛ ውይይትና ድርድር እንዲካሄድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖርም ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። ድርድሩ ግን የኢትዮጵያን ህዝብ መሰረታዊ የለውጥ ጥያቄዎች በእርግጠኝነት ሊፈታ ይገባል ነው ያለው። ይህም በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኙትንም እንዲጨምር ሰማያዊ ፓርቲ ፍላጎት እንዳለው ጠቁሟል። ሰማያዊ ፓርቲ የእንደራደር ጥያቄውን በአዎንታዊነት እንደሚቀበለው ቢገልፅም ነፃና ገለልተኛ አስማሚ በሌለበት ግን ወደ ውይይት መመለስ እንደማይፈልግ አስታወቋል። ኢህአዴግ ያቀረበው የእንወያይ ጥያቄ በገለልተኛ አደራዳሪ የሚመራ ከሆነ ሰማያዊ ፓርቲ የመደራደሪያ መነሻ ሀሳቦችን ያቀርባል ብሏል። በኢትዮጵያ የተከሰተውን ህዝባዊ ታቃውሞ ተከትሎ በሀገሪቱ በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ ፓርቲዎች ድርድር መጀምራቸው ይታወሳል። ድርድሩ ከተጀመረ በኋላም ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢዴፓ እና ኢራፓ ቆይተው ከሂደቱ ራሳቸውን አገልግለዋል። ፓርቲዎቹ ከዚህ ቀደም በገለልተኛ አደራዳሪ ውይይቱ እንዲካሄድ ጠይቀው በኢህአዴግ በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱ ይታወሳል።
ሰማያዊ ፓርቲ ከተቋረጠው የድርድር ሂደት እንደገና እንዲመለስ ተጠየቀ
ባለፉት አስር አመታት የተለያዩ ራስን የማበልፀግና የአመራር ስልጠናዎችን ለመካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች በመስጠት የሚታወቀው የስልጠና ማእከል፤በዘንድሮ ክረምት ሰማኒያ ለሚሆኑ ህፃናትና ወጣቶች እራስን የማበልፀግ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ። ስልጠናው በዋናነት ህፃናትና ወጣቶች ከትምህርት እውቀታቸው በተጨማሪ በባህሪያቸው ታንፀው በራሳቸው የሚተማመኑ፣አላማ መር ህይወት የሚመሩና ሀላፊነትን የሚቀበሉ የነገ አገር ተረካቢዎች እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል። በሶስት ዙር በተሰጡት ስልጠናዎች ተሳታፊ የነበሩ ተማሪዎች እንዲሁም ወላጆች እርካታቸውን የገለፁ ሲሆን ስልጠናው በአስርኛው ቀን ሲጠናቀቅ የ አልችልም አስተሳሰብ የቀብር ስነስርአት ይካሄዳል። የቀብር ስነስርአቱ ከመካሄዱ በፊት የሬሳ ሳጥን ይዘጋጅና ሁሉም ተማሪዎች ወደ ኋላ የሚያስቀሯቸው አስተሳሰቦች፣ ለምሳሌ አልችልም፣ ይሉኝታ፣ ያበሻ ቀጠሮ፣ አይመለከተኝም፣ በጎ ነገሮችን ያለማድነቅ አባዜ፣ እኔ ብቻ ልጠቀም ወይም ሁለታችንም አንጠቀም ወዘተ ተፅፈው በሳጥኑ ውስጥ ይገቡና ይቆለፍባቸዋል። በቀብሩ ስነስርአት ወቅትም ተማሪዎች የደስታ ቀናቸው ስለሆነ፣ ሁሉም ነጭ ልብስ ለብሰው ወደ መቃብሩ ይሄዳሉ። በጉዞውም ላይ ቻው ቻው አልችልም፣ ባይ ባይ አልችልም የሚል መዝሙር ይዘምራሉ።የቀብሩን ጉድጓድ ተማሪዎች የሚያዘጋጁ ሲሆን የቀብሩም ቦታ ላይ የአልችልም አስተሳሰብ የቀብር ስነስርአት በንባብ ይሰማል። ከዚያም ሳጥኑ በጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ይቀበራል። በቀብሩ ስነስርአት ላይም ተማሪዎች እነዚህን የቀበሯቸውን ኋላ ቀር አስተሳሰቦች በድጋሚ እንዳያስቧቸው ቃል ይገባሉ። በቀብሩ ላይ የተነበበው ንባብ፣ በሰልጣኞች መኝታ ቤት ውስጥ እንዲለጠፍና ሁልጊዜ ተማሪዎቹ እንዲያዩት ይደረጋል። ሳይረፍድ በልጆቻችን አስተሳሰብ ላይ ለውጥ በማምጣት የወደፊት የህይወት መሰረታቸውን አብረን እንጣል የሚል ጥሪ ማስተላለፉን ያስታወሰው ማእከሉ፤ጉዞውን በዘንድሮ ክረምት በስልጠና መጀመሩን አመልክቷል። ስልጠናው መደበኛ ትምህርት በሚጀመርበት አዲሱ አመትም የሚቀጥል ሲሆን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በየቀኑ የየእለቱ ትምህርት ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚሰጥ ማእከሉ ጠቁሟል።የ የስልጠና ማእከል ራስን የማበልፀግ ስልጠናው እንደ ማንኛውም ትምህርት በአገራችን የትምህርት ስርአት ውስጥ ተካቶ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ተማሪ ከልጅነት ጀምሮ እንዲሰጥ ያለመ ሲሆን ይህም ውጤቱ በእውቀትና በባህሪ የተገነባ ትውልድ ማፍራት ነው ይላል። የአልችልም አስተሳሰብ የቀብር ስነስርአትእኛ ዛሬ እዚህ የተሰበሰብነው እራስን የማበልፀግ ስልጠና የወሰድን ተማሪዎች፣ በዋናነት አልችልም የሚለውን አስተሳሰብና ሌሎችም እራስን ወደ ሀላ የሚያስቀሩ አስተሳሰቦችን ለምሳሌ፡ እድለኛ አይደለሁም ብሎ ማሰብንለይሉኝታ መገዛትንየአበሻ ቀጠሮ የሚባለውን ሰአት የማርፈድ አስተሳሰብሌላ ሰውን ለመምሰል የመፈለግ አባዜአይመለከተኝም የሚለውን አስተሳሰብአሉታዊ ጎኞች ላይ የማተኮር አስተሳሰብድርድር ላይ መሸነፍ፣ መሸነፍ የሚለውን ወይም የዜሮ ድምር አስተሳሰብ ዛሬ ነሀሴ ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት ከቀኑ አምስት ሰአት ላይ ቀብሬያቸዋለሁና ከዚህ በኋላ አነዚህ አስተሳሰቦች ከእኔ ጋር ቦታ የላቸውም። እነዚህ አሮጌ አስተሳሰቦች የአገራችን እድገት ጠንቅ በመሆናቸው በህይወት ዘመናችን ሁሉ ታግለን ከአገራችን ልናጠፋቸው ቆርጠን ተነስተናል። ዛሬ በቀበርናቸው አሮጌ አስተሳሰቦች ፋንታ የሚከተሉትን አስር አዲስ አስተሳሰቦች ለመተግበር ወሰነናል። እራሴን በቀጣይነት በእውቀት ለማሳደግእራሴን ተቀብዬ በማንነቴ ለመኩራት በራሴ ለመተማመንእችላለሁ በማለት በህይወቴ ለስንፍና ቦታ ላለመስጠትበጎ አመለካከትን የህይወቴ መርህ ለማድረግየማድነቅ ባህልን የህይወት መመርያዬ ለማድረግሀላፊነት መቀበልን ከህይወቴ ጋር ለማላመድ የጋራ ተጠቃሚነትን ሁልጊዜ በህይወቴ ለመተግበርጊዜዬን በአግባቡ በመጠቀም ያበሻ ቀጠሮ የሚለውን አስተሳሰብ ለመሻር ኑሮዩን በራይና በአላማ ለመምራት ይህንንም የአልችልም አስተሳብ የቀብር ስነስርአት ፅሁፍ፣ በመኝታ ቤቴ ግድግዳ ላይ ለጥፌ ሁልጊዜ ለማንበብ፤ቃል እገባለሁ ቃል እገባለሁ ቃል እገባለሁ
አሉታዊ አስተሳሰቦችን ቀብሮ፣ በጎ በጎዎቹን ማፅደቅ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ሳኡዲ አረቢያ በአገሯ ውስጥ ለሚገኙ ምእመናን የኡምራ ፀሎትን ከመስከረም ሀያ አራት ጀምሮ እንዲያካሂዱ መፍቀዷን አስታወቀች።ሳኡዲ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለሰባት ወራት እገዳ ጥላ እንደነበር ይታወቃል።አሁን ይፋ በሆነው ውሳኔ በየእለቱ ስድስት ሺህ ዜጎች የፀሎት ስነስርአት እንዲያካሂዱ መወሰኑ ነው የተሰማው።ይህ ቁጥር ከጥቅምት ስምንት ጀምሮ አሁን ካለበት ወደ ሰባ አምስት በመቶ እንደሚያድግ ነው የተገለፀው።ከዚህ በተጨማሪም ሳኡዲ ከጥቅምት ሀያ ሁለት ጀምሮ ከተወሰኑ አገራት የሀጅና ኡምራ ተጓዦችን እንደምታስተናግድ አስታውቃለች።ኮሮና ቫይረስ እስከሚያበቃ ድረስም ይህ አሰራር እንደሚቀጥል የሳኡዲ ዜና አውታሮች ዘግበዋል።የሀጅና ኡምራ ጉዳዮች ሚኒስትር ምእመናኑን የሚመዘግብበት የሞባይል መተግበሪያ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።በዚህም ተመዝጋቢዎች በመተግበሪያው ላይ የሰፈሩ የጤና መመሪያዎችን መከተል እንደሚገባቸው ነው የተነሳው።የሳኡዲ መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በሀምሌ ወር በተካሄደው የፀሎት ስነስርአት ላይ አስር ሺህ ምእመናን መካፈላቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።ይህም በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ ቁጥሩ እጅግ አነስተኛ የሆነ ምእመናን የተሳተፉበት ነበር ተብሏል።ሳኡዲ በሀጅና ኡምራ በየአመቱ ወደ ቢሊየን ዶላር እንደምታገኝ ይፋዊ መረጃዎች ያሳያሉ።በሳኡዲ በአሁኑ ወቅት በቫይረሱ ከተያዙ ሶስት መቶ ስላሳ ሺህ ሰዎች ሶስት መቶ ሺህ የሚሆኑት ሲያገግሙ አራት ሺህ አምስት መቶዎቹ ህይወታቸውን አጥተዋል።ባለፈው ሳምንት አገሪቱ በኮቪድ ምክንያት ለስድስት ወራት ጥላ የቆየችውን የአለም አቀፍ በረራ እገዳ በከፊል ማንሳቷ የሚታወስ ነው።ምንጭ፡ አልጀዚራ
ሳኡዲ አረቢያ የኡምራ ፀሎት ከመስከረም ሀያ አራት ጀምሮ እንዲካሄድ ወሰነች
ዘሀበሻ የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ አወጋን በሚል ራሱን የሚጠራው ድርጅት ከሰሞኑ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው የሙሉ መግለጫዎችን ሲያወጣ ነበር። ይህን ተከትሎ አወጋን ማን ነው አላማውስ ምንድን ነው የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ከአንባቢያን ይነሳሉ። አወጋን ይህን ጥያቄ ለመመለስ አላማውን እና ለምን መመስረት እንዳስፈለገው በፅሁፍ ይተነትናል። መልካም ንባብመግቢያ የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ አማራው ወዶ ሳይሆን ተገዶ እራሱን ከፈፅሞ ጥፋት ይታደግ ዘንድ በአማራ ተወላጅ ወጣቶች ና ሙህራን የተመሰረተ የነፍሳድን ቡድን ሲሆን በአንዲህ አይነት አላማ የተደራጁ የፖለትካም ሆነ የሲቪል ማሀበራትን የሚደግፍ እና መታሰቢያነቱ ከመተከል አውራጃ አማራ በመሆናቸው ብቻ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የመኪና አደጋ በሚል ሰበብ ጅምላ ግድያ ለተፈፀመባቸው ንፁሀን አማራ ወገኖቻችን ነው ።አወጋን ማለት ምን ማለት ነው አወጋን የፖለቲካ ድርጅት ወይንም ነፃ አውጭ ግንባር አይደለም ነገር ግን ኢትዮጵያዊነቱን በመቀማት ላይ የለውን እና በተደጋጋሚ አራሱን እንደወንጀለኛ እንዲቆጥር የተደረገውን የተሳሳተ ፀረአማራ አስተምህሮ እና ስብከት ከአማራ ተወላጅ እንደበት እንዲሁም ይህን ፀረአማራ ስብከት ለተሰበኩ እና ለአማራ ህዝብ መጥፎ አመለካከት እንዲያድርባቸው በተደረጉ ኢትዮጵያውያን ዘንድ አስወግዶ እውነቱን ና የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያስተምረውን በማሳወቅ ና በማስተባበር የአማራ ወጣት ቀጣዩን የሀገርን እድል እጣ ፋንታ መወሰን ሚያስችለውን ስነልቦናዊ እና አካላዊ ብቃት ለመፍጠር የሚደረግ የወጣቶች እንቅስቃሴ ነው ።አወጋን በዋናነት የሚታገለው ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ከገዥው ፓርቲ የቋንቋ ትስስር ካላቸው ጎሳወች ወይም ብሄሮች ጋር ሳይሆን አማራን በዳይ አስመስሎ ከሚነዛ ፀረአማራ የፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር ነው አወጋን አማራው በኢትዮጵያዊነቱ ሀገር ወዳድ በመሆኑ እና ለአንድነት መሰረት ሁኖ መታየቱን እንደ ወንጀል የሚቆጥሩት እና የኢትዮጵያን ና የኢትዮጵያውያንን በመከባበር ላይ የተመሰረተ የጋራ አንድነትን አጥብቀው በሚጠሉ ባእዳን እና ባለፉት የውጭ ሀገር የወረራ ሰአት አባቶቻቸው ስህተት ሰርተው በታሪክ ተወቃሽ ያደረጓቸው የከዳተኛ ልጆች ራሳቸውን ከታሪክ ተወቃሽነት ለማዳን በአማራው ላይ የጥላቻ የፀረአማራ ፖለቲካ ስብከት የተፈፀመውን እና የሚፈፀመውን ወንጀል በመመከት አማራው አሁንም ሳያወላውል እና አንዳቺም ወደኋላ ሳይል ኢትዮጵያን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን አባቶች እናቶችወንድምች እና አህቶቹ ጋር በመሆን ጠብቆ እንዲኖር የሚያነሳሳ የመጀመሪያ ዙር ትግል ነው ።አማራው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለቱን እንደወንጀል የሚቆጥሩት በኢትዮጵያዊነት ዉስጥ ምንም የታሪክ ድርሻ የሌላቸው የባንዳ ልጆች አማራውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እየገደሉት አያስገደሉት ምእተ አመትን ያስቆጠሩ ሲሆን ከዚህ ማሀበረሰብ አብራክ የወጡ ልጆች ሳይቀሩ ነጣጥሎ ማየት እና የዚህ ህዝብ ችግር መፍትሄ በመስጠት ፋንታ ደጋግመው ስለነገሯቸው ውሸት ግራ ተጋብተው አንዳንዶቹም ስለ ወገናቸው አንስተው ቢናገሩ ዘረኛ አንባላለን በሚል ደካማ አስተሳሰብ እና አንዳንዶቹ የሚያገኙት ጥቂት የስልጣን ወይንም የስጦታ መጠን ይቀንስብናል ብለው በሚያስቡ ሆዳሞች ችል ተብሎ አማራው በእጅጉ ተጎድቷል እየተጎዳም ይገኛል።ፀረአማራ ፅንሰ ሀሳብ ይዘው በተነሱ አናሳና ደካማ ግለሰቦች በመሰረቷቸው ድርጅቶች ወያኔና ሻብያ በአማራ ላይና በኢትዮጵያ ላይ ያደረሱተንና እያደረሱ ያሉትን ስህተትወንጀል ና ግፍ ለአማራና ለኢትዮጵያ ህዝብ መዘርዘርና በመዘርዘር ለማሳወቅ መሞከር ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች እንዳይሆን የችግሩ ገፈት ቀማሽ በመሆናቸው ዱዳዩ ተዘርዝሮም ስለማያልቅ እንዴው ለወጉ ያክልአማራ የሆነ ምርኮኛ በሙሉ ይገደል ነበር አማራ ህሙማን በሆስፒታል እንደተኙ በሙሉ በጥይት ተፈጅተዋል አማራው ከገዥው ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚ ነኝ ብለው ከሚታገሉ ድርጅቶች ሞት ብቻ ተችሮት በቀይ ሽህብር እና ነጭ ሽብር በተሰኘው ቀውስ አማራው ቀዳሚ ተጠቂ ነበር ወያኔ እና ሻቢያ ትግላቸው በዋናነት ፀረአማራ ነበር አማራው ከዚህ ሁሉ አምልጦ ከሀገር እንዳይወጣ በጎረቤት ሀገሮች ፅህፈት ቤት ከፍተው እና ተደራጅተው አማራ የሆነውን በሙሉ ያስገድሉት ነበር በ ሶማሊያ በጅቡት በሱዳን በኬንያ አማራ የሆነ እና ጉራጌ ወንድሞቻችን እየተመረጡ በሌላ አስር ቤት እየታጎሩ እና ያለ ፍርድ ትእዛዝ ደካማ አመለካከት ባላቸው ጎሳዎች አማራ በመሆናቸው ብቻ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ አንገታቸው አንደበግ ይታረዱ ነበር ።አወጋን ይሄን በዘረኝነነት ላይ የተመሰረተን ፀረአማራ እና ታሪክ አልባ የሆኑ ጥቂት ደካማ የባናዳ ልጆች የፈጠሩትን የተሳሳተ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ድርጅት ዳግም አንዳይነሳ አፈራርሶ መቅበርና በቦታው በመዋደድ እና መከባበር ላይ ፅኑ የአንድነት ስርአት እንዲመሰረት እና አማራ በዳይ አለመሆኑን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን በማስገንዘብ ብሄራዊ አርቅ ተደርጎ መካሰስ እና መበቀቃል አንዲቀር በጋራ ለሚመሰረተው ጠንካራ ስርአት አማራው እራሱን ብቁ እንዲያደርግ የሚያደርግ የመጀመሪያ ዙር ትግል ነው ። ድል ለወጣቶች የህዝብ ልጆችሞት ለዘረኞች የህዝበ ጠላቶች
የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የተነሳለትን አላማ አስረዳ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት ሀያ ሶስት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለ ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ስምንት መቶ የፖሊስ አባላት በዛሬው እለት አስመርቋል ። በምረቃ ስነ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ዜጎች ሰላምና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሶማሌ ክልል መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ፖሊስ በፖሊሳዊ ሙያቸው ዜጎችን እንዲያገለግሉና ሰላምን እንዲጠብቁ ትልቅ ሀላፊነት አለበትም ነው ያሉት አቶ ሙስጠፌ። የክልሉን ሰላም የበለጠ ለማጠናከርም ሌሎች አንድ ሺህ ምልምል ፖሊሶች በቀጣይ እንደሚመረቁና በሁሉም የፀጥታ መዋቅሩ ላይ በቁሳቁስና በሰው ሀይል ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የክልሉ ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሁሴን ሀሽ በበኩላቸው በሶማሌ ክልል ያለውን አስተማማኝ ሰላም ለማስጠበቅ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ገልፀው በፀጥታ ሀይሉ ላይ በተሰራው ለውጥ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ሶማሌ ብዙሀን መገናኛ ዘግቧል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ፖሊሶች አስመረቀ
በእግር ኳስ ስፖርት ዝናን ያተረፉ እንዲሁም በአመቱ በተሻለ ብቃት ማንፀባረቅ የቻሉ ኮከቦች ክብር የሚያገኙበት ስነ ስርአት ነው፤ የፓሪሱ ባሎን ድ ኦር። ይህ ሽልማት እአአ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስድስት በፈረንሳዩ የእግር ኳስ መፅሄት የአመቱን ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች በመምረጥ ነበር የተጀመረው። እአአ ከሁለት ሺህ አስር ሁለት ሺህ ድረስም ከፊፋ ጋር በመሆን ስነ ስርአቱ ሲካሄድ ቢቆይም ፊፋ በድጋሚ ለብቻው የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ምርጫን ወደ ማድረጉ ተመልሷል። ባሎን ድ ኦር በተለመደው መልኩ በየአመቱ ብልጫ ያላቸውን ተጫዋቾች በማጨት ለሽልማት እያበቃቸው ይገኛል። ዘንድሮም ለዚህ ሽልማት ብቁ ይሆናሉ በሚል የመጀመሪያዎቹን ስላሳ እጩዎች አሳውቋል። ከዝርዝሩ መካከልም ግማሽ የሚሆኑት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች መሆናቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል። የቻምፒዮንስ ሊጉ አሸናፊ የሆነው ሊቨርፑል እንደ ክለብ በርካታ እጩዎችን በማስመረጥ ቀዳሚው ሲሆን፤ የፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ ባለቤት ማንቸስተር ሲቲ ሁለተኛው ክለብ ነው። የሊጉን ዋንጫ ባያነሱም ድንቅ አቋማቸውን በማሳየት፣ ባለ ትልቁን ጆሮ ዋንጫ በማሳካትና በሊጉ ያላቸውን ክብረወሰን በማጠናከር የቀያዮቹ ተጫዋቾች፤ ቨርጅል ቫን ዳይክ፣ ሮቤርቶ ፈርሚኒሆ፣ አሊሰን ቤከር፣ ጆርጂኒዮ ዋይናልደም፣ ትሬንት አሊክሳንደር አርኖልድ፣ ሳዲዮ ማኔ እና ሞሀመድ ሳላህ በዝርዝሩ ተካተዋል። ውሀ ሰማያዊዎቹ በበኩላቸው በርናርዶ ሲልቫ፣ ሰርጂዮ አጉዌሮ፣ ሪያድ ማህሬዝ፣ ኬቨን ደ ብሩይነ እና ራሂም ስተርሊንግን አስመርጠዋል። ባርሴሎና አራት ተጫዋቾቹ በእጩነት ሲቀርቡ፤ ቶትንሀም፣ ጁቬንቱስ፣ ሪያል ማድሪድ፣ አያክስ እና ፒኤስጂ ሁለት ሁለት ተጫዋቾቻቸው በዝርዝሩ ተካተዋል። አርሰናል፣ ባየር ሙኒክ፣ ናፖሊ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ደግሞ በአንድ አንድ ተጫዋቾች ተወክለዋል። አርጀንቲናዊው ምትሀተኛ ሊዮኔል ሚሲና ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ባለፉት አስራ አምስት አመታት በመፈራረቅ ይህን ክብር መጎናፀፍ ችለዋል። ዘንድሮ ይህ ሽልማት ለአዲስ ተጫዋች ወይስ ከሁለቱ ታሪካዊ ኮከቦች ለአንዱ ይደርሳል የሚለውም ከአንድ ወር በኋላ በፓሪስ በሚኖረው መርሀ ግብር ይፋ የሚደረግ ይሆናል። ባለፉት በርካታ አመታት የቻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ያነሱ ኮከቦች የአውሮፓ፣የፊፋና የባሎን ድኦር ሽልማቶችን የማንሳት ሰፊ እድል እንዳላቸው ታይቷል። ይህም ከወራት በፊት የአውሮፓ ኮከብ ተብሎ የተመረጠው ቨርጅል ቫንዳይክ የዘንድሮውን የባሎን ድኦር ሽልማት የማሸነፍ የተሻለ እድል እንደሚኖረው ብዙዎች ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ክሮሺያዊው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ሉካ ሞድሪች ያለፈውን አመት ክብር ማግኘቱ የሚታወስ ነው። አዲስ ዘመን ጥቅምት ሁለት ሺህ ብርሀን ፈይሳ
የባሎን ድ ኦር አዲስና ነባር ንጉሶች ፍጥጫ
በአሜሪካው ግዙፉ ያም ብራንድስ አለም አቀፍ ኩባንያ እና በኢትዮጵያው በላይ አብ ፉድስ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት ፒዛ ሀት ዛሬ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ላይ ከፍቷል። በያዝነው ሳምንት መገባደጃ ላይም አንድ ተጨማሪ ቅርንጫፍ እንደሚከፈት ይጠበቃል። በሚቀጥሉት ሁለት አመታት ደግሞ የቅርንጫፎቹን ቁጥር አስር ለማድረስ ድርጅቶቹ ተስማምተዋል። ስላሳ አምስት ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት ይህ ስምምነት በሁለቱ ቅርንጫፎቹ ሀምሳ አምስት ሰራተኞች ያቀፈ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በሰሀራ ክፍለ ግዛት ለፒዛ ሀት መዳረሻ ሆናለች። እውን ፒዛ ሀት ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ መንግስት ለአለም አቀፍ ንግድ ተቋማት ገበያውን ነፃ እያደረገ እንደሆነ ሊያሳየን ይቻላል የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አብዱልመናን መሀመድ እንዲህ አይነት መደምደሚያ ላይ መድረስ እንደሚከብድ ይናገራሉ። እንዳዛ ማለት ይከብዳል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ከአውሮፓውያኑ ሁለት ሺህ ጀምሮ የኢንቨስትመንት አዋጁን በብዙ መልኩ በማሻሻል የውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች ሊሰማሩ የሚችሉበትን የንግድ ዘርፎች ብዛት እንዲጨምር አድርጓል፤ ይላሉ ባለሙያው። አቶ አብዱልመናን ፒዛ ሀት ኢትዮጵያ ውስጥ የገባበት መንገድ ለየት ባለ ሁኔታ እንደሆነ ይናገራሉ። ፒዛ ሀት ፍራንቻይዝ የንግድ ስም ሽያጭ ነው። ኢትዮጵያውያን ናቸው የድርጅቱን ስም በመውሰድ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ምርቶችን ለተጠቃሚ የሚያቀርቡት፤ ብለዋል። አንደ ምጣኔ ሀብት ባለሙያው ፒዛ ሀት ወደ ኢትዮጵያ የመጣበት ዋነኛ ምክንያት የኢትዮጵያውያን የመግዛት አቅም እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ይያያዛል። በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ የንግድ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ለሌሎች የንግድ ተቋማትም መማበረታቻ ነው፤ ሲሉ ይሞግታሉ። የሚያዘጋጃቸውን ፒዛዎች ከዘጠና እስከ ሶስት መቶ ሀምሳ ብር ለገበያ የሚያቀርበው ፒዛ ሀት ምግቡን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብአቶች በጠቅላላ ከውጭ ሀገር እንደሚያስገባ አስታውቋል። ይህ የድርጅቱ እርምጃ ጥሬ ግብአቶችን በማቅረብ ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ዜጎችን ሊጎዳ አይችልም ወይ ለሚለው ጥያቄ ባለሙያው ምላሽ ሲሰጡ ፣ እንደ ፒዛ ሀት ያሉ ፍራንቻይዝ ተቋማት ለምርቶቻቸው ጥራት እጅጉን ይጠነቀቃሉ። ለዚህም ነው ግብአቶቹ በሙሉ ከአንድ ቦታ እንዲሆኑ የሚመርጡት። በዚህ አካሄዳቸውም ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያን በመጠየቅ ትርፋማ ይሆናሉ ፤ በማለት ሂደቱን ያስረዳሉ። አብዱልመናን ድርጅቱ በገበያው ውስጥ ምን ያህል ስኬታማ ሊሆን የሚችለው ምርቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ሲችል እንደሆነ ይጠቁማሉ። በሳምንት ወደ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሽያጭ ለማከናወን እቅድ እንዳለው ፒዛ ሀት ያሳወቀ ሲሆን ፣አሁን የተተመነለት ዋጋ የተጋነነ እንደሆነ ባለሙያው ይናገራሉ። ዋጋው በሌሎች ሀገራት ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው። በኢትዮጵያም ከሶስት የአሜሪካን ዶላር ለመሸጠት ነው ያሰቡት። ከፍተኛው ሶስት መቶ ሀምሳ ብር አካባቢ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከፍተኛ ገቢ ላለው የህብረተሰብ ክፍል ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፤ ይላሉ። መቀመጫውን ኬንታኪ ግዛት ያደረገው ፒዛ ሀት በአፍሪካ ከአንድ ሺህ በላይ ፒዛዎችን በመለያው የሚሸጡ ሱቆች ያሉት ሲሆን ፣ኩባንያው በአህጉሪቱ አንድ መቶ ሰማኒያ ስምንት ፍቃድ ያላቸው ቅርንጫፎች እንዳሉትም ተዘግቧል።
አለም አቀፍ የንግድ ተቋማትና ኢትዮጵያ ፒዛ ሀት
በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን በተለይም በወራቤ ከተማ በተፈፀመው ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ግጭት ላይ ምርመራ ያደረገው የፍትህ ሚኒስቴር፣ በግጭቱ አፈፃፀም፣ ምርመራና የፍትህ ሂደቶች ላይ የዞኑን አመራሮች፣ የፀጥታ አካላትንና ፍርድ ቤትን በወንጀል ተባባሪነት ወቀሰ። ሚኒስቴሩ በተለይ በዞኑ የሚገኘውን ፍርድ ቤት፣ ፍፁም ገለልተኛ መሆን ያቃተው በሚል የገለፀ ሲሆን፣ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎችን ሆን ብሎ በዋስትና እንዲለቀቁ ማድረጉን በመጥቀስ ወቀሳውን አሰምቷል። በዞኑ የተከሰተው ግጭት ሚያዝያ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰው ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ግጭት ቅጥያ ነው። ሚኒስቴሩ በጎንደር ከተማ ግጭቱን ለመመርመር ባደረገው ጥረት፣ ከእስልምናም ሆነ ከክርስትና ሀይማኖት አባቶች በአግባቡ ድጋፍ እንዳላገኘና በአንዳንድ ቦታዎች ለምርመራ ቡድኑ ቃል እንዳይሰጥ ቅስቀሳ ሲደረግ እንደነበር አስታውቋል። በዚህም የተነሳ ምርመራው በእለቱ የደረሰውን ጉዳት በሙሉና እያንዳንዱን ተደርሶበታል በማያስብል ሁኔታ የተጠናቀቀ እንደሆነ ገልጿል። ፍትህ ሚኒስቴር እነዚህን ወቀሳዎች ያቀረበው በጎንደርና በስልጤ ዞን የተነሱ ሀይማኖትን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች ፣ እንዲሁም በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ የተነሳውን ማንነትን መሰረት ያደረገ ግጭት አስመልክቶ ስለተደረጉ ምርመራዎች፣ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመሆን ሀሙስ ሀምሌ ሰባት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው። በሚኒስቴሩ በኩል መግለጫውን የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ፈቃዱ ፀጋ፣ መጀመሪያ ጎንደር ቀጥሎም ወደ ስልጤ ዞን ለተዛመተው ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ግጭት መነሻው፣ በሀጂ ኤልያስ መካነ መቃብር ይፈፀም የነበረው የሼኽ ከማል ለጋስ ቀብር መሆኑን አስታውሰዋል። መካነ መቃብሩ አበራ ጊዮርጊስ ከሚባል ቤተ ክርስቲያን ጋር እንደሚጎራበት ገልፀው፣ በቤተ ክርስቲያኑ የነበሩ የአብነት ተማሪዎች ድንበር ሊያካልሉ ነው በሚል ለቀብሩ ድንጋይ ሲወስዱ በነበሩ ሰዎች ላይ ድንጋይ መወርወራቸውን፣ የቤተ ክርስቲያኑ ጥበቃ የሆኑ ግለሰብ ደግሞ ጥይት ወደ ህዝቡ በመተኮስ ቦምብ እንዲወረወር ማድረጋቸውን ገልፀዋል። በዚህም በስፍራው የሶስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን አስረድተዋል። በእንዲህ አይነት ሁኔታ በተጀመረው ግጭት የሞቱ ሰዎች ሚያዝያ ሀያ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ሲቀበሩና በተከታታይ ቀናት መቀጠሉ ተገልጿል። ሚኒስትር ዴኤታው፣ ግጭቱ ወደ ከተማ ከሄደ በኋላ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የእስልምና እምነት ተከታዮችን የማምለኪያ ቦታ፣ የንግድ ቦታና የመኖሪያ ቤት በመምረጥ ጉዳት ማድረሳቸውን፣ የእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ አፀፋ መልስ በሚሆን መንገድ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የንግድ ድርጅቶች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የምርመራ መዝገቦቻችን ያስረዳሉ፤ ብለዋል። በጎንደሩ ክስተት ሀያ ሰዎች መሞታቸውንና ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁለት መቶ ሀምሳ የሰው ምስክሮች ከተሰበሰቡ በኋላ፣ በስልሳ ዘጠኝ የተያዙና በስላሳ አራት ያልተያዙ ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱን አቶ ፈቃዱ ተናግረዋል። የጎንደሩን ክስተት የተከተለው የስልጤ ዞን ግጭት ሚያዝያ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ምሽት ላይ በአንድ አሰጋጅና በአንድ ኡስታዝ አማካይነት ቅስቀሳ እንደተፈፀመ የገለፁት አቶ ፈቃዱ፣ ጎንደር የፈሰሰው ደም እናንተ ልትበቀሉት የሚገባ ነው፤ የሚልና ተመሳሳይ ቅስቀሳዎች ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። በማግስቱም በትምህርት ቤቶች መስጊድ ተቃጥሏል የሚል ወሬ በመሰራጨቱ ወደ ብጥብጥ መገባቱን አስረድተዋል። በእነዚህ ቅስቀሳዎች የተነሳሱ ሰዎች በወራቤ ከተማ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ውድመት ማድረስ ሲጀምሩ፣ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ደግሞ፣ ቤተ ክርስቲያናችን እየተቃጠለ ነው፤ ብለው በመምጣታቸው ብጥብጡ መባባሱን አቶ ፈቃዱ አውስተዋል። ቀጥሎም በአካባቢው ያለ መስጊድም ሊቃጠል ነው ከሚል የአደጋ ጊዜ የአዛን ድምፅ በማሰማቱ፣ የበለጠ የሰው ቁጥር እንዲመጣ መደረጉንና ቤተ ክርስቲያኑ ላይ ቤንዚን ተርከፍክፎ ሙሉ ለሙሉ መቃጠሉን ተናግረዋል። በአጠቃላይ በስልጤ ዞን አራት የኦርቶዶክስና ሶስት የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያኖች መቃጠላቸው ተገልጿል። ሚኒስትር ዴኤታው፣ በዚህ መዝገብ ዘጠና ሰባት ሰዎች ላይ ክስ መስርተናል። ከዚህ ውስጥ በእኛ እጅ ያሉት አስር ብቻ ናቸው። ሀያ አንድ ሰዎች አስቀድመን ይዘን በተለያዩ ምክንያቶች ተፈተዋል፤ ካሉ በኋላ፣ ሚኒስቴሩ ከእነዚህ ክስተቶች ጋር በተያያዙ የወንጀል ምርመራዎች ላይ ያገጠሙትን ችግሮች ገልፀዋል። የስልጤ ዞን ከዋና አስተዳዳሪው ጀምሮ ያሉ አመራሮች የፌዴራል መንግስት የምርመራ መዋቅር ወንጀሉን ለመርመር መግባቱን መቃወማቸውን፣ በሂደቱም ለምርመራው ተባባሪ እንዳልሆኑ አቶ ፈቃዱ ተናግረዋል። ወንጀሉ በተፈፀመበት ቦታ በተለይም ወራቤ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠል በቦታው የነበረው የፀጥታ መዋቅር ሰዎች ድርጊቱን ለማስቆም ፍፁም ፈቃደኛ ያልነበሩ፣ ጥረት ያላደረጉ፣ በቦታው ቆመው እንደ ታዛቢ ሲያዩ እንደነበሩ የምርመራ መዝገባችን ያሳያል፤ በማለትም የፀጥታ መዋቅሩን ተችተዋል። በመጠርጠራቸው ክስ የተመሰረተባቸው፣ ነገር ግን በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ሰዎችን በተመለከተም፣ አሁንም ከተማው ውስጥ እንደ ልባቸው እየተንቀሳቀሱ የዞኑ የፀጥታ መዋቅር ለመያዝ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተረድተናል፤ ብለዋል። አቶ ፈቃዱ በምርመራው ሂደት የጊዜ ቀጠሮ የሚሰጠውን ፍርድ ቤት፣ ፍፁም ገለልተኛ መሆን ያቃተው በማለት ወቅሰው፣ በንብረት ማውደም፣ ቤተ ክርስቲያንን በሚያህል ቃጠሎና የሰው ህይወት ባለፈበት የተጠረጠሩ ሰዎች፣ በዋስትና ሆነ ተብሎ የተለቀቀበትና የወንጀሉ ተባባሪ የሆነበት፣ የመንግስት የፍትህ ስርአት መዋቅሩ ወንጀሉን የደገፈበት ሆኖ ያገኘንበት ቦታ ነው፤ በማለት ቅሬታ አሰምተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው መስሪያ ቤታቸው በዞኑ ባካሄደው የምርመራ ሂደት ላይ በመንግስት መዋቅር ካጋጠሙት ችግሮች የከፋው ሲሉ የገለፁት የፍርድ ቤቱን ሁኔታ ሲሆን፣ ሰው የሞተበት ወንጀል ዋስትና የሚያስከለክል ስለመሆኑ ጭምር እየታወቀ ተጠርጣሪዎች የመለቀቃቸውን ጉዳይ ደጋግመው አንስተውታል። ዘጠና ሰባት ሰዎችን መጀመርያ ከተያዙት ስላሳ አንድ ሰዎች ውስጥ ሀያ አንድ በዋስ እንዲወጡ መደረጉን ተቃውመዋል። የፌዴራል አቃቤ ህግ ወለጋና ጋምቤላ ክልልን ጨምሮ ወንጀል በተፈፀመባቸው አካባቢዎች ምርመራ እያደረገ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ፈቃዱ፣ ለምርመራው በየደረጃው ያለው የመንግስት መዋቅር የማያግዝ፣ የማይተባብር፣ ሀብረተሰቡም ደግሞ ኩርፊያ ውስጥ ሳይገባ የማያግዝ፣ የማይተባበር ከሆነ ወንጀልን በአግባቡ መርምሮ ዳር ማድረስ ፈተና እንደሚሆን መታወቅ አለበት፤ ብለዋል።
ፍትህ ሚኒስቴር የስልጤ ዞን አመራሮችን የፀጥታ አካላትንና ፍርድ ቤትን ወቀሰ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ ሶስት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት የሚመራው እና ከስልሳ በላይ አባላትን የያዘው የልኡካን ቡድን ወደ ኤርትራ ሊያቀና ነው። ልኡኩ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከብሄራዊ ቲያትር፣ ከታዋቂ ደምፃውያንና የጃኖ ባንድ ሙዚቀኞችን ያካተተ ከስልሳ በላይ አባላትን የያዘ ነው። የባህል በድኑ ጉዞ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የተፈጠረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው። ቡድኑ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ ከመጭው ሰኞ ጀምሮ ወደ ኤርትራ ይጓዛል። የባህል ቡድኑ በቆይታው በአስመራ፣ ከረን እና ምፅዋ ከተሞች የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶችን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። የኤርትራ የባህል ቡድን ባለፈው አመት የካቲት ወር ላይ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ተመሳሳይ ዝግጅቱን በአዲስ አበባ፣ ባህር ዳር እና ሀዋሳ ከተሞች ማቅረቡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ የባህል ቡድን ወደ ኤርትራ ያቀናል
ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለመጠጥ ውሀ እጥረት ተጋልጠዋል ችግሩን ለመቋቋም አንድ ነጥብ ሁለትአምስት ቢ ዶላር ያስፈልጋልባለፈው ሚያዚያ ሰባት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን የነበረው የድርቅ ተረጂዎች ቁጥር በአሁን ወቅት ወደ ስምንት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ከፍ ማለቱን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለአዲስ አድማስ በሰጠው መረጃ የጠቆመ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት በበኩሉ፤በሀገሪቱ አስር ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሰዎች ለከፍተኛ የመጠጥ ውሀ እጥረት ተጋልጠዋል ብሏል። በሀገሪቱ የድርቅ ተረጂዎች ቁጥር ማሻቀቡ የታወቀው በበልግ አብቃይና በአርብቶ አደር አካባቢዎች ከግንቦት እስከ ሰኔ ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት በተደረገ ጥናት መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል። የወቅቱ የዝናብ ሁኔታ፣ የእርሻ እንቅስቃሴ፣ በማሳ ላይ ያለ የሰብል ሁኔታና የምርት ግምትን ጨምሮ የግጦሽና የውሀ አቅርቦት፣ የእንስሳት አቋምና ጤና እንዲሁም የእርዳታ አቅርቦቱን መሰረት በማድረግ፣ የዳሰሳ ጥናቱ መካሄዱን የጠቆመው ኮሚሽኑ፤ በተገኘው ውጤትም ቀደም ሲል ሰባት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን የነበረው የተረጂዎች ቁጥር ወደ ስምንት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ማሻቀቡ መረጋገጡን ገልጿል። እነዚህ ዜጎችም ለቀጣዩ አምስት ወራት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል። በዚህ የዳሰሳ ጥናት፤ የበልግ ዝናብ መዛባት፣ የመኖና የግጦሽ እጥረት እንዲሁም የምርት መቀነስና የውሀ እጥረት ለተረጅዎች ቁጥር ማሻቀብ ምክንያት እንደሆኑ ተጠቁሟል። የተባበሩት መንግስታት፣ የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት፤ በጥር ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት የተረጅዎች ቁጥር አምስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን እንደነበር፣ በሚያዚያ ወደ ሰባት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ማደጉን፣ አሁን ደግሞ ወደ ስምንት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ማሻቀቡን ጠቁሞ፣ አለማቀፍ ተቋማት ለችግሩ ተገቢውን ትኩረት አለመስጠታቸው አሳሳቢ ነው ብሏል። ሶስት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ በአስቸኳይ ይፈልጋሉ ብሏል ሪፖርቱ። አስር ነጥብ አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ለመጠጥ ውሀ እጥረት መጋለጣቸውን የጠቆመው ይኸው ሪፖርት፤ ሁለት ነጥብ ሁለትአምስት ሚሊዮን አባወራዎች ለከብቶቻቸው አስቸኳይ መኖ እንደሚፈልጉ አስታውቋል። ችግሩን ለመቋቋም አንድ ነጥብ ሁለትአምስት ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ያለው የተባበሩት መንግስታት፤ ሶስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶችም በከፍተኛ የምግብ እጥረት ውስጥ ናቸው ብሏል በሪፖርቱ። በእርዳታ አሰጣጡ ላይ ከደቡብ ሱዳን የሚፈልሱ ስደተኞች መጠን መጨመር ተግዳሮት መፍጠሩንም ጠቁሟል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሜቲሪዎሎጂ ትንበያን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎች በክረምቱ የጎርፍ አደጋ የተጋረጠባቸው ሲሆን እስካሁንም አምስት መቶ ሺህ ያህሉ በጎርፍ ምክንያት ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ይጠቁማል። ከስምንት ነጥብ አምስት ሚሊዮን የድርቅ ተረጂዎች በተጨማሪ፣ በሀገሪቱ አራት ሚሊዮን የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተረጂዎች እንዳሉ ተመልክቷል።
የድርቅ ተረጂዎች ቁጥር ወደ ስምንት ነጥብ አምስት ሚሊዮን አሻቀበ
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ዘሬ ህዳር ሰባት ቀን ሁለት ሺህ አም በኡጋንዳ ተገኝተው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ከፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር መምከራቸው ተሰማ። ኡጋንዳ በፌደራልና በትግራይ ያለውን ጦርነት በውይይት ለመፍታት እንዲቻል የፌዴሬል መንግስት አመራሮችንና የህወሀት አመራሮችን ልታደራድር እንደሆነ የተለያዩ መረጃዎች ከትላንት ምሽት ጀምሮ ሲያሰራጩ እንደነበር ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅመው ግብረ ሀይል መረጃው የተሳሳተ እንደሆነና የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል ለጀመረው የህግ ማስከበር እርመጃ ቁርጠኛ መሆኑን ዛሬ ጠዋት አስታውቋል። ይህ ቢሆንም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ በኡጋንዳ ተገኝተው ከፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር መወያየታቸውን ፕሬዝዳንቱ በቲውተር ገፃቸው ይፋ አድርገዋል። ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ከአቶ ደመቀ ጋር በትግራይ ክልል ያለውን ግጭት በሚመለከት መወያየታቸውንና መምከራቸውን ገልፀው ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ጦርነት ለአፍሪካ አህጉር መጥፎ ገፅታ የሚፈጥር ነው ብለዋል። በአፍሪካ የፖለቲካ ርእዮተአለም ላይ ያሉ ልዩነቶችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በውይይት የመፍታት ትልቅ ችግር መኖሩን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ፤ እኔ ብሄርን መሰረት ያደረገ የፌዴራሊዝም ፖለቲካን ሙሉ በሙሉ አልስማማበትም ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉበትን ምክንያት ግን አልገለፁም።
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ ከኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ጋር በኢትዮጵያ ሁኔታ ዙሪያ መከሩ
የባለስልጣናቱ ሙት አመት በተለያዩ ዝግጅቶች ተዘክሯል ባለፈው አመት ሰኔ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በባህር ዳርና በአዲስ አበባ ከተሞች በጥይት ተደብድበው ህይወታቸው ያለፈው ከፍተኛ የአማራ ክልል ባልስልጣናትና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ላይ የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት፣ በገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለህዝብ እንዲገለፅ የሟቾች ቤተሰቦች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ፃፉ። የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አምባቸው መኰንን ዶክተር ፣ አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴና የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ምግባሩ ከበደ፣ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሰአረ መኰንንና የሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ ሙት አመት በተለያየ ቦታዎች በተለያዩ ዝግጅቶች ሰኔ እና ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ተዘክሯል። የሶስቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት የሙት አመት መታሰቢያ ደም እንለግሳለን እንጂ፣ ደም አናፈስም በሚል መሪ ቃል ጤና ሚኒስቴር አጠገብ በሚገኘው የደም ባንክ ማእከል ደም በመለገስ ታስቦ ውሏል። በመታሰቢያ ስነ ስርአቱ ላይ በክብር እንግድነት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበልና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የከተማ ልማት ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዣንጥራር አባይ ሲገኙ፣ የሟቾቹ ቤተሰቦች ጓደኞቻቸው ተገኝተዋል። በስራ ላይ እያሉ በጥይት ተደብድበው ስለተገደሉት የክልሉ ባለስልጣናት የሚያወሳ ሰፋ ያለ መጣጥፍ የያዘ አምባዬ የተካደው ፍትህ የሚል መፅሄትም ታትሞ ለስነ ስርአቱ ታዳሚዎች ታድሏል። በሀትመቱ ውስጥ ከተካተቱት መጣጥፎች ውስጥ የሟቾች ቤተሰቦች ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዶክተር በቀጥታ ተፅፎ ለ ከፍተኛ የፌዴራል፣ የክልልና የሀይማኖት ተቋማት ግልባጭ የተደረገ ደብዳቤም ተካቷል። በሟቾች ቤተሰቦች በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፃፈው ፍትህ እንፈልጋለን ደብዳቤ እንደሚያብራራው፣ ሰኔ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በአማራ ክልል ባለስልጣናትና በአገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ላይ የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት እንደ ህዝብም ሆነ እንደ አገር አንገት የሚያስደፋ ነው። በወንጀሉ አፈፃፀም ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የነበሩ ተዋንያን፣ በሀሳብ፣ በገንዘብና በቁሳቁስ የደገፉ አካላት እንዳሉ የፀና እምነት እንዳላቸው ሰፍሯል። በክስ ሂደቱም ቁንጮ ተጠርጣሪዎችን ዘንግቶ ጥቂት የሂደቱ ተጠርጣሪዎችን ብቻ ማካተቱ፣ ይባስ ብሎም የአብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች ክስ በፖለቲካ ውሳኔ መዘጋቱና ከእስር እንዲፈቱ መደረጉ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የፍትህ ጠበቃዎችን እንዳሳዘነ ገልፀዋል። የአገረ መንግስቱን ህልውና አደጋ ላይ ለጣሉበት ክህደታቸው ምንም አይነት የወንጀል ተጠያቂ ሳይሆኑ መቅረታቸው፣ አገራዊና ፖለቲካዊ የሽግግር ለውጡን ፍትሀዊነት አደጋ ላይ ጥሎታል የሚል እምነት እንዳላቸውም አክለዋል። የክልል ፕሬዚዳንትና ሁለት ወሳኝ ባለስልጣናት፣ እንዲሁም በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሆነውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ከእነጓደኛቸው ህይወት እንዲቀጠፍ ያደረጉ ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠይቀዋል። የሟቾች ቤተሰቦች የገዳይ አስገዳይ ቡድን የፈፀመው ወንጀል የመላው አገሪቱን የለውጥ አካሄድ ቅርቃር ውስጥ የከተተ፣ አገራዊ ተስፋን ያጨለመና ህዝቡን እጅግ ያሳዘነ በብሄራዊ ክህደት የሚበየን አውዳሚ ተግባር መሆኑንም አበክረው ገልፀዋል። በወንጀሉ የተሳተፉ፣ በገንዘብና በተለያዩ መንገዶች ለግድያው ተባባሪ የነበሩ ተጠያቂ ካለመደረጋቸውም በላይ፣ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩትም ተጠያቂ ሳይደረጉ ክሳቸው በፖለቲካ ውሳኔ መቋረጡ የወንጀሉ ተዋንያንን የልብ ልብ እንዲሰማቸው እንዳደረጋቸውም አክለዋል። እነዚህ ተዋንያን ተጨማሪ ሴራ እንዲጎነጉኑ ህዝባዊ አንድነትን እንዲሸረሽሩ ተጨማሪ እድል እንዲያገኙና ህዝብ ሲታገለው ወደነበረው የቀድሞው አስከፊ ስርአት መመለስ እንዳይሆንም ስጋታቸውን አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወንጀሉን ድርጊት አጣርቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ እውነታውን የሚገልፅ ገለልተኛ ኮሚሽን እንዲቋቋም ትእዛዝ እንዲሰጡላቸውና ወንጀሉን ያቀናበሩ፣ የተሳተፉ፣ ወንጀሉ እንዲፈፀም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሲያደርጉ በነበሩ መንግስታዊ አካላትና ተባባሪዎች ላይ ተገቢው ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የሟቾች ሙት አመት በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ የአምባቸው ዶክተር የትውልድ ስፍራ ፣ እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም ዞን በተለያዩ ስነ ስርአቶችና ለመታሰቢያቸው ችግኝ በመትከል ታስቦ ውሏል። በተመሳሳይ ሰኔ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በአጃቢያቸው በጥይት ተመትው የተገደሉት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሰአረ መኰንንና የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አመራር የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ የሙት አመት መታሰቢያ ስነ ስርአት ተከናውኗል። ከአትላስ ወደ ሯንዳ የሚወስደው መንገድ ጄኔራል ሰአረ መኰንን ጎዳና የሚል ስያሜ ተሰጥቶት መታሰቢያ ሆኗል። በተገደሉበት ሞተ እለት ሰኔ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ታስቦ በዋለው የሙት አመት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ተገኝተው የመንገድ ስያሜውን ቀይ ሪባን የገለጡት፣ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ኢንጂነር ናቸው። ምክትል ከንቲባው የመታሰቢያውን መንገድ ስያሜ ካበሰሩና ወደ ቢሮአቸው ከተመለሱ በኋላ፣ ለአገር ለፍቶ ለአገር መሞት ከክብርም በላይ ክብር ነው። ይኼንን ደግሞ አገሩን ያለ እረፍት በፅናትና በብርታት እያገለገለ የተሰዋው ወንድሜ ጄኔራል ሰአረ ህይወቱ ከማለፉ ከሰአታት በፊት በጋራ ችግኝ ተክለን ነበር። ለጄኔራሉ መታሰቢያነትም በጋራ ችግኝ የተከልንበት ቦታ የመታሰቢያ ፓርክ አስጀምረናል። ቦታው ላይ ያለው መንገድ ከሯንዳ ወደ አትላስ የሚወስደውንም በጄኔራል ሰአረ ስም ሰይመናል፤ ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል።
የሰኔ ግድያ በገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለህዝብ እንዲገለፅ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ቀረበ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአገራዊ መግባባት፣ ለፍቅርና ለይቅርታ የሰጡት ትልቅ ቦታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ድጋፋችን አይለያቸውም ሲሉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ባከሄዱት የድጋፍ ሰልፍ አስታወቁ።ቁጥራቸው በብዙ ሺህ የሚገመት የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በከተማው ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጉት ድጋፍ በሰላማዊ መንገድ ተጠናቋል።በሰልፉ ላይ ከተገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ወጣት ቢኒያም ሰለሞን በሰጠው አስተያየት ወጣቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የለውጥ እርምጃ በመደገፍ ከጎናቸው ይቆማል ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያሳዩት ፅኑ አቋም አስደስቶኛል፤ ዛሬ በሰልፉ የተቀላቀልኩትም ይህን በመደገፍ ነው ያሉት ደግሞ አቶ አለባቸው መኩሪያ የተባሉ የከተማው ነዋሪ ናቸው። አገራችን በርካታ ብሄር ብሄረሰቦችን ያቀፈች እንደመሆኗ በእኩልነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተውን የቀደምት ታሪካዊ እሴቶች ማጠናከር ከምንም በላይ የወቅቱ አጀንዳ ነው ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ ሀላፊነት ከመጡ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያከናወኗቸው ተግባራት የህዝቡን የለውጥ እንቅስቃሴ እንዳቀጣጠለው የገለፁት ደግሞ ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ መሳፍንት ካሴ ናቸው።ህዝቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጀመሩት የለውጥ ጅማሮ አጋርነቱን በተግባር እንደሚያረጋግጥ የገለፁት አቶ መሳፍንት የለውጥ እርምጃው እንዳይቀለበስ እኔም ሆንኩ መላ ህዝቡ የለውጥ ሀይሉን በመደገፍ እንረባረባለን ሲሉ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገራችን ለረጅም አመታት ደብዝዞ የነበረውን ኢትዮጵያዊነት ፍቅርና አንድነት ዳግም እንዲጠናከር የጀመሩት ጥረት አስደስቶኛል ያለችው ደግሞ ወጣት ሳምራዊት ቤተልሄም ናት።በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኝነት የተጀመረውን የዴሞክራሲ የለውጥ ጉዞ ከግቡ ስለማያደርስ ህዝቡ ከዳር አስከዳር የጀመረውን ህዝባዊ ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ወጣት ሳምራዊት ገልፃለች።በህዝባዊ የድጋፉ ሰልፉ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም ፣ ጊዜው የፍቅር ነው ፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሁላችንም በጋራ እንቆማለን የሚሉና የጠቅላይ ሚኒስትሩን የለውጥ ጅማሮ የሚደግፉ በርካታ መፈክሮች ተስተጋብተዋል።የሀይማኖት አባቶችም ሰላምና አንድነትን የሚሰብኩ መልእክቶችን አስተላልፈዋል።ሰልፈኞቹ በአዲስ አበባ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የለውጥ እንቅስቃሴ ለመደገፍና ለሰሯቸው ስራዎች ምስጋና ለማቅረብ ሰልፍ በወጡ ንፁሀን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን የቦንብ ጥቃትም በፅኑ አውግዘዋል።በከተማው የተካሄደው የድጋፍ ሰልፉም ያለአንዳች የፀጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል። ኢዜአ
ዶክተር አብይ አህመድ ለአገራዊ መግባባት፣ ለፍቅርና ለይቅርታ የሰጡት ትልቅ ቦታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ድጋፍ እናደርጋለን የጎንደር ነዋሪዎች
ከእንግዲህም በቀላሉ ከኢትዮጵያ እንደማይወጣ ባለሙያዎች አስታውቀዋል ምንጩ ከወደ ፓስፊክ አገሮች፣ ማእከላዊ አሜሪካ ከመሆኑም በላይ የአሜሪካ የፀደይ ወራት ስያሜ በመያዝና በዩኤስ አሜሪካም ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ የሚጠቀስለትና ፎል አርሚዎርም በመባል የሚጠራው የተምች ወረርሽኝ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገሮችን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ አዳርሶ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅትም ካለፈው አመት የበለጠ ጥፋት በኢትዮጵያ ሊያስከትል እንደሚችል ተገምቷል። በአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ ዩኤስአይዲ አማካይነት በሚመራው ፊድ ዘ ፊውቸር የኢትዮጵያ እሴት ሰንሰለት ፕሮግራም ቺፍ ኦፍ ስታፍ ኢያን ቼስተርማን ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ ወቅት እንዳስታወቁት፣ የተምች ወረርሽኙ የአገሪቱን ሰብሎች በመላመዱና የአየሩ ጠባይ ለመራባት ምቹ ስለሆነለት በዚህ አመት ሊያደርስ የሚችለው ጥፋት ካለፈው አመት ይልቅ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል አስታውቀዋል። በአገሪቱ በተለይም በበቆሎ ሰብል ምርት በሚታወቁ አካባቢዎች እየተዛመተ የሚገኘው የተምች ወረርኝ፣ በበቆሎ እርሻ የሚተዳደሩ አስር ሚሊዮን አርሶ አደሮችን ህልውና የመፈታተን አቅም ላይ ደርሷል ያሉት ቼስተርማን፣ በዚህ አመት ሊደርስ የሚችለው የሰብል ጥፋት በገበሬዎች ከሚመረተው ግማሽ ያህል ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በአገሪቱ የተንሰራፋው ተምች፣ በመጀመሪያ የታወቀው በደቡብ ክልል ሲሆን፣ በወቅቱ ስላሳ በመቶ ሰብል ማጥፋቱን፣ በኦሮሚያ ሀያ አምስት በመቶ፣ በአማራ ክልል ሀያ በመቶ እንዲሁም በትግራይ ክልል በመቶ የሰብል ምርት በተምች መረርሽኝ መጠቃቱን መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ቼስተርማን ገልፀዋል። ቤንሻንጉል ጉሙዝና ጋምቤላም በተምቹ የተጠቁ አካባቢዎች መሆናቸው ታውቋል። የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ሄክታር ገደማ የሚጠጋ የበቆሎ ማሳ በተምች ተጠቅቷል። ይህም በአገሪቱ በበቆሎ ሰብል ከተሸፈነው አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ እንደሆነ የሚኒስቴሩ መረጃዎች አመላክተው ነበር። ይሁንና የመረጃ ክፍተቶች እንዳሉ ሆነውም በዚህ አመት ከዚህም የከፋ ጉዳት ሊከሰት እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል። ባለፈው አመት የወረርሽኙ መምጣትን ተከትሎ በአብዛኛው የግብርና ዘርፍ ተዋናዮች ዘንድ ተምቹ ለአጭር ቆይታ እንደመጣ ይታሰብ ነበር ያሉት ቼስተርማን፣ ተምቹ የመጣው በቱሪስትነት አይደለም። ለብዙ ጊዜ ለመቆየት ነው የመጣው። አሁን ዜግነቱን አግኝቷል፤ ሲሉም አብራርተዋል። በዚህ ሳቢያ መወሰድ ያለባቸው የመከላከል እርምጃዎች እንዲጠናከሩ፣ አርሶ አደሮችም የግብርና ዘዴዎቻቸውን በማሻሻል የተምች ወረርሽኙን መከላከል ወይም ሊያስከትል የሚችላቸውን አደጋዎች መቀነስ ስለሚቻልባቸው መንገዶች ጠቅሰዋል። በመከላከል ረገድ በተለይ አርሶ አደሮች በአግባቡ ያልታረሱ የእርሻ መሬቶቻቸውን በአግባቡ እንዲያርሱ፣ ተገቢውን የአፈር ክብካቤና አያያዝ እንዲተገብሩ፣ ማዳበሪያ በአግባቡ እንዲጠቀሙና ተስማሚና ጥራት ያላቸውን ዘሮች እንዲጠቀሙ መክረዋል። ይህ ሳይደረግ እየቀረ ተምች በራሱ ጥፋት እንዳደረሰ በማሰብ የሚደመጠው እሮሮ ሊጤን ይገባዋል በማለትም ቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ ትኩረት መስጠት የመፍትሄው መጀመሪያ እንደሆነ ጠቅሰዋል። በአገሪቱ የተምች ወረርሽኙን ለመከላከል ከተወሰዱት እርምጃዎች መካከል በእጅ መልቀምና የመድሀኒት ርጭት የተወሰነ ውጤት ማስገኘታቸውን ያስታወሱት ቼስተርማን፣ ከዚህ ባሻገር ግን ተገቢውን የተቀናጀ የተባይ ቁጥጥር ስርአት መተግበርም ከመፍትሄዎች መካከል እንደሚመደብ አስታውቀዋል። በተፈጥሮ ከአሜሪካዎቹ አካባቢ የመጣው ተምች በዝናብ አማካይነት መከላከል እንደሚቻል ሲያብራሩም፣ አርሶ አደሮች ዝናብ በሚጥልበት ወቅት የፀረ ተባይ ርጭት ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። ከዚህ በተጓዳኝ እዚሁ አፍሪካ መገኛው የሆነው ተምች የአሜሪካውያኑ ተምች ዋነኛ ጠላት በመሆኑም በዚህም ረገድ የወረርሽኙን መንሰራፋት መከላከል የሚቻልበት እድል እንዳለ አስታውሰው፣ ይህም ሁሉ ሆኖ ግን ዘንድሮ ከአምናው የበለጠ ወረርሽኝ ሊከሰት ስለሚችል ተገቢው ቅድመ ጥንቃቄ፣ የመረጃ ልውውጥና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩም ጥሪ አቅርበዋል። ባለፉት ወራት ብቻ በአፍሪካ በርካታ አገሮችን ለማዳረስ የበቃው የተምች ወረርሽኝ ተገቢውን የመከላከል እርምጃ ካልተወሰደበት ከሶስት እስከ ስድስት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የሰብል ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ሰሞኑን የአሜሪካ ኤምባሲ ያሰራጨው መረጃ አመላክቷል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ ዋና ዋና የበቆሎ አምራች አገሮች በተምች ወረርሽኝ ተጠቅተዋል። በአፍሪካ በበቆሎ ምርት የሚተዳደሩ የሶስት መቶ ሚሊዮን ሰዎች የወደፊት የምግብ ዋስትና ጉዳይ በተምች ወረርሽኝ አደጋ እንዳንዣበበበት መረጃዎች እያመላከቱ ይገኛሉ። በፍጥነት የሚራባውና የሚስፋፋው ይህ ተምች፣ ጥሩ የአየር ፀባይ ካጋጠመው በቀን እስከ አንድ መቶ ሀምሳ ኪሎ ሜትር የመብረር ብቃት ሲኖረው፣ በአንድ ጊዜ በብዙ ሄክታር ላይ መሬት ላይ የሚገኝ ሰብል ያለ ችግር የመመገብ አቅም ያለው ነው።
የተምች ወረርሽኝ በዚህ አመት ከፍተኛ አደጋ መደቀኑ ተገለፀ
ሁለት መቶ ሰባ አንድ በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የሌላ ብሄር ተወላጆች አቤቱታቸውን ለምርጫ ቦርድ አቀረቡ የሀዋሳ ከተማን ህዝብ መብትና ጥቅም ሊያስከብር የሚችል ገለልተኛ አካል ከከተማው ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በምርጫ ቦርድ አማካኝነት እንዲደራጅ የጠየቁ አካላት አቤቱታቸውን ለምርጫ ቦርድ እንዳቀረቡ ጠየቁ። ቢቢሲ ከኢትየጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳረጋጋጠው የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችን ጥያቄ ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ የተሰባሰበው ኮሚቴ አባላት ጥያቄታቸውን የያዘ ደብዳቤ ለቦርዱ መዝገብ ቤት አስገብቷል። ኮሚቴው ስድስት አመራር አባላት ያሉት ሲሆን የሀዋሳ ከተማን ጉዳይ በተመለከተ ለሲዳማ አመራሮች ብቻ ሳይተው ራሱ ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን እንዲያስፈፅም ለመጠየቅ የተቋቋመ መሆንን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኮሚቴው ዛሬ በፅሁፍ ባቀረበው አቤቱታ ላይ አማራጭ ያላቸውን አምስት ነጥቦችን ያስቀመጠ ሲሆን በሀዋሳ ከተማ ውስጥ አንድ ሚሊዮን ያህል ነዋሪ ስለሚኖር የእነርሱ ድምፅ በሚገባ መደመጥ አለበት ሲል ገልጿል። በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ለመወሰን በአምስት ወራት ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መወሰኑ ይታወቃል። ምርጫ ቦርድ ከባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ብሎ ካስቀመጣቸው ተግባራት መካከል የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ከክልሉ መንግስትና ከዞኑ መስተዳደር ጋር በመመካከር በአሁኑ ወቅት የክልሉና የዞኑ አስተዳደር ዋና ከተማ ሆና የምታገለግለው የሀዋሳ ከተማን ይመለከታል። በዚህም የህዝበ ውሳኔው ውጤት የሲዳማን ክልል መሆን የሚያረጋግጥ ቢሆን በከተማዋ ላይ ሁለቱ አካላት የሚኖራቸውን መብትና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚነሱ የሀብት ክፍፍል ጥያቄዎችን የሚያስተናግዱበትን አሰራር አዘጋጅተው ለቦርዱ እንዲያሳውቁ ጠይቋል። ደኢህዴን የከተማውን ህዝብ ጥቅምና መብት ለማስከብር አቅም የለውም ያሉት የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ታገሰ ማዴቦ የክልሉ አመራርም ሆኑ የከተማው አስተዳደር አካላት በተወሰኑ ሰዎች የተያዙ ናቸው ይላሉ። የኮሚቴው ሰብሳቢ እንደሚሉት ከሆነ የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት፣ የፕሬዝዳንቱ ፅህፈት ቤት ሀላፊ፣ የካቢኔ ጉዳዮች ሀላፊ፣ የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪን የመሳሰሉ የክልሉ ቁልፍ የአመራር ቦታዎች በአንድ ወገን የተያዙ ሲሆን በሀዋሳ ከተማ አስተዳደርም ተመሳሳይ ሁኔታ በመኖሩ የምርጫ ቦርድ የከተማዋን እጣ ፈንታ በተመለከተ የዞኑ አስተዳደር ብቻ አጥንቶ እንዲያቀርብ እንዳያደርግ ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል። የኮሚቴው አባላት በደብዳቤያቸው ላይ እንዳስቀመጡት የዞኑ አመራር ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ ክልል የመሆን ጥያቄውን ሲያቀርብ የሌሎችን ሰዎች በህገ መንግስቱ የተሰጠ የመኖር መብት የሚገድቡ የወጣቶች እንቅስቃሴ ታይቷል ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። ለዚህም ከሀምሌ ሁለት ሺህ ጀምሮ በተለያዩ የሲዳማ ዞን ከተሞች የታየውን የንብረት ውድመት እና ሞት በመጥቀስ ስጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ስለዚህ የምርጫ ቦርድ የከተማዋን እጣ ፈንታ በሚወስነው ውሳኔ ውስጥ ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የተውጣጡ የከተማዋን ነዋሪዎች በገለልተኝነት አደራጅቶ ራሱ እንዲመራው፤ የሀብት ክፍፍልና ሊኖር የሚችል የመብት ጥያቄ ላይም የእነርሱን ተሳትፎ ባካተተ መልኩ እንዲወሰን ጠይቀዋል። ኮሚቴው አክሎም የሀዋሳ ከተማ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ህገ መንግስት፣ አንቀፅ ስድስት የተለያዩ ማህበረሰብ አባላት ተሰባጥረው የሚኖሩባት ከተማ መሆኗ በግልፅ የተቀመጠ በመሆኑ የከተማዋን ተጠሪነት ለፌደራል መንግስቱ እንዲሆን ጠይቀዋል። ኮሚቴው አክሎም የክልሉ ምክር ቤትና ምርጫ ቦርድ ከሚያቋቁመው አካል ጋር የሀብት ክፈልሉንም ሆነ የሚኖሩ መብቶችን እንዲያስከብር ጠይቀዋል። አቤቱታቸውን ከምርጫ ቦርድ ውጪ ለሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት፣ ለፌዴሬሽን ምክርቤትና ለተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ማስገባታቸውን የገለፁት የኮሚቴው ሰብሳቢ ጥያቄያቸው በጎ ምላሽ እንደሚያገኝ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል። ሁለት መቶ ሰባ አንድ
ሀዋሳ ተጠሪነቷ ለፌዴራል እንድትሆን የከተማዋ ህብረ ብሄራዊ ነዋሪዎች ጠየቁ
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ አንድ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በተጠናቀቀው በጀት አመት ሶስት ነጥብ አራት ቢሊየን ዶላር ካፒታል ያስመዘገቡ ሁለት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ስራ መጀመራቸውን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር የሁለት ሺህ በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀሙን አቅርቦ አስገምግማል። የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሚ እንደገለፁት ግብርና፣ አምራች ኢንዱስትሪ፣ ማእድን እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የውጭ ባለሀብቶች በስፋት የተሳተፉባቸው ዘርፎች ናቸው። ኢንቨስት ኢትዮጵያ ፎረም ከአንድ ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን ከሀያ ዘጠኝ ሀገራት ማሰባሰብ መቻሉን እና በፎረሙ ወቅት አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊየን ዶላር ካፒታል ካላቸው ኩባንያዎች ጋር ስምምነት መፈረሙን ጠቁመዋል። በበጀት አመቱ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሰባ አንድ ፕሮጀክቶች ፣ በአገልግሎት ሀያ ሁለት ፕሮጀክቶች እንዲሁም በግብርናው ዘርፍ አንድ ፕሮጀክት ስራ መጀመሩን አንስተዋል። ከእነዚህ ዘርፎችም አንድ መቶ አርባ ስምንት ነጥብ ሶስት ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ምርት ኤክስፖርት መደረጉን ነው ከሚሽነሯ የተናገሩት። በሌላ በኩል ስልሳ ሰባት ሺህ በላይ የስራ እድል መፈጠሩን ጠቁመው ሶስት የግል ኢንዱስትሪ ፓርኮች በግንባታ ላይ እንደሚገኙ መግለፃቸውንም የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ሶስት ነጥብ አራት ቢሊየን ዶላር ካፒታል ያስመዘገቡ ሁለት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ስራ ጀምረዋል
በፖለቲካው አለም ጉልህ ስፍራ ያላቸው ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ በሚል ርእስ የፃፉትን አዲስ መፅሀፍ ያነበብኩት ዘግይቼ ነው ፤ ለመዘግየቴ ሶስት መሰራታዊ ምክንያቶች ነበሩኝ፣ አንዱና ዋናው ዶ ሩ በተለያዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አመለካከት በመገናኛ ብዙሀን በስፋት ስላቀረቡ በመፅሀፉ ውስጥ እምብዛም አዲስ ነገር ያቀርባሉ የሚል እምነት ስላልነበረኝ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ዶ ሩ ራሳቸው በከፊል የጠቀሱት ነው፣ በአገሪቱ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት የሚደረገው ትግል ውስጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ያለ የተቃዋሚ ድርጅት አመራር አባል መሆኑን ሲመለከት፣ ከቅንጦትም ባሻገር በተወሰነ ደረጃ የስራ ፈትነት ወይንም የበለጠ ጠርጣራ ለሆነ ሰው በተግባር ስራ ለመስራት ካለመቻል የመጣ፤ ተግባራዊ ድክመትን ለመሸፈን የሚደረግ ሙከራ ሊመስል ይችላል የሚለው ነው። ሶስተኛው ምክንያቴ ደግሞ ፣ ፋሽን በሚመስል መልኩ በአገር ቤት የሚኖሩ ፖለቲከኞች በተከታታይ መፅሀፎችን በማሳተማቸው ለእነሱ ቅድሚያ ለመስጠት በመፈለግ ነው። ዶክተር ብርሀኑን ያነበብኩት ሁለቱ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ ዶክተር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የህይወቴ ትዝታዎች ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢህአዴግ እንዲሁም ኢንጂነር ሀይሉ ሻውል ህይወቴ እና የፖለቲካ እርምጃዬ በሚሉ ርእሶች ያሳተሟቸውን መፅሀፎች ካነበብኩ በኋላ በመሆኑ፣ በሶስቱም ስራዎች ላይ መጠነኛ ንፅፅር ለማድረግ አስችሎኛል። ዶክተር መረራ ከተማሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ዛሬ ያለውን የአገራችንን ፖለቲካ ግሩም በሆነ መንገድ አቅርበዋል፤ መፅሀፉ ብዙ አስቂኝ ገጠመኞች የተካተቱበት በመሆኑ ፣ በቋንቋና በአርትኦት በኩል የሚታይበትን ጉልህ ችግር አይተን እንዳላየን እንድናልፈው ያስገድደናል። መፅሀፉ በጥሩ አርታኢ እንደገና ቢታረምና ቢታተም የተዋጣላቸው ከሚባሉት የአገራችን መፅሀፎች ተርታ የመመደቡ እድል ከፍተኛ ነው። ዶክተር መረራ የአገራችንን ህልውና እየተፈታተነ የመጣውን፣ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳዎቹ ተዘርቶ በእነ አቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ ተኮትኮቶ ያደገውን የብሄር ፖለቲካ መነሻ ፣ ያመጣውን ግሳንግስ እና የግሳንግሱን ማራገፊያ መፍትሄ አስቀምጠዋል። መፍትሄ ብለው ያስቀመጡትም በመፅሀፉ የመጨረሻ ገፅ እንደሚከተለው ሰፍሯል፣ ለታሪክም ለህዝብም አስቀምጬ ማለፍ የምፈልገው መሰረታዊ ነጥብ ፣ አብዛኛው የትግራይ ሊሂቃን ስልጣን ወይም ሞት ብሎ ስልጣን ላይ የሙጥኝ እስካለ ድረስ ፣ አብዛኛው የአማራ ሊህቃን በአፄዎች ዘመን የነበረውን የበላይነትን መልሼ አገኛለሁ ብሎ የሚገፋውን የህልም ፖለቲካ እስካልተወ ድረስ፣ ብዙሀኑ የኦሮሞ ሊህቃን ኦሮሚያን ለብቻ የማውጣቱን ህልም እስካልተወ ድረስ ሀገራችን ከአደጋ ቀጠና የምትወጣ አይመስለኝም። በሌላ ቋንቋ ለነዚህ መሰረታዊ በሽታዎቻችን መድሀኒት እስካላገኘን ድረስ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምም ሆነ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ፈፅሞ የምታገኝ አይመስለኝም። ገፅ ሁለት መቶ ስልሳ አራት ። ምንም እንኳ አብዛኛው የሚለው ቃል አወዛጋቢ ሊሆን እንደሚችል ቢሰማኝም ፣ ዶ ሩ ያቀረቡት የመፍትሄ ሀሳብ በትኩረት ሊታይ እንደሚገባው ሳላስታውስ አላልፍም፤ በተለይ እነዚህ የሶስቱ ብሄሮች ሊህቃን ህልማቸውን እንዲተው ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው የሚለው ጥያቄ ለእኔ ቁልፍ ይመስለኛል። ዶክተር መረራ በዚህ ዙሪያ የተብራራ መልስ ቢሰጡ ኖሮ መፅሀፋቸውን የበለጠ ሙሉ ማደረግ ይችሉ ነበር እላለሁ። የኢንጂነር ሀይሉ መፅሀፍ የአገራችንን የፖለቲካ ችግር ከግለሰቦች ባህሪ ጋይ ያያዘው በመሆኑ ብዙም ክብደት የሚሰጠው ሆኖ አላገኘሁትም፤ ንድፈሀሳባዊ ትንተናዎች ይጎድሉታል፣ የተአማኒነት ችግሮችም አሉበት በተለይ ከቅንጅት መሪዎች ጋር ስለነበረው የሽምግልና ሂደትና ከዚያ በኋላ ስለተፈጠሩት ኩነቶች ፤ ለተተኪው ትውልድ የሚሰጠው ትምህርት ስለመኖሩም በእጅጉ እጠራጠራለሁ፤ በእርግጥ ኢንጂነር ሀይሉ ብዙ ውጣውረዶችን አልፈው እስካሁን በህይወት ለመቆየት መቻላቸው እድለኛ ሰው እንደሆኑ በመፅሀፋ ለማየት ችለናል፣ አገራቸውን የሚወዱ ሰው መሆናቸውንም አስገንዝቦናል። ኢንጂነር ሀይሉ የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን መንገድ በመከተል መፅሀፉን በሌላ ሰው በማስፃፋቸው ስለፀሀፊነት ችሎታቸው አስተያየት ለመስጠት አያስችልም ። የዶክተር ብርሀኑ ዲሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ የሚለው ርእስ ዘጊ ወይም ለማንበብ የማይጋብዝ ነው፤ በትምህርቱ አለም የዘለቁና የጥናትና ምርምር ወረቀቶችን ለማንበብ ፍላጎት ያላቸው ምሁራን ካልሆኑ በስተቀር፣ እንደ እኔ አይነቱ ተራ አንባቢ በርእሱ ማልሎ መፅሀፉን ለማንበብ ስለመነሳሳቱ እጠራጠራለሁ። መፅሀፉ ውጫዊ ገፅታው ባያማልልም ውስጣዊ ይዘቱ ግን ድንቅ ነው። እንደምንም የጀመርኩትን መፅሀፍ እየተጨነቁና እየፈራሁ፣ እያዘንኩና ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ፣ እግረ መንገዴንም የፀፊውን እይታ፣ የትንታኔ እና የቋንቋ አጠቃቀም ችሎታ እያደነቁኩ ጨርሸዋለሁ። መፅሀፉን እንደጨረስኩ የተናደድኩበት ነገር ቢኖር ፃሀፊው የኢትዮጵያን ችግሮች እንዲያ አድርገው ካቀረቡ በኋላ መፍትሄውን በይደር በመተዋቸው ነው። ከዚህ ቀደም የአገራችንን ሁለተናዊ ችግሮች ማለትም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የተፈጥሮና የህዝብ ብዛትን በአንድነት አጣምሮ፣ በአገራችን ህልውና ላይ የደቀኑትን ፈተናዎች ቅልብጭ አድርጎ ያሳየ ከገብረህይወት ባይከዳኝ መንግስትና የህዝብ አስተዳደር በኋላ የተፃፈ መፅሀፍ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፤ ይህን ስል ሌሎች ድንቅ የፖለቲካ መፅሀፎች አልተፃፉም እያልኩ አይደለም፤ የዶክተር ብርሀኑን መፅሀፍ ለየት የሚያደርገው የተለያዩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ችግሮችን ለይተው በማውጣት እርስበርስ ያላቸውን ትስስር ከግሩም ትንተና ጋር ሁሉም ሊረዳውና ሊጠቀምበት በሚችለው መንገድ ማቅረባቸው ነው ። የምጣኔ ሀብት ትምህርት የማይገባው ሰው እንኳ ቢሆን፣ መፅሀፉን አንብቦ ስለአገራችን ኢኮኖሚ ለመረዳት አይሳነውም። መፅሀፉ የባራክ ኦባማን እንዳስታወሰኝ ብገልፅ ያጋነንኩ አይመስለኝም፣ አጋነኸዋል የምትሉኝ ካላችሁም አንብቡትና ሞግቱኝ። የዚህ መፅሀፍ ትልቁ መልእክት፣ ለእኔ እንደገባኝ፣ የአገራችን ችግር ዲሞክራሲያዊ ስርአትን በመገንባት ይፈታል የሚለው አስተሳሰብ እንደሚታሰበው ቀላል አለመሆኑንና ከአሁኑ መፍትሄ ካልተበጀለት በኋላ ላይ ይዞት የሚመጣው ችግር ቀላል አለመሆኑን ማሳየት ነው ። የብሄር ፖለቲካው በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ የሚኖረው ተፅእኖ፣ በአገራችን ልማትን ለማምጣት የሚገጥሙ ፖለቲካዊና መዋቅራዊ ችግሮች፣ ከአካባቢ ውድመትና ከህዝብ ብዛት ጋር ተያይዞ በመፅሀፉ በዝርዝር ቀርቧል። በአሁኑ ጊዜ በአገራችን እየታየ ያለውን የገቢ አለመመጣጠንም አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር የሚያወጣውን የአንድ መለኪያ ውስኪ ግብዣ በምሳሌነት በማንሳት በደቡብ አፍሪካ እንደታየው በአገራችንም ለወደፊቱ ይዞ ሊመጣ የሚችለውን ጣጣ ፀሀፊው በደንብ አሳይተውናል። መፅሀፉ የውጩ ፖለቲካ በአገራችን ፖለቲካ ላይ የሚያሳርፈውን ተፅእኖ እንዲሁም የአለማቀፉ የንግድ ስርአት በኢትዮጵያ እድገት ላይ ያለውን ተፅእኖ ቢያካትት ኖሮ የበለጠ ድንቅ ይሆን እንደነበር አስባለሁ ። ከዚያ በተረፈ ግን መፍትሄዎቹ በሌላ ክፍል እንደሚቀርቡ መገለፁ በመፅሀፉ ላይ በቂ ክርክር እንዳይነሳ ያደረገው ይመስለኛል። በመፅሀፉ በቀረቡት ችግሮች እና ትንተናዎች ላይ ተቃውሞ የሚኖረው ሰው ይኖራል ብየ አላስብም፣ ተቃውሞ የሚነሳው ችግሮችን ለመፍታት በሚቀርቡት የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ እንደሚሆን በመገመት ቀጣዩ መፅሀፍ አወያይ አካራካሪ ይሆናል እላለሁ። ስለአገራቸው እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ ሁሉ መፅሀፉን እንዲያነቡት እመክራለሁ የዶክተር መረራንም ጨምሮ ። በተለይ በሰላማዊው የትግል ሜዳ ለመፋለም የሚያስቡ ጀማሪም ሆኑ ነባር ፖለቲከኞች የብርሀኑን መፅሀፍ በማንበብና በምርጫ ክርክር ወቅት ይዞ በመቅረብ የመፍትሄው መፅሀፍ ቶሎ እንደሚደረስ በመገመት ምርጫውን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ አልጠራጠርም፤ ስልጣኑን ይረከባሉ ብዬ ባላስብም።
በዶክተር ብርሀኑ ነጋ ዴሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ ና በሁለት ተጨማሪ መፅሀፎች ላይ የቀረበ አጭር አስተያየት ከፋሲል የኔአለም ጋዜጠኛ
የፋይናንስ ተቋማት በሁለት ሺህ ግማሽ አመት አፈፃፀማቸው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አኳያ ብልጫ አስመዝግበዋል። ከ ቱ የግል ባንኮች አሀዛዊ መረጃዎች ውስጥ የተቀማጭ ገንዘብ መጠናቸው ጭማሪ አንዱ ሲሆን፣ በግርድፉ ከሚቀርቡ ሪፖርቶች መረዳት እንደተቻለው፣ ተቀማጭ ሂሳባቸው ከአራት መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል። በሁለት ሺህ መጀመርያ ግማሽ አመት የተመዘገበው ተቀማጭ ሂሳብ ሶስት መቶ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ነበር። የብድር መጠናቸውም ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፣ በግማሽ አመቱ ያስመዘገቡት አጠቃላይ የብድር ክምችት ሶስት መቶ ቢሊዮን ብር ገደማ ነበር። በአመቱ አጋማሽ ያቀረቡት አዲስ የብድር መጠን ሀምሳ ሁለት ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ታውቋል። ባንኮች የገንዘብ እጥረት እንደገጠማቸው በሚገልፁበት በዚህ ወቅት ጭማሪ የታየበት የብድር ስርጭት አስመዝግበዋል። ወደ ኢኮኖሚው የገባው የገንዘብ መጠን ጭማሪ ከማሳየቱም በላይ የባንኮች እንቅስቃሴ አሁንም ቢሆን በተሻለ አካሄድ እየተጓዘ እንደሚገኝ አመላክቷል። ከትርፍ አኳያም የግል ባንኮች የትርፍ ህዳጋቸውን በማሳደግ ውጤታማ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል። ታክስና ሌሎች ተቀናሽ ሂሳቦች ሳይታሰቡ የሁሉም ባንኮች የትርፍ መጠን ከዘጠኝ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ሆኗል። ከ ቱ የግል ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ በግማሽ አመቱ ያስመዘገበው ግርድፍ ትርፍ ሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ዳሸን ባንክ በበኩሉ አንድ ነጥብ አንድስድስት ቢሊዮን ብር ግርድፍ ትርፍ ማስመዝገብ ችሏል። ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ግርድፍ ትርፍ ማስመዝገብ ከቻሉ ባንኮች ውስጥ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ የኦሮሚያ የሀብረት ስራ ባንክ፣ ዘመን ባንክ፣ አንበሳ ባንክና አቢሲኒያ ባንክ ተጠቃሾች ናቸው። ባንኮቹ ከአምስት መቶ እስከ ዘጠኝ መቶ ሚሊዮን ብር ግርድፍ ትርፍ አስመዝግበዋል። ይህም በዚህ አመት መጨረሻ ከቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ሊያስመዘግቡ የሚችሉ ባንኮች፣ ከዚህ ቀደም ከነበሩትና በጣት ከሚቆጠሩት ባንኮች የበለጠ ቁጥር ሊመዘገብ እንደሚችል አመላካች ሆኗል። በሁለት ሺህ አመተ ምህረት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ያገኙት የግል ባንኮች፣ አዋሽ ባንክ ዳሸን ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እንደነበሩ ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የግማሽ አመት አፈፃፀሙን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የሀያ አራት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ እንደቻለ አስታውቋል። እቅዱ ስላሳ አራት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ እንደነበር፣ በውጤቱም የሰባ አንድ በመቶ አፈፃፀም እንዳስመዘገበ ባንኩ ገልጿል። የንግድ ባንክ ከግሉ ዘርፍ ያሰባሰበው የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት ከሶስት መቶ ዘጠና ቢሊዮን ብር በላይ እንደደረሰና የተቀማጭ ሂሳብ ደንበኞቹ ብዛትም በአመቱ መጀመርያ ላይ ከነበረው ሀያ አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ግማሽ አመቱ ላይ የአንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን አዳዲስ አስቀማጮች ታክለው አጠቃላይ የአስቀማጮች ብዛት ወደ ሀያ ሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሊያድግ መቻሉን ባንኩ ጠቅሷል። በዚህ ሳቢያም ከሀያ ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ለማሰባሰብ ችሏል። የሞባይልና የኢንተርኔት ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን በማሳደግ፣ በሂሳብ አመቱ ስድስት ወራት አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የሞባይል ተጠቃሚዎችን ለማፍራት በቅቷል። በግማሽ አመቱ የውጭ ምንዛሪ ገቢው ሶስት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ያስታወቀው ንግድ ባንክ፣ ከወጪ ንግድ ዘርፍ አንድ መቶ ስላሳ ዘጠኝ ነጥብ አራት ሚሊዮን ዶላር፣ ከውጭ ሀዋላ አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ማሰባሰብ በመቻሉና ከብሄራዊ ባንክ አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በማግኘቱ፣ በጠቅላላው ከሶስት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ እንዳስመዘገበ ገልጿል።
በግማሽ አመቱ የግል ባንኮች ከአራት መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ሂሳብ አስመዘገቡ
በሀያኛው ክፍለ ዘመን የመጀመርያው ሩብ ኢትዮጵያ ከውጭው አለም ጋር በአየር ትራንስፖርት ለመገናኛት በር ከፋች አጋጣሚ የተፈጠረበት ነበር። በንግስተ ነገስት ዘውዲቱ ምኒልክ ዘመን፣ በልኡል አልጋ ወራሽ ንጉስ ተፈሪ መኰንን አማካይነት በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀያ አንድ አመተ ምህረት የመጀመርያው አውሮፕላን አዲስ አበባ መድረሱ ይወሳል። ከአውሮፕላን ጋር የተያያዘው ታሪክ እመርታ ማሳየት የጀመረው በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ዘመን ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታሀሳስ ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስላሳ ስምንት አመተ ምህረት ከተመሰረተ በኋላ የመጀመርያውን በረራ መጋቢት ስላሳ ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስላሳ ስምንት አመተ ምህረት ወደ ካይሮ በአስመራ በኩል አድርጓል። ከሰባት አሰርታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለይ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳዎቹና በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳዎቹ ወደ ጄት ዘመን ሲሸጋገር ከፋና ወጊ አብራሪዎች ተጠቃሹ ካፒቴን አለማየሁ አበበ ነበሩ። ከሀምሳ አምስት አመት በፊት የመጀመርያው ቦይንግ ሰባት መቶ ሀያ አውሮፕላን በካፒቴንነት ያበረሩት ካፒቴን አለማየሁ የመጀመርያው አፍሪካዊም አሰኝቷቸዋል። የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት የስራ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሊቀመንበር የነበሩት ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም እንደሚያስታውሱት፣ ቦይንግ ጄት ከአሜሪካ ሲያትል ከቦይንግ ፋብሪካ አውሮፕላኑን እንዲያመጡ የተደረጉት ካፒቴን አለማየሁ አበበና ካፒቴን አዳሙ መድሀኔ ነበሩ። ከስድሳ አመት በፊት በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ አመተ ምህረት የመጀመርያውን የንግድ አውሮፕላን አዛዥ በመሆንና ብቻቸውን ዲሲ ሶስት ሲአርባ ሰባት አውሮፕላን በማብረር ነበር ካፒቴን አለማየሁ አቢይ ተግባራቸውን ማከናወን የጀመሩት።በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ሁለት አመተ ምህረት አየር መንገዱ ወደ ጄት አውሮፕላኖች ለመግባት ሲዘጋጅና ቦይንግ ሰባት መቶ ሀያ ለማስመጣት ሲወሰን መሰረታዊ መስፈርቱን ለማሟላት የልደታ ኤርፖርት ኦልድ ኤርፖርት መለወጥ ነበረበት። በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀያ ስምንት አመተ ምህረት የተቋቋመው የልደታ ኦልድ ኤርፖርት ጄቶችን ለማሳረፍና ለማስተናገድ ምቹ ባለመሆኑ፣ አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ኤርፖርት በሁለት አመት ውስጥ በቦሌ እንዲታነፅ ተደረገ። በሀዳር አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ አምስት አመተ ምህረት በካፒቴን አለማየሁ አበበና ካፒቴን አዳሙ መድሀኔ አማካይነት ጄት አውሮፕላኑ ገባ።የበረራ ትውስታካፒቴን አለማየሁ ህይወቴ በምድርና በአየር በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ ትውስታቸውን እንዲህ አስፍረዋል። የአብራሪነት ሀላፊነቱን ከተረከብኩ በኋላ አንዳንድ መንገደኞች አብራሪው ነጭ ባለመሆኑ ከሚያሳዩት መደናገጥ በቀር ምንም እንከን ሳያጋጥመኝ አየር መንገዱ በሚገለገልባቸው አፍሪካና አውሮፓ መብረር ጀመርኩ። በስልሳዎቹ አሰርታት መጀመርያ ላይ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ ገዥዎች ቀንበር ነፃ ለመውጣት የሚታገሉበት ወቅት ስለነበር ጥቁር ፓይለት በሚያበረው ዘመናዊ ጄት ለመሳፈር እንኳን ለባእዳን ለወገኖቻችንም ቢሆን መደናገጥን ፈጥሮ ነበር። ይኸው የመጀመርያ አለም አቀፍ በረራ አብቅቶ መሬት እንዳረፍን መንገደኞቹ ሲሰናበቱን ከልብ የመነጨ ምስጋና ያቀርቡልን ነበር። አንዳንዶች ኢትዮጵያውያንማ ማመኑም እየቸገራቸው ሳይሆን አይቀርም በአድናቆት ይመለከቱንና ያነጋግሩን ነበር። በተከታታይ በረራዎች የመንገደኞቼ ስጋትና ጥርጣሬ ወደ መተማመን ተለውጦ ባየሁትና በሰማሁት ቁጥር የስራ ባልደረቦቼም ሆኑ እኔ ደስታ ይሰማን ነበር። በስራ ውጤት እምነት ከማግኘት የበለጠ ምን ነገር ይኖራል እርግጥ ነው ስንት ፈተና በትእግስት አልፌ ለዚያ ደረጃ እንደበቃሁ መንገደኞቼ አያውቁም ነበር። ቢያውቁስ ኑሮ አፍሪካዊ ጄት ሲያበር ለመጀመርያ ጊዜ በማየታችሁ ለምን ትፈራላችሁ ለምንስ ትጠራጠራላችሁ ብሎ መጠየቅስ ይቻል ነበር በእኔ ላይ የደረሰው አይነት በተከታዮቹ አብራሪዎች ላይም ደርሶ እነሱም በትእግስትና በፅናት አልፈውታል። የአየር ሀይሉ አለማየሁ አበበካፒቴን አለማየሁ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለመቀላቀል የቻሉት በኢትዮጵያ አየር ሀይል በኩል በማለፍ ነው። በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው ለከፍተኛ ውጤት የበቁ ተማሪዎች ወደ አቪዬሽን ትምህርት እንዲገቡ ሲደረግ የእድሉ ተጠቃሚ ነበሩ። ገፀ ታሪካቸው እንደሚያመለክተው በአየር በነበራቸው የስልጠና ጊዜ ከስዊድን የበረራ አሰልጣኞች የቀሰሙትን ሙያ በመጠቀም የመጀመርያውን የብቻ በረራ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስላሳ ስምንት አመተ ምህረት ለማድረግ ችለዋል። በዚያው አመት ለተጨማሪ የበረራ ትምህርት ስዊድን በመሄድ በአመቱ አጠናቀው ተመልሰዋል። ከስዊድን መልስም በደብረ ዘይት ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የአየር ሀይል ውስጥ በምክትል መቶ አለቃነት ማእረግ የበረራ ክንፍ ዊንግ አግኝተዋል።በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት አመተ ምህረት ከአየር ሀይል ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጥ የሆኑ አብራሪዎች እንዲዛወሩ በተወሰነው መሰረት፣ ከተመራጮቹ አንዱ የነበሩት ካፒቴን አለማየሁ ናቸው። ከሶስት አሰርታት የአገልግሎት ዘመናቸውም ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ስምንት እስከ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አመተ ምህረት ከመጀመርያ የበረራ መኰንንነት እስከ ካፒቴንነት፣ ከመጀመርያው የቦይንግ ሰባት መቶ ሀያ ጄት ካፒቴንነት እስከ አየር መንገዱ የበረራ ዘርፍ ምክትልና ዋና ሀላፊነት ሰርተዋል። ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አንድ እስከ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሁለት አመተ ምህረት ድረስ የኢንተርናሽናል በረራዎች ዳይሬክተር፣ የበረራ ኦፕሬሽን ረዳት ጄኔራል ማኔጀር ሆነው ሲሰሩ፣ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት አመተ ምህረት የመጀመርያው አፍሪካዊ የቦይንግ ሰባት መቶ ሰባት ጄት ካፒቴን ሆነው ሲሾሙ፣ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሁለት የጄት ካፒቴኖች ፈታኝ በመሆን አገልግለዋል።ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አገልግሎታቸውን በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አራት አመተ ምህረት ፈፅመው ከተሰናበቱ በኋላ፣ በኡጋንዳና በየመን አየር መንገዶች ውስጥ በአሰልጣኝነትና በአማካሪነት ለአምስት አመታት ካገለገሉ በኋላ የበረራ ምእራፋቸውን ቋጭተዋል።ከአባታቸው ከአቶ አበበ ደስታና ከእናታቸው ከወይዘሮ ጥሩነሽ ጎበና በቀድሞ የሀረር ጠቅላይ ግዛት ጨርጨር አውራጃ የካቲት ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አመተ ምህረት የተወለዱት ካፒቴን አለማየሁ፣ በሀረር ራስ መኰንን ትምህርት ቤት በአማርኛና በፈረንሳይኛ የሚሰጠውን የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት የተከታተሉ ሲሆን፣ ቀሪውን የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በካቶሊክ ሚሲዮን አጠናቀዋል።በጣሊያን ወረራ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀያ ስምንት አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስላሳ ሶስት ምክንያት ትምህርታቸውን በማቋረጥ በፖስታ ቤት ተቀጥረው ጣሊያን እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ቆይተዋል። ከድል በኋላ በአዲስ አበባ በቀድሞው የባላባት በኋላም መድሀኔ አለም ትምህርት ቤት ገብተው ያቋረጡትን ትምህርት በመቀጠል፣ የሁለተኛ ደረጃ በኮተቤ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል። ባስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤትም ከንጉሰ ነገስቱ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ እጅ ሽልማት ተቀብለዋል። በሶስቱ መንግስታት ዘመን በከፍተኛ የአገርና የሙያ ፍቅር አገራቸውን ያገለገሉት ካፒቴን አለማየሁ፣ ባለትዳርና የአራት ሴቶችና የአራት ወንዶች ልጆች አባት፣ እንዲሁም የአራት የልጅ ልጆች አያት ነበሩ። እውቅትና ልምድን ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በማሰብ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት አመተ ምህረት ህይወቴ በምድርና በአየር የሚል መፅሀፍም አሳትመዋል።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ የቆዩት ካፒቴን አለማየሁ፣ ታሀሳስ ሀያ ስድስት ቀን ሁለት ሺህ አስር አመተ ምህረት በተወለዱ በዘጠና አራት አመታቸው አርፈው ታሀሳስ ሀያ ስምንት ቀን በጴጥሮስ ወጳውሎስ የካቶሊክ መካነ መቃብር ስርአተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁእ ካርዲናል አቡነ ብርሀነየሱስ መሪነት በለገሀር መድሀኔአለም ቤተ ክርስቲያን ፀሎት ፍትሀት ሲከናወን፣ ከወዳጅ ዘመድ ውጪ በቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ በስርአተ ቀብሩ የመንግስት ከፍተኛ ሹማምንትም ሆኑ የአየር መንገዱ ከፍተኛ ሀላፊዎች አለመገኘታቸው ታይቷል።በኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት የስራ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሊቀመንበር የነበሩት ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም፣ ልእልት ሳራ ግዛው፣ ልኡል በእደ ማርያም መኰንን ሀይለ ስላሴ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮሎኔል ስምረት መድሀኔ በስርአተ ቀብሩ ተገኝተዋል። ከኢትዮጵያ አየር ሀይል እስከ አየር መንገድ ለአፍሪካም ጭምር ያኮሩ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ስርአተ ቀብር በክብር ዘብና በማርሽ ባንድ አለመፈፀሙም ቅሬታ አሳድሯል።
ካፒቴን አለማየሁ አበበ የመጀመርያው አፍሪካዊ ጄት አብራሪ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሁለት ሺህ አስር
አዲስ አበባ ስድስቱን ዋና ዋና በሮቿን ከፍታ እንግዶቿን ስትቀበል ሰንብታለች። መስከረም ሀያ አራት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት መስቀል አደባባይ የባህል ልብስ ለብሰው ጣእመ ዜማ እያሰሙ በሚተሙ ህዝቦች ተሞልታ ጠጠር መጣያ ጠፍቷታል። የሸዋ ፣የባሌ፣ የአርሲ፣ የወለጋ፣የጉጂ፣ የቦረና የሀረር የጂማ የከሚሴና ሌሎችም የኦሮሞ ብሄረሰብ ባህላዊ ጭፈራዎች እዚህና እዚያም ይደመጣሉ። አብሮነታቸውን፣ አክብሮታቸውን፣ ፍቅራቸውንና አንድነታቸውን ለመግለፅ የታደሙ ሌሎች ብሄረሰቦችም በባህላዊ ልብሳቸው ተውበው በጭፈራ የመስቀል አደባባይን አድምቀውታል። የሲዳማ ፣ የሶማሌ፣ የማረቆ፣ የቀቤና የከንባታ እና ሌሎችም ብሄር ብሄረሰቦች በኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በአል ላይ ተገኝተው የዚህን ታላቅ የምስጋና በአል በረከት ከወንድሞቻቸው ጋር በመሆን ተቋድሰዋል። አቶ ውባ ባልቻ ከደቡብ ክልል ማረቆ ብሄረሰብ የመጡ የበአሉ ታዳሚ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት የኢሬቻ ባህል ፈጣሪን የማመስገኛ ቀን ከመሆን ባለፈ የሰው ልጆችን አንድነትና ፍቅር የሚያጠናክር የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ እሴት ነው። በዚህ በአል ላይ ሲገኙ የመጀመሪያቸው እንደሆነ የተናገሩት አቶ ውባ ኢሬቻ ከሚነገርለት በላይ ህዝቦችን የማስተሳሰርና በአንድላይ የማቆም ሀይል አለው።የሀገራችን ይህን መሰል ባህላዊ እሴቶቻችን አባቶቻችንን ለዘመናት በመቻቻልና በፍቅር እንዲኖሩ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ኢሬቻ አስረድቶኛል ብለዋል። ወጣቱ የአባቶቹን እሴቶች ጠብቆ አንድነቱን በማጠናከር የሀገሩን ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበትም ጠቁመዋል። በሁሉም ብሄረሰብ ውስጥ ችግር ፈቺ የሆኑ ባህላዊ እሴቶች እንዳሉ በመጥቀስም ሁሉንም የጋራ ጥቅም ላይ በማዋል ለህዝቦች ሰላማዊ ግንኙነት ድልድይ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። የማረቆ ብሄረሰብ ከኦሮሞ ጋር ጉርብትና ብቻ ሳይሆን የደም፣ የባህልና የቋንቋ መወራረስ እንዳለው የተናገሩት አቶ ውባ በተለይም ሁለቱም ብሄረሰቦች የሚከተሉት የገዳ ስርአት ተቀራራቢነት እንዳለውና የኩሽ ነገድ መሰረት ያላቸው መሆናቸውን አስረድተዋል። በሽምግልና ፣ በጋብቻና በሀዘን በአጠቃላይ በአኗኗር ዘይቤ ተመሳሳይ የሆኑ ባህሎች እንዳላቸው ጠቁመዋል። ከሲዳማ ብሄረሰብ በበአሉ ላይ የታደሙት አቶ ወልደየሱስ ዮሴፍ ናቸው። እርሳቸውም የገለፁት የሲዳማና የኦሮሞ ብሄረሰቦች ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ናቸው።ሁለቱ ብሄረሰቦች በደም፣ በቋንቋና በባህል የተሳሰሩ መሆናቸውን በማመላከት ልክ እንደ ኢሬቻ ሁሉ ጨንበላላም የተጣሉ የሚታረቁበት፣ ቂምና ቁርሾ የሚወገድበት፣ ፍቅርና አንድነት የሚጎለብትበት ባህላዊ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል። በጨንበላላ በአል ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ እንስሳትም ጭምር ተፈጥሯዊ መብታቸው ተጠብቆላቸው በነፃነት የግጦሽ ሳር ወደሚያገኙበት መስክ ይሰማራሉ። ሁለቱም ባህላዊ እሴቶች ሰላምና ፍቅርን የሚሰብኩና ከአንድ ወንዝ የተቀዱም ናቸው ብለዋል። ብሄር ብሄረሰቦች ገንቢ የሆኑ በህላዊ እሴቶችን በጋራ በማክበርም ለማህበራዊ መስተጋብራቸው ገንቢ የሆኑ ቱርፋትን ማቆየት እንዳለባቸው አቶ ወልደየሱስ መክረዋል።ባህላዊ እሴቶችን በጋራ የማክበር ጅማሮም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። ህዝቦች ሁልጊዜ የሚያለያይዋቸውን ወደ ጎን ትተው አንድ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች ላይ መተባበራቸው ለሰላማቸውና ለብልፅግናቸው ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። ኢሬቻ የኦሮሞ ፣ ፊቼ ጨንበላላ የሲዳማ መገለጫዎች ብቻ ሳይሆኑ የሀገር ቅርስና የቱሪስት መስህብ በመሆን በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎችም ጉልህ ሚና እንዳላቸው በማጤን ሁሉም ዜጋ ባህሎቹን የእኔ ነው ሊል ይገባል ብለዋል። ሌላው ከቀቤና ብሄረሰብ የመጣው ወጣት ሀቢብ ከድር ነው። ወጣቱ እንደሚለው የኢሬቻበአል የፍቅርና የአንድነት መገለጫ ነው። ስለዚህ ወንድማማችነታችንንና አጋርነታችንን ለማሳየት፣ ከሚዘራው ፍቅርና ሰላምም ለመቋደስ ከዋዜማው ጀምሮ በበአሉ ተሳትፈናል። ሀገራችን በተለያዩ ችግሮች እየተፈተነች ባለችበት ወቅት ባህላዊ እሴቶችን በጋራ ማክበር ህዝቦችን ለማስተሳሰርና ችግርም ሲኖር በይቅርታ እንዲሻገሩ የሚያስችል መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ተናግሯል ። በተለይም ወጣቱ ትውልድ የአባቶቹን ፈር በመከተል ባህላዊ እሴቶችንና የሰላም አማራጮችን ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባም ይመክራል። የኢሬቻ የምስጋና በአል በሚሊየን የሚቆጠሩ ህዝቦች የተሳተፉበት መሆኑን የተናገረው ወጣት ከድር ሁሉም ሰው የበአሉን አላማ ተረድቶ በየአካባቢው የሚከሰቱ ችግሮችን በይቅርባይነት፣ በመቻቻልና በሰላማዊ መንገድ መሻገር አለበት። በየብሄረሰቡ ውስጥ ያሉ እንደዚህ አይነት ጠንካራ ፋይዳ ያላቸው ባህላዊ እሴቶችም በጋራ ማክበር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጿል።አዲስ ዘመን መስከረም ሀያ አምስት ሁለት ሺህ ኢያሱ መሰለ
ብሄር ብሄረሰቦችን አቃፊው ሆራ ፊንፊኔ
ምን ሆነህ ነው ከስራ መልስ ኮምፒዩተር ላይ የተጠመድከው ዛሬ እንኳን ልጆቹን አታገኛቸውም አስቸኳይ ስራ ላይ ነኝ፣ አልችልም። ቢቀር ይሻል ነበር። ምኑ ስልጣኑ። እንዴ ምነው ለምን ቤተሰብን ችላ የሚያስብል ስልጣን ቢቀር ይሻላል። ህዝብን ማገልገል ቤተሰብን ማገልገል ነው ተባብለንና ተስማምተን አይደል እንዴ የተቀበልኩት ዛሬ ምን ተፈጠረ ህዝብን ማገልገል ከቤተሰብ የሚነጥል ከሆነ ቢቀር ይሻል ነበር። እኔ ስራ ሲበዛብኝ አንቺ አለሽ፣ ዛሬ በአጋጣሚ አስቸኳይ ጉዳይ ገጠመኝ እንጂ ለቤተሰቤ ጊዜ እንደማልሰስት የምታውቂው ነው። ቤተሰቡን ጥሎ ቢሮ ውስጥ መሰወርን ምን ልትለው ነው ነገርኩሽ እኮ ዙም አለብኝ አልኩሽ። ምን አለብኝ መኖሪያ ቤት ውስጥ ብዙ አያቆይም፣ ይኸው ሊጀምር ነው እንዴ እዚህ መኖሪያ ቤት ውስጥ ለቤተሰቡ አታስብም እንዴ ምን እያልሽ ነው እንዴ ቢታወቅስ ይታወቃ፣ ምን ችግር አለው ምን ችግር አለው ጤነኛ አይደለህም እንዴ ልታስጨርሰን ነው ፍላጎትህ አልገባኝም እስኪ ልየው ኮምፒዩተሩን አሳየኝ ተመልከች ይኸው፣ ምንድነው እንደዚህ ያሰጋሽ ዙ አልነበር እንዴ ያልከው ዙም ነው ያልኩሽ፣ የቪዲዮ ስብሰባ ነው። ወይ ጉድ እንደዚያ ነው እንዴ ምን መስሎሽ ነው እኔማ ዙ ያልክ መስሎኝ ነበር። ዙ እ እኔማ ሊያስጨርሰን ነው እንዴ ብዬ ሰግቼ ነበር። ክቡር ሚኒስትሩ ዘወትር ጠዋት ቢሮ ሲገቡ እንደሚያደርጉት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አማካሪያቸው የሚያቀርበውን የህዝብ ስሜትና አስተያየት ለማዳመጥ ተዘጋጅተዋል እሺ የህዝቡ ስሜት በዚህ ሳምንት ምን ይመስላል ክቡር ሚኒስትር በዚህ ሳምንት ትንሽ በአመዛኙ በአንድ ጉዳይ ላይ ያተኮረ፣ ነገር ግን ጠንካር ያለ ስሜትና ትችት እየተንፀባረቀ ነው። በምን ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው የመስሪያ ቤታችን ባልደረቦች እንደተሳተፉበት እንዳለፈው ሳምንት በኑሮ ውድነት ላይ ያተኮረ አይደለም። አንተ ደግሞ መንግስት ካልወሰነ እኔ ደመወዝ ጭማሪ መወሰን አልችል፣ ምን አድርግ ነው የምትለኝ እኔ ምን አጠፋሁ ክቡር ሚኒስትር የኑሮ ውድነትን ከማሀበረሰቡ በላይ የዚህ መስሪያ ቤት ሰራተኞች ጉዳይ ታደርገዋለህ፣ አስሬ ታነሳዋለህ፣ ምን አድርግ ነው የምትለኝ በየሳምንቱ የሚነሳ ጉዳይ ስለሆነና በዚያውም ለማስታወስ ያህል እንጂ፣ በዚህ ሳምንት እንኳን የኑሮ ውድነት አልተነሳም። ይኸው አሁንም አነሳኸው። አልኩ እንዴ ሳይታወቀኝ ነው። በል የዚህን ሳምንት ጉዳይ አቅርብ። እሺ ክቡር ሚኒስትር፣ ቀደም ብዬ እንዳልኩት በዚህ ሳምንት ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዘ ነገር ባይነሳም ጠንካራ ትችቶች ተሰንዝረዋል። ኑሮ አደረግከው እኮ ሪፖርቱን ወደ ዋናው ነጥብ እየመጣሁ ነው ክቡር ሚኒስትር፣ በዚህ ሳምንት ኧረ እባክህ እባክህ ተቸግሬ እኮ ነው ክቡር ሚኒስትር ምንድነው ያስቸገረህ በዚህ ሳምንት የተነሳውን እንደ ኑሮ ውድነት ጉዳይ በቀላሉ ለመግለፅ ያስቸግራል። ምን ጉድ ነው ዛሬ የገጠመኝ ይኸው ከቡር ሚኒስትር ላወራው ነው። እሺ ቀጥል። ሀሳቡ ሲጠቃለል አሁን ያለውን መንግስት ካለፈው መንግስት ጋር አነፃፅረው ተችተውታል። ሀሳቡ ሲጠቃለል ምን እንደሆነ ሳትገልፅ ምን ብለው ነው ያነፃፀሩት ተናገር ካሉኝ ምን አደርጋለሁ እንግዲህ ስሙኝ፣ የበፊቱ መንግስት ኪስ አውላቂ ነበር ብለው ይነሳሉ እሺ አሁን ያለውንስ ምን አሉ የአሁኑ ልብ አውላቂ ነው ይላሉ፣ ይኸው ነው። መነሻው ምንድነው አፍ የሚያስከድን የተባለው ጉዳይ እ እሱ ነው። እሱ ምን እሱ ነው መነሻው። ክቡር ሚኒስትሩ ከአውሮፓ አገሮች ተወክለው ከመጡ ዲፕሎማቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው መልካም፣ ካነሳችሁት ሀሳብ የተረዳሁት ነገር ለዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችን እንዲሁም ለአገራችን ዋጋ እንደምትሰጡ ነው። ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር በትክክል ተረድተውታል ክቡር ሚኒስትር ነገር ግን አንድ ቀን እንኳ በስህተት ቡድኑን ስትተቹ አላስተዋልንም። ክቡር ሚኒስትር በይፋ አልተናገርነውም ማለት እንደግፈዋለን ማለት አይደለም፣ በይፋ ያላወገዝነው ከሰብአዊነት ጋር የሚቃረን ሆኖብን ነው። አልገባኝም ክቡር ሚኒስትር እንደሚያውቁት ቡድኑ ከበባውን ለማስከፈት እንጂ ሌላ ፍላጎት እንደሌለው ግልፅ አድርጓል፣ ይህ ደግሞ ከሰብአዊነት ጋር የተገናኘ በመሆኑ ለመቃወም አስቸግሮናል። ከበባውን ለማስከፈት የቱ ጋ ነው ከበባው የሚከፈተው ወይስ በጋራ ያወጣችሁለት ስም ነው በጭራሽ እንደዚያ አይደለም ክቡር ሚኒስትር። እንደዚያ ካልሆነ ከበባው የቱ ጋ እንደሚከፈት የምታውቁትን አስረዱኛ ምነው ዝም አላቸሁ ከበባው የሚከፈተው ምኒልክ ቤተ መንግስት ነው አሁን ግልፅ ሆኖልናል፣ እኛ ከሰብአዊነት አንፃር እንጂ በዚህ መንገድ አላየነውም፣ ተቀራርቦ የመነጋገር ጠቀሜታው ይህ ነው፣ በእርግጠኝነት ጉዳዩን አሁን ካሉት ነገር አኳያ መርምረን የመንግስታችንን አቋም በፍጥነት እናሳውቃለን። ተስፋ አደርጋለሁ። ሌላው በቀጣናው ካሉት አጋሮቻችን መካከል ሱዳንና ኢትዮጵያ ቅድሚያ የምንሰጣቸው ወዳጆቻችን ናቸው፣ አንዱ የመጣንበት አንገብጋቢ ጉዳይም በሱዳን የተፈጠረውን አሳሳቢ ሁኔታ ይመለከታል። ዋናው የመጣችሁበት ጉዳይ እንደሆነ እገነዘባለሁ፣ ምክንያቱ ምን ይሁን ቀደም ብላችሁ እንደ ጠቀሳችሁት ተቀራርቦ መመካከር የተሻለ ነው
ክቡር ሚኒስትሩ አምሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ቢመለሱም በቀጥታ ቤታቸው በሚገኘው ቢሮ ውስጥ ገብተው በር በመዝጋታቸው ግራ የተጋቡት ባለቤታቸው ቀስ ብለው ወደ ቢሮው ዘለቁ
ጥር ፳፰ ሀያ ስምንት ቀን ፳፻፯ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና በአማራና በትግራይ ክልል ድንበሮች አካባቢ የተነሳውን ችግር ለመፍታት ከፌደራል መንግስት ፣ ከትግራይና ከአማራ ክልል የተውጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጥር ሀያ ስድስት ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አም ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጡ ሶስት መቶ ነዋሪዎችን ሰብስበው ያነጋገሩ ቢሆንም፣ መግባባት ሳይቻል በመቅረቱ ለየካቲት አራት በድጋሜ መቀጠሩን የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል።የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ሽፈራው ተክለማርያም፣ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ገዱ አንዳርጋቸው፣ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ፣ ቴዎድሮስ ሀጎስ፣ የሰሜን ምእራብ እዝ አዛዥ ሌተናል ጄነራል ብርሀኑ ጁላ፣ የመከላከያ ዘመቻ ሀላፊ ሜጀር ጄኔራልኔራል ገብረእግዚአብሄር መብራቱ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣኖች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። በመጀመሪያው ቀን ስምምነት ባለመደረሱ በማግስቱ ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጡ ስላሳ ነዋሪዎች ከባለስልጣናቱ ጋር ተሰብስበው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ሳይሳሙ በመቅረታቸው ለየካቲት አራት ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል። በአማራ ክልል በኩል የሚኖሩ ነዋሪዎች የትግራይና የአማራ ክልሎች ድንበር ተከዜ ሆኖ እያለ ፣ ክልሉ ከዚህ ቀደም በጉልበት ከተከዜ በመሻገር ሁመራ እና ዳንሻ የመሳሰሉ ቦታዎችን መቆጣጠሩንና አሁን ደግሞ እስከመተማ ያለውን ቦታ በመያዝ ሰሜን ጎንደርን በግማሽ ለማጠቃለል ያስባል በማለት የክልሉን የመስፋፋት ፖሊሲ ተቃውመዋል። በትግራይ ባለስልጣናት በኩል ደግሞ የክልሉ ድንበር እስከመተማ ይደርሳል የሚል አቋም የተንፀባረቀ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች የያዙት አቋም የትግራይ ክልል ባለስልጣናትን አበሳጭቷል። በአካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰራዊት አባላትና የፌደራል ፖሊሶች የተሰማሩ ሲሆን፣ ህዝቡን ያስተባብራሉ የተባሉ የአካባቢው መሪዎች እየተለቀሙ በመታሰር ላይ ናቸው።በአካባቢው ያለው ውጥረት በቀላሉ አይበርድም የሚሉት ነዋሪዎች፣ ችግሩ ቶሎ ካልተፈታ ወደ ግጭት ሊያመራ ይችላል በማለት ያስጠነቅቃሉ። በቋንቋና ዘር ላይ የተመሰረተ የፌደራል ስርአት ከተመሰረተ ጊዜ አንስቶ በክልሎች መካከል የሚታየው የድንበር ውዝግብ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው።በኦሮምያና በሶማሊ፣ በኦሮምያና በደቡብ፣ በአፋርና በአማራ፣ በአማራና በትግራይ፣ በደቡብና በጋንቤላ፣ በትግራይና አፋር እንዲሁም በሶማሊና በአፋር ባልተፈቱ የድንበር ግጭቶች በርካታ ዜጎች አልቀዋል። ።
በአማራና ትግራይ ድንበር የተነሳውን ውዝግብ ለመፍታት የተጠራው ስብሰባ ተበተነ
ሰኔ ሶስት ቀን አመተ ምህረትኢሳት ዜናበስራ አለምም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጊዜያዊ ፅህፈት ቤት በተለያዩ ሀላፊነቶች የሰሩትና የፈረንሳይ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ሀይሉ ወልደጊዮርጊስ ይህን የገለፁት እሁድ ለህትመት ከበቃው ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር በ አባይ ግድብ ዙሪያ ባደረጉት ቃለምልልስ ነው። የ አባይ ውሀ በህግ ላይ የሚያቀርበው ፈተና በሚል ርእስ በፈረንሳይኛ መፅሀፍ ያሳተሙት አምባሳደር ሀይሉ ለህዳሴው ግድብ እስካሁን ከህዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ ገና ከ ቢሊዮን ብር እንዳላለፈ አመልክተዋል።የግድቡ ግንባታ የሚጠይቀው ከ ቢሊዮን ብር በላይ ነው ያሉት አምባሳደር ሀይሉይህን ያህል ገንዘብ በራሳችን ለማዋጣት ያዳግተናል ብለዋል።የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የ አባይን ግድብ ያለምንም የውጪ እርዳታ በራሳችን እንሰራዋለን በማለት በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወሳል።ያለ እርዳታ ግድቡ የማይቻል መሀኑን ያብራሩት አምባሳደሩ ግብፅ የኤክስፐርቶች ቡድን ያቀረበውን ሪፖርት ተቀብያለሁ ብላ ካረጋገጠች ኢትዮጵያ የውጭ እርዳታ ታገኛለች የሚል አመለካከትና እምነት ስላላት ነው ብለዋል።አምባሳደሩ አክለውምግድቡ ተጠናቅቆ ስራ ላይ ቢውል ግን ተጠቃሚዋ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ግብፅና ሱዳንም የጥቅሙ ተጋሪ ይሆናሉ ።እነሱ ግን ይህ በጎ ጐኑ አይታያቸውም። የግብፆች ትልቁ ጥርጣሬያቸው ኢትዮጵያ በህዝቡ መዋጮ ብቻ የግድቡን ግንባታ የማጠናቀቅ ወይም ዳር የማድረስ አቅም ስለሌላት ይህንን ክፍተት ለመሸፈን ከሌሎች አገሮች በስውር እርዳታና ብድር ልታገኝ ትችላለች የሚል ነውብለዋል።ስለሆነም ይህንን ለማጨናገፍ ሲሉ የማስፈራራት ዘመቻ እያካሄዱ እንደሆነ እና ለዚህም ተግባራዊነት መልእክተኞቻቸውን ወደተለያዩ አገሮች በመላክ የማግባባት ስራ እያካሄዱ ስለመሆናቸው የገለፁት አምባሳደር ሀይሌ ደቡብ ሱዳን እንኳን የትብብር ማእቀፍ ስምምነቱን እንዳትቀበል ወይም እንዳትፈርም ብዙ ተፅእኖ አድርገውባት ነበር። ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐንም እንዲሁ አግባብተዋል።ከ አምባሳደሩ ገለፃ ለመረዳት እንደተቻለው ከ ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ለሚባለው ለግድቡ ስራ እስካሁን የተዋጣው ገና በመቶ ያህሉ ነው። ይህ ማለት ከተጀመረ ሁለተኛ አመቱን ያስቆጠረው ግድብ ገና በመቶ የሚሆነው ወጭ ይጠብቀዋል። የ ኢትዮጵያ ህዝብ በውድምበግዳጅም እንዲያዋጣና ቦንድ እንዲገዛ ተደርጎ የተሰበሰው በመቶ ከሆነ አምባሳደሩ እንዳሉት ግድቡን ያለውጪ እርዳታ ካለበት ቦታ ብዙም ማንቀሳቀስ አይቻልም።ከዚህ አኳያ የግድቡ ስራ መቀጠልና አለመቀጠል የሚወሰነው ኢትዮጵያ እርዳታን ለማግኘትግብፅ እርዳታን ለማስከልከል እያደረጉ ባሉት ትግል እንደሆነ የዘርፉ ሙያተኞች ይናገራሉ።
የህዳሴውን ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ ህዝብ መዋጮ ብቻ መሸፈን ወይም ዳር ማድረስ አይቻልም ተባለ
ለበጀት ድጋፍ፤ እርዳታና ብድር ከአርባ ቢሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ በሁለት ሺህ የመጀመ ሪያው በጀት አመት ሶስት ወራት ውስጥ አምስት ነጥብ አምስት መቶ ስልሳ ሶስት ቢሊዮን ብር የውጭና የአገር ውስጥ ብድር ክፍያ ፈፅማለች።በአንፃሩ የተለያዩ ተቋማት እና መንግስታት ድጋፍ በመጠናከሩም ለቀጥታ በጀት ድጋፍ፤እርዳታና ብድር ከአርባ ቢሊዮን ብር በላይ መገኘቱን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። የገንዘብ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ እንደገለፁት፤ በሁለት ሺህ የመጀመሪያ ሩብ አመት ለማእከላዊ መንግስት የውጭ ብድር ለዋና እዳ ክፍያ ብር በድምሩ ብር ሶስት ነጥብ አምስት መቶ ሀያ ቢሊዮን ብር ክፍያ ለመፈፀም ታቅዶ ለዋና እዳ አንድ ነጥብ ሰባ ስድስት ቢሊዮን ብር ክፍያ የተፈፀመ ሲሆን ለወለድ እና ለባንክ ማስተላለፊያ ክፍያ ደግሞ አንድ ነጥብ ስላሳ ስድስት ቢሊዮን ብር በድምሩ ብር ከሶስት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያ በመፈፀም የእቅዱን ሰማኒያ ስምንት ነጥብ ስድስት ከመቶ አፈፃፀም ማስመዝገብ ተችሏል። እንደ ሚኒስቴሩ መረጃ ከሆነ፤ በሌላ በኩል ለአገር ውስጥ የማእከላዊ መንግስት ብድር ለዋና እና ወለድ እንዲሁም ለቀጥታ ግምጃ ቤት ሰነድ ብድር ወለድ በድምሩ ብር ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር እዳ ክፍያ ለመፈፀም ታቅዶ ነበር። ለማእከላዊ መንግስት ብድር ዋና እና ወለድ አራት መቶ ስልሳ ሁለት ነጥብ ሀያ ስምንት ሚሊዮን ብር እንዲሁም ለቀጥታ የግምጃ ቤት ሰነድ ብድር ወለድ አንድ ነጥብ ዘጠና ስምንት ቢሊዮን ብር በድምሩ ከሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር በላይ እዳ ተከፍሏል። ክፍያው ከእቅዱ አንፃር የአንድ መቶ በመቶ አፈፃፀም አለው። ከብድር ክፍያ በዘለለ ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ ተቋማትና መንግስታት ጋር ያላት የኢኮኖሚ ትብብር እና የፋይናንስ ግኝት መጨመሩን የገለፁት አቶ ሀጂ፤ በበጀት አመቱ በመጀመሪያዎች ሶስት ወራት አንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር መገኘቱን ገልፀዋል። ከአውሮፓ ህብረት እና ከአለም አቀፍ የልማት ማህበር ለፍትሀዊ መሰረታዊ አገልግሎት ለጋራ ብልፅግና ፕሮግራም የተገኘውን ገንዘቡን ቀጥታ ወደ ማእከላዊ ትሬዠሪ ፈሰስ የሚደረጉ ሲሆን፤ መንግስት የፈለገውን የልማት እቅድ ለመፈፀም እንዲሁም የበጀት ጉድለቱን ፋይናንስ ለማድረግ የሚያስችሉ ናቸው። እንደ አቶ ሀጂ ገለፃ፤ የውጭ ሀብት ፍሰት እና ግኝት አፈፃፀም በተመለከተ በሶስት ወራቱ ከተለያዩ ለጋሽና አበዳሪ ተቋማት እና የልማት አጋር መንግስታት በብድርና በእርዳታ ወደ አገር ውስጥ ከአንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ተገኝቷል። ከዚህ ውስጥ ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና ከመንግስታት ትብብር የተገኘው ገንዘብ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል። ከአለም አቀፍ ተቋማትና መንግስታት ጋር ያደረገቻቸው የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነቶችን እየጨመሩ መምጣታቸውን የገለፁት አቶ ሀጂ፤ ይህም የኢትዮጵያ የፋይናስን ምንጭ መጠናከሩን እንደሚያሳይ ገልፀዋል። እንደ እርሳቸው በልዩ ልዩ ዘርፎች የታቀዱ የመንግስት የልማት ስራዎችን ለመደገፍ የሚያስችሉ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፎችን እንዲሁም የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎች አሁንም እየተገኙ ነው። ድጋፎቹም መንግስት ቀጣይና ዘላቂ የሆነ ልማት እና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ጉልህ ሚና አላቸው። ለአብነትም በቅርቡ የጀርመን መንግ ስት ያደረገው የሶስት መቶ ሀምሳ ሁለት ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያ በተለያዩ ሀገራትና ተቋ ማት ዘንድ ያላት ተቀባይነት እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል። አዲስ ዘመን ህዳር ሀያ ሰባት ሁለት ሺህ ጌትነት ተስፋማርያም
በሁለት ሺህ የመጀመሪያ ሩብ አመት የአምስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ብድር ተከፍሏል
ኢሳት ታህሳስ ሀያ አራት ፥ ሁለት ሺህ ዘጠኝ እሁድ በቻይና በተካሄደ አለም አቀፍ የማራቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ፆታዎች ተከታትለው በመግባት ድል ተቀዳጁ። ከስላሳ ሺ በላይ ሰዎችና የተለያዩ ሀገራት አትሌቶች በተሳተፉበት በዚሁ የቤጂንግ የማራቶን ውድድር አትሌት ለሚ ብርሀኑ እና መሰረት መንግስቱ በአንደኝነት ማጠናቀቃቸውን የቻይና መገናኛ ብዙሀን ሰኞ ዘግበዋል። ባለፈው አመት በዚሁ በአሜሪካ ቦስተን ከተማ ተካሄዶ በነበረው የማራቶን ውድድር አሸናፊ የነበረው አትሌት ለሚ፣ በ ሁለት ሰአት ስምንት ደቂቃ በመግባት በመግባት የወርቅ ሜዳሊያን ያገኘ ሲሆን፣ አትሌት መሰረት መንግስቱ ደግሞ በሴቶች በሁለት ሰአት ከሀያ አምስት ደቂቃ በመግባት የወርቅ ተሸላሚ ለመሆን ችላለች። ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሚ ብርሀኑ በቦታው በኬንያ አትሌት ተይዞ የቆየውን የሁለት ሰአት ከስድስት ደቂቃ ሰአት ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረትን ቢያደርግም ሳይሳካለት መቅረቱን ሲንሀአ በዘገባው አስነብቧል።
በቻይና አለም አቀፍ የማራቶች ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያውያን ድል ተቀዳጁ
አዳማ ከተማ ዳዋ ሁቴሳን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል። ዳዋ በሁለት ሺህ ስድስት ክረምት ናሽናል ሴሚንትን ለቆ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከተቀላቀለ ወዲህ በመደበኛነት መጫወት የተሳነው ሲሆን በዘንድሮው የውድድር ዘመን ክለቡን እንደሚለቅ ሲጠበቅ ነበር።አዳማ ዳዋ ሁቴሳን ጨምሮ ሙጂብ ቃሲም ፣ ኤፍሬም ቀሬ ፣ ኄኖክ ካሳሁን እና ጥላሁን ወልዴን በማስፈረም ስብስቡን ከወዲሁ እያጠናከረ ይገኛል።ሲዳማ ቡና የአርባምንጭ ከተማዎቹን ትርታዬ ደመቀ እና አበበ ጥላሁንን ለማስፈረም እንደተስማማ ተሰምቷል።ድንቅ የውድድር አመት ያሳለፈው ተከላካዩ አበበ ጥላሁን የአንተነህ ተስፋዬን ክፍተት በሚገባ የሸፈነ ሲሆን አሁን ደግሞ በሲዳማ አጣማሪው ለመሆን ከይርጋለሙ ክለብ ጋር በቃል ደረጃ መስማማቱ ተነግሯል።ሲዳማ ቡና በሁለት ሺህ ስድስት ክረምት እንዳለ ከበደን ፣ በሁለት ሺህ ሰባት ክረምት ሙሏለም መስፍን ፣ አንተነህ ተስፋዬ እና አሰልጣኝ አለማየሁ አባይነህን ከአርባምንጭ ያስኮበለለ ሲሆን የዘንድሮው ተረኞች ደግሞ ትርታዬ እና አበበ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።ሀዋሳ ከተማ የደደቢቱ አማካይ ያሬድ ዝናቡ እና የደቡብ ፖሊሱ ግብ አዳኝ ወንድሜነህ አይናለምን በእጁ ለማስገባት መቃረቡ ታውቋል።ያሬድ ዝናቡ ደደቢትን የለቀቀ ሲሆን ለሀዋሳ ከፈረመ ከቀድሞ አሰልጣኙ ውበቱ አባተ ጋር በድጋሚ ይገናኛል።ሌላው ለሀዋሳ ከተማ ለመፈረም ከስምምነት እንደደረሰ እየተነገረ የሚገኘው ወንድሜነህ አይናለም በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከፍተኛ ሊግ ድነንቅ አቋሙን በማሳየት ላይ የሚገኝ ሲሆን ግቦች ማስቆጠር ችሏል። አጥቂ አማካይነት እና አጥቂነት ተሰልፎ መጫወትም ይችላል።አርባምንጭ ከተማ የአዳማው ወንድወሰን ሚልኪያስን በእጁ አስገብቷል።ወንድወሰን በጉዳት ጥሩ የውድድር ዘመነ ያላሳለፈ ሲሆን በአዳማ ኮንትራታቸው ካልታደሰላቸው ተጫዋቾች አንዱ ነበር።በሌላ በኩል የደደቢቱ የቀኝ መስመር ተከላካይ ተካልኝ ደጀኔ ወደ አርባምንጭ ከተማ ለማምራት መቃረቡን ከወደ አርባምንጬ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣዩ ወር መጨረሻ ከሲሸልስ ጋር የሚያደርገው የሁለት ሺህ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም ይደረጋል።የብሄራዊ ቡድኑ ዋንኛ ሜዳ የሆነው አዲስ አበባ ስታድየም በተደራራቢ ጨዋታዎች እና ዝናብ ከጥቅም ውጪ በሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በሜዳው ላይ መለስተኛ ጥገና በመደረግ ላይ ይገኛል።ኢትዮጵያ ጨዋታውን በሀዋሳ ለማድረግ ለካፍ ጥያቄዋን ማቅረቧን ተከትሎ የሴካፋ የምድብ ውድድሮችን ያስተናገደውን ስታድየም ለማካሄድ ፍቃድ መስጠቱ ታውቋል።ደደቢት በመጨረሻም የሎዛ አበራን ኮንትራት ለተጨማሪ ሁለት አመታት አድሷል።በሁለት ሺህ ስድስት ክረምት ሀዋሳ ከተማን ለቃ ደደቢትን የተቀላቀለችው ሎዛ በሁለት የውድድር ዘመናት ብቻ ዘጠና የሊግ ግቦች በማስቆጠር የሴቶች እግርኳስ ክስተትነቷን አስመስክራለች።ደደቢት የመስከረም ካንኮ ፣ አልፊያ ጃርሶ እና ሰናይት ባሩዳን ጨምሮ የአብዛኞቹ ተጫዋቾችን ውል ያደሰ ሲሆን ኤደን ሽፈራውና ሰናይት ቦጋለ እስካሁን ውል ያላደሱ ተጫዋቾች መሆናቸው ታውቋል።ከሊጉ ለመውረድ ለጥቂት የተረፈው ኤሌክትሪክ የአሰልጣኙ ብርሀኑ ባዩን ኮንትራት አድሷል። አሰልጣኙ ከደካማው የውድድር ዘመን ፍፃሜ በኀላ ሊሰናበቱ እንደሚችሉ ቢነገርም ለከርሞ በቀዮቹ ቤት እንደሚቆዩ አረጋግጠዋል።ኤሌክትሪክ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የማይገኝ ሲሆን አሰልጣኙ ለማስፈረም ያሰቧቸው አዳዲስ ተጫዋቾች እና ኮንትራታቸውን እንዲያድሱ የሚፈልጓቸው ተጫዋቾችን ለክለቡ ቦርድ አቅርበው ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑ ታውቋል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን የሀዋሳ ከተማዋ አማካይ አዲስ ንጉሴ ፣ የሲዳማ ቡናዋ የካቲት መንግስቱ እና የዳሽን ቢራዋ አጥቂ ሄለን እሸቱን ለማስፈረም ድርድር እንደጀመረ ታውቋል። ስሟ ከደደቢት ዝውውር ጋር የተያያዘው ብሩክታዊት ግርማም በክለቡ የሚያቆያትን ውል ለማደስ በድርድር ላይ እንደምትገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የቅዳሜ ሀምሌ ምሽት አጫጭር ዜናዎች
በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ላይ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዲሞክራቶችን በመወከል የትራምፕ ተቀናቃኝ ሆነው ሊቀርቡ ይችላሉ ተባለ። መራጮች ዲሞክራቶችን ወክሎ ሪፓብሊካኑን ዶናልድ ትራምፕን የሚገዳደር እጩ እየመረጡ ይገኛሉ። በደቡብ ካሮላይና በተደረገው ምርጫ ጆ ባይደን ማሸነፍ ችለዋል። ይህም በቀጣይ ምርጫ ዲሞክራቶችን ወክለው እንዲወዳደሩ ሊያስችላቸው ይችላል ተብሏል። ግራ ዘመሙ በርኒ ሳንደርስ፤ በደቡብ ካሮላይና በተደረገው ምርጫ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የፊታችን ማክሰኞ ዲሞክራቶችን ወክሎ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፈው እጩ ይለያል። ለሶስተኛ ጊዜ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፉት ጆ ባይደን፤ በአፍሪካ አሜሪካውያን ዘንድ ድጋፍ እንዳላቸው ይታመናል። በደቡብ ካሮላይና እንዲያሸነፉ ያስቻላቸው ከጥቁሩ የኮንግረስ አባል ጄምስ ክላይበርን ይሁንታ በማግኘታቸው ነው የሚሉም በርካቶች ናቸው። በቀጣይ ምን ይፈጠራል ሱፐር ቲዩስደይ የሚል ስያሜ የተሰጠው የፊታችን ማክሰኞ የዲሞክራቶች እጩ ማን ሊሆን እንደሚችል የሚቀበት ቀን ነው። በ ግዛቶች የሚገኙ ዲሞክራቶች ድምፅ ይሰጣሉ። ከእነዚህም መካከል በርካታ የህዝብ ቁጥር ያላቸው ካሊፎርኒያ እና ቴክሳስ ይገኙበታል። በርኒ ሳንደርስም ሆኑ የኒው ዮርኩ ቢሊየነር ማይክል ብሎምበርግ ዲሞራቶችን በመወከል የትራምፕ ተቀናቃኝ ሆነው ሊቀርቡ የሚችሉበት እድል አለ። የሰባ ስምንት አመቱ አዛውንት በርኒ ሳንደርስ ድጋፋቸው በዋናነት የሚመነጨው ከወጣቶች ነው። ባለፈው ምርጫ በሂላሪ ክሊንተን ተሸንፈው ከዲሞክራት እጩነት መውጣታቸው ይታወሳል። በዘንድሮ ምርጫም ከጆ ባይደን በተጨማሪ ዲሞክራቶችን ወክሎ የትራምፕ ተቀናቃኝ የመሆን ስፊ እድል ያላቸው ሴናተር ናቸው።
ጆ ባይደን በመጪው ምርጫ የትራምፕ ተቀናቀኝ ሆነው ሊቀርቡ ይችላሉ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ ሰባት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ናዛት ካን፣ ለሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባላት እንዲሁም ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባቼሌት ግልፅ ደብዳቤ ፃፈ። የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ፥ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል እስከ ፈረንጆቹ ህዳር ሶስት ቀን ሁለት ሺህ ሀያ አንድድረስ የተፈፀሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በሌላ አካል በድጋሚ እንዲጣራ ማድረግ በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት እና በኢትጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በጥምረት የተካሄደውን ምርመራ እውቅና መንፈግ ነው ብሏል። ኮሚሽኑ ምርመራ ተደርጎ በሪፖርት የቀረበውን ጉዳት በሌላ አካል ከማስደገምና ሂደቱን ከማጓተት፣ ቀደም ብሎ በወጣው የምርመራ ሪፖርት መሰረት ተጎጂዎች እንዲያገግሙ፣ ወደ ተፈናቀሉበት ቦታ እንዲመለሱ እንዲሁም እንዲካሱ ብሎም ወንጀል የፈፀሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ መሰራት ነበረበትም ብሏል በደብዳቤው። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በደብዳቤው የሰብአዊ መብት ጥሰቱ እንደገና ይጣራ ከተባለ አጥፊዎቹ አካላት የፈፀሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመካድና እና ኮሚሽኑ የሰራውን ምርመራ ለማጣጣል እድል ከመስጠቱም ባሻገር የኮሚሽኑን ተግባር ዝቅ የሚያደርግ ይሆናል ማለቱንም ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ። አካባቢዎን ይጠብቁ ወደ ግንባር ይዝመቱ መከላከያን ይደግፉ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ለተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ግልፅ ደብዳቤ ፃፈ
ወይም የፈጠራ ወሬ በተለይ አሁን አሁን ብዙ አድማጭና አንባቢ ከሚታወቁ የዜና ማሰራጫ ጣቢያዎች ይልቅ ከተለያዩ ማሀበራዊ መገናኛዎች ዜና በሚፈልግበት፣ በሚቃርምበትና ሀሳቡንም በሚያንሸራሽርበት ዘመን አደጋው ከፍተኛ ሆኗል። ወይም የፈጠራ ወሬ በማሀበረሰብ ውስጥ መተማመንን ያሳጣል፤ መንግስትና ህዝብን፣ ህዝብን ከህዝብ ያጋጫል።በ ወይም በፈጠራ ወሬ ስርጭት ላይ ጥናት ያደረጉ ማርከሻውንም የሚመክሩ ባለሙያ አቶ ዳኛቸው ተሾመ ለጥያቄዎችዎ መልስ ይሰጣሉ።አቶ ዳኛቸው ተሾመ ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ የሚኖሩ ላለፉት ሰላሳ አመታት በትምህርት፣ በምርምርና በስራም ከኮምፕዩተር ሳይንስ ጋር ያሉ ሰው ናቸው። በዳታ ቤዝ ዲዛይንና አርክቴክቸር ላይ ሰርተዋል። የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ምርምርና ፅሁፍም የሰሩት ድምፅን በመፈተሽና ለይቶ በማወቅ ክህሎት ላይ መሆኑን ይናገራሉ። ከዚያ በተለይ ግን አቶ ዳኛቸው እራሴን ማሳወቅ የምፈልገው ህይወቱን ለሰው ልጅ መብት መከበር እንደሰጠ ሰው ነው ይላሉ።የጄነራል አሳምነው ፅጌና የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሀን ሀላፊ የመጨረሻ የስልክ ምልልስ የድምፅ ቅጂም ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ ዲጂታል አሻራ መርማሪ ቡድን አስመርምረው ያገኙትን ውጤትም ያካፍላሉ። የዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች ዲጂታል ፎረንሲክ ኤክፐርትስ ድርጅት ሪፖርት ከስር ሰፍሯል ይመልከቱት አንድ ይህ የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ የድርጅቱ ስም ነው ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች ሙያዊ አስተያየት ነው። ሪፖርተሩና ሟቹ አሁን ተናጋሪው የሚባሉት የተቀረፁት በአንድ ጊዜ በተመሳሳይ ጊዜ ወይም አንድ ላይ ነው፤ ወይም የሁለቱም ድምፅ እንደገና ተቀርፆም ከሆነ የተቀረፀው በአንድ ጊዜ ወይም አንድ ላይ ሊሆን ይችላል። ያልተቋረጠ ወይም የተያያዘና ተከታታይ ኢ ኤን ኤፍ የእንግሊዝኛ አባባል ምሀፃር ነው የኤሌክትሪክ ትስስር ኔትወርክ ሞገድ አለ። የድምፁ ሂደት የተሰባበረ አይደለም፤ ይህ ማለት ለእኛ በተላከልን የተቀረፀ ድምፅ ላይ ሪፖርተሩና ተናጋሪው የተቀረፁት በአንድ ጊዜ በተመሳሳይ ጊዜ ወይም በአንድ ላይ መሆኑን ያረጋግጣል። በሌላ በኩል ደግሞ የኤሌክትሪክ ትስስር ሞገዱ ኢ ኤን ኤፍ እንዳይቆራረጥ ለማድረግ ሪፖርተሩ መጠይቆቹን ተገቢ ጊዜያቸውን እየጠበቀ የተናጋሪውን ቀድሞ የተቀረፀ ድምፅ እያጫወተ ቀርፆ ሊሆንም ይችላል። የሪፖርተሩ ድምፅ ከተናጋሪው ድምፅ ጋር እየተቆራረጠ አልተቀጣጠለም። ሁለት ይህ የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ የድርጅቱ ስም ነው ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች ሙያዊ አስተያየት ነው። ምንጩ ላይ ለማስተካከል ወይም ለመቀማመር ተብሎ በእጅ የተከናወነ ስራ የለም። አንዱን ድምፅ በሌላኛው ላይ ማስኬድን፣ ወጥነት የሌላቸው የድምፅ ውጣ ውረድ አይነቶችን፣ ቆርጦ መቀጠልን ወይም መሰል ለማጭበርበር ተብሎ የተፈፀመ የአርትኦት ስራ የለበትም። ሶስት በመጨረሻም ሪፖርተሩ ያወጣው የተቀረፀ ድምፅና የቀረቡት ሁለት ናሙናዎች ተመሳሳይ ወይም አንድ መሆናቸውን የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ የድርጅቱ ስም ነው ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች ሙያዊ አስተያየት ያረጋግጣል። የተቀረፀውን ድምፅ አሻራ የያዘውን ድምፅ በጊዜ ውስጥ የሚያሳየውን ሞገድ ሂደት የሚያመላክቱ ምስሎች ስፔክቶግራምስ በተለይ የተከበቡትን ሞገዶች ይመልከቱ። ከተናጋሪው ድምፅ ጋር የተቀላቀሉ ሌሎች የጀርባ የድምፅ ሞገዶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አነስተኛ ለውጦችን ቢያሳዩም ዋናዎቹ ነጥቦች፣ እንዲሁም ቁልፍ በሆኑት ሞገዶች መካከል ያሉት ክፍተቶች ግን አሉ።
ፌክ ኒውስ የፈጠራ ወሬ፡ ምንጩ፣ መገለጫው፣ መዘዙ፣ ማርከሻው
ሶስት መቶ ስልሳ አንድ በስሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ፣ አማርኛ ተናጋሪዎች እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በማንሳት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂዷል። በወለጋ፣ በሀረርጌ በርካታ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች መጠነ ሰፊ የፀጥታ ችግሮች አያሉ፣ ካልጠፋ ቦታ ሰላማዊ በሆነው በደራ የክልሉ የፀጥታ ሀላፊ ጀነራል ከማል ገልቹ ተገኝተው የነበረ ሲሆን፣ የጀነራሉ በደራ መገኘት በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው። የፀጥታው ሀላፊው ምን አልባት በደራ የተነሳውን የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ፣ የፖለቲካና ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ከመስጠት፣ በሀይል እርምጃ ለማፈን ከመታሰቡ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ ያላቸው አንዳንድ ወገኖች ቢኖሩም የተደረገው ሰልፍ ፍፁም ሰላማዊና ምንም አይነት ችግር ያልታየበት ሰልፍ ነበር። በደራ ወረዳ ከ ሰማኒያ አምስት ነዋሪዎች አማርኛ ተናጋሪ ሲሆኑ፣ ኦሮምኛ ካልተናገራችሁ በሚል፣ ኦሮምኛ ባለማዋቃቸው ምንም አይነት የወረዳው፣ የዞኑና የክልል መንግስት አገልግሎት የማያገኙ ሲሆን፣ የመምረጥ፣ የመመረጥ መብታቸውን ተነፍገው በአገራቸው በቃያቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረው ነው እየሰሩ ያሉት። በደራ ወረዳ በቀዳሚነት ጥያቄው ገንፍሎ ወጣ እንጂ ከሰባ አምስት በላይ የኦሮሞ ክልል ወረዳዎች ኦሮምኛ የማይናገሩ፣ ወይም ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰባት በብዛት የሚኖሩባቸው ናቸው። እዚያው ሰሜን ሸዋ ሳንወጣ፣ በቅምብቢት ወረዳ ስልሳ ፣ በአብቹ ወረዳ ሀምሳ አምስት ነዋሪዎች አማርኛ ተናጋሪዎች ይኖራሉ። ወደ ምስራቅ ሸዋ ስንሄድ በአዳማ ልዩ፣ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ወረዳዎች ቢያንስ ከሰባ በመቶ በላይ ነዋሪው አማርኛ ተናጋሪ ነው። በጂማ በአሰላና አካባቢው፣ በተለያዩ የምስራቅ አርሲ ቦታዎች ቁጥራቸው ኦሮሞ ያልሆኑ ወይንም ህብረሄራዊ የሆኑ ማህበረሰባት ብዙ ናቸው። የደራ ህዝብ ያነሳው ጥያቄ በመላው የኦሮሞ ክልል የሚኖሩ ማሀበረሰባት የሚያንሱት ጥያቄ ነው ። ከዚህም የተነሳ የደራ ንቅንቃ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ጮራ ፈንጣቂ ንቃናቄ ሊሆን ይችላል ተብሎም ይጠበቃል። ሶስት መቶ ስልሳ አንድ
የኦሮሚያ የፀጥታው ጀነራል ከማል በደራ መገኘትና የህዝቡ የራስ ገዝ ጥየቃ ናኦሚን በጋሻው
ክሱ የድርጅቱን ስም ለማጠልሸት የሚደረግ ጥረት ነው አየር መንገዱአዲስ አበባ፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስተዳደር የሚያደርስባቸው የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት መባባሱን ሰራተኞች ተናገሩ። አየር መንገዱ በበኩሉ ተቋሙ በጥብቅ ስነ ምግባር በመመራቱ የተቋሙን ገፅታ ለማጠልሸት ጥረት የሚያደርጉ ሰራተኞች ወቀሳ ነው ሲል ክሱን አስተባብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር ካፒቴን የሺዋስ ፈንታሁን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ ምንም እንኳ በተቋሙ አለቃ የመፍራት መንፈስ የቆየ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ሁኔታው ተጠናክሮ አስተዳደሩ ቢሮ ድረስ ጠርቶ ያስፈራራል። በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎችም አስተዳደሩን ዘልፋችኋል በሚል ብቻ ከዋና አብራሪዎች ጀምሮ የስራ እግድና ስንብቶች ይደረጋሉ። በሌላ በኩል ተቋሙ የስራ ልምድ የማይሰጥ፣ ባለሙያዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድረው መቀጠር እንዳይችሉ የሙያ ማረጋገጫ ማስረጃቸውን የሚከለክልና አልፎም ፓስፖርት የመቀማት ልምድ አለው። እንዲሁም የምዘና ስርአቱ የሰራተኞችን የስራ ተነሳሽነት የሚቀንስ፣ ተፈጥሯዊ የሆነውን ህመምና የሴቶች ወሊድን እንደባከነ ጊዜ የሚቆጥር ነው። ይህንን ትግል የሚያደርግ የሰራተኛ ማህበር የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ከተቋቋመ በኋላም ሊሰራው አልቻለም። ይልቁንም ለሌላኛው ማህበር እውቅና እንደሰጠ ይገልፃል። ይህም ችግሮቹ እንዳይቃለሉ ምንጭ ስለሚሆን መንግስት በትኩረት ሊያየው እንደሚገባ ሊቀመንበሩ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፤ ከሰሞኑ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረበላቸው አስተያየትና ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፤ አየር መንገዱ ለስኬታማነቱ ትልቁ ሚስጥሩ ስነምግባር እንደሆነ ገልፀዋል። ነገር ግን በአገሪቱ ካለው የስራ ባህል አንፃር ይህ የማይዋጥላቸውና ምቾት የሚነሳቸው ሰራተኞች አይጠፉም። አራት መቶ መንገደኞችን ይዞ ከባህር ወለል አርባ ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ የሚበር አውሮፕላን የሚጠግን ቴክኒሺያን ትንሿ ስህተት ህይወት ልታስከፍል ስለምትችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠበቅበታል። በዚህ ደረጃ ህጉን ለማስፈፀም ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ሲወሰዱ ደግሞ ቅሬታዎች ይበዛሉ። አቶ ተወልደ አየር መንገዱ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሰው ሀብት አስተዳደር እንዳለው ገልፀው፤ በአገሪቱ የይቅርታ ፖሊሲ ያለው ብቸኛ ተቋም እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህም ሰራተኛው ከስራ እስከመሰናበት የሚያደርስ ስህተት ሰርቶ ስድስት ወር ቆይቶ አጥፍቻለሁ ይቅርታ ይደረግልኝ በሚልበት ወቅት ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሳያመራ ድርጅቱ ይቅርታ አድርጎለት እንዲመለስ ይደረጋል። የሰራተኛ ደመወዝ በድርድር ሳይሆን በፈቃደኝነት የሚጨምር፣ ከስራ ወደ መስሪያ ቤትና ከመስሪያ ቦታ ወደ መኖሪያ ቤት ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎት ያለው፣ ሽሮ በስድስት ብር የሚበላበት ድርጅት፣ የመኖሪያ ቤት ገንብቶ ለሰራተኞቹ የሰጠና መሰል ጥቅማ ጥቅሞችን የሚሰጥ በመሆኑ ሰራተኛው በአጠቃላይ ደስተኛ ነው። በማለት አረጋግጠዋል። አየር መንገዱ ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆች የሚፅፉ አካላት ተቋሙን ፖለቲካ ውስጥ ለመክተት ፍላጎት ቢኖራቸውም ድርጅቱ ግን በምንም መልኩ ፖለቲካ ውስጥ አይገባም። ሰራተኞች በተቋሙ ለረጅም አመት የሚቆዩትም አየር መንገዱ ለአገሪቱ ወሳኝ በመሆኑና በቁጭት ለማሳደግ ካላቸው ተነሳሽነት እንደሆነ አቶ ተወልደ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሰው ሀብት ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ መሳይ ሽፈራው፤ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ይገፉናል ይጨቁኑናል ከማለታቸው በፊት አካሄዱን ያውቁታል ወይ ማህበር ማለትስ ምን ማለት ነው የሚለውንስ ያውቃሉ ወይ በሚል መታየት አለበት። የሰራተኞች የስራ ስንብትም በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆች ስለሚያደርጉት እንቅስቃሴ አይደለም። ይልቁንም ማንም ሰው እውነትነት በሌለው ጉዳይ ድርጅቱንም ሆነ አስተዳደሩን መወነጃጀል እንዲቆም ማሳሰቢያ አውጥተናል። ማሳሰቢያውን ተከትሎ ተግባራዊ ካልተደረገ ግን የኢንዱስትሪ ሰላሙን የሚያናጋ በመሆኑ ይህንን ተላልፎ በተገኘ ሰራተኛ ላይ እርምጃ ይሰወዳል ብለዋል። በዚህ ሂደት ያለው መመሪያና አካሄድ የማያሰራ ሆኖ ከተገኘ ደግሞ ውስጥ ሆኖ አሰራር የመቀየር የእያንዳንዱ ሰራተኛ ሀላፊነት ነው። ከዚህ ውጪ ግን የድርጅቱን አሰራር በጣሰ መንገድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ህጋዊ አያደርጉም። ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ የምዘና ስርአቱ፣ እንዲሁም የህመም ፈቃድና ወሊድ ላይ የሚነሱት ቅሬታዎችም ተገቢነት የጎደላቸው እንደሆኑ ተናግረዋል። አየር መንገዱን የሚያክል ግዙፍ ድርጅት ያለምዘና ስርአት መምራት አይቻልም። ተቋሙ በውድድር ውስጥ እንዳለ ሁሉ በውስጡ የሚገኙ ሰራተኞችም መወዳደር መቻል አለባቸው። ፍትሀዊ እንዲሆን ደግሞ የሰራተኞች ተሳትፎ ታክሎበት ነው የሚሰራው። በምዘናው አፈፃፀም ዝቅ ያሉ ሰራተኞች ደግሞ ያሉበት ደረጃ ታውቆ ክፍተታቸውን የሚሞሉ ስራዎች ይሰራሉ። በዚህም ተቋሙ ግቡን ለመምታትና ውጤታማ ለመሆን ይረዳዋል ብለዋል። የህመምና የወሊድ ፈቃድም ሰራተኞቹ ደመወዝም ሆነ የህክምና ጥቅም ሳይነካባቸው በህጉ መሰረት ፈቃድ ይወስዳሉ። በአመቱ መጨረሻ የሚከፈለው ጉርሻ ግን በህግ የሚመራ በመሆኑና የሚበረታታው ደግሞ የሰራና በየደረጃው ውጤታማ ሆኖ ድርጅቱን ለተሻለ ትርፋማነት ማብቃት የቻለ ሰራተኛ ነው። በተቋሙ የሚነሱ ችግሮችን ለማቃለል ውይይቶች እየተደረጉ ሲሆን፤ ዘላቂ መፍትሄውም ዳር ሆኖ መመልከት ሳይሆን ክፍተት ካለ ለመሙላት ጥረት ማድረግ መሆኑን ገልፀዋል። ለዚህም ሁሉም ሰራተኛ በባለቤትነት መንፈስ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚገባው ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ጥር ስድስት ሁለት ሺህ ፍዮሪ ተወልደ
አየር መንገዱ የመብት ጥሰት እያደረሰብን ነው የድርጅቱ ሰራተኞች
አዲስ አበባ፣ ህዳር ስላሳ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከፅዳት ባለሙያዎችና ከጃንሜዳ አካባቢ ማህበረሰብ ጋር በመሆን አካባቢውን የማፅዳት ስራ አከናውነዋል።በጃንሜዳ ውስጥ ያሉ አትክልት ነጋዴዎች ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ተዘጋጀላቸው የአትክልት መሸጫ ስፍራዎች እንደሚዘዋወሩ ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል ።ጃንሜዳን ለጥምቀት በአል ዝግጁ ለማድረግ እና ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ ለመመለስ በተከታታይ የማፅዳት ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ከንቲባዋ ገልፀዋል ።ሸማቹን እና አምራቹን አንድ ላይ ማገናኘት የሚያስችሉ የአትክልት እና መሰል መገበያያ ስፍራዎች በየክፍለ ከተማው ተደራሽ የማድረግ ስራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ወይዘሮ አዳነች ጠቁመዋል።ነጋዴውም ሆነ ነዋሪው ህብረተሰብ ጃንሜዳን ወደ ቀድሞው አገልግሎቱ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከተማው ፕሬስ ሰክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ የፋና ድረ ገፅ ይጎብኙ፤ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች ከፅዳት ባለሙያዎችና ከጃንሜዳ አካባቢ ማህበረሰብ ጋር የፅዳት ስራ አከናወኑ
በአይነ ሀሊና ጥቂት ወደፊት ልውሰዳችሁ ስድስት ወራት ያህል። ከጓደኛዎ፣ ከባለቤትዎ፣ ከፍቅረኛዎ ወይም ከስራ ባልደረባዎ ጋር ሆነው ካዛንቺስ እምብርት ኛ ፎቅ አናት ላይ በሚገኘው ካፌና ሬስቶራንት አዲስ አበባ ከተማን ሶስት መቶ ስልሳ ዲግሪ ዙሪያ ገባዋን እየቃኙ እየበሉ፣ እየጠጡ እየተዝናኑ እየተደሰቱና እየተጫወቱ፣ ነው። በደራው ጨዋታ መሀል መጣሁ ብለው ተነስተው መታጠቢያ ወይም መፀዳጃ ቤት ደርሰው ሲመለሱ የነበሩበት ጠረጴዛና አብረዎት የነበሩትን ሰው ትተው በሄዱበት ስፍራ አጡ። ምን ጉድ ነው ተሳስቼ ወደ ሌላ ጠረጴዛ ሄድኩ ዴ ብለው ትንሽ ደንገጥ አሉና አካባቢውን መቃኘት ያዙ። ከነበሩበት ስፍራ ትንሽ ፈቀቅ ብሎ ወዳጅዎ መመለስዎን አይተው ፈገግ ሲሉ፣ ድንጋጤው ጠፋና ወደ ስፍራው አመሩ። የነበሩበት ስፍራ የጠፋዎት ሬስቶራንቱ በዝግታ ስለሚሽከረከር ነው። እንዴት ህንፃ ይሽከረከራል በማለት ሊገረሙ ይችላሉ። የሚሽከረከረው መላው ህንፃ ሳይሆን ሰገነቱ መጨረሻ ላይ ያለው ባርና ሬስቶራንት ብቻ ነው። ይህ አዲስ አበባ ከተማን ቀንም ሆነ ምሽት ሶስት መቶ ስልሳ ዲግሪ በማየት የሚዝናኑበትና የሚደሰቱበት ቴክኖሎጂ፣ ለአገራችን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም የመጀመሪያው ነው። ይህ አስገራሚና አስደናቂ ትእይንት የሚቀርበው የት ነው በማለት ማወቅ እንደምትፈልጉ እገምታለሁ። ትእይንቱ ያለው ባለፈው ረቡእ በተጠናቀቀው የአውሮፓውያን ሁለት ሺህ አመት፣ ከአፍሪካ ምርጥ አስር ሆቴሎች አስር አንዱ ሆኖ ባለፈው ሳምንት በተሸለመው ኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል ነው። ይህ ተሽከርካሪ ካፌና ሬስቶራንት የኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል የማስፋፊያ ውጤት ነው ያሉት የሆቴሉ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ዜናዊ መስፍን፣ ግንባታው ከመቶ ዘጠና የተጠናቀቀ ስለሆነ በሚቀጥሉት አራት እና አምስት ወራት እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል። ማስፋፊያው አምስት መቶ ሚሊዮን ብር ግማሽ ቢሊዮን ብር መፍጀቱን የጠቀሱት ስራ አስኪያጁ አንድ አምስት መቶ ሰዎች የሚይዝ ትልቅ አዳራሽ፣ ሁለት መቶ ሰዎች የመያዝ አቅም ያላቸው አራት አነስ ያሉ አዳራሾች፣ ከአራት መቶ እስከ አምስት መቶ ሰዎች ማስተናገድ የሚችል ሬስቶራንት፣ ሁለት መቶ መኪኖች መያዝ የሚችል ሁለት ፎቅ የመኪና ማቆሚያ፣ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ሰማኒያ ሆቴል አፓርትመንት ክፍሎች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ እንዳሉት ገልፀዋል፡ በአሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ ስካይ ዶም፣ በአትላንታ ዌስቲን ሆቴል በሂልተን ሆቴል ስር ተሽከርካሪ ሬስቶራንት እንዳላቸው የተናገሩት አቶ ዜናዊ፤ እነዚህን ሆቴሎች ለመጎብኘት በየአመቱ ብዙ ሚሊዮን ህዝቦች ወደ ስፍራው እንደሚጓዙ ገልፀዋል። አቶ ዜናዊ፣ እነዚያ ተሽከርካሪ ሬስቶራንት ያላቸው ሆቴሎች በየአመቱ ከጎብኚዎቻቸው ብዙ ሚሊዮኖች ዶላር እንደሚያፍሱ ጠቅሰው፣ ሆቴላቸው ከአለም አቀፍ ሆቴሎች ጋር ተወዳድሮ ማሸነፍ መቻሉ በመላው አለም እየናኘ ስለሆነ ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ደረጃ ያሟሉ ሆቴሎች የላትም ለሚለው ምላሽ ከመስጠቱም በላይ ተሽከርካሪ ሬስቶራንቱን ለመጎብኘት ከሚመጡ በርካታ ቁጥር ካላቸው ኢትዮጵያውያንና የውጭ ቱሪስቶች፣ የቢዝነስ ሰዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ዳጎስ ያለ ገቢ በመሰብሰብ ታሪክ እንደምንሰራ ፅኑ እምነት አለኝ ብለዋል። በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ተሽከርካሪ ሬስቶራንት መስራታችና በአለም ታዋቂ ከሆኑ አስር ሆቴሎች አንዱ መሆን፣ የአገሪቷን ገፅታ ከመንገባት አኳያ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ አቶ ዜናዊ ገልፀዋል። ኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ በአለም አቀፍ ደረጃ ለሽልማት የበቃው ለመታወቅ ብሎ ተንቀሳቅሶ ሳይሆን የዘወትር ተግባሩን እያከናወነ ነው። ሴኩሪቲው፣ ወደሆቴላቸው የመጡት እንግዶች እነሱን ለመገምገም መምጣታቸውን በፍፁም አያውቅም። የአንደኛው ገምጋሚ ጃኬት ቆሻሻ ነክቶት ነበር። ጃኬቱ ቆሻሻ እንደነካው ነግሮት ለማፅዳት እንዲሰጠው በትህትና ጠየቀው። እንግዳውም ጃኬቱን አውልቆ ሰጠው በአጭር ጊዜ ላውንደሪ ወስዶ ቆሻሻውን አስለቅቆ አምጥቶ ሰጠው። ወደ ውስጥ ሲገቡ የተቀበሏቸው ሰራተኞች ያሳዩዋቸው ፈገግታና የአክብሮት አቀባበል፣ በሻይ ቡና መስተንግዶ ወቅት ያደረጉት መስተንግዶ ማረካቸው። ይህ ብቻ አይደለም። ክፍላቸው ከገቡ ከ ደቂቃ በኋላ ደውለው፣ ሆቴሉን እንዴት እንዳገኙት፣ የተስማማቸው መሆኑንና የሚፈልጉት የጎደለ ነገር እንዳለ ጠየቁ። አንደኛው ገምጋሚ ያስመዘገበውን የልደት ቀን አስታውሰው፣ አራት ሴቶች በማለት ሰርፕራይዝ አደረጉት። በእነዚህና በሌሎችም መስተንግዷቸው እጅግ መርካታቸውን በሽልማት ስነ ስርአቱ ወቅት እንደነገሯቸው አቶ ዜናዊ ተናግረዋል። አቶ ዜናዊ መስፍን በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት እ ኤ አ ማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ከሀንጋሪ ቡዳፔስት ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሳይንስ ያገኙ ሲሆን የመጀመሪ ዲግሪያቸውን በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት ከዚያው አገር በሆቴል ምግብ ዝግጅትና በቱሪዝም ማኔጅመንት አግኝተዋል። ከሰሩባቸው አመታት ስምንትቱን አመት ያሳለፉት የከፍተኛ ሆቴሎች ስራ አስኪያጅ ሆነው ነው። ኢንተር ኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል፤ ሂልተን ጋርደን ኢን ፣ ሂልተን ዋሽንግተን ዲሲ፣ ሂልተን ዋሽንግተን ፕላዛ፣ በስራ አስኪያጅነት ከሰሩባቸው ትላልቅ ሆቴሎች ጥቂቱ ናቸው።
ኢንተር ኮንቲኔንታል በአፍሪካ የመጀመሪያው ተሽከርካሪ ካፌና ሬስቶራንት
አዲስ አበባ፣ መስከረም አስር፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አመራርና ሰራተኞች ዘጠኝ ነጥብ ስድስት ሚሊየን ብር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል። በርክክብ ስነ ስርአቱ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው እንዳሉት ተቋሙ የህዝብ ሚዲያ መሆኑን ለማረጋገጥ ልማትን በማገዝና የህዝብ ፍላጎቶችን በማስጠበቅ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። ፋና በመረጃ ብቻ ሳይሆን በህዝቡ ሰላምና ደህንነት ሀዘንና ደስታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ስራ አስፈፃሚው አውስተውዋል። የፋና አመራርና ሰራተኞችም ከጀግናው መከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመሆን የአንድ ወር ደመወዛቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል። ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አለምሰገድ ወንድወሰን ፋና በመከላከያ ውሎዎች እየዋለ ገድሉን የሚዘግብ ጀግና ሚዲያ ነው ብለዋል። ጠላት የሚያሰራጨውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በመመከትም ሙያዊ እገዛ አድርጓል ነው ያሉት። በአፈወርቅ እያዩ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አመራርና ሰራተኞች ዘጠኝ ነጥብ ስድስት ሚሊየን ብር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ
በሶስትኛው ሳምንት ሌላኛው መርሀ ግብር በሀዋሳ ሰውሰራሽ ሜዳ ሀዋሳ ከተማ ባህር ዳር ከተማን የሚያስተናግድበት ጨዋታን በቀጣዩ ዳሰሳ ተመልክተነዋል።ከመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት አራት አራት ነጥብ ይዘው መልካም ጅማሮን በማድረግ ገና በማለዳው በሊጉ ሰንጠረዥ ከአናት በሚገኙ ሁለት ቡድኖች መካከል የሚደረገው ጨዋታ ጠንካራ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።ባለሜዳዎቹ ሀዋሳ ከተማዎች በሁለቱም የሊግ ጨዋታዎችና በአዳማ ከተማ ዋንጫ ላይ በነበራቸው ቆይታ ቡድኑ ለመከላከል አደረጃጀት ከፍተኛ አፅንኦት እንደሚሰጥ ለመመልከት ተችሏል። ባሳለፍነው ሳምንት ከሆሳእና ነጥብ ይዞ ሲመለስ በአመዛኙ ከተወሰኑ የጨዋታ ቅፅበቶች ውጪ በቁጥር በርከት ብለው ለራሳቸው ግብ ቀርበው ሲከላከሉ ተስተውሏል።ቡድኑ ጨዋታውን በሜዳው እንደማከናወኑ ማሸነፍን ኢላማ ያደረገ ቀጥተኛ የማጥቃት አቀራረብ እንደሚኖረው ሲጠበቅ ወጣቶቹ መስፍን ታፈሰ እና እስራኤል እሸቱን በማጣመር ተሻጋሪ ኳሶች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ይገመታል።በሀዋሳ በኩል አስጨናቂ ሉቃስ፣ ወንድማገኝ ማእረግ እና አላዛር መርኔ ባለፈው አመት በጥሎ ማለፉ እና ፕሪምየር ሊጉ በተመለከቱት ቀይ ካርድ፤ ተከላካዩ መሳይ ጳውሎስ ደግሞ በጉዳት ለጨዋታው አይደርሱም።በአዲስ መልኩ በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተገነባ የሚገኘው ባህርዳር ከተማ በመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ በተደጋጋሚ አደጋ ለመፍጠር ጥረት የሚያደርግ ቡድን ነው። በቡድኑ በኩል መልካሙ ዜና በመቐለው ጨዋታ ቡድኑ ከተለያዩ ክፍሎች ግብን ማስቆጠር የሚችሉ ተጫዋቾችን መያዙ እና የቆሙ ተሻጋሪ ኳሶች አጠቃቀሙ መሻሻሉ አምና እንድክመት የሚቀርብበትን ግብ የማስቆጠር ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።የነገው ጨዋታ ከኳስ ቁጥጥር ይልቅ ቀጥተኛ ማጥቃትን በሚመርጡ ቡድኖች እንደመካሄዱ የእርስ በእርስ ግንኙነቶች ትልቅ ልዩነት እንደሚፈጥሩ ይገመታል። የሀዋሳ አጥቂዎች ከባህር ዳር ተከላካዮች እንዲሁም በሁለቱም በኩል የሚገኙ የመስመር ተጫዋቾች የሚያደርጉት የአንድ ለአንድ ግንኙነት የጨዋታንው ውጤት የመወሰን ሀይል ይኖረዋል።ለነገው ጨዋታ በጣናው ሞገድ በኩል በመቐለው ጨዋታ የተጎዳው ዜናው ፈረደ ከቡድኑ ጋር ወደ ሀዋሳ ያልተጓዘ ሲሆን ቀሪዎቹ ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ለጨዋታው ዝግጁ ሆነዋል።እርስ በርስ ግንኙነትሁለቱ ቡድኖች ሁለት ጊዜ ተገናኝተው ሁለቱንም ጨዋታዎች በአቻ ውጤት አንድ አንድ እና አጠናቀዋል።ግምታዊ አሰላለፍሀዋሳ ከተማ አራት ሶስት ሶስት ቤሌንጋ ኢኖህዳንኤል ደርቤ አዲስአለም ተስፋዬ ላውረንስ ላውንቴ ኦሊቨር ኳሜአለልኝ አዘነ ተስፋዬ መላኩ ሄኖክ ድልቢብርሀኑ በቀለ መስፍን ታፈሰ እስራኤል እሸቱባህር ዳር ከተማ አራት ሶስት ሶስት ሀሪሰን ሄሱሳላምላክ ተገኝ አዳማ ሲሶኮ አቤል ውዱ ሳሙኤል ተስፋዬፍ ሚካኤል አለሙ ሳምሶን ጥላሁን ፍፁም አለሙፍቃዱ ወርቁ ማማዱ ሲዲቤ ወሰኑ አሊ
ቅድመ ዳሰሳ ሀዋሳ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ
ኢሳት ጥቅምት በኢትዮጵያ እየተባባሰ መጥቷል ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ግምት ውስጥ በማስገባት የአውሮፓ ህብረትና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ።የአውሮፓ ፓርላማ ንኡስ ኮሚቴ በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ባዘጋጀው መደረክ ላይ የታደመው ሂውማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እጅጉን አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አብራርቷል።በመድረኩ ለተሳተፉ የአውሮፓ ህብረትና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ተወካዮች የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ አፋጣኝና ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።ህብረቱም ሆነ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ከሀገሪቱ ጋር ያላቸውን የጥቅም ትስስር በማስቀደም በቂ ትኩረት እየሰጡ እንዳልሆነና ድርጊቱ ተገቢ አለመሆኑን የሂህማን ራይትስ ዎች ተወካዮች በመድረኩ ቅሬታቸውን አስተጋብተዋል።የኢትዮጵያ የልማት አጋር የሆነ የአውሮፓ ህብረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በመግባት የተፈፀሙ ግድያዎችንና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣራ ግፊትን ማድረግ እንዳለበት በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ተመራማሪ የሆኑት ፊሊክስ ሆርን ለመገኛና ብዙሀን አስታውቀዋል።በመድረኩ ታዳሚ የነበሩ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት የጀርመኗ ቻንስለር አንጀላ መርከል በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት በመኮነን ተቃውሞ ማሰማታቸውንም ለመረዳት ተችሏል።መርከል ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጥሪን ቢያቀርቡም ጀርመን በአውሮፕላ ህብረት ካላት አስተዋፅኦ እና ሀላፊነት አንፃር ሲነፃፀር ቀርቦ የነበረው ጥሪ ደካማ እንደነበር የፓርላማ አባል አና ጎሜዝ ለ እንግሊዝኛው ክፍል አስረድተዋል።በኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርበው ንግግርን ለማድረግ ፈቃደኛ ያልነበሩት አንጀላ መርከል የኢትዮጵያ መንግስት እየቀረቡ ላሉ የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥና የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።የአውሮፓ ህብረት በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ተፈፅሟል ያላቸውን ግድያዎች በማውገዝ ድርጊቱ በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲካሄድበርት ሲያሳስብ ቆይቷል።አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት ተመሳሳይ ጥሪን ቢያቀርቡም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተባባሪ እንደማይሆኑ ምላሽ ሰጥተዋል።
የአውሮፓ ህብረትና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ
በማይጠብሪ ግንባር የተሰለፈው የህወሀት ሀይል በደባርቅ በኩል አድርጎ ወደ ሱዳን ድንበር ለመገናኘት የከፈተውን ጥቃት በመቀልበስ፣ ጥቃት የሰነዘረውን ሀይል መደምሰሱን የአገር መከላከያ ሚኒስቴርና የአማራ ክልል አመራሮች ባወጡት መረጃ አስታውቀዋል። ሚኒስቴሩ ነሀሴ ሀያ አምስት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳስታወቀው፣ በማይጠብሪ ግንባር የተሰለፈው የህወሀት ሀይል በአማራ ክልል በደባርቅ በኩል የቆረጣ ጥቃት በመክፈት ወደ ጭና አካባቢ ቆርጦ ለመግባት ሙከራ አድርጓል። የህወሀት ሀይል በደባርቅ በኩል በዳባት ወረዳ ጭና አካባቢ ቆርጦ ለመግባት መምከሩን፣ የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰውነት ውባለም ገልፀዋል። አላማው በአካባቢው ሽብር ፈጥሮ ከግብፅ ተላላኪዎች ለመገናኘት እንደ ነበር፣ የፀጥታው ሀይል ከአራት ቀን በላይ ውጊያ ማድረጉን፣ በተሰራው ጠንካራ ስራም ማለፍ አልቻለም ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው አስረድተዋል። ቆርጦ በመግባት ደባርቅንና ዳባትን ለማለያየት ያሰበው አላማም ከሽፏል ብለዋል። የቡድኑ አላማ በዳባት አካባቢ ሽብር ፈጥሮ ወደ ሱዳን ድንበር በማቅናት ከግብፅ ተላላኪዎች ለመገናኘት ነበር፤ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻዎች በመቀናጀት ለአራት ተከታታይ ቀናት ባደረጉት ፀረ ማጥቃት ቡድኑ መደምሰሱንና መበታተኑን ገልፀዋል። የህወሀት ሀይል አጅሬ ጃኖራን ቆርጦ ለመሄድ ቢያስብም ተደምስሶ መቅረቱን ተናግረዋል። የመከላከያ ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ በተመሳሳይ ከማይጠብሪ ግንባር በኩል የመጣው የህወሀት ሀይል በተለይም በጫንቅ፣ በጭና፣ በአጅሬ ጃኖራና በዙሪያ ገባዎቹ ጥቃት ሲያደርስ እንደነበር ገልጿል። በዳባት ቆርጦ የመጣው የህወሀት ሀይል፣ ወቅን በተባለው አካባቢ በማለፍ፣ ደባርቅን ለመቆጣጠርና ወደፊት ለመገስገስ እቅድ እንደነበረውም የመከላከያ መግለጫ ያመለክታል። ይሁን እንጂ በዚህ ግንባር የተሰለፉት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ሀይል፣ እንዲሁም ሌሎች ሀይሎች መክረውና ተቀናጅተው በሜካናይዝድ ሀይል መድፎችና ሮኬቶች በመታገዝ የመጣውን ሀይል መምታቻውን መረጃው ገልጿል። በዚህም መሰረት በጫንቅ፣ ጭና፣ አጅሬ ጃኖራ፣ ወቅንና ዙሪያ ገባዎቹ በደረሰበት ምት ተደምስሶ መበተኑን አስታውቋል።
በደባርቅ በኩል ወደ ሱዳን ለመገናኘት ጥቃት የሰነዘረው የህወሀት ሀይል ተመትቶ መበተኑ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ጥር አንድ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ጋናዊቷ ሼፍ ፋይላቱ አብዱል ራዛክ ያለማቋረጥ ከሁለት መቶ ሀያ ሰባት ሰአታት በላይ ምግብ የማዘጋጀት ተግባር አከናውናለች። ይህም ያለማቋረጥ ምግብ በማዘጋጀት የአለም ክብረ ወሰን ባለቤት ሊያደርጋት እንደሚችል ተነግሯል። ጋናዊቷ የምግብ ማብሰል ባለሙያዋ እንስት ለቀናት የቆየው የምግብ ማብሰል ቆይታዋ ፈታኝ ቢሆንም ለሀገሬ ጋና ስል ያደረኩት ነው ስትል ተናግራለች። በሀገሯ ባንዲራ ተጎናፅፋ ምግብ ስታበስል የነበረችው ሼፍ ፋይላቱ ምግቧን ለቀናት ቀጥ ብላ ስታበስል ቆይታ ስታጠናቅቅ በምግብ ቤቱ የነበሩ ሁሉ አሞካሽተዋታል። ይህን የምግብ ማብሰል ሂደት የሚያሳይ መረጃም ለጊነስ የአለም አቀፍ ክብረወሰን መላኩም ነው የተጠቆመው። አሁን ላይ ረጅም ሰአት የምግብ ማብሰል ሪከርዱ አላን ፊሸር በተባለ አየርላንዳዊ የተያዘ ሲሆን ፥ ሰአቱም አንድ መቶ ሰአት ከሀምሳ ሰባት ደቂቃ እንደሆነ ተገልጿል። የምግብ ማብሰል ባለሙያዋ እንዳለችው፥ ማንኛውም ያሻሻልኩትን ሪከርድ ለመስበር ያሰበ ሰው አሰቸጋሪ ይሆንበታል ስትል ተናግራለች። ፖለቲከኞች፣ የጋና ምክትል ፕሬዚዳንት ማሀሙዱ ባውሚያን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ሰዎች እና የጋና ጦር ሰራዊት አባላት ሳይቀሩ በምግብ ማብሰል ሂደቱ ለባለሙያዋ ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል። ባለፈው የፈረንጆቹ አመት ሂልዳ ባሲ በናይጄሪያ ውስጥ በሼፍ ፊሸር ከመበልጧ በፊት ሪከርዱን መስበሯ የሚታወስ ነው።
ያለማቋረጥ ከሁለት መቶ ሀያ ሰባት ሰአታት በላይ ምግብ ያዘጋጀችው ጋናዊት ሼፍ
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቫሌንሽያው ማራቶን ውድድር ላይ ተካፍለዋል። እሁድ ሀዳር ሀያ ስድስት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በስፔንዋ ከተማ ቫሌንሽያ በተደረገው የማራቶን ውድድር በኬንያውያን የበላይነት ሲጠናቀቅ፣ ኢትዮጵያውኑ ሁለተኛና ከዚያ በታች ያለውን ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል። በወንዶች ጫሉ ደምሴ ሁለት፡አምስት ነጥብ አንድስድስት በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቅ፣ አበበ ነገዎ ሁለት፡አምስት ነጥብ ሁለትሰባት አምስተኛ እንዲሁም ክንዴ አጥናው ሁለት፡አምስት ነጥብ አምስትአራት ሰባተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአስረኛ ደረጃ እስከ ሀያ ሶስትኛ ማጠናቀቅ ችለዋል። ርቀቱን ኬንያዊው ቼሮኖ ላውረንስ ሁለት፡አምስት ነጥብ አንድሁለት በሆነ ሰአት በበላይነት አጠናቋል። በሴቶች ውድድር እታገኝ ወልዱ ሁለት፡ሀያ ነጥብ አንድስድስት በሆነ ሰአት ሁለተኛ፣ በየቀኑ ደገፋ ሁለት፡ሀያ ሶስት ነጥብ አራት በሆነ ጊዜ ሶስተኛ፣ እንዲሁም ረሀማ ቱሳ ሁለት፡ሀያ ሶስት ነጥብ ሁለት አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል። በሴቶች ምድብ በርካታ ኢትዮጵያውያት የተሳተፉ ሲሆን፣ ከወንዶቹ የተሻለ ውጤት ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል። በሴቶቹም ኬንያዊቷ ናንሲይ ጄልጋት ሁለት፡ሀያ ዘጠኝ ነጥብ ሶስትአንድ በሆነ ሰአት በአንደኝነት አጠናቃለች። በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች በሚከናወኑ የጎዳና ውድድሮች ላይ የማይጠፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ሆኖም በውጤት ደረጃ የሴቶች የተሻለ ነው። ከዚህም ባሻገር አዳዲስ ስሞችን መመልከት ተለምዷል። የቫሌንሽያ ማራቶን በመጀመሪያዎቹ አምስትና ስድስት አመታት በአገራቸው ስፔናውያን አትሌቶች የበላይነት ቢያዝም እ ኤ አ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት በኋላ ግን ኬንያውያን አትሌቶች ተቆጣጥረውታል። እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች በሁለቱም ፆታ ስፔናውያን ሀያ ስድስት ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚ ሲሆኑ፣ ኬኒያ ጊዜ በማሸነፍ ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያ በወንዶች ሶስት ጊዜ እንዲሁም በሴቶች ዘጠኝ ጊዜ በድምሩ ጊዜ በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በስፖንሰር አድራጊዎች ምክንያት በየአመቱ የውድድር ስያሜው የሚቀየረው የቫሌንሽያው ማራቶን ውድድር፣ አምና በኮቪድ ምክንያት መሰረዙ ይታወሳል።
በቫሌንሽያው ማራቶን ኢትዮጵያውያቱ ደምቀው አልፈዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት ሀያ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የሽመና ስራን በማቅለል ምርታማነትን ከሶስት መቶ በመቶ በላይ ያሳደገው በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ አውቶማቲክ መሸመኛ ማሽን በሀገር ልጆች ተመርቶ ጥቅም ላይ ውሏል። ቴክኖሎጂው የበለፀገው አዲስ አበባ በሚገኘው ሚርካ ኢንጂነሪንግ የግል ኢንተርፕራይዝ መሆኑን የኢንተር ፕራይዙ ባለቤት ኢንጂነር ቻላቸው ሰጠኝ ይናገራሉ። ያበለፀጓቸው የፈጠራ ስራዎችም የክር የድርና ማግ ማጠንጠኛ እና አውቶማቲክ መሸመኛ ማሽኖች መሆናቸውን ይናገራሉ። አውቶማቲክ የመሸመኛ ማሽኑ የኤሌክትሪክ ሀይል በመጠቀም የተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ ልብሶችን ያመርታል ሲሉ አገልግሎቱን ያስረዳሉ። ቴክኖሎጂዎቹ በአብዛኛው በራስ ፈጠራ መሰራታቸውን እና ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት አመተ ምህረት ጀምሮ በመሻሻል ላይ ስለመሆናቸውም ገልፀዋል። ከምርታማነት አኳያ የማጠንጠኛ ማሽኑ እስከ ስድስት መቶ በመቶ ምርታማነትን ይጨምራል ነው ያሉት። አውቶማቲክ መሸመኛ ማሽኑም ከሶስት መቶ እስከ አንድ ሺህ በመቶ ምርታማነትን እንደሚጨምር የፈጠራ ባለሙያው ተናግረዋል። ኢንጂነር ቻላቸው ስለ ፈጠራ ስራዎቹ ጠቀሜታ ሲናገሩ በተለይም አውቶማቲክ የመሸመኛ ማሽኑ በሞተር ስለሚንቀሳቀስ ጊዜና ጉልበትን በመቆጠብ እና በሰአት በአማካይ ከአምስት እስከ ዘጠኝ ሜትር ልብስ በማምረት ጥቅሙ የጎላ ነው ብለዋል። የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ እና የሴቶችን የስራ ጫና በመቀነስ፣ ለዘመናት በሰው ሀይል የታጠረውን የሽመና አሰራር በቴክኖሎጂ በመተካት ረገድ ፋይዳው የጎላ ስለመሆኑም ነው የሚናገሩት። ለአሰራር ምቹ መሆኑና ለስራ ፈላጊዎች የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር የራሱን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትም አስረድተዋል። የፈጠራ ስራዎቹም በተመጣጣኝ ዋጋ ገበያ ላይ ውለው አገልግሎት እየሰጡ ስለመሆኑም አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣንም ለፈጠራ ባለሙያው ስራዎች እውቅና ሰጥቷል። እንዲሁም የፈጠራ ስራዎቹ ተጨማሪ ማሻሻያ ተደርጎባቸው ለባለስልጣኑ ቀርበው በሂደት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። በዮሀንስ ደርበው ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ኢንስታግራም፦ ቲክቶክ፦ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
የሽመና ስራ ምርታማነትን ከሶስት መቶ በመቶ በላይ ያሳደገው ቴክኖሎጂ
ሰኔ ሀያ ሰባት ቀን አመተ ምህረትኢሳት ዜናበጣሊያን ሮም በተደረገው ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያን ወክላ በ ሜትር ውድድር ያሸነፈችው የአትሌት አበባ አረጋዊ የዜግነት ጉዳይ ውዝግብ አስነሳ።አበባ ከሳምንታት በፊት ሮም ላይ በተደረገው ዳይመንድ ሊግ ውድድር ገንዘቤ ዲባባንና ሌሎች የአለማችንንታላላቅ አትሌቶች አስከትላ በመግባት አንፀባራቂ ድል መቀዳጀቷ ይታወሳል። አበባበሮሙ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ አገሯን ወክላ ከመሮጧ አኳያ ኢትዮጵያ ለለንደኑ ኦሊምፒክ ከገንዘቤ ዲባባ በተጨማሪ በ ሜትር የምታሰልፈው አትሌት እንዳገኘች ሲነገር ቆይቷል።ይሁንና የስዊድን መንግስት አትሌት አበባ እኤአ በ አመተ ምህረት ወደ ስዊድን አምርታ ዜግነት መጠየቋን በማስታወስ በጥያቄዋ መሰረት በቅርቡ ሰኔ ቀን አመተ ምህረት ዜጋ መሆኗን በይፋ ገልጿል።የስዊድን መንግስት ለአበባ የዜግነት ጥያቄ ምላሽ የሰጠው በቅርቡ በተካሄደው በሮሙ የዲያመንድ ሊግ አሸናፊ በሆነች ማግስት ነው።የስዊድን መንግስት ከዚህም በተጨማሪ አትሌት አበባ አረጋዊ ከሶስት ሳምንት በኋላ በሚጀመረው የለንደን ኦሊምፒክ ለስዊድን የምትሮጥ መሆኗን ጭምር በመጥቀስ ጉዳዩን ለአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር እንዳቀረበው ለአትሌቷ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል።የኢትዮጵያ ብሀራዊ አትሌቲክስ ቡድን አባል የሆነችው አበባ በአሁኑ ጊዜ ከቡድኑ አባላት ጋር በዝግጅት ላይ ትገኛለች።በተፈጠረው ሁኔታ ቅሬታ ያደረበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስዊድን መንግስት ለአለማቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያቀረበው ጥያቄ አግባብነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ ፌዴሬሽኑ አቤቱታውን ውድቅ እንዲያደርግ መጠየቁ ተሰምቷል።አበባ ጉዳዩን አስመልክቶ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያላትን ሀሳብ እንድትገልፅ በጠየቃት መሰረት እኤአ በ አመተ ምህረት ወደ ስዊዲን አምርታ የዜግነት ጥያቄዋንም ለስዊድን መንግስት ማቅረቧን ሆኖም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መኖርያ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ዜግነት እንዳልተሰጣት መናገሯን ሪፖርተር አመልክቷል።እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ከአገር አገር እየተንቀሳቀሰች ስትወዳደር የቆየችው ኢትዮጵያዊት መሆኗን በሚያረጋግጠው የኢትዮጵያ ፓስፖርት መሆኑን ያብራራችው አትሌት አበባ አሁን ውጤታማ መሆኗ ከተረጋገጠ በኋላ የዜግነት ጥያቄዋ መልስ ማግኘቱ ብዙም እንዳላስደሰታት ጠቅሳለች።በመሆኑምበቀጣዩ የለንደን በኦሊምፒክም ሆነ በሌሎች አለም አቀፍ ውድድሮች መሮጥ የምትፈልገው ለኢትዮጵያ መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ለአለማቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዳስገባች ተናግራለች።በአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ደንብ መሰረት አንድ አትሌት በአለም አቀፍ ውድድር ላይ የአንድን አገር መለያ አድርጐ ከተወዳደረ በኋላ ዜግነት ቀይሮ ዜጋ ለሆነበት አገር መሮጥ የሚችለው የግድ ሶስት አመት ከማንኛውም ውድድር ተገልሎ ከቆየ በኋላ ነው።ከዚህ አኳያ ከሶስት አመት በፊት ሞሪሸስ ላይ በተካሄደው የ አፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና በቅርቡ በሮም በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ አገሯን ወክላ የተወዳደረችው አትሌት አበባ በለንደን ኦሎምፒክም ለኢትዮጵያ ለመሰለፍ ላላት ፍላጎት ህጉ እንደሚያግዛት የዘርፉ ባለሙያዎች አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል።
የስዊድን መንግስት አትሌት አበባ ስዊድናዊ ነት ይላል
ሁለት ነፍስጡር ተፈናቃዮች መኪና ላይ ወልዷል በመስከረም አያሌው በቤኒሻንጉል ክልል የሚኖሩ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ያፈናቀለውን አካል ጉዳይ ለአለም ፍርድ ቤት ለማቅረብ ማቀዱን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አስታወቀ። የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ወንድማገኘኝ ደነቀ እንደገለፁት በቤኒሻንጉል ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆናቸው ብቻ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመባቸው በመሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ክስ ለመመስረት ታስቧል። ባለፈው ሳምንት ከቤኒሻንጉል ቡለን ወረዳ ብቻ አምስትሺ አምስት መቶ ስላሳ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወደ ባህርዳር፣ ጐንደር፣ ደጀን እና ቻግኒ እንደተሰደዱ የገለፁት አቶ ወንድማገኝ፤ ከትናንት በስትያም ከከማሼ ዞን ያርሶ ወረዳ ሁለትሺ አምስት መቶ ተጨማሪ ሰዎች ተሰደው ፍኖተሰላም ሰፍረዋል ብለዋል። እነዚህ የአማርኛ ቋንቋ በመናገራቸው ብቻ ከስላሳ አመት በላይ ከኖሩበት አካባቢያቸው እንዲሰደዱ የተደረጉ ሰዎችም ከሆቴል ባለቤት እስከ የቀን ሰራተኛ የሚደርሱ መሆናቸው ተገልጿል። በተለይ በከማሼ ዞን እነዚህ ሰዎች የኖሩበት ነባር አካባቢያቸው መሆኑን እና አንዳንዶቹም አማራ ብቻ ሳይሆኑ ቅልቅል መሆናቸው ተገልጿል። በተለይ ከትናንት በስትያ ወደ ፍኖተ ሰላም እንዲሰደዱ ከተደረጉት ሰዎች መካከል ሁለት ነፍሰጡሮች መኪና ላይ መውለዳቸውንም አቶ ወንድማገኝ ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች ሀላፊነት በጐደለው ሁኔታ በአንድ መኪና እየታጨቁ እና እየተደበደቡ ወደነዚህ አካባቢዎች በመጓዝ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ለረጅም አመት የኖሩበትን ቀዬ እና ሀብት ንብረት ትተው ወደ ሌላ አካባቢ እንዲሰደዱ የተደረጉት እነዚህ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ ከመሆናቸውም በላይ ህፃናት እና ታዳጊዎች ለጐዳና ህይወት እየተዳረጉ መሆናቸው ተገልጿል። በየጊዜው በዜጐች ላይ እየተከሰተ ያለውን ከቀዬ የማፈናቀል ሂደት ለማስቆም የፓርቲው አመራሮች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል። የውይይቱ ዋና አላማ እነዚህ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጐች አስቸኳይ እርዳታ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነበር። ለተፈናቃዮቹ ከተለያዩ አካላት ገንዘብ የማሰባሰብ እና የተሰበሰበውን ገንዘብም በአግባቡ አገልግሎት ላይ ማዋል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪም በእነዚህ ሰዎች ላይ በቋንቋቸው ምክንያት ብቻ እየተወሰደባቸው ያለው እርምጃ የዘር ማጥፋት እርምጃ በመሆኑ በአለም አቀፍ ህግ ለመጠየቅ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል። አንድን ሰው በቋንቋ፣ በእምነቱ ወይም በሌላ ብቻ መግደል፣ ማሰር፣ ማሰቃየት፣ ማፈናቀል ዘር ማጥፋት ነው። በቻርተሩ የተቀመጠ ነገር ነው። እነዚህ ሰዎች የራሳቸው መረጃ ስላላቸው የህግ አማካሪዎችም ያሉን ይሄንኑ ነው። ስለዚህ ጉዳዩን ወደ አለም ፍርድ ቤት ለመውሰድ አስበናል ያሉት አቶ ወንድማገኝ፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ያሉ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንዲቃወሙ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል። የቀረው ነገር ቢኖር እንደ ሂትለር በሞተር መፍጨት ብቻ ነው የሚሉት አቶ ወንድማገኝ ያ ከመሆኑ በፊት ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንዲቃወሙ ጥሪ አቅርበዋል። እነዚህ ከቦታቸው የተፈናቀሉ ዜጐች ህይወታቸው መቀጠል ስላለበት እና ህፃናት የምግብ፣ የጤና እና የመጠለያ አገልግሎት ማግኘት ስላለባቸው የመላው ኢትዮጵያዊያን ርብርብ እንደሚያስፈልግ ነው የተገለፀው። ተፈናቃዮቹ ያረፉባቸው አካባቢዎችም የምግብ አቅርቦቱ ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በዚሁ ጉዳይ በተመሳሳይ የተቃውሞ መግለጫ አውጥቷል። አንድነት በመግለጫው የከዚህ በፊቱን የማፈናቀል ግፍ ትተን በቅርቡ እንኳ በጉረፈርዳና በሌሎች አካባቢዎች በቀጥታ በክልሉ ባለስልጣናት በተፃፈ ደብዳቤ ይሄ ሀገራችሁ አይደለም ተብለው፣ ሀብትና ንብረታቸው ተዘርፎ፣ የወለዱ አራሶች እንኳን የማገገሚያ ጊዜ ሳይሰጣቸው ደማቸውን እያዘሩ ሲባረሩ ከመንግስት የተሰጠው ምላሽ ሞፈር ዘመቶች ናቸው ማረሻውን ብቻ ተሸክሞ ወደ ሌላ ሀገር የሚሰደድ ለማለት ይመስለናል የሚል ነበር። ይሄም ቢሆን የማንኛውም ዜጋ መብት ነው። መንግስት እነዚህ ዜጎች ሀገራችን የት ነው በማለት ለሚያነሱት ጥያቄ መልስ የለውም። ገዥው ፓርቲ ሀላፊነትን መዘንጋትንና ስህተትን በማረም ፈንታ አፋፍሞ በመቀጠል ዜጎች ሀብትና ንብረታቸው እየተዘረፈ መባረራቸውን ቀጥለዋል። ይህም በጋምቤላና ቤኒሻንጉል በከፋ መልኩ ቀጥሏል። በተለይ ከቤኒሻንጉል ክልል የአማራ ተወላጅ የሆኑትን ዜጐች የዘመናችን ሹመኞች ከኢ ሰብአዊነት ባፈነገጠ መልኩ ለእቃ ከሚሰጥ ክብር ባነሰ ሁኔታ ንብረታቸውን ሳይሰበስቡ በጅምላ እየተጫኑ መጣላቸውን ቀጥለዋል። በርካታ ህፃናትም የዚህ ግፍ ሰለባ ሆነዋል፤ እየታፈኑ የሚሞቱትም ቁጥራቸው በርካታ ነው፤ በጣም የሚያሳቅቀው ደግሞ የዚህ ግፍ ሰለባ የሆኑት ሀምሳ ዘጠኝ ሰዎች ሞት ጉዳይ ነው። ካላግባብ በጭካኔ ለብዙ አመታት ከኖሩበት፣ ከወለዱበትና ከከበዱበት ስፍራ ሀላፊነት በጎደለው ሁኔታ በአንድ መኪና እየታጨቁ እንዲወጡ በማድረግ ገደል ውስጥ ገብተው እንዲሞቱ የተፈረደባቸው ዜጎችን ህይወት እንዲቀጠፍ ያደረገውም በቸልታ እየገዛ ያለው የኢአዴግ መንግስት ነው። መንግስት በነዚህ ዜጎች ላይ ለደረሰው ኢ ሰብአዊ ድርጊትና ህይወት ማጣት ተጠያቂ ነው በማለት ፓርቲያችን ያምናል ሲል በመግለጫው ላይ አመልክቷል። ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ ኤፕሪል ሶስት እትም
መኢአድ ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ጉዳይ ለአለም ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ነው
ከመሀመድ ፖሊስ የኛ አይደለም ሊሆንም አይገባውም። ፖሊስ ለዚህ ፅሁፍ ሲባል ኢህአዴግ የተባለ የማፊያዎች ስብስብን ለመጠበቅ ህዝብን በአደባባይ ሊያሸብር ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው የደደቦች ስብስብ ነው። ፖሊስ ደደብ ነው። ማገናዘቢያውን በኢህአዴግ የሽብር ቡድን የተቀማ ህፃናት ፣ ሀረጋውያን ፣ ነብሰ ጡር ፣ ሴት ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ፣ መንገደኛ መለየት የተሳነው እንሰሳ ነው። ፖሊስ ክብሪት ነው። አምጣ የወለደችውን እናቱን ለመደብደብ የማያቅማማ ቅል ራስ። ጉዞ በጦር ቀጠና ከብሄራዊ በአዋሽ ወደ ኮሜርስ ቱርርር ድጋሚ ወደ አዋሽ ባንክ ፣ በአርቲስቲክ ወደ ብሄራዊ ባንክ ሆም መዘክር ፣ ታጥሯል መንገዱ ቱርርር ወደ ተገኘው ቅያስ ሰዎች ተደብድበዋል ፣ መስገጃ ፣ ጫማዎች ፣ አማይማ ፣ ኮፊያ ፣ የተፈነከቱ ሰዎች ፣ የተያዙ ወጣቶች ፣ ረጃጅም አጠና የያዙ የባንዳው ውሾች ፣ በፋራረሱት መንደሮች አቆራርጠን እዚያችው ትንሽ ፈቀቅ ብለን አትሩጡ አትሩጡ ጥግህን ያዝ ጥግጥጉን ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች የሙስሊሙ እስር ቤት ሆነዋል። ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በብዙ ውሾች መሀል የተያዙ ወንድሞቼን ተመለከትኩኝ አንዱ ውሻ ጋረደኝ ሁሉንም ለመቁጠር አልቻልኩም አንድ እእ ሁለት ተነጥለው ሌላ ሁለት ወዲ ያ ሌሎች የታሰሩ ግን በስንቱ መስሪያ ቤቶች ስንቱ ሙስሊም ታስሯል መስሪያ ቤቶች ባጠቃላይ ያሲን ኑሩ በሆነው ሲዲው ላይ አጀልህ ከደረሰ ሁሉም ነገር አንተን ለመግደል ሰበቢያ መሆን ይችላል ብሎን ነበር ሙስሊሙን ለማሰር አፋቸውን ከፍተው ሲጠብቁን አስተዋልኩ ናሽናል ጂዎግራፊ ቲቪ ላይ በብዙ ነብሮች የተከበበችውን ሚዳቋ ትዝ አለችኝ ከመንጋዋ የተነጠለችውን አንዷን ሚዳቋ ጥቂት የነብር መንጋ ከበው ሲበሏት ለመን መንጋው አይታደጋትም ስል ጠየኩ ዛሬም ከጀምአው እየነጠሉ የሚደበደቡትን ወንድሞቼን ለመርዳት ሳይሞክሩ ነብስን ለማዳን የሚራወጡት ወንድሞቻቸውን ለመርዳት ከሚናዝኑት ከብዙው የህዝን መንጋ ጥቂቱን ብቻ አስተዋልኩ ጥቂት ናቸውና የባንዳው ሰራዊት በቀላሉ አጠቃቸው አንድም ባስ አልተሰበረም ፣ አንድም ድንጋይ ሲወረውር የተመለከትኩት ሰው አልነበረም። በእርግጥ መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም ፣ እራሱ ገዳይ እራሱ ከሳሽ ፣ በሀገራችን ሰላም አጣን ፣ መንግስት የለም ወይ ፣ እንትን የህዝብ ነው ይሄን እኔ አላልኩም ፣ ኢቴቪ ፣ዛሚ ፣ ፋና ፣ መንግስት ፣ ወዘተረፈዎች ሌባ ናቸው ብለናል። የህዝብን አደራ የበሉ ፣ ከህዝብ አብራክ ወጥተው ህዝብ ላይ ቁልቁል የሚተፋ ወሽካታ አድርባይነታቸውን ነግረናቸዋል። ጥፋታችን በግፍ የታሰሩብንን መሪዎቻችንን እንዲፈቱልን መጠየቃችን ነበር። በሀይማኖት ጣልቃ አትግቡብን ፣ ህገ መንግስቱ ካልተተገበረ የወረቀት ነብር ነው ብለን ብሶታችንን ማሰማታችን በአጠና ተነረትን ፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፊት ለፊት ግንቡ ጥግ ስር እራሱን ስቶ የወደቀው በግምት እድሜው ወደ ስልሳዎቹ የሚጠጋው አዛውንት መሀል አናቱ ተበርቅሶ ደሙ እየፈሰሰ ማንም እንዳይረዳው የባንዳው ሰራዊት ከበው ሞቱን ይጠብቃሉ ፣ ጉዞ ወደ ጥቁር አንበሳ ብሄራዊ ሜትሪዮሎጂ ፊት ለፊት ያለው የባንዳው ሰራዊት ጣቢያ ፊት ለፊት ባለው ሚዲያን የአስባልት አካፋይ ተዘርግፈው የወደቁ ሰዎች ይታዩኛል ፣ አንድ አባት ከሁለት በግምት የአስራ አራት እና ከአስራ ስምንት የማይበልጡ ልጆቹ ጋር አፈር መስለው ሶስቱም በባዶ እግራቸው የሰውዬው ኮት በጭቃ ጨቅይቶ የሴቶቹ ልብሶች አፈር መስሎና ፀጉራቸው ተንጨባሮ በቢታንያ ክሊኒክ ቅያስ ብቅ አሉ። የሰራዊቱ ጣብያ በር ላይ ደም ረግጠን በቅያስ ወደ ሞሀ እድገት በስራ ት ት ቤት ደረስን። ከጦር አውድማው ወጥተን መስሎን ጫማችንን ሱሪያችንን ልናነፃ ቀልባችንን ልናረጋጋ ሊስትሮ ፍለጋ ስንኳትን ከእናቱ ጋር የተለያየ አንድ ከአስራሁለት አመት የማይበልጥ ልጅ አይኖቹ ወዲያ ወዲህ ሲሉ አይን ለአይን ተገጣጠምን። እየተቅለሰለሰና እየተርበተበተ ከእናቴን ጋር ተጠፋፋን ወደ መሳለሚያ አንድ መንገዱን አሳዩኝ ሲል ልመናውን አቀረበ። እናቱ ታየችኝ ልክ ብሄራዊ ባንክ ጋር ጥጉን ካሰለፏቸው ሰዎች መካከል አንዲት ነብሰ ጡር ሁለት ልጆቿን ይዛ ርህራሄ የማያውቁትን እነዚህን የባንዳውን ሰራዊት ያዝኑላት ዘንድ ስትለምናቸው ሚጣ በሚሯሯጡት ሰዎች ተረግጣ እሪሪሪ ስትል ከልጇ እኩል የምታነባዋ ብሄራዊ ቲያትር ጋር የየኋት እናት በአይኔ ይዞሩ ጀመር። እናትህ ስልክ ይኖራታል የኔ ጥያቄ ነበር ከልጁ ይልቅ የእናቱ ጭንቀት በአይኔ እየዞረ የላትም ና በል ጉዞ በሞሀ ወደ በርበሬ በረንዳ ከአብነት ፣ ከምራብ ፣ ከተክለሀይማኖትና ከሜክሲኮ ያሚመጡ መንገዶችን የሚያገናኘው መስቀለኛው መንገድ ላይ ሊስትሮ ስንፈልግ ከተክለሀይማኖት ቱርርር እያሉ አናታችን ላይ ሊወጡ ወደ ጭድ ተራ ቱርር ሀደሬ ሰፈር ውስጥ ውስጡን ሰዎች ይሯሯጣሉ ዞር ስል ልጁ ከአጠገቤ የለም የት ገባ በቃ አንድ ሰው ያሳየዋል ብዬ ጥሩውን ጠረጠርኩ ከጭድ ተራ ወደ ምናለሽ ተራ ምናለሽ ተራ ጋር የሰላም ቀጠና ነው ብለን እርግት ፣ ቅዝቅዝ ፣ ትክዝ ፣ ፍዝዝ እንዳልን ከወደ ሰላም ባልትና አካባቢ ቱርርር ወይ ዛሬ ምናለሽ ተራ ያላትን ቁሶች ሁላ ቆሽ ኮሽ ስብር ብረታብረቶችን ድስጣድስጦችን ፣ ማንኪያዎችን ምናምኖችን ሽክም ይዞ ቱርርር የጭንቅ ቀን አይመሽም በሀያሁለት ቀበሌ ወደ ድሬ ህንፃ ሰባተኛ። አሁን ሰላም ነው። ስለምን ይሄ ሁላ ውርጅብኝ አንድም ጠጠር እንኳ ባላነሳ ህዝብ ላይ ግን ለምን የመንግስትን መግለጫ ለማዳመጥ ሞባይሌን አውጥቼ ዛሚን ከፈትኩ ኤንሶ ኤንሶ ይላል ወደ መስተዳድሩ ኤፍ ኤም አይኬ ጫምባላላ ይላል ወደ ዘጠና ሰባት ነጥብ አንድ የእስፖርት ዝውውር ይዘግባል አንዱን ሀገር በቀል ተጫዋች ጋብዘው ዘጠና ስምንት ነጥብ አንድ የአምስት ሰአት ዜና ጀመረ ጆሮዬን ሰክቼ ቀልቤን ሰብስቤ በትካዜ ማድመጥ ጀመርኩ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ፅህፈት ቤትት አቶ እከሌ በአዲስ አበባ እስታዲየም በመገኘት መንግስት ድህነትን ለመቀነስ በሚያደርገው እርብርብ ህዝበ ሙስሊሙ እያደረገ ያለውን አስተዋፅዎ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገነዘቡ። የኢድ ሶላትም ህዝበ ሙስሊሙ በተገኘበት በአዲስ አበባ እስታዲየም በሰላም ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ ከኢዜአ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል ብሎ ኩም አደረገኝ። አሁን አመመኝ። አሁን ጆሮዬን ጠዘጠዘኝ።
ፌደራል ፖሊስ በረመዳን ፆም ፍቺ በሙስሊሞች ላይ ድብደባ ፈፀመ
መቀመጫውን ዋሽንግተን ያደረገው ኒስክ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለፀ።በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ አለም ከተቋሙ የምስራቅ አፍሪካ ቢሮ ሀላፊ ኢሬኔ ዱኩምዌናዮ ጋር ተወያይተዋል።በውይይታቸው ኒስክ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በሚሰራበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።በውይይቱ አምባሳደር መለስ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተወሰደ ካለው ፈጣን የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንፃር ኒስክ ካፒታል በኢንቨስትመንት ለመሰማራት እድሉ እንዳለው ገልፀዋል።ኢሬኔ ዱኩምዌናዮም የፋይናንስ ተቋሙ በኢትዮጵያ ለመስራት የሚያስችል ሰፊ የፋይናንስ አቅም እንዳለው መግለፃቸውን ከኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።ባንኩ ኬንያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የተለያዩ ሀገራት ፅህፈት ቤቱን ከፍቶ በመስራት ላይ ይገኛል።
ኒስክ ካፒታል የኢንቨስትመንት ባንክ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልግ ገለፀ
ኢትዮጵያ ከግሎባል ፈንድ ባለፉት አመታት ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ አግኝታለች በመላው አለም ከሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት እስከ ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ድረስ ኤችአይቪን፣ ቲቢንና ወባን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለሚካሄደው የአምስተኛው ዙር ግሎባል ፈንድ እንቅስቃሴ ተግባራዊነት ከ ቢሊዮን ዶላር ያላነሰ ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ተገለፀ። ይህም ገንዘብ የሚገኘው በተለይ በኢኮኖሚ የበለፀጉ አምስት አገሮች ለፈንዱ ከሚሰጡት መዋጮ ሲሆን፣ ከእነዚህም አገሮች መካከል ጀርመንና ቻይና መዋጮአቸውን ከፍ እንዲያደርጉና እንዲያሳውቁ አዲስ አበባ ለሚገኙት ኤምባሲዎቻቸው ጥሪ ቀርቧል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ጥሪውን ያቀረበው በኢትዮጵያ የሚገኙና በሶስቱ በሽታዎች ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ ስላሳ ሁለት ሲቪክ ማሀበራትንና አለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን ካቀፈው ፈንድ አድቮኬሲ ጥምረት አሊያንስ የተውጣጣው ጥምር ኮሚቴ ነው። በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የኤድስ ቢሮን ጨምሮ፣ ከጥምረቱ የተውጣጡ ስምንት ድርጅቶችን በአባልነት የያዘው ይኸው ጥምር ኮሚቴ፣ ለኤምባሲዎቹ ጥያቄውን ያቀረበው በደብዳቤና በቃል ሲሆን፣ በዚህም ስለኮሚቴው የስራ እንቅስቃሴ፤ ግሎባል ፈንድ ከተዋቀረበት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያበረከተውን ስኬትና ያጋጠመውንም ተግዳሮት በተመለከተ በማስረጃ የተደገፈ ገለፃና ማብራሪያ አድርጓል። በጀርመን ኤምባሲ ስም ጥያቄውን የተቀበሉት፣ ሚስተር ጂንስ ሸሚድ የኤምባሲው የኮሙዩኒኬሽን ምክትል ሀላፊ ሲሆኑ፣ የቻይና ኤምባሲን ወክለው የተቀበሉት ደግሞ፣ ሚስ ሊ ዩ የኤምባሲው የኢኮኖሚክና ኮሜርሻል ካውንስለር ናቸው። ተወካዮቹም ይህንኑ የህዝብ ጥያቄ ለአገራቸው መንግስት እንደሚያሳውቁ ገልፀዋል። ኮሚቴው በጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በፌዴራል የኤችአይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት ይደገፋል። በአገር ውስጥ የሚካሄደውን የጉትጐታ አድቮኬሲ ስራ የሚያስተባብረው ዋና መስሪያ ቤቱ ሎስ አንጀለስ የሚገኘውና ኤድስ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን ኤኤችኤፍ የኢትዮጵያ ቢሮ ሲሆን፣ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከናወን ተመሳሳይ ስራ የሚያቀናጀው ደግሞ የኮሚቴው የበላይ ሀላፊ የሆነው የተባበሩት መንግስታት የኤድስ ቢሮ ኢትዮጵያ ነው። ዶክተር መንግስቱ ገብረሚካኤል የኤኤችኤፍ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅና የኮሚቴው ሰብሳቢ እንደገለፁት፣ ጀርመንና ቻይና የሚያዋጡትን የገንዘብ መጠን አምስቱ ሀያላንና ሌሎቹም የቡድን ሀያ አባል አገሮች በግሎባል ፈንድ ዙሪያ ካናዳ ውስጥ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ከሚያካሂዱት ስብሰባ በፊት ወይም አስቀድሞ በኤምባሲዎቻቸው በኩል መልሱን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኤኤችኤፍ በሚንቀሳቀስባቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ በስላሳ ስድስት አገሮች፤ እንዲሁም ሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች ጫና የማሳደር ስራ የሚካሄድ ይሆናል። ከዋና ስራ አስኪያጁ ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው ከሁለት ሺህ ሁለት አመተ ምህረት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ባለው ጊዜ የግሎባል ፈንድ እንቅስቃሴ አሜሪካ ስድስት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር፣ ዩናይትድ ኪንግደም ሁለት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ዶላር፣ ጀርመን አንድ ነጥብ አምስትስድስት ቢሊዮን ዶላር፣ ጃፓን አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ዶላር፣ ቻይና ሀያ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ሲያዋጡ፣ በኢኮኖሚ እድገቷ በአለም ውስጥ ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ የሆነችው ቻይና ያበረከተችው አስተዋፅኦ በኢኮኖሚ እድገቷ ሶስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ጃፓን ከለገሰችው ሀምሳ ጊዜ ያነሰ ነው። ዩናይትድ ኪንግደም ያበረከተችው መዋጮ ደግሞ ከጀርመን አንድ ነጥብ አምስት ጊዜና ከቻይና አንድ ነጥብ ስምንት ጊዜ የላቀ ነው። በኢኮኖሚ ከአምስተኛ ደረጃ በታች የሚገኙ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ዴንማርክና ስዊድን የመሳሰሉ አገሮች ከቻይና የበለጠ ነው የሰጡት። የግሎባል ፈንድ ቋት ውስጥ በየሶስት አመቱ የሚገባው ገንዘብ እየቀነሰ መጥቷል። በዚህም መሰረት ከሁለት ሺህ ሶስት አመተ ምህረት እስከ ሁለት ሺህ አምስት አመተ ምህረት ድረስ በተካሄደው የመጀመሪያው ዙር እንቅስቃሴ ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ታቅዶ የተገኘው ግን ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ከሁለት ሺህ ስድስት አመተ ምህረት እስከ ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት በተከናወነው የአራተኛው ዙር እንቅስቃሴ ቢሊዮን ዶላር ታቅዶ የተገኘው ግን፣ ቢሊዮን ዶላር ነው። ከሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት እስከ ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ድረስ የተያዘው ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህም የታቀደው በአራተኛው ዙር የተገኘውን የገንዘብ ወጪ ታሳቢ በማድረግ ነው። እንደ ተባበሩት መንግስታት የኤድስ ቢሮ ጥናት፣ ለአራተኛው ዙር የስራ እንቅስቃሴ የታቀደው የገንዘብ መጠን የአለም አቀፍ ፈንድ ቋት ውስጥ ካልገባ፣ መዋጮው በየሶስት አመቱ ከፍ እያለ ወይም ካልጨመረና ሁኔታው በዚህ መልኩ ከቀጠለ ኤችአይቪ ኤድስ፣ ወባና ቲቢ በሁለት ሺህ ሀያ ሁለት አመተ ምህረት በሀብረተሰቡ ላይ በከፍተኛ ደረጃ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራሉ ተብሎ ተገምቷል። በዚህም ግምት መሰረት ሀያ አንድ ሚሊዮን ያህል ሰዎች ለህልፈተ ህይወት እንደሚዳረጉ፣ ተጨማሪ ሀያ ስምንት ሚሊዮን አዳዲስ ሰዎች በኤድስ ሊያዙ እንደሚችሉ፣ ፀረ ኤችአይቪ መግዣ በየአመቱ ተጨማሪ ሀያ አራት ሚሊዮን ዶላር ሊያስወጣ እንደሚችል ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል። ግሎባል ፈንድ ከተዋቀረበት ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት አመተ ምህረት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ከአራት መቶ ሰባ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የኤችአይቪ ምርመራ ተደርጓል። ከዚህም ሌላ የኤችአይቪና የቲቢ በሽታዎች ላደረባቸው ሚሊዮን ሰዎችና ሶስት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ለሚጠጉ እናቶች ኤችአይቪ ከእናት ወደ ህፃን እንዳይተላለፍ ለመከላከል የሚያስችል፣ ህክምና ተሰጥቷቸዋል። አምስት መቶ ስልሳ ሚሊዮን የሚጠጉ የወባ ህሙማንም ተገቢውን ህክምና አግኝተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ስምንት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ፀረ ኤችአይቪ መድሀኒት እንዲያገኙ ተደርጓል። ኢትዮጵያም በእነዚሁ አመታት ኤችአይቪ፣ ወባና ቲቢን ለመከላከልና ለጤና ስርአቱ ማጠናሪያ ከዚሁ አለም አቀፍ ፈንድ አምስት መቶ ዘጠና አንድ ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች። ከዚህም ገንዘብ ውስጥ ለኤችአይቪ ኤድስ ሶስት መቶ ሰባ ሰባት ሚሊዮን ዶላር፣ ለወባ አንድ መቶ ሀምሳ ሚሊዮን ዶላር፣ ለቲቢ ሀምሳ ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር፣ ለስርአቱ ማጠናከሪያ አራት ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሆነ ታውቋል። ከግሎባል ፈንድ በተገኘው በዚሁ ገንዘብ ሶስት መቶ አስር ሺህ ሰዎች የፀረ ኤችአይቪ ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል። አርባ ሁለት ሚሊዮን የወባ መከላከያ አጎበር ለሀብረተሰቡ ተሰራጭቷል። ስላሳ ስምንት ሺህ ሰዎች የቲቢ ምርመራና ህክምና አግኝተዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ በኤችአይቪ የመጠቃቱ ወይም ከኤችአይቪ ጋር አብረው የሚኖሩ ሰዎች ቀደም ሲል የያዛቸውን አዲስ የተያዙትንም ጭምር ያካትታል መጠን አንድ ነጥብ አንድ በመቶ ሲሆን፣ በደቡብ አፍሪካ አገሮች ደግሞ ከሀያ እስከ ሀያ አምስት በመቶ ነው። ዶክተር ሜሪያም ማሏ በተባበሩት መንግስታት የኤድስ ቢሮ በኢትዮጵያ ተወካይ ይህንኑ አስመልክተው እንዳብራሩት፣ የሁለቱም አገሮች ማለትም የጀርመንና የቻይና ኤምባሲዎች ተወካዮች አገሮቻቸው ለግሎባል ፈንድ የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለፃቸውን ተናግረዋል። በተለይ ቻይናና ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ አብረው ለመስራት የሚያስችላቸው ጥሩ የሆነ የሁለትዮሽ ግንኙነት መስርተዋል። ከዚህ ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ቻይና ለግሎባል ፈንድ የምታደርገውን አስተዋፅኦ አጠናክራ እንደምትቀጥል ይታመናል።
በመላው አለም ወባ ቲቢና ኤችአይቪን ለሶስት አመት ለመከላከል ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል
የዚምባብዌ ጦር ሀገሪቱን የተቆጣጠርኩት በሙጋቤ ዙሪያ ያሉትን የጦር ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው ማለቱ ይታወሳል። በዚምባብዌ ፖለቲካዊ ቀውስ መስተዋል የጀመረው ሮበርት ሙጋቤ ምክትላቸው የነበሩትን ኤመርሰን ምናንጋግዋ ከስልጣን በማንሳት በምትካቸው ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤን ሊተኩ ካቀዱ በኋላ ነው። የሀገሪቱ የጦር አዛዥ ጀነራል ኮስታንቲኖ ቺዌንጋ ባሳለፍነው ሰኞ በዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ውስጥ መከፋፈል ካልቆመ ጦሩ ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል አስጠንቅቀውም ነበር። የዚምባብዌ ጦር ጣልቃ እንደሚገባ አስጠነቀቀ የፖለቲካ ተንታኞች አሁን ላይ የአለም ህዝብ ቀልብን መሳብ በቻለው የዚምባብዌ ፖለቲካ ኡደት ውስጥ አራት ቁልፍ ሰዎች አሉ ይላሉ። አንድ ሮበርት ሙጋቤ ዚምባብዌ በአውሮፓውያኑ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ነፃነቷን ከቅኝ ገዢዋ እንግሊዝ ከተቀዳጀች በኋላ በተደረገ ምርጫ ነበር አሸንፈው ወደ ስልጣን የመጡት። ሙጋቤ በስልጣን ዘመናቸው ከከወኗቸው ተግባራት በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠናዎቹ መባቻ ላይ ያከናወኑት ሁሌም ይወሳል። በወቅቱ ሙጋቤ በጥቂት ነጮች ተይዞ የነበረውን ሰፊ መሬት በመንጠቅ ለጥቁር ዚምባብዌውያን አከፋፈሉ። ከሶስት አስርት አመታት በላይ በስልጣን የቆዩት የዘጠና ሶስት አመቱ የእድሜ ባለፀጋ ሙጋቤ ስልጣን ለመልቀቅ ምንም አይነት ፍላጎት ባያሳዩም ጤናቸው ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ መምጣቱን ተከትሎ የሚተካቸው ማነው የሚለው ጥያቄ በበርካቶች ዘንድ ነበር። በተለይም ደግሞ በቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤና በቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት በኤመርሰን ምናንጋግዋ መካከል ውጠረት ተፈጥሮ ቆይቷል። ሁለት ግሬስ ሙጋቤ የሮበርት ሙጋቤ ሁለተኛ ሚስት የሆኑትና ከሙጋቤ በአርባ አመት የሚያንሱት ግሬስ ሙጋቤ ከፕሬዝዳንቱ የቢሮ ፀሀፊነት በመነሳት በሀገራቸው ተፅእኖ ፈጣሪ ሴት ለመሆን በቅተዋል። ወዳጅና ደጋፊዎቻቸው የድሆች እናት እያሉ የሚጠሯቸው ግሬስ በነቃፊዎቻቸው ዘንድ ደግሞ ለስልጣንና ሀብት እንደሚስገበገቡ ተደርገው ሲሳሉ ይስተዋላል። የሀገሪቱ ቀዳማዊ እምቤት መሆናቸውን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ ሙጋቤ ላይ የጣሉት የጉዞና ሀብት ማንቀሳቀስ እገዳ ለእርሳቸውም አልቀረላቸውም። ግሬስ ሀይለኛ ተናጋሪ እንደሆኑም ይነገራል፤ ሙጋቤ ምክትላቸውን ባባረሩበት ወቅት ምናንናግዋ እባብ ስለሆነ ጭንቅላቱ መመታት አለበት ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም። ሶስት ኤመርሰን ምናንናግዋ ግሬስ ሙጋቤ ብቅ ብቅ ከማለታቸው በፊት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የሙጋቤ ትክክለኛ ምትክ ተደርገው ነበር የሚቆጠሩት። ከምክትል ፕሬዝደንትነታቸው ከተባረሩ በኋላ ለህይወቴ ያሰጋኛል በማለት ሀገር ጥለው ሸሽተው ነበር። የልተረጋገጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ግን ጦሩ ሀገሪቱ ከተቆጣጠረ በኋላ ኤመርሰን ምናንጋግዋ ወደ ዚምባብዌ ተመልሰዋል። በግብፅና በቻይና ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱት ኤመርሰን ላይቤሪያን ከቅኝ ግዛት ለማስወጣት በነበረው ትግል የራሳቸውን ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳደረጉ ይነገራል። ከነፃነት በኋላ በነበሩት አመታት በተከሰተ ግጭት በርካቶች እንደሞቱ ሲነገር በዚያን ጊዜ የደህንነት ሚኒስቴር የነበሩት ኤመርሰን በደረሰው ጥፋት ውስጥ ምንም አይነት ድርሻ የለኝም ብለውም ነበር። በዚምባቡዌያን ዘንድ አዞ እየተባሉ የሚጠሩት ኤመርሰን የደህንነት ሚኒስቴር ሆነው ከመስራታቸው አንፃር የሀገሪቱን ጦር ሀይልና የደህንነት ኤጀንሲውን በደንብ እንደሚያውቁት ይነገራል። አራት ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ የምናንጋግዋ ቅርብ ወዳጅ ናቸው የሚባሉት የስልሳ አንድ አመቱ ጄኔራል ኮንስታንቲኖ የዚምባብዌን ጦር ሀይል ከአውሮፓውያኑ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት ጀምሮ መርተዋል። በሁለት ሺህ ሁለት የአውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካና ኒውዚላንድ የጉዞና የንብረት ማንቀሳቃስ እገዳ ከጣሉባቸው የዚምባብዌ ባለስልጣናት አንዱ ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ነበሩ። እለተ ሰኞ የዚምባብዌ ጦር ሀይል በፖለቲካ ኡደቱ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ግልፅ የሆነ መልእክት ሲያስተላልፉ ብዙዎች እጅግ ተገርመው ነበር። እርሳቸው ይህን ባሉ በሁለተኛው ቀን የዚምባብዌ ጦር ሀገሪቱን የተቆጣጠሩ ሲሆን መፈንቅለ መንግስት አለመሆኑን በቴሌቪዠን ቀርበው ተናግረዋል። አሁን ላይ ሙጋቤ በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ምን ሊሆን እንደሚችል በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።
በዚምባብዌ የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ አራቱ ቁልፍ ግለሰቦች
ከዳዊት ሰለሞን ባሳለፍነው እሁድ ለንባብ የበቃው የአማርኛው ሪፖርተር ጋዜጣ በደብዳቤዎች አምዱ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተላከ ያለውን ደብዳቤ አስነብቧል።ከተቋሙ ተላከ የተባለው ደብዳቤ ማህተምየአስተዳደሩን ፊርማና ወጪ የተደረገበትን ቀን ያላካተተ ቢሆንም ጋዜጣው ሪፖርተር ታማኝ በመሆኑ ከማረሚያ ቤቱ የተላከ ነው ለማለት በግሌ ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ።በሪፖርተር ታማኝ ምንጭነት ዙሪያ ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች ደብዳቤውን ሰንደቅና አዲስ ዘመን ገፅ ላይ የሚፅፉ ያዘጋጁት ይሆናል በማለት መጠርጠር መብታችሁ ይመስለኛል።ወደ ደብዳቤው ዝርዝር ስንገባ ያልታረሙ ሰዎች እነርእዮትን እናርማለን ብለው በአስተዳደርነት መቀመጣቸውን ወለል ብለውላችሁ ትመለከታላችሁ ።ታገሱኝማ አስተዳደሩ ደብዳቤውን የላከው አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅትሲፒጄበማረሚያ ቤቱ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙን በማስመልከት መግለጫ ማውጣቱን ተከትሎ የድርጅቱን ክስ ለማስተባበል ነው።ሲፒጄ በመግለጫው ርእዮት በርቀት ሁለተኛ ድግሪዋን ለማግኘት ከተመዘገበች በኋላ በማረሚያ ቤቱ እንዳትማር መከልከሏንና ደረጃውን የጠበቀ የህክምና ክትትል እንደማይደረግላት ማተቱ አይዘነጋም።ለወቀሳው ምላሹን በሪፖርተር የሰጠው ማረሚያ ቤቱ ርእዮት ለብቻዋ በዝግ ቤት ታስራለች የተባለው ውሸት ነው።እንዲህ በማለት መናገርም አብረዋት የታሰሩና በአንድ ክፍል ውስጥ የሚገኙ እስረኞችን ሰው አይደሉም በማለት እንደመናገር ይቆጠራል።ብሏል።አስቂኙ ነገር ሲፒጄ በመግለጫው ርእዮት ለብቻዋ በዝግ ቤት ታስራለች አለማለቱ ነውከዚህ ይልቅ ሲፒጄ ያለው ርእዮት በቀጣይ ለብቻዋ ልትታሰር ትችላለች ነው።ያልተፃፈ መግለጫ በማንበብ መልስ መስጠት ምን ሊሰኝ እንደሚችል ለማንም ግልፅ አይመስለኝም። ርእዮት የርቀት ትምህርቱን በመከታተል ላይ ትገኛለች።ይህንንም ከቅድስት ማርያም ዮኒቨርስቲ ኮሌጅ በመጠየቅ ማረጋገጥ ይቻላልተብሏል።ወዳጆቼ ተቋም ሲዋሽ ምን ይባላል ጋዜጠኛዋ ቤተሰብወዳጅአድናቂና በየሳምንቱ እየሄደ የሚጎበኛት ቁጥሩ ቀላል የማይሰኝ አጋር አላት።ማረሚያ ቤቱ ቢያንስ እነዚህ ምን ይሉኛል አይልም እንዴት ነው እነዚህ ሰዎች የታረሙ ሰዎችን ሊያፈሩ የሚችሉትእውነቱ ግን እነርሱ እንደሚሉት አይደለም።ለርእዮት ከህንዱ ዮኒቨርስቲ የመጡ የመማሪያ መፃህፍት ወደ ማረሚያ ቤቱ እንዲገቡ ያልተፈቀደላቸው በመሆኑ የሚገኙት የጋዜጠኛዋ ወኪል ጋር ነው።እናንተም ተመልክታችሁ ትፈርዱ ዘንድ መፃህፍቱን ፎቶግራፍ አንስቻለሁ ርእዮት የዲሲፕሊን ችግር አለባት ያለው የማረሚያ ቤቱ ደብዳቤ በስነ ምግባር ጉድለት መከሰሷን በመጥቀስ እንደ አስፈላጊነቱ በቀጣይ በቀረበባት ክስ ቅጣት ሊጣልባት እንደሚችል አስፈራርቷል። ርእዮትን የከሰሳትና የሚመሰክርባት ማን ነውዳኞቹስ እነማን ናቸው መቼስ በሪፖርተር ላይ የወጣውን ደብዳቤ የፃፉ ከሆኑ መጨረሻው ምን እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት አያስቸግርምጋዜጠኛዋ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ለቀረበባት ክስ ጠበቆቿን በማማከር ምላሽ መስጠት ትችላለችምስክሮችን የማቅረብ መብትስ አላትደብዳቤው ስለ እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች የሚለው አንዳች ነገር የለውም። ባሳለፍነው እሁድ ለንባብ የበቃው የአማርኛው ሪፖርተር ጋዜጣ በደብዳቤዎች አምዱ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተላከ ያለውን ደብዳቤ አስነብቧል።ከተቋሙ ተላከ የተባለው ደብዳቤ ማህተምየአስተዳደሩን ፊርማና ወጪ የተደረገበትን ቀን ያላካተተ ቢሆንም ጋዜጣው ሪፖርተር ታማኝ በመሆኑ ከማረሚያ ቤቱ የተላከ ነው ለማለት በግሌ ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ።በሪፖርተር ታማኝ ምንጭነት ዙሪያ ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች ደብዳቤውን ሰንደቅና አዲስ ዘመን ገፅ ላይ የሚፅፉ ያዘጋጁት ይሆናል በማለት መጠርጠር መብታችሁ ይመስለኛል።ወደ ደብዳቤው ዝርዝር ስንገባ ያልታረሙ ሰዎች እነርእዮትን እናርማለን ብለው በአስተዳደርነት መቀመጣቸውን ወለል ብለውላችሁ ትመለከታላችሁ ።ታገሱኝማ አስተዳደሩ ደብዳቤውን የላከው አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅትሲፒጄበማረሚያ ቤቱ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙን በማስመልከት መግለጫ ማውጣቱን ተከትሎ የድርጅቱን ክስ ለማስተባበል ነው።ሲፒጄ በመግለጫው ርእዮት በርቀት ሁለተኛ ድግሪዋን ለማግኘት ከተመዘገበች በኋላ በማረሚያ ቤቱ እንዳትማር መከልከሏንና ደረጃውን የጠበቀ የህክምና ክትትል እንደማይደረግላት ማተቱ አይዘነጋም።ለወቀሳው ምላሹን በሪፖርተር የሰጠው ማረሚያ ቤቱ ርእዮት ለብቻዋ በዝግ ቤት ታስራለች የተባለው ውሸት ነው።እንዲህ በማለት መናገርም አብረዋት የታሰሩና በአንድ ክፍል ውስጥ የሚገኙ እስረኞችን ሰው አይደሉም በማለት እንደመናገር ይቆጠራል።ብሏል።አስቂኙ ነገር ሲፒጄ በመግለጫው ርእዮት ለብቻዋ በዝግ ቤት ታስራለች አለማለቱ ነውከዚህ ይልቅ ሲፒጄ ያለው ርእዮት በቀጣይ ለብቻዋ ልትታሰር ትችላለች ነው።ያልተፃፈ መግለጫ በማንበብ መልስ መስጠት ምን ሊሰኝ እንደሚችል ለማንም ግልፅ አይመስለኝም። ርእዮት የርቀት ትምህርቱን በመከታተል ላይ ትገኛለች።ይህንንም ከቅድስት ማርያም ዮኒቨርስቲ ኮሌጅ በመጠየቅ ማረጋገጥ ይቻላልተብሏል።ወዳጆቼ ተቋም ሲዋሽ ምን ይባላል ጋዜጠኛዋ ቤተሰብወዳጅአድናቂና በየሳምንቱ እየሄደ የሚጎበኛት ቁጥሩ ቀላል የማይሰኝ አጋር አላት።ማረሚያ ቤቱ ቢያንስ እነዚህ ምን ይሉኛል አይልም እንዴት ነው እነዚህ ሰዎች የታረሙ ሰዎችን ሊያፈሩ የሚችሉትእውነቱ ግን እነርሱ እንደሚሉት አይደለም።ለርእዮት ከህንዱ ዮኒቨርስቲ የመጡ የመማሪያ መፃህፍት ወደ ማረሚያ ቤቱ እንዲገቡ ያልተፈቀደላቸው በመሆኑ የሚገኙት የጋዜጠኛዋ ወኪል ጋር ነው።እናንተም ተመልክታችሁ ትፈርዱ ዘንድ መፃህፍቱን ፎቶግራፍ አንስቻለሁ ርእዮት የዲሲፕሊን ችግር አለባት ያለው የማረሚያ ቤቱ ደብዳቤ በስነ ምግባር ጉድለት መከሰሷን በመጥቀስ እንደ አስፈላጊነቱ በቀጣይ በቀረበባት ክስ ቅጣት ሊጣልባት እንደሚችል አስፈራርቷል። ርእዮትን የከሰሳትና የሚመሰክርባት ማን ነውዳኞቹስ እነማን ናቸው መቼስ በሪፖርተር ላይ የወጣውን ደብዳቤ የፃፉ ከሆኑ መጨረሻው ምን እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት አያስቸግርምጋዜጠኛዋ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ለቀረበባት ክስ ጠበቆቿን በማማከር ምላሽ መስጠት ትችላለችምስክሮችን የማቅረብ መብትስ አላትደብዳቤው ስለ እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች የሚለው አንዳች ነገር የለውም።
ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በርእዮት ጉዳይ ያልተጠየቀውን መለሰ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ውስጥ በስፖርት አመራርነት እጅግ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው አቶ ያሚ ከበደ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አቶ ያሚ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በስልሳ ስድስት አመታቸው በትናንትናው እለት ነው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት። አቶ ያሚ ስራ ከጀመሩበት ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አምስት አመተ ምህረት ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር በሰውነት ማጎልመሻ በመምህርነት፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝነት እና የቴክኒክ ዳይሬክተርነት የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር እና በተለያዩ ሀላፊነቶች ላይ አገልግለዋል። እንዲሁም የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ እንዲሁም በተቋሙ እስከ ሁለት ሺህ አምስት አመተ ምህረት ድረስ በአማካሪነት መስራታቸው ተነግሯል። የአቶ ያሚ ከበደ የቀብር ስነስርአት በዛሬው እለት ጉለሌ አዲሱ ገበያ በቅዱስ እግዚአብሄር አብ ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በስፖርት አመራርነት የሚታወቁት አቶ ያሚ ከበደ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ሳላይሽ የተሰኘ ተወዳጅ አልበሙን ለህዝብ ካቀረበ በኋላ ከፍተኛ ተቀባይነትን በማግኘቱ በየሀገራቱ እየተዘዋወረ የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን በማቅረብ ላይ ያለው ድምፃዊ ብዟየሁ ደምሴ በካናዳ ዊኒፔግ ግዛት ትናንት ሴፕቴበር አምርቶ ነበር። ኮንሰርቱን ለመስራት ወደዚያው ያመራው ይሀው ተወዳጅ ድምፃዊ በአንድ ወጣት በተወረወረ ጠርሙስ ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር ከስፍራው ማለዳ ታይምስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በጠርሙስ ፍንከታ የደረሰበት አካሉ መሰፋቱን የገለፁልን ምንጮቻችንን ጠርሙሱን የወረወረበትን ሰው ለመያዝ ፖሊስ እየጣረ መሆኑም ተሰምቷል። ብዟየሁ በዌኒፒግ ኮንሰርት ሊያቀርብ ሲሄድ የም እራብ ካናዳ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ውድድር ይካሄድ እንደነበር ታውቋል። ዘሀበሻ ወደ ብዟየሁ ደምሴ ደውላ ጉዳዩን ከ እርሱ አፍ ለመስማት ያደረገችው ሙከራ ባይሳካም ከርሱ እንደሰማን የምናቀርብ መሆናችንን እንገልፃለን። ኢትዮጵያውያን በውጭ ሀገር ኮንሰርት ለማየት ሄደው በኮንሰርት ላይ መደባደብን እንደ ትልቅ ጀብዱ ማየታቸው የሚያሳዝን ጉዳይ ሲሆን ይህን አይነቱን ድብድብ የሚፈጥሩት ደግሞ የራሳቸው ወገን ባዘጋጀው ኮንሰርት ላይ እንጂ በውጭ ሀገር ኮንሰርቶች ላይ አለመሆኑ ብዙዎችን ያሳዘነ ጉዳይ ነው።
ድምፃዊ ብዟየሁ ደምሴ በካናዳ ከአንድ ወጣት በተወረወረ ጠርሙስ ጉዳት እንደደረሰበት ተሰማ
ሞሀመድ ሳላህ ለሊቨርፑል መፈረሙን ተከትሎ በከተማዋ ሙስሊም ጠልነት መቀነሱን አንድ ጥናት ጠቆመ። ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ጥናት ሞሀመድ ሳላህ ለሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ መፈረሙ በሊቨርፑል ከተማ ሙስሊም ጠልነት በቀጥታ እንዲቀንስ ማድረጉን አረጋግጧል። ሳላህ ከሁለት አመት በፊት ለሊቨርፑል ከፈረመ በኋላ በሊቨርፑል ከተማ የሙስሊም ጠል የሆኑ የወንጀሎች ቁጥር በ ነጥብ ዘጠኝ በመቶ ቀንሰዋል። በሞ ሳላህ ቅርፅ የተሰራው ሀውልት መሳቂያ ሆኗል ሊቨርፑል ሞ ሳላህን ለፖሊስ አሳልፎ ሰጠ ሞ ሳላህ የአመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ ታዋቂ ግለሰቦችን ማወቅ እና ማድነቅ ጭንፍን ጥላቻን ይቀንሳል ወይ ሞሀመድ ሳላህ በሙስሊም ጠልነት በባህርይ እና አመለካከት በመቀየር ረገድ የለው ተፅእኖ ምን ይመስላል በሚል እርእስ ነው ጥናቱ በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሰራው። በእንግሊዝ ጥላቻን መሰረት ያደረጉ ወንጀሎች እና ሚሊዮን የትዊተር መልእክቶችን በጥናቱ ተንትነዋል። ጥናቱ ሊቨርፑል እግር ኳስ ቡድን በሚገኝበት ግዛት ውስጥ ሙስሊም ጠል የሆኑት ወንጀሎች ከመቀነሳቸው በተጨማሪ የሊቨርቱል ክለብ ደጋፊዎች ፀረ እስልማና ይዘት ያላቸውን የትዊተር መልእክት በግማሽ ቀንሷል። ጥናቱ ይህ አዎንታዊ ለውጥ የመጣው ሰዎች ስለ እስልምና ያላቸው እውቀት በመጨመሩ ነው ይላል።
ሞ ሳላህ ለሊቨርፑል መፈረሙ በከተማዋ ሙስሊም ጠልነት ቀነሰ
እጣ የደረሳቸው ግንባታው ለዘገየበት ወለድ እንዲከፍሉ ተደርጓል በሀምሌ ወር ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት መጀመርያ ሳምንት በእጣ ከተላለፉ የአርባ ስልሳ የጋራ መኖርያ ቤቶች፣ በእጣ ከደረሳቸው የተወሰኑት የህንፃው ግንባታ ሙሉ በሙሉ እንደተጠናቀቀ ተደርጎ ሙሉ ክፍያ እንዲፈፅሙ የተደረጉት ትክክል አለመሆኑን፣ ህንፃው ብዙ መጠናቀቅ የሚገባቸው ነገሮች እንደቀሩት ተናገሩ። ንግድ ባንክ እንዲያስረክቡት ሲጠይቁት አልተጠናቀቀም መባላቸውንም ገልፀዋል። የእጣው እድለኞች ለሪፖርተር እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እጣውን ካወጣ ከአንድ ወር በኋላ እጣ ለደረሳቸው ተመዝጋቢዎች ስልክ በመደወል ክፍያ እንዲያጠናቅቁና ቤታቸውን እንዲረከቡ ነግሯቸዋል። ምንም እንኳን የግንባታ ግብአቶች ዋጋ መጨመርን ምክንያት በማድረግ፣ ሲመዘገቡ ትከፍላላችሁ ከተባሉትና ውል ከፈፀሙበት ዋጋ ከእጥፍ በላይ ዋጋ እንደተጨመረባቸው ቢያውቁም፣ ለመክፈል አለማንገራገራቸውን እድለኞቹ ተናግረዋል። በተሰጣቸው የመክፈያ አጭር ቀናት ውስጥ ለባለሶስት መኝታ ቤት ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሶስት ብር ሙሉ ክፍያ ከፈፀሙ በኋላ ለማስረከብ እንደሚጠሩ የተነገራቸው ቢሆንም፣ ዝም እንደተባሉ አክለዋል። ጊዜው ሲረዝምባቸው ራሳቸው ተመልሰው በመሄድ እንዲያስረክቧቸው ሲጠይቋቸው፣ እጣ የወጣላቸው የተወሰኑ እድለኞች የደረሳቸው የህንፃ ብሎክ አሳንሰር ያልገባለት መሆኑንና እንዲጠብቁ እንደተነገራቸው ገልፀዋል። ወይዘሮ ቤተልሄም በቀለ ባለሶስት መኝታ ቤት እጣ ከደረሳቸው መካከል አንዷ ናቸው። ሌሎቹ ባለእጣዎች እንደሚናገሩት እሳቸውም የደረሳቸው ብሎክ ብዙ ግንባታ ይቀረዋል። የንፅህና እቃዎቹ ያልተሟሉና የተሰባበሩ፣ የውስጥ በሮች ያልተገጠሙለት፣ ግድግዳዎቹ የተሰነጣጠቁ፣ የውሀ ማስተላለፊያ መስመሮች ያልተገናኙ፣ ለምን እንደ ተተው ያልተገለፁ ቀዳዳዎችና ሌሎችም ጉድለቶች እንዳሉበት አስረድተዋል።ዋጋው ከመናሩ በተጨማሪ ግንባታው በሁለት አመት ውስጥ ተጠናቆ ለተመዝጋቢዎች እንደሚተላለፍ የተገለፀ ቢሆንም፣ በተባለው ቀን ባለመድረሱ አንድ መቶ ሀያ ሶስት ብር ወለድ እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ወይዘሮ ቤተልሄም ይናገራሉ። ወለድ መክፈል ያለበት መቶ በመቶ ቅድሚያ የፈፀመውና በተባለበት ጊዜ ያልተረከበው ነው ወይስ ግንባታውን ያዘገየው በማለት የሚጠይቁት ደግሞ አቶ ሳሙኤል ፍሰሀና ወይዘሪት ፀሀይ ሀድጉ ሲሆኑ፣ ይህንን ለመንግስትና ለህዝብ እንደሚተውት ጠቁመው፣ ባልተጠናቀቀ ግንባታ ተጨማሪ ሙሉ ክፍያና ወለድ እንዲከፍሉ መደረጋቸው አሳዛኝ እንደሆነ ይናገራሉ። ከቤት ኪራይ ስቃይ ለመላቀቅ ያላቸውን ገንዘብ አሟጠው የከፈሉ በመሆናቸው፣ የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ የሚጠናቀቅበትን መንገድ ፈጥሮ እንዲያስረክባቸው ጠይቀዋል። ገንዘቡን ለመቀበል በሙሉ ፈገግታ የተቀበላቸው ንግድ ባንክ፣ በከፈሉት ልክ የፀዳ ቤት ማስረከብ ሲገባው ባለማድረጉ ቅሬታቸውን ሊያቀርቡ ሲሄዱ የሚያናግራቸው መጥፋቱን ተናግረዋል። ግንባታውን ያካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤቶቹን ሲያስተላልፍ፣ አንዳንድ ጉድለቶች ቢገኙ ለማስተካከል መፈራረሙንና ነዋሪዎች በሚያቀርቡት ማንኛውም ቅሬታ ላይ አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥ የገለፀ ቢሆንም፣ ወደ ተግባር ሲገባ ግን ምንም አይነት ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀላፊ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ በልሁ ታከለ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ባንኩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ሲረከብ የተጓደሉ ስራዎችን እንደሚያስተካክል ቃል ገብቷል። የሚጠበቀውም እንዲያስተካክል ነበር። ነገር ግን በተደጋጋሚ ደብዳቤ የተፃፈለት ቢሆንም ምላሽ አለመስጠቱን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል። በእርግጥ የተጓደሉ ነገሮች መኖራቸው እርግጥ ቢሆንም፣ ቀለም መቀባትና የውስጥ በሮችን መግጠም ኢንተርፕራይዙን አይመለከተውም፤ ብለዋል። ምክንያቱም እድለኛው በምርጫው የሚያደርጋቸው በመሆኑ እንደሆነና በውሉም ውስጥ አለመካተታቸውን አስረድተዋል። ኢንተርፕራይዙ በገባው ቃል መሰረት የማይፈፅም ከሆነ በቀጣይ የሚታይ መሆኑን አክለዋል። ግንባታውን ለማጠናቀቅ ቃል መግባቱንና መፈራረሙ የተገለፀው የአዲስ አበባ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን የስራ ሂደት መሪ አቶ ዮሀንስ አባይነህ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ባንኩ ከተረከባቸው ህንፃዎች መካከል ጥቃቅን ስራዎች የቀራቸውና ኢንተርፕራይዙ እንደሚያስተካክል ቃል የገባው ለሁለት ህንፃዎች ብቻ ነው። እነሱንም እየሰራና እያስተካከለ ነው። ሊፍት ያልተገጠመለት ህንፃ ግን የለም። ይህ ሁሉ ችግር የመጣው ከተቋራጩ ነው ብለዋል። ህንፃዎቹን ለባንኩ ገና ስላላስረከቡ፣ ለማስረከብ እየሰሩ ስለሆነ በቅርብ ቀን አጠናቀው እንደሚያስረክቡ አቶ ዮሀንስ ተናግረዋል። ባንኩ ስለፃፈው ደብዳቤ ግን የሚያውቁት እንደሌለ አስታውቀዋል።
የአርባ ስልሳ የጋራ ቤቶች እድለኞች ንግድ ባንክ ግንባታው አልተጠናቀቀም በማለት ሊያስረክበን አልቻለም አሉ
በኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ ኛ ሳምንት ደደቢት ከ ጅማ አባጅፈር ባገናኘው ጨዋታ እንግዶቹ ደደቢትን ሁለት አንድ አሸንፈው መውታታቸው ይታወሳል። አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታም ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት በዳኝነት ተሸንፈን ወጥተናል። የእኛ ሀገር እግርኳስ የሚገድሉት ዳኞች ናቸው። የተሰጠው ቀይ ካርድ ከመነሻው ጀምሮ ደደቢትን ለመግደል የተፈለገ ሴራ ነው ብዬ የማስበው። ማለታቸው ከጨዋታው ውጤት በላይ የብዙ ስፖርት ባለሙያዎች እና የስፖርት አፍቃርያን መነጋገርያ እርስ ሆኖ ቆይቷል።የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በሰጡት አስተያየት ዙርያ ትላንት ስብሰባ የተቀመጠ ሲሆን በጉዳዩ ዙርያ የጨዋታው ኮምሽነር የቀረበለትን ሪፖርት ከተመለከተ በኋላ ውሰኔ ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ውሳኔ ለመስጠት ደጋፊ ሰነድ እንዲቀርብለት እንደፈለገ እና ሰነዱን መርምሮ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ጥፋተኛ ሆነው ካገኘ ከበድ ያለ ቅጣት ለማስተላለፍ ለየካቲት አንድ ቀጠሮ ሰጥቶ ወጥቷል።አሰልጣኝ ንጉሴ በሰጡት አሰትያየት ዙርያ የክለቡ አቋም ምን እንደሆነ የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሚካኤል አምደመስቀል ለሶከር ኢትዮጵያ የሚከተለውን ብለዋል። አሰልጣኝ ንጉሴ የሰጠው አስተያየት የክለቡ አቋም እንዳልሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን። ሆን ተብሎ ደደቢት ላይ የተሰራብን ሴራ አለ ብለን አናምንም። ለዳኞቻችን ትልቅ ክብር አለን። አልቢትር ሀይለየሱስ ባዘዘው ትልቅ ስብእና ያለው ሙያውን የሚያከብር እና ትልቅ አድናቆት ከምንሰጣቸው ዳኞች መካከል አንዱ ነው። ይሄንንም ደውለን ለራሱ ለሀይለየሱስ ባዘዘው በሚገባ ገልፀንለታል። አሰልጣኝ ንጉሴም ከዚህ በኋላ እንደነዚህ ካሉ ስሜታዊ መግለጫዎች እንዲቆጠቡ አሳስበናል ብለዋል ።በዚህ ዙርያ አሰልጣኝ ንጉሴን ደስታ ከመግለጫው በኋላ ያላቸውን ሀሳብ ለማስተናገድ ያደረግነው ጥረት ያልተሳካ ሲሆን የኢትዮዽያ ዳኞች ብሄራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ልኡልሰገድ በጋሻው ጉዳዩን አስመልክቶ ያላቸውን ሀሳብ ጠይቀን ጉዳዩን ከመስማት ውጭ ምንም መረጃ እንደሌላቸውና ውሳኔ ሰጪው የዲሲፒሊን ኮሚቴ የሚወስነውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ መረጃ እንዲሰጡ ገልፀዋል።
አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በዳኛ ውሳኔ ላይ በሰጡት አስተያየት ቅጣት ሊተላለፍባቸው ይችላል
አዲስ አበባ ፣ የካቲት ስላሳ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ግብፅ በአፍሪካ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት አስመዘገበች። የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሟቹ የስልሳ አመት ጀርመናዊ ሲሆኑ፥ ከሳምንት በፊት ነበር ግብፅ የገቡት። ግለሰቡ ግብፅ ከገቡ በኋላ በቀይ ባህር ዳርቻ መዝናኛ ሁርጋዳ ሆስፒታል የህክምና ክትትል ተደርጎላቸዋል። ሚኒስቴሩ በአንድ ቀን ብቻ አርባ አምስት አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን ገልጿል፤ ይህም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር አርባ ስምንት ያደርሰዋል ነው የተባለው። የቫይረሱ ተጠቂዎች የመርከብ ጉዞ ያደረጉ እንደነበሩም ተገልጿል። አሁን ላይም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ክፍል እንዲቆዩ መደረጉን አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የተገኘባቸው ሀገራት ግብፅን ጨምሮ ዘጠኝ ሲሆኑ፥ አልጀሪያ ፣ ሴኔጋል አራት፣ ደቡብ አፍሪካ ሶስት፣ ሞሮኮ ሁለት፣ ካሜሮን ሁለት፣ ቱኒዚያ አንድ፣ ቶጎ አንድ እና ናይጀሪያ አንድ ሰው በቫይረሱ ተይዘዋል። ምንጭ፦ ቢቢሲ እና ሬውተርስ
ግብፅ በአፍሪካ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት አስመዘገበች
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ ስድስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሳምንታዊ አማካይ የሞት መጠን በእጥፍ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለፀ። የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ ወደ ህክምና ተቋማት የሚገቡ የህሙማን ቁጥርም የ ሁለት ነጥብ አምስት በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ሳምንታዊ አማካይ የሞት መጠን ደግሞ ከ ወደ ስላሳ ስድስት አድጓል ያሉ ሲሆን በፅኑ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። እንደ ሚኒስትሯ ገለፃ የቫይረሱ ስረጭት እየጨመረ ቢሆንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የሚቀሙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። በዚህም በአዲስ አበበ ሀምሳ ዘጠኝ በመቶ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ ከተሞች ደግሞ ሀያ በመቶ ብቻ ናቸው የአፍና አፍንጫ ማስክ የሚጠቀሙት ብለዋል ሚኒስትሯ። አሁን ቫይረሱ ያለበት ስርጭት ሶስትኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ የስርጭት ማእበል የጀመረ መሆኑን ያመለክታል ያሉት ዶክተር ሊያ ህብረተሰቡ ቫይረሱ የሚያደርሰውን ከፍተኛ ጉዳት ከሌሎች ሀገሮች በመማር ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል ከመጋቢት አራት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ጀምሮ እስካሁን ሁለት ሚሊየን ሁለት መቶ ሀምሳ አራት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን ወስዷል። ከ ሶስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ሁለተኛ ዙር ክትባት መውሰዳቸውን የተናገሩት ሚኒስትሯ ቀሪውን የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ስራ እይተሰራ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ቫይረሱ ካለው የስርጭት አሳሳቢነት በመነሳት ከዚህ ቀደም የኮሮና ቫይረስ ክትባት ያልወሰዱ እድሜያቸው ከ ስላሳ አምስት አመት በላይ የሆኑ ፣በሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ደግሞ እድሜያቸው ከ ሀምሳ አምስት አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ክትባቱ ይሰጣቸዋል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው እድሜያቸው ከ አመት በላይ የሆኑ በአዲስ አበባም ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ ሰዎች እንዲሁም በስራቸው ምክንያት ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችም ክትባቱ ይሰጣቸዋል። ክትባቱም በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ በሁሉም ክልሎች ደግሞ ከነሀሴ ጀምሮ እንደሚሰጥ ታውቋል። በዙፋን ካሳሁን ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ጨመረ
ከኢየሩሳሌም አረአያ ዝማም ትባላለች፤ የህወሀት ታጋይ ናት። ባለቤቷ አቶ ቢተው በላይ ይባላሉ። ቢተው እስከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሶስት አመተ ምህረት የደቡብን ክልል በበላይነት ሲያሽከረክሩና ሲመሩ የቆዩ ናቸው። በመጋቢት ዘጠና ሶስት ከአቶ መለስ ጋር በተፈጠረ የፖለቲካ ውዝግብ ከሌሎች ጋር ተነጥለው ወጡ። ከዚያም ከደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አባተ ኪሾ ጋር በሙስና ተከሰው ዘብጥያ ወረዱ። ፍርድ ቤት መቅረብ እንደጀመሩ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ጋር ለዜና ዘገባ ስንመላለስ የቢተውን ባለቤት ዝማምን ተዋወቅኳት። በክልል ቢሮ ተመድባ ነበር የምትሰራው። ባለቤትዋ ከታሰረ በኋላ ግን ዝቅ ተደርጋ በቀበሌ ደረጃ ተመደበች። ዝማም በርካታ ምስጢሮችን ታውቃለች። አርከበ ወደ ከንቲባነት ሊመጡ እንደሆነና ሌሎች ቁልፍ መረጃዎችን አቀብላኝ በኢትኦጵ ጋዜጣ ሰርቼዋለሁ። ዝማምን ዛሬ እስር ቤት የሚገኘው የደህንነት ሹም ወልደ ስላሴና አየር መንገድ ያለው ሀይሌ አጠመዷት። የህወሀት ነወረኛ ደህንነቶች ጋር መጠጥ እየተጋተች አንሶላ እንደተጋፈፈች ስገልፅ ከልብ እያዘንኩና ይህን ዘገባ ለምታነበው ሴት ልጇ እየተሸማቀቅኩ ነው። ነገር ግን ይህን ነውረኛ ድርጊቷን ባልዋ አቶ ቢተው እስር ቤት ሆኖ ያውቅ ነበር። እቤቱ ውስጥ በፓርቲው አንጃዎች ይካሄድ የነበረ ስብሰባ እየተቀረፀ አቶ መለስ ዘንድ ተልኳል። ይህ ሁሉ በዝማም የተከናወነ ነበር። ሳይታወቅ የቆየውን ኢየሩሳሌም አ የብእር ስም በመጠቆምና ለነወልደ ስላሴ አሳልፋ በመስጠት የግድያ ሙከራ እንዲፈፀምብኝ ያደረገችው ዝማም ናት። ንጉሴ የተባለ መቶ አለቃ ተገድሎ ሬሳው ጅብ እንዲበላው የተደረገው በዝማም የሴራ ተባባሪነት ነው። ታሪኩ ረጅም ሲሆን ይህን ጠንቅቀው የሚያውቁት መፅሀፍ ፅፈው ሲያበቁ ይህን ታሪክ አለማካተታቸው ያሳዝናል እንደ ዝማም ሁሉ ባለቤትዋ ከስድስት አመት እስር በኋላ ሲፈታ ያሳየው መገለባበጥ አሳፋሪ ነበር። ከአቶ መለስ ተጠግቶ የአፋር ክልል ባለስልጣን ሆነ። ከዚያም ወደ መከላከያ ኢንጂነሪንግ አመራ።ጭራሽ በዚህ አመት በህወሀት የተፈጠረው ቀውስ አስታራቂ ሽማግሌ ሆኖ ተሰየመ። የስብሀት ተከታይነቱንም አረጋገጠ። ባልና ሚስት እጅግ የለየለት ርካሽ ቁማር የተጫወቱ ናቸው። ባለፈው ሳምንት አንድ ወጣት ልጃቸው በሞት መለየቱን ሰማሁ። ከነርሱ ተግባር ጋር ልጁ የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ በመሞቱ ከልብ አዝኛለሁ። ፈጣሪ ነፍስ ይማር ነውረኛዋና ሰላይዋ ዝማም ይህቺ ናት
ነውረኛዋና ሰላይዋ ዝማም ኢየሩሳሌም አርአያ
ሩስያ በረንዳ ላይ ማጤስ መከልከሏ ተሰምቷል። በአገሪቱ አዲስ በተረቀቀው የእሳት አደጋ መከላከያ መመሪያ መሰረት፤ በጋራ መኖሪያ ቤቶች በረንዳ ላይ ሲጋራ ማጤስ አይቻልም። በአገሪቱ አዲስ እየተረቀቀ ባለው የእሳት አደጋ መከላከያ መመሪያ መሰረት፤ በጋራ መኖሪያ ቤቶች በረንዳ ላይ ሲጋራ ማጤስ አይቻልም ልባችን ከእድሜያችን ቀድሞ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ ከጤናማ የህይወት ዘይቤነት ወደ ገዳይ ልማድነት የተሻገረው ሲጋራ በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች አዲሱ መመሪያ፤ ሰዎች በሚሰባሰቡበት የትምህርት ቤት መኝታ ክፍል እና በሆቴል የእንግዳ መቀበያ ውስጥ ሲጋራ ማጤስ ይከለክላል። በረንዳ ላይ ክባብ የተባለውን ምግብ ማዘጋጀት እና ሻማ ማብራት እንደማይቻልም ተዘግቧል። ሲጋራ ማጤስ እንዲሁም ክብሪት መለኮስም ለእሳት አደጋ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሩስያ ባለስልጣኖች የተናገሩ ሲሆን፤ መመሪያውን ጥሶ የተገኘ ግለሰብ፤ አርባ ሰባት ዶላር ሶስት ሩብል ይቀጣል ተብሏል። በርካታ ሩስያውያን ሲጋራ የሚያጠሱት በረንዳ ላይ ሲሆን፤ መመሪያው ተግባራዊ ሲደረግ በጋራ መኖሪያ ህንፃዎች የምድር ቤት ለማጤስ ይገደዳሉ። አዲሱ መመሪያ ያልተዋጠላቸው ሩስያውያን መንግስት ሰዎች በገዛ ንብረታቸው እንዳይጠቀሙ እያደረገ ነው፤ በረንዳ ላይ ካልተጤሰ ታዲያ የት ይኬዳል ሲሉ ማሀበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየታቸውን ፅፈዋል። የሩስያ የሲጋራ አጫሾች መብት ተሟጋች ሀላፊ አንድሬይ ሎስክቶቭ፤ መንግስት ሲጋራ ማጤስ መከልከል የሚችልበት ቦታ ሁሉ እንዳይጤስ ከልክሏል። የቀረው በረንዳ ላይ ማጤስ ነበር፤ አሁን ግን እሱም ተከለከለ ብሏል።
ሩስያ በረንዳ ላይ ማጤስ ከለከለች
አዲስ አበባ፣ ታሀሳስ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በገጠርና በከተማ ለስራ እድል የተሰራጨ ከሶስት መቶ ሚሊየን ብር በላይ አለመመለሱን የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በሁለት ሺህ የመጀመሪያው ሩብ አመት አፈፃፀም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቴፒ ከተማ ውይይት አድርጓል። የቢሮው ምክትል ሀላፊና የገጠር ስራ እድል ዘርፍ ሀላፊ ሰሎሞን አየለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ያልተመለሰው ብድር በገጠር ከሁለት ሺህ አምስት አመተ ምህረት በከተማ ደግሞ ከሁለት ሺህ ዘጠኝ ጀምሮ ለወጣቶች የተሰራጨ ብድር ነው። በፌደራል፣ በክልል፣ በዞን፣ በወረዳ እንዲሁም በከተማ አስተዳደር አማካኝነት በክልሉ ከሁለት ሺህ አምስት አመተ ምህረት ጀምሮ ከአምስት መቶ ስላሳ ዘጠኝ ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ በብድር መሰራጨቱን እና ከዚህ ውስጥ እስከ ሁለት ሺህ አመተ ምህረት የተመለሰው ገንዘብ ሁለት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሚሊየን ብር ገደማ ነው ብለዋል። ከሶስት መቶ ሚሊየን ብር በላይ ውዝፍ ብድር አለመመለሱ በክልሉ የተለዩ ከዘጠና ስምንትሺህ በላይ ወጣቶችን በስራ ማሰማራት እንዳይቻል እንቅፋት ሆኗል ነው ያሉት። ብድር የማስመለስ ስራውን በባለቤትነት መምራት አለመቻል፣ ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠት፣ የተጠያቂነት ስርአቱ የላላ መሆንና ሌሎችም ችግሮች የተሰራጨው ብድር እንዳይመለስ ያደረጉ ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል። በተስፋየ ምሬሳ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ለስራ እድል ፈጠራ የተሰራጨ ከሶስት መቶ ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ አልተሰበሰበም
ጥቅምት ፳፰ ሀያ ስምንት ቀን ፳፻፮ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ የሚማሩ ተማሪዎች ከማንነት እና መብት መከበር ጋር በተያያዘ ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ የአንደኛ እና መለስተኛ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትምህርት ማቆማቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ተማሪዎቹ በቋንቋችን እንማር፣ በአካባቢያችን የሚታየው የመብት ረገጣ ይቁም የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ አካባቢውን ከተቆጣጠረው በኋላ ቁጥራቸው ከሀያ አምስት እስከ አርባ የሚደርሱ ተማሪዎችን ይዞ አስሯል። ውጥረቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ፣ ቀደም ብሎ ያለበቂ ምክንያት ታስረው የተፈቱት አርባ ሰዎች በዛሬው እለት ተመልሰው እንዲታሰሩ ተደርጓል። መምህራን ትናንትና ዛሬ ስብሰባ ላይ የነበሩ ሲሆን፣ የአካባቢው ባለስልጣናት ለተፈጠረው ችግር መምህራንን ተጠያቄ አድርገዋል። ባለስልጣናቱ ለኢሳት፣ ለጀርመን ወይም ለአሜሪካ ሬዲዮ ከመናገር ውጭ ምንም የምታመጡት ነገር የለም መባላቸውን ያነጋጋርናቸው አንድ መምህር ገልፀዋል ። የአካባቢውን የፖሊስ ሀላፊዎች ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
በቁጫ ወረዳ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ መንቀሳቀስ ከጀመረ ከስድስት አሰርታት በላይ እንዳስቆጠረ ማስረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህ ታሪካዊ ጉዞው ፌዴሬሽኑም ሆነ ክለቦች ከመነሻው እንደሌሎቹ አገሮች ወጥ የሆነ አደረጃጀት ኖሯቸው ሊቀጥሉ ባለመቻላቸው ዛሬም በተለያዩ የአሰራር ክፍተቶች እሰጣ ገባ ውስጥ ይገኛሉ። የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማሀበር ፊፋ ፣ የአገሪቱ ክለቦች በፊፋ የክለብ አደረጃጀትና የተጨዋቾች የዝውውር መርህ እንዲተዳደሩ የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱ እንደማሳያ ሊወሰድ እንደሚገባውም የሚናገሩ አሉ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ክለቦች በአገሪቱ የሚፈፀመው የእግር ኳስ ተጨዋቾች ደረጃና ዝውውር በህግና በስርአት እንዲመራ በፊፋ ዝቅተኛውን የተጨዋቾች ደረጃና ዝውውር መስፈርት ያሟላ እንዲሆን፣ በተጨማሪም አሰራሩ በህጋዊ ወኪል እንዲመራና ሂደቱም ተጨዋቾችን፣ ክለቦችንና መንግስትን ተጠቃሚ በማድረግ ለአገሪቱ የእግር ኳስ እድገት መፋጠን የራሱን አወንታዊ ሚና ይጫወታል በሚል የተለያዩ አንቀፆችን የያዘ የተጨዋቾች ደረጃና የዝውውር መመሪያ ረቂቅ ሰነድ ለውይይት አቅርበዋል። ረቂቅ ሰነዱ ከጥር ሀያ አምስት ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት በኋላ ህጋዊ መመሪያ ሆኖ በፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንደሚፀድቅና እስከዚያ ግን ክለቦች በረቂቅ ሰነዱ በተካተቱ ነጥቦች ውስጥ አለን የሚሉትን ሀሳብ እንዲያንሸራሽሩ ጥር ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት ፌዴሬሽኑና ክለቦች በካፒታል ሆቴል ባደረጉት የመጀመሪያ የውይይት መድረክ ከስምምነት ደርሰዋል። ሆኖም ግን መመሪያው ደንብ ሆኖ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ረቂቅ ሰነዱ ለክለቦች ቀደም ብሎ እንዲደርስ ተደርጎ በተለይ የክለብ አስተዳዳሪዎችና ባለቤቶች ጉዳዩን በሰከነና በጥልቀት እንዲመክሩበት መደረግ ነበረበት በሚል አንዳንድ ክለቦችና ተጨዋቾች ቅሬታቸውን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ። በአገሪቱ የተጨዋቾች ደረጃና ዝውውር ላይ መሰረታዊ የሚባሉ ችግሮች በጣም ብዙ መሆናቸውን የሚገልፁት የብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ፣ መመሪያው ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ያለው የተጨዋቾች የዝውውር ስርአት አለም አቀፍ አሰራርን የተከተለ አለመሆኑ፣ እንደዚህ አይነቱ የዝውውር ስርአት በተለይም የፊርማ ክፍያ የሚባለው በማንኛውም አገር የማይታወቅ በመሆኑ፣ በስርአቱም ያለውን የገንዘብ ዝውውር ለመቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑ፣ ክለቦች ለተጨዋቾች የሚከፍሉት የፊርማ ገንዘብና ተጨዋቾች ለክለቦች የሚሰጡት አገልግሎት ሊጣጣም ባለመቻሉ፣ አሰራሩ በክለቦች መካከል ተመጣጣኝ ፉክክር እንዳይኖር ከማድረጉም በላይ በተለይ በሂደቱ የፊርማ ገንዘብ የማይጠየቅባቸው ታዳጊዎችና ወጣት ተጨዋች ትኩረት እንዳያገኙ የሚያደርግ መሆኑንና በዋናነትም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት እንዲስፋፋ በማድረጉና መንግስት ከዘርፉ ማግኘት የሚገባው የገቢ ግብር ማሳጣቱን በማስረዳት የመመሪያው አስፈላጊነት አብራርተዋል። ጊዜ ተወስዶ በደንብ መታየት አለበት ስለሚባለው አቶ ተክለወይኒ፣ ረቂቅ ሰነዱን ያዘጋጀው ኮሚቴ ከራሳቸው ከክለቦችና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች እንደተመለከቱትና ስለመመሪያው አስፈላጊነት ተገቢውን ጊዜ ወስደው ተነጋግረውበታል። ከዚህ በላይ ጊዜ ያስፈልገናል የሚሉ ካሉ ከመመሪያው በተቃራኒ ያሉ አካሎች ሊሆኑ ይችላሉ። መመሪያው ባለመኖሩ የአገሪቱ እግር ኳስ የተፎካካሪነት አቅም ብቻ ሳይሆን፣ በክለቦች መካከልም ያለመመጣጠን ችግር እየተፈጠረ ነው። ባለው ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የክለቦች የፋይናንስ አቅም እየተደካመ ነው። መንግስት ተገቢውን የገቢ ግብር እያገኘ አይደለም፤ ብለዋል። ይህን ሁሉ ህገወጥ እንቅስቃሴ በማስቆምና ስርአት ለማስያዝ የማንሰራ ከሆነ የእኛ እዚህ መቀመጥ አስፈላጊነቱ ምንድነው በማለት ነው ስለረቂቅ ሰነዱ ምንነት ለተሳታፊዎች ያስረዱት። የስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አምበሳው እንየው በበኩላቸው፣ መንግስት ለስፖርቱ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ የተጨዋቾችን ዝውውር ሽፋን በማድረግ እያቆጠቆጠ የመጣው የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት መፍትሄ ሊቀመጥለት እንደሚገባ ተናግረዋል። ችግሩን ለማስወገድ እንደ አማራጭ እየተዘጋጀ ያለውን ይህን ሰነድ ክለቦች ትኩረት ሰጥተው ተገቢውን ውይይት እንዲያደርጉበትም ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ረቂቅ ሰነዱን ካዘጋጁት አንዱ ናቸው። ባለሙያው፣ ይህ የተጨዋቾች ደረጃና ዝውውርን አስመልክቶ የተዘጋጀው ረቂቅ ሰነድ ክለቦችና ፌዴሬሽኑ ቀደም ሲል በተስማሙበት መሰረት ተዘጎጅቶ በውይይት እንዲዳብር የቀረበ ስለመሆኑም ተናግረዋል። የጥናት ቡድኑ ስብስብ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ከዳሸን ቢራ፣ ከአርባ ምንጭ ከነማ፣ ከሊግ ኮሚቴ፣ ከይግባኝ ሰሚ ኮሚቴና ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጡ ባለሙያዎች እንደሆኑና ስብስቡ የተቋቋመውም ካለፈው ሁለት ሺህ ስድስት ክረምት ጀምሮ መሆኑን ተናግረዋል። የፌዴሬሽኑ አመራር ቦርድ የጥናት ቡድኑ ባቀረበለት የጥናት ሰነድ መሰረት በዋናነት፣ የተጨዋቾች የፊርማ ገንዘብ፣ የሚለው ቀርቶ በወርሀዊ ክፍያ በሚለው እንዲተካና ለዚያ ደግሞ እንደገና ጥናት ተደርጎ ለውይይት የሚሆን ረቂቅ ሰነድ የሚያዘጋጅ ቡድን ከኢትዮጵያ ቡና አቶ ገዛኸኝ ወልዴ፣ ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት አቶ ስንታየሁ በቀለ፣ ከፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን አቶ አበባው ከልካይ፣ ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አቶ ንጉሴ ለማና የጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ እንዲሆኑ ማድረጉን ጭምር ተናግረዋል። ጥናቱ እንደ ክፍተት የተመለከተው በኢትዮጵያ በተለይም በአሁኑ ወቅት ከተጨዋቾች ዝውውር ጋር ተያይዞ እየተሰራበት የሚገኘው አሰራር ለአገሪቱ እግር ኳስም ሆነ ለክለቦች፣ ተጨዋቾችና መንግስት ምንም አይነት ጥቅም እያስገኘ እንዳልሆነ፣ ይልቁንም የክለቦችን የፋይናንስ አቅም እያዳከመ ስለመሆኑ፣ ለተጨዋቾችም ቢሆን በስማቸው እንደወሰዱ ተደርጎ የሚነገረው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ የእነሱ እንዳልሆነ፣ በመሀል ለህገወጥ ደላሎች እንደሚውል፣ በዚህ አይነቱ ህገወጥ አሰራር በፕሮፌሽናል ስም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ተጨዋቾች ሳይቀር የፊርማ ገንዘብ ወስደው የጠፉ እንዳሉ፣ በፕሮፌሽናል ስም የሚመጡት ብዙዎቹ ተጨዋቾች የችሎታቸው ጉዳይ ጥያቄ እያስነሳ መሆኑ፣ ተጨዋቾች ከደመወዝ ይልቅ ትኩረት ሰጥተው የሚከራከሩት ለፊርማ ተብሎ ስለሚሰጣቸው ገንዘብ መሆኑ፣ ገንዘቡን ከወሰዱ በኋላ ለክለባቸው ተገቢውን አገልግሎት እንደማይሰጡ፣ ክለቦች የቅጣት እርምጃ እንውሰድ ቢሉ እንኳን የተጨዋቾች ወርሀዊ ክፍያ ከሁለትና ሶስት ሺህ ብር ስለማይበልጥ ተጫዋቾች የሚጣልባቸውን የቅጣት ውሳኔ በፀጋ እንደሚቀበሉት፣ ክለቦች ታዳጊዎችን አሳድገው ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም ማሳጣቱ፣ በዚህም ክለቦች ለታዳጊና ለወጣት ተጨዋቾች የሚሰጡት ትኩረት እያነሰ መምጣቱና እንደዚህ አይነት የዝውውር ስርአት በየትኛውም አገር አለመኖሩ ሲጠቀስ፣ ሌላውና ትልቁ ነገር በአንድ የውድድር አመት ለተጨዋቾች ዝውውር በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ብቻ አንድ መቶ አርባ ሚሊዮን ብር ቢንቀሳከስ መንግስት ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አርባ ሁለት ሚሊዮን ብር የሚያጣ ስለመሆኑም ጭምር ክፍተት ተብሎ መወሰዱን አቶ ገዛኸኝ አስረድተዋል። ረቂቅ ደንቡን አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሌሎች የፕሪሚየርና ብሄራዊ ሊግ ክለቦች፣ ሰነዱ በአብዛኛው የሚደገፍ ጎን እንዳለው፣ ሆኖም ደንቡን ክለቦች በአንድ ቀን ያውም በፕሮጀክተር በመታገዝ እንዲመለከቱ ተደርጎ ወደ ህጋዊ መመርያነት ይለወጥ መባሉ አግባብ እንደልሆነ፣ ከዚህ ይልቅ ሰነዱ ቀድሞ ለክለቦች እንዲደርሳቸው ተደርጎ ክለቦችም ግብረ መልሶቻቸውን ይዘው መጥተው እንዲወያዩበት ቢደረግ የበለጠ ተአማኒነት ያለው የዝውውር መመሪያ ይሆን እንደነበር ነው ያስረዱት። በተጨማሪም እንደ ማሳያ የተነሳው በውድድር አመቱ በብሄራዊ ሊግ እየተወዳደረ የሚገኘው የሀረር ሲቲ ክለብ ለያዛቸው ሀያ አምስት ተጫዋቾች፣ ለአንዳቸውም የፊርማ በሚል ገንዘብ አለመክፈሉና ሁሉንም ተጫዋቾች ያስፈረማቸው በወርሀዊ ክፍያ መሆኑን ነው። ክለቡም ተጫዋቾች ከሚያገኙት ጥቅም ተገቢውን የመንግስት የስራ ግብር እንደሚከፍል ጭምር ተነግሯል። ሊሻሻል የሚገባው የረቂቅ ሰነዱ ይዘት ጥር ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት በካፒታል ሆቴል በተደረገው ውይይት ላይ ከፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ፣ ከብሄራዊ ሊግ ክለቦች ደግሞ አርባ ሁለት ተገኝተዋል። በውይይቱ ያልተሳተፉ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ደደቢትና ሲዳማ ቡና ሲሆኑ፣ ከብሄራዊ ሊግ ደግሞ ያልተገኙት በጠቅላላው አርባ ሁለት ናቸው። ረቂቅ ሰነዱ ምንም እንኳ በተለያዩ አገሮች የተጨዋቾች ደረጃና የዝውውር ስርአቱን አስመልክቶ የሚሰራባቸውን መመሪያዎች በአስረጂነት የተጠቀመ ቢሆንም፣ ከአገሪቱ ህገ መንግስትም ሆነ የክለቦችን መብቶች የሚጋፉ አንዳንድ አንቀፆች መካተታቸውን የሚገልፁ አሉ። ከእነዚህ ውስጥ የፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ዝውውር በሚለው ስር በአንቀፅ በንኡስ አንቀፅ አራት ነጥብ አምስት እንደሚገልፀው፣ አንድ ተጨዋችና አንድ ክለብ በሚያደርጉት የዝውውር የውል ስምምነት ውስጥ የጊዜ ገደቡን ወይም መጠን በስምምነት ሊወስኑ ይችላሉ። ነገር ግን የውሉ ዘመን ከአንድ አመት ማነስ ወይም ከአምስት አመት መብለጥ የለበትም፤ በሚል የተቀመጠው ተገቢ እንዳልሆነ፣ ይህም በክለቡና በተጨዋቹ የሚወሰን እንጂ አስገዳጅ ሊሆን እንደማይገባውና መታየት እንዳለበት ይጠይቃሉ። የውጭ አገር ተጨዋቾችን ዝውውር አስመልክቶ በአንቀፅ ንኡስ አንቀፅ አንድ ነጥብ ሰባት እንደተመለከተው፣ አንድ ክለብ ሶስት የሚሆኑ የውጭ አገር ተጨዋቾችን ለክለቡ እንዲጫወቱ ማስመዝገብ እንደሚችል በደንብ መገደቡ አግባብነት የሌለው መሆኑ፣ ምክንያቱም የአገሪቱ ክለቦች በየአመቱ በአህጉራዊው ውድድር ላይ ማለት በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮናና በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ ጨዋታውም በፊፋ ህግና ደንብ መሰረት የውጭ ተጨዋቾችን አዘዋውረው ከሚያጫውቱ አገሮች ጋር በመሆኑ በኢትዮጵያ በሶስት መወሰኑ ተገቢ እንዳልሆነ ሊጤን እንደሚገባው ያሳስባሉ። የውሰት ዝውውር በሚለው ስር በአንቀፅ በንኡስ አንቀፅ ሰባት፣ አንድ ተጨዋች ከአንድ ክለብ ወደ ሌላ ክለብ በትውስት በሚዛወርበት ወቅት ቀደም ሲል ከነበረበት ክለብ ያገኝ የነበረው ጥቅማ ጥቅም አይቀንሱበትም፣ ወይም ቀሪ አይሆንበትም፤ የሚለው በህግ ፊት ተጨዋቹ ከሁለቱም ክለቦች ተጠቃሚ ይሆናል የሚለውን ትርጉም ስለሚይዝ ሊስተካከል እንደሚገባውም ይገልፃሉ። በክፍል አምስት የወጣት ተጨዋቾች ተገቢነት፣ ምዝገባ፣ መብቶችና ግዴታዎች በሚለው፣ አንቀፅ በንኡስ አንቀፅ አንድ ነጥብ ሁለት እንደተመለከተው፣ እድሜው ከ እስከ አመት የሆነ ወጣት ከ አመት በታች የወጣቶች የሻምፒዮና ውድድሮች ተመዝግቦ መጫወት እንደሚችል ይገልፃል። ይህ ማለት በቅርቡ እድሜያቸው ከ አመት በታች የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና የተጫወተው የኢትዮጵያ ወጣት ብሄራዊ ቡድን ላይ የደረሰው አይነት ችግር የሚፈጥር በመሆኑ ማሻሻያ ሊበጅለት እንደሚገባ፣ እዚሁ ላይ በአንቀፅ ንኡስ አንቀፅ አንድ ነጥብ ሶስት እድሜው እና ከዚያ በላይ የሆነው ወጣት ተጨዋች በአዋቂዎች ውድድር ተመዝግቦ መጫወት አይችልም የሚለው የሚወሰነው በተጫዋቹ አቅምና ችሎታ እንጂ በደንብ ሊሆን እንደማይገባው፣ ለዚህም ብራዚላዊው ሮናልዶ ዳሲልቫ፣ አርጀንቲናዊውን ሊዮኔል መሲ እና ሌሎችም በርካታ ተጨዋቾች በ አመታቸው ለዋናው ብሄራዊ ቡድኖቻቸው መጫወት መቻላቸው በአስረጂነት ጠቅሰው፣ አንቀፁ መሻሻል እንዳለበትም ይጠቁማሉ። ከዚህ ውጪ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ክለቦች እንደነዚህ አይነቶቹን ደንብና መመሪያዎች በሚያወጡበት ወቅት ጉዳዩን ከህግና መሰል ጉዳዮች ጋር አጣጥመው ማስኬድ የሚችሉ የህግ ባለሙያዎችን ማካተት እንደሚገባቸው እነዚሁ ረቂቅ ደንቡን አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ይገልፃሉ። ከዚህ ባለፈ ግን ረቂቅ ሰነዱን አስመልክቶ በአገሪቱ እየተደመጠ የሚገኘው ቅሬታና ትችት አግባብ አለመሆኑንም ያክላሉ።
የተጫዋቾች የዝውውር ረቂቅ ሰነድ ለምን አነጋጋሪ ሆነ
ነሀሴ ፳፪ ሀያ ሁለት ቀን ፳፻፭ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምኦን ይህን የተናገሩት በመካሄድ ላይ ባለው የሀይማኖቶች ጉባኤ ላይ ነው። በጉባኤው ላይ የተገኙት አንዳንድ የሀይማኖት አባቶች መንግስት ትእግስቱን አብዝቶታል፣ እርምጃ ይውሰድልን እያሉ መጠየቃቸውን ተከትሎ፣ አቶ በረከት መንግስት ሀይሉ እንዳለውና መታገሱ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ይላሉ አቶ በረከት የተፈጠረው ችግር ጊዜ የሚሰጥ አልሆነም ። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ትናንት ባደረጉት ንግግር መንግስት እየወሰደ ያለውን የሀይል እርምጃ እንደሚቀጥል ተናግረው ነበር። በተለይም በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች አክራሪነትንና ሽብረተኝነትን መደገፋቸውን ካላቆሙ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አቶ ሀይለማርያም ገልፀዋል። በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚገኘው መንግስት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻውን ከልማት ወደ ሀይማኖት ማዞሩን ዘጋቢያችን ገልጿል።
በሀይማኖት ጉዳይ የመጣው ችግር ጊዜ የሚሰጥ አልሆነም ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ
ከ አመት በላይ ወጣቷ የት እንደገባች አልታወቀምኤጀንሲው የተጣለበት የፈቃድ እገዳ ተግባራዊ አልሆነም ከሁለት አመት በፊት አልኢስማኤል በተባለ የውጪ አገር የግል ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ በኩል በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኮንትራት ውሏ ፀድቆ ወደ ሳውዲ አረቢያ የተላከችው ወጣት ደብዛ መጥፋት እያወዛገበ ነው። ወጣቷ ላለፉት ወራት የት እንደገባች የሚያመለክት አንዳችም ፍንጭ አልተገኘም። ሀያት አሊ መሀመድ በሚል ስም የካቲት ቀን አመተ ምህረት ወደ ሳውዲ የተጓዘችው ወጣቷ ከአገር ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ከቤተሰቦችዋ ጋር አንዳችም ግንኙነት ባለማድረግዋ ቤተሰቦችዋ የትና በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለች ሊያውቁ እንዳልቻሉ ይገልፃሉ። ወደ ሳውዲ የላካት ኤጀንሲ ሀያት አሊ ያለችበትን ሁኔታና የት እንደምትገኝ እንዲያሳውቃቸው ቤተሰቦቿ ኤጀንሲውን ቢጠይቁም ኤጀንሲው ምላሽ ባለመስጠቱ ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ማመልከታቸውን ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ኤጀንሲው ወጣቷ ያለችበትን ሁኔታ በአፋጣኝ ተከታትሎ እንዲያሳውቅ ያሳስባል። ኤጀንሲውም ሳውዲ ድረስ ሄዶ ወጣቷን ለማግኘት ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ሀያት አሊ መሀመድ የተባለችው ወጣት በምን ሁኔታና የት እንደምትገኝ ተጣርቶ ምላሽ እንዲሰጠው ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለቆንስላዎች ጉዳይ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ጥያቄ ያቀርባል። የቆንስላ ጉዳይ ክትትል ቢሮው በበኩሉ ወጣቷ የምትገኝበት ሁኔታ ተጣርቶ እንዲገለፅለት ሪያድ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጥያቄ ቢያቀርብም ከኤምባሲው ምላሽ ሊገኝ ባለመቻሉ የሀያት ቤተሰቦች እጅግ በከፋ ሀዘንና ሰቆቃ ውስጥ እንደሚገኙ የወጣቷ እህት የኔነሽ አያሌው ለአዲስ አድማስ ገልፃለች። የወጣቷ ደብዛ መጥፋት በእጅጉ ያሳሰባቸው ቤተሰቦች የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በተደጋጋሚ የአፋልጉን ጥሪ ቢያቀርቡም እስካሁን ምላሽ አለማግኘታቸውን የጠቆመችው የኔነሽ ኤጀንሲው ተግባሩን በአግባቡ ባለመውጣቱ የስራ ፈቃዱ እንዲታገድ በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀምሌ ቀን አመተ ምህረት ትእዛዝ ቢተላለፍበትም ኤጀንሲው አሁንም በስራ ላይ እንደሚገኝ ገልፃለች። መንግስት ህገ ወጥ ስደትን እቃወማለሁ ዜጎች በህጋዊ መንገድ ወደሚፈልጉበት አገር ለስራ መሄድ ይችላሉ ባለው መሰረት እድሉን ተጠቅማ በህጋዊ መንገድ የሄደችው እህቴ ያለችበት ሳይታወቅ ሁለት አመት ከሶስት ወራት ማለፉ እጅግ የሚያሳዝንና ስጋት የሚፈጥር ነው ያለችው የኔነሽ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተረባርበው እህቴ ያለችበትን ሁኔታ እንዲያሳውቁንና ከስጋት እንዲያወጡን እማፀናለሁ ብላለች። ስለጉዳዩ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን ለመጠየቅ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ሳይሳካልን ቀርቷል።
ወደ ሳውዲ የተላከችው ወጣት ደብዛ መጥፋት እያወዛገበ ነው
ከአቤ ቶኪቻው ሰላም ወዳጄ ተጠፋፍተናል ግዴለም እቅፍ አድርጌ ሰላም ልበልዎት እንዴት አሉልኝ እኔ የምለው አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሞቱ እንዷዛ አንድ አመት ሞላቸው አይደለም እንዴ ወይ ጉድ ጊዜው እንዴት ይሮጣል ጃል ምን እንደሚያመጣልን እንጃለቱ አሯሯጡ ግን ወርቅ በወርቅ እንደሚያንበሻብሽ አትሌት ነው። ይሁና እኛ እንደሆነ በርታ ግፋ እያልን ከመደገፍ ወደ ኋላ አንልም አረ እንደውም ጊዜ ሆይ ሩጥልኝ ልጄ አምልጠልኝ ልጄ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ለኔውም አልበጄ ብለን እንደ ዶክተር ፈቃደ አዘዘ እንቀኛለንእናልዎ ወዳጄ ዛሬ የመጣው ይምጣ ብዬ ሙት ወቃሽ አታድርገኝም ሳልል የአቶ መለስ መሞት ለሰፊው ህዝብም ሰፊ መሆን ለተሳነው ኢህአዴግም መጠን አልባ ለሆኑት ተቃዋሚዎችም በጣም ስንሳለቅ ደግሞ ለወይዘሮ ሀዜብ ሳይቀር በርካታ ጥቅማጥቅሞች አሉት ብዬ ልሟገትልዎ ነውበ አመት ውስጥ ያየናቸው አቶ መለስ እንደው ዝም ብለው የእነ ስምሀል አባት እንደው ዝም ብለው የነ ወይዘሮ አዜብ ባለቤት እንደው ዝም ብለው የአቶ ዜናዊ አስረስ ልጅ ብቻ አልነበሩም። አቶ መለስ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ኢህአዴግ ሊቀመንበር ከዛም ውስጥ ደግሞ እጅግ አደገኛ የሚባለው ህውሀት አባወራ የሀገሪቱ ጦር ሀይሎቹ አዛዥ አሀ ለካስ ጦር ሀይሎች የድሮው ነው እንደው የድሮ ስርአት ናፋቂ የሆንኩ ሰውዬ አሁን መከላከያ ነው ማለት ያለብን በመከላከያው ውስጥ ጦር አለ ከተባለ እንኳ ጦሩ አቶ መለስ ነበሩ ስለዚህ የጦር ሀይሎች አዛዥ ሳይሆኑ በመከላከያ ውስጥ ጦር የሆኑ ሰውዬ ነበሩ ብሎ አለመመስከር ጡር ነው በጥቅሉ ሰውዬው የመላዋ ኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ ነበሩ። አሁን እኒህ ሰውዬ ሞተዋል እስቲ ከተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ጋር አያይዘን የሞታቸውን ጥቅማ ጥቅሞች እንዘርዝር ለአባይ ግድብ ሲሉ አቶ መለስ እንኳን ሞቱ አባይን አቶ መለስ እንዴት እንዴት ይገደብ ብለው እንደጀመሩት ተነጋግረን ተነጋግረን መቼም ከስምምነት ላይ የደረስን መስለኛል። አባይዬ ድንገት ያለ እቅድ ያቺ እነ ሙባረክን እንደ ሾላ ፍሬ ርግፍ ርግፍ ያደረገች አብዮት ወደ እኛም ትመጣ ይሆናል በሚል ስጋት ነው ለማስቀየሻ ተብላ ነው የተጀመረችው። ለዚህ ዋና ማስረጃ በአምስት አመቱ ትራስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አለመፃፏ ሲሆን ሌላው ደግሞ የፕሮጀክቷ ስም አሁንም አሁንም መቀያየሩ ድሮውንም ቃሚዎች በምርቃና እንደሚሉት አይነት የታሰበች ድንገቴ ስራ መሆኗን ያሳብቃል። በነገራችን ላይ አሁንም ጭምር በተለይ ውጪ ሀገር የሚኖሩ የኢህአዴግ ወጣት ክንፎች የአባይን ግድብ ሚሊንየም ዳም ነው የሚሏት ህዳሴ መባሏን ከነጭርሹም አለሰሙም የሆነው ሆኖ አባይን አቶ መለስ ድንገት እንደጀመሯት ሁሉ ድነገት ያቋርጧታል የሚል ስጋት ሰቅዞ የያዛቸው ብዙዎች ነበሩ ብዙዎች ያልኩት አካብዶ ለማውራት እንዲመቸኝ ብዬ እንጂ እንዲህ የሚያስቡት ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ ስታስቲክስ አልሰራሁም። ነገር ግን ያናገርኳቸው ሁሉ የሰጡኝ ማብራሪያ አሳማኝ ነበር። እንደሚታወቀው አባይን ለመገደብ የሚጠይቀው የገንዘብ አቅም ቀላል አይደለም። በየመስሪያቤቱ በጥፊም በርግጫም የሚደረገው መዋጮ አስከምን ድረስ እንደሚያስኬድ የሚያውቁት እርሳቸው ብቻ ነበሩ እናም የሆነ ቀን የሆነ ቀን ማጣፊያው ያጠራቸው ቀን መለኛው መሌ በሆነ መላ ግንባታው እንዲቋረጥ ያደርጉ ነበር የሚለው ነገር ውሀ የሚያነሳ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ይህንን እያንሰላሰልን ታድያ ምን ይበጃል እያልን ስንጨነቅ አቶ መለስ ሞቱ ለአባይ ሲባልስ እንኳን ሞቱ ልክ እርሳቸው ሲሞቱ ሌጋሲን ማስቀጠል በሚለው መርህ ከዋናዎቹ አንዱ አባይ ግድብ አይቋረጥም የሚለው ሆነ። እሰይ እንኳንም አልተቋረጠ። እንኳንም ሞቱልን ለተቃዋሚዎች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ ተቃዋሚዎች በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግን ሲቃወሙ ከሁሉ በላይ የሚበረታባቸው የአቶ መለስ ግልምጫ ሽሙጥ እና እርምጃ ነበር። ሲያሻቸው ጣት እንቆርጣለን እያሉ ሲያሰኛቸው ሰብስበው እስርቤት እየላኩ አቶ መለስ ተቃዋሚዎች ላይ እንደሚጨክኑት ኢህአዴግ አይጨክንባቸውም። እውነቱን እንበለው ካልን ደግሞ መጨከን ብቻም ሳይሆን በፖለቲካው ቼዝም አቶ መለስን ተቃዋሚዎቹ አይችሏቸውም ነበር። ተቃዋሚዎቹ ፈረሳቸውን ቆስቁሰው ገና ቼ ብለው ሮጥ ሮጥ ማለት ሲጀምሩ መለስ በወታደሮቻቸው ፈረሶቻቸውን እየሰነከሉ ንግስታቸውን ቼዝ እያሉ ተቃዋሚዎቹን መላወሻ አሳጥተዋቸው ነበር። አሁን አቶ መለስ ሞተውላቸዋል። ተቃዋሚዎች መቼም ጨካኞች እንዳይባሉ ሰግተው በአቶ መለስ ሞት ሀዘናቸውን ሲገልፁ ቢሰማም ውስጥ ውስጡን ግን እሰይ ግልግል እንደሚሉ ማወቅ አያቅተንም። በአሁኑ ጊዜ ተቃዋሚዎቹ ትንሽ ጠንከር ካሉ ኢህአዴግ ውስጥ ክፉኛ የሚገዳደራቸው አለ ብሎ ማመን ይቸግራል። ስለዚህም ለተቃዋሚዎች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ ለራሱ ለኢህአዴግ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ በተለይ ከሆነ ጊዜ በኋላ ይመስለኛል ህውሀት ለሁለት ቃቃቃቃ ብሎ ከተሰነጠቀ ጊዜ በኋላ የኢህአዴግ ስብእና ኮስምኖ የአቶ መለስ ዜናዊ ስብእና ደግሞ እጅግ በጣም የጎላበት ወቅት ነበር። አረ ከነጭርሹ መለስ ከልለውን ኢህአዴግን ማየት ተስኖን ነበር በዛ አያያዙ ጥቂት አመታት ቢገፉ ኖሮ ኢህአዴግዬ መለስ በተባለ ቅብ ተሸፍና እሰከመፈጠሯም እንረሳት ነበር። አሁን ግን መለስ ሞቱ ኢህአዴግ የሚባል ፓርቲም ምን አይነት ቅርፅ እና መልክ እንዳለው ሊታወቅ በቃ። ታድያ ለኢህአዴግ ሲባል ቅርፀ ግንባሯ እንዲታይ ሲባል ያለ መለስ መኖር እንደምትችል ለማሳየት ሲባል እንኳን መለስ ሞቱላት ብንል ምን ግፍ ተናገርን ይባላል። ወላ ለወይዘሮ አዜብ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ መጣች ስላቋ ወይዘሮ አዜብ ቀላል ክብሮ ሆኑ እንዴ ክብሮ ማለት አራዶቹ ከበረ ከሚለው አማርኛ ቃል የወሰዷት ስትሆን የተከበረ ለሚባል ሰው የሚሰጥ ማእረግ ነው። አዎ ወሮ አዜብ ክብሮ ሆነዋል። የመለስ ፋውንዴሽን ፕረዘዳንትነት አቶ መለስ ባይሞቱ ኖሮ ከየት ይመጣ ነበር አረ እንኳን ሞቱላቸው እዝችጋ እንኳ ጨክኛለሁ ይቅር ይበለኝ የምር ግን ወይዘሮ አዜብ እንደልቸው መልካም ገፅታቸውን እንዲገነቡ የአቶ መለስ ሞት ትልቅ እድል ሰጥቷቸዋል ብዬ አምናለሁ ዝም ብለን ከመረመርን ወይዘሮ አዜብ በአቶ መለስ ሞት ጉዳት እንደገጠማቸው ሁላ በርካታ ትቅማጥቅሞችንም እንዳገኙ ግን መጠርጠር አያቅተንም ለችግኝ ተከላ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት ዘመናቸው እና በበትረ ስልጣናቸው ጊዜ ሰዎች አጥብቀው የሚያማርሯቸው በችግር ተከላ ነበር። አሁን ግን ሞቱ አመትም ሞላቸው በስማቸውም በርካታ ችግኞች እየተተከሉላቸው ነው። በእውኑ ለእነዚህ ችግኞች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ ብንል ማነው እርኩስ የሚለን ማንም የአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ ስላቅ እና ሀቅየአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ ስላቅ እና ሀቅ ሰላም ወዳጄ ተጠፋፍተናል ግዴለም እቅፍ አድርጌ ሰላም ልበልዎት እንዴት አሉልኝ እኔ የምለው አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሞቱ እንዷዛ አንድ አመት ሞላቸው አይደለም እንዴ ወይ ጉድ ጊዜው እንዴት ይሮጣል ጃል ምን እንደሚያመጣልን እንጃለቱ
የአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ ስላቅ እና ሀቅ ከአቤ ቶኪቻው
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ ሀያ ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የኢትዮጵያ ስጋ ደዌ ተጠቂዎች ብሄራዊ ማህበር ለገቢ ማስገኛና ለስልጠና አገልግሎት የሚውል ማእከል አሰርቶ አስመረቀ። ማህበሩ ለአባላቱ ገቢ ማስገኛና ለስልጠና አገልግሎቶች የሚውል አንድ ሺህ አምስት መቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ባለአምስት ወለል ህንፃ ነው አሰርቶ ያስመረቀው። በምረቃ መረሀ ግብሩ የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰን ጭምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተገኝተዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ማእከሉ በዋናነት አቅመ ደካማ የሆኑ የስጋ ደዌ ተጠቂ አካል ጉዳተኞች፣ ወላጅ ያጡ ህፃናትን፣ አረጋውያንና ሴቶችን እንዲሁም ተፈናቃዮች እንደሚደጎሙበት ያላቸውን እምነት ገልፀዋል። የስልጠና ማእከሉ አካል ጉዳተኞች ዘንድ የይቻላልን መንፈስ ለማስረፅ እና የኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን ቀርፈው ከጥገኘነት እንዲላቀቁ እንደሚያግዝም ተገልጿል። የአለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ተወካይ ቦሪይማ ሀማ በበኩላቸው በሳሳካዋ አጋዥነት ለተሰራው ማእከል አድናቆታቸውን ገልፀው ድርጅታቸው በቀጣይ በስጋ ደዌ ምክንያት የሚከሰቱ የጤና እክሎችን ለመቅረፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። የሳሳካዋ ግሎባል ፋውንዴሽን መስራች ዮሂ ሳሳካዋ ለማህበሩ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር እንዲሁም በትብብር የመስራት ሂደቱንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ታካኮ ኢቶ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ ስጋ ደዌ ተጠቂዎች ብሄራዊ ማህበር የስልጠና ማእከል አስመረቀ
የካቲት ስላሳ ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ዘጠኝ አመተ ምህረት መላ ጋናውያን ትልቅ ቦታ የሚሰጡት፣ የታሪካቸውን አንድ ወሳኝ ምእራፍ በደማቅ ቀለም የፃፉበት ቀን ነው። ጋናውያን ከዛሬ ስልሳ አመት በፊት የእንግሊዝን የቅኝ አገዛዝ ቀንበር በመስበር ነፃነታቸውን ማስመለስ የቻሉት በዚህ ቀን ነው። በዚህ የተነሳ ላለፉት ስልሳ አመታት ዘመን ተቀይሮ ቀኑ በመጣ ቁጥር በአደባባይ እየተሰበሰቡ ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነፃነታቸውን ለማስመለስ ሲታገሉ የህይወትና የአካል መስዋእትነት የከፈሉ ጀግኖቻቸውን ውለታ በማስታወስ እለቱን ይዘክራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በርካታ ጋናውያን ከየካቲት ስላሳ ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ዘጠኝ አመተ ምህረት ይልቅ ሰኔ ሀያ ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አራት አመተ ምህረት በጋና የነፃነት ታሪክ ውስጥ እጅግ የላቀ ቦታ አለው ይላሉ። ሰኔ ሀያ ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አራት አመተ ምህረት ጋና በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነውን የመድብል ፓርቲ ምርጫ ያካሄደችበት ቀን ነው። ለዚህ ቀን የተለየ ትኩረት የሚሰጡት ጋናውያን፤ ምነውሳ ሲባሉ የሚሰጡት መልስ ቀላልና ግልፅ ነው። በየካቲት ስላሳ ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ዘጠኝ አመተ ምህረት ያገኘነው የባንዲራ ነፃነት ብቻ ነው። ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ በኋላ የወደቅነው በአንድ ፓርቲና በወታደራዊ አምባገነን አገዛዝ ላይ ነው። ለነፃነታችን፣ ለእኩልነትና፣ ለመብታችን መከበር ቁብ የማይሰጠውን ይህን ክፉ አገዛዝ ሳንወድ በግድ ተሸክመን ለስላሳ አምስት አመታት ኖረናል። ከዚህ ክፉ አገዛዝ ተላቀን ወደ መድብለ ፓርቲ ስርአት የተሸጋገርነውና ስርአት መሰረቱ የተጣለው ሰኔ ሀያ ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አራት አመተ ምህረት ነው በማለት ይመልሳሉ።ለአለማችን ጥንታውያን ከሚባሉት ጥቂት ሀገራት አንዱ ተደርጎ በሚቆጠረው የሀገራችን የሏላዊ መንግስትነት የታሪክ መዝገብ ውስጥ ጉልህ ፋይዳ ያለው ታሪካዊ ክንውን ከተካሄደባቸው እጅግ በርካታ ታሪካዊ ቀኖች አንዱ ግንቦት ሀያ ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት አመተ ምህረት ነው። በዘር ላይ የተመሰረተ ፌደራላዊ የአስተዳደር ስርአትና በዋናነት ዘርን መሰረት ያደረገ የመድብለ ፓርቲ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ምህዳር የተዘረጋው ከዚህ ቀን ጀምሮ ነው። ይህም ብቻ አይደለም። ለዜጎች ነፃነትና እኩልነት እውቅና የሚሰጥ፣ ለሰብአዊና ዲሞክራሲያው መብቶቻቸው መከበርም ዋስትናና ጥበቃ የሚያጎናፅፍ፣ ህገመንግስት ፀድቆ፣ በስራ ላይ እንዲውል የተደረገው ግንቦት ሀያን ተከትሎ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን፣ በኢህአዴግ የሚመራው መንግስት፣ ቀኑ በብሄራዊ በአልነት ተመዝግቦ እንዲከበር በወሰነው መሰረት፣ ላለፉ ሀያ ስድስት አመታት ግንቦት ሀያ ቀን በመጣ ቁጥር ደግሱ የተባሉትን ድግስ እየጣሉ፣ አድርጉ የተባሉን እያደረጉና ዘላለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማእታት የሚል መፈክር እያሰሙ አክብረውታል። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ለኢትዮጰያውያንም ሆነ ለጋናውያን ትልቁ ጉዳይ ግንቦት ሀያንና ሰኔ ሀያ ቀንን ዳስ ጥለው፣ ቅጠል ጎዝጉዘው ማክበራቸው አይደለም። ይልቁንስ በየአመቱ የሚዘክሯቸው ቀኖች በፖለቲካ ስርአታቸው ውስጥ ለህዝቡ የሚበጅ ምን ሰናይ ትሩፋት አመጡላቸው በተለይም የዛሬ ሀያ አምስት አመት በሰኔ ሀያ እና ግንቦት ሀያ የጀመሩት የመድብል ፓርቲ ስርአት ዛሬ የት ላይ ደርሷል የሚለው ነው።ጋናውያን የመድብለ ፓርቲ ስርአታቸውን አሀዱ ብለው የጀመሩት ስልጣን የጨበጠ ፓርቲ ጊዜ ሰጠኝ ብሎ ጉልበት የተሰማው ቀን እንደፈለገ ከፍ ዝቅ፤ ሰፋ ጠበብ የማያደርገውና ሁሉንም የፖለቲካ ቡድን እኩል ማስተናገድ የሚችል የፖለቲካ መጫወቻ ሜዳ በመገንባት ነው። የእስልምና የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ ሰባ አምስት ብሄርና ብሄረሰቦች የሚኖሩባት ጋና፤ ዜጎቿ በፖለቲካ የተነሳ በዘርና በሀይማኖት ተከፋፍለው ብሄራዊ አንድነቷ እንዳይላላ፣ እርስ በርሳቸውም እንዳይጫረሱ ሁነኛ የህግ መላ መፈለግ ቀጣዩ የቤት ስራዋ ነበር። እናም በሁለት ሺህ አመተ ምህረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ ቁጥር አምስት መቶ ሰባ አራትን አወጀች። የዚህ አዋጅ አንቀፅ ሶስት ቁጥር አንድ ሀ፤ በዘር፣ በፆታ፣ በሀይማኖት፣ በአካባቢና በሙያ ዘርፍ ተደራጅቶ የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም የተከለከለ መሆኑን ይደነግጋል። በዚህ የተነሳ በታህሳስ ወር አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አራት አመተ ምህረት በተደረገው የመጀመሪያ የመድብለ ፓርቲ ብሄራዊ የምርጫ ውድድር ለመካፈል፣ በአወዳዳሪው የጋና ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ተመዝግበው የቀረቡት ሀያ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው። ከእነዚህ ሀያ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በሂደት በጋና የፖለቲካ መድረክ ላይ ጎልተው የወጡትና የጋናን የምርጫ ፖለቲካ መቆጣጠር የቻሉት ግን የሊበራል ዲሞክራሲ ርእዮተ አለም አቀንቃኝ ነው የሚባለው ኒው ፓትሪዮቲክ ፓርቲ እና የግራ መሀል ርእዮተ አለም የሚያራምደው የብሄራዊ ዲሞክራቲክ ኮንግረስ ናቸው። ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አራት አመተ ምህረት ጀምሮ በጋና የተካሄዱትን ብሄራዊ ምርጫዎች በማሸነፍ የስልጣን ወንበሩን የተፈራረቁበት እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ናቸው። እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ለዚህ የበቁት የስልጣን መንበሩን ሲቆጣጠሩ ተፎካካሪያቸውን በማዋከብ እያዳከሙ፤ ወይም መሪዎቻቸውን በሰበብ አስባቡ እስር ቤት በማጎር እያፈረሱ ከቶውንም አይደለም። ይህን ለማድረግ ቢፈልጉም እንኳ በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባው የጋና የፍትህ ስርአትና የዲሞክራሲ ተቋማት እድልም ቀዳዳም የሚሰጡ አይደሉም። እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች በጋና የመድብለ ፓርቲ ስርአት ውስጥ ይህን የመሰለ ተፅእኖ መፍጠር የቻሉት የጠራ የፖለቲካ ፕሮግራም፣ ከፍተኛ የማደራጀትና የማንቀሳቀስ ችሎታ ያለው ንቁ አመራር ባለቤቶች በመሆናቸው ነው። ጋናውያን ካለፉት ሀያ አምስት አመታት ወዲህ አባል በሆኑበት ወይም በሚደግፉት የፖለቲካ ፓርቲ የተነሳ አንዳች አይነት ችግር ይገጥመኛል ብለው መጨነቅ አቁመዋል። የጋና የፖለቲካ ፓርቲዎችም የቢሮና የስብሰባ አዳራሽ ኪራይ ጉዳይ ጨርሶ የሚጨነቁበትና እንደ ቁምነገር የሚያዩት ጉዳይ አይደለም። ይህ ሁኔታ መላ ጋናውያን በሀገራቸው የፖለቲካ መድረክ በነፃነትና በሙሉ ፍላጎት ተካፋይ እንዲሆኑ ትልቅ እድል ፈጥሮላቸዋል። በጋና የፖለቲካ መድረክ ስልጣን የጨበጠ ፓርቲ፤ የፓርቲውንና የመንግስቱን ስራና ሀላፊነት ማደበላለቅና ማምታታት፣ በመንግስት ሀብትና ገንዘብ የፓርቲውን ስራ ማከናወን፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን እንዳይጠቀሙ መከልከል እንዲሁም ሌሎች ህጋዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን እንዳያካሂዱ መከልከል ወይም ማደናቀፍ አይችልም። ከሁሉ በላይ በምርጫ ወቅት ኮረጆ መገልበጥ፣ የትኛውም በስልጣን ላይ ያለ ፓርቲ ደፍሮ የሚፈፅመው ነገር አይደለም። የምርጫ አስፈፃሚ ተቋማቱ፣ ይህ እንዲሆን ክፍተት የሚፈጥሩ አይደሉም። ስለዚህ የፈለገው አይነት ገዢ ፓርቲ፣ በምርጫ ዘጠና ዘጠኝ ድምፅ አግኝቶ ማሸነፍ መቸም ቢሆን አይችልም። ለምሳሌ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አራት በተካሄደው ምርጫ የ እጩ ጀሪ ሮውንግስ ተቀባይነት ጣራ ነክቶ ለተፎካካሪያቸው አንድም ሰው ድምፅ አይሰጣቸውም ተብሎ በሰፊው በተገመተበት ወቅት፣ ጀሪ ሮውንግስ ማግኘት የቻሉት ሀምሳ አምስት ድምፅ ብቻ ነበር። ይህ ሁኔታ ደግሞ ጋናውያን በምርጫ ጊዜ የሚሰጡት ድምፅ ትልቅ ዋጋ እንዳለውና በማንም እንደማይሰረቅ በሙሉ ልብ እንዲተማመኑ አስችሏቸዋል። ከሁሉም በእጅጉ የላቀው የመድብለ ፓርቲ ስርአታቸው ትሩፋት ጋናውያን ያስፈለጉትን መንግስት አመፅ ማስነሳት ሳያስፈልጋቸው በድምፃቸው ብቻ ማስወገድና የሚፈልጉትን ወደ ስልጣን ማምጣት መቻላቸው ነው። አምና በታህሳስ ወር የተካሄደውና በስልጣን ላይ የነበረው ፓርቲና ፕሬዚዳንቱ ጆን ማሀማ ከስልጣን የተወገዱበት ምርጫ፣ ለዚህ ማለፊያ ምሳሌ ነው። ፕሬዚዳንት ጆን ማሀማና ፓርቲያቸው ማሽቆልቆል የጀመረውን የጋናን የኢኮኖሚ እድገትና በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣውን የወጣት ስራ አጥነት በአፋጣኝ መላ እንዲፈለጉለት ህዝቡ ላደረገው ጉትጎታ የሰጡት መልስ ቸልታ ነበር። በታህሳስ ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት ህዝቡን በድጋሚ በፕሬዚዳንትነት እንዲመርጣቸው አይናቸውን በጨው አጥበው ሲጠይቁት ያገኙት መልስም እንዲሁ ቸልታ ነበር።፡ የህዝቡ ቸልታ ውጤትም፣ በተቀናቃኛቸው የአዲስ አርበኞች ፓርቲ እጩ ናና አኩርፎ አዶ፣ በአስተማማኝ የድምፅ ልዩነት ተሸንፎ ከፕሬዚዳንታዊው የጋና ቤተመንግስት መባረር ሆነ። ለመሆኑ የእኛ የመድብል ፓርቲ ስርአትስ ከየት ተጀምሮ ዛሬ ከምን ላይ ደረሰ የሳምንት ሰው ይበለን።
የመድብለ ፓርቲ ስርአት ጋናና እኛ
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ፅንፍ የያዙ አመለካከቶች የሀገሪቱ ሁኔታ ወደ ውጥረት እየከተቱ፣ ዜጐችን ለጥቃት እያጋለጡ መሆኑን የጠቆመው በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው የኢትዮጵያ ሲቪል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ኦሲዴፓ ፤ መንግስት የዜጐችን ደህንነት የማስጠበቅ ሀላፊነቱን እንዲወጣ አሳስቧል። በኢትዮጵያ በተፈጠሩ ኢ መደበኛ አደረጃጀቶች ምክንያት እየከሰቱ ያሉ ችግሮች የሰላማዊ ዜጐችን በሰላም የመኖር ዋስትና በእጅጉ እየፈታተኑ መሆኑን የገለፀው ፓርቲው፤ ህግ የማስከበር ሀላፊነት የተጣለበት መንግስት አፋጣኝ እርምጃዎችን በመውሰድ የዜጐችን መብት ማስከበር አለበት ብሏል። ኢትዮጵያ የምትተዳደረው በህገ መንግስት ሆኖ ሳለ ግለሰብ አክቲቢስቶችና ኢ መደበኛ አደረጃጀቶች የሀገሪቱን ዜነች ሰላም እያናጉ ነው ያለው ፓርቲው፤ እነዚህ ሀይሎች ሀሳባቸውን ማቀንቀንና ፍላጐታቸውን ማስከበር ያለባቸው አሁን በስራ ላይ ባለው የሀገሪቱ ህገ መንግስት ማእቀፍ ውስጥ መሆን አለበት ብሏል። ተገቢነት የሌላቸውና ወቅት ያልጠበቁ የይገባኛል ጥያቄ በማንሳት የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን በህግ መሰረት ስርአት ማስያዝ ይገባል ያለው መግለጫው፤ መንግስትም ይሄን ስርአት የማስያዝ ሀላፊነቱን በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት እንዲወጣ አሳስቧል። በተያያዘም ፓርቲው፣ አወዛጋቢ የሆነው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ማሻሻያ እንዲደረግበት ጠይቋል።
መንግስት በህግ በተሰጠው ስልጣን የዜጐችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ ተጠየቀ
በዘንድሮው የሰሜን አሜሪካ እና የአውሮፓ ስፖርት እና ባህል ፌስቲቫሎች ላይ የቦይኮት እቀባ ዘመቻዎች ተነስተው ነበር። የዘመቻዎቹን ውጤቶችም አይተናቸዋል። በዚች አጭር ፅሁፌ የማተኩረው በውጤቶቹ ላይ አይደለም። በሲያትሉም ሆነ በሮም ዝግጅቶች ላይ ስለነበርኩ፣ የቦይኮት ዘመቻዎቹ ከጅምሩ ጥቅም እና ጉዳቶችን አመዛዝነው ነበር ወይ የሚለውን በጥቂቱ ለመፈተሽ እሞክራለሁ። በዚህ ርእስ ላይ ስፅፍ አዋራ እንደሚነሳ አምናለሁ። በጉዳዩ ላይ እጅግ ብዙ ሰዎች ሲወያዩ ብታዘብም በፍርሀት ይሁን በሌላ ምክንያት ሀሳባቸውን በአደባባይ ለመናገር ግን ሲደፍሩ አይታይም። ሀሳባቸውን በድፍረት የሚሰነዝሩ ወገኖችም ቦይኮት ስለሚደረጉ ብዙዎች ዝምታን ቢመርጡ አይደንቅም። አህያ የለኝ ከጅበ አልጣላ ብሎ ሀሳቡን በነፃ ለመግለፅ የሚሞክር ደግሞ ይሰደባል። በሳይበሩ አለም፣ ወቅትን እየጠበቀች በምትነደው እሳት ላይ ማን ቤንዚን እንደሚጨምርበት አሁን ግልፅ ሆኗል። አንዳንዶቹን የቦይኮት ዘመቻዎች ማን እንደሚጠራው እንኳን አይታወቅም። ምክንያቱም ሀላፊነቱን የሚወስድ አካል ስም እና አድራሻ የላቸውም። አንድ ሾልኮ የወጣ መረጃ የሚጠቁመን ገዥው ፓርቲ ሰባት ሺ የሳይበር ላይ አጥቂዎችን የወር ደሞዝ እየከፈለ አሰማርቷል። ፕሮፌሰር እንድርያስ እሼቴ በቨርጂንያ ግዛት በምትገኝ፣ ኪንግስታውን ስታርባክስ በራፍ ላይ ፕሮፌሰር እንድርያስ እሼቴ ሲጋራውን እንደ ሲኖ ትራክ ጭስ እያቦነነ ተቀምጧል። የወቅቱ ሙቀት በጭስና በአልኮል ደከምከም ያለ ሰውነቱ ላይ ተጨምሮበት የሉሲን አፅም አስመስሎታል። ከሁለት ባለግዜዎች ጋር ጠቀምጦ ህወሀትኛ ወጉን በነፃነት ይሰልቃል የሞት ሞቱን። ከዚያ አለፍ ብሎ ያለው ሞል ውስጥም ሆነ ስቶር ገባን። እዚያ የምናገኛቸው ሸማቾች ደግሞ በሙሉ ማለት ይቻላል ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የባለስልጣናቱ ዘመድ አዝማዶች መሆናቸው ተነገረን። በባንክ ብድር ሳይሆን ካሽ በማውጣት ዘመናዊ ቪላ ቤቶች የመግዛት አቅም ያላቸው ኢትዮጵያውያውያን ሚሊየነሮች። የአካባቢው ነዋሪ እንደነገረን ከሆነ እነዚህ ምንጩ ያልታወቀ ሚሊየነሮች ያንን መንደር ሁለት አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ነው ገዝተው የሰፈሩበት። በአሁኑ ሰአት በዲሲ፣ በቨርጂንያ እና በሜሪላንድ ግዛቶች የመኖርያም ሆነ የንግድ ቤት አከራዮቹ እነሱው ሆነዋል። ልብ በሉ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል እና የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቦ ኢምቤኪ በአምስት አመታት ግዜ ዉስጥ ብቻ ከኢትዮጵያ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ አስር ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወደ ዉጭ እንዲወጣ ነግረውናል። ይህን ጉዳይ ለግዜው በዚህ ልተወውና ወደ ቦይኮቱ ልሂድ። ይህንን ሰው እንድርያስን የዲሲው ግብረሀይል አላየውም እንዴ ሲል አብሮኝ ከነበሩት አንዱ ጠየቀ። የስርአቱ ቀንደኛ አማካሪ በቨርጂንያ ግዛት ውስጥ በግላጭ ተገኝቶ በዋዛ እንደማይታለፍ ሁሉም የሚያውቀው ነው። እንድርያስ እሼቴ እንዲህ በግላጭ እና በነፃነት ያለምንም ተቃውሞ ተቀምጦ በመገኘቱ እድለኛ ነው። ምስል ግብረሀይሉ በ ቦይኮቱ ጉዳይ ላይ ተጠምዷል። በእርግጥም የኳሱ ቦይኮት ነገር ሁሉንም ወገኖች ያግባባ አልመሰለም። ምክንያቱም ፍትሀዊነቱ፣ አድሏዊነቱ እና የፖለቲካ ጠቀሜታው በአግባቡ መፈተሹ አከራካሪ ስለሆነ ይመስለኛል። ይቅርታ የሚጠይቁ አርቲስቶች አሉ፣ ይቅርታ የማይጠይቁ አርቲስቶችም አሉ፣ ይቅርታ ቢጠይቁም ተቀባይነት የማይኖራቸው አሉ ። የዚህን ጉዳይ ቅድመ ሁኔታ እና መስፈርቱ እንዴት እና በማን እንደሚወጣ ግልፅ አይደለም። አልያም ሁሉንም የሚያግባባ አይደለም። ቦይኮት ማእቀብ የሰላማዊ ትግል አንደኛው መንገድ ነው። ሁሉም ተሳታፊ ሲስማማበት፣ ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ሲያመዝን እና ወቅቱን የጠበቀ ሲሆን ደግሞ በተግባር ሲተረጎም ውጤታማ ይሆናል። ማን በምን መስፈርት ቦይኮት እንደሚደረግ ህብረተሰቡ ተስማምቶ ሲፈቅድ እንጂ አንድ ቡድን በግል ጉዳይም ይሁን በቅናት ተነሳስቶ ሲሰራው ችግሩ እዚያ ላይ ይሆናል። በአመክንዮ እንጂ ከጥላቻ ለመሆኑ መስፈርቱ የሁሉም ይሁንታ ሲያገኝ ይመስለኛል። ሀመልማል አባተ ይቅርታ ብላ ትቀላቀል ዘንድ፣ ፋሲል ደሞዝ ከራዳሩ ውጭ ይሆን ዘንድ፣ የአስቴር አወቀ ጉዳይ በዝግ ችሎት ይታይ ዘንድ ከመድረክ ጀርባ ያሉ ጀብዱዎችን ታዝበናል። ጎሳዬ ተስፋዬ በስፖርት ፌዴሬሽኑ ለስራ ተጋብዞ የመጣ ድምፃዊ ነው። ጉዞው ግን ቀላል አልነበረም። አያሌ ውጣ ውረዶችን አልፎ ስራውን ለወገኑ ሊያሳይ ብቅ ሲል እመንገዱ ላይ የኬላ ፍተሻ ገጠመው። እዚያው ላይ ቀጭን ትእዛዝ ተሰጠው አውቆም ይሁን ሳያውቅ ለፈፀመው በደል ይቅርታ እንዲጠይቅ። ጎሳዬ ይህችን ትንሽ የ እለት ፀሎት አይነት
ኳስ እና የ ቦይኮት ፖለቲካ
ሴቶች በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ አነስተኛ በመሆኑ፣ በመጪው አገራዊ ምርጫ የመሳተፍና በላይኛው የስልጣን እርከን የመወከል እድላቸው ሊቀንስ እንደሚችል ተለገፀ። የኢትዮጵያ ሴቶች ማሀበራት ቅንጅት ኢሴማቅ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርአተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ከማብቃት ክፍል ዩኤን ውሜን ጋር በመተባበር፣ የሲቪል ማሀበረሰብ ድርጅቶችን በማጠናከር የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማጎልበት በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የምክክር መድረክ፣ ሲቪል ማሀበረሰብ ድርጅቶች የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲጎለብት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። ሴቶች መራጭ፣ ተመራጭ፣ ታዛቢና አጀንዳ እንዲሆኑ እንፈልጋለን፤ ያሉት የኢሴማቅ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳባ ገብረ መድሀን፣ የሲቪል ማሀበረሰብ ድርጅቶችና በሴቶች ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት ይህንን ሊያደርጉ ይችላሉ ብለዋል። የሲቪል ማሀበረሰብ ድርጅቶች ምርጫ ላይ እንዲሰሩ መፈቀዱን በመግለፅ፣ የሲቪል ማሀበራት በተናጠል ሆነው ተደጋጋሚ የምርጫ ስራ ላይ እንዲሳተፉ በመቀናጀትና መርሀ ግብር በማውጣት ለመስራት ኢሴማቅ ውይይቶችን እያደረገ መሆኑንም አክለዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሴቶች ውክልና አነስተኛ መሆን በፓርላማም ሆነ በካቢኔ ሴቶችን ለማምጣት እክል ሊሆን እንደሚችል የገለፁት ወይዘሮ ሳባ፣ በምርጫ ቦርድ ህግ ላይ የተቀመጠው የፖለቲካ ፓርቲዎች ሴቶችን ሲያሳትፉ የሚገኙት ጥቅም ብዙም ሲያበረታታ ባለመታየቱ፣ ሌሎች መንገዶችን መፈለግ እንደሚገባ አሳስበዋል። ፓርቲዎች ሴቶችን በማሳተፋቸው እንደሚጠቀሙ ማሳወቅና አቅም መስጠትም ያስፈልጋል ብለዋል። ያለው የፖለቲካ ምሀዳር ሴቶችን የማይጋብዝ ከሆነ ሴቶች ተሳተፉ ቢባሉም እንደማይመጡ፣ በመሆኑም ተመራጮች ላይ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፓርቲዎቹ፣ፕሮግራሞቻቸውና የፆታ ፖሊሲዎቻቸው ላይ ጭምር መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። የሴቶች የፖለቲካ ውክልናን አስመልክቶ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በትንሹ ምን ያህል ሴት እጩዎች ማምጣት እንዳለባቸው የምርጫ ህጉ ላይ እንዲገባ ከዚህ ቀደም ሀሳብ ቢቀርብም ተቀባይነት እንዳላገኘ የገለፁት የገለፁት ወይዘሮ ሳባ፣ ይህ ካልሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ላይ መስራትና እንዲያምኑበት ማድረግ እንዲሁም ማበረታቻ መስጠት ይገባል ብለዋል። የሴቶች የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ አለመገኘት እኛም ያሳስበናል፤ በማለትም፣ ሴቷ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ካልገባች መወከል የምትችልበት መድረክ ስለሌለ ፓርቲዎች ሴቶችን እንዲያሳትፉ የጀመሩትን እንቅስቃሴ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
ሴቶች በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ አናሳ በመሆኑ ውክልናቸው ሊቀንስ እንደሚችል ተገለፀ
የፍትህና የነፃነት ጥያቄያችን ደም በማፍሰስ አይቀለበስምፓርቲያችን አንድነት ገዥው ፓርቲ ምርጫ ቦርድና የገዥው ፓርቲ ልሳን በመሆን እያገለገሉ ያሉ ሚዲያዎች በመተባበር ከምርጫ ለማስወጣትና ተለጣፊ አንድነት ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው።የተቃውሞ ሰልፉን ጥር ቀን አመተ ምህረት እንደምናከናውን ለአዲስ አበባ መስተዳድር ብናሳውቅም መስተዳድሩ በ ሰአት ውስጥ በፅሁፍ ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ ሰልፉ እውቅና አለው። መስተዳድሩ ግን የተጣለበትን ሀላፊነት ከመወጣት ይልቅ ወደ ጎን በመግፋት የተወሰኑና የማይታወቁ ግለሰቦች ፔቲሽን ተፈራርመው አምጥተዋል በማለት ብዥታ ለመፍጠር ሞክሯል። ፓርቲያችን ህጉን ጠብቆ ህጋዊ የሆነ ሰልፍ ለማካሄድ ቢሞክርም አሁንም ሀላፊነት በጎደለው ሁኔታ የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል። በተደጋጋሚ እንዳየነው ፖሊስ ደንብ ማስከበር ሲገባው አድሎ ለፈፀመው አካል በመወገን ድብደባ መፈፀሙ ከወገንተኝነት ያልፀዳ መሆኑን እንድናረጋግጥ አድርጎናል።ጥያቄያችን አሁንም የፍትህ የእኩልነትና ህግ እንዲጠበቅ የማድረግ ነው። ገዥው ፓርቲ የመንግስትነት ስልጣኑን በመጠቀም የስልጣን ዘመኑን ለማስረዘም እየከወነ ያለውን ሴራ ማስቆም ነው። ጥያቄያችን የነፃነትና ያልተሸራረፈ ዴሞክራሲ ይረጋገጥ የሚል ነው። ጥቄያችን ምርጫ ቦርድ የገዥው ፓርቲ አጋር መሆኑ ቀርቶ ገለልተኛ ሚናውን ይወጣ የሚል ነው። እነዚህ ጥያቄዎቻችን ደግሞ ደም በማሰስ በድብደባም ሆነ በእስር ፈፅሞ አይቆሙም። ትግላችን የአንድ ፓርቲ የበላይነት አገዛዝ እስከሚያበቃ ድረስ የሚቀጥል ይሆናል።በሚቀጥለው ሳምንትም በተለያዩ ከተሞችና በአዲስ አበባ የሰላማዊ ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን እናሰማለን። ትግሉ ይቀጥላል።ድል የህዝብ ነው
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
አዲስ አበባ፣ ጥር አንድ፣ ሁለት ሺህ ኤፍቢሲ የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሀት ነጋን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዘጠኝ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።የሀገር መከላከያ ሰራዊት የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሀት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን መግለፁ ይታወሳል።የጁንታው አመራሮች የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና ሌሎች የፌደራል ፀጥታ ተቋማት ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ ከተደበቁበት ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሰርጥ ውስጥ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።የጥፋት ቡድኑ አመራሮችን ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ የጁንታው ታጣቂ ሀይል መደምሰሱም በወቅቱ ተገልጿል።በዚሁ መሰረትአንድ የጁንታው ቁንጮ አመራርና የጥፋት ስትራቴጂስት፣ ስብሀት ነጋሁለት ቅዱሳን ነጋ የትግራይ ክልል አፈ ጉባኤ የነበረች የምእራብ እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል መሰለ መሰረት ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የጁንታውን ሀይል ድል አድርጎ አሁን ደግሞ የቡድኑን አመራሮች በቁጥጥር ስር እያወለ መሆኑን ተናግረዋል።ሰራዊቱ በህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻ አንፀባራቂ ድሎችን ያስመዘገበ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሀት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ነው የተናገሩት።የሀያ አራትኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል አማረ በአታ በበኩላቸው፣ ሰራዊቱ ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ቀሪ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከያሉበት እያደነ እንደሚገኝ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ የፋና ድረ ገፅ ይጎብኙ፤ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገፃችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
ስብሀት ነጋን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዘጠኝ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ
አለም ስለአፍሪካ የሚያደርገውን ንግግር ቃና መለወጥ አለበት ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አሳሰቡ።የአፍሪካን እጅግ የገዘፉ እምቅ አቅሞች ለመገንዘብ፣ ግጭቶቿን ለመከላከልና በአግባቡ ለመያዝ ሀገሮች ከአህጉሪቱ ጋር ይበልጥ መተባበር እንዳለባቸው ዋና ፀሀፊው መክረዋል።ግጭቶች እንዳይነሱ በመከላከልና ከተጫሩም የሚያዙበትን ሁኔታ በሚመለከት የአፍሪካ ሀብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው ጉቴሬሽ ለፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ዛሬ ሲናገሩ። የአፍሪካን አቅም ማጠናከር ለአለም አቀፍ የሰላምና የደሀንነት ፈተናዎቻችን ለምንሰጠው ምላሽም ሆነ ለአፍሪካ እራሷን የመቻል ጉዳይ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል ጉቴሬሽ።ሶማሊያ ውስጥ የሸመቀውን አል ሻባብን ጨምሮ በሽብር ፈጠራና በፅንፈኛ ቡድኖች አፍሪካ ላይ የተደቀነውን አደጋም ጉቴሬሽ አንስተዋል።ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
ጉቴሬሽ ለአፍሪካ ድጋፍ እየለመኑ ነው
ሀዳር ፳፯ ሀያ ሰባት ቀን ፳፻፱ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና በሰሜን ጎንደር በነፃነት ሀይሎች እና በአገዛዙ ወታደሮች መካከል የሚካሄደው ውጊያ እንደቀጠለ ሲሆን፣ ያልጠበቀው ጉዳት የደረሰበት አገዛዙ የአርሶአደሮችን ቤቶችን በማቃጠል የበቀል እርምጃ እየወሰደ ነው። በወገራ ወረዳ በእንቃሽ ከትናንት በስቲያ ከአስር በላይ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን፣ ዛሬ ማክሰኞ ደግሞ በጃኖራ አቶ መስፍን የተባሉ ታጋይ ሁለት ቤቶቻቸው የተቃጠሉባቸው ሲሆን፣ ከጠዋት እስካሁን የተኩስ ለውውጥ እየተካሄደ ነው። ባለፉት ሳምንታት በተደረገው ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰው ጉዳት በመከላከያ ላይ መሆኑን የሚገልፁት የአካባቢው ምንጮች፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች አስከሬን ዛሬ መቀበሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሌላ በኩል በቋራ ወረዳ በርካታ ዜጎች መሳሪያ አስረክቡ እየተባሉ እየተደበደቡና እየታሰሩ ነው ። በሰሜን ጎንደር ዞን በ ቋራ ወረዳ በሊገበር ቀበሌ የሚገኙ በርካታ አርሶአደሮች በአካባቢው በተሰማሩት ታጣቂዎች ክፉኛ መደብደባቸውን ፣ አንዳንዶች ደግሞ ወደ ጫካ መግባታቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል። ድብደባውንና እስራቱን ለማምለጥ ጫካ የገቡ አርሶአደሮች ሚስቶች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ፣ በታጣቂዎች ተገደው መደፈራቸውንም የአካባቢው ነዋሪዎች በምሬት ይገልፃሉ። ዋና ሀይሌ እና ደረበ ደማስ የተባሉት አርሶአደሮች በድብደባ ብዛት እጃቸው ከጥቅም ውጭ መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎች፣ ሌላ አርሶአደር ሽፍታ አብልታችኋል በመባላቸው ባልና ሚስቱ ታስረው፣ አምስት ልጆቻቸው ለችግር ተደርገዋል። አገዛዙ ራሱ ያስታጠቃቸውን ሚሊሺያዎች ሳይቀር መሳሪያቸውን መግፈፍ መጀመሩን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ህብረተሰቡ ለታጣቂዎች በግዳጅ ምግብ እንዲያቀርብ እየተደረገ መሆኑንም ነዋሪዎች ገልፀዋል። መሳሪያ የማስፈታቱ እንቅስቃሴ በሌሎችም የክልሉ ዞኖች እየተካሄደ ሲሆን፣ የጦር መሳሪያ እንደሌላቸው የገለፁ አርሶአደሮች እስር ቤቶችን እያጨናነቁ ነው። በሰሜን ጎንደር በአገዛዙ ወታደሮችና በነፃነት ሀይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ አገዛዙ መሳሪያ የማስፈታቱን እንቅስቃሴ አጠንክሮ እንዲገፋበት አድርጎታል።
በሰሜን ጎንደር ውጊያው ቀጥሎአል በርካታ ቤቶችም ተቃጥለዋል
ታዋቂው የኳታር አየር መንገድ ካተሪንግ አገልግሎት፤ አዲስ አለም አቀፍ ካተሪንግ የምግብና የመጠጥ ዝግጅት የሁለት ሺህ ምርጥ የአፍሪካ ምግብ አዘጋጅ በሚል ለሁለተኛ ጊዜ ሸለመ። ከአሁን ቀደምም በሁለት ሺህ በተመሳሳይ መሸለሙ አይዘነጋም። የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባል የሆነው አዲስ አለም አቀፍ ካቴሪንግ፣ ለኢትዮጵያና ለሌሎች አገሮች አየር መንገዶች፣ ለአለም አቀፍ ጉባኤዎችና በአዲስ አበባ አካባቢ ለሚደረጉ ትላልቅ ዝግጅቶች አለም አቀፍ ደረጃ ያለው ምግብ ለማቅረብ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት የተመሰረተ ተቋም ነው። በመላው አለም ከአንድ መቶ ሀምሳ በሚበልጡ መዳረሻዎች የሚበረው ባለ አምስት ኮከቡ የኳታር አየር መንገድ፣ በሚበርባቸው አገሮች አንድ መቶ አምስት የምግብና መጠጥ አዘጋጆች ካተርስ ሲኖሩት በአፍሪካ ወደ ሀያ አራት መዳረሻዎች ይበራል። የተሳፋሪዎችን አስተያየት፣ ወቅታዊ ኦን ታይም አቅርቦት፣ የተሳፋሪዎች ግብረ ምላሽና ከምግብና ከደህንነት ጋር የተያያዙ በርካታ ጉዳዮችን የመዘኑ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፤ ከምግብ አዘጋጆች ናሙና እንደሚወስዱ፣ መሳሪያዎች እንደሚመረምሩ፣ ግንኙነት እንደሚታይ፣ የአለቃ ሪፖርትና የአዘጋጃጀት ቅልጥፍና እንደሚታይ ተገልጿል።አዲስ አለም አቀፍ ካተሪንግ ከኳታር አየር መንገድ በተጨማሪ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለሚጠቀሙ ሌሎች ደንበኞች ለምሳሌ ለጂቢቲ፣ ለግብፅ፣ ለኢምሬትና ለኬንያ አየር መንገዶች አገልግሎት እንደሚሰጥ የጠቀሰው መግለጫው፤ ለቪአይፒ፣ ለኪራይና በግል ለሚንቀሳቀሱ አውሮፕላኖች፡ እንደ አቢሲኒያ ፍላይት ሰርቪስና እንደ ትራንስ ኔሽን ላሉ ትናንሽ በረራዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል። በተጨማሪም፣ አዲስ አለም አቀፍ ካተሪንግ፣ ለጀርመን ኤምባሲ ትምህርት ቤት፣ ለአለም አቀፍ ኮሙኒቲ ትምህርት ቤት፣ ለየን ሀርት አካዳሚና ለሳንፎርድ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በተለያዩ ኤምባሲዎች፣ ባንኮችና ለግል ዝግጅቶች አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።
አዲስ አለም አቀፍ ካተሪንግ የሁለት ሺህ የአፍሪካ ምርጥ ምግብ አዘጋጅ በመባል ተሸለመ
አዲስ አበባ ፣ ሀምሌ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪው የህወሀት ጁንታ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወም፣ ለመከላከያ ሰራዊት እና ለሌሎች የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ለተሰማሩ የፀጥታ አካላት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ እንዲሁም የሰራዊቱ ደጀን መሆናቸውን ለማሳየት በተጨማሪም ሁለትኛው ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሀ ሙሌት በሰላም መጠናቀቅን በማስመልከት ዛሬ በመስቀል አደባባይ ያደረጉት ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል ። መርሀ ግብሩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌደራል ፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት መስራታቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ፖሊስ በዚህ ስራ ላይ ለተሳተፉ እና ሀላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ለመላው የከተማው ነዋሪዎች በፍፁም ጨዋነት፣ በትእግስት እና በተባባሪነት መንፈስ የፀጥታ አካሉን በመደገፋቸው ምስጋና ማቅረቡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን ሀያ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አንድ
በአዲስ አበባ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት ስድስት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ግንባታቸው ተጠናቀው ወደ ስራ የገቡ እና በግንባታ ላይ የሚገኙ አንድ ሺህ አምስት መቶ ስልሳ አራት የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መሰማራታቸው ተገለፀ። በዚህም የቻይና ኩባንያዎች በፕሮጀክቶች የቁጥር መጠንም ሆነ ባፈሰሱት መዋእለ ነዋይ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ቀዳሚዎቹ እንደሆኑ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል። እነዚህ የቻይና ኩባንያዎቹ ከፈረንጆቹ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት እስከ ባለፈው የፈረንጆቹ መጋቢት ወር ሁለት ሺህ ሀያ ድረስ የተመዘገቡ መሆናቸውን በኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መኮንን ሀይሉ ለሺንዋ ተናግረዋል። ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ስልሳ አራት ኩባንያዎቹ መካከል ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሰባትቱ ስራ ሲጀምሩ፥ አንድ መቶ ሰማኒያ ስድስትቱ ደግሞ በትግበራ ሂደት ላይ የሚገኙ ናቸው ብለዋል። ቀሪዎቹ ሶስት መቶ ዘጠና አንድ ደግሞ በቅድመ ትግበራ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ከአጠቃላይ ፕሮጀክቶቹ ውስጥ አንድ ሺህ አንድ መቶ ስላሳ ሶስት ፕሮጀክቶች በማምረቻው ዘርፍ የተሰማሩ ሲሆን ሌሎች በሆቴል፣ ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ኮሙዩኒኬሽ እና ግንባታ ዘርፎች የተሰማሩ ናቸው። እነዚህ ፕሮጀክቶች አርባ ሶስት ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ወይም አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ዶላር ሀብት ያስመዘገቡ መሆናቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።
አርባ ሶስት ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ ከአንድ ሺህ በላይ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ተሰማርተዋል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ከየመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አዋዳህ ቢን ሙባረክ ጋር ተወያዩ። በውይይቱ አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በሁለቱ ሀገራት መካከል ዘመናትን ያስቆጠረ ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች እንደነበሩ ጠቅሰው በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር ስራዎች እንደሚሰሩ አመላክተዋል። የየመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር አህመድ አዋዳህ በበኩላቸው በየመን በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው እየሰሩ እንደሚኖሩ ገልፀዋል። ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ የተጀመረውን ጥረት መንግስታቸው እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል። እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት በተለይ በአፍሪካ ቀንድ የሚስተዋለውን ሽብርተኝነት ለመከላከል ያላውን ፅኑ ፍላጎትና ተነሳሽነት መንግስታቸው እንደሚደግፍና ለዚህም አድናቆት እንዳለው መግለፃቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ከየመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ጥር ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የሲቪክ ማህበራት ለመጪው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ማህበረሰቡን የማንቃት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ምሁራን አሳሰቡ። ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስተያየታቸውን የሰጡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፓለቲካ ሳይንስ መምህር ዶክተር ደመቀ አጪሶ፥ መጪው ምርጫ ተአማኒ፣ ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን የዜጎችን ሰላም ማስከበር ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ አንስተዋል። ማህበረሰቡ የዜጎችን ሰላም የሚያውኩ ድርጊቶችን ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ አለበት ያሉት ዶክተር ደመቀ፥ የፀጥታ አካላትም ተገቢው ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር ሽመልስ አሻግሬ በበኩላቸው፥ ዜጎች በምርጫ ሂደት ላይ የሚከናወኑ የሀሳብ ፍጭቶችን ምክንያታዊ በሆነ መልኩ መገንዘብ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል። ለዚህም በሀገሪቱ የሚገኙ የሲቪክ ማህበራት ዜጎች ስለ ምርጫ ያላቸውን ግንዛቤ የማስፋት ስራ ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያሰራጯቸውን መረጃዎች በትክክለኛ እና በሚመለከታቸው አካላት ማስተላለፍ ያለባቸው መሆኑንም አንስተዋል። ዜጎች መረጃዎችን በጥንቃቄ ማዳመጥ እና በሰከነ መልኩ መረዳት ይጠበቅባቸውል ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር ሽመልስ፥ በምርጫው ምህዳር የሚገቡ አካላት የያዟቸውን ፕሮግራሞችና አላማዎች በሚገባ ሊያጤኑ እንደሚገባም ጠቁመዋል። በቅድመ ምርጫም ሆነ በምርጫው ወቅት ህዝቡን የማንቃት ሀላፊነት ያለባቸው የሲቪክ ማህበራትም፥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፖሊሲያቸውን እና ፕሮግራማቸውን የሚያጋሩበት መድረክ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። ከለውጡ በኋላ የሲቪክ ማህበራት የሚሰሩበት ህግ መሻሻልን እንደ ጥሩ መንደርደሪያ የሚያነሱት ፕሮፌሰሩ፥ በመጪው ምርጫ ጠንካራ ተሳትፎ ለማድረግ የሚያመች ምህዳር መኖሩን አንስተዋል። በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል አንትሮፖሎጂ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ወርቁ ያእቆብ፥ የሲቪክ ማህበራት መሰረታዊ የፍትሀዊነት መርሆችን ጠብቀው ለሁሉም የምርጫ ተሳታፊዎች እኩል ምህዳርን ሊከፍቱ እንደሚገባቸው ገልፀዋል። ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ሰላማዊ፣ ተአማኒ፣ ፍትሀዊ፣ አሳታፊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ህብረተሰቡም ሆነ የሲቪክ ማህበራት በንቃት እንዲሳተፉ ምሁራኑ ጥሪ አቅርበዋል። በሀይለኢየሱስ መኮንን
የሲቪክ ማህበራት ለመጪው ምርጫ ማህበረሰቡን የማንቃት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ምሁራን
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት ሶስት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበለት ህገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የሚመለከታቸውን ተቋማት እና ባለሙያዎች አስተያየት እንዲያቀርቡ ጥሪ አድርጓል።ጉባኤው ባለሙያዎች ተቋማት የሚሰሙበትን መድረክ ማዘጋጀቱንም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።ወይዘሮ መአዛ እርምጃው የሂደቱን እና የውጤቱን ተአማኒነት እንደሚያሳድግም ጠቅሰዋል።ከዚህ ባለፈም የህገ መንግስታዊ ስርአት ባህል በኢትዮጵያ እንዲዳብር ይረዳል የሚል እምነት መኖሩንም ጠቁመዋል።ከሙያ አስተያየት ተቀባይነት ጋር በተያያዘ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በቀረበው የህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ምላሽ ላይ ለሚሰጠው ውሳኔ ወይም የውሳኔ ሀሳብ ባለሙያዎች የሚያቀርቡትን የሙያ አስተያየት የመመልከት፣ በግብአትነት የመጠቀም ወይም በማጣቀሻነት ለመውሰድ አይገደድም።ከዚህ ባለፈም ጉባኤው የሙያ አስተያየት የሚያቀርቡ ባለሙያዎችን ለመስማት ወይም በማናቸውም መንገድ ማወያየት ከፈለገ ሊጋብዛቸው እንደሚችል የተጠቀሰ ሲሆን፥ ይህን የማድረግ ግዴታ እንደሌለበት ተገልጿል።የዜና ሰአት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልእክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ብለው ይላኩ።
ጉባኤው ከምክር ቤቱ በቀረበለት ህገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የሚመለከታቸው አካላት አስተያየት እንዲያቀርቡ ጥሪ አደረገ
የምስራቅና የደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ ኮሜሳ ባንክ እየተባለ የሚታወቀው የንግድና የልማት ባንክ ፕሬዚዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት አቶ አድማሱ ታደሰ፣ የአፍሪካ የአመቱ የባንክ ባለሙያ የተሰኘውን የአፍሪካ ልማት ባንክ ሽልማት ተቀዳጅተዋል። በኢኳቶሪያን ጊኒ፣ ማላቡ ከተማ በተካሄደው የአፍሪካ ልማት ባንክ አመታዊ አቶ አድማሱ ብቻም ሳይሆኑ፣ የሚመሩት ባንክም የአመቱ ምርጥ ባንክ የተሰኘበትን ሽልማት ያገኘ ሲሆን፣ ለሞዛምቢክ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት በሰጠው ብድር፣ ክሬዲት አግሪኮል ከተሰኘው ባንክ ጋር በጋር እንዲሁም ለኬንያ ባስገኘው የአንድ ነጥብ ሁለትአምስት ቢሊዮን ዶላር የውጭ የቦንድ ብድር ሶቨሪን ቦንድ ሁለት ሽልማቶች አግኝቷል። ሞዛምቢክ የስምንት ቢሊዮን ዶላር ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ፕሮጀክት ይፋ አድርጋለች። ለዚህ ፕሮጀክት ከሚያስፈልገው ፋይናንስ ውስጥ ከዘጠና ሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆነውን አቶ አድማሱ የሚመሩት የንግድና የልማት ባንክ ለማቅረብ ተስማምቷል። እ ኤ አ በሁለት ሺህ አንድ ቢሊዮን ዶላር የነበረው የንግድና የልማት ባንክ፣ በአሁኑ ወቅት ከስድስት ቢሊዮን ዶላር ካፒታል ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን፣ የተበላሸ የብድር መጠኑም ከሶስት በመቶ በታች በመሆኑም ጭምር ጤናማና በልማት ባንኮች ከሚታየው የበለጠ ዘመናዊነትን መላበስ የቻለ ባንክ እየተባለ የሚሞከሸው ይህ የኮሜሳ ባንክ፣ እያሳየ ላለው ውጤታማነት በዋናነት የሚጠቀሱት አቶ አድማሱ ናቸው። አቶ አድማሱ በፋይናንስ ኢንዱስትሪው መስክ በአፍሪካ ስመጥር ከሚባሉ ባለሙያዎች ተርታ የሚመደቡ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ፣ በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በልዩ ልዩ የሀላፊነት መደቦች ማገልገላቸውንም ግለ ማሀደራቸው ያሳያል። በአገር ቤትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ሀበሻ ሲሚንቶ፣ ጋቴፕሮ የብረት ውጤቶች ማምረቻ፣ እንይና ሌሎችም ኩባንያዎች ከባንኩ በየጊዜው ብድር ማግኘት የቻሉት በአብዛኛው አቶ አድማሱ ባንኩን ማስተዳደር ከጀመሩ ወዲህ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በርካታ መስኮች በአንድ ጊዜ እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማቅረብ የሚቻልባቸው ፕሮጀክቶች እንዳሉ በአንድ ወቅት ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ መናገራቸው ይታወሳል። የፋሽን አልባሳት አምራችና የወጣት ዲዛይነሮች መፍለቂያ እየሆነ ከመጣው አፍሪካን ሞዛይክ መስራችና የቀድሞዋ አለም አቀፍ ሞዴሊስት የአና ጌታነህ የትዳር አጋር የሆኑት አቶ አድማሱ፣ ከባለቤታቸው ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ህፃናት ፈንድ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ውስጥም ተሳትፎ ያደርጋሉ። በአብዛኛው የባለቤታቸው የአና ጌታነህ ጥንስስ የሆነው ይህ የበጎ አድርጎት ተቋም ወላጆቻቸውን ያጡና የተቸገሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናትን በመንከባከብና በማስተማር ይታወቃል።
ኢትዮጵያዊው የኮሜሳ ባንክ ፕሬዚዳንት የአመቱ የባንክ ባለሙያ የተሰኘውንና እንደ ኦስካር የሚታየውን ሽልማት ተቀዳጁ
ለህዝብ ጥቅም ሲባል ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ስምንት አመተ ምህረት ጀምሮ ከአዲስ አበባ ከተማ የማስፋፊያ ቦታዎች ሲፈናቀሉ የቆዩ አርሶ አደሮች፣ ባቋቋሙት ኮሚቴ አማካይነት ለከንቲባ ድሪባ ኩማ ባቀረቡት አቤቱታ፣ እነሱ የተፈናቀሉባቸው አብዛኛዎቹ ቦታዎች ለአመታት ታጥረው ያለስራ የተቀመጡ በመሆናቸው ኪሳራው ተሰልቶ እንዲከፈላቸው ጥያቄ አቀረቡ።አርሶ አደሮቹ ታሀሳስ አስር ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ለከንቲባ ድሪባ በፃፉት አቤቱታ፣ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ስምንት አመተ ምህረት ጀምሮ ለህዝብ ጥቅም ሲባል መፈናቀላቸውን ገልፀዋል። ነገር ግን አርሶ አደሮቹ ከቀያቸው በመፈናቀላቸው ሀብትና ንብረት አልባ ሆነው ሲቀመጡ የተባለው የህዝብ ጥቅም ሳይከበር፣ የታለመው ልማትም ሳይመጣ መሬቱ ታጥሮ ያለ ስራ መቀመጡ እንዳስቆጫቸው ገልፀዋል።በዚህ መሰረት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች እስካሁን ድረስ ቢያለሙ ሊያገኙ የሚችሉትን ሀብት፣ መንግስት በቅጣት መልክ መሬቱን ከወሰዱ አካላት ተቀብሎ እንዲከፍላቸው ጠይቀዋል።እስከ ዛሬ ከመሬታቸው ባይፈናቀሉ፣ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በልማት ምክንያት ቢነሱ ሊከፈላቸው የሚችለውን የካሳ ክፍያ አርሶ አደሮቹ አስልተው ለከንቲባው አቅርበዋል።በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራኒዮ፣ በቦሌ፣ በአቃቂ ቃሊቲና በየካ ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ አርሶ አደሮች ኮሚቴ አቋቁመዋል። በኮሚቴ አባላት አቶ ተስፋ ረጋሳ፣ አቶ ተሾመ ፈይሳ፣ አቶ ሰቦቃ ለታና አቶ መገርሳ ሚደቅሳ ፊርማ ለከንቲባ ድሪባ የቀረበው አቤቱታ እንደሚገልፀው፣ አርሶ አደሮችን በድጋሚ ለማቋቋም የተያዘው እቅድ ከዚህ ጋር የተቆራኘ መሆኑ መልካም ነው።የአርሶ አደሮች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋ ረጋሳ ለሪፖርተር እንደገለፁት፣ መንግስት ሊመረት የሚችለውን ሰብል፣ የእንስሳት ተዋፅኦና በአሁኑ ወቅት አርሶ አደሩ በልማት ቢነሳ የሚከፈለውን የወቅቱ የገበያ ዋጋ አስልቶ፣ መሬቱን ሆን ብለው በመያዝ ወደ ልማት ያልገቡ አካላትንም በህጉ መሰረት በመቅጣት ከቦታው ላይ ለተፈናቀሉና በችግር ውስጥ ለሚገኙ አርሶ አደሮች መክፈል ይኖርበታል።ኮሚቴው ባቀረበው አቤቱታ ለአብነት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት አመተ ምህረት የተሰጠ ስልሳ ሄክታር መሬት፣ ከሪቬራ ሆቴል ፊት ለፊት ለአፍሪካ ሀብረት የተሰጠ ሀያ ሄክታር፣ ለቤቶች ልማት የተሰጠ ስምንት መቶ ሰማኒያ ስምንት ነጥብ ስድስትሁለት ሄክታር መሬት፣ ኮዬ አካባቢ ለተለያዩ በርካታ ልማቶች የተሰጡ መሬቶች ታጥረው ይገኛሉ ብሏል።ቦሌ ክፍለ ከተማ ለውሀና ፍሳሽ የተሰጠ አንድ መቶ አምስት ሄክታር፣ ለአይሲቲ ፓርክ የተሰጠ አርባ ሄክታር፣ ለአየር መንገድ ማስፋፊያ የተሰጠ አርባ ሄክታር መሬት፣ ከ እስከ ሀያ ሶስት አመታት ታጥረው ያለ ስራ መቀመጣቸው ተጠቁሟል።የአርሶ አደሮቹ ኮሚቴ ለአብነት ለካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠው ስልሳ ሄክታር መሬት በሄክታር አስር ኩንታል ቢመረትበት አንዱ ኩንታል በአንድ ስምንት መቶ ብር ቢሸጥ ጠቅላላ ዋጋው ሀያ ስምንት ስምንት መቶ ብር እንደሚሆን፣ ይህም በ አመታት ሲባዛ ከ ሚሊዮን ብር በላይ ሊገኝ እንደሚችል በማስላት ኪሳራው ለተፈናቃይ አርሶ አደሮች ሊከፈል እንደሚገባ አበክሮ ጠይቋል።ከዚህ በተጨማሪም ቀደም ሲል አንድ ካሬ ሜትር መሬት የሚከፈለው ሀያ ዘጠኝ ነጥብ ሶስትአንድ ብር ነበር። አሁን ደግሞ በተደረገው መጠነ ሰፊ ውትወታ አስተዳደሩ የአንድ ካሬ ሜትር መሬት ካሳ በካሬ ሀምሳ አራት ብር አሳድጓል።ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ወቅት ቢነሱ ሊያገኙ የሚችሉትን ገንዘብ በከንቱ ማጣታቸውን በመጥቀስ፣ የከተማው አስተዳደር ጉዳዩን በድጋሚ ሊያጤን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።በአጠቃላይ የአርሶ አደሮቹ ኮሚቴ በልማት ስም ከአርሶ አደሩ የተወሰዱ የእርሻ መሬቶች ወደ ልማት እስኪገቡ ድረስ ገበሬው እንዳያርስ መከልከል አግባብ አለመሆኑን፣ መሬቱን በልማት ሽፋን አጥረው ለበለጠ ትርፍ ያቆዩ አካላት የተፈጠረውን የካሳ ክፍያ ልዩነት እንዳኪፍሉ መደረግ አለበት ይላል። ይህ አሰራር የህግ ማስከበር አካል እንዲሆን ከማድረግ ባሻገር የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ነው፤ ሲሉ አቶ ተስፋ ለሪፖርተር ተናግረዋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተፈናቃይ አርሶ አደሮችን በድጋሚ ለማቋቋም የፕሮጀክት ፅህፈት ቤት አቋቁሟል። የፕሮጀክት ፅህፈት ቤቱ በዚህ አመት ሀያ ሺህ ተፈናቃይ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም የስምንት መቶ ሰማኒያ አንድ ሚሊዮን ብር በጀት መያዙን ለማወቅ ተችሏል።እስካሁን በተሰበሰበው መረጃ በአዲስ አበባ አንድ መቶ ስላሳ አራት ሺህ ተፈናቃይ አርሶ አደሮች የሚገኙ ሲሆን፣ እነዚህንም በአምስት አመታት ውስጥ በድጋሚ ለማቋቋም እቅድ መያዙን መዘገባችን ይታወሳል።
ተፈናቃይ አርሶ አደሮች ለአመታት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎቻቸው ኪሳራ ተሰልቶ ካሳ እንዲከፈላቸው ጠየቁ
አዲስ አበባ፣ የካቲት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በቀጣዮቹ ስምንት አመታት ሀያ ሚሊየን ወጣቶችን ለማሰልጠን እና አስር ሺህ ወጣቶችን በአሰልጣኞች ስልጠና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ የለውጥ ትውልድ የተሰኘ ስምምነት ተፈረመ። ስምምነቱ የተፈረመው በሴቶችና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ብሬክ ስሩ ትሬዲንግ አ ማ ድርጅት መካከል ነው። የሴቶችና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ዶክተር እንደገለፁት ሀገራችንን ወደ ብልፅግና ለማሻገር በሚደረገው ጥረት የወጣቶችን አስተሳሰብ በማልማት የለውጥ ትውልድ መፍጠር ዋነኛ መንገድ ነው። ተከታታይነት ያላቸው የሰብእና ልማት፣ የአስተሳሰብ ለውጥ የልቦና ውቅርን የሚያስተካክሉ ስልጠናዎች መስጠትም ሀገራችን ለጀመረችው የለውጥ ጉዞ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ስልጠናዎችና መርሀ ግብሮችም ሚኒስቴሩ ከብሬክ ስሩ ትሬዲንግ አ ማ ጋር በመተባበር እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። የብሬክ ስሩ ትሬዲንግ የቦርድ ስብሳቢ ነፃነት ዘነበ በበኩላቸው የፕሮጀክቱ ዋና አላማ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ማሀበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶችን ማብቃት መሆኑን አስገንዝበዋል። ስልጠናውም በቀጣዮቹ ስምንት አመታት በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እንደሚተገበር ጠቁመው በዚህም ሀያ ሚሊየን ወጣቶችና አስር ሺህ ወጣቶች በአሰልጣኞች ስልጠና ተደራሽ ይሆናሉ ብለዋል።
ሀያ ሚሊየን ወጣቶችን በስልጠና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ስምምነት ተፈረመ
ሁለት መቶ ሰሞኑን ብዙዎች ስለሀገርና ህዝባቸዉ በመጨነቅ አሁን ማድረግ ያለብን ምንድን ነዉ ሲሉ ይደመጣሉ። ትክክል ይመስሉኛል አዎን አሁን ምን እናድርግ ጥያቄዉ ግን በዚህ መቆም የሚችል አይመስለኝም። ምክንያቱም ከጠቅላዩ የዛሬዉ መግለጫ በስተጀርባ እኔን ጨምሮ ብዙዎች የሰሙት የድረሱልኝ ጩኸት ለሰዉዬዉ ምን እናድርግላቸዉ የሚልን ጥያቄ ይዞ በመምጣት ዛሬ መልሱን መፈለግ የእኛ እዳ ሆኗል። ዶክተር አብይ አህመድን ያህል በፍቅር የህዝብ ድጋፍ ሊያሰባስብ የቻለ መሬ በዘመኔ በየትኛዉም የመሬት ጠርዝ እንደነበር አላስታዉስም። በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት መጀመሪያ ላይ እንግሊዝ በጀርመን ልትወረር ስትልና በሀላም የእንግሊዝ ከተሞች የጀርመን አዉሮፕላኖች በሚጥሏቸዉ ቦንብ ሲደበደቡ ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት ቸርችል የነበራቸዉን ፍቅር በበለጠ የወያኔ በደል ለሀያ ሰባት አመታት ያንገሸገሸዉ ኢትዮጵያዊ ለዶክርተር አብይ ዘርግፎ ነበር። የዛሬ ሰባ አምስት አመታት ገደማ ቸርችል ህዝባቸዉ ላይ የናዚ ቦንብ ሌት ተቀን እየዘነበ የህዝባቸዉ መሪና ተስፋ መሆን ሲችሉ የእኛዉ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ግን ላለፉት ጥቂት ወራት በጥቂት ወንጀለኞች ሴራ ተጠልፈዉ ተጎሳቁለዉ ጥቁርቁር ብለዉ በሰዉ ልጅ እኩይ ባህሪ አዝነዉ ተበሳጭተዉ ለወትሮዉ ደመቅመቅና ፈካ ብለዉ የምናያቸዉ ጎልማሳ የለበሱት ኮት ሳሞራ የለበሰዉ ይመስል ከትከሻቸዉ ላይ ሊወርድ ሲንሸራተት ተዘናግተዉ ለተመለከተ ሁሉ እኛ ብቻ ሳንሆን እሳቸዉም ቸርችልን እየፈለጉ መሆኑን በቀላሉ የሚረዳ ይመስለኛል። ስለዚህ ምናልባት ቸርችልን ልንሆንላቸዉ ባንችል ቸርችልን ማፋለጉ ሳይበጀን አይቀርም። አቶ ታዬ ደንድአ ከሁለት ቀናት በፊት የአንቦን ፀረ አብይ ሰልፍ አያይዘዉ እንደገለፁት፤ ጠማሪ ስዩም ተሾመም ያንን አስታኮ ሊያብራራ እንደሞከረዉ የጃዋር ቅጥረኛ ቄሮዎች የኦሮሚያ ፖሊስ ጥቂት አባላትን ጨምሮ የስዉር አደረጃጀትና እንቅስቃሴ ከጠቅላዩ ቸልተኛነት ጋር ተዳምሮ ነገሮችን በማወሳሰቡ ሰዉዬውን አስደንግጧቸዋል። ማስደንገጥ ብቻ ሳይሆን አስፈርቷቸዋል። በነገራችን ላይ ታዬ ደንዷም ሶስት አራት የሚሆኑ በጥፋት መዋቅሩ ዉስጥ የነበሩ በማለት ከአምቦ ልሰልፍ ጋር በማያያዝ ነገሩን በጣም አሳንሶ ማየቱ ለምን እንደሆን ባላዉቅም የአምቦን ጨምሮ በርካታ የኦሮሚያና አማራ ከተሞች ዉስጥ በቄሮ ስም ኦዴፓ አደራጅቷቸዉ ከነበሩ በርካታ ተወርዋሪ አመፅ ቀስቃሾች ዉስጥ ቢያንስ ከሁለት መቶ በላይ ስልካቸዉን በተጠንቀቅ ይዘዉ የሚጠብቁ የጅዋር ምልምሎች አሉ። እንደ መረጃ ምንጬ አባባል ከዞንና ከወረዳ ባለስልጣናት ጀምሮ የፖሊስ አባላት የመከላከያ አባላት የፓርላማ አባላት በቆንፅላ ደረጃ በተለያየ ሀገር ያሉ አባላትን ያካትታል። እነኚህን አደገኛ የሚያደርጋቸዉ ጥቂቶቹ ከዶክተር አብይ ጋር በጣም የቀረበ ግኑኝነት ያላቸዉ በመሆናቸዉ ነዉ። የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ በከፍተኛ የመንግስት ስልጣንና በጃዋር መዋቅር ዉስጥ ላይ ያሉ ጥቂት ተዋናዬችን ያዉቃል። ስለዚህ ይህን መረብ ለመበጣጠስ እኛ ኢትዮጵያዊያን ምን በማድረግ ሀገራችን እንታደግ የሚለዉ ነዉ አሁኑኑ መመለስ ያለበት ጥያቄ። ምናልባት ሰዉየዉን መታደግ ጥሩ አማራጭ ላይሆን ይችላል የጃዋርን ሰንሰለት መበጣጠስ ግን አማራጭ አይኖረዉም። ሁለት መቶ
የጠቅላዩ የድረሱልኝ ጩኸት ዶክተር መኮንን ብሩ
የማሀፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ለሀምሳ አምስት ሶስት መቶ አርባ ሁለት ልጃገረዶች ሊሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ። ክትባቱ የሚሰጠው በሁለት ሺህ አመተ ምህረት የመጀመርያውን የማሀፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ወስደው፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሁለተኛ ዙር ያልወሰዱና በዘንድሮ አመት ለሞላቸው ታዳጊዎች መሆኑን፣ ጥር አምስት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዮሀንስ ጫላ ዶክተር እንደተናገሩት፣ ክትባቱ የሚሰጠው እድሜያቸው አመት ለሆናቸው በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በጤና ጣቢያ ውስጥ ነው። በዚህ አመት አመት የሞላቸውና ክትባቱን ለመጀመርያ ጊዜ የሚወስዱ ልጃገረዶች የሚከተቡም ይሆናል። የመጀመርያ ዙር ክትባትን የሚያገኙት ሀያ ስምንት ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ልጃገረዶች ሲሆኑ፣ ሀያ ሰባት ሀምሳ አንድ የሚሆኑ ደግሞ ሁለተኛ ዙር የሚወስዱ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የማሀፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከጥር አራት እስከ ጥር አስር ቀን በዘመቻ እንደሚሰጥ ሀላፊው ተናግረዋል። እድሜያቸው አመት የሞላቸው ልጃገረዶች ክትባቱን በትምህርት ቤቶችና ከትምህርት ውጪ ያሉት ደግሞ በጤና ጣቢያዎች እንዲያገኙ ይደረጋልም ብለዋል። የኮቪድ ወረርሽኝ ክትባት የወሰዱ ታዳጊዎች እንዳሉ የጠቆሙት ዮሀንስ ዶክተር ፣ እነዚህ ታዳጊዎች ልጃገረዶች ክትባቱን ከወሰዱ ከ ቀን በኋላ የማሀፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባትን እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክትባት ወስደው ቀን ያልሞላቸው ልጃገረዶች የማሀፀን በር ካንሰር ክትባቱን እንዲያገኙም ተመቻችቷል ብለዋል። እድሜያቸው አመት ለሞላቸው ልጃገረዶች ብቻ መስጠት ያስፈለገው፣ ለማሀፀን በር ካንሰር ተጋላጭ ከመሆናቸው በፊት ክትባቱን በመስጠት ትውልድን መታደግ ስለሚጠበቅ መሆኑን አክለዋል። የ አመት በሞላቸውን ላይ ብቻ ትኩረት የተደረገውም የክትባት እጥረት በመኖሩ መሆኑን፣ የ እና የ አመት ታዳጊዎችንም መከተብ ያስፈልግ እንደነበር አስረድተዋል። ለማሀፀን በር ካንሰር በይበልጥ ተጋላጭ የሚሆኑበት እድሜ አመት ሲሞላቸው መሆኑን፣ ከዚህ እድሜ በላይ ላሉ የሀብረተሰብ ክፍሎች የማይሰጠው መጀመርያ ምርመራ ማድረግ ስላለባቸው መሆኑን አብራርተዋል። ዮሀንስ ዶክተር ፣ እነዚህ ልጃገረዶች መጀመርያ ቅድሚያ የተሰጣቸው ፆታዊ ግንኙነት ከመጀመራቸው በፊት ክትባቱን ካገኙ ለቫይረሱ ተጋላጭ ስለማይሆኑ ነው፤ ብለዋል። የማሀፀን በር ካንሰር በአለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ፣ ሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች በአራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል። የአለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ ሂውማንፓፒሎማ ቫይረስ ኤችፒቪ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ቫይረስ ነው። ቫይረሱ ለማሀፀን በር ካንሰር ዋነኛ አጋላጭ ነው። ከዘጠና ዘጠኝ በመቶ በላይ የሚሆነው የማሀፀን በር ካንሰር ከሂውማንፓፒሎማ ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚመጣ ሲሆን፣ በወቅቱና በጊዜው ክትባት ከተወሰደ ቫይረሱን በቀላሉ መከላከል ይቻላል። በዚህ ቫይረስ በየአመቱ ሰባት የሚሆኑ ሴቶች ሲጠቁ፣ ከእነዚህ ውስጥ አምስት የሚሆኑት ደግሞ ይሞታሉ። እየተስፋፋ የመጣውን የማሀፀን በር ካንሰር ለመከላከል በአገር አቀፍ ደረጃና በአዲስ አበባ ከተማ ከሁለት ሺህ አመተ ምህረት ጀምሮ ክትባቱ ሲሰጥ ቆይቷል። የማሀፀን በር ካንሰር ክትባቱ አመት ለሆናቸው ልጃገረዶች በአመት ሁለት ጊዜ በየስድስት ወራት ልዩነት የሚሰጥ ሲሆን፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ሶስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን በአዲስ አበባ ከተማ ደግሞ አንድ መቶ ሀምሳ ለሚሆኑ ልጃገረዶች ክትባቱ መሰጠቱ ተገልጿል።
የማሀፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከሀምሳ አምስት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ልጃገረዶች ሊሰጥ ነው
የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ነፃ አውጪ ግንባር ኤታ ማጆር ሹም ጄኔራል ኦያይ ደንግ አጃክ፣ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ለሰላም ስምምነቱ ተገዢ እንዲሆኑ ወይም ከስልጠናቸው ይለቁ ዘንድ ጫና እንድታደርግ አሳሰቡ።ካለፈው ሀሙስ የካቲት ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የነበሩት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለ ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሁለትዮሽና በቀጣናው ሰላምና ጉዳዮች ላይ መክረዋል።በነሀሴ ወር ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት በሁለቱም የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች መካከል የተፈረመው ስምምነት ተግባራዊ ሳይሆን ከአመት በላይ ቆይቷል። የሰላም ሂደቱን የመራው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስት ድርጅት ኢጋድ ሊቀመንበር የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ለስምምነቱ አለመፈፀም ምክንያት የሆኑት በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ላይ ግፊት እንድታደርግ ጄኔራሉ አጥብቀው ጠይቀዋል።ጄኔራል ኦያይ የነፃ አውጪውን ጦር ግንባር በበላይነት የመሩ ሲሆኑ፣ አገሪቱ ነፃነቷን ከተቀዳጀች ጀምሮም በተለያዩ ከፍተኛ ሀላፊነቶች አገልግለዋል። በተለይ የብሄራዊ ደሀንነቱን፣ ቀጥለውም ብሄራዊ ኢንቨስትመንቱን በሚኒስትርነት የመሩት ጄኔራሉ፣ በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተጠርጥረው ለስድስት ወራት በእስር ካሳለፉ ሚኒስትሮች መካከል ናቸው። በአሁኑ ወቅት በደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ጦርነት እንዳለና የአገሪቱ ህዝብ ለስደት እየተዳረገና እየተሰቃየ መሆኑን ይናገራሉ።በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ውጊያ መኖሩንና ሰላም ፈፅሞ የጠፋ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ እንዲገነዘብ የጠየቁት ጄኔራል ኦያይ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እንደወዳጅ ጎረቤት በፕሬዚዳንቱ የሀሰት ንግግር ሳይሞኝ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።ጄኔራል ኦያይ በአሁኑ ወቅት ከዋና ተፋላሚው ከዶክተር ሪክ ማቻር ጋር በመሆን ፕሬዚዳንቱን የሚቃወሙ ሲሆኑ፣ ይህንን የተናገሩት ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። ጄኔራሉ እንደሚሉት፣ የስምምነቱ አካል የሆነው ብሄራዊ ውይይት በገለልተኛ አካል እንዲመራና ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የድርድሩ አካል እንዲሆኑ፣ ወይም ከስልጣናቸው እንዲወርዱና በአገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ኢትዮጵያ የበኩሏን ሚና እንድትጫወት ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህ ውጪ ደቡብ ሱዳን መንግስት አልባ የመሆን እድሏ ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ።ይህ በዚህ እንዳለ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ሰሞኑን በኢትዮጵያ ይፋ ጉብኝት አድርገዋል። ባለፈው አርብ የካቲት ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ዘጠኝ የትብብር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። በስምምነቶቹ መሰረት የሁለት መንገዶች ግንባታ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ተብሏል። በኢነርጂ፣ በድንበር አካባቢ የንግድ ፕሮቶኮል፣ ለመደበኛ ንግድ፣ ለኮሙዩኒኬሽን፣ ለኢንፎርሜሽንና ለሚዲያ ደግሞ የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል። ሁለቱም አገሮች በአሁኑ ወቅት ያላቸው መልካም ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል። በፀጥታ፣ በንግድ፣ በልማትና በመሰረተ ልማት የበለጠ አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
የደቡብ ሱዳን ነፃ አውጪ ግንባር የቀድሞ ኤታ ማጆር ሹም ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ላይ ግፊት እንድታደርግ አሳሰቡ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም አምስት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ከአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ በአንድ ወር ብቻ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከሰባ አንድ ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ። የአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ የህዳሴ ግድብ ዋንጫን ለአራዳ ክፍለ ከተማ ያስረከበ ሲሆን በዚህ ወቅት የአዲስ አበባ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ይህን አስመልክቶም አቶ ጃንጥራር አባይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሉት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሁለት ሺህ አመተ ምህረት በድፕሎማሲው በኩል ስኬት አስመዝግበናል፣ የመጀመሪያውን የውሀ ሙሌትም በድል አጠናቀናል። ያም ሆኖ በመጪው ሶስት አመታት ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ አሁንም የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ያሉት አቶ ጃንጥራር የተፈጠረውን ህዝባዊ መነቃቃት አስጠብቀን በሁለት ሺህ አመተ ምህረት የግድቡን ወሳኝ ምእራፍ እንሰራለን ነው ያሉት። ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ የታዘብኩትም ይህንኑ ነው ያሉ ሲሆን በክፍለ ከተማው በሁሉም ወረዳዎች የታላቁን ህዳሴ ዋንጫ በማዘዋወር ከሀምሌ ስላሳ ሁለት ሺህ ጀምሮ ከሰባ አንድ ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል ብለዋል። ለዚህም መላው የክፍለ ከተማ ነዋሪዎችን ፣ አመራሮችን እና ባለ ሀብቶችን አመስግነዋል። ዋንጫውንም ተረኛ የሆነው አራዳ ክፍለ ከተማ ተረክቧል። የዜና ሰአት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልእክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ብለው ይላኩ።
ለታላቁ ህዳሴ ግድብ በልደታ ክፍለ ከተማተማ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከሰባ አንድ ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ ስምንት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት አመራሮች በሀገር ህልውና ማስከበር ዘመቻ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ የዘማች ቤተሰቦች በዛሬው እለት ድጋፍ አድርገዋል። አመራሮቹ በአዲስ አበባ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ ሁለት መቶ ሀያ የዘማች ቤተሰቦች ነው ለእያንዳንዳቸው ሀምሳ ኪሎ ግራም ፍርኖ ዱቄትና አምስት ሊትር ዘይት ድጋፍ ያደረጉት። የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ካሊድ አልዋን ከጀግኖች ዘማች ቤተሰቦች ጋር በመሆን የፓርቲዬን አጋርነት ስገልፅ ከፍተኛ ክብር ይሰማኛል ብለዋል። የጀግኖች ቤተሰቦች በዘማቾች የተነሳ ሊደርስባቸው የሚችለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማቃለል እንዳለበትም አሳስበዋል። አቶ ካሊድ ብልፅግና ፓርቲ በዚህ ረገድ ያለበትን ሀላፊነት በብቃት ለመወጣት ዝግጁነቱን አሳይቷል ማለታቸውን ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ሀገር ለማፍረስ የተነሳውን ጠላት ሁሉም ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ዘርፎች በመሰማራት እየተዋጉት ነው ያሉት ሀላፊው ብልፅግና ፓርቲም የዘመቻ ግንባሮች የመሪነት ሚናውን እየተወጣ መሆኑን አብራርተዋል። የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችና ሰራተኞች ባለፈው ሳምንትም በበራኽ ወረዳ በመገኘት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል መሰብሰባቸው ይታወሳል። አካባቢዎን ይጠብቁ ወደ ግንባር ይዝመቱ መከላከያን ይደግፉ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣የካቲት ፣ሁለት ሺህ ኤፍ ቢሲ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለወልቃይት ጠገዴ አማራ ወጣቶች በፍቼ ከተማ አቀባበልና የምሳ ግብዣ አድርጎላቸዋል። የወልቃይት ወጣቶች ኦሮሚያ ክልል ፍቼ ከተማ ሲደርሱ የከተማዋ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች እና አባገዳዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበልና የምሳ ግብዣም አድርገውላቸዋል። ወንድም የአማራ ህዝብ የኦሮሞ ደም የእኔም ደም ነው ብሎ ግንባሩን ለጥይት የሰጠው በለውጡም ከኦሮሞ ህዝብ ጋር አብሮ ከጎኑ የቆመ መሆኑ በዚሁ አቀባበል ላይ ተነስቷል። ወጣቶቹ በአማራ ክልል በጎንደርና ጎጃም የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው በዛሬው እለት ወደ ሸዋ እያቀኑ ሲሆን የአማራ ወጣቶች በዚህ ሳምንት እየተካሄደ በሚገኘው የታሪካዊ እና የቱሪዝም ስፍራዎች ጉብኝት እና የወንድማማችነት መርሀ ግብር ደብረ ብርሀን የሚደርሱ ይሆናል። ደብረ ብረሀን ከተማ ሲደርሱም ልዩ ልዩ መርሀ ግብሮች እንደሚከናወን ከአማራ ብልፅግና ፓርቲ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለወልቃይት ጠገዴ አማራ ወጣቶች አቀባበል አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት አንድ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ያስገነባው ዘመናዊ የስልጠና ማእከል ተመረቀ። ማእከሉ በዛሬው እለት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል። ማእከሉ በአንድ ሺህ ሰማኒያ ሜትር ስኩየር መሬት ላይ የተገነባ ዘመናዊ ህንፃ ሲሆን የመማሪያ ክፍሎችንና ከአርባ በላይ የመኝታ ክፍሎችን ያካተተ ነው ተብሏል። በቴክኖሎጂ የታገዘ ስልጠና መስጠት እንዲያስችል ዘመኑ የደረሰባቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ያካተተ መሆኑም ተመልክቷል። ከዚህ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የተመሰረተበትን ሀምሳኛ አመት በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር ላይ ይገኛል። በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ሌሎች እንግዶች መፃደማቸውን ኢዜአ ዘግቧል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ያስገነባው ዘመናዊ የስልጠና ማእከል ተመረቀ
የአማራ ክልል የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የስምሪት ተቆጣጣሪ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ግለሰብ ህይወት በተሽከርካሪ አደጋ ማለፉን የሪፖርተር ምንጮች ገለፁ። ሀሙስ ሚያዝያ ሀያ ስድስት ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ከባህር ዳር ወደ ዳንግላ በኮስተር መኪና ተሳፍረው ሲጓዙ የነበሩት የአማራ ክልል የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ስምሪት ተቆጣጣሪ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስማቸው አማረ፣ በተሽከርካሪ አደጋ ህይወታቸው ማለፉን ምንጮች ጠቁመዋል።አቶ ስማቸው የአማራ ክልል የመንገድና ትራንስፖርት ስምሪትን በዋና ዳይሬክተርነት መምራት የጀመሩት በቅርብ ጊዜ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የክልሉ የመንገድና የትራንስፖርት ስምሪት ያለበትን ችግር በማጥናትና አዲስ የአሰራር ስርአት በመዘርጋት፣ በክልሉ የሚደርሰውን የተሽከርካሪ አደጋና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን ለዘለቄታው ለመፍታት ጥረት ሲያደርጉ እንደነበረ የሪፖርተር ምንጮች ገልፀዋል።አቶ ስማቸው ህይወታቸው ከማለፉ ሳምንት ቀደም ብሎ ከአማራ ክልል ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በባህር ዳር ከተማ ስላለው አዲሱና አሮጌው የአውቶብስ መናኸሪያ ጉዳይ ሰፋ ያለ መረጃ ለክልሉ ህዝብ ሲሰጡ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።አቶ ስማቸው ቤተሰቦቻቸው ዳንግላ ከተማ ስለሚኖሩ ዘወትር ቅዳሜና እሁድ ወደ ዳንግላ ከተማ እንደሚመላለሱ የታወቀ ሲሆን፣ በዚህ የትራፊክ አደጋም ከአራት የሚበልጡ ሰዎች ህይወት እንዳለፈ ተሰምቷል።
በተሽከርካሪ አደጋ የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ስምሪት ተቆጣጣሪ ዋና ዳይሬክተር ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ህዳር ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በሱዳን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አእምሮ ከሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡመር ጋማር አልዲን ኢስማኤል ጋር ተወያይተዋል።በውይይታቸው ወቅትም አምባሳደር ይበልጣል በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ገለፃ ማድረጋቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።በዚህም አምባሳደር ይበልጣል አእምሮ የፌደራል መንግስት በህወሀት የጥፋት ቡድን ላይ እያካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር ዘመቻ ከመንስኤው ጀምሮ አሁን ያለበት ደረጃ በተመለከተ ለተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለፃ አድርገዋል።አምባሳደር ይበልጣል በገለፃቸው፥ ህግ የማስከበር ዘመቻው አሁን ወሳኝ ምእራፍ ላይ መድረሱን፣ ተጨማሪ ጉዳት ለመቀነስ የህወሀት የጥፋት ቡድን በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጥ መጠየቁን ገልፀዋል።በተጨማሪም የህወሀት የጥፋት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት የመፈፀመ፣ የዘር ጭፍጨፋ ያደረገ፣ በህዝቦች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት እንዲፈጠር በገንዘብ እና በሎጅስቲክስ ድጋፍ በማድረግ በርካታ ወንጀል ከፈፀመ የጥፋት ቡድን ጋር ድርድር ማድረግ እንደማይቻልም አብራርተዋል።በቀጣይ ጥቂት ጊዜያት ውስጥ ቡድኑ ለፍርድ እንደሚቀርብም ነው በገለፃቸው ያነሱት።የሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡመር ጋማር አልዲን ኢስማኤል በበኩላቸው፥ ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተሉት፣ የተደረገላቸው ገለፃ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እንደረዳቸው አስታውቀዋል።ኢትዮጵያና ሱዳን ወንድም እና እህት የሆኑ ሀገሮች በመሆናቸው እንደ ቤተሰብ የኢትዮጵያ ጉዳት እንደሚሰማቸው እንዲሁም በስደተኞች ጉዳይ ተባብረው እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
አምባሳደር ይበልጣል አእምሮ ከሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
በአማራ ክልል በፀጥታ አካላት እየተያዘ ያለው ሀሰተኛ የብር ኖት ሀይ ኮፒ ወይም አንደኛ ደረጃ ቅጅ እንጅ ተመሳስሎ የተሰራ ፎርጅድ የብር ኖት አለመሆኑን የክልሉ መንግስት ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው መስከረም ወር መጀመሪያ ሳምንት የብር ኖቶች ቅያሬ ማድረጉን ይፋ አድርጎ ነበር፤ ቅያሬውን ተከትሎ በአማራ ክልል በተለያየ ጊዜ አዲሶቹን የብር ኖቶች በሚመስሉ ሀሰተኛ የብር ኖቶች ለመቀየር ሲንቀሳቀሱ ግለሰቦችን መያዙን በተከታታይ እያሳወቀ ይገኛል። የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ለአል አይን ኒውስ እንደገለፁት በቅርቡ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እየተያዙ ያሉት ሀሰተኛ የብር ኖቶች ፎርጅድ ተብለው የሚገለፁ አይደሉም፤ ፎርጅድ ተመሳስሎ የሚሰራ ነው ብለዋል። ሀላፊው ትክክለኛውን የብር ኖት በቀላሉ በማንኛውም ስካን መሳሪያ ኮፒ በማድረግ በህገወጥ መንገድ እየተሰራጨ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ከባንክ ውጭ በሚደረግ ቅያሬ መታለል ሊጋጥም እንደሚችል ገልፀዋል። አሁን ላይ አዲስ ስለሆነ በተለይ አስር ብር፤ የሀምሳ ብር የአንድ መቶ ብር ኖቶች በማመሳስል ተመሳሳይ ብር በአንደኛ ቅጅ ሀይ ኮፒ በማድረግ ነው ለቀየር ነው እየተሞከረ ያለው ብለዋል ሀላፊው። አቶ ግዛቸው ኮፒ የተደረገውን ብር ወደ ገጠር አካባቢ በመሄድ በከብትና እህል ሽያጭ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ለማጭበርበር መሞከሩን ገልፀዋል። እስካሁን በክልሉ በአጠቃላይ ወደ ሶስት መቶሺ የሚጠጋ ሀሰተኛ ብር መያዙን የገለፁት ሀላፊው ፖሊስ ሀሰተኛ የብር ኖት ይዘው የተገኙ ሰዎች መያዙን ተጠቅሷል። የሀሰተኛ የብር ኖቱን ምንጭ በተመለከተ ላነሳንላቸው ጥያቄ ሀላፊው ፎርጀሪ ቢሆን ምንጩን ለማወቅ ጥረት ይደረጋል፤ ነግርግን በኮፒ ማሽን የትኛውም ቦታ ሊታተም ይችላል የሚል መልስ ሰጥተውናል። በእጁ አዲሱን ብር ይዞ የሚያውቅ ሰው አይሸወድም፤ ምክንያቱን ሀሰተኛው ብር ከትክክለኛው የብር ኖት የሚለይበት ገፅታ አለው። ከዚህ በተጨማሪም ኮፒው በውሀ ሲነካ ቀለሙ የመልቀቅ ባህሪም አለው። አዲሱን ብር አይቶ የማያውቅ በተለይም አርሶ አደር እንዳይታለል በማሰብ ከባንክ ውጭ ከግለሰብ ብር መየቀየር እንደማይገባ አሳስበናል ብለዋል ሀላፊው። አቶ ግዛቸው በክልሉ እስካሁን በስድስቱ ዞኖች የሀሰተኛ ብር መያዙ መያዛቸውን የገለፁ ሲሆን ማሀበረሰቡ በሀሰተኛ ብር እንዳይሸወድ በክልሉ በሁሉም ወረዳዎች ያሉ የንግድ ባንክ ሀላፊዎችንና የየወረዳውን የኮሚኒኬሽን ሀላፊዎች በማሰማራት የማንቃት ስራ ተሰርቷል ብለዋል። አቶ ግዛቸው እንዳሉት ሰው በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ቤተክርስቲያንንና መስጅድን ጨምሮ በብቅያሬው ዙሪያ ትምህርት ተሰጥቷል። ይህን ተከትሎም ከህብተሰብ በርካታ ጥቆማ በመምጣቱ እስካሁን በትንሹ ሀሰተኛ የብር ኖት ይዘው የተገኙ በትንሹ አስር ሰዎቸ በፖሊስ መያዛቸውን አቶ ግዛቸው ተናግረዋል። ከባንክ ውጭ እየተዘዋወረ ያለው ብር ወደ ባንክ እንዲገባ ለማድረግና ሙስናን ለመከላከል መንግስት የብር ኖት ለመቀየር እንደምክንያት አስቀምጦ ነበር።በቅያሬውም በሶስት ነጥብ ሰባትቢሊዮን ብር ወጭ ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን የብር ኖቶች ማተሙን መግለፁ ይታወሳል።
በክልሉ እስካሁን ሶስት መቶሺ ሀሰተኛ የብር ኖት መያዙን ሀለፊው ግዛቸው ተናግረዋል
አቶ ምናለ አቤ በምእራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ ጣሪንጋ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ናቸው። የክረምት ወራትን ብቻ ጠብቀው በአመት አንድ ጊዜ ከማምረት ወጥተው በመስኖ እርሻ ሁለት ጊዜ በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። እንደ አርሶ አደሩ ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከስድስት መቶ ሺህ ብር በላይ በማውጣት ዘመናዊ ቤት ሰርተዋል። ገቢያቸውም ከበፊቱ በተሻለ ቤተሰቡን ለመምራት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።በዚህ ወቅት በሁለት ሄክታር መሬት ላይ እንደ ቆስጣና ቃሪያ ያሉ አትክልቶችን በመስኖ እያለሙ ነው። ከምርቱም ከአራት መቶ ሺህ ብር በላይ አገኛለሁ ብለው ይጠብቃሉ፤ እስካሁን ለገበያ ካቀረቡት የቃሪያ ምርት ሁለት መቶ ሺህ ብር ያህል እንዳገኙም ተናግረዋል። ልክ እንደ አቶ ምናለ አቤ ሁሉ የመስኖን ጥቅም የተረዱ ሌሎች የአካባቢው አርሶ አደሮችም በዘርፉ በስፋት ተሰማርተው እየተጠቀሙ መሆኑን ተናግረዋል።በአማራ ክልል በተያዘው የምርት ዘመን ሁለት መቶ ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ሄክታር መሬት በአዲስ እና በነባር የመስኖ ልማት ይሸፈናል ተብሎ በእቅድ መያዙን መዘገባችን ይታወሳል። በምርት ዘመኑ ከሚለማው የመስኖ እርሻ በአንደኛ ዙር ስላሳ አንድ ሚሊዮን ኩንታል የሚሆን፣ በሁለተኛ ዙር ደግሞ ሰባት ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ምርት ለማግኘት እየተሰራ ነው።በሀገር አቀፍ ደረጃ በያዝነው የበጋ ወቅት አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሀያ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሄክታር መሬት በተለያዩ አዝእርትና ፍራፍሬ ተሸፍኖ እየለማ መሆኑን ደግሞ ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በያዝነው የበጋ ወቅት በመስኖ እየለማ ካለው መሬት እስካሁን ከ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከሁለት ሳምንት በፊት፣ በዚህ ኪነ ጥበብን ጨምሮ ባህልን በሚያንፀባርቅ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ኤፍሬም ታምሩ ሮሀ ባንድ እንደገና እፁብ ድንቅ ልእልና ብዬ በፃፍኩት ፅሁፍ ላይ፣ በባለፈው ሳምንት የጋዜጣው እትም የኤፍሬም ታምሩ አልበም ያለቅጥ ተሞገሰ በሚል ርእስ አቶ ብለውኝ፣ ትችታቸውን ፅሁፉ ላይ ሳይሆን እኔ ላይ አተኩረው፣ ከሆነ ቡና ቤት እየተሳለቁብኝ የፃፉትን የሁለት ልጆችን የጋራ ፅሁፍ ሳይ፣ ትችቱ ምንም ይሁን ምን፣ ይሄ በለጋ ብእሬ የከተብኩት ፅሁፍ፤ ለ ትችት በመብቃቱ ደስ አለኝ። ለዚህም ብቻ ትችቱን የፃፉትን ሁለቱንም ጥበቃና አሽቃሩ የተባሉትን ልጆች አመስግኛቸዋለሁ።በነገራቸው ላይ ግን፣ የመማማሪያ መድረክ እንዲሆን፣ አንድ ሰው በሰራው ስራ ላይ አስተያየት ሲሰጥ በአማርኛችን ገድሎ ማዳን ወይም አድኖ መግደል እንደሚባለው አይነት ነገር፣ በእንግሊዘኛውም ለምሳሌ ወይም የሚባለውን የአስተያየት አሰጣጥ መንገድ መጠቀሙ ጤናማና ገንቢ የሀሳብ ልውውጥ እንደሆነ ሳልጠቁማቸው አላልፍም። ማለትም፣ ልክ በእንቁላል ሳንድዊች አቀራረብ ላይ፣ የዚህ ምግብ ዋናው የሆነው እንቁላሉ መሀል ላይ ይቀመጥና ከስርና ከላዩ ደግሞ ዳቦ እንደሚሸፈንበት ሁሉ፤ እንደዚሁ፣ አንድን ሰውም በሰራው ስራ ስንተቸው፣ ዋናውን ድክመቱንና ስህተቱን ከላይ በማድረግ ወይም መጀመሪያ ላይ አስቀድመን በማምጣት በቀጥታ መንገር ሳይሆን፣ እንደ እንቁላል ሳንድዊቹ አቀራረብ መሀል ላይ እናደርገውና፣ የመግቢያውን ንግግር ግን ያ ሰው ስለሰራው በጎ ወይም መልካም ነገር ወይም ጥንካሬውን በመንገር እንጀምራለን። በመቀጠልም፣ የንግግሩም ሆነ የፅሁፉ ዋናው አላማችን ችግሩን ወይም ስህተቱን ለመተቸት ነውና፤ ነገር ግን፣ ብለን ልንነግረው የፈለግነውን ዋናውን ድክመቱንም ሆነ ስህተቱን በደንብ እንነግረዋለን ማለት ነው። በመሆኑም፣ ይህ ሰው በጎ ነገሩንም አስቀድመን የነገርነው ስለሆነ በዚህ በተሰጠው ትችት አይደናገጥም ወይም ክው አይልም። አሁንም እንደገና፣ ድክመቱንና ስህተቱን ነግረነው ስናበቃ፣ አስተያየታችንን በዚሁ ከዘጋነው አድኖ መግደል እንደ ማለት ነው የስህተቱንና ድክመቶቹን ስሜት ብቻ ይዞ እንዳይሄድና ተደናግጦ እንዳይቀር ብሎም የስራ ተነሳሽነቱም ሆነ አጠቃላይ ስነ ልቦናው እንዳይጎዳ፣ ነገር ግን፣ ከእነኚህ ስህተቶችህ ባሻገር እነኚህ ጠንካራ ወይም መልካም ነገሮችህ እንዳሉ ናቸውና የበለጠ በርታ የተሻለም ስራ እንደምትሰራ እርግጠኞች ነን አይነት ነገር ብለን የአስተያየታችንን መደምደሚያ በመልካሙ ንግግራችን ከዘጋንለት፣ መልካምና ገንቢ የመማሪያ ልውውጥ አስተያየት ይሆናል ማለት ነው። ማለትም፡ መጀመሪያ ላይ መልካሙን ነገሩን አስቀድመን በመንገር ሳምነው አደረግነው፣ ቀጥለን ደግሞ ድክመቱ ላይ አስረግጠን ደበደብነው አደረግነው፣ ከዚያም በመጨረሻውና መዝጊያው ላይም ስመነው ወጣን አደረግነው ማለት ነው ይሄ የ ማለት። እንግዲህ ይሄን ካልኩ በኋላ፣ እነኚህ እኔን በጋራ ፅሁፋቸው የተቹኝ ሁለቱ ጥበቃና አሽቃሩ የተባሉት ልጆች ግን፣ ከላይ ባወራነው መልኩ ሳይሆን በተቃራኒው፣ ሲጀምሩም መሀሉም መጨረሻውም ስድብ አዘል በሆነ ትችትና ጨለምተኝነት ነው አስተያየት ባሉት ጋጠ ወጥነታቸው ምላሽ የሰጡኝ። ወደ ቁምነገሩ የምላሽ ነጥቤ ስመጣ፣ ባለፈው በፃፍኩት ፅሁፍ ላይ አላማዬ ስለ ኤፍሬምና ሮሀ ባንድ እንደገና አልበም እፁብ ድንቅነት ብቻ በደምሳሳው ለማውራት ሳይሆን፣ አጋጣሚውን ተጠቅሜ እግረ መንገዴን ሙዚቃ ሙያቸው ላልሆነና ስለ ሙዚቃ ስራ ሙያዊ ግብአቶች ግንዛቤ ለሌላቸው ላገራችን ሰፊው አዳማጮች፣ ያቅሜን ያህል በሚገባና ቀለል ባለ መንገድ በመንገር ግንዛቤ እንዲያገኙና፣ ያገራችንን ጥራት ያለውንና የሌለውን የሙዚቃ ምርት ለይተው በማወቅ ተገቢውን ዋጋ እንዲሰጡ ለማድረግ፣ ከብዙ የሙዚቃ ስራ ክንውኖች መሀከል፣ ከአባይ ወንዝ በጭልፋ እንደመቀንጨብ ያህል፣ በሙዚቃ አልበም ስራ ላይ እጅግ ወሳኝ ስለሆኑት ሶስቱ ተግባራት ማለትም፡ ስለ የሙዚቃ ቅንብር፣ የሙዚቃ ሚክሲንግ እና የሙዚቃ ማስተሪንግ ምንነትና ሚና መሬት ላይ በወረደ ቀላል የምሳሌ አገላለፅ ለማስቀመጥ ነበር የሞከርኩት። ያላነበባችሁት ወደ ኋላ ሄዳችሁ ብታነቡት ደስ ይለኛል በተለይም በሀገራችን ላይ ከባለፉት አስር አመታት በላይ፣ የባንድ የሙዚቃ ቅንብር ቀርቶ የኪቦርድ ወይም ድራም ማሽን ቅንብር ከተንሰራፋ ጀምሮ፣ ፍሬውን ከገለባው መለየት ሳይሆን ገለባውን ከፍሬው መለየት ሆነና፤ ጥቂት በማይባሉ ብዙ የሀገራችን የአሁን ትውልድ ወጣቶችም ሆነ ከፍ ያሉት ዘንድ፣ የተበላሹ የቅንብር ስራዎችና የሙዚቃ ድምጫዎች እንደ ትክክለኛ፣ ትክክለኛው ሙሉ የባንድ ሙዚቃ ስራና ደረጃውን የጠበቀ የሙዚቃ ድምፅ ደግሞ እንደ ብልሽት እየተቆጠሩ በመታየታቸው፤ እኔም ራሴ በዙሪያዬ ካሉ ብዙ ሰዎች ይሄን የተሳሳተ አመለካከት ስለማይ፤ እንደማንኛውም የሀገራችንን ሙዚቃ በፍቅር እንደሚወድና ለሀገራችን የሙዚቃ እድገት በእጅጉ እንደሚቆረቆር ሰው ሁሉ፣ እኔም የማውቀውን ያህል የሙዚቃ እውቀቴን ተጠቅሜ ነበር ፅሁፉን የፃፍኩት። በእርግጥም ይህ የሙከራ ፅሁፌ በዚህ የኤፍሬምና ሮሀ ባንድ እንደገና አልበም ላይ ተሳካልኝ እንጂ፣ ሀሳቡን ጀምሬ የተውኩት ያኔ የፀጋዬ እሸቱ እንደገና በኤክስፕረስ ሙሉ ባንድ የተቀናበረው፣ ደረጃውን የጠበቀው ጥሩ የሙዚቃ ስራ አልበም በወጣ ጊዜ ነበር። እናም፣ አንድ የታንዛኒያኖች አባባል፡ የሆነ የተማርከውን ትምህርትም ሆነ ያወቅኸውን እውቀት በደንብ እንዳወቅኸውና ያም እውቀት በውስጥህ የተዋሀደ መሆኑ የሚታወቀው፣ ያንን ያወቅኸውን እውቀት ቢያንስ ለቅድመ አያትህ ሊገባ በሚችል ቀላል መልኩ ማስረዳት ስትችል ነው፤ አለበለዚያ ግን ያ አውቀዋለሁ የምትለው እውቀት በላይህ ላይ ተንሳፍፎ እንዳለ እንጂ እንዳወቅኸው አይቆጠርም እንደሚለው ሁሉ፤ እኔም እንዳቅሚቲ፣ሁሉም ያገራችን ሰው የሚያውቀው ነው ባልኩት የምግባችንን የወጥ አሰራር ሙያን ምሳሌ አድርጌ ስለ ሶስቱ ወሳኝ የሙዚቃ ስራዎች ምንነትና ጠቀሜታነት በቀላሉ ለመግለፅ ከሞከርኩ በኋላ፣ ይሄም የኤፍሬም ታምሩ እና ሮሀ ባንድ እንደገና የሙዚቃ አልበም፣ ሶስቱንም ስራዎች ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ያሟላ እፁብ ድንቅ ልእልና የተሞላበት ስራ ነው ስላልኩኝ፤ እነኚህ በሙዚቃ ዙሪያ ውስጥ ያሉ የሚመስሉት ጥበቃና አሽቃሩ የተባሉት ልጆች በፃፍኩት ጉዳይ ላይ፣ የሀገራችን ሙዚቃ ኢንዱስትሪ እንዲህ በታመመበት ወቅት፣ የበኩሉን ግንዛቤ ሊፈጥር ጥሯል ብለው ደስ ሊላቸው ሲገባና ባጎደልኩት ላይ ሊሞሉ ሲገባ፣ ጭራሹኑ ቁምነገሬን ጆሮ ዳባ ብለው በእኔ ላይ በማሾፍ እየተሳለቁ አንዴ ጥጥ፣ አንዴ ወጥ፣ አንዴ ሙሽራ፣ እያለ በመዘባረቅ አንድም ነገር ላያሳውቀን እንዲሁ አደከመን፣ ወዘተ ብለው ዘለፋቸውን በመፃፋቸው በጣም ነው የገረመኝና ያሳዘነኝ፤ ብሎም የመዚቃችንን ኦሪጅናል ሲዲ ሽፋን መረጃ አይተው የማያውቁ እንደሆኑም የገባኝ። ሲቀጥልም፣ እንደ የሀገራችን መንግስታት ታሪክ፣ በባለፈው መንግስት የነበሩትን መልካም የሀገር ነገሮችን በጎደለው ላይ ሞልተው፣ መስተካከል ያለበትን አስተካክለው በዚያው ላይ እንዳለ መቀጠል ሲገባቸው፣ ያንን መልካም ነገር በስድብ ድምጥማጡን አጥፍተው በማፍረስ፣ የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ ብለው፣ የራሳቸውን ነገር ሀ ብለው ከዜሮ እንደሚጀምሩትና ሀገር እንደሚያምሱት ሁሉ፤ እነኚህ ከሆነ ቡና ቤት ነን ያሉት ሁለቱ ጥበቃና አሽቃሩ የተባሉ ልጆችም፣ እኔ ከፃፍኩት የሙዚቃ ቁም ነገር ላይ አንዲትም ሰበዝ ሳይመዙለት በዘለፋ ድባቅ ከመቱት በኋላ፤ በፅሁፌ ላይ ሳይሆን በእኔ ላይ በፀሀፊው ላይ ያለንን አስተያየት በዚሁ እናብቃና ስለ ሙዚቃ አንዳንድ ነገሮችን እናንሳ ብለው፣ ይሄን የማህበረሰብ ጋዜጣ ለሚያነብ ሰፊው ማህበረሰብ ሊገባው በሚችልና በጠቃሚነት ሊያውቀው በሚገባ አስፈላጊ የሙዚቃ ጉዳዮች ላይ ሳይሆን፣ ለሙዚቃ ሙያተኞች ብቻ የሚሆንን ሙዚቀኞቻችንም ቢሆን የሚያውቁትን ችክ ያለ የሙዚቃ እውቀታቸውን ከዜሮ ጀምረው የራሳቸውን ፃፉ። ውድ አንባቢዎች እስኪ ወደ እነርሱ ልመለስ።እናንተ ጥበቃና አሽቃሩ ከጠማማነታችሁ የመነጨ የዘለፋ እስር ችቧችሁ ውስጥ ሁሉ በተለይ የገረመኝና ያሳቀኝ ነገራችሁ መቼም፣ ማንኛውም ሙዚቃም ሆነ ዜማ ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ ኧ ኧ ኧ ኧ ብቻ እያለ የሚቀጥል የቀጥታ መስመር ድምፅ ሳይሆን፣ ከዝቅተኛው የድምፅ እርከን ወደ ላይኛው ድምፅ እየወጣ የሚወርድ፣ እጥፋቶችን እየሰራ የሚምዘገዘግ ከርቭ የሚሰራ እንደሆነ እያወቃችሁት ሳለ፣ አሁን ዘፋኞቻችን የድምፅ ከርቭ ማለት ምን ማለት ነው ብለው ቢጠይቁት ምን ብሎ ይመልስ ይሆን ብላችሁ በመሳለቃችሁ፣ አይገርማችሁም በደንብ ተሳልቄባችኋለሁ እንዴ በዚህ የማህበረስብ ገፀ አምድ ላይ ለብዙሀኑ አንባቢ ሰው የማይጠቅም እንካ ስላንትያ እንደሆነ አውቃለሁና፤ በዚህም አንባቢዎችን ይቅርታ እየጠየኩ፤ ንገረኝ ካልሽማ እንዳለው ዘፋኛችን፣ ይልቅስ እናንተ ስለሙዚቃ ከፃፋችሁት ውስጥ ለምሳሌ ስለ ትዝታ ቅኝት አገላለፃችሁ ላይ በሀሜት ሳይሆን በእውነተኛው መንገድ ልሳለቅባችሁ። ይሄውም፡ እናንተ ትዝታ ሁለት እና ትዝታ አምስት ብላችሁ የገለፃችሁትን ላንድ ፕሮፌሽናል ሙዚቀኛ ብትነግሩት እንዲህ የሚባል ሳይንቲፊክ ስያሜ የለም ብሎ ጆሮውን እንደሚይዝባችሁ ያለጥርጥር አውቃለሁ። እኔ ግን በሀገርኛ የእውቀት ስያሜ መግባቢያ ምን ለማለት እንደፈለጋችሁ ገብቶኛል። ለምሳሌ፡ በትዝታ ሜጀር ስኬል ውስጥ ሆኖ ማለትም፡ ስኬል ውስጥ ሆኖ ከ ሁለትኛው ኪይ ከ ወይም ከ አምስትኛው ኪይ ከ ተነስቶ እዚያው ላይ በማረፍ መጫወት ማለታችሁ ነው። ነገር ግን፣ በ ቅኝት ውስጥ ሆነው ሳይሆን፣ ራሳቸውን ችለው በራሳቸው ስያሜ ነው፡ ትዝታ ሜጀር ስኬል እንዲሁም ትዝታ ሜጀር ስኬል ሆኖ ቅኝታቸው የሚመሰረትና ማንም ኢትዮጵያዊ ያልሆነ የውጭ ሀገር ፕሮፌሽናል ስያሜውን ብቻ ይዞ ዘፈናችንን የማያውቀው እንኳን ሊጫወት የሚችለው፤ እንጂ እናንተ ያላችሁትን ትዝታ ሁለት እና ትዝታ አምስት ስያሜ ጆሮውን ብትቆርጡት አይገባውም። እናም፣ ሙዚቃ ሙያቸውም ሆነ ስራቸው ያልሆነውን ያገራችንን መደበኛ ሙዚቃ አዳማጮች እንዲህ ያለውን ለሙዚቀኛ ብቻ የሚገባውን ዝባዝንኬ በማህበረሰብ ገፅ ጋዜጣ ላይ እየፃፍን አይደለም በከንቱ የምናደነቁረውና ምንም ግንዛቤ እንዳያገኝ የምናደርገው። በመጨረሻም ሀሳቤን ሳጠቃልል፣ ይሄን ሁሉ የፃፍኩበት ምክንያቴ፣ በዋነኛነት ለእናንተ ለጥበቃና አሽቃሩ ለተባላችሁት ሁለት ልጆች የትችትን ባህሪ ለማያሟላው ትችት ሳይሆን ዘለፋችሁ ምላሽ ለመስጠት ሳይሆን፣ ከሁለት ሳምንት በፊት ፅሁፌን ያነበቡት ሌሎች የተከበሩ አንባቢዎች በከንቱ ያስነበብኳቸው እንዳይመስላቸውና እንዳይደናገሩ ብዬ ነው። በተረፈ ግን፣ እናንተ ሁለታችሁ አሁንም በፃፍኩት ማብራሪያዬ ላይ አውቆ የተኛን እንዲሉ ላለመማር በሩን በዘጋው ልቦናችሁ አሁንም ደግማችሁ እንደምትሳለቁብኝ እገምታለሁ።ስሰናበትም፣ ለዚህ ሁሉ ሀሳብ ገለፃ መነሻ ምክንያት የሆነውና፣ ስመ ጥር በሆኑ የሀገራችን ፕሮፌሽናል የሙዚቃ ሀያሲ ባለሙያዎች በኩል አልበሙ ብቻውንና ራሱን የቻለ የሙዚቃ ትንታኔ ሊሰራለት የሚገባና መማሪያም ሊሆን የሚችለው ይህ ድንቅ የኤፍሬም ታምሩ እና ሮሀ ባንድ እንደገና የሙዚቃ አልበም፤ ያላዳመጠው ሊያዳምጠው የሚገባ፣ ያዳመጠውም በደንብ እያደጋገመ የሚያጣጥመው ደረጃውን የጠበቀ የሙዚቃ ስራ ነውና፤ አሁንም እኔ በድጋሚ፣ ይህንን አልበም ያለቅጥ ያሞገስኩት ስራ ነው ሳይሆን፣ መጀመሪያም እንዳልኩት፡ እፁብ ድንቅ ልእልና የተሞላበት ነው እላለሁ። በዚህ ሁሉ መሀልም፣ በድጋሚ ሌላ ተጨማሪ ሀሳቤን እንድገልፅ ምክንያት ስለሆናችሁኝ ሁለታችሁንም ባመጣችሁ ንፋስ በኩል አመሰግናችኋለሁ።በሙዚቃ ሰላም እንጂ ንትርክ አያምርም።
ሙዚቃን ከፍላሽ ሜሞሪ ዲስክ የሚያጫውቱ
በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘው ለውጥ በርካታ የውጭ ኩባንያዎችን እየሳበ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ እንደገለፁት በሀገሪቱ ለመሰማራት ፍላጎት እያሳዩ የሚገኙት የውጭ ኩባንያዎች የውጭ ንግድ አፈፃፀሙን ከፍ የሚያደርጉና በርካታ የስራ እድሎችን መፍጠር የሚችሉና የህዝቦችን የስራ ባህል የሚያሻሽሉ ናቸው ብለዋል።እንዲሁም የውጭ ኩባንያዎችን ለመቀበል የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ምቹ የማድረግ ስራም እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።በስፋት እየተከናወነ ከሚገኘው የፖለቲካ ማሻሻያ ስራ ጎን ለጎንም የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ቀጣይነት ባለው መልኩ የኢኮኖሚውን እድገት ማፋጠን እንደሚያስፈልግ ታምኖበት ኮሚሽኑ በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑንም ነው የተናገሩት።የኢኮኖሚ ማሻሻያው አላማም የሀገሪቱን እድገት በማስቀጠልና የህዝቡን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ለወጣቱ የስራ እድል ማስፋፋት መሆኑንም ጠቅሰዋል።እየተካሄደ ያለው ለውጥ ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ መካሄዱም የውጭ ባለሀብቶች ከዚህ ቀደሙ በተሻለ መልኩ ፊታቸውን ወደ ኢትዮጵያ የማድረግ ፍላጎታቸውን እያሳዩ ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ።በቅርቡ የጀርመኑ የቮልስ ዋገን ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ በዘርፉ የመሰማራት ፍላጎት ማሳየቱን ተከትሎ የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን መከናወኑን አስታውሰዋል።በተመሳሳይም የአበባ አምራች ኩባንያዎች በአማራ ክልል ቁንዝላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰፊ ቦታ ወስደው ወደልማት እንዲገቡ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።እንዲሁም በኦሮሚያ እና በሌሎች ክልሎችም አዳዲስ የውጭ ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውን አንስተዋል። ምንጭ፡ ኤፍ ቢ ሲ
በኢትዮጵያ ያለው ለውጥ በርካታ የውጭ ኩባንያዎችን እየሳበ ነው