translation
translation
{ "amh": "የሊባኖስ አዲሱ ፓርላማ ዓለም-አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕግጋትን የሚጥሱትን፣ አላስፈላጊዎቹንና ኢ-ፍትሃዊዎቹን የስም ማጥፋት ወንጀልን ለመቅረፍ የወጡትን ሕጎች በአስቸኳይ መሰረዝ አለበት፡፡", "en": "Lebanon’s new parliament should act quickly to abolish laws that criminalize defamation, which are disproportionate, unnecessary, and violate international human rights law." }
{ "amh": "የሊባኖስ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስም ማጥፋትን እንደወንጀል የሚቆጥርና በፕሬዝደንቱ፣ በባንዲራውና በሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት መሳለቅ ላይ ልዩ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው፡፡", "en": "Indeed, Lebanon's penal code criminalizes defamation and makes special provisions against insulting the president, the flag, and other public officials." }
{ "amh": "የሃገሪቱ ወታደራዊ ሕግ ‹‹በባንዲራው ወይም በሰራዊቱ መቀለድ››ን እንደወንጀል ይቆጥራል፡፡", "en": "The country's military code criminalizes insulting the flag or army." }
{ "amh": "የተዘረዘሩት ወንጀሎችን መፈፀም፣ የገንዘብ ቅጣትና እስር ያስፈርዳል፤ ለጋዜጠኝነት ስራ ልዩ ከለላ አልተሰጠም፡፡", "en": "These offenses all are punishable with fines and prison time, and offer no special exception for journalistic work." }
{ "amh": "ፍሪደምሃውስ 2016 ላይ ስለሊባኖስ ባወጣው ዘገባ መሰረት፣", "en": "According to Freedom House 2016 Report on Lebanon:" }
{ "amh": "ሊባኖሳዊያን ጋዜጠኞች የሚዲያ ሕጎቹ እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ፣ ምስቅልቅላቸው የወጣና በአሻሚ ቃላት የተሞሉ መሆናቸውን ይገልፃሉ፡፡", "en": "Lebanese journalists complain that media laws are chaotic, contradictory, and ambiguously worded." }
{ "amh": "ጋዜጠኞችን ለመክሰስ የሚውሉ፣ ስለሚዲያ የሚያወሩ አንቀፆች፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ውስጥ አሉ፤ የህትመት ሕግ፣ 1994 ላይ የወጣው- የኦዲዮቪዥዋል ሚዲያ ሕግና ወታደራዊ ሕጉ ከዚሁ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡", "en": "Provisions concerning the media, which justify the prosecution of journalists, can be found in the penal code, the Publications Law, the 1994 Audiovisual Media Law, and the military justice code." }
{ "amh": "ሊባኖስ ውስጥ የንግግር ነፃነት ላይ ጫና መፈጠር", "en": "Rising pressure on free expression in Lebanon" }
{ "amh": "በሊባኖስ የሕግ ሁኔታ ውስጥ ጋዜጠኞች ላይ ክሶች መቅረባቸው፣ የተለመደ ነገር ነው፡፡", "en": "In Lebanon's legal landscape, court cases against journalists are not a new phenomenon, but such incidents have multiplied in recent months, with a smattering of charges against journalists, TV show hosts, and commentators." }
{ "amh": "ከቅርብ ወራት ወዲህ ግን ክሶች ተደጋግመው ጋዜጠኞች፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢዎችና አስተያየት ሰጪዎች ላይ እየቀረቡ ነው፡፡", "en": "On January 24, 2018, TV comedy show host Hisham Haddad was prosecuted for making jokes at the expense of Prime Minister Saad Hariri and Saudi crown prince Mohammad Bin Salman." }
{ "amh": "የLebanon Debate የጉምሩክ ዲሬክተሩን ስም በማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ፣ መጋቢት፣ 2018 ላይ ለስድስት ወራት እንዲታሰርና 10 ሚሊየን የሊባኖስ ሊራ እንዲቀጣ ተፈርዶበታል፡፡", "en": "In March 2018, the owner of the website Lebanon Debate was sentenced to six months in prison and was ordered to pay 10 million Lebanese Lira, after being found guilty of libel in a case brought by the Director General of Customs." }
{ "amh": "ሊባኖሳዊው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ ማርሴል ጋኔም አንግዳ አድርጎ ያቀረባቸው፣ ፕሬዝደንት ኡውንና ሚኒስትር ባሲልን ‹‹የሂዝቦላህን የሽብር እንቅስቃሴ ይደግፋሉ›› ብለው የተቹ- ሁለት የሳዑዲ ጋዜጠኞች ላይ የቀረበውን ክስ ከተከላከለ በኋላ፣ ሕጋዊነትን በመፃረር ክስ እንደገና ተከስሷል፡፡", "en": "In November 2017, prominent Lebanese TV host Marcel Ghanem was prosecuted for obstruction of justice after he resisted charges brought against two of his guests, both Saudi journalists, who denounced Lebanese President Aoun and Minister Bassil of being Hezbollah's partner in terrorism." }
{ "amh": "ጋኔም ላይ የቀረበው ከስ ቆይቶ ውድቅ ተደርጓል፡፡", "en": "The case against Ghanem was dropped." }
{ "amh": "በ L'Orient Le Jour ጋዜጣ በቀረበ ፅሁፍ ማርሴል ጋኔም ‹‹ገዢው ቡድን ሽብርተኝነትን ወይም እስራኤልን በመፋለም ስም›› ጋዜጠኞችን እንደሚያስርና እንደሚወነጅል ተናግሯል፡፡", "en": "In another article written by L'Orient Le Jour, Marcel Ghanem was reported saying that the arrests of journalists and their convictions was the result of muzzling practiced by the ruling powers under the cover of the struggle against terrorism or Israel." }
{ "amh": "የሚዲያ ሰዎች ላይ የስም ማጥፋት ክሶችን የሚያቀርቡት መንግስታዊ ፍርድ ቤቶች ብቻ አይደሉም፡፡", "en": "But public prosecutors are not the only legal entities bringing charges of defamation and libel against media workers." }
{ "amh": "ጥር 10፣ 2018 ላይ የለየለት ጨካኝ እንደሆነ የሚገለጽለት ወታደራዊ ፍረድ ቤት፤ ሊባኖሳዊቷ ጋዜጠኛና አጥኚ ሃኒን ጋዳር 2014 አሜሪካ ውስጥ የተካሄደ ስብሰባ በመገኘት፣ የሊባኖስን ጦር ስም በማጥፋቷ፣ በሌለችበት ፈርዶባት ነበር፡፡", "en": "On January 10, 2018, the Lebanon's notoriously harsh military court sentenced in absentia Lebanese journalist and researcher Hanin Ghaddar for defaming the Lebanese army at a conference held in the USA in 2014." }
{ "amh": "ብዙም ሳይቆይ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡", "en": "Her sentence was later overturned." }
{ "amh": "ይህ ከሆነ ከአስር ቀናት በኋላ፣ ወታደራዊ ደህንነቱ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ የሆነው፣ ኦቫዳ ዩሱፍ ፌስቡክ ላይ በፃፈው ፅሁፍ ሰበብ፣ ከስሶት ነበር፡፡", "en": "Ten days later, military intelligence summoned human rights defender Ovada Yousef over Facebook posts." }
{ "amh": "ዩሱፍ ለሂዩማን ራይትስ ዎች እንደተናገረው ለአራት ቀናት በጦርና በፖሊስ ሰራዊት አማካኝነት ታስሮ ነበር፡፡", "en": "Yousef told Human Rights Watch that he was detained by the military and police for four days." }
{ "amh": "ለሚዲያና የንግግር ነፃነት የሚታገለው፣ ማሃራት ፋውንዴሽን ለሊባኖስ የሕግ ሃላፊዎች፣ ባለስልጣናትን የመተቸት መብት እንዲያስከብሩ ጥሪ አቅርቧል፣", "en": "Maharat Foundation, a media and free speech NGO, has called for Lebanese judicial authorities to take into account the right of criticism against public persons:" }
{ "amh": "ማሃራት አዲሱ ፓርላማ በተከበሩ ጋሰን ሙካቢር የቀረበውን- ማንም ሰው ኢንተርኔትና ተዛማጅ መድረኮች ላይ ሃሳቡን ስለገለፀ ብቻ የሚታሰርበትን ሁኔታ አንዳይኖር የሚያደርግ የሕግ ማሻሻያ ሃሳብ ተቀብሎ፣ በአፋጣኝ እንዲያጸድቅ ጥሪውን ያቀርባል፡፡", "en": "Maharat also calls on the new parliament to speed up the reforms it has introduced with the MP Ghassan Mukhaiber, notably the abolition of the prison sentence and the preventive detention of anyone expressing his opinion by any means, including the Internet, and broadening the concept of public criticism." }
{ "amh": "በአሁኑ ሰዓት እየተደረጉ ያሉት ጥረቶች፣ ሃገሪቷ ውስጥ ዕውነተኛ ለውጥን ያመጡ እንደሆነ፣ በጊዜ ሂደት ውስጥ የምንመለከት ይሆናል፡፡", "en": "Time will tell if their initiative amounts to real change in the country's free speech environment." }
{ "amh": "የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እንዴት ነውጥ ቀሰቀሰ (ክፍል አንድ)", "en": "How the murder of musician Hachalu Hundessa incited violence in Ethiopia: Part I" }
{ "amh": "ግምቶች በረዥም ጊዜ የብሔር ውጥረቶች ላይ ተመሥርተው ይራገቡ ጀመር", "en": "Speculation began to fly amid long-standing ethnic and political tensions" }
{ "amh": "የአርታኢ ማስታወሻ፦ ይህ ባለ ሁለት ክፍል ትንታኔ የታዋቂው ኦሮሞ ሙዚቀኛ ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ የተቀሰቀሰው የብሔረሃይማኖት ነውጥ በመረጃ ማዛባት እንዴት እንደተቀጣጠለ ያሳያል። ክፍል ሁለትን እዚህ ያንብቡ!", "en": "Editor’s note: This is a two-part analysis on Hachalu Hundessa, a popular Oromo musician whose murder incited ethnoreligious violence fueled by disinformation online. Read Part II here." }
{ "amh": "ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ሀጫሉ ሁንዴሳ የፈጠራ ተሰጥኦውን ተጠቅሞ የኦሮሞ ሕዝብን በማነቃቃቱ ዝናን አትርፏል።", "en": "Iconic Ethiopian singer Hachalu Hundessa gained prominence for using his creative talent to raise the consciousness of the Oromo people." }
{ "amh": "አርቲስቱ ሰኔ 22 ቀን፣ በአዲስ አበባ ዳርቻ ባለ የመኖሪያ ስፍራ ተገድሏል።", "en": "He was assassinated in a suburb of Ethiopia’s capital, Addis Ababa, on June 29." }
{ "amh": "የዛን ዕለት ምሽት 3፡30 ላይ ጥላሁን ይልማ ነው የተባለ ሰው ሀጫሉ ከመኪናው እየወረደ ሳለ፣ ደረቱን በጥይት ተኩሶ መታው።", "en": "That night, at 9:30 pm, as Hachalu was exiting his vehicle, a man named Tilahun Yami allegedly walked up to his car and fired a gun into the artist’s chest." }
{ "amh": "በቅርብ ወደ ሚገኘው ሆስፒታል ቢወሰድም ከሞት ሊተርፍ አልቻለም።", "en": "He was rushed to the nearest hospital, where he was officially declared dead." }
{ "amh": "ጥይቱ የውስጥ የሰውነት አካሉ ላይ ጉዳት እንዳደረሰ በኋላ ተገልጿል።", "en": "It was later determined that the bullet severely damaged his internal organs." }
{ "amh": "የአዲስ አበባ ፖሊስ ሁለት ሰዎች ተጠርጥረው መታሰራቸውን አሳውቋል።", "en": "Addis Ababa’s police chief reported two suspects were arrested." }
{ "amh": "ከሁለት ቀን በኋላ፣ ባለሥልጣናቱ ከሌሎች ሁለት ሌሎች አባሪዎቹ ጋር ተጠርጣሪውን ነፍሰ ገዳይ ክስ መሥርተውበታል።", "en": "After a few days, government authorities charged an alleged assassin along with two other accomplices." }
{ "amh": "የግድያው ዜና ከተሰማ በኋላ አገሪቱ ተከትሎ የመጣውን ነውጥ ለመጋፈጥ ተገድዳለች።", "en": "In the wake of his murder, the country has struggled to come to terms with the violence that followed." }
{ "amh": "የሀጫሉ ግድያ እውነታ ገና ሳይጠራ፣ ፖለቲከኞች እና አራማጆች ግምታቸውን በመናገር ለረዥም ጊዜ በውጥረት ውስጥ የኖሩትን በኢትዮጵያ ሁለት ብዙኃን ብሔሮች ማለትም አማራ እና ኦሮሞ ልኂቃን መካከል ያለ ውጥረት አባባሱት።", "en": "The truth of Hachalu's assassination is not yet fully clear, and in its aftermath, speculation began to fly as politicians and activists stoked long-standing tensions between Oromo and Amahara elites, two of Ethiopia's largest ethnic groups." }
{ "amh": "የዛኑ ዕለት ሐዘንተኞች የአዲስ አበባን እና የኦሮሚያን ከተሞች አጥለቀለቋቸው።", "en": "That day, mourners flooded the streets of Addis Ababa and cities and towns across Oromia state." }
{ "amh": "በማግስቱ፣ ሀጫሉ የመጨረሻ አወዛጋቢ የነበረ ቃለ ምልልሱን የሰጠበት የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ፣ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) የአርቲስቱ አስከሬን ከአዲስ አበባ ወደ ትውልድ ስፍራው አምቦ አሸኛኘት በቀጥታ እያስተላለፈ ነበር።", "en": "The next morning, Oromia Media Network (OMN), a satellite TV station on which Hachalu had his last contentious interview, provided online and TV coverage as his casket was transferred from Addis Ababa to Hachalu’s hometown, Ambo." }
{ "amh": "በቴሌቪዥን እየተላለፈ የነበረው ይህ አሸኛኘት ሀጫሉ የት ነው መቀበር ያለበት በሚል የባለሥልጣናት እና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ደም አፋሳሽ ትግል መድረክነት ተቀየረ። የኦኤምኤን ስርጭት የአስከሬን መኪናው ወደ አዲስ አበባ ሲዞር ተቋረጠ።", "en": "The slow, televised journey turned into a deadly battle between government authorities and opposition politicians over where Hachalu would be buried, and OMN interrupted its coverage as the hearse was forced to return to Addis Ababa." }
{ "amh": "ያኔ በአዲስ አበባ ቢያንስ ዐሥር ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ ጉዳት ደረሰባቸው።", "en": "At least ten people were killed and several were injured in Addis Ababa." }
{ "amh": "ግርግሩ የኦኤምኤን የቀድሞ መሪ ጃዋር መሐመድንና በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞችን እስር ግጭቱን ቀስቀሰዋል በሚል አስከተለ።", "en": "The scuffle led to the arrest of several opposition politicians including Jawar Mohammed, an OMN figurehead, and opposition politician Bekele Gerba, who were both charged with instigating the mayhem." }
{ "amh": "ግራ መጋባቱ መንግሥት የሀጫሉን አስከሬን በሄሊኮፍተር ወደ አንቦ ከወሰደው በኋላም ቀጠለ። ተቀናቃኞቹ ግጭታቸው በመቀጠሉ ቤተሰቦቹ ተገቢውን የቀብር ስርዓት ለማድረግ ተቸግረዋል።", "en": "Confusion swirled after government authorities eventually took Halachu's body back to Ambo by helicopter, where feuding parties continued to clash, denying the bereaved family members a proper burial." }
{ "amh": "ይህ በእንዲህ እያለ ግርግሩ እና ነውጡ ቀጥሏል።", "en": "Meanwhile, turmoil and violence ensued." }
{ "amh": "የሦስት ቀናት ነውጥ በኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ቀጥሎ ብዙ ዋጋ አስከፈለ፦ 239 ሰዎች ሞቱ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ተጎዱ፣ ከ7,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ነውጥ በማስነሳት እና በሚሊዮን ብሮች የሚቆጠር የንብረት ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረው ታሰሩ።", "en": "A three-day rampage gripped parts of Oromia and Addis Ababa, at a substantial cost: 239 people were left dead; hundreds of others were injured and more than 7,000 people were arrested for violence and property damage worth millions of Ethiopian birr." }
{ "amh": "ሰኔ 23 ቀን፣ መንግሥት ነውጦችን ለመከላከል በሚል ኢንተርኔት ተዘግቶ ለሦስት ሳምንት እንዲቆይ አደረገ።", "en": "On June 30, the government imposed an internet shutdown to attempt to halt calls for violence circulating on social media that lasted three weeks." }
{ "amh": "በርካታ ሰዎች በመንግሥት ጥይት ተመትተው ተገድለዋል። ሆኖም የአሜሪካ ድምፅ እና አዲስ ስታንዳርድን ጨምሮ፣ በርካታ የዜና አውታሮች በኦሮሚያ ብዝኀ-ብሔር እና ብዝኀ-እምነት ከተሞች ውስጥ የተፈፀሙ ኦሮሞ ያልሆኑ እና ሙስሊም ያልሆኑ ቤተሰቦች ላይ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ የደረሰውን ጥቃት ዘገቡ።", "en": "A number of people were shot and killed by government security forces, but several news outlets including Voice of America and Addis Standard reported that angry mobs from the Oromo ethnic group attacked multiethnic, interfaith towns and cities in southeastern Oromia, targeting non-Oromo, non-Muslim families in the region." }
{ "amh": "ብዙዎቹ ነውጦች በአማራ-ኦሮሞ መሥመር የተጠመዱ ይሁኑ እንጂ ሃይማኖት ውስብስብና መንደርተኛ በሆነ የብሔር አረዳድ ሳቢያ ማዕከላዊ ሚና ሳይጫወት አልቀረም፦ የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሞ ማኅበረሰብ ማንነት ሁኔታ በእስልምና አማኝነት እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪነት ጥምር የሚገለጽ ነው።", "en": "Most of the violence fell along ethnic Amahara-Oromo lines, but religion may have played a more central role due to an intricate, localized understanding of ethnicity: The southeast Oromo community’s ethnic identity markers usually combine the religion of Islam and the Afan-Oromo language." }
{ "amh": "አንድ የአካባቢው ነዋሪ የሀጫሉን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ትውፊት የተዘጋጀ የቀብር ሥነ ስርዓት በቴሌቪዥን ከተመለከተ በኋላ “እኛ እኮ ሀጫሉ ኦሮሞ መስሎን ነበር” ብሏል ተብሏል።", "en": "A local farmer reportedly said “we thought Hachalu was Oromo” after he watched Hachalu's televised funeral rites that followed the traditions of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church." }
{ "amh": "የተለያዩ ዘገባዎች እንደገለጹት፣ ብዙዎቹ የዘግናኝ ነውጥ ጥቃት ሰለባዎች አነስተኛ ብዛት ያላቸው ክርስቲያን አማራዎች፣ ክርስቲያን ኦሮሞዎች እና ጉራጌዎች ነበሩ።", "en": "According to reports, most victims of the most gruesome violence were minority Christian Amharas, Christian Oromos and Gurage people." }
{ "amh": "የዓይን እማኞች እንደተናገሩት በደቦ የወጡ ሰዎች ንብረቶችን አቃጥለው አውድመዋል፣ በአደባባይ ስቅላት ፈፅመዋል፣ እንዲሁም አንገት ቀልተዋል፣ ብሎም ሰውነት ቆራርጠዋል።", "en": "Eyewitnesses say mobs destroyed and burned property, committed lynching and beheadings and dismembered victims." }
{ "amh": "አሳዛኙ ቃለ መጠይቅ", "en": "A fateful interview" }
{ "amh": "የሀጫሉ ግድያ እንደተሰማ የዳያስፖራ ሚዲያ አውታሮች፣ ግድያውን ከግድያው ሳምነት ቀድሞ አርቲስቱ ለኦኤምኤን ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ከሰጠው ቃለ ምልልስ ጋር አያያዙት።", "en": "When news of Hachalu’s assassination first hit, Oromo diaspora media outlets zeroed in on Hachalu’s fateful interview with OMN host Guyo Wariyo, that aired the week before Halachu was killed." }
{ "amh": "በቃለ ምልልሱ ወቅት፣ ጉዮ ሀጫሉን በተደጋጋሚ ለገዢው ፓርቲ ያለውን ድጋፍ የተመለከተ ጥያቄዎች ሲጠይቀውና መልሱን እያቋረጠ ሲሞግተው ነበር።", "en": "During the interview, Guyo repeatedly asked Hachalu provocative questions about his alleged sympathy for the ruling party, interrupting him multiple times to challenge his answers." }
{ "amh": "ሀጫሉ ለገዢው ፓርቲ ድጋፍ አለህ የተባለውን ያስተባበለ ሲሆን፣ በኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ያለውን መከፋፈልም በመተቸት እንደሙዚቀኛ እና አሳቢ ገለልተኛ መሆኑን ለማሳየት ሞክሯል – ይህ ባሕሪው እስከ ግድያው ድረስ የበይነመረብ ላይ መዘባበቻ አድርጎ አሰንብቶት ነበር።", "en": "Hachalu fiercely denied any sympathies with the ruling party, but also decried the deeply discordant and fractionalized Oromo political parties, demonstrating his staunch independence as a thinker and musician — a quality that made him a target for online abuse until the day of his murder." }
{ "amh": "በዚህ መሐል ጉዮ ሀጫሉን የዘመናዊት ኢትዮጵያን በመገንባት ረገድ ጉልህ ሚና የተጫወቱትን የ19ኛው ክፍለ ዘመን ዐጤ ዳግማዊ ምኒልክ ኦሮሞ ላይ አድርሰውታል ስለሚባለው ኢፍትሐዊነት ጠይቆት ነበር።", "en": "At one point, however, Guyo asked Hachalu about the historical injustices allegedly committed against the Oromo people by Menelik II, Ethiopia’s 19th-century emperor who shaped modern Ethiopia." }
{ "amh": "ሀጫሉ በአዲስ አበባ የሚገኘው የምኒልክ ሀውልት ላይ የሚታየው የሚጋልቡት ፈረስ የእርሳቸው ሳይሆን ሲዳ ደበሌ የተባለ የኦሮሞ ገበሬ ፈረስ ዘርፈው እንደሆነ በመናገር ብዙዎችን አስድንግጦ ነበር።", "en": "Hachalu shocked some listeners when he answered that the horse seen immortalized in Menelik’s equestrian statue in Addis Ababa belongs to an Oromo farmer called Sida Debelle, and that Menelik robbed that horse." }
{ "amh": "ይህ አስተያየቱ ተቺዎችም፣ አወዳሾችም ፌስቡክ ላይ እንዲስተወዋሉ አድርጓል።", "en": "This exchange attracted applause — and criticism — from commentators on Facebook and Twitter." }
{ "amh": "ሀጫሉ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሲገደል፣ ብዙ የኦሮሞ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት ወዲያውኑ የዳግማዊ ምኒልክ ፈረስን አስመልክቶ የሰነዘረው ትችት በዐጤያዊቷ ኢትዮጵያ ደጋፊዎች አስገድሎታል ብለው ግምታቸውን አሳለፉ።", "en": "When Hachalu was killed one week later, many members of the Oromo diaspora community immediately speculated that Hachalu’s criticism of the Menelik II statue infuriated sympathizers of imperial Ethiopia, which may have led to his murder." }
{ "amh": "በማኅበራዊ ሚዲያ፣ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የሀጫሉ ምኒልክ ላይ የተሰነዘረ ትችት ላይ የሙጥኝ ብለው ቢያተኩሩምና ወደ ተዛባ መረጃ ቢያሳድጉትም፣ ሌሎቹ የቃለ ምልልሱ ይዘቶች በኦሮሞ ማኅበረሰቦች ውስጥ ስላሉ ክፍፍሎችና ተቃርኖዎች በብዛት የሚያተኩሩ ነበሩ።", "en": "On social media, Oromo netizens focused obsessively on Hachalu’s Menelik-related remarks, which led many down a winding path to an insidious disinformation campaign. The rest of the interview contains other loaded issues of divisions and contradictions within the Oromo community." }
{ "amh": "በቃለ ምልልሱ ውስጥ፣ ጉዮ ሀጫሉን በአገሪቱ ውስጥ እየተስተዋለ ባለው ፖለቲካዊ ለውጥ ላይ፣ በተለይም ራሳቸው ኦሮሞ በሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉዳይ እና የ2010ሩ ለውጥ ከመጣ ወዲህ የኦሮሞ ሕዝብ የሚጠብቀውን አግኝቷል ወይ እያለ መንግሥትን በሚያብጠለጥል ስሜት አስተያየት እንዲሰጥ ሲወተውተው ነበር።", "en": "Throughout the interview, Guyo grilled Hachalu about the country’s ongoing political reforms, stoking anti-government sentiment with questions about Prime Minister Abiy Ahmed, himself an Oromo, and whether or not the government had met the demands of the Oromo people after the prime minister came to power in 2018." }
{ "amh": "ሀጫሉ በኦሮሞ ፖለቲካ ክፍፍል ውስጥ ለማንም ላለመወገን ጥረት ቢያደርግም፣ የዐቢይ አሕመድን ኦሮሞ ማንነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ ሰዎችን ግን ተችቶ አልፏል።", "en": "Hachalu reiterated his non-involvement in the rabid partisanship of Oromo politics but he did criticize those who question Abiy’s Oromo identity." }
{ "amh": "ሀጫሉ በአንድ ወቅት ኢሕአዴግ ውስጥ በመሆን ኢትዮጵያን በበላይነት ሲመራ የነበረው ሕወሓት ጋር የሚፈጠሩ አጋርነቶች ላይ ያለውን የተቃውሞ አቋም አጠናክሯል።", "en": "He defended his position against top Oromo opposition leaders who sought an alliance with the Tigray People's Liberation Front (TPLF), a once-dominant party with historic ties to the now-defunct Ethiopian People's Revolutionary Front (the EPRDF)." }
{ "amh": "ሕወሓት ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ኢሕአዴግን ሲያፈርሱ ተቃዋሚ መሆኑ ይታወቃል።", "en": "The TPLF turned into an opposition party after Abiy dismantled the EPRDF." }
{ "amh": "ሀጫሉ በኦሮሚያ የተከሰተውን የፖለቲካ ነውጥም በተመለከተ በማንሳት የመንግሥት ባለሥልጣናትን እና በተለምዶ ኦነግ-ሸኔ በመባል የሚታወቀው፣ የኦነግ ወታደራዊ ቀኝ-ዘመም ክንፍ የነበረውን ትችትም ሰንዘሮ ነበር።", "en": "Hachalu also addressed the political violence in the Oromia region, blaming both government authorities and the militant, splinter right-wing Oromo Liberation Front (OLF) militia group (informally known as OLF-Shane)." }
{ "amh": "የሀጫሉን ግድያ ተከትሎ፣ መንግሥት የቃለ ምልልሱን ሙሉ 71 ደቂቃ በማግኘት ለዕይታ አቅርቦታል።", "en": "Following Hachalu’s murder, the government was able to acquire and release the full 71-minute interview to the public." }
{ "amh": "የተቆረጠው ክፍል ሀጫሉ ኦነግ ሸኔ በንቃት ይንቀሳቀሳል ከሚባልበት ምዕራብ ኦሮሚያ የግድያ ዛቻ ይቀርብበት የነበረ መሆኑን የገለጸበት ክፍል ይገኛል።", "en": "The missing tape included Hachalu’s accounts of death threats he received from parts of western Oromia, where the radical OLF-Shane militia is active." }
{ "amh": "ሀጫሉ ኦነግ-ሸኔን ቢያወድስ ኖሮ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይደርስበት የነበረው ጥቃት ላይደርስበት ይችል እንደነበር ገልጿል።", "en": "Hachalu said he believed he would not have been attacked on social media if he had praised OLF-Shan" }
{ "amh": "በሕወሓት ጊዜ የኢትዮፕያ ደኅንነት ኃላፊ ከነበረው ጌታቸው አሰፋ ጋር የነበረውን ግጭትም አንስቷል።", "en": "He addressed a direct conflict he had with Getachew Assefa, Ethiopia’s security and intelligence chief during the TPLF period." }
{ "amh": "ጉዮ፣ ይህንን ቃለ ምልልስ በፌስቡክ “የግድ መታየት ያለበት” በሚል ከስርጭቱ በፊት ሲያስተዋውቅ ነበር። አሁን ጉዮ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን፥ ሙሉ የ71 ደቂቃ ቃለ ምልልሱ ከሀጫሉ ግድያ ጋር የተያያዘ መረጃ ይገኝበት እንደሁ በሚል እየተመረመረ ነው።", "en": "Guyo, who promoted this interview on Facebook as “must-see TV” in the days before its broadcast, has since been arrested and the government is investigating the full 71-minutes of interview tape for further clues that may help determine the facts regarding Hachalu's murder." }
{ "amh": "የሀጫሉ ግድያ ያስከተለውን ጦስ በተመለከተ ክፍል ሁለትን ያንብቡ።", "en": "Read more about the consequences of Hachalu Hundessa's murder in Part II." }
{ "amh": "የኖቤል የሰላም ሽልማት ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ያለወቅቱ የተበረከተ ነበርን ?", "en": "Was the Nobel Peace Prize for Ethiopia’s prime minister premature?" }
{ "amh": "እ.ኤ.አ ጥቅምት 12፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ አሊ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ከተሸለሙ 24 ሰዓታት ሊሞላቸው ጥቂት ሲቀራቸው፣ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች ታስረው፣ አዲስ አበባ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት ታግደው ነበር፡፡", "en": "On October 12, barely 24 hours after Ethiopian Prime Minister Dr. Abiy Ahmed Ali was awarded the Nobel Peace Prize for 2019, the organizers of a protest were arrested and prevented from addressing a press conference in Addis Ababa." }
{ "amh": "‹‹በኦሮሞ ፖለቲከኞች አዲስ አበባ ላይ የሚቀርበው የባለቤትነት ጥያቄ››ን እና የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪል ማህበረሰቡ ‹‹ጭቆናን›› በመቃወም ለጥቅምት 13 የሃገሪቱ ርዕሰ-መዲና ውስጥ መስቀል አደባባይ ላይ ለማካሄድ የታሰበው ሰልፍ የተሰናዳው በባላደራው ምክር ቤት ንቅናቄ ነበር፡፡", "en": "The demonstration, scheduled for October 13 in Meskel Square in the Ethiopian capital, was organized by the Baladera Council movement to protest the “ownership claim by Oromo politicians over Addis Ababa,” and the “suppression” of political parties and civil society." }
{ "amh": "የባላደራ ምክር ቤት ለበርካታ ጊዜያት የተለያዩ ክሶች እየቀረቡበት በመንግስት ሲታሰር በነበረው፣ ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ እና ጦማሪ እስክንድር ነጋ ይመራል፡፡", "en": "The Baldera Council is led by Eskinder Nega, an Ethiopian journalist and blogger who has been jailed several times by the government on various charges." }
{ "amh": "አቢይ፤ ግርማ ሞገስ ያላቸው ወጣት መሪ", "en": "Abiy, the charismatic young leader" }
{ "amh": "የኖርዌዩ የኖቤል ኮሚቴ፣ ጥቅምት 11 የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሲታወቅ፣ የዶክተር አቢይ አህመድ አሊ ‹‹ከጎረቤት ኤርትራ ጋር የነበረውን የድንበር ግጭት ለመፍታት የወሰዱት ወሳኝ ተነሳሽነት›› ተጠቅሶ ነበር፡፡", "en": "The Norwegian Nobel Committee announced the Nobel Peace Prize for 2019 on October 11, citing Dr. Abiy Ahmed Ali's “decisive initiative to resolve the border conflict with neighbouring Eritrea.”" }
{ "amh": "ዜናው በደስታ ተቀባይነትን ሲያገኝ፣ በተወሰነ ጥርጣሬም የተቀበለ ወገን አልጠፋም፡፡", "en": "The news was received with enthusiasm, but also some ambivalence." }
{ "amh": "የ43 ዓመቱ የቀድሞ የድህንነት ሃላፊ፣ አቢይ በመጋቢት 2፣ 2018 አራተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን በቅተዋል፡፡", "en": "Abiy, a 43-year-old former intelligence officer, became the fourth prime minister of Ethiopia on April 2, 2018." }
{ "amh": "ወዲያውኑ ባልተገመተ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን፣ ከአምስት ዓመት በፊት ሊሆኑ የማይችሉ ተከታታይ ለውጦችን ጀምረዋል፡፡", "en": "He immediately launched a series of reforms that were not only unprecedented but which would have seemed impossible five years ago." }
{ "amh": "የእርሳቸው ቀዳሚ የሆኑት፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያን በብረት ጡጫ በመግዛት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በማፈን፣ የተቃዋሚ መሪዎችን እና ፖለቲካዊ ተቃውሞዎችን በሃይል በመጨፍለቅ ነበር ያስተዳደሯት፡፡", "en": "His predecessor, Hailemariam Desalegn, governed Ethiopia with an iron fist, stifling free speech, sending opposition leaders and journalists to jail and violently suppressing political dissent." }
{ "amh": "ከ80 በላይ ብሔረሰቦች ቢኖሩም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሔር-ተኮር ግጭቶች አዲስ አይደሉም፡፡", "en": "Ethnically-motivated conflicts are not new in Ethiopia, which has over 80 ethnic groups." }
{ "amh": "ነገር ግን አለመረጋጋቶች እና ተቃውሞዎች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ሁለት ትላልቅ ክልሎች፣ ኦሮሚያ እና አማራ፣ የአማራ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል በመስፋፋት ሰበብ ተነስተው የምስራቅ አፍሪካዋን ሃገር ከ2015 እስከ 2018 መባቻ ድረስ ለሁለት ሰንጥቋት፣ ሃይለማርያምን ‹‹ላልተጠበቀ›› የስልጣን መልቀቅ፣ መጋቢት 2018 ላይ አብቅቷቸዋል፡፡", "en": "But the unrest and protests in Ethiopia's two largest regions, Oromia and Amhara, sparked by encroachment on Oromia lands resulting from the expansion of the Amhara region, practically tore the Horn of African country apart from 2015 to early 2018 — and drove Desalegn to a “surprise” resignation in April 2018." }
{ "amh": "አቢይ የገዢውን – የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ)ን ምርጫዎች - ከ180 ድምፆች፣ 108 ድምፆችን በማግኘት አሸንፈው፣ ሃይለማርያምን ተክተው የፓርቲው ሊቀ-መንበር፣ ከዛም የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን በቅተዋል፡፡", "en": "Abiy contested the elections of the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF), winning 108 votes out of 180 to replace Desalegn as party chairman and, consequently, as prime minister of the country." }
{ "amh": "የኦሮሞ ብሔር አባልነታቸው ከክርስቲያን እና ሙስሊም መነሻቸው ጋር፣ በወትድርና ልምዳቸው እና በወታደራዊ ስለላ ባለሙያነታቸው፣ አቢይ ሃገሪቷ ውስጥ ያለውን ውጥረት ሊያረግቡ እንደሚችሉ መሪ ታይተው ነበር፡፡", "en": "An ethnic Oromo with a mixed Christian and Muslim background, along with military experience and expertise in military intelligence, Abiy was seen as a figure capable of easing the turmoil in the country." }
{ "amh": "አንድ የቻተኸም ሃውስ ተንታኝ፣ ‹‹ምስጢራዊው እና ውስብስቡ የትብብር ውቅር›› የሆነው ኢህአዴግ ውስጥ በተካሄዱ ምርጫዎች ድል ስላገኙት አቢይ ሲፅፍ፣ ‹‹እርሳቸው ከመጀመሪያውኑ ብዙዎችን ለሃገሪቱ መረጋጋት፣ አንድነት እና ለውጥን እንደሚያመጡ አሳምነው ነበር፡፡›› ብሏል፡፡", "en": "One Chatham House analyst writing about the elections ascribed his victory to the “secretive and complex alliance-building” among the four political parties that make up the EPRDF, and noted that he “seems early on to have persuaded many he can bring stability, unity and reform to the country.”" }
{ "amh": "በአንፃራዊ አጭር አካሄድ፣ አቢይ በባለፈው አስተዳደር ወቅት አለመረጋጋቶችን ለመደምሰስ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማንሳት፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን አስለቅቀዋል፡፡", "en": "In relatively short order, Abiy lifted the state of emergency the previous administration had imposed to quell unrest, and released thousands of political prisoners." }
{ "amh": "በፍጥነት የሚቀያየረው የፖለቲካ ምህዳር ብዙ ስደተኛ ተቃዋሚዎች እንዲመለሱ እና በመቶዎች የሚታሰቡ ድረ-ገፆች እና የቲቪ ጣቢያዎች ከአፈና እንዲላቀቁ አድርጓል፡፡", "en": "The rapid turnaround of the political landscape paved the way for the return of exiled dissidents and the unblocking of hundreds of websites and TV channels." }
{ "amh": "እንደሚታወቀው፣ አቢይ ጨካኙን የፖለቲካ መጨቆኛ መሳሪያን – የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኛነት ህግ አሻሽለዋል፡፡", "en": "Notably, Abiy amended that draconian tool of political repression, Ethiopia’s anti-terrorism law." }
{ "amh": "ግን የእርሳቸው በጣም የሚጠቀሰው ስኬት፣ ለ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሳጫቸው ተግባር ከጎረቤት ኤርትራ ጋር የፈጠሩት ታሪካዊ የሰላም ስምምነት ነው፣", "en": "But his most outstanding achievement has been the historic peace deal with neighbouring Eritrea, which netted him the 2019 Nobel Peace Prize:" }
{ "amh": "ነገር ግን የአቢይ የለውጥ ስራዎች ያለተቃውሞ ወደፊት መጓዝ አልቻሉም", "en": "But Abiy’s reforms have not proceeded without opposition." }
{ "amh": "፡፡ ሰኔ 2018 ትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደ የፖለቲካ ሰለማዊ ሰልፍ ላይ ከተፈጠረ ፍንዳታ እርሳቸው ሲተርፉ፣ ሌሎች ሁለት ሰዎች ተገድለዋል", "en": "In June 2018, he survived an explosion that killed two other people during a political rally in the Tigray province." }
{ "amh": "፡፡ እንደታንዛኒያዊው የፓርላማ አባል ጃኑዋሪ ማካምባ – የአቢይ ዘመን አጋር፣ በፃፉት አወዳሽ የትዊተር መልዕክት እንደጠቀሱት፣ ‹‹ኢትዮጵያ ከባድ እና ውስብስብ ሃገር ነች፡፡›› ብለዋል፡፡", "en": "As Tanzanian MP January Makamba, one of Abiy's generational peers, has noted in an otherwise laudatory tweet: “Ethiopia is a tough and complicated place.”" }
{ "amh": "የብሔር ግጭቶች 2.9 ሚሊዮን ተፈናቃዮችን 2018 ላይ ሲያስከትሉ፣ ያለፈው ሰኔ ወር አማራ ክልል ውስጥ የከሸፈው መፈንቅለ-መንግስት የሚቀጥለው ዓመት የታቀደው ብሔራዊ ምርጫን ሊገዳደሩ የሚችሉ የፀጥታ ስጋቶች ሆነው አልፈዋል፡፡", "en": "Ethnic violence resulting in 2.9 million displacements in 2018 and a failed coup in the Amhara region last June are arguably two security threats capable of undermining the national elections scheduled for next year." }
{ "amh": "በተጨማሪም፣ ኢትዮጵያ እስከአሁን ድረስ ከፍተኛ የድህነት መጠን ያለባት ሃገር መሆኗን፣ በጠንካራ የኢኮኖሚ መዘርዝሮች የተጠቀሰ ነው፡፡ የአቢይ ‹‹ሊብራላዊ ለውጥ-አምጭነት›› ምስል የሚወሰነው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን በመቀየር አቅማቸው ላይ ነው፡፡", "en": "In addition, Ethiopia still has the highest poverty prevalence rate in the world despite strong economic indices. Abiy's “liberal reformer” image hinges on his ability to transform the Ethiopian economy." }
{ "amh": "ኢትዮጵያ ውስጥ – በአብይ ቁጥጥር ስር – የኢንተርኔት አገልግሎት መዘጋት መቀጠሉ፣ የተፈጠሩት መቀያየሮች ‹‹ከፖለቲካ ለውጦች በፊት ይልቅ በጣም እየተወሳሰቡ ስለመጡ›› ለማርገብ ነው፡፡", "en": "Ethiopia, under Abiy’s watch, also continues to shut down the internet amidst dynamics “more complicated than they had been prior to the start of the political reforms.”" }
{ "amh": "ሃገር-አቀፉ የኢንተርኔት መዘጋት ከሰኔ 11 – 14 የነበረ ሲሆን፣ የአጭር ፅሁፍ መልዕክት አገልግሎቶችም ተዘግተው ነበር፡፡", "en": "A nationwide internet blackout occurred from June 11-14, during which SMS messaging services were also inaccessible." }
{ "amh": "መስከረም 26 ላይ የኢትዮጵያው የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያን የወከሉት የምርታማነት ጭመራ ሴክተር ባለስልጣን አቶ ጀማል በከር ውይይት የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ (FIFAfrica) ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት፣ ‹‹መንግስት የሃገሪቱን ዲጂታል ቦታ ክፍት ቢያደርግም፣ አሁንም በተለያዩ ዘዴዎች የኢንተርኔት ነፃነትን የሚያውኩ የጥላቻ ንግግሮች እና ሃሰተኛ ዜናዎችን ለመቆጣጠር መሰራት አለበት፡፡›› ብለዋል፡፡", "en": "On September 26, Dr. Getahun Mekuria, Ethiopia's Minister of Innovation and Technology, represented by State Minister of the Productivity Enhancement Sector Ato Jemal Beker, stated in his opening remarks at the Forum on Internet Freedom in Africa (FIFAfrica), that although the government has opened up digital space in the country, there remains “a strong need to temper internet freedom with mechanisms in place to control hate speech and mis- and disinformation online.”" }
{ "amh": "በዚህ ፅሁፍ መጀመሪያ ላይ እንደተገለፀው ዓይነት ሁነት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ እና የፖለቲካ ተቃውሞን የማንፀባረቅ መብት በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር በተበጣሽ ገመድ ላይ የሚረማመድ ይመስላል፡፡", "en": "As the incident described at the beginning of this essay shows, Abiy's ability to sustain freedom of expression and political dissent in this Horn of Africa nation hangs on a fragile thread." }
{ "amh": "ጊዜውን የጠበቀ? ወይስ የሚገባቸው?", "en": "Premature, or well-deserved?" }
{ "amh": "ኢትዮጵያን ያስጨነቁ ችግሮች አሁንም ቢቀጥሉም፣ ለምን አቢይ ልክ እንደንፁህ አየር ጥሩ አቀባበል ያገኙበትን ምክንያት በቀላሉ ማስተዋል ይቻላል፡፡ አብዛኛዎቹ ገዢዎች ሽማግሌ የሆኑ እና አንዳንዴ አጋር መሪዎች በሚገዙባት አህጉር፣ ነፃው የ43 ዓመት ወጣት ከሽማግሌዎቹ ገዢዎች፣ በብዙ ሁኔታዎች አፈንግጠው ወደ ስልጣን መውጣታቸው የሚያስገርም ነው፡፡", "en": "In spite of the problems that continue to plague Ethiopia, however, it is easy to see understand why Abiy has been welcomed as a breath of fresh air. In a continent ruled by elderly and sometimes ailing leaders, the dynamic 43-year-old represents a break from an old guard which, in many cases, has clung to power against all odds." }
{ "amh": "የዩጋንዳው የ75 ዓመት ባለፀጋው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ፣ 1986 ላይ ስልጣን እንደያዙ በፅናት የእርሳቸው አመራር የተቃወሟቸውን በመደምሰስ፣ የምስራቅ አፍሪካዊቷን ሃገር የፖለቲካ ምህዳር አጥብበውታል፡፡", "en": "Uganda’s 75-year-old President Yoweri Kaguta Museveni has held on to power since 1986, consistently shrinking the political space in the East African country by destroying any opposition to his rule." }
{ "amh": "የጆን ማጉፉሊዋ ታንዛኒያ በፖሊሳዊ አያያዝ ስር ያለች ሲሆን፣ የተቃውሞ ፖለቲካ፣ ሰብዓዊ መብቶች እና የፕሬስ ነፃነትን በቅርቡ – በሃይል እርምጃ አፍናለች፡፡", "en": "John Magufuli’s Tanzania is a practically a police state with the recent clampdown on opposition politics, human rights and press freedom." }