category
large_stringclasses
7 values
headline
large_stringlengths
10
171
text
large_stringlengths
1
26.4k
url
large_stringlengths
13
180
lang
large_stringclasses
16 values
politics
የፈረንሳይ ዜጎች በማዳጋስካር መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተፈረደባቸው
በማዳጋስካር ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆኤሊና ላይ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ በማቀድ ሁለት የፈረንሳይ ዜጎች የ10 እና 20 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል። ፖል ራፋኖሃራና እና ፊሊፕ ፍራንኮይስ የተባሉት ግለሰቦች የመንግስትን ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል፣ ፕሬዚዳንቱን ለመግደር በማሴርና የወንጀል ማህበር በመፍጠር በሚል ተከሰው ነበር። ሌሎች 20 ተከሳሾችም በእስር ተቀጥተዋል። የግለሰቦቹ ጠበቃ ቅጣቱን በመቃወም ይግባኝ ለማቅረብ ማቀዱን ተናግሯል። "እኔ እንደጠበቅኩት ሳይሆን ፍትሃዊ ያልሆነ ፍርድ ነው...የፖለቲካ ክስ ነው" ሲሉ ጠበቃ ሶሎ ራድሰን መናገራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ባለሥልጣናቱ እንዳሉት በሐምሌ ወር በግለሰቦቹ ላይ ባደረጉት ብርበራ ማስረጃ የሚሆኑ "ኢሜይሎችን ፣መሳሪያዎችን እና ገንዘቦችን ከያዙ በኋላ "አፖሎ 21" የተሰኘውን የመፈንቅለ መንግሥት ሴራ ማግኘታቸውን ተናግረዋል ። በመረጃውም መሰረት ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን "የማጥፋት እና የማስወገድ" ዕቅዶችን እንዳካተተም ተናግረዋል። ፊሊፕ ፍራንኮይስ የተባለው የፈረንሳይ ጦር የቀድሞ ኮሎኔል በ10 አመት እስራት ተቀጥቷል። በአንድ ወቅት የፕሬዚዳንት ራጆኤሊና አማካሪ ሆኖ ያገለገለውና የፈረንሳይና የማዳጋስካር ጥምር ዜግነት ያለው ፖል ራፋኖሃራና የ20 አመት እስር ተፈርዶበታል። ባለቤቱም የአምስት አመት እስር ተፈርዶባታል። የቀድሞ የማዳጋስካር ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ራማሃትራ የአምስት አመት የእስር ቅጣት ተበይኖባቸዋል። ማዳጋስካር ከቅኝ ገዥዋ ፈረንሳይ ነፃነቷን ከተጎናፀፈችበት ከአውሮፓውያኑ 1960 ጀምሮ በርካታ መፈንቅለ መንግሥቶችን አስተናግዳለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-59699569
amh
politics
እንደ አዲስ የተቀሰቀሰው የኢትዮ-ሱዳን ውዝግብ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮቼን ገድሏል ስትል ሱዳን ክስ አሰምታለች። የሱዳን መንግሥት ድምፅ የሆነው ሱና እንደዘገበው አንድ ሲቪልን ጨምሮ ሰባት ወታደሮች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተገድለዋል። የሱዳን መከላከያ ኃይል ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሱዳናውያኑን ከገደሉ በኋላ “አስክሬናቸውን ለሕዝብ በአደባባይ አሳይተዋል” ሲል ከሷል። የሱዳን መንግሥት በመግለጫው ለድርጊቱ “ምላሽ እሰጣለሁ” ሲል ዝቷል። ኢትዮጵያ ግን ይህ ሆን ተብሎ በሱዳን በኩል የተፈጸመ ጠብ ጫሪነት ያስከተለው ጉዳት መሆኑን በመግለጽ፣ ውጥረቱ ረግቦ አለመግባባቶች በንግግር መፍትሔ እንዲገኝላቸው ጠይቃለች። በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር ለዘመናት በቆየው ውዝግብ ምክንያት በሁለቱ አገራት ሠራዊቶች መካከል ግልጽ ወታደራዊ ግጭት ከዚህ በፊት እምብዛም ባይስተዋልም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ውጥረቱ እያየለ መጥቷል። ቢቢሲ ሱዳን አጋጥሟል ላለችው ክስተት ከኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ባለፈው ወር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ መንግሥት የአልፋሻጋን ጉዳይ "በወዳጅነት ለመፍታት ሰላማዊ የውይይት መንገድን ይመርጣል” ማለታቸውን ይታወሳል። ሆኖም "የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜኑ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ላይ በነበረበት ወቅት ሱዳን የድንበር ማካለሉን መጣሷ በጣም አሳዛኝ ነው” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሱዳን ኃይሎች ኢትዮጵያውያንን አፈናቅለዋል፤ ንብረታቸውንም አውድመዋል ሲሉ ከሰዋል። ሱዳን ትሪቡን የተሰኘው የግል አውታር ባለፈው ሳምንት ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የሱዳን ወታደሮች በድንበር አካባቢ በምትገኘው አል-ቁሬይሻ ከተማ ላይ እርምጃ ከወሰዱ በኋላ ነው ግጭት የተቀሰቀሰው። ሱዳን፤ የኢትዮጵያ ሠራዊት እና ሚሊሻዎች በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገበሬዎችን ለመጠበቅ በሚል ሠፍረዋል መባሉን ተከትሎ እርምጃ የሚወስዱ ወታደሮች መላኳ ይነገራል። በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት የወጡ ዘገባዎች ከሰዱን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው የምዕራብ ጎንደሯ መተማ ከተማ ግጭቶች እንደነበሩ ይጠቁማሉ። በመተማ ከተማ በሚገኘው ሽመት መገዱቃ በተባለው ቀበሌ፤ በሱዳን ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለው ጥቃት የአካባቢው አርሶ አደሮች የግብርና ሥራቸው እንደተስተጓጎለ ተገልጧል። የአሜሪካ ድምጽ፤ የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቁን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ “በአንድ ዓመት ውስጥ በእርሻ ሥራ የተሰማሩ 246 ባለሀብቶች ሥራቸውን አቁመዋል” ብሏል። እንደ አልጀዚራና ሮይተርስ ያሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ሱናን ጠቅሰው የሱዳን መንግሥት "እርምጃ እውስዳለሁ" ማለቱን ዘግበዋል። በዚህም ሳቢያ ሱዳም በአዲስ አበባ ያሏትን አምባሳደር የጠራች ሲሆን፣ በተጨማሪም በካርቱም ያሉትን የኢትዮጵያን አምባሳደር በመጥራት ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠያቋ ተዘግበወል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰኞ ከሰዓት በኋላ ባወጣው መግለጫ የሱዳን ወታደሮች ድንበር አልፈው በመግባት ግጭቱን መቀስቀሳቸውን ገልጾ፣ በሱዳን በኩል የቀረበውን ውንጀላ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ አድርጎታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ግጭቱ የተከሰተው በህወሓት ድጋፍ የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በገቡ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች መሆኑን በመግለጽ የሱዳንን ክስ አጣጥሎታል። ጨምሮም በሱዳን ሠራዊትና በአካባቢው ሚሊሻዎች መካከል በተከሰተው ግጭት በጠፋው ህይወት የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚያዝን ገልጾ ምርመራ እንደሚደረግ አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ክስተት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ለማደናቀፍ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን በማመልከት፣ የሱዳን መንግሥትም ከስተቱን የበለጠ ከሚያባብስ እርምጃ እንደሚቆጠብ ተስፋ እንዳለው ገልጿል። የትግራይ ጦርነት በተቀሰቀሰ በቀናት ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የይገባኛል ውዝግብ ከሚነሳባት የአልፋሻጋ አካባቢ ለቆ ወጣ። ጦርነቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ድንበሬ ነው የምትለው አልፋሻጋ በሱዳን ጦር እጅ ወደቀ። ለዘመናት ኢትዮጵያ፤ የሱዳን ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው በመግባት ቆስቋሽ ድርጊት ፈፅመዋል ስትል ትከሳለች። የቀድሞው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በቅርቡ "የሱዳን ወታደራዊ ኃይል በድንበር አካባቢ ወደ ተጨማሪ ቦታዎች ዘልቆ ለመግባት የተጠናከረ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው" ሲሉ ተደምጠው ነበር። አምባሳደሩ አክለው፤ ችግሩን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት መሞከር "ፍርሃት ወይም መወላወል አይደለም" ብለዋል። "አካባቢውን ከግጭት ለመጠበቅ ሲባል ኢትዮጵያ ነገሮች እንዳይካረሩ ለማድረግ እየጣረች ቢሆንም ይህ ታጋሽነት ገደብ አለው" የሚል አስተያየት አክለዋል። ኢትዮጵያ አለመግባባቱን በድርድር ለመፍታት ሱዳን የያዘችውን መሬት መልቀቅ አለባት የሚል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች። ሱዳን በበኩሏ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ያለውንና በቅርቡ መልሳ የወሰደችውን መሬት እንደማትለቅ አስታወቃ ነበር። "ሱዳን ከአልፋሻጋ ይዞታ ቅንጣት ታህል እንደማትሰጥ ሜጀር ጀነራል ሀይደር አልቲራፊ አረጋግጠዋል። ለወታደራዊ ኃይል ምልመላ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል" ይላል የሱዳን መንግሥት ድምፅ የሆነው ሱና ዘገባ። ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በይገባኛል የምትወዛገብብት አካባቢ ረዥም የግዛት ድንበር ነው ያላት። ሁለቱም አገሮች ለም ነው የሚባለውን ፋሻጋ አካባቢን እጅጉኑ ይፈልጉታል። ይህ በሁለቱ አገራት ዐይን ውስጥ ያለው አካባቢ የአልፋሻጋ ማዕዘን ወይም የአልፋሻጋ ጥግ ተብሎ ይጠራል። በዚህ ድንበር ሁለቱም አቅጣጫ የሚገኙ ገበሬዎች ባሻገራቸው ያሉ ለም መሬቶች ላይ ያማትራሉ። የአልፋሻጋ ማዕዘን በደቡብ ምሥራቅ ሱዳን የምሥራቃዊ ገዳሪፍ በአዋሳኝ የሚገኝ ለም መሬት ነው። የአልፋሻጋ መሬት 250 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍንና 600 ሺህ ኤክር አሊያም ከ240 ሺህ በላይ ሄክታር ለም መሬትን የሚሸፍን ነው። ለለምነቱ ምክንያት የሆኑት እንደ አትባራ፣ ሰቲት እና ባስላም ወንዞችም በቅርብ ይገኛሉ። ሁለቱ መንግሥታት ከዚህ ቀደም ይህንን አወዛጋቢ ድንበር በድጋሚ ለማስመር፣ የጋራ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር እና የአካባቢው ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ድንበሮች ብዙውን ጊዜ ውዝግብ ሲያነሱ ይስተዋላል። ከአስርት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያና ሶማሊያ በኦጋዴን የተነሳ ጦርነት አድርገዋል። እንዲሁም ከ20 ዓመታት በፊት በባድመ ይገባኛል ምክንያት ኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ውስጥ ገብተው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያና ሱዳን ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረውን 744 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ድንበራቸውን ለይቶ ለማመላከት የሚያስችል ንግግርን መልሰው ጀመሩ። በዚህ መፍትሄ ለመስጠት አስቸጋሪ የሆነው አካባቢ ፋሻጋ የሚባለው ነበር። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1902 እና በ1907 በነበረው የቅኝ ግዛት ስምምነት መሰረት ዓለም አቀፉ ድንበር ወደ ምሥራቅ ይዘልቃል። በዚህም ሳቢያ መሬቱ ወደ ሱዳን የሚካተት ይሆናል። ነገር ግን ቦታው ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት ሲሆን የግብርና ሥራ በማከናወንም የሚጠበቅባቸውን ግብር ለኢትዮጵያ መንግሥት ሲከፍሉም ቆይተዋል። ሁለቱ አገራት ሲደረጉ በነበሩ የድንበር ድርድሮች አማካይነት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 2008 ከመግባባት ደርሰው ነበር። በዚህም ኢትዮጵያ ለሕጋዊው ድንበር ዕውቅና ስትሰጥ ሱዳን ደግሞ ኢትዮጵያውያኑ በስፍራው ያለችግር ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ ፈቀደች። ይህም አስከ ቅርብ ጊዜ በድንበር አካባቢ ያሉ የነዋሪዎችን ህይወት ሳያደናቅፍ ኢትዮጵያ ግልጽ የድንበር መለያ እንዲኖር እስክትጠይቅ ድረስ ቀጥሎ ነበር። በሁለቱ አገራት መካከል ከስምምነት የተደረሰበትን የዚህ የድርድር ልዑክ የተመራው የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣን በሆኑት በአባይ ፀሐዬ ነበር። ህወሓት ከማዕከላዊው መንግሥት የሥልጣን መንበር ሲወገድ የአማራ ክልል መሪዎች ከሱዳን ጋር የተደረሰው ስምምነት በአግባቡ ሳያውቁት የተደረገ ድብቅ ውል ነው ሲሉ ተቃውመውታል። ቱርክ ባለፈው ዓመት፤ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ያላቸውን የድንበር ውዝግብ በውይይት እንዲፈቱ ለማሸማገል ጥያቄ አቅርባ ነበር። ነገር ግን ሱዳን ሠራዊቷን ከተቆጣጠረቻቸው አካባቢዎች እንደማታስወጣ ስትገልጥ ኢትዮጵያ ደግሞ የሱዳን እርምጃ ወረራ መሆኑን በመግለጥ ድርድር ከመደረጉ የሱዳን ኃይሎች ድንበሯን ለቃ እንድትወጣ ትጠይቃለች።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2694mlq6jo
amh
politics
ኔቶ ከቻይና ተደቅኗል ስላለው ወታደራዊ ስጋት አስጠነቀቀ
በብራሰልስ የተገናኙት የየሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) መሪዎች በቻይና ተደቅኗል ስላሉት ወታደራዊ ስጋት ያስጠነቀቁ ሲሆን "ስልታዊ እንቅፋት" ሲሉ የአገሪቷን ባህሪይ ገልጸውታል። ቻይና የኒኩለር የጦር መሳሪያዋን በፍጥነት እያሰፋች መሆኗን ጠቅሰው የወታደራዊ አቅሟን በማዘመን ረገድ ግልፅ ነበረች ብሎም ከሩሲያ ጋርም በወታደራዊ ትብብር እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል። የኔቶ ዋና ሃላፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ቻይና በወታደራዊ እና በቴክኖሎጂ ረገድ ወደ ኔቶ "እየቀረበች" እንደሆነ አስጠንቅቀዋል ። ነገር ግን ጥምረቱ ከቻይና ጋር አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ መግባት እንደማይፈልግ አጥብቀው ተናግረዋል ። ኔቶ በ 30 የአውሮፓ አገራት እና በሰሜን አሜሪካ ሀገሮች መካከል የተመሰተ ጠንካራ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ጥምረት ነው ። የተቋቋመውም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ሲሆን በተለይም ለኮሚኒስት ስርአት መስፋፋት ስጋት ምላሽ ለመስጠት ያሰበ ነበር። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መሪዎች በዓላማው ብሎም የገንዘብ መዋጮን በተመለከተ ያለመግባባት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ጥምረቱ ውጥረት ውስጥ ከርሟል ። በዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ወቅት ሀገራቸው ለህብረቱ በምታዋጣው የገንዘብ መጠን ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ የቆዩ ሲሆን አሜሪካ የአውሮፓ አገራትን ለመከላከል ያላትን ቀርጠኝነት ጥያቄ ውስጥ የከተተ ነበር። የእሳቸው ተተኪ ጆ ባይደን ስልጣኑን ከያዙ ወዲህ የመጀመሪያ የኔቶ ስብሰባ ሲሆን አዲሱ ፕሬዝዳንት ለ 72 ዓመቱ ህብረት የአሜሪካን ድጋፍ በድጋሚ ለማሳየት ሞክረዋል ። ባይደን ኔቶ "ለአሜሪካ ፍላጎቶች" ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው እና አባላት የጥመረቱን የመመሰረቻ ውል አንቀጽ 5 ን በመተግበር እርስ በእርስ ከጥቃት ለመከላከል የተቀመጠውን "የተቀደሰ ግዴታ" እንዲተገብሩ ጠይቀዋል ። መጪው ረቡዕ ከሩሲያው መሪ ከቭላድሚር ፑቲል ጋር በጄኔቫ ስለሚያካሂዱት ስብሰባ ሲጠየቁ ‹‹ጠንካራ ተፎካካሪ›› ሲሉ ፑቲንን ገልፀዋቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57479656
amh
politics
ቀጣይ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ እኩለ ቀን ይለያል
ተሰናባቹን የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት በመወዳደር ላይ ከሚገኙት ሊዝ ትረስ ወይም ሪሺ ሱናክ መካከል አሸናፊው ዛሬ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር እኩለ ቀን ላይ ይታወቃል። አሸናፊው ግለሰብ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለ ኢኮኖሚን እና በ40 ዓመታት ከፍተኛው የተባለለትን የዋጋ ግሽበት የሚረከብ ይሆናል። ቀጣዩ መሪ የተከማቸ ኤሌክትሪክ ኃይል ክፍያን መሰረዝን ጨምሮ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን ለመርዳት እቅድ መያዙን ቢቢሲ ከምንጮቹ ተርድቷል። ይህን ምርጫ ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብሎ ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው ሊዝ ትረስ ኃላፊነቱን በተረከቡ በአንድ ሳምንት ግዜ በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ጫና ውስጥ የሚገኙ ሸማቾችን መደገፍ የሚያስችሉ እገዛዎችን ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። እንዲሁም በመስከረም ወር መጨረሻ ወደ 30 ቢሊዮን ፓውንድ ገደማ የግብር ቅነሳ ይፋ ለማድረግ ማሰባቸውንም ትረስ አስታውቀዋል። ተቀናቃኛቸው ሱናክ ውድድሩን ተሸንፌአለሁ ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመው “አሁን ዋና ስራዬ ወግ አጥባቂው ፓርቲ የሚመራውን መንግሥት መደገፍ ብቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ትረስ ከኃይል አቅርቦት ዋጋ ቅናሽ እንዲሁም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ከማቀዳቸው ባሻገር ዝርዝር የእርምጃ እቅዳቸውን እስካሁን ድረስ ይፋ አላደረጉም። በአሁን ወቅት የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱን በመምራት ላይ የሚገኙት እጩዋ እሁድ በቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የእቅዳቸውን ዝርዝር ሁኔታ ይፋ ለማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ላይ ተቀምጠው ተጨማሪ ግዜ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል። ዕቅዳቸው ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው ሰዎች ብቻ ነው ወይስ ለሁሉም ዜጎች የሚለውን ሳይመልሱም ቀርተዋል። ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታም ባለፉት 20 ዓመታት ለነበረው ዝቅተኛ የኢኮኖሚ እድገት ተጠያቂው ፍትሃዊ የሃብት ስርጭትን ማስፈን በሚል ሲተገበር የቆየው የግብር ፖሊሲ ነው ብለዋል። የሠራተኛ ፓርቲ፣ ሊበራል ዴሞክራቶች እና ኤስኤንፒ መንግሥት ቢሊዮን ፓውንዶችን አውጥቶ የኃይል ዋጋ ድጎማ እንዲያደርግ የጠየቁ ሲሆን የግሪን ፓርቲ አባላት ደግሞ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አምስት ግዙፍ የኃይል አቅራቢ ተቋማትን ባለቤትነቱን ከግለሰቦች እንዲረከብ ጠይቀዋል። የመሪነቱን ቦታ ይረከባሉ ተብለው የሚጠበቁት ትረስ የተከማቸ የኃይል ክፍያን መሰረዝን ውድቅ ባያደርጉም ከዚህ ቀደም ባደረጉት ክርክር አገራቸው እንግሊዝ የአገር ውስጥ የኃይል አቅርቦት ምንጮቿን ማሳደግ ግድ እንደሚላት ትኩረት ሰጥተው ነበር። ለሰባት ሳምታት የዘለቀው የዩኬ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ለመያዝ የተደረገው ፉክክር የቦሪስ ጆንሰንን የሶስት ዓመት የስልጣን ዘመን ቆይታ ማብቂያ የሚያሰምር ይሆናል። ላለፉት ሁለት ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩት ቦሪስ ጆንሰን ከፓርቲያቸው መሪነት ለመልቀቅ የወሰኑት ሪሺ ሱናክን ጨምሮ በርካታ ሚኒስትሮቻቸው አመራራቸውን በመቃወም በ48 ሰዓታት ውስጥ በፈቃዳቸው ሥልጣን ከለቀቁ በኋላ ነው። በመጀመሪያው ዙር 11 ተወዳዳሪዎች የወግ አጥባቂውን ፓርቲ ለመምራት አቅደው ወደ ውድድር ግብተው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ወደ ሁለት ዝቅ ብሏል። ምንም እንኳን የሕንድ የዘር ግንድ ያላቸው ሱናክ በፓርላማ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ቢኖራቸውም የውጪ ጉዳይ ኃላፊዋ ትረስት አሸናፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ትንበያዎች ያሳያሉ። ተሰናባቹ ቦሪስ ጆንሰን የስልጣን ርክክብ ከመደረጉ በፊት ማክሰኞ የስንብት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን የሚያሸንፈው ተወዳዳሪ እስካሁን ባለው ባህል መሠረት በባኪንግሃም ፓላስ ሳይሆን ወደ ስኮትላንድ በመጓዝ በባልሞራል ቤተ-መንግሥት ሲመቱን ከንግስቲቱ የሚቀበል ይሆናል። ለዚህም ምክንያቱ ንግስቲቱ በጤና ምክንያት እንደልባቸው መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ባለፈው ሳምንት ይፋ መደረጉን ተከትሎ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/crg22eqq4gxo
amh
politics
"የተጠየቅኩባቸው ጉዳዮች ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር የሚገናኙ አልነበሩም" እያስፔድ ተስፋዬ
ማኅበራዊ አንቂና በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ሲሰራ የቆው ከኢያስፔድ ተስፋዬ ከ43 ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ ከቀናት በፊት ተለቋል። ኢያስፔድ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት አስር ዓመታት ያህል በተለያዩ ወቅቶች የቅርቡን ጨምሮ ለዘጠኝ ጊዜያት ያህል ታስሯል። ነገር ግን ከአንድ ወር በላይ ሲታሰር የአሁኑ ለሦስተኛ ጊዜ ነው። ከአንድ ባልደረባው ጋር በቅርብ በመሰረቱት 'ኡቡንቱ' በተሰኘ ዩቲዩብ ቴሌቪዥን ላይ ሲሰራ ከነበረው ኢያስፔድ ከአስር ከወጣ ከቀናት በኋላ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጓል። ቢቢሲ፡ በታሰርክበት ወቅት ታመህ እንደነበር ከቤሰተቦችህ እና ከወዳጆችህ ስንሰማ ነበር። ህክምና እንዳላገኘህም ጭምር። ምን ነበር ያጋጠመህ? እያስፔድ፡ የኢትዮጵያ እስር ቤቶች እንደሚታወቀው በጠባብ ቦታ ውስጥ በርካታ ሰው ይታሰራል። ከንጽህና ጉድለት የሚመጡ በሽታዎች እና በትንፋሽ የሚተላለፉ በሽታዎች ያሉ ናቸው። የተለየ ነገር ከመታሰሬ ከጥቂት ቀናት በፊት የጥርስ ህክምና ጀምሬ ነበር። ይህ እንደሚታወቀው ሂደት አለው። የመጀመሪያ ቀን ህክምናውን ጀምሬ እሱን አቋርጬ ነው የታሰርኩት። በእሱ በጣም ተቸግሬ ነበር። ወደተሻለ ህክምና ለመሄድ ብጠይቅም ፈቃደኛ አልነበሩም። በ43 ቀን ውስጥ ከ7 ኪሎ በላይ ቀንሼ ነው የወጣሁት። ቢቢሲ፡ በታሰርክበት ቀን ስለ ነበሩ ነገሮች የተወሰኑ ነገሮች ሰምተናል። በአጭሩ ግን እንዴት እንደነበር ንገረን? እያስፔድ፡ ቤት ውስጥ ነበርኩ በአጋጣሚ። በዚያ ሰሞን በርካቶች ይታሰር እያሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ዘመቻ ያደርጉ ነበር። እናም ያን ያህል እንቅስቃሴ አላደርግም ነበር። ስለዚህ በጣም በርካታ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም በርካታ መኪኖች ነበሩ። በጣም ትልቅ ወንጀለኛ የሚያዝ ነበር የሚመስለው። ያው አብዛኛው ሰው በተያዘበት መልኩ የቤትና የቢሮ ብርበራዎች ተደርገው ነበር። ብዙ የተለየ አልነበረም። ቢቢሲ፡ በጠቀስከው የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ምክንያት ነው ብለህ ታምናለህ? ወይም በአጠቃላይ ከታሰርክ በኋላ ለምን እንደታሰርክ የተሰጠህ ምክንያት አለ? እያስፔድ፡ በአጠቃላይ ሁለት ቀን ለምርመራ ተጠርቼ ነበር። አንደኛው የገባሁ ቀን ሌላ ቀን ደሞ ከታሰርኩ ከአንድ ወር በኋላ። ሁለቱም ቀን የተነገሩኝ ነገሮች ይለያያል። የመጀመሪያ ቀን አንድ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚታወቅ አካውንት አለ። መረጃ ደርሶናል እሱ አንተ ነህ ወይ? የሚል ነው። ለማስረዳት ሞክሬ የተቀበሉኝ ይመስለኛል። ከ30 ቀን በኋላ ደግሞ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የሰራው እና ለክስ መነሻ የሚሆን የሚዲያ ሞኒተሪንግ (ክትትል) ሰነድ ልኮላቸው ነበር። በጣም የደነቀኝ ነገር ከወቅታዊ ነገሮች ጋር አይገናኝም። ወደ ኋላ የዛሬ ሦስት ዓመት ተመልሶ በአዲስ ቲቪ አንድ የክርክር መድረክ ላይ የተናገርኳቸውን ነገሮች የሚዘረዝር ሰነድ ነው። እኔ እንደጠረጠርኩት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ብዙም የሚገናኝ ነገር የለውም። ቃል የሰጠሁበት የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በጻፈው ክስ ላይ ነው። ለምሳሌ የዛሬ ሦስት ዓመት "የሶማሌ ሕዝብ ባሕል፣ ማንነት እና ወዘተ በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ አልተገለጸም ብሎ በአዲስ ቲቪ ላይ በመናገር አንድን ሕዝብ በሌላው ላይ ለማነሳሳት ሞክሯል" የሚል ይገኝበታል። የዛሬ ሁለት ዓመት ቢቢሲ ላይ ይመስለኛል ቀርቦ አንድን ሕዝብ ሊያነሳሳ ሞክሯል የሚሉ ወደ 10 ገጽ የሚሆኑ፣ ወቅታዊ ያልሆኑ እና ከሦስት ዓመት በፊት ጀምሮ ስናገራቸው የቆዩ ነገሮች እየተለቀሙ ክስ በሚመስል መልኩ ነው የመጡት። በእርግጥ በቅርብ የተናገርኳቸው ነገሮችም ተጨምረዋል። አጠቃላይ ይዘቱ ግን እኔ እንደሚታወቀው አሁን ያለው የፌደራል ሥርዓት ደጋፊ ነኝ። ያንን በተመለከተ የተናገርኳቸው ነገሮች ናቸው ሕዝብን ከሕዝብ እንደማጋጨት የታዩት። ቢቢሲ፡ ስትፈታስ በምን ምክንያት ነው እንድትለቀቅ የተወሰነው? እያስፔድ፡ ፖሊስ የመታወቂያ ዋስ የሚለው ነገር አለ፤ በእሱ ነው የወጣሁት። እንደሚመስለኝ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንም ይሁን ከተለያዩ አካላት የደረሳቸው ነገሮች ክስ ለመመስረት በቂ አለመሆኑን ተረድተው ነው ብዬ አስባለሁ። ሚዛን የሚያነሳ ነገር ስላልነበረ ተለቅቄያለሁ ብዬ አምናለሁ። ቢቢሲ፡ ተባባሪ መስራች የሆንክበት ኡቡንቱ ቲቪ ንብረቶቹ ተመልሰዋል ወይ? በቅርቡ ወደ ሥራ የመመለስ እቅድስ አላችሁ? እያስፔድ፡ ሚዲያችን ተበርብሮ ነበር። እቃዎቹም ተወስደዋል። እንደሚታወቀው የሚዲያ እቃዎች ውድ ናቸው። በርካታ ካሜራዎች እና ቁሳቁሶች ተወስደውብናል። ሲወሰዱ በቃለ ጉባኤ ምስክር ባለበት ተፈርሞ ነው የተወሰዱት። እነዚህ እቃዎች የሚመለሱት ዐቃቤ ሕግ እቃዎቹ ከዚህ በኋላ አያስፈልጉም ለባለቤቱ ይመለስ ካለ በኋላ በመሆኑ እንደተፈታሁ እቃዎቹን ለማግኘት አልቻልኩም። ፖሊስ ለመመለስ ፈቃደኛ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ የሥነ ሥርዓት ጉዳይ ስለሆነ እሱ እንዳለቀ ይመለሳል ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን እቃዎቹ ተመለሱም አልተመለሱም ሚዲያችን በሚቀጥሉት ሁለት እና ሦስት ቀናት ውስጥ ይመለሳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ተመልሰን ሥራችንን ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ ነን። ቢቢሲ፡ ታስረህበት በነበረው ጣቢያ ሌሎች ጋዜጠኞች ነበሩ? እነማን ናቸው? ሁኔታውስ ምን ይመስላል? እያስፔድ፡ የተለያዩ ቦታዎች ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ከወጣሁ በኋላም ውስጥም ሆኜ ሰምቻለሁ። እኔ የታሰርኩበት ቦታ የኤፒ ጋዜጠኛ የነበረው አሚር አማን እና የካሜራ ባለሞያው ቶማስ እንግዳ ይገኙ ነበር። እስካሁን በእስር ላይ ነው ያሉት። እንደሚታወቀው የጋዜጠኝነት ሥራ ብዙ ውጣ ውረድ ያለው እና ብዙ ሪስክ (አደጋ) ተወስዶ የሚሰራ ሥራ ነው። እነሱም ያንን የጋዜጠኝነት ሥራ ነው ሲሰሩ የቆዩት። ምን አልባት መንግሥት የማይወዳቸውን አካላት አናግረው ሊሆን ይችላል። ይህ ግን በጋዜጠኝነት ሥራ እንደ ወንጀል ይሚታይ ነው ብዬ አላስብም። ወንጀል ነው ከተባለም ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት ሊኖራቸው ይገባል። እኔ እስከምወጣ ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። ስለዚህ መንግሥት የቀሩትን ጋዜጠኞች በሙሉ መፍታት ይገባዋል። ለእኛ ደረሰው እድል ለእነሱም እንዲደርስ አደራ እላለሁ። ቢቢሲ፡ በእስር ላይ የነበሩ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ ዘመቻዎችን ስታስተባብር እንደነበር ይታወቃል። በታሰርክበት ወቅት ነው እነዚህ ሰዎች የተፈቱት። እንዴት ነበር ዜናውን የሰማኸው ምን ነበር ስሜቱ? እያስፔድ፡ እርግጥ ነው ላለፈው አንድ ዓመት በላይ ዘመቻዎችን እና እንቅስቃሴዎችን ስናደርግ ቆይተናል። መንግሥት በመጨረሻም ወደዚህ አቋም መምጣቱ በራሱ የሚያስደስት ነው። በተፈቱ በማግስቱ ነው ዜናውን የሰማነው። አብዛኛው ሰው ራሱ እንደተፈታ ነው የቆጠረው። እኔ ራሴ በጣም ደስተኛ ነበርኩ። ራሴ የተፈታሁ ያህል ነው ደስ ያለኝ። አንዳንዶቹ ከፖለቲካ አቋምም ባለፈ ወዳጆቼ ስለሆኑ ደስ ብሎኛል። በአጠቃላይ ግን ሁለት እንድምታዎችን ማንሳት አለብኝ። አንደኛው ለረጅም ጊዜ ስንለው እንደነበር እስረኞች ተፈተው ሁሉም ነገር ወደ ጠረጴዛ መምጣት አለበት የሚለውን፤ የፖለቲካ ልዩነቶች በሰላም በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈቱ የሚለው እኔ በግሌም በሚዲያችንም ስንለው ቆየነው ነው። መንግሥት ይህንን እርምጃ መውሰድ መጀመሩ የሚበረታታ ተግባር ነው። ነገር ግን አሁንም በርካታ እስረኞች ይቀራሉ። እኔ እንኳን ታስሬ በነበርኩበት ቦታ በርካታ ጋዜጠኞችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች አሉ። በተለያዩ እስር ቤት የተለያዩ የፓርቲ አመራሮች አሉ። እርምጃው የተቆራራጠ ባይሆን ጥሩ ነው። ያ ካልሆነ የተወሰነ የፖለቲካ ነጥብ ለማግኘት የሚደረግ እና ተመልሰን ወደነበርበት አዘቅት ውስጥ እንዳንገባ እላለሁ። ነገሩ ካፊያ ሳይሆን ለሁሉም መዝነብ አለበት። ከእስር ስወጣ በርካታ ነገር ተቀይሮ ነው የጠበቀኝ። አንዱ የአገራዊ ምክክር ጉዳይ ነው። ይህ መልካም ነገር ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ነገር ሞክረናል። ለመሞከር ያህል ብቻ የምናደርገውከሆነ ማግኘት ያለብንን ነገር እንዳናጣ እሰጋለሁ። ለምሳሌ ምርጫ ተደርጓል። ለማድረግ ያህል ማድረግ እና በትክክለኛ መንገድ ማድረግ ይለያያል። እድሉን እንዳናባክነው እፈራለሁ። ብሔራዊ መግባባበትን ለመፍጠር የሚደረግ ውይይት ገና ያልተሞከረ ነገር ነው። ከተሞከረ አይቀር በደንብ ተጠንቶ እና ታስቦበት ሁሉንም ወገን ያሳተፈ ካልሆነ የአገራችንን እድል እያስመለጥን ነው ብዬ አስባለሁ። ከመነሻው ጀምሮ የኮሚሽነሮችን ምርጫ፣ ተሳታፊ መምረጥ ብሎም መርሃ ግብሩን ማዘጋጀት ላይ የተለያዩ አመለካከቶችን ያሳተፈ መሆን አለበት። ሰርቶ እና ጨርሶ "ኑ እና እኔ ያቦካሁትን ጋግሩ" መሆን የለበትም። ቢቢሲ፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንደሚከታተል ሰው ጦርነቱን በተመለከተም ያሉ ለውጦችን ጨምሮ አሁን ያሉ የፖለቲካ እውነታዎች በአጠቃላይ በምኅዳሩ ላይ ምን ውጤት ይዘው የሚመጡ ይመስልሃል? እያስፔድ፡ በእስር ላይ ስለነበርኩ በጉዳዩ ላይ ያልበሰለ እና የማይመጥን ትንታኔ እንዳልሰጥ ስለምሰጋ አንድ ነገር ብቻ ልበል። ጦርነቱን በተመለከተ መስከረም አንድ ላይ ምን ሊመጣ ይችላል የሚሉ የቢሆን መላምቶችን አስቀምጠን ነበር። አንዱ ካስቀመጥናቸው ግምቶች ውስጥ በጦርነቱ ውስጥ በቆዩ ቁጥር በሁለቱም አካላት ዘንድ ዝለት ይመጣል ብለን ነበር። ጦርነት ኢኮኖሚንም ሆነ የሰው ህይወትን የሚበላ አድካሚ ነገር ነው ብለን ነበር። ሁለቱም ወገኖች አሁን ወደ ዝለት ሲመጡ ለድርድር ይቀመጣሉ የሚል ትንታኔ ሰጥተን ነበር። አሁን ወደዚያ ዝለት እየሄዱ ይመስለኛል። ሁለቱም አካላት ይህንን እድል እንደ ጊዜ መግዣ እና ትንፋሽ መሰብሰቢያ እንደማይወሰዱት፣ ብሎም ባግባቡ እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ። በመጣው ነገር ደስተኛ ያልሆኑ አካላት እንዳሉ ይሰማኛል። ከደረሰው ውድመት ብሎም ወደፊት ከሚደርሰው ውድመት ይልቅ አሁን የተወሰዱ እርምጃዎች ይሻላሉ ሊበረታቱም ይገባል ብዬ ነው የማስበው። በተጀመረው ቅድመ ውይይት ላይ ትኩረት ቢደረግ መልካም ይመሰለኛል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60082637
amh
politics
ባይደን እና ፑቲን የጄኔቫውን ንግግር ቢያወድሱም አለመግባባቱ እንደቀጠለ ነው
የአሜሪካ እና የሩሲያ ፕሬዚዳንቶች በጄኔቫ ያደረጉትን ውይይት ቢያደንቁም እአአ ከ 2018 ወዲህ በተደረገው የመጀመሪያ ስብሰባ ብዙም ተጨባጭ ውጤት አልተገኘበትም፡፡ አለመግባባቶች እንደተነሱ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ገልጸው ሩሲያም አዲስ ቀዝቃዛ ጦርነት እንደማትፈልግ ተናግረዋል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው ባይደን ልምድ ያካበቱ የሀገር መሪ እንደሆኑና ሁለቱም "ተመሳሳይ ቋንቋ" ስለመናገራቸው አስረድተዋል፡፡ ውይይቱ ከተያዘለት ጊዜ አጥሮ ለሦስት ሰዓታት ያህል የተካሄደ ነበር፡፡ ባይደን ለመነጋገር ብዙ ጊዜ ማሳለፍ እንደማያስፈልጋቸውና ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል አሁን እውነተኛ ተስፋ አለ ብለዋል፡፡ ባይደን ለሩስያው መሪ መነጽር ማበርከታቸው ታውቋል። ፑቲን በተመሳሳይ ለባይደን ስጦታ ስለመስጠታቸው አልታወቀም። የሩሲያው መሪ በ 2018 ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፊንላንድ ሄልሲንኪ ከተደረገ ውይይት በኋላ የእግር ኳስ ኳስ በስጦታ ሰጥተዋቸዋል። ሁለቱ ወገኖች በኒውክሊየር ቁጥጥር ዙሪያ ውይይት ለመጀመር ተስማምተዋል፡፡ አምባሳደሮችን ወደ ሁለቱም ሃገሮች መዲናዎች እንመልሳለን ብለዋል። አሜሪካ እአአ በ 2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሩሲያ ጣልቃ ገብታለች በሚል ከከሰሰች በኋላ መልዕክተኞቻቸው በመጋቢት ወር ምክክር እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ የሳይበር ደህንነት፣ ዩክሬን እና የሩሲያ ተቃዋሚ መሪው አሌክሲ ናቫልኒ ዕጣ ፈንታን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ስምምነት ስለመደረሱ ምልክት የለም። ናቫልኒ ሁለት ዓመት ተኩል ቅጣት ተላልፎበት በእስር ላይ ይገኛል። ባይደን ናቫልኒ በእስር ቤት ውስጥ ቢሞት ለሩስያ "አስከፊ መዘዞች" እንደሚኖሩት ተናግረዋል፡፡ መሪዎቹ ምን ተወያዩ? ከጉባኤው በፊት ሁለቱም ወገኖች ግንኙነታቸው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ፑቲቲን እስረኞችን መለዋወጥ በሚቻልበት ስምምነት ላይ እንደሚደረስ ፍንጭ ሰጥተው ነበር፡፡ ፑቲን በሳይበር ጥቃቶች ላይ ሩሲያን ነጻ በማድረግ በሃገራቸው የሚፈጸሙ አብዛኛዎቹ የሳይበር ጥቃቶች መነሻቸው ከአሜሪካ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባይደን እንደ ውሃ ወይም ኢነርጂ ያሉ ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ለጠለፋም ሆነ ለሌላ ጥቃት "የተከለከሉ" መሆን አለባቸው ብለው ለፑቲን መናገራቸውን አስታውቀዋል፡፡ "ተመለከትኩትና በነዳጅ ቱቦዎቻችሁ ላይ ላይ ጠለፋ ቢደረግ ምን ይሰማዎታል? አልኩኝ። ይህ ችግር አለው ብሎኛል" ሲሉ ባይደን ተናግረዋል። ሩሲያ እነዚህን "መሠረታዊ ደንቦች" ብትጥስ አሜሪካ እርምጃ እንደምትወስድ ገልጸዋል ፡፡ የተቃውሞ ሰልፍ የማድረግ መብትን ጨምሮ ሁለቱም ወገኖች በሰብዓዊ መብቶች ላይ ልዩነት ነበራቸው። ፑቲን በቅርቡ የ 24 ቀናት የረሃብ አድማ ስላደረገው ናቫልኒ አሜሪካ ያላትን ስጋት አጣጥለዋል፡፡ ናቫልኒ ህጉን ችላ በማለት ጀርመን ህክምና ካገኘ በኋላ ወደ ሩሲያ ሲመለስ እስራት እንደሚገጥመው ያውቅ ነበር ብለዋል፡፡ ናቫልኒ በፑቲን ትዕዛዝ ነርቭ በሚጎዳ ኬሚካል መመረዙን ቢገልጽም ፑቲን ክሱን አጣጥለዋል። ሩሲያ በግዛቷ ላይ ከካፒቶል አመፅ ወይም 'ከብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ሁከት አትፈቅድም ብለዋል፡፡ ፑቲን ስለ ስለ ብላክ ላይቭስ ማተር እንቅስቃሴ የሰጡትን አስተያየት ባይደን "አስቂኝ" ሲሉ አጣጥለው የሰብዓዊ መብቶች "ሁል ጊዜም ዋነኛ ጉዳይ ነው" ብለዋል፡፡ ሩሲያ ከአሜሪካ ጋር ለመተባበር ለምን እንደምትፈልግ የተጠየቁት ባይደን "[ሩሲያ] በአሁኑ ሰዓት በጣም አስቸጋሪ በሆነ ቦታ ላይ" መሆኗን ተናግረዋል፡፡ "በቻይና ግፊት እያደረባቸው ነው፡፡ ዋነኛ ኃያል ሃገር ሆነው ለመቀጠል በጣም ይፈልጋሉ" ብለዋል ጄኔቫን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት በጋዜጣዊ መግለጫቸው መሃል በፑቲን ይተማመኑ እንደሆነ ለጠየቃቸው ጋዜጠኛ ራሳቸውን ላይ ታች በመወዝወዝ ምላሽ የሰጡ መስለው ታይተዋል፡፡ በኋላ ግን ኋይት ሃውስ ባይደን "በጣም ግልጽ በሆነ መንገድ ለማንኛውም ጥያቄ ምላሽ የሰጡ ሳይሆን በአጠቃላይ ለመገናኛ ብዙሃን እውቅና ሰጥተዋል" ሲል በትዊተር መልዕክቱን አስታላልፏል። አንድ የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ፑቲን ባህሪያቸውን እንደሚለውጡ በምን እንደሚተማመኑ ባይደንን ሲጠይቅ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት "ያንን ካልተገነዘብክ በተሳሳተ ሥራ ውስጥ ነህ" በማለት በብስጭት መልሰዋል። በኋላም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-57508109
amh
politics
ጃዋር መሐመድ፡ እነ አቶ ጃዋር ወደ ግል ሆስፒታል ተወሰዱ
አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አደነ ወደ መረጡት የግል ሆስፒታል ዛሬ ረፋዱ ላይ ተወሰዱ። ከ30 ቀናት በላይ በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ የተነገራለቸው ተከሳሾች፤ የተወሰዱት ላንድማርክ ተብሎ ወደሚጠራው ሆስፒታል መሆኑን ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች እና የቤሰተብ አባላት መረዳት ችሏል። ተከሳሾቹ ታሰረው ይገኙበት ከነበረው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በአምቡላንስ ተጭነው በጸጥታ ኃይሎች ታጅበው ወደ ሆስፒታሉ ተወሰደዋል። የቤተሰብ አባላት እና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ እንደሚሉት፤ የተከሳሽ ቤተሰብ አባላት ወደ ሆስፒታሉ እንዳይገቡ መከልከላቸውን እና ተከሳሾቹ ስለሚገኙበት የጤና ሁኔታ ማወቅ እንዳልተቻለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ተከሳሾቹ ከግል ሃኪሞቻቸው ጋር እንደሚገኙ የቤተሰብ አባላቱ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በሆስፒታሉ ዙሪያም በርካታ የጸጥታ አካላት ተሰማርተው እንደሚገኙ ምንጮቹ ተናግረዋል። የተከሳሽ ጠበቆች እና የቤተሰብ አባላት እንደሚሉት ከሆነ፤ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ እና ሐምዛ አዳነ የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ ዛሬ 34ኛ ቀናቸው ላይ ይገኛሉ። ተከሳሾቹ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰው ወከባ ይቁም እንዲሁም የቤተሰብ አባላት ችሎት እና ማረሚያ ቤት ለጥየቃ ሲመጡ የሚደርስባቸው ወከባ ይቁም በማለት የረሃብ አድማውን እያደረጉ እንደሆነ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። በተከሳሽ ጠበቆች አቤቱታ የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሾች በመረጡት የጤና ተቋም እና ሆስፒታል ይታከሙ ሲል ፈቅዶ ነበር። ይሁን እንጂ ከአንድ ሳምንት በፊት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ይግባኝ ተከትሎ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የላንድማርክ ሆስፒታል ሃኪሞች በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝተው ለተከሳሾች ሕክምና እንዲሰጥ በይኖ ነበር። ጠበቆች በበኩላቸው የሆስፒታሉ ሠራተኞች በቃሊቲ ማረሚያ የህክምና አገልግሎት ይስጡ መባሉ አግባብ አይደለም በሚል ተከራክረው ነበር። ጠበቆች ደንበኞቻቸው የ24 የህክምና ክትትል አልያም የሕክምና ማሽን ድጋፍ ቢያስፈልጋቸው፤ አገልግሎቱን በማረሚያ ቤቱ ማግኘት አይችሉም በማለት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ ብለዋል። ሰበር ሰሚ ችሎቱም ትናንት በዋለው ችሎት ተከሳሾች በሆስፒታሉ ተገኝተው የሕክምና አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ በይኗል። ሰበር ሰሚ ችሎቱ ይህን ብይን ትናንት ከሰዓት የሰጠው፤ ትናንት ረፋድ ላይ ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የነበራቸው ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ከተሰጠበት በኋላ ነው። ትናንት ረፋድ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ የ24 ሰዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ቀጠሮ ይዞ ነበር። ከእነዚህ መካከል እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ሰዎች በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር። ይኹን እንጂ ጠበቆች ደንበኞቻቸው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ደጀኔ ጣፋ የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ለፍርድ ቤት ተናግረው፤ ደንበኞቻቸው አሁን ባሉበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠት አይችሉም በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ዐቃቤ ሕግም ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥ እንደማይቃወም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። በዚህም ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ችሎት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለመጋቢት 6/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በዚህ ችሎት ላይ የተገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር፤ ተከሳሾች አካላቸው ደክሞ እና ከስተው ተመልክቷል። አንዳንድ ተከሳሾች በሰዎች ድጋፍ ወደ ችሎቱ ሲገቡ እና የተከሳሽ ቤተሰብ አባላት መካከል አንዳንዶቹ በችሎት ውስጥ ሲያለቅሱ ሪፖርተራችን ተመልክቷል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ጋር በተያያዘ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። እነ አቶ ጃዋር ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ መወሰኑ ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56235748
amh
politics
ኦብነግ ከምርጫው ራሱን ያገለለው ለቦርዱ ያቀረበው አቤቱታው መፍትሄ ባለመግኘቱ እንደሆነ ገለጸ
በተራዘመውና መስከረም 20 ሊካሄድ በታቀደው የሶማሌ ክልል ምርጫ ላይ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) እንደማይሳተፍ አስታወቀ። ግንባሩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባና ሌሎች ችግሮችን በተመለከተ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ መፍትሄ ባለማግኘቱ እንደሆነ፣ የኦብነግ የአዲስ አበባ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ አብዱላሂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኦብነግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በክልሏ ዋና ከተማ ጅግጅግጋ ውስጥ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ነው ከምርጫው እራሱን ማግለሉ ያሳለፈበት ውሳኔ ላይ ደረሰው። ፓርቲው ከምርጫው ራሱን ለማግለል የወሰነበትን ሁኔታ አቶ አህመድ ሲያስረዱ "ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ ችግሮች እንዳሉና የምርጫ ካርድም የተሰራጨው ለሕዝቡ ሳይሆን ለገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ደጋፊዎች እንደሆነ እንዲሁም ገዥው ፓርቲ ለራሳቸው ወገኖች ሲያድሉ ነበር" ይላሉ። ይህንንም በተመለከተ ለምርጫ ቦርድ ከተለያዩ ማስረጃዎች ጋር በማያያዝ ማስገባታቸውን ገልጸዋል። በሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባን አስመልክቶ በምርጫ ቦርድ አጣሪ ቡድን ተሰማርቶ የነበረ ሲሆን በክልሉ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ብቻ ድጋሚ የመራጮች ምዝገባ እንዲካሄድ መወሰኑንና ምርጫ ቦርድም ይህንን ውሳኔ ማሳለፉን ያስረዳሉ። "በዚህም ምርጫ ቦርድ ለችግሩ መፍትሄ የሚሆን ውሳኔ አላስተላለፈም። ያቀረብናቸው በርካታ አቤቱታዎችና ማስረጃ በመራጮች ምዝገባ ላይ የነበሩ ችግሮች መፍትሄ ያገኛሉ ብለን ነበር። ነገር ግን መፍትሄ ይሆናል የምንለውን ነገር አላገኘንም" በማለት ተናግረዋል። ኦብነግ ውሳኔውን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ የመራጮች የምዝገባ ሂደት ማጭበርበር የተሞላበት እንደሆነ ጠቅሶ ማስረጃዎችን ማስገባቱንና አቤቱታዎችን በተደጋጋሚ ቢያስገባም አልተስተካከለም ብሏል። በሶማሌ ክልል ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ቀርተዋል ብሏል። "ምርጫውን ለሦስት ወራት በማራዘም የተፈጠረው የሕዝብ ተስፋ፣ ምርጫ ቦርድ የተበላሸውን አሰራር ባለማስቆሙ ሂደቱ ጠልሽቷል" በማለት መግለጫው አስፍሯል። ኦብነግ በዚህ ውሳኔ ማዘኑንና በቀላሉም እዚህ ላይ እንዳልደረሰ ገልጿል። ኦብነግ የትጥቅ ትግሉን ለማቆም ዋናው ምክንያት የሶማሌ ሕዝብ መብቶችን በሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማስከበር በመሆኑ ነው ቢልም ከምርጫው ተገዶ መውጣቱን ገልጿል። መግለጫው አክሎም በኦብነግ እና በሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የዕጩዎች ምዝገባን ማገድ፣ ዕጩዎችን እና አባላትን ማጥቃትና ማዋከብ እንዲሁም ትክክለኛ የመራጮች ምዝገባ በመደናቀፉ "ለእውነተኛ ፍትህ ምንም መንገድ ባለመኖሩ በመጨረሻ ኦብነግን ከምርጫው እንዲወጣ ተገዷል" በማለት አስፍሯል። አቶ አህመድ በበኩላቸው በአጠቃላይ የአገሪቱ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ በሶማሌ ክልል በበለጠ የፖለቲካ ምህዳሩ ጠባብ ነበር ይላሉ። ነገር ግን ከሰሞኑ ከምርጫው ጋር ተያይዞ ችግሮች መጉላታቸውን ያስረዳሉ። በክልሉ ዕጩዎች የሚታሰሩበትና እንዳይመዘገቡ የሚደረጉበት እንቅስቃሴዎች ነበሩ ይላሉ። ከዚህም ጋር ተያይዞ ኦብነግ ብቻ ሳይሆን ሶማሌ ክልል ላይ ሲወዳደሩ የነበሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ተናግረዋል። ምናልባት ውሳኔያቸውን አስቀልብሶ በምርጫ የሚሳተፉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችል ይሆን ወይ? ተብለው ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ አህመድ ሲመልሱ "ምርጫው አስር ቀን እንደመቅረቱ ይህ ሁኔታ የሚስተካከልበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም" ብለዋል። በሶማሌ ሕዝብ ላይ ሲደርስ የነበረውን ግፍና በደል ሰላማዊ በሆነ መንገድ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድርና መፍትሄም እንዲመጣ የሚገኝበትን ርብርብና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ በክልሉ በመንግሥትና ፓርቲ መካከል ልዩነት ባለመኖሩ በምርጫው ሂደት ላይ ችግሩን እንዳጎላው ይናገራሉ። ለአስርት ዓመታት በትጥቅ ትግል የቆየ ፓርቲ እንደ መሆኑ መጠን ከዚህ በኋላ ፓርቲው ምን አይነት አካሄድ ይኖረዋል ለሚለው ጥያቄም፤ የሶማሌን ሕዝብ መብት ለማስከበር በሰላማዊ መንገድ ትግሉን እንደሚቀጥልና በእውነተኛ ብሔራዊ ውይይትም ለመሳተፍ ፈቃደኛ ነው በማለት መግለጫው የወደፊቱን አቅጣጫ አስቀምጧል። በኢትዮጵያ መንግሥትና በኦብነግ መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ፓርቲው በርካታ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም ሰላማዊ በሆነ መንገድና በውይይት ለመቀጠል ቁርጠኝነት እንዳለው አስታውቋል። ሆኖም በሶማሌ ክልል ውስጥ አሁን ያለውን ሰላምና መረጋጋት ለማስቀጠል ሁሉም ወገኖች ሰላሙን ለማስጠበቅ ሊሰሩ ይገባል ብሏል። "በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች ጦርነት ባለበት ወቅት ሰላም በአንድ ግዛት ውስጥ ስለማይሰፍን፣ ኦብነግ አሁን ባለው አጥፊ ጦርነት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና በሚቀጥሉት ጊዜያት የሚጎዱትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ለማዳን" ጥሪ አቅርቧል። ጥቂት ስለ ኦብነግ ለበርካታ ዓመታት በምሥራቃዊው የአገሪቱ አካባቢ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ወደ አገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ለመሳተፍ መወሰኑ ይታወሳል። ኦብነግ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ትግል ያደርጉ ከነበሩ አማጺ ቡድኖች መካከል አንዱ ሲሆን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1984 ነበር የተመሰረተው። ቡድኑ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ተብለው ከተሰየሙ ቡድኖች ዝርዝር ውስጥ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ሦስት የፖለቲካ ቡድኖች ከሽብር ቡድን ዝርዝር ውስጥ በፓርላማው ውሳኔ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ በውጭ የሚገኙ የታጠቁ ተቃዋሚዎች ወደ አገር ቤት መመለሳቸው ይታወቃል። አብነግ የኦጋዴን ሕዝብ ብሎ የሚጠራውን በምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚገኘው የሶማሌ ሕዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለማስከበር በፖለቲካዊና ወታደራዊ መስኮች ትግል ሲያደርግ ቆይቷል። ኦብነግ ከምስረታው አስራ አራት ዓመታት በኋላ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ሊግ ጋር በመዋሃድ የሶማሊ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን መስርተው ነበር። መስከረም 20 ሶማሌ ክልልን ጨምሮ የሚካሄደው ምርጫ ስድስተኛው አጠቃላይ ብሔራዊ ምርጫ በዋናነት ሰኔ 14/2013 ዓ.ም የተካሄደ ቢሆንም በፀጥታ ችግር፣ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ በታዩ ግድፈቶች፣ በመራጮች ምዝገባ ላይ የቀረቡ አቤቱታዎችን ለማጣራት ጊዜ በማስፈለጉ የድምፅ መስጫው ቀን በአንዳንድ ክልልሎችና የምርጫ ክልሎች እንዲራዘም መወሰኑ ይታወቃል። ምርጫ የተራዘመባቸው ሶማሌ፣ ሐረሪ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መስከረም 20 ምርጫ እንዲካሄድ ተወስኗል። ምርጫ ያልተደረገበት የሶማሌ ክልልንም በተመለከተ የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ በነበረበት ወቅት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ለቦርዱ አቤቱታ ቀርቦ ነበር። ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱ መጣራት እንደሚገባው አምኖ የመራጮች ምዝገባ እንዲቆም በመወሰን 10 የምርጫ ክልሎች ላይ ምርመራ ተደርጓል። ከተለያዩ ሲቪል ማኅበራት የተውጣጣ አጣሪ ቡድን በመላክ ምዝገባ ሂደቱ ላይ የቀረቡትን አቤቱታዎች አጣርቷል። የቡድኑንም ግኝት መሰረት በማድረግ ጅጅጋ 1፣ በጅጅጋ 2 የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ በድጋሚ እንዲከናወን ተወስኗል። ከዚህም በተጨማሪ በቀብሪደሃር ከተማ፣ በቀብሪደሃር ወረዳ፣ በመኢሶ፣ በአፍደም የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች እንዲሁም የመራጮች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ በድጋሚ የሚካሄድባቸው ስፍራዎች ናቸው ተብሏል። በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ እንዲደገምባቸው የተላለፈባቸው ደግሞ በዋርዴር ምርጫ ክልል ውስጥ በ2 ምርጫ ጣቢያዎች፤ በፊቅ ምርጫ ክልል በ1 ምርጫ ጣቢያ፣ በገላዴን ምርጫ ክልል በ1 ምርጫ ጣቢያ፣ በጎዴ ከተማ ምርጫ ክልል በ4 ምርጫ ጣቢያዎች ፣ በምሥራቅ ኢሜ ምርጫ ክልል በ3 ምርጫ ጣቢያዎችና በቤራኖ ምርጫ ክልል በ3 ምርጫ ጣቢያዎች እንደሆነም ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58582805
amh
politics
ሰሜን ኮሪያ ወጣቶች የደቡብ ኮሪያን መደበኛ ያልሆነ ቋንቋ እንዳይጠቀሙ አስጠነቀቀች
የሰሜን ኮሪያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ወጣቶች የደቡብ ኮሪያ መደበኛ ያልሆነ ቋንቋ እንዳይጠቀሙና የሰሜን ኮሪያን መደበኛ ቋንቋ እንዲገለገሉ አሳሰቡ። ወጣቶች ከደቡብ ኮሪያ የተቀዱ የፋሽን፣ የፀጉር ስታይል እንዳይጠቀሙ እና ሙዚቃ እንዳያዳምጡ የሰሜን ኮሪያ ይፋዊ ጋዜጦችም አዲስ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር። ይህ የውጭ ጫናን ለማስቆም ያለመና ከባድ ቅጣት የሚያስከትለው አዲስ ሕግ አካል ነው። ሕጉን ጥሰው የተገኙም ከእስራት እስከ ሞት ድረስ ሊቀጡ ይችላሉ። ሮዶንግ ሲንመን ጋዜጣ ወጣቶች የደቡብ ኮሪያን የፖፕ ባህል መከተላቸው የሚያደርስባቸውን ተፅዕኖ አስጠንቅቋል። "በተዋበና በቀለም ባሸበረቀ ስክሪን ሰርስረው የሚገቡ ርዕዮተ ዓለሞችና እና ባህሎች የጦር መሣሪያ ከያዙ ጠላቶች ይበልጥ አደገኛ ናቸው" ብሏል ጋዜጣው። ጋዜጣው አክሎም ወጣቶች ኮሪያ ላይ የተመሠረተ የፕዮንግያንግ ቋንቋን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስቧል። የውጭ ተፅዕኖው ኪም የሚመሩት የሰሜን ኮሪያ ኮሚዩኒስት ሥርዓት ስጋት ተደርጎ ይታያል። የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን 'ኬ ፖፕ' [ደቡብ ኮሪያ መሰረቱ የሆነ የሙዚቃ ስልት] የሰሜን ኮሪያ ወጣቶችን አዕምሮ ጨምድዶ የያዘ 'የማይለቅ ካንሰር' ሲሉ መጥራታቸውን ኒዮርክ ታይምስ ዘግቧል። ከደቡብ ኮሪያ፣ ከአሜሪካ ወይም ጃፓን ከፍተኛ መጠን ያለው ሙዚቃ ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው የሞት ቅጣት ይጠብቀዋል። ይህንን ሲመለከት የተያዘ ሰውም የ15 ዓመታት እስር ይተላለፍበታል። ቅጣቱ ከባድ ቢሆንም ወደ ሰሜን ኮሪያ የሚገባው የውጭ ጫና ግን አሁንም አልቆመም። ጉዳዩም እጅግ ውስብስብ ሲሆን በዚህ ሳቢያ የታገዱ ሚዲያዎችም በሕገ ወጥ መንገድ መስራታቸውን ቀጥለዋል። አንዳንድ ሰሜን ኮሪያውያን ተገንጣዮች የደቡብ ኮሪያ ድራማ ማየታቸው አገራቸውን ጥለው ለመውጣታቸው አንዱ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። በሰሜን ኮሪያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ያንግ ሞ ጂን በስዊትዘርላንድ የተማሩት ኪም ጆንግ ኡን "ኬ ፖፕ ወይም የምዕራባውያን ባህል በቀላሉ ወደ ወጣቶች ሊገባ እንደሚችልና በሶሻሊስት ሥርዓት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ያውቃሉ" ሲሉ ለኮሪያ ሄራልድ ተናግረዋል። "መሪው ይህ ባህልም ለሥርዓቱ ጫና እንደሚሆን ያውቃሉ። ስለዚህም ነው ይህንን ማስቆም የፈለጉት። ኪም ወደፊት የሚመጡ ችግሮችን ለመከላከል እየሞከሩ ነው" ብለዋል ፕሮፌሰሩ።
https://www.bbc.com/amharic/news-57872237
amh
politics
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተሾሙ
ከእስር የተፈቱት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተሾሙ። የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ በዛሬው ዕለት ባወጣው መረጃ የክልሉ ርዕሰ መስታድር አገኘሁ ተሻገር ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ አድርገው መሾማቸውን ነው። ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግሥትና ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ ጋር ተያይዞ አንደኛው ተጠርጣሪ ነበሩ። ከሰኔ 15 ክስተት በፊት የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩ ሲሆን የነ ዶክተር አምባቸውና ሌሎች ባለስልጣናት ግድያ ጋር ተያይዞም ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱ ይታወሳል። ብርጋዴር ጄኔራሉ ከተጠረጠሩበት ክስም ነጻ ሆነው ከወራት እስር በኋላ ተፈትተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪም ለሌሎች ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖችም ልዩ ልዩ የፀጥታ ተቋማትን እንዲመሩ መመደባቸውም ተጠቁሟል። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በተጨማሪ ጄኔራል አዳምነህ መንግሥቴ የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ልዩ ረዳት ሆነው መሾማቸውን ዘግቧል። ጄኔራል አዳምነህ የትግራይ ጦርነት እስከተከሰተበት ወቅት የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ነበሩ። ርዕሰ መስተዳደሩ የክልሉን ጸጥታ መዋቅር ለማጠናከር ከብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ እና ከጄነራል አዳምነህ መንግሥቴ በተጨማሪ ሌሎች ሰባት ሰዎችን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ መሾማቸው ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57922563
amh
politics
ባይደን በፑቲን ላይ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ሩሲያ አምባሳደሯን ጠራች
ሩሲያ ዋሽንግተን የሚገኙ አምባሳደሯን ለውይይት በሚል ከሰሞኑ ጠርታለች። ከአሜሪካ ጋር ያለው የሻከረ ግንኙነት የማይቀለበስ ደረጃ ላይ እንዳይደርስም ለመምከር ነው ተብሏል። የሩሲያ መንግሥት እንዳሳወቀው አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭ ወደ ሞስኮ የተጠሩበት ምክንያት አገሪቷ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት መጥፎ ሁኔታ ላይ በመድረሱ ያንን አቅጣጫ ለማስያዝ ነው ብሏል። ይህንን ውሳኔ ሩሲያ ያሳወቀችው ፕሬዚዳንት ባይደን በአሜሪካ ምርጫ ላይ ጣልቃ ገብተዋል የሚባሉትን ቭላድሚር ፑቲንን "ዋጋ ይከፍላሉ" ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ከቅርብ ወራት በፊት የአሜሪካ መንበረ ስልጣንን የተቆጣጠሩት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከኤቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ፕሬዚዳንት ፑቲን "ነፍሰ ገዳይ ናቸው" ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል። በጥቅምት ወር መጨረሻ በተደረገው የአሜሪካ ምርጫ ላይ ጣልቃ የመግባት ዘመቻን ፕሬዚዳንት ፑቲን መፍቀዳቸውን አንድ የአሜሪካ ደህንነት ሪፖርት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው ባይደን ይህንን የተናገሩት። ሪፖርቱ ሩሲያ ተሰናባቹን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሸናፊ እንዲሆኑ ጣልቃ በመግባት አስተዋፅኦ አድርጋለች በማለት ወንጅሏታል። ሩሲያ ጣልቃ በመግባቷ ምን አይነት ውጤቶች ሊኖሩ ይችላሉ ተብለው የተጠየቁት ፕሬዚዳንት ባይደን"በቅርቡ ታዩታላችሁ" ብለዋል። የፕሬዚዳንት ፑቲን ቃለ አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በበኩላቸው ውንጀላው በመረጃ ያልታገዘና የሁለትዮሽ ግንኙነቱንም በቀጣዩ የሚጎዳ ነው ብለውታል። የሪፖርቱ ማጠቃለያን ተከትሎ አሜሪካ በሚቀጥለው ሳምንት በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ትጥላለች ተብሎ ይጠበቃል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ምን አለ? "በአሜሪካ የሚገኙት የሩሲያ አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭ ወደ ሞስኮ የተጠሩት ለምክክር ነው። የሁለቱን አገራት ግንኙነት በተመለከተ አውዱ ምን ሊሆን ይገባል የሚለው ላይ ትንታኔም ይሰጣል" በማለት መግለጫው አትቷል። ሩሲያ አክላም በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት መሻከር የማይቀለበስ ደረጃ ከመድረሱ በፊትም መካላከል እንደምትፈልግ አስታውቃለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-56440705
amh
politics
በናይጄሪያ ከ1800 በላይ ታራሚዎች ከእስር ቤት ማምለጣቸው ተሰማ
በናይጄሪያ የሚገኝ እስር ቤት በታጣቂዎች ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ከ1 ሺህ 800 በላይ ታራሚዎች ማምለጣቸው ተገልጿል። ክስተቱ ያጋጠመው በደቡብ ምስራቅ በምትገኘው ኦውሪ ግዛት ሲሆን ታጣቂዎች የእስር ቤቱን ሰብረው በመግባቱ የህንፃውን የተወሰነ ክፍልም በቦንብ አፈንድተውታል ተብሏል። ኦውሪ ማረሚያ ማዕከል ተብሎ በሚታወቀው እስር ቤት ታጣቂዎቹ በጭነት መኪናና በአውቶብስ ተጭነው የመጡት በትናንትናው እለት ነው። ፖሊስ ጥቃቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ታጣቂዎች ተወንጫፊ ሮኬቶችን ጨምሮ፣ ከባድ መሳሪያዎችና ቦንቦችን ይዘው ነበር ብሏል። በዚህም አጋጣሚ በርካታ ታራሚዎች ማምለጥ እንደቻሉም ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። ለዚህ የእስር ቤት ጥቃት አድራሹ የቢያፍራ ቀደምት ህዝቦችን በመወከል የሚታገለውና በናይጄሪያ የታገደው ተገንጣዩ ቡድን ነው ሲል ፖሊስ አስታውቋል። የናይጄሪያ ማረሚያዎች ማዕከል እንዳስታወቀው እስካሁን ድረስ ያመለጡ የታራሚዎች ቁጥር 1 ሺህ 844 መሆኑን ነው። የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ጥቃቱን "በስርዓት አልበኞች የተፈፀመ የሽብር ጥቃት" ሲሉ አውግዘውታል። ከዚህም በተጨማሪ የፀጥታው ሁኔታ እንዲጠናከር የተጨማሪ ሃይል አስፈላጊነትን አፅንኦት በመስጠት ከመናገር በተጨማሪ፤ ጥቃቱን ያደረሱት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንዲሁም ያመለጡት ታራሚዎችም በአስቸኳይ እንዲያዙ ብለዋል። ኢንዲጂኒየስ ፒፕል ኦፍ ባያፍራ ተብሎ የሚታወቀው የተገንጣዩ ቡድን እንቅስቃሴ ቃለ አቀባይ በበኩላቸው የሰኞውን ጥቃት አድርሰዋል መባላቸው "ሃሰት" እንደሆነ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። በማዕከላዊው መንግሥትና በአካባቢው በሚኖሩ ኢግቦ ህዝቦች መካከል ያለው ግንኙነት የባላንጣ መሆኑን ተከትሎ ግዛቲቷ የተገንጣዮች ቡድን መፈልፈያ ሆናለች። ከጥር ወር ጀምሮ በርካታ የፖሊስ ጣቢያዎች ጥቃትን ያስተናገዱ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ የፖሊስ መኪኖች ተቃጥለዋል እንዲሁም ቦምቦችና ተቀጣጣይ ፈንጆች ተዘርፈዋል። ለዚህኛው ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-56645972
amh
politics
በጀርመን በተካሄደው ምርጫ የአንጌላ ሜርክል ፓርቲ ተሸነፈ
የጀርመኑ ሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ የመራሄተ መንግሥቷ አጌላ ሜርክልን ፓርቲ በጠባብ ውጤት ማሸነፉን ቀዳሚ የምርጫ ውጤቶች አመላከቱ። ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ 25.7 በመቶውን ድምጽ ሲያገኝ ገዢው ወግ አጥባቂው ፓርቲ ደግሞ 24.1 በመቶ ድምጽ አግኝቷል። የግሪን ፓርቲ በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን 14̇ በመቶ ድምጽ ማግኘቱም አነጋጋሪ ሆኗል። በቀጣይም መንግሥት ለመመስረት የሚያስፈልገውን አብላጫ ድምጽ አንድ ፓርቲ ባለማግኘቱ ፓርቲዎቹ ጥምር መንግሥት መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። ምርጫው ከጅማሮው ውጤቱን ለመገመት የሚያስቸግር መሆኑን በርካቶች ሲናገሩ ነበር። ጥምር መንግሥት በቀላሉ መመስረት የሚቻል እንዳልሆነም ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ። ጥምር መንግሥት እስከሚመሰረት ድረስ ተሰናባቿ መራሄተ መንግሥት ሜርክል በሥልጣናቸው ላይ መቀጠላቸው አይቀሬ ነው። ይህም እስከ መጪው ጥር ወር ድረስ ሊቆይ ይችላል። አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት በአውሮፓ የጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችውን ጀርመን ለቀጣይ አራት ዓመታት በተለይም የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳን በዋናነት በመያዝ ይመራል። ከፍተኛውን ድምጽ ያገኘው የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ መሪ ኦላፍ ሾልትስ በቴሌቪዢን በተላለፈ ንግግራቸው መራጮች "ለጀርመን መልካም ብሎም ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ መንግሥት" የመመስረት ሥራ ሰጥተውኛል ሲሉ ተደምጠዋል። የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪው በበኩላቸው ጥምር መንግሥትን የመመስረት እንዲሁም ያሸነፈው ሁሉንም ጠቅልሎ የማይወስድበት ሂደት ነው ሲሉ ሾልትስን የሚቃረን ንግግር አድርገዋል። የሊበራል እና የግሪን ፓርቲዎች ከ30 ዓመት በታች ባሉ ወጣቶች ዘንድ ዝነኛ ናቸው። ጥምር መንግሥት ሊመሰረት የሚችለውም በእነዚህ ሁለት ፓርቲዎች አማካኝነት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ። ውጤቱን ተከትሎም አራት የተለያዩ የጥምር መንግሥት አማራጮች የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያው አማራጭ "የትራፊክ መብራት" ቀለሞችን የያዘ ነው። የሶሻል ዴሞክራቶችን ቀይ ቀለም፣ የኤፍዲፒን ቢጫ እንዲሁም የግሪን ፓርቲ አረንጓዴ የያዘ የጥምረት አማራጭ ነው። ሁተኛው "ጃማይካ" የተሰኘው አማራጭ ሲሆን ይህም የጃማይካን ባንዲራ ቀለሞች ያያዙትን ሦስቱን ፓርቲዎች የያዘ ጥምረት ነው። ሾሳል ዴሞክራቶችን፣ ኤፍዲፒን እንዲሁም ግሪን ፓርቲን። ይህ በጀርመን ታሪክ ሦስት አማራጮችን የቀረቡበት የጥምር መንግሥት የመመስረት ሂደት መሆኑ ተነግሯል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58704015
amh
politics
የሕንድ የዘር ግንድ ያላቸው ሪሺ ሱናክ ቀጣዩ የዩኬ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን ፉክክሩን እየመሩ ነው
ተሰናባቹን የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት እየተደረገ ያለውን ትንቅንቅ የሕንድ የዘር ግንድ ያላቸው ሪሺ ሱናክ እየመሩ ይገኛሉ። ሱናክ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ለመሆን እስካሁን የተካሄዱ ሁለት ተከታታይ ምርጫዎችን አሸንፈዋል። ከሕንዳውያን ወላጆች የተወለዱት ሪሽ ሱናክ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ 88 ድምጽ ያገኙ ሲሆን የንግድ ሚንስትሯ ፔኒ ሞርደንት 67 ድምጽ በማግኘት ሁለተኛ ሆነው ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ሊዝ ትረስ ደግሞ በ50 ድምጽ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ነበር በመጀመሪያው ዙር ምርጫ። በሁለተኛው ምርጫ ሱናክ 101 ድምጽ ሲሰበስቡ ሞርደንት 83፤ ትረስ ደግሞ 64 ድምጽ አግኝንተዋል። እስካሁን በተካሄደው ምርጫ ቻንስለር ናዲም ዛሃዊ እና የቀድሞው የጤና ሚንስትር ጀረሚ ሃንት ከውድድሩ ተሰናብተዋል። አሁን ውድድሩ ላይ ያሉት ዕጩዎች ሌላ ፉክክር ይጠብቃቸዋል። በተጨማሪም ዛሬ አርብ ሐምሌ 15/2014 ዓ.ም. አምስት እጩዎች በቀጥታ የቴሌቪዥን መስኮት ክርክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ውድድሩ በዚህ መልኩ ከቀጠለ በኋላ በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ሁለት ተወዳዳሪዎች ብቻ እንዲቀሩ ይደረጋል። ሁለቱን ተወዳዳሪዎች ደግሞ 160 ሺህ አካባቢ የቶሪ አባላት ድምጽ ሰጥተውባቸው አሸናፊው የፓርቲ መሪ እና ጠቅላይ ሚንስትር ይሆናል። ውጤቱ በአውሮፓውያኑ መስከረም አምስት ይፋ ይደረጋል። አሁን ውድድሩ ላይ የቀሩት ተፎካካሪዎች ቀጣዩን ዙር ለማሸነፍ ከሁለቱ ተሰናባች መራጮች [ጀረሚ ሃንት እና ዛሃዊ] ተጨማሪ ድምጽ ለመቀራመት ይፎካከራሉ። ተሰናባቹ ጀረሚ ሃነት ሱናክን እንደሚደግፉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት የቦሪስ ጆንሰንን አመራር በመቃወም ከቻንስለርነታቸው የለቀቁት ሱናክ በውጤቱ ደስተኛ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የትረስ ቃል አቀባይ “አሁን ወዳጆች ተሰባስበው ታክስ የሚቀንስ፣ እውነተኛ የምጣኔ ሃብት ለውጥ የሚያመጣ እና ዩክሬን ውስጥ የፑቲንን ሽንፈት የሚያፋጥን መሪ ያስፈልገናል” ብለዋል። “ሊዝ የብሬግዚትን ጉዳይ በማፋጠን እና የምጣኔ ሃብት እድገት በማምጣት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል” ብለዋል። ለረጅም ጊዜ የፓርላማ አባል የሆኑት ቱጌንዳት በትዊተር ገጻቸው “በጣም ደስ የሚል ውጤት ነው። አገራችንን ወደተሻለ ደረጃ ለመለወጥ በሚቀጥለው የምርጫ ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ። አገራችን ግልጽ የሆነ አጀማመር ሊኖራት ይገባል” ብለዋል። በአውሮፓውያኑ 2019 በነበረው ውድድር ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ጀረሚ ሃንት ወግ አጥባቂ ፓርቲ በቀጣይ “አስደናቂ ዘመን” ይኖረዋል ብለዋል። ለተወዳዳሪዎቹም ምክር ለግሰዋል። “መሞካሸት እና መዘላለፍ ለአጭር ጊዜ እምርታ ሊያመጣ ይችላል፤ በረጅም ጊዜ ሂደት ግን አደጋ አለው” ብለዋል።  ሌላኛው የውድድሩ ተሰናባች ዛሃዊ ደግሞ “አሁን ጣልቃ መግባት ባልፈልግም ለሁሉም ተወዳዳሪዎች መልካም ዕድል እመኛለሁ” ብለዋል። ይህ ውድድር እየተካሄደ ያለው ባለፈው ሳምንት ቦሪስ ጀንሰን ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ካሳወቁ በኋላ ነው። ቦሪስ ጆንሰን በኮሮናቫይረስ እገዳ ወቅት መመሪያ በመጣስ ጎዳና ዘግተው ድግስ አዘጋጅተዋል በሚል እና በሌሎች ክሶች ሲወቅሱ ሰነባብተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c3ge94zjr29o
amh
politics
የሱዳን ጦር የተባበሩት መንግሥታትን ድጋፍ ጠየቀ
የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የተባበሩት መንግሥታት የሽግግር መንግሥቱን እንዲደግፍ ጥሪ አቀረቡ። ጀነራል አል-ቡርሃን ይህን ጥያቄ ያቀረቡት የተመድ የሱዳን ተወካይ የሆኑትን ቮልከር ፔርዝስ አግኝተው ባነጋገሩበት ወቅት ነው። የተመድ ተወካዮ ከአል-ቡርሃን ጋር መገናኘታቸውን በትዊተር ገጻቸው የገለጹ ሲሆን፤ ምንም አንኳ ሱዳን ሕገ መንግሥታዊው ሥርዓት እንዲመለስ ብትስማም፤ ሌሎች ቁልፍ የሆኑ ጉዳዮች መከናወን አለባቸው ብለዋል። ጀነራል አል-ቡርሃን ወደ ሥልጣናቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት የሲቪል መንግሥት መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር አብሮ ለመሥራት እና ምርጫ እስኪከናወን ድረስ አብደላ ሐምዶክ ለሚመሰርቱት የሽግግር መንግሥት ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። ከጥቂት ወራት በፊት የሱዳን ጦር በጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክ የሚመራውን የቪሲል መንግሥት ገልብጦ ሥልጣን ተቆጣጥሮ እንደነበረ ይታወሳል። በቁም እስር ላይ የቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ከቀናት በፊት ከሱዳን ጦር ጋር ከስምምነት ደርሰው ወደ ሥልጣናቸው ተመልሰዋል። ከሁለት ዓመት በፊት አብደላ ሐምዶክን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የሾመው የሲቪል ፖለቲከኞች ስብስብ ግን ከወታደሮች ጋር የሚደረግን ማንኛውንም አይነት አዲስ ስምምነት አልቀበልም ሲል ነበር። ይሁን እንጂ በሱዳን የመንግሥት ግልበጣ ማግስት የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ድምጻቸውን በአደባባይ ለማሰማት የሚወጡ ሰዎች በሱዳን ጦር መሪዎች ላይ ያላቸው ተቃውሞ እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ያላቸውን ድጋፍ ሲገልጹ ቆይተዋል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሩን አመራሮች ከበተነና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃውመው አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ የአገሪቱ ዜጎች ሱዳን ወደ ሰላማዊ የዲሞክራሲ ሽግግር እንድትመለስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። የሱዳን የሽግግር ምክር ቤት በ18 ወራት ውስጥ ምርጫ እንዲያካሂድ ጫና እየተደረገበት ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-59515622
amh
politics
ከጀርመኑ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጀርባ ያለው ግለሰብ እና ቡድን ማነው?
ቱሪንጋ የሚባለው የምሥራቅ ጀርመን ቀጠና ውስጥ ነው የሚኖሩት። እስከ ዛሬ እምብዛም ያልተወራለት ቡድን ነው። ባለፈው ሳምንት በጀርመን ከተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ጋር ተያይዞ ግን ስማቸው ይነሳ ጀምሯል። የጀርመንን ምክር ቤት ተቆጣጥረው የዘመናዊ ጀርመን ሥርዓተ መንግሥትን በንጉሣውያን አስተዳደር ለመቀየር ነበር የወጠኑት። የውጥኑ መሪ ቤተሰቦች አካባቢውን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በፊት መርተዋል። መሪው አሁን ዘብጥያ ወርዷል። ሆኖም ግን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው የጀርመን ፖሊሶችን አስደንብሯል። ከጀርመን አልፈው በኦስትሪያ እና በጣልያን ጭምር ፍተሻ እያደረጉ ይገኛሉ። ለፍተሻው 3 ሺህ ፖሊሶች ናቸው የተሰማሩት። 150 ቦታዎችን አስሰው እስካሁን 25 ሰዎችን አስረዋል። ምርመራው ስለሚቀጥል ተጨማሪ ሰዎች እንደሚታሰሩም የደኅንነት ባለሥልጣናት ተናግረዋል። የጀርመን የፌደራል እና የክልል ምክር ቤቶች ጥበቃ ተጠናክሯል። ቢቢሲ በቱሪንጋ የጎበኘው ሹሎስ ዋልድማንሺል የተባለ መዝናኛ ነው። መዝናኛውን የሚያዘወትሩ ሰዎች ከሕዝብ ዕይታ የራቁ እንደሆኑ የቱሪንጋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ሊመሠርቱ ላሰቡት አዲስ የጀርመን መንግሥት፣ ሚኒስትሮች እስከ መሾም እና ወታደራዊ ክንፍ እስከማዋቀር ደርሰዋል። ቡድኑን የሚመራው ልዑል ቤተሰቦች የሚኖሩት ኦስትሪያ ነው። “በሰማነው ነገር ደንግጠናል። ሐሳቡ የተጠነሰሰው ከዓመታት በፊት ነው። ፀረ ሴማዊ አካሄድ ያለው የሴራ ትንታኔ ገፍቶት ነው ይህን የፈጸመው። የእኛን ቤተሰብ አይወክልም” ሲል ቤተሰቡ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል። ልዑሉ ሄንሪሽ 13ኛ ይባላል። ሬሲንግ ሄንሪሽ በሚል ቅጽል ስም ይጠራል። ሄንሪሽ በተባለው የቤተሰብ ስም የሚጠሩ 30 ሰዎች በሕይወት አሉ። ‘ሬሲንግ’ የሚለው ስም ለሄንሪሽ የተሰጠው ለፈጣን መኪኖች ባለው ፍቅር እንደሆነ ቤተሰቦቹ ይናገራሉ። ቢቢሲ የጎበኘው መዝናኛ ለ100 ዓመታት የቤተሰቡ ንብረት ሆኖ ቆይቷል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ግን በምሥራቅ ጀርመን ኮምኒስት መንግሥት ተወርሷል። ሄንሪሽ በዓመታት ውስጥ ቁጡ ሰው እየሆነ መምጣቱን ቤተሰቦቹ ይናገራሉ። ልጁ በጠና ታማለች። የሪል ስቴት ንግዱም ስኬታማ አልሆነም። የቀድሞ ንብረቶችን ከጀርመን መንግሥት ለማስመለስ ያደረገው ጥረት በፍርድ ቤት አወንታዊ ብይን አልተሰጠውም። በሕይወቱ ለደረሱበት ምስቅልቅሎች የጀርመን መንግሥትን ተጠያቂ ያደርጋል። ፉርስት የተባለው ቤተሰቡ ለቢቢሲ እንደገለጸው፣ በምሥራቅ ጀርመን የሚገኘውን መዝናኛ መልሶ ከገዛ በኋላ “ከአልባሌ ሰዎች ጋር መዋል አብዝቷል።” ልዑሉ 71 ዓመቱ ነው። ወጣት ሩሲያዊት ሴት ጓደኛ አለችው። ሴት ጓደኛው ለመፈንቅለ መንግሥቱ ከክሬምሊን ድጋፍ ለማግኘት ሞክራ ነበር። ስብስቡ ውስጥ የቀድሞ የጀርመን ልዩ ኃይል አባል፣ የቀድሞ የፖሊስ አመራር፣ የቀድሞ ዳኛ እና በቀኝ ዘመም ፓርቲ የቀድሞ የምክር ቤት አባል አሉበት። ብሪጅት ማልሳክ-ዊንክማን የፍትሕ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብሎ ነበር። የመፈንቅለ መንግሥቱ ቀን የተቆረጠው ሥነ ፈለክን ተከትሎ እንደሆነ የፖሊስ ምርመራ አጋልጧል። ከገና በዓል በፊት በተወጠነው መፈንቅለ መንግሥት “ሊሞቱ የሚችሉ ሰዎች” እንዳሉ ቡድኑ መምከሩም ታውቋል። ለጀርመን ደኅንነት አስደናቂ የሆነው ይህ ቡድን ያዋቀረው ወታደራዊ ክንፍ ነው። ሩጀር ቮን ፒ በተባለ ግለሰብ ነው የሚመራው። ቡድኑ የአገሪቱን ምክር ቤቱን ጥሶ እንዲገባና ፖሊሶችን እንዲከላከል ኃላፊነት ተሰጥቶታል። የቀድሞ ሉተነንት ኮሎኔሉ ሩጀር በሥራ ላይ ሳለ መሣሪያ ያከማች እንደነበር ፖሊሶች ያምናሉ። አንድሬስ ኤም የተባለ የልዩ ኃይል አመራር እና ማክሲሚላን ኤደር የተባለ ኮሎኔል በሥሩ ይገኛሉ። በሴራ ትንታኔ የሚታወቀው ማይክል ኤፍ እና አፍቃሪ-ናዚው ፒተር ደብሊውም አሉበት። ፖሊስ ከፈተሻቸው ቤቶች በ50ው መሣሪያ አግኝቷል። የቀኝ ዘመም ዘረኝነት ላይ ጥናት የሠሩት ኒኮላስ ፖተር ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ የዚህ ቡድን ጽንፈኛ ሐሳብ ምን ያህል ደጋፊዎች እንዳሉት በትክክል አለመታወቁ አስጊ ነው። በጀርመን ልዩ ኃይል ውስጥ የሚገኝ ኬኤስኬ የተባለ ክፍል ቀኝ ዘመም አስተሳሰብ በማንጸባረቁ እንዲበተን መደረጉን ጠቅሰው “መሣሪያ እየተመዘበረ በቀኝ ዘመሞች እጅ ሲገባ እናያለን። ይህ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ትንሹ ስጋታችን ነው። ችግሩ ከዚህም እንደሚብስ እጠረጥራለሁ። በጣም አስጊ ነው” ይላሉ። በመፈንቅለ መንግሥቱ ከተሳተፉ መካከል ሪችስቡርገር የተባለ ቡድን አባላት ይገኙበታል። እነዚህ ወደ 21 ሺህ ገደማ የሚሆኑት የቡድኑ አባላት ለጀርመን ፌደራል መንግሥት ዕውቅና አይሰጡም። ግብር አይከፍሉም። በጀርመን ዳኞች የተላለፈ ውሳኔን አይቀበሉም። የጀርመን የተሽከርካሪ የሰሌዳ ቁጥርም አይጠቀሙም። ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በኋላ ትክክለኛው የጀርመን አስተዳደር እንደፈረሰ ነው የሚያምኑት። እአአ በ2016 ከዚህ ቡድን አባላት የአንዱ ቤት ሲፈተሽ የቤቱ ባለቤት ፖሊሶች ላይ ተኩሶ አንድ ፖሊስ ገድሏል። ይህ ጽንፈኛ ቡድን አስጊነቱ እየጨመረ እንደመጣ የሚገልጸው የጀርመን ፖሊስ፣ ከመካከላቸው ወደ ነውጥ ሊገቡ የሚችሉ ግን በቁጥር ውስን እንደሆኑ ያስረዳል። ልዑል ሄንሪሽ ከዚህ ቀደም በበተነው በራሪ ወረቀት የጀርመን ፌደራል መንግሥት መታወቂያ ያላቸው ሰዎች ‘ትክክለኛ ጀርመናዊ’ እንዳልሆኑ ተናግሮ ነበር። በራሪ ወረቀቱን በበተነበት አካባቢ የሚኖሩ አዛውንት “ጤነኛ አይመስለኝም። በራሪ ወረቀቱ ላይ በቀድሞው የጀርመን አርማ ቀይ፣ ጥቁርና ነጭ የተሠራ መታወቂያ የምናገኝበት ድረ ገጽ ተጽፏል። አነስተኛ ግዛት ለመፍጠር ድምጽ እንድንሰጥም ይጠይቃል። በራሪ ወረቀቱን ቀዳድጄ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ከተትኩት” ብለዋል። ልዑሉን የሚነቅፉት ሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎች አይደሉም። ሐሳቡን የሚደግፉም አሉ። “ጀርመን አሁን ባለችበት ሁኔታ ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች ይደግፉታል። ያሳዝናል። ሌላ ዓይነት ጀርመን ማየት ነው የሚፈልጉት” ሲሉ አንድ ነዋሪ ተናግረዋል። በአገሪቱ ሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ላይ ጥናት የሚሠራው ጆሴፍ ሆልንበርገር እንደሚለው፣ 20 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ለሴራ ትንታኔ ተጋላጭ ናቸው። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፣ ከምጣኔ ሀብት መሽመድመድ እና ከኃይል አቅርቦት መቆራረጥ ጋር በተያያዘ መንግሥታቸውን ይወቅሳሉ። የደኅንነት ኃላፊው ስቴፈን ክሬመር “አክራሪዎች እንደ ኮሮናቫይረስ ባለ ወረርሽ ወቅት ይበረታታሉ። ከወረርሽኙ ጋር የተያያዙ የተቃውሞ ሰልፎች መበራከታቸው ቀኝ አክራሪዎችን አደፋፍሯል” ይላሉ። እነዚህ ቡድኖች የጀርመን ፌደራል መንግሥት የመጣል ዒላማ አስተሳስሯቸዋል። ከመካከላቸው የፌደራል መንግሥቱን ዕውቅና የማይሰጡና፣ ዕውቅና ቢሰጡም ነቅለው መጣል የሚፈልጉ እንዳሉ የደኅንነት ኃላፊው ያስረዳሉ። ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የተጣሉ ክልከላዎችን በመቃወም ከተካሄዱ ሰልፎች በአንዱ 40 ሺህ ሰዎች የተሳተፉበት የበርሊን ተቃውሞ ይጠቀሳል። በወቅቱም ምክር ቤቱን ጥሰው ለመግባት ውስን እንቅስቃሴም አድርገው ነበር። እነዚህ ግለሰቦች የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አድናቂ ናቸው። ሁለቱም መሪዎችም ‘ወግ አጥባቂና ክርስቲያናዊ’ አስተዳደር ተምሳሌት አድርገው ነው የሚመለከቷቸው። ‘ኪውአኖን’ የተባለው የሴራ ትንታኔ ቡድን መነሻውን ያደረገው አሜሪካ ሲሆን፣ ለትራምፕ ጽኑ ፍቅር አለው። ከእንግሊዝኛ ተናጋሪ አገራት ውጭ ኪውአኖን ከፍተኛ ድጋፍ ያለው በጀርመን ነው። ክትባት የሚያጣጥሉ፣ አፍቃሪ-ናዚ ተከታዮች አሉት። የጀርመን አስተዳደር ባለበት እንዲቀጥል የሚፈልጉ አመራሮች የግድያ ዛቻ ሲደርስባቸው እንደሚስተዋል ቢቢሲ ተረድቷል። የቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች ተንታኙ ኒኮላስ ፖተር እና የፀረ ፋሺዝም አቀንቃኟ ማርቲና ሬነር በተደጋጋሚ ዛቻ ከሚሰነዘርባቸው መካከል ይጠቀሳሉ። ቡድኑ ግድያን ጨምሮ አካላዊ ጥቃቶችም ያደርሳል። እንደ ማንኛውም ሰው ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ስለሚሳተፉ ቀኝ አክራሪዎችን በቀላሉ የደኅንነት አባላት መለየት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ። ቀኝ አክራሪዎች የሚፈጽሟቸው ጥቃቶች ‘የተናጠል’ እርምጃ እንደሆኑ እንደሚነገር የሚገልጸው ተንታኙ ኒኮላስ ፖተር፣ ስጋቱ ሥር እየሰደደ እንደመጣና የጀርመን አንዱ ገጽታ እንደሆነ እንዲታወቅ ያሳስባል። የደኅንነት ኃላፊው ስቴፈን ክራመር “እጅግ የከፋ ነገር ይመጣል ብዬ ብሰጋም በጎ ነገር ይመጣል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ” ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c72qdge04zno
amh
politics
የፊደል ካስትሮ ወንድም ራውል ካስትሮ ከኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ መሪነት ለቀቁ
የፊደል ካስተሮ ወንድም ራውል ካስትሮ ከኩባ ብቸና ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበርነት ለቀቁ። ራውል ካስትሮ ከደሴቲቱ አገር ኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ መሪነታቸው መነሳታቸውን ሲገልጹ ቤተሰቦቻቸው ለስድስት አስርት ዓመታት የቆየበትን የሥልጣን ጊዜ አጠናቋል። የ89 ዓመቱ ካስትሮ አመራሩን "በጋለ ስሜት እና በፀረ-ኢምፔሪያሊዝም መንፈስ ለተሞላ" የወጣቱ ትውልድ እንደሚያስተላልፉ ለፓርቲው ጉባኤ ተናግረዋል። ተተኪያቸውም ለአራት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ መገባደጃ ላይ ይመረጣል። እርምጃው በ1959 አብዮት የጀመረው የእርሳቸው እና የወንድማቸው ፊደል ካስትሮ የመሪነት ዘመን ማብቂያ ይሆናል። ካስትሮ አርብ ዕለት በሃቫና ለተገኙ የፓርቲው ልዑካን "እኔ በአገሬ ሰዎች ጥንካሬ እና አርአያነት ባለው ተፈጥሮ እና ግንዛቤ በጣም አምናለሁ" ብለዋል። ካስትሮ ተተኪያቸውን ባያሳውቁም የፓርቲው አመራር እአአ በ2018 የደሴቲቱን ፕሬዝዳንትነት ለተረከቡት ሚጉኤል ዲያዝ-ካኔል ኃላፊነቱን ይተላለፋል የሚል ሰፊ እምነት አለ። የዘመን ፍጻሜ የእርሳቸው ከኃላፊነት መነሳት ከስድስት አስርት ዓመታት በኋላ፤ ኩባ ለመጀመሪያ ጊዜ የካስትሮ ቤተሰብ አባል የፖለቲካ መሪዋ አይሆንም ማለት ነው። ራውል እአአ በ2011 ታላቅ ወንድማቸው ፊደልን በመተካት የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ሆነው አገልግለዋል። ፊደል ካስትሮ እአአ በ1959 የኩባን መንግሥት ከሥልጣን ያወረደውን የኮሚኒስት አብዮት የመሩ ሲሆን ራውል ደግሞ ከአዛዦቻቸው አንዱ ሆነው አገልግለዋል። ፊደል ካስትሮ በ2006 እስከታመሙበት ጊዜ ድረስ የአገሪቱ መሪ ነበሩ። ይሁን እንጂ በ2008 ፕሬዝዳንትነቱን ለወንድማቸው አስረክበዋል። ከዚያም እአአ በ2016 ፊደል ካስትሮ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኩባ በራውል ስር ራውል ካስትሮ እንደ መሪ የኮሚኒስትን የአንድ ፓርቲ የሥልጣን ጉዞ እንዲቀጥል አደረጉ። በ2014 ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋር የተደረገውን ታሪካዊ ውይይትን ጨምሮ ከ 2014 እስከ 2016 መካከል ከአሜሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነቶች መሻሻልን በበላይነት መርተዋል። ማዕቀቡን ባጠናከረው በዶናልድ ትራምፕ ዘመን ግን ውጥረቱ ተባብሷል። የዋይት ሐውስ በኩባ ፖሊሲ ላይ የሚደረግ ለውጥ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አለመሆኑን ቢጠቅስም፤ የወቅቱ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተወሰኑትን የትራምፕ ማዕቀቦችን ለማቃለል ቃል ገብተዋል። አርብ ዕለት በተካሄደው ኮንግረስ ላይ ራውል ካስትሮ አገራቸው ከአሜሪካ ጋር "መከባበር ያለበት ውይይት ለማዳበር ፈቃደኛ መሆኗን" ገልፀው፤ ነገር ግን "የውጭ ፖሊሲዋን እና ሀሳቧን በተመለከተ ለውጥ ማድረግን" እንደማትቀበል ተናግረዋል። ቀጥሎ ምን ይሆናል? በኩባ አስተዳደር ፓርቲ አመራር ላይ የተደረገው ለውጥ ደሴቲቱ በአስርተ ዓመታት ውስጥ እጅግ አስከፊ የሆነውን የኢኮኖሚ ቀውስ ለመቋቋም በምትሠራበት ወቅት ነው። በትራምፕ አስተዳደር የተላለፈው ማዕቀብ፣ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ኢኮኖሚው ባለፈው ዓመት በ11 በመቶ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል። በጥር 1 የተጀመረው እና ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የገንዘብ ማሻሻያ ኢኮኖሚውን እና የመንግሥት ኩባንያዎችን ውጤታማ ለማድረግ ጥረት ቢያደርግም የኩባ ዜጎችን በጀት ጎድቷል። ብዙዎችም በአገሪቱ የበለጠ ኢኮኖሚያዊ ነፃነት እንዲኖር ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሌላው ተግዳሮት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን የዜጎችን የርዕዮተ ዓለም አንድነትና ድጋፋቸውን ጠብቆ ማስቀጠል ነው። በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ በማሰማት እና በቀጥታ ሥርጭት ታዳሚዎችን በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ። የአመራር ለውጥ ቢኖርም በፖሊሲ አቅጣጫው ላይ ለውጥ ያመጣል ብለው የሚጠብቁት ጥቂቶች ናቸው። የ2019ቱ አዲስ ሕገ-መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ የመንግሥት የበላይነት እና "ሶሻሊዝም" የማይቀለበስ መሆኑን አረጋግጧል። የ60 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዲያዝ-ካኔል አርብ ዕለት ባሰፈሩት የትዊተር ጽሑፍ ጉባኤውን "ጠንካራ ሐሳቦች፣ የታሪክ እውቅና እና የወደፊቱ የሚወያዩበት ይሆናል" ብለዋል። ቀጣይነት እንደሚኖርም አክለው ገልጸዋል። ራውል ካስትሮ በጉባኤው "መደበኛ አብዮታዊ ታጋይ" ተብለው ጡረታ እንደሚወጡ ተናግረዋል። "እናም በሕይወት እስካለሁ ድረስ የአባት አገርን፣ አብዮቱን እና ሶሻሊዝምን ለመከላከል በሚነሳው ችግር ውስጥ ለመግባት አገሬን አዘጋጃለሁ" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56737752
amh
politics
የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ ይጠበቃሉ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት ለአራት ቀናት ወደ አዲስ አበባ፣ ካርቱም እና ሪያድ በመጓዝ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገለጸ። ባለሥልጣናቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና በአምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ምትክ በቅርቡ የተሾሙት አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ናቸው። ከሰኞ ጥር 09 እስከ ጥር 12/2014 ዓ.ም በሚደረገው በዚህ የዲፕሎማቶቹ ጉዞ በኢትዮጵያና በሱዳን ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። ባለሥልጣናቱ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ ፕሬዝዳንት ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ሰኞ ጥር 02/2014 ዓ.ም ያደረጉት "ገንቢ የስልክ ውይይት ተከታይ ጉዳዮችን" ያነሳሉ ብሏል። በዚህም ዲፕሎማቶቹ የአየር ጥቃቶች እና ሌሎች ግጭቶች እንዲቆሙ፣ በድርድር ላይ የተመሰረተ ተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻችና ለሁሉ አቀፍ ብሔራዊ ውይይት የሚያስፈልጉ ነገሮች እንዲመቻቹ በአሁኑ ወቅት የተከፈተውን የሰላም ዕድል እንዲጠቀሙበት የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትን ያበረታታሉ ተብሏል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣኗ ሞሊ ፊ እና ልዩ መልዕክተኛው ሳተርፊልድ ወደ አዲስ አበባ ከመሄዳቸው በፊት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሪያድና ወደ ጎረቤት ሱዳን እንደሚያመሩ ተገልጿል። በዚህም ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በቀውስ ውስጥ ለምትገኘው ሱዳን በሲቪሎች የሚመራ ዴሞክራሲያዊ ሽግግርን በተመለከተ በተባበሩት መንግሥታት አማካይነት በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ። ከሳዑዲ በማስከተልም ሁለቱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ኃላፊዎች ወደ ሱዳን ካርቱም በማቅናት ከዴሞክራሲ ደጋፊ አክቲቪስቶች፣ ከሴቶችና ከወጣቶች ቡድኖች፣ ከሲቪል ማኅበራት፣ ከጦር ኃይሉ መሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ይወያያሉ ተብሏል። ከዚያ በማስከተል የመጨረሻ የጉዟቸው መዳረሻ የምትሆነው አዲስ አበባ ስትሆን፣ እዚያም ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ወይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለቱ መሪዎች በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ጦርነትና በአገሪቱ ስላሉ ፖለቲካዊ ጉዳዮች መወያየታቸውን የወጡ መግለጫዎች አመልክተዋል። ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀስ ተከትሎ አሜሪካ በያዘችው አቋምና በወሰደቻቸው እርምጃዎች ምክንያት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የነበረው መልካም ግንኙነት ሻክሮ ቆይቷል። የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ጨምሮ በጦርነቱ ተሳታፊዎች ላይ ከጣለው የቪዛ እገዳ እንዲሁም ከሁለት ሳምንት በፊት ተግባራዊ የሆነው ኢትዮጵያ ከቀረጥና ከታሪፍ ነጻ ምርቶችን ወደ አሜሪካ ታስገባበት የነበረው የአጎዋ ተጠቃሚነት የእገዳ እርምጃ ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ መንግሥትም አሜሪካ ለአማጺያኑ የሚያደላ መግለጫና እርምጃ እየወሰደች ነው በማለት አሜሪካን በወገንተኝነት ሲከስ ቆይቷል። ባለፈው ሳምንት ተሰናባቹ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን አዲስ አበባ ደርሰው ከተመለሱ በኋላ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በስልክ መነጋገራቸው የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማሻሻል ጅማሬ ሊሆን እንደሚችል በስፋት ተነግሯል። አሜሪካ ጦርነቱ በድርድር መቋጫ እንዲያገኝ ልዩ መልዕክተኛ በመሰየም ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነት ስታደርግ ብትቆይም እስካሁን ውጤት ሳይገኝ ቆይቷል። ከሰኞ ጀምሮ ወደ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ የሚያቀኑት ሁለቱ የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ሙያ ያዳበሩ ዲፕሎማቶች መሆናቸው ይነገራል። ሜሪ ካትሪን ሞሊ ፊ ሜሪ አሁን ያሉበትን የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊነት የተረከቡት ባለፈው መስከረም ወር ሲሆን ከዚያ በፊት ለሦስት ዓመታት ያህል በደቡብ ሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ውስጥም በከፍተኛ ኃላፊነት አገልግለዋል። አዲሱ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መዕክተኛ ሆነው የተሾሙት ዴቪድ ሳተርፊልድ ደግሞ በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን በመካከለኛው ምሥራቅ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ለአራት አስርት ዓመታት የዘለቀ ልምድ እንዳካበቱ ይነገርላቸዋል። አምባሳደር ሳተርፊልድ በቱርክ፣ በሶሪያ፣ በቱኒዚያ፣ በሳዑዲ አረቢያ እና ሊባኖስ ውስጥ አገራቸውን ወክለው በዲፕሎማትነት ሰርተዋል። አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በዶናልድ ትራምፕ የሥልጣን ዘመን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ማይክ ፖምፔዮ ከፍተኛ አማካሪ ነበሩ።
https://www.bbc.com/amharic/news-59988906
amh
politics
ታሊባን በርካታ ግዛቶችን መቆጣጠሩን ተከትሎ የሰዓት እላፊ ታወጀ
የታሊባን ታጣቂዎች በርካታ ግዛቶችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የአፍጋኒስታን መንግሥት የሰዓት እላፊ አውጇል። የአፍጋኒስታን መንግሥት ይህንን የሰዓት እላፊ ያወጀውም የታሊባን ታጣቂዎች ሌሎች ከተሞችን ከመውረር ለማስቆም ነው ብሏል። ከመዲናዋ ካቡልና ሌሎች ሁለት ግዛቶች ውጭ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ሌሊት 10 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ አይችልም። በባለፉት ሁለት ወራት በታሊባንና በአፍጋኒስታን የመንግሥት ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያው ተባብሷል። በቅርብ ሳምንት ዓለም አቀፍ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል። ታሊባን ከአገሪቱ ግዛቶች ውስጥ እስከ ግማሽ ያህሉን እንደተቆጣጠረ ይገመታል። በተለይም የአሜሪካ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የድንበር መሸጋገሪያዎችንና በርካታ ገጠራማ ቦታዎችን መቆጣጠራቸው ተገልጿል። ከ 20 ዓመታት ገደማ በፊት በአሜሪካ ወረራ ከስልጣን ተገፍተው የወጡት ታሊባን እንዲሁ የአቅርቦት መንገዶችን ለመቁረጥ በመፈለግ ቁልፍ ጎዳናዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል ተብሏል። የታሊባን ተዋጊዎች ወደ በርካታ ቁልፍ ከተሞች የሚሄዱ መንገዶችን ቢዘጉም እስካሁን ዋና ዋና ከተሞችን መቆጣጠር አልቻሉም። ካቡል ፣ ፓንጅሺር እና ናንጋርሃር ነፃ መሆናቸውን በመግለፅ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ "አመፅን ለመግታት እና የታሊባንን እንቅስቃሴ ለመገደብ በ 31 ግዛቶች የሰዓት እላፊ አዋጅ ተጥሏል" ብለዋል። ታሊባን ወደፊት እየገሰገሰ ባለበት በዚህ ሳምንት በካንዳሃር ከተማ ዳርቻ ላይ ከባድ ወጊያዎች ተካሂደዋል። በምላሹ የአሜሪካ መንግሥት ታሊባን በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ላይ በያዝነው ሳምንት ሃሙስ የአየር ጥቃት መፈፀሙን አስታውቋል። ነገር ግን አሜሪካ በአፍጋኒስታን ውስጥ ታደርገው የነበረው ዘመቻ ይፋዊ በሆነ ሁኔታ በአውሮፓውያኑ ነሐሴ መጨረሻ የሚጠናቀቅ ቢሆንም በመጪዎቹ ወራቶች ምን ሊከሰት ይችላል በሚለው ሁኔታ ላይ ስጋቶች አሉ ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57960082
amh
politics
ማክሮን “የአዕምሮ ጤና ምርመራ” ያስፈልጋቸዋል ሲሉ የቱርኩ ኤርዶጋን ተናገሩ
የቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኤማኑኤል ማክሮን “የአዕምሮ ጤና ምርመራ” ያስፈልጋቸዋል ማለታቸውን ተከትሎ ፈረንሳይ የቱርክ አምባሳደሯን ጠራች። ኤርዶጋን የፈረንሳዩን ፕሬዝደንት የአዕምሮ ጤና ምርመራ ያስፈልጋቸዋል ያሉት ፕሬዝደንት ማክሮን ጽንፈኛ እስላማዊነትን ለመዋጋት ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው። ፈረንሳያዊው መምህር አወዛጋቢውን የነብዩ መሐመድን የካርቱን ምስሎች ክፍል ውስጥ ማሳየቱን ተከትሎ አንገቱ ተቀልቶ መገደሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ማክሮን በጉዳዩ ላይ ጠንከር ያለ አቋም እየንጸባረቁ ይገኛሉ። የፈረንሳይ መንግሥት የአንድን ማህበረሰብ ወይም እምነት ተከታዮችን ስሜት ለመጠበቅ ሲባል የሰዎች የመናገር መብት ሊገደብ አይደባም የሚል ጠንካራ አቋም ይዟል። ፈረንሳይ የሰዎች የመናገር መብትን መገደብ የፈረንሳይን አንድነት ጥያቄ ውስጥ ይጥላል የሚል አቋም አላት። ማክሮን ይህን የፈረንሳይ እሴትን ለመጠበቅ ዘመቻ ላይ ናቸው። የቱርኩ ፕሬዝደንት በዚህ ላይ አስተያየታቸውን ሲሰጡ፤ “ማክሮን የሚባለው ግለሰብ ከእስልምና እና ሙስሊም ጋር ያለው ችግር ምንድነው?” ሲሉ ጠይቀዋል። “ማክሮን የአዕምሮ ጤና ሕክምና ያስፈልገዋል” ሲሉም ጨምረዋል። የቱርኩ ፕሬዝደንት ይህን ማለታቸውን ተከትሎ በቱርክ የፈረንሳይ አምባሳደር ለምክክር ወደ ፓሪስ መጠራታቸውን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል አንድ የፈረንሳይ ከፍተኛ ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። አምባሰደሩ ከማክሮን ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ ተብሏል። እኚህ የፈረንሳይ ከፍተኛ ባለስልጣን “የፕሬዝደንት ኤርዶጋን አስተያየት ተቀባይነት የለውም” ስለማለታቸው ኤኤፍፒ ጨምሮ ዘግቧል። ይህ የኤርዶጋን አስተያየት በፈረንሳይ እና ቱርክ መካከል ያሉ ልዩነቶች እየሰፉ ስለመምጣታቸው አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል። ሁለቱም የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል አገራት ይሁኑ እንጂ የማይሰማሙባቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። በሊቢያ እና ሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ሁለቱ አገራት በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው ይገኛሉ። በአርሜኒያ እና አዘርባጃን ግጭት ውስጥም የሁለቱ አገራት ፍላጎት የተለያየ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-54681088
amh
politics
ሩሲያ ዩክሬንን 'መውረር ጀምራለች' ያሉት ባይደን ሞስኮ ላይ ማዕቀብ ጣሉ
አሜሪካ ሩሲያ ላይ የተለያዩ ማዕቀቦችን ጣለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያ ዩክሬንን 'መውረር ጀምራለች' ካሉ በኋላ አስተዳደራቸው በሞስኮ ላይ ጠንካራ መዕቀብ መጣሉን ያስታወቁት። "ሩሲያን ከምዕራቡ ዓለም አገራት የፋይናንስ ፈሰስ እንቆርጣታለን" ብለዋል። ውሳኔው ላይ የደረሱት ሩሲያ ወታደሮቿን ወደ ሁለት የዩክሬን ክልሎች ከላከች በኋላ ነው። ሁለቱ ክልሎች በአማጽያን የተያዙ ሲሆኑ፤ ሩሲያ ከሰሞኑ ራሳቸውን የቻሉ ግዛቶች ናቸው ስትል እውቅና ሰጥታለች። ሁለቱ በአማጽያን የተያዙ ክልሎችን ሩሲያ ነጻ ብላ ማወጇን ዩክሬን በጥብቅ ተቃውማለች። በተመሳሳይ በርካታ ምዕራባውያን አገራት በፑቲን እርጅማ ተበሳጭተዋል። ሩሲያ ወደ ሁለቱ ክልሎች የገባችው ወረራውን ለማስፋፋት እንደሆነ ምዕራባውያኑ ሰግተዋል። ዶንቴስክ እና ሉሀንስክ ወደተባሉት ክልሎች ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወታደሮቻቸውን የላኩት "ሰላም ለማስከበር ነው" ብለዋል። ከሳተላይት የተገኘ ምስል እንደሚያሳየው ባለፉት 24 ሰዓታት አዳዲስ ወታደሮች እና መሣሪያዎች ወደ ምዕራብ ሩሲያ ተጠግተዋል። በዩክሬን ጎረቤት ቤላሩስ ውስጥ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎችም ታይተዋል። በጉዳዩ ላይ ሩሲያ አስተያየት አልሰጠችም። "ሩሲያ ከዩክሬን ግዙፍ ክፍል ልትወስድ እንደሆነ አስታውቃለች" ሲሉ ባይደን ተናግረዋል። የጣሉት ማዕቀብ የሩሲያን የውጭ ብድር የሚገታ ሲሆን፣ ሩሲያ ከምዕራባውያን የፋይናንስ ተቋማት መበደር አትችልም ማለት ነው። ባይደን የሩሲያ አመራሮችም "ሊቀጡ ይገባል" ብለው ማዕቀብ ጥለውባቸዋል። በዩክሬን በአማጽያን የተያዙት ሁለት ክልሎች ውስጥ አሜሪካውያን እንዳይነግዱ ውሳኔ ተላልፏል። 17ቱ የአውሮፓ ኅብረት አገራት የሩሲያ ምክር ቤት አባላት ላይ ማዕቀብ ለመጣል ተስማምተዋል። ይህም ሁለቱ የዩክሬን ክልሎችን ነጻ ግዛት ብለው ውሳኔ ያሳለፉ አመራሮችን ይጨምራል። የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እንዳሉት በአምስት ባንኮች የሩሲያውያን ሀብታሞች ተቀማጭ ገንዘብ ታግዷል። በተጨማሪም ዩኬ የጉዞ እገዳ ጥላለች። ጀርመን ከሩሲያ ወደ አውሮፓ ነዳጅ የሚያስተላልፈውን ግዙፍ ትቦ ሥራ አቋርጣለች። አሜሪካ ጦሯን በሩሲያ አቅራቢያ ወደሚገኙት የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) አባል አገራት ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ እን ሊቱኒያ እያስጣጋች ነው። ጣልያንም ተዋጊ ጀቶችና ሄሊኮፕተሮችን ጨምሮ በፖላንድ ጦር እያሰፈረች ትገኛል። የሩሲያ እና ዩክሬንን ፍጥጫ ለማርገብ የተሞከሩ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ፍሬ አላፈሩም። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዲፕሎማሲን ፊት የነሳችው ሩሲያ አቋሟን ከለወጠች አሜሪካ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ናት ብለዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር አገራቸው ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደሚያቋርጡ ተናግረዋል። ዩክሬን አሁንም ዴፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንደምትሻ ቢናገሩም ለጥንቃቄ ሲሉ ወታደሮችን ወደ ሥልጠና ጠርተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60489368
amh
politics
ዴሞክራቶች የትራምፕ ደጋፊ የሆኑትን ሴት ከኮንግረስ ለመፈንገል እያሴሩ ነው
በአሜሪካ ፖለቲካ ቁንጮ ከሆኑት ሁለት ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዴሞክራቶች፤ የትራምፕ ደጋፊ የሆኑትን ሕግ አውጭ ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ እየጣሩ ነው። የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት ወግ አጥባቂዋ ፖለቲከኛ በማሕበራዊ ድር አምባ ገፆቿ ላይ በጻፉት ጉዳይ ነው ከኃላፊነቷ ትነሳ እየተባለ ያለው። ማርጆሪ ታይለር ግሪን የተባሉት ሪፐብሊካን በሴራ ትንተና ያምናሉ። የመስከረም 9/11 የሽብር ጥቃት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነው ብለው ከሚያምኑ አሜሪካዊያን መካከልም አንዷ ናቸው። ጆርጂያ ግዛት ወኪል የሆኑት የኮንግረስ አባል ባለፈው ወር አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ለመክሰስ ደፋ ቀና ሲሉ ነበር። ማርጆሪ ግሪን ባሳለፍነው ሰኞ በትዊተር ገጻቸው ላይ "ዴሞክራቶች ከተወከልኩበት ኮሚቴ ካባረሩኝ ቃል እገባላችኋለሁ እኛ በ2022 [በቀጣዩ የምክር ቤት ምርጫ] አብላጫ ድምፅ ስናገኝ አፀፋውን እጥፍ ድርብ አድርገን እንመልሳለን" ሲሉ ጽፈው ነበር። "አብላጫ ድምፅ ማግኘታችን የማይቀር ነው፤ እሱን እንዳትሳሳቱ" ሲሉም ዝተዋል። ባለፈው ኅዳር ወደ አሜሪካ ኮንግረስ የሚያስገባትን ድምፅ ያገኘችው ማርጆሪ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የትምህርትና ሰው ኃይል እንዲሁም የበጀት ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል። የኮሚቴው አባል እንዲሆኑ የመረጧቸው በምክር ቤቱ የሪፐብሊካኖች መሪ የሆኑት ኬቪን ማካርቲ ናቸው። ዴሞክራቶቹ ለምን ሊያስወግዷቸው ፈለጉ? ዴሞክራቶች የትራምፕ ደጋፊ የሆኑት ግለሰብ ከዚህ በፊት የፈፀሟቸው ድርጊቶች የኮሚቴ አባል እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው አይደለም ሲሉ ይከራከራሉ። በተለይ ደግሞ ከትምህርት ኮሚቴው እንዲፈነገሉ ነው ፍላጎታቸው። ሴትዬዋን ከኮሚቴው የመፈንገል ሂደቱን እየመሩ ያሉት ዴሞክራቷ ዴቢ ሹልትዝ "ሪፐብሊካኖች እሷን መተካት ካልቻሉ እኛ እንተካላቸዋለን" ሲሉ ተደምጠዋል። ትላንት [ሰኞ] በምክር ቤቱ አብላጫ ድምፅ ያላቸው ዴሞክራቶች መሪ የሆኑት ስቴኒ ሆዬር ለሪብሊካኖች መሪ 'ግለሰቧን ያውርዱልን' የሚል ጥሪ አቅርበዋል። ማርጆሪ ከኮሚቴዎቹ በ72 ሰዓታት ውስጥ ካልወረዱ ግን ዴሞክራቶች ይህንን ጉዳይ በራሳቸው እንደሚወጡ ዝተዋል። ዴሞክራቶች ግለሰቧ ከኮሚቴዎቹ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው ከኮንግረሱ እንዲባረሩ ይፈልፈጋሉ። ከወግ አጥባቂነታቸው አልፈው አክራሪ ሆነዋል ብለው የሚያምኑ ሪፐብሊካኖችም ጭምር ማርጆሪ ከኮንግረስ እንዲባረሩ ጥሪ እያቀረቡ ነው። በሴኔቱ አናሳ ድምፅ ያላቸው ሪብሊካኖች መሪ የሆኑት ሚች ማኮኔል ሴትዬዋ የምታምንባቸውን የሴራ ትንተናዎች 'ለሪብሊካን ፓርቲ ካንሰር ናቸው' ሲሉ ወርፈዋል። በፈረንጆቹ 2019 በኮንግረሱ የአዮዋ ግዛት ተወካይ የሆኑት ሰው በአንድ ቃለ መጠይቅ ወቅት የነጭ የበላይነትን አጣጥለው አስተያየት በመስጠታቸው ከሁለት ኮሚቴዎች መወገዳቸው አይዘነጋም። ነገር ግን ሪፐብሊካኖች አሁንም በፖርቲ አጋራቸው ላይ ይህን ዓይነት እርምጃ ይወስዳሉ ወይ የሚለው እርግጥ አይደለም። አንድ የኮንግረስ አባልን ከኮንግረሱ ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ሁለት ሶስተኛ ድምፅ ያሻል። በአሜሪካ ታሪክ ከኮንግረስ አባልነታቸው የተወገዱ ሰዎች ቁጥር አምስት ብቻ ነው። ማርጆሪ የኮንግረስ አባል ሆነው አነጋጋሪ አስተያየት የሰጡ የመጀመሪያዋ ሴት አይደሉም። በ2019 የሚኒሶታዋ ኢልሃን ኦማር ፀረ-አይሁድ ናቸው ተብለው በተፈረጁ አስተያየታቸው ምክንያት ብዙ ትችት ደርሶባቸው ነበር። በወቅቱ ኢልሃን ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው ነበር። የትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊዋ ማርጆሪ ግሪን ግን በተደጋጋሚ አነጋጋሪ አስተያየት ከመስጠት ባለፈው በይፋ የሴራ ትንተና አማኝ መሆናቸው ነው ለየት የሚያደርጋቸው። ማርጆሪ፤ በ2016 የአሜሪካ ምርጫ የትራምፕ ተፎካካሪ የሆኑት ሂላሪ ክሊንተን ሕፅናትን ይገርዛሉ ብለው ያምናሉ። አልፎም በፈረንጆቹ 2001 የደረሰው የ9/11 አደጋ የአሜሪካ መንግሥት ሴራ ነው ብለው ነው የሚያምኑት። ይህም አልበቃ ብሏቸው ካሊፎርኒያ ውስጥ የተከሰተው የሰደድ እሳት ሆን ተብሎ ከሕዋ ላይ በተለቀቀ ጨረር የተነሳ ነው ይላሉ። በአንድ ወቅት 'ጥቁሮች የዴሞክራቲክ ፓርቲ ባሪያዎች ናቸው'፤ ነጭ ወንዶች ደግሞ አሜሪካ ውስጥ በጣም በደል የሚደርስባቸው ናቸው ሲሉ አስተያየት ሰጥተው ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-55899058
amh
politics
ጆን ማጉፉሊ፡ ኮሮናቫይረስን ከአገር አባረዋለሁ ያሉት መሪ
የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የኮሮረናቫይረስን በተመለከተ በሚሰጧቸው አስተያየቶችና በሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች የዓለምን ትኩረት መሳብ የቻሉ መሪ ናቸው። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዚዳንት ሆነው ለመመረጥ እየሰሩ ነው። ኮቪድ-19 ታንዛኒያ ሲደርስ ፕሬዚዳንቱ ሰዎች በቤታቸው መቆየት የለባቸውም ብለው አጥብቀው ይከራከሩ ነበር። እንዳውም ቫይረሱ እንዲጠፋ ቤተክርስቲያን እና መስጂድ ሄደው እንዲጸልዩ አበረታትተዋል። ''ኮሮናቫይረስ እርኩስ መንፈስ ነው፤ በክርስቶስ ሰውነት ውስጥ ሊቆይ አይችልም. . . . . ወዲያውኑ ይቃጠላል'' ሲሉም ተደምጠዋል አጥባቂ ክርስቲያኑ መሪ ጆን ማጉፉሊ። ፕሬዚዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ስለማድረግ በተመለከተ ሲናገሩ ምንም አይጠቅመንም ብለዋል። አክለውም የምርመራው እውነተኛነት ላይ ጥርጣሬ እንዳለቸው በመግለጽ በተለያዩ ፍራፍሬዎችና አንዲት ፍየል ላይ ምርመራ ተደርጎ ቫይረሱ በፓፓዬና በፍየሏ ላይ መገኘቱን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ጎረቤት አገራት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣላቸውን በመተቸትም እሳቸው ግን በዚህ መልኩ ኢኮኖሚውን መጉዳት እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ በርካታ አወዛጋቢና አነጋጋሪ ውሳኔዎችንም በማሳለፍ ይታወቃሉ። በአገሪቱ ታሪክ ከ54 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የነጻነት ቀን ብዙ ገንዘብ እያስወጣን ስለሆነ በህዝባዊ በአል አናከብረውም ማለታቸው የሚታወስ ነው። በአሉን በማክበር ፋንታም ህዝቡ ወጥቶ አካባቢውን እንዲያጸዳ ኣደረጉ ሲሆን እራሳቸውም በመንገድ ላይ በመውጣት በእጃቸው ቆሻሻ ሲሰበስቡ ውለዋል በነጻነት ቀን ላይ። ጆን ማጉፉሊ ፕሬዚዳንቱ በሆኑበት የመጀመሪያ ዓመት ላይ የሚወስዷቸው እርምጃዎች በበርካቶች ዘንድ ሙገሳን አስገኝቶላቸው ነበር። እንዳውም ታንዛንያውያን በትዊተር በኩል ማጉፉሊ ቢሆኑ ምን ያደርጉ ነበር እያሉ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ሲጋሩት ከርመዋል። ጉዳዩን ወደ ቀልድ የወሰዱት በርካቶች ቢሆንም ለጊዜውም ቢሆን ፕሬዚዳንቱ የአገሬውን ዜጋ መነጋገሪያ ጉዳይ ሰጥተውት ነበር። ከአገራቸው አልፎም በጎረቤት አገራት ከፍተኛ ተጽዕኖ መፍጠር ችለው ነበር። በአውሮፓውያኑ 2017 አንድ ኬንያዊ ፕሮፌሰር በዳሬሰላም ዩኒቨርሲቲ ንግግር ሲያደርጉ አፍሪካ በማጉፉሊ አስተሳሰብ መቃኘት አለባት ሲሉ ተደምጠው እንደነበር የሚታወስ ነው። ነገር ግን ቀስ በቀስ ፕሬዚዳንቱ የነበራቸው ድጋፍና ተቀባይነት እየተሸረሸረ መጥቷል። የማጉፉሊ አስተዳደር ያልተለመዱና በድፍረት የሚወሰዱ በርካታ ሕጎችንና መመሪያዎችንም ሲያወጣ ነበር። በተለይ ደግሞ ከዓለምአቀፍ የማዕድን አውጭ ተቋማት ከፍተኛ ገቢ ለመሰብሰብ ያለሙ ሕጎች ተጠቃሽ ናቸው። 2017 ላይ 'አኬሺያ ማይኒንግ' የተባለው ዓለምአቀፍ የማዕድን አውጭ ድርጅት 190 ቢሊየን ዶላር ግብር እንዲከፍል ተጠይቆ የነበረ ሲሆን ከብዙ ክርክር በኋላ ግን ድርጅቱ 300 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል ተስማምቷል። በመቀጠልም የታንዛንያ መንግሥት በድርጅቱ 16 በመቶ ድርሻ እንዲኖረውና ወደፊት ለሚገኙ ትርፍና መሰል ጥቅማትቅሞች እኩል ለመካፈል ተስማምተዋል። ፕሬዚዳንቱን በእጅጉ ከሚያስተቿቸው ውሳኔዎች መካከል ደግሞ ሴት ተማሪዎች በትምሀርት ላይ እያሉ ካረገዙ ተመልሰው ወደ ትምህርት ቤት መግባት አይችሉም የሚለው ነበር። ኢኮኖሚውን ከማነቃቃት አንጻር ደግሞ ፕሬዚዳንቱ በርካታ ስራዎችን መስራት ችለዋል። ታንዛንያን ከጎረቤት አገራት የሚገናኘው የባቡር መስመርን ጨምሮ በአገሪቱ አሉ የሚባሉ ትልልቅ ፕሮጀክቶች እንዲሰሩ አድርገዋል። በመንግሥት ቁጥጥር ስር የሚገኘው ብሄራዊ አየር መንገድም ከእዳው ተላቆ በአዲስ መልክ እንዲዋቀርና ወደ ገበያ እንዲገባም የሰሩ ሲሆን በአገሪቱ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እስከ አራተኛ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ድረስ ትምህርት በነጻ እንዲሰጥ አድርገዋል። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ኮሮረናቫይረስን በመቆጣጠር ረገድ ለወራት ይወስዷቸው የነበሩ እርምጃዎች ከአገሬው ዜጋም ሆነ ከዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ትችትን አስከትሎባቸዋል። ምንም እንኳን አገሪቱ የመጀመሪያውን የኮሮረናቫይረስ ምልክት ካየች በኋላ ትምህርት ቤቶችን በመዝጋትና ገደቦችን ማስቀመጥ ብትጀምርም የዓለም ጤና ድርጅት ግን ታንዛንያ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የወሰደችው እርምጃ የዘገየና ውጤታማ ያልነበረ ነው ብሏል። በወቅቱ ገበያዎችና የስራ አካባቢዎች ክፍት የነበሩ ሲሆን የእምነት ቤቶችም ቢሆኑ ለአማኞች ክፍት ሆነው እንዲቆዩ ተደርገው ነበር። ''በአገራችን በርካታ በቫይረስ የሚተላለፉ በሽታዎች አሉ፤ እንደ ኤችአይቪ ኤድስ ያሉትን መጥቀስ ይቻላል። ሁሌም ቢሆን ኢኮኖሚያችን መቅደም አለበት። ኢኮኖሚው እንዲተኛ መፍቀድ የለብንም፤ ሕይወትም መቀጠል አለባት'' ብለው ነበር ፕሬዚዳንቱ። በተጨማሪም ''ሌሎች የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚያቸውን ቸኩለው በመዝጋታቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስለሚገቡ በቅርብ ዓመታት ምግብ ከእኛ ለመግዛት መምጣታቸው አይቀርም'' ሲሉም ተደምጠው ነበር። በአሁኑ ሰአት ታንዛንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ስትሆን ፕሬዝዳንቱም በድጋሚ ለመመረጥ እንደሚፈልጉ እየገለጹ ነው። ዋነኛ ተቀናቃኞቻቸው ደግሞ የቻዴማ ፓርቲ ተወካዩ ቱንዱ ሊሱ ናቸው። ሰውዬው በአውሮፓውያኑ 2017 ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው የነበረ ሲሆን ላለፉት ሶስት ዓመታት በውጪ አገር በሕክምናና ማገገም ላይ አተኩረው ቆይተዋል። በአገሪቱ ታሪክ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የሚመሩት ፓርቲ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሸንፎ አለማወቁ እሳቸውም በድጋሚ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ በርካቶች ግምታቸውን እያስቀመጡ ነው። ተቀናቃኛቸው ቱንዱ ሊሱ ደግሞ በአገሪቱ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንደሚያደርጉና ሰብአዊ መብት እንዲከበር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል። ሌላኛው ተፎካካሪ በርናርድ ሜምቤ ደግሞ የቀድሞ ሚኒስትር ሲሆኑ እሳቸውም በምርጫው ካሸነፉ በርካታ ለውጦችን እንደሚያደርጉ እየገለጹ ነው። ጆን ማጉፉሊ በምርጫው የሚያሸንፉ ከሆነ በአገሪቱ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ እንደሚያተኩሩና የዜጎችን ኑሮ ለመቀየር በርካታ ፖሊሲዎች ማርቀቅና ተግባራዊ ማድረግ ላይ ትኩረት እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54643712
amh
politics
በሶማሊያ ምርጫ ዋዜማ አንድ አጥፍቶ ጠፊ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ
ሶማሊያ ውስጥ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። አጥፍቶ ጠፊው ጥቃቱን ያደረሰው ሶማሊያ ምርጫ ለማካሄድ አንድ ቀን ሲቀራት ነው። ፍንዳታው የደረሰው በልደወይኔ በተሰኘችው ማዕከላዊ ሶማሊያ በምትገኝ ከተማ ሲሆን የከተማዋ ባለሥልጣና በሚያዘወትሩት አንድ ሬስቶራንት ውስጥ ነው ጥቃቱ የተፈፀመው። ሮይተርስ የተሰኘው የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሟቾቹ መካከል ለሶማሊያ ፓርላማ ለመመረጥ ዕጩ የነበሩ ግለሰብ ይገኙበታል። የአል-ሸባብ ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈፀምነው እኛ ነን ብለዋል። ፅንፈኛው ቡድን አል-ሸባብ የሶማሊያ መንግሥትን ከአስር ዓመት በላይ ሲዋጋ ቆይቷል። በአንዳንድ የሃገሪቱ አካባቢዎችም ጠንካራ ይዞታ መሥርቷል። ቡድኑ በተለይ በቅርብ ጊዜያት በርካታ ጥቃቶችን እየሰነዘረ ይገኛል። ኤኤፍፒ የተባለው የዜና ወኪል፤ የፓርላማ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀች ባለችው በልደወይኔ ከተማ የፀጥታ ኃይሎች በርከት ብለው ተሰማርተዋል ሲል ፅፏል። የሶማሊያ ምርጫ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በፕሬዝደንቱ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ለወራት ሲጓተት ቆይቷል። የፓርላማ ምርጫው በሚቀጥለው ሳምንት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። በሶማሊያ ምርጫ መሠረት የጎሳ መሪዎችና ሌሎች ተወካዮች ሕግ አውጭዎችን ከመረጡ በኋላ እኒህ ተመራጮች ደግሞ በተራቸው ፕሬዝደንት ይመርጣሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-60451325
amh
politics
ዕጸ ፋርስ እና የእባብ መርዝ የወጪ ንግድን አቀላጥፋለሁ የሚሉት የኬንያ ዕጩ ፕሬዚዳንት
በልጅነታቸው የኬንያ ጎዳና ተዳዳሪ በኋላም በአንድ ወቅት በዩናይትድ ኪንግደም የመቃብር ቆፋሪ የነበሩት የአሁኑ የኬንያ ዕጩ ፕሬዝዳንት፣ ጆርጅ ዋጃኮያህ ለአገራቸ ዕጸ ፋርስ፣ የእባብ መርዝ እና የጅብ ዘር ፍሬን የወጭ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ አቀላጥፋለሁ እያሉ ነው። ብዙዎች የዕቅዳቸውን ተግባራዊነት ቢጠራጠሩትም የኬንያው ዕጩ ፕሬዚዳንት የምርጫ ቅስቀሳ በርካቶችን አስደምሟል። የ63 ዓመቱ ፕሮፌሰር እንዲሁም 17 ዲግሪ እንዳላቸው የሚናገሩት ዋጃኮያህ በመጪው ነሐሴ በሚካሄደው የኬንያ ምርጫ ከሚወዳደሩት አራት ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች መካከል እንደ እንግዳና ድንቅ ነገር በመታየት ቀልብን ስበዋል። የብዙዎችን ትኩረት ቢስቡም በምርጫው ያሸንፉ ይሆን? የሚለው ላይ የተሰበሰበው የሕዝብ አስተያየት ያንን አያሳይም። ከቀናት በፊት በወጣው የሕዝብ አስተያየት መሰረት 'ሩትስ' የተሰኘ ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩት ዋጃኮያህ፣ 4 በመቶ ድምፅ ብቻ እንደሚያገኙና በደረጃም ደካማ በሚባል ሁኔታ ሦስተኛ ላይ ነው የተቀመጡት። ነገር ግን የዘርፉ ባለሙያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ዕጩ ተወዳዳሪ ለሆኑ ግለሰብ ጥሩ ደረጃ ላይ ናቸው ይላሉ። በተለይም ግንባር ቀደም ተፎካካሪዎቹ 43 በመቶ የተሰጣቸው የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ እና 39 በመቶ የተተነበየላቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ምንም አይነት ድምፅን ማጣት ባይፈልጉም ዋጃኮያህ የተወሰነውን መውሰድ እንደሚችሉ ተገምቷል። “ዋጃኮያህ ከዚህ ቀደም በርካቶች ሊስቁበት የሚችሉበትን ሃሳቦች አንስቶ እየሞገተ ነው ቅስቀሳ እያደረገ ያለው። ነገር ግን በከተማም ሆነ በገጠር የተናደዱ፣ ምጣኔ ሀብቱ ያጎሳቆላቸው ወጣቶችን ቀልብ መግዛት ችሏል። በተለያየ ብሔር፣ እምነትና ፓርቲ አባላት ወጣቶችም እየተሰማ ነው” በማለት በኬንያ ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ ዋና አምደኛ የሆነው ማቻሪያ ጋይቶ ጽፏል። በምርጫ ቅስቀሳ ጎዳናዎች ላይ በሚወጡበት ወቅት ሙሉ ሱፍ ኮትና ሱሪ ከማድረግ ይልቅ ቲሸርት፣ ኮፍያ፣ ስካርፍ፣ ጂንስ፣ ቱታ በማድረግ ነው። በዚህም በአገሪቱ የሰፈነው የሚወቅሱት እና የሚጠየፉት መጠነ ሰፊ ሙስና አካል አለመሆናቸውን ያሳያሉ። በተጨማሪም ዕጸ ፋርስ እንደሚያጨስ በማስመሰል በጣቶቻቸው ምልክት ያሳያሉ፤ በሬጌ ዘፈኖችም በሚጨፍሩበት ወቅት የተሰበሰበው ሕዝብም በደስታ ይዘላል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ የፕሬዝዳንቱን መንበር ካሸነፉ የኬንያ ሁለቱን ትላልቅ ችግሮች፣ ሥራ አጥነትን ለመፍታት እና ብሔራዊ ዕዳዋን ለማቃለል፣ ለኢንዱስትሪ እንዲሁም ለህክምና አገልግሎት የሚውል የዕጸ ፋርስ ግብርና እና ምርቱን የሚቆጣጠር ሕግ እንደሚያወጡ ተናግረዋል። እሳቸው እንደሚሉት ይህ እርምጃ ኬንያን በዓመት ከዘጠኝ ትሪሊዮን ሽልንግ በላይ ወይም 76 ቢሊዮን ዶላር ያስገኝላታል፣ በዚህም መንግሥት እንደገና “አንድ ሳንቲም መበደር የለበትም" ይላሉ። “የምዕራባውያን አገሮች ዕጸ ፋርስን (ማሪዋና) ሕጋዊ አድርገውታል። እኛስ ለምንድን ነው ሕጋዊ የማናደርገው?” ሲሉም ይጠይቃሉ። ምንም እንኳን የሚሏቸውን ጉዳዮች በጥናት ባያስደግፉም ዕጸ ፋርስ (ማሪዋና) ለኢንዱስትሪ እንዲሁም ለመድኃኒትነት ለመጠቀም ሕጋዊ ማድረግ የምርጫ ቅስቀሳቸው ዋነኛ ማጠንጠኛ ነው። የአፍሪካ ቼክ ድረ ገፅ ዕቅዶቻቸውን አሳሳች ናቸው ሲል ገልጾታል። ሆኖም በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ላይ መነጋገሪያ መሆናቸው ቀጥሏል፣ እንዲሁም በሥራ አጥነት ክፉኛ የተጎዱ የአገሪቱ ወጣቶችን ደስ አሰኝቷል። የፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ሃሳብ የሚሳካ ከሆነ ኬንያን ዓለም አቀፍ የዕጸ ፋርስ (ማሪዋና) ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን እየሞከሩ ካሉት የአፍሪካ አገራት ከሌሶቶ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከዛምቢያ እና ከዚምባብዌ ጋር ያሰልፋታል። የዕጸ ፋርስ (ማሪዋና) በአንዳንድ ግምቶች መሰረት በአውሮፓውያኑ 2028፣ 70 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ማሪዋና አጭሰው እንደማያውቁ ቢናገሩም፣ ነገር ግን ኬንያ ዕጹን ሕጋዊ ካደረገችው ደስታቸውን ለመግለፅ ማሪዋና የሚያጨሱ የመጀመሪያው ሰው እንደሚሆኑ ተናግረዋል። “ዕጸ ፋርስ (ማሪዋና) ሕጋዊ ከሆነ፣ ተቆጣጣሪ አካላትም የሚፈቅዱ ከሆነ ማጨሱ ምንም ችግር የለውም” ይላሉ። የፕሮፌሰር ዋጃኮያህ አስተያየት በኬንያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውግዘት ደርሶበታል። ቤተ ክርስቲያኗ ማሪዋና ሕጋዊ ከሆነ ወጣቶች የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚነታቸው ይባባሳል ስትል ወቅሳለች። “ቤተሰቦች የአደንዛዥ ዕጽ ስጋት ተደቅኖባዋል። ይህም ወደ መለያየት፣ ሁከት አልፎ አልፎም ለሞት ይዳርጋል” ሲሉ ጳጳስ ጄምስ ማሪያ ዋይናና አስጠንቅቀዋል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ በተጨማሪም በፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መንግሥት ለቻይና ኩባንያዎች የተሰጡ ውሎችን በሙሉ እንደገና እንደሚገመግሙም ቃል ገብተዋል። ኬንያ ካለባት የውጭቻ ዕዳ 21 በመቶውን ከቻይና የተወሰደ ሲሆን ይህም ብሔራዊ ቅሬታን አስከትሏል። በተለይም በአብዛኛው እንደ መንገድ እና ባቡር ያሉ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት አገራቱ የገቧቸው ውሎች ሲሆኑ፣ ለሕዝብ ይፋ አለማሆናቸው የዕጩው ፕሬዝዳንት የሚያነሱት ጥያቄ ነው ነው። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ የእባብ እርባታን እንደ ሌላው የኬንያ ምጣኔ ሀብት ዋና ምሰሶ አድርገው ይመለከቱታል። “ከወርቅ የበለጠ ውድ ነው” የሚሉትን የእባብ መርዝ፣ ለመድኃኒትነት የሚውል ፀረ-የእባብ መርዝ ለማምረት እንዲሁም የእባብ ሥጋን ደግሞ እንደ ጣፋጭ ምግብ ለሚቆጥሩት እንደ ቻይና ላሉ አገራት እንደሚላክ ይናገራሉ። “ምጣኔ ሀብቱን በተረጋጋ ሁኔታ ለማስቀጠል በየዓመቱ አንድ ቢሊዮን ዶላር ሊኖረን ይችላል” ይላሉ ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ። በተጨማሪም በቻይና ለመድኃኒትነት የሚያገለግለውን የጅብ የዘር ፍሬን ኬንያ ወደ ውጭ መላክ አለባት በማለት ከማሪዋና የበለጠ ገቢ እንደሚያስገኝ ያስረዳሉ። ይህ ንግግራቸው ከዱር እንስሳት ጥበቃ ቡድኖች እና ከኬንያ የእንስሳት ሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር በኩል ቁጣን አስከትሏል። “የጅብ ዘር ፍሬዎች እና እባቦች ንግድ የተከለከለ እና ለዱር ዝርያዎች ህልውና ስጋት ነው” ሲል የእንስሳት ማኅበር በመግለጫው አስታውቋል። የዕጩው ፕሬዝዳንት ዕቅድ “ለሌላ ወረርሽኝ ግብዓት ነው” ምክንያቱም ቫይረሶች፣ ባክቴሪያዎች እና ጥገኛ ተህዋሲያን ከጅብ እና ከእባቦች ወደ ሰው በከፍተኛ ሁኔታ እንዲዛመቱ ሊያደርግ ይችላል ብሏል መግለጫው። ምንም እንኳን ተቺዎች ተወዳጅነትን ፍለጋ ነው በሚል የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸውን ቢያወግዙትም፣ የፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ደጋፊዎችና ወዳጆች ፈታኝ የሚባል የሕይወት ችግሮችን ድል በመንሳት ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር በመነሳታቸው ያደንቋቸዋል። ፕሮፌሰሩ ትውልዳቸው በምዕራብ ኬንያ ገጠር ሲሆን፣ ወላጆቻቸው መፋታታቸውን ተከትሎ ወደ ዋና ከተማዋ ናይሮቢ ጎዳናዎች ላይ ወጡ። የሃሬ ክሪሽና ቤተ ምኩራብ አገልጋዮች ቤት የተቸገሩና የሚበሉት የሌላቸውን እየመገቡ በነበረበትም ወቅት ነው ታዳጊውን ያገኙት። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ በቤተ ምኩራቡም መኖር ጀመሩ በኋላም የሃሬ ክሪሽና ካህን ሆኑ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዲያጠናቅቁ ድጋፍ ተደረገላቸው። ከተመረቁ በኋላም የኬንያ ፖሊስን ተቀላቀሉ። በደረጃም ከፍ በማለት የደኅንነትና የስለላ ክፍሉን ተቀላቀሉ። ምንም እንኳን ለዝርዝር መረጃው ግልፅ ባይሆኑም ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ በአውሮፓውያኑ 1990 በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮበርት ኦኮ ግድያ ዙሪያ ምስጢራዊ መረጃ ካገኙ በኋላ ችግር እንደገጠማቸው ተናግረዋል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ እንደታሰሩ እና እንደተሰቃዩ የተናገሩ ሲሆን፣ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ናይሮቢ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እርዳታ ከኬንያ መሰደዳቸውን አስረድተዋል። በአውሮፓውያኑ 2010 የፓርላማ አጣሪ ኮሚቴ ባደረገው ምርመራ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተገደሉት በፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ አንደኛው መኖሪያ ቤት መሆኑን ይፋ እስካደረገበት ድረስ የባለሥልጣኑ ግድያ ለሕዝብ ምስጢር ሆኖ ቆይቷል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ኬንያን ጥለው ከወጡ በኋላ ወደ እንግሊዝ አመሩ። እዚያም ዝቅተኛ የሚባሉ ሥራዎችን እየሰሩ በለንደኑ ሶአስ ዩኒቨርሲቲ፣ በዋርዊክ ዩኒቨርሲቲ እና በዎልቨርሃምፕተን ዩኒቨርስቲ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በዎልቨርሃምፕተን ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ በነበረበት ወቅት ኑሮን ለማሸነፍ ሲሉ የጥበቃ ሠራተኛ፣ የመቃብር ቆፋሪ እና የሬሳ አጥቢ ሆነው ሰርተዋል። እነዚህ ሥራዎች “ትሁት እንዳደረጓቸውና ዕይታቸውንም እንዳሰፋላቸው” ለዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ ተናግረዋል። በወቅቱም ለትምህርት እና ለሥራ የሚሆናቸውን ጊዜ አመጣጥኖ መሄድ ፈታኝ ነበር ይላሉ። በዩናይትድ ኪንግደም ሳሉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለውጥ ለማምጣት በፖለቲካ ዘመቻዎች ውስጥ ተሳትፈዋል። በአውሮፓውያኑ 1981 በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ይዘው እስከ 2000 ድረስ ጋናን ከመሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጄሪ ራውሊንግስ ጋር በቅርበት ሰርተዋል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ መኖሪያቸውን ወደ አሜሪካ ካደረጉ በኋላም፣ አፍሪካ አሜሪካዊት ባለቤታቸውን ተዋወቁ። ጥንዶቹ ሦስት ልጆች እንዳሏቸው ተነግሯል። ከዋልደን ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ጨምሮ፣ በተለያዩ የአሜሪካ ተቋማትም ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በአጠቃላይ 17 ዲግሪዎች እንዳላቸው የሚናገሩ ሲሆን፣ ትምህርታቸውም ስደት፣ ዓለም አቀፍ እና የስደተኛ ሕግን ያካትታል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ ወደ ኬንያ የተመለሱት በአውሮፖውያኑ 2010 ሲሆን፣ ለፕሬዝዳንትነት መወዳደር እንደሚፈልጉ አስታውቀው ነበር። ሆኖም በወቅቱ የነበረውን ሃሳባቸውን የተውት ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ነሐሴ ወር ላይ በሚደረገው ምርጫም የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ለመሆን ለየት ያሉ ሃሳቦችን እያነሱ መራጩን ሕዝቡ እየቀሰቀሱ ይገኛሉ። የፕሮፌሰሩ ሌላ አወዛጋቢ የምርጫ ቅስቀሳ ተስፋ የተባለው ሠራተኞች በሳምንት አራት ቀን ብቻ እንዲሰሩ በማድረግ የሥራ እና የሕይወት ሁኔታን እንደሚያሻሽሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም ለሙስሊሞች አርብን፣ ቅዳሜ ለአድቬንቲስቶች እና ለሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ እሁድን የአምልኮ ቀናት እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል። ፕሮፌሰር ዋጃኮያህ የሞት ቅጣትን ለመመለስ ቃል የገቡ ሲሆን  በሙስና የተከሰሱ ሰዎች “ኡጋሊ [የኬንያ ባህላዊ ምግብ] ከተመገቡ በኋላ” በጥይት ወይም በመሰቀል ሞትን መርጠው ቅጣቱ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cmlelnl7rklo
amh
politics
ቦሪስ ጆንሰን ከምርጫ ራሳቸውን በማግለላቸው በተፎካካሪያቸው ተሞገሱ
ሪሺ ሱናክ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰንን በይፋ አሞገሱ። ሙገሳው የመጣው ጆንሰን ለጠቅላይ ሚንስትርነት በድጋሚ እንደማይወዳደሩ ካስታወቁ በኋላ ነው። “ቦሪስ ጆንሰን ብሬግዚት እና የክትባት ስርጭት ላይ ስኬታማ ነበሩ” ሲሉ ሪሺ ሱናክ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። “ፈታኝ ከሆኑ ጊዜያቶች በአንዱ አገራችንን መርተዋል። ፑቲን በዩክሬን የጀመሩት አረመኔያዊ  ጦርነት ወቅትም ነበሩ። ለዚህም ሁሌም እናመሰግናቸዋለን።" በቀጣይ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን የተሻለ ዕድል አላቸው የተባሉት ሪሺ ሱናክ “በድጋሚ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን ፍላጎት ባይኖረውም በአገር ውስጥ እና በውጭ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አምናለሁ” ብለዋል። በተሾሙ በ45 ቀናት ስልጣን በቃኝ ያሉትን የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስን ለመተካት የሚደረገው ውድድር ቀነ ገደብ ተቃርቧል። ሪሺ ሱናክ የቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አጋሮችን ጨምሮ ከፓርቲያቸው 128 የፓርላማ አባላትን ድጋፍ በመሰብሰብ ውድድሩን እየመሩ ይገኛሉ ተብሎ ነበር። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በ53 የድምጽ ድጋፍ ሁለተኛ ሆነው እየተከተሉ ስለመሆናቸው ቢቢሲ መረጃ አግኝቷል። ሆኖም ደጋፊዎቻቸው ወደ ውድድሩ ለመግባት የሚያስፈልገው የድምፅ ድጋፍ እንዳላቸው በመጥቀስ 100 የፖርላማ አባላት የድጋፍ ድምጽ እንዳገኙ ይከራከራሉ። ቦሪስ ጆንሰን የህዝብ እንደራሴዎች ድጋፍ ቢኖረኝም “አሁን ይህንን የማድረጊያው ትክክለኛ ጊዜ አይደለም። በፓርላማ ውስጥ የተዋሃደ ፓርቲ ሳይኖር ማስተዳደር ይከብዳል” ብለዋል። እስከ 102 የሚደርሱ የሕዝብ እንደራሴዎች ድጋፍ እንዳላቸውም አስታውቀዋል። ቢቢሲ 57 የሕዝብ እንደራሴዎች እንደሚደግፏቸው በይፋ ቢያረጋግጡም የቀሪዎቹን ለማረጋገጥ አልቻለም። ፔኒ ሞርዳውንት ውድድሩ መቀላቀላቸውን በይፋ ያሳወቁ ብቸኛ እጩ ናቸው ነገር ግን በ23 የፓርላማ አባላት ድጋፍ ወደ ኋላ ቀርተዋል። የቢቢሲዋ ላውራ ኩንስስበርግ ቦሪስ ጆንሰን እና ሪሺ ሱናክ ቅዳሜ አመሻሹ ላይ ተገናኝተው እንደነበር  ገልጻ  ነገር ግን በውይይታቸው ላይ መግለጫ ይወጣ እንደሆነ እርግጠኛ አልነበረችም። ቢቢሲ ድጋፍ የሰጡ የፓርላማ አባላትን መረጃ ሲሰበስብ ቆይቷል። ከ357 ወግ አጥባቂ የፓርላማ አባላት መካከል የ204ቱ የመምረጥ ፍላጎታቸው የሚታወቅ እና በቢቢሲ የተረጋገጠ ሲሆን የበርካቶች ፍላጎት ግን እስካሁን ግልጽ አልሆነም። ለውድድሩ በቂ ድጋፍ ለማግኘት እስከ ፊታችን ሰኞ  8 ሰዓት ድረስ ጊዜ አላቸው። በዚህም ለሚቀጥለው የውድድር ደረጃ ብቁ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። የፓርቲው የፓርላማ አባላት አንድ እጩን ብቻ የሚደግፉ ከሆነ ሰኞ ከሰዓት በኋላ ዩናይትድ ኪንግደም አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኖራት ይችላል። ካልሆነ ግን የወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ምርጫ በኦንላይን የሚያካሂዱ ሲሆን ውጤቱም በመጪው ሳምንት አርብ ይፋ ይሆናል። የምርጫ አስተያየቶች እንደሚያሳዩት በዚህ ኦንላይን ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከምርጫው ራሳቸውን ባያገሉ ኖሮ የአባላቱን ድምጽ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ተገምቶ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cx0yn2vkv22o
amh
politics
የዩክሬን ብሔራዊ ቡድን ማልያ ሩስያን አስቆጣ
የዩክሬን የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ማልያ ላይ በሩሲያ ቁጥጥር ስር የምትኘው ክሬሚያን ያካተተ ካርታ መካተቱን ተከትሎ ሞስኮ ቁጣዋን እየገለጸች ነው። ዩክሬን በዩሮ 2020 የምትጫወትበትን ማልያ ይፋ ያደረገች ሲሆን ማልያውም የከፍተኛ ውዝግብ ምክንያት የሆነችው ክሬሚያን ያካተተ ነው። በማልያውም ላይ ‘ድል ለዩክሬን’ የሚል መልዕክት ተጸዕፏል። ሩሲያ በአውሮፓውያኑ 2014 ነበር የክሬሚያን አካባቢ ከዩክሬን ወስዳ የራሷ ያደረገችው። በዚህም ሩሲያ አካባቢውን የግዛቷ አካል አድርጋ የምትቆጥረው ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግን እስካሁን እውቅና አልሰጠም። የዩክሬንን ብሄራዊ ቡድን መለያ በተመለከተ መልዕክት ያስተላለፉ አንድ የፓርላማ አባል ጉዳዩን ‘’ፖለቲካዊ ትንኮሳ’’ ነው ብለውታል። የዩክሬን እግር ኳስ ማህበር ኃላፊው አንድሬይ ፓቬልኮ ነበሩ ትናንት እሁድ ዕለት የብሄራዊ ቡድኑን መለያ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ያስተዋወቁት። የአውሮፓ እግር ኳስ ውድድር ወይም ዩሮ 2020 ከቀናት በኋላ ይጀመራል። በቢጫው የብሄራዊ ቡድኑ መለያ ፊትለፊት ላይ በነጭ መስመር የአገሪቱን ክልል የተገለጸ ሲሆን ክሪሚያንም ያካተተ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በተገንጣይ ቡድኖች ቁጥጥር ስር የሚገኙት ዶኔስክ እና ሉጋንስክም ጭምር በማልያው ላይ እንዲካተቱ ተደርጓል። በማልያው ጀርባ ደግሞ ‘ድል ለዩክሬን’ የሚል መፈክር ሰፍሯል። ይህ መፈክር በአውሮፓውያኑ 2014 ሩሲያን የሚደግፉት ፕሬዝደንት ቪክቶር ያኑኮቪችን ከስልጣን ያስወገዱት ሰልፈኞች በተደጋጋሚ ይጠቀሙበት የነበረ ነው። ‘’ይህ የዩክሬን ሁኔታ ተጫዋቾቹ ጥንካሬ እንዲያገኙና ለሁሉም ዩክሬን እንዲጫወቱ እንደሚያደርግ እምነት አለን’’ ብለዋል የዩክሬን እግር ኳስ ማህበር ኃላፊው አንድሬይ ፓቬልኮ። ነገር ግን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የብሄራዊ ቡድኑን መለያ ተችተዋል። ‘’ብሄራዊ ቡድኑ የሩሲያ አካል የሆነችውን ክሪሚያን ማካተቱ ሊሆን የማይችልን ነገር እንደ ማሰብ ነው’’ ብለዋል። የተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ዲሜትሪ ስቪሽኮቭ በበኩላቸው የብሄራዊ ቡድኑ መለያ ‘’ከነጭራሹ ተገቢ ያልሆነ’’ ነው ያሉ ሲሆን የየዑሮ 2020 አዘጋጆችና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። የዘንድሮው ዩሮ 20202 በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ 11 የአውሮፓ ከተሞች ከሰኔ 4 ጀምሮ ለአንድ ወር ይካሄዳል። ውድድሩን ከሚያስተናግዱት ከተሞች መካከል ደግሞ የሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ትገኝበታለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-57380988
amh
politics
የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ወቅት ወታደሮች ሚኒስትሮችን አግተው ነበር ተባለ
የደቡብ አፍሪካ ግብረ ኃይል በኦፓርታይድ አገዛዝ ወቅት ላደረጉት ትግል ካሳ ይከፈለን በሚል የነፃነት ወቅት ወታደሮች ሁለት ሚኒስትሮችን አግተው እንደነበርና ነፃ መውጣታቸውንም አስታውቋል። ኤኤንሲ ከነጮች አፓርታይድ አገዛዛዝ ወቅት ነፃ ለመውጣት በሚደረገው ትግል ወታደራዊ ክንፍ አቋቁሞ የነበረ ሲሆን የዚህም ክንፍ አባላት ናቸው በአሁኑ ወቅት ለቤተሰቦቻቸው የመኖሪያ ቤት እና የህክምና መድን የሚሆን 280 ሺህ ዶላር የአንድ ጊዜ ክፍያ እየጠየቁ ያሉት። ትናንት ማምሻውን በዋና ከተማዋ ፕሪቶሪያ በሚገኝ ሆቴል የካሳ ጥያቄያቸውን ለመደራደር የፕሬዚዳንት ሚኒስትሩ ሞንድሊ ጉንጉቤሌ ፣ መከላከያ ሚኒስትሩ ታንዲ ሞዲሴ እና ምክትላቸው ታባንግ ማክዌትላ ተገናኝተው ነበር። ድርድሮቹ ፍሬ አለማፍራታቸውን ተከትሎ የመንግስት ባለስልጣናቱ ታግተው ነበር። በኋላ ላይ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ለመደራደር የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ የቀረ ሲሆን ከ50 በላይ ሰዎች ተሳትፎ ነበራቸው በሚል ተዘግቧል። ሁኔታው ከመጋጋሉም ጋር ተያይዞ በፀረ-ሽብርተኝነት እና በታጋቾች ሁኔታዎች ውስጥ የሰለጠነው ልዩ ግብረ ኃይል መጠራት ነበረበት። ሚኒስትሩ ሞንድሊ ጉንጉቤሌ ድርጊቱ "የማይታለፍ" እና "በሕግ ተቀባይነት የሌለው" ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም እነዚህ የነፃነት ታጋዮች ች በጭካኔ የተሞላውን የአፓርታይድ መንግስት ለመዋጋት ላደረጉት አስተዋፅኦ ካሳ ስላልተከፈላቸው በኤኤንሲ መንግሥት እንደተከዱ እንደሚሰማቸው ተናግረዋል። ነገር ግን፣ ወታደራዊ አርበኞቹ በየወሩ በመንግሥት የሚደገፍ ጡረታ ይሰጣቸዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይቡድኑ ከገዥው ፓርቲ ኤኤንሲ ዋና መሥሪያ ቤት ውጭ በመውጣት የተቃውሞ ሰልፍ በማሰማታቸው ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርገዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58908172
amh
politics
የደቡብ ሱዳን የውሃ ሚኒስትር ግብፅ ውስጥ ሕይወታቸው አለፈ
የደቡብ ሱዳን ውሃ ሃብት እና መስኖ ሚኒስትር ማናዋ ፒተር ጋትኩት ጉአል በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉን የአገራቸው መንግሥት አስታወቀ። ሚኒስትሩ በደረታቸው አካባቢ የነበረው ህመም ጸንቶባቸው ባለፈው አርብ ወደ ግብፅ ለህክምና ተጉዘው እንደነበር የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ገልጸዋል። የታመሙት የውሃ ሚኒስትር ግብፅ ከደረሱ በኋላ ቅዳሜ ዕለት ቀዶ ሕክምና የተረገላቸው ቢሆነም የዚያኑ ዕለት ማምሻውን ሕይወታቸው ማለፉን ነው ሪክ ማቻር የተናገሩት። “ማናዋ በዩኒቨርሲቲ በነበሩበት ጊዜ ጠንካራ የተማሪዎች መሪ ነበሩ። በሱዳንም የወጣቶች ንቅናቄ ላይ ጥሩ መሪ ነበሩ። ቆራጥ እና አገራዊ ፍቅር ያላቸው ነበሩ። በደቡብ ሱዳን ላይ ጠንካራ እምነት የነበራቸውም ሰው ነበሩ” ብለዋል ማቻር ለቤተቦቻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ። የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳለቫ ኪር በበኩላቸው የውሃ ሚኒስትሩን ሞት ሲሰሙ “ታላቅ ሐዘን” እንደተሰማቸው ገልጸዋል። የደቡብ ሱዳን ውሃ ሃብት እና መስኖ ሚኒስትር ማናዋ ከመንግሥታዊ ሥልጣናቸው ባሻገር የደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ [ኤስፒኤልኤም - አይኦ] የተባለው ቡድን የፖለተካ ዘርፍ አባልም ነበሩ። የሚኒስትሩ አባት ፒተር ጋትኩት ጉአል በደቡብ ሱዳን ሰፊ እውቅና ያላቸው ፖለቲከኛ ነበሩ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cw0dqp5n0ezo
amh
politics
'የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች' 11ኛው ክልል በመሆን ሊቋቋም ነው
የኢትዮጵያ አስራ አንደኛው ክልል እንዲዋቀር የሚያስችል ድምጽ በቅርቡ ከተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ውጤት መገኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። መስከረም 20/2014 ዓ.ም ከተካሄደው ሁለተኛ ዙር ምርጫ ጋር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልን ለማወቀር በተሰጠው የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ መሠረት በአብላጫ ድምጽ ክልል የመሆን ድጋፍ አግኝቷል። በዚህም መሠረት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር በተለያየ የአወቃቀር ደረጃ ላይ የነበሩት የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ የምዕራብ ኦሞ፣ የቤንች ሸኮ፣ የካፋ፣ የዳውሮ እና የሸካ ዞኖች በአንድነት የአገሪቱ አስራ አንደኛ ክልል ሆነው ይመሠረታሉ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅዳሜ መስከረም 28/2014 ዓ.ም ከአንድ ሳምንት በፊት የተካሄደውን የሕዝበ ውሳኔ ውጤት ባሳወቀበት ውቅት እንደገለጸው፤ በሕዝበ ውሳኔው ላይ ድምጽ ለመስጠት ከ1.3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተመዝግበው 1.2 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ድምጽ ሰጥተዋል። ድምጽ ከሰጡት መካከልም አምስቱ ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ከደቡብ ብሔር፣ ቤሔረሰብና ሕዝቦች ክልል ስር ወጥተው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በመባል መዋቀራቸውን በመደገፍ 1ሚሊየን 221 ሺህ 92 ሰዎች ድምጽ ሰጥተዋል። በዚህም ከ50 በላይ ብሔረሰቦች ከሚገኙበት የደቡብ ክልል ከሁለት ዓመት በፊት በመውጣት በሕዝበ ውሳኔ የራሱን ክልል የመሠረተውን የሲዳማ ክልልን በመከተል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሁለተኛው ሲሆን የአገሪቱም 11ኛ ክልል ይሆናል። የሕዝበ ውሳኔው ውጤት ለፌደሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርባና 11ኛው ክልል እንደሚዋቀር ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝቦች ክልል ውስጥ የሚገኙ በርካታ ዞኖች በክልልነት ለመዋቀር ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል። ለረጅም ጊዜ በክልልነት የመዋቀር ጥያቄን ሲያነሳ የነበረው የሲዳማ ክልል በቀዳሚነት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ሕዝበ ውሳኔ ተዘጋጅቶለት ነበር ክልል ሆኖ ለመደራጀት የበቃው። በደቡብ ክልል ለቀረቡ ክልል የመሆን ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በፌደራል መንግሥቱና በክልሉ አማካይነት ጥናቶች መካሄዳቸው የተነገረ ሲሆን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ እንዲቋጭ ተደርጓል። ከዚህ ውጪ ያሉና ጥያቄ ያቀረቡ ዞኖች ጉዳይን በተመለከተ አስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም። የደቡብ ምዕራን ኢትዮጵያ ብሔሮች ክልል እንዲመሰረት በሕዝበ ውሳኔ አስፋለጊው ድምጽ በመገኘቱ ክልሉን ለማደራጀት የሚያስፈልጉ ሥራዎች በደቡብ ክልልና በዞኖቹ አማካይነት እንደሚከናወን ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58858515
amh
politics
የካፒቶሉን ነውጥ ተከትሎ ኩባንያዎች ፖለቲካዊ የገንዘብ ልገሳቸውን ሰረዙ
በባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን የተነሳውን ነውጥ ተከትሎ በአሜሪካ ምክር ቤት ያሉ ሪፐብሊካኖች ከአገሪቱ ኩባንያዎች ዘንድ ከፍተኛ ውግዘትን አትርፈዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው የአሜሪካ ኩባንያዎች ለምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያበረክቱት የነበረውንም ልገሳ እንሰርዛለን ብለዋል። በተለይም ጆ ባይደን እንዳይመረጡ ለማድረግ ልገሳ ያበረከቱት ኩባንያዎች ለምርጫ ቅስቀሳ ገንዘብ ከአሁን በኋላ አንለግስም ብለዋል። የፖለቲካ ልገሳዎችን ከሰረዙት ኩባንያዎች መካከል በሆቴል ዘርፉ ስመ ጥር የሆነው ማሪዮት፣ ሲቲ ባንክ እንዲሁም ስመ ገናናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል ይገኙበታል። የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶልን ሰብረው መግባታቸውን ተከትሎ ሌሎች ኩባንያዎችም እንዲሁ ስትራቴጂያቸውን እያጤኑት እንደሆነ ተናግረዋል። ተመራጩን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን የፕሬዚዳንትነት ማረጋገጫ ለማስቆም ባለመው በዚህ ነውጥ የአምስት ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል። በርካታ ቁጥር ያላቸው የአሜሪካ ኩባንያዎች ለሁለቱም ፓርቲ አባላት የሚሆን ልገሳ ማድረግ የተለመደ ነው። ሆኖም በቅርቡ የደረሰውን ነውጥ ተከትሎ ከህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት በመፈጠሩ እነዚህም ኩባንያዎች ልገሳቸውን እንደገና እንዲያጤኑት በር ከፍቶላቸዋል። በአካውንቲንጉ ዘርፍ የታወቀው ዴሎይቴ፣ የቴሌኮሙ ኤቲ ኤንድ ቲ እንዲሁም የክሬዲት ካርድ ኩባንያዎቹ አሜሪካን ኤክስፕረስና ማስተር ካርድ ማንኛውንም አይነት ልገሳ ለጊዜው አንሰጥም ብለዋል። "ፖሊሲያችን እንዲህ አይነት የጥላቻ ቡድኖችን አባልነት አይቀበልም፤ ስለዚህ እነዚህን ግለሰቦች አባል መሆናቸውን ካወቅን እናግዳቸዋለን" በማለትም በአለም አቀፍ ዘንድ ግለሰቦች ቤቶቻቸውን እንዲያከራዩ የሚያስችለው ኤይርቢኤንቢ የተባለው ኩባንያ አስታውቋል። ኩባንያው የ ጆ ባይደንን የመጪው ፕሬዚዳንትነት ማረጋገጫን የተቃወሙትን በሙሉ ምንም አይነት ድጋፍ አልሰጥም በማለትም አስታውቋል። የሰላምታ ካርዶች አምራች ሆልማርክ በበኩሉ የጆ ባይደንን ፕሬዚዳንትንት ተቃውመዋል ያላቸውን ሁለት የሪፐብሊካን ሴናተሮች የሰጣቸውን ልገሳ እንዲመልሱ ጠይቋል። ኩባንያው በካንሰስ ዋነኛ የሚባልም ቀጣሪ ነው። የኬሚካል ንጥረ ነገሮች አምራቹ ዶውም ከሌሎች ኩባንያዎች በተለየ መልኩ ለሪፐብሪካኖች የምክር ቤት አባላት በስልጣን ባሉበት አመታት ሁሉ ማንኛውም የገንዘብ ልገሳ አላድርግም ብሏል። የአንዳንዶቹ ኩባንያዎች የገንዘብ እገዳ እስከተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ሲሆን ከነዚህም መካከከል ጄኔራል ኤሌክትሪክ እስከ አውሮፓውያኑ 2022 ይዘልቃል ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55629199
amh
politics
"ሕዝብን ከማገልገል በላይ ክብር የለም"- አዲሱ የባህርዳር ምክትል ከንቲባ
በትናንትናው ዕለት፣ ጥቅምት 6፣ 2013 ዓ.ም ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል። የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በስራ አመራርና ፍልስፍና ቻይና አገር ከሚገኘው ኋጁንግ ዩኒቨርስቲ በቅርቡ አጠናቀው የመጡት ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የምሁራን ተሳትፎና አደረጃጀት ዘርፍ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አማካሪ፣ የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ፣ የሕዝብ ግንኙነትና የከተማ አደረጃት አማካሪና በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ ምክትል አስተዳደሪና ግብርና ጽኅፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ካገለገሉባቸው መካከል የተወሰኑት ናቸው። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በመልክዓምድርና አካባቢ ጥናት ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲና ሁለተኛ ዲግሪ በመልካም አስተዳደርና በአመራር ጥበብ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በተለያዩ የአመራር ቦታዎችም ላይ ሆነው አገልግለዋል። በባሕርዳር ከተማ አስተዳደር በተቀዳሚ ምክትል ከንቲባነታቸውን ሹመት፣ ሊያከናውኗቸው ያሰቧቸውን እቅዶችና ሌሎች ጉዳዮች በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ቢቢሲ፦ በትናንትናው ዕለት ሹመቱን ሲቀበሉ ምን እሰራለሁ? ምን ለውጥ አመጣለሁ ብለው ነው ሹመቱን የተቀበሉት? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደርን በተቀዳሚ ምክትል ከንቲባነት እንድመራ የድርጅትና የመንግሥት ኃላፊነት ሲሾመኝ፣ አንደኛ ይሄ ተልእኮ ነው። የፓርቲው አባል ነኝ፤ ከፓርቲዬ የተሰጠኝን ተልዕኮ መቀበል የግድ ስለሚል ይህንን የተሰጠኝን ተልዕኮ ተረክቤ ከዚህ በፊት በግንባር ላይ እየሰሩ ካሉ አመራሮች ጋር በመካከር፤ በቀጣይ ባህር ዳር የኢንቨስትመንት መዳረሻ፣ ኢንዱስትሪ የተስፋፋባት፣ ሰላም የሰፈነባት፣ ፍትሃዊነት የተረጋገጠባት እና የሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ ስራዎችን ህዝብ ጋር በመካከር ለመስራት ነው። የባህር ዳር ከተማ እንድታድግ እንድትበለፅግ የከተማዋ ነዋሪዎች ፍላጎት ነው። እኔም ይህንን ኃላፊነት የከተማዋን ነዋሪ ፍላጎት ለማሳካት በበኩሌ የሚጠበቅብኝን አስተዋፅኦ ለማበርከት ነው። በቀጣይ አመራሩ ጋር ተነጋግረን፤ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሂደን ከዚህ በፊት የተጀመሩ ስራዎችን፣ የታቀዱ እቅዶችንና ጅምሮችን ለማስቀጠል እናስባለን። በአዳዲስ የከተማ አስተዳደር ስርአቱን ዘመኑ በሚጠይቀው ልክ ለማዘመን አቅሜ የፈቀደውን ያህል የተጣለብኝን አደራና ለመወጣት ዝግጁነት የያዝኩ ብቻ መሆኔን ነው የማረጋግጠው በዚህ ሰዓት። ምክንያቱም አሁን ገና ወደ ስራ እየገባሁ ነው። ከዚህ በፊት ይሄ ስራ እንደሚሰጠኝ ባለማወቄ እንዲሁም ይሄ ተልእኮ በመሆኑም ጊዜ ወስጄ ችግሮችን ለይቼ ከአመራሩ እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ ተወያይተን የከተማዋን አጠቃላይ እድገት አንድ ደረጃ ወደፊት የሚያራምድ የአመራር ስርአት ለመዘርጋት ነው በግሌ ለማድረግ ያሰብኩት። ቢቢሲ፡ በተለያየ የስራ ኃላፊነት ከመስራትዎ አንፃር እንዲሁም ከተማዋን ያውቁታል ብዬ ከማሰብም ከዚህ በፊት በነበሩ ሂደቶች ምን ክፍተት አዩ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ከዚህ በፊት የሰራሁባቸው የአመራር ተልእኮዎች በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ውስጥ አይደለም። በምእራብና ምስራቅ ጎጃም የሚባሉ ዞኖች ነው ሳገለግል የቆየሁት፤ በመሃልም የውጭ የትምህርት እድል አግኝቼ ትምህርቴንም ተከታትዬ ነው የተመለስኩት። አሁን ገና ትምህርቴን አጠናቅቄ ከምረቃ በኋላ የተሰጠኝ አዲስ የስራ ስምሪት ነው። በአሁኑ ወቅት ባህርዳር ከተማ ላይ እንዲህ አይነት ጉድለቶች አሉ ብሎ ለመናገር ግምገማ ያላካሄድኩበት በመሆኔ ገና የተሰጠኝን ተልዕኮ ተቀብዬ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅት ላይ ነኝ። ክፍተቶቹን ወይም ጠንካራ ጎኖች እነዚህ ናቸው ብዬ አሁን ባለሁበት ሰዓት ላይ ልናገር አልችልም። ምክንያቱም ገና ያልተገመገመ ነገር ይዤ በዚህ ላይ አስተያየት መስጠት ይከብደኛል። ቢቢሲ፡ የድህረ ምረቃዎን ትምህርት የተከታተሉት በቻይና ነው። የተለያዩ የቻይና ከተሞችን ለማየት እድል አግኝተው ከሆነ ከዛ የቀዱት ነገር አለ ወደዚህ ባመጣው ብለው ያሰቡት? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ቻይና የደረሰችበት የከተማ ልማት እና የኛ አገር ምንም እንኳን ለማወዳደር ልዩነቱ የሰፋ ነው። እዚያ ያየሁዋቸውን አንዳንድ ነገሮች በተለይም የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ላይ፤ የዘመናዊና ቀልጣፋ የአሰራር ስርአት ከመዘርጋት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ የአገልግሎት አቅርቦት ላይ የተሻለ ነገር አይቻለሁ። አቅም በፈቀደ መጠን ከኛ አገር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ስርአት ጋር የተገናዘበ የከተማ ስርአት አገልግሎት አቅርቦት ለማድረግ የዩኒቨርስቲ ምሁራንን እንዲሁም በዘርፉ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን በማማከር አሰራርን ለማዘመን ጥረት ማድረግ የሚገባ መሆኑ ይሰማኛል። እዚህ ላይም አቅሜ የፈቀደውን አስተዋፅኦ ለማድረግ ጥረት አደርጋለሁ ብዬ አስባለሁ። ቢቢሲ፡ ምክትል ከንቲባ ሆነው በትናንትናው ዕለት ተሾመዋል። በስልጣን ላይ ሆኜ እሰራለሁ ብለው ቅድሚያ የሚሰጧቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ በትናንትናው ዕለት ቃለ መሃላ ከፈፀምኩ በኋላ ለምክር ቤቱ ያቀረብኩት የመክፈቻ ንግግር ነበር። ከአመራሩም ሆነ ህብረተሰቡን በማሰለፍ ብንረባረብባቸው አጠቃላይ የከተማይቱን እድገት ያፋጥናል ብዬ የማምንባቸውን አቅጣጫዎች አቅም በፈቀደ መጠን ለማስቀመጥ ሞክሬያለሁ። ከነዚህም መካከልም በተለይ በከተማ የመጀመሪያው ስራ- ኢትዮጵያ በሽግግር ላይ ያለች አገር ናት። ፖለቲካዊ ለውጦች እያካሄደችም ትገኛለች። አሁን ያለው ፓርቲ ከኢህአዴግ ወደ ብልፅግና የተሸጋገረበት፣ አመራሩ ከላይ እስከ ታች በአዲስ እየተደራጀና እየተጠናከረ ያለበት፣ አዳዲስ አስተሳሰቦች ወደ መንግሥት አሰራር የገቡበት ማግስት ላይ ነው ወደ ስራ እየገባሁ ያለሁት። ከዚህ ጋር የተጣጣመ የትኩረት አቅጣጫ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን አስቀምጫለሁ። ከነዚህም መካከል በተለይም የከተማው አስተዳደር ውስጥ የህግ የበላይነትን ማስፈን፣ ሰላምን ማረጋገጥ የመልካም አስተዳደሮችን ለይቶ በህዝቡ ተሳትፎ መፍታት የሚሉት ይገኙበታል። የከተማዋ ያላትን ስመ ገናናነትና የከተማዋ እድገትን ሊመጥን የሚችል የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ስራ ላይ በተለይም የእንጨት ልማት ፕሮጀክቶች ላይ አተኩረን የእለት ተግባራችን አድርገን መንቀሳቀስ ይገባል። የከተማውን የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት ችግር፣ ከዚህም የዘለሉ ሌሎች ተደራራቢ ጥያቄዎችን የህዝብ መድረኮች እየፈጠርን በመልቀም እንደ መንግሥት አቅም መፈታት የሚገባቸውን ቅድሚያ እየሰጠን እንሰራለን የሚሉ አቅጣጫዎች ነው ለማስቀመጥ የተሞከረው። በተለይም የወጣቱን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ የስራ እድል መስኮችን በመፍጠር ላይ ያተኮረ ስራ እንሰራለን። የስራ እድል ፈጠራ ለሰፊው ህዝብ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው ይሄ ከተማ ላይ ያለ የድህነት ቅነሳ አካል ነው። እነኚህ ጉዳዮች መልክ ከያዙ ከተማዋ ወደተሻለ ህይወት ውስጥ የምንገባበት አጋጣሚ ስለሚኖር እነዚህ ላይ አተኩረን ብንሰራ የሚል እሳቤ ይዤ ነው ወደ ስራ እየገባሁ ያለሁት። እንግዲህ ቀጣዩን ከእግዚአብሔር ጋር ከህብረተሰቡ፣ ከቅርብ አመራር ጋር በመሆን የምንችለውን ሁሉ በቅንነት ግልፅ (ትራንስፓረንት) በሆነ መንገድ፣ ህዝቡን አሳታፊ በሆነ መንገድ የከተማ አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎቱ አለኝ። ያው ውጤቱን የምናየው ይሆናል። ቢቢሲ፡ የጠቀሷቸውን ተግባሮች ለማከናወን ምን አይነት ተግዳሮት ይገጥመኛል ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ በባለፉት ሶስት አመታትና ከዚያ በላይ ከአመራር ስርአት ውጭ ብሆንም በተለምዶ የሚታወቁ የከተማ ስራን ለመስራት የሚገዳደሩ ችግሮች አሉ። እኛንም ትንሽ ይፈትነናል ብለን የምናስበው ከተማ የተለያዩ ፍላጎቶች አሉት። ግማሹ ህጋዊ በሆነ መንገድ ከተማ እንዲለማ የመፈለግ፤ ግማሹ ደግሞ በህገወጥ ወይም በአቋራጭ መንገድ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተቃራኒ ፍላጎቶች የሚሳተፉበት መድረክ ነው። ፖለቲካዊ ፍላጎቱ ብዙና የተለያዬ የሆነበትና ሌሎች እንዲሁም ውስብስብ ችግሮች ያሉበት ነው- የከተማ ስራ። ስለዚህ እነዚህን ችግሮች አጣጥሞ ለመምራት የሚያስችል ብቁና ቅቡልነት ያለው በስነ ምግባር የታነፀ አመራር የመፍጠር፣ የማሰማራትና ከህብረተሰቡ ጋር አዋህዶ የማሰራት ሂደት ፈታኝ ሊሆን ይችላል። እዚህ ላይ እኛም አተኩረን እንረባረባለን። ነገር ግን የሰው ልጅ ፍላጎት የተወሰነ ባለመሆኑ ህጋዊ ስርአት ተከትሎ በሚሰራበት ጊዜ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ሊነኩ ይችላሉ። በዚያን ጊዜ ማማረር ሊከሰት ይችላል።እኛ እነዚህን አስቀድመን ስለምናውቅ በተቻለ መጠን ከአመራሩ ጋር ተነጋግረን የሁሉንም ዜጎች ፍላጎት አጣጥሞ ከህግና ስርአት ውጭ ሳይሆን ከተማዋን በከተማ እቅድ (ፕላን) ማስተዳደር። በዚያም መሰረት እንድትመራ የማድረግ ስራ እንሰራለን። እንግዲህ እዚህ ላይ ህብረተሰቡም ያግዘናል ብዬ ተስፋ የማደርገው ህጋዊነትን ብቻ ተከትለን ስንሰራ ከጎናችን የሚሆን ከሆነ ለውጥ እናመጣለን። ነገር ግን በመሃል አንዳንድ መንጠባጠቦች፤ ከዚህ ባፈነገጠ መንገድ መጠቀም የሚፈልጉ ኃይሎች ትንሽ ያስቸግሩን ይሆናል፤ በውይይት እየፈታን እንሄዳለን። እንሻገራለዋን የሚል ተስፋ እንዲሁም እምነት አለኝ። በመወያየት የማይፈታ ችግር የለም ተብሎ ስለሚታሰብ ዋናው ነገር አመራሩንም ህዝቡንም ያሳተፈ የአመራር ዘይቤን መከተል፤ እነዚህን ተግዳሮቶች እናልፋቸዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ከዚህ በዘለለ በስራ ሂደት የሚፈጠሩ ችግሮች ይኖራሉ እንደዬ አፈጣጠራቸውና እንደ አመጣጣቸው እንመልሳለን ብዬ አስባለሁ። ቢቢሲ፡ባህርዳር ከተማን የተለያየ ከንቲባዎች መርተዋታል፤ ባለን መረጃ ቶሎ ቶሎ የመቃየየር ሁኔታም አለ። ከዚህ ቀደም የነበሩት ከንቲባ በውበት፣ በፅዳት ጋር ተያይዞም ይወደሳሉ። እርስዎስ በየትኛው በኩል እወደሳለሁ ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ከዚህ በፊት የነበሩ ከንቲባዎች ባህርዳር ዛሬ ለደረሰችበት የእድገት ደረጃ የየበኩላቸውን አሻራ ጥለው አልፈዋል። በርካታ ጥሩ ጥሩ የሚባሉ ከተማዋን ወደፊት ያራመዱ ተግባራትን ፈፅመዋል። ይሄም የሚያስመሰግናቸው ነው። በዚያኑ ልክ ግን የሰው ልጅ ወደ ስራ በሚሰማራበት ወቅት ጥንካሬዎች እንዳሉ ድክመቶችም ሊኖሩ ይችላሉ። እኛ መከተል የምንፈልገው እነሱ ሰርተውት በሄዱት ላይ ተጨማሪ ስራ እየሰራን ጥሩውን እያስቀጠልን ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ መቀጠል። ድክመት ነበሩ ተብለው የሚታሰቡ ጉዳዮች ላይ ደግሞ ደግመው እንዳይፈፀሙ እያስተካከልን ነው ለመሄድ ያሰብነው። በቅርብ ከለቀቁት ከንቲባ ጋር ተያይዞ በርካታ ተስፋ ሰጭ ብዙ ደስ ደስ የሚሉ ስራዎችን ጀምረው የሄዱ መስሎ ነው የሚሰማኝ። እርሳቸው የጀመሯቸውን በጎ ተግባራት አጠናክረን እንቀጥላለን። ከዚህ ውጭ ደግሞ ክፍተት በምንላቸው ነገሮችን እንሞላለን። እሱ በምን ይሳካልዎታል ለሚለው? እሱን በቀጣይ በተግባር ብናየው ይሻላል። ምክንያቱም አሁን ወደ ስራ ባልተገባበት ሰዓት ላይ በዚህ ስራ የተሳካልኝ እሆናለሁ ማለት የአካባቢውን ሁኔታ በደንብ ሳላይ፣ ገምግሜ ክፍተቱን በጥሩ ሁኔታ ለይቼ ባልገባሁበት ወቅት ላይ ይሄ ውጤታማ ያደርገኛል፣ አያደርገኝም ብሎ ለመናገር የሚያስቸግረኝ ይመስለኛል። ቢቢሲ፦ ሹመቱ ያልጠበቁት ይመስላል። በርግጥ እሾማለሁ ብለው ላያስቡ ይችላሉ። ለዚህ ሹመት የሚታጩ ሰዎች አካባቢውን በደንብ የሚረዳ ፣ ከተማውን በደንብ የሚያውቅ፣ ክፍተት ሊሞላ የሚችል፣ ጎዶሎውን ሊያውቅ ይችላል ተብሎ የሚታሰብ ሰው ነው ብዬ አስባለሁ…. ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ልክ ነው፤ ሹመት በሚሰጥበት ጊዜ በበለጠ አካባቢውን የሚያውቅ ሰው ቢሆን ይመረጣል። አካባቢውን በማወቅ ብዙ ችግር ያለብኝ አይመስለኝም። ከዚህ በፊት ባህርዳር ላይ የተወሰነ ጊዜ ሰርቻለሁ። ባህርዳር ዩኒቨርስቲ እንዲሁም አሁን ካለው አመራር ጋር በመቀናጀት በአመራርነት ብዙ ጊዜ ስላሳለፍኩኝ መረጃዎቹም አሉኝ። እውነት ለመናገር እሾማለሁ ብዬ አልጠበቅኩም። እኔ ትምህርቴን ጨርሸ ስመጣ፤ በድርጅታችን አሰራር መሰረት የፖለቲካ ሹመት የሚሰጠው ተነግሮ አይደለም። የትምህርት እድል ተሰጥቶኝ ተምሬ ስመጣ አመራር ቦታ ላይ እንደምመደብ አውቃለሁ፤ የትኛው ቦታ እንደሆነ የሚወስነው የፓርቲው ፅህፈት ቤት ነው። አንድ ሰው ካለው የትምህርት ዝግጅት፣ የስራ ባህርይና ሌሎችም ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ገብተው ነው ሹመት የሚሰጠው። እንግዲህ ፓርቲው በዚህ ቦታ ላይ ሲመድበኝ ለዚህ ስራ ይመጥናል የሚል እምነት ይዟል ማለት ነው። እኔ ግን እንደ አንድ አመራርና አባል የተሰጠኝን ተልእኮ ስፈፅም ቆይቼ፣ ትምህርቴን አጠናቅቄ መምጣቴንና ሌላ ተጨማሪ ተልዕኮ ፓርቲዬ እንዲሰጠኝ እየጠበቅኩ ስለነበር የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ሆኜ እሾማለሁ ብዬ አልጠበቅኩም። ይሄ ተልእኮ ሲሰጠኝ ግን ህዝቡን ከማገልገል በላይ ሌላ ክብር ስለሌለ ፤ ህዝብን ማገልገል ኩራት ስለሆነ፤ ከዚህም በላይ ኃላፊነት ስለሌለ ከታመነብኝና ይህንን ስራ ይሰራል ብሎ ሹመቱን የሰጠኝ አካል አለ። ምክር ቤቱም ይህንን የቤት ሰራ ወስዶ ተቀብሎ ካፀደቀው በኔ በኩል ባገለግል ምንም ችግር የለውም። የተማርኩትም ህዝቡን ለማገልገል ነው። ቢቢሲ፡ ነፃ ሆኜ እስራለሁ፤ ነፃ ሆኜ ያሰብኳቸውን ነገሮች አሳካለሁ ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ፈተናዎች ይኖራሉ። ይሄ ግልፅ ነገር ነው። ከተማ ላይ ብዙ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች አሉ። ያንን ሁሉ ፍላጎት ለሟሟላት ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ጠንቅቄ አውቃለሁ። ነገር ግን አቅም በፈቀደ መጠን ህሊናዬ የሚገፋኝን ለመስራት ዝግጁ ነኝ። ከዚህ በፊትም የአመራር ህይወቴ ልምዱም ስላለኝ የምችለውን ሁሉ ለመስራት እሞክራለሁ። የፓርቲ አመራሮችም ድጋፍ እንደሚያደርጉልኝም ሙሉ ቃል ገብተውልኛል። በተቻለ መጠን ህሊናዬ የሚያምንበትን ነገር ለመስራት እንቅስቃሴ አደርጋለሁ፤ እታገላለሁ። ከአቅም በላይ ሲሆን ደግሞ ብዙ አማራጮች አሉ ማለት ነው። ግን እኔ ከአቅም በላይ የሚሆን ነገር ይገጥመኛል ብዬ አላስብም። በአሁኑ ሰዓት ፓርቲውም ሆነ መንግሥት የሚፈልገው የህብረተሰቡን ፍላጎት ማሟላት ነው። የህብረተሰቡን ፍላጎት ተረድተን በምንቀሳቀስበት ወቅት የሚመጣውን እንቅፋት የሚታገል በርካታ ኃይል ከጎን አለ።ይህንን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የምሞክረው ይሆናል ማለት ነው። ቢቢሲ፡ ነፃ ሆነው እንዳይሰሩ ችግር ሊገጥምዎት ይችላል በስራ አጋጣሚ የሚገጥም ነው። እነዚህ ችግሮች ከየት በኩል ይመጣል ብለው ያስባሉ? ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፡ ወደ ስራ ሳይገባ እንደዚህ አይነት ትንበያዎች (ፕሪዲክሽን) መስጠት ያሳስታል (ሚስሊድ ያደርጋል)። ምክንያቱም እኔ ዛሬ ተንብዬ ከዚህ አካባቢ ችግር ይመጣብኛል ብዬ ብናገር፤ ይመጣብኛል ብለሽ የምታስቢውን አካባቢ ማሳሰብም ስለሚሆን ወደ ስራ ገብቶ በተግባር ላይ የሚገጥም ችግርን ፊት ለፊት መጋፈጥ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ይመስለኛል። ችግር የሌለው ስራ የለም። ህዝብን መምራት ትልቅ ከባድ እና አስቸጋሪ ነው። እያንዳንዱ አመራር ይህንን አውቆ ነው የሚገባው ። ምንጊዜም ወደ ስራ ስንገባ ችግሮች እንደሚኖሩ አውቃለሁ። እንደየአመጣጣቸው ለመመለስ ራሴን አዘጋጅቻለሁ።
https://www.bbc.com/amharic/news-54575536
amh
politics
በሄይቲ ፕሬዝደንት ግድያ 'ዋነኛው' የተባለ ተጠርጣሪ ተያዘ
ባለፈው ሳምንት በፕሬዝደንት ጆቨኔል ሞይዝ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በማቀናጀት ቁልፍ ተጠርጣሪ ነው ብሎ ያመነውን ዶክተር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሄይቲ ፖሊስ ገለጸ። የ63 ዓመቱ የሄይቲ ተወላጅ ክርስቲያን ኢማኑኤል ሳኖን ሰኔ መጀመሪያ ላይ "በፖለቲካዊ ዓላማዎች" ምክንያት በግል አውሮፕላን ወደ ሄይቲ መብረሩን ይናገራሉ። የ53 ዓመቱ ሞይዝ ሐምሌ 7 መኖሪያ ቤታቸው በ 28 የውጭ ቅጥረኞች መገደላቸውን ፖሊስ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር። ቀዳሚ እመቤቷ በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለህክምና ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። ማርቲን ሞይዝ ነፍሰ ገዳዮች እኩለ ሌሊት ወደ ቤታቸው ከገቡ በኋላ ባለቤታቸውን በጥይት "የመቱበትን" ቅጽበት ገልጸዋል። ጥቃቱ በፍጥነት በመከናወኑ ባለቤታቸው ጆቨኔል "አንዲትም ቃል ለመናገር" አልቻሉም ብለዋል። የተልዕኮ ለውጥ ሳኖን መያዙ የተዘገበው እሁድ አመሻሽ ላይ በዋና ከተማው ፖርቶ ፕሪንስ በፖሊስ በሰጠው መግለጫ ነው። የሄይቲ የፖሊስ አዛዥ ሊዮን ቻርለስ "ይህ ለፖለቲካ ዓላማ በግል አውሮፕላን ሄይቲ የገባ ግለሰብ ነው" ብለዋል። የመጀመሪያ ዕቅዱ ፕሬዝዳንት ሞይዝን በቁጥጥር ስር ለማዋል ቢሆንም "ተልዕኮው በኋላ ላይ ተቀይሯል" ብለዋል። ስለጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ግን አልሰጡም። "ወንጀሉ ከተፈጸመ በኋላ እኛ ፖሊሶች የእነዚህን ሽፍቶች እንቅስቃሴ በገታንበት ጊዜ ከጥቃት አድራሾቹ አንዱ ለክርስቲያን አማኑኤል ሳኖን ነው የደወለው" ብለዋል ቻርለስ። "የፕሬዚዳንት ጆቨኔል ሞይዝ የግድያ አቀናባሪዎች ናቸው የምንላቸውን ሌሎች ሁለት ሰዎችም አነጋግሯል።" የፖሊስ አዛዡ ሌሎች ሁለት ሰዎች እንማን እንደሆኑ አልተናገሩም። የአሜሪካ ድጋፍ የሃገሪቱን የጸጥታ ሁኔታ ለመገምገም እሑድ ዕለት የአሜሪካ ከፍተኛ የደህንነት እና የፍትህ ባለስልጣናት ልዑክ ሄይቲ ገብቷል። ቡድኑ ሦስት የሄይቲ ፖለቲከኞችንም አግኝቶ ያነጋግራል። ሦስቱም የአገሪቱ ህጋዊ መሪ ነን እያሉ ነው። ከጥቃቱ በኋላ የሄይቲ ባለሥልጣናት ቁልፍ የመሠረተ ልማት አውታሮችን ለመጠበቅ አሜሪካ እና የተባበሩት መንግስታት ወታደሮችን እንዲልኩ ጠይቀዋል። የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ጥያቄውን በመጀመሪያ ውድቅ ቢያደርገውም አሁን ግን ሁኔታውን በጥልቀት ለመመርመር ወስኗል። ጆቨኔል ሞይዝ እአአ ከ2017 ጀምሮ በአሜሪካ በጣም ድሃ የሆነችውን ሄይቲን ሲመሩ ቆይተዋል። በስልጣን ዘመናቸውም በሙስና ክስ ሲመሰረትባቸው ቆይቶ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይም በዋና ከተማው እና በሌሎች ከተሞች ሰፊ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። የፓርላማ ምርጫ ጥቅምት 2019 መካሄድ የነበረበት ቢሆንም አለመግባባቶች ተከስተው ምርጫ ሳይካሄድ ቆይተዋል። በዚህም ጆቨኔል ሞይዝ በአዋጅ ሃገሪቱን እያስተዳደሩ ነበር ማለት ነው። በቀረቡ የሕገ-መንግስት ለውጦች በመጪው መስከረም ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ታቅዶ ነበር። ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን ጥቃት ማን እና ለምን ዓላማ እንደደረሰ አሁንም ድረስ ግልፅ አይደለም። ገዳዮች ናቸው የተባሉት እንዴት ወደ ግቢው ለመግባት ቻሉ የሚለውን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎች እስካሁን አልተመለሱም። ሄይቲን ማን እየመራት ነው? ህገ-መንግስቱ ብሔራዊው ምክር ቤት ሌላ ፕሬዝዳንት መምረጥ አለበት ይላል። 2019 ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ምርጫ ባለመካሄዱ ጆቨኔል ሞይዝ በአዋጅ እየመሩ ነበር። ሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ባይኖረውም በሕገ-መንግስቱ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦታውን መረከብ እንዳለባቸው ይጠቁማል። ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር ክላውድ ጆሴፍ እና አዲሱ ተሿሚው ኤሪየል ሄነሪ ስልጣኑ ይገባናል እያሉ ነው። አርብ ዕለት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቡድን ሄንሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲያገለግሉ እና አዲሱን ፕሬዝደንት ደግሞ ጆሴፍ ላምበርት እንዲሆኑ በማወጅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተፈራርመዋል። የመፍትሔ ሃሳቡ አገሪቱ ለረጅም ጊዜ ሲያምሳት የኖረውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ለመፍታት እምብዛም እየሠራ አይደለም።
https://www.bbc.com/amharic/57802063
amh
politics
አዲስ የተመሰረተው የተቃዋሚዎች ጥምረት እና የመንግሥት አስተያየት
የኢትዮጵያ ፌደራሊስት እና ኮንፌደራሊስት ኃይሎች ጥምረት በሚል በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ለመተካት በሚል ዘጠኝ የፖለቲካ ቡድኖች ዋሽንግተን አንድ ጥምረት መመስረታቸውን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ፣ ጥምረቱ ይህ ነው የሚባል የፖለቲካ መሰረት የሌለው ደካማ ስብስብ ነው ሲል አጣጥለውታል። በጥምረቱ ውስጥ ትብብር ለመፈጠር ከፈረሙት መካከል ህወሓት፣ የኦሮሞ ነጻነት ጦር፣ የሲዳማ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፣ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ይገኙበታል። ይህም ጥምረት በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት የመመሥረት ዓላማ እንዳለው የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቃል አቀባይ ኦዳ ታርቢ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ይህ አዲስ የተመሰረተው ጥምረት በትናንትናው ዕለት በዋሺንግተን የፊርማ ስነስርዓት ሲያካሂድ፣ የሕወሓት አማፂያንን በመወከል የተገኙት አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትን በኃይል አልያም በድርድር በማስወገድ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል። የአዲሱን ስብስብ መመስረት ያጣጣለው የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ፣ ከበደ ዴሲሳ፣ ከቢቢሲ ኒውስ አወር ጋር በነበራቸው ቆይታ "ደካማ የፖለቲካ ኃይል ነው" በማለት ገልጸውታል። በተጨማሪም ሚኒስትር ዲኤታው በዚህ ጥምረት መመስረት "አለመደነቃቸውን" አመልከተዋል፤ ጥምረቱ በአገሪቱ ውስጥ ይህ ነው የሚባል ድጋፍ የሌለው ነው ብለዋል። "እነዚህ አማጺያን ቡድኖች መሠረት የላቸውም። ምንም አይነት ማኅበራዊ መሠረት የላቸውም፤ ምንም ለውጥ ሳያመጡ ላለፉት 40 ዓመታት እዚያው የቆዩ ናቸው።" አቶ ከበደ ዴሲሳ ጨምረውም "በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት በሚያስፈልግበት ጊዜ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች መንግሥት ተዳክሟል፣ ሥልጣን ላይ መቆየት አይችልም ብለው ሲያስቡ ተሰባስበው ትብብር ይፈጥራሉ" በማለት ሁኔታው የተለመደ መሆኑንም ተናግረዋል። የጥምረቱ አባላት ይህንን ስብስብ የፈጠሩት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት እየተባባሰ ባለበት ወቅት ሲሆን፤ ወደፊት በአገሪቱ ይመጣል ብለው ለሚያስቡት የሽግግር መንግሥት እና ጊዜያዊ መንግሥት የመጀመሪያ ሂደት ነው ብለዋል። ይህ ጥምረት በውስጡ ዘጠኝ ቡድኖችን ያካተተ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ጋምቤላ፣ ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሊ፣ ትግራይ፣ ኦሮሞ፣ ቅማንት፣ አገውን የፖለቲካ ቡድኖች ይወክላል ተብሏል። ስብስቡ እነዚህን ቡድኖች ብቻ በመያዝ የሚቀጥል አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን ሌሎችም ቡድኖች እንደሚቀላቀሏቸውና ውይይትም እያደረጉ መሆናቸውን አመልክተዋል። ጥምረቱ ፌደራሊስት እና ኮንፌደራሊስ የሆኑ ኃይሎች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አሁን ያለውን የአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሰረት ባደረገው የፌደራሊዝም ሥርዓት ለመቀጠል መስማማታቸው ተነግሯል። "በረዥም ጊዜ ሂደትም ሁላችንም የምናስበው ኮንፌደራሊስት ወደሆነ ሥርዓት መሻገር ነው። እዚያ ላይ ተስማምተናል" ብለዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አንድ ዓመት በቆየ ጦርነት ውስጥ የሚገኘው ህወሓት፣ ከዚህ በፊት ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር በትብብር ለመንቀሳቀስ ከስምምነት መድረሳቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። ህወሓት እና ጦር መንግሥት ሸኔ የሚለው የኦሮሞ ነጻነት ጦር ባለፈው ዓመት ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ቡድኖች ተብለው መፈረጃቸው ይታወሳል። አሁን ጥምረት እንደፈጠሩ ያስታወቁት ቡድኖቹ በቀጣይ ስለሚያከናውኑት እንቅስቃሴ በዝርዝር ያሉት ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-59166791
amh
politics
“ታይዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድትገለል ቻይና ስትሞክር ቆይታለች” ታይዋን
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በአገራቸው ያደረጉትን አወዛጋቢ ጉዞ ትክክል ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የናንሲ ፔሎሲን ጉብኝት ተከትሎም ቻይና በታይዋን ደሴት ዙሪያ የምታደርገውን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ልምምድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆሴፍ ው አውግዘዋል። ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ያደረጉት ጉብኝት “በጣም ጠቃሚ ነው” እና ቻይና እያደረገቸው ባለው “የጠብ አጫሪነት” ምላሽ ዲሞክራቶችን ወደ ታይዋን ከመጋበዝ አያስቆማቸውም ብለዋል። የቻይና ግዛት የማስፋፋት ከታይዋን በላይ እንደሚሄድም አስጠንቅቀዋል። ላለፉት ስድስት አመታት የታይዋኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ ው አገሪቷ ለበለጠ አለም አቀፍ እውቅና የምታደርገው ዘመቻን ሲመሩ ነበር። የአሜሪካን የአፈ ጉባኤ ጉብኝትንም ተደራድረው ሲሆን ያመጡት በአሁኑ ወቅት ቻይና የምታደርገውን ወታደራዊ ምላሽ አስፈሪ ሁኔታም መጋፈጥ አለባቸው። ሆኖም የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቅርታ የመጠየቅ እቅድ የላቸውም። የአፈ ጉባኤዋ ጉብኝት በርካቶች የረሷት እናም ብዙም መረዳት ያላገኘችውን የታይዋን ደሴት ትኩረት እንድታገኝ ማድረግ ላይ ነው። ቻይና ታይዋንን እንደ ተገንጣይ ግዛቷ ነው የምታያት ውሎ አድሮም እንደገና በቁጥጥሬ ስር ትሆናለችም በሚልም ነው የምታስባት። ታይዋን በበኩሏ ራሷን እንደ ነጻ ሃገር ነው የምትመለከተው። የአለም መሪዎች ለታይዋን እውቅና መስጠታቸው ቻይናን ያስቆጣታል በቅርቡ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲና ቤተሰባቸው ላይ ማዕቀብ መጣሉም በዛሬው ዕለት ታውቋል። “ታይዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድትገለል ቻይና ስትሞክር ቆይታለች። “ ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ "የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ፔሎሲ ያለ ከፍተኛ መሪ ታይዋንን መጎብኘታቸው ትልቅ ጠቀሜታ አለው። የታይዋንን ገፅታ ከፍ ለማድረግ እንዲሁም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ታይዋን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የምትመራ መሆኗን እንዲረዳ እድል ይፈጥራል” ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የተፈጠረውን ቀውስ የቀሰቀሰችው ታይዋን ሳትሆን እውነታዎችን ለመቀየር እየሞከረች ያለችው ቻይና ናት ሲሉ ወቀሳቸውን አቅርበዋል። “ታይዋን ነጻ ሃገር ናት። ታይዋን በቻይና ላይ ስልጣን እንደሌላት ሁሉ ቻይናም በታይዋን ላይ ምንም አይነት ስልጣን የላትም። እውነታው ይህ ነው” ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cjqxdk2y39wo
amh
politics
"የአማራ ብቻ ሳይሆን የጋምቤላ፣ የሲዳማና ደቡብ ክልል ልዩ ኃይሎች ቤንሻንጉል ጉሙዝ ገብተዋል"
ከሰሞኑ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ቡለን ወረዳ መግባቱን የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል። ከአማራ ክልል በተጨማሪ የጋምቤላ፣ የሲዳማ እንዲሁም የደቡብ ክልል ልዩ ኃይሎች ወደ አካባቢው መግባታቸውን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ የሰላም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ ለቢቢሲ ገልፀዋል። እነዚህ ኃይሎች በክልሉ በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ስር ሆነው የሰላም ማስከበር ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን አቶ አብዮት ተናግረዋል። በተለይም የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደ ክልሉ ከመግባቱ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችን አስመልክተው የጸጥታ ኃላፊው "ከአማራ ክልል ጋር ሰፊ አስተዳደራዊ ወሰን እንጋራለን፣ የተለያዩ ሥራዎችን በጋራ እናከናውናለን። በተጨማሪም ወንድማማች ሕዝቦች ነን። ስለዚህ በሰላምም ሆነ በልማት ሥራዎች ላይ በመቀናጀት እንሰራለን" በማለት አስረድተዋል። በየትኛውም ክልል ያለ የልዩ ኃይል በኮማንድ ፖስቱ ስር ሆኖ ሊሳተፍ እንደሚችል የሚገልጹት አቶ አብዮት ይህ የሆነውም አካባቢው የሕዳሴው ግድብ መገኛ በመሆኑም ነው ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኃላፊው እንደ ምክንያት የሚያነሱት "ህወሓት በሱዳን በኩል ሰርጎ እየገባ በዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽመበት ብሎም የሕዳሴ ግድቡን ለማጥቃት የሚሞክርበት አካባቢ በመሆኑ የሁላችንንም ትብብር የሚፈልግ አካባቢ ነው" ነው ሲሉ ተናግረዋል። የመተከል ዞን በኮማንድ ፖስት የሚመራ እንደመሆኑ የኃይል ስምሪት በሚያስፈልግበት ጊዜ ከክልሉ ጸጥታ ኃይል ጋር ተቀናጅቶ እንዳይሰራ የሚከለክል ነገር እንደሌለ አመልክተዋል። በተለያዩ ጊዜያት በመተከል ዞን ውስጥ በታጣቂዎች በሚፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ነዋሪዎች የተገደሉ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል። በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ለመቆጣጠር ከአንድ ዓመት በፊት በክልሉና በፌደራል የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት የዕዝ ማዕከል (ኮማንድ ፖስት) ተቋቁሞ እየሰራ ቢሆንም አሁን ድረስ ጥቃቱ እንደቀጠለ ነው። በቅርቡም ከሱዳን በኩል ወደ ክልሉ ሰርገው በመግባት ጥቃት ሊፈጽሙ ነበር የተባሉ ታጣቂዎች በአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት እርምጃ እንደተወሰደባቸው መዘገቡ ይታወሳል። በክልሉ ውስጥ መረጋጋት ለማምጣት ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ የልዩ ኃይል አባላት መሰማራታቸውን የገለጹት ኃላፊው ጉዳዩ ከጸጥታ ጋር ስለሚያያዝ የሠራዊቱን ቁጥርና እንቅስቃሴ መግለጽ እንደማይችሉ አስረድተዋል። ከሰሞኑ የክልሉ መንግስት እና የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ከአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከክልሎች የልዩ ኃይል አባላት፣ ከሚሊሺያ አባላትና ከግል ታጣቂዎች ጋር በመሆን "የጥፋት ቡድን" ብለው በጠሩት ታጣቂ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ክልሉ አስታውቋል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ታጣቂ የነበረው ኃይል ጋር ሰላማዊ ድርድር ለመፍጠር ቢሞከርም በአሁኑ ወቅት የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱት ጭምር ወደ ጫካ መግባታቸውን ከሰሞኑ በክልሉ መንግሥት ተገልጿል። "ምንም እንኳን ቡድኑ በፈጠረው የጸጥታ ችግርና ጥቃት በሰው ህይወት፣ በአካል በንብረት ከፍተኛ ጉዳት ቢያደርስም የክልሉ መንግሥት ችግሩን በሰላማዊ መንገድና በውይይት ለመፍታት ከፍተኛ የሆነ የበጀት፣ የጊዜ፣ የሰው ኃይል በመመደብ ለወራት የዘለቀ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል" በማለት ክልሉ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የክልሉ መንግሥት በመተከልና ካማሺ ዞኖች ከሚንቀሳቀሰው የታጣቂ ቡድኑ አባላት መካከል የተወሰኑት የቀረበውን ሰላማዊ ድርድር በመቀበላቸው የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ክልሉ አመልክቷል። የክልሉ መንግሥት ታጣቂውን ቡድን "ጸረ- ሰላም ኃይልና የህወሓት ተላላኪ" በሚል ከመጥራት ውጪ በስም አልጠቀሰውም። ከዚህ ቀደም የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥትና ታጣቂው በጉሙዝ ሕዝብ ዴሞከራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) ቡድን በክልሉ በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58557737
amh
politics
የፈረንሳዩ ማክሮን የሩሲያና ዩክሬንን ፍጥጫ ለማርገብ እየጣሩ ነው
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መጪዎቹ ቀናት እጅግ ወሳኝ ናቸው አሉ፡፡ ማክሮን ይህን ያሉት ትናንት ሰኞ ከሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለሰዓታት የቆየ ንግግር ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ ማክሮን ከፑቲን ጋር ያደረጉት ውይይት ፍሬ እንደሚያፈራ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ምዕራብ አገራት ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር ዝግጅቷን ጨርሳለች በሚል በአካባቢው ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል መናገር ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ አንዳንድ ከአሜሪካ ምድር የሚወጡ መረጃዎች ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር ከሚያስችላት ወታደራዊ አቅም 70 ከመቶውን ወደ ድንበር ማስጠጋቷን እየገለጡ ነው፡፡ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ሩሲያ መቶ ሺህ የታጠቁ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር አስጠግታ ማስፈሯን ተናግረዋል፡፡ ሩሲያ ግን ምንም ዓይነት የወረራ ፍላጎት የለኝም ብላለች፡፡ ሰኞ ዕለት የአሜሪካኑ ጆ ባይደን ከጀርመኑ መራሒ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ጋር በዋሺንግተን ተገናኝተው በሩሲያ ጉዳይ ላይ በዝግ መክረዋል፡፡ ጆ ባይደን ለሩሲያ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ የሰጡ ሲኾን እንደተፈራው ፑቲን ዩክሬንን በወረራ ለመያዝ ከሞከሩ ሩሲያ ወደ ጀርመን የዘረጋችውን የጋዝ መስመር እንደሚዘጉ ዝተዋል፡፡ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በበኩላቸው ፑቲን አይተውና ሰምተው የማያውቁት ዓይነት ማዕቀብ ሊጣልባቸው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ ቦሪስ ጆንሰን ለዘታይምስ ጋዜጣ በጻፉት መጣጥፍ እንዳሉት በዩክሬን ላይ ወረራ ከተፈጸመ አገራቸው ዩኬ የሮያል አየር ኃይልን ብቻም ሳይኾን የባሕር ኃይሏንም ጭምር በአካባቢው እንደምታሰማራ አረጋግጠዋል፡፡ ዩኬን ጨምሮ ምዕራብ አገራት ዩክሬንን ከወረራ ለማዳን ያላቸውን አቅም ሁሉ እያስተባበሩ ይገኛሉ፡፡ ሩሲያ በበኩሏ እንዲያ ያለ ሐሳብ እንደሌላት ብትጎተጉትም ቁልፍ የደኅንነት ስጋቶቿ እንዲቀረፉላት ግን ትሻለች፡፡ ከነዚህ መካከል ዋንኞቹ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) ወደ ምሥራቅ አውሮጳ የሚያደርገውን መስፋፋት እንዲያቆም፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ዩክሬንን በአባልነት የማካተት ሐሳቡን እርግፍ አድርጎ እንዲተው የሚሉ ናቸው፡፡ ትናንት ወደ ሞስኮ ያቀኑት የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን ከፑቲን ጋር ለአምስት ሰዓታት ያህል የእራት ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ቆይታቸው ተስፋ ሰጪ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ ማክሮን ከፑቲን ጋር በነበራቸው ዘለግ ያለ የእራት ሰዓት ውይይት የአጋዘን ሥጋ፣ ስኳር ድንችና ብላክቤሪ ጭምር እንደተቋደሱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ ፑቲን በበኩላቸው ከእራት ግብዣው በኋላ በሰጡት አጭር አስተያየት የማክሮን ነጥቦች ሊዳብሩ የሚችሉና ተስፋ ሰጪ ናቸው ብለዋል፡፡ ኾኖም ዝርዝር ጉዳዮችን ለመናገር ጊዜው ገና ነው ሲሉ አስተያየታቸውን በአጭር ቋጭተዋል፡፡ ማክሮንና ፑቲን የሁለትዮሽ ውይይታቸውን ነገ የሚቀጥሉ ሲሆን ይህም የሚሆነው ማክሮን ወደ ኪያቭ አቅንተው የዩክሬኑን አቻቸውን አነጋግረው ሲመለሱ ነው፡፡ ሩሲያ ከምታነሳቸው የደኅንነት ስጋቶች አንዱና ዋንኛው ዩክሬን ኔቶን ከተቀላቀለች ክሬሚያን ለማስመለስ ታልማለች የሚል ነው፡፡ ሩሲያ የክሬሚያን ባሕረ ገብ ግዛት በወረራ የወሰደችው የዛሬ ስምንት ዓመት ግድም ነበር፡፡ ፑቲን ከሁለትዮሹ ንግግር በኋላ በአቅራቢያቸው ለተሰበሰቡ የፈንሳይ ጋዜጠኞች፣ ‹ፈረንሳይ ከሩሲያ ጋር እንድትዋጋ ትሻላችሁን?› ሲሉ ድንገቴ ጥያቄ የሰነዘሩላቸው ሲሆን፣ ‹ጦርነት ከተጀመረ ማንም አሸናፊ አይሆንም› ሲሉ ያልተጠበቀ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ይህ በአንዲህ ሳለ አዲሱ የጀርመን መራሒ መንግሥት ሾልዝ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ዋሺንግተን አቅንተው ከባይደን ጋር በሩሲያ ጉዳይ መክረዋል፡፡ ሩሲያ ዪክሬንን ከወረረች ፍጹም የማትቋቋመው ብቻ ሳይሆን አከርካሪዋን የሚሰብር ማዕቀብ ይጠብቃታል ሲሉም ዝተዋል፡፡ ባይደን በበኩላቸው ፑቲን ወረራ ከፈጸሙ ኖርድ ስትሪም2 ተብሎ የሚጠራውንና ወደ ጀርመን የተዘረጋውን የጋዝ መስመር እንደሚያቆሙት ዝተዋል፡፡ የዚህ መስመር መዘጋት ሩሲያን እንደሚጎዳት ሁሉ አውሮጳዊያኑንም በኃይል አቅርቦት በእጅጉ ይጎዳል ይላሉ ተንታኞች፡፡ ጆ ባይደን ይህን እንዴት ያሳካሉ ተብለው ሲጠየቁ በቀጥታ ለመመለስ ባይችሉም ለጋዜጠኞች፣ ‹እመኑኝ እናደርገዋለን› ሲሉ በድፍኑ ዝተዋል፡፡ ከ1ሺህ 225 ኪሎ ሜትር በላይ የተዘረጋው የኖርድ ስትሪም2 የጋዝ መስመር ከሞስኮ ወደ ጀርመን የሚደርስ ነው፡፡ መስመሩን ለመዘርጋት ድፍን 5 ዓመት የወሰደ ሲሆን 11 ቢሊዮን ዶላር ወጥቶበታል፡፡ ሆኖም እስከዛሬ ሥራ አልጀመረም፡፡ እንደተፈራው በሩሲያና በዩክሬን መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮጳ ምድር የሚደረግ ሰፊ ጦርነት ሊሆን ይችላል ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-60278395
amh
politics
ጄኔራል ባጫ እና ኢንጂነር ስለሺን ጨምሮ ለ27 ግለሰቦች የአምባሳደርነት ሹመት ተሰጠ
ጄኔራል ባጫ ደበሌ፣ ጄኔራል ሃሰን ኢብራሂምና፣ ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ለ27 አምባሳደሮች ሹመት መሰጠቱን የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የአምባሳደርነት ሹመት የሰጡት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት ጥር 18/2014 ዓ.ም መሆኑም ተገልጿል። ከፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ጽህፈት ቤት የወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው ፕሬዚዳንቷ የሰጡት ሹመት ለ16 ግለሰቦች የባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እንዲሁም ለሌሎች 11 ግለሰቦች ደግሞ የአምባሳደርነት ሹመቶች ናቸው። በሙሉ አምባሳደርነት ከተሾሙት ውስጥ በትግራይ የተካሄደውን ጦርነት ጋር ተያይዞ ስማቸው የሚነሳው የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ጦር ጄኔሎቹ ጄኔራል ባጫ ደበሌ እና ጄኔራል ሃሰን ኢብራሂም ተካትተውበታል። ጄኔራል ባጫ ደበሌ ወደ ጦሩ እንደገና እንዲካተቱ የተደረጉት የትግራይ ጦርነት በተቀሰቀበት ዕለት ነበር። በቅርቡም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቅራቢነት በአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የጄነራል ማዕረግ ከተሰጣቸው ወታደራዊ መኮንኖች መካከል አንዱ የነበሩትና በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ የሆኑት ጄነራል ባጫ ደበሌ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙ ሲሆን የሚላኩበት አገር እስካሁን አልተገለጸም። እንዲሁም የቀድሞው የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የሕዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሆነው እያገለገሉ ያሉት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለም ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነዋል። በተጨማሪም በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ በአጠቃላይ 27 ሰዎች በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነትና በአምባሳደርነት ሹመት ተሰጥቷቸዋል። በባለሙሉ ባለስልጣን አምባሳደርነት የተሾሙት ግለሰቦች በአምባሳደርነት የተሾሙት ግለሰቦች
https://www.bbc.com/amharic/news-60144166
amh
politics
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኒስትሮቻቸው በምሽት ክበቦች በመገኘታቸው ይቅርታ ጠየቁ
በጃፓን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የወጣውን መመሪያ ተላልፈው ወደ ምሽት ክበቦች የሄዱ የአገሪቱ ባለስልጣናት ጉዳይ ከፍተኛ ትችትን አስከትሏል። ይህንንም ተከትሎ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሚኒስትሮቻቸው ስም ለህዝቡ ይቅርታ ለመጠየቅ ተገደዋል። መንግሥት በተደጋጋሚ አላስፈላጊ የሆኑ ስብሰባዎችን ህዝቡ እንዲያስወግድ ሲናገር የነበረ ሲሆን ይህንንም ሁኔታ ሚኒስትሮቹ አለማክበራቸው አወዛጋቢ ሆኗል። "ዜጎቻችንን ከምሽት ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ሬስቶራንቶች ወጥታችሁ አንዳትበሉ እንዲሁም አላስፈላጊ የሆኑና አስቸኳይ ካልሆነ ከቤታችሁ አትውጡ በምንልበት ወቅት ይህ በመፈጠሩ በጣም አዝኛለሁ" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂዴ ሱጋ በዛሬው እለት ለፓርላማው አስረድተዋል። የጃፓን የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ሪፖርት ባደረጉት መሰረት አንደኛው ሚኒስትር ባለፈው ሳምንት የጣልያን ሬስቶራንት ውስጥ እራት ከበሉ በኋላ ሞቅ ደመቅ ባለው የመዲናዋ ቶክዮ ማዕከል በሆነው ጊንዛ ወደሚገኙ ሁለት የምሽት ክበቦች አምርተው ነበር ብለዋል። እንዲሁ ሌላኛው ሚኒስትር ጊንዛ በሚገኝ ታዋቂ ክለብ በተደጋጋሚ መሄዳቸውን የአገሪቱ ሚዲያ አስነብቧል። የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ ለሁለተኛ ዙር እያገረሸ ባለባት ቶክዮ ባለስልጣናቱ የአስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል። በጃፓን ከ370 ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከ5 ሺህ በላይ ዜጎቿንም አጥታለች።
https://www.bbc.com/amharic/55810201
amh
politics
ምርጫ 2013፡ ዛሬ ድምጽ የሚሰጥባቸው ቦታዎች መኖራቸው ተገለጸ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከረፋድ 5 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ የሚሰጥባቸው ቦታዎች መኖራቸውን አስታወቀ። ቦርዱ ይህን ያለው ትናንት ምሽት 5፡30 ላይ በሰጠው መግለጫው ነው። በመግለጫው ላይ የምርጫ ቦርድ አምስት አባላት መግለጫ ለመስጠት የተገኙ ሲሆን የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱኳን ሚደቅሳ ምርጫ "ከሞላ ጎደል እጅግ ጥሩ ነበር" ብለዋል። የድምጽ መስጫ ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት እንዲራዘም ስለመወሰኑ ያስታወሱት ሰብሳቢዋ፤ የድምጽ መስጫ ሰዓት ማራዘም ሳያስፈልጋቸው የድምጽ አሰጣጥ ስነ-ስርዓታቸውን ያካሄዱ ምርጫ ጣቢያዎች ትናንት ምሽት ድምጽ ቆጠራ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ከምርጫ ጣቢያዎች ከፍተኛ ቁጥር አንጻር ሁሉም ሊባል በሚችል መጠን የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ ሲያሰጡ ውለው አጠናቅቀዋል ብለዋል። ኢትዮጵያ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ከትግራይ፣ ሶማሊ እና ሐረሪ ክልሎች በስተቀር በትናንትናው ዕለት፣ ሰኔ 14 2013 ዓ.ም ማከናወኗ ይታወሳል። በሶማሊ እና በሐረሪ ክልሎች ደግሞ ጳጉሜን 1 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ የምርጫ ቦርድ መረጃ ያሳያል። በትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተነሳ ላልተወሰነ ጊዜ ምርጫ አይካሄድም። ከ37 ሚሊዮን በላይ መራጮች በተመዘገቡበት እና 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተፎካከሩበት ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ትናንት ከምሽቱ 3፡00 መጠናቀቁን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ለህዝባቸው አስተላልፈዋል። ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለመታዘብ ከ40ሺህ በላይ የአገር ውስጥ እና ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ተሰማርተዋል። የምርጫ ቦርድ አባላትም የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን መጎብኘታቸውን የገለፁ ሲሆን፣ ምርጫው ሴቶች እና ወጣቶችን ያሳተፈ መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል። ታዛቢዎቹ በቀጣይ ጥቂት ቀናት የቅደሚያ ሪፖርት ዋና ዋና ግኝት የሚሏቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ትናንት በተካሄደው ምርጫ ይህ ነው የሚባል የጸጥታ ችግር አላጋጠመም ሲሉ ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ በበኩሉ በተመሳሳእ ምርጫው በሰላም ተካሄዶ መጠናቀቁን በሰጠው መግለጫው ላይ አመልክቷል። በአማራ ክልል በአንድ ምርጫ ጣቢያ ላይ ያልታጠቁ ሰዎች እርስ በእርስ ግጭት ፈጥረው የምርጫው ሂደት የተቋረጠበት ሁኔታ እንደነበር ሰብሳቢዋ አስታውሰዋል። በአማራ ክልል ጎንጂ ምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኝ አንድ ምርጫ ጣቢያ ውስጥ የአካባቢው ባለስልጣናት ገብተው አልወጣም ማለታቸው ስጋት ፈጥሮ፣ አንድ የምርጫ ቦርድ ምርጫ አስፈጻሚ አካባቢውን ለቅቆ ሊወጣ ችሏል። ይህን ለሚመለከተው አሳውቀናል ሲሉም አክለዋል። በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ምርጫ አስፈጻሚዎች ስጋት ገብቷቸው ምርጫ ጣቢያ ያልከፈቱባቸው ቦታዎች እንደነበሩ ተናግረዋል። አክለውም ምስራቅ ሐረርጌ ምርጫ ክልል ውስጥ ያልተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች አሉ። ይህ የመጀመሪያ ሪፖርት ነው ጉዳዩን እንመለከተዋለን ሲሉም አብራርተዋል። በምዕራብ ሸዋ ኖኖ ምርጫ ክልል ሁለት ጣቢያዎች ላይ የታጠቁ ሰዎች ሂደቱን ረብሸው የድምጽ አሰጣጥ ስነ-ስርዓቱ ተቋርጦ እንደነበር የተናገሩት ወ/ት ብርቱካን "ከዚህ ውጪ ይህ ነው የሚባል የጸጥታ ችግር የለም" ሲሉ አረጋግጠዋል። በአዲስ አበባ የድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት አጋጥሞ እንደነበር ያስረዱት የቦርዱ ሰብሳቢ፣ ይሁን እንጂ ይህ ችግር ማጋጠሙ እንደታወቀ በተወሰደው የማስተካከያ እርምጃ ችግሩ መቀረፉ ተመልክቷል። ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሲዳማ ክልሎች የቁሳቁስ እጥረት ማጋጠሙን ወ/ት ብርቱካን ተናግረዋል። የድምጽ መስጫ ወረቀቶች በባለ 100 ተደርጎ መታሸግ ሲኖርባቸው በባለ 50 ተደርገው በመታሸጋቸው እጥረት ማጋጠሙን ያስረዱት ሰብሳቢዋ፣ 19 የምርጫ ክልሎች ላይ የምርጫ ወረቀት ብዛት በ50 በመቶ አጥረት ማጋጠሙን ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት በሲዳማ ክልል ሁሉም ምርጫ ክልሎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደት መቋረጡን አብራርተዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት የሚያስፈልገው ሰነድ ለ19 የምርጫ ክልሎች እንዲደርስ መደረጉንም አስረድተዋል። ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለማድረስ ግን ከመሰረተ ልማት እና ከርቀት አንጻር አስቸጋሪ ነበር ያሉት ሰብሳቢዋ፣ ቦርዱ 1162 የምርጫ አዋጁ በሚፈቅደው መሠረት ምርጫው እንዲቋረጥ አድርጎ ዛሬ ማክሰኞ፣ ከረፋዱ 5 ጀምሮ በሲዳማ የምርጫ ክልሎች በሙሉ ሂደቱ ይቀጥላል ብለዋል። የምርጫ አዋጅ 1162 ምርጫ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ በሚቋረጥበት ጊዜ፣ ለጊዜው ምርጫው እንዲቋረጥ ተደርጎ ሁኔታዎች የሚስተካከሉበት ሰዓት ተወስዶ ሂደቱ መቀጠል እንደሚቻል ይደነግጋል። ጋምቤላ በአራት የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት አጋጥሞ ነበር። በእነዚህ ምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ በቁሳቁስ እጥረት ምርጫው ተቋርጦ እንደነበረ የቦርዱ ሰብሳቡ ወ/ት ብርቱካን ተናግረዋል። የድምጽ አሰጣጡ በተቋረጠባቸው አራቱ የምርጫ ክልሎች ጉዳይ ቦርዱ የሚሰጠው ውሳኔ ግልጽ ይደረጋል ብለዋል። በጋምቤላ ያሉ ሌሎች ምርጫ ክልሎች ግን ድምጽ አሰጥተው ወደ ቆጠራ መግባታቸውን እና ውጤትን በሂደት እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል። በሁለት የምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት በማጋጠሙ ምርጫ መቋረጡን የተናገሩት ሰብሳቢዋ፣ ቻርተር አውሮፕላን በመጠቀም ቁሳቁሶች ወደ ጋምቤላ መላካቸውን ተናግረው በጉዳዩ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ ግልጽ ይደረጋል ብለዋል። ሰብሳቢዋ በዚህ ረገድ ለተፈጠሩ ጉድለቶች ሕዝቡን ይቅርታ እንጠይቃለን ሲሉ አክለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዛሬ ጀምሮ በየምርጫ ጣብያው ውጤት መግለጽ እንደሚጀመር አስረድቷል። አክሎም ቆጠራ ያጠናቀቁ ጣብያዎች በሙሉ በምርጫው የተገኘውን ውጤት ከዛሬ ጀምሮ መግለጽ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል። ምርጫ ክልሎች ቢበዛ አምስት ቀን ድረስ ውጤት ለማሳወቅ ጊዜ እንደሚፈጅባቸው የተናገረው ቦርዱ፣ ነገር ግን በጊዜያዊነት ከስር ከስር እንደሚያሳውቅ ገልጿል። ምርጫ ቦርድ በ አስር ቀን ውስጥ ውድድር በተደረገባቸው የምርጫ ክልሎች ቢያንስ በጊዜያዊነት ውጤቶችን ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57526249
amh
politics
ያልተከተቡ ሰዎችን ከህዝብ አገልግሎት የሚያግድ ህግ የደገፉ የፈረንሳይ የፓርላማ አባላት የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው
በርካታ የፈረንሳይ የፓርላማ አባላት ያልተከተቡትን ሰዎች በሀገሪቱ ከበርካታ ህዝባዊ አገልግሎት እንዲታገዱ የሚያዘውን ረቂቅ መደገፋቸውን ተከትሎ የግድያ ዛቻ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። የፈረንሳይ መንግሥት ሰዎች ወደ የጋራ ስፍራዎች ላይ ለመገልገል እና በትራንስፖርት ለማጓጓዝ መከተባቸውን የሚያረጋገጥ ሰነድ እንዲያሳዩ የሚያስገድድ ሕግ በማውጣት ላይ ይገኛል። ህጉ በዚህ ሳምንት በድምጽ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ክትባትን አንፈልግም የሚሉትን አስቆጥቷል። ፈረንሳይ በአውሮፓ ህብረት በከፍተኛ ምጣኔ የኮቪድ19 ክትባትን አዳርሳለች። የሀገሪቱ መንግሥት እንደገለጸው በፈረንሳይ ቢያንስ 91 በመቶው የሚሆኑት አዋቂዎች ሙሉ በሙሉ ተከትቧል። ባለፈው እሁድ የፓርላማ አባል የሆኑት አጀንስ ፊርሚን ክትባት በአንዳንድ ስፍራዎች አስገዳጅ እንዲሆን ደግፈው በመከራከራቸው ሊገደሉ እንዲችሉ የሚያሳይ ስዕላዊ ማስፈራሪያ የያዘ እና በኢሜል የተላከላቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፍረው ነበር። የፋርማሲ ባለሙያ የሆኑት እና የኮቪድ 19 ክትባትንም የሚሰጡት እኚሁ የፓርላማ አባል "ዲሞክራሲያችን አደጋ ላይ ነው" ሲሉም ጽፈዋል። ቢኤፍኤም ቲቪ ከተሰኘ መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዛቻውን ለፖሊስ ሪፖርት እንዳደረጉ እና ክትባቱን አስገዳጅ ለማድረግ ከመደገፍ እንደማይገታቸው አብራርተዋል። ሌላዋ የፓርላማ አባል የሆኑት ናኢማ ሙችቹ በኢሜል የተላከላቸውን ማስፈራሪያ የሚያሳይ ከስክሪን የተወሰደ ምስል በትዊተር አማካኝነት አሰራጭተዋል። ትላንት በፓርላማ የተገኙት የጤና ሚኒስትሩ ኦሊቪየር ቬራን የክትባት ተቃዋሚዎችን እያደረሱ ያሉትን የሞት ዛቻ እና "ራስ ወዳድነት" አውግዘዋል። ባለፈው ሳምንት የፈረንሳይ ሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጄራልድ ዳርማኒን ክትባትን የተመለከተው ህግ ላይ ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት ፖሊስ ለተመረጡት ባለስልጣናት ጥበቃውን እንደሚያጠናክር ተናግረዋል። የገዢው ፓርቲ እና የፓርላማው አባል የሆኑት ባርባራ ቤሶት "ነጻነታችንን በማጥቃት" የፓርላማ አባላት እንደሚገደሉ የሚያስፈራራ መልዕክቶች እንደደረሳቸው ፓርቲው ገልጿል። በትዊተር ገጻቸው ላይ ደግሞ "እነዚያ የግድያ ዛቻዎች ተቀባይነት የላቸውም" ሲሉ ጽፈዋል። በፈረንሳይ ወረርሽኙ በተስፋፋበት ጊዜ ተቺዎች የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሚመሩት መንግስት ኮቪድ ለመቆጣጠር ህጎችን በመጣል ነፃነቶችን ጥሷል ሲሉ ከሰዋል። በዚህም ምክንያት እነዚህን ህግጋት የሚቃወሙ ሰልፎች በየጊዜው ተካሂደዋል። በፈርንሳይ በበርካታ የጋራ ቦታዎች ለመገልገል ሰዎች የክትባት ማረጋገጫ ወይም ከኮቪድ ነጻ መሆንን የሚያረጋግጭ ሰነድ እንዲያሳዩ ለወራት ስትጠይቅ ቆይታለች። ሆኖም የፈረንሣይ መንግሥት በከፍተኛ ፍጥነት የሚዛመቱት የኦሚክሮን እና ዴልታ ዝርያዎች ተከስተው በቫይረሱ የሚያዙሰዎችን መጨመር ተከትሎ ከቫይረሱ ነጻ መሆንን የሚያሳይ ሰነድ ማቅረብን ከምርጫ ውጪ አድርጋዋለች። የፈረንሳይ መንግሥት ክትባቱን አስገዳጅ የሚያደርገው ህግ በፓርላማ ከፀደቀ ከተያዘው ወር አጋማሽ ጅምሮ ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ ይዟል። ነገ በሀገሪቱ ሴኔት ውስጥ በጉዳይ ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን ከዚህ በፊት አብዛኛዎቹ የፓርላማ አባላት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታችኛው ምክር ቤት ባደረጉት ምክክር በህዝብ አገልግሎት ለመጠቀም አስገዳጅ መሆኑን ይደግፋሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-59864474
amh
politics
በምዕራብ ኦሮሚያ 'ሦስት ቻይናውያን ታግተዋል የተባለው ሐሰት ነው'
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ሦስት ቻይናውያን የማዕድን አውጪ ኩባንያ ሠራተኞች በታጣቂዎች ታግተዋል መባሉን ሐሰት ነው ሲሉ የዞኑ ባለሥልጣን አስተባበሉ። እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራ ቡድን ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ አቅራቢያ ሦስት የቻይና ዜጋ የሆኑ የማዕድን ሠራተኞችን አግቼ ይዣለሁ ብሎ ነበር። ይሁን እንጂ የምዕራብ ወላጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በዞኑ ውስጥ ታግቶ የሚገኝ የውጭ ዜጋ የለም በማለት ቡድኑ ያወጣው መግለጫ ሐሰት ነው ብለዋል። አቶ ኤልያስ ጨምረውም "በዞኑ ውስጥ ታግቶ የሚገኝ ቻይናዊ አለመኖሩን አረጋግጫለሁ" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ የተለያዩ ጥቃቶችን እንደሚፈጽም የሚነገረውና መንግሥት 'ሸኔ' እያለ የሚጠራው ቡድን በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ተብሎ መፈረጁ ይታወሳል። ይህ ቡድን ባለፈው ቅዳሜ በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ከተማ አቅራቢያ በማዕድን ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሦስት የቻይና ዜጎችን አግቼ ይዣላሁ ማለቱ ይታወሳል። በመግለጫው ተፈጸመ ላለው እገታ ምክንያቱ "በመንግሥት እና በማዕድን አውጪዎቹ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ሕጋዊ አይደለም" የሚል ነው። ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተገንጥሎ የትጥቅ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የሚገልጸው ይህ ቡድን በአካባቢው የሚደረገው የማዕድን ቁፋሮ በርካቶችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፣ በአካባቢያዊ ላይም ጉዳት እያስከተለ ነው ብሏል። ይህ ቡድን ሦስት ቻይናውያን ማዕድን አውጪ ሠራተኞችን አግቼ ያዝኩ ይበል እንጂ ሦስቱ ቻይናውያን የሚሰሩበት ድርጅት ማንነት፣ በየትኛው የማዕድን ማውጣት ተግባራት ላይ ተሰማርተው እንደነበረና የቻይናውያኑ ኃላፊነት ምን እንደሆነ ያለው ነገር የለም። የታጣቂ ቡድኑ ነው ከተባለው መግለጫ ጋር ታግተዋል የተባሉ የሦስት ሰዎች ፎቶግራፍ የተሰራጨ ቢሆንም ስለግለሰቦቹ ማንነት የሚገልጽ ዝርዝር መረጃ ግን አልተገኘም። ጉዳዩን በተመለከተ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ አዲስ አበባ ከሚገኘው የቻይና ኤምባሲ የተባለ ነገር የለም። የአካባቢው ባለስልጣናት ምን ይላሉ? በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የምዕራብ ወላጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ፤ እገታውን በተመለከተ "በማኅበራዊ ሚዲያ የተባለውን አንብበናል፤ ውሸት ነው። አረጋግጠናል" ብለዋል። "በወረዳችን፣ በቀበሌያችን መሰል ነገር አለመከሰቱን አረጋግጠናል" ያሉት አቶ ኤልያስ፤ ጨምረውም በአካባቢው የኢንቨስትመንት ፍቃድ የወሰዱ ቻይናውያን አለመታገታቸውን እንዳረጋገጡ ተናግረዋል። መንዲ ከተማ የቱርክ እና የሕንድ ዜጎች ማዕድን የማውጣት ሥራ ተሰማርተው እንደሚገኙ የሚናገሩት አቶ ኤልያስ፤ በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ዘወትር በሥራ ገበታቸው እንደማይገኙ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የመነ ሲቡ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ ታመነ ይህ ክስተት እርሳቸው በሚያስተዳድሩት ወረዳ አለመከሰቱን ተናግረው፤ "በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኦዳ ቢልዲጊሉ ወረዳ እገታው ተፈጽሟል" የሚል መረጃ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህን በተመለከተ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለው ነገር የለም። የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው ስለ ጉዳዩ የማውቀው የለም ብለዋል። "ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የውጭ አገር ዜጎች ታፍነዋል የሚል መረጃ የለኝም። ኦሮሚያ ውስጥ ቢሆን ኖሮ መረጃው ይደርሰን ነበር" ብለዋል። ከሁለት ዓመት በፊት መንዲ ከተማ አቅራቢያ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ሁለት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ አምስት ማዕድን አውጪዎች መገደላቸው ይታወሳል። በምዕራብ እና ደቡብ የኦሮሚያ አካባቢዎች ባለፉት ጥቂት ዓመታት በታጣቂዎች በሚፈጸሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች በርካታ የመንግሥት ባለስልጣናት እና ንጹሃን ዜጎች ተገድለዋል። ለእነዚህ ጥቃቶችም ለረጅም ዓመታት በትጥቅ ትግል ላይ ከነበረው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ተለይቶ የወጣውና እራሱን 'የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት' ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት ደግሞ 'ሸኔ' የተባለው ቡድን ስም በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል። የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቡድኑን የሽብር ቡድን አድርጎ ከጥቂት ሳምንታት በፊት መሰየሙ ይታወሳል። በኦሮሚያ ክልል በዚህ ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ 18 የመንግሥት ባለስልጣናት፣ 112 የፖሊስ አባላት እና 42 የሚሊሻ አባላት በታጣቂዎች መገደላቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57146501
amh
politics
በምዕራብ ኦሮሚያ ላለው የሰላም እጦት አምስት ምክንያቶች
*ባለፉት ሦስት ዓመታት የምዕራብ ኦሮሚያ ክፍል ሰዎች በግፍ የሚገደሉበት፣ የሚፈናቀሉበት እና ንብረት የሚወድምበት አካባቢ ሆኖ እስካሁን ቀጥሏል። በ2013 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ በተከታታይ ለቀናት በተፈጸሙ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በታጣቂዎች መገደላቸው መዘገቡ ይታወሳል። ከዚህ ጥቃት በተጨማሪ በተለያዩ ጊዜያት በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች፣ አስተዳዳሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና ሌሎችም የጥቃቶቹ ሰለባዎች ሆነዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ወለጋ ዞኖች ውስጥ የሚፈጸሙት ግድያዎች፣ ማፈናቀሎች እና ዝርፊያዎች በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄድ በሚገኘው ጦርነት ምክንያት የሚገባውን ትኩረት ሳያገኝ እንደቀጠለ ነው። መልኩን እየቀያየር የሚያጋጥመው ጥቃት ለበርካታ ዓመታት በሰላም አብሮ ሲኖር የነበረን ማኅበረሰብ በዓይነ ቁራኛ እንዲተያይ ምክንያት እየሆነ ነው። ከትግራዩ ጦርነት በፊት የጀመረው በአካባቢው ያለው የሰላም መደፍረስ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ለመሆኑ ቀደም ሲል በሰላማዊነቱ የሚታወቀው የምዕራብ የኦሮሚያው ክፍል ወለጋን መረጋጋት እንዲርቃትና በርካቶችን ሰለባ እንዲሆኑ ያደረጉት ጥቃቶች እንዲቀጥሉ ያደረጉ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? አምስቱ ዋነኛ ምክንያቶችን እነሆ። የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መንግሥት 'ሸኔ' የሚለውን እና እራሱን 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር' ብሎ የሚጠራው ቡድን በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ በስፋት በመንቀሳቀስ ለክልሉ እና ለፌደራል መንግሥት ፈተና ሆኖ ቆይቷል። 'ሸኔ' ወይም 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር' የሚንቀሳቀስባቸው ስፍራዎች የደኅንነት እጦት ያጋጠማቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች ሆነዋል። ከሦስት ዓመት በፊት ይህ ቡድን ተጠያቂ በሆነበትና በካማሺ ዞን አስተዳዳሪዎች ላይ የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ ከ100 ሺህ በላይ ሕዝብ ከመኖሪያው እንዲፈናቀል እና በርካቶች በጥቃቱ እንዲገደሉ ምክንያት ሆኖ ነበር። የሸኔ ወይም የኦሮሞ ነጻነት ጦር በጀምላ ግድያ፣ ዘረፋ፣ በንጹሃን እና በመንግሥት ባለሥልጣናት ግድያ፣ መንገድ በመዝጋት፣ የሕዝብ እና የመንግሥት ንብረት በማውደም፣ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ እና በሌሎች ወንጀሎችም ይከሰሳል። በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ እና ባቦ ጋምቤል ወረዳዎች እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ዞን አቤ ዶንጎሮ፣ አሙሩ እና አባያ ጮመን ግፍ ከተፈጸመባቸው ወረዳዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። በተመሳሳይ በተቀሩት ሁለት የወለጋ ዞኖች፤ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ወንጀሎች ተፈጽመዋል። ሰኔ 2013 ዓ.ም. በኪራሙ በተፈጸመው እና ከ100 በላይ ሰዎች ከተገደሉበት ጥቃት በሕይወት መትረፍ የቻለው አርሶ አደር ለቢቢሲ እንደተናገረው በአሁኑ ወቅት በሽሽት በአማራ ክልል ውስጥ ይገኛል። ለደኅንነቱ ሲባል ስሙን የማንጠቅሰው ይህ አርሶ አደር ትውልድ እና አድገቱ ወለጋ ውስጥ መሆኑን በመናገር በአካባቢው ለተፈጠረው የሰላም እጦት ዋነኛው ምክንያት 'የሸኔ' ታጣቂዎች ናቸው ይላል። "ይሄን ሁሉ የሚያደርገው ሸኔ ነው። ኦነግ ሸኔ ነው ይህን ችግር ያመጣው እንጂ እኛማ ተጋብተን፣ ተዛምደን አይደል እንዴት አብረን ስንኖር የነበረው?" በማለት ይናገራል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በምዕራብ ኦሮሚያ ያለውን ሁኔታ በቅርበት የሚከታተሉት የፖለቲካ ተንታኝም፤ በአካባቢው ያለውን የደኅንነት እጦት ያባባሰው "የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ነው" በማለት ከአርሶ አደሩ ጋር ተመሳሳይ ሃሳብ ይሰነዝራሉ። ጨምረውም "ዘንድሮ ሳይታረሰ የቀረ ሰፊ መሬት አለ" በማለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአማራ ብሔር ተወላጅ ከአካባቢው ተፈናቅለው መውጣታቸውን ይገራሉ። በምዕራብ ኦሮሚያ የሚሰነዘሩት በርካቶቹ የታጣቂዎች ጥቃቶች ኢላማቸውን የሚያደርጉት በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ይሁን እንጂ በጥቃቶቹ ሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎችም የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል። መሰል ጥቃቶች የበቀል እርምጃ እንዲወስድም ምክንያት እየሆኑ ነው። የአማራ ታጣቂዎች በምሥራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ጥቃቶች መሰንዘር ከጀመሩ በኋላ የአማራ ታጣቂዎችም በበቀል እርምጃዎችን በመወሰድ መከሰስ ጀምረዋል። በሁለቱ ዞኖች ውስጥ በደርግ መንግሥት ወቅት የሰፈሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአማራ ብሔር ተወላጆች ይኖራሉ። ከዚህ ቀደም በነበሩት ዓመታት የኦሮሞ እና የአማራ ብሔር ተወላጆች በሰላም እና በመተጋገዝ ይኖሩ ነበር። ይሁን እንጂ ከታጣቂዎች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ወቅት በሁለቱ ብሔር ተወላጆች መካከል ግጭት መከሰት ጀምሯል። "ከዚህ ቀደም ታጣቂዎች ብዙ ሰው ገድለዋል (የአማራ ብሔር ተወላጆችን)። አሁን ላይ ታጣቂዎች የገደሉትን ለመበቀል ያገኙትን ኦሮሞ በመግደል በቀል እየተወጡ ነው። 'ትናንት አብሮን የበላው እራሱ ነው ያስገደለን' ይላሉ። በየቀኑ ሰው እየተገደለ ነው" በማለት የምዕራብ ኦሮሚያን የፀጥታ ሁኔታን በቅርበት የሚከታተሉት ተንታኝ ይናገራሉ። ታኅሣሥ 2014 ዓ.ም. በምሥራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የአማራ ታጣቂዎች የወሰዱት የበቀል እርምጃ ነው በተባለ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ንብረትም ወድሟል። በሆሮ ጉዱሩ ዞን፤ የጃርዳጋ ጃርቴ ወረዳ ሃርቡ ነጋሶ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩት ግለሰብ በዚህ ጥቃት ንብረታቸው ስለወደመባቸው አካባቢውን ጥለው ተሰደዋል። "ዘጠኝ ሰዎች ተገድለው ነበር። ሟቾቹ ደግሞ መሸሽ የማይችሉ ሰዎች ናቸው። የ90 ዓመት አዛውንት ከሟቾቹ መካከል ይገኙበታል" በማለት ተፈናቃዩ ይናገራሉ። ሌላ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አርሶ አደር፤ በሁለቱ ብሔር ተወላጆች መካከል እርቅ ለማውረድ ለውውይት በተቀመጡ ወቅት፤ የአማራ ብሔር ተወላጆች 'ለደኅንነታችን ሰግተን ፋኖን አስመጥተናል' ብለው ስለመናገራቸው ይገልጻሉ። ሌላኛው ንብረታቸው ወድሞ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉት የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ እንደሚሉት የአማራ ታጣቂዎች ጥቃት ሲፈጽሙ የቆዩት መንግሥት ሸኔ የሚለው ታጣቂ ቡድን ሲንቀሳቀስ በነበረበት ቦታ ነው ይላሉ። "ሲንቀሳቀሱ በነበሩት ቦታ ነው ያቃጠሉት። አሁን እነሱ (የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቡድን) በቦታው የሉም። ይህ የብሔር ግጭት ሳይሆን የፖለቲካ መልክ ነው ያለው። በቀል የሚወጡም ይመስላል" በማለት ያስረዳሉ። የቀድሞው የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አለማሁ ተስፋ ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በአካባቢው 'በአማራ ታጣቂዎች' ጥቃት ተፈጽሟል ሲሉ ተናግረው ነበር። ከዚህ አንጻር ከጥቃቶቹ ጋር በተያያዘ ተጠያቂ ናቸው የተባሉ 'የአማራ ታጣቂዎች' የተባሉትን ሃሳብ አግኝቶ ለማካተት አልተቻለም። የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሻፊ ሁሴን በበኩላቸው በቅርብ ጊዜያት የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችን ዒላማ ባደረገው ጥቃት ተሳታፊ የሆኑት በዚያው በክልሉ ውስጥ የሚኖሩት ናቸው ይላሉ። እንደ ኃላፊው ከሆነ ታጣቂዎቹ የመንግሥት እንቅስቃሴን ተከትለው ከቦታ ቦታ እንደሚንቀሳቀሱ ያስረዳሉ። መንግሥት ከመንግሥት ቀዳሚ ኃላፊነቶች መካከል የዜጎችን ደኅንነት ማረጋገጥ እንዱ ቢሆንም፤ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚኖሩ የሁለቱም ብሔር ተወላጆች መንግሥት ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አልቻለም ይላሉ። "የመንግሥት አካል ሁኔታውን መቆጣጠር ነበረበት። ለጠፋው ሕይወት እና ንብረት መንግሥት ተጠያቂ መሆን አለበት" በማለት የጃርዳጋ ጃርቴ ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር ይናገራሉ። ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ግጭት እየተበራከተ ሲሄድ እንኳን መንግሥት 'ዝምታን' መርጧል ይላሉ። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ግን በዚህ አይስማሙም። አቶ ሻፊ፤ "እንደውም ያለን ኃይል በምዕራብ ነው ያለው። መንግሥት የተለያየ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል" ይላሉ። በሌላ በኩል በክልሉ መንግሥት ላይ የሚነሳው ቅሬታ፤ አርሶ አደሩ እራሱን ሊከላከል የሚችልበትን ትጥቅ ያስፈታል የሚለው ነው። በአንዳንድ ስፍራዎች መንግሥት ጦር መሳሪያ በታጣቂዎች እጅ ሊገባ ይችላል በሚል ስጋት ነዋሪዎችን ትጥቅ ሲያስፈታ ነበር ተብሏል። አንድ አርሶ አደር "ሸኔን ምክንያት ያደርጋሉ እንጂ እንዴት አንድ ሰው ለሸኔ እንካ ብሎ መሳሪያ ይሰጣል?" ሲሉ ይጠይቃሉ። አቶ ሻፊ ግን መንግሥት ሚሊሻውንም ሆነ አንድ ወገንን ለይቶ ትጥቅ አያስፈታም ይላሉ። ይሁን እንጂ በጦር መሳሪያ አማካኝነት ጉዳት እንደሚደርስ ይናገራሉ። ሌላ መንግሥት ላይ የሚነሳው ትችት፤ የወታደራዊ እርምጃ አማራጭን በመጠቀም በምዕራብ ኦሮሚያ ሰላም ማምጣት ባለመቻሉ የእርቅ መንገድን መጠቀም አለበት የሚለው ይገኝበታል። አቶ ሻፊ ግን መንግሥት ለዚህ በሩ ክፍት ነው ይላሉ። ይሁን እንጂ "ታጣቂው እንዲሁ ለቃል ካልሆነ በቀር ለሰላም ዝግጁ አይደሉም" ሲሉ ይከሳሉ። የፖለቲካ ፍላጎት የኦሮሚያ ክልል በአገሪቱ ካሉት ክልሎች በቆዳ ሰፋቱም ሆነ በሕዝብ ብዛት ቀዳሚው ነው። በዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች የክልሉ መንግሥት የአገሪቱን ፖለቲካ መቆጣጠር የሚፈልጉ አካላት ክልሉን ዒላማ ሊያደርጉት ይችላሉ የሚል ስጋት አለው። አቶ ሻፊም ይህን ሁኔታ "የፖለቲካ ፍላጎት ነው" ሲሉ ይገልጹታል። በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ፍላጎታቸው ምንም ቢሆን ግባቸው ግን ተመሳሳይ መሆኑን ያስረዳሉ። "አገር ማፍረስ፣ ሕዝብ ማፈናቀል፣ ንብረት ማውደም፣ ሁከት መፍጠር፣ ከተቻለም ይህን መንግሥት አፍርሰው የሽግግር መንግሥት መመስረት ነው" በማለት ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትን በይፋ ሲኮንኑ አይስተዋልም። በዚህም ታጣቂዎች የልብ ልብ እንዲያገኙ ምክንያት ሆኗቸዋል ይላሉ። ሌሎች ምክንያቶች ለዓመታት የተካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በየአካባቢው የሚስተዋሉ ብሔር ተኮር ግጭቶች ተበራክተዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ የሚታየውም ከዚህ የሚለይ አይደለም። ለበርካታ ዓመታት በሰላም አብረው ይኖሩ የነበሩ ማኅበረሰቦች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን አዲስ ነገር እንዳጋጠማቸው ይናገራሉ። ሰዎች እርስ በእርሳቸው እንዲጠራጠሩ እና በሕዝቦች መካከል ያለው መልካም ግንኙነት እንዲሻክር የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም የማኅበረሰብ አንቂዎች አሉታዊ ሚና እንደተጫወቱ በርካቶች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለሦስት አስርት ዓመታት በበላይነት ሲመራ የቆየው ህወሓት በሕዝቦች መካከል መጠራጠርና ግጭት በመፍጠር በመሆኑ አሁን የሚታየው ሁኔታም የዚያ ተከታይ እንደሆነ ባለሥልጣናት ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪ ሰፊውን የአገሪቱን ሕዝብ ቁጥር በሚሸፍኑት ወጣቶች ዘንድ የተንሰራፋው ሥራ አጥነት እና የእርሻ መሬት እጥረትን የመሳሳሉ ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ለሰላም እጦት እንደ ምክንያት ይቀርባሉ። * በዚህ ታሪክ ውስጥ የተካተቱት ሰዎች ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀዋል
https://www.bbc.com/amharic/news-60195626
amh
politics
የሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ ኢትዮጵያ ላይ ምን አንድምታ ይኖረው ይሆን?
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን ያሳወቁት እሁድ ምሽት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን መልቀቂያ የተሰማው በአገሪቱ ውስጥ ለተከታታይ ሳምንታት ሲካሄድ በቆየውና እሁድ ዕለት ካርቱም ውስጥ የተደረገውን ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን መልቀቅ ከአብደላ ሐምዶክ ጋር ስምምነት መስርተው ለነበሩት ወታደራዊ መሪዎች ራስ ምታት ነው ሲሉ የአገሪቱን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ከሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣኑን ሊጠቀልል፣ አገሪቱም ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸገገር የምታደርገውንም ጥረት ሊያኮላሽ ይችላል። ይህ ብቻ ሳይሆን አሁን በአገሪቱ ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ፣ ወታደራዊ ኃይሉን ወደ አምባገነናዊ አስተዳደር ሊመራው የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። አብደላ ሐምዶክ አብደላ ሐምዶክ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሐላ ፈጽመው ሥልጣን ሲረከቡ ዋነኛ ግባቸው የነበረው አገሪቱን ማረጋጋትና ለገጠማት ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ መፍትሄ መፈለግ ሲሆን በዚያውም በሕዝብ የሚመረጥ መንግሥት ለመመስረት መንገድ ማመቻቸት ይገኝበታል። የአብደላ ሐምዶክ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ለረጅም ዘመን ከወታደሩ በወጡ መኮንኖች ስትመራ የነበረችውን ሱዳንን፣ ከጦር ኃይሉ ተጽዕኖ በማላቀቅ ወደ ሲቪል መንግሥት ይመልሳታል የሚል ተስፋን በሕዝቡ ውስጥ ፈጥሮ ቆይቷል። በ60ዎቹ አጋማሽ የሚገኙት አብደላ ሐምዶክ በምጣኔ ሀብት የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአፍሪካ አህጉራዊ ተቋማት ውስጥ በሙያቸው የረጅም ጊዜ ልምድ አላቸው። አገራቸው በወሳኙ የሽግግር ወቅት እንዲያገለግሏት ስትጠራቸው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ እያገለገሉ ነበር። ቀደም ሲል ፕሬዝዳንት አልበሽር መሪ በነበሩበት ወቅት፣ ሐምዶክ ለገንዘብ ሚኒስትርነት ታጭተው የነበረ ሲሆን እርሳቸው ግን ሳይቀበሉት መቅረታቸው ይነገራል። በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል የነበረው አለመግባባት ረግቦ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት ከስምምነት የተደረሰ ቢሆንም፣ በጦር ኃይሉና በሲቪል ባለሥልጣናት መካከል የነበረው ግንኙነት የሰመረ አልነበረም። ይህ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲዋቀር በሚፈልጉ ለውጥ ጠያቂዎች ዘንድ ጥርጣሬን ፈጥሮ ቆይቷል። በተለይ የጦር ኃይሉ ጄነራሎች ጎልተው መውጣት አገሪቱን መልሶ ወደ ወታደራዊ አስተዳደር አዙሪት ውስጥ ሊከታት ይችላል የሚል የዘወትር ስጋት ነበረ። የኢትዮጵያ ሚና ፕሬዝዳንት አልበሽር ከሥልጣን ተወግደው በሱዳን ፖለቲካዊ ኃይሎች መካከል አለመግባባቱ በጦዘበት ጊዜ፣ ጦር ኃይሉና ሲቪል ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከስምምነት ደርሰው የተሳካ የሽግግር ሂደት እንዲኖር የኢትዮጵያ ሚና የጎላ እንደነበር ይታወሳል። በሕዝባዊው ተቃውሞ ወቅት በተገደሉ ሰዎች ምክንያት የተቃዋሚ መሪዎች የጦር ኃይሉን መሪዎች ተጠያቂ በማድረግ በሽግግር መንግሥቱ ውስጥ እንዳይሳተፉ ሲጠይቁና ጄነራሎቹም የአገሪቱን ደኅንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንደወስዱበት በሚናገሩበት ጊዜ ሌላ ዙር ደም መፋሰስ እንዳይከሰት ተሰግቶ ነበር። በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ካርቱም በማምራት ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸውን አጥብበው ሱዳን ወደ ተረጋጋ የሽግግር ሂደት እንድታመራ ጥረት አድርገዋል። በዚህም በተቀናቃኞቹ ኃይሎች መካከል ስምምነት ተደርሶ አሳሳቢው ውጥረት ለጊዜውም ቢሆን ለመርገብ ችሎ ነበር። ከኢትዮጵያ ጋር ረዥም ድንበር የምትጋራው ሱዳን በአል በሽር ትመራ በነረበት ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መምጣት በፊት ከነበረው አስተዳደር ጋር ጠንካራ ግንኙነት ገንብታ የቆየች ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የአመራር ለውጥ ከመጣ በኋላም ይህንኑ ለማስቀጠል ፍላጎት እንዳለ ታይቷል። በተለይ አልበሽር ከሥልጣን ወርደው የሽግግር መንግሥት በሚቋቋምበት ጊዜ ለሱዳን መረጋጋት ኢትዮጵያ ያላትን ድጋፍ ለማሳየት ጥረት አድረጋለች። በተመሳሳይም ሱዳንን ከጎኗ ለማሰለፍ የምትፈልገው ግብፅም የበኩሏን ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል። ውጥረት የነገሰበት የድንበር ጉዳይ ኢትዮጵያና ሱዳን ለረጅም ጊዜ መፍትሔ ሳያገኝ የቆየውን የድንበር ጥያቄያቸውን ለመፍታት ዓመታት የቆየ የድንበር ኮሚሽን አዋቅረው አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርጉም የመጨረሻ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ቆይተዋል። ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የሚገኙበትና ሱዳን ይገባኛል የምትለው አል ፋሽቃ የተባለው ሰፊ ለም መሬት፣ አንድ ጊዜ አጀንዳ ሲሆን ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲተው ቆይቶ ነበር። ሁለቱም አገራት የራሳቸው እንደሆነ ቢገልጹም ግንኙነታቸውን ከሚያበላሽ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ለአመታት ቆይቷል። ነገር ግን ትግራይ ውስጥ ጦርነት በተቀሰቀሰበት ጊዜ የኢትዮጵያ ወታደሮች የድንበር አካባቢውን ለቅቀው መውጣታቸውን ተከትሎ የሱዳን ሠራዊት በኃይል ቦታውን መቆጣጠሩ በኢትዮጵያ በኩል ቁጣን አጭሯል። በውስጣዊ አለመረጋጋር ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ ወረራ ያለችውን ድርጊት ለመከላከል እርምጃ ሳትወስድ ቆይታለች። የሱዳን ከፍተኛ ባለሥልጣናት በይፋ ወጥተው በኢትዮጵያ የተያዘባቸውን መሬት ማስመለሳቸውን ሲገልጹ፣ በኢትዮጵያ በኩል ግን ለችግሩ በውይይት መፍትሔ እንዲፈለግ በተደጋጋሚ እየጠየቀች ነው። በዚህም ሳቢያ በሁለቱ መንግሥታት መካከል የነበረው መተማመን ከዚህ በፊት በነበረው ደረጃ ላይ እንዳይገኝ ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪ በሕዳሴው ግድብ ግንባታና የውሃ አሞላል ሂደትን በተመለከተ ለዓመታት ከኢትዮጵያ ጋር ተቀራራቢ አቋም የነበራት ሱዳን ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ለውጦችን አሳይታለች። ግድቡን በተመለከተ ከመጀመሪያው አንስቶ ተቃውሞ የነበራት ግብፅ የምታነሳቸው ሐሳቦችን በመደገፍ ወይንም ከዚህ በፊት ስምምነት በተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን በማንሳት ሱዳን ጫና ለመፍጠር ሙከራ ስታደርግ ተስተውሏል። እንደ ኢትዮጵያ መንግሥት ገለጻ በዚህ ሳቢያ ሲካሄዱ የነበሩ ድርድሮች ግብፅ ወይም ሱዳን በሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች ምክንያት ውጤት ሳያስገኙ ቀርተዋል። በተጨማሪም የግድቡ ጉዳይ አስከ ፀጥታው ምክር ቤት ድረስ እንዲሄድ ለማድረግ ችለዋል። ስለዚህም ኢትዮጵያና ሱዳን ካላቸው ረዥም የጋራ ድንበር በተጨማሪ ግንባታው እየተጠናቀቀ ሥራ ሊጀምር በተቃረበው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ መፍትሔ የሚፈልጉለት ነገር ነው። ተቀማጭነታቸው ለንደን የሆነው የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አብዱራህማን ሰይድ እንደሚሉት ሱዳን በጄነራል ቡርሐን በሚመራ ወታደራዊ መንግሥት እጅ ከገባች የድንበርም የሆነ የሕዳሴው ግድብ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ የማለቁ ነገር የጠበበይሆናል። የሱዳንና የግብፅ ጦር በሱዳን የሽግግር መንግሥት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የያዘው የሱዳን ጦር ኃይል ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ አጠቃላይ ፖለቲካዊ ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ነበረው። ይህ አካል ከኢትዮጵያ ጋር በማያስማማው የድንበር አካባቢ ተሰማርቶ አወዛጋቢ ቦታዎች ከመቆጣጠሩ ባሻገር ከግብፅ አቻው ጋር ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ የቀረበ ግንኙነት ለመመስረት ችሏል። በዚህም የሁለቱ አገራት ሠራዊት የጦር ልምምድ ከማድረግ ባሻገር አስፈላጊ ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ በኩል ስጋት እንዲፈጠር በማድረግ በአካባቢው ያለውን ውጥረት ያብሰዋል። የአማጺያንና ወታደራዊ እንቅስቃሴ በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነትና በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ የደኅንነት ስጋቶች እንዳሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ይገልጻሉ። በይፋ ከሱዳን በኩል ድጋፍ ያገኛሉ ባይሉም የኢትዮጵያ ወታደራዊ ባለሥልጣንት ከሱዳን በኩል ድንበር አቋርጠው ለመግባት የሚሞክሩ ታጣቂ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን በተለያዩ ጊዜያት ሲገልጹ ቆይተዋል። ይህም ኢትዮጵያ በምዕራባዊ ድንበሯ በኩል ለሚፈጸሙ ጥቃቶችና የጥቃት ሙከራዎች በሱዳን በኩል መተላለፊያ እንዳገኙ ያመለክታል። ይህንንም አገራቱ ከወዲሁ መፍትሔ ካላበጁለት ለአለመግባባት የሚያበቃ የፀጥታ ስጋት ሊሆን መቻሉ አይቀርም። የድንበር ጉዳይን በተመለከተ ቢሆን፣ ኢትዮጵያ የሱዳን ጦር ወደነበረበት ተመልሶ ሲካሄድ በነበረው ውይይት አማካኝነት መፍትሔ እንዲፈለግ ብትጠይቅም ሱዳን ግን በመሠረተ ልማት ግብታ ይዞታዋን እያጠናከረች ነው። በተደጋጋሚ እንደተዘገበውም የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ኃይሎች ጥቃት እንደደረሰበት እንዲሁም በቅርቡ ኢትዮጵያ ሠራዊቷን በድንበር አካባቢ እያሰፈረች ነው የሚል ክስ ሲቀርብ ይሰማል። ይህ ደግሞ ሁለቱ አገራት ድንበር አካባቢ ያለውን ውጥረት ሊያባብሰው ይችላል። ከሐምዶክ በኋላ ከሐምዶክ ሥልጣን መልቀቅ በኋላ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንበር ማን እንደሚመጣ አስካሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ጦር ኃይሉ የሱዳን መንግሥት ሥልጣንን ጠቅልሎ የሚይዝ ከሆነ በአገሪቱ ውስጥ ያለው ቀውስ የበለጠ ሊባባስ ይችላል። እንዲሁም ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ባላት ግንኙነት ላይ የጦር ኃይሉ ምን አይነት መንገድ እንደሚከተል በትክክል ባይታወቅም፣ ከዚህ በፊት በነበሩት የድንበር፣ የሕዳሴው ግድብ እና ከግብፅ ጋር ባዳበረው ግንኙነት የተነሳ ያለው ሁኔታ ላይረግብ የሚችልበት ዕድል አለ። የምሥራቅ አፍሪካ የፖለቲካ ተንታኙ አብዱራህማን እንደሚሉት በቀጣናው የተለያየ ፍላጎት ያላቸው አገራት ጥቅማቸውን ለማስከበር ሲሉ የሚችሉትን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ እንዳማይሉ ይጠቅሳሉ። ይህም ጄነራል አል ቡርሐን በሥልጣን ላይ ለመቆየት በአካባቢውና በሌሎች አገራት ተጽእኖ ስር ሆነው ያልጠተበቁ እና ሰላምን የማያመጡ ውሳኔዎችን ሊሰጡ የሚችሉብት ዕድል እንዳለ ያስረዳሉ። በአጠቃላይ ግን የአብደላ ሐምዶክ ከሥልጣን መልቀቅ የሱዳን ጦር ኃይልን ከመንግሥት ኃላፊነት ገለል እንዲል የማድረጉን ተስፋ ከማጨንገፉ በተጨማሪ በአካባቢው ሰላምና ደኅንነት ላይ ተጽእኖ ይናረዋል ብለዋል የፖለቲካ ተንታኙ።
https://www.bbc.com/amharic/news-59854354
amh
politics
ጠ/ሚ ዐቢይን ጨምሮ የአፍሪካ መሪዎች ማክሮንን እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ሌሎችም የአፍሪካ መሪዎች ኢማኑኤል ማክሮን በድጋሚ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው ደስታቸውን እየገለጹ ነው። ማክሮን ትናንት በተደረገ አገር አቀፍ ምርጫ ተቀናቃኛቸው ማሪን ሌ ፔንን በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋቸዋል፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት ከማክሮን ውጭ ለሁለተኛ ጊዜ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆኖ የተመረጠ መሪ አልነበረም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው "ወዳጄ ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠህ ታሪክ በመሥራትህ እንኳን ደስ አለህ! በአገራችን መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለው ጽፈዋል። ማክሮን ቀኝ አክራሪዋን ማሪን ሌ ፔንን ማሸነፋቸው በአውሮፓ ኅብረት አባላት ዘንድ እፎይታን መፍጠሩ ተዘግቧል። ሌ ፔን ስደተኞችን የማባረር፣ ፈረንሳይን ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እንዲሁም ከአውሮፓ ኅብረት የማስወጣት ዕቅድ እንዳላቸው ሲገልጹ ቆይተዋል። ማክሮን ያሸነፉት ከድምጽ ሰጪው ሕዝብ 58.55 ከመቶ በማግኘት ሲሆን፣ ሌ ፔን ድምጽ ማግኘት የቻሉት ግን 41.45 የሚሆነውን ብቻ ነው። ለማክሮን የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ካስተላለፉ አፍሪካውያን መሪዎች መካከል የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር የሆኑት የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ይገኙበታል። የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜም በትዊተር ገጻቸው ላይ "የማክሮን አመራር ከክፍፍል ይልቅ አንድነትን ያሰፍናል" ብለዋል። ማክሮን ከድል በኋላ ባደረጉት ንግግር የተከፋፈለውን የፈረንሳይ ሕዝብ አንድ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ ማክሮን በተለይም በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ዘንድ ሲተቹ ቆይተዋል። የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር አለመቻላቸውም ከፍተኛ ተቃውሞን አስነስቶባቸዋል፡፡ የምርጫ ውጤቱ ይፋ ከሆነ በኋላ ሌ ፔን ሽንፈታቸውን የተቀበሉ ሲሆን ያገኙት ድምጽ በራሱ ለፓርቲያቸው ትልቅ ድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/61218338
amh
politics
ህወሓት ተኩስ ለማቆም ቅድመ ሁኔታዎቹን አሻሽሎ አቀረበ
የፌደራል መንግሥቱ የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጁን ተከትሎ ባለ ሰባት ነጥብ ቅድመ ሁኔታዎችን አቅርበው የነበሩት የትግራይ ኃይሎች በድርድር ላይ የተመሰረተ ተኩስ አቁም ለማድረግ የተሻሻለ አዲስ ቅድመ ሁኔታ አቀረቡ። በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ "የትግራይ መንግሥት አቋም" በሚል የወጣው መግለጫ፤ “በፍጥነት እየተቀያየረ ያለው ወታደራዊ እና ፖሊቲካዊ ሁኔታ በአገሪቱ ሰላም እና ደኅንነት ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ ከግምት በማስገባት የትግራይ መንግሥት ከዚህ ቀደም የተኩስ አቁም ለማድረግ ያቀረባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማሻሻል አስፈልጎታል" ብሏል። ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፍላጎቱን አለኝ ያለው ህወሓት፤ ዳግም ባወጣው የተኩስ አቁም ቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ ውይይት እና የሽግግር ሂደት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል። የአቋም መግለጫው የትግራይ መንግሥት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፍላጎቱን እና ምርጫውን ሲያንጸባርቅ ቆይቷል ብሏል። የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ ትግራይን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ የትግራይ ኃይሎች በርካታ የክልሉን ስፍራዎች ተቆጣጥረው የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ባለ ሰባት ነጥብ ቅድመ ሁኔታዎችን ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ማውጣታቸው ይታወሳል። ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ በወጣው ቅድመ ሁኔታ ላይ በኤርትራ ወታደሮች እና በአማራ ኃይሎች ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ወገን ምርመራ እንዲደረግባቸው እና እነዚህ ኃይሎች የትግራይ ስፍራዎችን ለቀው ይውጡ ብሎ ነበር። የተቋረጡ መሠረተ ልማቶችን መልሰው ሥራ እንዲጀምሩ፣ ዓለም አቀፍ በረራዎች ትግራይ ከሚገኙ አየር ማረፊያዎች በቀጥታ በረራ ያደርጉ፣ ያለ ምንም ገደብ የሰብአዊ እርዳታ የሚቀርብበት መንገድ እንዲመቻች እና የክልሉ በጀት እንዲለቀቅ የሚሉ ቅድመ ሁኔታዎችን አቅርቦ ነበር። በአዲሱ ቅድም ሁኔታ ህወሓት ምን አለ? ዛሬ የአቋም መግለጫው ይፋ የተደረገው በፓርቲው ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ይፋዊ የትዊተር ገጽ ሲሆን፤ ከአቋም መግለጫው በታች ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም. የሚል ቀን ተመልክቷል። የትግራይ መንግሥት ወቅታዊ የአቋም መግለጫ በሚል ርዕስ በወጣው መግለጫ ላይ፤ "አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት አገሪቱን መምራት የሚያስችለው ሕገ መንግሥታዊ መብት የለውም" ካለ በኋላ፤ በአገሪቱ የተከሰተውን ፖለቲካዊ እና ሕገ መንግሥታዊ ችግሮችን ለመፍታት ዋና የፖለቲካ ተዋናዮችን ያቀፈ አካታች ፖለቲካዊ ሂደት እና የሽግግር ሥርዓት እንዲካሄድ ጥሪ እናቀርባለን ይላል የመጀመሪያው ነጥብ። ከዚህ በተጨማሪም የትግራይ መንግሥት በድርድር የሚደረስ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸው አለባቸው ሲል ከዚህ ቀደም ካወጣው የአቋም መግለጫ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ስድስት ነጥቦችን ዘርዝሯል። ከእነዚህ ነጥቦች የመጀመሪያው በትግራይ ተቋርጠው የቆዩ እንደ ኤሌክትሪክ፣ ቴሌኮምዩኒኬሽን፣ የባንክ፣ የትራንስፖርት፣ የጤና እና የንግድ እንቅስቃሴዎች በፍጥነት መጀመር አለባቸው የሚለው ነው። የአገር መከላከያ አባላት የሆኑትን ጨምሮ ማንነታቸውን መሠረት ተደርጎ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ በመላው አገሪቷ የትግራይ ተወላጆች የጅምላ እስር ይቁም ይላል። የ2013 ዓ.ም. እና የ2014 ዓ.ም. በጀት በፍጥነት መለቀቅ አለበት፣ የኤርትራ ጦር እና የአማራ ኃይሎች ከትግራይ ይውጡ (ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ መረጋገጥ አለበት) ብሏል። የሰብዓዊ እርዳታ ለማድስ ለሁሉም አይነት የትራንስፖርት አማራጮች በርካታ መተላለፊያ ኮሪደሮች ክፍት መደረግ አለባቸው የሚሉት ቅድመ ሁኔታዎች በአቋም መገለጫው ላይ ሰፍሯል። የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ከላይ የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች ተፈጻሚ ሆነው ይህም በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ለሕዝብ ይፋ መደረግ አለበት ይላል መግለጫው። በህወሓት የሚመራው የክልሉ መንግሥት ከመንበሩ ከተወገደ በኋላ በፌደራል መንግሥቱ የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሰኔ 21/2013 ዓ.ም የአገሪቱ ፌዴራል መንግሥት "ሰብዓዊነትን መሰረት ባደረገና ተጨማሪ ጉዳት በማያስከትል መልኩ" የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርግ ጥያቄ ማቀረቡ ይታወሳል። የፌደራሉ መንግሥትም የጊዜያዊ አስተዳደሩን ጥያቄ ተቀብሎ በክልሉ የሚገኙ አርሶ አደሮች በክረምቱ ወራት የእርሻ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ እና የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እንዲቻል የተናጠል ተኩስ አቁም አውጃለሁ ብሎ ነበር። የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር የነበረው የህወሓት ኃይሎች በአገሪቱ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በተካሄደ ወታደራዊ ዘመቻ ከሥልጣኑ ተወግዶ የነበረ ሲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የክልሉን አስተዳደር ሕገወጥ ብሎ መበተኑ ይታወሳል። ከጥቂት ወራት በፊትም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የክልሉ ገዢ ፓርቲ የነበረውን ህወሓትን ሽብርተኛ ቡድን ብሎ ሰይሞታል። የፌደራል መንግሥቱ የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ ሠራዊቱን ከትግራይ ካስወጣ በኋላ ወደ መቀለ ተመለሱት የህወሓት አመራሮች ግን "በሕዝብ የተመረጥን ሕጋዊ የክልሉ አስተዳዳሪዎች ነን" ማለታቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58015467
amh
politics
"ፈጣሪ ብቻ ነው ከስልጣን ሊያነሳኝ የሚችለው"የብራዚሉ ፕሬዚዳንት
የብራዚሉ ቀኝ ዘመም ፕሬዝዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ የአገሪቱ ነጻነት በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር በርካቶችን ያስገረመና አንዳንዶችን ደግሞ ያበሳጨ መልእክት አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንቱ በሳኦ ፖሎ ባደረጉት ንግግር '' ፈጣሪ ብቻ ነው ከስልጣን ሊያነሳኝ የሚችለው'' ብለዋል። በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ላይ ትችት የሰነዘሩ ሲሆን እነዚህ ተቋማት እሳቸውን እና የፖለቲካ ወዳጆቻቸውን እያጠቁ እንደሆነ ገልጸዋል። በቅርቡ የአገሪቱ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ላይ ምርምራ እንዲደረግ ፈቃድ መስጡ የሚታወስ ነው። ፕሬዝደንት ቦልሶናሮ በሚያደርጓቸው በስሜት በተሞሉ ንግግሮች ትችት የሚሰነዝሩባቸውን ሰዎች ከማብጠልጠል ባለፈ የተለያየ አይነት ስም በመስጠትና ሁሌም ተጠቂ እንደሆኑ ለማመላከት ሲጥሩ ይታያሉ። ደጋፊዎቻቸው ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ይህንን ንግግራቸውን በሚያደርጉባት ሳኦ ፖሎ ከተማ የብራዚልን ባንዲራ በመያዝ ተሰባስበዋል። ድጋፋቸውንና ሁሌም አብረዋቸው እንደሆኑም ሲገልጹ ታይተዋል። ነገር ግን በቅርቡ የተጀመረባቸው ምርመራ እና እየጨመረ የመጣው ከስልጣን ይውረዱ ጥያቄ ፕሬዝዳንቱ በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ጠንከር ያለ እና ቁጣ የተቀላቀለበት መልዕክት እንዲያስተላልፉ አድርጓቸዋል። ምንም እንኳን ብራዚል ምርጫ የምታካሂደው በመጪው የፈርንጆቹ ዓመት 2022 ጥቅምት ወር ላይ ቢሆንም ከወዲሁ ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ተቀባይነታቸውና ድጋፋቸው እየቀነሰ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። እንዳውም ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዝቅተኛ ድጋፍ እንዳላቸው መረጃዎች ጠቁመዋል። አትላስ ኢንስቲትዩት የተባለው ተቋም በሰራው ጥናት መሰረት 61 በመቶ የሚሆኑት ብራዚላውያን የአገራቸውን መንግስት መጥፎ አልያም እጅግ በጣም ጥፎ ነው ብለው የሚያስቡ ናቸው። ይህ ቁጥር ደግሞ ፕሬዝዳንቱ በአውሮፓውያኑ 2019 ወደ ስልጣን ሲመጡ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ23 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ፕሬዝዳንቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በአግባቢ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ከስልጣናቸው ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም የታችኛው ኮንግረስ አፈ ጉባኤ ውሳኔውን በመቃወማቸው ቦልሶናሮ በስልጣን እንዲቆዩ ሆኗል። ይህንን ተከትሎም ፕሬዝዳንቱ ከሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንደሆነና ኮንግረሱም ሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እሳቸውን ከስልጣን ለማስወገድ እየሰሩ እንደሆነ በተጋጋሚ ይገልጻሉ። ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንቱ በርካታ ደጋፊዎቻቸውን የሚወክሉ የኢቫንጀሊካል ሃይማኖታዊ መሪዎችን ባገኙበት ወቅት ሶስት ምርጫዎች እንዳላቸው ነግረዋቸው ነበር። ''ወደፊት ሶስት ምርጫዎች ብቻ ናቸው ያሉኝ፤ በቁጥጥር ስር መዋል፣ መገደል ወይም ደግሞ ማሸነፍ'' ብለዋል። የብራዚል የነጻነት ቀን ላይ ባደረጉተው ንግግርም ይህንኑ አስተያየታቸውን የደገሙ ሲሆን ''ከዚህ በኋላ እኔን ከስልጣን ሊያነሳኝ የሚችለው ፈጣሪ ብቻ ነው'' ሲሉ ተደምጠዋል። እስከ 140 ሺ የሚደርሱ የፕሬዝዳንቱ ደጋፊዎችም በስነስርአቱ በመገኘት የአገራቸውን ባንዲራ እያውለበለቡ ለፕሬዝዳንቱ ያላቸውን ድጋፊ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ ቀደም ብለዋ ወደ ዋና ከተማዋ ብራዚሊያ ተጉዘው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸውን አግኝተዋል። በወቅቱም በርካታ ፖሊሶች በቦታው የነበሩ ሲሆን ደጋፊዎቻቸውም ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለመግባት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል። ነገር ግን ከነበረው የፖሊስ ቁጥር አንጻር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን መቆጣጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። በርካታ የቦልሶናሮ ደጋፊዎች ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ኮንግረስ እንዲዘጉ የጠየቁ ሲሆን ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም ፕሬዝዳንቱን እያጠቁ ነው ሲሉም ይከሳሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-58497052
amh
politics
በቶማስ ሳንካራ ግድያ በቀድሞው የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝደንት ላይ የ30 ዓመት እስር ተጠየቀ
በቀድሞ በቡርኪና ፋሶ መሪ ቶማስ ሳንካራ ግድያ ተባባሪ ናቸው የተባሉት የቀድሞው የአገሪቱ መሪ ብሌስ ኮምፓዎሬ ላይ የ30 ዓመት የእስር ቅጣት ተጠየቀባቸው። የቡርኪና ፋሶ ዐቃቤ ሕግ የቀድሞው ፕሬዝደንት በለውጥ ሃዋሪያው ቶማስ ሳንካራ ግድያ ተሳታፊ በመሆናቸው የሦስት አስርት ዓመታት እስር ሊበየንባቸው ይገባል ብሏል። ቶማሳ ሳንካራ እአአ 1987 ላይ መገደላቸው ይታወሳል። የፈረንሳይ መንግሥት የቶማስ ሳንካራን ግድያ የሚመለከት ዝርዝር የጦር ሠራዊት ሰነድ ይፋ ለማድረግ መስማማቱን ተከትሎ በቀድሞው መሪ ግድያ ዙሪያ ባለፈው ዓመት ምርመራ መጀመሩ ይታወሳል። የቀድሞ የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝደንት ቶማስ ሳንካራ በአገሪቱ መዲና ዋጋዱጉ ውስጥ በ37 ዓመታቸው ከተገደሉ በኋላ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዷል። ይህንንም ተከትሎ በዚያው ዓመት ብሌስ ኮምፓዎሬ በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ሥልጣን መጥተዋል። ፕሬዝደንት ኮምፓዎሬ በሕዝባዊ አመጽ ከመንበራቸው እስተወገዱበት እአአ 2014 ድረስ ለ27 ዓመታት ቡርኪና ፋሶን መርተዋል። ኮምፓዎሬ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ከአገር ተሰደው መኖሪያቸውን በጎረቤት አገር አይቮሪ ኮስት አድርገዋል። ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን እየተመለከተ ያለው የጦር ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዝደንት በሌሉበት "በአገር ደኅንነት ላይ ጥቃት በማድረስ" ወንጀል ጥፋተኛ እንዲላቸው ጠይቋል። ከዚህ በተጨማሪም የቶማስ ሳንካራ እና 12 የሳንካራ ባልደረቦች ግድያን በማቀነባበር ኮምፓዎሬ እንዲጠየቁ ከሳሾች ጠይቀዋል። የቀድሞ ፕሬዝደንት የሳንካራ የቅርብ ወዳጅ የነበሩ ሲሆን በሳንካራ ግድያ ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ የለኝም ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ ቶማስ ሳንካራን የገደለ የኮማንዶ ቡድን መርተዋል የተባሉት ሃይሲንዝ ካዳንዶ በ30 ዓመት እስር እንዲቀጡ እና ቶማስ ሳንካራ ከሥልጣን ባስወገደው መፈንቅለ መንግሥት ውስጥ ተሳታፊ ነበሩ የተባሉት ጊልበርት ዲኤንዴሬ በ20 ዓመት እንዲቀጡ ጠይቋል። ጊልበርት ዲኤንዴሬ እአአ 2015 ላይ በተፈጸም የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጥፋተኛ ተብለው የ20 ዓመት እስር ተበይኖባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በቶማስ ሳንካራ ጉዳይ በአካል ከችሎት ፊት ቀርበዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60309094
amh
politics
ከደኅንነት ኃላፊው ጉብኝት በኋላ ጠ/ሚ ዐቢይ ከሱዳን ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት አባላት ጋር መወያየታቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያው የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ወደ ሱዳን አቅንተው ከአገሪቱ ምክትል ወታደራዊ መሪ ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የልዑካን ቡድኑን አባላት ሰኞ ኅዳር 12/2015 ዓ.ም. በጽህፈት ቤታቸው ባገኙበት ወቅት በሁለቱ አገራት የጋራ ጉዳዮች መነጋገራቸው ተገልጿል። ከአንድ ዓመት በላይ በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ውስጥ ያለችው ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት በታላቁ ሕዳሴ ግድብና በድንበር ይገባኛል ምክንያት እንዲሁም በትግራይ ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ ግንኙነታቸው ሻክሮ ቆይቷል። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ ከሚካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ ሱዳንን አንስተው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ሱዳን ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ ባገረሸው ጦርነት ውስጥ ምንም አይነት ሚና እንዳልነበራት ተናግረው ነበር። የሁለቱ አገራት መሪዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገናኝተው በግንኙነታቸው ዙሪያ መወያየታቸው የተዘገበ ሲሆን፣ የሱዳን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን ባለፈው ጥቅምት ወር በጣና ፎረም ላይ ለመሳተፍ ባሕር ዳር በመገኘት ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገራቸው ይታወሳል። ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ካርቱም ውስጥ ከአገሪቱ ምክትል ወታደራዊ መሪ ሌፍተናንት ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሐሜቲ) ጋር መነጋገራቸውን የሱዳን መንግሥት ዜና ወኪል ዘግቧል። በውይይታቸውም በአገራቱ መካከል በደኅንነት እና በሌሎች ዘርፎች ስለሚደረግ ትብብር መወያየታቸውንና ሱዳንም በመንግሥት እና በህወሓት መካከል ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት ጄኔራሉ አድናቆታቸውን መግለጻቸው ተዘግቧል። ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሚዋሰኑበት የአል ፋሽካ ለም የእርሻ መሬት ላይ ለዓመታት የቆየ የይገባኛል ጥያቄ የነበረ ሲሆን፣ ከሁለት ዓመት በፊት ትግራይ ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት በተቀሰቀሰበት ጊዜ ሱዳን ሠራዊቷን አሰማርታ አካባቢውን መቆጣጠሯ ይታወሳል። በጦርነቱ ወቅትም ከሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው የሚገቡ ታጣቂዎች እንዳሉ በባለሥልጣናት ወቀሳ ሲሰነዘር ነበር። በትግራይ ጦርነት ተወጥራ የቆየችው ኢትዮጵያ የሱዳን ሠራዊት ከያዛቸው የድንበር አካባቢዎች ለቅቆ እንዲወጣ እና በንግግር ችግሩ እንዲፈታ በተደጋጋሚ ስትጠይቅ የቆየች ቢሆንም፣ ከሱዳን በኩል ግን ግዛቱ እራሷ መሆኑን በመግለጽ ይዞታዋን ስታጠናክር ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ጄኔራል አል ቡርሐን ባለፈው ዓመት ኬንያ ውስጥ በተደረገው በኢጋድ ስብሰባ፣ ከወር በፊት ባሕር ዳር ላይ በጣና ፎረም እና ባለፈው ሳምንት ደግሞ ግብፅ በአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ መገናኘታቸው ተዘግቧል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1ve0rg627o
amh
politics
ምርጫ 2013፡ የሐረሪ ክልል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን መክሰሱን አስታወቀ
ከሐረሪ ክልል ውጭ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጅ አባላት በሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አባላት ምርጫ ላይ መሳተፍ አይችሉም የሚለውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዱን የሐረሪ ክልል አስታወቀ። የሐረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ጽህፈት ቤት ኃላፊና የፖለቲካና የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልሃኪም ኡመር ለቢቢሲ እንደገለፁት ቦርዱ "ሕጋዊ አግባብን አልተከተለም፤ የሕግ ጥሰት ፈፅሟል" በማለት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት መክሰሳቸውን አስታውቀዋል። የሐረሪ ክልል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ከመውሰዱ በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "ለምርጫ ቦርድ የላካችሁት ሰነድ ማህተም የሌለውና ፍትሃዊ ባለመሆኑ ውድቅ ተደርጓል" በሚል አቤቱታ ማቅረባቸውን ይናገራሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰነዶቹን ማህተም አድርጎ ለምርጫ ቦርድ ቢልክም ውሳኔው ባለመቀልበሱ ወደ ፍርድ ቤት ማምራታቸውን ይናገራሉ። የሐረሪ ሕዝብ ክልል ምክር ቤት፣ የሐረሪ ሕዝባዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤትና የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የሐረሪ ሕዝብ የክልሉ ምክር ቤት አካል ለሆነው ለሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ እንዲመርጡ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄያቸውን አቅርበው ነበር። ጥያቄው መነሻውን ያደረገው መጋቢት 6/1987 የሽግግር መንግሥቱ የተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀውን ውሳኔ ተንተርሶ መሆኑንም ከምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ከዚህም በተጨማሪ የሐረሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 50 ቁጥር 2 እንደሚያትተው የክልሉ ምክር ቤት አባላት የሆኑትና 14 አባላት ያሉት "የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አባላት በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጭ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎችና ከተሞች ከሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ አባላት ይመረጣል" የሚለውን መሰረት ያደረገ እንደሆነ አቶ አብዱልሃኪም ያስረዳሉ። ምርጫ ቦርድም ክልሉ ያቀረባቸውንና በ1987 የሽግግር መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት የወሰናቸውን ውሳኔዎችና ሰነዶቹን ከሕገ መንግሥት አንፃር እንደመረመረ አስታውቆ፤ ከክልሉ ውጭ ያሉ የሐረሪ ተወላጆች በመጪው ምርጫ የመሳተፋቸውን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉን ሚያዝያ 1/2013 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ቦርዱ ለዚህም ሕገ መንግሥቱን የጠቀሰ ሲሆን "ቦርዱ በሕገ መንግሥቱ መሰረት በአንድ ክልል የመንግሥት መዋቀር ውስጥ የሚገኙ የምክር ቤት አባላት መመረጥ የሚኖርባቸው በክልሉ ድምፅ መስጠት በሚችሉ ነዋሪዎች ነው" በማለት ገልጿል። ጨምሮም "ከዚህ ውጭ ሕገ መንግሥቱ አንድ ቁጥሩ አነስተኛ የሆነ ብሔረሰብ ለክልል ምክር ቤቶች ሲያስመርጥ ከክልሉ ውጭ ያሉ የብሔረሰብ አባላት እንዲመርጡ የደነገገው እንዲሁም ለዚህ ብሔረሰብ አባላት ለብቻው የተለየ አሰራር መተግበር የሚያስችል በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለ ድንጋጌ በምርመራው ቦርዱ ያገኘው ነገር የለም" ብሏል። የሐረሪ ክልል ብሔራዊ ጉባኤ ሚያዝያ 3/2013 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ እንደማይቀበል አስታውቆ ነበር። "ምርጫ ቦርድ ይህንን የመወሰን ስልጣን የለውም" የሚሉት አቶ አብዱልሃኪም እንደ ምክንያትነት የሚያቀርቡትም የሽግግር መንግሥቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወሰነውን ውሳኔና የክልሉን ሕገ መንግሥት በመጥቀስ ሲሆን "በሕግ የተደነገገ ነው" ይላሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1987 ውሳኔ ባልተሻረበት ሁኔታ የክልሉ ሕገ መንግሥት በግልፅ ባስቀመጠበት ሁኔታ "እነዚህን ሕጎች መፃረሩ ከአንድ ትልቅ ተቋም የሚጠበቅ አይደለም" ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ምርጫ ቦርዱ የሽግግር መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከክልሉ ውጭ ነዋሪ በሆኑ የብሔረሰቡ አባላት ይመረጣል የሚለውን ውሳኔ የሚደግፍ ሕገ መንግሥታዊ አንቀፅ አለመጠቀሱን ምርጫ ቦርድ ገልጿል። ይህንን በተመለከተም አቶ አብዱልሃኪም እንደሚሉት ምርጫ ቦርድ የአገሪቱንና የክልሎችን ሕገ መንግሥት መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚሰራ ጠቅሰው፤ አንዳንድ የፌደራል ሕገ መንግሥት ላይ ያልተጠቀሱ ጉዳዮች በክልል ሕገ መንግሥቶች ላይ በዝርዝር ሊቀመጡም እንደሚችሉ ይናገራሉ። እንደ ምሳሌነትም የደቡብ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤትን ይጠቅሳሉ። የብሔረሰቦች ምክር ቤት በፌደራል ሕገ መንግሥት ባይቀመጥም በክልሉ ሕገ መንግሥት የተቀመጠና ምርጫ ቦርድም ይህንኑ መነሻ አድርጎ ነው ምርጫውን እያስፈፀመ ነው ያለው ይላሉ። ቦርዱ የክልሎችን ሕገ መንግሥቶች ባከበረ መልኩ ነው ሲሰራ የነበረው። ከዚህም በተጨማሪ ምርጫ ቦርድ በስድስተኛውም የአገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ክልሎችን (ጣቢያዎችን) ሲያቋቁም መነሻው የፌደራል እንዲሁም የክልሉ ሕገ መንግሥት እንደሆነ ያወሳሉ። ምርጫ ቦርድ ከዚህም በተጨማሪ መጋቢት 6/1987 የሽግግር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 102ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔ የምክር ቤቱ ማህተም ያረፈበት ስላልሆነ ውሳኔው አግባብ አለመሆኑ አመልካች ነው፤ እንዲሁም የሰነዱን ተቀባይነት ችግር ላይ ጥሎታል ብሏል። ሰነዱ ማህተም የለውም ወይ? የሚል ጥያቄ ከቢቢሲ የቀረበላቸው አቶ አብዱልሃኪም በበኩላቸው ለምርጫ ቦርድ ስለቀረቡ ሰነዶች ምላሽ አላቸው። ስድስት ገፆች ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ ከመሸኛ ደብዳቤ ጋር የተያያዘ ሲሆን መሸኛ ደብዳቤው ላይ ቀን፣ ቁጥርና ማህተም አለው። ከዚህም በተጨማሪ በጊዜው የነበረው ኮሚቴ ያቀረበው ሪፖርት 17 ገጽም ተያይዟል። የተያያዙት ሰነዶች ላይ ምንም አይነት ማህተም እንደሌለው የሚናገሩት አቶ አብዱልሃኪም "በዚህኛው ውሳኔ ብቻ የተፈጠረ ነው? ወይስ ከዚህም በፊት የነበሩ ውሳኔዎች ተመሳሳይ ሂደት ነው ያላቸው? አሰራሩን መፈተሽ ያለበት ምርጫ ቦርድ ነው" ይላሉ። እንደ አቶ አብዱልሃኪም ምርጫ ቦርድ ሰነዶቹ ማህተም የላቸውም ከተባለ ውሳኔውን ከማሳለፉ በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት አቅርቦ ጠይቆ፣ ፈትሾና መርምሮ በዚያ መሰረት መወሰን ይገባው ነበር ይላሉ። "በዚያ መነሻነት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ መሆን አለመሆኑን ሲያረጋግጥላቸው ምላሹን ከሰሙ በኋላ ውሳኔ መወሰን በተገባቸው ነበር። ተቋማዊ አሰራር ያልተከተለ ነው" ይላሉ። የሐረሪ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰነዶቹ ተቀባይነት እንደሌላቸው ጠቅሶ አቤቱታ ማስገባቱን ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበኩሉ የ1987 ሰነዶችን መነሻ በማድረግ የራሱንም ውሳኔ ጨምሮ ክልሉ ያቀረበለትን ደብዳቤ ጨምሮ ወደ 39 ገጽ በራሱ ማህተም ለምርጫ ቦርድ መላኩንም ይናገራሉ። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ "የወሰንነውን ውሳኔ መልሰን የምናይበት አግባብ ስለማይኖር ሌላ ውሳኔ የሚሰጥ አካል ውሳኔ የሚሰጥበት መንፈስ ያለው አይነት ምላሽ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ልኳል" ይላሉ። በሕዝብ ተወካዮች በኩል ያለው ጉዳይ በራሱ እየሄደ ቢሆንም በፍርድ ቤትም በኩል እንዲወሰን በመሻት ክልሉ መክሰሱን ይናገራሉ። በሌላ በኩል አቶ አብዱልሃኪም ምርጫ ቦርድ ባለፉት አምስት ብሔራዊ ምርጫዎች ይጠቀምበት የነበረውን መመሪያ "በዚህ ውሳኔ እውቅናን ነፍጓል" ቢሉም ቦርዱ በበኩሉ መመሪያውን ከጽህፈት ቤቱ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል። ዝርዝር መመሪያው የ1987ቱን የተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት ያደረገና የባለፉትንም አምስት ምርጫዎች በዚሁ መልኩ ሲያስፈጽም የነበረ መሆኑ ተጠቅሷል። አቶ አብዱልሃኪም በዚህ አባባል አይስማሙም "ሥራ ላይ ያሉት መመሪያዎች የእኔ አይደሉም፤ አላውቃቸውም ማለቱ ትክክል አይደለም" ይላሉ። ነገር ግን ቦርዱ በፃፈው ደብዳቤ እንደጠቀሰው ምንም እንኳን ለሐረሪ ጉባኤ የሚመረጡ ተወካዮች ከክልሉ ውጭ ባሉ የብሔረሰብ አባላት ምርጫ ቦርድ ሲያስመርጥ ቆይቶም ከሆነ ሕገ መንግሥታዊና የምርጫ ሕጉ መሰረት የሌላቸውን አሰራሮች እንደማይከተል አስታውቋል። ቦርዱም በምርጫ ማሻሻያው እንዲህ አይነት ልምዶች እንዲቀሩ እየሰራ ነው ብሏል። ምንም እንኳን ላለፉት አስርት ዓመታት የተተገበረ ጉዳይ ነው ብሎ ቦርዱ ቢወስን "ሌሎች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ብሔረሰቦች ከክልላቸው ውጭ ያሉ አባሎቻቸው በምርጫው እንዲሳተፉ ቢጠይቁ ቦርዱ ልፈፅም አልችልም ቢል የቦርዱን በፍትሐዊነት እና በገለልተኛነት ምርጫን የማስተዳደሩ ጉዳይ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል" ይላል። አቶ አብዱልሃኪም በበኩላቸው "ባለው ነገር ላይ መጨመር ነው እንጂ ሌሎች አናሳ ብሔሮችም እንዲህ አይነት የመብት ጥያቄ ቢጠይቁኝ መመለስ ስለማልችል የናንተንም በዚህ ወቅት ማስተናገድ አልችልም የሚለው ትክክል አይደለም" ይላሉ። ኢትዮጵያም ውስጥ የመከላከያ ሰራዊት፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየአካባቢያቸው የሚመርጡበት አሰራር እንዳለና በሌሎች አገራትም እንዲሁ በየኤምባሲዎቻቸው የሚመርጡበት ሁኔታ ልምድ መኖሩን ጠቅሰው የ "ሃረር የተለየ እንዳዳልሆነ" ይናገራሉ። "አገራችን ላይ ሕጉ አለ፤ ይሄንንም በተመለከተ ምርጫ ቦርድ መመሪያ ያወጣል የሚል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ አለ፤ የምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅም ላይ አለ" ይላሉ አቶ አብዱልሃኪም። "ያንን ከመተግበር አንፃር የኢኮኖሚ አቅማችንና የእድገታችን ደረጃ ገና ስለሆነ ይሄ የመተግበርና ያለ መተግበር ጉዳይ ነው" ሲሉ ያክላሉ። የሐረሪ ሕዝብ ክልል ምክር ቤት ከሁለት ጉባኤዎች የተዋቀረ ሲሆን እነዚህም የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤና የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ናቸው። የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤ 22 አባላት ሲኖሩት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ደግሞ 14 የሐረሪ ብሔረሰብ አባላትን የያዘ ነው። ምርጫ ቦርዱ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ የሐረሪ ተወላጆች በጉባኤው ምርጫ መሳተፍ አይችልም የሚል ውሳኔን ቢያስተላልፍም የሐረሪ ጉባኤ 14 መቀመጫ በሐረሪ ብሔረሰብ አባላት የመያዙን ሁኔታ አይቀይረውም። ጉባኤው ከሐረሪዎች ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ በተያያዘ ማንነትና ህልውናቸው እንዲቀጥል ከማድረግ ጋር የተያያዙ ውሳኔዎችን የሚያስተላልፍና በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው የሚኖሩ የሐረሪ ተወላጆችን የሚያስተሳስር እንደሆነ አቶ አብዱልሃኪም ይናገራሉ።
https://www.bbc.com/amharic/56841527
amh
politics
የቤንያሚን ኔታንያሁ የሙስና ክስ በቅጣት ድርድር ሊቋጭ እንደሚችል ተገለጸ
በሙስና የተከሰሱት የእስራኤል የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የፍርድ ሂደቱን ለማስቆም የቅጣት ድርድር እያደረጉ እንደሆነ ቢቢሲ ከቅርብ ምንጭ ተረድቷል። በቅጣት ድርድሩ መሰረት የ72 አመቱ ቤንያሚን ኔታንያሁ በተወሰነ ደረጃ ጥፋተኝነታቸውን ማመን የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህም ከሆነ ወንጀላቸው ተቀንሶ በእስር ፋንታ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሳተፉ ሊያደርግ የሚያስችል ነው። ኔታንያሁ በበኩላቸው ጥፋተነኝነታቸውን ካመኑ ከፖለቲካው ዓለም እንዲገለሉ የሚያስገድደውን ይህንን የቅጣት ድርድር ለመቀበል መቃወማቸውን በተመለከተ ሪፖርቶች ወጥተዋል። እስራኤልን ለረዥም ዘመን ያስተዳደሯት ቤንያሚን ኔታንያሁ ባለፈው አመት ከተካሄደው ምርጫ በኋላ ራሳቸውን ከፖለቲካው ገለል አድርገዋል። በእስራኤል ፓርላማ ውስጥ ትልቁ ፓርቲ የሆነው የቀኝ ክንፉ ሊኩድ መሪ ሲሆኑ አገራቸውንም ለ15 ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል። ባለፉት አምስት አመታት የስልጣን ዘመናቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች ፖሊስ ምርመራ የከፈተባቸው ሲሆን የፍርድ ሂደቱም በአውሮፓውያኑ 2020 ተጀምሯል። በጉቦ፣ በማጭበርበር እና እምነት በማጉደል የተከሰሱት ቤንያሚን ኔታንያሁ እሳቸው ግን ክሶቹ ፖለቲካዊ አላማ አላቸው በማለት ውድቅ አድርገዋቸዋል። ኔታንያሁ ከጠቅላይ አቃቤ ህግ አቪቻይ ማንደልብሊት ጋር በቅጣት ድርድር ላይ መወያየታቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች በቅርብ ቀናት ውስጥ ከእስራኤል ሚዲያዎች ተስምተዋል። ለቅጣት ድርድሩ ጋር ቅርበት ያላቸውና ስማቸው ያልተጠቀሰ ምንጭ እሁድ እለት የቅጣት ድርድሩ መካሄዱን አረጋግጠዋል ሲሉ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል። የእስራኤሉ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ኔታንያሁ በተወሰነ መልኩ የጥፋተኝነት ደረጃን መቀበላቸውን ቤተሰቦቻቸው ቢቃወሙም ጠበቆቻቸው ውይይቱን እንዲቀጥሉ ማዘዛቸውን ተናግረዋል። የመጀመሪያው ክስ ከሀብታም ወዳጃቸው ሻምፓኝ፣ ሲጋራና ሌሎችም ውድ ስጦታዎች በጉቦ ተቀብለዋል የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የዜና ሽፋን ለማግኘት ከጋዜጣ አሳታሚ ጋር ተዋውለዋል የሚል ነው። ከሁሉም ክሶች ከባዱ የተባለው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ለዜና ሽፋን ሲሉ አውራ የቴሌኮም ድርጅትን የሚጠቅም ሕግ አስተዋውቀዋል የሚለው ነው። በወቅቱ ሕጉ በባለሙያዎች የተደገፈ እንደሆነ የገለጹት ኔታንያሁ ይህ ክስ እስከ አስር ዓመት የሚሆን እስር እንዲሁም የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣቸዋል ተብሎ ነበር። እኚሁ ምንጭ እንደተናገሩት ክሶቻቸው እንዲቋረጡ ጥፋተኝነታቸውን እንዲያምኑና "የሞራል ውድቀት" የተባለውን ክስ እንዲቀበሉ ተጠይቀዋል። በዚህም መሰረት ለሰባት ዓመታት በፖለቲካው የሚታገዱ ሲሆን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን እየተቃወሙ ነው ተብሏል። በፖለቲካዊ መሰረታቸው ጠንካራ ድጋፍ ያላቸው ኔታንያሁ አሁን ያለውን ጥምር መንግሥት ተቃውመው በቅርቡም ወደ ስልጣን የመመለስ አላማ እንዳላቸው ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60016069
amh
politics
ሩሲያ ኒዩክሌር የመታጠቅ አቅም ያላቸው ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለቤላሩስ ለመስጠት ቃል ገባች
ሩሲያ በሚቀጥሉት ወራት ኒዩክሌር የመታጠቅ አቅም ያላቸውን አጭር ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለመተኮስ የሚያስችል ሥርዓት ወደ አጋሯ ቤላሩስ እንደምትልክ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ። ፕሬዚደንቱ እንዳሉት ኢስካንድር- ኤም የተበላው ሥርዓት የባልስቲክ እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን መተኮስ የሚያስችል ሲሆን እስከ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ኢላማዎችን መምታት ይችላል። የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቱን ባለፈው የካቲት ወር ላይ በዩክሬን ላይ ወረራ ማወጃቸውን ተከትሎ በሩሲያና በምዕራባውያኑ መካከል ያለው ውጥረት ጨምሯል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ፑቲን ስለ ኒዩክሌር የጦር መሣሪያዎች ብዙ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህንን ንግግራቸውን አንዳንዶች የምዕራብ አገራት ጣልቃ እንዳይገቡ ለማስጠንቀቅ ያለመ ነው ብለውታል። ፑቲን  የሩሲያ የወደብ ከተማ በሆነችው ሴንት ፒተርስበርግ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ከቤላሩስ ፕሬዚደንት ሉካሽንኮ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ሩሲያ የቤላሩስ ኤስዩ-25 የጦር አውሮፕላኖች የኒዩክሌር የጦር መሣሪያዎችን መያዝ እንዲችሉ ለማድረግ ትረዳለች ብለዋል። ፕሬዚደንት ፑቲን ከአቻቸው የቤላሩሱ ፕሬዚደንት አሌክሳንደር ሉካሸንኮ ጋር ባደረጉትና ቅዳሜ ዕለት በቴሌቪዥን በተላለፈው ስብሰባ ላይ “ ወስነናል። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ለቤላሩስ ኢስካንደር- ኤም የተባለውን የሚሳኤል መተኮሻ ሥርዓት እናስረክባለን” ብለዋል። መሣሪያዎቹን የማስረከብ ዝርዝር ሂደቱን በተመለከተ የሁለቱ አገራት መከላከያ ሚኒስትሮች እንደሚሰሩም ፕሬዚደንቱ አክለዋል። ኢስካንደር ሚሳኤሎች የኔቶ አባል በሆኑት ሉትዌንያ እና ፖላንድ መካከል በምትገኘው የሩሲያ ባልቲክ ባህር ዳርቻዋ ካሊኒንግራድ ተሰማርተዋል። ሁለቱ ፕሬዚደንቶች የሉትዌኒያ አንዳንድ እቃዎች ወደ ካሊኒንግራድ እንዳይጓዙ ለመከለካል ባደረገችው ውሳኔ ላይ የተወያዩ ሲሆን እርምጃው ሞስኮን አስቆጥቷል። የቤላሩሱ ፕሬዚደንትም የሉትዌንያ እርምጃ “ የጦርነት አዋጅ እና ተቀባይነት የሌለው ነው” ብለዋል። ሉትዌንያ ግን እርምጃዋ ተፅዕኖ የሚያሳድረው ለወትሮው በወደቡ ከሚተላለፉ የሩሲያ ምርቶች መካከል አንድ በመቶ በሚሆነው ላይ  ነው ስትል ሩሲያ ካሊኒንግራድ እንቅስቃሴውን አግዳለች ስትል ያቀረበችውን ክስ አጣጥላለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ እሁድ ዕለት ጠዋት በዩክሬን ኪዬቭ በርካታ ፍንዳታዎች መከሰታቸውን የከተማዋ ከንቲባ ቫይታሊ ክሊሽኮ ተናግረዋል። “አምቡላንሶችና የነፍስ አድን ሰራተኞች በሥፍራው ይገኛሉ። በሁለት ሕንጻዎች ላይ የነፍስ ማዳንና ሰዎችን የማስወጣት ሥራ እየተከናወነ ነው “ ብለዋል ከንቲባው። ኤኤፍፒ የዜና ወኪል በከተማ የሚገኘው የመኖሪያ ቤት ሕንጻ መመታቱን ዘግቧል። ለሳምንታት ከባድ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ ዩክሬን የሩሲያ ኃይሎች ቅዳሜ ዕለት ምሥራቃዊ ከተማዋን ስቨሮዶንስክ “ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን” አስታውቃለች። ይህ ማለት ሩሲያ የዩክሬንን ሰፊውን የኢንደስትሪ ግዛት፣ዶንባስን የሚፈጥሩትን ሉሃንስክ ክልል ሙሉ በሙሉ በሚቻል ደረጃ እንዲሁም አብዛኛውን ዶንስክ ክልል ተቆጣጥራለች ማለት ነው። የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ቅዳሜ ዕለት ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት፣ በሩሲያ የተያዙ ከተሞቻቸውን ለመመለስ ቃል ገብተዋል። ሆኖም ከሩሲያ ጋር ያለው ጦርነት በስሜታዊነት አስቸጋሪ ደረጃ ላይ መድረሱንና ምን ያህል ድብደባዎች እና ኪሳራዎች እንደሚኖሩ እንደማያውቁ ፕሬዚደንት ዜሌንስኪ ተናግረዋል። አርብ ዕለት ምሽት ሩሲያ ኢላማዋ ወደሆኑት ሰሜንና ምዕራብ ዩክሬን አካባቢዎች የሚሳኤል ጥቃት ከፍታለች። በዚህ ጥቃት በምዕራብ ኪዬቭ ሳርኒይ በተባለች ከተማ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች በፍርስራሽ ሥር ሳይቀበሩ እንዳልቀረ የአካባቢው ባለሥልጣን ተናግረዋል። ዩክሬን የተወሰኑት ሮኬቶች የተተኮሱት ከቤላሩስ ነው ብላለች። ቤላሩስ ለሩሲያ የሎጂስቲክስ ድጋፍ እያደረገች ሲሆን ጦሯ ግን በይፋ በጦርነቱ ላይ አልተሳተፈም። የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት የሚሳኤል ጥቃቱ ሩሲያ ቤላሩስን ወደ ጦርነቱ ለማስገባት የምታደርገው ጥረት አካል ነው ብለዋል። ሩሲያ ሴቬሮዶኔትስክን በቁጥጥር ሥር ማዋሏ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በኔቶ ንግግር ካደረጉ በኋላ ለጂ7 ስብሰባ ወደ ጀርመን ከማቅናታቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ነው። በቅርብ ወራት ውስጥ የምዕራቡ ዓለም ጥምረት ጭንቀትና ድካም ታይቶበታል። ይሁን እንጂ ቅዳሜ ዕለት የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዩክሬን ጦርነቱን እንደምታሸንፍ ተናግረዋል። “ አሁን በዩክሬን ተስፋ የምንቆርጥበት ሰዓት አይደለም” ብለዋል ቦሪስ ጆንሰን። እሁድ እለት የኢንዶኔዥያ ፕሬዚደንት ጆኮ ዊዶዶ፣ የዩክሬንና የሩሲያ መሪዎች ንግግራቸውን እንደገና እንዲጀምሩ አሳስበዋል። “ ጦርነት መቆም አለበት፤ የዓለም የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትም ማንሰራራት አለበት” ብለዋል ፕሬዚደንት ጆኮ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c51748vv37ko
amh
politics
ሩሲያ የኒውክሌር መሳሪያዎቿ ላይ አሜሪካ ፍተሻ እንዳታደርግ አገደች
ሩሲያ 'ስታርት' ተብሎ በሚታወቀው ስምምነት መሰረት አሜሪካ በስትራቴጅያዊ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎቿ ላይ የምታደርገውን ፍተሻ "ለጊዜው" ማገዷን አስታወቀች። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አሜሪካ እየተጠቀመችብን ነው ባለውና፣ ሩሲያ በአሜሪካ ግዛት ውስጥ የምታደርገውን ተመሳሳይ የፍተሻ መብቷን በመንፈጓ መሰል እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል። አሜሪካ በበኩሏ የዩክሬን ወረራን ተከትሎ በሩሲያ ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች በአገራቱ መካከል ያለውን ሁኔታ ቀይሯል ብሏል። ሁለቱ አገራት የኒውክሌር የጦር መሳሪያዎቻቸውን በተመለከተ ፍተሻዎችን የሚያደርጉበትን ስምምነት እኤአ በ2011 ነበር ተግባራዊ የሆነው። ስታርት በቀድሞ የቀዝቃዛ ጦርነት ተቀናቃኞች አሜሪካ እና ሩሲያ መካከል ተግባራዊ እየተደረገ ያለ የመጨረሻው የጦር መሳሪያ ቅነሳ ስምምነት ነው። ስምምነቱ ሁለቱ አገራት ሊያሰማሩ የሚችሉትን የረዥም ርቀት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ 1,550 ላይ የገደበ ስምምነት ነው። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እገዳው የተላለፈው በስምምነቱ ላይ በተቀመጠው "ልዩ ሁኔታዎች" መሰረት ነው ብሏል። እገዳው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር አዲስ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ስምምነት ላይ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ከገለጹ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው። አሁን በሥራ ላይ ያለው ስምምነት እኤአ 2026 የሥራ ጊዜው ያበቃል። ሚኒስቴሩ አሜሪካ የአየር ግንኙነትን ማቋረጥን የመሳሰሉ "ከዚህ ቀደም የነበሩ እውነታዎችን" ወደ ጎን ብለላች ሲሉ ከሰዋል። የስታርት ስምምነት በቀድሞዋ ሲቪየት ኅብረት እና አሜሪካ መካከል ለዓመታት የተካሄዱ የኒውክሌር ጦርነትን ለማስቀረት ያለሙ የጦር መሳሪያ ቅነሳ ንግግር ተከትሎ ነበር የጸደቀው። ሩሲያ በየካቲት ወር ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ በሁለቱም ወገኖች ግጭቱ ወደ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ሊሸጋገር እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መስጠትን ጨምሮ፣ ጠብ አጫሪ ፕሮፖጋንዳዎች ሲሰሙ ቆይተዋል። በአንዳንድ የሩሲያ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ሩሲያ ከኔቶ ጋር ውጥረት ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ተንታኞች ስለሞስኮ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ፉክክር አዘል ንግግሮችን ሲያደርጉ ተደምጠዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c0wnv3x9r0yo
amh
politics
ምርጫ 2013፡ ቦርዱ ለ54 የምርጫ ክልሎች የታተሙ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ጉድለቶች አለባቸው አለ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ54 የምርጫ ክልሎች በታተሙ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ላይ የተለያዩ ጉድለቶችን ማግኘቱን አስታወቀ። ቦርዱ ረቡዕ ሰኔ 2/2013 ዓ.ም ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ባደረገበት ወቅት ይህንን ማሳወቁን በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የድምፅ መስጫ ወረቀት ህትመትን አስመልክቶ ያጋጠሙ ችግሮችን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ሪፖርት አቅርቧል። የዕጩዎችን ቁጥር መሰረት አድርጎ በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ወቅት ፓርቲዎች የዕጩዎች ቁጥር ላይ ባቀረቡት አቤቱታ፣ በድምፅ መስጫ ወረቀት እና በውጤት ማሳወቂያ ፎርሞች ላይ የማስታረቅ ሥራ ሲሰራ በድምፅ መስጫ ወረቀቶቹ ላይ ጉድለቶች መገኘታቸውን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ መግለፃቸው ተጠቅሷል። ቦርዱ ባደረገው ማጣራት ጉድለት የተገኘባቸው የድምፅ መስጫ ወረቆች ድጋሚ ህትመት ያስፈልጋቸዋልም ተብሏል። ጉድለት የተገኘባቸው የምርጫ ክልሎች በአፋር ስድስት፣ በአማራ 11፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ 2፣ በጋምቤላ 3፣ በኦሮሚያ 2፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች 15፣ በሶማሌ 14 እና በድሬዳዋ 1 ድጋሚ ህትመት የሚያስፈልጋቸው ምርጫ ክልሎች መሆናቸው ተመልክቷል። በዚሁ ምክክር ወቅት የቦርዱ ሰብሳቢ ለተፈጠረው ችግር በቦርዱ የተወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን አቅርበዋል። ጉድለቶች በተፈጠሩባቸው ምርጫ ክልሎች የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን አትሞ ለማድረስ የሚኖረው ችግርና የሚያመጣውን የእሸጋ እና የስርጭት ተፅእኖንም በተመለከተ ብርቱካን አብራርተዋል። በእነዚህ 54 የምርጫ ክልሎች የድምጭ መስጫ ወረቀቶችን ሰኔ 14 ለሚደረገው ምርጫ ለማድረስ የሚደረጉ ጥረቶችንም በተመለከተ ፓርቲዎች ሃሳብ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። ፓርቲዎቹ በበኩላቸው የድጋሚ ህትመቱ በአገር ውስጥ ቢደረግ እንዲሁም ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ምርጫ የማይደረግባቸው የምርጫ ክልሎች ጋር አብረው ድምፅ እንዲሰጡ ቢደረግስ የሚሉ አማራጭ ሃሳብ ማቅረባቸውም ተገልጿል። ይህንንም መሰረት በማድረግ ቦርዱ በእነዚህ የምርጫ ክልሎች ላይ ያጋጠመውን የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ጉድለት ችግር ለመፍታት በመጀመሪያ ደረጃ የድምፅ መስጫ ወረቀቶቹን አገር ውስጥ ማሳተም ሲሆን በሌላ አማራጭ ደግሞ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ድምፅ ከማይሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ጋር አብሮ ማካሄድ የሚሉትን አቅርቧል። በመጪው አገር አቀፍ ምርጫ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሶማሌና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ምርጫ የማይካሄድባቸው ቦታዎችን ዝርዝር ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። በእነዚህ ስፍራዎች ምርጫ የማይካሄደው በጸጥታ ችግር ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ባለመጀመሩ፣ የመራጮች ምዝገባ ተጀምሮ በመቋረጡና የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ አቤቱታ የቀረበ መሆኑን ቦርዱ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱ ላይ ጉልህ የአሰራር ችግር በማየቱ ማጣራት እንዲካሄድ የወሰነባቸው ቦታዎችም እንዲሁ ምርጫው እንደማይከናወን አስታውቋል። ግንቦት 28/2013 ዓ.ም ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ብሔራዊ ምርጫ፣ የመራጮች ምዝገባ እና ሌሎች ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠነቃቀቸው የተነሳ ምርጫው ለሁለት ሳምንታት እንዲገፋ ሆኖ ሰኔ 14 እንዲካሄድ ተወስኗል። ኢትዮጵያ በየአምስት ዓመቱ የምታካሂደው ምርጫ መካሄድ የነበረበት ባለፈው ዓመት ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ምርጫው እንዲራዘም መደረጉ የሚታወስ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-57423972
amh
politics
ኬንያ ምርጫ፡ የኬንያው ፕሬዚደንት ምክትላቸው ሥልጣን እንዲለቁ ጠየቁ
የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ከሥልጣናቸው እንዲለቁ ጠየቁ። ፕሬዚደንቱ ይህንን የጠየቁት በነሐሴ ወር ከሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ በፊት በሁለቱ መካከል ያለው ውዝግብ እየከረረ በመምጣቱ ነው። ፕሬዚደንት ኡሁሩ ምክትላቸው ሩቶ አገሪቷን እየተፈታተነ ያለውን የምጣኔ ሃብት ችግር ለመፍታት በቂ ጥረት አላደረጉም ሲሉ የከሰሷቸው ሲሆን መንግሥትን ከውስጥ ሆነው መተቸት እንደሌለባቸውም ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ምክትል ፕሬዚደንት ሩቶ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ካቢኔው ከሁለት ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ስብሰባ እንዳላደረገ እና ነገሮች ለፕሬዚደንቱ ስልክ በመደወል ብቻ እንደሚቀሩ ተናግረዋል። በአገሪቷ ሕግ መሠረት ፕሬዚደንት ኡሁሩ ምክትላቸውን ለማባረር ሥልጣን የላቸውም። በመሆኑም ምክትል ፕሬዚደንቱ ሩቶ ከሥልጣን ሊነሱ የሚችሉት ክስ ከቀረበባቸው አሊያም ሥራቸውን ለማከናወን የሚያስችል ብቃት ከሌላቸው ነው። በፕሬዚደንት ኡሁሩ እና በምክትላቸው መካከል ያለው ልዩነት አገሪቱ በቀድሞው የአገሪቷ ፕሬዚደንት ምዋይ ኪባኪ ሞት ሀዘን ላይ ባለችበት ወቅት በግልጽ ተስተውሏል። አርብ ዕለት በተካሄደው የቀድሞ ፕሬዚደንቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ፕሬዚደንት ኡሁሩ የምክትላቸውን ሩቶን እጅ ለመጨበጥ ፈቃደኛ አልነበሩም። በሁለቱ ባለሥልጣናት መካከል ያለው አለመግባባት የተፈጠረው ነሐሴ ላይ በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ምክንያት ነው። ምክትል ፕሬዚደንት ሩቶ በመጪው ምርጫ ለፕሬዚደንትነት መወዳደር የሚፈልጉ ሲሆን ፕሬዚደንት ኡሁሩ የሚደግፉት ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪውን ራይላ ኦዲንጋን ነው። በዘንድሮው ምርጫ መዳረሻ ወቅቶች የአገሪቷ ምጣኔ ሃብት ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል። ኬንያ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት እያጋጠማት ሲሆን በተለይ እንደ የምግብ ዘይት እና ነዳጅ ያሉ መሠረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ ጨምሯል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61277151
amh
politics
የጋዳፊን ልጅ ጉዳይ በሚመለከተው ፍርድ ቤት ላይ የደረሰው ጥቃት አሳስቦኛል - ተመድ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞ የሊቢያ መሪ ልጅ ሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ ይግባኝ ባቀረበበት ፍርድ ቤት ላይ የተፈጸመው ጥቃት አሳስቦኛል አለ። ሰይፍ አል-ኢስላም በሊቢያ ለሚካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እንዳይሳተፍ መከልከሉን ተከትሎ ጠበቃው ይግባኝ ባሉበት ፍርድ ቤት ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ ነው የመንግሥታቱ ድርጅት ጉዳዩ እንዳሳሰበው የገለጸው። የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ ጋዳፊ ከሳምንታት በኋላ በአገሪቱ ከሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድድር ውጪ የተገደረገው ሐሙስ ዕለት ነበር። የአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ሰይፍ አል ኢስላም ጋዳፊን እአአ 2015 ከቀረቡበት የጦር ወንጀሎች ጋር በተያያዘ ነበር ከምርጫ ተሳታፊነቱ ያገደው። ኮሚሽኑ ከጋዳፊ ልጅ በተጨማሪ በርካታ ዕጩዎችን "በሕጋዊ ምክንያቶች" በምርጫው እንዳይሳተፉ ማገዱን አሳውቋል። አል ኢስላም ጋዳፊ አባቱ የሰሜን አፍሪካዊት አገር ሊቢያን በሚያስተዳደሩበት ወቅት በተፈጸሙ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል እና በነፍስ ግድያ የሚፈለግ ሰው ነበር። በዚህም ሳቢያ የጋዳፊ ልጅ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ ከተሰማ በኋላ ውዝግብ አስነስቷል። የሰይፍ አል-ኢስላም ጠበቃ ካህሊ አል-ዛኢዲ ሴባህ ከተማ በሚገኘው ፍርድ ቤት የደንበኛውን አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ እንዳያቀርብ የታጠቁ ሰዎች እንደከለከሉት ተናግሯል። ሴባህ ከተማ ሊቢያን ለመቆጣጠር ነፍጥ ካነሱት አንዱ በሆኑት ጄነራል ኻሊፍ ሃፍጣር ቁጥጥር ሥር ትገኛለች። በተመሳሳይ በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች የወንጀል ክስ የቀረበባቸው ዝነኛው ኻሊፍ ሃፍጣር ለዚሁ ምርጫ ለመወዳደር መዘጋጃታቸው በአገሪቱ ውስጥ ውዥንብር ፈጥሯል። ነገር ግን ምርጫ ኮሚሽኑ ኻሊፍ ሃፍጣርን ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ውጪ ያድርጋቸው አይድርጋቸው የታወቀ ነገር የለም። የሊቢያ ወታደራዊ ዐቃቤ ሕግ የጋዳፊ ልጅ እና የሃፍታር በቀረበባቸው ክስ ላይ ተገቢ መልስ እስኪያቀርቡ ድረስ የምርጫ ኮሚሽኑን በዕጩነት ለማሳተፍ የሚያደርገውን ሂደት እንዲያቆም ጠይቀው ነበር። ሰኞ በተጠናቀቀው የዕጩዎች ምዝገባ ስልሳ ሰዎች ሊቢያን በፕሬዝዳንት ለመምራት የተመዘገቡ ሲሆን የ46 ዓመቷ የሴቶች መብት ተሟጋች ሊላ ቤን ካሊፋ ብቸኛዋ ሴት ተወዳዳሪ ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-59427036
amh
politics
የእስራኤሉ የስለላ ተቋም ሞሳድ የኢራንን ጥብቅ የደኅንነት መዋቅር እንዴት ዘልቆ ገባ?
እአአ በጥቅምት 2020 ታዋቂው ኢራናዊ የኒውክሌር ሳይንቲስት ሞህሴን ፋክኽሪዛደህ ይጓዝበት የነበረው መኪና ጋየ። በሰው ሠራሽ ክህሎት [አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ] አማካይነት በርቀት ቁጥጥር ከሚደረግበት መትረየስ በተተኮሰ ጥይትም ተገደለ። ጉዞ ላይ ባለ መኪና ውስጥ የተሳፈረን ኢላማ ከሌሎች ሰዎች ለይቶ በዚህ መንገድ መግደል እጅግ ጠንካራ የስለላ ክህሎትን ይጠይቃል። ሳይንቲስቱ ከተገደለ በኋላ የኢራን የደኅንነት ኃላፊ ማሕሙድ አልቪ ይህን መሰል ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ሰጥተው እንደነበር ተናግረዋል። ግድያው ከመፈጸሙ ከሁለት ወራት በፊት፤ ሳይንቲስቱ በተገደለበት ስፍራ አንዳች ጥቃት እንደሚደርስ መሐሙድ አስጠንቅቀው ነበር። የደኅንነት ኃላፊው እንዳሉት ግድያው የተፈጸመው "በአገሪቱ ጦር ሠራዊት አባል ሲሆን፣ የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ደግሞ በወታደራዊ ኃይል ውስጥ ለመንቀሳቀስና እርምጃ ለመውሰድ አይችልም።" ኃላፊው በቀጥታ ባይናገሩም በተዘዋዋሪ ተጠያቂ ያደረጉት በኢራን እስላማዊ የአብዮታዊ ዘብ ጓድ (ኢስላሚክ ሪቮሉሽን ጋርድ ኮርፕስ) ውስጥ ያለ ሰርጎ ገብን ነው። ይህ ቡድን በኢራን እጅግ የተከበረ ወታደራዊ ስብስብ ነው። የደኅንነት ኃላፊው እንደሚሉት ለሳይንቲስቱ ግድያ ተጠያቂው የዚህ ቡድን አባል የሆነ ግለሰብ ከሆነ ያ ሰው የቡድኑ ከፍተኛ አመራር ደረጃ ሳይደርስ አይቀርም። ይህ ሰው ከደኅንነት ኃላፊው የተሰጠውን ጥቆማ ችላ ብሎ ጥቃቱ በታቀደው ቀን፣ ቦታ እና ሰዓት እንዲከናወን መንገድ ጠርጓል። ሟቹ ሳይንቲስት የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ አባል እንደነበር ይነገራል። በእርግጥ የኢራን መንግሥት የቡድኑን አባላት ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ አያደርግም። በቴህራን በሚገኘው ኤርቪን እስር ቤት የሚገኝ የቢቢሲ ምንጭ እንደጠቆመው፤ ለውጭ አገራት በመሰለል የተጠረጠሩ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በእስር ቤቱ ታግተዋል። በዚህ ቡድን የውጭ አገራት ቅርንጫፍ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ የቀድሞ የደኅንነት ባለሙያ ለቢቢሲ እንደገለጹት፤ በውጭ አገራት ባሉ በበርካታ የኢራን አምባሳደሮች እንዲሁም የቡድኑ አባላት ላይ መረጃ ሰብስበዋል። ይህ መረጃ እነዚህ ግለሰቦች ከሴቶች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይጨምራል። ከሴቶች ጋር ስላላቸው ግንኙነት የሚሰበሰበው መረጃ ኋላ ላይ ኢራናውያኑ ከውጭ አገራት ሰላዮች ጋር እንዲተባበሩ ጫና መፍጠሪያ ይሆናል። እአአ በ2018 ከቴህራን በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የኢንዱስትሪ ቀጠና ውስጥ ያለ መጋዘን በበርካታ ሰዎች በድንገት ተወረረ። መጋዘኑን ጥሰው የገቡት ሰዎች ውድ እቃ የተቀመጠባቸውን ሳጥኖች መርጠው ቁልፋቸውን አቀለጡ። ከሰባት ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በመጋዘኑ ውስጥ ከነበሩት 32 ሳጥኖች የ27ቱን ቁልፍ ሰበሩ። ከዚያም ከባድ የኒውክሌር ምስጢር የያዙ ሰነዶች መዝብረው ተሰወሩ። ዘረፋው በኢራን ታሪክ እጅግ አሳፋሪው ቢሆንም የኢራን መንግሥት ስለጉዳዩ ብዙ ከማውራት ተቆጠበ። ከዘረፋው ከሦስት ወራት በኋላ የተዘረፉት ሰነዶች ከኢራን 2,000 ኪሎ ሜትር ርቀው ቴል አቪቭ፣ እስራኤል ተገኙ። የያኔው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተዘረፉትን ሰነዶች አስጎበኙ። ሰነዶቹ የሞሳድ ኦፕሬሽን ውጤት እንደሆኑም በይፋ ተናገሩ። የኢራን ባለሥልጣናት ግን እነዚህ ሰነዶች ሐሰተኛ እንደሆኑና የኢራን መጋዘን እንዳልተዘረፈ አስተባበሉ። ነሐሴ 2021 ላይ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሮሀኒ በመጨረሻው የሥልጣን ቀናቸው እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ሰነዶች ዘርፋ ለቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳሳየች አመኑ። ኔታንያሁ በ2018 የተሰረቁትን የኢራን ሰነዶች ሲያስጎበኙ የኒውክሌር ሳይንቲስቱ ሞህሴን ፋክኽሪዛደህ በኢራን ምስጢራዊ ኒውክሌር ማብላያ ከሚያስገነቡት ዋነኛው መሆናቸውን ተናግረዋል። "ዶ/ር ሞህሴን ፋክኽሪዛደህ የሚለውን ስም እንዳትዘነጉ" ሲሉም ኔታንያሁ ተደምጠዋል። ይህን ካሉ ከሁለት ዓመታት በኋላ ሳይንቲስቱ ተገደለ። "አታውሩ፣ ተኩሱ" ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ብዙ የኢራን ታዋቂ የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ተገድለዋል። የኢራን ኒውክሌር ማብላያ ፋብሪካዎች ሥራቸውን የሚያስተጓጉል ስውር ጥቃት ተሰንዝሮባቸዋል። ኢራን እስካሁን ድረስ ጥቃት አድራሾችን ወይም አቀነባባሪዎችን መያዝ አልቻለችም። የፀጥታ ኃይሏ ጥቃቶቹን ማስቆምም ተስኖታል። በማሕሙድ አሕመዲንጃድ የመጨረሻው የፕሬዝዳንትነት ዘመን (2013 ገደማ) የኢስላማዊ አብዮት ጠባቂ ቡድን ኮማንደሮች፣ ሃይማኖታዊ አባቶች እንዲሁም የደኅንነት አመራሮች ለሞሳድ በመሰለል ተጠርጥረው ታስረው ነበር። ስለእስሩ በይፋ የተባለ ነገር ግን የለም። ተጠርጣሪ ከተባሉት አንዱ በኢራን የእስራኤል ስለላ ቡድን አመራር ነበሩ። በሚስጥር ተከሰው፣ የሞት ፍርድ ተወስኖባቸው፣ በአደባባይ ተገድለዋል። ማሕሙድ ባለፈው ዓመት "ሞሳድ የደኅንነት ሚኒስቴራችንን ጥሶ መግባቱ እሙን" ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም "የእስራኤል ሰላዮችን እንዲቆጣጠር የተመደበው እና የእስራኤል ሰላዮችን ያጋልጣል የተባለው ሰው የእስራኤል ሰላይ ሆኖ ተገኝቷል" ብለዋል። እስራኤል ስለ ሞሳድ እንቅስቃሴ እምብዛም በይፋ ምላሽ አትሰጥም። ከእስራኤል መከላከያ ጡረታ የወጡት የቀድሞው አመራር አሞስ ጊላድ እስራኤል ስለ ሞሳድ መረጃ የማትሰጠው ምክንያት ስላላት ነው ይላሉ። "መረጃን ይፋ ማድረግን እቃወማለሁ። መተኮስ ካስፈለገ ዝም ብሎ መተኮስ ነው። አታውሩ፣ ተኩሱ!" ብለዋል አሞስ። ጨምረውም "ሞሳድ የሚታወቀው ብዙ በማይወራላቸው ድንቅ ኦፕሬሽኖቹ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የቀድሞው የኢራን አመራሮች ሞሳድ በኢራን የፀጥታ እና የደኅንነት ክፍል እስከ ከፍተኛ አመራሮች የሚደርስ መዋቅር ዘርግቷል ብለው ይሰጋሉ። የቀድሞው የኢራን የደኅንነት ሚኒስትር እና የሮሐኒ አማካሪ አሊ ዩኒሲ ከዚህ ቀደም ባለደጉት ቃለ ምልልስ "ሞሳድ በኢራን ውስጥ ያለው መዋቅር እስከ ከፍተኛ አመራሮች ስለሚደርስ እያንዳንዱ የኢራን ባለሥልጣን ለሕይወቱ እና ለደኅንነቱ መፍራት አለበት" በማለት ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60291116
amh
politics
ካማላ ሐሪስ የመጀመሪያዋ ሴት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ለአንድ ሰዓት ተኩል መሩ
ካማላ ሐሪስ በአሜሪካ ታሪክ ለ85 ደቂቃዎች ያህልም ቢሆን አገሪቱን በመምራት የመጀመሪያዋ ሴት ሆኑ። ምክትል ፕሬዝዳንቷ ሐሪስ የፕሬዝዳንትነት መንበሩን የጨበጡት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሕክምና ላይ ስለነበሩ ነው። ባይደን ለሕክምና የማደንዘዥ መድኃኒት መውሰዳቸውን ተከትሎ ሥልጣናቸውን ለ57 ዓመቷ ምክትላቸው ሐሪስ አስተላልፈው ነበር። የባይደን ሐኪም ፕሬዝዳንቱ ደህና እንደሆኑና ወደ ሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ባይደን 79ኛ ዓመት ልደታቸውን ከሰሞኑ ያከብራሉ። ፕሬዝዳንቱ ሕክምና ላይ በነበሩበት ጊዜ ምክትሏ ሐሪስ ከዋይት ሐውስ የምሥራቅ ክንፍ ካለው ቢሯቸው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ነበር ተብሏል። ካማላ ሐሪስ ለአጭር ጊዜ በቆየው የመሪነት ሥልጣናቸው የመጀመሪያዋ ሴት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ብቻ ሳይሆኑ የመጀመሪያዋ ጥቁር እና ደቡብ እስያዊት ሴት ፕሬዝዳንትም ናቸው። በጊዜያዊነት የመሪነት ሥልጣንን ማስተላለፍ በአሜሪካ ሕገ መንግሥት የተለመደ እንደሆነ የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ተናግራለች። ከዚህ በፊት እአአ በ2002 እና 2007 ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ሕክምና ሲያደርጉ ሥልጣናቸውን ለምክትላቸው አስተላልፈው ነበር። የጆ ባይደን ሐኪም ኬቨን ኦኮነር "የ78 ዓመቱ መሪ ጤናማና ጠንካራ ናቸው። ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ይችላሉ" ብሏል። ባይደን ከሆስፒታል ወደ ዋይት ሐውስ ሲመለሱ "ጥሩ ስሜት ይሰማኛል" ብለው መናጋረቸው ተዘግቧል። ባይደን በአሜሪካ ታሪክ በዕድሜ ትልቁ መሪ ናቸው። አምና ሕክምና ሲደረግላቸው "ጤናማ እና ብርቱ" ተብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59357886
amh
politics
ሩሲያ በማንኛውም ቅጽበት ዩክሬንን ልትወር እንደምትችል አሜሪካ አስጠነቀቀች
ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር ሁሉን ነገር አጠናቃለች ስትል አሜሪካ አስጠነቀቀች፡፡ እንደ አሜሪካ ባለሥልጣናት ከሆነ ሩሲያ ወታደሮቿን ከዛሬ ጀምሮ በማንኛውም ቅጽበት ልታንቀሳቅስና ወረራውን ልትፈጽምት ትችላለች፡፡ በመሆኑም ዜጎቿ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መክራለች፡፡ ወረራው የሚጀምረው በአየር ድብደባ ሊሆን እንደሚችልም የተነበየች ሲሆን ይህም የሚያመላክተው ጦርነቱ አንዴ ከተጀመረ በኋላ ከሩሲያ ምድር መልቀቅ ቀላል እንደማይሆን ነው፡፡ ሞስኮ በአንጻሩ ወረራ የሚባል ነገር በሐሳቤም የለም ትላለች፡፡ ይሁንና ከ100 ሺህ የሚልቁ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር ማስጠጋቷን አላስተባበለችም፡፡ ከአሜሪካ ባሻገር ሌሎች የምዕራብ አገራትም ዜጎቻችን እባካችሁ የሩሲያ ምድርን ልቀቁ ሲሉ መክረዋል፡፡ ዩኬ፣ ካናዳ፣ ኔዘርላንድስ፣ ላቲቪያ ለዜጎቻቸው መመሪያን የሰጡ ሲሆን ጃፓንና ደቡብ ኮሪያም ዜጎቻችን ከሩሲያ ብትወጡ ነው የሚሻለው ሲሉ መክረዋል፡፡ የሩሲያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ምዕራብ አገራት ሐሰተኛ ዜና እያሰራጩ ሕዝብ ያሸብራሉ ሲል ከሷል፡፡ የአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት ከፍተኛ አማካሪ ጄክ ሰሊቫን "በሚቀጥሉት ደቂቃዎች ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ከባድ ነው፤ የሩሲያ ወታደሮች ጥቃት ለመሰንዘር ተጠንቀቅ ላይ ናቸው" ብለዋል፡፡ የደኅንነት አማካሪው ጨምረው፣ ቭላድሚር ፑቲን በወረራው ዙርያ የመጨረሻ ውሳኔ ይስጡ አይስጡ አሜሪካ መረጃ የላትም ያሉ ሲሆን፣ ይሁንና ክሬምሊን ወረራውን ቅቡል ለማድረግ አንድ አሳማኝ ሰበብ እየፈለገች መሆኑን መረጃ እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡ የደኅንነት አማካሪው ጄክ ሩሲያ የመጀመርያውን ጥቃት የምትሰነዝረው ከአየር እንደሆነ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊከን የሩሲያ ጠብ አጫሪነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ቀደም ሲል ተናግረው ነበር። ብሊንከንም በተመሳሳይ የሩሲያ ጥቃት በማንኛውም ቅጽበት ሊጀመር እንደሚችል ጠቁመው በተለይ በፌብሩዋሪ 20 የኦሎምፒክ ፍጻሜ ዕለት ሊሆን እንደሚችል ምልክቶች እንዳሉ አብራርተዋል፡፡ አሜሪካ ለዚህ ጥቃት ምላሽ 3 ሺህ የሠራዊት አባላትን ከኖርዝ ካሮላይና ቀጠና ወደ ፖላንድ አንቀሳቅሳለች፡፡ ይሁንና እነዚህ ወታደሮች ከዩክሬን ወታደሮች ጋር ተሰልፈው አይዋጉም ተብሏል፡፡ ሆኖም ከአጋር አገራት ጋር ኾነው በተጠንቀቅ አካባቢውን ይቃኛሉ የሚል ግምት አለ፡፡ የፈረንሳዩ ማክሮን ከሰኞ ጀምሮ፣ ኪያቭ፣ ሞስኮና በርሊን ሲመላለሱ ነው የሰነበቱት፡፡ የማክሮን ወዲያ ወዲህ ማለት አይቀሬ ነው ለሚባለው ጦርነት የዲፕሎማሲ መፍትሄ ለመሻት ነበር፡፡ አንጌላን የተኩት የጀርመኑ መራሒ መንግሥት ሾልዝ በበኩላቸው ማክሰኞ ዕለት በዋሺንግተን ከባይደን ጋር መክረው ሩሲያ እንደተፈራው ወረራ ከፈጸመች በምን መልኩ ልንቀጣት ይገባል በሚለው ላይ ከመግባባት ደርሰው ነው የተመለሱት፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት የፈረንሳዩ ማክሮንና የአሜሪካው ባይደን ከቭላድሚር ፑቲን ጋር የመጨረሻ ሊሆን ይችላል የተባለ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሩሲያ በተለይ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት በምህጻሩ ኔቶ፣ ወደ ምሥራቅ አውሮጳ አይስፋፋብኝ፣ በተለይ ደግሞ ባላንጣዬን ዩክሬንንም አባል አድርጎ አይመዝግባት ስትል በጥብቅ ስትጠይቅ ኖራለች፡፡ ይህ ቁልፍ የደኅንነት ጥያቄዋ ግን በምዕራብ አገራት ገሸሽ ሲደረግባት ነው የኖረው፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-60358584
amh
politics
የሲሪላንካ ፓርላማ የሕዝብ ድጋፍ የሌላቸውን ፖለቲከኛ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ
የሲሪላንካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸውን ራኒል ዊክርሜሲንግህ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ። ዊክርሜሲንግህ ፕሬዝዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊት የቀድሞ ፕሬዝደንት አገር ጥለው መሸሻቸውን ተከትሎ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ከዚያ በፊት ደግሞ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። ግለሰቡ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው በአገሪቱ ሌላ ተቃውሞ እና አለመረጋገትን ይፈጥራል ተብሎ ተሰግቷል። አዲሱ ፕሬዘዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር እና ተጠባበቂ ፕሬዝዳንት ሳሉ፤ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስሪላካውያን ሲጠይቁ ቆይተዋል። በአገሪቱ የተከሰተውን ከፍተኛ ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ተከትሎ ሕዝባዊ አመጽ በርትቶባቸው የነበሩት የቀድሞ የሲሪላንካው ፕሬዝዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ በጦር አውሮፕላን ከአገር ከሸሹ በኋላ ሥልጣናቸውን በይፋ መልቀቃቸው ይታወሳል። ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ሲሪላንካውያን የቀድሞ ፕሬዝዳንት አስተዳደር አካል የሆኑት እና አሁን ፕሬዝዳንት ተብለው የተሾሙት ዊክርሜሲንግህ ለምጣኔ ሃብታዊ ቀውሱ ተጠያቂ ናቸው ይላሉ። ዊክርሜሲንግህ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተሾሙ በመላው አገሪቱ የሚጸና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ብዙዎችን ያስቆጣ ነበር። ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ተላልፈውታል። በወቅቱ ዊክርሜሲንግህ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉትን “ፋሺስቶች” ሲሉ ጠርተዋቸዋል። ዊክርሜሲንግህ እራሳቸውን ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ አድርገው ከማቅረብ እንዲቆጠቡ ቢጠየቁም ፕሬዝዳንት ሆኖ ከመሾም ያገዳቸው የለም። አዲሱ ፕሬዝዳንት አገሪቱን ከምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ የማውጣት እና የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት መዘርጋት ቀዳሚው ኃላፊነታቸው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ሲሪላንካ የውጭ ምንዛሬ ክምችቷን የጨረሰች ሲሆን፣ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት አጋጥሟታል። እንደ መድኃኒት፣ ነዳጅ እና ምግብ የመሳሰሉ መሠረታዊ ቁሶችን ወደ አገር ውስጥ ማስገባትም ተስኗታል። ሲሪላንካውያን ለዚህ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የአገሪቱን መንግሥት ተጠያቂ ያደርጋሉ። አዲሱ ፕሬዝዳንትም የቀድሞ መንግሥት አስተዳደር አካል ናቸው ይላሉ። ከፍተኛ ሃብት ካካበቱ ፖለቲከኛ ቤተሰብ የተገኙት ዊክርሜሲንግህ፤ የሕዝብ ተወካዮች አባል የሆኑት ከአራት አስርት ዓመታት በፊት እአአ 1977 ነበር። ከእአአ 1993 ጀምሮ ዊክርሜሲንግህ በተለያዩ ጊዜያት የሲሪላንካ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cx7p55g0zjno
amh
politics
የኢትዮጵያ ምርጫ 2013፡ ኦነግ ከምርጫው መውጣቱን ሲያሳውቅ ሌሎች አመራሮች ደግሞ የመሳተፍ ፍላጎት አለን አሉ
በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከጥቂት ወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ እንደማይሳተፍ ባወጣው መግለጫ አሳወቀ። በሌላ በኩል በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው ሌላኛው የግንባሩ ቡድን ግን በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ቢገልፅም ዕጩ ስለማስመዝገቡ ግን ምንም ያለው ነገር የለም። በአቶ ዳውድ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በምርጫው ለመሳተፍ የሚያስችሉት አመቺ ሁኔታዎች አለመኖራቸውን ገልጾ፤ በገዢው የብልጽግና ፓርቲ ዘንድ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊ መስፈርቶች ለማሟላት ፍላጎት አለመኖሩ ከምርጫው ለመውጣቱ ምክንያት መሆኑን አመልክቷል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ግንቦት 28 2013 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ደግሞ ሰኔ 5 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ የምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ያስረዳል። በዚህ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን መራጮች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳሉ። በበርካታ የአገሪቱ ክፍል ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ያስመዘገቡ ሲሆን የዕጩዎች ምዝገባ በተራዘመባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ የካቲት 30/2013 ዓ.ም ያበቃል። ኦነግ በምርጫው ውስጥ እንደማይሳተፍ ባመለከተበት መግለጫው ላይ ለአገሪቱ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ተግባራዊ ቢደረጉ ይጠቅማሉ ያላቸውን እርምጃዎችን ጠቅሷል። በዚህም መሠረት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉም የፓለቲካ እስረኞችን እንዲለቀቁ፣ የተዘጉና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጽ/ቤቶች እንዲከፈቱ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚስተዋሉ ሁሉም ጦርነቶች በማቆም ሁሉን ያካተተ ድርድር እንዲደረግ፣ የአገሪቱ ቁልፍ ተቋማት ገለልተኛና ከአድልዎ የፀዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት ሁሉም ወገኖች የሚሳተፉበት የፓለቲካ ውይይት ሂደት እንዲጀመር ጠይቋል። በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ በመግለጫው በምርጫው እንደማይሳተፍ ይግለጽ እንጂ፤ ሌላኛው በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የግንባሩ አካል ግን በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ለቢቢሲ ገልጿል። ባለፈው ዓመት ጥር በኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ግንባሩ በሁለት ወገን በመሆን የተለያዩ አቋሞችን እያንጸባረቀ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም የረጅም ጊዜ የድርጅቱ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ በአንድ ወገን ሆነው ድርጅቱን እየመሩ ሲሆን፤ በሌላ ወገን ደግሞ በአቶ አራርሳ ቢቂላ የሚመሩ ሌሎች የግንባሩ አመራር አባላት በግንባሩ ስም እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። ሁለቱ ወገኖች በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ሳቢያ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ አስገብተው የነበረ ሲሆን፣ ቦርዱም በግንባሩ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባትና ልዩነት ሁለቱም ወገኖች በሕገ ደንባቸው መሠረት ተነጋግረው እንዲፈቱ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። በአቶ አራርሶ የሚመራው የኦነግ አመራር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንዳሉት ግንባሩ ከምርጫው መውጣትን በተመለከተ ውሳኔ ላይ አልደረሰም። "ሊቀ መንበሩ ማለት ድርጅቱ ማለት አይደለም" ያሉት አቶ ቀጀላ፣ ድርጅታቸው የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩበትም በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው አመልክተዋል። "በአሁኑ ጊዜ እንቅፋት የሆነብን የውስጣችን ችግር ነው። የፓርቲው ሊቀ መንበር የሚጠበቅባቸውን እያደረጉ አይደለም" በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ግንባሩ አሁን ባለበት ሁኔታ እንዴት በምርጫው እንደሚሳተፍ አቶ ቀጀላ ሲገልጹ "የድርጅቱን ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተን አዲስ አመራር ለመምረጥ እየሰራን ነው" በማለት ሊቀ መንበሩ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠሩ ግፊት እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ኦነግ ባወጣው መግለጫ ላይ ግንባሩ ተዘግተውብኛል ያላቸውን ጽህፈት ቤቶቻቸውን በተመለከተ የተጠየቁት አቶ ቀጀላ አዲስ አበባ የሚገኘው ጽህፈት ቤቱ በግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር እጅ ስር መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ውጪ በተለያዩ ቦታዎች ያሉት የግንባሩ ጽህፈት ቤቶች የተዘጉት በአቅም ማጣት ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸውና አለ ባሉት የአስተዳደር ችግር ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል። "ችግር የለም ማለት አይደለም ነገር አብዛኞቹ የራሳችን የውስጥ ችግሮች ናቸው። እኛ የፈጠርናቸው የውስጥ ችግሮችና አመራሮች ተገቢውን አመራር ባለመስጠቱ ነው" በማለት ከምርጫው ተገፍተን ነው የወጣነው የሚለውን ሃሳብ አይቀበሉትም። በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍላጎቱ ውጪ በደረሱበት ጫናዎች ለመውጣት መገደዱን ማስታወቁ ይታወሳል። ኦፌኮ ይህን ውሳኔውን ያሳወቀው በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የሚገኙት ጽህፈት ቤቶቹ መዘጋትና የአመራርና የአባላቱ መታሰርን እንደምክንያት በማስቀመጥ ከመጪው ምርጫ ተገፍቼ ወጥቻለሁ በማለት ነው። ከምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን የገለጹ ፓርቲዎችን በተመለከተ በሚቀርቡ ቅሬታዎች ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ቢቢሲ ከቀናት በፊት የገዢው የብልጽግና ፓርቲ የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳን (ዶ/ር) ጠይቆ ነበር። ቢቂላ (ዶ/ር) እንደሚሉት በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመሳተፍ ታግሎ ከማሻሻል ይልቅ፣ በትንሹም በትልቁም ምክንያት ከምርጫ መውጣት ሕዝቡ የፖሊሲ አማራጭ እንዳያገኝ የሚያደርግ ውሳኔ ነው ብለዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎቹ አባላትና ጽህፈት ቤቶች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በተመለከተም "እነዚህን የቀረቡ ስሞታዎች በዝርዝር ቀርበው ማጣራት ተደርጎ አብዛኞቹ ክሶች መሰረተ ቢስ ሆነው ተገኝተዋል" ሲሉ ተናግረዋል። ችግሮች አያጋጥሙም ማለት እንደማይቻል የገለጹት ቢቂላ (ዶ/ር)፤ እነዚህንም ለማረምና ለማስተካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና የአስተዳደር መዋቅሩ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56318087
amh
politics
ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ፡ 'ቡልዶዘር' የተባሉት የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ማን ነበሩ?
ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ ነው ሙሉ ስማቸው። ቡልዶዘር ነው ቅጽል ስማቸው። ሲወለዱ የጭሰኛ ልጅ ነበሩ። ሲሞቱ ግን ፕሬዝዳንት ነበሩ። ቡልዶዘር የሚለው ቅጽል ስም ከየት መጣ? ቡልዶዘር (ሺዶማ) የተባሉት ያለምክንያት አይደለም። ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት የሥራና ከተማ ሚኒስትር ነበሩ። መንገድ በስፋት ያሠሩ ነበር ያን ጊዜ። የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ነፍሳቸው ነበር ማጉፉሊ። ሕዝቡ ቡልዶዘር ሲል ቅጽል አወጣላቸው። ይህ ቅጽል ስም ግን ኋላ ላይ እየሰፋ ሄዶ መነሻውን ሳተ። ቡልዶዘር የሚለው ስም ሰውየው የመንግሥት ወጪን በመቀነስና ሙሰኞችን መጠራረግ ስለሚወዱም ነው ተባለ። የአስተዳደር ዘያቸው መጠራረግ ስለነበር ስሙ የተስማማቸው ይመስላል። ማጉፉሊ ሚዲያ ማስደንበር ይወዳሉ፤ ነጻ ድምጾችን ያፍኑም ነበር። ተቃዋሚዎችን አሸብረዋል። ሆኖም ሞታቸውን ያጀበው ያ ሳይሆን ለኮሮናቫይረስ ያሳዩት የነበረው ንቀት ነበር። ምናልባት እሱው ይሆን ከዚህ ዓለም ያሰናበታቸው? "ኮሮናቫይረስ ጂኒ ነው" ኮሮናቫይረስ ታንዛኒያ ሲገባ ማጉፉሊ ተበሳጩ። ሕዝቡ ቀን ተሌት እንዲሠራ እንጂ ቤቱ እንዲቀመጥ በፍጹም አይፈልጉም። አንድ መላ ዘየዱ። "ሕዝቤ ሆይ! ለዚህ ተህዋሲ አትንበርከክ! ቤተክርስቲያን ሄደህ ጸልይ እንጂ በፍጹም ቤት አትቀመጥ" አሉ። ሕዝቡም ያን አደረገ። "ኮሮና ጂኒ ሰይጣን ነው እንጂ ተህዋሲ አይደለም" የሚለውን ሐሳብ በሕዝባቸው ውስጥ አሰረጹ። ሳይንስ ግን ሰውየውን ታዘባቸው። ቫይረሱም ሳይናደድባቸው አልቀረም። ከሰኔ 2020 ጀምሮ ማጉፉሊ አገሬ ታንዛኒያ ከኮቪድ-19 ተህዋሲ ነጻ ነች ሲሉ አወጁ። ጭምብል ማጥለቅን ተሳለቁበት። ኮቪድ-19ን ንቀው የዜና ማድመቂያ አደረጉት። በአገራቸው አልበቃ ብሎ ጎረቤት አገሮች የእንቅስቃሴ ገደብ ሲያደርጉ "የማይረቡ ፈሪዎች" አሏቸው። ለምዕራቡ ተንበርካኪ አድርገው ሳሏቸው። ማጉፉሊ በ2015 የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ፣ ታንዛኒያ የሚያስፈልጓት ዓይነት ፕሬዝዳንት ሆነው ነበር የተገኙት። ሙስናን የሚጸየፉና በሥራ የሚያምኑ። ቀን ተሌት ቢሠሩ አይደክማቸውም። ቡልዶዘራዊነታቸውን አጠናክረው ቀጠሉበት። ውጤት ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ነድፎ የማስፈጸም አቅማቸው ተደነቀላቸው። ለሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ምሳሌ መሆን ጀመሩ። ገና ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡ በመጀመርያው ቀን የገንዘብ ሚኒስቴር ቢሮ ሄዱ። ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ተሟልተው አልተገኙም ነበር። ማጉፉሉ ጦፉ። ይህን በፍጹም እንደማይታገሱ እቅጩን ተናገሩ። ከሥራ የቀረ አለቀለት። ለደመወዝ ቀን ብቅ እያለ የሚጠፋ "ጎስት ዎርከርስ" እየተባለ የሚጠራን ታንዛኒያዊ ጠራርገው አባረሩ። ሥራውን የማይፈልግ የመንግሥት ሠራተኛ ብቻ ነው ከዚያ ወዲህ ከቢሮ ሥራ የሚቀር። ማጉፉሊ የዛቻ ብቻ አይደለም፤ የድርጊት ሰው ናቸው። ከሥራ የሚቀሩትን ብቻ ሳይሆን ሙሰኛ አለቆችን ጠራርገዋል። አንዳንድ ጊዜ ሹመኞችን የሚያባርሩት ታዲያ በቀጥታ በብሔራዊ ቴሌቪዥን እየታዩ ጭምር ነበር። ለሌላው መቀጣጫ እንዲሆኑ። በዚህ ጊዜ ቡልዶዘር ኑርልን አላቸው አገሬው። እሳቸውም ተበረታቱ። ማጉፉሊ ገና ድሮ ወጪ የሚባል ነገር ያበሳጫቸዋል። በተለይ ያልተገባ ብልጭልጭ ወጪ ታንዛኒያ ማውጣት የለባትም ብለው በጽኑ ያምኑ ነበር። "ምክንያቱም ድሆች ነን" ይላሉ። በዚህ የተነሳ በድምቀት ይከበሩ የነበሩ በርከት ያሉ ክብረ በዓላትን አስቀርተዋል። በ54 ዓመታት የታንዛኒያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የነጻነት ቀን እንዳይከበር ያደረጉት እሳቸው ናቸው። "ቸበርቻቻ አያስፈልግም ሥራ ነው እንጂ" አሉ። "ሕዝቤ ሆይ! ነጻ የምትወጣው የነጻነት በዓልን በማክበር ሳይሆን ተግቶ በመሥራት ነው፤ ስለዚህ እጅህ መቁሸሽ አለበት" ሲሉ ጮኹ። ማጉፉሉ ሕዝቡን በማዘዝ ወደ ቅንጡ ቤተ መንግሥት የሚገቡ ሰው አልነበሩም። እሳቸውም በዘመቻ ይሳተፉ ነበር። ሠርተው ያሳያሉ። ለምሳሌ የቤተ መንግሥቱን ደጅ የሚጠርጉት እሳቸው ራሳቸው ነበሩ። ኃላፊዎቻቸው በሆነ ባልሆነው ወደ አሜሪካና አውሮፓ ይጓዙ ነበር። ለሕክምና፣ ለጉብኝት፣ ወዘተ። ይህ ሁሉ የሚሆነው በሕዝብ ገንዘብ ነበር። አንድ ኃላፊ የውጭ አገር ጉዞ ቢያደርግ ወዮለት ብለው ደነገጉ። ተፈጻሚም ሆነ። ይህ እርምጃቸው በታንዛኒያውያን ዘንድ እጅግ ተወዶላቸው ነበር። እንዲያውም በማኅበራዊ የትስስር መድረክ መነጋገርያ ሆነው ነበር። "ማጉፉሊ ቀጥሎ ምን ያደርጋሉ" የሚል የድራምባ ሐረግ (Hashtag) ተፈጥሮም ነበር። ማጉፉሊ ከአገራቸው ባሻገር በሌሎች አፍሪካውያን ዘንድ ውስጥ ውስጡን አድናቆት ማግኘት ጀማምረውም ነበር። ለምሳሌ በ2017 አንድ እውቅ የኬንያ ፕሮፌሰር በዳሬ ሰላም ዩነቨርስቲ ተገኝተው በሰጡት የአደባባይ ዲስኩር "አፍሪካ አዲስ አስተዳደር ያሻታል" ካሉ በኋላ ይህ አፍሪካን የሚለውጠውን የአስተዳደርም ዘዬ "ማጉፉሊኬሽን" ሲሉ ሰይመውታል። ማጉፉሊ በዚህን ያህል ተጽእኖ መፍጠር ቢችሉም የዲሞክራሲ ጸር ሆነው ነበር የሚታዩት። ተቃዋሚ በማሽመድመድ፣ ነቃፊዎቻቸውን ነቅሶ በማሰር፣ ነጻ ሚዲያን በማፈን ስማቸው ይነሳል። ጆን ማጉፉሊ በአጭሩ ማጉፉሊ መጀመሪያ ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡ በሁለተኛ ወራቸው የፓርላማ የቀጥታ ሥርጭት እንዳይተላለፍ አገዱ። ያን ጊዜ ሰበብ ያደረጉት ወጪ ቅነሳን ነበር። ተቃዋሚዎች ግን ይህ ነገር ለሳንሱር እንዲመች አድርጎ የፓርላማን ክርክር ለሕዝብ ለማቅረብ ነው ብለው ከሰሷቸው። እንዲያውም ይህን እርምጃ ተቃውመን ሰልፍ እንወጣለን አሉ። ሆኖም ሰልፉ በማጉፉሊ ሰዎች እውቅና ተነፈገውና ታገደ። በ2017 ደግሞ ማጉፉሊ የታንዛኒያው ራፐር ናይ ዋ ሚቴጎ ዘፈን ዘፈነባቸው። ሚቴጎ ሙዚቃውን በለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ራሱን እስር ቤት አገኘው። ይህ ዘፋኝ በራፕ ሙዚቃው ያዜመው ግጥም በደምሳሳው ሲተረጎም እንዲህ የሚል ስንኞች ነበሩበት፣ እስኪ ንገሪኝ አገሬ፣ ነጻነት አለ ወይ በሰፈሬ ያሻኝን ብዘፍን ጉራማይሌ አገኘው ይሆን ራሴን ከርቸሌ? ማጉፉሊ ራፐሩን እንደምኞቱ ከርቸሌ ወረወሩት። በዳሬ ሰላም ማዕከላዊ እስር ቤት ታጎረ። በዚህም ማጉፉሊ ለትችት ቦታ እንደሌላቸው አሳዩ። ማጉፉሊ ለሚዲያ ርዕስ የሚመቹና አንዳንዴም አስቂኝ ሰው ነበሩ። ለምሳሌ ይህን ተቺ ሙዚቃ ያቀነቀነውን ናይ ዋ ሚቴጎን ከአንድ ቀን በኋላ ከእስር ሲያስፈቱት አንድ ምክር መከሩት። "ስለ ግብር አጭበርባሪዎች ሙዚቃ ሥራልኝ" በማለት። ፕሬዝዳንት ማጉፉሊን ግብር አጭበርባሪዎች በጣም ያናድዷቸው ስለነበር ነው ለዘፋኙ ይህን ምክር የሰጡት። በ2017 ደግሞ ዋንኛ ተቃዋሚያቸውና የምክር ቤት አባሉ ቱንዱ ሊሱ ቤታቸው ሳሉ ተተኮሰባቸውና ክፉኛ ቆሰሉ። የማጉፉሊ ሰዎች እንዳደረጉት ይታመናል። ሆኖም ሰውየው እንደምንም ድነው ከ3 ዓመት በኋላ ተገዳዳሪያቸው ሆነው ለፕሬዝዳንትነት ተወዳደሩ። ሚስተር ሊሱ የግድያ ሙከራ እንደተረገባቸውና ታንዛኒያን እየመሯት ያሉት ሰው አምባገነን እንደሆኑ በተደጋጋሚ ይናገሩ ነበር። ማጉፉሊ እስከወዲያኛው ያሰናብቱታል ቢባልም ተፎካካሪያቸው እንዲሆን ፈቀዱለት። ምዕራብ ጠልነትና ማጉፉሊ ማጉፉሊ ምዕራባዊያን አፍሪካን በዝብዘዋታል ብለው ያምናሉ። ስለዚህ በተራችን እነሱን መበዝበዝ አለብን ሲሉ ያስባሉ። በዚህ ረገድ በየጊዜው የውጭ ድርጅቶችን የሚያስጨንቁ አዳዲስ መመርያዎችን ያወጡ ነበር። ከነዚህ መሐል የካናዳው ባሪክ ወርቅ እህት ኩባንያ የሆነውን አካሺያ ማዕድን ድርጅትን 190 ቢሊዮን ዶላር ለመንግሥት ክፈል ብለው አነቁት። ለምንድነው የምከፍለው ቢላቸው፣ በቃ እስከዛሬ የከበሩ ማዕድናትን ከታንዛኒያ ስታወጣ ነበር። ገቢህን ስንደምረው ታንዛኒያ ይህን ያህል ማግኘት እንዳለባት ደረስንበት አሉት። ኩባንያው ደነገጠ። ከብዙ ድርድር በኋላ 300 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ። ከዚህ ዕለት በኋላም ይህ የካናዳው ባሪክ ወርቅ አውጪ ኩባንያ ከሚያወጣቸው ማዕድናት 50 ከመቶውን ለመንግሥት ገቢ እንዲያደርግም ተገደደ። ማጉፉሊ የአስተዳደር ዘይቤያቸው የተቀዳው ከአገሪቱ የነጻነት አባት ጁሊየስ ኔሬሬ እንደሆነ ይነገራል። እሳቸውም ይህንን ብለውት ያውቃሉ። ማንም እንዴት አገሬን መምራት እንዳለብኝ ሊነግረኝ አይገባም ይሉ ነበር። በአንድ ወቅት ኮሮናቫይረስ የእንቅስቃሴ ገደብን በተመለከተ የተናገሩት ይህንኑ የሚመሰክር ነበር። "አባቶቻችን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እየተነገራቸው አይደለም ያስተዳደሩን።…እንዲህ ዓይነት ቤት ዘግታችሁ ተቀመጡ የሚል መመርያ የሚያወጡ ሰዎች ከሩቅ ሊያስተዳድሩን ነው የሚሹት። የእኛ አባቶች እንዲህ አይነቱን ነገር አይቀበሉም ነበር" ሲሉ ምዕራባዊያንን ተችተዋል። "ድህነት ምን ማለት እንደሆነ አውቀዋለሁ" ማጉፉሊ ከጭሰኛ ቤተሰብ በሰሜን ምዕራብ ቻቶ በሚባል ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ነው የተወለዱት። "ድህነትን በደንብ አውቀዋለሁ" ይሉም ነበር። እሳቸው ልጅ እያሉ ታንዛኒያን የሚያስተዳድሯት ጁሊየስ ኔሬሬ ነበሩ። "ቤታችን ከጭቃ ነበር የተሰራው፣ በልጅነቴ ከብቶችን አግድ ነበር። ቤተሰቤን ለመታደግ ወተትና ዓሳ እያዞርኩ ነበር የምሸጠው። ድህነት ምን ማለት እንደሆነ ለእኔ አትነግሩኝም፤ ለዚህ ነው ድሆችን ለማገዝ ፖለቲካ ውስጥ የገባሁት" ሲሉም ተናግረዋል። ማጉፉሊ ጭሰኛ ሆነው ተወልደው ፕሬዝዳንት ሆነው ሞቱ። በተወለዱ በ61 ዓመታቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-56439789
amh
politics
የትራምፕ የክስ ሂደት እስከሚቀጥለው ወር ተራዘመ
ሁለተኛው የዶናልድ ትራምፕ ክስ በቀጣዩ ወር እንዲታይ የዲሞክራት እና ሪፐብሊካን እንደራሴዎች ተስማሙ። ዲሞክራቶች ሰኞ ዕለት "አመፅ በማስነሳት" የተከፈተውን ክስ ይልካሉ፡፡ ክርክሮች እስከ የካቲት 8 ድረስ የማይጀመሩ ሲሆን፤ ይህም የትራምፕ ጠበቆች በሁለት ሳምንት መከላከያቸውን እንዲያዘጋጁ ያስችላቸዋል፡፡ ዲሞክራቶች የቀድሞውን ፕሬዝዳንት በአሜሪካ ካፒቶል ሂል ሞት ያስከተለውን አመፅ በማነሳሳት ይከሳሉ፡፡ አምስት ሰዎች የሞቱበትን ሁከት በማነሳሳት ትራምፕን በመክሰስ ባለፈው ሳምንት ምክር ቤቱ ለክሱ ሂደት መንገድ ከፍቷል፡፡ ሁለተኛው የሕግ ጥሰት ክስ በሴኔቱ ሥልጣን አላግባብ በመጠቀማቸው እና ኮንግረስን በማደናቀፋቸው ክስ ከተመሰረተባቸው ከአንድ ዓመት በኋላ ይጀምራል፡፡ የጆ ባይደንን እና የልጃቸውን ስም ለማጥፋት እንዲረዷቸው ዩክሬይን ላይ ጫና አድረሰዋል በሚል ነበር ጉዳዩ፡፡ ትራምፕ የሥልጣን ዘመናቸው ረቡዕ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የተተኪውን ጆ ባይደን በዓለ ሲመት ላይ ሳይገኙ ነጩን ቤተ መንግሥት ለቀዋል፡፡ የሴኔቱ አመራሮች በምን ተስማሙ? የሴኔቱ ከፍተኛ ዲሞክራት ቹክ ሹመር አርብ ዕለት እንዳሉት ምክር ቤቱ ሰኞ ዕለት ክሱን ያቀርባል። "ሴኔቱ የዶናልድ ትራምፕን ክስ ይመለከታል። ሙሉ የፍርድ ሂደትም ይከናወናል፡፡ ፍትሐዊ የፍርድ ሂደት ይሆናል" ሲሉ ሹመር ለሴኔቱ ተናግረዋል፡፡ የምክር ቤቱ ዲሞክራቶች አንቀጹ ሰኞ ወደ ላይኛው ኮንግረስ ይተላለፋል ብለዋል፡፡ በሴኔቱ የፍርድ ሂደት ወቅት እንደ አቃቤ ሕግ ሆነው የሚያገለግሉ የዲሞክራቶቹ የክሱ ኃላፊዎች እና የሕግ ባለሙያዎች ማክሰኞ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ፡፡ ሹመር በቅድመ ችሎት ሂደት ለተጨማሪ ጊዜ ጥያቄያቸውን ፍቃድ መሰጠቱ እንዳስደሰታቸውና የፍርድ ሂደቱ የካቲት 9 ቀን እንደሚጀመር የሴኔቱ የሪፐብሊካን መሪ ሚች ማኮኔል ተናግረዋል፡፡ "ዓላማው ተሳክቷል፡፡ ይህም ለፍትሕ ሂደቱ እና ለፍትሐዊነት ድል ነው" ብለዋል፡፡ የኋይት ሀውስ አቋም ምንድነው? ፕሬዚደንት ባይደን የፍርድ ሂደቱን እንዲዘገይ እንደሚመርጡ ጠቆም አድርገዋል፡፡ ለጋዜጠኞችም "እነዚህን ቀውሶች ለመፍታት ጊዜ በወሰድን ቁጥር የተሻለ ይሆናል" ብለዋል፡፡ ሆኖም ግን ዋይት ኃውስ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጥፋተኛ ስለመሆናቸው ባይደን ማሰባቸውን በተመለከተ ያለው ነገር የለም። ቃል አቀባዩ ጄን ፕሳኪ አርብ ዕለት "[ጆ ባይደን] ከአሁን በኋላ በሴኔት ውስጥ ስለሌሉ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ተጠያቂ የማድረግ ጉዳይ በሴኔት እና በኮንግረሱ ላይ የሚጣል ነው" ብለዋል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፡፡ ትራምፕ ይፈረድባቸዋል? ምንም እንኳን ዲሞክራቶች በሴኔቱ አነስተኛ አብላጫ ድምፅ ቢይዙም ትራምፕን ጥፋተኛ ለማድረግ ቢያንስ የ17 ሪፐብሊካኖች ድጋፍ ይፈልጋሉ። ምክንያቱም የሴኔቱ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ ያስፈልጋቸዋል። የሚሲሲፒው ሪፐብሊካን እንደራሴ ሮጀር ዊከር አርብ ዕለት ለሲኤንኤን እንደተናገሩት "የጥፋተኝነት ፍርድ የማግኘት ዕድሉ ወደ ዜሮ የሚጠጋ ነው።" ሚት ሮምኒ፣ ሊዛ ሙርኮቭስኪ፣ ቤን ሳሴ፣ ሱዛን ኮሊንስ እና ፓት ቶሚ አምስቱ የሪፐብሊካን እንደራሴዎች ብቻ ናቸው ክሱን በመደገፍ ከዲሞክራቶች ጋር ይቆማሉ የሚባሉት፡፡ ትራምፕ በሴኔቱ የተከሰሱ የመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው የተጠናቀቀ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ፡፡ በእንደዚህ አይነት ክሶች ጥፋተኛ ተብሎ የተከሰሰ ፕሬዝዳንት የሌለ ሲሆን ትራምፕም ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከዚህ በኋላ ሥልጣን እንዳይዙ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ አርብ ዕለት ትራምፕ፤ በዋሽንግተን ኤግዛማይነር ዘጋቢ በትራምፕ ዓለም አቀፍ የጎልፍ ክበብ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። ስለ ወደፊት ዕቅዳቸው ሲጠየቁ "የምንሠራው ነገር ቢኖርም ገና አልተወሰነም" ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/55777883
amh
politics
ምርጫ 2013፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኤርትራና ሱዳን ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ እየሰሩ መሆኑን ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ድምጻቸውን በትውልድ አካባቢያቸው በሻሻ ከሰጡ በኋላ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የኤርትራ እና የሱዳን ወታደሮች ከኢትዯጵያ ድንበር ለቅቀው እንዲወጡ ከመንግሥታቱ ጋር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57550254
amh
politics
የቀድሞ የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ገላሳ ዲልቦ አረፉ
በኢህአዴግ የሽግግር ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀ መንበር የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የፓርላማ አባሉ አቶ ገላሳ ዲልቦ ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸውን አንድ የቤተሰብ አባል ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። እኚሁ የቤተሰብ አባል "ሌሊት ላይ በድንገተኛ ህመም መሞታቸውን" ለቢቢሲ አስረድተዋል። ሞታቸው ከተሰማ በኋላም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሃዘናቸውን በክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ማኅበራዊ ትስስር ገፅ አስፍረዋል። "ኦሮሚያ አንድ ዋርካ አጥታለች። በኦሮሞ የነፃነት ትግል ውሰጥ ትልቅ ስም የነበራቸው፤ በአስቸጋሪ ወቅቶች እድሜያቸውን ለአሮሞ ህዝብ እየታገሉ ያሳለፉት ገላሳ ዲልቦ ከዚህ ዓለም በመለያታቸው የተሰማኝን ሃዘን እየገለፅኩ ለኦሮሞ ሕዝብ መፅናናትን እመኛለሁ" ብለዋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንዱ መስራች የሆኑት አቶ ገላሳ ዲልቦ ባለፈው ዓመት በነበረው ምርጫ የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጎላኦዳ ቁምቢ መልካ በሎ ወረዳዎችን በመወከል በግል ተወዳድረው በማሸነፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበሩ። አቶ ገላሳ ዲልቦ ለረጅም ዓመታት በስደት ኑሯቸውን በለንደን አድርገው የነበሩ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በውጭ አገራት የነበሩ ተቃዋሚ ኃይሎች ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ ወደ አገር ቤት ከተመለሱ አንጋፋ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ነበሩ። አቶ ገላሳ ከቢቢሲ በነበራቸው ቆይታ ከ27 ዓመታት ስደት በኋላ ወደ አገር ቤት መመለሳቸውን ተናግረው የነበረ ሲሆን፣ ኢህአዴግ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ በነበረው የሽግግር መንግሥቱ ጉባኤ ላይ መሳተፋቸውንና ከሁለት ቀናት በኋላ በህመም ምክንያት ወደ አውሮፓ ሄዱ። ህክምና አግኝተው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቢመለሱም የወቅቱ ሁኔታ እንደጠበቁት አላገኙትም "ሁኔታዎች ስለተበላሹ ተመልሰን ወደ ትጥቅ ትግል ለመግባት ተገደድን። በሽግግሩ ወቅት የኦነግ ሊቀ መንበር የነበርኩት እኔ ነበርኩኝ" ብለዋል። በአሁኑ ሊቀ መንበር ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው የኦነግ ፓርቲ የወጡት በአውሮፓውያኑ 1998 የኦነግ መከፋፈልን ተከትሎ ሲሆን፣ "አባኦ ቃማ ጨኡምሳ" የሚባል ሌላኛውን የኦነግ ፓርቲን መስርተው በሊቀ መንበርነት ለረጅም ዓመታት ሲያገለልግሉ ነበር። አቶ ገላሳ ዲልቦ የተወለዱት ምሥራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ሲሆን አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዚያው ነበር የተከታሉት። በአውሮፓውያኑ 1974 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የገቡ ቢሆንም የመጀመሪያ ዓመት ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ ደርግ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ ለትግል ወደ ሶማሊያ መሄዳቸውን በወቅቱ ተናግረው ነበር። ሆኖም የሶማሊያ መንግሥት ወደ አገር ቤት ስለመለሳቸው በአገር ቤት የነበረውን የትጥቅ ትግል መቀላቀላቸውንና የትግል ሕይወታቸውም በዚያው እንደተጠነሰሰም በወቅቱ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60937910
amh
politics
በቤንሻንጉል ጉሙዝ የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ዕርምጃዎች መወሰድ እንዳለበት ተገለፀ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በከማሽ ዞን ምንጅጋ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 8፣ 2013 ዓ.ም በደንቤ ቀበሌ 8 ነዋሪዎች በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። ኢሰመኮ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ስጋት ያደረባቸው ከአራት ሺህ ያላነሱ የቀበሌው ነዋሪዎች መፈናቀላቸውንና ምጅንጋ (በሎይጂንጋፎይ) ወረዳ ላይ ተጠልለው እንደሚገኙም ጠቅሷል። ኢሰመኮ መግለጫውን እስካወጣበት ድረስ የተኩስ ድምፅ አየተሰማ መሆኑንና የፀጥታ ኃይሎች ወደ ቦታው ያልደረሱ መሆኑንም ተፈናቃዮች ለኮሚሽኑ መናገራቸውን ገልጿል። ኢሰመኮ የሲቪል ሰዎች ደህንነትን ለማረጋገጥ አስቸኳይ እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸውም አፅንኦት ሰጥቷል። ከቀናት በፊት ሐምሌ 3 እና 4 2013 ዓ.ም በተከሰተም ግጭት ቢያንስ 16 ነዋሪዎች መገደላቸውንም በመግለጫው ተጠቁሟል። በክልሉ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ በምትገኘው ኢማንጅ ቀበሌ ነው ግጭቱ የደረሰው ብሏል ኢሰመኮ በደረሰው መረጃ ኢሰመኮ ክትትል ሲያደርግና ከአካባቢው የፀጥታና አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ሲነጋገርም እንደቆየ በመግለጫው አስፍሯል። በታጠቁ ኃይሎች ተገድለዋል ተብሎ በሚነገር አንድ የኢማንጅ ቀበሌ ነዋሪ የቀብር ስነ ስርዓት በደረሰ ጥቃትም ተጨማሪ 15 ሰዎች ህይወት እንዳለፈም ተገልጿል። ሐምሌ 4፣ 2013 ዓ.ም የደረሰው የአፀፋ ጥቃት ስለመሆኑም መነገሩን ኢሰመኮ ገልጿል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ሐምሌ 4፣ 2013 ዓ.ም በክልሉ መንግሥት እና በኮማንድ ፖስት የማረጋጋትና የደህንነት እርምጃ ተወስዷል ብሏል። ሆኖም ከዚህም በተጨማሪም በምጅንጋ ተጠልለው ለሚገኙ ነዋሪዎች ጥበቃ እንዲደረግም ኢሰመኮ አሳስቧል። የክልሉን ሰላምና ደህንነትም በዘላቂነት ለመመለስ አጥፊዎች በአፋጣኝ ለህግ ማቅረብ ያስፈልጋል ብሏል። እንዲሁም የነዋሪዎችን ሰላም እና ደህንነት በተሟላ መልኩ ማረጋገጥ አስፈላጊነቱንም አስምሯል።
https://www.bbc.com/amharic/57864967
amh
politics
ፋኖ ማን ነው? በማንስ ይደገፋል?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ፋኖ ስሙ ይነሳ የነበረው በህቡዕ ትግል ነበር። በወቅቱ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የነበሩ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ፋኖም በአማራ በተለይ ደግሞ በጎንደር አካባቢ የወጣቶች የህቡዕ አደረጃጀት እንደነበር ይነገራል። ከዚያ በኋላ ግን በአገሪቱ የተከሰቱ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ ስሙ በተደጋጋሚ የሚነሳው 'የታጣቂዎች ኢመደበኛ አደረጃጀት' በሚል ሆኗል። ፋኖ የፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ ኃይሎች ጋር ባደረገው ትግል በተለይ ደግሞ የህወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል የተወሰኑ ስፍራዎችን ተቆጣጥረው በነበረበት ወቅት ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጎን በመሆን በቀጥታ ተሳትፏል። ምንም እንኳን ፋኖ የሚለው ስያሜ አሁን ካለው ታጣቂ ኃይል ጋር ተያይዞ በብዙዎች ዘንድ ቢታወቅም የፋኖ ፅንሰ ሃሳብ ዘመናትን ያስቆጠረ እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ያስቃኛሉ። ስለ ፋኖ ትንታኔ የሚሰጡ ሰዎች ትርጓሜው በበደል ተገፍቶ ዱርን የመረጠ፣ መጨቆንን ጠልቶ ጠመንጃ የጨበጠ ሰው 'ፋኖ' የሚል መጠሪያ እንደሚሰጠው ይናገራሉ። እንደ እነዚህ ሰዎች አባባል ፋኖ መገፋት የወለደው የለውጥ ኃይል ሲሆን ለዘመናትም ይህንን የሚያንጸባርቁ ፉከራዎች፣ ግጥሞችና ዘፈኖች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲቀባበሉ እዚህ ደርሰዋል። ፋኖ የሚለው ስያሜ 'ለበርካታ ሺህ ዓመታት የአማራ ህዘብ ማስተሳሰሪያ ክሩ ሆኖ፣ ለችግር ጊዜ መፍትሄ ማፍለቅያ እሴቱ ሆኖ የመጣ እንደሆነም ሲናገሩ ይደመጣል። ከጥንት ጀምሮ ብዙ ሲባልለት የቆየው የፋኖ እሳቤ አሁን ያለውን ቡድን ይገልጸው ይሆን? ቡድኑ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ የተለያዬ ስያሜ ተሰጥቶታል። ቡድኑ በአማራ ክልል መንግሥት የህዝብ ደጀን ተደርጎ ሲቀርብ፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ደግሞ 'አንዳንድ የአማራ ጽንፈኛ ታጣቂዎች' በሚል ይወገዛል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ደግሞ ቡድኑን በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመፈፀም ይወነጅሉታል። የፋኖ አደረጃጀት በአማራ ክልል በተለያዩ ስፍራዎች ይገኛል። በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎንደር እና በጎጃም የራሱ አመራር ያለው ፋኖ የተደራጀበት ጊዜ እና ባህርያትም እንዲሁ የተለያዩ ናቸው። በጎጃም የሚንቀሳቀው ፋኖ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ እንደሚባልም ሰብሳቢው አቶ ዘመነ ካሴ ይናገራሉ። ፋኖ በአማራ ክልል በአራት የተለያዩ ሥፍራዎች ሲደራጅ እርሳቸው ላለፉት ስምንት ወራት በጎጃም የሚንቀሳቀሰውን ፋኖ በማደራጀት እና በመምራት ላይ ይገኛሉ። የትግራይ ታጣቂዎች በአማራ ክልል ውጊያ በከፈቱበት ወቅትም በአቀስታ በኩል ተሰልፈው መዋጋታቸውንም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ራሳቸውን የአማራ ህዝባዊ ኃይል በሚል ለምን ማደራጀት እንደፈለጉ ሲጠየቁም "ሕዝባዊ ጦርነት ታውጆብናል፤ ሕዝባዊ ጦርነት ማድረግ አለብን። ሕዝባዊ ዘመቻ ተካሄዶብናል፤ ሕዝባዊ ምላሽ መስጠት አለብን'" በማለት ያስረዳሉ። ከጎጃም ወደ ወሎና ሸዋ ስንመጣ ደግሞ የነዚህ ኃይሎች ጥምረት የምስራቅ አማራ ፋኖ በሚል አደረጃጀት ስር መሰባሰባቸውን የቡድኑ ትምህርት ሥልጠናና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ ፈንታው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ስለ ፋኖ አመሰራረትም ሲያስረዱ በ2008 በአገር አቀፍ ደረጃ የነበረውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ በራያ ፋኖ በህቡዕ ተደራጅተው መንቀሳቀስ መጀመሩን ነው። በትግራይ ተነስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተውን ጦርነት በተለይም የትግራይ ኃይሎች በነሓሴ ወር ወደ አማራ ክልል ማቅናታቸውን ተከትሎ ደሴ ላይ የወሎ ፋኖን ማቋቋማቸውን ያስረዳሉ። እስከ 2011 ዓ.ም. ድረስ በይፋ መሳርያ ታጥቀው ይንቀሳቀሱ እንዳልነበርም አቶ አበበ ገልፀዋል። ሥልጠናም ቢሆን በ2014 ዓ.ም. የትግራይ ኃይሎች ጋር ከነበረው ውጊያ ጋር ተያይዞ የክልሉ መንግሥት እና የፌደራል መንግሥት ጥሪ ተከትሎ የተጀመረ እንጂ ቀድሞ እንዳልነበር ያስታውሳሉ። የትግራይ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን ተከትሎ በደቡብ እና በሰሜን ወሎ በርካታ ግንባሮች ከመከላከያ እና ከልዩ ኃይሉ ጎን በመሆን መዋጋታቸውን አቶ አበበ ይናገራሉ። አቶ ዘመነ ከስምንት ወር በፊት፣ ነሐሴ 2013 ዓ.ም. ፋኖን ማደራጀት የፈለጉበትን ምከንያት ሲያስረዱ የትግራይ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል መገስገስ በመጀመራቸው መሆኑን በቀዳሚነት ያነሳሉ። ነገር ግን 'በሌሎች አካባቢዎች የአማራን ሕዝብ በጠላትነት የፈረጁ ቡድኖች እና ኃይሎች ራሳቸውን ማፈርጠም እና ማደራጀት ሲጀምሩ' የአማራን ሕዘብን ለመታደግ መደራጀት እና መሰልጠን ያስፈልግ እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ የአጭር ጊዜ ግብ ነው የሚሉት አቶ ዘመነ ከረዥም ጊዜ ግብ አንጻር ደግሞ ላለፉት አስርት ዓመታት 'የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማጠንጠኛ አማራ ጠልነት ነው' ይላሉ። ይህ ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስር የሰደደ አስተሳሰብ በአንድ እና በሁለት ዓመት ትግል ብቻ ይገታል ብለው እንደማያምኑ የሚናገሩት አቶ ዘመነ፤ "በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሁሉም ሕዝቦች እንደ ዜጋ በነጻነት፣ በእኩልነት፣ በመከባበር፣ በፍትህ የሚኖሩበት ዘመን እስኪመጣ. . .የአማራ ህዘብ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ አንገቱን ቀና አድርጎ በእኩልነት መኖር እስኪችል ድረስ' ሕዝብን ማደራጀት፣ ማንቃት፣ ማሰልጠን አስፈላጊም ሲሆን ማስታጠቅ የሚችል አደረጃጀት ያስፈልጋል ብለው በማመናቸው የአማራ ህዝባዊ ኃይል በሚል መሰባሰባቸውን ያስረዳሉ። የአማራ ህዝባዊ ኃይል በመላው አማራ የሚንቀሳቀስ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዘመነ ይኹንና ጠንከር ያለ አደረጃጃት ያለው በጎጃም መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የፋኖ አመራሮች የአማራን ህዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱም መፃኢ እድል በትከሻቸው ላይ እንደሆነ ያምናሉ። የአማራን ህዝብ ብቻ ሳይሆን አገሪቱ ከገባችበት ውጥንቅጥ ለማውጣትም እየታገሉ እንደሆነ የህዝባዊ ኃይሉ አመራሮች በልበ ሙሉነት የሚናገሩት ነው። "ይህ ትውልድ አዲስ ቀመር ይፈልጋል። ያ አዲስ ቀመር ተምጦ መወለድ ካለበት አዲሱ 'ሜተዶሎጂ' አስተሳሰብን መሰረት ያደረገ፣ አላማን መሰረት ያደረገ፣ የአማራን ሕዝብ መሰረት ያደረገ፣ . . .ኢትዮጵያንም ከመፍረስ መታደግ ላይ መሰረት ያደረገ አስተሳሰብ ላይ የቆመ ትግል" ነው ይላሉ አቶ ዘመነ አቶ ዘመነ ትግላቸው አዲስ ቀመርና የኢትዮጵያን አንድነት መጠበቅ አስተሳሳብ ላይ ያተኮረ ከሆነ ነፍጥ አንስቶ እየታገሉ ይህንን አስተሳሰብ ማስፈፀም አይቃረንም።ለዚህ ትግል የፖለቲካ ፓርቲ መስርቶ መንቀሳቀስ አይሻልም ተብለው በቢቢሲ የተጠየቁ ሲሆን እርሳቸው እና አማራን ህዝባዊ ኃይል ፋኖን የሚመሩ አመራሮች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ከፓርቲ ፖለቲካ የዘለለ ነው ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። "በተለይ ለአማራ ህዘብ ጥያቄዎች የፖለቲካ ፓርቲ በዚህ ወቅት ያን ያክል አመርቂ ውጤት ያመጣል ብለን አናምንም" ሲሉ ያስረዳሉ። አቶ ዘመነ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ታግለው ከተፈቱ የእነርሱ መሳሪያ አላስፈላጊ እንደሆነና እስከዚያው ግን በትጥቅ መታገላቸውን እንደሚቀጥሉ ይናገራሉ። "የመሳሪያን አፈሙዝ የሚደፍነው ፍትህ ነው፣ የመሳሪያን አፈሙዝ የሚደፍነው በእኩልነት በአንድነት በፍቅር እንደ ዜጋ ተቻችሎ መኖር ነው። አንዱ አንበርካኪ ሌላው ተንበርካኪ ሆኖ በሚኖርነት ዓለም ውስጥ መሳሪያ አፈሙዝ ሁሌም ክፍት ነው። ሁሌም ምላጭ ይሳባል። " በማለት የትጥቅ ትግልን አስፈላጊነት ያብራራሉ። በተለያዩ አካባቢዎች ስሙ የሚነሳው 'ፋኖ' ፋኖ በተደጋጋሚ በአራቱ የወለጋ ዞኖች እና ምዕራብ ሸዋ ዞን ንፁኀንን በመግደል፣ ቤት ንብረትን በማቃጠል ውንጀላ ይቀርብታል። በቅርቡ ደግሞ ሰሜን ሸዋ አካባቢ ላጋጠመው ክስተት በኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና ነዋሪዎች ውንጀላ ቀርቦበታል። ባለፈው ወር የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች በሚዋሰኑበት አካባቢ ጥቃት ተፈጽሞ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የአካባቢ ሚሊሻዎችና በነዋሪዎች ላይ ሞትና ጉዳት ደርሷል። ቢቢሲ በኦሮሚያ ውስጥ በመንቀሳቀስ ጥቃት ያደርሳሉ በሚል ስለሚወነጀሉት 'ፋኖዎች' ምላሽ የሚሰጥ አካል አላገኘም። ባለፈው ሳምንት ደግሞ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ለተከሰተው ግጭት ተጠያቂ ሆነው ከቀረቡት ኃይሎች መካከል አንዱ ፋኖ ነው። ለዚህ ጥፋት የአካባቢው የአማራ ክልል አመራሮች 'ሸኔ'ን ተጠያቂ ሲያደርጉ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ደግሞ ተጠያቂዎቹ የፋኖ ታጣቂዎች ናቸው ይላሉ። በፋኖዎች ላይ የሚቀርበው ውንጀላ ከኦሮሚያ ክልል አልፎ በቤንሻንጉል መተከል ዞንም ይሰማል። በቅርቡም ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በምዕራብ ትግራይ፣ የትግራይ ተወላጆች ላይ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ተፈጽመዋል በሚል ባወጡት ሪፖርት ላይ የፋኖ ታጣቂዎች ስማቸው ተነስቷል። በዚህ ሪፖርት ላይ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ መንግሥት ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን ያፍርስ ሲሉ ጠይቀዋል። የፋኖ ታጣቂዎች ከክልሉ ውጪ የተለያዩ ጥቃቶች በመፈፀም ስማቸው እንደሚነሳ የተጠየቁት የአማራ ህዝባዊ ኃይል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዘመነ 'እኛ የምናውቃቸው የሉም፤ ይኖራሉ ብለን አናምንምም' ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የአማራ ህዘብ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንደሚኖር አንስተው አማራ በየደረሰበት ተከባብሮ፣ ተቻችሎ የሚኖር እንጂ ራሱን በፋኖነት አደራጅቶ፣ በታጣቂነት ራሱን አደራጅቶ. . .አብሮት ከኖረው ማህበረሰብ ጋር የሚናቆር ወይንም አብሮት የሚኖረውን ማህበረሰብ መሳሪያ አንስቶ የሚታገል፣ የሚረብሽ ማህበረሰብ አይደለም እሴቱም አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ። አቶ አበበ በበኩላቸው ከወለጋ፣ ከመተከል እንዲሁም ከተለያዩ የደቡብ ክልል አካባቢዎች እነርሱ ጋር በመምጣት ስልጠና የወሰዱ የአማራ ተወላጆች መኖራቸውን ይናገራሉ። አቶ ዘመነ ግን ከክልሉ ውጪ መጥተው እነርሱ ጋር ስልጠና የወሰዱ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደሌሉ ያስረዳሉ። አቶ ዘመነ አክለውም በክልሉ ከሚንቀሳቀሱት ከጎንደር፣ ከሸዋ እና ወሎ የፋኖ አመራሮች ጋር እንደሚገናኙ ፣ እንደሚነጋገሩ እና እንደሚመካከሩ ያስረዳሉ። አቶ አበበም ቢሆኑ በተለያዩ የክልሉ ስፍራዎች የሚገኙ የአማራ አደረጃጀቶች በተለያየ ጊዜ እየተገናኙ እንደሚመካከሩ ገልፀዋል። አቶ ዘመነም ሆኑ አቶ አበበ በቅርቡ አንድ መዋቅር በመፍጠር በአንድ ጥላ ስር የመሰባሰብ ፍላጎት መኖሩን ለዚህም በጋራ እየሰሩ መሆኑን ይናገራሉ። በዚህም ይላሉ አቶ ዘመነ "ከአንድ እዝ ሰንሰለት የሚታዘዝ ፋኖ እንፈጥራለን ብለን ነው የምናስበው" ይላሉ። ይህ በአንድ እዝ ስር የሚታዘዝ ፋኖ ግን መቼ ይፋ እንደሚሆን አቶ አበበም ሆኑ አቶ ዘመነ ቁርጥ ያለ ቀን አላስቀመጡም። 'ስልጠናና ምልመላዎች ቀጥለዋል' የትግራይ ኃይሎች ከአማራ ክልል ከወጡም በኋላ በክልሉ አሁንም እንደ አዲስ ለፋኖ አባልነት የሚመለመሉ እና የሚሰለጥኑ መኖራቸው ይናገራል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? ተብለው የተጠየቁት የፋኖ አመራሮች አሁንም የትግራይ ኃይሎች ከአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ አለመውጣታቸውን ይናገራሉ። ለዚህም ማስረጃ ሲያቀርቡ ከፊል ራያ እና ከፊል ዋግ በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆናቸውን አቶ አበበም ሆኑ አቶ ዘመነ ይናገራሉ። አቶ ዘመነ "የትግራይ ኃይሎች በወልቃይት እና ሁመራ ምሽግ እየቆፈሩ ጦር እያደራጁ ነው" በማለት "የወረራ ስጋት መኖሩንም" ያነሳሉ። አቶ አበበ በበኩላቸው "የምንዘጋጀው ለታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶችም ጭምር ነው፤ በአቅማችን አገራችን በፈለገችን ልክ ለመገኘት እንሰለጥናለን፤ እንታጠቃለን' ይላሉ። ቀድሞ መዘጋጀት ቀድሞ ስጋትን ያስወግዳል የሚሉት አቶ ዘመነ 'ስለዚህ ፋኖ መመልመሉ፣ ፋኖ ማሰልጠኑ፣ ፋኖ ማስታጠቁ ይቀጥላል" ሲሉ ያስረዳሉ። ከዚህም ባሻገር "አማራ እንደ ሌሎች ዜጎች በእኩልነት ተከብሮ ሌሎችንም አክብሮ . . . የሚኖርበት ዘመን እስኪመጣ ራስን ማዘጋጀት እና ራሰን ማስታጠቅ አስፈላጊ ነው ብለን ነው የምናምነው" ይላሉ። የፋኖ አመራሮቹ የሚያስቡት እና ለአማራ ህዝብ ይገባዋል የሚሉት ሰላም ቢሳካ እቅዳቸው ምን እንደሆነ ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሁለቱም በአንድነት ሁላችንም ወደ የሙያችን እንመለሳለን ሲሉ ይናገራሉ። አቶ አበበ ደግሞ ልዩ ኃይሉም ሆነ መከላከያ ስልጠና እንዳይሰጡ አግደዋቸው እንደማያውቁ በመግለጽ ስልጠናው እንደሚቀጥል ገልፀዋል። የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች በተለያየ ጊዜ መከላከያ እና ልዩ ኃይሉ የመሳሪያ ድጋፍ እንዳደረገላቸው ይናገራሉ። አቶ አበበ የአገር መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን ተከትሎ 30 ክላሽ አራት ላውንቸር፣ ብሬን እና ስናይፐር መስጠቱን ይናገራሉ። የአማራ ክልል መንግሥትም አንድ ዲሽቃ እንደ ሸለማቸው ይናገራሉ። ከዚህ አልፎ የስንቅ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ያስረዳሉ። አቶ አበበ 'አጠቃላይ ትዕዛዝ፣ አመራር የምንቀበለው ከአገር መከላከያ ሠራዊት ነው' ይላሉ። አልፎ አልፎ ከልዩ ኃይሉ ትዕዛዝ መቀበል ቢኖርም በዋናነት ግን ግንባሩን የሚመራው የአገር መከላከያ ሠራዊት መሆኑን ያስረዳሉ። አቶ ዘመነ በበኩላቸው "ሙሉ በሙሉ ድጋፋችን ከህዝብ ነው" በማለት ከክልሉ ልዩ ኃይልም ሆነ ከመከላከያ አንድም የመሳርያ እና የስንቅ ድጋፍ አግኝተው እንደማያውቁ ያብራራሉ። አቶ ዘመነ የክልሉ መንግሥት በተለያየ ጊዜያት ፋኖ ትጥቁን አይፈታም ማለቱን አንስተው "ይህ ግን እናስታጥቀዋለን ማለት አይደለም፤ እናሰለጥነዋለን ማለት አይደለም" በማለት ከክልሉም ሆነ ከአገር መከላከያ ሠራዊት የሚደረግላቸው ምንም ዓይነት ድጋፍ እንደሌለ ተናግረዋል። አቶ ዘመነ ምንም ዓይነት መሳርያ እንደታጠቁ ሲጠየቁ "በቂ ልብ ስላለን እኛ ቤት ቁመህ ጠብቀኝም ቢሆን ቁም ነገር አለው" በማለት ዝርዝር ጉዳይ ከመመለስ ተቆጥበዋል። የምስራቅ አማራ ፋኖ አደረጃጀትን በሚመለከትም አቶ አበበ ሲናገሩ፣ አንድ በብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ስም የተሰየመ ብርጌድ ስር ኃይሎቻቸውን ማደራጀታቸውን ይናገራሉ። ይህ አንድ ብርጌድ ግን ምሽግ ላይ ያለ ብቻ መሆኑን እና ከኋላ ያለው ተደራጅቶ ቢመጣ 'ብዙ ብርጌዶች' እንደሚሆን ያስረዳሉ። አቶ ዘመነን በስራቸው ምን ያህል ፋኖዎች ስልጠና ወስደው እንደሚገኙ ተጠይቀው "በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ፤ ነገ ደግሞ በብዙ ሚሊዮኖች እንሆናል" በማለት በደፈናው መመለስን መርጠዋል። አደረጃጀታቸውንም በሚመለከት ለየት ያለ ራሱን የቻለ አደረጃጀት ያለው ከማለት ውጪ ዝርዝሩን ከመመለስ ተቆጥበዋል። አቶ አበበ በበኩላቸው "ሙሉ ወሎ እና ሙሉ ሸዋ ሰልጥኗል ማለት ትችላለህ" በማለት በወሎ ብቻ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰልጥነው እንደሚገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ገለጻና የሥራ መመሪያ በሰጡበት ወቅት በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅን ማስፈታት እንደሚያስፈልግ ተናግረው ነበር። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትይዩ የቆሙ ኃይሎች (Parallel Forces) በማለት ስሙን የጠሩት "ሸኔ"ን ብቻ ሲሆን እነዚህ ኃይሎች 'ተቋም በሚገዳደር' መልኩ መሄድ እንደሌለባቸውም አብራርተዋል። ቢቢሲ በቅርቡ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኞች ከዚህ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ጋር ተመሳሳይ የሆነ ኃሳብ አንስተዋል። እነዚህ ምሁራን አሁን በየአካባቢው የሚታየውን የታጠቁ ኃይሎች መብዛት በማንሳት፣ በአንድ አገር የጦር መሳሪያ የበላይነት መያዝ ያለበት መንግሥት ብቻ ነው ይላሉ። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ከባሕር ዳር ሕዝብ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት የትግራይ ኃይሎች ወደ ደሴ እየተቃረቡ በሚመጡበት ወቅት የአማራ ክልል ወጣቶች እንዲዘምቱ ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውሰዋል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ተሰልፈው መሞታቸውን፣ መቁሰላቸውን፣ ጊዜና ጉልበታቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል። አክለውም "ለእነዚህ ትልቅ ክብር አለን፤ እውቅና እና ሽልማት እያዘጋጀን ነው" ብለዋል። "ከዚህ አንጻር ለአገር መስዋዕትነት የከፈሉ ፋኖዎች ለክልሉ ብርቅ ድንቅ ናቸው" በማለት ትጥቃቸውን እንደማይፈቱ እንዲሁም እንደማይዋከቡ በይፋ ተናግረዋል። በዚሁ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ የትግራይ ኃይሎች ከክልሉ መውጣታቸውን ተከትሎ በርካቶች ፋኖ ነን በማለት መነሳታቸውን ጠቅሰዋል። ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) "ፋኖ ነን ብሎ ይቁም ጥሩ ነው፤ ነገ ችግር ሲያጋጥመን ሊጋፈጥ ይችላል። ሊዋጋ ይችላል፤ መከታ ሊሆን ይችላል ብለን እናስባለን" ካሉ በኋላ በተለያየ አካባቢ በፋኖ ስም ተነስተው ጥፋት ያደረሱ አካላትን ኮንነዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ "የሕግ የበላይነት፣ የክልሉ ሕዝብ ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ" እንዳለበት አሳስበው "በየትኛውም መንግሥት ባለበት አገር ከመንግሥት ውጪ ወታደራዊ ሙያ የለም፤ አይኖርም" ብለዋል። ከኖረም የሚኖረውን አደጋም ሲያስረዱ ልክ እንደ ሶማሊያ፣ የመንና ሊብያን በመጥቀስ አገር በተለያዩ 'ጎበዝ አለቆች ስር' ትሆናለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ርዕሰ መስተዳደሩ ፋኖ ለሚያካሄደው ሥልጠና የጠነከረ ወታደራዊ ሥነ ምግባር እንደሚያስፈልግ በመግለጽ እንደዚህ ከሕግ እና ሥርዓት ውጪ የሚሆኑ እና ስርዓት አልበኝነት የሚያሰፍኑ አካላት የፋኖ ስም አይገባቸውም ሲሉ ኮንነዋቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/61244459
amh
politics
የሶማሊያ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ውዝግብ ወዴት ያመራ ይሆን?
የሶማሊያ ምርጫ መራዘሙን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በፖለቲከኞች መካከል አለመተማመንን ከፈጠረ ሰነባበተ። የአገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት የምርጫ ማራዘሚያ ውሳኔ በማጽደቅ የፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆን የሥልጣን ዘመን ለሁለት ዓመት ማራዘሙን ተከትሎ ነበር አለመግባባቱ የተባሰው። የሶማሊያ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የሥልጣን ማራዘሚያውን ውድቅ ከማድረግ ባለፈ ፋርማጆን በሥልጣን ቅሚያ ከሰዋል። ይህን ተከትሎ በርዕሰ መዲናዋ ሞቃዲሾ የሰዎችን ህይወት የነጠቀ ሁከትና ብጥብጥ ተከስቶ ነበር። ባለፈው ሚያዝያ በፌደራል መንግሥቱ ደጋፊዎችና በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል። የውዝግቡ ቁልፍ ተዋናዮች ተቃዋሚዎች የፕሬዝዳንት ፋርማጆ የሥልጣን ዘመን ስላበቃ ከእንግዲህ እውቅና አንሰጥም ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ ናሽናል ሳልቬሽን ፎረም የተባለ ተሰሚነት ባላቸው የተቃዋሚዎች ብሔራዊ መድረክ አቋቋሙ። ይህም የፋርማጆ ቀንደኛ ተቃዋሚ የሆኑት የሴኔቱ አፈ ጉባኤ አብዲ ሀሺ አብዱላሂ፣ የጁባላንድ እና ፑንትላንድ መሪዎችን ያካተተ ጥምረት ነው። ሕገ-መንግሥታዊ አይደለም ያሉት የስልጣን ማራዘሚያ ላይ "አስፈላጊ እርምጃዎችን እንወስዳለን" ሲሉም ዛቱ። የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒ እና የጁባው አቻቸው አህመድ መሐመድ ኢስላም በሞቃዲሾ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ነበር። ተወካዮቹን "ሶማሊያን ከማይቀረው የትርምስ አዘቅት ውስጥ እንዳትገባ እንዲያድኑ" ጠይቀዋል። የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ምክር ቤት ፋርማጆን ለመተካት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ጥምረት ነው። በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሻሪፍ ሼክ አህመድ የሚመራ ሲሆን ፕሬዚዳንቱን "የጦር አበጋዝ" ብለዋቸዋል። በወቅቱ አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና የአውሮፓ ሕብረት የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ጊዜ የማራዘሙ ውሳኔ ሶማሊያ ወደ ሠላምና መንግሥት ግንባታ የምታደርገውን ጉዞ የሚያደናቅፍ ብለዋል። ግንኙነታቸውን በድጋሚ እንደሚያጤኑትም አስጠንቅቀዋል።አሜሪካ "ሰላምን እና መረጋጋትን በማደናቀፍ" በሥልጣን ማራዘሙ በተሳተፉት ላይ ማዕቀብ እንደምትጥልም ዝታ ነበር የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት የሥልጣን ጊዜ ማራዘሙን ውድቅ አድርጎታል። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ መሪዎች በምርጫ ውዝግቡ ዙሪያ ውይይት እንዲቀጥሉ ያቀረበውን ሃሳብ እንደሚደግፍም አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ከፍተኛ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም በታችኛው ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴዎች እና በጋልሙዱግ፣ በሂውማሌ እና በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ሰፊ ድጋፍ አላቸው። የፌዴራል መንግሥት ፈተና የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሥርዓት ሥር የሰደደውን የጎሳ ግጭት ለማስቆም እና አሃዳዊ መንግሥት ለመመስረት የሚደረገው ጥረት በመሰናከሉ የተመሠረተ ነው። የተከፋፈለና ደካማ ቢሆንም የብሔራዊ ደኅንነት ግንባታው እያዘገመም እንዲጓዝ መንገዱን ጠርጓል። አገሪቱ ከ30 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሃብት ሥርዓት ለመቀላቀልም የፋይናንስ ተቋማቷን እንደገና አደራጅታለች። ምርጫው ያስከተለው አለመረጋጋት በማዕከላዊ መንግሥት እና ቀድሞውንም የፋርማጆን ሥልጣንን 'በሚያኮስሱት' አንዳንድ የክልል መንግሥታት መካከል ውዝግቡን አጡዞታል። እአአ መስከረም 2018 አምስት የአገሪቱ የክልል ፕሬዚዳንቶች በሥልጣን እና በሃብት ክፍፍል አለመግባባት ምክንያት ከፌዴራል መንግሥት ጋር እንደማይተባበሩ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆም ለምላሽ አልዘገዩም። ክልሎችን በራሳቸው ቁጥጥር ስር ማድረግ ጀመሩ። ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን በማንሳት አጋሮቻቸውን በጋልሙዱግ እና በደቡብ ምዕራብ ግዛቶች አስቀምጠዋል። የፌዴራሉ መንግሥት በፑንትላንድ እና በጁባላንድ ባሉ ምርጫዎች ላይ ተመሳሳይ ተጽዕኖ ማሳደር ግን አልቻለም። የእነዚህ አካባቢ መሪዎች ፋርማጆ እንደገና እንዳይመረጡ እየሠሩ ነው። መስከረም ላይ የተደረገው ስምምነት ፕሬዝዳንት ፋርማጆ የሥልጣን ጊዜ በይፋ ያበቃው በፈረንጆቹ የካቲት ወር ላይ ቢሆንም አዲስ ፕሬዝዳንት እንዴት እንደሚመረጥ በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ምርጫው ተራዝሟል። ለምርጫው መስተጓጎል ፕሬዝዳንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ እርስ በእርሳቸው እየተወነጃጀሉም ነው። ብሔራዊው የምርጫ ኮሚሽን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያለው ሕዝባዊ ምርጫ ለማድረግ እንደማይቻል አስታወቀ። ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ለማዘጋጀት እስከ 13 ወራት ድረስ እንደሚያስፈልገው እአአ ሰኔ 2020 ለሕዝብ እንደራሴዎች ገለጸ። የጁባላንድ፣ ፑንትንትላንድ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫውን መዘግየት ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ እአአ ሐምሌ 2020 አስደንጋጭ ነበር የተባለለት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሃሰን አሊ ኬይሬ ከሥልጣን መነሳት በምርጫው ሂደት ላይ ያላቸውን እምነት ይብስ ሸረሸረው። የጁባላንድ እና የፑንትላንድ መሪዎች በማዕከላዊው ዱሳማሬብ ከተማ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። በስብሰባው ከምርጫ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ስምምነት ተደርሷል። እአአ መስከረም 17 ቀን 2020 ከሳምንታት የዓለም አቀፍ ግፊት በኋላ በምርጫ ሁኔታዎች ላይ ስምምነት ተፈረመ። በስምምነቱ መሠረት ሁለት የምርጫ ክልሎች በእያንዳንዱ ክልል ይኖራሉ። ምርጫዎች የሚካሄዱት በየክልል ተሰብሳቢዎች ላይ የተመሠረተ ሲሆን በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ውስጥ 101 የምርጫ ልዑካን ድምጽ ይሰጣሉ። በአማጽያን ጥያቄ መሠረት ምርጫውን በበላይነት የሚቆጣጠር ብሔራዊ እና ክልላዊ የምርጫ ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ ተወሰነ። የጁባላንዱ ማዶቤ እና የፑንትላንዱ ዴኒ በፌዴራል መንግሥት የተቋቋመውን የምርጫ ኮሚሽን ባለመቀበላቸው የስምምነቱ ትግበራ ድጋሚ እንቅፋት ገጠመው። የፀጥታ አዛዦች እንዲነሱ እና ፓርላማው እንዲበተንም ጠየቁ። የምርጫውን መዘግየት አስቀድሞ የገመተው የፌዴራልሉ ፓርላማ እአአ ኅዳር 2020 አዲስ ተመራጮች እስኪተኩ ድረስ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል። የጎሳ ፖለቲካ እና ግጭት አለመተማመኑ እየጠነከረ ሲሄድ ፖለቲከኞች እና ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናት ወደ ጎሳቸው መመሸግ ጀመሩ። እነዚህም በጎሳ ሚሊሻዎች፣ በጎበዝ አለቆች እና በቀድሞ የጦር መሪዎች የሚጠበቁ ናቸው። የተወሰኑ የተቃዋሚ የፓርቲ አመራሮች ለትጥቅ ትግል መዘጋጀት ያዙ። የጦር መሳሪያዎችና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የገዙም አሉ። በመዲናዋ ሞቃዲሾ የዘገየውን ምርጫ የሚቃወሙ ሰልፈኞችን በሚደግፉ ወታደሮች እና በፖሊስ መካከል መጋቢት 15 ግጭት ተፈጠረ። የፖሊስ መኮንኖቹ በቱርክ የሰለጠነው ልዩው የሃርማድ የፖሊስ ኃይል አባላት ነበሩ። ከዚህ በፊት መንግሥት ፍላጎቱን በክልል መንግሥታት ላይ ለመጫን ይህን ልዩ ኃይል ይጠቀም ነበር። የቀድሞው የሞቃዲሾ የፖሊስ አዛዥ ሳዲቅ ኦማር ሐሃሰን (ሳዲቅ ጆን) እአአ ሚያዝያ 13 በምርጫ ውዝግብ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀውን የፓርላማ ስብሰባ በማገድ ፊታቸውን መንግሥት ላይ አዞሩ። ከኃላፊነት ተነስተው ማዕረጋቸውም ተገፈፈ። የቀድሞው የፖሊስ አዛዥ ከቀናት በኋላ በጎበዝ አለቆች እና ከጎሳቸው በተገኙ ሚሊሺያዎች እየተጠበቁ በከተማው ዳይናል አካባቢ ካምፕ መሠረቱ። መንግሥት የታጠቁ የፀጥታ ኃይሎችን በአቅራቢያው ወደሚገኙ አካባቢዎች በማሰማራቱ ውጥረቱ ዋና ከተማዋን አዳርሷል። በኋላ ላይ ሁኔታው ተረጋጋ። ምርጫው መፍትሔ ያገኘ መሰለ ሚያዝያ ላይ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን ለሁለት ዓመታት ለማራዘም ያደረጉትን ሙከራ ማቆማቸውን ይፋ አደረጉ። ለሕዝቡ ባደረጉት ንግግርም አዲስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበው ጠቅላይ ሚኒስትራቸው ያደረጉትን ጥረት አድንቀዋል። በቀጣይ ቀናትም የሶማሊያ የፖለቲካ መሪዎች ምርጫ ለማካሄድ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተስማሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሁሴን ሮብሌ እና የክልል ፕሬዝዳንቶች በ60 ቀናት ውስጥ ሂደቱን ለመጀመር የሚያስችል ስምምነትም ተፈራርሙ። ምርጫው በተለያየ የጊዜ ሰሌዳ እንደመካሄዱ ሐምሌ ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች ምርጫው ተጀመረ። የሶማሊያ የጁባላንድ ክልል ምክር ቤት ኢሊያስ ባዳል ጋቦሴን የመጀመርያው የሶማሊያ ሴኔት አባል አድርጎ መርጧል። የጎሳ መሪዎች የፓርላማ አባላትን የሚመረጡበት የተወሳሰበው የሶማሊያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ከኅዳር ወር ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን ከቀናት በፊት መጠናቀቅ ነበረበት። ግን እሳካሁን አላለቀም። የደኅንነት ሠራተኛዋ መጥፋት መስከረም ላይ ደግሞ ሌላ ውዝግብ ተከተለ። በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ኢክራን ታህሊል የተባለች የደኅንነት ሠራተኛ በመጥፋቷ ምክንያት በፕሬዝዳንቱ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል ውዝግብ አገረሸ። የደኅንነት ቢሮው ኢክራን ታህሊል በአልሸባብ ታግታ መገደሏን ቢገልጽም፣ አሸባሪው ቡድን ጉዳዩን አስተባብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሁሴን ሮብሌ የደኅንነት ቢሮው ኃላፊ ጉዳዩን የያዙበት መንገድ ቅር አሰንቶኛል በማለት ከሥራ አግዷቸው። ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ደግሞ የደኅንነት ኃላፊው ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ አዘዙ። ከጠፋችው የደኅንነት ሠራተኛ በተጨማሪ በደኅንነት ቢሮው ተጠሪነት ጉዳይ ጭምር ነው የሁለቱን አውራ ፖለቲከኞች ልዩነት ያሰፋው። በሁለቱ መሪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት የሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎችን የመከፋፈል አደጋም አስከትለ። ጥቅምት ላይ ሁለቱ ባለሥልጣናት የአገሪቱን ምርጫ ሊያደናቅፍ ይችላል የተባለለትን አለመግባባት ለማቆም ተስማሙ። የጠፋችውን የደኅንነት ቢሮ ባልደረባ ጉዳይም ለፍርድ ቤት እንደሚተው ተስማምተዋል። አዲሱ ውዝግብ ከቀናት በፊት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ሞሐመድ ፋርማጆ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ ሁሴን ሮብሌን ከሥልጣናቸው ማገዳቸውን አስታወቁ። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታገድ እንደ ምክንያት የቀረበው ሥልጣንን አላግባብ መጠቀምና የመንግሥት የሆነ መሬትን መቀራመት የሚል ነው። ፕሬዝዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሶማሊያ ብሔራዊ ሠራዊት ይዞታ የሆነን የሕዝብ መሬትን ወስደዋል እና የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር በሚያካሂደው ምርመራ ውስጥ ጣልቃ ገብተዋል ሲሉ ከሰዋቸል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የሶማሊያ ባሕር ኃይል አዛዥ የሆኑትን ጄነራል አብዲሃሚድ ሞሐመድ ዲሪርንም ከኃላፊነታቸው አግደዋል። ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ ሁሴን ሮብሌ የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አድርገው ፕሬዚዳንቱ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሞክረዋል በማለት የወነጀሏቸው ሲሆን በሥልጣናቸው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል። ከዚያም አልፈው የአገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች ትዕዛዝ መቀበል ያለባቸው ከፕሬዝዳንት ፋርማጆ ሳይሆን ከእሳቸው እንደሆነም አሳስበዋል። አዲሱ ውዝግቡ በሶማሊያ ተጨማሪ አለመረጋጋት እንዳያስከትል ስጋት ፈጥሯል። በሶማሊያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ መሪዎቹ "ከጸብ ጫሪ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እና የኃይል እርምጃዎችን እንዲያስወግዱ" አሳስቧል። አገሪቱ በተለያዩ ጎራ በተሰለፉ ፖለቲከኞች እና በጎሳዎች መካከል ፈተና ውስጥ የምትገኝ ሲሆን ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ካለው አልሸባብ አማጽያን ጋርም እየተዋጋች ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-59827781
amh
politics
በጋምቢያው ምርጫ ሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው አሸንፊያለሁ አሉ
የጋምቢያው ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው በአገሪቱ የተካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ አሸንፊያለሁ ሲሉ አዋጁ። አዳማ ባሮው የጋምቢያ የረዥም ጊዜ መሪ ያህያ ጃሜህ ሳይወዳደሩ የቀሩበትን ምርጫ በቀላሉ በድጋሚ ማሸነፋቸውን አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ባሮው ከቅዳሜውን ምርጫ ድምጽ 53 በመቶ አካባቢ ያገኙ ሲሆን፣ የቅርብ ተቀናቃኛቸው የሆኑት ጠበቃ ኦሳኢኖ ዳርቦ 28 ከመቶውን ድምጽ አግኝተዋል። ዳርቦ እና ሌሎች ተቃዋሚ ዕጩዎች የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉ ቀደም ብለው አስታውቀው ነበር። ምርጫው የጋምቢያን የዴሞክራሲ ሥርዓት የሚፈተንበት ነውም ተብሎለታል። ባለፈው ምርጫ ያህያ ጃሜህ በባሮው የተሸነፉ ሲሆን ውጤቱን ለመቀበል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው በስደት ለመኖር መርጠዋል። የጃሜህ የ22 ዓመታት የሥልጣን ዘመን በበርካታ የበደል ውንጀላዎች የታጀበ ሲሆን በቅርቡ ለአገሪቱ የእውነት አፈላላጊ ኮሚቴ ቃላቸው የሰጡ የዓይን እማኞች በያያ ጃሜህ አስተዳደር ወቅት በመንግሥት የሚደገፉ ግድያዎች ስለመኖራቸው እንዲሁም የኤድስ ታማሚዎች የማይፈውስ የውሸት ሕክምና እንዲወስዱ ይገደዳሉ ብለዋል። ጃሜህ በውጭ አገር ቢሆንም ተጽእኖ ፈጣሪነታቸው እንደቀጠለ ነው። ከአገር ውጪ ሆነው በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ደጋፊዎቻቸው ለባሮው ድምጻቸውን እንዳይስጡ ሲወተውቱ ነበር። አዳማ ባሮው የተሳካላቸው የሪልስቴት አልሚ ሲሆኑ በአንድ ወቅት ለንደን ውስጥ የጥበቃ ሠራተኛ እንደነበሩ ይነገራል። እ.ኤ.አ. 2017 ላይ በተደረገው ምርጫ ጃሜህን ማሸነፋቸው ግርምትን የፈጠረ ነበር። የማሸነፋቸው ዜና ሲሰማም ደጋፊዎቻቸው በጎዳናዎች ላይ በመውጣት ደስታቸውን እየገለጹ ነው። ባሮው በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል ባደረጉት የድል ንግግር በአገሪቱ የፖለቲካ አንጃዎች መካከል አንድነት እንዲኖር ጠይቀዋል። "የእናንተ የፖለቲካ ልዩነት ምንም ይሁን ምን ሁሉም የጋምቢያ ተወላጆች የፖለቲካ እና ሌሎች ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን ትተን እንደ አንድ ሕዝብ በመሰባሰብ ለአገራችን እድገት እንድንረባረብ ጥሪዬን አቀርባለሁ" ብለዋል። ጋምቢያ በአፍሪካ ከሚገኙ ትንሽ አገራት መካከል አንዷ ሰትሆን፤ 2.4 ሚሊዮን ሕዝብ ብቻ አላት።
https://www.bbc.com/amharic/news-59544920
amh
politics
የዩናይትድ ኪንግደም ምክር ቤት አባል በስለት ተወግተው ተገደሉ
ወግ አጥባቂው የዩናይትድ ኪንግደም የፓርላማ አባል ሰር ዴቪድ አሜስ አርብ ዕለት በስለት ተወግተው ተገደሉ። የምክር ቤት አባሉ ለንደን በሚገኘው ኢሴክስ የምርጫ ክልላቸው ውስጥ ነው ህይወታቸው ያለፈው። ሊይ ኦን ሲ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመራጮች ጋር በነበሩበት ወቅት በስለት ወግቷቸዋል በሚልም ፖሊስ አንድ የ25 አመት ወጣት ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አውሏል። የወጋበትን ስለት እንዳገኙና ከምክር ቤቱ አባል ግድያ ጋር በተያያዘ ሌላ ተጠርጣሪ እንደማይፈልጉ ፖሊሶች አስታውቀዋል። የ69 ዓመቱ ሰር ዴቪድ ከአውሮፓውያኑ 1983 ጀምሮ በምክር ቤት አባልነት ያገለገሉ ባለትዳር እና የአምስት ልጆች አባት ነበሩ። "ታላቅ ሰው፣ ታላቅ ጓደኛ እና ታላቅ የፓርላማ አባል፣ ዴሞክራሲያዊ ሚናውን ሲወጣ ተገድሏል" በማለት የጤና ሚኒስትሩ ሳጂድ ጃቪድ ሐዘናቸውን ገልፀዋል። "ከሁሉ የከፋው የአመፅ ገጽታ ኢሰብአዊነት ነው። ከዓለም ደስታን ይሰርቃል እናም እኛ በጣም የምንወደውንም ሰው ከእኛ ወስዷል" በማለት ቻንስለር ሪሺ ሱናክ ተናግረዋል። "ዛሬ አባት፣ ባል እና የተከበረ ባልደረባችንን ተነጠቅን። ለሚወዱት በሙሉ በጸሎት አስባቸዋለሁ። መፅናናትንም እመኛለሁ" በማለት አክለዋል። የሳውዝ ኢንድ ዌስት ተወካይ የሆኑት ሰር ዴቪድ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው በምርጫ ወረዳቸው የመረጧቸው አባላቶቻቸው አሳሳቢ የሚሏቸውን ጉዳዮች እንዲሁም ቃል የገቡትን ሁኔታ የሚያነሱበት ውይይት እያካሄዱ ነበር። ውይይቱም እየተካሄደ የነበረው በሜቶዲስት ቤተክርስቲያን ነበር። የኢሴክስ ፖሊስ እንደገለጸው አንድ ሰው በስለት ተወግቶ መጎዳቱ ሪፖርት የደረሰው በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር አርብ 6፡05 ነበር። በስፍራው በአስቸኳይ የአደጋ ጊዜ ህክምና ቢደረግላቸውም ህይወታቸው ያለፈው ወዲያው ነው። ሰር ዴቪድ በአውሮፓውያኑ 2016 የፓርላማ አባል ጆ ኮክስን ግድያ ተከትሎ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የተገደሉ ሁለተኛው የምክር ቤት አባል ናቸው። ጆ ኮክሰን የምርጫ ውይይት ለማድረግ በምዕራብ ዮርክሻዮር ባቀኑበት ወቅት ነበር ከቤተ መጽሃፍት ውጪ የተገደሉት።
https://www.bbc.com/amharic/news-58932871
amh
politics
አሜሪካ የሳን ሱ ቺ እስርን ተከትሎ ሚያናማር ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ስትል አስጠነቀቀች
በሚያናማር የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶ ባይደን በሚያናማር ላይማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ። በቀድሞዋ በርማ በዛሬዋ ሚያናማር የነበረውን አምባገነናዊ ወታደራዊ መንግሥት ተከትሎ በአሜሪካ ለረዥም ጊዜ ማዕቀብ ተጥሎ ቆይቶ ነበር። ትናንት በሚያንማር የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት አከናውኗል። ወታደሮች ሥልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ያደረጉት የሲቪል መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ሥር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል። የተባበሩት መንግሥታት፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የአውሮፓ ሕብረት በበርማ የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት አጥብቀው ኮንነዋል። ከእአአ 1989-2010 በእስር ቆይተው የነበሩት ሳን ሱ ቺ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፊት ለደጋፊዎቻቸው በጻፉት ደብዳቤ “መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃወሙ” ብለዋል። ሳን ሱ ቺ መፈንቅለ መንግሥቱ በአገሪቱ ወታደራዊ አምባገነናዊ ስርዓትን ያመጣል ሲሉ ጽፈዋል ተብሏል። በሚያንማር በወታደሩ እና በሲቪል አስተዳደሩ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጥረት ተከስቶ ነበር። ባለፈው ሕዳር በተደረገ ምርጫ የሳን ሱ ቺ ፓርቲ 'ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ' መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችለውን የመቀመጫ ቁጥር ማግኘት ችሎ ነበር። ሆኖም የአገሪቱ ጦር ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ቆይቷል። ጦሩ መፈንቅለ መንግሥቱን ካደረገ በኋላ የ11 ሚንስትሮችን እና ሚንስትር ዲኤታዎችን ሹም ሽር አድርጓል። በሌሎች እንዲተኩ ከተደረጉ ሚንሰትሮች መካከል የፋይናንስ፣ የጤና እና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ይገኙበታል። ፕሬዝደንት ባይደን ባወጡት መግለጫ የአገሪቱ ጦር የሕዝቡን ፍላጎት ቀልብሶ ስልጣን መቆጣጠሩ አግባብ አይደለም ብለዋል። አሜሪካ ከ10 ዓመታት በላይ በበርማ ላይ ጥላ የነበረውን ማዕቀብ ያነሳችው አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሸጋገሯን ተከትሎ ነው። ባይደን፤ “በየትኛውም ስፍራ በዲሞክራሲ ላይ ጥቃት ሲደርስ አሜሪካ ወደጎን አትልም” ብለዋል። ይሁን እንጂ የፖለቲካ ተንታኞች የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥቱን ለማደረግ ሲነሳ አሜሪካ ማዕቀብ እንደምትጥል ቀድሞ ያውቃል። ከአሜሪካ ማዕቀብ ይልቅ መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ ቻይና፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ የሚሰጡት ምላሽ ለጦሩ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም ቻይና የሚያንማር ጉዳይ ውስጣዊ ጉዳይ ነው በማለት ዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነትን ተቃውማ ነበር። በቀጠናው ከሚገኙት አገራት መካከል ካምቦዲያ፣ ታይናላንድ እና ፊሊፒንስ በበኩላቸው የበርማ ጉዳይ የአገሪቱ ውስጣዊ ጉዳይ ነው በማለት ጣልቃ መግባት እንደማይሹ ገልጸዋል። ይህ መፈንቅለ መንግሥት በአገሪቷ ዜጎች ዘንድ ከፍተኛ ፍርሃትን ፈጥሯል። በርማ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትእንደምትሸጋገር ተስፋን ሰንቀው ለነበሩት ዜጎች የሳን ሱ ቺ እና ሌሎች ሲቪል ፖለቲከኞች እስር እና መፈንቅለመግሥት የዲሞክራሲ ተስፋን ያጨለመ ሆኖባቸዋል። አውራ ጊዳናዎች ጸጥ እረጭ ብለው ታይተዋል። በዋና ከተማ ጎዳናዎች ላይ ብዛት ያላቸው የአገሪቱ ጦር አባላትተሰማርተው ታይተዋል። ሰኞ ዕለት ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና ኢንተርኔት ግነኙነት ማክሰኞ ንጋት ላይ ተመልሷል። የአገሪቱ ዋነኛ አየር ማረፊያ ግን አሁንም ዝግ እንደሆነ ነው። ትናንት [ሰኞ] ወታደሮች የአገሪቱን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውና መሪያቸውም ኮማንደር ሚነ ኦንግ ሌይንግመሆናቸውን ተናግረዋል። በርካታ ወታደሮች በአገሪቱ ዋና ከተማ ናይፒታው እና በሌላኛዋ ትልቋ ከተማ ያንጎን ጎዳናዎች በብዛት ታይተዋል። የሞባይልና ኢንተርኔ አገልግሎት እንዲሁም ስልክ በስፋት የተቋረጠባቸው ዋና ዋና ከተሞች ላይ ሲሆን የአገሪቱብሔራዊ ቴሌቪዥን ሥርጭት ለማድረስ እክል ገጥሞኛል በማለት ተቋርጧል። በርካታ ወታደሮችም በተለያዩ ቦታዎች እየሄዱ የሲቪል አስተዳደሩ ሚኒስትሮች የነበሩ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ሲያውሉነበር። የቢቢሲዋ የደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ወኪል እንደምትለው ከሆነ ሳን ሱ ቺ በአገሪቱ ዜጎች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትአላቸው። ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ ያላትን ሳን ሱ ቺን የመሰሉ ፖለቲከኞችን ማሰር ትልቅ ውሳኔ ነው። ይህ ምርጫ የወታደራዊ መንግሥት አስተዳደር ካበቃበት ከ2011 ወዲህ ሲካሄድ ለ2ኛ ጊዜ ነው። ነገር ግን ይህን ምርጫ ወታደሩ ሳይቀበለው ቀርቶ ነበር። ይህን ተከትሎም ምናልባት ወታደሩ መፈንቅለ መንግሥት ያደርግ ይሆናል የሚል ፍርሃት ነግሶ ቆይቶ ነበር። ሳን ሱ ቺ የበርማ የነጻነት አባት የሚባሉት የጄኔራል ኦንግ ሳን ሴት ልጅ ናቸው። አባቷ የተገደሉት እሷ ገና የ2 ዓመት ልጅ ሳለች ነበር። የተገደሉትም በርማ ከእንግሊዝ ነጻነቷን ከመቀዳጀቷ ጥቂትቀደም ብሎ በፈረንጆቹ በ1948 ነበር። ሳን ሱ ቺ በአንድ ወቅት ለዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ትልቅ ተምሳሌት ተደርገው ነበር የሚታዩት። ምክንያቱምምሕረት አያውቁም ከሚባሉት የምያንማር ወታደራዊ ኃይሎች በተጻጻራሪ በመቆም በአገሪቱ ዲሞክራሲ እንዲሰፍንበመታገል ረዥም ዓመታት ሳልፈዋል። ይህን ተከትሎም በ1991 የኖቤል የሰላም ሽልማትን ማሸነፍ ችለው ነበር። ሳን ሱ ቺ ሽልማቱን ያሸነፉት በቁም እስር ላይ ሳሉ ነበር። ሳን ሱ ቺ ለ15 ዓመታት በእስር ከቆዩ በኋላ በ2010 ነጻ ወጥተዋል። በ25 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገ ምርጫም ፓርቲያቸው ትልቅ ድል አግኝቶ ወደ ሥልጣን መምጣት ችሎነበር። ሆኖም የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሳን ሱ ቺ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ አልፈቀደም። ምክንያቱም የሳን ሱ ቺ ልጆችየውጭ ዜጎች ስለሆኑ ነበር። በዚህም የተነሳ መንግሥትን የሚመሩት ከጀርባ ሆነው ነው። ሳን ሱ ቺ አሁን 75 ዓመትሆኗቸዋል። የሰላም ኖቤል አሸናፊ የሆኑት ሳን ሱ ቺ በሚያናማር የሮሒንጋ ሙስሊሞች ላይ ለደረሰው ግፍና መከራ ቸልተኝነትበማሳየታቸው ከበርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያገኟቸው ክብርና እውቅናዎችን ተነጥቀዋል። ሆኖም በአገሯ ውስጥ ሳን ሱ ቺ በቡድሃ ብዙኃን ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት አላት።
https://www.bbc.com/amharic/news-55899183
amh
politics
“በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ የታቀዱ የሽብር ጥቃቶች ከሽፈዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
በዚህ ሳምንት ብቻ በአዲስ አበባ ከስድስት በላይ የሽብር ጥቃቶች መክሸፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ። በዛሬው ዕለትም አሶሳ ላይ የሽብር ጥቃት የመፈጸም እቅድ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የቀረቡላቸውን ጥያቄ አስመልክቶ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው የተናገሩት። የዛሬው ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሎን ረዘም ባለ መልኩ የፈጀው ከሰሞኑ በቄለም ወለጋ የደረሰውን ጭፍጨፋ ጨምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰሞኑ በደረሱ የጅምላ ግድያዎች ላይ አተኩሯል። ከፓርላማ አባላትም ዘንድ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋ እልባት የሚያገኘው መቼ ይሆን? የመንግሥት መዋቅሮች ተሳትፎ አለበት? የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ችላ ብለውታልና ሌሎች ጥያቄዎች ቀርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግራቸውን የጀመሩት በግፍ ሕይወታቸውን ላጡ፣ ለተገደሉ ንጹሃን ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ ነው። “ሕይወታቸውን ለመታደግ እንደ አገር፣ እንደ ሕዝብ፣ እንደ መንግሥት ባለመቻላችን ጥልቅ ሐዘን ይሰማናል” ብለዋል። በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ የደረሰው ጥቃት ኢላማ ያደረገው ከወሎ ወደ ወለጋ በ1977 ዓ.ም ረሃብ ወቅት ወደ ስፍራው የሄዱትን ሲሆን፣ እነዚህ ግለሰቦች ለአስርት ዓመታት የኖሩበትና ቀያቸው አገራቸው ነው ብለዋል። ሰሞኑን በሕዝብ ላይ ከተፈጸሙት ጥቃቶች ባሻገር “በአዲስ አበባ በዚህ ሳምንት የታቀዱ የሽብር ጥቃቶች ከሽፈዋል” ብለዋልጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ። “እነዚህን ሰዎች በግፍ መግደል የሚያሳካው የፖለቲካ አላማ የለም። ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሹ ወገኖች የደቀኑት አላማ ማሳያ ነው” ብለዋል። በአዲስ አበባ ላይ በየቀኑ ሰፋፊ ጥቃቶች ታቅደው ቦምቦች፣ መሳሪያዎች፣ መሳሪያዎችና የሰለጠኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል። በኦሮሚያ ክልል የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከሦስት ቀን በኋላ ሃምሳ አምስት ሰዎች ወደ ከተማዋ ለመግባት ሲሞክሩ ለገጣፎ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስረድተዋል። በትናንትናው ዕለትም በቁጥጥር የዋሉ እንዳሉም አስረድተዋል። ከሰሞኑ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉሙዝ በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሱ የጅምላ ግድያዎች የመንግሥት ፀጥታ ተቋማት በቸልታ እየተመለከቱት ነው፤ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚለው አስተያየት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አይስማሙም። “በርካታ የፀጥታ ኃይሎች ሕይወታቸውን እየገበሩ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በተለያየ እርከን ላይ የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች መስዋዕትነት ከመክፈላቸው በተጨማሪ በዝቅተኛ ደመወዝና በፈታኝ ሁኔታ እየሰሩ ነው ብለዋል። “ዜጎቻቸውን ለመታደግና ሕዝባቸውን ስለሚወዱ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ ነው” በማለትም አክለዋል። ለዚህም እንደ ምሳሌ የጠቀሱት በደራሼ ላይ በነበረው ግጭት ፖሊስና የአካባቢው አስተዳሪዎች ከ80 በላይ ሞተዋል፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል፣ በጋምቤላና በሌሎች አካባቢዎች በርካታ የፀጥታ ኃይሎች እንደተገደሉም ገልጸዋል። በዚህም በርካታ ዜጎችን መታደግም እንደተቻለ አበክረው ተናግረዋል። ሆኖም "የንጹሃንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ የትኛውም ስብስብ ሸኔም ይሁን የትኛውም አሸባሪ ኃይልን ለማጥፋት በጀመርነው ጥረት የምንቀጥል ከሆነ ይጠፋሉ።" ሲሉ የመንግሥታቸውን አቋም አስረድተዋል። “አሸባሪዎች የራሳቸው ጭንቅላት የላቸውም ታስቦ ሥራ ሲሰጣቸው ጥቃት ይፈፅማሉ፣ ሕዝቡ አሸባሪውን ከለየ በኋላ ከመንግሥት ጎን ቆሞ ጥፋት እንዲቀንስ ማድረግ ይኖርባታል። የንጹሃንን ደም በከንቱ የሚያፈስ የትኛውም አሸባሪ ኃይል እስኪጠፋ የጀመርነው እርምጃ ይቀጥላል” ሲሉም አጠናክረዋል። ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል በደረሱ ጥቃቶችም የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ ሰዎች ተሳትፎ አለበት በሚል የተለያዩ አካላት ወቀሳዎችን ሲያቀርቡ ተሰምቷል። በዛሬውም ዕለት አንዳንድ የምክር ቤት አባላት ይህንን ጉዳይ ያነሱ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የተገዙ ሰዎች አሉ" ሲሉ “መዋቅር ውስጥ ችግር አለ” በማለት አምነዋል። ከዚህ ቀደም በመንግሥት መዋቅር ውስጥ 5 ሺህ ያህል የተባረሩ፣ የታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን ጠቅሰው የማጥራት ሥራው እንደሚቀጥልም በዚህ ወቅት ተናግረዋል። በጅምላ ግድያዎቹ ላይ የተጠረጠሩ ሰዎች ምን ያህል ለፍርድ ይቀርባሉ በሚል በርካታ የፓርላማ አባላት የሽብር ህጉን አንቀፅ እየጠቀሱ ጥያቄ አቅርበዋል። በባለፉት ዓመታት በተፈጸሙ የጅምላ ግድያዎች ላይ 11 ሺህ ክስ መቅረቡን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። ከእነዚህም ውስጥ ከሙዚቀኛ ሃጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞ በደረሱ ጥቃቶች በሺዎች ላይ ክስ ቀርቦ በብዙዎች ላይ መፈረዱንም አስረድተዋል። ከሰሞኑ የደረሱ ጥቃቶችን ያደረሰው መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ነው በማለት መንግሥትና ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በበኩሉ ጥቃቱ በመንግሥት ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው በማለት አስተባብሏል። "ሸኔ የሚያደርሳቸውን ጥቃቶችን አላወገዙም የሚል ሃሜት ይቀርብብዎታል?" ተብለው የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄው ተገቢ አይደለም ብለዋል። "ሃሜት በምክር ቤት አባላት መቅረቡ ተገቢ አይደለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሸኔን አሸባሪ ያለው ይህ ምክር ቤት ሳይሆን እኛ ነን፤ ቸል እንዳልነው አታስመስሉት” ሲሉም ወቅሰዋል። በቅርቡ አባቱን ያቃጠለ የሸኔ አባልን ጠቅሰው እንዲሁም ልጆቻቸውን ወደ ጦርነቱ የላኩ ቤተሰቦችን የገደሉ የሸኔ አባላት አሉ በማለት “እንደነዚህ አይነት አውሬዎች የኦሮሞ ተወካይ አይደሉም። ህፃናትንና ቤተሰብን የሚገድሉት አካላት የፖለቲካ አላማ የላቸውም፣ አገርም ማስተዳደር አይችሉም” ብለዋል። ጉዳዩን ከዘር (ብሔር) ጋር የምታይይዙ ሰዎች ሸኔ በኦሮሞነቱ ብቻ ሳይሆን “የኦሮሞ ጠላት ነው” ሲሉ ወቅሰዋል። ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ከተሰለፉት ውስጥ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ከደቡብና ከትግራይ የማረክናቸው አሉ በማለት “ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ጠላት ሁሉ ስብስብ ነው” ብለዋል። ወለጋ ላይ በመቶ የሚቆጠሩ የወረዳና የዞን አመራሮች መገደላቸውን በመጥቀስ እንዲሁም ወለጋ ላይ የሚሰሩ መሠረተ ልማቶች መቆማቸውን በማንሳት የኦሮሞ ሕዝብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዳ ነው ብለዋል። "ብልጽግናን “እኛን” በብሔር መነጽር ማየቱ ትክክል አይደለም" ሲሉ በወቀሳ መልኩ ተናግረዋል “በሰፈር የተደራጃችሁና ያልኖራችሁበትና በዘር ለማየት የምትፈልጉ ትክክል አይደለም። እኛ ከዘር በላይ ነን። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖርባት አገር ነው የምንፈልገው። እኛ ኢትዮጵያዊ ነን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ጨምረውም “ሳናቅ የምናበላሸው ነገር ካለ በእናንተ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብና በእናቶች ምክር እንታረማለን እንጂ ሆን ብለን አንዱን ብሔር የበላይ በማድረግ የማፋጀት ሥራ አንሰራም” ብለዋል። ሽብርተኝነት ዓለም አቀፉ ፈተና እንደሆነ ለምክር ቤቱ ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለኢትዮጵያ ተለይቶ የሚያጋጥማት ፈተና አይደለም ብለዋል። በበርካታ አገራትም ቀዳሚና ዋነኛም አጀንዳም እንደሆነ ጠቅሰው፣ ጠንካራ የፀጥታ ኃይል፣ የላቀ ቴክኖሎጂና ሃብታም በሆኑ እንደ አሜሪካ ያሉ አገራትም ሽብርተኝነት እየፈተናቸው ነው ብለዋል። ሽብርተኝነት በዓለም ላይ ባሉ ሃገራት የሚከሰትና የኢትዮጵያ ፀጥታ ኃይሎች መግታት ያልቻሉት የሚል አንድምታ መሰጠት የለበትም ብለዋል። "ሽብርን መገንዘብ ያስፈልጋል" የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት በተሻለ መንገድ መረጃ ስላለው የተሻለ ሥራ መስራት እንደሚችል ሕዝቡ መገንዝብ ያስፈልጋል ብለዋል። የመከላከያና የፀጥታ ኃይል ከአስራ አምስት ዓመት በፊት ከነበረው በላይ ቁመና ላይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም የሆነው አገሪቷ የሽብር ጥቃት ስለተደቀነባት እንደሆነ ያስረዳሉ። ይህንንም በመገንዘብ መከላከያን፣ ፖሊስን፣ የፌደራል ፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች ተጠናክረዋል ብለዋል። እነዚህ የፀጥታ ኃይሎች በሚጠናከሩበት ወቅት ከዘር፣ ከእምነት እና ከፖለቲካ አመለካከት ነፃ በሆነ መልኩና በጥቅም እንዳይገዛ ባደረገ ሁኔታ ተጠናክሮ እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል። “ትናንት ከነበረው በተሻለ ሁኔታና በማይወዳደር መልኩ በደህንነት ተቋማት ላይ ባተኮረ መልኩ ለወደፊቱ ትውልድ የሚሆንና ኢትዮጵያን በሚታደግ መልኩ ተገንብቷል” ብለዋል። በዚህም 95 በመቶ ተሳክቶለታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም መቶ በመቶ ማድረግ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል። "በየትኛውም አገር የሽብር ጥቃቶችን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አልተቻለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያም ከዚያ ማዕቀፍ ውጭ ባትሆንም አገሪቱ መከላከል፣ መከታተል፣ መጠበቅ፣ መዘጋጀት በሚሉ አራት ዕቅዶችን ይዛ እየተንቀሳቀች ነው ብለዋል። የኢትዮጵያን ፈተና በሁለት ፈርጆች መታዬት አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ይህም ኢትዮጵያ ለዓለም ያላት አስተዋፅኦና ኢትዮጵያ ለማደግ ያላት አቅም ነው” ብለዋል። “ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጦርነት የግራጫ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም ሲያብራሩ የመረጃ ጦርነት አንደኛው ነው ብለዋል። ጭፍጨፋዎች ወይንም ግድያዎችን አጀንዳ ያደረገና የኢትዮጵያን ልማት ባላየ መልኩ የመረጃ ጦርነት ይደረጋል የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህም አገሪቱ የተከፈተባት መጠነ ሰፊ ጥቃት ነው ይላሉ። በተጨማሪም ዲፕሎማሲያዊ፣ የሳይበር ጥቃትና የተልዕኮ ውጊያም እንደተጋረጠባት አስረድተዋል። በተልዕኮ ውጊያ “እግር አልባ ባንዳዎች” ብለው የጠሯቸው ኃይላት የሕዝቡን ስሪት እያፈራረሱ ነው በማለት፣ በዚህም አማራና ኦሮሞን ማፋጀት፣ አማራን እርስ በርስ፣ ኦሮሚያን እርስ በርስ፣ ሶማሌና አፋርና፣ እንዲሁም ክርስቲያንና እስላምን ማፋጀት በዋነኝነት አጀንዳቸው ነው ይላሉ። "ሰው አብሮ ከተዋለደው፣ ከኖረው ጎረቤቱ ጋር ጠላት መሆን አይቻልም። አማራና ኦሮሞ በጠላትነት ተሳስበው መቀጠል አይቻልም።" በማለትም የማህበረሰቡን ስሪት አስረድተዋል “በዚህ ሁሉ መጠነ ሰፊ ጥቃት ኢትዮጵያን ማፍረስ አልተቻለም። ኢትዮጵያን ማጋደል፣ ማሸበር፣ በኢኮኖሚ ጫና ለማንበርከክ ቢሞከርም  ማፍረስም አይቻልም” ብለዋል። "ሆኖም የኢትዮጵያ ጠላቶች አጥብቀው አይተኙም" በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል። “በየቀኑ እየተወጋን፣ መስዋዕትነት እየከፈልን፣ በማይታመኑ ነገሮች ውስጥ እያለፍን ቢሆንም እየጠነከርን ነው፤ ወደፊት እየተጓዝን ነው።” "ከማበልጸግና አገር ከማሻገር አላማችን ንቅንቅ አንልም አስፈላጊ ከሆነም መስዋዕት እየከፈልን፣ በየቀኑ እየቀበርን፣ የሕፃናቱ ደም ቢጣራም በዚህ ፈተና ውስጥ እናሸንፋለን፤ ኢትዮጵያ ዳገት ላይ ናት” ሲሉ አስተዳደራቸው እያለፈበት ያለውን ሁኔታ ለምክር ቤቱ ገልጸዋል። ሌላኛው ከምክር ቤት አባላት የቀረበው ጥያቄ ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ከህወሓት ጋር ድርድር ማድረግ ብቻውን ለምን ወሰነ? የሚል ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሲመልሱ ገዥው ፓርቲና ሕዝቡ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሰላም ነው ብለዋል። የአገሪቱን ሉዓላዊነትና ደኅንነትን በሰላም ለማስጠበቅ ካልተቻለ ብቻ ነው ወደ ጦርነት የሚገባው በማለት “ሰላምን እንዴት እንጠላለን” ሲሉም ጠይቀዋል። ሆኖም ለውይይቱ አጠቃላይ የመንግሥት ሠራተኞችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተወያዩም አስታውሰዋል። ህወሃት በፓርላማ አሸባሪ ተብሎ ከመፈረጁም ጋር ተያይዞ “ከአሸባሪ ጋር ድርድር አይካሄድም የሚለውን በጥልቀት ሊታይ ይገባል ብለዋል። በርካታ አገራት በጦርነት ወቅት ሆነው አሸባሪ ብለው ከፈረጇቸው አካላት ጋር ድርድር እንደሚያደርጉም የተለያዩ ሃገራትን ተሞክሮ ጠቅሰዋል። ሁልጊዜም ድርድር ይደረጋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደርግ ከህወሓትና ከሻዕቢያ ጋር ያደረገውን ድርድር በምሳሌነት ጠቅሰዋል። ሌላው በምክር ቤት አባላቱ የተነሳው ጥያቄ የሽግግር መንግሥት ምስረታ ያስፈልጋታል የሚሉ አካላትን አስመልክቶ ነው። የሽግግር መንግሥት ምሥረታ ጉዳይ ለዓመታት ሲንከባለል የመጣ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን የሚጠይቁ ሥርዓት የማፍረስ አደጋ አልታያቸውም ብለዋል። “የሽግግር መንግሥት ሃሳብ የሚያነሱ ግለሰቦች ቀበሌ መርተው የማያቁና ስለተቋምም የማያቁ ናቸው” ሲሉ ተችተዋል። ገለልተኛ የሆነ የምርጫ ቦርድ ማቋቋምን ጨምሮ፣ በምርጫ እንዲወዳደሩ መድረክ ክፍት በማድረግ ምህዳሩ ሰፍቷል ብለዋል። "ያለፈው ምርጫ በዲሞክራሲያዊነቱ እስካሁን ካለው የተሻለ መሆኑን ዓለም መስክሮከለታል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚህ ምርጫም ብልጽግና በከፍተኛ ድምፅ መንግሥት መመስረት ችሏል ብለዋል። “ሆኖም ከተሸነፉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማምጣት አብረን እንስራ በሚል ብልጽግና ሥልጣን አጋርቷል” ሲሉ ተናግረዋል። እነዚህም ተግባሮች ተከናውነው ችግሮች ባለመፈታቱ እየተንከባለሉ ያሉ ጥያቄዎች በተገቢው መልኩ እንዲፈታ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ መቋቋሙን በማንሳት “በሕዝብ ድምፅ የመጣ ኃይልን በጋጋታ ማፍረስ አይቻልም” በማለት አስረድተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c1v320k5xlno
amh
politics
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጀዋር የህክምና ቦታ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የሕክምና ቦታ ክርክር ላይ ብይን ለመስጠት በዛሬው ዕለት፣ የካቲት 12/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ቀጠሮ ሰጥቷል። ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እነ አቶ ጀዋር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላንድማርክ የግል ሆስፒታል እንዲታከሙ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ክርክር ተካሂዷል። ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቶ ጀዋርን ጨምሮ አምስት ሰዎች በመረጡት የላንድ ማርክ የግል ሆስፒታል እንዲታከሙ ማዘዙን በመቃወም ማክሰኞ የካቲት 9/ 2013 ዓ.ም ይግባኝ ቢጠይቅም ውድቅ በመደረጉ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወስዶታል። በዛሬው ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሀምዛ አዳነ፣ አቶ ሸምሰዲን ጠሃ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ እንዲገኙ ቢያዝም ማረሚያ ቤቱ ሳያቀርባቸው መቅረቱን ከተከሳሾቹ ጠበቆች መካከል አንዱ አቶ ሚልኪያስ ቡልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የማረሚያ ቤቱ ተወካዮችም እንዲሁ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ሲሆን ተከሳሾችን እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ቢደርሳቸውም፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ተከሳሾቹ በአካል በማቅረብ ፈንታ በማረሚያ ቤቱ እንዳሉ በቪዲዮ እንዲሳተፉ እንዲያደርጉ መታዘዛቸውን ጠበቃቸው ጨምረው አስረድተዋል። በመቀጠልም እነ አቶ ጀዋር በሌሉበት ጉዳዩ መታየት የለበትም በሚለው ላይ በጠበቆችና በዓቃቤ ሕግ መካከል ክርክር መካሄዱንም አቶ ሚልኪያስ ተናግረዋል። የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የግራ እና ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ እነ አቶ ጀዋር በሌሉበት ጉዳዩ እንዲታይ ማዘዙን ተናግረዋል። የሕክምና ጉዳይ ክርክር ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የእነ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ፣ አቶ ሸምሰዲን ጠሃ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ በላንድ ማርክ የግል ሆስፒታል እንዲታከሙ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት መወሰኑ ትክክል እንዳልሆነ በመጥቀስ አቤቱታ አቅርቧል። "የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ የሕግ ክርክርን ያልተከተለ፣ የእኩልነትን መብትና ሕገ መንግሥቱን የተቃረነ፣ የፌደራል ማረሚያ ቤት የተመሰረተበትን አዋጅ የሚፃረር ነው" በማለት አቃቤ ሕጉ መከራከሪያ ማቅረባቸውን አቶ ሚልኪያስ ይናገራሉ። ጠበቆች በበኩላቸው "የታችኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ትክክል ነው። ጊዜው ያለፈበት ስለሆነም ዓቃቤ ሕግ አቤቱታ ማቅረብ አይችልም። ደንበኞቻችንም በግል ሀኪማቸው እና ራሳቸው በመረጡት የሕክምና ተቋም እንዲታከሙ ትዕዛዝ የተሰጠው በመስከረም 2013 ዓ.ም ነው ብለዋል። ስለዚህ ዓቃቤ ሕጉ በጊዜው አቤቱታ አላቀረበም በማለት የአቃቤ ሕጉ አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ መከራከራቸውን ይናገራሉ። ጀዋርን ጨምሮ የሌሎች 24 ተከሳሾች ጠበቆች ከሆኑት መካከል አንዱ አቶ ሚልኪያስ ቡልቻ፤ ዓቃቤ ሕግም ሆነ ግለሰብ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ አቤቱታ ካላቸው በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ማቅረብ እንዲችሉ ወይንም ደግሞ አቤቱታ ለማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው ማሳወቅ እንዳለባቸው ሕግ እንደሚያዝ ይናገራሉ። ከዚህም ውጪ ደንበኞቻቸው በተለያየ የግል ሕክምና ተቋም ሲታከሙ እንደቆዩ የተናገሩት አቶ ሚልኪያስ፤ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 21 ቁጥር 2 በሕግ ጥላ ስር የዋሉ ሰዎች በግል ሐኪም የመታከም መብት እንዳላቸው እንደሚገልጽ በመጥቀስ መከራከራቸውን ይናገራሉ። የሁለቱንም ወገን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመስጠት ለየካቲት 16፣ 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል። ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤቱ በግል ሃኪም ቤት እንዲታከሙ የወሰነላቸው ሲሆን፤ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በበኩሉ የፀጥታና ደህንንነት በተመለከተ ያለውን ሁኔታ አቅርቦ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም የካቲት 2፣ 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንዲወሰዱ ወስኖ ነበር። በወቅቱ ማረሚያ ቤቱ ታሳሪዎቹ የረሃብ አድማ ላይ በመሆናቸው "ታመው ከወደቁ ዝም ብለን ማየት ስለማንችል፣ ቀደም ብለው ስለማይነግሩንና በዛ አጭር ሰዓት ውስጥ እነሱ የፈለጉት ሆስፒታል ላይ ሃይል አሰባስበን ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ስለምንቸገር ድንገት ከወደቁ ግን ጦር ሃይሎች ሆስፒታል እንድናሳክም ይፈቀድልን" ብለው በማመልከታቸው ለጊዜው ፍርድ ቤቱ ይኼንን ፈቅዶላቸው እንደነበር ከጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሃመድ ጅማ ያስረዳሉ። ጠበቆቻቸው በበኩላቸው ሆስፒታሉን ከስምንት ሰዓት በፊት እንደጠየቁና ደንበኞቻቸው በመረጡት ሆስፒታል እንዲታከሙ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲያስተላልፍና ከዚህ ቀደም የነበረውን ውሳኔ እንዲያፀና ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም ሰኞ እለት የካቲት 8፣ 2013 ዓ.ም እነ አቶ በቀለ ገርባን የግል የጤና ተቋም በሆነውና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላንድ ማርክ ሆስፒታል እንዲታከሙ ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው። በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ አቶ በቀለ ገርባ በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ መንግሥታዊው የጤና ማዕከል ጦር ሃይሎች ሆስፒታል መወሰዳቸውን ሃኪማቸውና ጠበቃቸው ተናግረዋል። የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመተላለፍ አቶ በቀለ ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል በኃይል መወሰዳቸው "ከህግ አግባብ ውጭ ነው" ሲሉ ከአቶ በቀለ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሃመድ ጅማ ለቢቢሲ አስረድተዋል። እነ አቶ በቀለ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚሄዱ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነ ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። ከጥር 19፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ውሃ ምንም የማይቀምሱትና የረሃብ አድማ ላይ ናቸው የተባሉት እነ አቶ በቀለ ገርባ የጤና ሁኔታም አሳሳቢ ነው ተብሏል። እነ አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች መካከል ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር ወር ላይ መወሰኑ ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/56115854
amh
politics
የኬንያ ፖለቲከኞች ሕገ-መንግሥቱን ለማሻሻል ያደረጉት ጥረት በፍርድ ቤት ታገደ
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በገዢው መንግሥት ድጋፍ ያገኘውን የሕገ-መንግሥት ማሻሻል ሐሳብ ውድቅ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ የወሰነው ውሳኔ በፈረንጆቹ 2017 ኡሁሩ ኬንያታ ምርጫውን አላሸነፉም ብሎ ፍርድ ቤት ከሰጠው ፍርድ በኋላ ትልቁ ነው ተብሏል። ዳኛው በተለምዶ ቢቢአይ እየተባለ የሚጠራው የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ዕቅድ ሕገ-መንግሥታዊ አይደለም ሲሉ ብይናቸው ሰጥተዋል። ዳኛው አክለው ማሻሻያው ሕገ ወጥና ቅርፅ አልባ ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ዋነኛ ተቀናቃኛቸው የነበሩት የአሁኑ ጓደቸው ራይላ ኦዲንጋ ሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያው እውን እንዲሆን ደፋ ቀና ሲሉ ነበር የከረሙት። ሁለቱ መሪዎች ማሻሻያው ሕግ አውጪው የመንግሥት ክንፍ እንዲስፋፋና የሃገሪቱ ፖለቲካ የበለጠ አሳታፊ እንዲሆን ያስችላል ሲሉ ይሞግታሉ። ነገር ግን ተቺዎች ማሻሻያው የፖለቲካ ፓርቲዎች እርስ በርስ ለመጠቃቀም ያመቻመቹት ነው ሲሉ ይከራከራሉ። ነቃፊዎቹ አክለው ማሻሻያው የሕዝብ እንደራሴዎች ቁጥርን ከፍ ያደርገዋል፤ ይህ ደግሞ ዕዳ ውስጥ ተዘፍቃ ለምትገኘው ኬንያ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው ይላሉ። ቢቢአይ በተሰኘ ቅፅል ስሙ የሚታወቀው የማሻሻያ ሐሳብ ወደ ብሔራዊው ሸንጎና ሴኔት ተልኮ በአብላጫ ድምፅ አልፎ ነበር። ነገር ግን ወደ ፕሬዝደንቱ ጠረጴዛ ተልኮ የመጨረሻው ፊርማ ከማረፉ በፊት ነው ሐሙስ ዕለት በፍርድ ቤት የታገደው። ማሻሻያው ፀደቀ ማለት ኬንያዊያን በሚቀጥለው ዓመት ከሚደረገው ምርጫ በፊት ለሕዝበ ውሳኔ ድምፃቸውን ይሰጣሉ ማለት ነው። ዳኞች ምን አሉ? ለአራት ሰዓታት በቴሌቪዥን መስኮት ቀጥታ በተላለፈው ችሎት ዳኞቹ ፕሬዝደንት ኬንያታ የሃገሪቱን ሕገ-መንግሥት ጥሰዋል ብለዋል። አክለው ኡሁሩ የመሠረቱት የቢቢአይ ኮሚቴ ሕገ-ወጥ ነው፤ ፕሬዝደንቱ የተሰጣቸውን የመሪነት ሚና በአግባቡ አልተወጡም ብለዋል። ዳኞቹ፤ ፕሬዝደንቱን በግላቸው ሊከሷቸው እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። ፖለቲከኞቹ ማሻሻያውን ለማፅደቅ በሚል የሰበሰቡት 5 ሚሊዮን ድምፅ ይህንን ሐሳብ የዜጎች አያደርገውምም ብለዋል ዳኞቹ። የፍርደ ቤቱ ውሳኔ ፕሬዝደንቱን ከሥልጣናቸው ሊያስነሳቸው የሚችል ቢሆንም ነገር ግን የማሻሻያውን ሐሳብ በአብለጫ ድምፅ ያሳለፈው ፓርላማ ይሄን ያደርጋል ተብሎ አይጠበቅም። ቢቢአይ፤ ኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲኖራት፤ ቢያንስ 70 አውራጃዎችና 300 ተጨማሪ የፓርላማ መቀመጫዎች እንዲጨመሩ ሐሳብ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱ የማሻሻያ ሐሳቡን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ መንግሥት ይግባኝ ይጠይቃል ተብሎ ቢጠበቅም ሕግ አዋቂዎች ግን ውጤቱ ከዚህ የተሻለ ይሆናል ብለው አያምኑም።
https://www.bbc.com/amharic/news-57118311
amh
politics
ሱዳናውያን ተቃዋሚዎች ከግብፅ ጋር የሚያገናኘውን አውራ ጎዳና ከዘጉ ከሳምንት በላይ ሆነ
በሰሜናዊ ሱዳን ያሉ ተቃዋሚዎች ሱዳንን ከግብፅ ጋር የሚያገናኘውን አውራ ጎዳናን ከዘጉ ከሳምንት በላይ እንደሆናቸው ተዘገበ። ሱዳናውያኑ ተቃዋሚዎች ሁለቱን አገራት የሚያገናኘውን መንገድ በርካታ ቦታዎች ላይ በመዝጋታቸው ምክንያት ከሱዳን የቁም ከብቶችንና ሌሎች ሸቀጦችን የጫኑ የግብጽ የጭነት መኪኖች ድንበሩን ተሻግረው መሄድ አልቻሉም። አብዛኞቹ አርሶ አደር የሆኑት ተቃዋሚ ሰልፈኞች በመጀመሪያ ላይ አውራ ጎዳናውን የዘጉት መንግሥት የኤሌክትሪክ ዋጋ ላይ ጭማሪ ካደረገ በኋላ ውሳኔውን ለማስቀየር ነበር። ነገር ግን ተቃውሞው ቀስ በቀስ እየሰፋ በመሄድ በሱዳን ጦር ሠራዊቱ ያካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት ወደ መቃወምና የጦር ኃይሉን በሚደግፉ የአካባቢው የፖለቲካ ኃይሎች እና ግብፅ ላይ አነጣጥሮ ለቀናት ዘልቋል። ተቃዋሚዎቹ ሱዳንን ከሰሜናዊ ጎረቤቷ ግብፅ ጋር የሚያገናኛትን ዋነኛ መንገድ ከዘጉት አሁን ዘጠነኛ ቀኑ እንደሆነ ተዘግቧል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት ከካርቱም ተነስቶ አስከ ድንበር ከተማዋ ኢርጊን ድረስ ባለው የበረሃ መንገድ ላይ ማለፍ ያልቻሉ የግብፃውያን ከባድ ተሽከርካሪዎች ቆመዋል። በተመሳሳይ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ወደ ግብፅ በሚያመሩት ተሽከርካሪዎች ላይ ተቃውሞዎች እየተሰሙ ሲሆን መኪኖቹ ከሱዳን እንዳይወጡ እየቀሰቀሱ የሚገኙ ሰዎችም በርካታ ናቸው። በሰሜናዊው የሱዳን ክፍል ያሉ የዴሞክረሲ ለውጥ አቀንቃኞች ወደ ግብፅ የሚላኩት የቁም ከብቶችና ሌሎች የግብርና ምርቶች በሥልጣን ላይ ያለውን ወታደራዊ ኃይልና የሚያንቀሳቅሳቸውን ተቋማት የሚጠቅሙ በመሆናቸው ከአገር መውጣታቸውን አጥብቀው ይቃወማሉ። ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ወደ ከፋ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ የገባችው ሱዳን፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሥልጣን ላይ ያሉትን የጦር ኃይሉን መሪዎች የሚቃወሙ ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን እያስተናገደች ነው። በዋና ከተማ ካርቱምም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን ለሲቪሎች እንዲያስረክቡ የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች መካሄድ ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል። በዚህም ሳቢያ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ተቃዋሚ ሰልፈኞች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው የዶክተሮች ቡድን አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60227694
amh
politics
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ "ተገፍቶ መውጣቱን" ገለፀ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከሦስት ወራት በኋላ ይካሄዳል ከተባለው ምርጫ ከፍላጎቱ ውጪ በደረሱበት ጫናዎች ለመውጣት መገደዱን አስታወቀ። የፓርቲው ፀሐፊ የሆኑት አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ "ተገፍቶ ለመውጣት ተገድዷል" ብለዋል። ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲያወጣቸው በነበሩ መግለጫዎች የታሰሩ አመራሮቹ እንዲፈቱ፣ በኦሮሚያ የተለያዩ ስፍራዎች የተዘጉ ቢሮዎቻቸው እንዲከፈቱ፣ እንዲሁም ታማኝነት ያለው ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል አገራዊ ምክክር እንዲደረግ ጥሪ ሲያቀርብ ነበር። ኦፌኮ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ በተካሄዱ አገራዊ ምርጫዎች ላይ ተሳታፊ የነበረ ሲሆን ከምርጫ ውድድር እራሱን ሲያገል ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል። አቶ ጥሩነህ ገምታ ባለፈው ሳምንት ከምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች ጋር ፖለቲካ ፓርቲዎች የዕጩ ምዝገባን በተመለከተ በተደረገ ውይይት ላይ መሳተፋቸውን አስታውሰው፤ ኦፌኮ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ ዕጩ እያስመዘገበ እንዳልሆነ እና ማስመዝገብም እንደማይችል፣ ስለዚህም ምርጫው ላይ መሳተፍ እንደማይችል ለምርጫ ቦርድ አስታውቋል ብለዋል። በተጨማሪም የፖለቲካ ምኅዳር መጥበብ እና ምርጫው ላይ አገራዊ መግባባት አለመኖር ምርጫው ፍትሃዊ እና ተዓማኒነት እንዲኖረው እንደማያደርግ በስበሰባው ላይ መናገራቸው አስታወሰዋል። ሆኖም ግን ፓርቲያቸው ላነሳው ሃሳብም ሆነ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምንም ምላሽ አለማግኘታቸውን አቶ ጥሩነህ ተናግረዋል። በመሆኑም እነዚህ ጥያቄዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ ፓርቲው በምርጫው ላይ ለመሳተፍ እንደማይችል አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እስካሁን ድረስ ቢሮዎቻቸው በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ተዘግተው እንዳሉ የሚናገሩት አቶ ጥሩነህ፣ ከዋናው የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምርጫውን እንዲያስፈጽሙ ከተመደቡ አምስት ሰዎች አራቱ እስር ቤት መሆናቸውን ተናግረዋል። ስለዚህም "አፌን ሞልቼ መናገር የምችለው ከዚህ ምርጫ የወጣነው ተገፍተን እንደሆነ ሕዝባችንም ሆነ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሊያውቅልን እንደሚገባ ነው።" እስር ቤት ካሉ የኢፌኮ አመራሮች መካከል የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ እንዲሁም ባለፈው ዓመት ፓርቲውን የተቀላቀሉት አቶ ጃዋር መሐመድን እና ሐምዛ አዳነ (ቦረና) ይገኙበታል። "አንድ ፓርቲ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ቢያንስ ነጻ ሆኖ መንቀሳቀስ መቻል አለበት። እኛ ግን አሁንም አባላቶቻችን፣ በወረዳና በዞን ደረጃ ያሉ አመራሮች፣ እጩ ተወዳዳሪ እና ታዛቢ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች እስር ቤት ነው ያሉት። ስለዚህ እንሳተፍ እንኳ ብንል መሳተፍ አንችልም፤ ከምርጫው የመውጣት ውሳኔ ላይ የደረሰነው ተገደን ነው" ብለዋል። እነዚህ የምናነሳቸው ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ስንጠይቅ የቆየን ቢሆንም ባለፈው ሳምንት ግን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ካልተመለሱ ምርጫው ላይ ላለመሳተፍ ወስኗል ብለዋል። ከኦፌኮ በተጨማሪ በኦሮሚያ ካሉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የአመራሮቹ መታሰር እና የቢሮዎች መዘጋትን በማንሳት ምርጫው ላይ ለመሳተፍ እንደሚቸገር ከዚህ በፊት ለቢቢሲ መናገሩ ይታወሳል። በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ ኦፌኮ እስከ ትናነትናው ዕለት ድረስ ምንም ዓይነት ዕጩ እንዳላስመዘገበ ለቢቢሲ አረጋግጧል። አቶ ጥሩነህም የዕጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቅ መሆኑን ጠቅሰው ያነሷቸው ጥያቄዎች፤ የፓርቲ አመራሮቻቸው መፈታትን ጨምሮ ምላሸ የሚያገኙ ከሆነ እና የዕጩ ምዝገባ ጊዜ የሚራዘም ከሆነ ድርጅቱ አሁንም በምርጫው ውስጥ ለመቆየት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል። አቶ ጥሩነህ ከዚህ ቀደም የኦነግም ሆነ የኦፌኮ አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ተገናኝተው በጉዳዩ ላይ እንደተወያዩ ተናግረው ከዚህ ውይይት በኋላ ግን ምንም ዓይነት ለውጥ አለማየታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ከምርጫ ቦርድም ሆነ ከመንግሥት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም። በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱና ዋነኛ ከሚባሉት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አንዱ ዮነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፤ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ይመራ በነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) እና በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሚመራው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦሕኮ) መካከል በሐምሌ 2004 ዓ.ም በተደረገ ውህደት የተመሰረተ ድርጅት ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-56277294
amh
politics
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢው ፕ/ር መስፍን አርአያ ማን ናቸው?
ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የቀረቡ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮችን ሲያጸድቅ፣ ፕ/ር መስፍን አርአያ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል። ከአስራ አንዱ ኮሚሽነሮች መካከል በሰብሳቢነት ፕ/ር መስፍን ሲሾሙ፣ ወይዘሮ ሒሩት ገብረሥላሴ ደግሞ የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ ሆነዋል። ለመሆኑ ፕ/ር መስፍን አርአያ ማናቸው? እስካሁንስ በሙያቸው ምን አበርክተዋል? ፕ/ር መስፍን ከሩሲያ ትምህርት ቤት እስከ ኢትዮጵያ ሆስፒታሎች የተወለዱት በአዲስ አበባ ከተማ ነሐሴ 1946 ዓ. ም. ነው። በ1972 ዓ. ም. ከሩሲያው ቅዱስ ፒተርስበርግ የሕክምና ትምህርት ቤት በሕክምና የዶክትሬት ዲግሪ (MD) አግኝተዋል። ከዚያም በ1982 ዓ. ም. ኔዘርላንድስ ከሚገኘው ግሮኒንገን ዩኒቨርሲቲ በአእምሮ ሕክምና ስፔሻሊቲ ዲፕሎማ (DPM) ተቀብለዋል፡፡ በተጨማሪም በ2000 ዓ. ም. ስዊድን ከሚገኘው ኡሜዮ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ኦፍ ፊሎሶፊ ዲግሪ (PhD) አግኝተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች እንዲሁም የሕክምና ተቋሞች ለዓመታት አገልግለዋል። ከእነዚህም መካከል ከ1974-75 ዓ. ም. በትግራይ፣ አዲግራት ከተማ በራስ ስብሐት ሆስፒታል በጠቅላላ ሐኪምና የሕክምና ዳይሬክተርነት እንዲሁም ደሴ በሚገኘው ደሴ ሆስፒታል ከ1975-76 ዓ. ም. በጠቅላላ ሐኪምና የሕክምና ዳይሬክተርነት ማገልገላቸው ይጠቀሳል። ከ1976-79 ዓ. ም. በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ በጠቅላላ ሐኪምና የሕክምና ዳይሬክተርነት ሠርተዋል። ከ1982 እስከ 1987 ዓ. ም. ደግሞ በዚያው ሆስፒታል በአእምሮ ሐኪምነት አገልግለዋል። ፕ/ር መስፍን፣ ከ1987 አንስቶ ለዓመታት በዘውዲቱና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች በአእምሮ ሐኪምና መምህርነት ሠርተዋል። ከ1997 ዓ. ም. ጀምሮ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም መምህር ሆነው አገልግለዋል። ከ2001-2003 ዓ. ም. የቅዱስ ጳውሎስ የሕክምና ትምህርት ቤት ዲን እንዲሁም ከ2003-2006 ዓ. ም. የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ ከፍተኛ የትምህርት አመራር ሆነዋል። የፕ/ር መስፍን ተሳትፎና አበርክቶ ፕ/ር መስፍን በተለይም በጤናው ዘርፍ በርካታ ማኅበራትን በመመሥረት፣ በአባልነት በማገልገልና እና በመምራትም ይታወቃሉ። ለአብነት የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ጤና አጠባባቅ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ የአእምሮ ሕክምና ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይጠቀሳሉ። የብሔራዊ ኤችአይቪ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት አደራጅ ግብረ ኃይል አባል፣ የብሔራዊ ኤችአይቪ መከላከልና መቆጣጠር ምክር ቤት መሥራችና አባል በተጨማሪም የተስፋ ጎሕ ቫይረሱ በደማቸው ያለ ወገኖች ማኅበር የአማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሠርተዋል። ፕ/ር መስፍን የብሔራዊ ይቅርታ ቦርድ አባል፣ የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ጆርናል ዋና አዘጋጅ፣ የመድኃኒትና ሕክምና አቅራቢ ድርጅት (ፋርሚድ) የቦርድ ሰብሳቢ፣ የአእምሮ ጤና ክብካቤ ማኅበር በኢትዮጵያ የቦርድ አባልም ናቸው። በተጨማሪም የፌዴራል ሆስፒታሎች አመራር ቦርድ አባል፣ የአማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራር ቦርድ አባል እንዲሁም የመድኃኒትና ምግብ ቁጥጥርና አስተዳደር የአማካሪ ቦርድ አባል ሆነው ሠርተዋል። ወደ 30 በሚጠጉ ታዋቂ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የሕክምና መጽሔቶች ጽሑፎቻቸውን አሳትመዋል። ፕ/ር መስፍን ያገኟቸው ሽልማቶች ፕ/ር መስፍን ከአገራዊው የበጎ ሰው ሽልማት አንስቶ በአገር ውስጥና በውጭ አገራትም የተለያዩ የዕውቅና ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል። የበጎ ሰው ሽልማት መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ነበር የሸለማቸው። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ላከናወኗቸው የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች ከአሜሪካው ቴዎዶርና ቫዳ ስታንሊ ፋውንዴሽን ሽልማት አግኝተዋል። ፒፕል ቱ ፒፐል፣ የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር፣ ተስፋ ጎህ ቫይረሱ በደማቸው ያለ ወገኖች ማኅበር፣ ፋርሚድ እና ራድዮ ፋናም ለአበርክቷቸው እውቅና ሰጥተዋል። በተጨማሪም በ1998 ዓ.ም. የአእምሮ ጤናን ለማሻሻል ባበረከቱት አስተዋጽኦ የሮበርት ጊል የወርቅ ሜዳሊያን አግኝተዋል። የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር በ2003 ዓ. ም. ለተምሳሌታዊ የሕክምና አገልግሎት የወርቅ ሜዳሊያ ሰጥቷቸዋል። በ2006 ዓ. ም. የጤና ሚኒስቴር ለረዥም ጊዜ ተምሳሌታዊ የጤና አገልግሎት የወርቅ ሜዳሊያ አበርክቶላቸዋል። በተጨማሪም የምግብና መድኃኒት ቁጥጥርና አስተዳደር ለዓመታት የጤናው ዘርፍ አገልግሎታቸው በ2006 ዓ. ም. የወርቅ ዋንጫ ሰጥቷቸዋል። የበጎ ሰው ሽልማት መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ነበር የሸለማቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-60465012
amh
politics
ኢትዮጵያ አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያግዝ የምክክር ኮሚሸን ልታቋቁም ነው
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሸን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ረቂቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት አስታወቀ። ሚኒስትሮች ምክር ቤት አርብ ታኅሣሥ 1 ቀን 2014 ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው ብልጽግና ፓርቲ ምርጫ አሸንፎ መንግሥት ሲመሰርት ለማከናወን ከወሰናቸው ተግባራት መካከል ኮሚሽኑን ማቋቋም እንደሚገኝበት ገልጿል። በዚህም "ሁሉን አካታች የሆነ አገራዊ ምክክርና ውይይት በማካሄድ አገራዊ መግባባት እና በአገር ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲኖር የሚያስችሉ ሥራዎችን መስራት አንዱ መሆኑ ይታወቃል" ይላል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የወጣው መግለጫ። መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በተለያየ ጎራ የተሰለፉ ፖለቲከኞች እና ሕዝቡ ተቀራራቢ እና አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ተቀባይነት ያለው ተቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ መሠረትም የሚንስትሮች ምክር ቤት 'የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን' ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ቀርቦ ተቀባይነት በማግኘቱ ረቂቅ አዋጁ በቀጣይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸደቀ ተፈጻሚነት ይኖረዋል። ሐሙስ ዕለት ኅዳር 30/2014 ዓ.ም. የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውይይት ባደረገበት ወቅት በኢትዮጵያ የፖለቲካ የሽግግር ሂደት ተወያይቶ እንደነበረ የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። አደም ፋራህ ፓርቲው በውይይቱ አስፈላጊ ነው ያለው አገራዊው ምክክር ስኬታማ እንዲሆነ ገለልተኛ እና ብቃት ባለው ተቋም መመራት እንዳለበት ሥራ አስፈጻሚው አምኖበታል ስለማለታቸው ፋና ዘግቧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59594069
amh
politics
በኢትዮጵያ፣ በዩክሬን እና በሌሎችም አገራት የቱርክ ድሮኖች የጦርነት ቅርጽን እንዴት ቀየሩ?
በመላው ዓለም ያሉ ወታደራዊ ግጭቶች በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) አማካይነት አካሄዳቸውን እየለወጡ ነው። ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት አንስቶ የተለያዩ አገራት ግጭቶች በሰው አልባ አውሮፕላን ምክንያት የኃይል ሚዛን ለውጥ ታይቶባቸዋል። ከሰሞኑ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በተከሰተው ውጥረትም የድሮን ሚና ቀላል አይደለም። ከእነዚህ ሁለት አገራት በስተ ደቡብ የምትገኘው ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላን ምርት ስሟ በተደጋጋሚ ይነሳል። ዩክሬን ራሷን ከሩስያ የምትከላከለው በቱርክ ሠራሽ ድሮኖች ሊሆን ይችላል። በእርግጥ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ከሞላ ጎደል የቱርክ ድሮኖችን ማግኘት እየተለመደ መጥቷል። ቱርክ በድሮን ምርት ምን ያህል ገናና ናት? ቱርክ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) አባል ናት። በምዕራባውያኑ ወታደራዊ ስብስብ ኔቶ ውስጥ ያለች ብቸኛው ሙስሊም አገር ናት ቱርክ። በቱርክ የሚኖሩት ገለልተኛ ወታደራዊ ተንታኝ አርዳ ሜቭሉቶግሉ "የአንካራው መንግሥት ላለፉት 20 ዓመታት አስተማማኝ የድሮን ኃይል አዘጋጅቷል" ይላሉ። ቱርክ ሰው አልባ አውሮፕላኖቿን የአገር ውስጥ ደኅንነት ለማስጠበቅና ከድንበሯ በዘለለም ጥቅም ላይ እንዳዋለችው ይናገራሉ። እአአ ከ1990ዎቹ አጋማሽ ወዲህ የኩርድ ተገንጣይ ታጣቂዎች ላይ የደረሰው ጥቃት በዋነኛነት ይጠቀሳል። የቱርክ መከላከያ አቅም ግንባታ ዋነኛ ትኩረት የሚሰጠው ለድሮን እንደሆነ ተንታኙ ያስረዳሉ። "በምርት ጥራትና ብዛት ድሮን ቅድሚያ ይሰጠዋል። ቱርክ በቀጠናው በአስተማማኝ አቋም በመገንባት ከእስራኤል ውጭ የሚበልጣት" ይላሉ ቱርክ ውስጥ ሰው አልባ በራሪ መሣሪያዎች ወይም በእንግሊዘኛው unmanned aerial vehicles (UAVs) የሚያመርቱ ሁለት ግዙፍ ፋብሪካዎች አሉ። ባይካር መከላከያ የተባለው ፋብሪካ ባይራክታር ቲቢ2 (Bayraktar TB2) እና ባይራክታር አኪንቺ (Bayraktar Akinci) ድሮኖች ያመርታል። የፋብሪካው ዋና የቴክኒክ ኃላፊ ሴልሁክ ባይራክታር የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ልጅ ባል ነው። ሌላው ግዙፍ ድሮን አምራች ተርኪሽ ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪስ ሲሆን፤ ታይ አንካ (TAI Anka) እና ታይ አኩሱንገር (TAI Aksungur) የተባሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ያመርታል። የወታደራዊ ጉዳዮች ተንታኙ አርዳ ሜቭሉቶግሉ እንደሚሉት፤ የቱርክ መከላከያ እና ደኅንነት ተቋሞች ከእነዚህ ድሮኖች 150 የሚሆኑትን ያበራሉ። ይህም ከአነስተኛ የስለላ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ካሚካዚ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በተጨማሪ ነው። ቱርክ እና ዩክሬንን ምን አገናኛቸው? እአአ በ2019 ቱርክ ለዩክሬን ብዙ ባይራክታር ቲቢ2 ድሮኖች ሸጣላታለች። ዩክሬን ከቱርክ ጎን ኔቶን መቀላቀል ትፈልጋለች። ዩክሬን ሩሲያ ከምትደግፋቸውና በምሥራቃዊ ክፍል ከሚንቀሳቀሱ አማጺያን ጋር ትግል ገጥማለች። ከሩሲያ ሊሰነዘር የሚችል ጥቃትም ያሰጋታል። ሩሲያ በዩክሬን ድንበር ወታደሮቿን በተጠንቀቅ አሰልፋ ትገኛለች። ያለፈው የካቲት ኤርዶዋን ወደ ዩክሬን አቅንተው በሁለቱ አገራት መካከል ተጨማሪ የድሮን ግብይት የሚፈቅድ ስምምነት ፈርመዋል። የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስተር ስምምነቱ የቱርክ ድሮን አምራቾች ዩክሬን ውስጥ እንዲሠሩ መንገድ የሚከፍት እንደሆነ ለሮይተርስ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ያሳለፍነው ጥቅምት ዩክሬን የቱርክን ድሮን ተጠቅማ ሩሲያ የምትደግፋቸው ተገንጣዮች ይገለገሉበት የነበረ ዲ30 የአየር መሣሪያን ማውደሟን አስታውቋለች። ሩሲያ ይህንን ተከትሎ ቱርክ የምትሸጣቸው ድሮኖች ቀጠናውን "ሰላም እየነሱ" እንደሆነ ኮንናለች። በሌላ በኩል ደግሞ ቱርክ ሩሲያ እና ዩክሬንን ላሸማግላችሁ ብላለች። ሽምግልናው ከድሮን ሽያጭ ጋር መጋጨቱ ግን አይቀርም። የሶርያ ጦርነት ከተነሳ ወዲህ የቱርክ እና የሩሲያ ግንኙነት ውጥረት የነገሠበት ነው። ሁለቱ አገሮች ሶርያ ውስጥ የተለያየ ፍላጎት ቢኖራቸውም ለመስማማትም ፍላጎት አሳይተዋል። ቱርክ ኤስ400 (S-400) የተባለ የአየር መከላከያ ከሩሲያ መግዛቷ የወዳጅነት መጀመሪያ ተደርጎ ተወስዷል። የመሣሪያ ግዢውን ኔቶ እና አሜሪካ ተችተውታል። ዩክሬን ስንት ባይራክታር ቲቢ2 እንዳላት በውል አይታወቅም። ነገር ግን ድሮኖቹ በዶንባስ ቀጠና ያሉትን አማጽያን ለመዋጋት እንደሚረዳት ይታመናል። እነዚህ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ዘመነኛ ካሜራ፣ ከተቆጣጣሪ ሥርዓት ጋር የሚያስተሳስር መሣሪያ እንዲሁም ኢላማ አስተካካይ ቁልፍ ተገጥሞላቸዋል። ይህም ኢላማን አስተካክሎ ፈንጂ ለመጣል ያስችላቸዋል። ወታደራዊ ተንታኙ አርዳ ሜቭሉቶግሉ እንደሚሉት፤ እነዚህ ድሮኖች ተንቀሳቃሽ ቡድንን ኢላማ ለማድረግ ይመረጣሉ። "ሆኖም የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል በብዛትም በቴክኖሎጂ ረቂቅነትም ከዩክሬን ይልቃል" ይላሉ። የቱርክን ድሮኖች የሚጠቀሙት የትኞቹ አገራት ናቸው? ቱርክ ሠራሽ ድሮኖች የሚገዙ አገራት ቁጥር እየናረ መጥቷል። የአገሪቱ የኤክስፖርት ዝርዝር ምን ያህል ድሮን እንደሚሸጥ አይጠቁምም። ነገር ግን ከ15 አገራት በላይ ቱርክ ሠራሾቹን ባይራክታር እና ታይ ድሮኖች እንዳዘዙ ይታወቃል። ባይራክታር ቲቢ2 ድሮኖች በሶሪያ፣ ሊቢያ እና በናጎርኖ-ካራባግህ (በአርሜኒያ እና በአዘርባጃን መካከል ለ44 ቀናት ውጊያ የተካሄደበት) ጦርነቶች ውጤታማ ከሆኑ በኋላ ፈላጊያቸው ተበራክቷል። በዚህ ጦርነት የአዚሪ ኃይሎች የአርሜኒያን ወታደሮች፣ የውጊያ ተሽከርካሪዎች እና የአየር ኃይል የመቱት በቱርክ ሠራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ነው። ይህም አወዛጋቢው ግዛት በእጃቸው እንዲገባ አግዟቸዋል። አምና የፖላንድ መከላከያ ሚኒስትር ከቱርክ 24 ተዋጊ ድሮኖች እንደሚገዙ አስታውቀዋል። ግዢው ፖላንድን ከኔቶ አባል አገራት የመጀመሪያዋ ያደርጋታል። ለቱርክ አፍሪካም ትልቅ ገበያዋ ናት። በቱርክ የሚኖሩት ገለልተኛ ወታደራዊ ተንታኝ አርዳ ሜቭሉቶግሉ "በአፍሪካ ገበያ የቻይና አምራቾች ዋነኛ ተቀናቃኝ ቱርክ ነች። የቱርክ ርካሽ ድሮኖች የኔቶን የጥራት ልኬት የጠበቁም ናቸው" ይላሉ። የቱርክን ድሮኖች ከገዙ መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ሩዋንዳ እና ናይጄርያም ይጠቀሳሉ። ቱርክ እና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል። ሆኖም ስለ ድሮን ግብይት በግልጽ ይፋ አልተደረገም። አምና የቱርክ ኤክስፖርት ሪፖርት የበረራ ዘርፍ ከፍተኛ እድገት እንዳሳየ ይጠቁማል። ያሳለፍነው ጥቅምት ላይ አሜሪካ፤ ቱርክ ለኢትዮጵያ ድሮን እየሸጠች መሆኑ እንዳሳሰባት ተናግራለች። ወጣም ወረደ ቱርክ ለምታመርታቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖች አዲስ ገበያ ከማፈላለግ የምትቦዝን አይመስልም። ወታደራዊ ጉዳዮች ተንታኙ "የድሮን ሽያጭ ዘላቂነት ያለው ወታደራዊ የንግድ ትስስር እንዲፈጠር ያስችላሉ። ይህም ቱርክ ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጫና እንድትፈጥር ያግዛታል" ይላሉ። አፍሪካ ውስጥ ያለውን የገበያ ፍላጎት ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ጠንቅቀው ተገንዝበዋል። ጥቅምት ላይ "አፍሪካ ውስጥ የትም አገር ስሄድ የምጠየቀው ስለ ሰው አልባ አውሮፕላን ነው" ብለው መናገራቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60358589
amh
politics
ትግራይ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በትግራይ ረሃብ አሉ የሚሉ ሪፖርቶችን አስተባበሉ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጦርነት በተጎዳችው ትግራይ ክልል ውስጥ ረሃብ አለ የሚሉ ሪፖርቶችን አስተባበሉ። አገሪቱ ብሔራዊ ምርጫዋን ባደረገችበት በትናንትናው ዕለት በምርጫ ጣቢያ ላይ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ችግር መኖሩን አምነው ይህ ግን መንግሥት የሚፈታው ነው ብለዋል። ስምንተኛ ወሩን ያስቆጠረው የትግራይ ጦርነት አምስት ሚሊዮን የክልሉን ነዋሪዎች የምግብ እርዳታ ፈላጊ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ያስረዳል። ከ350 ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎች ደግሞ በረሃብ ቋፍ ላይ መሆናቸውን በቅርቡ የወጣ ተባበሩት መንግሥታት ግምገማ ሪፖርት ያሳያል። "በትግራይ ረሃብ የለም" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ድምፃቸውን በትውልድ ስፍራቸው ከሰጡ በኋላ ለቢቢሲዋ ካትሪን ባያሩሃንጋ ተናግረዋል። "ችግር አለ ነገር ግን መንግሥት ይህንንም መቅረፍ ይችላል" በማለት አክለዋል። ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በፀጥታው ምክር ቤት ዝግ ስብሰባ ላይ በትግራይ ረሃብ አለ ብለው ነበር። ኃላፊው በትግራይ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጎን ተሰልፎ እየተዋጋ ያለው የኤርትራ ሠራዊት ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅሞበታል ብለዋል። ኤርትራ ይሄንን ውንጀላ አትቀበለውም። በዚሁ ወቅትም ስለ ኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መቼ እንደሚወጡ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ የኤርትራ ወታደሮችን ገፍታ እንደማታስወጣና ሁኔታውንም በሰላም ለማጠናቀቅ ከኤርትራ ጋር እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። ከአስር ቀናት በፊት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ የወጣ ኢንተግሬትድ ፉድ ሴኩሪቲ ፌዝ ክላሲፊኬሽን የተባለ ግምገማ መሰረት 350 ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎች "ካታስትሮፍ" በሚባል ሁኔታ በረሃብ ቋፍ ላይ እንደሚገኙ አትቷል። በወቅቱም የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ረሃብ የለም እንዲሁም እርዳታ እየተዳረሰ ነው ብለዋል። ይሄው ግምገማ ተጨማሪ አምስት ሚሊዮን የሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች በቀውስ ላይ ወይም አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በበኩላቸው ምግብ እያዳረሱ እንደሆነና የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች እንዳይገቡ ከልክለዋል የሚለውንም ሪፖርቶች ተቀባይነት የለውም ብለዋል። "ምንም የምንበላውነገር የለም" በምዕራብ ትግራይ ቃፍታ ሁመራ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለቢቢሲ በቅርቡ እንደተናገሩት መራባቸውን ነው። "ምንም የምንበላው ነገር የለንም" በማለት አንድ ግለሰብ በስልክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይኸው ግለሰብ ለወራት በዘለቀው ጦርነት እህላቸው እንዲሁም ከብቶቻቸው እንደተዘረፈ ነው። ጥቅምት 24 የተጀመረው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉን ነዋሪዎች አፈናቅሏል፤ የእርሻ ተግባሩንም አስተጓጉሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ የክልሉ አስተዳዳሪ የነበረውን ህወሓትን ከስልጣን ለማስወገድ ወታደራዊ ዘመቻ ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሚያደርጓቸው የፖለቲካ ማሻሻያዎች ጋር ተያይዞ ከህወሓት ጋር ያለው ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ የሻከረ ሲሆን ግጭቱንም ያቀጣጠለው የህወሓት የፌደራል መከላከያ ዕዝን መቆጣጠሩን ተከትሎ ነው። "የሱዳን ወታደሮችም በኢትዮጵያ አሉ" በዚሀ ጦርነት ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ተባብራለች። የኤርትራ ሠራዊት ድንበሩን አቋርጦ በመግባት የሰብዓዊ ጥሰት ፈፅመዋል ተብለው ይወነጀላሉ። ከዚህም ውስጥ የምግብ ዕጥረት እንዲፈጠር ሆን ብለው እየሰሩ ነው የሚል ሲሆን ኤርትራ ግን ይህንን አስተባብላለች። በግጭቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የኢትዮጵያ ወታደሮችም ሆነ ሌሎች አካላት ጥሰቶችን በመፈፀም ተወንጅለዋል። መጋቢት ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኤርትራ ወታደሮች ይወጣሉ ቢሉም ቀኑን አልጠቀሱም። በቅርቡም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃለ አቀባይ በበኩላቸው መከላከያ ሚኒስትርን ዋቢ አድርገው የኤርትራ ሠራዊት ለቀው እየወጡ ነው ብለው ነበር። "ገፍተን አናስወጣቸውም በሰላም ነው እንዲወጡ የምንፈልገው። ይሄም እርግጠኛ ነኝ ይሆናል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለቢቢሲ። "ከኤርትራ ጋር ጉዳዩን በሰላም ለመቋጨት አብረን እየሰራን ነው" በማለትም አክለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሱዳን ወታደሮችም በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንዳሉም ተናግረዋል። የሱዳን ወታደሮች ሁለቱም አገራት ግዛቴ ነው የሚሉት የአል ፋሽጋ ትሪያንግልን መቆጣጠራቸው ይታወሳል። ከሦስት ዓመት በፊት ወደ ስልጣን የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በብልጽግና ስም ሲወዳደሩ የመጀመሪያቸው ነው። በስልጣን ማግስት ያሳዩት የለውጥ መንፈስ አገሪቱ ዲሞከራሲያዊና ክፍት እንድትሆን ማድረጋቸው በአገሪቱ ባሉ በርካታ ዜጎች ድጋፍን አስገኝቶላቸው ነበር። ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠውበት የነበረውን የኤርትራና የኢትዮጵያን የድንበር ፍጥጫ መቋጨታቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት የኖቤል ተሸላሚ ሆነዋል። ነገር ግን በትግራይ ያለው ጦርነት ይህንን ምስላቸውን አጠልሽቶታል። በክልሉም ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ምርጫ አይካሄድም።
https://www.bbc.com/amharic/news-57564194
amh
politics
መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙ ሱዳናውያን በአደባባይ ድምጻቸውን ማሰማት ቀጥለዋል
የሱዳን ጦር ኃይል መፈንቅለ መንግሥት ማካሄዱን ተከትሎ የአገሪቱ ዜጎች ለሁለተኛ ቀን አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል። በመዲናዋ ካርቱም እንዲሁም በሌሎችም ከተሞች መንገድ ዘግተው የሱዳንን ሰንደቅ አላማ እያውለበለቡ ተቃውሟቸውን ገፍተውበታል። መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም ለሁለተኛ ቀን አደባባይ ከወጡት ዜጎች መካከል ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መጎዳታቸው ተዘግቧል። ፖሊሶች በተቃዋሚዎች ላይ እንደተኮሱ እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል ተሰማርቶ ካርቱምን ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ድልድዮች እንደተዘጉም ተገልጿል። የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን የሲቪል አመራሩን በትነው፣ አመራሮቹን በቁጥጥር ስር አውለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገጉት ትናንት ነበር። የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ በሱዳን ጉዳይ ላይ እንደሚመክር የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። ጄነራል ቡርሐን ፖለቲካዊ ስምምነት ባለመኖሩ ምክንያት መፈንቅለ መንግሥቱ እንደተካሄደ ተናግረዋል። ወታደሮች ካርቱም ውስጥ ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ የሕዝባዊ ተቃውሞ መሪዎችን እያሰሩ ይገኛሉ። የካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከመዘጋቱም ባሻገር አብዛኛው የስልክ መስመር እና ኢንተርኔት ተቋርጧል። የሱዳን ብሔራዊ ባንክ ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ እንደመቱ የተዘገበ ሲሆን፤ የጤና ባለሙያዎች በወታደራዊ ኃይሉ በሚመሩ ሆስፒታሎች ውስጥ አገልግሎት አንሰጥም ማለታቸውም ተሰምቷል። እአአ በ2019 የቀድሞው መሪ ኦማር አልበሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ በሲቪል የሚመራው እና ወታደራዊው የሽግግር አስተዳደር መካከል እምብዛም ስምምነት አልነበረም። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ወታደራዊ ኃይሉ የወሰደውን እርምጃ "የሱዳንን ሰላማዊ አብዮት የከዳ" ሲሉ ገልጸውታል። አሜሪካ 700 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ለሱዳን ላለመስጠት ወስናለች። ትናንት ለሊቱን በሙሉ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ሱዳናውያን ዛሬም የሲቪል አመራሩ እንዲመለስ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። "ሕዝቡ የሚፈልገው የሲቪል አመራር ነው" "ወታራዊ አስተዳደር አንፈልግም" ሲሉ መፈክር አሰምተዋል። ከተቃዋሚዎቹ መካከል በርካታ ሴቶችም ይገኙበታል። ፖሊሶች ተቃዋሚዎች ላይ ቢተኩሱም እንኳን ሕዝቡ ድምጹን ማሰማቱን ቀጥሏል። አንድ ጉዳት የደረሰበት ተቃዋሚ ለሮይተርስ የዜና ወኪል በወታደራዊው አስተዳደር ጽህፈት ቤት አቅራቢያ በወታደሮች እግሩን በጥይት መመታቱን ገልጸዋል። ወታደሮች መጀመሪያ ላይ የፕላስቲክ ጥይት ቆየት ብለው ግን እውነተኛ ጥይት መተኮስ እንደጀመሩ ሌላ ተቃዋሚ ተናግሯል። አልታይብ ሞሐመድ አሕመድ የተባለ ግለሰብ "ሁለት ሰዎች ሞተው አይቻለሁ" ብሏል። የሱዳን የሐኪሞች ማኅበር እና የማስታወቂያ ሚንስቴር ከወታደራዊ አስተዳደር ዋና መቀመጫው ቅጥር ጊቢ ውጪ ተኩስ እንደነበር በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል። ከሆስፒታሎች የወጡ ምስሎች ሰዎች የተለያየ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው እና ልብሳቸው በደም ተነክሮ ያሳያሉ። የአፍሪካ ሕብረት፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የተባበሩት መንግሥታት የሲቪል አመራሮች ከቁም እስር እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክን ጨምሮ እነዚህ በቁም እስር ላይ ያሉት አመራሮች አሁን ላይ የት እንደታሰሩ አይታወቅም። ሐምዶክ መፈንቅለ መንግሥቱን ለመደገፍ ባለመስማማታቸው ትላንት ከመኖሪያ ቤታቸው ጦር ኃይሉ ልዩ ኃይል መወሰዳቸው ይታወሳል። እአአ 2019 ላይ በወታደራዊው እና በሲቪሉ አመራር መካከል የተደረሰው ስምምነት ሱዳንን ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማሸጋገር ያለመ ነበር። ነገር ግን የአመራሮች አለመስማማት እና የመፈንቅለ መንግሠት ሙከራን ጨምሮ ብዙ መሰናክሎች ገጥመውታል። የሽግግር ወቅት ሥልጣን የመጋራት ሉአላዊ ምክር ቤትን ይመሩ የነበሩት የአሁኑ የመፈንቅለ መንግሥት መሪ ጄነራል ቡርሐን ናቸው። ሱዳንን ወደ ሲቪል አመራር ለማሸጋገር ቁርጠኛ እንደሆኑ ሲናገሩም ተደምጠዋል። በሱዳን እአአ በሐምሌ 2023 ምርጫ ይደረጋል ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59052195
amh
sports
የአምናው ሻምፒዮና ሲሳይን ጨምሮ ቀነኒሳ ስለሚሳተፉበት የለንደን ማራቶን በጥቂቱ
በአለም ላይ ከሚጠበቁ የአትሌቲክስ ዝግጅቶች አንዱ የሆነው የለንደን ማራቶን በዛሬው ዕለት መስከረም 22፣ 2015 ዓ.ም እየተካሄደ ነው። አምና አንደኛ በመውጣት ሻምፒዮና የነበረው ሲሳይ ለማን ጨምሮ በአትሌቲክስ ዘርፉ ስመ ጥር የሆነው ቀነኒሳ በቀለ ኢትዮጵያን ወክለው ለ42ኛ ጊዜ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን ይወዳደራሉ። በሴቶች የማራቶን ውድድር ደግሞ በማራቶን ሁለተኛ ፈጣን ሰዓት ያላት ያለምዘርፍ የኋላው ኢትዮጵያን ወክላለች። በዛሬው ዕለት ወደ 42 ሺህ የሚጠጉ ሯጮች ከግሪንዊች አስከ ዘ ሞል ድረስ ድረስ ያለውን 42 ኪሎሜትር በመሸፈን ይሮጣሉ። በዚያውም ሚሊዮን ፓውንዶችን ለእርዳታ ያሰባስባሉ። የዘንድሮው የማራቶን ውድድር በአውሮፓውያኑ ጥቅምት ወር የሚካሄደው ሶስተኛው እና የመጨረሻው ነው። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በጥቅምት ወር እንዲካሄድ ቢደረግም በሚቀጥለው ዓመት በአውሮፓውያኑ 2023 ወደተለመደው የጸደይ ወቅት ይመለሳል። ስለ 2022 የለንደን ማራቶን በጥቂቱ የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሞ ፋራህ በዘንድሮው የማራቶን ውድድር ተስፋ ከተጣለባቸው አንዱ አትሌት መሆኑ ይዘገብ የነበረ ቢሆንም በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ባጋጠመው የዳሌ ጉዳት ምክንያት ራሱን አግልሏል። የሴቶች የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤትና በለንደን ማራቶን ሁለት ጊዘተ አሸናፊ ብሪጊድ ኮስጌይ ከውድድሩ ራሷን ለማግለል ተገዳለች። ባለፈው ሳምንት በርሊን ላይ በራሱ ተይዞ የነበረውን የወንዶች ማራቶን የአለም ክብረ ወሰን የሰበረው ኢሊዩድ ኪፕቾጌ በዚህ ውድድር ባይሳተፍም ቅዳሜ በነበረው ሚኒ ማራቶን ውድድር ለአሸናፊዎች ሜዳሊያ ለማበርከት ለንደን ይገኛል። ኪፕቾጌ በሌለበርት የአምናው የለንደን ማራቶን ሻምፒዮና ሲሳይ ለማ እና ሌላኛው ስመ ጥር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በወንዶች የማራቶን ሻምፒዮናነት ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው መካከል ናቸው። ሲሳይ ለማ የአምናውን የለንደን ማራቶን ያሸነፈው 2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ 01 ሴኮንዶች በመግባት ነበር። በማራቶን ታሪክ ሶስተኛው ፈጣን ሰአት ያለው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ብርሃኑ ለገሰ ዛሬ በለንደን ጎዳናዎች እየሮጠ ይገኛል። ብርሃኑ በአውሮፓውያኑ 2019 በነበረው የበርሊን ማራቶን 2፡02፡48 በሆነ ሰዓት ቀነኒሳ በቀለን በመከተል ሁለተኛ መውጣቱ ይታወሳል። በዚህ ውድድር ላይ ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የአምናው የለንደን ማራቶን አሸናፊ ሲሳይ ለማ ነበር። የሴቶች የማራቶን ወድድር ያለፈው አመት ሻምፒዮና ጆይሲሊን ጄፕኮስጌ እንዲሁም በማራቶን ሁለተኛ ፈጣን ሰዓት ያላት ኢትዮጵያዊቷ ያለምዘርፍ የኋላው በውድድሩ ስፍራ ተሰጥቷቸዋል። የሁለቱም የወንዶች እና የሴቶች ውድድር አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው 55 ሺህ ዶላር የሚሸለሙ ሲሆን በዊልቸር ለሚወዳደሩ 35 ሺህ ዶላር ሽልማት ይሰጣቸዋል። በዘንድሮው የለንደን ማራቶን በአለም አቀፉ የድንቃ ድንቅ መዝገብ ጊነስ ለማስመዝገብ 28 ሙከራዎች እየተደረጉ ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል እንደ ጠርሙስ በመልበስ፣ ሁከቶችን ለመከላከል የሚደረጉ አልባሳት እንዲሁም በክራንች የሚወደዳሩ አሉ።በዚህ ውድድር ላይ የ89 አመቱ ጃፓናዊው ኮይቺ ኪታባታኬ የሚወደዳር ሲሆን እንግሊዛዊው አሌክስ ሆርስሌይ 18ኛ ልደቱን በማራቶን ውድድር ያከብራል። በዛሬው ውድድር ላይ አሌክስን ጨምሮ 205 ግለሰቦች ልደታቸውን በሩጫ ያከብራሉ። ሆኖም በለንደን የተከሰተው የባቡር የስራ ማቆም አድማ ወደ ለንደን ለሚመጡ ተወዳዳሪዎች እንቅፋት እንደሆነ ተገልጿል። በባቡር ሰራተኞች በታቀደው የስራ ማቆም አድማ ምክንያት የጉዞ መስተጓጎል የሚገጥማቸው ሯጮችን ለመርዳት "የምንችለውን ሁሉ" እያደረግን ነው” ብለዋል አዘጋጆቹ። የባቡር አገልግሎቶች ቅዳሜ እለት አገልግሎት መስጠት አቁመው የነበረ ሲሆን በዚህም ምክንያት ጥዋት ለሚደረገው ሩጫ በርካቶች ላይደርሱ ይችላሉ ብለዋል። የሩጫው ዳይሬክተር ሂዩ ብራሸር ለቢቢሲ ስፖርት እንደተናገሩት ዘግይተው የሚመጡ ሯጮች በኋላ እንዲጀምሩ ይፈቀድላቸዋል ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/crgxgx71dklo
amh
sports
ኤርትራዊው የጌንት-ዌል የብስክሌት ውድድር በማሸነፍ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ
ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ በቤልጂየም የሚካሄደውን የጌንት-ዌል የብስክሌት የዕለት ውድድር በማሸነፍ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ። ቢንያም ግርማይ እሑድ በተካሄደው የጌንት-ዌል የብስክሌት ውድድር የዕለቱ አሸናፊ በመሆን ታሪክ ሠርቷል። ማሸነፉን ተከትሎ በሰጠው ቃለ ምልልስ "የማይታመንና የሚገርም ነው። ይህን አልጠበቅኩም ነበር" ብሏል የ21 ዓመቱ ኤርትራዊ። "አርብ ነበር ዕቅዴን የቀየርነው። የመጣነው ለጥሩ ውጤት ነው። ውድድሩ አስደናቂና የማይታመን ነው" ብሏል ቢንያም። ቢንያም 30 ኪሎ ሜትር ሲቀር መምራት ከጀመሩት አራት ብስክሌተኞች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን፤ የውድድሩ መጠናቀቂያ 250 ሜትር ርቀት ሲቀረው አፈትልኮ በመውጣትም ማሸነፍ ችሏል። የኢንተርማርቼ-ዋንቲ ጎበርት ጋላቢው ቢኒያም ግርማይ "ድሉ በተለይም ለአፍሪካውያን ብስክሌተኞች ትልቅ ለውጥ ያመጣል" ሲል ሃሳቡን ገልጿል። የጃምቦ ቪስማው ብስክሌተኛ ክሪስቶፍ ላፖርት እስከመጨረሻው ከቢኒያም ጋር ቢታገልም ፈረንሳዊው ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። 248.8 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የጌንት-ዌል በሚቀጥለው ሳምንት ለሚጀመረው እና ቱር ኦፍ ፍላንደርስ ለሚባለው የቤልጂየም ትልቁ ውድድር እንደመዘጋጃ ይቆጠራል። በድንጋይ ንጣፍ፣ ኮብል መንገድ፣ ላይ የመጀመሪያ ውድድሩን ያደረገው ቢኒያም "በኮብል ላይ ተቸግሬ ነበር። አልተመቸኝም ነበር" ብሏል። "መጨረሻ ላይ ሌሎቹ ጠንካሮች እንደሆኑ ባውቅም በራስ የመተማመን ስሜት ተሰማኝ።" ቢንያም በፍላንደርስ ለመሳተፍ አልተመዘገበም። የሴቶቹን ውድድር በጎዳና ውድድር ሻምፒዮን የሆነችው የትሬክ-ሴጋፍሬዶዋ ኤሊሳ ባልሳሞ አሸንፋለች። ኮሎምቢያዊው ሰርጂዮ ሂጉይታ የቮልታ ሲክሊስታን ካታሎንያ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል። ኢኳዶራዊው ሪቻርድ ካራፓዝ በሁለተኝነት አጠናቋል። ሂጉይታ አንድ ሳምንት የፈጀውን ውድድር ከካራፓዝ በ16 ሰከንዶች ቀድሞ አጠናቋል። ፖርቹጋላዊው ጆአዎ አልሜዳ ደግሞ ሦስተኛ ሆኗል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60897788
amh
sports
ናኦሚ ኦሳካ ከፈረንሳይ ውድድር ራሷን አገለለች
የአለም ቁጥር ሁለት የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናኦሚ ኦሳካ ከፈረንሳይ ውድድር ራሷን እንዳገለለች አስታወቀች። ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ለመናገር ፈቃደኛ ካልሆነች ትታገዳለች የሚል ውዝግብን ተከትሎ ነው በፈረንሳይ ኦፕን እንደማትወዳደር ያሳወቀችው። ይህንን ባሳወቀችበት የትዊተር መልዕክትም ናኦሚ በጭንቀት (ዲፕረሽን) ህመም እየተሰቃየች እንደሆነ አስፍራለች። ህመሟም የጀመረው ከሶስት አመት በፊት በሜዳ ቴኒስ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠውን የመጀመሪያዋን ግራንድ ስላም ካሸነፈች ጀምሮ ነው። የ23 አመቷ አትሌት የአዕምሮ ጤንነቷን ለመጠበቅ በሮላንድ ጋሮስ ጋዜጣዊ መግለጫ አልሳተፍም ያለችው ባለፈው ሳምንት ነበር። ባለፈው ሳምንት እሁድ ከሮማኒያዊቷ ፖትሪሺያ ማሪያ ቲግ ጋር በነበረው ውድድር በአሸናፊነት ያጠናቀቀችበት ጨዋታ ተከትሎ ከሚዲያዎች ጋር ቆይታ አላደርግም በማለቷ 15 ሺህ ዶላር ተቀጥታለች። በዚያኑ ቀን የግራንድ ስላም ውድድር አዘጋጆች ባወጡት የጋራ መግለጫ አትሌቷ ሚዲያ አላናግርም በሚል ባህርይዋ ከቀጠለች ከጨዋታዎች እንደምትታገድ አስጠንቅቀው ነበር። አትሌቷም በትናንትናው ዕለት ከፈረንሳይ ኦፕን ራሷን እንዳገለለች ገልፃ "ለተወሰነ ጊዜም ከሜዳ ራሴን አርቄያለሁ " ብላለች። "ትክክለኛው ወቅት ሲመጣ ከውድድር አዘጋጆች ጋር ለአትሌቶች፣ ለሚዲያዎችና ለተመልካቾች በምን መንገድ ውድድሮችን ማሻሻል እንችላለን የሚለው ላይ መወያየት እፈልጋለሁ' ብላለች። የፈረንሳይ ቴኒስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጊለስ ሞሬቴን የናኦሚን ራሷን ከውድድር ማግለል አስመልክቶ "አሳዛኝ" ብለውታል። "ናኦሚ በገጠማት ሁኔታ ሃዘን ተሰምቶናል። በፍጥነትም እንድታገግም ምኞታችንን እየገለፅን በሚቀጥለው አመት ውድድራችን እናያታለን ብለን እንጠብቃለን" ብለዋል ። "ሁሉም የግራንድ ስላምስ ውድድሮች ማለት ደብልዩ ቲ ኤ፣ ኤቲፒና አይቲኤ ለአትሌቶች ጤና ቅድሚያ በመስጠት በሌሎችም ዘርፎች አትሌቶች የሚሻሻሉበትን መንገድ እንቀይሳለን። ከዚህም ጋር ተያይዞ አትሌቶች ከሚዲያዎች ጋር ያላቸው ግንኙነቶች እንዲሻሻሉ ስንሰራ ነበር። አሁንም እንሰራለን" በማለት አስረድተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57312692
amh
sports
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል. . . .ግምቶችን ይዘናል
የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ዛሬ ምሽት ይጀምራል። ለአዲሱ የውድድር ዘመን ቢቢሲ ሳምታዊ የውጤት ግምት የሚሰጥ አዲስ ባለሙያ ይዞ መጥቷል- ታዋቂው ክሪስ ሱቶን። ሱቶን ቀደም ሲል ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ነበር። ቼልሲ፣ አስቶን ቪላ እና ሴልቲክ የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው። በኋላም በአሰልጣኝነት እና በተንታኝነት ሰርቷል። ለመሆኑ የ2022/23 ውድድር ዘመን የመክፈጫ ጨዋታዎች በምን መልኩ ይጠናቀቃሉ? ክሪስታል ፓላስ ከ አርሰናል አርሰናል ጥሩ የቅድመ ውድድር ዘመን ነበረው። ኮኖር ጋላገር ወደ ቼልሲ ከተመለሰ በኋላ ክሪስታል ፓላስ እንደቀድሞው ጠንካራ ተፎካካሪ መሆኑ ላይ ጥያቄ አለኝ። ለሚኬል አርቴታ ቡድን ጠንካራ ጨዋታ ይሆናል። ብዙ ነገሮች ግን መድፈኞቹ እንደሚያሸንፉ ይቁማሉ። ግምት፡ 1- 2 ፉልሃም ከ ሊቨርፑል እንደ ላውሮ በየሳምንቱ ሊቨርፑል ያሸንፋል እያልኩ መገመት የለብኝም። እንደዚህ አይነት መድሎ ማቆም አለብኝ። ይህንን ጨዋታ ግን ሊቨርፑል ይሸነፋል ብሎ መገመትም ስህተት ነው። ሊቨርፑል በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ወቅት ድንቅ ነበር። ቅዳሜ ለፉልሃም ከባድ ጨዋታ ይሆናል። ዓመቱን ሙሉም የሚከብዳቸው ይመስለኛል። ግምት፡ 0-3 ሊድስ ከ ዎልቭስ ከፉልሃም እና በርንማውዝ ጋር ሦስተኛው ቡድን ሆኖ የሚወርደው ቡድን ሊድስ ይመስለኛል። ባለፈው ዓመትም ለጥቂት ነው የተረፉት። ካልቪን ፍሊፕስ እና ራፊንሃን የመሰሉ ድንቅ ተጫዋቾቻቸውን ሸጠዋል። ዎልቭስ ደግሞ ድንቅ ኳስ አቀጣጣይ ተቻዋቾች አሉት። የተጎዳው ራዉል ሂሚኔዝ ባለመኖሩ የአጥቂ ችግር አለባቸው። ስለዚህ የፊት መስመሩን ማን ይመራል? ይህ ለመገመት ከባድ ጨዋታ ነው። ግምት፡ 1-1 በርንማውዝ ከ አስቶን ቪላ በርንማውዝ ያስፈራኛል። ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካደጉ በኋላ ዝውውሮች ላይ በስፋት አልተሳተፉም። አስቶን ቪላም በምጠብቀው ልክ ተጫዋቾችን አላስፈረመም። ግን በጣም ብዙ ምርጥ ምርጥ ተጫዋቾች አሏቸው። በጥሩ ውጤት ለመጀመርም ዕድል ያላቸው ቪላዎች ናቸው። ግምት፡ 0-1 ኒውካስል ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ፎረስት ከ23 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ መምጣቱ አስደሳች ነው። ቡድኑ ሮበርትሰንን የመሳሰሉ ጥሩ ተጫዋቾች አሉት። ሄዜ ሊንጋርድ እና ኦሬል ማንጋላን የመሰሉ ድንቅ ተጫዋቾችንም አስፈርመዋል። ኒውካስል ደግሞ ዘንድሮ መውረድ ስጋት የለበትም። ኤዲ ሃው ድንቅ ሥራ አከናውነዋል። ዘንድሮም ይህንኑ ያስቀጥላሉ ብዬ አስባለሁ። ጀምስ ማዲሰንን ከሌስተር ለመግዛት እየሞከሩ ሲሆን ለምን እንደዘገዩ ግልጽ አይደለም። ይህም ለመገመት የሚከብድ ጨዋታ ይሆናል። ግምት፡ 1-0 ቶተንሃም ከ ሳውዝሃምፕተን በቶተንሃም ዙሪያ ብዙ አስደሳች ዜናዎች አሉ። ይህ ግን በየውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ላይ የሚፈጠር ነገር ነው። ሪቻርልሰን በቅጣት በዚህ ጨዋታ ባይሰለፍም እንዴት ከዚህ ቡድን ጋር እንደሚዋሃድ ማየት እፈልጋለሁ። ዴያን ኩሉስቭስኪ በጥር ወር ቡድን ከተቀላቀለ በኋላ ጥሩ እየተንቀሳቀሰ ነው። እነዚህን ሁሉ እንዴት አንድ ላይ እንደሚያቀናጁ አላውቅም። ሳውዝሃምፕተኖች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግምት ሳይሰጣቸው ሜዳ ገብተው ብዙዎችን እያስገረሙ ይወጣሉ። ከባድ ሽንፈት እና አስደናቂ ድሎችንም አስመዝግበዋል። ከማንቸስተር ሲቲ ጋር አቻ ተለያይተው የኮንቴው ቶተንሃም አሸንፈዋል። ይህ ግን የሚደገም አይመስለኝም። ግምት፡  2-1 ኤቨርተን ከ ቼልሲ ቼልሲ ለውድድር ዓመቱ የተዘጋጀ አለመመስሉ አስገራሚ ነው። ቡድኑ ገና ተጫዋቾችችን አስፈርሞ አላጠናቀቀም። የተዘጋጀ ቡድንም አይመስለም። ኤቨርተንም ክፍተቶች አሉበት። ዶምኒክ ካልቨርት-ልዊን በጉዳት ሳሎሞን ሮንዶን እና ሪቻርሊሰን ደግሞ ተዘዋውረዋል። ስለዚህ አጥቂ መስመሩን የሚመራ የለም። ይህንን ጨዋታ ለማሸነፍ የጉዲሰን ፓርክን ደጋፊ እገዛ ይፈልጋሉ። ደጋፊው ሊያግዛቸው እንጂ ጎል ሊያስቆጥርላቸው ግን አይችልም። ግምት፡ 0-2 ሌስተር ከ ብሬንትፎርድ ያለፈው ዓመት ለሌስተር መጥፎ የውድድር ዘመን አልነበረም። ከሁለት ዓመት የአምስተኛነት ደረጃ የኋሊት ተንሸራተዋል።። በረኛቸው ካስፐር ሺማይክል ቡድኑን ለቋል። ዌስሊ ፎፋና እና ማዲሰንም ከለቀቁ ለቡድኑ ከባድ ይሆናል። በሬንትፎርድ ከሳምፕዶሪያ ያስፈረመው አማካዩ ሚኬል ዳምስጋርድ ጥሩ ዝውውር ይመስላል። ከታች ለመጡ ቡድኖች ሁለተኛው የውድድር ዓመት ከባድ ሲሆን ይታያል። የብሬንትፎርድም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል። ይህ ጨዋታም ከባድ ሊሆንባቸው ይችላል። ግምት፡ 1-1 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብራይተን ከማንችስተር ዩናይትድ ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም። የክርስቲያኖ ሮናልዶ ጉዳይ አለመረጋጋትን ይፈጥራል። አዲሱ አሰልጣን ኤሪክ ቴን ሃግ ያለ አጥቂውም ሊሠሩ ይችላሉ። በፊት በፊት ኦልድ ትራፎርድ ላይ መጫወት ከባድ ነበር። አሁን አሁን ግን ነገሮች ተለውጠዋል። አሜክስ ስታዲየም ላይ ባለፈው ዓመት 4 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል። ስለዚህ አይፈሯቸውም። በግራሀም ፖተር የሚመራውን ብራይተን ይመቸኛል። ከዚህ ጨዋታም ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ግምት፡ 1-1 ዌስት ሃም ከ ማንቸስተር ሲቲ ዌስት ሃም አጥቂውን ጂያንሉካ ስካማካን ከሳምፕዶሪያ አስፈርሟል። ወደ ሙሉ የጨዋታ አቋም የደረሰ ግን አይመስለኝም። የቡድኑ ችግር የሚመስለኝ የተከላካይ ክፍሉ ነው። በቅርቡ ያስፈረሙት ተከላካዩ ናይፍ አጉዋርድ በጉዳት አይሰለፍም። ባለፈው ዓመት እንደደረጉት ከሲቲ ጋር አቻ የሚለያዩ አይመስለኝም። ከሁለት ዓመት በፊት ማንቸስተር ሲቲ በሊጉ መክፈቻ 5 ለ 0 ዌስት ሃምን አሸንፎ ነበር። አሁንም ድሉ የሲቲ ይመስላል። የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ከሊቨርፑል ጋር ጥሩ አልነበረም። ቡድኑ በዚህ ጨዋታ የሚነቃቃ ሲሆን ኤርሊንግ ሃላንድም የጎል ካዝናውን ይከፍታል የሚል ግምት አለኝ። ግምት፡ 0-3
https://www.bbc.com/amharic/articles/cx84590j44yo
amh
sports
"በኳስ ወቅታዊ አቋም እንጂ ታሪክ ብዙም ቦታ የለውም" ጋቶች ፓኖም
ሐሙስ ሰኔ 02/2014 ዓ.ም. ዋሊያዎቹ በግሩም ብቃት ፈርዖኖቹን አንበረከኩ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም እግር ኳስ ስሟ ከገነነው ግብፅ ለመግጠም ሲሰናዳ ብዙ ተባለ። በርካቶች ሽንፈት ጠበቁ። "አቻ ብንወጣ በምን ዕድላችን" ሲሉ አንሾካሾኩ። ዋሊያዎቹ ግን የሆዳቸውን በሆዳቸው ይዘው በባዳ ሜዳ ግብፅን ገጠሙ። ብሩንዲያዊው የዕለቱ የመሃል ዳኛ ፊሽካቸውን ነፉ። ጨዋታው ተጀመረ። ዋሊያዎቹ የግብፅን በር ያንኳኩ ጀመር። ፈርዖኖቹ ኳስ መግፋት ከበዳቸው። አቡበከር ሲሸልል፣ ሽመልስ ሲያታልል፣ ጋቶች ሜዳውን ሲያካልል ቆመው ይመለከቱ ጀመር። ጨዋታውን በስጋት የጀመረው ደጋፊ የልቡ ምት መለስ ይልለት ጀመር። 21ኛው ደቂቃ ደረሰ። ዳዋ ሆቴሳ ወደ ግብፁ ግብ ጠባቂ ሞሐመድ አቡጋባል ገሰገሰ። በዚህች ደቂቃ በኢትዮጵያውያን ደጋፊዎች ዘንድ ድቅድቅ ዝምታ ሰፈነ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ኳሷ ተንከባላ መረቡን ስትነካ ምድር ተንቀጠቀጠ። ኢትዮጵያ 1 - ግብፅ 0። ዋሊያዎቹ በአንድ ጎል ተማምነን ለዕረፍት ከሜዳ አንወጣም ያሉ ይመስላሉ። የግብፅን የሜዳ አጋማሽ ፈነጩበት። ተረኛው አምበሉ ሽመልስ በቀለ ነው። ለግብፁ ክለብ ኤል ጉና የሚጫወተው ሽመልስ የፈርዖኖቹን ነገር ለኔ ተዉት ያለ ይመስላል። ከአማኑዔል ገብረሚካዔል የተሻገረለትን ኳስ በአቡጋባል አናት አሻግሮ የዋሊያዎቹን የጎል ድርሻ እጥፍ አደረገው። ፈርዖኖቹ ከወራት በፊት በተረገው የአፍሪካ ዋንጫ ለፍፃሜ ደርሰው በሴኔጋል ተረተው የአህጉሪቱ ሁለተኛ ኃያል ቡድን ለመሆን ችለዋል። በፊፋ የዓለም እግር ኳስ ሚዛን ግብፅ 32ኛ ናት። ኢትዮጵያ ደግሞ 140ኛ። የእግር ኳስ ውጤት ተንታኞች ግብፅ ትረታለች ብለው ቢገምቱ አይገርምም። ከውጤቱ በኋላም ኢትዮጵያ ረታች ሳይሆን፣ ግብፅ ተረታች ብለው ቢፅፉም በውጤቱ ደንግጠው መሆኑን እሙን ነው። ግን ግን ዋሊያዎቹ ለጨዋታው የሰጡት ግምት ምን ነበር? "ኧረ እኛ ምንም ዓይነት ፍራቻ አልነበረንም" ይላል ጋቶች። "ማሸነፍ እንደምንችል ራሳችንን አሳምነን ነው የገባነው። በእግር ኳስ ወቅታዊ አቋም እንጂ ታሪክ ብዙ ቦታ የለውምና ዓላማችን የነበረው ማሸነፍ ነበር።" አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከሚታወቁበት የ4-3-3 ፍልስፍና ፈቀቅ ብለው በአዲስ አሰላለፍ ነበር ግብፅን የገጠሟት። ውበቱ በግብፁ ጨዋታ 4-2-3-1 በተሰኘው አጨዋወት ነው የተከሰቱት። አቡበከር ናስር የፊቱን መስመሩን እንዲሾፍር፤ ጋቶችና አማኑዔል ዮሐንስ ተከላካዩንና አጥቂውን ክፍል እንዲያሳልጡ በማሰብ ያደረጉት ነበር። የአሠልጣኙ ውበቱ ያደረጉት ለውጥ ግን ፍሬያማ ነበር። "ከማላዊ ሽንፈት መልስ ነው ግብፅን የገጠምነው። ጨዋታው ቀላል እንደማይሆን እናውቃለን። ይኸው አሸንፈን እኛም ደስ ብሎን የኢትዮጵያም ሕዝብ ተደስቷል" ይላል ጋቶች ፈገግታ በሚነበብበት ድምፅ። በአስገራሚ ብቃቱ መሃል ሜዳውን በብቸኝነት ሲሾፍር የነበረው ጋቶች ፓኖም፣ በቋሚ አሰላለፍ ኢትዮጵያን ከወከለ ሰንበትበት ብሏል። በአፍሪካ ዋንጫ ጋቶችን ለማየት የቋመጡ ዓይኖች አልተሳካላቸውም። ጋቶችን ግን ለታሪካዊው የግብፅ ፍልሚያ ደረሰ። "እርግጥ ነው በአፍሪካ ዋንጫ አንድም ጨዋታ አልተጫወትኩም። ይህ የአሠልጣኙ ውሳኔ ነው። ነገር ግን እኔ ወደ ሜዳ ግባ ስባል ለመግባት ሁሌም ዝግጁ ነኝ።" ጋቶች ይህን ይላል. . . "ወደ ሜዳ ግባ ስትባል ያለህን አቅም ነው ማሳየት ያለብህ።" እነሆ በቃል ያለውን በግብፅ ጨዋታ ለብዙዎች አሳይቷል። ከግብፅ 27 ክልሎች አንዱ የሆነው ሬድ ሲ ገቨርኔት የኤል ጉናን መቀመጫ ነው። ኤል ጉናን ለኢትዮጵያዊያን እግር ኳሰኞች አዲስ አይደለም። ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾችም ለግብፅ ሊግ ባዳ አይደሉም። ጋቶች ፓኖም አንድ የእግር ኳስ ዘመን በኤል ጉናን አሳልፏል። ለሃራስ ኤል ሆዱድም ተሰልፎ ያውቃል። ሽመልስ በቀለ ደግሞ የወቅቱ የኤል-ጉና የወቅቱ የቡድኑ አማካይ ነው። ሌሎችም ስማቸው የከበደ ኢትዮጵያውያን ኳስ ተጫዋቾች የግብፅን ሊግ ያውቁታል። ዋሊያዎቹ ግብፅን ለመርታታቸው ይሄ አንዱ ምክንያት ይሆን? "አብዛኛዎቹ የግብፅ ተጫዋቾች ከአል-አህሊና ዛማሌክ የተመረጡ ናቸው። እዚያ ሳለሁ ተቃራኒ ሆኜ የተፋለምኳቸው ናቸው" ይላል ጋቶች። "ይሄ ረድቶኛል ብዬ አስባለሁ።" የግብፅ ድል ለቀጣይ ጨዋታዎች ጠንካራ መንፈስ እንደሚፈጥር ጋቶች ያምናል። "በስኬትም በደረጃም ከእኛ ላቅ ያሉ ናቸው። ግብፅን መርታታችን ጠንከር ካልን ማንንም ማሸነፍ እንደምንችል ያሳየን ነው።" የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ካፍ፤ ኢትዮጵያ አህጉራዊ ጨዋታ ለማድረግ የሚችል ሜዳ የላትም ብሏል። ይሄ ዜና የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ጨምሮ ደጋፊውን አንገት ያስደፋ ነበር። ፌዴሬሽኑ የባሕር ዳር ስታድዬምን አድሻለሁ ቢልም ካፍ ተወካይ ልኮ ካስፈተሸ በኋላ መመዛኛዬን አላሟላችሁም የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ለዚህ ነው ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ማድረግ የሚገባቸውን ጨዋታ በማላዊ ስታድዬም ሊያደርጉ የተገደዱት። ቢሆንም በማላዊው ሊሎንግዌ ስታድዬም ለዋሊያዎቹ የነበረው ድጋፍ ደመቅ ያለ ነበር። "እርግጥ ነው በሜዳችን ቢሆን የተሻለ የራስ መተማመን ይኖረን ነበር" ባይ ነው ጋቶች። ነገር ግን ይላል የመሃል ሜዳው ሞተር "ነገር ግን በማላዊ የነበረው ድጋፍ ሜዳችን ላይ እየተጫወትን ያክል እንዲሰማን አድርጎናል።" ጋቶች ጨዋታው ሲገባደድ ከስታድዬሙ ግዙፍ ድምፅ ማጉያ በሚወጣው ሙዚቃ ከደጋፊዎች ጋር ሲቦርቁ እንደነበር ያወሳል። "እንግዲህ የእኛ ሜዳ ከደረሰ ቀጣዩን ጨዋታ [ኢትዮጵያ ከጊኒ] በደጋፊያችን ፊት እንደምናደርግ ተስፋ አደርጋለሁ" ይላል። ፈርዖኖቹ አለን የሚሉት ኮከብ ተጫዋቻቸውን በኢትዮጵያው ጨዋታ ማሰለፍ አልቻሉም። የሊቨርፑሉ አጥቂ ሞሐመድ ሳላህ በጉዳት ምክንያት ይህ ጨዋታ አምልጦታል። ቁጥሩ አንዱ ግብ ጠባቂ ኤልሻናዊና ትሬዝጌም እንዲሁ አገራቸውን መወከል ሳይችሉ ቀርተዋል። እውን የሞሐመድ ሳላህ አለመኖር ለዋሊያዎቹ መልካም አጋጣሚ ነበር? "እርግጥ ነው ሞሐመድ ሳላህ ትልቅ ተጫዋች ነው" የጋቶች አስተያየት ነው። "ነገር ግን ሳላህ ብቻውን ምንም ሊያደርግ አይችልም። ምክንያቱም እኛ በዕለቱ የተሻልን ነበርን። የሚገባንን ውጤት ነው ያገኘነው።" አሠልጣኝ ውበቱ አባተም አገር ቤት ከገቡ በኋላ በሰጡት መግለጫ ያሉት ይሄንኑ ነው። "እኛ በልጠን እንጂ ግብፅ ደክማ አይደለም" ብለዋል። በግብፅ ሽንፈት የደነገጡ በርካታ ዓለም አቀፍ የኳስ አውታሮችም የዋሊያዎቹን ውጤት ከማድነቅ አልቦዘኑም። የግብፅ መገናኛ ብዙኃን አዲሱን የፈርዖኖቹን አሠልጣኝ ኢሃብ ጋላልን የሚወቅስ ፅሑፍ አስነብበዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን ማጣሪያ በሚቀጥለው ወር ደቡብ ሱዳንን ይገጥማል። ቻን አገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሰለፉበት አህጉራዊ ውድድር ነው። ይህም አሠልጣኝ ውበቱ አዳዲስ ተጫዋቾች እንዲሞክሩበት ዕድል የሚሰጣቸው ነው። ከዚያ ቀጥሎ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ይከተላሉ። ዋሊያዎቹ በወርሃ መስከረም በደርሶ መልስ ጨዋታ ጊኒን ይገጥማሉ። መጋቢት ደግሞ ሁለቱ ቀሪ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከማላዊና ከግብፅ ጋር ይደረጋሉ። አሁን ኢትዮጵያ የምድብ 'መ' ቁንጮ ናት። ምንም እንኳ ሁሉም የምድቡ ቡድኖች ተመሳሳይ 3 ነጥብ ቢያካብቱም ዋሊያዎቹ በአንድ ንፁህ ጎል ከምድቡ አናት ተቀምጠዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cxwnnlpxdpvo
amh
sports
እግር ኳስ ፡ ከማራዶና ሞት ጋር በተያያዘ ፖሊስ ሐኪሙ ላይ ምርመራ ጀመረ
የአርጀንቲና ፖሊስ በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ሞት ጋር ተያይዞ የዝነኛውን እግር ኳስ ተጫዋች ሐኪም እየመረመረ ይገኛል። ፖሊስ በዋና ከተማዋ ቦነስ አይረስ የሚገኘውን የዶ/ር ሊዮፖልዶ ሉኮን መኖርያ ቤትና የግል ክሊኒክ በርብሯል። ምርመራው ሊጀመር የቻለው ማራዶና የተሳካ የተባለ ቀዶ ህክምና ማድረጉን ተከትሎ በድንገት መሞቱ ምናልባት የሕክምና ቸልተኝነት ተጫዋቹን ለሞት ዳርጎታል የሚል ጥርጣሬ በመፈጠሩ ነው። የ60 ዓመቱ የእግርኳስ ኮከብ የሞተው ከ4 ቀናት በፊት በልብ ድካም ነው። ማራዶና ከሕመሙ እያገገመ ሳለ ነበር በድንገት የሞተው። ዶ/ር ሊዮፖልዶ እስካሁን ክስ አልተመሰረተበትም። ሆኖም አንድም ጥፋት የለብኝ ሲል እንባ እየተናነቀው ለጋዜጠኞች ተናግሯል። ማራዶና ከመሞቱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የተሳካ የተባለ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና አድርጎ ነበር። ቀዶ ጥገናው ያስፈለገው በጭንቅላቱ ውስጥ የደም መርጋት ምልክቶች በመታየታቸው ነበር። በሚቀጥለው ወር ደግሞ ከአልኮል ሱስ ለመውጣት አዲስ ሕክምና ይጀምራል ተብሎ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር። የማራዶና ሴት ልጆች ስለ አባታቸው የሕክምና ሁኔታ ምርመራ እንዲደረግ ግፊት አድርገዋል ተብሏል። ትናንት እሑድ ወደ 30 የሚሆኑ ፖሊሶች የማራዶና የግል ሐኪም ወደ ሆነው የ39 ዓመቱ ዶ/ር ሊዮፖልዶ ቤት በድንገት በመድረስ ብርበራ አድርገዋል። ሌሎች 20 የሚሆኑ ፖሊሶች ደግሞ ክሊኒኩን ፈትሸዋል። ፖሊስ የማራዶና የመጨረሻ ቀናት ሕክምና ምን ይመስል እንደነበር ለመፈተሽ ነው ፍላጎቱ። ኮምፒውተሮችን፣ ስልኮቹንና የሕክምና ማስታወሻዎችን ጭምር አንድ በአንድ እየመረመሩ ነው ተብሏል። ፖሊስ ጥርጣሬ አለኝ የሚለው የማራዶና ቀዶ ጥገናን ተከትሎ ምናልባት ሐኪሙ ሊያደርጋቸው ይገቡ የነበሩ ጥንቃቄዎችን ሳያደርግ ቀርቶ ከሆነ በሚል ነው። ማራዶና ቀዶ ጥገናውን አሳክቶ ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ እንዲያገግም የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ነበሩ ወይ? የሚለው በምርመራው ይካተታል። ለምሳሌ 24 ሰዓት በተጠንቀቅ የሚንከባከቡት ነርሶች መኖር፣ በአደገኛ እጽ ሱስ ለሚሰቃይ ሰው ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች መኖር፣ በአስቸኳይ ሊጠሩ የሚችሉ ሐኪሞች እና በተጠንቀቅ የሚቆም አምቡላንስ ነበረ ወይ? የሚለው ይፈተሻል። መርማሪ ፖሊስ ዶ/ር ሊዮፖልዶ እነዚህ ሁኔታዎች ለታማሚው አሟልቶ ነበር ወይ፣ የሐኪሙ የመጨረሻ ቀናትን ምን ይመስላሉ የሚለውን እየመረመረ ነው። የ39 ዓመቱ የማራዶና የግል ሐኪም ዶ/ር ሊዮፖልዶ ደንበኛው ከሞተ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ትናንት ዝምታውን ሰብሯል። ዶ/ር ሊዮፖልዶ ስሜታዊ ሆኖ በእንባ እየታጠበ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የማራዶናን ሕይወት ለማትረፍ የሚችለውን ሁሉ እንዳደረገለት ተናግሯል። ማራዶና በመጨረሻ ቀናት ከፍተኛ ሐዘን ይሰማው እንደነበረም ጠቅሷል። ዶ/ር ሊዮፖልዶ በጋዜጠኞች በእንዝህላልነት ለደንበኛው መሞት ተጠያቂ ይሆን እንደሆነ ሲጠየቅ በቁጣ እንዲህ መልሷል፣ "እኔ ተጠያቂ የምሆነው በምን ምክንያት እንደሆነ ልናገር? ማራዶናን በጣም በመውደዴ፣ ለእሱ በጣም እንክብካቤ በማድረጌ፣ በአጭር ይቀጭ የነበረውን ሕይወቱን በማራዘሜ፣ እስከመጨረሻው ከእሱ ጋር በመሆኔ ነው መጠየቅ ካለብኝ" ሲል በድንገተኛ ቁጣ ገንፍሎ ምላሽ ሰጥቷል። ፖሊስ በበኩሉ ዶ/ር ሊዮፖልዶ ለማራዶና ቀዶ ጥገና ካደረገለት በኋላ ክትትል ማድረግ ሲገባው አላደረገለትም ብሎ ጠርጥሮታል። በዚህ ረገድ ዶ/ር ሊዮፖልዶ ሲመልስ "የእኔ ሙያ የአንጎል ቀዶ ህክምና ነው። እኔ ህክምናውን ጨርሻለሁ" በማለት ማራዶና ከእሱ ክሊኒክ ከወጣ በኋላ ላለው ነገር ተጠያቂ እንዳልሆነ አስገንዝቧል። ዶ/ር ሊዮፖልዶ እንደሚለው ማራዶና ከቀዶ ህክምናው በኋላ መሄድ የነበረበት ወደ አደገኛ እጽ ማገገሚያ ማዕከል እንጂ ወደ ቤት አልነበረም። ማራዶና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሳለ ቤቱ የተዘጋጀና የሕክምና ቁሶች የተሟሉለት አምቡላንስ እንዴት ላይኖር ቻለ የሚለው እያነጋገረ ነው። ማራዶና በመጨረሻው ሰዓት ልጆቹንም፣ ቤተሰቡንም ማስጠጋት አልፈለገም፣ ከፍ ያለ ሐዘን ይሰማው ስለነበር ብቻውን መሆን ፈልጓል ሲል ሐኪሙ አብራርቷል። ማራዶና የድኅረ ዝና መስቅልቅልና የኮኬይን ሱሰኝነት ለሕይወቱ ማጠር ሚና እንደነበራቸው ይታመናል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55112959
amh
sports
በ38 ዓመት ከብር ሜዳልያ ወደ ወርቅ የተሻገረችው ዋናተኛ
የሲንጋፖር ተወላጇ ክርስቲና ታም ለመጀመሪያ ጊዜ አገሯን ወክላ ሜዳልያ ያገኘችው የ12 ዓመት ታዳጊ ሳለች ነበር። ያኔ የብር ሜዳልያ ያገኘችው ክርስቲና፤ ከ38 ዓመታት በኋላ ባለፈው ሳምንት ሁለት የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች። የ50 ዓመቷ ክርስቲና፤ በፊሊፒንስ እየተካሄደ ባለው የደቡብ ምዕራብ እስያ ውድድር ከተሳተፉ አንዷ ናት። የወርቅ ሜዳልያ ያገኘችው ከውሀ በታች በሚካሄድ የ 'ሆኪ' (የገና ጨዋታን የሚመስል) ውድድር ነው። "ወደ ውድድሩ ተመልሼ የወርቅ ሜዳልያ አገኛለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር" ሰትልም ክርስቲና የተሰማትን ገልጻለች። • ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ ያለማቋረጥ የዋኘችው የጡት ካንሰር ታማሚ • ውሃ ውስጥ ለፍቅረኛው የአግቢኝ ጥያቄ ያቀረበው ግለሰብ ሰጥሞ ሞተ • ገንዘብ ያለው ሊገዛው የሚችለው 'ወርቃማው' ፓስፖርት ለምን ተፈላጊ ሆነ? ወደ ዋና ስፖርት የገባችው በሰባት ዓመቷ ከአንድ አጋጣሚ በኋላ ነበር። ያኔ በ40ዎቹ መጨረሻ ላይ የነበሩ አባቷ ዋና ባይችሉም፤ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በጀልባ ሲጓዙ ነፍስ አድን ጃኬት ለመልበስ ፍቃደኛ አልነበሩም። ቤተሰቡ ለሽርሽር በጀልባ ወደ ማሌዢያ ለመጓዝ ሲወስን፤ የክርስቲና አባት በባለቤታቸው ጉትጎታ ነፍስ አድን ጃኬት ለመልበስ ተስማሙ። ጉዞ ላይ ሳሉ፤ የክርስቲና አባት ከጀልባ መውደቃቸውን ታስታውሳለች። አባቷ በነፍስ አድን ጃኬቱ አማካይነት ሕይወታቸው ከተረፈ በኋላ፤ መላ ቤተሰቡ ዋና እንዲማር ያደረጋሉ። አጋጣሚውም ክርስቲናን ከስፖርቱ ጋር አስተዋወቃት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1981 ሲንጋፖርን ወክላ ስትወዳደር 12 ዓመቷ ነበር። የብር ሜዳልያም አግኝታለች። "ያኔ ብዙም ለውጤቴ ቦታ አልሰጠሁትም ነበር። እድሜዬ እየጨመረ ሲመጣ ግን የድሉ ዋጋ ገባኝ" ትላለች። ከሁለት ዓመት በኋላ በ200 ሜትር ስትወዳደርም የብር ሜዳልያ ብታገኝም፤ ስፓርቱን ለሠላሳ ዓመት አቋርጣ በሕግ ዘርፍ ተሰማራች። 2005 ላይ ስለ 'አንደር ዋተር ሆኪ (ከውሀ በታች የሚካሄድ የ 'ሆኪ') አንድ ጽሑፍ ስታነብ ግን፤ ለ38 ዓመት ወደተወችው ስፖርት የመመለስ ፍላጎት አደረባት። ፊሊፒንስ በተካሄደው ውድድር ተሳትፋም፤ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ አስመዝግባለች። "ልምምድ ማድረጉን እወደዋለሁ፤ የምፈልገው ቦታ እስክደርስ ያለው ሂደትም ያስደስተኛል" ያለችው ክርስቲና፤ 2021 ላይ በሚካሄደው ውድድር መካፈል እንደምትፈልግም ተናግራለች።
https://www.bbc.com/amharic/50697610
amh
sports
ቶኪዮ ኦሊምፒክ 2020፡ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው ውድድሮች የትኞቹ ናቸው? መቼስ ይካሄዳሉ?
ባለፈው ሳምንት አርብ የተጀመረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በድምቀት መካሄዱን ቀጥሏል። በቶኪዮ ኦሊምፒክ 33 አይነት ስፖርታዊ ውድድሮች የሚካሄዱ ሲሆን ኢትዮጵያም በአራት አይነት የስፖርት አይነቶች ማለትም በአትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ውሃ ዋናና በቴኳንዶ ትሳተፋለች። በጉጉት በሚጠበቀው የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ለተሰንበት ጊደይ፤ ሹራ ቂጣታ፤ ሰለሞን ባረጋ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ በሚወዳደሩባቸው ርቀቶች ሜዳሊያ ያስገኛሉ ተበሎ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል። ለመሆኑ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው ውድድሮች የትኞቹ ናቸው? መቼስ ነው የሚካሄዱት? የወንዶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ነገ አርብ ሐምሌ 23 የወንዶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል የማጣሪያ ውድድር ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ሦስት ኢትዮጵያውን አትሌቶች ይሰለፋሉ። ተወዳዳሪዎቹ አትሌቶችም ታደሰ ታከለ፣ አብረሃም ስሜ እና ኃ/ማርያም አማረ ናቸው። የማጣሪያ ውድድሩ በሦስት ቡድን ተከፍሎ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ሌሊት 9፡30 እስከ 4፡05 ድረስ ይካሄዳል። የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በተመሳሳይ የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በስድስት ቡድን ተከፍሎ አርብ ከ10፡25 እስከ ንጋት 11፡05 ድረስ ይካሄዳል። ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩት አትሌቶች ሀብታም አለሙ፣ ወርቅነሽ መሰለ እና ነጻነት ደስታ ናቸው። የሴቶች 5ሺህ ሜትር ማጣሪያ በዚሁ ቀን ሌላኛው የሴቶች 5ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር በሁለት ቡድን ተከፍሎ ይካሄዳል። የመጀመሪያው ቡድን የማጣሪያ ውድድሩን ቀን 7 ሰዓት የሚጀምር ሲሆን ሁለተኛው ማጠሪያ ደግሞ 7፡26 ደቂቃ ሲል ይጀምራል። በ5ሺህ ውድድር ላይ ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን እነሱም ጉዳፍ ጸጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ሰምበሬ ተፈሪ ናቸው። ጉዳፍ ፀጋይ በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ በፈረንሳይ በተካሄደ የ1ሺህ 500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረ ወሰን ማሻሻል ችላለች። በዚህ ምድብ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሐሰን ቀንደኛ ተፎካካሪዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል። የወንዶች 10ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ነገ ከሚካሄዱት ውድድሮች እጅግ በጉጉት ከሚጠበቁት አንዱ የወንዶች 10ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ነው። ኢትዮጵያ በዚህ መስክ በሰለሞን ባረጋ፣ በዮሚፍ ቀጄልቻ እና በበሪሁ አረጋዊ የምትወከል ሲሆን ውድድሩም ከቀኑ 8፡30 ላይ እንደሚካሄድ የቶኪዮ ኦሊምፒክ መርሃ ግብር ላይ ተመልክቷል። ሰለሞን ባረጋ ከሁለት ዓመት በፊት በዶሃ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች የ5ሺህ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝቷል። ዮሚፍ ቀጄልቻ ደግሞ በተመሳሳይ የውድድር መድረክ በ10 ሺህ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝቷል። ሰለሞን እና ዮሚፍ በኦሊምፒክ መድረክ ሲሳተፉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው። ሌላኛው አትሌት በሪሁ አረጋዊ በኔዘርላንድስ ሄንግሎ በተካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ ላይ ሦስተኛ ሆኖ መጨረስ ችሏል። የወንዶች የ800 ሜትር ማጣሪያ ቅዳሜ ሌሊት ከ9፡50 እስከ 10፡30 ድረስ በስድስት ቡድኖች ተከፍሎ የወንዶች የ800 ሜትር ማጣሪያ ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ላይ ብቸኛው አትሌት መለሰ ንብረት ኢትዮጵያን ወክሎ ይወዳደራል። የሴቶች 800 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ በተመሳሳይ የፊታችን ቅዳሜ የሴቶች 800 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያ ውድድር በሦስት ቡድኖች ተከፋፍሎ ይካሄዳል። የመጀመሪያውን ማጣሪያ ማለፍ የሚችሉ ከሆነ አትሌት ሀብታም አለሙ፣ ወርቅነሽ መሰለ እና ነጻነት ደስታ የግማሽ ፍጻሜ ውድድሩ ተሳታፊ የሆናሉ። የሴቶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ እሁድ ለሰኞ አጥቢያ የሴቶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ሌሊት 3፡40 እስከ 10፡10 ድረስ በሦስት ቡድን ተከፍሎ ውድድሩ ይከናወናል። በዚህ ማጣሪያ ኢትዮጵያም በመቅደስ አበበ፣ በሎሚ ሙለታ እና በዘርፌ ወንድማገኝ ትወከላለች። የወንዶች 800 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ አትሌት መለሰ ንብረት የመጀመሪያውን የ800 ሜትር ማጣሪያ የሚያልፍ ከሆነ በዚሁ ቀን የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ያደርጋል። የ1500 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 26 ደግሞ የ1500 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ይደረጋል። በዚህም ኢትዮጵያውያኑ ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ለምለም ኃይሉ ይወዳደራሉ። ይህ የማጣሪያ ውድድር ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ለሊት 9፡35-10፡00 ድረስ ይካሄዳል። የወንዶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ታደሰ ታከለ፣ አብራሀም ስሜ እና ኃ/ማርያም አማረ የ3ሺህ ማጣሪያን የሚያልፉ ከሆነ የፊታችን ሰኞ ከቀኑ 9፡15 ላይ ለፍጻሜ ይወዳደራሉ። የሴቶች 5ሺህ ሜትር ፍጻሜ በጉጉት በሚጠበቀውና ሰኞ ቀን 9፡40 ሲል በሚደረገው የ5ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያኑ ጉዳፍ ጸጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ሰምበሬ ተፈሪ ማጣሪያውን ካለፉ ተጠባቂ አትሌቶች ይሆናሉ። ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ እንዲሁም ሲፋን ሐሰን ሌሎች ተጠባቂ አትሌቶች ናቸው። የወንዶች 1500 ሜትር ማጣሪያ የፊታችን ማክሰኞ የወንዶች 1500 ሜትር ማጣሪያ የሚደረግ ሲሆን ታደሰ ለሚ፣ ሳሙኤል አባተ እና ሳሙኤል ተፈራ አገራቸውን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ናቸው። ይህ ውድድር ማክሰኞ ለዕረቡ አጥቢያ ከለሊቱ 9 ሰዓት እስከ 9፡30 ድረስ በሦስት ቡድኖች ተከፋፍሎ የሚደረግ ይሆናል። የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ በተመሳሳይ የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ በተመሳሳይ ቀን ይካሄዳል። በማጣሪያውም ጌትነት ዋለ፣ ንብረት መላክ እና ሚልኬሳ መንገሻ የሚሳተፉ ይሆናል። በሁለት ቡድን ተከፍሎ የሚካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከቀኑ 7 ሰዓት እና 7፡20 ላይ ይካሄዳል። የወንዶች 800 ሜትር ፍጻሜ የወንዶች 800 ሜትር ፍጻሜም የሚካሄደው ማክሰኞ ዕለት ይሆናል። አትሌት መለሰ ንብረት የመጀመሪያውን ዙር ማጣሪያ እና ግማሽ ፍጻሜን የሚያልፍ ከሆነ የፊታችን ማክሰኞ የ800 ሜትር ፍጻሜ ተወዳዳሪ ይሆናል። የሴቶች 1500 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ የሴቶች 1500 ሜትር ግማሽ የፍጻሜ ውድድር ረቡዕ ዕለት የሚካሄደው ይሆናል። ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ለምለም ኃይሉ በዚህ ርቀት አገራቸውን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ናቸው። የሴቶች 3 ሺ ሜትር መሰናክል ፍጻሜ አትሌት መቅደስ አበበ፣ ሎሚ ሙለታ እና ዘርፌ ወንድማገኝ ማጣሪያውን የሚያልፉ ከሆነ የ3ሺህ ሜትር መሰናክል ፍጻሜ ተወዳዳሪ መሆን ይችላሉ። ውድድሩ ከቀኑ 8 ሰዓት ሲል ይጀምራል። የወንዶች የ5ሺህ ሜትር ፍጻሜ አርብ ዕለት በጉጉት የሚጠበቀው የወንዶች የ5ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ቀን 9 ሰዓት ላይ ይካሄዳል። አትሌት ጌትነት ዋለ፣ ንብረት መላክ እና ሚልኬሳ መንገሻ ማጣሪያውን አልፈው በ5ሺህ ሜትር የወንዶች ፍጻሜ ውድድር ላይ እንደሚኖሩ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎባቸዋል። የሴቶች ማራቶን ቅዳሜ ጠዋት 1 ሰዓት ላይ የሴቶች ማራቶን ይካሄዳል። ኢትዮጵያውያኑ ትዕግስት ግርማ፣ ብርሀኔ ዲባባ እና ሮዛ ደረጄ ደግሞ ለአገራቸው ሜዳሊያ ለማስገኘት የሚፋለሙት አትሌቶች ናቸው። የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ቅዳሜ ከቀኑ 7፡45 ላይ የሴቶች 10ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል። በመድረኩም ኢትዮጵያ በአትሌት ለተሰንበት ጊደይ፣ ጽጌ ገ/ሰላማ እና ፀሐይ ገመቹ ትወከላለች። የ23 ዓመቷ ወጣት አትሌት ለተሰንበት ጊደይ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ክብረ ወሰን ባለቤት ስትሆን በቅርቡም የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን አሻሽላለች። በዚህ ውድድር የለተሰንበት ግደይ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሐሰን ፉክክር በበርካቶች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። የወንዶች ማራቶን በቀጣዩ ቀን እሁድ ነሐሴ 01/2013 ዓ.ም ደግሞ የወንዶች ማራቶን ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የሚወክሏት አትሌቶች ሹራ ቂጣታ፣ ሌሊሳ ዴሲሳ እና ሲሳይ ለማ ናቸው። አትሌት ሹራ ቂጣታ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በኦሊምፒክ የሚወዳደረው። አትሌት ሹራ "በዚህ ውድድር ለአገርም ለግልም ወርቅ ማምጣት አለብን በሚል ነው እየተዘጋጀን ያለነው" ብሎ ነበር ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። ከአንድ ዓመት በፊት በለንደን ማራቶን የኬንያውን ኢሉድ ኪፕቾጌን ያሸነፈው ሹራ፤ በቶኪዮ ኦሊምፒክም የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ከኪፕቾጌ ጋር ይወዳደራል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊው የማራቶን ሯጭ ሌሊሳ ዴሲሳ ከሁለት ዓመት በፊት በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፉ ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57994755
amh
sports
በሩሲያ በእስር ላይ ያለችው አሜሪካዊት የቅርጫት ኳስ ኮከብ ባይደንን ተማፀነች
በሩሲያ በእስር ላይ የምትገኘው አሜሪካዊት የቅርጫት ኳስ ኮከብ  ብሪትኒ ግሪነር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንዲረዷት በደብዳቤ ተማጸነች። ብሪትኒ በአደንዛዥ እፅ ክስ ሩሲያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ከዋለች ከአራት ወራት በላይ ተቆጥረዋል። ብሪትኒ ለባይደን በጻፈችውና ሰኞ ዕለት በደረሳቸው ደብዳቤ ላይ፣ የአሜሪካን ምድር ዳግም ላልረግጥ እችላለሁ የሚለውን ስጋቷን ገልጻለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፊኒክስ ሜርኩሪ የቅርጫት ኳስ ቡድን ተጫዋች የሆነችውን የብሪትኒንን ደብዳቤ እንዳነበቡት ዋይት ሐውስ አረጋግጧል። ሰኞ ዕለት የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ፣ ባይደን ብሪትኒ ግሪነርን ጨምሮ በውጭ አገራት ታግተው አሊያም ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በእስር ላይ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች መለቀቅ አለባቸው የሚል አቋም አላቸው ሲሉ ተናግረዋል። የአሜሪካ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ያሉትን ሁሉ መንገዶች ተጠቅመው ብሪትኒን ወደ አገሯ ለመመለስ እየሰሩ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ብሪትኒ ለፕሬዝዳንት ባይደን የጻፈችው ደብዳቤ አብዛኛው ክፍል በምስጢር ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም፤ አንዳንድ ተቀንጭበው የወጡ ሃሳቦች በእስር ላይ ያለችበትን የአዕምሮ ጤና ሁኔታዋን ያሳያሉ ተብሏል። “እዚህ በሩሲያ እስር ቤት ተቀምጬ፣ ያለ ባለቤቴ፣ ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼ ጥበቃ፣ ያለ ኦሊምፒክ ማሊያ እና ያለ ስኬት ብቻዬን ከሃሳቤ ጋር እየተሟገትኩ ነው ያለሁት። እዚህ ለዘላለም ልቆይ እችላለሁ ብዬ ፈርቻለሁ” ስትል ስጋቷን በደብዳቤዋ ላይ አስፍራለች። “ባለቤቴ፣ ቤተሰቦቼ፣ የቡድን አባሎቼ ናፍቀውኛል። ከዚህ በላይ ደግሞ አሁን ላይ በእኔ ምክንያት እየተሰቃዩ መሆኑን ማወቄ ደግሞ ጭንቀቴን አባብሶታል። እኔን ወደ ቤት ለመመለስ ለምታደርጉት ጥረት ክብር ይሰማኛል” ብላለች ብሪትኒ። ከዚህም በተጨማሪ ብሪትኒ ለፕሬዝዳንቱ በጻፈችውና በአሜሪካ የነጻነት ቀን መታሰቢያ ዕለት በደረሰው ደብዳቤ ላይ አባቷ በቬትናም የሰጡትን ወታደራዊ አገልግሎት አስታውሳለች። ፕሬዝዳንት ባይደን በሩሲያ በእስር ላይ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎችን እንዳይረሱም ብሪትኒ ጠይቃለች። “እባክዎን ሁላችንንም ወደ አገራችን ውሰዱን። ለመጀመሪያ ጊዜ ምርጫ የመረጥኩት በ2020 ነው ። የመረጥኩትም እርስዎን ነው። በእርስዎ እተማመናለሁ” ብላለች። ብሪትኒ በቁጥጥር ሥር የዋለችው እንደ አውሮፓውያኑ የካቲት 17 በሞስኮ፣ ሽረሜትየቮ አየር ማረፊያ ውስጥ የካናቢስ እጽ ዘይት ሻንጣዋ ውስጥ መገኘቱን ተከትሎ ነበር። አሁን ላይ የፍርድ ሂደቷን እየተከታተለች ሲሆን ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች እስከ አስር ዓመት በሚደርስ እስራት ልትቀጣ ትችላለች። በሩሲያ ውስጥ በወንጀል ጉዳዮች ከተከሰሱት ውስጥ ከአንድ በመቶ የሚያንሱት ተከሳሾች ነጻ ናቸው። ሆኖም ነጻ ብትባልም ከአሜሪካ ፍርድ ቤቶች አሰራር በተለየ የሩሲያ መንግሥት ማንኛውንም ውሳኔ በመሻር ወደ እስር ቤት የመላክ ሥልጣን አለው። ሰኔ ወር ላይ የአሜሪካ ኮንግረንስ አባል የሆኑት ጆን ጋራሜንዲ “ብሪትኒ በአሁኑ ሰዓት በመላው ዓለም እየተካሄደ ባለው የፖለቲካ ጦርነት መጠቀሚያ እንድትሆን አንፈልግም” ብለው ነበር። ሩሲያ ግን የቅርጫት ኳስ ተጨዋቿ እስር “በአሜሪካ እና በሩሲያ ውጥረት የተነሳ አይደለም” ስትል አስተባብላለች።
https://www.bbc.com/amharic/articles/crg71438vx3o
amh
sports
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ግምት
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ ይካሄዳሉ። የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን ለዚህ ሳምንት ጨዋታዎች ግምቱን አካፍሏል። እንደ ሱቶን ከሆነ ባለፈው ሳምንት ማንቸስተር ዩናይትድ በሊቨርፑል እንደሚሸነፍ ገምቶ ነበር። ይህ የብዙዎች ግምት ቢሆንም ጨዋታውን ማንቸስተር አሸንፏል። “ቀለል አድርጌ ነበር ያሰብኳቸው። ዩናይትድ በጨዋታው ላይ ድንቅ ነበሩ። አሁን ዋናው ጥያቄ በዚሁ ይቀጥላሉ ወይ የሚለው ነው” ይላል። “አስገራሚ ሳምንታት ያለፉ ሲሆን ቡድኖችም ወጥ አቋም ማሳየት አልተቻላቸውም።” ለዚህ ሳምንትም ሱቶን የሊጉን ጨዋታዎች ግምት አዘጋጅቷል። ቅዳሜ ሳውዛምፕተን ከ ማንቸስተር ዩናይትድ ሳውዛምፕተን ባለፈው ሳምንት ከሌስተር ጋር በነበረው ጨዋታ መጀመሪያ ላይ ቢበለጥም የኋላ ኋላ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ችሏል። በመጨረሻም በማሸነፍ ሦስት ነጥቡን ማግኘት ችሏል። ለማንቸስተር ዩናይትድም ቀላል ተጋጣሚ አይሆኑም። ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታ ራሱን አሻሽሎ ይቀርባል ብዬ አላሰብኩም ነበር። የብዙዎችም አስተሳሰብ ተመሳሳይ ነበር። በዚህ ጨዋታ ዩናይትድ ሦስት ነጥቡን ያሳካል። ግምት፡ 1-2 ብሬንትፎርድ ከ ኤቨርተን ኤቨርተን በተወሰነ ደረጃ ዕድለኛ አይደለም። ባለፈው ሳምንት ከኖቲንገሃም ፎረስ ጋር ብዙ ዕድል ቢፈጥሩም ማሸነፍ አልቻሉም። ዴማራይ ግራይ በጨዋታው ጥሩ በመንቀሳቀስ ጎል ቢያስቆጥርም ቡድኑ የአጥቂ ችግር አለበት። ብሬንትፎርድ ባለፈው ሳምንት በፉልሃም ተሸንፏል። በዚህ ሳምንት በሜዳው እንደመጫወቱ በጠባብ ውጤት ያሸንፋል። ግምት፡ 1-0 ** ብራይተን ከ ሊድስ ሊድስ ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ከወዲሁ አስደንቆኛል። አዳዲስ ፈራሚዎቻቸው ጥሩ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ። ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ዓመት ሁለቱንም የሊግ ጨዋታቸውን አቻ አጠናቀዋል። ሁለቱም ጎል አስቆጥረው አቻ ይለያያሉ። ግምት፡1-1 ** ቼልሲ ከ ሌስተር ቼልሲ ከተቀናቃኛቸው ሌስተር ተከላካዩን ዌስሊ ፎፋናን ለማስፈርም የሚያደርጉት ጥረት እስከ ቅዳሜ የሚሳካ አይመስልም። ቼልሲ በኤላን ሮድ ከደረሰበት አስደንጋጭ ሽንፈት እንደሚያንሰራራ እገምታለሁ። በጨዋታው ሊድስ የበላይ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ቼልሲ ግን ተቀዛቅዞ ነበር ያመሸው። የቶማስ ቱሄል ቡድን ጎል አስቆጣሪ ችግር ቢኖርበትም ይህንን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ግምት፡ 2-1 ** ሊቨርፑል ከ ብርንማውዝ ሊጉ ገና ረዥም ርቀት ቢቀረውም ሊቨርፑል በዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥብ ማሳካት ይኖርበታል። አማካይ ስፍራ ላይ የፈጣሪ ተጫዋች ችግር ያለባቸው ሲሆን አጥቂው ዳርዊን ኑኔዝ በቅጣት አለመሰለፉም እንደጎዳቸው በዩናይትድ ጨዋታ ታይቷል። ወደ ድል ለመመለስ ደግሞ በሜዳቸው ከበርንማውዝ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ትልቅ ዕድል ይዞላቸው መጥቷል። በርንማውዝ ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ሲቲ ቢሸነፍም ተከላካይ ክፍሉ ጠንካራ ነው። በዚህ ጨዋታ ሊቨርፑል ቀድሞ ጎል ማስቆጠር ይገባዋል። ግምት፡ 3-0 ** ማንቸስተር ሲቲ ከ ክሪስታል ፓላስ ክሪስታል ፓላስ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲቲን በሜዳው ማሸነፍ ችሏል። ፓላስ በመልሶ ማጥቃት ጠንካራ ከሆኑ የሊጉ ክለቦች አንደኛው ቢሆንም ሲቲ ላይ አይሳካለትም። ኒውካስል ነጥብ ለማግኘት ከሲቲ ጋር ኣደረገው ፉክክር ጠንካራ ሲሆን ፓላስ ግን ይህንን ያደርጋል ብዬ አለሳብም። ጎል ግን ያስቆጥራል። ግምት፡ 3-1 ** አርሴናል ከ ፉልሃም አርሴናል ደጋፊዎች በቡድናቸው ተስፋ መሰነቅ ጀምረዋል። ጋብርኤል ጂሰስ ድንቅ አጀማመር ያደረገ ሲሆን አርሴናል እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ፉልሃም ባለፈው ሳምንት ከብሬንትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ ተገቢ የሆነ ድል አስመዝግቧል። ውድድር ዓመቱ ሲጀመር ማንም ባይገምትም ፉልሃም ጠንካራ መሆኑን እያሳየ ነው። የባለፈው ሳምንቱ ውጤታቸው ጥሩ ቢሆንም በዚህ ሳምንት በአርሴናል ይፈተናሉ። ግምት፡ 2-0 አስቶን ቪላ ከ ዌስት ሃም ሁለቱ ቡድኖች ውድድር ዓመቱን ተመሳሳይ መልክ ይዘው ነው የጀመሩት። አስቶን ቪላ ባለፈው ሳምንት ከክሪስታል ፓላስ ጋር በነበረው ጨዋታ ሽንፈት ገጥሞታል። ኤቨርተንን ቢያሸንፉም ከበርንማውዝ ጋር በነበራቸው ጨዋታም በመሸነፋቸው የዚህን ሳምንት ጨዋታ ይጠብቃሉ። ዌስት ሃምም ውጤታማ መሆን አልቻለም። የመጀመሪያዎቹን ሦስት ጨዋታወች የተሸነፉ ሲሆን አሰልጣኝ ዴቪድ ሞዬስም ጫና እየመጣባቸው ነው። ቡድናቸው ከፎረስት ጋር ጥሩ ቢጫወትም ውጤታማ አልሆኑም። ከብራይተን ጋር ጥሩ አልተጫወቱም። የተከላካይ መስመር ችግርም አለባቸው። ግምት፡ 1-1 ** ዎልቭስ ከ ኒውካስል ዎልቭስ ጎል ማስቆጠር እየከበደው ነው። ጥሩ ዕድል በመፍጠር እና ጥሩ ተጫዋቾችን በመያዝ በኩል ባይታሙም አፈጻጸም ላይ ችግር አለባቸው። ይህ በተደጋጋሚ የተባለ ነው። በዚህ ምክንያት ተንከር ብለው የሚጫወቱ ቢሆንም ባለፈው ሳምንት ከማንቸስተር ሲቲ ጋር አቻ ከተለያየው ኒውካስል ጠንካራ ፉክክር ይጠብቃቸዋል። አጨዋወታቸው፣ ወደ ፊት በከሚሄዱበት መንገድ እና ከማጥቃት ሂደታቸው አንጻር ኒውካስል ያሸንፋል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1-2 ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ቶተንሃም በፎረስት አጀማመር ተደንቄያለሁ። ቡድኑ ከፍተኛ ገንዘብ ለተጫዋቾች ዝውውር ያወጣ መሆኑ መረሳት የለበትም። ስቲቭ ኩፐርን የመሰለ ጥሩ አሰልጣኝ ቢኖራቸውም አጨዋወታቸው ለስፐርስ የተመቸ ነው። በቶተንሃም ባልከፋም ከቼልሲ ነጥብ ተጋርተው ዎልቭስን በጠባብ ውጤት በማሸነፍ ጥሩ ውጤት አስመዝግበዋል። የፎረስት አጨዋወት ለኮንቴ ቡድን የሚመች ይመስለኛል። ግምት፡ 0-5
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn039e35y9wo
amh
sports
አሜሪካዊቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች በሩሲያ የዘጠኝ ዓመት እስር ተፈረደባት
ሩሲያ አሜሪካዊቷን ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግሪነር ለመልቀቅ ስምምነት ላይ እንድትደርስ አሜሪካ ጠየቀች። አደንዛዥ እጽ ይዛ ወደ ሩሲያ በመግባቷ የታሰረችው ብሪትኒ፣ በሩሲያ ፍርድ ቤት የዘጠኝ ዓመት እስራት ተፈርዶባታል። ሀለት ጊዜ የኦሎምፒክ ባለድል የሆነችው ቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ የካናቢስ ዘይት ይዛ መገኘቷን በፍርድ ቤት አምናለች። የዋይት ሀውስ ብሔራዊ ደኅንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ፣ አሜሪካ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር የምትችልበት የስምምነት ሰነድ እንዳዘጋጀች ገልጸዋል። መገናኛ ብዙኃን እንደሚሉት፤ አሜሪካ ብሪትኒን በሩሲያዊው የመሣሪያ አዘዋዋሪ ልትለውጣት ትችላለች። “የሞት ነጋዴው” እየተባለ የሚጠራው ቪክተር ቦውት በአሜሪካ የ25 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል። የእስረኛ ልውውጡ ይሄንን መሣሪያ አዘዋዋሪ በቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ እንዲሁም በቀድሞው የአሜሪካ ባሕር ኃይል ፖል ዌላን የሚቀይር ነው። የአሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ እና አየርላንድ ፓስፓርት ያለው ግለሰቡ፣ በስለላ ተከሶ 16 ዓመት እስር በሩሲያ ፍርድ ቤት ተፈርዶበታል። የዋይት ሀውስ ብሔራዊ ደኅንነት ቃል አቀባይ ጆን፤ ሁለቱ አሜሪካውያን ያለአግባብ እንደታሰሩና መለቀቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል። “ያቀረብነውን የስምምነት ሐሳብ ከሳምንታት በፊት መቀበል ነበረባቸው” ብለዋል። ሮይተርስ እንደሚለው፣ ሩሲያ ስምምነቱን ያልተቀበለችው ጀርመን እስር ቤት ያለው ቫዳም ክራስኮቭ በእስረኛ ልውውጡ እንዲካተት ስለምትፈልግ ነው። የ31 ዓመቷ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ “ስህተት መሥራቴን አምናለሁ። ሕግ ለመጣስ ብዬ አልነበረም” ብላለች። ምርጥ ከሚባሉ ተጫዋቾች አንዷ ስትሆን ወደ ሩሲያ ያቀናችው ለቅርጫት ኳስ ጨዋታ ነበር። አውሮፕላን ማረፊያ ሳለች ሻንጣዋ ውስጥ የካናቢስ ዘይት ተይዞ ነው በቁጥጥር ሥር የዋለችው። ታስራ ብዙም ሳይቆይ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ተነሳ። ብሪትኒም በአሜሪካ እና በሩሲያ የዲፕሎማሲ ሽኩቻ አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች። ጠበቆቿ ለሩሲያ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚሉ ገልጸዋል። የብሪትኒ ቡድን ፊኒክስ ሜርኩሪ፣ ኮኒክቲክት ሰን ቡድንን ሲገጥም ለብሪትኒ ያለውን ድጋፍ ለማሳየት ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾቹ ለ42 ሰከንድ በጥሞና አሳልፈዋል። መታሰቢያነቱ ብሪትኒ ለምትለብሰው 42 ቁጥር መለያ ነው። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፍርድ ቤቱን ብይን “ተቀባይነት የሌለው” ብለውታል። “ሩሲያ በአፋጣኝ ለቃት ብሪትኒ ከባለቤቷ፣ ከጓደኞቿ፣ ከቡድን ጓደኞቿና ከወዳጆቿ ጋር እንድትቀላቀል እጠይቃለሁ” ሲሉም አቋማቸውን ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን “ሩሲያም ትሁን ሌሎች አገራት ያልተገባ እስር የሚፈጽሙ ከሆነ ወደተለያዩ አገራት እየሄዱ የሚሠሩ ሰዎች ደኅንነት ስጋት ውስጥ ይወድቃል” ብለዋል። ብሊንከን ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ሳምንት በስልክ ተነጋግረዋል። አሁን ሁለቱም ለደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት ውይይት ካምቦዲያ ይገኛሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c72k1z7w858o
amh
sports
በኳታር የዓለም ዋንጫ ስታዲየሞች ቢራ እንዳይሸጥ ታገደ
የዓለም ዋንጫ ውድድሮች በሚካሄድባቸው የኳታር ስታዲየሞች ቢራን ጨምሮ ማንኛውም የአልኮል መጠጦች እንዳይሸጥ ታገደ። ፊፋ ውድድሩ ሊጀመር ሁለት ቀናት ሲቀረው ፖሊሲውንም ቀይሮ የአልኮል ሽያጭን አግዷል። የአልኮል ሽያጭ በሙስሊም አገራት ውስጥ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት ቢሆንም “በስታዲየሞች ውስጥ በተመረጡ ቦታዎች” እንዲቀርብ ተወስኖ ነበር። የዓለም ዋንጫ ውድድር ኅዳር 11/2015 ዓ.ም. የሚጀመር ሲሆን፣ በመክፈቻው ዕለትም አስተናጋጇ ኳታር ከኢኳዶር ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የፊፋ ዋነኛ ስፖንሰር የሆነው ቡድዌይዘር የተባለው የቢራ ጠማቂው ድርጅት ኤቢ ኢንቤቭ ስር ሲሆን በዓለም ዋንጫ ላይ ቢራ የመሸጥ ብቸኛ መብት ነበረው። “በአዘጋጇ አገር ባለሥልጣናት እና በፊፋ መካከል የተደረገውን ውይይት ተከትሎ የአልኮል መጠጦች ሽያጭ በፊፋ የደጋፊዎች ፌስቲቫል፣ በሌሎች የደጋፊዎች መዳረሻዎች እና ፍቃድ በተሰጣቸው ቦታዎች ላይ ብቻ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል። “የቢራ ሽያጭ በኳታር የዓለም ዋንጫ ስታዲየሞችም ሆነ ግቢው ውስጥ አይቻልም” ይላል የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል መግለጫ። ሆኖም በሁሉም የኳታር የዓለም ዋንጫ ስታዲየሞች ላይ የቢራ ጣዕም ያለውና አልኮል የሌለው በድ ዜሮ ሽያጭ እንደተለመደው ይከናወናል ተብሏል። መግለጫው አክሎም “የአስተናጋጇ አገር ባለሥልጣናት እና ፊፋ ስታዲየሞች እና አካባቢዎቻቸው ለሁሉም ደጋፊዎች አስደሳች እንዲሆኑ ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ” ብሏል። “የውድድሩ አዘጋጆች በኳታር በሚደረገው የዓለም ዋንጫ 2022 ሁሉንም ደጋፊዎች ባማከለ መልኩ ለምናደርጋቸው የጋራ ውሳኔዎች ኤቢ ኢንቤቭ ተረድቶ የሚያደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ያደንቃሉ” ብሏል። ቡድዌይዘር በበኩሉ በዛሬው ዕለት በትዊተር ገጹ “ይህ ትንሽ ያሳፍራል” የሚል መልዕክት ቢለጥፍም ወዲያውኑ ሰርዞታል። የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማኅበር (ኤፍኤስኤ) ለአብዛኞቹ ደጋፊዎች የቢራ ሽያጭ የተከለከለበትን ጊዜ ተችቷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c84pv22p40eo
amh
sports
ኡጋንዳ የጠፉት ኤርትራውያን ኳስ ተጫዋቾች ስጋት ላይ ነን አሉ
ኡጋንዳ ውስጥ የጠፉት አራት ኤርትራውያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ስጋት ላይ መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ። ባለፈው ወር በደቡብ ምዕራብ ኡጋንዳ ጂንጋ ከተማ ከሆቴላቸው የጠፉት የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን አባላት ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦብናልም ብለዋል። የእግር ኳስ ቡድኑን ትተው ኡጋንዳ ውስጥ በመጥፋታቸው ድረ ገጽ ላይ ማስፈራሪያዎች እየደረሷቸው እንደሆነ ተጫዋቾቹ ገልጸዋል። የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ከ20 ዓመት በታች እግር ኳስ ውድድር ግማሽ ፍጻሜ ላይ መሰናበቱ ይታወሳል። • አራት የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት ኡጋንዳ ውስጥ ጠፉ • ኢትዮጵያና ግብፅ በአሜሪካ ለውይይት እንጂ ለድርድር አይገናኙም ተባለ • የአማራ ክልል ረዳት ፖሊስ ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ በዋስትና እንዲለቀቁ ተወሰነ ተጫዋቾቹ ታፍነው ወደ ኤርትራ ሊወሰዱ እንደሚችሉ ስጋት እንደገባቸው ገልጸው፤ ከኡጋንዳ አስወጡን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። ከተጫዋቾቹ አንዱ፤ "ስለኛ ግድ የሚሰጠው አካል ካለ ከዚህ አገር እንዲያወጣን እንለምናለን። በየሳምንቱ ከቤት ቤት እየቀየርን፣ እየተሽሎኮሎክን እየኖርን ነው" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ተጫዋቾቹ ወደ ኤርትራ ከተመለሱ ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸውም ገልጸዋል። አሜሪካዊ ጠበቃቸው ኪምበርሊ ሞተሊ እንዳሉት፤ ተጫዋቾቹ ኡጋንዳ ውስጥ እየተፈለጉ እንደሆነ ሰምተዋል። በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተራድኦ ድርጅት (ዩኤንኤችሲአር) ጥገኝነት ቢጠይቁም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኙም ጠበቃዋ ተናግረዋል። ተጫዋቾቹ እንዳሉት፤ ሰዎች ስለሚያውቋቸውና ሊለይዋቸው ስለሚችሉ ከቦታ ቦታ በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻሉም። ሕይወታቸውን እየገፉ ያሉትም ከበጎ ፍቃደኞች በሚያገኙት እርዳታ ነው። ኤርትራ በተሳተፈችባቸው ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ኤርትራውያን ተጫዋቾች ሲጠፉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።
https://www.bbc.com/amharic/50249069
amh
sports
የሊቨርፑሉ ሳዲዮ ማኔ በቫይረሱ በመያዙ እራሱን ለይቶ እያቆየ ነው ተባለ
የሊቨርፑል እና የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋቹ ሳዲዮ ማኔ በኮሮናቫይረስ መያዙን ክለቡ አረጋገጠ። ይህንንም ተከትሎ ማኔ እራሱን ለይቶ እያቆየ እንደሚገኝ ክለቡ አስታውቋል። የማኔ ኮቪድ-19 ውጤት የተሰማው አዲሱ የሊቨርፑል ፈራሚው ቲአጎ አልካንትራ በኮሮናቫይረሱ መያዙ ይፋ ከተደረገ ከሶስት ቀናት በኋላ ነው። ማኔ "መለስተኛ የበሽታው ምልክት ከማሳየት ውጪ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል" ሲል ሊቨርፑል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ማኔ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ሊቨርፑል ከአርሰናል በነበራቸው የፕሪሚየር ሊግ ፍልሚያ ለክለቡ ተሰልፎ ጎልም አስቆጥሮ እንደነበረ ይታወሳል። ከሁለት ቀናት በፊት በተካሄደው እና ሊቨርፑል እና አርሰናል ባገናኘው የካራባኦ ካፕ ግጥሚያ ላይ ደግሞ ማኔ የሊቨርፑል ቡድን አባላት ውስጥ አልተካተተም ነበር። ማኔ የመንግሥት ምክረ ሃሳብን በመከተል ከበሽታው እስኪያገግም ድረስ እራሱን ለይቶ ይቆያል ሲል ሊቨርፑል የእግር ኳስ ክለብ አስታውቋል። በአዲሱ የውድድር ዘመን ለሊቨርፑል ሶስት ጊዜ ኳስን ከመረብ ማገናኘት የቻለው ሳዲዮ ማኔ በኮቪድ በመያዙ ምክንያት ቢያንስ አንድ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ያመልጠዋል ተብሏል። ሰኞ ዕለት ፕሪሚየር ሊጉ በሊጉ የሚጫወቱ 10 ተጫዋቾች በቫይረሱ ተይዘዋል በማለት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54400082
amh
sports
በዓለም ዋንጫ ታሪክ ታላቅ የተባሉት የውድድሩ አስር አሸናፊ አገራት እነማን ናቸው?
ታላቁ የእግር ኳስ መድረክ የዓለም ዋንጫ በአየራት ዓመቱ እየመጣ የማይረሳ ክስተት ትቶ ያልፋል። ነገር ግን አስካሁን በተካሄዱት ዓለም ዋንጫ ውድድሮች ታሪክ ታላቁ ድል የማነው? ጋሪ ሊኒከር፣ አለን ሺረር እና ሚካህ ሪካርድስ እነሆ አስሩ ድንቅ የዓለም ዋንጫ ድሎች እነዚህ ናቸው ይላሉ። አርጀንቲና ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ያነሳችው በፈረንጆቹ 1978 ነበር። የማራዶና ቡድን በወቅቱ ኔዘርላንድስን 3 ለ 1 በማሸነፍ ታላቁን የእግር ኳስ ዋንጫ ማንሳት የቻለው በማሪዮ ኬምፔስ እና በዳኒኤል ቤርቶኒ ጎሎች ነው። እንግሊዛዊው እግር ኳስ ተጫዋች ሊኒከር በወቅቱ ማሪዮ ኬምፔስ ብዙ ጎሎች አስቆጥሮ የወርቅ ጫማ ሲቀበል ያስታውሳል። አርጀንቲና ዋንጫውን ለማንሳት ከኔዘርላንድስ የገጠማት ፈተና ቀላል የሚባል አልነበረም። የወቅቱ የዓለም ዋንጫ ባለቤት ፈረንሳይ ክሮሺያን 4 ለ 2 አሸንፋ ነው ዋንጫውን ያነሳችው። ሩሲያ ባዘጋጀችው በዚህ የዓለም ዋንጫ በአሠልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ የተመራው ቡድን አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ፣ አልፎም በዙር 16 አርጀንቲናን 4 ለ 3 በመርታት ነው ለፍፃሜው የደረሰው። አለን ሺረር የ2018ቱ የፈረንሳይ ቡድን በጣም ጠንካራ እንደነበር የሚረሳ አይደለም፤ ዋንጫውን ማንሳትም ይገባቸው ነበር ይላል። ሚካህ ሪካርድስ በበኩሉ በፈረንሳይ ቡድን ውስጥ ከበረኛው አንስቶ እስከ አጥቂው መልካም ብቃት ላይ እንደነበሩ ያወሳል። ሊነከርም በሙያ አጋሮቹ ሐሳብ ይስማማል። ጣልያን በ1982 የዓለም ዋንጫን በማንሳት ከብራዚል ጋር እኩል ሦስት ጊዜ ዋንጫውን የግሏ ያደረገች ሆና ተመዝግባለች። ጣልያን በወቅቱ ስፔን ማድሪድ ላይ በተስተናገደው የፍፃሜ ጨዋታ ምዕራብ ጀርመንን 3 ለ 1 በመርታት ነው ባለድል የሆነችው። በጊዜው የጣልያን ግብ ጠባቂ እና አምበል የነበረው የ40 ዓመቱ ዲኖ ዞፍ በዕድሜ ትልቁ የዓለም ዋንጫ ተሰላፊ ሆኖ ታሪክ ሠርቷል። በ1982 የወርቅ ጫማውን የወሰደው ፓውሎ ሮሲ ነበር። ሺረር እንደሚያስታውሰው ጣልያን በጊዜው የመጀሪያዎቹን ሦስት ጨዋታዎች አቻ ከወጣች በኋላ አርጀንቲና እና ብራዚልን በመርታት ነው ለፍፃሜው የደረሰችው። ቲኪ-ቲካ በተሰኘው የእግር ኳስ ስልት የሚታወቀው የ2010 የስፔን ብሔራዊ ቡድን የተመልካቾችን ቀልብ የሳበ ነበር። ስፔን ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዋን በስዊትዘርላንድ ተሸንፋ ነው የጀመረችው። በፍፃሜው በተጨማሪ ሰዓት ኔዘርላንድስን 1 ለ 0 በመርታት የዋንጫ ባለድል የሆነችው ስፔን አንድሬስ ኢኒዬስታ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ነው። ሺረር እንደሚያስታውሰው ስፔን ከመጀመሪያ ጨዋታቸው በኋላ በጣም ልዩ ሆነው ነው የቀረቡት። ምዕራብ ጀመርን ከምሥራቁ ክፍል ጋር ከመዋሃዷ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያነሳችው የዓለም ዋንጫ ሲሆን፣ ከዚያ ቀድም ሁለት ጊዜ ዋንጫ አንስታለች። በፍፃሜው ከአርጀንቲና የገጠመችው ምዕራብ ጀርመን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በመርታት ነው ዋንጫውን ከፍ ያደረግችው። ምዕራብ ጀርመን ለዋንጫ ለመድረስ በነበረው የግማሽ ፍፃሜ ፍልሚያ እንግሊዝን በፍፁም ቅጣት ምት መርታቷን ሊኒከር ያስታውሳል። “ጨዋታውን እንግሊዝ ልታሸንፍ እንደምትችል ሳስብ ምናልባት ለፍፃሜ ደርሰንስ ቢሆን ኖሮ ብዬ አስባለሁ” ይላል ሊኒከር። ፈረንሳይ በ1998 ያዘጋጀችውን የዓለም ዋንጫ ራሷ በማንሳት ለመጀመሪያ ጊዜ ባለድል መሆኗን ብዙዎች ያስታውሱታል። በፍፃሜው ከተቆጠሩት ሦስት ጎሎች ሁለቱን ዚነዲን ዚዳን ነበር ማስቆጠር የቻለው። ፈረንሳይ በዚህ የዓለም ዋንጫ በአንድም ጨዋታ ሽንፈት አላጋጠማትም። ነገር ግን በሩብ ፍፃሜው እና በዙር 16 ከ90 ደቂቃ አልፎ ተጨማሪ 30 ደቂቃ እንዲሁም የፍፁም ቅጣት ምት አስፈልጓት ነበር። አርጀንቲና ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማንሳት የቻለችው በ1986 ነበር። በሜክሲኮ የተዘጋጀውን የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና ምዕራብ ጀርመንን 3 ለ 2 በመርታት ዋንጫውን አንስታለች። ይህ የዓለም ዋንጫ የማይዘነጋው ማራዶና ‘የእግዚያብሔር እጅ’ የተሰኘችውን ጎል በሩብ ፍፃሜው እንግሊዝ ላይ ያስቆጠረበት በመሆኑ ነው። ጋሪ ሊኒከር በወቅቱ ስድስት ጎሎች በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ አጠናቋል። ሊኒከር እንደሚያስታውሰው አርጀንቲና፤ ማራዶና ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ድንቅ የነበሩ ተጫዋቾች የነበሩበት ቡድን ይዛ ነው የመጣችው። የማራዶና ተዓምር ግን የሚረሳ አልነበረም ይላል ሊኒከር። ብራዚል አምስተኛ የዓለም ዋንጫዋን ያነሳችበት ዓመት ነበር 2002። በውድድሩ ሰባቱንም ጨዋታዎች በመርታት ዋንጫውን ያነሱት ብራዚሎች አሠልጣኝ የነበሩት ሉዊዝ ፊሊፔ ስኮላሪ ነበሩ። በአምበሉ ካፉ እየተመሩ አምስተኛ ዋንጫቸውን ያጣጣሙት ብራዚሎች በፍፃሜው ጀርመንን 2 ለምንም ረትተዋል። ጃፓን ባዘጋጀችው በዚህ የዓለም ዋንጫ ሮናልዲንሆ እንግሊዝ ላይ ያስቆጠራት የቅጣት ምት የምትታወስ ናት። እንግሊዝ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያነሳችው በ1966 ነበር። በወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ አልፍ ራምሴ፤ አምበሉ ደግሞ ቦቢ ሙር ነበሩ። በገዛ አገሯ የተጫወተችው እንግሊዝ በፍፃሜው ምዕራብ ጀርመንን 4 ለ 2 በመርታት ዋንጫውን ከፍ አድርጋለች። ሊኒከር፤ “ምናልባትም ምርጡ እንግሊዛዊ አጥቂ ነው ብዬ የማምነው ጂሚ ግሪቭስ በወቅቱ ድንቅ ነበር” ይላል። ብራዚል ሦስተኛ የዓለም ዋንጫውን ያነሳችው በአሠልጣኝ ካርሎስ አልቤርቶ እና በአምበሉ ፔሌ እየተመራች ነበር። የወቅቱ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ምናልባትም የምንም ጊዜም ታላቁ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ አስተያየቶች ይሰማሉ። ሁሉንም ጨዋታዎች አሸንፈው ለፍፃሜ የደረሱት ብራዚሎች ጣልያንን 4 ለ 1 በመርታት ዋንጫውን ከፍ አድርገዋል። በርካታ ያልተጠበቁ ነገሮች የታዩበት በኳታር የተስተናገደው የዓለም ዋንጫስ ስንተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጥ ይሆን?
https://www.bbc.com/amharic/articles/crgk9214rkko
amh
sports
ሎዛ አበራ በአንድ ጨዋታ ሰባት ግቦችን አስቆጠረች
ለማልታው ቢርኪርካራ እግር ኳስ ቡድን የምትጫወተው ኢትዮጵያዊቷ እግር ኳሰኛ ሎዛ አበራ ቡድኗ ትናንት ከሂበርኒያንስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሰባት ግቦችን በስሟ ማስመዝገብ ችላለች። ጨዋታው በቢርኪርካራ 17 ለምንም አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን ቡድኑ በ19 ነጥብ ሊጉን በአንደኛነት እየመራው ይገኛል። ሰባት ልጆች ላፈሩት እናት እና አባቷ አምስተኛ ልጅ የሆነችው ሎዛ ተወልዳ ያደገችው የከንባታ ጠምባሮ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ዱራሜ ነው። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' • የሆንግ ኮንግን የዘር መድልዎ የሚፋለሙ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ባደገችበት ሠፈር ካሉ ወንድ እኩዮቿ ጋር እየተጋፋች ኳስን ተጫውታለች። የሎዛ ፕሮፌሽናል ኳስ ተጫዋችነት ጉዞ የተጀመረው የከንባታ ዞንን ወክላ ስትጫወት ባይዋት መልማዮች አማካይነት ነው። ብዙም ሳትቆይ ሎዛ የሐዋሳ ሴቶች እግር ኳስ ቡድንን ተቀላቀለች። ከሐዋሳ ጋር ዋንጫ ባታነሳም እዚያ በቆየችባቸው ሁለት ተከታታይ ዓመታት የክለቡ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ነበረች። ሐዋሳን ከለቀቀች በኋላ በደደቢት አራት ዓመታትን ያሳለፈችው ሎዛ በሁሉም ዓመታት በተከታታይ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ነበረች።። ለሶስት ተከታታይ ዓመት ደግሞ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ሻምፒዮን ሆናለች ከደደቢት ጋር። በአሁኑ ሰአት በማልታ ደሴት ከፍተኛ ሊግ ላይ ለሚሳተፈው ቢርኪርካራ የምትጫወተው ሎዛ በትዊተር ገጿ ላይ ባሰፈረችው መልእክት ''ዛሬ በነበረን ጨዋታ በማልታ ሊግ ላይ በአንድ ጨዋታ ብቻ ሰባት ጎል በማስቆጠር ሌላ ታሪክ መፃፍ እና መስራት ስለቻልኩ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ላይ በአንድ ጨዋታ ብቻ ዘጠኝ ጎል አግብቼ ነበር'' ብላለች።
https://www.bbc.com/amharic/50739166
amh
sports
አራት የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት ኡጋንዳ ውስጥ ጠፉ
አራት የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት ኡጋንዳ ውስጥ መጥፋታቸው ታወቀ። ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ እግር ኳስ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ኡጋንዳ ካቀኑት ተጫዋቾች መካከል አራቱ ወደ ሆቴላቸው ያልተመለሱ ሲሆን፤ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ በተዘጋጀው ልምምድ ላይም አልተገኙም ተብሏል። • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ • የኤርትራ ወጣቶችና ምኞታቸው የቢቢሲ ትግርኛ ክፍል ከምንጮቹ ማረጋገጥ እንደቻለው ከሆነ አራቱም ተጫዋቾች በኡጋንዳ የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበዋል። የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ የሆኑት ኤማብል ሃቢማና የተጫዋቾቹን መጥፋት ማረጋገጣቸውን የኡጋንዳ ሚዲያዎች የዘገቡ ሲሆን፤ እስካሁን የት እንደሚገኙ የታወቀ ነገር የለም ተብሏል። ዋና ጸሃፊው ''አራቱም ተጫዋቾች ከማረፊያቸው ጠፍተዋል። ከክስተቱ በኋላ በሆቴሉ አካባቢ ያለውን ጥበቃ አጠናክረናል። ውድድሩ በጥሩ መንፈስ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ነው የምንፈልገው'' ማለታቸውን ደይሊ ሞኒተር የተባለው የኡጋንዳ ጋዜጣ ዘግቧል። የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን እስካሁን ጥሩ እየተጫወተ የነበረ ሲሆን፤ ዛሬ ከሰአት ላይ በግማሽ ፍጻሜ ከኬንያ አቻው ጋር ተጫውቶ 1 ለምንም ተሸንፏል። በሴካፋ ውድድር ስድስት ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ጎል አግቢነቱን እየመራ የሚገኘው ኤርትራዊው ማወል ተስፋይ በጉዳት ምክንያት በጨዋታው ላይ እንደማይሰለፍ ታውቋል። ምናልባትም ጥገኝነት ከጠየቁት አራት ተጫዋቾች መካከል ሊሆን እንደሚችልም ተገምቷል። የተጫዋቾቹ መጥፋት ብሔራዊ ቡድኑ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል እስካሁን ባይታወቅም በውድድሩ እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል። • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች ተጫዋቾቹ ሊጠፉ የቻሉት "ጉዳት አጋጥሞናል" ብለው በሆቴላቸው ከቀሩ በኋላ መሆኑንም ደይሊ ሞኒተር ዘግቧል። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ በቀሪ 14 ተጫዋቾች ውድድሩን የሚጨርሱ ሲሆን፤ የቀሩት ተጫዋቾች ግን በህምም ምክንያት ሊገኙ አልቻሉም ሲሉ ተደምጠዋል። በተመሳሳይ እ.አ.አ. በ2015 አሥር የዋና ብሔራዊ ቡድኑ አባላት ወደ ቦትስዋና ከሄዱ በኋላ አንመለስም ማለታቸው ይታወሳል። በ2013ትም ዘጠኝ የሚሆኑ የቡድኑ አባላትና አሰልጣኙም ጭምር ኬንያ ውስጥ ተሰውረው ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-49909587
amh
sports
ታይሮን ሚንግስ፡ ከመጠጥ ቀጅነት ወደ እንግሊዝ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን
መጠጥ ቀጅነት፤ ቤት አሻሻጭ፤ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን። ከ10 ዓመት በፊት ሳውዝሃምፕተኖች ቀጫጫ ነው በማለት ያሰናበቱት ወጣት ዛሬ [እሁድ ኅዳር 7] ደግሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ወክሎ ይጫወታል፤ ታይሮን ሚንግስ። ታድያ በእነዚህ 10 ዓመታት ብዙ አሳልፏል። ለጠጪዎች መጠጥ ቀድቷል። የ100 ፓውንድ መኪናውን እያሽከረከረ ሰዎች ከባንክ የቤት መሥሪያ ብድር እንዲወስዱ አስማምቷል። ኢፕስዊች ታውን ለተሰኘው ክለብ መጫወት ፈልጎ ሳይታመም አሞኞል ብሎ ከሥራ ቀርቷል በሚል ቅጣት ድርሶበታል። ከአየርላንድ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ጋር ቡጢ ቀረሽ ቁርሾ ነበረው። ሚንግስ አሁን ለሚጫወትበት አስቶን ቪላ የፈረመው በውሰት ከመጣበት ቦርንመዝ ነው። የ26 ዓመቱ ተከላካይ ዘንድሮ የተቀላቀለው ፕሪሚዬር ሊግ ብዙ የከበደው አይመስልም። 195 ሴንቲሜትር የሚረዝመው ተከላካዩ ሚንግስ በፕሪሚዬር ሊግ ብዙ ኳሶችን ከግብ ክልሉ በማራቅ [ክሊራንስ] ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የአካዳሚ ጓደኛው አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይን ነገሮች ተመቻችተውለት ታላላቅ ክለቦችን እየቀያየረ አሁን ሊቨርፑል ሲደርስ ሚንግስ ግን ብዙ ክለቦች አንፈልግህም እያሉ አባረውታል። ብሪስቶል ሮቨርስ አታዋጣንም ብለው ያባረሩት ሚንግስ ወደ ተማረበት ት/ቤት ተመልሶ መጫወት ጀመረ። በወቅቱ አንድ ባር ውስጥ መጠጥ ቀጅ ነበር። ቀን ቀን ደግሞ ለባንክ ቤት በኮሚሽን ተቀጥሮ የቤት ኪራይ ብድር ያስማማ ነበር። ታድያ በዚህ ጊዜ ያልተለየችው በደጉ ዘመን የሸመታት የ100 ፓውንድ [በአሁኑ ገበያ 3,700 ብር ገደማ] መኪናው ነች። ከዚያ ኢፕስዊች ታውን ለሙከራ ጊዜ ብሎ ወሰደው። ነገር ግን የወቅቱ የቡድኑ አሠልጣኝ ከነበሩት ሚክ ማካርቲ ጋር ሊስማማ አልቻለም። ቢሆንም ችሎታውን ያስተዋሉት አሠልጣኝ ለ18 ወራት አስፈረሙት። ይህ የሆነው ከዛሬ ስድስት ዓመታት በፊት ነበር። ፊርማውን ካኖረ ከስድስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢፕስዊች ተሰለፈ። ከዚያ በኋላ ባሉት 18 ጨዋታዎችም ይህን ያህል የመሰለፍ ዕድል አላገኘም። የወቅቱ የክለብ ጓደኞቹ 'ለምን አልተሰልፍኩም?' ብሎ ከአሠልጣኞች ጋር ይጋጭ ነበር ይሉታል። 2015 ላይ ለቦርንመዝ ፈረመ፤ በ8 ሚሊዮን ፓውንድ። ነገር ግን የመጀመሪያ ጨዋታውን ለማድረግ በገባ በ6 ደቂቃ ውስጥ ተጎድቶ ወጣ። ለ17 ወራትም ምንም ዓይነት ጨዋታ ማድረግ አልቻለም ነበር። ይሄኔ ነው ቦርንመዝ ለአስቶን ቪላ አሳልፈው በውሰት የሰጠው። ቪላ ፕሪሚዬር ሊጉን እንዲቀላቀል ሚንግስ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ክለቡ በቋሚነት እንዲያስፈርመውም ሆነ። ሚንግስ ለአንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን መጫወት እንደሚፈልግ እና ህልሙ እውን እንደሚሆንም በዙሪያው ላሉ ሰዎች ይነግራቸው ነበር። እነሆ ህልሙ እውን ሆኖ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተመርጧል። እንግሊዝ ዛሬ ምሽት ከኮሶቮ ጋር በምታደርገው ጨዋታም ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል። አልፈልግህም ያለው ሳውዝሃምፕተን በዚህ ዓመት በጣም ብዙ ጎል ተቆጥሮበታል። በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ 19ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት። ብዙዎች እንደው ሳውዝሃምፕተኖች ታይሮን ሚንግስን ቀጫጫ ነው ብለው ማሰናበታቸው ይቆጫቸው ይሆን? ሲሉ ይጠየቃሉ። ሚንግስ ግን ምንም ዓይነት ቁጭትም ቂምም የለበትም።
https://www.bbc.com/amharic/news-50450022
amh
sports
ጣሊያን በደረሰ የስለት ጥቃት የአርሰናሉ ተጫዋች ፓብሎ ማሪ ጉዳት ደረሰበት
በጣሊያኗ ሚላን ከተማ አቅራቢያ በደረሰ ጥቃት አንድ ሰው ሲገደል በትንሹ አምስት የሚሆኑት ቆስለዋል። አንዳንዶቹ ከፍተኛ ጉዳት እንዳስተናገዱ ፖሊስ አስታውቋል። ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል በውሰት ጣሊያን በመጫወት ላይ የሚገኘው ፓብሎ ማሪ ይገኝበታል። አሳጎ በሚባል ስፋራ በደረሰው ጉዳት አንድ የ30 ዓመት የሱፐር ማርኬት ገንዘብ ተቀባይ ሕይወቱ አልፏል። የ46 ዓመቱ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሏል። ፖሊስ ጉዳዩን ከሽብረተኝነት ጋር አይያያዝም ብሏል። ግለሰቡ የአእምሮ ጤና ችግር እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን ስለቱን ከሱፐርማርኬቱ መደርደሪያ ወስዶ መጠቀሙን ተናግሯል። ግለሰቡ በከተማዋ በሚገኘው ካርፉር ሱፐርማርኬት ጥቃቱን መፈጸሙ ተነግሯል። ጥቃቱ ሲፈጸም የደንገጡ ሰዎች ከአካባቢው እየጮኹ ሲሸሹ ታይተዋል። ብዙ ሰዎች ተጋግዘው ግለሰቡን ለመያዝ የቻሉ ሲሆን ፖሊስ ሲመጣም ማስረከባቸው ታውቋል። ጀርባው ላይ በስለት የተወጋው ስፔናዊው የ29 ዓመት ተከላካይ ማሪ ለሕይወቱ የሚያሰጋ ነገር አለመኖሩ ተጠቁሟል። ወኪሉ አርቱሮ ካናሌስ በበኩላቸው ወሳኝ የሰውነት ክፍሉ ላይ ጉዳት አለመድረሱን እና ራሱን እንደሚያውቅ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ማሪ ከባለቤቱ እና ወንድ ልጃቸው ጋር ለግብይት ወጥቶ እንደነበር በውስት የሚጫወትለት የሞንዛ ክልብ ሥራ አስፈጻሚ አድሪያኖ ጋሊያኒ ተናግረዋል። “ልጁን ተሽከርካሪ እቃ መያዣ ላይ አድርጎ ሚስቱ ደግሞ ከጎኑ ነበረች። ምንም ነገር አላየም ነበር።” ብለዋል ጋሊያኒ። “በሚያሳዝን ሁኔታ ጥቃት አድራሹ የሌላ ሰው አንገት ላይ ጥቃት ሲፈጽም ተመልክቷል። የተፈጸመውን ሁሉ በመመልከቱ በጣም የሚረበሽ ስሜት ነገር ነው” ሲሉ አክለዋል። ጀርባው ላይ የደረሰበት ጥቃት ጠለቅ ላይ ቁስል ቢፈጥርም ሕይወቱ አደጋ ላይ ካለመሆኑም በላይ  በፍጥነት እንደሚያገግምም ተስፋቸውን ገልጸዋል። ማሪ ለአርሰናል የፈረመው ከብራዚሉ ፍላሚንጎ እአአ በ2020 ነበር። 19 ጨዋታዎችን ለመድፈኞቹ ከተጫወተ በኋላ ለጣሊያኑ ሞንዛ ክለብ በውሰት ፈርሟል። “አሁን መስማቴ ነው። ኤዱ [የአርሴናል ቴክኒካል ዳይሬክተር] ከቤተሰቦቹ ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ አውቃለሁ። ” ሲል የአርሴናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግሯል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c13xrkp62yno
amh