translation
translation
{ "amh": "ነገር ግን የፍርድ ሒደቱ፣ እንደሌሎች ብዙ የፍርድ ቤት ሒደቶች ሁሉ ዘግይቷል።", "en": "But their case, like so many others court cases, had been delayed." }
{ "amh": "በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪዎችን የሚያካትቱ የፍርድ ሒደቶች ከሌሎች ጉዳዮች የባሰ ረዥም ጊዜ መውሰዳቸው ያልተለመደ ነገር አይደለም።", "en": "In Ethiopia, it is not uncommon for court cases involving bloggers journalists and politicians to take longer than other cases." }
{ "amh": "ይህ፣ ለተከላካዮቹ መሰላቸትን እና ለወዳጆቻቸው መንገላታት መንስዔ ነው።", "en": "This causes exhaustion for defendants and brings pain to their loved ones." }
{ "amh": "ዮናታን እና ጌታቸው ፍርዱን ከመቀበላቸው በፊት ሁለቱም በወኅኒ 18 ወራት አሳልፈዋል።", "en": "Yonatan and Getachew each spent 18 months in jail before they learned their fate." }
{ "amh": "ቢያንስ ደርዘን ለሚያህል ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።", "en": "They were brought before the court at least a dozen times." }
{ "amh": "የፌስቡክ ገጾቻቸው በባለሥልጣናት እጅ ወድቀዋል።", "en": "Their private Facebook accounts were laid bare by authorities." }
{ "amh": "አንዳንዴ ዳኞቹ ሳይቀርቡ ይቀራሉ፣ አንዳንዴ ደግሞ ፖሊስ እስረኞቹን ሳያቀርብ በመቅረት ጉዳዩ ለ18 ወራት ተንጓትቷል።", "en": "Judges failed to appear in court, and police failed to bring defendants to court on their trial days, causing their cases to drag on for 18 months." }
{ "amh": "ፌስቡክ ለኢትዮጵያ የመብት አራማጆች የሰብኣዊ መብቶች ጥሰትን ለማጋለጥ እና ለመመዝገብ ወሳኝ መድረክ ሆኖላቸዋል።", "en": "Facebook has been a critical platform for Ethiopian activists and rights advocates working to document and communicate human rights violations." }
{ "amh": "ይህም፣ የዮናታን እና ጌታቸውን ጉዳይ ለኢትዮጵያውያን አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚሰማ እንዲሆን ያደርገዋል።", "en": "This makes the experience of Yonatan and Getachew an especially chilling story for Ethiopians." }
{ "amh": "ሳኡዲ ያሉ ኢትዮጵያውያን በኤምባሲያቸው ውስጥ ያለው ቀርፋፋ አሠራር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ከሚያሳይ የኢትዮትዩብ ቪዲዮ ሪፖርት ላይ የተወሰደ ምስል።", "en": "Screenshot from report 'Ethiopians in Saudi Arabia are complaining about the slow performance of their Embassy' on Ethiotube." }
{ "amh": "በሳኡዲአረቢያ ተሰደው የሚሠሩ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የገልፏ አገር ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያንን አሽጋ ከመመለሷ በፊት መውጫ ቪዛቸውን ለማግኘት እንዲችሉ የሚያስችላቸውን ሰነድ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲያዘጋጅላቸው መንግሥትን እየለመኑ ነው።", "en": "Thousands of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia have pleaded to the Ethiopian government to expedite their return by helping them prepare documents to secure exit visas, as the Gulf country prepares to begin deporting as many as half a million Ethiopians." }
{ "amh": "ሳኡዲ አረቢያ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኛ ሠራተኞች አገሯን ለቀው እንዲወጡ የዘጠና ቀን የእፎይታ ግዜ ከሰጠች 3 ወር ሊሞላት ነው።", "en": "It has been nearly three months since the Saudi Arabian government gave 90 days to all unauthorized migrant workers in Saudi Arabia to leave the country." }
{ "amh": "ሳኡዲአረቢያ እና ጎረቤቷ ኳታር ከአገራቸው የሚወጡ ስደተኛ ሠራተኞች የመውጫ ቪዛ እንዲይዙ ከሚያስገድዱ ጥቂት የዓለማችን አገራት ውስጥ ናቸው።", "en": "Saudi Arabia and neighbouring Qatar are among the few countries in the world that force foreign workers to secure exit visas before they leave the country." }
{ "amh": "ቪዛውን ለማግኘት ደግሞ መሟላት ያለባቸው ሰነዶች አሉ።", "en": "In order to secure the visas, other documents must also be in order." }
{ "amh": "ዳያስፖራ ተቀማጩ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የሚከተለውን ተናግሯል:", "en": "As the Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT) outlet run from outside Ethiopia reported:" }
{ "amh": "የሳኡዲ ባለሥልጣናት ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ሠራኞች አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ከተናገሩ ጀምሮ፣ ሳኡዲአረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እርዳታ እንዳላደረገላቸው በመናገር ስደተኞቹ ጠንካራ ወቀሳ እያቀረቡ ነው።", "en": "Since Saudi officials announced those with illegal status to leave the country Ethiopian immigrants are strongly accusing Ethiopian embassy in Saudi Arabia for not helping them to return to Ethiopia." }
{ "amh": "የ90 ቀኑ የእፎይታ ግዜ ከማለቁ ሳምንት በፊት እና ወራት ከፈጀ ቢሮክራሲያዊ መዘግየት በኋላ፣ ኤምባሲው 80 ሺሕ ኢትዮጵያውያን ብቻ በሕጋዊ መንገድ የመውጫ ቪዛ የሚያስገኝላቸውን ሰነድ መስጠት ችሏል።", "en": "Yet roughly a week until the 90 days grace period ends and after months of bureaucratic delays at the Ethiopian Embassy in Saudi Arabia, only 80,000 Ethiopians were able to get travel documents that will legally help them exit the country." }
{ "amh": "400 ሺሕ ከሚገመቱ በሳኡዲአረቢያ ያልተመዘገቡ የኢትዮጵያ ስደተኞች መካከል፣ 80 ሺሕ ጥቂት የበለጡት ብቻ \"የመውጫ ቪዛ አግኝተዋል\"፤ የእፎይታ ግዜው በ11 ቀናት ውስጥ ያልቃል። - አዲስ ስታንዳርድ", "en": "of the estimated 400,000 undocumented #Ethiopians living in #SaudiArabia, only 80, 000+ secured exit visas; 11 days for amnesty to expire pic.twitter.com/T2s3w9wEOz — Addis Standard (@addisstandard) June 15, 2017" }
{ "amh": "750 ሺሕ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳኡዲአረቢያ እንደሚኖሩ ይገመታል። ከነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ የሥራ ፈቃድ የላቸውም።", "en": "An estimated 750,000 Ethiopian migrants live in Saudi Arabia, among which a significant majority are unauthorized workers." }
{ "amh": "ኢትዮጵያውያን ወደ ሳኡዲአረቢያ በተለያዩ መንገዶች ይገባሉ።", "en": "Ethiopians enter to Saudi Arabia through various channels." }
{ "amh": "ጥቂቶች ፈቃድ አግኝተው በፕሌን ወደአገሪቷ ሲገቡ፣ ብዙዎቹ ግን በአስኮብላዮች ታግዘው በመሬት ወደአገሪቷ ይዘልቃሉ።", "en": "Some traveled as authorized workers on planes but more people enter the country by land with the help of smugglers." }
{ "amh": "ሙስሊሞች ወደመካ የሚያደርጉትን ሒጅራ አስታከው በመሔድ በዚያው የሚቀሩም አሉ።", "en": "There are also some who remained in the country after they travelled there for the Islamic pilgrimage to Mecca." }
{ "amh": "እስካሁን 30 ሺሕ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተጓጉዘዋል።", "en": "So far, only 30,000 migrants were shuttled back to Ethiopia." }
{ "amh": "ነገር ግን የአሁኑ ወደ አገር ቤት የመመለስ ዘመቻ ፍጥነት ሲታይ የእፎይታ ግዜው ካለቀ በኋላም ቢሆን ብዙዎቹ ስደተኞች ሳኡዲአረቢያ ይቆያሉ።", "en": "However, with the current pace of repatriation, most migrants will still be in Saudi Arabia when the grace period ends." }
{ "amh": "የሳኡዲ ባለሥልጣናት ሐምሌ 3 ጀምረው ሐሰሳ በማድረግ ስደተኞቹን ወደ አገር ቤት አስገድደው ይመልሷቸዋል።", "en": "Saudi authorities have said they will start to raid and deport migrant workers on June 30." }
{ "amh": "በ2006 የሳኡዲ ባለሥልጣናት ተመሳሳይ እርምጃ ሲወስዱ፣ ኢትዮጵያውያን እስከሞት የሚዘልቅ አካላዊ ጥቃት ከደረሰባቸው ውስጥ ነበሩ።", "en": "In 2013 when Saudi authorities engaged in similar operations, Ethiopian migrants were the victims of deadly physical assaults." }
{ "amh": "ወደ ኢትዮጵያ ሊመለሱ ማቆያ እስር ቤት የታሸጉት ስደተኞች ጥሩ መጠለያና ምግብ አልቀረበላቸውም ነበር።", "en": "Workers who sought to return to Ethiopia were held in makeshift detention centers without adequate food or shelter." }
{ "amh": "በ2006ቱ አስገድዶ የመመለስ ዘመቻ ግዜ፣ ኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ሚድያን በመጠቀም ሳኡዲአረቢያ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አስተባብረው ነበር።", "en": "During the 2013 deportation, Ethiopians used social media to organize their protest against Saudi Arabia." }
{ "amh": "ከዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ በተቃራኒ እና የኢትዮጵያ መንግሥት በፍጥነት ተመላሾችን ለማደላደል ከሚሰጠው ቃል በተቃራኒ አገሪቱ ውስጥ ባለው ውሱን የኢኮኖሚ ዕድል ሳቢያ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የማይፈልጉ ስደተኞችም አሉ።", "en": "Despite these hardships and the Ethiopian government's promises of a swift resettlement, there are migrants who do not want to return to Ethiopia, where there are few economic opportunities." }
{ "amh": "ጥቃት ሊደርስባቸው እንደሚችል እያወቁ ብዙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት ለመመለስ ፍላጎት አለማሳየታቸው ያስደነግጣል።", "en": "It is horrifying that most Ethiopians have not shown an interest in returning home despite risk of violence." }
{ "amh": "ሠራተኞቹ ስለ ወደፊቱ ሕይወታቸው ሲጨነቁ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚመለሱ ስደተኞች የመሳፈሪያ ዋጋውን በግማሽ ለመቀነስ እና ከተመለሱ በኋላ ወዲያው በሥራ ለማደላደል ቃል እየገባ ነው።", "en": "As the workers fret for their futures, the Ethiopian government has pledged to cut by half the price of a plane ticket home for those who will fly with Ethiopian Airlines, as well as offering resettlement and jobs upon arrival." }
{ "amh": "ነገር ግን ቃል ለብዙዎች ይህ የውሸት ቃል ኪዳን ነው።", "en": "Most view these as false promises however." }
{ "amh": "በዩቱዩብ ከ200,000 በላይ ተመልካች ያገኘው የተፈሪ መኮንን የሐዘን ዜማ ላይ የተወሰደ የስክሪን ፎቶ።", "en": "Screenshot from one the more melancholic music videos of Teferi Mekonen viewed more than 200,000 times from the group's YouTube channel." }
{ "amh": "ባለፈው ዓመት፣ የመብት አራማጆች \"የእምቢተኝነት ዘፈኖች\" የሚሏቸው ዜማዎች የኢትዮጵያን የበሬ ግምባር የምታክል የበይነመረብ መስክ አጥለቅልቀዋታል።", "en": "Over the past year, what activists call resistance songs have flooded a tiny corner of the Ethiopian internet." }
{ "amh": "ነገር ግን የፖለቲካ ዘፈኖቹ የሕዝቡን ቀልብ በይነመረብ ላይ መሳባቸውን ሲመለከቱ፣ ባለሥልጣናቱም የተለያዩ የማፈኛ ዘዴዎችን ለተቃዋሚ ያደላሉ ያሏቸው ዘፋኞች ላይ አድርገዋል።", "en": "But as political music has become more visible in public life and online, Ethiopian authorities have expanded their political repression tactics to musicians whom they see as sympathizers with opposition." }
{ "amh": "ከታኅሣሥ 2008 ጀምሮ ራሳቸውን በአገሪቱ ከተጋጋለው የተቃውሞ ንቅናቄ ጋር ያጠጋጉ ታዋቂ የኢትዮጵያ ዘፋኞች እየታደኑ ሲታሰሩ ነበር።", "en": "Since December 2016, multiple popular Ethiopian musicians aligned with the country's growing opposition movement have been arrested and jailed." }
{ "amh": "ባለፈው ሳምንት ተቀባይነቷ እያደገ የመጣላት ጀማሪ ዘፋኝ ሴና ሰሎሞን \"የሚያነሳሱ\" ግጥሞች ያሏቸውን የሙዚቃ ቪዲዮዎች በዩቱዩብ ላይ በመለጠፍ የሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባታል።", "en": "Last month, the prominent group of rising start singer Seenaa Solomon was charged with terrorism for inciting lyrics and uploading their music video to YouTube." }
{ "amh": "በተንኳሹ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምኅዳር የዚህ ዓይነቱ የእስር ዘመቻ የኢትዮጵያ መንግሥት የዋና ከተማይቱ አዲስ አበባን የማስፋፋት ዕቅዱን ያወጀ ሰሞን ተበራክቶ ነበር።", "en": "The contentious political environment in which these arrests took place has grown out of the Ethiopian government's plan to expand Addis Ababa, the nation's capital." }
{ "amh": "በ2006 ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ወደአዋሳኟ እና በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆኑት የኦሮሞ ሕዝቦች ክልል፣ የኦሮምያ ገበሬዎች መሬት የማስፋፋት ዕቅዱን ተናግሮ ነበር።", "en": "In 2014, the ruling EPRDF party announced plans to expand the capital into adjacent farm lands of Oromia, Ethiopia’s largest region that is primarily home to the country's largest ethnic group, the Oromo." }
{ "amh": "ዕቅዱ መጠነ ሰፊ አመፅ የቀሰቀሰ ሲሆን የመንግሥት በኃይል የማስቆም ሙከራ ደግሞ የበርካቶችን ሕይወት ከመቅጠፉም ባሻገር፣ እስካሁን የዘለቀ አስቸኳይ ግዜ አዋጅን በጥቅምት 2009 እንዲታወጅ አድርጓል።", "en": "The plan led to wide-scale protests and a violent government crackdown, ultimately resulting in a state of emergency declared in October 2016 and still effective today." }
{ "amh": "አንዳንዶች በመጋቢት ለአራት ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ከሁለት ዓመታት ሕዝባዊ አመፅ በኋላ የተወሰነ ፀጥታ አምጥቷል ይላሉ።", "en": "Some say the state of emergency, which was extended to four more months in March 2017 has brought some calm after two years of political unrest." }
{ "amh": "የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የአደባባይ ተቃውሞዎቹን ቢያስቆምም፣ የእምቢተኝነቱ ስሜት እና ትርክት ግን ሳይነካ አሁንም አለ።", "en": "While the state of emergency may be curbing the demonstrations, feelings and narratives of resistance remain alive and well." }
{ "amh": "እናም (የአካባቢው የትልቁ ቋንቋ) የኦሮምኛ ዘፋኞች ጉልህ - እና ተደማጭ - የተቃውሞ ንቅናቄው ማነቃቂያ ሆነው እያንሰራሩ ነው።", "en": "And Afan Oromo (the region's language) musicians have begun to rise as a visible — and audible — driving inspiration for the opposition movement." }
{ "amh": "በርካታ የዩቱዩብ ቻናሎች እና የፌስቡክ ገጾች ተከፍተው የአመፁን ባሕላዊ ገጽታ እየመዘገቡ ነው።", "en": "Large numbers of YouTube channels and Facebook pages have sprung up, documenting the cultural aspects of the protest." }
{ "amh": "ድረገጾችና ጦማሮች የእምቢተኝነት ዘፈኖችን ያጋራሉ።", "en": "Websites and blogs frequently post resistance songs." }
{ "amh": "ዩቱዩብ ላይ፣ የአመፅ ምስሎች ተገጣጥመው ከእምቢተኝነት ዘፈኖቹ ጋር በቅንብር ሲቀርቡ፣ በየለቱ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን ያገኛሉ።", "en": "On YouTube, channels carrying montages of protest images linked to the resistance songs regularly garner hundreds of thousands of views." }
{ "amh": "አዲስ አበባ ጀምበር ከመጥለቋ አስቀድማ።", "en": "Addis Ababa in the late afternoon." }
{ "amh": "ፎቶ አማንዳ ሊሽቴንስቴን።", "en": "Photo by Amanda Lichtenstein." }
{ "amh": "በይነመረብ ለማይጠቀሙ ሰዎች የጎዳና ዳር ሲዲ ሻጮች እና አከራዮች ዋነኞቹ የእምቢተኝነት ዘፈኖቹ አሰራጮች ናቸው።", "en": "Offline, street CD vendors and small CD rental shops are part of an informal chain of supply of resistance songs for Ethiopians who don’t have internet access." }
{ "amh": "መንግሥት ‘የእምቢተኝነት ዘፈኖችን’ ሳንሱር ለማድረግ ሁሉንም ዘዴዎች ሞክሯል።", "en": "The government has tried all methods to censor ‘resistance songs’." }
{ "amh": "ዘፋኞችን አስሯል፣ ኮንሰርት ከልክሏቸዋል፣ ከአገር አሰድዷቸዋል።", "en": "It has arrested singers, denied them gigs and even driven them out of Ethiopia." }
{ "amh": "ዳያስፖራ ተቀማጭ የሳተላይት ቴሌቪዥኖችን አፍኗል።", "en": "It haas blocked YouTube channels and jammed diaspora-based satellite television stations." }
{ "amh": "ከ2004 ጀምሮ እንቦጭ የተባለ ተስፋፊ አረም በብዙ ሺ ሔክታር የሚቆጠር የጣናን ውኃማ አካል፣ በዙሪያው ያለውን ረግረጋማ ስፍራ፣ እንዲሁም የከብቶች ማሰማሪያ አካባቢ ወርሮታል።", "en": "Since 2012, an invasive weed known as the water hyacinth has been subsuming tens of thousands of acreage of the surface of Lake Tana, as well as adjacent wetlands and ranches surrounding the lake." }
{ "amh": "በአካባቢው የተፈጥሮ ጥበቃ እና እንክብካቤ ላይ የሚሠራው የጀርመን መንግሥታዊ ያልሆነ የተፈጥሮ እና ባዮዳይቨርስቲ ጠባቂው ኅብረት (ናቡ) ጣና ሐይቅ፣ በውኃው፣ በዙሪያው ባለው የከብቶች ማሰማሪያ እና ሌሎችም ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ 2 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ጥገኛ እንደሆኑ ተናግሯል።", "en": "About two million Ethiopians directly depend on the lake as well as adjacent wetlands and ranches for their livelihood, according to Nature And Biodiversity Conservation Union (NABU), a German non-governmental organization focused on sustainability and conservation in the region." }
{ "amh": "እንቦጭ የተባለው አረም በተለይ የተስፋፋው፣ በሐይቁ ምዕራባዊው ክፍል ሲሆን ይህ አካባቢ ብዙ የአሳ አጥማጆች፣ ገበሬዎች እና ከብቶቻቸውን የሚያሰማሩ ሰዎች ይሰማሩበታል።", "en": "The steady growth of the water hyacinth has taken a toll, particularly on the western side of the lake, an area populated by fishermen, farmers, and ranchers whose work depends on it." }
{ "amh": "832 ስኵዌር ማይል የሚሰፋው ጣና ሐይቅ የኢኮሎጂ፣ ባሕላዊ፣ እና ታሪካዊ ሀብት የታቀፈ ሐይቅ ነው።", "en": "The vast, 832-square-mile body of water is Ethiopia's largest lake, and is packed with ecological, cultural and historical charm." }
{ "amh": "ጣና በትልቅነቱ ሁለተኛ የሆነው የኢትዮጵያ ክልል - አማራ ክልላዊ አስተዳደር - ውስጥ ይገኛል።", "en": "It is situated in the highlands of Ethiopia’s second-largest region, Amhara administrative state." }
{ "amh": "የጣና ሐይቅ ዝርያቸው ሊጠፋ የተቃረቡት ባለ ጥቁር ኮከን መንቁራም ወፎችን እና ሌሎችም ተሰዳጅ አእዋፋትን አቅፎ ይዟል።", "en": "Ecologically, Lake Tana is home to rare and endangered bird species such as the black-crowned crane and also hosts several migratory birds." }
{ "amh": "ጣና ሐይቅ፣ የሱዳን ዋና ከተማ፣ ካርቱም ላይ ከነጭ አባይ ጋር ለመቀላቀል ወደምዕራብ የሚፈሰው የጥቁር አባይ ምንጭም መሆኑም ይታወቃል።", "en": "Lake Tana is also notable for being the headwaters of the Blue Nile river that flows westward before it merges with White Nile at Khartoum, Sudan’s Capital." }
{ "amh": "የኢትዮጵያ ሕዝብ በፍጥነት በማደጉ በዚያው ልክ ፍላጎቱ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ ሐይቁ ላይ ያጠላበት አደጋ የተፈጥሮ ሀብቶች ላይ ያንዣበበው ችግር ልዩ ትዕምርት ሆኗል።", "en": "Now, the lake is a very different symbol — of the dire state of Ethiopia’s natural resources at a time when the country’s fast-growing population needs more of everything." }
{ "amh": "ለመንግሥት ብዙኃን መገናኛ የተናገሩት ባለሙያዎች እንዳብራሩት ከሆነ፣ 155 ስኵዌር ማይል የሸፈነው እንቦጭ ሙሉ ለሙሉ የተስፋፋው ከ2004 ወዲህ ነው።", "en": "According to experts who spoke to government media, the water hyacinth has grown nearly 100 percent from 2012 to about 155 square miles, though a relatively dry winter season in 2016 slowed its expansion." }
{ "amh": "የዚህ ተስፋፊ እንግዳ አረም መንስዔ ሰዎች በሐይቁ ዙሪያ የሚሠሩት ሥራ ነው።", "en": "The spread of this invasive alien species is the result of human activity around Lake Tana." }
{ "amh": "አንድ በሁለት ምሁራን የተዘጋጀ የጥናት ወረቀት እንደሚያስረዳው የዚህ አደገኛ አረም መስፋፋት መንስዔ በዙሪያው ካሉ የከተማ እና የግብርና ተረፈ ምርቶች ወደሐይቁ የሚገባው ምግብ አዘል ፈሳሽ ውኃ እና እንደ ሐዋሳ ሐይቅ እና ዝዋይ ሐይቅ ያሉትን ሌሎች የኢትዮጵያ ሐይቆችን ጭምር አደጋ ላይ የጣለው የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርት ነው።", "en": "According to a paper written by two academicians, the rapid growth of the pernicious weed is caused by the inflow of nutrient rich water from urban and agricultural runoff and products of industrial waste, threatening other Ethiopian lakes as well such as Lake Hawasa, and Lake Zeway." }
{ "amh": "ከ2007 ጀምሮ፣ ዩኔስኮ ጣና ሐይቅ ለያዘው ልዩ የኢኮሎጂ እና ባዮስፌር ሀብት፣ ናቡ የተባለው ድርጅት በውስጡ ያሉትን ሀብቶች ለመጠበቅ እንዲያስችለው ባደረገው ጥረት፣ የዓለም ቅርስነት ዕውቅና ሰጥቶታል።", "en": "Since 2015, UNESCO has recognized Lake Tana as a World Heritage site for its unique ecological biosphere reserve, due to NABU's efforts to secure this status as part of its conservation efforts in the region." }
{ "amh": "ዩኔስኮ የሐይቁ ደሴቶች ላይ ለሚገኙት ታሪካዊ፣ ባሕላዊ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስትያን ትልቅ ዋጋ የሚሰጣቸው ሀይማኖታዊ ቅርሶችም ዕውቅና ሰጥቷል።", "en": "UNESCO also recognizes the islands' rich historical, cultural and religious significance with deep ties to the Ethiopian Coptic Orthodox Church." }
{ "amh": "ሐይቁ የታሪካዊ ገዳማት እና ቤተ ክርስቲያኖች መገኛ ነው።", "en": "The lake is also home to historical monasteries and churches." }
{ "amh": "ነገር ግን አስደንጋጩ የእምቦጭ ወረራ ሐይቁ ላይ ያሉትን እና የገቢ ምንጫቸው ሐይቁ ላይ የተመረኮዘውን ሰዎች እንዲሁም የጣና ሀይቅ የተፈጥሮ ሀብቶች ሁሉ አደጋ ላይ ናቸው።", "en": "Their relatively isolated location on islands has aided their preservation, but as the menacing water hyacinth threatens to clog the entire lake, their survival is at stake as well as the livelihoods of all who live near and depend on Lake Tana as a natural resource." }
{ "amh": "የቦረና ሰዎች - በደማቅ አልባሳት፤ የቦረና ሕዝቦች በኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ናቸው።", "en": "The Borana people live in Ethiopia's Oromia region." }
{ "amh": "ፎቶ፦ ካርስተን ቴን ብሪንክ Flickr.", "en": "Photo by Carsten ten Brink via Flickr." }
{ "amh": "CC BY 2.0", "en": "CC BY 2.0" }
{ "amh": "በሁለቱ የኢትዮጵያ ክልሎች፣ ኦሮምያ እና ሶማሊ መካከል የነበረው የዘውግ ቡድኖች ውጥረት ወደ አመፃዊ ግጭት በማደጉ ቢያንስ ደርዘን ያህሎችን ለሞት፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናትን ደግሞ ለስደት ዳርጓል።", "en": "Ethnic tensions between Ethiopia’s two regions, Oromia and Somali erupted into violent conflict that killed at least dozens of people and drove thousands of men, women and children from their homes during the second week of September 2017." }
{ "amh": "የሟቾች ቁጥርን በተመለከተ በማኅበራዊ ሚድያዎች የሚወጡት ቁጥሮች እንደ ሪፖርት አድራጊዎቹ ማንነት የተለያየ ነው።", "en": "Reports on social media about the death toll and displacement of people are wildly different depending on who reports them." }
{ "amh": "ለመንግሥት የሚወግኑ ጋዜጠኞች የሟቾቹን ቁጥር ደርዘን አካባቢ ሲወስኑት፣ ዳያስፖራ ተቀማጭ ሚድያ ግን በጣም ብዙ ያደርገዋል።", "en": "Pro-government journalists based in the capital Addis Ababa reported dozens of deaths while diaspora-based media put the number much higher." }
{ "amh": "ሁለቱም ግን የተናፈቀሉት ሰዎች በሺሕዎች የሚቆጠሩ እንደሆኑ ተናግረዋል።", "en": "However, both reported that thousands of people were displaced." }
{ "amh": "ከሪፈረንደሙ ከ14 ዓመታት በኋላ ግጨቱ አገርሽቷል", "en": "A referendum still reverberates 14 years later" }
{ "amh": "በኢትዮጵያ ክልሎች ትልቁን ድንበር የሚጋሩት ኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች ናቸው።", "en": "The longest border in Ethiopia is shared between Oromia and Ethiopian Somali region, which are respectively the country's first and second largest administrative regions by area." }
{ "amh": "በዚህ ክልላዊ ድንበር አካባቢ ለረዥም ግዜ የቆየ ውጥረት በተለይ በኦሮሞዎች እና በሶማሌዎች መካከል ነበር።", "en": "Tension has been simmering for years along this border which led to intermittent clashes involving mostly Oromos and Somalis." }
{ "amh": "በ1987 የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የሶማሊ ክልል የደቡብ ምሥራቅ የኦሮሚያ ክልልን ጥሶ እየገባ ነው በማለት ወቀሳ አቅርቦ ነበር።", "en": "In 1994 an opposition political party known as Oromo Liberation Front (OLF) accused the Ethiopian Somali Region of infringing into the south-eastern provinces of Oromia Region." }
{ "amh": "ኦነግ ከዚያ በኋላ በአገዛዙ አሸባሪ ተብሎ ተፈርጇል።", "en": "OLF was eventually labeled as a terrorist organization by the Ethiopian regime." }
{ "amh": "በሰኔ 1992፣ ኦነግ በኦሮሞዎች እና ሶማሊዎች መካከል በተደረገ የትጥቅ ግጭት 70 ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርት አድርጎ ነበር።", "en": "In June 2000, OLF reported that at least 70 people were killed in an armed conflict that ensued between Oromos and Somalis." }
{ "amh": "በታኅሣሥ 1996 በውኃ እና ደረቅ መሬት ሀብት ሳቢያ በተቀሰቀሰ አመፅ የቀላቀለበት ግጭት ደግሞ ከክልሎቹ ድንበር አካባቢ 19ሺሕ ያህል ሰዎች ተፈናቅለዋል።", "en": "In December 2003, a violent clash over scarce water and land resources led to the displacement of 19,000 people in the border." }
{ "amh": "በ1996 የኢትዮጵያ መንግሥት ሪፈረንደም አዘጋጅቶ ግጭቶቹን ለመፍታት ሞክሯል።", "en": "In 2004, the Ethiopian government held a referendum to settle the territorial dispute." }
{ "amh": "በውጤቱም 80 በመቶ የሚሆኑት አጨቃጫቂ ወረዳዎች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሥር እንዲካለሉ ተወስኗል።", "en": "The official results of the referendum gave about 80 percent of the disputed districts to Oromia Regional State." }
{ "amh": "ታኅሣሥ 1998፣ መንግሥት ሕዝበ ውሳኔውን ተግባራዊ ሊያደርግ ሲሞክር አመፁ ተባብሶ አገረሸ።", "en": "But in December 2005, all hell broke loose when the federal government attempted to enforce the results of the vote." }
{ "amh": "ሪሊፍ ዌብ የተባለ ዓለማቀፍ ድርጅት እንዳወጠው መረጃ ከሆነ፣ በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በወቅቱ ከአካባቢው ተፈናቅለዋል። በዚህ ሳቢያ የኢትዮጵያ መንግሥት በሕዝበ ውሳኔው ወደ ኦሮሚያ እንዲካለሉ የተወሰኑትን አካባቢዎች የማካለሉን ሥራ ለሌላ ግዜ ለማስተላለፍ ተገዷል።", "en": "According to Relief Web International, tens of thousands of people have been displaced from both regions forcing the Ethiopian government to defer to transfer of the districts that have voted to be redistricted as part of Oromia Regional State." }
{ "amh": "ከዚያ በኋላ ነገሮች በአንፃራዊ ሁኔታ ተቀዛቅዘው ነበር።", "en": "Things remained relatively quiet since then." }
{ "amh": "የአሁኑ ግጭት እንዴት ተቀሰቀሰ?", "en": "How did the latest conflict begin?" }
{ "amh": "በሚያዝያ ወር 1999፣ በደቡባዊ የሞያሌ ከተማ ድንበር አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት ከኦሮሞዎቹም፣ ከሶማሌዎችም ሰዎች መገደላቸው ሪፖርት ተደርጓል።", "en": "In April 2017, violent conflicts were reported in the southern border town of Moyale where members from both Oromo and Ethiopian Somali ethnic groups were killed." }
{ "amh": "በዚህ ወቅትም የግጭቱ መንስዔ የውኃ እና የደረቅ መሬት ሀብት እጥረት ነው።", "en": "The cause of the violence again was scarce water and land resources." }
{ "amh": "መንግሥት በዚያው ወር፣ በ1996ቱ ሕዝበ ውሳኔ በተስማሙበት መሠረት ድንበሮቹን አሠምራለሁ ብሎ አሳወቀ።", "en": "During the same month, the Ethiopian government announced that the two regions have agreed to rearrange their boundaries per the outcome of the 2004 referendum." }
{ "amh": "ይህም ለመጨረሻ ግዜ በ1996 የታየውን ግጭት እንደገና ቀስቅሶት ከፍ ያለ ደረጃ አደረሰው።", "en": "This was when the conflict picked up and reached the level of violence that was last seen in 2005." }
{ "amh": "የኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልል ባለሥልጣናት እንዲሁም አራማጆችም የታጣቂ ኃይሎች ሲቪሎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ወንጅለዋል።", "en": "Authorities and activists from both Oromia and Ethiopia-Somali started to trade accusations of unleashing paramilitary groups against civilians." }
{ "amh": "ምንም እንኳን ብዙ የኦሮሞ ማኅበራዊ ሚድያ አራማጆች የአሁኑን ግጭት በዘውግ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ለማመን ባይፈልጉም፣ ግጭት ውስጥ የገቡት ዜጎች ግን በዘውግ በጣም ተከፋፍለዋል።", "en": "While most Oromo activists on social media refuse to view the latest conflict in ethnic terms, the civilians caught in the conflict are actually divided largely along ethnic lines." }
{ "amh": "ባለፈው ሳምንት፣ ቢያንስ 32 በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች ሲገደሉ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ደግሞ ከሶማሊያ ክልል ጥቃት ፍራቻ እየሸሹ ነው።", "en": "Last week, at least 32 people were killed both in Oromia and Somali regions. Thousands of Oromos have been fleeing the Somali Region as they have come to be a target of violence." }
{ "amh": "የፌዴራል መንግሥቱ ስለዚህ ምን አደረገ?", "en": "What has the Federal Government done about it?" }
{ "amh": "የመንግሥት ሚድያ እንደገለጸው፣ የፌዴራል መንግሥቱ የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ጣልቃ ገብቷል።", "en": "According to the state media, the Federal Government has stepped in to protect civilians." }
{ "amh": "ነገር ግን ብዙዎች የመንግሥትን ሚና በጥርጣሬ ነው የተመለከቱት።", "en": "However, many see the government’s role with suspicion." }
{ "amh": "እንዲያውም አንዳንዶች፣ መንግሥት የዘውግ ቡድኖችን በማጋጨት በአገሪቱ እያደገ የመጣውን ተቃውሞ ለመቆጣጠር የደገሰው ውጥረት ነው እስከማለት ደርሰዋል።", "en": "Some even accused the government of deliberately stoking tensions and exploiting political fissures among different ethnic groups in the country to control the growing discontent in Ethiopia." }
{ "amh": "ባለፉት ሦስት ዓመታት፣ ብዙ ኢትዮጵያውያን በተለይም በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች የበለጠ ፖለቲካዊ መብቶችን እና ማኅበራዊ ፍትሕ ለመጠየቅ እንዲሁም የመሬት መቀራመትም ለማስቆም አምፀዋል።", "en": "Over the last three years, thousands across Ethiopia mainly in the Oromia and Amhara regions rose up, demanding more political freedoms and social equality and a stop to government land grabs." }
{ "amh": "የመንግሥት ምላሽ ደግሞ ፈጣንና ክፉ ነበር፣ በዚህም ብዙዎች ታስረዋል፣ ተገድለውማል።", "en": "The government's response was swift and brutal which led to mass arrests and killings." }