text
stringlengths
0
2.31k
ጥበብ አውደ ርዕይ
የቤተሰብ ትጥቆች እና አኗኗር
ህፃን, እርግዝና እና ልጅ መውለድ
ትምህርት, ኪንደርጋርተን እና ትምህርት ቤት
የምግብ ምግብ ማብሰል
ጤና እና ጤናማ አመጋገብ
ለልጆች የቤት እንስሳት
የልጆች የልደት ቀን, የበዓላት ቀኖች እና በዓላት
አስቂኝ - አስቂኝ አባባሎችን የያዘ ምስል
የሚዲያ ዘይቤ - መጽሐፍት ከ ኢንተርኔት እና ስማርትፎን
ፋሽን እና ሞዴሎች
ትብብር እና ግንኙነት
ጉዞ, በዓላት እና ጂኦግራፊ
ጨዋታዎችና ስፖርቶች
ጤና, ውበት እና አመጋገብ
አፓርታማ, ቤት እና የአትክልት ስፍራ
ጥቅሶች, ንግግሮች, ጥበብ እና ሀረግ
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
በክረምት በበሽ ታመም - ለምን?
በክረምት ውስጥ መንዳት
የወላጅነት ፈተና - ወላጆች እና ቤተሰብ
ክትባት ድካም አደገኛ ነው
ለህፃናት ደስ የሚል መታጠቢያ
በዓለም ላይ ምርጡ ምግብ: ሜክሲኮ
ይህ ድር ጣቢያ ኩኪዎችን ለድር ጣቢያ መዳረሻ / የገበያ ትንተና ይጠቀማል. ድር ጣቢያውን መጠቀም በመቀጠል በዚህ አጠቃቀም ይስማማሉ. ስለ ኩኪዎች እና ለመቃወም ስለሚኖረው አማራጭ መረጃ
ለማውረድ ነፃ የሆኑ የማጣቀሻ ገጾች የግላዊነት ፖሊሲ በፌስቡክ የተጎላበተ
ተጨማሪ መረጃዎች እሺ
Amharic አማርኛ
ሳይንስ እና ኅብረተሰብ
የዶይቸ ቬለ 60ኛ ዓመት
የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል
የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል ሙሉ ይዘት
ኧልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ፅንፈኛ ቡድን ቅዳሜ፣ መስከረም 11 ቀን 2006 ዓም ኬንያ መዲና ናይሮቢ በሚገኝ አንድ ሰፊ የገበያ አዳራሽ ውስጥ በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት ቢያንስ 72 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። በገበያ አዳራሹ የነበረው የእገታ ርምጃ ከአራት ቀናት ቆይታ በኋላ መጠናቀን ታውቋል። ለመሆኑየኧልሸባብ ማንነት እና አነሳስ ምን ይመስላል?
ፅንፈኛ እንደሆነ እና ከኧል ቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው ይነገርለታል፤ የሶማሊያው ታጣቂ ቡድን ኧልሸባብ። ይህ ፅንፈኛ ቡድን በተለይ ባሳለፍነው ቅዳሜ ኬንያ መዲና ናይሮቢ ውስጥ ያደረሰው አሰቃቂ የሽብር ጥቃት የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ጥብቅ የሸሪዓ ሕግ በመላ ሶማሊያ ለመዘርጋት ከሚታገለው የኧልሸባብ አንዱ ክፍል አንስቶ ቡድኑ የተለያዩ ገጽታዎች እና የትግል ስልቶች አሉት። ዶ/ር መሀሪ ተድላ የፀጥታ ጥበቃ ጥናት ተቋም ባልደረባ ናቸው። የኧል ሸባብ ሌላኛው ገጽታ ምን እንደሚመስል እንዲህ ይገልፃሉ።
የኧልሸባብ አነሳስ በሶማሊያ። ከሁለት ዓስርት ዓመት አንስቶ የእርስ በእርስ ጦርነት ባልተለያት ሶማሊያ እጎ አ በ2006 «በሶማሊያ የሸሪአ ፍርድ ቤቶች ህብረት» የተሰኘው ቡድን የሀገሪቱ ዋና ከተማ ሞቃዲሾን ይቆጣጠራል። መዲናዋን ብቻም አይደለም የመንግሥት አስተዳደሩንም በመያዝ ይህ አክራሪ ቡድን በመላ ሶማሊያ የሸሪዓ ሕግ መዘርጋቱን ያውጃል። ከሶማሊያ የሸሪአ ፍርድ ቤቶች ህብረት ውስጥ አንድ ጽንፈኛ ቡድንም የኢትዮጵያ አካል የሆነውን የኦጋዴን ክፍል እንደሚወር ይዝታል። ብዙም ሳይቆይ የኢትዮጵያ ጦር በዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ እየተደረገለት ወደ ሶማሊያ ድንበር ይዘልቃል።
የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ከ18 ዓመታት ቀደም ብሎ በተመድ ጥላ ስር በመሆን ሶማሊያ መግባቱን እንደጣልቃ ገብነት ይመለከቱ የነበሩ ሶማሊያውያን የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ መዝለቅን ሁለተኛ ወረራ ሲሉ እንዲመለከቱት አድርጓል። በእዚህ መሀከል ነበር ኧል ሸባብ የተሰኘው አክራሪ ቡድን ተጠናክሮ ሊወጣ የቻለው። በጀርመኑ ማክስ ፕላንክ ተቋም ውስጥ ስለ ሶማሊያ ለ12 ዓመታት ያጠኑት ማርኩስ ሆህነ።
«በሶማሊያ ሽብርን የመዋጋቱ ተግባር በመሠረቱ ሽብርን አስፋፍቷል። በእርግጥ ስር የሰደደው ቀደም ብሎ ነው። በአሜሪካኖች አለያም በኢትዮጵያኖች የተተከለ አይደለም። ሆኖም እነዚህ አነስተኛ፣ ፅንፈኛ ቡድኖች ማቆጥቆጥ የመጀመራቸው ነገር በሶማሊያ አቅጣጫውን ከሳተው ሽብርን የመዋጋት ተግባር ጋር ይያያዛል። »
ኧል ሸባብ ከሶሥት ዓመታት በፊት ኡጋንዳ ውስጥ የሽብር ጥቃት ፈፅሞ ቢያንስ 76 ሰዎችን መግደሉ ይታወሳል። ልክ እንደኬንያ ሁሉ ዩጋንዳም ጦሯን ወደ ሶማሊያ መላኳ ይታወቃል። ኧልሸባብ ቀደም ሲል የሰነዘረውን ዛቻ በኬንያ ምድር ተግባራዊ አድርጎ በርካታ ሠላማዊ ሰዎችን ገድሏል። የተለያዩ የዜና ምንጮች የሟቾቹ ቁጥር ቢያንስ 72 ነው ሲሉ እየዘገቡ ነው።
ኧልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ፅንፈኛ ቡድን አሁንም ድረስ በተለይ በደቡባዊ ሶማሊያ አንዳንድ ክፍሎች በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
በኢትዮጵያ እና ሱዳን የወሰን ድንበሮች የሚገኙ የኢትዮጵያ የእርሻ መሬቶች ፓርላማ ተወያይቶ ሳያጸድቅ ስልጣን ላይ በነበሩ የኢሃዲግ አመራር ፊርማ ለሱዳን ተላልፈው መሰጠታቸው ስህተት እንደነበር አንድ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሃላፊ አስታወቁ ።
የአፍሪቃ፣ የከራይብ እና የፓሲፊክ አካባቢ አገሮች እና የአውሮጳ ህብረት የድህረ ኮቶኑ የትብብር ስምምነት ላይ ድርድር ጀመሩ። ህብረቱ ስምምነቱን የተፈራረመው 79 የአፍሪቃ፣ የከራይብና የፓሲፊክ አካባቢ አገሮች የሚጠቃለሉበት በምህፃሩ ከኤ ሲ ፒ ቡድን ጋር ነው።
© 2018 Deutsche Welle _ የግለሰቦች/ድርጅቶች ሰነድ ጥበቃ _ Legal notice _ አድራሻ _ ለሞባይል የተዘጋጀ
Amharic አማርኛ
ሳይንስ እና ኅብረተሰብ
የዶይቸ ቬለ 60ኛ ዓመት
የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል
የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል ሙሉ ይዘት
በደቡባዊው አልጀሪያ አሜናስ እተባለችው ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ጣቢያ ፣ አክራሪ እስላማውያን ታጣቂዎች፤ ይዘዋቸው የነበሩ 30 ታጋቾች ፣ 7 የውጭ አገር ተወላጆች ጭምር ፤ ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ተነገረ። ይህ የሆነው፣ የአልጀሪያ
መንግሥት ልዩ ግብረ ኃይል ፤ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ በወሰደው እርምጃ ሳቢያ ነው። 4 ሰዎች አሁንም በአጋቾቹ ቁጥጥር ሥር ናቸው። 14 ጃፓናውያንና 8 የኖርዌይ ተወላጆች፤ የደረሱበት አልታወቀም ነው የተባለው።
ከተገደሉት 30 ሰዎች ሌላ፤ በታጣቂ እስላማውያን ስላተገቱት ሰዎች አኀዝና ስለተለቀቁትም ሰዎች ብዛት በየሰዓቱም ሆነ ደቂቃው፣ ከአየቅጣጫው የተለያዩ ዜናዎች ይነገሩ እንጂ፤ አሜናስ አጠገብ በሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ጣቢያ በትክክልና በዝርዝር ስላጋጠመው ሁኔታ የቀረበ ዘገባ የለም። የአልጀሪያ ልዩ ግብረ ኃይል 650 ታጋቾችን አስለቅቄአለሁ ነው የሚለው። ከአነዚህ ውስጥ 70 ገደማ የሚሆኑት የውC ሃገራት ተወላጆች መሆናቸውን አስታውቋል። ከተገደሉት ቢያንስ 7 የውጫ ሀገራት ተወላጅ ታጋቾች መካከል፣ 2 ጃፓናውያን፤ 2 የብሪታንያ ተወላጆች፤ እንዲሁም አንድ የፈረንሳይ ዜጋ እንደሚገኙበት ሮይተርስ ዜና አገልግሎት ዛሬ ረፋድ ላይ ጠቅሶ ነበር። የአልጀሪያ ዜጎች የሆኑ 8 ታጋቾች ፤ በአጋቾቹ እጅ ተገድለዋል። ከአጋቾቹም ቢያንስ 11ዱ በአልጀሪያ ልዩ ግብረ ኃይል ነው የተገደሉት። ከእገታው ስላመለጡ በዛ ያሉ ሰዎች ዜግነት ገና የታወቀ ጉዳይ የለም። ከአልጀሪያ በጎ ዜና እንዳልተሰማ የተናገሩት የብሪታንያው ጠ/ሚንስትር ዴቪድ ኬምረን---
«የአልጀሪያ ጠ/ሚንስትር እንዳረጋገጡልኝ፤ የተፈጠረውን ቀውስ ለማስወገድ ማንኛውም እርምጃ ይወሰዳል። አደጋ ያንዣበበባቸው የብሪታንያ ዜጎች ቁጥራቸው ከ 30 በታች ነው። በመጀመሪያ አኀዙ ከዚህ የላቀ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት ነበረን።»
ጃፓን፣ ስለሁኔታው ምንም ሳይነገራት የአልጀሪያ ጦር ኃይል እርምጃ መውሰዱ አሳዝኗታል። ኖርዌይም ፤ የሁኔታውን አስቸጋሪነትም ሆነ ውስብስብነት ብትገነዘብም ሳይነገራት በተወሰደው እርምጃ ሳቢያ ቅር ሳትሰኝ አልቀረችም። ከኦስሎ፣ የኖርዌይ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ እንዲህ ብለዋል።
«ውጭ ጉዳይ ሚንስትራችን እንዳሉት ኖርዌይም በበኩሏ ወታደራዊ እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ለምክክር ጥሪ ቢቀርብላት ነበረ የምትመርጠው። ያም ሆኖ ጨምረው እንዳብራሩት፤ የአልጀሪያ መንግሥት፤ በወሰደው እርምጃ ላይ ትክክል አልነበረም ብሎ አቋም ለመውሰድ ጊዜው አይፈቅድም። እርምጃው በተወሰደበት ቅጽበት፤ የነበረውን ሁኔታ አጣርቶ ማወቅ ያስፈልጋልና! መገምገም ያለበት፤ ታጋቾቹን ሁሉ የማስለቀቁ ተግባር ከተደመደመ በኋላ ነው።»
«የደም ባታሊዮን» እያለ ራሱን የሚጠራው የታጣቂ እስላማውያን ቡድን፤ አልጀሪያ ውስጥ የተጠቀሰውን እርምጃ የወሰደው፤ ፈረንሳይ ወደ ማሊ ጦር በማዝመት በአየርም በየብስም ውስጥ የማጥቃት እርምጃ መውሰዷን በመቃወም መሆኑን አስታውቋል። በሰሐራ ምድረበዳ ከምዕራብ እስከምሥራቅ የተለያዩ አገሮች ዜጎች የሆኑ ታጣቂዎች ተባብረው መነሳታቸውን ፤ የአፍሪቃና የምዕራባውያን መንግሥታት ሲያስገነዝቡ መቆየታቸው አይታበልም። ከተገደሉት 11 አጋቾች መካከል፤ አልጀሪያውያኑ 2 ብቻ ናቸው ፤ ከተገደሉት መካከል አንደኛው የአጥቂው ቡድን መሪ ነበር ተብሏል። ከተገደሉት አጋቾች መካከል፤ 3 ቱ ግብጻውያን፤ 2ቱ ቱኒሲያውያን፣ 2ቱ ሊቢያውያን፤ አንድ የማሊ፤ እንዲሁም አንድ የፈረንሳይ ዜጋ እንደነበሩ ታውቋል። ከአልጀርስ ዘግየት ብሎ በደረሰን ዜና መሠረት ከ 30 በላይ ከሚሆኑት ታጣቂዎች 18ቱ ተገድለዋል። በደቡብ አልጀሪያ የተፈጸመውን ድርጊት አስመልክተው የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ዖላንድ፣
«ሰዎችን አግቶ በቁጥጥር ሥር የማድረጉ እርምጃ የሚያሳየው፤ በማሊ ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑ በይበልጥ ትክክል እንደነበረ ማለታቸው ተጠቅሷል።»
© 2018 Deutsche Welle _ የግለሰቦች/ድርጅቶች ሰነድ ጥበቃ _ Legal notice _ አድራሻ _ ለሞባይል የተዘጋጀ
የተሠረዘው የቴዲ አፍሮ አልበም ምረቃና ባለ መስቀሉ ቢራ _ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት _ DW _ 08.09.2017
ተጨማሪ መረጃዎች እሺ
Amharic አማርኛ
ሳይንስ እና ኅብረተሰብ
የዶይቸ ቬለ 60ኛ ዓመት
የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል
የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል ሙሉ ይዘት
ከረዥም ውጣ ውረድ በኋላ በሒልተን ሆቴል ሊመረቅ ነበር የተባለለት የቴዲ አፍሮ «ኢትዮጵያ» አልበም ምረቃ መሰረዝ መነጋገሪያ ሆኗል። አንገቱ ላይ መስቀል ታስሮለት በቪዲዮ የማንቀሳቀስ ስልት የሚውረገረገው የራያ ቢራ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ በበኩሉ ከቁጣ አልፎ ብዙዎችን በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች እጅግ አነታርኳል።
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
በተደጋጋሚ ጊዜያት አንዴ በመንግሥት ሌላ ጊዜ ደግሞ አርቲስቱን በሚቃወሙ ወገኖች አስተባባሪነት ያቀዳቸው የሙዚቃ ድግሶች ተሰርዘውበታል፤ አሁን ደግሞ የሙዚቃ አልበሙ ምረቃ። አርቲስት ቴዲ አፍሮ፤ ባሳለፍነው እሁድ በሂልተን ሆቴል ሊያኪያሂድ የነበረው «ኢትዮጵያ» የተሰኘው የአልበም ምርቃት መሰረዙ በርካታ ደጋፊዎቹን አስቆጥቷል። ራያ ቢራ በቴሌቪዥን ያቀረበው ማስታወቂያ አንገታቸው ላይ መስቀል የተንጠለጠለባቸው ሦስት የቢራ ጠርሙሶች በምስል ቅንብር ሲወዛወዙ ይታያል። የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች አብይ መነጋገሪያ ሆኗል። በበርማ የሰላማዊ ሰዎች ጭፍጨፋ እና ግፍ ሰሚ አላገኘም የሚሉ አስተያየቶችም ተበራክተዋል። ጣና ሐይቅን የወረረው እምቦጭ አረምን ለማጥፋት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ያሳዩት እልህና ርብርብ ብዙዎችን አስደምሟል።
ነሐሴ 28 ቀን፤ 2009 ዓ.ም. አንድ ሺህ ግድም አድናቂዎች ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በጉጉት የሚጥብቁት አንዳች ነገር ነበር። አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ለአድናቂዎቹ ያቀረበውና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈለት፤ በዓለም የአልበም ሽያጭ በአንድ ዘርፍም ለሳምንታት አንደኛ ሆኖ የዘለቀለት «ኢትዮጵያ» የተሰኘው የሙዚቃ ዓልበሙ የሚመረቅበት ቀን ነበር። አርቲስቱ እሁድ ከሰአት 11 ሰአት ከሩብ አካባቢ በፌስቡክ ይፋዊ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሩ «በደመቀ ሁኔታ» ሊካሂድ የነበረው የ«ኢትዮጵያ» አልበም ምርቃት መሰረዙን የገለጠው በ«ከፍተኛ ሀዘን» ነበር።
ቴዲ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ዝግጅቱ ሳይጀመር የተቋረጠው በጸጥታ ኃይላት ትእዛዝ መሆኑን ጽፏል። «ይህን ዝግጅት ለማካሄድ ፍቃድ መጠየቅ ማለት አንድ ዜጋ የሠርግ ወይም የልደት በዓሉን ለማክበር ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ከመንግሥት ፍቃድ የመጠየቅን ያህል ሥራ ላይ ውሎ የማያውቅ አሠራር» ነው ሲልም ገልጧል። ቀጠል አድርጎም «ከአገሪቱ የሕግ አካሄድ ጋር የሚጣረስ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ለጊዜውም ቢሆን ሁኔታውን ለማስቀጠል ባደረግነው ሙከራ ምንም አይነት የሙዚቃ መሣሪያና ለዝግጅቱ አስፈላጊው የሆኑ ግብዕቶች በሙሉ ወደ ሆቴሉ እንዳይገቡና ከመኪና እንዳይወርዱ መለዮ በለበሱ የመንግስት ታጣቂዎች በመከልከላችን ያለውን ሁኔታ ለመቀበል ተገደናል» ሲልም ማን እንደከለከላቸው ይፋ አድርጓል
ጥሪ የተደረገላቸው አድናቂዎቹንም ለተፈጠረው ነገር ይቅርታ ጠይቋል። «ክቡራን እንግዶቻችን እና ለመላው ውድ አድናቂዎቻችን ይህን ይቅርታ ያዘለ መልዕክታችንን ስናስተላልፍ መጪው አዲስ አመት የሰላምና የፍቅር ከምንም በላይ ደግሞ መላው የኢትዮጵያ ልጆች በዕኩል ዓይን የሚታዩበት የፍትሕ ዘመን እንዲሆን በመመኝት ነው» ያለው ቴዲ አፍሮ ጽሑፉን የቋጨው «ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፤ ፍቅር ያሸንፋል» በሚል ማሰሪያ ነው።
ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ በፌስቡክ ገጹ «የተወዳጁ ቴዲ አፍሮ ጥፋቱ ምንድን ነው ?» ሲል ጠይቋል። «አስራ ሰባት መርፌ ብሎ በመዝፈኑ፣ አስራ ሰባት አመት ሊቀጡት ወሰኑ። ግና እሱ ሆነ እንጅ አስራ ሰባት ፅኑ። ቴዲ አፍሮ» ሲል በትዊተር ገጹ የጻፈው ደግሞ ዘመናት ነው። ዓሚር ቢን ያስር «ቴዲ አፍሮ ዝግጅቱን እንዳያቀርብ በሚያደርጉ ኃይሎች እና በእነ ጎሳይ ላይ Boycott በሚጠሩ ኃይሎች መካከል ያለውን ልዩነት የሚያስረዳኝ ይኖር ይሆን?» ብሏል።
«ቴዲ አፍሮ ብቻ አይደለም ሙዚቃውን እንዳያቀርብ የተከለከለው። ሌሎችም በጣም ብዙ አሉ" የሚባል መጃጃል ምንድነው? በሱ ብቻ የመጣ አይደለም ስለዚህ ችግር የለውም ነው?» ሲል አውራሪስ በትዊተር ገጹ ጠይቋል። አሉላ ሰለሞን ደግሞ፦ «ኢትዮጵያን ስለምወድ በደል ደረሰብኝ" የምትል አዲስ ከረሜላ ገበያ ላይ ውላለች» ሲል በፌስ ቡክ ጽፏል።
አቤል ሺፈራው፦ «ቴዲ አፍሮ በሁለት ዘረኞች መከራውን የሚያየው ኢትዮጵያን ስላለ ነው። ቴዲ አፍሮን መጠበቅ የኢትዮጵያዊነት ግዴታችን ነው» ብሏል። ደረጀ ምንዳዬ፦ «የፍቅር ቀን መቼ ነበር? የፍቅር ቀን ፍቅር ያሸንፋል!ኢትዮጵያዊነት ያበራል!ቴዲ አፍሮ ከማማው፣ ከሰገነቱ ከከፍታው ተሰይሞ ኢትዮጵያዊነትን ይዘምራል። ይብላኝ ለበቀለኞች ይብላኝላቸው ለክፉዎች!» የሚል ጽሑፉን አስነብቧል። የሁለቱም ጽሑፍ በፌስቡክ ነው የቀረበው። ዮና ብር በትዊተር ገጹ፦ «ተራ ካድሬ ከሕገ መንግሥት በላይ በሚያዝባት አገር ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ብቻውን ታግሎ አሸነፏል» ብሏል። ጋዜጠኛ ቆንጂት ተሾመ፦ «ከፍታው የአንተ ነው ቴዲ አፍሮ! ቢሰረዝ ባይሰረዝ...በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ ንግስናህ ጽኑ ነው! ምንም የሚሰበር መንፈስ የለም!» ስትል ቴዲ አፍሮ እና ኢትዮጵያ በሚሉ ቃላት አስተያየቷን ቋጭታለች።
ታወቂያ ነበር። «ርሑስ በዓል አሸንዳ» በሚል በትግሪኛ ቋንቋ የቀረበው የቴሌቪዥን ማስታወቂያ በርካቶችን ያበሳጨው መስቀል የተንጠለጠለባቸው ሦስት የቢራ ጠርሙሶችን በማስታወቂያነት በመጠቀሙ ነበር።
ኢንትዮጵያን ዲጄ የተሰኘው በርካታ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ፦ «ምነው ራያ ቢራ? መስቀል በቢራ ማንጠልጠል ምን አይነት ንቀት ነው?» በሚል አጠር ያለ ዐረፍተ ነገር ከተንቀሳቃሽ ምስል ጋር አያይዟል።
ተንቀሳቃሽ ምስሉ እንደ ሰው አንገታቸውን የሚያረገርጉ ሦስት ቢራዎች ይታዩበታል። ቢራዎቹ የፎቶግራፍ ምስልን በማንቀሳቀስ ስልት ማለትም (animation) የተሠሩ ናቸው። ወገባቸው ላይ የተረዘረዘ የቅጠል ዝንጣፊ በአጭሩ አገልድመዋል። ሲወዛወዙ ብትን ዘርጋ የሚል ዝንጣፊ። የቢራዎቹ አናት ላይ ከቆርኪው በቀለማት የተገመደ ቀጭን ሻሽ መሳይ ነገር አስረዋል። አወዛጋቢው የሆነዉ ነገር -እንደ ሰው አንገት በሚቅለሰለሰው የቢራው አንገት ላይ የታሰረው መስቀል ነው።
«ቢራ ላይ መስቀል አጥልቆ ፕሮሞሽን የመስራቱ ሐሳብ ስንት ቢራ ቀምቅመው ነው የመጣላቻው?» ሲል የጻፈው አዲስ አብነት ነው። አየለ አዲስ እዛው ፌስቡክ ላይ፦ «ራያ ቢራ ላይ መስቀል መኖሩ ምንም አይገርምም፤ ቢራ ሃይማኖትን መሰረት አድርጎ አልተጠመቀም፤ ቢጠመቅም እየጠጣ ያለው ክርስቲያኑ ነው» ብሏል።
ሳባዊ ደሳለኝ በበኩሉ፦ «ከ90 ዓመት በላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚል ስያሜ ያለው ቢራ ያለምንም ጥያቄ ሲጠጣ ኖሮ ምንም ያላለው ሰው( እኔን ጨምሮ) አንድ የማስታወቅያ ስህተት ሲያይ ዓይኑ ቀልቶ ራያ ቢራ ላይ ይዘምታል!» ሲል ተችቷል። «ራያ ቢራ መስቀል በቢራ መጠቀሙ ተሳስተዋል ብየ አምናለው!» ያለው ሳባዊ «የራያ ቢራ ስህተት በአንድ ደቂቃ በማይሞላ ማስታወቂያ የሚስተካከል ነው!» ሲልም አክሏል።
ቴዲ ማይጨው፦ «ራያ ቢራ ውስጤ ነው» ሲል ፌስቡክ ላይ ጽፏል በአጭሩ። «የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ሲገርመን አሁን ደግሞ ራያ ቢራ የፈጣሪ ያለኽ» ያለችው ሚጣ ናት። የራያ ቢራ ቁጣ ለቀሰቀሰው ማስታወቂያ ማስተባበያ አልተሰጠም የሚሉ ሰዎች አሁንም እንደተቆጡ ነው። በአንጻሩ የራያ ቢራን «አትጠጡ» የሚል ዘመቻም መጀመሩ ተሰምቷል።
ጪቅሳው ወርቁ፦ «ፍትህ በርማ ውስጥ ለሚገኙ ሙስሊሞች» ሲል ጽፏል። ሙስሊም ለሙስሊም በፌስ ቡክ ገጹ፦ «በርማ የሩሃኒንግ ሙስሊሞች ስቃይ በሰው አይደለም በእንስሳትም ላይ ሊፈፀም የማይገባ እና ይህንን ለመቃወም ደግሞ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው» ብሏል። «ሙስሊም አይደለሁም። ሆኖም ግን በርማ በሚባል አገር የሰው ልጅ የመጨረሻውን የጭካኔ ጣራ በነካ አገዳደል ሲገደል እያየሁ ዝም አልልም» ያለው ደግሞ የቅዱሳን ኅብረት ነው።
ብዙኃን የቡድሒዝም እምነት ተከታዮች በሚኖሩባት ሚያንማር ወይንም በርማ፤ በመንግስት ጦር የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎች ሕጻናትን ጨምሮ የሚታይባቸው ምስሎች በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ተሰራጭተዋል። በሚያንማሩ ኹከት ከሮሂንግያ ሙስሊሞች በተጨማሪ የሒንዱ እና የቡድሂዝም እምነት ተከታዮችም መገደላቸው ተዘግቧል። የበርማ መንግሥት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 430 ግድም ይደርሳል ሲል ቀደም ብሎ አስታውቆ ነበር። ቁጥሩ በሌላ ወገን አልተጣራም። ግድያው አሁንም አልተቋረጠም። የበርማ መንግሥት ጦርን ግፍና በደል በመፍራት ደግሞ ወደ ባንግላዴሽ የተሰደዱት የሮሒንግያ ሙስሊሞች ቁጥር ከ164ሺ መብለጡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል። ይኽም ዜና በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተሠራጭቷል።
ቁልፍ ቃላት ኢትዮጵያ, ቴዲ አፍሮ, አልበም ምረቃ, ራያ ቢራ, መስቀል
© 2018 Deutsche Welle _ የግለሰቦች/ድርጅቶች ሰነድ ጥበቃ _ Legal notice _ አድራሻ _ ለሞባይል የተዘጋጀ
ተጨማሪ መረጃዎች እሺ
Amharic አማርኛ
ሳይንስ እና ኅብረተሰብ
የዶይቸ ቬለ 60ኛ ዓመት
የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል
የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል ሙሉ ይዘት
ይዘት / ኢትዮጵያ
በጎንደር ቦምብ ፍንዳታ 1 ሰው ሞቶ 18 ቆስለዋል
በጎንደር ከተማ በአንድ ሆቴል ላይ ትላንት ምሽት ጥር ሁለት በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ አንድ ሰው ሞቶ 18 ሰዎች መቁሰላቸውን የአማራ ክልል አስታውቋል፡፡ ጥቃቱን ያደረሱት ሰዎች ማንነት አለመታወቁን የክልሉ ኮሚዩኔኬሽን ጉዳዩች ኃላፊ ተናግረዋል፡፡ የዓይን እማኞች በበኩላቸው ሟቾቹ ሁለት መሆናቸውን 10 ሰዎችም በጽኑ መቁሰላቸውን ይገልጻሉ፡፡
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
ፍንዳታው የደረሰው በማራኪ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 18 በሚገኘው ኢንታሶል አነስተኛ ሆቴል ነበር፡፡ ሆቴሉ ትላንት ምሽቱን እንደወትሮው ደንበኞቹን እያስተናገደ በነበረበት ጊዜ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ፍንዳታ መሰማቱን የዓይን እማኞች ይናገራሉ፡፡ በፍንዳታው ሁለት ሰዎች መሞታቸውን እና 10 በጸና መቁሰላቸውን እማኞቹ ተናግረዋል፡፡ ከፍተኛ አደጋ ከደረሳባቸው ውስጥ ሁለቱ በሆቴሉ ውስጥ በአስተናጋጅነት የሚያገለግሉ እንደነበሩ ይገልጻሉ፡፡
“አካባቢው ወደ [ጎንደር መምህራን] ኮሌጅ አካባቢ ነው፡፡ ወደመሰጊድ ታክሲ የሚያዝበት አካባቢ ነው፡፡ ማታ ነበር፡፡ ፋሲል ከነማ ጨዋታ ነበረው በዚያ ላይ በዓል ስለነበር በርካታ ሰው በሚንቀሳቀስበት አካባቢ ነው ይህ አደጋ የደረሰው፡፡ ሁለት ሰዎች ሞተዋል ነው የተባለው፡፡ አስር የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል፣ ከባድ አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ ወደ ሆስፒታል ነው የተወሰዱት የተባለው፡፡ ሆስፒታል መግባት እይቻልም፡፡ እንደዚህ ዓይነት አደጋ ሲደርስ ጎንደር አንዳንዴ ከበድ ይላል፡፡ [ወደሆስፒታል] መግባት የማይቻልበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ የህዝብ ሆስፒታል ቢሆንም ብዙ ጊዜ ለመጠየቅም፣ ለመግባትም የሚከብድበት ሁኔታ ይፈጠራል” ይላሉ የአካባቢው ነዋሪ፡፡
የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ቦምብ ፈንድቶ ጉዳት መድረሱን ለዶይቸ ቨለ አረጋግጠዋል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በተመለከተ ግን ከዓይን እማኞች ይለያሉ፡፡ አጠቃላይ ቁስለኞችን ቁጥር ከፍ ያደርጉታል፡፡
“ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ ሰዎች በሚዝናኑበት ሆቴል ቦምብ ተጥሎ፣ ፈንድቶ የአንድ ሰው ህይወት አጥፍቷል፡፡ አስራ ስምንት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ከእነዚህ ውስት የሶስቱ ከባድ ነው፡፡ የአስራ አምስቱ ቀላል የአካል ጉዳት ነው፡፡ የሚታከሙት በጎንደር ሆስፒታል በህክምና ላይ ናቸው፡፡ መለስተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና የሚደረግላቸው ተደርጎላቸው ወደየቤተቦቻቸውና መኖሪያዎቻቸው ተመልሰዋል” ይላሉ ኃላፊው፡፡