headline
stringlengths
2
1.42k
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
9
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
63
36.2k
link
stringlengths
28
740
word_len
int64
16
6.74k
label
class label
6 classes
ቂም በቀል በቁራዎች
መዝናኛ
September 10, 2019
48
ሰዎች በልዩ ልዩ ጉዳዮች በተለይ እነርሱ በማያምኑባቸው ምክንያቶች ቤተሰቦቻቸውን አልያም የቅርብ ወዳጆቻቸውን በሞት ሲነጠቁ በከባድ ኀዘን ውስጥ ይወድቃሉ። ዘመዳቸው ወይም የቅርብ ወዳጃቸው ሕይወቱ ሆን ተብሎ በግለሰብ እጅ ያለፈ ከሆነም አሟሟቱን በማሰብ በንዴት ይበግናሉ። በቂም በቀል ተነሳስተውም የገዳዩን ሕይወት እስከማጥፋትም ይደርሳሉ። በእኛም ሀገር ቀደም ሲል እንደነበረው አይብዛ እንጂ አሁንም ድረስ በተለይ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ በዚህ መልኩ ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ የሟች ቤተሰቦች ደም ለመመለስ በሚል በቂም በቀል ተነሳስተው በገዳይ ቤተሰቦች ላይ እርምጃ ይወስዳሉ። ይህ ጉዳይ እንደባህል ተቆጥሮ ዛሬም አልፎ አልፎ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ገዳዩ ዘመድ እንኳን ባይኖረው ልጁን እስከመግደል የሚደረስበት ሁኔታም ይፈጠራል። ይህ የቂም በቀል ተግባር ታዲያ በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚታይና የተለመደ ቢሆንም፤ በእንስሳት በተለይም በአእዋፋት በኩል አለ ቢባል ግን ትንሽ ያስገርማል። ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ድረገፅ ከሰሞኑ ያወጣው መረጃም ልክ እንደሰው ሁሉ አእዋፍም በቂም በቀል ተነሳስተው ጥቃት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ያሳያል። እንደዘገባው ከሆነ፤ ላለፉት ሦስት ዓመታት በሕንድ ማድሃያ ፕራዴሽ ግዛት ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ህልም የሚመስል ግን እውነተኛ ሕይወትን ከቁራዎች ጋር አሳልፏል። በቀን ሠራተኝነት የሚተዳደረውና ሱሜላ በተሰኘች መንደር ነዋሪው ሺቫ ኪዋት እርሱ ባልተረዳው መልኩ ከቁራዎቹ ጋር ያጋጠመው ችግር ከሦስት ዓመት በፊት እንደነበር ያስታውሳል። ከዕለታት በአንዱ ቀን በመንገድ ላይ ሲጓዝ አንዲት ቁራ በብረት መረብ ውስጥ ተጣብቃ ይመለክትና ወደ እርሷ ቀረብ ይላል። ይሁንና ቁራዋን ከተጣበቀችበት መረብ ውስጥ ለማላቀቅ ጥረት ቢያደርግም ሳይሳካለት ቀርቶ ቁራዋ እጁ ላይ ትሞታለች። ይህ ሲሆን የተመለከቱት ሌሎች ቁራዎችም ምንአልባት የቁራዋን ሕይወት የቀጠፈው እርሱ ሳይሆን አይቀርም በሚል ሁሌም ቁራዋ በሞተችበት አካባቢ ሲያልፍ ጥቃት ያደርሱበታል። ጥቃታቸውንም አንዴ በቡድን ሌላ ጊዜ ደግሞ በተናጠል ያካሂዱበታል። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም ኪዋት ከቁራዎቹ ሹል መንቁርና ስል ጥፍር ጥቃት ለመሸሽ ሁሌም ልምጭ ይዞ መንቀሳቀስ ይጀምራል። ኪዋት «ቁራዋ የሞተችው እጄ ላይ ነው፤ ቁራዎቹ ሃሳቤን መረዳት ቢችሉ ኖሮ ቁራዋን ልረዳት እንደነበር እገልፅላቸው ነበር» ሲል ለታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ገልጿል። «ራሴን ለመከላከል ልምጭ እጠቀማለሁ፤ ይመስለኛል ቁሯዋን የገደልኳት እኔ መስያቸዋለሁ» ሲልም ተደምጧል። ኪዋት እንደተናገረው፤ እርሱ ብቻ የጥቃቱ ኢላማ መሆኑንና ቁራዎቹ ከሌሎች ሰዎች ጋር ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለባቸው እስኪያውቅ ድረስ የቁራዎቹን ጥቃት በደንብ እንዳላጤነው ተናግሯል። ቁራዎቹ እርሱን ለማጥቃት በአናቱ ላይ ሲያንዣብቡ በእርሱ ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ለመመልከት በርካታ ሰዎች በየቀኑ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ እስከመሰባሰብም ደርሰዋል። ብዙዎቹ በጉዳዩ የተገረሙ ሲሆን፤ ሌሎቹ ደግሞ ድርጊቱን «ድንገተኛና አስደንጋጭ» ሲሉ ገልፀውታል። ከኪዋት ጎረቤቶች ውስጥ አንዱ «ቁራዎቹ ኢላማቸውን እንዳዩ ልክ እንደ ተዋጊ ጄቶች ዝቅ ብለው በመብረር ጥቃቱን በኪዋት ላይ ያደርሳሉ» ሲል የቁራዎቹን ድንገተኛ ጥቃት ገልጿል። በባራካቱላህ ዩኒቨርሲቲ በወፎች ባህሪ ዙሪያ ጥናት ያካሄዱት ፕሮፌሰር አሾክ ኩማር በበኩላቸው፤ ቁራዎች የማስታወስ ችሎታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፤ በተለይ በእነርሱ ላይ ጉዳት ያስከተሉትን እንደማይዘነጉ ተናግረዋል። የበቀል ሃሳባቸው ልክ እንደሰዎች የተወሳሰበ ባይሆንም፤ በሚያስቆጣቸው ጉዳይ ላይ በቡድን ወይም በተናጠል የማጥቃት ባህርይ እንዳላቸውም ጠቁመዋል። በመሰረታዊነት ቂም የሚይዙ በመሆናቸው ኪዋት ያገጠመው ችግርም ይኸው መሆኑን አመልክተዋል።  አዲስ ዘመን  ጳጉሜን 5 /2011 አስናቀ ፀጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=17594
413
1መዝናኛ
ቦርዱ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 30, 2020
18
ሶሎሞን በየነአዲስ አበባ:- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ገለጸ።የቦርዱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ቦርዱ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ቀደም ሲል ከተካሄዱ ምርጫዎች በእጅጉ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ ይገኛል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ባለፉት ከተካሄዱ ምርጫዎች በእጅጉ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ቁሳቁሶች 90 በመቶ ተገዝተው መጠናቀቃቸውን ያመለከቱት ስራ አስኪያጇ፣ የተገዙት የምርጫ ቁሳቁሶቹና ህትመቶች ከዚህ በፊት ምርጫ ከተደረገባቸው ቁሳቁሶችና ህትመቶች በእጅጉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሆኑ አስታውቀዋል።የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹና የመራጭ ካርዶቹ ደግመው መታተም የማይችሉ፣ ከተነካኩ የሚያስታውቁ፣ የራሳቸው የሆነ ቀሪ ያላቸው፣ ኮፒ ለመደረግ የሚያስቸግሩ እንዲሁም የድምጽ መስጫ ሳጥኖቹ አስተማማኝና መራጩ ድምጽ ሲሰጥ በነጻነት ለመስጠት የሚያስችል መከለያዎች ያሉት እንደሆነም ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ የተለያዩ ማጭበርበሮችን የሚያስቀሩ የምርጫ ቁሳቁሶች መዘጋጀታቸውንም አመልክተዋል። ምርጫውን በህጉ መሰረት ለማከናወን የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መጠበቂያ ፕሮሲጀር መዘጋጀቱን የጠቆሙት ወይዘሪት ሶሊያና ፤ ይህም ምርጫው በህጉ መሰረት ተከናውኗል አልተከናወነም ብሎ ለመለየት የሚቻልበት እድል እንዲኖር የሚያደርግና የድምጽ ቆጠራው የምርጫ ሂደቱን ተከትሎ መከናወን አለመከናወኑን ለመለየት እንደሚረዳም አስታውቀዋል። ቦርዱ ከዚህ ቀደም እንደነበረው አሰራር ለይስሙላ የተዋቀረ ሳይሆን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ባላቸው፣ የትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ባልሆኑና ገለልተኛ በሆኑ የቦርድ አባላት እንደ አዲስ የተዋቀረ መሆኑን ጠቁመው ፤ ቦርዱ ሪፎርም ከተደረገ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ባለው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት በተቻለ መጠን ጠንካራና ፍትሃዊነት ያላቸውን ውሳኔዎችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። በውሳኔ አሰጣጡ በኩል የተአማኒነት ችግር ወይም ጥያቄ እንደሌለበት የጠቆሙት ወይዘሪት ሶሊያና፣ ቦርዱ ይሄንን ጠንካራ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ የሆነ የውሳኔ አሰጣጥ አቅሙን ይዞ ወደ ምርጫው እንደሚገባ አስታውቀዋል። ይህም ለምርጫው ተአማኒ መሆን የራሱን አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ተናግረዋል። ለምርጫው የተገዙ ቁሳቁሶችና ምርጫውን ለማካሄድ የተነደፉ የአሰራር ስርዓት በተቻለ መጠን ምርጫውን ተአማኒ እንደሚያደርጉት ወይዘሪት ሶሊያና ገልጸው፤ መጪው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ምርጫዎች ለየት የሚያደርገው ምርጫው የሚካሄደው በምርጫ ህጉ የነበሩ ማነቆዎች ተስተካክለውና የቦርድ አመራሩ አደረጃጀትም በአዲስ መልኩ ተዋቅሮ መሆኑን አመልክተዋል። ይህም ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38456
310
0ሀገር አቀፍ ዜና
“በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ ነው” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 30, 2020
16
 በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ በኢትዮ- ሱዳን ድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህ ሳምንት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 328 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለስ መቻሉን ገለጹ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስወቁት ፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ በአሁኑ ወቅት ውጥረቱ ቀንሷል።ችግሩ እንዲፈጠር ያደረጉት ቀጠናው እንዳይረጋጋ የሚፈልጉ ኃይሎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የሱዳን የተወሰኑ ልሂቃኖችም ከእነዚህ ኃይሎች ጋር መወገናቸውን አመልክተዋል።“እነዚህ ኃይሎች በግልጽ የሚታወቁ ናቸው” ያሉት ቃል አቀባዩ፣ በትርምሱ የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸምና ጥቅማቸውን ለማስከበር ያለሙ መሆናቸውን አስታውቀዋል።እነዚህ ኃይሎች ለሱዳን ህዝብም ሆነ ለቀጠናው ጠቃሚ አለመሆናቸውን መንግሥት በተለይ ለሱዳን ህዝብ መልዕክት የማስተላለፍ ሥራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።ጎን ለጎንም እነዚህን ኃይሎችን የማጋለጥ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ ችግሮቹን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች መቀጠላቸውን ገልጸዋል።በመግለጫቸው በትግራይ ክልል መረጋጋት መስፈኑንና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ጠቁመዋል ።አንዳንድ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ክልሉ ላይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በሃቀኝነት መዘገብ እንዳልቻሉ አስታውቀዋል።እነዚህ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ጉዳዩን በሚመለከት እየተከተሉት ያለው አካሄድ ትክክል ባለመሆኑ ሊታረሙ እንደሚገባም ጠቁመዋል። የውጭ ኢንቨስትመንትን አስመልክቶም የእስራኤል፤ የህንድ፣ የዱባይ፣ የቻይናና የቱርክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት አመራጮችን ለመጠቀም ፍላጎት መሳየታቸውን አመልክተዋል። “በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አማካኝነትም ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው ውጭ አገራት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ናቸው” ብለዋል።በተለይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች ወደ አገራቸው ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ሳምንት ብቻ 328 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለስ መቻሉን ገልጸዋል። ከእነዚህ ውስጥ 286ቱ ከሳዑዲ አረቢያ የተቀሩት ከሊባኖስ መመለሳቸውን ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38465
225
0ሀገር አቀፍ ዜና
አስከፊውን ጊዜ በብልሃት የማለፍ ጅምር
ስፖርት
April 8, 2020
22
የዓለም ሕዝብ ሁሉ ጭንቀትና ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ ከሀብታም እስከ ድሃ፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዋነኛ ትኩረቱ እንዲሆን ካስገደደ ሰንብቷል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት እንደ ሰደድ እሳት ያላዳረሰው የዓለም ክፍል የለም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዓለም ሕዝቦች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ከቫይረሱ ቢያገግሙም የሟቾች ቁጥር ይህ ነው በማይባል ፍጥነት እየጨመረ ይሄዳል:: ከሁሉም በላይ በቫይረሱ ስጋት በየቤቱ የከተመው የዓለም ሕዝብ ጭንቀትና ድብርት ውስጥ እንዲገባ ማስገደዱ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እየሆነ ይገኛል፡፡ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የዓለምን ሕዝብ ያጠቃው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያልገባበበት ቤት፣ ያላንኳኳው በር የለም፡፡ ከዓለም ታላላቅ አገራት መሪዎች እስከ ተራው ሕዝብ፣ ከዝነኛ ሰዎች እስከ ሕፃናትና አዛውንት ድረስ የዚህ አስከፊ ወረርሽኝ ተጠቂ ሆነዋል፡፡ ቫይረሱን ለመቋቋም በሽታን የመመከት ከፍተኛ አቅም ያላቸው የስፖርቱ ዓለም ሰዎች ሳይቀሩ በዚህ ወረርሽኝ ተለክፈዋል፣ ሕይወታቸውን ያጡም ጥቂት አይደሉም፡፡ የስፖርት ቤተሰቡ በቫይረሱ ስርጭት ስጋት የዓለም ታላላቅ የስፖርት መድረኮች ተቆልፈውበት ሁነኛ የመዝናኛ አማራጩን አጥቶ በየቤቱ ቆዝሟል፡፡ የስፖርቱዓለም ታላላቅ ከዋክብትም ረብጣ ገንዘብና ዝናቸው ከደጃፋቸው እንዲወጡ አቅም አልሆናቸውም፡፡ ይሄ ክፉ ጊዜ እስኪያልፍ ሁሉም በየቤቱ እንዲቆይ ማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተሻለ አማራጭ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅትና መንግሥታት በየጊዜው ሲወተውቱ ይታያሉ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ኢኮኖሚያቸው ዝቅተኛ የሆኑ አገራት ዜጎች የተሻለ የመዝናኛ አማራጭና በየቤቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚቸገሩ መሆናቸው ከጭንቀትና ድብርት ጋር ተያይዞ ለሚመጣው ቀውስ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ አስቸጋሪ ጊዜ እስኪያልፍ ከስፖርቱ አኳያ ማህበረሰቡ በያለበት ሆኖ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርግ መላ መዘየድ እንደሚያስፈልግ ግልፅ ነው፡፡ ለዚህም የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ትናንት የወሰደው ርምጃ አንድ ምሳሌ ይሆናል፡፡ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግቢ እና በረንዳዎች ላይ ርቀትን በመጠበቅ ቀለል ያሉ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በመስራት ኅብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ እራሱን እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡ በአዲስ አበባ ከተማ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሉ በረንዳ ላይ ቀለል ያሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማካሄድም ግንዛቤ ፈጥሯል:: በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሳቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች ዝግ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከፊት ኮርነር ስፖርት ጋር በመቀናጀት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በረንዳ ላይ ነዋሪዎች በተገኙበት ተገቢውን ርቀት በመጠበቅ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሰርተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይ፣ «የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በቤታቸው ተወስነው ያሉ ነዋሪዎች በቤታቸው ሆነው ቀለል ያሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ከጭንቀት እና ከድብርት ተላቀው ጤናማ ኑሮ እንዲኖሩ ያስፈልጋል» ማለታቸውን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት መረጃ ያመለክታል፡፡ ኅብረተሰቡም የማህበራዊና አካላዊ ርቀቱን ጠብቆ በዚህ ጊዜ በመጠኑ አካላዊ አዝናኝ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ያለጭንቀት ጤናውን በመጠበቅ ይህን አስከፊ ጊዜ ማለፍ እንደሚኖርበት ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይም በሌሎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ኅብረተሰቡ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲሰራ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን ኮሚሽነር ዮናስ ተናግረዋል። በአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ፕሮግራም ላይ ከነዋሪዎች በተጨማሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አመራሮች ኮሜዲያን እና የስፖርት ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 30/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=30017
432
2ስፖርት
ከፓራጓይ ሰማይ ሥር-የወደቀው የብራዚላዊው እግር ኳስ ኮከብ ዝና
ስፖርት
April 10, 2020
24
ዳንኤል ዘነበ በዓለም ዙሪያ በማራኪነቱ፤ በአዝናኝነቱም ሆነ በልብ ሰቃይነቱ ወደር አልተገኘለትም፣ ዘመናዊው የእግር ኳስ ስፖርት። ለእግር ኳስ ፍቅር በከፍተኛ ደረጃ ባለቤት በመሆን ረገድ ብራዚላውያንን የሚስተካከል ስለመኖሩ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ይነገራል፡፡ ብራዚል ብዙ ሚሊዮን የእግር ኳስ ስፖርት ፍቅር ያለው ሕዝብ ባለቤት ብቻም አይደለችም። ብራዚል የእግር ኳስ ክዋክብቶችን በማፍራት ተጠቃሽ ናት። በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ተጫዋቾችን በማፍራት ነጥፋ አታውቅም። የብራዚላውያን የኳስ ጥበበኛነትን ዓለም አምኖ እንዲቀበል ካደረጉ የዘመናቸን ድንቅ ተጫዋቾች መካከል ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሬራ!! ሮናልዲንሆ ጎቾ በተጫዋችነት ዘመኑ የሰራቸው ገድሎች «ዘመናዊ እግር ኳስ እንግሊዝ ውስጥ ተወልዶ ብራዚል አደገ» እስኪባል ድረስ ሀገሩን ብሎም ዓለምን በማስደመም ስሙን መትከል ችሏል። በዓለም ዋንጫ መድረክ ብቻም ሳይሆን ሌሎች መድረኮች ላይ በሜዳ ላይ በሚያሳያቸው እንቅስቃሴዎች፣ አብዶዎች ከስፖርት ቤተሰቡ ልብ ትዝታው ዛሬም የሚነሳለት ድንቅ ጥበበኛ፤ እኤአ በመጋቢት 1980 በብራዚል በደቡብ ብራዚል ፖርት ኤሌግሪ ተወለደ። እግር ኳስ ወዳድ ከሆነ ቤተሰብ የተገኘው ጎቾ ኳስን በ8 ዓመቱ ኳስ ከሰፈሩ ልጆች ጋር በፖርት አሌግሪ የባህር ዳርቻ በማንከባለል ነበር የጀመረው። ሜዳው ላይ በዕድሜው አነስተኛው ልጅ እሱ ሲሆን፤ በችሎታው የሰውን ዓይን በቀላሉ መማረክ የሚችልና ብዙዎች ከዓይን ያውጣህ ማስባል የጀመረው ያኔ ገና ነበር። ሮናልዲንሆ እስከ 13 ዓመቱ ከሰፈሩ በዘለለ ለትልልቅ ክለቦችም ሆነ ለታዳጊ መጫወት አልቻለም። ውሎው የባህርዳርቻ ነበር። በ13 ዓመቱ ግን አንድ ነገር ተከሰተ፣የወንድሙ ክለብ የሆነው የግሪሚዩ መልማዮች ጎበዝ ተጫዋቾችን ሊመለምሉ የነ ሮናልዲንሆ ሰፈር ደረሱ። ለምልመላው ይረዳቸው ዘንድም ተጫዋቾችን ለሁለት ከፍለው ግጥሚያ እንዲያደርጉ አዘዙ። ክፍፍሉም ፍትሃዊ እንዲሆን በሰፈር አደረጉት። የላይኛው ሰፈር ልጆችና የታችኛው ሰፈር ልጆች። ጨዋታው ተጀመረ። ልክ እንደተጀመረ ሮናልዲንሆ ተከላካዮችን አተራምሶ አስደናቂ ጎል አስቆጠረ። ከደቂቃዎች በኋላም የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ሌላ ጎል ደገመ። ውጤቱም 23 ለ 0 ነበር። የሚገርመው 23ቱንም ጎሎች ያስቆጠረው ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሬራ ነው። መልማዮቹ ወደ ካምፓቸው ሲመለሱ አንድ ሳቂታ ልጅ አስከትለው ተመለሱ። ሮናልዲንሆም ከወንድሙ ጋር አንድ ክለብ ውስጥ የመጫወት ዕድል አገኘ። ሮናልዲንሆ ለታዳጊዎቹ ሮቤርቶ ደግሞ ለዋናው ቡድን፡፡ ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ወንድሙ ሮቤርቶ በደረሰበት ጉዳት ከኳስ ተሰናበተ። ሮናልዲንሆ ወንድሙ ባጋጠመው ነገር ቢያዝንም ኳስ ከመጫወት ግን ለደቂቃም አልቦዘነም። በግሪሚዩ የእግር ኳስ ካምፕ ውስጥ ኳስን ጓደኛው አደረጋት። ቀኑን ሙሉ ውሎው ከኳስ ጋር ሆነ። ከጓደኞቹ ቀድሞ ልምምድ ቦታ መገኘት እንዲሁም ከሁሉም በኋላ መውጣት ባህሪው ሆነ። ይህ ታታሪነቱ ወደ ታላላቅ የዓለማችን ክለቦች አምርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ በእግር ኳሱ ዓለም እስከዛሬም የማይዘነጉ ተዓምሮችን መፍጠር ቢያስችለውም ዝናና ገንዘብ ይዞት የሚመጣውን ጣጣ እንዲቋቋም አላደረገውም፡፡ ውሎና አዳሩ በየጭፈራ ቤቱ ሆነ፡፡ አብዝቶ መዝናናት ከድህነት ሕይወት ያስመለጠውን ኳስ አስረሳው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥም ሆኖ ግን ዓለምን በእግር ኳስ ጥበቡ ማስደመም ለእሱ ቀላል ነበር፡፡ በታላቁ ኤልክላሲኮ ታሪክም ከማራዶና በኋላ በተቃራኒ ደጋፊዎች ሜዳ የተጨበጨበለት ተጫዋች እስከመሆን ደረሰ፡፡ በኳሱ ተዝናንቶበታል፣ ተመልካቹንም አዝናንቶበታል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ከአምስት ዓመታት በላይ እንዲዘልቅ አብዝቶ መዝናናቱ አልፈቀደለትም:: ብራዚላውያን ለዚህ ዘመን ድንቅ ኮከባቸው ያላቸው ጥልቅ ስሜት ዛሬም እንደ አዲስ እየተቀሰቀሰ በትዝታው አብረው ሲደሰቱና ሲኮሩ ይሰተዋላሉ። ብዙዎች ጥበቡን ሳይጠግቡ የእግር ኳስ ሕይወቱ በአጭሩ ሊቀጭ ችሏል፡ ፡ እኤአ 2002 ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችሏል። ሮናልዲንሆ የ2005 ባለንደኦር [የዓለም ኮከብ ተጫዋች ሽልማት] አሸናፊ ነበር። በኳስ ሕይወት ስኬትና ዝናንን በመጨበጥ አድናቆትን ማትረፍ የቻለው ሮናልዲንሆ በ800 ሺህ ዶላር ዋስ ሆቴል እንዲታሠር ታዘዘ ይላል የቢቢሲ ዘገባ። ሮናልዲንሆና ወንድሙ ፓራጓይ ውስጥ ሃሰተኛ ፓስፖርትና ሌሎች ሰነዶች ይዘው ተገኝተዋል በሚል በፖሊስ ሊያዙ ችለዋል። ወንድማማቾቹ በወቅቱ እንዲለቀቁ ይግባኝ አመልክተው የነበረ ቢሆንም ሰሚ ጠፍቶ ከአንድ ወር በላይ እሥር ቤት ውስጥ ለመሰንበት ተገደዋል። ብራዚላዊው የእግር ኳስ ጠቢብ ሮናልዲንሆ ጎቹ እና ወንድሙ ፓራጓይ ከሚገኘው እሥር ቤት ተለቀው ውሳኔ እስኪሰጣቸው ድረስ ሆቴል ታስረው እንዲቆይ ውሳኔ ተላልፏል። በተጨማሪ እያንዳንዳቸው 800 ሺህ ዶላር ዋስ ጠርተው የፓራጓይ ዋና ከተማ አሱንሲዮን የሚገኝ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ውስጥ እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተላልፎባቸዋል ሲል ዘግቧል። በብራዚላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሮናልዲንሆ ጎቾና ወንድሙ ላይ ውሳኔውን ያስተላለፉት ዳኛ ገንዘቡ ጫን ያለ እንዲሆን የተደረገው ግለሰቦቹ ሀገር ጥለው እንዳይጠፉ በማሰብ መሆኑን አስገንዝበዋል። «የ40 ዓመቱ የእግር ኳስ ሰው ሮናልዲንሆና ወንድሙ አሲስ እኛ ሃሰተኛ ሰነድ መሆኑን አላወቅንም ነበር »ሲሉ ቢሟገቱም፤ ጠበቃቸውም «የወንድማማቾቹ እሥር ሕገ-ወጥ ነው» ሲል ቢከራከርም ውሳኔው ተፈጻሚ ከመሆን አላዳናቸውም ሲል ቢቢሲ ዘገባውን ቋጭቷል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 2/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=30124
600
2ስፖርት
ሉሲዎቹ ድጋፍ ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው
ስፖርት
April 11, 2020
10
ስፖርት በባህሪው ተጽእኖ ፈጣሪ እንደመሆኑ በቀላሉ መልዕክትን ሊያስተላልፍና ንቅናቄ ሊፈጥር እንደሚችል እሙን ነው። ይህ በመሆኑም ዓለም በአንድነት ከተላላፊው ቫይረስ ጋር እያደረገ ባለው ፍልሚያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያም የስፖርት ማህበራት፣ ክለቦች፣ ስፖርተኞችና ሌሎች ባለሙያዎች የበኩላቸውን ማበርከት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ሉሲዎቹም በዋና አሰልጣኛቸው ብርሃኑ ግዛው አስተባሪነት የድርሻቸውን ለመወጣት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። እንደ ሀገር የመጣውን ፈተና ለመመከት የሚደረገውን እቅስቃሴ ለማገዝ በቅድሚያ የተነሱት የዋናው ሴት ብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች ነበሩ። ነገር ግን የገንዘቡን መጠን በመመልከት ለ20 እና 17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን፣ የንግድ ባንክ ሴቶች ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ደጋፊዎች ጥሪ አቅርበው ተቀባይነት ማግኘታቸውን አስተባባሪው አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ይገልጻል። በመገናኛ ብዙሃን የተደረገውን ጥሪ ተከትለው ብዙዎች ሚናቸውንለመወጣት እንቅስቃሴውን በመቀላቀላቸው ገንዘብ ማሰባሰቡን በቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ ገቢ የሚደረግም ይሆናል። የገንዘብ ማሰባሰቡ ስራ ተጫዋቾች በውድድሮች ተሳታፊ በመሆን ሃገራቸውን ከመወከል ባሻገር ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያስችላቸዋል። ከዚያ ባሻገር ግን ተጫዋቾች ተጽእኖ የመፍጠር አቅማቸውን በመጠቀም ደጋፊዎችንና ህዝቡን ማነሳሳትን ዓላማው ያደረገ መሆኑንም አሰልጣኙ ይጠቁማሉ። ለማሰባሰብ የታቀደው የገንዘብ መጠን 100ሺ ብር ሲሆን እስካሁን የተዋጣው ከ55ሺ ብር በላይ ደርሷል፤ በቀጣይ ቀናትም እቅዱን ለማሳካት ጥረት ይደረጋል። ከድጋፉ ባሻገር ኢትዮጵያን ጨምሮ ዓለምን እያናወጠ ያለው ቫይረስ ማለፉ አይቀርምና ካለፈ በኋላ ላለመቸገር ተጫዋቾች ላይ መስራት ተገቢ ነው። በዚህ ላይም የግንዛቤ ችግር መኖሩን ያነሳው አሰልጣኙ ‹‹ በስፖርቱ ውስጥ ሆነን ኃላፊነታችንን ተወጥተናል፤ በዚያ ልክ ግን በየደጃችን ትንሽ እንቅስቃሴ የመስራትና የስፖርት ቁሳቁሶችን በማዘጋጀት በግል የመስራት ልምድ ችግር አለብን። ሁሌም አሰልጣኞችን እንጠብቃለን። ይህ ሁኔታ ካለፈ በኋላ ስፖርቱ አንዳይቀዛቀዝና እንደ አዲስ ከዜሮ ጀምረን ውጤት እንዳናጣ የትኛውን ስራ መቼ መስራት አንዳለበን አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን እያደረገን ነው። ይህ የበለጠ ጥሩ ይሆናል ብለን አንጠብቃለን፤ እኛ አንደ ባለሙያ ከምንሰጣቸው ባለፈ ተጫዋቾቹ ተዘናግተው ስራቸው ላይ ወደ ኋላ እንዳይሉ እየሰራን እንገኛለን›› ሲል ያብራራል። በዚህ ሁሉም ቤቱ እንዲቆይ በተደረገበት ወቅት ስፖርተኞች እንደ ቀድሞው ልምምዳቸውን ለመስራት ከባድ ይሆንባቸዋል። ባደጉት ሃገራት አሰልጣኞች ተጫዋቾቻቸውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዘው ክትትል ያደርጉላቸዋል። ተጫዋቾቹም ከቤታቸው ሆነው በየግላቸው የሚያደርጉትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በተንቀሳቃሽ ምስል ለዓለም በማጋራት ላይ ይገኛሉ። እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ግን ይህ የተለመደ ካለመሆኑም ባለፈ በምን መልኩ መስራት እንደሚቻል ግንዛቤውም የለም። ለዚህም አሰልጣኞች በማህበራዊ ትስስር ዘዴዎችን በመጠቀም (በቴሌግራም) ከተጫዋቾቻቸው ጋር ግንኙነት እንደሚያደርጉ አሰልጣኙ ያስረዳል። በዚህም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዴት መስራት እንደሚችሉ ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ። ቴክኒካዊ የሆኑ የስልጠና ክፍሎችንም በተለያዩ የአሰልጣኝነት ስልጠናዎች ባገኟቸው ልምዶች ታግዘው ለተጫዋቾቻቸው ያጋራሉ። ከዚህ በተጓዳኝ ተጫዋቾች በመገናኛ ብዙሃን በሚሰሙትና በሚመለከቱት በመረበሽና በመጨነቅ ስነ-ልቦናቸው እንዳይጎዳ ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ለማሳወቅ የአሰልጣኞች ቡድኑ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ለሉሲዎቹም ሆነ ለዋልያዎቹ, ባለውለታ እንደመሆኑ በዚህ ወቅት ስፖርት፤ ህዝቡ ሚናውን በመወጣት ከጎኑ መሆኑን ማሳየት አለበት። ዝናብ፣ ብርድና ጸሃይ ሳይል ቡድኑን ሲደግፍና እንዲሁም ወደ ውጪ ሃገራት ሲጓዝ ከጎኑ የነበረውን ህዝብ በዚህ ወቅት የማጽናናትና የማረጋጋት ግዴታ እንዳለበት አሰልጣኙ ይገልጻል። የስፖርቱ ቤተሰብ ህዝቡ በቫይረሱ ተጠቂ እንዳይሆን እንዴት መጠንቀቅ እንደሚገባው ከማስተማር ባሻገር በግልና በቡድን የሚያደርገው አስተዋጽኦ በቂ ነው የሚል እምነት የሌለው አሰልጣኙ፤ ከዚህ በላይ አስፈላጊ መሆኑን አመላክቷል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=30194
439
2ስፖርት
አትሌቶች ፈታኙን ጊዜ እንዴትይወጡታል?
ስፖርት
April 13, 2020
38
በአትሌቲክስ ስፖርት ዝና እና ክብሯን የገነባችው ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችንም አግኝታበታለች። ስፖርቱ አንድ የስራ ዘርፍ በመሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት አትሌቶችን ያቅፋል። አትሌቶችም በዓለም አቀፍ ውድድሮች ሲሳተፉ ከውጤት ባሻገር የውጭ ምንዛሪን በማስገኘት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ያግዛሉ። በሚያፈሱት መዋዕለ ነዋይም ለበርካቶች የስራ እድል ፈጥረዋል። እንደሚታወቀው በዚህ ወቅት ይህ ዘርፍ እንደሌሎች ስፖርቶች ሁሉ ለውድድር ዝግ ሆኗል። ማልዶ ለልምምድ ይወጣ የነበረውና በዓመት ውስጥ ተደጋጋሚ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበረው እረፍት የለሽ አትሌትም ከተላላፊው ቫይረስ ጋር ተያይዞ ከቤት ውሏል። በብሄራዊ ቡድን የተያዙ፣ በተለያዩ ክለቦች የተካተቱ እንዲሁም የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ተቋማት ሰልጣኝ የሆኑ አትሌቶችም እንዲበተኑ ተደርጓል። በግላቸው የሚሰለጥኑትም ቢሆን እንደ ቀድሞው ከመኖሪያቸው ርቀው የማይጓዙበት ሁኔታ ተጋርጦባቸዋል። ለአንድ ዓመት የተራዘመውን ኦሊምፒክ ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ቻምፒዮናዎች ላይ ተሳታፊ ለመሆን በብሄራዊ ቡድን የተካተቱ አትሌቶች ደግሞ ከሌሎች በተለየ ሁለት አማራጮችን ያስተናግዳሉ። የመጀመሪያው ለተላላፊው የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ላለመሆን በሚደረገው የቤት ውስጥ ቆይታ ከልምምድ በመራቃቸው የአቋም መውረድን ማስተናገድ ነው። ሌላኛው ደግሞ የውድድሮችን መራዘም እንደ መልካም እድል በመጠቀም በተደጋጋሚ ውድድር ላይ ያሳለፉ አትሌቶች እንደ ማገገሚያ ጊዜ በመመልከት በተሻለ ብቃት ለመመለስ የራሳቸውን ጥረት ማድረግ ነው። በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ስፖርተኞች ከስፖርቱ ላለመራቅ ምን ማድረግ አለባቸው፣ ፌዴሬሽኑስ ሚናውን በምን መልኩ እየተወጣ ነው ለሚለው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ህክምና ከፍተኛ ባለሙያና እና የጸረ አበረታች ቅመሞች ተጠሪዋ ቅድስት ታደሰ ከአዲስ ዘመን ጋር ቆይታ አድርገዋል። የመጀመሪያው ነገር ስነ-ልቦና መሆኑን ባለሙያዋ ይገልጻሉ።በዓለምና በሃገር በመጣው በዚህ ቫይረስ ምክንያት በቤታቸው እስኪቆዩ ድረስ ኦሊምፒክን ጨምሮ ለዚህ የውድድር ወቅት በዝግጅት ላይ የነበሩ አትሌቶች በጥሩ አቋም ላይ ነበሩ። በዚህም ምክንያት አቋማቸው እንዳይወርድና ጂምናዚየሞችም በመዘጋታቸው በቤት ውስጥ የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ይገደዳሉ። ከትንፋሽ ጋር በተያያዘ ያለውን ደግሞ የሰዎች ንክኪ በሌለበት በግላቸው ጫካ አካባቢ መስራት ይችላሉ። ይህም ወቅታዊ ብቃታቸው እንዳይወርድ እንጂ ለውድድር በሚደረግ ልክ አይሆንም። ይህ እንዲሆን ደግሞ አስቀድሞ እንደተገለጸው ዋናው ነገር በመልካም ስነ-ልቦና ላይ መገኘት መሆኑን ይጠቁማሉ። በማብራሪያቸውም ‹‹የሰው ልጅ በተፈጥሮው በጭንቀት ወቅት ሰውነቱ በሚሰጠው ግብረመልስ የተለያዩ ቅመሞችን ስለሚያመነጭ ለውጥረትና ለመደበት ስሜት ይጋለጣል። አትሌትሌቲክስ የሙሉ ጊዜ ስራው የሆነው አትሌትም ውድድሮች ከሌሉ በእንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ ሊገባ ይችላል። ይህ እንዳይከሰትም አትሌቶች ራሳቸውን በስነ-ልቦና ማዘጋጀት ይገባቸዋል›› ሲሉ ያስረዳሉ ባለሙያዋ። ሁኔታዎችን አእምሮ ሲቀበል ሌሎች አካላትን ማዘዝ ስለሚቻል ስነ-ልቦና የመጀመሪያውና ዋነኛው ጉዳይ ነው። ከዚህ ባሻገር በአትሌቲክስ ስፖርት የሚፈራው ነገር ክብደት መጨመር ነው። በክብደት ተወስነው እንደሚካሄዱት የቦክስና የማርሻል አርት ስፖርቶች ሁሉ የረጅም ርቀት በአትሌቲክስም ክብደት መጨመር የራሱ አደጋ ይኖረዋል። በመሆኑም የቡድን እና ጫና ያላቸውን ልምምዶችን በማስቀረት ሰውነትን ባለበት እንዲቆይና የብቃት መዋዠቅ እንዳይከተል የሚያደርግ መሆን እንዳለበት ባለሙያዋ ያስገነዝባሉ። አመጋገብ ላይም አትሌቶች የራሳቸውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፤ አመጋገብ ከሚወጣው ኃይል ጋር ተመጣጣኝ መሆን ይኖርበታል። በዚህ ወቅት ቀለል ያሉ ልምምዶችን እየሰሩ እንደ ወትሯቸው የሚመገቡ ከሆነ ግን ሰውነት ያንን ለማስተናገድ ስለሚከብደው የክብደት መጨመር ይከሰታል። በመሆኑም ይህንን መከታተልና ከቻሉ በየዕለቱ ያሉበትን ሁኔታ በመመዝገብ ማስታወሻ እንዲይዙ ይመከራል። የዓለም አትሌቲክስም በየወቅቱ የሚያወጣውን መረጃ መከታተልም አስፈላጊ ነው። በዚህ ሂደት ሊዘነጋ የማይገባው ዋናው ነገር በቤት ውስጥ የሚሰሩ ማሳሳቢያዎችና ሌሎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ንጹህ አየር ባለበት ስፍራ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ሰው የማይበዛበትና ነፋሻማ አየር ባለበት ስፍራ ቢንቀሳቀሱ ደግሞ የተሻለ ይሆናል። እንደ ዓለም አትሌቲክስ መረጃ ከሆነ አትሌቶች በተለይም የረጅም ርቀት ሯጮች ትንፋሻቸው የዳበረ በመሆኑ ከሌላው በተለየ ተጋላጭነታቸው የሰፋ ይሆናል። በመሆኑም ራሳቸውን ለየት ባለመልኩ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ፈሳሽ በብዛት መውሰድና በሽታን ሊቋቋሙ የሚችሉ ምግቦችንም ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ሁኔታ ማዘውተርና በዓለም የጤና ድርጅት እንዲሁም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ከመሳሰሉ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎችን መከታተል ለአትሌቱ ጠቃሚም ነው። ምክንያቱም አብዛኛው የማህበራዊ ትስስር ገጾችን የሚጠቀም እንደመሆኑ መረጃዎችን የሚያገኙበት መንገድ በራሱ ጎጂ ሊሆን ይችላል። ይህንንና መሰል ግንዛቤዎችን ከማስጨበጥ አንጻር ባለሙያዎች አትሌቱን በአካል ለማግኘት አዳጋች በመሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለያዩ ስራዎችን እንደጀመረም ባለሙያዋ ይጠቁማሉ። የፌዴሬሽኑ አመራሮች ባደረጉት ውይይት አትሌቱ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ክልሎችም የሚገኝ እንደመሆኑ ሁሉንም ተደራሽ ለማድረግ በቴሌቪዥንና በሬዲዮኖች መልዕክቶችን ማስተላለፍ የተሻለ አማራጭ ሆኖ አግኝቶታል። በመሆኑም ሰፊ ሽፋን ካላቸውና ከክልል የመገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር፤ አትሌቱ ልምምዱን እንዴትና በምን ሁኔታ መስራት እንዳለበት በባለሙያዎች ግንዛቤ የሚሰጥ ይሆናል። ከዚህ ባሻገር ከወቅታዊው ሁኔታና ከቫይረሱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን፣ ስነ- ምግብ፣ ስፖርታዊ ስነ-ልቦና፣ የስፖርት ህክምና፣ የመረጃ ክትትል ምን መምሰል አለበት የሚሉና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ነባራዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ ለአትሌቱ እንዲደርስ ይደረጋል። በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ ግን መዘንጋት የሌለበት ዋነኛ ጉዳይ አበረታች ቅመም መሆኑን ያሳስባሉ። ይህንን ግንዛቤ የሚሰጡትም በስፖርቱ ላይ ለረጅም ጊዜ ያሳለፉ ባለሙያዎች እና ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች ላይ ስኬታማ የሆኑ አንጋፋና ተምሳሌት አትሌቶች ሲሆኑ፤ መልእክቶችን፣ ምክሮችንና በተግባር የታገዙ እንቅስቃሴዎችንም ለአትሌቶች የሚያስተላልፉ ይሆናል። ከፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ከስልጠና ጥናትና ምርምር ክፍል ጋር በመሆንም በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች መልእክቶችን ለማስተላለፍም በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ባለሙያዋ ጨምረው ገልጸዋል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 5/ 2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=30273
674
2ስፖርት
የሦስት ታላላቅ ክለቦች አለቃው መጨረሻ
ስፖርት
April 12, 2020
43
ዓለም በኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተሸበረች በምትገኝበት በዚህ ጊዜ የስፖርቱ ዓለም ተቆልፎበት ይገኛል። በቫይረሱ ሳቢያ የስፖርቱ ዓለም ሰዎች ከሚወዱት መድረክ እንዲቆጠቡ ከመገደዳቸው በተጨማሪ የቫይረሱ ሰለባ ከመሆን ባሻገር ሕይወታቸውን ያጡም አልጠፉም። የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ዓለም ሌላ የጤና ፈተናዎች የሌሉባት እስኪመስል ድረስ ትኩረት ሁሉ ወደ አንድ አቅጣጫ አዘንብሏል። ከስፖርቱ ዓለም ሰዎች ማን በቫይረሱ ተያዘ? ማንስ ሕይወቱ አለፈ? በሚል የስፖርት ቤተሰቡ ትኩረት ወደ አንድ አቅጣጫ በተጓዘበት ወቅት የስፔን ሦስት ታላላቅ ክለቦችን በማሰልጠን ብቸኛው የሆነው ራዶሚር አንቲች ባለፈው ሰኞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የስፔን ታላላቅ ክለቦች የሆኑት ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎናና አትሌቲኮ ማድሪድ ብቸኛ አሰልጣኝ የሆነው ሰርቢያዊው አንቲች በሰባ አንድ ዓመቱ በማድሪድ ከተማ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ታሪካዊው አሰልጣኝ ስፔንን እያመሳት በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሕይወቱ እንዳለፈ በርካቶች ግምታቸውን ቢያስቀምጡም ለሞት የበቃው ላለፉት ዓመታት ሲያሰቃየው በቆየው ሌላ ሕመም ምክንያት እንደሆነ ተዘግቧል። በሰርቢያ ዛይቲስ ከተማ የተወለደው አንቲች እንደ በርካቶቹ የእግር ኳስ አሰልጣኞች በተጫዋችነት አሳልፏል። የተጫዋችነት ዘመኑ የሚጀምረውም በስሎቦዳ ዩዚስ ክለብ ሲሆን በርካታ የውድድር ዓመታትን በቤልግሬዱ ፓርቲዛን ክለብ እየተጫወተ አሳልፏል። ከዚህ ክለብ ጋርም እ.ኤ.አ በ1975/76 የውድድር ዓመት የዩጎዝላቪያ ሊግ ዋንጫን ማሳካት ችሏል። ወደ ቱርኩ ክለብ ፊነርባቼ በማቅናትም የሊጉን ዋንጫ አንስቷል። ወደ ሪያል ዛራጎዛ አምርቶም ሁለት የውድድር ዓመታትን አሳልፏል። እ.ኤ.አ በ1980 ወደ እንግሊዙ ክለብ ሉተን ታውን አቅንቶም ከአራት የውድድር ዓመታት ቆይታ በኋላ ጫማውን ሰቅሏል። አንቲች ጫማውን ከሰቀለ ወዲህ የአሰልጣኝነት ሕይወቱን የጀመረው በአገሩና ተጫውቶ ባለፈበት የቤልግሬዱ ክለብ ፓርቲዛን ሲሆን በክለቡ ቆይታው ሁለት የቻምፒዮንሺፕ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል። ከዚያም እ.ኤ.አ በ1988 በተጫዋችነት ወዳሳለፈበት ዛራጎዛ ክለብ አምርቶ ክለቡን የአውሮፓ ካፕ ተሳታፊ ማድረግ ችሏል። እ.ኤ.አ በ1990/91 የውድድር ዓመት አልፍሬዶ ዲ ስቲፋኖን በመተካት የታላቁ ክለብ ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ለመሆን በቅቷል። ይሁን እንጂ ከታላቁ ክለብ ጋር ውጤታማ ጊዜን ባለማሳለፉ ቆይታው አጭር ነበር። ከሪያል ማድሪድ ያልተሳካ የአሰልጣኝነት ዘመን አጭር ቆይታ በኋላ አንቲች ወደ ሪያል ኦቪዶ በማቅናት ለሁለት የውድድር ዓመታት ስኬቶችን አስመዝግቧል። ይህም ስኬቱ ወደ ታላቁ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ዋና አሰልጣኝነት በር የከፈተለት ሲሆን ገና በመጀመሪያ የውድድር ዓመቱ እ.ኤ.አ 1995/96 የውድድር ዓመት የሊጉን ዋንጫና የኮፓዲላሬ ስኬቶችን መጎናፀፍ ችሏል። ይህም በክለቡ ታሪክ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ሲሆን ዛሬም ድረስ የሚዘከር ነው። አንቲች በአትሌቲኮ ማድሪድ ያሳለፋቸው አምስት ዓመታትም ክለቡ ከምንም ተነስቶ አሁን ላይ ከስፔን ታላላቅ ክለቦች አንዱ ለመሆኑ መሰረት የያዘበት ሆኖ ይነገራል። ከአትሌቲኮ ማድሪድ ስኬታማ አምስት ዓመታት በኋላ ወደ ሪያል ኦቪዶ የተመለሰው አንቲች በውድድር ዓመቱ ክለቡ ከሊጉ በመውረዱ ብዙም ሳይቆይ እ.ኤ.አ 2003 ላይ ወደ ታላቁ የካታላን ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ሊውስ ቫንሃልን ተክቶ ሊፈርም ችሏል። በወቅቱ ባርሴሎና ወራጅ ቀጠና ከነበረው ክለብ በሦስት ነጥብ ከፍብሎ የመውረድ ሥጋት የተጋረጠበት ቢሆንም በአንቲች አሰልጣኝነት ስድስተኛ ደረጃን ይዞ ሊያጠናቅቅ ችሏል። ይህም በአውሮፓ ካፕ ተሳታፊነቱን አረጋግጦለታል። እንደ አጋጣሚ ሆኖ በቀጣይ የውድድር ዓመት ክለቡን ለመምራት የተመረጡት አዲሱ ፕሬዚዳንት ሁዋን ላፖርታ አንቲች በካታላኑ ሃያል ክለብ አሰልጣኝነት እንዲቀጥል አልፈለጉም። ይህም ወደ ሴልታቪጎ እንዲያመራ አድርጎታል። እዚያም ግን ቆይታው አጭር ነበር። እ.ኤ.አ 2008 ላይ የሰርቢያን ብሔራዊ ቡድን ወደ 2010 የደቡብ አፍሪካ ዓለም ዋንጫ ለማሳለፍ ሃላፊነቱን የወሰደው አንቲች በማጣሪያው ሊሳካለት አልቻለም። ከአገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር የነበረው ቆይታም በዚሁ በአጭር ተቀጭቷል። ከዚያ በኋላ ግን ለአራት ዓመታት እ.ኤ.አ እስከ 2016 ድረስ በቻይና ሊግ በርካታ ክለቦችን በአሰልጣኝነት መርቷል። ሦስቱን ታላላቅ የስፔን ክለቦች በአሰልጣኝነት በመምራት ብቸኛው ሰው የነበረው አንቲች ባለፈው ሰኞች ለረጅም ጊዜ በቆየበት ሕመም ሕይወቱ ካለፈ በኋላ የስፖርት ቤተሰቡ በተለያዩ መንገዶች ሐዘኑን እየገለፀ ይገኛል። ከነዚህ መካከል የአትሌቲኮ ማድሪዱ ፕሬዚዳንት ኪኮ ‹‹የአትሌቲኮ ማድሪድን ድንቅ መሐንዲስ አጣን፣ እሱ የአትሌቲኮ ማድሪድ ወርቃማ ዘመን የቀየሰ ድንቅ ሰው ነው›› ሲል ገልፆታል። የአትሌቲኮ ማድሪድ የቀድሞ ተጫዋች፣ የአሁን ፕሬዚዳንትና በባርሴሎና ኦሊምፒክ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ዋንጫ ያነሳው ኪኮ‹‹ አንቲች የፈጠራ ሰው ነው፣ የሊጉንና የኮፓ ዲላሬን ዋንጫ እንድናነሳ አድርጓል፣ እሱ ለእኔ ምርጡ አሰልጣኝ ነው›› በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። በአንቲች ስር ከሰለጠኑ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ፖርቹጋላዊው ፓውሎ ፉተር በበኩሉ‹‹አንቲች በአትሌቲኮ ማድሪድ ስለፈፀመው ገድል ለመናገር ቃላት የሉኝም፣ እሱ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ብቻ ሳይሆን ለእግር ኳስም ጀግና ነው፣ ነብሱን ይማር›› ብሏል። የቀድሞው የሊቨርፑልና አትሌቲኮ ማድሪድ ኮከብ ፈርናንዶ ቶሬስ በአንቲች አሰልጣኝነት ስር የማይረሳ ትዝታ ካላቸው ተጫዋቾች አንዱ ነው። ‹‹አንቲች ጥሎን ሄዷል፣ እሱ እግር ኳስን ያስከበረ ጀግና ነው፣ በአትሌቲኮ ማድሪድ የድል ታሪክ ውስጥ ሁልጊዜም ሲዘከር ይኖራል›› በማለት ቶሬስ ሐዘኑን ገልጿል። አንቲች በአሰልጣኝነት ዘመኑ ባሰለጠናቸው ተጫዋቾች ብቻም ሳይሆን በተቀናቃኝ ክለብ ተጫዋቾች ክብር የሚሰጠው መሆኑን የሪያል ማድሪዱ ተከላካይና አምበል ሰርጂዮ ራሞስ አስተያየት ምስክር ይሆናል። ራሞስ ‹‹ተቀናቃኛችን አትሌቲኮ ማድሪድን ታላቅ ክለብ አድርጓል›› በማለትም ሐዘኑን ገልጿል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 4/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=30231
646
2ስፖርት
የዲያጎ ጋርዚያቶ ማረፊያ ታውቋል
ስፖርት
April 14, 2020
22
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ትልቅ አሻራን ማሳረፍ የቻሉ አሰልጣኝ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ኢትዮጵያ በታሪኳ በዓለም ዋንጫ ከ 20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በማሳተፍ አይረሴ ታሪክ ሰርተዋል። በትውልድ ፈረንሳዊው፤ በዜግነት ጣሊያናዊ ዲያጐ ጋርዚያቶ። በኢትዮጵያን ዘንድ የተለየ አክብሮት የሚሰጣቸው አሰልጣኝ ዲያጎ ጋርዚያቶ ርቀው ከነበሩት የአሰልጣኝነት ሙያ መመለሳቸው ተሰምቷል። የ70 ዓመቱ አዛውንት የዲሞክራቲክ ኮንጎው ክለብ ሴንት ኢሎይ ሉፖፖን ለማሰልጠን ከስምምነት መድረሳቸውን ታውቋል:: እኤአ በ1950 ሌስቲዛ የተወለዱት እኝህ አሰልጣኝ በተጨዋችነት ዘመናቸው የተከላካይ መስመር ተሰላፊ ነበሩ።ከ1984 እ.ኤ.አ ጀምሮ በአሰልጣኝነት ማገልገል ሲጀምሩ የፈረንሳይ ዝቅተኛ ሊግ ክለቦችን በማሰልጠን ነበር የቆዩት። የዲያጎ ጋርዚያቶ የአሰልጣኝነት ምዕራፍ ከፍ እያለ መምጣት የቻለ ሲሆን፤ ጅማሮውም ከኢትዮጵያ ይነሳል። አሰልጣኙ ትልቁን ኃላፊነት የተረከቡት በ2001 እ.ኤ.አ ላይ የኢትዮጵያ ሀ 20 ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ሲመደቡ ነበር። በዚሁ ጊዜም የኢትዮጵያን ወጣት ቡድን በአርጀንቲና ለተደረገው 14ኛው የዓለም ወጣቶች ዋንጫ እንዲሳተፍ አብቅተዋል። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት ቡድን ዋና አሰልጣኝነት ከለቀቁ በኋላ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት በክለብ ደረጃ ሲሰሩ ቆይተው በ2007 እ.ኤ.አ ላይ የቶጐ ብሔራዊ ቡድን ተረክበው ነበር። አሰልጣኝ ዲያጎ ጋርዚያቶ የቶጎ ቆይታቸው ከ2 ወራት አልዘለለም።በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ትልቅ ውጤት በማስመዝገብ የተደነቁ ሲሆን ለሁለት ጊዜያት ያሰለጠኑትን የዲ ሪፖብሊክ ኮንጎውን ቲፒ ማዜምቤ በ2009 እ.ኤ.አ የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ እንዲያሸንፍ አድርገዋል።የአሰልጣኙ ውጤታማነት በመረዳት ቲፒ ማዜምቤ ዳግም በአሰልጣኝነት ቀጥሯቸዋል። እኤአ በ2003 እስከ 04 ቲፒ ማዜምቤን ማሰልጠን የቻሉት ዲያጎ ጋርዚያቶ ክለቡ እኤአ በ2010 ዳግም አሰፈረማቸው። አሰልጣኙ አሰልጣኙን ክለቡን እንዲያሰለጥኑ ዳግም በተሰጣቸው እድል ውጤት አልቀናቸውም ነበር። ከቲፒ ማዜምቤ ጋር ለአንድ ዓመት ቆይታ ካደረጉ በኋላ መለያየት ግድ ብሏቸዋል። የዲያጎ ጋርዚያቶ ቀጣዩ አቅጣጫ ወደ ዋይዳድ ካዛብላንካም ሆነ። የዲያጎ ጋርዚያቶ ቆይታ በተመሳሳይ ውጤት አልባ መሆኑን ተከትሎ ክለቡን ጥለው ዳግም ወደ ኢትዮጵያ መጡ። በእኤአ 2012 ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮትጵያ የተመለሱት የ70 ዓመቱ አዛውንት ታሪክን መድገም ሳይችሉ ቀርተዋል። አሰልጣኙ ወደ ሀገራችን ሲመጡ በአወዛጋቢ ሁኔታዎች ዋና ብሔራዊ ቡድኑን በኃላፊነት መያዝ ቢችሉም ፤ ከ2 ወራት በኋላ ተሰናብተዋል።በዚሁ ዓመት ወደ አል ሂላላ ኦምዱር ማን ክለብ ያመሩት አሰልጣኙ የጉዟቸው ምዕራፍ ሁሉ ውጤት አልባ ነበር። የዲያጎ ጋርዚያቶ ከክለብ ወደ ክለብ መሽከርከር በሙያው ውጤት እየራቃቸው ከመምጣቱ ጋር ሰፊ ትችቶችን አስተናግደዋል። አሰልጣኙ በአል ሂላላ ኦምዱርማን ክለብ ጋር ቆይታቸው ውጤት አልባ በመሆኑ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ተሰናበቱ። እኤአ በ2014 አል ሜሪኤሪክ ክለብ ፊርማቸውን ያኖሩት ጋርዚያቶ ፤ከዚህ ክለብ ጋር ጥሩ የሚባል የሶስት ዓመት ቆይታ አድርገዋል። እኤአ በ2017 ከክለቡ ጋር የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ አል ኢተሃድ ተረክበው ነበር ። የ70 ዓመቱ አዛውንት ከሊቢያው ክለብ አል ኢተሃድ ጋር ከአጭር ጊዜ ቆይታ በኋላ ነበር የተለያዩት። የጣልያን ዜጋ የሆኑት ጋርዚያቶ ከሊቢያ ከተሰናበቱ በኋላ ፈላጊ ክለብ ለማግኘት አዳግቷቸው ነበር። የአሰልጣኙ ፈላጊ ማጣት ደግሞ ከውጤት ጋር የሚያያዝ ሲሆን፤ አዛውንቱ ላለፉት ዓመታት ከሙያው እንዲርቁ ያደረጋቸውም ነበር። በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው ዲያጎ ጋርዚያቶን ወደ ስራ መመለሳቸው ተሰምቷል:: አሰልጣኙ የዲሞክራቲክ ኮንጎው ክለብ ሴንት ኢሎይ ሉፖፖን ለማሰልጠን መስማማታቸው ታውቋል:: የዲያጎ ጋርዚያቶ የውጤታማነት ጀንበር እየጠለቀች ቢሆንም፤ ከአዲሱ ክለባቸው ጋር ለማድመቅ እንደሚታትሩ ይጠበቃል። የ70 ዓመቱ አዛውንት ፈታኙ ጉዞ ከሰማያዊ እና ቢጫ ለባሾቹ ጋር የሚነጉድ ይሆናል:: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 6/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=30329
440
2ስፖርት
ያልነጠፈው የስፖርት ቤተሰቡ ድጋፍ
ስፖርት
April 14, 2020
7
የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ስታድየም አካባቢ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ድጋፍ አደረጉ። የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ኮሮና ቫይረስን በጋራ ለመከላከል ይቻል ዘንድ ለበርካታ የጎዳና ተዳዳሪዎች ቫይረሱን ሊከላከሉ የሚችሉበትን የማክስ እና የሳሙና ድጋፍ አድርገዋል። የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ ስታድየም በነበረው ልዩ ፕሮግራም ላይ እስከ 350 ለሚደርሱ የጎዳና ተዳዳሪዎች ምሳ አብልተዋል። በምሳ ማብላት መርሃ ግብሩ ላይም ኮሮና ቫይረስን እንዴት መከላከል እንደሚቻል የግንዛቤ ማስበጫ ትምህርት ተሰጥቷል። «መርሃ ግብሩ የተዘጋጀበት ዋና ዓላማም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለጎዳና ተዳዳሪዎች እንደሌላው ማህበረሰብ ‹በአሁን ወቅት ማን አለላቸው› በሚል ከእነሱ ጎን ለመቆም ነው » ሲሉ የክለቦቹ ደጋፊ ተወካዮች ገልጸዋል። በተጨማሪም ከሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች የተሰባሰበው የገንዘብ እርዳታም ገቢው ለእነዚህ የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆኖ የመጪውን የፋሲካ በዓል በሌላ ልዩ ፕሮግራም እንዲያሳልፉበት እንደሚደረግ ተገልጿል። የስፖርት ማህበረሰቡ ወገናዊነት በቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች እንደተፈጸመው ሁሉ፤ በሌሎች ማህበራትም በኩል ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠሉን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ አሰልጣኞች ይፋዊ ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በእግር ኳስ ስፖርት የሚገኙ አሰልጣኞች የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠርና ለማጥፋት እየተደረገ ባለው ርብርብ በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ጽፏል። በመሆኑም በእግር ኳስ ሙያ ውስጥ የሚገኙ አሰልጣኞች ድጋፎቹን እስከ ሚያዚያ 06 ቀን 2012 ዓ.ም ረፋድ ድረስ ሲደረግ የነበረ ሲሆን ፤በዚህም 118 ሺ 500 ብር በመሰብሰብ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ገቢ ሊደረግ መሆኑ መረጃው አመልክቷል። በዓለማችን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከልና ለመግታት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ላለው ርብርብ የስፖርት ማህበረሰቡ እያደረገ ያለውን አበርክቶ አጠናክሮ መቀጠሉን የሚያስረዳ ተግባር ሆኗል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 6/2012
https://www.press.et/Ama/?p=30351
222
2ስፖርት
የኮሮና ቫይረስ በተራዘመው ኦሊምፒክም ተፅዕኖው ሊቀጥል ይችላል
ስፖርት
April 16, 2020
23
የዓለምን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ ወደተለየ አቅጣጫ ያዞረው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በስፖርቱ ዓለም ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ተዘርዝሮ የሚልቅ አይደለም።አንዳች ውድድር በዓለም ላይ እንዳይኖር ከማስገደድ ባለፈ የስፖርቱን ዓለም ሽባ አድርጎታል።ብዙ ታቅዶባቸው፣ ብዙም ተለፍቶባቸው ለዓመታት በዝግጅት ላይ የነበሩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች በትልቅ ኪሳራ የሚካሄዱበት ጊዜ እንዲራዘም ግድ ብሏል። ጃፓን ካለፉት ሰባት ዓመታት በላይ ከፍተኛ ዝግጅት ስታደርግበት የቆየችው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በትልቅ ኪሳራ ለአስራ ስድስት ወራት የተራዘመና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ታላቅ የስፖርት መድረክ ነው።ይህን ታላቅ የስፖርት መድረክ ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እየተናነቀውም ቢሆን ለ2021 ለማራዘም ተገዷል።ኦሊምፒኩን ጨምሮ በርካቶቹ ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮችና ጉባዔዎች ወደ ቀጣይ ዓመት የተሸጋገሩት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በቁጥጥር ስር ይውላል በሚል ተስፋ ነው።ይሁን እንጂ በዓለም ላይ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከተስፋ በስተቀር የቫይረሱ ስርጭት በጊዜ የሚገታ ወይም ፈውስና ክትባት በዚህ ጊዜ እውን ይሆናል የሚያስብል እንዳልሆነ መታዘብ ይቻላል።ይህንን ከግምት ያስገቡት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቶሺሮ ሙቶ ኦሊምፒኩ የቫይረሱን ስጋት ለማምለጥ በአስራ ስድስት ወራት ቢራዘምም ከቫይረሱ ተፅዕኖ ሊያመልጥ እንደማይችል ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማመልከታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ አስነብቦታል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩ ወደ 2021 እንዲዘዋወር ውሳኔ ላይ ከደረሰ ወዲህ በቫይረሱ ስጋት በአስተናጋጇ ጃፓን ቶኪዮን ጨምሮ በሰባት ከተሞች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።ከቀናት በፊት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም በኮሮና ቫይረስ በጃፓን ከስድስት ሺ በላይ ሕዝቦች ሲጠቁ ከመቶ በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸውን አጥተዋል።ኦሊምፒኩ እስከሚካሄድ ገና አስራ ስድስት ወራት የቀሩት ቢሆንም የቫይረሱን ስርጭት በነዚህ ጊዜያት በቁጥጥር ስር ማዋል ካልተቻለ ኦሊምፒኩ አሁንም ከስጋት ውጪ ሊሆን እንደማይችል ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።‹‹በዚህ ወቅት ማንም በእርግጠኝነት ቫይረሱን በቁጥጥር ስር አውላለሁ የሚል እምነት የለውም፣ ስለዚህ የተራዘመው ኦሊምፒክ ከቫይረሱ ስጋት ነፃ ይሆናል ብለን ለመናገር ይቸግረናል›› በማለትም ሃሳባቸውን አጠናክረዋል። በቫይረሱ ስጋት ኦሊምፒኩን ከአንድ ዓመት በላይ ለማራዘም እንደተወሰነ ያስታወሱት ስራ አስፈፃሚው፣ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዚህ ወቅት ለተራዘመው ኦሊምፒክ ጠንክሮ ከመዘጋጀት ውጪ ሌላ ነገር ሊያደርግ እንደማይችል አስረድተዋል።ይሁን እንጂ የሰው ልጅ እስከዚያው ቫይረሱን በቁጥጥር ስር ያውላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል።የተራዘመው ኦሊምፒክ ዘንድሮ ሊካሄድ በታቀደበት ተመሳሳይ ወቅት እንዲካሄድ ከመወሰኑ ውጪ በየትኛው ቀን እንደሚካሄድ ቁርጥ ያለ ቀን አልተቀመጠለትም።ይህንንም ለመወሰን ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተለየ አማራጭ እስካሁን እንዳልተመለከተ አስረድተዋል።ከዚህ ይልቅ ኦሊምፒኩን ቀጣይ ዓመት ላይ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የተቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ የሚቻልበትን አማራጭ ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የቶኪዮ ኦሊምፒክ ወደ ቀጣዩ ዓመት በመራዘሙ ብቻ በጃፓንም ይሁን በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደሚያስከትል ቀደም ሲልም ሲነገር ነበር።ይሁን እንጂ ይህ ኪሳራ ምን ያህል እንደሚሆን አሁን ላይ ማስቀመጥ ከባድ እንደሚሆን ስራ አስፈፃሚው ጠቁመዋል።ነገር ግን ኪሳራው ከባድ እንደሚሆን አስቀምጠዋል። የኦሊምፒክ ውድድሩ ከመራዘሙ አስቀድሞ የወጡ ጥናቶች እንዳመለከቱት ኦሊምፒኩ ከተሰረዘ ወይም ከተራዘመ የጃፓን ጠቅላላ የአገር ውስጥ ገቢዋ 1ነጥብ 4 በመቶ ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ተጠቁሟል።ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ብቻ የጃፓን መንግስትን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ እንደሚገቡ ቀደም ሲል ተዘግቧል።የጃፓኑ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴም ገና ከመጀመሪያው ከፍተኛ ኪሳራ ሊገጥም እንደሚችል ተናግሯል።ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለዚህ ኪሳራ ስጋት ሰላሳ ሦስቱንም ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች የሚመለከት መድህን የገባ ቢሆንም በቂ እንደማይሆን ታምኖበታል።ፕሬዚዳንቱ ቶማስ ባኽም ኦሊምፒኩ መራዘሙን በገለፁበት ወቅት ከባድ ኪሳራ እንደሚኖር በማመን ሁሉም ባለድርሻ አካላት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ለመጠቆም ሞክረዋል፡፡አዲስ ዘመን ሚያዝያ 8/2012
https://www.press.et/Ama/?p=30486
457
2ስፖርት
የስፖርት ማህበራት በአዲስ መልክ ይዋቀራሉ
ስፖርት
April 15, 2020
15
በአንድ አገር ስፖርት እድገትና ውጤታማነት ላይ ሚና ያላቸው በርካታ አካላትን መጥቀስ ቢቻልም፤ ስፖርቱን የሚመሩ አካላት መሰረት መሆናቸው ይታመናል። በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ስፖርቱ የሚመራው በሁለት አካላት ሲሆን፤ ይኸውም ህዝባዊ እና መንግስታዊ ውክልና ባላቸው ነው። ከህዝቡ የተወከሉና ስፖርቱን ለማገዝ በበጎ ፈቃዳቸው እውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ጊዜና ጉልበታቸውን የሚሰጡት አማተር ባለሙያዎች ስፖርትን በበላይነት ይመራሉ። መንግስታዊው አካል ደግሞ በስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ማህበራቱን ለመምራት በተሰጠው ስልጣን መሰረት ስራዎችን ያከናውናል። የመሪው አካል ጥንካሬ እና ድክመት በስፖርቱ እድገት ላይ ከፍተኛ ሚና ያለው እንደመሆኑ የስፖርት ማህበራቱ እንቅስቃሴ ወሳኝ ይሆናል። በኢትዮጵያ ስፖርት ማህበራት ባለው ሁኔታ ጥንካሬውም ሆነ ድክመቱ በአብዛኛው ከህዝባዊው አካል ጋር ማያያዝ የተለመደ ነው። ነገር ግን ከብሄራዊ እስከ ክልሎች ያሉት የስፖርት ማህበራቱ ባለሙያዎች ቅንጅት፣ ከዓለም አቀፍ ሁነት ጋር የመራመድ አቅም፣ ውድድሮችንና ስልጠናዎችን በተያዘላቸው ጊዜና ሁኔታ እንዲካሄዱ ማድረግ፣ ህግና ደንብን ባማከለ መልኩ መንቀሳቀስ እንዲሁም ለስፖርቱ እድገት መታተር ከስራዎቻቸው ጥቂቱ ናቸው። ሆኖም አብዛኛዎቹ ፌዴሬሽኖች ለውጤታማነት በአዲስ ስልትና በተሻለ ሁኔታ ከመቅረብ ይልቅ የበጀት እጥረትንና ሌሎች ጉዳዮችን እንደ እክል ሙጥኝ ማለታቸው ስፖርቱ በዘገምተኛ አካሄድ እንዲገፋ አድርጓል። ይህንን የተመለከተው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም በዚህ ላይ እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል። ኮሚሽኑ በቅርቡ አገር አቀፍ የስፖርት ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱ ይታወቃል። በዚህ ላይ ተመስርቶም የስፖርት ዘርፍ የአስር ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተዘጋጅቷል። በሪፎርሙ የተጠቆሙ ጉዳዮች በእቅድ እንዲካተቱ የተደረገ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል የስፖርት ማህበራትን ማጠናከር አንዱ ነው። በዚህ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤ የኮሚሽኑን የቀጣይ አስር ዓመት ስራ ሪፎርሙን መነሻ በማድረግ በተለዩ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ከስራዎቹ መካከል አንዱ ደግሞ የስፖርት ማህበራትን ማጠናከር ነው። ከዚህ አንጻር በእያንዳንዱ ፌዴሬሽን የሱፐርቪዥን ዝርዝር ስራዎች የሚከናወን ይሆናል። ከዚህ በኋላም ኮሚሽኑ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የማህበራቱን ደንቦችና መመሪያዎች የማሻሻል ስራ ይሰራል። በመቀጠልም አገሪቷ ባሏትና ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን የመቀመር ስራዎችን የሚመዝን አዲስ ስታንዳርድ የሚዘጋጅ ይሆናል። በስታንዳርዱ መነሻነትም በብሄራዊ ደረጃ ያለ አንድ ፌዴሬሽን ምን ምን ስራዎችን እንዲያከናውን ይጠበቅበታል እንዲሁም በክልል ደረጃ ያሉ ፌዴሬሽኖች ምን ማሟላት ይገባቸዋል የሚለው በአዲስ መልክ የሚለይ ይሆናል። ኮሚሽኑም የራሱን መስፈርት የሚፈትሽ ሲሆን፤ ፌዴሬሽኖች በስታንዳርዱ መሰረት ለስፖርት ማህበርነት ብቁ ከሆኑ ይመዘገባሉ፣ ካልሆኑ ደግሞ በምዝገባው የማይካተቱ ይሆናል። ፌዴሬሽኖቹን ተከትለው የተቋቋሙ ክለቦችም በተመሳሳይ የማጠናከር ስራም ጎን ለጎን የሚከናወን ይሆናል። ክለቦች ህዝባዊ መሰረት ያላቸው መሆኑ፣ የገቢ ምንጫቸው ከምን እንደሆነ፣ የክለብነት መስፈርቱን አሟልተው ስለመቋቋማቸው እንዲሁም ስላሉበት አጠቃላይ ሁኔታ የመፈተሽ ስራዎችም ይከናወናሉ። በታዳጊዎች የስፖርት ማሰልጠኛ ተቋማትም በተመሳሳይ ፍተሻ በማድረግ በተቀመጠላቸው መስፈርት መሰረት እንዲሰሩ የሚደረግ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ያመላክታሉ። በማዘውተሪያ ስፍራዎች ልማት ላይም በተመሳሳይ ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚሰራበትና በሚማርበት አካባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚደረግበት እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው በሚለው ላይም ምዘና የሚደረግ ይሆናል። መንግስት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማውጣት በሚያስገነባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ሪፎርሙ ትኩረት ያደርጋል። በተለይ በማዘውተሪያዎች መተዳደሪያ አዋጅ ላይ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ የሚሰራ ይሆናል። ከዚህ ባሻገር የስራዎቹ አካል በሆኑት ሰራተኞች ላይ ክለሳ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በተቋሙ ቢፒአር እየተሰራ ይገኛል። በስፖርቱ ልማት ላይ ለውጥ ባለመምጣቱ በሪፎርሙ ዝግጅት ወቅት በተደረገው ጥናት በተለዩ ጉዳዮች ላይ በመንተራስ ወደ ስራ ተገብቷል። መሰል ስራዎችን ማከናወን ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም የስፖርት ማህበራትን በአዲስ መልክ ማደራጀቱ ግን ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ኮሚሽነሩ አስረግጠዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ ዱቤ ጂሎ በበኩላቸው ከተወሰኑ ማህበራት ባሻገር አብዛኛዎቹ ያሉት በስም መሆኑን ይገልጻሉ። ዘርፉ በርካታ ችግሮች ያሉበትና ሰፊ ስራን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ስትራቴጂካዊ አካሄድ አስፈላጊ ነው። ማህበራት ካልተጠናከሩ፣ የክለቦች አደረጃጀት ላይ ካልተሰራ፣ ታዳጊና ወጣቶችን ላይ ከላይ ጀምሮ የአሰራር ስርዓት ካልተዘረጋ እንዲሁም አካዳሚዎች ላይ የተወሰነ ስራ ሳይከናወን ውድድር ብቻ ማዘጋጀት የትም ሊያደርስ አይችልም። ስራው ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም ማህበራት ራሳቸውን የሚችሉበትን ሁኔታ ከክልል እስከ ዓለም አቀፍ ድረስ የተስተካከለ ግንኙነት ያላቸው እንዲሆኑ የሚሰራ መሆኑን ያብራራሉ።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 7/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=30421
522
2ስፖርት
የእንቁጣጣሽ ትውስታ
መዝናኛ
September 16, 2019
45
 የዘንድሮው እንቁጣጣሽ በጣም አስደሳች ነበር። አበቦቼን ሁሉ ሰጥቼ ጨረስኩ። ጎረቤቶቻችን ብዙ ሽልንጎች፣ ከርኮች፣ ዲናሬዎች ሰጥተውኛል። የፍራንኩ ብዛት ቁጥሩን አሳሳተኝ። ያም ሆነ ይህ ብዙ ገንዘብ አግኝቻለሁ። ያሰብኩትን ሁሉ እንደምገዛ እርግጠኛ ሆንኩኝ። በድንቡሎ አራት ከገዛሁት ደስታ ከረሜላ አንዷን ከመጠቅለያዋ ፈትቼ እየመጠጥኩ እማዬን ሂሳብ እንድናደርግ ጠየቅኳት። «መለዮህንና ማሊያህን እሚገዛልህ አምስት ሽልንግ አለህ» አለችኝ። ተደሰትኩ። (ዳቦ ብላ ብለው እማማ ሸጊቱ ባያስቀምጡኝ ኖሮ ብዙ እሸቅል ነበር) እቤት ቁጭ ብዬ እማዬ ጠብሳ የሰጠችኝን ስጋ እየበላሁ የአንዳንዶቹ ጎረቤቶቻችን ሁኔታ ትውስ አለኝ። አንድ ዓይናው አባባ አጋፋሪ ዓይናቸውን አፍጥጠው አበባዎቹን አንድ በአንድ «ይሄ ማን መሆኑ ነው?» «እመቤታችን ከጌታችን ጋር ነች!» አልኳቸው። መለዮአቸውን ሲያወልቁት ጸሃይ አርፎበት የማያውቀው መላጣ አናታቸው ነጭ ሆኖ ያብለጨልጫል። «ይሄ ጌታችን መሆኑ ነው? ኧረ ልጅ ሳይሆን ትልቅ ሰው ነው እሚመስለው! አስተያየቱስ ቢሆን? ኤድያ! ይሄ አላማረኝም ይቀየርልኝ። ቅዱስ ሚካኤል ጎራዴውን መዞ ሳጥናኤልን ሲቀጣ የሚያሳየውን አበባ ሰጠኋቸው። «ምነው ሰይፉን ጎራዴ አስመሰልከው?» «ጎራዴና ሰይፍ አንድ አይደለም?» «ዝም በል! ጎራዴና ሰይፍ አንድ ነው ይለኛል? ‘ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች’ እሺ ይሁንልህ፣ ደግሞስ ሺ በክንፉ ሺ ባክናፉ የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል አንድ ብቻውን በሳጥናኤል ላይ ዘምቶ ሳልከው? አይ የልጅ ነገር! እስኪ ሌላውን አሳየኝ።» የቅዱስ ገብርኤልን ስሰጣቸው አፍጥጠው ሲያዩት ዓይናቸው እንደዓሳ ዓይን ቅንድብ አልባ ሆነ። ትንሽ ፈገግ ብለው የምስራች ነጋሪው ኃያሉ ቅዱስ ገብርኤል ምነው በእሳት ላይ መራመዱን፣ በሚንተገተግ እቶን ላይ ማዝገሙን ገደፍከው?» ብለው ሁሉም ስዕሎች ላይ አቃቂር አውጥተው በገንቦ አበባ የተደረደረበትን ስዕል መረጡ። ራስጌያቸው ካስቀመጡ ዝርዝር ፍራንክ ከርክ አንስተው ሰጡኝ «እድግ በል ልጄ! የሰለሞንን ጥበብ፣ የማቱሳላን እድሜ፣ የኢዮብን ትዕግስት እርሱ አንድዬ ይስጥህ! እናትና አባትህን ጧሪና ቀባሪ ያድርግህ» ብለው መርቀውኝ «ያ አባትህ እንዴት አደረ?» «አንበሳው ሲያገሳ እርሱ ነው የነገረኝ።» «መናገር ጀመረ? ለእርሱ ለአንድዬ ምን ይሳነዋል?አይዞህ እየተሻለው ነው» ብለውኝ ወጣሁ። ለከርሞው ለአበባ አጋፋሪ አበባ እምሰጣቸው መጨረሻ ላይ ነው ብዬ እየዛትኩ ወደ ቤቴ ተመለስኩ። እቤቴ ስገባ የስጋ ጥብስ ሽታ አወደኝ። «ስጋ ከየት አመጣሽ?» «እድሜ ላንተ! አንተ ነህ የገዛህልን» «አበባ ሰጥቼ ባመጣሁት ፍራንክ?» «ታዲያ! እግዚአብሄር ውለታህን ይክፈልህ። በአምስት ሽልንግ ግማሽ መደብ ከማርገጃ ገዝቼ መጣሁ። አሁን ደግሞ ቡና አፈላና ቤታችን ዓመት በዓል ዓመት በዓል ይሸታል።» ኩራት ተሰማኝ። «ግን ከማሊያዬና መለዮዬ መግዣ ፍራንክ ላይ ወሰድሽ?» «በፍጹም! ከእርሱማ አልነካብህም።» ተደሰትኩ። ብር ከስሙኒን ሰጥታኝ ከጉልት ሄጄ መለዮዬን ከእነመነጽሩ እንድገዛ ጠየቅኳት። «ያታልሉሃል» ብላ እምቢ አለችኝ። በዚህ ስንጨቃጨቅ የክርስትና እናቴ እማማ ቦጋለች አንድ በዳንቴል የተሸፈነ ሳህን ይዘው ገቡና «ምንድነው?» ኮስተር ብለው ጠየቁኝ። ነገርኳቸው «ስጪው፣ ጓደኞቹ ውጪ አሉ ያጋዙታል» ሲሉ ፈጥኜ ወጥቼ እኔ ያሰብኳትን ባለመነጽሩን ባርኔጣ ያደረገውን ሲሳይ ጎቢጥን ጠራሁት። አንድ ዓይና መነጽሩን ዛሬ ቀይሮታል።«ና! ባለመነጽሩን ኮፍያህን ለእማዬ ግባና አሳያት!» «እሺ» አለና እየዘነጠ ከፊት ለፊቴ ተራመደ። እናቴን በዚያ ፈጣን ምላሱ አሳመናትና ብር ከስሙኒውን ተቀብለን ወደ ጉልት ሄድን። «የበግ ቆዳ ያለው?!» እየጮኸ ይለፈልፋል ነጋዴው። «የዶሮ ቆዳ ያለው!» አብረውት ይጮኻሉ የሰፈሩ ልጆች። ነጋዴው ጸጥ ብሏቸው ስራውን እየለፈፈ አለፈ። ከገበያ ስንመለስ የሰፈር ልጆች እኛ ቤት አበባየሆይ ይጨፍራሉ። አስናቀች በድርብ ጥርሷ እየሳቀች ከበሮ ትመታለች። መሰረት፣ ሰብለ፣ ፋንቲሽ፣ ጸሃይ፣ አሰገደች፣ ሃዋ፣… እያጨበጨቡ ይቀበሏታል። የካፊያው ጭቃ ከቤት ቤት ሲዞሩ ጫማቸው ላይ ክፈፍ ሰርቷል። ሸራ ጫማ፣ ኮንጎ ጫማ፣ ባዶ እግር ይታየኛል። የሃገር ባህል ልብስ፣ ሻማ፣ ሽንሽን ለብሰው ዘንጠዋል። እማዬ ስሙኒ ሰጠቻቸው። ከብረው ይቆዩን ከብረው በዓመት ወንድ ልጅ ወልደው ሰላሳ ጥጆች አስረው … ከብረው ይቆዩን ከብረው በመነፅሬ ሳያቸው አረንጓዴ ይመስላሉ። ጎረቤታችን እማማ በለጡ ቤት እየጨፈሩ ሲሄዱ እኔ ወደ ጓደኞቼ ሄድኩኝ። ቀጢሳው ፊኛ ይነፋል፣ ተረፈ ገልጆ ሆዱን እያባበሰ ስለበላው ምግብ ደስ እያለው ያወራል፣ ጎቢጥ መነጽሩን አስሬ እያስተካከለ ሲያድግ ስፖርተኛ እንደሚሆን ያወራል፣ ሴምላል ከረሜላውን ቆርጥሞ ያከፋፍለዋል፣ ሻቃ ስለሚገዛው ባለ ብር ኳስ ያወራል፣ ይጥና ትምህርት ቤት ሲጋባ ስለሚገዛቸው ደብተሮች፣ እርሳስና ላጲስ ላውራ እያለ ይወተውታል፣… … አለሚቱ አንጎሏ አበባዬን ተቀብለው ፍራንኬን ሳይሰጡኝ ብዙ አመላለሱኝ። እንደዋዛ ጎራ እያልኩ በሌላ ጉዳይ በበራቸው የማልፍ እየመሰልኩ ታየኋቸው። እርሳቸው ግን ከእነመፈጠሬም የረሱኝ መሰሉ። በመጨረሻም እኔም የማላውቃቸው፣ እነርሱም የማይሰጡን ሆነን እንደተፋጠጥን፣ እንቁጣጣሽ አለፈ። በማግስቱ በራቸው አጠገብ ከጓደኞቼ ጋር ስንጫወት ጠሩኝና ስሙኒ ሰጡኝ። ድካሜን ቋንቋ አልባ ውትወታዬን ሁሉ ረሳሁት። ለነገ «ሙቪ» መግቢያ ቼላ ኖረኛ!!! (ዘነበ ወላ፥ ልጅነት)አዲስ ዘመን መስከረም 5/2012
https://www.press.et/Ama/?p=18098
586
1መዝናኛ
“… አፈር ስሆን !”
መዝናኛ
September 15, 2019
54
 ጠረጴዛ ሙሉ ምግብ በአይነት በአይነቱ ደርድረን ‹‹ኧረ ብሎ! ምነው ብሉ እንጂ በሞቴ! … አፈር ስሆን!›› ብሎ ለምኖ የሚጋብዝ ሰው ከኢትዮጵያውያን ውጪ የትም አገር ላይ ያለ አይመስለኝም:: ይሄ የኛ ማንነት ነው:: ‹‹እንዲያው ለምዶብን ነው ›› እንዳትሉኝ እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን ከሌላው ዓለም የምንለይበት ብዙ ባህሎችና ልምዶች ያሉን ህዝቦች ነን:: መዘመን ሳይከፋ አሁን አሁን ያለ ባህል ወጉ ፈር የለቀቀ ስልጣኔ አለኝ ባዩ በዝቶ ካልሆነ በስተቀር፤ የሚያምርብን ወጉ አብሮ መብላት መጠጣቱ ነው:: ምክንያት ፈልገው አብረናቸው እንድንሆን የሚሹት ቤተሰቦቻችን:: ወላጆቻችን:: ጎረቤቶቻችን:: ጓደኞቻችን… ቤታቸው እስክንሄድ ጉጉቱ ሊገላቸው ነው የሚደርሰው፤ አግኝተውን ነው:: ፍቅር አስገድዷቸው ያለ የሌላቸውን ሁሉ አቅርበው ‹‹ኧረ አፈር ስሆን!›› ይሉናል:: አፈር ስሆን ብሎ ለሚጋብዝ ወዳጅ በወጉ በባህሉ ‹‹ኧረ ጠላትሽ! ለምን አፈር ትሆኛለሽ/ትሆናለህ›› ብለን ቤት ያፈራውን መመገብ ነው፤ እየተገባበዙ መተሳሰቡ:: ያን ጊዜ አቤት ጨዋታው መድራቱ፤ በተለይ ኢትዮጵያዊ ወጉ። እስኪ የዚህን ዘመን የኑሮ ውድነቱን አስቡት። ከዚያ መልስ ወግ ባህላችንን። እውነት ዘመኑ ያገባብዛል? እንዳለው የኑሮ ውድነት፤ ዶሮ በአራት መቶ ብር ገዝቶ ማለቴ ድሮ ሰንጋ በሚጎተትበት ብር። ምን አራት መቶ ብቻ ዶሮ ከነልጆቿ ከነማጠፈጫው የአንድ ሺ ብር ጌታ ሆና ሰው ሁሉ በሩን ዘግቶ መብላት አልነበረበትም ትላላችሁ? ነገሩ ግን ወዲህ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያኖች ነን።ባህላችን አይፈቅድም። በር ዘግተን አንበላም። ኑሮ ለምን ከፈለገ ጣሪያ አይነካም። የምን ሰስቶ ቆንጥሮ መመገብ ነው። የኛ ማንነት ይሄ በመሆኑ በራችንን ከፈት አድርገን ‹‹ግቡ… ግቡ ጎራ በሉ:: አረፍ በሉ›› እንላለን። ወዲያው ይከተላል ከምግብ ከመጠጥ በአይነት በአይነቱ። ያቀረብነውን ማእድ እንግዳ እያማረጠ ሲበላ እያየንም አንረካም፤ እንቀጥላለን ‹‹ኧረ ብሉ! አፈር ስሆን… በሞቴ!››። ደስ ብሏቸው እንዲመገቡት ከምግቡም ቀመስ እያደረግን ‹‹ጣፋጭ ነው ‹‹በባለሙያ የተዘጋጀ ነው›› እንላለን። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን ነን። ብርጭቆውን ሞልተን ቀድተን ወደ አንደኛው የእጃችን መዳፍ ከመጠጡ ፈሰስ እያደረግን ‹‹እንዴት ጥሩ ጠላ›› የማር ጠጅ መሰሎት፤ ጠጁ በቤት የተዘጋጀ ነው ፤ ጠላው ገብስ ? ለስላሳ ጉሽ ነው እራስ አይነካም›› እያልንም ለጤናም ዋስትና እንሰጣለን። ባህል ወግ መከባበራችንን እናሳያለን። ሁሉም እንዲበላልን፤ እንዲጠጣልን በመጓጓት። አቤት ሲያምርብን ምክንያቱም ባህላችን ነዋ። ያለውን ሁሉ በአይነት በዓይነቱ አቅርቦ ብሉልኝ በሚል ተማጽዕኖ አድርጎ ብቻ የሚረካ ጥቂቱ ነው። ይሄ ነው የእኛ ባህላችን ግቡልኝ ብሉልኝ ጠጡልኝ ማለታችን። ያለውን ተካፍሎ ተቋድሶ መመገብ ፤ደግሞ መመራረቅ ‹‹ለከርሞ በሰላም ያድርሰን›› ብለን ለቀጣዩ ዓመት መልካም ተመኝተን ‹‹ለሰጫችን ይስጥልን›› ብለን እንለያያለን። እኛም ተራ አለንና ልንጋብዝ እንዘጋጃለን። ይሄ የእኛነታችን ባህል ታዲያ ከወንዝ ወዲህና ከወንዝ ወዲያ አይልም። ብሄር? ቋንቋ? ፆታ? ቀለም? አይጠይቅም። ኑ አብረን እንብላ እንጂ ‹‹አንተ ቆይ ከብሄርህ ጋር ተቀላቀል›› የተባባለበትን ዘመን እኔ በበኩሌ አላስታውስም። ኧረ እንዲያውም የለም። ሁሉም ሰው ጓዳው ሲሞላ በዓል ሲመጣ በአንድ ገበታ መቋደሱ የነበረ ነው። አሁንም ያለ ወደፊትም አጠናከረን የምንቀጥለው። የትም እግራችን እስኪቀጥን ሄደን የማናገኘው ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነው። መታወቂያችን! ስለኛ ብዙ ካልኩ አይቀር ባህል ወጋችን ልዩ የሚያደርገን ውብ ማንነታችን መሆኑን ለማሳየት እስቲ አንድ ትዝታዬን ላውጋችሁ። ባህር ማዶ አንድ ወቅት ብቅ ባልኩበት ጊዜ የገጠመኝን ነበር። ሁሌም አስታውሰዋለሁ። ደቡብ አፍሪካ ነው። በቆይታዬ አገሪቷን ከባልደረቦቼ ጋር ዞር ዞር ብለን ከጎበኘን በኋላ ሰብሰብ ብለን እራት ለመመገብ ወደ አንድ ምግብ ቤት ገባን ። እኛ ካዘዝነው ምግብ በቁጥር እንበልጥ ነበር። ከሰው ቁጥር በአንድ የሚያንስ ምግብ አዘዝን። ማይነስ ዋን እንደሚባለው ማለት ነው። አስተናጋጁ ግን ‹‹አንድ ሰው ያላዘዘ አለ›› በሚል ደጋግሞ እንዲታዘዝ ጠየቀ። አንዱን ምግብ ለሁለት ልንመገበው መሆኑ ሲነገረው በጣም ግር አለው። ኧረ እንዲያውም ገረመው። ይህን አይነቱን ባህል አያውቅምና የታዘዘው አይነት ተጨማሪ ምግብ እንዲመጣ የተነገረው መስሎ ተሰማው። አሁንም አለመሆኑ ተነገረው። ሲመለስ ግን ‹‹ማንም የማንንም ምግብ መመገብ እንደማይችል ፤ ያዘዘውን ምግብ በልቶ ካልጨረሰ ደግሞ አስጠቅልሎ በቴክ አዌይ መልክ አስደርጎ ወደ ቤቱ መውሰድ አለበት›› በማለት ሊያስረዳን ሞከረ። የሆቴሉ ህግም ሆነ የእነሱ ባህል ሁሉም የራሱን ይበላል እንጂ የሌላውን መካፈል አይችልም የሚል አይነት ነበር። እኛም ተገረምን እነሱም ደነቃቸው። አንድ ሰሀን ላይ በጋራ መመገብ። ለዚያውም እየተጎራረሱ መመገብ ለለመደ ሰው ይሄ በጣም እንግዳ ሊሆን ይችላል። በእኛም ላይ ይሄ ነበር የተፈጠረው። በአንድ ገበታ ላይ ከአምስት ያላነሱ እጆች ተዘርግተው እንደ ፍላጎታችን ጠቅለል አድርገን በመጉረስ ካለማንም ገሳጭ የምንበላው ምግብ ነው። አንድ ምግብ ለሶስት ብንበላስ ማን ከልክሎን። በወቅቱ የሌላውን እና የራሳችንን ባህል እያነፃፀርኩ ተገረምኩ ። አጋጣሚውን ግን የጨዋታ ማድመቂያ አድርገነው ምግባችንን አወራረድን። ‹‹ኧረ ብሉ አፈር ስሆን›› እየተባለ ምግብ ከሚጋበዝበት አገር የመጣን እንግዶች፤ ኢትዮጵያውያን መሆናችንን አላወቀምና አይፈረድበትም። መለስ ብዬ ኢትዮጵያዊነት አስተዳደጋችንን ሳየው አሁንም እኮራለሁ። ቤተሰቦቻችን አንድ በሬ ለአስር ተካፍለው ቅርጫ አብልተውናል። እኛም ዓመት በዓል በመጣ ቁጥር ቅርጫ የለም እንዴ ብለን በጉጉት እንጠብቃለን። የስጋ አምሮታችንን የምንወጣው በጋራ ከምናርደው የዓመት በዓል በሬ ነው። ከልጅነት አእምሮ የማይረሳው አንዱ ቅርጫ ነው። አባቴ ወደ ቅርጫው ቦታ በማለዳ የሚያመራው ‹‹ረፈድ ሲል ዘንቢል ይዛችሁ ኑ›› የሚለውን መልዕክቱን አስቀድሞ ነው። እኛስ ብንሆን አዲሱን ቀሚስ ለማስመረቅ ከጓደኞቻችን ጋር ለመገናኘት ያ ጥሩ አጋጣሚ አይደል? ከተባላው ሰዓት ቀደም ብለን ተጠራርተን ዘንቢል አንጠልጥለን በበሬ ማረጃው ስፍራ ከተፍ ነው። ልጆች አንዳንዴም ሴቶች ዘንቢላቸውን ይዘው ዳር ላይ ቁጭ ብለው ይጠባበቃሉ ምኔ በደረሰ እያሉ። ወንዶቹ ከዚህ ወደዚያ ተፍተፍ ይላሉ። አባቶቻቸውን ይረዳሉ። የእርድ እና የመከፋፈሉ ስራ ሳይጠናቀቅ እንጀራ በትሪ‹› አዋዜ እና ሚጥሚጣ ከች ይላሉ። አዋዜው ካልደረሰም ችግር የለም በርበሬው በአረቄ ተለውሶ አዋዜ ይሆናል። ይሄኔ በስፍራው የተገኘው ሁሉ ጉበት ማወራረድ ላይ ይሳተፋል። ‹‹ግሩም ነው›› ከሚለው ጀምሮ ‹‹ጉበት እኮ ለደም ማነስ ፍቱን መድሃኒት ነው›› እስከሚለው የጉበት ጠቀሜታ ተንታኝ ሆኖ ቁጭ ይላል። ከጉበቱም ከቁርጡም በሚጥሚጣ እየተለወሰ በስራ ለተጠመዱት ከስር ከስር ጉርሻው ይካሄዳል። ወባ እንደያዘው ሰው የሚንቀጠቀጠውን ትኩሱ የበሬ ስጋ እየቆራረጡ መመደቡ ምን ያህል ፍትሀዊነት እንዳለው አስቡት ። በእያንዳንዱ ሰው ላይ ያለው እምነት ሙሉ ነው ።ሚዛን አይጠየቅ፤ የሀይማኖት አባት ወይም ሽማግሌ አይጠራ ብቻ በራስ እጅ ? በአይን ሚዛን እጅ እንዳመጣው ይመደባል። ድልድሉ ሲያበቃ አነስ ያለ ልጅ ይጠራና በወረቀት ላይ ተፅፎ የተጠቀለለውን ስም በየመደቡ ላይ እንዲያስቀምጥ ይደረጋል። ያኔ በቃ ተመራርቆ ምድቡን ማንሳት እንጂ የእከሌ ትልቅ የአያ እከሌ ትንሽ የሚል ፈፅሞ አይነሳም። ከዚህ ብሄር ከዚያ ፆታ ብሎ የሚከፋፍል ቀርቶ በሀሳቡ የሚመጣበት የለም። በጊዜው የቅርጫ እንጂ የብሄር ክፍፍል የማይታሰብ ነው። አንድ በሬ ለአስር ቤተሰብ፤ በአንድ ቤተሰብ አምስት ሰው ቢኖር፤ አንድ በሬ ለሀምሳ ሰው በፍቅር ተካፍለን እንበላለን። ደግሞ እንመራረቃለን፤ ለቀጣዩ ዓመት በሰላም? በደስታ ? በጤና ያገናኘን ብለን። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን ነንና። ሁላችንም ጎረቤታሞች ስጋውን ተካፍለናል ፤በሁሉም ሰው ቤት ስጋ አለ፤ ስጋ የምለው ለእኛ ትልቁ ክብርም የምንሰጠው ምግባችን ስለሆነ እንጂ በዕለቱ ጠላው? ጠጁ? ዳቦው? ፈንድሻው ? ቡናው… ሁሉ ሳይቀር በእያንዳንዳችን ቤት አለ። ምን ቢሞላ ያለ ሰውና ካለ ጎረቤት አይጥምም። ስለዚህ ‹‹ኑ ቡና ጠጡ›› እንላለን። አብሮ የበላና አብሮ የጠጣ በሀዘን በደስታውም አይተጣጣም እንደማለት ነው ። እናም ምሳ አንዱ ቤት፤ እራት ሌላኛው ቤት። አብሮ ይጫወታል ፤አብሮ ይደሰታል ይሄ ሀሳብ የምንለዋወጥበት መድረክም ነው። የተጣላ ማስታረቂያም ነው። መቼም ከሰው ጋር በተለያየ ምክንያት መጋጨቱ አይቀሬ ነው። በልጅም በውሻም፤ በሌላውም በሌላው ብቻ የጠብ ምንጭ አይጠፋም። ግን ፀቡ አይዘልቅም። ቢሆንም ግን ዘር ማንዘር፣ ብሄር ብሎ አይቆጠርም። ‹‹እገሌና እገሊት ተቀያይመዋል›› ከሚል አያልፍም። ለዚህ ደግሞ ‹‹በዳይ ተበዳይ›› ተለይቶ ይቅርታ እንዲጠያየቁ ይደረጋል። የይቅርታው ማሳረጊያም አብሮ መብላት ይሆናል። አብሮ የበላ ጥርስ አይሳበርም፤ ሰላም ለመንደሩ፤ ሰላም ለቤተሰብ፤ ሰላም ለሁላችን ይሆናል:: ይሄ ነው ኢትዮጵያዊነት ባህላችን። አብሮ በልቶ፣ አብሮ ጠጥቶ፣ ሲጣሉ ታርቆ፣ ደስታና ሀዘንን በጋራ ተካፍሎ ማሳለፍ። ታዲያ ይሄ ሆኖ ስር መሰረታችን፣ ማንነታችን፤ ዛሬ ላይ በሆነው ባልሆነው መጎነታተሉን ምን አመጣው? በሉ እንግዲህ መቼም ‹‹ችግር አይፈጠር›› ሳይሆን ሲፈጠር ባሉን ባህላዊ እሴት ማረቅ እንደምንችል መረዳት ነው ዋናው ቁምነገሩ። ኑ ማዕድ ዳር እንሰባሰብ! መጎነታተሉን ተወት አድርገን ‹‹እስቲ በሞቴ አፈር ስሆን…..ብሉልኝ ጠጡልኝ›› እያልን አብሮነታችንን እናድስ:: ሰላም!አዲስ ዘመን መስከረም 4/2012 አልማዝ አያሌው
https://www.press.et/Ama/?p=18056
1,063
1መዝናኛ
የበዓል ሰሞን ስብሰባዎች!
መዝናኛ
September 13, 2019
29
አበባ አየሁ ወይ፤ ለምለም… አበባ አየሁ ወይ ለምለም….ባልንጀሮቼ፤ ለምለም ግቡ በተራ …” ጠዋት ቀድሜ የሰማሁት የአዲስ ዓመት መዳረሻ ብስራት መንገሪያ የልጃገረዶች ጨዋታ ነው ። እርግጥ የዘመኑን ያህል በለውጤ ላይ ባላምን ደስ ብሎኛል። አዲስ ዓመት እንደኛ የሚደምቅለት ወይም የሚደምቅበት አለ? ግን አይመስለኝም፤ ተፈጥሮ ሁላ አበባ አፍክታ፤ የሰማዩ ደመና ሁሉ ተገፍፎ፤ ብርሃኑ ሲገልጥ አዲስነት በተፈጥሮም ላይ ሲነግስ እኮ ነው ዘመናችንን የምንለውጠው፡፡ ይህ ከተፈጥሮ ጋር በጋራ የምንለውጠው አዲስነት አያስደስትም? በጣም እንጂ! “አዲስን ዘመን በአዲስ መንፈስ መጀመር ጥሩ ነው፤” ሲሉ ደጋግሜ ሰምቻለሁ ። ደስ ሲል! ያ ለውጥም በአዲስነት ላይ መገኘት ትልቅ ነው ። አዲስነት ተሰማኝ! ለዚያውም በማለዳ ስንት መርዶ በሚነገርበት ሀገር ላይ የአዲስ ዓመት ብስራት፤ አዲስ ዘመን ነጋ ዜማ መስማት መታደል አይደል? አዲስ አበባ የበዓል ሰሞን ሩጫዋ ሰርገኛ ጠርታ ደጅ ላይ ያስቆመች፤ የምታበላው ያለሰናዳች ሙሽራ ያስመስላታል ። የበዓል ሰሞንማ ባልዋን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየች ሙሽራ ያህል ጭንቀቷ ይበረታል ። የበዓል ድባቡ ከትርምስ ጋር የተደበላለቀ ሁነት፤ ደስም ጭንቅም ያሰኛል ። አውዳመት የኛን ያህል የሚደምቅለት አለ ግን? በዓሉን ለማክበር የምናሰናዳው ነገር መብዛቱ የምነከውነው ተግባር ማየሉ አንድ ቀን ብቻ አክብረነው የሚያልፍ እኮ አይመስለም ። እኔ ምለው? ይሄ ሁሉ የበዛ ክብረ ባዓላችን ድምቅምቅ አድርገን እያከበርን ምግብ በየአይነቱ፤ የሚጠጣ በየወንጪቱ፤ አቅርበን እየላፍን…፤ እያሻመድን የኑሮ መወደድ ሳያነቃንቀን፤ የጊዜ መቀየር ሳይለውጠን፤ የቀጠልነው በምን ይሆን? ኑሮ ተወደደ፤ ረከሰ፤ ተሰቀለ፤ ተዘፈዘፈ፤ ዓመት በዓል ዓመት በዓል ነው። ሁላችንም ዘንድ ከየትም ተጠረቃቅሞ ቤት ይሞላል ። በእኩልነት ሁሉም በጋራ ይስቃል፤ በአብሮነት ጨዋታው ይደራል ። እንደምናከብራቸው በዓላት ብዛት፤ እንደምንደግሰው ድግስ ስፋት አዘውትረን ችግር የምናወራ፤ ድሎት የራቀን አንመስልም እኮ! ውዶቼ፤ ትናንት ቤታችሁን የዋላችሁበትን አስቡት እስኪ? ከኑሮና አኗኗራችን በላቀ፤ ከምግብና አመጋገባችን በተለየ የአውዳመት ድግሳችን የተለየ ነው ። እንዲያው በበረከቱ ቤታችንን እየሞላው እንጂ ተማርረን የምንገልፀው አጥተን ነጣን የበዓል ቀን ላይ በልተን ወዛን ይለወጣል ። ሰው ግን ከየት ነው ይሄን ብር የሚመጣው፤ አውዳመት እየጠበቀ የሚረጨው? የሆነ ያልታወቀማ ምንጭ አለ ። ግድ የላችሁም ውዶቼ፤ ሰዎች ከገቢያቸው በላይ ሲያወጡ ካላቸው በላይ ሲነጩ መጠርጠር ጥሩ ነው ። በዓመት በዓል ላይ የሚፈልቅ፤ አውዳመት ላይ የሚፍለቀለቅ አንድ ያለታወቀማ ምንጭ አለ መሰለኝ ። የሰዎች ብር ማግኛ መንገድ የተለያየ፤ የገቢ ምንጫቸው ለየቅል ቢሆንም ሰሞኑን በአንድ አጋጣሚ ከስራ ባልደረባዬ የሰማሁት የበዓል ሰሞን ስብሰባዎች ገጠመኝ ግን ገርሞኛል ። በዓላት በደረሱ ጊዜ የስብሰባዎችን መብዛት ዋነኛ ምክንያት እንዳጤነው አደረገኝ። እኔ ምለው በዓውዳመት ሰሞን ስብሰባ የሚበዛው ለምን እንደሆነ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? ጉዳዩ ወዲህ ነው ወገኖች፤ ግርግሩን ተጠቅሞ ኪስ ለመሙላት፤ በዓልን አስታኮ ትርፍ ለመብላት ነው። የበዓልን ግርግርና አውዳመት በመጣ ቁጥር የሚዘጋጁ ስብሰባዎች የዛሬው ትዝብት ማጠንጠኛዬ ሆኗል ። የዓውዳመት ሰሞን፤ በተለይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በስብሰባ ይጨናነቃሉ ። በዓል ሲቃረብ ስልጠና መስጠት፤ ሰበብ ፈጥሮ መሰባሰብ ተለምዷል። ሰብሳቢውም ተሰብሳቢውም በስብሰባው አላማ ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ከስብሰባው የሚገኘው ብር ወይም አበል ላይ ያተኩራሉ ። በአንድ ጊዜ ሁለት ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ከሁለቱም ቱርፋት ለመቋደስ የማይወጡት ዳገት የማይወርዱት ቁልቁለት የለም። ለወጌ መነሻ የሆነኝ ባልደረባዬ በስራ አጋጣሚ በታደመባቸው ስብሰባዎች የገጠመውን ሲነግረኝ፤ የታዘበውን ሲያወጋኝ የተገረምኩበት ጉዳይ ለዚህ ጽሁፌ መነሻ መሆኑን ነግሬያችሁ የለ ። አግራሞቴ እንዲጋባባችሁ የራሴን ገጠመኝ አክዬ ገጠመኙን ላውጋችሁማ ። ስበሰባ የሚበዛበት የበዓል ሰሞን ላይ የተከሰተ ነው ጉዳዩ፤ ለበዓል መዋያ ይሆን ዘንድ አበል ተበጅቶ መርሀ ግብር ተነድፎ የሁለት ቀን ስብሰባ አራት ወይም አምስት ቀን ተብሎ የሚከፈልበት ሰሞን፤ አውዳመትን ለመውጣት የሚያስችል ገቢ ማግኛ ይሆን ዘንድ የታሰበ ስብሰባ፤ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኝ መስሪያ ቤቶች በክፍለ ሀገር አበል ለመክፈል ሲያስቡ ስብሰባ አብዝተው የሚያደርጉበት ከተማ ላይ ነው የባልደረባዬ ትዝብት መነሻ ቦታው፤ አንድ ተሰብሳቢ በሁኔታው የባልደረባዬን ትኩረት ይስብና ባልደረባዬ ሰውዬውን መከታተል ይጀምራል። ሰውዬው በተደጋጋሚ ከስብሰባው ወጥቶ ይገባል፤ በመሀል እየጠፋ አመሻሽ ላይ ይመጣል ። ይሄን የተመለከተው ወዳጄ “የት እየቆየህ ነው ምትመጣው?” ብሎ በገደምዳሜ ይጠይቀዋል ። ያ ወጥቶ ይገባ የነበረው፤ ጠፍቶ አምሽቶ ይከሰት የነበረው ሰው ምላሹ አስገራሚ ነበር ። ሌላ ቦታም ስብሰባ እየተካፈለ መሆኑንና በአንዴ ሁለት ስብሰባ ላይ እየታደመ መሆኑ አበል ሁለቱም ቦታ እንዳያመልጠው ለፊርማ እየተመላለሰ መሆኑን ነገረው ። ጉዳዩ አግራሞትን አጭሮበት ነበርና ከትውስታ ማህደሩ በጫወታችን መሀል አካፈለኝ ። የሰውዬው ሁሉ አይቅርብኝ ባይነት አያስገርምም? ባልደረባዬ የስብሰባ ገጠመኙ ሌላ ተመሳሳይ ሁለት ስበሰባ ተካፋይ ሰው ጋርም አገናኝቶት አልፏል። ይሄኛው ሰውዬ ግን አትራፊ ሳይሆን አጉዳይም ነበር ። ከአንደኛው ስብሰባ ወደሌላው እየተመላለሰ የትራንስፖርት ወጪ እያወጣ ለቀናት ሁለቱም ቦታ ‘አለው’ ሲል ከርሞ ስብሰባው አበል አልባ መሆኑ ተነግሮት አተርፍ ባይ አጉዳይ አድርጎታል። ሃላፊዎችስ ቢሆኑ የተቋማቸውን አደራ፤ የህዝብን ተልዕኮ ለመፈፀም ተቀምጠው የዓመት በዓል ኪስ መሙያ፤ የአውዳመት ወጪ መሸፈኛ የሚሆን አበል መፍቀዳቸው ለምን ይሆን? ይህቺ ሀገር ሌላ አሳቢ፤ ሌላ ተቆርቋሪ ያላት ይመስል ክፍተቷን መሙያ ደጅ ደጁን እያየች ከኪስዋ የምናጎድለው ለምንድን ነው? እንደ ዜጋ እንቆርቆር! የራሳችንን ለመሙላት ስንሮጥ ከሀገር ላይ ማጉደላችን ምን የሚሉት በደል ነው? አዲስ ዘመን ጀምረናል ። እኛ አዲስ ባንሆን እንኳን በተዘጋጀልን አዲስነት ውስጥ የምናልፍ፤ ባናቅድ እንኳን ለአዲሱ ዘመን በታቀደ የምንምቧች፤ ንቁዎች መሆን ግድ ይለናል ። ለሀገር ማሰብ፤ ለወገን መቆርቆር የተጣለብንን አደራ ለመወጣት የምንጥር አዲስ ሰው መሆን ያሻናል ። ተገቢ ያልሆነ አሮጌነትን ከውስጣችን አውጥተን የሚገባንን መልካምነት ወደኛ ማስረጫ አዲስ ጅማሮ፤ አዲስ ሀሳብ፤ አዲስ ዘመን! ውዶቼ፤ አዲስ ለመሆን ተዘጋጅታችሁ፤ አዳዲስ ውጥን ወጥናችሁ በአዲስ መንፈስ አዲሱን ዓመት ከጀመርን ይሄው ሁለተኛ ቀን ላይ ተገኝተናል ። አዲሱ ዓመት ለማንም አይገባም ለኛ ማድረግ በአዲስነቱ የምንታደስበት ሊሆን ይገባል ። ዘመኑን የኛ ለማድረግ ዘመኑ ላይ የሚመጥን መልካም ነገር ማቅረብ ተገቢ ነው ። በነገራችን ላይ፤ የዘመኑ ሳይሆን የኛ መቀየር የኛ መለወጥ ነው ለሀገርም ለኛም የሚጠቅመው ። ወቅቱማ ዑደት ነው። ዝነፍ ሳይል የሚለዋወጥ፤ በሁሉም ስብዕናቸው ውስጥ ለውጥ ሳይኖርም የሚሄድ የሚያልፍ ። የኛ ለውጥ ነው ወሳኝ፤ በውስጣችን የምንፈጥረው፤ በልካችን የምንሰፋው አዲስ ልብስ አዲስ የሆነ መልካም ነገርን የሚያለብሰን፤ በታደሰው ዘመን እኛ አሮጌ ሆነን ከተገኘን አዲስነታችን ግን ምኑ ላይ ነው? አዲስ መሆናችን ግን የቱ ጋር ነው? ዘመኑ ሲቀየር የኛን ለውጥ በዘመኑ ካልተለካ፤ ጊዜው ሲለወጥ የኛን ለውጥ ካላሳየ የወቅት መቀያየር የጊዜ መለዋወጥ ምንም እኮ ነው ። የዘመኑ በጎዎች፤ የወቅቱ ጀግኖች፤ የጊዜው ሰላማዊ ተጓዦች ሆነን ያረጀውን ሃሳብ ወዲያ ጥለን አዲስ ዘመንን የሚመጥን አዲስነት ተላብሰን እንጀምረው፤ ዛሬ ላይ የተገኘን የዘመኑ መታደስም ሆነ ማርጀት ምክንያት እኛው ነንና ነገ በሚታየው የታሪክ ማህደር ውስጥ ዘመን አዳሾች ሆነን እንጠቀስ ዘንድ የዘመኑን ያህል በአዲስ እና ጠቃሚ ለሀገር ገንቢ በሆነ ሀሳብ እራሳችንን እናድስ ። አበቃሁ፤ ቸር ይግጠመን!አዲስ ዘመን መስከረም 2/2011ተገኝ ብሩ
https://www.press.et/Ama/?p=17890
904
1መዝናኛ
መልሶ ልማት እንዲህም ይካሄዳል
መዝናኛ
September 17, 2019
9
በሀገራችን እየተካሄደ ያለውን መልሶ ልማት ስንመለከት የግል ቤት ላለው ቦታ እና ቤት የመስሪያ ገንዘብ ፤በአስቸኳይ እንዲነሱ ሲፈለግ ደግሞ ለተወሰነ ጊዜ የሚሆን የቤት መከራያ ገንዘብም ይሰጣል።የኪራይ ቤት ውስጥ የሚገኙት ደግሞ ሌላ የኪራይ ቤት ወይም በጋራ መኖሪያ ቤት መንደር ቅድሚያ ክፍያ እንዲፈጽሙ ተደርጎ ቀሪውን በሂደት በሚከፍሉበት ሁኔታ ቤት ይሰጣቸዋል።እስከ አሁን ያለው አካሄድ ይሄው ነው። መልሶ ልማት በኛ ሀገር ብቻ የሚካሄድ ይመስለኝ ነበር። ለካስ ባደጉት ሀገሮችም መልሶ ልማቱ ይሰራበታል።የእነዚህ ሀገሮች አንዳንድ ከተሞች በተደጋጋሚ መልሶ ልማት እንዳካሄዱም የከተማ ልማት ባለሙያዎች ይገልጻሉ።ልዩነት የሚኖረው ልማቱ ሲካሄድ ለተነሺዎች አስፈላጊው ካሳ መስጠቱ ፣መጠለያ ማቅረቡ ላይ ሊሆን ይችላል ።ከዚህ በተረፈ ካሳ ይከፈላል።የመስሪያ ቦታ ይሰጣል። መልሶ ልማት ባደጉት ሀገሮችም ይካሄዳል። የጣልያኗ ሞሊይስ ግዛት አንድ ከተማ መልሶ ልማት ለማካሄድ ማቀዷን በቅርቡ የወጣ የዩፒአይ መረጃ ያመለክታል።ከተማዋ 106 መንደሮች ያሏት ስትሆን ፣ የሁለት ሺ ሰዎች መኖሪያም ናት። ይህችን ከተማ  እንደገና ለመገንባት ሲታሰብም ነዋሪዎቹ የት ሄደው ነው ልማቱ የሚካሄደው የሚለው በሚገባ መላ ተፈልጎለታል። ነዋሪዎቹ ለቤት ኪራይ የሚሆን ብር በየወሩ እየተከፈላቸው ለንግድ ሥራ የሚሆን ገንዘብ ተሰጥቷቸው በጣም ብዙ ሰው በሚኖርባቸው አካባቢዎች በመሄድ የንግድ ሥራ እንዲሰሩ ነው የሚፈለገው። በፈቃደኝነት ለሚነሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ይህ የተመቻቸው።ለእነዚህ ተነሺዎች የንግድ እንቅስቃሴ ማካሄጃ ከ27 ሺ ዶላር በላይ እንደሚሰጥ የከተማዋ ባለስልጣናት በቅርቡ ይፋ አድርገዋል። ይህ ብቻም አይደለም ይህን የከተማዋን ራእይ ለማሳካት በፈቃደኝነት ለሚነሱ ነዋሪዎች በወር 770 ዶላር ለሦስት ዓመት ለመስጠትም ተወስኗል ። የመልሶ ልማቱን ሀሳብ ያመነጩት የአካባቢው አማካሪ አንቶኒዮ ቴዴስቺ ‹‹ የከተማዬ ህዳሴ እውን እንዲሆን ፍላጎቱ አለኝ፤የተጎሳቆሉት መንደሮች ታምር የሚታይባቸው እንዲሆኑ እፈልጋለሁ››ሲሉ ተናግረዋል።ይህንንም እውን በማደረግ መሰረታችንን ለመጠበቅ እንሰራለን ሲሉም ለሲኤን ኤን መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል። አማካሪው በመልሶ ማልማቱ በመነሳት ሌላ አካባቢ የሚሄዱ ነዋሪዎችን የመመዝገቡ ሥራ በመጪው መስከረም 16 እንደሚጀመር ጠቅሰው፣ በቅድሚያም ልጆች ያሏቸው ወጣቶት ባለትዳሮች በተፈጠረው እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚደረግም ተጠቁሟል። የመልሶ ልማቱ ግብ በመንደሯ ላይ አዲስ አየር እንዲነፍስ ማድረግና የገጠሩን ኢኮኖሚ ማነቃቃት ነው ያሉት አማካሪው ፣ወደ አካባቢው የሚመጡ ሁሉ በፈለጉት መስክ ኢንቨስት በማድረግ የመንደሯ የፋይናንስ የገቢ ምንጭ እንደሚሆኑም ተናግረዋል።ሆቴሎች ሬስቶራንቶች ቡና ቤቶች መክፈት ፣አነስተኛ የከተማ ግብርና ማካሄድ ፣የልብስ ቤቶችንና የጌጣጌጥ መደብሮችን ፣ቤተመጻህፍት ሱቆችን መክፈት እንደሚችሉም ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን መስከረም 6 / 2012  ዘካርያስ
https://www.press.et/Ama/?p=18139
310
1መዝናኛ
መንታ ልጆቿን ለእዳ መክፈያ እና ሞባይል መግዣ
መዝናኛ
September 17, 2019
30
በሀገራችን ወልዶ መሳም ብዙ ትርጉም አለው። ልጅ ሲወለድ ያለው ደስታም ከዚህ ሁሉ የመነጨ ነው።ልጅ መውለድ ዘር መቀጠሉን ማረጋገጥ ከመሆኑም በተጨማሪ ትዳርን ለማጽናት ወሳኝ እንደሆነም ይገለጻል። እናት የምትከበረውም አንድም ሕይወት በመስጠቷ ነው። እናቶችም ልጆቻቸውን በማጥባት እና የተለያዩ እንክብካቤዎችን በማድረግ ለቁምነገር ያበቃሉ። ከልጅ በላይ ምንም ነገር እንደሌለም በማመን ብዙ ጥቅሞቻቸውን እስከ ማጣት ይደርሳሉ። ሰሞኑን ከወደ ቻይና የወጣ መረጃ እንዳመለከ ተው ግን የልጅ ጉዳይ ብዙም ቁብ ያልሰጣት አንዲት እናት መንታ ልጆቿን መሳም ፣አሳድጎ ለቁም ነገር ማብቃት አልፈለገችም። ልጆቿን ስትል መጎዳትም  አልፈለገችም። ከዚህ ሁሉ ይልቅ የወለደቻቸውን መንታ እምቦቀቅላዎች በ65ሺ የን ማለትም በ9ሺ 100 ዶላር ትሸጣቸዋለች። ይህን በማድረጓም ተደርሶባት በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውላለች። ስሟ ያልተጠቀሰው ይህች ቻይናዊት መንታ ልጆቿን የሸጠችው እንደተራራ እየወለደና እየተከመረ ያለውን ዕዳዋን ለመክፈል እንዲሁም አዲስ ዘመናዊ የኪስ ስልክ ለመግዛት አስባ ነው። ኒኝቦ ኢኒንግ ኒውስ የተባለው የቻይና ጋዜጣ ዕድሜዎቿ በ20ዎቹ እድሜ ውስጥ የምትገኘው ይህች እናት መንትያ ህጸናቱን የሸጠቻቸው የዛሬ ዓመት ነው።ለመሸጥ ስታስማም የተጠቀመችባቸው ምክንያት በችልተኛነት መጠቃቷንና በዕዳ ውስጥ መዘፈቋን ነው ብሏል። በቅፅል ስሟ ማ የምትባለው ይህቺ ልበደንዳና እናት እንደተናገረችው ቤተሰቦቿ በቅድመ ጋብቻ ከተከሰተው እርግዝና ጀምሮ ሲናደዱና ሲንገበገቡ ቆይተዋል። በዚህ የተነሳም እርሷን ለመርዳትና ሕጻናቱን ለማሳደግ አልፈቀዱም። ዉ በመባል ብቻ የሚታወቀው የልጆቹ አባት ከህጻናቱ ጋር ምንም ነገር ማድረግ እንደማይፈልግ ግልፅ አድርጎላታል። የመንትያዎቹ እናት የአንድ ወር ዕድሜ ላላቸው መንትያ ልጆቿ ገዢዎችን ማግኘት እንዳልተቸገረች ገልጻለች። ፖሊስ ይህን አስደንጋጭ የጨቅላ ህጻናት ሽያጭ መረዳት የቻለው አንድ ተመሳሳይ አስደንጋጭ የህጻናት የሽያጭ ሁኔታዎች ፍንጭ ማየቱንና ምርመራም እያደረገ መሆኑን ነው። ፖሊሶች ጥልቅ ምርመራ ካደረጉ በኋላ ህጻናቱ በአንሁይ ግዛት ለሁለት የተለያዩ ጥንዶች መሸጣቸውን ደርሰውበታል። አንደኛው በፉያንግ ሌላኛው ደግሞ በሱዦይ ማለት ነው ሲል ፓሊስ አብራርቷል። ምንም ዓይነት ነገር ማድረግ ያልፈለገው ድምፁን አጠፍቶ የነበረው የህጻናቶቹ አባት ተቆርቋሪ መስሎና ለምን በሚል የአንደኛውን ህጻን ድርሻ ለመካፈል ከተሸጡ በኋላ መታየቱ ተጠቁሟል። እናትየው ለፖሊስ እንደተናገረችው ሕጻናቱን የሸጠችበትን ገንዘብ ለልጆቿ አባትም አካፍላለች። የራሱዋን ድርሻ የባንክ ዕዳዋን ለመክፈል እና አዲስ ስማርትፎን ለመግዛት የተጠቀመችበት ሲሆን፣ ዉ ደግሞ የቁማር ዕዳዎቹን ይወጣበታል እየተባለ ነው። ፖሊስ ህጻናቱን ለማግኘት በአንሁይ በመረባረብ ላይ ሲሆን፣ ከማ ወላጆች ዘንድ ለማኖርም ፈልጓል። በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ኃላፊነት የማይሰማቸው ወላጆች ፅኑ የእስራት ጊዜ ይጠብቃቸዋል። በተያዙ ጊዜ ለፈጸሙት የማይገባ ተግባርም የሸጡት ገንዘብም እነሱም በቁጥጥር ሥር ይውላሉ።አዲስ ዘመን መስከረም 6 / 2012  በኃይለማርያም ወንድሙ
https://www.press.et/Ama/?p=18142
331
1መዝናኛ
ከ32 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ መሆናቸው ተነገረ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 29, 2020
13
ከ32 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ መሆናቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደስ ገለጹ። በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና የጤና መድህን ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የንቅናቄ ዘመቻ ውይይት እየተካሄደ ሲሆን፤ በውይይቱ የክልሉ ርዕሸ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ ሃላፊዎች እንዲሁም የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።በዚህ ወቅት ዶክተር ሊያ ባደረጉት ንግግር፤ የጤና መድህን ሥርዓት በገጠርና በከተሞች መደበኛ ባልሆነው የኢኮኖሚ ዘርፍ ተሠማርተው ለሚገኙ ዜጎች ተጠቃሚነትን የሚረጋግጥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል። የሁሉን አቀፍ የጤና መድህን ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች እንዳለው የገለጹት ዶክተር ሊያ አንደኛው ከኪስ በሚወጣ ወጪ ለሚታከሙ ዜጎች ለድህነት እንዳይጋለጡና አስፈላጊውን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ያለመ እንደሆነም ተናግረዋል።ሁለተኛው የጤና ስርዓት ዘላቂ የሆነ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው በማድረግ ትልቅ ሚና የሚጫወት ፕሮግራም ለማድረግ ያለመ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፤ በሀገር ደረጃ በ2003 ዓ.ም በ13 ወረዳዎች ተጀመረው የጤና መድህን ሥርዓት በ2012 ዓ.ም በ770 ወረዳዎች ተተግብሮ 32 ሚሊዮን ዜጎች የጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ብለዋል። ከአባላቱም 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን በመግለጽ፤ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች በጤና መድህኑ ወጪ ተሸፍኖላቸው የህክምና ጤና አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል። የጤና መድህኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ አባላት በማፍራት ያለው አፈፃፀም 82 በመቶ ሲሆን በአማራ ክልል ያለው አፈፃፀም ደግሞ 92 መሆኑን ገልጸዋል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንደ ሀገርና ክልል ስርጭቱ እና ወደ ፅኑ ህሙማን የሚገቡ የኮሮና ቫይረስ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ የመጣ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም ሚኒስትሯ አሳስበዋል:: የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ በበኩላቸው፤ የተቀዛቀዘውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የመከላከል ስራና የጤና መድህን ተደራሽነት ለማረጋገጥ ከጥር 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም የአንድ ወር የንቅናቄ ዘመቻ በአማራ ክልል እንደሚካሄድ ተናግረዋል:: የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በኩላቸው፤ ህብረተሰቡ በሠላም ማስከበር ያደረገውን የተቀናጀ ስራ የኮሮና ቫይረስን በመከላከልና የጤና መድህን ተደራሽነትን በማረጋገጥ ሊደግመው እንደሚገባ ገልጸዋል::የክልሉ መንግስት ከዚህ በፊት ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ አሁንም የኮሮና ቫይረስን የመከላከል እና የጤና መድህን ተደራሽነትን የማረጋገጥ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን የዘገበው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ነው::አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38384
296
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኦሊምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደሚወያዩ ተገለጸ
ስፖርት
March 28, 2020
14
በስፖርት ማህበራት ስራ አስፈጻሚዎች መካከል የሚፈጠረውን አለመግባባት ለመቅረፍ ውይይት እንደሚካሄድ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ። ማህበራቱ በአዋጅና በህግ የተቋቋሙ እንደመሆናቸው ህጉን አክብረው መስራት እንደሚገባቸውም ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የውይይት መድረክ እንደሚዘጋጅም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ጠቁሟል። የሁለቱ የስፖርት ተቋማት ስራ አስፈጻሚዎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ለወራት የቆየ ሲሆን፤ በዚሁ ምክንያት ስፖርቱ በተለያዩ አመለካከቶች ለመንቀሳቀስ መገደዱ ይታወቃል። የስፖርት ቤተሰቡን በሁለት ጎራ የከፈለው ይህ ጉዳይ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ስፖርቱን አደጋ ላይ እንደሚጥለው የብዙዎች ስጋት ነበር። በቀጣዩ ዓመት እንዲካሄድ ከተራዘመው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጋር ተያይዞ አትሌቶች ወደ ስልጠና መግባት አለባቸው በሚል ኦሊምፒክ ኮሚቴው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ቢጀምርም ፌዴሬሽኑ በበኩሉ ዓለም ባለችበት የኮሮና ቫይረስ ስጋት አትሌቶችን ወደ ሆቴል ማስገባት ትክክል አለመሆኑን ገልጿል። ይህንን ተከትሎም የተቋማቱ ስራ አስፈጻሚዎች በየፊናቸው በተለያዩ ጊዜያት ተቃራኒ ሃሳቦችን በመያዝ በመገናኛ ብዙሃን መግለጫዎችን ሲሰጡ ነበር። ተቃርኖው በዚሁ ካልተገታም ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችልም እሙን ነበር። ኦሊምፒኩ በዚህ ወቅት ይሰረዝ እንጂ፤ በየወቅቱ የሚፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት ኮሚሽኑ አመራሮቹን ለማነጋገር ቀጠሮ መያዙን ኮሚሽነሩ ኤልያስ ሽኩር ጠቁመዋል። ተመሳሳይ ድርሻ ባላቸው በስራ ሂደቶች ውስጥ ተቋማዊ፣ የአሰራር አሊያም በግለሰቦች መካከል አለመግባባቶች መፈጠራቸው አይቀሬ ነው። ነገር ግን ማህበራቱ በአዋጅና በህግ የተቋቋሙ እንደመሆቸው ኮሚሽኑ ያወጣውን ደንብ አክብረው መስራት አለባቸው። ስለዚህም የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት በንግግር እንዲፈታ ጥረት ይደረጋል ሲሉ ማረጋገጫቸውን ሰጥተዋል። ቀደም ሲል በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር የነበሩት የስፖርት ምክትል ኮሚሽነሩ ዱቤ ጂሎ በበኩላቸው፤ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አለመግባባት ከሁለት ዓመታት በላይ የቆየ መሆኑን ያስታውሳሉ። ፌዴሬሽኑም ሆነ ኮሚቴው የራሱ የስራ ድርሻ አላቸው የሚሉት አቶ ዱቤ፤ በቀጣይ ሁለቱም አካላት በየስራ ድርሻቸው እንዲሰሩ እንደሚደረግም ገልጸዋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 19 / 2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=29342
245
2ስፖርት
ብራዚላዊው ጥበበኛ በሌላ የሕይወት ምዕራፍ
ስፖርት
March 29, 2020
35
  እኤአ በመጋቢት 1980 የእግር ኳስ ሀገር በሆነችው ብራዚል እግር ኳስ ወዳድ ከሆኑ ቤተሰቦች በደቡብ ብራዚል ፖርት ኤሌግሪ ተወለደ። ስሙ እንደሚያመለክተው ጠረፍ ላይ የምትገኝ አነስተኛ መንደር ነች። ይህቺ መንደር በጣም ድሃ ሕዝቦች የሚኖሩባት ናት። ቤቶቹ የተጎሳቆሉ እንዲሁም ኑሮም ከእጅ ወደ አፍ የሆነባት መንደር፡፡ በዚህች ጎስቋላ መንደር በአንድ ወቅት ወደ ዓለም እግር ኳስ ብቅ ብሎ በአጭር ጊዜ ቆይታው ዛሬም ድረስ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ልብ ውስጥ እየኖረ የሚገኘው ሮናልዲንሆ በጣም ታታሪ ቢሆንም በጣም ድሆች ከነበሩ ቤተሰቦች ተገኘ። እናቱ ዶና ሚግዌሊና ትባላለች። የቀድሞ ሥራዋ የሽያጭ ባለሙያ ስትሆን በሂደት ነርስ ለመሆን በቅታለች፡፡ አባቱ ጃኦ ለኩርዜሮ የሚጫወት ጎበዝ ኳስ ተጫዋች ነበር። ነገር ግን ዕድሜው ሲገፋና እንደድሮው ኳስ መምታት ሲያቅተው ጫማውን ሰቀለ። የድሮ ኳስ ተጫዋቾች እንዳሁኖቹ የደላቸው አልነበሩምና ደመወዛቸውም ትንሽ ስለነበር ኳስ ሲያቆሙ ኑሮን ለማሸነፍ ሌላ ሥራ መስራት ግድ ይላቸዋል። ስለዚህ ጃኦም ኳስ እንዳቆሙ ወዲያው እዚያው ወደብ ላይ የመርከብ ሠራተኛ ሆኑ። ሁለቱም በየፊናቸው እንዲህ ቢታገሉም ኑሮን ግን ማሸነፍ አልቻሉም፣ እንዲያውም እየመራቸው መጣ። ጃኦና ዶና 3 ልጆች ያላቸው ሲሆን የመጀመሪያው ልጅ ሮቤርቶ ይባላል፣ ኳስ ተጫዋችም ነበር። ሁለተኛዋ ዴሲ ትባላለች:: ሦስተኛው ልጃቸው በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችን ልናስታውሰው የወደድነው ፈገግታ ከፊቱ የማይለየው መልከ ጥፉው ነገር ግን ጥበበኛው «ትንሹ ሮናልዶ» ሮናልዲንሆ ጎቾ ነው።ሮናልዲንሆ ዕድሜው 8 ሲደርስ አባቱ ጃኦ በድንገተኛ የልብ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ሌላ ከባድ ፈተና ለድሆቹ የሮናልዲንሆ ቤተሰቦች። አሁን እቤቱን የማስተዳደር ብቸኛዋ ኃላፊነት ነርሷ እናቱ ላይ ወደቀ። ሆኖም ብዙም ሳይቆዩ በዚያው ዓመት የቤቱ ትልቅ ልጅ የሮናልዲንሆ ታላቅና ብቸኛው ወንድሙ የሆነው ሮቤርቶ ግሪሚዩ ከተባለው ክለብ ጋር ኮንትራት ተፈራረመ። በሱም ጥሩ የሚባል ገንዘብ አገኘ። ቤተሰቡም ከተጎሳቆለ ቤት ወጥተው ወደ ተሻለ ቤት ገቡ። በዚህ ጊዜ ነበር ትንሹ ሮናልዶ አዕምሮ ውስጥ አንድ ጥያቄ መመላለስ የጀመረው፡፡«ኳስ ገንዘብ የሚያስገኝ ከሆነ ለምን ኳስ ተጫዋች ሆኜ ቤተሰቤን አልረዳም?» የሚል። ጥበብ ልጇን ጠራች:: ሮናልዲንሆም ወደ ተፈጠረለት እግር ኳስ ኑሮን ለማሸነፍ በሚል ምክንያት ገባ። ትንሹ ሮናልዶ ኳስን በ8 ዓመቱ ኳስ ከሰፈሩ ልጆች ጋር በፖርት አሌግሪ የባህር ዳርቻ እንደፈለገ ያዛት ጀመር። ሜዳው ላይ በዕድሜው አነስተኛው ልጅ እሱ ነበር። ነገር ግን በችሎታው የሰውን ዓይን በቀላሉ መማረክ የሚችልና ብዙዎች ከዓይን ያውጣህ ይሉት ገቡ። እዚህም ሜዳ ላይ ነው ሮናልዲንሆ የሚለውን ስም ያገኘው። ዛሬ ላይ በመላው ዓለም መለያ መጠሪያው ይሁን እንጂ ብራዚላውያን «ሮናልዲንሆ» በሚለው ስም አያውቁትም ነበር። ትክክለኛው ሮናልዲንሆ ትልቁ ሮናልዶ ወይም «ኤልፌኖሜኖ» በሚለው ቅፅል የሚታወቀው ነው። ብራዚላውያን ስመ ረጃጅሞች ቢሆኑም አጠር አድርገው ስያሜ በመፍጠርና በማቆላመጥ ጣጣ አይወዱም። ባጭሩ መጥራት ይቀናቸዋል። የቀድሞ መሪያቸውን «ሉላ» ይሏቸዋል። ባለብዙ ጅራቱ የባህር እንሰሳ «ስኩዊድ» የሚል ትርጉም ይኑረው እንጂ ሉዊዝ ኢግናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ እያሉ ጊዜ ማባከን አይፈልጉም። ሮናልዶ ሉዊዝ ናዛሪዮ ደ ሊማ ከማለት ይልቅ «ሮናልዶ» የሚቀላቸውም ለዚህ ነው። ግን ሁለት ድንቅ ሮናልዶች በአንድ ዘመን ተገኙና ብራዚላውያን ግራ ገባቸው። ያ ታላቅ ግብ አዳኝ ‹ሮናልዲንሆ› ተብሎ በሚጠራበት አገር ሌላ ‹ሮናልዲንሆ› የተባለ አስገራሚ ተጫዋች በእግር ኳስ ኮከቦች መፍለቂያ አገር ብቅ አለ። ትርጓሜው ‹ትንሹ ሮናልድ› እንደማለት ነው። ኤልፌኖሜኖ ‹ትንሹ› መባሉ አብቅቶ በዝናም፣ በክብርም ሲያድግ ብራዚላውያን ወደ ‹ሮናልዶነት› አሳደጉት።ሮናልዲንሆ እስከ 13 ዓመቱ ከሰፈሩ በዘለለ ለትልልቅ ክለቦችም ሆነ ለታዳጊ መጫወት አልቻለም። ውሎው የባህርዳርቻ ነበር። በ13 ዓመቱ ግን አንድ ነገር ተከሰተ፣ የወንድሙ ክለብ የሆነው የግሪሚዩ መልማዮች ጎበዝ ተጫዋቾችን ሊመለምሉ የነ ሮናልዲንሆ ሰፈር ደረሱ። ለምልመላው ይረዳቸው ዘንድም ተጫዋቾችን ለሁለት ከፍለው ግጥሚያ እንዲያደርጉ አዘዙ። ክፍፍሉም ፍትሃዊ እንዲሆን በሰፈር አደረጉት። የላይኛው ሰፈር ልጆችና የታችኛው ሰፈር ልጆች። ጨዋታው ተጀመረ። ልክ እንደተጀመረ ሮናልዲንሆ ተከላካዮችን አተራምሶ አስደናቂ ጎል አስቆጠረ። ከደቂቃዎች በኋላም የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ሌላ ጎል ደገመ። ውጤቱም 23 ለ 0 ነበር። የሚገርመው 23ቱንም ጎሎች ያስቆጠረው አንድ ልጅ ነው። ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲ አሲስ ሞሬራ!!መልማዮቹ ወደ ካምፓቸው ሲመለሱ አንድ ሳቂታ ልጅ አስከትለው ተመለሱ። ሮናልዲንሆም ከወንድሙ ጋር አንድ ክለብ ውስጥ የመጫወት ዕድል አገኘ። ሮናልዲንሆ ለታዳጊዎቹ ሮቤርቶ ደግሞ ለዋናው ቡድን፡፡ ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ወንድሙ ሮቤርቶ በደረሰበት ጉዳት ከኳስ ተሰናበተ። ሮናልዲንሆ ወንድሙ ባጋጠመው ነገር ቢያዝንም ኳስ ከመጫወት ግን ለደቂቃም አልቦዘነም። በግሪሚዩ የእግር ኳስ ካምፕ ውስጥ ኳስን ጓደኛው አደረጋት። ቀኑን ሙሉ ውሎው ከኳስ ጋር ሆነ። ከጓደኞቹ ቀድሞ ልምምድ ቦታ መገኘት እንዲሁም ከሁሉም በኋላ መውጣት ባህሪው ሆነ።ይህ ታታሪነቱ ወደ ታላላቅ የዓለማችን ክለቦች አምርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ በእግር ኳሱ ዓለም እስከዛሬም የማይዘነጉ ተዓምሮችን መፍጠር ቢያስችለውም ዝናና ገንዘብ ይዞት የሚመጣውን ጣጣ እንዲቋቋም አላደረገውም፡፡ ውሎና አዳሩ በየጭፈራ ቤቱ ሆነ፡፡ አብዝቶ መዝናናት ከድህነት ሕይወት ያስመለጠውን ኳስ አስረሳው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥም ሆኖ ግን ዓለምን በእግር ኳስ ጥበቡ ማስደመም ለእሱ ቀላል ነበር፡፡ በታላቁ ኤልክላሲኮ ታሪክም ከማራዶና በኋላ በተቃራኒ ደጋፊዎች ሜዳ የተጨበጨበለት ተጫዋች እስከመሆን ደረሰ፡፡ በኳሱ ተዝናንቶበታል፣ ተመልካቹንም አዝናንቶበታል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ከአምስት ዓመታት በላይ እንዲዘልቅ አብዝቶ መዝናናቱ አልፈቀደለትም፡፡ ብዙዎች ጥበቡን ሳይጠግቡ የእግር ኳስ ሕይወቱ በአጭሩ ሊቀጭ ችሏል፡፡ ያም ሆኖ በትንሽ ዓመታት የሰራው ተዓምር አሁን ላይ በመጫወት ላይ የሚገኝ የትኛውም ተጫዋች ያላሳካውን ዓለም ዋንጫን፣ ባሎንዶርንና ቻምፒየንስ ሊግን ያሸነፈ ተጫዋች አድርጎታል፡፡ አሁን ላይ ግን የጎቾ ሕይወት በሌላ የታሪክ መፅሐፍ ውስጥ በአሳዛኝ ሁኔታ እየተገለፅ ይገኛል። በፓራጓይ ከተጭበረበረ የፓስፖርት ሰነድ ጋር በተያያዘ እስር ቤት ውስጥ ሆና 40ኛ ዓመቱን ባሳለፍነው ሳምንት እንዲያከብር አስገድዶታል፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ምቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=29389
735
2ስፖርት
የዓለም ከዋክብት በቤታቸው ከትመው ልምምዳቸውን ቀጥለዋል
ስፖርት
April 3, 2020
11
ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪመየር ሊግ አዲስ ውሳኔ ካላስተላለፈ በቀር በተያዘው ወር መጨረሻ ዳግም ወደ ውድድር ለመመለስ ማቀዱ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎም ማንቸስተር ዩናይትድ ከቀናት በኋላ ልምምድ ይጀምራል:: ታዲያ ተጫዋቾች ከአቋማቸው ላለመውረድ በቤታቸው ሆነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ማተኮራቸውን በተለያዩ ጊዜያት ለደጋፊዎቻቸው በሚያጋሩት ተንቀሳቃሽ ምስል ያስመለክታሉ፡፡ ይህ ሁኔታም ቀድሞ ለረጅም ሰዓታት አብረዋቸው ያሳልፉ ለነበሩትና አሁን ግን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች መልዕክት ለሚለዋወጡት አሰልጣኞች መልካም መሆኑን የቀያዮቹ አሰልጣኝ ኦሊጉነር ሶልሻየር ለኢቭኒንግ ስታንዳርድ ገልጸዋል፡፡ ተጫዋቾች ጤናቸውንና አቋማቸውን በመጠበቁ ሂደት ቤተሰቦቻቸውም እንዲያግዟቸው ጭምር ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በርካታ ስፖርታዊ ክንዋኔዎች መታገዳቸውን ተከትሎ ስፖርተኞች ከቤታቸው እንዳይወጡ በመከልከላቸው በቤታቸው ሆነው በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲያሳልፉ አስገድዷቸዋል፡፡ በተንቀሳቃሽ ምስል ሁሉም ከገዳዩ ቫይረስ ራሱን እንዲጠብቅ መልእክት በማስተላለፍና ቫይረሱን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ድጋፍ ከማድረግ ባለፈም በቤታቸው ውስጥ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በምን መልኩ እንደሚሰሩ ለሌሎች በማስመልከት ላይም ይገኛሉ፡፡ ከተራዘሙ ውድድሮች መካከል አንዱ ኦሊምፒክ እንደመሆኑ በብሄራዊ ቡድን የተካተቱ ስፖርተኞችም ለአንድ ዓመት በምን መልኩ ብቃታቸውን ጠብቀው መቆየት እንደሚችሉ ልምዳቸውን እያካፈሉ ይገኛሉ፡፡ እንግሊዛዊቷ የሁለት ጊዜ የወርልድ ቴኳንዶ የዓለም ቻምፒዮናዋ ጃዴ ጆንስ ለኦሊምፒኩ በተሻለ ብቃት ለመመለስ በአንድ ዓመት መራዘሙን እንደ መልካም አጋጣሚ የምትመለከተው መሆኑን ትገልጻለች፡፡ ውድድሮች፣ የልምምድ አካዳሚዎች እንዲሁም ጂምናዚየሞች በዚህ ወቅት የተዘጉ ቢሆንም በቤት ውስጥ ልምምድ በማድረግ በስፖርቱ የሶስት ጊዜ ቻምፒዮን በመሆን ታሪክ ለመስራት እየተዘጋጀችም ትገኛለች፡፡ ከዚህም ባሻገር ወቅቱን እንደማገገሚያ ጊዜ በመውሰድ ያለመዘናጋት ልምምድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን እንደገለፀች ዘ ጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል፡፡ ሌላኛዋ ዋናተኛም በተመሳሳይ የራሷንና የሌሎችን ህይወት አደጋ ላይ ላለመጣል በቤቷ መሆንን አማራጭ የሌለው መሆኑን ታምናለች፡፡ የአምስት ጊዜ ኦሊምፒክ ቻምፒዮናዋ ኬት ሌዴኪ ከሲኤንኤን ጋር በነበራት ቆይታ ከዓመት በኋላ በሚካሄደው ኦሊምፒክ በደካማ አቋም ላለመሳተፍ ልምምዱን በጎረቤቶቿ መዋኛ ገንዳ ላይ አጠናክራ መቀጠሏን ገልጻለች፡፡ በእርግጥ ለ800 ሜትር ነጻ ዋና ቻምፒዮናዋ ልምምድ የምታደርግበት ገንዳ በቂ ባይሆንም ከአቋሟ ዝንፍ ብላ ላለመገኘት ስትል በልምምድ ላይ ትቆያለች፡፡ አንጋፋው ህንዳዊ የስፖርት ጋዜጠኛ ሮሂት ብሪጅናዝ በበኩላቸው ስፖርቱ ሲመለስ የተሻለ ነገር ማግኘት ይሻል ይላሉ፡፡ በቤት ውስጥ መቆየት አስፈላጊ በሆነበት በዚህ ወቅት ውድድሮች ባይኖሩም ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ውድድሮችን እንዲሁም ዘጋቢ ፊልሞችን በመመልከት እያሳለፉ መሆኑን ዘ ስቴር ታይምስ አስነብቧል፡፡ በኢትዮጵያም ከዚህ ቫይረስ መስፋትን ተከትሎ ክለቦች፣ ማሰልጠኛ ማዕከላት እንዲሁም ብሄራዊ ቡድኖች ስፖርተኞቻቸውን እንዲበትኑ ተደርጓል:: ስፖርተኞቹ በቡላቸው ባላቸው አቅም ቫይረሱን ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ከደጋፊዎቻቸውና በተናጥል በመሆን ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ብቃታቸውን ጠብቀው ለመቆየት ምን እያደረጉ እንደሆነ መረዳት አልተቻለም፡፡ ስፖርተኛ ሁሌም ብቁና ዝግጁ ሆኖ መገኘት ያለበት እንደመሆኑ ከሌሎች ተሞክሮ በመውሰድ ይህንን በቤት ውስጥ የማሳለፍ ወቅት አቅማቸው በቻለ መጠን ዝግጅታቸውን ማከናወን ተገቢ መሆኑን የስፖርት ባለሙያዎችም ይመክራሉ፡፡ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽንም ስፖርተኞች በየግላቸው ጊዜውን እንዲያሳልፉና መመሪያዎችን መከተል እንደሚገባቸው በመግለጫው ጠቁሟል፡፡ በሌላ በኩል በአትሌቲክስ ስፖርት የምትታወቀው ኢትዮጵያ አትሌቶች ከአበረታች መድሃኒት የጸዳ ጊዜ ማሳለፍ እንደሚገባቸው ተመልክቷል፡፡ ብሄራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት አትሌቶች ሳይዘናጉ ራሳቸውን እንዲጠብቁና በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የህግ ጥሰት በሚፈጽሙት ላይ የእርምት እርምጅ ይወሰዳል፡፡ ከዚህ ቀደም ይከናወን የነበረው የአትሌቶችን ናሙና የመውሰድና የመመርመር ሂደትም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጽህፈት ቤቱ አሳስቧል፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 24/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=29639
445
2ስፖርት
የዊምብልደን ፈተና ከ2ኛው የዓለም ጦርነት እስከ ኮቪድ- 19
ስፖርት
April 3, 2020
45
እኤአ ታኅሣሥ 31 ቀን 2019 በቻይና ዉሃን ግዛት የኮሮና ቫይረስ እንደተከሰተ የዓለም የጤና ድርጅት ማስታወቁን ተከትሎ የቻይና መንግሥት በአፋጣኝ የቫይረሱን ስርጭት በአጭሩ ለመቅጨት እርምጃ ወደ መውሰድ ገብቶ ነበር። የቫይረሱን ስርጭት እንደተባለው በቀላሉ ለመቆጣጠር ሳይቻል ቀርቷል። አሁንም ቢሆን በዓለም አራቱም አቅጣጫዎች የተሰራጨውን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያስቻለ ፈውስ በዓለም ሳይንቲስቶች፣ የህክምና ጠቢባንም ይሁን በሀያላን አገራት አቅም ማምጣት አልተቻለም። ይህም የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ከመለወጥ አንስቶ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በርካታ አሉታዊ ተፅዕኖው እንዲያርፍ አድርጓል፡፡ የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ተጽእኖ እያስተናገደ ከመሆኑ ባሻገር፤ ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ የኮሮና ቫይረስ ለዓለም ራስ ምታት እንደሆነ በመቀጠሉ የስፖርቱ እንቅስቃሴ ዛሬም መፈተኑን ቀጥሏል። ስፖርታዊ ክንውኖች ለማድረግ አስቸጋሪ የመሆኑን ያህል በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ግምት ያለውን ኦሊምፒክ ጨዋታ እንዲራዘም ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ከሳምንት በፊት የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ በምንም አይነት ሁኔታ ይካሄዳል የሚል አቋም የነበረ ቢሆንም በተቃራኒው ውሳኔ እንዲተላለፍ የቫይረሱ ስርጭት አስገድዷል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስፖርትን መፈተኑን እንደሚቀጥልም የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል። የዓለም ህዝብ የጋራ ስጋት በሆነው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ በስፖርቱ ላይ እየደረሰ የሚገኘው ተጽእኖ እየጨመረ ይገኛል። በእንግሊዝ ዊምብልደን ላይ የሚደረገው እና የዓለማችንን ሥመጥር የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾች የሚያሳትፈው ታላቅ ውድድር እንዲሰረዝ ውሳኔ ተደርሷል። በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እጅግ ተጠባቂ የሆነው ውድድር ለመሰረዙ የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሆኗል። የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የስፖርቱን ገጽታን ምንኛ እየጎዳው እንደሚገኝ ይህ ትልቅ ማሳያ መሆኑንም ዘገባው ያትታል፡፡ ዘጋርዲያን ደግሞ፤ በእንግሊዝ ዊምብልደን ላይ የሚደረገው እና የዓለማችንን ሥመጥር የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾችን የሚያሳትፈው ውድድር ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተሰረዘ ጽፏል። የዊምብልደን ቻምፒዮና የተቋረጠው እኤአ ከ1940 እስከ 1935 ድረስ የዘለቀው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት እንደነበር አስታውሷል። በዚህ ጦርነት መጨረሻ የአክሲስ ሃያላት ማለትም ጀርመን፣ ጣልያንና ጃፓን ተሸነፉ። እኤአ ታህሣሥ 2019 በተነሳው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የ134ኛ ዊምብልደን ቻምፒዮና ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ሊደርሰው እንደቻለ ዘገባው ተመልክቷል። የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ስፖርታዊ ክንውን ለማድረግ ፈታኝ እንደሆነው ሁሉ በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ የዓለምን ህዝብ እያሸበረ መሆኑን ተከትሎ ቻምፒዮናውን በተያዘለት መርሃ ግብር ለማካሄድ እንዳይቻል አድርጎታል።በዚሁ መሰረት ለሁለት ሳምንታት የሚካሄደው ይህ ስፖርታዊ ውድድር በሜዳ ቴኒስ ስፖርት አፍቃሪያንና ተወዳዳሪዎች ዘንድ ትልቅ ስፍራ ነበረው። ውድድሩ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው በሐምሌ ወር መጀመሪያ እንደነበር ታውቋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስከ ሐምሌ ወር መጨረሻ ድረስ አንድም የቴኒስ ጨዋታ እንዳይካሄድም ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ዘጋርዲያን 134ኛው የዊምብልደን ቴኒስ ቻምፒዮና መርሃ ግበር መሰረዙን ተከትሎ የዓለማችን እውቅ ተጫዋቾች ልብ እንደ ደማ ዘግቧል። የዊምብልደን የ8 ጊዜ ቻምፒዮናው ሮጀር ፌደረር ለዚህ ታላቅ መድረክ ባለፉት ሁለት ወራት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደረግ ነበር። ‹‹በቻምፒዮናው ላይ አዲስ ውጤት ለማስመዝገብ የነበረንን ተነሳሽነት ጨምሮ ሁሉም ነገር ተበላሽቷል» ሲል መከፋቱን ፌደረር ገልጿል። ሰሬና ዊሊያምስ በተመሳሳይ «የተሰማው ዜና እጅግ አስደንጋጭ ነው» ስትል የቻምፒዮናው መራዘም በስፖርቱ ቤተሰብ ላይ ሀዘን እንደፈጠረ ተናግራለች። ዶቼቬሌ በበኩሉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የስፖርቱን እንቅስቃሴና ገቢ ክፉኛ መጉዳቱን እንደቀጠለ ዘግቧል። ቶኪዮ-ጃፓን ሊደረግ ታቅዶ የነበረው የዘንድሮው ኦሊምፒክ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ወደ መጪው ዓመት እንደተራዘመው ሁሉ የዊምብልደን ውድድር መራዘሙ ትልቅ ሀዘን የፈጠረ ውሳኔ መሆኑን አመልክቷል። የቫይረሱን ስርጭት ተከትሎ በየአገሩ የተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ተቋርጠዋል። ክለቦች፣ ተጫዋቾች፣ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ የስፖርት ጋዜጠኞችና ሌሎችም ገቢ ማጣታቸውን እያስታወቁም ይገኛል። በዚህ ወቅት የዌምብልደን ቻምፒዮና መሰረዙ በስፖርቱ ላይ ተጨማሪ ድብርትን የሚፈጥር መሆኑን አመልክቷል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ተከትሎ በዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ አደጋ እየጣለ መምጣቱን ዛሬም መቀጠሉን ተከትሎ በስፖርቱ ዘርፍ ላይ የማይሻር ጠባሳ እንዲያርፍ ማድረጉን ዘግቧል። አዲስ ዘመን መጋቢት 25/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29701
496
2ስፖርት
የስፖርት አጋርነት በኮሮና ቫይረስ ውጊያ
ስፖርት
March 28, 2020
23
  በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ አስኳል ሃሳብ ወዳጅነትና መተሳሰብ መሆኑ ይታወቃል። በታሪክ ገጾች እንደሰፈረውም በሰው ልጅ ታሪክ ባጋጠሙ በጎም ሆኑ መጥፎ ክስተቶች ስፖርት በአጋርነት ተሳትፏል። ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ሰላምንና አንድነትን የሚሰብኩ እንደመሆናቸው በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በመግባት ሚናቸውን ሲወጡም ኖረዋል። የወቅቱ የዓለም ራስ ምታት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘም ስፖርት መገኘት ባለበት ሁሉ አጋርነቱን በማስመስከር ላይ ይገኛል። የቫይረሱ ስጋትነት በዓለም አቀፉ የጤና ተቋም ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ፤ ውድድሮችን ከማቋረጥና ከመሰረዝ ባለፈ የስፖርቱ ተዋንያን በተናጥልም ሆነ በተቋማዊ ደረጃ አበርክቷቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። በእግር ኳስ ጠቢብነታቸው ዓለም የመሰከረላቸው ተጫዋቾችና ስመ ጥር አሰልጣኞችም፤ ለደጋፊዎቻቸው መልእክት ከማስተላለፍና ገንዘብ ከመለገስ ባሻገር ሆቴሎቻቸውን ለህክምና አገልግሎት እንዲውሉም ጭምር መስጠታቸው ይታወሳል። ክለቦችም በተመሳሳይ ስታዲየሞቻቸውን ቫይረሱን ለመዋጋት ለሚደረገው ጥረት እያዋሉት ይገኛሉ። የነጫጮቹ ስታዲየም ሳንቲያጎ በርናባው ለቫይረሱ የሚሆኑ መድሃኒቶችና የህክምና እቃዎች ማከማቻ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እየደረሰ እንደሚገኝ ይታወቃል። ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያንቀሳቅሱ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው ስፖርትም በዚሁ ምክንያት የገንዘብ ችግር በማስተናገድ ላይ ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ለተጫዋቾቻቸው ሙሉ ደሞዛቸውን መክፈል ከማይችሉበት ደረጃ ደርሰዋል። ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በጊዜያዊነት እስከ መጪው ወር መጨረሻ ድረስ መቋረጡ ይታወሳል። ክለቦች ከስታዲየም ገቢ እና ለሌሎችም የሚያገኙት ገቢ ላይ መቀነስ ተከትሎ ከፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ተጫዋቾቹ የደመወዛቸው ግማሽ እንዲከፈላቸው በመስማማት ስፖርት የመተሳሰብ መድረክ መሆኑን አረጋግጠዋል። ጥያቄውን በቅድሚያ ያቀረበው የሊጉ ክለብ የሆነው በርሚንግሃም ሲቲ ሲሆን፤ ለአራት ወራት በዚህ መልክ ደመወዝ እንደሚከፍል ማስታወቁን ዘጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል። ቅድሚያ አንዳንድ ተጫዋቾች ሃሳቡን ባይቀበሉም በሂደት በበጎ ፈቃደኝነት መስማማታቸውን አሳይተዋል። ክፍያው ከተጫዋቾችና የአሰልጣኞች ቡድን ባለፈ ያሉ የክለብ ሰራቶችን እንደማይመለከትም ታውቋል። ወደ ኢትዮጵያ መለስ ስንልም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 2 ሚሊዮን ብር ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እንዲሁም ለታላቁ የህዳሴ ግድብ መስጠቱ ከትናንት በስቲያ የተሰማ ዜና ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉም በግሏ ለጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ለታላቁ የህዳሴ ግድብ በድምሩ 400ሺ ብር መለገሷ ታውቋል። የኢትዮጵያ ዳኞችና ታዛቢዎች ሙያ ማህበርም በበኩሉ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የ 50ሺ ብር ድጋፍ አድርገዋል። የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ምክትል ፕሬዚዳንት የገንዘብ እንዲሁም የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ለመጓጓዣ እንዲውል የተሽከርካሪ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ሶከር ኢትዮጵያ በድረ ገጹ አስነብቧል። ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=29350
327
2ስፖርት
ሥራ ላይ ያልዋሉ ማዘውተሪያ ስፍራዎች በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ ጥረት እየተደረገ ነው
ስፖርት
April 4, 2020
18
በኢትዮጵያ ከ27 ሺ በላይ የጥርጊያ ሜዳዎች እንዲሁም 12 ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች መኖራቸውን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በሥራ ላይ ያልዋሉ ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን በፍጥነት ወደ ሥራ ለማስገባትም ኮሚሽኑ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ አገሪቷ በስፖርት ዘርፍ ትኩረት ሰጥታ ከምታከናውናቸው ሥራዎች መካከል አንዱ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ነው፡፡ በቅርቡ የማዘውተሪያ ስፍራዎች የወጣውን የመተዳደሪያ ደንብ ተከትሎ በተደረገው ቆጠራ በዚህ ወቅት ከ27 ሺ በላይ የጥርጊያ ሜዳዎች በአገሪቷ የሚገኙ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሟል፡፡ ግንባታቸው ሙሉ ለሙሉ ያልተጠናቀቁና አንዳንዶቹም የስታንዳርድ ችግር ያለባቸው ቢሆኑም በአገሪቷ ውስጥ የሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታው የተጀመረውን ብሄራዊ ስታዲየም ጨምሮ 12 ትልልቅ ስታዲየሞች ይገኛሉ፡፡ ይህም በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገነቡት አጠቃላይ ስታዲየሞች ቢደመሩ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የሚያሳይ መሆኑን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ገልጸዋል፡፡ መንግሥት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከትንንሽ እስከ ትልልቅ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ እያወጣ ቢሆንም በተለያዩ አካባቢዎች በተገቢው ጊዜ ተጠናቀው ወደ ሥራ ያልገቡ አሉ፡፡ በመሆኑም በፍጥነት ወደ አገልግሎት ማስገባት አስፈላጊ በመሆኑ ተጀምረው በወቅቱ ያልተጠናቀቁና ጥራታቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎች በፍጥነትና በጥራት እንዲጠናቀቁ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡ ፡ የካፍና የፊፋን መስፈርት የማያሟሉትም ለማሟላት ጥረት እያደረጉ፤ ክልሎችም ሃብት መድበው ርብርብ እያደረጉ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ በኮሚሽኑ ስር ያሉትንም በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ በሲኤምሲ አካባቢ 31ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በስፖርት ኮሚሽን የተያዘና ለውሃ ዋና እና ለቴኒስ ስፖርቶች ማዘውተሪያ የሚውል ቦታ አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም በቅርብ ቀን ጨረታ አውጥቶ የማጠር እንዲሁም በቀጣይ ዓመት ወደ ግንባታ ለመግባት ታቅዷል፡፡ በተመሳሳይ በዚያው በሲኤምሲ አካባቢ ካፍ የገነባው ትልቅ ማዕከል ቢኖርም ለብዙ ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጥ ቆይቷል፡፡ ማዕከሉ ስታንዳርዱን የጠበቀ ቢሆንም ብዙ ጊዜ ብሄራዊ ቡድን ለማሳረፍ ችግሮች እንዳሉበት ይነሳል፡፡ በመሆኑም ማዕከል በቅርቡ ወደ ሥራ እንዲገባ ይደረጋል፡፡ ለረጅም ጊዜ በብቸኝነት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው አዲስ አበባ ስታዲየም ተጎድቷል፡፡ በመሆኑም በጀት ለሚመለከተው አካል በማቅረብ በክረምት ወቅት እድሳትና ጥገና በማድረግ በድጋሚ ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ማድረግ እንዲችል ጥረት የሚደረግ መሆኑን ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው አሳውቀዋል፡፡ እንደ ማዘውተሪያ ስፍራዎች በአጠቃላይ ያለው ሁኔታ ሲታይ መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው ዘርፍ ነው፡፡ ከቀበሌ ጀምሮ ለስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሆኑ የተዘጋጁ ስፍራዎች በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ሊካሄድባቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ ስፖርቱ የልማቱ አንድ አካል፤ ህብረተሰቡም በስፖርታዊ እንቅስቃሴ መሳተፍ መብቱ በመሆኑ በሚመለከታቸው አካላት ያለው የመሬት አቅርቦት መልካም የሚባል ነው፡፡ በቅርቡ በተዘጋጀው ብሄራዊ የስፖርት ሪፎርም ላይ በጉልህ ከተመላከቱ ጉዳዮች መካከል አንዱ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ልማት ነው፡፡ ከማዘውተሪያ ስፍራዎች ጋር በተያያዘ የስፖርት ፖሊሲው ሲቀረጽ እንደ ጉድለት የተያዘው አንዱ የመተዳደሪያ አዋጅ አለመኖሩ ነው፡፡ በቅርቡ ደንብ መውጣቱን ተከትሎም እነዚህ ሜዳዎች ‹ስታንዳርዱን ያሟሉ፣ የይዞታ ማረጋገጫ አላቸው፣ ጥራትና ተደራሽነታቸው ከፍላጎቶች አንጻር ተገቢ ነው፡፡ እንዲሁም ሥራ ላይ ውለው ማህበረሰቡ እየተገለገለባቸው ነው?› የሚለው ዋነኛው ጥያቄ ነው፡፡ በመሆኑም ለጥያቄዎቹ ምላሽ ሊሰጡ የሚችሉ ሥራዎች በኮሚሽኑ በኩል በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ነው ኮሚሽነሩ የጠቆሙት፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 26/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=29780
402
2ስፖርት
በኮሮና ቫይረስ ሕይወቱን ያጣው የስፖርት ጋዜጠኛ
ስፖርት
April 5, 2020
47
ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊየን በላይ የዓለምን ሕዝብ ያጠቃው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያልገባበት ቤት፣ ያላንኳኳው በር የለም። ከዓለም ታላላቅ አገራት መሪዎች እስከ ተራው ሕዝብ፣ ከዝነኛ ሰዎች እስከ ሕፃናትና አዛውንት ድረስ የዚህ አስከፊ ወረርሽኝ ተጠቂ ሆነዋል። ቫይረሱን ለመቋቋም በሽታን የመመከት ከፍተኛ አቅም ያላቸው የስፖርቱ ዓለም ሰዎች ሳይቀሩ በዚህ ወረርሽኝ ተለክፈዋል፣ ሕይወታቸውን ያጡም ጥቂት አይደሉም። የስፖርት ቤተሰቡ በቫይረሱ ስርጭት ስጋት የዓለም ታላላቅ የስፖርት መድረኮች ተቆልፈውበት ሁነኛ የመዝናኛ አማራጩን አጥቶ በየቤቱ ቆዝሟል። የስፖርቱ ዓለም ታላላቅ ከዋክብትም ረብጣ ገንዘብና ዝናቸው ከደጃፋቸው እንዲወጡ አቅም አልሆናቸውም። የኮሮና ቫይረስ በስፖርቱ ዓለምና በስፖርት ቤተሰቡ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ በሳምንቱ አጋማሽ ወደ ሃዘን የቀየረ አጋጣሚ ፈጥሯል። ፈረንሳዊው እውቅ የስፖርት ጋዜጠኛ ፔፕ ዲዉፍ ባለፈው ረቡዕ በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት ሴኔጋል መዲና ዳካር ውስጥ በስልሳ ስምንት ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የመለየቱ ዜና ተሰምቷል። ይህም በመላው ሴኔጋልና አፍሪካ እንዲሁም ፈረንሳይ ትልቅ የስፖርቱ ዓለም አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። ትውልዱን በቻድ አቢቼ ያደረገው ዲዉፍ ከሴኔጋላዊ ቤተሰቦች የተገኘ ሲሆን የቻድ፣ ሴኔጋልና ፈረንሳይ ዜግነት አለው። ገና የአስራ ሰባት ዓመት ወጣት እያለ ለብቻው ወደ ፈረንሳይ ያቀናው ዲዉፍ የፖለቲካል ሳይንስ ካጠና በኋላ የፈረንሳዩ ክለብ ኦሊምፒክ ደ ማርሴል ጋዜጣ ላይ ፅሁፎችን በማበርከት ነበር ወደ ስፖርት ጋዜጠኝነት ሕይወት የገባው። ይህም በኋላ ላይ የተጫዋቾች ወኪል ሆኖ ለመስራቱ ትልቅ በር የከፈተለት አጋጣሚ እንደነበር የታሪኩ ፀሐፊዎች ይናገራሉ። ዲዉፍ የተጫዋቾች ወኪልነት ስራውን የጀመረው የቀድሞውን ፈረንሳዊ ተከላካይ ባሲል ቦሊ እንዲሁም ካሜሩናዊው ግብጠባቂ ጆሴፍ አንቶኒ ቤልን ወደ ማርሴል ክለብ በማምጣት ሲሆን በሂደት ዊሊያም ጋላስ፣ ሳሚር ናስሪና ሌሎችም እውቅ ተጫዋቾችን በደንበኝነት ይዞ ወኪል በመሆን አገልግሏል። በተለይም ኮትዲቯራዊው ኮከብ ዲዲየር ድሮግባ እኤአ ከ2003 እስከ 2004 በማርሴል ቆይታው ወቅት ወኪሉ በመሆን የተሳካ ጊዜ እንደነበረው ይጠቀሳል። ይህም በእርግር ኳስ ውስጥ የነበረው የነቃ ተሳትፎ እኤአ 2005 ላይ የማርሴል ክለብ ፕሬዚዳንት እስከ መሆን አድርሶታል። ዲዉፍ በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሚሳተፍ ክለብ ፕሬዚዳንት ሲሆን በታሪክ የመጀመሪያው ጥቁር ሆኖ ይነሳል። ዲዉፍ የማርሴል ክለብ ፕሬዚዳንት ሆኖ ሲያገለግል ክለቡ በፈረንሳይ የመጀመሪያው ሊግ ሁለት ጊዜ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ትልቅ ሚና ነበረው። እኤአ 2009 ላይም ዲዉፍ አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሾን ወደ ማርሴል በማምጣት ክለቡ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ አድርጓል። ይህም ክብር ክለቡ ከአስራ ስምንት ዓመታት በኋላ ያጣጣመው ሆኖ ተመዝግቧል። አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሾ ባለፈው የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ፈረንሳይ ከሃያ ዓመታት በኋላ ስታሸንፍ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ እንደነበሩ አይዘነጋም። ከዚህ ድል በኋላ ከክለቡ ፕሬዚዳንትነት የለቀቀው ዲዉፍ የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበርን መርቷል። እኤአ 2009 ላይ በፊፋ ጠቅላላ ጉባዔ ዙሪክ ላይ ተገኝቶ በፈረንሳይ እግር ኳስ ደረጃና በአጠቃላይ እግር ኳስ ውስጥ ስላለው ዘረኝነት ያደረገው ንግግር በታሪኩ ይጠቀስለታል። ዲዉፍ በአውሮፓ እግር ኳስ ውስጥ አሳሳቢ ስለሆነው የዘረኝነት ጉዳይ ጥቁሮች ሰለባ እንዳይሆኑ በጠንካራ ቃላት በዓለም ሕዝብ ፊት ቆሞ በመሟገት ይታወቃል። በስፖርት ጋዜጠኝነት ሕይወቱም ብዙዎችን በማንቃትና ጠንካራ ስራዎችን በማቅረብ የተጨበጨበለት መሆኑን በርካቶች ይመሰክሩለታል። በዚህ ወቅት ዓለምን እያስጨነቀ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ተይዞ የነበረው ዲዉፍ በቤተሰቦቹ አገር ሴኔጋል እርዳታ እየተደረገለት የቆየ ሲሆን ለተሻለ ሕክምና ወደ ፈረንሳይ ለማቅናት በተዘጋጀበት ወቅት ሕይወቱ ማለፉ ተዘግቧል። ይህም በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በሴኔጋል የተመዘገበ የመጀመሪያው የሞት ዜና ሆኗል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ የእግር ኳሱ ዓለም ከዋክብቶች በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሃዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። ዲዉፍ ድንቅ ታሪክ የሰራለት ማርሴል ክለብ በትዊተር ገፁ ‹‹ፔፕ ሁል ጊዜም በማርሴል ልብ ውስጥ ይኖራል፣ የማርሴል የምን ጊዜም ታሪካዊ ሰው ነው›› በማለት ሃዘኑን ገልጿል። የፕሮፌሽል ተጫዋቾች ማህበር በበኩሉ ‹‹ጋዜጠኛ፣ወኪልና የቀድሞ የማርሴል ፕሬዚዳንት ፔፕ ዲዉፍ ሕይወቱን ሙሉ እግር ኳስን ሲያገለግል የኖረ ሰው ነው›› በማለት አስታውሶ ሃዘኑን ገልጿል። ፈረንሳዊው የቀድሞ የሊቨርፑል አጥቂ ጅብሪል ሲሴ ዲዉፍ የማርሴል ፕሬዚዳንት እያለ ለክለቡ ተጫውቷል።‹‹የፈረንሳይ እግር ኳስ ዛሬ ድንቅ ሰው አጥቷል›› በማለት ሲሴ የተሰማውን ሃዘን በትዊተር ገፁ አስፍሯል። ሌላኛው ፈረንሳዊ የማንቸስተር ሲቲ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ቤንጃሚን ሜንዲ በበኩሉ ‹‹ድንቅ የክለብ ፕሬዚዳንት ነው፣ ከዚያም በላይ ሁል ጊዜ ለማርሴል እሴቶች የሚጨነቅ ትልቅ ሰው ነው›› በማለት ተናግሯል። አዲስ ዘመን መጋቢት 27/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=29803
554
2ስፖርት
ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከወዲሁ ፈተናዎችን መጋፈጥ ጀምሯል
ስፖርት
April 6, 2020
12
ኦ ሊምፒክ ከጤና ስጋት ጋር የተያያዘ ባይሆንም በተለያዩ ጊዜዎች የመሰረዝና የቦታ ለውጥ ሲደረግበት ታይቷል፡፡ እኤአ የ1916 የበጋ ኦሊምፒክ በጀርመን በርሊን ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት በአንደኛ የዓለም ጦርነት ሳቢያ ተሰርዟል:: በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅትም የ1940 የክረምት ኦሊምፒክና የ1944 የበጋ ኦሊምፒክ ውድድሮች የመሰረዝ እድል ገጥሟቸዋል:: እኤአ የ1976 የክረምት ኦሊምፒክም በዴንቨር ኮሎራዶ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የኮሎራዶ ግዛት ሕዝብ ለውድድሩ የሚወጣውን ወጪ በመቃወሙ ውድድሩ የቦታ ለውጥ ተደርጎበት በአውስትራሊያ ኢንስብረክ ለመካሄድ ተገዷል፡፡ ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ በወቅቱ እንደዘገበው የኮሎራዶው ኦሊምፒክ የቦታ ለውጥ እንዲደረግበት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ውድድሩ ከመካሄዱ ከሦስት ዓመታት አስቀድሞ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ኦሊምፒክ በታሪክ ተራዝሞ የሚያውቅበት አጋጣሚ አልነበረም:: ዓለም በአሁኑ ወቅት እየተሸበረችበት በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ግን የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለአሥራ ስድስት ወራት ሲራዘም በታሪከ የመጀመሪያው ለመሆን በቅቷል፡፡ ይህም ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ለውድድሩ አዘጋጆች አዲስ ተሞክሮ ብቻ ሳይሆን አዲስ ፈተና ይዞ መምጣቱ አልቀረም፡፡ ይህን አዲስ ፈተናም ለመጋፈጥና ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ከወዲሁ ለማስተካከል ዓለም አቀፍ ኮሚቴውና አዘጋጆቹ ከወዲሁ ሌት ከቀን እየሰሩ እንደሚገኙ ሰሞኑን ገልፀዋል፡፡ የኦሊምፒክ ስፖርቶች ዳይሬክተሩ ክሪስቶፍ ዱቢ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ‹‹ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ውስብስብ ብቻ ሳይሆን አዲስ ፈተና ገጥሞናል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከጃፓን መንግሥት ጋር በመሆን ይህን ፈተና ለመወጣትና አሁን ዝግጁ የሆኑ ነገሮችን ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ተግባራዊ እንዲሆኑ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ ይህም ማለት ኦሊምፒኩ ከመራዘሙ አስቀድሞ በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ ዝግጁ የነበሩ የኦሊምፒክ መንደሮችን፣አርባ አንድ ዋነኛየውድድር ቦታዎች፣ ከአርባ ሺ በላይ የሆቴል ክፍሎች፣ከሁለት ሺ በላይ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን እንዲሁም አገልግሎትና በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ቁሶችን ለማቅረብ የተደረጉ ውሎችን መልክ ማስያዝና ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ተግባራዊ የሚሆኑበትን አቅጣጫ የማስቀመጥና መልክ የማስያዝ ሥራዎች ከወዲሁ እየተሰሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የዓለምን እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሽባ ያደረገው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ነገሮችን መልክ ለማስያዝ በሚያደርገው እንቅስቃሴ አሁንም ፈተና እየሆነ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አልሸሸጉም፡፡ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከተጠቀሱት ፈተናዎች በተጨማሪ ሌሎችም እንቅፋቶች ይኖሩበታል:: ከውድድር ጋር በተያያዘ ለኦሊምፒኩ አስፈላጊውን መስፈርት (ሚኒማ) በተለያዩ ስፖርቶች አሟልተው የነበሩ በሺ የሚቆጠሩ አትሌቶች መስፈርታቸው ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ለሚካሄደው ኦሊምፒክ ይስራ አይስራ እርግጠኞች አይደሉም፡፡ በኦሊምፒክ ለመሳተፍ በየትኛውም ስፖርት አንድ አትሌት መስፈርቶችን ማሟላት የግድ ይለዋል፡፡ ከአስራ ስድስት ወር በፊት መስፈርት ያሟላ አትሌት ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ያሟላል ወይም አሁን ያለውን አቋም ይዞ ይቆያል ማለት አይቻልም፡፡ የተራዘመው ኦሊምፒክ ሲቃረብ አትሌቶች ዳግም መስፈርት አሟልተው ይወዳደሩ ማለት ደግሞ ሌላ ጣጣ ይዞ ይመጣል፡፡ ዛሬ መስፈርቱን ያሟላ አትሌት ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ ዳግም ላያሟላ ይችላል፡፡ ስለዚህ ይህን ጉዳይ ለማስተካከል ራሱን የቻለ ትልቅ የቤት ሥራ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ይሁን እንጂ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ኃላፊው ኪት ማክኮኔል አሁን መስፈርቱን ያሟሉ አትሌቶች ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ መስፈርታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ይቆያል ብለዋል፡፡ ይህ በራሱ ግን ኋላ ላይ ጭቅጭቅ አለማስነሳቱን እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ ከሰላሳ ሦስት ዓለም አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ከአስራ አንድ ሺ በላይ አትሌቶች መስፈርቱን አሟልተው ለውድድር እየተዘጋጁ ባሉበት ሁኔታ ኦሊምፒኩ መራዘሙ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በኦሊምፒክ እግር ኳስ ውድድር የሚሳተፉ የወንድ ተጫዋቾች እድሜ ከሃያ ሦስት እስከ ሃያ አራት መሆን እንዳለበት ይታወቃል፡፡አሁን ኦሊምፒኩ በመራዘሙ በርካታ ተጫዋቾች ከዚህ እድሜ ሊያልፉ መቻላቸው ሌላው ፈተና ይሆናል፡፡ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴም ይህን ጉዳይ መልክ ለማስያዝ ጉዳዩ ከሚመለከተው ፊፋ ጋር በቅርቡ ውይይት ለማድረግ እንዳሰበ ተጠቁሟል፡፡ ኦሊምፒኩን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ለማስተላለፍ የተዋዋለው የአሜሪካን ኩባንያ ኦሊምፒኩ በሚካሄድበት ወቅት ከምንም በላይ የሚጠብቀው የኤንቢኤና ሌሎች ታላላቅ የአሜሪካን ቅርጫት ኳስ ውድድሮች ስለሚኖሩበት የፍላጎትና የጥቅም ግጭቶች ሊፈጠር ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ አንዱን ወገን በቢሊዮን ዶላሮች ኪሳራ ላይ ሊጥል ስለሚችል ከባድ ፈተና እንደሚሆን ይታመናል:: በተመሳሳይ ከዚህ ዓመት የተላለፉ በርካቶቹ ዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚካሄዱበት መሆኑ ሌላ ጣጣ ይዞ መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ በነዚህ ወራት ከሚካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮች መካከል የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናና የዓለም ውሃ ዋና ቻምፒዮና ዋነኞቹ ቢሆኑም ውድድራቸውን ለመሰረዝ ፍቃደኛነታቸውን መግለፃቸው ይታወቃል፡፡ ይህ አበረታችና ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተስፋ የሰጠ ቢሆንም በነዚህ አካላት መካከል ተጨማሪ የውል ስምምነት እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡ ይህ ምናልባትም ሌሎቹ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖችም ለኦሊምፒክ ቅድሚያ እንዲሰጡ ማነሳሳት ቢችልም ወቅቱ በጣም ከፍተኛ ሙቀት የሚኖርበት መሆኑ ለውድድሮች አስቸጋሪ እንደሚሆን ስጋት አሳድሯል:: ምንም ይሁን ምንም ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ብቻ የጃፓን መንግሥትን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ እንደሚገቡ ቀደም ሲል ተዘግቧል፡፡ የጃፓኑ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴም ገና ከመጀመሪያው ከፍተኛ ኪሳራ ሊገጥም እንደሚችል ተናግሯል፡፡ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለዚህ ኪሳራ ስጋት ሰላሳ ሦስቱንም ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች የሚመለከት መድህን የገባ ቢሆንም በቂ እንደማይሆን ታምኖበታል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ቶማስ ባኽም ኦሊምፒኩ መራዘሙን በገለፁበት ወቅት ከባድ ኪሳራ እንደሚኖር በማመን ሁሉም ባለድርሻ አካላት መስዋዕትነት መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ለመጠቆም ሞክረዋል:: ከባዱን መስዋዕትነት ማን እንደሚከፍልና ጫናው በየትኛው ወገን ትከሻ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ግን ዛሬ ላይ ቆሞ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 28/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=29896
682
2ስፖርት
ኮቪድን ለመከላከል የስፖርት ቤተሰቡ ርብርብ ቀጥሏል
ስፖርት
April 5, 2020
16
በመላው ዓለም የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ-19) ለመዋጋት የሚደረገው ርብርብ እንደቀጠለ ነው። በኢትዮጵያም የስፖርት ቤተሰቡ ተሳትፎ ገና ከጅምሩ አበረታች የሆነ መንገድ ያሳየ ሲሆን፤ እውቅ ስፖርተኞችና የስፖርት ማህበራት ድጋፋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦችና ተጫዋቾች በገንዘብና በዓይነት ድጋፋቸውን በመስጠት ላይ ካሉት መካከል በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። የሃዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና የጽህፈት ቤት ሰራተኞች የደመወዛቸውን 50 በመቶ መስጠታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል። በዚህም 443 ሺ 366 ብር ስርጭቱን ለመቆጣጠር ለሚቋቋመው ግብረ ኃይል አበርክቷል። የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና አጠቃላይ የክለቡ ሠራተኞች 130 ሺ ብር ድጋፍን አድርገዋል። የድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾችና አባላት በበኩላቸው ሙሉ ደመወዛቸውን ለዚሁ ዓላማ እንዲውል ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ታውቋል። የሲዳማ ቡናው አጥቂ አዲስ ግደይ፣ የመከላከያው አጥቂ ሀብታሙ ወልዴ፣ የጅማ አባጅፋሩ አማካይ ንጋቱ ገብረስላሴ፣ የሃላባ ከተማው ልመንህ ታደሰ እና የጅማ አባጅፋር ተከላካይ መላኩ ወልዴ በጋራ ለትውልድ ከተማቸው አጋሮ በጥሬ ዕቃ ድጋፋቸውን አድርገዋል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች 80 ሺ ብር የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ማስረከባቸውን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪም ቆሼ ተብሎ ወደ ሚጠራው ስፍራ በመጓዝ ለ541 አቅመ ደካሞች ርዳታ ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ኮሚሽኑን ጨምሮ በስሩ የሚገኙ የስፖርት ማህበራት ድጋፋቸውን አጠናክረው ከቀጠሉት መካከል ይገኛሉ። በከተማው የውሹ ፌዴሬሽን 45 ሺ 800 ብር በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው ኮሚቴ የሚውል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ስፖርት ኮሚሽነር አበርክቷል። ከዚህም ውስጥ በስራ አስፈፃሚው ውሳኔ ፌዴሬሽኑ 20 ሺ ብር፣ 15 ሺ 800 ብር እና የምግብ ግብዓቶች ከክለብ አሰልጣኞች እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ማስተር ፍሬህይወት ሽታዬ በግላቸው 10 ሺ ብር አበርክተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽንም በስሩ ያሉ ማዕከላትን እስከ ታችኛው የወረዳ መዋቅር ድረስ ለቅድመ መከላከልና መቆጣጠር ለሚያስፈልጉ ተግባራት ሁሉ እንዲውሉ መወሰኑ ይታወቃል። ከዚህ መካከል አንዱ የሆነው የጃን ሜዳ ስፖርት ማዕከል በጊዜያዊነት ወደ አትክልት ተራነት ተዘዋውሮ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።አዲስ ዘመን መጋቢት 27/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29814
275
2ስፖርት
የስፖርቱ በቫይረሱ ሳቢያ ብዙ ተጽዕኖ እያስተናገደ ነው
ስፖርት
April 7, 2020
26
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያስቻለ ፈውስ በዓለም ሳይንቲስቶች፣ የህክምና ጠቢባንም ይሁን በሀያላን አገራት አቅም ማምጣት አልተቻለም። ይህም የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ከመለወጥ አንስቶ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በርካታ አሉታዊ ተፅዕኖው እንዲያርፍ አድርጓል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ተጽዕኖ እያስተናገደ ከመሆኑ ባሻገር፤ ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉን መረጃዎች ያመላክታሉ። የስፖርት ቤተሰቡ በቫይረሱ ስርጭት ስጋት የዓለም ታላላቅ የስፖርት መድረኮች ተቆልፈውበት ሁነኛ የመዝናኛ አማራጩን አጥቶ በየቤቱ ቆዝሟል። የስፖርቱ ዓለም ታላላቅ ከዋክብትም ረብጣ ገንዘብና ዝናቸው ከደጃቸው እንዲወጡ አቅም አልሆናቸውም። የቫይረሱን አደጋ ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም፤ ለመከላከል የሚደረገው ርብርብ በተጠናከረ መልኩ እንደቀጠለ ነው። የአለም ህዝብ እያሸበረ ያለውን ተህዋሲ ለመቆጣጠርና ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ በስፖርቱ ማህበረሰብ በኩል እየተደረገ ያለው ተሳትፎ ትልቅ ስፍራ ይወስዳል። በተለያዩ ሀገራት በከፍተኛ ፍጥነት የዓለምን ክፍል እያዳረሰ የሚገኘው ቫይረስ ለመቆጣጠርና አደጋ ለመቀነስ በሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ የስፖርት ማህበራት፣ የስፖርቱ ቤተሰብ፣ ተጫዋቾች ትልቅ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ በተመሳሳይ ኮሮና ቫይረስ የቅድመ መከላከል ተግባራትን በመደገፍና በመሳተፍ ትልቅ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ለመታዘብ ተችሏል። የአዲስ አበባ ከተማ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን እንቅስቃሴ መሰረት በተለየ መልኩ ህዝብን አሳታፊ የሆነ የቅድመ መከላከል ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመዲናዋ የኮሮና ቫይረስን ቅድመ ጥንቃቄና መከላከል አስመልክቶ የተደረገው የድጋፍ ማሠባሰብ ጥሪ የዚሁ አካል ተደርጎ የሚጠቀስ ይሆናል። በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጥሪ ከተደረገ ጀምሮ የተጠናከረ ድጋፍ በከተማዋ በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተደረገ ባለው ተሳትፎ ውስጥ የስፖርት ማህበረሰብ ተሳትፎ አንጸባራቂ እንደነበር መታዘብ ተችሏል። የስፖርቱ አንዱ ባህሪና መገለጫው በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ በማድርግ ኃላፊነት መወጣት እንደሆነ ይታመናል። የስፖርት ቤተሰቡ ይሄንኑ መርህ መሰረት በማድረግ ለከንቲባው ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ህዝባዊነታቸውን እያረጋገጡ ካሉት አካላት መካከል በፊት አውራሪነት ይቀመጣል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሎም በመዲናችን የስፖርት ቤተሰቡ ተሳትፎ ገና ከጅምሩ አበረታች የሆነ መንገድ ያሳየ ሲሆን፤ እውቅ ስፖርተኞችና የስፖርት ማህበራት የነበራቸው ድጋፍ ተሳትፎ ለዚህ ምስክር ይሆናሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር አባላት መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም የጀመሩት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ይሄንኑ ያመላክታል። የማህበሩ አባላት በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ ሊያጋጥም የሚችለውን አደጋ ለመከላከል እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ የሚያስችል ስራ ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር አባላት ይሄንኑ መሰረት በማድረግ «ወገን ለወገን ደራሽ ነው» የሚል መሪ ቃልን በማንገብ መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ስራ ተገብቷል። ማህበሩ ከህብረተሰብና ከተለያዩ ለጋሾች የምግብ፣ የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ህዝባዊነቱን የሚያሳይ ይሆናል። በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ በመገኘት አርዓያነቱ እንዲጠናከርና ተግባሩ እንዲቀጥል የተጋረጠውን ቫይረስ ለመግታት፣ ህብረትንና አንድነትን ለማሳየት፣ ወሳኝነቱን በመግለፅና ለማበረታታት በርካቶች የታሪኩ አካል በመሆን እየተንቀሳቀሱ ይገኛል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብርሀቱ እና የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ቢኒያም ምሩፅ ይፍጠር ደግሞ ፊት አውራሪ በመሆን ተግባሩን እየመሩ ህዝባዊነታቸውን ያሳዩ መሆናቸው ታውቋል። በማህበሩ በኩል በሚደረገው እንቅስቃሴ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ለዚህ አላማ እጃቸውን እየዘረጉ የወገን አሌንታነታቸውን እያሳዩም ይገኛሉ። ለዚህም እንደ ማሳያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግበሩ ለማጠናቀቅ የተያዘው ቀን ማክሰኞ ቢሆንም የተሳትፎው ከፍተኛ መሆን ወደ ረቡዕ መሸጋገሩ እንደ ማሳያ ይጠቀሳል። የማህበሩ አባላት አንዱ የሆነችው አሰልጣኝ ሰላም ዘርአይ፤ ቀደም ብሎ እስከ ሰኞ ድረስ ይጠናቀቃል በሚል ተይዞ የነበረው ቀነ ገደብ በመላ ሀገሪቱ ያሉ አሰልጣኞች የሚሰጡት ምላሽ እየጨመረ መጥቷል። በዚህ መሰረት መዋጮውን ለማሰባሰብ ተጨማሪ ጊዜ እንዲኖር በመጣው ጥያቄ መሰረት እስከ ረቡዕ ስምንት ሰዓት ድረስ ሊራዘም ችሏል። ‹‹በመሆኑ አሰልጣኞች ቀደም ሲል በተጠቀሰው የባንክ ቁጥር አቅማችን የፈቀደውን እንድናደርግ ከአክብሮት ጋር እንጠይቃለን›› ስትል አሰልጣኝ ሰላ በፌስቡክ ገጿ አሳውቃለች። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር አባላት በዚህ መሰረት የገንዘብ፣ የአይነትና የቁሳቁሶች ድጋፍ እስከ ረቡዕ ከተካሄደ በኃላ በሚወጣ ፕሮግራም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት ያስረክባሉ ተብሏል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር አባላት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከመጋቢት 26 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም የሚዘልቅ ይሆናል። አዲስ ዘመን መጋቢት 29/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29948
555
2ስፖርት
ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመንገድ፣ የወደብ አገልግሎቶችንና የመኪና ማቆሚያ ጣቢያዎችን ለማሻሻል ተስማሙ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 29, 2020
7
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመንገድ፣ የወደብ አገልግሎቶችንና የመኪና ማቆሚያ ጣቢያዎችን ለማሻሻል መስማማታቸው ተገለጸ:: በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጅቡቲ ወደቦች ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ሊቀመንበር አቶ አቡባከር ኦመር ሀዲ ጋር የመንገድ፣ የወደብ አገልግሎቶችንና የመኪና ማቆሚያ ጣቢያዎችን ለማሻሻል ተስማምተዋል:: አምባሳደር ብርሃኑ፣ ለሁለቱ አገራት ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክተው የዲኪል-ዳጉሩ መንገድ በፍጥነት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ክትትል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል::የመንገዱ ግንባታ ቀሪው 80 ኪሎ ሜትር መንገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክረዋል:: የዶራሌ ሁለገብ ወደብና የጅቡቲ ኮንቴይነር ተርሚናልን ከኢትዮጵያ-ጅቡቲ የባቡር ሀዲድ ጋር በማገናኘት የወደብ አገልግሎቶችን አቅም ማሻሻል በሚቻልባቸው ሁኔታ ላይ መምክራቸውንም ነው አምባሳደሩ የገለጹት:: ጅቡቲ በሆራይዘን ነዳጅ ማደያንና በአዋሽ የሚገኘው የኢትዮጵያ የነዳጅ ማከማቻን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት ከስምምነት ተደርሷል። ይህም የነዳጅ ጭነት ፍሰት በማቀላጠፍ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመከላከል ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል:: ከደረቅ የመኪና ማቆሚያ ተርሚናል ጋር ተመሳሳይ የሆነ አስተዳደራዊ አሠራር ለማስቀመጥ ለነዳጅ ተርሚናል የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ መንግሥት ያቀረበው ጥያቄም በወደብ እና በነፃ ዞን ባለሥልጣን ተቀባይነት አግኝቷል:: ሊቀመንበሩ የባለቤትነት ማረጋገጫ ወረቀቱን ለኢትዮጵያ ወገን በፍጥነት ለመስጠት ቃል መግባታቸቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል::አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38387
173
0ሀገር አቀፍ ዜና
በመቀሌ ከተማ የባንክ አገልግሎት መስጠት ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 29, 2020
8
አማንሚካኤል መስፍን መቐለ፡- በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የባንክ አገልግሎት መጀመሩን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ። ከንቲባው አቶ አታክልቲ ሃይለስላሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ እንዳስታወቁት፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ከሰሞኑ ባካሄደው ተከታታይ ውይይት የተነሳውን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ በተደረገው የተቀናጀ ስራ ትናንት ከሰአት በኋላ ጀምሮ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። በጁንታው አማካኝነት በመቀሌ ከተማ ሆን ተብለው በተለቀቁ የህግ ታራሚዎችና ሌሎች ዘራፊዎች የተነሳ በከተማዋ ላይ የጸጥታ ችግር መኖሩን በማንሳት ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲያስተካክልላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የጠየቁ ሲሆን፤ በትናንትናው እለት በነበረው የወጣቶች ውይይትም ወጣቱ የከተማውን ሰላምና ጸጥታ ከአስተዳደሩ ጋር ሆኖ ለመጠበቅ ቃል መግባቱ ይታወሳል።የከተማዋ ነዋሪና ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ከዛሬ ከሰአት ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኖ ደንበኞች መጠቀም መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ በየቅርንጫፎቹ ተገኝቶ ተመልክቷል። የግል ባንኮችም አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ትዛዝ እንደተላለፈላቸው የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38393
133
0ሀገር አቀፍ ዜና
የፌዴራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ድንጋጌ ጸደቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 29, 2020
9
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- የፌዴራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ድንጋጌ ጅግጅጋ በተካሄደው የተቋማቱ የጋራ የምክክር መድረክ ቀርቦ ጸድቋል:: የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጫላ ለሚ የፌዴራል ተጠሪ ተቋማት የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ድንጋጌንም ለጉባኤ አቅርበው አጽድቀዋል::በመተዳደሪያ ድንጋጌው ዝግጅት ላይ ባለድርሻ አካላትና የህግ ባለሙያዎች መሳተፋቸውንና ሰፊ ውይይቶች መደረጉን አብራርተዋል:: መተዳደሪያ ድንጋጌውን ያቀረቡት አቶ ደበበ ወ/ጊዮርጊስ ሰነዱ ከመዘጋጀቱ በፊት በ9 ነፃና ገለልተኛ ሆነው በሚሰሩና ተጠሪ ተቋማት ከም/ቤቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ተጠያቂነት፣ ለህዝብ ያላቸውን ተደራሽነት፣ የበጀትና የሰው ሀብት አስተዳደራቸው እና ያጋጠማቸውን ችግሮች በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት መደረጉን ገልጸዋል:: አክለውም የተዘጋጀው መተዳደሪያ ድንጋጌም የፎረሙ አባላት በመደበኛነት በመገናኘት የጋራ ዕቅድ የሚያወጡበትና የአፈጻጸም ግምገማ እና የምክክርና የልምድ ልውውጥ የሚፈጥሩበትን ምህዳር ይፈጥራልም ብለዋል:: በቀረበው ሰነድ ላይም ከተሳታፊዎች በርከት ያሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል::ተቋማቱ ‹‹የዴሞክራሲ ተቋማት›› ከሚባሉ ‹‹ነፃ ወይም ገለልተኛ ተቋማት ቢባሉ›› የሚል ሃሳብ ተነስቷል:: የም/ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ተቋማቱ ነጻና ገለልተኛ ሆነው የሚሰሩ ቢሆንም ተጠሪነታቸው ለም/ቤቱ በመሆኑ ‹‹ተጠሪ ተቋማት›› በሚል ቢጠሩ አግባብነት እንዳለው ጠቁመዋል:: የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፎርም ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል::የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድን ሪፎርም ያቀረቡት ም/ኮሚሽነር አቶ ውብሸት አየለ ሲሆኑ ቦርዱ አንድ አዋጅ እና 29 ማስፈጸሚያ መመሪያዎችን ማውጣት፣ የሰው ሃይልን ማደራጀት፣ የምርጫ ቁሳቁሶችን ማሟላት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ እና የህዝብ ግንኙነት ተግባራት በዋናነት ማከናወኑን አብራርተዋል:: በተመሳይም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፎርም በዋና ኮሚሽነር በዶ/ር ዳንኤል በቀለ ቀርቧል::ኮሚሽኑ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ ለመስራት የሚያስችለውን የህግ ማዕቀፍ ከማሻሻል ጀምሮ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ከህዝብ ተወካዮች የተገኘው መረጃ ያመላክታል::አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38390
226
0ሀገር አቀፍ ዜና
ክልሉ የደን ሽፋኑን ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 29, 2020
18
አዲሱ ገረመው አዲስ አበባ፡- የደቡብ ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚመጣውን ተግዳሮት ለመቀነስ ባደረገው አገራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የድርሻውን ለመወጣት እንዲችል የክልሉን የደን ሽፋን ከ23 በመቶ ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ::በተያዘው ዓመት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ እንደሚዘጋጅ እና 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ችግኝ እንደሚተከልም ተጠቁሟል:: የደቡብ ክልል አካባቢ ጥበቃ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ቀቀቦ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አጠቃላይ የክልሉ የደን ሽፋን 19 በመቶ የነበረ ሲሆን፤ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ደግሞ 25 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ በመሰራቱ 23 በመቶ ማድረስተችሏል::በቀጣይም እንደ አገር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ክልሉ የሚጠበቅበትን ለማበርከት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን፤ በአስር ዓመት ውስጥም ሽፋኑን 30 በመቶ ለማድረስ ይሰራል   እንደ አቶ ሳሙኤል ገለጻ፤ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ የደን ሽፋንን ለማሳደግ በተደረገው ሰፊ ርብርብም ባለፈው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የደን ሽፋኑን 23 በመቶ ማድረስ ተችሏል::የደቡብ ክልል አጠቃላይ የደን ልማትን በተመለከተ ዋና ዓላማ ተደርጎ እየተሰራ ያለውም የክልሉን የደን ሽፋን ለማሳደግ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ከ2013 እስከ 2022 ዓ.ም በሚደረገው አጠቃላይ እንቅስቃሴ በየዓመቱ ዜሮ ነጥብ ሰባት በመቶ የደን ሽፋን በመጨመር የክልሉን ደን ሽፋን 30 በመቶ ለማድረስ ግብ ተቀምጦ እየተሰራ ነው::በዚህም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ በሚደረገው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ሥራ ክልሉ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው::ከዚህ አኳያ ክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታትም ይህንኑ መሠረት በማድረግ ሲሰራ ቆይቷል::በተለይ የአረንጓዴ አሻራ ስራን በተመለከተ በዋናነት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ ጀምበር በርካታ ችግኞችን የመትከልና ሰፊ   አካባቢን በደን የመሸፈን ሥራ በትኩረት ተሰርቷል::በዚህም በ2011 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 55 ሚሊዮን ችግኞችን፣ እንዲሁም በ2012 ዓ.ም 77 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ተችሏል::የደን ዘርፉ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን ፋይዳ ከግምት በማስገባትም ነው በሚቀጥሉት አስር ዓመታት የደን ሽፋኑን 30 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ያለ መሆኑንም ነው አቶ ሳሙኤል የተናገሩት:: ግቡን ለማሳካት መጠነ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን እና በዋናነት በየአካባቢው ያለውን የደን ሁኔታ የማጥናት ሥራ መከናወኑን የገለጹት አቶ ሳሙኤል፤ በተለይ በደቡብ ምዕራብ አካባቢ ያለውን የተፈጥሮ ደን የጥበቃ ሥራውን በከፍተኛ ደረጃ ለማጠናከርና ደኖች በሳሱባቸው አካባቢዎች መልሶ የመተካት ተግባራት እንደሚከናወኑ ተናግረዋል::በማዕከላዊ ዞን አካባቢዎችም በተለይ ከፍተኛ የሆነ የደን ውድመት ያለበትና ከፍተኛ የሆነ የህዝብ መጨናነቅ ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ለተለያዩ ዓላማዎች ሊውሉ የሚችሉ የችግኝ ተከላ ሥራም ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል:: ባለፈው ዓመት በአንድ ጀምበር ወደ 40ሺ ሄክታር መሬት በችግኝ መሸፈኑንና በተያዘው ዓመትም ወደ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ በማዘጋጀት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ችግኝ እንደሚተከልም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል::ለዚህም የዛፍ ችግኝ ዝግጅት፣ ችግኝ ለማፍላት የሚያስችሉ ፕላስቲኮችን የማዘጋጀት፣ ችግኝ ጣቢያዎችን የማዘጋጀትና ሌሎችም ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰዋል::አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38395
376
0ሀገር አቀፍ ዜና
”ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት አገራዊ የአንድነት ስሜት መፍጠሩን ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ገለጹ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 29, 2020
9
አዲስ አበባ፡- የገበታ ለአገር ፕሮጀክት እንደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ አገራዊ የአንድነት ስሜት መፍጠሩን የሃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ገለጹ። ኢዜአ በአካባቢ ጥበቃና ኢኮ ቱሪዝም ላይ የሚሰራውን በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝና በባለቤታቸው የተመሰረተውን የሃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚን አነጋግሯል። የፋውንዴሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ በአገሪቷ በተፈጥሮ ብቻ የተገኙ በርካታ ድንቅ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች መኖራቸውን ይናገራሉ። ወይዘሮ ሮማን ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የ”ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የፈጠረውን አይነት አገራዊ የአንድነት ስሜት ፈጥሯል::ኢትዮጵያ ያሏት በርካታ የቱሪስት መስህቦችም የተፈጥሮ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ታሪካዊ አሻራ ያረፈባቸው፣ እምቅ ሀብትና ቅርሶችን ጭምር የያዙ በመሆናቸው እንደ “ገበታ ለአገር” አይነት ፕሮጀክቶች መጠናከር እንዳለባቸው ነው የተናገሩት። ወይዘሮ ሮማን፤ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷ ብቻ በቢሊዮን ብር የሚቆጠር ገቢ ስለሚያመጣ ሀብቱን ጥቅም ላይ በማዋል ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻልም አንስተዋል። በዚህም እንደ “ገበታ ለአገር” ያሉ ፕሮጀክቶችን አቅም በፈቀደ መጠን ማስፋት እንደሚገባና ሕዝቡም ለዚህ ድንቅ ዓላማ ድጋፍ በማድረግ የሚሳተፍበት መሆን እንዳለበት ነው የተናገሩት። ወይዘሮ ሮማን የ”ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የፈጠረውን አይነት አገራዊ የአንድነት ስሜት መፍጠሩንም ገልጸዋል:: መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም፤ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ሀብቷ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም ከሆኑ አገሮች መካከል አንዷ ብትሆንም ከዘርፉ የሚጠበቀውን ያህል ጥቅም እያገኘች አይደለም። የቱሪስት መዳረሻዎችን በሚፈለገው ልክ ማስተዋወቅና ማልማት አለመቻሏ ደግሞ ለዘርፉ መቀጨጭ በምክንያትነት ይጠቀሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዘርፉ እንዲያንሰራራ ያደርጋል ያሉትን “ገበታ ለአገር” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። በዚህም ትኩረት ተነፍጎት የቆየው የአገሪቷን የተፈጥሮ ሀብት የማልማት ስራ በጎርጎራ፣ በኮይሻና በወንጪ አካባቢዎች ለመስራት ታቅዶ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38398
233
0ሀገር አቀፍ ዜና
የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸው የመከላከያ እና የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አባላትን ጎበኙ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 29, 2020
12
አዲስ አበባ፡- ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸው የመከላከያ እና የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አባላትን ጎበኙ:: በጉብኝቱ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ አበበን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የምዕራብ እዝ መከላከያ ሆስፒታል እና የልዩ ሃይል የቁስለኞች ማቆያ በመገኘት በትግራይ ክልል በተደረገው የሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን የመከላከያ እና የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አባላት በመጎብኘት አበረታተዋል::በሕግ ማስከበር ሀገራዊ ተልዕኮው ወቅት ለደረሰው የአካል ጉዳት ድጋፍ እንዲሆን ለሆስፒታሎቹ የዊልቸር፣ ክራንች እና ዎከር ድጋፍም ተደርጓል:: በተመሳሳይ በተያያዘ ዜናም በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ይኖሩበት የነበረውና የፈረሰውን የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባን ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል::ለሀገር የዋሉ ጀግኖች ማግኘት የሚገባቸውን ክብርና ትኩረት ወደጎን በማለት የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ ከለውጡ በፊት በነበረው ስርዓት አገልግሎት እንዲያቆም በመደረጉ በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ለሀገር ያበረከቱትን ውለታ የዘነጋ ተግባር ሲፈፀምባቸው ቆይቷል:: በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋእት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ይኖሩበት የነበረውና የፈረሰውን የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባን ለማቋቋም በበጎ ፈቃደኝነት የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ አደራጅ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱን ብሔራዊ የጀግኖችና የሕፃናት አምባ በጎ አድራጎት ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር ዶክተር አዳሙ አንለይ ተናግረዋል:: የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ መቋቋም ለሀገር ክብር ዘብ በመቆም እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለከፈሉና እየከፈሉ ላሉ ጀግኖችና ወላጆቻቸውን መስዋእት ላደረጉ የጀግኖች ልጆች ተገቢውን ቦታ እና ክብር መስጠት ያስችላል መባሉን የዘገበው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ነው::አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38401
255
0ሀገር አቀፍ ዜና
የቄራ ድርጅቶች አፈጻጸም 25 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
14
ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ ሙሉ ሰርተፊኬት ወስደው ወደምርት የገቡት አስር የቄራ ድርጅቶች ማምረት ከሚችሉት ውስጥ 25 በመቶውን ብቻ እያመረቱ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።በግብርና ሚኒስቴር የኤክስፖርት ቄራዎች ድርጅት ሰርተፊኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጌዲዮን ይልማ (ዶ/ር) በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፣ በሀገር ደረጃ ሰርተፊኬት ወስደው ወደሥራ የገቡ የቄራ ድርጅቶች 14 ቢሆኑም አራቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሥራቸውን አቁመዋል።በሌላ በኩል በሥራ ላይ ያሉትም ቢሆኑ በአግባቡ እያመረቱ አይደለም ያሉት አቶ ጌዲዮን፣ በሥራ ላይ የሚገኙት አስሩ ቄራዎች ማምረት ከሚችሉት 25 በመቶ ብቻ እያመረቱ ይገኛሉ ብለዋል።እንደ ዶክተር ጌዲዮን ገለፃ የቄራ ድርጅቶቹ በሙሉ አቅማቸው ማምረት ያልቻሉት በገጠማቸው ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮች ሲሆን ከነዚህም አንዱ የግብአት አቅርቦት ማነስ ነው።በተለይም ለእርድ የሚሆኑ እንስሳት በሚፈለገው ልክ አይቀርቡላቸውም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ይህም የሚከሰተው ከአቅርቦት ሰንሰለቱ፣ የኮንትሮባንድ፣ የውጪ ገበያ ትስስር ውስን መሆን እና የእርድ እንስሳት አቅርቦት ማነስ ከችግሮቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ገልፀዋል።ለዚህም ጉዳዩ የሚመለከታቸው እንደ ግብርና ሚኒስቴር፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ማህበራት እና የመሳሰሉት ተቋማት ተቀናጅተው እና ተናበው በሚፈለገው ልክ አለመስራታቸው ምክንያት መሆኑንም ጠቁመዋል። በዚህ የተነሳ ከዘርፉ የሚገኘውን ምርት ወደ ውጭ በመላክ ከዘርፉ ሊገኝ የሚገባው የውጭ ምንዛሪ በአግባቡ እንዳልተገኘ ጠቁመዋል። ድርጅቶቹ እስካሁን ድረስ ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ስምምነት አድርገው የሚልኩት በሁለት ሀገሮች ብቻ በተንጠለጠለ የንግድ ሰንሰለት ስለሆነ የሚፈለገውን ገቢ ለማግኘት ይቸግራል ያሉት ዶክተር ጌዲዮን ይህም የማምረት አቅማቸውን ሙሉ በሙሉ እንዳይጠቀሙ ማነቆ እንደሆነና የተቀባይ ሀገሮች በየጊዜው መለዋወጥ እና የቅበላ መስፈርታቸው በየጊዜው መቀያየር ሌላው እንቅፋት እንደሆነ ገልጸዋል። በሌላ በኩልም በቋሚነት ለውጭ ገበያ ተብለው እንስሳት እየረቡ የሚቀርቡበት ሁኔታ ባለመኖሩ ከገበሬ እየተለቀመ እየተወሰደ የሚታረደው እንስሳ ለወደፊትም ሌላ አደጋ እንደሚያስከትል ጠቁመዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በእንስሳት አቅርቦትና እንስሳት አቅራቢ ነጋዴዎችን አርብቶ አደሮችንና መሰል አካላትን ለማስተሳሰር በግብርና ሚኒስቴር በኩል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ቢደረግም ውጤት አልተገኘም ብለዋል። ይህ እንዳይሆን ያደረገው ደግሞ በዘርፉ ውጤታማ ሥራ ለመስራት ተብለው የተቋቋሙ ባለድርሻ አካላት በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያለው የኢትዮጵያ ወተት ሥጋና ልማት ኢንስቲትዩት፣ ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከቄራዎች፣ ከግል ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን መሬት ላይ የወረደ ሥራ በቅንጅት ባለመስራታቸው እንደሆነ ዶክተር ጌዲዮን ገልፀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38319
297
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአሶሳ ከተማ ከ552 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ሕገ-ወጥ የትምባሆ ምርቶች ተያዙ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
4
አዲስ አበባ፡- በአሶሳ ከተማ በትምባሆ ምርቶች ላይ የኦፕሬሽን ሥራዎችን በማከናወን ከ552 ሺህ 750 ብር በላይ የሚገመት ሕገ-ወጥ የተለያዩ የትምባሆ ምርቶች መያዛቸውን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ባለሥልጣኑ እንዳስታወቀው፤ በጸጥታ እና በባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ክትትልና ቁጥጥር በአሶሳ ከተማ በትምባሆ ምርቶች ላይ የኦፕሬሽን ሥራዎችን በማከናወን ከ552 ሺህ 750 ብር በላይ የሚገመት ሕገ-ወጥ የተለያዩ የትምባሆ ምርቶች ተይዘዋል፡፡በደቡብ ምዕራብ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ተቆጣጣሪዎች ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ተቆጣጣሪዎች እና ከከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አባሎች ጋር በመቀናጀት ባከናወነው ኦፕሬሽን ሥራ የትንባሆ ምርቶቹ መያዛቸውን ከኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38316
100
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአፋር ክልል ሕግ የማስከበር ዘመቻ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ድጋፍ አደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
6
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህወሓት ጁንታ ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በከፈተው ጦርነት ሳቢያ በተለያዩ አጎራባች ክልሎች በሕግ ማስከበር ሥራ ለተሳተፉ የልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት እንዲሁም የተፈናቀሉ ዜጐችን ለመደገፍ ቃል በገባው መሠረት 2ሺህ 400 ኩንታል እህል ለአፋር ክልል አስረክቧል።ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ እና የአዲስ አበባ ከተማ አቃቢ ሕግ ቢሮ ኃላፊ አብዱልቃድር መሀመድ ለአፋር ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኃላፊ ለአቶ መሀመድ ሁሴን አስረክበዋል።የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕከት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍም በክልሉ ሕዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጁንታው የጥፋት እኩይ ተግባር ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ለመደገፍ ለአፋር ክልል 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነት እና 94 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ በጠቅላላው 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ የተገኘው መረጃ ያመለክታልአዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38313
139
0ሀገር አቀፍ ዜና
ለኦሎምፒክ የተመረጡ አትሌቶች ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ወደ ዝግጅት ይገባሉ
ስፖርት
March 7, 2020
28
ዓለምን እያሳሰበ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሳቢያ መካሄድ አለመካሄዱ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አምስት ወራት የቀሩት ቢሆንም በርካታ የዓለማችን አገራት በተለያዩ ስፖርቶች የሚያደርጉትን ዝግጅት አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ኢትዮጵያም በዚህ ታላቅ የስፖርት መድረክ በተለይም በአትሌቲክስ ረጅምና መካከለኛ ርቀቶች ውጤታማ እንደምትሆን ይጠበቃል፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቀድሞው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አባዱላ ገመዳ የሚመራ ብሔራዊ የዝግጅት ኮሚቴ በማዋቀር የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያከናውን ሰንብቷል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውጤት በሚጠበቅበት የአትሌቲክስ ስፖርት ኢትዮጵያን እንዲወክሉ የተመረጡ አትሌቶች ከመጋቢት ሦስት ጀምሮ ወደ ሆቴል ገብተው ዝግጅት እንዲጀምሩ ውሳኔ ላይ መድረሱን ያሳወቀ ሲሆን፣ አትሌቶችና አሰልጣኞች ከትናንት ጀምሮ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ፅሕፈት ቤት በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሁለት ሳምንት በፊት በኦሊምፒኩ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችና አሰልጣኞችን መልምሎ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን በመካከለኛ ርቀት፣ ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል፣ ረጅም ርቀት፣ ማራቶንና ርምጃ ውድድሮች አሰልጣኞችና አትሌቶች መመረጣቸው ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት በመካከለኛ ርቀት አሰልጣኝ ብርሃኑ መኮንን፣ ሃብታሙ ግርማ፣ ኢሳ ሽቦ እና ጉዲሳ ታሱ በአሰልጣኝነት ተመርጠዋል፡፡ አሰልጣኝ አብርሃም ኃይለማሪያም እና ስንታየሁ ካሳሁን ደግሞ በተጠባባቂነት ተይዘዋል፡፡ በ3ሺ ሜትር መሰናክል ደግሞ አሰልጣኝ ተሾመ ከበደ እና ዶክተር ብዙአየሁ ታረቀኝ ሲመረጡ አሰልጣን ከፍያለው አለሙ ተጠባባቂ ሆነዋል፡፡ አገሪቷ በኦሊምፒክ መድረክ በተለይ ውጤታማ በሆነችባቸው የ5ሺ እና 10ሺ ሜትር ርቀቶችም አራት አሰልጣኞች ተመራጭ ሆነዋል፡፡ አሰልጣኝ ሁሴን ሸቦ፣ ቶሌራ ዲንቃ፣ ንጋቱ ወርቁ እና ኃይሌ እያሱ ሲመረጡ፤ አሰልጣኝ ተፈሪ መኮንን እና በሪሁን ተስፋይ ደግሞ የተጠባባቂነት ስፍራን ይዘዋል፡፡ በረጅሙ የአትሌቲክስ ውድድር ማራቶን በማናጀር አሰልጣኝነት ስኬታማ የሆኑት አሰልጣኝ ሃጂ አደሎ ከሌላው ስኬታማ አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ጋር በመሆን የርቀቱን እንዲመሩም ተመርጠዋል፡፡ አሰልጣኝ ጌታነህ ተሰማ እና ይረፉ ብርሃኑ ደግሞ ተጠባባቂ ሆነው ተይዘዋል፡፡ የእርምጃ ቡድኑም በሻለቃ ባየ አሰፋ አሰልጣኝነት የሚያመራ ይሆናል፡፡ ውጤት በሚጠበቅበትና ታሪካዊ ሊሆን እንደሚችል በሚታሰበው የወንዶች ማራቶን ውድድር የ5ና 10ሺ ሜትር የኦሊምፒክ ቻምፒዮኑና የዓለም ክብረወሰን ባለቤቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ባለፈው መስከረም በበርሊን ማራቶን ባስመዘገበው ፈጣን ሰዓት መሰረት በዋናነት መመረጡ የሚታወስ ሲሆን ማራቶንን ጨምሮ በሌሎች ርቀትም ጠንካራ አትሌቶች በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ለመወከል ወደ ዝግጅት ይገባሉ፡፡ ከነዚህም መካከል በዶሃው ቻምፒዮና ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው አትሌት ሞስነት ገረመው 2፡02፡55 የሆነ ሰዓት ባለፈው ለንደን ማራቶን ላይ በማስመዝገቡ በማራቶን ቡድኑ ውስጥ በሦስተኛ ደረጃ ተመራጭ ሆኗል፡፡ ብርሃኑ ለገሰ በ2፡02፡48 በሁለተኛነት ሲመረጥ የዓለም ሻምፒዮኑ አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ ከሌሎች አትሌቶች አኳያ ያለው የቅርብ ጊዜ ፈጣን ሰዓት በቡድኑ ሊያካትተው እንደማይችል ይፋ ከተደረገው የእጩዎቹ ዝርዝር መረዳት ተችሏል፡፡ በሴቶች ማራቶን የዱባይ ማራቶን አሸናፊዋ ወርቅነሽ ደገፋ 2፡17፡41 ሰዓት በመያዝ በቀዳሚነት ስሟ ሲቀመጥ ሮዛ ደረጄ 2፡18፡30ና በ2፡18፡34 ሰዓት ሩቲ አጋ በቀዳሚነት ታጭተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን በሚጠበቁበት የአስር ሺ ሜትር ውድድር የዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ዮሚፍ ቀጄልቻ 26፡49፡34 በሆነ ሰዓት ሲመረጥ አንዱአምላክ በልሁ 26፡53፡15ና በ26፡54፡34 ጀማል ይመር በቀዳሚነት ተመርጠዋል፡፡ በሴቶች የኦሊምፒክ ቻምፒዮኗ አልማዝ አያና ከዓመት በላይ በጉዳት ላይ የቆየች ቢሆንም ቀዳሚዋ ተመራጭ መሆን ችላለች፡፡የዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ ለተሰንበት ግደይና ነፃነት ጉደታም ከቀዳሚዎቹ እጩዎች መካከል ተካተዋል፡፡ በወንዶች አምስት ሺ ሜትር በዶሃው የዓለም ሻምፒዮና የወርቅና የብር ሜዳሊያ ያጠለቁት ሙክታር ኢድሪስና ሰለሞን ባረጋ እንዲሁም ሃጎስ ገብረህይወትና ጥላሁን ሃይሌ በቀዳሚነት ሊመረጡ ችለዋል፡፡ በሴቶች ደግሞ ጸሐይ ገመቹ፣ ሐዊ ፈይሳና ፋንቱ ወርቁ ባስመዘገቡት ሰዓት መሰረት ሊመረጡ ችለዋል፡፡ኢትዮጵያ በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ከአትሌቲክስ ውድድሮች በተጨማሪ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ተሳታፊ መሆኗን ከሁለት ሳምንት በፊት ማረጋገጥ ችላለች፡፡ በሞሮኮ ራባት ተካሂዶ በነበረው የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት የኦሊምፒክ ማጣሪያ ውድድር ማስተር ሰለሞን ቱፋ በኦሎምፒክ እንደሚወዳደር ማረጋገጡ አይዘነጋም፡፡አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 28/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=28667
497
2ስፖርት
«ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ» የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል
ስፖርት
March 10, 2020
42
«ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ» በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ለማካሄድ ፍቃድ መገኘቱን አዘጋጁ ፍቅር ያሸንፋል በጎ አድራጎት ማኅበር አስታወቀ። የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅና መስራች አቶ ሚስባህ ከድር እንደገለፁት፤ ስፖርት ጉልህ ሚናውን ከሚጫወትባቸው መስኮች አንዱ በሰላም ላይ ተጽዕኖ የመፍጠር አቅሙ ነው። ማህበሩ ይሄንኑ መሰረት በማድረግ «ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ» በሚል መሪ ቃል መስቀል አደባባይ ባዘጋጀው ውድድር ላይ 40 ሺ ተሳታፊዎች የሚጠበቁ ይሆናል።የጎዳና ሩጫው ቀደም ሲል የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ለማካሄድ ታስቦ እንደነበር የገለፁት አቶ ሚስባህ፣ በወቅቱ በከተማው ላይ ሊከናወኑ የነበሩ የተለያዩ መርሐ ግብሮች ከመኖራቸው ጋር ተያይዞ ውድድሩን በተያዘለት ጊዜ ለማድረግ እንዳልተቻለ ተናግረዋል። አሁን ግን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽፈት ቤት ውድድሩን ለማድረግ በደብዳቤ ጥያቄ በማቅረብ ፍቃድ ማግኘት መቻሉን አብራርተዋል ለውድድሩ የሰላም ሚኒስቴር ዕውቅና የሰጠው ሲሆን አመስት ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ውድድር ለማካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል። «በዓይነቱና በይዘቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስቶችና ታዋቂ ግለሰቦችን፣ አርቲስቶች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች ያለምንም የፆታና የዕድሜ ልዩነት ይታደሙበታል›› ያሉት አቶ ሚስባህ፣ ከሩጫው መርሐ ግብር በኋላ ትልቅ እንጀራ በማዘጋጀት በአንድ ላይ የመቁረስ ሥነ ሥርዓት እንደሚኖር አስረድተዋል ይህም ‹ሰፊ እንጀራ አለን ተካፍለን እንብላ፤ እርስ በርስ አንባላ› የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ታስቦ እንደሚከናወን አክለዋል። በሽብር ወንጀል ክስ ከአራት ዓመት በላይ በወህኒ ቤት መቆየታቸውን የሚናገሩት አቶ ሚስባህ፣ የማህበሩ የክብር አምባሳደር አርቲስት ቻቺ ታደሰ እና አርቲስት ዳዊት ፅጌን በማድረግ ባለፉት 12 ወራት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰዋል። የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ የመጣውን ሰላም በጋራ በመጠበቅ የተሻለችውን ኢትዮጵያን ለትውልድ ማውረስ ይቻል ዘንድ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነም አመልክተዋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 1/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=28836
244
2ስፖርት
የኦሊምፒክ ችቦው ቅብብሎሽ ደማቅ ጉዞ
ስፖርት
March 10, 2020
41
4ተኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ችቦ መለኮስ ሥነ ሥርዓት ከትናንት በስቲያ በመቖለ ሮማናት አደባባይ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች በተገኙበት ተከናውኗል። በሥነ ሥረዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ የትግራይ ክልል በተለያዩ ስፖርቶች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን በማስመረጡ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል የትግራይ ክልል በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ በአትሌቲክስ 10 እና በብስክሌት 1 አትሌት ማስመረጥ መቻሉን ያስታወሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ክልሉ ስፖርቱን ለማጠናከርና የኦሊምፒክ ቡድኑን ለመደገፍና የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ከኦሊምፒክ ኮሚቴው ጎን እንደሚቆም በማረጋገጥ ከወዲሁ ለኦሊምፒክ ቡድኑ መልካም ዕድል ተመኝተዋል።የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ የቶኪዮ 2020 ብሔራዊ የዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ በትግራይ የተለኮሰው የኦሊምፒክ ችቦ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ‹‹ትግራይ ብዙ ጀግኖችን አፍርታለች፣ በስፖርቱም በቀጣይ በተለያዩ ስፖርቶች አገርን የሚወክሉ አትሌቶች ማፍራት ይጠበቃል›› ብለዋል አቶ አባዱላ ንግግራቸውን በድንገት ገታ አድርገውም በቶኪዮ 2020 በብስክሌት ኢትዮጵያን በብቸኝነት የምትወክለው የትራንስ ኢትዮጵያ ክለብ ብስክሌት ጋላቢዋን ሰላም ዓመሀን ወደ መድረክ በመጥራት ‹‹በብቸኝነት ኢትዮጵያን በመወከልሽ ትልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ከህዝብ በስጦታ የተበረከተልኝ ነው›› በማለት ከአንገታቸው የወርቅ ሀብል አውልቀው ሽልማት አበርክተውላታል።በችቦ መለኮስ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ችቦውን ከትግራይ ክልል የተረከቡት የጋምቤላ ክልል አፈጉባኤ አቶ ላክደር ላባክ በበኩላቸው ‹‹የኦሊምፒክ ቡድኑን ለመደገፍ በቀጣይም በስፖርቱ መሠረተ ልማት ላይ የበኩላችንን ለመወጣት እድሉን በማግኘታችን ደስተኞች ነን›› በማለት ተናግረዋል 5ተኛው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ችቦ መለኮስ ሥነ ሥርዓት መጋቢት 6/2012 በጋምቤላ ክልል የሚከናወን ሲሆን የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ታይዶር ቻምባንግ መቖለ በነበረው የችቦ መለኮስ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ችቦው ሲረከቡ ‹‹በስፖርት ህብረተሰቡን ተሳታፊ ማድረግ እንዴት እንደሆነ ከትግራይ ክልል ትምህት ወስደናል›› ብለዋል። ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ቡድን እደክልል በተገቢው መንገድ እንደሚደግፉም አብራርተዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ከጀግናው አትሌት ሻበል ምሩፅ ይፍጠር ልጅና የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቢኒያም_ምሩፅ ጋር መገናኘታቸውን ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅትን በተለየ መልኩ ለማከናወንና ለትውልድ የሚተላለፍ ዘመናዊ የኦሊምፒክ አካዳሚን የመገንባት ዕቅድ በመያዝ የብሔራዊ ዝግጅት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራዎችን ከጀመረ ሰንብቷል። ኮሚቴው ሕዝቡን በነቂስ የሚያሳትፍ የመጀመሪያ መርሐግብሩን የካቲት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ የኦሊምፒክ ችቦ በመለኮስ መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ሌሎች ክልሎች እንዲዞር በማድረግ መጀመሩ ይታወሳል። የኦሊምፒኩን ችቦ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተረከበ ሲሆን ከድሬዳዋ ተከትሎ ሶማሌ፣ ትግራይ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሐረሪ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ላይ መጨረሻውን ያደርጋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 1/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=28830
348
2ስፖርት
የሴቶችን የማራቶን ታሪክ የቀየረችው ታሪካዊ ቅፅበት
ስፖርት
March 8, 2020
49
 የታሪክ ድርሳናት እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ የዓለም ስፖርት ካንቀላፋበት ፆታን እኩል ያለመመልከት ቅዠት እንዳልነቃ ይመሰክራሉ። ባልተሞከረና ባልተረጋገጠ ሁኔታ ‹‹አትችልም›› የሚል መላ ምት ሚዛን ደፍቶ ዘመናትን በመሻገሩ እጅግ ተወዳጁና ተመራጩ የመዝናኛ ዘርፍ ወደ አንድ ጎን ያዘነበለ ነበር። ሴት በስፖርት ትጥቅ ከሜዳ መገኘቷን ባለመቀበል አስተሳሰብ የተሸበቡትን ለማሳመንም በርካቶች ባልተፈቀደ መንገድ መገኘት ግድ ሆኖባቸዋል። ‹‹ነውር›› ለሚሏቸው ጆሯቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን በሰጡ ደፋርና ቆራጥ ሴቶች መቻላቸውን በማስመስከር ዓለም የዛሬውን ቅርጽ እንዲይዝ አድርገዋል። የዛሬውን የሴቶች ቀን አስመልክቶም ‹‹ባልተፈቀደው›› መንገድ ከተጓዙ እንስቶች መካከል የአንዲትን ሴት ታሪክ ልናስታውስ ወደድን። በዓለም ላይ ዋና ዋና ከሚባሉት ስድስት ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ የቦስተን ማራቶን ነው። መነሻውን እኤአ 1897 ያደረገው አንጋፋው የጎዳና ላይ ሩጫ የ122 ዓመት እድሜ ባለጸጋም ነው። ታዲያ በዚህ ውድድር ተሳታፊ እንዲሆኑ ይፈቀድላቸው የነበሩት ወንድ አትሌቶች ብቻ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የሴቶች ተሳትፎ የሚጀምረው ዘግየት ብሎ ነው። በዓለም አትሌቲክስ ታላቅ ስፍራ ያለው ይህ ማራቶን የተለያዩ ክስተቶችን በተለያዩ ዓመታት ቢያስተናግድም ከሁሉም ይልቅ ሴቶች በሩጫው ላይ እንዲታዩ መሰረት የጣለው ድራማዊ ክስተት መቼም የሚዘነጋ አይደለም። እኤአ 1967 የቦስተን ማራቶን ተሳታፊ ለመሆን ከተመዘገቡት ወንድ ሯጮች መካከል ኬቪ ስዊዘር የሚል ስም ይገኝበታል። ስሙ በአጭሩ የተመዘገበ በመሆኑ ጾታው በትክክል የሚለይ ባይሆንም ለሩጫው ፈቃድ የሚያገኙት ወንዶች ብቻ በመሆናቸው ይህ ይከሰታል በሚል የጠረጠረ አልነበረም። የውድድሩ ዕለት ደርሶ የሩጫ ማስጀመሪያው ከተበሰረ በኃላ ግን ሯጮች ያዩትን ማመን አልቻሉም። ምክንያቱ ደግሞ በከባዱ የማራቶን ሩጫ ከእነዚያ ሁሉ ወንዶች መካከል አንዲት ሴት በመታየቷ ነው። ከቆይታ በኋላ ግን ክስተቱ ከሯጮችም አልፎ ከመንገዱ ዳር ቆመው ከሚያበረታቱና ለዘገባ በተሰየሙ የመገናኛ ብዙሃን እይታ ውስጥ ይገባል። ጉዳዩ ያስደነቃቸው የፎቶግራፍ ባለሙያዎችም ሩጫውን እየተከተሉ ካሜራቸውን ወደዚያው መደቀናቸውን ተያያዙት። ይህ ትዕይንት በዚህ ሁኔታ እንዳለ ግን በጎዳናው ግራና ቀኝ ካሉት ተመልካቾች መካከል ባልተለመደ መልኩ አንድ ሰው ሩጫውን ተቀላቀለ። የውድድሩን ክልል ጥሰው የገቡት አንጋፋ ሰውም እሳት ለብሰውና እሳት ጎርሰው ከሴቷ ሯጭ ጋር ግብግብ ጀመሩ፤ ነገር ግን ገላጋዮች በመሃል በመግባታቸው ከጀመረችው ሩጫ ሊገቷት አልቻሉም።ዕድሜ ሰጥቷት ዛሬን ለመመልከት የበቃችው የዚህ ታሪክ ባለቤት ካትሪን ስዊዘር ትባላለች። በጊዜው የሆነውን ስትተርክም ‹‹በረጅም ርቀት ሩጫዎች ላይ ሴቶች ለምን አይሳተፉም የሚለው የሁልጊዜም ጥያቄዬ ነበር። በሩጫው ላይ ለመሳተፍ ስነሳም እንዳይለዩኝ በሚል ስሜን አሳጥሬ ኬቪ ስዊዘር አደረኩት፤ በውድድሩ ዕለትም ከአሰልጣኜና የእግር ኳስ ተጫዋች ከሆነው ፍቅረኛዬ ጋር ተገኘሁ። ሩጫውን እንደጀመርንም ብዙዎች ሴት መሆኔን በመመልከት ተደንቀው ሲያዩኝ ‹‹አዎ እኔ ሴት ነኝ›› እላቸው ነበር፤ የካሜራ ባለሙያዎችም ፎቶ ሊያነሱኝ ሲከተሉኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። ከቆይታ በኋላ ግን የውድድሩ ዳይሬክተር በንዴት ወደእኔ መጣ፤ የመሮጫ ቁጥሩን ስጪኝና ከዚህ ውድድር ውጪ እያለ ይጮህና ይጎትተኝም ነበር። በፊቱ ላይ ይታይ የነበረው ብስጭት የሚያስፈራ ቢሆንም አብሮኝ የነበረው ፍቅረኛዬ በመሃላችን በመግባት እኔን ወደፊት እንድሄድ ነገረኝ። አንዳንድ ሯጮች ግን ከኋላዬ እስኪቀሩ ድረስ ‘መቻልሽን ለማስመስከር ነው ምትሮጪው፣…?’ በማለት ሲያሾፉብኝ ነበር›› ትላለች በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘውን የዚያኔውን ሁኔታ ስታስታውስ።ካትሪን ከዚያ በኋላ የነበሩትን ኪሎ ሜትሮች የሸፈነቻቸው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ነበር። ፍቅረኛዋ ሩጫውን ስለማጠናቀቅ በጠየቃት ጊዜም ‹‹በእጄና ጉልበቴ ድኼም ቢሆን እጨርሰዋለሁ አልኩት፤ ምክንያቱም ሩጫውን ካላጠናቀቅኩ ማንም የሴትን መቻል አይረዳም እያልኩ አስብ ነበር። እጨርሰዋለሁ እንዳልኩትም በ 4ሰዓት ከ20 ደቂቃ የመጨረሻውን መስመር ረገጥኩ፤ ምሽት ላይ ወደ ቤታችን ስንመለስም ክስተቱ ህይወቴን እንደቀየረው ተገነዘብኩ። ምክንያቱም በመንገዳችን ላይ ቡና ለመጠጣት ካረፍንበት ስፍራ ፎቶዬን የያዙና እኔን ዜና ያደረጉ በርካታ ጋዜጦችን በመመልከቴ ነው። በመጨረሻም ያደረኩት ነገር ሴቶች በስፖርት ያላቸውን ታሪክ ይቀይር ይሆናል በሚል ተስፋ አሳደረብኝ›› ትላለች ጠንካራዋ ካትሪን ስዊዘር። የ73 ዓመቷ ካትሪን ዛሬ ደራሲና የቴሌቪዥን አስተዋዋቂ ሆናለች። እርሷ የጀመረችው በቦስተን ማራቶን የሴቶች ተሳትፎም ከአምስት ዓመት በኋላ እኤአ በ1972 እውን ሲሆን፤ እኤአ በ1975 ለሁለተኛ ጊዜ ተሳትፋ የራሷን ምርጥ ሰዓት (2:51:37) በማስመዝገብ አሸናፊ ሆናበታለች። አሁን ዓመታዊው የቦስተን ማራቶን ሲካሄድ በክብር እንግድነት ትገኛለች፤ ሌሎች ሴቶች ሲመለከቷትም ለቅሶ እንደሚቀድማቸው ትናገራለች። የመጀመሪያ ሩጫዋን ባደረገችበት ዓመት የመሰረተችው የሴቶች ማህበርም እስከሁንም በአሜሪካ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። አዲስ ዘመን የካቲት 29 /2012  ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=28730
549
2ስፖርት
‹‹ወደ ቶኪዮ የምንሄደው ለተሳትፎ ሳይሆን ለማሸነፍ ነው››
ስፖርት
March 24, 2020
10
ኢትዮጵያ ለኦሊምፒክ ድል አዲስ ባትሆንም ውጤቷ በአትሌቲክስ ብቻ የተገደበ ስለመሆኑ እርግጥ ነው።ተሳትፎዋም ቢሆን ከቦክስ፣ ብስክሌትና ውሃ ዋና ስፖርቶች ያልዘለለ ነው።ጃፓን በመዲናዋ ቶኪዮ ከአራት ወራት በኋላ በምታስተናግደው የ2020 ኦሊምፒክ ግን ኢትዮጵያ በታሪኳ አዲስ በሆነ ስፖርት ተሳታፊ መሆኗ ታውቋል።ይህ ብስራት የተሰማው ከኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ስፖርት ሲሆን፤ ወጣቱ አትሌት ሰለሞን ቱፋ የታሪኩ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል።ሰለሞን ለዚህ ስኬት እንዲበቃ ከስድስት ዓመታት በላይ በአሰልጣኝነት አብሮት የደከመው ማስተር አዲስ ኡርጌሳም ከዚህ ታሪክ ባለቤትነት ጋር አብሮ ይነሳል።በአፍሪካ ካሉ ስመ ጥር የወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች ትልቁ ነው።በዓለም አቀፉ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ደግሞ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ የአሰልጣኞች እና የዳኞች አሰልጣኝ ነው። የአፍሪካ ወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች ሊቀመንበር በመሆንም እያገለገለ ነው።ማስተር አዲስ ዑርጌሳ።በ2010/11 የውድድር ዓመት በተሳተፈባቸው ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ውድድሮች ላይ ባልተመቻቸ ሁኔታ በጥቂት ስፖርተኞች ተሳትፎ 5 ወርቅ 2 ብር እና 3 የነሀስ ሜዳሊያዎች በሚያሰለጥናቸው ስፖርተኞች አማካኝነት ለኢትዮጵያ አስገኝቷል።ባለፈው ሪዮ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድሮች በሁለቱም ፆታ ያሰለጠናቸው ተወዳዳሪዎች ወደ ታላቁ መድረክ ለማለፍ ከጫፍ ደርሰው ሳይሳካላቸው ቀርቷል።ከሃያ ዓመታት በላይ በስፖርቱ ውስጥ ያሳለፈው ማስተር አዲስ ዛሬ ላይ ህልሙ እውን ሆኖ ታላቁ የስፖርት መድረክ ላይ ደርሷል።በአገራችን ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ተስፋና ስጋት እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው ይናገራል። አዲስ ዘመን፡- በዓለም ላይ ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ተከትሎ ኦሊምፒክ ሊራዘም እንደሚችል ስጋት አለ፣ ምናልባት የሚራዘመው ለረጅም ጊዜ ከሆነ እንደ ወርልድ ቴኳንዶ አይነት ብዙ ልፋትና ዋጋ የሚከፈልባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ዳግም ወደ ማጣሪያ የሚገቡበት አጋጣሚ ይኖራል? ማስተር አዲስ፡- አይመስለኝም፤ እስካሁንም እንዲህ የሚል ህግ አላየሁም።ምናልባት ከአንድ ዓመት በላይ የሚራዘም ከሆነ ሊባል ይችል ይሆናል።ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ እስከ መጨረሻው ነገሮችን ሳይመለከቱ ወደዚህ ውሳኔ ይገባሉ የሚል እምነት የለኝም፤ ቢያራዝሙ እንኳን ጥቂት ወራትን ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ነው ያለኝ። አዲስ ዘመን፡- የኦሊምፒክ ማጣሪያውን አልፋችሁ ትልቅ ደረጃ ላይ ስትደርሱ የነበረው ሂደት እንዴት ነበር? ማስተር አዲስ፡- ማጣሪያው ወደ 34 የአፍሪካ አገራት የተሳተፉበት ትልቅ ውድድር ነበር።ለአራት ዓመታት ያደረግነውን ዝግጅትም ከ100 በላይ ከሚደርሱ ስፖርተኞች ጋር ተወዳድረን ነው የመዘንነው።እንደሚታወቀው ሰለሞን ሶስቱን ዓመት እስከ አውሮፓ በመጓዝ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ነው ያሳለፈው።በቱርክና በፖላንድ ከተሳተፈባቸው ውድድሮች ባሻገር የአፍሪካ ዋንጫንና ፕሬዚዴንሺያል ዋንጫን ጠቅልሎ በመውሰድ በአፍሪካም ኮከብ በመባል ነበር ያጠናቀቀው።ይህም ወደ ማጣሪያው ሲገባ ትልቅ ደረጃን ይዞ በመሆኑ ውጤቱም መልካም ሆኗል፡፡አዲስ ዘመን፡- ቀደም ባሉት ዓመታት በወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ውጤት ይመጣበታል የሚል ብዙም እምነት አልነበረም፣ ይህን አስተሳሰብ ሰብሮ ፈታኝ የሆኑ ማጣሪያዎችን በማለፍ ለኦሊምፒክ ስፖርተኛን ማብቃት ከባድ መሆኑን መገንዘብ አይከብድም፣ ነገር ግን ይህ ስኬት ትልቅ ቦታ ተሰጥቶታል ብለህ ታምናለህ? ማስተር አዲስ፡- በማጣሪያው ላይ ከሰለሞን ጋር ውድድር ያደረገው ስፖርተኛ በዓመት ውስጥ ከ13 ያላነሱ ውድድሮችን አድርጓል፤ በዓለምና በአፍሪካ ያለው ደረጃም በጣም ጥሩ ነው።ሰለሞን በአንጻሩ ከአራት ያልበለጡ ውድድሮች ላይ ብቻ ተሳታፊ ሆኖ ነው ለአሸናፊነት የበቃው።ይህንን ድል መድገም አይቻልም ነገር ግን የተሰጠው ክብር ብዙም አይደለም። አዲስ ዘመን፡- ከዚህ ቀደም በምትሳተፉባቸው ውድድሮች ብዙም ድጋፍ እንደማይደረግላችሁ ይታወቃል።በዚህ ማጣሪያስ ድጋፉ እንዴት ነበር? ማስተር አዲስ፡- ድሮ ከነበረው በጣም የተሻለ ነበር፤ በተለይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥሩ ድጋፍ አድርጎልናል።ፌዴሬሽኑም ያለውን አቅም ተጠቅሟል፤ ከዚህ ቀደም ውድድሮች ሲኖሩብን ለአጭር ጊዜ ነበር ቡድናችንን የምናዘጋጀው አሁን ግን ለረጅም ጊዜ በዝግጅት ላይ እንድንቆይ መደረጉ መልካም ነው።በአንጻራዊነት እንደ አጠቃላይ ያለው ነገር የተሻለ ነው ለማለት ያስችላል።አዲስ ዘመን፡- ማለፋችሁን ተከትሎስ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምን አደረገላችሁ? ማስተር አዲስ፡- እስካሁን ምንም የተደረገልን ነገር የለም፡፡ አዲስ ዘመን፡- ከሰለሞን ባሻገር በአፍሪካ ደረጃ ውጤት ያስመዘገቡ ስፖርተኞች ተስፋ ቢጣልባቸውም አሁን ላይ አናያቸውም ምክኒያቱ ምንድነው? ማስተር አዲስ፡- በእኛ ስፖርት ችግሩ የክለቦች አለመኖር ነው፤ ስለዚህም ወጣቶቹ ስራ ሳይሰሩና ትምህርት ሳይማሩ ስፖርቱ ላይ ብቻ ተሳታፊ እየሆኑ መቆየት አስቸጋሪ ነው።ብዙዎቹ ሰልጣኞች ሌላ ገቢ ስለሌላቸው ከብሄራዊ ቡድን በኋላ ወደ ሌላ ነገር ይሰማራሉ፣ አሊያም ስፖርቱን ይተውታል።ስለዚህም ፌዴሬሽኑ አሁን የመጣው ውጤት ላይ ተመርኩዞ በርካታ ስራዎችን ማከናወንና የማስተዋወቅ ስራ ይጠበቅበታል።በመገናኛ ብዙሃን በኩልም አበረታች የሆኑ ስራዎች በይበልጥ መሰራት ተገቢ ነው።አዲስ ዘመን፡- በኢትዮጵያ እጅግ ተዘውታሪ ከሆኑ ስፖርቶች መካከል የማርሻል አርት ስፖርቶች ተጠቃሽ ናቸው።ነገር ግን በሺዎች ከሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ከዓመታት በኋላ ነው አንድ ስፖርተኛ ያገኘነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? ማስተር አዲስ፡- ከሩቅ ሆኖ ሲታይ ነገሮች ተመቻችተው ይመስላል፤ ነገር ግን እንደ ሌሎች አገሮች ስፖርቱ ኢንቨስት እየተደረገበት አይደለም።ሌሎች አገራት ዝግጅት የሚያደርጉት ለዓመታት ነው፤ በተለያዩ ውድድሮች ላይም ተሳታፊ በመሆን አቅማቸውን ይፈትሻሉ።እኛጋ ግን በዚያ ደረጃ እየሄደ አይደለም፤ ከስር በርካታ ማሰልጠኛ ማዕከላት ይኑሩ እንጂ ከዚያ የሚወጡትን ሰልጣኞች የሚያቅፍ ክለብ የለም።ለአብነት ያህል ከሰለሞን ጋር ዝግጅት የሚያደርግና በእርሱ ደረጃ የሚገኝ ስፖርተኛ ማግኘት ከባድ ነው።ወደ ሌሎች ክለቦች ሄደንም የወዳጅነት ልምምድ ለማድረግም ለእኛ ከባድ ነው።አዲስ ዘመን፡- በቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ የተለየ እቅድ አላችሁ? ማስተር አዲስ፡- ከ20 ዓመት በፊት በተካሄደው የሲድኒ ኦሊምፒክ ላይ የመገኘት እድል ገጥሞኝ ነበር፤ ወቅቱ ቴኳንዶ የኦሊምፒክ ስፖርት የሆነበት ስለነበር ተጋባዥ በመሆን ነው የታደምኩት።የዚያኔ ለራሴ በኦሊምፒክ ተሳታፊ እንደምሆን ነግሬው ከዓመታት በኋላ ስኬታማ ሆኛለሁ።አራት ኦሊምፒኮችን ከሞከርኩ በኋላም በአምስተኛው እድል ቀንቶኛል።ወደ ቶኪዮ የምንሄደው ደግሞ ለተሳትፎ ሳይሆን ለማሸነፍ ነው።አዲስ ዘመን፡- የአገራችን በርካታ ፌዴሬሽኖች እንኳን ለ20 ዓመታት የአንድ ዓመት እቅድም ሲያወጡና ሲፈፅሙ አይታዩም፣ አንተ በግልህ ይህን አሳክተሃልና ከዚህ ምን መማር ይቻላል? ማስተር አዲስ፡- እኔ በተለያዩ አገራት ተዘዋውሬ እንደተመለከትኩት ከሆነ ለአንድ ስፖርት መሰረትም አስፈላጊውም አሰልጣኝ ነው።አሰልጣኞችን ለማብቃት ደግሞ ፌዴሬሽኖች መስራት ይገባቸዋል፤ ምክንያቱም አሰልጣኝ ሁሌም በልጦ መገኘት አለበት።መንግስትም የፌዴሬሽኖች በጀት ላይ ድጎማ ማድረጉ ተገቢ ነው፤ የሚሰሩትንም ማበረታታት ያስፈልጋል።ሌላው ነገር በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ መሆን ነው፤ ከዚያ በኋላ በደረጃ ወደ ዓለም ማውጣት ይቻላል።አዲስ ዘመን፡- እንዲህ አይነት ስኬቶች ሲመዘገቡ ከእውቅናና ማበረታቻ ጋር በተያያዘ ምን መደረግ ይኖርበታል ትላለህ? ማስተር አዲስ፡- ሁሌም ስለ አንድ ነገር መወራት ያለበት ውጤት ሲመጣ ብቻ መሆን የለበትም።ውጤት ባይመጣም ስፖርተኞች መበረታታት አለባቸው፤ ምክንያቱም በውድድር ዕለት በጥቂት አጋጣሚ ከውጤት ውጪ መሆን ይከተላል።በመሆኑም ውጣ ውረዱና ልፋቱ ሊታይ እንዲሁም ላሉበት ደረጃ በመብቃታቸው ሊበረታቱ ይገባል።ይህ ሲሆን ደግሞ ለቀጣይ መነሳትን ይፈጥራል። አዲስ ዘመን፡- ማስተር አዲስ ለሰጠኽን ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ ማስተር አዲስ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 14 /2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=28968
833
2ስፖርት
ካናዳ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ እራሷን አገለለች
ስፖርት
March 24, 2020
19
ካናዳ በኮሮና ቫይረስ ስጋት በዚህ ዓመት ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ራሷን ማግለሏን ቢቢሲ ዘግቧል። ጃፓን ለማስተናገድ ለዓመታት ስትዘጋጅለት የነበረው የ2020ው ኦሊምፒክ ውድድር ከአራት ወራት በኋላ በሐምሌ ወር የሚካሄድ ቢሆንም በቫይረሱ ስርጭት ሳቢያ ላይካሄድ እንደሚችል ስጋት አድሯል፡፡ ኦሊምፒኩ ይካሄድም አይካሄድም በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ካናዳ ከኦሎምፒክ መድረክ ራሷን ከወዲሁ ማግለሏ ተረጋግጧል፡፡ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሊምፒክ ውድድሩ ለሌላ ጊዜ ሊተላለፍ እንደሚችል ከተናገሩ በኋላ ካናዳ ይህንን ውሳኔዋን ልትወስን መቻሏን የዘገበው ቢቢሲ ፤ካናዳ የጨዋታው ዋነኛ ተሳታፊ ከሚባሉት መካከል መሆኗን ገልጾ ፤እራሷን በማግለሏ በውድድሩ መካሄድ ላይ ተጨማሪ ጥርጣሬ ፈጥሯል ብሏል። የካናዳ የኦሊምፒክና ፓራኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔውን በተመለከተ እንደገለፀው፤ ከውድድሩ ለመውጣት ከውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ከአትሌቶች፣ ከስፖርት ቡድኖችና ከካናዳ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ተመካክሯል፡፡ ኮሚቴው ጨምሮም ለዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ለዓለም አቀፉ የፓራኦሊምፒክ ኮሚቴና የዓለም የጤና ድርጅት የኦሊምፒክ ውድድሩ በአንድ ዓመት እንዲዘገይ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። «ውድድሩን ለሌላ ጊዜ በማሸጋገር ሂደት ውስጥ የሚያጋጥመውን ውስብስብ ሁኔታን ብንረዳውም፤ ምንም ነገር ከአትሌቶቻችንና ከዓለም ሕዝብ ጤናና ደህንነት የሚበልጥ አይሆንም» ሲል የካናዳ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫም አስታውቋል። ካናዳ በኦሊምፒክ መድረኩ አልሳተፍም ማለቷን ተከትሎ የአውስትራሊያ የኦሊምፒክ ቡድን ውሳኔውን በመደገፍ መግለጫ ማውጣቱን ቢቢሲ አስነብቧል። የአውስትራሊያ የኦሊምፒክ ቡድን እንዳለው አሁን ባለው ሁኔታ ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንደማይካሄድ ግልጽ እየሆነ በመምጣቱ ተሳታፊ አትሌቶች ለቀጣዩ ዓመት እንዲዘጋጁ ተነግሯቸዋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 15/ 2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29026
205
2ስፖርት
ስፖርቱ ስለምን ይሸበራል?!
ስፖርት
March 27, 2020
18
እኤአ ታኅሣሥ 31 ቀን 2019 በቻይና ዉሃን ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን የዓለም የጤና ድርጅት ማስታወቁን ተከትሎ የቻይና መንግሥት በአፋጣኝ የቫይረሱን ስርጭት በአጭሩ ለመቅጨት እርምጃ ወደ መውሰድ ገብቶ ነበር። የቫይረሱን ስርጭት እንደተባለው በቀላሉ ለመቆጣጠር ሳይቻል ቀርቷል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱ ወረርሽኝ ደረጃ መድረሱን ተከትሎ በዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ አደጋ ጥሏል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ለውጦችን ከማስተናገድ አልፎ ቆሞ ቀር ለመሆን ተገዷል፡፡ የስፖርት መገናኛ ብዙኃንም እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ መካሄድ አለማኬዱ ያለየለት ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ብቻ የዜና ግብዓታቸው የሆነ መስሏል፡፡ ዓለም በእንዲህ ዓይነት አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩን በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ ለረጅም ጊዜ ደረቅ አቋም መያዙ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣትና የአንድ ሀገር ስጋት ከመሆን ወደ ዓለም አቀፍ ስጋትነት እያደገ መምጣት ነገሮችን እንዲቀየሩ አድርጓል፡፡ በኦሊምፒክ መድረክ የሚሳተፍ አገራት «በመድረኩ እንሳተፍ» ወደሚል ውሳኔ ላይ እንዲደርሱም አድርጓል። የ2020 ኦሊምፒክ መካሄድ የለበትም የሚሉ ሀሳቦች ቀስ በቀስ መነሳታቸውም ውድድሩ ይራዘም የሚሉ ድምጾች ከቀን ወደ ቀን ብዛትና ጉልበት እንዲያገኙ አቅም ፈጥሮላቸዋል፡፡ የኦሊምፒክ መድረኩ የማይራዘም ከሆነ ስፖርተኞቻችንን ለአደጋ አናጋልጥም፣ ዓለም በጭንቅ ውስጥ እያለች ከሚካሄደው የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ይቅርብን ያሉ እንደ ካናዳ ያሉ አገራት ራሳቸውን እስከማግለል ደርሰዋል። የካናዳን እግር በመከተል እንደ አውስትራሊያ ያሉ አንዳንድ አገራት ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያም የተሳትፎ ጉዳይ በአንድ ልብ ውሳኔ መስጠት ሳይቻል ቀርቶ ከፍተኛ ውዝግብ እስከማስነሳት የደረሰ ነበር። «የኢትዮጵያ አትሌቶች በውድድሩ ለመሳተፍ አንድ ላይ ሆቴል ገብተው ዝግጅት መጀመር አለባቸው የለባቸውም» በሚል በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መካከል ብርቱ የሆነ እሰጣ አገባ መፈጠሩ አይዘነጋም፡፡ ይሁን እንጂ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከቀናት በፊት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ለአንድ ዓመት ማራዘሙን ተከትሎ በሁለቱ አካላት መካከል የነበረው የሃሳብ ልዩነት መቋጫ አግኝቷል፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት አመራሮች መካከል ሰሞነኛው ውዝግብ ዓለም አቀፉ ኮሚቴ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የረገበ ይምሰል እንጂ ነገ እንደ አዲስ አለመነሳቱን በርካቶች ይጠራጠሩታል፡፡ በሁለት ጎራ የተቧደኑ የስፖርት አመራሮች ውዝግብ ከየት ተነሳ?ብለን በመጠየቅ ወደ ኋላ መለሰ ብለን የተፈጠረውን ጉዳይ እንመርምር። ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አዱላላ ሪዞርት፣የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዝግ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቷል። ወቅቱ ደግሞ የዓለም አገራት በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ የሚኖራቸውን ተሳትፎ በጎ መልክ ለማስያዝ ሽርጉድ እያሉ የሚገኙበት ነው። የኦሊምፒክ ኮሚቴ በዝግ ስብሰባ የቶኪዮ ኦሊምፒክን መሠረት ያደረገ ውሳኔን ይዞ ከመምጣት ይልቅ፤ «የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የሥራ አመራር ቦርድ የአገልግሎት ዘመንና ተቋሙን በዋና ጸሐፊነት እንዲመራ፣ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የሥራ አመራር ቦርድ የቆይታ ጊዜ ከአራት ዓመት ወደ ስምንት ዓመት እንዲሻሻል ተደርጓል» የሚል ነበር። የኦሊምፒክ ኮሚቴ ይሄንኑ ውሳኔውን ተከትሎ ኮሚቴው ስፖርቱን ለማሳደግ የያዘውን ወንበር የሥልጣን ጊዜውን ለማሳደግ እየተውተረተረ መሆኑን አሳዛኝ እንደሆነ ከተለያዩ አካላት ትችቶች ሲሰነዘሩበት ነበር። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዚህ ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ጉባዔው ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጉዳዮች ተገቢነት ላይ ‹‹አልተስማማሁም›› ሲል ተቃውሞውን አሳውቋል፡፡ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የፌዴሬሽኑን ሀሳብ በመደገፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ሊታረም እንደሚገባ እስከ ማስገንዘብ ደርሶም ነበር። በዚህ መልክ የሚደረግ ሙግት ስፖርቱን መሠረት በማድረግ እንዲህ ዓይነት የሀሳብ ተቃርኖዎች የሚበረታቱ ቢሆንም፤ የስፖርቱ አመራሮች በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በመውጣት የሚሰጧቸው ምላሾችና የቃላት ልውውጦች ስፖርቱን መሠረት ያደረጉ አልነበሩም። በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ በኩል በወቅቱ ይሰጧቸው በነበሩት ቃለ ምልልሶች ይሄንኑ በሚገባ የሚያንፀባርቁ ነበሩ። ስፖርቱን የሚመሩ ሌሎች አመራሮች የሚሰጡ አስተያየቶች ተመሳሳይ የነበሩ ሲሆን፤ ይህም ስፖርቱን መሠረት ያደረገ ቅራኔ አለመሆኑን በተጨባጭ መገንዘብ ያስችላል። ከስፖርቱ አመራሮች ውዝግብ ጀርባ ያለው ሴራ እንዳለ ሆኖ በክስተቱ ብዙዎችን ማስቆጣቱን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር። የስፖርት አመራሮቹ ሲወዛገቡበት የነበረበት ወቅት ለቁጣው ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ዙሪያ ከማተኮር ይልቅ፤ ባልተገባ ትርምስና ሽኩቻ ስፖርቱን ለመጥቀም ወይስ ለመጉዳት? ያስባለም ነበር። በዚህ ደረጃ ቅሬታን ካስነሳ በኋላ በሁለቱ ጎራ የነበረው ፀብ በይደር እንዲቆይ በማድረግ ተቋማቱ ትኩረታቸውን ወደ ኦሊምፒክ ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር፡፡ ስፖርቱን የማሸበሩ ዜና ግን ዳግመኛ ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ተፈጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቶኪዮ 2020 አሊምፒክ ላይ ለሚደረገው ዝግጅትና ተሳትፎ በሚመለከት ባለድርሻ አካላትን ጋር ያዘጋጀው የምክክር መድረክ ለዚህ እንደመነሻ ሆኗል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ‹‹በመድረኩ እንድንሳተፍ መልዕክት አልደረሰኝም›› ሲል ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ትልቁን ባለድርሻ አካል ሳያሳትፍ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱ ቅር መሰኘቱን አስታውቋል። አጋጣሚውም የሁለቱ ተቋማት ቁርሾ ለኦሊምፒክ እየተደረገ ያለው ዝግጅት በተናጠል እንዲሆን በር ከፍቷል፡፡ «በዝሆኖች ፀብ የሚጎዳው ሳሩ ነው» እንደሚባለው በስፖርቱ አመራሮች ሽኩቻ አገሪቷ ዋጋ እንዳትከፍል መፍትሄ መስጠት አስፈላጊ ቢሆንም በዝምታ ታልፏል፡፡ የአመራሮቹ ቁርሾ መፍትሄ አለማግኘቱን ተከትሎ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ ፤ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት እንደሚካሄድ ገልጿል፡፡ በዚህ መሠረት አትሌቲክሱን ጨምሮ ለቶኪዮ 2020 የተመረጡ ብሔራዊ አትሌቶች ዝግጅት መጀመር እንዳለባቸው አስታወቀ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ደግሞ ፤ «የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሔ ሳያገኝ ብሔራዊ አትሌቶችን በሆቴል አሰባስቦ ዝግጅት ማድረጉ አደጋ አለው» ሲል አስገነዘበ። ለብሔራዊ አትሌቶች የተደረገው ጥሪን ኃላፊነት የጎደለው እንደሆነ በመሞገት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ውሳኔ ፊት ለፊት ተጋፈጠ። የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አቋም እንደፀና የኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔው ተገቢና የማይቀለበስ መሆኑን አቋም በመያዝ ፍጥጫ ውስጥ ገቡ። በመጨረሻም ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ እንዲሰረዝ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ማስታወቁ ተከትሎ፤ በስፖርት አመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ግብ ግብ ረገበ። ይህ ሽኩቻ እንዳለፉት ጊዜያቶች ተዳፈነ እንጂ አልጠፋም፡፡ ነገ እንደረመጥ የሚቆሰቁሰው አንድ አካል እንደሚኖር ሁለቱ አካላት አንዴ ሲሻኮቱ አንዴም ተስማማን እያሉ ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ እንደሚባለው መሆናቸውን ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ለዚህም የሁለቱም ተቋሞች የበላይ የሆነው ስፖርት ኮሚሽን ኦሊምፒክ ሲመጣ ሳይሆን ከወዲሁ የሚስማሙበትን መንገድ መፈለግ እንዳለበት ይታመናል፡፡ በግለሰቦች ፍጥጫና የግል ፍላጎት ትልቁ የአገር ገፅታ ኦሊምፒክ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የነገ ሳይሆን የዛሬ ጉዳይ ነው፡፡ አዲስ ዘመን መጋቢት 18/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29263
802
2ስፖርት
የማይቀረው ውሳኔ ተወስኗል
ስፖርት
March 26, 2020
9
የመላው ዓለም ሕዝብ ትኩረትና ጭንቀት በሆነው የኮሮና ቫይረስ ፈጣንና አስደንጋጭ ስርጭት የተነሳ መደበኛ እንቅስቃሴዎች በብዙ የዓለማችን አገራት ተገተዋል። የስፖርቱ ዓለም በቫይረሱ ስጋት ሳቢያ ብዙ ለውጦችን ከማስተናገድ አልፎ ሽባ ሆኗል። የስፖርት መገናኛ ብዙኃንም በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ በማጠንጠን ቆመዋል። ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የሁሉም የስፖርት ቤተሰብ ልብ አንጠልጣይ ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል። ዓለም በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውድድሩን በተያዘለት ጊዜ ለማካሄድ ድርቅ ማለቱ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። ያም ሆኖ የዓለም አቀፍ ኮሚቴውን ደረቅ አቋም የሚፈታተን አዲስ ዜና ከየአቅጣጫው ብቅ ማለቱ ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠሩ አልቀረም። በተለይም ካናዳና አውስትራሊያን የመሳሰሉ አገራት ከቀናት በፊት ራሳቸውን ከኦሊምፒክ እንዳገለሉ መግለፃቸውን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ኮሚቴው ከግትር አቋሙ እየተለሳለሰ እንዲመጣ አስገድዶታል። ፈረንሳይና እንግሊዝን የመሳሰሉ አገራትም ዓለም አቀፍ ኮሚቴው በአስቸኳይ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ መጠየቃቸውን ተከትሎ ኦሊምፒኩ ላይ ለውጥ ስለመኖሩ በርካቶችን እርግጠኛ ያደረገ ነበር። የኦሊምፒክ ትልቁ ባለድርሻ አካል የዓለም አትሌቲክስ ከቀናት በፊት የቶኪዮ ኦሊምፒክ እንዲራዘም ጥያቄ ማሳቱን ተከትሎም በቅርቡ አዲስ ነገር እንዲጠበቅ አድርጓል። የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮ ኦሊምፒኩ ወደ 2021 የሚሸጋገር ከሆነ በኦሬገን አሜሪካ በተመሳሳይ ወቅት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወደ ሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ሙሉ በሙሉ ፈቃደኛ እና ዝግጁ መሆናቸውን ለኮሚቴው ባስገቡት ‹‹ውድድሩ ለሌላ ጊዜ ይተላለፍልን›› መጠየቂያ ደብዳቤያቸው ማረጋገጣቸውም ኦሊምፒኩ እንደሚራዘም ያረጋገጠ ርምጃ ነበር። ይህ ሁሉ ተፅዕኖ የተፈጠረበት የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴም እየመረረውም ቢሆን ውድድሩን ወደ 2021 ለማስተላለፍ ያስገደደውን የማይቀር ውሳኔ ማሳለፉን አሳው ቋል። የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ ከትናት በስቲያ ምሽት ባደረጉት የቪዲዮ ኮንፍረንስ ከቫይረሱ ስርጭት ጋር በተያያዘ ያለውን አደጋ ከግምት በማስገባት ኦሊምፒኩ ወደ 2021 እንዲራዘም ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን አሳውቀዋል። ኦሊም ፒኩ ወደ 2021 መሸጋገሩ ይጠቀስ እንጂ በየትኛው ወቅት እንደሚካሄድ የተገለፀ ነገር የለም። ያም ሆኖ የበጋ ኦሊምፒክ እንደመሆኑ መጠን በቀጣይ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ላይ ሊካሄድ እንደሚችል ተገምቷል። ይህንን ውሳኔ ተከትሎም የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ከጦርነት ውጪ ባሉ ምክንያቶች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተላለፈ ሊሆን ችሏል። ኦሊምፒክ ከጤና ስጋት ጋር የተያያዘ ባይሆንም በተለያዩ ጊዜዎች የመራዘም፣የመሰረዝና የቦታ ለውጥ ሲደረግበት ታይቷል። እኤአ የ1916 የበጋ ኦሊምፒክ በጀርመን በርሊን ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት በአንደኛ የዓለም ጦርነት ሳቢያ ተሰርዟል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅትም የ1940 የክረምት ኦሊምፒክና የ1944 የበጋ ኦሊምፒክ ውድድሮች የመሰረዝ ዕድል ገጥሟቸዋል። እኤአ የ1976 የክረምት ኦሊምፒክም በዴንቨር ኮሎራዶ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የኮሎራዶ ግዛት ሕዝብ ለውድድሩ የሚወጣውን ወጪ በመቃወሙ ውድድሩ የቦታ ለውጥ ተደርጎበት በአውስትራሊያ ኢንስብረክ ለመካሄድ ተገዷል። ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ በወቅቱ እንደዘገበው የኮሎራዶው ኦሊምፒክ የቦታ ለውጥ እንዲደረግበት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ውድድሩ ከመካሄዱ ከሦስት ዓመታት አስቀድሞ ነበር። ይህም ከጥንት ጀምሮ የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ የቦታ ለውጥ ለማድረግ ቢያንስ ከሁለት ዓመት በፊት ውሳኔ ላይ መደረስ ይኖርበታል። የሪዮ 2016 ኦሊምፒክም ከመድረሱ ከዓመታት በፊት የዚካ ቫይረስ ስጋት መሆኑ ቢታወቅ ሊሰረዝ፣ሊራዘምና የቦታ ለውጥ ሊደረግበት ይችል እንደነበር በርካቶች አስተያየት ሲሰጡ ይስተዋላል። የዚካ ቫይረስ የሪዮ ኦሊምፒክ ስጋት መሆኑ የታወቀው ውድድሩ ከመካሄዱ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ መታወቁ የቫይረሱ ስርጭት ያን ያህል ስጋት ካለመሆኑ ጋር ተደምሮ የመሰረዝ፣ የመራዘምና የቦታ ለውጥ ሳይደረግበት ለመቅረቱ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የሚያብራሩም ጥቂት አይደሉም። ዘንድሮም ከአራት ዓመት በኋላ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ከጥር ጀምሮ በቻይና በተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ተመሳሳይ አደጋ ሊራዘም በቅቷል። አዲስ ዘመን መጋቢት 17/2012
https://www.press.et/Ama/?p=29163
466
2ስፖርት
ለእጅ ኳስ ስፖርት 40 ዓመታት የተዘረጉ እጆች
ስፖርት
March 24, 2020
29
በኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ስፖርት ታሪክ ውስጥ አንቱታን ማትረፍ ችለዋል። የእጅ ኳስ ስፖርትና እርሳቸው የሚነጣጠሉ አለመሆኑን ብዙዎች ይመሰክሩላቸው። ለእጅ ኳስ ስፖርት ጥልቅ ፍቅር ያላቸው ኢንስትራክተር አሰፋ ገለቱ። በእጅ ኳስ ስፖርት በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ተጫውተው ከማለፍ ባሻገር በርካታ ወጣት አሰልጣኞችን ማፍራት መቻላቸው ለዚህ ክብር እንዲበቁ አድርጓል። የኢንስትራክተር አሰፋ የስፖርት ህይወት ጅማሮ ከ40 ዓመታት በፊት እንደነበር እንዲህ ይናገራሉ። «ስፖርታዊ እንቅስቃሴን የጀመርኩት በሰፈር ውስጥ ሲሆን ከልጅነት ጀምሮ ንቁ ተሳትፎ አደርግ ነበር። በስፖርቱ የነበረው ተሳትፎ ግን እግር ኳስን ያስቀደመ ነው።›› ኢንስትራክተር አሰፋ ከእግር ኳሱ እኩል ቅርጫት ኳስ እና እጅ ኳስን ይጫወቱም ነበር። በተለያዩ ስፖርቶች ተወጥሮ የነበረው የስፖርት ፍቅር በአንድ አጋጣሚ ነበር ወደ እጅ ኳሱ ብቻ ሊያመዝን እንደቻለ የሚናገሩት፡፡ ‹‹በወቅቱ ከአዲስ አባባ ፖሊስ የእጅ ኳስ ቡድን ጋር በመሆን እጅ ኳስ እጫወት ነበር። ከቡድኑ ጋር አደርገው በነበረው እንቅስቃሴ ከቡድኑ ተጫዋቾች ብሎም አሰልጣኞች በእጅ ኳሱ እንድገፋበት አድርጎኛል። በዚህ ግፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ የእጅ ኳስ ቡድንን በመቀላቀል ወደ እጅ ኳስ ስፖርት ሙሉ ለሙሉ መግባት ቻልኩ›› ይላሉ። ኢንስትራክተር አሰፋና እጅ ኳስ በዚህ መልኩ ትውውቅ ካደረጉ በኋላ በበርካታ የከተማ አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ውድድሮች ላይ የመጫወት እድሎችን አገኙ። በእጅ ኳሱ የተጫዋችነት ሂደት ውስጥ ከክለብ ባለፈ እስከ ብሔራዊ ቡድን ውክልና ዘልቋል፡፡ ለኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ብሄራዊ ቡድን በመመረጥ ለአምስት ዓመታት እስከ መጫወትም ደርሰዋል፡፡ ኢንስትራክተር አሰፋ በተጫዋችነት ብቻ 20 ዓመታት ማሳለፍ የቻሉ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ «በተጫዋችነት ዘመኔ የማይቆጩኝን 20 ዓመታትን አሳልፌያለሁ። በስፖርቱ ሀገሬን በመወከል በብሄራዊ ቡድን ደረጃ የተጫወትኩበት እነኚህ ዓመታት ለእኔ ልዩ ኩራቴና ትዝታዎቼ ነበሩ» ሲሉ ያለፈውን የተጫዋችነት ዘመን ያስታውሳሉ፡፡ ለሀገር ክብርና ፍቅር እንዳላቸው ደጋግመው የሚናገሩት ኢንስትራከተር አሰፋ የተጫዋችነት ዘመናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ አሰልጣኝነት ነበር የተሸጋገሩት። ኢንስትራከተር አሰፋ በእጅ ኳሱ አሰልጣኝ በመሆን በአዲስ መንፈስ እንዴት ብቅ እንዳሉ ሲያስታውሱ፤ «የእጅ ኳስ አሰልጣኝነትን የአዲስ አበባ ፖሊስ እጅ ኳስ ቡድን በመያዝ ነበረ የተጀመረው። ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በርካታ ጊዜያትን ካሳለፍኩኝ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻዬ የነበረው ኦሜድላ ነበር» ይላሉ። የኦሜድላን እጅ ኳስ ቡድን ወደ ማሰልጠኑ መሸጋገራቸው ለስፖርቱ የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ እንዲጨምር እንዳደረገላቸው ይናገራሉ። በኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ታሪክ በተለይ በ70ዎቹ ውስጥ በጥንካሬያቸው ከሚጠቀሱት ክለቦች መካከል ኦሜድላ ዋነኛው ነው። ከክለቡ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስፖርቱን ወደ ፊት ማራመድ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት እንዳስቻላቸው ኢንስትራክተር አሰፋ ይናገራሉ፡፡ በአሰልጣኝነት ቆይታቸው ጊዜ እየተመዘገቡ ባሉ ውጤቶች ደስተኛ የነበሩት ኢንስትራክተር አሰፋ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የእጅ ኳስ ስፖርት መዳከምና ውጤት አልባ እየሆነ መምጣት በቁጭት እንዲሞሉ ያደረጋቸው ነበር። በወቅቱ ስፖርቱ ረጅም ዓመት እንደቆየ ባለሙያ መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባ ለሚመለከተው አካል ሃሳብ እስከ ማቀበል መድረሳቸውን ያስታውሳሉ፡፡ በሃሳብ ብቻ መወሰን ግን አልፈለጉም ነበር ። ከኦሜድላ ክለብ ጋር የነበራቸውን ጉዞ በመግታት መፍትሄው ላይ ወደ ማነጣጠር አዘነበሉ፡፡ ስፖርቱን መሰረት አሳጥቶ ውጤት አልባ ያደረገው የተተኪ ችግር እንደሆነ በማጥናት ታዳጊዎች ላይ መስራት ይጀምራሉ፡፡ በ1990 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤት ያጣውን የእጅ ኳስ ስፖርት ለመታደግ ታዳጊዎችን መሰረት ያደረገውን ተግባር በቁጭት ጀመሩ። ከአዲስ አበባ እጅ ኳስ ፌዴሬሽንና ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር በመቀናጀት ታዳጊዎችን በፕሮጀክት ደረጃ በማቀፍ ስልጠናዎችን በስፋት መስጠት ተያያዙት፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም ውጤታማ ስራዎች ማከናወን ቻሉ፡፡ የኢንስትራክተር አሰፋ ታዳጊዎችን መሰረት ያደረገ ስልጠና በትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ወደ መስራት ሽግግር ያደረገ ነበር። በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የአንድኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በመመልመል የእጅ ኳስ ስፖርት ወደ ማሰልጠን ነበር የተሸጋገሩት። ኢንስትራክተር አሰፋ ትምህርት ቤቶች ላይ መሰረት በማድረግ በርካታ ታዳጊዎችን አሰልጥነው ማስመረቅ እንደቻሉ ይናገራሉ። «የአምናውን ብቻ ብናስታውስ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆኑ 300 ታዳጊዎችን በፕሮጀክት ደረጃ በማሰልጠን ተመርቀዋል።በዘንድሮ ዓመትም በተመሳሳይ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከ20 በላይ መንታዎች ሰልጠነው ተመርቀዋል» ሲሉ ይናገራሉ። በእጅ ኳስ ስፖርት ውስጥ ትልቅ አሻራ ማሳረፍ የቻሉት ኢንስትራክተር አሰፋ፤ የስፖርት ህይወት ጉዞን አስደናቂ የሚያደርገው ለስፖርቱ እድገት ታዳጊዎችን መሰረት አድርጎ መስራት እንደሚበጅ በማመን በሰሩት ውጤታማ ተግባር የተቸራቸው ምስጋና ሳያባራ፤ በሀገራችን ባልተለመደ መልኩ መስማት የተሳናቸውን ዜጎች እጅ ኳስ ለማሰልጠን የሚያስችል ንድፈ ሀሳብ በመያዝ መስማት የተሳናቸውን ታዳጊዎች ማሰልጠን መጀመራቸው ነው፡፡ ኢንስትራክተር አሰፋ ለዚህ እንደመነሻ የነበራቸውን አጋጣሚ ሲያስረዱ፤« በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ስልጠና በሚሰጡበት ወቅት የታዘብኳቸው ነገሮች ወደዚህ እንድገባ ያደረጉኝ። ለተማሪዎች እጅ ኳስ ስልጠና በምሰጥበት ወቅት እዛ አካባቢ መስማት የተሳናቸው እኔ የምሰጠውን ስልጠና ቁጭ ብለው ይመለከቱ ነበር። በእነዚህ ታዳጊዎች ተግባር ውስጤ ተነሳሳ። ስልጠናውን ወደ መስጠት ከመሸጋገሬ በፊት ግን ከተማሪዎቹ ጋር ለመግባባት እንድችል የምልክት ቋንቋ መቻል አስፈላጊ ነበር። በመሆኑም ቋንቋውን ለሶስት ወራት ያህል ተማርኩ። በዚህ መሰረት በአዲስ አበባ መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች ከሚያስተምሩ ሶስት ትምህርት ቤቶች ጋር በመነጋገር እንዲሰለጥኑ ማድረግ ችያለሁ» ይላሉ፡፡ ኢንስትራክተር አሰፋ በእጅ ኳስ ስፖርት ውስጥ ያከናወኗቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ቢሆኑም እሳቸው ዛሬም በአዲስ ወኔ ለመስራት ያሰቧቸው ስራዎች መኖራቸውን ይናገራሉ። «ስፖርት ለእኔ ህይወቴ ነው፤ ልጅነቴን ፣ ወጣትነቴን ከእጅ ኳስ ስፖርት ሳልነጠል አሳልፌያለሁ። ዛሬም ነጭ ፀጉር አብቅዬም ከስፖርቱ መለየት አልሻም። ስፖርቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ አማራጭ ያልኳቸውን ተግባራት ለማከናወን አልተኛም» የሚል ጽኑ እምነት አላቸው። ስፖርቱን ለማሳደግ እንደ እርሳቸው ሁሉ በርካታ ባለሙያዎች ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸውና ለዚህ ደግሞ ስፖርቱን ከሚመሩት አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ የሚገባ መሆኑን ማስገንዘብ እንደሚፈልጉ ያብራራሉ፡፡አዲስ ዘመን መጋቢት 15/ 2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29023
723
2ስፖርት
የህዳሴው ዋንጫ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ15 ቀን ቆይታ ከ226 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
9
በኃይሉ አበራ አዲስ አበባ:- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተዘዋወረ የሚገኘው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ዋንጫ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ15 ቀን ቆይታው በደረሰባቸው ወረዳዎች 226 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ። በክፍለ ከተማው ቀሪ ሦስት ወረዳዎች ላይ ዋንጫው የሚዞር መሆኑም ታውቋል።በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚና የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተጫነ አዱኛ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከገባ ጊዜ ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 16 ቀን 2013 ድረስ ከ226 ሚሊዮን ብር በላይ አሰባስቧል።ቀደም ሲል በክፍለ ከተማ ደረጃ ለህዳሴ ግድቡ 94 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ በታቀደው ማሻሻያ ተደርጎ 212 ሚሊዮን ለማሰባሰብ እንደታቀደ የጠቆሙት አቶ ተጫነ፤ እስከ ታኅሣሥ 16 2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ በቦንድና በተለያየ ድጋፍ ከ226 ሚሊዮን ብር በላይ በማስገኘት ከእቅድ በላይ ማሰባሰብ መቻሉን ገልጸዋል። አቶ ተጫነ እንደሚሉት፤ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ግድቡ የኔ ነው በሚል መንፈስ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፤ በብሔር በፖለቲካም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ልዩነት ሳይፈጥር በሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ተሳትፎ እያደረገም ይገኛል። የኅብረተሰቡ ምላሽ ከወረዳ ወረዳ እየተሻሻለ እና ድጋፉም በዚያው ልክ እየጨመረ ነው የሄደው። በቀጣይም እስከ ታኅሣሥ 25 ድረስ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚያደርገው ቆይታው በሚቀሩ ሦስት ወረዳዎች ለህዳሴ ግድቡ ግንባታ ሀብት የማሰባሰብ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ለቦሌ ክፍለ ከተማ ርክክብ ይደረጋል። የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ ስድስት የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ናሆም መንግስቱ በበኩላቸው እንዳሉት፤ የወረዳ ስድስት ዋንጫውን ከወረዳ አምስት ሲቀበል ከቡልጋሪያ ጀምሮ የኅብረተሰቡን እንቅስቃሴ በማነቃቃት መቆየቱን አስታውሰዋል። በወረዳውም እስካሁን 26 ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉን ገልጸዋል። አቶ ናሆም እንደሚሉት፤ ኅብረተሰቡ ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት በፊት የህዳሴ ግድቡ የመሠረት ድንጋይ ሲጣል የነበረውን መነሳሳት፣ አንድነት እና አብሮነት በማደሱ ረገድ ዳግም ሕዝባዊ አንድነታችንን የመለሰ እና የሀገራችን ኩራት የሆነ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ነው ብለዋል። ይሄንንም የህዳሴ ግድብ ከዳር ለማድረስ በመሐል ተቋርጦ የነበረውን የሕዝብ ድጋፍ ወደ ነበረበት በመመለስ የኢትዮጵያን አንድነት፣ እድገትና ብልጽግና ሊያረጋግጥ እንደሚችል ይታመናልም ብለዋል። በመሆኑም የግድቡ ቀሪ ሥራዎች እንዲጠናቀቁ ኅብረተሰቡ ግንባታውን ከሚያከናውኑ ኃይሎች ጎን በመሆን ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል። የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የህዳሴ ግድብ ዋንጫውን ከትናንት በስቲያ ከወረዳ ስድስት ሲረከብ በነበረው ንቅናቄ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ማርሽ ባንድ፣ የኪነት ባለሙያዎች፣ ተማሪዎች፣ ባለሀብቶችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 የህዳሴ ግድብ ዋና አስተባባሪ አቶ ዳግም በልሁ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹትም፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ደረጃ ዋንጫው እስከሚገባ 11 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ እቅድ ተይዞ ሲሰራ ቆይቷል። እስከትናንት በስቲያም ዘጠኝ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉን ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38323
364
0ሀገር አቀፍ ዜና
«ሀገራችንን እየተፈታተናት ያለው ዓይነ ሥውርነት ሳይሆን የልብ ሥውርነት ነው” – ዶክተር ሙሉነሽ አበበ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
17
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- «ሀገራችንን እየተፈታተናት ያለው ዓይነ ሥውርነት ሳይሆን የልብ ሥውርነት ነው» ሲሉ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ ተናገሩ። «አካል ጉዳተኞችን አካታች፣ ምቹ እና ዘላቂ የተሻለ ዓለምን በድኅረ ኮቪድ 19 እንገንባ» በሚል መሪ ሐሳብ የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓለም ለ29ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ28ኛ ጊዜ በባሕር ዳር ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ እንደሚያመለክተው ዶክተር ሙሉነሽ በበዓሉ ሥነሥርዓት ወቅት እንደተናገሩት፤ አካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው ሙሉ አካል እንዳላቸው ሰዎች እኩል ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ መሥራት ይችላሉ። ለዚህም በርካታ ምስክሮች አሉ። ዋናው ጉዳይ ግን ሀገራችንን እየተፈታተናት ያለው ዓይነ ሥውርነት ሳይሆን የልብ ሥውርነት ነው። ልባቸው የተሠወሩት እኩያን ከሰው ስብእና ውጪ በመሆን ወገኖቻችንን በአሰቃቂ ሁኔታ እየጨፈጨፉ ይገኛሉ። በመሆኑም ከዚህ መጥፎ ተግባር ለመውጣት ሁሉም ቆም ብሎ ማሰብ ይጠበቅበታል።የፌዴራል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ለዓለማችን ታላላቅ አስተዋጽኦ አበርክተው ያለፉ አካል ጉዳተኞች ስማቸው ከመቃብር በላይ ሆኖ ሁሌም ሲዘከሩ ይኖራሉ። ለሀገራችንም እድገት እና ብልጽግና አስተዋጽኦ እያደረጉ የሚገኙ በርካታ አካል ጉዳተኞች አሉ። በመሆኑም አካል ጉዳተኞች ጠንክራችሁ ከሠራችሁ «ለሀገራችን ጠቃሚ እንጂ ተጠቃሚ አንሆንም» የሚለውን አስተሳሰብ መያዝ ይገባል። በሀገራችን የአካል ጉዳተኞች አስገዳጅ ሕግ አልነበረም፤ በዚህ ዓመት ግን የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ ይውላል፤ ይህም መንግሥት ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት መስጠቱን ያመላክታል።የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይነህ ጉጆ በበኩላቸው፣ የበዓሉ ተቀዳሚ ዓላማ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ያለውን የተዛባ አስተሳሰብ ግንዛቤ ፈጥሮ ማስተካከል መሆኑን ጠቁመው፣ ፌዴሬሽኑም የመንግሥት አካላት ስለአካል ጉዳተኞች ግንዛቤ ኖሯቸው በትምህርት፣ በጤና፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በፖለቲካ እና በማኅበራዊ ተግባራት አካትተው እንዲሠሩ የግንዛቤ ፈጠራ እየሠራ ነው።
https://www.press.et/Ama/?p=38342
251
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኤጀንሲው ከኦፓል የወጪ ንግድ 210 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት፤ ለ604ሺ በላይ ዜጎችም የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዷል
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
10
 ኤጀንሲው ከኦፓል የወጪ ንግድ 210 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት፤ ለ604ሺ በላይ ዜጎችም የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዷል  አስናቀ ፀጋዬአዲስ አበባ፡- ከኦፓል ማዕድን የወጪ ንግድ 210 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት በአስር ዓመቱ መሪ እቅድ ውስጥ አካቶ እየሰራ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ገለፀ። በዚሁ ዘርፍም ለ604 ሺ 210 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ማቀዱን ተናግሯል።፡የአማራ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይታየው ተስፋሁን ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ ኤጀንሲው ከኦፓል ማዕድን የወጪ ንግድ በአስር ዓመቱ መሪ አቅድ ውስጥ 210 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አቅዷል። ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃርም በኦፓል ማዕድን ማምረት ሥራ ለ604 ሺ 210 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አስቧል።እንደ ኃላፊው ገለፃ፤ ከውጪ ምንዛሬ ገቢ በተጨማሪ በዚሁ የአስር ዓመት መሪ እቅድ ውስጥ ኤጀሲው ከሮያሊቲና ከአገልግሎት ክፍያ 1 ቢሊዮን 117 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ወጥኗል። ይህንኑ እቅድ ለማሳካትም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ለሚገኙ የዘርፉ ፈፃሚዎች ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙና በቀጣይም ስልጠናው ለሌሎች በተከታታይ የሚሰጥ ይሆናል። በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ኤጀንሲው ሃያ የሚሆኑ የምርመራና የማምረት ፍቃድ ለአልሚዎች መስጠቱንም የጠቀሱት ኃላፊው፤ ኅብረተሰቡና ባለሀብቱም ጥቅሙን በመረዳት ወደዚህ የማዕድን ማምረት ሥራ እየተሳበ እንደሚገኝም አመልክተዋል። ይህም በቀጣይ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል። በ2013 ዓ.ም ብቻ ባጠቃላይ 44 ሺ 125 ለሚሆኑ ዜጎች በማዕድን ዘርፍ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ኤጀንሲው እቅድ መያዙንም አያይዘው የገለፁት ኃላፊው፤ ከውጭ ምንዛሬ አኳያ 18 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘትና ከሮያሊቲና አገልግሎት ክፍያም 100 ሚሊዮን ብር የሀገር ውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ ማሰቡን ጠቁመዋል፡፡
https://www.press.et/Ama/?p=38345
221
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢንስቲትዩቱ በአሥር ዓመቱ መጨረሻ ዓመታዊ የኤክስፖርት ገቢን 1ነጥብ2 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እየሰራ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
13
ውብሸት ሰንደቁአዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ ወደውጭ ከምትልካቸው የኬሚካልና ኢንዱስትሪ ግብዓት ዘርፍ ምርቶች በአስር ዓመቱ መጨረሻ ዓመታዊ የወጪ ንግድ ገቢዋን ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማድረስ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ሀላላ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ከኤክስፖርት በዓመት አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታስቧል። ይህንን ግብ ለማሳካትም በየዓመቱ በአማካኝ 120 ሚሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ገቢ አፈጻጸም ማስመዝገብ ይጠበቃል፡፡የኤክስፖርት ሥራ በዋናነት ሀገሪቷ እየተጠቀመች ካለችው በላይ ማምረትን ይጠይቃል ያሉት አቶ ሳሙኤል፤ በኦጋዴን አካባቢ የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝ በከፍተኛ ደረጃ ለኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ምርት ምቹ መሆኑ ለዕቅዱ ስኬት መልካም አጋጣሚዎችን እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ አስር ዓመታትም በዚህ ረገድ ከውጭ የሚገቡ ግብዓቶችን በአገር ውስጥ ከመሸፈን አልፎ በዕቅዱ ማጠናቀቂያ ዓመት ላይ የዘርፉ የኤክስፖርት ገቢ 1ነጥብ2 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በቀጣይ አሥር ዓመታት የመሠረታዊ ኬሚካል የማምረት ሥራ የሚሠሩ ኢንዱስትሪዎችን የማስፋት ሥራ በትኩረት እንደሚሠራና ይህም ያላለቀላቸው ግብዓቶች ከውጭ እያስመጡ ከመሥራት ይልቅ የሀገሪቱን የማዕድናትና የግብርና ግብዓቶችን መሠረት የሚያደርጉ ትላልቅና መሠረታዊ ኬሚካሎችን በሀገር ውስጥ ማምረት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ሥራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡ አቶ ሳሙኤል እንዳሉት፤ በስፋት ከፔትሮ ኬሚካል ውጤቶች የሚገኙ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ግብዓቶች የፕላስቲክ ወለል ንጣፎች፣ ፓይፖች እና የተለያዩ የቤቶች የማስዋቢያ ምርቶች በሀገር ውስጥ በስፋት እንዲመረቱ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡ በተጨማሪም የአፈር ማዳበሪያ የሀገር ውስጥ ፍጆታ ተሸፍኖ ኤክስፖርት ለማድረግ እየተሠራ ይገኛል፡፡ ፔትሮ ኬሚካል ጋር በተያያዘ የብዙ ምርት ግብዓት መሆን የሚችሉ ጥሬ ዕቃዎችን የማምረት ሥራም ትኩረት እንደተሰጠና ሌሎች የስፔሻሊቲ ኬሚካሎችንም ማምረት በመጀመር ሰፊ ኤክስፖርት አቅም እንዲኖራት ይሠራል፡፡ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ያለ ኢንዱስትሪ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ግብዓት አምራቾች በጥሩ ሁኔታ እያደጉ ያሉ ሲሆን፤ በሀገር ውስጥ የሲሚንቶ ምርትን መተካት እንደተቻለው ሁሉ ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፉ ግብዓት የሆኑትን የእምነበረድ፣ የግራናይት፣ የቴራዞ፣ የጂብሰም እና የፊኒሽንግ ቁሶችን የማምረት አቅም በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣ ነው፡፡ አብዛኛው ለነዚህ ምርቶች ግብዓት የሚውለው ነገር ከሀገር ውስጥ የሚገኝ ስለሆነ እነዚህን ግብዓቶች ተጠቅሞ በስፋት ለማምረት በትኩረት ይሠራል፡፡ይህንን ግብ ለማሳካት ደግሞ በየዓመቱ በአማካኝ 120 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከወጪ ንግድ ገቢ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደሚጠበቅ የታወቀ ሲሆን፤ ባለፉት አምሥት ዓመታትም 196 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው ምርት በኢንዱስትሪዎች መመረቱን እና ይህም በአማካይ ሲሰላ በየዓመቱ 39ነጥብ24 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ምርቶች መመረታቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2020
https://www.press.et/Ama/?p=38348
340
0ሀገር አቀፍ ዜና
ለስፖርት ማህበራት የሚላኩ አመራሮች በግለሰቦች ትውውቅ መሆን የለበትም
ስፖርት
March 27, 2020
11
የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ክልሎች ለሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት የሚላኩ አመራሮች በግለሰቦች ትውውቅና በተወሰኑ አካላት ፍላጎት ብቻ መሆን እንደሌለባቸው አስታወቀ። የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንደተናገሩት፤ ክልሎች ለሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት አመራርነት የሚልኳቸውን ተወካዮች በተወሰኑ አካላት ፍላጎትና በግለሰቦች ትውውቅ መሆን የለበትም። በመሆኑም ለአመራርነት የሚላኩ ተወካዮች የተወከሉበትን ስፖርት ወደፊት ሊያሻግሩ ይችላሉ የሚለው በሚገባ ተተችቶ አሳታፊ በሆነ መልኩ ሊልኩ ይገባል ብለዋል። ለሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት የሚላኩ አመራሮች ምክንያታዊ አለመሆኑን ተከትሎ የሴቶችን በስፖርት ማህበራት የሴቶች ተሳትፎ ውስን እንዲሆን አድርጎታል። በሀገር አቀፍ ደረጃ 30 የስፖርት ማህበራት የሚገኙ ሲሆን በዚህ ውስጥ የሴቶች የአመራርነት ድርሻ ከ10 በመቶ አይበልጡም። ክልሎች በአብዛኛው የሚልኳቸው ዕጩ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ወንዶች በመሆናቸው ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል። ሴቶች በተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ በየደረጃው የሚገኙ እና የአመራርነት ዕድሉን ያገኙ ሴቶች ማሳየት ችለዋል። በስፖርቱ ዘርፍ ግን ክፍተት የሚታይ መሆኑን የገለጹት አቶ ኤልያስ፤ «ኮሚሽኑ በቀጣይ በትኩረት ከሚሰራቸው ሥራዎች አንዱ ሴቶች በስፖርት አደረጃጀቶች ውስጥ በበቂ ሁኔታ በአመራርነት እንዲሳተፉ ማድረግ ላይ ይሆናል። ለዚህ ደግሞ ከክልሎች ጋር ከመነጋገር ባሻገር በመመሪያ እና በአሠራር የሚደገፍ ይሆናል» ብለዋል። የሴቶች የአመራርነት ተሳትፎ ቢያንስ 30 በመቶ ሊሆን እንደሚገባ የኦሊምፒክ ቻርተርን ጨምሮ የዓለም አቀፍ የስፖርት ማህበራት ሕጎች ያስቀምጣሉ። በኮሚሽኑ የስፖርት ማህበራት ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ የአወጣው መመሪያ አንቀፅ 31 ንዑስ አንቀፅ 7 ይህን ሀሳብ የሚያጠናክር መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። አዲስ ዘመን መጋቢት 18/2012 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=29266
199
2ስፖርት
“ በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያትም እንኳ፣ ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን የዜጎችን እና የተቋማትን የቅርብ ተሳትፎ የሚፈልጉ በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 29, 2020
5
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያትም እንኳ፣ ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን የዜጎችን እና የተቋማትን የቅርብ ተሳትፎ የሚፈልጉ በርካታ ርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳስታወቀቁት፤ የአስር ዓመቱ ብሔራዊ የልማት እቅድ ፍኖተ ብልጽግና ዘላቂ ሰላምን በሚያመጣ የልማት ጉዞን መሰረት ያደረገ ነው::ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን ደግሞ የዜጎችን እና የተቋማትን የቅርብ ተሳትፎ የሚፈልጉ በርካታ ርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ:: “ልማት ዘላቂ ሰላምን ያመጣል። የ10 ዓመት ብሔራዊ የልማት ዕቅድ ፍኖተ ብልጽግና ይህንን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፤” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዕቅዱ ሰላምን እና የሕግ የበላይነትን ወሳኝ ግቦች አድርጎ ማስቀመጡ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል:: አያይዘውም፣ “በእነዚህ ፈታኝ ጊዜያትም እንኳ፣ ዘላቂ ሰላም እውን እንዲሆን የዜጎችን እና የተቋማትን የቅርብ ተሳትፎ የሚፈልጉ በርካታ ርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ፤” ሲሉ ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38376
119
0ሀገር አቀፍ ዜና
‹‹ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆን እንደ እኔ ያሉ የፖርቲ አባል ያልሆኑ ግለሰቦች የተካተቱበት ስለሆነ አሁን ያለው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አቃፊ ነው›› – ዶክተር አሰፋ በቀለ የትግራይ ክልል መንገድና ትራንስፖርት አስተባባሪ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 29, 2020
30
ክፍለዮሐንስ አንበርብር አዲስ አበባ፡- በትግራይ ክልል አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊና የተለያዩ የፖለቲካ አባላት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ያሳተፈ መሆኑን የትግራይ ክልል በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር አሰፋ በቀለ ተናገሩ::ከአማራ ክልልና የፀጥታ አካላት ጋር በመነጋገር ከመቐለ አዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት መጀመሩም ተገልጿል::የትግራይ ክልል በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር አሰፋ በቀለ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በትግራይ ክልል አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊና የተለያዩ ፖለቲካዊ እሳቤ ያዙ ሰዎችን ያቀፈ ነው::በዚህም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዲሁም ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ ሆነው ህዝብን ለማገልገል ፍላጎት ያላቸውን አካላት ጭምር በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ውስጥ አካትተዋል:: ‹‹ቀደም ሲል የነበረው አሰራር ብዙ ጉድለት ነበረበት::አሁን ባለው አስዳደር ግን በፖለቲካ አመለካከት   ሳይገደብ ህዝብ ማገልገል ተችሏል፤” ያሉት ዶክተር አሰፋ፤ አሁን ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር በጣም አቃፊ በመሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ አባላት በጊዜያዊ አስተዳደር ታቅፈው እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል::“እኔን ጨምሮ የፓርቲ አባል ያልሆንን ግለሰቦች ህዝቡን በማገልገል ላይ እንገኛለን›› ብለዋል:: “ህዝብ ለማገልገል የፖለቲካ ፓርቲ የበላይ መሆን አይጠበቅም” ያሉት ዶክተር አሰፋ፤ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በጣም የተሻለ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን እና የትግራይ ህዝብ ያጋጠመው ችግም ከየትኛው ፓርቲ በላይ መሆኑን ገልጸዋል:: በዚህ ወቅት ደግሞ ህዝብን ማገልገል ኩራት ነው ሲሉም ተናግረዋል::በዴሞክራሲ አኳያም በጣም የተሻለና አቀፊነት ስሜት ያለው እንደሆነ እና ሰዎች በአረዳዳቸው፣ የፖለቲካ ፓርቲነታቸው ሳይገለሉ በጊዜያዊ አስተዳደር መታቀፋቸው አበረታች እንደሆነ ጠቁመዋል:: እንደ ዶክተር አሰፋ ገለጻ፤ ቀደም ሲል ህዝቡ ከቤት ለመውጣት ስጋት የነበረውና ጦርነት ተመልሶ ይቀሰቀሳል በሚል እሳቤ እንቅስቃሴ ገታ ብሎ ነበር::ይሁንና የሀገር መከላከያ ሰራዊት መቐለ ከገባ በኋላ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በአግባቡ ተጀምሯል::በአሁኑ ወቅትም ታክሲዎች በተሰጣቸው የጉዞ መስርመር አገልግሎት እየሰጡ ነው::ከታሪፍ አኳያ ማጋነን እና የተሰጠውን ቦታ አለመጠቀም ይስተዋል እንደነበርና ፌዴራል ፖሊስ፣ የትራፊክ ፖሊስና የክልሉ ፖሊስ ጋር የተቀናጀ ስራ በመጀመሩ በጣም የተሻሻለ ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል:: በአሁኑ ወቅት ደግሞ በዋናነት የማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ሲሆን፤ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትና የፌዴራል መንግስት መዋቅር ጋር በቅርበት እየሰሩም ነው::የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በተመለከተም ከፌዴራል ትራንስፖርት ጋር በመደዋወልና መረጃ በመለዋወጥ እየተሰራ ሲሆን አስፈላጊ በሆነ ቦታ እና ሁኔታ ሁሉ ድጋፍ ለማድረግም ቃል ገብተውላቸዋል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ ከአማራ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመነጋገርም ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ትራንስፖርት መጀመሩን የገለጹት ዶክተር አሰፋ፤ በተጨማሪም ከመቀሌ ወደ ተለያዩ የትግራይ አካባቢዎችም እንቅስቃሴ መጀመሩን አብራርተዋል:: የሀገር መከላከያ ሰራዊትም ፀጥታውን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝም ተናግረዋል:: በአሁኑ ወቅት ከውጭ አገር ጭምር ለእርሳቸው የሚደውሉላቸው ሰዎች መኖራቸውን የገለፁት ዶክተር አሰፋ፤ የሚደውሉላቸው አብዛኞቹ ሰዎችም ጊዜያዊ አስተዳደር የሚደግፉ መሆናቸውን ነው የገለጹት::ህዝቡን ለመታደግና ወደነበረበት ሠላም ለመመለስም ዳያስፖራው ከጎናችን እንደሆኑ እየነገሩን ነው ሲሉም አስረድተዋል:: ዶክተር አሰፋ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሙሉ ለሙሉ ካቢኔ አቋቁሞ ሥራ ያልጀመረ ሲሆን የቀሩ ካቢኔዎች ሲሟሉ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ የሚገባ መሆኑን በመጠቆም፤ በአሁኑ ወቅት የዳያስፖራና ወጣት ምሁራን ተጋሩዎች ክልሉን መልሶ በማደራጀትና በመደገፍ ረገድ ሚናቸው የጎላ ስለሆነ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋልአዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20 /2013
https://www.press.et/Ama/?p=38379
411
0ሀገር አቀፍ ዜና
በከተማው የክለቦች ቻምፒዮና ክብረወሰን ተሻሻለ
ስፖርት
February 26, 2020
27
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓመታዊው ፔፕሲ የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለ37ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል።ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን የያዘው ውድድሩ በተለያዩ ርቀቶች የሩጫና ሜዳ ተግባራት አትሌቶችን በማፎካከር በርካታ ክብረወሰኖች እየተሻሻሉበት ይገኛል። በውድድሩ ሁለተኛ ቀን ውሎ ትናንት በተካሄደው የሴቶች አንደኛ ዲቪዚዮን አስር ሺ ሜትር ውድድር ክብረወሰን ተሰብሯል።በኢትዮጵያ ቻምፒዮና በአትሌት ለተሰንበት ግደይ 32፡10፡90 ተይዞ የነበረው የርቀቱ የኢትዮጵያ ክብረወሰን ዘንድሮ በአትሌት ዘይነባ ይመር በስድስት ሰከንድ ሊሻሻል ችሏል። በቻምፒዮናው ላይ በአንደኛ ዲቪዚዮን ከታቀፉ አምስት ክለቦች የተሳተፉ ሲሆን በሁለተኛ ዲቪዚዮን ከታቀፉ ሃያ ክለቦች የተውጣጡ በአጠቃላይ አንድ ሺ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል።ውድድሩ ክለቦች የአትሌቶቻቸውን አቅም ከመለካት ባሻገር በሃገር አቀፉ የአትሌቲክስ ቻምፒዮና ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችላቸውን ምዘና የሚያደርጉበት እንዲሁም ስልጠናቸውን በመገምገም ራሳቸውን የሚያጎለብቱበት መድረክም መሆኑ ተነግሯል። ትናንት በተካሄደው የሁለተኛ ቀን ውሎ የተለያዩ የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድሮች ተካሂደዋል።በሁለተኛ ዲቪዚዮን የ100 ሜትር ሩጫ በሁለቱም ፆታ የፍፃሜ ውድድሮች የተከናወነ ሲሆን፤ በሴቶች ትዝታ ደጋ ከአራዳ ክፍለ ከተማ እንዲሁም ሜሮን ተመስገን እና ፍቅርተ ሽፈራው ከዳሎል ክለብ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።በወንዶች በኩል ኤርሚያስ ሻጠው ከኮልፌ ቀራኔዮ ክፍለ ከተማ አንደኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዷል።የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲው አትሌት ሲሳይ አየሁ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ክለብ አትሌቱ ዘገየ ለገሰ ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል።በተመሳሳይ በ10ሺ ሜትር በወንዶችና ሴቶች ውድድር ፍጻሜያቸውን ሲያገኙ፤ በ1ሺ500 ሜትር፣ በአሎሎ ውርወራ እና በከፍታ ዝላይ አሸናፊ የሆኑ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ነገ ቀጥሎ በሚውለው ቻምፒዮና የተለያዩ የፍጻሜ ግማሽ ፍጻሜና የማጣሪያ ውድድሮች የሚካሄዱም ይሆናል።በ5ኪሎ ሜትር በሴቶች እንዲሁም በ10ኪሎ ሜትር የወንዶች እርምጃ ውድድሮች ፍጻሜያቸውን ከሚያገኙት መካከል ይጠቀሳል።በሁለተኛ ዲቪዚዮን የሱሉዝ ዝላይ በሴቶች የማጣሪያ፣ በዲስከስ ውርወራ ወንዶች ግማሽ ፍጻሜ፣ በሁለቱም ጾታ የ400 ሜትር ፍጻሜ፣ 5ሺ ሜትር ሴት ግማሽ ፍጻሜ፣ 100ሜትር መሰናክል የሴቶች ግማሽ ፍጻሜ እና በ110ሜትር መሰናክል ሴት ግማሽ ፍጻሜ ይከናወናሉ።በአንደኛ ዲቪዚዮን ደግሞ በ100 ሜትር ሴትና ወንድ ግማሽ ፍጽሜ እንዲሁም በ110 ሜትር መሰናክል የወንዶች ግማሽ ፍጻሜ ውድድሮች በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሰረት ይካሄዳሉ። ይህ ዓመታዊ ቻምፒዮና በ1975 ዓ.ም መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ በፌዴሬሽኑ የተመዘገቡ ብዛት ያላቸው ክለቦች ሲሳተፉበት መቆየታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።ከ1991ዓ.ም ጀምሮም ፌዴሬሽኑ አቅሙን በማጎልበት ከሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር ውድድሩ ለዓመታት በቋሚነት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ፍጻሜያቸውን ባያገኙ ውድድሮች በቀዳሚነት ለሚያጠናቅቁ አትሌቶችም የወርቅ፣ ብርና ነሃስ ሜዳሊያ የሚበረከትላቸው ይሆናል።ውድድሩ ከትናንት በስቲያ የተጀመረ ሲሆን በመጪው እሁድ 22/2012 ዓ.ም የሚጠናቀቅም ይሆናል። አዲስ ዘመን ረቡዕ የካቲት 18/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=27938
347
2ስፖርት
ኢትዮጵያዊው ብስክሌተኛ በቱር ደ ሩዋንዳ አሸነፈ
ስፖርት
February 26, 2020
35
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓመታዊው ፔፕሲ የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለ37ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል።ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን የያዘው ውድድሩ በተለያዩ ርቀቶች የሩጫና ሜዳ ተግባራት አትሌቶችን በማፎካከር በርካታ ክብረወሰኖች እየተሻሻሉበት ይገኛል። በውድድሩ ሁለተኛ ቀን ውሎ ትናንት በተካሄደው የሴቶች አንደኛ ዲቪዚዮን አስር ሺ ሜትር ውድድር ክብረወሰን ተሰብሯል።በኢትዮጵያ ቻምፒዮና በአትሌት ለተሰንበት ግደይ 32፡10፡90 ተይዞ የነበረው የርቀቱ የኢትዮጵያ ክብረወሰን ዘንድሮ በአትሌት ዘይነባ ይመር በስድስት ሰከንድ ሊሻሻል ችሏል። በቻምፒዮናው ላይ በአንደኛ ዲቪዚዮን ከታቀፉ አምስት ክለቦች የተሳተፉ ሲሆን በሁለተኛ ዲቪዚዮን ከታቀፉ ሃያ ክለቦች የተውጣጡ በአጠቃላይ አንድ ሺ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል።ውድድሩ ክለቦች የአትሌቶቻቸውን አቅም ከመለካት ባሻገር በሃገር አቀፉ የአትሌቲክስ ቻምፒዮና ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችላቸውን ምዘና የሚያደርጉበት እንዲሁም ስልጠናቸውን በመገምገም ራሳቸውን የሚያጎለብቱበት መድረክም መሆኑ ተነግሯል። ትናንት በተካሄደው የሁለተኛ ቀን ውሎ የተለያዩ የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድሮች ተካሂደዋል።በሁለተኛ ዲቪዚዮን የ100 ሜትር ሩጫ በሁለቱም ፆታ የፍፃሜ ውድድሮች የተከናወነ ሲሆን፤ በሴቶች ትዝታ ደጋ ከአራዳ ክፍለ ከተማ እንዲሁም ሜሮን ተመስገን እና ፍቅርተ ሽፈራው ከዳሎል ክለብ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።በወንዶች በኩል ኤርሚያስ ሻጠው ከኮልፌ ቀራኔዮ ክፍለ ከተማ አንደኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዷል።የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲው አትሌት ሲሳይ አየሁ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ክለብ አትሌቱ ዘገየ ለገሰ ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል።በተመሳሳይ በ10ሺ ሜትር በወንዶችና ሴቶች ውድድር ፍጻሜያቸውን ሲያገኙ፤ በ1ሺ500 ሜትር፣ በአሎሎ ውርወራ እና በከፍታ ዝላይ አሸናፊ የሆኑ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ነገ ቀጥሎ በሚውለው ቻምፒዮና የተለያዩ የፍጻሜ ግማሽ ፍጻሜና የማጣሪያ ውድድሮች የሚካሄዱም ይሆናል።በ5ኪሎ ሜትር በሴቶች እንዲሁም በ10ኪሎ ሜትር የወንዶች እርምጃ ውድድሮች ፍጻሜያቸውን ከሚያገኙት መካከል ይጠቀሳል።በሁለተኛ ዲቪዚዮን የሱሉዝ ዝላይ በሴቶች የማጣሪያ፣ በዲስከስ ውርወራ ወንዶች ግማሽ ፍጻሜ፣ በሁለቱም ጾታ የ400 ሜትር ፍጻሜ፣ 5ሺ ሜትር ሴት ግማሽ ፍጻሜ፣ 100ሜትር መሰናክል የሴቶች ግማሽ ፍጻሜ እና በ110ሜትር መሰናክል ሴት ግማሽ ፍጻሜ ይከናወናሉ።በአንደኛ ዲቪዚዮን ደግሞ በ100 ሜትር ሴትና ወንድ ግማሽ ፍጽሜ እንዲሁም በ110 ሜትር መሰናክል የወንዶች ግማሽ ፍጻሜ ውድድሮች በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሰረት ይካሄዳሉ። ይህ ዓመታዊ ቻምፒዮና በ1975 ዓ.ም መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ በፌዴሬሽኑ የተመዘገቡ ብዛት ያላቸው ክለቦች ሲሳተፉበት መቆየታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።ከ1991ዓ.ም ጀምሮም ፌዴሬሽኑ አቅሙን በማጎልበት ከሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር ውድድሩ ለዓመታት በቋሚነት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ፍጻሜያቸውን ባያገኙ ውድድሮች በቀዳሚነት ለሚያጠናቅቁ አትሌቶችም የወርቅ፣ ብርና ነሃስ ሜዳሊያ የሚበረከትላቸው ይሆናል።ውድድሩ ከትናንት በስቲያ የተጀመረ ሲሆን በመጪው እሁድ 22/2012 ዓ.ም የሚጠናቀቅም ይሆናል። በቻምፒዮናው ከ1ሺ በላይ አትሌቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፣ ኢትዮጵያዊው ብስክሌተኛ በቱር ደ ሩዋንዳ አሸነፈ በሩዋንዳ በተካሄደ የ‹‹ቱር ደ ሩዋንዳ›› የብስክሌት ውድድር ኢትዮጵያዊው ሙሉ ኃይለሚካኤል አሸነፈ። ብስክሌተኛው 120 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በሸፈነውና ከዋና ከተማዋ ኪጋሊ ወደ ሁዬ ዲስትሪሲ የነበረውን ርቀት ለመሸፈንም 3ሰዓት ከ3ደቂቃ ከ21 ሰከንድ የሆነ ጊዜ እንደፈጀበት ዘ ኒው ታይምስ ዘግቧል።ለ12ኛ ጊዜ የሚካሄደው ውድድሩ እስከ መጪው እሁድ በተለያዩ ፉክክሮች የሚቀጥል ይሆናል። አትሌቶች ለቻምፒዮናው አልፈዋል ሰባት ዙሮች ያሉት የዓለም የቤት ውስጥ የዙር ውድድር የተጠናቀቀ ሲሆን ለዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና በቀጥታ ማለፍ የቻሉት 11 አትሌቶችም ተለይተዋል።ከእነዚህ አትሌቶች መካከልም የ3ሺ ሜትር ተወዳዳሪው ጌትነት ዋለ በወንዶች እንዲሁም በሴቶች ጉዳፍ ጸጋዬ 1ሺ500 ሜትር ማለፋቸውን ያረጋገጡ አትሌቶች ሆነዋል።ይሁን እንጂ የቻምፒዮናዋ አዘጋጅ የሆነችው ቻይና ከኮረና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ውድድሩ ወደ ሚቀጥለው ዓመት (እአአ 2021) መሸጋገሩ የሚታወስ ነው።በዙር ውድድሩ ቀዳሚ በመሆን ያጠናቀቁት አትሌቶች 20ሺ የአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ መሆናቸውንም የዓለም አትሌቲክስ በድረ ገጹ አስነብቧል። ሊጉ ከሁለት ሳምንት በኋላ ይመለሳል የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የካቲት 29 እና 30/2012 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑ ታውቋል።የግማሽ ዓመት ውድድር ከትናንት በስቲያ በቅዱስ ጊዮርጊስና አዳማ ከተማ መካከል በተደረገ ጨዋታ መጠናቀቁ ይታወቃል።ይህንንም ተከትሎ ሊጉን የሚመራው አቢይ ኮሚቴ ከሁለት ሳምንት እረፍት በኃላ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲጀመር ውሳኔ ላይ መደረሱ ተረጋግጧል። የወርልድ ቴኳንዶ ቡድኑ አቀባበል ሰሞኑን ሞሮኮ ላይ ሲካሄድ በነበረው የወርልድ ቴኳንዶ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ላይ ኢትዮጵያን የወከለው ቡድን ትናት አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፣የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፣ የአዲስ አበባ የወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች ማህበር እና የስፖርቱ ቤተሰብ ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርስ ልዩ አቀባበል አድርጓል። ሰለሞን ቱፋ በማጣሪያ ውድድሩ በወርልድ ቴኳንዶ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለመሳተፍ የሚያስችለውን ውጤት ማስመዝገቡ ይታወሳል። ለሴት መምህራን ስልጠና ሊሰጥ ነው ለሴት የስፖርት ሳይንስ መምህራን የአሰልጣኝነት ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የ ‹‹ዲ ላይሰንስ›› አሰልጣኞች ስልጠና ለተመረጡ ሃገራት የሚሰጥም ይሆናል። ከሁሉም ክልሎች ለተወጣጡ 30 መምህራን የሚሰጠው ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 25/2012 ዓ.ም የሚቆይም ነው። ስልጠናው የሴቶች እግር ኳስ ልማትን ለማሳደግና ብቃታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችን ለማፍራት የሚጠቅምም ይሆናል። በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈው ስልጠናው በኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ኢንስትራክተር ሰላማዊት ዘርዓይ እና በተጋባዦች የሚካሄድ መሆኑንም የፌዴሬሽኑ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት በመረጃ ጠቁሟል። ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኃላም እድሜያቸው 15 ዓመት በታች በሆኑ 10 የሴት ተማሪዎች ቡድን መካከል ውድድር ይካሄዳል። ቀነኒሳ በዓለም የግማሽ ማራቶን የሃገር አቋራጭ ንጉሱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዓለም የግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና ለአሸናፊነት ይጠበቃል። ከቀናት በኃላ በፖላንድ በሚካሄደው ቻምፒዮና በማራቶን የሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ባለቤት የሆነው አትሌት ተሳታፊ እንደሚሆን የቢቢሲ ዘግቧል። አትሌቱ በውድድሩ ከእንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ ፈታኝ ፉክክር ይገጥመዋል በሚል ቢጠበቅም፤ አትሌቱ በጉዳት ምክንያት የማይሳተፍ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የአሸናፊነት ግምቱን አግኝቷል። አዲስ ዘመን ረቡዕ የካቲት 18/2012
https://www.press.et/Ama/?p=27942
747
2ስፖርት
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ዓለም አቀፍ ኃላፊነቷን እየተወጣች መሆኗ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 27, 2020
19
 አዲሱ ገረመውአዳማ፡- ኢትዮጵያ የደን ሀብት መመናመንና የአየር ብረት ለውጥ እያስከተሉ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች ከግምት በማስገባት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ አገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በመዘርጋት ዓለም አቀፍ ኃላፊነቷን እየተወጣች መሆኗ ተገለጸ። በዘንድሮ ዓመትም ስድስት ቢሊዮን ችግኝ ለማፍላት መታቀዱም ተነግሯል።የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን እስካሁን የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤና ጥበቃ ሥራዎችን እንዲሁም የ2013 በጀት ዓመት የችግኝ ተከላን የተመለከተ የውይይት መድረክ ትናንት በአዳማ ከተማ አካሂዷል። በውይይት መድረኩ የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ እንዳሉት፤ የደን ሀብት መመናመንና የአየር ብረት ለውጥ እያስከተሉ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች ከግምት በማስገባት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ አገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በመዘርጋት የአረንጓዴ ልማት ሥራን በማጠናከር እየተሰራ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ኃላፊነቷን እየተወጣች መሆኑን ያሳያል። የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር እንደ ድርቅና ጎርፍ የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል ይረዳል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ዘንድሮ የሚከናወነው የችግኝ ተከላ ከኢትዮጵያ አልፎ ጎረቤት አገራትንም ተደራሽ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ስድስት ቢሊዮን ችግኞችን ለማፍላት እንደታቀደና ከነዚህ ውስጥም አንድ ቢሊዮኑ ለጎረቤት አገራት እንደሚውሉ ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካና ታዳጊ አገራት ቃል ሆና በተለያዩ መድረኮች ስታነሳ እንደቆየች ሁሉ፤ ችግሩ በመድረክ ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ በተጨባጭ በአገር ቤት የሚሰራውን ሥራ በጎረቤት አገራትም ተግባራዊ በማድረግ ሚናዋን እንደምትወጣ አስታውቀዋል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ አረንጓዴ አሻራ በአገሪቱ የቆየውን የደን ሀብት ጥበቃ በማሻሻል ሌሎች የደን ሀብት ልማትን ለማሳደግና በእውቀት ለመምራት ያስችላል። በዚህም መንግሥት ኅብረተሰቡን በሰፊው በማሳተፍ ብሔራዊ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብርን ተግባራዊ ማድረግ ችሏል። በዚህም ባለፉት ሁለት የክረምት ወራት ብቻ ከ9 ቢሊዮን በላይ የደን የጥምር ግብርናና የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን መትከል ተችሏል። በተለይም ባሳለፍነው ዓመት የኮቪድ 19 ያስከተለውን ኢ-ተገማች ተጽዕኖ በመቋቋም ሥራው ተሳክቷል። ይህም ራስን ከቫይረሱ በመከላከል ማምረት እንደሚቻል ተሞክሮ የተወሰደበት አዲስ ሀሳብና ተግባር ሆኗል።ኮሚሽነሩ አክለውም፤ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመቋቋምና ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚያስችል የልማት ስልት ቀይሳ እየሰራች ትገኛለች ብለዋል። ይህንን በማድረግና አገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የደን ልማት ያለው ጠቀሜታ ከግምት በማስገባት ተጨባጭ ስኬት ማምጣት በሚያስችል መልኩ ወደ ሥራ መገባቱንም ጠቁመዋል። ደኖችን በተገቢው መንገድ ማልማት ለማህበራዊ ብልጽግና የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ውጤቶችን እንደ ተሞክሮ በመውሰድ እንዲሁም የቀጣይ ጊዜ ሥራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል። ኮሚሽነሩ፤ እ.አ.አ በ2018፣ 15 ነጥብ 5 በመቶ ላይ የነበረውን የደን ሽፋን እ.አ.አ በ2030 ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ የተያዘውን ግብ ሊያሳካ በሚችል ሁኔታ ስትራቴጂካዊ ሥራዎች እንደተሰሩ ገልጸው፤ በአንድ ሰሞን ዘመቻ ተክሎ ገለል ማለት ብቻ ሳይሆን ለጽድቀቱም መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል። በእስካሁኑ ክንውን አበረታችና አዎንታዊ ሁኔታዎች ቢታዩም አሁንም መሻገር የሚገባቸው በርከታ ክፍተቶች እንደተስተዋሉ በማንሳት፤ ሁሉም ለችግኞች ተከላ ያሳየውን ርብርብ ለእንክብካቤና ጥበቃ ተግባር መነሳሳት እንዳለበት አስገንዝበዋል። በምክክር መድረኩ ሥራውን በአቢይና በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ የሚመሩና የሚያስተባብሩ፣ ከፌዴራልና ከክልል መንግሥታት የዘርፍ መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብራት ትምህርት የተወሰደባቸውና በቀጣይ በተሻለ ለመሥራት የሚያግዙ መሆናቸው ተመላክቷል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38230
418
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ሰላም በመጠቀም በንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጤታማ ሥራዎችን መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 27, 2020
11
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ሰላም በመጠቀም በንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጤታማ ሥራዎችን መስራት እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ አሳስበዋል። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ከታኅሣሥ 17 እስከ 21 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆይ የኢንዱስትሪ፣ የግብርና እና የተፈጥሮ ሀብት ውጤቶች ኤግዚቢሽን ተጀምሯል። ኢቢሲ እንደዘገበው፤ በክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በተዘጋጀው በዚሁ ኤግዚቢሽን ላይ የተገኙት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በሶማሌ ክልል የነበረው የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት ተወግዶ በሰላምና በፀጥታ ተጠቃሽ ክልል መፍጠር በመቻሉ የክልሉ የለውጥ አመራር ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።«ዓለማችንን ለሥልጣኔ ካበቋት ተግባራቶች መካከል አንዱ ንግድ ነው» ያሉት አፈ ጉባኤው፤ የአውሮፓ የኢንዱስትሪ አብዮትም ለዚህ ተጠቃሽ መሆኑን ገልፀዋል። ሰላም የንግዱን እና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴውን ለማገዝ ቁልፍ ሚናን እንደሚጫወት በመግለጽም፤ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ባለሀብቶች በሶማሌ ክልል ኢንቨስት ቢያደርጉ አዋጭ መሆኑን ተናግረዋል። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፣ ከዚህ ቀደም የነበረው የሰላም እጦት በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የንግድና የኢንዱስትሪ አቅም በሚፈለገው ደረጃ ለመጠቀም አዳጋች አድርጎት እንደነበር ጠቅሰው፤ የክልሉ መንግሥት አሁን ላይ የተጀመረውን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ከዳር እንዲደርስ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ባለሀብቶችን ለመሳብ በትኩረት እየሰራእንደሚገኝ አስታውቀዋል። የሶማሌ ክልል ሰፊ ያልታረሰ መሬት፣ የገፀ ምድርና የከርሰ ምድር ሀብት፣ የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ባለቤት መሆኑን የገለጹት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው፤ ክልሉም እንዲህ ዓይነት ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀትና በመሳተፍ የክልሉን የኢንዱስትሪና የንግድ ዘርፍ ማሳደግ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ፣ ይህም ገቢ ምርትን ለመተካትና ወጪ ንግድን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተናግረዋል። የሶማሌ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ኃላፊ በሽር ሻፊ በበኩላቸው፤ የተዘጋጀው የኢንዱስትሪ፣ የግብርና እና የተፈጥሮ ሀብት ውጤቶች ኤግዚቢሽን የክልሉን እምቅ የኢንዱስትሪ እና የተፈጥሮ ሀብቶችን ለማስተዋወቅ እንደሚረዳ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38228
236
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሚኒስቴሩ በፀጥታ ችግር ትምህርት ያልተጀመረባቸው አካባቢዎች ላይ ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 27, 2020
16
ዋቅሹም ፍቃዱአዲስ አበባ፡- በኮሮና ወረርሽኝ ዙሪያ ተገቢ ጥንቃቄ እየተደረገ በአብዛኛው አካባቢዎች ትምህርት ቢጀመርም በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ያልጀመሩ አካባቢዎችም ትምህርት እንዲጀምሩ እየሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፤ በአሁኑ ሰዓት ሁሉም አካባቢ በሚባል ደረጃ ትምህርት ተጀምሯል። ነገር ግን ከወቅታዊ የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልልና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ትምህርት አልተጀመረም። በመሆኑም በእነዚህ አካባቢዎች ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።በዚህ ረገድ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በተለይ በትግራይ ክልል ትምህርት ለመጀመር ጁንታው ከተመደሰሰ በኋላ ነባራዊ ሁኔታን የሚገመግም ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ አካባቢው ልኳል። ሆኖም ግን ትምህርት ቤቶች በጁንታው ኃይል በመውደማቸው ምክንያት የመጠገን ሥራ ጊዜ መውሰዱ አይቀርም። በመተከል ላይም ተመሳሳይ ሥራ የሚሰራ ይሆናል።እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ፤ በትምህርት ቤቶች የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል ለ25 ሚሊዮን ተማሪዎች 50 ሚሊዮን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስኮች ለማቅረብ ታቅዶ ነበር። እነዚህን ማስኮችም በሁለት ሳምንት ውስጥ አምርተን አናቀርባለን ብለው ስምምነት የፈረሙት የአዳማና የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግን በሁለት ሳምንት ቀርቶ በሁለት ወር ውስጥም ማቅረብ አልቻሉም። ይህ ደግሞ ሚኒስቴሩን ለትችት ዳርጎት ነበር።የመማሪያ ክፍሎችን በተመለከተም፣ አምና በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ቤቶች እንደ ተዘጉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ አንድ መፍትሔ አፈላላጊ ተዋቅሮ ነበር። ይህ የቴክኒክና የሁኔታ አጥኚ ኮሚቴ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች እንዲሰሩ ወሰነ። በዚሁ መሰረት ደረጃቸውን ጠብቀው 700ሺህ የመማሪያ ክፍሎች ተገንብተዋል።ከእነዚህ ውስጥም 34ሺህ የሚሆኑ በኦሮሚያ የተገነቡ ናቸው።በሌላ በኩል፤ ከዚህ በፊት የግል ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት የሚፈለገው ደረጃ የሚቆጣጠር አካል ባለመኖሩ ከአገሪቱ ሥርዓተ ትምህርት ባፈነገጠ መልኩ የመማር ማስተማር ሂደት ሲያከናወኑ መቆየታቸውን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ አሁን ግን ጉዳዩን የሚከታተል አካል ከመሰየሙም በተጨማሪ ቀጣዩ ዓመት አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ሥራ ላይ ስለሚውል በአጠቃላይ በግልም ይሁን በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በመማር ማስተማር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች እንደሚቀረፉ ተናግረዋል።የ12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መለቀቂያ ፈተናን በተመለከተም በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ። ይህንን ለማሳካት ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል። ለ270 ቴክኒሻኖችም ስልጠና ተሰጥተዋል። ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል፤ ሁለት ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል። በትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ወደ አገር ገብተው ለፈተናው የሚውሉ ሲሆን፤ ፈተናውም ጥር 30 የሚጠናቀቅ ይሆናል።የመምህራን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ጋር ተያይዘው ከመምህራን የሚነሱ ቅሬታዎችን በተመለከተም የሥራ ግምገማና ደረጃ የተደረገው ደመወዝ ለመጨመር ሳይሆን ሥራና ሠራተኛን ለማገናኘት ታስቦ እንደነበር የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ትምህርት ሚኒስቴርም ኃላፊነቱን ወስዶ መምህራን ተጠቃሚ በሚያደርግ መምህራንን ተጠቃሚ ለማድረግ መስራቱን ተናግረዋል። በዚህም ማስተካከያውን የሦስት ወር ለመምህራን ከፍሎ የቀሩት የሦስት ወር ክፍያ ለመክፈል ሲል ኮሮና በመከሰቱ ምክንያት ለተጠባባቂነት በመያዝ ሳይከፍል ቀርቷል። ካሁን በኋላ ግን ሁሉም ክልሎች ይህንን ደመወዝ ለመምህራኖቻቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲከፍሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38242
432
0ሀገር አቀፍ ዜና
በ2022 የቱሪዝም ገቢን 23 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እየተሰራ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 27, 2020
23
ለምለም መንግሥቱ አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ በ2022ዓ.ም ሰባት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን የሚሆን ቱሪስት በመሳብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ 23 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እየሰራች መሆኑ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተናገረ። በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ዘርፍ አማካሪ አቶ አህመድ መሐመድ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በአስር ዓመቱ መሪ ዕቅድ የመጨረሻ ዓመት በሆነው 2022 ዓ.ም ሰባት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን የሚሆን ቱሪስት በመሳብ 23 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ለማግኘት እየተሰራ ነው። በዚህም አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል። አቶ አህመድ እንደሚሉት፤ በሀገር ደረጃ አዲስ የሆነውን የቱሪዝም ኤክስፖርት በመተግበርና 26 በመቶ ድርሻ እንዲኖረው በማድረግ ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ወደ ትግበራ የተገባ ሲሆን፤ መሪ ዕቅዱም ለቱሪዝም ዕድገት ማነቆ የነበሩ ችግሮችን በመለየት ዘርፉን በሚያሳድጉት ላይ ቢሰራ የሚፈለግበት ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል የሚያሳይ ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ ተወዳዳሪነትን መፍጠር፣ የመረጃ ልዕቀትን ማጎልበት፣ ጥናትና ምርምር ማካሄድ ላይ ትኩረት ማድረጉን የጠቆሙት አቶ አህመድ፤ በሀገሪቷ እየተገነባ ካለው ዕውቀት መር የኢኮኖሚ ሥርዓት ጋር ቱሪዝምን ለማስተሳሰር ጥራት ያለው ጥናትና ምርምር እንዲሁም ዕውቀት በማጎልበት ላይ ሥራዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በትኩረት ከተሰራም ቱሪዝምን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ይቻላል የሚል እምነት መያዙን አስረድተዋል። በዓለም የቱሪዝም ገበያ ውስጥ እነ ቻይና፣ ጃፓን፣ ሩሲያ እና የመካከለኛ ምሥራቅ ሀገራት እየገቡ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ አህመድ፤ እነዚህን ማዕከል ባደረገ የቱሪዝም መዳረሻና አቅርቦት መኖር አለበት በሚል ዕቅዱ መቃኘቱንም አመልክተዋል። ተመልካች ብቻ ሳይሆን በሚጎበኘው አካባቢም ተሳትፎ ያለው ቱሪስት ነው የሚፈለገው ብለዋል። ቱሪዝም አካታች የቱሪዝም ገበያ ነው ያሉት አቶ አህመድ፤ ለሕግ የሚገዛ፣ በእውቀት የሚመራ፣ በቀጣሪና በተቀጣሪ መካከል መልካም ግንኙነት እንዲሰፍን የሚያደርግ ሥርዓት በመፍጠር የጎላ ሚና እንዲኖረው፣ በአነሥተኛ፣ በመካከለኛና በከፍተኛ የተደራጁ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ዘርፉን እንዲቀላቀሉ፣ ሆቴል ቤቶችም እንዲስፋፉ እስትራቴጂው የሚያግዝ እንደሆነ አስረድተዋል። ዕቅዱ በተዘጋጀበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ተገዳ ወደ አላስፈላጊ ጦርነት እንድትገባ ያደረጋት ነገር አዲስ ክስተት ነው ያሉት አቶ አህመድ፤ በአሁኑ ጊዜ ወደተረጋጋ ሥርዓት እየገባች በመሆኑ ዘርፉ መልሶ እንዲያንሰራራ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃንን ሳይቀር በመጠቀም የማስተዋወቅ ሥራው ይጠናከራል ብለዋል። በመንግሥት ሕግን ለማስከበር የወሰደው እርምጃ ዓለምአቀፍ ተቀባይነትን ለመጨመር እንደ አንድ የፖለቲካ አቅም መወሰዱን አቶ አህመድ ጠቁመው፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃንን ሳይቀር በመጠቀም ያደረገው እንቅስቃሴ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያደርስ ይችል ነበር ብለዋል። ነገር ግን ፖለቲካል ካፒታል የሚባለው የዲፕሎማሲ እና ሌሎችም ጥረቶች ግጭቱን በፍጥነት ለመቀልበስ እንዳስቻላትም አንስተዋል። የአስር ዓመቱ የቱሪዝም መሪ ዕቅድ ላይ በዘርፉ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የሆኑ አካላት፣ በከፍተኛ አመራር ላይ ያሉ የተቋሙ ሠራተኞች፣ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ እውቀት ያላቸው የተካተቱበት አካላት ያዘጋጁትና ተተችቶ የዳበረ ሰነድና ለትግበራ የበቃ እንደሆነ አቶ አህመድ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38243
374
0ሀገር አቀፍ ዜና
በጁንታው ላይ የተመዘገበው ድል በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግድያዎች በማስቆም እንዲደግም የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
14
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የአገር መከላከያ ሰራዊት በትህነግ ጁንታ የጥፋት ቡድን ላይ ያስመዘገበውን ድል በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግድያዎችን በማስቆም እንዲደግመው የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ። በሕገ ወጡ የትህነግ ቡድን ታግተው መከራ እና ስቃይ ያሳለፉትን የሰራዊት አባላት ተቀብለው ለተንከባከቡት የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር በደባርቅ ከተማ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ወቅት እንደተገለጸው፤ በሕገ ወጡ የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት የኢትዮጵያውያንን ስሜት ክፉኛ ጎድቶ ነበር። ሕግ በማስከበሩ ርምጃም በአራቱም ጫፍ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመከላከያ ጎን መቆሙን ሲገልፅ ቆይቷል። ጥቃቱ በተፈፀመባቸው የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኙ ሕዝቦች ደግሞ መከላከያ ኃይሉ ከተሰነዘረበት ጥቃት አገግሞ ለድል እንዲበቃ  ታሪክ የማይሽረው አኩሪ ገድል ፈፅመዋል።ትህነግ በሰነዘረው ጥቃት ቀጥተኛ ዒላማ መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ሕዝቦች በመሆናቸው ይህንን ጥቃት ከመከላከል አልፎ በተለያየ የጉዳት ደረጃ ላይ የነበሩ የመከላከያ እና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን ተቀብሎ አስተናግዷል። በሕገ ወጡ ቡድን አፈና ደርሶባቸው ለሳምንታት በርሃብ፣ በውሃጥም እና ድካም በሕይወት እና ሞት መካከል የነበሩት የመከላከያ አባላት በበየዳ እና ጠለምት ወረዳዎች በኩል አድርገው ወደ ሰሜን ጎንደር ዞን አካባቢዎች ሲገቡ ሕዝቡ በፍቅር ተቀብሎ አስተናግዷቸዋል።የአማራ ሕዝብ ለሰራዊቱ ላደረገው እንክብካቤ፣ ፍቅር እና ድጋፍ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ጎንደር እና ምዕራብ ጎንደር ዞን ኮማንድ ፖስት የምስጋና እና እውቅና መርሃ ግብር ከትናንት በስቲያ በደባርቅ ከተማ አዘጋጅቷል። በምስጋና መርሃ ግብሩ የተገኙት የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎችም የሀገር መከላከያ ሰራዊት የትህነግን የጥፋት ቡድን በማያዳግም መልኩ በማስወገድ ያሳየውን አኩሪ ጀብዱ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚፈጠሩ የሰላም መደፍረስ ችግሮችን እንዲያስቆም ጠይቀዋል። «የትናንቱ ድል የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድል ነው» ያሉት የደባርቅ ከተማ ነዋሪ አቶ መኳንንት ደሳለኝ፤ ጦርነቱ ቢያልቅም ዛሬም የተልዕኮ ፈፃሚዎች ሴራ ፈፅሞ አልከሰመም ብለዋል። በመተከል እና በሌሎች አካባቢዎች ያለውን ግድያና መፈናቀል ማስቆም የሰራዊቱን ተልዕኮ የሚሻ በመሆኑ የትናንቱን ገድላችሁን በመፈፀም ኢትዮጵያን መታደግ ይኖርባችኋል ሲሉም ጠይቀዋል።ሰራዊቱ ከልጆቻችን መካከል እንደ አንዱ ነው ያሉት ሌላዋ የደባርቅ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ እናንየ መስፍን፤ ከደረሰበት የስነ ልቦና ስብራት አገግሞ እና ተልዕኮን በብቃት ፈፅሞ በዚህ መልኩ ለምስጋና መገኘታችን አስደሳች ነው ብለዋል። የሰሜን ሕዝብ ያሳየው ፍቅር፣ እንክብካቤ እና ጀግንነትም አማራ ጠላቶቹ እንደሚሉት ሳይሆን ለኢትዮጵያ አንድነት ያለውን ጥልቅ ፍቅር ዳግም ያስመሰከረ በመሆኑ ኮርተንበታል ብለዋል። በዕለቱ ለምስጋና የተገኙት የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትም ሕዝቡ በሕግ ማስከበር ርምጃው ያደረገውን ገድል ታሪክ እና የመከላከያ ኃይሉ ዘላለም ሲዘክረው እንደሚኖር መግለጻቸውን የዘገበው የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ነው።
https://www.press.et/Ama/?p=38303
335
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሃይማኖታዊ በዓላት ወቅትና በአገልግሎት መስጫዎች የኮቪድ-19 መመሪያዎች እንዲተገበሩ ተጠየቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 27, 2020
13
በኃይሉ አበራአዲስ አበባ:- በሃይማኖት ተቋማትና በሁሉም አገልግሎት መስጫዎች የኮቪድ-19 መመሪያ ተግባራዊ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠየቁ። በተለይ በመጪው ሳምንታት የሕዝብ መሰብሰብን የሚፈልጉ ሃይማኖታዊ በዓላት ወቅት የኮቪድ-19 ይበልጥ እንዳይስፋፋ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች በብዙኃን መገናኛ በኩል እንዲሰሩም ተጠይቀዋል።የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ በመግለጫቸው ወቅት እንዳሳሰቡት፤ የኮቪድ -19 በዓለማችን ከተከሰተ አንድ ዓመት መሆኑን እና በቅርብ ጊዜም ባህሪውን ቀይሮ በመምጣቱ የዓለም ሀገራት ዳግም ገደቦችን እየጣሉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያም የብዙዎችን ሕይወት መቅጠፉን እና ዛሬም ቢሆን ተጨባጭ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት አይገባም በመሆኑም በሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የሚገኙ አማኞች የተቋማቸውን የኮቪድ-19 መመሪያ በምልዓት ሊተገብሩት ያስፈልጋል። ይህ እንዲሆን ደግሞ መመሪያዎችን አስመልክቶ በየቤተ ዕምነቱ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችና ሁሉም አማኞች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የተጠቆሞ ሲሆን፤ በቀጣይ ሳምንታት እና ቀናት በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ተከታታይ ሃይማኖታዊ በዓላት የሚከበርበት ወቅት ከመሆኑ አንጻር የቫይረሱ ስርጭት እንዳይባባስ ሁሉም የበዓሉ አክባሪዎች ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ በአጽንኦት አሳስቧል።የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ በበኩላቸው፤ የኮቪድ 19 መመሪያ ቁጥር 30 ካስቀመጣቸው ድንጋጌዎች አንዱ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ እጅን በውሃና ሳሙና መታጠብ፣ የፊት ማስክ በትክክለኛው ማድረግ ሲሆኑ፤ እነዚህን የመመሪያውን ግዴታዎች መተግበር የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነትእንደሆነ አሳስበዋል። የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም «ማስክ ከሌለ አገልግሎት የለም» የሚለውን መርህ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።በሀገራችን እስካሁን ድረስ የአንድ ሺህ 882 ሰዎችን ሕይወት ያጣን መሆኑን አስታውሰው ቀጣይ ጊዜ የተሻለ እንዲሆን በመመኘት በተለይ እንደ ቁልቢ ገብርኤል ባሉ በዓላት ብዙ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች አካላዊ ርቀት እንዲጠበቅ፣ የአፍና የአፍንጫ ጭንብል ማድረግ አስገዳጅ እንዲሆኑ፣ እጅን በውሃና በሳሙና መታጠብ ካልሆነም ሳኒታይዘር እና አልኮል በመጠቀም አስፈላጊ ጥንቃቄዎች ሊደረጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።እነዚህን መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረግ ከተቻለ የቫይረሱን ስርጭት እና ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መቀነስ እንደሚቻል የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳይ በመጠቆምም፤ በኮቪድ-19 መመሪያዎች ተግባራዊነት ላይ ከበጎፍቃደኞች፣ ከሴቶችና ወጣት አደረጃጀቶች እንዲሁም ከብዙኃን መገናኛዎች ጋር በስፋት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።በቀጣይ ስድስት ወራት የተለያዩ አካላት በሚሳተፉበት የዘመቻ መርሃ ግብር በጉራማይሌም ቢሆን በአዲስ አበባ ብቻ የሚስተዋለው የፊት ማስክ አጠቃቀም በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በትክክል ተግባራዊ እንዲደረግ፣ እጅን በውሃና በሳሙና መታጠብ ወይም ሳኒታይዘር ማጽዳት እንዲሁም አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ ሥርዓቶችን የማጠናከር ሥራዎች ይሰራሉ ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38246
318
0ሀገር አቀፍ ዜና
የትግራይ ወጣት ከሁሉም ወንድም ብሔር ብሔረሰብ እንዲጣላ ጁንታው በመስራቱ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የማቀራረብ ሥራ ሊሰራ ይገባል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
6
በአማንመስፍን ሚካኤል መቐለ፡- የህወሓት ጁንታ የትግራይ ወጣት በኢትዮጵያዊነቱ እንዲደራደር ሁለት ዓመት መርዝ ሲነዛበት እና ከሁሉም ወንድም ብሔር ብሔረሰብ ጋር እንዲጣላ በመስራቱ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የማቀራረብ ሥራ ሊሰራ ይገባል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ፡፡ የመቐለ ከተማ ወጣቶች በከተማዋ ፀጥታ እና መረጋጋት ዙሪያ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ትናንት ተወያይተዋል፡፡ በከተማው እየተነዛ ያለው የውሸት ወሬዎችን ሳይሰሙ ስለ ከተማው ፀጥታ ለመወያየት ወደ ውይይቱ የመጡ ወጣቶችን የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለሥላሴ አመስግነዋል። የመድረኩ ተሳታፊ የመቐለ ወጣቶች በበኩላቸው፤ «የትግራይ ወጣት በኢትዮጵያዊነቱ እንዲደራደር ሁለት  ዓመት መርዝ ተዘርቶለታል፣ ከሁሉም ወንድም ብሔር ብሔረሰብ እንዲጣላ ጁንታው ሰርቷል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የማቀራረብ ሥራ ሊሰራ ይገባል» ሲሉ ተናግረዋል። ውይይቱን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፣ የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራር  ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የመቐለ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ኃይለሥላሴ የመሩት ሲሆን፤ በመቐለ ከተማ ያጋጠመው ዝርፊያ ከማረሚያቤት በተለቀቁ ታራሚዎች እና ሌሎች ሌቦች እንደሆነ ዶክተር ሙሉ ለተወያዮቹ አብራርተዋል።የክልሉም ሆነ የከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደር ለፀጥታ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራበት የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ በመቐለ ከተማ የተበተነ የጦር መሣሪያ እንዳለ እና በሰላማዊ መንገድ ወደ ፀጥታ አካላት ማስረከብ እንደሚገባ ዶክተር ሙሉ አስታውቀዋል። የከተማዋ ወጣቶች የውሸት ወሬዎችን መታገል እንዳለባቸውም ገልፀዋል። ጁንታው የከተማዋ መሠረተ ልማት እንዲወድም ያደረገ ሲሆን የፌዴራል መንግሥት በአፋጣኝ መሠረተ ልማቱ በመጠገን ወደሥራ እንዲገቡ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ «ሌቦችም ከእኛው፣ የሚሰረቀውም የእኛው ስለሆነ ሁላችንም ፀጥታችንን ማስከበር አለብን» ሲሉ ተናግረዋል። በየሰፈሩ የውሸት ወሬዎች የሚፈበርኩ ሰዎችም ሆነ በውጪ ሆነው ሕዝብ እያደናገሩ ሕዝቡ እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ ሚዲያዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶቹ ጠይቀዋል። አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38300
228
0ሀገር አቀፍ ዜና
«የትግራይን ሕዝብ እንደማንኛውም ዜጋ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ እንጂ እንዲጎዳ በማሰብ የሚሰራ ሥራ የለም» – አቶ ዛድግ አብርሃ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
14
እፀገነት አክሊሉ አዲስ አበባ፦ መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንደማንኛውም ዜጋ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ እንጂ ሆን ተብሎ እንዲጎዳ የተሰራም ሆነ የሚሰራ ሥራ አለመኖሩን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር አስታወቁ፡፡ ሚኒሰትሩ አቶ ዛድግ አብርሃ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት፣ መንግሥት የሰሜን ዕዝ መጠቃቱን ተከትሎ ራሱን ለመከላከል የወሰደው እርምጃ እንዳለ ሆኖ ወደ ጦርነት የገባበት ዋናው ምክንያት መስዋዕትነትም ተከፍሎ ቢሆን የጁንታው ቡድን እንደመያዣ የያዘውን የትግራይን ሕዝብ ነፃ ለማውጣት ነው። የትግራይ ሕዝብ ሕዝባችን እንደመሆኑ እንደማንኛውም ዜጋ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ እንጂ እንዲጎዳ በማሰብ የሚሰራ ሥራ የለም ብለዋል አቶ ዛዲግ። እንደ አቶ ዛድግ ገለጻ ጁንታው ቡድን መንገድ፣ ድልድይ፣ አየር ማረፊያ አውድሟል፤ ተንቀሳቃሽ የገንዘብ መስጫ (ኤቲኤም) ማሽኖች ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ አድርጓል፤ በኢትዮ ቴሌኮም መስመሮች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አድርሶባቸዋል፤ ከዚህ አንጻር በክልሉ የደረሰው የመሠረተ ልማት ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ በአንድ ጀምበር መልሶ መገንባቱም ከባድ ነው። እንደዚህ ዓይነት አቅም ቢኖረንማ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የመሠረተ ልማት ችግር ባልተፈጠረ ነበር ያሉት አቶ ዛድግ እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም ፤ የፈራረሱትን ወደነበሩበት ለመመለስ ጊዜ ይወስዳል ፤ አሁንም ግን ሥራዎች እየተሰሩ ነው፤ በክልሉ የባንክ አገልግሎት ለምን አይጀመርም ተብሎ ለሚቀርበው ጥያቄም መልሱ ይኸው ነው ብለዋል። ጁንታው በስንት ዓመት በብዙ ልፋትና ጥረት የተገነባን መሠረተ ልማት በ30 ቀን ነው ያወደመው፤ በአሁኑ ወቅትም መንግሥት የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው፤ መንገዶች እየተጠገኑ፣ የቴሌኮም መሠረተ ልማቱም እንደገና ወደ ሥራ እንዲገባ ሰፋፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፤ የባንክ አገልግሎቱም እንደዚያው፤ ነገር ግን ሕዝቡም አክቲቪስቱም ሌላውም እንደሚፈልገው በአንድ ቀን መስራት አይቻልም፤ ይህም ቢሆን ግን መንግሥት የለጋሽ አካላትን አቅም በማንቀሳቀስ ሁሉ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል። እንደ አቶ ዛድግ ገለጻ አንዳንድ አካላት እንደሚሉት ሆን ተብሎ የትግራይን ሕዝብ ለመበደል የተሰራ ሥራ የለም፤ ይህንን ለማድረግ የሚያስብ መንግሥትም አለመኖሩን አብራርተዋል። በሌላ በኩል በመሰረተ ልማቱ ላይ የደረሰው አደጋ ከፍተኛ በመሆኑና መንግሥት ብቻውን የሚፈታው ባለመሆኑ ሕዝቡም ሌላውም አቅሙን አሟጦ እንዲጠቀም ኮማንድ ፖስቱ እና ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጥረት እያደረጉ መሆኑን አቶ ዛድግ ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013 ዓ .ም
https://www.press.et/Ama/?p=38297
288
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሀዋሳ ከተማ በ1ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 28, 2020
6
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ የሆነው የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ በ1ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ሊገነባ ነው።ፋብሪካውን የሚገነባው አማ ቢዝነስ ግሩፕ ሲሆን፤ ለሚያስገነባው ፕሮጀክት የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል።በወቅቱ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ፖሊሲ የግል ባለሀብቶችን የሚያበረታታ ነው። በክልሉ ማልማት ለሚፈልጉ መሰል ባለሀብቶችም ለኢንቨስትመንት የሚሆን ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ወደክልሉ ሄደው መዋዕለ ንዋያቸውን ሊያፈስሱ ይገባል።የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው፤ እንደሀገር ለዘይት ምርት በየወሩ 48 ሚሊዮን ብር እንደሚወጣ ገልጸዋል። የሀገራችን የዘይት ፋብሪካዎች 12 በመቶ ብቻ የሚሸፍኑ መሆኑን በመጠቆምም፤ ፕሮጀክቱ እንደ ሀገር የዘርፉን ችግር የሚቀርፍ መሆኑን አስረድተዋል።የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በበኩላቸው፤ እንደነዚህ ዓይነት ፕሮጀክቶች ሥራ አጥነትን ከመቀነስ አንጻር የጎላ ፋይዳ ያለው ብቻ ሳይሆን የከተማዋንም ተመራጭነት የሚያሰፋ መሆኑን ተናግረዋል። ከተሞችን ለሰው ልጆች ምቹ ለማድረግ አስተዳደሩ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።የድርጅቱ ባለቤት አቶ አንድነት ጌታቸው በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ወደ ኢንቨስትመንት መግባታቸውን ገልፀው፤ የዚህ ፕሮጀክት ግንባታ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ተናግረዋል። ድርጅቱ በፍጥነት እንደሚጠናቀቅ እና ለ2 ሺህ44 ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጠርም መናገራቸውን የዘገበው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 19/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38310
183
0ሀገር አቀፍ ዜና
የፕሪሚየር ሊጉ የአንደኛ ዙር ቆይታ- ከስፖርታዊ ጨዋነት አንፃር
ስፖርት
February 28, 2020
53
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመቱ አንደኛ ዙር መርሐ ግብር ከሦስት ወራት ቆይታ በኋላ ባሳለፍነው ሰኞ የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ተጠናቋል። የመጀመሪያው ምዕራፍ በተለያዩ ክስተቶች የታጀበ ሆኖም አልፏል።የመጀመሪያው ዙር ቆይታ የኢትዮጵያ እግር ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ከገባበት የስፖርታዊ ጨዋነት ስጋት አንፃራዊ በሆነ መልኩ መሻሻል የታየበት ነው።ፕሪሚየር ሊጉ ሲወቀስበት ከነበረው የስፖርታዊ ጨዋነት ስጋት ወጥቶ አዲስ መልክ እንዲይዝ በማድረግም የሊግ ኮሚቴው ውጤት ማሳየት የጀመረበት ነበር።በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተለይ ከሦስት ዓመት ወዲህ የስፖርታዊነት ጨዋነት ችግር የእግር ኳሱ ትልቅ ፈተና ሲሆን ታዝበናል። በየጨዋታዎች በደጋፊዎች መካከል የሚነሱ ፀቦች እንደ ፋሽን መታየት የጀመሩበት ጊዜም ነበር። በፌዴሬሽኑ፣ በክለቦች ፣በመንግሥት በኩል ለችግሩ መፍትሔ ማምጣት የሚያስችሉ ሥራዎች እንደተሠሩ ቢነገርም ስታዲየሞችን የፀብ መነኸሪያ ከመሆን መታደግ አልተቻለም ነበር።ስታዲየሞች የእግር ኳስ ስሜትን ሳይሆን የፖለቲካ ስሜትን ማንፀባረቂያ መድረክ ወደ መሆን እስከመሻገር ደርሰዋል።የትግራይና የአማራ ክልል ክለቦች ፤በደቡብ ክልል የሚገኙ ክለቦች እርስ በዕርስ ተገናኝተው ለመጫወት አዳጋች እስከመሆን ያደረሰንም ስርዓት አልበኝነት ሰፍኖ ነበር።በ2009 ዓ.ም በርካታ ቁጥር ያለው የስቴዲየም ሁከት በተለይም በፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቢከሰቱም ከብጥብጦቹ ጀርባ እግር ኳስን የሚሻገሩ ገፊ ምክንያቶች እምብዛም እንዳልነበሩ ይጠቀሳል። ከ2009 ወዲህ ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚለኮሱ የስቴድየም ግጭቶችና ረብሻዎች ቁጥር ከዘንድሮው የውድድር ዓመት በፊት አይለው ነበር።በ2010 የውድድር ዓመት ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዲግራት፣ ጅማና ወልዲያ ከተሞች ውስጥ የስቴድየም ሁከትና ግጭቶች ተበራክተው እንደነበር ይታወሳል።በተለይም በውድድር ዓመቱ በወልዲያ ስፖርት ክለብና በመቀሌ ከተማ መካከል ሊደረግ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት በሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ህይወት የጠፋ ሲሆን ንብረት ላይ ዘረፋና ወድመት ተከስቷል። በዕለቱም ማገባደጃ ላይ በመቀሌ ከተማ መንገዶች ላይ ክስተቱን ለመቃወም በርካታ ሰዎች ወጥተው እንደነበር አይዘነጋም። ጨዋታው ካለመካሄዱ በተጨማሪም የግጭቱ አሻራ እስከ ቀጣይ ቀናት ሲሻገርና ከእግር ኳሳዊ ምክኒያት ይልቅ ፖለቲካዊ አንደምታው ሚዛን ሲደፋ ታይቷል።በወቅቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ጁነዲን ባሻ ክስተቱ ከእግር ኳስ የሚሻገር ገፅታ እንዳለው ተናግረው ነበር፡፡የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ከረብሻዎች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ ክለቦች ላይ የጣለው ቅጣት ግማሽ ሚሊዮን ብር ገደማ መሰብሰብ መቻሉ ግጭቶች በምን ያህል ደረጃ እንደተበራከቱ ማሳያ ነው።በእንቁላሉ ጊዜ ያልተቀጣው እግር ኳስ ከፖለቲካም በላይ ጦዞ ለፀጥታ አስከባሪዎች ፈተና ከመሆን አልፎ እንደ አገር ስጋት የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሶም ነበር።ሰላም በራቃቸው የስፖርት ማዘውተሪያዎች መደበኛ የውድድር መርሐ ግብሮች መተማመኛ ማግኘት አልቻሉም ነበር።በክልል የሚካሄዱ ጨዋታዎች በፖለቲካ ትኩሳት ሳቢያ ተጨማሪ ራስ ምታት እየሆኑ መምጣታቸውም አሳሳቢ ነበር።በስፖርቱ ዓለም የተመልካቾች ነውጠኝነት ምክንያቶች ብዙ መሆናቸውን በስፖርቱ ጥልቅ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣል።ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ወይንም ምጣኔ ሀብታዊ ብሶቶች ስቴዲየም ላይ ሊያጠሉ እንደሚችሉም ይታመናል።በኢትዮጵያ እግር ኳስን የታከከ ግጭትና ሁከት ሲከሰት የመጀመሪያው ባይሆንም በተለይም ባለፈው የውድድር ዓመት ቀይ መስመር አልፎ ነበር።የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ስናጤን ደግሞ ከእግር ኳስ ባሻገር ከእነዚህ ምክኒያቶች ሁሉ ለስፖርት ጠንቅ የሆነ የፖለቲካ አጀንዳ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ራሳቸው አስተውለውታል።እግር ኳስ ማኅበረሰባዊ መሰረት ከሌለው በስተቀር የጠነከረ የእኔነት ስሜት ሊፈጥር አይቻለውም የሚሉ ተንታኞች፤ ክለቦች ከማኅበረሰባዊ መሰረታቸው በዘለለ ብሔር ተኮር መልክን እየተላበሱ የመምጣታቸው አዝማሚያ አደገኛ መሆኑ የበርካታ ስፖርት ቤተሰቦች እምነት ነው፡፡ክለቦች ሲቋቋሙ ወይንም ሲዋቀሩ አካባቢያዊ መገለጫ ወይንም ከተማዊ ስያሜ ሊኖራቸው ቢችልም ከብሔር፣ ከዘር ወይንም ከኃይማኖት ጋር በተቆራኘ መልኩ መደራጀት ክልክል መሆኑን የስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ማኅበራት ማደራጃ መመሪያ አንቀፅ 50 ቁጥር 2 ይገልፃል። ነገር ግን ባለፉት ዓመታት ብቻ ፌዴሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ሊጎች የብሔር ስም የተቀጠላላቸው በርካታ ክለቦች ውድድር እያደረጉ መጥተው ነበር።እግር ኳሱ ከአንዳንድ ሁከቶች አልፎ እጅግ ወደተደራጀ ነውጠኛነት እያመራ ስለመሆኑም ሲነገር ቆይቷል።ቀስ በቀስም ወደ መቧደን እየተጓዘ ነበር።ይህ አዝማሚያ የ2012 ዓ.ም የውድድር ዓመት ከመጀመሩ አስቀድሞ በእግር ኳሱ ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል በበርካቶች ዘንድ ስጋት ፈጥሮ ነበር።በዚህ ስጋት ውስጥ እያለ ኅዳር 21 ቀን 2012 ዓ.ም የተጀመረው ፕሪሚየር ሊግ ከፌዴሬሽኑ መሪነት ወጥቶ በሊግ ኮሚቴ መመራቱን ተከትሎ ቢያንስ ቢያንስ በመጀመሪያው ዙር የታሰበው ስጋት ሊረግብ ችሏል።በውድድር ዓመቱ በመጀመሪያ ዙር ከተደረጉ 30 ጨዋታዎች ቢያንስ 25 ጨዋታዎች ስፖርታዊ ጨዋነት የነገሠባቸው ነበሩ። ስፖርቱን ከፖለቲካ በመቀላቀል ስታዲየሞችን የፀብ መናገሻ የማድረጉ ዝንባሌ እንዳይኖሩ የተደረጉ ጥረቶችም ከሞላ ጎደል ፍሬያማ ነበሩ ማለት ይቻላል።ለዚህ ደግሞ የአማራ ክልልና ትግራይ ክልል ክለቦችን እንደ ማሳያ ማንሳት ይገባል። አምና በሁለቱ ክልል ክለቦች ደጋፊዎች መካከል የነበረውን መፋጠጥ በውድድር ዓመቱ እንዳይደገም ማድረግ ተችሏል። የባህር ዳር ወጣቶች የመቐለ 70 እንደርታ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች በወንድማዊ ስሜት ‹‹እንኳን ወደ ውቢቷ ከተማችሁ በደህና መጣችሁ›› ሲሉ በፍቅር በመቀበል ፀብን ለማራቅ የሄዱበት ርቀት ትልቅ ርምጃ ነበር።የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች ከባህር ዳር ከነማ ደጋፊዎች በጋራ በመሆን ከተማዋን በማፅዳት አንድነታቸውን ያሳዩበት ድርጊት የከረረውን ስጋት መበጠስ ችሏል።የሁለቱ ክለቦች ደጋፊ ማህበራት በአብሮነት መሥራት መቻላቸው ስፖርት ለሰላም፣ ለአንድነትና ለወንድማማችነት መርህን በተግባር እንዲታይ አድርጓል። የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ወደ መቐለ ከተማ ባቀናበት ወቅት የነበረው ሁኔታ ፤በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች መካከል ተጨማሪ የአንድነት ስሜት እንዲጎለብት ያደረገ ነበር። የመቐለ ከተማ ወጣቶች የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾችና ደጋፊዎችን ፍጹም ፍቅር በተሞላበት መልኩ ተቀብለው በመሸኘት የልዩነቱን ግንብ ማፍረስ የቻሉበትን አጋጣሚ ፈጥረዋል። በሁለቱ ክልሎች የሚገኙ የክለቦች ደጋፊ ማህበራት በኩል የታየው ቆራጥነት ለዚህ ውጤት መገኘት ትልቅ ድርሻ የያዘም ነበር። የሁለቱ ክልሎች የመንግሥት አመራሮች በኩል የታየው ቀናኢነትና ከደጋፊ ማህበራቱ መቀናጀት ጋር ተደምሮ የእግር ኳሱ ስጋት ሊረግብ ችሏል። በደቡብ ክልል የሚገኙ ክለቦች ደጋፊዎች ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲሰፍን ያሳዩት ቁርጠኝነትም የመጀመሪያው ዙር አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍንበት ትልቅ ሚና ነበረው።በወላይታ ድቻና ሲዳማ ቡና ክለብ ደጋፊዎች መካከል የነበረውን መፋጠጠ በውድድር ዓመቱ አዲስ የሰላም መልክ መያዝ መቻሉ ለዚህ ስኬት ምሳሌ ነው፡፡ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውበት ከሆኑ ክለቦች መካከል የሸገር ደርቢዎቹ ኢትዮጵያ ቡናንና ቅዱስ ጊዮርጊስን እዚህ ላይ ሳይጠቅሱ ማለፍ አይቻልም።የከተማዋ ተፎካካሪ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ተመልካቾች መካከል የተስተዋለው መከባበርና ሥነ ሥርዓት ለክልል ክለብ ደጋፊዎች እንደማሳያ መወሰድ እንዳለበት የብዙኃን አስተያየት ጭምር ነበር።ቀደም ሲል ሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ሲኖራቸው በከተማዋ የሚኖረው ውጥረትና የፀጥታ ስጋት በዚህ ዓመት ከከተማዋ ዋንጫ ጀምሮ ሰላማዊና የሚያስመሰግናቸው ጭምር ነበር።የሁሉም ክለቦች ደጋፊ ማኅበር ፕሬዚዳንቶች በጥምረት የመሠረቱትን ማኅበር ተከትሎ፣ እንደዚህ ዓይነት ችግሮች ዳግም እንዳይከሰቱ የሸገር ደርቢዎች የነበራቸውን ሚናም በጉልህ የሚጠቀስ ነው።የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሚና ከዚህ ስኬት ጋር አብሮ መነሳት ይገባዋል። ከንቲባው በተለያዩ ጊዜያት ከኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ክለብ አመራሮች ጋር በወቅታዊ እና መሠረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት በደጋፊዎች መካከል ይፈጠር የነበረውን ግጭት እንዲከስም ያላሳለሰ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። በሸገር ደርቢ ጨዋታ ወቅት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይሰማ የነበረው የፀብ ዜና በሰላም እንዲተካ በማድረግ ረገድ ምክትል ከንቲባውና የሁለቱ ክለቦች ደጋፊ ማህበራት ቆራጥነት ሳይደነቅ የሚታለፍ አይደለም።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2012 ዓ.ም የውድድር ዓመት አንደኛ ዙር ቆይታ ከስፖርታዊ ጨዋነት አኳያ አበረታች ውጤት የታየበት ቢሆንም በመጨረሻዎቹ ሁለትና ሦስት ጨዋታዎች እንከኖች መታየታቸው አልቀረም።ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ በነበራቸው ጨዋታ፣ ወልቂጤ ከተማና ሲዳማ ቡና በነበራቸው ጨዋታ በደጋፊዎች መካከል የተፈጠረ ግጭት ቢኖርም እንዳለፉት ዓመታት የተጋነነ ነው ለማለት አይቻልም።ያም ሆኖ የሊግ ኮሚቴው እንዲህ ዓይነት ግጭቶች ወደ ሁለተኛው ዙር እንዳይዛመቱ ሰሞኑን ፋሲል ከነማንና ቅዱስ ጊዮርጊስን ከዚሁ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር በተያያዘ ቅጣት እንዳስተላለፈባቸው ሌሎቹንም ተመልክቶ ፍትሐዊ ቅጣት ማስተላለፍ ይጠበቅበታል።ይህም ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ የመጀመሪያው ዙር በተሻለ ስፖርታዊ ጨዋነት እንደተጠናቀቀው ሁሉ ለሁለተኛውም ዙር ከወዲሁ የቤት ሥራዎችን ጨርሶ መሻገር ለነገ የሚባል አይደለም።አዲስ ዘመን አርብ የካቲት 20/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=28042
1,007
2ስፖርት
የበጋ ወራት ውድድሮች ጠንካራ ፉክክር እያስተናገዱ ነው
ስፖርት
February 27, 2020
43
ካለፈው ታኅሣሥ አጋማሽ አንስቶ እየተካሄደ የሚገኘው የሠራተኞች የበጋ ወራት የስፖርት ውድድር በጠንካራ ፉክክር ታጅቦ ቀጥሏል። በተለይም በሁለት ዲቪዚዮን ተከፍሎ የሚካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ጠንካራ ፉክክር በማስተናገድ ላይ መሆኑን የውድድሩ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) የስፖርት ክፍል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ካሳ ተናግረዋል። በስምንት ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የአንደኛ ዲቪዚዮን የእግር ኳስ ውድድር ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በአራት ጨዋታ አስራ ሁለት ነጥብና አስራ ሁለት ንፁህ ግብ በመሰብሰብ እየመራ ይገኛል። የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በሦስት ጨዋታዎች በሰበሰበው ዘጠኝ ነጥብና ሰባት ንፁህ ግብ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በቅርብ ርቀት እየተከተለ ይገኛል። አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በበኩሉ በአራት ጨዋታ ዘጠን ነጥብና ስድስት የግብ ዕዳ ይዞ በሦስተኛነት ይከተላል። አዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በሦስት ጨዋታ ሦስት ንፁህ ግብና አራት ነጥብ ይዞ ጠንካራ ፉክክር እያደረገ ይገኛል። ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ከሦስት ጨዋታ ሦስት ነጥብና ሁለት የግብ ዕዳ ይዞ አምስተኛ ላይ ይገኛል። አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በሦስት ጨዋታ አንድ ነጥብና ስምንት የግብ ዕዳ ይዞ ይከተላል። ኢትዮጵያ መድህን ድርጅትና መከላከያ ኮንስትራክሽን በሦስት ጨዋታ ስምንትና አስር የግብ ዕዳ ይዘው ካለምንም ነጥብ በአንደኛው ዲቪዚዮን እየተፎካከሩ የሚገኙ ቡድኖች ናቸው። በመጀመሪያው ዲቪዚዮን እሁድ ዕለት ሁለት ጨዋታዎች ሲካሄዱ ኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ከኢትዮጵያ መድህን በኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ የሚገናኙ ይሆናል። ቀሪው አንድ ጨዋታ በተመሳሳይ ዕለትና ቦታ አዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ከአንበሳ አውቶቡስ ጋር የሚያገናኝ ነው። በሁለተኛ ዲቪዚዮን እየተፎካከሩ የሚገኙ አስራ ስምንት ቡድኖች የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ወሳኝ ጨዋታዎችን የሚያከናውኑ ሲሆን በምድብ ‹ሀ› ከሦስት ጨዋታዎች ሙሉ ዘጠኝ ነጥብና ሦስት ንፁህ ግብ ማግኘት የቻለው ሞዔንኮ ኩባንያ እሁድ ዕለት በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ቃሊቲ ብረታብረት ፋብሪካን ይገጥማል። ቃሊቲ ብረታብረት በምድቡ ከሦስት ጨዋታዎች ሰባት ነጥብና ስድስት ንፁህ ግብ በመሰብሰብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዚሁ ምድብ በሦስት ጨዋታ ሰባት ነጥብና ዘጠኝ ግብ በመያዝ ሁለተኛ ላይ ይገኛል። አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ከኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ይሆናል። ሁለቱ ቡድኖች በምድብ ‹ለ›የሚገኙ ሲሆን አዋሽ ወይን በሁለት ጨዋታ አራት ነጥብና ሁለት ግብ ይዞ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ክፍያ መንገዶች በበኩሉ በሁለት ጨዋታ አንድ ነጥብና ሁለት የግብ ዕዳ ይዞ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዚሁ ምድብ ሦስተኛ ላይ የሚገኘው ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ካምፓኒ(ኮካ ኮላ) በሁለት ጨዋታ ሦስት ግብና አራት ነጥብ ይዞ በአራት ጨዋታ ሰባት ነጥብና አንድ ግብ ይዞ ሁለተኛ ላይ የሚገኘው አምቼ ኩባንያን ይገጥማል። ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት፣ኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ከ ይርጋለም አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የሚያደርጉት ጨዋታም ይጠበቃል። ከእግር ኳስ በተጨማሪ ቅዳሜ ዕለት በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት በሴቶች ቮሊ ቦል የሚካሄዱ ሦስት ጨዋታዎች የሚጠበቁ ሲሆን በተመሳሳይ ዕለት በጠረጴዛ ቴኒስ በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት የሚካሄዱ አምስት ጨዋታዎች ጠንካራ ፉክክር ያስተናግዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዳርት፣ ቼስ፣ ዳማና ከረንቦላ ጨዋታዎችም የተለያዩ ፉክክሮች ይጠበቃሉ። አዲስ ዘመን የካቲት 19/2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=27995
400
2ስፖርት
የአዲስ አበባ ኢትዮ ዩናይትድ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ተመሰረተ
ስፖርት
February 29, 2020
61
ምስረታውን በ1985ዓም ያደረገው ኢትዮ ዩናይትድ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለው መከፋፈል መሰረት በኢትዮጵያም በሶስት አሶሴሽኖች ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በኢትዮጵያ በተለይ በወጣቱ ዘንድ እጅግ ከተስፋፉ ስፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የማርሻል አርት ስፖርት በፌዴሬሽን ደረጃ ለመደራጀትም ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን 2003ዓ.ም በወጣው የስፖርት ማህበራት ማቋቋሚያ መመሪያ መሰረትም የድሬዳዋ ኢትዮ ዩናይትድ ኢንተር ናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ሊመሰረት ችሏል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ስር የነበሩት ሶስት አሶሴሽኖችም በመጣመር ፌዴሬሽን ያቋቋመ ሁለተኛው ከተማ አስተዳደር ሆኗል። በፌዴሬሽኑ ማቋቋሚያ ጉባኤ ላይም የስፖርት ኮሚሽኑ ተወካይ አቶ መኮንን ገብረህይወት የፌዴሬሽኑን ምስረታ አብስረዋል። ተወካዩ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የአሰራር ሂደቱንና ደንቡን በተከተለ መልኩ የፌዴሬሽን ምስረታ መካሄዱን አረጋግጠዋል። ፌዴሬሽኑ በስድስት ክፍለ ከተሞች ውስጥ ብቃታቸው የተረጋገጠ 16 ክለቦችን ያቀፈ፣ በ ‹‹ኤ ላይሰንስ›› ሁለት፣ በ ‹‹ቢ ላይሰንስ›› ስድስት፣ በ ‹‹ሲ ላይሰንስ›› አስር ዳኞች እንዲሁም ከ2-7ኛ ዳን ያላቸው 16 አሰልጣኞች ያሉት በመሆኑ የማቋቋሚያ ጉባኤ ማድረግ የሚያስችላቸው መሆኑን ጠቁመዋል። በዚሁም መሰረት ስራ አስፈጻሚዎችን በመምረጥ ወደ ስራ እንዲገቡ፤ በሂደትም ጽህፈት ቤትና የስፖርት ማዘውተሪያ ገንብተው ከመንግስት ድጎማ እስኪላቀቁ በኮሚሽኑ ቢሮ እንዲሁም በትምህርትና ስልጠና ማዕከላት እንዲገለገሉ ፈቃድ ተሰጥቷል። በመጀመሪያው ጉባኤ ላይም አዲስ ፌዴሬሽን እንደመሆኑ ሪፖርት ማቅረብ ባይቻልም ቀጣይ እቅዶች ግን ለጉባየተኛው ቀርበዋል። በዚህም የክለቦችን ቁጥር አሁን ካለበት ቁጥር ወደ 33 ማሳደግ፣ ጠንካራ ፌዴሬሽን እንዲሆን መስራት፣ ገቢውን በማሳደግ ከኮሚሽኑ ድጋፍ የሚላቀቅበትን መሰረት መጣል፣ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላትን ማሳደግ፣ ስፖርተኞችን በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ማሳተፍ፣ የተለያዩ ቻምፒዮናዎችን በማዘጋጀት ከተማ አስተዳደሩን እንዲሁም ሀገርን ለመወከል የሚችሉ ስፖርተኞችን ማፍራት፣ በትምህርትና ስልጠና የዳኞችንና አሰልጣኞችን ቁጥር ወደ 100 ማሳደግ እንዲሁም በክትትልና ድጋፍ ላይ ለመስራት መታቀዱ ተገልጿል። ገለጻውን ያዳመጠው ጉባኤም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በመተዳደሪያ ደንቡ ላይም ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ በጉባኤው አባላት ይሁንታ ሊያገኝ ችሏል።ከተሳታፊዎች በተሰጠው አስተያየትም ስፖርቱ እስከ ወረዳ በመውረድ በይበልጥ እንዲስፋፋ ፌዴሬሽኑ ከክፍለ ከተሞች ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት እና ከመንግስት ድጎማ ለመላቀቅ የሚያስችለውን መንገድ ማፈላለግ እንዲሁም የሀብት አሰባሰብ ላይ ማተኮር እንደሚገባው ተጠቁሟል። በተካሄደው የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫም አቶ በቀለ በዳዳ በ14 ድምጽ በማሸነፋቸው ከቀድሞው የአሶሴሽኑ ፕሬዚዳንት ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሲኒየር ሳቦም ተሾመ አበበ የስራ ደንብና መመሪያ ተረክበዋል። አቶ መንሱር ጀማል ምክትል ፕሬዚደንት ሲሆኑ፤ ወይዘሮ ሰብለወንጌል ቁምላቸው አቃቤ ነዋይ እንዲሁም ሌሎች አራት ግለሰቦች የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በመሆን ተመርጠዋል። ተመራጮችም በጋራ በመሆን ስፖርቱን ለማሳደግ የሚሰሩ መሆኑን ቃል ገብተዋል። ከማርሻል አርት ስፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ እአአ 1966 በጄኔራል ቾይ ሆንግ ሃይ ነው የተመሰረተው። የሁለቱን ኮሪያዎች መነጣጠል ተከትሎም ኢንተርናሽናልና ወርልድ ቴኳንዶ በሚል ሲከፈል፤ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ በሰሜን ኮሪያ በስፋት ይከወናል። በሲኒየር ማስተር አብዲ ከድር መስራችነትም በኢትዮጵያ አሶሴሽኑ እስካሁን ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በዚህ ወቅት የዓለም አቀፉ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን መቀመጫ በኦስትሪያ ቬና ሲሆን፤ ኢትዮጵያም አባል አገር ናት።አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 21/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=28137
396
2ስፖርት
ለጥቁር ሕዝቦች የታገሉ የስፖርቱ ዓለም ከዋክብት
ስፖርት
March 1, 2020
45
የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከአስር ዓመት በፊት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው በተለያዩ ዓለምአቀፍ የስፖርት መድረኮች ስፖርተኞች በዘርና በቆዳ ቀለማቸው መገለል የተለመደ እንደሆነ ያትታል። ይህ እውነታ አሁን ላይ አደጉ በምንላቸው አገራት ስፖርት ላይ እንኳን ነቀርሳ መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች እንመለከታለን። በተለይም እንደ አሜሪካ፤ አውስትራሊያና አውሮፓ የመሳሰሉ አገራት ላይ ጥቁር ስፖርተኞች አሁንም ድረስ በዘረኝነት ሲዘለፉ፤ ሲንቋሸሹና ዝቅ ተደርገው የሚታዩባቸው አጋጣሚዎች እየተበራከቱ መምጣታቸው ከዘር፤ ከሃይማኖትና ከፖለቲካ ነፃ መሆን የሚገባው ስፖርት ላይ መጥፎ አሻራ እንዲያርፍ እያደረገ ይገኛል። በስፖርት ጥቁሮች አሁን ላይ በየትኛውም ዓለምአቀፍ መድረክ ተፎካካሪ እንዲሆኑ ከማስቻል ባሻገር በትልቅ ደረጃ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ለማሳየት በርካታ ጥቁር ከዋክብት ብዙ ችግሮችን ተጋፍጠዋል። በተለይም ጥቁር አሜሪካውያን አትሌቶች በዚህ ረገድ ያዩት ፈተና ሳይጠቀስ የሚታለፍ አይደለም። አፍሪካውያንም ቢሆኑ በርካታ መከራዎችን ተጋፍጠው ለታላቅ ክብር በመብቃት ለአሁኖቹ አትሌቶች ፋና ወጊ ሆነው እኩልነትን ማንፀባረቃቸው አይካድም። ለዚህም ታሪካዊውን ኢትዮጵያዊ የማራቶን ኮከብ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ በትልቁ የሚነሳ የጥቁር ህዝቦች ኩራት ሆኖ እናገኘዋለን። ኢትዮጵያውያን በስፖርቱ ብቻም ሳይሆን በዓደዋ ድል የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌትና የመዓዘን ድንጋይ ሆነዋል። የጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነው የዓደዋ ድል የሚዘከርበት የካቲት ወር በመላው ዓለምም የጥቁር ህዝቦች መታሰቢያ ሆኖ ይከበራል። በስፖርቱ ዓለም ለእኩልነት የታገሉ ቁንጮ አትሌቶችም በዚህ ወር ሳይዘከሩ አይታለፉም። በእርግጥ በስፖርት መድረክ ዘረኝነትን የታገሉ፤ እኩልነትን ያንፀባረቁና በድላቸው የጥቁር ህዝቦችን አንገት ያቀኑ በርካታ ጥቁር ከዋክብቶች መኖራቸው አይካድም። ከእነዚህ ከዋክብቶች ግን ተፅዕኗቸው ከፍተኛ የነበረ፤ ድላቸው በርካታ ትርጉም የነበረውና በትልቅ ደረጃ የሚነሱትን ሦስት ጀግኖች ብቻ በዓድዋ ድል ዋዜማ ላይ ሆነን በስፖርት ማህደር አምዳችን እንመልከት። አበበ ቢቂላ 1928 ፋሺስት ጣሊያን በአምባገነኑ ቤኒቶ ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን ወረረ፤ ምስጋና ለማይዘነጉት ጀግኖቹ አርበኞቻችን ይግባና ሞሶሎኒና ግብረአበሮቹ ብዙም ሳይደላደሉ ከአገር ቤት በቅሌት ተባረሩ። ከሃያ አራት ዓመታት በኋላ ታላቁ አበበ ቢቂላ ሮምን በባዶ እግሩ ወሮ ዓለምን ጉድ አሰኘ፤ የምን ጊዜም የማራቶን ንጉሡ የአፍሪካውያን ኩራትና የነፃነት ተምሳሌት እንዲሁም፤ የመጀመሪያው ጥቁር የማራቶን ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ በጥቁሮቹ በጀግኖቹ መታሰቢያ ወር የካቲት የጥቁር ህዝቦች ኩራት ሆኖ ከሃምሳ አምስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ዋዜማ በሮም ኦሊምፒክ የፈፀመው ታሪካዊ ጀብድ በመላው ዓለም ያሉ ጥቁር አትሌቶችን በእጅጉ ያኮራና ያነሳሳ ነበር። ጷግሜ 5ቀን 1952 አስራ ሰባተኛው የሮም ኦሊምፒያድ በታላቋ ሮም ጎዳናዎች አንድ ተዓምር ታየ፤ በርካቶች ዓይናቸውን ለማመን ተቸገሩ፤ በአንባገነኑ ሞሶሎኒ አገር በበርካታ ነጮች መሃል አንድ ጥቁር በባዶ እግሩ ታየ። የጥቁር ህዝቦች ተዓምርን ለመቀበል የሚተናነቃቸው ዘረኝነትን በደማቸው ያሰረፁ ነጮች እንዴት ይህ ሊሆን እንደቻለ ግራ ተጋቡ። አፍሪካውያንን ያኮራ ኢትዮጵያውያንን ከልብ ያስፈነጠዘ ታሪካዊ ድል። የአራት ዓመት ታዳጊ ሆኖ እናት አገሩ ኢትዮጵያ በጣሊያን ፋሺስት ስትወረር መጥፎውን ጊዜ ገና ባልጎለበተ የሕፃን አዕምሮው የሚያስታውሰው አበበ ቢቂላ ሃያ ስድስት ዓመታት ጠብቆ ታላቁን የሮም ጎዳና በባዶ እግሩ ወሮ የማይደገመውን ታሪክ ሠራ። ከአራት ዓመት በኋላም 1956 በድጋሜ ጫማ አጥልቆ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፎ ጥቁሮች በማይደፈረው ርቀት አሁን ላይ ቁንጮ እንዲሆኑ መሰረቱን አኖረ። እሱ በከፈተው በርም ቁጥር ስፍር የሌላቸው የማራቶን አትሌቶች ለዘመናት ርቀቱን የግላቸው አድርገው አሁን ድረስ ዘልቀዋል። ጄሴ ኦውንስ ታላቁ የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክ እንደ 1936ቱ በዘረኝነት የተጨማለቀበትን ወቅት ማስታወስ ከባድ ነው። ገና ከጅምሩ አይሁዶችንና ጥቁሮችን ከኦሊምፒኩ ለማግለል እንዲሁም የነጮችን የበላይነት አስተሳሰብ የመደገፍ አባዜ የተጠናወተው ዘረኛው የናዚ መሪ አዶልፍ ሂትለር ውድድሩ በአገሩ ጀርመን እንደሚካሄድ ካወቀ አንስቶ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። ይህ ኦሊምፒክ ብዙ ተቃውሞ ቢገጥመውም ከውድድሩ ራሳቸውን ያገለሉና እንዳይሳተፉ የተደረጉ አይሁዳውያን ነበሩ። በውድድሩ የተሳተፉትም ቢሆኑ በሂትለር ትዕዛዝ የተገለለ የመለማመጃ ሜዳና የውድድር ቁሳቁስ እንዲጠቀሙ ተደርገዋል። ጥቁሮችም በዚህ ኦሊምፒክ ተመሳሳይ ዕጣ ፋንታ የገጠማቸው ሲሆን የበታች እንደሆኑ ለማሳየት ያልተደረገ ጥረት አልነበረም። ይህን ጥረት ሁሉ ውድቅ አድርጎ የሂትለርን ቆሽት ያሳረረ አንድ ክስተት ግን በጥቁሩ አሜሪካዊ አትሌት ጄሴ ኦውንስ ተፈፀመ። ኦውንስ በዚህ የበርሊን ኦሊምፒክ በመቶ፤ በሁለት መቶ፤ በረጅም ዝላይና አራት በመቶ የዱላ ቅብብል ውድድሮች አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጠራርጎ በመውሰድ ጥቁሮች አንገታቸውን ያቀኑበት ነጮች ደግሞ የተሸማቀቁበትና ለመቀበል ያቃራቸውን ድል አጣጣመ። ይህ አልዋጥለት ያለው ሂትለር ግን በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ኦውንስን ላለመጨበጥና ለድሉም እውቅና ላለመሰጠት ራሱን አሳምኖ ስቴድየሙን በድንፋታ ለቆ ወጣ። የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ፍራንክሊን ሩዝቬልትም ቢሆኑ ለኦውንስ ድል እውቅና ሳይሰጡት ቀርተዋል። ኦውንስ ይህ ገድሉ በዘረኛ ነጮች እውቅና ይነፈገው እንጂ ነጮች ወደዱም ጠሉም ከጥቁሮች እኩል እንደሆኑ ልቦናቸው እንዲያምን አስገድዷቸዋል። በአንድ አገር ውድድሮች የነጭና የጥቁር ተብሎ ተከፍሎ በሚካሄድባት አሜሪካም በወቅቱ የኦውንስ ድል ትልቅ ትርጉም ነበረው። በዚህም ኋላ ላይ እኤአ 1976 የአሜሪካውያን ትልቁ ሽልማት የሆነውን የነፃነት ሜዳሊያ ሊሸለም በቅቷል። ኦውንስ ህይወቱን በሙሉም የጥቁሮች መብት እንዲከበር ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ጥብቅና ከመቆም ባሻገር የእሱን ፋና ተክለው ለመጡ ጥቁር አትሌቶች ሁሉ ትልቅ የመንፈስ ብርታት በመሆን ከጎናቸው ሲቆምና ሲሟገት ኖሯል። መሐመድ አሊየምን ጊዜም የቦክስ ስፖርት ንጉሡ መሐመድ አሊ የዓለም የቦክስ ቻምፒዮንና ታላቅ የቡጢ ተፋላሚ ብቻ አልነበረም። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፤ የጥቁር ህዝቦች ሰንደቅ፤ በመላው ዓለም በስፖርትና በታላቅ ስብዕና ተምሳሌትም ጭምር ነው። ብዙዎች ቦክስ ስፖርት ሳይሆን የጥጋበኞች ድብድብ አድርገው ከመሳል አስተሳሰብ አውጥቶ የቦክስን ስፖርት ጥበባዊ ገፅታ በማላበስ ተወዳጅና አሁን ላይ በዓለማችን በአንድ ጊዜ በርካታ ሚሊየን ዶላሮች የሚያሳቅፍ ግንባር ቀደም ስፖርት እንዲሆን ተፅዕኖውን አሳርፏል። መሐመድ የትውልድ ስሙ ካሴስ ክሌይ ቢሆንም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ባሮችን ነፃ ለማውጣት በታገሉ ታላቅ ሰው መታሰቢያነት የወጣለት ስም ነበር፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ የዓለም ከባድ ሚዛን ቻምፒዮን ከሆነ በኋላ በማግስቱ ስሙን ለመቀየር ወሰነ፡፡ የነፃነት ታጋዩን ማልኮለም ኤክስ ከጎኑ አድርጎ በሰጠው መግለጫ «ዘ ኔሽን ኦፍ ኢስላም» የተባለውን ተቋም መቀላቀሉን በማሳወቅ የባርያ ስም ይለው የነበረውን ካሴስ ክሌይ በመቀየር በቀድሞ ስሙ ላለመጠራት ወሰነ። በወቅቱ «ኔሽን ኦፍ ኢስላምን» ይመራ የነበረው ኤልጅያህ መሃመድ እኤአ በ1964 ላይ መሐመድ አሊ የሚለውን ስም ካወጣለት በኋላ እሱን በማፅደቅ እስከ ህይወት ዘመኑ መጨረሻ ተጠራበት። ታሪካዊው ኢትዮጵያዊ አትሌት አበበ ቢቂላ በ196o የሮም ኦሊምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ለጥቁር ህዝቦች የመጀመሪያውን የማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ሲያስመዘግብ መሐመድ አሊም በቦክስ የወርቅ ሜዳሊያ አጥልቆ ነበር። ሁለቱ ታሪካዊ የጥቁር ህዝቦች ከዋክብት ፊርማቸውን ተለዋውጠውም ነበር። ይሁንና መሐመድ አሊ ይህን የወርቅ ሜዳሊያውን ለአገሩ ከማበርከት ይልቅ በሊውስ ቪል ግዛት በሚገኘው የኦሃዮ ወንዝ ጨምሮታል። ሜዳሊያውን ለአሜሪካና ለትውልድ ከተማው ሊውስ ቪል ቢቀዳጅም በርገር የመግዛት መብት ባለመኖሩ ተቃውሞውን ለመግለፅ ነበር ይህን ርምጃ የወሰደው። በ1996 አገሩ አሜሪካ ባስተናገደችው የአትላንታ ኦሊምፒክ ችቦውን እንዲለኩስ ከመደረጉ ባሻገር ወንዝ የጨመረው የወርቅ ሜዳሊያ ምትክ ሌላ ሜዳሊያ በአንገቱ ተጠልቆለታል። በ1970 የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ ሽልማት የተቀበለው መሐመድ አሊ፤ የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነት ተምሳሌት ሆኖም ያውቃል። የተባበሩት መንግሥታት የሰላም መልዕክተኛ ሆኖም ከ1998 እሰከ 2008 በታዳጊ አገራት በመዘዋወር አገልግሏል። ታላቁን የደቡብ አፍሪካ ነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ከእስር እንደተፈቱ በአካል ተገኝቶ ደስታውን ለመግለፅ መሐመድን የቀደመው አልነበረም። አዲስ ዘመን የካቲት 22/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=28169
927
2ስፖርት
የኦሎምፒክ ተሳትፎ ያልተሳካለት ብሄራዊ ቡድን
ስፖርት
March 2, 2020
26
ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ በብዛት ተሳታፊ ከሆነችባቸው የአትሌቲክስና ብስክሌት ስፖርቶች በመቀጠል ይጠቀሳል፤ ቦክስ፡፡ በቦክስ ስፖርት የመጀመሪያው የኦሊምፒክ መድረክ ተሳትፎ እአአ በ1968 በተካሄደው የሜክሲኮ ኦሊምፒክ ሲሆን፤ በወቅቱም አራት ቦክሰኞች ተካፋይ ነበሩ። ከዚያ በኃላ በተካሄዱ ስምንት ኦሊምፒኮች ላይም ሃገሪቷ ስፖርተኞቿን ማሳተፏን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን መረጃ ይጠቁማል፡፡ በመድረኩ ለመጨረሻው ተሳትፎ ካደረገችበት እአአ የ2008 ቤጂንግ ኦሊምፒክ በኋላም ተሳታፊ የሚያደርጋትን እድል ሳታገኝ በመቅረቷ ኢትዮጵያ በስፖርቱ አልተወከለችም፡፡ ከወራት በኋላ ጃፓን በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ የአዘጋጅነት እድሉን ባገኘችበት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፤ ከአትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ቴኳንዶ እና የውሃ ዋና ስፖርቶች በተጓዳኝ ተሳታፊ ለመሆን ያቀደበት ሌላኛው ስፖርት ቦክስ ነበር፡፡ ለእቅዱ መሳካት ይረዳ ዘንድም በማጣሪያ ውድድር ላይ ብሄራዊ ቡድኑ ተካፋይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሴኔጋሏ ዳካር አስተናጋጅነት በተካሄደው በዚህ ቻምፒዮና ላይም ስድስት ወንድ እና አንዲት ሴት ቦክሰኞች፤ በ48፣ 52፣ 57፣ 63፣ 69፣ 75 እና 81 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪ ሆነው ነበር፡፡ ከዳካር የአየር ጸባይ ጋር ለመለማመድ እንዲያስችላቸውም መቀመጫቸውን በአርባ ምንጭ በማድረግ ለረጅም ጊዜ በልምምድ ላይ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥቂቱ መነቃቃት የታየበት የቦክስ ስፖርት በአህጉር አቀፍ ውድድሮች ላይ ሜዳሊያዎችን ማስቆጠርና ተወዳዳሪነቱን በማስመስከር ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ትናንት ወደ ሃገሩ የተመለሰው ብሄራዊ ቡድኑ በማጣሪያው የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ቶኪዮ ያቀናል የሚል ከፍተኛ ግምትም አግኝቶ ነበር፡፡ በሴኔጋል በነበራቸው ቆይታም የመጀመሪያዎቹን ዙሮች በብቃት በማለፍ ያላቸውን ተስፋ ማሳየት ችለዋል፡፡ ዙሩ እየገፋና እየከበደ መሄዱን ተከትሎም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ ይሁን እንጂ ሶስት ቦክሰኞች እስከ ስምንት ባለው ደረጃ በመግባት ጥቂት ትኩረት ቢያገኙ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚችሉ ማረጋገጣቸውን በኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን የውድድር ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ተስፋዬ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡ በአልጀሪያ በተካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ እንዲሁም በሞሮኮ ራባት የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረው የ48 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪው ዳዊት በቀለ ስምንት ውስጥ ከገቡት መካከል አንዱ ነው፡፡ የ57 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪው ፍቅረማሪያም ያደሳ እና በ81 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪው ሰይፈ ከበደም ስምንት ውስጥ መግባት የቻሉ ቦክሰኞች ናቸው፡፡ ቡድኑ ባይሳካለትም ወደ ሴኔጋል ያቀናው በኦሊምፒኩ ተካፋይ ለመሆን የሚያስቻለውን ውጤት ለማስመዝገብ ካልተቻለ ደግሞ እስከ አራት ያለውን ደረጃ ለመያዝ ነበር፡፡ ነገር ግን የትኩረትና የልምድ ማነስ እንዲሁም በልምምድ ወቅት ባጋጠመው የቁሳቁስ እጥረት ወደ ታላቁ የስፖርት መድረክ ማለፍ ሳይቻል መቅረቱን ባለሙያው ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህ ባሻገር ዳኝነት ላይም መስራት እንደሚገባም ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ አዲስ ዘመን የካቲት 23/2012  ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=28199
331
2ስፖርት
የ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ በተመራጭ ፎቶ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንደሚሆን ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
11
ጽጌረዳ ጫንያለውአዲስ አበባ፡- ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ መራጭ የሚያውቀውን ሰው በትክክል አውቆ እንዲመርጥ በፎቶ የተደገፈ መረጃ እንደሚሰጠውና ሙሉ ምርጫው በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሁም የመረጃ ማስገቢያ ባለሙያ የተመደበበት ሆኖ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ። ስድስተኛው አገራዋ ምርጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ በጊዜያዊነት ቀን ተይዞለታል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተወያየበት ወቅት እንደተገለፀው፤ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ ጊዜያዊ የቀን ቀጠሮ የተያዘለት በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በርካታ አዳዲስ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎች ይተገበራሉ። ከእነዚህ መካከልም መራጭ ማንነቱንና ምንነቱን እየለየ እንዲመርጠው የሚያስችል ተመራጭ እንዲኖረው ለማድረግ በፎቶ የተደገፈ ምርጫ መሆኑ ተጠቃሽ ሲሆን፤ ሌላው በባለሙያ የተደገፈ መረጃ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ላይ እንዲኖር ለማድረግ የመረጃ ማስገቢያ ባለሙያ ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸው ነው። አጠቃላይ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ተግባሩ የዘንድሮው ምርጫ ለየት የሚያደርገው እንደሆነ የገለፀው ቦርዱ፤ ከምርጫ ምዝገባ እስከ ውጤት ድረስ ያሉ ተግባራት በቴክኖሎጂው አማካኝነት የሚከናወኑ እንደሆነም አስታውቋል። የምርጫ ምልክቶችም ቢሆኑ በሚገባ እንዲመረመሩ የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱንም ጠቁሟል። ቦርዱ በዕለቱ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ፊርማ ማሰባሰቡ ሂደት ላይ፤ የእጩ ምዝገባና ምርጫው የሚደረገው በኮቪድ ውስጥ ሆነን በመሆኑ የወረቀት ልውውጦችና የሰው ለሰው ግንኙነቶች በተቻለ መጠ ንግድ ያልሆኑትን መቀነስ ስለሚያስፈልግ እንዲሁ የፓርቲ ድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ላይ የታዩ ውስብስብ ሂደቶች በመኖራቸው ምክንያት በሕግ የተቀመጠውን ምርጫ ቦርድ መወሰን ስለማይችል ምክርቤቱ ምላሽ እንዲሰጥበት ማስገባታቸውን የገለፁት ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ናቸው። ወይዘሪት ብርቱካን እንደተናገሩት፤ ምርጫው በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ከማድረግ ጎን ለጎን ለፖለቲካ ፓርቲዎች የተደላደለ ሜዳ የመፍጠሩ ግዴታ የቦርዱ ሃላፊነት ነው። መንግሥትም ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የመሥራት ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል። ከዚህ ባለፈም ቀደም ሲል በነበሩ ምርጫዎች የተስተዋሉ የአሠራር ግድፈቶች እና ጫናዎች አሁን ላይ ቢሆን በታችኛው የመንግሥት መዋቅር አካባቢ በተወሰነ መልኩ የሚስተዋሉ በመሆኑ በዚህኛው ምርጫ እንዳይደገሙ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል።እንደብልጽግና ይህ ምርጫ የሚታየው በማሸነፍና በመሸነፍ ጠባብ ትርጉም ሳይሆን ታሪካዊ ክስተት በመፍጠር ታሪክ መሥራት እንዴት እንደምንችል አስበን እየተንቀሳቀስንበት ነው፣ ያሉት ደግሞ ገዢውን የብልጽግና ፓርቲን ወክለው በመድረኩ የተገኙት አቶ ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው፤ ታሪካዊ ምርጫ፣ ከተሸነፍን በሰላማዊ መንገድ ማስረከብ እንጂ እንደባለፈው የባከነ ዕድል እያሉ ከንፈር እየመጠጡ መቀጠል አንፈልግም ብለዋል። ካሸነፍን የበለጠ ብልጽግናን እናረጋግጣለን፤ ከተሸነፍን ደግሞ በታሪክ የሚጻፍ ሥራ ሠርተን ቦታውን ለተተኪው እንለቃለን። ምክንያቱም ይህ ምርጫ ለትውልዱ የሚሰጠውን ትርጉምም ስለምናውቅ ማጭበርበር ሳይሆን እውነተኛ ዴሞክራሲን በአገር ላይ ማሳየትም ዋና አላማችን ነው ሲሉም አብራርተዋል።ብልጽግና እንከን የለበትም፣ ንፁህ አባል ያለበት ነው ማለት አይቻልም የሚሉት አቶ ዛዲግ፤ የምርጫውን ሕግ የተላለፉ ሁሉ ቅጣታቸውን እንዲያገኙ እናደርጋለን ብለዋል። ከዚህ በፊትም የተለያዩ ስህተቶችን በማየታችን በሚገባ መፍትሄ ስንሰጥ ቆይተናል፤ ስለሆነም አሁንም አለ የተባለውን ነገር ከሥር መሠረቱ አጥንተንና አይተን መፍትሄ የምናስቀምጥ ይሆናል፤ ለዚህ ደግሞ መጀመሪያውኑ አባሎቻችን ሕግ ሲጥሱ መቃወም ያለብን እኛ በመሆናችን ይህንን ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።የትግራይ ክልል ምርጫ ቋሚ የሥራ አመራሮች እስኪመደብ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ በመድረኩ የተጠቀሰ ሲሆን፤ የአገር አቀፍ ምርጫው አጠቃላይ ውጤትም ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋ እንደሚሆንም ታውቋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38161
424
0ሀገር አቀፍ ዜና
ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ለ“ትንሿ ኢትዮጵያ” ሕጋዊ እውቅና ሰጠች
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
11
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ለ“ትንሿ ኢትዮጵያ” ሕጋዊ እውቅና ማግኘቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍፁም አረጋ በማህበራዊ ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ አስታውቁ።አምባሳደሩ እንዳስታወቁት፤ የተሰጠው እውቅና ሁለቱ አገራት ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማሳደግ ባሻገር በማህበራዊና በባህላዊ ዘርፉ የሚደረጉ ግንኙነቶችን ይበልጥ የሚያጠናክረው ነው።አምባሳደር ፍፁም አረጋ የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አስተዳደር እና የአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለ”ትንሿ ኢትዮጵያ” እውቅና እንዲያገኝ ላበረከቱት ድጋፍና አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38158
67
0ሀገር አቀፍ ዜና
መረጃ ፈላጊዎች ባሉበት ሆነው መረጃ ማግኘት የሚችሉበት የተቀናጀ የመረጃ ሥርዓት ይፋተደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
31
መላኩ ኤሮሴቢሾፍቱ፡- የመረጃ ፈላጊዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በይነ መረብን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ማግኘት የሚችሉበት የተቀናጀ የመረጃ ሥርዓት ይፋ ተደረገ፡፡አዲሱን የተቀናጀ የመረጃ ሥርጭት ሥርዓቱን የፌዴራል፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ሴክተር መሥሪያ ቤቶች እንዲጠቀሙበት ለማድረግና ሥርዓቱን የማስተዋወቅ ሥልጠና መርሃ ግብር በማዕከላዊ ስታትስቲክ ኤጀንሲ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፖፑሌሽን ፈንድ (UNF­PA) ትብብር በቢሾፍቱ ተካሂዷል፡፡በስልጠና መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አሳልፈው አበረ እንደተናገሩት፤ ከዚህ በፊት በነበረው የመረጃ ሥርጭት ሥርዓት የመረጃ ተጠቃሚዎች በአካል በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በመገኘት በወረቀት፣ በሲዲ እና በፍላሽ መረጃዎችን ሲቀበሉ ነበር፡፡ ይህ ሥርዓት ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ አንፃር አዋጭ ባለመሆኑ አዲስ የተቀናጀ የመረጃ ሥርጭት ሥርዓት ተዘጋጅቷል፡፡አዲስ ይፋ የተደረገው ሥርዓት ውስጥ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የሚያሰባስባቸው ሳይንሳዊ እና ደረጃቸውን የጠበቁ መረጃዎች እንዲሁም ክልሎች የሚያጠናቅሯቸው የአስተዳደር መረጃዎች ተዓማኒነታቸው እና ጥራታቸው ተረጋግጦ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡ በዚህም የቴሌኮም መሠረተ ልማት ባለበት በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ የሚገኝ ዜጋ አዲስ ወደ ተዘጋጀው ድረ ገፅ በመግባት የሚፈልገውን መረጃ መጠቀም ይችላል፡፡እንደ አቶ አሳልፈው ማብራሪያ፤ የመረጃ ተጠቃሚዎች በአዲሱ ሥርዓት ውስጥ በመግባት የናሙና ጥናት፣ የቆጠራ፣ የአስተዳደር መዛግብት እና ከሌሎች ምንጮች የተሰበሰቡ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ እና ለሚፈልጉት ዓላማ እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል፡፡ሥርዓቱም በሥራ፣ በትምህርት ቤት እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች ሆነው የሚፈልጉትን መረጃ ከተቀናጀ የመረጃ ሥርዓት አውጥተው እንዲጠቀሙ የሚያስችል በመሆኑ፤ ከዚህ ቀደም የመረጃ ተጠቃሚዎች መረጃ ከኤጀንሲው በአካል መጥተው ለመውሰድ በሚያደርጉት ጥረት ያጋጥማቸው የነበረ እንግልት እና ጉዞ የሚያስቀር መሆኑን ነው አቶ አሳልፈው ያብራሩት፡፡ከዚህም ባሻገር መረጃ ለመውሰድ በሚደረገው እንቅስቃሴ ይጠፋ የነበረው ጊዜ፣ ጉልበት እና ገንዘብ ለመቆጠብ የሚያስችል ሲሆን፤ ሥርዓቱ የመረጃ ተጠቃሚዎችን እርካታ ከማሳደግ ባሻገር፤ መሥሪያ ቤቱ የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት እንደሚያስችለውም አስረድተዋል፡፡እንደ አቶ አሳልፈው ማብራሪያ፤ ሥርዓቱ በርካታ መረጃዎችን የመያዝ አቅም ያለው ነው፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩ መረጃዎችንም ወደዚህ ሥርዓት ውስጥ የማስገባት ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ እስካሁን ድረስ የ1987 እና የ1999 የሕዝብና ቤት ቆጠራ መረጃዎች ገብተዋል፡፡ እነዚህ መረጃዎች በዚህ ሥርዓት ውስጥ መግባታቸው ትልቅ ፋይዳ አላቸው፡፡ለተለያዩ ዓላማዎች የተለያዩ መረጃዎችን የሚፈልጉ ግለሰቦች እና ተቋማት ከአሁን ጀምሮ ከአዲሱ ሥርዓት መረጃ በመውሰድ መጠቀም እንደሚችሉም አቶ አሳልፈው ጠቁመዋል፡፡የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፖፑሌሽን ፈንድ ተወካይ አቶ አለማየሁ ገብረጻድቅ በበኩላቸው፤ ሥርዓቱን የመዘርጋት ሥራ ዓመታትን እንደወሰደ ገልፀው፤ አማራ እና ደቡብ ክልል ሥርዓት በመዘርጋት ጥሩ ጅምር ማሳየታቸውን አብራርተዋል፡፡ አንዳንድ የውጭ ተቋማት ጭምር መረጃዎችን ከአዲሱ ሥርዓት ወስደው እየተጠቀሙ መሆኑን በመጠቆምም፤ ሌሎች ክልሎችም በአጭር ጊዜ ውስጥ አሠራሩን ወደ መተግበር እንዲገቡ ይሠራል ብለዋል፡፡አዲሱ የመረጃ ማሰራጫ ሥርዓት ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ሰፊ ልዩነት እንዳለው የጠቆሙት አቶ አለማየሁ፤ በአዲሱ ሥርዓት አንዴ መረጃው ወደ ሥርዓቱ ውስጥ ከገባ መቀየር የማይቻል መሆኑ ለየት እንደሚያደርገው አብራርተዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38159
368
0ሀገር አቀፍ ዜና
መቀሌ ያሉ የመንግሥት መሥርያ ቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
10
 አማን ሚካኤል መስፍንመቀሌ፡- መቀሌ ያሉ የመንግሥት መሥርያ ቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ በሰማዕታት አደራሽ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት፤ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የደረሰው ክህደትና ጥቃት ያወገዙት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በአጭር ጊዜ ሕግ የማስከበሩን ሥራ በማጠናቀቁ አመስግነዋል። በአንፃሩ መቀሌ ያሉ የመንግሥት መሥርያ ቤቶች ህዝብ እንዳያገለግሉ በህወሓት ጁንታ ሆን ተብለው እንዲዘረፉና እንዲወድሙ ተደርጓል፤ በዚህም ህብረተሰቡ እየተጉላላ ይገኛል። የህወሓት ጁንታ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የሕግ ታራሚዎችን ሆን ብሎ በመቀሌ በትኖ ሄዷል ያሉት ተወያዮቹ፤ በእነዚህ ከማረሚያ ቤት ሆን ተብለው በተለቀቁ የሕግ ታራሚዎች ምክንያት በከተማው የፀጥታ ችግር እንዲፈጠር ተደርጓል ሲሉም ነው ያስታወቁት። የሀሰት ወሬ በመቀሌ ከተማ እየተነዛ ህዝቡ እየተሸበረ ስለሆነ አስተዳደሩ ይሄን ያጥራልን ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፤ ነጋዴው ከመሃል አገር ሸቀጥ እንዳያመጣ “ጦርነት አላለቀም” በሚል ወሬ እየተነዛ ወደ ሥራ እንዳይገባም አድርገውታል ነው ያሉት።በአገር ውስጥም ይሁን በውጭ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ጊዚያዊ አስተዳደሩንም ሆነ ህዝቡን ማገዝ አለበት ያሉት ተወያዮቹ፤ በደቡብ ትግራይ እና ምዕራብ ትግራይ አካባቢ ያሉ ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድ መፈታት አለበት ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል። የሰሜን ዕዝ አዛዡ ጄነራል በላይ ስዩም በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መከላከያ የአገር ዳር ድንበርን የሚያስከብር ሃይል ነው። ነገር ግን ጁንታው የገደለው ይሄንን ሃይል ነው በማለት የተፈፀመውን ክህደትና ግፍ ለተወያዮቹ አብራርተዋል። “እንደመከላከያ ጓዶቻችን በጁንታው ተገድለዋል፣ የሠራዊቱ ንብረት ተዘርፏል፤ እንደ አገርም በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅዕኖ ተፈጥሯል” ያሉት ጄነራሉ፤ የዘጠና ዓመት አዛውንቶች መጥተው ይመሩናል ብላችሁ ተስፋ እንዳታደርጉ፤ በእርግጠኝነት የምነግራችሁ ጁንታው ከዚህ በኋላ አይመለስም፤ ስለዚህ ተረጋግታችሁ ጊዚያዊ አስተዳደሩን ማገዝ አለባችሁ” ሲሉም ለመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።በውይይት መድረኩ ላይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፣ የመቀሌ ከንቲባ አቶ ኣታኽልቲ ሃይለሥላሴ እና የሰሜን ዕዝ አዛዥ ጀነራል በላይ ስዩም የተገኙ ሲሆን፤ በወቅቱም የትግራይ ህዝብ የህወሓት ጁንታ ተመልሶ ይመጣል ከሚል ሃሳብ መውጣት እንዳለበት የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር አብረሃም በላይ ተናግረዋል፡፡በዚሁ መድረክ ላይ ለተነሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ምላሽ እየሰጡ ካሉት አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራሩ ዶክተር አብረሃም በላይ እንዳሉት፤ በከተማዋም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ላይ የህወሓት ጁንታን በተመለከተ “ተመልሰው ይመጣሉ” የሚል የሀሰት ወሬ እየተሰራጨ ይገኛል። ይህ የተሳሳተ መሆኑን ህዝቡ ማወቅ አለበት።ህዝባችን በውሸት ሊደናገር አይገባም ያሉት ዶክተር አብረሃም፤ ድሮ ጃንሆይ ከወረዱ በኋላ ህዝቡ ይመለሳሉ ብሎ ሲጠብቅ ነበር፤ ደርግም ከወደቀ በኋላ ይመለሳል ብሎ የሚጠብቅ ሰው ነበር። አሁንም እንደዛ እየጠበቀ ያለ ሰው አለ። ይህ መሆን የለበትም” ሲሉ ተወያዮቹ ላቀረቡት ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ የመንግሥት ሠራተኛ ማለት የህዝብ አገልጋይ ነው፤ ሁሉም ወደ ሥራው ገብቶ ከልብ ማገልገል አለበት። በፊት ህዝብ ያሰቃዩ፣ ጥሩ ሥነ ምግባር የሌላቸው ማልያ ቀይረው ወደ አመራር እንዳይመጡ ህዝቡ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጎን ሆኖ ማገዝ ይኖርበታል፡፡ዶከተር ሙሉ አያይዘውም፤ “የትግራይን ህዝብ ከምትናገረው ስትሰማው ብዙ ትምህርት ትወስዳለህ። እኛ እየሠራን ነው፤ የቀረውን ህዝቡ ሊያግዘን ይገባል። ህዝባችን ያለንን ልንሰማ፣ ራሱ የፈለገውንም ሊመርጥ ይገባል” ሲሉ ለተወያዮቹ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38160
435
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ100 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
13
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ100 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ የብድር ስምምነቱን በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ያስሚን ወሀብሬቢ እና በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ተፈርሟል።በስምምነቱ ወቅት ሚኒስትር ዴታዋ ያስሚን እንደተናገሩት፤ ከዓለም ባንክ የተገኘው የ100 ሚሊዮን ዶላር የብድር በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍና አዳዲስ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያግዛል። ገንዘቡም በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የክህሎት ስልጠና አግኝተው ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል።አበዳሪ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትንና ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ቢሮዎች የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚረዳቸው የጠቆሙት ሚንስትር ዴኤታዋ፤ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የምታደርገውን የልማት ሥራ ለመደገፍ ለሰጠው የፈጣን ምላሽም አመስግነዋል።በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን በበኩላቸው፤ ብድሩ በአነስተኛና ጥቃቅን ዘርፍ የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶችን ለማገዝ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተደረገው የብድር ስምምነትም በአነስተኛና ጥቃቅን ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች ክህሎታቸውን በማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል፣ አዳዲስ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ገቢን ለማሳደግ እንደሚስችላቸው ገልፀዋል።የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ሴቶችና ወጣቶችን ለማበረታታት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ የሚያደርገው ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ የብድር ስምምነቱ ከ38 ሺህ በላይ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ የሚውል መሆኑንም አንስተዋል። የሚገኘው ገንዘብ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ መቀሌ፣ አክሱም፣ ባህር-ዳር፣ ጎንደር፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ አዳማ፣ አሰላ እና በመላ አገሪቱ በሚገኙ ሌሎች 89 የሥራ ዕድል መፍጠሪያ ማዕከላት (ሳተላይቶች) ተግባራዊ እንደሚሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ የገንዘብ እጥረት ያለባቸውን ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ብድር የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት ብሎም ኮቪድ-19 በሥራቸው ላይ ጫና ያሳደረባቸውን ሴቶች ለመደገፍ እንደሚያግዝ ተነግሯል።በአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ሥራ ፈጣሪ ሴቶችም ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ከፍተኛ ማስያዣ ብድር ለማግኘት እንደሚያስችላቸው፤ እንዲሁም በአነስተኛና ጥቃቅን ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ የካናዳ፣ ጣሊያን፣ የጃፓን መንግሥትና እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እገዛ ሲያደርጉ የቆዩ መሆኑን እና ወደ ፊትም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ስለመነገሩ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38170
266
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የተፈናቀሉ ወገኖች ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን ተናገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
17
መሀመድ ሁሴን አዲስ አበባ፡- በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች በንፁሃን ላይ ከተፈፀመው ጥቃት አምልጠው በቡለን ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮች በረሃብና በጥም የተነሳ ለሞት አደጋ መጋለጣቸውን ተናገሩ፡፡ አስተያየታቸውን ትናንት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰጡት እነዚሁ ተፈናቃዮች፤ ከግድያው ለማምለጥ ምንም ነገር ሳይዙ ከቤታቸው በመውጣታቸው የተነሳ አሁን ላይ የሚበሉትና የሚጠጡት እንዳጡና ከመንግሥትም ያገኙት ድጋፍ እንደሌለ በምሬት ተናግረዋል። የስምንት ልጆች አባት የሆኑትና በበኩጂ ቀበሌ ከአስር ዓመታት በላይ የኖሩት አርሶ አደር ደረጀ በየነ እንደገለፁት፤ ከሞት አምልጠውና ከአርባ አምስት ኪሎ ሜትር በላይ በእግራቸው ተጉዘው ቡለን ወረዳ መድረስ ቢችሉም፣ በርሃብና በጥም የተነሳ ሌላ ሞት እንደተጋፈጡና ጠያቂ የመንግሥት አካል እስካሁን አላገኙም። በወረዳው ሥር የሚገኙ ሁሉም የቀበሌ ነዋሪዎች የእግር መርገጫ እስኪጠፋ ድረስ በቡለን ወረዳ ተሰባስበው በረሃብ እየተቆሉ ይገኛሉ ያሉት አርሶ አደር ደረጀ፤ ‹‹ህይወታቸውን ካጡት እህት ወንድሞቻችን ሐዘንና ድንጋጤ ሳንወጣ ይዘን የሸሸናቸውን ልጆቻችንን ልናጣ የምንችልበት አደገኛ የረሃብ ችግር ውስጥ ወድቀናል፡፡ ጠያቂ አካል አላገኘንም፡፡ ትምህርት ቤቶች እና አዳራሾች በተፈናቃዮች ሞልተው ተጨናንቀዋል፡፡ ህፃናት ልጆቻችን የሚልሱት የሚቀምሱት አጥተዋል፡፡ በዚህ የተነሳም በከፍተኛ ጭንቀት ላይ እንገኛለን›› ሲሉ ሀሳባቸውን በምሬት ገልፀዋል፡፡ ‹‹በፍራቻና በሥጋት ሰቀቀን ውስጥ መኖር ከጀመርን ዓመት አልፎናል፡፡ ከወረዳና ከክልል የሚመጡ አመራሮች የጉሙዝ ማህበረሰብን ብቻ ለይተው ይሰበስባሉ፡፡ ለእኛ ዞረው ሰላም ነው፤ ምንም ችግር አይደርስባችሁም እያሉ ሲያዘናጉን ኖረዋል፡፡ ስለዚህ ከጀርባ ሌላ የጭፍጨፋ ሴራ እየተዘጋጀ ሕዝቡ እንዳይነቃ እና ወደሌላ አካባቢ እንዳይሸሽ ሲደረግ ኖሯል፡፡ በዚህ የተነሳም ከበኩጂ ብቻ ያለቀው ሰው ብዙ ነው፡፡ እኔ በዓይኔ ተሰብስቦ የተመለከትኩት 207 አስከሬን ነው” ያሉት አርሶ አደር ደረጀ፤ የወንድማቸው አምስት ልጆችና ባልና ሚስትን ጨምሮ ሰባት ቤተሰባቸው እንደተገደሉባቸው በሐዘን ተናግረዋል፡፡ የጭላንቆ ቀበሌ ነዋሪው የሆኑት ሌላው አስተያየት ሰጪ አርሶ አደር ወንድማገኝ ሻምበል በበኩላቸው፤ የተፈፀመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ አስከፊ ከመሆኑም በላይ በህይወት የተረፍነውም ለከፍተኛ መከራ ዳርጎናል ብለዋል፡፡ “ህፃናት እና ሴቶች ከጭፍጨፋው አምልጠው በቡለን ወረዳ በመሰባሰብ በከፍተኛ ረሃብ ላይ ወድቀዋል፡፡ ማንም የሚጠይቅ አካል የለም፡፡ በዚህ የተነሳ ከፍተኛ ተጨማሪ እልቂት መፈጠሩ አይቀርም” ሲሉ አርሶአደሩ ሥጋታቸውን አስረድተዋል፡፡ አመራሩ የችግሩ ዋና አካል መሆኑን ያነሱት አርሶ አደር ወንድም አገኝ ፤ ‹‹ከወረዳ ወደ ቀበሌ የሚመጡ አመራሮች እኛን ሊያስገድሉን ነበር፡፡ ከጭላንቆ ቀበሌ ሩጠን በማምለጥ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አዲስ ዓለም ከምትባል ቀበሌ ገብተን ተቀመጡ መከላከያ ሠራዊት መጥቶላችኋል ብለው አታለሉን። በዚህም የተነሳ ወንድማችን በአራት ቀስት ተመትቶ ሞቷል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሕብረተሰቡ አብሮ ከጉምዝ ብሔረሰቦች ጋር ቡና የሚጠጣ ሕዝብ ነው ያሉት አርሶ አደሩ፤ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እኛ ወደ ማሣ ሥራ ስንሄድ ከወረዳ ከሚመጡ አመራሮች ጋር ብቻቸውን ይመክራሉ፤ በዚህም የተነሳ ጥቃቱ እየጨመረ መጥቷል›› ብለዋል፡፡ “ብዙ ወገኖቻችንን በግድያው ከማጣታችን በላይ በመከራ ላይ መከራ፣ በችግር ላይ ችግር እያሰቃየን እንገኛለን፡፡ የሦስት ቀን አራስ ህፃን ልጅ በዘንቢል ይዘን ነው የወጣነው፡፡ አዝመራዬን ወቅቼ 180 ኩንታል ሜዳ ላይ እንደደረደርኩት ትቼው ወጥቻለሁ፡፡ መኪና እንኳን ማግኘት አልቻልንም፡፡ አምልጠን የወጣነውም በእግራችን ነው፡፡ ባዶ ራቁታችንን ወጥተን ቡለን ብንደርስም ሌላ መከራ ነው የጠበቀን፡፡ ወድቀን ያለነው ከሕብረተሰቡ ላይ ነው፡፡ እኔ አመራር ነኝ ብሎ ተፈናቃዮችን ያነጋገረና የጠየቀ አካል እስካሁን የለም›› በማለት ብሶታቸውን ተናግረዋል፡፡ በጉሙዝ ማህበረሰብ እና በሌላው ሕብረተሰብ መካከል ምንም አይነት ችግር እንደሌለ የገለፁት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ “የሚያስፈጁን በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጣቸው አመራሮች እኩይ ድርጊት በመሆኑ አጥርቶ እርምጃ መውሰድ እና የተፈናቀለውን ማቋቋም አስፈላጊ ነው” ሲሉ መፍትሄ ያሉትን ጠቁመዋል፡፡ እንደ ዝግጅት ክፍል የነዋሪዎቹን አስተያየት በመያዝ ወደሚመለከታቸው የቤንሻንጉል ክልል የሥራ ኃላፊዎች በመደወል ጉዳዩን ለማጣራትና አስተያየታቸውን እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ሆኖም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለኢቢሲ በሰጡት አስተያየት፤ በግድያው እጃቸው አለበት ተብለው የሚጠረጠሩት አመራርም ይሁን፣ ግለሰቦችም ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል። “አሁንም ቢሆን በህብረተሰቡ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ በግጭቱ ላይ የአመራሮች ተሳትፎ አለበት የሚል ነገር አለ፡፡ እኛ ዝግ አላደረግነውም፤ እንደክልል መንግሥት የሚወራው ወሬ እንደተጠበቀ ሆኖ የማጥራት ሥራዎች በመሥራት ተጨባጭ ማስረጃዎች ስናገኝ ማንኛውም ሰው ወደ ሕግ እንዲቀርብ እያደረግን ነው ያለነው” ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ። አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=38181
545
0ሀገር አቀፍ ዜና
በትግራይ ክልል ያሉ ኢንዱስትሪዎችን ሥራ ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
13
ፋንታነሽ ክንዴአዲስ አበባ፡-ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ሥራ ለማስጀመር እየሠራ መሆኑን አስታወቀ። በክልሉ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋርም ውይይት አድርጓል።የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዮሐንስ ድንቃየሁ በትግራይ ክልል ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ትናንት ውይይት ባካሄዱበት ወቅት እንደገለጹት፤ በክልሉ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ያሉበት ደረጃ እየተጣራ ሲሆን፤ ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በትግራይ ክልል በተወሰደው ሕግ ማስከበር እርምጃ ወቅት የተጎዱ ኢንዱስትሪዎች ካሉ በትክክለኛ መረጃ ላይ በመመስረት ተገቢውን ድጋፍ አግኝተው በተቻለ ፍጥነት ወደሥራ እንዲመለሱ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህንንም ተከትሎ በኢንዱስትሪዎች ላይ የደረሰውን ችግርና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ የሚያጠና ቡድን በሚኒስቴሩ መቋቋሙን አስታውቀዋል። በውይይቱ ላይ የተገኙ ባለሀብቶችም በሕግ ማስከበሩ ምክንያት ፋብሪካቸው ላይ የደረሰውን ጉዳትና ከመንግሥት የሚፈልጉትን ድጋፍ አቅርበዋል። በወቅቱ እንደገለጹትም፤ የፋብሪካዎችና ማምረቻ መሣሪያዎች ውድመት፣ ለሠራተኛ ደመወዝ ለመክፈል መቸገር፣ የወደብ ኪራይ፣ ምርት ለማቅረብ ውል ፈጽመው በወቅቱ ማቅረብ አለመቻል፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ከጉምሩክና ባንክ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች በባለሀብቶቹ ከተነሱት ችግሮች መካከል ናቸው። አንዳንድ ባለሀብቶች በደረሰባቸው ከፍተኛ ውድመት ምክንያት መንግስት ከፍ ያለ ድጋፍ ካላደረገላቸው ወደ ሥራ ለመመለስ እንደሚቸገሩ ሲገልጹ፤ ሌሎች ደግሞ በፋብሪካቸው ላይ የከፋ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው በመግለጽ የተወሰነ እገዛ ካገኙ በአጭር ጊዜ ሥራ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ እንዳሉት፤ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በአጭር ጊዜ፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን እየለዩ በፍጥነት እየፈታ ይሄዳል። ባለሀብቶችም ትክክለኛ መረጃ በመስጠት የሚያስፈልጋቸውን እገዛ እንዲጠይቁ አሳስበዋል። ከወደብ፣ ከመሰረተ ልማትና ከጉምሩክ ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥ አብራርተዋል።በቅርቡ ሥራ መጀመር የሚችሉና የውጭ ምንዛሬ ችግር ያለባቸው ባለሀብቶች የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ በብሔራዊ ባንክ መፈቀዱን በመግለጽም፤ ሥራ ማስኬጃ የሚፈልጉ ካሉም ተገቢው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል። ኢንዱስትሪዎችም ሠራተኞችን ሳይበትኑ በተቻለ ፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38172
256
0ሀገር አቀፍ ዜና
«ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለግለሰብ እና ለቡድን ጥቅም ሲባል በእሳት መጫወት አደጋው ከፍተኛ ነው» ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት
ሀገር አቀፍ ዜና
December 27, 2020
8
 ዳንኤል ዘነበአዲስ አበባ፦ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለግለሰብ እና ለቡድን ጥቅም ሲባል በእሳት መጫወት አደጋው ከፍተኛ መሆኑ፤ በእሳት መጫወቱ ካልተጠነቀቁ ማንንም ወደማይምር ሰደድ እሳት እንደሚለውጥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አሳሰቡ።አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በቀን፣ በማታ ያሰለጠናቸውን 4ሺህ 87 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሰላም ሚኒስትርና ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በተገኙበት ትናንት አስመርቋል። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ለተመራቂ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት፤ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለግለሰብ እና ለቡድን ጥቅም ሲባል በእሳት መጫወት አደጋው ከፍተኛ ነው። በእሳት መጫወቱ ካልተጠነቀቁ ማንንም ወደማይምር ሰደድ እሳት ይለወጣል። እኔ ላይ አይደርስም ማለት የዋህነት ነው፤ ይህንን ደግሞ ከሌሎች ሀገሮች መማር ይገባል። በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ንፁሃን ዜጎቻችን እና ለፍቶ አደር ሕዝባችን በማንነት፣ በዘር እና በሃይማኖት ምክንያት ውድ ሕይወታቸውን እጅግ ዘግናኝ በሆነ መንገድ እያጡ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቷ፤ በሕይወት የመኖር መብትን የቀደመ ሌላ መብት ባለመኖሩ በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል ንፁሃን ሕይወታቸውን እንዲያጡ ማንም መፍቀድ እንደሌለበት ተናግረዋል።ከተደገሰልን እልቂት ለማዳን ሕግን የማስከበር ተግባራት በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ ለሁላችንም ተስፋ ሰጪ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፤ ሞትን እና ቀውስን የሚደግሱልን እንዳሉ አይተናል እያየንም ነው፤ በታሪካችን የሀገራችንን ኅልውናን የሚፈታተኑ አደጋዎች ጥለውብን ካለፉት ጥቁር ጠባሳዎች ተገቢውን ትምህርት ወስደን ማንኛውንም ስጋት አራግፈን በጋራ መነሳት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፣ «ዛሬ የተመረቃችሁ ተማሪዎች የሕይወታችሁን አዲስ ምዕራፍ ጀምራችኋል፤ ኢትዮጵያን ነገ የምትመሯት፣ የምታስተዳድሯት፣ የምትታገሉላት፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች የምትወክሏት እናንተ ናችሁ። የምትኮሩባት ሀገር ብዙ ተስፋ ያላት መሆኗ የማያጠራጥር ሲሆን፣ ያሳለፍናቸው እና እያሳለፍነው ያለው ጊዜ ግን ብዙ ፈተናዎች የተጋረጠበት ነው። እነዚህ የተጋፈጥናቸው ፈተናዎች ያነጣጠሩት በአንድነታችን፣ በሀገር ሉዓላዊነት፣ በኅልውናችን እና በሰላማዊ ዜጎች በሕይወት የመኖር መሠረታዊ መብት ላይ በመሆኑ ልዩ ትኩረት የሚሹ ናቸው፤ ዛሬ የሕይወታችሁን አዲስ ምዕራፍ ስትጀምሩ ልትጽፉበት የተዘጋጃችሁት አዲስ ነጭ ገጽ በታሪክ ስህተት እንዳይበላሽ፣ እንዳይበከል በእጅጉ ተጠንቀቁ» ሲሉ ተመራቂ ተማሪዎች ኢትዮጵያን እንዲጠብቁ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ አስገንዝበዋልም። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በበኩላቸው፤ የዘንድሮው የምረቃ ሥነ ሥርዓት በተለያዩ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ክስተቶች፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የተነሳ ከቀደሙት የምረቃ በዓላት በእጅጉ የሚለይ መሆኑን ገልጸዋል። የመማር ማስተማር ሂደቱ በተለይ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ቢቋረጥም፤ ተማሪዎቹ የማካካሻ ትምህርት መውሰዳቸውን አስታውሰዋል። በዕለቱም ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 4ሺህ 87 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችንለማስመረቅ መብቃቱን አመልክተዋል። ከተመረቁት አጠቃላይ ተማሪዎች ውስጥ አንድ ሺህ 452 ከምሩቃን ሴት ተማሪዎች ሲሆኑ ከጠቅላላው 35 ነጥብ 5 በመቶ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ከጠቅላላው ተመራቂዎቹ ውስጥ 48ቱ በዶክትሬት ዲግሪ የተመረቁ ናቸው ብለዋል። በ1953 ዓ.ም የተቋቋመው አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2012/2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትናንቱን ጨምሮ ለ70ኛ ጊዜ ያስመረቀ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ብቻ በሁለት ዙር ከ10 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ በማታ ፕሮግራም 809 ተማሪዎችን፣ በቀን 3 ሺህ 39 እንዲሁም በርቀት 18 ተማሪዎቹን ለምርቃት አብቅቷል። ከእነዚህ መሀከል 5045 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 313 በ3ኛ ዲግሪ እና 2226 በማታ ፕሮግራም ያሰለጠናቸው መሆናቸው ተጠቁሟል። እንዲሁም በርቀት 180፣ በክረምት 2252፣ በስፔሻሊቲ 265፣ ከፍተኛ ዲፕሎማ በመምህርነት ፕሮግራም 269 ናቸው። ዩኒቨርሲቲው በዓመቱ በአጠቃላይ 10561 ተማሪዎችን አስመርቋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38229
437
0ሀገር አቀፍ ዜና
ፌዴሬሽኑ አሰልጣኞችን መረጠ
ስፖርት
February 19, 2020
20
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞችን ስም ዝርዝር አስታወቀ። ፌዴሬሽኑ በቅርቡ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ እንደሚገባም ይጠበቃል። በጃፓን አስተናጋጅነት የሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ የወራት እድሜ ብቻ የቀረው መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ወደ ዝግጅት ለመግባት የሚያስችለውን የአሰልጣኞች ምርጫ ማድረጉን አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ምርጫውን ባዘጋጀው መስፈርት መሰረት አወዳድሮ ያከናወነ መሆኑንም በድረ ገጹ አስነብቧል። ፌዴሬሽኑ በአፋጣኝ ወደ ስልጠና ለመግባት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅርቡ ምክክር ማድረጉ የሚታወስ ነው። ከስድስት ወራት ያነሰ ጊዜ ብቻ ለቀረው ውድድር ካለፉት የሪዮ ኦሊምፒክና የዶሃ ዓለም ሻምፒዮና ተሞክሮ በመውሰድ ስልጠና እንዲታቀድና በአፋጣኝ ወደ ትግበራ እንዲገባ ሁኔታዎች እንዲመቻቹም አቅጣጫ አስቀምጧል። ለተግባራዊነቱም ፌዴሬሽኑ በሚያወጣው የምልመላና የስልጠና ዝግጅት ሚናውን እንደሚወጣ ባስታወቀው መሰረት የአሰልጣኞችን ምርጫ ያከናወነ ሲሆን፤ በቅርቡ አትሌቶችን በመምረጥ ወደ ስልጠና እንደሚገባም ይጠበቃል። ምርጫው እርምጃን ጨምሮ ኢትዮጵያ በምትታወ ቅባቸው አምስት ርቀቶች ተደርጓል። በዚህም መሰረት በመካከለኛ ርቀት አሰልጣኝ ብርሃኑ መኮንን፣ ሃብታሙ ግርማ፣ ኢሳ ሽቦ እና ጉዲሳ ታሱ ተመርጠዋል። አሰልጣኝ አብርሃም ኃይለማሪያም እና ስንታየሁ ካሳሁን ደግሞ በተጠባባቂነት የሚቆዩ ይሆናል። በ3ሺ ሜትር ደግሞ አሰልጣኝ ተሾመ ከበደ እና ዶክተር ብዙአየሁ ታረቀኝ ሲመረጡ አሰልጣን ከፍያለው አለሙ ተጠባባቂ ሆነዋል። ሃገሪቷ በኦሊምፒክ መድረክ በተለይ ውጤታማ በሆነችባቸው የ5ሺ እና 10ሺ ሜትር ርቀቶችም አራት አሰልጣኞች ተመራጭ ሆነዋል። አሰልጣኝ ሁሴን ሸቦ፣ ቶሌራ ዲንቃ፣ ንጋቱ ወርቁ እና ኃይሌ እያሱ ሲመረጡ፤ አሰልጣኝ ተፈሪ መኮንን እና በሪሁን ተስፋይ ደግሞ የተጠባባቂነት ስፍራን ይዘዋል። በረጅሙ የአትሌቲክስ ውድድር ማራቶን በማናጀር አሰልጣኝነት ስኬታማ የሆኑት አሰልጣኝ ሃጂ አደሎ ከሌላው አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ጋር በመሆን የርቀቱን እንደሚመሩም በዝርዝሩ ተመልክቷል። አሰልጣኝ ጌታነህ ተሰማ እና ይረፉ ብርሃኑ ደግሞ ተጠባባቂ ሆነው ተመርጠዋል። የእርምጃ ቡድኑም በሻለቃ ባየ አሰፋ አሰልጣኝነት ወደ ቶኪዮ የሚያመራ ይሆናል። ፌዴሬሽኑ ምርጫውን ያሳወቀው ከትናንት በስቲያ ሲሆን፣ በምርጫው ላይ ቅሬታ ያለው አካል እስከ ዛሬ ድረስ ጉርድ ሾላ በሚገኘው ጽህፈት ቤቱ በመገኘት ማሳወቅ እንደሚችልም ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን ረቡዕ የካቲት 11/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=27523
271
2ስፖርት
«የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ሆነው አያውቁም፤ ህወሓት ሳይፈጠር የትግራይ ሕዝብ ነበር»የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች
ሀገር አቀፍ ዜና
December 27, 2020
20
መቀሌ(ኢዜአ)፡- «የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ሆነው አያውቁም፤ ህወሓት ሳይፈጠር የትግራይ ሕዝብ ነበር ወደ ፊትም ይኖራል» ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ትናንት ተወያይቷል።የመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች «የህወሓት ቡድን» በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት ያወገዙ ሲሆን፤ ቡድኑ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት የትግራይን ሕዝብ የማይወክልና ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ድርጊት መሆኑንም ነው የተናገሩት።ከዚህ ቀደም የፓርቲና የመንግሥት ሥራ ተደበላልቆእንደነበረ ያስታወሱት ነዋሪዎቹ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከዚህ ተምሮ ማስተካከል እንዳለበት የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ «የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ሆነው አያውቁም፤ ህወሓት ሳይፈጠር የትግራይ ሕዝብ ነበር ወደ ፊትም ይኖራል» ብለዋል። በከተማዋ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር ሕዝባዊ ፖሊሶች በአግባቡ ተደራጅተው ወደ ሥራ እንዲገቡም ጠይቀዋል። የትግራይ ሕዝብ ከስጋት ነፃ እንዲሆን የጁንታው አባላት ታድነው ለሕግ መቅረብ ይኖርባቸዋል ያሉት ነዋሪዎቹ፤ ለዚህም ሕዝቡና የፀጥታ ኃይሉ እንዲሁም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ተባብረው መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል። በመቀሌ ከተማ የተቋረጠው የባንክ፣ የትራንስፖርትና የኢንተርኔት አገልግሎት በአስቸኳይ እልባት አግኝቶ ሥራ እንዲጀምርም ጠይቀዋል። «በሰሜን ዕዝ ላይ የህወሓት ቡድን ያደረሰው ጥቃት ሕዝቡን እንደማይወክል እንረዳለን» ያሉት በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም፤ መከላከያው ወንጀለኞችን ከማደንና መልሶ ግንባታ በተጓዳኝ በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ በበኩላቸው፤ መንግሥት ጉዳት የደረሰባቸውን መሠረተ ልማቶች በመልሶ የመገንባት ሥራ ላይ ርብርብ እያደረገ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥም በርካታ የመሠረተ ልማቶች ወደ ሥራ እንደሚገቡ አረጋግጠዋል። የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ በበኩላቸው፤ «ከዚህ በኋላ በትግራይ ክልል የሰላም፣ የአንድነትና ልማት ጉዳይ በትኩረት ይሰራል» ብለዋል።  አሁን ላይ መቀሌ ከተማ ሰላምና መረጋጋት በመፈጠሩ በርካታ ማህበራዊ አገልገሎቶች በመከናወን ላይ መሆናቸውም ታውቋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 18/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38227
255
0ሀገር አቀፍ ዜና
ባየር ሙኒክ በኢትዮጵያ ሥልጠና ይሰጣል
ስፖርት
February 17, 2020
19
 የጀርመኑ ኃያል ክለብ ባየር ሙኒክ በኢትዮጵያ ለክለቦች የተለያዩ ሥልጠናዎችን እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ሥልጠናው ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ባለሙያዎቹም ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ጋር የተለያዩ ሥራዎችን በጋራ ለማከናወን ማቀዱ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎም ከዚህ ቀደም የልምድ ልውውጥና ሥልጠናዎችን ሰጥቷል፡፡ አሁንም ከፌዴሬሽኑ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክተር ጋር ባደረገው ቅድመ ዝግጅት፤ ለወጣት አሰልጣኞች ለ15 ቀናት የሚቆይ ሥልጠና የሚሰጥ መሆኑን ፌዴሬሽኑ በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡ ሥልጠናውን የሚሰጡት ባለሙያዎች ትናንት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ለቀጣይ 15 ቀናትም ቆይታ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡ ሥልጠናው የሚካሄደው በሁለት ዙር ሲሆን፤ የመጀመሪያው ዙር ሰልጣኞች ከየክልሉ የተውጣጡ ወጣትና ጀማሪ አሰልጣኞች ናቸው፡፡ ወጣቶቹ ከዚህ ቀደም በተሰጠው ሥልጠና ተገቢውን ውጤት በማሟላት ለቀጣይ ያለፉ 30 አሰልጣኞች ሲሆኑ፤ ለተከታታይ አምስት ቀናት በሥልጠና ላይ የሚቆዩም ይሆናል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚሰጠው ሥልጠናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 13/2012 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑም በዘገባው ተመላክቷል፡፡ሁለተኛው ዙር ሥልጠናም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወንድ ክለብ አሰልጣኞችንና አንደኛ ዲቪዚዮን ሴቶች ፕሪሚየርሊግ ክለብ አሰልጣኞችን የሚያካትት ነው፡፡ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናው ከየካቲት 16-18/2012 ዓ.ም ለሦስት ቀናት የሚሰጥም ይሆናል፡፡ ቀጣዩ መርሃ ግብርም ክለቡ በሚያዘጋጀው የባየር ሙኒክ የወጣቶች ዋንጫ ላይ ተሳታፊ ሊሆኑ የሚችሉ ከ15 ዓመት በታች ታዳጊዎችን መመልመል ነው፡፡ የሚመለመሉት አስር ተጫዋቾችም በሚያዝያ ወር መጨረሻ በጀርመን የሙኒክ ከተማ በሚካሄደው የባየርሙኒክ ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆኑበትን ዕድል የሚያመቻች መሆኑንም በዘገባው ተጠቁሟል፡፡ አዲስ ዘመን የካቲት 9/ 2012 ዓ.ም ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=27414
206
2ስፖርት
ለኦሊምፒክ ዝግጅት አትሌቶች በከፍተኛ ደመወዝ ወደ ልምምድ ይገባሉ
ስፖርት
February 21, 2020
16
እአአ የ1964ቱ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በታሪኳ ተሳታፊ የሆነችበት ሶስተኛው ኦሊምፒክ ነው። ታላቁ አትሌት አበበ ቢቂላ በኦሊምፒክ ማራቶን ለራሱ እና ለአገሩ ሁለተኛውን፣ በውድድሩ ደግሞ ብቸኛውን ሜዳሊያ ያገኘበትም ነበር። አሁን ደግሞ ጃፓን ከሃምሳ ስድስት ዓመታት በኋላ ኦሊምፒክን በምድሯ ለማስተናገድ ወራት ብቻ የቀሩበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። በዚህ ታላቅ የስፖርት መድረክም የተሻለ ታሪክ ለማስመዝገብ ኢትዮጵያ በተለየ ትኩረት በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች። በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ ከውጤታማነት ባሻገር ተሳትፎም ክብርን ያስገኛል። በውጤታማነት ድርብ ክብርን ለመጎናጸፍ ደግሞ ትኩረት፣ ጥረትና ጽናት አስፈላጊ መሆናቸው ይታመናል።በኦሊምፒክ መድረክ የአገሪቷን ስም በተደጋጋሚ ያስጠራው እንዲሁም ከፍተኛውን የውጤታማነት ስፍራ የሚይዘው የአትሌቲክስ ስፖርት ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ በዚህ ስፖርት በተመዘገቡ ሜዳሊያዎች አማካኝነት ከውጤታማዎቹ አገራት መካከል 36ኛ ስፍራ ላይ ትገኛለች። ነገር ግን በዚህ መድረክ ውጤታማ ያደረጓት አትሌቶች የኋላ ታሪክ ቢጠና በግላቸው የሚያደርጉት ጥረትና ጽናት ሰፊውን ድርሻ ይይዛል። በመሆኑም መንግስት የተሻለ ትኩረት በመስጠት ውጤታማነቱን ለማሳደግና ለማገዝ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል። ለዚህም የመጀመሪያው ርምጃ አትሌቶች የዝግጅት ጊዜያቸውን በትኩረት እንዲያሳልፉ በተሻለ ስፍራ እንዲያርፉ ማድረግ ነው። በመሆኑም የዝግጅት ኮሚቴው ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት ለውድድሩ የተመረጡ አትሌቶች ካምፓቸውን ከፍተኛ ደረጃ ካላቸው ሆቴሎች መካከል በአንዱ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተሰጥቷል። በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጥሪ የተደረገላቸው አትሌቶች ተሰባስበው ወደ ልምምድ እንደሚገቡ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም በብሄራዊ ቡድን የታቀፉ አትሌቶች የላብ መተኪያ ወጪ እጅግ አናሳ መሆኑ በቅሬታ መልክ የሚነሳ ነበር። ይህንንም ለመቅረፍ በመንግስት በኩል በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ለታዋቂ አትሌቶች 50ሺ ብር ደሞዝ እንዲያገኙ እንዲሁም ለሌሎች ጀማሪ አትሌቶች 10ሺ ብር በየወሩ የሚከፈላቸው ይሆናል። በልምምድ ግብዓት እንዲሁም ትጥቅ በኩልም ችግር እንዳይገጥማቸው እየተሰራ መሆኑም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ከትናንት በስቲያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጧል። ዝግጅቱን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከስፖርት ማህበራትና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በመሆን ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ለዝግጅቱም የቶኪዮ ብሄራዊ ዝግጅት ኮሚቴ እንዲሁም የቶኪዮ ኦሊምፒክ ቴክኒክ ኮሚቴ በሚልም ሁለት ኮሚቴዎችን አዋቅሯል። ብሄራዊ ኮሚቴው በቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ የሚመራ ሲሆን፣ ትኩረቱን በሃብት አሰባሰብ፣ የልማት ስራዎች፣ የደጋፊ አባላት ላይ እንዲሁም በስፖርተኞች ሽኝትና አቀባበል ላይ ያደርጋል። በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጂሎ የሚመራው የቴክኒክ ኮሚቴው ደግሞ ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በአትሌቶችና አሰልጣኞቻቸው ምርጫ ላይ የሚሰራ ይሆናል። በዚህም መሰረት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እጩ አትሌቶችንና አሰልጣኞቻቸውን ከቀናት በፊት አሳውቋል። በማጣሪያ ውድድር ላይ ያሉት የቦክስና ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርቶችን ጨምሮ ከውሃ ስፖርቶችና ብስክሌት ፌዴሬሽኖችም ጋር ኮሚቴው በትብብር በመስራት ላይ ይገኛል። ቀደም ብሎ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ በመግባት ላይ የሚገኘው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በበኩሉ 90 አትሌቶችንና 15 አሰልጣኞችን በማጨት ወደ ልምምድ ለመግባት በመንደርደር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ብሄራዊ ቡድኑ በሶስት ምዕራፍ የተከፈለ ዝግጅት የሚያደርግ ሲሆን፤ በመጨረሻም 50 አትሌቶች ወደ ቶኪዮ የሚጓዙ ይሆናል። ለጊዜው በተሳትፎ ደረጃ የተያዘው ከ800ሜትር እስከ እርምጃ ባሉት ርቀቶች ቢሆንም ሚኒማውን ማሟላት ከተቻለ በ400ሜትርም ተሳታፊ የመሆን እድል እንደሚኖር ተጠቁሟል።የቴክኒክ ኮሚቴው ቀድሞ ዝርዝራቸው ይፋ የተደረጉትን አሰልጣኞች የተመረጡበት መስፈርትም በርካታ አትሌቶችን በማስመረጥ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ውድድሮች ባላቸው ልምድ መሆኑን ገልጿል። የአትሌቶች የምርጫ መስፈርት ደግሞ እአአ በ2019 ባስመዘገቡት ሰዓት መሰረት በመምረጥ በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የጸደቀ መሆኑ ተብራርቷል። ለኦሊምፒክ የሚደረገው ዝግጅት አገርን ለማስጠራት የሚደረግ እንደመሆኑ በሁሉም አካላት ዘንድ በተለይም በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች በኩል ያለው አለመግባባትን ከወደ ጎን በመተው ለውጤታማነት በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑ በመግለጫው ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን አርብ የካቲት 13/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=27626
482
2ስፖርት
አድዋን ለመዘከር በደብረ ብርሃን ከተማ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ይካሄዳል
ስፖርት
February 22, 2020
22
በቀድሞዋ የስምንት መቶ ሜትር ኮከብ አትሌት ፋንቱ ሚጌሶ የተቋቋመው ‹ፋን ኢትዮጵያ የስፖርት አገልግሎት› ድርጅት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ከተሞች የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮችን እያካሄደ ይገኛል።የተለያዩ ወቅታዊ ነገሮችን መነሻ በማድረግ የጎዳና ላይ ውድድሮችን በተለያዩ ከተሞች የሚያካሂደው ፋን ኢትዮጵያ ተተኪ አትሌቶችን ከማፍራት ባሻገር ለበርካታ አትሌቶች የውድድር እድሎችን እየፈጠረም ይገኛል።በተለይም የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች እምብዛም በማይካሄድባቸው ከተሞች ትኩረት በማድረግ አትሌቲክስን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ በመፍጠር በህብረተሰብ አቀፍ ስፖርት(ማስ ስፖርት) እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ውጤቶች እያስመዘገበ ነው።በሀዲያ ሆሳዕና፣ አርባ ምንጭና ሀላባ ከተሞች በቅርቡ የተለያዩ የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድሮችን በስኬት በማድረግ በርካታ ህዝብ አሳትፎ ተወዳጅነትን ማግኘት ችሏል።በቀጣይም የካቲት 22 ቀን 2012 ዓ.ም የ124ኛው አድዋ ድል በዓል ዋዜማ በደብረ ብርሃን ከተማ ‹‹ኑ ለእምዬ ምኒልክ ክብር እንሩጥ›› በሚል መሪ ቃል ተመሳሳይ ውድድር ለማድረግ ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ ታውቋል።የፋን ኢትዮጵያ መስራች አትሌት ፋንቱና የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ መርከብ ለማ ከትናት በስቲያ በውድድሩ ዙሪያ በኢልጌል ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል።በውድድሩ ከአርባ ሺ በላይ ህዝብ ለመሳተፍ የቲሸርት ኩፖን መግዛቱን የገለፀችው አትሌት ፋንቱ ታዋቂና ወጣት አትሌቶች በውድድሩ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ተናግራለች።በውድድሩ ውጤታማ የሚሆኑ ወጣት አትሌቶችን ከክለቦች ጋር ከማገናኘት ባለፈ ዓለም አቀፍ ውድድር እንዲያገኙ ሁኔታዎች እንደሚመቻቹም አትሌት ፋንቱ ጠቁማለች።ፋን ኢትዮጵያ ብዙም ባልተለመደው የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ደፍሮ በመግባት አበረታች ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ የገለጸችው አትሌት ፋንቱ ካለፉት ውድድሮች ልምድ በመቅሰም ወደፊት የሚያካሂዳቸውን ውድድሮች በተሻለ የጥራት ደረጃ ለማከናወን ጥረት እንደሚያደርግ አስረድታለች።መሰል ውድድሮች በየዞኑ እና ወረዳው ማካሄድ ቢቻል፤ ህዝቡ ስፖርቱንና አትሌቶችን በባለቤትነት ስሜት በመደገፍ የተለያዩ አካባቢዎችን የአትሌቶች መፍለቂያ ማድረግ እንደሚቻልም አትሌት ፋንቱ ጠቁማለች፡፡ፋን ኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች የሚያደርጋቸው ውድድሮች ከስፖርታዊ ኩነትነቱ ባሻገር ሰላም፣ ፍቅርና አንድነትን የተመለከቱ መልዕክቶች የሚተላለፉበት ቢሆንም ውድድሩን ስፖንሰር በማድረግ በአጋርነት የሚሰሩ ድርጅቶች እንደሌሉ የተናገረችው አትሌት ፋንቱ መገናኛ ብዙሃንና የተለያዩ ከተሞች ውድድሩን ለማሳደግ ያሳዩትን ጥረት በመጥቀስ ምስጋና አቅርባለች።የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ መርከብ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ የምኒልክ የትውልድ ስፍራ የሆነችው ደብረ ብርሃንን ለማሳደግ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች መካሄዳቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል።ከተማ አስተዳደሩ የሰሜን ሸዋ ዞን መቀመጫ እንደመሆኑም የአድዋን ድል ለመዘከር ከሩጫ ውድድሩ ባሻገር የምኒልክን ጀግንነት የሚያሳዩ የተለያዩ መርሃግብሮችን ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።በውድድሩ ወቅት የጸጥታ ጉዳይ እንደማያሰጋ የገለፁም ሲሆን ዞኑና ከተማ አስተዳደሩ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረጋቸውን አረጋግጠዋል።ፋን ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች በማካሄድ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በሚደረገው አገር አቀፍ ርብርብ የራሱን ድርሻ እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን፤ ዘንድሮ የሀላባን ዘመን መለወጫ ‹‹ሴራ›› በዓልን አስመልክቶ በሀላባ ከተማ ጥር 2 ቀን የተሳካ የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ለ3ኛ ጊዜ ማካሄዱ ይታወሳል።ከዚያ በፊትም በሆሳህና ከተማ ላይ የመጀመሪያ የጎዳና ላይ ውድድር ያካሄደ ሲሆን ለ2ኛ ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ ማካሄዱ ይታወቃል።ውድድሮቹን  በየዓመቱ ለማካሄድ እንደታሰበም ታውቋል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 14/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=27704
398
2ስፖርት
ሳይበራ የጠፋው የረጅም ርቀት ኮከብ
ስፖርት
February 9, 2020
49
 በስፖርቱ ዓለም በወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኙ ጀግኖች በድንገተኛ አደጋ ሕይወታቸው የሚያልፍበት አጋጣሚ የተለመደ ነው። ይሁን እንጂ በአጭርም ይሁን በረጅም ጊዜ ሕመም ሕይወታቸው የማለፉ ዜና ሲሰማ የብዙዎችን ልብ የሚሰብርና ያልተለመደ መሆኑ አይቀርም። ከሳምንት በፊት አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ኮቤ ብርያንት በገዛ ሄሊኮፕተሩ በደረሰበት የመከስከስ አደጋ በአርባ ዓመቱ ከታዳጊ ልጁ ጋር ሕይወቱ በማለፉ ዓለማችን አዝናለች። ከዚህ የሃዘን ድባብ ሳትወጣም ከቀናት በፊት ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት አትሌት አባዲ ሃዲስ በህመም ምክንያት በመቖለ ሃይደር ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥር 26/2012 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ ሳምንቱ ለስፖርት ቤተሰቡ መጥፎ ሆኖ አልፏል። በተለይም ኦሊምፒክን ጨምሮ በዓለም አቀፍና አህጉራዊ ውድድሮች አገሩን በመወከል የሚታወቀው የ22 ዓመት ወጣት አትሌት አባዲ ሀዲስ ሕልፈተ ሕይወት ለኢትዮጵያውያን አስደንጋጭና መሪር ሃዘን ነው። አትሌት አባዲ ሃዲስ ባደረጋቸው ውድድሮች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ በአትሌቲክሱ ውጤታማ ከሆኑት አትሌቶች ተጠቃሽ ከመሆኑ ባሻገር እድሜው ገና ብዙ መስራት የሚችልበት ወጣት መሆኑ ሃዘኑን መሪር ያደርገዋል። አትሌት አባዲ ሃዲስ በትግራይ ክልል ማይጨው ከተማ ልዩ ስሙ እንዳመሆኒ ወረዳ ጥር 27/1990 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን የአትሌቲክስ ህይወቱን በእንዳመሆኒ የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ጣቢያ ነበር የጀመረው። በመቀጠልም በማይጨው አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ገብቶ መደበኛ ስልጠናውን ሲያጠናቅቅ ትራንስ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ክለብ በመቀላቀል ህይወቱ እስካለፈበት እለት ድረስ በውጤታማነት ክለቡን፣ ክልሉንና አገሩ ሲያስጠራ የነበረ ጀግና ነው። አትሌት አባዲ በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ በተካሄደው የ2016 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ10 ሺ ሜትር 27፡36.34 በሆነ ሰዓት 15ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ በዶሃ ኳታር በተካሄደው የ2019 የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ5ሺ ሜትር አገሩን ወክሎ ተሳትፏል። በለንደን በተካሄደው የ2017 የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናም በ10ሺ ሜትር 26፡59.19 በሆነ ሰዓት 7ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።በኡጋንዳ ካምላ በ2017 በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና በአዋቂ ወንዶች 10 ኪሎ ሜትር. ውድድር በ28፡43 ሰዓት 3ኛ ደረጃ በመያዝ የነሐስ ሜዳልያ ለአገሩ ማስመዝገብ የቻለው አትሌት አባዲ በሞሮኮ ራባት በ2019 በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ10ሺ ሜትር 28፡27.38 7ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሎ ነበር። በ2016 በተካሄደው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ10ሺ ሜትር 28፡43.2 በሆነ ሰዓት 1ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀበት አጋጣሚም ከስኬቶቹ መካከል ይጠቀሳል። አባዲ ሩጫን በዓለም አቀፍ ደረጃ በ 5ሺ ሜትር ጀምሮ በ 5ሺ ሜትር ከአራት ወር በፊት በዶሃ የዓለም ቻምፒዮና ላይ አገሩን ወክሎ በመሳተፍ ይቺን ምድር ተሰናብቷል። አባዲ በአትሌቲክስ ሕይወቱ አገሩን ወክሎ በተሳተፈባቸው ውድድሮች ከግል ውጤቱ ይልቅ ለአገር ቅድሚያ የሚሰጥ፣ የቡድን ስራ ጠፍቷል በሚባልበት ወቅት ለቡድን ውጤት የሚጨነቅ ሩቅ አሳቢ ኮከብ መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ምስክርነታቸውን የሰጡት ሕይወቱ ከማለፉ በኋላ አይደለም። ታታሪው ወጣት አትሌት በአትሌቲክስ ሕይወቱ አንድ አትሌት ሊደርስበት የሚመኘው ደረጃ ላይ በአጭር ጊዜ መድረስ ቢችልም ህልሙና ግቡ እንዲህ በአጭሩ የሚቋጭ አልነበረም። አባዲ ሕይወቱ ከማለፉ አስቀድሞ በረጅም ርቀት ዓለማችን ላይ ካሉ ኮከብ አትሌቶች አንዱ ቢሆንም የበለጠው ስኬት ከፊት የሚጠብቀው እንደነበር ብዙዎች በቁጭት ይናገራሉ። ይህ የረጅም ርቀት ኮከብ እንዳለው አቅምና ህልም እስካሁን አላበራም። በረጅም ርቀት በበለጠ ስኬት የሚያበራበት ጊዜ ከፊቱ ቢጠብቀውም ሳይበራ ሞት ቀድሞታል። ከሩጫ ችሎታው በተጨማሪ በባህሪው ዝምተኛና ሰው ቀና ብሎ የማያይ የመልካም ፀባይ ባለቤት የሆነው አባዲ በአጭር ጊዜ የደረሰበት የስኬት ጫፍ ግን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ ሲታወስ እንዲኖር ያደርገዋል። አባዲ በዓለም አቀፍ ደረጃ 34 ውድድሮችን አድርጓል። የ 1 ሜትር ከ70 ሳንቲ ሜትር ቁመት እንዲሁም 63 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ኮከብ ዓለም አቀፍ ውድድር ማድረግ የጀመረው እ.ኤ.አ 2015 በ5 ሺ ሜትር ሲሆን በወቅቱ 13:13፡17 በመሮጥ 13ኛ ደረጃን አገኘ። የመጨረሻውን ውድድርም በዶሀ ዓለም ቻምፒዮና በ 5 ሺ ሜትር 13:42፡89 መሮጥ ችሏል። በ 3 ሺ ሜትር 7:39፡10 እ.ኤ.አ በ2018 ካናዳ ላይ ያስመዘገበው ፈጣን ሰዓቱ ሲሆን በተመሳሳይ ዓመት በ 5 ሺ ሜትር 12:56፡27 ብራሰልስ ላይ ያስመዘገበው የርቀቱ የግሉ ፈጣን ሰዓት ነው። በ10 ሺ ሜትር 26:56፡46 በሄንግሎ ያስመዘገበው ፈጣን ሰዓት ሲሆን በግማሽ ማራቶን 58:44 ቫሌንሲያ ላይ ያስመዘገበው ሰዓት ወደ ፊት ብዙ ተስፋ እንዲጣልበት ያደረገ ነው። አባዲ በአራት ዓመት የሩጫ ህይወት ቆይታው 3 ሺ ሜትርን ሁለት ጊዜ ሮጧል። ስኬታማ በሆነበት 5 ሺ ሜትር ደግሞ አስራ ሦስት ውድድሮችን አድርጓል።አገሩን በኦሊምፒክና በዓለም ቻምፒዮና በወከለበት የ10 ሺ ሜትር ርቀት ዘጠኝ ውድድሮችን ሲያደርግ በ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር አንድ ጊዜ ብቻ ሮጧል። 21 ኪሎ ሜትር ወይም ግማሽ ማራቶንን አራት ጊዜ በመወዳደር ትልቅ ተስፋ የሰጠ ሰዓት ማስመዝገቡም ይታወቃል። በአገር አቋራጭ ውድድሮች በ9፣ 10.4፣10.796 እና 11.1 ኪሎ ሜትር ውድድሮች አንዳንድ ጊዜ ብቻ ሮጧል። አዲስ ዘመን የካቲት 1 / 2012 ዓ.ም ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=26976
629
2ስፖርት
ብልጽግና በንጹሃን ዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈጸምን ጥቃት አወገዘ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 25, 2020
10
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ብልጽግና ፓርቲ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት በማድረግ እየተካሄደ ያለውን ጥቃት አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገለጸ።ፓርቲው እንዳስታወቀው፤ ዜጎችን በማንነት ለይቶ በማጥቃት ምንም አይነት የፖለቲካ ትርፍ ሊገኝ አይችልም። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተደጋጋሚ በዜጎች ላይ እየተካሄደ ያለው ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት የትኛውንም የሕዝብ ክፍል የማይወክልና ኃላፊነት የማይሰማቸው የግጭት ነጋዴዎች ሴራ መሆኑን መላው የሀገራችን ሕዝቦች ሊገነዘቡ ይገባል።በጨካኝ አረመኔ የጥፋት ኃይሎች ጥቃት በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ላለው ጉዳት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸን ለዘመናት ተከባብሮ ክፉና ደጉን አብሮ ያሳለፈን ህዝብ በማጋጨት ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚጣጣሩ የውስጥም ሆነ የውጭ ኃይሎች የማይሳካላቸው መሆኑን አጥብቀን ልንገልጽላቸው እንወዳለን።በዜጎች ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ውስጥ ተሳትፎ ያላቸውንና ችግሩ እንዲፈታ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ባልተወጡ የስራ ኃላፊዎች ላይ ጥብቅ ፖለቲካዊ፣ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን እንገልጻለን።ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን ለፍቶ አዳሪ ንጹሃን ዜጎችን በማንነታቸው ብቻ ለይቶ በማጥቃት ሀገርንና ሕዝብን ወደ ትርምስ ለማስገባት ተቀናጅተው የሚንቀሳቀሱ የውስጥም ሆነ የውጭ ጨካኝ የጥፋት ኃይሎችን አጥብቆ የሚያወግዝና በእነዚህ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶ የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ ብልጽግና ፓርቲ አጥብቆ የሚታገል መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38084
168
0ሀገር አቀፍ ዜና
የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች የኮቪድ-19 የሕይወት ኢንሹራንስ ሊገባላቸው ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 25, 2020
9
ፍሬህይወት አወቀአዲስ አበባ፡- ኮቪድ-19 ወረርሽኝ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ተከትሎ ለድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች እና ለረዳት አሽከርካሪዎች የሕይወት ኢንሹራንስ ሊገባላቸው መሆኑን የኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ገለጸ።የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ኤጀንሲው ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች የሕይወት ኢንሹራንስ እንዲኖራቸው ከባለድርሻዎች ጋር ሰፋፊ ውይይቶችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎችና ረዳት አሽከርካሪዎች በኮቪድ 19 ምክንያት ለሚደርስባቸው ጉዳት የሕይወት ኢንሹራንስ ሊገባላቸው ነው።እንደ ወይዘሮ ወርቅነሽ ማብራሪያ፤ አሽከርካሪዎች በወረርሽኙ ቢጠቁ ከኢንሹራንስ አንጻር ህብረተሰቡን እንዴት መጥቀምና መደገፍ ይቻላል የሚለውን በተለያየ መንገድ ማየትና መደገፍ አስፈላጊ እንደሆነ ታምኖበታል።የሕይወት ኢንሹራንሱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ሚና ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ ሀገር ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ የተለያዩ ምርቶችን የሚያመላልሱ ሾፌሮችን ያለስጋት እንዲንቀሳቀሱ ያስችላል።ሹፌሮችና ረዳቶች በስራቸው በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለወረርሽኙ ተጋላጭ በመሆናቸው የተለያዩ መገለሎች የሚደርስባቸው መሆኑ ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ የሕይወት ኢንሹራንሱ መገባቱ ወሳኝ መሆኑን ያስረዱት ወይዘሮ ወርቅነሽ፤ ሾፌሮች ለሚያስተዳድሯቸው የቤተሰብ አባላትም ዋስትና እንደሚሆን ገልጸዋል። ሹፌሮችም ሆኑ ረዳቶች ዋስትና ያላቸው መሆኑን በመረዳት ስራቸውን በልበ ሙሉነት እንዲወጡ ያስችላቸዋልም ብለዋል።በወረርሽኙ ስርጭት ምክንያት የተቀነሱ በርካታ ረዳቶች መኖራቸውን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ሾፌሮች ብቻ ወደ ጅቡቲ ወደብ የሚገቡ መሆኑን ተናግረው የሕይወት ኢንሹራንስ መገባቱ ረዳቶቹንም ሆነ ስራ ፈተው የተቀመጡ ሹፌሮችን ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ያደርጋል ብለዋል።ሹፌሮችና ረዳቶች ያለስጋት መስራት ከቻሉ ባለንብረቶችም ተጠቃሚ ይሆናሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በሀገሪቱ ያሉት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በተለይም በሕይወት ኢንሹራንስ ብዙ ልምድ የሌላቸው በመሆናቸው በህብረተሰቡ ውስጥ ሰርጸው እንዲገቡና እንዲታወቁ ዕድል የሚፈጥርላቸው መሆኑን አመልክተዋል። ከሚፈጥርላቸው ጥሩ አጋጣሚ ባለፈም ወደፊት ቀጣይነት ባለው መንገድ ከድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች በተጨማሪ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችም እንዲቀላቀሉት ያደርጋል። ከዚህም ባሻገር የኢንሹራንስ ኩባንያዎቻችን እያደጉ ሄደው ለሀገሪቱ ትልቅ አቅም መፍጠር የሚችሉ ኢንዱስትሪዎች እንደሚሆኑም ተናግረዋል። ለድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች የሕይወት ኢንሹራንስ በመስጠት ተባባሪ የሆኑት የመድህን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችና የድንበር ተሸጋሪ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ማህበራት መሆናቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚና የኢትዮጵያ መድህን ሰጪዎች ማህበር ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ነጻነት ለሜሳ፤ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች በኮቪድ 19 ምክንያት ሞትና ስራ የማቋረጥ አደጋ ቢደርስባቸው ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን ለማቃለል ያለመ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል። ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ለሾፌሮችና ለረዳቶቻቸው ሊከፈል ከሚገባው የአረቦን መጠን 50 በመቶ ብቻ እንዲከፍሉ ያደረጉ ሲሆን ቀሪውን 50 በመቶ ደግሞ የተሽከርካሪዎች ባለንብረቶች እንዲከፍሉ ማድረጋቸውንም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል። በዓመት የሚከፈል የአረቦን መጠን ለእያንዳንዳቸው በነፍስ ወከፍ ለሾፌር 2046 ብር ከስድስት ሳንቲም ሲሆን ለረዳቶች ደግሞ 754 ብር ከሃምሳ ሳንቲም ይከፈላል። በቫይረሱ ምክንያት የሞት አደጋ ሲደርስባቸው ለሾፌር 250 ሺ ብር ለረዳት ደግሞ 150 ሺ ብር የሚከፈል መሆኑን አቶ ነጻነት ገልጸው፤ በተጨማሪም በኮቪድ ምክንያት ታሞ ለሁለት ወራት ስራ ካቋረጠ ለሾፌር ስድስት ሺ ብር ለረዳት ደግሞ ሶስት ሺ ብር የሚከፈል መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደጀኔ ሉጬ በበኩላቸው፤ እንደ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ኮቪድ 19ኝ በህብረተሰቡ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እንደተሰሩ አስታውሰው፤ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አደጋ ከደረሰ በኋላ ሰዎችን ለመርዳት ከመሄድ ይልቅ አስፈላጊውን በጀት መድበው በቅድመ ጥንቃቄ ላይ ቢሰሩ የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል። ከሕይወት ኢንሹራንስ ጋር ተያይዞም ቫይረሱ ባህሪውን እየቀያየረና እየተስፋፋ የመጣ በመሆኑ የሾፌሮችን ደህንነት መጠበቅ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተው፤ ሾፌሮች ከዚህ ቀደም በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ ሲያነሱት የነበረ ጥያቄ መሆኑንም ተናግረዋል።ለሾፌሮችና ለረዳቶች የሕይወት ኢንሹራንስ መገባቱ አስፈላጊና ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ደጀኔ፤ አሽከርካሪዎች እየተሳቀቁ መጓዝ የሌለባቸው መሆኑን ገልጸው እያንዳንዱ ባለድርሻ አካላትም ለተግባራዊነቱ የበኩሉን መወጣት እንደሚገባ አመልክተዋል። በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የአሽከርካሪዎች እጥረት መኖሩን የገለጹት አቶ ደጀኔ፤ ያሉትን ሾፌሮች በአደጋና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ማጣት የለብንም። አሽከርካሪዎች የኢትዮጵያ ወደቦች እንደመሆናቸው ሾፌሮችን በአደጋ የምናጣ ከሆነ ወደብ አይኖረንም። ስለዚህ ወደብ ሆነው እያገለገሉ ላሉት ሾፌሮች ልዩ ትኩረት መስጠት አስፈላጊ ነው ሲሉም ተናግረዋል።የሕይወት ኢንሹራንሱን ያቀላጥፋሉ ተብለው የሚታሰቡት ማህበራት በመሆናቸውና ማህበራት ደግሞ ከአደረጃጀት መመሪያ ጋር ተያይዞ የመፍረስ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ደጀኔ፤ ለዚህም አሰሪዎች ራሳቸው የህይወት ኢንሹራንሱን ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩና ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪ አስተላልፈዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38070
563
0ሀገር አቀፍ ዜና
በተመድ ሲሰሩ የነበሩና በጡረታ የተገለሉ ሴት ኢትዮጵያውያን በህዳሴው ግድብ እየሰሩ ለሚገኙ ሴቶች የ600 ሺ ብር ስጦታ አበረከቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 25, 2020
33
ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡- ሀገራቸውን ወክለው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለያየ ደረጃ ሲያገለግሉ የነበሩና በጡረታ የተገለሉ ሴት ኢትዮጵያውያን በህዳሴው ግድብ ላይ እየሰሩ ለሚገኙ ሴቶች የ600 ሺህ ብር ሥጦታ ማበርከታቸውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ብሔራዊ ምክር ቤት አስተባባሪ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።በሥጦታ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የፅሕፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሔ እንደገለፁት፤ ሀገራቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለያየ የሥራ መስክ ሲያገለግሉ የቆዩ እና አሁን ላይ በጡረታ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ እናቶች በታላቁ በህዳሴ ግድብ ላይ በጥበቃ ለሚገኙ ሴት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለሳሊኒ ፕሮጀክት ሰራተኞች እያደረጉት ላለው ታሪካዊ ስራ ያላቸውን ፍቅር ‹‹የእናቶች መቀነት ለግድባችን ልማት›› በሚል ሀሳብ ስጦታ አበርክተዋል።እንደ ዶክተር አረጋዊ ገለፃ፤ በግድቡ ላይና በግድቡ ዙሪያ በበርካታ አካባቢያዊ ተፈጥሯዊና ማህበራዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆነው የትውልድ ሃውልት በማቆም ሥራ ላይ እየተሳተፉ ላሉ 450 ወጣት ሴቶችና በግድቡ ግንባታ ያለውን የሰላም እና የፀጥታ ሥራ ለሚሰሩ ለእያንዳንዳቸው የአንድ ሺ ብር ቦንድ፣ ግድቡን ለሚገነባው ተቋራጭ 50 ሺብር፣ ለውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት 50ሺ ብር፣ በድምሩ 600 ሺ ብር ቦንድ በመግዛት ትውልድ የማይረሳው ትልቅ አሻራ አስቀምጠዋል።በሌላ በኩል በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መሥሪያ ቤት ለ27 ዓመት አገልግለው በጡረታ የተመለሱት ወይዘሮ ገነት ገብረ ክርስቶስ እንደገለፁት፤ ከራሳቸው ጡረታ ደመወዝና ልጆቻቸውን ጠይቀው በጭስና በእንጨት ሸክም ለሚደክሙ የኢትዮጵያ እናቶችን ችግር እንዲቀርፍ ለሚገነባው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰራተኞች የቦንድ ሥጦታ ለማበርከት እንደተነሳሱ ተናግረዋል።ግድቡ የሁላችን በመሆኑ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት እንዳለበት ጭምር ለማሳየት ተርፏቸው ሳይሆን ከሚያገኙት ትንሽ የጡረታ ደሞዛቸው ቀንሰው ማበርከታቸው የዜግነት ግዴታ ከመሆኑም ባሻገር ለሀገር ያላቸውን ፍቅር ለመግለፅ እንደሆነ ወይዘሮ ገነት ገልፀዋል።እናቶች ሥጦታውን ያበረከቱት የመከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል መሃመድ ተሰማ፣ የፌደራል ፖሊስ ተወካይ ኢንስፔክተር ፀደይ አቤኔዘር፣ የህዳሴው ግድብ ምክትል ስራ አስኪጅ አቶ በላቸው፤ የሳሊኒ ኮንስትራክሽን ተወካይ አቶ ታምሩ እና የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍሬ ህይወት በተገኙበት በሴቶች፣ ህፃናት ወጣቶች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚኒስትሯ በተገኙበት ቦንዱን አስረክበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38083
277
0ሀገር አቀፍ ዜና
በመተከል ዞን ለሕዝብ ጥቅም የሚሠራ አመራርና አደረጃጀት እንዲመቻች ተጠየቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 25, 2020
22
አሶሳ(ኢዜአ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በየጊዜው የሚከሰተው ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት ለሕዝብ ጥቅም የሚሠራ አደረጃጀት፣ አመራር እና አሰራር እንዲመቻች ተጠየቀ። በዞኑ የጸጥታ ችግር ላይ የክልሉ ነዋሪዎች በአሶሳ ከተማ ሲያካሂዱ የቆዩት የማህበረሰብ ምክክር ከትናንት በስቲያ ማምሻውን የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ነዋሪዎቹ በአስር ቡድኖች ተከፋፍለው ባደረጉት ውይይት በዞኑ ዋነኛ ችግሮች እና መፍትሔ ያሏቸውን ሀሳቦች አንስተዋል።ከቡድኖቹ አስተባባሪዎች መካከል አቶ ሞላ አስማረ ለዞኑ የጸጥታ ችግር መባባስ በየደረጃው የሚገኘው አብዛኛው አመራር አድሎአዊ አሠራር መከተሉ መሆኑን ነዋሪዎቹ ማንሳታቸውን አመልክተዋል። የዞኑ አመራር ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ የራሱን ሲያስቀድም እንደነበር ተወያዮቹ አንስተዋል ብለዋል።ችግሮች ሲፈጠሩ አመራሩ ኃላፊነት ወስዶ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ተጠያቂነትን ይሸሹ እንደነበር ያስታወሱት አስተባባሪው፤ በየደረጃው ባሉ አመራሮች በችግሩ ላይ በሚደረጉ ውይይቶች የሃሰት ሪፖርት ይቀርቡ እንደነበረ ጠቁመዋል።የዞኑ የጸጥታ ችግር በአብዛኛው በመገናኛ ብዙሃን ተገቢውን ሽፋን አላገኘም ያሉት አቶ ሞላ፤ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚቀርበው የፈጠራ ወሬም ችግሩን እንዳባባሰው አስረድተዋል። የሕግ የበላይነትን በማስከበር በዞኑ ፖሊስ፣ ፍርድ ቤት እና ሌሎችም ፍትህ አስከባሪ ተቋማት ችግሮች እንደሚታዩባቸው አንስተዋል።ሌላው የቡድኑ አስተባባሪ አቶ በሱፈቃድ አስረስ በበኩላቸው፣ የመሬት ወረራ ለዞኑ ግጭት ሌላው ተጠቃሽ ምክንያት እንደሆነ አመልክተው፤ በአጠቃላይ ሕግን በማስከበር ደረጃ የሚታየው ክፍተት የአካባቢው ጸጥታ ችግር በፍጥነት እንዳይፈታ እንዳደረገው ተናግረዋል። በዞኑ ብልሹ አሰራርን የሚታገል፣ ለሕዝብ ጥቅም የሚሰራ አመራር እና አደረጃጀት መፍጠር ዋነኛው እንደሆነ ነዋሪዎቹ ለችግሮቹ መፍትሔነት ሀሳብ ማቅረባቸውንጠቅሰዋል። የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረገ መሠረተ ልማት ማስፋፋት፣ የመንግስት አደረጃጀት እና መዋቅርን በጎጠኛ አስተሳሰብ ከሚያራምዱ አመራሮች ማጽዳት እንደሚገባም አመላክተዋል።በዞኑ በተለይም የመሬት አስተዳደር ሕግን በሚገባ የሚተገበርና መልካም ስነ-ምግባር ያለው እና ሕገ-መንግሥቱን የሚያስከብር አመራር መፍጠር ሌላው የውይይቱ ተሳታፊዎች ያስቀመጡት መፍትሔ እንደሆኑ ያመለከቱት ደግሞ ሌላው አስተባባሪ አቶ ሻምበል ተገኝ ናቸው።አቶ ሻምበል፣ በዞኑ አስተዳደር ከሕዝብ ስብጥር እና ቁጥር ጋር የተመጣጠነ ውክልና ያለው አሠራር ሊኖር እንደሚገባ ነዋሪዎቹ ሀሳብ ማቅረባቸውንም ጠቁመዋል። በፍትህ ተቋማትም ሕጉን በአግባቡ የሚተገብር ባለሙያ እና አመራር መመደብ እንደሚያስፈልግም ተጠቅሷል።ሃዋርያ ክፍሌ ይልማ በበኩላቸው፣ እያንዳንዱ የዞኑ ነዋሪ ለጸጥታ አካላት ትክክለኛ መረጃ በመስጠት አብሮ መስራት እንዳለበት ጠቁመው ፤ መንግስትም ህብረተሰቡ የጸጥታ ስጋትን አስመልክቶ የሚሰጠውን መረጃ ተቀብሎ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥም ጠይቀዋል። የህብረተሰቡን ሠላም እያወከ በሚገኘው ሃሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መንግስት አፋጣኝ የመፍትሔ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም ገልጸዋል።በተለይ ለህብረተሰቡ ቅርብ የሆኑ የጎጥ፣ ቀበሌ እና ወረዳ አደረጃጀቶች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አመልክተው ፤ የሚመደቡ አመራሮችም ንቁ፣ ታማኝ እና ሕዝቡን ያለአድሎ የሚያገለግሉ ሆነው መመረጥ አለባቸው ብለዋል። ከምንም በላይ የህብረተሰቡን አንድነት በማጠናከር ዘረኝነትን ማስወገድ እና አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያን መፍጠር አጽንኦት እንዲሰጠው ነዋሪዎቹ ማመልከታቸውን አስተባባሪዎቹ አብራርተዋል።ነዋሪዎቹ በምክክር መድረኩ ለችግሩ ያነሷቸውን የመፍትሔ ሀሳቦች መንግሥት ተቀብሎ እንዲተገብርም ጠይቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38086
362
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሜጀር ጄኔራል ከድር አራርሳ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 25, 2020
20
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥና የሎጂስቲክስ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ከድር አራርሳ ትናንት ፍርድ ቤት ቀረቡ።እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ ሜጀር ጀኔራል ከድር አራርሶ የሰሜን እዝ የጦር መሳሪያ በሕወሓት ልዩ ኃይል እንዲዘረፍ መረጃ ሰጥተዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ ትናንት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል። እንደ ዘገባው፣ ተጠርጣሪው የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥና የሎጂስቲክስ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ በነበረበት ጊዜ ከሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር መረጃ ሲሰጡ ነበር ተብሏል። ከዚህ በፊት በእዙ ስር ያሉ መሳሪያዎችን ከአካባቢው ለማንሳት ሙከራ በተደረገበት ወቅት እንቅስቃሴው እንዲሰናከል ስለማድረጋቸው መረጃ ማሰባሰቡን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷል። ተጠርጣሪው ከህወሓት ቡድን ጋር ባላቸው ግንኙነት በአድሏዊ አሰራር በተደጋጋሚ የውጭ አገር እድል ይሰጣቸው እንደነበርም ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል። በመሆኑም ፖሊስ ለቀሪ የምርመራ ስራዎች 14 ቀን እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ተጠርጣሪው በበኩላቸው “በተባለው ጉዳይ ጥፋት የለብኝም ፍርድ ቤቱ በነፃ ያሰናብተኝ” ሲሉ ጠይቀዋል።የግራ ቀኝ ክርክሩን ያደመጠው ችሎቱ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀን 11 ቀን በመፍቀድ ለታሕሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38071
162
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የተፈናቀሉ ወገኖች ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን ተናገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
5
መሀመድ ሁሴንአዲስ አበባ፡- በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች በንፁሃን ላይ ከተፈፀመው ጥቃት አምልጠው በቡለን ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮች በረሃብና በጥም የተነሳ ለሞት አደጋ መጋለጣቸውን ተናገሩ፡፡አስተያየታቸውን ትናንት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰጡት እነዚሁ ተፈናቃዮች፤ ከግድያው ለማምለጥ ምንም ነገር ሳይዙ ከቤታቸው በመውጣታቸው የተነሳ አሁን ላይ የሚበሉትና የሚጠጡት እንዳጡና ከመንግሥትም ያገኙት ድጋፍ እንደሌለ በምሬት ተናግረዋል።የስምንት ልጆች አባት የሆኑትና በበኩጂ ቀበሌ ከአስር ዓመታት በላይ የኖሩት አርሶ አደር ደረጀ በየነ እንደገለፁት፤ ከሞት አምልጠውና ከአርባ አምስት ኪሎ ሜትር በላይ በእግራቸው ተጉዘው ቡለን ወረዳ መድረስ ቢችሉም፣ በርሃብና በጥም የተነሳ ሌላ ሞት እንደተጋፈጡና ጠያቂ የመንግሥት አካል እስካሁን አላገኙም። በወረዳው ሥር የሚገኙ ሁሉም የቀበሌ ነዋሪዎች የእግር መርገጫ እስኪጠፋ ድረስ በቡለን ወረዳ ተሰባስበው በረሃብ እየተቆሉ ይገኛሉ ያሉት አርሶ አደር ደረጀ፤ ‹‹ህይወታቸውን ካጡት እህት ወንድሞቻችን ሐዘንና ድንጋጤ ሳንወጣ ይዘን የሸሸናቸውን ልጆቻችንን ልናጣ የምንችልበት አደገኛ የረሃብ ችግር ውስጥ ወድቀናል፡፡ ጠያቂ አካል አላገኘንም፡፡ ትምህርት ቤቶች እና አዳራሾች በተፈናቃዮች ሞልተው ተጨናንቀዋል፡፡ ህፃናት ልጆቻችን የሚልሱት የሚቀምሱት አጥተዋል፡፡ በዚህ የተነሳም በከፍተኛ ጭንቀት ላይ እንገኛለን›› ሲሉ ሀሳባቸውን በምሬት ገልፀዋል፡፡ ‹‹በፍራቻና በሥጋት ሰቀቀን ውስጥ መኖር ከጀመርን ዓመት አልፎናል፡፡ ከወረዳና ከክልል የሚመጡ አመራሮች የጉሙዝ ማህበረሰብን ብቻ ለይተው ይሰበስባሉ፡፡ ለእኛ ዞረው ሰላም ነው፤ ምንም ችግር አይደርስባችሁም እያሉ ሲያዘናጉን ኖረዋል፡፡ ስለዚህ ከጀርባ ሌላ የጭፍጨፋ ሴራ እየተዘጋጀ ሕዝቡ እንዳይነቃ እና ወደሌላ አካባቢ እንዳይሸሽ ሲደረግ ኖሯል፡፡ በዚህ የተነሳም ከበኩጂ ብቻ ያለቀው ሰው ብዙ ነው፡፡ እኔ በዓይኔ ተሰብስቦ የተመለከትኩት 207 አስከሬን ነው” ያሉት አርሶ አደር ደረጀ፤ የወንድማቸው አምስት ልጆችና ባልና ሚስትን ጨምሮ ሰባት ቤተሰባቸው እንደተገደሉባቸው በሐዘን ተናግረዋል፡፡ የጭላንቆ ቀበሌ ነዋሪው የሆኑት ሌላው አስተያየት ሰጪ አርሶ አደር ወንድማገኝ ሻምበል በበኩላቸው፤ የተፈፀመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ አስከፊ ከመሆኑም በላይ በህይወት የተረፍነውም ለከፍተኛ መከራ ዳርጎናል ብለዋል፡፡ “ህፃናት እና ሴቶች ከጭፍጨፋው አምልጠው በቡለን ወረዳ በመሰባሰብ በከፍተኛ ረሃብ ላይ ወድቀዋል፡፡ ማንም የሚጠይቅ አካል የለም፡፡ በዚህ የተነሳ ከፍተኛ ተጨማሪ እልቂት መፈጠሩ አይቀርም” ሲሉ አርሶአደሩ ሥጋታቸውን አስረድተዋል፡፡አመራሩ የችግሩ ዋና አካል መሆኑን ያነሱት አርሶ አደር ወንድም አገኝ ፤ ‹‹ከወረዳ ወደ ቀበሌ የሚመጡ አመራሮች እኛን ሊያስገድሉን ነበር፡፡ ከጭላንቆ ቀበሌ ሩጠን በማምለጥ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አዲስ ዓለም ከምትባል ቀበሌ ገብተን ተቀመጡ መከላከያ ሠራዊት መጥቶላችኋል ብለው አታለሉን። በዚህም የተነሳ ወንድማችን በአራት ቀስት ተመትቶ ሞቷል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ሕብረተሰቡ አብሮ ከጉምዝ ብሔረሰቦች ጋር ቡና የሚጠጣ ሕዝብ ነው ያሉት አርሶ አደሩ፤ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እኛ ወደ ማሣ ሥራ ስንሄድ ከወረዳ ከሚመጡ አመራሮች ጋር ብቻቸውን ይመክራሉ፤ በዚህም የተነሳ ጥቃቱ እየጨመረ መጥቷል›› ብለዋል፡፡“ብዙ ወገኖቻችንን በግድያው ከማጣታችን በላይ በመከራ ላይ መከራ፣ በችግር ላይ ችግር እያሰቃየን እንገኛለን፡፡ የሦስት ቀን አራስ ህፃን ልጅ በዘንቢል ይዘን ነው የወጣነው፡፡ አዝመራዬን ወቅቼ 180 ኩንታል ሜዳ ላይ እንደደረደርኩት ትቼው ወጥቻለሁ፡፡ መኪና እንኳን ማግኘት አልቻልንም፡፡ አምልጠን የወጣነውም በእግራችን ነው፡፡ ባዶ ራቁታችንን ወጥተን ቡለን ብንደርስም ሌላ መከራ ነው የጠበቀን፡፡ ወድቀን ያለነው ከሕብረተሰቡ ላይ ነው፡፡ እኔ አመራር ነኝ ብሎ ተፈናቃዮችን ያነጋገረና የጠየቀ አካል እስካሁን የለም›› በማለት ብሶታቸውን ተናግረዋል፡፡ በጉሙዝ ማህበረሰብ እና በሌላው ሕብረተሰብ መካከል ምንም አይነት ችግር እንደሌለ የገለፁት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ “የሚያስፈጁን በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጣቸው አመራሮች እኩይ ድርጊት በመሆኑ አጥርቶ እርምጃ መውሰድ እና የተፈናቀለውን ማቋቋም አስፈላጊ ነው” ሲሉ መፍትሄ ያሉትን ጠቁመዋል፡፡ እንደ ዝግጅት ክፍል የነዋሪዎቹን አስተያየት በመያዝ ወደሚመለከታቸው የቤንሻንጉል ክልል የሥራ ኃላፊዎች በመደወል ጉዳዩን ለማጣራትና አስተያየታቸውን እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ሆኖም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለኢቢሲ በሰጡት አስተያየት፤ በግድያው እጃቸው አለበት ተብለው የሚጠረጠሩት አመራርም ይሁን፣ ግለሰቦችም ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል።“አሁንም ቢሆን በህብረተሰቡ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ በግጭቱ ላይ የአመራሮች ተሳትፎ አለበት የሚል ነገር አለ፡፡ እኛ ዝግ አላደረግነውም፤ እንደክልል መንግሥት የሚወራው ወሬ እንደተጠበቀ ሆኖ የማጥራት ሥራዎች በመሥራት ተጨባጭ ማስረጃዎች ስናገኝ ማንኛውም ሰው ወደ ሕግ እንዲቀርብ እያደረግን ነው ያለነው” ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38147
536
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን በማጠናከር የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች በጋራ መክተው ማለፍ ይገባቸዋል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
16
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ከመቼውም ጊዜ በላይ ዜጎች አንድነታቸውን በማጠናከር በኢትዮጵያ እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በመመከት ለማሸነፍ ማለፍ እንደሚገባቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለሦስት ቀናት የሚካሄደው የፌዴራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እንደተናገሩት፤ የለውጡ እውን መሆን ሕዝቡን ሲመዘብሩ የነበሩ ቡድኖች ጥቅማቸው መቅረቱን ተከትሎ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ዜጎች ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ነው። ከሰሞኑም በነዚህ ቡድኖች ሴራ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በንፁሃን ዜጎች ላይ እጅጉን አሳዛኝ ግድያ የተፈፀመ ሲሆን፤ ተግባሩም እጅጉን የሚያሳዝን ነው፡፡በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ የገጠሟትን ፈተናዎች በልጆቿ የተባበረ ክንድ ማለፏን ያወሱት አፈ-ጉባኤው፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን በማጠናከር የሚገጥሙንን ፈተናዎች መሻገር ይገባናል ብለዋል። የዴሞክራሲ ተቋማትም ለዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር በትኩረት መሥራት ይኖርባቸዋል ብለዋል። ይሄን ኃላፊነታቸውን ለመወጣትም በተለይም የዴሞክራሲ ተቋማት ነፃና ገለልተኝነታቸውን ጠብቀው ለዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን በበኩላቸው፣ የሶማሌ ክልል ከለውጡ በፊት በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በዜጎች ሰቆቃ የሚታወቅ እንደነበር በማስታወስ፤ የለውጡ አመራር በወሰዳቸው ዘርፈ-ብዙ ማሻሻያዎች የክልሉ ችግር ደረጃ በደረጃ እየተፈታ መምጣቱን ተናግረዋል።በመድረኩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪዎችና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የፌደራል የዴሞክራሲ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ሲሆን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአምስት ዓመት ዕቅድ፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ስላላቸው የሥራ ግንኙነት ተቋማቱን ለማጠናከር በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የማሻሻያ ሥራዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38148
240
0ሀገር አቀፍ ዜና
በወሰን አካባቢ የተከሰተው ግጭት የሁለቱ አገራትን ሕዝቦች እና መንግሥታት አለመሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 25, 2020
10
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ እና የሱዳን ወሰን አካባቢ የተከሰተው ግጭት የሁለቱ አገራትን ሕዝቦች እና መንግስታት የማይወክል፤ ይልቁንም በሁለቱ አገራት ሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እና ግጭት እንዲፈጠር ድብቅ አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት ሴራ መሆኑንም ነው የተገለጸው።እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ ክስተቱን አስመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በአረብኛ ባወጣው መግለጫ የተፈጠረው ችግር የኢትዮጵያም ሆነ የሱዳን መንግስት ፍላጎት አይደለም። እንዲያውም በሁለቱ አገራት ሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እና ግጭት እንዲፈጠር ድብቅ አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት ሴራ መሆኑን መንግስት ይገነዘባል። ይሁን እንጂ ሁለቱ አገራት ችግሩን በጋራ በሠላማዊ ውይይት ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ መንግስት አስታውቋል::ግጭቱ መፈጠሩ አሳዛኝ ቢሆንም በተለይም የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ሕግ የማስከበር ስራውን አጠናቆ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እያከናወነ ባለበት ወቅት እና በተመሳሳይ መልኩ ሱዳን ደግሞ በሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ደፋ ቀና በምትልበት ጊዜ መፈጠሩ የበለጠ አሳዛኝ እንደሚያደርገው የኢትዮጵያ መንግስት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል:: በሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የተከሰተው የፀጥታ ችግርም የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስትን የሚመጥንና የሚወክል አለመሆኑንም መግለጫው አስታውቋል:: ለዘመናት የዘለቀው የሁለቱ አገራት እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በሴረኞች እንደማይሰናከል የገለፀው መግለጫው፣ የሁለቱ አገራት ሕዝቦች ነጻነታቸውን ከማረጋገጥ ባሻገርም፣ ከራሳቸው አልፈው ለአካባቢውም ጭምር ስልጣኔና ቅርስ አበርክቷቸው በጋራ የሚያስተሳስራቸው መሆኑም ተመልክቷል::በፈተናም ጊዜ የሁለቱ አገራት ሕዝቦች ሲተጋገዙ እንደነበር በመግለጽም፣ በአሁኑ ጊዜም ቢሆን በዓለም አቀፍ መድረኮች ጭምር ኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ ጥቅሞቻቸውን በአብሮነት በማስከበር ላይ መሆናቸውንም መግለጫው አስታውሷል፣ይህም ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን አገራቱ ለዘመናት ባዳበሩት አብሮነት ጭምር የተገኘ እሴት መሆኑን ተመልክቷል::በሱዳን በቅርቡ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አብዮት ሕዝቡ በፍላጎት ያደረገው በመሆኑ እንዲሳካም ኢትዮጵያ ከሱዳን ሕዝብ እና መንግስት ጎን በመቆም ሠላም እና መረጋጋት እንዲመጣ ስታግዝ ቆይታለችም ብሏል:: ይህም በሁለቱ አገራት እና ሕዝቦች መካከል ያለውን ወንድማዊ ግንኙነት የሚያሳይ መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል::ይሁን እንጂ በቅርቡ አንዳንድ አካላት በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ መንግስት በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን አስታውቋል:: ድርጊቱንም ሁለቱ አገራትን የማይወክል እና የተፈጠረውን ችግር በሠላማዊ ውይይት እንደሚፈቱት የኢትዮጵያ መንግስት አቋሙን ገልጿል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38074
280
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኬንያዊው አትሌት የአስር ዓመቱ ምርጥ ተሰኝቷል
ስፖርት
February 10, 2020
16
ባለፉት አስር ዓመታት በአትሌቲክስ ስፖርት ውስጥ በርካታ ክስተቶች ተስተናግደው አልፈዋል። ለቁጥር የሚታክቱ ክብረወሰኖች ከመሻሻላቸውም ባለፈ በሰው ልጅ ሊደፈሩ ይችላሉ በሚል የማይጠበቁና የማይገመቱ ታሪካዊ ክንውኖችም ታይተዋል። ከእነዚህ መካከል በተለይ በስፖርቱ አጭር ርቀት ውድድር (100ሜትር) እና በረጅሙ ርቀት (ማራቶን) የተመዘገቡት ስኬቶች የሰውን ልጅ አቅም በትክክልም ማሳየት የሚያስችሉ ሆነዋል። ታዲያ በአስሩ ዓመታት ከታዩና ክብረወሰንም ካስመዘገቡ አትሌቶች መካከል የተሻለው ማን ነው? በዚህ ጥያቄ ላይ ተንተርሶ ምርጫውን ያካሄደው ደግሞ እአአ በ1940 መሰረቱን በአሜሪካ በማድረግ የተቋቋመውና ትኩረቱን በመምና ሜዳ ተግባራት ስፖርቶች ላይ ያደረገው መጽሄት ነው። መጽሄቱ እአአ ከ2010-2019 ድረስ ባሉት ዓመታት ከጎዳና ላይ ውድድሮች ባሻገር ባሉት ውድድሮች አስር አትሌቶችን በእጩነት በማቅረብ ምርጫውን በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ነበር የጀመረው። በተሰጠው ድምጽ መሰረትም ኬንያዊው የ800 ሜትር አትሌት ዴቪድ ሩዲሽያ ተመራጭ ሊሆን ችሏል። በእጩነት ከቀረቡት አትሌቶች መካከል አንዱ በአጭር ርቀት የአትሌቲክስ ተጽእኖ ማሳደር የቻለው ጃማይካዊ አትሌት ዩሲያን ቦልት ነው። አሁን ራሱን ከተወዳዳሪነት ያገለለው ቁመተ መለሎ አትሌት በ100 ሜትር የሸፈነበት 9ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ የምንጊዜም የርቀቱ ምርጥ አትሌት ያደርገዋል። በውድድር ተሳትፎው ከደረጃ ወርዶ የማያውቀው አትሌት አራት የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ከማጥለቅ ባሻገር የዓለም ቻምፒዮን በመሆንም ክብረወሰኑን አርቆ የሰቀለ አትሌት መሆኑ ምርጫውን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል በሚል ይጠበቅ ነበር። በረጅም ርቀት የመም ላይ ውድድሮች በኢትዮጵያዊያኑ ጀግና አትሌቶች እግር የተተካው እንግሊዛዊ አትሌት ሞሃመድ ፋራም በእጩነት ከቀረቡት መካከል ነበር። የዓለም ቻምፒዮናው በኦሊምፒክ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያሳካ ሲሆን፤ በ5ሺ እና 10ሺ ርቀቶች ሃገሩን በተደጋጋሚ ለማስጠራት ችሏል። አትሌቱ ምንም እንኳን ከመም ወደ ጎዳና ላይ ውድድሮች ባደረገው ሽግግር እንደሚጠበቀው ውጤታማ ባይሆንም ያለፉት አስር ዓመታት ግን ለእርሱ አስደሳች ነበሩ። ከመም ይልቅ በማራቶን ስሙ የገነነውና የዚህ ወቅት የርቀቱ ቁጥር አንድ አትሌት የሆነው ኬንያዊ ኢሉድ ኪፕቾጌም ቀዳሚ ተመራጭ ይሆናል በሚል ከሚጠበቁት እጩዎች መካከል ነበር። የዓለም ክብረወሰን ባለቤቱ እንዲሁም ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች የመግባት ሙከራውን ያሳካው አትሌት በሮጠበት ጫማ ምክንያት ውዝግቦችን ያስተናግድ እንጂ የጎዳና ላይ ሩጫዎች ንጉስነቱን ማንም ሊቀማው እንደማይችል ነው አዘጋ ጆቹ ያረጋገጡት። አሜሪካዊያኑ ክርስ ቲያን ቴይለርና አሽተን ኢትን፣ ደቡብ አፍሪካዊው ዋይዴ ቫን ኔኬርክ፣ ፈረንሳ ዊው ሬናውድ ላቪሌኔ፣ የኳታሩ ሙታዝ ባርሺም እንዲሁም ጀርመናዊው ሮበርት ሃርቲንግም ከአስሩ እጩዎች መካከል ይገኙበታል። ከእጩዎቹ መካከል በተለይ ‹‹የዓለም ፈጣኑ ሰው›› በሚል የሚታወቀው ጃማይካዊ አትሌት አብላጫውን ድምጽ ያገኛል የሚል ግምት ያግኝ እንጂ አሸናፊ የሆነው ግን ዴቪድ ሩዲሽያ ነው። የለንደንና ሪዮ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ እንዲሁም የዴጉና ቤጂንግ የዓለም ቻምፒዮናው አትሌት፣ በተለይ እአአ በ2012ቱ የለንደን ኦሊምፒክ ርቀቱን ያጠናቀቀበት ሁኔታ በአስር ዓመታት ከማይዘነጉ ትዝታዎች መካከል ቀዳሚው በሚል በዓለም አትሌቲክስ መመረጡ የሚታወስ ነው። አትሌቱን አስደናቂ ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል አንዱ፣ በርቀቱ የዓለም ክብረወሰንን ለሶስት ጊዜያት(1:41.09፣ 1:41.01፣ 1:40.91) መስበር መቻሉ ነው። መጽሄቱ መሰል ምርጫዎችን ማካሄድ የጀመረው እአአ በ1960ዎቹ ሲሆን፣ የመጀመሪያው አሸናፊም ኒውዝላንዳዊው ፒተር ስኔል ነበር። እአአ የ1970ዎቹን ክብር ደግሞ የሶቬት ህብረት አትሌት የሆነው ቪክቶር ሳኔይቭ ነበር የወሰደው። በ1980ዎቹ አሜሪካዊው ካርል ሉዊስ ምርጥ ሲሰኝ፤ የ90ዎቹንም ሌላኛው የሃገሩ ልጅ ሚካኤል ጆሃንሰን አሸናፊ ሆኗል። እአአ ከ2000-2009 ባሉት ዓመታት ምርጥ አትሌትነት ምርጫ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን፤ አንበሳው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቀዳሚ ሊሆን ችሏል። አዲስ ዘመን የካቲት 2/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=27019
441
2ስፖርት
በዜጎች ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ ይወስዳል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
9
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በዜጎች ላይ ጭካኔ በተሞላበት ጥቃት እየፈፀሙ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ። የብሔራዊ የሰዎች መነገድ፣ ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ብሔራዊ ምክር ቤት የ2013 ዓ.ም ዓመታዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በዜጎች ላይ የተፈፀመው ድርጊት ጭካኔ የተሞላበት የወንጀለኞች ተግባር መሆኑን የገለፁ ሲሆን፤ በዜጎች ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድም ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያዊያን የሚጋሩትና የወረሱት የዳበረ እሴት ባለቤቶች መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ደመቀ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አንዳንዶች በዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እየፈፀሙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይሄ ችግር ወደ የት እያመራ እንደሆነ ሁሉም ቆም ብሎ ሊያስብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ዜጎችን እየጨፈጨፉ ባሉ ወንጀለኞች ላይ መንግሥት ጠንካራ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን የገለፁት አቶ ደመቀ፤ ለዚህም የተለያዩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ድርጊቱን ለማስቆምና ወንጀለኞችን ለማደን የሁሉም ጥረትና ትብብር የሚያስፈልግ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ዜጎችን ለነዋይ ብሎ መደለል፣ ድንበር አሻግሮ ለወንጀለኞች አሳልፎ በመስጠትና ለከፋ ችግር የማጋለጥ ተግባሩ መቀጠሉን በመጠቆምም፤ ለዚህ ችግር ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች ቢኖሩም ወንጀሉን ለመከላከልና ለማስቆም አሁንም የሁሉም ጥረትና ትብብር ያስፈልጋል በማለት ጥሪ ማስተላለፋቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡በተያያዘ ዜና፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር እና ችግሩን ለመቅረፍ ምቹ የሆነች ሀገርን የመፍጠር ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ በዚሁ መድረክ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መናገራቸውን ፋና ቢሲ ዘግቧል፡፡በዘገባው እንደተመላከተው፤ የመድረኩ አላማ በሕገወጥ መንገድ ለስደት የሚዳረጉ ዜጎችን ለመቆጣጠር እና ለችግር እንዳይጋለጡ ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እና ያለፉትንም መገምገም ሲሆን፤ በዚህም በ2012 እና 2013 ዓ.ም በሕገወጥ መንገድ ከሚሰደዱት በተሻለ የተመላሾች ቁጥር ከፍ ያለበት እንደነበር በመድረኩ ተነስቷል።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን በቀጣይ ዜጎችን ከሕገ ወጥ ስደት ለመታደግ በሚደረገው ጥረት አገርን ለመኖር ምቹ ማድረግ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩትን ሥጋቶች ማስወገድ እንደሚያስፈልግ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን፤ ለዚህም መንግሥት የሰላም የማረጋገጥ ሥራ ላይ አተኩሮ እየሠራ እንደሚገኝ አቶ ደመቀ ተናግረዋል።በመድረኩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ፣ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38149
328
0ሀገር አቀፍ ዜና
“ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚናገሩት እና የሚተገብሩት አንድ ሊሆን ይገባል” ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር
ሀገር አቀፍ ዜና
December 26, 2020
54
ሙሉቀን ታደገ አዲስ አበባ፡- ቀጣዩን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ለማድረግ ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚናገሩት እና በተጨባጭ የሚተገብሩት አንድ አይነት ሊሆን ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናገሩ፡፡ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ባለው ሁኔታ ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚናገሩት እና በተጨባጭ የሚተገብሩት ለየቅል ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ ደግሞ አንዳንድ ፓርቲዎች ሲመቻቸው የሃይል አማራጭን በሌላ ጊዜ ደግሞ ሰላማዊ መስለው እንዲታዩ አድርጓቸዋል፡፡በመሆኑም ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ሕጉን እና የሥነ ምግባር ደንቡን አክብሮ መንቀሳቀስ ይገባቸዋል፡፡ በዚህም ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ጊዜ እና በደህረ ምርጫ በሀገሪቱ ማንኛውም አይነት ግጭት እንዳይከሰት ከማድረግ አንፃር ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የራሳቸውን ሚና መጫወት ይገባቸዋል፡፡ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳባቸውን በመሸጥ ህዝቡን አሳምነውእንዲመረጡ ለማድረግ በምርጫ ሕጉ እና በምርጫ ሥነ ምግባሩ መሰረት ሊንቀሳቀሱ ይገባል የሚሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ በዚህም ቀጣዩን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ማድርግ እንደሚቻል ጠቁመዋል።እንደ ፕሮፌሰር በየነ ገለፃ፤ ሰላማዊ ፖለቲካ የሚያራምዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀገሪቱን ሰላም የሚያናጋ እንቅስቃሴ ውስጥ አይገቡም። ምክንያቱም ሰላማዊ ፖለቲካ የሚያራምዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ሕጉ እና የምርጫ ሥነ ምግባር ደንቡን አክብረው የሚንቀሳቀሱ ናቸው። ካለፉት ዓመታት የምርጫ ልምዶቻችን መገንዘብ እንደቻልነው የምርጫ ሂደትን የሚያደፈርሱ እንቅስቃሴዎች ብዙ ጊዜ በዋነኛነት የሚስተዋለው ከገዢው ፓርቲ ከሚፈፀሙ ያልተገቡ ተፅዕኖዎች እና የምርጫ ህጉን እና የስነ ምግባር ደንቡን ባልተከተሉ የመንግሥት አካላት መሆኑን የገለፁት ፕሮፌሰር በየነ፤ አሁንም በቀጣይ ለሚደረገው ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማድረግ በቀበሌ እና በወረዳ ደረጃ የሚገኙ የገዢው መንግሥት ባለስልጣናት የምርጫ ህጉን እና የስነ ምግባር ደንቡን ማክበር እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል። እንደ ፕሮፌሰር በየነ ገለፃ፤ ምርጫ የሚካሄደው ከፌዴራልና ከክልል ባሻገር በቀበሌ እና በወረዳ ደረጃ ስለሆነ በቀበሌ እና በወረዳ ደረጃ ያሉ የገዢው ፓርቲ አባላት እና የመንግሥት የፖለቲካ ሥራ የሚሠሩ አካላት ከቀድሞው ከኢህአዴጋዊ መንፈስ የፀዱ ሊሆኑ ይገባል። ይህን በቀበሌ እና በወረዳ ደረጃ ያሉ ከኢህአዴጋዊ እንቅስቃሴ ያልተላቀቁ የገዢው መንግሥት የፖለቲካ ሹመኞች በምርጫ ህጉ እንዲገዙ ለማድረግ እስከ ምርጫ ባለው ጊዜ ድረስ የብልፅግና ፓርቲ ማስተካከያ ያደርጋል የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልፀዋል።የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም እንደ አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ ደጋፊዎቹን እና ተከታዮቹን የምርጫ ሕጉን እና የሥነ ምግባር ደንቡን ተከትለው እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ ፓርቲው እየሠራ እንደሚገኝ ፕሮፌሰር በየነ አመላክተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013
https://www.press.et/Ama/?p=38146
308
0ሀገር አቀፍ ዜና
የስፖርት ለሁሉምና የማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴ ፌስቲቫል
ስፖርት
February 10, 2020
23
የማህበረሰብ ስፖርትን «ሁሉም ሰው በስፖርት እንቅስቃሴ እንደ ፍላጎቱና ችሎታው አቅሙ በፈቀደ መጠን መሳተፍ የሚችልበት መድረክ ነው» ሲሉ የስፖርት አዋቂዎች ይገልጹታል። የተሳትፎው ሁኔታ እንደ ዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ መርህ የስፖርት መርሃ ግብር ዓላማ፤ ሰዎች በተወዳዳሪነት ለአሸናፊነት ክብር እንዲበቁ የሚያደርግ አለመሆኑንም ያስቀምጣሉ። ከዚህ ይልቅ ሰዎች በስፖርቱ እንዲዝናኑ፣ ጤንነታቸውን እንዲጠብቁ፣ አካላቸው ለእለት ተዕለት ተግባራት ዝግጁ እንዲሆን፣ በሰዎች መካከል መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር የሚያደርግ መንፈስ እንደሆነ ብያኔ ይሰጣል። በ1990 ዓ.ም በማህበራችን ተግባራዊ የተደረገው የስፖርት ፖሊሲም ይህንኑ በመደገፍ ሕዝቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሰራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባውም አስቀምጧል።ስፖርት ለሁሉ ደግሞ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግና የውድድር አጋጣሚዎችን ቀርጾ ተግባራዊ በማድረጉ አንዱና ዋነኛው አማራጭ እንደሆነ ይታመናል። በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው የስፖርት ለሁሉም የማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴ ፌስቲቫልም ይሄንኑ መሰረት በማድረግ ከሚከናወኑ የስፖርት ሁነቶች መካከል አንዱ ነው። በፌደራል መስሪያ ቤቶች መካከል በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች የሚሳተፉበት የስፖርት ለሁሉምና የማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴ ፌስቲቫል ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል። ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በልዩ ድምቀት የተጀመረው ፌስቲቫሉ፤ ዘንድሮ በተለየ መልኩ ዝግጅት የተደረገበትና በርካታ ቁጥር ያላቸው የፌደራል መስሪያ ቤቶች የተሳተፉበት መሆኑ ተነግሯል ። “ስፖርት ለጤንነት፣ ለወዳጅንት፣ ለሠላም፣ ለአንድነትና ለብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጂሎ፤ ስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል አካላዊና አእምሯዊ ጤንነትን ከመገንባት ባለፈ የጋራ ዓላማ ያለው ኅብረተሰብ ለመገንባት እንደሚረዳ በመክፈቻው ላይ ተናግረዋል። የብሔራዊ ስፖርት ፖሊሲው የትኩረት አቅጣጫም ኅብረተሰቡን በሚኖርበት፣ በሚሰራበትና በሚዝናናበት አካባቢ እንደ ችሎታውና ፍላጎቱ በግልና በቡድን ተሳታፊ ማድረግ ስለሆነ የስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል ይህን ዓላማ ይዞ በየዓመቱ እንደሚከናወንም አመልክተዋል።የስፖርት ፌስቲቫሉ የተዘጋጀው በኦሊምፒክ መርህ መሰረት ህብረተሰቡ በሚማርበት፣ በሚሰራበትና በሚኖርበት አካባቢ በስፖርት እንቅስቃሴ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ እንደሆነም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል። በሌላ በኩል በመንግስት ተቋማት የሚገኙ ሠራተኞች በሚሰሩበት ቦታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የማድረግ ግንዛቤ፣ ፍላጎትና መነሳሳት እንዲኖራቸው ያደርጋልም ተብሏል።በተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች ሠራተኞች መካከል በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች የሚደረገው ውድድር እስከ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን፤ በየስፖርት ዓይነቱ የበላይነትን ይዘው ያጠናቀቁ መስሪያ ቤቶች በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት ሀገር አቀፍ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ። 1ኛው ሀገር አቀፍ የሰራተኞች ስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት ከሰኔ 05 -14/2012 ዓ.ም በባቱ ከተማ ይካሄዳልም ተብሏል።አዲስ ዘመን የካቲት 2/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=27020
322
2ስፖርት
ከተሞች ለቅርጫት ኳስ ያላቸውን ግምት ትዝብት ላይ የጣሉበት ውድድር
ስፖርት
February 11, 2020
17
የቅርጫት ኳስ ስፖርት በዓለማችን ላይ ተወዳጅ ከሆኑ ስፖርቶች መካከል በቀዳሚነት ይቀመጣል። በአገራችንም ቢሆን የቅርጫት ኳስ ስፖርት ጥሩ እንቅስቃሴ የሚደረግበትና በተለይም በከተሞችና ትምህርት ቤቶች አካባቢ በወጣቶች እጅግ ተወዳጅ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ስፖርቱን ለማስፋፋትና ለማሳደግ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን የቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲካሄድ ማድረጉ አንዱ ትልቅ እርምጃ ነው። ከዚህ ጎን ለጎን ስፖርቱ ሰፊ መሰረት ያለው በከተሞች አካባቢ እንደመሆኑ ከሰባት ዓመት በፊት የከተሞች የቅርጫት ኳስ ውድድርን በየዓመቱ በማካሄድ አበረታች እርምጃ ወስዷል። ፌዴሬሽኑ ዘንድሮም የከተሞችን የቅርጫት ኳስ ውድድር ከኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር በቢሾፍቱ ከተማ እንዲካሄድ አድርጓል። ለአምስት ተከታታይ ቀናት ተካሂዶ ባለፈው አርብ በተጠናቀቀው የከተሞች የቅርጫት ኳስ ውድድር በወንዶች መካከል በሚደረገው ፉክክር አዘጋጁ ቢሾፍቱ ከተማን ጨምሮ አዳማ፣ድሬዳዋ፣ሐረሪ፣ቡታጅራ ከተሞች እንዲሁም የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ተሳታፊ ሆነውበታል። በሴቶች መካከል በሚደረገው ፉክክር ግን ባልተጠበቀ መልኩ አሰላ ከተማና የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ብቻ ተሳታፊ ሆነዋል። ከመሐል አገር ራቅ ያሉ ከተሞች በውድድሩ ለመሳተፍ ያሳዩትን ተነሳሽነት ያህል በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች በፉክክሩ ላይ መገኘት አለመቻላቸው ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ መሆኑ የአገራችን ከተሞች ለስፖርቱ እየሰጡት ያለውን ትኩረት ትዝብት ላይ የጣለ ነው። አንዳንድ ከተሞች በውድድሩ መሳተፍ ያልቻሉት የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው የቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው ሲሆን ራቅ ያሉት ከተሞች በአገራችን ከሚታየው የፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ ምክኒያት እንደሆነ የፌዴሬሽኑ የስራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ ይመር ሃይሌ ለአዲስ ዘመን ገልፀዋል።በዚህ ውድድር አግራሞትን ካጫሩት ሁነቶች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አፍንጫው ስር በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ በሚካሄድ ውድድር በወንዶችም በሴቶችም መሳተፍ አለመቻሉ ነው። ከተማውን በሁለቱም ፆታ ወክለው ለመወዳደር ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩት ወጣቶች ከበጀት እጥረት ጋር በተያያዘ መጨረሻ ሰዓት ላይ መሳተፍ እንዳልቻሉ ከተለያዩ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አዲስ አበባ በየወረዳው እንኳ መሳተፍ የሚያስችል እምቅና ሀይል ያለው መሆኑ ይታወቃል። በየትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ያለውን የአዲስ አበባ የወጣቶች ቅርጫት ኳስ ፍቅርና አቅምን አሰባስቦ አለመሳተፉ አሳፋሪ ነው። በአገራችን ከሚገኙ ከተሞች ሁሉ በአፍሪካ ደረጃ ለሚካሄዱ ውድድሮች ጠንካራ ቡድን መገንባት የሚያስችል የቅርጫት ኳስ ፍቅር፣ ጉልበት፣ የፋይናንስና የተጫዋቾች አቅም ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ነገር ግን በዚህ የወጣቶችን ችሎታ፣ አቅምና ጉልበት ለማወቅና ጠንካራ ቡድንን ለመገንባት የሚረዳ የከተሞች ውድድር ላይ አዲስ አበባ ለማሸነፍ ወይም ለመወዳደር ለምን እንዳልቻለ፣ ወይም እንዳልፈለገ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶት ማስተካከል መቻል እንዳለበት የብዙዎች እምነት ነው።አዲስ አበባ የአፍሪካና የኢትዮጵያ መዲና ናት። ወጣቶች፣ ታዳጊዎችና ህጻናት በስፖርት እንዲሳተፉ እድል በመስጠት በስነልቦናና በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ መገንባት፣ በአገር ደረጃ ትውልድን ከሱስና አልባሌ ስፍራ ማራቅ ብቻም ሳይሆን ከተሞቻችንንና ትውልድን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል ግዴታ እንጂ ውዴታ አይደለም። አዲስ አበባ በበጀት እጥረት በውድድሩ አለመሳተፉ የማይመስል ነገር ነው። የከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን የቅርጫት ኳስ ውድድሩ ከተጠናቀቀ አንድ ቀን በኋላ እዚያው ቢሾፍቱ ላይ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ የስፖርት ማህበራት አመራሮችን ለሁለት ቀን ሰብስቦ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሲሰጥ ነበር። በዚህ ስልጠና ላይ ሰላሳ አምስት ከሚጠጉ የስፖርት ማህበራት የተውጣጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል። ለዚህም የሁለት ቀን ስልጠና ከተማ አስተዳደሩ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ማድረጉ አይቀሬ ነው። ጥያቄው ከተማ አስተዳደሩ በስሩ የሚገኙ የስፖርት ማህበራት አመራሮችን አያሰልጥን ሳይሆን ቅድሚያ ለየትኛው መስጠት አለበት ይሆናል። በቅርጫት ኳስ ውድድሩ በሁለቱም ፆታ ለመሳተፍ ቢበዛ ሃያ የሚሆን ተጫዋችና የልዑካን ቡድን ነው የሚያስፈልገው። የበጀት እጥረት ቢኖር እንኳን ውድድሩ በቅርብ ርቀት እንደመካሄዱ ተጫዋቾች እየተመላለሱ እንዲሳተፉ ማድረግ ቀላሉ አማራጭ ነበር። የከተማ አስተዳደሩ የስፖርት ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ በአመራሮቹ ስልጠና ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ‹‹ የአዲስ አበባን የስፖርት ማዕከልነት መልሰን እንገነባለን›› ሲሉ ተደምጠዋል። የከተማዋን የስፖርት ማዕከልነትና ገፅታ መገንባት ከተማዋ በስፖርቱ ያላትን ትልቅ አቅም አውጥታ በማሳየት እንደ ቅርጫት ኳስ ውድድሩ ባሉ አገር አቀፍ መድረኮች ተሳታፊ በመሆንና ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ በመስጠት እንደሚጀምር ሌሎቹም ቢሆኑ ሊማሩበት ይገባል። አዲስ ዘመን የካቲት 3/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=27070
550
2ስፖርት
ስፖርቱን ለማሻገር ተስፋ የተጣለበት ስትራቴጂክ እቅድ
ስፖርት
January 31, 2020
16
የስፖርት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው በእጅጉ እየጨመረ እንደመጣ ይታወቃል። የዓለም አገራት የስፖርት ሴክተሩን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በመረዳት ብቻ የሚቆሙ እንዳልሆኑ በዘርፉ ያስመዘገቡት ውጤት ማሳያ ነው። በዓለማችን በበርካታ አገራት ከሌሎች ሴክተሮች ባልተናነሰ መልኩ ለስፖርት ልማቱ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይን በማፍሰስ ስማቸውን በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ከማድረግ አልፈው ብዙ ማትረፍ ችለዋል፡፡ ለስፖርት ሴክተሩ ትልቅ ትኩረት መስጠት በማህበራዊ ፋይዳው አምራችና ጤናማ ዜጋን በማፍራት ረገድ ያለውን ውጤት ከመረዳት ይመነጫል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ትላልቅ ውድድሮች በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ከሚገኘው ድል ጀርባ ለአገር ፖለቲካዊ ትርፍ ማጣጣም ማስቻሉንም መታዘብ ይቻላል፡፡ ስፖርተኞች ከውድድር ድል በኋላ የሚያገኙት ረብጣ የሽልማት ገንዘብና የአገር ኢኮኖሚን በማንቀሳቀስ የሚገኘው ትርፍም ቀላል አይደለም፡፡ የስፖርቱን ዘርፈ ብዙ ፋይዳን በጥልቅ በመረዳት የስኬት ማማ ላይ የወጡ እንደ ጀርመን ያሉ አገራትን ማንሳት ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስፖርት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ረገድ ጀርመን በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ናት። ይህች አገር ስፖርቱ በጠንካራ የፋይናንስ መሠረት ላይ ማቆም መቻሏ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መሠረቱን ሳይለቅ መጓዝ የቻለ አደረጃጀት መፍጠሯ ለስኬቷ ምክንያት ተደርጎ ይነሳል፡፡ የጀርመን መንግሥት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ከሚያፈስባቸው ዘርፎች ዋነኛው ስፖርት ሊሆን የቻለውም ለዚህ ነው፡፡ ስፖርት በጀርመን ኢኮኖሚ ውስጥ 2 ነጥብ 2 በመቶ ድርሻ ይይዛል። ስፖርቱን በፋይናንስ አቅም እንዲጎለብት ከማድረግ በተጓዳኝ፤ ጠንካራ አደረጃጀት የተዘረጋለት ነው። በጀርመን የስፖርት ዘርፍ ይህን መልክ መላበሱ ከዘርፉ የሚገኘው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ እንዲጎላ ማድረጉ ይነሳል። በኢትዮጵያ ለስፖርቱ ዘርፍ የተሰጠውን ትኩረትና ውጤት ከሌሎች አገራት አንጻር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ በቀደሙት ጥቂት ዓመታት ለስፖርቱ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች፣ ከመንግሥትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በኩል ኢትዮጵያ ለስፖርቱ ዘርፍ ተገቢ ትኩረት መስጠቷ ይነገራል፡፡ ለስፖርት ዘርፍ በተገቢው ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ አለመሆኑንና የዘርፉ እድገት በቁልቁለት ጉዞ ውስጥ መሆኑም በሌላ ወገን ይነሳል። የስፖርት ሴክተሩ ውጤት አልባ መሆኑ ግን ሁለቱንም ወገኖች እንደሚያስማማ ለመታዘብ ይቻላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በመንግሥት ደረጃ ይኸው እውነታ ታምኖበት እየተሰራ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ እየተነገረ ይገኛል። በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የዕቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንድሪስ አብዱ፤ በአገሪቱ ባለፉት ሁለት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመናት ዘርፉ ለአገሪቱ ማበርከት ካለበት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታዎች አንፃር በሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመገኘቱና ውጤቱም በመላ አገሪቱ ተደራሽነት ላይ ክፍተቶች መኖራቸው እንደታመነበት ይናገራሉ:: ለዚህም የስፖርት ሴክተሩን መሠረታዊ ችግር በተረዳ መልኩ የ10 ዓመት የስፖርት ሴክተር ስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲሆን በኮሚሽኑ በኩል እንቅስቃሴ ከተጀመረ መሰንበቱን ያስረዳሉ፡፡ ስፖርቱን ወደፊት ለማራመድ እንቅፋት ከሆኑ መሠረታዊ ምክንያቶች መካከል በዋነኛነት ከአደረ ጃጀት፣ ከፋይናንስ፣ ከሰው ኃይል ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች መሆናቸውን የጠቆሙት የኮሚሽኑ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ እንየው አሊ፤ የ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅድ የተጠቀሱትን ክፍተቶች በጥናት እንዲመልስ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ያስቀምጣሉ፡፡ ስትራቴጂክ ዕቅዱ አገራዊ የስፖርት ሪፎርምን መነሻ በማድረግ በስፋት የተዘጋጀ መሆኑንም ይገልፃሉ። በመሆኑም በአገሪቷ ቀጣይ የስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ለውጥና ውጤት ማምጣት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡ የስፖርት ሴክተሩ ሪፎርም ፕሮግራም ዘርፍን መለወጥ የሚችሉ ብዙ ያመላከታቸው ነጥቦች እንዳሉም ያስረዳሉ። በዚህም ከአደረጃጀት ፣ ከፋይናንስ፣ ከሰው ኃይልና ሌሎችም ጉዳዮች አንፃር ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚቻል ተስፋ የተጣለበት መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ በሪፎርሙ ላይ የሴክተሩ ችግሮች የተለዩ ሲሆን በተመሳሳይ መፍትሄዎች መመላከታቸውንም ያክላሉ። ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገውና ከስፖርት ሪፎርሙ የሚቀዳው የ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅድ ዘርፍን የተሻለ እንደሚያደርገውም ያላቸውን እምነት ይገልፃሉ፡፡ አቶ እንድሪስ በበኩላቸው፤ በቀጣይ ዓመት ተግባራዊ የሚደረገው ስትራቴጂክ ዕቅድ ትኩረት ያደረጋቸው አንኳር ጉዳዮች መኖራቸውን በመጥቀስ በሴክተሩ በቀጣይ 10 ዓመታት በትኩረት የሚሰራባቸው ተብለው የቀረቡት ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች እንዳሉ ይናገራሉ:: በመጀመሪያ መንግሥታዊ የስፖርት አደረጃጀቶችን የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም በማጎልበት፤ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን እና የአሠራር ሥርዓቶችን ተግባር ላይ ማዋል ፤ ሕዝባዊ የስፖርት አደረጃጀቶችን በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ መስፈርቶች መሠረት ማደራጀት የስትራቴጂክ እቅዱ ትኩረት መሆናቸውን ያስቀምጣሉ:: በሁለተኛ ደረጃ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የማሰልጠኛ ማዕከላት ተደራሽነት፣ ሕጋዊነት እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን መሠረት በማድረግ በጥራት የሚገነቡበትን ስልት ሥራ ላይ ማዋል ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ያስረዳሉ። በአህጉር እና ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች በተፈጥሮ ብቃታቸውን መሠረት በማድረግ አገራችንን የሚወክሉ እና ውጤታማ የሆኑ ተተኪ ስፖርተኞችን በሳይንሳዊ ስልጠናዎች ማፍራት ትኩረት ተደርጎ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑንም ያብራራሉ፡፡ ስፖርት ለማህበራዊ ልማትና ለአገር ብልፅግና ፣ ለሕዝቦች መቀራረብ ፣ ለገፅታ ግንባታ እና ለቱሪዝም ዕድገት መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ትኩረት ሰጥቶ መስራትም የስትራቴጂክ እቅዱ ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው። በስትራቴጂክ ዕቅዱ የተጠቀሱትን አንኳር ጉዳዮች መሠረት አድርጎ የተዘጋጀው ግብ ወደ ተግባር መቀየር ከተቻለም የስፖርት ሴክተሩ ውጤታማ መሆን እንደሚችል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፤ በአገር አቀፍ የስፖርት ፖሊሲ ባለፉት ሁለት አስር ዓመታት የተመዘገቡ በርካታ አበረታች ውጤቶች ቢኖሩም የአገራችን የስፖርት ዕድገት ከዕድሜው አኳያ ሲመዘን በሚፈለገው ደረጃ ባለማደጉ ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ያመላክታሉ። በአሁኑ ወቅት መንግሥት ስፖርቱን እንደ አንድ የልማትና ብልፅግና መሣሪያ አድርጎ በመውሰድ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየሰራ እንደሚገኝ የሚናገሩት አቶ ሃብታሙ ፤ የስፖርት ዘርፍ በታሪኩ በዚህ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እንደማያውቅ ያብራራሉ:: የብሔራዊ የስፖርት ምክር ቤት በኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሰብሳቢነትና የበላይ ጠባቂነት መመራቱ መንግሥት ለስፖርቱ ሴክተር የሰጠውን ትኩረት እንደሚያሳይም ያስቀምጣሉ፡፡ በመሆኑም የስፖርት ዘርፍን ከትናንት በተሻለ መልኩ ዛሬ ትኩረት በማግኘቱ ዕድሉን በአግባቡ በመጠቀም ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡አዲስ ዘመን አርብ ጥር 22/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=26437
722
2ስፖርት
የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ
ስፖርት
January 31, 2020
47
የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በቻይና የሚካሄደውን የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ማራዘሙን አስታወቀ። እአአ ከመጋቢት 13 እስከ 15 ቀን 2020 በቻይና ናጂንግ ከተማ ሊካሄድ የነበረው 18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክውድድር ለ12 ወራት ያህል እንዲራዘም መደረጉን የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ዋቤ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል። የዓለም አትሌቲክስ የጤና ቡድን ከዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ጋር በቻይናና ከቻይና ውጪ በሌሎች አገራት የኮሮኖ ቫይረስን አስመልክቶ በቅርበት መረጃዎችን በመለዋወጥ ባገኘው መረጃ ኮሮና ቫይረስ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ለመረዳት መቻሉን ዘገባው አመልክቷል። በቻይና መነሻውን ያደረገው ኮሮና ቫይረስ 130 ሰዎችን የገደለ ሲሆን፤ በ16 ሀገራት ተስፋፍቷል። ከስድስት ሺህ ሰዎች በላይም በቫይረሱ መጠቃታቸውን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በመነሳት የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቻይና በተስፋፋው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ውድድሩን በተባለለት ጊዜ ማካሄድ አስቸጋሪ መሆኑን በማመን ውድድሩ እንዲራዘም ውሳኔ አሳልፏል። በመሆኑም እ.አ.አ በ2021 ውድድሩ እንዲካሄድ አማራጭ መቅረቡን አስታውቋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድሩን በሌሎች አገራት ለማድረግ አስቦ እንደነበር ያስታወቀው ፌዴሬሽኑ ቫይረሱ ከቻይና ውጪ ወደ ሌሎች አገራት የመሰራጨቱ ጉዳይ አሳሳቢ ስለሚሆን አገር የመቀየር ምርጫውን መሰረዙን አመልክቷል። ብዙ አትሌቶች ውድድሩ እንዲካሄድ ካላቸው ፍላጎት አንጻርም የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድሩን ሙሉ ለመሉ የመሰረዝ ምርጫውንም እንደተወውም ነው ተጠቀሰው። ይህ በመሆኑ ምክንያት ናንጂንግ እ.አ.አ በ2021 ውድድሩን የሚካሄድበት ምቹ ጊዜ ማግኘት እንደምትችል የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል። የዓለም አትሌቲክስ ከአትሌቶች፣ ከናንጂንግ የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴና ከአጋሮች ጋር የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር እ.አ.አ 2021 የሚካሄድበት ቀን ለመወሰን በቅርበት እንደሚሰራም አስታውቋል። የዓለም አትሌቲክስ ቻይና የኮሮኖ ቫይረስን ለመከላከል እያደረገች ያለችውን ጥረት እየተከታተለ እንደሆነና ተቋሙ አገሪቷ እያከናወነች ላለው ሥራ ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል መግባቱንም አስፍሯል። ቫይረሱን አስመልክቶ ለአትሌቶች፣ ለብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖችና አጋሮች በፍጥነት እየተለዋወጡ ያሉ ጉዳዮችን ማሳወቅ ተገቢ እንደሆነም ማመልክቱን ቢቢሲ ዘግቧል። የእስያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በየካቲት ወር 2012 ዓ.ም በቻይና ሀንግዙ ግዛት ሊካሄድ የነበረውን ዘጠነኛው የእስያ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር መሰረዙን ከአራት ቀናት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል።አዲስ ዘመን አርብ ጥር 22/2012ዳነኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=26439
282
2ስፖርት
በደቡብ ክልል በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ተሳትፎ ያደረጉ 711 አመራሮች ከኃላፊነት ተነሱ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 24, 2020
18
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በደቡብ ክልል ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ተሳትፎ ያደረጉ 711 አመራሮች ከኃላፊነት መነሳታቸውን የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሰናይት ሰለሞን አስታወቁ። ኃላፊዋ በክልሉ የተካሄደውን የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫው ወቅትም፣ በክልሉ በጉራፈርዳ፣ በወላይታ፣ በኮንሶ ዞን እና በዙሪያው ባሉ ልዩ ወረዳዎች የአደረጃጀት እና የወሰን ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ የሕዝቡን ጥያቄዎች በኃይል ማስፈጸም ይቻላል በማለት የህወሓት ጁንታ ለግጭት አመቺ የሆኑ ቦታዎችን በመጠቀም ህብረተሰቡ ያልተገባ ዋጋ እንዲከፍል ማድረጉን ተናግረዋል።በብዝሀነቱ የሚታወቅና ለሌሎች አካባቢዎችም ተምሳሌት የሆነውን የደቡብ ክልል ጽንፈኛው የህወሓት ጁንታ ኃይል ለእኩይ አላማ ሲጠቀምበት እንደነበርም በዝርዝር መገምገሙን የገለጹት ወይዘሮ ሰናይት፤ ጽንፈኛው ቡድን ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችንበመጠቀም ሀብት በመመደብ ሲንቀሳቀስ መቆየቱንም አብራርተዋል።በዚህ ምክንያት በተፈጠረው ችግር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው መኖሩ የተረጋገጠ 711 አመራሮች ከኃላፊነት መነሳታቸውን በመጠቆምም፤ 918 የሚሆኑት ደግሞ ከቦታቸው እንዲሸጋሸጉ መደረጉን ተናግረዋል። በተጨማሪም 1 ሺህ 966 አመራሮች በማስጠንቀቂያ መታለፋቸውን መግለጻቸውን ነው ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት የክልሉን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጠቅሶ የዘገበው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37996
146
0ሀገር አቀፍ ዜና
ፎረሙ፣ የሕንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 24, 2020
9
በኃይሉ አበራአዲስ አበባ፡- የሕንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባሉ ሰፊ የኢንቨስትመንት ዘርፍ አማራጮች እንዲሰማሩ የማማከርና የግንዛቤ ድጋፍና እንደሚያደርግ በኢትዮጵያ የሕንድ ኢንቨስተሮች ፎረም አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከትናንት በስቲያ በተሻሻለው የኢንቨስትመንት ሕግ ዙሪያ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የሕንድ ባለሃብቶች ገለጻ አድርጓል።በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ የሕንድ ኢንቨስተሮች ፎረም ሊቀመንበር ማዮር ኮታሪ እንደገለጹት፤ ፎረሙ የህንድ ባለሀብቶችን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ነው። ኢትዮጵያ ያፀደቀችው አዲሱ የኢንቨስትመንት ዓዋጅ ደግሞ በተለይ ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ የነበሩ ዘርፎችን ክፍት በማድረጉ ባለሀብቶችን ያበረታታል። በመሆኑም የሕንድ ባለሃብቶች ይሄን እድል ተጠቅመው በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ ፎረሙ ድጋፍ ያደርጋል።የሕንድ ባለሀብቶችና በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በእርሻ፣ በቱሪዝም፣ በትምህርትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በኬሚካል፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ በመድኃኒት መስኮች ተሰማርተው እየሰሩ መሆኑን ያስታወቁት ሊቀመንበሩ፤ ፎረሙ ከሕንድ የሚመጡ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ጥረት እንደሚያደርግም ገልጸዋል። እንደ ሊቀመንበሩ ገለጻ፤ የህንድ ቢዝነስ ፎረም ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የማበረታታት እና የማማከር ስራ እየሰራ ይገኛል። ከውጭ ሀገር የሚመጡ ኢንቨስተሮች ወደ ኤምባሲ ሲሄዱ ኤምባሲው የህንድ ኢንቨስትመንት ፎረም የማማከር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚልክበት የትስስር አሰራርም አለው። በመሆኑም በፎረሙ አማካኝነት ያሉትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ከፎረሙ ጋር በመወያየት አዋጭ በሆነው የኢንቨስትመንት ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ።የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እያዘጋጀ በሚገኘው ዓይነት ሴሚናሮችም ከመንግስት አካላት ጋር ውይይት የሚያስፈልግ ከሆነ በኤምባሲው በኩል የምክክር መድረክ በማዘጋጀት ፎረሙ የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ የገለጹት ሊቀመንበሩ፤ ይሄን አይነት አሰራር መኖሩ ደግሞ በርካታ ችግሮችን ተወያይቶ ለመፍታትም ሆነ በውጭ ያሉ ባለሃብቶች ግንዛቤ ፈጥረው ወደኢትዮጵያ እንዲመጡ እድል የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል።ከህንድ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ በመሆናቸው እና ባለሙያዎችም ጭምር አብረው የሚገቡ በመሆኑ ለቴክኖሎጂ ሽግግሩም ሆነ በኢትዮጵያ ካለው የኢኮኖሚ አቅም አኳያ በቀላሉ የሚለመዱ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑን በመግለጽም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ኢንጂነሮች እና ቴክኒሽያኖች ከህንድ ከመጡት ባለሙያዎች ልምድ እየወሰዱ በመሆኑ በተለያዩ ፋብሪካዎች የሚበረታታ የቴክኖሎጂ ሽግግር እየተስተዋለ መሆኑንም አመልክተዋል። “ኢትዮጵያ ገና በጣም የሚሰራባት አገር ነች፤ ለመስራትም ብዙ እድሎች ስላሉ የሚመጣው ኢንቨስተርንም ብዙ አማራጮችን መኖሩን እየተመለከተ ነው” ያሉት ሊቀመንበሩ፤ በማዕድን፣ በፋርማሲ፣ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ በኬሚካል፣ በቴክኖሎጂ፣ በሶፍትዌር ማበልጸግ እና ሌሎችም ዘርፎች ላይ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎች መጠቀም እንደሚገባም ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37995
303
0ሀገር አቀፍ ዜና