text
stringlengths
140
24k
summary
stringlengths
13
164
አንድ ዳኛ ምንም ማድረግ አይችልም ዳኛ ዘሪሁን ደሳለኝ ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል በእስር ላይ ያሉ ጦማሪያን በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ የከሳሽ አቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦባቸው ለብይን የተቀጠሩት አራት ጦማሪያን፣ ለአራተኛ ጊዜ ጳጉሜን ሁለት ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ተቃወሙ። ተከሳሾቹ ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሀኔና በፍቃዱ ሀይሉ ጳጉሜን ሁለት ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት ብይን እንደሚሰጥ የጠበቁ ቢሆንም፣ ጉዳያቸው በሶስት ዳኞች የሚታይ ከመሆኑ አንፃር በእለቱ አንድ ዳኛ አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ ብቻ የተገኙ በመሆናቸው ብይኑ ሳይሰጥ ቀርቷል። ብይኑ ተሰርቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ ዳኞች ባለመሟላታቸውና በመዝገቡ ላይ ባለመፈረማቸው ብይኑ ሊነገር እንደማይችል ዳኛ ዘሪሁን ገልፀዋል። በዳኞች አለመሟላት ለሁለተኛ ጊዜ መቀጠሩ ያበሳጫቸው ተከሳሾቹ፣ እኛ ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም። ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል። የምንፈልገው ቁርጥ ያለው እንዲነገረን ነው። ወይ በነፃ እንሰናበት ወይም ተከላከሉ እንባል። ብይን ለመስጠት በሚቀጠሩት ቀናት መካከል ያለው ጊዜ ለእኛ ህመም ነው፤ በማለት ቅሬታቸውን ተናግረዋል። የጦማሪያኑ ጠበቃ አቶ አመሀ መኰንን ዳኞች እንዲሟሉ መተባበር ያለብን ነገር ካለ እንተባበር ወይም ለፍርድ ቤቱ አስተዳደር እናመልክት፤ የሚል ሀሳብ ለዳኛ ዘሪሁን አቅርበዋል። ዳኛው በሰጡት ምላሽ፣ የሚቻል ከሆነ ሞክሩ፤ ብለዋል። እሳቸውም ብይኑ ቢሰጥ እንደሚመርጡ፣ ተጠርጣሪዎቹን አይናቸውን ባያዩ ደስ እንደሚላቸውና በተደጋጋሚ በመመላለሳቸው በግላቸው እንደሚከብዳቸው ተናግረዋል። ያልተሟሉት ዳኞች በተለያዩ ምክንያቶች መቅረታቸውን በመጠቆም፣ እንደተሟሉ እስከ መስከረም አስር ቀን ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት ድረስ ለማረሚያ ቤቱ ተነግሮ ብይኑ ሊሰጥ እንደሚችል በፅህፈት ቤት አስታውቀዋል።
ጦማሪያኑ ለአራተኛ ጊዜ ለብይን መቀጠራቸውን ተቃወሙ
ትራምፕ ስልክ እየደወሉ ጆ ባይደንን እንዳሸንፈው ትንሽ ድምፅ እንዴትም ብላችሁ አሟሉልልኝ እያሉ የግዛት አስመራጮችን ይለምኑ እንደነበር ዋሺንግተን ፖስት አጋለጠ።ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደንን እንዳሸንፍ ድምፅ ከየትም ብላችሁ ፈልጉ እያሉ ከደወሉባቸው የግዛት የምርጫ ሀላፊዎች አንዱ የጆርጂያ ግዛት ምርጫ አስፈፃሚ ብራድ ራፍነስፐርግ ናቸው።ዋሺንግተን ፖስት ይፋ ባደረገው የስልክ ቅጂ ንግግር ትራምፕ ሺ ሰባት መቶ ሰማኒያ ድምፅ ከየትም ብለህ ፈልግ እያሉ ሲለምኑ እንደነበር ያሰማል።ብራድ በበኩላቸው የጆርጂያ ግዛት ቆጠራው በትክክል ተቆጥሮ መጠናቀቁን ለትራምፕ ሲናገሩ ይሰማሉ።ሆኖም ትራምፕ አስፈፃሚውን በማባበልና በማግባባት ትንሽ የተጭበረበሩ ድምፆችን ካገኘ እሳቸው አሸናፊ እንደሚሆኑ በማስረዳት እንደምንም ተባባሪ እንዲሆን ሲያበረታቱት ተሰምቷል።
የትራምፕ ድምፅ አጭበርብሩልኝ የስልክ ንግግር ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት ሀያ ስድስት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በመላ ኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖችና ከተሞች ሽብርተኞቹ ወያኔና ሸኔ ኢትዮጵያያን ለማፍረስና ህዝቦቿን ለማጥፋት እያካሄዱ ያሉትን እንቅስቃሴ በማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ። ሰልፈኞቹ የወያኔ አሽከር ሆኖ የሚያገለግለው ሸኔ እና ጨፍጫፊውና ዘራፊው ወያኔ የሚያካሂዱት አገርና ህዝብን የማጥፋት ሴራ እኛ በህይወት እያለን ሊሳካ አይችልም፥ የክተት ጥሪውን ተቀብለን በመዝመት የኢትዮጵያን ሏላዊነት እናስከብራለን ብለዋል። በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን ባደረሱን መረጃ መሰረት፥ ታጋሽና ሰላማዊ የሆነው የኦሮሞ ህዝብ ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች ኢትዮጵያ ጠል የሆነውን የባእዳን ተልእኮ ለማስፈፀም እያካሄዱ ያሉትን እንቅስቃሴ በጥብቅ እንደሚያወግዙ ሰልፈኞቹ ገልፀዋል። ሰልፈኞቹ ይዘዋቸው ከወጡት መፈክሮች መካከልም ወያኔ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት ናት፣ እኔ እያለሁ ወያኔ ዳግም በህዝባችን ትከሻ ላይ የጭቆና ቀንበር አትጭንም፣ ወያኔን ማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ ነው፣ አልረሳም ወያኔ የኦሮሞ ቄሮና ቀሬ ጠላት ናት፣ እዘምታለሁ የኢትዮጵያን ሏላዊነት አስከብራለሁ፣ በአንድ እጃችን ልማታችንን ለማፋጠን፣ በሌላ እጃችን ጠላቶቻችንን ለመቅበር ተግተን እሰራለን የሚሉ ይገኝበታል። አካባቢዎን ይጠብቁ ወደ ግንባር ይዝመቱ መከላከያን ይደግፉ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
በመላ ኦሮሚያ የወያኔንና የሸኔን አገር የማፍረስ ሴራ በማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
የኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች፣ የቲያትር ባለሙያዎች ፣ የሙዚቀኞችና የሰአሊያን ማህበራት እንዲሁም አላቲኖስ የፊልም ሰሪዎች ማህበር ሰሞኑን በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ አዲሱ የ ቃና ቴሌቪዥን የፕሮግራም ይዘት የአገሪቱን የሲኒማ ጥበብ አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ይዘቱን ሊያስተካክል ይገባል አሉ። ቃና ቴሌቪዥን በበኩሉ፤ የአገሪቱን የፊልም ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እተጋለሁ ብሏል። ቃና ሰባ በመቶ የውጭ ሀገር ፊልሞችን፣ ስላሳ በመቶ የአገር ውስጥ ፕሮግራሞችን ሊያቀርብ መዘጋጀቱን የጠቆሙት ማህበራቱ፤ የይዘት ምጣኔው የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያላገነዘበና የባህል ወረራን የሚያስፋፋ ነው ሲሉ ነቅፈዋል። የአደጋው ምንጭ በዋናነት የውጭ ሀገር ፊልሞችን ተርጉሞ በዳቢንግ ድምፅ በመቅዳትና አስመስሎ በመለጠፍ ማቅረቡ ነው ብለዋል። በቴሌቪዥን ጣቢያው የሚቀርቡት የውጭ ሀገር ፊልሞች ንግድ ተኮር በመሆናቸው ምንም አይነት ትምህርታዊና ሞራላዊ ይዘት የላቸውም ያሉት ማህበራቱ፤ የባህል ወረራን በማስፋፋት ትውልድን ከማጥፋታቸው በፊት መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል። ጣቢያው አጭር እድሜ ያለውን የተከታታይ ድራማ ታሪካችንን በማቀጨጭ የፊልም ኢንዱስትሪውን እድገት የሚያሰናክል በመሆኑ ፕሮግራሙን በድጋሚ ሊከልስ ይገባዋል ብለዋል፤ ማህበራቱ። ባለፈው አመት ዳና የቴሌቪዥን ድራማ ስምንት ሚሊዬን ብር ገቢ ለመንግስት ማስገኘቱን የጠቀሱት ማህበራቱ፤ ቃና በዚህ ይዘቱ የሚቀጥል ከሆነ ግን ትውልድ ከማጥፋቱ በተጨማሪ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ያሳጣዋል ብለዋል።ባለፈው ረቡእ በብሄራዊ ቲያትር በሰጡት በመግለጫ ላይ የቴሌቪዥን ጣቢያውን የስራ ሀላፊዎች ለምን እንዳልጋበዙ የተጠየቁት ማህበራቱ፤ የተቻላቸውን ያህል ጥረት ቢያደርጉም ሊያገኟቸው እንዳልቻሉ ተናግረዋል። የ ቃና ቴሌቪዥን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀይሉ ተክለሀይማኖት በበኩላቸው፤ ጣቢያው በመግለጫው ላይ አለመጋበዙን ገልፀው፤ በይዘቱ ዙሪያም ቀርቦ ሊያናግራቸው የሞከረ ማህበርም ሆነ ግለሰብ አለመኖሩን ተናግረዋል። በፕሮግራሙ ይዘት ላይ ችግር አለ ብሎ የሚያምን አካል በማንኛውም ጊዜ ሊያነጋግራቸው እንደሚችልም ገልፀዋል ሀላፊው።ባለፉት ሀምሳ አመታት የቴሌቭዥን ታሪክ በተለያዩ አገራት በራሳቸው ቋንቋ ተተርጉመው ባህልና እሴቶችን ሳይጋፉ የቀረቡና እየቀረቡ ያሉ የመዝናኛ ስራዎች፣ በየአገሩ ያሉትን የፊልምና የቴሌቪዥን ኢንዱስትሪ አሁን ላለበት ደረጃ አድርሰውታልም ሲሉ አስረድተዋል። ጣቢያው ከመቋቋሙ በፊት በአገሪቱ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው፤ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ከሚመለከቱ ኢትዮጵያውያን ግማሽ ያህሉ የሚያዩት የውጭ አገር ይዘት ያላቸውንና በሌላ ቋንቋ የተሰሩትን ሲሆን የሚያዩትም እንዲሁ እንደወረዱ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሀይሉ፤ አሁን ጣቢያው ለእይታ የሚያበቃቸው ፊልሞች ግን የተመረጡና ለማህበረሰቡ ትርጉም ሊሰጡ የሚችሉት ብቻ ናቸው። ፊልሞቹ በቀጥታ የተተረጐሙ ሳይሆኑ በእኛ ሀገር ባህል፣ አባባልና አስተሳሰብ የተቃኙ እንደሆኑም ጠቁመው፤ ያልተገቡ የተባሉ የፊልሙ ክፍሎችም ተቆርጠው እንደሚወጡ ሀላፊው ተናግረዋል። ጣቢያው በቲያትር ጥበባት የተመረቁ ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን በፀሀፊነት፣ በዳይሬክቲንግ፣ በድምፅና በቪዲዮ ኤዲቲንግ ቀጥሮ እያሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሀይሉ፤ በቀጣይም የእራሱን አገራዊ ስራዎች ለመስራት በእንቅስቃሴ ላይ ነው ብለዋል። ለ ቃና ፕሮግራሞቹን የሚያቀርበው ቢ ሚዲያ የተባለው ኢትዮጵያዊ ድርጅትም ፕሮግራሙን በዶላር በመሸጥ፣ የውጪ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ እንደሚያስገባም የጣቢያው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አክለው ገልፀዋል።ደራሲያንና የፊልም ምሁራን በጉዳዩ ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት ለማወቅ አዲስ አድማስ ሁለት አንጋፋ ባለሙያዎችን አነጋግሯል። የጣቢያው ይዘት ለኢትዮጵያዊው ተመልካች ያን ያህል ይጠቅማል ብዬ አላምንም፤ ጉዳቱ ግን ከፍተኛ ነው ያለው ደራሲ ሀይሉ ፀጋዬ፤ የፕሮግራሙ ይዘት የአገር ውስጥ ስላሳ፣ የውጪው ሰባ እጅ መሆኑ ለአገር ውስጥ እጅግ ዝቅተኛ ትኩረት መሰጠቱን ያሳያል፤ ይሄ ደግሞ እየተንገዳገደ ያለውን የፊልም ኢንዱስትሪ ያቀጭጨዋል ብሏል። የጣቢያው የፕሮግራም ይዘት ከፍተኛ የባህል ወረራን ከማስፋፋቱም በላይ ለጥቂት ሰዎች የስራ እድል በመፍጠር በመስኩ የተሰማሩ ከአስር ሺህ በላይ ሰዎችን ስራ እንደሚያሳጣም ደራሲው ገልጿል። ተቋሙ ገንዘብን መሰረት ያደረገ መሆኑን የገለፀው ሀይሉ ፀጋዬ፤ ይህ ደግሞ ሀላፊነት የጎደለው ስራ ነው ብሏል። የትያትር ባለሙያው ረዳት ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ጀዋሬ በበኩሉ፤ የጣቢያው መፈጠር ገንቢ ነገር አለው፤ ለምሳሌ የህብረተሰቡን የፊልም ማጣጣም አቅም ይጨምራል። ሆኖም ጣቢያው ለውጪ ፊልሞች የሚሰጠው ድርሻ ዝቅ ማለት አለበት ሲል አስተያየቱን ሰንዝሯል። ባህልን ባላገናዘበና ይህንን ለመቆጣጠር የሚያስችል ህግ ባልተረቀቀበት ሁኔታ በስፋት መልቀቁ ግን አደጋ አለው ያለው ፕሮፌሰሩ፤ መጀመሪያ ህግ መውጣት አለበት፤ ፊልሞቹ ባህልን፣ ስነ ልቦናንና፣ እምነትን ጠብቀው ተጣርተው የሚቀርቡና በህግ የሚመሩ መሆን አለባቸው ብሏል። በርግጥ ውድድር መኖር አለበት፤ ውድድር መኖር ያለበት ግን በእኩል የመወዳደሪያ ሜዳ ላይ ነው። ካልሆነ ግን የውድድር አምዱን ኢ ፍትሀዊ ያደርገዋል። ይህ ለኔ ወንጀል ነው ሲልም አስረድቷል ሙሉጌታ ጀዋሬ። በሳተላይት የሚሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ፤ በሳተላይት ለሚሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ፍቃድ አልሰጥም፤ እነዚህ ጣቢያዎች ከውጪ አገራት ፍቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ከባለስልጣኑ እውቅና ውጪ ናቸው ብሏል። ሆኖም ጣቢያዎቹ በኢትዮጵያ የሚያዘጋጁአቸው ፕሮግራሞች ሲኖሩ ባለስልጣን መ ቤቱ የብቃት ማረጋገጫን እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል። የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን የፕሮግራሞች ይዘት የሚቆጣጠርበት አሰራር ግን እንደሌለው ለአዲስ አድማስ ተናግሯል።
አዲሱ ቃና ቴሌቭዥን የአርቲስቶችን መንደር አናወጠ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከደሴ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።በውይይት መድረኩ የተሳተፉት የከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ስራ አጥነት፣ የመሰረተ ልማት አለመሟላትና የህግ የበላይነት አለመከበርን በተመለከተ ጥያቄዎች አንስተዋል።ነዋሪዎቹ የመንገድ፣ ኤሌክትሪክና ሆስፒታል አገልግሎት በተሟላ መልኩ እንዲቀርብላቸውም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።ከነዋሪዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፤ የደሴ ሪፈራል ሆስፒታልን ለመጀመር በጀት ተይዟል ብለዋል።መንግስት የአገሪቱን የኤሌክትሪክ ስርጭት ለማሻሻል የሚያስችል ጥረት መጀመሩን ገልፀው በዚህም የደሴ ከተማም ተጠቃሚ እንደምትሆን ተናግረዋል።የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄውን ለመመለስ በመጪው በጀት አመት ከተያዙ አጠቃላይ ፕሮጀክቶች መካከል ከሀይቅ እስከ ጭፍራ የሚዘልቀው መንገድ አንዱ እንደሆነ አመልክተዋል።በመጨረሻም የወሎ ህዝብ የሚታወቅበትን የመቻቻል እሴት ጠብቆ መቆየት እንደሚገባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መክረዋል።በውይይቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር አምባቸው መኮንንና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል መረጃዉ የኢዜአ ነዉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከደሴ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ
ኢትዮጵያና ሱዳን በወንጀል ጉዳይ ግለሰቦችን ለመለዋወጥ በግንቦት ወር ሁለት ሺህ አራት አመተ ምህረት ያደረጉት ስምምነት ለፓርላማ ቀረበ።ስምምነቱ በሁለቱ አገሮች መካከል ሰላምንና መረጋጋትን ለማስፈን እንዲሁም ሽብርተኝነትን ለመወጋት ጠቃሚ እንደሚሆን የስምምነቱ አባሪ ማብራሪያ ያስረዳል። በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ አገሮች በብሄራዊ ህጎቻቸው ከአንድ አመት ጀምሮ ሊያስቀጣ በሚችል ወንጀል ክስ የቀረበበት ወይም የተቀጣ ግለሰብን ለጠያቂው አገር አሳልፎ ለመስጠት ግዴታ እንዲገቡ የሚያደርጋቸው ነው። ከላይ የተገለፀው እንዳለ ሆኖ የታክስ፣ የጉምሩክና የውጭ ምንዛሪን የተመለከቱ የወንጀል ድርጊቶች የተጠረጠረ ግለሰብ ተላልፎ እንዲሰጥ በሚጠየቅበት ጊዜ ጥያቄው በቀረበበት ወገን ህግ መሰረት መሰል የግብር ወይም የቀረጥ ግዴታ አለመኖሩ የቀረበውን አሳልፎ የመሰጠት ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ እንደማይቻል በስምምነቱ ተገልጿል።በስምምነቱ አንቀፅ አራት መሰረት አሳልፎ የመስጠት ጥያቄ ውድቅ ሊደረግ የሚችልባቸውን ሁኔታዎችም ያስቀምጣል። በዚህም መሰረት ጥያቄ በቀረበለት አገር የወንጀል ድርጊቱ ፖለቲካዊ ይዘት አለው ተብሎ ሲታመን፣ ጥያቄው የቀረበው ግለሰቡን በዘሩ፣ በሀይማኖት፣ በዜግነቱ፣ በፆታው፣ በፖለቲካዊ አመለካከቱ ወይም በመሰል ምክንያቶች ለመክሰስ መሆኑን በሚመለከት በቂ መረጃ ሲኖር እንዲሁም የሚፈለገው ሰው ያለመከሰስ መብት ሲኖረውና ቅጣቱ ወይም ክሱ በይርጋ የታገደ እንደሆነ አሳልፎ የመስጠት ጥያቄው ውድቅ ሊደረግ ይችላል።ጥያቄውን የሚያቀርበው አገር የግለሰቡን ማንነት በተሟላ ሁኔታ የሚገልፁ ማስረጃዎች፣ በፍርድ ቤት የወጣ የእስር ማዘዣ ዋናውንና ኮፒውን፣ የወንጀለኛነት ውሳኔ የመሳሰሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርበታል።በስምምነቱ አንቀፅ ስምንት መሰረት አስቸኳይ ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ ጠያቂው ወገን አሳልፎ የመስጠት ጥያቄ ከማቅረቡ በፊት በወንጀል የሚፈለገው ግለሰብ በጊዜያዊነት በቁጥጥር ስር እንዲውል ሊጠየቅ ይችላል።የስምምነቱ ማፅደቂያ ረቂቅ ለዝርዝር እይታ ለውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርጧል።
ኢትዮጵያና ሱዳን በወንጀል ጉዳዮች ግለሰቦችን ለመለዋወጥ ያደረጉት ስምምነት ለፓርላማ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህርዳር ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲን ሁለት ለ አሸንፏል። በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የተጫወተው ባህር ዳር ከተማ በኦሴ ማውሊ እና ፏድ ፈረጃ ሁለት ጎሎች አዲስ አዳጊውን ለገጣፎ ለገዳዲን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችለዋል። ውጤቱን ተከትሎም ባህር ዳር ከተማ ከነበረበት የውጤት ቀውስ ማገገም ችሏል። አስር ሰአት ላይ መቻል ከኢትዮጵያ መድን ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። በሌላ መርሀ ግብር አስር፡ ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን መቻልን ሁለት ለ አንድ አሸንፏል።
ባህርዳር ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲን ሁለት ለ አሸነፈ
ከረጅም አመታትበፊት በልዩ ዲዛይን በአፄ ሀስላሴና በምስካየ ህዙናን መድሀኒአለም የጋራ ገንዘብ የተሰራውና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሆነው ባንኮ ዲሮማ ህንፃ ያለበቂ ጥናትና ጥንቃቄ በተያዘ የሌላ ህንፃ ግንባታ እቅድ ለመደርመስ አደጋ መጋለጡን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ። በሀገሪቱ በስነህንፃው ዘርፍ ቅርስ የሆነው ፒያሳ አካባቢ የሚገኘው ባንኮ ዲሮማ ህንፃ የመደርመስ አደጋው የተጋረጠበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በህንፃው ቅጥር ግቢ በስተሰሜን በኩል በሚገኘውና ከህንፃው መሰረት ጋር ይገናኛል ተብሎ በሚገመተው ባዶ ቦታ ላይ ለመስራት በተያዘው የሌላ ህንፃ ግንባታ የመሰረት ቁፋሮ ጋር በተያያዘ ነው። ከህንፃው ሜትር እንኳን በማይርቅ ክፍት ቦታ የህንፃው ፓርኪንግ ላይ ቁፋሮ ለመጀመር ማሽነሪዎች የገቡ ሲሆን ቁፋሮው ወደ መሬት ሜትር ጥልቀት እንዳለው ከባለሙያዎች ለመረዳት መቻላቸውን ተናግረዋል። በተለይ ከተወሰኑ ሜትሮች ጥልቀት በኋላ አለት ድንጋይ ይገኛል የሚል ግምት መኖሩን በቁፋሮ ወቅት የአለቱ መገኘት እውን ከሆነ የነባሩን ባንኮ ዲሮማ ህንፃ መሰረት ሊያናጋውና ለመደርመስ አደጋ ሊያጋልጠው እንደሚችል በህንፃ ግንባታ ሙያተኞች ጭምር እንደተገለፀላቸውና በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ስጋት ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። የግንባታ ስራውን የወሰደው ተቋራጭ ድርጅትም ባለው ከፍተኛ ስጋት የተነሳ ለባንኮ ዲሮማ ህንፃ ቀድሞ ኢንሹራንስ የገባለት መሆኑ ተሰምቷል። ኢንሹራንስ ቀድሞ መግባቱ ደግሞ ህንፃው ለአደጋ የመጋለጥ ስጋቱ ምንያህል ከባድ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ነው። በመዲናችን በስነ ህንፃው ዘርፍ ቀደምት ከሆኑት ሁለት ህንፃዎች አንዱ የሆነው ባንኮ ዲሮማ ህንፃ ሊደርስበት ለሚችለው ጉዳት ኢንሹራንስ መገባቱ ከቅርስ ጥበቃ አኳያ ሲታይ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ምክንያቱም ህንፃው ከተደረመሰ በኋላ በተገባለት ኢንሹራንስ መሰረት ሊገነባ ቢችልም እንኳን ታሪካዊነቱንና ቅርስነቱ ሙሉ ለሙሉ የሚያጣ በመሆኑ ነው። ስለዚህ እንዲህ አይነት የሀገርና የህዝብ ሀብት የሆኑ ቅርሶችን የመጠበቅ ታሪካቸውን አፈላልጎና አደራጅቶ የመመዝገብ ሀላፊነት ያለበት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ተቋም ይህንን በህዝብ ልብ ውስጥ በቅርስነት ተመዝግቦ እንደ አይን ብሌን የሚታይ ህንፃ ከውድመት ለማዳን ፈጥኖ እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አቅርበዋል። ህንፃው በቅርስነት ተመዝግቧል ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ዋናው ቁምነገር በቅርስነት የተመዘገበ ያልተመዘገበ የሚለው ሳይሆን የሀገር ቅርስ መሆኑ በህዝቡ መታመኑ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከመዲናችን አዲስ አበባ ቀደምት ከሆነውና ባንድ ወቅት ትልቅ ፎቅ ነው ተብሎ ጉዳት ደርሶበት ከነበረው ገብረ ወልድ ህንፃ ተመጣጣኝ እድሜ ያለው ባንኮ ዲሮማ ህንፃ ያለበቂ ጥናት በሚደረግ የሌላ ህንፃ ግንባታ ምክንያት እንዳይደረመስና ቅርስነቱ እንዳይጠፋ የሚመለከተው አካል ሁሉ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ተቋም ፈጥነው ሊደርሱለትና ከግንባታ በፊት ለነበሩ ህንፃ ደህንነት ሲባል በቂ ጥናት ሊደረግበት ይገባል። ከጥቂት አመታት በፊት ተፈጥሮአዊ ቀለሙን ሊያሳጣ የሚችል ቀለም የመቀባት እድሳት ሊደረግ ሁሉ ነገር ካለቀ በኋላ ታሪካዊነቱን ወይም ቅርስነቱን ያጣል በሚል የነበረውን የቀለም ይዘት ይዞ እንዲቀጥል መደረጉን አስታውሰዋል። ሌላው ስጋት ከህንፃው መሰረት ስር መነሻው ያልታወቀ ከፍተኛ የውሀ ክምችት መኖሩ አሁን ከታቀደው ስራ ጋር ተያይዞ ህንፃውን ለውድመት ይዳርገዋል የሚል ነው። በባንኮዲሮማ ፓርኪንግ ውስጥ ሊሰራ ስለታቀደው አዲስ ህንፃ እና ነዋሪዎች ያቀረቡትን ስጋት በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ
ጥንታዊው ባንኮ ዲሮማ ህንፃ የመደርመስ አደጋ ተጋርጦበታል
አዲስ አበባ፣ ህዳር ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የሊቢያ ድርድር ጊዜያዊ አዲስ የሽግግር መንግስት እና የፕሬዚዳንት ምክር ቤት ሳይሰየም ተጠናቀቀ።በሊቢያ የተባበሩት መንግስታት መልእክተኛ ስቴፋኒ ዊሊያምስ በሀገሪቱ አዲስ የሽግግር መንግስት እንዳልተሰየመ ተናግረዋል።በድርድሩ ተፋላሚ ወገኖቹ በ ወራት ውስጥ በሀገሪቱ በሚካሄደው ምርጫ ፍኖተ ካርታ ላይ መስማማታቸው ይታወሳል።በውይይቱ የምርጫ ሂደቱን የሚታዘብ የሽግግር ጊዜ አስተዳደር ማቋቋምን ያለመ መሆኑ ተጠቅሶ የነበረ ቢሆንም የሽግግር መንግስቱ ሳይሰየም መጠናቀቁ ነው የተነገረው።ሆኖም ተደራዳሪዎቹ በጊዜያዊነት ሊቢያን የሚመራ የሽግግር መንግስት ለመምረጥ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸውን አስታውቀዋል።ውይይቱ የተካሄደው በጎረቤት ሀገር ቱኒዚያ ሲሆን የሰላም ድርድሩ ባለፈው ወር በጄኔቫ በተፎካካሪ ወገኖች መካከል የተፈረመውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ ሰኞ መጀመሩ ይታወቃል።ምንጭ፡ አልጀዚራ
የሊቢያ የሰላም ድርድር የሽግግር መንግስት ሳይሰየም ተጠናቀቀ
ሶስት መቶ ስላሳ ሶስት በትናትናው እለት ታላቁ የጥቁር ህዝቦች ድል የአድዋ ድል ተከብሮ ውሎ ነበር። በርካታ ዝግጅቶችም ተደርገው፣ ድሉ እንደሞገስ ሆኗል። እኔ በምኖርባት በባህር ዳር ከተማ፣ የድል በአሉ እለት ጠዋት ላይ በአደባባይ ሲከበር፣ ከሰአት ላይ ደግሞ በ በአቫንቲ ቡሉ ናይል ሪዞርት በተለያዩ ክዋኔዎች ድሉ ተዘክሯል። የግዮን ቀለም የተሰኘው ቡድን ያዘጋጀው ሰው መሆን ክቡር ዝግጅት ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ነበር የተጀመረው። ታዳሚያኑ መጀመሪያ የተዘጋጀው ሸራ ላይ ካንቫስ ስሜታቸውን በሚፈልጉትና በሚችሉት ቀለም ሲገልጡ ነበር። ከቆይታ በኋላ የስእል አውደ ርእዩ ተከፈተ። በተለያዩ ሰአልያን የተሳሉ ስእሎች፣ የተቀረፁ ቅርፃ ቅርፆች ለእድምተኛው ከሰፊ ማብራሪያ ጋር ቀረቡ። የአውደ ርእዩ ምልከታው ሲጠናቀቅ፣ የመድረክ ላይ ዝግጅቱ ተጀመረ። ከጣና ሀይቅ ዳርቻ ላይ የተሰራው መድረክ ለተሳታፊዎችም የመመልከቻ ቦታ አስቀርቷል። ለስላሳና አረጋጊው የጣና ነፋስ ጋር እየተወያዩ በጎን ዝግጅቱን መመልከት ሰላም ይሰጣል። የግዮን ቀለም ን ቡድን ወክለው አቶ እንዳልካቸው ሙሉ ስለሀሳብ ልእልናና ስለልዩነት ውበትነት ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል። የሀሳብ ገበያዎች መሸሽ፣ የጠብ ሜዳዎች እንዲሰፉ በር ከፍቷል ያሉት አቶ እንዳልካቸው፣ የሀሳብ አምጪዎች ዝምታ ለሀገር ህልውና ፀር ነው። ብለዋል። ንግግራቸውን በመቀጠል፣ የግዮን ቀለም አላማ የሀሳብ ገበያ መመስረት ነው። ሲሉ ሀሳባቸውን በማስረገጥ ንግግራቸውን ቋጭተዋል። የሻማ ልኮሳ በዶክተር አለማየሁ ዋሴ የሶስት መፅሀፍት ደራሲ ናቸው እመጓ ፣ ዝጎራ ና መርበብት ። ሲደረግ፣ ሊቀ ሀሩያን በላይ መኮንን የዳቦ ቆረሳ ስነ ስረአት አድርገዋል። አቢሲንያ የውዝዋዜ ቡድን የአድዋ ድልን በጉልህ የሚያሳይ የዳንስ ትርኢት አቅርቧል። የድምፃዊ ቻላቸው አሸናፊ ወንድም የሆነው ድምፃዊ ዋኘው አሸናፊ በመሰንቆ የታጀበ ቀረርቶውን አቅርቧል። እርሱ ብቻ አይደለም፣ አንድ ወጣት ድምፃዊም ልብን በሀይል የሚሞላ ሽለላ በማቅረብ፣ የታዳሚያኑን ልብ ሲያነዝር ቆይቷል። እነዚህ ዝግጅቶች እንዳቀረቡ ቀጥታ የተሄደው ወደ ማነቃቂያ ንግግር ነው። መጀመሪያው ተናጋሪ ፕሮፌሰር መርሻ ሲሻኝ ነበሩ። ፕሮፌሰር መርሻ ሲሻኝ የታሪክ ምሁር ናቸው። ዝግጅቱ ላይ ወጣቶች በበርካታ ቁጥር ስለተገኙ መደሰታቸውን በመግለጥ ንግግራቸውን የጀመሩት ፕሮፌሰር መርሻ፣ የአድዋ ድል ሆድ ስለባሰን ብቻ የምናነሳሳው ድል አይደለም። ብለዋል። የአድዋ ድል የሶስተኛው አለም ሀገራትን መፃኢ እድል የወሰነ መሆኑን ተናግረዋል። ነጮች የለመዱት እነርሱ ሲያሸንፉ እንጂ ሲሸነፉ አይደለም ነጮች አፍሪካውያንን የሚያስተሳስር ሀሳብ አላቸው ብለው አያስቡም ነገር ግን ኢትዮጵያውያንን የሚያስተሳስራቸው ሀሳብ መንግስት ይባላል፤ ለሀሳቡ ሁሉም ተገዢዎች ናቸው ቀውጢ ቀን በሚመጣበት ሰሞን ነው ያ ሀሳብ የሚያስተሳስራቸው የአድዋ ድል ደግነት ያስገኘው ድል ነው አድዋ አንድ ትልቅ ትምህርት አስተምሮናል። እርሱም ፍቅር አሸናፊ መሆኑን ነው ደግነት ካሰቀመጡት፣ ትልቅ ካፒታል ነው። አጤ ምኒልክ ካፒታሉን በአግባቡ ተጠቅመውበታል በጣልያን የተሸረበው የሸር ገመድ የተበጠሰው በአጤ ምኒልክ ደግነትና ይሉኝታ አስያዥነት ነው ዳግማዊ ምኒል ልዩ ተሰጥኦ ያለው ግለሰብ ካዩ ወደ እልፍኛቸው ማቅረቡን ያውቁበታል ጀግንነት በጦርና በጋሻ ሳይሆን በደግነት፣ በርሀሩሀነትና በይሉኝታ የሚመጣ መሆኑን በአድዋ ድል ላይ ተመልክተናል የዋግሹም ጓንጉል ታሪክ ለዚህ ምሳሌ ነው ዋግሹም በዛው ሰሞን ሸፍተው ነበር። አጤ ምኒልክ ለአድዋው ጦርነት መሰናዳታቸውን ሲሰሙ፣ ጌታዬ፣ ይማሩኝ እርስዎ ጋር በአንድ ጉድጓድ ብቀበር ይሻላል። ብለው፣ አማላጅ ልከው ወደ አጤ ምኒልክ ሰራዊት ተቀላቀሉ ፕሮፌሰር መርሻ በሰፊው ንግግር አድርገዋል። አሁን ያለንበትን አስከፊ ሁኔታ በቻሉት መጠን በምሳሌ ካስረዱ በኋላ፣ በእልህ የተሰለፉት በመጨረሻ ታቅፈው የቀሩት አመድ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ወጣቱን ትውልድ በአፅንኦት ለአንድነቱ ዘብ እንዲቆም አሳስበው ንግግራቸውን ቋጭተዋል። ቀጣዩ ተናጋሪ የሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆነው ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ነበር። ኡስታዝ ስለአንድነትና ስለታሪክ ጠለቅ ያለ ንግግር አድርጓል። የትናንት አሻራችን ለዛሬ ስራችን ወሳኝ ነው። ብሎ የተንደረደረው ኡስታዝ አቡበክር፣ ታሪኩን አድዋን አሁን ካለንበት ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ማስተያየት አለብን። አሁን በተስፋ ውስጥ ብንገኝም፣ በዛው ልክ በርካታ አደጋዎች ተጋርጠውብናል። ሲል ተናግሯል። ስለየጋራነት ስሜት ሲናገርም፣ ከ እኔ ነት ስሜት ወጥተን እኛ ነትን በማዳበር እንደሀገር በመቆም፣ የልጆቿ ተስፋና የሌሎች የነፃነት ተምሳሌትነቷን ያስከበረች ሀገር ይዘን መዝለቅ አለብን። ብሏል። ዛሬ ላይ እኛ ነን ያለነውና የነገውን ቀን ማሰማመር አለብን ልዩነቶችን አክብሮ ወደ መግባባት ለመሄድ የምንከፍለው ዋጋ ኢትዮጵያን ሰው በስውነቱ ተከብሮ የሚኖርባት ሀገር እንዲያደርግ እንጣር። መልካም አሻራችንን አሳርፈን እንለፍ አንድነታችን ሀገራችንን ወደ ተሻለ ደረጃ ያሸጋግረናል ንግግሩን አጠናቅቋል። ግጥም በትወና ቀርቦ እንደቀረርቶውና ሽለላው ታዳሚውን አስፍንጥዟል። የጂጂ ታዋቂ ዘፈን የዝግጅቱ መሪ ስም በአንዲት ወጣት ድምፃዊት ተደምጧል። በየመሀሉ ቀላል ዝናብ እየጣለ ታዳሚያኑን ከየመቀመጫቸው እያስነሳ ወደ ጥላማ ቦታዎች ቢያስሄድም፣ ዝግጅቱ በወጣት ገጣሚን በቀረቡ ግጥሞች አመሻሹ ላይ ተሟሽቷል፤ ከምስጋና ጋር ጭምር። የግዮን ቀለም የሀሳብ ምሽት ለከተማዋ ለባህር ዳር አዲስ ነገር ይዞ እየመጣ ነው። በቅርቡ ለየት ባለ መልኩ፣ የስነ ፅሁፍና የሀሳብ ምሽት እንደሚዘጋጅ ተረድቼአለሁ። ወደፊት ትልቅ መሰናድኦ እንደሚሆን አልጠራጠርም። የአድዋ ድልን በውብ ሁኔታ እንዳሳልፍ ያደረጉትን የዝግጅቱ አዘጋጆች ምስጋና ይደረሳቸው። ዘላለማዊ ክብር ለአድዋ ጀግኖች ሶስት መቶ ስላሳ ሶስት
የአድዋ ድልን በ ግዮን ቀለም ዝግጅት ላይ ሚኪያስ ጥላሁን
ከግዢ መስፈርቱ የወረደ ጥራት ታይቶባቸዋል በተባሉ ሰባት መቶ ስልሳ አምስት ትራንስፎርመሮች ሳቢያ ውዝግብ ውስጥ የገቡትን መንግስታዊ ተቋምና የህንድ ኩባንያ ሲያደራድር የቆየው ፍትህ ሚኒስቴር፣ የመጨረሻውን የመደራደሪያ ሀሳብ ማቅረቡን አስታወቀ። በመንግስት ግዢ አስተዳደርና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አማካይነት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ግዢ ተፈፅሞባቸው ወደ አገር ውስጥ የገቡት ትራንስፎርመሮች፣ ከህንድ ኩባንያ የተገዙ መሆናቸው ይታወቃል። ፍትህ ሚኒስቴር የማደራደሪያ ሀሳቡን ረቡእ የካቲት ሁለት ቀን ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት ለሁለቱም ወገኖች የላከ ሲሆን፣ ከበላይ አመራሮቻቸው ጋር መክረው የውሳኔ ሀሳባቸውን በ ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቁ ማሳሰቡን ፍትህ ሚኒስቴር ለሪፖርተር ገልጿል። በአገሪቱ ውስጥ ከሁለት አመታት በፊት ተፈጥሮ የነበረውን የሀይል እጥረት ለመቅረፍ የትራንስፎርመር ግዢ ለመፈፀም፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የግዢ መስፈርቱን ለመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከሰጠ በኋላ፣ አገልግሎቱ ባወጣው አለም አቀፍ ጨረታ ፌደረር ሎይድ የተባለ የህንድ ኩባንያ አሸንፎ ነበር። አሸናፊው ኩባንያም ከአገልግሎቱ ጋር ወዲያው ውል ፈፅሞ በስምምነቱ የተጠቀሱትን ሁለት ስልሳ አምስት ትራንስፎርመሮች ወደ አገር ውስጥ ቢያስገባም፣ ከገቡት ውስጥ ሰባት መቶ ስልሳ አምስት ያህሉ ከሚፈለገው የጥራት መስፈርት በታች በመሆናቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል እንደማይረካባቸው አስታውቋል ተብሏል። ይልቁንም ካሳ ሊከፈለው እንደሚገባ በማስታወቁ በአቅራቢው የህንድ ኩባንያና የግዢ ትእዛዝ በፈፀመው መንግስታዊ ድርጅት መካከል ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር። ባለፈው ሳምንት የግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና የፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ በጠራው ስብሰባ ላይ የመስሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ ከምክር ቤቱ አባላት ትራንስፎርመሮቹ ለምን ይህን ያህል ጊዜ በወደብ ያለስራ እንደተቀመጡ ተጠይቀው ነበር። እሳቸውም በሰጡት ምላሽ በውዝግቡ ምክንያት በፍትህ ሚኒስቴር የግልግል ዳኝነት እየታየ በመሆኑ ትራንስፎርመሮቹ አለመነሳታቸውን ገልፀው ነበር። ነገር ግን ጉዳዩን በግልግል ይዞታል የተባለው የፍትህ ሚኒስቴር የፍትሀ ብሄር ዳይሬክቶሬት ጉዳዩ የግልግል ጉዳይ ሳይሆን የማደራደር ስራ ተሰጥቶት ላለፉት ዘጠኝ ወራት ሲመረምርና ሁለቱን ወገኖች ልዩነታቸውን ለማቀራረብ እየሰራ መቆየቱን፣ ዳይሬክተሩ አቶ ሙሉጌታ አያሌው ለሪፖርተር ገልፀዋል። ሆኖም ለትራንስፎርመሮቹ በወደብ መቆየት የፍትህ ሚኒስቴር አደራዳሪነት እንደ ምክንያት ሊጠቀስ እንደማይገባው አመልክተዋል። ፌደረር ሎይድ የተባለው የህንድ ኩባንያ ትራንስፎርመሮቹን ህንድ ውስጥ በሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት ጥራታቸው ተረጋግጦ ያስገባቸው በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው ምርመራ የተገኘው ውጤት በስምምነቱ መሰረት የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አላሟሉም መባሉን አለመቀበሉ ተገልጿል። የማደራደር ሂደቱን ከሌሎች ሁለት የፍትህ ሚኒስቴር ባልደረቦች ጋር እየመሩ ያሉት አቶ ሙሉጌታ እንደገለፁት፣ ሁለቱ ወገኖች በሶስት ጉዳዮች ላይ ባለመግባባታቸው ምክንያት ነበር ድርድሩ ረዘም ያለ ጊዜ የወሰደው። ሲከራከሩባቸው ከቆዩባቸው ጉዳዮች መካከል በዋነኛነት ሊግባቡ ያልቻሉት በትራንስፎርመሮቹ የሀይል መጠን ቅነሳ በሚባለው ሲሆን፣ ይህም እያንዳንዱ ትራንስፎርመር ሀይል ማመቅ ሲጀምር የሀይል ብክነት መጠኑን በሚመለከት ልኬት ላይ ያተኮረ ነው። ቀሪዎቹ ደግሞ የተጣራ የጉዳት ካሳ እና የዲመሬጅ ክፍያን በተመለከተ እንደነበሩ አቶ ሙሉጌታ አብራርተዋል። ሁለቱንም የማስማማት ስራው እየተገባደደ ነው። የሁለቱም ተቋማት የበላይ ሀላፊዎቻቸው ባቀረብንላቸው ሀሳብ መሰረት በየግላቸው ተወያይተው እስከ የካቲት ቀን ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት አቋማቸውን እንዲገልፁ አሳውቀናቸዋል። ባቀረብንላቸው ሀሳብ ከተስማሙ ጉዳዩ በዚያው እንዲያልቅ እንፈልጋለን። ነገር ግን በዚህም መስማማት ካልቻሉ ጉዳዩ ቀድሞ ተቋርጦ ወደነበረው መደበኛ ፍርድ ቤት ይሄዳል፤ ሲሉ አቶ ሙሉጌታ አስረድተዋል። ይሁን እንጂ የመጨረሻ ሀሳብ የተባለውን የድርድር ሀሳብ ከሁለቱም ወገኖች መልስ እስከሚመጣ ድረስ ሊገለፅ እንደማይችል አደራዳሪው ገልፀዋል። ትራንስፎርመሮቹ አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ የሀይል ብክነት መጠናቸውን ምርመራ ያከናወነው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን መሆኑን፣ የግዢ ስራው ህንድ ውስጥ ሲከናወን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ተወክለው እንዲታዘቡ የተላኩ ባለሙያዎች ተልከው እንደነበር የሚሉ ነጥቦች ተነስተውላቸው፣ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ራሱ ትራንስፎርመር እያመረተ፣ በሌላ ኩባንያ ተገዝተው አገር ውስጥ የገቡ ትራንስፎርመሮችን የመመርመር ስራ በምን የህግ አግባብ እንዳከናወነና የጥቅም ግጭትን በተመለከተ ተጠይቀው ነበር። የድርድር ስራው ገና ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠቡት ዳይሬክተሩ፣ ኮርፖሬሽኑ እንደዚያም ቢሆን እንኳ ትራንስፎርመር ቢያመርትም የግዢ ጨረታው ወጥቶ ግዢ እስከተፈፀመበት ጊዜ ድረስ የራሱን ትራንስፎርመር ማምረት አልጀመረም፤ በማለት መልሰዋል። ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ የትራንስፎርመር ግዢ ያስፈለገው በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የሀይል እጥረት በመኖሩ ምክንያት ነው ብለዋል። አስቸኳይ ግዢ ተደርጐ ከውጭ አገር ማስገባት ማስፈለጉም ሌላው ጉዳይ መሆኑን አክለዋል። እንዲሁም የግዥ ሂደቱን ለመታዘብ ወደ ህንድ እንደሄዱ የተገለፁት ባለሙያዎች፣ ከጥራት በታች ተገዝተዋል በተባሉ ትራንስፎርመሮች ጉዳይ ሊኖራቸው የሚገባ ተጠያቂነት ካለ የሚል ጥያቄ ሲነሳላቸውም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ነገር ግን የግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ውሉን ከመፈራረሙ በፊት ፍትህ ሚኒስቴርን አማክሮ ቢሆን ኖሮ፣ ውዝግቡ እዚህ አይደርስም ነበር ሲሉ አቶ ሙሉጌታ ገልፀዋል። ባለፈው ሳምንት ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ የሰጡት አቶ ይገዙ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የአምስት ሚሊዮን ዶላር ካሳ መጠየቁን አስታውሰው፣ የህንዱ ኩባንያ ግን ከሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለመክፈል ፈቃደኛ አለመሆኑን መጥቀሳቸው ይታወሳል።
ፍትህ ሚኒስቴር በትራንስፎርመር ጥራት የተወዛገቡ መንግስታዊ ተቋምና የህንድ ኩባንያ እያደራደረ ነው
ኢትዮጵያ ዉስጥ ህፃናትን በጉዲፈቻ ስም ለፈረንጆች አዘጋጅተው ከሚያቀብሉት የንግድ ድርጅቶች አንዱ እናት አለም ወላጅ አልባ ህፃናት ወይም ቀደም ሲል ድርጅቱ ህፃናቱን ምግብ በመከልከል ሲታመሙ ተገቢውን ህክምና ባለመስጠትና በአጠቃላይ ለህፃናቶቹ እንክብካቤ ባለማድረግ ስሙ የተነሳ ሲሆን አሁን ደግሞ የተገኙት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ድርጅቱ ድሀ እናቶችን እያፈላለገ ልጆቻቸውን በእናት አለም ወላጅ አልባ ህፃናት በኩል ጉዲፈቻ እንዲሰጡ እንደሚያግባባ ተደርሶበታል።ከድርጅቱ ሰራተኞች አንዱ ግርማ ቀበለ በእናት አለም ወላጅ አልባ ህፃናት የጥበቃ ሰራተኛ ሲሆን ለሲውዲን ጋዜጠኞች እንደተናገረው ሌሊቱን በየመንደሩ እየተዘዋወረ ደሀ እናቶች ልጆቻቸውን ለፈረንጆች ጉዲፈቻ እንዲሰጡ እንደሚያግባባና እስካሁን በ ጉዲፈቻዎች ውስጥ እጁ እንዳለበት ተናግሯል።የወያኔ ባለስልጣናት ተሯሩጠው የተጋለጠውን ድርጅት ዘግተውታል ይሁንና አብዛኞቹ በጉዲፈቻ ስም ህፃናትን ከድሀ እናቶች ላይ ወስደው በመሸጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ስውር የወያኔ ባለስልጣናት እጅ እንዳለባቸው ይጠረጠራል።በርካታ የመብት ተሟጋች ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን አምርረው ያወግዙታል። ነዋሪነቱ በኖርዌይ የሆነው ሀያሲ ጌታባለው በቀለ ሰሞኑን ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ህፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው በሚል ርእስ ባስነበበው ጦማሩ እንዲህ ብሎ ይጠይቃል ህፃናት አሳዳጊ የሚያጡት ባብዛኛው የርስበርስ ጦርነት ሲኖር ወይንም ሰላም በተናጋበት ጊዜ ነው። ኢትዮጵያ ግን ጎዳና የወጡት ህፃናቶቿ የበዙት በአንፃሩም ቢሆን ጦርነቱ ከቆመ ጊዜ ጀምሮ ነው ለምን።ከዚህ ቀደም የአውስትራሊያው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ቅጥ ያጣ ጉዲፈቻ ባጋለጠበት ወቅት ድረገፃችን ጉዳዩን ዘግቦ ነበር። ከጥቂት ወራቶች በሗላ በዋሽንግተን ዲሲ በሚኖሩ የወያኔ አባላት በኩል የተቀጠረ ጠበቃ የጉዲፈቻ ድርጅቱን ስም በማጉደፍ ድረገፃችንን ለመክሰስ እየተሰናዳ መሆኑን አሳወቀን። ከጠበቃው ጋር በተነጋገርንበት ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ስላለው በጉዲፈቻ ስም ህፃናትን የመሸጥ ጉዳይ በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች መነሳቱን እንደምንፈልገውና እንዲያውም የኢትዮጵያ ባለስልጣናትን የበለጠ ለማጋለጥ እንደሚረዳን አሳወቅነው ነበር። ይሁንና ጠበቃው በጉዳዩ ዙሪያ ተመልሶ አላነጋገረንም።
በጉዲፈቻ ስም ህፃናትን መሸጥ እንደቀጠለ ነው
ሞርኒንግ ስታር ሞል የገና ልዩ ቅናሽ ቦሌ ኤድናሞል ጎን የሚገኘውና አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ አመት በላይ የሆነው ሞርኒንግ ስታር ሞል ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ የጌታን ልደት ለማስታወስ በአይነቱ ልዩ የሆነና ሜትር ርዝመት ያለው የገና ዛፍ ሰርቶ በሩ ላይ አቁሟል። ይህ ግዙፍ የገበያ ማእከል ከዛፉ በተጨማሪ ጌታ የተወለደበትን ቦታ ለማስታወስም በረት የሰራ ሲሆን ከማእከሉ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ቡና አፈላል ስነ ስርአት የሚካሄድበት ዳስ ጥሎ ሰዎች ቡና እየጠጡ የሚፈልጉትን እቃ ለገና በአል በተደረገ ልዩ ቅናሽ እየሸመቱ የሚዝናኑበትን ሁኔታ አመቻችቷል። ይህ ግዙፍና ሜትር ርዝመት ያለው ዛፍ የፈረንጆቹንም የሀበሻንም የገና ዛፍ አሰራር ያጣመረና አካባቢን በማያቆሽሽ መልኩ የተሰራ ሲሆን በአጠቃላይ ሺህ ብር መፍጀቱን የሞርኒንግ ስታር ሞል የማርኬቲንግ ባለሙያ አቶ ሳሙኤል ሙሉጌታ ጠቁመው እስከ ዛሬ ምሽት በሚቆየው ልዩ ዝግጅት ሰዎች እንዲታደሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ቪአይፒ ሬስቶራንት ባለ አምስት ኮከቡ ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴልም እንደዚሁ ልዩ የገና የእራት ምሽት ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው እጅግ ምቹና ዘመናዊ በሆነው ቪአይፒ ሬስቶራንቱ አዘጋጅቷል። ዴሉክስ ሜኑ የተባለው ልዩ እራት በምቹው ሬስቶራንት ውስጥ በለስላሳ ሙዚቃ ታጅበው ከወይን መጠጥና ቢራ ጋር የሚያጣጥሙበት ልዩ ምሽት መሆኑን የሆቴሉ የህዝብ ግንኙነት አቶ ታሪኩ ዋስይሁን ተናግረዋል። ከምሽት እስከ እኩለ ሌሊት በሚዘልቀው በዚህ የእራት ምሽት ላይ ለመታደም ለአንድ ሰው ብር ለጥንዶች ብር ክፍያ እንዳለውም አቶ ታሪኩ ጨምረው ገልፀዋል። ኢንተርኮንትኔንታል እራትና ሙዚቃ በባንድ ባለ አራት ኮከቡ ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘውና አዲስ ባሰራው ተሽከርካሪ ሬስቶራንቱ ልዩ የገና እራትና በባንድ ቀጥታ የሚተላለፍ የሙዚቃ ዝግጅት አሰናድቷል። ዛሬ በበአሉ ዋዜማ ከምሽቱ እስከ እኩለ ሌሊት በሚዘልቀው በዚህ የመዝናኛ መሰናዶ በተለይ በገና ወቅት በብዛት የሚበሉት ተርኪ ቺክንና መሰል ምግቦች በልዩ ሁኔታ ተከሽነው የሚቀርቡ ሲሆን እንግዶች ያሻቸውን መጠጥ መጠቀም እንደሚችሉም ተገልጿል። በዚህ ምሽት እራት ለመመገብ ብር የሚያስከፍል ሲሆን አስርና ከዚያ በላይ በቡድን ለሚመጡ የ በመቶ ቅናሽ እንደሚደረግላቸው የሆቴሉ የሽያጭና ገበያ ዳይሬክተር አቶ ወገኔ ታደሰ ገልፀዋል። በተጨማሪም በሆቴሉ የሚገኘው ቮልቴጅ ክለብ ከምሽቱ ጀምሮ ልዩ የገና የዲጄ ሙዚቃ መዘጋጀቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ መግቢያው ነፃ እንደሆነና እስከ ሌሊቱ እንደሚዘልቅ ተናግረዋል። ራማዳ አዲስ ልዩ እራት ከአንድ አመት ተኩል በፊት በመሀል ቦሌ ከአገልግሎት መስጠት የጀመረው ባለ ኮከቡ ራማዳ አዲስ ሆቴል ለገና ዋዜማ ሼፍስ ክለብ እና ፎጎ ኖቾ በተባሉት ሁለት ታዋቂ ሬስቶራንቶች ውስጥ ልዩ የእራት ምሽት አዘጋጅቷል። በዚህ ልዩ የእራት ምሽት ኢትዮ ኳርቴት የተባለ የሙዚቃ ባንድ ልዩ የሙዚቃ ትርኢት በቀጥታ ለታዳሚው እንደሚያቀርቡም የሆቴሉ ፀሀፊ አቶ የኔአለም ክፍሉ አስታውቀዋል። በብሄራዊ ቴአትር ልዩ ሙዚቃ ታላቁ ብሄራዊ ቴአትር በገና በአል እለት እሁድ ከሰአት በኋላ ከቀኑ ጀምሮ ልዩ የሙዚቃ ዝግጅት ያቀርባል። ባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃዎች በልዩ ሁኔታ በሚቀርቡበት በዚህ የበአል የሙዚቃ ዝግጅት የቴአትር ቤቱ አንጋፋና ወጣት ድምፃዊያን ቫራይቲ በተሰኘው የቴአትር ቤቱ ኦርኬስትራ ታጅበው ታዳሚውን እንደሚያዝናኑ የታወቀ ሲሆን የባህል ሙዚቃ ኦርኬስትራውም ከባህላዊ ሙዚቃ ድምፃውያን ጋር ሆኖ በአሉን በአል እንደሚያስመስሉት የቴአትር ቤቱ የሙዚቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወሰን የለህ መብረቁ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል። እስከ ቀኑ በሚዘልቀው የበአል ልዩ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ለመታደም መግቢያው ብር እንደሆነ ታውቋል። ሀፒ ኢቨንትስ ልዩ የገና ዋዜማ ጨዋታዎችን አዘጋጅቷል ለልጆች የደስታ ቀን ለመፍጠር የታሰበ ነው ግሩም ሰይፉ ሀፒ ኢቨንትስ አዳዲስና የተለያዩ የገና ዋዜማ ጨዋታዎችን ለልጆች ማዘጋጀቱን አስታወቀ። የዋዜማ ዝግጅቱ ቦሌ ድልድይ አካባቢ ከቦራ መዝናኛ ማእከል አቅራቢያ በሚገኘው በቦሌ ህብረተሰብ ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ዛሬ ከጠዋቱ ሰአት ጀምሮ እስከ ሰአት የሚካሄድ ሲሆን መግቢያው ለህፃናት ብር ለወላጆች በነፃ መሆኑ ታውቋል።አዘጋጆቹ ልዩ የገና ዋዜማ ጨዋታዎችና መዝናኛዎችን ያሰናዱበትን ምክንያት ለአዲስ አድማስ ሲገልፁከፈተና መልስ ለልጆች የገናን በአል ምክንያት በማድረግ የደስታ ቀን ለመፍጠር በማሰብ ነው ብለዋል። የሀፒ ኢቨንትስ ሁለት አርቲስቶች የሻማ ቀራፂና ሰአሊ አስናቀ ክፍሌ እና ሳሮን ከፍአለ ሲሆኑ አብሯቸው የሚሰራው ደግሞ የህፃናት አጫዋችና የሰርከስ ባለሙያ የሆነው ተመስገን ግርማ ነው። አርቲስት አስናቀና ሳሮን ለህፃናት በአዲስ መልክ የፈጠሯቸውንና ከሌሎች አገራት በመመልከት በሰሯቸው ልዩ ልዩ ጨዋታዎችና ውድድሮች ህፃናትን የሚያዝናኑ ሲሆን መዝለያዎች የቅርጫት ኳስ ቀለም መቀባት የህፃናት ፎቶየፊት ላይ ስእሎች የህፃናት አዝናኝ ትረካና ሌሎች የተለያዩ መዝናኛዎችን እንደሚያቀርቡ ለማወቅ ተችሏል። በበርካታ ህፃናት ዘንድ ጥሩንቤ በሚለው ስሙ የሚታወቀው ተመስገን ግርማከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሳሙና አረፋዎች በሚሰራቸው አስደናቂ ትርኢቶች አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን በዛሬው እለት ህፃናትን ለማዝናናት ዝግጁ ሆኖ ይጠብቃል ተብሏል።
በገና ዋዜማና በበአሉ የት እንሂድ
የዲሞክራቲክ ተቋማት አለመጠናከር በምርጫው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳርፏል የአሜሪካ እምባሲየዘንድሮውን ምርጫ የመታዘብ እድል ያላገኘው የአውሮፓ ህብረት ምርጫው በተለያዩ ተፅእኖዎች መሀል የተደረገ እንደነበር የገለፀ ሲሆን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ ምርጫው ሰላማዊ ቢሆንም የዲሞክራሲ ተቋማት አለመጠናከር በምርጫው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳርፏል ብሏል።የአውሮፓ ህብረት ትናንት ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱ ሰላማዊ የምርጫ ሂደት ማስተናገዷን ጠቅሶ ከምርጫው በፊት የጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች መታሰር መታሰር እንዲሁም የጋዜጦችና መፅሄቶች መዘጋት ፓርቲዎች በፖሊሲያቸው ላይ ሰፊ ክርክር እንዳያደርጉ እንቅፋት በመሆን በአጠቃላይ የምርጫው እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳርፏል ብሏል።በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ ባለፈው ረቡእ ባወጣው መግለጫ ምርጫው ሰላማዊና ፍትሀዊ እንዲሆን ምርጫ ቦርድ ላሳየው ትጋትና የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድን ላቀረበው የትዝብት ሪፖርት እውቅና ሰጥቶ በሀገሪቱ የሲቪክ ማህበራት ላይ የተጣለው ገደብ የሚዲያ ነፃነትና ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት በሚገባ አለመከበሩ አሳሳቢና በዲሞክራሲያዊ ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚያሳርፍ እንደሆነ ጠቁሟል።ምርጫውን ለመታዘብ ፈልገን ተከልክለናል ያለው ኤምባሲው ሌሎች አካላትም ምርጫውን እንዳይታዘቡ መደረጉና የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎች ምርጫውን በተገቢው ሁኔታ መታዘብ አለመቻላቸው በምርጫው የታዩ ጉልህ ግድፈቶች መሆናቸውን ጠቁሟል።የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የአሜሪካ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የቆየ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሰረት በማድረግ በአካባቢያዊና አለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጋር ለወደፊትም በጋራ እንደሚሰሩ በመግለጫቸው አስገንዝበዋል። የዘንድሮው ምርጫ ብቸኛ አለማቀፍ ታዛቢ ቡድን በመሆን የታዘበው በናሚቢያው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሄፊኬቱንዬ ፖሀምባ የተመራው የአፍሪካ ህብረት የታዛቢ ቡድን ባለፈው ማክሰኞ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ ምርጫው ተአማኒና ሰላማዊ ነው ቢልም በምርጫው እለት የታዘባቸውን ግድፈቶች በዝርዝር ገልጿል። ህብረቱ በሀገሪቱ ካሉት ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች በቱ ብቻ አባላቱን በማሰማራት መታዘቡን ጠቁሞ ከታዘባቸው ጣቢያዎች መካከል በ በመቶ በሚሆኑት የምርጫው እለት የቅስቀሳ መልእክቶችና ፖስተሮች ሲሰራጩ እንደነበር በመቶ በሚሆኑት ደግሞ በምርጫ ጣቢያ ውስጥ ቅስቀሳ ሲካሄድ መታዘቡን ሪፖርት አድርጓል። ህብረቱ ከተመዘገበው መራጭ በላይ የምርጫ ወረቀት በኮሮጆ ውስጥ የተገኘበት የምርጫ ጣቢያ እንዳጋጠመውና የኮሮጆ ፍተሻ ሳይካሄድ ምርጫ የተጀመረባቸው ጣቢያዎችን እንደታዘበ ጠቁሟል። ህብረቱ ይፋ ባደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ጉድለቶች ቢኖሩም ምርጫው ሰላማዊ የተረጋጋና ተአማኒ እንደነበር የገለፀ ሲሆን ከሁለት ወር በኋላ ሙሉ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።
ምርጫው በተለያዩ ተፅእኖዎች መሀል የተደረገ ነው የአውሮፓ ህብረት
ለቀድሞ ሚስቱ ሚ ዶላር እንዲያካፍል ተበይኖበታልየሆሊዉዱ ዝነኛ የፊልም ባለሙያው ሜል ጊብሰን በተደጋጋሚ በገጠመው የጋብቻ ፍቺ ለከፍተኛ ኪሳራ እየተዳረገ እንደሆነ ተገለፀ። ለ አመት ያህል በትዳር አብራው የዘለቀችው የቀድሞ ሚስቱ ሮቢን ዴነስ በጠብ እንደተለየችው የሚታወቅ ሲሆን ከሁለት አመት በፊት ፍቤት የሀብት ክፍፍል እንዲወስንላት በጠየቀችው መሰረት ሰሞኑን ጊብሰን ካለው የ ሚዶላር ሀብት ላይ ሚ ዶላር እንድትካፈል ተፈርዶላታል። የ አመቷ ሮቢን ዴነስ የተካፈለችው የሀብት መጠን በሆሊዉድ ታሪክ በከፍተኛነቱ ሪከርድ እንደያዘ ሮይተርስ ዘግቧል። ከ አመት በፊት ደግሞ በፍቺ ለተለያያት ሚስቱ ከሀብቱ ላይ ሚሊዮን ዶላር ያካፈለው ስቲቨን ስፒልበርግ ከሜል ጊብሰን ቀጥሎ ከፍተኛውን ገንዘብ የከፈለ የሆሊውድ ሰው ሆኗል።የሜል ጊብሰንን ለየት የሚያደርገው ከስድስት ወር በፊት ኦክሳና ግሪግሮቫ ከተባለች ፍቅረኛው ጋር በፀብ ተለያይቶ በፍቤት በተወሰነበት መሰረት ተጨማሪ ሺ ዶላር መክፈሉ ነው። ሜል ጊብሰን በተዋናይነት በፕሮዱዩሰርነትና በዲያሬክተርነት በሰራባቸው ከ በላይ ፊልሞች በአጠቃላይ ከ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አስገኝቷል።
ሚል ጊብሰን በፍች ለኪሳራ ተዳርጓል
በኦሮሞና ሶማሌ ወሰኖች ላይ የተጀመረው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ። በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከሶማሌ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተፈናቅለው ወደ ሀረር መግባታቸው ታውቋል። ሁለቱ ክልሎች እየተወዛገቡ ነው። ከሁለቱም ወገኖች በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱ ወደ አጠቃልይ ቀውስ ሊያመራ እንደሚችል እየተነገረ ነው። የሀይማኖት አባቶች ጥሪ አስተላልፈዋል። ይህ ግጭት በአገዛዙና በህዝብ መካከል ብቻ መሆኑን በሶማሌ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢሳት በኩል መልእክት እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል። የሁለቱ ክልሎች መንግስታት እየተወነጃጀሉ ነው። ሁለቱም ወገኖች በየፊናቸው የሚያሰራጯቸው መልእክቶች ግጭቱን ከማብረድ ይልቅ እንዲባባስ ምክንያት መሆኑም እየተነገረ ነው። ይሄን ያህል ዜጎች ሲገደሉና ከሚኖሩበት ተባረው ሲወጡ በዝምታ እየተመለከተ ያለው የህወሀት መንግስት ለሀያ ስድስት አመታት የተከተለው የዘር ፖለቲካ ውጤት ነው የሚለው ድምዳሜ በብዙ ወገኖች ዘንድ እየተሰጠ ነው። ለኢሳት የሚደረሱ መረጃዎች አሰቃቂ በመሆናቸው ለህዝብ ደህንነት ሲባል እንዳይተላለፉ መደረጋቸው ተገልጿል። ባለፉት ሶስት ቀናት ከሶማሌ ክልል የተለያዩ ከተሞች በተለይም ከጂጂጋና ውጫሌ በመታወቂያቸው በሰፈረ የብሄር ማንነት እየተለዩ የሚገደሉ፣ የሚታሰሩ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር እየጨመረ መቷል። ይህን በመስጋት ቤት ንብረታቸውን ትተው የተሰደዱ የኦሮሞ ተወላጆች ወደ አቅራቢያ የኦሮሚያ መንደሮች እየገቡ ሲሆን በሀረር ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ መድረሳቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ለኢሳት ዛሬ በደረሰው መረጃ በሺ ዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከጅጅጋ በመውጣት ላይ ናቸው። እስከ ሺ የሚሆኑት ከሶማሌ ክልል እንደሚፈናቀሉ አንድ ባለስልጣን ለዘጋቢያችን ገልፀዋል። ተፈናቃዮቹ በሽሽት ላይ እያሉ በመንገድ ላይ ግጭት ተከስቷል ተብሏል። ስለደረሰው ጉዳት ግን ዝርዝር መረጃ እየጠበቅን ነው። ጥቃቱን እየፈፀሙ ያሉት የሶማሌ ልዩ ሀይል አባላት መሆናቸውን ተፈናቃዮች ይናገራሉ። በሶማሌ ተወላጆች በኩልም ግድያና መፈናቀል እንደደረሰባቸው የሚገለፁ መረጃዎች በመውጣት ላይ ናቸው። የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫ በሶማሌ ልዩ ሀይል የጭካኔ እርምጃ የተቆጡ የኦሮሞ ተወላጆች ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ግጭት ተፈጥሮ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል። ከእነዚህም ውስጥ ቱ የሶማሌ ተወላጆች መሆናቸው ተገልጿል። ዛሬ በሀረር ተቃውሞ መካሄዱ ተሰምቷል። ሸዋ በር እና ፈረስ መጋላ አካባቢ የአጋዚ ወታደሮች አንድ ሰው መግደላቸው የተገለፀ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ውጥረት መንገሱን ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት። በድሬዷም እንዲሁ ግጭት እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን ስለደረሰው ጉዳት ግን የታወቀ ነገር የለም። ሶማሌላንድ በተባለችው ሀገር የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት በመፈፀም ላይ መሆኑን ዘግይቶ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ የኦሮሞ ተወላጆች በሶማሌላንድ መገደላቸውንም ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። በሌላ በኩል ለኢሳት በስልክ፣ በኢሜይና በፌስቡክ ከሀገር ቤት በተለይም በሶማሌና ኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን በርካታ መልእክቶች እየደረሱ ሲሆን ህዝቡ ከማንኛውም የእርስ በእርስ ግጭት ራሱን እንዲጠብቅና እንዲከላከል የሚጠይቁ ናቸው። ይህ የህወሀት መንግስት ከህዝብ ጋር የገባበት ግጭት እንጂ በኢትዮጵያውያን መሀል የተፈጠረ አይደለም የሚለው መልእክት በሁለቱም ክልሎች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተላለፉ ናቸው።
በኦሮሞና ሶማሌ ወሰኖች ላይ የተጀመረው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ ሀያ ዘጠኝ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ማእከል ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ዶክተር ገለፁ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ሀያ አምስትኛ መደበኛ ስብሰባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የሁለት ሺህ አመተ ምህረት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ገምግሟል። በለጠ ሞላ ዶክተር የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ተማሪዎችን ወደ ቻይና እና ሩሲያ በመላክ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት እንዲማሩ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል። በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ማእከል ለመገንባትም ከሩሲያው የኒውክሌር ኩባንያ ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ብለዋል። የአዋጭነት ጥናቱ ካለቀ በኋላ የማእከል ግንባታውን የማከናወን ስራ እንደሚጀመር በመግለፅ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ከቻይና መንግስት ጋር በመተባበር ሁለት ሳተላይቶችንም ወደ ህዋ እንዳመጠቀች አስታውሰዋል። እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ የፈጠራ ሀሳብ ስርአት ባለው መልኩ ዘላቂነትና ግልፅነት እንዲኖረው ለማስቻል የኢኖቬሽን ስታርታፕ ድጋፍ ማእከል ማዘጋጀት ትኩረት ተሰጥቶት የተከናወነ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በሀገር ውስጥ በመሆን የውጭ ሀገር ስራዎችን ለመስራት ለተሰማሩ ስድስት ድርጅቶች ከታክስ ነፃ አገልግሎትና የውጭ ሀገር የስራ ፈቃድ እንዲያገኙ መደረጉንም ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂዎች በአግባቡና በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የጎንዮሽ ጉዳታቸውን ለመቀነስ ሲሰራ እንደነበርም በመግለፅ ለሁለት ሺህ አራት መቶ ሰባ ሁለት የቴክኖሎጂ ቁሶች ፈቃድ መሰጠቱን ተናግረዋል። ተቋማቸው የምርምር ስራዎችን እንደሚደግፍ ገልፀው የምርምር ውጤቶችም ችግር የሚፈቱና ማህበረሰብን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችሉ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ብለዋል። ዘርፉ የሚፈልጋቸው አዋጆችና ደንቦች ተቋሙ በሚፈልገው ልክ መፅደቅ አለመቻላቸውና ለቴክኖሎጂ ግዥዎች የውጭ ምንዛሬ በሚፈለገው ደረጃ ማግኘት አለመቻል ያጋጠሙ ተግዳሮቶች መሆናቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ በቀጣይ የምርምር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም በትኩረት ይሰራል ብለዋል። እያንዳንዱ የምርምር ውጤት ለአገልግሎት ከመዋሉ በፊት ማለፍ ያለበትን የሴፍቲ ስታንዳርድ አሟልቶ ሲያልፍ ለአገልግሎት እንዲውል እንደሚደረግም ተናግረዋል። የሳይበር ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው የዲጂታል ፋይናንስ የክፍያ ስርአት መገንባት እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል። በከተማና በገጠር፣ በወንዶችና በሴቶች እንዲሁም በክልሎችና በከተሞች መካከል በዲጂታል ትስራቴጂው ትግበራ ልዩነቶች እየሰፉ እንዳይሄዱ መስራት እንደሚያስፈልግ እና ይህም ትኩረት የሚያስፈልገው ጉዳይ መሆኑን አመላክተዋል። የዘርፉ አሰራር ጥምረትንና ትብብር እንደሚጠይቅ ጠቅሰው ተቋማት እያለሟቸው ያሉ የዲጂታል ሲስተሞችና እየገነቡ ያሏቸው መሰረተ ልማቶች ላይም የክትትልና የድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል። በምክር ቤቱ የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለፈጠራ ሀሳብ ባለቤት ወጣቶች ድጋፍ በማድረግ በየአካባቢው የሚገኙትን ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም እንደሀገር ሀብት መጠቀም እንዲቻል በየክልሎች ማእከላትን በመክፈት ረገድ ተቋሙ እንዲሰራ ጠቁሟል። በየሻምበል ምህረት
የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ማእከል ለመገንባት እየተሰራ ነው በለጠ ሞላ ዶክተር
አዲስ አበባ፡ በኢሬቻ ህግ መሰረት ዛፎችን መንከባከብ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው በመሆኑ የደን ሀብት እንዲጠበቅና ተፈጥሮ ፀጋዋን ጠብቃ እንድትቀጥል ትልቅ ሚና እንዳለው የቀድሞ አባገዳ ሰንበቶ በየነ ተናገሩ። ላለፉት አመታት ቀድሞ በአባገዳነትና ሌሎች ሀላፊነቶች ላይ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በአባገዳዎች ህብረት ውስጥ እያገለገሉ ያሉት አባገዳ ሰንበቶ በየነ ለኢትዮጵያን ሄራልድ እንደገለፁት፤ ገዳ ሰማይን ምድር፣ እናትና አባት ብሎም ለቱሉና መልካ ትልቅ ክብር የሚሰጥና ከፈጣሪ ዘንድ ከማይጣሱ ስድስት ህጎች ውስጥ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ መልካና ቱሉ ሰዎች ለአምላካቸው ምስጋና የያሚቀርቡበት ስፍራ ነው። የምስጋና መርሀ ግብሩ በሀይቆች ዳርቻ ከማክበር በዘለለም የገዳ ስርአቱ ስምንት ከፍተኛ ተራሮችን የዚሁ መርሀ ግብር መፈፀሚያ ስፍራዎች አድርጎ መርጧል። በመሆኑም ከእነዚህ ስፍራዎች ዛፎችን መቁረጥ በጥብቅ የተከለከለ ነው። በተጨማሪም በኢሬቻ ህግ መሰረት ዛፎችን መንከባከብ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው መሆኑንም አመልክተዋል። የገዳ ስርአትም የደን ሀብት እንዲጠበቅና ተፈጥሮ ፀጋዋን ጠብቃ እንድትቀጥል ትልቅ ሚና እንዳለው አረጋግጠዋል። የገዳ ኮሌጅ ለመክፈት ውጥን እንዳላቸው እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተወያዩ መሆኑንም አባ ገዳ ሰንበቶ ጠቁመዋል። የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው፤ ገዳ እና ኢሬቻ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ብለዋል። ገዳ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ስነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ እሴቶችን ሁሉንም በአንድ አጠቃሎ የያዘ ነው። ኢሬቻ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ ለፈጣሪው ዋቃ ምስጋና የሚያቀርብበት መርሀ ግብር ነው። ኢሬቻ ለፈጣሪ ብቻ ሳይሆንም መልካም ሰዎችም የሚመሰገኑበት በአል ነው። እንደ አቶ ከበደ ገለፃ፤ ውሀ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ አለው። ከፍጥረታት ቀድሞ ውሀ የተፈጠረ ሲሆን በኦሮሞ ባህል ጠላት እንኳን ቢሆን ውሀ አይከለክልም። በዚህም የተነሳ ኢሬቻ በተመረጡ የውሀ እና ተራራማ ቦታዎች ይከበራል።በባህሉ መሰረት ጉማ እና የመሳሰሉ እሴቶች ደግሞ የወጣቶችን አስተሳሰብ በመልካም ለመቀየር ብሎም፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ድህነት ቅነሳ፣ ወዳጅነትን ለማጠናከርና ለመሳሰሉት የጎላ ፋይዳ እንዳለውም አስረድተዋል። በአሉም ከአንድ መቶ ሀምሳ አመታት በኋላ በአዲስ አበባ መከበሩ የህዝቦችን የዘመናት ጥያቄ የመለሰ ሲሆን ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው አብራርተዋል። ቢሮውም ኢሬቻ በአል አከባበር ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ እንዲሆንና የበአሉ እሴቶች ብቻ እንዲንፀባረቁበት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይሰራል ብለዋል። የገዳ እና ኢሬቻን ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲከበርም በአገርውስጥና በውጭ ጥናቶችን የማካሄድ ውጥን መኖሩን አቶ ከበደ አረጋግጠዋል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ መስከረም ሀያ አራት ሁለት ሺህ ክፍለዮሀንስ አንበርብር
ኢሬቻ የተፈጥሮ ሀብቶች በዘላቂነት እንዲጠበቁ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል
ሁለት ባጃጆች ሙሉ በሙሉ ሲቃጠሉ በአንድ ሆቴል ላይ ጉዳት ደርሷልበኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን፣ የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ወርቁ ጫላ ማክሰኞ ጥቅምት ሀያ አንድ ቀን ሁለት ሺህ አስር አመተ ምህረት ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ እሁድ ጥቅምት ቀን ሁለት ሺህ አስር አመተ ምህረት በከተማዋ የኢሬቻ በአል ሲከበር ቦምብ ይዘው የመጡ ወጣቶች አሉ በሚል ሰበብ በተነሳው ግጭት ሁለት ሰዎች ሞተዋል። ሟቾችም በእውቀቱ ውበት ሙሉጌታ፣ ደገባስ ፈቃደ ካባና ኤርሚያስ ባዩ ምትኬ እንደሚባሉ ገልፀዋል። ደገባስ ፈቃደ ካባ ህይወታቸው ሊያልፍ የቻለበት ምክንያትም እሁድ በነበረው የኢሬቻ በአል ለመዋኘት ወደ ወንዝ ገብተው እንደሆነ ተናግረዋል። ከቀሪዎቹ ሁለቱ ሟቾች መካከል አንደኛው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ፣ ሁለተኛው ደግሞ ጉዳት የደረሰበት ሆቴል ስራ አስኪያጅ እንደነበር አቶ ወርቁ ገልፀዋል። የዩኒቨርሲቲው ተማሪ በኢሬቻ በአል ላይ ድብደባ ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ከሄደ በኋላ በማግስቱ ህይወቱ እንዳለፈ ገልፀዋል። ሁለተኛው ሟች ደግሞ ሁከቱ በተፈጠረበት እለት በድንጋይ ተደብድቦ ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ተናግረዋል። በግጭቱ አስር ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበርና ከእነዚህ መካከል ስድስቱ የህክምና እርዳታ አግኝተው ወደ ቤታቸው እንደተመለሱ ገልፀዋል። አራቱ ሰዎች ግን ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በመሆኑ፣ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚኙ ጠቁመዋል። በእለቱ ተነስቶ በነበረው ግጭትም ሁለት ባጃጆች ሙሉ በሙሉ እንደተቃጠሉና በአንድ ሆቴል ላይ የመሰባበር ጉዳት እንደደረሰ ገልፀዋል። ግጭቱ የተቀሰቀሰበትን ምክንያት አስመልክቶም አቶ ወርቁ፣ በበአሉ ላይ አደጋ ለማድረስ የመጡ ሰዎች አሉ በሚል ጥርጣሬ ሰዎች እየተፈተሹ ነበር። በዚህ ሂደት ቦምብ ይዘው ተገኝተዋል ተብሎ ግጭት ተነስቶ ነው ድብደባው ሲካሄድ የነበረው፤ ሲሉ አስረድተዋል። ግጭቱ በተፈጠረበት ወቅት የከተማዋ ፖሊስ ከዚህ በላይ በንብረትና በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ስራ ማከናወኑንና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑንም ተናግረዋል። በተለያዩ ብሄሮች ተወላጆች ላይ ጉዳት መድረሱንም አክለዋል።በዚህ ግጭት እጃቸው አለበት የተባሉ ሰዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም አቶ ወርቁ አስረድተዋል። የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ መምርያ ሀላፊ ኮማንደር ጌታቸው ኢታና እንዳሉት፣ ግጭቱን ከለላ በማድረግ የግለሰቦችን ሱቆችና መጋዘኖችን የዘረፉ ግለሰቦች አሉ። ፖሊስ ከሀብረተሰቡ ጋር ባደረገው የጋራ ጥረት ከተማው ተረጋግቷል ብለዋል። በኦሮሚያ ክልል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት የስላሳ ሶስት ሰዎች ህይወት እንዳለፈና ከሁለት መቶ ሀምሳ ስድስት በላይ ተጠርጣሪዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ከክልሉ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
በነቀምቴ ከተማ ሶስት ሰዎች ተገደሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሳውዲ አረቢያን ከፍተኛ የሜዳልያ ሽልማት ተሸለሙ ።ኢትዮጲያና እና ኤርትራ በሳውዲ አረቢያ ጅዳ ባለ ሰባት ነጥብ ስምምነት ማድረጋቸውም ታውቋል ።የሁለቱ ሀገራት መሪዎችም ጦርነቱ አብቅቷል በማለት ከዚህ በኋላ አዲስ በሆነ መንፈስም የሰላም፤የወንድማማችነትና የተጣመረ ግንኙነታቸውን አጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ይፋ አድርገዋል ።ከዚህ ባለፈም መሪዎቹ ትልቅ የኢንቨስትመንት ስራዎችን ለመጀመርም ተስማምተዋል።የሳውዲ ንጉሳዊ ቤተሰቦች እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመራሮች በስነ ስርአቱ ላይ ተገኝተዋል ። ምንጭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሳውዲ አረቢያን ከፍተኛ ሽልማት ተሸለሙ
ሰላም ክቡር ሚኒስቴር ህዝብዎ ባለፈው ባደረገው ምርጫ እርሶ የማይፈልጉትን መምረጡን ተከትሎ ስልጣንዎን ሊለቁ እንደሆነ በሰማን ግዜ በውነት ተደነቀንለዚህ እኮ ነው እናንተ አውሮፓውያን ሁሌም የምትገርሙን ሰልጠነናል አውቀናል ትላላችሁ እንጂ ገና ብዙ ይቀራችኋል። ሲጀመር ህዝቡ ድምፅ የሰጠው እርስዎ ከስልጣንዎ እንዲለቁ አይደለም ቢሆንስ የምን ለህዝብ ፊት መስጠት ነው በእንዲህ ያለው ሆድ የሚያስብስ ጊዜ የሚባለው ድርጅቴ ከፈቀደልኝ ስልጣኔን እለቃለሁ ነው ከዛ ስልጣንዎን ባይለቁም ድርጅታቸው አልፈቀደም ማለት ነው ይባላል። ከሁሉ ከሁሉ ግን ህዝቡ ምን ሆንኩኝ ብሎ ነው እርስዎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማይፈልጉትን እና ያልደገፉትን ነገር የሚፈልገው። አንዴ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ እርስዎስ ህዝብን ማማከር ብሎ ፈሊጥ ከየት አመጡት ዝም ብለው ያሻዎትን ወስነው ሲያበቁ ህዝቡ እንዴት ብሎ ሲጠይቅዎ ይሄንን ጉዳይ ለዚህ ህዝብ የማሳወቅ ግዴታ ያለብኝ አይመስለኝም። ይባላል እንጂ ህዝብን ወስን ብሎ መጥራት ነውር አይደለም እንዴእርግጥ ነው ህዝብ ባለጌ ነው አንዳንድ ጊዜም ሆ ብሎ ተቃውሞ ያስነሳ ይሆናል ይሄንን መከላከል ታድያ ከባድ ነው ሊሉ ይሆናል እኮ የሽብርተንነት አዋጅ አላችሁ አይደል እንዴ እኛ ራሳችን እኮ አዋጁን ከናንተ ነው ቀጥታ ቃል በቃል የቀዳነው ታድያ ከቃልዎ የሚያፈነግጠውን ሁላ ያፈነገጠውን ብቻ ሳይሆን ያሰበውን ሳይቀር የሽብርተኝነት አዋጁን እየጠቀሱ መጠፍነግ ሲችሉ የምን ለህዝብ ፊት መስጠት ነው እሺ እምቢኝ ብለው አንዳንድ ነውጠኞች ስራዎን ተቃውመው አደባባይ ወጡ እንበል እንዲህ ያለ ነገር ሲገጥም በመጀመሪያ ደረጃ ማድረግ የሚገባዎ ሌሎች የርስዎ ደጋፊዎችን በቴሌቪዥን ጣቢያዎ አቅርበው አንዳንድ ፀረ ሰላም ሀይሎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልካም ሀሳብ መቃወማቸው ተገቢ አለመሆኑ ተገለፀ የሚል ዜና ማሰራት። እንደውም የምን መልካም ሀሳብ ራእይ ይበሉት እንጂ አዎ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ራእይ እንደውም የምን ጠቅላይ ሚኒስትር ብሎ ማቃለል ነው የታላቁን መሪ ይበሉት አዎ አንዳንድ ፀረ ሰላም ሀይሎች የታላቁን መሪያችንን ራእይ ለማደናቀፍ መሞከራቸው ተገቢ አለመሆኑን የለንደን ነዋሪዎች ገለፁ። ነዋሪዎቹ አክለውም ይህንን ታላቅ ራእይ ለማደናቀፍ እና ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ የሚሞክሩ የሻቢያ ተላላኪዎች ላይ መንስግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን ብለዋል። ብሎ ዜና ማሰራት። ያው የሻቢያ ተላላኪ ያልንልዎ ከተቸገሩ ይጠቀሙበት ብለን ነው ሰርተው ይከፍላሉ። የራስዎ ተላላኪ ሲያገኙ ይመልሳሉ እኛ ኦነግ ኦብነግ ግንቦት ሰባት እና ሌሎችም ስላሉን ችግር የለውም።ከዛ ህዝቡ በዜና እርምጃ ይወሰድ ብሎ የለ በቃ በነጋታው ስናይፐር የያዘ ወታደር አሰማርቶ ለተቃውሞ የወጣውን ሁላ ጠብ ጠብ ማድረግ ነው።ህዝብ ደም ካየ ይሸሻል። ፀጥ ይላል። ግፋ ቢል አንድ አራት መቶ አምስት መቶ ሰው ቢገድሉ በቃ የተቀረው ህዝብ ዝም ይላል ከሁሉ ከሁሉ ደሞ ህዝቡ ራስ በራሱ እንዲጠባበቅ የማድረግ ዘዴን መጠቀም አለብዎ ይሄንንም እኛ ድሮ እና ከናንተ እና ከጥሊያን ነበር የተማርነው እርስዎ ዛሬ እንዴት ይሄ እንደጠፋዎ ገርሞናል።የምእራቡ አካባቢ ሰው በሀሳብዎ ያልተስማማ እንደሆነ ለሰሜኑ ህብረተሰብ የድሮን ስርአት ሊያመጡብህ ነው ወይም ደግሞ ሀገሪቷን ሊበታትኑ አስበው ነው እና ህዝብ ሆይ በንቃት ጠብቅ ብሎ ህዝቡ ራስ በራሱ እንዲጠባበቅ ማድረግ ጥሩ መላ ነው። ለስንቱ ወታደር አቁመው ይዘልቁታል።የሆነው ሆኖ ግን ግራም ነፈሰ ቀኝ ጠቅላይ ሚኒስትቴርነት ዝም ተብሎ የሚለቀቅ ስልጣን አይደለም። እኛ ሀገር መጥተው ልምድ ቢቀስሙ ሀያ አምስቱንም አመት አንድ መሪ ብቻ ይዘን ያገኙናል። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለፈው ሰሞን ድርጅቴ ከፈቀደ ስልጣን እለቃለሁ ብለው አስደንገጠውን ነበር አዩ አይደል እንዲህ ነው የሚባለው ይሄው ድርጅታቸው ስላልፈቀደ አሁንም ድረስ ሞተው ሁላ ስልጣን አለቀቁም።እና ክቡር ዴቪድ ካሜሮን በትንሽ ነገር ተከፍተው ስልጣን ለቃለሁ በማለት ለኛ ህዝብም ክፉ ነገር ባያሳዩብን መልካም ነው አሁንም ያስቡበት እና ድርጅቴ አለቅም አለኝ ብለው ስልጣንዎን ያጥብቁ እኛ ላይም ትችት አያምጡብን ለነገሩ እኛጋ ሁሉ ነገር በህግ ነው በአዲሱ የኮምፒውተር ደህነነት ጥበቃ አዋጅ ስም ማጥፋት የሚያስከስሰውን ክስ ደፍሮ የሚተችን ካለ ይሞክረን።ከሁሉ ግራ የገባን ቆይ አቃቤ ህጎቻችሁ ፖሊሶቻችሁ እና ባጠቃላይ የፀረ ሽብር ግብረ ሀይሎቻችሁ ምን ሰርተው ሊበሉ ነው። ከርሶ ሀሳብ ውጪ የሆኑትን አስራ ሰባት ሚሊዮን ሰዎችን ሽብርተኛ ብሎ መፍረድ ያልቻለ ፍርድ ቤትስ ምኑን ፍርድ ቤት ተባለው በእውነት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ደግ አልሰሩም ለማንኛውም ያስቡበት።
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ከ ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት
የናይጀሪያዊው ባለሀብት የዳንጎቴ ሲሚንቶ የኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ እና ሁለት ኢትዮጵያውያን የስራ ባልደረቦቹ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለመገደላቸው ዋናው መስሪያ ቤት ማብራሪያ ሰጠኢሳት ዜና ግንቦት ቀን አመተ ምህረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በበኩላቸው በተፈፀመው ግድያ ሀዘናቸውን መግለፃቸው ተነግሯል።የድርጅቱ የማርኬቲንግ ምክትል ስራ አስኪያጁን አቶ ታሪኩ አለማየሁ ለብሉምበርግ በስልክ እንደገለፁት ዲፕ ካማራ እና ሁለቱ ኢትዮጵያውያን የድርጅቱ ሰራተኞች ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል።ሶስቱም የተገደሉት ከአዲስ አበባ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በሙገር ሲሚንቶ አቅራቢያ በጠራራ ፀሀይ እንደሆነ የኩባንያው ዋና ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኤድኒን ዳቫኩማር ከሌሎስ በኢሜይል ገልፀዋል።ገዳዮቹ መጀመሪያ ላይ ትልልቅ ድንጋዮች ከሚጓዙባት መኪና ፊት በማስቀመጥ ሾፌሩን እንዲያቆም ማስገደዳቸውን የጠቀሱት ዴቫኩማር ልክ መኪናዋ መቆሟን ተከትሎ ዲፕ ካማራ በመውረድ ለማምለጥ ሲሞክር ተኩሰው እግሩን እንደመቱት ገልፀዋል።ህንዳዊው ስራ አስኪያጅ ተመልሶ ወደ ጂፕ መኪናዋ ዘልሎ ለመግባት ሲሞክር ሰዎቹ በመቅረብ በበርካታ ጥይት በተደጋጋሚ ተኩሰው እንደገደሉት እና እሱን ከጨረሱ በኋላ ሾፌራቸውንና ፀሀፊያቸውን በተመሳሳይ መንገድ መግደላቸውን ዴቫኩማር አብራርተዋል።የተፈፀመው ንፁሀንን የመጨፍጨፍ ወንጀል ነው ብለዋል የኩባንያው ዋና ሀላፊ ከሌጎስ በሰጡት በዚሁ መግለጫ።ዳንጎቴ ሲሚንቶ የሚተዳደረው በናይጀሪያው ቢሊየነር በአሊኮ ዳንጎቴ ሲሆን ባለሀብቱ በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጃቸውና ሰራተኞቻቸው ላይ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።በኢኦትዮጵያ የሚገኘው የህንድ ኤምባሲ በበኩሉ የዲፕ ካማራን አስከሬን ወደ ቤተሰቦቹ ህንድ ለመላክ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ በሆኑት በዲፕ ካማራና በሁለት ኢትዮጵያውያን የስራ ባልደረቦቻቸው ላይ በትናንትናው እለት በተፈፀመው ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀዘናቸውን መግለፃቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።ዶክተር አብይ በዚሁ መግለጫቸው ለሟቾቹ ቤተሰቦች እና ለመላው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች መፅናናትን የተመኙ ሲሆን መንግስት ግድያውን የፈፀሙትን አካላት እያጣራ መሆኑን እና አጥፊዎችን ለህግ እንደሚያቀርብም ቃል ገብተዋል።
የናይጀሪያዊው ባለሀብት የዳንጎቴ ሲሚንቶ የኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ እና ሁለት ኢትዮጵያውያን የስራ ባልደረቦቹ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለመገደላቸው ዋናው መስሪያ ቤት ማብራሪያ ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን ሁለት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በአማራ ክልል ሰላም መስፈን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና የመስጠት ስነ ስርአት ተከናወነ። ለዘላቂ ልማትና አብሮነት የህግ የበላይነት በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ስነ ስርአት የፌዴራል እና የክልሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል። በስነ ስርአቱ ላይ የአማራ ከልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባደረጉት ንግግር በክልሉ ጠንካራ አመራር በመስጠት የፀጥታ መዋቅሩን በማስተካከል እና ህዝቡን በየደረጃው በማወያየት ለህግ መከበር እና ለሰላም መስፈን ዘብ እንዲቆም ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል። ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ህገ ወጦችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና ቀስ በቀስ ክልሉን ከነበረበት የሰላም መደፍረስ እንዲወጣ ማድረግ ተችሏል ሲሉ አንስተዋል። አሁን ለመጣው ሰላም የጎላ ሚና ለነበራቸው እና አጠቃላይ ከክልሉ ለተውጣጡ ለሀይማኖት አባቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች፣ ለወጣቶችና ለፀጥታ አካላት የእውቅና መስጠት ስነ ስርአት ተከናውኗል። በስነ ስርአቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የኢፌዴሪ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አደም መሀመድ፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል። በአጠቃላይ ለክልሉ ሰላም መምጣት ጉልህ አስተዋፅኦ ላደረጉ አንድ መቶ ሀምሳ ግለሰቦች፣ ለክልሉና ለፌደራል ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል። ስነ ስርአቱ በክልሉ ርእስ መስተዳድርና በክልሉ ሰላምና ደህንነት ግንባታ ቢሮ በጋራ የተዘጋጀ የሰላም ምስጋና እውቅና ፕሮግራም ነው። በናትናኤል ጥጋቡ
በአማራ ክልል ሰላም መስፈን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጠ
ሮናልዲንሆን ከሌሎች ብራዚላውያን ተጫዋቾች ልቆ ልዩ የሚያደርገው ነገር አለ። ይሄም በብሄራዊ ቡድን ውስጥ በሁሉም የእድሜ ክለል ላይ የሚደረጉ ለአለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፉ ነበር። በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት የፊፋ በግብፅ ባካሄደው ከ አመት በታች የአለም ዋንጫ፣ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ የደቡብ አሜሪካ ወጣቶች የእግር ኳስ ሻምፒዮና ከሀያ አመት በታች እንዲሁም በዚያው አመት በተመሳሳይ ናይጄሪያ ውስጥ በተሰናዳው የአለም ወጣቶች ዋንጫ ውድድሮች ላይ ተካፋይ ሆኗል። በዚህም የሚከተሉትን ስኬቶች አግኝቷል። ሮናልዲንሆ በብራዚል ብሄራዊ ቡድን በተለያዩ የእድሜ ደረጃዎች የጫወተ ሲሆን በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ኮፓ አሜሪካን ውድድር ላይ ላቲቪያን ሶስትለ በሆነ ውጤት ብራዚል ስታሸንፍ የመጀመሪያውን ዋንጫ ማንሳት ችሏል። በዚያው አመት በተመሳሳይ ወር ላይ በተካሄደው የፊፋ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ በተደረጉት እያንዳንዱ ጨዋታዎች ላይ ከዋንጫ ጨዋታው በስተቀር ለብሄራዊ ቡድኑ ግብ ማስቆጠር ችሏል። በዋንጫ ጨዋታው ላይ ብራዚል በሜክሲኮ የአራትለሶስት ሽንፈት ደርሶባት ዋንጫውን ማግኘት ባትችልም ኮንፌዴሬሽን ካፕ ጎቾ የ ጎልደን ግሎብ የምርጥ ተጫዋችነት ሽልማት እና የወርቅ ጫማን በግሉ አሳክቷል። በሁለት ሺህ ላይ ደግሞ ሲድኒ ላይ በተካሄደው ኦሎምፒክ ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር በመጓዝ ተጫውቷል። በቅድመ ኦሎምፒክ ውድድሮች ላይም በሰባት ጨዋታዎች ዘጠኝ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል። ጎቾ በአለም ዋንጫ ታሪኩ ከብራዚል ጋር የማይረሳ ትዝታን ያስተናገደው በኮሪያና ጃፓን አስተናጋጅነት በሁለት ሺህ ሁለት አመተ ምህረት ነው። በዚህ ውድድር ላይ በስሙ ሁለት ግቦች እና በርካታ ለግብ የሚሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ችሏል። በተለይ በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ከእንግሊዝ ጋር የተገናኘችውን ብራዚል ጨዋታውን በድል እንድትወጣ ያስቻላትን አስደናቂ ቅጣት ምት አስቆጥሯል። በተለይ ጎሏን ልዩ የሚያደርጋት ከአርባ ሜትር ርቀት ላይ የተቆጠረች እና ዴቨድ ሴማንን በእጅጉ የፈተነች በመሆኗ ነበር። በሁለት ሺህ አምስት ሮናልዲንሆ የብራዚል ብሄራዊ ቡድንን በአንበልነት እየመራ የፊፋ ኮንፌደሬሽን ካፕን አንስቷል። በተለይ በውድድሩ በሜክሲኳዊው ኩቲሞክ ብላንኮ የተያዘውን የዘጠኝ ጎል ክብረ ወሰን መጋራት ችሏል። በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ አሜሪካን ካፕ እንዲሁም በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት በፊፋ አመት በታች የአለም ሻምፒዮን ዋንጫን አንስቷል። በዋናው የብራዚል ብሄራዊ ቡድን በዘጠና ሰባት ጨዋታዎች ተሰልፎ ያስመዘገባቸው ስላሳ ሶስት ጎሎች ናቸው። ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስድስት ጀምሮ በብራዚል ከ አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በስድስት ጨዋታዎች ሁለት ግብ አስቆጥሯል። ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ጀምሮ በብራዚል ሀያ ብሄራዊ ቡድን በአምስት ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን፤ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ እስከ ሁለት ሺህ ስምንት በብራዚል ሀያ ሶስት አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በሀያ ሰባት ጨዋታዎች ጎሎች፤ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ እስከ ሁለት ሺህ በብራዚል ብሄራዊ ቡድን በዘጠና ሰባት ጨዋታዎች ስላሳ ሶስት ጎሎች አስመዝግቧል። ሁለት ሺህ ስድስት ለጎቾ ጥሩ ጊዜ አልነበረም። ምክንያቱ ደግሞ አንድ ነው። የአለም ዋንጫ። እርሱን፣ አድሪያኖን እና ካካን የያዘው ብሄራዊ ቡድን ዋንጫውን ያነሳል የሚል ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት ነበር። ነገር ግን በግልባጩ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ። ስምንት ውስጥ ቢደርሱም በፈረንሳይ የአንድለ ሽንፈት ስለገጠማቸው ከውድድሩ ውጪ ለመሆን ተገደዱ። ጎቾ በዚህ ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አቋሙ ወርዶ ነበር። አለምን ያስደነቀው ምርጥ ተጫዋች በዚያን አመት ለአገሩ ሊደርስላት አልቻለም። በዚህ የተናደዱት ደጋፊዎችም ሰባት ነጥብ አምስት ሜትር የሚደርሰውን ለክብሩ የተተከለለት ሀውልት ጥቃት አድርሰውበት ነበር።አዲስ ዘመን ሚያዝያ ስድስት ሁለት ሺህ
የኮከቡ የብሄራዊ ቡድን ቆይታና አስገራሚ ክስተቶች
ጥቅምት አንድቀን አመተ ምህረት ኢሳት ዜና በእስር ላይ የምትገኘው የጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ እህት እስከዳር አለሙ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን ይቅርታ ካልጠየቀች እህቷን መጎብኘት እንደማትችል ተገለፀላት።እስከዳር አስቂኝምአስገራሚም ነገርበሚል ርእስ በፌስ ቡክ ገጿ ላይ እንዳሰፈረችውማረሚያ ቤቱ በደብዳቤ ይቅርታ ካልጠየቅሽ ሁለተኛ እህትሽን አታያትም እንዳላት ገልፃለች።ሰብአዊ ጥሰት የተፈፀመብን የተጉላላን የተሰደብን የተዛተንብየተደበደብን እኛ። ይሄ ሆኖ ሳለ ነዉ እንግዲህ በእህትሽ ጉዳይ የማረሚያ ቤቱን ስም በየመፅሄቱ አጥፍተሻል የተባልኩት። ስም ማጥፋት የተባለውም ስለርእዮት የረሀብ አድማንና ስለ ተፈፀመባት የሰብአዊ መብት ጥሰት መግለፄ ነውብላለችእስከዳር አለሙ። ስለዚህ ነው ይቅርታ ጠይቂ የተባልኩት ያለችው እስከዳር እኔ የምለዉ እነዚህ ሰዎች ይህንን ይቅርታ እንዴት ነዉ የሚወዱትበማለት ጠይቃለች።
የጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ እህት ይቅርታ እንድትጠይቅ ተጠየቀች
አዲስ አበባ፣ ጥር ሀያ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት ከወጪ ንግድ አንድ ነጥብ ስላሳ ሶስት ቢሊየን ዶላር ማግኘቱን አስታወቀ።ሚኒስቴሩ በግማሽ አመቱ አንድ ነጥብ ስልሳ ስድስት ቢሊየን ዶላር ለማግኘት አቅዶ ነው ይህን ገቢ ማግኘት የቻለው፤ ይህም የእቅዱን ሰማኒያ በመቶ መሆኑ ተነግሯል።የዘንድሮው የግማሽ አመት የወጪ ንግድ አፈፃፀም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የአስር በመቶ ብልጫ እንዳለውም ተገልጿል።የአገዳ ሰብሎች፣ የተፈጥሮ ሙጫ እና እጣን፣ ጫት፣ አበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም ኤሌክትሪክ በበጀት አመቱ ስድስት ወራት ከተያዘላቸው እቅድ በላይ አፈፃፀም ማስመዝገባቸው ተገልጿል።ባህር ዛፍ፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት እንዲሁም ቡና የእቅዱን ከሰባ አምስት በመቶ እስከ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ አፈፃፀም አስመዝግበዋል። መጠጥ እና ፋርማሲዩቲካል፣ የቁም እንስሳት፣ ወተት እና የወተት ተዋእፅኦ፣ ማር እና ማእድናት ዝቅተኛ አፈፃፀም ካስመዘገቡ ምርቶች መካከል መሆናቸው ተጠቅሷል።፡ከዘርፍ አፈፃፀም የግብርና ምርቶች ቀዳሚውን ቦታ ሲይዙ የማምረቻው ዘርፍ ውጤቶች፣ ማእድናት እና ሌሎች ምርቶች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።ባለፉት ስድስት ወራት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሰራሩን ለማዘመን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ ገልፀዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት ከወጪ ንግድ አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊየን ዶላር ተገኘ
ኦህዴድእንዴት ኢትዮጵያውያንን አታለለክፍል አንድየኦሮሞ ፖለቲካ ትርክት ከትግራይ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ቅኝት መሳለመሳ የሚሄድ ከፍ ሲል የብሶት ዝቅ ሲል የተንኮል ፖለቲካ ነው።የትግራይ ህዝብ ያበቀላቸው ህወሀቶች አናሳ ብሄር እንዴት ብዙሀንን መምራት እንደሚችልና ሁለመናውን መጠርነፍ እንደሚችል ተንኮል ሲማሩና ሲተገብሩ ነው የኖሩት።የኦሮሞ ፖለቲከኞች ይህንን የአናሳዎች እሳቤ በመዋጋት የትግራይዎችን ስልት ትንሽ ቀየር በማድረግ የእነርሱ የሚሉትን ህዝብ ብቻ ተጠቃሚ ለማድረግ ምን ስልት መከተል እንዳለባቸው ላለፉት አምስትና ከዛ በላይ አመታት መክረዋል።ባለፈው አመት ወደ ስልጣን ለመውጣት ሲታገሉ በጓዳ የመከሩት ይህ ስልታቸው አልፎ ሳያስቡት ይታወቅባቸው የነበረ ቢሆንም በእነ ለማና አብይ ቅብ ንግግሮች እየተሸፈኑ ብዙዎችን ቀልባቸውን ገዝተው ቆይተዋል። ኦህዴድ እንዴት ህዝቡን አታለለውየትግራይ ኢሊቶች ስልጣናቸውን ለማደላደል አናሳ ብሄረሰቦች በማሰባሰብ በምትኩ አማራውን በማስጠላት ስልጣኑን ሲይዙ ትልልቆቹ ብሄሮችን ደግሞ ምስለኔዎችን በማስቀመጥ ሲገዙ ቆይተዋል።ኦሮሞዎች ደግሞ የረጅም ጊዜ የህወሀት ተቃዋሚዎችን በጓዳና በፊት በማሞኙት ህወሀትን በቀንጅብነት በመሳል እርግጥ ህወሀት የቀን ጅብ ነው ኢትዬጵያ ከሚለው ስም ጋር ሞታቸው እንደሚሆን በመስበክ ከህወሀት በተቃራኒ በመቆም ደጋፊዎችን አሰባስበው ፈታኝ ብለው ያስቡትን ወቅት ለመሻገር ሞክረዋል።ከዚህም ባለፈው ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አደጋ ይሆናሉ ያሏቸውን ምእራባውያን በህዝባዉ አመፅ በተቀረፀ ቪዲዮኖ በፎርጅድ የታሪክ ትንትነና ሽብር ውስጥ በመክተት እጃቸው ውስጥ ለማስገባት ሞክረዋል።ህወሀትን በመታገል የነበረው የውጩ ማህበረሰብም ይህንን ስላልጠበቀ ደግፏቸው ነበር።እዚህ ላይ በቴዎድሮስ ትርፌ የሚመራው በሰሜን አሜሪካ የአማራ ማህበር እና ሌሎች ማህበራትን በማቀናጀት ድል የተቀዳጁትን የእነርሱን ትግል ለኦሮሞው እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም አሜሪካንም ለዚህ ዋና አጋዣቸው አድርጉው ተጠቅመዋል።አውሮፓ ህዝብረትም በዚህ ከተታለሉት ይገኝበታል።ኦዴፓ ከኢትዮጵያ ጥቅም ተቃራኒ ይቆማሉ የተባሉትን የአረብ ሀገራት ጭምር በማድረግ ኢትዮጵያን ሁሉ እንደሚሸጡላቸው እስከመስማማት የደረሱ በሚመስል መልኩ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለእነ ግብፅ እና ሳውዲ በመስጠት ጭምር ድርድር እንዳደረጉ ይገመታል።ለዚህ ነጩ እውነት ማሳያ የኢንጅነር ስመኘው ግድያ ነው።ከዚህ በተጨማሪም ምንም አይነት የህግና መመሪያ ማሻሻያ ሳያደርጉ ለፕሮፖጋንዳ ሲባል ጥሩ ስም ያላቸውን ሰዎች የስልጣን ቦታ በመስጠት ህዝቡን ለማማለል ሞክረዋል።ቆተይ ብለው ደግሞ ትንሽ የቀሩ ርዝራዥ ተቃዋሚዎችን አሀዳዉ መንግስትን ለመመስረት የሚታገሉ በሚል ማሸማቀቂያ ከገበያ ውጭ በማድረግ የእነርሱ ጫማ ክር አሳሪ አድርገዋቸዋል። ኦሮማራ በሚል የውሸት ግንኙነት ላይ በመመስረት ሁለቱን ትልልቅ ብሄሮች ወደ አንድነት ለማምጣት በሚል የሰሩት ስራ የብዙዎቻችን ቀልብ ስቦ ነበር።ይሁንና ይህ ስልታቸው ከእውነት የመነጨ ሳይሆን ወንዙን ለመሻገር የተጠቀሙበት መሆኑን ለመገንዘብ ብዙ ጊዜ ፈጅቶብናል።ይህ ስልት በተለይም ኢትዮጵያን ይወዳል ለተባለው የአማራ ህዝብ በደንብ ታቅዶ የተቀመመበህወሀት ምክንያት የተለያየውን ነገር ግን በታሪክ የሚቀራረበውን የአማራና ትግራይን ህዝብም ስልታዊ በሆነ መልኩ የነጠሉበት ነው።የኦሮሞ ፖለቲካ ቅኝት ታድያ ይህንን ሁሉ አድርጎ ሁሉንም በጥርጥሬ የሚያየውን የኢትዮጵያን ህዝብ ማማለልና ማታለል የቻሉት አንድ አመት ብቻ ነው።ከዚህ ቅኝታቸው በኋላ ስልጣኑን አደላድለናል ብለው ሲያስቡ መጀመሪያ ለብሰውት የመጡትን የኢትዮጵያዊነት ካባ በእነርሱ ቀለም መቀባትን ተያያዙት።መድረኮች ሁሉ የአብሲኒያዋን ኢትዮጵያ መገለጫዎች በእነርሱ አርማና ትርክት የመቀየር ስራን ተያያዙት።ይህንን ጊዜ ነው እንግዲህ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ስሪታቸው ከህወሀት ያልተናነሰ መሆኑን ሁሉም እየተገነዘበው የመጣ።በዚህ ረገድ ወደፊት ተረጋግተን እንዳንገዛ ያስቸግረናል ያሉትን የአማራ ህዝብ አራት የቤት ስራዎች እንስጠው የሚል አጀንዳ ቀረፁ።ክፍል ሁለት ይቀጥላል
አማራን አጣብቂኝ ውስጥ በመክተትህልሜን አሳካለው ያለውቅርብ ወራጁ የኦሮሞ ፖለቲካ አያሌው መንበር
መጋቢት አስራ ሁለት ቀን አመተ ምህረት ኢሳት ዜና የወልቃይትን የአማራ ማንነት ጥያቄ ከሚመሩት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ሊለይ ብርሀነ በትግራይ ፖሊሶች ታፍነው መወሰዳቸውን ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ የጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ሲሆን ተቃውሞውን ለመበተን በደንሻ ነዋሪዎች ላይ ጥይቶችን ተኩሰዋል። የፖሊስ እርምጃ ያበሳጫቸው ነዋሪዎች መንግዶችን በመዝጋት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ ያደረጉ ሲሆን በአካባቢው ያለው ውጥረት ይህን ዜና እሳካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ቀጥሎአል።የትግራይ ልዩ ሀይለ ፖሊስ አባላት የወልቃይትን የአማራ ማንነት ጥያቄ ይመራሉ የሚሏቸውን ሰዎች ሲያስፋራሩ ቆይተዋል። አቶ ሊለይ አቋማቸውን በአደባባይ በድፍረት በመግለፅ የሚታወቁ ሲሆንየህወሀት አስተዳደርቀድም ብሎ ሲልከው የነበረውን ማስፈራሪያ ትኩረት ባለመስጠት አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ለመንግስት ጥያቄ ያቀረቡ ናቸው።ግጭቱ እንደተነሳ የስልክ መስመር እንዲቋረጥ መደረጉን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ተናግረዋል። የኮሚቴው አባላት የትግራይ መስተዳደር እየወሰደ ያለው እርምጃ ችግሩን የሚያባብሰው ነው በማለት እያሰጠነቀቁ ነው።
በዳንሻና ሰሮቃ የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ነው
ኄኖክ ካሳሁን በውድድር ዘመኑ አጋማሽ አዳማ ከተማን ለቆ በውሰት ወደ ጅማ አባ ቡና ካመራ ወዲህ መልካም ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል። ጠንካራው የተከላካይ አማካይ በደደቢት እና አዳማ ስላሳለፈው ጊዜ እንዲሁም ስለ ጅማ አባ ቡና ቆይታው ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።በደደቢት እና በአዳማ ከተማ ብዙም የመሰለፍ እድል አላገኘህም ደደቢት እያለሁ እጫወት ነበር። ሁለት ሺህ ስድስት ከተስፋ ቡድን ወደ ዋናው ቡድን እንዳደኩኝ አልተጫወትኩም ነበር። ሆኖም በቀሩት ሁለት አመታት ብዙ ባይባልም በቂ የመጫወት እድል አግኝቼ ተጫውቻለው። በአዳማ ከተማ ግን የመጫወት አቅም እያለኝ በአሰልጣኙ ውሳኔ ነው ያልተጫወትኩት ይህን ደግሞ አሰልጣኙ ቢመልሰው ጥሩ ነው። እኔም የመጫወቱ አቅሙ እንዳለኝ ስለማውቅ ነው ከአዳማ ለቅቄ ጅማ አባ ቡና ላመራ የቻልኩት። ያልተጫወትኩትም በአቋም ችግር እንዳልሆነ በሁለተኛው ዙር በሚገባ ማሳየት ችያለው ብዬ አስባለው።ወደ ጅማ አባቡና ካመራህ ጀምሮ ጥሩ ጊዜ እያሳለፍክ ነው። ይህን እንዴት ትገልፀዋለህ አሁን በጅማ አባቡና እያሳለፍኩት ባለው ጊዜ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ። ከክሪዚስቶም ንታንቢ ፣ ሀይደር ሸረፋ እና ዳዊት ጋር ባለኝ ጥምረትም ደስተኛ ነኝ። በአጠቃላይ ስብስባችን በጣም ጠንካራ ነው። እናንተም እንዳያችሁት ቡድኑ አቅም አለው ፤ በአንዳንድ ጥቃቅን ችግሮች ምክንያት ነው እዚህ ደረጃ እንዲገኝ ያደረገው እንጂ ቡድናችን አቅም ባላቸው ተጨዋቾች የተሞላ ነው። አሰልጣኛችንም በሚሰጠን ስልጠና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ያለን ነገር አሪፍ ነው ።ሁሉም ጨዋታዎች ላይ ያሳየኸው እንቅስቃሴ መልካም ነው። ሆኖም ከደደቢት እና ከአዳማ ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ የተለየ ስሜት ፣ ፍላጎት እልህ ይታይብህ ነበር። ምናልባት በውስጥህ የፈጠረብህ ስሜት አለ ከሁለቱ ቡድኖች ጋር ስትጫወት ደደቢት ያደኩበት እና የቆየሁበት ቡድን ነው ። ከዚህ ውጭ ሌላ ቡድን አልተጫወትኩም ነበር። አዳማም ቢሆን የመሰለፍ እድል አላገኘሁም እንጂ የነበርኩበት ቡድን ነው። ያው የነበርክበትን ቡድን ስትገጥም እና የወጣህበት ሁኔታ ብዙ የማያሳምንህ ሲሆን በውስጥህ የሚፈጥርብህ ነገር ይኖራል። እሱ ሊሆን ይችላል የተለየ ነገር የፈጠረብኝ። ያም ቢሆን ግን የተለየ ነገር አላደረኩም ፤ ከሁሉም ቡድን ጋር ስጫወት እንደዛው በእልህ በአልሸነፍ ባይነት ነው የተጫወትኩት።ጅማ አባ ቡና ላለመውረድ እየተጫወተ ይገኛል። በቀሩት ሶስት ጨዋታዎች ከቡድን አጋሮችህ ጋር በመሆን ቡድኑ እንዳይወርድ ምን እየሰራችሁ ትገኛላችሁ እስካሁን ድረስ እኛ ቡድኑ እንደማይወርድ እና እንደሚተርፍ አምነን ነው የምንጫወተው። እየተጫወትን ያለንውም ይህን አምነን ነው። ጥሩ ነገርም እያሳየን እንገኛለን። በዚህ ላለመውረድ በሚደረገው ትግል ውስጥ ጫና ላይ ሆነን እንዲህ መጫወት ከቻልን ከዚህ የተሻለ ነገር ካገኘን ደግሞ ትልቅ ነገር መስራት እንችላለን። ቡድኑንም በፕሪሚየር ሊጉ ለማቆየት ጠንክረን እንሰራለን።
ቡድኑ እንደማይወርድ አምነን ነው የምንጫወተው ኄኖክ ካሳሁን
በአገሪቱ ለዘመናት የቆየው የፖለቲካ ባህል ደም ከመቃባት ወጥቶ ወደ አዲስ ምእራፍ እንዲሸጋገርና በሰላማዊ መንገድ አንድ የስልጣን ዘመን አገልግሎና ተመሰጋግኖ የመለያየት ምእራፍ መከፈት እንዳለበት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዶክተር አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያስታወቁት አርብ ታህሳስ አስር ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በአርባ የአማራና የኦሮሚያ ባለሀብቶች የተቋቋመ ኮሚቴ፣ ለሁላችን የምትመች ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ በሚል ርእስ በሚሊኒየም አዳራሽ ባሰናዳው የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ነው። በኮንፈረንሱ በርካታ ባለሀብቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ምሁራን፣ እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ሀላፊዎች ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አርብ ንጋት ላይ ስለመጠቀችው የኢትዮጵያ ሳተላይት፣ ስለሰላም፣ ስለዩኒቨርሲቲዎች፣ እንዲሁም አብሮ በጋራ በመኖር ስለሚገኙ ትሩፋቶች ላይ ንግግር ያደረጉ ቢሆንም፣ በተለይ አፅንኦት ሰጥተው ያብራሩት ግን የደም መቃባት ፖለቲካ ማብቃት ይኖርበታል በሚለው ጉዳይ ላይ ነው። መንግስት በእስካሁኑ ሂደት የሚያጋጥሙትን ችግሮችና ፈተናዎች በትእግስት የሚመለከተው አቅሙና ልምዱ ስለሌለ ሳይሆን፣ ደም ላለመቃባት መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ አንፃር አዲስ የፖለቲካ ባህል ለመገንባት ትእግስት እንደሚጠይቅ አስረድተው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ አንድ የስልጣን ዘመን አገልግለን አመሰግናለሁ ብለን መለያየት መጀመር አለብን። ያ እንዲሆን ከፈለጋችሁ ደግሞ ደም መቃባት የለብንም፤ ብለዋል። መንግስት በትእግስት የቆየባቸውን ጊዜዎች ደካማ እንደሆነ ያሰበ ካለ በጣም ቀላሉ ነገር ደካማ ሆኖ ዴሞክራሲን መገንባት ነው እንጂ፣ አምባገነን ሆኖ ብዙዎችን መጨረስ ቢያንስ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ብዙ ልምምድ አያስፈልገንም፤ በማለት፣ ትእግስት የተመረጠው አዲስ የፖለቲካ ባህል ለመገንባት በማለም መሆኑን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ ባህል እንዲገነባ ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጠይቀዋል። እኔ በሰላም በተወሰነ የስልጣን ዘመን ስልጣን የማስረከብ ባህልን ኢትዮጵያ ውስጥ መጀመር እፈልጋለሁ። በሰላም ማለት እንዳለፈው በቄሮና በፋኖ ግፊት ማለት አይደለም፣ በምርጫ እንጂ። ያ እንዲሆን ካስፈለገ ደግሞ ደም መቃባት የለብንም። ደም ካለማመዳችሁኝ እንደከዚህ ቀደሙ እኔም እዚያው ነው የምሆነው። ስለዚህ ለራሳችሁ ስትሉ ደም ሳንቃባ ዴሞክራሲ የምንገነባባት ኢትዮጵያ እውን እንድትሆን ልባችንና ትከሻችን የሰፋ፣ አርቀን የምናስብና የምናስተውል ቢሆን መልካም ነው፤ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ከሰሞኑ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚፈጠሩ አለመረጋጋቶችን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት ደግሞ፣ መንግስት ከእንግዲህ ባገኘው የመረጃ ልክ ህጋዊ ማስተካከያዎችን እንደሚወስድም አስታውቀዋል። በዩኒቨርሲቲዎች ወጣቶችን ለግጭት የሚጠቀሙ አካላት እንዳሉና በጥፋተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደም መቃባት ፖለቲካ ማብቃት እንዳለበት አስታወቁ
ብሄራዊ ሎተሪ ከሀምሳ አመታት በላይ ጉዞው ለኢትዮጵያ ህዝብ የሰጠው አገልግሎት ቀላል ባይሆንም፣ የሎተሪ ባለእድለኞችን ከማብዛትና ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ግን ገና ብዙ ይቀረዋል። በሌላ አገላለፅ የህዝብ ተደራሽነቱን ለማስፋት ገና ብዙ መስራት ይጠበቅበታል። የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ዘጠና ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። እንደ ህዝቡ ብዛትም የሎተሪ ደንበኛው ቁጥርም ጨምሯል። ሎተሪ ይደርሰኛል በሚል ተስፋ ትኬት የሚገዛው ሰው በጣም አነስተኛ የገቢ ምንጭ ካላቸው ጫማ ጠራጊዎች አንስቶ እስከ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸውን ጭምር ያጠቃልላል። የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ድርጅት በህዝብና በመንግስት አመኔታ የተቋቋመ እንደመሆኑ፣ የብዙሀኑን ተስፋ በሚያለመልም አግባብ የአሰራር ፖሊሲውን መፈተሽ፣ እንደወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ የሚተዳደርበትን ፖሊሲ መለወጥና ማሻሻል እንዳለበት ግልፅ ሆኖ ይታያል። የውጭ አገሮች የሎተሪ አሰራር ተሞክሮም ማየትና ልምድ መውሰድም ጠቃሚ ነው። የብሄራዊ ሎተሪ ድርጅት የስራ ፕሮግራምና እቅድ መንግስት ከዘረጋው የአገሪቱ ሁሉ አቀፍ መርሀ ግብር ጋር በጣም የሚጣጣምበት፣ የሚቀናጅበትና የሚተሳሰርበት ጊዜ አሁን ነው። አሁን አሁን ዜጎች ከመቼውም በበለጠ ድህነትን ለማስወገድ በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞ ተደራጅተው የመሳተፍና በስራ የመለወጥ ዝንባሌና ፍላጐት እየጨመረ ባለበት ወቅት፣ ብሄራዊ ሎተሪ የከፍተኛ እጣ ተጠቃሚ የመሆን እድልን እንደ ሰማይ ከማራቅ ወይም እጅግ በጣም ብርቅ ከማድረግ ይልቅ፣ ወደ ህዝቡ ዘንድ መቅረብና ሎተሪ አዘውትረው ከገዙት በአስተማማኝ እንደሚደርስና ችግር ፈቺ የገንዘብ ምንጭ ሆኖ እንደሚያገለግል ሰርቶ በማሳየት ህዝብን ማሳመን ይገባዋል። ብሄራዊ ሎተሪ የሚሰጠው የገንዘብ ሽልማት በአንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ከፍተኛ እጣዎች ብቻ መታጠር የለበትም። በየካቲት ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት መጨረሻ ላይ የሚወጣው የባለዝሆኑ የሎተሪ እጣ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ከፍተኛ እጣዎች እንዳሉት ተገልጿል። ስድስተኛው ከፍተኛ እጣ ብር አንድ መቶ ሰባ አምስት እንደሚያስገኝም ተመልክቷል። ይህ መልካም ጅምር ነው። ይሁን እንጂ ህዝብን ከመድረስ አኳያ ያንሳል። ለምን ቢባል ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በጣም ወደ ህዝቡ ልውረድ፣ የተሸላሚዎችን ቁጥር ላስፋ ካለ፣ አሁን እንደ ከፍተኛ እጣ የተቆጠረው የብር አንድ መቶ ሰባ አምስት ስድስተኛ እጣ ወደ ሀምሳኛ የሎተሪ እጣ የማያድግበት አንዳችም ምክንያት የለም። የህዝብ ተደራሽነት የሚሰፋበት አንዱ መንገድም ይኸው ነው። የህዝብ ተደራሽነት ከማስፋት አኳያ ሌላ ጥሩ አብነት ሊሆን የሚችለው፣ ብሄራዊ ሎተሪ በቅርቡ ለህዳሴ ግድብ ያዘጋጀው ሎተሪ ነው። ይህ ሎተሪ፣ አንደኛ እጣ ብር አስር እንደሆነ ተመልክቷል። የህዝቡ ተደራሽነት ለማስፋት ሲባል የአራቱም እጣዎች ድምር የሆነውን ብር ለአራት ሰዎች ከማስረከብ ይልቅ ባለእድለኞችን መጥቀም ይቻላል። እንዴት እንደሚከተለው፡ አንድኛ እጣ ብር ሶስት ያሸልማል ሁለትኛ እጣ ብር ሁለት ያሸልማል ሶስትኛ እጣ ብር አንድ ሰባት መቶ ያሸልማል አራትኛ እጣ ብር አንድ ስድስት መቶ ያሸልማል አምስትኛ እጣ ብር አንድ አምስት መቶ ያሸልማል ስድስትኛ እጣ ብር አንድ አራት መቶ ያሸልማል ሰባትኛ እጣ ብር አንድ ሶስት መቶ ያሸልማል ስምንትኛ እጣ ብር አንድ ሁለት መቶ ያሸልማል ዘጠኝኛ እጣ ብር አንድ አንድ መቶ ያሸልማል አስርኛ እጣ ብር አንድ ያሸልማል ኛ እጣ ብር ዘጠኝ መቶ ያሸልማል ኛ እጣ ብር ስምንት መቶ ያሸልማል ኛ እጣ ብር አምስት መቶ ያሸልማል በአንድ ወቅት የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ድርጅት በየአመቱ ለመንግስት ብር አንድ መቶ ፈሰስ እንደሚያደርግ ገልጿል። ለመንግስት የተደረገው ፈሰስ በተዘዋዋሪ ለህዝብ ጥቅም እንደሚውል ቢታመንም፣ ከስንት ድሀና ተስፈኛ የተሰበሰበ የሎተሪ ሽያጭ ገንዘብ ለመንግስት ካዝና ፈሰስ መደረጉ ተገቢ አይመስለኝም። ምክንያቱም ከቀድሞ መንግስታት የተወረሰ ተለምዶአዊ አሰራር ሆኖ ነው እንጂ የቀጠለው፣ አሁን ያለው የመንግስት አስተዳደር ቆም ብሎ ቢያስተውለው ትክክል አለመሆኑን ይረዳል። ከህዝብ የተሰበሰበው የሎተሪ ሽያጭ ገንዘብ አስተማማኝነቱ በተረጋገጠ ትክክለኛ አሰራር ወደ ህዝቡ መመለስ እንዳለበት ያምናል። በሌላ አባባል፣ ብዙ የሎተሪ ባለእድለኞች ተጠቀሙ ማለት ከብድርና ወለድ ነፃ የሆነ የመስሪያ ካፒታል ዜጎች አገኙ ብሎም ደግሞ ድህነት ቀነሰ ማለት ስለሆነ መንግስት ፈሰስ ከሚደረግለት ይልቅ የሚጠቅመው ይህኛው የአሰራር ስትራተጂ ነው ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በህዝብና መንግስት መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ በማገልገል የመስሪያ ካፒታል ያጣውን የስራ ሀይል ተደራሽነት ለማስፋት የሎተሪ ተሸላሚዎችን ቁጥር ማበርከት ይኖርበታል። የከፍተኛ እጣ ተሸላሚዎች ቁጥር ሲበረክት፣ የሎተሪ አጓጊነት ይጨምራል፣ ብዙ የሎተሪ ደንበኞችንም ይስባል። በመጨረሻም ብሄራዊ ሎተሪ የነጋዴ ባህሪ ጎልቶ ይንፀባረቅበታል። በአጭር ጊዜ ብዙ ትርፍ ለማስገኘት እንደ ተቋቋመ የግል ድርጅት ይመስላል። ይህ ስህተት ነው። ስለምን ድርጅቱ በሎተሪ ትኬት ሽያጭ የሰበሰበውን የህዝብ ገንዘብ የእጣ አወጣጥ ካላንደር በማዘጋጀት አሁን እንደሚያደርገው አስተማማኝነቱ በተረጋገጠ የእጣ አወጣጥ ዘዴ የራሱን የስራ ማስኬጃና የመንግስት የስራ ግብር ከቀነሰ በኋላ መልሶ ለደንበኞቹ ማከፋፈል ይኖርበታል። ይህን ሲያደርግ ብቻ ነው የስራ ፍላጐቱ ላልበረደውና እየተጋጋለ ለመጣው አዲሱ ትውልድ የማያቋርጥ የገንዘብ ምንጭነቱን ሊያረጋግጥ የሚችለው። በተጨማሪም የብሄራዊ ሎተሪ ድርጅት ከደንበኞቹ ጋር የሚገናኝበት የራሱ የሆነ መጠነኛ የጋዜጣ ልሳን ቢኖረው መልካም ነው። ሙሉጌታ ደንበል፣ ከአዲስ አበባ የቴብምርን ጉዳይ ለማን አቤት እንበል ቴምብር የተለያዩ ጥቅሞች እንዳሉት ይታወቃል። ለምሳሌ ሰዎች ደብዳቤ ፅፈው በፖስታ ቤት በሚልኩበት ጊዜ ይጠቀሙበታል። ከዚሁም ባሻገር በአገራችን በመንግስት መስሪያ ቤት ለሚሰጡ የተለያዩ አገልግሎቶች ቴምብርን መጠቀም አስገዳጅ የሆኑባቸው አገልግሎቶች እንዳሉ ይታወቃል። ከእነዚህ አገልግሎቶች መካከል የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፉ አንዱ ነው። ዜጎች መንጃ ፈቃድ ለማውጣት ወይም ለማደስ ሲፈልጉ፣ አዲስ ሰሌዳ ማውጣት ወይም ሊብሬ ለመውሰድ በዶክመንታቸው ላይ ቴምበር መለጠፍ ግድ ይላቸዋል። እኔም ሰሞኑን አዲስ ለገዛሁት መኪናዬ ሰሌዳ ለመውሰድ በመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ተገኝቼ ነበር። ሰሌዳውን ለማውጣት የሚያስፈልገውን የቴምብር ቀረጥ ለመክፈል ግን አልቻልኩም ነበር። ይሄም የሆነው በመስሪያ ቤቱ የሚሸጥ ቴምብር ባለመኖሩ ነው። ምክንያቱንም ስጠይቅ ቴምብር አልታተመም የሚል ነበር። ለስራ የምፈልገውን መኪና ያለሰሌዳ መንዳት የማይቻል ሲሆን፣ ሰሌዳውን ለማግኘት ደግሞ ቴምብር ማግኘት ግድ ሆነብኝ። እኔም ቴምብር የት እንደማገኝ የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ሰራተኞቹን ስጠይቅ፣ ደጃፍ ላይ ቴምብር እንደሚሸጥ ይነግሩኛል። የባለስልጣኑ ደጃፍ ላይ ግን የሚሰራው ስራ ዛሬ ይህቺን ፅሁፍ እንድፅፍ አስገድዶኛል። መንግስት አምስት ብር የሚሸጠውን ቴምብር ደጃፍ ላይ ያሉ ደላሎች ሀምሳ ብር እና ስልሳ ብር ይሸጡታል። እኔም ይህ ድርጊት አበሳጭቶኝ በአካባቢው ለሚገኙ የፖሊስ አካላት ባስታውቅም፣ ምላሻቸው ይሄ ጉዳይ እኛን አይመለከትም የሚል ነበር። መንግስት ማቅረብ የነበረበት ቴምብር አልታተመም በሚል ተልካሻ ምክንያት የመንግስትንም ሆነ የተገልጋዩን ስራ ማስተጓጎል ተገቢ አይደለም። ከዚህም ባለፈ በዘርፉ ላሉ ደላሎች በር በመክፈት የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲሰፍን መንገድ ይከፍታል። ህግ ያስከብራሉ የተባሉት ፖሊሶችም ይህን ህገወጥ ተግባር አይመለከተኝም ካሉ፣ የት ሄደን አቤት እንበል ስለዚህ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በጉዳዩ ላይ አፋጣኝ መፍትሄ ቢሰጡ፣ የመንግስትም ሆነ የህዝብ ስራ ከመስተጓጎል ይድናል። አበራ ፋና፣ ከአዲስ አበባ
የብሄራዊ ሎተሪ የህዝብ ተደራሽነት ይስፋ
መግቢያ መውጫ አሳጥቶ፤ የወንድ በር እንኳን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን በማን አለብኝነትና በትምክህት ስነልቦና ተወጥሮ በአፈና ጅራፉ ሲገርፈን ፀጥ ብለን የምናይበት የፈሪ ልብ፤ መጠን ያለፈውን የጭቆና ቀንበር የምንሸከምበት ጫንቃ የለንም። አዎን ኢህአዴግ የደም መስዋእትነት የከፈልኩበትን ስልጣን በቀላሉ አለቅም በሚል የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርግ ሁሉ እኛም ጓዶቻችን የታሰሩበትን ትግል እና ፓርቲ ወደጎን ትተን የትም አንሄድም። አንዱአለም አራጌ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሀ ደስታ፣ አግባው ሰጠኝ እና ሌሎቹም የታገሉለትን አላማ ከግብ ሳናደርስ ወደኋላ ማለት የለም። ትግሉ ሰላማዊ እና ሰላማዊ ብቻ እንዲሆን ከአንድ ወገን ብቻ ከተቃዋሚዎች በኩል እየተደረገ ያለውን ጥረት ኢህአዴግ እንደፈሪነት እየቆጠረው በትእቢት ተወጥሮ ያስራል ይገላል። ነገም ኢህአዴግ ከዚህ የተለየ ነገር አያደርግም። ፓርቲያችን አንድነትን ለጀሌዎችህ ስትሰጣቸው እጃችንን አጣጥፈን ዝም ብለን አናይህም በሚል ነገ የአንድነት አባላቶች እና ደጋፊዎች ሰልፍ ሲወጡ ወያኔ እንደለመደው ያስራል። ዛሬ በልሳኑ ኢቲቪ ኢቢሲ ደግሞ ሰማያዊ ምርጫው ሰላማዊ እንዳይሆን እሰራለሁ አመፅንም እጠራለሁ ብሏል ሲል በሬ ጥጃ ወለደ ዲስኩሩን ደስኩሯል። አንድነትን ለእነ ትእግስቱ አወሉ ሰጥቼ እውነተኛ አመራሮቹንም አስሬ አፈርሰዋለሁ፤ ሰማያዊን ደግሞ አመፅ ሊጠራ ነው በሚል ፓርቲውን አግዳለሁ አመራሮቹንም አስራለሁ በሚል ስሌት እየሰራ እንደሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልፅ ሆኗል። እንግዲያው ፓርቲዎችን ከዘጋ፣ ህጋዊ አመራሮችንም ካሰረ እና ሰላማዊውን መንገድ ከዘጋው የኢትዮጲያ ፖለቲካ መልኩን ይቀይራል። ጓዶቹ የታሰሩለትን ፓርቲ፣ አላማ እንዲሁም ትግል ወደጎን ትቶ የሚሄድ የለምና አሁን ትግሉ ሞትን ፊት ለፊት የመጋፈጥ እና ነፃነትን የመሻት ነው። የሰላም በሮች ሲዘጉ የአብዮት በሮች ይከፈታሉ እንዲል ጋዜጠኛው ነቢዩ።
የኢትዮጲያ ፖለቲካ መልኩን የሚቀይርበት ኛው ሰአት ላይ ደርሷል
በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በአቶ ኦባንግ ሜቶ በተጠራው ስብስባ ላይ የመገኘት እድል አጋጥሞኝ ነበር። በስብሰባው ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎችና ከአሜሪካ ግዛቶች የተሰባሰቡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።የስብሰባው መሪ ሀሳብ ስለ እያንዳንዳችን ከመናገር እያንዳንዳችን እንነጋገር የሚል ድፍረትን ግልፅነትን መከባበርን መነጋገር መቻልን ሀላፊነት በተሞላበት ስሜት ይቀርቡ በነበሩት አስተያየቶች የሚያረጋግጡ ከመሆናቸውም በላይ የተለየዩ የፖለቲካ አመለካከት እምነት እንዲሁም የተለየዩ ብሄረሰቦች ዉሁድ ኢትዮጵያውያን በአንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምጠው ያነሷቸው የነበሩት ሀሳቦች በጥንታዊት ኢትዮጵያና በአዲሲቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ገመድ ጉተታ ግራ ለተጋቡ ጥሩ አስተማሪ መድረክ ነበር።ኢትዮጵያ የምትባል ጥንታዊት ሀገርን የሲኦል መገለጫ አድርገው ለሚስሏት የህወሀት ኢሀዴግ ደጋፊዎችና ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸው የፖለቲካ ሰአሊዎች ወይም ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ያላቸውን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቁርኝት በፖለቲካ ብሩሽ ለማጥፋት የሚንደፋደፉ ያሉትን ያህል አዲሲቱን ኢትዮጵያን በጎሪጥና በሀሳባቸው የተለየ ቅርፅ ሰጥተው ለሚባንኑትም ሁለቱም አካሄዳቸው ሀገራችንን መጉዳቱን የስብሰባው ተሳታፊዎች አማካይ መንገድ እንዳለ በማሳየት ለዚህም ብቸኛ መንገዱ እውነትን መጋፈጥና መነጋገር ብቻ እንደሆነ ያሰመሩበት ጉዳይ ነው።ስለ ዲሞክራሲ ማውራትና በዲሞክራሲ ህይወት ውስጥ መኖር ያለውን ልዩነት በተሳታፊዎቹ አቀራረብና በመድረኩ አመራር ያለው የዳበረ የፖለቲካ ግንነት አመላካች ነበር።ይህ ወቅቱ የጠየቀውና አብዛኛው መድረክ ያጣና የታፈነ ኢትዮጵያዊ ድምፅ በመሆኑ ወንድማችን ኦባንግና ሶሊዳሪቲ ይህን መድረክ በመክፈታቸው ከፍተኛ ምስጋናና ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል። ከተለያዩ ክፍለ አለማትና ከአሜሪካ ስቴቶች በስፍራው ተገኝታችሁ አሁን በሀገራችን የሚታየውን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ የበሰሉ ሀሳቦችን ላቀረባችሁ ምሁራን የሀይማኖት አባቶችና እናቶች ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ይድረሳችሁ።ኢትዮጵያውያን ዝርዝር ሂደቱን ክፍል ክፍል እና ክፍል ከዚህ ማግኘት ትችላላችሁ።በተለይም በዲያስፖራው የሚታየው ጫፍና ጫፍ ቆሞ በስልጣን ላይ ካለው አምባገነን የህወሀት ኢሀዴግ መንግስት ባልተናነሰ ሁኔታ ባለፉት አመታት ኢትዮጵያውያንን እየከፋፈሉ ያሉት ጥቂት የፖለቲካ ሀይሎችና በስመ ደጋፊነት የተሰለፍን ወገኖች አካሄድ ትግሉን ወደ ኋላ ከማስኬድ በስተቀር ያስገኘው ፋይዳ እንደሌለውና አሁንም መፍትሄው ድፍረትና የመቻቻል ፖለቲካ ብቻ እንደሆነ ከምንም በፊት ለእውነት እራስን ም ማስገዛት ተቀዳሚ ተግባር ና የፖለቲካው ወሳነ ሀይል ህዝብን ማእከል ያደረገ ትግል ብቻ መ ሆኑን ከዚህ ስብሰባ መገንዘብ ይቻላል።ዲያስፖራው የኢትዮጵያን ፖለቲካ በአብዛኛው የሚገመግምበት መድረኩ የፓልቶክ ክፍሎች በመሆናቸው በአካል ተገናኝቶ በመነጋገርና በኮምፒዩተር ጀርባ ሀሳብንም ሆነ ልዩነትን ማስተናገድ ያላቸውን ልዩነት በመገንዘብ ለአካላዊ ግንኙነት ትኩረት በመስጠት መሰባሰቡ ያለውን ፋይዳ መገንዘቡ የወቅቱ ጥያቄ ይመስለኛል።በፓልቶኮች የሚደረጉ ውይይቶች በአብዛኛዎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉና ዲሞክራሲያዊ ባህርያቸውም እያደገ የመጣና የትግላቸውም ማእከል በሀገር ቤት ያለው ትግል መሆኑ የሚያበረታታ ሲሆን የሶሊዳሪትና የአቶ ኦባንግ አካሄድ ለዲያስፖራው ፖለቲካ መጎልበት አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተስፋ አለኝ።
የኦባንግ ጉዞና ለዲያስፖራው ፖለቲካ ያለው አስተዋፅኦ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው አስቀድሞ ለረዥም አመታት ሲያራምዱት ከነበረው ቅድሚያ ለአሜሪካ ከሚለው አቋማቸው ጋር በእኩል ሲያራምዱት የነበረው፣ አሜሪካ የአለም ፖሊስነትን ማቆም አለባት የሚለው አቋማቸው ነው። ዶናልድ ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ከተመረጡ በኋላም ሲወስዷቸው የነበሩ የንግድና የደሀንነት እርምጃዎች ሙሉ በሙሉ በዚህ እሳቤ የተቃኙ ናቸው። ፕሬዚዳንቱ ለአሜሪካ ጥቅም የማይሰጡ ናቸው ካሏቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች ያለምንም ማመንታት ሲወጡ፣ በኋላም በትዊተር ገፃቸው ይኼንን እርምጃቸውን ሲያውጁ ቆይተዋል። ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥና ከኢራን የኑክሌር ስምምነቶች መውጣት በተጨማሪ፣ በአጋር አገሮች ላይ የጣሉትን የገቢ እቃዎች ቀረጥ እንደ ማሳያ ማንሳት ይቻላል። ይኼንንም ተከትሎ አሜሪካ በአለም ላይ የነበራት የመሪነት ስፍራ ክፍተት በመፈጠሩ፣ ሌሎች አገሮች ይኼንን ክፍተት የመሙላት ሀላፊነት እንዲረከቡ ግድ ሆነባቸው። ይኼንንም ሀላፊነት ለመውሰድ የሚንቀሳቀሱት ከምእራቡ አለም ጀርመን በጉልህነት ስትጠቀስ፣ ከምስራቁ ደግሞ ቻይናንና ሩሲያን ያቀፈው ቡድን ይጠቀሳል። ጀርመን ነባራዊውን የአለም አመራር ለማስቀጠል ጥረት ስታደርግ፣ በአሜሪካ ላይ ያላት እምነት እንደተሸረሸረና ያለ አሜሪካ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ መግደርደር መቅረት አለበት ስትል፣ ቻይናና አጋሮቿ ደግሞ በዚያኛው ጥግ የራሳቸውን አዲስ የአለም አመራር ቡድን በማቋቋምና በማጠናከር ተጠምዷል። ከፓሪሱ ስምምነት በኋላ ዶናልድ ትራምፕ ከቡድን ሰባት አባል አገሮች ጋር በካናዳ ኩቤክ ያደረጉት ስብሰባ ውጤትና የእሳቸው የትዊተር መግለጫ፣ የቆየውን የአለም አመራር ጥሰት የሚያሳይ እንደሆነ የሚናገሩ በርካቶች ናቸው። ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምንም አይነት ወዳጅነት ላይ የሚገኝ አገር ቢሆን እንኳን፣ ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው የንግድና ሌላ ስምምነት አሜሪካን በማይጠቅም መንገድ ነው ካሉ፣ ስምምነቱን ከመሰረዝና እርምጃዎችን ከመውሰድ የማይመለሱ መሆናቸውንም ያሳዩበት ነው። ፕሬዚዳንቱ በአገሮቹ ላይ የጣሉትን የገቢ እቃ ቀረጥ በምንም ሁኔታ ሊያጥፉ ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው፣ ስብሰባው ሲካሄድባት የነበረችው ካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ የመንግስታቸውን የመልስ ምት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሲንጋፖር ለማቅናት በወጡ በሰአት ውስጥ ያስታውቃሉ። በዚህም የተበሳጩት ዶናልድ ትራምፕ የስብሰባውን መግለጫ እንደማይቀበሉና ያኖሩትን ፊርማም እንደሰረዙ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስታወቁ። ይህም በቡድን ሰባት አባል አገሮች መካከል እየተፈጠረ ያለውን ክፍተት የሚያሳይ እንደሆነ እየተጠቆመ ነው። የምእራቡ አለም እየተከፋፈለ ባለበት በዚህ ወቅት ግን የምስራቁ አለም እየጠነከረና ብቁ ተቋማትን እየገነባ የአለም አመራርን ጉልህ ስፍራን ለመያዝ የሚያስችሉትን ውጥኖች እያዘጋጀ ነው። ይኼንንም ግብ ለማሳካት ከተቋቋሙ ተቋማት አንዱ የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ይባላል። በሩሲያና በቻይና ጠንሳሽነት በይፋ የዛሬ አስር አመት የተቋቋመው ይህ የሻንጋይ የትብብር ድርጅት፣ የቡድን ሰባት አባል አገሮች በካናዳ ስብሰባ ባደረጉበት ሳምንት ስብሰባውን በቻይና ሻንጋይ ከተማ በድምቀት ሲያካሂድ ነበር። ይሁንና ከስብሰባዎቹ በኋላ የወጡት ፎቶዎችና የውይይቶቹ ውጤቶች የሚሳዩት በአሜሪካ የሚመራው የአለም አስተዳደር እየተፍረከረከና ሌላ ጠንካራ የምስራቁ አለም የአለም አስተዳደር እያደገ እንደመጣ ማሳያ ናቸው ሲሉ እይታቸውን ያጋሩ ነበሩ። ይህ ስምንት አባል ድርጅቶች ያሉት የሻንጋይ የትብብር ድርጅት የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ይቀናቀናል የተባለለት ነው። በደሀንነት፣ በፖለቲካና በኢኮኖሚ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው። በዋናነት ሩሲያን፣ ቻይናን፣ ህንድን፣ ካዛኪስታንን ያቀፈ ሲሆን፣ በርካታ አገሮችንም በታዛቢነት የያዘ ነው። ይህ ድርጅት በተለይ በአባል አገሮቹ መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን፣ በየአመቱ በሚቀያየሩ የአባል ድርጅቶቹ መሪዎች ሊቀመንበርነት የሚመራ ተቋም ነው። በአመት አንዴ በወቅቱ ሊቀመንበር አገር ስብሰባውን ያደርጋል። በእነዚህ ስብሰባዎች ሚናዎቹን እያሳደገ የሚመጣ ድርጅት ሆኗል። በመጀመርያ አካባቢ በአገሮቹ መካከል ወዳጅነትን ለማጠንከር በማለት የተቋቋመው ድርጅት፣ አሁን ወደ ደሀንነትና ወደ ንግድ አድጎ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። በተለይም ለሽብርተኝነት ዋነኛ የገቢ ምንጭ የሆነውን የአደንዛዥ እፅ ዝውውር በመከላከል ላይ በትኩረት ይሰራል ተብሏል። የአሜሪካ የግምጃ ቤት ሰነድን በመግዛት ቀዳሚ የሆነችውና አንድ ነጥብ አንድስምንት ትሪሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሰነድ የያዘችው ቻይና የምትመራው ድርጅት በመሆኑ፣ ሩሲያም የአሜሪካን የግምጃ ቤት ሰነድ በመግዛት ሀያ አምስትኛ ስፍራ ያላት በመሆኗ በዚህ አቅማቸው አገሮቹ የአለምን አመራር አቅጣጫ የማስቀየር እድል ሊኖራቸው ይችላል ይባልላቸዋል። የአሜሪካ ከኢራን የኑክሌር ስምምነት መውጣቷና የአውሮፓ አገሮች ከኢራን ጋር በሚያደርጉት የነዳጅ ግዥ ስምምነት ዶላርን እየተው መምጣታቸው፣ ይባስ ብሎም ሩሲያ ካላት የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሰነድ ግማሽ ያህሉን ዋጋ የሚይዘውን ሰነድ በመሸጧ አገሮች በሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ ዶላርን ወደ ጎን እያሉት ነው። ይህም የተባለውን ለውጥ በአመታት ውስጥ ካልሆነ ከአሰርት አመታት ባልዘለለ ጊዜ ውስጥ ሊያመጣ ይችላል የሚል መላምት እንዲሰጥ አድርጓል። ከዚህ በተቃራኒ የቻይና ፕሬዚዳንት ለአለም አገሮች አንድነትና መቀራረብን ሲሰብኩ በሌላ ወገን ዶናልድ ትራምፕ ስለአለም ምን አገባኝ እያሉ መሆናቸው፣ የሌላው አገር ፖለቲካ ውስጥ አልገባም ስትል የነበረችው ቻይና ወደ አለም አመራር ስፍራ እንዴት እየመጣች እንዳለች ማሳያ አድርገውም የሚያቀርቡ አሉ። ግሎባል ታይምስ የተባለውና በቻይና የሚታተመው መፅሄት ርእሰ አንቀፅ ሁከት ከበዛበት የቡድን ሰባት አባል አገሮች ስብሰባ ይልቅ፣ የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ውጤታማና ትኩረት ሳቢ መሆን ችሏል ብሏል። በአሜሪካ ላይ የተመሰረተው አሀዳዊ የአለም አመራር እንዳበቃለትና ብዝሀዊ የአለም አስተዳደር እየመጣ እንዳለም ማሳያ ነው ይላል ይህ ርእሰ አንቀፅ። አሀዳዊ ስርአት ከላዩ ሲታይ ጠንካራ ቢመስልም፣ በእውን ቀጣይነት የሌለው ነው ሲል ይደመድማል። በማእከላዊነት በአገር መሪዎች ምክር ቤት የሚመራው የሻንጋይ ትብብር ድርጅት እንደ ህንድ ያሉ አገሮችን እያቀፈ መምጣቱም ጥንካሬ እንደሚሰጠው ይነገራል። የዚህ ድርጅት ጥንካሬም በአለም ጉዳዮች ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሌላ ጠንካራ ሀይልን ሊፈጥር ይችላል እየተባለም ነው።
አቅጣጫውን እየቀየረ ያለው የአለም አመራር
ጌጡ ተመስገንአመራርነት ወንበር ይዞ መቀመጥ ብቻ መሆን የለበትም በስራ መታየት አለበትሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አስታወቁ። በአመራር ክፍተት በክልሉ ከዚህ ቀደም የተፈጠሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ አመራሩ ለተሻለ ስራ መንቀሳቀስ እንዳለበት አሳስበዋል።ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ለማ መገርሳ በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት በተካሄደው አምስተኛው የጨፌ ኦሮሚያ አራተኛ አመት የስራ ዘመን ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ እንደተናገሩት ህዝቡ የክልሉን የልማት ስራ በማገዝ የኩሉን አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይገባል።ቀደም ሲል በማህበራዊበኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ በህዝቡ ዘንድ ይነሱ የነበሩና በአመራር ክፍተት የተፈጠሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ አመራሩ ምን ውጤት አመጣለሁ ብሎ እራሱን በመፈተሽ ለተሻለ ውጤት መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ ይህን የማያደርግ ከሆነ ተሸክሞ መሄድ ያስቸግራል ብለዋል። አመራርነት ወንበር ይዞ መቀመጥ ብቻ መሆን የለበትም። በስራ መታየት አለበት። ከስራ ጋር ቶሎ ተላምዶ ለውጤት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ለማ ከአዛዥነት ወጥቶ በተጠያቂነት መስራት ከአመራሩ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል። በክልሉ የሰው ሀይል ፍልሰት አሁን እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም መታየት እንዳለበት ጠቁመዋል።የክልሉ ህዝብም በአካባቢው በመንግስትም ሆነ በኢንቨስትመንት የሚሰራውን የልማት ስራ በመደገፍ የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለው በክልሉ የሚገነቡ የትምህርትየጤናእና ሌሎች የልማት ስራዎች የኦሮሚያ ናቸው የሚል አስተሳሰብ መኖር እንዳለበትም ገልፀዋል።በአንድ በኩል ልማት እየተፈለገ በሌላ በኩል ልማትን የሚያርቅ ስራ መስራት ለክልሉ ስምም ሆነ ለክልሉ እድገት አይበጅምሲሉም ተናግረዋል።
አመራርነት ወንበር ይዞ መቀመጥ ብቻ ሳይሆን በስራ መታየት አለበት አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ከኩዌት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሀመድ አል መሻ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።ወይዘሮ ሂሩት ሁለቱ ሀገራት ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ታሪካዊ ግንኙነትና ትብብር እንዳላቸው ጠቅሰው፥ የሀገራቱን ህዝቦች ጥቅም ለማሳደግ ይህን ትብብር በንግድና ኢንቨስትመንት እንደሚያጠናክሩም ገልፀዋል።የኩዌት ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በሚገኙ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች በተለይም በማምረቻና በግብርናው ኢንዱስትሪ ዘርፍ ቢሰማሩ ውጤታማ እንደሚሆኑም ተናግረዋል።ኩዌት ለኢትዮጵያ ልማት እያደረገች ላለው ድጋፍም ሚኒስትር ዲኤታዋ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።የኩዌት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሀመድ አል መሻን በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ አድንቀዋል።ሀገራችውም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራች መሆኑንም አንስተዋል።በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርም የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በሰኔ ወር በአዲስ አበባ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያና ኩዌት ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከረ እየሰሩ መሆኑ ተገለፀ
ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅና ከዚያ በፊት በነበረው ሁኔታ የኢንተርኔት መቆራረጥና መታገድ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ማድረሱ የተጠቀሰ ሲሆን ባለፈው አንድ አመት አገሪቱን ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማሳጣቱን የአሜሪካው ብሩኪንግ ኢንስቲቲዩት ይፋ ያደረገው ጥናት አመልክቷል። ዴልዮት የተባለው አለማቀፍ አማካሪ ተቋም በበኩሉ የሞባይል ኢንተርኔት መዘጋት ሀገሪቱን በቀን መቶ ሺህ ዶላር እያሳጣት ነው ብሏል።በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞና ግጭቶች መከሰታቸውን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎቶች መቆራረጥ ሀገሪቱን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ ሚሊዮን ብር በላይ አሳጥቷል ብሏል ዴልዮት። የኢንተርኔት አገልግሎት መቃወስ የኢኮኖሚ እድገቱን እንዲቀዛቀዝ አድርጓል ያለው አፍሪካን ቢዝነስ ፈጠራዎች እንዳይበረታቱ የገቢ ታክሶች በአግባቡ እንዳይሰበሰቡና ነጋዴዎች በቴክኖሎጂው ላይ ያላቸው እምነት እንዲሸረሸር ማድረጉን የብሩኪንግ ኢንስቲቲዩት ምፕሬዚዳንት ዳረል ዌስትን ጠቅሶ ዘግቧል።ዘመናዊ የኢኮኖሚ እድገት በኢንተርኔት ላይ ጥገኛ መሆኑን የጠቆመው ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ ታዳጊ ሀገራት በአመታዊ ጠቅላላ አገራዊ ምርት እድገታቸው ላይ የ በመቶ ድርሻ እንዳለው ያመለክታል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀበት ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በተለይ የሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ግንኙነት መቋረጡ በመንግስት ገቢ ላይ ጉዳት ከማድረሱ በተጨማሪ የእለት ተለት ስራቸው በቀጥታ ከኢንተርኔት ጋር ለተቆራኙ ነጋዴዎችም ከፍተኛ ኪሳራ እያስከተለባቸው እንደቆየ ጠቁሟል።ከኢንተርኔት አገልግሎት ባሻገር ከፍተኛ ገቢ ከሚያስገኙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አንዱ የሆነው የተለያዩ የተንቀሳቃሽ ስልኮች መተግበሪያ እየተገደበ መሆኑን ሪፖርቱ ይጠቁማል ቫይበር ዋትሳፕና ሜሴንጀር የመሳሰሉ የኢንተርኔት የግንኙነት አውታሮች በዚህ መንገድ እየተገደቡ መሆኑን በመጥቀስ።ባለፈው አመት በኢንተርኔት የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ላይ የተደረገው ጥናት በአሜሪካ የኢንተርኔት አገልግሎት በአመት እስከ ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በመቶ ድርሻ እንዳለው የተጠቆመ ሲሆን ሌሎች ሀገራት ግን ከዚህ ቴክኖሎጂ ማግኘት የሚገባቸውን ከፍተኛ ገቢ አገልግሎቱን በመገደብ እያጡ መሆኑ ተመልክቷል።የኢንተርኔት አገልግሎትን በመገደብ ከአፍሪካ በቀዳሚነት የተጠቀሰችው ሞሮኮ በአመት ሚሊዮን ዶላር ማጣቷ የተጠቀሰ ሲሆን ኮንጎ ሚሊዮን ዶላር አልጄሪያ ሚሊዮን ዶላር በአመት አጥተዋል ተብሏል። ኢትዮጵያ በበኩሏ ባለፈው አመት ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን ሪፖርቱ ጠቁሟል።ከአፍሪካ ሀገራት ደቡብ አፍሪካ ኬንያና ግብፅ የተሻለ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳላቸው የተጠቆመ ሲሆን ኢትዮጵያ ናሚቢያና ደቡብ ሱዳን የኢንተርኔት አገልግሎታቸው ዝቅተኛና አርኪ አለመሆኑ ተመልክቷል። በጉዳዩ ዙሪያ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅቤትም ሆነ ከኢትዮቴሌኮም ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች ስብሰባ ላይ ናቸው ሳይሳካልን ቀርቷል። አለማየሁ አንበሴ
መንግስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተነሳ ኢንተርኔት በማቋረጡ ሚ ዶላር አጥቷል ተባለ
አንድ መቶ ዘጠና ስድስት ህዝባዊ ተቀባይነቱን ያጣው ወያኔ በሽፍትነት ዘመኑ ትግራይ ውስጥ ሲያደርግ እንደረነበረው ሁሉ፣ መንግስታዊ ስልጣኑን ከያዘም በኋላ መሰልጠን አቅቶትና እንደመንግስት ማሰብ ተስኖት፣ አገዛዜን ይቃወማሉ ብሎ የሚጠረጥራቸውን ዜጎች የቅርብ ቤተሰቦችና የሩቅ ዘመዶች ሳይቀር ማሰቃየት መጀመሩን ከአራቱም የአገራችን ማእዘናት በየቀኑ የሚደርሱን ሪፖርቶች ያመለክታሉ። በቅርቡ በአርባ ምንጭ ከተማ ለአገራቸው ነፃነት በገዛ ፈቃዳቸው ተነሳስተው ታሪካዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በሞከሩ ወጣቶች ላይ የስርአቱ ታማኝ ጥቂት የደህንነት ሀይሎች የወሰዱት እርምጃ ዘግናኝና ልብ የሚያቆስል ነው። ይህም አልበቃ ብሎ የተፈላጊ ወጣቶች መኖሪያ ቤቶች በታጠቁ የደህንነት ሀይሎች ተወረው ፍተሻ ተካሂዶባቸዋል። እናቶች ህፃናት ልጆቻቸው ፊት የተደበቁ ልጆቻችሁን አምጡ ተብለው መሳሪያ ተደቅኖባቸው፣ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ተፈፅሞባቸዋል። በአገዛዙ ዘረኛና የተጨማለቀ ፖሊሲ ተማረው ተቃውሞአቸውን ለመግለፅ እርምጃ መውሰድ የጀመሩ የቴፒ ወጣቶችን ለማደን የተደረገው ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ የፈደራል ፖሊስና መከላኪያ ሰራዊት በወላጆች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ወስዷል። ወጣት ሴቶች እና እናቶች ርህራሄ በጎደላቸው የስርአቱ ታማኝ ወታደሮች ተደብድበዋል፣ ተደፍረዋል፣ ታስረዋል። በሰሜን ጎንደርም እንዲሁ መብታችን ይከበር ብለው በተነሱ ወጣት ቤተሰቦች ላይ የገዢው ሀይል ታማኞች ፣ ግድያና አስገድዶ መድፈር ፈፅመዋል። እህትማማች ሴቶች መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ ተገድለዋል። በወታደሮች የተደፈሩ ሴቶች ቅስማቸው ተሰብሮ ወደ አደባባይ ለመውጣት እንኳ የማይችሉበት ደረጃ ደርሰዋል። በመርአዊ ከተማ መኳንንት ፀጋዬ የተባሉ በሰላማዊ ትግል ስርአቱን የሚቃወሙ ግለሰብ፣ በልጆቻቸውና በባለቤታቸው ፊት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ የልጆችን ስነልቦና በሚነካ መልኩም ሰዋዊ ክብራቸው እንዲዋረድ ተደርጓል። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ድንበር የለውም፤ የወያኔን የበቀል ዱላ ያልቀመሰ፣ ማንነቱና ክብሩ ያልተዋረደ ህዝብ ማግኘት አይቻልም። በገዳዩ ስርአት እየደረሰ ያለው ግፍ አንድ ጊዜ በሰሜን፣ ሌላ ጊዜ በደቡብ፣ ሌላ ጊዜ በምስራቅ እያለ ቀጥሎአል። የዚህ ፍፁማዊ የአፈና አገዛዝ ህልውና እንዲቀጥል እስከተፈቀደለት ድረስ ጭቆናው፣ መዋረዱ፣ መታሰሩና መሞቱ አይቆምም። የአገዛዙ ባህሪ እነዚህን ሰይጣናዊ ድርጊቶች ለመፈፀም እንጅ መልካም ነገር ለመፈፀም አያስችለውም። ለነፃነት የሚደረገው ትግል በመሬት ላይ አድማሱን እያሰፋ በመጣ ቁጥር የጥቃቱ አይነትና መጠንም እየጨመረ እንደሚመጣ ስናስብ፣ ይህን ጥቃት የምናስቆምበት ወይም የምንቀንስበትን መንገድም መሻት ተገቢ ነው። ወያኔ በነፃነት ታጋይ ቤተሰቦች ላይ ጥቃቱን ሲፈፅም ከሚጠቅሳቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ልጅህ ወይም ወንድምህ መንግስታችንን ለመናድ ሌት ተቀን እየሰራ አንተ በሰላም ልትኖር አትችልም የሚል ነው። ይህ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ወያኔን ከሚመሩ ሰዎች የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ፖለቲካ ወይም የነፃነት ጉዳይ በደም የሚወረስ ሳይሆን ከግለሰቦች ማንነት ጋር ተያያዞ የሚመጣ መሆኑን፣ ቀድም ብለው በሁለት ጎራ ለይተው ሲፋለሙ የነበሩ ወጣቶችን ታሪክ ማስታወስ በቂ ነው። ከአንድ ማህፀን የወጡ የአንድ እናት ልጆች የተለያዬ የፖለቲካ አመለካከት እንደሚይዙ ታሪካችን ብቻ ሳይሆን፣ የወያኔ ታሪክ ራሱ ምስክር ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ በጅምላ በቤተሰብ ላይ የሚደርሰው ጥቃት፣ ከኋላ ቀርነትና ከግንዛቤ ማነስ የመጣ ነው ተብሎ የሚመጣ ብቻ ሳይሆን፣ ድርጊቱን ከሚፈፅሙት ሰዎች ስነልቦና ቀውስና የኋላ ታሪክ ጋር የሚያያዝ ነው። በንፁህ ዜጎች ላይ ጭካኔና ግፍ የሚፈፅሙ ሰዎች፣ የሰው ማንነት የሌላቸው፣ ከአስተዳደጋቸው ጀምሮ የተበላሹና ማህበረሰቡ አይመጥኑም ብሎ የተፋቸው ናቸው። አሁን በስልጣን ላይ ያሉና በህዝባችን ላይ የጭካኔ ዱላቸውን የሚያሳርፉ ገዢዎች የኋላ ታሪክ ቢጠና ከዚህ የተለየ እውነታ አይኖረውም። ሌላው የወያኔ ስልት ደግሞ በአገር ውስጥ ያሉትን ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጭ የሚንቀሳቀሱ የነፃነት ታጋዮችን ቤተሰቦችና ዘመዶች እየተከታተሉ እባካችሁ ዘመዶቻችሁ ከፖለቲካው እንዲርቁ አድርጉ፣ እንዲህ ካደረጋችሁ የምትፈልጉትን ነገር እናድርግላችኋለን፣ ለእነሱም የፈለጉትን ነገር እናደርግላችኋለን በማለት ለመደለል መሞከራቸው ነው። ለወያኔ ነፃነት ማለት ገንዘብ ነው፤ ቤት ነው፤ ሆድ ነው፤ ነፃነት የህሊናና የማንነት ጉዳይ መሆኑን ገና አላወቀም። ሁሉም ሰዎች ነፃነታቸውን በገንዘብ፣ በቤት፣ በሆድ ወይም በብልጭልጭ ምድራዊ ነገር ይሸጣሉ ብሎ ያስባል፤ በርግጥ በእነዚህ አላፊና ጠፊ ነገሮች ተታለው ነፃነታቸውን የሸጡ ቢኖሩም፣ ሁሉም ሰው ግን እንደዛ አይደለም። የወያኔን የግፍ አገዛዝ ተቃውመው ለነፃነት የሚታገሉ ሀይሎች ሁሉ፣ ቁሳዊ ፍላጎታቸውን ትተው፣ ህሊናዊና ማንነታዊ ፍላጎትን ለራሳቸውም ለህዝባቸውም ለማምጣት የሚታገሉ ናቸው። በወያኔና በእነዚህ ታጋዮች መካከል ያለው ልዩነትም ይህ ነው፤ ወያኔ ለአላፊ ጠፊው ምድራዊ ህይወት ሲጨነቅ፣ እነዚህ ተጋዮች፣ ዘላለማዊ ለሆነው ለነፃነትና ለማንነት ክብር ይጨነቃሉ። ስለዚህ ወያኔ ለህሊናቸውና ለማንነታቸው የሚታገሉ ሀይሎችን በቁሳዊ ፍላጎት ለመደለል የሚያደርገው ጥረት መቼውንም ፍሬ አያፈራምና ቤተሰቦችን እየጠራ ባያንገላታቸው ይመረጣል። የአገዛዝ እድሜን ለማራዘም ሲባል በነፃነት ታጋይ ቤተሰቦች ላይ እየተወሰደ ያለው ጥቃት ከዚህ ቀደም በነበሩ ሁለት መንግስታት ዘመን እንኳ ታይቶ የማይታወቅ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልግም። መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት በተለየበት ሰሞን የአገዛዙ ጋዜጠኞች አዷ የሚገኘውን የወላጆቹን መኖርያ ቤት በቴለቪዥን ለህዝብ እይታ አቅርበው ፣ መለስ ዜናዊ ከጫካ እየሾለከ መጥቶ ያርፍ እንደነበር በገዛ ወንድሙ አፍ እንዲነገር አድርገዋል። በአጭሩ ፓለቲካ በደም አይተላለፍም፤ ደምን ቆጥሮ በፖለቲካ ታጋይ ቤተሰቦች ላይ የሚደርስ ጥቃትም፣ ቂምና በቀልን ከመውለድ ውጭ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። ህዝባዊ የነፃነትን ትግልን፣ የታጋዮችን ቤተሰቦች በማሰቃየት ወይም በመደለል ማስቆም አይቻልም። አፈናና ሰቆቃ ባለበት ቦታ ሁሉ ፣ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር፣ አመፅ የማይቀር ማህበራዊ ክስተት ነው ። በተለይ የህዝብ ብሶት ወለደኝ በማለት መሳሪያ አንስቶ አመት ታገልኩ ለሚለው ወያኔ ይህ ግልፅ እውነታ ምርምር የሚጠይቅ ውስብስብ ፍልስፋና ሊሆንበት ባልቻለ ነበር ። ዳሩ ከተጣመመ አፈጣጠሩ፣ ከመሪዎቹ ምንነትና ማንነት እንዲሁም ስልጣን ከተያዘም በኋላ በዘረፋ የተሰበሰበው ሀብት የፈጠረው የኑሮ ምቾትና የተከማቸው የጦር መሳሪያ ያቀዳጀው እብሪት አይነ ልቦናውን ጋርዶታልና ለወያኔ ይህ ሀቅ ሊገባው አይችልም። አርበኞች ግንቦት ሰባት የወያኔ የአፈና ክንዶች ሺ ጊዜ ቢፈረጥሙም ፤ በተቃዋሚዎችና የነፃነት ታጋዮች ቤተሰብ ላይ የሚወሰደው እርምጃ የህይወት መስዋትነት እያስከፈለ ቢመጣም እንኳ ለነፃነት የሚያደረገው ትግል ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል እንጂ ለአፍታም ቢሆን አይዘናጋም። የታጋይ ቤተሰቦችና ዘመዶችም፣ አሁን በወያኔ የሚደርስባችሁ ግፍና በደል፣ ለመላው አገራችን ነፃነት ሲባል የሚከፈል ዋጋ በመሆኑ ልትኮሩ እንጅ ልለትሸማቀቁ አይገባም ። በህዝብ ፊት የነጠሏችሁና ከማህበራዊ ህይወታችሁ እንድትገለሉ ያደረጓችሁ ቢመስላችሁ፣ እውነታው ተቃራኒው ነው፤ ከህዝብ የተገለሉት እነሱ ናቸው፤ የሚዋረዱትና የሚያፍሩት እነሱ ናቸው። በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ስር የሚማቅቅ እያንዳንዱ ዜጋ አርበኞች ግንቦት ሰባት የለኮሰውን የነፃነት ትግል ችቦ አንግቦ በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ የታፈረች የተከበረችና የዜጎቿን መብት በእኩልነት የምታስከብር አገር ለመገንባት በሚደረገው ትግል እንዲቀላቀል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪውን ያቀርባል። የወያኔ የጥቃት እጆች የሚያጥሩትና ዜጎች በአገራቸው ተከብረው የሚኖሩት ወያኔ ሲወገድ ብቻ ነው ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ፖለቲካ በደም አይጋባም አርበኞች ግንቦትሰባት ኢዲቶርያል
ጭማሪው በኪሎ ግራም ብር ከ ሳንቲም ሲሆን ከፍተኛ ነው በሚል እየተተቸ ነው።ሚኒስቴሩ ለዚህ ጭማሪ የሰጠው ምክንያት የማምረቻ ዋጋ ጭማሪ አሳይቶአል የሚል ቢሆንም ለስኳር ኮርፖሬሽን ቅርበትያላቸው ምንጮች ግን መንግስት ከድርቁ ችግር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ በመግባቱናስኳር መሰረታዊ ፍላጎት አይደለም በሚል እንዲጨመር መደረጉን ጠቁመዋል።የስኳር የማምረቻ ዋጋ በኪሎግራም ከ ብር እንደማይበልጥ የጠቀሱት ውስጥ አዋቂዎች ነገር ግን ዋጋ እንዲያረጋጉ በተቋቋሙሸማች ማህበራት በኩል ለአዲስአበባ ነዋሪዎች አንድ ኪሎ በ ብር እንዲሸጥላቸው ሲደረግ ቆይቶአል። ካለፈው ሳምንትጀምሮ በድንገት የአንድ ኪሎ ስኳር ዋጋ ብር ከ ሳንቲም እንዲሆን ተደርጎአል። ጭማሪውንተከትሎ በመደበኛ ሱቆች የአንድ ኪሎ ግራም ስኳር የችርቻሮ ዋጋ እስከ ብር አሻቅቦአል።ይህ ያልተጠበቀ የዋጋ ጭማሪ በተለያዩ የምግብ ውጤቶች ላይ ሊንፀባረቅ ስለሚችል በቀጣይ በምግብ ነክ ውጤቶችላይ የማይናቅ የዋጋ ንረት ያስከለትላል የሚል ስጋት አሳድሮአል።በተመሳሳይ ሁኔታ የነዳጅ ምርትም በአለም አቀፉ ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምርም አሁንም መንግስት የተለያዩምክንያቶችን በመደርደር የአለም ገበያን ተከትሎ ዋጋ ለመቀነስ እምቢታ ማሳየቱ የሚታወስ ነው።የመንግስት ሰራተኞች የኑሮ ውድነቱን መቋቋም እንደተሳናቸው በተለያዩ ጊዜዎች ሲገልፁ ቆይተዋል።
ንግድ ሚኒስቴር በስኳር መሸጫ የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ
በስልክዎ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ባለዎት የኢንተርኔት ፍጥነት የተለያዩ ምልክቶችን ይመለከታሉ። ፣ ፣ ፣ ሶስት ጂ እና አራት ጂጥቂቶቹ ናቸው። አራት ጂ ከእነዚህ መካከል ፈጣን የሚባለው ነው። አራት ጂ ኤል ቲ ኢ በሚልም ሊገለፅ ይችላል ወይም በግርድፉ የረጅም ጊዜ ዝግመተ ለውጥ በሚል ሊተረጎም ይችላል። እጅግ ፈጣን የተባለለት የ አምስተኛ ትውልድ ወይም አምስት ጂ የሞባይል ኢንተርኔት ጥቅም ላይ ከዋለም ዋል አደር ብሏል። ቴክኖሎጂው ሁሉም ዘንድ አልደረሰም። ቢደርስም ለዚህ የተዘጋጀ ስልክ ያስፈልጋል። ለሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት አለም አቀፍ ደረጃዎች ባይኖሩም የኢንተርኔት አቅራቢዎች አንደኛው ትውልድ ወደሌላኛው በማቅናት ወደ አራተኛው እና አምስተኛው ትውልድ እየዘለቁ ነው። ኢትዮ ቴሌኮም ኢትዮ ቴሌኮም ከሀምሳ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት ይገልፃል። ኩባንያው አሉኝ ከሚላቸው ከሀምሳ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን በላይ ደንበኞች መካከል ከ አርባ ስምንት ዘጠኝ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ናቸው። ከ ሀያ ሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የዳታ እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው። የኢንተርኔት አገልግሎትን እአአ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ይፋ ሲያደርግ ከሁለት አመት በኋላ ደግሞ የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት ጀመረ። በሁለት ሺህ ሰባት የሶስትጂ አገልግሎት ይፋ አድርጓል። የአራት ጂ ኤልቲኢ አገልግሎት ከፍተኛ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ እንደመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድግ ነው በሚል ኢትዮ ቴሌኮም አራትጂ ኤልቲኢ ኢንተርኔትን በሁለት ሺህ ነበር በአዲስ አበባ ያስጀመረው። ለአመታት በአዲስ አበባ ብቻ ይሰጥ የነበረው የ አራት ጂ አገልግሎትን በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የአራት ጂ ኤልቲኢ አገልግሎት የማስፋፊያ ስራዎችን በማከናወን በቀጣይ በሌሎች የክልል ከተሞች ተመሳሳይ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ ብሏል ኩባንያው በድረገፁ። አገልግሎቱን በተለያዩ አካባቢዎች በማድረስ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ አገልግሎቱን አስጀምሯል። ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ ምስራቅ ሪጅን በሚገኙት አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ዱከም፣ ገላን፣ ሞጆ እና አዋሽ መልካሳ አገልግሎቱን ለደንበኞቹ ማድረስ ችሏል። ቀጣይ ተረኞች ደግሞ ባህር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ቡሬ፣ ዳንግላ፣ እንጅባራ እና ቻግኒ ሆነዋል። በደቡብ ደቡብ ምእራብ ሪጅን ውስጥ በሚገኙ ስድስት ከተሞች ማለትም በወላይታ ሶዶ፣ በአርባ ምንጭ፣ በሆሳእና፣ በወልቂጤ፣ በቡታጅራ እና በጂንካ የአራተኛው ትውልድ የማስፋፊያ ፕሮጀከቱን አጠናቆ አገልግሎቱ ተጀምሯል። ኩባንያው ለህብረተሰቡ ያቀረበውን የአራት ጂ ኢንተርኔት ለመጠቀም የሚያስፈልገውን የተንቀስቃቃሽ ስልክ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ አስተላልፏል። በኩባንያችን የሶስት አመት የእድገት ስትራቴጂ ላይ እንዳመላከትነው በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የየአራት ጂ ኤልቲኢ አገልግሎት የማስፋፊያ ስራዎችን ለማከናወን ታቅዶ እየሰራ ይገኛል ብሏል። በቀጣይ ወራትም በሌሎች የክልል ከተሞች ተመሳሳይ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ስራዎች እያከናወንኩ ሲል በድረገፁ አስነብቧል። ለመሆኑ እነዚህ ኢትዮቴሌኮም አስፋፋው ያለው አራት ጂ እና ሌሎች የተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት ትውልዶች ምንድናቸው አንድጂ አንድጂ ወይም የመጀመሪያው ትውልድ የሞባይል ዳታ እአአ በ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አንድ ተዋወቀ። አንድ ጂ አናሎግ የሆነ የመረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡ በ አንድ ጂ ጥሪዎችን ማስተላል ብቻ ነው የሚቻለው። ሁለትጂ ሁለት ጂ የፅሁፍ መልእክቶችን አስተዋውቋል። በኤስኤምኤስ በመባል የሚታወቀው ሁለት ጂ የፅሁፍ መልእክቶችን ለመላክ አስችሏል። ሁለት ጂ በተጨማሪም ኤምኤምኤስ መልቲሚዲያ ሜሴጂንግ ሰርቪስ የተባለ የምስል መልእክቶች ማስተላለፊያም አስተዋውቋል። በሞባይል ስልኮች ላይ ጂኤስኤም፣ ጂፒአርኤስ ፣ ኢዲጂኢ የሚባሉ አገልግሎቶች አሉት። ሶስትጂ የቪዲዮ ጥሪ እአአ በ ሁለት ሺህ አንድ ይፋ ሆነ። ሶስትጂ እና የሁለት ሜጋባይትስ በሰከንድ ወይም በሰከንድ ነጥብ ሁለትአምስት ሜጋ ባይት መረጃው መለዋወጥ የሚያስችል አገልግሎት የመጀመሪያዎቹ ስማርት ተንቀሳቃሽ ስልኮች ለገበያ ሲቀርቡ ተዋወቀ። እጅግ ፈጣን ባይሆንም ገመድ አልባ የኢንተርኔት በማቅረብ የመጀመሪያው ሲሆን የቪዲዮ ጥሪ እንዲኖር አስችሏል። ለማስረዳት ያህልም አራት ነጥብ ሁለትስድስት ጊጋ ባይት መረጃ ለማውረድ ከአምስት ሰአት በላይ ይጠይቃል። አራትጂ ሁለት ሺህ አስር ደግሞ አራት ጂን ይዞ ብቅ አለ። በሚሰጠው ፈጣን ግንኙነትም የሞባይል ጌሞችን እስከወዲያኛው ቀይሯል። አሁን በስራ ላይ የሚገኘው በጣም ፈጣኑ አራት ጂ የሞባይል ኔትዎርክ በአማካይ በሰከንድ አርባ አምስት ሜጋ ባይት ይሰጣል። ኢንዱስትሪው በሰከንድ አንድ ጊጋ ባይት የመድረስ ህልም አለው። በ ሶስት ጂ ተመሳሳይ ፊልም ለማውረድ ከአምስት ሰአታት በላይ ይወስድ የነበረው ጊዜ አራት ጂ ላይ ከ ስምንት ደቂቃ በታች እንዲሆን አስችሏል ተብሎ ይገመታል። አምስትጂ ምን ማለት ነው የቀጣዩ ትውልድ የሞባይል በይነመረብ ግንኙነት ሲሆን በጣም ፈጣን ዳታ የማውረድ እና የመጫን አገልግሎትን ይሰጣል። የሬዲዮ ሰፔክትረም በመጠቀም እጅግ በጣም ብዙ መሳሪያዎችን በአንድ ጊዜ የሞባይል ኢንተርኔቱን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ። አሁን በስማርት ስልኮቻችን የምንሰራቸውን ማንኛውንም ነገር በፍጥነት እና በተሻለ ለማከናወን ያስችለናል። ድሮኖች፣ መኪኖች እና የሞባይል ጌሞች በዚህ ፈጣን ኢንተርኔት በመጠቀም የተሻለ ግልጋሎት ይሰጣሉ። የሞባይል ቪዲዮዎች በቅፅበት እና ከመቆራረጥ ነፃ በሆነ መልኩ ይቀርባሉ ። የቪዲዮ ጥሪዎች ይበልጥ ንፁህ እና መንቀጥቀጥ ሳይኖራቸው ለደንበኞች ይደርሳሉ። ቴክኖሎጂውን በመጠቀም በሚጠለቁ ቁሳቁሶች አማካኝነት ድንገተኛ ሁኔታ ሲከሰት ወዲያውኑ ሀኪሞችን በማሳወቅ ጤንነትዎን በወቅቱ ሊቆጣጠሩት ይችላሉ ። አምስት ጂ ከ አስር እስከ ሀያ እጥፍ የሆነ ፍጥነት ማሳካት ይችላል ይላል የቺፕ አምራቹ ኳልኮም። በዚህ ፍጥነት በአንድ ደቂቃ ባለከፍተኛ ጥራት ፊልም ማውረድ ያስችሉዎታል። ኢትዮቴሌኮም አምስት ጂን ለደንበኞቹ ለማድረስ የያዘው እቅድ እንዳለ ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም።
ኢትዮ ቴሌኮም አስፋፋሁት ያለው አራት ጂ ምንድን ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም ዘጠኝ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የአማራ ክልል የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የሁለት ሺህ በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የሁለት ሺህ በጀት አመት እቅድ ትውውቅ እያካሄደ ነው። ቢሮው ከተሞችን የለውጥና የብልፅግና ማእከል እናደርጋለን በሚል መሪ ቃል ነው በደብረ ማርቆስ ከተማ የእቅድ ትውውቁን እያካሄደ የሚገኘው። በመድረኩ እንደክልል የከተሞች የገቢ አሰባሰብ ስርአት፣ የቤቶች መረጃ አስተዳደር ሂደት፣ ህገ ወጥ ግንባታና የከተሞች አረንጓዴ ልማት ስራ ይቀርባል ተብሏል። በጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም ስራና አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል መልካም አስተዳደርን የማስፈን ተግባራት ተገምግመው አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል። የአማራ ክልል የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ ቢያዝን እንኳሆነ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት ባለፉት አስር አመታት በክልሉ የነበሩትን ሁለት መቶ ስልሳ አንድ ከተሞች አሁን ላይ ስድስት መቶ ሰማኒያ አንድ ማድረስ ተችሏል። ክልሉ በጦርነት ውስጥ ሆኖም ባከናወናቸው የልማት ተግባራት በቢሮው የዘጠና ቀናት እቅድ ከሰማኒያ አንድ ሺህ በላይ ዜጎችን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ይህም ካለፉት አራት አመታት የበለጠ አፈፃፀም እንደሆነ ተናግረዋል። ስንቃችን ስራችን ነው ያሉት ሀላፊው ስንቅ የሌለው ረዢም ጉዞ መጓዝ አይችልምና አሁንም ጠንክረን ልንሰራ ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል። በመድረኩ ባለፈው አመት የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ተሞክሯቸውን ለውይይት አቅርበዋል። በሙሉጌታ ደሴ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
የአማራ ክልል የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የሁለት ሺህ በጀት አመት እቅድ ትውውቅ እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የአማራ ክልል የሀብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ የመጀመሪያ የሆነውን የኢንፍሎዌንዛ ቫይረስ ቤተሙከራ ምርመራ አገልግሎትን ዛሬ አስጀመረ። የክልሉ የሀብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ ከኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ የጤና ፕሮግራም ጋር በመተባበር ያስጀመረው ቤተሙከራ የመተንፈሻ አካላትን ለሚያጠቁ በሽታዎች የምርመራ አገልግሎት በመስጠት የህሙማንን ገንዘብ፣ ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ ረገድ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ነው የተባለው። ቤተሙከራው የሚያስፈልጉትን ግብአት በማሟላት ለስራ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ በሰጡት ማብራሪያ ለሀብረተሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት ለመስጠት የኢትዮጵያ የጤና አብያተ ሙከራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ነው የጠቆሙት። የኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ የጤና ፕሮግራም በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ለተዘረፉና ለወደሙ ዘጠኝ ሆስፒታሎች መልሶ ግንባታ ድጋፍ ማድረጉንም አውስተዋል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ በበኩላቸው በጤናው ዘርፍ ለሀብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በሽታዎችን መመርመርና ማወቅ ተገቢ እንደሆነ ጠቅሰው ትብብር ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል። በአራት ክልሎች የኢንፍሎዌንዛ መመርመሪያ ቤተ ሙከራ ስራ መጀመሩ የተገለፀ ሲሆን ወደ ሌሎች ክልሎችም የማስፋፋት ጥረቱ ይቀጥላል ተብሏል። የኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ የጤና ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ወንዶሰን ገብረየስ በበኩላቸው፥ በአማራ ክልል የኢንፍሎዌንዛና ሌሎች ተዛማች በሽታዎችን ለመከላከል እየሰሩ መሆናቸውን ነው የገለፁት። ተቋሙ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መጋለፃቸውንም አሚኮ ዘግቧል።
በአማራ ክልል የመጀመሪያው የኢንፍሎዌንዛ መመርመሪያ ቤተሙከራ ስራ ጀመረ
መስከረም ፳፭ ሀያ አምስት ቀን ፳፻፰ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና የዩኒቨርሳል ቲቪ ጋዜጠኞች የታሰሩት፣ ሁለት የፓርላማ አባላትን ጋብዘው የኢትዮጵያ ጦር በአገሪቱ ውስጥ መቆየት አለበት የለበትም የሚል ክርክር በማድረጋቸው መሆኑን የጣቢያው የዜና ክፍል ሀላፊ የሆነው ጋዜጠኛ አብዱላዚዝ ኢብራሂም ሙሀመድ ተናግሯል። በርካታ የሶማሊያ ዜጎች የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ መቆየቱን መቃወም ጀምረዋል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርኒስትር መለስ ዜናዊ አልሸባብን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ደምስሰን እንወጣለን ቢሉም ፣ ጦሩ ግን ያለፉትን አስር አመታት በሶማሊያ ለማሳለፍ ተገዷል። ጦሩ አገሪቱን ለቆ የሚወጣበት ቀን በውል አይታወቅም። አልሸባብ ተዳክሞ ቢገኝም፣ ሙሉ በሙሉ ባለመጥፋቱ አሁንም ለሶማሊያ መንግስት ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።
የኢትዮጵያን ጦር በሶማሊያ መቆየትን ለውይይት ያቀረቡ ጋዜጠኞች ታሰሩ
መጋቢት አስራ ዘጠኝ ቀን አመተ ምህረትኢሳት ዜናበብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ የመንገደኞች የይለፍ ማረጋገጫአሰጣጥ እና የአገልግሎት ክፍያ ገንዘብ ገቢ አሰባሰብ የአሰራር ስርአት በሙስናና ብልሹ አሰራር የተጨማለቀመሆኑን ከፌዴራል የስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮምሽን የተገኘ አንድ ጥናት አመለከተ።በመምሪያው በይለፍ ማረጋገጫ አሰራር ስርአት ላይ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ ተብለው በጥናቱ ከቀረቡትሁኔታዎች ውስጥ የመረጃ አያያዝና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደካማ መሆንየሙስናና ብልሹ አሰራርመንሰራፋትየሰለጠነ የሰው ሀይል አለመመደብግልፅ የስራ መመሪያና ማኗል ያለመኖር የሚሉት ተጠቅሰዋል።ለሰራተኞች የሚያገለግል የስነምግባር መመሪያ ባለመኖሩ ጠንካራና አስተማሪ የሆነ አስተዳደራዊና የዲሲፕሊን እርምጃ ለመውሰድ ባለመቻሉ ደላሎች የካውንተር ሰራተኞችና ሀላፊዎች ተባባሪና የጥቅም ተጋሪ በመሆን መንገደኞች በፎርጅድ ፓስፖርትና ቪዛ ከአገር እንዲወጡ ያደርጋሉ። ቪዛ በህገወጥ መንገድ ከተለያዩ ኤምባሲዎች እንዲወጡና ቪዛ ከሌሎች አገሮች እንዲመጣ በማድረግ መሸጥ ቪዛ የሚሰጡ አገሮች ለተጓዦች የሰጡትን የቪዛ ሊስትና ቁጥር ለኢሚግሬሽን በሚልኩበት ጊዜ ቦሌ አንዳንድ የመቤቱ ሰራተኞች ዝርዝሩን የመሰረዝና የመፋቅ ከዚያም በማመሳሰል ቪዛውን ፓስፖርት ላይ በመምታት ገንዘብ እንደሚያጋብሱ ተመልክቷል።እንዲሁም ደላሎችና የካውንተር ሰራተኞች በምን ሰአት ማን እንዳለ በተለምዶ በመለየት መንገደኛውን በመላክና በህገወጥ መንገድ እንዲያልፍ በማድረግ ቪዛ በማያስፈልገው የኬንያን በመሳሰሉ ፓስፖርቶች በመጠቀም መንገደኛው በቦሌ በኩል ካለፈ በኋላ ኬንያ ሲደርስ የሌሎችን አገሮች ቪዛ በመለጠፍ ትራንዚት ነን እንዲሉ በማድረግ ከተለያዩ አገሮች የተባረሩ ተጓዦችን ኤርፖርት ከያዙና አስፈላጊውን መረጃ ከሰነዳቸው ላይ ከወሰዱ በኋላ ምርመራ መከናወን ሲገባው በጥቅማጥቅምና በቸልተኝነት እንዲበተኑ በማድረግ ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑ ተመልክቷል።መቤቱ ለመንግስት ከፍተኛ ገቢ ከሚሰበስቡት ተቋማት መካከል አንዱ ቢሆንም የፋይናንስ አስተዳደርናሌሎች ጉዳዮች ላይ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ለማከናወን የሚችል የውስጥ ኦዲት የስራ ክፍል የለውም። በዚህም የተነሳ ይላል ጥናቱ ወቅታዊና ድንገተኛ ኦዲት በአግባቡ ለማድረግ ባለመቻሉ የሚሰበሰበው ገቢ በትክክል ለመንግስት ገቢ መደረጉን ለማረጋገጥ አልተቻለም። በሚፈጠሩ ችግሮች ላይ ወቅታዊ የማስተካከያ እርምጃ አለመውሰድበፌዴራል ዋናው ኦዲተር መቤት አመታዊ ኦዲት ሪፖርት መሰረት የማሻሻያ ስራ አለማከናወን የአሰራር ስርአቱ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ እንዲሆን አድርጎታል።በመቤቱ በሁለቱም የስራ ክፍሎች ተመድበው የሚሰሩ አብዛኛዎቹ ሰራተኞች ብቃታቸውና ክህሎታቸው አነስተኛመሆኑም ተመልክቷል።ለሰራተኞች የስራ ላይ ስልጠና የሚሰጥ ቢሆንም እንኳን የፎርጀሪና ማጭበርበር መንገዶች እንደ ወቅታዊ ቴክኖሎጂ ደረጃ የሚሻሻሉና የሚለወጡ በመሆኑ በብቃት ለመከላከል የሚያስችል የአሰራር ስርአት አለመዘርጋቱን በጥናቱ ተጠቅሷል።የአሰራር ስርአት ችግሩን ለመፍታት በስራ ክፍሎች አሰራር ስርአት ላይ በባለሙያ እጥረት ምክንያት እያጋጠመያለውን ችግር ለመቅረፍ ብቃትና ክህሎት ያለውን ባለሙያ ለማስመደብ ወይም ለመቅጠር በቅድሚያ ለስራ መደቦችየሚያስፈልገውን የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ እንዲወጣለት በማድረግ ማሟላት ከዚህም በተጨማሪ አዲስሰራተኞች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ስለአሰራሩ በቂ ስልጠና የሚያገኙበት ሁኔታ ማመቻቸትና በስራ ላይ እያሉየማጠናከሪያ ስልጠና እንዲሰጥ ማድረግ በጥናቱ የተጠቆመ የመፍትሄ ሀሳቦች ናቸው።የ ተለያዩ የስራ ክፍሎችን የሚመሩ የስራ ሀላፊዎች ስራውን የሚመሩት በግልፅ መመሪያ ሳይሆን በልምድ በቃል ትእዛዝ እና በማስታወሻ መሆኑ ይህ አይነቱ አሰራር ደግሞ ግለሰቦች እንደፈለጉት ስራውን የሚመሩበት በመሆኑ በተፈለገው ጊዜ የሚሰራበት በማይመች ጊዜ እንዲቆም የሚታዘዝበት አሰራር ዘይቤ እንዲከተልና ለግለሰብ አመለካከት የተጋለጠ መሆኑም በጥናቱ ተጠቅሷል።የይለፍ ማረጋገጫ አሰጣጥ አሰራር ሂደት በባህሪው በየቀኑ በርካታ ተገልጋዮችና መንገደኞች የሚስተናገዱበት የስራ ክፍል ቢሆንም በአሰራር ስርአቱ ላይ የመንገደኛው የሀሳብ መስጫ አስተያየት ማቅረቢያ ቅፅም ሆነ ሳጥን አለመኖር የቅሬታ ማስተናገጃ ክፍልም ሆነ ኦፊሰር አለመደራጀት ተገልጋዩ በአቅራቢው ችግሩን የሚፈታበት ስርአት ያልተዘረጋ ስለሆነ ችግር ሲያጋጥመው ከቦሌ ወደ ዋናው መቤት እንዲመጣ ማድረግና ማጉላላት ስላለ ለሙስናና ብልሹ አሰራር በቀላሉ የተጋለጠ ሆኗልከአሰራር ጋር በተያያዙ የተጠቀሱት ሌሎች ችግሮች ከአገልግሎት የሚሰበሰብ ገንዘብ በየእለቱ ወደ ባንክ ገቢአለማድረግ ከመጠን በላይ በካዝና ገንዘብ ማሳደር የእለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች በየእለቱ የሚሰበስቡትን ገንዘብአግባብ ያለው ወቅታዊ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገበት ለባንክ ገቢ አለመሆን የሂሳብ ምዝገባ በየቀኑስለማይመዘገብ አግባብ ያለውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ አለመቻልና የገቢ ሂሳብ ምዝገባ ሳይከናወን ለረጅም ወራትማከማቸት የገቢ ሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ በኮምፒውተር በየጊዜው ስለማይመዘገብ ሂሳቡን በወቅቱ አለመዝጋትየገንዘብ መቀበያ ደረሰኞች አያያዝና አጠቃቀም ብክነት ያለበት መሆን እንዲሁም የሚሰበሰበውገንዘብና ወደ ባንክ ገቢ የሚሆነው ገንዘብ ከደረሰኞች ጋር በወቅቱና በእለቱ ማመዛዘኛ አለመሰራት የሚሉት ይገኙበታል።ከመረጃ አያያዝ ጋር በተገናኘ ከተጠቀሱት ችግሮች መካከል ደግሞ ውዝፍ ስራዎች በመብዛታቸው ምክንያትስራዎችን በዘመቻ በመስራት የስራ ጫና መኖር ፋይሎች በአመታትና በየወሩ ተለይተው በቀላሉ የሚገኙና የተደራጁ አለመሆኑ ምክንያት ለክትትልና ለቁጥጥር አለመመቸት ከክልል ኬላዎች ቅርንጫፍ ፅቤቶች ጋር የተቀናጀ ግንኙነት ባለመኖሩ የሰበሰቡትን ገንዘብ በወቅቱ በባንክ በኩል ፈሰስ አድርገው ማስረጃውን እንዲልኩ አለማድረግና የገቢ ደረሰኝ በወቅቱ አለመስራት ፋይሊንግ ሲስተሙ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ አለመሆን ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ማእከላዊ ሂሳብ መምሪያ ጋር ተናቦ ሪፖርቶችን በወቅቱ አለማዘጋጀት ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ብሄራዊ ባንክና በመስሪያ ቤቱ መካከል ልዩነት መኖር የሚሉት ተካተዋል።ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ፓስፖርት ለማውጣትም ሆነለማሳደስ ዜጎች እስከ አራት ወራት የሚደርስ ቀጠሮና መጉላላት የሚደርስባቸው ሲሆን ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘትበነፍስወከፍ እስከ አምስት ሺ ብር ጉቦ በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን በቅርቡ መዘገባችን ይታወሳል።መቤቱ በቂ የትምህርት ዝግጅት በሌላቸው በቀድሞ የህወሀት ኢህአዴግ ታጋዮች ከላይ እስከታች የተሞላ መሆኑም ይታወቃል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ በሙስና መጨማለቁን አንድ ጥናት አመለከተ
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ስድስትኛ ሳምንት መርሀ ግብር ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ወልዲያን አስተናግዶ አንድ አንድ በሆነ አቻ ውጤት በመለያየት ድል አልባ የውድድር ዘመኑን ገፍቶበታል።እምብዛም ማራኪ እንቅስቃሴ እና ፉክክር ባልታየበት የመጀመሪያ አጋማሽ የተሻለ የእንቅስቃሴ የበላይነት የነበራቸው ወልድያዎች በጎል ሙከራ ረገድም የተሻሉ ነበሩ። አስርኛው ደቂቃ ላይ ሰለሞን ገብረመድህን የሰጠውና ፍፁም ገብረ ማርያም ሳይጠቀምበት የቀረበት ፣ ሀያ ስድስትኛው ደቂቃ ላይ ኤደም ኮድዞ ከፍፁም የተሻገረለትን ኳስ በቀጥታ መትቶ ፍቅሩ ወዴሳ እንደምንም ተወርውሮ ያወጣበት እንዲሁም ሰለሞን ገብረ መድህን ተጫዋቾችን አታሎ ወደ ግብ የሞከራትና የግቡን ቋሚ ታካ የወጣችበት ሙከራዎች ወልዲያን ቀዳሚ ሊያደርጉ የሚችሉ አጋጣሚዎች ነበሩ።በሲዳማ በኩል ሀያኛው ደቂቃ ላይ ወንድሜነህ አይናለም በረጅም ያሻገረውን ኳስ ባዬ ገዛኸኝ በግል ጥረቱ አልፎ ወደ ሳጥን በመግባት የመታት ኳስ ኢላማውን ሳጠብቅ ወደ ውጭ የወጣችበት እና አርባ ሶስትኛው ደቂቃ ላይ አብዱለጢፍ መሀመድ በረጅሙ ከግራ መስመር ያሻገራትን ኳስ ባዬ ገዛኸኝ ሞክሮ ቢሌንጌ ሲመልስበት ሀብታሙ ገዛኸኝ አግኝቷት ወደ ላይ የሰደዳት ሙከራ የሚጠቀሱ ነበሩ።የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ የዳኛ ፊሽካ በሚጠበቅበት ወቅት አብዱለጢፍ መሀመድ በረጅሙ ያሻማትን ኳስ ጋናዊው የመሀል ተከላካይ ሚካኤል አናን በግንባሩ ገጭቶ ሲዳማ ቡናን መሪ በማድረግ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ሲዳማ ቡናዎች ተሽለው ቢቀርቡም በቀጣዩቹ ሀያ ደቂቃዎች አድራሻ ከሌላቸው ተሻጋሪ ኳሶች ውጪ የጠራ የግብ እድል መፍጠር አልቻሉም። ይልቁንም በስልሳ ሶስትኛው ደቂቃ ላይ ፍፀም ገብረ ማርያም ወደ ግብ ሲመታት ዮናታን ፍሰሀ በእጅ በመንካቱ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ኤደም ኮድዞ በአግባቡ በመጠቀም ወልዲያን አቻ ማድረግ ችሏል።ከአቻነት ጎሉ በኋላ ሲዳማዎች በርካታ የግብ እድሎችን መፍጠር ቢችሉም በድጋሚ መሪ የሚያደርጋቸውን ጎል ማግኘት አልቻሉም። ሰማኒያኛው ደቂቃ ላይ ሲዳማዎች ባዬ ገዛኸኝ የእለቱ ዳኛ ዳዊት አሳምነው የሰጡትን ውሳኔ በመቃወም ባሳየው ያልተገባ ባህሪ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ በመውጣቱ ቀሪዎቹን ደቂቃዎች በጎዶሎ ተጫዋቾች ለመጫወት ቢገደዱም አሸንፈው ለመውጣት ጫና መፍጠር ችለዋል። በተለይ በሰማኒያ አምስትኛ ደቂቃ አምሀ በለጠ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ወንድሜነህ አይናለም ሞክሮ ኤሚክሪል ቢሌንጌ በአስደናቂ ሁኔታ ያወጣበት ኳስ ባለሜዳዎቹን የማታ ማታ ሶስት ነጥቦች ልታስገኝ የተቃረበች ሙከራ ነበረች።ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ በውድድር አመቱ እስካሁን ሙሉ ሶስት ነጥብ ማሳካት ያልቻለው ሲዳማ ቡና በአምስት ነጥብ ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልዲያ በአንድ ነጥብ ከፍ ብሎ ዘጠኝኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።የአሰልጣኞች አስተያየትአለማየሁ አባይነህ ሲዳማ ቡና በዛሬው ጨዋታ ጥሩ አልነበርንም። በቅጣት እና በጉዳት። እንዲሁም በብሄራዊ ቡድን ጥሪ ወሳኝ ተጫዋቾቻችንን አጥተናል። በመጀመሪያ አጋማሽ በተጫዋቾቼ ድክመት ተበልጠናል። ይህም የሆነበት ተጫዋቾች በቦታቸው አልነበረም አብዛኛዎቹ የተጫወቱት። በመጨረሻዎቹ ደቂቃ ላይ ግን የታክቲክ ለውጥ አድርገን ተጭነን ተጫውተናል። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻልን ነበርን የባዬ መውጣት ግን የነበረንን ነገር አሳጥቶናል። ያገቡብንም በራሳችን ስህተት እንጂ እነሱ በፈጠሩት አልነበረም። እስከ አሁን አለማሸነፋችን ግን ተፅኖ አይፈጥርብንም። ቡድኔ ሲሟላ ወደ አሸናፊነት እንመለሳለን ዘማርያም ወልደ ጊዮርጊስ ወልዲያ በቅድሚያ ሜዳ ላይ ውጤት ያማረ ባይሆንም ደጋፊዎች የሚያደርጉትን ድጋፍ ማድነቅ እፈልጋለሁ። ለኔ ከጨዋታው ይልቅ ከፍ ብሎ የታየኝ የደጋፊዎች ድጋፍ ነበር። ጨዋታውን ግን በመጀመሪያው አጋማሽ ጨርሰን መውጣት ነበረብን። ወደዚህ ስንመጣ ባለፉት ሲዳማ በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ተጋጣሚያዎቹን ባለማሸነፉ ጫና ውስጥ እንዳለ ስለምናቅ በጥንቃቄ መጫወትን መርጠናል። ብዙ እድህ ፈጥረናል ፤ አሸንፈን መውጣትም እንችል ነበር። ያን ባለማድረጋችን ከእረፍት በፊት ግብ አስተናገድን ሌላ ስራ ፈጥሮብን ለማስገባት ጥረት አድርገን አስቆጥረናል። ቢሆንም ለኔ ጨዋታው አስከፊ አልነበረም። ብዙ ወሳኝ ተጫዋቾቻችንንን እኛም እነሱም አተናል። በቀጣይ ጨዋታወች ግን ትክክለኛውን ወልዲያን ጠብቁ። በተለያዩ ጊዜያት ችግሮች ነበሩ። እነሱ በቅርቡ ስለተፈቱ በቀጣይ በሙሉ ጥንካሬ እንቀርባለን።
ሪፖርት ሲዳማ ቡና በድል አልባ የውድድር ዘመን አጀማመሩ ዘልቋል
በትግራይና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ።ኢሳት ዜና ሚያዝያ ቀን አመተ ምህረት በአፋር ክልል ኩናባ ወረዳ ዋህደስ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሱዳ በተባለ ተራራ ትናንት ማክሰኞ በትግራይ ታጣቂ ሚሊሻዎችና በአፋር አርብቶ አደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከትግራይ ሚሊሻዎች በኩል ሁለት መሞታቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልፀዋል።እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ በዚህ አካባቢ በሚሊሻዎቹና በአርብቶ አደሮቹ መካከል ተደጋጋሚ ግጭቶች ሲቀሰቀሱ ቆይተዋል።እንደ አውሮፓውያኑ አቆእጣጠር በ በአካባቢው በተፈጠረ ተውመሳሳይ ግጭት አብደላ ኢድሪስ የተባለ የአፋር ተወላጅ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በትግራይ ሚሊሻዎች መገደሉን ያወሱት የአካባቢው ነዋሪዎችገዳዮቹ እስካሁን ለፍርድ አለመቅረባቸው በተደጋጋሚ ለሚያገረሹት ግጭቶች አንድኛው ምክንያት መሆኑንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።የአፋር ህዝብ የነፃነት ታጋይና አክቲቪስት አባድር ጉዳዩን አስመልክቶ ለኢሳት በሰጠው ማብራሪ ግጭቶች የሚነሱት የአፋርን ለም መሬትና ደን ለመውሰድ በተደረገ ሙከራ ነው ብሏል።
በትግራይና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ።
አዲስ አበባ፣ ሰኔ ሀያ ሶስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በደሴ ከተማ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተሰሩ ስላሳ ሶስት የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና ጉብኝት እየተካሄደ ይገኛል። በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል። የህዝብን የልማት ጥያቄ መሰረት ያደረጉ የመንገድ፣ የመናኸሪያ፣ የቢሮ፣ የውሀ፣ የጤና፣ የትምህርት ቤት እና ሌሎች በርካታ ተቋማት ፕሮጀክቶች ናቸው እየተመረቁ የሚገኙት። አብዛኞቹም ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እንደሆኑም ነው የተገለፀው። ከፕሮጀክቶቹ ውስጥ ሰማኒያ ሰባት ሚሊየን ብር የሚያወጡ ልማቶቾ በማህበረሰቡ የተሸፈኑ ናቸው ተብሏል። የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን ምርቃ መርሀ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት ፥ በከተማው የታየው የልማት እንቅስቃሴ መንግስትና ማህበረሰቡ ሲደመር ያመጣው ውጤት ነው። የአከባቢው ማህበረሰብ አሁንም ያለውን ሰላም በማስቀጠል ልማቱን ማፍጠን ይገባዋል ሲሉም ገልፀዋል። በከተማዋ ከአንድነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር በላይ የወጣባቸው የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ናቸው ያሉት የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትልከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው ፥ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በማከናወን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግና ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በግንባታ ላይ ያሉና የተጠናቀቁ የአስፋልት መንገድ፣ መናኸሪያ፣ ጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት፣ መድሀኒት ቤት፣ የዳቦና የዱቄት ፋብሪካ፣ የወጣት ማእከል እና ሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም ነው ያብራሩት። ዛሬ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የወጣባቸው የልማት ስራዎች መመረቃቸውን ያነሱት ከንቲባው ፥ ከሰማኒያ ሰባት ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው የማህበረሰብ ተሳትፎ መሆኑን ገልፀዋል። ማህበረሰቡ ለልማቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል። በከድር መሀመድ
በደሴ ከተማ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ምርቃትና ጉብኝት እየተካሄደ ነው
ህገ መንግስቱ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ሏላዊነታቸው የሚገለፀው በዚህ ህገመንግስት መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸው እና በቀጥታ በሚያደርጉት ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ ይሆናል እንደሚል የጠቆመው መድረክ በአዲሱ የሊዝ አዋጅ ግን ይሄ ተግባራዊ አልሆነም ሲል ይተቻል። መሬትን በመሰለ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ የሏላዊ ስልጣን ባለቤት የሆነውና በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከተው ህዝብ ጉዳዩ ቀርቦለት በነፃነት እና በግልፅነት እንዲወያይበት አልተደረገም ብሏል ፓርቲው።በፓርላማው የወጣው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስነ ምግባር ደምብና አሰራር የአንድ አዋጅ ረቂቅ ለምክር ቤቱ አባል ከስብሰባው ሰአት በፊት መድረስ እንዳለበት ይደነግጋል ያለው መግለጫው የሊዝ አዋጁ ሲፀድቅ ግን የስነምግባር ደምብና አሰራርን የተከተለ አልነበረም ብሏል ረቂቅ አዋጁ ለፓርላማ አባላት ማምሻውን ሰአት ላይ ታድሎ ጧት ሰአት አዋጅ ሆኖ እንዲፀድቅ መድረጉን በመጥቀስ።የሊዝ አዋጁ የዜጐችን ንብረት የማፍራት ህገ መንግስታዊ መብት ይጥሳል የሚለው የፓርቲው መግለጫ በኢህአዴግ መንግስት የሚኮነነው ደርግ እንኳን የከተማ ቦታና ትርፍ ቤትን የመንግስት ንብረት ለማድረግ ባወጣው አዋጅ ዜጐች እስከ ካሬ ሜትር የሚደርስ ቦታ ለቤት መስሪያነት ሊሰጣቸው እንደሚችል እንዲሁም ባለይዞታ የሟች ሚስት ወይም ባል ወይም ልጆች በቦታው ተተክተው የመጠቀም መብት ይኖራቸዋል እንደሚል አስታውሷል። ከዚህም በተጨማሪ የከተማ ቤት ማስተላለፍን በተመለከተ በደርግ ዘመን የወጣው አዋጅ አንድ ቤተሰብ ግለሰብ ወይም ድርጅት በከተማ ቤቱ የመጠቀም ወይም ይህንኑ ቤት የማውረስ የመሸጥ ወይም የመለወጥ መብት አለው እንደሚል የመድረክ መግለጫ ያወሳል።ከዚህ አንፃር ሲታይ ደርግ ያወጣው አዋጅ የአገሪቱን የከተማ ነዋሪዎች ከግለሰብ ጭሰኝነት ነፃ ያወጣ የከተማ ቦታን የመሸጥ የመለወጥ እና የባለቤትነት ክብር እንዲጐናፀፉ ያስቻለ ነው ሲልም ያወድሳል መድረክ። በሌላ በኩል ኢህአዴግ በየጊዜው የሚያወጣቸው አዋጆች ገዢዎችን የሚጠቅም ህዝብና ሀገርን የሚጐዳ የዜጐችን መብትና ጥቅም የሚጋፋ ነው ሲል ኮንኗል።የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በቅርቡ የወጣው አዋጅ ክፍል ሁለት አንቀፅ ስድስት ነባር ይዞታዎች ወደ ሊዝ ስሪት ስለሚቀየሩበት ሁኔታ በዝርዝር መቀመጡን የጠቆመው ፓርቲው የኢህአዴግ ሹመኞች ግን አዋጁ የነባር ይዞታዎችን አይመለከትም ዝርዝር መመሪያ አልወጣም ተረጋጉ እያሉ በህዝብ ላይ ውዥንብር ይፈጥራሉ ሲል ነቅፏል። የኢህአዴግ ሹመኞች አዋጁ ነባር ይዞታዎችን አይመለከትም ይበሉ እንጂ ሲሸጥ ሲለወጥ ሊዝ ውስጥ እንደሚገባ በግልፅ ደንግጓል ይላል መግለጫው።አንድ ነባር ይዞታን ሲገዛ ለባለንብረቱ ከሚከፍለው ክፍያ በተጨማሪ ለመንግስት ያንኑ ቦታ የሊዝ ዋጋ ይከፍልበታል። ይህ አሰራር ብዙ ምርምር ሳይጠይቅ ንብረት በማስተላለፍ ላይ ተፅእኖ እንደሚያሳድር ለማንም ግልፅ ነው። የነባር ይዞታው ባለቤት ቦታውን ሸጦ ሌላ አነስተኛ ቦታ ገዝቼ በተረፈችኝ ገንዘብ ህይወቴን ልምራ ቢል የሚገዛው በሊዝ ነው። ነባር ይዞታዎች ከሊዝ የሚያመልጡት እንዴት ነው በማለት የሚጠይቀው መድረክ ይዞታው ሳይሸጥ ሳይለወጥ የንብረት ዋጋ ሳይኖረው እንደ ጉልቻ በመቀመጡ ብቻ ከሊዝ አመለጠ ማለት ነውን ሲል ተሳልቋል በመግለጫው።የሊዝ አዋጁ የሀገሪቱን ህዝብ ከይዞታ ባለቤትነት አሽቀንጥሮ በመጣል መንግስትን የመሬት ባለቤት የሚያደርግ ነው ያለው ፓርቲው ህገ መንግስቱ መሬት የህዝብና የመንግስት ነው ቢልም ኢህአዴግ ግን ራሱ ጠቅልሎ ህዝብን ጭሰኛ እያደረገ ነው ሲል ተችቷል።ኢህአዴግ አዋጁ ከወጣ በኋላ ከህዝቡ ጋር ያደረገውን ውይይት አስመልክቶም መድረክ ለይስሙላ የተደረጉ ስብሰባዎች ሲል አጣጥሎታል።በዚህም ውይይት ቢሆን በመንግስት መገናኛ ብዙሀን ከሚተላለፈው በተለየ ህዝቡ በአዋጁ ላይ ተቃውሞውን በመግለፅ ትክክለኛ አቋም ወስዷል ሲል ድጋፉን ጠቁሟልበአዋጁ ዙሪያ በመንግስት ባለስልጣናትና ካድሬዎች የሚሰጠው መግለጫና ከህዝብ ለሚቀርበው ጥያቄ የሚሰጡ መልሶች የፌዝ መሆናቸው እንዳስገረመውም መድረክ በመግለጫው ጠቁሟል።ነባር ይዞታ እስኪሰጥ እና እስኪለወጥ ድረስ ሊዝ ውስጥ አይገባም ማለት ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት አይነት ነው ሲል የተረተው መድረክ ነባር ይዞታዎች ወደ ሊዝ ስርአት የሚቀየሩበት ሁኔታ ዝርዝር ጥናት ተደርጐ በአራት አመት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንደሚሆን መገለፁም አዋጁ ከመውጣቱ በፊት ተገቢው ጥናት አለመካሄዱን ያሳያል ብሏል።በመድረክ እምነት አዋጁ ከመውጣቱ በፊት ተገቢው ጥናት መካሄድ ነበረበት ይላል የፓርቲው መግለጫ። ህዝብ የመደመጥ መብት አለው መንግስት በተቆጣጠራቸው የሚዲያ ተቋማት በህዝብ ስም የሚያስተላልፍው ፕሮፓጋንዳ ለራሱም ለህዝቡም ለሀገርም እንደማይጠቅም አውቆ ሊያስብበት ይገባል ሲልም አሳስቧል።አርሶ አደሩ የይዞታው ባለቤት መሆን እንዳለበትና የከተማ ነዋሪውም መኖርያ ቤት የሰራበት መሬት ባለቤትነቱን እንዲያረጋግጥ መድረክ በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ ማስፈሩን ያወሳው መግለጫው ይሀንን እውን ለማደረግ በጀመረው የተቃውሞ ትግል እንደሚቀጥል አስታውቋል።የመሬት ሊዝ አዋጁን እንደሚቃወም የገለፀው ሌላው ፓርቲ የኢትዮጵያ ራእይ ፓርቲ ኢራፓ ነው። ፓርቲው በላከው መግለጫ ላይ እንደገለፀው መንግስት እንደ መንግስት ህዝብን ወይም ዜጐችን በአገልጋይነቱ እና አስተዳዳሪነቱ ከመታወቅ በስተቀር የአንድ ሀገር ዜጐችን መሰረታዊ ንብረት በሆነው የገጠር የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት የባለቤትነት መብት ላይ የይገባኛል ክርክር ሊያነሳ እንደማይገባ ያትታል።አዋጁ የዜጐችን ህገመንግስታዊ ነፃነት የማፈታተን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የሚጎዳ እና የዲሞክራሲ ግንባታን ጥያቄ ላይ የሚጥል በጥቂት ሀብታሞችና ብዙሀኑ ድሀ ዜጐች መካከል ከፍተኛ የኑሮ እና የኢኮኖሚ ክፍተት የሚፈጥር ማህበራዊ ችግሮችን የሚያባብስ ቤተሰባዊነትን የሚሸረሽር ዛሬም ሆነ ነገ ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ አዋጁና አፈፃፀሙ እንዲፈተሽ የጠየቀው ፓርቲው የከተማ መሬት ባለቤትነትን የመንግስትና የህዝብ ተደርጐ ከመውሰድ ይልቅ የህዝብና የመንግስት ተብሎ እንዲጠራ እና ህዝብ ባለቤትነቱ ያለአንዳች ችግር እንዲረጋገጥ በመግለጫው ጠይቋል። በሌላ በኩል አንድነት ፓርቲ በነገው እለት በእየሩሳሌም ሆቴል ከምሁራኖች ጋር በሊዝ አዋጁ ላይ እንደሚወያይ ታውቋል።
መድረክና ኢራፓ የሊዝ አዋጁን ተቃወሙት
አዲስ አበባ ፣ ጥር ስምንት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የደቡብ ክልል ተወላጆች ምሁራን መድረክ ተጠናቀቀ። በምሁራን መድረኩ ላይ የክልል አደረጃጀት ጥያቄን በተመለከተ በቀረበ ፅሁፍ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። ምሁራኑ በክልሉ ህዝቦች የሚነሱ ጥያቄዎች ህገ መንግስቱን በተከተለ እና ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሊፈታ ይገባል ብለዋል። በጥናቱ ባቀረቡት አማራጮችም ከህዝቡ ጋር ውይይት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች የክልሉን ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ በሚሰጥ አግባብ ሊታዩ ይገባልም ነው ያሉት። ሀገራዊ ለውጡ እንዳይደናቀፍ ምሁራን ሚና እንዲወጡ፣ የክልል ጥያቄ ትኩረት ቢሰጣቸው እና ህገ መንግስቱ የወቅቱን የሀገሪቱን ተግዳሮቶች መፍታት እንዲችል ዳግም ቢታይ የሚሉ ምክረ ሀሳቦችንም ምሁራኑ አቅርበዋል ። መድረኩ የክልሉ የምሁራን ፎረምን ለሟቋቋም ኮሚቴ በማቋቋም ተጠናቋል። በትናንትናው እለት በነበረው ውሎ ምሁራን ከዚህ ቀደም ልዩነትን በሚያሰፉ ስራዎች ላይ ልሂቃኑም ሆነ አመራሩ ማተኮራቸው አሁን ለሚታየው ችግር ምክንያት በመሆኑ በጋራ ለመቆም አንድነቱ ላይ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል። በሀይለየሱስ መኮንን
የደቡብ ክልል ተወላጆች ምሁራን መድረክ ተጠናቀቀ
በተከታታይ ሶስት ሳምንታት ስለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና ክለቦች እውነታዎችን ስናነሳ ቆይተናል። ዛሬም ሊጉ እና ክለቦችን የተመለከተውን ክፍል አራት ጥንቅር ይዘንላችሁ ቀርበናል። ማስታወሻ እውነታዎቹ በኮቪድ ምክንያት የተሰረዘው የሁለት ሺህ ውድድርን አያካትቱም።አንድ በሊጉ የሀያ ሁለት አመት ጉዞ በርካታ ጨዋታዎችን ያሸነፈው ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። ቡድኑ በሊጉ በተካፈለባቸው ሀያ አንድ አመታት ባከናወናቸው አምስት መቶ ስልሳ አምስት ጨዋታዎች በድምሩ ሶስት መቶ ሀምሳ ድሎችን አግኝቷል።ሁለት በሊጉ ታሪክ ባደጉበት አመት ዋንጫ የወሰዱ ክለቦች ሁለት ብቻ ናቸው። እነርሱም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ጅማ አባጅፋር ናቸው። ሊጉ በአዲስ መልክ እና መዋቅር በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሲጀመር ተሳትፎ ያላደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይ አመት አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አንድ ከሁለተኛው የሀገሪቱ የሊግ እርከን በማደግ ዋንጫውን የግሉ ማድረግ ችሏል። በተመሳሳይ ጅማ አባጅፋር ከ አመታት ሁለት ሺህ አስር በኋላ ይህንን ታሪክ በመስራት ስሙን የታሪክ መዝገብ ላይ አፅፏል።ሶስት በአሁኑ ሰአት በሊጉ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ ክለቦች መካከል በእድሜ ትንሹ ስሁል ሽረ ነው። ቡድኑ በሁለት ሺህ አምስት አመተ ምህረት ነበር የተመሰረተው። ቡድኑ ምስረታውን ካደረገ ከስድስት አመታት ሁለት ሺህ በኋላ ደግሞ ወደ ዋናው የሀገሪቱ የሊግ እርከን አድጓል።አራት ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አመተ ምህረት ጀምሮ በሊጉ ከተሳተፉት ሀምሳ አንድ ክለቦች መካከል አምስትቱ መጠሪያ ስያሜያቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች ቀይረዋል። በዚህም መብራት ሀይል ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሶስት ፣ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ሺህ ሶስት ፣ ሀረር ቢራ ወደ ሀረር ሲቲ ሁለት ሺህ ስድስት ፣ ወልዲያ ከነማ ወደ ወልዲያ ሁለት ሺህ ዘጠኝ እንዲሁም ኒያላ ወደ ልደታ ኒያላ ሁለት ሺህ ሶስት ስያሜያቸውን ለውጠዋል። መቐለ ሰባ እንድርታ፣ ሀዲያ ሆሳእና እና ጅማ አባጅፋር ደግሞ ወደ ሊጉ ባደጉበት ክረምት ነበር ስያሜያቸውን የቀየሩት።አምስት እስካሁን በሊጉ በትንሽ የውድድር አመታት የተሳተፉ ክለቦች ናቸው። እነሱም ፐልፕ እና ወረቀት፣ ብርሀንና ሰላም፣ ኦሜድላ፣ እህል ንግድ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ፣ ሜታ አቦ ቢራ፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና፣ ሀዲያ ሆሳእና፣ ባህር ዳር ከተማ፣ ስሁል ሽረ እና አዲስ አበባ ፖሊስ ናቸው። እነዚህ ክለቦች በሊጉ ላይ በአንድ የውድድር አመት ብቻ ነው ተሳትፎ ያደረጉት። የዘንድሮ የውድድር ዘመን መሰረዙ ልብ ይሏል። ስድስት ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ጀምሮ በሊጉ እየተሳተፉ ካሉት ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ ውጪ በሊጉ ለረጅም አመታት ያልወረደው ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። ቡድኑ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አንድ አመተ ምህረት ጀምሮ በሊጉ መሳተፍ ከጀመረ በኋላ ለሀያ አንድ የውድድር አመታት ወደ ታችኛው የሊግ እርከን አልወረደም። በዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ሊጉ አድጎ ለረጅም አመታት በሊጉ የዘለቀ ክለብ አስብሎታል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ የውድድር አመት ቀጣዩ ረጅም አመት የቆየ ክለብ ነው።ሰባት ከመውጣት መውረድ ጋር በተያያዘ በወረዱበት አመት ተመልሰው የመጡ ክለቦች ስድስት ናቸው። እነሱም ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሶስት ፣ ወንጂ ስኳር አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስድስት ፣ ጉና ንግድ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስድስት እና ሁለት ሺህ ፣ ኒያላ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት እና ሁለት ሺህ ሶስት ፣ ወልዲያ ሁለት ሺህ ዘጠኝ እና አዳማ ከተማ ሁለት ሺህ ሰባት ናቸው።ስምንት በሀገሪቱ ከሚገኙ ከተሞች ብዙ ክለቦችን በሊጉ ያሳተፈው ከተማ አዲስ አበባ ነው። መዲናዋ በድምሩ ክለቦችን እስካሁን አሳትፋለች። እሱም ኢትዮጵያ መድን፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ሙገር ሲሚንቶ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኒያላ፣ ብርሀንና ሰላም፣ መከላከያ፣ ውሀ ስፖርት፣ አዲስ አበባ ፖሊስ፣ እህል ንግድ፣ ኦሜድላ፣ ደደቢት እና አዲስ አበባ ከተማ ናቸው። ክለቦቹ የተካተቱት መጀመሪያ መቀመጫቸውን ካደረጉበት ከተማ አንፃር ነው ዘጠኝ ጅማሮውን ብሄራዊ ሊግ ብሎ የጀመረው ሊጉ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አመተ ምህረት በኋላ በተደረጉት ሀያ ሁለት የውድድር አመታት አራት የተለያዩ ስያሜዎችን ተጠቅሟል። በዚህም ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ፕሪምየር ሊግ፣ በሁለት ሺህ አመተ ምህረት ላይ ሚድሮክ ሚሌኒየም ፕሪምየር ሊግ፣ በሁለት ሺህ አንድ ሚድሮክ ፕሪምየር ሊግ ሲባል ሁለት ሺህ አምስት ላይ ደግሞ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ተብሏል። ከሁለት ሺህ ስድስት ጀምሮ እስካሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመባል እየተጠራ ይገኛል።አስር ሊጉ ላይ ከተሳተፉ ሀምሳ አንድ ክለቦች አንጋፋው እና እድሜ ጠገቡ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። ቡድኑ በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀያ ስምንት አመተ ምህረት በመመስረቱ እና ዘንድሮ ሰማኒያ አራትኛ የምስረታ በአሉን በማክበሩ የሊጉ አንጋፋው ክለብ አስብሎታል።
ይህንን ያውቁ ኖራል ፬ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና ክለቦች
ኢሳት ጥር ሶስት ፥ ሁለት ሺህ ስምንት የአክሰስ ሪል ስቴት እንዲሁም የዘመን ባንክ መስራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ መታሰራቸውን ከአዲስ አበባ የደረስን ዜና አመለከተ። በመንግስት ዋስትና ወደሀገር ቤት ከተመለሱ ወራት ብቻ ያስቆጠሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ ተመልሰው የታሰሩበት ዝርዝር ምክንያት ባይገለፅም፣ ከአክሰስ ሪል ስቴት ጋር የተያያዘ መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ሀይላንድ ውሀን በማምረት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ በመግባት በንግዱ አለም ታዋቂ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በየካቲት ወር ሁለት ሺህ አምስት አ ም ከመንግስት ጋር ባለመግባባት ከሀገር የወጡ ሲሆን፣ በመንግስት ተሰጣቸው በተባለ ዋስትና በየካቲት ወር ሁለት ሺህ ሰባት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል። ለሁለት አመታት ያክል በዱባይ ቆይተው ወደኢትዮጵያ የተመለሱት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በነሀሴ ወር ሁለት ሺህ ሰባት ከአክሰስ ቦርድ ሊቀመንበርነታቸው እንዲነሱ የተደረጉ ሲሆን፣ በርሳቸው ምትክ ወይዘሮ መብራት ወልደትንሳኤ የተባሉ ባለአክሲዮን መሾማቸው ታውቋል። በዋስትና ወደሀገር ቤት የተመለሱት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የተገባላቸውን በአደባባይ የተነገረው ቃል ታጥፎ ወደእስር ቤት የገቡበት ሁኔታ ግልፅ አልሆነም።
የአክሰስ ሪል ስቴትና የዘመን ባንክ መስራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ታሰሩ
በሰሜን እዝ ላይ የተደረገው አይነት ጥቃት በቀጣይ ለአገሪቱ ስጋት እንደማይሆን፣ የአገር መከላያ ሚኒስትሩ ቀነአ ያደታ ዶክተር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ታሀሳስ ስድስት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ገለፁ።ከሀያ ሰባት አመታት በላይ በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርአት የተጠመቀውን ሰራዊት፣ ሙሉ በሙሉ ለመለወጥና ለማስተካከል የተሰራው ስራ፣ ጠላት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ቢሞክር እንደማይሳካለት የታየበት ስራ መሆኑን ተናግረዋል።ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ከሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በመሆን፣ ከፓርላማው ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት በፓርላማ ተገኝተው ነው።ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል በመከላከያ ሀይል ሲከናወን የነበረውን የህግ ማስከበር ዘመቻ አስመልክተው ለፓርላማ አባላቱ ሲናገሩ፣ የህወሀት ሀይል የሰሜን እዝን የመጀመርያ አላማው ቢያደርግም፣ አነሳሱ በተለያዩ የክልል ከተሞች ኢመደበኛ መዋቅሮችን በመዘርጋት፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አገርን አበጣብጦ ወደ ስልጣን የመምጣት እሳቤ እንደነበረው ገልፀዋል።ነገር ግን መንግስት በወሰደው ፈጣን እርምጃና የነቃ አመራር፣ በአገር ላይ ተደቅኖ የነበረውን አደጋ በአስቸኳይ ማክሸፍ መቻሉን፣ የመከላከያ ሀይሉም ያከናወነው ጥበብ የተሞላበት ዘመቻ፣ ለቀጣዩ ትውልድ ትምህርት እንደሚሆን አስረድተዋል። የመከላከያ ሀይሉ ያደረገው ጥበብ የተሞላበት ተጋድሎ፣ ለቀጣይ ትውልድ በቪዲዮ ተቀርፆ ለማስተማሪያነት እንዲያገለግል እንደሚቀመጥ የገለፁት ሚኒስትሩ፣ ከዚህ በኋላ በሰሜን እዝ ላይ የተደረገው አይነት ጥቃት አገሪቱን ሊያሳስባት እንደማይገባ ተናግረዋል።ከፓርላማ አባላቱ በመንግስት የመያዣና የእስር ትእዛ ወጥቶባቸው እየተፈለጉ ስላሉ የህወሀት አመራሮች የተጠየቁት ሚኒስትሩ መልስ ሲሰጡ፣ ተፈላጊዎቹ ያሉበት ቦታ የታወቀ ቢሆንም፣ ቀድመው ካዘጋጁዋቸው ጉድጓዶችና መደበቂያዎች በየጊዜው ስለሚቀያይሩ ይዞ ለማቅረብ አዳጋች እንደሆነ ተናግረዋል። የህዝቡን ፍላጎት የምንረዳው ቢሆንም በእኔ ግምገማ ሰራዊቱ ቶሎ ይዞ አላቀረበም የሚለው ትችት የፈጠነ ነው፤ ሲሉ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። ዝም ብሎ እንደተቀመጠ እቃ ከሆነ ቦታ አንስቶ ማምጣት አይደለም። ወይም ደግሞ ከሆነ ጓሮ እንደ ጎመንና ካሮት ተቆርጦ የሚመጣ ነገር አይደለም፤ በማለት ለፓርላማ አባላቱ ሂደቱ አስቸጋሪና ጊዜ የሚፈልግ መሆኑን ገልፀዋል።ሚኒስትሩ አክለውም ስራው ሌት ተቀን እየተከናወነ እንደሆነና የሚፈለጉት ሰዎችም መያዛቸው እንደማይቀር አስታውቀዋል።
በሰሜን እዝ ላይ የተቃጣው አይነት ጥቃት በቀጣይ ስጋት አይሆንም ቀንአ ያደታ ዶክተር ፣ የአገር መከላከያ ሚኒስትር
ልኡል አለሜ ዜና ደቡብ አፍሪካበነፃነት ታጋዩ በገዛህኝ ነበሮ ህልፈተ ህይወት ምክንያት ከመላዉ አለም የተሰባሰብቡት የቀድሞ የመከላከያና የፖሊስ ባልደረባዎች በመስራች ጉባኤዉ ላይ ተገኝተዋል።ስብሰባዉን በመክፈቻ ንግግር የመሩት ሻለቃ ደምሴ ዮሀናስ በሀምሳ አለቃ ገዛኝ ነብሮ የክብር ሞት ምክንያት የተሰማቸውን ዉስጣዊ ስሜት ከገለፁ በኋላ ለዚህ ጀግና ወንድማችን የተደረገዉን ፕሬዘዳንታዊ የቀብር ስነ ስርአት ስመለከት የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባል በመሆኔ ኮርቻለዉ ብለዋል።በአለም አቀፍ ደረጃ የምንኖር የቀድሞ የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት አባላቶች ገዛህኝ ነብሮ የሞተለትን አላማ ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቹን ጭምር የመንከባከብና የመደገፍ ሀላፊነት አለብን በመሆኑም በአሜሪካ የቀድሞ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላቶች ማህበር ተወካይ እንደመሆኔ ይህ የደቡብ አፍሪካዉ መስራች ጉባኤ በማንኛዉም መልኩ እህትማማች ማህበር በመሆን እንደ አንድ አካል አብሮን እንዲጓዝ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የቀድሞ ጦር አባላቶች መሰባሰብና አለባቸዉ በሚል መሪ ሀሳብ ተሰብሳቢዉን አስደስተዋል።ከሻለቃ ደምሰ ዮሀንስ በመቀጠል አጠር ያለች መልእክት ያስተላለፉት ሻምበል አባተ ደረስ ሀገራችን ወደ ከፋ የደም መፋሰስ እንዳትገባ ብለን መሳሪያ አዝለን ዉሀ እየለመንን ወደ ህዝባችን የተቀልን የቀድሞ ጦር ሰራዊት አባላቶች ብዙና ከባድ መሰዋትነት እንደከፈልን ተረሰተን መቅረት የለብንም ሁላችንም መሰባሰብና መደራጀት ግዴታችን ነዉ ለወገኖቻችን መድረስ የምንችለዉ አንድ ሆነንን ስንሰባሰብ ነዉ በማለት መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል።ሌላው በጀግናዉ የሀምሳ አለቃ ገዛህኝ ነብሮ የቀብር ስነ ስረአት ላይ ለመገኘት በጆሀንስበርግ የተገኘዉ ነዋሪነቱ በአሜሪካ የሆነዉ ዮሀንስ ታከለ ወይም የዲሲ ግብረ ሀይሉ ነብር መሀበሩ በመስረቱ የተሰማዉን ደስታ ገልፆ በማንኛዉም መልኩ ከጎን እንደሚቆም አስታዉቋል።የአስተባባሪ ኮሚቴዎችን በመምረጥ የተገባደደዉ የመስራች ጉባኤዉ ስብሰባ በቅርቡ አጠቃላይ የቀድሞ ጦር አባላቶችን ጠርቶ ቋሚ ተመራጮችን በማቀፍ ወደ ቀጣይ ተግባር እንደሚገባ አስታዉቋል።
የቀድሞ ጦር ሀይሎች የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት መሀበር መስራች ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ተካሄደ
የሀገራችን ፖለቲካ ብሄርን መሰረት ያደረገና በአማራው ህዝብ ጥላቻ ላይ የተቸከለ ሆኖ ቆይቷል። ካለው ተጨባጭ ፖለቲካዊ ሁኔታና ከአማራ ጠል የፅንፈኛ ሀይሎች የሀይል አሰልለፍ አኳያ ወደፊትም የሚያስከትለው አደጋ ለመገመት የሚከብድና እጅግ አደገኛ ነው።ከዚህ አኳያ የአማራው ህዝብ የራሱን ህልውና ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሏላዊነትና የህዝቡን አንድነት ለማረጋገጥ በሁለገብ ሁኔታ አቅሙን ማጠናከር እንዲችል አዴፓን ማገዝና ማጠናከር ይኖርበታል።እያየለ የመጣውን የፅንፈኛ ሀይሎችን የፀረ አማራ የፀረ አንድነትና የፀረ ኢትዮጵያዊነት ትንቅንቅ ውስጥ የአማራው ህብረተስብ ጥቅም ለማስጠበቅ ህልውናውን ከጥቃት ለመከላከልና በሀይል አሰላለፉ ውስጥ ሚዛኑን የጠበቀ ተገቢ ቦታ አዴፓ እንዲኖረው የመላው ህብረተስቡ ድጋፍ ያስፈልገዋል።ከዚህ አንፃር በየትም ያለ የአማራው ተወላጅ በሚቻለውና ባለው አቅም የተቃጣበትን የህልውና አደጋ ለመከላከል በአዴፓ ዙሪያ ተሰባስቦ ትግሉን ለማጠናከር ከታች የቀረቡት ማድረግ ቢችል ጠቃሚ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። የአማራውን አንድነት ከሚከፉፍሉ አፍራሾችና ከጎጠኛ አስተሳሰብ እርቆ በጋራ ጥቅሞቹ ዙሪያ በመሰለፍ ጥንካሬውን መገንባት አዴፖ ከቀድሞ የፖለቲካና የርእዩተአለም ቅርቃሩ ወጥቶ በአማራው ወግና ባህል ትውፊትና ስነልቦና ልክ ቁመና እንዲኖረው ምሁራን ገንቢ ሂስ በማቅረብ ድርጅቱን ማረቅ አመራሩን ማጠናከር የሶሻል ሚድያ ብሎገሮች አክቲቪስቶችና የአማራ ፖለቲካ አቀንቃኞች አዴፖን እንደ ድርጅት ከሚዘረጥጥ አመራሩን ከሚያዋርድና ከሚከፋፍል አቅጣጫ ወጥታችሁ በወገናዊ አቀራረብ በጨዋነትና በብስለት ድርጅቱ የህዝብን ጥያቄ እንዲመልስና ህዝባዊነት እንዲላበስ የተቀናጀ ዘመቻ ማካሄድ መሪ የሚፈልቀው ከህዝብ አብራክ በመሆኑ ወደ አመራር የሚመጡ ፖለቲከኞችን ሞራል በመስጠት እገዛ በማድረግ ብቁ እንዲሆን መርዳት። በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት በስሜት ከግንዛቤ እጥረትና ከፖሊሲ አተናተን አኳያ የሚከሰት የአደባባይ ስህተትን በደቦ ስድብና ዘመቻ ሳይሆን በምክርና በተግሳፅ እንዲታረም እድል መስጠት። በአዴፓና በአብን መካከል ጤናማ የሆነ አብሮነት እንዲፈጠር መርዳት። በአማራ ህልውና እና በጥቅሞቹ ዙሪያ በጋራና በትብብር እንዲሰሩ ማቀራረብአዴፖ የአማራው ህዝብ ያለው ትጥቅ የመያዝ መብት እንዲያከብር። የአማራው መታጠቅ ለአዴፖ አመራሮች ሞገስ ለህዝቡ ህልውና መጠበቂያና ብሎም ኢትዮጵያን ሊታደግ የሚችል መሆኑ ማሳወቅ። በውጭ ያለው የአማራ ተወላጅ እራሱን በተለያየ መስክ በሀገር ውስጥ የሚካሄደውን ትግል ሊያግዝ በሚችልበት መንገድ ማደራጀት ። በዲፕሎማሲ በሎቢና በእውቀት ሽግግርና ዘርፍ ድጋፍ ሊያደርግ የሚችልበትን መስመር ማበጀት። የአማራውን ህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉ የሚድያ ተቋማትን በእውቀት በገንዘብና በምችለው አቅም ማጠናከር። የአማራው ልሂቅ ሶሻል ሚድያ ላይ ተጥዶ ዝና ከመገንባትና ውዳሴ ላይክ ከማሳደድ ወጥቶ የተደራጀ ምሁራዊ ድጋፍ መስጠት ወደሚችልበት ምእራፍ መሸጋገር ከጥቂት ግዜ ወዲህ የአማራን ፖለቲካ በሶሻል ሚድያ የሚያቀነቅኑ ከአማራው ባህል ወግና ስነምግባር ያፈነገጡ ጦማሪያን ከዚህ ህዝባችንን ከማይመጥን ነውረኛ ተግባር እንዲቆጠቡ መምከር። ትውልዱ ሀሳብን በሀሳብ የመታገልን ስልጡንነትና ዲሞክራሲያዊ ባህል እንዲያዳብር መርዳት በኢትዮጵያ አንድነት ፅኑ አቋም ያላቸውን ብሄረሰቦች ከአማራው ህዝብ ጋር ቆመው ሀገራቸውን ከጥፉት ለመከላከል ከሚፈልጉ የደቡብ የአፋር የጋንቤላ የሶማሌ የትግራይና የኦሮሞ ህዝቦች ጋር በጋራ በሀገር ሏላዊነትና በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ትብብር መፍጠርና ማጠናከር እንዲችል አዴፖን መቀስቀስ መርዳት።እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
አዴፓን በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ ማጠናከር ይገባል ሀይለገብርኤል
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ ሶስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ላቀረበችው ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ የአለም ንግድ ድርጅት የአክሴሽን ዲቪዥን ዳይሬክተር ማይካ ኦሺካዋ ገልፀዋል። የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ዶክተር ከማይካ ኦሺካዋ ጋር በኢትዮጵያ የአባልነት ድርድር ሂደት ዙሪያ መነጋገራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት ገልፀዋል። የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ጥያቄ ካቀረበች ረዥም ጊዜ የሆናት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እየተገበረቻቸው ያሉ በርካታ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የድርድር ሂደቱን በተሻለ ፍጥነት ለማጠናቀቅ እንደሚያግዙ ማብራራታቸውን አመልክተዋል። ስለሆነም በቀጣይ ለአምስትኛው የስራ ቡድን ስብሰባ የሚቀርቡ ሰነዶች ወደ ተግባር የገቡ በርካታ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ያካተተ እንዲሆን ከድርጅቱ ባለሙያዎች ጋር በመከለስ ሂደት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዳይሬክተሯ በበኩላቸው ለኢትዮጵያ የአባልነት ሂደት እስካሁን በማነቆነት ከሚጠቀሱ የፖሊሲ እና የህግ ጉዳዮች መካከል በቅርቡ የተካሄደው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም የአለም ንግድ ድርጅት ያለ ኢትዮጵያ ተሳትፎ ሙሉ አይሆንም ያሉት ዳይሬክተሯ፤ ድርድሩን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በሴክሬታሪያቱ በኩል ቴክኒካል ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚሰጥ መግለፃቸውንም አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ ምላሽ እንደሚያገኝ ተጠቆመ
መጋቢት ፳፮ ሀያ ስድስት ቀን ፪፲፻፱ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በጋምቤላ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ታሪካዊውየሀመረ ኖሀ ኪዳነምህረት ፅላት ማነታቸው በማይታወቁ ግለሰቦች መዘረፉን የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ምእመናን ገልፀዋል። የደብሩ ካህናት በበኩላቸው ከየካቲት ሀያ አራት ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ቀን ጀምሮ ታቦቱ ከመንበሩ አለመኖሩን አሳውቀዋል። በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ አመተ ምህረት በቀዳማዊ ንጉሰ ነገስት ሀይለስላሴ እንደተሰራ የሚነገርለት ይህ ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ታቦቱ በቅርስነት ተይዞ ጥበቃ ሊደረግለት ሲገባ ያለበት አድራሻ አለመታወቁ እንዳሳዘናቸው ምእመናኑ ይናገራሉ። ፅላቱ በመንበሩ አለመኖሩን አስቀድመው ያወቁት የሀመረ ኖሀ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ካቴድራል አተዳዳሪ በበኩላቸው ታቦቱ የት ገባ ብለው ቄስ ገበዙን ሲጠይቋቸው ቄሰ ገበዙ እኔን ለምን ትጠይቁኛላችሁ ስራ አስኪያጁን ጠይቁ የሚል ምላሽ መስጠታቸው ሁኔታውን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎብናል ሲሉ ምእመናኑ ተናግረዋል። እነኚሁ የፅላቱ መጥፋት ያሳሰባቸው ምእመናን መጋቢት እና ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ጉዳዩን አስመልክቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ ፅህፈት ቤትት፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤትትና ለፓትርያርኩ ልዩ ፅህፈት ቤትትቢያቀርቡም እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ምላሽ ሊያገኙ አልቻሉም። ፅላቱ የሚቀመጥበት መንበር ባዶ መሆኑን የሚያሳይ በወቅቱ የተቀረፀ የቪዲዮ ምስል በአባሪነት ማቅረባቸውን የገለፁት ምእመናኑ ፣ ፅላቱ በመንበሩ ላይ ተገኘ ቢባል እንኳ እድሜ ጠገብ ፅላት መሆኑን ለይተውበሚያውቁ ካህናት ታይቶ መረጋገጥ እንደሚኖርበት አሳስበዋል። ስለጉዳዩ የሚያውቁት መረጃ እንዳለ የተጠየቁት የማህበረ ቅዱሳን አመራር ዲያቆን አብይ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላለቸው በመጥቀስ፤ ሆኖም ይህ ጉዳይ በዋናነት የሚመለከተው የአጥቢያውን ደብር እንጂ ማህበረ ቅዱሳንን እንዳልሆነ አስረድተዋል።
ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተለበጠው ታሪካዊው የጋምቤላ የሀመረ ኖሀ ኪዳነ ምህረት ካቴድራል ፅላት መዘረፉን ሳምንታዊው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገበ።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአለም አቀፍ እግር ኳስ ማሀበር ፊፋ ጋር በመተባበር ለእግር ኳስ ዳኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እየሰጠ ነው። ስልጠናው አርብ ሀምሌ ሶስት ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተነግሯል። ከሰኔ ሀያ ዘጠኝ እስከ ሀምሌ ሶስት ቀን በካፒታል ሆቴል እየተሰጠ የሚገኘው ከፍተኛ የእግር ኳስ ዳኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ላይ ስላሳ አምስት ዳኞች ተካፋይ ናቸው። ፌዴሬሽኑ የላከው መግለጫ እንደሚያስረዳው ከሆነ፣ ስልጠናው በየጊዜው እያደገ የመጣውን እግር ኳስ የበለጠ ተወዳጅ ሆኖ እንዲቀጥል የእግር ኳስ ዳኞች ሚና ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ለዚህም በሙያው ውስጥ የሚገኙ ዳኞች ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተጣጥመው እንዲቀጥሉ በየጊዜው የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ የግድ መሆኑን ይጠቀሳል። በዚሁ መሰረት ስልጠናው በተለያዩ የፅሁፍና የምስል መረጃዎች እንዲሁም በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ እንዲሆን በሙያው ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የፊፋ ባለሙያ በሄንሪኩሰን ካርሎስና በአፍሪካ የደቡብ ዞን የዳኞች ኦፊሰር ማርክ አማካይነት እየተሰጠ ይገኛል። ከአገር ውስጥ ደግሞ የካፍ ኢንስትራክተር አቶ ይግዛው ብዟየሁ፣ በአቶ ግዛቴ አለሙና በአቶ ፈቃዱ ግርማ በረዳት አሰልጣኝነት መካተታቸው ተገልጿል።
ለእግር ኳስ ዳኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እየተሰጠ ነው
በህንድ ደቡባዊ ግዛት አንድህራ ፕራደሽ የሰባ ሶስት አመቷ አዛውንት የመንታ ሴት ልጆች እናት ሆነዋል። አዛውንቷ ባሳለፍነው ሀሙስ በሀኪሞች እገዛ የሴትን እንቁላልና የወንድ ዘር ፈሳሽ ስፐርም በቤተ ሙከራ በማዋሀድ መንትዮች ፀንሰው አይናቸውን በአይናቸው ማየት ችለዋል። የሰባ ሶስት አመቷ ማንጋያማ ያራማቲ በህይወት ከሌለች እናት የተወለደችው ህፃን መንታ ጠብቃ አምስት የተገላገለችው እናት የሰባ ሶስት አመቷ ማንጋያማያ ማርቲ እንዳሉት፤ እሳቸውና የሰማኒያ ሁለት አመቱ ባለቤታቸው ልጅ መውለድ ቢፈልጉም እስካሁን ድረስ ሳይሳካላቸው ቆይቶ ነበር። ማንጋያማያ ሁለቱን መንታ ሴት ልጆች የወለዷቸው በቀዶ ህክምና ነው። ሀኪማቸው የነበሩት ዶክተር ኡማ ሳንካራም፤ እኝህ እናት ከነልጆቻቸው በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። ልጆቹ ከተወለዱ ከሰአታት በኋላ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አባት ሲታራማ ራጃሮ በበኩላቸው በጣም ተደስተናል ብለዋል። ይሁን እንጂ ይህንን በተናገሩ ማግስት ድንገተኛ ስትሮክ ስላጋጠማቸው በሆስፒታል ውስጥ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ። አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው እድሜያቸው በመግፋቱ ምክንያት በባለቤታቸውና በእሳቸው ላይ አንድ ነገር ቢፈጠር ልጆቹን ማን ሊያሳድጋቸው ይችላል ተብለው የተጠየቁት የሰማኒያ ሁለት አመቱ አዛውንት ሮጀር፤ በእጃችን ላይ ምንም ነገር የለም፤ መሆን ያለበት ይሆናል፤ ሁሉም ነገር በፈጣሪ እጅ ነው ያለው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በመንደራቸው ልጅ ባለመውለዳቸው መገለል ይደርስባቸው እንደነበር የሚናገሩት ጥንዶቹ፤ ልጆች መውለድ ለነሱ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያስረዳሉ። እናት ማንጋያማያ፤ ልጅ አልባዋ ሴት እያሉ ይጠሩኝ ነበር ሲሉ ይደርስባቸው የነበረውን የስነ ልቦና ጫና ያስታውሳሉ። ብዙ ጊዜ ሞክረናል፤ በርካታ የህክምና ተቋማትንም ጎብኝተናል በማለት አሁን ግን በህይወት ዘመናቸው ደስታን የተጎናፀፉበት ጊዜ እንደሆነ ይገልፃሉ። ከሶስት አመታት በፊትም እዚያው ህንድ ውስጥ በሰባዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኙ ዳለጂንደር ካዩር የተባሉ አዛውንት ወንድ ልጅ መውለዳቸው ይታወሳል።
ህንዳዊቷ በሰባ ሶስት አመታቸው መንታ ተገላገሉ
ከለውጡ ወዲህ እየተተገበረ ያለው ፌዴራሊዝም የህዝቦችን ፍላጎት መመለሱ ተመላከተ አዲስ አበባ፣ ህዳር ሀያ ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በለውጡ ማግስት ኢትዮጵያ ውጤታማ የፌዴራሊዝም ስርአትን ተግባራዊ በማድረጓ ብዝኀነትን እና የህዝቦችን መልከ ብዙ ፍላጎቶች መመለስ ችላለች ተባለ። ኢትዮጵያ የብዝኀነት ሀገር በመሆኗ ነገን ከግምት ያስገባ፣ ዛሬ ላይ ያሉ መልከ ብዙ ፍላጎቶችን ማስተናገድ የሚችል ከሀገሪቱ ህገ መንግስት የመነጨ የፌዴራሊዝም ስርአት ተግባራዊ እያደረገች መሆኗንም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአለም አቀፍ ግንኙነት ሀላፊ እና የህግ ምሁር ማሩ አብዲ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት የፌዴራሊዝም ስርአት ከህገ መንግስት የተሰፈረ የስልጣን ተዋረድ እና ውክልና ያለው መንግስት እንዲሁም የተከፋፈለ ፍላጎት ያላቸው ህዝቦች በጋራ የሚኖሩበትን መንገድ የሚያመቻች ስርአት ነው። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት የውክልና እና የማንነት ጥያቄዎችን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የሀሳብ እና የታሪክ እውነታዎችን እንዲሁም የፍላጎት ብዝኀነትን ጭምር እያስተናገደ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል። ሁሉም ብሄረሰቦች በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውክልና ማግኘታቸው፣ የሀሳብ ልዩነቶች የሚስተናገዱበት አግባብ እንዲሁም ተዳፍነው የቆዩ የክልልነት ጥያቄዎች በተግባር የተፈቱበት መንገድ ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል። በመራኦል ከድር ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ ኢንስታግራም፦ ቲክቶክ፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
ከለውጡ ወዲህ እየተተገበረ ያለው ፌዴራሊዝም የህዝቦችን ፍላጎት መመለሱ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ህዳር አስር፣ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በሳይበር ምህዳር ደህንነት እና ዝማኔ ላይ ትኩረት ያደረገ የመጀመሪያው የቻይና የበይነ መረብ ስልጣኔ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። በቤጂንግ እየተካሄደ ባለው ኮንፈረንስ በቀረበውና በቻይናው ፕሬዚደንት ቺ ጂንፒንግ የተላከው መልእክት፤ አዎንታዊ ሀይልን እና ጥንካሬን በመጠቀም የተሻለ የሳይበር ምህዳር ለመፍጠር የጋራ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። ፕሬዚደንቱ በይነ መረብ የማህበራዊ ስልጣኔ አካል መሆኑን ጠቅሰው የሳይበር ምህዳር አስተዳደርን የበለጠ ለማጎልበት እና የበይነ መረብ ግንባታን ለማስተዋወቅ በትኩረት እንዲሰራም ጠይቀዋል። ኮንፈረንሱ እየተካሄደ ያለው የበይነ መረብ ስልጣኔን በጋራ እንገንባ በሚል መሪ ሀሳብ ሲሆን በሳይበር ምህዳር ደህንነት እና በበይነ መረብ ስልጣኔ ምክክር ሲደረግ በሀገሪቱ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። የዘርፉ ባለሙያዎች፥ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተሻለ የሳይበር ምህዳር ለመፍጠር ከመንግስታት ጋር በጋራ ሊሰሩ ይገባልም ነው የተባለው። ከቅርብ አመታት ወዲህ የበይነ መረብ ስልጣኔን በመገንባት ሂደት አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል። በየሻምበል ምህረት አካባቢዎን ይጠብቁ ወደ ግንባር ይዝመቱ መከላከያን ይደግፉ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
በሳይበር ምህዳር ደህንነት ላይ ያተኮረ የበይነ መረብ ስልጣኔ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው
ሰኔ ሀያ አንድ ቀን አመተ ምህረትኢሳት ዜና በአዳማ በአቡበክር መስጊድ በተካሄደው ተቃውሞ ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ መንግስት ድምፃችንን ይስማ በሀሰት ክስ አንገዛም አሸባሪዎች አይደለንም የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል። በአሳሳ ከተማም እንዲሁ በአል ከራም መስጂድ ተቃውሞ መካሄዱን ለማወቅ ተችሎአል። በወልድያም እንዲሁ ሙስሊሙ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰምተዋል።በሁለቱም ቦታዎች የተካሄዱት ተቃውሞዎች በሰላም ተጠናቀዋል። መንግስት የድምፃችን ይሰማ መሪዎችን ከእስር በመፍታት ለሙስሊሞች ጥያቄ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፍተኛ ጫና ቢደረግበትም አቋሙን የሚቀይር ሆኖ አልተገኘም። ዘወትር አርብ የሚደረጉ ተቃውሞዎችን መንግስት አሸባሪዎች የሚያቀናብሩት ነው በማለት ተደጋጋሚ መግለጫ ሲሰጥ ቆይቷል።
በክልል ከተሞች ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን አሰሙ
ሸንቁጥ አየለበራሱ በህዉሀትኢህአዴግ በጎ ፈቃድ የተሰዬመዉን እና የህዉሀትኢህአዴግ መሪ የሆነዉን አቢይን አንድ ሰሞን አቢዮት ሊያመጣ ነዉ ወያኔን ሊያፈርስ ነዉ ብላችሁ ያልተመጠነ ድጋፋችሁን ለአቢይ ስትቸሩ የሰነበታችሁ ሰዎች አሁን በፍጥነት በአቢይ ላይ ተቀይማችሁ ባይ ተገረምሁ እና ጥያቄ ልጠይቃችሁ ፈለግሁ።ጥያቄዬ ቀላል ነዉ። አቢይ ህዉሀትን ከማወደስ እና የህዉሀትን ተጋድሎ ከማወደስ ዉጭ ምን አማራጭ አለዉ መለስን የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ሰዉ እና ታጋይ እያለ ከማወደስ ዉጭ ምን ምርጫ አለዉ የህዉሀት ታጋዮችን ስም አንድ በአንድ እየጠራ ከማወደስ ዉጭ ምን አማራጭ አለዉ የህዉሀት ሰማእታት ሀዉልት ስር ቆሞ የህዉሀትን ኢትዮጵያን የማፍረስ ታሪክ እና ተጋድሎ ከማወደስ ዉጭ ምን አማራጭ አለዉ መልሱ ምንም አማራጭ የለዉም ነዉ። አቢይ በህዉሀት ቁጥጥር ስር ነዉ።ጥሩ ተናጋሪ ስለሆነ የተፃፈለትን አቀላጥፎ ከመናገር በዘለለ ምርጫ የለዉም።አንዳንዶቻችሁ ደግሞ የከፋችሁ አቢይ የተገፋዉን የወልቃይትን ህዝብ ለምን አልጎበኝም እያላችሁ መሆኑን አስተዉያለሁ።ለ እናንተም ጥያቄ አለኝ የአቢይን ፕሮግራም ማን የሚነድፍለት ይመስላችኋል መልሱ ቀላል ነዉ።አቢይ የሚዉልበትን የሚጎበነዉን የሚናገረዉን ንግግር ቀርፆ የሚሰጠዉ ህዉሀትኢህአዴግ ነዉ። ህዉሀት ደግሞ የወልቃይት ጉዳይ የሞት ሽረቱ ጉዳይ ነዉ።የወልቃይትንት ጉዳይ አቢይ ከወልቃይት ህዝብ ጋር ሄዶ እንዲፈታዉ ነፃ መድረክ ለአቢይ አይሰጠዉም።ለማንኛዉም አቢይ ህዉሀትን አወደስ ብላችሁ አትዘኑ።አቢይ እራሱ ህዉሀትኢህአዴግ እንጅ ተቃዋሚ ፓርቲ አይደልም።ህዉሀትን ከማወደስ ዉጭ ምርጫ የለዉም።በርካታ ብዥታዎች በሂደት እየጠሩ መምጣታቸዉ አይቀርም። ከነዚህ ብዥታዎች ዉስጥም አንዱ እና በሂደት የሚጠራዉ ህዉሀትኢህአዴግ እንዴት የአንድነትኢትዮጵያዊነት አጀንዳን በተራቀቀ መንገድ ከተቃዋሚዎች እንደነጠቀዉና የመጭዉ ጊዜ የስልጣን ዘመኑን ማራዘሚያ ሊያደርገዉ በቂ ዝግጅት እንዳደረገ ነዉ።በዚህ አጀንዳ ነጠቃ ላይ ከዚህ ቀደም ሰፋ ያለ ፅሁፍ ስለፃፍኩበት አሁን ወደዚያ አልመለስም።ለማንኛዉም ልክ እንደ ሀይለማሪያም አቢይ ህዉሀትን ከማወደስ ዉጭ ምርጫ እንደሌለዉ አትዘንጉት ለማለት ያህል ነዉ።
አቢይ ህዉሀትን በማወደሱ ለተከፋችሁ ደጋፊዎች የቀረበ ጥያቄ አቢይ ህዉሀትን ከማወደስ ዉጭ ምን ምርጫ አለዉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በቻይና እና በአለም አቀፍ ደረጃ በገዳይነቱ የሚታወቀውን የሳንባ ካንሰር በቀላል ቀዶ ጥገና ማከም እና ማዳን የሚቻልበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን በቻይና ቤጂንግ የሚገኝ የህክምና ምርምር ማእከል አስታወቀ። በቻይና ቤጂንግ የህክምና ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኝ የሳንባ ካንሰር ምርመራ እና ህክምና ምእከል ዳይሬክተር የሆኑት ዢ ዡዪ እንደተናገሩት ለኮቪድ ወረርሽኝ ሲካሄዱ የቆዩ የሳንባ ምርመራዎች ለሳንባ ካንሰር መነሻ የሆኑ ምክንያቶችን እንድንለይ አስችሎናል ብለዋል። የሳንባ ካንሰርን በጊዜ መለየት ከተቻለና ህክምና ከተደረገ የመዳን እድሉን በእጅጉ ማፍጠን እንደሚቻል ተመልክቷል። የሳንባ ካንሰር ህሙማኑ እንደ ቀድሞው ቀዶ ጥገና ሳያስፈልጋቸው በደረት አካባቢ አነስተኛ ክፍተት በመፍጠር ቀጭን ቱቦ ላይ በተገጠመ ካሜራ እና ብርሀን ተመርቶ በሚሰራ አነስተኛ ቀዶ ጥገና እንደሚድኑም ነው ሲጂቲ ኤን የዘገበው። የአለም ጤና ድርጅት በፈረንጆቹ ሁለት ሺህ ሀያ ባወጣው ሪፖርት መሰረት የሳንባ ካንሰር በገዳይነቱ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠ ህመም ነው። በቻይና የሳንባ ካንሰር በገዳይነቱ በቀዳሚነት የሚቀመጥ ሲሆን በየአመቱ ስምንት መቶ ሀያ ሺህ አዳዲስ ሰዎች በህመሙ ይጠቃሉ ፤ ሰባት መቶ አስር ሺህ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን ያጣሉ። ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
ቻይና የሳንባ ካንሰርን ማዳን የሚያስችል ትልቅ ግኝት ይፋ አደረገች
ዮሀንስ አንበርብርሀላፊዎቹ ጥያቄውን አልመለሱምየአገሪቱን ኢኮኖሚ ከመጉዳት ባለፈ የፖለቲካ ቀውስ እየፈጠሩ ናቸው የሚባሉ ኮንትሮባንዲስቶች ማንነት በግልፅ ለፓርላማው እንዲቀርብ የፓርላማው አባላት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል።የፓርላማው አባላት በከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ሳይቀሩ በአገሪቱ ለሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ጣታቸውን የሚቀስሩት ኮንትሮባንዲስት በተባሉ ማንነታቸው በማይታወቅ ሀይሎች ላይ ስለሆነ የእነዚህን ማንነት ፓርላማው በግልፅ የማወቅ ሀላፊነት ያለበት በመሆኑ ማንነታቸው እንዲገለፅላቸው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አመራሮችን ጠይቀዋል።የፓርላማ አባላቱ ጥያቄውን ያቀረቡት ማክሰኞ ጥር ቀን አመተ ምህረት የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀማቸውን ሪፖርት ለማድረግ ፓርላማው ለተገኙት ለባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞገስ ባልቻና ሌሎች አመራሮች ነበር።አንድ የፓርላማ አባል ስሙ የማይጠራው ኮንትሮባንዲስት ማነው ሲሉ በስላቅ ጠይቀዋል። በአገሪቱ የብሄር ግጭት እየፈጠሩ ያሉት እነዚህ ኮንትሮባንዲስት የሚል ስም የወጣላቸው በኔትወርክ ተሳስረው የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች እንደሆኑ የጠቆሙት ሌላ የምክር ቤቱ አባል ደግሞ በእነዚህ ሀይሎች ጡንቻ ገቢዎችና ጉምሩክ ራሱ ታስሯል ሲሉ ተችተዋል። በተለይ በጉምሩክ ቅርንጫፎች ላይ የሚመደቡ የስራ ሀላፊዎች ለዚሁ ህገወጥ ስራ እንዲመቹ ሆነው የሚመለመሉ መሆኑን በዚህም የተነሳ በአሁኑ ወቅት አንድ ብሄር ነጥሎ የማጥቃት ግጭት እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል ሲሉ እኚሁ የምክር ቤት አባላት ወቅሰዋል።በአገሪቱ የወጪ ንግድ መስመሮች በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በድንገት የኤሌክትሪክ ሀይል ተቋረጠ ማለት ኮንትሮባንድ የጫኑ ተሽከርካሪዎች እያለፉ እንደሆነ በገሀድ የሚታወቅ መሆኑን የጠቀሱ ሌላ የምክር ቤት አባል በዚህ ኔትወርክ ውስጥ የተቋሙ ሰራተኞች ሊኖሩ እንደሚችሉ ያሳያል ብለዋል።የባለስልጣኑ የስራ ሀላፊዎች የግማሽ አመት ሪፖርት በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሰ ቢሆንም ኮንትሮባንዲስቶችን በተመለከተ የተነሳው ጥያቄ አመዛኙን ጊዜ የያዘ ነበር።ለተነሳው ጥያቄ በቅድሚያ ምላሽ የሰጡት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የህግ ማስከበር ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዘመድ ተፈራ ሲሆኑ የኮንትሮባንዲስቶቹን ማንነት መግለፅ የሚቻል ቢሆንም የሚወሰደውን እርምጃ መጠበቅ የተሻለ እንደሚሆን ተናግረዋል።በከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩ ኮንትሮባንድን ለመዋጋት ቁርጠኝነት በመታየቱና ለይተን እንደናቀርብ በታዘዝነው መሰረት ቀንደኞቹን በጥናት ለይተን በአገር አቀፍ ደረጃ ለተቋቋመው ግብረ ሀይል አቅርበናል ያሉት አቶ ዘመድ እከሌ እከሌ ብሎ ማቅረብ ይቻላል ነገር ግን የሚወሰደውን እርምጃ በጋራ ብናይ ይሻላል ብለዋል።የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው በፓርላማ አባላቱ እንደተነሳው ኮንትሮባንዲስቶቹ የራሳቸው መጋዘን ያላቸው በኔትወርክ የተደራጁና ተግባራቸውም በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ የሚባል መሆኑን ጠቁመዋል።ይኼንን መበጣጠስ ካልተቻለ ከኢኮኖሚ ጉዳቱ በላይ የፖለቲካ ቀውስ የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።ይሁን እንጂ የአገሪቱ የፖለቲካ አመራር በጉዳዩ ላይ ቁርጠኛነቱን ያሳየ በመሆኑ እርምጃ ይወስዳል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል። በግማሽ አመት ውስጥ ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ንብረቶች በኮንትሮባንድ ሊገቡ ሲሉ የተያዙ መሆኑን ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ደግሞ ሊወጣ ሲል መያዙ ተገልጿል።ሪፖርተር
ኮንትሮባንዲስቶች እነማን እንደሆኑ ለፓርላማው በግልፅ እንዲናገሩ የገቢዎችና ጉምሩክ ሀላፊዎች ተጠየቁ
የኢትዮጵያ፣የሱዳንና የግብፅ የቴክኒክና የህግ ቡድኖች ባደረጉት ወይይት በጣም ወሳኝ በሆኑ የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ውሀ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ቡድኖቹ ከተወያዩ በሀላ የደረሱበትን ውጤት ለሶስትዮሹ የሚኒስትሮች ስብሰባ ሪፖርት አድርገዋል ብሏል። ሶስቱ ሀገራት በኢትዮጵያ ተቃውሞ ምክንያት ከወራት በፊት ከተቋረጠው የዋሽንግተን ድርድር በሀላ በድጋሚ ድርድር ከጀመሩ ትናንትና ሰባተኛ ቀን ማስቆጠራቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል። መግለጫው ምንም እንኳን በወሳኝ ገዳዮች ላይ መግባባት ቢደረስም ስምምነቱን ሙሉበሙሉ ለማጠናቀቅ በህግ ገዳዮች ላይ መስማማት ያስፈልጋል ብሏል። የሱዳን ልኡክ ቡድን የተደረሰበትን መሻሻል ሪፖርት በማድረግ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር መመሪያ ይቀበላል ያለው መግለጫው ስብስባው የተጠናቀቀው ሱዳን ምክክሯን ከጨረሰች በኋላ ለመቀጠል በመስማማት ነው። ግድቡን በጥንቃቄ ከማስተዳደር ባሻገር ስምምነቱ ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ ያላትን ዘላቂ ጥቅም በሚጠብቅ መልኩ መሆን እንዳለበት መግለጫው ጠቅሷል። የግድቡ ሙሌትና አስተዳደር ከአመታት በፊት ሱዳን ላይ በተፈረመው የመርሆች ስምምነት መሰረት መሆን አለበት ያለቸው ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ የሶስቱንም ሀገራት የጋራ ጥቅም ባስከበረ መልኩ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ገልፃለች። የሱዳን የውሀና መስኖ ሚኒስቴት ያሰር አባስ ፕሮፌሰር በትናንትናው እለት በሰጡት መግለጫ በግድቡ የቴክኒክ ጉዳይ ዘጠና አምስት በመቶ መግባባት የተደረሰበት ሲሆን መግባባት ያልተደረሰባቸው የህግ ጉዳዮች በመሪዎች ደረጃ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲሰጥባቸው ለሶስቱም ሀገራት መሪዎች ተልኳል ብለዋል። ኢትዮጵያ የግድቡን ሙሌትና አስተዳደር የሚመለከት የመርህ ስምምነት እንጅ አስገዳጅ ስምምነት አልፈርምም የሚል አቋም ማንፀባረቋ ከሱዳንና ግብፅ ጋር ልዩነት ውስጥ መግባቷን ያሰር አባስ ፕሮፌሰር ገልፀዋል። በድርድሩ ላይ ሰፊ ልዩነት ያላት ግብፅ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት እወስዷለሁ እያለች ነው። ኢትዮጵያ ግድቡን የምትገነባው ልማትን ለማፋጠን መሆኑን በተደጋጋሚ ብትገልፅም በግብፅ በኩል ከናይል የማገኘው የውሀ መጠን ይቀንሳል የሚል ቅሬታ ስታነሳ ቆይታለች። ሱዳን በአንፃሩ የግድቡን መገንባት እንደማትቃወም ስትገልፅ ቆይታለች። በመጭው ሀምሌ ወር የግድቡን ውሀ ሙሌት ለመጀመር ኢትዮጵያ እቅድ አውጥታ እየሰራች ሲሆን ሱዳንና ግብፅ ስምምነት ላይ ሳይረስ ሙሌቱ መጀመር የለበትም የሚል አቋም ይዘዋል።
ከተቋረጠው የዋሽንግተን የሶስትዮች ድርድር በኋላ በድጋሚ የተጀመረው ድርድር ትናንት ሰባትኛ ቀኑን አስቆጥሯል
አዲስ አበባ፣ የካቲት ስላሳ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎችን በቅርበት የሚያስተሳስረው የዳዬ ጭሪ ናንሴቦ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀም ሰማኒያ አራት በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ። የመንገድ ግንባታው ሰባ አንድ ነጥብ አራት ኪሎ ሜትር የሚረዝም ሲሆን ከዚህ ውስጥ አርባ ሰባት ኪሎ ሜትሩ የአስፋልት ንጣፍ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል ተብሏል። ለግንባታው የሚውለው አንድ ቢሊየን ሰባት መቶ ሀያ ሶስት ሚሊየን ስድስት መቶ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ብርም በኢትዮጵያ መንግስት መሸፈኑ ተመላክቷል። የመንገድ ፕሮጀክቱ ከዳዬ ከተማ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል እየተገነባ ከሚገኘው የኤዶ ሴሮፍታ ወርቃ መንገድ ፕሮጀክት ጋር እንደሚገናኝ ተጠቅሷል። መንገዱ በገጠር አስር ሜትር እና በከተማ ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ መሆኑን ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ ኢንስታግራም፦ ቲክቶክ፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
ሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎችን የሚያገናኘው የዳዬ ጭሪ ናንሴቦ መንገድ ግንባታ ሰማኒያ አራት በመቶ ደረሰ
ሁለት መቶ ሰባ ስድስት እነዚህ ፓርቲ መሪ ነን ባዮች ምን ሆኑ ለእብዳናቸው መደሀኒት ወደ ሚሆን ሆስቢታል ወይ እሱር ቤት ጠበል የሚወስድ ሰው አጡ ለመሆኑ እነዚህ ቡዱኖች በሀያኛው ክፍለዘመን ወደ የባርያ ስርአት ጦርነት መመለሳቸው ከእብዶች ውጭ ምን ያስብላቸዋል የወልቃይት ፀገዴ የማንነት ጥያቄ ከሆነ ሀወሀት ኢህአደግ ሀገመንግስት አያግደውም እንጅ የሁለቱ ቡዱኖች ጣልቃ ከመግባት ይልቅ እጃቸው ቢያወጡ እና የዛ ቅምጡ ፈደረሽን ምክር ቤት ሀላፍነቱ ቢወጣ መልካም ነበር ግን ደግሞ ችግሩ ቅምጡ ፈደረሽን ምክር ቤት በሚነዱት ስለሚነዳ ወጤቱ ባዶ ነው ። ምክንያቱም ካሁን በፊት በጋንቤለ እና በአኝዋክ በደቡብ ህዝቦች የነበረ የአናሳዎች ገጭትነ ጥያቄ አሁን ደግሞ ተልቁ ጥያቄ የኦሮሞ ጉዳይ የአኝወክና ኑዌር እልቂት የአማራና ቅማንት ግጭት በሚመለከት ልየነቱ አባብሶ ወጣ እንጅ መፍትሄ አላመጣም። የአሁኑ የወለቃይት ፀገዴ ጉዳይም ወጤቱ የተለየ አይሆንም። በእኔ እምነት እነዚህ ቡዱኖች የህዝብ ፍቅር አንድነትብ መተሳሰብን አብሮ መኖርን አይፈልጉም። ምክንያቱም ህዝቦች ተፋቅረው ተቃቅፈው ከነሩ እየተማከሩ ወዳጅና ጠላታቸው ስለሚያውቁ የገዥዎች እድሜ ያሰጥራሉ። በመሆኑም የህወሀትና በአዴን ችኩቻም የሚየራሙዱት ለዚሁ አላማ ነው። ለህዝብ ችግር ቢቆረቆሩ ነረው በአሁኑ ጊዜ የኢሊኖ ድርቅና የመሰበሰ አስተዳደራቸው የፈጠው ረሀብ ውሀ ጥም ስደት በሽታ ወደ መፍታት በተረባረቡ ነበር። ይህ የሚያሰዬን እነዚህ ሰዎች ስለህዝብ ደንታ እንደሌላቸው አንድ ተጨባጭ ማስረጃ ነው ። እነዚህ ቡዱኖች ይህ ብቻነው ችገራቸው በእኔ እምነት ዋነኛው ችግራቸወ የበታችነት እና የበላይነት ወይ አባታውነት እና ሎሌነት የፈጠረው ፈጥጫ ነው። ለዚሁ ምክንያት የሆነው በአዴ በህወሀት መሪዎች የተሰራና በሀወሀት የተሰጠው ፕሮግራም መመሪያ እሽ ብሎ እየተቀበለ በመምጣቱ የህወሀት መሪዎቸ አባታውነትም ለበአዴንም ለኦሆዴድም ለደቡ ብም ህዝቦች ለሁሉም አጋር የክልል መንግስታት የበላይ ሆኖ በመቆዬቱ የበአዴን አመራር ደግም በሁለት ተሰንጥቆ እነዛ የበአዴን መስራች እና አንጋፋ አማራር እየተባሉ የሚታወቁና አዳዲስ ተተኪ አማራሮች በመካከላቸው መናናቅና አለመተማመን እየሰፈነ መጣ። አዲሱ ትውልድ ለአንጋፋዎቹ ከህወሀት አባታዊ ተፅኖ እንውጣ ሲላቸው አንጋፋዎችም የህወሀት አማራር አባታውነት በመውረስ ለወጣት አማራሮች ተፀእኖ ማሳደር ጀመሩ ። የአማራ ህዝብም ለበአዴን ቡዱን የሀወሀት በአዴን በማለት ያናንቃቸው ጀመሩ የበአዴን አመራር የበታችነት እየባሰው ሄደ ። የህወሀት መሪዎችም ያአባታዊ የበላይነታቸው እየወረዱ እና እያጡ እየሄዱ እነዳሉ እየገባቸው መጣ። ሀወሀቶች በባአዴን ብቻ ሳይሆን በኦሆዴድ በአናሳዎችም የቅርቡን እንኳ በአፋር ሳይቀር እየተናቀ መጣ። መናደድ ጀመሩ።በተለይ ደደግሞ አቶ መለስ ወደህመም የደረሰበት ሁኔታ ነበር። አጀንዳዬ የበአደን ስለሆነ አሱን ላጣቃልል የበአዴን እና ሀወሀት አማራር በዱኖች በጎድን መተያየት እና መደፋፈር ከጀመሩ ወደ ስድስት አመት አስቆጥረዋል። ቀደም ሲል የሀወሀት አማራር በጉባኤ በኮንፍረንስ የወሰኑት ውሳኔዎች ፖሊሲዎች እንዷባታውነታቸው ወደ ሁሉ አባል ፓርቲዎች እና አጋር ባርቲዎች ፖሊሲ መመርያ ሆነው ተግባራዊ ይሆኑ ነበር። ሁሉም ክልሎችም በትግራይ የተሰሩ ስራዎች ለተሞክሮ እየተባሉ ቡዙ ገንዘብ ለውሎ አበል እየተከፈላቸው ይዘሩ ነበር የሚቀስሙት ተሞኩሮ ግን ጭቆና አፈና ብቻ ነበር። የበአዴን አመራር ድሮየነበራቸው ታዛዥነት በመጣስ ከመለስ ጋር ም መፋጠጥ ጀመሩ። የአማራ ህዝብም ባገር ውስጥ በወጭ ያሉ ነፃነት የላችሁም የአማራ ህወሀት ናችሁ ብሎ ስለሰየማቸው የባሰውን ወደ የበታችነት አዘቅት ገቡ። በአዴኖች የበታችነታቸውን ለመሸፈን አራት አጀንዳ ይዘው ተነሱ ከነሱም አንድኛ በቡዙሀን መገናኛ በአዴን የመንም አካል ጥገኛ ተላላኪ አይደለም በማለት እየተጠነቀቁ መናገር ጀመሩ። ሁለት የበአዴን የትግል ታሪክ ጨራሹን ያልሰሩት ያልነበሩሩበት እና የትግራይ ሀዝብና ልጆቹ ታሪክ በመቀማት የውሼት ታሪክ ፅፈዋል። ያታሪክ ግን ውሼት መሆኑ የሰሜን ጎንደር ወለቃይት ፀገዴ አርማጮሆ ጋይነት ንፋስ መውጫ ጉና ድብረታቡርና ፋርጣ ሰሜን ሽዋ በተለይ እነአለምም ከተማ መኸል ሜዳ መላው መርሀቤቴ አጅባር የጎጃም ሀዝብም በመጠኑ ወሎ ሀይቅ ማርሳሳ ተንታ ጭፍራና አፋር ሰቆጣና ላላስታ ሀዝበች አይቀበሉቱም በተግባር ልጆቻቸው ለህወሀት ሰጥተው እጅግ ቡዙ መስዋእት በመክፈላቸው ንበረታቸው ራሳቸው አዲስ አበባ እስከእምንገባ አብረው ስለነበሩ ሀቁን ስለሚያውቁ ። የትግራይ ህዝብና ታጋዮችም አግራሞትን ፈጥሯል። ሶስት ኛበአንድአንድ መድረኮች ከህወሀት አባታዊ አማራር የወጣ ወይ የጣሱ ውሳኔዎች ይወስኑ ነበሩ። እነዛ ውሳኔዎች ለህወሀት አማራር እጅጉን ያናድዷቸው ነበሩ ። አራትኛ የወልቃይት ፀገዴ ጥያቄ አስመልክተው የገቡበትም የበታችነት ስሜት ለመስበር እና በአዴን የበታችነት ስሜት የለውም የሚል በአማራ ሀዝብ ተቀባይነትን ለማግኜት ያደረጉት የወረደ እና ኋላ ቀር እርምጃ ነው። ስለዚህ የበአዴን ቡዱኖች በፀገዴ እና በወልቃይት ያለ የማንነት ጥያቄ በህዝብ ፍላጎት በነፃ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንደመፍታት ፈንታ ህዝብ ለህዝብ በመጋጨት ድሮ የወደቀ የበታችነት ለመመለስ መሞኮሩ በአማራ ህብ ይሁን በትግራይ ህዝብ ተቀባይነት የለውም። ይልቅኑስ አሁንም እጃቹ አውጡ ። ህዝብ የራሱ እድል ራሱ ይወስን። በሌላ በኩል የህወሀት የአማራር በዱን እና ተላላኪ ካድሬዎቹ በትግራይ ክልል ከማንም ጊዜ የነበሩ የድረቅ ዘመናት የከፋ ዘመን እያለ በመልካም አስተዳደር እጦት እየተሰቃዮ እያለ ለአምስትሚሊዮን ህዝበ ውሀ ሊያጠጣ ያልቻለ በውሸት ልማት የሚያጭበርብ ያለ ስርአት ነው። ይህ በዱን ህዝብ በመኖርና አለመኖሮ በጨለማ አዘቅት እያለ ልክ እንደበአዴን የአርባ ሁለት አመት የውሼት ታሪክ ለመፃፍ ሁለት መቶ ሚሊዮን ብ ር በመመደብ የመሪዎች የውሸት ታሪክ መፅሀፍ ለመፃፍእየተሯሯጠ ይገኛል። በተጨማሪ ህዝብን ለማዳን እርዳታ እንደመሰባሰብ ፈንታ ለመፅሀፉ ለመፃፍ ሌላ በሰበቡ ለመፅሀፉ አመካኝቶ በሀገር ውስጥና ውጭ ያሉ የተግራይ ተወላጆች ገንዘብ ለመሰባሰብ ብሎም የባንክ ጎተራቸው ለሞሙላት እየተሯሯጡ ናቸው። እነዚህ ቡዱኖችም ከበአዴን ጋር የሚያደርጉት ያሉ ችኩቻ የአባታውነታቸው የበላይነት ለመረጋገጥ ብለው ህዝብ ለህዝብ ለመጋጨት የሚያደርጉት ሩጫ የውስጥ ብልሽውነተቸው ለመሸፈን ነው። ግን ሁለቱ ቡዱኖች ምን ያህል ከጅዎች ናቸው ስለነዚህ የተባለሹ ቡዱኖች ብዙ ባለኩ ነበር የነዚህ ጉድ ተተርኮ የሚያልቅ አይደለም በመጨረሻ የማስተላልፈው መልእክት በአጠቃለይ የኢትዮጱያ ህዝብ በተለይ ደግሞ አሁን እያናከሧችሁ ያሉ የአማራና የተግራይ ህዝቦች የነዚህ ውስጠጉድ ተመልክታችሁ የነዚህ የተበላሹ ቡዱኖች መሳርያ አትሁኑ ዛሬ ነገ ለዘአለሙ ወንድም አማቾች ነን እና ። ለዛሬ ይበቃኛል ። ይቀጥላል ሁለት መቶ ሰባ ስድስት
ይነበብ ለምን ያብዳሉ አስገደ ገብረስላሴ
አዲስ አበባ፣ የካቲት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የአፍሪካ ህብረት ባለ ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ትብብርን በማጎልበት ረገድ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለፁ። ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስላሳ ስድስትኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን አስመልክተው ለተሳታፊዎች የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክት አስተላልፈዋል። በመልእክታቸው የአፍሪካ ሀገራት ለሩሲያ የምንጊዜም አጋር መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ፕሬዚዳንቱ በፈረንጆቹ ሁለት ሺህ የተካሄደው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ በአገራቸውና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሁለትዮሽና አለምአቀፋዊ ግንኙነት ማጠናከር ያስቻለ መሰረት መጣሉንም ገልፀዋል። በመጪው ሀምሌ በሩሲያ ፒተርስበርግ ከተማ የሚካሄደው ሁለተኛው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ በቀጣይ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ፍሬያማ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ምክክር መድረክ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት መገለፃቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የአፍሪካ ህብረት አለምአቀፋዊ ትብብርን በማጎልበት ረገድ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ነው ቭላድሚር ፑቲን
ኢሳት ዲሲግንቦት የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ደቡብ ሱዳን ጦርነቱን አቁማ የሰላም ድርድሩን እንድትፈርም የአንድ ወር ቀነ ገደብ አስቀመጠ።ሀገሪቱ ያንን የማታደርግ ከሆነ ግን የከፋ ማእቀብ ሊጠብቃት ይችላል ብሏል።እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ ጀምሮ ነበር ደቡብ ሱዳን በእርስ በርስ ጦርነት መታመስ የጀመረችው።ለአስር ሺዎች ሞትና ለሚሊዮኖች መፈናቀል ምክንያት የሆነው ይህ የእርስበርስ ጦርነት ለእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ሳይቀር አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል።በተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ የተጠራውና እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ ሰኔ ድረስ ቀነ ገደብን ያስቀመጠው ውይይት ደቡብ ሱዳን እስከ አንድ ወር ድረስ የሰላም ስምምነቱን እንድትፈርም ያስገድዳል።ሀገሪቱ በአንድ ወር ውስጥ ይህንን ማድረግ ካልቻለች ግን የጦር መሳሪያን ጨምሮ ሌላ ከበድ ያሉ ማእቀቦች ይጠብቋታል ይላል የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት።በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ውሳኔውን የማያከብሩ ከሆነ ግን ሀገሪቱ ላይ መአቀብ እንደሚጥል ነው ያሳወቀው።ስምምነቱን በተመለከተም ሪፖርት እንዲያደርጉ ያስጠነቅቃል።ይህ የተባበሩት መንግስታት ውሳኔ ከመንግስታቱ ድርጅት ድምፅ ማግኘት የሚጠበቅበት ሲሆን በእስካሁኑ ሂደት ድምፅ ማግኘቱ ተመልክቷል።
ደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድሩን እንድትፈርም የአንድ ወር ቀነ ገደብ ተቀመጠላት
አዲስ አበባ፣ ታሀሳስ ስድስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ መቀሌን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል። አገልግሎቱ በትግራይ፣ አማራና በአፋር ክልሎች በተከሰተው ጦርነት በዲስትሪቢዩሽን መሰረተ ልማቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት የፀጥታ ችግር በሌለባቸው አካባቢዎች ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን ከስር ከስር መልሶ በመጠገን የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች ዳግም ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑ ተገልጿል። እስካሁንም በክልሎቹ በርካታ አካባቢዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ነው የተመላከተው። የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ እስከ ታህሳስ አራት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ድረስ ከአማራና አፋር ክልል በተጨማሪ በትግራይ ክልልም የቴክኒክ ባለሙያዎችን በማሰማራትና አስፈላጊ ግብአቶችን በሟሟላት አገልግሎት የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች ዳግም ተጠቃሚ እየተደረጉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል። በዚህም ከመቀሌ እና መሆኒ ሰብስቴሽን አገልግሎት የሚያገኙት መቀሌ፣ መሆኒ፣ ኩይሀ፣ ሳምረ፣ ሀገረ ሰላም፣ ጨርጨርና፣ የርብሀ አዲስ ቅኝ ቀበሌ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል ነው ያለው አገልግሎቱ። ከውቅሮ እና አዲግራት ሰብስቴሽን አገልግሎት የሚያገኙት ውቅሮ፣ ሀውዜን፣ አፅቢ፣ ፍሬወይኒ፣ አዲግራት፣ ብዘት፣ ኢንትጮና አካባቢዎቻቸው ከዛላንበሳ በስተቀር ዳግም ተጠቃሚ መሆናቸውም ተገልጿል። ከአላማጣ ሰብስቴሽን አገልግሎት የሚያገኙት አላማጣና ማይጨው ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት መመለስ መቻሉ ተመላክቷል። ከሽረ ሰብስቴሽን አገልግሎት የሚያገኙ የሽረ፣ የሰለክላካና እንዳባጉና ከተሞች ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን ከሽረ አድዋ አክሱም ያለው መስመር የጥገና ስራው በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። ይህ ሲጠናቀቅም አድዋና አክሱም ከተሞች ዳግም አገልግሎቱን የሚያገኙ ይሆናል ነው የተባለው። ከሽረ ሰብስቴሽን አገልግሎት የሚያገኙት ሽራሮ፣ ማይሀንሳይና አዲዳእሮ ከተሞች በተዘረጋው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ በጥገና ሂደት ላይ መሆኑንም የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል። ከአድዋ ሰብስቴሽን አገልግሎት የሚያገኙት አድዋ፣ ራማ፣ ነበለት፣ እዳጋ አርቢ፣ እዳጋ ሀሙስ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የጥገና ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተገልጿል።
መቀሌን ጨምሮ በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ
አቤ ቶኪቻውየአሁኑ አመጣጤ ክርስቲያን ወዳጆቼን አንኳን ለፆመ ፍልሰታ አደረሳችሁ ለማለት እና ሙስሊም ወዳጆቼን ደግሞ የተጀመረው ዱአ ይቀጥልልን ብሎ ለማበከር ቢሆንም በልጅ አመካኝቶ ይበላል እንኩቶ እንዲል እንኮቶ ያማረው አባት እግረ መንገዴን ከመጣሁ አይቀር ኮስተር ብዬ የማነሳው አንድ ጉዳይ አለኝ።ትላንት አንድ መረጃ ለጥፌ ነበር። መረጃው በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በህቡእ የሚንቀሳቀስ አንድ ንቅናቄ ያወጣው መግለጫ ነበር። ይህ መግለጫ የሰራዊቱ አባላት ከዚህ በኋላ ህዝብ ላይ አንተኩስም እስከ መቼ ለአምባገነን መሪዎች አግዘን እኛ መሳሪያ ታጥቀን ቀበቶ እና መቀነት ብቻ የታጠቀውን ህዝብ እንደበድባለን ይሄ ነገር ነውር መሆኑን አየን ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነት ነገር ላለመፈፀም ዝግጅታችንን አጠናቀናል የሚል ነበር።ታድያ በዚህ ወሬ የተነሳ በርካታ አስተያየቶችን ተቀብያለሁ። እሰይ የኔ ወሬ አቀባይ በርታልኝ ብለው ያበረታቱኝ እንዳሉ ሆነው አንዳንድ ወዳጆች ደግሞ አንተ ከሀገር ወጥተህ እኛን ልታስጨርስ ነው የሚል ወቀሳ ሰንዝረዋል። ይህ ወቀሳ ቢያንስ በሁለት ምክንያቶች ፉርሽ መሆኑን እንደሚከተለው አስረዳለሁሀ የንቅናቄው መግለጫ የሚለው የመንግስት ግልበጣ ላድርግ አይደለም ጫካ ገብቼ ጦርነት ልክፈትም አላለም። ከዚህ በኋላ መንግስት ተኩስ ባለኝ ቁጥር ግን ህዝቤ ላይ አልተኩስም ነው ያለው። በኛ የጨዋታ ስልት ሲቀርብ ደግሞ ክላሽ እኮ ካውያ አይደለም ሰውን ያበላሻል እንጂ ልብስን አያሳምርም ስለዚህ ከእንግዲህ ፖሊስም ሆነ ሌላው የጦር ሀይል ከህዝቡ ወገን ነው እንጂ የህዝቡ ወጊ አይደለም ነው ያለው። ታድያ ይሄ እንዴት ሆኖ ነው ህዝብ ማስጨረስ የሚሆነው ጥያቄ ምልክት ጨምሩልኝለ ንቅናቄው ይቺን ብሎግ እንደሚዲያ አክብሮ መግለጫውን ላከልኝ እኔም ጉዳዩ የህዝብ ነውና ለአንባቢያኖቼ አካፈልኩ እንጂ መግለጫውን ያወጣሁት እኮ እኔ አይደለሁም። እኔ ከሀገር ብወጣም ባልወጣም ይህ ንቅናቄ መፈጠሩ አይቀርም ነበር። እንጂ እኔ ኮሎኔር አይደለሁ ጄነራል አይደለሁ አማረኝ እናንተ ሀሀ እዛ ሆነህ ልታስጨርሰን የምባለው በምን የተነሳ እንደሆነ አልገባኝም።በጥቅሉ ከዚህ በፊትም አንዳንድ ወዳጆች ከመሬት ተነስተው እዛ ሆናችሁ እኛን ልታስጨርሱ እያሉ በውጪ ያለው ኢትዮጵያዊ ላይ ወቀሳ መሰንዘር አመል ሆኖባቸዋል። አንዳንዴማ አሜሪካ እና አውሮፓ ለሚደረግ ተቃውሞ ሰልፍ ሁሉ እዛ ሆናችሁ አታስጨርሱን የሚሉ ወቀሳዎች ይመጣሉ። የሚገርመው ብዙ ግዜ እንደዚህ የሚሉት ከእኛ በላይ ለመንግስት አሳቢ ላሳር የሚሉ የመንግስታችን ደጋፊ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ናቸው። እውነቱን ለመናገር እነዚህ ወዳጆቻችን የሚደግፉት ይጨርሰናል የሚሉትን መንግስት ከሆነ በጨራሽነታቸው ወደር የሌላቸውን እንደ አተት የመሳሰሉ በሽታዎችን እንደደገፉ አውቀው ዛሬ ነገ ሳይሉ ንስሀ ሊገቡ ይገባል።እኔ በበኩሌ መንግስቴ ጨራሽ ነው ብዬ አላምንም አሁንማ እራሱ አልቋል ብለው አያሽሟጡ እኔ ስለ እርሳቸው አላወራሁም ነገር ግን ከእኔ የበለጡ የመንግስቴ ደጋፊዎች እንደሚሉት ጨራሽ እንኳ ቢሆን አንተ ውጪ ሆነህ እኛን ልታስጨርስ የሚለው ንግግር አግባ አይደለም። ለመሆኑ እኔ ወጥቻለሁ እንዴ እኔም ሆንኩ ሌላው በውጪ ሀገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ከተሰደደው እሱ ይልቅ ሀገር ውስጥ ያለው እሱ አይበልጥምን እውነት እውነት እላችኋለሁ ውጪ ካለሁት እኔ ይልቅ ሀገር ውስጥ የቀረሁት እኔ የእጥፍ እጥፍ እበልጣለሁ። እናም የማስጨርሰው ሌላ አካል የለም። የሰማሁትን ወሬ ማቀበል ማንንም የማስጨረስ አላማ የለውም። ሰዎቻችን አይምሯቸው ተነክቶ ሊጨርሱን ከተነሱ ደግሞ የማልቀው እኔው ራሴ ነኝ የገደልንም እኛ የሞትንም እኛ ያሉት ማን ነበሩለማንኛውም ክርስቲያን ወዳጆች እንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ። እንግዲህ አሁን እስላም ክርስቲያኑ ፆሙ ገጥሟል። ሁለቱም ወገኖች በየ ቤተ አምልኳቸው ከሚያደርጉት ፀሎት በተጨማሪ በየ እስር ቤቱ መከራቸውን የሚያዩ ዋና ዋና ወኪሎች አሏቸው። ለክርስቲያኑ የዋልድባ መነኮሳት ለሙስሊሙም የአንዋር ኡስታዞች በር ተቆልፎባቸው ወደ አምላክ እየጮሁ ነው።ከዚህ ስንንነሳ ዘንድሮ ፆማችን ብቻ ሳይሆን መከራችንም ገጥሟል ማለት ይቻላል። ይህም ወዳጅነታችንን ያጠነክረዋል። አንዳችን ለአንዳችን ድምፃችንን ከፍ አድርገን ከፀለይን ደግሞ ከፈጣሪ ዘንድ ተሰሚነታችን ይጨምራል። እናም እንበርታወደ በኋላ በሌላ ጨዋታ እስክንገናኝ ሰላም ይቆዩኝ ወዳጄ
እስላም ክርስቲያኑ ባንድ ሆነ ፆማቸው ከአምላክ ለመድረስ ቀጠሮ እንዳላቸው ማን ያውቃል
ዘሀበሻ እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን። የዘሀበሻ አንባቢያን ከሶስት አመት በፊት መምህር የኔሰው ገብሬን የአመቱ ምርጥ ሰው ሲሉ በ አመተ ምህረት መርጠው ነበር። ቀጠሉና በ አመተ ምህረት የአመቱ ምርጥ ሰው አድርገው የሰየሙት እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘውውን አንዷለም አራጌን ነበር። ዘንድሮም እንዲሁ ዘሀበሻ ለአንባቢዎቿ የአመቱን ምርጥ ሰው ምረጡ በሚል ባቀረበችው መጠይቅ መሰረት የተለያዩ ምርጥ ታጋይ ኢትዮጵያዉያን የአንባቢዎቻችንን ድምፅ አግኝተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ መራጮች በሰጡት ድምፅ መሰረት ለአመቱ ምርጥ ሰውነት የታጩት የሚከተሉት ናቸው። ኛ ቴዲ አፍሮኛ አበበ ገላውኛ ታማኝ በየነኛ አብርሀ ደስታኛ ጥሩነሽ ዲባባኛ መሰረት ደፋርኛ ሄኖክ አለማየሁኛ አንዷአለም አራጌኛ እስክንድር ነጋኛ አንዳርጋቸው ፅጌኛ ሌንጮ ለታኛ ጄነራል ከማል ገልቹኛ ታጋይ ሞላ አስገዶምኛ ርእዮት አለሙኛ አቡበከር አህመድኛ ዶክተር ብርሀኑ ነጋኛ ሀይለማርያም ደሳለኝኛ ካፒቴን ሀይለመድህን አበራኛ ሊያ ከበደኛ የሺዋስ አሰፋኛ በቀለ ገርባና ኦልባና ሌሊሳኛ ፕር ተካልኝ ማሞኛ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝኛ ፕሮፌሰር መስፍን ወማርያምኛ ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ በወህኒ ቤት ያረፉኛ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትኛ ዶክተር መረራ ጉዲናኛ ሀብታሙ አያሌውኛ የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሀኔአለም ቤክ ምእመናንኛ ኦባንግ ሜቶኛ ቴዎድሮስ አድሀኖምኛ በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵዮጵያውያንኛ ጃዋር መሀመድኛ ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክኛ ኤርሚያስ ለገሰኛ ዞን ኛ ሀይሌ ገብረስላሴእና ሌሎችም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ገልሰቦች ድምፅ ያግኙ ኢትዮጵያውያን ሲሆኖ ክነዚህ ውስጥ ድምፆችን ያገኘው ታዋቂው ታጋይና በአሁኑ ወቅት በእስር ቤት የሚገኘው አብርሀ ደስታ ነው። ከሱ በመቀጠል ተቀራራቢ ድምፅ ያገኘው ታጋይ በወያኔ እስር ቤት የሚገኘው አንዳርጋቸው ፅጌ ነው። ድምፆችን ያገኘው አንዳርጋቸው ፅጌ በቀጣይ ሲቀመጥ የሚሆን ድምፅ ያገኘው ደግሞ ታጋይ ሀብታሙ አያሌው ነው። የአመቱ ምርጥ ዘፋኝ የሚለውን የአንባቢዎቻችንን ክብር ያገኘው ቴዲ አፍሮ ሲሆን ድምፆችን አግኝቶ ከሌሎች አርቲድቶች የተለየ ሆኗል። ጥቂት ስለ አብርሀ ደስታ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የዘሀበሻ አንባቢያን የአመቱ ምርጥ ሰው መምህር አብርሀ ደስታ ሆነ
ሶስት መቶ አንድ ህግ የሚገባን ግን መቼ ነው ጠሚው የሟቾችን ብሄር ተናግረው እንዴት የገዳዮችን ብሄር አልተናገሩም የሚል የሆነ ነገር ካልተነፈሰ የሚሞት የሚመስለው ስንት መርህ የለሽ ሞልቷል። ገዳዮችና ጥፋተኞች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ እና ወደፊት የፍትህ ተቋማቱ ጥፋተኛውን ያሳውቃሉ ብለው ተናገሩ። ባላቸው መረጃ መሰረት የሟቾቹን ሁኔታ አሳውቀዋል፤ በብሄር፣ በሀይማኖትና በፆታ መተንተናቸው ምክንያቱ ለምን እነደሆነም ገልፀዋል። ህግ የሚያውቅ ሰው ጠሚውን ገዳዮች ማን እንደሆኑ ይናገራሉ ብሎ አይጠብቅም። ደግሞ እነዚሁ ሰወች በሰኔ ጊዜ ጠሚው በስሜት ውስጥ ሆነው የጀነራል ሰአረ ገዳይ ጠባቂው ነው ብለው በተናገሩ ጊዜ እንዴት ከምርመራ በፊት ገዳዩን ተናገሩ የፍርድ ቤት ሂደቱን የሚጣረስ ነው ሲሉ የነበሩ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ የምንናገረው ነገር ካጣን ዝም ብንል የተሻለ ነው። ገዳዮቹን የሚያውቅ ሰው ወይም ቡድን ከማውራት ለምን ፋይል ከፍቶ ፍርድ ቤት አይከስም ለግጭቱ መንስኤ የሆኑ ግለሰቦችንም ቢሆን የመንግስትን አካሄድ ወደፊት የምናየው ቢሆንም ከማውራት ይልቅ በቡድን ወይም በግለሰብ ደረጃ ገዳዮችን አልያም መንስኤወችን እስኪ ከሳችሁ አሳዩን። አጠራጣሪ መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በመግለጫቸውም ከሰሞኑ በተከሰተው ግጭት የሰማኒያ ስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል ያሉ ሲሆን፥ ከሟቾች መካከል ሰማኒያ ሁለት ወንድ፣ አራት ሴቶች መሆናቸውንም አስታውቅዋል። በብሄር ደግሞ ሀምሳ ኦሮሞ፣ ሀያ አማራ፣ ስምንት ጋሞ፣ ሁለት ስልጤ፣ አንድ ጉራጌ፣ ሁለት ሀዲያ እና አንድ አርጎባ ሲሆኑ፥ የአንዱ ሟች ብሄር እንዳልታወቀም አስታውቀዋል። በሀይማኖት ደግሞ ከሟቾቹ መካከልም አርባ ክርስቲያን ሲሆኑ፥ ስላሳ አራት ሙስሊም እና የሌላ እምነት ተከታዮች መሆናቸውንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በመግለጫቸው ያስታወቁት። ግጭቱ ብሄርንና ሀይማኖትን መሰረት በማድረግ የተፈፀመ እንደመሆኑ በገለልተኛ አካል እስካልተጣራ ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትርሩ ያቀረቡት የሟቾች የብሄርና ሀይማኖት ስብጥር በጣም አጠራጣሪ ነው። የናፈቀን መግለጫ ሳይሆን ፍትህ ነው ጥቃቱ እንዲፈፀም ከቀሰቀሱት ጀምረው ወንጀሉን እስከፈፀሙት ድረስ ሁሉም ለፍርድ መቅረብና ዋጋቸውን ማግኘት አለባቸው። የሟቾች የብሄርና የሀይማኖት ተዋፅኦ መደርደር ምንም ፋይዳ የለውም። ለፈሰሰው ደም ፤ ደም አፍሳሹ አካል ተለይቶ መቀጣት አለበት። በቀጣይነትም ህግና ስርአት ተከብሮ ስርአት አልበኝነት ሊወገድ የዜጎች ሰላምና ደህንነት ሊከበር ተጎጂዎችም ሊካሱ ይገባል ። መንግስት አለ ወይ በጣም እጅጉን የሚዘገንን ቄሮዎች አንድን ወጣት በዱላ ሲቀጠቅጡ የሚያሳይ ቪዲዮ ወዳጆች ልከወልኝ አየሁት። ወንጀለኞቹ ባለዱላዎቹ ብቻ አይደሉም። ተባባሪው እና ህግ ማስከበር ያቃተው መንግስት፤ በኦሮምኛ ተናጋሪው ህዝብ ስም ተደራጅተው አንድም ቀን ይሄን ድርጊት ያላወገዙ ጉምቱ የሚባሉ ፖለቲከኞች እና ከስርአቱ ጋር ቁርኝት የፈጠሩ ሁሉ ናቸው። ታሪክ ይፈርዳል፤ ፍትህም ተዳፍኖ አይቀርም። ያሬድ ሀይለማርያም ሶስት መቶ አንድ
አጠራጣሪ መግለጫ ጠሚው የሟቾችን ብሄር ተናግረው እንዴት የገዳዮችን ብሄር አልተናገሩም
በፋና ቴሌቭዥን ሲቀርብ የነበረውና በይዘቱ ፖለቲካዊ ሽሙጥ ላይ ያተኮረው ምን ልታዘዝ ሳምንታዊ ድራማ በተደረገበት የተቀነባበረ ዘመቻ ለመቋረጥ መገደዱን የድራማው አዘጋጆች ተናገሩ።ከድራማው ፀሀፊዎች አንዱ የሆነውና የፊልም ባለሙያ በኋይሉ ዋሴ ዋጀ እንደነገረን ያለፉትን ወራት የገጠሟቸው ፈተናዎች በተቀነባበረ መልክ ወደ ህዝብ ተመልሰው እንዳይቀርቡ እንዳደረጋቸው ይገልፃል።ድራማውን በፋይናንስ ሲደግፍ የነበረውና የድራማው ተባባሪ አዘጋጅ የሆነው አያልነህ ተሾመ ለ ቀናት ያህል በፖሊስ ተይዞ መታሰሩንና በዋስ መለቀቁን ዋዜማ ከፖሊስ ከምንጮቿ ሰምታለች። አያልነህ የታሰረው ለምን እንደሆነ ያልተገለፀለት ሲሆን ፍርድ ቤትም ሳይቀርብ ቆይቶ በዋስ መለቀቁንና በምርመራ ወቅት ምን ልታዘዝ ድራማን ማን በፋይናንስ እንደሚረዳው ጥያቄ ቀርቦለት እንደነበር ስምተናል።ምን ልታዘዝ በነፃ በተገኘ የግለሰብ መጋዘን ውስጥ ቀረፃው ይካሄድ የነበረ ሲሆን ሁለት ስፖንስሮችም ይደግፉት ነበር አዋሽ ባንክና ኖህ ሪል ስቴት። ድርጅቶቹ በሳምንት ልዩነት ድጋፋቸውን ያቋረጡ ሲሆን ሌሎች ስፖንሰሮችም ድጋፍ ለማድረግ ከመጡ በኋላ በድንገት ሀሳባቸውን ቀይረው ይመለሱ ነበር። ለሀገር የሚጠቅም የመናገር ነፃነትን የሚያበረታታ የተሻለ ስራ ሰርተን ለተመልካቹ ማሳየት እንፈልጋለን። አሁን ባለው ሁኔታ በፋና ተመልሰን እንደማንመጣ ግልፅ ሆኗል። ሌሎች የግል ሚዲያዎችም ምን ልታዘዝን ለመቀበል የሚደፍሩ አይደሉም። ስለዚህ በድረ ገፅ ወደ ተመልካች ለመድረስ ሀሳብ አለን ይላል በኋይሉ።ምን ልታዘዝ ድራማ የሀገሪቱ የሚዲያ ነፃነት ትኩሳት መለኪያ ተደርጎ ሲታይ ቆይቷል በተለያዩ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንም ሽፋን አግኝቷል።ምንጭ ዋዜማ
ምን ልታዘዝ ሳምንታዊ የቴሌቭዥን ድራማ ተቋረጠ
የስድስት ሰአሊያን ስራዎች ለእይታ ይቀርባሉ የስድስት ሰአሊያን ስራዎች ለእይታ የሚቀርቡበት ታዛ አርት ኤግዚቢሽን በዛሬው እለት ከጠዋቱ አራት ሰአት ላይ ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ በሚገኘው ታዛ ጋለሪ እንደሚከፈት ተገለፀ።የስእል ኤግዚቢሽኑ ከመጋቢት እስከ ሀያ ስድስት ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት ለአስራ አራት ቀናት፣ ከማክሰኞ እስከ እሁድ ከጠዋቱ አራት ሰአት እስከ ምሽቱ አንድ ሰአት ለእይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል። በ ታዛ አርት ኤግዚቢሽን የሰአሊ ሱራፌል አማረ፣ ንፁሰው ተረፈ፣ ለይኩን ወንድይፍራው፣ ንጋቱ ሰለሞንና ዮናታን ወንድወሰን የስነጥበብ ስራዎች እንደሚቀርቡ ታውቋል። የአሁኑ ኤግዚቢሽን ለታዛ አርት ጋለሪ ሁለተኛው ሲሆን የመጀመሪያው አዲስ አበባ ቤቴ በሚል ርእስ እንደቀረበ ተገልጿል። በየሁለት ወሩ አዳዲስ የስእል ኤግዚቢሽኖችን ለማዘጋጀት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጋለሪው በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ታዛ አርት ኤግዚቢሽን ዛሬ ይከፈታል
በኦሮሞና ሶማሌ ህዝቦች የሰላም ኮንፍረንስ ላይ በመሳተፍ ሂደት ለሁለት ቀናት በጅግጅጋ የቆየው ልኡክ ትናንት በሶስተኛ ቀን ውሎው መነሻውን ጅግጅጋ መዳረሻውን ደግሞ ደገሀቡር ለማድረግ የአንድ መቶ ስልሳ አምስት ኪሎ ሜትሮችን ጉዞ ማለዳ ሶስት ሰአት ላይ ጀምሯል። የጉዞው አላማ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን የአብሮነት መተማመን ከማረጋገጥ ባለፈ፤ የሶማሌ ክልልን ሰላምና ደህንነትን ብሎም የህዝቦችን በሰላም የመንቀሳቀስ እውነት ለማረጋገጥ ነበር። በሁለቱ ክልሎች ምክትል ርእሳነ መስተዳድሮች በተመራው በዚህ ጉዞ፤ እንደ ምንጣፍ የተዘረጋውን ለጥ ያለ ሜዳ ሰንጥቆ በሚያልፈውን ጥቁር አስፓልት ላይ በምቾት ከመጓዝ ባለፈ፤ ከአካባቢው ማህበረሰብ የሚደረግላቸው አቀባበል እውነትም ወንድማማች ህዝቦች መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ነበር። የአካባቢው ህብረተሰብ እንግዶቹን ያስደስትልኛል ያለውን ሁሉ አድርጓል፤ ገሚሱ ሰንደቅ አላማዎችን ገሚሱም እርጥብ ቅጠል በእጁ ይዞ በዘፈን፣ በጭፈራና እልልታ በታገዘው አቀባበል በየደረሱበት ከተማና ቀበሌ ቆም እያሉ የሚቀበላቸውን ህዝብ ሰላምታ እያቀረቡና እያመሰገኑ ጉዟቸውን ቀጥለዋል። በዚህ መልኩ የቀጠለው ጉዞ ከመዳረሻው ደገሀቡር ሲቃረብ፤ የደገሀቡር ህዝብ የፆታና እድሜ ልዩነት ሳያገድበው በነቂስ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አደረገ። እልልታና ጭፈራው፤ ወንድማማቻዊ መተቃቀፉ ልዩ ድባብ ሰጠው። ቤት ለእንቦሳ ብሎም እንግዶቹን ወዳዘጋጀላቸው ቦታ አሳረፋቸው አቶ ኡስማን አሊ፣ ከባሌ ዞን ራይቱ ወረዳ መጥተው በጉባኤው ከተሳተፉት መካከል አንዱ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት በሶስት ቀን ቆይታቸው የመጡበት አላማ መሳካቱን አረጋግጠዋል። ቀድሞውንም ቢሆን ሁለቱ ህዝቦች በውሀና ግጦሽ ላይ ከተመሰረተ የግለሰቦች ግጭት የዘለለ ነገር በመካከላቸው አልነበረም። ከዚህ አኳያ መድረኩ በቅርቡ የተፈጠረው ችግር የፖለቲካ ሰዎች ተግባር እንጂ የህዝብ ያለመሆኑን አረጋግጧል። ጉዞውም ቢሆን የክልሉን ህዝብ ሰውና ሰላም ወዳድነት ያሳየ ሲሆን፤ በቀጣይም የሁለቱ ህዝቦች የውይይት ሂደት እስከ ዞንና ወረዳ ሊወርድ ይገባዋል። ብለዋል። ይህን ሁነት የተመለከቱ የጉባኤው ተሳታፊዎችም ይህ መድረክና ጉዞ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን አንድነት ያደሰ፤ በቀጣይ በሚኖራቸው የጋራ አገር ግንባታ ሂደት ውስጥም የድርሻቸውን ለማበርከት ተባብረው መስራት የሚችሉበትን መተማመን የፈጠረ ስለመሆኑ መሰከሩ። ተጋባዥ እንግዶችም የሁለቱ ህዝቦች በጋራ መስራት ከራሳቸው አልፎ በአገር ሁለንተናዊ እድገት ውስጥ ተኪ የሌለው ሚና የሚያበረክት እንደመሆኑ፤ ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን ማጠንከር እንጂ ልዩነትን ለመፍጠር ለሚጥሩ አካላት ቦታ መስጠትእንደሌለባቸው መከሩ። የደገሀቡር ከተማ ነዋሪና የመድረኩ ተሳታፊ የነበረው አቶ ሙሀመድ በሽር በበኩሉ፤ ውይይቱ ጥሩና መልካም ውጤት የታየበት ነው። ሁለቱ ህዝቦችም ያላቸው አንድነታቸውን የሚያፀኑበትን እድል የሚያጠናክር ብቻም ሳይሆን ለኢትዮጵያ እድገት በጋራ ለመስራት የጋራ መተማመን የፈጠሩበትም ነው። ይህ ደግሞ ሁለቱ ህዝቦች በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ችግር እንደሌለው አመላካች ሲሆን፤ አንድነቱና መዋደዱ በፖለቲካ አመራሮች ሴራ ሊፈታ የማይችል መሆኑን ያሳየ ነው፡ ሲል የተሰማውን ስሜት ገልጿል፡ በመድረኩ መልእክት ካስተላለፉ ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች መካከል ዶክተር ሌንጮ ባቲ እንደተናገሩት፤ ምንም እንኳን ሁለቱ ህዝቦች ታሪካዊ የሆነ ሰፊ ወሰን የሚጋሩ ቢሆኑም ጠንካራ የሆነው አንድነትና ታሪካዊ ትብብራቸው በሂደቱ መጥፎ የታሪክ ገፅታ አልነበረውም።አካባቢው ሊለማ የሚችል እምቅ አቅም ያለው ብቻ ሳይሆን መልካም መሪዎችም ስላገኘ፤ ይሄ እድል ለሁለቱም ጠቃሚ መሆኑን ተገንዝቦ መስራት ያስፈልጋል። ከኬኒያ በእንግድነት በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙትና በኬንያ ያሉ የኦሮሞና ሶማሌ ህዝቦችን የአብሮነት ተሞክሮ በማንሳት መልእክት ያስተላለፉት ፋራህ ሟሊም በበኩላቸው፤ ይህ አጋጣሚ ሁለቱ ህዝቦች የነበራቸውን ታሪክ በአዲስና ጠንካራ መሰረት ላይ አኑረው የፈረጠመ አቅም ለመፍጠር መልካም አጋጣሚ ይሆንላቸዋል። ይህ አቅም ደግሞ ሁለቱ ህዝቦች ለስራቸውም ሆነ ለአገራቸው የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ፤ ቀጣናዊ ትስስሩም እንዲጠናከር የሚያስችል ነው። በመሆኑም በመድረኩ የተፈጠረውን መልካም ውጤትና መተማመን በማፅናት ይህ እድል ሳያልፋቸው በአግባቡ ሊጠቀሙበት ያስፈልጋል ብለዋል። የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ እንደተናገሩት፤ ሁለቱ ህዝቦች በባህል፣ በቋንቋና ማህበራዊ እሴት መመሳሰላቸውና አንድ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ያላቸው ጥንካሬም ሆነ ልማት የተሳሰረና የማይለያይ ነው። የኦሮሞ ህዝብ መጠንከር ለሶማሌ ህዝብ ጥንካሬ፤ የኦሮሞ ህዝብ መልማትም ለሶማሌ ህዝብ ልማት ነው። ይሄን ተገንዝቦ በመተባበር መስራት ከተቻለም ሁለቱ ህዝቦች እስከዛሬም ሆነ ዛሬ ካላቸው ትብብርና ልማት በላቀ ይጓዛሉ፤ የህዝቦቻቸውንም ተጠቃሚነት ያረጋግጣሉ። ከዚህ ባለፈም መተባበራቸው የሚፈጥርላቸው አቅም ከራሳቸው አልፎ የጋራ ቤታቸው የሆነችውን ኢትዮጵያ ለማሳደግ ተኪ የሌለው ሚናቸውን እንዲወጡ ያስችላል። መድረኩም ሆነ የጉዞ መርሀ ግብሩም ይሄንኑ ማድረግ እንደሚቻል ያሰየ፤ የነገ የአብሮነት ግስጋሴንም በመተማመን ላይ ያፀና ሆኗል። የኦሮሞና ሶማሌ ህዝቦች መካከል የገቡ ትናንሽ ሰይጣኖች ነበሩ እነርሱ አሁን ታስረዋል፤ በመሆኑም ትናንት ለተፈጠረው ችግር ይቅር ተባብሎ እነዚህ ትናንሽ ሰይጣኖች ዳግም በመካከላችን እንዳይገቡ ተግተን መስራት አለብን ሲሉ መልእክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው፤ የሁለቱ ህዝቦች መተባበር ከራሳቸው አልፎ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ለውጥ መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። ለዚህም ሲባል ሶማሊኛን በኦሮሚያ፣ ኦሮምኛን ደግሞ በሶማሌ ክልሎች እንዲማሩ በማድረግ ጭምር የሁለቱን ህዝቦች በባህልና ቋንቋ የበለጠ የማስተሳሰር ስራ መከናወን እንደሚገባው ተናግረዋል። አቶ ሽመልስ እንደሚሉት፤ ደገሀቡር የሶማሌ ህዝብ የነፃነት ትግል ማእከል ናት። ይህ ህዝብ ወድቆ መነሳትን የሚያውቅ፣ ስለ ነፃነት ጠንቅቆ የሚያውቅ፤ ስለ ነፃነትም የታገለ፤ አሁንም በተገኘው ለውጥ ውስጥ የድርሻውን እየተወጣ ያለ ነው። ሆኖም ነፃነት አንድ ቦታ ተጀምሮ በአንድ ጀንበር የሚጠናቀቅ ሳይሆን የሁልጊዜም ትግል የሚፈልግ መሆኑን በመገንዘብ፤ ወድቆ የመነሳት ልምዱን ተጠቅሞ ወንድም ከሆነው የኦሮሞ ህዝብ ጋር ሁሉም እኩል የሚገባውን ቦታ የሚያገኝባትን አገር እውን ለማድረግ ያላሰለሰ ትግሉን መቀጠል ይኖርበታል።አዲስ ዘመን ሀምሌ ስላሳ ሁለት ሺህ
የኦሮ ሶማሌ የሰላም፣ የመተማመንና የአብሮነት ጉዞ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በሀያ ዘጠኝኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ረፋድ ላይ በተካሄደ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን ሶስት ለ አሸንፏል። የወልቂጤ ከተማን የአሸናፊነት ጎሎች ዋህብ አዳምስ፣ በሀይሉ ተሻገር እና ጫላ ተሸታ አስቆጥረዋል። ክትፎዎቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን ስላሳ አምስት በማድረስ ከሀዲያ ሆሳእና ጋር ስምንትኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል። ጅማ አባ ጅፋር እና ሰበታ ከነማ ከቀናት በፊት ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዳቸውን ማረጋገጣቸው ይታወሳል። ቀትር ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ሀዲያ ሆሳእና ከወላይታ ዲቻ ሁለት አቻ ተለያይተዋል። ኡመድ ኡኩሪ የሀዲያን ጎሎች ሲያስቆጥር አናጋው ባደግ እና ፍሬዘር ካሳ የወላይታ ዲቻን የአቻነት ጎሎች አስቆጥረዋል። ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ ጅማ አባጅፋርን አሸነፈ
የፌደራል መንግስቱ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ ተጠየቀ። የፌደራል መንግስቱ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንዲገባ የጠየቀው የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ነው። ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ እንዳለው በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ ህወሀት እየፈፀመ ያለው በደል ወደ ባሰ አደጋ ሊሸጋገር ይችላል። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ እንደገለፀው የትግራይ መንግስት በወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት አካባቢ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን ከመንግስት ግምጃ ቤት መሳሪያ እያወጣ እያስታጠቃቸው ይገኛል። በምእራባዊ ዞን የወልቃይት፣ጠገዴና ቃፍታ ሁመራ አካባቢ ብቻ ሰባት የውትድርና ማሰልጠኛ ማእከላትን በመክፈትም ለገበትሬዎች የውትድርና ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛልም ብሏል ኮሚቴው። እንደ ኮሚቴው ገለፃ የአካባቢው ህዝብ በተወለደበት አካባቢ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሮ ሀብቱ፣ንብረቱ እና መሬቱ ተቀምቶ ለትግራይ ተወላጆች ተሰጥቶበታል። ማእከላዊ መንግስቱም ይህንኑ አውቆ እንዳላወቀ የሚያደርገው ዝምታ ነገ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል ነው ያለው። በወልቃይት ጠገዴ ዜጎች በግፍ ተገድለዋል ዘመዶቻቸው እርማቸውን ሳይወጡ የሟች ዘመዶቻቸውንም መቃብር ሳያውቁ ይገኛሉ። ህዝቡ አማርኛ ቋንቋውንና አማራዊ ባህሉን እንዲያጠፋ የተለያየ ተፅእኖ ይደርስበታልም ብሏል መግለጫው። ይህ ሁሉ ወታደራዊ ዝግጅት ሲደረግም ማእከላዊ መንግስቱ ዝምታን መምረጡ እግባብ አይደለም ነው ያለው። ህብረተሰቡ እየተፈፀመበት ካለው ስነልቦናዊ ሽብርና ስጋት፣ አለፍ ሲልም ሰብአዊነት የጎደለው አካላዊ ጥቃትና መበደል ነፃ እንዲሆን መንግስት እጁን እንዲያስገባም ኮሚቴው አሳስቧል። ህዝቡን በጉልበት መግዛት በፍፁም አይቻልም ያለው የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ መግለጫ የፌደራል መንግስቱ በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊቱን በማሰማራት ህወሀት በህዝብ ላይ የሚፈፅመውን ግፍ ሊከላከል ይገባል ሲል አሳስቧል።
መንግስት በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ ተጠየቀ
የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን በየአመቱ የሚያዘጋጀው የሲቲ ካፕ ውድድር ዘንድሮ ለ ኛ ጊዜ እንደሚከናወን ይጠበቃል። ፌደሬሽኑም ውድድሩን ለማከናወን ያሰበበትን ቀን ይፋ አድርጓል።የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከመጀመሩ በፊት የክልል ፌደሬሽኖች የሚያዘጋጇዋቸው የሲቲ ካፕ ውድድሮች ዘንድሮም ሲከናወኑ ከሳምንት በፊት የፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚ የሟሟያ ምርጫውን ያደረገው የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከምርጫው በሀላ ውድድሩ በደመቀ ሁኔታ እንዲከናወን ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።ሶከር ኢትዮጵያ ከፌደሬሽኑ ባገኘችው መረጃ መሰረት ከጥቅምት ሶስት ድረስ በአዲስ አበባ ስታዲየም ውድድሩ ለማከናወን ፌዴሬሽኑ እንዳሰበ የገለፀ ሲሆን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጥቅምት ይጀመራል ብሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ካስቀመጠው ቀን ጋር ተጋጭቷል። ይህንን ተከትሎ ለአዲሱ የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ሀይለየሱስ ፍስሀ ለሶከር ኢትዮጵያ ይህን ብለዋል። እኛ ያሰብነው ውድድሩን ከጥቅምት ሶስት ለማድረግ ነው። ይህንን ደግሞ የወሰንነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መስከረም ስላሳ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ጨዋታ ያደርጋል እየተባለ ስለሆነ ሜዳው ስለሚያዝብን ነው። ያለን አማራጭ ከብሄራዊ ቡድኑ ጨዋታ በኋላ ውድድራችን ማድረግ ነው። ብለዋል። በመቀጠል ከፌደሬሽኑ ጋር ድርድር አድርጋችኋል ወይ የሚለውን ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጋር ለመደራደር ሰኞ ቀጠሮ ይዘናል። በምንችለው አቅም ፌደሬሽኑ ፕሪምየር ሊጉን የሚጀምርበትን ቀን እንዲቀይር ለማሳመን እንሞክራለን። ካለሆነ እና የማይቀየር ነገር ከሌለ ግን ከጥቅምት አንድ ውድድሩን ለማከናወን እንገደዳለን ብለዋል።ተሳታፊ ክለቦችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሳተፉት ሶስቱ የአዲስ አበባ ክለቦችን መከላከያ፣ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ተጨማሪ የሀገር ውስጥ እና የምስራቅ አፍሪካ ተጋባዥ ክለቦችን በውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ተብሏል። ከተጋባዥ የሀገር ውስጥ የአዲስ አበባ ክለቦች ውስጥ ዘንድሮ ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አልያም አምና በከፍተኛው ሊግ ሲወዳደር ቆይቶ አምስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ወደ ፕሪምየር ሊግ የማደግ አላማውን ሳያሳካ የቀረው አዲስ አበባ ከተማን በውድድሩ ለማሳተፍ እንዲሁም ከክልል ተጋባዥ ክለቦች ውስጥ ደግሞ ከፋሲል ከተማ፣ከወላይታ ዲቻ፣ከጅማ አባጅፋር እና ከአዳማ ከተማ ውስጥ የተስማሙ ክለቦችን ለመጋበዝ በአጠቃላይ በስምንት ቡድኖች መካከል ውድድሩን ለማድረግ እንደታሰበ ተነግሯል።
የአአ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሲቲ ካፑን ለመጀመር ያሰበበትን ቀን አሳውቋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት ስላሳ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የሁለት ሺህ የትምህርት ዘመን ክልላዊ የስምንትኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ ሀያ ስድስት እስከ ሀያ ሰባት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ማተብ ታፈረ ዶክተር ክልል አቀፍ የስምንትኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ ሀያ ስድስት እስከ ሀያ ሰባት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ድረስ እንደሚሰጥ ተናግረዋል። ፈተናው እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በክልል ደረጃ እንደሚዘጋጅ ጠቅሰው የፈተና ጥያቄዎችም በአዲሱ የስርአተ ትምህርት ለውጥ ምክንያት ስምንትኛ ክፍል ከተማሩት ብቻ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። ወላጆች፣ መምህራንና አመራሮች በቀሪ ጊዜያት ለስምንትኛና ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በተዘጋጁበት ልክ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። ተፈታኝ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥቡ ሀምሳ በመቶ እና በላይ መሆኑን አውቀው ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ቀሪ ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል። ከሰኔ ሀያ ስድስት እስከ ሀያ ሰባት ቀን በሚሰጠው የስምንትኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሶስት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስድስት ተማሪዎች በአምስት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ሁለት ትምህርት ቤቶች እንደሚወስዱም የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
በአማራ ክልል የስምንትኛ ክፍል ፈተና ከፊታችን ሰኔ ሀያ ስድስት እስከ ሀያ ሰባት ቀን ይሰጣል
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት ሁለት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የታንዛንያ ተወካይ ማውሪዚዮ ቡሳቲ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም በታንዛኒያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍለስተኞች ወደ አገራቸው መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር አደርገዋል። አምባሳደር ሽብሩ የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ዜጎችን ወደ አገር ቤት ለመመለስ ቀደም ብሎ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል። ለዚህም የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት አምባሳደሩ ዜጎች በእስር ቤት ቆያታቸው ሰብአዊ መብታቸው መጠበቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል። አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በእስር ላይ ረዥም ጊዜ የቆዩና ለታማሚዎች ቅድሚያ መሰጠት እንዳለበትም አሳስበዋል። በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የታንዛኒያ ተወካይ ማውሪዚዮ ቡሳቲ በበኩላቸው ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የብዙ ሀገር ዜጎች በህገ ወጥ መንገድ ወደ ታንዛኒያ ገብተው በሀገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ጥረት እንደሚያደርግ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤትት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የስራ ሀላፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት ሀያ ስድስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር በትግራይ ክልል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፀደቀ። የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስትኛ አመት የስራ ዘመን ሶስትኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ አካሂዷል። በመደበኛ ስብሰባውም በኢፌዴሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ከአደጋ ለመከላከል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመቀበልና ለማፅደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ተመልክቷል። ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላም የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። የኢፌዴሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በትናትናው እለት ባደረገው ሀያ አንድኛ አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ፥ በትግራይ ብሄራዊ ክልል ውስጥ ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ፀጥታ አደጋ ላይ የሚጥሉ በተለይም የሀገርን ሏላዊነት የሚገዳደሩ፣ የፌደራል መንግስት በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ስልጣንና ሀላፊነት በክልሉ እንዳይወጣ እና ሀገሪቷን የጦር አውድማ የሚያደርጉ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎችን ጭምር በመጣስ በርካታ ህገ ወጥ ተግባራት እየተፈፀሙ በመሆኑ፤ ይህን ሁኔታ በመደበኛው የህግ ማስከበር ስርአት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የማይቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱን በመረዳት፤ በህገ መንግስቱ በተደነገገው መሰረት ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመጠበቅ ልዩ እርምጃዎችን መውሰድ የሚያስችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመደንገግ እና ተግባራዊ በማድረግ ሁኔታውን በመቆጣጠር በሀገሪቱ ሰላምና ህልውና ላይ የተጋረጠውን አደጋ መከላከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀፅ ዘጠና ሶስት አንድ ሀ መሰረት የሚከተለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን፥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተውጣጡ አባላት ያሉት ግብረሀይል በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል። ግብረሀይሉ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረሀይል ተብሎ እንደሚጠራም ተነግሯል። አዋጁ በመላው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር ተፈፃሚ የሚደረግ ሲሆን፣ እንደ አስፈላጊነቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈፃሚ ወይም ቀሪ የሚሆንባቸውን ተጨማሪ አካባቢዎችን ግብረሀይሉ በሚያወጣው በመመሪያ ይወስናል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃዎች በየጊዜው ለህብረተሰቡ የሚሰጡ ይሆናል።
ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፀደቀ
ኢሳት ዜና ሰኔ ፥ ሁለት ሺህ ሰባት በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ባለው ዘረኝነትና አስተዳደራዊ በደል በመንገፍገፍ ከሰራቱ የሚለዩት የበረራ ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መገኘቱን እንዲሁም ሙስና በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱን የአየር ሀይል ምንጮች ለኢሳት ገለፁ። በህገ ወጥ የሰው ዘውውር የአየር ሀይል አባላት የታሰሩ መሆናቸውንም ለመረዳት ተችሏል። በሁለት ሺህ ሰባት አ ም ብቻ አስር የበረራ ባለሙያዎች ስርአቱን በመክዳትና ወደ እስር ቤት በመጋዝ ከአየር ሀይሉ የተለዩ ሲሆን ፤ በአየር ሀይሉ ውስጥ የሰፈነው የአንድ ብሄር የበላይነት ወደ መንደር እየወረደ ስለመሆኑም በአስረጂነት ይጠቅሳሉ። የምስራቅ አየር ምድብ ሙሉ በሙሉ በበላይነት የሚቆጣጠሩት የትግራይ ክልል ውቅሮ ተወላጆች እንደሆኑ ተጠቅሷል። የአየር ምድብ አዛዥ ኮሎኔል አበበ ተካ፣ የዘመቻ መኮንን ኮሎኔል ሙሉ ገብሬ፣ የዊንግ አዛዥ ሻለቃ ፀጋአብ ካሳ፣ የስኳድሮን አዛዥ መቶ አለቃ አማኑኤል ወልደ ገብርኤል ሁሉም የውቅሮ ተወላጆች መሆናቸን ከአየር ሀይል ምንጭ መረዳት ተችሏል። በማእከላዊ ሆነ በአየር ምድብ ከምእራብ አየር ምድብ ውጭ በሁሉም የሀላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙት የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ፣ በተመሳሳይ ወደታች ወደ መንደር እየተሳሳሳቡ መሆኑንም ተመልክቷል። በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ከአየር ምድብ አዛዦች ብቸኛ የሌላ ብሄር ተወላጅ የምእራብ አየር ምድብ አዛዥ ኮሎኔል ይልማ መርዳሳ ብቻ መሆናቸውን መረዳት ተችሏል። በሙስና ረገድም ያለጠያቂ በዘረፋ ውስጥ የተዘፈቁት የህወሀት ታጋይ የነበሩ መሆናቸው የተገለፅ ሲሆን፣ በ ሁለት ሺህ ስድስት አም ሁለት መቶ ስልሳ የተባለ የመለማመጃ አውሮፕላን ጥገና ተብሎ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር የወጣ ሲሆን፣ ጥገናው የተካሄደበት በሀገር ቤት ባለሙያና ቁሳቁስ ቢሆንም በዘረፋው የተጠረጠሩት አልተጠየቁም። በተመሳሳይም በቀድሞ አየር ሀይል አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሞላ ሀይለማሪያም ትእዛዝ በ ሀያ ሚሊዮን ብር መለዋወጫ እንዲገዛ ተወስኖ፣ በሳምንት ጊዜ ውስጥ በኪሳራ ተመልሶ እንዲሸጥ ሲደረግ የጠየቀ ሰው አልነበረም። በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በሀላፊነት ቦታ ላይ ያሉት የህወሀት ታጋዮች፣ የመንግስት ሄሊኮፕተሮችን ሴቶችን ለማዝናናት እንደሚጠቀሙበትና፣ አብራሪዎችም ለዚህ ተግባት ተመድበው ሲሰሩ መቆየታቸውን የአየር ሀይል ምንጮቻችን ይገልፃሉ። በአሁኑ ወቅት ግንቦት ሰባትን ልትቀላቀሉ ስትሉ ተደርሶባችኋል በሚል ከታሰሩት አብራሪዎች አንዱ፣ የአንድን ባለስልጣን ወዳጅ ከደብረዘይት ወደባህርዳር፣ ከባህርዳር ወዷዋሳ እንደሚያመላልስ ለአስር ቀን ግዳጅ ተሰጥቶት ይህንኑ ሲፈፅም መቆየቱን ምንጮች ያስታውሳሉ። የትራስፖርት ሄሊኮፕተር በተለይ ወደሶማሊያ ሄደው ሲመለሱ የኮንትሮባንድ እቃ ጭነው የሚመለሱ ሲሆን፣ ንብረትነቱ የበረራ ሀላፊዎች ይሆናል። የኢትዮጵያ አየር ሀይል በላስልጣኖች ኮንትሮባንድን ጨምሮ በልዩ ልዩ ህገወጥ ተግባሮች በሙስና ሲዘፈቁ፣ በተዋረድ ያለ ግለሰብም በህገወጥ የሰዎች ማዘዋወር ድርጊት ተሳታፊ በመሆን፣ እንዷቅማቸው ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ ለኢሳት የደረሰው ማስረጃ ያስረዳል። በዚህ ድርጊት ተዋናይ ናቸው የተባሉ መቶ አለቃ ዳንኤል ገብረ መድህን፣ መቶ አለቃ ተክሌ አብርሀ የተባሉ የህወሀት አባላት፣ ከደላሎቹ ጋር የታሰሩ ቢሆንም፣ በኮሎኔል አበበ ተካ ጣልቃ ገብነት ሁለቱ በነፃ ሲለቀቁ ደላላው ሀያ አመት ተፈርዶበታል። የኢትዮጵያ አየር ሀይል ከ ምርጫ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ወዲህ ከ ስላሳ የሚበልጡ አብራሪዎች የከዱት ሲሆን፣ በ ሁለት ሺህ ሰባት አም ብቻ ከስርአቱ የተለዩትና የታሰሩት ደግሞ አስር ያህል መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። ባለፈው ታህሳስ ስላሳ አምስት ሄሊኮፕተር ይዘው ሁለት አብራሪዎችና አንድ ቴክኒሺያን መክዳታቸው ይታወቃል። ሌሎች አምስት አብራሪዎች ማለትም መቶ አለቃለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ መቶ አለቃለቃ ዳንኤል ግርማ፣ መቶ አለቃለቃ ብሩህ አጥናዬ፣ መቶ አለቃለቃ አንተነህ ታደመ ደግሞ ስርአቱን ከድታችሁ ግንቦት ሰባትን ልትቀላቀሉ አስባችኋል በሚል ታስረዋል።
የአየር ሀይል ሀላፊዎች በዘረኝነትና በሙስና ተዘፍቀዋል ተባለ
እየሩሳሌም ተስፋው በርሀኑ ተክለያሬድ እና ፍቅረማርያም አስማማው የተባሉት ታዋቂና ወጣት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወያኔ የፖለቲካ እስረኞችን በሚያጉርበትና ስቃይ በሚፈፅምበት ማእከላዊ እስር ቤት እንደሚገኙ ታውቋል።ወጣቶቹ በማእከላዊ እስር ቤት መሆናቸው በይፋ ከመታወቁ በፊት ጓደኞቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ ሳያውቁ ሰንብተዋል።ወጣቶቹ የት እንዳሉ ባልታወቀበት ሰአት አንዳንድ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ከወጣቶቹ መሰወር ጋር በተየያያዘ በፌስቡክ ላይ የሚያውቋቸውን እነርሱ የአርበኞች ግንቦት አባላት ወይንም ደጋፊዎች ያሏቸውን ግለሰቦች ሲወቅሱ ከርመዋል።እንደ ሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወቀሳ ከሆነ ኢሳት በማእከላዊ ታስረው ስለሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ወጣቶቹ አርበኞች ግንቦት ን ለመቀላቀል ሲንቀሳቀሱ ታሰሩ ብሎ መዘገብ ነበረበት ይላሉ።ኢሳት በዚህ ጉዳይ ላይ ይፋዊ መልስ ባይሰጥም የኢሳት ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ደረጀ ሀብተወልድ የሚከተለውን ብሏልይድረስ ለሰማያዊዎችከሁሉም በቅድሚያ የሰማያዊ ልጆች ተይዘው ታስረዋል በመባሉ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልፃለሁ።በመጀመሪያ የማዝነው እነዚያ የሚያሳሱ ወጣቶች በክፉዎች መዳፍ ስር በመግባታቸው ሲሆን ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ ገዥው ፓርቲ ይህን ጉዳይ ሰበብ አድርጎ በፓርቲያችሁ እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት ሊፈጥርባችሁ ይችል ይሆናል የሚል ስጋት ስላደረብኝ ነው።ምንም የአንድን አባል ፍላጎትና ውሳኔ መቆጣጠር ባትችሉምይህ እንዳለ ሆኖ ተይዘዋል የተባሉትን ልጆች አስመልክቶ በፌስቡክ ላይ እየተሰራጬ ያለው ፅሁፍ ግራ አጋብቶኛል።አንዱ ግራ ያጋባኝ ነገር አንዳንድ ሰዎች ጉዳዩን ከኢሳት ጋር ሲያያይዙት በማዬቴ ነው።ሁለተኛው ነገር ልጆቹ ለፖሊስ ምን ብለው ቃላቸውን እንደሰጡ ባልታወቀበት ሁኔታ በጉዳዩ ላይ በእርግጠኝነት መፃፍ በልጆቹ ላይ ለመመስከር ከመቸኮል በምን ይለያል ምናለ ጥቂት ትእግስት ቢኖር የሚል ነው።እሽ እናንትስ የሆነ ነገር ብትሉ ስጋታችሁን እረዳለሁ። አንዳንድ ሰዎችም ከቅንነት በመነሳት ቁጣቸውንና ንዴታቸውን መግለፃቸው የሚጠበቅ ነው። ሁላችንም ብንሆን የምናደርገው ነው።በሌላ በኩል ግን እንደነ ግርማ አይነቶቹ የፓርቲ ሽኩቻና ቂም ያለባቸው የሌሎች ድርጅት ሰዎች ይችን ምክንያት አድርገው ቂማቸውንና ጥላቻቸውን ለመወጣት ሲሉ ለልጆቹ ቅንጣት ታህል ባለማሰብ ያለምንም መረጃ በዘፈቀደ እንደመጣላቸው ጉዳዩን ሲያራግቡት ማዬት በጣም ያሳዝናል።በጥያቄ ላጠቃልልኢሳቶች ምን አጠፋን እስኪ ከላይ ከጠቀስኩት ውጪ የኢሳት ስህተት የምትሏቸውን አንድሁለት ብላችሁ ጠቁሙንና በስብሰባችን በግልፅ እንነጋገርባቸው።እንወያይባቸው።ኢሳት ስህተት ሰርቶ ከተገኘ በበኩሌ በአደባባይ ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ ነኝ።በአደባባይ ይቅርታ መጠየቅ ቀላል አይደለም። ሀላፊነትን መውሰድእዳን መሸከም ማለት ነው።ከስሜት ውጪ ሰከን ብለን እንነጋገር።ይህ በዚህ እንዳለ ወጣቶቹ በማእከላዊ እስር ቤት መሆናቸው ከታወቀ በኋላ ደግሞ ኢሳት የሚከተለውን ዜና አሰራጭቷልመጋቢት ዘጠኝ ቀን አመተ ምህረት ኢሳት ዜና የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ።ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ወጣት ፍቅረማርያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ኢሳት አረጋግጧል።ወጣቶቹ በምን ምክንያት እንደታሰሩ ለማወቅ አልተቻለም። መንግስትም እስካሁን የሰጠው ይፋ መግለጫ የለም። በሌላ በኩል ደግሞ የፓርቲው ሊመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ወደ ሰሜን አሜሪካ በማቅናት በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ውስጥለሚሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ የአንድነት የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና የሰማያዊፓርቲ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።ኢር ይልቃል በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል ምርጫው ውስጥ መቆየት ያለው ፋይዳ የሰማያዊ ፓርቲ አጠቃላይ ገፅታና እንቅስቃሴ ምን ይመስላል በሚሉት ጥያቄዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ኮሚቴው ገልጿል።የፓርቲውን የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂዎች በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ማስረዳትና በነዚህ ጉዳዮች እንዲሁም ባጠቃላይ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ዉይይት ማኪያሄድም የዝግጅቱ አንድ አካል መሆኑም በመግለጫው ተጠቅሷል።እየሩሳሌም ተስፋው በርሀኑ ተክለያሬድ እና ፍቅረማርያም አስማማው በማእከላዊ እስር ቤት ናቸው ለምንና እንዴት ለእስር እንደበቁ ከፓርቲያቸው ሰማያዊም ይሁን ካሰሯቸው ወያኔዎች ምንም የተሰማ ነገር የለም። በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ አባላቱ ሲታሰሩ ጉዳዩን ተከታትሎ ስለ ታሳሪዎቹ ሁኔታ ለህዝብና ለቤተሰቦቻቸው መግለፅ ያለበት ይመስለናል።
ሰማያዊ ፓርቲ ስለ ወጣት ታጋዮቹ መታሰር ምንም አለማለቱ እያነጋገረ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሀሳስ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ግጭት ስራ ካቆሙ አንድ መቶ ቅርንጫፎች መካከል እስካሁን ድረስ ወደ ስራ ተመልሰው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን ወጋገን ባንክ አስታውቋል። በባንኩ የሀብት ማሰባሰብና ቅርንጫፍ ባንኪንግ ዳይሬክተር መንግስቱ ታደሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ባለፉት ሁለት አመታት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ግጭት ምክንያት አንድ መቶ ቅርንጫፎች በተለያየ ጊዜ የአገልግሎት መቆራረጥ ደርሶባቸዋል። ይሁን እንጅ ባንኩ ያቋቋማቸው ኮሚቴዎች ባከናወኑት ስራ ከሰላም ስምምነቱ በፊት አራት ቅርንጫፎቹ ወደ ስራ ተመልሰው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን አስታውሰዋል። ከዚህ ባለፈም ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ደግሞ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በራያ ጥሙጋ እና አላማጣ ከተማ እንዲሁም ከትናንት ጀምሮ ደግሞ በሽረ ከተማ የሚገኙ ስድስት ቅርንጫፎች ዳግም ወደ አገልግሎት መመለሳቸውን አረጋግጠዋል። ባንኩ በሽረ ዲስትሪክት ስር በሚገኙት ሽረ፣ እንዳስላሴ፣ ምድረ ገነት፣ እዳጋ ሽረ፣ ስሁል ሽረ እና ምድረ ሀየሎም ቅርንጫፎቹ ነው ዳግም በትናንትናው እለት አገልግሎት መስጠት የጀመረው። ዳግም ስራ በጀመሩ ቅርንጫፎችም መሰረታዊ የሚባሉ የባንክ አገልግሎቶች ማለትም ገንዘብ መቀበል፣ ገንዘብ መክፈል፣ ገንዘብ ማስተላለፍ እና የውጭ ሀገር ሀዋላን ለደንበኞች ማድረስ የሀዋላ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰዋል። አገልግሎቱ ዳግም በተጀመረባቸው ቅርንጫፎች የብሄራዊ ባንክ አሰራርን በተከተለ ሁኔታ ደንበኞች ከዚህ ቀደም እንደነበረው መታወቂያ እና የባንክ ደብተር በማቅረብ ያለምንም ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ አገልግሎቱን እያገኙ መሆኑንም አመላክተዋል። በአክሱም እና አድዋ ከተሞች ደግሞ በቅርቡ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቃቸውንም ነው የተናገሩት። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ታሀሳስ አስር ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም እንዲሁም አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ደግሞ ታሀሳስ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በሽረ እንዳ ስላሴ እና አካባቢው ዳግም አገልግሎት እንደጀመሩ መናገራቸው ይታወሳል። በዮሀንስ ደርበው
ወጋገን ባንክ ሽረ ከተማን ጨምሮ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ቅርንጫፎቹ ዳግም አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት ስድስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የስራና ክሀሎት ሚኒስትር ሙፈሪሀት ካሚል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እንደ ተቋም በጋራ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ። በውይይታቸውም በክልሉ ያለውን ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት በማልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በክሀሎት፣ ቴክኖሎጂ ልማት፣ በስራ እድል ፈጠራና ተያያዥ ጉዳዮች ትኩረት በሚሹ ስራዎች ላይ መምከራቸውን ሚኒስትሯ በማሀበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልፀዋል። በዚህም የእሴት ሰንሰለትን መሰረት ያደረገው ክሀሎት መር የስራ እድል ፈጠራ አቅጣጫችን እሴት አካይ ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልገው እና ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ወደ ህብረተሰቡ ማድረስ እንደሚያስፈልግ የጋራ ሀሳብ ይዘናል ብለዋል። እንዲሁም በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አለም አቀፍ እውቅና ባገኘው የብየዳ ማእከል በልዩ የክረምት ወራት የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ እና የፈጠራ ሀሳቦች ማሻሻያ መርሀ ግብር እየተሰሩ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን መጎብኘታቸውንም አመላክተዋል። በጉብኝታቸውም በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ፀጋዎችን በአግባቡ አልምቶ ከመጠቀም ባለፈ ተኪ ምርቶች ላይ ሀገራዊ አቅም ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ ጥረቶች እና ውጤቶች አበረታች መሆናቸውን ተመልክተናል ብለዋል። አቶ አሻድሊ ከሚኒስቴሩ ጋር በረጋራ ለመስራት ላሰዩት ቁርጠኝነትም ሚኒስትሯ አመስግነዋል።
ሚኒስቴሩ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋር በጋራ በሚሰራባቸው ዘርፎች ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ኢትዮ ቴሌኮም በድሬዳዋ የአምስተኛው ትውልድ አምስትጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎትን አስጀመረ። የአምስትጂ የሞባይል ኔትወርክን በማስፋፋት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ኢትዮ ቴሌኮም እየተጋ እንደሚገኝ ተገልጿል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ አገልግሎቱን በድሬዳዋ ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት፤ በአዲስ ፍጥነትና ምቾት የሰው ልጆችን አኗኗር ለማቅለል የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እየተተገበሩ ነው። አምስትጂ ከመደበኛው የስልክ ግንኙነት ባሻገር በርካታ መረጃዎችን በፍጥነት ለማስተላለፍ እንደሚያስችል ገልፀው፤ የአምስትጂ ቴክኖሎጂ ችግር ፈቺ በመሆኑ ምርታማነትን እንደሚጨምር ተናግረዋል። የስራ እድል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አመልክተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትልከንቲባ አቶ ሀርቢህ ቡኽ በበኩላቸው ድሬዳዋ የኢንደስትሪ፣ የንግድና የስልጣኔ መግቢያ በር እንደመሆኗ አምስትጂ ቴክኖሎጂ የላቀ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ድሬዳዋ ከአራት መቶ ሀምሳ በላይ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙባት በመሆኑ ፈጣኑ ኔትወርክ ስራን ለማቅለል ያግዛል ብለዋል። አምስትጂ ኔትወርክ ከድሬዳዋ ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ፣ አዳማና ጂግጂጋ ከተሞች በይፋ የተጀመረ ሲሆን በአጭር ጊዜ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍራት መቻሉ በእለቱ ተገልጿል። በእዮናዳብ አንዱአለም ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ ኢንስታግራም፦ ቲክቶክ፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
በድሬዳዋ አምስትጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በይፋ ጀመረ
ታሀሳስ ፳፯ ሀያ ሰባት ቀን ፳፻፱ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና በደቡብ ኦሞ ዞን የሀመር ወጣቶች በጥር ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት የጀመሩትን ተቃውሞና ከመንግስት ታጣቂ ሀይሎች ጋር የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በዞኑ የሚንቀሳቀሰውን የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ሀብረት ኦህዲሀ አመራሮች ለመወንጀል የዞኑ ፀጥታና ደህንነት ሹምክትል ሀላፊ አቶ አልአዛር ቶይሳ የተጀመረው የሀሰት ውንጀላና እስራት እስከዛሬ እንደቀጠለ መሆኑን የድርጅቱ አባላትና የታሳሪዎች ቤተሰቦች አስታወቁ። አቶ አልአዛር ባለፈው አመት ፣ሚያዚያ ሁለት ሺህ ስምንት አም፣ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ሀብረት ኦህዲሀ ምክትል ሊቀ መንበር መምህር አለማዬሁ መኮንን ፣ የድርጅቱ አባል አቶ አብረሀም ብዙነህ እና የከተማዋን ነዋሪ አቶ ስለሺ ጌታቸው በሽብር ወንጀል እጠረጥራቸዋለሁ በማለት ከቤተሰባቸውና መኖሪያቸው ከአምስት መቶ ኪ ሜትር በላይ ተወስደው በሀዋሳ እንዲታሰሩ አድርገው የነበረ ቢሆንም ታሳሪዎቹ ምንም ጥፋት ሳይገኝባቸው በነፃ ተለቀዋል። አቶ አልአዛር በድጋሚ በዚህ አመት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጠቀም ለክልሉ ኮማንድ ፖስት መሰረተ ቢስ መረጃ በመስጠት ከጂንካ ከተማ አልፈው የወረዳ ነዋሪዎችን ጨምሮ ከህዳር አራት ሁለት ሺህ ዘጠኝ ጀምሮ አስራ አንድ የዞኑን ነዋሪዎች አሳስረዋል። የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ሀብረት ኦህዲሀ ምክትል ሊቀ መንበር መምህር አለማዬሁ መኮንን፣ እንዲሁም የዞኑ ስራ አስፈፃሚ አባል ወጣት ዳዊት ታመነ የእያንዳንዳቸው ቤት በ ታጣቂዎች ተፈትሾ ምንም ባልተገኘበት፣ በመቀጠልም የዞኑን ምክትልሰብሳቢ መምህር እንድሪስ መናን እና የስራ አስፈፃሚ አባል ወጣት መሀመድ ጀማል ጨምረው በማሰር የድርጅቱን እንቅስቃሴ እንዲገታ አድርገዋል። እስከዛሬ ድረስ ታሳሪዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታሰራቸው ከመነገሩ በቀር ይህን አደረጋችሁ ወይም በዚህ የወንጀል ድርጊት ተጠረጠራችሁ ሳይባሉ በዞኑ ፖሊስ መምሪያ በእስር ላይ ይገኛሉ ። በታህሳስ ሀያ አራት ዘጠኝ ሁለት ከማእከል የመጡ የኮማንድ ፖስት አጣሪዎች የእነ አቶ አለማዬሁን ጉዳይ ለማጣራት ከዞኑ መድረሳቸውና ስለጉዳዩ ታሳሪዎችን ማነጋገር መጀመራቸው ታውቋል። ይሁን እንጅ አቶ አለማየሁ በተያዙበት ወቅት ከቤታቸው ተወስዶ ከአንድ ወር ተኩል በላይ በአቶ አላዛር እጅ የሚገኘውን ላፕቶፕ ኮምፑዩተር መረጃ እንፈልጋለን በማለት የኢሜይል እና ፌስቡክ አድራሻቸውን ተቀብለው አቶ አለማዬሁ ባሉበት ኮምፒዩተሩን ከከፈቱ በኋላ ባትሪው ደክሟልና ከቤት አስመጣ ብለው አስወጥተዋቸው ፍላሽ ዲስክ በመጠቀም በኮምፒተሩ ውስጥ ያሉትን የግል የሙያም ሆነ ሌሎች መረጃዎች ሁሉ ገልብጠው ወስዷል። ታህሳስ ሀያ ስድስት፣ ሁለት ሺህ ዘጠኝ አም ደግሞ ከኮምፒዩተር መረጃዎችን ሲገለብጡ በድንገት ያገኟቸውን አቶ አላዛርን፣ በዚህ መልክ በተቀነባበረ ሴራ የማላውቀው መረጃ ተገኘ ተብሎ ለመወንጀል የተደረገውን በህግ ፊት እንደማልቀበለው ይታወቅልኝ በማለት አቶ አለማየሁ ተናግረዋል። ይህን የተቀነባበረ መረጃ ሲፈጥሩና በኮምፒዩተር ላይ ሺጭኑ የዞኑ ወንጀል ምርመራ ክፍል አባላት ኢንስፐክተር በሀይሉ ተካ፣ ኢንስፐክተር ትእዛዙ ምስክር እና ኮንስታብል መልካሙ በቦታው ሆነው ሁኔታውን እንደተመለከቱም የመረጃ ምንጮቹ ገልፀዋል።
በጂንካ የፖለቲካ እስረኞችን ለመወንጀል የፈጠራ ማስረጃዎች እየተሰበሰቡ ነው
የተሿሚዎች መስፈርት ብቃት ልምድና ኢትዮጵያዊነት ነው ቀደም ሲል የካቢኔ አባላት የነበሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባላቱን ወደ ዝቅያደረገ ሲሆን አዳዲስ የካቢኔው አባላትም በምከንቲባው አቅራቢነት በምክር ቤቱ ተሾመዋል። አስራ ስምንቱ የካቢኔ አባላትም የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አፈጉባኤ የነበሩት ዶክተር ታቦር ገመድህን የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ረፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ኢር ሰናይት ዳምጠው የቤቶች ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የጥቃቅን እና አነስተኛ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ የጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ደረጀ ፈቃዱ የፕላን ኮሚሽን ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።በተጨማሪም ኢር ሽመልስ እሸቱ የመሬት ልማትና ማናጅመንት ቢሮ ሀላፊ ኢር ዮናስ አያሌው የኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘውዴ ቀፀላ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ አቶ ሺሰማ ገስላሴ የገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮኤ ኖፎላ የፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ፍሬህይወት ተፈራ የፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ጀማል ጀምበር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልፈታ ዮሱፍ የንግድ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ አልማዝ አብረሀ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ፍሬህይወት ገህይወት የፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ኢር ኤርሚያስ ኪሮስ የኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም አቶ አሰፋ ዮሀንስ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሀላፊዎች ሆነው መሾማቸው ታውቋል።ወይዘሮ አበበች ነጋሽ የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ በመሆን ተመርጠዋል። ተሿሚዎች የተመረጡበት መስፈርት ብቃት ልምድና ኢትዮጵያዊነት መሆኑን ምከንቲባ ኢር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላትን ሾመ
ከሶማሊያ አቻው ጋር ነገ በአዲስ አበባ ስታድየም በአፍሪካ ዞን የኦሊምፒክ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታውን የሚያደርገው ከሀያ ሶስት አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል።ከጥቅምት ሀያ አንድ ጀምሮ ዝግጅቱን አጠናክሮ እየሰራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከሀያ ሶስት አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ከሱዳኑ አል ሂላል ኦቢዬድ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ በማድረግ ሁለት በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል።የቡድኑን አቅም ለማሳደግ በማሰብ ከዋናው ብሄራዊ ቡድን አማኑኤል ገብረ ሚካኤል እና ተመስገን ካስትሮ ተካተው የነበረ ሲሆን በተጨማሪም ከንአን ማርክነህ ከባለፈው እሁድ ጀምሮ ከቡድኑ ጋር ተቀላቅሎ ልምምድ መስራት መጀመሩን ለማወቅ ችለናል።በዛሬው ጠዋት ሶስት ስላሳ በጀመረው የመጨረሻ ልምምድ ጊዜም ሁሉም የብሄራዊ ቡድኑ አባላት በሙሉ ጤንነት ላይ በመሆን ቀለል ያሉ ልምምዶችን ሰርተዋል። ከዋና ብሄራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገላቸው አማኑኤል ገብረ ሚካኤል ፣ ተመስገን ካስትሮ እና ከንአን ማርክነህ ደግሞ ዛሬ እረፍት ተሰጥቷቸው በልምምድ ወቅት ያልነበሩ ቢሆንም ለነገው ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸው ተነግሮናል።ነገ በአስር አዲስ አበባ ስታድየም የሚደረገውን የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጨዋታ ቱኒዚያዊያኑ ጉዊራት ሀይተም ዋና ፣ ረምዚ ሄርች ረዳት እና ኸሊል ሀሰን ረዳት የሚመሩት ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ የስቴዲየም የተመልካች መግቢያ ዋጋ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መደበኛ የመግቢያ ዋጋ መሰረት እንደሆነ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።
ከሀያ ሶስት አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን አከናወነ
በኮሮና ቫይረስ ኮቪድ በሽታ የተያዙ አራት ኢትዮጵያውያን በመገኘታቸው በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሀያ ስድስት መድረሱን የኢትዮጵያ ሀብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መጋቢት ሀያ ሁለት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ኢንስቲትዩቱ በመግለጫው የታማሚዎችን ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከተለው ገልፆታል። የኢትዮጵያ የሀብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መረጃውን እስካዘጋጀበት መጋቢት ሀያ ሁለት እኩለ ቀን ድረስ በአጠቃላይ አንድ ሺህ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረጉን፣ በተለይ በሀያ አራት ሰአት ውስጥ ባካሄደው ስልሳ ስድስት የላቦራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ አራት ሰዎች መኖራቸውን አረጋገግጧል። በዚህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ሀያ ስድስት መድረሱን ገልፆ፣ ኛዋ ታማሚ ግን ሶስት ጊዜ በተደረገላት ተደጋጋሚ የላቦራቶሪ ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆኗንም አስታውቋል። እንደ ኢንስቲትዩቱ መግለጫ፣ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት የስላሳ አመትና የስላሳ ስድስት አመት ኢትዮጵያውያን፣ በተመሳሳይ በረራ ከዱባይ መጋቢት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ወደ አገር እንደገቡ በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን፣ የበሽታውን ምልክት ታይቶባቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሶስተኛዋ ታማሚ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዋ ባለስልሳ አመት እድሜ ሲሆኑ መጋቢት ስድስት ቀን ከፈረንሳይ የተመለሱና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ የበሽታውን ምልክት በማሳየታቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው በተደረገላቸው የላቦራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አራተኛው በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ የአርባ ሁለት አመት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ፣ የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ አስቀድሞ መጋቢት ዘጠኝ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ከአውስትራሊያ አዲስ አበባ እንዲሁም በማግስቱ መጋቢት አስር ቀን ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ተጉዟል። ግለሰቡ የበሽታው ምልክት በማሳየቱ በላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። በአሁን ሰአት ግለሰቡ በድሬዳዋ የለይቶ ህክምና መስጫ ማእከል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል። አራቱም ታማሚዎች በለይቶ ህክምና መስጫ ማእከል እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የጠቆመው ኢንስቲትዩቱ፣ በአሁኑ ወቅት በለይቶ ህክምና መስጫ ማእከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ ሀያ አንድ ታማሚዎች መኖራቸውን፣ ሁለት ታማሚዎች በፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጿል። ሁለት ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ ቢያገግሙም ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ያለው መግለጫው ታማሚዎች የነበሩ ሁለት የውጭ አገር ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን አስታውሷል። ሀብረተሰቡ የበሽታውን ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት የሚተላለፉ እርምጃዎችን ትኩረት በመስጠት እንዲተገበር ማሳሰቢያ በመስጠትም ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር ስምንት ሺህ ሶስት መቶ ስላሳ አምስት፣ ወይም በዘጠኝ መቶ ሀምሳ ሁለት ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር ቢሊዮን ሰማኒያ ሁለት ሚሊዮን ሰባ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ስድስት ወይም በኢሜይል አድራሻ በመጠቀም ማግኘት ይቻላል ብሏል። በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ያለበት የመጀመሪያው ሰው የተገኘው መጋቢት አራት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት መሆኑ ይታወሳል። አለም አቀፍ መረጃ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በድረ ገፁ እስከ መጋቢት ሀያ ሁለት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ምሽት አንድ ስላሳ ሰአት ድረስ ያሰፈረው መረጃ በአለም ዙርያ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ስምንት መቶ ዘጠኝ ስድስት መቶ ስምንት ሰዎች መካከል አሜሪካ አንድ መቶ ስልሳ አራት ሰባት መቶ ፣ ጣሊያን አንድ መቶ አንድ ሰባት መቶ ስላሳ ዘጠኝ፣ ስፔን ዘጠና አራት አራት መቶ ቻይና ሰማኒያ ሁለት ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሲያስመዘግቡ፣ ከአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገበችው ደቡብ አፍሪካ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሀያ ስድስት ስትሆን፣ ግብፅ ስድስት መቶ ሀምሳ ስድስት፣ ከምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ደግሞ ሯንዳ ሰባ፣ ኬንያ ሀምሳ፣ ዛምቢያ ስላሳ አምስት፣ ኡጋንዳ ስላሳ ሶስት፣ ኢትዮጵያ ሀያ ስድስት፣ ታንዛንያ ፣ ጅቡቲ ፣ ኤርትራ ፣ ሶማሊያ ሶስት፣ ሱዳን ሰባት አስመዝግበዋል። በአለም የሟቾች ቁጥር ስላሳ ዘጠኝ አምስት መቶ አርባ አምስት ሲሆን ያገገሙት ደግሞ አንድ መቶ ሰባ ሁለት ስምንት መቶ ስልሳ ዘጠኝ መሆኑ ታውቋል። መንግስታዊ ማሳሰቢያ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሀብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መንግስት የበሽታውን ስርጭት ለመግታትና ለመቆጣጠር ተገቢውን እርምጃ እየወሰደ መሆኑን እያረጋገጡ፣ ማሀበረሰቡ የሚከተሉትን የመከላከያ መንገዶችን ችላ ሳይል እና ሳይደናገጥ ተግባር ላይ በማዋል፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የበኩሉን እንዲወጣ ያሳስባል። ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል መራቅ እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን አይንኩ ከሰዎች ጋር አይጨባበጡ፣ እጅን በንፁህ ውሀና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣ ሰዎች ወደሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣ በሚያነጥሱበትና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣ በስራ ቦታ፣ በትራንስፖርት እና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣ መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገርና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ሀያ ስድስት ደረሱ
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኛ እና ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሲደረጉ አራት ጨዋታዎች ሽግሽግ ተደርጎባቸዋል። ኛ ሳምንትየአፍሪካ ሀብረት የመሪዎች ጉባኤን ተከትሎ ወደ ሀሙስ በተሸጋገረው የኢትዮጵያ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ ጨዋታ ኛ ሳምንት ምክንያት ሁለቱ ቡድኖች በ ኛ ሳምንት የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ወደ ሰኞ ተሸጋግሮላቸዋል። በዚህም መሰረት ሰበታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና ሰኞ የካቲት ዘጠኝ አአ ስታዲየም ላይ በአስር የሚጫወቱ ሲሆን ወልቂጤ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና ወልቂጤ ላይ በተመሳሳይ ሰኞ የካቲት ዘጠኝ ወልቂጤ ላይ ይጫወታሉ።የ ኛ ሳምንት ሙሉ መርሀ ግብርቅዳሜ የካቲት ሰባ ዘጠኝ መቐለ ሰባ እንደርታ ከ ሀዋሳ ከተማእሁድ የካቲት ሰማኒያ ዘጠኝ ጅማ አባ ጅፋር ከ ድሬዳዋ ከተማ ዘጠኝ ስሁል ሽረ ከ ሀዲያ ሆሳእና ዘጠኝ አዳማ ከተማ ከ ወልዋሎ ዘጠኝ ወላይታ ድቻ ከ ባህር ዳር ከተማ ዘጠኝ ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስሰኞ የካቲት ዘጠና ዘጠኝ ወልቂጤ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና አስር ሰበታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና ኛ ሳምንትበዚህም ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ላይ ሽግሽግ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ሁለተኛ የሜዳ ቅጣቱን ተግባራዊ የሚያደርገው ሀዲያ ሆሳእና ከጅማ አባ ጅፋር የሚያደርገው ጨዋታ ሀዋሳ ላይ አርብ የካቲት ሲደረግ ሲዳማ ቡና ከሰበታ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ቅዳሜ የካቲት የሚከናወን ይሆናል።የ ኛ ሳምንት ሙሉ መርሀ ግብርአርብ የካቲት አንድ መቶ ስላሳ ዘጠኝ ሀዲያ ሆሳእና ከ ጅማ አባ ጅፋር ሀዋሳ ቅዳሜ የካቲት አንድ መቶ አርባ ዘጠኝ ሲዳማ ቡና ከ ሰበታ ከተማ ዘጠኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማእሁድ የካቲት አንድ መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ወልዋሎ ከ ወልቂጤ ከተማ አዲግራት ዘጠኝ ኢትዮጵያ ቡና ከ ወላይታ ድቻ ዘጠኝ ሀዋሳ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ ዘጠኝ ባህር ዳር ከተማ ከ ስሁል ሽረ ዘጠኝ ድሬዳዋ ከተማ ከ መቐለ ሰባ እንደርታ ሶከር ኢትዮጵያ
በቀጣይ ሳምንታት የሚደረጉ አራት ጨዋታዎች ላይ ሽግሽግ ተደርጓል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በሏላዊት ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ኢፍትሀዊ አካሄድ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ሲል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለፀ። ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ እቆማለሁ፤ ድምፄን አሰማለሁ በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ሰልፍ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አንዳንድ የውጭ ሀይሎች በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የያዙትን አቋም በፅኑ አውግዟል። የተባበሩት መንግስታትና የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ ለመጣል የያዙት አቋም የሀገሪቱን ንፁሀን የሚጎዳ ከመሆኑም በላይ በሏላዊት ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ሲል ምክር ቤቱ አውግዟል። እነዚህ የውጭ ሀሎች ከዚህ አቋማቸው ታርመው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት ከኢትዮጵያህዝብ ጎን እንዲቆሙ ሲል ምክር ቤቱ ጠይቋል። በአፍሪካ ህብረት የተጀመረውን የሰላም ውይይት ከግቡ ለማድረስ የበኩላቸውን እንዲወጡም ነው ምክር ቤቱ የጠየቀው። ነገ እና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልልሎች ለኢትዮጵያ እቆማለሁ፤ ድምፄን አሰማለሁ በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው ሰልፍ ኢትዮጵያውያን እንዲሳተፉ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ተቀባይነት የለውም ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለፀ
ዘሀበሻ ዘገባውን በድምፅና በምስል ለማየት እዚህ ይጫኑ የትውልድ ሀገሩን ኢትዮጵያ በብዙ ሺህ ማይል ርቀት ጥሎ በሰሜን አሜሪካ ቴነሲ ግዛት ኑሮውን ያደረገው የ አመቱ ጎልማሳ ጌትም ሽመልስ ደምሴ ህይወቱን ለማሸነፍና ቤተሰቡን ለመርዳት አይቤክስ የተባለ ሬስቶራንት ከፍቶ ሲሰራ ነበር። ቅዳሜ ለ እሁድ አጥቢያ ግጥም ሬስቶራንቱን እኩለ ሌሎት አካባቢ እየዘጋ ባለበት ሰአት የአይን ምስክር እንዳሉት ጥቁር በጥቁር የለበሰና ማስክ ያጠለቀ ሰው ሬስቶራንቱ ውስጥ በመግባት ተኮሰበት። ከአንድ ጊዜ በላይ እንደሆነ በተገመተ ተኩስ ሰውነቱ የተመታው ግጥም ህይወቱ ማለፉን የናሽብል ቴነሲ ፖሊስ አስታውቋል። እንደ አይን ምስክር ገለፃ የሬስቶራንቱ ባለቤት ላይ ተኩሶ የገደለው ሰው ቁመቱ ጫማ በ ኢንች ይሆናል። እንደዚሁም ቆዳው ጠየም ያለ እንደሆነ ተናግረዋል። ጥቁር ጅንስ እና ጥቁር ረጅም እጅጌ ሙሉ ሸሚዝ ለብሷል። ፖሊስ በምርመራ ላይ ያለ መሆኑን አስታውቋል። እንዲሁም ጥቁማ መስጠት የሚፈልግ ካለም እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል። ጥቆማ መስጠት ለምትፈልጉ የስልክ ቁጥሩ ነው።
በአሜሪካ ቴነሲ ግዛት የሚኖረው ኢትዮጵያውዊው የአይቤክስ የሬስቶራንት ባለቤት ህይወቱ በሰው እጅ አለፈች
አገሪቱ በአሁኑ ወቅት የምትገኝበትን የእድገት ደረጃ የሚመጥንና የሚያስተናግድ የአመራር ብቃትና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ አዲስ ምእራፍ የተከፈተ መሆኑን የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አስታወቀ ።የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ስላሳ አምስትኛውን የምስረታ በአል አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በመላ አገሪቱና በአማራ ክልል ቁልፍ የለውጥ መስኮች የሆኑትን የድርጅትን፣የመንግስትንና የህዝብን አቅሞችን በተደራጀ ሁኔታ መምራት የሚችል ብቃትና ቁርጠኝነት የተላበሰ የአመራር አዲስ ምእራፍ መከፈቱ አስፈላጊ መሆኑን ተገልጿል።ለወደፊቱ ከተደቀኑት ፈተናዎችና ችግሮች መካከል የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር ዋነኛው መሆኑን የጠቆመው መግለጫው በተደራጀ ንቅናቄ በመምራት ብአዴን በአኩሪ የትግል ታሪክ ታጅቦ እየተራመደ ስላሳ አምስትኛ አመቱን እያከበረ እንደሚገኝ መግለጫው አክሎ ገልጿል ።ብአዴን የህዝቦችን ዴሞክራሲያዊ አንድነት በማጎልበት ያበረከተውንና እያበረከተ ያለውን ጉልህ አስተዋፅኦ ወደ ላቀ ደረጃ በማሳደግ አገራችን የነደፈችውን የሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ለመተግበር መላው ህብረተሰብ እንዲረባረብ በሚያደርግ አግባብ በመላ አገሪቱ በመከበር ላይ መሆኑን ጨምሮ አመልክቷል ።በአሉ ብአዴንን የትግል ታሪክ ለህዝባዊ አላማ በፅናት መስዋእትነት የከፈሉ ታጋዮችን አኩሪ ገድል በመዘከር ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ ትዉልድ ድርጅቱን ለድል ያበቁትን አስተሳሰቦች፣ በትግል ሂደት የገነባቸዉን እሴቶች፣ የገጠሙትን ፈተናዎች እንዲያውቃቸው እና የፀረ ድህነት ትግሉን በድል ለመወጣት በመሳሪያነት እንዲጠቀምባቸው መልእክት በሚያስተላልፍ መንገድ እንዲከበር እየተደረገ ነው ብሏል ።ብአዴን በመግለጫው ለክቡር ህዝባዊ አላማ መስዋእት የሆኑ ጀግኖች የከፈሉት ህይወትና የህዝቡ የዘመናት ተጋድሎ ከንቱ ሳይቀር አሁን የምንመለከተውን የለውጥና የእድገት ፍሬ አስገኝቷል ብሏል ።በዚህ ሂደት ውስጥም የአማራ ክልል ህዝቦችም ሆኑ የአገራችን ህዝቦች በመስዋእትነት ያገኙትን ድል አስጠብቀው እንዲዘልቁ ብአዴን የበኩሉን አኩሪ የአመራር ተልእኮውን መወጣቱን አንስቷል ።ባለፉት አመታት ለተመዘገቡት ለውጦች ግብርና የላቀ ድርሻ የነበረው ከመሆኑም ባሻገር ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ለሚደረገው ሽግግር ሁነኛ መሰረት መገንባት መጀመሩን ጠቅሷል ።በከተሞች በጥቃቅንና አነስተኛ ልማት መስክ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ለማከናወን ጥረት ተደርጓል ያለው መግለጫው ፤ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት የተጀመሩ ተግባራት ከመኖራቸው ባሻገር ለቀጣይ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ አስረድቷል ።በብዝሀነት፣ በመቻቻልና በመከባበር ላይ ለተመሰረተ አንድነት እንቅፋት የሆኑት ትምክህት፣ አክራሪነትና መሰል ኋላቀር አስተሳሰቦችም በሚፈለገው ደረጃ አልተወገዱም ብሏል መግለጫው ።የጉልበት እና የመሬት ምርታማነትም ማደግ በሚገባው ደረጃ እንዲያድግ ገና ብዙ ስራ ይጠይቃል ያለው መግለጫው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራችንም የላቀ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው የልማት መስኮች በሚፈለገው ደረጃ እንዳልተሟላም አመልክቷል ።የአየር ፀባይ ለውጥና የድርቅ አደጋ አሁንም በህብረተሰባችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳረፈ በመሆኑ በድርቅ ተጠቂነትን ለመቀነስ የሚያስችል የመስኖና እርጥበት እቀባ ልማትን ማጠናከር እንደሚገባም አስረድቷል ።የለውጥ እንቅፋት የሆኑትን ፀረ ዴሞክራሲንና አድርባይነትን እንዲሁም የቁርጠኝነት ማነስ ችግሮችን በማስወገድ የድርጅቱን አኩሪ እሴቶች የሆኑት ህዝባዊ ወገንተኛነት፣ የአላማ ፅናት፣ ራስን በራስማረም፣ ዴሞክራሲያዊ ባህሪን ማጠናከር፣ የዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት አስተሳሰብን ማሳደግ በትኩረት የሚረባረብባቸው መስኮች ናቸው ብሏል።በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የግብርናን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ፣ የቀላልና የመካከለኛ ኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን፣ ብሎም በመልካም አስተዳደር መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣትና የህዝባችንን ፍላጎት ለማርካት አሁንም ሙያዊ ችሎታውንና አገልግሎቱን በማበርከት በላቀ የዝግጁነት መንፈስ ለውጥ ለማምጣት እንዲረባረብ ብአዴን ጥሪውንአቅርቧል።ኢህዴን ብአዴን ብዙ የትግል ሀይሎች ተስፋ በቆረጡበት፣ አልችልም ባይነትና ጨለምተኝነት በሰፈነበት አስቸጋሪ ነባራዊና ህሊናዊ ሁኔታ ውስጥ በአንንበረከክም መንፈስ በጥቂት ቆራጥ የህዝብ ልጆች በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሶስት አመተ ምህረት የተመሰረተ፣ ህዝቡን በብቃት በመምራት ለድል ያበቃና ደማቅ ታሪኩንም የፃፈ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል ።
የአመራር ብቃትና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ አዲስ ምእራፍን መከፈቱን ብአዴን አስታወቀ
አሜሪካ በሳኡዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ወታደሮቿን ልትልክ መሆኑን አስታወቀች።የመከላከያ ሚኒስቴር ፀሀፊ የሆኑት ማርክ ኤስፐር፤ በሳኡዲ የሚሰማራው ጦር መከላከል ላይ ያተኮረ ተልእኮ ሊሰጠው እንደሚችል ለጋዜጠኞች ጠቁመዋል። ምን ያህል ወታደር እንደሚሰማራ ግን ያሉት ነገር የለም።በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቱ አማፂያን ባለፈው ሳምንት በሳኡዲ ሁለት የነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ ለደረሰው ጥቃት ሀላፊነቱን እንወስዳለን ብለዋል። ሆኖም አሜሪካም ሆነች ሳኡዲ አረቢያ ለጥቃቱ ተጠያቂ ያደረጉት ኢራንን ነው።አርብ እለት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ወታደራዊ እሰጥ አገባ ውስጥ ላለመግባት በሚል ከፍተኛ የሆነ ማእቀብ ሊጣል እንደሚችል ተናግረው እንደነበር የሚታወስ ነው።አዲሱ ማእቀብ የሚያነጣጥረው የኢራን ማእከላዊ ባንክንና ሏላዊ የሀብት ፈንድን መሆኑን ትራምፕ ተናግረዋል።ሚስተር ኤስፐር መግለጫ የሰጡት የጥምር ጦሩ የበላይ ሀላፊ ከሆኑት ጄነራል ጆሴፍ ደንፎርድ ጁኒየር ጋር ነው።ሳኡዲ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን ድጋፍ ጠይቀዋል ብለዋል ሚስተር ኤስፐር። የሚላከው ሀይል የአየርና የሚሳኤል መከላከል አቅምን ከፍ ያደርጋል ተብሎ የታቀደ ሲሆን፤ አሜሪካ ደግሞ ለሁለቱ አገራት ወታደራዊ ቁሳቁስን ማቅረቡን ታፋጥናለች ብለዋል።ጄነራል ደንፎርድ የወታደራዊ ስምሪቱን የተለሳለሰ ያሉ ሲሆን፤ በሺዎች የሚቆጠር እንዳልሆነም አስታውቀዋል። ከዚህ ውጪ ግን ምን አይነት ጦር እንደሚሰማራ ፍንጭ አልሰጡም።እንደ ኒውዮርክ ታይምስ ከሆነ፤ ጋዜጠኞች ሚስተር ኤስፐርን ኢራን ላይ የአየር ድብደባ ለማካሄድ ታቅዶ እንደሆነ ሲጠየቁ በአሁኑ ሰአት እዚያ ውሳኔ ላይ አልደረስንም ማለታቸውን ዘግቧል።የሳኡዲ መከላከያ ሚኒስትር፤ በአገሪቱ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማት ላይ ከደረሰው ጥቃት የተሰበሰቡ ናቸው ያላቸውን የድሮን እና የሚሳኤል ስብርባሪዎች በማሳየት ጥቃቱን ያደረሰችው ኢራን ነች ሲል ከስሷል። ድሮኖች እና ሰባት ሚሳኤሎች ወደ ሳኡዲ ተተኩሰዋል ያለው የሳኡዲ መከላከያ፤ የጥቃቶቹ መነሻ የመን አይደለችም ሲል አስረግጦ ይናገራል። ምንጭ፡ ቢቢሲ
አሜሪካ ጦሯን ወደ ሳኡዲ ልትልክ መሆኑን አስታወቀች
ጫንያለው በዛበህቀዝነው ከኢሀፖ ፍርጥጠው ህወሀት የተወሸቁ ኤርትራዊያንና ትግሬዎች የመሰረቱት የትግሬ ድርጅት ብአዴን ህወሀት ስላዘለው እንደታገለ ተደርጎ ፖሮፖጋንዳ ሲዘራ በጣም ያሳፍራል።የአማራውን ደም ጠጥቶ የሰከረው ኤርትራዊው በረከት ስሞን ሳያስበው አምልጦት እኛ ብአዴኖች ወያኔ ነን ብሎ በግልፅ ተናግርዋል።በትግሬ ዘረኝነት ህሊናውን ስቶ ያበደው ህወሀት ገና ከጅምሩ አማራውን በአውራ ጠላትነት በመፈረጅ አማራውን ከምድረገፅ ለማጥፋት ፕሮግራም አውጥቶ በትግራይ በተለያዩ ማህበራዊ ግንዝኙነቶች በስራ በጋብቻ ወዘተ ምክንያት ይኖሩ የነበሩ አማሮችን አማራ በመሆናቸውብቻ አንድ በአንድ ለቅሞ በመፍጀት የዘር ማጥፋት ዘመቻውን ጀመረ በ የአማራውን መሬት ለመንጠቅ የዘር ማጥፋት አድማሱን ወደ ሰሜን ጎንደር በማስፋት የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ሰቲት ሁመራ አማሮችን ወጣቶችን ታሪክ ነገሪ እንዳይኖር አዛውንቶችን ሳይቀር በአሰቃቂ ሁኔታ በመፍጀት ጠላትነቱን አስመሰከረ በቦታውን ከሺ በላይ መጤ ስፋሪዎችን ከትግራይ በማምጣት አሰፈረበፕሮግራሙም አማራው ማህበራዊ እረፍ እንዳይኖረ እንደሚያደርግ እቅድ አውጥቶ በመላው ኢትዮጵያ የሚኖሩ አማሬችን ከ ጀምሩ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም በመፍጀትበማፈናቀልበርሀብ በበሽታ እንዲያልቁ በማድረግ እስካሁን የዘር ማጥፋት ዘመቻውን እያካሄደ ይገኛልስለዚህ ብአዴኖች የአማራውን ዘር እያጠፋ ያለው ጠንቀኛው ጠላት ህወሀት ናቸውይገርማልበረከት ብአዴን በግልፅ የአማራ ጠላት መሆኑን በመናገሩ ሊመሰገን ይገባል።አማራውን ለማታለል የተቅዋቅዋመው የህወሀት ክንፍ ብአዴንበአዴን በሚል ስም ሽፋን በአማራው ውስጥ ገብቶ የትግሬን መብት ብቻ ለማስከበር የሚንቀሳቀሰው ህወሀት።አስካሁን የአማራን ህዝብ መብት ለማስከበር የሚሰራ ድርጅት አለመኖሩን ያውቃሉብዙዎች የትግሬው ድርጅት በአዴን የአማራ እየመሰላቸው ተታለው ይገባሉ እውስጡ ገብተው ሲያዩት ግን ሙሉ በሙሉ ለትግሬ መብትና የበላይነት የሚታገልእና አማራውን በረቀቀ ስልት ለማዳከም እንደሚሰራ ይገነዘባልሉ።በአዴን አዘውትሬ አማራውን ሲያንቅዋሽሽ ትግሬን ሲክብ ይታዘባሉ።ምክንያቱም ብአዴን የተመሰረተው በትግሬዎች የሚሰራውም ለትግሬ ብቻ ነው የብአዴን አንቀሳቃሽ ሞተር ህወሀት ነውመሪውምቹም መሉ ለሙሉ ትግሬዎች ናቸው ለማታለል አማሮችን ለይስሙላ ያስቀምጣሉ።ብአዴን ስለ አማራ ከሚያወራ ስለ ትግሬ ብያወራ ይቀለዋል የትግሬ ድርጅት ስለሆን።የያኔው ኢህዴንየአሁኑ ብአዴን ከኢሀፖ ፈርጥጠው ወደ ህወሀት የተወሸቁ ኤርትርያኖች እና ትግሬዎች አማራው ጋር ሰብሮ ለመግባት አማራውን ለማዳከም በህወሀት ተጠፍጥፎ የተሰራ የትግሬ ድርጅት ነውዋና መስራቾቹም መብራቱ ግብረ ሂወትበረከት ስሞንኤርትራዊህላዊ ዮሴፍኤርትራዊአዲሱ ለገሰትግሬታደሰ ጥንቅሹትግሬተፈራ ዋልዋሲዳሞ ጊምራጌታቸውታምራት ላይኔሲዳማዮሴፍ ረታ ትግሬወዘተ ናቸው።በጥቅሉ ብአዴን የትግሬ ድርጅት ሲሆን አለማውም የትግሬ መብት በመላው ኢትዮጵያ ማስከበርና በረጅምና በረቀቀ ስልት አማራውን አዳክሞ ከምድረ ገፅ በማጥፋት የህወሀትን ናዚፖሮጀክት በማሳካት የአማራውን መሬት ሙሉ በሙሉ ወደ ትግራይ በመጠቅለል ታላቅዋን ትግራይ ሪፕብሊክ መመስረት ነው።
ብአዴን ቅርፁን የቀየረው ህወሀት ብአዴን የነ ወዲ ሀጎስ ድርጅት
በዚሁ መሰረት ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካዊ ሙዚቀኛ ነገ ከቀኑ ፡ስላሳ በጃዝ ክለብ አብሮት ከመጣው ቡድን ጋር ስራዎቹን የሚያቀርብ ሲሆን ረቡእ ምሽት በአሜሪካ ኤምባሲ የሚል የክብ ጠረጴዛ ውይይትም ይካሄዳል ተብሏል። በምሽቱ ደግሞ በጣይቱ ሆቴል እና በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መሰል ዝግጅቶች ይኖራሉ። በሌላ በኩል ህይወት እዚህ ቦታ የተሰኘ የግጥምና ሙዚቃ ዝግጅት ዛሬ ማታ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ይቀርባል። ዝግጅቱ አሜሪካ ሀገር ከሚገኘው ጣይቱ ባህል ማእከል ጋር በመተባበር ተቀርፆ እዚያው ሀገር በሚገኝ ሬዲዮ ጣቢያ እንደሚተላለፍም ታውቋል። ከገጣሚዎቹ መካከል ኤፍሬም ስዩም፣ ሰለሞን ሳህለ፣ ዮሀንስ ሀብተማርያም ይገኙበታል።
የአኬሽያ አለም አቀፍ የጃዝና ሙዚቃ ፌስቲቫል ተጀመረ ህይወት እዚህ ቦታ ዛሬ ይቀርባል
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው ሰማኒያ ሶስትኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።ምክር ቤቱ የጂኦተርማል ሀብት ልማት አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ የተወያየ ሲሆን፥ የአዋጁን የተወሰኑ ድንጋጌዎች ለማሻሻል የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባቀረበው የማሻሻያ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቶታል።ከዚህ ባለፈም የጤና ሚኒስቴር የኮቪድ ወረርሽኝን በመከላከልና የህክምና አገልግሎት በመስጠት በቀጥታ ለሚሳተፉ የጤና ዘርፍ ሰራተኞች የማበረታቻ አበል ክፍያን ለመወሰን ባዘጋጀው መመሪያ ላይ ከተወያየ በኋላ በስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል።በተጨማሪም በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት በኢኮኖሚው ላይ የተከሰተውን ተፅእኖ ለመቋቋም እና የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ለመሸፈን የሁለት ሺህ በጀት አመት የተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የመካከለኛ ዘመን የሁለት ሺህ ሁለት ሺህ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማእቀፍ ላይ በመወያየትም አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል አዋጁ ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ እንዲሁም ማእቀፉም በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።እንዲሁም በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በተዘጋጀውና ለህዝብ ጥቅም መሬት ሲለቀቅ ስለሚከፈል ካሳ እና የልማት ተነሺዎችን መልሶ ስለማቋቋም በወጣ ደንብ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣና በስራ ላይ እንዲውል መወሰኑን ምክር ቤቱ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል። የዜና ሰአት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልእክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ብለው ይላኩ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ታምራት ተስፋዬአዲስ አበባ፦ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማትን ተጠቅሞ ድህነትን ለማሸነፍና ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር የእቅድ ተግባራዊነትን ማረጋገጥና እስከዛሬ ከተመጣበት የተለየ መንገድን መከተል እንደሚያስፈልግ ተገለፀ። የሁለት ሺህ የመጀመሪያ ዙር ሀገር አቀፍ ሞዴል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አውደ ርእይና ባዛር በአዲስ አበባ ከተማ ጀሞ አንድ ትናንት በተከፈተበት ወቅት፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማትን ተጠቅመን ድህነትን ለማሸነፍ ብሎም ወደ ኢንዱስሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር የያዝነውን እቅድ ተግባራዊነት ማረጋገጥና እስከዛሬ ከመጣንበት የተለየ መንገድን መከተል ግድ ይላል ብለዋል።የስራ እድል ፈጠራ ስራ ከሰዎች ህልውና ጋር የተያይዘ በመሆኑ ሀላፊነቱ ከባድ መሆኑን ያስገነዘቡት ሚኒስትሯ፣ በአሁንም ወቅትም ከዩኒቨርሲቲና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተመርቀው ስራ እንዲፈጠርላቸው የሚጠብቁ ዜጎች በርካታ ናቸው፣ በዘርፉ የታቀፉና በስኬትና በውድቀት መካከል የሚንገዳገዱ አንቀሳቃሾችን ህልውን መታደግም ሌላው ፈታኝ የቤት ስራ መሆኑን አመልክተዋል። ከፍተኛ የህዝብ ሀብት ፈሶባቸው የሚገነቡ የመስሪያና መሸጫ ቦታዎች ሰርተው የእለት ጉርሳቸውን ለመሙላት ለተዘጋጁ ዜጎች በፍትሀዊነት ተደራሽ ማድረግም ከእያንዳንዱ የሚጠበቅ ሀላፊነት መሆኑን ያመላከቱት ኢንጂነር አይሻ፣ በአደራ የተቀበልነውን የህዝብ ገንዘብና መነሻ ጥሪት ለሌላቸው መገኖቻችን ያለ እጅ መንሻና ያለ ውጣ ውረድ በብድር ማቅረብም ለድርድር የማይቀርብ ግዴታችን ነው ብለዋል።ሀላፊነቱ ለአንድ ወገን የሚተው ባለመሆኑም አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ከወትሮው በተለየ መጠናከውና መተባበር እንዳለባቸው አመልክተው ፣ ሞዴል የጥቃቅንና አነስተኛ አነቅሳቃሾችም መንግስት በሚያደርገው የገበያ ትስስርና ድጋፎች ሳይወሰኑ በየትኛውም ገበያ ውስጥ ገብቶ የመወዳደርና ብቃት ማዳበር እንዳለባቸው አስታውቀዋል። መንግስታዊ ድጋፎች የሚደረጉት አንቀሳቃሾቹ በሁለት እግራችው እስኪቆሙ እንጂ እድሜ ልክ አለመሆኑን በመረዳት እስከዛሬ የመጡበትን የአሸናፊነት፣ የመለወጥና ድህነትን ድል የመንሳት ፅናት እንዲያጠናክሩ አስገንዝበዋል።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማእረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዣንጥራር አባይ በበኩላቸው፣ በትምህርት ገበታ መምጠቃቸው፣ ዲግሪና ማስትሬት መጎናፀፋቸው፣ ሳያስኮፍሳቸው ቀን ከሌት ሰርተው፣ የላብና ወዛቸውን ፍሬ በሚያጭዱ፣ የስራ ክቡርነት በተግባር በተገለጠበት መስክ በኩራት የተሰማሩ በርካታ ዜጎች በዘርፉ ፈርተዋል ብለዋል።ለዚህ ስኬት የበቁበት መንገድ ቀናና ምቹ እንዳልነበር አፅእኖት የሰጡት አቶ ዣንጥራር፣ ከመደራጀት ጀምሮ በስትራቴጂ ላይ የተቀመጡና መብታቸው የሆነውን መንግስታዊ ድጋፍ በተገቢው መንገድ ለማግኘት ብዙ ፈተናዎች መጋፈጣቸውን አስታውሰዋል። ጥቃቅን ከሚለው ስያሜ አንስቶ የምርት፣ ግብአትና የገበያ እጥረት የማምረቻና መሸጫ ቦታ በተገቢው አለመመቻቸታቸውና የኪራይ ሰብሳቢነት ተግዳሮቶች በመንገዳቸው በብርቱ እንደፈተናቸው ተናግረዋል።ሀላፊው፣አነቀሳቃሾቹ መሰል ፈተናዎችን ተቋቁመው ለስኬት መብቃታቸውን በማድነቅም፣ ልፋታቸው ፍሬ እንዲያፈራ፣ ድካማቸው ከራስ አልፎ ለወገን እንዲተርፍ፣ የስራ ተነሳሽነታቸው ለብዙዎች አርአያ ሆኖ አገር እንድትኮራ የከተማ አስተዳደሩ ምንጊዜም ከጎናቸው እንደሚሆንም ማረጋገጫን ሰጥተዋል። በቀጣይም ዜጎችን ከማደራጀት ጀምሮ መንግስታዊ ድጋፎችን ውጤታማ ለማድረግ እስከአሁን የመጣንበትን አሰራር በመፈተሸና አዳዲስ አሰራሮችን በመተግበር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንሰራለን ብለዋል።የፌዴራል የከተሞችና የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ ገብረ መስቀል ጫላ በበኩላቸው፣ በአውደ ርእይና ባዛር ላይ ከመላ አገሪቱ ከሁለት መቶ በላይ ሞዴል ጥቃቅንና አንስተኛ ኢንተርፕራይዞች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መስፋፋት መከላከል በሚያስችል መልኩ እንዲሳተፉ መደረጉን አስታውቀዋል። ዘላቂነት ያለው የገበያ ትስስር ለስራ እድል ፈጠራና ለኢንተርፕራይዞች ልማት መሰረት ነው በሚል የተዘጋጀው አውደ ርእይና ባዛር ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር ይፈጠራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ እስከ ገና ዋዜማ ክፍት ሆኖ ይቆያል።አዲስ ዘመን ታህሳስ ሀያ ሶስት ሁለት ሺህ
በኢንተርፕራይዞች ልማት ውጤታማ ለመሆን ከቀድሞው የተለየ መንገድን መከተል እንደሚያስፈልግ ተገለፀ