id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-51207494
https://www.bbc.com/amharic/news-51207494
የኢቢሲ ጋዜጠኞች ለምን ይጠፋሉ?
በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ከ4 ያላነሱ ነባር ጋዜጠኞች ባለፉት ጥቂት ወራት በተለያዩ አጋጣሚዎች ባቀኑባቸው ምዕራባውያን ሃገራት ጥገኝነት ጠይቀዋል።
ከእነዚህም መካከል አንዱ ለ9 ዓመታት በኢቢሲ ከሪፖርተርነት እስከ ዜና ክፍል ምክትል ዋና አዘጋጅነት ያገለገለው ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁ ይገኝበታል። ጋዜጠኛው ቢላል በዚህ ሳምንት ሰኞ የተካሄደውን የዩኬ-አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ለመዘገብ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ከሚመራ ልዑክ ጋር ወደ ለንደን የተጓዘ ሲሆን ጥገኝነት መጠየቁን ለቢቢሲ አረጋግጧል። • የኢቢሲ የትግርኛ ክፍል ሠራተኞች በተቋሙ አስተዳደር ጫና ይደርስብናል አሉ ከቢላል በተጨማሪ ሌሎች ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኢቢሲ ነባር ጋዜጠኞች በተለያዩ አጋጣሚዎች በሄዱባቸው ምዕራባውያን ሃገራት ጥገኝነት ለመጠየቅ የተገደዱት ከጋዜጠኝነት ሥራቸው ጋር በተያያዘ በሚደርሱባቸው ጫናዎች እንደሆነ ተናግረዋል። "ጋዜጠኞች የኤዲቶሪያል ነጻነት የላቸውም" ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት እና በውጪ አገራት የሚገኙት የቀድሞ የኢቢሲ ጋዜጠኞች ለቢቢሲ በላኩት የጽሑፍ መልዕክት በጋዜጠኝነት ሥራቸው የኤዲቶሪያ ነጻነት እንደሌላቸው ተናግረዋል። "ጉዳዮች እየተመረጡ ነው የሚዘገቡት" ያሉት ጋዜጠኞቹ እንደምሳሌ፤ በጅግጅጋ አብያት ክርስቲያናት ሲቀጣሉ በፍጥነት ሳይዘገብ መቆየቱን፣ የሃይማኖት ተቋማት መግለጫዎች ለምሳሌ ሲኖዶሱ የኦሮሚያ ቤተክነት መቋቋምን አወግዛለሁ ማለቱ አለመዘገቡ፣ በሞጣ የተፈፀመው ጥቃት ሰፊ ሽፋን ሳይሰጠው እንደቀረ፣ የትግራይ ክልል እና የህውሃት መግለጫዎች አለመዘገባቸው፣ የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ የተዘገበበት መንገድ እና ሌሎችን ጉዳዮችን በመጥቀስ የዜና ሽፋን የሚሰጣቸው ጉዳዮች የተመረጡት ብቻ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁም፤ ኢቢሲ "እንደ ከዚህ ቀደሙ እኔን ብቻ አገልግሉ የሚልና ሌላውን ሰምቶ እንዳልሰማ የሚሆን መገናኛ ብዙኃን በመሆኑ የድርጅቱ አገልጋይ ሆኖ ላለመቀጠል ወስኛለሁ" ብሏል። ገዥውን ፓርቲ ማገልገል ብቻ አላማቸው ያደረጉና ከዚያ ውጭ የሕዝብም ሆነ የትኛውም ፓርቲ ፍላጎት የማይነሱበት፤ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን ለመዘገብ የሚያስችል ሁኔታዎች የሉም ሲል ያክላል። እርሱ እንደሚለው አሁን ላይ ተባብሰው የመጡት የብሔርና እምነት ጉዳዮች በሙያው ውስጥ ጣልቃ የሚገቡ ችግሮች ናቸው። እነዚህ ችግሮች በእርሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ባልደረቦቹም ላይ የሚያጋጥሙ እንደሆኑ ይናገራል። ጋዜጠኞችም በሚያነሱት ጉዳዮች በማንነታቸውና ኃይማኖታቸው የሚፈረጁበት አጋጣሚዎችም በርካታ መሆናቸውን ያነሳል። ከዚህም ባሻገር ኢቢሲ የሚዘገቡ ጉዳዮችን ከመምረጡም ባሻገር ጋዜጠኞች በጉዳዮቹ ላይ ዘገባ ለመስራት ሲጠይቁ ይሁንታ እንደማይሰጣቸው ይናገራል። የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የቴሌቪዥን ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልጀሊል ሃሚድ ግን በተቋሙ የኢዲቶሪያል ነጻነት የለም የሚሉ ክሶችን ሙሉ በሙሉ ያጣጥላሉ። • "የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝ" መሐመድ አደሞ • ጋዜጠኞች ስለ ለውጡ ማግስት ሚዲያ ምን ይላሉ? "የራሳችን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ አለን። በዛ መሠረት ነው በነጻነት የሚሰሩት። ምንም የተቀየረ ነገር የለም። ማንም ጣልቃ አይገባም። ሁሉም ነገር የሚሰራው በጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር ነው። አቶ ቢላል በራሱ ፍቃድ ለኑሮ ይሻለኛል ብሎ ነው የቀረው እንጂ የኤዲቶሪያል ነጻነት የለም የሚለው አያስኬድም" በማለት ጉዳዩን ለማብራራት ይሞክራሉ። ጋዜጠኞቹ እንደምሳሌ የጠቀሱትን በማንሳት ዜናዎች እየተመረጡ ነው የሚሰሩት ለሚለው ቅሬታ ምላሽ የተጠየቁት አቶ አብዱልጀሊል፤ "እኛ አገርን በማይንድ ፣ ሕዝብን በማያራርቅ መልኩ ነው ዜናዎችን የምንመርጠው። እንደውም የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጉዳይ ቀድመን የዘገብነው እኛ ነን" ይላሉ። የጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ፕሬስ ሴክረታሪያት በኢቢሲ ቀርበው ስለታገቱት ተማሪዎች ከሰጡት መግለጫ ውጪ ኢቢሲ ተከታታይ ዘገባ አለመስራቱን እና ጋዜጠኞች በጉዳዩ ዝርዝር ዘገባዎችን ለመስራት ጠይቀው መከልከላቸውን የቀድሞ የኢቢሲ ጋዜጠኞች ይናገራሉ። አቶ አብዱልጀሊል ግን፤ "ይሄ ዘበት ነው። ዛሬ ጠዋት በነበረው ስብሰባ ላይ እንኳን ተከታታይ ዘገባዎች ለምን አይሰሩም ብለን ጥያቄ አቅርበን ነበር። አቶ ቢላልም እራሱ ቡድን መሪ ስለሆነ ይህን ሃሳብ አቅርቦ በኤዲቶሪያሉ ጸድቆለት ነበር። እሱ የቤቱን ስም ለማጠልሸት ካልሆነ በቀር ከዚህ ጋር የተገናኘ ነገር የለም" ይላሉ። ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁ "ተቋሙ ብቃት በሌላቸው ሰዎች ነው የሚመራው" ጋዜጠኛ ቢላል ተቋሙን የሚመሩት "ምንም ዓይነት የሚዲያ ልምድ እና በቂ የትምህርት ዝግጅት የሌላቸው እንደ ፌደሬሽን ምክር ቤት በብሔር ውክልና የተቀመጡ ናቸው፤ ሃሳቦችም ሲነሱ በብሔር ነው የሚቃኙት" ይላል። ለቢቢሲ በጽሁፍ ሃሳባቸውን የላኩ ጋዜጠኞችም በተመሳሳይ መልኩ ከአርታኢዎቻቸው መካከል ጥቂት የማይባሉት በቂ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት እንደሌላቸው ጠቁመዋል። አቶ አብዱልጀሊል በበኩላቸው "ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች አገር ነች። ይሄ ሚዲያም የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ነው ብለን ነው የምናምነው። እየተሰራ ያለውም በዚሁ መልክ ነው። ሰዎቹ አቅም የላቸውም ለሚባለው፤ አቅሙን ማነው የሚወስነው? ዩኒቨርሲቲዎች አስተምረው ሰርተፊኬት ስጥተዋል። እስከ ሁለት ማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ጋዜጠኞች አሉ" ሲሉ መልሰዋል። • የድኅረ ዐብይ ሚዲያ በምሁራኑ ዕይታ የቀድሞ የኢቢሲ ጋዜጠኞች ከሚያነሷቸው ቅሬታዎች መካከል የጋዜጠኝነት ሙያን እና ልምድን በሚጠይቁ የኤዲቶሪያል ስብሰባዎች ላይ እንደ ጠቅላላ አገልግሎት እና የሹፌሮች ስምሪት ኃላፊዎች ያሉ በኤዲቶሪያል ስብሰባዎች ላይ ተገኝተው በዜናዎች አዘጋጋብ እና ይዘት ዙሪያ አስተያየት ይሰጣሉ ይህም በሥራችን ላይ አሉታዊ ጫና ያሳድራል የሚለው ይገኝበታል። አቶ አብዱልጀሊል ለዚህ ምላሽ ሲሰጡ፤ "በኤዲቶሪያል ፖሊሲያችን ላይ የኤዲቶሪያል አባላት እነማናቸው ተብሎ ተጽፎ ተቀምጧል። የሹፌሮች ስምሪት ኃላፊዎችም ሆኑ ጠቅላላ አገልግሎት እንዲሳተፉ የሚደረገው ከሎጂስቲኩ በተጨማሪ በሚዲያው ላይ ብዙ ዓመት ስለቆዩ በዜናዎች ላይ ሃሳብ ይሰጣሉ፤ ሃሳባቸው ተቀባይነት ካገኘ ይወሰዳል"። የመንግሥት ባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት በጋዜጠኝነት ሥራችን ላይ የመንግሥት ኃላፊዎች እና መሥሪያ ቤቶች ጣልቃ ገብነት ሥራችንን በገለልተኛነት እንዳናከናውን ጫና ያሳድራል የሚለው ሌላው የጋዜጠኞቹ ቅሬታ ነው። የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የቴሌቪዥን ዘርፍ ኃላፊው ለዚህ ቅሬታ ምላሽ ሲሰጡ፤ "ጫና የሚያሳድሩ የሉም ማለት ባይቻልም ይህ ገፍቶ የመጣ ጉዳይ አይደለም" ይላሉ። አቶ አብዱልጀሊል እንደሚሉት ከሆነ ከዚህ ቀደም አንዳንድ ዜናዎች እና ፕሮግራሞች 'አይተላለፉ' እያሉ የሚደውሉ ኃላፊዎች አሉ። እሳቸው እንደሚሉት ግን የተቋሙ ኤዲቶሪያ ፖሊሲ ላይ በመመርኮዝ የውጪ ጫና በተቋሙ ሥራዎች እና በጋዜጠኞች ላይ እንዳይደረግ ያደርጋሉ። አሁን ለምን? ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ፤ በርካታ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ከእስር ተለቀዋል። እግድ ተጥሎባቸው የነበሩ መገናኛ ብዙኃን ወደ ሃገር ገብተዋል። በኢትዮጵያም የተሻለ የመናገር ነጻነት ሰፍኗል ተብሏል። ይህ አዎንታዊ ለውጥ አለ በሚባልበት ወቅት ጋዜጠኞቹ ለምን በሄዱባቸው አገራት መቅረትን መረጡ? ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጠን ጋዜጠኛ ቢላል፤ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለውጡ ሲመጣ ትልቅ ተስፋ እንደነበረው እና ደስተኛ እንደነበር ይናገራል። ቢላል ከዚህ ቀደም ወደ ምዕራብ አፍሪካ እና መካካለኛው ምስራቅ አገራት ለዘገባ መጓዙን በማስታወስ በለውጡ ትልቅ ተስፋ ስለነበረው ከዚህ በፊት ባደረጋቸው ጉዞዎች በዚያው ለመቅረት እንዳላሰበ ይናገራል። "አሁን ላይ ግን 'እኛ ያልንህን ብቻ ሥራ። ባዘዝንህ መልኩ አገልግል።' የሚለውን እንደ ጋዜጠኛ መሸከም ስላልቻልኩ ለመወሰን ተገድጃለሁ" ይላል። ቢላል "በነበርኩበት የሥራ ኃላፊነት ከመንግሥት ባለሥልጣናትና ሚኒስትሮችም በስልክ ማስፈራሪያዎች ይደርሱብኝ ነበር" ይላል። ዝርዝር ሁኔታውን የጠየቅነው ጋዜጠኛው፤ ለቤተሰቦቹ ደህንነት ስለሚሰጋ ለጊዜው መናገር እንደማይፈልግ ገልፆልናል። በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ከ4 ያላነሱ ነባር ጋዜጠኞች ባለፉት ጥቂት ወራት በተለያዩ አጋጣሚዎች ባቀኑባቸው አገራት ጥገኝነት ጠይቀዋል።
42686440
https://www.bbc.com/amharic/42686440
የዶክተር መረራ ጉዲና ክስ ተቋረጠ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር የሆኑትና ታዋቂው ፖለቲከኛ የዶ/ር መረራ ጉዲና ክስ ተቋረጠ። ዶ/ር መረራ በ2016 በብራስልስ የአውሮፓ የፓርላማ አባላትን ስብሰባ ተካፍለው ሲመለሱ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ሕግ በሰጠው መግለጫ የፍርድ ሂደታቸው በመታየት ላይ የሚገኙ የ528 ተጠርጣሪዎች ክስ መቋረጡን አስታውቋል። ከሚፈቱት እስረኞች መካከል 115 በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ሥር የሚገኙ ሲሆን በክልል ደረጃ የሚገኙትን ደግሞ ክልሉ በሚወስነው መሠረት ተግባራዊ ይሆናል። እሰካሁን ድረስም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ብቻ 413 የሚሆኑ የእስረኞችን ስም ዝርዝር አቅርቦ ክሳቸውን ለማቋረጥ ወስኗል ብለዋል። በመግለጫው ወቅት ክሳቸው ተቋርጦ ከሚፈቱ እሰረኞች መካከል የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የሚገኙበት አንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፤ ''በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ስም ዝርዝራቸው ይፋ ሲደረግ የምንመለከተው ይሆናል'' ብለው ነበር። አቶ ጌታቸው በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ የለም በማለት አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። እንደ አቶ ጌታቸው አምባዬ መግለጫ ከሆነ እስረኞቹ በሁለት ቀናት ውስጥ ይፈታሉ።
news-42114608
https://www.bbc.com/amharic/news-42114608
"የአባይን ችግር የሚያጎላው የፖለቲከኞች አመለካከት ነው"
ሞሓመድ ዋዴ ሳዳ ኢልባላድ ለተባለ የግብፅ ቴሌቪዥን ጣብያና ድረ ገፅ የሚሰራ ጋዜጠኛ ሲሆን በተፋሰሱ ዙርያ ከሚፅፉ ጋዜጠኞች አንዱ ነው።
"በአገራችን ኑሮ ተወዷል። ለሁሉም ነገር ብዙ እየከፈልን ነው። ህዝቡ ለውሃም ክፈል እንዳይባል ጭንቀት ውስጥ ገብቷል" በማለት ለቢቢሲ ይናገራል። ሞሓመድ ባለፈው ዓመት ነሀሴ ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከጎበኙት መካከልም ነበር። "ግድቡ ለግብፅ ህዝብ አንዳች ጉዳት እንደሌለው ፅፌአለሁኝ። እንዳውም ለግብፅ ምን ያህል ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ ግድብ እንደሆነ አውቄያለሁ" ይላል። "ለኢትዮጵያዊ ወንድሞቼ ትልቅ ፕሮጀክት ነው። ውኃቸውን መጠቀምና መበልፀግ ደግሞ መብታቸው ነው። የግብፅ ህዝብ ፍላጎት ውኃው እንዳይቋረጥባት ብቻ ነው" ይላል የአገሪቱ ሚድያ ኢትዮጵያ የናይል ውኃ ልታቋርጠው እንደሆነ በህዝቡ ዘንድ የተሳሰተ ግንዛቤ መፍጠሩን በመናገር። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጋቢት 5, 2004 ዓ/ም ይፋ ሲደረግ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የቃላት ጦርነት ተበራክተው ነበር። በሁለቱም ኣገሮች መካከል የነበረው ግንኙነትም ሻክሮ ነበር። ይህ በአፍሪካ ትልቁ የሆነው ግድብ በዓመት ከ6ሺህ ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ የሚታመንበት የ80 ቢልዮን ብር ፕሮጀክት ነው። ግድቡ በአምስት ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ግንባታው በቅርቡ 65 በመቶ ብቻ መድረሱ ይነገራል። በብድርና በእርዳታ መቋረጥ ምክንያት የግድቡ ግንባታ እንዳይስተጓጎል በማሰብም መንግስት ከህዝቡ ጋር በመተባበር ለመስራት ነበር እየተንቀሳቀሰ ያለው። ከፕሮጀክቱ ጋር ስማቸው ደጋግሞ የሚነሳውና የመሰረት ድንጋዩን ያሰቀመጡት የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ በግድቡ ዙርያ የሚደረጉ ንግግሮችና የሚሰጡ መግለጫዎች "ቁጭት" አዘል ነበሩ። የኢትዮጵያዊያኖች "ቁጭት" ኑሮውን በኬንያ ናይሮቢ ያደረገው አለም አለማዮ ከስድስት ዓመታት በፊት የግድቡ ዜና ይፋ ሲሆን ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶት እንደነበር ያስታውሳል። "የመለወጥ ተስፋና ኃይል የማግኘት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር" በማለት። ነገር ግን የግድቡ ግንባታ ከታቀደው ጊዜ በመዘግየቱ ስሜቱ እንደ ቀዝቀዘ ይናገራል። "ከሚገባው በላይ ጊዜ የወሰደ ይመስለኛል። ስለ ግድቡ ትዝ የሚለኝ ዜና ሲኖር ብቻ ነው" ይላል። "አባይ ግብፅ ብቻ የምትጠቀምበት ነው የሚለው ስሜት ላይመለስ የተቀየረ ይመስለኛል" ወንድወሰን ሚቻጎ ሰይድ ከዚህ በፊት በተለያዩ የውኃ ተቋማት በተለይ በምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት የውኃ ምርምር ሲያደርግ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅትም በስዊድን አገር ሉንድ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ የዶክትሬት ትምህርቱን በመከታተል ላይ ሲሆን በአባይ (ናይል) 'ሀይድሮ ዲፕሎማሲ' እና አመለካከት ላይ ጥናት እያደረገ ይገኛል። "ኢትዮጵያኖች ድሃ ሊሆኑ ይችላሉ ግን ኩሩ ህዝቦች ናቸው። የባርነት፣ የቅኝ መገዛት ታሪክ አለመኖር በራስ የመተማመን መንፈስን ፈጥሯል። የተለየ የኢትዮጵያዊነት ስሜት አለ። በአባይ ላይ ደግሞ አንድ የሆነ አስተሳሰብ ተፈጥሯል" ይላል። "በኢትዮጵያኖች ዘንድ ያለው አመለካከት የራስህ የሆነ ነገርን ያለመጠቀም ቁጭት ነው። ግጥሞቹንና ዘፈኖቹን ብታያቸው እሱን ነው የሚነግሩህ" ይላል። ለምሳሌም ያህል የሎሬት ፀጋየ ገብረ መድህንን እና የባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሀንስ (ገሞራው) ግጥሞችን ይጠቅሳል። "ይሄ አመለካከት ግን የአባይ ግድብ ከተጀመረ በኋላ ተቀይሯል። በራሰ የመተማመን፣ በውሀው የመጠቀም ከፍ ያለ ስነልቦና ተፈጥሯል፤ ኢትዮጵያ እንደ ወኃ ሰብሳቢ፣ እንደ ውኃ ማጠራቀምያ ነበር የምትታየው"ይላል አቶ ወንደወሰን እንደሚለው ሃገሪቱ የአፍሪካ ቀንድ የውኃ ማማ እየተባለች ነበር የምትጠራው። ግድቡ ግን ይህንን አመለካከት በአመዛኙ ቀይሮታል። "እኔ በተለየ መልኩ ለማየት እየሞከርኩ ነው" የሚለው ኣቶ ወንድወሰን በዋናነት በአመለካከት (ፖለቲካል ሳይኮሎጂ) ወይም ደግሞ እሱ እንደሚጠራው 'ሃይደሮሜንታሊቲ' የተሻጋሪ ወንዞችን አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ እያጠና እንደሆነ ይናገራል። ለምሳሌ በሁለቱም አገሮች መካከል በአስተዋፀኦ እና በመጠቀም ያለው ግንኙነት ተቃራኒ ነው። ኢትዮጵያ (85 በመቶ) አስተዋፀኦ ታደርጋለች የታችኛው ተፋሰስ አገሮች ደግሞ ብቸኛ ተጠቃሚ ናቸው። ስለዚህ "የላይኛውና የታችኛው ተፋሰስ የሚል ተቋማዊም ህጋዊም ሆኖ ቆይቷል" ይላል ይህንን አመለካከት ደግሞ ማናቸውም ድርድርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመናገር። አቶ ወንድወሰን ሚቻጎ መሀል ላይ "የትኛው የውኃ ድርሻ"? በ1959 ሱዳንና ግብፅ ያደረጉት በብዙዎች አግላይ ተብሎ የሚገለፅ ስምምነት ነበር። ስምምነቱ "ውሃውን ሙሉ ጥቅም ላይ ማዋል" የሚል ሲሆን የናይል ወንዝ በግብፅና በሱዳን መካከል ጥቅም ላይ እንዲውል ይደነግጋል። ያኔ የተፋሰሱ አገሮች ቁጥር 9 ነበር። አሁን 11 ሆኗል። "ዘጠኝ አገሮች ባሉበት ሁለት ለብቻቸው ስምምነት ሲያደርጉ፤ የታችናው ተፋሰስ ሜንታሊቲ (አስተሳሰብ) ማለት ይሄ ነው። ሌሎችን አግልሎ ራስን ብቻ መጥቀም።" በማለት ሃሳቡን ያብራራል። ሆኖም በ2015 በስድስት አገሮች የተፈረመው የናይል የውሃ አጠቃቀም የህግ ማእቀፍ በሚል እንደተካው ይታወቃል። አዲሱ የህግ ማእቀፍ ለ1959ኙ ስምምነት እውቅና አይሰጥም። በቅርቡ የግብፅ ፕሬዚደንት አፈታህ አል-ሲሲ ይህንን ስምምነት መሰረት አድርገው የግብፅ የውሃ ድርሻ አይነካም ማለታቸውን አቶ ወንደወሰን "የትኛው ድርሻ" በማለት ይጠይቃል። "ይህንን ድርሻ ኢትዮጵያ የምታውቀው ስምምነት አይደለም" ይላል። ሶስቱም አገሮች የግድቡን ከአካባብያዊ ተፅእኖ ስምምነት በተመለከተ በጋራ ሲያካሂዱት የቆዩት ድርድር እክል እንደገጠመው እየተነገረ ነው። የግድቡ ግንባት ከ65 በመቶ መድረሱን እየተነገረ ሲሆን፤ ትልቁ ችግር አሁን ግድቡን እንዴት ነው መሙላት የሚቻለው የሚል ነው። የምስራቅ ናይል ቴክኒካል ኦፊስ (ኢንትሮ) ምክትል ዴይሬክተር አቶ ፈቅ አሐምድ "በአገሮቹ መካከል ከፍተኛ ትብብር በሚደረግበት በአሁኑ ወቅት እንዲህ ዓይነት መግለጫዎች እና የሚዲያ ቅስቀሳዎችን ማድረግ ማንንም አይጠቅምም" በማለት እንቅስቃሴው ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ለቢቢሲ ይናገራሉ። እስከአሁን ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ጉዳዮች "ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውኃ አጠቃቀም እና በታችኛው አገሮች ላይ የከፋ ጉዳት አለማድረስ" የሚሉ መርሆች መሆናቸውም ይናገራሉ። "ታሪካዊ መብት" መልሶ የሚነሳበት ጉዳይ እንደሌለ በማስረዳት። የአባይ ጉዳይ ሃይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ሥነ-ልቦናዊ ሁኔታዎች ያለበት በመሆኑ ግን በቀላሉ የአመለካከት ለውጥ ይመጣል ተብሎ አይታሰብም። "ውኃው በስምምነት ከተጠቀምንበት በቂ ነው፤ ነገር ግን ውኃን ከብሄራዊ ደህንነት ጋር ማገናኘት ለድርድርም አይመችም" ይላሉ። ጥቁር ዓባይና ነጭ ዓባይ ካርቱም ላይ ይገናኛሉ 'ሰሌክቲቭ ሚሞሪ' (የተመረጠ ትዝታ) የአባይ ጉዳይ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ኣካል ተደርጎ ይታይ ነበር። አሁን ደግሞ "ገልፍናይዜሽን ኦፍ ዘ ናይል" አለ ይላል አቶ ወንድወሰን አሁን የተከሰተው አለመግባባት በገልፍ አከባቢ ያለው ቀውስ ነፀብራቅ መሆኑን ይናገራል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ኳታር መሄዳቸው በግብፆች ሌላ ትርጉም እየተሰጠው እንደሆነ በመናገር። "ሌላው በታችኛው ተፋሰስ ያለው ችግር ኢትዮጵያ ሁሌም ዝናብ ያላት አድርገው ነው የሚስሏት። ኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ እንዳለ አያውቁም ሁለቱም ዝናብና ድርቅ የሚፈራረቁባት አገር ነች። ድርቅ ደግሞ ሌላ ትርጉም የለውም፤ የወሃ ዕጥረት የሚያመጣው ነው፤ እርጥበት ማጣት ነው።" የናይል ጉዳይ የመሪዎችና የፖለቲከኞች ጉዳይ ሆኖ መቅረቱ ችግሩ ውስብስብ እንዲሆን ማድረጉ ኣቶ ወንድ ወሰን ይናገራል። "የአባይን ችግር የሚያጎላው የፖለቲከኞች ሜንታሊቲ ነው። ህዝቦች ግን መስማማት የሚችሉ ይመስለኛል" ብሏል። በ500 ዓመተ ዓለም "ግብፅ የአባይ ፀጋ" ነች በሚል ሄሮድስ የተናገረው እስከ ዛሬ ይጠቀሳል። "ይህ የማይለወጥ አመለካከት ነው የሚያሳየው። ሄሮድቶስ ይህንን ነገር ሲናገር ስለ የአባይ ምንጭ የሚያውቀው ነገር አልነበረም" ይላል ወንድወሰን። "ውኃ ሁሌም ይንቀሳቀሳል፥ ይወርዳል። አእምሮኣችን ግን እንደቆመ ነው። ለሚንቀሳቀስ ወንዝ ስታቲክ የሆነ ጭንቅላት ነው ያለን። ይህንን መገንዘብ ያለብን ይመስለኛል።"
news-56939405
https://www.bbc.com/amharic/news-56939405
ሙዚቃ፡ በሦስት ሳምንት ውስጥ ከ3 ሚሊየን በላይ ተመልካቾች ያገኘው ዲሽታግና
የልጆች ለቅሶ፣ የእናቶች ሃዘን፣ የአባቶች ተስፋ መቁረጥ በበረታበት ወቅት ድንገት የመጣ የፍቅር ጥሪ።
ከልጅ እስከ አዋቂ፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ መልዕክቱ ደርሷቸው አጣጥመውታል። እንደ ወጀብ ጠዋት ማታ እየበጠበጣቸው ካለው መጥፎ ዜና ትንሽ እፎይታን ያገኙበት ይመስላል። የእንዋደድ መልዕክቱ ምናለ ምድር ላይ ቢወርድ፣ ብንዳንስሰው፣ ብንጨብጠው፣ ሁል ጊዜ ብንኖረው ሲሉ የተመኙም ብዙ ናቸው- ዲሽታግናን። ዲሺታግና አዲስ ነጠላ ዜማ ነው። ድምጻዊው ታሪኩ ጋንኪሲ ይባላል። በዩትዩብ ከተለቀቀ የተቆጠሩት ሦስት ሳምንታት ብቻ ናቸው። በሦስት ሳምንታት ውስጥ ከ3 ሚሊየን በላይ ተመልካቾችን አግኝቷል። በርካቶች በማሕበራዊ ሚዲያ ተቀባብለውታል። ዲሺታግና በተከፈተ ቁጥር ባለበት የማይወዛወዝ ማግኘትም ዘበት ነው። ዲሺታግና ዲሽታግና የአሪ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት ወይም ዘመን መለወጫ ነው። ዲሽታግና አብረን እንብላ፣ አብረን እንጠጣ፣ የተጣሉትን እናስታርቅ ፣ ለሌላቸው እንስጥ፣ እንደጋገፍ ማለት ነው። ክብረ በዓሉ "12 ወራትን በድካም፣ በልፋት፣ በደስታና በሃዘን አሳልፈናል። አሁን ደግሞ 12 ወራት ወደ ፊት ይጠብቀናል። ስለዚህ በጥል ማሳለፍ ሳይሆን በፍቅር ፣ በሰላም፣ በመደጋገፍና ያጡትን በመርዳት እናሳልፍ" የሚል የመተሳሰብ መልዕክት የሚሰበክበት፤ በተግባርም የሚታይበት ነው። ታሪኩ ሙዚቃውን ለመሥራት የተነሳውም ይህ ፍቅር አዘልና አስታራቂ ባህል ቢኮረኩረው ጊዜ ነው። ታዲያ በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኘው የአሪ ልማት ማሕበር ገፋፊነትም ሳይዘነጋ ነው። "ይህንን ሥራ እኛ ብቻ ከምናውቀው ሰው ሁሉ ይወቀው" ሲል ማሕበሩ ጠርቶ እንዳነጋገረው የሚናገረው ታሪኩ፤ የሙዚቃ ሥራውንም እንደ ማሕበረሰቡ ባህል ተደጋግፈው እንደሠሩት ይናገራል። ማሕበሩ ምንም እንኳን አቅሙ ያልጠና ቢሆንም ለዚህ ሙዚቃ ግን አስተዋፅኦው ከፍተኛ ነበር ይላል ታሪኩ። የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶም ድጋፍ ቀላል አይደለም። ግጥሞቹን በማስተካከልና በማረም አግዘውታል። "የተሳሳትኩት ነገር ካለ ብዬ ሰግቼ ነበር፤ ፖለቲካ ከሆነ እንዳልጠፋ ብዬ አስቤ ነበር" ይላል። በእርግጥ የራሱን ስሜት ለመግለፅ ያህል እንጂ እንዲህ ዓይነት ተቀባይነት አገኛለሁ ብሎ አላሰበም ነበር። "እኔ ራሴን የገለፅኩበት ለካስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቅር ይፈልግ ነበር። እንዲህ ዓይነት ፍቅር ይፈልግ ነበር፤ ተወደደ።" ይላል። ታሪኩ "የሰው ልጅ ሲሠራ ያገኛል፤ እኛ ይዘን የመጣነው የለም፤ ወደፊትም ይዘነው የምንሄደው ነገር የለም፤ እስካለን ለምን እንጣላለን? ሲልም ይጠይቃል። በርግጥስ የሚያጣላን ምን ይሆን? ድምጻዊው ለዚህ ሁለት ምክንያቶችን ያስቀምጣል። ራስ ወዳድነትንና ፈጣሪን አለመፍራት። "የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈጣሪን የሚፈራ ነው። አሁንም የሚያወጣን ፈጣሪን መፍራት ነው" ይላል ታሪኩ። "ይህችን ምድር የተቀላቀልነው ባዷችንን ነው፤ የምንመለሰውም እንደዚያው" የሚለው ታሪኩ፤ ከሰውነት የወጡ ተግባራት የሚፈፀሙት ይህንን ማሰብ የዘነጋን ጊዜ እንደሆነ ይናገራል። ድምጻዊው እንደሚለው ራስ ወዳድ የመሆንም ውጤቱ እርስ በርስ መናከስ ነው። "ራስ ወዳድ ስትሆኝ ጠባብ ትሆኛለሽ፤ ሰው ትጠያለሽ፣ ከሰው ትርቂያለሽ፤ ጭንቅላትሽ የሚመግበው አንቺ የምታደርጊው ላንቺም ለሰውም እንደሚመች ነው" ሲል ያስረዳል። "እኔን እንኳን ይህችን ሰራህ ብለው 'አንተ ጀማሪ ነህ ከማን ትበልጣለህ' ሲሉ ሞራሌን የሚነኩ አሉ" የሚለው ታሪኩ፤ ወደዚች አለም መጥተን የምንሄድበት ትኬት እስኪቆረጥ ድረስ ምናለ በፍቅር ብንኖር ይላል። በስንኞቹም እንዲህ ገልጾታል። ". . . ያ ባቢሎን እኛን በታተነን ይሄው እስከ ዛሬ የእውነት ፍቅር አጣን . . . እኔ አና አዳም አንድ አባቴ አንችና ሄዋን አንዱ አጥንቴ . . ." በሙዚቃው ግጥም በአማርኛ ቋንቋ የተገለፁት ስንኞች የሰው ልጅ አመጣጥን የሚገልፁ ናቸው። ግንዱ አንድ ነው እሱም አዳም(አደም) የሚል። በአሪኛ ቋንቋ የተሰናሰሉት ስንኞችም የሚገልፁት ይህንኑ ነው። ሙዚቃው ተወዳጅነትን ያግኝ እንጂ በገቢ ደረጃ ግን ያገኘው እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ ይናገራል። ታሪኩ "ዘፈኑ የተሸጠበትን ዋጋ ሚዲያ ላይ ማውራት ሰዎችን ያስቀይማል" ሲል አሃዝ ከመጥቀስ ተቆጥቧል። ነገር ግን " ትንሽ ብር ናት በጣም አዝኘ ነው የወሰድኩት" ብሏል ታሪኩ ጋንኪሲ። ታሪኩ ጋንኪሲ ማን ነው? ትውልድ እና እድገቱ ከደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጂንካ 20 ኪሎ ሜትር በምትርቀው በርቃ ቀበሌ ነው። የተቃኘውም በዚሁ ዞን ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ በሆነው አሪ ብሔረሰብ። የውትድርና ሕይወትን ተቀላቅሎ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተዋግቷል። ለ6 ዓመታት ያህልም ነዋሪነቱን በአዲስ አበባ አድርጎ ነበር። በቆይታው በቀን ሥራና በጎዳና ተዳዳሪነት ሕይወቱን ገፍቷል። ታሪኩ አዲስ አበባ በቀን ሠራተኝነት ተቀጥሮ ሲሰራ "የሚከፈለኝ በቀን ሰባት ብር ነበር" ብሏል። የሕይወት ውጣ ውረድን አይቷል። ሕይወቱን ለማሻሻል ያልሰራው ሥራ የለም። ሳይክልና ጆተኒም ያከራይ ነበር። እየቆየ ሲሄድ ግን የከተማ ሕይወት ከእርሱ ነፍስ ጋር የተስማማ አልመስልህ አለው። የከተማ ኑሮ በቃኝ ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ኑሮውን ጂንካ አደረገ። የእርሻ ሥራም መተዳደሪያው ሆነ። "የጫካ ሕይወት አሪፍ ነው። ጫካ አይናገር ፣ አይሳደብ፣ ከየት መጣህ አይል? እዚያው መኖር ነው። ሳሩም መድሃኒት ነው። ከተማው ግፊ በዛበት" ይላል ታሪኩ። ከተማ ውስጥ ያለው መገፋፋት፣ የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ሽኩቻ ሰላም ቢነሳው ጊዜ " በመጣሁበት ጭንቅላቴ ወደ አገሬ ተመልሼ ብሔድ ይሻላል" ሲል ውሳኔ ላይ መድረሱን ተናግሯል። ታሪኩ ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት ነው። ከአባይ የተጋባው የኦሞ ወንዝ ቁጭት በአፈር ያደፈ ወንዝ በጸጥታ ይጓዛል። በርቀት ለሚያየው ከመሬት የፈለቀ አንዳች ቡናማ ቀለም እንጂ የሚፈሰው ውሃ አይመስልም። ከወንዙ ዳርቻ ታሪኩ ፣ አንድ ወንድና አንድ ሴት ቆመው ይጨዋወታሉ። ስለ ወንዙ መሆኑ ነው። "ይህ ወንዝ እንጨት ፣ ሳር፣ አፈር ይዞ ሲሄድ 'ትርፍ ጭኗል ?' ብሎ የጠየቀው አለ?" ሲሉ መንግሥትንም፣ ሕዝቡንም፣ አፈሩንም ይወቅሳሉ። ይህ ጭውውት የሚታየው በማሕበራዊ ሚዲያ በተለቀቀ አንድ አጭር ተንቀሳቃሽ ምሥል ነው። ታሪኩ እንዳለው ምሥሉ የተቀረፀው የደቡብ ኦሞና ኬንያ ድንበር ላይ ነው። ጊዜው ደግሞ ከሁለት ወይም ከሦስት ዓመታት በፊት። ሃሳቡ ይህ ወንዝ እያለ እንዴት እንራባለን፣ እንዴት የእርዳታ እህል እንለምናለን? የሚል ነው። "ውሃው ለልማት መዋል እየቻለ ያንጋቶም፣ ዳሰነች፣ ሃመር የእርዳታ እህል ነው የሚበሉት እና ባለሃብቶች እዚያ ላይ ቢያለሙ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነበር በጨዋታ መልክ የሠራነው" ሲል ያስታውሳል። ቪዲዮውን ለተመለከተው ታሪኩ የትወና ችሎታ እንዳለው መገመት ቀላል ነው። እርሱም እንደሚለው ድራማ ይሞክራል። ግን ዕድሉን ብዙም አላገኘም። " ትልቅ ሞያ ያለው እያለ ትንሽ ሞያ ያለው በዘመድ አሊያም በሌላ ነገር ይገባል። ስለዚህ ዕድሉን ፈጣሪ እስከሚያመጣ መጠበቅ ነው። ችሎታን ይዞ ወደ አፈርም መግባት ይቻላል፤ እርሱንም ሰጥቶ ወደ አፈር መግባት ይቻላል። ዞሮ ዞሮ ሁለቱም ወደ አፈር ይገባሉ" ሲል ሰው ያለውን አበርክቶ ቢያልፍ የተሻለ መሆኑን ያስረዳል። ጥቂት ስለአሪ ብሔረሰብ ደቡብ ኦሞ በደቡብ ክልል ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ነው። በውስጡም የተለያየ ባህል፣ ቋንቋና አኗኗር ያላቸው 16 ብሔረሰቦች ይኖራሉ። ከእነዚህ ብሔረሰቦች መካከል የአሪ ብሔረሰብ አንዱ ነው። በአሪ ብሔረሰብ ከሕዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ የዘመን መለወጫ በዓል ይከበራል። በብሔረሰቡ አቆጣጠር የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ተደርጎ የሚቆጠረው ታኅሳስ ወር ነው። በመሆኑም ታኅሳስ 1 የብሔረሰቡ አዲስ ዓመት ወይም የዘመን መለወጫ ሆኖ በድምቀት ይከበራል። የዘመን መለወጫው በዓል በብሔረሰቡ ቋንቋ ዲሽታግና ይባላል። ይህ የብሔረሰቡ የጊዜ አቆጣጠር 'ሎንጋ' ተብሎ ይጠራል።
53047758
https://www.bbc.com/amharic/53047758
ለ'አገራችን አፈር አብቁን' ሲሉ የሚማፀኑት ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ
በሊባኖስ ለበርካታ አስርተ ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ የኢኮኖሚ ድቀት መከሰቱን ተከትሎ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ለከፋ መጋለጣቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በምጣኔ ሃብት ድቀቱ ምክንያት አሰሪዎች ደሞዝ መክፈል ባለመቻላቸው ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ጎዳና ላይ እየተጣሉ ይገኛሉ። በሊባኖስ ለበርካታ ዓመታት የኖረችው ትነበብ ኃይሉ በርካታ ኢትዮጵያውን በአሰሪዎቻቸው እየተጣሉ ጎዳና ላይ መውደቃቸውን ነግራናለች። ''ሜዳ ላይ ከመጣል" ምግብ እና መጠለያ ለማግኘት ብለው ደሞዝ ሳይከፈላቸው እየሰሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ቁጥራቸው እንደሚልቅ ጨምራ ትናገራለች። የሊባኖስ የኢኮኖሚ ድቀት የአገሪቱ መገበያያ ገንዘብ 'ሊባኒስ ፓዎንድ' ከአሜሪካ ዶላር ጋር ያለው ግነኙነት ሰማይ ነክቷል። ሊባኒስ ፓዎንድ በታሪክ ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ 70 በመቶ ወርዷል። የዓለም ምጣኔ ሃብት ፎረም በዓለማችን ላይ በከፍተኛ ውዝፍ እዳ ውስጥ ከሚገኙ አገራት መካከል ሊባኖስን በሦስተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል። በውዝፍ እድ ውስጥ የምትገኘው ሌባኖስ፤ ሥራ አጥ በሆኑ ወጣቶች በተቃውሞ ስትናጥ ቆይታለች። የቫይረሱን ስርጭት ተከትሎ የተጣለው ገደብ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ግን 'ከድጡ ወደ ማጡ' እንዲገባ ሊያደርገው እንደሚችል ተገምቷል። ይህ የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት መዳከም፤ በሊባኖስ ለሚገኙ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩት ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ፈተናን ይዞ መጥቷል። "ማዳም . . . ጥለኝ ሄደች" በአሰሪዎቻቸው እንዲወጡ ከተደረጉት መካከል ጣይቱ ሙለታ አንዷ ነች። ጣይቱ ወደ ሊባኖስ መዲና ቤሩት ከመጣች ዓመታት መቆጠራቸውን ታስታውሳለች። ጣይቱ አሰሪዎቿ ሁለት ቦታ ያሰሯት እንደነበረ ትገልጻለች። "ሱቅ እና ምግብ ቤት አጸዳለሁ። የሚከፍሉት ሲያጡ ሁለት ዓመት ሰርቼ 'ያለሸ የአምስት ነው' አሉኝ። ከዛ ደግሞ የሰጡኝ የሶስት ወር ብቻ ነው" በማለት የደረሰባትን በደል ትናገራለች። ከጣይቱ ጋር ተመሳሳይ ታሪክ የምትጋራው ወርቂቱ ቦኬ ነች። ወርቂቱ 3 ዓመታትን በሊባኖስ ስታሳለፍ "የማይነግር መከራን አይቻለሁ" ትላለች። "ያለ እረፍት ስሠራ ነበር። በሽታው ከመጣ በኋላ ማዳም (አሰሪዋ) የምትከፍለው ስታጣ እጥልሻለሁ እያለች ታስፈራራኝ ነበር። ከሁለት ሳምንት በፊት ምንም ነገር ሳልይዝ በታክሲ ይዛኝ ወጥታ ኢምባሲው ጋር ጥላኝ ሄደች" በማለት አሰሪዋ ያደረገችውን ታስረዳለች። ጣይቱም ሆነች ወርቂቱ፤ አሰሪዎቻቸው አውጥተው ከጣሏቸው በኋላ "በረንዳ ላይ ለማደር" መገደዳቸውን ይናገራሉ። "የመጀመሪያዎቹን ቀናት በረንዳ ላይ ነው ያደርኩት። ከእኔ ጋር ብዙ ልጆች ነበሩ። ከዛ የኢትዮጵያ ልጆች አንስተውን ሆቴል አስቀምጠውናል። ምግብ እየሰጡን ነው። እዛ ቆንስላው ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች መዝገበውናል። በዚህ ሁኔታ እዚህ እስከመቼ እንደምቆይ አላውቅም" ትላለች ወርቂቱ። "ሆቴል ውስጥ ነኝ። በአንድ ክፍል ውስጥ ሁለት ሆነን ነው ያለነው። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከማዳም ቤት የተጣሉ ናቸው" በማለት ጣይቱ ለቢቢሲ ተናግራለች። ወርቂቱ ለሶስት ዓመታት በቤሩት ስትኖር ከቤት ወጥታ እንደማታውቅ እና የኢትዮጵያውያኑ ድጋፍ ቢቋረጥ መሄጃ እንደሌላት ትናገራለች። "አገሩን አላውቅም፤ አንድም የማውቀው ሰው የለም። ሶስት ዓመት ሙሉ ከቤት ወጥቼ አላውቅም" ትላለች። የኢትዮጵያውያኑ ድጋፍ እንደ ወርቂቱ እና ጣይቱ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከመንገድ እያነሱ በሆቴል እና በመኖሪያ ቤት እያቆዩ እና የምግብ ድጋፍ እያደረጉ ካሉ አካላት መካከል አንዱ 'እኛ ለኛ በስደት' የተሰኘው በጎ አድራጊ ድርጅት አንዱ ነው። በእና ለኛ በስደት አስተባባሪ የሆነችው ጽጌሬዳ ብርሃኑ፤ ድርጅቱ ከተመሰረት ሶስት ዓመት እንዳስቆጠረ እና በእስካሁኑ ቆይታቸው በሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የተለያየ መልክ ያለው ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ታስረዳለች። የክህሎት ስልጠና መስጠት፣ ቤት አልባ ለሆኑ መጠለያ ማቅረብ፣ ለታማሚዎች እና አቅመ ደካሞች ቲኬት ገዝቶ ወደ አገር ቤት ከመላክ በተጨማሪ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አስተማሪ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ያዘጋጃሉ። በሊባኖስ የአንድ የቤት ሠራተኛ ደሞዝ በአማካይ 150 የአሜሪካ ዶላር እንደሆነ የምትናገረው ጽጌሬዳ፤ የአገሪቱ ዜጎች በኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት የመክፈል አቅማቸውም እጅጉን ተዳክሟል። ዶላር ከባንክ ማውጣትም አይችሉም። በዚህም ምክንያት የምጣኔ ሃብት ቀውሱ መከሰት ከጀመረበት ከእአአ ኦክቶበር 2017 ጀምሮ ደሞዝ ያልተከፈላቸው በርካታ ሠራተኞች አሉ ትላለች። ለመክፈል አቅም እና ፍላጎት ያላቸውም ቢሆኑ ደሞዝ ለሰራተኞች እየከፈሉ ያሉት በአገሪቱ መገበያያ ገንዘብ ነው። "አንድ ልጅ ለምሳሌ ወደ ሃገር ቤት ገንዘብ መላክ ብትፈልግ፤ በሃዋላ ገንዘብ የሚልኩ ድርጅቶች ዶላር ብቻ ስለሚቀበሉ፤ ዶላር ከጥቁር ገበያ ላይ ገዝተው ሲልኩ የገንዘባቸው 80 በመቶ ያጣሉ" ትላለች። ከቤት ሠራተኝነት ውጩ በተለያዩ ኩባንያዎች ውስጥ ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ኢትዮጵያንም የምጣኔ ሃብቱ ድቀት ከኮቪድ-19 ጋር ተደማምሮ ከሥራ ውጪ መሆናቸውን ታስረዳለች። ወደ አገር ቤት መመለስ ጣይቱ እና ወርቂቱ ከምንም በላይ "ወደ አገራችን መመለስ ብቻ ነው የምንፈልገው" ይላሉ። ለዓመታት በአሰሪዎቻቸው የደረሰባቸው በደል ረስተው፤ ለዓመታት ያልተከፈላቸው ውዝፍ ክፍያ ይቅርብን ብለው ማየት የሚሹት የአገራቸውን ምድር ብቻ ነው። በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ከዚህ ቀደም የጉዞ ሰነድ ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን የጉዞ ሰነድ አዘጋጅቶ፤ በሁለት በረራዎች 658 ሰዎች ከቤሩት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ማድረጉን በሌባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ቆንስል የሆኑት አቶ አክሊሉ ታጠረ ውቤ ያስታውሳሉ። በእስር ላይ፣ በመጠለያ፣ ከአገር እንዲወጡ ውሳኔ የተላለፈባቸው፣ በህመም ምክንያት መስራት ባለመቻላቸው ከሊባኖስ ለመውጣት ያመለከቱ ዜጎች በሁለቱ በረራዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጉን ያስታውሳሉ። ከእነዚህ በረራዎች በአንዱ ላይ የነበረችው እና ስሟ እንዲጠቀሰ ያልፈለገች ኢትዮጵያዊት፤ አዲስ አበባ ከደረሰች በኋለ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ካምፓስ በለይቶ ማቆያ የነበራትን ጊዜ አጠናቅቃ ለመውጣት እየተጠባበቀች እንደሆነ ተናግራለች። "አሁን የአእምሮ ሰላም አግቻለሁ" ትላለች። በመካከለኛ ምሥራቅ በምትገኘው ሊባኖስ ከ400 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውን እንዳሉ ይገመታል። ከእነዚህም መካከል ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው መሆናቸውን ከቆንስላ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። የቆንስላው ቆንስል የሆኑት አቶ አክሊሉ ታጠረ ውቤ በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ እንዳሉ ይናገራሉ። አቶ አክሊሉ "ሕጋዊ የሆኑ ሠራተኞች ለብዙ ወራት የሰሩበት ደሞዝ ሳይከፈላቸው አሰሪዎቻቸው 'ቆንስላ ጽ/ቤት የአየር ቲኬት ከፍሎ ይልካችኋል' ብለው በማታለል ሜዳ ላይ ጥለው እየሄዱ ነው" ይላሉ። እንደ ማሳያም ባለፉት ሳምንታት 133 የሚሆኑ ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን በአሰሪዎቻቸው ተጥለዋል። ይህ የአሰሪዎች ተግባር ዓለም አቀፍ የሠራተኛ መብትን የሚጥስ ከመሆኑም በተጨማሪ ኢሰብዓዊ ስለሆን ይህን ድርጊት በደብዳቤ ለአገሪቱ የሠራተኛ ሚንስቴር አሳውቀናል ብለዋል። "በደብዳቤው ላይ ሊባኖሳውያን አሰሪዎች ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እና ውዝፍ ያልተከፈለ ደሞዝ ያለባቸው በአስቸኳይ ለሰራተኞች እንዲከፍሉ ጠይቀናል" ሲሉ ተናግረዋል። ለቆንስሉ ጥያቄ የሊባኖስ መንግሥት የሰጠው ምላሽ "እየሰራንበት ነው" የሚል መሆኑን አቶ አክሊሉ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር እና የሊባኖስ የሠራተኛ ሚንስትር በጉዳዩ ላይ በስልክ መነጋገራቸውንም አስታውሰዋል። የሊባኖስ መንግሥት ግዴታውን አልተወጣም የሚሉት አቶ አክሊሉ፤ "የሊባኖስ መንግሥት አሰሪ በሆኑ ዜጎቹ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እየወሰደ አይደለም። በሠራተኞች ላይ የሚደርሰውን በደል እያሳወቅናቸው ነው። አሰሪዎቹን ጠርቶ ለፈጸሙት በደል የሚገባቸውን ካልሰጠ ከባድ ነው የሚሆነው። እኛም ጫና እያሳደርን ነው። ውጪ ጉዳይም ይህን እንዲያደረገ ነው" ይላሉ። የሊባኖስ የሠራተኞች ሚኒስቴር ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጄኔራል የሆኑት ማርሊን አታላህ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሠራተኞቹ እየደረሰባቸው ያለውን ችግር ለመፍታት ከኢትዮጵያ ቆንስላ ጋር አብረን እየሰራን ነው ብለዋል። ኢትዮጵያውያኑ የቤት ሠራተኞችን በሆቴል ውስጥ ለሁለት ቀናት ያህል እንዳሳደሯቸውና ወደ መጠለያዎችም መውሰዳቸውን ተናግረዋል። ለቤት ሠራተኞቹ ደመወዝ ባለመከፈልም ሆነ በመባረራቸው የተከሰሰ አሰሪ አለመኖሩን ማርሊን አታላህ የተናገሩ ሲሆን፤ በጉዳዩ ላይ ግን ምርመራዎች እንደተጀመሩ ገልፀዋል።
50135330
https://www.bbc.com/amharic/50135330
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "መደመር" መጽሐፍ ምን ይዟል?
"ከኢትዮጵያዊያን መሠረታዊ ሥሪት የሚነሳ፣ ችግሮቻችንን ሊፈታ የሚችል፣ እኛው እያቃናነውና እያሟላነው የምንሄደው፣ ከዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ፣ ሁላችንንም ሊያግባባና ሊያስተሳስር የሚችል አንዳች ሉዓላዊና ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና ያስፈልገናል" ይላሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፤
ባለፈው ቅዳሜ በመዲናዋ አዲስ አበባ እና በሌሎችም በርከት ያሉ ከተሞች በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች ባስመረቁት አዲስ መፅሐፋቸው "መደመር" ሁለተኛ ምዕራፍ ላይ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ ከሁለት ዓመት ገደማ በፊት የአገሪቱን ከፍተኛ ሥልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ በተለያዩ አጋጣሚዎች ደጋግመው ያወሱትና መደመር ሲሉ የሚጠሩትን የአመራር እሳቤያቸውን ጠቅለል ባለ አኳኋን ለመተንተን የሞከሩበት፣ በልዩ ልዩ የመንግሥት እንደዚሁም የአኗኗር አፅቆች እሳቤያቸው እንዴት ሊተገበር እንደሚችል ለማመላከት የጣሩበት፣ ከዚህም በዘለለ የአስተዳደራቸውን ቀጣይ አቅጣጫዎች በተመለከተ ፍንጭ የሰጡበት ድርሳን ነው "መደመር"። • "ለውጡ ሐዲዱን ስቷል ብዬ ነው የማምነው" አርቲስት ታማኝ በየነ • አዲስ አበባ ውስጥ ሲካሄዱ የነበሩ ስብሰባዎች በወጣቶች መስተጓጎላቸው ተነግሯል በአስራ ስድስት ምዕራፋት የተቀነበበው መደመር የጠቅላይ ሚኒስትሩን ግላዊ ምልከታዎች ጥንስስ እና ዕድገት አስረድቶ አያበቃም፤ ኢትዮጵያ በእርሳቸው አመራር በፖለቲካ፣ በምጣኔ ኃብት እና በውጭ ግንኙነት መስኮች ምን መልክ እንዲኖራት እንደሚሹ የሚጠቁም ሲያልፍም በግላጭ የሚያስቀምጥ ጭምርም ነው። "ጊዜያችንን የሚዋጅ እሳቤ ነው" የሚሉትን የመደመርን ፅንሰ ኃሳብ በጥቅሉ ሲበይኑት "ከትንተና አንፃር ሀገር በቀል"፣ ከመፍትሔ ፍለጋ አንፃር ደግሞ "ከሀገር ውስጥም ከውጭም ትምህርት በመውሰድ የተቀመረ ነው" ይሉታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመፅሐፋቸው ሙግታቸውን የሚጀምሩት ስለሰው ልጅ ፍላጎቶች ከፍልስፍናም ከሥነ ልቦና ሳይንስ ደጆች የሚታከክ ትንተና በማቅረብ ነው። ሰዎች በህይወቶቻቸው ቀጥተኛ የህልውና ፍላጎቶች፣ የስጋ ፍላጎቶች እንዲሁም የመልካም ስም ወይንም የክብር ፍላጎቶች ሰንገው እንደሚይዟቸው ያስረዱና የመደመር እሳቤ እነዚህን ፍላጎቶች በቅደም ተከተል ሳይሆን እንደነባራዊ ሁኔታው እየታዩ በእኩልነት እንደሚያስተናግድ ያስረዳሉ። የኢትዮጵያንም ዕጣ ፈንታ በዚሁ የሰው ልጆች የፍላጎቶች መስተጋብር ይተነትኑትና የስም እና የነፃነትን ጥያቄዎች በአግባቡ ሳትመልስ ህልውናዋን ለማረጋገጥ ስትሞክር ሊያጠፏት ይችሉ የነበሩ አደጋዎችን በራሷ ላይ ጋብዛለች ይላሉ። ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ መንግስታት ባለፉት አስርት ዓመታት የተከተሏቸውን ርዕዮተ ዓለማት በተቹበት ንዑስ ምዕራፋቸው ባለፈው ግማሽ ምዕተ ዓመት በአገሪቱ "የነበረው ትርምስ ከውጭ ያገኘነውን ዕውቀት ከሀገራችን ሁኔታ ጋር በደፈናው ስናላትመው የተፈጠረ ችግር ነው" ይላሉ። ከእርሳቸው ወደ መሪነት ማማ መምጣት በፊት ፓርቲያቸው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) እከተለዋለሁ ይለው የነበረውን የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ስድስት ነጥቦችን ነቅሰው የነቀፉት ሲሆን ችግሮችን ሁሉ በምጣኔ ኃብቱ ላይ ያሳብባል፤ ስለግሉ ዘርፍ ልሂቃን የተዛነፈ ምልከታ አለው፤ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታን ቸል ብሎ አውራ ፓርቲን አፈርጥሟል፤ ከጠንካራ የመንግስት ቢሮክራሲ ይልቅ ጠንካራ ፓርቲን ለማጎልመስ ታትሯል ብለውታል። ይህም መፅሐፋቸው ለፓርቲያቸው አባላት እና ደጋፊዎች አዲስ ርዕዮተ ዓለማዊ መመርያ (ማኑዋል) የመስጠት ዓላማ የያዘ መሆኑን የሚያስጠረጥር ነው። • "ውስኪ ጠጪ ኢህአዴጎች እባካችሁ ውሃ የናፈቀው ሕዝብ እንዳለ አትርሱ" ጠ/ሚ ዐብይ መደመርን እንቅፋት ሆነው ሊያሰናክሉት ይችላሉ ያሏቸውን ጉዳዮችም ዘርዝረዋል፤ ዋልታ ረገጥነት፣ የጊዜ እስረኛ መሆን፣ ውስብስብ ችግሮችን ያለቅጥ አቅልሎ መመልከት ይገኙባቸዋል። የብሔር ፖለቲካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በመደመር መፅሐፋቸው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተዋስዖ የብሔር ማንነት ከሌሎች ማንነቶች አንፃር የተጋነነ ስፍራ መያዙን ይገልፃሉ። ተቺዎች የሀገሪቱ የቡድን ሥሪት በአካባቢያዊነት እና በሃይማኖት እንጅ በብሔረተኛነት ዙርያ አልተገነባም ሲሉ መሞገታቸውን፣ የሰው ልጆች የተለያዩ ቡድናዊ ማንነቶች ያሏቸው ሆኖ እያለ በብሔር ላይ ብቻ ማተኮር የሕዝብን ችግር በአግባቡ ያለመረዳት ነው እያሉ መከራከራቸውን ያወሳሉ። ይሁንና የተጠቀሱት መከራከሪያዎች "ብሔር ለምን ከሌሎቹ የቡድን ማንነቶች በላይ ገንኖ ሊወጣ ቻለ?" የሚለውን ግን አይመልሱም ሲሉ መልሰው ይተቿቸዋል። "ሌሎች ምክንያቶች እንደተጠበቁ ሆነው ብሔር ከሌሎቹ ማንነቶች ገንኖ የወጣበት አንዱ ምክንያት የብሔር ጭቆና መኖር ነው።" የግለሰብ መብት መከበር ላይ የሚያተኮሩ የፖለቲካ ልሂቃንን "የቡድን ማንነትን በማጥፋት ስም ጭቆናን የሚያድበሰብስ" እና "የጭቆና ቅሪት" እንዲቆይ የሚያደርግ መፍትሔ ነው ያላቸው ይሏቸዋል። የቡድን ማንነትን ይዞ ከጭቆና ለመውጣት መታገል ደግሞ "የቡድን አክራሪነትን በመፍጠር ከሚፈታው ይልቅ የሚፈጥረው ችግር እየባሰ መጥቷል" ይሉታል። የቡድን አክራሪነት ተጨቁነናል ብለው የታገሉ ቡድኖች "ትግላቸው ገደቡን አልፎና መሥመሩን ጥሶ እነርሱም በምላሹ" ሌሎችን ለመጨቆን የሚሞክሩበትን እና እርሳቸው "አፀፋዊ ጭቆና" ያሉትን ችግር ያመጣል ይላሉ። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "መደመር" መጽሐፍ ተመረቀ በመፍትሔነትም እርሳቸው የሚሟገቱለት የመደመር ፍልስፍና ማኅበረሰባዊ ብሔርተኝነት ያሉትን ብሔር ተኮር የፖለቲካ እንቅስቃሴ እና ሲቪክ ብሔርተኝነት ሲሉ የጠሩትን ዜግነት ወይንም አገር ተኮር ፖለቲካ እንቅስቃሴ አመቻምቾ እንደሚጓዝ ያስረዳሉ።፥ "በብሔር ልሂቃን መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብና" ተገቢ ቦታ አላገኘም ያሉትን ሲቪክ ብሔርተኝነት ለማካተት "ቀጣይ ተዋስኦ መር ድርድሮችን ማድረግ አስፈላጊ ነው" ይላሉ። "የጥራት ችግር ያለበት" ዕድገት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምጣኔ ኃብቱን በተመለከተ በመፅሐፋቸው አራት ምዕራፎችንና 83 ገፆችን ሰጥተው ፅፈዋል። ከመነሻቸው ባለፉት ሃያ ስምንት ዓመታት ምጣኔ ኃብታዊ ዕደገት እና ማኅበራዊ ለውጦች መመዝገባቸውን ያትታሉ፤ ይለጥቁናም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው አዲስ የኃይል አሰላለፍ ለምጣኔ ኃብታዊ ዕድገቱ ምቹ ከባቢ በመፍጠሩ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው የልማት ፋይናንስ በብድርም በዕርዳታም ተገኝቶ መንግስት ማኅበራዊ አገልገሎቶችንና መሠረተ ልማትን እንዲያስፋፋ አስቸሎታል ይላሉ። ሆኖም የተመዘገበው ዕድገት የጥራት ችግር ነበረበት ሲሉ ይሟገታሉ፤ ለሙግታቸውም በአስረጂነት "የኢኮኖሚ በሽታ ምልክቶች" ናቸው ያሏቸውን የኑሮ ውድነትን፣ የሥራ አጥነትን፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን፣ የበጀት ጉድለትን፣ የኤክስፖርት ንግድ መዳከምን፣ ኮንትሮባንድን እና የመሳሰሉትን ይዘረዝራሉ። ምርታማነት እንዲጨምር፣ በዚያውም ልክ ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር መትጋትን የሚሰብኩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምጣኔ ኃብት ስርዓት ተዋናዮች የሚሏቸውን አካላት በቅንጅት እና በመናበብ መስራት አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው ይገልፃሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩ የምጣኔ ኃብት ችግሮችን መንስዔዎች ገበያ ነክ፣ መንግስታዊ እና ሥርዓታዊ ብለው ይፈርጁና በገበያው ውስጥ ፍትሐዊ ውድድር እና ፉክክር እንዳይኖሩ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን ገበያ ነክ ጉድለቶች ናቸው ይሏቸዋል። • "አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው" አቦይ ስብሃት የግሉን ዘርፍ ደካማ መሆን እና የገበያ መረጃዎች በደላላዎች አማካይነት መዛባትን ከዚህ ምድብ ያካትታሉ። መንግስት ከሚገባው በላይ በገበያው ውስጥ ጣልቃ መግባቱ እና ዳተኛ ሆኖ መውሰድ ያለባቸውን የማረጋጋት እርምጃዎች ያለመውሰዱን ደግሞ መንግስታዊ የምጣኔ ኃብት ጉድለት አድርገው ያወሱታል፤ ቀዳሚው በኢትዮጵያ ጎልቶ እንደሚታይም አክለው ፅፈዋል። "የኢኮኖሚ ሥርዓት የደም ሥር" ነው ያሉትን ፋይናንስን በተመለከተ ሲፅፉ "በዓለም አቀፍ የለጋሽ እና አበዳሪ አገራት የፖሊሲ ለውጥ ምክንያት ከውጭ የሚገኘው የልማት ፋይናንስ እንደሚቀንስ ይጠበቃል" ይላሉ። በመሆኑም "በዕዳ ጫና እና በፖሊሲ ለውጥ ምክንያት ባለፉት ዓመታት የተመዘገበውን የኢኮኖሚ እድገት በመጣበት ተመሳሳይ የፋይናንስ ግኝት ሞዴል ማስቀጠል አይቻልም።" ከግብር የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ እስካሁን በግብር ያልተካተቱ ዘርፎችን ማካተትን፣ ከግብር ነፃ ሆነው የቆዩ ዘርፎችን መከለስን እና ሕግን ማስከበርን በመፍትሔነት ይዘረዝራሉ። የመንግስት እና የገበያ ጉድለትን "ለማከም"ም የመንግስት የፕሮጀክት ኃሳቦችን በፖሊሲ ተፅዕኖ ሳይሆን በአዋጭነታቸው ተመሥርቶ መፍቀድም መፈፀምም እንደሚገባ ይከራከራሉ። "ወዳጅም ጠላትም የለም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከውጭ ግንኙነት ጋር በተያያዘ "ወዳጅና ጠላት ብሎ ነገር የለም የሚል መርሕ የምንከተል ይሆናል" ይላሉ። የውጭ ጉዳይ ግንኙነቶች ሊያተኩሩባቸው የሚገቡ ጉዳዮችንም "ጎረቤት ሀገራትን ማስቀደም እና ብሔራዊ ክብርን ከፍ ማድረግ ናቸው" ሲሉ ፅፈዋል። • የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ከየት ወደ የት? ከጎረቤት አገራት ጋር በተገናኘ በደህንነት ሥጋት ላይ ከተመሠረተ ግንኙነት ወጥቶ በምጣኔ ኃብታዊ ትብብር እና ውህደት ላይ ማተኮር እንደሚገባ የሞገቱት ዐብይ የአረብ ሀገራትንም እንደችግር እና ታሪካዊ ጠላት መመልከትን ትቶ እንደአጋር ማየት እንደሚገባ መክረዋል።
news-54917272
https://www.bbc.com/amharic/news-54917272
የአሜሪካ ምርጫ፡ የትራምፕ መሸነፍ አረብ አገራትን ለምን አስደነገጠ?
የዛሬ ሳምንት አካባቢ ነው፤ አምባሳደሩ ስልካቸውን ይበረብራሉ። ትኩረታቸው ተበታትኗል። ቶሎ ቶሎ ይተነፍሳሉ። “ይቅርታ፣ ትኩረት አጣሁ አይደል?” አሉ፣ ከትህትና ጋር።
እኚህ ሰው በታላቋ ብሪታኒያ የሳኡዲ አምባሳደር ናቸው። ዐይናቸውን ከስልካቸው መንቀል ያልቻሉበት ምክንያት አለ። አሜሪካ ‘ማሊያ’ እየቀየረች ነው። የአሜሪካንን ምርጫ በአንክሮ እየተከታተሉ ነው የተረበሹት። አብረዋቸው ያሉትን ሰዎች ደጋግመው ይቅርታ ሲጠይቁ በነበረበት በዚያ ቅጽበት የአሜሪካ ግዛት ዊስኮንሰን ቆጠራ ውጤት እየተገለጸ ነበር። ዊስኮንሰን እንደ ሚሺጋን ሁሉ ባይደን አሸንፈዋል። አምባሳደሩ ያለ ምክንያት አልደነገጡም። ያለ ምክንያት ትኩረታቸው አልተበታተነም። አገራቸው ሳኡዲ ትራምፕን አጣች ማለት ነዳጅ ማውጫዋ ደረቀ ከማለት የሚተናነስ መርዶ አይደለም። ምናልባት ይህ ዐረፍተ ነገር ተጋኖ ይሆናል። በዲፕሎማሲ ዋጋ ግን አልተጋነነም። ለዚህም ይመስላል ሳኡዲዎች ለጆ ባይደን እንኳን ደስ ያለዎት ለማለት እንኳ ጊዜ የወሰደባቸው። ከድንጋጤያቸው የበረዱት ዘግይተው ነው። ትልቅ አጋራቸውን፣ ትልቅ ወዳጃቸውን፣ ቀኝ እጃቸው ነው በሽንፈት ያጡት። ዶናልድ ትራምፕ። የባይደን ድል ለሳኡዲ አረቢያና ሌሎች የገልፍ አገሮች ብዙ ጦስ ይዞ መምጣቱ ከወዲሁ እየተነገረ ነው። አሜሪካ ከገልፍ አገራት ጋር ያላት አጋርነት ከ1945 ዓ ም የሚጀምር ነው። በነዚያ ሁሉ ዘመናት በአመዛኙ መልካም የሚባል ሆኖ ነው የዘለቀው። ይህ ግሩም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በባይደን ጊዜ መልኩን ይለውጣል ማለትም አይደለም። ነገር ግን የትራምፕ ዘመን ግንኙነት ላይመለስ ሄዷል። ትራምፕ ለሳኡዲ የልኡላን ቤተሰብ እንደ አጎት ነበሩ። ትራምፕ ገና እንደተመረጡ በ2017 መጀመርያ እግራቸውን ያነሱት ወደ ሪያድ ነበር። አንድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እንደተመረጠ ቀድሞ ወደ አረብ አገር ይሄዳል ተብሎ አይጠበቅም። የዶናልድ ትራምፕ አማቻቸው (የሴት ልጃቸው ባል) ጃረድ ኩሽነር ከኃያሉ ልዑል ከመሐመድ ቢን ሳልማን ጋ ጥብቅ ምስጢረኛ ነው። የትራምፕ ቤተሰብና የሳኡዲ ልዑላን ፍቅራቸው ከዓይን ያውጣችሁ በሚባል ደረጃ መድረሱን የሚያሳዩ ብዙ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል። በ2018 ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ በግፍ ኢስታንቡል የሳኡዲ ቆንጽላ ውስጥ ሲገደል ዓለም በሙሉ በሳኡዲው ልዑል ፊቱን አዞረበት። ልዑሉ በሕግም በዲፕሎማሲም እንዲጠየቁ ግፊቱ በረታ። ነገሩ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ደረሰ። ቱርክ ዓለምን አስተባብራ ብዙ ርቀት ሄደች። በዚህ አስጨናቂ ጊዜ ለልዑሉ አንድ ሰው ነበራቸው። ያን ግፊት ያቆሙላቸው ሰው ዶናልድ ትራምፕ ይባላሉ። ትራምፕ ለልዑላዊያኑ የዋሉት ውለታ በዚህ አላበቃም። የአሜሪካ የላይኛው ምክር ቤታቸው ለሳኡዲ ውስብስብና ውድ የጦር መሣሪያዎች ከእንግዲህ እንዳይሸጡላት ብሎ ነበር። ይህም የመጣው የጋዜጠኛውን እጅግ አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ ነበር። ይህን ለመወሰን ጫፍ ሲደርስ የነበረው ሴኔት ትራምፕ ነገሩን አከሸፉበት። ይህ የትራምፕ ከሰብአዊ ጨቋኞች ጎን የመቆም ውለታ ለሳኡዲ ብቻ አልነበረም። ለባሕሬን፣ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስም ተመሳሳይ ውለታን ሰርተዋል። ለዚህም ነው እነዚህ አገሮች የትራምፕ መሸነፍ ክው ብለው እንዲቀሩ ያደረጋቸው። ለመሆኑ የትራምፕ መሄድና የባይደን መምጣት በገልፍ አገሮች በተጨባጭ ምን ይቀይራል? የየመን ጦርነት ባራክ ኦባማ በዋይት ሐውስ ለ8 ዓመት ሲኖሩ ምቾት ከነሷቸው ነገሮች አንዱ ሳኡዲ በየመን ዜጎች ላይ ታደርስ የነበረው የአየር ድብደባ ነበር። ሳኡዲ በሁቲ አማጺዎች ላይ ቦምብ ስታዘንብ ነው የኖረችው። ሁቲዎች በኢራን ይደገፋሉ። ኢራን የሺአ ኢስላም መሪ አገር ናት። የመን በሳኡዲ ተጽእኖ ሥር ሆና የሱኒ ኢስላም መስመርን እንድትከተል ነው ትግሉ። ነገሩ በሃይማኖታዊ መስመር ውስጥ ፖለቲካዊ ተጽእኖን ለማሳደርና የአካባቢው ዋና አለቃ ሆኖ ለመቀጠል የሚደረግ ፉክክር እንጂ ያን ያህልም መንፈሳዊ ተልእኮ አለበት ለማለት አያስደፍርም። ነገሩ ያልጣማቸው ኦባማ ዋይት ሐውስን ሲለቁ ታዲያ ሳኡዲ ለ2 ዓመታት የመንን በአውሮፕላን ደብድባ ያገኘችው ውጤት እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። እንዲያውም ንጹሐንን ፈጅታለች። በመጨረሻ በካፒቶል ሂል ጉምጉምታው ሲበረታ ኦባማ በመጨረሻዎቹ የሥልጣን ዓመታት ቶሎ ብለው አሜሪካ ለሳኡዲ የምታደርገውን የወታደራዊና የደህንነት ድጋፍ አቋረጡ። ትራምፕ ዋይት ሐውስ ሲገቡ ግን ይህንን ቀለበሱት። የየመን ሰቆቃ የበረታው ከዚህ በኋላ ነበር። አሁን ግን ነገሮች ይለወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባይደን ከኦባማ ሥር ሆነው አሜሪካንን በመሩበት ዘመን የየመን ጦርነትና የሳኡዲ ድብደባ ያደረሰውን ሰብአዊ እልቂት ተመልክተዋል። ትርፍና ኪሳራውን መዝነዋል። ሺዎች የተቀጠፉበት፣ ሕጻናት በረሀብ አለንጋ የተቀጡበት የየመን ጦርነት ከንቱ የከንቱ ከንቱ እንደሆነ አገናዝበዋል። እርግጥ ነው የሁቲ ሚሊሻ የመንን በሙሉ ቁጥጥር ሥሩ ማድረግ ለአሜሪካ የሚጥም አይሆንም። ይህም ኢራን አጋር ታገኛለች ከሚል ፍራቻ ነው። ሆኖም ባይደን ከሰሞኑ ላቋቋሙት የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ካውንስል እንደተናገሩት ከሳኡዲ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንደገና እንደሚያጠኑት ጠቁመዋል። የየመን ተዋጊዎችና ሳኡዲዎች ከዚህ በኋላ ችግራቸውን በጠረጴዛ ዙርያ እንዲፈቱ ባይደን ግፊት ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል። ለነገሩ ሳኡዲም ሆነች ብልጹጓ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ይሄ የየመን ጦርነት ማብቂያ እንደማይኖረው ዘግይተውም ቢሆን የተረዱ ይመስላሉ። በቅርብ ጊዜ የጦር ማቆም ስምምነቶችን ያደረጉትም ለዚህ ይሆናል። ኳታር የፔንታጎን ሳሎን ናት ይላሉ የአካባቢ ፖለቲካ አዋቂዎች። እጅግ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውና በመካከለኛው ምሥራቅ ወሳኙ የጦር ስፍራ አልኡደይድ የሚገኘው በኳታር ነው። አሜሪካ ከአልኡደይድ ቀጠና ሆና ነው አፍጋኒስታንንም ሆነ ሶሪያን የአየር ኃይል ጥቃት የምትሰነዝረው። መካከለኛው ምሥራቅንና የአየር ክልሉን የምትቆጣጠረውም ከዚህ ከአልኡይዲ ነው። ይህ የኳታር ውለታ ታዲያ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ እንዲመለስ ይፈለጋል። እርግጥ ነው አሜሪካ ለኳታር ልዩ ጥበቃ ታደርጋለች። ሆኖም የኳታር ፍላጎት ሌላ ነው። ኳታር ሀብታም አገር ብትሆንም ማንም የማይቋቋመው እቀባ ጥለውባታል፣ የገዛ ወዳጅ አገሮቿ። የገዛ ጎረቤቶቿ። ሳኡዲዎች፣ ኢምሬቶች፣ ባህሬኖችና ግብጽ በኳታር ላይ የጨከኑት በየአገሮቻችን አብዮት ታስነሳብናለች፣ የሕዝብ አመጽ በገንዘብ ትደግፍብናለች ብለው ነው። የግዙፉ አልጀዚራ ዜና ጣቢያም ለአረብ አገራቱ የጎን ውጋት ሆኖባቸዋል። ኳታር አልጀዚራን እንድትዘጋላቸው አገራቱ ይሻሉ። ግብጽም አልጀዚራን እንደ ጦር ነው የምትፈራው። ከኳታር ጋር ያላቸውን ድንበር የመክፈትና ግንኙነቶችን የማሻሻሉ ነገር እውን የሚሆነው ከ11 ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ የአልጀዚራ መዘጋትም ሲጨመርበት ነው። ይህ በኳታር ላይ አረብ ወገኖቿ የጣሉት ማዕቀብ የተጀመረው ትራምፕ ሪያድን በጎበኙበት በ2017 አካባቢ ነበር። ኳታሮች ትራምፕ ይህንን ጉዳይ በዋዛ ያልፉታል ብለው በጭራሽ አላሰቡም ነበር። አገራቱን ተቆጥተው ወደ ድርድር ያመጧቸዋል ብለው የኳታር ኤሚሮች ተስፋ አድርገው ነበር። ያ ግን አልሆነም። በእርግጥ ትራምፕ የኳታር ወዳጅነትን በደንብ አያውቁም ነበር ነው የሚባለው። ያን ጊዜ የፖለቲካ ግንዛቤያቸው የሳሳ ነበር የሚሉት ተንታኞች ኳታር ለፔንታጎን እጅግ ወሳኙን የአል ኡደይድ የጦር ሰፈር እንደምታቀርብ ሲነገራቸው ግን ኳታርን በይፋ ደግፈው ይህ የገልፍ አገሮች እቀባ እንዲነሳላት መናገር ጀምረው ነበር። ሆኖም ጉዳዩን አልገፉበትም። ምናልባት ውስብስብ ፖለቲካዊ ኩነቶች ተፈጥረው ይሆናል። ምናልባትም ሁነኛ የጦር መሣሪያ ሸማቿን ሳኡዲን ላለማስቀየም ይሆናል። ብቻ ትራምፕ ነገሩን ዘነጉት። ባይደን መምጣታቸውን ተከትሎ ኳታር ወንድም አገሮች የጣሉባት እቀባ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል። አረብ አገራትና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ብዙዎቹ የገልፍ አገራት የሰብአዊ መብት አያያዛቸው አሳፋሪ የሚባል ነው። ትራምፕ ግን ለዚህ ግድ ያላቸው ሰው አልነበሩም። በአረብ አገራቱ ሰብአዊ መብት አያያዝ እንዲሻሻሉ በንጉሣዊያኑ ላይ ጫና አድርገውም አያውቁም። የርሳቸው ትኩረት የነበረው ከአረብ አገራቱ የሚገኝ የነዳጅ ሪያል ነበር። ባይደን ከዚህ ምጣኔ ሀብታዊ ጠባብ እይታ በከፊልም ቢሆን ዞር ብለው የሰብአዊ መብት አያያዞች እንዲሻሻል ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይገመታል። ሳኡዲ ለሴቶች ነጻነት የምትመች አልሆነችም። ቢን ሰልማን በዚህ ረገድ ጥቂት ማሻሻያ ካደረጉ በኋላ ትንሽ ውዳሴን እንዳገኙ ብዙ የመብት ታጋይ ሴቶችን እስር ቤታቸው አጉረዋል። ኳታር በውጭ አገራት ሰራተኞች አያያዝ ላይ አሳፋሪ ታሪክ አላት። ኢምሬትሶችም በሰብአዊ መብት ረገጣ በደፈናው ይተቻሉ። ከሁሉ ከሁሉ ሳኡዲ በኻሾግጂ ላይ ያደረገችው ይቅር የሚባል አልሆነም። መቺ ኃይል ልካ የገዛ ዜጋዋን በኢስታንቡል የገዛ ኤምባሲዋ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቱን ካጠፋች በኋላ ሬሳው እንኳ የት እንደተጣለ አንዳይታወቅ አድርጋ ዓለምን ያስደነገጠ ኢሰብአዊ ድርጊትን ፈጽማለች። ጆ ባይደን የዋሺንግተን ፖስት ጋዜጠኛው ጀማል ኻጆግኒን ጉዳይ ተንተርሰው ሳኡዲን ያስጨንቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
news-55891532
https://www.bbc.com/amharic/news-55891532
በአውስትራሊያዊቷ ፀሐፊ የተፃፈው የፈይሳ ሌሊሳ ታሪክ
'ኧ ታይም ቱ ቢ ቦርን' - የፈይሳ ሌሊሳ ታሪክን የሚዳስስ መፅሐፍ ነው።
"ለተቃውሞው ያለኝን ድጋፍ ለማሳየት ለየት ያለ መንገድ መርጫለሁ። በ2016 [በፈረንጆቹ] የተካሄደው የሪዮ ኦለምፒክ ላይ እጄን አጣምሬ ወደ ላይ ማንሳቴ ምን ያክል ትርጉም እንዳለው ሳስብ አሁንም ድረስ እገረማለሁ።" ዓለም በጉጉት ሲመለከተው በነበረው የሪዮ ዲ ጄኔሪዮ ኦለምፒክ መድረክ ላይ ፈይሳ አንድ ያልተጠበቀ ድርጊት ፈፀመ። ይህ ጉዳይ ከሃገር ቤት አልፎ የዓለም መነጋገሪያ ለመሆን በቃ። በወቅቱ ኢትዮጵያን ያስተዳድር የነበረው መንግሥት ከሃገር ውስጥና ከውጭ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር። በዚህ ተቃውሞ ላይ የኦሮሞ ወጣቶች ሚና ጎልቶ የወጣ እንደነበር የማይካድ ነው። ሁለት እጆችን ወደላይ ከፍ አድርጎ ማጣመር ደግሞ የተቃውሞው አርማ ነበር። ሌሊሳም ያደረገው ይህንን ነው። በማራቶን ውድድር ተሳትፎውን ጨርሶ የመጨረሻው መስመር ላይ ሲደርስ ሁለቱን እጆቹን በማጣመር ተቃውሞውን በይፋ ተቀላቀለ። ዓለምም ጉድ አለ። አውስትራሊያዊቷ ፀሐፊ ስቴፋኒ ይህን ተከትላ በፈይሳ ሕይወት ዙሪያ አንድ መፅሐፍ ለመፃፍ ቆርጣ ተነሳች። ያሰበቸውም ተሳክቶ 'ኧ ታይም ቱ ቢ ቦርን - ዘ ስቶሪ ኦፍ ፈይሳ ሌሊሳ' የተሰኘ ታሪክ አሳትማለች። ዘንድሮ በታተመው በዚህ መፅሐፍ የመጀመሪያ ክፍል ፈይሳ ከብሪታኒያዊው ሞ ፋራህ ስለተበረከተለት ስጦታ ይዘክራል። "ለኔ በጣም ጎልተው ከሚወጡ ነገሮች አንዱ ይሄ ነው" ይላል ፈይሳ ከሩጫው በኋላ ስለተፈጠረው ነገር ሲያወራ። "ከ ሞ ፋራህ በጣም ውድ ስጦታ ተሰጠኝ። ተቃውሞዬን ከግምት በማስገባት ልዩ የሆነ ጫማ አበረከተልኝ።" "ፈይሳ፤ እኔም በአንድ ወቅት እንዳንተ ነበርኩኝ። የምጫማው ጫማ አልነበረኝም" ሲል ሞ ፋራህ ነገረኝ ይላል ፈይሳ። ፈይሳ ሞ ፋራህ ጫማውን ሲያበረክትልኝ ዓይሞቹ እምባ ቀሯቸው ነበር ይላል። "እኔም እንዳንተ ፈተና የበዛባት ሃገር ነው ትቼ የመጣሁት" ሲል እንደነገረው ፈይሳ በመፅሐፉ አስነብቧል። መፅሐፉ ስለ ፈይሳ እጅ ማጣመር ብቻ የሚያወራ አይደለም። ስለ ኦሮሞ ተቃውሞ ጭምር እንጂ። የፈይሳ የተጣመሩ እጆች ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ተቃውሞ ለዓለም ተናግረዋል። የመፅሐፉ ተያቢ ምንም እንኳ መፅሐፉን የፃፈችው አውስትራሊያዊቷ ስቴጋል ትሁን እንጂ የሚተርከው ፈይሳ ነው። የፈይሳ ትዝታዎች በጉልህ የተቀመጡ ናቸው። ፀሐፊዋ ፈይሳ የት እንዳደገ፤ ያደገበትን ሥፍራ መልክዓ ምድር፤ ቤተሰቦቹን፤ ሲያድግ ያስተውለው የነበረው ኢ-ፍትሐዊነትን አጥንታለች። ፈይሳን ካደገበት ሥፍራ ጋር ምን ያህል የተቆራኘ ማንነት እንዳለው መፅሐፉ ይተነትናል። አውስትራሊያዊቷ ፀሐፊና አስተማሪ ዶክተር ስቴፋኒ ስቴጋል አዲስ አበባ የመጣችው የበጎ ሥራ ተግባራት ላይ ለመሠማራት ነው። ታድያ ሸገር ሳለች ፈይሳን እጁን አጣምሮ ሃገር አጀብ ሲያሰኝ፣ ዓለምን ሲያነጋግር ተመለከተች። ይሄኔ ነው የፈይሳ ሕይወት ቀልቧን የገዛው። "ኢትዮጵያ ጥንታዊና ለመረዳት አስቸጋሪ የሆነች ሃገር ናት። ምንም እንኳ ስሟ ከድህነት ጋር ይያያዝ እንጂ በረዥም ርቀት ሯጮቿም ትታወቃለች። ይህ ነው ሁሌም እንድገረም የሚያደርገኝ" ትላለች ዶ/ር ስቴጋል። ዶ/ር ስቴጋል ወደ ኢትዮጵያ ያቀናችው በፈረንጆቹ ነሃሴ 2016 ነበር። ስትመጣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማገልገል ነበር። አዲስ አበባ ከመግባቷ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ከተማዋ በተቃውሞ ታምሳ ነበር። "ልክ እንደ መጣሁ ሰዉን መታዘብ ጀመርኩ። የአኗኗር ዘይቤያቸውን እና ውስጣቸውን ያለውን ቁጣ ማየት ችዬ ነበር" የምትለው ፀሐፊዋ የፈይሳን ሕይወት ማጥናት ተያያዘች። ከፈይሳ ፈቃድ ካገኘች በኋላ ነው ወደ ሥራዋ የገባችው። ከዚያ በኋላ ያለው ታሪክ በመፅሐፉ ላይ ቁልጭ ብሎ ታትሟል። "ኢትዮጵያ ውስጥ ያሳለፍኩት፣ ከፈይሳ ጋር የነበረኝ ግንኙነት፣ ከሌሎች ወዳጆቼ ጋር የነበረኝ ቆይታ እንደሁም ቃል ምልልስ ያደርግኳቸው ሰዎች ናቸው ይህን መፅሐፍ እንዳገባድደው የረዱኝ" ትላለች ፀሐፊዋ። ዶ/ር ስቴጋል ለፈይሳ ያላት አድናቆት እጅግ ለየት ያለ ነው። እሱም ታሪኩን ሳይሸሽግና ሳይነፍግ ሙሉ በሙሉ አጫውቷታል። የሱን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክን ጭምር። ነሃሴ - 2016 - ሪዮ ፀሐፊዋ መፅሐፉን የምትጀምረው ከታች በተጠቀሰው የፈይሳ ንግግር ነው። "የሪዮ ኦለምፒክ ላይ ስሳተፍ ልቤ ሙሉ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶችና ወንዶች፣ አብዛኛዎቹ በኔ ዕድሜ ያሉ በመንግሥት እጅ በጭካኔ ተገድለዋል። ይሄን እያሰብኩ ነው የሮጥኩት። የቅርብ ጓደኞቼ ትዝታ፣ ቤተሰቤ፣ ዘመዶቼ ኦሮሞ ስለሆኑ ብቻ ተገድለዋል፣ ተሰቃይተዋል፣ ታሥረዋል፣ ታፍነው ተወስደዋል፣ ሰብዓዊ ክብራቸው ተገፏል። ይህንን ኢ-ፍትሐዊነት በውስጤ አድርጌ ነበር ስሮጥ የነበረው። ይህን ጭካኔ እኔም አይቼዋለሁ፤ ስሰማው የኖርኩትም ታሪክ ነው። ለዚህ ነው በሪዮ ኦለምፒክ መድረክ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞዬን ማሰማት የመረጥኩት" ምንም እንኳ የወንዶች ማራቶን ውድድርን ኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ ቢያሸንፈውም ፈይሳ ሌሊሳ ሁለተኛ ከመውጣት ባለፈ ታሪክ መሥራት ችሏል። የፈይሳ ሚስት ኢፍቱ ሙሊሳ በወቅቱ አዲስ አበባ ነበረች። ሩጫውን በቴሌቪዥን መስኮት ስትከታተልም ነበር። "በጣም ፈርቼ ነበር። ነገር ግን ብዙ አልተገረምኩም። ምክንያቱም ውስጡ የነበረውን ቁጣ አውቅ ነበር" ትላለች ኢፍቱ። ፈይሳ ልክ እንደሌሎቹ ተቃዋሚዎች መንግሥት በሕዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ጭቆና ይጠየፍ ነበር። በ1982 ዓመተ ምሕረት ቱሉ ቡልቱማ በተሰኘች ከተማ የተወለደው ፈይሳ የቤተሰቦቹን ከብት በመጠበቅ ነበር ልጅነቱን ያሳለፈው። የልጅነት ምኞቱ ሲያድርግ ወታደር መሆን ነበር። ነገር ግን በረዥም ርቀት ሩጫ ኮከቦቹ አበበ ቢቂላና በኃይሌ ገብረስላሴ ታሪክም ይመሰጥ ነበር። ፈይሳ ስለ ወንዱ አያቱ ተናግሮ አይጠግብም። አያቱ የሚነግሩትን ታሪክ እየሰማ ነበር ያደገው። በልጅነቱ ከሚያዘውትራቸው ጨዋታዎች አንዱ የፈረስ ግልቢያ ነበር። ወደ ትምህርት ቤት በሩጫ መሄድ፣ ቅዳሜ ገበያ ሄዶ ዶሮና በግ ለመሸጥ የሚያቋርጣቸው አረንጓዴ መስኮች፣ ማራኪው መልክዓ ምድር፣ ማሕበረሰባዊ እሴቶች በፈይሳ ትዝታ ማሕደር ውስጥ ታትመው የተቀመጡ ናቸው። ይህን የፈይሳን መፅሐፍ የሚያነብ ሰው ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ ማወቁም የማይቀር ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ባሕል፣ እምነትና ቋንቋ ይዳሰሱበታል መፅሐፉ። ፀሐፊዋ የፈይሳን አስተሳሰብ ለመረደት ብዙ ጊዜ አብራው ቁጭ ብላ ወግ ትጠርቅ እንደነበር፤ አንዳንዴ ክርክር ሁላ ውስጥ እንደሚገበ ኡ ትናገራለች። የቀረውን ለአንባቢው መተው ሳያዋጣ አይቀርም። ነገር ግን መፅሐፉ ከፈይሳ ታሪክ እጆችና ከሕይወቱ በዘለለ በርካታ እሴቶች የታጨቁበት እንደሆነ ሹክ ማለት ያሻል። ፈይሳን ለተቃውሞ እጆቹን ለምን አነሳ? ከትውልድ መንደሩ ወደ አዲስ አበባ ያደረገው ጉዞ ምን ይመስል ነበር? ከዓለም አቀፍ ውድድሮች ያገኘው ነገር ምንድነው? ለሁለት ዓመታት በስደት መኖር ምን ይመስላል? ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ለምን ወሰነ? ሲመለስ ምን ገጠመው? መፅሐፉ ከሚመልሳቸው ጥያቄዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። መፅሐፉ ወደ ኢትዮጵያ ቋንቋዎቹ መቼ ሊተረጎም ይችላል የሚለው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም። ፀሐፊዋ በኋላኛው የመፅሐፉ ገፆች ከጥቅምት 2018 [በፈረንጆቹ] ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠሩ ክስተቶችንና ፈይሳ ላይ የፈጠሩትን ተፅዕኖ ትዳስሳለች። ነገር ግን የመፅሐፉ ኦፊሴላዊ መጠናቀቂያ ክፍል ፈይሳ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት መፅሐፉ የተጠናቀቀው ከአንድ ዓመት በፊት ስለሆነ ነው ትላለች።
news-44478998
https://www.bbc.com/amharic/news-44478998
"አንዳርጋቸው ይለቀቅ አለበለዚያ ሥልጣኔን እለቃለሁ"
ማክሰኞ ግንቦት 21 2010 ዓ.ም ከእስር የተፈቱት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ነፃ ከወጡ በኋላ በቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ከተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል ባሻገር ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተገናኝተው ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ መወያየታቸውን ለቢቢሲ ሃርድ ቶክ ተናግረዋል።
አቶ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላደረጉት ውይይት ለየትኛውም የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሃን ሳይናገሩ ቆይተው ለቢቢሲ አንዳንድ ጉዳዮችን አንስተው ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለየያዩ ተፎካካሪ ኃይሎች ጋር ምን አይነት እርምጃ ለመውሰድ ስለማሰባቸው እንደገለፁላቸውና በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እምነት እንዳደረባቸውም ገልፀዋል። "ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው'' አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኢህአዴግ ውስጥ የእርሳቸውን መፈታት የማይፈልጉ ግለሰቦች እንደነበሩ እንደነገሯቸውና እርሳቸው ግን "ልቀቁት አለበለዚያ ሥልጣኔን እለቃለሁ" በማለት እንደተከራከሩ እንደነገሯቸው ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለእርሳቸው መለቀቅ ያላቸውን ሥልጣንና ኃላፊነት አደጋ ላይ መጣላቸውን መስማታቸው ለመቀራረባቸው አንድ ምክንያት እንደሆነ አቶ አንዳርጋቸው ተናግረዋል። "እነዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ትክክለኛ ቃላት ናቸው፤ ደግሞም አምናቸዋለሁ፤ ምክንያቱም በግንባሩ ውስጥ የእኔን መፈታት በተመለከተ ሊገጥማቸው የሚችለውን ተግዳሮት አውቃለሁ" ሲሉ ለቢቢሲ ሃርድ ቶክ ገልፀዋል። የትጥቅ ትግልና ግንቦት 7 ለአቶ አንዳርጋቸው የትጥቅ ትግል ማድረግ የድርጅታችሁ መሰረታዊ አቋም ነው ተብለው ሲጠየቁ በ1997 ምርጫ ወቅት የተከሰተውን ከተመለከትን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት የወሰደው እርምጃ ወደ አንድ ጥግ ገፍቶናል ብለዋል። ከዚያም በኋላ በየትኛውም የትግል ስልት ለመሳተፍ ወሰንን ሲሉም አስረድተዋል። ይህንን በይፋ ካወጅን በኋላ ግን አንድም ጥይት ኢትዮጵያ ውስጥ ተኩሰን አናውቅም ሲሉም አክለዋል። እርስዎ በሽብረ ተግባር በመሰማራት ከተከሰሱ እና በሌሉበት ከተፈረደብዎ በኋላ በበላይነት የሚመሩት ግንቦት 7 በተለያየ ጊዜ በሰሜን ኢትዮጵያ፤ በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ጥቃቶችን እንዳደረሰ ሲገልፅ በአርባምንጭ ደግሞ 20 ወታደሮችን እንደገደለና 15 እንዳቆሰለ ገልጿል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም ስለጥቃቶቹ በወቅቱ መግለጫ ሰጥተዋል ተብለው የተጠየቁት አቶ አንዳርጋቸው "በእስር ላይ ብሆንም ግንቦት 7 አንድም ጥይት በኢትዮጵያ ምድር እንዳላጮኸ ነው የማውቀው።" ብርሃኑም ቢሆን አጠቃላይ ያለውን ተቃውሞ እና እምቢተኝነት መግለፁ ይሆናል በማለት በእስር ላይ እያሉ ምንም አይነት መረጃ ይደርሳቸው እንዳልነበር ጨምረው ገልፀዋል። አክለውም ከተፈቱም በኋላ እንዲህ አይነት እርምጃ ስለመወሰዳቸው ማንም እንዳልነገራቸው አስረድተው ከግንቦት 7 ይልቅ ሌሎች በሀገሪቱ የታጠቁና የሚታገሉ ኃይሎች ይህንን እርምጃ ወስደዋል ብለው እንደሚያምኑ አስረድተዋል።። በተጨማሪም አሁን በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ባለበት መልኩ እየተሻሻለ ከሄደ እና እርምጃው ካሳመናቸው የትጥቅ ትግልን ከማውገዝ ወደኋላ እንደማይሉ ተናግረዋል።
48935082
https://www.bbc.com/amharic/48935082
“የመከላከያው በአደባባይ ሚዲዎችን እከሳለሁ ማለት አስፈሪ ነው” ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል የቀድሞ ዲን እና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካው ኒው ሜክሲኮ ዩኒቨርሲቲ በማስተማር ላይ የሚገኙት ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ ከጥቂት ወራት በፊት ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ ለውጡን ተከትሎ የመጣውን የሚዲያ ነፃነት ሚዲያው በአግባቡ ካልተጠቀመበት መንግሥት ዳግም ሚዲያውን ወደ መጫን ሊሄድ ይችላል ብለው ነበር።
በአገር ውስጥ በተለይም በውጭ ሃገር በአክቲቪዝምና በተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩ ሚዲያዎች አካሄዳቸውን አስተካክለው ነው ወደ ጨዋታው ሜዳ መግባት ያለባቸው ብለው ነበር። አሁን ደግሞ በቅርቡ ሚዲያው ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ነገሮችን በማስመልከት የተወሰኑ ጥያቄዎችን አንስተንላቸዋል። ጋዜጠኞች እየታሰሩ ነው፤ አንዳንድ ፕሮግራሞችም እየታጠፉ ነው። ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ የመከላከያ የተቋሙን ስም አጥፍተዋል፤ ሕዝብ ተቋሙን እንዲጠራጠር የሚያደርጉ ሐሰተኛ መረጃዎችን አሰራጭተዋል ያላቸውን ሚዲያዎች እከሳለሁ፤ ለመክሰስም ዝግጅቴን ጨርሻለሁ የሚል መግለጫ ሰጥቷል። እነዚህ እስሮችና እንደ መከላከያ አይነት ትልቅ የመንግሥት ተቋም ምንም እንኳን ሚዲያዎቹን በስም ባይጠቅስም የምከሳቸው ሚዲያዎች አሉ ማለቱን እንዴት ነው የሚያዩት? ከዚህ ቀደምም ተመልሶ ወደኋላ የመሄድ ነገር ሊያመጣ ይችላል ብለውን ነበር። ዶ/ር አብዲሳ፡ ሚዲያው የተሰጠውን ነፃነት በአግባቡ መጠቀም ካልቻለ መንግሥት ዞሮ እንዳሁኑ ወዳለ ነገር ሊመጣ ይችላል የሚል ነገር ነበረኝ። በተለይም ደግሞ ህብረተሰቡ ሚዲያው ከመስመር የመውጣቱን ነገር እያየ ሲሄድ የመጀመሪያ የሚመጣው ምንድን ነው፤ ይህንን አድርግ [ኮንትሮል አድርግ] የሚል ነገር ስለሆነ መንግሥት ከዚያ በኋላ ለሚወስደው ነገር በሙሉ ትክክል እንደሆነ ህብረተሰቡ እንዲያይ የሚያደርግ ነገር ይሆናል። ተገቢ ባይሆንም እንዲሁም ዞሮ ዞሮ የሐሳብ ነፃነትን እየገደበ የሚሄድና ነፃነት እያጨለመ የሚሄድ ነገር ቢሆንም በነፃነቱ ጊዜ የነበረው የሚዲያው ያልተገባ አካሄድ በማህበረሰቡ ዘንድ በአሉታዊ መልክ ስለሚታይ መንግሥት የሚወስደውን ከባድ እርምጃ ሁሉ እንደ ትክክለኛ ነገር የማየት አዝማሚያ ሊኖረው ይችላል። ከዚህ ቀደም የሚዲያ ነፃነቱን በአግባቡና ሙያዊ መርህን በተከተለ መንገድ ኃላፊነትን ታሳቢ አድርጎ መጠቀም አለበት ያልኩትም ነገር ይህ ነው። አሁን አገሪቱ ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ የፖለቲካ ሁኔታዎች ሥርዓቱ ራሱ የተጨነቀ፤ የደነገጠበት[ነርቨስ] ሰዓት ነው። የትኛውም ዓለም ላይ የመንግሥታት የመጀመሪያው ተግባር [ኢንስቲንክታቸው] የራሳቸውን ደህንነት የማረጋገጥ ነው። ከዚያ በኋላ ነው ሌላው ነገር የሚመጣው። (ስለዚህ የራሱን ደህንንት ማረጋገጥ የየትኛውም መንግሥት የመጀመሪያ እርምጃ ነው።) • "ከውጪ የገቡ ሚዲያዎች 'ማገገምያ' መግባት ያለባቸው ይመስለኛል" በአማራ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ የተከሰተውንና መንግሥት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ነው የሚለውን ነገር እንዲሁ ካመንን መንግሥት ምን ያህል ውጥረት ውስጥ እንደገባ የሚያመለክት ነው። (ስለዚህ የመጀመሪያው ኢንስቲንክት የራሱን ሰርቫይቫል ኢንሹር የማርደግ ጉዳይ ነው)። ይሄን ለማድረግ ደግሞ የትኛውንም አይነት እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ የሚልበት አይደለም የሚሆነው። ስለዚህ አሁን እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች በጣም አሳሳቢ ናቸው። የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ይታወቃሉ፤ በገንዘብም በሙያዊ አቅምም የዳበሩ አይደሉም። እንደ መከላከያ አይነት ትልቅ የመንግሥት የፀጥታ ተቋም ሚዲያዎችን እከሳለሁ ማለቱ ምን ያህል ሚዲያዎችን ሊያስፈራና ተፅኖ ሊያሳድር ይችላል ብለው ይገምታሉ? ዶ/ር አብዲሳ፡ በጣም አስጊ ነገር ነው። 'ሚሊተሪ' [ወታደራዊ ኃይል] በአፍሪካ ውስጥ ሁሉም ነገረ ነው። በአብዛኛው የአፍሪካ አህጉር የወታደሩ ኃይል ታሪክ ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነገር ነው። ስለዚህ በአሁን ሰዓት በወታደሩ በኩል መጥቶ በዚህ መንገድ በአደባባይ ላይ ይህንን ነገር ወደ ተግባር ባያመጣውም እንኳን አስፈሪ ነገር ነው። ሚዲያ ላይ የሚሠሩ ሰዎች በፍርሀት ራሳቸውን በጣም ሴንሰር እንዲያደርጉ፣ ነገ ምን ይከሰታል? ብለው የመደናገጥ ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርግም ጭምር ነው የሚሆነው። ሚዲያ ላይ ወጥቶ አስተያየት ለመስጠት የሚጋበዙ ሰዎችም ሁሉ እንደ ድሮው በፈቃደኝነት አስተያየት ከመስጠታቸው በፊት ሁለት ጊዜ እንዲያስቡ የሚያደርግበት እድልም ሰፊ ነው። • 'ለአደጋ የተጋለጠው' የኢትዮጵያ ህትመት ሚድያ ስለዚህ በተለይ አሁን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በሚል ስለሆነ የተቀመጠው [ዲፋይን] የተደረገው፤ መንግሥት ከዚህ ጋር ይገናኛል ወይም ለእሱ ድጋፍ ያደርጋል ያለውን ሁሉ የሚዲያ ተቋማትን ጨምሮ እንደ ጠላት የመወሰድ እድሉ ሰፊ ነው። መንግሥት በዚህ ሰዓት የራሱን ህልውና ለማረጋገጥ ማንኛውንም ርቀት መሄድ የሚችልበት እድም ሰፊ ነው። በእኔ ፀሎት መከላከያ ይህንን ዛቻ ወደ ተግባር አይቀይረውም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። አለበለዚያ በጣም ትልቅ የሆነ ችግር ነው ይዞ የሚመጣው። መንግሥት ታዲያ ምንድነው ማድረግ ያለበት? ዶ/ር አብዲሳ፡አግባብ በሆነ የሕግ ማዕቀፍ መሄዱ ነው አስፈላጊ የሚሆነው። ለዚህም ነው ሚዲያ እንዴት ነው የሕግ አግባቦችን የሚከታተለው? እንዴት ነው የሚዳኘው? የሚሉትን ነገሮች መጀመሪያውኑ እየሠሩ የማስቀመጥ ነገር አስፈላጊ የሚሆነው። ጋዜጠኞችን ጨምሮ ብዙዎችን ለእስርና ለስደት ያበቃው የፀረ ሽብር አዋጁ አሁን የታሰሩ ሰዎች ላይ እንደተጠቀሰ እየሰማን ነው? ዶ/ር አብዲሳ፡አዎ አሁን ሰዎች እየተጠየቁ ያለው በቀድሞው የፀረ ሽብር ሕግ ነው። ሕጉ በመሻሻል ላይ እንዳለ ይታወቃል። መንግሥት በፍርሀት ውስጥ እየገባ የሚሄድ ከሆነ፤ አሁን የደቡብ ክልል ውስጥ ያለው የክልልነት ጥያቄ ሐምሌ 11 ይምጣና እንግዲህ እንተያያለን የሚሉት ነገሮች ሁሉም ምን አስከትለው እንደሚመጡ የሚታወቅ ነገር የለም። የቀድሞ መንግሥት አሸባሪ ነው ብለው ጠቅላይ ሚንስትሩ ራሳቸው በፓርላማ የተናገሩበት ሕግ እየተጠቀሰ አሁን ሌሎች እየታሰሩበት ነው። ነገሮች በዚህ አለመረጋጋት ከቀጠሉ አዲሱ ማሻሻያ እንደውም ወደ ተግባርም ላይመጣ የሚችልበት እድል አለ። ምክንያቱም ይሄኛው ብዙ ነገሮችን ለማሰርና እንደተፈለገ ለማድረግ ብዙ ቀዳዳዎችን የሚሰጥ ስለሆነ ይሄንን አሻሽሎ የማምጣት የመንግሥትን ተነሳሽነት ሊያዳፍን ይችላል ብዬ አስባለሁ። ይህ ደግሞ ሚዲያው ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ እጅግ ከባድ ስለሆነ በአንክሮ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው። ሚዲያውን ራሳችሁ ባደረጋችሁት ይኽው ደረሰባችሁ ብለን የምናዜመው ነገር አይደለም። ሚዲያው መንገድ ሲስት መስመሩን ተከትሎ እንዲሄድ ምክር መስጠትና ወደ ተገቢው መስመር እንዲገባ ማድረግ ተገቢ ነገር ነው። አጠቃላይ ነገሩን ገልብጦ እንዲህ ካልሆነ በቀደመው መንገድ ምላሽ እንሰጣለን የሚል አይነት ነገር ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ ፓርላማ ላይ እየተናገሩ የነበረው። • ሲፒጄ ስለኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ያለውን ስጋቱን ገለጸ ያ የቀደመ መንገድ ምን ማለት ነው? ሲተችና ሲኮነን የነበረ መንገድ ነው። ነገር ግን በአጠቃላይ ይሄ ነገር በደንብ ቆም ተብሎ ካልታሰበ፣ በረዥም ሁኔታ ካልታየ በስተቀር በሚፈጠሩ አጋጣሚዎች ሁሉ በችኮላ ለመፍታት ወደ እርምጃ መውሰድ ከተሄደ አሁን የታየውን ጭላንጭል ጨርሶውንም ሊያጠፋ የሚችልበት እድሉ ሰፊ ነው የሚመስለኝ። ሚዲያው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ እንዴት እንዲንቀሳቀስ ይመክራሉ? ዶ/ር አብዲሳ፡ ሚዲያዎች የራሳቸው ጠላት መሆን የለባቸውም። የተሰጠውን እድል አግባብ ባለው መንገድ መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው። በየክልሉና በተለያየ አይነት ብሔር ላይ እየተደራጀ የሚወጣው ሚዲያ በጣም በተመረጠ መንገድ ነገሮችን ቅርጽ የሚያሲዝበት መንገድ ከባድ ችግር ነው። በአማራ ክልል የተከሰተውና አዲስ አበባ ላይ የሆነውን ነገር ፍሬም (የሚያቀርቡበት) የሚደረጉበትን መንገድ ብትመለከቺ በጣም ወገንተኝነት ባለው መንገድ ነው። ይሄ ራሱ ሚድያው ምን እየሆነ ነው የሚያስብል ነገር አለ። ትርክቶችን መፈተሽ [ቻሌንጅ] ማድረግ ተገቢ ነገር ሆኖ ግን ምሉዕ በሆነ መንገድ በትክክል ነገሮችን ህብረተሰቡ በሚረዳበት መንገድ ማቅረብ ነው የሚገባው። ከአማራ ጋር የተገናኘ ሚዲያን ብትመለከቺ፤ በዳያስፖራ ያለውም ነገሮቹን ቅርፅ የሚያስይዝበት [ፍሬም] ፣ የመንግሥት ሚዲያም ለዚያ ምላሽ [ካውንተር] ለመስጠት እንደ "ጂሀዳዊ ሀረካት" የሚመስል አይነት ሪፖርት ማቅረብም ጀምሯል፤ አስደንጋጭ ነገር ነው። በጣም ፈጣን በሆነ መንገድ የተገጣጠሙና ክፍተቶች የበዙባቸው በደንም በበሰለ መንገድ ያልቀረቡ ነገሮች ብዙ ቢተነተኑ መዓት ነገር ሊወጣቸው የሚችሉና ትዝብት ውስጥ የሚጥሉ ነገሮችንም እያደረጉ ያሉበት ሁኔታ አለ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ትልቅ ስህተቶች እየተፈጠሩ የሚመጡበት እድል ሰፊ ነው። ማህበረሰቡን በጣም ጽንፍ እያስያዘ ሊሄድ የሚችልበት፤ ሕዝቡም መንግሥት ላይም ሚዲያ ላይም እምነት እንዲያጣ፤ እርስ በእርሱም እምነት የሚተጣጣበት ነገር እየሰፋ እንዲሄድ የሚያድረግ ነው። ሚዲያውም ሰከን ብሎ ያለውን ችግር፤ ባገኘው መረጃ ላይ ተነስቶ በይሆናል ከመሄድ ይልቅ ምሉዕ [ኮምፕርሄንሲቭ] ሁሉንም አቅጣጫ ያካተተ ነገር ማቅረብ በጣም የሚጠበቅ ነው። የሆነውን እውነታ [ፋክትን] ተቀብሎ ግን ደግሞ ሊጠየቁ የሚገባቸውን ነገሮች አግባብ ባለው መንገድ ጥያቄ ውስጥ ማስገባት ተገቢ ነው። ያለውን [ፋክት] እየካዱ [የሴራ ትንታኔን] እያገዘፉ የመሄዱ ጉዳይ መልሶ ጉዳት ሊያመጣ የሚችልበት ሁኔታ አለ። መንግሥትም አሁን እንደሚንለው አካሄዱ ጠንከር ባለው መንገድ ወደ ድሮው እንዲያውም በባሰ ሊሄድ የሚችልበት እድሎች ሰፊ ናቸው። አገርን ለመታደግ ነው በሚል [ዲስኮርስ] በዚህ መንገድ ሊቀጥል ይችላል። ራስን መጠበቅ የመንግሥት የመጀመሪያው ደመ ነፍስ ነው ስለዚህ ራስን ለመጠበቅ በሚወስደው እርምጃ ምንም ነገር የሚመርጥ አይደለም የሚሆነው። ስለዚህ ሁሉም ወገን በሰከነ መንገድ ኃላፊነት በተሞላው መንገድ ሊንቀሳቀስ ይገባል።
news-52260511
https://www.bbc.com/amharic/news-52260511
የአንድ ሩሲያዊ ቢሊየነር ሚስት ምስቅልቅል ታሪክ
አሌክሳንድራ ቶልስቶይ ምን ይወጣላታል። ቆንጆ ናት . . . ሰልካካ አፍንጫ፣ መቃ አንገት. . .
ሰርጌይ አሌክሳንድራን የተዋወቃት እንግሊዝኛ እንድታስተምረው ስትቀጠር ነበር እንግሊዛዊት ናት። እንግሊዝኛ አስተማሪም ነበረች። ከዕለታት አንድ ቀን ስለቷ ሰመረ። ቢሊየነር አገባች። ሩሲያዊ ቢሊየነር። ይህ እጅግ የናጠጠ ሩሲያዊ ሰርጌይ ፑጋቼቭ ይባላል። እንግሊዝኛውን ማሻሻል ይፈልግ ነበር። በአጋጣሚ ወይዘሪት አሌክሳንድራ ቶልስቶይ አስተማሪው ሆና ተቀጠረች። በእንግሊዝኛ ልምምድ መሀል ታዲያ መላመድ መጣ። በቋንቋ ጥናት መሀል መጠናናት መጣ። ቀስ በቀስ ትወደው ጀመር፤ ቀስ በቀስ በፍቅሩ ከነፈች። በመጨረሻም ወደደችው፤ ወደዳት። ተጋቡ። ነገሮች መልካቸውን ለመለወጥ ግን ብዙ ጊዜ አልወሰደባቸውም። የቢሊየነር ትዳር ውስጥ ንፋስ ይገባል? ታሪኩ የሚጀምረው የዛሬ 5 ዓመት በሎንዶን ከተማ ነው። መጀመርያ በሎንዶን የዲታዎች ሰፈር ቼልሲ ውሰጥ መኖር ጀመሩ። ሚሊዮን ዶላሮች የሚያወጣ ቤተ መንግሥት የመሰለ ቤት ገዙ። ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ገቡበት። "አንዳች የጎደለብን ነገር አልነበረም" ትላለች አሌክሳ። "ለሁለታችንም የግል ረዳቶች፣ የቤት ሠራተኞች፣ የግቢያችን ውበት ጠባቂዎች፣ የልጆቻችን ተንከባካቢዎች፣ የግል ጠባቂዎች፣ ጤናችንን የሚከታተሉ ሐኪሞች፣ ሾፌሮች፣ ፈረንሳይኛ ቋንቋ አስተማሪ. . . ብቻ ሁሉም ዓይነት ረዳቶች ነበሩን።" አሌክሳ ለቢቢሲ ዘጋቢ ቀድሞ ይኖሩበት የነበረውን ቤት እያስጎኘች ነው ይህን የምትናገረው። "ወደዚህ ቤታችን የተዘዋወርነው የመጀመሪያ ልጄን እንደወለድኩ ነበር፤ ቀጥለን ደግሞ ይሄን የጎረቤታችን ቤት ገዛን። ቀጥለን ደግሞ ያንን፣ ቀጥለን ደግሞ ያኛውን. . ." አሌክሳና ሰርጌይ ያዩትን፣ ያማራቸውን ሁሉ ለመግዛት የሚያበቃ ሀብት ነበራቸው። የወደዱትን የእነርሱ ለማድረግ እንደተቀረው ዜጋ ሁለት ጊዜ ማሰብ አይጠበቅባቸውም። በደህናው ጊዜ ሰርጌይና አሌክሳንድራ ኑሯቸው ለንደን፣ ሩሲያና ፓሪስ ውስጥ ነበረ የደራሲው ሊዮ ቶልስቶይ ዘመድ የአሌክሳ ቅምጥል ሕይወት ቢሊየነሩን ሰርጌይን ስታገባ የጀመረ አይደለም። ቢያንስ በችጋር አላደገችም። ልጅነቷ ይህ ጎደለው የሚባል አልነበረም። እርግጥ ነው የናጠጡ ሀብታሞች አልነበሩም፡፡ ሆኖም ተብቃቅተው ነው የኖሩት ማለት ይቻላል። አባቷ የዕውቁ ሩሲያዊ ደራሲ የሊዮ ቶልስቶይ የሩቅ ዘመድ ነበር። የተማረችው ውድ በሚባል ትምህርት ቤት ነው፤ በኋላ የቤት አሻሻጭ ሆነች። እሱንም እርግፍ አድርጋ ትታ የጉዞ ወኪል ከፈተች። በኋላ ግን እንግሊዝን ትታ፣ ሥራዋን ሁሉ ታትታ ወደ ሩሲያ አቀናች። ትንሽዬ የቱሪዝም አስጎብኚ ድርጅት ከፈተች። በጉርድሚኒስታን እና ኪርጊስታን ጎብኚዎችን ይዛ ፈረስ እያስጋለበች ገጠሩን ክፍል ታስጎበኝ ጀመር። ይህን ሥራ ስትሰራ አንድ የኡዝቤክ ኮሳክ ተወላጅ ሰው አግብታ ነበር። ትዳራቸው ግን ብዙም አልሰመረም። ሁሉን ትታ እንግሊዝኛ ወደ ማስተማሩ ተመለሰች። በዚህ መሀል ነበር ቢሊየነሩን ሰርጌይን ያገኘችው። "ገበያ የምወጣው በግል አውሮፕላኔ ነው" ሰርጌይን ያገኘሁ ዕለት ደስታዬ ወደር አልነበረመው። በፍቅሩ ሙትት አልኩኝ። ዓለሜ ሁሉ ሰርጌይ ሆነ፤ እሱን ከማግኘቴ በፊት እንደዚህ ዓይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ነበር" ትላለች አሌክሳንድራ። በመጀርያዎቹ ጊዜያት እሱም እንደዚያ ነበር የሚለው፤ ሕይወታችን አልጋ በአልጋ ነበር። አንድ ቦታ መኖር ለእኛ ከባድ ነበር። ስለዚህ በፓሪስ፣ ሞስኮና ሎንዶን ቤቶቻችን እያፈራረቅን እንኖራለን። "በእውነቱ ባሌ ሰርጌይ ከተማ ውስጥ በሌለ ሰዓት፣ ወይም ሞስኮ በሥራ ሲወጠር ክሬዲት ካርዱን ይሰጠኝና ገበያ እወጣለሁ፤ መገዛዛት ሲያምረኝ የግል ጀቴን አስነስቼ ወዳማረኝ አገር መብረር ነው. . . ።" አሌክሳ የሀብታቸውን መንዛዛት ስታስረዳ. . . "ብዙ ቤቶች ስለነበሩን አንድ ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜ ለማሳለፍ አልታደልንም። ለምሳሌ የ12 ሚሊዮን ፓውንዱ ቤት በባተርሲ ሎንዶን፣ ሌላ ቤት በሄልፎልሻየር፣ ሌላ ቤት በፓሪስ. . . ደግሞ በካሪቢያን የሚገኘው የ40 ሚሊዮን ፓውንድ የባሕር ዳርቻ ቪላ. . . ብቻ ያማረን ቤት ውስጥ ነበር የምንኖረው። እንደ ወቅቱና አየሩ ጠባይ።" የአሌክሳንድራና ሰርጌይ ሕይወት ሕልም ነበር የሚመስለው። በድንገት ታዲያ ነገሮች መለዋወጥ ጀመሩ። ሩሲያ ውስጥ ፖለቲካው ተቀየረ። ቆፍጣናው ፑቲን የእርሷን ባል ጨምሮ በአንዳንድ የሩሲያ ቢሊየነሮች ላይ ፊቱን አዞረ። ሰርጌይ ከዚያ በኋላ የሆነውን እንዲህ ይናገራል. . . ፕሬዝዳንት ፑቲን ቱጃሮችን ከአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለማስወጣት ዘመቻ ጀመሩ 'የፑቲን ሳምሶናይት' ሰርጌይ ፒካቼቭ ብዙዎች የሚያውቁት የፑቲን የገንዘብ ሳምሶናይት በሚል ተቀጽላ ነው። ያለ ምክንያት አይደለም። አንድ ወቅት ላይ ለፑቲን መንግሥት ገንዘብ አበድሮ ያውቃል። ሰርጌይ መጀመርያ ወደ 15 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ያካበተው ከኮሚኒስቷ ሩሲያ በኋላ በተፈጠረ ቢዝነስ ነው። የከሰል ማዕድን አለው፤ የመርከብ ጋራዥም እንዲሁ። ከሩሲያ የግል ባንኮች ውስጥ ትልቁ የእሱ ነበር። ታዲያ የሰርጌይ ፒካቼቭ ሀብት ይህ ብቻ ነው? አይደለም። ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሌሎች ንግዶች አሉት። ሰርጌይ ቪላድሚር ፑቲንን "ከእኔ የተሻለ የሚቀርበው ሰው አልነበረም" ይላል። "የዚህ ማሳያም ለምሳሌ አውዳመት አብረን ነበር የምናሳልፈው፤ ሁልጊዜም።" የሆነ ወቅት ላይ ፑቲንና መንግሥታቸው ገንዘብ ቸገራቸው፤ ሰርጌይ ፒካቼቭ ለፑቲን ገንዘብ አበደረ። ከዚህ በኋላ ነበር "የፑቲን ሳምሶናይት" የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ብለናል። ሆኖም በዚህ ሁሉ ቀርርባቸው ውስጥ አንድ ፑቲን ያልወደዱለት ነገር ነበር፤ ሚስቱን አሌክሳንድራን። "ፑቲን አሌክሳንድራ ቶልስቶይን አልወደዳትም። መጀመርያ ላገባት ነው ብዬ ስነግረው በጣም ነው የተገረመው። 'ምን ነካህ? ለምን እሷን መረጥክ? ለዚያውም እንግሊዛዊት. . .!? ሩሲያ ውስጥ 140 ሚሊዮን ሰው እያለልህ?' ብሎ ተቆጣኝ።" ሰርጌይንና ሰርጌይን የመሳሰሉ የራሺያ የገዢ መደብ ባለጸጎች (ኦሊጋርክስ) ላይ ፑቲን ድንገት ተነሱባቸው። ምክንያታቸው በትክክል ምን እንደሆነ እርሳቸውና ፈጣሪ ነው የሚያውቀው። ብቻ በጎርጎሮሲያኑ 2006 ሩሲያ አዲስ ሕግ አወጣች፤ ማንኛውንም በውጭ የሚኖርና ለእናት አገሩ ሩሲያ ጠላት የሆነ ባለጸጋ በተገኘበት እርምጃ ይወሰድበት። የፑቲን ሰዎች በሰርጌይ ፒካቼቭ ላይ የዘመቱት ከዚህ በኋላ ነበር። ከኮሚኒስት ውድቀት በኋላ ሰርጌይ ሩሲያ ውስጥ የ15 ቢሊየን ዶላር ሐብት አፍርቷል በ2008 የሰርጌይ ባንክ የገንዘብ ችግር ገጠመው። የሩሲያ መንግሥት አንድ ቢሊየን ዶላር ብድር ሰጥቶ ከመውደቅ ታደገው ተባለ። ያም ሆኖ ከ2 ዓመት በኋላ ባንኩ ኪሳራ አወጀ። ሰርጌይ እንደሚለው ባንኩን ቀደም ብሎ ሽጦታል። ሩሲያ ግን በፍጹም አለች። እንዲያውም ላደረስከው ኪሳራ ትጠየቃለህ አለችው። ያበደርንህን አንድ ቢሊየን ዶላር መልስ አለችው. . . ። ተፋረሱ። የሩሲያ ፍርድ ቤት ለባንኩ መንኮታኮት ተጠያቂው ፑካቼቭ ነው ሲል ወሰነ። ሰርጌይ ፑካቼቭ ከዚህ በኋላ አገር ለቆ ተሰደደ። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን ሰርጌይን ከምሽቶች በአንዱ የሩሲያ ዲፖዚት ኢንሹራንስ ኤጀንሲ ሰዎች "እዳ አለብህ" አሉት። "የምን እዳ?" አላቸው። "ያንተ ባንክ እኛን ለኪሳራ ዳርጎናልና ብር እንፈልጋለን" አሉት። ይህ ትንኮሳ ጋብ እያለ ቀጠለ። ስለሚመጣው ነገር ምልክት ነበር. . . "በሌላ ቀን ደግሞ ሬስቶራንት ለእራት ቀጠሩኝና እራት ከበላን በኋላ 350 ሚሊዮን ዶላር በአካውንታችን አስገባ አሉኝ፤ ካልሆነ አንተና ቤተሰብህን እንገድላለን አሉኝ።" "ይህ እንደማይሆን ስነግራቸው 'የልጅህን ጣቶች ቆርጠን በፖስታ ቤት እንልክልሃለን' አሉኝ።" ኤጀንሲው ግን ይህን ስለማለቱ ይክዳል፤ ሆኖም ሰርጌይ ፑካቼቭ የተጠየቀውን ለመክፈል አልፈቀደም። ከአገር መሰደድን መረጠ፤ ወደ እንግሊዝ። ሰርጌይ በስደት በነበረበት ወቅት የሩሲያ ጠላቶች የተባሉ ሁሉ በየቦታው እንደቅጠል መርገፍ ጀመሩ። እሱም በእንግሊዝ ሳለ ክስ ከፈቱበት፤ አብዛኛው ሀብቱ እንዳይንቀሳቀስ አደረጉ፤ ፓስፖርቱ እንዲቀማ አደረጉ. . . አንድ ቢሊየነር ዶላር ከአካውንቱ ማሸሽ ቻሉ. . .ነገሮች አላምርህ ሲሉት ታዲያ ሰርጌይ ወደ ፈረንሳይ ተሰደደ። "የእናት ሩሲሺያ ጠላቶች በተገኙበት እርምጃ ይወሰድባቸው" በ2012 ከሩሲያ ቢሊየነሮች አንዱ የነበረውና የሩሲያን ምስጢር አዝረክርኳል ተብሎ የሚታመነው አሌክሳንደር ፐረፒልቺኒ በእንግሊዝ ደቡብ ምሥራቅ ሎንዶን ከቤቱ ዱብ ዱብ ሊል ደጅ በወጣበት ተገድሎ፣ ተጥሎ ተገኘ። በ2013 የፑቲን ተቀናቃኝ ቦሪስ ቤሬቮስኪም እንዲሁ እንግሊዝ በአስኮት አካባቢ ቤቱ ውስጥ ሳለ ተገድሎ ተገኘ። በ2015 የሩሲያ ተቃዋሚ የነበረው ቦሪስ ኔምሶቭ በሞስኮ አደባባይ ላይ ተገደለ። ሰርጌይም ይህ እጣ እንደሚጠብቀው አላጣውም። ለዚህም ነው ከእንግሊዝ ወደ ደቡብ ፈረንሳይ የሸሸው። አሌክሳንድራ ከቢሊየነሩ ባሏ ሰርጌይ ጋር የነበረት ግንኙነት የተበላሸው ወደ ፈረንሳይ ሸሽቶ ከሄደ በኋላ ነበር የሽሽት ሕይወትና የትዳር መፍረስ አሌክሳንድራ ባሏ ሰርጌይ በሽሽት ላይ መሆኑ ሕይወታቸውን እንዳመሰቃቀለው ትናገራለች። "ባሌ ሰርጌይ ሁልጊዜም በሽሽት ነው የሚያሳልፈው፤ እኔና ልጆቼም ክትትል አለብን።" ነገሮች ለእርሷና ለልጆቿ መልካም አልነበሩም። ይህ ሁኔታ በሚያስቀናው ትዳራቸው ላይ ንፋስ እንዲገባ አደረገ። በተለይ ከ2016 ጀምሮ ነገሮች መልካቸውን ለወጡ። "ፈረንሳይ በሚገኘው ቤታችን አብረን ከልጆቻችን ጋር በቋሚነት እንኑር ሲለኝ አቅማማሁ፤ ምክንያቱም ተደብቄ መኖር አልፈልግም፣ እስከመቼ?" ". . . አንድ ቀን ታዲያ ፈረንሳይ ካለው ቤት ሳለን ባሌ ሰርጌይ በጥፊ አላጋኝ። ልጆቹን ደግሞ ከእኔ ለያይቶ አንድ ክፍል ውስጥ አስገብቶ ቆለፈባቸው። ፓስፖርቴን የሆነ ቦታ ወስዶ ደበቀው።. . ." "…ያን ቀን በቃ ከእሱ ጋር ያለኝ ነገር እንዳበቃ ተሰማኝ። ከዚህ በኋላ በጸደይ ወር 2016 በድንገት ከደቡብ ፈረንሳይ ቤታችን ልጆቼን ይዤ ወደ እንግሊዝ አመለጥኩ። እስከወዲያኛው ላልመለስ. . . " ከቢሊየነርነት ማማ መውረድ ከዚያ ጊዜ በኋላ ሰርጌይ እኔም ልጆቼንም በገንዘብ ይቀጣን ጀመር። እጄ ላይ ምንም አልነበረም. . . "ሰዎች ሲያገኙኝ ሕይወትሽ አባጣ ጎርባጣ የለበት፤ እንዴት የሚያስቀና ሕይወት ነው ያለሽ ይሉኛል፤ ውስጤን አያውቁልኝም" ስትል እንባ እየተናነቃት ለቢቢሲ ተናግራለች፤ አሌክሳ። "የሚያስቀና ሕይወት ማለት በፍቅር አብሮ መኖር ነው፤ ያለ ፍርሃት፤ ደኅንነት እየተሰማ. . . እንጂ የገንዘብ መኖር ብቻውን የተሻለ ሕይወት አያኖርም. . . " አሌክሳ እንደምትለው ከፈረንሳይ ከሰርጌይ ካመለጠች ወዲህ ከልጆቿ ጋር የሚኖሩበትን የቤተሰብ ቤት የሩሲያ መንግሥት በሕግ አሳግዶት ለገበያ ሊያቀርበው በሂደት ላይ ነበር። "ለአንድ ዓመት በነጻ እንድትኖሪ ከፈለግሽ አስገዳጅ ስምምነት ፈርሚ አሉኝ. . . ። ወደ ሌላ ክስ አልሄድም ብለሽ ፈርሚ አለበለዚያ ባዶሽን ትቀሪያለሽ ነው ያሉኝ።" ከተፈጸመባቸው ጥቃት የተረፉት የቀድሞው የሩሲያ ሰላይ ሰርጌይ ስክሪፓል እና ልጁ ዩሊያ የሩሲያና የእንግሊዝ ግንኙነት መሻከር በ2018 የሩሲያ ድርብ ሰላይ የነበረው ሰርጌይ ስክሪፓል እንግሊዝ ውስጥ ተመረዘ። ከዚህ በኋላ የእንግሊዝ የአገር ውስጥ ቢሮ ተያያዥ ጉዳዮችን እንዲመረምር ታዘዘ። 14 ተመሳሳይ ግድያዎችን ሲያጣራ ከብዙዎቹ ጀርባ የሩሲያ ሰላዮች እጅ እንዳለበት አረጋገጠ። በዚህን ጊዜ የእንግሊዝና የሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በእጅጉ ሻከረ። "ኪሴ ላይ የቀረችኝ 70 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ናት" ሰርጌይ ሰርጌይ ከዚያ ሁሉ ቢሊዮን ዶላር በኋላ የፑቲን መንግሥት ፊቱን ሲያዞርበት አግኝቶ ያጣ ሆነ። አሁን ደቡብ ፈረንሳይ በሚገኘው ቤቱ ነው የሚኖረው። ብቻውን። 'ሕይወቴን ያመሰቃቀሉት የፑቲን ሰዎች ናቸው' ይላል። "ልጆቼን እወዳቸዋለሁ፤ አንድ ቀን ልጆቼ ከአባታቸው ጋር ይሆናሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ይላል። አሁን የሰርጌይ ልጆች የሚኖሩት ከአሌክሳ ጋር በኦክስፎርድሻየር በትንሽ ቤት ውስጥ ነው። ከ2016 ጀምሮ አባታቸውን አይተውት አያውቁም። "አንድ ቀን ነገሮች መልክ ሲይዙ ታገኙታላችሁ፤ ወይም ትልቅ ስትሆኑ ሄዳችሁ ትጎበኙታላችሁ እላቸዋለው" ትላለች እናታቸው አሌክሳንድራ። አሁን ከልጆቿ ጋር ኦክስፎርድሻየር ውስጥ በአንድ ጎጆ ቤት የምትኖረው አሌክሳንድራ ቶልስቶይ አሁን አሌክሳንድራ ወደ ድሮው ማንነቷ ተመልሳለች። ከቢሊየነርነቷ ወርዳ በኪርጊስታን ፈረስ እየጋለበች ቱሪስቶችን ታስጎበኛለች። "ሩሲያን እወዳታለሁ፤ በሚገርም ሁኔታ እኔ ከሩሲያ ጋር ያለኝ ግንኙነት ከሰርጌይ ጋር ካለኝ ግንኙነት የተሻለ ነው" ትላለች። ከቅንጡ ሕይወቷ ለአንዴና ለመጨረሻ ተፋታለች። "እንዲያውም ያንን የሕይወቴን ክፍል የምጠላው ይመስለኛል፤ ቅንጡ ነገሮችን ሳይ ያ የማልወደውን ሕይወቴን ነው የሚያስታውሱኝ" ትላለች። "ከፊቴ ገና ብዙ ሕይወት አለ፤ ወደምወዳቸው ነገሮች ለመመለስ እችላለሁ፤ ውስጤን ደስ የሚያሰኙት እንደዚያ ያሉ ነገሮች ናቸው።" "የቀድሞ ባሌ፤ ቢሊየነሩ ባሌ ከሱና ከገንዘቡ ተጣብቄ የምኖር ይመስለው ነበር፤ ተሳስቷል።"
news-47716377
https://www.bbc.com/amharic/news-47716377
ጀብድ የፈጸመው ተማሪ ጣልያናዊ ዜግነት ሊሰጠው ነው
ባለፈው ሳምንት በጣልያን 50 ተማሪዎችን አሳፍሮ የነበር የተማሪዎች አውቶቡስ ሾፌር መኪናውን ወዳልሆነ አቅጣጫ በመንዳት በመጨረሻም አውቶቡሱን በእሳት ሲለኩሰው የ13 ዓመቱ አዳጊ ራሚ ሺሃታ ደብቆ በያዘው ስልኩ ለፖሊስ ምልክት በመስጠት ጓደኞቹን ከሞት ማዳን ችሏል።
ስለዚህም አሁን የጣልያኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቶ ሳልቪኒ ለግብጻዊው ራሚ የጣልያን ዜግነት እንዲሰጠው ፈቅደዋል። የጣልያን ባለሥልጣናት ባለፈው ሳምንት ራሚ በፈጸመው ጀብድ ምክንያት ወዲኣውኑ ዜግነት ሊሰጡት ሲሉ የፀረ ስደተኛ አቋም ያለው ፓርቲ መሪ የሆኑት ሳልቪኒ ግን አንገራግረው ነበር። ራሚ ምንም እንኳ ጣልያን ውስጥ ከግብፃዊ አባት ቢወለድም ጣልያን ከስደተኛ ለሚወለዱ ልጆች 18 ዓመት እስኪሆናቸው ድረስ ዜግነት ስለማትሰጥ ጣልያናዊ አልሆነም ነበር። • አንዳንድ ጥያቄዎች ለ"108ኛው" ፓርቲ • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት ሳልቪኒ ታዳጊው ላሳየው ጀግንነት ዜግነት እንደሚገባው ሲናገሩ፣ "አዎ ለራሚ ዜግነት ይሰጠዋል። ምክንያቱም ልክ እንደ ልጄ ስለሆነ እና የዚህን አገር እሴት እንደተረዳ ስላሳየን" በማለት ተናግረዋል። ተማሪዎቹ የነበሩበት አውቶቡስ ውስጥ የነበረው ሌላው ሞሮካዊ ታዳጊ አዳም ኢል ሃማሚም ምንም እንኳ እሱም እንደ ራሚ በድብቅ ስለ አደጋው በስልኩ ለፖሊስ ጥሪ ቢያደርግም ለሱ ብዙ ትኩረት እየተሰጠው አይደለም። ስለዚህም አባቱ ካሊድ ኢል ሃማሚ እንደ ራሚ ሁሉ ለልጃቸው አዳምም ዜግነት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል። ሁሉም ስለ ራሚ ብቻ እያወራ በመሆኑም ልጃቸው እየተበሳጨ መሆኑንም አባቱ ተናግረዋል። የጣልያን ባለሥልጣናት ግን አዳም የጣልያን ፓስፖርት ስለማግኘት አለማግኘቱ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። • ከድምፃዊት ቤቲ ጂ እና ቸሊና ጀርባ
42550183
https://www.bbc.com/amharic/42550183
የኢትዮጵያ ገና ለምን ታህሳስ 29 ይከበራል?
የአውሮፓውያንን የጊዜ ቀመር በሚከተሉ ሃገራት የክርስቶስ ልደት ዲሴምበር 25 (ታህሳስ 16) ይከበራል። ኢትዮጵያዊንን ጨምሮ ከ10 በላይ ሃገራት ደግሞ ከ12 ቀናት በኋላ ታህሳስ 29 ያከብራሉ። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ስንል የኃይማኖት ሊቃውንትን ጠይቀናል። " የጎርጎሮሳውያን የዘመን አቆጣጠር ያመጣው ፍልሰት "
ምዕመናን ፀሎት ሲያደርሱ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን የዘመን አቆጣጠር ከአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር የተለየ ነው። አንደኛ ሰባት ዓመት ከስምንት ወር ከአስር ቀን ልዩነት አለ። ሁለተኛ እያንዳንዱ ወር የሚይዛቸው ቀናት ልዩነት አላቸው። ''በእያንዳንዱ ወር ውስጥ ከስድስት እስከ አስር ቀናት የሚደርሱ ልዩነቶች አሉ'' ይላሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የዘመን ቀመር (ባህረ ሃሳብ) ዙሪያ መጽሃፍ ያሳተሙት መጋቤ ጥበብ በእምነት ምትኩ ። "የጎርጎሮሳውያኑ የዘመን አቆጣጠር እስከተጀመረበት ድረስ መላው ዓለም ተመሳሳይ የዘመን አቆጣጠር እንደነበረው ይታመናል"የሚሉት መጋቤ ጥበብ በእምነት" ነገር ግን በ1382 ዓ.ም የካቶሊክ ቤተክርስትያን ጳጳስ የነበረው ጎርጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠሩ ችግር አለበት በሚል እንደገና እንዲሰላ ወሰነ። ከዚያም በአንድ ዓመት ውስጥ 365 ቀን ከ6 ሰዓት ነው ያለው የሚለውን ሃሳብ በማንሳት በየዓመቱ አንድ አንድ ሰዓት ተጨምሮብናል'' ይላሉ። ስለዚህ እንደ መጋቤ ጥበብ በእምነት ይህ አንድ ሰዓት ተጠራቅሞ መጨመር አለበት በማለት ከኒቂያ ጉባኤ ጀምሮ ያለውን አስልቶ በማሳሰብ 10 ቀን በመሙላቱ ኦክቶበር 5 የነበረውን ኦክቶበር 15 ነው ሲል አውጇል። "ስለዚህ በእኛና በእነሱ መካከል እየቀነሰ የሚሄድ ቢሆንም የ10 ቀን ያህል ልዩነት አለን።" እንግዲህ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ከኖህ ዘመን ጀምሮ የነበራትን የቀን አቆጣጠር ጠብቃ ይዛ የቀጠለችና ምንም ነገር ያላሻሻለች በመሆኑ የነበረው እንዳለ ነው ሲሉ ያስረዳሉ። "በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ብቻ ሳትሆን የግብፅ ቤተክርስትያንም ምንም አይነት ማሻሻያ አላደረገችም።'' "ዘመን በአንድ ክብ ላይ አንድ ነጥቡን መነሻ አድርጎ ክቡን የመቁጠር ሂደት ነው" የሚሉት ደግሞ መጋቢ ሰለሞን አበበ ገ/መድህን ናቸው ። ዘመን መቁጠር የጀመረው ክርስትናው አይደለም የሚሉት መጋቢ ሰለሞን ክርስትናው ከመጣ በኋላ ታላቁን ክስተት የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ መነሻ አደረጉ ብለዋል። "ይህም በአንድ ክብ ላይ የትኛው ነጥብ ላይ ሄጄ ነው መቁጠር የምጀምረው እንደማለት ነው። ምክንያቱም ዞረው በሚገጥሙ በማያቋርጡ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች የምድርን ዙረት መሠረት አድርጎ ዘመናችን ስለሚለዋወጥ ነው የምንቆጥረው።" ስለዚህ እንደ መጋቢ ሰለሞን በጁሊያን አቆጣጠር ለቆጠራ እንዲመቸውና እንዲሞላለት በዘፈቀደ ያስገባቸው ወደ 44 ደቂቃ እና 56 ቁርጥራጭ ሰከንዶች ተጨምረዋል። "በኋላ ላይ ጎርጎሪዮስ ሲያርመው ከዓመታት በኋላ ተጠራቅመው እነዛ ድቃቂዎች አስር ተጨማሪ ቀናት ወልደው ተገኙ።" ጎርጎሪዮስ እነዚህ አስር ቀናት ከናካቴው ተጎርደው ይውጡ የሚል አቋም ወሰደ ሲሉ ያስረዳሉ መጋቢ ሰለሞን። እርማቱ ሲካሄድ ለጊዜው በዓመት፣ በአስር ዓመት የማይታሰቡ ቁርጥራጭ ደቂቃዎች ቀን በመውለዳቸው ልዩነቱ እንደፈጠረ የሚናገሩት መጋቢ ሰለሞን "እኛ እንግዲህ የጁሊያን ሳይታረም የቀረውን ይዘን በመሄዳችን በወራቱ ላይና በቀናቱ ላይ አስርም ስምንትም እንዲሁም በዓመታቱ ላይ ልዩነቶችን እየፈጠረ መጣ። ስለዚህ የመጀመሪያው ልዩነት ሲታረም የታረመውን አለማካተታችን ነው።" የክርስቶስ ልደት መጽሐፍ ቅዱሳዊና ታሪካዊ መሠረቶች እንደ መጋቤ ጥበብ በእምነት የአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር መሠረት ያደረገው በ735 ዓ.ም የተከሰተውን የሮም መቃጠልን ነው። "ከዛ ተነስተው ነው የአዲስ ኪዳን ዓመተ ምህረታቸውን የቀመሩት።" የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስትያን ግን እንዲህ ዓይነት ክስተቶችን መሠረት እንዳላደረገች የሚናገሩት መጋቤ ጥበብ በእምነት ምክንያቱ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክስተቶች የዓመት ልዩነት ሊፈጥሩ ስለሚችሉ እንደሆነ ይገልፃሉ። "የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስትያን ለልደተ-ክርስቶስ መነሻ የምታደርገው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይኸውም የሉቃስ መጽሐፍ ምዕራፍ አንድ ላይ ቅዱስ ገብርኤል በስድስተኛው ወር ወደ ድንግል ማርያም ተላከ ይላል። ስድስት ወር ማለት ከዛ በፊት አንድ ታሪክ አለ ማለት ነው።" "በዚያው ምዕራፍ ላይ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ዘካርያስ ሄዶ ዮሐንስ እንደሚፀነስ ብስራት ነግሮታል። የዮሐንስ ፅንሰት ከተከናወነ ከስድስተኛው ወር በኋላ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እመቤታችን ሄደ ማለት ነው።" "ስለዚህ የጌታ ልደት መነሻ የሆነው የዮሐንስ ፅንሰት ወይም ልደት ነው። ዮሐንስ ደግሞ መቼ ነው የተፀነሰው የሚለውን ስናይ ዘካርያስ በቤተመቅደስ ገብቶ ያጥን ነበር ይላል። ይህ ሥርዓት ደግሞ በዓመት አንዴ የሚፈፀም ነው።" እንደ መጋቤ ጥበብ በእምነት ያንን ጊዜ ለማወቅ ደግሞ ብሉይ ኪዳን ላይ ዘካርያስ ገብቶ ቤተ መቅደሱን ያጠነበት ቀን በሰባተኛው ወር ከቀኑም በአስረኛው ቀን ነው (ዘሌ 16፥29፣ ዘሌ 23፥27 ) የሚለውን ማየት ያስፈልጋል። በተጨማሪም የአይሁዳውያን የቀን አቆጣጠር ደግሞ የሚጀምረው ከመጋቢት ነው። ከዚያ ተነስተን መስከረም ድረስ ስንቆጥር ሰባተኛው ወር ላይ እንደርሳለን። ስለዚህ ካህኑ ለሕዝቡ ስርየተ-ኃጢዓት የሚለምነው በመስከረም ወር ነው ማለት ነው ይላሉ መጋቤ ጥበብ። "ስለዚህ በቤተክርስትያናችን የብስራቱ ቀን መስከረም 27 ነው። ከዛ በኋላ ደግሞ ከሦስት ቀናት በኋላ ለሚስቱ ሄዶ ነግሯት ዮሐንስ ተፀነሰ። ከዚህ ከስድስት ወር በኋላ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እመቤታችን የሄደበትን ቀን ስንቆጥረው መጋቢት 29 ቀን ይሆናል። ከዛ ደግሞ ተነስተን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስንቆጥር ታህሳስ 29 ላይ እንደርሳለን" ይላሉ። የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት መቼ ነው በትክክል መከበር ያለበት? የሚለውን ለመመለስ ቤተ-ክርስትያን በይፋ በሚታወቅ መልኩ ልደቱን ማክበር የጀመረችው መቼ ነው? የሚለውን ማየት አስፈላጊ እንደሆነ ደግሞ መጋቢ ሰለሞን ይናገራሉ። ቅዱስ መጽሐፍ የጌታን ልደት እንጂ የተወለደበትን ቀን አይነግረንም የሚሉት መጋቢ ሰለሞን በይፋ የተመዘገበ ታሪክ የምናገኘው በ4ኛው ምዕተ-ዓመት ላይ ነው ይላሉ። "አንዳንዶች በሦስተኛው ምዕተ-ዓመትም የመከበሩ ምልክቶች አሉ የሚል ዘገባ ያቀርባሉ። ይህ ከሆነ በዚህ የቀን ፍለጋው ውስጥ አሁንም ልዩነቶች ተፈጥረዋል።" የተለያዩ ምሁራን የቀን ቆጠራን ለማካሄድ ባህረ-ሃሳብም ሆነ ጎሪጎሪያውያን ወደ ኋላ ሲሄዱ ስህተት መፈፀማቸውን የሚናገሩት መጋቢ ሰለሞን፤ ከዛ ይልቅ ከኢየሱስ ልደት ጋር ያለውን ቀን ለመለየት መጽሐፍ ቅዱስን መመልከት ይሻላል ይላሉ። ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ የነበሩ ምልክቶች የታላቁ ቄሳር መኖር፣ የሕዝብ ቆጠራ እንዲካሄድ ማዘዙ፣ የኮከቡ መታየት (ስነ-ከዋክብት ተመራማሪዎች ወደ ኋላ ሄደው አንዲመረምሩ ስለሚያስችላቸው)፣ በይሁዳ ላይ ሄሮድስ የሚባል ንጉስ መኖሩ፣ ጴንጤናዊው ጲላጦስ በሮም ላይ ገዢ ሆኖ መሾሙ፣ እነዚህ ታሪካዊ ክስተቶችን ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ካሉ ሰነዶች ጋር አያይዘን ካየን ሁለቱም የዘመን አቆጣጠሮች ወደኋላ ተሄዶ ሲመረመሩ ስህተት አለባቸው ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። "በጎሪጎሪዮሳውያኑ 7 ዓመት ወደ ኋላ፤ በእኛ ደግሞ 15 ዓመት ወደኋላ ተመልሶ ነው የታሪካዊ ሁነቶች የተከሰቱት የሚሉ ጥናቶች ወጥተዋል" ይላሉ መጋቢ ሰለሞን። የኢትዮጵያ ወንጌላውያንና ካቶሊኮች እንደ መጋቢ ሰለሞን ከሆነ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን ክርስትያኖች ልደት፣ ሞትና ትንሳዔን አበይት በዓላት አድርገው የሚቆጥሩ ናቸው። "በኢትዮጵያ ውስጥ ቀደምት ክርስትና ነበር። ቀዳሚውም ክርስትና ወደ 2000 ዓመት ኖሯል። ይህ ሃገር የክርስትና ውርስና ቅርስ አለው" ይላሉ። "...ምንም እንኳ ወንጌል አማኞች በአንዳንድ አስተምህሮዎች እና ትውፊታቸው ከቀዳሚቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን ቢለዩም ነገር ግን የጌታን ልደት በማክበሩ ላይ ያንኑ የቀዳሚውን ይዞ መሄዱን መርጠዋል" ሲሉም ያስረዳሉ። ምክንያታቸው ደግሞ የትኛውንም ለመምረጥ ምንም የተለየ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለም የሚል ነው። "ይልቁንም ትውፊትን ነው የመረጥነው ማለት ነው" ብለዋል። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስትያን በሄደችበት ሃገር ያለውን ባህል እና አካሄድ በመከተል የእምነት ስብከቷን እንደምታካሂድ የሚናገሩት መጋቤ ጥበብ በእምነት፤ በዚህ የተነሳም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የተለየ የቀን አቆጣጠር አትከተልም ብለዋል።
45675458
https://www.bbc.com/amharic/45675458
«የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ
ሰሞኑን የኦሮሞ ሕዝብ አንድነት እና አንገብጋቢ የወቅቱ ጉዳዮችን አስመልክቶ አምስት የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ መግለጫ አውጥተው ነበር።
ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው የኦሮሞ ማንነትን ለማጥፋት እየተደረገ ያለው ሙከራ ያሉትን፣ የአዲስ አበባ ጉዳይን፣ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ስላሏቸው ሚድያዎች፣ በሃገሪቱ እየታየ ስላለው ለውጥን እና በቋንቋ ላይ ስለተመሰረተ ፌዴራሊዝም ትኩረትን ሰጥተዋል። መግለጫው ከተሰማ ወዲህ አነጋጋሪ ሆኖ የተገኘ ሲሆን ጊዜውን የጠበቀ አይደለም፣ ከፋፋይ እንዲሁም አንድ ፓርቲ ላይ ያነጣጠረ ነው የሚሉ ትችቶች ሲሰነዘሩበት ቆይቷል። እኛም ይህን አስመልከተን ከፓርቲዎቹ መካከል አንዱ የሆነው የኦፌኮ ምክትል ተቀዳሚ ሊቀ-መንበር ከሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ጋር ቆይታ አድርገናል። ቢቢሲ፦ መግለጫውን አሁን ማውጣት ያስፈለገበት ምክንያት ምንድነው? አቶ በቀለ፦ ሰሞኑን ውጭ ሃገር ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሃገር ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ በተለይም ከመስከረም 5 በኋላ ባሉ ቀናት የኦሮሞ ንብረት የሆኑ ተቋማት ላይ፣ የክልሉን ታርጋ በለጠፉ መኪናዎች ላይ እንዲሁም በኦሮምኛ ተናጋሪዎች ላይ ከተማው ወስጥ ጥቃት ተፈፅሟል። ይህ ነገር ዝም ብሎ ሊታለፍ የሚገባው ባለመሆኑ መግለጫውን ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። የኦሮሞ ማንነት ላይ ጥቃት እየተሰነዘረ በመሆኑና ይህን የሚያደርጉ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ነው መግለጫውን ያወጣነው። • «ኦሮሞ እና አማራን የሚነጣጥሉ አይሳካላቸውም» • «ማስተር ፕላኑ ተመልሶ ይመጣል» አቶ ኩማ ደመቅሳ ቢቢሲ፦ መግለጫው ስሜታዊነት ይነበብበታል፤ በተፈጠሩት ግጭቶች ሕይወታቸው ላለፈ እንኳን የሃዘን መግለጫ አልሰጠም የሚሉ ትችቶች ይሰማሉ። ይስማሙበታል? አቶ በቀለ፦ ከዚህ መግለጫ በፊት ሌላ መግለጫ ማውጣታችን ይታወቃል። የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሌሎችም ፓርቲዎች ጥቃቱን በማውገዝ መግለጫ አውጥተናል። ድርጊቱ አሳዛኝ መሆኑንና የዜጎች መሞት ተገቢ አለመሆኑን አስፍረን ሃዘናችንን ገልፀናል። በዚህኛውም መግለጫ ላይ በፅሁፍ ባይሰፍርም በቃል በሰጠነው መግለጫ ላይ የማንም ሰው ሕይወት መጥፋት አንደሌለበትና በድርጊቱ ማዘናችንን ገልፀናል። በፅሁፍ መግለጫው ላይ አለመካተቱ ስህተት ሊሆን ይችላል፤ ለዚያም ይቅርታ መጠየቅ ይገባል። ከዚያም ባለፈ የኦሮሞ ቄሮዎች መስቀልን ምክንያት በማድረግ ወደ አርባምንጭ ይቅርታ እንዲጠይቁ የተደረገ መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን። ቢቢሲ፦መግለጫችሁ ላይ ፀረ-ኦሮሞ አቋም ያለው ድርጅት እንዳለ መረጃ አለን ብላችኋል። የዚህን ድርጅት ስም መጠቀስ ያልፈለጋችሁት ለምንድነው? አቶ በቀለ፦ ይሄ ወደፊት ወደ ሕግ አግባብ ሲገባ ይፋ ሊሆን የሚችል ነው። ነገር ግን የተደራጀ ስለመሆኑ የሚያመልክቱ ነገሮች አሉ። በተለያዩ ቦታዎች ላይ የኦሮሞ ንብረቶች ላይ ጥቃት ሲፈፀም ይህ በአጋጣሚ ነው ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። ስለዚህ ከላይ ሆኖ የሚያስታባብር አካል ስለመኖሩ እሙን ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ከሕግ አግባብም ጭምር ይሄ ድርጅት ነው ብሎ ማለት አስፈላጊ አይደለም። ወደፊት አስፈላጊ ከሆነ ማጋለጥ የሚያስፈልግበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል ማለት ነው። ቢቢሲ፦ እናንተ የኦሮሞ ንበረቶች ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው ብላቸሁ እንደምትሉት ሁሉ የተለያዩ ሰዎች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ጥቃት ደረሰብን ሲሉ ይሰማል። በዚህ ምክንያት እናንተም እየፈረጃችሁ ነው ማለት አይቻልም? አቶ በቀለ፦ እንደዚህ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ጉዳዩ ከምን ተነሳ የሚለው ነው። ጉዳዩ ከምን ተነሳ የሚለውን መንግሥት ሊያጣራ ይችላል። ከፓርቲዎች አቀባበል ጋር በተያያዘ ብዙ የተፈፀሙ ጥቃቶችን ማንሳት ሃዘን መቀስቀስ ነው። ተቃውሞ ሰልፍ ፈቃድ መጠየቅ፣ በሚድያዎች ላይ ማራገብ የመሳሰሉ ጉዳዮችን አስተውለናል። ግን በማናቸውም ዜጋ ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ፈፅሞ ትክክል ያልሆነና እኛ የማንፈልገው መሆኑን ለማሳሰብ ነው። ከየትኛውም ወገን ችግሮች ደርሶ ሊሆን ይችላል፤ ሰዎችም ሞተዋል፤ ይህ ትክክል ነው። በሁለቱም ወገን ይህንን ጉዳይ የፈፀሙ ሰዎች ወደ ሕግ መቅረብ እንዳለባቸው በመግለጫችንም ጠይቀናል። • ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን? • ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው ቢቢሲ፦ሌላኛው የመግለጫው አከራካሪ ክፍል አዲስ አበባን አስመልክቶ የወጣ ነው፤ መግለጫው 'አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት' ይላል። መግለጫው ከወጣ በኋላ 'አዲስ አበባ የናንተ ሳትሆን የኛ ናት' የሚሉ ወገኖች በዝተዋል። ስለዚህ አዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ ለማንሳት አሁን ጊዜው ነው ብለው ያስባሉ? አቶ በቀለ፦ እርግጥ ጊዜውም አይደለም። ይህ አካባቢ የኔ ነው ያንተ ነው ለማት ጊዜው እንዳልሆነ ይታወቃል። አስፈላጊነቱም ያን ያህል ነው። ነገር ግን ይህንን እንድንል ያነሳሳን የአንድ ፓርቲ አርማ የያዙ ሰዎች አዲስ አበባ የኦሮሞ አይደለችም፤ ኦሮሞ ከአዲስ አበባ ይውጣ የሚል ግልፅ መፈክር ይዘው ወጥተዋል። መታወቅ ያለበት ጉዳይ ስለሆነ እንዲታወቅ የተደረገ ስለሆነ እና ተያያዥ ጥቃቶች ስለደረሱ እንጂ ጊዜው እንዳልሆነ እሙን ነው። ቢቢሲ፦ 'አርማውን ይዘው ወጥጠተው ያልተገባ ነገር አሳይተዋል' የተባለውን ፓርቲ ማነጋገር አይቀልም ነበር፤ መሰል አከራካሪ መግለጫ ከመስጠት? አቶ በቀለ፦ በፓርቲዎች መካከል መሰል ውይይት አልተለመደም፤ ነገር ግን ሁኔታው በተፈጠረ ማግስት ፓርቲዎች ተሰብስበን የጋራ መግለጫ አውጥተን ነበር። ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከማናቸውም ተንኳሽ ተግባሮች እንዲቆጠቡ የሚል ግንዛቤም ወስደን ነበር። ቢሆንም ይህንን ስምምነት ተግባራዊ ያላደረጉ ኃይሎች በመገኘታቸው እና ከዛ በላይ መነጋገርም ብዙም አዋጭ ሆኖ ባለመገኘቱ መግለጫ ማውጣትና በዛ መልክ መገናኘት ይሻላል በሚል ነው ወደዚያ ያመራነው። እኛ ቃላችንን ሳናጥፍ ደጋፊዎቻችንና አባሎቻችን ራሳቸውን እንዲያቅቡ አድርገናል፤ ሙከራ አላደረግንም ማለት ግን አይቻልም። ቢቢሲ፦ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ሚድያዎች ሊተቃቡ ይገባል ብላችሁ ኢሳት የተሰኘው የሚድያ ተቋም ላይም አተኩራችኋል። ኢሳት ላይ ማተኮር ለምን አስፈለገ? አቶ በቀለ፦ ኢሳት ሃገሪቱን አንድ የማድረግ ሚና አይደለም እየተጫወተ ያለው። ሕዝቡን አንድ የሚያደርግ ሚና አይደለም እየተጫወተ ያለው። የተወሰኑ ድርጅቶችን ወይም የፖለቲካ ፓርቲን ግምት ውስጥ በማስገባት በሌሎች ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ ግን ዘመቻ በመክፈት ላይ ያለ መሆኑን የምንገነዘበው። መሰል ሁኔታዎች የሚስተዋሉት ደግሞ 'የፖለቲካ ተንታኝ' ተብለው በሚጠሩ ግለሰቦች አማካይነት ነው። ይህንን ለማስተዋል ተቀርፀው የተቀመጡ ማህደሮችን ማገላበጥ ይበቃል። ከዚህ መግለጫ በኋላ እንኳን ተንታኞቹ የሰጡት አስተያየት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው። ከመግለጫው ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች ሁሉ ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶባቸዋል። በጣም ተንኳሽ የሆኑ ቃላትን በመጠቀም የኔን ስም ሁሉ ሳይቀር ሲያንኳስሱ ነበር። ከበፊት ጀምሮ ኢሳት የሚያስተላልፋቸው ዘገባዎች ሃገር ገንቢ አለመሆናቸውን ሁሉም ያውቀዋል። እኔ መግለጫውን ካወጡት መካከል ነኝ። በአቋሞቹ አምንበታለሁ። ምላሴን አላጥፍም። ነገር ግን በግሰለሰብ ደረጃ ሳይሆን በድርጅት ደረጃ ያወጣነው መግለጫ ነው። እኔ ብቻዬን እንዳወጣሁ አድርጎ በማቅረብ ኃላፊነት የጎደለው ሥራ ሠርተዋል። ኢሳት ትላንትም ዛሬም ሚዛናዊ አይደለም፤ ትላንትም ዛሬም ለኢትዮጵያ አንድነት እየሠራ ያለ ተቋም ነው ብዬ አላስብም። • አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ • ስለጉግል የማያውቋቸው 10 እውነታዎች ቢቢሲ፦ ከሚድያ ጋር ተያይዞ የተነሳው ሌላው ትችት፤ ሌሎች ሃገር በውስጥም በውጭም ያሉ ሚድያዎች መወቀስ አለባቸው የሚሉ አሉ። አቶ በቀለ፦ እኛ ሁሉንም ሞኒተር (መቆጣጠር) ማደረግ የምንችልበት አቅም የለንም። ነገር ግን የግልም የመንግሥትም ሚድያዎች ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ ሲያስተላልፉ እንደበሩ ገልፀናል። ዛሬም እምነታችን ነው። ኢሳትን የሚያህል ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ የሚያቀርብ እስከዛሬ ድረስ አላየሁም። ኢሳትን የሚስተካከል የለም ማለታችን ነው እንጂ ሌሎቹ አይደሉም ማለታችን አይደለም። ኦኤምኤን ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በዚህ ደረጃ ሊወዳደሩ የሚችሉ ተቋማት ናቸው ብዬ አላምንም። ቢቢሲ፦ ሌላው መከራከሪያ ደግሞ አቶ በቀለ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በፊት የነበረውን አመራር የተዋጉት ኢሳትን የመሳሰሉ ሚድያዎችን በመጠቀም ነበር የሚል ነው። አቶ በቀለ፦ እኔ እንደ ፖለቲከኛ ማንኛውንም ሚድያ እጠቀማለሁ። የእናንተን ሚድያ ተጠቅምኩ ማለት እናንተን ደገፍኩ ማለት አይደለም። ሚድያ ደግሞ አንደ ሁኔታው 'ስትራቴጂ' ይቀይራል። ከማን ጋር መቼ መሥራት እንዳለበት ይወጥናል። እኔ የነሱን ሚድያ ከተጠቀምኩ ቆይቻለሁ። ሰሞኑን የነበረውን ጉዳይ ለማብራራት ፈልጌ ላገኛቸው አልቻልኩም፤ የተወራው ግን ተቃራኒው ነው። ማንኛውም ሚድያ ሚዛናዊ እስከሆነ ድረስ ሃሳቤን እገልፃለሁ። ትላንትና እነሱን በመጠቀሜ ዛሬ ልተቻቸው አልችልም ማለት አይደለም። ቢቢሲ፦ የእርስዎን ፓርቲ (ኦፌኮ) ጨምሮ መግለጫ ያወጡት ድርጅቶች በቋንቋ ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝም የሥርዓቱ ችግር መንስዔ ነው ብላችሁ እንደማታምኑ አሳውቋችኋል። በእርስዎ እምነት የችግሩ መንስዔ ምንድነው? አቶ በቀለ፦ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አለመገንባቱ ነው። ሕገ-መንግሥቱ ላይ ያሉ ዴሞክራሲያዊ መብቶች መሬት ላይ መውረድ አለመቻላቸው፣ ሕዝቡ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር አለመደረጉ፣ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ አለመካሄዱ እና የሰው ልጅ መብት መረጋገጡ ነው ትልቁ ችግር። አሁን ያለው በቋንቋ ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝም ያመጣው ችግር ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ አንዳችም ጥናት የለም። እንዲህም ሆኖ ሕዝቡ አሁን ያለውን የፌዴራሊዝም ሥርዓት አንፈልግም፤ ሕገ-መንግሥቱ መሻሻያ ይደረግበት ካለ ሕግን ተከትሎ ማድረግ ይቻላል። ቢቢሲ፦ ጥናት ባይኖር አንኳ ሃገሪቱ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ተመልክተን ሥርዓቱ አዋጭ አለመሆኑን መናገር እንችላለን የሚሉ ወገኖች ደግሞ አሉ። አቶ በቀለ፦ እርግጥ ነው እንደዚህ የሚሉ አሉ። እኛ ደግሞ የከፋፈለን የፌዴራሊዝም ሥርዓቱ አይደለም፤ የከፋፈለን ነገር ሌላ እንደሆነ ነው የምናምነው። ይህ አይደለም፤ ይህ ነው የከፋፈለን እያሉ ሌላ መከፋፈያ ምክንያት ከመስጠት ለሕዝቡ በመረጠው መሪ እንዲተዳደር ዕድሉን እንስጠው ነው የምንለው። ቢቢሲ፦ የከፋፈለን ማነው? ወይም ምንድነው ብለው ነው የሚያስቡት? አቶ በቀለ፦ የከፋፈለን አተገባበሩ ነው። ሕዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ማስተዳደር አለመቻላቸው ነው። ራሳቸው በመረጡት መንግሥት መተዳደር አለመቻላቸው ነው። ሕገ-መንግሥቱ በትክክል ሥራ ላይ አለመዋሉ ነው። እኔ አውቅልሃለሁ፣ የእኔ ቋንቋ፣ የኔ ባህል ካንተ ይሻላል የሚሉ ሰዎች ጫና ለመፍጠር በሚያደርጉት ሩጫ ሃገር ወደትርምስ ገብታለች የምንለው። ቢቢሲ፦ አሁን ባለው የሃገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ የኦሮሞ የበላይነት አለ ብለው ያስባሉ? አቶ በቀለ፦ እኔ አለ ብዬ አላስብም። አለ ብዬ ባስብ በመጀመሪያ ደረጃ ለመቃወም የምነሳው እኔ ነኝ። የታሠርኩት፣ የታገልኩት ወደፊትም የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም። የማንም ብሔር የበላይነት ባለበት ሃገር ውስጥ ዝም ብዬ መቀመጥ አልሻም። እኔ ሰብዓዊ ፍጡር ነኝ፤ በአጋጣሚ ከአንድ ብሔር የተወለድኩ ሰው ነኝ። ትላንት ለተገኘሁበት ብሔር መብት የታገልኩ ሰው ነኝ። የታገልኩትም የሌላውን ብሔር መብት ለመንፈግ አይደለም። የአንድ ብሔር የበላይነት ምልክት ባይ እንኳ እቃወማለሁ። ቢቢሲ፦ ፓርቲዎ (ኦፌኮ) አሁን የሚታገለው ማንን ነው? ገዢውን መንግሥት? አቶ በቀለ፦ እኛ የምንታገለው ምንም የተወሰነ ብሔር የለንም፤ የምንታገለው ለሕዝቦች ነፃ ምርጫ ነው። እኛም አንድ አንድ ፓርቲ በነፃነት ተወዳድረን፣ ሃሳባችንን አቅርበን፣ ሕዝቡ ከፈለገን ተመርጠን ካልሆነ ደግሞ ለተመረጠው መገዛት ነው የምንፈልገው። ከተወሰነ ቡድን፣ ብሔር ወይም ፓርቲ ጋር አይደለም ትግላችን፤ ለሕዝቦች ነፃነት እንጂ። ለኦሮሞ ነፃነት ብቻ አይደለም። ሁኔታዎች አስገድደውን ነው ዝቅ ብለን በብሄር ደረጃ እንድንታገልን የሆነው። ወደፊት ሕብረ-ብሔራዊ እና ሁሉንም ሕዝብ እኩል የሚመለከት ፓርቲ በሚፈጠር ጊዜ የእኛም ፓርቲ ህልውና አላስፈላጊ ይሆናል ማለት ነው። ቢቢሲ፦ አሁን ላይ በሃገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ እየተንቀሳቀሰ እንዳለ አንድ የፖለቲካ ሰው ስለወደፊቱ ሲያስቡ ምን ይሰማዎታል? ስለኢትዯጵያ ሲያስቡ? አቶ በቀለ፦ እኔ ባለሙሉ ተስ ፋ ነኝ። አንድ የማምንበት ነገር አለ። ፍትህ፣ እውነት ብትረገጥም አንድ ቀን ቀና ማለቷ አይቀርም። ሃሰት የሚነዙ ግለሰቦች የትም እንደማይደርሱ አውቃለሁ። መንገጫገጭ ሊኖር ይችላል፤ እኔ ግን የሚታየኝ አሁንም መልካም ነገር ነው። ይኼ ሀገር ተስፋ ያለው በእግዚአብሄርም ዘንድ ቃል የተገባለት ሀገር ነው። ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። የማስመሰል ፖለቲካ ሊኖር ይችላል። ግጭቶች እዚህም እዚያም ሊኖር ይችላል። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ሁሉም ነገር ይረጋጋል የሚል እምነት ነው ያለኝ።
news-48796796
https://www.bbc.com/amharic/news-48796796
ዓይናሞችን ዓይነ ስውር የሚያደርገው እራት
ረዥሙ መተላለፊያ ላይ ድንግዝግዝ ባለ መልኩ ብርሃን አለ። ድቅድቅ ጨለማ ከዋጠው ክፍል የአንድ ሰው ድምፅ ይሰማል። ወደ ጨለማው ክፍል ለሚገቡ ሰዎች አንድ እጃቸውን ከፊታቸው ያለ ሰው ትከሻ ላይ አድርገው ወደፊት እንዲራመዱ ትእዛዝ ይሰጣል። ሁሉም ሰው ስልኩን እንዲያጠፋም ቀደም ብሎ ተነግሯል።
እንደ ተባልነው አድርገን ወደ ፊት አንድ ሁለት እያልን ተራምደን ድቅድቅ ጨለማ ከዋጠው ክፍል ውስጥ ገባን። ቀጥሎ እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ ማሰብ በጣም የሚያስፈራ ነገር አለው። ምክንያቱም ከድቅድቅ ጨለማ ጋር ከመፋጠጥ ውጪ ምንም የሚታይ አንዳች ነገር የለምና፤ ድምፅ ብቻ ነው የሚሰማው። በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛና በጣልያንኛ የሚነጋገሩ ሰዎች ድምፅ በተለያየ ርቀት ይሰማል። በጨለማ ወዲያ ወዲህ እያሉ ሰዎች ቦታ ቦታቸውን እንዲይዙ የሚያደርጉ አስተናጋጆች አሉ። አንደኛው ወደ እኛ መጥቶ ወንበራችንን እንድንይዝ አደረገ። ሁለት ኢትዮጵያዊያን እና አንድ የውጭ ዜጋ ጠረጴዛ ተጋርተን ተቀመጥን። በድቅድቁ ጨለማ ገፅታችን ምን እንደሚመስል ሳንተያይ ተዋወቅን። የትና ምን እንደምንሰራ እንዲሁም ስለ ብዙ ነገሮች እያወራን ደቂቃዎች ሄዱ። አስተናጋጁ የሚጠጣ ነገር እንድናዝ ጠይቆ ይዞልን መጣ። ብርጭቋችንን ከጠጴዛ ላይ በዳበሳ ከማንሳትና በውስጡ ያለውን መጠጥ ለማሽተት ከመሞከር ውጭ ምንም ምርጫ አልነበረንም። አሁንም አሁንም ብርጭቋችንን በዳሰሳ እየፈለግን በማንሳት የቀረበልንን እየተጎነጨን ጨዋታችንን ቀጠልን። • "እናቴ የሞተችው ኤች አይ ቪ እንዳለብኝ ሳትነግረኝ ነው" እዚያ ቦታ ላይ መገኘት ጨለማን እንዲፈሩ፤ አለማየት ሊነገር ከሚችለው በላይ ከባድ እንደሆነ እንዲያስቡ ግድ ይላል። ለቀናት፣ ለዓመታት ብሎም ህይወትን ሙሉ እንዲህ ባለ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መኖር እጅግ ፈታኝ እንደሆነ አወራን። ይህ የእኔ እጣ ቢሆንስ? የሚል ጥያቄ በእያንዳንዳችን ውስጥ መኖሩ ይሰማል። አስተናጋጁ ዳግም ወደ እኛ መጥቶ ሾርባ አቅርቦልን ዋናው የምግብ ምርጫችንን ጠይቆን ሄደ። በዳበሳ ማንኪያና ሹካ ከሳሃን እያጋጨን ጨለማም ቢሆን እጅና አፍ አይተጣጡም እንደሚባለው በድቅድቁ ጨለማ ሳናይ አጣጥመን ተመገብን። ቀጥሎም 'ዲዘርት' ኬክ መጣልን። ምንም እንኳ እየበላን፣ እየጠጣንና እየተጨዋወትን ቢሆንም ጨለማው ጭንቅ የሚያደርግ ነገር አለው። ቀጥሎ ደግሞ የተለያዩ ቀርፃ ቅርፅና ሌሎች ነገሮችን እየመጡልን በመዳሰስ እና በማሽተት ምን እንደሆኑ እንድንለይ ተጠየቅን። በዙሪያችን ያለውን ነገር እንደ ዓይነ ስውር በመስማት፣ በመዳሰስና በማሽተት ለመረዳት መሞከራችንን ቀጠልን። በመጨረሻም በአይነ ስውር አስተናጋጆቻችን እየተመራን ከድቅድቁ ጨለማ ክፍል ወጣን። ይህ ለአንድ ሰዓት ተኩል የሚቆይ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የቀረበ ማዕድ የሚዘጋጀው ዓይናሞች የዓይነ ስውራን ህይወት ምን እንደሚመስል ለደቂቃዎችም ቢሆን እንዲሰማቸው ለማድረግ ታስቦ ነው። አይነ ስውራን እንዴት ይህን ወይም ያን ማድረግ ይችላሉ? ለሚሉ ጥያቄዎችም መልስ ለመስጠትና አጠቃላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው። አቶ ብርሃኑ በላይ የ 'ቱጌዘር ኢትዮጵያ' ሥራ አስኪያጅ ናቸው። የሦስት ልጆች አባት ሲሆኑ ልጆቻቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ገብተው በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ድርጅቶች በመስራት ላይ ይገኛሉ። • በንቅለ ተከላ ዕይታው የተመለሰለት ኢትዮጵያዊ ታዳጊ አቶ ብርሃኑ ለ40 ዓመታት ያስተማሩ መምህር ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት 'ማዕድ በጨለማ' ስለ ዓይነ ስውራን ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን መለወጥን ያለመ አንድ የድርጅቱ ተግባር ነው። በጨለማው ማዕድ ላይ ከተካፈሉ በኋላ በሙያዊና በገንዘብ ድጋፍ ከድርጅቱ ጎን የቆሙ በርካቶች እንደሆኑ ይናገራሉ። ነገሩን ለማስፋት በሌሎች አውሮፓ አገራት እንዳሉ ዓይነ ስውራን የሚያስተናግዱባቸው የጨለማ ምግብ ቤት የመክፈት ሃሳብ እንዳላቸውም ይናገራሉ። ድርጅታቸው ሴት ዓይነ ስውራን መጠለያ እንዲያገኙና እንዲማሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ፣ ለዓይነ ስውራን የኮምፒውተር እንዲሁም ዓይነ ስውራን እንዴት መንገድ መሪ በትርን መጠቀም እንዳለባቸውም ስልጠና እንደሚሰጥ አቶ ብርሃኑ ይገልፃሉ። ኮምፒውተር ለዓይነስውራን እንዴት? ሣሙኤል ኃይለማሪያም የአስራ ሁለት ዓመት ታዳጊ ሳለ በመኪና አደጋ ነበር የዓይን ብርሃኑን ያጣው። ከታደምንበት የጨለማው እራት ሁለት ዓይነ ስውራን አስተናጋጆች መካከል አንዱ ነበር። "ሙሉ በሙሉ የእኛን ስሜት ያገኙታል ባይባልም የጨለማው እራት ዓይናሞች የግድ እያንዳንዷን ነገር በእኛ ውስጥ ሆነው እንዲያዩ ያደርጋል። ዓይኔ ከጊዜ በኋላ ስለጠፋ እኔም ራሴን በእነሱ ቦታ አስቀምጣለሁ" ይላል። ራሳቸውን የሚስቱ፣ ከባድ የእራስ ምታት የሚቀሰቀስባቸውና ወደ ድቅድቁ ጨለማ ክፍል መግባት ፈርተው ገና ከበር የሚመለሱም አጋጥመውታል። • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" በሕግና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ሲሆን በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እየሰራ ይገኛል። ላለፉት ስድስት ዓመታት እራቱን የሚያዘጋጀው 'ቱጌዘር ኢትዮጵያ' የተሰኘው በጎ አድራጎት ድርጅት ለዓይነ ስውራን የኮምፒውተር ስልጠናዎችን የሚሰጥ ሲሆን ሣሙኤልም ከስልጠናው ተጠቃሚዎች አንዱ ነው። ኮምፒውተር መጠቀም መቻል ለሥራው የግድ አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራል። ከስልጠናው በፊት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳለ ሶፍት ኮፒ ፅሁፎችን ኮምፒውተር ላይ ጭኖ ከማድመጥ በስተቀር በስፋት ኮምፒውተር የመጠቀም ልምድ አልነበረውም። አሁን ግን የለት ተለት ሥራው ከኮምፒውተር ጋር የተቆራኘ እንደሆነ በመግለጽ፤ "ኢንተርኔት እጠቀማለሁ ራሴ ሶፍትዌሮችን እጭናለሁ" ሲል ያስረዳል። ብዙ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩት፤ ውይይቶችና ክርክሮችም የሚደረጉት በማህበራዊ ሚዲያ ነው። የግል ወሬዎች የሚደሩትም እንዲሁ በእነዚህ የበይነ መረብ መድረኮች ላይ ሆኗል። ከዚህ አንፃር ዓይነስውራን የማህበራዊ ሚዲያ ተሳትፎ እንዴት ነው? ለሳሙኤል ያነሳነው ጥያቄ ነበር። "ፌስቡክ አካውንት የከፈትኩት እንዳውም ዩኒቨርሲቲ እያለሁ ነው። ኮሜንት፣ ላይክም ሼርም አደርጋለሁ" በማለት በኮምፒውተር ባይሆንም ቀድሞም በስልክ ኢንተርኔት ይጠቀም እንደነበር አጫወተን። አሁን ደግሞ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕና ኢሞም ይጠቀማል። የአውሮፓ እግር ኳስ ውጤቶችን በይበልጥ የሚከታተለው በኢንተርኔት ነው። ኢንተርኔት ቤት ጎራ ብለህ ታውቃለህ? ኤን ቪ ዲ ኤ (NVDA) Non Visual Desktop Access የተሰኘ የኮምፒውተር ገፅን በድምፅ ለማንበብ የሚረዳ ሶፍትዌር በፍላሽ ይዞ ኢንተርኔት ቤት ይሄዳል። ብዙ ጊዜ የኢንተርኔት ባለቤቶቹም ሆኑ ተጠቃሚዎች ወንበር ስቦ ከኮምፒውተር ፊት ቁጭ ሲል ግራ ይጋባሉ። • በዓይነ ስውሯ የተሠራው የሚያይ ሻንጣ "የኢንተርኔት ቤቱ ልጅ አይነ ስውራን ኢንተርኔት እንደሚጠቀሙ ያውቃል። እና ወንበር ሲያሲዘኝ የተጠቃሚው አይን ሁሉ እኔ ላይ እንደሆነ ተሰማኝ። እኔ ኢሜልም እንዲሁ አንዳንድ ገፆችንም ቼክ ሳደርግ የራሳቸው ብር እየቆጠረ ሌሎቹ ተጠቃሚዎች እኔን ያዩ ነበር" እያዩህ እንደሆነ እንዴት አወቅክ? ወይስ ሹክሹክታም ነበር? "ሰው ከጀርባሽ ሲኖር ወይም ሲያይሽ የሚሰማሽ፤ የሚታወቅሽ ነገር አለ። መጨረሻ ላይ ሂሳቤን ከፍዬ ስወጣም የኢንተርኔት ቤቱ ልጅም ነግሮኛል" ድንገተኛ ስራዎች ኖረው ባለበት አካባቢ አቅራቢያ ከሚገኝ ካፍቴሪያ ቁጭ ብሎ ኮምፒውተር ሲከፍት ደግሞ "እንዴት ነው ኮምፒውተር የምትጠቀመው" የሚለው ጥያቄና ግራ መጋባት ይበረታል። ስራ ፍለጋ ለአይነ ስውራን ምን ያህል ከባድ ነው? "ወደ ሰላሳ ቦታዎች አመልክቼ ነው በመጨረሻ የአሁኑን ስራ ያገኘሁት። ለምሳሌ አንድ ቦታ የፅሁፍ ፈተና ጥያቄን ሙሉ በሙሉ ደፍኜ ለቃለ መጠይቅ ተጠርቼ ሄጄ ሲያዩኝ አይነ ስውር ነኝ። ሳላልፍ ቀረሁ። ህግ ያጠና የሚል ማስታወቂያ አውጥተው ስሄድ ላንተ አይሆንም ይሉኛል።" በጥሩ ውጤት መመረቅስ? "በአራት ነጥብ ተመርቀሽ ውጤትሽ ምንም ያህል ያማረ ቢሆን ቀድመው የሚያዩት አካል ጉዳተኛ መሆንሽን ነው" በማለት በተለይም ለአይነ ስውራን በግል ተቋማት መቀጠር የማይታሰብ እንደሆነ ይናገራል። "ጥሎ የማይጥለን መንግሥት ብቻ ይመስለኛል" ይላል። "ጅቡቲ ድረስ ወስደው አስለምነውኛል" እናንዬ ያለው 36 ዓመቷ ነው። "ቱጌዘር" ከሚደግፋቸው ሴት ዓይነ ስውራን አንዷ ነች። ሁለት ልጆቿን ለብቻዋ ታሳድጋለች። የተወለደችው ሰሜን ጎንደር ወቅን በሚባል ቦታ ሲሆን የዓይን ብርሃኗን ያጣችው የስምንት ዓመት ህፃን ሳለች ነው። በወቅቱ በአካባቢያቸው ወረርሽኝ ገብቶ በየቤቱ ሁለት ሦስት ሰዎች በዓይን በሽታ መታወራቸውንና ከእነሱ ቤትም እሷና ወንድሟ ላይ ይህ ክፉ እጣ መድረሱን ትናገራለች። እናንዬ እንደምታስታውሰው "መንግሥት ልኮን ነው" ያሉ ግለሰቦች እናስተምራቸዋለን ብለው እሷና ወንድሟን ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት ጉዞ ይጀመራሉ። ሰዎቹ ወንድሟን ሁመራ ላይ እንዲለምን ሲያደርጉ እሷን ደግሞ እያስለመኑ ወደ አዲስ አበባ አመጧት። ያኔ የዘጠኝ ዓመት ልጅ ነበረች። ከዚያም በአስራ ሦስት ዓመቷ ድሬደዋ ከዚያም ደወሌ ወስደዋት ባልጠና የልጅ ጉልበት በእግር ጉዞ ጅቡቲ ይዘዋት ይገባሉ። አዲስ አበባም ጅቡቲም መሪም ተቆጣጣሪም የሚሆን አንድ ሰው እየተመደበላት ከጠዋት እስከ ማታ እየለመነች ለሰራቂዎቿ የለመነችውን ገንዘብ እያስረከበች ዓመታት አስቆጥራለች። ሰዎቹ ከሚያስለምኑት ሌላ አካል ጉዳተኛ ህፃን ጋር ጅቡቲ ውስጥ ለሦስት ዓመታት ቆይታለች። ስቃዩ ሲበረታባት ከአጋቾቿ ጠፍታ እዚያው ጅቡቲ ሃበሾች ከሚኖሩበት ሰፈር ሄደች። ሃበሾቹ እረድተዋት አምልጣ ወደ ድሬዳዋ ሄደች። አጋቾቿ ግን ብዙም ሳትቆይ በጥቆማ ደርሰውባት ወደ አዲስ አበባ ይዘዋት መጡ። እንደገና ረዥም ዓመታትን አስለመኗት። "በአጠቃላይ ከዘጠኝ እስከ አስራ ሰባት ዓመቴ ለእነሱ አገልግያለሁ" ትላለች። የሚያስለምኑሽ እንዴት ያሉ ሰዎች ነበሩ? "ባልና ሚስት ናቸው። የምትቆጣጠረን ደግሞ አንዲት ሴት ልጅ ነበረች" እናንዬ "ቱጌዘር ኢትዮጵያ" ከሚደግፋቸው ሴት አይነ ስውራን አንዷ ስትሆን ዓይነ ስውራን ተደራጅተው የእደ ጥበብ ሥራዎችን ከሚያመርቱበት ድርጅት ውስጥ እየሰራች በምታገኘው እጅግ አነስተኛ ገቢ ልጆቿን ለማሳደግ ትታገላለች። እንደ እሷ ያሉ ዓይነ ስውራን እናቶች ልጆቻችሁን እንዴት ነው የምታለብሱት? የምታጥቡት? በአጠቃላይ መንከባከብ የምትችሉት የሚሉ ጥያቄዎች ሁሌም ይቀርቡላቸዋል። ዓይነ ስውር መሆን በተለይም ሴት ሆኖ ብዙ ከባድ ነገሮች ቢኖሩትም እናት ለልጇ የምታደርገውን ሁሉ ማድረግ እንደሚችሉ እናንዬ ትናገራለች። "ቢሆንም ግን ህብረተሰቡ ሴት ዓይነ ስውራንን ማገዝ አለበት" ትላለች። ዓይነ ስውራንበትራቸውን ይዘው ሊመሯችው ሲሞክሩለምን ይቆጣሉ? ዓይነ ስውራንን ለመምራት በትር ወይም ኬን መያዝ እንደሌለበት የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ "በትሩ የዓይነ ስውራኑ ዓይን ነው" ይላሉ። ምንም እንኳ ዓይናሞች በቅንነት የሚያደርጉት ቢሆንም ይህ ድርጊት "ዓይንህን ይዤ ልምራህ" እንደማለት እንደሆነ ያስረዳሉ። ልብሳቸውን ይዘው እየጎተቱ ሊመሯቸው የሚሞክሩም ራሳቸውን አጋጥመዋቸዋል። ይህ ደግሞ በዓይነ ስውራኑ ዘንድ ተፀይፈውን ነው አይነት ስሜት ይፈጥራል። የሚገባው እጅ መያዝ አልያም ከዓይነ ስውራኑ ጋር እጅ ለእጅ ተጣምሮ መምራት ተመራጭ ነው ይላሉ። "ልርዳህ? ልምራህ?" ብሎ የዓይነ ስውሩን ፍላጎት መጠየቅም ጥሩ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ልምራችሁ ተብለው የተሰረቁ ዓይነ ስውራንም እንዳጋጠሟቸው ይናገራሉ። "ቱጌዘር" ዓይናሞችና ዓይነ ስውራን በአንድ ላይ የሚሰሩበት ድርጅት ነው። የዓይነ ስውራንን አቅም መገንባትና ዓይነ ስውራንን ተወዳዳሪ ማድረግ አንዱ አላማቸው ነው። ተደፍረው ትምህርታቸውን ያቋረጡ ሴት ዓይነ ስውራንን ወደ አዘጋጀው መጠለያ ማስገባትና ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ የድርጅቱ ቀዳሚ አላማ ነው። ብዙዎች በዚህ መልኩ ድጋፍ ተደርጎላቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መግባታቸውን የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ በመጠለያው ያዘጋጁት የህፃናት ማቆያ ደግሞ የሚማሩ ሴት ዓይነ ስውራንን ብቻም ሳይሆን ሎተሪ የሚያዞሩና የሚለምኑ ዓይነ ስውራን ሴት ልጆችንም እንደሚያውልና እንደሚመግቡ ይገልፃሉ። ለአይነ ስውር እናቶቹ ብቻ ሳይሆን ለልጆቻቸውም ጭምር የትምህርት ድጋፍም ይደረጋል።
news-51455301
https://www.bbc.com/amharic/news-51455301
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ በጋራ ማዘጋጀት እንዳልተቻለ ተገለፀ
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና የድርቅ ማካካሻ ላይ የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የህግና ቴክኒክ ባለሙያዎች ውይይት ቢያደርጉም ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ በጋራ ማዘጋጀት እንዳልተቻለ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በፌስ ቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።
ባለፈው ሳምንት አሜሪካና የአለም ባንክ በአደራዳሪነት በተገኙበት የሶስቱ ሃገራት የውጭና የውሀ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከህግና የቴክኒክ ባለሙያዎቻቸው ጋር በመሆን ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል። የአገራቱ ተወካዮች የግድቡን የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው በድርቅ ወቅት፣ ለዓመታት የተራዘመ ድርቅ በሚያጋጥምበት ወቅትና ለዓመታት የተራዘመ ደረቅ ወቅት ላይ ስለሚኖረው የውሃ አሞላልን በተመለከተ መሰረታዊ መግባባት ላይ መደረሱ ተነግሯል። • ክፍል 1 ፡በፅኑ የታመመው የዓባይ ወንዝ • የግዙፉ ግድብ ግንባታ፡ የኢትዮጵያና ግብፅ ቅራኔ የአገራቱ ሚኒስትሮችም የቴክኒክና የሕግ ቡድኖቻቸው በመሰረታዊነት መግባባት ላይ የተደረሱባቸው ነጥቦችን በማካተት እስከ ፈረንጆቹ የካቲት ወር ማብቂያ ድረስ የመጨረሻ የስምምነት ሰነድ እንዲያዘጋጁ ማዘዛቸውንም በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ አስፍረው ነበር። የውጭና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ወደየሃገራቸው ቢመለሱም የቴክኒክና የውሃ ባለሙያዎቹ በስብሰባው ለሳምንት ያህል ቀጥለዋል። ከሶስትዮሽ ምክክራቸው በኋላ በውሃ አሞላልና ድርቅ ማካካሻ ሰነድ ላይ ላይ ለመፈረም በነገው ዕለት ቀጠሮ በተያዘው መሰረት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ዋሽንግተን ዲሲ መግባታቸውንም አቶ ፍፁም አሳውቀዋል። ዶ/ር ስለሺ ዋሽንግተን ከገቡ በኋላም ከግብፅ እና ሱዳን ልዑካን ጋር የተደረገውን የህግ ማዕቀፍ ድርድር ውጤት ከኢትዮጵያ ልዑካን ጋር አብረውም ገምግመዋል። የልዑካን ቡድኑ በውሃ አሞላልና ድርቅ ማካካሻ ጉዳዮች ላይ ውይይት ቢያደርግም ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ በጋራ ማዘጋጀት እንዳልተቻለ አምባሳደር ፍፁም በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል። በሦስቱ አገራት መካከል በሕዳሴው ግድብ ላይ እየተደረገ ያለው ድርድር በጥር ወር አጋማሽ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም በተደራዳሪዎቹ መካከል ከስምምነት ላይ ባለመደረሱ እስከ ፈረንጆቹ የካቲት ወር ማብቂያ ድረስ ለመዝለቅ ተገዷል። •አል-ሲሲ በአባይ ጉዳይ ጦርነት መፍትሄ አይሆንም አሉ •ግብጽ በአባይ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች አገራቱ በተለይ ከስምምነት ላይ እንዳይደርሱ ያደረጋቸው ጉዳይ ኢትዮጵያ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በማውጣት እየገነባቸው ያለው ግድብ የውሃ አሞላል ሂደት ነው። ግብጽ የውሃ ሙሌቱ እስከ 20 ዓመታት በሚደርስ ጊዜ እንዲሆን ስትጠይቅ ኢትዮጵያ ግን ሙሌቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሆን ትፈልጋለች። በድርድሩ ላይ ወሳኝ ሚና ያላቸው የኢትዮጵያና ግብጽ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም የየአገራቱ የሕግና የቴክኒክ አማካሪዎችን ተሳታፊ ሆነዋል። ከኢትዮጵያ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን፤ ግብጽ ደግሞ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚህ ሹክሪና የመስኖ ሚኒስትሩ ሞሐመድ አብደል አቲ በዋሽንግተኑ ውይይት ላይ በመሪነት ሲሳተፉ ቆይተዋል። አሜሪካና የአለም ባንክ በተዳራዳሪዎች ላይ ጫና አሳድረዋል እንዲሁም ለግብፅ ወግነዋል የሚሉ መረጃዎችም ሲወጡ የነበረ ቢሆንም አቶ ፍፁም ኢትዮጵያ በጥቅሟ እንደማትደራደር አሳውቀዋል። "ኢትዮጵያ በፍትሃዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት የምታምን ሲሆን፤ በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን አሳልፎ የሚሰጥ ምንም ዓይነት ስምምነት አትፈጽምም" በሚል አስፍረዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ድርድሩ "በግድቡ ብቻ ላይ የተወሰነ መሆኑን፣ እንዲሁም የሀገራችንን ነባርና የወደፊት በአባይ ወንዝ የመጠቀም መብትን በሙሉ የሚያስከብር ማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት የማይቀየር አቋም ነው" ሲል መግለፁም የሚታወስ ነው።
43343487
https://www.bbc.com/amharic/43343487
ጤፍ ሃገሩ የት ነው? ደቡብ አፍሪካ? አውስትራሊያ? . . .
ፈረንሳይ የምትኖረው የ28 ዓመቷ አትዮጵያዊት ሩት ሊሻኑ በንግድ ሥራ እራሷን ካቋቋመች 3 ዓመታትን አስቆጥራለች፤ የተሰማራችውም ከአፍሪካ የሚመጡ የተለያዩ ምርቶችን በማከፋፈል ነው። ሩት ለገበያ ከምታቀርባቸው ምርቶች መካከል ጤፍ እንዱ ነው።
ሩት ወደ ፈረንሳይ የሄደችው የዛሬ 10 ዓመት ነበር። አካሄዷም ለትምህርት ሲሆን በትምህርቷ ገፍታ ሁለተኛ ዲግሪዋን በንግድ ሥራ ለመያዝ በቅታለች። በትምህርቷ ማጠናቀቂያ ላይ ለመመረቂያ የሚሆን በንግድ ሃሳብ ላይ የሚያተኩር ወረቀት ማቅረብ ነበረባት። ይህም አሁን የተሰማራችበትን ሥራ እንድትጀምር ጠቅሟታል። የዛሬ አራት ዓመትም ሩት በምን ዓይነት የንግድ ሥራ መሰማራት እንደምትችል ማጥናት ጀመረች። በዚያን ጊዜ ለጤና ተስማሚ እንደሆኑ የሚነገርላቸው 'ግሉተን' የተባለው ይዘት የሌላቸው ምግቦች በጣም ተፈላጊነት ነበራቸው። ጤፍ ደግሞ ከእነዚህ ምርቶች መካከል ቀዳሚው ነው። በዓለም ዙሪያ ታዋቂ ከሆኑት ሰዎች መካከልም እንደእነ ቪክቶሪያ ቤክሃም ያሉ ሰዎችም የጤፍን ጠቀሜታና ከ'ግሉተን' ነፃ መሆኑን የመሰከሩበት ጊዜ በመሆኑ ትኩረቷን ወደምታውቀው የሃገሯ ምርት ጤፍ አዞረች። በዚህ መልኩ የጤፍ ገበያውን አዋጪነት የተረዳችው ሩት ጤፍና የጤፍ ምርቶች ላይ ትኩረቷን ማድረግ ጀመረች። እግረ መንገዷንም ሌሎች ምርቶችን በንግድ ሃሳቧ ላይ አካተተች። ሩት የኢትዮጵያን ጤፍ ወደ ፈረንሳይ ለማስመጣት የንግድ ሃሳቧን ስታቀርብ ሩት የገበያ ጥናት ባካሄደችበት ጊዜ በአዋጪነቱ ላይ ብቻ ሳይሆን የበርካቶችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምርቶች ለማቅረብ ወሰነች። ከኢትዮጵያ በተጨማሪም ከደቡብ አፍሪካ፣ ከናይጄሪያና ከሌሎችም ሃገራት የተወጣጡ መሰል ምርቶችን ወደ ፈረንሳይ አስመጥቶ ለገበያ ማቅረብ ጀመረች። ባለችበት ሃገር የጤፍን ጠቃሚነት ለማስረገጥ ጊዜ ፈጅቶባት እንደነበር ሩት ትናገራለች። በወቅቱ ፈረንሳይ ውስጥ ጤፍ ብዙም ባለመታወቁ ''በላቦራቶሪ ተገቢው ምርመራ ተደርጎበት ተፈላጊዎቹ የምግብ ንጥረ-ነገሮች እንዳለውና ለጤና ጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ ነበረብኝ'' ትላለች። በተለያዩ ባለሙያዎች በጤፍ ላይ የተደረጉት ጥናቶች ለጤና ተስማሚ እንደሆነ ከማረጋገጥ ባሻገር ጤፍን 'ሱፐርፉድ' ወይም 'ልዕለ-ምግብ' የሚል ስያሜ እሰጥቶት እውቅና እንዲያገኝ አድርገዋል። ''ይህ ውጤት ከተገኘ በኋላም ጤፍን የበለጠ ለማወቅ በምርቱ ላይ የሚካሄደው ጥናትም ሆነ ምርምሩ አላበቃም'' ትላለች ሩት። የሥነ-ምግብ ባለሙያዎች ባደረጉት ጥናት ጤፍ ባለው ይዘት መሠረት በሚያስገርም ሁኔታ የተለያዩ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ተረጋግጧል። የተለያዩ ቫይታሚኖች፣ ፕሮቲን እና ሌሎችም ይዘቶች ስላለው በተለይ ለስፖርተኞች 'አይረን' የተሰኘው ንጥረ-ነገር በኃይል ሰጪነቱ ተፈላጊ ነው። በተጨማሪም በፈረንሳይ ውስጥ ሥጋን የማይመገቡ በርካታ ሰዎች ስላሉና ከሥጋ ያገኙ የነበረውን ለጤንነታቸው አስፈላጊ የሆነውን 'ቫይታሚን ቢ'ን ለማሟላት ከሩዝና ከበቆሎ በተሻለ የጤፍ ምርትን ይመርጣሉ ይህ ደግሞ የጤፍን ተፈላጊነት እንዲጨምር አደረገው። ''እኔ ጤፍን የማውቀው በእንጀራ መልኩ ብቻ ነበር። ነገር ግን ከእንጀራ ባሻገር የጤፍ ዱቄት በምን ዓይነት መልክ ለምግብነት ሊቀርብ እንደሚችል መሞከርና ማወቅ ነበረብኝ'' ትላለች ሩት። በጤፍ የተሠራ ዳቦ ሩት ሊሻኑ ነዋሪነቷን ያደረገችው ሊዮ በምትባለው የፈረንሳይ ከተማ ነው። ሊዮ ደግሞ የሃገሪቱ የምግብ ከተማ በመባል ትታወቃለች። በዚህች ከተማ በጣም ታዋቂ የሆኑ ምግብ ቤቶችና የምግብ ባለሙያዎች (ሼፎች) አሉ። ከእነዚህም መካከል 'ቦኩስ' የሚባለው በጣም ታዋቂው ምግብ ቤት በከተማዋ ይገኛል። እዚያ ከሚገኙት የምግብ ባለሙያዎች ጋር ተነጋግራ በጤፉ ዱቄት የተለያዩ ምን ዓይነት የምግቦች ሊዘጋጁ እንደሚችሉ አሠራሩን በሙከራ እንዲያረጋግጡ ሰጠቻቸው። ባለሙያዎቹም ከሃገሬው የምግብ ልምድ ጋር አብረው ሊሄዱ በሚችል መልኩ በፓስታ፣ በፓንኬክና በኬክ ውስጥ እንደ ዋነኛ ግብዓት ሆኖ በተለያየ መንገድ ለየት ያሉ የምግብ ዓይነቶችን ሠርተው ማረጋገጥ ቻሉ። በተጨማሪም ባለሙያዎቹ ጤፍ ከእንጀራ ባሻገር በተለያየ መልክና ቅርጽ ተዘጋጅቶ መቅረብ እንደሚችል ከማረጋገጣቸው ጎን ለጎን፤ በጤፍ የተዘጋጁት ምግቦች ያላቸው ጣዕም ከሃገሬው የምግብ ጣዕም ጋር የሚሄድ መሆኑን ተረዱ። ሙከራው ተደርጎ አውንታዊ ውጤት መገኘቱን ተከትሎ ''ገበያውም ሆነ ተጠቃሚው ለጤፍ ያላቸውን አመለካከትና አቀባበልን ከተረዳሁ በኋላ የጤፍ ምርትን ወደ ፈረንሳይ ሃገር ለማስመጣት ወሰንኩ'' ትላለች ሩት። ስለጤፍ ሲነሳ ቀድሞ ምንጩ ነው የሚታወሰው። ሩትም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅትና ሙከራ ካደረገች በኋላ ጤፍን ወደማስመጣቱ ተሸጋገረች። ''ኢትዮጵያዊ እንደመሆኔ ጤፍ ከኢትዮጵያ ማስመጣት ብፈልግም በጣም ብዙ ውጣ ውረዶች ገጥመውኝ ነበር'' ትላለች። በመቀጠልም ''የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማሟላት የግብርና ሽግግር ኤጀንሲም ሄጄ ነበር። የዛሬ ሦስት ዓመት ጤፍ ከኢትዮጵያ ማስመጣት ይቻላል ተብሎ ወዲያውኑ ደግሞ ጤፍ ከሃገር እንዳይወጣ ተከለከለ'' ብላ ከዚያም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ጤፍ ወደ ፈረንሳይ ለመግባት ተገቢው ፈቃድ እንደሌለውም አጫውታናለች። ምክንያቱን ስታስረዳም የኢትዮጵያ ጤፍ ሙሉ በመሉ ተፈጥሮሯና ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጫ ስለሌለው እንደሆነ ተናግራለች። ይህ ማረጋገጫ የሚያስፈልገው ምርቱ ከተለያዩ ኬሚካሎች ንክኪ ነፃ መሆኑ በምርመራ ተረጋግጦ ለተጠቃሚው እንዲደርስ በፈረንሳይ የሚመለከተው ተቋም ፈቃድ አግኝቶ ወደሃገር ውስጥ እንዲገባ መፈቀድ ስላለበት ነው። ተፈላጊውን ፈቃድ ለማግኘት መታለፍ ያለበት ሂደት ድግሞ ከ14 ሺህ ዬሮ በላይ ወጪን የሚፈልግ ጉዳይ ነው ብላለች ሩት። ይህም ደግሞ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ጤፍ አምራች በጣም ከፍ ያለ ወጪ ነው። ስለዚህም ይህ ሂደት ነው የኢትዮጵያን የጤፍ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ እንዳይቀርብ እንቅፋት የሆነባት። ''የጤፉ ምንጭ ከኢትዮጵያ ሆኖ ሌሎች ከእኛ በተሻለ እየሸጡ እንዲጠቀሙበት አድርጓል'' በማለት ትቆጣለች። በዚህም ምክንያት ሥራዋን ከጀመረችና ደንበኞችን ካስለመደች በኋላ ምርቱን ማቅረብ ካልቻለች የንግድ ሥራዋን የሚያበላሽ ሆኖ ስለታያት ሌላ አማራጮችን መፈለግ ጀመረች። የጤፍ ምርትን ለማግኘትም ከኢትዮጵያ ውጪ ወደ ደቡብ አፍሪካና ወደ አውስትራሊያ ፊቷን ለማዞር ተገደደች። በጤፍ የተሠራ ብስኩትና ቸኮሌት ከደቡብ አፍሪካ ያገኘችውን ጤፍ ወደ ፈረንሳይ ከማስመጣቷ በፊት ለመሞከር ወደዚያው ሄዳ ነበር። ጣዕሙም ከኢትዮጵያ ጤፍ ጋር ምንም ልዩነት እንደሌለው ተናግራለች። ከዚህ በኋላ በምታስመጣው ጤፍ ፓንኬክ፣ ኬክ፣ ፓሰታ፣ ብስኩቶች እና ቸኮሌት የመሳሰሉት ምግቦች ይሠሩበታል። የጤፍ ይዘት ለጤና ተስማሚ ከመሆኑም ባሻገር የማያወፈር በመሆኑ ኬክም ሆነ ፓስታ ለመሥራት ተመራጭነት አለው። እነዚህንም ምርቶች 'አዲሲኒያ' በሚል ስያሜ ለገበያ አቅርባለች። ሩት እንዳጫወተችን በፈረንሳይ ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች ቢኖሩም እሷ የምታስመጣውን ጤፍ አይጠቀሙም። ምክንያቱም ዋጋው ስለሚወደድ አብዛኛውን ጊዜ ከሩዝ የተሠራ እንጀራ መሸጥ እንደሚመርጡ ነግራናለች። ''ጤፍ ቢጠቀሙም እንኳን ከእስራኤል ወይም ከዮርዳኖስ ነው የሚያስመጡት።'' ከመጋዘን ሲወጣ 250 ግራም በ7 ዩሮ እንደሚሸጥ የነገረችን ሩት፤ ፈረንሳይ ሃገር ጤፍ በብዛት ስለማይገባ ዋጋው ውድ መሆኑንም አስረድታናለች። ገበያው እንደ አሜሪካና ጀርመን ሃገር አይደለም የምትለው ሩት፤ ዋጋው ከፍ እንዳለ ሊቆይ እንደሚችል ትላለች። ሩት ይህንን ሥራ የጀመረችው የጤፍ ዱቄትን በማስመጣት ለመሸጥ ቢሆንም አሁን ግን ትኩረቷን ከጤፍ የተሠሩ ምርቶች ማቅረብ ላይ እያደረገች ነው። በየስድስት ወሩ እስከ 300 ኪሎ ጤፍ ወደ ፈረንሳይ የምታስመጣው ሩት፤ የኢትዮጵያ ጤፍ ፈቃድ አግኝቶ ለገበያ ብታቀርብ ምርጫዋ እንደሆነ ተናገግራለች። ለጊዜው የምታቀርባቸውን ምርቶች ዓይነት የመጨመር ሃሳብ እንዳላትና ከፈረንሳይ በተጨማሪ ደግሞ ወደ ጣሊያን ሃገር የማከፋፈል ዕቅድ እንዳላት ነግራናለች። አያቷ የጤፍ ነጋዴ እንደነበሩ የምታስታውሰው ሩት 'ለዚያ ሳይሆን አይቀርም ወደ ጤፍ ያዘነበልኩት' በማለት አጫውታናለች። በተጨማሪም አባቷ የነበራቸው የሆቴል ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜዋን ታሳልፍ ስለነበር ለምግብ ዝግጅት ያላትን ፍቅር ሳያዳብርላት እንዳልቀረ ሩት ታስባለች።
news-56201441
https://www.bbc.com/amharic/news-56201441
ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለዓለም ያስገኛቸው አስር ትሩፋቶች
በአንድ ዓመት ውስጥ ከ115 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የያዘውና ከ2.5 በላይ ሰዎችን ደግሞ ለሞት ዳረገውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመጣል ሳይንስ፣ ዕውቀትና ትብብር ተጣምረው ብዙ ታግለዋል፤ እየታገሉም ይገኛሉ።
ቫይረሱ አዲስ ዝርያ ማፍራቱን ተከትሎ በሚቀጥሉት ሳምንታትና ወራት ምን ሊከሰት እንደሚችል መገመት ቢያዳግትም አንድ ዓመት የሞላው ወረርሽኝ ብዙ አስተምሮናል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ብዙዎችን ቢቀጥፍም ከዚህ በፊት በአዕምሯችን ውል ያላሉ በጎ ትሩፋቶችን አስገኝቷል ይላሉ ባለሙያዎች። ከእዚህ ውስጥም እስቲ አስሩን ከኮቪድ-19 ትሩፋቶች እንመልከት። 1 - ኮቪድ-19 የወባን ማዕረግ መረከቡ ከአንድ ዓመት በፊት ማለትም ስለወረርሽኙ መዘገብ ከጀመረ ከአንድ ወር በኋላ በሕክምና መጽሔቶች ላይ ከ164 በላይ ፅሑፎች ስለኮቪድ-19 ታትሞ ወጥቷል። ከአንድ ዓመት በኋላ ዛሬ ስለወረርሽኙ የተፃፉ የጥናትና የምርምር ዘገባዎች ቁጥር በ600 እጥፍ ጨምሮ ከ100 ሺህ በላይ ሆኗል። ይህን ማዕረግ ቀድሞ ይዞ ነበር ወባ ነበር። ዘንድሮ ለወትሮው አብዝተን ከምንሰማቸው የበሽታ ዘገባዎች በላይ ስለ ኮቪድ-19 በብዛት ይነገራል። በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ከወባ በላይ ስለኮቪድ-19 የበለጠ ዕውቀት አለ። 2 - ከ200 በላይ ክትባቶች ከአንድ ዓመት በፊት ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ይረዳሉ ተብለው ጥናት ሲደረግባቸው የነበሩ ክትባቶች ቁጥር ስምንት ነበር። ባዮሬንደር የተሰኘው ድርጅት እንደሚለው አሁን ከ195 በላይ ክትባቶች በተለያዩ የሂደት ደረጃ ላይ ሲሆኑ 71 ያህሉ ደግሞ በሙከራ ደረጃ ላይ ናቸው። ፀረ-ኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለማምረት የወጣውን ወጪ፣ ትብብርና ጥናት ያክል ለሌሎች በሽታዎች ይህን የመሰለ ርብርብ አልተደረገም ይላሉ ባለሙያዎች። በዚህ ጥናት ላይ ሕዝቡ፣ የግል ድርጅቶች፣ አጥኚዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ መድኃኒት አምራቾች፣ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳትፈዋል። እርግጥ ነው አንዳንድ የጥናት ሂደቶች በእንጭጭ ቀርተዋል። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅተ ያፀደቃቸው ደግሞ በርካታ ናቸው። ፋይዘር/ባዮንቴክ፣ ሞደርና፣ አስታራዜኔካ/ኦክስፎርድ፣ ስፑትኒክ 5 እንዲሁም የቻይናው ሲኖፋርምና ጎል ተብለው የሚጠቀሱ ክትባቶች ናቸው። ቢያንስ 20 ሌሎች ክትባቶች ደግሞ የሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ምናልባትም በሚቀጥሉት ሳምንታት አሊያም ወራት ውጤታቸው ተለይቶ ወደ ሥራ ሊገቡ ይችላሉ። ተመራማሪዎች ከ200 በላይ በሚሆኑ ክትባቶች ላይ እየሰሩ 3 - የክትባቶች የጎንዮሽ ጉዳት አነስተኛ መሆን የክትባቶች ትልቁ ደንቃራ በሳይንስ ቋንቋ አናፊላክሲስ ይባላል። ይህም የክትባቶቹ ጎንዮሽ ጉዳት ሲሆን ክትባት ከተወሰደ በኋላ ወዲያው የሚከሰት ሲሆን እስከሞት ሊያደርስ ይችላል። አሜሪካ ውስጥ ክትባቱ በተሰጠበት የመጀመሪያው ወር ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚጠቁመው 17.5 ሚሊየን ክትባቶች ተሰጥዋል። ከእነዚህ የፋይዘርና የሞደርና ክትባቶችን ከወሰዱ ሰዎች መካከል 66ቱ ብቻ ናቸው ይህ የጎንዮሽ ጉዳት የገጠማቸው። ይህ በሚሊዮንኛ ሲሰላ ከአንድ ሚሊዮን ሰው 4 ብቻ ነው ማለት ነው። በመቶኛ ሲሰላ ደግሞ 0.0003 ይሆናል። ከ66ቱ ሰዎች መካከል 21 ሰዎች ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው ያውቃል። በዚህ የጎንዮሽ ጉዳት ምክንያት እስከዛሬ ድረስ የሞተ ሰው የለም። የዚህ ጥናት ውጤት ለጊዜውም ቢሆን የሚጠቁመው ክትባቶች ከጉዳታቸው ጥቅማቸው በእጅጉ እንደሚያመዝን መሆኑ ነው። በተለይ ደግሞ የሞደርና ክትባት ከሌሎቹ በላቀ ደኅንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ተነግሯል። 4 - ክትባቶች ውጤታማ ናቸው እስራኤል በርካታውን ዜጎቿን በመከተብ ከዓለም ቀዳሚ ናት። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ3.67 በላይ እስራኤላዊያን የፋይዘርን የመጀመሪያ ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ከአገሪቱ ሕዝብ 40 በመቶውን የሚይዝ ነው። ከ28 በመቶ በላዩ ደግሞ ሁለተኛውን ዙር ክትባት ወስደዋል። ከ60 ዓመት በላይ ከሆናቸው ዜጎቿ መካከል ደግሞ 80 በመቶው ተከትበዋል። የክትባቶቹ የመጀመሪያ ዙር ውጤት እንደሚያሳየው ክትባቶች እስካሁን ድረስ ባለው ጥናት መሠረት ውጤታማ መሆናቸውን ነው። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም ከጊዜ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል፤ በለተይ ደግሞ ዕድሜያቸውን 60ና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ። ሁለቱንም ዙር ክትባት ከወሰዱ 523 ሺህ እስራኤላዊያን መካከል 544 ሰዎች ላይ ብቻ ነው ኮቪድ-19 የተገኘው። እስካሁን ድረስ የተመዘገበ ሞት ግን የለም። ነገር ግን የክትባቱን ውጤታማነት ለማየት የግድ ወደ እስራኤል መሻገር አይጠበቅብንም። የክትባቶችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በአዛውንቶች ማቆያ ማዕከላት የሚኖሩና አሁን ክትባቱ የደረሳቸውን ሰዎች ቁጥር ማየት ይቻላል። በአብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ያሉ በዕድሜ የገፉ ሰዎች አሁን ክትባቱን ካገኙ በኋላ የመያዝ ዕድላቸውና የሞት ቁጥር በእጅጉ እየቀነሰ ነው። ለጽኑ ህሙማን የሚሰተው መድኃኒትና ህክምና ውጤታማ እሆነ ነው 5 - በክትባት ላይ መተማመን መጨመር በዓለም ዙሪያ እስካሁን ድረስ ከ160 ሚሊዮን በላይ ብልቃጦች ጥቅም ላይ ውለዋል። የዚያኑ ያህል ሰዎች በክትባት ላይ ያላቸው መተማንም ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው። ለምሳሌ በአውሮፓ፣ እስያና አውስትራሊያ አገራት የሚኖሩ 13 ሺህ 500 ሰዎችን መሠረት አድርጎ አንድ ጥናት ተሠርቷል። ጥናቱ ከኅዳር እስከ ጥር ባለው ጊዜ የተሠራ ነው። ኅዳር ላይ አገራት ክትባት መስጠት ከመጀመራቸው በፊት 40 በመቶ ሰዎች ብቻ ነበሩ በክትባቱ ሙሉ እምነት የነበራቸው። ነገር ግን ጥር ላይ ከ50 በመቶ በላይ ሰዎች በክትባቶች ላይ ያላቸው እምነት ሲጨምር ክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት አለው ብለው የሚያምኑ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ቀንሷል። በዩናይት ኪንግደም ካሉ ሰዎች በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ከ78 በመቶ በላይ ሰዎች ክትባቱን ለመውሰድ ዝግጁ ናቸው። 6 - በሽታን የመከላከል አቅም ከ8 ወራት በላይ አይዘልቅም አንድ ሰው በኮቪድ-19 ተይዞ ከተሻለው በኋላ የሚኖረው የመከላከል አቅም ምን ያህል ነው? የሚለውን ለመለየት የተሠሩ ጥናቶች ሙሉ ገፅታውን አያሳዩም። የበሽታ የመከላከል አቅም ምን ያህል ይቆያል የሚለውን መለየት እጅግ ጠቃሚ ነው። ይህ የክትባት የመከላከል አቅምን ለመለየትም ያስችላል። ምንም እንኳ የእያንዳንዱ ሰው በሽታን የመከላከል አቅም ቢለያይም በበርካታ አገራት የተሠሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቆይታው ከ6 አስከ 8 ወራት መሆኑን ነው። ይህ የመከላከል አቅም ቆይታ ሰዎች በበሽታው እጅጉን ተጠቁም አልተጠቁም ተመሳሳይ ነው። 7 - በጣም ለተጎዱ ሰዎች መድኃኒት ፍለጋ ኮቪድ-19 ከሳንባ ምች [ኒሞኒያ] በላይ የከፋ መሆኑን መረዳት ተችሏል። ምንም እንኳ ኮሮናቫይረስን ነጥሎ የሚያጠቃ መድኃኒት ባይኖርም በጣም ለተጎዱ ሰዎች ከሞት የሚታደጉ መድኃኒቶችን ደባልቆ መስጠት ተችሏል። እኒህን መድኃኒቶች ደባልቆ መስጠት ያለውን ሚና የሚለዩ ከ400 በላይ ጥናቶች የሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በየቀኑ የኮሮናቫይረስ በሽታ ለጠናባቸው ሰዎች የሚሆኑ መድኃኒቶች ቅመማ ከጊዜ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል። ከሌሎቹ ወረርሽኞች በተለየ በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረትን አግኝቷል 8 - ጉንፋን መጥፋት ኮሮናቫይረስ ዓለምን ማዳረስ በጀመረበት ወቅት የነበረው አንዱ ፍራቻ በክረምት ወራት ከሚነሱ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ጋር እንዴት ያደርገናል የሚለው ነበር። እንደ ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛና አስም የመሳሰሉ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ በሽታዎች ወደ ሳንባ ምችና ብሮንካይትስ ሊያመሩ ይችላሉ። እነዚህ በሽታዎች በበርካታ የዓለማችን ክፍሎች በተለይ ደግሞ ተጋላጭ በሚባሉቱ አገራት እስከ ሞት የሚያደርሱ ናቸው። በኢንፍሉዌንዛና በኮሮናቫይረስ በአንድ ጊዜ የተጠቁ ሰዎች የመሞት ዕድል በኮቪድ-19 ብቻ ከተያዙት ላቅ ያለ ነው። በተለይ ደግሞ ዕድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ አደጋው ይጨምራል። ነገር ግን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችን መጠቀም እንደ ጉንፋን ያሉ በሽታዎች እንዲቀንሱ ትልቅ ምክንያት ሆኗል። መልካሙ ዜና በክረምት ወራት የሚከሰቱ በሽታዎች ጉዳት እንደሌላው ጊዜ አለመሆን ነው። ነገር ግን ይህ ጉዳይ በቀጣዩ ዓመት ክረምት ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል ይገመታል። ኢንፍሉዌንዛ ኮሮናቫይረስ በባሕሪ በጣም የተለያዩ በሽታዎች መሆናቸውን ልብ ማለት ያሻል። 9 - የበሽታውን ዕድገት በየደቂቃው መከታተል እንችላለን አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ጥቅም ላይ እየዋሉ ባሉ ክትባቶች ላይ ያለው ኃያልነት እስካሁን በውል አልተረጋገጠም። ቢሆንም አንድ መልካም ዜና አለ። አሁን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ላይ እያንዳንዱን ለውጥ በቅርበት መከታተል ይቻላል። ሳይንቲስቶች የበሽታውን ዕድገት የሚያጠኑበትን መንገድ አዳብረዋል። ጥናቶቹ ካለፈው ዓመት የካቲት እስካሁድ ድረስ ያለውን የበሽታውን ዕድገት ከሥር ከሥሩ የሚከታተሉ ናቸው። እኒህ ጥናቶች የበሽታውን አካሄድ አጥንቶ መፍትሄ ለማበጀት ይረዳሉ። የአንድን ወረርሽኝ እያንዳንዱ ዕድገትና ለውጥ በየደቂቃው ማጥናት የተቻለው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። 10 - የወረርሽኙ መቀዛቀዝ ተደጋግሞ እንደተጠቀሰው የኮሮናቫይረስ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል የሚለው አሁንም እርግጠኛ መልስ አልተገኘለትም። ነገር ግን እስካሁን የነበረውን አካሄድ በማየት በየጊዜ የወረርሽኙ ማዕበሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም። ቢሆንም ተፅዕኗቸው ከዚህ በፊት ከነበረው ዝቅ እያለ የሚመጣ ነው። አሁን እንደ መልካም ዜና እየተቆጠረ ያለው ወረርሽኙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር መቀዛቀዝ ማሳየቱ ነው። ለዚህ እንደምክንያት ከሚጠቀሱ ነገሮች መካከል አንደኛው በሽታውን የመከላከል አቅም መዳበር ነው። ለመከላከል አቅም አንዱ አጋዥ መሣሪያ ደግሞ ክትባት ነው። ይህም የሽታውን መስፋፋት ለመግታት ትልቅ ተስፋን ሰጥቷል።
news-42389949
https://www.bbc.com/amharic/news-42389949
ሂጃብ ለባሿ የሕግ ብቃት መመዘኛ ፈተና ላይ እንዳትቀመጥ ተከለከለች
የሕግ ምሩቅ የሆነችው ናይጄሪያዊት ሕጋዊ ጠበቃ ሆኖ ለመሥራት የሚያስፈልገውን ፈተና ላይ ሂጃቧን አላወልቅም በማለቷ እንዳትቀመጥ ተደረገች።
የኦሎን ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ የሆነችው አማሳ ፊርደኡስ በአለባበሷ ምክንያት በአቡጃ ፈተናው ወደሚሰጥበት አዳራሽ ከመግባት ታግዳለች። አማሳ ሂጃቧን ከማወልቀው ይልቅ ከላይ ሰው ሠራሽ ጸጉር(ዊግ) ማጠለቅ እንደፈቅድላት ስትጠይቅ እንደነበረ የሀገረቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ይህ ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የሕግ ክፍል የወጣውን የአለባበስ ሥርዓት እንደመቃወም ተደርጎ ነው በየኒቨርሲቲው የተወሰደው። እርሷ ግን እርምጃውን "ሰብዓዊ መብቴን የጣሰ" ብላዋለች። ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያም ከፍተኛ ትኩረት ስቧል።
50730150
https://www.bbc.com/amharic/50730150
የቀድሞው የፀረ ሽብር አዋጅ ታሳሪዎች ያልተመለሱ ጥያቄዎች
በፀረ ሽብር አዋጅ ተከሰው እስር ቤት የነበሩና ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ክሳቸው ተሽሮ ነጻ የወጡ 300 የሚደርሱ ግለሰቦች ተሰባስበው የአዲስ አበባ የፖለቲካ እስረኞች ማኅበር መስርተዋል። የቀድሞ እስረኞች የህክምና፣ የትምህርት፣ የመኖሪያ ቤት፣ የመቋቋሚያና ሌሎችም ሊሟሉልን ይገባሉ ያሏቸውን ካሳዎች ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ቢሮ ጥያቄ ቢያቀርቡም አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ ገልጸዋል። የአዲስ አበባ የፖለቲካ እስረኞች አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ ዳሰማ ሶሪን አነጋግረናል። የአዲስ አበባ የፖለቲካ እስረኞች የተመሰረተው በነማን ነው? ለምንስ?
2010 ዓ. ም. መጨረሻ አካባቢ አብዛኞቻችን ከእስር ስንፈታ ምንም የምንሰባሰብበበት ወይም በመንግሥት በኩል ምንም የተደረገልን ነገር አልነበረም። ከተለያየ ቦታ ሰብስበው አሰሩን፤ ከዓመታት በኋላ ውጡ ተብለን፣ ወጣን። ሜዳ ላይ ነበር የተበተነው። 2011 ዓ. ም. መስከረም አካባቢ የተቸገሩ ሰዎችን ለመርዳት ፒያሳ አካባቢ መሰባሰብ ጀመርን። በማዕከላዊ የተደረገብን በደል አለ። የተዘረፍነው ንብረት አለ። ሌሎችም የመብት ጥያቄዎች አሉን ብለን ተሰባሰብን። ብዙ መጠለያ የሌላቸው አሉ። እስር ቤት ለዓመታት የቆዩ ናቸው። ቤተሰቦቻቸው ተበትነዋል። እነዚህን እንዴት ከመብት አኳያ መጠየቅ አለብን? ብለን የተለያዩ ጠበቆችን አነጋገርን። ጥያቄያችንን ይዘን ጠቅላይ ሚንስተር ቢሮ ሄድን። ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ያሉ ሰዎች ማመልከቻችንን ተቀበሉና አዲስ አበባ ከንቲባ ቢሮ ሂዱ አሉን። ከንቲባ ቢሮ ለሦስት ወራት ጥያቄያችንን ያለማቋረጥ አቀረብን። መጨረሻ ላይ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ጥር 26 ካፒታል ሆቴል ፕሮግራም ይዘውልን ጥያቄያችንን አቀረብን። ጥያቄያችንን ሙሉ በሙሉ ተቀብለው፤ ያቀረባችኋቸው ጥያቄዎች በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕግም፣ በሕገ መንግሥታችንም አግባብ ያላቸው ጥያቄዎች ናቸው፤ ጥያቄዎቻችሁ በአስቸኳይ ይመለሳሉ አሉን። በናንተ በኩል ማድረግ ያለባችሁን አድርጉና አቅርቡልን የሚል ምላሽ ሰጡን። ከዛ እያንዳንዱ የፖለቲካ እስረኛ የት እንደታሰረ፣ መቼ እንደታሰረ፣ የተፈረደበትን ፍርድ፣ የደረሰበት በደል፣ የትምህርት መረጃውን እና የቤተሰብ ኃላፊ መሆኑን በ1215 ገጽ ጽፈን ለከንቲባው ቢሮ አስገባን። • “በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ ያነሳችኋቸው ጥያቄዎች ምንድን ናቸው? የመጀመሪያው ጥያቄ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በነበርንበት ጊዜ ተገደን የሰጠናቸው ቃሎች፣ አሻራ እና የተሰጠብን ፍርድ አለ። ይህ መንግሥት በወቅቱ ይቅርታ የጠየቀበትና "እኛ ነን ሽብርተኛ" ብሎ ያመነው በመሆኑ፤ ሙሉ በሙሉ አሻራችን እንዲሰረዝልን፣ ፍርዱ እንዲነሳልን ነው የጠየቅነው። አንዳንድ ልጆች ሥራ ሲያመለክቱ አሻራቸው በመጥፎ ይገኛል። የተፈረደብን በሽብር በመሆኑ ሥራ ለመግባት በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳልን ነው የጠየቅነው። በማዕከላዊ የተወሰደብን ንብረት እንዲመለስልን ነው። ብዙ ንብረት ተወስዶብናል። በማዕከላዊ፣ በቃሊቲ፣ በቂሊንጦም ሆነ በሌሎች እሥር ቤቶች ውስጥ በደረሰብን ድብደባ አካላችን የጎደለ፣ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰብን ስላለን ህክምና የምናገኝበት መንገድ እንዲመቻችልን ነው ሌላው ጥያቄ። ሦስተኛው ጥያቄያችን ደግሞ ትምህርትን የተመለከተ ነው። በዩኒቨርስቲና የተለያዩ ተቋሞች ውስጥ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ እና ያላግባብ ያቋረጡ አሉ። ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበት መንገድ እንዲመቻችላቸው ጠይቀናል። ሌላው መጠለያን የሚመለከት ነው። እስር ላይ የነበሩ የተለያዩ የቤት እድሎችን እንዳያገኙ ሆነዋል። ሌላው መቋቋሚያን በተመለከተ ነው። ተዘዋዋሪ ፈንድ የሚባል አለ። በእስር ላይ በነበርንበት ወቅት ቤተሰቦቻችን ተበትነዋል። አሁንም ምንም ሥራ የሌላቸው ሰዎች ስላሉ ለነሱ ከተዘዋዋሪ ፈንድ መቋቋሚያ የሚያገኙበት መንገድ እንዲመቻችላቸው ነው የጠየቅነው። ሌላው በ27 ዓመታት በኢሕአዴግ መንግሥት ሕይወታቸው ያለፈ ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚህ አጽማቸው ተሰብስቦ አንድ ቦታ እንዲቀበርና የመታሰቢያ ሀውልት እንዲቆምላቸው ነው ጥያቄያችን። የምታነሷቸው ጥያቄዎች ምን ያህል የሕግ አግባብነት አላቸው? ጥር 26 ከንቲባው በሰበሰቡን ወቅት አራት ጠበቆች ከኛ ጋር ተገኝተው ነበር። ጠበቃ አዲስ መሐመድ፣ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ እና ሌሎችም ተገኝተው ከሕግ አንጻር አስፈላጊውን [ትንታኔ] አቅርበዋል። አብዛኞቹ የፖለቲካ እስረኞች ያ ነገር ሲፈጸምባቸው የነበረው፣ ሲጎዱ የነበሩት ተገደው ነው፤ ዓለም አቀፍ ሕጉም ያግዛቸዋል [ብለዋል]። ሕገ መንግሥቱ ላይም የእያንዳንዱ ዜጋ መብት እና የአካል ደህንነት የተከበረ ነው፤ [መንግሥትም] ግዴታ አለበት [ብለዋል]። በመንግሥት ደረጃ ያሉ ሰዎች የሰውን አካል አጉድለው፣ የሰውን ንብረት ዘርፈው፣ ሰውን እንደ ዜጋ እንዳይኖር ከልክለውት፤ እነሱ በሕግ ሳይጠየቁና ይሄ ሰው ከተፈታ በኋላም ሕጋዊ ድጋፍ ወይም ሽፋን እንዳያገኝ ማድረግ አግባብ ባለመሆኑ [ምላሽ] ይገባቸዋል ብለዋል። ወደፊት በሕግም እንሄድበታለን። አሁንም አንዳንድ የሕግ ሥራዎች እየተሠሩ ነው። ሲሆኑ በይፋ እንገልጻቸዋለን። ጥያቄዎችችሁን ካቀረባችሁ በኋላ ምን ምላሽ አገኛችሁ? ከሚገባው በላይ ነው የተመላለስነው። መጀመሪያ ላይ ያቀረብናቸው ሰነዶች ኮፒ ጠፍቷል ተባለ። እንደገና ሌላ አዘጋጅተን ነው የሄድነው። ቤት የሌላቸው ዝርዝር አቅርቡ ተብለን፤ አዲስ አበባ ውስጥ ነዋሪ መሆናቸውን፣ ቤት እንደሌላቸው ከሚኖሩበት አካባቢ አጽፈው ያመጧቸውን ደብዳቤዎች ኮፒ ሰጥተን፤ በድጋሚ ጠፋ ከተባለ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ ነው ያስገባነው። ሆን ተብሎ ጥያቄያችንን ላለመመለስ የሚደረግ ጥረት እንደነበረ ነው [የምረዳው]። ትምህርትና ህክምናን በተመለከተ ጽፈንላችኋል ኑና ደብዳቤ ውሰዱ ብለውን ነበር። ሰው ግን ምን በልቶ ይማራል? ምን እየሠራ ይማራል? ቢሳካም እንኳን [ደብዳቤውን ሲሰጡን] የትምህርት ሰዓቱ አልፏል። አብዛኞቹ ተቋሞች የምዝገባ ጊዜያቸው ተጠናቋል። ትምህርትም ተጀምሯል። አምና በክረምት የጠየቅነውን ጥያቄ፤ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ሲንከባለል የነበረ ጥያቄ፤ አሁን ጥቅምት ላይ ነው ለህክምናና ትምህርት ጽፈንላችኋል ያሉት። መቋቋሚያን በተመለከተ እያንዳንዱ የፖለቲካ እስረኛ በአምስት በአምስት ተደራጅተው፣ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ነድፈው እንዲያመጡ ተደርጎ፤ ፕሮፖዛል ሠርተው ካቀረቡ በኋላ ከተዘዋዋሪ ፈንዱ ላይ እንዲመራ ተደርጎ ነበር። ቢያንስ ቢያንስ ሥራ ሠርተው ሌሎች ችግሮቻቸው ቀስ እያሉ ይመለሳሉ ብለን እዚህ [ጉዳይ] ላይ አጣድፈናቸው ነበር። በኋላ ግን የጻፉልን ደብዳቤ አነስተኛ የሥራ እድል እና ፈጠራ እንዲሁም አዲስ ብድርና ተቋም በአግባቡ እንዳይረዱን የሚያደርግ ነበር። • ፖለቲከኞችን የመፍታት እርምጃ? ደብዳቤው እንዳንረዳ አድርጓል ያልከው ምን የሚል ይዘት ስላለው ነው? ተዘዋዋሪ ፈንዱ የተፈቀደው እድሜያቸው ከ34 ዓመት በታች ለሆኑ ነው። ከንቲባው ያሉት፤ ምንም ይሁን ምንም በልዩ ትዕዛዝ፣ በልዩ ሁኔታ እንድትስተናገዱ ይደረጋል ነበር። በልዩ ሁኔታ የምንስተናገድ ከሆነ የእድሜ ገደቡ ለኛ ተነስቷል ማለት ነው። እኛጋ እድሜው ከ21 እስከ 78 ዓመት የሚደርስ ሰው ነው ያለው። ደብዳቤውን ሲጽፉልን ግን ተባበሯቸው የሚል እንጂ የእድሜ ገደቡ መነሳቱን የሚመለከት ምንም ነገር አልጻፉልንም። ስንደራጅ ደግሞ ሁሉም በእድሜ ከሚመጥነው ጋር ስለሆነ የተደራጀው ለመምረጥ አስቸጋሪ ሆነ። ደብዳቤው ከተበተነ በኋላ አስፈላጊውን ትብብር ያደረጉልን ሰዎች አሉ። አነስተኛና የሥራ እድል ፈጠራ ላይ የሚገኙ ሰዎች፤ በአንድ ሳምንት 141 ሰው የተደራጀበትን ወደ 30 ምናምን ፕሮጀክት አጥንተው፣ የሚስተካከለውን አስተካክለው ወደ ታች እንዲወርድ አደረጉልን። ክፍለ ከተማ ስንሄድ፤ ታች ውረዱና በወረዳ ላይ ተደራጁ እንጂ እኛ አናደራጃችሁም ብለው መለሱን። ከላይ ፕሮጀክቱ ተሠርቶ አልቆ፣ ፕሮጀክቱ ታርሞ፣ ተስተካክሎ ነው የመጣው፤ እንዴት ከታች እንደራጃለን? ስንል ምንም የምናውቀው ነገር የለም ብለው መለሱን። ደብዳቤያችን በዚህ ምክንያት ተቀባይነት አጣ። ከዛ ደብዳቤውን አስተካክሉልን ብለናቸው፤ ደብዳቤው ተስተካክሎ ሲሰጠን ደግሞ ለተዘዋዋሪ ፈንዱ የተመደበው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ አልቆ ነው ያገኘነው። አልቋልና ድጋሚ ገንዘብ እስኪመጣ ጠብቁ ነው የተባልነው። ለዓመታት በእስር ሲማቅቅ የነበሩ ሰው፣ ቤተሰቦቹ የተበተኑ፣ አካሉ የጎደለ ሰው ነው ያለው። ይህን ሰው ለመድዳት ዳተኛ ከመሆን የመነጨ እንጂ ፍላጎቱ ቢኖር ኖሮ የአንድ እና ሁለት ሳምንት ሥራ ነበር። የህክምና አገልግሎት ለማግኘት የጠየቃችሁትን እስካሁን ያገኘ አለ? ማንም አገልግሎት ያገኘ ሰው የለም። 1215 ገጽ የሆነው ሰነድ የምን ያህል ሰዎች ኬዝ ነው? 300 ገደማ እንደርሳለን። እያንዳንዱ ሰው ባለ ትዳር መሆኑ እና አለመሆኑን ያረጋገጥንበት ሰነድ አለ። ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ የተፈረደበት ፍርድና መፈታቱን የሚገልጽ ደብዳቤ አለ። ከወህኒ ቤት የተፈታበት ደብዳቤም አለ። የአዲስ አበባ ነዋሪ ለመሆኑ የቀበሌ መታወቂያው ኮፒ አለ። የአዲስ አበባ ነዋሪ ሆኖ በስሙ የተመዘገበ መጠለያ የሌለው (የኪራይ ቤቶች አስተዳደርም ሆነ የግል ቤት) መሆኑን፣ የትምህርት ደረጃውን፣ ከትምህርት መባረሩን እና ህክምና እንደሚያስፈልገው የሚገልጹ ሰነዶች ናቸው። • ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚጠበቁ 10 ነገሮች ለጠየቃችኋቸው ጥያቄዎች የተሰጧችሁ መልሶች ውጤታማ እንዳልሆኑ ማለትም፤ ተዘዋዋሪ ፈንዱ በእድሜ መገደቡ፣ የትምህርት መመዝገቢያ ጊዜ ማለፉ፣ የህክምና አገልግሎት አለማግኘታችሁንም ገልጻችሁ ዳግመኛ ጥያቄ አቅርባችኋል? አቅርበናል። ተዘዋዋሪ ፈንዱን በተመለከተ ከንቲባው ጋር ቀርቧል ነው ያሉን። ከሁለት ወር በላይ ጠብቀናል። ምንም መልስ የለም። ከንቲባውን ለማግኘት ሦስት ጊዜ ጠይቀናል ምላሽ አላገኘንም። የሚነገረን ሌላ ነው። የሚሠራው ሌላ ነው። ለጥያቄዎቻችሁ መልስ እንዳላገኛችሁና ወደ ቀጣዩ እርምጃ እንደምትሄዱ ተናግራችኋል ቀጣዩ እርምጃችሁ ምንድን ነው? የመጀመሪያው እርምጃችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳዩን እንዲያውቅልን ማድረግ ነው። ይህ ብቻም አይደለም። ለምሳሌ በእስር ሲማቅቁ ለነበሩ መቋቋሚያ የሚሆን ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተረዱ የተባሉ ገንዘቦች አሉ። በአሀዝ ተጠቅሶ ያለው ገንዘብ ይታወቃል። የእነዚህን ማስረጃ እየሰበሰብን ነው። ክቡር ከንቲባው ማዕከላዊ ሄደው፣ ቀለም አስቀብተው፣ ለዓመታት ሰዎች ሲሰቃዩበት፣ አካል ሲጎድልበት የነበረውን ቦታ ሙዝየም እንዲሆን ክር በጥሰው ገብተዋል። ጥሩ ነው። ማዕከላዊን ቀለም ከመቀባት ባለፈ እዛው ሲሰቃዩ የነበሩ ሰዎች ግን አንድም ሰው ዞር ብሎ አላያቸውም። ሜዳ ላይ ተበትነው ነው የቀሩት። የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅ የፈለግነው ይህን ነው። የፖለቲካ ጨዋታ ነው የተያዘው። ከዚህ በፊት ትግል ስናደርግ የነበረው ካሳ እንድናገኝ የተለየ ጥቅም እንድናገኝ አይደለም። ቢያንስ ያፈሰሱትን ደም ይጥረጉ፣ የሰበሩትን አጥንት ይጠግኑ፣ ያረገፉትን ጥርስ ይተኩ ነው ያልነው። ጥያቄያችን ሌላ አይደለም። ያደረሱብንን በደል፤ ከቃላት ባለፈ፤ በኛ ይብቃ የሚባልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያረጋግጥ የሆነ ነገር ያድርጉ ብለን ነው የጠየቅነው። ግን አንዱንም ለማድረግ ፍቃደኛ አይደሉም። ለቀድሞ እስረኞች መቋቋሚያ የሚሆን የገንዘብ እርዳታ አለ ያልከውን ብታብራራልን? እሱን እኛ ራሳችን እያጣራን ነው። ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዲያውቁልን የፈለግናቸው ነገሮች አሉ። ሆነ ተብለው ተሸፍነው የተዘለሉ ነገሮች አሉ። እነሱን ጊዜው ሲደርስ እናወጣቸዋለን። ለሕዝብ ከማሳወቅ ባለፈ ለጥያቄዎቻችሁ አሁንም መልስ ካላገኛችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ወደ ሕግ ከመሄዳችን በፊት ያቀድናቸው ነገሮች አሉ። ቤተሰቦቻችንን እና የተጎዱ ሰዎችን እና ደጋፊዎቻችንን ሰብስበን ሰላማዊ ሰልፍ የመጥራት እቅድ አለን። የረሀብ እድማና ሌላም ያቀድናቸው ነገሮች አሉ። ጊዜያቸው ሲደርስ እንገልጻቸዋለን። አንተ የታሰርከው መቼ ነበር? ፍሪላንስ ሆኜ የተለያዩ የግል ጋዜጣዎች ላይ እሠራ ነበር። አሁን በተፈረደብኝ ፍርድ የታሰርኩት 2007 ዓ. ም. ላይ ነበር። በጻፍኩትና በሬድዮ ላይ በሠራሁት ነገር ነበር የተከሰስኩት። ከተፈረደብኝ በኋላ እስከ 2010 ዓ. ም. ታስሬያለሁ። ግን ከዛ በፊትም በተደጋጋሚ በጋዜጠኝነት ሥራዬ ማዕከላዊና ሦስተኛ ወንጀል ምርመራም ታስሬያለሁ።
50513606
https://www.bbc.com/amharic/50513606
እቴጌ፡ የጡት ካንሰርን በቀላሉ በስልክዎ መለየት እንደሚችሉ ያውቃሉ?
ቤተል ሳምሶን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጥቁር አንበሳ የሕክምና ትምህርት ቤት የአምስተኛ ዓመት የሕክምና ተማሪ ናት። ቤተል፣ የሕክምና ተማሪዎች ማህበር ውስጥ በአባልነት የምትሳተፍ ሲሆን በስነ ተዋልዶና ኤች አይ ቪ ላይ የሚሰራን አንድ ኮሚቴ በዳይሬክተርነት ትመራለች።
የሕክምና ባለሙያ ከሆኑት አባቷና ከሥነ-ሕንፃ ባለሙያ እናቷ አዲስ አበባ ውስጥ ተወልዳ ያደገችው ቤተል የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ናዝሬት ስኩል ነው የተከታተለችው። ለኔም ሆነ ለወንድሜ ሕክምና ማጥናት የቤተሰቦቼ አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም የምትለው ቤተል፣ በናዝሬት ስኩል ስትማር በሴቶች ላይ የሚሠሩ ሥራዎች ላይ እንዳታተኩር የሚያስችላትን ምክር ከመምህራኖቿ ተቀብላለች። "ሴቶች ትምህርት ቤት መማሬ..." ትላለች ቤተል፣ "...ሁል ጊዜ የሚነገረን እኛ ዕድለኛ መሆናችንና በርካታ ሴቶች እኛ ያገኘነውን እድል ስለማያገኙ የሴቶችን ሕይወት ለመለወጥና ለማሻሻል መሥራት እንዳለብን ነበር።" የሕክምና ተማሪዎች ማሕበር ውስጥ ከገባች በኋላ የበጎ አድራጎት ሥራ አልያም የሕክምና ትምህርቱን ለማዘመን፣ ካልሆነ ደግሞ የማሕበረሰብ ጤና ላይ መሥራት እንደምትችል አማራጮች ቀረቡላት። • ኤምአርአይ ምንድነው? • ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ ምን ያህል ያውቃሉ? • የወንድሙን ገዳይ ለመበቀል ወደ ፈጠራ ሥራ የገባው ኢትዮጵያዊ ያኔ ነው እናቶችና ሕፃናት ላይ ከስነ ተዋልዶ ጤና ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመሥራት የወሰነችው። ሴቶች ላይ ለመሥራት ስትወስን ሃሳቡ ከባህር በላይ ሰፊ እንደሆነባት ታስታውሳለች፤ ስለዚህ ከሴቶች መብት ጋር በተያያዘ፣ የሴቶች ጥቃትን ለማስቆም የስነተዋልዶ ትምህርት ለመስጠት እንዲሁም የጡትና የማሕፀን ጫፍ ካንሰር ላይ ብትሠራ እንደምትወጣው ተረዳች። ይህንን ፍንጭ ለማግኘት የረዳትን ስታብራራም በማሕበር ውስጥ 'ደብል ኢምፓክት' የተባለ ፕሮጀክት መኖሩ ነው ትላለች። ደብል ኢምፓክት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደማለት ነው። ስለ ካንሰር ሲያስተምሩ የጡትና የማሕፀን ጫፍን በጋራ ማስተማር እንደማለት። በተለያዩ ተቋማት እየሄደች ስለጡትና ስለ ማህፀን ጫፍ ካንሰር ታስተምራለች፣ ጡታቸውን ራሳቸው እንዲፈትሹ፣ አልትራ ሳውንድና የማሞግራፊ ምርመራ እንዲያደርጉ መልዕክት ታስተላልፋለች። የማህፀን ጫፍ ካንሰርንም ቢሆን በአቅራቢያቸው በሚገኝ የጤና ጣቢያ ጎራ በማለት እንዲመረመሩ ታበረታታለች። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ለማስተማሪያነት አልያም ለመርጃ መሣሪያነት የሚያገለግል በኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተዘጋጀ መርጃ ልታገኝ አልቻለችም። ያኔ እቴጌ ተፀነሰች። እቴጌ ስትፀነስ ግን ከእርሷ ጋር አብረውት የሚማሩት፤ ሜሪ መሬሳ፣ መህቡባ በጊቾ፣ ቅድስት ዓለም ሰገድ አብረውኝ ነበሩ ትላለች። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ካንሰር ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች መካከል አንዱ ነው። በዓለማችን ላይ ካንሰር ብቻውን በየዓመቱ 7.9 ሚሊየን ሰው እንደሚገድል ጥናቶች ያሳያሉ። ምንም እንኳ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገራት ውስጥ አሁንም በገዳይነት ግንባር ቀደምነቱን የያዙት ተላላፊ በሽታዎች ቢሆንም እንደ ካንሰር ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችም እያደጉ ይገኛሉ። ከሁሉም የካንሰር ዓይነቶች የጡት ካንሰር የከፋ መሆኑን የሚያሳየው እ.ኤ.አ. በ2018 የተደረገ ጥናት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡ የካንሰር ሕሙማን ቁጥር 25.5 በመቶው የጡት ካንሰር የተያዙ መሆናቸውን ያሳያል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳው በመላ ሀገሪቱ ከሚከሰቱ ሞቶች ካንሰር 5.8 በመቶውን ድርሻ ይይዛል። በኢትዮጵያ በካንሰር ታምመው ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች አብዛኛዎቹ በሽታው ከተሰራጨና ደረጃው ከፍ ካለ በኋላ እንደሚመጡ ቤተል ትናገራለች። • አመጋገባችን ማረጥን ሊያፋጥን ወይም ሊያዘገይ ይችላል • "ዓላማችን ችግሮችን ፈተን ገንዘብ ማግኘት ነው " የጠብታ አምቡላንስ ባለቤት • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ በዓለማችን ላይ በስፋት ከሚታዩት የካንሰር ዓይነቶች መካከል የሳንባና የጡት ካንሰር ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ በኢትዮጵያም የጡትና የማህፀን በር ካንሰር ቀዳሚውን ተርታ ይይዛሉ። በሀገሪቱ ውስጥ በካንሰር ተይዘው ከሚሞቱ ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ሴቶች መሆናቸውንም ጥናቶች ያሳያሉ። ቤተል የጡትና የማህፀን ጫፍ ካንሰርን ስታስተምር ባገኘችው መርጃ መሣሪያ ተነሳስታ የእቴጌ መተግበሪያን ለመሥራት መወሰኗን ለቢቢሲ ትናግራለች። ቤተልና ጓደኞቿ፣ የጡትና የማሕፀን ጫፍ ካንሰር ማስተማሪያ መሣሪያዎችን ማዘጋጀት ሲያስቡ የተለያዩ አማራጮች በቅድሚያ ተነስተው እንደነበር አትዘነጋም። ስለ በሽታው የተንቀሳቃሽ ምስል ብናዘጋጅ ሴቶች ስልካቸው ላይ ጭነውት ምን ያህል ጊዜ ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚለውን ከግምት አስገብተዋል። ከዚህም ተነስተው የስልክ መተግበሪያ ቢሆን፣ የቀን መቁጠሪያ በማካተትም በየወሩ ራሳቸውን እንዲፈትሹ ለማድረግ እንዲያስታውሳቸው ተደርጎ ሊሰራ እንደሚችል በመረዳታቸው መተግበሪያውን ለመሥራት ወሰኑ። ይህ መተግበሪያ ስልክ ላይ ተጭኖ በየወሩ የሚያስታውስ ከሆነ፣ አንዲት ሴት ራሷን በየወሩ በመፈተሽ ጤናዋን መጠበቅ፣ ካንሰር ከተከሰተም ሳይባባስ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ እንደምትችል ታስረዳለች። አሰሳ ማህበራዊ ሚዲያ ቤተል የሕክምና ተማሪ እንደመሆኗ ሀሳቡ እንጂ መተግበሪያውን የመሥራት አቅሙም ሆነ ችሎታው አልነበራትም። ስለዚህ አንዳንድ ድርጅቶችን በር ለማንኳኳት የማህበራዊ ድረገ ጾችን ማሰስ ጀመረች። ሊንክድኢን ላይ ዞካ አይቲ ሶሊውሺንስ፣ ቴሌግራም ላይ ደግሞ እዝራ ደሜን አገኘቻቸው። ያሰበችውን ስታካፍላቸውም ተገናኝተው ቁጭ ብሎ ለማውራት ቀጠሮ ያዙ። እነዚህ አካላት ስለቤቲ ፕሮጀክት ሲሰሙ ደስተኛ መሆን ብቻ ሳይሆን ሥራውን ወዲያው ለመጀመር ዓይናቸውን አላሹም። የዞካ አይቲ ሶሊውሺንስ መስራችና ዳይሬክተር አቶ ብሩክ ብርሃኔ፣ በነፃ ለመስራት ፈቃደኛ ሆነ። ዞካ አይቲ ሶሊውሺንስ ሶፍትዌርን መስራትና የመረጃ ደህንንት ላይ ስልጠና የሚሰጥ በመሆኑ መተግበሪያውን ሰርተዋል። • "ወንዶች በጡት ካንሠር እንደሚያዙ አላውቅም ነበር" • ስለ ወንዶች ፊስቱላ ምን ያህል ያውቃሉ? እቴጌ መተግበሪያ ላይ ስለጡት ካንሰር ስታስተምር አቶ ብሩክ ብርሃኔ ቤተል ወደ ድርጅታቸው ስትመጣና ስትነግራቸው ለምን መተግበሪያውን ለመሥራት እንደተስማሙ ሲናገሩ፣ በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት 64 ሚሊየን የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ መኖሩን በማንሳት ነው። ከእነዚህ መካከል 18 ሚሊየኑ የኢንተርኔት ዳታን የሚጠቀም መሆኑን በማከል እንዲህ ዓይነት የጤና መልዕክቶች በቀላሉ በስልክ ላይ እንዲሠሩ መሆናቸው፣ ለተጠቃሚ በቀላሉ ተደራሽ ያደርጋቸዋል ሲሉ ይናገራሉ። ከ18 ሚሊየኑ የሴቶች ቁጥርም ቀላል አይሆንም የሚሉት አቶ ብሩክ፣ በአንድሮይድ ስልኮች ላይ የሚሠራ መተግበሪያ መስራታቸውን ያስራሉ። በሀገራችን አብዛኛው ሰው የሚጠቀመው አንድሮይድ ስልክ ነው የሚሉት አቶ ብሩክ፣ ለዚህም ቅድሚያ በመስጠት መስራታቸውን ይናገራሉ። ድርጅታቸው ይህንን መተግበሪያ ለመሥራት ከካዝናው፣ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ከ50 ሺህ ብር በላይ ማውጣቱን ተናግረው ከዚህ መተግበሪያ የሚያገኙት ምንም ክፍያ እንደሌለ ይጠቅሳሉ። እዝራ ደሜ በበኩሉ በሥነ-ሕንፃ የተመረቀ ቢሆንም በግሉ የተለያዩ የአኒሜሽኖችን ሥራዎችን ይሠራ ስለነበር እቴጌን፣ መተግበሪያው ላይ እንደሚታየው መልዕክቱ ሴቶች እንዴት ጡታቸውን በመንካት ለካንሰር ተጋልጠው መሆን አለመሆኑን እንደሚፈትሹ የሚያሳየውን በአኒሜሽን መታየት በሚችል መልኩ የመሥራት ኃላፊነቱን በመውሰድ ሠራ። ቤተል ከዞካዎችም ሆነ ከእዝራ ጋር መተግበሪያው ላይ ምን ምን ነገሮች መግባት እንዳለባቸው የሚለውን በዝርዝር ቁጭ ብላ መሥራቷን፣ እነርሱ በበኩላቸው ቴክኒካዊ ጉዳዮችን ሁሉ መወጣታቸውን ትናገራለች። መተግበሪያው በአሁኑ ሰዓት በጉግል ፕሌይ ስቶር ላይ ተጭኖ እንደሚገኝ የምትናገረው ቤተል፣ ወደ ፊት መሻሻል ያለባቸውን ለማሻሻል ሀሳብ መኖሩን አልሸሸገችም። እቴጌ ለምን? በመተግበሪያው ላይ ተቀርጻ መልዕክት የምታስተላልፈው ሴት፣ በተቻለ አቅም ኢትዮጵያዊ መልክ እንዲኖራት እና ኢትዮጵያዊ ባህል እንድታንፀባርቅ ማድረጋቸውን ቤተል ትጠቅሳለች። በዚያ ላይ ይህንን መተግበሪያ ለመስራት ከመነሻው ጀምሮ አብረዋት የነበሩ፣ ጓደኞቿ፣ ሀሳቡን ስጋ በማልበስ፣ ነፍስ በመዝራት አብረዋት በመሆናቸው እቴጌ የሚለውን ስም መርጠናል ስትል ታስረዳለች። ሴቶች በተለያየ ማህበራዊ ግንኙነታቸው ጤናንም አንስተው ስለሚወያዩ፣ ሴቶች ለሌላ ሴቶች የጤና ምክር እንዲሰጡ ለማድረግ በማሰብ አኒሜሽኗ ከሕክምና ባለሙያ ይልቅ በዕለት ተዕለት የምናገኛት ዓይነት ሴት የምትመስል ገፀባህሪን መጠቀማቸውን ታብራራለች። የስሟም እቴጌ መሆን ተጠቃሚው ሲሰማም በቀላሉ ለመረዳትና ለመቀበል እንደሚያደርገው በማሰብ መሆኑንም ትገልጻለች። እዝራ ደሜ፣ እቴጌን መጀመሪያ ሥሠራት ወጣት ነበረች ሲል ያስታውሳል፤ ነገር ግን ቤቲ እድሜዋ ሰላሳዎቹ ውስጥ ቢሆን የተሻለ እንደሚሆን ሀሳብ በማቅረቧ አሁን ያለውን መልክና ዕድሜ መያዟን ይናገራል። የጡት ካንሰር 12 ምልክቶች ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የጡት ካንሰር አብዛኛው የሚያጠቃቸው ሴቶች ዕድሜያቸው በሰላሳዎቹ ውስጥ ያሉትን በመሆኑ እንደሆነ መናገሯን ይገልጻል። እቴጌ መጀመሪያ ሥትሠራ የገጠሩ ማህበረሰብ የሚለብሰው አረንጓዴ ሸማ ቀሚስ፣ ኮንጎ ጫማ አድርጋ እንደነበር በመግለጽም፣ በኋላ ግን አስተያየቶችን በመቀበል የጥበብ ልብስ እንድትለብስ መደረጉን ይናገራል። መተግበሪያው በአሁኑ ሰዓት በአማርኛ ብቻ እንደሚሠራ የምትናገረው ቤተል፣ በቀጣይ ሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ለመጨመር ማሰባቸውን ታስረዳለች። አቶ ብሩክ ዋናው ሀሳባችን ሰዎች ጭነውት ጤናቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ ብቻ ነው በማለት ድጋፍ ቢገኝ በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መሥራት እንደሚቻል ይናገራሉ። ይህንን መተግበሪያ የሰራነው የዜግነት ግዴታችንን ለመወጣት ብቻ ነው የሚሉት አቶ ብሩክ፣ በሽታውን ቀድሞ ማወቅ የመከላከሉ ግማሽ አካል በመሆኑ መረጃውን ለማዳረስና የበርካታ ሴቶች ህይወትን መታደግ አላማቸው መሆኑን ያስረዳሉ። እዝራ በበኩሉ ይህንን መተግበሪያ ከካንሰር ውጪም ወደ ሌላ የተለያዩ በሽታዎችን ለማስተማር መጠቀም እንደሚቻል ያስባል።
news-53074876
https://www.bbc.com/amharic/news-53074876
በቤጂንግ የተነሳው አዲስ ወረርሽኝ ተከትሎ ተነስቶ የነበረው የጉዞ እገዳ ተጣለ
የኮሮናቫይረስ መነሻ በሆነችው ቻይና በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እንደ አዲስ ጭማሬ በማሳየቱ አንስታቸው የነበሩ አስገዳጅ መመሪያዎች እንደገና ለመጣል ወስናለች። የማህበረሰቡ ስርጭት ቀጥ ብሎ በነረባት ቤጂንግ በዛሬው ዕለት 31 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከተማዋ በሳምንቱም 137 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች።
አዲሱ ጭማሬ ከመመዝገቡ በፊት ለአምሳ ሰባት ቀናት ያህል የማህበረሰቡ ስርጭት አልነበረም። ወረርሽኙ የተነሳው ዚንፋንዲ ከተሰኘ ትልቁ ገበያ ነው ተብሏል። ገበያው የከተማዋን 80 በመቶ ስጋና አትክልት አቅራቢ ነው። የሃገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው ቫይረሱ መጀመሪያ የተገኘው ከውጭ የመጣ ሳልመን አሳ ለመቆራረጥ በተጠቀሙበት ጣውላ ላይ ነው ብለዋል። የገበያው ዋና ሃላፊም ሆነ የአካባቢው ባለስልጣናት ዘገባውን አጣጥለውታል። ገበያው በቀን ከአስር ሺህ በላይ ጎብኚዎች ነበሩት። አዳዲሶቹ እገዳዎች ምንድናቸው? በከተማዋ የሚገኙ 27 ሰፈሮች መካከለኛ ስጋት አለባቸው ተብለው የተለዩ ሲሆን ገበያው አካባቢ የሚገኝ አንድ ሰፈር ደግሞ ከፍተኛ ስጋት አለበት ተብሏል። በመካከለኛም ሆነ በከፍተኛ ስጋት የሚኖሩ ሰዎች ከተማዋን ለቀው መሄድ አይችሉም። ስጋት በሌለባቸው ሰፈሮች የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደፈለጉት መንቀሳሰቀስ የሚችሉትም ተመርምረው ነፃ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ነው። ነገር ግን ምርመራው እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አልሆነም። ሶስት የመርመሪያ ማዕከላት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ምርመራ የሚጀምሩት ከሁለት ሳምንታት በኋላ መሆኑን ነው። በ ተለያዩ መመርመሪያ ማዕከላትም ሰልፎች ታይተዋል። በርካታ በረራዎችም የተሰረዙ ሲሆን የባቡር አገልግሎቶችም ለሶስት ሳምንታት ያህል ጉዟቸውን እንዲቀንሱ ተደርጓል። ተከፍተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ መዋኛ ቦታዎች እንዲሁ እንዲዘጉ ውሳኔ ተላልፏል። ስፖርታዊ ውድድሮችም ተቋርጠዋል። በከተማዋ እግድ የተላለፈባቸው ሰፈሮች የሚኖሩ ባለስልጣናትም ቢሆኑ መንቀሳቀስ አይችሉም በሚል መንግሥት አስጠንቅቋል። ነገር ግን መንገዶች ክፍት ሲሆኑ ኩባንያዎችና ፋብሪካዎችም ስራቸውን ቀጥለዋል። ከተማዋ ሁለተኛ ደረጃ ስጋት ውስጥ ናትም ተብሏል። በቻይና በአጠቃላይ ባለፉት ወራት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ቫይረሱ ከተነሳ ጀምሮ እስከ መጋቢት ድረስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 80 ሺህ ሲሆን ከዚያም በኋላ የተያዙ ሰዎች 3ሺህ 200 ነው። በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ሰላሳ ሁለት የማህበረሰብ ስርጭት በመላው ሃገሪቷ የተመዘገበ ሲሆን 27ቱ በቤጂንግ አራቱ ደግሞ በከተማዋ አቅራቢያ በምትገኝ ሄቤ ግዛት ነው።
46161572
https://www.bbc.com/amharic/46161572
"ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ
ከሰሞኑ ከ7 ዓመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ መንግሥት ያቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት የቀድሞዋ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ አመራርና የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መስራችና መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ያለፈውን የፖለቲካ ትግላቸውንና የወደፊት ውጥናቸውን በተመለከተ ከቢሲሲ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ቢቢሲ - አሁን ጊዜው ወደሀገር ቤት የምመለስበት ነው ብለው የወሰኑበት ዋነኛ ምክንያት ምንድን ነው?
ወ/ት ብርቱካን-የወሰንኩበት ቀንና ሁኔታ እንደዚህ ነው ብዬ መናገር ባልችልም በሀገራችን ያለው የለውጥ ሂደት ከመነሻው ጀምሮ በዚህ የለውጥ ሂደት ሕይወቱን ሰጥቶ እንደነበረ ሰው በደስታም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በመስጋትም የምከታተለው ነገር ነበር። በጣም ጥሩ የሚባሉ ነገሮች ተከናውነዋል፤ አንደኛ ለውጡ ከውስጡ ጭቆናን ሲፈጥር በነበረው አገዛዝ አካል መሪነት የሚከናወን መሆኑ ሀገራችን ልትገባበት ከነበረው ቀውስ ያዳናት ይመስለኛል። ያው የፖለቲካ እስረኞች ሲፈቱ ፣ለሚዲያ የተሻለ ነገር ሲፈጠር ጎን ለጎን ደግሞ የሚያሳስቡኝ ነገሮች ይታዩኝ ነበር ፤ የህግ የበላይነትን ማስጠበቅ እንዲሁም ሰላምና መረጋጋትን በማረጋገጥ በኩል የታዩ ችግሮችን እንደ ሀገር ካላስወገድንና የዲሞክራሲ ለውጡን ወደ ተሻለ ሂደት ካልለወጥነው፤ በፊት ከነበርንበትም ወደበለጠ ችግር ውስጥ ልንገባ እንደምንችል ተመልክቻለሁ ። እናም ሁላችንም የምንችለውን ነገር አድርገን የዴሞክራሲ ለውጡ ሊመለስ ወደማይችልበት ሁኔታ ካላሳደግነው ችግር ውስጥ እንደምንወድቅ በምረዳበት ጊዜ የራሴን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብኝ ብዬ ወስኜ ነው እንግዲህ የመጣሁት። • "በሰላማዊ ትግል እስከመጨረሻው በፅናት እንታገላለን" እስክንድር ነጋ • "ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ • ጀግኒት ከትናንት እስከ ዛሬ ቢቢሲ- ምን ዓይነት አስተዋጽኦ? ወ/ት ብርቱካን-እስካሁን ያደረግኩት የትግል ሂደት የዴሞክራሲ ስርዓት ከማምጣት ጋር፣ ነጻና ገለልተኛ የሆኑ የዴሞክራሲ ተቋማትን ከመገንባት ጋር የተያያዘ ነው ። በፖለቲካ ትግል የተሳተፍኩትም እነዚህ ተቋማት፣ ለምሳሌ እኔ ራሴ ስሰራበት የነበረው ፍርድ ቤት፣ የዜጎችን መብት ለመጠበቅ አስተዋጽኦ ማድረግ ያለበት ነገር ግን በአብዛኛው አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያደርግ የነበረው የፖሊስ ኃይል፣ የአቃቤ ህግ መስሪያ ቤት፣ የምርጫ አካላትና የመሳሰሉትን ተቋማት በገለልተኝነትና በጠንካራ ሁኔታ ተቋቁመው እንዲታዩ ስለምፈልግ ነው፤ አሁን ይህን እውን ለማድረግ የተሻለ ሁኔታ ነው ያለው። የግድ በፖለቲካ በመቀናቀን መሆን የለበትም የሚል አረዳድ አለኝ፤ ምክንያቱም ሥልጣኑን ይዘው እየመሩ ያሉ ወገኖች ያንን ለማድረግ ፈቃደኝነት ስላሳዩ ማለት ነው። የኔም አሰተዋጽኦ በዚሁ ላይ የሚያተኩር ይሆናል፤ በየትኛው ተቋም ላይ እሳተፋለሁ የሚለውን ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሳውቅ እነግራችኋለሁ። ቢቢሲ-መቼም ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ ነገር እየተባለ እንደሆነ እርሶም ሳይሰሙ አይቀሩም፤ ሰዎች ፍላጎታቸውን እየገለጹ ነው ወይስ በእርግጥም የተሰማ ነገር አለ? ወ/ት ብርቱካን-ወሬው ከየት እንደመጣ ይሄ ነው ማለት አልችልም፤ በብዙ ሰዎች እንደሚነሳ አውቃለሁ። ከመንግሥትም ጋር በምነጋገርበት ጊዜ ከሙያዬና ከልምዴ አንጻር የተለያዩ የዴሞክራሲ ተቋማትን አይተን ልታግዢ ትችያለሽ? የሚል ጥያቄ ቀርቦልኛል፤ እኔም አስቤያለሁ፤ ግን ጨርሰን ይህን አደርጋለሁ የሚለው ላይ ገና ስላልደረስኩኝ ምንም ማለት አልችልም። ሰዎች ምኞታቸውንም ሊሆን ይችላል የገለጹት፤ በበጎ መልኩ ነው የማየው። ቢቢሲ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሜሪካ እያሉ 'በኢትዮጵያ የሴቶች ትግል ውስጥ ደማቅ ቀለም የጻፈች ጀግና ሴትን እንዳመሰግን ፍቀዱልኝ" ሲሉ ምን ተሰማዎት? ወ/ት ብርቱካን-እኔ ራሴን የተለየ አድናቆት እንደሚቸረው፣ ወይም የተለየ ጥንካሬ እንዳሳየ ሰው አልቆጥርም፤ ሀገሬ ላይ የተሻለ ነገር ማየትን እፈልጋለሁ፤ ሕይወቴን የህዝብ ተጠያቂነት ያለበት ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ለማምጣት፣ ለዜጎችም የተሻለ ሕይወትን ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ውስጥ በመሳተፍ ማሳለፍ እፈልጋለሁ። ግን ሀገራችን የነበረችበት ሁኔታ መጥፎ ሆኖ ያ ጥረቴ በአብዛኛው በውጣ ውረድ ፣ ስቃይን በሚያመጡ እስራትና መንገላታት የታጀበ ነው፤ ውጭ በነበርኩበትም ጊዜ በብዙ ሰዎች ላይ ተመሳሳይ ስቃይ ሲፈጸም ሁልጊዜ የሚሰማኝ ህመም ነበር፤ እና በእርሳቸው ደረጃ የኔን አስተዋጾ በዚያ መልኩ ሲያቀርቡት ደስ ብሎኛል። ለሀገራችን በአጠቃላይ የሚሰጠው ተስፋ ደግሞ ይበልጥ አስደስቶኛል፤ ብቻ የተደበላለቀ ስሜት ነው፤ ግን የዚያ የስቃይና የእንግልት ዘመን ምዕራፍ መዝጊያ መሆኑን እንዲሰማኝ አድርገዋል። ቢቢሲ-ይህንን ጥያቄ የጠየቅኩበት ምክንያት ያው ያኔም ስለ ጨቋኝነቱ የሚናገሩለትና ወህኒ ያወረዶት የኢሕአዴግ መንግሥት ነበር፤ አሁንም የተመለሱበትን ሀገር የሚመራው ኢሕአዴግ ነው። በሁለቱ መካከል መሰረታዊ የሆነ ለውጥ አለ ብለው ያምናሉ? ወ/ት ብርቱካን-በውስጥ ያሉ ለውጦች ወደ አደባባይ እየወጡ የሚታይ እውነት ነው? ወይስ ከውጭ የሚደረግ የመቀባባት ሂደት ነው? ለሚለውን ጥያቄያችን በሂደት መልስ እያገኘንለት መጥተናል። ማንም ሊክዳቸው የማይችላቸው ተጨባጭ እርምጃዎች ተወስደዋል፤ የፖለቲካ እስረኞች ተፈተዋል፣ በሚዲያ ላይ የነበረው ተጽዕኖ ተነስቷል፤ ንግግሮችም ቢሆኑ በቀላሉ የሚታለፉ አይደሉም፤ ምክንያቱም ንግግርና ያንን ለማሳካት የሚታየው ቁርጠኝነት ነው ወደተግባር የሚወስዱት፤ ግን ያ ተግባር አሁን የበላይነቱን በተቆጣጠረውና ለውጡን በሚደግፉ በተወሰኑ ቡድኖች ወይም ሰዎች ላይ ብቻ የሚመረኮዝ ከሆነ አሁንም በስጋት ነው የምንኖረው፤ ለዚያ ነው ተቋማዊ መሰረት በጣም አስፈላጊ ነው የምለው። ቢቢሲ- በቀጣዩ ዓመት ጠቅላላ ምርጫ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፤ ኢትዮጵያውያን በዚህ ምርጫ ከእርስዎ ምን ይጠብቁ? ወ/ት ብርቱካን-አንድ ነገር በእርግጠኝነት መጠበቅ ይችላሉ ፤ በምርጫው አልወዳደርም። እውነት ለመናገር የፖለቲካ ፉክክርን በጣም ከሚመኙት ሰዎች መካከል አይደለሁም፤ ከፉክክር በላይ መተጋገዝን፣ መተሳሰብን፣ የቡድን ሥራን ነው ግብ ማድረግ የምፈልገው ። መጀመሪያውኑም የገባሁበት መንግሥት ጨቋኝ ስለነበረ፣ የምፈልጋቸውን የህግ የበላይነት፣ የሰብዓዊ መብት መከበርና የዴሞክራሲ አስተዳደር የምንላቸውን ነገሮች ለማምጣት የግድ የፖለቲካ ትግል አስፈላጊ ስለነበረ ነው፤ አሁን ግን የፖለቲካ ውድድር ውስጥ ለመግባት ምንም ፍላጎት የለኝም፤ ህዝቡን ለማገልገል እድል አለ ብዬ አምናለሁኝ፤ ምርጫውን ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም። ቢቢሲ- በእስካሁኑ የፖለቲካ ተሳትፎዎ ይህን ባለደረግኩኝ ብለው የሚጸጸቱበት ነገር አለ? ወ/ት ብርቱካን-በፍጹም የለም ካልኩኝ ሰው አይደለሁኝም ማለት ነው፤ ወደ ኋላ ስትመለከቺው ልታሻሽይው የምትችይው ፣የተሻለ ምርጫ ልትወስጂበት የምትችይው ነገር ሁልጊዜም ይኖራል፤ ግን ባለኝ መረዳት የሞራል መርሆዎቼን ጠብቄ ባለሁበት ጊዜ ትክክለኛ ነው የምለውን ውሳኔ ወስኛለሁ። በዚህ ደግሞ ሁልጊዜም ትልቅ የህሊና ነጻነት ይሰማኛል፤ በሄድኩበትና በመረጥኩት መንገድ አንድም ቀን ጸጸት ተሰምቶኝ አያውቅም ፤ድጋሚም ህይወቴን ብኖረው በዛው መንገድ እኖረዋለሁ።
news-49494319
https://www.bbc.com/amharic/news-49494319
"የስብኀት ሥራዎች ለረዥም ዓመታት ተቀምጠው የተገኙትና የተረፉት በኔ ምክንያት ነው" ስንዱ አበበ
አዲስ አበባ ነው ተወልዳ ያደገችው። ዘበኛ ሰፈር ብትወለድም ያደገችው አዲሱ ገበያ ነው። ከአምስት ልጆች መካከል ሦስተኛ ልጅ ናት። ጋዜጠኛና ደራሲ ስንዱ አበበ ፊት ለፊት የምትናገር፣ ላመነችበት ወደ ኋላ የማትልም ናት። ከፀሀፊነት፣ ጋዜጠኝነት እና ከአሳታሚነት በተጨማሪም በመንግሥታዊ መዋቅር ለመሳተፍ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነትም ተወዳድራ ነበር።
መኀልየ መኀልይ ዘ ካዛንቺስ፣ እብዱ፣ ራምቦ፣ ጠብታ ፍቅር፣ ከርቸሌ በውስጥ ዓይን፣ ወንድም ጌታ፣ ሲራኖ፣ የባለቅኔው ምህላ እና ዛዚ የተሰኙት መጻህፍት የታተሙት በስንዱ አበበ አሳታሚ በኩል ነው። እነዚህ ሥራዎች የታዋቂ ደራሲያንና የራሷ የስንዱ አበበም ጭምር ናቸው። መኀልየ መኀልየ የተድባበ ጥላሁን፣ ወንድም ጌታ እና ሲራኖ የባሴ ሐብቴ፣ ዛዚ የስብኀት ገብረ እግዚአብሔር ስራዎች ሲሆኑ፣ የዜማና ግጥም ደራሲው ሙሉጌታ ተስፋዬ የግጥም ስብስቦችን የያዘው መጽሐፍ ደግሞ የባለቅኔው ምህላ ይሰኛል። ስንዱ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር በስራዎቿ ዙሪያ ቆይታ አድርጋለች። •ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ያናገሩና ያነጋገሩ ድርሰቶቹ ወደ አሳታሚነት ለመግባት የገፋሽ ምን ነበር? አንደኛ ጋዜጠኝነት ወከባው ምኑም ምኑም ታከተኝ፤ አስጠላኝ። ሁለተኛው መኀልየ የሚለውን መጽሐፍ ሳየው በጣም ነው የተናደድኩት። እንዴት እንዲህ ዓይነት ነገር ይከናወናል? ይኼማ ታትሞ ሕዝቡ መፍረድ አለበት ብዬ የማሳተም ሥራዬን ተድባበ ጥላሁን[ደራሲውን] ጠይቄ በመኀልየ መኃልይ ዘ-ካዛንችስ ጀመርኩ። በወቅቱ ትስሪ የነበረው ለየትኛው ጋዜጣ ነበር? ኡ. . . እኔ በጣም ብዙ ጋዜጣ ላይ ነው የሰራሁት። ከኢህአዴግ ልሳኑ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጀምሮ፣ ኔሽን፣ ሪፖርተር. . . ብዙ ጋዜጣ ላይ ጽሑፎቼ ታትመዋል። አንዱ አላትምም ቢለኝ ወደ ሌላው ወስጄ እሰጣለሁ። በመስራት ደረጃ ግን ተቀጥሬ የሰራሁትና ረዥም ዓመታት የቆየሁባቸው አብዮታዊ ዲሞክራሲና ሪፖርተር ጋዜጦች ናቸው። አንቺ መኀልየ መኀልይን ስታትሚ ኢትዮጵያ ውስጥ በአሳታሚነት የሚሰሩ በርካታ ግለሰቦች ነበሩ? ኡ. . . አልነበሩም። አንደኛ መጽሐፍ ማሳተም ውድም ነው። የሚጠይቀው ገንዘብም ብዙ ነው። በወቅቱ በግል የሚያሳትሙ የነበሩት ብሔራዊ አካባቢ እንደነ ዓይናለም፣ እነርሱም አሁን ነው ፌመስ [ዝነኛ] የሆኑት እንጂ፣ ያኔ አልፎ አልፎ ነበር የሚሞክሩት። እነ ክብሩ እንጂ ሌላ ብዙም አልነበረም። ሴት አሳታሚዎችስ ነበሩ? አይመስለኝም. . . መኀልየ መኀልይ እንደታተመ በጣም ዝነኛ ነበር። ያለ ማጋነን እንደ ትኩስ ኬክ የተቸበቸበ መጽሐፍ ነበር። አዎ! •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም ከዚያም በኋላ በእርሱ የአጻጻፍ ዘይቤ እና የመጽሐፉን ርዕስ በተመሳሳይ መልኩ በመቅዳት ሌሎች መጻሕፍትም ታትመዋል። በወቅቱ የነበረው የአንባቢዎች ምን ምላሽ ምን ነበር? ምላሹ ሁለት ፅንፍ የያዘ ነበር። አንደኛው ወገን 'ባህላችን ተነካ፣ ተደፈርን፣ እንዲህ ዓይነት መጽሐፍ መታተም የለበትም' በማለት አክርሮ የሚቃወም ሲሆን ሌላው ደግሞ 'ይኼ በጣም ጠቃሚ መጽሐፍ ነው' የሚል ነበር። ጥናት ላይ ተመስርቶ የተጻፈ መጽሐፍ ስለነበርም በተለይ ከጤና ቢሮ አካባቢ በጣም ድጋፍና አድናቆት ነበረው። እነዚህ ሁለት አስተያየቶች እንዳሉ ሆነው የግል የምትላቸው ሚዲያዎች ሆነ ብለው ነጌቲቭ [አሉታዊ] ጎኑ ላይ ያተኮሩ ፅሁፎች (አርቲክሎች) ነበር የሚያትሙት። ካልተሳሳትኩ ያኔመጽሐፉ ገበያ ላይ በዋለበት ወቅት ስለ ኤችአይ ቪ በጣም ይወራ ነበር አይደል? በጣም. . . ምን ያህል ጊዜ ታተመ? አምስት ጊዜ፣ ወዲያው ወዲያው ነው ያተምኩት። መጽሐፍ ላይ 'አምስተኛ፣ ስምንተኛ እትም' የሚል መጻፍ የጀመረው አሁን ነው። በዚያ ዘመን ተደጋግሞ የታተመ መጽሐፍ መኀልየ መኀልየ ነው። •"የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ ስንት ኮፒ ተሸጠ? በኔ ሕትመት ሠላሳ ሺህ ግድም መጽሐፉን ከአንቺ በኋላም ያሳተመው ሌላ አካል አለ ማለት ነው? አዎ። እኔ እዚህ ከመጣሁ በኋላ አሳትመውታል። በደራሲው ፈቃድ? አዎ!. . . ደራሲውን ሲጠይቁት... የምልህ እኔ እንዲታተም እፈልጋለሁ። እንዲነበብ እፈልጋለሁ እናም ተድባበ ሲጠይቀኝ የሚያትመው ሰው ከተገኘ የግድ እኔ መጠበቅ የለብኝም ብዬ ፈቀድኩ። ተድባበ እንዳተሙት ነግሮኛል ... አላየሁትም፤ መታተሙን ግን ሰምቻለሁ። መኀልየ እንዳልሽኝ የመጀመሪያ ሕትመትሽ ነው። ሁለተኛ ያሳተምሽው የማንን ሥራ ነው? የመስፍን አሸብር 'ጠብታ ፍቅር' የሚል የግጥም መጽሐፍ ነው። መሥፍን አሸብር አብሮ አደግ ጓደኛዬ ነው። በጣም የምወደው ሰው ነው። ጋዜጠኛ ነው ለረዥም ዓመታት ሬዲዮ ፋና ሰርቷል። መስፍን ሲሞት፤ ሬዲዮ ፋና የመስፍንን ግጥሞች አትማለሁ ብሎ እኔ ጋርም የተወሰኑ ግጥሞች ስለነበሩት አምጪ ልናሳትም ነው ብለውኝ ሰጥቻቸዋለሁ። ያኔ ደግሞ ፎቶ ኮፒም ምንም የለም ኦሪጂናል [ዋናውን ቅጂ] ነው የሰጠኋቸው። እና ለስምንት ዓመታት ሳያትሙት መቅረታቸው በጣም ነበር የሚያብሰለስለኝ። እና መኀልየን አትሜ ፍራንክ ሳገኝ ወዲያውኑ የመስፍንን ሥራ ነው ያሳተምኩት። ጓደኛዬም ስለሆነ ሐውልቱን የማቆም ያህል ማለት ነው። •"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ የሙሉጌታ ተስፋዬን የግጥም ሥራዎችም [የባለቅኔው ምህላ] ያሳተምሽው አንቺ ነሽ። የግጥም ስራዎችን ስለምታደንቂ ነው ወይስ ጓደኝነትን ስለምታስቀድሚ ነው እነዚህ ስራዎች ያሳተምሽው? ጓደኝነት አንድ ነገር ነው። ነገር ግን እኔ ያተምኳቸው መጻህፍት ዋጋ (ቫልዩ) ስለምሰጣቸው ነው።ትውልዱ ሊያውቃቸው ሀገሪቱ ውስጥ ታትመው ሊኖሩ ይገባል [የምላቸውን ነው።]፣ ቢዝነስ አይደለም እንደሰዉ የምሰራው። ድሮ፣ ከኛ በፊት በነበረው ጊዜ ኩራዝ ነበር፤ ኩራዝ ዋጋ አላቸው፣ ሀገሪቱን ይመጥናሉ የሚባሉ ስራዎችን ያትም ነበር። ኩራዝ ከጠፋ በኋላ ግን ሥራው [አሳታሚነት] የነጋዴው ነው የሆነው። ነጋዴ ደግሞ የሚያዋጣውን ብቻ ቶሎ ቶሎ የሚሸጡትን 'ቤስት ሴለር' የሚባሉትን እንጂ ዋጋ (ቫሊዩ) ያላቸውን ማተም ተዉ። እና እኔ እርሱን ጋፕ [ክፍተት] ለመሙላት ነበር ሀሳቤ። በርግጥ አሁን እንዳልሽኝ አንድን መጽሐፍ ለማሳተም አንቺ ዋጋ የምትሰጪያቸው መሆን አለባቸው። ነገር ግን ሌሎች መጽሐፍን ለማሳተም የምትመርጪበት መስፈርት አለሽ? ዉይ. . . በጣም ብዙ። በእኔ የንባብ ባህልና ልማድ ያነበብኳቸውንና የወደድኳቸውን ነገሮች ኮፒ አድርጌ አስቀምጣለሁ። እና በጣም የብዙ ሰዎች ስራ ነው እጄ ላይ የነበረው። እና ሁሌም ነው የሚቆጨኝ አለመታተማቸው ነው። እና እሱ ቁጭት ነው ወደ ስራውም የገፋኝ። ከዝነኛ ደራሲያን ጋር ትውይ ነበር። ጋሽ ስብኀት ገብረ እግዚአብሔር፣ ባሴ ሐብቴ ወዳጆችሽ ነበሩ። እንደነሱ ያሉ ወዳጆች በዙሪያሽ መኖራቸው ወደ አሳታሚነት ገፍቶሽ ይሆን? አዎ። የጋሽ ስብኀት ስራዎች በጣም ብዙ አመታት እኔ እጅ ነው የነበሩት። 'ሌቱም አይነጋልኝ'፣ 'ትኩሳት'፣ 'ሰባተኛው መልዓክ'፣ በእሳቸው እጅ የተፃፉት እኔ ጋር ተቀምጠው ነበር። እና በጣም ነበር እነርሱም እንዲታተሙ እፈልግ የነበረው። ሳይጠፉ ለረዥም ዓመታት ተቀምጠው የተገኙትና የተረፉት በኔ ምክንያት ነው ብዬ ነው የማስበው። ድሮ እንደውም 'ስብኀት ስራ ላይ ቆልፋ' ምናምን እያሉ፣ ይወቅሱኝ ነበር። 'ትኩሳትን'ና 'ሌቱም አይነጋልኝ'ን ታይፕ አስደርጌ (አስፅፌ) በኪራይ አሸናፊ መጻህፍት መደብር ለሚባል ሰጥቸው ነበር። እያከራየ ትንሽ ለአቦይም [ስብኀት] እንዲሰጣቸው እርሱም እንዲጠቀም አንባቢም አንዲያነባቸው በማሰብ። ከዚያ በኋላ የመታተም እድል ሲመጣ መጀመሪያ 'ታድቶ' (በሳንሱር ምክንያት ተቆራርጦ) ታተመና በጣም አዘንኩ፤ ተናደድኩ። በኋላ ኖሮ ኖሮ እንደ ተጻፉ፣ እንደወረዱ ታትመዋል። በጣም ሀሪፍ ነው። ሜጋ አሳታሚ ነበር አይደል 'አሳድቶ' ያሳተመው? አዎ ሜጋ ነው ያሳተመው። የማይሆን ነገር እኮ ነው የሰሩት። የሕዝቡን ባህል፣ አኗኗር ወግና ስርዓት ታውቂዋለሽ፣ በጋዜጠኝነት ለረዥም ጊዜም ሰርተሻል። ታዲያ ለምንድን ነው የስብኀት ስራዎች መታደታቸው ያበሳጨሽ? ጋዜጠኝነት ላይ ኤዲቲንግ የሚባል ነገር አለ። ያ ለጋዜጠኝነት ስራ ሊሰራ ይችላል። እንደነዚህ አይነት ስራዎች ላይ ግን እኔ አልቀበልም። ወይ ማተም ነው፤ ወይ አለማተም ነው፤ በቃ ተጽፏል። ለምንድን ነው እጁን ቆርጠህ፣ እግሩን ቆርጠህ የምታሳትመው? ምን ስለሆንክ ነው? እምልህ ልክ አይደለም። እኔ ያኔ ከነደምሴ [ደራሲ ደምሴ ጽጌ]ጋርም ተጣልተናል። ኤዲት እያደረግነው ሲሉ ሁሉ ኡኡ ብያለሁ። የሚሰማኝ ነበር የጠፋው። 'ኤዲት' ተደርጎ ከሚታተም አይታተም፤ ጊዜው ሲደርስ ይታተማል ብል ኖ . . . ኖ ብለው፣ ሜጋም ፍራንኩን ስለሚፈልገው ታተመ። ኤኒዌይ[ለማንኛውም] ለኔ 'ኤዲት' የተደረገው አልተመቸኝም። እግዜር የተመሰገነ ይሁን ጊዜው ሲደርስ ኦሪጂናሎቹ (ዋና ስራዎቹ) ታትመዋል። መኀልየ መኀልይ ወደ ሌላ ቋንቋ መተርጎሙን ሰምቻለሁ ልበል? ቆይቷል፤ ወደ ፈረንሳይኛ ከተተረጎመ ቆይቷል። ላርታዥ ሚኖተር የሚባል አንድ የፈረንሳይ አሳታሚ፣ መጽሐፉ በጣም ዝነኛ በነበረበትና ጋዜጦቹ ልክ አይደለም በማለት በሚጮሁበት ወቅት ሰማ። ያኔ ደግሞ ሌሎች ሰዎች መጽሐፉን መተርጎም ጀምረው ነበር። አንድ ወቅት አንድ ብሩክ የሚባል ልጅ መጥቶ 'መኀልየ መኀልየን እኮ እየተረጎምነው ነው' አለኝ። 'ወደ ምን ቋንቋ' ስለው 'ወደ ፈረንሳይኛ' 'ከማን ጋር' ስለው 'ሊሴ ከሚያስተምር መምህር ፋንስዋ ከሚባል ጋር' 'ለምን' ስለው 'ወደነው' አለኝ። 'ጥሩ ነው ተርጉሙት' ብዬው ረዥም ጊዜ ቆይቷል። በኋላ ይኼኛው አሳታሚ መጥቶ 'ስለመጽሐፉ ምንነት እንድናውቅ ትንሽ ኤክስትራትክት [ቅንጭብ ታሪክ] የሚተረጉምልን' ሲሉኝ፣ ' ኧረ ተርጉመነዋል የሚሉ አጋጥመውኝ ያውቃሉ' ብዬ እነርሱን ፈልጌ አገናኘኋቸው። ከዚያ ሲያዩት ማተም ፈለጉ፤ ለማሳተም ሲጠይቁኝም 'አትሙ' ብዬ ፈቀድኩ። ቅድሚያ ተድባበን ጠየቅሁት እርሱ በመጽሐፉ ላይ አንቺ ማዘዝ ትቺያለሽ ከእኔ ወጥቷል አለኝ። ፈቀድኩላቸው። ሰዎቹ መጀመሪያ በፍላጎት ነበር መተርጎም የጀመሩት በኋላ ግን አሳታሚው ስራው እንዲጠናቀቅ ከፍሎ አስተረጎማቸው። ከዚህ ውጪ አንቺ ካሳተምሻቸው ውስጥ ወደሌላ የተተረጎሙ ስራዎች አሉ? የለም። ከማሳተም ውጪ የራስሽ የሆኑ ስራዎች የፃፍሽው አለ? ካተምኳቸው ውስጥ ሁለቱ የኔ ስራዎች ናቸው። የትኞቹ ማለት ናቸው? አንዱ 'ከርቸሌ በውስጥ ዓይን' ይላል እውነተኛ ታሪክ ነው። ጥናት ላይ የተመሰረተ ስራ ነው። ሁለተኛው 'ራምቦ' ነው። 'ራምቦ ድንቅ ሰው' ይሰኛል። ራምቦ ፈረንሳያዊ ገጣሚ ነው። ሐረር ውስጥ የኖረው ራምቦ ነው አይደል? አዎ አስር ዓመት ሐረር ኖሯል። እዚያ የኖረበትም አሁን ሙዚየም ሆኗል። ለንጉሥ ምኒሊክ መሳሪያ ሸጧል። የሚገርም ሰው ነው በጣም፣ በጣም። እርሱንም የፈረንሳይ ኤምባሲ ስፖንሰር [ ድጋፍ] አድርጎልኝ ነው ያጠናሁት። ምክንያቱም መጀመሪያ ራምቦ፣ ራምቦ ሲሉ ምንድን ነው እናንተ ታጋንናላችሁ እንጂ ምንድን ነው ራምቦ ስል እስቲ አንቺ ቼክ አድርጊው (አጥኚው) አሉኝ። እኔ የማውቀው' የሰከረ መርከብ' የሚለውንና ዶ/ር ብርሃኑ አበበ የተረጎሙትን አንድ ግጥሙን ብቻ ነበር። በጣም ነበር ያን ግጥሙን የምወደው። በኋላ ግን የሕይወት ታሪኩን ሳጠና የልጄ ያህል ነው የወደድኩት። ልጄ ስትይ ወልደሻል እንዴ? አልወለድኩም (ሳቅ) ዘጠኝ መጽሐፎችን ግን ወልጄያለሁ፤ አዋልጃለሁ። በጋዜጠኝነት ሕይወትሽ አወዛጋቢና አከራካሪ አስተያየቶችን ስትሰጪ እና ስትጽፊ አስታውሳለሁ። አንቺ ራስሽን አወዛጋቢ እና አከራካሪ ጉዳዮችን እንደሚያነሳ ሰው ትቆጠሪያለሽ? እንደሱ ሳይሆን። የተማርኩት የሰለጠንኩት ዘርፍ 'ክሪቲካል ቲንኪንግ'(ጥልቅና ተንታኝ እሳቤ)ና ኢንቨስቲጌቲቭ ጆርናሊዝም [የምርመራ ዘገባ ጋዜጠኝነት] ነው። ስለዚህ በተማርኩት መሰረት ነው ለመስራት የሞከርኩት። ብዙ ሰው ኡኡ ይላል። እኔ ግን ያየሁትን የሰማሁትን እንደገና ደግሞ ሙያው እንደሚጠይቀው፣ ሁሉንም አካላት፣ ጉዳዩ ላይ ይመለከታቸዋል የሚባሉትን አካላት በሙሉ እድል በመስጠት 'ፌር' [ሚዛናዊ] የሆነ ነገር ነው የምሰራው። ግን ይናደዳሉ። እኛ ሀገር ደግሞ አንደኛ በሚዲያው ላይ ባለቤቶቹ ከጀርባው ስላሉ የሚተች ስራ ስሰራ አይፈለግም ነበር። እና አብዛኛው ጽሑፌ በጭቅጭቅ ነበር ቢሮ ውስጥ ራሱ የሚታተምልኝ። እንጂ ለመለየት፣ አከራካሪ ለመሆን በማለት አይደለም። ሴት በመሆኔ ነው እንጂ ይህንን ሀሳብ ወንድ ቢለው ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ኖ [በጭራሽ] ሴት ምናምን የሚል ሀሳብ አይመጣብኝም። ግን እኔ ለቆምኩለት ነገር አላፈገፍግም። እስከ ጥግ ድረስ ነው የምሄደው። አንተ እንቢ ብትለኝ ቀጥሎ ያለው ሰውዬ ጋር፣ ቀጥሎ ያለው እንቢ ቢለኝ የበላዩ ጋር እሄዳለሁ። አላቆምም፤ እልህ ስለሚይዘኝ አይ እንቢ ብለዋል ብዬ አላቆመውም። ምክንያቱም እኔ በጣም ዋጋ የምሰጠው ነገር ጊዜ ነው። ጊዜዬን ያጠፋሁበትን ጉዳይ ልትከለክለኝ አትችልም።ማንም እንዲያሳምነኝ መልካም ፈቃድ አለኝ። ስንዱ ይህ ጉዳይ በዚህ መልኩ ችግር ያመጣል። መስተካከል አለበት ካልከኝና ከታየኝ እሺ እላለሁ። ካልመሰለኝ ደግሞ እስከ ጥግ ነው አላቆምም። እና ስለምከራከርና ስለምጨቃጨቅም ነው ልዩ የምመስላቸው። ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ተወዳድረሽ ነበር አይደል? አዎ! ምርጫ 97 ነዋ ያውም ከባዱ ጊዜ። አሸነፍሽ ወይስ ተሸነፍሽ? እንዴ ቅንጅት አይደል እንዴ ጆከር ጥሎ የቦነሰው (በከፍተኛ ድምፅ ነው ያሸነፈው) በግልሽ ነበር የተወዳደርሽው? አዎ በግሌ ነው የተወዳደርኩት። በቂ የሕዝብ ድምጽ አግኝተሽየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትብትገቢ ኖሮ ምን ለማሳካት ነበር ሀሳብሽ የነበረው? ዋናው ዓላማዬ ለመወዳደር ከጻፍኩት የመወዳደሪያ ሀሳብ ውጪ በግል አንደኛ ፕሮቴክሽን [ጥበቃ]ፍለጋ ነው። ጋዜጠኛ ነበርኩ፤ እና በብዙ ጉዳዮች ስጋትና እየተጠራህ በፖሊስ መጠየቅ በጻፍክ ቁጥር የሚያስደነግጡህ ነገሮች ነበሩ፤ ከእነሱ ፕሮቴክሽን [ከለላ]ፍለጋ ነው። ሁለት ፋይሎችን እንደልብ ለማየት ነው። ብዙ ሐሜቶች ብዙ ጭቅጭቆች አሉ። ግን ፋይሎቹን ለማየት አቅም የለንም። መንግሥት ይከለክልሀል። ወይ ባለሀብት ይከለክልሀል። ብቻ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ስትሆን አቅም ይሰጥሀል እነዚህን ጉዳዮች፣ ፋይሎች ለማየት፣ ኢሚውኒቲ ራይት [ያለመከሰስ መብት] አለህ። ስለዚህ በርከት ያሉ ስራዎችን ለመስራት ነበር ሀሳቤ የነበረው። የትኞቹን ፋይሎች ነበር በወቅቱ ለማየት ትፈልጊ የነበረው? ለምሳሌ በከፍተኛ ደረጃ ብሔራዊ ባንክ ላይ ይካሄድ የነበረውን ዝርፊያ፣ ጉሙሩኩ፣ ባለስልጣናቱ። ብዙ ናቸው በጣም ብዙ። ዝም ብሎ አንድ የሰላሳ፣ የሰላሳ አራት ዓመት ልጅ ሚሊዮነር ሆነ ይሉሀል። እኛ ከተማው ላይ ተወልደን አድገን ሰባራ ሳንቲም የለንም። ከየት መጡ የምትላቸው አንድ ፍሬ ልጆች ግን ሚሊዮነር መሆናቸውን ትሰማለህ። እነዚህ ጥያቄዎችና ጉዳዮችን ለመመርመርና ለመከታተል አቅም ይፈልጋል። አቅም ስልህ ደግሞ በተለይ ፕሮቴክሽን [ከለላ]። የምልህ ሐሜቱ፣ ጭቅጭቁና ጥቆማው እኮ አለ። ግን ለማጣራት ስትሄድ ፋይሉን የሚሰጥህና የሚፈቅድልህ አካል የለም። ስለዚህ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ከሆንክ ግን እነዚህን [አካላት] ለመጠየቅ ማንም ሊከለክልህ አይችልም፤ መታወቂያው ራሱ በቂ ነው። ምክንያቱም የ100ሺህ ሕዝብ ድምጽ ነህ። ስንዱ ብቻ አይደለችም። ከስንዱ ጀርባ የ100 ሺህ መራጭ ሕዘብ ድምጽ ይዣለሁ ማለት ነው። የምትኖሪው በኪራይ ቤቶች ቤት አራት ኪሎ ስለነበር፣ የምትሰሪውም ለፓርቲው ልሳን አብዮታዊ ዲሞክራሲ ስለነበር፣ የኢህአዴግ ደጋፊ እንደነበርሽ በተደጋጋሚ ሲነሳ አስታውሳለሁ። በወቅቱ አንቺ የኢህአዴግ ደጋፊ አልነበርሽም? እኔ የምቃወመውም ሆነ የምደግፈው የግል የሆነ ነገር የለም። ካለው እንቅስቃሴ ውስጥ ልክ የሆነውን ልክ ነው እላለሁ። ልክ ያልሆነውን ልክ አይደለም እላለሁ። አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሲቀጥረኝ መጀመሪያ ዩኒቨርስቲ እየተማርኩ ቲያትር ትምህርት ክፍል ልግባ ብዬ ስከለከል ግቢ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ አደረግኩ። ለብቻዬ! ማለት ከመንግሥት ፈቃድ አውጥቼ፣ ሕጉን ተከትዬ ማለት ነው። እርሱን ሲያዩ እኛ ጋር ስራ ግቢ ሲሉኝ አላመነታሁም። ሄጄ ገባሁ፤ አብዮታዊ ዲሞክራሲ። ያኔ አብዮት ነው፤ ለውጥ ነው። ብዙዎቻችን ተስፋ አድርገናል ለውጡ ጥሩ ነገር ያመጣል ብለን። ግን አብዮታዊ ዲሞክራሲ ገብቼ እየሰራሁ ብዙ ልክ ያልሆኑ ነገሮች አየሁ። እናም ሶስት ዓመት ያልሞላ ሳንሰራ ነው አብረን የገባነው በሙሉየ ተባረርነው። ። ሁላችንም በአንድ ላይ ተጠራርገን ነው የወጣነው። እና ባጋጠመኝ ጉዳይ ብዙ ነገር የማየትና መደናገጥ ይዤ ነው የወጣሁት። ይህን እያየን፣ ይህን እየሰማን እንዴት እንዲህ ይሆናል? የሚል ስሜት ይፈጠርብሀል እና እሱኑ ነው ይዤ የቀጠልኩት። የሰልፉን ጉዳይ ካነሳሽው. . . ስለ አንቺ የሚያነሱ ሰዎች 'ስንዱ እኮ ብቻዋን ሰልፍ የወጣች ነች' ይላሉ። በወቅቱ ለብቻ ሰልፍ መውጣት፣ ያውም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ ከባድ አልነበረም? ንዴተኛ ስለሆንኩ እኮ ነው። ከባድ መሆን አለመሆኑን በምን ታውቃለህ? በወቅቱ ወጣት ነኝ፣ ንዴት ተሰምቶኛል። የምፈልገው የትምህርት ክፍል እንዳልገባ ተከልክያለሁ፣ ተበድያለሁ የሚል ስሜት አዳብሬያለሁ። ስለዚህ መጀመሪያ ጠየቅሁ። ከትምህርት ክፍሉ ጀምሬ ከዚያ ቋንቋዎች ጥናትን ጠየቅሁ። ከዚያ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንቱን ጠየቅሁ። ማንም መልስ የሚሰጥ የለም። ለነገሩ አብዮት ነው። ሁሉም ፈርቷል። ተደነጋግጧል። እና ሴኔቱ ፈርሷል። እንደነዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን መጨረሻ ላይ ሊፈታቸው የሚችለው ሴኔቱ ነበር። የዩኒቨርስቲው ሴኔት የለም። እና እኔ በንዴቴ እያንዳንዱን እርከን እየተከተልኩ ሰልፍ ጋር ደረስኩ። መፈክር ይዘሽ ነበር? ኦፍ ኮርስ! (በትክክል)፣ ዘፈን ሁሉ እዘፍን ነበር፤ ሰው ከተሰማራ እንደየስሜቱ የሚለውን እዘፍን ነበር። (ሳቅ) ምን ይል ነበር መፈክሩ? "የዩኒቨርስቲ መምህራን የተማሪዎች ፍላጎት ላይ መቀለድ ያቁሙ" የሚል ነበር። "ባለሰልጣናት ስልጣናችሁን እኛን ለመጨቆኛ አታውሉት" የሚልና ሌላም መፈክርም አሰማ ነበር። መጀመሪያ የት ትምህርት ክፍል ነበር የተመደብሽው? የአማርኛ ቋንቋ በኋላ ወደምትፈልጊው የቲያትር ትምህርት ክፍል መደቡሽ? ቀረ እንጂ! በወቅቱ ውሳኔ የሚሰጥ ጠፋ። ስለዚህ ዊዝድሮው [ለጊዜው ለማቋረጥ መልቀቂያ ጠይቄ] አድርጌ ወጣሁ። ከዚያ ጋዜጠኝነት ቀጠሩኝ፤ በዛው ጋዜጠኝነት ውስጥ ቀልጬ ቀረሁ። ግን አስተማሩኝ ጋዜጠኝነት። የት ተማርሽ ጋዜጠኝነት? በዩኒቨርስቲ ደረጃ ሳይሆን ከየቦታው አስተማሪ ያመጡና በየአንዳንዱ ጉዳይ ላይ የሶስት ወር፣ የስድስት ወር ስልጠና ይሰጡን ነበር። እንደዛ እያደረጉ ነው ያሰለጠኑን። ከበርካታ ታዋቂ ደራሲያን ጋር እንደማሳለፍሽ፣ የበርካታ ደራሲያንን ስራ እንደማንበብሽ የማን ስራ የበለጠ ይመስጥሻል? ሙሉጌታ ተስፋዬና ጋሽ ስብኀት። ስራቸው ውስጥ ደግነታቸው ቸርነታቸው ሁሉ ይታያል። እኔ መርዝ ከመድኀኒት እየቀላቀሉ የሚግቱንን ጸሐፊያን አልወድም፤ ችግር አለብኝ። እገሌ ከእገሌ ልልህ አልችልም። ግን ብዙ ጽሑፎች መርዝ ከመድኀኒት የቀላቀሉ ናቸው። የሆነ የፀብ ደቦን የሚሰብኩ ምናምን ናቸው። እነ አቦይና ሙሉጌታን ስታይ ግን እንደሱ አይደሉም። ማህበረሰቡን የሚወዱ ክብር ያላቸው ናቸው። ስለዚህ እነርሱን ነው የምወደው። ባሴ ሐብቴንም በጣም ነው የምወደው። ከኢትዮጵያ ከወጣሽ ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ? ስድስት ዓመት ሆነኝ። ከሀገር ቤት ከሕትመቱ ዓለም ከደራሲያኑ ውሎ የምትናፍቂው፣ አጣሁት የምትይው ነገር የለም ሩቅ እንደመኖርሽ? ሀሬን በጣም ነው የምናፍቀው፣ ከደራሲያኑም ከድርሰቱም ውጪ የሕዝቡ ፈገግታ ፣ ከነድህነቱ፣ ኢትዮጵያዊ ሲለምንህ እንኳ ፈገግ ብሎ ነው። የዓመት በዓል ጊዜ ውል የሚልህ ቄጠማው፣ እጣኑ አለ። እኔ ጭንቅላቴ የሚያስበው በአማርኛ ነው። አሁንም ብትጠይቀኝ ማንኛውንም ነገር ተነስቼ ማሰብ የምችለው ከአዲስ አበባ ነው። እና ሀገሬን እናፍቃለሁ እወዳለሁ። በእርግጥ የሀገር አንደኛ የለም። ሕይወትን ደግሞ በምርጫ ብቻ አትኖራትም። ግን ተገፍተህ እዚህ ጋር ትደርሳለህ። አላማርርም፤ ግን ሀገሬ ይናፍቀኛል። አሁን የነገርሽኝ የሀገር ናፍቆትሽን ነው። ከደራሲያኑ ዓለምስ ምን ይናፍቅሻል? አብሮ ማበድ፣ አብሮ መሳቅ መጫወት። አብሮ መፈላሰፍ። ጸሐፊ ስትሆን ከየትም አታመጣውም ኢኒስፓይሬሽን [መቀስቀስ] ይፈልጋል። መነሻህ ሁሌ አካባቢህ፣ ሕዝቡ፣ ኑሮህ ነው። ስለዚህ ሁሉም ይናፍቁኛል። እና ጓደኞቼም በጣም ይናፍቁኛል። አራት ኪሎ፣ ማለዳ ካፌ የኔ ካፌ ነበር የሚመስለኝ። ጠዋት ጠዋት አረፋፍጄ ሶስት ሰአት ተኩል ላይ ወጥቼ እዚያ ስቀመጥ ሁሉም ይመጣሉ።ጋዜጠኛው፣ ሰዓሊው፣ ደራሲው። አራት ኪሎ ማዕከል ነው። የአዲስ አበባ እርግብግቢቱ ማለት ነው። ስለዚህ በጣም ነው የምናፍቀው አራት ኪሎን። በዛ ላይ ሐያ ዓመት የኖርኩበት ነው። ብዙ ደራሲ፣ ጋዜጠኛ ቤቴ ይመጣል። ለመጨረሻ ጊዜ የአማርኛ ድርሰት ያነበብሽው የማንን ነው? እንዴ አሁንም አነባለሁ። አሁን ለምሳሌ የአለማየሁ ዋሴ እሸቴ መጽሐፍ፣ መርገምት አጠገቤ አለ። ከዚህ በፊት አንድ ስራቸውን አንብቤያለሁ። አነባለሁ። በተለይ ወጥ ስራዎች ከሆኑ።
48762110
https://www.bbc.com/amharic/48762110
ሳፋሪኮም የተጠቃሚዎችን መረጃ በማውጣት ተከሰሰ
የኬንያው ግዙፍ ቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ሆን ብሎ የግል መረጃን የመጠበቅ መብት በመተላለፍ የ 11.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን መረጃ በማውጣት ተከሰሰ።
ኩባንያው የስፖርት ውርርድ መረጃዬን እንዲሁም የግለ ታሪኬን አደባባይ አስጥቶብኛል ያለ አንድ ተጠቃሚ ነው ሳፋሪኮምን ለመክሰስ የመጀመሪያውን እርምጃ የወሰደው። ግለሰቡ የበርካታ ተጠቃሚዎችን ፊርማ በማሰባሰብ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አምርቷል። ኩባንያው የግል መረጃዬን ሆን ብሎ አውጥቶብኛል ሲልም የአስር ሚሊዮን ዶላር ካሳ ጠይቋል። •ኢትዮጵያ እና ኤርትራ - ከሰኔ እስከ ሰኔ •የሰኔ 16ቱ ጥቃትና ብዙም ያልተነገረላቸው ክስተቶች • "እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" መሠረት ማኒ ሳፋሪኮም አባከነ የተባለው መረጃ ሙሉ ስም፣ የሞባይል ቁጥር፣ ፆታ፣ እድሜ፣ የመታወቂያ ቁጥር፣ የፓስፖርት ቁጥር እንዲሁም ምን ያህል ጊዜ የስፖርት ቁማር ላይ እንዳሳለፉ የሚያሳይ እንደሆነ ተገልጿል። እስካሁን ሳፋሪኮም ስለ ጉዳዩ ያለው ነገር የለም።
news-55717280
https://www.bbc.com/amharic/news-55717280
ህወሓት ፡ ሽምቅ ተዋጊ፣ የአገር መሪ፣ የክልል አስተዳዳሪ በመጨረሻም . . .
ሦስት አስርት ዓመታት ለሚደርስ ጊዜ በአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ዋነኛው ኃይል ሆኖ የቆየው ህወሓት ባለፈው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ኃይልን መሠረት ባደረገ የአመጻ ተግባር ላይ በመሣተፉ በብሔራዊ ምርጫ ሕጋዊ ሰውነቱን አጥቶ እንዲሰረዝ ተደርጓል።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ኃያል የነበረውና በእድሜ ጎምቱ ከሚባሉት ፓርቲዎች መካከል አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ህወሓት ከሽምቅ ተዋጊነት፣ የአገር መሪነት፣ ከዚያም ወደ ክልል አስተዳዳሪነት በመጨረሻም ሕጋዊ ዕውቅናውን አጥቷል። ታዲያ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ከየት ተነስቶ አሁን ካለበት ደረሰ? እነሆ በአጭሩ . . . ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የንጉሡ አስተዳደር ወድቆ ወታደራዊው መንግሥት ወደሥልጣን መውጣቱን ተከትሎ ነበር የካቲት 11/1967 ዓ.ም የትጥቅ ትግል መጀመሩን ያስታወቀው። ለህወሓት የትጥቅ ትግል መነሻ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያቋቋሙት ማገብት (ማህበረ ገስገስቲ ብሔረ ትግራይ) የተባለው መደበኛ ያልሆነ ቡድን ነበር። ማገብት የህወሐት ጥንስስ የትግራይ ተማሪዎች ስብስብ የነበረው ማገብት ከ45 ዓመታት በላይ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና ለነበረው ለህወሓት መመስረት ዋነኛው ትንስስ ነበር። ማገብት በስምንት አባላት ተመሰረተ ሲሆን እነዚሁ መስራቾቹም ኋላ ላይ ለህወሓት እንቅስቃሴ መመስረት ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ስምነቱ ግለሰቦች በሪሁ በርሀ (አረጋዊ በርሄ ዶ/ር)፣ ፋንታሁን ዘርአጽዮን (ግደይ ዘርአጽዮን)፣ ሙሉጌታ ሐጐስ፣ አምባዬ መስፍን (ስዩም መስፍን)፣ አመሃ ፀሃዬ (አባይ ፀሃዬ)፣ ዕቁባዝጊ በየነ፣ አለምሰገድ መንገሻ እና ዘርኡ ገሰሰ (አግአዚ) ናቸው። ከጅማሬው ደርግን የተቃወመው ማገብት በትግራይ ሕዝብ ላይ ደረሰ ያለውን ጭቆና ለማስወገድ የትጥቅ ትግል ማድረግና መሪ ድርጅት እንደሚያስፈልግ ወሰነ፡፡ ለዚህም የተወሰኑት አባላቱ የኤርትራ አማጺ ቡድኖች ከነበሩት ከጀብሃና ከሕዝባዊ ግንባር ጋር ግንኙነት ለመመስረት ወደ ኤርትራ ሲሄዱ ሌሎቹ ደግሞ ከተማ ውስጥ ሆነው ሕዝብ ማደራጀት ጀመሩ። ይህንን ተከትሎም አስራ አንድ የቡድኑ አባላት የትጥቅ ትግሉን ለመጀመር ወደ ጫካ ሲወጡ የመረጡት ደደቢት የተባለውን በረሀ ነበር። የህወሓት አላማ ቡድኑ የትጥቅት ትግሉ በጀመረበት ወቅት ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠልና 'የሪፐብሊክ' የመመስረት ጉዳይ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም ይህ ሐሳብ ከአንድ ዓመት በላይ እንዳልቆየ መስራቾቹ ይናገራሉ። በ1968 ዓ.ም በተካሄደው የመጀመሪያው የድርጅቱ ጉባኤ 'ነጻ ትግራይ' የሚለው አጀንዳ በአብዛኛው አባል ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ውድቅ ተደረገ። ከዚያም የድርጅቱ አላማ የመደብ ትግል በማድረግ ለጭቁን ሕዝቦችን 'የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት' እንደሚታገል ቢገልጽም ህወሐትን የሚቃወሙ ድርጅቶት ግን ቡድኑ የትግራይን ሕዝብ ለመነጠል እንደተቋቋመ በመግለጽ ሲተቹት ቆይተዋል። ክፍፍል በህወሓት ውስጥ ህወሓት ከተመሰረተ ከአንድ ዓመት በኋላ በ1968 ዓ.ም በድርጅቱ ውስጥ ባሉ አመራሮች መካከል መከፋፈል አጋጥሞት የነበረ ሲሆን ይህም 'ሕንፍሽፍሽ' በመባል ይታወቃል። በዚህ ወቅትም በአመራሮቹ መካከል የነበረውን መከፋፈል ለመፍታት የወሰደው እርምጃም ፀረ-ዲሞክራሲያዊ እንደነበር አንዳንድ ነባር ታጋዮች ያስታውሳሉ። ከዚህም በኋላ በ1977 ዓ.ም በአመራር አባላቱ መካከል በድጋሚ ልዩነት ተፈጥሮ ከመስራቾቹ መካከል ከነበሩት ውስጥ አረጋዊ በርሀ (ዶ/ር) እና ግደይ ዘርአጽዮን የተባሉት አባላቱ ድርጅቱን ጥለው እንዲወጡ ተደርገዋል። በወቅቱ የተደረገውን ግምገማና የተግባራዊ እንዲደረግ የቀረበውን አዲስ ወታደራዊ ዕቅድ ብዙዎቹ የድርጅቱ አባላት ቢደግፉትም "በጊዜው የተመሠረተው ማርክሲስት ሌኒኒስት ሊግ ትግራይ (ማሌሊት) የተባለ የፖለቲካ ክንፍ ግን ድርጅቱን በጠቃላይ እንቀየረው" የሚል ሐሳብ እንደነበረው የህወሓት ቀደምት አባል የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት በመጽሐፋቸው አስፍረዋል። የህወሓት ኮሚኒስታዊ ባህሪ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃለት ቢመስልም የድርጅቱ ውስጣዊ ባህሪና አደረጃጀት ሳይቀየር 'አብዮታዊ ዲሞክራሲ' የሚል መልክ በመያዝ እስከ መጨረሻው መዝለቁ ይነገራል። የሩስያና የቻይና አብዮቶች አድናቂ የነበረው ህወሓት እንደ መርህ ግን ብዙም የማትታወቀው በምሥራቅ አውሮፓ ውስጥ ያለችውን የአልባንያን ኮሚኒዝም ይከተል ነበር። ህወሓት በአገሪቱ የሥልጣን እርከን ላይ ጉልህ ሚና በነበረው ወቅትና ከኤርትራ ጋር የተካሄደው የድንበር ጦርነት ካበቃ በኋላ በ1993 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ በአመራሩ ውስጥ ከፍተኛ ክፍፍል ገጠመው። በዚህ የክፍፍል ወቅት በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሚመራው ቡድን የበላይነቱን ይዞ በህወሓት ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነትና ተጽእኖ የመፍጠር አቅም የነበራቸውን ከፍተኛ የቡድኑን አመራር አባላት ከድርጅቱ እንዲባረሩ ተደረገ። በዚህም ሳቢያ የተወሰኑትም በውሙስና ተከሰው ለእስር ተዳርገው ነበር። ከዚህም በኋላ በአቶ መለስ ዜናዊ የሚመራው አንጃ ድርጅታዊና መንግሥታዊውን ስልጣን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የበላይነት ለብቻው ለመያዝ ቻለ። የህወሓት ግጭት አፈታት ህወሓት ለ17 ዓመታት ባካሄደው የትጥቅ ትግል ወቅት ከፍልሚያ ውስጥ ገብቶ የነበረው ከወታደራዊው መንግሥት ጋር ብቻ አልነበረም። ቡድኑ የትጥቅ ትግል በሚያደርግበት ጊዜ በተመሳሳይ ወታደራዊው መንግሥትን ተቃውመው ከወጡት ከኢዲዩ፣ ከጀበሃ፣ ከኢህአፓና ከሌሎችም ቡድኖች ጋር በወቅቱ የነበረውን ፖለቲካዊ ልዩነት በኃይል ነበር የተፈታው። ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ በትግራይ ሕዝብ ስም ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ስብስቦች መካከል አንዱ የነበረው የግንባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (ግገሐት) መሪዎቹን በተንኮል በመግደል ተጋዮቹን ድራሻቸው እንዳጠፋ ይነገራል። ነገር ግን ከደርግ ጋር የሚደረገው ጦርነት እየሰፋ ከትግራይ ባሻገር ወደ ሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ሲሸጋገር በየአካባቢዎቹ ያሉትን ሕዝቦች ይወክላሉ የተባሉ ድርጅቶችን ማቀፍ እንዲሁም ሊወክሉ ይችላሉ በሚል እንዲቋቋሙ ህወሓት ጉልህ ሚና ተጫውቷል። ይህንንም ተከትሎ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህዴን)፣ ከኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ጋር በመጣመር ኢሕአዴግ የተባለውን ግንባር ፈጠረ። በህወሓት የበላይነት ይመራ ነበር የሚባለው ኢሕአዴግ የደርግ መንግሥትን ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ የሽግግር መንግሥት በማቋቋም በ1987 ዓ.ም አዲስ ሕገ መንግሥት ጸድቆ ምንም እንኳን ተግባራዊነቱ ላይ የተላዩ ጥያቄዎችና ትችቶች ቢነሱበትም ለአገሪቱ ብሔሮች እውቅናን ሰጥቷል። በሌላ በኩል ደግሞ ሥርዓቱ የኢትዮጵያን አገራዊ አንድነት ችላ ያለ ነው እየተባለ ሲወቀስ ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግን በግንባሩ ውስጥ ለዓመታት የቆየው ቅሬታ ስር እየሰደደና እየጎላ መጣ። የኢሕአዴግ ግንባር አባላት በድርጅቱና በአገሪቱ ላይ የለውጥ እርምጃዎች መውሰድ ሲጀመርሩና የግንባሩ መለያ የነበረውን 'አብዮታዊ ዲሞክራሲን' ሲተዉት ለህወሓት የሚዋጥ ጉዳይ አልነበረም የሚካሄዱት ለውጦች እየበረቱ ሲሂዱ የህወሓት ቅሬታም እየጠነከረ ሄደ። በመጨረሻም የአራት ብሔራዊ ድርጅቶች ጥምረት የነበረው ኢህአዴግ ከስሞ የብልጽግና ፓርቲ ሲተካው ህወሓት በአዲሱ ስብስብ ውስጥ ላለመግባት ከመወሰኑ ባሻገር "ውህደቱ ሕጋዊ አደለም'' በማለት ተቃውሞውን አስምቶ ነበር። ስኬትና ትችት የብሔር ጭቆና በኢትዮጵያ ውስጥ ነበረ ብለው በሚያምኑ ወገኖች በኩል ከዚህ ቀደም ከነበረው ሁኔታ በተለየ ህወሓት ወደ ስልጣን ከወጣ በኋላ በተዋቀረው ፌደራሊዝምና ሕገ መንግሥት ውስጥ ተገቢውን እውቅና እንዲያገኙ አድርጓል ብለው የሚቀበሉት አሉ። ከዚህ በተጨማሪም በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ማኅበረሰቦች ምንም እንኳን በወረቀት ላይ እውቅና ቢያገኙም በተግባር ላይ በመተርጎሙ በኩል የጎላ ችግር እንደነበረም ይተቻሉ። ህወሓት የደርግ መንግሥትን በመጣል የአገሪቱን ሥልጣን ተቆጣጥሮ ለሦስት አስርት ዓመታት መቆየቱና በሥልጣን ዘመኑ ውስጥ የተፈጸሙ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ደግሞ ሌሎች የሚያነሱት አሉታዊ ገጽታው ናቸው። ከኤርትራ ነጻነትና ለኢትዮጵያ የወደብ ባለቤትነት መብት ቸልተኛ ነበር ብለው የሚወቅሱት ተቃዋሚዎችም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። ህወሓት በበላይነት በሚመራው መንግሥት የመጨረሻ አስር ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት መመዝገቡ ዓለም አቀፍ ተቋማት በተደጋጋሚ ቢመሰክሩም እየተንሰራፋ የመጣው ሙስናና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የተገኘው ውጤት ላይ አሉታዊ አሻራን አሳርፈውበታል። የህወሓት መሪዎች ህወሓት እንደተመሰረት ለአንድ ዓመት ያህል ከመስራቾቹ አንዱ የነበረው ገሰሰ አየለ (ስሁል) በጊዜያዊነት ከመራው በኋላ አቶ ስብሐት ነጋ ከ1971 ዓ.ም እስከ 1981 ዓ.ም ድረስ የድርጅቱ ሊቀ መንበር በመሆን መርተውታል። ቀጥሎም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ በሞት እስከ ተለዩበት ጊዜ ድረስ ከ20 ዓመታት በላይ የህወሓት ሊቀ መንበር በመሆን አገልግለዋል። ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎም በ2004 ዓ.ም አቶ አባይ ወልዱ የድርጀቱን ሊቀመንበርነት ቢረከቡም ብዙም ሳይቆዩ ድርጅቱን በተገቢው ሁኔታ መምራት አልቻሉም ተብለው እንዲነሱ ተደረገ። በመጨረሻም በደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) መመራት የጀመረው ህወሓት በአገር አቀፍ ደረጃ የነበረውን ተሰሚነት አጥቶ በትግራይ ክልል ውስጥ ብቻ ተወስኖ ለመቆየት ከተገደደ በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ከባድ ጉዳት ደርሶባታል። የህወሓት ፈተና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከተመራው ለውጥ በኋላ በማዕከላዊው መንግሥት ውስጥ የነበረውን ጉልህ ሚና ያጣው ህወሓት ከፍተኛ አመራሮቹን ይዞ በገዢ ፓርቲነት ወደ ሚያስተዳድረው ትግራይ ካቀና በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የነበረው ግንኙነት ከመሻከር አልፎ ወደ ፍጥጫ መሸጋገሩ ይታወሳል። በተለይ በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት ይካሄዳል ተብሎ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው ምርጫ ወደ ቀጣይ ዓመት እንዲሸጋገር ሲደረግ ህወሓት ተቃውሞውን በማሰማት በፌደራል መንግሥቱ ሕገ ወጥ የተባለውን የተናጠል ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ መወሰኑ አለመግባባቱን የበለጠ አባባሰው። ምርጫው ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ ተካሂዶ ህወሓት መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ ማሸነፉ ተገልጾ አዲስ ክልላዊ መስተዳደር መመስረት ቢችልም፤ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጦ ያገኝ የነበረው በጀትም ከክልሉ ይልቅ ለታችኛው የአስተዳደር አካል እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል። ህወሓት ባለፉት ሁለት ዓመታት የክልሉን ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በስፋት በማሰልጠን የተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶችን በተደጋጋሚ ሲያሳይ በቆበት ወቅት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ከዛሬ ነገ ይፈነዳል በሚባል ፍጥጫ ውስጥ ቆይቶ ነበር። በመጨረሻም የህወሓት ኃይሎች በክልሉ ውስጥ ለዓመታት በየቆው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት በሦስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከመቀመጫው መቀለ እንዲባረር እንዳደረገው ይታወሳል። በዚህም ሳቢያ ኢትዮጵያን ለ27 ዓመታት እንዲሁም ላለፉት ሦስት ዓመታት ደግሞ የትግራይ ክልልን በበላይነት የመራው ህወሓት በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ከባድ ጉዳት ደርሶበታል። የቡድኑ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች በተለያዩ ከፍተኛ ወንጀሎች ተጠርጥረው የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው ሁለት ወራት ተቆጥረዋል። ባለፉት ሳምንታትም በርካታ የህወሓት የአሁንና የቀድሞ አመራሮች በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውና ሌሎች ደግሞ መገደላቸው በአገሪቱ ሠራዊት መገለጹ ይታወሳል።
news-49080512
https://www.bbc.com/amharic/news-49080512
"በኤችአይቪ የምሞት መስሎኝ ልጄን ለጉዲፈቻ ሰጠሁ"
"2007 ዓ. ም አካባቢ ይመስለኛል. . . ልደታ አካባቢአንድ ፈረንጅ ወንድ ልጅ አቅፎ አየሁ። ፈረንጁ የቤተሰብ ፎቶ እንጨት ላይ ይለጥፋል. . . ስልክ እየደወለምከሰዎች ጋር ያወራል. . . ያቀፈው ልጅ ቀላ ያለ ነው. . . ልጁን ትኩር ብዬ ሳየው ደነገጥኩ። ልጁ ልጄን ይመሰላል!
ሥራቸው ቆሜ ማልቀስ ጀመርኩ። ፈረንጁም ልጁም አማርኛ አይችሉም። ዝም ብዬ ሳለቅስ ግራ ሳይገባቸው አልቀረም። 'ዋት ኢት ኢዝ. . . ዋት ኢት ኢዝ' ምናምን አለኝ። ምን ብዬ ልመልስለት? ግራ ገባኝ። በቆምኩበት ማልቀሴን ቀጠልኩ። በአካባቢው እያለፈ የነበረ ሰውዬ መጣና 'ምንድን ነው?' አለኝ። እየተጣደፍኩ 'ፈረንጁ ያቀፈው ልጅ ልጄን ይመስላል፤ በእናትህ ከየት እንደመጡ ጠይቅልኝ' አልኩት። በእንግሊዘኛ አወሩና። ፈረንጁ የልጁን [የጉዲፈቻ ልጅ] ቤተሰቦች ለመፈለግ ከእንግሊዝ እንደመጣ ነገረኝ። • ከ43 ዓመት በኋላ የተገናኙት ኢትዮጵያዊ እናትና ስዊድናዊ ልጅ ማልቀስ ማቆም አልቻልኩም. . . እንደገና ደግሞ መሳቅ ጀመርኩ. . . እንደ ሞኝ መንገድ ላይ ቆሜ ሰዎቹን ማየት ቀጠልኩ። አለቅሳለሁ. . . እስቃለሁ. . . አለቅሳለሁ. . . መልሼ ደግሞ እስቃለሁ። ልጄን ሳፈላልግ የገጠመኝ ይሄ ብቻ አይደለም። የቱን ነግሬሽ የቱን እተወዋለሁ። ልጄ ይሆን? ብዬ ድንግጥ ያልኩት ብዙ ጊዜ ነው። ልደታ የገጠመኝን ግን መቼም መቼም አልረሳውም!" "ልጄን ለምኜም ቢሆን አሳድገዋለሁ" በላይነሽ (ለዚህ ጽሁፍ ሲባል ስሟ ተቀይሯል) ልጃቸውን ለጉዲፈቻ ከሰጡ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እናቶች አንዷ ናት። ልጇ በማደጎ ወደ ካናዳ ከሄደ በኋላ አድራሻው ጠፍቶባት ለዓመታት በፍለጋ ባዝናለች። መንገድ ላይ ከነጭ ጋር ያየችውን ጥቁር ልጅ 'የእኔ ይሆን?' ብላ መደንገጥ ካሳለፈችው መከራ ቀለል ያለው ነው። ጉልበቷ ከድቷት መንገድ ላይ ተዝለፍልፋ የወደቀችባቸውን ቀናት ቆጥራ አትጨርስም። በሯን ዘግታ ያነባችውን በእሷና በጠባብ ቤቷ መካከል መተው ትመርጣለች። • በባርነት ከመሸጥ የተረፉት 64 ኢትዮጵያዊያን እናትና አባቷ ከሞቱ ቆይተዋል። ክፍለ አገር የምትኖር አንድ እህት አለቻት። ግን በላይነሽ የት እንደምትኖር አታውቅም፤ አይጠያየቁምም። የቅርብ ዘመድ፣ ጓደኛም ከጎኗ የለም። የመጀመሪያ ልጇን ከአንድ ወታደር የወለደችው ከ20 ዓመት በፊት ነበር። ብዙም ሳይቆይ ከወታደሩ ጋር ተለያዩ። ልጁም ለሩቅ ዘመድ ተሰጠ። ያኔ በአስራዎቹ መጨረሻ ላይ የነበረችው በላይነሽ ከሌላ ወታደር ጋር ትዳር መስርታ ካምፕ ውስጥ መኖር ጀመረች። ሁለተኛ ልጇን አርግዛ በ1993 ዓ. ም ባለቤቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። 'ጆሮ ለባለቤቱ . . . ' እንዲሉ ባለቤቷ በምን ምክንያት እንደሞተ አቃውቅም ነበር። "ባለቤቴ በሽታው [ኤችአይቪ] እንዳለበት አላውቅም ነበር። ውትድርና ሄዶ ቆስሎ ነበር የመጣው። እንደዚህ አይነት ነገር መኖሩን ግን በጭራሽ አላውቅም ነበር። ሁሉንም ነገር ያወኩት ከወለድኩ በኋላ ነው። ለካ አንድ ጓደኛው ያውቅ ነበር። 'ልጁን አስወጪው' አለኝ። እንዴ ልጄን ለምን አስወርዳለሁ? ልጄ የሙት ልጅ ነው። ባሌም ልጁን ሳያይ ነው የሞተው። ልጄን ለምኜም ቢሆን አሳድገዋለሁ አልኩት።" • የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ 1994 ዓ. ም ሚያዝያ ላይ ልጇን ወለደች። ወዲያው ትኖርበት ከነበረው የወታደር ካምፕ እንድትወጣ ተደረገ። መጠለያ አልነበራትምና ቀበሌ ሄዳ ማልቀስ ጀመረች። ከብዙ ሄደት በኋላ አሁን የምትኖርበት አንድ ክፍል ቤት ተሰጣት። የባሏን የጡረታ 100 ብር እየተቀበለች ኑሮን እየተንገታገተች ጀመረች። ሀብቷ ልጇ ነበርና እሱው ላይ አተኮረች። አንድ ዓመት ሲሞላው ልደቱን አከበረችለት። አብረው ፎቶ ተነሱ. . . ደስ አላት። ከልደቱ በኋላ ያማት ጀመር። ቀስ በቀስ ህመሙ ጸንቶባት መንቀሳቀስ ተሳናት። "ሆስፒታል አልጋ ያዝኩ። በጉልኮስ ነበርኩ። ስታመም አንድም ሰው አጠገቤ አልነበረም።" "ያ ጠባሳ ይኖር ይሆን?" ሆስፒታል ተኝታ ልጇ አጠገቧ ድክ ድክ ይል ነበር። የሚጠብቀው ሰው ስላልነበረ አሁንም አሁንም ይወድቅ ነበር። ልጇን ከወደቀበት የማንሳት አቅም አልነበራትም እንጂ። አንድ ቀን ወድቆ ክፉኛ ተጎዳ። ያኔ ግንባሩ ቆስሎ እንደነበር ታስታውሳለች። ቁስሉ ዛሬ ከ18 ዓመታት በኋላ ግንባሩ ላይ ይኑር ይጥፋ አታውቅም። ያ ጠባሳ ይኖር ይሆን?. . . ታስባለች። የልጇ ምልክት፣ የቀደመ ሕይወቱ ማስታወሻ ጠባሳው ይሆናል. . . ሰው ቤት ያደገው የመጀመሪያ ልጇን አዘውትሮ የማየት እድል አልነበራትም። አንድ ጊዜ ብቻ ታናሽ ወንድሙ የአምስት ወር ልጅ ሳለ አይቶት ነበር። ህመሙ በላይነሽን ከእለት ወደ እለት እያዳከማት ሄደ። "በቃ አትተርፊም ተባልኩ። እንደምሞት ሲነግሩኝ ልጄን ማን ያሳድገዋል? ብዬ ፈራሁ። ልጅሽን ለጉዲፈቻ ስጪ ሲሉኝ ባንገራግርም በወቅቱ ተስፋ ቆርጬ ነበር። ከጉዲፈቻ ውጪ አማራጭ እንደሌለኝ አሰብኩ። ሞቼ እስክቀበር ድረስ እንኳን ልጄን የሚይዝልኝ ሰው ስለሌለኝ በማደጎ ለመስጠት ወሰንኩ።" • ዓለም አቀፍ ጉዲፈቻን ማገድ አዋጭ ነው? አዲስ አባበ ውስጥ ከሚገኝ የጉዲፈቻ ድርጅት ጋር ተነጋገረች። እዚያው ሆስፒታል ሆና ልጇን ወሰዱት። ልጇ ወደ ድርጅቱ ከተወሰደ በኋላ የእናት አንጀቷ አልችል አላት። እየተንገዳገደች ከሆስፒታል አልጋ፣ ወርዳ ታክሲ ተኮናትራ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልጇን በድርጅቱ ጊቢ ውስጥ አየችው። ተሰናብታው ሞቷን ወደምትጠባበቅበት አልጋ ተመለሰች። "አልቅሼ አልቅሼ አልቅሼ ተመለስኩ፤ ምን ላድርግ? ተስፋ ቆርጬ ነው እንጂ ከልጄ መለየትስ አልፈለኩም ነበር።" 1996 ዓ. ም ላይ ሳትሰማ ሳታይ ካናዳዊያን ጥንዶች የአንድ ዓመት ከስምንት ወልጇን በማደጎ ወሰዱት። "አንቺ ልትሞቺ ነው፤ ለምን የልጅሽን እድል ትዘጊያለሽ?" ሆስፒታል ሳለች ህመም፣ ሀዘን፣ ሰው ማጣት እንደተደራረበባት ታስታውሳለች። አንድ ሴት 'የአገሬ ልጅ ነሽ' ብላ ምግብ የምትሠራላትና የምታስታምማት ሠራተኛ ቀጥራላት ነበር። በመጠኑ ማገገም ጀመረች። ያኔም ዛሬም ልጇን በጉዲፈቻ ለመስጠት የወሰነችበትን ቅጽበት ደጋግማ ታስባለች። ልክ ነበርኩ? ስህተት ሠርቼ ይሆን? መልስ ያላገኙ ጥያቄዎች። ልጇን ለመስጠት ስታቅማማ 'አንቺ ልትሞቺ ነው፤ አትተርፊም፤ ለምን የልጅሽን እድል ትዘጊያለሽ?' ተብላለች። የድርጅቱ ሠራተኞች ሊያግባቡዋት፣ ሊያሳምኗትም ይሞክሩ ነበር። "ልጄን ለማደጎ ሊሰጡ ሲሉ በጣም ፈርቼ ነበር። ግን ምን ማድረግ እችላለሁ? እኔ ከሞትኩ ማን ያሳድገዋል? ሀኪሞቹም ሳይቀሩ አትተርፊም አሉኝ። መቆም አልችል፣ የምሄደው ተደግፌ. . . ልጄ ከሄደ በኋላ የቲቢ መድሀኒት መውሰድ ጀመርኩ። መድሀኒቱን ስጨርስ ፀረ ኤችአይቪ መድሀኒት መውሰድ ጀመርኩ። ከዚያ ቀስ በቀስ ጤናዬ እየተሻሻለ መጣ። በፍጹም ባልጠበቅኩት ሁኔታ ሳልሞት ቀረሁ። በስተመጨረሻም ከሆስፒታል ወጥቼ ቤት ገባሁ።" ኦና ቤት ተቀበላት። እንቅልፍ አጣች። አልጋዋን ስትዳብስ ልጇ አጠገቧ አለመኖሩን መቀበል አልቻለችም። 'ከሞት ተርፌ ልጄን እፈልጋለሁ' ብላ አስባ አታውቅም። • የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቀረቡ የፀረ ኤችአይቪ መድሀኒት እየወሰደች ብታገግምም አዕምሯዋ አልረጋጋ አለ። ለሁለት ዓመት ቀን ከሌሊት አነባች። "በጣም የተሰማኝ ከሀኪም ቤት ወጥቼ ቤቴ ስገባ ነው። እንዲህ ተሽሎኝ ቤቴ ልገባ ነው ልጄን የሰጠሁት? ጡት እንዳታጠቢው [ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ እናቶች እንዳያጠቡ ይመከራሉ] ስለተባለ አላጠባሁትም። ያደገው በወተትና በአጥሚት መሆኑን ሳስብ በጣም አዝንለታለሁ።" ልጇን ለጉዲፈቻ ወደ ሰጠው ድርጅት ሄዳ 'የልጄን አድራሻ ስጡኝ' ብላ ጠየቀች። ልጇ ሲወስዱ ለእሷ 'አሳቢ' የመሰሏት ሰዎች ተለውጠው እንደጠበቋት ትናገራለች። የድርጅቱ ሠራተኞች አንዳቸው ወደ ሌላቸው ይመሯት ጀመር። በሄደች ቁጥር በተለያየ መንገድ እምቢታቸውን ይገልጹላታል። 'ለምን አተይውም? 18 ዓመት ሲሞላው ይመጣል' 'ልጅሽን ፈቅደሽ ከሰጠሽ በኋላ አሁን አምጡ ማለት ምን ይባላል?' 'በቃ አሳልፈሽ ሰጥተሽዋል፤ አሁን ሌላ ቤተሰብ አለው!' ብዙ የሚያሳምሙ መልሶች ተሰጧት። • ከማደጎ ልጅነት ወደ እውቅ ገጣሚና የማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ሃላፊነት • ኮሎኔል መንግሥቱ ለህፃናት አምባ ልጆች ደብዳቤ ላኩ "አንዷ የድርጅቱ ሠራተኛ ስደውልላት 'በሽታሽ ነው የሚያቃዥሽ?' ያለችኝን አልረሳውም። በየቀኑ ያስለቅሱኝ ነበር። ይሰድቡኝ ነበር። ካናዳ ያለው ኤጀንሲ ተዘግቷል ብለውኝ አልቅሼ፣ አዙሮኝ ወድቄያለሁ። ለዓመታት ከተመላለስኩ በኋላ ተስፋ ቆርጬ ቀረሁ።" በወቅቱ ያገኘቻት አንድ ነርስ ልጇን ለማደጎ በመስጠቷ እንዳትፀፀት ትመክራት እንደነበር ታስታውሳለች። ልጇ ውጪ አገር በመሄዱ የተሻለ ትምህርት ሊያገኝ፣ የተሻለ ሕይወት ሊገጥመው እንደሚችልም ልታሳያት ትሞክር ነበር። "እሷም እኔም ልጆቻችንን እየፈለግን ነበር" በላይነሽ ፍርድ ቤት ውስጥ የፅዳት ሠራተኛ ናት። ብቸኛ ብትሆንም የፀረ ኤችአይቪ መድሀኒት እየወሰደች፣ ራሷን እየተንከባከበች ኑሮ ቀጠለች። ዘወትር የሚያቃጭለው የልጄ የት ደረሰ? ጥያቄ እረፍት ይነሳታል። ልጄ 'ለምን ለሰው ሰጠችኝ?' ብሎ ይጠላኝ ይሆን ብላ ትሰጋለች። አንዳዴም 'እነሱስ ወይ እስከምሞት ወይ እስከምተርፍ ድረስ ልጄን ቢይዙልኝ ኖሮ ምናለ?' ትላለች። ልጇን በሰጠው ድርጅት ተስፋ ስትቆርጥ ወደ ካናዳ ኤምባሲ መመላለስ ጀመረች። 'ውጪ ጉዳይ ጠይቂ' ተባለች። ውጪ ጉዳይ 'እስኪ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሂጂ' አሏት። የሦስቱ ተቋሞች ባለ ጉዳይ መሆን እንዳሰበችው አልጠቀማትም። አንዱ ከሌላው 'ደብዳቤ አምጪ' ሲላት. . . ሌላው 'የሚመለከተውን አካል ጠይቂ'. . . "ሁሉም ሲያመናጭቁኝና ሲያስለቅሱኝ ተውኳቸው። መመላለሱ ሰለቸኝ፤ ደከመኝ። ፀሀይ ሲመታኝ ያዞረኛል፤ መንገድ ስሄድ እግሬን ያመኛል። አንድ ቀን በጣም ተሰማኝና ብቻዬን መንገድ ላይ ቁጭ ብዬ አለቀስኩ።" ውጪ አገር የሄዱ ልጆች ወላጆቻቸውን ለማግኘት እንዳይጓጉ ለቤተሰቦቻቸው አድራሻ አይሰጥም ብትባልም ልጇ ካናዳ ካሉት አሳዳጊዎቹ ጋር የተነሳው ፎቶግራፍ 'ሪፖርት' ተብሎ እንደቀረበላት ትናገራለች። ከዚያ በዘለለ ስለ ልጇ አታውቅም። ከሁለት ዓመት በፊት ፍርድ ቤት መደበኛ ሥራዋ ላይ ሳለች ከአንድ ሴት ጋር ጨዋታ ጀመሩ። ሴቲቷ እንደ በላይነሽ ሁሉ ልጇ በጉዲፈቻ ካናዳ ከሄደ በኋላ ልታገኘው እንዳልቻለች ነገረቻት። የበላይነሽና የሴቲቷ ልጅ ለማደጎ የሰጠው ድርጅት ተመሳሳይ ነው። ልጁ የተሰጠው እናትና አባቱ ሞተዋል ተብሎ ነበር። እናቱ ልጁን መፈለግ ስትጀምር 'ቤተሰቡ ሞቷል ብለናል ስለዚህ ልናገናኝሽ አንችልም' የሚል መልስ ተሰጣት። ሴቲቷ 'ቤተሰብ ፍለጋ' የሚባል ድርጅት ልጇን እያፈላለገላት እንደሆነም ለበላይነሽ አጫወተቻት። ቤተሰብ ፍለጋ ከኢትዮጵያ በማደጎ የተወሰዱ ልጆችን ከወላጆቻቸው ጋር የሚያገናኝ ድርጅት ነው። ልጁን የሚፈልግ ቤተሰብ፤ ልጁ በጉዲፈቻ ስለተሰጠበት ሂደት የሚያውቀውን መረጃ ይሰጣል። • ለልመና ታግቶ የነበረው ታዳጊ ከዓመታት በኋላ ተገኘ የልጁ ስም፣ ፎቶ፣ የወሰደው ድርጅት፣ የሄደበት አገር. . . ልጁን ለማፈላለግ የሚረዳ ማንኛውም መረጃ ይመዘገባል። ቤተሰብ ፍለጋን የመሰረተችው አሜሪካዊት አንድርያ ኬሊ መረጃውን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በመልቀቅ ልጁን ወይም የልጁን አሳዳጊዎች ትፈልጋለች። የተስፋ ጭላንጭል የታያት በላይነሽ ስለ ልጇ ያላትን መረጃ ለአንድርያ አስተላለፈች። እጇ ላይ ልጇን ለማደጎ ከሰጠው ድርጅት የወሰደችው የልጇና የአሳዳጊ ቤተሰቦቹ ፎቶና ስም ነበር። ልጇና እሷ የተነሱት ፎቶ፣ 'የህጻኑ እናት በህመም ምክንያት ልጁ ለጉዲፈቻ እንዲሰጥ ፍቃደኛ ነች' የሚል የፍርድ ቤት ደብዳቤም ነበራት። መረጃው በማኅበራዊ ሚዲያ ተለቆ በጉጉት እየተጠባበቀች ሳለ፤ ከወደ ቶሮንቶ መልካም ዜና ተላከላት። የልጇ አሳዳጊ ቤተሰቦች ተገኙ። "ፎቶውንስ አየሁት፤ በአይነ ሥጋ የምንገናኘው መቼ ይሆን?" የበላይነሽ ልጅ አሳዳጊዎች የተገኙት ፌስቡክ ላይ ነበር። ካናዳ፣ ቶሮንቶ ይኖራሉ። የጉዲፈቻ ልጃቸው ወላጅ እናት ልጇን እየፈለገች መሆኑ ሲነገራቸው አባትየው የልጁን ፎቶ ሊልክላት እንደሚፈልግ ገለጸ። "አንድ ቀን ከአንድርያ ጋር የምትሠራ ልጅ ቤቴ መጣች። ልጄን የሚያሳድገው ሰው በቫይበር የላከላትን ፎቶ ይዛ። ሳየው እንዴት ደስ እንዳለኝ ልነግርሽ አልችልም። 17 ዓመቱን ጨርሶ 18ኛውን ይዟል። እኔ ያወጣሁለትን ስም ቢቀይሩትም አሁን የሚጠራበት ስም እኔ ከሰጠሁት ጋር ይቀራረባል። ቤተሰቦቹ 'አይዞሽ፤ ልጁ ጥሩ ነው፤ ትምህርትም ጎበዝ ነው' ብለውኛል። በጣም እንደሚወዱት፤ እንደሚንከባከቡትም ነግረውኛል።" ቤተሰቡ ልጁ ስላለበት ሁኔታ ለእሷ ለመንገርና ፎቶውን ለማሳየት ቢስማማም በአካል እንድታገኘው ፍቃደኛ ስለመሆናቸው አታውቅም። ለልጇ ወላጅ እናቱ እየፈለገችው እንደሆነ ይንገሩት አይንገሩትም እርግጠኛም አይደለችም። የልጇን ፎቶ ማየት የሰጣት እፎይታ 'ልጄን በአይነ ሥጋ የማየው መቼ ነው?' የሚለው ጥያቄ እንዳጠላበት ትናገራለች። "ልጄን የያዙበት መንገድ ደስ ብሎኛል። ጥሩ እድገት ላይ ነው። ሰዎቹን ባላያቸውም በጣም ጥሩ ሰዎች ይመስሉኛል።ይህን ያህል ፍንጭ ማግኘቴ ራሱ ተስፋ ይሰጠኛል።እግዚአብሔር ፍቃዱ ሆኖ ዓይን ለዓይን ብንተያይ በጣም ደስ ይለኛል። በዓይኔ ባየው. . . ባቅፈው. . . ብስመው. . . እመኛለሁ። ልጄ በሕይወት ይኖራል ብዬ አላስብም ነበር። አየዋለሁ ብዬ ገምቼም አላውቅም ነበር። አንድ ቀን እንደምንገናኝ ተስፋ ማድረግ የጀመርኩት አሁን ነው፤ ፎቶውን ሳየው።በእሱ ምክንያት ውስጤ በጣም ተጎድቷል። አንዴ እንኳን ልቀፈው እንጂ ሌላማ ምን እላለሁ?. . . መድሀኒቴን በትክክል እየወሰድኩ ነው፤ ቤት ያፈራውን እየቀመስኩ።እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ! አኗኗሬ ግን በጣም ያስጠላል። ብቸኛ ነኝ። በዚች ቀበሌ በሰጠኝ ቆርቆሮ ቤት የምኖረው ምኑ ይወራል? ብርዱ፣ ጭቃው. . . በዚህ ላይ ደሞ የኑሮ ውድነት አለ. . . አንዳንዴ ባልኖር ይሻላል እላለሁ. . . ግን ልጄን ሳላይ ለምን ልሙት?
48319422
https://www.bbc.com/amharic/48319422
"ሀኪሙ ትግሉን አቀጣጠለው እንጂ የሚታገለው ለታካሚው ነው" የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሬዚደንት ሐኪሞች
"አንድ አባት የአንጀት መታጠፍ ገጥሟቸው ወደሆስፒታላችን መጡ" ይላሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህክምና ፋኩልቲ የጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ድህረ ምረቃ ተማሪው ዶ/ር ዮናስ አደመ።
የመጡት ከመሸ ነበር። ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ቀዶ ጥገና እንዲደረግላቸው ተወሰነ። ቀዶ ጥገናው እንዳይደረግ ግን ጄኔሬተሩ ተበላሽቷል። መብራት ቢኖርም ያለጄኔሬተር ቀዶ ጥገና ማድረግ አይቻልም። ዶክተሩ እንደሚሉት የደም ምርመራ ማድረግ አልቻሉም። • "የሚያክሙን ሙዚቃዎች እንዳሉ ሁሉ የሚያውኩንም አሉ" ዶ/ር መልካሙ ኋላ ላይ ሀኪሞችና ነርሶች ገንዘብ አዋጥተው የደም ምርመራው ሌላ የግል ሆስፒታል ተሠራ። ያም ሆኖ በሆስፒታሉ ቀዶ ጥገና ማድረግ ስላልተቻለ ወደ ሌላ የመንግሥት ሆስፒታል ተላኩ። ሆስፒታሉ ደግሞ ታካሚው የሚያስፈልጋቸው የፅኑ ሕሙማን ክፍል ስለሌለው ሊቀበላቸው አልቻለም። ታካሚው ማግኘት ያለባቸውን ቀዶ ጥገና ሳያገኙ ሁለት ቀን ቆዩ። የአንጀት መታጠፍ ሲቆይ ወደ ጋንግሪን ይቀየራል የሚሉት ዶ/ር ዮናስ "ይህንን እያወቅን እኚህ አባት ማግኘት ያለባቸውን ሕክምና ሳያገኙ ቆዩ" ይላሉ። ከሁለት ቀናት በኋላ የማዋለጃ ክፍል ጄኔሬተርን በብዙ ቢሮክራሲ አስፈቅደን ቀዶ ጥገናው ተሠራላቸው ይላሉ። ሆኖም ታካሚው ከስድስት ሰአት በኋላ ሕይወታቸው አለፈ። የአንዳችን አባት ወይንም የቅርብ ጎረቤት የሚሆኑ አባት መትረፍ እየቻሉ በብልሹ የሕክምና ስርዓት ሳቢያ ሕይወታቸው እንዳለፈ ዶ/ር ዮናስ ይናገራሉ። ዶ/ር ዮናስ አሁን ያለውን የሀኪሞች ተቃውሞ ሀኪሙ አቀጣጠለው እንጂ፤ "ሀኪሙ የሚታገለው ምንም ማድረግ ለማይችለው ታካሚ ነው" ሲሉ የሰሞኑን የሀኪሞችና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የሥራ ማቆም አድማና የሰላማዊ ሰልፍ ምክንያት ያስረዳሉ። • በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? "የተሻለ ሕክምና ማግኘት የማይችለው ሕዝብ የሚገባውን የጤና አገልግሎት እያገኘ እንዲኖር ነው ትግላችን። በብልሹ የህክምና አሰራሮችና መሟላት ያለባቸው ነገሮች ባለመሟላታቸው መትረፍ የሚችሉ በርካታ ሰዎች እየሞቱ ነው። መትረፍ የሚችሉ እጆች፣ መትረፍ የሚችሉ እግሮች እየተቆረጡ ነው። ይህ መሆን የለበትም" ይላሉ። ጥያቄዎቻቸው ምንድን ናቸው? በዋናነት የተነሱት ጥያቄዎች ሦስት ናቸው ይላሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህክምና ፋኩልቲ የጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕፃናት ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊቲ ተማሪ የሆኑት ዶ/ር ዳንኤል ታምራት። አንደኛውና ዋነኛው የሕክምና አሰጣጥ ሂደት ነው። "የሕክምና አገልግሎቱ እጅግ በጣም አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው። በሕክምና ተቋማት ውስጥ ትንንሽ ከሚባሉት ጎዝ፣ ጓንት፣ መርፌ ጀምሮ ትልልቅ እስከሆኑት ምርመራዎችና ለሕክምና የሚያስፈልጉ እቃዎች እጥረት የታካሚዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ነው" የሚሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ ይህ እንዲስተካከል ሲጠይቁ በቂ ምላሽ ስላላገኙ ወደሰላማዊ ሰልፍና የሥራ ማቆም አድማ መሄዳቸውን ያስረዳሉ። ሁለተኛው ጥያቄ በቂ የህክምና ቁሳቁስና አለመኖሩ ነው። "ሕንፃ ስላለ ብቻ ጥሩ ህክምና የለም። ውጤቱ ጥሩ የሚሆነው በህክምና መስጫ ውስጥ ቁሳቁስ ሲሟላ ነው። የሕክምና ባለሙያው ውጤታማ፣ ደስተኛና በሙሉ አቅሙ የሚሠራ መሆን አለበት" ይላሉ ዶ/ር ዳንኤል። ዶክተሩ እንደሚሉት፤ የሕክምና ባለሙያው የኢኮኖሚ አቅም እጅጉን የተዳከመ ስለሆነ መሰረታዊ ፍላጎቶቹን አሟልቶ ሥራውን በተገቢው ሁኔታ መሥራት አልቻለም። "ጥያቄያችን የደመወዝ ብቻ ባለመሆኑ ህብረተሰቡ የህክምና ስርዓቱ እንዲቀየር አብሮን ሊቆም ይገባል" ሦስተኛው የሀኪሞቹ ጥያቄ የደህንነት ጉዳይ ነው። "በተለያዩ ቦታዎች የሕክምና ባለሙያዎች እየተመቱ ነው። ለባለሙያዎች ክብር አለመኖሩና ጥሩ የሆነ የሕግ ከለላ አለመኖሩም ሀኪሞችን ለተለያየ ችግር እያጋለጣቸው ነው" ይላሉ ሐኪሙ። የባህር ዳር ሀኪሞችም ተመሳሳይ ጥያቄ በማንገብ ትላንት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር። በሰልፉ ላይ የነበሩት ዶ/ር አብርሀም ሞላ "ሰልፍ የወጣነው ለደመወዝ ጥያቄ ባለመሆኑ ህብረተሰቡ የህክምና ስርዓቱ እንዲቀየር አብሮን ሊቆም ይገባል" ይላሉ። የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ የሆነው የስድስተኛ ዓመት የህክምና ተማሪ ገደፋው ክንዱ በበኩሉ፤ "እስካሁን የተሰጠን ምላሽ አጥጋቢ ስላልሆነ የመጨረሻ የማስጠንቀቂያ ደውል መሆኑን መንግሥትና ሕዝብ ይወቅልን" በማለት የሀኪሞቹን ምሬት ያስረዳል። በፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል ጠቅላላ ሐኪምና የሰልፉ የፕሬስ ኃላፊ ዶ/ር አብራራው ታደሰ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ባለሙያዎቹን ማነጋገራቸውን አድንቀው፤ ምላሽ የተሰጠበት መንገድ እንዳላስደሰታቸው ይናገራሉ። ዶ/ር አብራራው የሃኪሞች ማኅበርም ለመንግሥት ያደላ በመሆኑ የሀኪሞችን ችግር ይፈታል ብለው አያምኑም። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ጥራት ያላቸው የህክምና ተቋማት እንዲፈጠሩ፣ ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም በተገቢው መልኩ እንዲከፈል፣ በዘርፉ የፖለቲከኞች ሚና እንዳይኖር እንዲሁም የህክምና ፖሊሲው እንዲሻሻል ጥያቄ ቀርቧል። ለምን አሁን? በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህክምና ፋኩልቲ የጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስና ስፔላይዜሽን ክፍል ተማሪ የሆኑት ዶ/ር ጀማል ማርቆስ እነዚህ ጥያቄዎች አሁን የተነሱት በአገሪቱ እየተደረጉ ያሉ ለውጦች የጤናውን ዘርፍ ስላካተቱ መሆኑን ይጠቅሳሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህክምና ፋኩልቲ የጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ተማሪው ዶ/ር አብርሀም ገነቱም ሀሳቡን ይጋራሉ። ዶ/ር አብርሀም "በአሁኑ ሰዓት የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቶ ዜጎች ያሻቸውን መናገር የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ለዓመታት በሙያ ማኅበሩ በኩል ስናነሳቸው የነበሩ ጉዳዮች በቂ ምላሽ ባለማግኘታችውና ችግሮቹ እየተባባሱ በመምጣታቸው፤ እንዲሁም ሁሉም ሰው ሀሳቡን በደንብ መግለፅ ሲጀምር የሁላችንም አጀንዳ እየሆኑ ስለመጡ ነው" ይላሉ። የጤና ዘርፉ ለውጥ እንደሚያስፈልገውና የኢትዮጵያ ሕዝብም ለዓመታት ከለውጡ ተጠቃሚ እንዲሆን እንደሹ ይናራሉ። • "ማህበሩ የማያልፈው ቀይ መስመር የስራ ማቆም አድማ ነው"-ዶ/ር ገመቺስ ማሞ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህክምና ፋኩልቲ የጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአንጎልና ሕብለ ሰረሰር ቀዶ ሕክምና ክፍል ተማሪ ለሆኑት ዶ/ር አብዱላዚዝ አብደላ ተቃውሞው አሁን የተነሳው የመናገር ነፃነት ስላለ ብቻ አይደለም። በሕክምና ተቋማት የሚሰጥ አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን እንደምክንያት ያስቀምጣሉ። ይህን ሀሳባቸውን የሚያጠናክሩት በትምሀርት ክፍላቸውን የደረሰውን አጋጣሚ በማስታወስ ነው። "በአንጎል ቀዶ ጥገና ትምህርት ክፍል ውስጥ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እያለሁና አሁን አራተኛ ዓመት ሆኜ ነገሮች እየቀነሱ መጥተዋል። ይባስ ብሎ ከሁለት ሳምንት በፊት የ15 ዓመት ታዳጊ ሞተብን" ይላሉ። የ15 ዓመቱ ታዳጊ ሊያጠና ወደጎረቤት እየሄደ ሳለ በሞተር ተገጭቶ ነበር ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሄደው። "እኛ ጋር ሲደርስ ቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ ነበርን። ሁለት የሚሠራ ቀዶ ጥገና ክፍል ነበረን። የነበረን እቃ ውስን ነበር። የነበረንን እቃ ለሁለቱ አካፍለን መሥራት ጀመርን። ሁለተኛውን ቀዶ ጥገና ክፍለ ውስጥ እየሠራን ሳለ ይህ ልጅ በድንገተኛ ክፍል በኩል መምጣቱ ተነገረን። ሲቲ ስካን ታይቶ ውጤቱ ሲመጣ ጭንቅላቱ ውስጥ ከላይኛው ሽፋን በላይ የተጠራቀመ ደም አለ። ይህ ልጅ በአስቸኳይ ቀዶ ጥገና ማግኘት አለበት። ኦፕሬሽን ክፍል ውስት ግን እቃ የለም" በማለት የተጠቀሙበትን እቃ አጥበው ወደ ስቴሬላይዜሽን ክፍል ለመላክ እንኳ ውሃ አለመኖሩን በምሬት ያስረዳሉ። ጥቁር አንበሳ ውስጥ ረብዑና አርብና ውሀ የለም የሚሉት ሀኪሙ፤ "የሚሻለው አርብና እሮብ ውሃ የለም ብሎ መቀመጥ ነው ወይስ ታንከር ማስገባት ነው?" በማለት በቁጭት ይናገራሉ። የክፍሉ ችግር ግን ይህ ብቻ አይደለም። ከሁለት ሳምንት በፊት ቀዶ ጥገናዎች እየተሰረዙ ነበር። ምክንያቱም ቀዶ ጥገና ክፍል የሚለበሰው (ድሬፕ) አለመኖሩ ነበር። የልብስ ንፅህና መስጫው ተበላሽቷል መባሉን ያስታውሳሉ። የሕክምና ተቋሙን ችግር ለማስተካከል ፈቃደኝነት መጥፋቱንም ያክላሉ። • የአሜሪካው ፅንስ ማቋረጥ ሕግ ሆሊውድን አስቆጣ "እኛ ሕብለ ሰረሰር ሕክምና እንማር ነበር። ነገር ግን አንድ መሣሪያ የለም ተብሎ፤ ሦስት ዓመት ሙሉ ሲጠየቅ ቢቆይም ባለመገዛቱ እኛም ሳንማር፣ ታካሚውን ወደግል ተቋም በመላክ ለተጨማሪ ወጪ እየዳረግነው ነው" ይላሉ። አንድ የሕብለ ሰረሰር ቀዶ ጥገና ለመሥራት አምስት ወር እንደሚወስድባቸውና ታካሚዎች ወደግል ተቋማት ሲያቀኑ ደግሞ 120 ሺህ ብር ድረስ እንደሚከፍሉ ያስረዳሉ። "ይህን የቱ አቅመ ደካማ ነው የሚችለው?" ይላሉ ቁጭታቸው ፊታቸው ላይ እየተነበበ። የሥራ ማቆም አድማን እንደ መፍትሔ? ዶ/ር ዳንኤል "ሙሉ በሙሉ አድማ አልመታንም" በማለት የድንገተኛ ክፍል፣ የጽኑ ሕሙማን ክፍልና የወሊድ አገልግሎት ክፍል ሀኪሞች የሥራ ገበታቸው ላይ እንደነበሩ ያስረዳሉ። "የሕዝቡ ስጋት የነበረው የሕሙማን ሕይወት አደጋ ላይ ይወድቃል። በእነርሱ አድማ ምክንያት የሚሞት ሰው ይኖራል የሚል ነው። ነገር ግን እነዚህ የጠቀስኳቸው ክፍሎች እና የሰው ልጅ ሕይወት አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል የሚባልባቸው ክፍሎች የሚሠሩና ጥያቄያችንን የሚደግፉ ሐኪሞች ሥራ ገበታቸው ላይ ተገኝተው ሲያገለግሉ ነበር።" • የዘንድሮ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዎች • የጡት ካንሰር የያዛት የጡት ካንሰር ሀኪም መንግሥት ይህንን ጥያቄ ያነሱ ሐኪሞችን ማመስገን አለበት የሚሉት ሐኪሙ፤ የብሔርና የሐይማኖት ጥያቄዎች በብዛት በሚነሱበት ዘመን አገርን የሚጠቅም ጥያቄ ሲነሳ ጥያቄውን ማክበር ተገቢ መሆኑን ይገልጻሉ እንደዶክተሩ ገለጻ፤ ከመንግሥትም ሆነ ከሚመለከታቸው አካላት ችግሩን ለመፍታት ፈቃደኝነቱ ቢኖር መፍትሔ ይገን ነበር። "ነገር ግን አሁን እየታየ ያለው ማስፈራራትና ተመልሰዋል የተባሉ ጥቂት ጥያቄዎችን መላልሶ ማውራት ነው" ይላሉ። ዶ/ር ዮናስ ሀኪሞች የሚያደርጉት ትግል ግቡን እንደሚመታ ያምናሉ። "ባለኝ መረጃ መሰረት ዓለም ላይ ከሀምሳ በላይ አገራት ውስጥ ሐኪሞች እኛ ያነሳናቸውን ጥያቄዎች አንስተው አድማ መትተው ያውቃሉ። እነዚህ አድማዎች በአጠቃላይ ሙሉ በሙሉ ግባቸውን የመቱ ናቸው። የእኛም ትግል የፈጀውን ጊዜ ይፈጃል እንጂ ግቡን መምታቱ አይቀርም።" አሁን በጥቂት ሆስፒታሎች የሚስተዋለው ጥያቄና ሰልፍ ወደ ሌሎች ሆስፒታሎችና በተለያዩ ሆስፒታሎች ወደሚሰሩ ሀኪሞች ተሸጋግሮ አገር አቀፍ አድማ እንዳይሆን ይሰጋሉ። "ይህ ባይሆን ምኞታችን ነው። ከዛ በፊት ጥያቄያችንን ሰምተው ምላሽ ቢሰጡን ደስ ይለናል። አድማችንና ትግላችን በአገሪቱን የጤና ስርአት ለውጥ ያመጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ይላሉ። አክለውም "ጥያቄውን መጠየቅ የነበረበት ሕዝቡ ነበር ብለን እናምናለን" ይላሉ። ቀጣይ እርምጃዎች ምንድን ናቸው? ዶ/ር ዮናስ፤ መንግሥት ሁለት አይነት አማራጭ አለው ይላሉ። "እኛ ምንም አይነት ፖለቲካዊ አጀንዳ የለንም። የአገራችን የጤና ስርአት እንዲሻሻል እንፈልጋለን። ስለዚህ ከኛ ጋር ተወያይተው ችግሮች የሚሻሻሉበትን የጊዜ ሰሌዳ ቢያስቀምጡ፣ ከአገሪቷ አቅም በላይ ናቸው የሚባሉትን ችግሮችን ለይተውም ቁርጠኛነታቸውን ቢያሳዩን እኛም ወደሥራችን እንመለሳለን" ይላሉ። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ ጋር ያደረጉት ውይይትና የተሰጣቸው መልስ አጥጋቢ እንዳልሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ጀማል፤ ነገሮች ከመባባሳቸው በፊት ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው እርምጃ እንዲወሰድ ይጠይቃሉ። ዶ/ር ዮሐንስ በበኩላቸው፤ መንግሥት ተቃውሟቸውን ያሰሙትን ሀኪሞች ማባረርና ማሰር ሌላው "አማራጭ" አድርጎ እንደሚወስድ ያነሳሉ። ይህንን የሚሉት ሰሞኑን ከጥቁር አንበሳ አስተዳደሮች ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን በማጣቀስ ነው። "ይህ ከሆነ ግን ጥሩ ነገሮች አይፈጠሩም" ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። ዶ/ር ዳንኤል ሀኪሞች የአድማ ፍላጎት እንደሌላቸውና ሙያቸውን እንደሚወዱ ይናገራሉ። "ጠዋት ገብቶ ስምንት ሰዓት የሚወጣ ሀኪም የለም። ሰላሳ ስድስት ሰዓት ሰርቶ የሚወጣ ሀኪም ነው ያለው። የኛ ጥያቄ ሀያና ሰላሳ አመት ሲጠየቅ የኖረ ነው። ይህ ችግር በኛ እድሜ ካልተፈታ፣ ሀኪሙ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ የሚደበደብ ከሆነ ችግሩ አይፈታም" ይላሉ። • ጤና የራቀው የፈለገ ህይወት ሆስፒታል ችግሩን ፈጥረዋል ብለው የሚያስቧቸው ሰዎች "የመፍትሔው አካል ይሆናሉ" ተብለው ሲደራጁ ጥያቄያቸው እንደማይፈታ ይናገራሉ። "ጠቅላይ ሚኒስትሩን አነጋግረን 'ከሳቸው በታች ያሉ ሰዎች መፍትሔ ይሰጣችኋል' ሲባል ተስፋ አስቆራጭ ነው" ይላሉ።
news-53159019
https://www.bbc.com/amharic/news-53159019
"ለፖሊስ በመደወሌ የጎረቤቴ ልጅ ህይወት ተቀጠፈ"
በቴክሳስ ግዛት ፎርት ወርዝ ከተማ ነዋሪ የሆው ጄምስ ስሚዝ በተቻለ መጠን ከፖሊሶች ጋር ምንም ግንኙነት እንዳይኖረውም ብዙ ጥሯል።
አንዳንድ ጊዜ ግን ያው አስገዳጅ ሁኔታ መፈጠሩ አይቀርም እና በአንድ ምሽትም ግዴታ ፖሊስ ጋር የሚያስደውለው አጋጣሚ ተፈጠረ። በጣም መሽቷል ግን ጎረቤቱ ግን በሯ እንደተከፈተ ነው። ምን ሁና ይሆን? በሚል ፖሊስ ጋር ደወለ። ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ተኩስ ሰማ፤ ቀጥሎም የጎረቤቱ የ28 ዓመት ሴት ልጅ አስከሬን በቃሬዛ ሲወጣ አየ። በጣም ተረበሸ። ተናደደ፣ ደከመው፣ አመመው፤ ምን እንደሚያስብ ሁሉ ግራ ገባው። ከዚያ በኋላ ማንኛውም ጥቁር ሰው በፖሊስ ሲገደል አታቲና ጄፈርሰንን የተገደለችበትን መጥፎ ጊዜ ያስታውሰዋል። "ከፀፀት ጋር አብሬ ነው የምኖረው፤ በሚቀጥሉት ዓመታትም መቼም ቢሆን ሊቀለኝ የማይችለውን ሸክም ተሸክሜ ነው የምኖረው፤ እንደ ሰማይ ያህልም ከብዶኛል" በማለትም የሚናገረው ጄምስ ፖሊስ ጋር የደወለበትንም ምሽት ይረግማል። ጥቅምት 12 ቀን፣ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ተኩል ነበር። የጎረቤቱ በር እንደተከፈተና መብራትም እየበራ ነው ብለው የቀሰቀሱት የእህቱና የወንድሙ ልጆች ናቸው። ጎረቤቱና የቤቱ ባለቤት ዮላንዳ ካር የልብ ህመምተኛ ስትሆን፤ በቅርብ ጊዜም ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል በተደጋጋሚ ከመግባቷ አንፃር አንድ ነገር ሆና ይሆን በሚልም ተጨነቀ። ከግቢው ወጥቶ መንገዱ ላይ ሆኖ ሲያይ በግቢዋ ውስጥ የአትክልት መኮትኮቻ ቁሳቁሶቹ በቦታቸው ናቸው፤ ሶኬቶቹም አለመነቀላቸው ግራ አጋብቶት ፖሊስ ደኅንነቷን እንዲያረጋግጥ በሚል ስልክ ደወለ። ያሰበው ፖሊስ መጥቶ በሩን አንኳኩቶ ቤተሰቡ ደህና መሆናቸውን ይጠይቃል በሚልም ግምት ነበር። ጄምስ ያላወቀው ግን ጎረቤቱ ዮላንዳ በዚያ ምሽት ሆስፒታል ነበረች። እናም ልጇ አታቲያናና የልጅ ልጇ ቪዲዮ እየተጫወቱ እየጠበቋት ነበር። በፖሊስ የተገደለችው አታቲያና ጄፈርሰን ፖሊስ ሲደርስም ጄምስ በቤቱ ትዩዩ ቆሞ ነበር። አሮን ዲን የተባለው አንደኛው ፖሊስ ሽጉጡን አውጥቶ ወደ በሩ ተጠጋ፣ በመቀጠልም ቤቱን በመዞር በአትክልት ስፍራው በኩል በጓሮ በር ወደ መስኮቱ ተጠጋ። ከጥቂት ሰኮንዶች በኋላ የተኩስ ድምፅ ተሰማ። "ተኩሱ እንደተሰማም ' እንዳታስመልጣቸው ስትል ድምጿን ሰማሁት" ብሏል ጄምስ። በመቀጠልም ምን እየተከናወነ እንደሆነም አልገባውም፤ ነገር ግን በርካታ ፖሊሶች መጥተው ጎዳናውን ሞሉት፤ በአካባቢውም ውር ውር ማለት ጀመሩ። ተኩስ ከሰማ ከስድስት ሰዓታት በኋላ ነው ምን እንደተፈጠረ ያወቀው። የጎረቤቱ ልጅ አታቲያና ጄፈርሰን እንደተገደለችም ተረዳ። አስከሬኗን በቃሬዛ ይዘውት ወጡ። የጄምስ ቤተሰብና የዮላንዳ ጉርብትና በቅርብ ነው የጀመረው። ዮላንዳ ቤቱን የገዛችው ከአራት ዓመታት በፊት ሲሆን፤ በቤቷም በጣም ነበር የምትኮራው፤ ያለቻትን አጠራቅማ የገዛችው ቤት። የእሷንና የጄምስን ቤትም የሚለየው የአትክልት ቦታና መንገድ ነው። ጄምስ በሰፈሩ ለረዥም ዘመናት ኖሯል። ልጆቹን እዚህ ነው ያሳደገው፤ የልጅ ልጆቹም እዚሁ ሰፈር ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ አምስት የቤተሰቡ አባላትም እንዲሁ በዚያው አካባቢ ነው የሚኖሩት። ዮላንዳ ለዚህ ሰፈር አዲስ ብትሆንም ከጄምስ ጋር እየተቀራረቡ ነበር። ጄምስ ዮላንዳን ጠንካራ ሠራተኛ እንደሆነች ይናገራል "በህይወቷ ውስጥ ብዙ ፈተና ቢያጋጥማትም ያንን ተወጥታዋለች። ለዚያም ነው ቤት መግዛቷን እንደ ትልቅ ድል የምታየው" ብሏል። ልጇም አታቲያናም የእናቷን መታመም ተከትሎ ነው ልታስታምማት የመጣችው። እናቷን እንዲሁም የስምንት ዓመት የወንድሟን ልጅ ከመንከባከብ በተጨማሪ ለህክምና ትምህርት ቤትም የሚሆን ገንዘብ እየቆጠበች ነበር። ከመገደሏ ጥቂት ቀናት በፊት አካባቢያቸው ባለው መንገድ ላይ የመኪና አደጋ ተከስቶ ነበር። አታቲያናም በሩጫ ልትረዳቸው ከቤት ወጣች፤ እናም አምቡላንሱ እስኪመጣ ድረስ አብራቸው ቆየች በማለትም ቀናነቷን ያስታውሳል። "ዶክተር የመሆን ህልም ነበራት፤ ያንን እውን ሳታደርግ ተቀጨች" ይላል። ጄምስ አንዳንድ ጊዜ አትክልታቸውን ይኮተኩትላቸዋል፤ አታቲያናም የሚጠጣ ውሃ አምጥታ ይጫዋወቱ ነበር። የተገደለችበት ዕለት የወንድሟን ልጅ አትክልቶቹን እንዴት መንከባከብ እንዳለበት እያሳየችው ነበር። ከፖሊስ የተገኘው ቪዲዮ እንደሚያሳየው አሮን ዲን የተባለው ፖሊስ በጓሮ በኩል በሚገኘው መስኮት በኩል ሲሄድ የሚታይ ሲሆን፤ አታቲያናም በመስኮት በኩል ውልብ ስትል ትታያለች። "እጅ ወደ ላይ፣ እጅሽን አሳይ" በማለት ንግግሩን ሳይጨርስ በመስኮት በኩል ተኮሰ። ፖሊስ ነኝም አላለም። መሞቷንም ተከትሎ አሮን ዲን ከሥራ ከመባረሩ በፊት በራሱ ለቀቀ። ታህሳስ ወር ላይም በግድያም ወንጀል በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፤ ለአጭር ጊዜም በእስር ላይ ነበር። ነገር ግን የፍርድ ሂደቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲዘገይ ተደርጓል። የፎርት ወርዝ ፖሊስ ኃላፊ ኤድ ክራውስ "አታቲያና ጄፈርሰን ህይወቷን ያጣችበት መንገድ ምንም ትርጉም አይሰጥምም" ብለዋል። ኃላፊው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ዕለት ስሜታዊ ሆነው የታዩ ሲሆን የአታቲያና አሟሟትም በፖሊስና በማኅበረሰቡ መካከል ያለውን ድልድይ አፍርሶታል ብለዋል። ለጄምስ ግን ኃላፈው ያሉትም ትርጉም ሊሰጠው አልቻለም፤ በሕግ አስከባሪዎች ላይ የነበረውን ጥቂት እምነቱንም አጥቶታል። "ከፖሊስ ጋር ጥሩ ግንኙነት የለንም፤ ምክንያቱም አናምናቸውም። በጭራሽ የማንገናኝም ከሆነ በህይወት የመቆየት እድላችን ከፍተኛ ነው" ይላል ጄምስ። ጄምስ ከዚህ ክስተት በኋላ ተአምር ቢፈጠር ፖሊስ ጋር እንደማይደውል ያውቀዋል። በቅርቡ እህቱ በሰፈራቸው ውስጥ የተኩስ ድምፅ ሰምታ ፖሊስ ጋር ደውል ብትለውም እምቢ ብሏል። "ጥቁር ካልሆንክ ነገሩን አትረዳውም" የሚለው ጄምስ በቅርቡም ፖሊሶች ተቃዋሚዎችን ሲያቅፉ፣ ሲንበረከኩ ቢያይም ቲያትር እንደሆነ ነው የተረዳው። ለአስርት ዓመታትም እንዲሁ ፖሊሶች ሲያስመስሉ መቆየታቸውንም ይናገራል። በተለይም የጎረቤቱን ልጅ ከገደላት ፖሊስ ጋር ተያይዞ ያለው የፍርድ ሂደትም በርካታ ጥያቄዎችን ያጭሩበታል። የአይን እማኝ ቢሆንም ሊያናግረው የመጣ ሰው የለም። አሟሟቷ ለሚዲያ ይፋ ባይሆን ኖሮ ምርመራ እንደማይጀመርም ተረድቷል። ያለው የፍርድ ሂደትም በከፍተኛ ሁኔታ ያናድደዋል። ወረርሽኙን እንደ ምክንያት በመጠቀም የፍርድ ሂደቱ ለሚቀጥለው ዓመት የተራዘመ ሲሆን በወንጀል የተጠረጠረው ሰው ጥቁር ቢሆን ኖሮ፤ ክስ እንደሚመሰረትበት እንዲሁም የፍርድ ሂደቱም እንደሚፋጠን ምንም ጥርጣሬ የለውም። "ትንፋሻችንን እንደያዝን ነው፤ መተንፈስ አልቻልንም" ይላል። አታቲያና ጄፈርሰንን ተኩሶ የገደለው ፖሊስ አሮን ዲን በዓመታት ውስጥ በርካታ ፖሊሶች ብዙ ሰዎችን መግደላቸውን እንዲሁም ማቁሰላቸውን የተለያዩ ተቋማትና ተመራማሪዎች በአብዛኛው ከሚዲያ ከሚገኙ ሪፖርቶች መረጃ ሰብስበዋል። ከእነዚህም ውስጥ 'ማፒንግ ፖሊስ ቫዮለንስ' በተባለው ድርጅት በባለፈው ዓመት ከተገደሉት ሰዎች ውስጥ 24 በመቶ ጥቁሮች ሲሆኑ፤ የጥቁሮች የሕዝብ ቁጥርም አስራ ሦስት በመቶ ብቻ ነው። ሌሎች መረጃዎችም እንደሚያሳዩት ከሌሎች ዘሮች በበለጠ ጥቁሮች በፖሊስ ሊተኮስባቸው እንዲሁም ሊገደሉ ይችላሉ። ግድያ የፈፀሙ ፖሊሶ መከሰስም የተለመደ አይደለም። ድርጅቱ በጎርጎሳውያኑ 2013- 2019 ባለው ጊዜ 7 ሺህ 500 የሚሆኑ ሰዎች በፖሊስ ተተኩሶባቸዋል ወይም ተድለዋል ይላል። ከእነዚህም ውስጥ 71ዱ ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን 23ቱ ብቻ ናቸው የተፈረደባቸው። ጄምስም ስለ ጎረቤቱ ግድያ ለማውራት በቴሌቪዥን በቀረበበት ወቅት ከአንድ ሚሊዮን ያነሰ የሕዝብ ቁጥር ባለባት ፎርት ወርዝ ባለፈው ዓመት ብቻ ሰባት ሰዎች በፖሊስ መገደላቸውን ተረድቷል። የጆርጅ ፍሎይድ ግድያንም ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ አንዳንድ አሰቃቂ ታሪኮች ለሕዝብ ይፋ ሆነዋል። ከሁለት ዓመታት በፊት ክርስቶፈር ሎው የተባለው አጎቷ እንዴት በሁለት ፖሊስ ኃላፊዎች እንደተገደለ ቲፋኒ በንተን የተባለች ጥቁር ፖሊስ ተናግራለች። ከፖሊስ የተገኘው ቪዲዮ እንደሚያሳየው ክርስቶፈርን እየጎተቱ ይወስዱታል። ለማየት በሚረብሸው ቪዲዮ ላይ ክርስቶፈር ለመራመድም ሆነ ለመቆም ሲታገል ይታያል። "አሞኛል፤ መተንፈስ አልቻልኩም፤ እየሞትኩ ነው" ቢላቸውም ፖሊሶቹ ሐዘኔታ አልነበራቸውም። አንደኛው ፖሊስም "ምራቅህ ቢነካኝ ከጭቃው ጋር ነው የማደባይህ" ሲልም ይሰማል። ከአስራ ሦስት ደቂቃ በኋላም ክርስቶፈር መኪናው ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል። ቲፋኒ አጎቷ አሞኛል እያለ ሲማፀን ፖሊሶቹ አምቡላንስ ቢጠሩ ሞቱን ማስቀረት ይቻል እንደነበርም ታምናለች። ከግድያውም ጋር ተያይዞ አምስት ፖሊሶች ቢባረሩም ሁለቱ ከዓመት በኋላ ወደ ሥራቸው ተመልሰዋል። አታቲያና ከሞተች ከሁለት ሳምንታት በኋላ አባቷ ማርክስ ጄፈርሰን በልብ ድካም ሞተ። የአታቲያና አጎት ሐዘን ወንድሙን ሐዘን እንደገደለው ያምናል። እናቷም ዮላንዳ ካር ታማ ሆስፒታል ስለነበረች ልጇን መቅበር አልቻለችም። ከሆስፒታልም ከወጣች በኋላ የልጇን ምስል ያለበት ቲሸርት ለብሳ፣ ልቧም በሐዘን ተሰብሮ ጄምስ አግኝቷት ነበር። የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ የፎርት ወርዝ ከንቲባ ቤትሲ ፕራይስ በሰጡት መግለጫ የጆርጅን ስም በመጥቀስ ሐዘናቸውን የገለፁ ሲሆን የአታቲያናን ስም ሳይጠቅሱ በማለፋቸው ጄምስን በጣም ነው ያሳዘነው። የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ ተቃውሞ ቢቀጣጠልም ለምን የአታቲያና ሞትስ ተቃውሞን እንዳላነሳሳ ይጠይቃል። "ዝም ባልን ቁጥር መረሳቷ አይቀርም፤ እንድትረሳ አልፈልግም" ይላል። የአታቲያናንም ህይወት ለመዘከር እህቶቿና ወንድሞቿ በስሟ አንድ ፋውንዴሽን አቋቁመዋል። ፋውንዴሽኑ ትምህርት ላይ የሚያተኩር ሲሆን የተገደለችበት ቤትም እንደ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል። የፖስታ ቤት ሠራተኛ የሆነው ጄምስ ቤቱ በልጆቹ የዲግሪና የማስተርስ ምርቃት ፎቶዎች ያሸበረቀ ነው። በርካታ መልካም ነገሮችን ያየበት ቤቱ እንዲሁም ሰፈሩ ነው። ዮላንዳም ብትሆን ከነርስነቷ ከምታገኘው ደመወዝ ልጆቿን አስተምራለች። የተደላደለ ህይወትም ለመኖር አቅዳም ነበር፤ ሳይሆን ቀርቶ ልጇን አጣች። ለዮላንዳ ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ ለኖረው ጄምስም ሰፈሩ ሞትን ያስታውሰዋል። የአታትያና ሞት ከጭንቅላቱ ሊጠፋ አልቻለም። የተኩሱ ድምፅ በጭንቅላቱ ውስጥ ይሰማዋል። ባልሰራው ወንጀል ለሃያ ሶስት አመታት የታሰረው ሮበርት ጆንስ በአሜሪካ ውስጥ በጥቁሮች ላይ የሚፈጸም ኢ-ፍትሃዊነት አዲስ ነገር አይደለም። ሮበርት ጆንስ በጎርጎሳውያኑ 1992 በኒው ኦርሊያንስ ውስጥ እንግሊዛዊ ቱሪስቶችን ገድለሃል በሚል ወንጀል ተከሰሰ። ከአራት ዓመታት በኋላ የፍርድ ሂደቱ የተካሄደ ሲሆን በዚህም ወቅት ሌላ ግለሰብ በወንጀሉ ቢፈረድበትም ሮበርት ጆንስም በተመሳሳይ ወንጀል እንዲሁ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት። ንፁህ ቢሆንም ለሃያ ሦስት ዓመታት ያህል በእስር ቆይቷል። የፈረዱበት ዳኛ በቅርቡም የቆዳው ቀለም የህይወቱን መጥፎ እጣ ፈንታ ወስኖለታል ሲሉ ተሰምተዋል።
news-46068739
https://www.bbc.com/amharic/news-46068739
"ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ
የ1999 ዓም የገና ዋዜማ ለካሚላት መህዲ እና ለቤተሰቦቿ መልካም ነገር ይዞ አልመጣም። በካሚላትና በእህቶቿ ላይ የደረሰው ብዙዎችን ያስደነገጠ፤ የኢትዮጵያውያንን ልብም በጋራ ቀጥ ያደረገ የካሚላትን ሕይወት ደግሞ የቀየረ ነበር።
ካሚላት መህዲ በ1999 ዓ.ም የገና ዋዜማ ከእህቶቿ ጋር ከምትሰራበት ሱቅ አምሽታ ወደ ቤቷ ስትሄድ አንድ ሰው ወደ አጠገባቸው መጥቶ አሲድ ፊቷ ላይ ደፍቶ መሰወሩን በወቅቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበውታል። •አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው? ካሚላት በወቅቱ በደረሰባት የፊት መቃጠል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና ቢደረግላትም ቃጠሎው ከፍተኛ ስለነበር ከሀገር ወጥታ መታከም እንዳለበት ተገለፀ። ጥቃቱን የፈፀመውም ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ። ከዚያ በኋላ ካሚላት በሼህ መሀመድ አሊ አላሙዲ ድጋፍ በፈረንሳይ ሀገር ሕክምና ለማግኘት ሄደች። ከዚህ የህክምና ጉዞ በኋላ አልፎ አልፎ በመገናኛ ብዙኃን ላይ ስለእርሷ ቢሰማም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ታይታ አታውቅም። •የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? በዚህ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ፈረንሳይ ባመሩበት ወቅት በአየር መንገድ በመገኘት አቀባበል ካደረጉት የተለያዩ ሰዎች ምስል መካከል የካሚላትም አብሮ ታየ። ይሄኔ የካሚላት ጉዳይ ለማህበራዊ ሚዲያው መነጋገሪያ ሆነ። ካሚላት ፈረንሳይ ጠቅልላ መኖር ከጀመረች ስድስት ዓመት ሆኗታል። ባለትዳርና የአንድ ልጅ እናትም ሆናለች። ቢቢሲ አማርኛ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ፈረንሳይ እንደሚመጡ ስትሰሚ ምን ተሰማሽ? ካሚላት፡ ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ። እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ አንድ ቅን የሆነ መንግሥት ወዳለህበት ሊያይህ ሲመጣ የሚሰማህ ስሜት ነው የተሰማኝ። ቢቢሲ አማርኛ፡አየር መንገድ አቀባበል ከሚያደርጉት ሰዎች መካከል እንድትሆኚ እንዴት ተመረጥሽ? ካሚላት፡ እዚህ ለእርሳቸው አቀባበል የተቋቋመ ጊዜያዊ ኮሚቴ ነበር። ዲያስፖራው ከኤምባሲው ጋር በመሆን ማለት ነው። እዛ ላይ ነው የመረጡኝ። እና ተመርጠሻል ሲሉኝ በደስታ ተቀበልኩኝ። •ከኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እስከ ሣህለወርቅ ዘውዴ ቢቢሲ አማርኛ፡ለኤምባሲው ቅርብ ነሽ ማለት ነው። ካሚላት፡ ማለት ሁላችንም እዚህ ያለን ኢትዮጵያዊ ኤምባሲ የሚያስፈልገን ሲኖር እንሄዳለን፤ እንጠይቃለን። ከኤምባሲው በተሻለ እዚህ ካሉ ኢትዮጵያውያን ውስጥ ጥሩ ቦታ አለኝ። እኔም ለሰዉ ያለኝ አመለካከት ተመሳሳይ ነው። ቢቢሲ አማርኛ፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ አየር መንገድ ሲያገኙሽ ምን አሉ? ካሚላት፡ በጊዜው ሰላምታ ብቻ ነው የተለዋወጥነው። በጣም እንደተሰማቸው ያስታውቅ ነበር። እዛ ሰዓት ላይ ግን ምንም መነጋገር አትችልም ነበር። ይበርድ ነበር።ጊዜውም አጭር ነበር። ሰላምታ ብቻ ነው የተለዋወጥነው። ቢቢሲ አማርኛ፡ከዛ በኋላ የማውራት ጊዜ አላገኛችሁም። ካሚላት፡ አላገኘንም። ቢቢሲ አማርኛ፡ፈረንሳይ ኑሮሽን አድርገሻል። ሰዎች ሲያዩሽ ምን ሆነሽ ነው ብለው አይጠይቁም። ካሚላት፡ ይጠይቃሉ። መጀመሪያ ፊታቸው ላይ የምታየው ነገር ይኖራል። ከዛ በትህትና ይጠይቁሃል። እና እነግራቸዋለሁ። ቢቢሲ አማርኛ፡ሁሌ መጠየቅ አይረብሽሽም? ካሚላት፡ አይረብሸኝም አልልህም ይረብሻል። ቢቢሲ አማርኛ፡ አሁን አግብተሻል ወልደሻል ኑሮ እንዴት ነው? ካሚላት፡ ማግባት፣ መውለድ በጣም ደስ ይላል። ድርብ ኃላፊነት ነው። ኢትዮጵያ መጥቼ ካገባሁ በኋላ ልጄን እዚህ ፈረንሳይ ተመልሼ ነው የወለድኩት። ባለቤቴ ግን አሁንም ኢትዮጵያ ነው ያለው አልመጣም። እና ልጄን ብቻዬን ነው የማሳድገው። ቢቢሲ አማርኛ፡ልጅሽ ወንድ ነው ሴት ካሚላት- ወንድ ልጅ ነው፤ አራት ዓመት ሞልቶታል። ቢቢሲ አማርኛ፡ እና ፈረንሳይ ሕይወት እንዴት ነው? ካሚላት- ደስ ይላል ጥሩ ነው። በርግጥ እንደ ኢትዮጵያ አይደለም። ልጅ ስታሳድግ ብቻህን ነው። የምሄድበት ሁሉ ይዤው ነው የምዞረው። በተጨማሪም ባለቤቴ እዚህ ስላልሆነ የሕክምናዬን ነገር ለጊዜው ገታ አድርጌ ልጄን ማሳደግ ላይ አተኩሬያለሁ። ያው እርሱ ሲመጣ ወደ ሕክምናዬ ተመልሼ እገባለሁ። ቢቢሲ አማርኛ፡ ሕክምናው አላለቀም ማለት ነው? ካሚላት፡ አላለቀም እንዳየኸኝ ነው አይደል ያለሁት፤ ስለዚህ አላለቀም። ቢቢሲ አማርኛ፡ ሕክምናው ረዥም ጊዜ ይፈጃል ማለት ነው? ካሚላት፡አዎ ቢቢሲ አማርኛ፡ አሁንም ወጪውን ማን ነው የሚሸፍነው? ካሚላት፡ በፊት በነበረው ሁኔታ ለአንድ ዓመት በሼክ መሀመድ አሊ አላሙዲ ወጪ ስታከም ነው የነበረው። እዚህ ጠቅልዬ ከመጣሁ በኋላ የፈረንሳይ መንግስት ነው የሕክምና ወጪዬን የሚሸፍነው። ቢቢሲ አማርኛ፡ ልጅሽ ግን ይጠይቅሻል ምን እንደደረሰብሽ? ካሚላት፡ (ፈገግታ) እርሱ ነገር ትንሽ ከባድ ነው። ገና መጠየቅ አልጀመረም። ያው እናት እናት ናት ታውቃለህ። ወደፊት ሳስብ ግን ትንሽ የሚያስጨንቀኝ እርሱ ነው። በምን መልኩ ላስረዳው እንደምችል አላውቅም። ትንሽ ይከብዳል። በፊት ያለኝ ስሜትና አሁን ልጅ ሲኖረኝ ያለኝ ስሜት የተለያየ ነው። ቢቢሲ አማርኛ፡ ሴት ልጅ ብወልድ እንዲህ አይነት ጥቃት ሊደርስባት ይችላል ብለሽ ትሰጊያለሽ? ካሚላት፡ አይ ስለነገ አላህ ነው የሚያውቀው። እንደዛ ብዬ ማሰብ አልፈልግም። በአሁኑ ሰዓት የሚጠቃው ወንዱም ሴቱም ነው። ስጋቱ ጾታ ለይቶ ብቻ ሳይሆን የትኛውም ጾታ ላይ ስጋት ይኖርሃል። ቢቢሲ አማርኛ፡በወቅቱ አንቺ ላይ ጥቃት ሲደርስ እህትሽም ላይ ነበር ጥቃት የደረሰው አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነች? ካሚላት፡ አንዷ ብቻ ሳትሆን ሁለት ናቸው ከኔ ጋር ሆነው ጥቃት የደረሰባቸው። በጊዜው ሕክምና አድርገዋል።አሁን የየራሳቸውን ኑሮ እየኖሩ ነው። ቤተሰቤ አዲስ አበባ ነው ያለው። ቤተሰብ ሁል ጊዜ ሲያዝን ሲሰጋ ነው የሚኖረው።ስጋት ስልህ ከመፍራት አንፃር ሳይሆን ለኔ ይኼ ነገር ባይደርስ ይመርጣሉ። የትም ቦታ ሲያዩህ ከአንተ የበለጠ እነርሱ ናቸው ልባቸው የሚሰበረው። በርግጥ የኔ ማግባት መውለድ እናት አባቴን ቀና ሊያደርግ ይችላል። ምንም ቢሆን ግን ቤተሰብ ናቸውና ሁል ጊዜ አንደተጎዱ ነው። የእነርሱን ጉዳት መቀየር ብችል ደስ ይለኛል። ቢቢሲ አማርኛ፡ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን አየር መንገድ ስትቀበይ ሲያዩሽ የድሮውን ምስልሽን አውጥተው ማጋራት ጀመሩ። ቤተሰቦችሽ ጋር የድሮ ፎቶዎችሽ አልበሙ ውስጥ አለ። ቤት ውስጥ ያንን ምስል እያዩስ የመረበሽ ነገር አለ? ካሚላት፡ ቤተሰቦቼ እነዛን ፎቶዎች እንዳያቸው አይፈልጉም። እነርሱም እንዲረበሹበት አናደርግም። በርግጥ እንደዚህ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያጋሩት ይረብሻል። ለቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም። እነዛ ፎቶዎች ለትውስታ መውጣታቸው ጥሩ ቢመስልም እኛ ቤተሰብ ጋር ግን ሁሌ ረብሻ ይፈጥራል። አሁን ደግሞ ልጅ አለኝ። ልጄ ላይ ወደፊት ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል። ቢቢሲ አማርኛ፡አንቺ ላይ ጥቃት ከደረሰ በኋላ የተለያዩ ሴቶች ላይ ጥቃት ደርሶ ሰምተናል ፤ አንቺ እነዚህን ነገሮች ስትሰሚ የሚፈጥርብሽ ነገር ምንድን ነው? ካሚላት፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍራንክፈርት በአውሮጳ የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን ሰብስበው ሲያናግሩ ጥያቄ ያቀረብኩት ይህንን የሚመለከት ነው። የኔ ጥቃት እንደ ዋዛ እንደ ተራ ነገር ሆኖ ለሌሎቹ መጥፎ ምሳሌ ሆኗል። አሁን አሲድ ጥቃት እንደ ፌዝ ነገር ሆኖ የአይን ብርሀንን እስከማጥፋት ደርሷል። ያንን ሳይ የበለጠ በጣም ነው የሚሰማኝ። ምክንያቱም አንተ ላይ ሲሆን የሚሰማህን ስሜት ትቀበለዋለህ። ሌሎች ላይ ሆኖ ሳየው ግን ወደ ስሜቴ እመለሳለሁ። ሕመሜን መልሶ እንዳስታውሰው ያደርገኛል። ይህ በጣም ነው የሚረብሸኝ። ከዚህ አንፃር ነበር ጥያቄ ያነሳሁት። ቢቢሲ አማርኛ፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሾመዋል። ለኢትዮጵያ ሴቶች ፍትህን በማግኘት ረገድ ለውጥ ይኖራል ብለሽ ተስፋ ታደርጊያለሽ? ካሚላት፡ ኢንሻ አላህ። 10 ሴት ሚኒስትሮች አሉን። ፕሬዝዳንታችን ሴት ናቸው። አሁን ደግሞ ሴት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አግኝተናል። በጣም የሚያስደስት ነው።ለውጥ ይመጣል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ሁሉም ሰው ለውጥ የሚፈልግ ይመስለኛል። ተስፋ አደርጋለሁም ብዙ እጠብቃለሁም። ቢቢሲ አማርኛ፡ አንቺ ላይ ለደረሰው ጥቃት የተሰጠው ፍርድ አነስተኛ ነው በማለት ተሰምቶሽ ያውቃል? ካሚላት፡ አዎ በርግጥ በወቅቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ድምፅ ተረባርቦልኛል። የተለመደ አይነት ጥቃትም ስላልነበር ሁሉም ሰው ተረባርቧል። ከኔ የበለጠ ሰዉ ነበር ሆ ብሎ የወጣው። ፍርዱ ራሱ ከፍ ያለ ነበር የተሰጠው። የሞት ፍርድ። በኋላ ላይ ነው በይግባኝ የተቀነሰው። እንደገና የሴቶች ጉዳይ አቤት ብሎ ነው እድሜ ልክ ወይንም 25 ዓመት የሆነው። እኔ የማየው ይህ ነገር በሰዓቱ የማያዳግም ውሳኔ ቢወሰን ኖሮ ዛሬ በአሲድ የተጠቃን ሴቶች አንበረክትም ነበር እላለሁ። ለኔ ብቻ ሳይሆን ለሕብረተሰባችን ብሎ ነበር ፍርድ መሰጠት የነበረበት። አሁንም የማያዳግም ቅጣት እስካልተወሰነ ድረስ ይህ ነገር መቀጠሉ አይቀርም። ቢቢሲ አማርኛ፡የሴቶች ጥቃትን ለማስቆም የሚሰራ ትምህርት የሚሰጥ ተቋም የመመስረት ሀሳብ የለሽም? ካሚላት፡ አለኝ። አሁን ራሱ እዚህ ፈረንሳይ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ሉሲ ወይም ድንቅነሽ የሚሰኝ ማህበር አቋቁመን እየተንቀሳቀስን ነው። ቢቢሲ አማርኛ፡መቼ ነው ወደ ኢትዮጵያ የምትመጪው? ካሚላት፡ ኢንሻ አላህ! እኔ ከምመጣ የባለቤቴ መምጫ ቢፈጥንልኝ ይሻላል̈ (ሳቅ)
news-56104101
https://www.bbc.com/amharic/news-56104101
አዲስ የጸደቀው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ምን ይዞ ይመጣል?
በቅርቡ አዲሱ የመገናኛ ብዙኃን ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቁ ይታወሳል።
ይህ አዋጅ ከመጽደቁ በፊት ግን በ2012 ዓ.ም. ነሐሴ ወር ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ፖሊሲን አጽድቋል። ይህ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፀድቆ በሥራ ላይ የዋለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ፖሊሲው የመገናኛ ብዙኃን ሲመራበት የቆየው ሕግ ማሻሻያ ፀድቆ ከመውጣቱ ቀድሞ መውጣቱ አይዘነጋም፡፡ ፖሊሲው ከህትመትና ከብሮድካስት ሚዲያ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም በመገናኛ ብዙኃን ሕጎች ላይ ያልነበሩትን በበይነ መረብ አማካኝነት የሚሰራጭ የኦንላይን ሚዲያንና እና የማህበራዊ ሚዲያን እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ያካተተ ነው። በፖሊሲው ላይ የኢትዮጵያ ሚዲያ ምን ዓይነት መልክ ሊኖረው እንደሚገባ፣ አቅጣጫው ወዴት መሄድ እንዳለበት፣ የመንግሥት ድጋፍ ምን ድረስ መሆን እንዳለበት የሚያመላክቱ ነጥቦች እንደተካተቱበት ተዘግቧል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በረቂቅ አዋጁ ላይተሳትፎው ምን ነበር? የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ሕጋዊ ሰርተፍኬት አግኝቶ ሀገሪቱ ውስጥ ሥራ ከጀመረ የተወሰኑ ጊዜያትን አስቆጥሯል። የምክር ቤቱ አባላት በግልና በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የሚሠሩ ጋዜጠኞችና እንዲሁም የሙያ ማህበራት ናቸው። ምክር ቤቱ ሊያሳካ ካቀዳቸው ጉዳዮች አንዱና ዋንኛው ጋዜጠኞች ሙያው የሚጠይቀውን ሥነ ምግባር ጠብቀው እንዲሰሩ ማስቻል መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት አባልና ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቶ ታምራት ኃይሉ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል። የፕሬስ ሕጉ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ በጠቅላይ አቃቤ ሕግ ስር አንድ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሲሰራ እንደነበር አቶ ታምራት ያስታውሳሉ። የዚህ ግብረ ኃይል ቀዳሚ ተግባር የነበረው ቀደም ሲል በስራ ላይ በነበረው የፕሬስ ሕግ ላይ የተስተዋሉ ችግሮች ምንድን ናቸው? የሚለውን በጥናት መለየት እንደነበር አቶ ታምራት ተናግረዋል። በዚህ ጥናት የሕግ ማዕቀፍና የአፈጻጸም ችግሮች መለየታቸውን የሚናገሩት አቶ ታምራት፤ የተለየዩ ጋዜጠኞች ለዚህ ጥናት ግብዓት እንዲሆን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም ያስረዳሉ። ከዚህ በኋላ በተለዩ ችግሮች ዙሪያ ውይይት ተካሄዶ አዲሱ ሕግ ረቂቅ ተዘጋጀ። ረቂቁ ለውይይት በቀረበበት ወቅት ሙያተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና ሌሎች ሕጉ ላይ መግባት የለበትም አልያም አለባቸው ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ውይይቶች መካሄዳቸውን ያስታውሳሉ። በመጨረሻም ረቂቁ ከተወያዮች ያገኛቸውን ግብዓቶች አካትቶ ወደ ሚኒስትሮች ጉባዔ ተመርቷል። ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕጉ በተመራበት ወቅት ግን በውይይት ወቅት ያልነበሩ እና የሚዲያ ካውንስሉም ሆነ ሙያተኛው ያላያቸው አንቀጾች ተጨምሮበት ማግኘታቸውን አቶ ታምራት አልሸሸጉም። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ለተጨማሪ የውይይት ጊዜ ጥያቄ ቢያቀርቡም አዋጁ ወደ ምክር ቤቱ በተመራ በአስራ አምስት ቀናት ጊዜ ውስጥ መጽደቁን ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ያስተዋላቸው አንቀጾች የትኞቹ ናቸው? የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የተቋቋመው ስህተቶች ሲሰሩ መንግሥት ጋዜጠኞችን እያሳደደ ከሚያስር እርስ በእርስ ለመተራረም እና ለመመካከር እንዲቻል በማሰብ መሆኑን የሚያስታውሱት አቶ ታምራት፤ ከዚህ በፊት በሚዲያ ግድፈት ሲፈፀም የሚከታተለው ብሮድካስት ባለሥልጣን እንደሆነ ይገልጻሉ። ከዚህ ቀደም ምክር ቤቱ ስላልነበረ ብሮድካስት ባለስልጣን ይህንን ተልዕኮ መወጣቱ አሳማኝ ነበር የሚሉት አቶ ታምራት፤ አሁን ግን ምክር ቤቱ ስላለ የሚዲያ ፖሊሲው ይህንን ተልዕኮ እንዲወጣ እውቅና እንደሰጠው ይናገራሉ። የእርስ በእርስ ቁጥጥር (Self-Regulation) ጉዳይ መጠናከር እንዳለበትም በአዋጁ ላይ ተቀምጦ እንደሚገኝ አቶ ታምራት በመጥቀስ፤ ነገር ግን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ባለሥልጣኑ ይመለከታል መባሉ፣ ረቂቅ ሕጉ ከሚዲያ ፖሊሲው ጋር የሚቃረን እንደሆነ ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። ይህንንም አንቀጽ ምክር ቤታቸው መቃወሙን የሚገልፁት አቶ ታምራት፤ በአዋጁ ላይ ምክር ቤቱም ሆኑ ብሮድካስት ባለሥልጣን የራስን በራስ የማረም ሂደቱን በጋራ ሲያከናውኑ ቆይተው (co-regulation) በመጨረሻ መንግሥት በሚያደርገው ግምገማ ኃላፊነቱን ለምክር ቤቱ እንደሚያስተላልፍ በአዋጁ ላይ መቀመጡን ገልፀዋል፡፡ በመንግሥት ወገን ይቀርብ የነበረው ሐሳብ የሚዲያ ካውንስሉ አሁን ያለበት ቁመና ይህን ተግባር ለመፈጸም የሚያስችለው ስላልሆነ ቁጥጥሩን ብሮድካስት ባለሥልጣን ቢያንስ ለ3 ዓመታት ከካውንስሉ ጋር ሆኖ ሊመራው ይገባል የሚል ነበር። ሆኖም በ3 ዓመታት ውስጥ የሚዲያ ካውንስሉ ቁመና ተገምግሞ ይህ ራስን በራስ የመቆጣጠር ተግባርና ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ ወደ ካውንስሉ ሊተላለፍ የሚችልበት ዕድል እንደሚኖር ያመላክታል፡፡ ለአቶ ታምራት ግን ይህ የሚዋጥላቸው ሐሳብ አልሆነም፡፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት በሲቪል ሶሳይቲ ሕግ መሰረት የተቋቋመ ነጻና ገለልተኛ ማሕበር ነው የሚሉት አቶ ታምራት፤ መንግሥት እኛን ሊገመግም የሚችልበት አግባብ የለም ይላሉ። በመሆኑም ይህ የአዋጁ አንቀጽ የገለልተኝነት እና የነጻነት ጥያቄ ያስነሳል በማለት እንዲሻሻል ቢጠይቁም፤ መንግሥት የተለያዩ ምክንያቶች በማቅረብ ሳይቀበላቸው መቅረቱን ይገልጻሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የተቃወሙት ሌላ ጉዳይ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን የአሠራር የሥነ ምግባር ደንብ ያወጣል የሚለውን አንቀጽ ነው። በዚህ አዲስ አዋጅ ብሮድካስት ባለሥልጣን ስሙ የሚዲያ ባለሥልጣን ተብሎ እንደሚቀየር ይጠበቃል፡፡ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በዋናነት የተቋቋመው የሥነ ምግባር ደንብ ለማስጠበቅና ደረጃውን የጠበቀ መገናኛ ብዙኃን በአገር ውስጥ እየጎለበተ እንዲሄድ መሆኑንንም አስረድተዋል። ለአቶ ታምራት የሥነ ምግባር ደንብ ማውጣት የባለሙያዎችና የሚዲያ ባለቤቶች እንጂ የመንግሥት ጉዳይ መሆን የለበትም። መንግሥት ሕግ፣ መመሪያ እና ደንብ ሊያወጣ ቢችልም የሥነ ምግባር ደንብ (Code of Conduct) ግን ባለሙያዎች ራሳቸውን የሚያርሙበት ደንብ በመሆኑ ራሳቸው ማውጣት እንደሚገባቸው አጽንኦት በመስጠት ይናገራሉ። አቶ ታምራት ይህን ይበሉ እንጂ ብሮድካስት ባለሥልጣን አሁን ይህን የሥነ ምግባር ደንብ ረቂቅ አውጥቶ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ሰዎች ሰምተናል፡፡ ደንቡም በረቂቅ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ሌላው አቶ ታምራት ያነሱት የሥነ ምግባር ደንቡ ሲወጣም ተነጥሎ ለብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን ብቻ ሳይሆን ለኦንላየንም ሆነ ለፕሬስ ዘርፉም የሚያገለግል መሆን እንዳለበት ነው። አሁንም ቢሆን የሥነ ምግባር ደንቡ (Code of conduct) የኅትመት ሚዲያውን አለማካተቱንና የብሮድካስት መገናኛ ብዙኀን ብቻ ማቀፉን ገልፀዋል። አቶ ታምራት ሕጉ ላይ በረቂቅ ደረጃ ውይይት ሲደረግ ያልነበረ እና ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ሲመራ የተካተተ ነው በማለት ያነሷቸው ሌሎች ነጥቦችም አሉ። ከነዚህ መካከል የመገናኛ ብዙኃን ዓይነቶች ይገኙበታል፡፡ በውይይቱ ወቅት የግል፣ የመንግሥት እና የማህበረሰብ የሚባሉ ሦስት መገናኛ ብዙኀን አይነቶች መኖራቸው ብቻ ያውቁ እንደነበረ የገለፁት አቶ ታምራት፤ ነገር ግን ወደ ምክር ቤት የተመራው ረቂቅ ላይ ከዚያ ቀደም ሰምተውት የማያውቁት ልዩ የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን የሚል መካተቱን ተናግረዋል። ይህ አዲስ የተካተተው የመገናኛ ብዙኃን ዓይነት በበጎ አድራጎት አዋጁ የተመዘገቡ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያቋቁሙት የመገናኛ ብዙኃን ዓይነት መሆኑም መጠቀሱን ያስታውሳሉ። እነዚህ መገናኛ ብዙኃን የሚንቀሳቀሱት ከሕዝብ በልገሳ በተገኘ ገንዘብ ይሆናል የሚሉት አቶ ታምራት፤ በተጨማሪም የማስታወቂያ ውድድር ሽሚያ ውስጥ መግባታቸው የግል መገናኛ ብዙኃንን ያቀጭጫል ሲሉ ስጋታቸውን ያጋራሉ። የመገናኛ ብዙኃን ባለቤትነት የመገናኛ ብዙኃን ባለቤትነትን በተመለከተ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች እስከ 25 በመቶ ድረስ ድርሻ ሊኖራቸው እንደሚችል በረቂቅ ሕጉ ላይ መቀመጡን አቶ ታምራት ገልፀዋል። አቶ ታምራት ምክር ቤታቸው ለውጪ አገር ዜጎች በአጠቃላይ ሳይሆን ለትውልደ ኢትዮጵያውያን ብቻ የባለቤትነት ድርሻ መፈቀድ አለበት የሚል መከራከሪያ ማቅረቡን ያስታውሳሉ። ይህ ከብሔራዊ ደህንነት አንጸርም አደጋ ስላለው ክርክራቸው ተቀባይነት አግኝቶ በሚዲያ ፖሊሲው ላይ በግለጽ ለዲያስፖራዎች ብቻ እንደሚፈቀድ መቀመጡን ገልፀዋል። ነገር ግን ረቂቁ ሲመጣ ይህ ጉዳይ አዋጁ ላይ ሳይካተት መቅረቡ ስጋት እንዳጫረባቸው ይናገራሉ። አዋጁ የፀደቀው ይህ ሳይሻሻል ከሆነ ወደ ኋላ ተመልሶ ፖሊሲውን ማስተካከል እንደሚያስፈልግ አክለው ተናግረዋል፡፡ የጉዳዩን አሳሳቢነት ሲያስረዱም፤ አንድ ኢትዮጵያዊ ግብጽ ሄዶ የሚዲያ ባለቤት ልሁን ቢል እንደማይችል ሁሉ አንድ ግብጻዊ ባለሀብት በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ ድርሻ ሲኖረው በሉአላዊነት ጉዳይ እንዴት አደጋ ሊደቅን እንደሚችል ያስረዳሉ፡፡ ይህ ስጋት እንዳለ ሆኖ ረቂቁ በውይይት ደረጃ በቀረበበት ወቅት እንደተብራራው የመገናኛ ብዙኃን ድርሻ መያዝን በተመለከተ የውጭ ዜጎችና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በእኩል የማይታዩበት ዕድል እንዳለ ተመላክቶ ነበር፡፡ የኢትዮያን ባሕል ቋንቋና ታሪክ ማወቅ፣ ከአገሪቱ ጋር ያለ ቁርኝት እንደ ግዴታ ባይሆንም በባለቤትነት ጉዳይ ቅድሚያ ሊያሰጥ እንደሚችል የሚጠቁም አንቀጽ ተካቷል፡፡ ይህም ምናልባት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሚዲያ ድርሻ የማግኘት ዕድላቸውን የሚያሰፋ ተደርጎ በበጎ የሚነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ "የስም ማጥፋት ወንጀል" ድሮና ዘንድሮ እንደ አቶ ታምራት ገለፃ ከሆነ ይህ የተሻሻለው የፕሬስ ሕግ በሚዲያ ስም ማጥፋትን የወንጀል ተጠያቂነትን ማስቀረቱ ትልቅ ልዩነት ነው። ከዚህ በፊት በነበረው አዋጅ ግን በሥም ማጥፋት የሚከሰሱ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን የወንጀል ክስ ይቀርብባቸው እንደነበር አቶ ታምራት ያስታውሳሉ። በዚህ አዋጅ ስም ማጥፋት እንደ ወንጀል ተቆጥሮ መጠየቃቸው ተገቢ አለመሆኑ ክርክር በመቅረቡ ማሻሻያው መደረጉን ገልፀዋል። ስም ማጥፋት በመገናኛ ብዙኃን ላይ ሲሆን ከፍትሃ ብሔር ተጠያቂነት ውጪ የወንጀል ተጠያቂነት አያስከትልም ሲሉም ያክላሉ። ስለዚህ አንድ ጋዜጠኛ በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሌላ ሰውን ስም ቢያጠፋ የወንጀል ተጠያቂነት ሳይሆን የፍትሃ ብሔር ተጠያቂነት ብቻ ይኖርበታል ማለት ነው። ነገር ግን ይላሉ አቶ ታምራት፤ ግለሰቡ ያንኑ ተመሳሳይ ንግግር ከመገናኛ ብዙኃን ውጪ ሕዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ ቢናገረው በወንጀል እንደሚጠየቅ አስረድተዋል። ይህም ሰዎችን የወንጀል ተጠያቂነትን ለማስቀረት በሚል በሚዲያ ላይ ስም ማጥፋትን እንዲመርጡ ሊያደርግ ይችል ይሆን በማለት ስጋታቸውን ይናገራሉ። በሚዲያ ስም ማጥፋት የፍትሀ ብሔርም ተጠያቂነቱ የገንዘብ ቅጣቱ እስከ 300 ሺህ ብር ድረስ ከፍ ማለቱንም አክለው ገልፀዋል። የጥቅም ትስስር ከብሮድካስት ባለሥልጣን ጋር የመገናኛ ብዙኃንን በባለቤትን መያዝ የሚችሉ ሰዎችን በተመለከተ የብሮድካስት ባለሥልጣን ሰራተኞች በአዋጁ መገለላቸውን አቶ ታምራት ያስረዳሉ፡፡ ይህም የሆነው የብሮድካስት ባለስልጣን ሰራተኞች የጥቅም ትስስርን ለማስቀረት በሚል በመገናኛ ብዙኃን ላይ ድርሻ እንዳይኖራቸው አዋጁ መከልከሉ ነው፡፡ ይህ ግን ለአቶ ታምራት ሌላው ቅሬታ የፈጠረባቸው ጉዳይ ነው። የጥቅም ግጭት ሊፈጠር የሚችልበት ሁኔታ ስለመኖሩ የማይክዱት አቶ ታምራት፤ ያ ግን በከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ ደረጃ ላይ ባሉ የብሮድካስት ባለሥልጣናት ደረጃ እንጂ በዝቅተኛ በባለሥልጣኑ ሰራተኞች ጋር የሚገናኝ አይደለም ይላሉ፡፡ በአዋጁ ውስጥ ‹‹የብሮድካስት ሰራተኞች›› የሚል ሀረግ ማካተቱ ሙሉ ሰራተኞች በሚፈልጉት ሥራ ላይ ለመሰማራት ያላቸውን መብት የሚያግድ ነው በሚል ይገልፃሉ። በዚህ አዋጅ ብዙ ሚዲያዎች ያብባሉ ሲባል ለመክሰማቸው ምክንያት የሆነው የማስታወቂያ እጦት በምን ሁኔታ እንደተካተተ ማወቅ አልተቻለም፡፡ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በማስታወቂያ ብዛት ለደንበኞች ወረፋ በሚሰጡበት ሁኔታ የግል መገናኛ ብዙኃን ግን ይህ የሩቅ ህልማቸው ሆኖ ቆይቷል፡፡ የዚህ አንድ ምክንያት ተብሎ የሚነሳው ደግሞ የመንግሥት ተቋማትና የልማት ድርጅቶች ማስታወቂያ ለማስነገር የመንግሥት ሚዲያዎችን መምረጣቸው ነው፡፡ በረቂቁ የማስታወቂያ ቅርምት ፍትሐዊ እንዲሆን በርከት ያሉ ድምጾች ተሰምተው የነበረ ሲሆን ይህ ምን ያህል ተመልሷል የሚለው በሂደት የሚታይ ነው፡፡ አዲስ የጸደቀው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ባለመውጣቱ የትኞቹ የካውንስሉ ቅሬታዎች ወይም ገንቢ ሐሳቦች ተካተዋል፣ የትኞቹስ ቸል ተብለዋል የሚለውን ነቅሶ ለማውጣት አልተቻለም፡፡ ይህ አዲሱ አዋጅ ብሮድካስት ሚዲያዎች በይዘታቸው እስከ 80 ከመቶ የሚሆነው አገራዊ እንዲሆኑ እንዲያበረታቱም ያስገድዳል፡፡
news-44934222
https://www.bbc.com/amharic/news-44934222
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን የክፍፍል እና የውህደት ጉዞ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የተገቢነት ሙግት በሚያነሱ ሁለት ሲኖዶሶች ተከፍላ ስትወዘወዝ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ጊዜ ተቆጥሯል።
በመጀመሪያ በቀድሞው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ ከእርሳቸው ኅልፈተ ህይወት በኋላ ደግሞ በብፁዕ አቡነ ማቲያስ በሚመራው እና መቀመጫውን አገር ውስጥ ባደረገው ሲኖዶስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ መርቆሪዮስም ፓትርያርኩ አድርጎ በሚቆጥረውና ሰርክ 'ስደተኛው' እየተባለ በሚጠራው ሲኖዶስ መካከል ሰላም አውርዶ እርቅ ለመፍጠር ተደጋጋሚ ሙከራዎች መደረጋቸው ባይቀርም እስካሁን ድረስ ስኬት ሲናፍቃቸው ቆይቷል። • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ • የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' • ሬሳን ከሞት አስነሳለሁ ያለው 'ነብይ' የሟች ቤተሰብን እንዴት አሳመነ? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አንዲት ቤተ ክርስትያንን እና አማኞቿን እንወክላለን የሚሉትን ሁለቱን የእምነት አስተዳዳር መዋቅሮች ዓይን ለዓይን ከመተያየት ሲከለክል የቆየው ቁርሾ ተወግዶ ወደአንድነት እንዲመጡ ፍላጎታቸውን ከገለፁ በኋላ የተጀመረው እንቅስቃሴ ግን ፍሬ የያዘለት ይመስላል። ከትናንት አመሻሹ አንስቶ ሲኖዶሶች እርቀ ሰላም ይዘገብ ይዟል። ውህደቱ ምን ፋይዳ እና ትርጉም አለው? ቀጣይ እርምጃዎችስ ምን ይሆናሉ ስንል የእምነቱን ሊቃውንት አነጋገረናል። የቤተ ክርስትያኗ አመራር እንዴት ለሁለት ተከፈለ? በ1983 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) የደርግን ስርዓት ጥሎ ስልጣን ላይ ሲወጣ፣በአራተኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ ደስተኛ እንዳልነበር በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ማኅበረ ካህናት ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ ይናገራሉ። "በቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ ልዩነት መፈጠር የተጀመረው ብፁዕ አቡነ መርቆሪዮስ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ተደርጎ ብፅዕ አቡነ ጳውሎስ በስፍራቸው እንዲተኩ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ነው፤" ይላሉ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ። ቀሲስ ኤፍሬም እንደሚሉት አዲሱ መንግሥት የፖለቲካ ጉልበቱን በመጠቀም ፓትርያርኩ ከመንበራቸው እንዲነሱ በጉምቱ ባለስልጣናቱ ሳይቀር ጥረት አድርጓል። በዚህ አስተያየታቸው የሚስማሙት የቀድሞው የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ዲያቆን ዳንዔል ክብረት ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት በወቅቱ ብፁዕ አቡነ መርቆሪዮስ መንግስታዊውን ጫና መቋቋም ካለመቻላቸውም ባሻገር፤ አንዳንድ የኃይማኖት አባቶች የእርሳቸው መንበራቸውን መልቀቅ ብቸኛው መፍትሄ ነው ማመናቸው አልቀረም። የፓትርያሪኩን ከአገር መውጣት ተከትሎም ሌላ ምርጫ ተካሄደና ሌላ ፓትርያሪክ ተሾመ፤ አንዳንድ ጳጳሳት ስደተኛውን ፓትርያሪክ መከተልን መረጡ፤ ከጥቂት ዓመታት በኋላም በአገረ አሜሪካ ሌላ ሲኖዶስ መሰረቱ፤ ሌሎቹ ደግሞ አገር ውስጥ በነበረው ሲኖዶስ ለመቀጠል ወሰኑ። "ከዚህም የተነሳ ቤተ ክርስትያኒቷ በሁለት ሲኖዶስ፣ በሁለት ፓትርያሪክ የምትመራ ሆነች" ይላሉ ዲያቆን ዳንዔል። ለእርሳቸው ይህ ሂደት ሁለት የቤተ ክርስትያኒቷን አስተምህሮዎች የጣሰ ነው እንደሆነ ዲያቆን ዳንኤል ይናገራሉ። እንደ እርሳቸው አባባልም በመጀመሪያ "አንድ አባት ልጆቹን ትቶ መሄድ ተገቢ አይደለም፤" በመቀጠል "እኝህ አባት ከአገር ቢወጡም እርሳቸውን እና ሌሎቹን ከስደት ለመመለስ ጥረት መድረግ ሲገባው ሌላ አባት ተሾመ። ከበፊትም የሚመዘዝ ችግር ቢኖርም ይህንን ችግር በትዕግስት እና በብልሃት ማለፍ ቢቻል ኖሮ ይ. ነገር አይፈጠርም ነበር። የቤተክርስያኒቱ ስርዓት አንድ አባት በህይወት እያለ ሌላ አባት መሾም አይፈቅድምና።" ክፍፍሉ ምን ዳፋ አስከተለ? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን አሁንም ትልቋ የአገሪቱ የእምነት ተቋም ትሁን እንጅ የአማኞቿ ቁጥር ከአጠቃላዩ ምዕመን ያለው የመቶኛ ድርሻ እያሽቆለቆለ ነው የሚገኘው። ለመጨረሻ ጊዜ በ1999 ዓ.ም በተደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ መሰረት ከአገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ ከአርባ ሦስት በመቶ ከፍ የሚለው የእምነቱ ተከታይ ሲሆን፤ ቤተ ክርስትያኗ በ1977 ዓ.ም ቆጠራ ወቅት ከነበራት አገር አቀፍ የምዕመናን ድርሻ ግን ሃምሳ አራት በመቶ ገደማ ነበር። ዲያቆን ዳንዔል ለዚህ አብዩ ተጠያቂ "የቤተ ክህነቱ መዳከም ነው" ይላሉ። "ቤተ ክህነቱ ቤተ ክርስትያንዋን መሸከም ከሚችልበት አቅም በታች ነው። አሁን ላለው ቤተ ክህነት፣ አሁን ላለችው ኢትዮጵያ እና አሁን ላለው ትውልድ የሚመጥን አይደለም። ሁለቱም ቦታ፤ አሜሪካም ያለው እዚህም ያለው። ለዚህ የሚመጥን አቅም የለውም" ሲል ያብራራል። ለቤተ ክህነቱ መዳከም ደግሞ የሲኖዶስ፣ የኃይማኖት መሪዎችን እና የአማኞችን መከፋፈል ተወቃሽ ያደርጋሉ። ቤት ክህነቶች ዋና ተግባራቸውን "ውጊያ" ላይ በማድረጋቸው ምክንያት ተቀዳሚ ሥራቸው ሊሆን ይገባው የነበረው "ወንጌልን የማዳረስ ስራ፣ የሐዋርያዊነትን ስራና ምዕመናንን የመጠበቅን ስራ ተረስቷል" ይላሉ። • ሰባኪው አውሮፕላን ግዙልኝ አለ • ''ኤርትራ የእምነት ነፃነት የምታከብር ሃገር ነች'' አቶ የማነ ገብረ-መስቀል ቀሲስ ኤፍሬም በበኩላቸው የሁለት የተኮራርፉ አስተዳደሮች መኖር፣አንድ እምነት እና አንድ ስርዓት ያላቸው ምዕመናን እና ካህናት ለመራራቃቸው ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ይህም በፋንታው በርካታ ችግሮችን ወልዷል ይላሉ። "ቤተ ክርስትያኗ በአጠቃላይ አሁን ላለባት ድክመት፣ ለምዕመናኗ ቁጥር መቀነስ፣ ለአስተዳደሯ መበላሸት፣ ሙስና እና ዝርፊያ [በጓዳዋ] ለመሰልጠናቸው፣ ሙያው እና ስነ ምግባሩ የሌላቸው ሰዎች በልዩ ልዩ መዋቅሮች ለመሰግሰጋቸው ሁሉ በር የከፈተው ይህ በአባቶች መካከል ያለው ልዩነት ነው" ሲሉ ይናገራሉ። አሁንስ ከቤተ እምነት ላይ የቤተ መንግሥት ጥላ ተገፏል? ሲኖዶሶቹ አንዳቸው ሌላኛቸውን የእምነቱን ህግ እንደጣሱ ወይንም ኃይማኖታዊ ቅቡልነት እንደሌላቸው ያዩዋቸው የነበረ ለመሆኑ አንደኛው መገለጫ እርስ በራሳቸው መወጋገዛቸው ነው። አሁን ይካሄድ በያዘው ሽምግልና ላይ በጋራ ሲፀልዩ መስተዋላቸው ይሄንን ውግዘት በይፋዊ ባይሆን በተግባር ቀድመው ለማንሳታቸው ምስክር ነው የሚሉት ቀሲስ ኤፍሬም ናቸው። እርስ በእርስ የሚተያዩባቸው መንገዶች ምናልባትም በተደጋጋሚ የተደረጉትን የእርቅ ሙከራዎች የማክሰም ድርሻ ቢኖራቸውም፤ የአገሪቱ ፖለቲካዊ መልክ ጉልህ ሚና እንደነበረው ግን ሁለቱም ይስማማሉ። የአሁኑ እርቀ ሰላም ስኬትንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስተዳደር አቋም ጋር የሚያያይዙት ብዙ ናቸው። ቀሲስ ኤፍሬም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን በሌሎች የዓለም ክፍሎች ካሉ የክርስትና እምነቶች በተለየ መንግስታዊ ትስስር ከምስረታዋ አንስቶ እንዳላት ያስረዳሉ። "በሌሎች አገራት በአብዛኛው እምነቱ በህዝቡ ዘንድ ከሰረፀ በኋላ መንግስታት እንደተቀበሉት ታሪክ የሚያስረዳ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ግን የሆነው በተቃራኒው መንግስት እምነቱን ተቀብሎ ነው ከዚያ ወደሕዝቡ ያሰረፀው። ስለዚህም ከዚያ የሚመዘዝ መንግስታዊ ቁርኝት አለ" ይላሉ። በየዘመኑ የመጡ መንግስታት ቤተ ክርስትያኒቷን ዓላማቸውን ለማስፈፀሚያ ተጠቅመውባታል የሚሉት ቀሲስ እሸቴ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር መንግስት እና እምነትን ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የሚለያይ እርምጃ እንደሚወስድ ተስፋቸውን ይገልፃሉ። ከዚህ በኋላስ? ዲያቆን ዳንዔል የፖለቲካዊ ፍላጎት መጥፋት እንጅ ሲኖዶሶቹን በእርቅ ማጨባበጥ እስካሁንም የሚከብድ ነገር ሆኖ እንዳልነበር ያምናሉ። ከዚህ ቀደም የተደረጉ የእርቅ ጥረቶች "ላለመሳካታቸው አንዱ እንቅፋት የአገሪቱ ፖለቲካ ነው" ይላሉ አክለው "ምክንያቱም ሁለቱም በየራሳቸው የሚደግፏቸው የፖለቲካ አዝማሚያዎች አሏቸው። የአገር ቤቱ ሲኖዶስ የአገር ቤቱን ፖለቲካ፣ የውጭው ሲኖዶስ ደግሞ የውጭውን ፖለቲካ ስለሚደግፉ እና በፖለቲካው ጫና ውስጥ በመውደቃቸው ነው።" በውጭ አገር ያለው ሲኖዶስ በአማኞች ቁጥር ከተመዘነ ያለው አቅም በጣም ትንሽ ይሁን እንጅ በሚያንቀሳቅሰው የገንዘብ መጠን እና ባለው ተፅዕኖ ትከሻው የደረጀ ነው እንደ ዲያቆን ዳንዔል አስተያየት። ከሁለቱ ፓትርያሪኮች መካከል የስልጣን መንበሩ ላይ መቀመጥ ያለበት የሚለው ጥያቄ ሌላኛው ማነቆ ሆኖ የቆየ ቢሆንም እርሱን አሁን መፍታት ብዙም አይገድም ይላሉ። ብፁዕ አቡነ ማቲያስ የአስተዳደሩን ስራ እየሰሩ፤ አቡነ መርቆሪዮስን ደግሞ በመንበራቸው ሆነው ከአስተዳደሩ ስራ ግን ገለል እንዲሉ ስማቸውም በቅዳሴ እየተጠራ በሲኖዶሱም እየተገኙ እንዲቀጥሉ ማድረግ አማራጭ ሆኖ እንደሚታያቸው ይናገራሉ። "አቡነ መርቆሪዮስን የአስተዳደር ስራ ላይ እንዲሳተፉ ቢደረግ ከጤናም ከዕድሜም፣ከአገሪቱ ከሃያ ዓመት በላይ ርቀው ከመቆየታቸውም አንፃር ሊቸገሩ ይችላሉ።" ይላሉ። ቀሲስ ኤፍሬም በበኩላቸው በውጭ አገር ያሉት ፓትርያርክ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም አባቶችና ካህናት ወደአገር ቤት ተመለሰው በየአገር ስብከቱ እንዲመደቡና የአገልግሎት መዋሃድ እንዲፈጠር ይጠብቃሉ። ከዚህም ባለፈ ተመሳሳይ ክፍፍል እንዳይፈጠር "ህጎች ይወጣሉ፣መመሪያዎች ይወጣሉ፤ በተለይ ከመንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት ምን ዓይነት መሆን እንዳለበት ቤተ ክርስትያን ህግ ታወጣለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን።" ብለዋል።
49713869
https://www.bbc.com/amharic/49713869
አሥመራን አየናት፡ ከቅኝ ግዛት በኋላ ባለችበት ያለችው አሥመራ
ቢቢሲ በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን ከ15 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድርን እንድንዘግብ ፍቃድ ተሰጥቶን ወደ ኤርትራ አቅንተን ነበር። በኤርትራ በነበርን ቆይታ ያየነውን እና የሰማነውን በሦስት ክፍሎች አሰናድተናል። የመጀመሪያው ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል።
ማስታወሻ፡ በኤርትራ በነበረን ቆይታ የዘገባ ርዕሶቻችን እና እንቅስቃሴዎቻችን የተገደቡ ነበሩ። በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት እንደ ጎሮጎሳውያኑ አቆጣጠር ነው። መግቢያ ከ1880ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1914 በነበሩት ዓመታት ቅኝ ገዢዎቹ አውሮፓዊያን፤ አፍሪካን የመቀራመት እቅዳቸውን የወጠኑበት እና ያሳኩበት ዓመታት ነበሩ። 1890 ላይ ጣሊያን ኤርትራ የእርሷ ቅኝ ግዛት መሆኗን አወጀች። 1920ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሞሶሎኒ ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ ኤርትራ 'የአዲሲቷ ሮማ ግዛት' አካል ሆነች። ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ በኤርትራ የቆየው የጣሊያን ኃይል፤ በኤርትራ ቆይታው በመንገድ፣ በባቡር እና በህንጻ ግንባታዎች ላይ ተሳትፏል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በ1941 ዓ.ም ላይ የእንግሊዝ ጦር የጣሊያን ጦርን ከረን ላይ ድል አደረገ። • አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ ጣሊያን እና አጋሮቿ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሽንፈትን መከናነባቸውን ተከትሎ፤ ጣሊያን ኤርትራን ጨምሮ በአፍሪካ የነበሯትን ቅኝ ግዛቶች ለመልቀቅ ተገደደች። ከጣሊያን ቅኝ ግዛት በኋላ ኤርትራ ከ1942-1953 ያሉትን 11 ዓመታት በእንግሊዝ ጦር አስተዳደር ስር ነበረች። በወቅቱ ኤርትራዊያን ነጻ ኤርትራን ማየት ናፍቀዋል። እንግሊዝ በበኩሏ ኤርትራ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል እንድትከፈል ፍላጎቷ ነበር። አሜሪካ ግን ኤርትራ በፌዴሬሽን መልክ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትዋሃድ ምክረ ሃሳብ አቀረበች። የኃያሏ አሜሪካ ፍላጎት ተግባራዊ ሆኖ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን መልክ ተዋሃደች። ሉዓላዊ የሆነች ሃገር መፍጠርን ግብ ያደረጉ ኤርትራዊያን ከተለያዩ ሁለት የኢትዮጵያ መንግሥታት ጋር ለ30 ዓመታት ያክል የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ቆይተው እአአ 1991 ላይ የኤርትራን ነጻነትን አወጁ። ፕሬዝደንት ኢሳያስ ከሁለት አዛውንት መካከል ሆነው። የተራዘመው የኤርትራዊያን የትጥቅ ትግል በዓለማችን ከታዩ እጅግ ውጤታማ የሽምቅ ውጊያዎች አንዱ ነው ይባልለታል። 1991 ላይ ነጻነትን የተቀናጀችው ኤርትራ 1993 ላይ ሕዝብ ውሳኔ ከተካሄድ በኋላ ነበር በይፋ ነጻነቷን አውጃ በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተቸራት። በተባበሩት መንግሥታት በቅርበት ክትትል የተደረገበት ሕዝበ ውሳኔ፤ 99.8 በመቶ የሚሆኑት ኤርትራውያን ነጻነትን እንሻለን ሲሉ ድምጻቸውን ሰጥተዋል። • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ 1998 በሁለቱም ወገን ብዙ ደም ያፋሰሰው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ተቀሰቀሰ። ለሁለት ዓመታት ገደማ በዘለቀው ጦርነት በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሁለቱም ወገን ለሞት ተዳርገዋል። የአልጀርሱ ስምምነት በጦር ግንባር ላይ የነበረውን ጦርነት ያስቁመው እንጂ፤ ለ20 ዓመታት በሁለቱ ሃገራት መካከል ሰላምም ጦርነትም የሌለበት ሁኔታ ውስጥ ቆይተዋል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ በሁለቱ ሃገራት መካከል ቆይቶ የነበረው ቁርሾ ተገፎ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ተጀምሯል። እኛም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አሥመራ አቅንተናል። አሥመራ ቆሻሻ የማይታይባት፤ ጽዱ ከተማ። "ፃዕዳ አሥመራ" ሃገሬው አሥመራን "ፃዕዳ አሥመራ" እያለ ይጠራታል። "ፃዕዳ" በትግርኛ ነጭ ማለት ነው። እውነት ነው አሥመራ ንጹሕ ነች። ቆሻሻ የማይታይባት፤ ጽዱ ከተማ። በእድሜ ጠገብ ህንጻዎች የተሞላችው አሥመራ፤ ከሁለት ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ታሪካዊ ከተማ በመባል የዓለም የቅርስ መዝገብ ላይ ተመዝግባለች። የኤርትራ መዲና አሥመራ ከ1890ዎቹ ጀምሮ የቅኝ ገዢው የጣሊያን ጦር መቀመጫ ሆና ማገልገል ጀምራ ነበር። ቅኝ ገዢው በአሥመራ ጣሊያናዊ በሆነ የሥነ-ሕንጻ ጥበብ ስልት ግንባታዎች ማከናወን ጀመረ። • ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት በወቅቱ ቅንጡ የሆኑ ለመንግሥት አገልግሎቶች የሚውሉ ህንጻዎች፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ሆቴሎች እና የሲኒማ ቤቶች ግንባታ ተከናውነዋል። ከ1893 እስከ 1941 ድረስ የተገነቡት እነዚህ ህንጻዎች ዘመን ተሻግረው ዛሬ ላይ ታሪክን ያስታውሳሉ። የነዋሪው ቆሻሻን የመጠየፍ ባህሪ ካለው የፍሳሽ ማስወገጃ ሥርዓት ጋር ተደማምሮ ከተማዋን ንጹህ አድርጓታል። ጎዳናዎቿ ንጹሕ ናቸው። ስለዚህም የአፍንጫን ሰላም የሚነሳ ጠረን በአሥመራ ከተማ አልገጠመንም። በጥንቃቄ በመስመር የተተከሉት ዘንባባ እና 'ሽባካ' ተክሎች ሌላኛው የከተማዋ ውበት ናቸው። ቅኝ ገዢዎቹ ጣሊያኖች በአሥመራ አሻራቸውን ጥለው ካለፉባቸው ነገሮች አንዱ የፍሳሽ አወጋገድ ሥርዓት ግንባታ አንዱ ነው። ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች በከተማዋ ጎዳናዎች ሥር ተገንብተው እንደሚገኙ ከነዋሪዎች ሰምተናል። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ከተማዋ ጠዋት ከሥራ ስዓት በፊት ትታጠብ እንደነበርም ተነግሮናል። ይህ ብቻም አይደለም፤ በአሥመራ ሲጓዙ ቢያድሩ አባ ከና የሚልዎ አይኖርም። ሃገሬውም ሆነ የውጪ ዜጋው ከመሸ እንደፈቀደው በእግሩ ይጓዛል። በአሥመራ አንድ ምሽት እንዳሳለፉ ስለከተማዋ ሰላማዊነት ሌላ እማኝ አያሻዎትም። • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች ትሮቪላ፣ ፍራንሲስኮ፣ ዳንተ፣ ቪሊያጆ፣ ሳንታ ዓና፣ ቦላጆ . . . እኚህ ስሞች በሃገረ ጣሊያን የሚገኙ የከተማ ስሞች አይደሉም፤ የአሥመራ ሰፈሮች መጠሪያ እንጂ። የአሥመራ ሰፈሮች ብቻ አይደሉም፤ ብዙ የአሥመራ ካፍቴሪያዎችና ምግብ ቤቶች ጨምር መጠሪያቸውን ያገኙት ከጣሊያን ቋንቋ ነው። ሌላኛው የአሥመራ ውበት በጥንቃቄ በመስመር የተተከሉት ዛፎች ናቸው። ዘንባባ እና 'ሽባካ' ተብሎ የሚጠራው ዛፍ ለከተማዋ ልዩ ገጽታን አጎናጽፏታል። የብሌን ብሄርሰብ ተወላጆች (ግራ) የአፍር ወጣት እየጨፈረች (ቀኝ) ኤርትራ ኤርትራ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምሥራቅ ከጅቡቲ፣ በምዕራብ ከሱዳን፣ በምሥራቅ በኩል ደግሞ ከቀይ ባሕር ጋር ትዋሰናለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ የህዝብ ብዛት ወደ 5 ሚሊዮን ይገመታል ይላል። ወደ 400 ሺህ የሚጠጉት ደግሞ መኖሪያቸውን በመዲናዋ አድረገዋል። • ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አሥመራ ካቀኑ እነሆ አንድ ዓመት፤ ምን ተለወጠ? በስድስት ዞኖች የምትከፋፈለው ኤርትራ፤ ትግር፣ ትግርኛ፣ አፋር፣ ኩናማ፣ ብሌን፣ ሳሆ እና ራሻይዳን ጨምሮ እውቅና የሚሰጣቸው 9 ብሔሮች ኖሩባታል። በኤርትራ የሚገኘው አፋር በጅቡቲ እና ኢትዮጵያ ጋር ከሚኖሩት አፋሮች ጋር ተመሳሳይ ቋንቋ እና ባህል አላቸው። የራሻይዳ ሴት ከአምስት ዓመቷ ጀምሮ ከዓይኗ በስተቀረ የተቀረ ፊቷን በደማቅ ጨሌ ባማረ ጨርቅ ትሸፍናለች። ከተቀሩት የኤርትራ ብሔረሰቦች በመልክ እና በአኗኗር ዘዬ ለየት የሚሉት የራሻይዳ ህዝቦች ናቸው። መነሻቸው ሳዑዲ አረቢያ እንደሆነ የሚነገርላቸው ራሻይዳዎች አረብኛ ቋንቋ ተናገራሪዎች እና የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ናቸው። አርብቶ አደር እና ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚገቡ ሸቀጣ ሸቀጦችን በጭነት መኪና በመነገድ የሚታወቁት ራሻይዳዎች ቀይ ባህርን ተከትለው በኤርትራ በረሃማ ቦታዎች ላይ ይኖራሉ። • የአሥመራን ጎዳናዎች በፎቶ የራሻይዳ ሴት ከአምስት ዓመቷ ጀምሮ ከዓይኗ በስተቀር የተቀረ ፊቷን በደማቅ ጨሌ ባማረ ጨርቅ ትሸፍናለች። የሰዓት እና ቀን አቆጣጠር አገልግሎት ፍለጋ አርፍደው በደረሱበት ስፍራ "ነገ ጠዋት 8 ሰዓት ላይ ኑ" ልትባሉ ትችላለችሁ። ኤርትራዊያን ሰዓት የሚቆጥሩት ልክ እንደ ምዕራባውያኑ ነው። የቀን አቆጣጠር ሥርዓታቸውም ቢሆን እንደ ጎርጎርሳዊያኑ ነው። የኤርትራ መገበያያ ገንዘብ ናቅፋ ባለ 1፣5፣10፣20፣50 እና 100 ኖቶች አሉት። መገበያያ ገንዘብ የኤርትራ መገበያያ ገንዘብ ናቅፋ ይባላል። ባለ 1፣5፣10፣20፣50 እና 100 ኖቶች አሉት። አንድ የአሜሪካ ዶላር በ15 ናቅፋ በሕጋዊ መንገድ ይመነዘራል። በኤርትራ ዶላር በጥቁር ገበያ ላይ ለመመንዘር መሞከር ቀይ መስመር እንደማለፍ ከባድ ጥፋት ነው። ዶላር መመንዘር የሚቻለው በብቸኛው የኤርትራ ንግድ ባንክ ብቻ ነው። በአሁኑ ወቅት በባንክ እና በጥቁር ገበያ ላይ ያለው ልዩነት ሰፊ አይደለም። አንድ ዶላር በጥቁር ገብያ ላይ 17 ናቅፋ ብቻ ነው የሚመነዘረው። ሁነኛ የትራንስፖርት አማራጭ ብስክሌቶች ቢሆኑም፤ አውቶብሶች እና ቢጫ ታክሲዎችም ደንበኞቻቸውን ከቦታ ቦታ ያመላልሳሉ። የትራንስፖርት አማራጮች እንደ ዝርግ ሳህን ለጥ ባሉት የአሥመራ ጎዳናዎች ነዋሪው ብስክሌቶች እንደ ሁነኛ የትራንስፖርት አማራጭ የመረጠ ይመስላል። ትልቅ ትንሹ በብስክሌት ሽር ይላል። ቦርሳ በጀርባቸው ያነገቡ ታዳጊዎች በብስክሌት ወደ ትምህርት ቤት ያቀናሉ። ሰራተኛው ጉዳዩን ለመፈጸም በብስክሌት ይንቀሳቀሳል። አውቶብሶች እና ቢጫ ታክሲዎችም ደንበኞቻቸውን ከቦታ ቦታ ያመላልሳሉ። • የዛሬ 30 ዓመት... የኮ/ል መንግሥቱ አውሮፕላን ለምን አልጋየም? በኤርትራ አነስተኛ ደሞዝ፣ ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ መኪኖች ላይ የሚጫነው ከፍተኛ ግብር እንዲሁም ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ተደማምረው የግል መኪና ባለቤት መሆንን ከባድ ያደርጉታል። በዚህም በከተማዋ የሚስተዋሉት የተሽከርካሪዎች ቁጥር እጅግ አነስተኛ የሚባል ነው። ለመኪኖች በቅደም ተከተል የሚሰጠውን የሰሌዳ ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በኤርትራ የሚገኙ የግል መኪኖች ብዛት ከ40ሺህ እንደማይዘሉ ማስላት ይቻላል። አሥመራ የትራፊክ መጨናነቅ የማያቃት ከተማ በመሆኗ "ትራፊክ አልባዋ መዲና" የሚል ስያሜ ተሰጥቷታል። ወደየትኛውም አቅጣጫ መኪና ይዘው ቢንቀሳቀሱ በሌሎች የአፍሪካ ከተሞች የሚያስተውሉትን አይነት የትራፊክ መጭናነቅ አይመለከቱም። ፒዛ ወይስ ላዛኛ? የሚበላ ፍለጋ ወደ አንዱ ሬስቶራንት ጎራ ቢሉ፤ በምግብ ዝርዝር አማራጭ ውስጥ በቅድሚያ ተዘርዝረው የሚመለከቱት እነ ፓስታ፣ ላዛኛ እና ፒዛን የመሳሰሉ ምግቦችን ነው። ኤርትራዊያን የሚያሰናዱት ፓስታ እና ፒዛ እጅግ ድንቅ ጣዕም አላቸው። እንጀራ ከከጀሉ እንዲሁ በቀላሉ የሚያገኙት ሳይሆን "ባህላዊ ምግብ" የሚያዘጋጅ ምግብ ቤት መፈለግ ግድ ይልዎታል። የአሥመራ መስህብ ስፍራዎች እግር ጥሎዎት ወደ አሥመራ ካቀኑ ከተማዋ ለእንግዶቿ ጀባ ከምትላቸው በርካታ የመስህብ ስፍራዎች ቢያንስ የሚከተሉትን ሳይመለከቱ አይመለሱ። የሥነ-ሕንጻ ባለሙያው ፊያትን ለመገንባት እቅዱን ለአከባቢው መስተዳድሮች ሲያቀርብ፤ '15 ሜትር ርዝመት ያላቸው ክንፎች ያለድጋፍ ማቆም አይቻልም' በማለት እቅዱን ውድቅ ተደርጎበት ነበር። ፊያት ታግሊኤሮ ተገንብቶ የተጠናቀቀው እአአ 1938 ሲሆን የነዳጅ ማደያ፣ ጋራዥ እና የመኪና እጥበት አገልግሎት ይሰጥበት ነበር። ከታሪካዊነቱ በተጨማሪ ይህን በአውሮፕላን ክንፍ ቅርጽ የተገነባን ግንባታ ለየት የሚያደርገው፤ ወደ ጎን 15 ሜትር የሚረዝሙት ክንፎቹ ያለ ምሶሶ መቆማቸው ነው። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኤርትራ ውስጥ መኪና ሲያሽከረክሩ የሚያሳየው ቪዲዮ ፊያት የተገነባው በጣሊያኒያዊው የሥነ-ሕንጻ ባለሙያ ጁሴፔ ፔታዚ ሲሆን፤ አስጎብኚዎች ስለዚህ ህንጻ ግንባታ አንድ አስደናቂ ታሪክ ይናገራሉ። የሥነ-ሕንጻ ባለሙያው ጁሴፔ ፊያትን ለመገንባት ሃሳቡን ለአካባቢው መስተዳድሮች ባቀረበላቸው ወቅት፤ '15 ሜትር ርዝመት ያላቸው ክንፎች ያለድጋፍ ማቆም አይቻልም' በማለት እቅዱን ውድቅ አደርገውበት ነበር ይላሉ። በዚህ የተበሳጨው ጁሴፔ 'ይሄ ግንባታ ከፈረሰ እራሴን አጠፋለሁ' ብሎ ዝቶ ንድፉን ከልሶ ቋሚ ድጋፎችን ያስገባ በማስመሰል ግንታውን መጨረሱ ይነገራል። ፊያት በወቅቱ ከአሥመራ ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ እና የወደብ ከተሞች ለሚያቀኑ መኪኖች ነዳጅ የሚሞሉበት ብቸኛው ስፍራ ነበር። ዛሬ ላይ ከ80 ዓመታት በኋላ አገልግሎት ሳይሰጥ ብቻውን ተትቶ ቆሞ ይገኛል። አሥመራ የቅንጡ የሲኒማ፣ የቲያትር ቤቶች፣ የሬስቶራንቶች እና ካፍቴሪያዎች መገኛ ከተማ ነበረች። አሥመራ ዛሬ ላይ ሲያጤኗት ጭር ያለች ከተማ ናት። ከብዙ አስርት ዓመታት በፊት የነበራት ገጽታ ግን ሌላ ነበር። ቅንጡ የሲኒማና የቲያትር ቤቶች እንዲሁም የሬስቶራንቶች እና ካፍቴሪያዎች መገኛ ከተማ ነበረች። ዛሬ ላይ ባዷቸውን የቀሩት እነ ሲኒማ ሮማ፣ ሲኒማ ካፒቶል፣ ኦዲዮን ሲኒማ እና ሲኒማ አሥመራ ለዚህ እማኝ ናቸው። በ1920ዎቹ እና 30ዎቹ የተገነቡት እነዚህ ሲኒማ ቤቶች፤ በዘመናቸው አሉ የተባሉ የእንግሊዝኛ እና ጣሊያንኛ ፊልሞች የሚታዩባቸው ነበሩ። አሁን ላይ ገሚሱ ባዶውን ቀርቷል፤ የተቀሩት ደግሞ ሃገር በቀል ፊልሞችን እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ያሳያሉ። በተለያዩ ወቅቶች በኤርትራ በተደረጉ ጦርነቶች ከጥቅም ውጪ ሆኑ የጦር ተሽከርካሪዎች በአንድ ሥፍራ ተሰብስበው ይገኛሉ። በተለያዩ ወቅቶች በኤርትራ የተደረጉ ጦርነቶች ምን ያክል አስከፊ እንደነበሩ ይህን ስፍራ በመጎብኘት መገንብ ይቻላል። በዚህ "ታንክ ግሬቭ ያርድ" (የታንክ የመቃብር ቦታ) ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በጦርነት የወደመ የጦር ተሽከርካሪ አይነት አንድም የቀረ አይመስልም። ከታንክ እስከ አየር መቃወሚያ፤ ከአውቶቡስ እሰከ መድፍ፤ ብቻ ሁሉም አይነት ተቃጥሎ እና ወላልቆ በአንድ ቦታ ላይ ተሰብስበው ይገኛሉ። ቀረብ ብለው ሲመለከቱ የወደሙትን የተሽከርካሪ አካላት መኖሪያ ቤታቸው ያደረጉ ሰዎችን ያስተውላሉ። በቅኝ ግዛት ወቅት ህይወታቸው በኤርትራ ያለፈ ጣሊያውያን ይቀበሩ የነበረበት ሥፍራ። በቅኝ ግዛት ወቅት ህይወታቸው በኤርትራ ያለፈ ጣሊያዊያን ይቀበሩ የነበረበት ሥፍራ ነው። በጥሩ ሁኔታ ተይዞ የሚገኘው ይህ የመቃብር ስፍራ አሁንም ድረስ ከጣሊያን ድረስ እየመጡ በዘመዶቻቸው የመቃብር ላይ የአበባ ጉንጉን የሚያኖሩ ሰዎች እንዳሉ ይነገራል። ካቴድራል ቤተክርስቲያን፣ ሲኒማ ሮማ፣ እንዳ ማርያም ቤተክርስቲያን እና ሌሎች የጣሊያን ቅኝ ግዛት ዘመን የሥነ-ሕንጻ ጥበብ ያረፈባቸው የሚጎበኙ ታሪካዊ ስፍራዎችም በአሥመራ ይገኛሉ።
news-49672584
https://www.bbc.com/amharic/news-49672584
“በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማርን ዛሬም፣ ነገም፣ ወደፊትም የምከራከርበት ነው” ገነት ዘውዴ [ዶ/ር]
አዲሱን ዓመት አስመልክተን ከመገናኛ ብዙኃን ጠፍተው የቆዩ ሰዎችን ማፈላለጋችንን ቀጥለናል። አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ ሲነሳ ስማቸው አብሮ የሚነሳውን ገነት ዘውዴ [ዶ/ር]ን ፈልገን አግኝተናቸዋል።
ገነት ዘውዴ [ዶ/ር] በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 'ቴክኒካል ቲቸርስ ኤዱኬሽን' በረዳት መምህርነት አገልግለዋል። በዚያው ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር፣ መምህር፣ የቢዝነስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል። በቦስተን በንከር ሂል ኮሚዩኒቲ ኮሌጅ በትምህርት ክፍል የሥራ ልምምድ እንዳደረጉም መረጃዎች ያመለክታሉ። • "የሞራል ባቢሎን ውስጥ ነን፤ በጎና እኩይ መለየት አቅቶናል" ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ • ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች ከ1993 ዓ.ም በፊት ባሉት ጊዜያት በኬንያ፤ ኬንያታ ዩኒቨርሲቲ 'External examiner' [ከሌላ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ፈታኝ] ሆነው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ምክትል ሚንስትር፣ ከዚያም ከ1992 በኋላ በትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ሠርተዋል። በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደርም ነበሩ። የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪያቸውን በቢዝነስ ትምህርት ከአሜሪካ አገር አግኝተዋል። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኒው ሃምፕሸር ፤ ሁለተኛ ድግሪያቸው ሰፎክ ዩኒቨርሲቲ- ቦስተን ነው ያጠናቀቁት። ሦስተኛ ድግሪያቸውን ከሕንድ አገር ጃዋህራል ኔህሩ ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነት አግኝተዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የመጀመሪያዋ ሴት ሚንስትርም እንደነበሩ ገልፀውልናል። ገነት ዘውዴ [ዶ/ር] ሁለት መጻሕፍትን ጽፈዋል። አንዱ በሴቶች ላይ፣ ሌላው ደግሞ በትምህርት ፖሊሲው ላይ የሚያተኩር ነው። የመጀመሪያው Resistance, freedom and Empowerment: The Ethiopian women struggle [የኢትዮጵያ ሴቶች ትግል] የሚል ሲሆን በአማርኛ ተተርጉሟል። ሁለተኛው መጽሐፍ ወደ አማርኛ ባይመለስም ከሁለት ዓመታት በፊት ነው የወጣው። No One Left Behind የሚልና ስለ ትምህርት ፖሊሲው የሚያትት ነው። ከርሳቸው ጋር ያደረግነውን አጭር ቆይታ እነሆ። አሁን ምን ላይ ነው ያሉት? ምን እየሠሩ ነው? አሁን ጡረታ ወጥቻለሁ። ጡረታ ከወጣሁ ሦስት ዓመት ሆኖኛል፤ ነገር ግን ጡረታ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ 'የሴቶች ልማታዊ ስትራቴጅክ ሴንተር' አቋቁሜ እዚያ ላይ በጥናት እና የቅስቀሳ ሥራ እየሠራሁ ነው። ተቋሙ ምንድን ነው የሚያከናውነው? በዝርዝር ይንገሩኝ እስኪ. . . በሴቶች ሕይወት ዙሪያ ጥናቶች እያደረኩ ነው። አንዳንድ ጊዜ ሥልጠናም እንሰጣለን- የአመራርነትና የሥራ ፈጠራ ሥልጠናዎች አሉት። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሚዲያም የቅስቀሳ ሥራ እንሠራለን - ስለ ሴቶች ሕይወት። በሚዲያ ላይ የሚተላለፍ ፕሮግራም ነበረዎት ልበል? አዎ፤ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ነበረኝ። እናንተም ቢኖራችሁ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር። 'የሕይወት ወግ' የሚል በዋልታ ቴሌቪዥን የሚቀርብ ነበር። ነገር ግን በ'ስፖንሰር' [የገንዘብ ድጋፍ] መቋረጥ ምክንያት አሁን ተቋርጧል-ለትንሽ ጊዜ። በጣም ጥሩ ፕሮግራም ነበር። ከአንድ ዓመት በላይም ተላልፏል። በፕሮግራሙ በሴቶች ሕይወት ዙሪያ ውይይቶች ነበሩ። የተለያዩ የሴቶችን ጉዳዮች እያነሳን ነበር የምንወያየው። በድህነት ምክንያት ቀረ። • ትምህርት ዕድሜን እንደሚያስረዝም በጥናት ተረጋገጠ በትምህርቱ ዘርፍ ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋልና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚሠሩት አለ? ይሄ አይበቃኝም እንዴ በዚህ ዕድሜ? [ዘለግ ያለ ሳቅ] ይሄ በጣም ብዙ ሥራ ነው። በጣም ብዙ ጥናት፣ ሥልጠና፣ ቅስቀሳ አለው. . . ለአሮጊት ይሄ አነሰው ብለሽ ነው?. . . [ሳቅ] ዕድሜዎ ስንት ነው ዶክተር? ዕድሜ አይጠየቅም ይባላል። ግን. . . ግድ የለም። አሁን እኔ ባል ስለማልፈልግ ግድ የለም። [ሳቅ] 71 ዓመቴ ነው። አማካሪ ሆነው የሠሩበት አጋጣሚ አለ? አይ የለም። ምክር ለጠየቀኝ ሰው ግን እሰጣለሁ። ስለ ልጅነት፣ ስለ ሴትነት፣ ስለ አሮጊትነት ምናምን. . . የትምህርት ፖሊሲው ከእርስዎ ጊዜ ጀምሮ እንደተዳከመ ይወራል፤ እርስዎም ላይ ትችት ሲቀርብ ይሰማል። እንዲያውም እርስዎ ሚንስትር በነበሩበት ጊዜ በተቀረፀው ፖሊሲ እየተማሩ ያሉት ትውልዶች 'የገነት ዘውዴ ልጆች' የሚል ተቀፅላ ወጥቶላቸዋል። እርስዎ ይሰማሉ ስለዚህ? እሰማለሁ፤ ግን የለሁበትም። ከትምህርት ሥርዓቱ ከወጣሁኝ ዐሥር ዓመታትን በሕንድ ዲፕሎማት ነበርኩ። አሁን ጡረታ ከወጣሁ ሦስት ዓመቴ ነው። ስለዚህ ከትምህርት ሥርዓቱ 13 ዓመታት ተለይቻለሁ። እናም. . . እሰማለሁ ግን በዚህኛው ሥራ ሴቶች ላይ ስለማተኩር ብዙም እንትን አላልኩም. . . መስማቱን ግን እሰማለሁ። ሲሰሙ የሚሰጡት ምላሽ ምንድን ነው? ያው እንግዲህ. . . ጊዜ ኖሮኝ ቁጭ ብየ የሚባለው ነገር እውነት ነው፤ አይደለም? ምንድ ነው ችግሩ? ብዬ ባጠናው ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን አላጠናሁትም። ወደ ፊት ለማጥናት አላሰቡም ? እሱ እንግዲህ. . . እንዴ! እኔ አኮ አርጅቻለሁ [ ሳቅ] ምን ማለትሽ ነው? የተሰማኝን. . . ትምህርት ፖሊሲው ምን እንደነበር፣ እንዴት እንደነበር ጽፌያለሁ። ከዚያ በኋላ የፈለገ ሰው ያንን እየጻፈ ደግሞ ይቀጥል። ሁል ጊዜ አንድ ሰው ላይ ብቻ አይደለም መቀባበል። አለ አይደል. . . የድምፅዎ ጉልበት ግን እርጅና ላይ ያሉ አይመስሉም? [ሳቅ] . . . ስለዚህ እኔ የሚሰማኝን መጽሐፍ ላይ አስቀምጫለሁ። ከዛ በኋላ ደግሞ እየተቀባበሉ፤ ያንን እያስተካከሉ፤ እየተቀባበሉ መሄድ ደግሞ የአዲሱ ትውልድ ነው። አንድ ሰው ብቻ መሆን የለበትም። አይመስልሽም? ከዚሁ ከትምህርት ፖሊሲ ሳንወጣ፤ ሚንስትር በነበሩበት ጊዜ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ሐሳቡን ያመጡት እርስዎ ነዎት ይባላል። እዚህ ላይ ምን ይላሉ? ይሄ እኮ እኔ ዝም ብዬ በጭንቅላቴ ያመጣሁት አይደለም። የዩኔስኮ፣ የዓለም አቀፍም ትኩረት ነው። ትምህርት እየተስፋፋ፣ ዘመናዊ እየሆነ በመጣ ቁጥር በጣም ብዙ ምርምሮች ይወጣሉ። እናም ልጆች መጀመሪያ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ነው መማር ያለባቸው። ትምህርት ደግሞ ማሰብን ፣ ማሰላሰልን ይጠይቃል። የሰው ልጅ የሚያስበው . . . የሚያሰላስለው በአፍ መፍቻ ቋንቋው ነው። በመሆኑም ይህ የዩኔስኮም፣ የዓለም አቀፉም እንትን ነው... ገነት ስብሰባ ላይ ዱብ ያደረገችው አይደለም። በወቅቱ ብዙ እንደተሟገቱ ስለሰማሁ ነው. . . በጣም በጣም!. . . አሁንም ቢሆን ነገም ከነገ ወዲያም እሟገታለሁ። ልንገርሽ አይደል? እኔ አንደኛ ደረጃም አይደለም፤ ሁለተኛ ደረጃም እንደዚያ እንዲሆን ከአሁኑ ጀምረን እያሰብን. . . የቋንቋ አካዳሚዎችን እያቋቋምን ምን እያልን ዩኒቨርሲቲዎችም በቋንቋቸው እንዲሆን ብዬ አምናለሁ [የሕንድን ተሞክሮ ያነሳሉ] እንዲህ መሆኑ ችግሮች የሉትም ብለው ያስባሉ? አዎ! ችግሮች ይመጣሉ። ችግር የሌለው ነገር አለ አንዴ? ችግር እየፈታን እንሄዳለን እንጅ፤ ችግር ይመጣል ብለን ከችግር አንሸሽም። ቋንቋ የማንነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን. . . ወደ ትምህርት ፣ ወደ ሳይንስ ስንሄድ በጣም ትልቅ መሣሪያ ነው። እኔ ዛሬም ፣ ነገም፣ ከነገ ወዲያም የምከራከርበት ነው። በእኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ እንዲህ መሆኑ አይለያየንም? ለጋራማ፤ የጋራ ቋንቋ አለን እኮ! የፌደራል ቋንቋው አማርኛ እና እንግሊዝኛ ነው። ትምህርት ላይ ሲሆን ግን በእንግሊዝኛ ቋንቋም አይደለም. . . ። እስከ አምስት ስድስት ዓመቱ በቋንቋው ሲቦርቅ የነበረን ልጅ አምጥተሽ፤ አንደኛ ክፍል አስገብተሽ በሌላ ቋንቋ ተማር ስትይው ፍትሃዊ ነው? የፍትሃዊነት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን...ይገባዋል? እና . . . ቀላል ነገር አይደለም። በጣም ከቋንቋው ጋር የተያያዘ ነው። እኔ . . . እንደ ቀላል ለምን እንደሚያዩት አይገባኝም። ስለዚህ ነገም ከነገ ወዲያም የምከራከርበት ጉዳይ ነው። እስኪ አሁን ደግሞ፤ የግል ሕይወትዎን ያጫውቱኝ? የሁለት ሴቶች ልጆች እናት ነኝ። አሁን ደግሞ ሁለቱ ሴት ልጆቼ የሦስት ልጆች አያት አድርገውኛል። በግል ሕይወቴ በጣም ደስተኛ ነኝ . . . ያው ትዳር ፈት እንደሆንኩ ታውቂያለሽ ብዬ ነው። [ሳቅ] ግን በጣም ደስተኛ ነኝ። ከልጆቼ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ። በተለይ ከልጅ ልጆቼ ጋር. . . በቃ ፍቅር ይዞኝ . . . ፍቅር ወደታች አይደል? ከእነሱ ጋር ነው ትርፍ ጊዜዬን የማሳልፈው። በሕይወት ያሉ ጓደኞቼም አሉ ከእነርሱም ጋር . . .እ . . . ማንበብ እወዳለሁ፤ አነባለሁ. . . ይሄ ነው የግል ሕይወቴ። ምን ዓይነት መጽሐፍ ነው የሚያነቡት? ማንኛውንም። በኢትዮጵያ የተጻፉም በዓለም ላይ ያሉ. . . የኢኮኖሚ፣ የትምህርት ምናምን. . . ድሮ ወጣት ሆኜ ልብ ወለድ ነበር የምወደው፤ አሁን ግን ጠንከር ያሉ መጻሕፍትን. . . ልብ ወለድ ድሮ ልጅ እያለሁ እወድ ነበር፤ አሁን ግን አረጀሁ [ሳቅ] ግን ምርጫዎ የማን ነበር? በእኛ ግዜ አጋታ ክርስቲ፣ ዳኔላ ስቲል፤ ከኢትዮጵያ ደግሞ ፍቅር እስከመቃብርን ። ፍቅር እስከ መቃብርን ሦስት ጊዜ አንብቤዋለሁ። ሦስት ጊዜም ሳነበው አዳዲስ ነገር አግኝቸበታለሁ። ኦሮማይ ፣ ወንጀለኛው ዳኛ. . . ድሮ አያቴ መጽሐፍ ታነብ ነበር፣ እናም መጽሐፍ ማንበብ ያስተማረችኝ እርሷ ናት። ሙዚቃስ? ሙዚቃና እስክስታማ በጣም እወዳለሁ። እስክስታው አለ። አሁን ግን እያረጀሁ ጉልበቴም እየቀነሰ ብዙም አይደለሁ። ግን አሁንም ቢሆን ሙዚቃ ከሰማሁ ነሸጥ ያደርገኛል። እነ አስቴርን፣ ብዙዬን፣ ጥላሁን ገሠሠን እና በተለይ ደግሞ የበዛወርቅን ግጥሞቿን በጣም እወደዋለሁ። በተለይ አንድ ግጥም አላት መጽሐፌም ላይ ጠቅሸዋለሁ። '. . . የማነሽ ይሉኛል የማን ልበላቸው፣ ብቻየን ብቀርስ ምን አስጨነቃቸው. . .' የሚለውን። የተለየ ምክንያት አለው እንዴ? ለምን መሰለሽ . . . እኔ ከሴት ልጅ ጋር ነው የማያይዘው። ሁልጊዜ ሴት . . . የማነሽ? 'የሰው ነሽ' ነው እኮ። ዕቃ ነሽ ነው፤ የወንድ ዕቃ ነሽ ነው እኮ። ድምጿንም እወደዋለሁ። ከአዳዲሶቹ ቴዲ አፍሮ ደስ ይለኛል።
49848883
https://www.bbc.com/amharic/49848883
ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት
ኢማም ናቸው። የዩኒቨርስቲ መምሕር። የስድስት ልጆች አባት። ሼህ ካሚል አሊዩ ቃሲም።
ሼህ ካሚል አሊዩ ቃሲም እና ልጃቸው ረመዳን ካሚል የመጀመሪያ ልጃቸው ረመዳን ካሚልን ትምህርት ቤት ሊያስመዘግቡ ሲሄዱ እርሳቸውም አብረው ለመማር ወሰኑ። የምድር የሰማይ ፈጣሪ ምስጋናዬን እንካ፣ የልጄ አንደበት ፊደል ጠራ፣ እጁ ወረቀት ነካ ብለው ብቻ አልቀሩም። አብረውት ፊደል ቆጥረው፣ ዩኒቨርስቲ ገብተው ተመርቀዋል። እንዴት? ሼህ ካሚል የባሌ ጎባ ነዋሪ ናቸው። ከወ/ሮ ዘሀራ ሙሐመድ ጋር ተጋብተው ካፈሯቸው ልጆች መካከል ረመዳን ካሚል አሊዩ ለአቅመ ፊደል ሲደርስ ደብተር፣ ቦርሳ ገዝተው፣ እርሳስ ቀርፀው፣ የደንብ ልብስ አሰፍተው ተዘጋጁ። የነሐሴ ዝናብ አለቅ ብሎ እኝኝ. . . ቢልም እርሳቸው ልጃቸውን ለማስመዝገብ ወደ ቱሉ ዲምቱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አመሩ። ያኔ ቱሉ ዲምቱ እስከ ስድስተኛ ክፍል ድረስ ብቻ ነበር የሚያስተምረው ይላል ረመዳን። • የመስቀል ደመራ አከባበር ውዝግብ በቢሺፍቱ ከተማ • የደመራ አከባበር ከኢትዮጵያ እስከ ኬንያ ከዚያ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ስፍራው ላይ ለሚገኙት መምህራን የልጃቸውን ስም ነገሩ። ሼህ ካሚል በአካባቢው የታወቁ የሀይማኖት አባት ናቸው። ማንም ያጠመደ የማያጣቸው ደግሞ ሲቲ ካፌ ነው። ጎባ አለኝ የምትለው ካፌ ሳይሆን አይቀርም። ስለዚህ ከመምህራኖቹ ጋር ሰላምታ እየተለዋወጡ፣ እየተቀላለዱ ልጃቸውን አስመዝግበው ሲጨርሱ "እስኪ በዚያው ካሚል አልዩ በልና ፃፍ" አሉት መዝጋቢውን መምህር። "መዝጋቢው ሳቀ" ይላሉ ሼህ ካሚል። ለመማር ፈልገው እንዲመዘግቧቸው መጠየቃቸውን ያመነ አልነበረም። ሼሁ ግን "ቀለም ሀቀኛ ነው። ዝም ብላችሁ ስሜን ፃፉ" አሉ። አሁንም የመዝጋቢዎቹ ሳቃቸው ተራዘመ እንጂ ያመናቸው የለም። እንዲያውም "በሉ ሥራ አያስፈቱን፤ በኋላ ተገናኝተን ሻይ እንጠጣለን። አሁን ይሂዱ" እንዳሏቸው ያስታውሳሉ። እኚህ በአካባቢው ባለ መስጂድ በኢማምነት የሚታወቁ አባት፣ በጎባ የአገር ሽማግሌነት የተከበሩ ሰው፤ ልማር ብለው ፈትረው መያዛቸው መምህሮቹን ስለከበዳቸው መዘገቧቸው። "ፎቶ ይዘዋል?" ተጠየቁ። ሰጡ። የእርሳቸውንም የልጃቸውንም መመዝገብ የሚያሳይ ብጣቂ ወረቀት ይዘው ወደ ቤታቸው ተመለሱ። አንደኛ ክፍል ገቡ! ይህ የሆነው በ1993 ዓ. ም. ነው። ትምህርት የተጀመረ ዕለት እርሳቸውም ልጃቸውም ደብተራቸው ሸክፈው የትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ሲደርሱ፤ መምህር አለማየሁ ግቢ ውስጥ ይንጎራደዳሉ፤ መምህሩ የእንግሊዘኛ አስተማሪ መሆናቸውን ሼሁ ያውቃሉ። • ፌስቡክ 'የላይክ' ቁጥርን ማሳየት ሊያቆም ነው • ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በእንግሊዝ የክብር ማስታወሻ ምልክቶች ተቀመጠላቸው "ልጅ ይዘው መጡ ሼኪ?" አሉ መምህር አለማየሁ፤ እርሳቸውም እንደዋዛ "ልጅም አመጣሁ፤ ራሴም መጣሁ" ሲሉ መለሱ። የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ገብተው፣ መምህሩም በስፍራው ተሰይሞ በሩ ተዘግቶ ነው የደረሱት። በሩን ሲቆረቁሩ መምህር አለማየሁ ልጁን ትተው እንዲሄዱ ነገሯቸው። "አይ እገባለሁ" ቢሉም መምህሩ ግን "ሲቲ ካፌ እንገናኝ፤ አሁን ልጁን ትተው ይሂዱ" አሉ። እርሳቸውም ልጃቸውም የተመዘገቡበትን ወረቀት አሳይተው ገቡ። ሼህ ካሚል አሊዩ ቃሲም እና ልጃቸው ረመዳን ካሚል በአርባ ምንጭ ሲዝናኑ ቢቢሲ- ትምህርት ቤት ሲጀመር ወደ ክፍል ሲገቡ የክፍሉ ይዞታ ምን ይመስል ነበር? ሼህ ካሚል- ክፍሉ አቧራ ነው። እኔ በሕፃናቱ መካከል ስታይ ግመል ነው የማክለው። ክፍሉ ውስጥ መምህሩ ወረቀቴን አይቶ ስገባ ተማሪዎቹ ተነስተው "Akkam bultan barsiisaa?" አሉኝ። (ሳቅ) የደነገጥኩት ድንጋጤ. . . አቦ. . . ላብ አላበኝ አንተ. . . እንደምን አደሩ መምህር አሉኝ እኮ! (ሳቅ) ያው አንድ ኢብራሂም የሚባል ልጅ አለ። እርሱ ልጅ ቢሆንም ከሌሎቹ ረዥም ስለሆነ የመጨረሻ መደዳ ነበር የተቀመጠው። እርሱ ጋር ሄጄ ተቀመጥኩ። ልጆቹ በሞላ ወደ ሠሌዳው ማየታቸውን ትተው እኔን ዞረው እያዩ ክፍለ ጊዜው አበቃ። ቢቢሲ- በእረፍት ጊዜ ከእነማን ጋር ይጫወቱ ነበር? ጓደኛ ነበርዎ? ሼህ ካሚል- በእረፍት ሰዓት ወጥቼ የምጫወተው ጓደኛ የለም። አንድ ቶጎና የምትባል ወንዝ አለች። እርሷ ጋር ወርጄ፣ ተጣጥቤ፣ የእረፍት ጊዜዬን እዚያ አሳልፍ ነበር። ጓደኛ ምንም የለም። ቢቢሲ- በስፖርት ክፍለ ጊዜስ ከሕፃናት ጋር መሯሯጥ አልተቸገሩም? ሼህ ካሚል- ያው የስፖርት ነገር ታውቃለህ [ዝላይ አያጣውም]። አንዱ ጎንበስ ብሎ ሌላኛው በእርሱ ላይ ይዘላል። ተሰልፈን ተራዬ ደርሶ ጎንበስ ስል (ሳቅ) አልቻሉም። ተማሪው መዝለል አቅቶታል፤ ትልቅ ሆኜበት። መምህራችን 'Gadi cisaafii Sheekii gadi ciisaafii' አለኝ። ቢቢሲ- ምን ማለት ነው? ሼህ ካሚል- ተኙላቸው ማለቱ ነው። ልጁ መዝለል ስላልቻለ። አንድ ቀን ዩኒፎርሜን ሳላጓድል። የሰልፍ ሥነ ሥርዓት ሳላጓድል። አንድ ቀን አርፍጄ በር ላይ ሳልቆም ነው [ትምህርቴን የጨረስኩት]። ቢቢሲ- ለመሆኑ የኦሮሚያን ሕዝብ መዝሙር ዘምረዋል? ሼህ ካሚል- (በዜማ) Oromiyaa haadha seenaa guddaa. . . [ኦሮሚያ የአኩሪ ታሪክ ባለቤት]. . . እያልኩ ነዋ! መዝሙሩ ቀላል መሰለህ። እንደዚያ እየዘመርን ነው ያሳለፍነው። አንድ የማስታውሰው ነገር አለ፤ ታውቃለህ [መዝሙር ብትል] ዘርፌ ትባላለች የሙዚቃ አስተማሪያችን። ክፍል ውስጥ ሙዚቃ እያዘፈነች ማርክ ስትሰጥ፣ ተራው እኔ ጋር ደረሰ። እኔ ደግሞ መንዙማና ነሺዳ እንጂ ይሄ የሚዘፈነውን አላውቅም። ልታልፈኝ ስትል መምህር እኔም ልበል አልኳት። ቢቢሲ- ሊዘፍኑ ማለት ነው? ሼክ ካሚል- አዎ አስር ማርክ አለው እኮ። "በል" አለችኝ። ተነስቼ፣ ምንም የማላውቀው ሰውዬ [በዜማ] Iyyaaseen iyyoosaa, yuusee taree. . . (ሳቅ) [ይህ ዜማ በዚያ አካባቢ የሚዜም የሕዝብ ዘፈን ሲሆን ትክክለኛው ግጥሙ እንዲህ ነው። Iyyaaseen iyyoosaa kan foolinn shittoodhaa, siyaadeen marookoo] ግጥሙን ዛሬ ድረስ አላውቀውም። መምህሯ እየሳቀች ተማሪዎቹም እየሳቁብኝ ክፍለ ጊዜው አለቀ። ሼህ ካሚል አሊዩ ቃሲም እና ባለቤታቸው የአባትና ልጅ ፉክክር ረመዳን ካሚል ከአባቱ ጋር ሲማር የነበረውን ፉክክር ያስታውሳል። የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሳሉ አባቱ ከክፍሉ መጨረሻ ተቀምጠው ከክፍላቸው ግን ቀዳሚውን ደረጃ ሲይዙ እርሱ "ልጅነት አታልሎኝ በለጠኝ" ሲሉ ሁኔታውን ያስታውሳል። አባትና ልጅ አንድ ክፍል ተምረው፣ አብረው አጥንተው፣ በአንድነት የቤት ሥራ ሠርተው ለፈተና ሲቀመጡ፤ አንዱ ከአንዱ ለመብለጥ ቀን ከሌት ይጣጣሩ እንደነበር ይናገራሉ። • በወለደች በ30 ደቂቃ ውስጥ የተፈተነችው ተማሪ ስንት አስመዘገበች? • "ለስልጣን ተብሎ የሚፈጠር ውህደትን ህወሓት ፈጽሞ አይቀበለውም" አቶ ጌታቸው ረዳ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈትነው ዘጠነኛ ክፍል ጎባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከገቡ በኋላ ግን ታሪክ ተቀየረ። ረመዳን እንደሚለው አባቱ የራሳቸውን የክፍል ጓደኞች አበጁ። እርሱም ጓደኞች አደረጀ፤ ያኔ ፉክክሩ ተሟሟቀ። "እኔ" ይላል ረመዳን፣ "ሒሳብና ፊዚክስ ቶሎ ይገባኛል፤ አባቴ ደግሞ እንዳስረዳው ይጠይቀኛል። አሁን እንደተረዳሁት ትዕግስት የለኝም ነበር። አባቴ 'አንተ ያሳወቅኸውን ለሌሎች ማሳወቅ አትፈልግም እንዴ?' ብሎ የምንጨቃጨቀውን አስታውሳለሁ" ይላል። እርሳቸውም ቢሆኑ ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ ረመዳን የቀዳሚነቱን ደረጃ መያዙን ይመሰክራሉ። እርሱም ይህንኑ ያጠናክራል። አንድ ቀን ማታ ይላሉ ሼህ ካሚል፤ እርሱም ይህንን አጋጣሚ አይረሳውም፤ አብረው ሲያጠኑ አምሽተው ዞር ብለው ሲያዩት አይኑ እንቅልፍ ተኩሏል። አባትነታቸው ያዛቸውና "እንቅልፍህ መጣ" አሉት። እርሱ ግን ትንሽ ልቡ በፉክክር ዳገት ላይ ልትፈርስ ጫና ጫና ትተነፍስበታለች። "አይ" አለ። "ሂድ ተኛ" አሉ ሼህ ካሚል። "እሺ" ብሎ እግሩን እየጎተተ ወደ አልጋው አመራ። ጎኑ አልጋ ቢነካም ልቡ ግን እሺ አላለውም። "በብርድ ልብስ ተሸፍኜ አጮልቄ ስመለከተው እርሱ ቁጭ ብሎ ያጠናል" ይላል ረመዳን ሁኔታውን ሲያስታውስ። ከዚያ በፉክክር ሜዳ ሊበለጥ መሆኑን ሲያስብ እመር ብሎ ተነስቶ ውሃ በሳፋ አድርጎ እግሩን ዘፍዝፎ ማጥናት ጀመረ። ሼህ ካሚል "በነገራችን ላይ እንደዚያ ተነስቶ አጥንቶ በልጦኛል" ይላሉ። በርግጥ ስምንተኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት በማምጣት እርሳቸው ቢበልጡትም፤ 10ኛ ክፍል ግን እርሱ 3.6 ሲያመጣ እርሳቸው 3.4 እንዳመጡ ያስታውሳሉ። ወደ መሰናዶ መሸጋገራቸውን ሲያውቁ ቁጭ ብለው ተመካከሩ። ምክሩ እንዲህ የሚል ነበር። "ከአንድ ቤት በተመሳሳይ ፊልድ ከምናጠና፤ እኔ ማኅበራዊ ሳይንስ አንተ ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ አጥና።" ምክራቸው ሰመረ። ውጤታቸውን አይተው ባቱ ተራራ መሰናዶ ትምህርት ቤት ሲገቡ እንደተመካከሩት በተለያየ ትምህርት ክፍል ተማሩ። በኋላም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጥሩ ውጤት ስላመጡ እርሳቸው መደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ ሲመደቡ እርሱ ደግሞ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ደረሰው። እርሳቸው በማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ሲያጠኑ እርሱ ደግሞ ሀይድሮሊክ ኢንጂነሪንግ ተማረ። እንደው አንተም እርሳቸውም የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሆናችሁ ገንዘብ ላኩልኝ ብለህ የምትደውለው ለአባትህ ነበር? የኛ ጥያቄ ነው ለረመዳን። "እንዴ ታዲያ ለማን እደውላለሁ ብለህ ነው። እናቴ ከየት ታመጣለች" በማለት አባቱ እየተማሩም፣ መስጂድ ውስጥ በማገልገል፤ አነስተኛ ገቢ ያገኙ እንደነበር ያንንም ለቤተሰቡና ለእርሱ በማካፈል እንደተማሩ ያስታውሳል። እርሳቸው በመደወላቡ ዩኒቨርስቲ ሦስት ዓመት ተምረው በ2007 ሲመረቁ፤ እርሱ ደግሞ ገና ሁለት ዓመት ይቀረው ነበር። እርሳቸው ከፍተኛ ውጤት ስላመጡ ዩኒቨርስቲው አስቀርቷቸው እዛው ሁለተኛ ዲግሪያቸውን እንዲያጠኑ ተደረገ። ከዚያም በ2009 ዓ. ም. እርሳቸው ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሲይዙ ረመዳን ደግሞ የመጀመሪያ ዲግሪውን ስለጨረሰ አርባ ምንጭ ድረስ ጋወናቸውን ይዘው ሄደው እንዳስመረቁት ያስታውሳሉ። እኩል ትምህርት ጀምራችሁ ቀደሙህ? ስንለውም፤ "ተቀደምኩ የሚለው ስሜት አለ። ግን እንደምደርስ አውቃለሁ። አባት አይደል? ልጅ አይቀድመውም" በማለት ከሳቀ በኋላ፤ እርሱም የአባቱን ብርታት በመከተል ሁለተኛ ዲግሪውን እየተማረ እንደሆነና በአሁን ሰዓት ለማጠናቀቅ የምርምር ሥራ ላይ መሆኑን አውግቶናል። እንዲህ አባትና ልጅ ሲፎካከሩ የረመዳን ታናናሾችም ብርታት ሰንቀው መጎበዛቸውን ሁለቱም ያስታውሳሉ። ሼህ ካሚል ባለቤታቸውን እንዲማሩ እንደገፋፏቸው ነገር ግን ከስድስተኛ ክፍል በላይ መግፋት እንዳልቻሉ ይናገራል። ረመዳንም ስለ እናቱ "እናታችን ባትኖር እኛ ዛሬ የደረስንበት አንደርስም ነበር። አባቴን ሁሌም የምለው እናቴን ስለመረጥክ አመሰግናለሁ ነው" ይላል። ሼህ ካሚል አሊዩ ቃሲም፣ ልጃቸው ረመዳን ካሚል እና ባለቤታቸው የአባ ጥበቡ ቁምላቸው ምስክርነት አባ ጥበቡና ሼህ ካሚል ጓደኛሞች ናቸው። እርሳቸው የሚያገለግሉት ጎባ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ነው። እውቂያቸው የሚጀምረውም ሁለቱም በሀይማኖት አባትነት በሚገናኙበት ወቅት ነው። ሼህ ካሚል እየተማሩ የጓደኛቸው አለመማር ሲያሳስባቸው "አባ ትምህርት ተምረዋል ወይ? ብለው ጠየቋቸው" ይኼኔ "ለምን ጠየቅከኝ?" ብለው መበሳጨታቸውን አባ ጥበቡ ያስታውሳሉ። እኔ የሐይማኖት አባት የሆንኩት ሳልማር ነወይ? በሚል ቅሬታ ቢገባቸውም፤ ሼህ ካሚል "ዓለማዊ ትምህርት እኮ ነው ያልኩት" አሏቸው ። አባ ጥበቡ፤ "እርሱንስ አልተማርኩም" በማለት ሲመልሱ፤ ሼህ ካሚል ደብተርና እርሳስ ገዝተው፣ ኡርጂ በሬሳ የሚባል ትምህርት ቤት እንዳስመዘገቧቸው ያስታውሳሉ። አሁን ጎባ በሚገኘው እናት ኮሌጅ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆኑት አባ ጥበቡ፤ የሼኪን ውለታ አንስተው አይጠግቡም። "እኔ ኤቢሲዲ ቆጥሬ ይበቃኛል ስል እርሳቸው እለት በእለት እያበረታቱኝ ነው የተማርኩት" የሚሉት አባ ጥበቡ፤ ኦሮምኛ ስለማላውቅ የምማርበት ድረስ እየመጡ ያስጠኑኝ ነበር ይላሉ። ሼህ ካሚል ለአባ ጥበቡ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ትምህርት መቅሰም ምክንያት ሆነዋል። ሼህ ሁሴን ሂፈኑን እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ። "ይኸው እኔን አይቶ መማር ጀምሮ አራተኛ ክፍል ደርሷል" በማለት የእርሳቸው መማር ለሌሎች የብርታት ስንቅ መሆኑን ይመሰክራሉ። ሼህ ካሚል ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ለመሥራት ከፍተኛ ጉጉት እንዳላቸው አጫውተውናል። "እድሉ ከተገኘ አላቅማማም። ጨርቄን ማቄን አልልም" ሲሉም ያላቸውን ቁርጠኝነት ይናገራሉ። ለመሆኑ ዕድሜዎ ስንት ሆነ? የእኛ ጥያቄ ነው። ሀምሳ አይሆነኝም ብለህ ነው? ጥያቄያችንን በጥያቄ መለሱ! ቃለ መጠይቁን ከመቋጨታችን በፊት ዕድሜ ከጤና ይስጥልን አልን!
45180744
https://www.bbc.com/amharic/45180744
የአንቀጽ 39 ጉዳይ! የመገንጠል መብት ለማን? መቼ?
ከሃያ ሦስት ዓመታት በፊት የአህገሪቱ ላዕላይ ህግ ሆኖ የፀደቀው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አዋጅ በውስጡ 106 አናቅፅትን ይዟል።
አቶ ኪያ ፀጋዬ እና አቶ ውብሸት ሙላት ከመነሻውን አንስቶ በሕገ-መንግሥቱ ዙሪያ ተመሳሳይ ህዝባዊ አስተያየት ኖሮ ያውቃል ማለት ቢያዳግትም በ39ኛው አንቀፅ የሰፈሩትን "የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብቶች" ያህል አቋምን የከፋፈለ እና ጭቅጭቅ ያስነሳ የሕገ-መንግሥቱ አካል መኖሩ ያጠራጥራል። ዋነኛው የውዝግብ አስኳል በአንቀፁ ከተካተቱ አምስት መብቶች ቀዳሚ ሆኖ የተቀመጠ ሲሆን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን ገደብ አልባ መብት እንደተጎናፀፉ፤ ይህ መብታቸው ራሳቸውን ከፌዴሬሽኑ ገንጠለው ነፃ አገር እስከማድረግ የሚደርስ መሆኑን ያትታል። በአንድ በኩል አንቀፁን የአገር የግዛት አንድነት ላይ ፈተናን የሚደቅን፣ ፌዴሬሽኑን ከማፅናት ይልቅ መበታተንን የሚጋብዝ እምቅ አደጋዎችን ያቀፈ ጦሰኛ ሃሳብ የተካተተበት ነው እያሉ የሚነቅፉት አሉ። • እኛ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝቦች. . .? • ጥያቄን ያዘለው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያን ብዝሃነት በአግባቡ ለማስተናገድ እንዲሁም መከባበር የሰፈነበትን አብሮነት ለማጎልመስ በአገሪቱ ውስጥ ላሉ ብሔሮች እና ሕዝቦች ራሳቸውን እስከመገንጠል የሚደርስ ዋስትና መስጠት ብልህነት ነው ሲሉ አንቀፅ 39ን የሚያወድሱ ሞልተዋል። በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን "አንቀፅ 39" የተሰኘ መፅሐፍን ለህትመት ላበቁት ለሕግ ባለሙያው አቶ ውብሸት ሙላት፤ በአንቀፁ ዙርያ የሚሾረው ንትርክ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ መሻገሩ ምናልባትም ሕዝባዊ ውሳኔን የሚፈልግ የቤት ሥራ መኖሩን ጠቋሚ ነው። "ሕዝብ እንዲስማማበት ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነበር" ይላሉ አቶ ውብሸት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ። "ሲጀመርም ሕገ-መንግሥቱን ያረቀቁት እና በኋላም ያፀደቁት አካላት መካከል ያን ያህል መከፋፈል ከነበረ ይሻል የነበረው ወደ ሕዝቡ ማምጣት እና እንዲወስንበት ማድረግ ነበር። በመካከሉም ሕገ-መንግሥቱ ከፀደቀ በኋላም ይሄንን ማድረግ ይቻል ነበር።" ለመገንጠል ምን ያስፈልጋል? በቅርቡ በሶማሌ ክልል መዲና ጂግጂጋ ግጭት ተቀስቅሶ በርካቶች ከሞቱ በኋላና ለቀውሱ መባባስ አንዱ ምክንያት የክልሉ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሃመድ ኦማር አንቀፅ 39ን ተጠቅመው ክልሉን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል መሞከራቸው ነው ተብሎ ከተዘገበ በኋላ አንቀፁ በሚያጎናፅፋቸው መብቶች ዙርያ መጠነኛ ውይይት በማኅበራዊ ሚዲያ ሲንሸራሸር ተስተውሏል። በውይይቶቹ መገንጠል ቀላል እና ቅርብ መስሎ መታየቱ ስጋት የፈጠረባቸው ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ መገንዘብ ይቻላል። ሕገ-መንግሥቱ የመገንጠል መብትን ያለምንም ገደብ ያጎናፅፋል የሚሉት አቶ ውብሸት ሒደቱ የሚያልፋቸው ሥነ-ሥርዓቶች መኖራቸውን ግን ጨምረው ይገልፃሉ። • "ሕገ-መንግሥቱ ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትርን በሚመለከት ክፍተት አለበት" ውብሸት ሙላት የመገንጠል ጥያቄ ተቀባይነት እንዲኖረው በመጀመሪያ በብሔር፣ በብሔረሰቡ ወይንም በሕዝቡ የህግ አውጭ ምክር ቤት ሁለት ሦስተኛ ድጋፍ ማግኘት መቻል አለበት። የምክር ቤቱ ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ ባሉ ሦስት ዓመታት ውስጥ የፌዴራል መንግሥት ሕዝበ-ውሳኔን የማዘጋጀት ኅላፊነት የሚኖርበት ሲሆን፤ በሕዝበ-ውሳኔው ከጠቅላላው ሕዝብ ከግማሽ በላዩ የመገንጠል ሃሳቡን የሚደግፍ ሆኖ ከተገኘ የፌዴራል መንግሥት ስልጣኑን ያስረክባል፣ የሃብት ክፍፍልም ይደረጋል። የሕግ ባለሙያ እና የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አቶ ኪያ ፀጋዬ "ሰፊ እና ለትርጉም አሻሚ" ነው የሚሉት አንቀፅ 39 በቁጥር አራት ከዘረዘራቸው አምስት ሒደቶች ባሻገር ውስብስብ የሆነውን የመገንጠል ክንውን የሚያስፈፁሙ ዝርዝር ህግጋት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያለመውጣታቸውን ይገልፃሉ። "በእርግጥ ሕጉ በሚረቀቅበት እና በሚፀድቅበት ጊዜ የአርቃቂ ጉባዔው ይሄንን አንቀፅ በተመለከተ የነበረው ትክክለኛ ዓላማ ምንድን ነው? የሚለውን ለማወቅ በወቅቱ የነበረውን ቃለ-ጉባዔ መመልከት ያሻል" ሲሉ ያብራራሉ አቶ ኪያ "ሆኖም የመገንጠል መብት በወቅቱ የነበረውን የፖለቲካ ግለት ለማብረድ እና ጥርጣሬ ለነበራቸው የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ዋስትና ለመስጠት ታስቦ የተካተተ ይመስለኛል።" አቶ ኪያ እንደሚሉት በመገንጠል አፈፃፀም ዙርያ ዘርዘር ያሉ ሕግጋት ያልወጣው ዋነኛው አስፈላጊነቱ ፖለቲካ ዋስትና ለመስጠት ስለነበርና ይሄንንም ሕገ-መንግሥቱ ውስጥ አንቀፁን በማካተት ማሳካት በመቻሉ ነው። የአፈፃፀም ፈተናዎች የሕግ እና የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ኪያ ሕዝባዊ አመኔታ እና ቅቡልነት ያለው ዲሞክራሲ ማስፈን እስካልተቻለ ድረስ የአንድ ክልል ሕግ አውጪ ምክር ቤት ሕዝቡን በትክክል ይወክላል ማለት ይከብዳል ይላሉ። "የክልል ፓርላማዎችን ተዓማኒ ባለሆነ ምርጫ ተመሳሳይ የፖለቲካ ወገንተኝነት ባላቸው ሰዎች መሙላት ይቻላል። እነዚህ ሰዎች በትክክል [መገንጠል ይፈልጋል የተባለውን] ብሔር ወይንም ሕዝብ ፍላጎቶች ይወክላሉ ወይ? የሚለው ላይ ጥያቄ ይኖረኛል።" የሕዝብ ውሳኔውም ቢሆን በአብላጫ ድምፅ ወይንም ሃምሳ በመቶ ሲደመር አንድ መሆኑ መገንጠልን በሚያህል ትልቅ ውሳኔ ላይ ተገቢ እንደማይመስላቸው የሚገልፁት ደግሞ አቶ ውብሸት ናቸው። "አንድ መገንጠል የፈለገ ብሔር አንድ ሚሊዮን ሕዝብ አለው እንበል። ከእነዚህ መካከል ሃያ በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ባለመድረሱ እና በተለያዩ ምክንያቶች በሕዝበ-ውሳኔው ሳይሳተፉ ቢቀሩ፤ ከተሳተፉት ደግሞ ሃምሳ በመቶ እና አንድ የሚሆኑቱ መገንጠልን ወይንም መቆየትን ቢደግፉ፤ ይህ ውሳኔ ከጠቅላላው ሕዝብ የአርባ በመቶውን ብቻ ነው የሚወክለው ማለት ነው" ይላሉ። ሕገ-መንግሥቱ ከመፅደቁ በፊት በነበረው የሽግግር ሰነድ (ቻርተር) ላይ የመገንጠል መብትን ከመተገበር የሚያቅቡ ቅድመ ሁኔታዎች እንደነበሩ ያነሳሉ አቶ ውብሸት። "የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አንዱ ነው" እንደዚህ ዓይነት ቅድመ ሁኔታዎች በሕገ-መንግሥቱ ውስጥ ኖረው ቢሆን፤ እንዲሁም ሕዝበ-ውሳኔዎች ለስሜታዊነት ተጋላጭ የመሆን ዕድል እንዳላችው በዓለም ዙርያ በተደጋጋሚ በመታየቱም የማሰላሰያ ጊዜ ቢኖርና ዳግመኛ የሚከናወኑበት አማራጭ ቢኖር እንደሚመርጡም ጨምረው ይገልፃሉ። አሁን ባለው እውነታ ከመገንጠል ጋር ተያይዘው ከሚመጡ የራስ ምታቶች እንደኛው የንብረት ክፍፍል ነው። በምትገነጠለው ግዛትና በቀሪው ፌዴሬሽን መካከል የሚኖረውን የንብረት ክፍፍል የሚያብራሩ ሕግጋት ባለመኖራቸው "ሁኔታው የሚከናወነው በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ነው? ግልፅ አይደለም።" አቶ ኪያ ሕገ-መንግሥቱ የመገንጠልን መብት የሚሰጠው ለብሔሮች፣ ለብሔረሰቦች እና ለሕዝቦች እንጂ ለክልሎች ባለመሆኑ በክልሎቹ የሚኖሩ ሌሎች ብሔሮች በክልል ምክር ቤቶች ውስጥ መቀመጫ ያላቸው ሌሎች ብሔሮች ጉዳይ ሌላ ጥልፍልፍን ይፈጥራል ባይ ናቸው። የሕግ ባለሙያው አቶ ውብሸት ግን በኢትዮጵያ ክልላዊ አወቃቀር መሰረት ክልሎች የብሔሮች ናቸው ይላሉ። "የአማራ፣ የኦሮሚያ፣ የትግራይ፣ የሶማሌ ወዘተ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ነው የሚባሉት። ክልሎቹ የብሔሮቹ ናቸው ማለት ነው።" ለመገንጠል የሻተው ብሔር ወይንም ሕዝብ በሕዝበ ውሳኔ አማካይነት ድምፁን ካሰማ በኋላ፤ የሕዝበ-ውሳኔው ውጤት ላይ ቅሬታ ቢኖረው አቤቱታውን የሚያሰማው "ቅሬታ ለፈጠረበት ለፌዴራላዊው መንግሥት የምርጫ ቦርድ ነው። ይሄም ራሱ ሌላ እንቆቅልሽ ነው" ይላሉ አቶ ውብሸት። "ምርጫውንም የሚያከናውነው የኢትዮጵያው ምርጫ ቦርድ ነው።" የአንቀፅ 39 መፃዒ ቀናት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ አንስቶ በርካታ የአንቀፅ 39 ነቃፊዎች፤ በአንቀፁ የተካተተውን የመገንጠል ሃሳብ እንደሚፍቁላቸው ተስፋ የሰነቁ ይመስላል። በተለያዩ ትዕይንተ-ሕዝቦች ላይ በአንቀፁ ላይ ያነጣጠሩ የትችት መፈክሮች ተስተውለዋል። ይሁንና አንቀፁን መፋቅም ሆነ ለማስተካከል መሞከር አሁን ካለው የአገሪቱ የፖለቲካ እውነታ አንፃር የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ ነው ይላሉ አቶ ውብሸት። "ከደርግ ጊዜ አንስቶ ለሕግ ያለን አመኔታ እየወረደ መጥቷል፤ አሁንም በአንቀፅ 39ም ሆነ እንደ ሠንደቅ አላማ ባሉ አጨቃጫቂ ጉዳዮች የሚነሳው ንትርክ የእልህ ጉዳይ የሆነ ይመስለኛል" ይላሉ አቶ ውብሸት። "በመሆኑም ኅብረተሰቡም ሆነ የፖለቲካ ልኂቃን ሰክን ብለው በዚህ ጉዳይ ላይ ለመወያየት የሚችሉበት ጊዜ ላይ የደረስን አይመለኝም።"
news-44857477
https://www.bbc.com/amharic/news-44857477
የሐመሯ ወጣት፡ ከሞት አፋፍ ሕልምን ወደ መኖር
ስሜ ኢሪ ዲማኮ ቾርዲ ይባላል። ኢትዮጵያዊትና ፈረንሳዊት ነኝ። አሁን የምኖረው በሞንትሪያል ካናዳ ነው።
ኢሪ ዲማኮ ቾርዲ ዕድሜዬ አምስት እያለ ነው ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሐመር የወጣሁት። ለነገሩ ስለዕድሜዬ እርግጠኛ መሆን አልችልም። ምክንያቱም በደቡብ ኢትዮጵያ ዕድሜ አንቆጥርም ነበር። ቤተሰቦቼ እረኞች ናቸው። እነሱም የአየር ፀባይ ለማወቅ ከዋክብትን በመቁጠር፣ ከብቶቻችውን በማንበብ የሚተዳደሩ ናቸው። ከሞት መንጋጋ መሹለክ የተወለድኩበትን ለቅቄ ለመሄድ የተገደድኩት ስለልጆች በነበረ እምነት ምክንያት ነበር። 'ሚንጊ' ይባላል። በዚያ አካባቢ የአንድ ልጅ ጥርስ ሲበቅል በቅድሚያ የታችኛው ጥርስ ከበቀለ ልጁ ወይም ልጅቱ የተረገመ ነው ወይም ነች ተብሎ ይታመን ነበር። እንዲህ ዓይነቱ ልጅ በመንደሩ ቢቆይ ለቤተሰቡም ሆነ ለመንደሩ ክፉ ዕጣ ፈንታን ይጠራል ብለው ያስቡ ነበር። ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ ሲከሰት ቤተሰቡ ሦስት አማራጮች አሉት። አንደኛው ጠንቋይ ዘንድ ተሂዶ ኃጢያትን ማንፃት ሲሆን፤ ሁለተኛው እናት ልጇን ከመንደሩ አርቃ ወስዳ ጨክና መጣል ነው። ሦስትኛው አማራጭ ደግሞ የመንደሩ ነዋሪዎች ልጁን በደቦ እንዲገድሉ ማድረግ ነበር። በዚያን ወቅት አባቴ ሞቶ ነበር። እናቴ ደግሞ አራስ ነበረች። በእቅፏ ሁለት ልጆችን ይዛ ቀርታ ነበር። ልታድነኝ የአቅሟን ሞከረች። ጠንቋይ ዘንድ ወስዳኝ ስትመለስ የሚያምናት ሰው አልነበረም። በመጨረሻም የአንድ ሰዓት የእግር ጉዞ የሚያስኬድ ከተማ ይዛኝ ሄዳ ለሕጻናት ማሳደጊያ ሰጠችኝ። ያም ሆኖ እዚያ ብዙ አልቆየሁም። አንድ አስተማሪ ከእናቷ ጋር ከሚኖሩበት ቤት ወሰደችኝ። ብዙ ነገሮች ትዝ አይሉኝም። የማስታውሰው ነገር ቢኖር ሁለት የአየርላንድ ሚሽነሪዎች ጋር መኖር እንደጀመርኩኝ ከዕለታት አንድ ቀን ያሳደገችኝ እናቴ ከአጎቴ ጋር መጥተው ሲወስዱኝ ነው። ከደቡብ ወጥቼ አዲስ አበባ ስደርስ ሁለት ወራት ብቻ ነበር ያለፉት። • ካናዳን በጥበብ ሥራው ያስዋበው ኢትዮጵያዊ ኢሪ በተወለደችበት ሃገር ከዓመታት በኋላ ከአዲሳ'ባ እስከ ካናዳ 17 ዓመት እስኪሞላኝ ድረስ አዲስ አበባ ኖርኩኝ። አባቴ ለሥራ ወደ ኮሎምቢያ ሲላክ ከእናቴ ጋር አብረነው ሄድን። የሁለተኝ ደረጃ ትምህርቴን ለማጠናቀቅ የቀረኝን የመጨረሻ ዓመት ኮሎምቢያ እንደጨረስኩኝ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን ለመጀመር ወደ ካናዳ አመራሁ። እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2011 ጀምሮ እስካሁን በካናዳ ነው ያለሁት። በመሃሉ ወደ አገር ቤት ተመልሼ ነበር። ከሃገር ከወጣሁ ከአምስት ዓምታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ ለሦስት ወራት ያህል ተቀመጥኩኝ። በውስጤ ይመላለሱ የነበሩትን ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘትም ፍላጎት ነበረኝ። ባሳደጉኝም ቤተሰቦቼ እርዳታ ከዘመዶቼ ጋር ወደ ደቡብ አቀናን። ስሜቶቼ፣ እንባዬ፣ጭንቀቱ፣ምሬቱና ግራ መጋባቱ ከሐሳቦቼ ጋር ተቀላቅለው እንደ መርፌ እዚያም እዚም ይወጋጉኝ ነበር። ከረሳኋዋቸውም ሆነ ከማስታውሳቸው ሰዎች ጋር መገናኘቱ የደስታ ስሜት ፈጥሮብኝ ነበር። ተቆጥረው የማያልቁ ዘመዶቼን በማግኘቴና ከእህትና ከአክስቴ ልጆች ጋር ያለኝን መመሳሰል ሳየው በጣም ገረመኝ። አሁን ውስጤ ሰላም ስላገኘ መሄዴን እንደ ስጦታ እቆጥረዋለሁ። ሰላም በመፍጠሬም ሳልሸማቀቅና ሳላፍርበት ስለ ሕይወቴ ማውራት እችላለሁ። መልካሙ ዜና አሁን በሐመር እንደዚህ ዓይነት እምነት ቀርቷል። እኔ ከመጨረሻዎቹ አንዷ ነበርኩ። ከእናቴ ጋር ወደ አዲስ አበባ ያመጣኝ አጎቴ እንደነገረኝ ከሆነ መኪና ውስጥ የጂሚ ሄንድሪክስን ካሴት ሲያጫውት አብሬ ለመዝፈን ጊዜ እንዳልፈጀብኝ ያስታውሳል። ቤት ውስጥ ሁልጊዜም እዘፍን ነበር። አባቴ ደግሞ የድምፅ ትምህርት እንድወስድ ያበረታታኝ ነበር፤ ገና በ11 ዓመቴ። እራሴን እንዳውቅ ከረዱኝ ትምህርቶች አንዱ ሙዚቃ ነው። በተለይ የአተነፋፈስ ሥልት ሳጠና በጣም ተደንቄ ነበርና ምንጊዜም ቤት ስመለስ ቅልል ያለ ስሜትና ደስታ ይሰማኝ ነበር። ወላጆቼም ፒያኖ እንድማር ገፋፍተውኝ ለስምንት ዓመታት ተምሬያለሁ፤ ብዙም አልገፋሁበትም እንጂ። ያም ሆኖ መዝፈንና ግጥም መፃፍ እወድ ስለነበር ከሙዚቃ አልተላቀቅኩም። ካኢሪ (ግራ)፣ ኢሪ (ቀኝ) አሁን አብራኝ ከምትዘፍነው ጓደኛዬ ጋር የተዋወቅነው አንድ ሌላ ጓደኛዬ ባዘጋጀችው ምሽት ላይ ነበር። ከዚያን ጊዜ ወዲህ እነሆ አብረን እየሠራን እንገኛለን። እሷ ግማሽ ካናዳዊት፣ግማሽ ከቡርኪና ፋሶ ብትሆንም ያጋጣሚ ነገር ስማችን ተመሳሳይ ነው። እሷ ካኢሪ ትባላለች። ስለዚህ የቡድናችንን ስም ካ-ኢሪ አልነው።በሙዚቃችን የአፍሪካን ሙዚቃ ስልት ከጃዝ፣ ከሂፕሆፕና ከኤሌክትሮኒክ ሙዚቃዎች ጋር እያዳቀልን ነው የምንጫወተው። የመጀመሪያውን ሥራችንን ከሁለት ሳምንታት በፊት በአልበም መልክ ለሕዝብ አቀረብን። • ካለሁበት 5፡'ኑሮዬን ቶሮንቶ ያደረግኩት በአጋጣሚ ነበር' • ካለሁበት 31፡ ''ብዙ ትውስታዎቼ ከዛፍና ከጭቃ አያልፉም'' ሙዚቃ ሕይወቴ ሥራዬ ብዬ ሙዚቃ መጫወት ከጀመርኩኝ አራት ዓመታት አስቆጠርኩኝ። አምርሬ የያዝኩት ከዛሬ 6 ዓመት ጀምሮ ቢሆንም ግን ከሕጻንነቴ ጀምሮ ለሙዚቃ እንደተፈጠርኩኝ ይሰማኛል። ሙዚቃ ለመሥራት የሚገፋፋኝ ዋናው ነገር ለነፍሴ የሚሰጠኝ ነጻነት ነው። ስዘፍን በሕይወት እንዳለሁ ይሰማኛል። ሁሉን ነገር ትቶ መላው መንፈሴ በሙዚቃው ውስጥ ይንሳፈፋል። ብዙውን ጊዜ የምጽፈው ስለ ሰላምና ስለ ይቅር መባባል ነው። በውስጣቸውም መጥፎ ነገሮች ቢያጋጥሙም ሁልጊዜ እንደምንም ብዬ መጨረሻው ወደ ጥሩ ነገር እንዲያዘነብል አደርጋለሁ። በሙዚቃዬ ፍቅርን ማስተማርና ማንፅባረቅ ነው የምመኘው። በሕመም ውስጥ መዳን ይገኛልና። የተለያዩ የአርት ስልቶችን አቀላቅላለሁ። በማቀላቀሌም ችሎታዬንና ማንነቴን ማንፅባረቅ ችያልሁ። የማህበራዊ ድረ ገፆችን አጠቃቀም እየለመድኩ ቢሆንም በነሱ በኩል ግን ቢያንስ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ እመኛልሁ። ስለተለያዩ ሰዎችና ስለተለያዩ ብሔሮች የሚማሩበት እንዲሆን እፈልጋልሁ። ሰው ስለተፈጥሯዊ ይቅር መባባልና መዳን እንዲማሩ እፈልጋልሁ። ትንሽ ነኝ ብሎ የሚያስበውም ሰው ቢሆን ትልቅ ቦታ እንዳለው እንዲያውቁ ምኞቴ ነው። ካኢሪ (ግራ)፣ ኢሪ (ቀኝ) ሕልምና ምኞቴ ሕልሜ ሙዚቃዬን ለዓለም ማድረስ ነው። በዚህም ከማምንባቸው ነገሮች አንዱ የሆነውን ፍቅርን መቋደስ ነው። የተለያዩ ቋንቋዎች ተምሬ ደግሞ ዓለምን መዞር እመኛለሁ። ስለተለያዩ ባህሎች ማወቅ፣ ማንነቴን ማወቅ፣ እምነቴንና ደስታዬን ማሳደግም የምኞት ሰንዱቄ ውስጥ የሚገኙ ነገሮች ናቸው። መቼም ቢሆን ማደግ ማቆም አልፈልግም። ምክንያቱም ይህች ምድር ማቆምያ የላትም። ዓለም ብዙ የምትሰጥን ነገር አለ። እኔም ያለኝን ከመስጠት ወደ ኋላ አልልም። መቼም! • የካናዳ ፓርላማ ዕፀ-ፋርስን ለመዝናኛነት ህጋዊ አደረገ እኔና ካኢሪ የተለያዩ መድረኮች ላይ ተጫውተናል። ያኤል ናይሚ ለተሰኘ ታዋቂ ዘፋኝ ኮንሰርት መክፈቻ፣ንዊ ዳፍሪክ ላይና ሌሎችም። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ ኖማድ በተሰኘው ታዋቂ የሴኔጋል ፌስቲቫል ላይ እንድንጫወት ተጋብዘናልና። ብዙ አጋጣሚዎች እየተከፈቱልን እንድሆነ ይሰማኛል። እኛም ያለንን ፍቅር ለዓለም ለማካፈል ዝግጁ ነን። በአማርኛ፣ በእንግሊዘኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በቡርኪናፋሶ ቋንቋ (ሳሞ) እንዘፍናለን። ምን ይሄ ብቻ...አንዳንዴም እራሳችን በምንፈጥረው ቋንቋ ጭምር እንዘፍናለን።
news-43467269
https://www.bbc.com/amharic/news-43467269
ማንነቱን ፍለጋ በእግሩ ለ45 ቀናት ወደ ላሊበላ የተጓዘው አፍሪካ አሜሪካዊ
ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ሲሠራ ዓመታት ያስቆጠረው እንድሪያስ ጌታቸው ካሳዬ በውስጡ ታምቆ የቆየው የፀሃፊነት፣ ፊልም ሥራ ላይ የመሰማራትና ለተለያዩ ጥበባት ያለው ፍቅር 'ብሪዝ ኢን ዘ ሩትስ' የተሰኘውን ጥናታዊ ፊልም እንዲሠራ ገፋፍቶታል። ከኤፍራታ በላቸው እና ከስንታየሁ ንጉሴ ጋር በመተባበር ይህን ጥናታዊ ፊልም ለሕዝብ ማቅረብ ችለዋል።
ክሪስ ታይሮን ጆዜፍ 'ብሪዝ ኢን ዘ ሩትስ' የተሰኘው ጥናታዊ ፊልም ባለፈው ሳምንት በፈረንጆቹ የመጋቢት ወር መግቢያ ላይ ጀምሮ ከመጋቢት አጋማሽ በኋላ በተጠናቀቀው የኒው አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ እጩ ሆኖ ቀርቦ ነበር። ይህ የእንድሪያስ 'ብሪዝ ኢን ዘ ሩትስ' የተሰኘው ፊልም በፌስቲቫሉ ሲታጭ የመጀሪያው ኢትዯጵያዊው ሲኒማ ባይሆንም ይህ ፊልም እውነተኛ ክንውኖችን ማሳየቱ የተለየ ያደርገዋል። ከግራ ወደ ቀኝ ፡ ምዊዛ ሙንታሊ የኒው አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል መድረክ መሪ፣ ክሪስተን ታይሮንና እንድሪኣስ ጌታቸው ፊልሙ ክሪስተን ታይሮን ጆዜፍ የተባለ ጥቁር አሜሪካዊ ማንነቱን ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ አምርቶ ያደረገውን ጉዞ የሚያስቃኝ ነሥ። ክሪስ በመጀመሪያ ወደ አፍሪካ ሄዶ ማንነቱንና አመጣጡን ለማግኘት በፈለገ ጊዜ ወደየትኛው ሃገር እንደሚያመራ እርግጠኛ አልነበረም። ነገር ግን ወደ ሠር-መሠረቱ የመመለስ ፍላጎቱ በሕልም ተገልጾለት ወደ ላሊበላ መጓዝ እንደነበረበት ከተረዳ በኋላ ነበር ይህ መንፈሳዊ ጉዞው ሊጀመር የቻለው። ክሪስተን ጉዞውን ከመጀመሩ በፊት እቅዱን ለእንደሪያስ ሲያማክረው፤ እንድሪያስም ሃሳቡን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ አብሮት የሚጓዝ የቀረፃ ቡድን አብሮት እንዲጓዝ በጠየቀው መሰረት በመስማማቱ ሥራው ተጀመረ። ይህንን የክሪስ ጉዞ አስደናቂ የተለየ የሚያደርገው እንደማንኛውም ሰው በመኪና ወይም በአውሮፕላን የተደረገ አለመሆኑ ነው። ''ክሪስ 'እግዚአብሔር በሠራው እንሰሳና በእግሬ ብቻ ነው ወደ ላሊበላ የምጓዘው' ሲለኝ ደስ ነበር ያለኝ'' ሲል እንደሪያስ ያስታውሳል። ክሪስ በፈረስ ላይ ጉዞው በአጠቃላይ 45 ቀናት እንደፈጀ የሚናገረው እንድሪያስ፤ የክሪስን ጉዞ ሲያስረዳ ብዙ ነገሮች እንደተቀያየሩ በተለይ ክሪስ በብዙ መልኩ እንደተለወጠ ይናገራል። ይህ ጉዞ በአውሮፓውያኑ 2012 ይጀመር እንጂ እስከ ዛሬ እንደቀጠለ ነው። ይህም ማለት በጉዞው ሂደት የተጀመሩት ለውጦች በክሪስ ህይወት ውስጥ ሳይቆሙ መቀጠላቸው ነው። ምንም እንኳን ክሪስ ከአንድ ወር በላይ የፈጀ ጉዞ ያድርግ እንጂ የፊልሙ ሥራ አራት ዓመታት ያህልን ፈጅቷል። ወደ ሰፊው መድረክ ለመድረስ ደግሞ ተጨማሪ 2 ዓመታት እንደጠየቀ እንድሪያስ ያስረዳል። እንድሪያስ ''ይህ ሥራ ይህን ያህል ገንዘብ ፈጅቷል ለማለት ይከብደኛል። ምክንያቱም ካወጣው ወጪ በላይ የሚያስተላልፈው መልዕክት በገንዘብ ሊተመን የማይችል እንደሆነ ነው'' ይላል። እንድሪያስ ይህንን ፊልም ለመስራት እንደ አንድ ምክንያት የሚጠቅሰው ተማሪ በነበረበት ጊዜ የገጠመው ነገር ነው። ይህም የሁለተኛ ደረጃና የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በአሜሪካ በሚከታተልበተ ወቅት ኢትዮጵያ በአስከፊው የ1977ቱ ድርቅ ተመትታ ችግሩ የሃገሪቱ መለያ እስከመሆን ደርሶ ነበር። በዚህም ምክንያት በሚማርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሁለት ጥቁር አሜሪካውያን ተጣልተው ሲሰዳቡ 'አንተ ኢትዯጵያዊ' ይሉ ነበር። ይህም 'አንተ ድሃ ለማለት' እንደማለት ነበር። ''በዚህ በጣም ልቤ ያዝን ነበር። ምክንያቱም የኢትዮጵያን ታሪክ በትክክል ቢያውቁት ኖሮ ይህች ሃገር የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ ኩራት መሆኗን ይገነዘቡ ነበር'' ብሎ እንዲያስብ አደረገው። ''ፀሐፊና በመገናኛ ብዙሃን ውስጥ የምሠራ ሰው እንደመሆኔ ሁሌም እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ላላቸው ሰዎች እንዴት ብዬ ኢትዯጵያን ላስተዋውቃቸው እችላለሁ ብዬ አስብ ነበር'' ይላል። አንድሪያስ ክሪስተን ታይሮን ጆዜፍ ወደ ቢሮው መጥቶ ስለጉዞው ያለውን ሃሳብና ዕቅድ ሲያካፍለው ለዓመታት በውስጡ ለነበረው ፍላጎትና ምኞት ያገኘው ምላሽ እንደሆነ ነበር የቆጠረው። ''ከእኔ ይበልጥ እራሳቸውን የሚመስሉ ሰዎች ስለ ኢትዮጵያ ያለውን እውነታ ቢነግሯቸው ይሻላል'' የሚለው እንድሪያስ በዚህ በፊልም ላይ የሚትታየው ኢትዮጵያ የተሳሳተውን አመለካከት ለመቀየርና እውነታውን ለማሳየት ጠቃሚ ነው ብሎ ያምናል። እንድሪያስ በኒው አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ በ'ብሪዝ ኢን ዘ ሩትስ' ሥራው መታጨቱ በጣም እንዳስደሰተውና እንዳኮራው ገልጿል። በተለይ በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉ የፊልም ሠሪዎችና የፊልም ውጤቶች እኩል መድረክ ላይ መቅረቡ ትልቅ ነገር እንደሆነም ይናገራል። አብረውት የሠሩትና ለሥራው የተባበሩትን ባልደረቦቹን አመስግኖ፤ ፊልሙ በሁሉም ዘንድ ያለው ቦታ ትልቅ እንደሆነ እንድርያስ ይጠቅሳል። ''ፊልሙን እንዲመለከቱ የጋበዝኳቸው ሰዎችም ስሜታቸውን ሲኣካፍሉ፤ እነሱም የጉዞው ተሳታፊ የሆኑ ያህል እንደተሰማቸው ይናገራሉ።'' ሲጨምርም ''ብዙዎቹ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ ረዥም ዓመታት ሆኗቸው ስለነበር ሃገራቸው ምን ያህል እንደናፈቃቸው ታውቋቸው ነበር። ብዙዎቹም እኛም መቼ ይሆን እንደ ክሪስ አየሯን የምንተነፍሰው?'' ብለው እራሳቸውን ይጠይቁ እንደነበር ያስታውሳል። ይህ ፊልም ከበርካታ ፊልሞች መካከል ተመርጦ በኒው አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ ቀርቧል። የ'ብሪዝ ኢን ዘ ሩትስ'ን ቅንጫቢ ከዚህ በታች ይመልከቱ የተወሰደውም ከጆቢራው ፊልም ፕሮዳክሽን ነው። 'ብሪዝ ኢን ዘ ሩትስ' የተሰኘው ጥናታዊ ፊልም ክሪስተን ታይሮን ከአዲስ አበባ ወደ ላሊበላ በእግሩ የተጓዘውን መንገድ የሚሸፍን ነው።
55488485
https://www.bbc.com/amharic/55488485
ከአደገኛ እጽ አዘዋዋሪነት ወደ ፓስተርነት
ሚክ ፍሌሚንግ በ40ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው።
ሚክ ፍሌሚንግ አንድ ምሽት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያ በር ላይ ሰው እየጠበቀ ነበር። ሚክ የነበረበት የተሰረቀ መኪና ሞተሩ አልጠፋም። የሚጠብቀውን ሰው በፍጥነት ተገላግሎ ለመሄድ ወስኗል። "እሱም እንደኔው አደገኛ እጽ አዘዋዋሪ ስለሆነ እንቅስቃሴው ምን እንደሚመስል አውቃለሁ" ሲል ምሽቱን ያስታውሳል። ሚክ በሰሜን ምዕራብ እንግሊዝ እጽ አዘዋዋሪዎች ዘንድ ይታወቃል። የእጽ ዝውውር ክፍያ ያልፈጸመ ሰው ካለ የሚላከው እሱ ነው። እንዳይሞቱ እንዳይተርፉ አድርጎ ይቀጠቅጣቸዋል። "በዚያ ምሽት ሽጉጤ ፕላስቲክ ውስጥ ነበር። የጣት አሻራ አያርፍበትም። ስድስቱ ጥይት የሚፈለገውን ተግባር ለመፈጸም ይውላል።" ብዙም ሳይቆይ የሚጠበቀው ሰው መጣ። "ከስፖርት ማዘውተሪያው ሲወጣ ሁለት ልጆች ይዞ ነበር። አምስት ዓመት የሚሆናቸው ሴት ልጆች አብረውት ነበሩ። ከመኪናው ሽጉጡን ይዤ ወረድኩ። ስጠጋው እነዛን ንጹህ ልጆች በቅርበት አየኋቸው" ሲል ያስታውሳል። ከዚያ የተከሰተውን እንዲህ ይተርካል. . . "ከልጆቹ ከአንዷ መዳፍ ጨረር ይፈልቅ ነበር። በጣም ነጭ ነው። ለ15 ሰከንዶች ማየት አልቻልኩም። ፀሐይን ለማየት እንደመሞከር ነበር። አቅም አሳጣኝ። ራሴን ሳትኩ። ከዚያም እየተንገዳገድኩ ወደ መኪናዬ ተመለስኩ። ታመምኩ፤ ሰውነቴ ተንዘፈዘፈ፤ አላበኝ፤ ልቤ በጣም ይመታ ጀመር። ምን እየሆንኩ እንደሆነ አልታወቀኝም።" ፈጣሪ እንዲረዳው ቢማጸንም ምንም አልተፈጠረም። መኪናው ውስጥ ከሚጫወተው የጆኒ ካሽ ሙዚቃ ውጪ ምንም አይሰማም ነበር። ያቺ ምሽት የሚክን ሕይወት እስከወዲያኛው እንደቀየረችው ይናገራል። "ሽጉጡን ከፕላስቲኩ ሳላወጣ ራሴ ላይ አቀባበልኩ" በግድያ ሙከራ፣ በአፈና፣ መሣሪያ ይዞ በመገኘት ታስሯል። በዛች ምሽት የተመሰቃቀለ ሕይወቱ ተስፋ አስቆርጦት እንደነበር ያስታውሳል። "ሽጉጡን ከፕላስቲኩ ሳላወጣ ራሴ ላይ አቀባበልኩ። ስተኩስ ምንም ሳይፈጠር ቀረ። ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ። የመኪናውን ራድዮ በቡጢ ስመታው እጄ ደም በደም ሆነ። በዛ ቅጽበት እውነተኛ ማንነቴ ቁልጭ ብሎ ታየኝ። ከዚያ በፊት ለ30 ዓመት አላለቀስኩም ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ ያለቀስኩት በ11 ዓመቴ ነበርና እዛ መኪና ውስጥ አለቅስ የነበረው ለልጅነቴ፣ ሊኖረኝ ይችል ስለነረው ሕይወት ነው።" ሚክ አሰቃቂ ድርጊቶቹ ባጠቃላይ በህሊናው ይመላለሱ ጀመር። እአአ በ1966 ኢንግላንድ ውስጥ የተወለደው ሚክ ከሠራተኛ መደብ ቤተሰብ ነው የተገኘው። አባቱ መስኮት አጽጂ ነበሩ። ወግ አጥባቂ ቤተሰብ ውስጥ ነው ያደገው። ቤተ ክርስቲያን መሄድ ግዴታ ነበር። በ1977 ሚክ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ ፓርክ ውስጥ ወሲባዊ ጥቃት ደረሰበት። 11 ዓመቱ ነበር። "ልረጋጋ አልቻልኩም። ሕይወቴ ተናወጠ" ሲል ወቅቱን ያስታውሳል። ከዚያም እህቱ በልብ ድካም እንደሞተች አባቱ ነገሩት። የ20 ዓመቷ እህቱ አን ትንከባከበው ነበር። ከሷ ሞት በኋላ ሕይወቱ ሌላ መስመር እንደያዘ ይገልጻል። "አደገኛ እጽ እና አልኮል ጀመርኩ። ቀጣዩ 30 ዓመት ሲኦል ሆነብኝ" ይላል። "በእግዚአብሔር አምናለሁ። ግን የሚወደኝ አይመስለኝም" አደገኛ እጽ መሸጥ የጀመረው በ14 ዓመቱ ነው። "አደገኛ እጽ አዘዋዋሪ ሆንኩ። የገንዘብ እዳ ካለባቸው ሰዎች የምሰበስበውም እኔ ነኝ። ሰዎችን መጉዳት ብዙም አያስጨንቀኝም ነበር። ሁለቴ በግድያ፣ ሦስቴ በዝርፊያ ታስሬያለሁ። መሣሪያ በመያዝ ምን ያህል ጊዜ ዘብጥያ እንደወረድኩ ማስታወስ እንኳን አልችልም። በጣም ብዙ ገንዘብ አገኝ ነበር። ህመሜን ለመደበቅ ብሞክርም አልተሳካልኝም።" በ1990ዎቹ ሚክ ሁለት ጊዜ የግድያ ሙከራ ተደርጎበታል። አንደኛው የትራፊክ መብራት አስቁሞት የተሰነዘረ ጥቃት ነው። ቤት ሲዘርፍም ሕይወቱን ሊያጣ ተቃርቦ ነበር። ከወንጀል ውጪ ሌላ ሥራ መሥራት እንደማይችል አምኖ ነበር። በ16 ዓመቱ ጓደኛው ከመጠን በላይ ጠጥቶ ሞተ። በ17 ዓመቱ ደግሞ ሌላ ጓደኛው ከመጠን በላይ እጽ ተጠቅሞ ሕይወቱ ተቀጠፈ። "በእግዚአብሔር አምናለሁ። ግን የሚወደኝ አይመስለኝም" ይላል። አግብቶ 3 ልጆች ቢወልድም ልጆቹን መንከባከብ ባለመቻሉ እናቱ ያሳድጓቸው ነበር። ፖሊሶች አደንዛዥ እጽ ወይም መሣሪያ ፈልገው በተደጋጋሚ ቤቱን ይበረብሩ ነበር። "ሁሉም ነገር ተደማምሮ የአእምሮ ጤናዬን አቃወሰው። የበለጠ እጽ መውሰድ ጀመርኩ። እጅግ አደገኛ ሰው ሆንኩ። ሕይወቴ በአጭሩ እንደሚቀጭ ነበር የማስበው። እንዴት መለወጥ እንደምችል አላውቅም ነበር። መኖር አልፈልግም ነበር።" ሚክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያ በር ላይ የተገኘው በ2009 ነው። ራሱን ሊያጠፋ ከሞከረ በኋላ ወደ አእምሮ ህሙማን ማቆያ ገባ። ሌሎቹ የአእምሮ ህሙማን ይንከባከቡት እንደነበር ያስታውሳል። በማቆያው ሳለ ከፓስተር ቶኒ ጋር ተዋወቀ። ያወሩ፣ አብረው ይጸልዩ ጀመር። ሰዎችን ከመጉዳት ወደ መርዳት ተሸጋገረ። ማንችስተር ዩኒቨርስቲ ሥነ መለኮት መማር ጀመረ። ብዙም ማንበብና መጻፍ ስለማይችል የመጀመሪያውን ዓመት ቢወድቅም በርትቶ በማጥናት 2.1 አግኝቶ ዲግሪ ያዘ። "ከዚያ በኋላ አደገኛ እጽ መውሰድ፣ መጠጣት አቆምኩ።" ፓስተር ሚክ ዛሬ ፓስተር ሚክ በርንሌ ውስጥ እርዳታ በሚሰጥ ቤተ ክርስቲያን ይሠራል። የጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎችን ወዘተ. . . ይረዳል። በተለይ ደግሞ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ድጋፍ የሚሰጧቸው ተበራክተዋል። የጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎችን ወዘተ. . . ይረዳል። ከወዳጆቹ ጋር በመሆን ወረርሽኙ ክፉኛ ለጎዳቸው አቅመ ደካሞች ምግብና ልብስ ያቀርባል። እርዳታ ከሚሰጣቸው አንዷ "ገንዘብና ምግብ ማግኘት ከብዶናል። በየሁለት ቀኑ ምግብ ማግኘት ለኛ ትልቅ ትርጉም አለው" ስትል ነው የምትገልጸው። ሌላው ተረጂ በ30ዎቹ እድሜ ክልል ትገኛለች። ድብርት እንዳለባትና ወረርሽኙ ሁኔታዋን እንዳባባሰው ትናገራለች። "እነዚህ ሰዎች ባይረዱኝ ኖሮ ሞቼ ነበር" ትላለች። የፓስተር ሚክን እርዳታ የሚሹ ብዙ ናቸው። በ20ዎቹ እድሜ ክልል ያለ ወጣት ካልሲ አጥቶ በቅዝቃዜ እንደተሰቃየ ሲነግረው ያለብሰዋል። ልጇን ማስተኛ ላጣች እናት አልጋ ይሰጣል። በየቀኑ የተለያዩ ቤተሰቦችን እየተዘዋወረ ይጎበኛል። በርንሌይ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስለወደቁ ከሌሎች የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ጋር በመሆን ለመደገፍ ይሞክራሉ። በእዳ ውስጥ የተዘፈቁት ጥንዶችና ልጃቸው ፓስተር ሚክ ድጋፍ ከሰጧቸው መካከል ይገኛሉ። ባለ እዳው ፒት "የምንበላው የምንገዛበት ብድር ወስደን ከአንድ ሺህ ፓውንድ በላይ እዳ ውስጥ ገብተን ነበር። እድሜ ለፓስተር ሚክ አሁን እዳውን ከፍለን 300 ፓውንድ ብቻ ይቀርብናል። በእዳው ሳቢያ ልጄና ባለቤቴ ተደብተዋል" ይላል። የእንቅስቃሴ ገደብ ሲታወጅ የአእምሮ ጤናዋ የተነካው የ55 ዓመቷ ቪቭ "ለአንድ ሳምንት ስላልበላሁ መጸዳጃ ቤት መሬት ላይ ራሴን ስቼ ነበር" ትላለች። ከዚያም ሆስፒታል ገብታ አገግማ ወጥታለች። ሚክ ሰውነት ገንቢ ምግብና መጠጥ ያቀርብላታል። መድኃኒትም ይገዛላታል። የካንሰር ታማሚዋ የ50 ዓመቷ ሺላ ኮሮናቫይረስ በጣም ካስፈራቸው አንዷ ናት። "በየወሩ የደም ምርመራ ማድረግ አለብኝ። ግን ለስድስት ወራት ሕክምና አላገኘሁም። ቀዶ ሕክምና ከተደረገልኝ ላልተርፍ እችላለሁ"። ከፓስተሩ ውጪ የምታግዛት የ21 ዓመት የልጅ ልጇ ብቻ ናት። በኮሮናቫይረስ ወቅት እንዳስተዋለው አይነት ማኅበራዊ ቀውስ ገጥሞት እንደማያውቅ ይናገራል። "እርዳታ የምሰጣው ለቀደመ ጥፋቴ ራሴን ለመቅጣት አይደለም። ሰዎችን ማገልገል ክብር ነው" የሚለው ፓስተር ሚክ፤ በቀደመ ሕይወቱ ላደረገው ነገር ሁሉ ከራሱ ጋር ሰላም ማውረዱን ያስረዳል። ታዳጊ ሳለ ፓርክ ውስጥ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ እርዳታ ካደረገላቸው አንዱ መሆኑንም ይናገራል። ግለሰቡ የጎዳና ተዳዳሪና ጠጪ ነበር። መጠጥ እንዲያቆምና ከቤተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል የረዳው ሚክ ነበር። ከሁለት ዓመት በፊት ይህ ግለሰብ ሕይወቱ አልፏል። "ለሱም ይሁን ለቤተሰቡ ወይም ለፖሊስም ታዳጊ ሳለሁ እንደደፈረኝ አልተናገርኩም። ይህንን ያደረግኩት ለቀደመ ሕይወቴ ይቅር እንደተባልኩ ስላመንኩ ነው። እሱ እኔ ላይ ያደረገውን ሌሎች ላይ ባልፈጽምም ብዙ ሰው ጎድቻለሁ። በሱ ሀጢያት ውስጥ መኖር አልፈልግም። አሁን ነጻ ነኝ። ሕይወቴን በሀዘን ሳይሆን በይቅርታ አሳልፋለሁ።"
news-57297883
https://www.bbc.com/amharic/news-57297883
በካናዳ የቀድሞ ትምህርት ቤት የ215 ህፃናት አፅም በጅምላ መቃብር ተገኘ
በካናዳ 215 ህፃናት የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር ተገኝቷል።
ስፍራው የቀድሞ ትምህርት ቤት ሲሆን የካናዳ ቀደምት ህዝቦችን ወደ ነጭ ባህል ለማላመድ በሚል የተመሰረተ ነው። ካምሎፕስ ኢንዲያን ሬዚደንሻል ትምህርት ቤት የሚል መጠሪያ በተሰጠው ትምህርት ቤት ይማሩ የነበሩ ህፃናት ናቸው አፅማቸው የተገኘው። ትምህርት ቤቱ በአውሮፓውያኑ 1978 ተዘግቷል። የህፃናቱ በጅምላ መቀበር ያሳወቁት የቴኬኤምሉስፕ ቴ ሴክዌፑምክ ቀደምት ህዝቦች መሪ በያዝነው ሳምንት ሃሙስ ነው። ከነዚህ ተማሪዎች መካከል እስከ ሶስት አመት ድረስ ህፃናት እንደነበሩበት የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ ጠቁሟል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች የቀደምት ህዝቦች ልጆች በአዳሪነት የሚማሩባቸው ናቸው። ከአውሮፖውያኑ 1863-1998 150 ሺህ የሚሆኑት እነዚህ ህፃናት ከቤተሰቦቻቸው በአስገዳጅ ሁኔታ ተወስደው በነዚህ ትምህርት ቤቶች ይማሩ ነበር። በራሳቸው ቋንቋ መናገርም ሆነ ባህላቸውን እንዲከተሉ አይፈቀድላቸውም ነበር፤ ከፍተኛ ጥቃቶችንም አስተናግደዋል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስትን ትሩዶ "በአገራችን ታሪክ ውስጥ አሳፋሪ የሚባለውን በአሳዛኝ ሁኔታ የሚያስታውሰን ነው" ብለዋል። የካናዳ ቀደምት ህዘቦች ከሙዝየምና ሌሎች ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ህፃናቱ የሞቱበት ወቅት እንዲሁም ምክንያት ለማወቅ እየሰሩ ነው። ህፃናቱ እንዴት ሞቱ ለሚለው እስካሁን እርግጥ የሆነ ምላሽ አልተገኘም። ካምፕሉስፕ የተሰኝችው ከተማ የማህበረሰብ መሪ ሮዛኔ ካስሚር እንዳሉት የህፃናቱ ሞት በትምህርት ቤቱ አስተዳደር እንዳልተመዘገበና የማይታሰብ ጥፋት እንደተፈፀመ ማሳያ ነው ብለዋል። ካምሉፕስ ኢንዲያን ሬዚደንሻል ስኩል የነጮችን ባህል ለማላመድ ከተከፈቱ ትምህርት ቤቶች መካከል ትልቁ ነው። በሮማን ካቶሊክ አስተዳደር የበላይነትም ሲሆን የተከፈተው ወቅቱም በአውሮፓውያኑ 1890 ነው። የተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው በተባለበት በአውሮፓውያኑ 1950ዎቹ 500 ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተናግድ ነበር። ማዕከላዊው መንግሥት በአውሮፓውያኑ 1969 የማስተዳደሩን ሁኔታ ከተቀበለ በኋላ ለአካባቢው ተማሪዎች እንደ አዳሪ ትምህርት ቤት ይገለገሉበት የነበረ ሲሆን በ1978ም ተዘግቷል።
news-53473461
https://www.bbc.com/amharic/news-53473461
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የአርሶ አደሮችን ተስፋ ያሳካ ይሆን?
ጂፋሬ ግርማ አርባ ሁለት ዓመቷ ነው። ስምንት ልጆች አሏት። ሁሉም ልጆቿ አብረዋት ይኖራሉ። ትልቁ ሃያ ሁለት ዓመቱ ሲሆን የሙያ ስልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛል። ሌሎችም ልጆች እንደዚሁ ተማሪ ናቸው።
ወይዘሮ ጂፋሬ ግርማና ባለቤታቸው አቶ ለማ ሹሚ ከልጆቻቸው ጋር የኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝን ተከትሎ በተወሰዱ እርምጃዎች ምክንያት አሁን ሁሉም ልጆች ከመደበኛ ትምህርት ተራርቀዋል። እርግጥ ቤት ውስጥ ሲኖሩ ቤተሰባቸውን ሥራ ያግዛሉ፤ ከብቶችን ያግዳሉ፤ ኩሽና ውስጥ ምግብ በማብሰልም የሚችሉትን ይሰራሉ። የጅፋሬ ኩሽና በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ሚሊዮን የአርሶ አደር ቤተሰብ ማዕድ ቤቶች ብዙም የተለየ አይደለም። ከሳር የተበጀ ጣራ፣ ከጭቃ እና እንጨት የተሰራ ግድግዳ፣ እፍንፍን ያለ ክፍል። ሁለት በመጠን የተለያዩ ምድጃዎች ከእነሸክላ ጉልቻዎቻቸው ራቅ ራቅ ብለው አሉ፤ አንደኛው የእንጀራ መጋገሪያ ሲሆን ሌላኛው አነስ ያለ ለወጥ እና የመሳሰሉ ነገሮች መስሪያነት ያገለግላል። የኩሽናው ወለል ለወትሮው በእበት የሚለቀለቅ ቢሆንም ቢቢሲ በወርሃ ሐምሌ ቤቷ በተገኘ ጊዜ በክረምቱ ምክንያት ጨቅይቶ ነበር። ከኩሽናው ጋር በር በሚጋራ ክፍል ውስጥ ላሞች ይታለባሉ። ጂፋሬ ከአዲስ አበባ ብዙም በማትርቅ፤ ከእንጦጦ ተራራ ከአስር የማይበልጥ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ አካኮ በምትሰኝ መንደር ውስጥ ትኖራለች። መንደሪቷን የከበበውን ጫካ አቆራርጠው ትንሽ ከተጓዙ አመሻሽ ላይ መዲናይቱን ያጥለቀለቃት የኤሌክትሪክ ብርሃን ውቅያኖስ ሲንቦገቦግ ማስተዋል ይቻላል። የኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ ላይ ከተንቸረፈፈው የኤሌክትሪክ ኃይል ለአካኮ እንጥፍጣፊ አልደረሳትም። ወይዘሮ ጂፋሬ ግርማ ጭስ፣ ጥላሸት፣ አመድ ጂፋሬ ምግብ የምታበስለው፣ እንጀራ የምትጋግር ዳቦ የምትደፋው፣ ወጥ የምትወጠውጥው፣ ቡና የምታፈላው በአስር ሚሊዮኖች እንደሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን መሰሎቿ የኤሌክትሪክ ኃይል በሚሰጠው ምቾት፣ ቅልጥፍናና ሥራን የማቃለል ፀጋን በሚያላብሰው የአሌክትሪክ ኃይል ታግዛ አይደለም። ሁሉንም ነገር የምንሰራው በእንጨት ማገዶ ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ግን ከሰልም የቡታጋዝ (ኬሮሲን ምድጃ) እንጠቀማለን" ለቢቢሲ ብላለች። ኩሽና ውስጥ ከእንጨት ማገዶ ጋር መርመጥመጥ ፈታኝ ነገር ነውም ትላለች ጨምራ። "ሰውነታችን አመድ ይለብሳል፤ ጭሱ አሰከረን፤ ጥላሸቱን እንከናነባለን" በማለት ኩሽና ውስጥ የዕለት ከዕለት ገጠመኝ በአጭሩ ትገልጸዋልች። ለማገዶነት የሚውለው እንጨት በአካባቢው ካለው ጫካ የሚለቀም ሲሆን ይሄንን ማድረጉ "በጣም አድካሚ ነው" እንደ ጂፋሬ። ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ አካኮ መንደር የሚያቀና ተጓዥ በመንገዱ ዳርና ዳር ጉልበታቸውን እየተፈታተነ እንደሆነ አካላዊ ገፅታቸው የሚመስክርለትን ትልልቅ የማገዶ እንጨት ክምር የተሸከሙ ሴቶችን መመልከት ብርቅ አይሆንበትም። ብዙዎቹ የማገዶ እንጨቱን ሸጦ ጥቂት ገንዘብ ለማግኘት በሚመስል ምክንያት ወደ መዲናዋ ሸክሙን ይዘው ሲጓዙ ይስተዋላል። አንዳንዶቹ እንጨቱን ለግላቸው የማገዶ መጠቀሚያነት ወደ መንደራቸው ይዘው የሚሄዱ እናቶችና ወጣት ሴቶችም ማየት ይቻላል። ጂፋሬ እና ጎረቤቶቿ ወደቀያቸው የኤሌክትሪክ ኃይል በበቂ ሁኔታ ይዳረሳል ተብሎ ቃል ሲገባ ቢሰሙም ፍሬ ያለው ነገር ያለማስተዋላቸውን ለቢቢሲ ይናገራሉ። የኤሌክትሪክ ኃይል ቢገባ "ንፁህ እንሆናለን፤ ልብሳችን ይነፃል፤ በፍጥነት እንሰራለን፤ ሁሉ ነገራችን ይሻሻላል" ትላለች ጂፋሬ ለኤሌክትሪክ ኃይል እሷና ጎረቤቶቿ ያላቸውን ምኞችት ስትገልጽ። አቶ ለማ ሹሚ አስተዋጽኦ ለግድቡ ግንባታ ባለቤቷ ለማ ሹሚ ትንሽ ማሳው ላይ ገብስ ያበቅላል። ከዚህም በተረፈ ከብቶች ስላሉት እነርሱን ያረባል። ቤተሰቡን የሚደጉምበት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘትም መቀመጫውን ከመንደሪቷ መንደር ተጠግቶ ባደረገ አንድ የምርምር ተቋም በትርፍ ሰዐት በጥበቃነት ተቀጥሮ ይሰራል። ቢቢሲ ቤቱ በተገኘበት ማለዳ የእረፍት ቀኑ ስለነበር ቤት ውስጥ ተቀምጦ ከዘመዶችና ጎረቤቶቹ ጋር ይጨዋወት ነበር። አልፎ አልፎ በቅርብ ባለው መስክ ላይ ከብቶችን የሚያግድ አንደኛውን ልጁን ወጣ እያለ ያያል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለበርካቶች የኤሌክትሪክ ብርሃንን በማዳረስ፤ እያደገ ላለው የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት እየጨመረ የሚሄድ የኃይል ፍላጎትም ጥሩ መላ ይሆነኛል ብሎ ከጠኝ ዓመት በፊት የጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የለማን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያገኘ ነው። ለዚህም ለማ በጥበቃ ሥራ በሚያገለግልበት የምርምር ተቋም በኩል ከወርሃዊ ደምወዙ የሚቀነስ መዋጮ ከማድረጉም በዘለለ፤ መንግሥት ያቀረበውን ቦንድም ገዝቷል። "የሦስት መቶ ብር ነው የገዛሁት፤ ያው ባ'ቅማችን ልክ" ሲል ለግድቡ ያበረከተውን አስተዋጽኦ እየሳቀ ለቢቢሲ ተናግሯል። ገንዘቡ አምስት ዓመቱን ጠብቆ እንደተመለሰለትም ይናገራል። ከዚህም ባለፈ ከቀጣሪ መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ጋር በመሆን ከሦስት ዓመታት ገደማ በፊት የእኔ የሚለውን ግድብ በቦታው ተገኝቶ መጎብኘቱንም ይናገራል። "መቼም. . . እዚህ መድረሱ ተመስገን ነው" ይላል ከግድቡ ውሃ ለመሞላት መቃረብ ጋር በተያያዘ አስተያየቱን ሲጠየቅ። ለማ ግድቡ ኃይል ማመንጨት ሲጀምር ለመንደሩ የኤሌክትሪክ ኃይል ይዳረሳል የሚል እምነቱ ከወትሮውም የበለጠ የጨመረ ይመስላል፤ "ተስፋችን ብዙ ነው።" "ሰውነታችን አመድ ይለብሳል፤ ጭሱ አሰከረን፤ ጥላሸቱን እንከናነባለን" የአርሶ አደሩ ተስፋና ድርድሩ ኢትዮጵያ ካላት ሕዝብ ከ65 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው እንደ ጂፋሬ ግርማና ባለቤቷ ለማ ሹሚ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የሩቅ ህልም ነው። በዚህም ለዕለት ከዕለት የኃይል ፍልጎታቸው በርካታ እናቶችና ህጻናት የማገዶ እንጨት በመሰብሰብ በየቦታው መባዘን የዘወትር ህይወታቸው አካል ነው። ከዚህ ባሻገርም ምግብ ለማብሰልና ለብርሃን ጥቅም ላይ በሚውሉት ማገዶዎች የተነሳ ለተለያዩ ከባድ የጤና ችግሮች ይጋለጣሉ። በተጨማሪም በሴቶችና በታዳጊዎች የወደፊት ህይወት ላይም ከባድ ተጽእኖን ያሳርፋል። ግብጽና ሱዳን ግድቡ ለዘመናት የሕዝባቸው ህይወት መሰረት የሆነውን የአባይ ወንዝ ውሃ መጠን ይቀንስብናል በማለት በተፈጠረባቸው ስጋት እስካሁን በተደረጉት ድርድሮች ከስምምነት ላይ ባይደረስም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የገጠሩን ህዝብ ህይወት ለመቀየርና ምጣኔ ሃብቱ የሚፈልገውን ኃይል ለማቅረብ ግድቡን ሥራ ከማስጀመር ውጪ አማራጭ እንደሌለ እየገለጸ ነው። የኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተገንብቶ ይጠናቀቃል ተብሎ ከታሰበበት ጊዜ የዘገየ ቢሆንም አሁን የግንባታው ከሦስት አራተኛው በላይ መጠናቀቁ የተነገረለት ሲሆን በቀጣይ ዓመት የመጀመሪያ ደረጃ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል። አርሶ አደሩ ለማ ሹሚ ከሚያገኟት ትንሽዬ ወርሃዊ ገቢ አንስቶ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ለግንባተው አስተዋጽኦ ያደረገበት ይህ በአፍሪካ ትልቁ እንደሆነ የተነገረለት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ከ6 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ያመነጫል። ወደ አምሰት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ይደረግበትል ተብሎ የሚታሰበው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አብዛኛው በገጠር ነዋሪ ከሆነው ሕዝቧ መካከል በርከት ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋዳሽ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ባሻገርም ለበርካታ ሕዝቧ የሥራ ዕድልን ለሚፈጥሩ ኢንዱስትሪዎች ዋነኛ ግብአት የሆነውን ኃይል ከማቅረቡ ባሻገርም አሁን በውስን ደረጃ ለጎረቤቶቿ የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል በከፍተኛ መጠን ይጨምረዋል ተብሎ ይታመናል። ወይዘሮ ጂፋሬና ባለቤቷ አቶ ለማ የግድቡ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ ተስፋ የሰጣቸው ቢሆንም በወንዙ ውሃ ላይ የሚገባን ጥቅም ይከበር ከሚሉት ከሱዳንና ከግብጽ ጋር የሚደረገው ድርድር ገና መቋጫ አላገኘም። ቀድሞውንም ከስምነት ተደረሰም አልተደረሰ ግድቡን የውሃ ሙሌት እንደምትጀምር አስታውቃ የነበረችው ኢትዮጵያ የግንባታ ሥራዋን እያፋጠነችው እንደሆነ ይነገራል። በክረምቱ ምክንያት የሚጥለው ከፍተኛ የዝናብ መጠንም ለግድቡ ውሃ ማቀቢያነት በተዘጋጀው ቦታ ላይ መጠራቀም መጀመሩን የሳተላይት ምስሎች አሳይተዋል። በአገራቱ መካከል በአፍሪካ ሕብረት አማካይነት ሲካሄድ ቆይቶ ያለስምምነት የተጠናቀቀው ድርድር የተነሱ ጉዳዮችን በመመርመር ቀጣይ እርምጃዎችን እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።
43593602
https://www.bbc.com/amharic/43593602
241 ዓመት የተፈረደበት ጎረምሳ
በሚዙሪ ሁለት ሰዎች ላይ በመተኮስ ዝርፊያ የፈፀመው ጎረምሳ እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ድረስ እስርቤት እንዲቆይ ተፈርዶበታል።
ቦቢ ቦስቲክ በ2017 ቦቢ ቦስቲክ ምንጊዜም በጣም ማልዶ ነው ከእንቅልፉ የሚነቃው። ፊቱን ታጥቦ፣ ጥርሱን አፅድቶ ቁርሱን ይበላል። ከዛም ሲኤን ኤን አይቶ የማለዳ ፀሎቱን አድርሶ ማንበብ ይጀምራል። "ማረሚያ ቤቱ አደገኛ ነው። ባለፉት 20 ዓመታት ደግሞ የበለጠ ተበላሽቷል። በዚህ እስር ቤት ችግር እየዳኸም ቢሆን ይፈልግሃል" ይላል ቦስቲክ፤ ስለዚህ አንገቱን ደፍቶ ድምፁን አጥፍቶ መኖርን ምርጫው አድርጓል። የሕይወት ታሪኮችን ማንበብ ይወዳል፤ የሚፈልገው መፅሃፍ በእስርቤቱ ቤተ-መፃህፍት ውስጥ ከሌለ ቤተሰቦቹ ይልኩለታል። በቅርቡ ያነበበው በዋልተር አይሳክሰን የተፃፈውን "ዘ ኢኖቬተርስ"ን ነው። ቦስቲክ የቴሌቪዥኑን ድምፅ አጥፍቶ ከስር የሚመጣውን ፅሁፍ ብቻ ያነባል። ድንገት ሰበር ዜና ካለ ብቻ ድምፁን ከፍ ያደርገዋል ካልሆነ ግን ንባቡን ይቀጥላል። ከምግብ እና ንፋስ መቀበያ ሰዓት በኋላም ወደ ንባቡ ይመለሳል። ሲነጋም የተለመደው የህይወት ዑደቱ ይቀጥላል። ቦስቲክ በ16 ዓመቱ ነበር 17 ወንጀሎችን በመፈፀም ለተደራራቢ ወንጀሎቹ ተደራራቢ ፍርድ ተሰጠው። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ካልቀለበሰው በስተቀር እስከ 2091 ድረስ በእስር ላይ ይቆያል። አሁን 39 ዓመቱ ነው። ፍርዱን ሲያጠናቅቅ ደግሞ 112 አመት ይሞላዋል። ቦቢ ቦስቲክ አራት ወንድሞች እና እህቶች ያሉት ሲሆን ያለ አባት ነው ያደገው። "ምሳሌ የሚሆን ወንድ በቤታችን አልነበረም" ይላል "በጎዳናው ላይ እንደፈለኩ ስሆን የሚገስፀኝ ማንም አልነበረም።" የቦስቲክ ቤተሰቦች በድህነት ስለሚኖሩ በስፖርት ቡድኖች ውስጥ እንኳን ቁምጣ እና ጫማ አሟልቶ መሳተፍ አልቻለም። 10 ዓመት ሲሞላው ማጨስ እና መጠጣት ጀመረ። 12 ዓመት ሲሆነው ዕፅ መጠቀም፣ እድሜው አንድ ዓመት በጨመረ ቁጥር መኪና መስረቅና የተሰረቀ መኪና ማሽከርከር ጀመረ። "ለእኛ ያ ነበር የኑሮ ደረጃን መግለጫ" ይላል። "ሐብት ማለት የራሳችን ያልሆነን መኪና ማሽከርከርም እንደሆነ ነበር የሚሰማን።" አንድ ዕለት ግን ሕይወቱ አዲስ ምዕራፍ ጀመረች። ቦስቲክ 16 ዓመት ሞልቶት ነበር። ከሚኖርበት ከተማ ራቅ ብሎ የጓደኛው ጓደኛ የሆነ ልጅ ቤት ሀሽሽ እያጨሱ፣ ጅን እየጠጡ ነበር። ከዚያም የሴት ጓደኛቸው ወደ ደጅ ወጣች። "በጎረቤት ከሚኖር አንድ ልጅ ጋር እያወራች ነበር" ይላል፤ "መታት፤ እኛን እንደምትጠራን ነገረችው፤ እንድትጠራን ነገራት" ቦስቲክ እና ጓደኞቹ በስሜት ተሞልተው ወደ ልጁ ሄዱ። "ለዚያ ነው ሽጉጡን የያዝኩት" ይላል። ቦቢ ቦስቲክ በ2006 አንድ ጥይት እንኳ ሳይተኮስ ጠቡ በረደ። ቦስቲክ እና ጓደኛው ዶናልድ ሁትሰን ሽጉጡን እንደያዙ ተጨማሪ ሐሺሽ ለማጨስ ሄዱ። "እያጨስን እያለ አንድ ልጅ አየን፤ የዚያ ሰፈር ልጅ እንዳልሆነ ገብቶናል። በርካታ ነገሮች በመኪው ላይ ጭኗል።" ልጁ ለተቸገሩ ሰዎች ስጦታ እየሰጠ ሲሆን ሁለት መኪና ሙሉ ስጦታ ነበር። አንደኛው መኪና የገና ዛፍ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ያገለገለ ሶፋ ነው። "አቅደንበት አልነበረም" ይላል ቦስቲክ ። "አየናቸው፤ ከጓደኛዬ ጋር ተያየን፤ ሁሉም ነገር ቅፅበታዊ ነው ሽጉጤን መዝዤ አወጣሁ።" ቦስቲክ እና ሁትሰን ወደ መኪናው ተጠጉ። አንድ ልጅ ከመኪናው ላይ ሶፋውን እያወረደች ነበር። ሽጉጡን ጭንቅላቷ ላይ ደቀኑባት። ለማምለጥ ስትሮጥ ተከተሏት። ፍቅረኛዋ ስልክ እያነጋገረ ነበር። ሲያያቸው ጮኸባቸው። እርሷን ትተው እርሱን ማባረር ጀመሩ። ተኩሰው ከጣሉት በኋላ መቱት የያዘውንም ገንዘብ እንዲሰጣቸው ጠየቁት። ገንዘቡን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር ቦስቲክ ተኮሰበት። "ለምን እንዳደረኩት አላውቅም፣ ልጁን ለመግደል ፈልጌ አልነበረም፣ ላቆስለውም ፈልጌ አልነበረም፣ ማድረግ አልነበረብኝም፣ ይፀፅተኛል... " ጥይቱ ልጁን መታችው። ከዚያ በኋላ ያለውን 500 ዶላር አውጥቶ ሰጠው። ቦስቲክ እና ሁትሰን ግን አልበቃቸውም። ስጦታውን በሚሰጡት ቡድን ውስጥ የነበረችውን ሴት የቆዳ ጃኬት ወሰዱ። ከእርሷ ጋር ከነበረውም ሰው ብር ጠየቁ፤ የኪስ ቦርሳውን ወረወረላቸው፤ ተኩሰው መቱት። ቦስቲክ እና ሁትሰን መጀመሪያ ወደ ነበሩበት ልጅ ቤት ተመለሱ። እዚያ መቆየት እንደማይችሉ ነገረቻቸው። "ከቤቱ ወጥተን ወደ አንድ ጥግ ሄድን" ይላል ቦስቲክ። ያኔ ነው ሌላ መንገደኛ ያገኙት። ሴትየዋ ከመኪናዋ ውስጥ የታሸገ ጥቅል እያወጣች ነበር። ቦስቲክ እና ሁትሰን ሽጉጣቸውን ሴትየዋ ጭንቅላት ላይ ደቀኑባት። የመኪናዋን ቁልፍ ተቀብልው እርሷን ከኋላ ካስገቡ በኋላ አስነስተው ሄዱ። የለበሰችውን ኮት እና የጆሮ ጌጥ እንድታወልቅ አደረጉ፣ ቦርሳዋን ተቀበሏት። ሁትሰን የደበቀችው ብር ይኖራል ብሎ ስለጠረጠረ ጡቶቿን እየነካ ጭምር በረበራት። ቦስቲክ እና ሁትሰን ጥቂት ከተከራከሩ በኋላ ሴትየዋን ጭር ያለ ስፍራ ጥለዋት ሄዱ። ከአንድ ሰዓት በኋላም በቁጥጥር ስር ዋሉ። " በፖሊስ እስክያዝ ድረስ የጉዳዩ ክብደት አልታየኝም ነበር" በማለት "ከዛ በኋላ ነው ፀፀት ውስጤን ያኝክ የጀመረው" ይላል። ዶናልድ ሁትሰን በ2016። እንደ ሙዚሪ ማረሚያ ቤቶች ድረገፅ ከሆነ ቅፅል ስሙ "ኤኬ-ዲ" እና "ሱሳይድ" ይሰኛል። ከተያዘ ከአራት ወር በኋላ ቦስቲክ ችሎት ፊት ሳይቀርብ ጥፋቱን እንዲያምን እና 30 ዓመት እንዲታሰር ተነገረው። እስሩ አመክሮም እንዳለው ቢገለፅለት እምቢ አለ። ከስምንት ወራት በኋላ ደግሞ የችሎቱን ውሳኔ ሰምቶ ዳኛው ለጥፋተኝነቱ የሚሰጡትን እንዲቀበል ተነገረው። እርሱ ግን በእንቢተኝነቱ ፀና። "አባቴ፣ እንጀራ አባቴ ሌሎችም ይመክሩኛል። አባቴ እስር ቤት ቢሆንም ፃፍኩለትና የማታውቀውን ውሳኔ አትቀበል ምክንያቱም ቀጥሎ ምን ሊመጣ እንደሚችል አታውቅም አለኝ" ስለዚህ ችሎት ፊት ቀርቤ ለመከራከር ወሰንኩ ይላል። "ጥፋተኛ መሆኔን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ሁሌም በችሎት ፊት የተሻለ እድል እንደማገኝ አስብ ነበር። እንደ 17 ዓመት ወጣት በትክክል ማመዛዘን አልቻልኩም።" ቦስቲክ ፍርድቤት ሲቀርብ በ17 የተለያዩ ወንጀሎቹ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኘ። በተጨማሪም በስምንት መሳሪያ ታጥቆ ወንጀል በመስራት ሦስት የዘረፋ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባለ። በ1997 የጥፋተኝነት ውሳኔው ከመሰጠቱ በፊት ጠበቃው ለዳኛው ደብዳቤ እንዲፅፍ ሃሳብ አቀረበለት፤ ተስማምቶ አራት ጊዜ ፃፈ። እያንዳንዱ ደብዳቤው ነገሮችን ከማቅለል ይልቅ አባባሱት። ከሁለት እና ከሦስት ዓመት በፊት የፃፋቸውን ደብዳቤ ሲያነባቸው "መለስ ብዬ ሳያቸው፣ በቂ ፀፀት አላሳየሁም" ይላል ቦስቲክ። የቦስቲክ እናት ዲያናም ለዳኛው ደብዳቤ ፅፋለች "ከቤተሰቦቼ ከደረሱኝ ውብ ደብዳቤዎች አንዱ ነው፤ ነገር ግን ሊታደገኝ አልቻለም።" ችሎቱን ያስቻሉት ዳኛ ኢቭሊን ቤከር "ደብዳቤ ፃፍክልኝ፣ እንዴት ያለህ ብልህ ነህ፣ እንዴት ያለኸው ምጡቅ ነህ፣ በዓለም ላይ ካሉ ሁሉ እንደምን የተሻልከው ነህ" "በዚህ ችሎት ከቆሙት ሁሉ ቂሉ አንተ ሳትሆን አትቀርም። ትንሽ እንኳ ስለጥፋትህ ፀፀት አይሰማህም፤ ከዚያ ይልቅ ስለራስህ ታዝናለህ" በማለት ዳኛዋ ቦስቲክ ላጠፋቸው ጥፋቶች በጥቅሉ ከመቅጣት ይልቅ ለእያንዳንዱ ጥፋቶች ቅጣቱን እንዲቀበል ውሳኔ አስተላለፉ። "ማረሚያ ቤት ውስጥ ትሞታለህ" አሉት ከውሳኔው በኋላ። የቦስቲክ ጓደኛ ዶናልድ ሑትሰን ግን የችሎቱን ውሳኔ እቀበላለሁ ብሎ ቀድሞ ስለተስማማ 30 ዓመት ተፈረደበት። "241 ዓመት ሲፈረድብኝ እውነታው ፍንትው ብሎ ታየኝ፤ እናም እስር ቤት ውስጥ እንደምሞት ነገረችኝ" ይላል ቦስቲክ። "ይህ ሲሆን ዓለም ተገለባበጠችብኝ፤ እውነታው ገዝፎ ታየኝ፤ ሕይወቴ ተወስዷል። የማንቂያው ደወል የተሰማኝ ከዚህ በኋላ ነበር።" ቦስቲክ በ14 እና በ15 ዓመቱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ጀምሮ ቢያቋረጥም ሁለት እና ሦስት ዓመት እስር ቤት ካሳለፈ በኋላ ማንበብ ጀመረ። መጀመሪያ አንብቦ የተመሰጠበት የማልኮም ኤክስ ግለ ታሪክን ነው። "እኔ ባለፍኩበት ያለፈ ግለሰብ ነው" ይላል ከዚያ በኋላ በመፅሃፍ ላይ መፅሃፍ፣ በንባብ ላይ ንባብ ሆነ። ትምህርቱን አጠናቀቀ ከዚያም መጽሀፍ መጻፍ ጀመረ። አራት ኢ-ልቦለዶች እና ስምንት የግጥም መጽሐፍትን ጻፈ። የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎችን መውሰድ ጀመረ። ከወሰዳቸው ስልጠናዎች መካከል አንዱ የተበዳዮች መብት አቀንቃኝ ይሰኛል። "ከወንጀሉ መፈፀም ጀምሮ እስከ ፍፃሜ ድረስ ያለውን እና ተበዳዮች የሚያልፉበትን ያሳያል" ይላል ቦስቲክ። "ወንጀሉን ስፈፅም የበደልኳቸው ሰዎች እነማን እንደሆኑ አላሰብኩም ወይም ደግሞ ምን እንዳደረጉኝ አላሰብኩም። ስልጠናው የተበዳዮቹን ወገን እንዳይ አድረጎኛል። ስሜታቸውን እንድረዳ እና እነሱም መብት ያላቸው ሰዎች መሆናቸውን አሳይቶኛል። " "ስለሚያልፉበት የስሜት ስብራት፣ ከዚያም እንዴት እንደሚያገግሙ መርዳት እንደሚቻል ተምሬያለሁ። እኔ ያደርስኩባቸው ነገር ስሜታቸው እንዲሰበር በማድረጉ እና ተበዳዮችን ራሴ ስለፈጠርኳቸው ይህንን የማደርገው ከልቤ ነው።" ቦስቲክ ዲግሪውን ለማግኘት መውሰድ ያለበት ክፍሎች አሉ። "ግድ የለሽነት የእስር ቤቱ ህግ ነው" ይላል። "ወጣቶቹ ተኝተው ነው የሚውሉት። አያነቡም፣ አያጠኑም፣ እኔ እስር ቤት በገባሁበት ወቅት እናነብ ነበር አሁን ግን ቴሌቪዥንና ጨዋታ ብቻ ነው። ሁሉ ነገር ጨዋታ ሆኗል።" ቦስቲክ በትምህርት ያምናል።ወደፊት ክህሎቱን ተጠቅሞ እርሱ እየሰረቀ ይኖር የነበረበት ጎዳና ላይ የሚገኙ ህፃናትን መርዳት ይፈልጋል። መጀመሪያ ግን ከእስር ቤት መውጣት ይኖርበታል። ለ25 ዓመት በዳኝነት አገልግላ ጡረታ የወጣችው የ69 ዓመቷ ቤከር፤ ቦስቲክን በደንብ ታስታውሰዋለች። የፃፋቸውንም ደብዳቤዎች ጨምሮ። በሥራ ዘመኗ ከሰጠችው ውሳኔዎች ሁሉ ይህ የቦስቲክ 241 ዓመት የእስር ቅጣት ትልቁ ነው። "መለስ ብዬ ሳስታውሰው በወቅቱ ቦቢን ለአካለ መጠን እንደደረሰ፣ እንደ አዋቂ ሰው ነበር ያየሁት ያም ስህተት ነበር" ትላለች። 30 ዓመት ብቻ ቢታሰር ይበቃው ነበር ስትልም ትናገራለች። ያ ሆኖ ቢሆን ከአመክሮ ጋር ቦስቲክ በዚህ ዓመት ከእስር ይወጣ ነበር ማለት ነው። "ስለ ቦቢ እንዳነበብኩት ከሆነ አሁን ያኔ የቅጣት ውሳኔዬን ያስተላለፍኩበት የ16 ዓመት ልጅ አይደለም። በርካታ በጎ ተግባሮችን እያከናወነ ነው" ትላለች። ቦስቲክ ለበደላቸው ግለሰቦች የይቅርታ ደብዳቤ ለመፃፍ ከ10 ዓመት በላይ ፈጅቶበታል። ምንም ምላሽም አልሰጡትም። በመገናኛ ብዙሃንም ላይ ቀርቦ ይቅርታ ጠይቋል። "የበደልኳቸው ግለሰቦች በእስር ቤት ውስጥ እንድሞት የሚፈልጉ ከሆነ ውሳኔያቸውን አከብራለሁ።" የአሜሪካው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚቀጥለው ወር የቦስቲክን ጉዳይ ለማየት ይሰየማል። የሕግ ክርክር የሚነሳበት ቢሆንም የረዥም ጊዜ ፍርደኛው ቦስቲክ ሊለቀቅ ይችላል። ቦስቲክ ዛሬም ተስፋ ያደርጋል "ነፃነት አእምሮህን ለቆ አይሄድም፣ እዚህ እስር ቤት ቴሌቪዥን ስታይ፣ ወጥተህ አየር ስትቀበል፣ ነፃነት እንደሌለህ ታስባለህ፤ ስለዚህ ሁሌም ትመኘዋለህ" ይላል።
sport-46271738
https://www.bbc.com/amharic/sport-46271738
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን መግለጫ አንድምታ
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል መንግሥት ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከከፍተኛ ሙስና ጋር በተያያዘ የጀመረው ዘመቻ በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ከድህነት አረንቋ ለመውጣት በትጋት እየሰራ ያለን ህዝብ ወደ ማንበርከክ አጀንዳ ዞሯል ብለዋል።
"ነገሩ ከሰብዓዊ መብትና ሙስና ጥያቄዎች ወጥቶ ይህንን ህዝብ ወደ መምታት የፖለቲካ እርምጃ ሄዷል፤ ለዚህም ነው አንቀበለውም ያልነው'' ሲሉ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አቋማቸውን ገልጸዋል።። የቀድሞ የፌደራል ስነ ምግባርና ፀሩ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ ክፍል ሃላፊ የነበሩት አቶ ዮሃንስ ወልደ ገብርኤል የጠቅላይ አቃቤ ህግ በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ሙስና ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የማዋል እርምጃ አንድ ብሄር ላይ ያነጣጠረ ነው ብለው አያምኑም። • ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከጠበቃቸው ጋር ፍርድ ቤት ቀረቡ • ስደተኞቹ ሊቢያ ወደብ ላይ ከመርከብ አንወርድም አሉ ''የፍትህ አሰራሩ ሁሉ አሁን ባለው የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብ ቢቃኝ ለእኔ የሚደንቀኝ አይሆንም'' በማለት እነ አቶ ስዬ አብርሃ በሙስና የተከሰሱበትን ወቅት በምሳሌነት ያነሳሉ። በወቅቱ በወሳኝ የስልጣን ማማዎች ላይ የነበሩትና እነ አቶ ስዬንም የከሰሷቸው ከትግራይ የሆኑ ሰዎች በመሆናቸው በዚያ ወቅት ምንም የተባለ ነገር እንዳልነበር ይናገራሉ። ''የዚያን ጊዜ ግን የትግራይ ማህበረሰብን ለማጥቃት ነው አልተባለም ነበር'' ይላሉ አቶ ዮሃንስ። በተቃራኒው በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆኑት አቶ የማነ ዘርአይ የፀረ ሙስና ዘመቻው የትግራይ ብሄር ላይ ያነጣጠረ ነው በማለት ይከራከራሉ። አቶ የማነ አቃቤ ህግ መግለጫ አውጥቶ እስሮች ተፈጻሚ መሆን ከጀመሩ በኋላ ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸውም ሆነ የሌላቸው የመገናኛ ብዙሃን 'አንድ ቡድን፣ አንድ ቦታ ላይ የተሰበሰቡ' በማለት ይዘግቡ የነበረበት መንገድ ወደ ትግራይ ያነጣጠረ መሆኑን የመጀመሪያ መከራከሪያቸው አድርገው ያስቀምጣሉ። በሁለተኝነት ደግሞ እርምጃው ትኩረት ያደረገው በጣም ወሳኝ በሆኑ የመንግሥት ድርጅቶች እንደ መከላከያና ሜቴክ በመሰሉና በተጨማሪም ጨምሮ በንግድ ማህበረሰቡ ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች በብዛት ያነጣጠሩት በአንድ ብሄር ላይ ብቻ ነው ይላሉ። አክለውም ግለሰቦቹ አጥፍተው ከሆነ መታሰራቸው ምንም ችግር የለውም፤ ነገር ግን ለምሳሌ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ስር ሲውሉ ዜናው እና የምርመራ ዘጋቢ ፊልም የቀረበበት መንገድ ህግን የጣሰና አንድ ብሄር ላይ ያተኮረ ለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ ይገልፃሉ። በተጨማሪም ባለፉት ዓመታት የተሰሩትን ነገሮች ሁሉ መጥፎ እንደነበሩ አድርጎ ማቅረብም ሌላው ትልቅ ችግር ነው ብለው ያምናሉ። ''የደህንነትና የመከላከያ ኃይሉ የተሰበረ ተደርጎ ሲቀርብ ይህችን ሃገር በምን ሊያስተዳድሯት ነው በሚያስብል ደረጃ ነው።'' የሚሉት አቶ የማነ ''ኢትዮጵያ ውስጥ የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ችግር እንደነበረ ሁላችን የምናውቀው ነገር ሆኖ ሳለ፤ ኢኮኖሚው፣ መከላከያውና የደህንነት ቢሮው ጥሩ ተብለው የሚጠቀሱ ናቸው።'' እነዚህን ሁሉ ምንም ጥሩ ጎን እንዳልነበራቸው አድርጎ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት ሃሳባቸውን ያጠቃልላሉ። • "በኢትዮጵያ 93 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ መጸዳጃ ቤት የለውም" • የሰው ልጅ ዘር እየመነመነ ነው በሌላ በኩል ለአቶ ዮሃንስ ትልቁ ጥያቄ በብዙ ችግሮች የተተበተቡት የአገሪቱ የፍትህ ተቋማት አቅመ ቢስነት እንደሆነ አፅንኦት ይሰጣሉ። ''የምርመራ፣ የአቃቤ ህግ፣ የፍርድ ቤትና የማረሚያ ተቋማት ብቃታቸውንና አቅማቸውን አጥተዋል፤ ተዳክመዋል። የማህበረሰቡን አመኔታ ያገኙ ተቋማት ናቸው ብዬ አላምንም።'' የሚሉት አቶ ዮሃንስ ተቋማቱ አቅም ስለሌላቸው ግን መጠየቅ ያለባቸው ሰዎች ሳይጠየቁ ዝም መባል እንደሌለባቸው ያስረዳሉ። የፀረ ሙስና ዘመቻውን በሚመለከት የትግራይ ክልል ከፌደራል መንግስት የተለየ አቋም መያዙን እንዴት እንደሚረዱት የተጠየቁት አቶ ዮሃንስን ''ህገ መንግሥቱ ላይ ምንም የሚያምታታ ነገር የለም፤ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ስርአት ተከትሎና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካሟላ፤ አይደለም የፌደራል መንግስቱ ሃይል፤ የራሱ የክልሉ መንግስት ያንን ተጠርጣሪ ያለ ምንም ጥያቄ ማቅረብ ይገባዋል።'' በማለት ይህ ካልሆነ ግን ህገመንግስቱን ላይ የተቀመጠው ነገር እርባና ቢስ ሆነ ማለት እንደሚሆነ ያስረዳሉ።
48442224
https://www.bbc.com/amharic/48442224
"የግንቦት 20 ታሪካዊነት አጠያያቂ አይደለም" ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ
ግንቦት 20 እንደዘንድሮ አከራካሪ የሆነበት ጊዜ ያለ አይመስልም። በዓሉ አምባገነኑ የደርግ ሥርዓት የተወገደበትና ኢትዮጵያ ወደዲሞክራሲ ሥርዓት የተሸጋገረችበት ዕለት በመሆኑ በድምቀት መከበሩ መቀጠል አለበት የሚሉት እንዳሉ ሁሉ፤ ይህ ቀን ወንድም ወንድሙን ገድሎ ሥልጣን የያዘበት ዕለት ነው፤ ወደሥልጣን የመጣውም ሌላ አምባገነን ሆኖ እንዴት ክብረ በዓል ይሆናል የሚሉም አሉ።
በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ አሉላ ሰለሞን በዓሉን ማክበር አለብን ከሚሉት ወገን ናቸው። ምክንያታቸውን ሲጠቅሱም የነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት አብቅቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ሰላም የተሻጋገረበት ነው ይላሉ። አክለውም "ኢትዮጵያ እንደ አገር ወደአዲስ ፖለቲካዊ ምዕራፍ የተሸጋገረችበት ነው የሚለውን አብዛኛው ሰው ይስማማበታል። ተከትሎ በመጣው ፖለቲካዊ ሥርዓት ስምምነት ባይኖርም መሠረታዊ በሆኑ እውነታዎች መለያየት የሚቻል አይመስለኝም" በማለት ያለው የፖለቲካ ልዩነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ቀኑ መከበር አለበት ይላሉ። • "ጥቃት የደረሰባት ሴት ከግንኙነቱ ለመውጣት 10 ዓመት ይፈጅባታል" • ከሰላሳ በላይ የጴንጤ ቆስጣል አማኞች አሥመራ ውስጥ ታሰሩ • ኮሎኔል መንግሥቱ ለህፃናት አምባ ልጆች ደብዳቤ ላኩ አቶ አሉላ በዓሉ መከበር የለበትም የሚሉ ወገኖችንም ሀሳብ አከብራለሁ ያሉ ሲሆን፤ ሁሉም በግንቦት 20 ድል ደስተኛ እንደማይሆን አንደሚረዱም ሳይጠቅሱ አላለፉም። በአገሪቱ የፕሬስ ነፃነት ባልነበረበት ወቅት በግንቦት 20 የተገኘው ድል ለፕሬሱ ነፃነት የሰጠ ዕለት መሆኑንም ይጠቅሳሉ። በሂደት ፕሬሱም ሆነ ዲሞክራሲው ማደግ በነበረበት መጠን አላደገም የሚለው ሌላ መነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ የሚቆይ ነው የሚሉት አቶ አሉላ፤ በታሪክ ግን ነፃ ፕሬስ በኢትዮጵያ ውስጥ የመጣበት መሆኑ እንደማይካድ ይጠቅሳሉ። ጋዜጠኛና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚጽፉት አቶ ደጀኔ ተሰማ በበኩላቸው፤ ግንቦት 20 ''አምባገነን መንግሥት ተገርስሶ ሌላ አምባገነን መንግሥት ወደሥልጣን የመጣበት ቀን ቢሆንም በዚህኛው መንግሥት ለውጦች እንደመጡ እረዳለሁ'' ይላሉ። ደርግ መስከረም 2 ብሎ ሲያከብረው በነበረው በዓል እና ኢህአዴግ ግንቦት 20 ብሎ በሚያከብረው በዓል መካከል ምንም አይነት ልዩነት አይታየኝም የሚሉት አቶ ደጀኔ፤ ደርግ መሬት ላረሹ የሚለው የሕዝብ ጥያቄ መመለስ መቻሉን አስታውሰው፤ የግንቦት 20 ድልን ተከትሎ የመጣ ለውጥ ቢኖርም የለውጡ ተጠቃሚ የሆኑት ''ድሉ የኛ ነው የሚሉት ወገኖች ናቸው'' ይላሉ። የቀድሞው ግንቦት 7 አርበኞች ግንባር አመራር የነበሩት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ደግሞ በዓል የሚከበረው ለሕዝብ ነው፤ ሕዝብ ካላከበረው አልተቀበለውም ማለት ነው ስለዚህ መከበር የለበትም ባይ ናቸው። "ትንሽ ልጅ እያለሁ መስከረም 2 ይከበር ነበር" የሚሉት አቶ ኤፍሬም፤ ይህ የፊውዳሉ ሥርዓት የተገረሰሰበት በዓል በመሆኑ ትልቅ በዓል ነበር ይላሉ። ሕወሐት ሥልጣን ሲይዝ ይህንን በዓል ማክበር አቁመን እነሱ የገቡበትን ቀን ማክበር ጀመርን በማለት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት 20 ዓመታት ያለፈችበትን ሁኔታ ማሳያ በመሆኑ "የሚፈጥርብኝ ስሜት ጥሩ አይደለም" ይላሉ። አቶ ኤፍሬም "ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት የለውጥ ሂደት ራሳቸውን አግልለው አሁንም የሚያስቡት ኢትዮጵያን ወደኋላ መመለስ ነው" ይላሉ። አክለውም "እነሱ የቆሙለትን ዓላማና አሁንም የሚታገሉለትን ዓላማ ስመለከት መከበር የለበትም እላለሁ" በማለትም ሀሳባቸውን ይቋጫሉ። ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ በበኩላቸው የ17 ዓመቱ ጦርነት የአንድ እናት ልጆች የተጋደሉበት፤ የተዋደቁበት ጦርነት ነው ይላሉ። በዓሉ መድፍ እየተተኮሰ መከበሩ "ከመጀመሪያውም ደስ አላለኝም" በማለት፤ ወደፊትም መከበር ካለበት እስከዛሬ ይከበር እንደነበረው መሆን የለበትም ሲሉ ምክራቸውን ይሰጣሉ። ፕሮፌሰር ገብሩ ግንቦት 20 እንደ በዓል ባይቆጠርም ታሪካዊነቱ አጠያያቂ አይደለም ይላሉ። አቶ ደጀኔ በበኩላቸው ግንቦት 20 ልንጠየፈውም ሆነ ልናወድሰው የሚገባ ቀን አይደለም የሚል ሃሳብ ይሰነዝራሉ።
50969763
https://www.bbc.com/amharic/50969763
የቤሻንጉል ክልል ምክር ቤት አባል እና የኢኮኖሚ ዘርፍ ሰብሳቢ 'በታጣቂዎች' ተገደሉ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል እና የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አብዱላሂ ሶጃር፤ ዛሬ ማለዳ (ሐሙስ) በታጠቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት መገደላቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።
አቶ አብዱላሃይ ሶጃር የተከበሩ አቶ አብዱላሂ ለመንግሥት ሥራ ከአሶሳ ወደ ነቀምት በመጓዝ ላይ ሳሉ መገደላቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሠ በየነ ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ዛሬ ማለዳ 1፡30 ላይ ከአሶሳ ወደ ነቀምት በመጓዝ ላይ እያሉ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ቤንጓ አካባቢ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱም በመኪናው ውሰጥ የነበሩ አንድ ወንድና አንድሴት ላይ ጉዳት መድረሱን የተናገሩት ኃላፊ በህክምና እርዳታ ላይ እንደሚገኙም ጨምረው ገልፀዋል። አቶ መለስ በቅርቡ አንድ የፖሊስ ኃላፊ በታጣቂዎች መገደላቸውን ገልፀው፣ ከክልሉ ተነስቶ አሮሚያ ክልልን የሚያቋርጠው መንገድ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ስጋት የነበረበት መሆኑን አስታውሰዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ባሉ የተለያዩ አካባቢዎች የመንግሥት ኃላፊዎችን ኢላማ አድርገው በታጣቂዎች ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች ቢያንስ ስምንት ኃላፊዎች መገደላቸው ተነግሯል። በጥቃቱ ሌሎችም ሰዎች ሰለባ በመሆናቸው የሟቾች ቁጥር ከፍ ያለ ነው።
44625189
https://www.bbc.com/amharic/44625189
በዋሽንግተን ዲሲ ለጠ/ሚ አብይ የድጋፍ ሰልፍ ተደረገ
ነዋሪነታቸውን በአሜሪካን ሀገር ያደረጉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ትናንት ሰኔ 20/2010 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመደገፍ ያለመ ሰላማዊ ሰልፍ አከናውነዋል፡፡
ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት በተደረገው ሰልፍ ላይ፣ የአዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ርምጃዎች የሚደግፉ እና ስለ ኢትዮጵያ አንድነት የሚሰብኩ መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡ ለዓመታት የኢትዮጵያን መንግሥት በሚቃወሙ መድረኮች እና ሰልፎች ላይ በመገኘት ንግግሮችን በማድረግ የሚታወቀው አርቲስት ታማኝ በየነ ጨምሮ ታዋቂ የፖለቲካ እና የኪነጥበብ ሰዎች በሰልፉ ላይ መገኘታቸውም ታውቋል፡፡ በሰልፉ ላይ ቅዳሜ ሰኔ 16 በአዲስ አበባ በነበረው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ ለሞቱ እንዲሁም በዓመታት ውስጥ ‹ለፍትህ እና እኩልነት ሲታገሉ› ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የህሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡ ሽመልስ ወልደ ገብረ-ሰንበት የተባሉ የሰልፉ ተሳታፊ ‹‹ሰልፉከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ከተቃውሞ ወጥተው ለምስጋና እና ደስታ የተሰባሰቡበት ነበር ›› በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል፡
news-53101250
https://www.bbc.com/amharic/news-53101250
የህዳሴው ግድብ ድርድር ወደ ማይታረቅ ቅራኔ ደረጃ ደርሶ ይሆን?
ኢትዮጵያ የሦስትዮሽ ስምምነት ከመደረሱ በፊት የግድቡን ውሃ ሙሌት የምትጀምር ከሆነ ጉዳዩን ወደተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት እንወስደዋለን ስትል የነበረችው ግብፅ በባለፈው ሳምንት አርብ ምክር ቤቱ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቃለች።
ግብፅ ባስገባችው የስልሳ ሦስት ገፅ ደብዳቤ ላይ ሦስቱ አገራት በድርድሩ እንዲቀጥሉና ፍትሃዊና ሚዛናዊ ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ምክር ቤቱ ጣልቃ በመግባት እንዲያረጋግጥ ጠይቃለች። ምክር ቤቱ ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ኢትዮጵያ ውሃ ከመሙላት እንድትታቀብና ጣልቃ በመግባት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብላለች። በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይም በመገኘት ጉዳዪን ማስረዳትም እንደምትፈልግ በደብዳቤው ላይ ገልፃለች። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው ባለፈው ሳምንት አርብ ከአሶሺየትድ ፕሬስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ግድቡን ለመሙላት የሦስትዮሽ ስምምነት አስገዳጅ እንዳልሆነና በታቀደለትም የክረምት ወቅት የመጀመሪያ ደረጃ ሙሌት ይካሄዳል በማለት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ግብጽ "በወንዛችን ላይ የሚደረገውን ልማት ለመቆጣጠር እየሞከረችም ነው" በማለት ወቅሰዋል። ስምምነት ላይ መድረስ ፈታኝ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ገዱ " ስምምነት ላይ መድረስ ባንችልም በያዝነው ዕቅድ መሰረት የግድቡን የውሃ ሙሌት እንጀምራለን። የሌሎቹን ምርቃት የምንጠብቅ ከሆነ ግድቡ ለዓመታት ምንም ሳንሰራበት ጥቅም አልባ ነው የሚሆነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ አንፈቅድም" ብለዋል። አክለውም "ኢትዮጵያ በራሷ ውሃ ለማልማት ግብጽና ሱዳንን አትለምንም" ያሉት አቶ ገዱ ግድቡን በራሷ ወጪ መስራቷንም ጠቁመዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አክለውም ግድቡ የቀጠናው ትብብር ማጠናከሪያ ነው እንጂ፤ ውዝግብና ጦርነት መጎሰሚያ መሆን አይገባውም ብለዋል። "ግብጽውያን በህዳሴ ግድብ ላይ የያዙትን ፕሮፓጋንዳ አጠናክረውታል። የፖለቲካ ቁማርም ነው እየተጫወቱ ያሉት። አንዳንዶቹም ጦርነት እንዲነሳ የሚጠብቁ ይመስላሉ" ብለዋል። ግብጽ ኢትዮጵያ ግድቡን ውሃ የመሙላት ተግባር በቀጠናው እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ሰላምና ደኅንነት ጠንቅ ነው ማለቷ እንዳሳዘነውም በተጨማሪ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር ቤት በላከው ደብዳቤ ገልጿል። የሦስትዮሽ ስምምነቱ ሳይጠናቀቅ ግብጽ ምክር ቤቱን ጣልቃ እንዲገባ መጠየቋ ግራ የሚያጋባ ቢሆንም "ድርድሩ ፍሬ አልባ እንዲሆን እየሰራች ከነበረችው ግብጽ" የሚጠበቅ ነው ብሏል። የግድቡ ድርድር ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው እየጣረች እንደሆነ ያተተው መግለጫው ግብጽ ቀጠናዊ እንዲሁም አህጉራዊ መፍትሄዎችን ያልሻተችውና የዘለለችው በዚሁ ምክንያት ነው ይላል። ግብጽ በጎርጎሳውያኑ 1959 የተፈረመውና፣ የአብዛኛውን የውሃውን ድርሻ የሚሰጣትን የቅኝ ግዛት ስምምነት ሙጥኝ ብላ ታሪካዊ ተጠቃሚነት በሚል መርህ የወንዙን ውሃ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ለብቻዋ የመጠቀም ፍላጎት እንዳላት ደብዳቤው ጠቅሷል። ስምምነቱ ኢትዮጵያን ያላካተተ ከመሆኑ በተጨማሪ ግብጽ 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንዲሁም ሱዳን 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንድታገኝና 86 በመቶ የናይልን ውሃ የምትገብረውን ኢትዮጵያ ያለ ውሃ የሚያስቀር አግላይና ኢፍትሃዊ ስምምነት ነው። ግብፅጽ ድርድሩን ምክንያት በማድረግ ይህንን ስምምነት ኢትዮጵያ እንድትቀበል ኢትዮጵያ ላይ ጫና እያደረገች ሲሆን ይህ በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት የለውም ብላለች ኢትዮጵያ። ለዓመታት ሲካሄድ የነበረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ፍሬ ሳያፈራ ባለፈው ሳምንት ተቋርጧል። ከሰኔ 2-10 ድረስ የተካሄደው የህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቀቅን በተመለከተ በበይነመረብ የተካሄደው የቪዲዮ የሦስትዮሽ ድርድርም መቋጫ ሳያገኝ ቆሟል። ከሰሞኑ በህዳሴው ግድብ ቁልፍ የሕግ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ባለመደረሱ፣ ጉዳዩ ለአገራቱ መሪዎች እንዲተላለፍ ሱዳን ሃሳብ ማቅረቧን አልጀዚራ ዘግቧል። የሱዳን የውሃ እና መስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስን ዋቢ አድርጎ አልጀዚራ እንደዘገበው ሦስቱ አገራት በድርድሩ ስምምነት ላይ መድረስ አቅቷቸዋል ብሏል። የሦስትዮሽ ድርድሩ ለጊዜው የተቋረጠው ሱዳን ጉዳዩ በመሪዎች ደረጃ እንዲታይ ሃሳብ ማቅረቧን ተከትሎ እንደሆነም የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ አስረድቷል። ያሲር አባስ ለሪፖርተሮች እንደተናገሩት ከ90-95 በመቶ የሚሆኑ የቴክኒካል ጉዳዮች ላይ መስማማት እንደተቻለ፤ ነገር ግን ሕጋዊ ጉዳዮች ላይ አሁንም ቢሆን ምንም ስምምነት አለመደረሱን ተናግረዋል። በተለይም ከውሃ ክፍፍል ጋር በተገናኘ አገራቱ መስማማት ስላቃታቸው በመሪዎች ደረጃ ሊፈታ ይገባል እንደተባለም ዘገባው ጨምሮ አስነብቧል። የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርም በበኩሉ ተመሳሳይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ስምምነት ቢደረስም በውሃ ሙሌት እና አለቃቅ የሕግ ጉዳዮች ላይ መሠረታዊ ልዩነቶች እንዳሉ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ከሰሞኑም ድርድሩ ከህዳሴው ግድብ ውሃ አሞላልና አለቃቀቅ አልፎ በውሃ ድርሻና አጠቃቀም ላይም እንዲሆንና የኢትዮጵያን የወደፊት በአባይ ውሃ የመጠቀም መብትን የሚገድብ ዓይነት ስምምነት ላይ እንዲደረስ ፍላጎቶች ያሉ መሆናቸውንም ጠቁሟል። ደብዳቤውም ላይ እንደተጠቀሰው ግብጽ በተደጋጋሚ የውሃ ክፍፍል ድርድር ነው በማለት በላይኛው ተፋሰስ አገራት የሚሰሩ ልማቶችን ለማገድ ብትሞክርም በአንፃራዊው ይህ ድርድር የህዳሴ ግድብ ውሃ አለቃቀቅና የግድቡ አሰራርን በተመለከተ እንደሆነ ደብዳቤው ገልጿል። "የውሃ ክፍፍል ከሆነ ሌሎች የተፋሰሱ አገራትም ሊሳተፉ ይገባ ነበር፤ እነሱም ተጠቃሚዎች ከመሆናቸው አንፃር በውሃ ክፍፍሉ ሦስቱ አገራት ብቻ ሊወስኑላቸው አይችሉምም" ብሏል። ግብጽ ኢትዮጵያ ላይ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫና በመፍጠር ለማንበርከክና ምክር ቤቱንም በተሳሳተ መንገድ ለመውሰድ እየሞከረች ነው ያለችው ኢትዮጵያ ከሰሞኑ የደረሱባቸው ስምምነቶችም ኢትዮጵያ ምን ያህል ግድቧም ቢሆን ልዩነቶችን ለማጥበብ እየሰራች መሆኑን ማሳያ እንደሆነም ደብዳቤው ጠቅሷል። የግብፅጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ በበኩላቸው ግብጽ ጉዳዩን ወደ ምክር ቤቱ የወሰደችው የዓለም አቀፉን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ እንጂ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለማስጣልም ሆነ ሌላ እርምጃ እንዲወሰድባት አይደለም ማለታቸውን ኢጅፐት ኢንዲፔንደንት ዘግቧል። የ150 ሚሊዮን ግብጻውያንና ሱዳናውያን ህይወት ላይ ተፅእኖ የሚያደርስ ከመሆኑ አንፃር የግድቡን ቀውስ በኃላፊነት የመፍታቱ ጉዳይ የምክር ቤቱ ነውም ብለዋል። የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ስምምነቱ ሳይፈረም ግድቡን አልሞላም ትበል እንዲሁም ወደ ስምምነቱም ትመለስ ብሏል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አንዳርጋቸው ግብጽ ጉዳዩን ወደ ምክር ቤቱ የወሰደችው ከግድቡ ድርድር ለማምለጥ ነው ማለታቸውን እንደማይስማሙና አሁንም ቢሆን በድርድሩ እንደሚቀጥሉ ሳሜህ ምላሽ መስጠታቸውን ኢጅፕት ኢንዲፔንድንት ዘግቧል። ዘገባው አክሎም ኢትዮጵያ ስምምነቱ ከመደረሱ በፊት የመጀመሪያ ዙር የግድቡን ውሃ ሙሌት የማትጀምር ከሆነ በድርድሩ እንደሚሳተፉ ማስታወቃቸው ተዘግቧል። ሰኞ ዕለትም የሱዳኑ የውሃና የመስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስ በሰጡት መግለጫ የህዳሴ ግድብ መቋጨት የሚችለው በሦስትዮሽ ድርድር መሆኑን አስታውቀው ሱዳን በድርድሩ ተስፋ እንደምታደርግ አስምረዋል። ሁኔታው ከተባባሰ ወደ ግጭት እንደሚያመራ የጠቆሙት ሚኒስትሩ "ድርድሩ ብቻ ነው ተስፋው ብለዋል" አክለውም "የግድቡ ሙሌትን ለመጀመር ስምምነት ላይ ሊደረስ ይገባል ሱዳንም ይህንን ለመጠየቅ መብቱ አላት" ብለዋል። በግብጽ መንግሥትን በሚደግፉ ሚዲያዎችም ላይ ኢትዮጵያ ይህንን አቋሟን እንድትለውጥ ግብፅ እርምጃ መውሰድ አለባትም ሲሉ ተሰምተዋል። የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ግብጽ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደማትፈልግና ፖለቲካዊ መፍትሔን እንደምትሻ ጠቁመው ኢትዮጵያም ግድብ የመገንባት መብቱ አላት ብለዋል። "በባለፉት ስድስት ዓመታት ግብጽ ወታደራዊ እርምጃ እንወስዳለን የሚል ፍንጭ አላሳየችም" ያሉት ሚኒስትሩ ነገር ግን ምክር ቤቱ ኢትዮጵያን ወደ ድርድሩ የማያመጣት ከሆነና የግድቡ ሙሌት ከተጀመረ ግን " ምን አይነት እርምጃ እንደምንወስድ በዚያን ጊዜ ግልፅ አድርገን እናሳውቃለን። ሁኔታውን ዝም ብለን አናይም" ብለዋል። በግብጽም ጥያቄ መሰረት የአረብ ሊግ አገራት ጉዳዩን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አማካይነት ትላንት ማክሰኞ መወያየታቸው የተሰማ ሲሆን ግብጽ ግድቡን በተመለከተ ያቀረበችው ሃሳብ በአንዳንድ አባል አገራት ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተሰምቷል። በውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የሚካሄደው ድርድር ወደ መሪዎች ይመራ የሚለው መቋጫ ያላገኘ ሲሆን ኢትዮጵያ በበኩሏ ምንም አይነት ስምምነት ላይ ይደረስም አይደረስ የመጀመሪያ ደረጃ የግድቡ ውሃ ሙሌት ሐምሌ ወር ላይ የመጀመር እቅድ አላት። ይሄ ጉዳይ ግን በግብጽ ብቻ ሳይሆን ለግብጽ ወግናለች ተብላ ስትወቀስ በነበረችው አሜሪካም ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም። ከሰሞኑም የአሜሪካ ብሔራዊ ፀጥታ ምክር ቤት ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ ሙሌት ከመጀመሯ በፊት የሦስትዮሽ ስምምነት ሊደረስ ይገባል የሚል የማሳሰቢያ መልዕክት በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል። "257 ሚሊዮን የሚሆን የምሥራቅ አፍሪካ ሕዝብ ኢትዮጵያ ጠንካራ አመራር እንድታሳይ ይጠብቃል። ይህ ማለት ፍትሃዊ የሆነ ስምምነት ነው ብሏል። በህዳሴ ግድብ ላይ ያሉ የቴክኒክ ጉዳዮች መፍትሔ አግኝተዋል፤ አሁን ደግሞ የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት ስምምነት ላይ የሚደረስበት ጊዜ ሊሆን ይገባል" ብሏል በትዊተር ገፁ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ለዚህ በሰጠው ምላሽ "ግድቡን አስመልክቶ ከመንግሥትም ሆነ ከሌሎች ተቋማት የሚሰጡ መግለጫዎች ወገንተኝነትን አለማሳየታቸውን እንዲሁም የሚደረጉ ድርድሮች ላይ እክል እንዳይፈጥሩ ጥንቃቄ ያሻቸዋል። ፍትሃዊ የሆኑ መግለጫዎች መሆን አለባቸው አለበለዚያ መግለጫ ከመስጠት መቆጠብ ያስፈልጋል" ብሏል። የግብጽ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ቃል አቀባይም ከሰሞኑ ድርድሩ ፍሬ አልባ ነው ሲሉ የተቹ ሲሆን ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ የኢትዮጵያ "ግትርነት" ነው በማለት ተችተዋል። ቃለ አቀባዩ ኢትዮጵያ እያቀረበችው ያለው ሰነድ ቴክኒካልና ሕጋዊ መርሆችን የሚጥስ እንዲሁም የታችኛው ተፋሰስ አገራትን ፍላጎትንም ሆነ መብታቸውን የሚጋፋ ነው በማለት ወቅሰዋል። ሰነዱንም "የሚረብሽ" ያሉት ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ በድርድሩ ስምምነት ላይ ለመድረስ ፍላጎት የላትም ማለታቸውን የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በተደጋጋሚ ግብጽ የቅኝ ግዛት ውሎችን ሙጥኝ እንዳለችና ኢ-ፍትሃዊና አግላይ የሆነውን ስምምነት ተቀባይነት እንዲያገኝ ጫና እያደረገች ነው በማለትም ትወቀሳለች። ባልነበረችበት የተፈረመ ስምምነት ለናይል ወንዝ 77 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ለምታመነጨው ኢትዮጵያ ምንም ድርሻ የማይሰጥና ተፈጥሯዊም ሆነ ሕጋዊ መብቴን የሚነጥቅ ነው በማለትም ኢትዮጵያ ትከራከራለች። ግብጽ ከምታነሳቸው ቅሬታዎች መካከል ኢትዮጵያ ግድቡን ሙሉ አቅም እየተጠቀመች ድርቅ ቢያጋጥም ችግሩ የሦስቱም አገራት ጉዳይ ነው የሚል አቋም ላይ መድረሷን ነው። ረዘም ላለ ጊዜ ድርቅ የሚከሰት ከሆነ ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ አገራት ጥቅምን ለመጠበቅ ዋስትና ልትሰጠን ይገባል በማለትም ግብጽ ትከራከራለች። ኢትዮጵያ ያለ ታችኛው ተፋሰስ አገራት ስምምነትም ግድቡን ለመሙላት መወሰኗም ሁለቱን አገራት የማስገደድ ውሳኔ ነው ብለውታል ቃለ አቀባዩ። የሦስትዮሽ ስምምነቱ እልባት ሳያገኝ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዙር የግድቡን ውሃ ሙሌት ብትጀምርም አለመረጋጋቶችና ግጭቶች በቀጠናው እንደሚከሰትም ከሰሞኑም አስጠንቅቃለች። ይህንንም ተከትሎ ከሰሞኑም ኢትዮጵያውያን #ግድቡ የኔ ነው በሚል በትዊተር ላይ ዘመቻም ጀምረዋል። ኢትዮጵያ ግድቡን በመሙላት እንድትቀጥልበትም ድጋፋቸውን ለግሰዋል። የአሜሪካ፣ አውሮፓ ሕብረትና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርን አገራቱ በበይነ መረብ አማካይነት በርቀት የሚያደርጉትን ድርድር እየታዘቡት ይገኛሉ። የሦስቱ አገራት የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች እንዲሁም የሕግ እና የውሃ ጉዳይ የቴክኒክ ባለሞያዎች በዋሽንግተን ዲሲ ሲደራደሩ በነበረበት ወቅት በዓመታት የተራዘመ ድርቅ እንዲሁም በተራዘመ ዓመታት አነስተኛ የውሃ ፍሰት ላይም መሰረታዊ መግባባት ተደርሷል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ያለምንም ውጤት መቋረጡ ይታወሳል። በወቅቱም ግብጽ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቴን ይቀንሰዋል እንዲሁም ለእርሻ የሚያስፈልገኝ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በየዓመቱ ይገባኛል ስትል የቆየች ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በበኩሏ 31 ቢሊዮን ኪዩቡክ ውሃ በዓመት ለመልቀቅ ሃሳብ አቅርባ ነበር። ነገር ግን አሜሪካ በበኩሏ 37 ቢሊዮን ኪዩብክ ሜትር እንዲለቀቅ መጠየቋ ተነግሮ ነበር። ኢትዮጵያ ወንዙ በግድቡ ስፍራ እንደሚኖረው ዓመታዊ የፍሰት መጠን ከ4 -7 ዓመታትን በሚወስድ የሙሌት ደረጃ ግድቡን የመሙላት እቅድን ብታቀርብም ግብፅጽ በበኩሏ ጥቅሜን የሚጋፋ ነው በማለት ከ12 እስከ 21 ዓመታት መውሰድ አለበት ትላለች። ኢትዮጵያ ዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረውንም ድርድር ያቋረጠችበት ምክንያት በግብጽ ፍላጎት ታዛቢ እንዲሆኑ የገቡት አሜሪካና የዓለም ባንክ ለግብጽ ከመወገን አልፈው የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ላይ ጫና ለማሳደር ሞክረዋል በማለት ኢትዮጵያ መውቀሷ የሚታወስ ነው። አሜሪካ፣ የዓለም ባንክ ከግብጽ ጎን ቆመው ነበር በተባለው በዚህ ድርድር ላይ ከመጀመሪያው ሙሌት በኋላ ኢትዮጵያ ለምትጠቀመው ውሃ ለግብጽ የተጠራቀመ የውሃ ጉድለት ማካካሻ እንድትሰጥ የሚያስገድድ እንደሆነም ተገልጾ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ የግብጽ ሃሳብ በአባይ ወንዝ ላይ ተፈጥሯዊ መብት እንዳይኖራት ወይም ምንም ዓይነት የውሃ ልማት ያልተገነባበት ፍሰት እንዲኖር የሚጠብቅ ነው በማለትም ትተቻለች። የህዳሴ ግድብ በዚህ ዓመት መጋቢት ወር ላይ 90 በመቶ የተጠጋ የሲቪል ሥራው፣ 44 በመቶ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው እና 20 በመቶ የብረታ ብረት ሥራው እና አጠቃላይ የግንባታው ሂደት ወደ 75 በመቶ መድረሱም ተገልጿል።
47498956
https://www.bbc.com/amharic/47498956
"ከመቶ ምናምን ፓርቲ ሴት የምናገኘው አንድ ወይም ቢበዛ ሁለት ሊሆን ይችላል" ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
በመላው ዓለም ማርች 8 የሴቶች ቀን ሆኖ ይከበራል። ቀኑን በማስመልከት የቀድሞዋ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ አመራርና በቅርቡ የአትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሀላፊ ሆነው የተመረጡት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከቢቢሲ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል። ቢቢሲ፡ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ከአሁኑ ጋር እንዴት ያነጻጽሩታል?
ወ/ሪት ብርቱካን፡ ከዚህ በፊት በነበረው ሁኔታ ሴት ሆነህ በፖለቲካ ውስጥ ስትሠራ በጣም በብቸኝነት ነበር። እሱ ብዙ ችግሮች ነበሩት። ማንኛዉም ህብረተሰብ ውስጥ አንዱ የፍትህና የእኩልነት ጥያቄ ይህ ነው። የሴቶች አማራጮች ተብለው የሚቀርቡት ሃሳቦች ከምንም በላይ አስፈላጊ ናቸው። ካሏቸው ማህበራዊ ሃላፊነቶች የተነሳ ሴቶች ሲጎዱ አጠቃላይ ማህበረሰቡ እንደሚጎዳ ግልጽ ነው። እናም ተሳትፎው በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ነበር ማለት ትችላለህ። አሁን ግን የተሻለ ሁኔታ አይተናል። ግን የተሻለ ነገር ያየነው በመንግሥት ሃላፊነት ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎችን አደረጃጀትና የፖለቲካ አመራር ስታየው አሁንም ብዙ ልዩነት አላይም። የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆኜ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የውይይት መድረክ እመራለሁ። ከመቶ ምናምን ፓርቲ ሴት የምናገኘው አንድ ወይም ቢበዛ ሁለት ሊሆን ይችላል። ከፓርቲዎች አኳያ ስታየው "ሴቶችን እንዴት ወደ ፖለቲካ ማምጣት አለብን? ተቸገርን" ይላሉ። ነገር ግን የችግሮቹን መነሻዎች በደንብ ተመልክቶ ሥራዬ ብሎ የፖሊሲ አቅጣጫ አስቀምጦ እስከተሠራ ድረስ የማይቻል ሁኔታ ነው ተብሎ መተው የለበትም። እኛም እንደ ምርጫ ቦርድ የምናደርጋቸው ድጋፍና እገዛዎች ያንን ለማምጣት እንዲሆኑ እናረጋግጣለን። ይህንን የሚከታተል ራሱን የቻለ ክፍል አለ። እሱን እንከታተላለን። • ወ/ሪት ብርቱካን በወዳጆቻቸው አንደበት ቢቢሲ፡ ለውጡ ያለው ከላይ ባለው ክፍል እንጂ ታችባለው የህብረተሰብ ክፍል አልተደገፈም ይባላል፤ የእርሰዎ አስተያየት ምንድን ነው? እኔ እንግዲህ ሃሳቦችንና አስተያየቶቼን በተመለከተ ካለኝ ሃላፊነት ብቻ መወሰን እፈልጋለሁ። የፓርቲዎችን እንቅስቃሴና ራሱን የምርጫ ቦርድ አደረጃጀት በተመለከተ (ቀጥታ ስለሚመለከተኝ ማለት ነው) ወደታች ስትሄድ በጣም ውስንነት እንዳለው ወደ ላይም ያንን አረጋገጠናል ለማለት ያስቸግራል። በተለይ ከመንግሥት መሥርያ ቤቶች አንጻር ስናይው ልዩነቱ የሰማይና የመሬት ነው። እናም ከዛ አኳያ ስናየው፣ አዎ ልክ ነው ብዬ እስማማለሁ። • "ሃገሬን ሳላስብ የዋልኩበት፤ ያደርኩበት ቀን የለም" ብርቱካን ሚደቅሳ • የቦርዱ ማሻሻያና የብርቱካን ሹመት ምንና ምን ናቸው? ቢቢሲ፡ ምን መደረግ አለበት? ወ/ሪት ብርቱካን፡ ምን መደርግ አለበት? የሚል ጥያቄ ባብዛኛው በጣም ደስ አይለኝም። ለምን መሰለህ ደስ የማይለኝ? እንዲህ መደረግ አለበት ብለህ ወይም እንደዚህ መደረግ አለበት እያልክ ስትወስን ያንን ለማድረግ የሚያስችል ሃላፊነትና አቅም ሲኖርህ ትንሽ ትረጉም ይኖረዋል። እንዲያው ባጠቃላይ ግን እንደዚህ መደረግ አለበት ሲባል ዝም ብሎ ማውራት ይመስለኛል። ግን ትንሽ ልሞክር። የፖለቲካ ተሳተፎውን በተመለከተ፣ እኔ በምመራው ተቋም ሃሳቦችን እንዴት እንተግብራቸው በማለት የተለያዩ ክርክሮች አሉ። ክርክሮቹ በተለያዩ ሀገራት የራሳቸውን ጥሩ ዉጤት ያመጡ ናቸው። ሁልግዜ እንደገና ማሰብን ይጠይቃል። መፈክር ነገር ሰርተህ ወይም ሰርኩላር አስተላልፈህ የምትተወው ጉዳይ አይደለም። በጣም የተላመድነው ነገር ስለሆነ፣ እያንዳንዱን ነገር ጊዜ ሰጥቶ ማሰብና እያንዳንዱ የምትወስናቸው የፖሊሲ ውሳኔዎች ላይ ያንን ማካተትህን ማረጋገጥ ይኖርብሃል። ለእንደዚህ አይነት ሥራዎች አይኑ ሊጋረድበት የሚችለው ወንድ ብቻ አይደለም። ሴቶች ሆነንም እንደሱ ልንሆን እንችላለን። ምክንያቱም የነበረው ሁኔታ ከባድ ነበር። በደንብ ካላሰብከው እንደ ወራጅ ውሃ ይዞህ ይሄዳል። በተለይ የጾታ ጉዳይ ሲሆን ልዩነቱ ይሰፋል። ስለዚህ እያንዳንዱን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይጠይቃል። ልታሳካቸውና ልትለካቸው የምትችላቸውን ነገሮች ማድረግ ይኖርብሃል። ለምሳሌ በመንግሥት አመራር ደረጃ የታየው ነገር እንደዛ ይመስለኛል። መሥራት የሚችሉትን አቀዱ አደረጉት። ሴቶች እንዲሳተፉ ብዙ ተነጋግረናል ግን አይፈጸሙም። እኔ የፓርቲ አመራር ሆኜ ሠርቻለሁ። በርግጥ የተቃዋሚ ፓርቲ ላይ አሁን ሳይሆን በፊት ወጣቱ ላይም ችግር ነበር። ባጠቃላይ የፖለቲካ ሂደቱ ራስህን ለስቃይ የምትመለምልበት ነው። ሃሳብ አለኝ ስትል፣ ገና ግማሹን ውሳኔህን ሰጥተህ አደባባይ መጥተህ ልትናገር ስትል፣ "የመታሰር እድሌ ወደ 80 በመቶ ነው፤ ስለዚህ ስታሰር የትኛዉን መጽሃፍ አነባለሁ?" አይነት እቅድ ነው ያለው። በእንደሱ አይነት ሁኔታ ደግሞ ሀገሪቱ ላይ ያሉት መልካም ነገሮች ይመጣሉ ብለህ አታስብም። በእርግጥ ያንን መስዋትነት የሚከፍሉ ሰዎች ይኖራሉ። ግን ገምቺ ብትለኝ፣ በህብረተሰቡ የፖለቲካ ተሳትፎ ውስጥ በጣም ያልተማከለ ተሳትፎ ነው የሚኖረው። በዚህ ምክንያት ብዙ የሕዝብ ተሳትፎ አታገኝም። የወጣቶች ተሳተፎ ስትል አታገኝም። የሴቶችንም እንደዛው። ያው ባለህ ነው የምትሄደው ማለት ነው። እንደዛ ሆኖም ግን የሃላፊነት ቦታ ላይ በነበርንበት ጊዜ የፖሊሲ ውሳኔና እቅድ ኖሮን ማድረግ የምንችላቸውን ነገሮች በትክክል አድርገናል ብዬ አላስብም።
52335998
https://www.bbc.com/amharic/52335998
"ቀብር ከሩቁ እናይ ነበር" የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር ነዋሪዎች ታሪክ
ዘፈር ሱልጣን ለመጀመሪያ ልጇ ክርስትና ሽር ጉድ እያለች ነው።
ዘፈር ሱልጣን አዲግራት የሚገኘው ቤቷ ውስጥ ሹሩባ እየተሠራች፣ የሠርጓን ቪድዮ ትመለከታለች። "ሠርጋችን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ድንበር የተከፈተ ሰሞን ስለነበር በደስታ ላይ ደስታ ጨምሮልናል" ትላለች። ሰላምም ጦርነትም በሌለበት ሁኔታ ለዓመታት የዘለቁት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበራቸውን ሲከፍቱ ቤተሰብ፣ ዘመዳሞች፣ ጓደኛሞችም ዳግመኛ ለመተያየት በቅተዋል። በዘፈር ሠርግ ላይ ኢትዮጵያዊም ኤርትራዊም ዘመዶቿ ተገኝተዋል። የልጇ ክርስትና እንደ ሠርጓ የደመቀ እንደሚሆንም ተስፋ ታደረጋለች። ክርስትናው የሚካሄደው የዘፈር እና የባለቤቷ ዘርዓይ ቤተሰቦች በሚኖሩበት ዛላምበሳ ነው። ዛላምበሳ ውስጥ ከቤተሰቡ የተነጣጠለ ብዙ ሰው ነው። ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ ሕይወት እንደገና በድንበር ላይ "ቀብር ከሩቁ እናይ ነበር" በርካታ ቤተሰቦች ሠርግ፣ ክርስትና፣ ቀብርና ሌሎችም ጉልህ ማኅበራዊ ክንውኖችን በጋራ ማሳለፍ ሳይችሉ ዓመታት ተቆጥረዋል። ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ሳይሰናበቱ በሞት የተነጠቁትንም ቤቱ ይቁጠራቸው። አብርሓይ ገብረመድህን ኢትዮጵያዊ ፎቶ አንሺ ነው። ኤርትራ ይኖሩ የነበሩ ታማሚ አያቱ ሲያልፉ እንዳልተሰናበተ ይናገራል። "ቀብሩን ከሩቅ እያየን ከማዘን ውጪ ምርጫ አልነበረንም" ይላል። የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ከተከፈተ በኋላ አብርሓይ ሁለት ጊዜ ወደ ኤርትራ ሄዷል። አብርሓይ ገብረመድህን አብርሓይ፤ "የሁለቱን አገሮች ልጅ ነኝ" ይላል። ስሜቱን የሚጋሩ ጥቂት አይደሉም። በጦርነቱ ሳቢያ ወደ 100,000 የሚሆኑ ሰዎች ከሁለቱም ወገን ሞተዋል። በርካቶችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። ሆኖም ግን የሁለቱ አገራት ዜጎች ማኅበራዊ፣ ባህላዊም ትስስር አላቸው። የዘፈር አያት አቶ ገብረክርስቶስ ካህሳይ፤ "ፀቡ የመሪዎች እንጂ የሕዝቡ አልነበረም" ይላሉ። አቶ ገብረክርስቶስ ካህሳይ፤ "ፀቡ የመሪዎች እንጂ የሕዝቡ አልነበረም" ይላሉ የተከፈተው ድንበር ዳግመኛ የመዘጋቱ ነገር በሁለቱ አገሮች ጦርነትና ለዓመታት ድንበር በመዘጋቱ ሳቢያ ምጣኔ ሃብታዊ ጫና የደረሰባት ዛላምበሳ፤ ድንበር ሲከፈት ማገገም ጀምራ ነበር። ነጋዴዎች በነፃነት መንቀሳቀስ ጀምረው እንደነበርም ይታወሳል። ሆኖም ግን ድንበሩ ከተከፈተ ከወራት በኋላ ድጋሚ ተዘግቷል። በወቅቱ ድንበሩ የተዘጋበት ምክንያት በይፋ አልተገለጸም። ሁለቱም አገራት መፍትሔ ለማበጀት እየሞከርን ነው ቢሉም እስካሁን ስምምነት ላይ አልተደረሰም። በእርግጥ ድንበሩ ላይ እንደቀድሞው ወታደራዊ ጥበቃ አይደረግም። ተሽከርካሪ ከአንዱ አገር ወደ ሌላው እንዲገባ ባይፈቀድም፤ ነጋዴዎች በእግር ድንበር እያቋረጡ መገበያየት ቀጥለዋል። አንዲት ኤርትራዊት ትልቅ የእንጨት ጠረጴዛ በጀርባዋ ተሸክማ ለሦስት ሰዓት በእገር ተጉዛ ቤቷ መድረሷን የቢቢሲ ዘጋቢ አስተውሏል። ድንበሩ ከመከፈቱ በፊት ኤርትራ ውስጥ ገበያ ለመሄድ አምስት ሰዓት መጓዝ እንደነበረባትም ተናግራለች። ለህክምና ዛላምበሳ የሚሄዱት ኤርትራውያን በዛላምበሳ ጤና ተቋም ህክምና ለማግኘት ኤርትራውያን ይመጣሉ። ድንበሩ ከተዘጋ በኋላ የታካሚዎች ቁጥር ቢቀንስም አሁንም በእግር ወደ ኢትዮጵያ የሚያቀኑ አሉ። ዶ/ር ሳምራዊት በርሄ እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያውያንም ኤርትራውያንም እኩል የህክምና አገልግሎት ያገኛሉ። ከታካሚዎቹ ግማሹ ወደ ዛላምበሳ የሚመጡት፤ ኤርትራ ከሚገኘው ሀኪም ቤት የኢትዮጵያው ስለሚቀርባቸው ነው። የተቀሩት ደግሞ የተሻለ ህክምና እናገኛለን ይላሉ። ታካሚዎች በዛላምበሳ ሆስፒታል በርካታ ሴቶች የእርግዝና መቆጣጠሪያ ለማግኘት ወደ ክሊኒካቸው እንደሚሄዱም ዶ/ር ሳምራዊት ይናገራሉ። ኤርትራ ውስጥ መሰል የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ለማግኘት የባሎች ፍቃድ እንደሚያስፈልግ እና የእርግዝና መቆጣሪያ ባልና ሚስት በጋራ መግዛት እንዳለባቸው መስማታቸውን ዶክተሯ ይናገራሉ። "ብዙ ሴቶች በነዚህ ክልከላዎች ምክንያት እዚህ መምጣት እንደሚመርጡ ይነግሩናል" ሲሉም ያክላሉ። "ወንድማማቾች ነን አንነጣጠልም" ዛላምበሳ ወስጥ ግንባታ ላይ ያሉ ቤቶች ይስተዋላሉ። ድንበሩ ሲከፈት ብዙ ነጋዴዎች ወደ አገሪቱ መጥተው ሥራ ጀምረዋል። ከነዚህ አንዱ አቶ ፍስሀዬ ኃይሉ ናቸው። ለ13 ዓመት የፖለቲካ እስረኛ የነበሩት አቶ ፍስሀዬ አገራቸውን ጥለው ኢትዮጵያ እየኖሩ ነው። "ነገሮች እየተስተካከሉ ሲመጡ መሬት ገዛሁ" የሚሉት አቶ ፍስሀዬ ዛላምበሳ ውስጥ ባለ ሦስት ህንጻ ሆቴል እየሠሩ ነው። አቶ ፍስሃዬ ባለ ሦስት ህንጻ ሆቴል እየሠሩ ነው ሆቴሉ ሲጠናቀቅ 'ሁለቱ ወንድማማቾች' ብለው የሚሰይሙበትን ምክንያት ሲገልጹም "ወንድማማቾች ነን፤ አንነጣጠልም" ይላሉ። የሁለቱ አገራት አብሮነት የዘወትር ምኞታቸው መሆኑንም ያክላሉ። የዘፈር ልጅ ክርስትና የዘፈር ልጅ ክርስትና ላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ዘመዶቿም ተገኝተዋል። ባለቤቷ ዘርዓይ ከምጽዋ የመጣች የአጎቱን ልጅ ለዘመድ አዝማድ እያስተዋወቀ ነበር። ሠርጉ ላይና የልጁን ክርስትና በመታደሟም ደስተኛ ነው። "ከሠርጉ ጀምራ አብራኝ መሆኗ ፍቅራችንን፣ አንድነታችንን እና ባህላችንን ያሳያል" ይላል። እሷም ተመሳሳይ አስተያየት ነው ያላት። ቀድሞ የትኛው ዘመድ ሕይወቱ እንዳለፈ ለማወቅ እንኳን እንደማይችሉና ድንበሩ ሲከፈት ግን ነገሮች መለወጣቸውን ትናገራለች። "ድንበሩ ሳይከፈትና አሁን ያለው ልዩነት የሰማይና የመሬት ያህል ነው" ትላለች። ዘፈር እንደምትለው፤ ድንበሩ በድጋሚ በመዘጋቱ የልጇ ክርስትና ላይ የተገኙ ኤርትራውያን ቁጥር ከሠርጓ አንጻር ትንሽ ነው። "ድንበሩ እንደተዘጋ ከቀረ ወደፊት መቀጠል አንችልም፤ አሳሳቢ ነው" ትላለች። የዘፈር ልጅ ክርስትና
53509835
https://www.bbc.com/amharic/53509835
ሻሸመኔ፡ ቤት ንብረት የወደመባቸው ሰዎች በምን ሁኔታ ላይ ናቸው?
ሰኔ 23 ምሽት የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ከተሰማ በኋላ የተለያዩ ውድመቶችና ጥቃቶች ከደረሱባቸው አካባቢዎች መካከል ሻሸመኔ አንዷ ናት።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰቦች የሥራ ቦታ፣ ፋብሪካ፣ ህንጻ፣ መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውንና በርካቶችም የነበራቸውን ሁሉ በጥፋቱ አጥተው ባዶ እጃቸውን ቀርተዋል። "ስለወደመው ከማውራት ስለተረፈው ማውራቱ ይቀላል" የሚሉት ተጎጂዎች በአንድ ድምጽ 'መንግሥት ቶሎ ቢደርስልን' ሲሉ ይደመጣል። የአርቲስቱ ግድያ ከተሰማ በኋላ በኦሮሚያ ክልል፤ 523 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 499 መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የክልሉ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ በተፈጸመው ውድመት ቤት ንብረታቸውን አጥተው የመንግሥት እርዳታን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሺህ በላይ እንደሚሆኑ አመልክተዋል። ተጎጂዎች ምን ይላሉ? ሻሸመኔ ቀበሌ አስር ውስጥ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩት ግለሰብ በወቅቱ ጥቃት ከደረሰባቸው መካከል አንዱ ናቸው። ግለሰቡ ለቢቢሲ እንዳሉት በነበረው አለመረጋጋት ቤት ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ግለሰቡ ተወልደው ያደጉት ሻሻመኔ መሆኑን ተናግረው "ወላጆቼም የተወለዱት፤ አያቶቼም የኖሩት እዚህ ነው" ሲሉ ከሻሸመኔ ውጪ የሚያውቁት ቦታ እንደሌለ ለቢቢሲ አስረድተዋል። "የቤቴ ጣርያው፣ በሩ፣ መስኮቱ ተነቃቅሎ ተሰባብሯል" የሚሉት ግለሰቡ ንብረታቸው ሙልጭ ተደርጎ መዘረፉንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ቤት ንብረታቸው ሲወድም በስፍራው የነበሩ ቢሆንም ለመከላከልም ሆነ ንብረታቸውን ለማትረፍ የሚያስችል ሁኔታ እንዳልነበር የሚናገሩት ግለሰቡ፤ በጓሮ በኩል በሚገኝ ሌላ መውጫ ሾልከው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ከቤታቸው አቅራቢያ ወደሚገኘው ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን መሸሻቸውን ያስታውሳሉ። እኚህ የሦስት ልጆች አባት የሆኑት ግለሰብ ከአካባቢያቸው ካሉ ነዋሪዎች ተለይተው ጥቃት እንደደረሰባቸው እንደሚያምኑም ለቢቢሲ አስረድተዋል። በአካባቢያቸው ቤቶች ሲቃጠሉ የአንዱን ቤት ከሌላኛው ለመለየት ጥቃት ፈጻሚዎቹ የብሔርና የሐይማኖት ሽፋን መጠቀማቸውንም ይገልፃሉ። ግለሰቡ በአሁኑ ሰዓት ልጆቻቸውን ወደ ሐዋሳ አሽሽተው እርሳቸው ደግሞ በሻሸመኔ ከተማ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ በመግለጽ ከእርሳቸው ጋር 80 ያህል ንብረታቸው የወደመባቸው ሰዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ግለሰቡ እንደሚናገሩት የአካባቢው አስተዳደር ያረፉበት ድረስ በመምጣት ድጋፍ ያደረገላቸው ቢሆንም ወጥ አለመሆኑን አስረድተው መጠኑም ቢሆን ለሁሉም የሚበቃ አለመሆኑን ገልፀዋል። በተለያየ ጊዜ ከከተማው አስተዳደር ጋር ስብሰባ ማድረጋቸውን፣ ከቀበሌ እና ከፌደራል መጣን ያሉ ሰዎች እንዳናገሯቸው፣ የወደመ ንብረታቸውንም መመዝገባቸውን በመግለጽ አስተማማኝ የሆነ ድጋፍ እና መደረግ ያለበትን ግን አለመስማታቸውን ተናግረዋል። እኚህ በቤተክርስቲትያን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙት ግለሰብ በአሁኑ ወቅት "ከዚህ በኋላ የት ነው የምንሄደው? እንዴት ነው የምንኖረው? ሕይወታችንን እንዴት ነው የምንቀጥለው?" የሚሉ ጥያቄዎች መልስ እንደሚያሳስቧቸው ይገልጻሉ። ሌላኛው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው ግለሰብ አደጋው በደረሰባቸው ወቅት ቤታቸው ውስጥ የእርሳቸውን ልጆች ጨምሮ በእንግድነት የመጡ ሁለት ልጆች እንደነበሩ ይናገራሉ። ሻሸመኔ ውስጥ በንግድ ሥራ ተሰማርተው እየኖሩ እንደነበር የሚገልፁት ግለሰቡ፤ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት መሆናቸውንና አንድ የማደጎ ልጅ አብሯቸው እንደሚኖር ተናግረዋል። በወቅቱ የባለቤታቸው ወንድም ሁለት ልጆች በእንግድነት መጥተው አብረዋቸው እንደነበሩ የሚገልፁት እኚህ ግለሰብ፤ ሰፈራቸው ውስጥ ጥቃት አድራሾቹ መጥተው ስማቸውን እየጠሩ በራቸውን ሲደበድቡ ግቢ ውስጥ ለእቃ ማስቀመጫነት ወደ ተሰራች አነስተኛ ክፍል ሰባት ሆነው ገብተው መደበቃቸውን ያስታውሳሉ። የስኳር ህመምተኛ መሆናቸውን የሚናገሩት እኚህ ግለሰብ በዚያ ችግር ውስጥ ሁሉ ልጃቸው መድኃኒታቸውንና ስልካቸውን ኪሳቸው ውስጥ መክተታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በሚኖሩበት ሰፈር ውስጥ የእርሳቸው መኖሪያ ተመርጦ ጥቃት እንደደረሰበት የሚገልፁት እኚህ ግለሰብ በወቅቱ የግቢያቸውን በር ጥሰው የገቡ ጥቃት አድራሾች መኪናቸውን በመሰባበር እና ገፍተው ከግቢ በማውጣት በእሳት መለኮሳቸውን ተናግረዋል። መኖሪያ ቤታቸውም ቢሆን መሰባበሩንና መዘረፉን የሚናገሩት ግለሰቡ "ዋናውን ቤት ሰባብረው ከጨረሱ በኋላ ተደብቀን ወደነበርንበት ክፍል መጥተው በሩን መደብደብ ጀመሩ" ሲሉ ያስታውሳሉ። በወቅቱ እዚያው ባሉበት ክፍል ሆነው አደጋውን ከመቀበል፣ ወጥተው ልጆቻቸውንና ባለቤታቸውን እንዳይነኩባቸው መማፀን ጀመሩ። ከጥቃት አድራሾቹ መካከል አንድ ወንድና አንድ ሴት ወደፊት መጥተው እነርሱን ማንም እንዳይነካቸው እንደተናገሩና ከግቢያቸው ወጥተው እንዲሄዱ እንደፈቀዱላቸው ያስታውሳሉ። ከቤታቸው ወጥተው እየሄዱ በነበረበት ጊዜ የማያውቁት ሰው ደውሎ የልጆቻቸውና የእርሳቸው ህይወት እንዲተርፍ ከፈለጉ ገንዘብ እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን የሚናገሩት እኚህ ግለሰብ፤ በተለያየ ወቅት ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ጋር እየተደወለ ጥቆማ እንዳያደርጉ ማስፈራሪያ እንደሚደርስም ተናግረዋል። ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት ልጆቻቸው ያለጫማ፣ እርሳቸውና ባለቤታቸው ደግሞ በለሊት ልብስ መውጣታቸውን የሚናገሩት ግለሰቡ በቀጥታ በአካባቢው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ማምራታቸውን ያስታውሳሉ። በወቅቱ የተጠለሉበት ፖሊስ ጣቢያም ተኩስ እንደነበር የሚገልፁት ግለሰቡ ከመምሸቱ በፊት መሃል ከተማ ወደሚገኙ የቅርብ ወዳጆቻቸው ጋር ሄደው መጠለል መምረጣቸውን ይናገራሉ። ግጭቱን የተመለከቱ ልጆቻቸውና ዘመዶቻቸውን ስሜት ሲናገሩም መረበሻቸውን፣ መተኛት አለመቻላቸውን፣ በተደጋጋሚ ይባንኑ እንደነበር ያስረዳሉ። "ከወደመው ንብረት በላይ ታዳጊዎቹ ልጆች አእምሮ ውስጥ የተፈጠረው ነገር አስደንጋጭ ነው" የሚሉት እኚህ ግለሰብ "በፈጣሪ እርዳታ ተርፈናል" በማለት በአንድ ጊዜ ባዶ እጃቸውን መቅረታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት እርሳቸውና ቤተሰቦቻቸው በተጠለሉበት ስፍራ የአካባቢው ነዋሪ እየመጣ እንደሚያጽናናቸው በመናገር፤ በ49 ዓመታቸው መሬት መተኛታቸው፣ ያለ ቅያሪ ልብስ፣ ሙሉ ቤተሰባቸው ደግሞ ያለ ተገን መቅረታቸውን ማሰብ ከባድ ጭንቀት እንደሆነባቸው ይገልፃሉ። አሁን ያሉበት ደረጃ ለመድረስ እድሜያቸውን በሙሉ መልፋታቸውን የሚናገሩት እኚህ ግለሰብ ንብረታቸውን ወደ ነበረበት ለመመለስ አስቸጋሪ መሆኑንም ያስረዳሉ። ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት ከተማዋ ውስጥ የፀጥታ አካላት ቢኖሩም ተደራሽ ባለመሆናቸው ችግሩ መድረሱን ተናግረው መንግሥት እንዲያቋቁማቸው ጠይቀዋል። 'ጉዳቱ የደረሰው በሁሉም ላይ ነው' በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰው በምዕራብ አርሲ ሦስት ወረዳዎች ውስጥ መሆኑን የተናገሩት የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልጫ፤ በተለይ በሻሸመኔ እና ባቱ ከተሞች እንዲሁም በባሌ ዞን ሮቤ እና አጋርፋ ከተሞች የደረሰው ገዳት ከሌሎች አካባቢዎች አንጻር ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል። አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ ህይወታቸውን ያጡት፣ ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው ሰዎች የአንድ ብሔር ወይም ሐይማኖት ተከታይ ብቻ አይደሉም ብለዋል። "በአንደ ብሔር እና ሐይማኖት ላይ ብቻ ያነጣጠረ አልነበረም። ሁሉም ብሔር እና የሐይማኖት ተከታዮች ጉዳት ደርሶባቸዋል" ሲሉ አቶ ጌታቸው ተናግረዋል። መልሶ ማቋቋም ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎባቸው ባዶ እጃቸውን ቀርተው የእምነት ተቋማትን ጨምሮ በተለያዩ ስፍራዎች ተጠልለው የሚገኙ ዜጎች ቁጥር በርካታ መሆኑን አቶ ጌታቸው ገልጸው፤ በተፈጸመው ውድመት ንብረታቸው ወድሞባቸው የመንግሥት እርዳታን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሺህ በላይ እንደሚሆን አመልክተዋል። ንብረታቸው የወደመባቸው ሰዎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። "የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ በያሉበት እንዲደርሳቸው እየተደረገ ነው" ሲሉ አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ቁጥር ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በተፈጠረው አለመረጋጋት በኦሮሚያ ክልል በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች ቁጥር ሰባት ሺህ በላይ መሆኑን አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክልሉ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ጨምረውም በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሰዎች ጋር በተያያዘ ፖሊስ አና አቃቢ ሕግ ከ5 ሺህ በላይ በሚሆኑ መዝገቦች ተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ መመስረታቸውንም አመልክተዋል። አቶ ጌታቸው "መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ጠንክሮ እየሰራ ነው" ካሉ በኋላ፤ "በጸጥታ ኃይሎች የተያዙ ሰዎችም በቁጥጥር ከዋሉበት በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የማቅረብ ሥራ እየተሰራ" መሆኑን ጠቁመዋል።
news-55982291
https://www.bbc.com/amharic/news-55982291
ሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በተባለለት ጊዜ ማካሄድ ሳትችል ቀረች
ሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማካሄድ በነበረባት ወቅት ባለማካሄዷ የፖለቲካ ቀውስ ይገጥማታል ተብሎ ተፈርቷል። ሶማሊያ ምርጫ ማካሄድ የነበረባት ዛሬ ሲሆን የፕሬዝዳንት አብዱላሂ ፎርማጆ የሥልጣን ዘመንም በዛሬ ዕለት ይጠናቀቃል።
የፌደራል መንግሥቱ እና የክልል መንግሥታት ምርጫ ማካሄድ ስለሚቻልበት መንገድ እያደረጉት የነበረው ውይይት አርብ እለት ያለውጤት ተበትኗል። ዛሬ፣ ሰኞ መግለጫ ያወጡት ለፕሬዝዳንትነት የሚፎካከሩት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የፕሬዝዳንት ፎርማጆ የሥልጣን ዘመን በማብቃቱ እውቅና እንደማይሰጧቸው ገልፀዋል። አክለውም የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባዔዎች የተካተቱበት፣ የክልል አስተዳደሮችና አጋሮቻቸው በጋራ በመሆን እስከ ምርጫ ድረስ የሚያስተዳድር የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት ጠይቀዋል። የሶማሊያ ጦርንም ከፕሬዝዳንት ፎርማጆ ማንኛውንም ትዕዛዝ እንዳይቀበል ጥሪ አስተላልፈዋል። ሶማሊያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምርጫ ማካሄድ የነበረባት በታሕሳስ ወር ቢሆንም የፌደራል መንግሥቱ ከክልል አስተዳደሮች ጋር በገባው እሰጥ አገባ ምክንያት አልተካሄደም። የተለያዩ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች በፌደራል እና በክልል መንግሥታት መካከል የተቋረጠው ንግግር እንዲቀጥልና ምርጫ በተቻለ ፍጥነት እንዲካሄድ እየጠየቁ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ባወጠው መግለጫ ላይ እንዳለው ከዚህ ቀውስ ለመውጣት ያለው ብቸኛ መፍትሔ የተቋረጠውን ድርድር ማስቀጠል ነው። አሜሪካም ተመሳሳይ ይዘት የያዘ መግለጫ አውጥታለች። የተባበሩት መንግሥታት ፖለቲከኞች የሕዝቡን ፍላጎት ያማከለ ውሳኔ በፍጥነት እንዲወስኑ ጠይቋል።
news-47387851
https://www.bbc.com/amharic/news-47387851
ኮሎኔል ሪጃል ዑመር፡ 'ወጣት መሳዩ' የ108 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ?
ሲያዩዋቸው የ40 ዓመት ጎልማሳ ነው የሚመስሉት፤ የፈረጠመ ሰውነት ነው ያላቸው፤ እሳቸው ግን 108ኛ ዓመቴን ደፍኛለሁ ይላሉ።
አቋማቸው ከዕድሜያቸው ጋር አልስተካከል ያላቸው ግን ብዙዎች ናቸው። ቢቢሲ ከእኝህ የዕድሜ ባለጸጋ ነኝ ከሚሉት ኮሎኔል ሪጃል ኡመር ጋር ቆይታ አድርጓል። • "ፊደል መቁጠር የጀመርኩት በ60 ዓመቴ ነው" ቢቢሲ፡ ፎቶግራፍዎን አይቼ 'አንቱ' ለማለት ተቸገርኩ'ኮ? ኮሎኔል ሪጃል፡ እንዴ በቅርብ የወደድኳት አንድ ጓደኛዬ አለች። ከዚያ ደግሞ የልጅ ልጅ ልጄ (አራተኛ የልጀ ልጄ) 'አንተ ሪጃል!' ብላ ነው እንጂ የምትጠራኝ፤ 'አንቱ' ያለኝ ሰው እስካሁን የለም። ቢቢሲ፡ በቅርብ የወደድኳት ልጅ ነው ያሉኝ? ኮሎኔል ሪጃል፡ አለች። አዎ! ቢቢሲ፡ አሁን ወደድኳት ያሉኝ ሴት ዕድሜዋ ስንት ነው? ኮሎኔል ሪጃል፡ ስንት ዓመትሽ ነው አንቺ? ዕድሜሽ ስንት ነው? (ጠየቁዋት) እዚህ አጠገቤ ነው ያለችው... 35 ዓመቷ ነው። ቢቢሲ፡ ምኗን ነው የወደዱት? ኮሎኔል ሪጃል፡ አቋሟ ደስ ይላል!.. እዚህ አጠገቤ ነው ያለችው ታናግርህ። [ኮለኔል ስልኩን አሳልፈው ፍቅረኛዬ ለሚሏት ፀሐይ አቀበሉ። ሠላምታ ተለዋወጥን ጥያቄያችንንም ለእሳቸው አስከተልን።] • ተዋናይቷ በ54 ዓመቷ ሴት ልጅ ተገላገለች ቢቢሲ፡ ወድጃታለሁ ፍቅር ላይ ነን ይላሉ ኮለኔል? ወ/ሮ ፀሐይ፡ አዎ! እኔም ወድድድ...... አድርጌዋለሁ። ቢቢሲ፡ ምናቸውን ወደድሽ? ዕድሜው ገፋ ያለ ሰው ብዙም ....። ወ/ሮ ፀሐይ፡ እኔ ደግሞ ጠና ያለ ሰው በጣም ነው የምወደው። ቢቢሲ፡ አሁን ያንቺዕድሜ በእርሳቸው ዕድሜ ሲሰላ ሦስት እጥፍ ማለት እኮ ነው... ሦስት እጥፍ ከሦስት ዓመት ወ/ሮ ፀሐይ፡ እኔ ተመችቶኛል፤ እንግባባለን። ከዚያ በላይ ምን አለ ብለህ ነው? ቁመናውን፣ ሁሉንም ነገሩን ወድጃለሁ። ፍቅር እንግዲህ ዕድሜን አይወስንም። ደሞ ፍቅር እንዲህ ነው ተብሎ ለሰው አይገለፅም። ቢቢሲ፡ ኮሎኔልን ስታያቸው በጣም ብዙ ዕድሜ ነው የሚታይሽ ወይስ ወጣት ሆነው ነው? ወ/ሮ ፀሐይ፡ ለእኔ ወጣት ነው! ስንት ልበልህ?... በቃ አለ አይደል...እኔ በአርባዎቹ የዕድሜ ክልል ነው የሚመስለኝ። • ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው? [አሁን ደግሞ ለኮሎኔል ስልኩን አቀበሉ] ቢቢሲ፡ ኮሎኔል ፍቅር ዕድሜ ያረዝማል እንዴ? ኮሎኔል ሪጃል፡ (ሳቅ) እኔ ከመጀመሪያ ጀምሮ ጥል አላውቅም፤ አንድ ወቅት የሶማሊያ ወታደር በማረኩ ጊዜ የራሴን ልብስ ነው አውልቄ ያለበስኩት፤ ፍቅር ብቻ ነው የማውቀው። ቢቢሲ፡ እርስዎ ልጅ እያሉ አንድ በግ ዋጋው ስንት ነበር? ኮሎኔል ሪጃል፡ በግ ዋጋ የለውም። እኔ አንድ ጊዜ ትዝ የሚለኝ ወደ ኮሪያ ለመሄድ ብዬ ላሞች ነበሩና ሁለት ጥጃ ያላትን ላምና አንድ በሬ (ሦስቱን) በሰባት ብር ሸጬ ነው በ1943 ዓ. ም ወደ ኮሪያ የሄድኩት። ቢቢሲ፡ ከኮሪያ ዘማቾች ከተመለሱ በኋላ ዘማቾች ጃንሆይ ላይ የደመወዝ ጥያቄ አንስተው ነበር ይባላል... ኮሎኔል ሪጃል፡ አዎ! ልክ ነህ። ደመወዝ ከ20 ብር ወደ 60 ብር ይደግልን የሚል ነበር ጥያቄው። የኃይለ ሥላሴ ታማኝ ስለነበርኩና ቤተመንግሥት ውስጥ ስለማገለግል እኔ አመጹ ላይ አልተሳተፍኩም። ቢቢሲ፡ ከደርግ ባለሥልጣናት ማንን ያውቃሉ? ኮሎኔል ሪጃል፡ ጀኔራል ተፈሪ በንቲን። እንዲያውም አንዱን ልጄን ተፈሪ ያልኩት በጀኔራሉ ስም ነው። አዲስ አበባ ነው የሚኖረው... ፀጉሩን ተመልጧል እንጂ... አረጀ! ቢቢሲ፡ ዶክተር ዐብይን ያውቋቸዋል? ኮሎኔል ሪጃል፡ አዎ አውቃቸዋለሁ! ያባ ፊጣ ልጅ ናቸው። ቢቢሲ፡ ማናቸው ደግሞ አባ ፊጣ? ኮሎኔል ሪጃል፡ አባ ፊጣ አሊ ነው የሚባሉት። ብዙ ዕውቅና ባይኖረኝም አውቃቸዋለሁ። ቢቢሲ፡ ዶ/ር ዐብይን አግኝተዋቸዋል? ኮሎኔል ሪጃል፡ ማግኘት አልፈልግም። ቢቢሲ፡ ለምንድን ነው የማይፈልጉት? ብዙ ሰው ጠቅላይ ሚንስትሩን ማግኘት ይፈልጋል። ኮሎኔል ሪጃል፡ (ረዥም ሳቅ) እኔ አኮ... እየውልህ... ንጉሡ ከአገር ሸሽተው በኖሩበት ጊዜ በባዶ እግሬ አገሪቷን ነፃ ለማውጣት ጫካ የገባሁ ነኝ (ቆፍጠን አሉ) ንጉሥ ፈላጊ አይደለሁም! ኢትዮጵያዊነትና ነፃነት ፈላጊ እንጂ... ቢቢሲ፡ በማን ዘመን ነበር የተወለዱት ኮሎኔል? ኮሎኔል ሪጃል፡ በዳግማዊ ሚንሊክ ነበር። ከዚያ በኋላ በልጅ እያሱ ዘመን እረኛ ነበርኩ፤ ምን እንደነበር ግን አላውቅም። ቢቢሲ፡ አፄ ምንሊክ ትዝ ይሉዎታል? አይተዋቸው ያውቃሉ በሩቁም ቢሆን? ኮሎኔል ሪጃል፡ አላየሁም፤ ዘውዲቱንም አላየሁም፤ ኢያሱንም አላየሁም። በዐይኔ ያየኋቸውና እግራቸውን ያጠብኳቸው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ነው። ቢቢሲ፡ የመጀመሪያ ልጅዎት ስንት ዓመቱ ነው? ኮሎኔል ሪጃል፡ 75 ዓመቱ ነው፤ ባለፈው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው። ቢቢሲ፡ አሁንም ልጆች መውለድ ይፈልጋሉ? ኮሎኔል ሪጃል፡ዛሬም ድረስ ልጅ መውለድ እፈልጋለሁ። ልጅ ወልጄ ማሳደግ እችላለሁ። ቢቢሲ፡ ስንት ልጆች አለዎት? ኮሎኔል ሪጃል፡የልጆቼን ቁጥር አልናገርም። ልጅ አይቆጠርም። አሁን አንተን ሳዋራህ ራሱ ቤቴ [በልጆች ብዛት] ሆስፒታል መስሏል። ለሁሉም ልጆቼ ማውረስ የምችለው ቤት አለኝ። የሁሉንም ልጆቼን ስም አላውቅም። ይሄ ደግሞ ማነው እያልኩ እጠይቃለሁ። ቢቢሲ፡ ከልጆቸችዎ መካከል አብልጠው የሚወዱት ማንን ነው? ኮሎኔል ሪጃል፡ ልጆቼን አብዝቼ የምወዳቸው 8 ዓመት እስኪሞላቸው ነው። ከዚያ በኋላ ግን አልወዳቸውም። ቢቢሲ፡ እንደ እርስዎ 108 ዓመትና ከዚያ በላይ መኖር እፈልጋለሁ። ይምከሩኝ እስቲ ኮሎኔል? ኮሎኔል ሪጃል፡ ማንም ሰው የፈለገውን ቢጨማለቅ እንደ ቆሻሻ መቁጠር፤ ለተሳዳቢ ጆሮ አለመስጠት፤ እሳት የነካው ሥጋ አለመብላት፤ ስፖርት ሳይሠሩ ቁርስ አለመብላት። ቢቢሲ፡ ድሮ ሙዚቃ የማንን ነበር የሚውዱት? በምንድን ነበር የሚዝናኑት? ኮሎኔል ሪጃል፡ ( ማንጎራጎር ጀመሩ) መላ መላ በሉ እስኪ መላ፣ ልቤ ወዳንች እኮ አደላ፣ የማር እሸት፣ የማር ዛላ፣ የኔ ፍቅር የኔ ገላ ... የሚለውን እንዲሁም የይርጋ ዱባለን 'ዘብ ይቁም ሁሉም ለሀገሬ' የሚለውን ነው። [ኮሎኔሉ ሲያንጎራጉሩ ድምፃቸው በጉልበት የተሞላና ኩልል ያለ ነበር። በእርግጥም ይህን የሰማ ኮሎኔሉ የ108 ዓመት አዛውንት ለማመን ቢቸገር አያምንም?] ኮሎኔሉ ከወይዘሮ ምስኩ አባተማም ጋር በ1990 ዓ. ም. ጋብቻ ፈጽሚያለሁ ይላሉ። ባለቤታቸው ወ/ሮ ምስኩን ስለ ባለቤታቸው ኮሎኔል ሪጃል እንዲህ አጫውተውናል። "እኔ ዕድሜው አላውቅም። የመጨረሻ ሚስታቸው ነኝ። እኔን ጨምሮ 12 ሚስቶች አግብተዋል። የመጀመሪያ ሚስታቸው ትብለጽ ትባል ነበር። አሁን ሞታለች። ስትሞት ወደ 70 ዓመት ሆኗት ነበር። አግኝቻት ነበር። ፋጡማ፣ ሲቲና፣ ፋጤ የሚባሉ ሚስቶቻቸውን አውቃለሁ። አግኝቻቸዋለሁም። ዕድሜያቸው ከ100 ዓመት በላይ ነው። ትልልቅ ልጆች አሏቸው። ከኔ ጋ ግን የመጀመሪያ ልጃችን 20 ዓመቱ ነው። የመጨረሻዋ ልጃችን ደግሞ አስማ ትባላለች። ሁለት ዓመቷ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት ነው የወለድናት።" ኮሎኔል ሪጃልና ወ/ሮ ምስኩ የመጨረሻ ልጃቸውን የወለዱት ከሁለት ዓመት በፊት እንደሆነ ይናገራሉ። ኮለኔሉ እንደሚሉት አሁን 108 ዓመታቸው ከሆነ የመጨረሻ ልጃቸውን የወለዱት በ106 ዓመታቸው ነው ማለት ነው። ወ/ሮ ምስኩን ባለቤታቸው በ106 ዓመታቸው ስለመውለዳቸው ስንጠይቃቸው እንዲህ መልስ ሰጥተውናል። "አሁንም ቢሆን መውለድ ይችላሉ። ሦሰቱን ልጆቼን በቀዶ ህክምና ነው የወለድኳቸው። አሁንም መውለድ እፈልግ ነበር። ነገር ግን ሐኪሞቹ ከአሁን በኋላ መውለድ እንደሌለብኝ ነገሩኝ። ጥሩ አይደለም አሉኝ። ባለቤታቸው ወ/ሮ ምስኩ ጨምረው እንደሚሉት ከሌላ ሚስት የወለዱዋቸው ልጆቻቸው ትልልቆች ሰዎች ናቸው። አንዱ ልጃቸው አዲስ አበባ ነው የሚኖው። ጸጉሩ የገባ ነው። ዕድሜው ከ50 ዓመት በላይ ይሆናል።" ለወ/ሮ ምስኩ ሌላው ያቀረብነው ጥያቄ ስለ ኮለኔል ሪጃል አመጋገብ ነው። እሳቸው እንደሚሉት ኮሎኔሉ ብዙም እንጀራ መብላት አይወዱም። እራት አይመገቡም፤ የሚወዱት ጥራጥሬ ነገሮችን ነው። ጥሬ ሥጋም ነፍሳቸው ነው። ለኮለኔሉ ባለቤት ያቀረብነው የመጨረሻ ጥያቄ ኮሎኔል ሪጃል ጸባያቸው እንዴት ያለ ነው? የሚል ነበር። "ባህሪያቸው. . እምም. እሳቸው ሰው ያናድዳሉ እንጂ አይናደዱም።" ዕድሜን በሳይንስ እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? በተለያዩ ጊዜያት እንደ ኮሎኔል ሪጃል በዕድሜ እንደገፉ የሚናገሩ ሰዎች የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን ያገኛሉ። ከዚህ ቀደም ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ውስጥ የ165 ዓመት የዕድሜ ባለ ጸጋ ነኝ ያሉትን ግለሰብ መጥቀስ ይቻላል። ሆኖም እነዚህ ግለሰቦች ዕድሜያቸው እንደሚሉት ስለመሆኑ እስከአሁን በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠም። ኮ/ል ሪጃል ግን የኮሪያ መንግሥት ከዚህ ቀደም ገንዘብ ሊሰጠኝ ፈልጎ ዕድሜዬን ማመን ስለቸገራቸው ከጥርሴ ናሙና ወስደው መርምረው እኔ ስለመሆኔ አረጋግጠዋል። ዕድሜዬንም 101 ገምተውታል ብለዋል። ከዚያ በኋላ ገንዘብ እየተከፈላቸው እንደሆነ ተናግረዋል። የኮሎኔል ሪጃል ዕድሜና አካል አለመመሳሰል በተመለከ ያነጋገርናቸው ዶ/ር ኑረዲን ሉኬ ዕድሜ በትክክል የሚታወቅበት ሳይንሳዊ መንገድ እንዳለ ያረጋግጣሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ዓይነት የዕድሜ ይገባኛል ጉዳይ አጋጥሞ ስለማወቁ እንደማያውቁ የሚናገሩት ዶክተሩ፤ አስገድዶ መድፈር የተፈፀመባቸውና ያለዕድሜ ጋብቻ የተዳረጉ ሴቶች ዕድሜ ለማረጋገጥ ግን ምርመራ እንደሚደረግ ይናገራሉ። ዕድሜያቸው ከ22 ዓመት በታች ለሆኑት በተለይ በክንድና በእጅ አንጓ በሚሠራ የራጅ ምርመራ መረጃ ይገኛል። ነገር ግን ከዚያም በላይ ለሆኑት "200 ናኖ ግራም የሚሆን ዘረ መል ተወስዶ የሚደረግ ምርመራ ይኖራል" ይላሉ። ይሁን እንጂ በአገር ውስጥ እንዲህ ዓይነት አሠራር ስለመኖሩ ወቅታዊ መረጃ እንደሌላቸው ነግረውናል። የዚህ ዓይነት የዘረ መል ምርመራ የስህተት ህዳግ 5 ዓመት ሲሆን ከ22 ዓመት በታች ለሆናቸው የሚደረገው የራጅ ምርመራ የስህተት ህዳጉ ሁለት ዓመት ብቻ እንደሆነም አስረድተዋል። የኮ/ል ሪጃልን ሁኔታና ዕድሜዬ ነው የሚሉትን ቁጥር ጠቅሰን ያነጋገርናቸው ሌላው ባለሞያ ዶ/ር ዳንኤል ናቸው። ዶ/ር ዳንኤል በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፌዲዮሎጂ ስፔሻሊስት ሲሆኑ እዚያው ትቁር አንበሳ በመምህርነትም ያገለግላሉ። ዶ/ር ዳንኤል እንደሚሉት በኢሜጂንግ (ራጅ፣ ኤም አይ አር እና ሲቲ ስካንን ይጨምራል) በመጠቀም የኮ/ል ሪጃልን ዕድሜ ልናውቅ የምንችልበት እድል የለም። ይህም የሚሆነው የርሳቸው አጥንት እድገቱን ከጨረሰ ረዥም ጊዜ በመሆኑ ነው። በነዚህ የኢሜጂንግ ዘዴዎች በመጠቀም 95 ከመቶ ትክክለኛ ዕድሜ መናገር የሚቻለው አጥንታቸው በእድገት ላይ ያሉ ወጣቶች ላይ ነው። ይህም ዕድሜያቸው በሀያዎቹና በአስራዎቹ የሚገኙትና ከዚያ በታች ያሉትን ያጠቃልላል። ብዙዎቹ አጥንቶቻችን ዕድገት በጊዜ ሲያቆም ከ25 እስከ 30 ዓመት ዕድሜ ድረስ እድገት የሚያሳዩ አጥንቶቻችን መቀመጫችንን የሚሸከሙና ወገባችንና መቀመጫችን መሐል የሚገኝ አጥንት እንዲሁም ከትከሻ ወደ መሀል የሚወርደው አጥንት ነው ይላሉ ዶ/ር ዳንኤል። የኮ/ል ሪጃልን ዕድሜ ማወቅ የሚቻልበት ዕድል አገር ውስጥ ይኖር እንደሁ የተጠየቁት ዶ/ር ዳንኤል ምናልባት በሆርሞንና ቦንዴሴቶሜተር በሚባል ዘዴ የካልሺየም መጠንን በሚለካ መንገድ ፍንጭ ሊገኝ እንደሚችልና ይህ ግን እኛ አገር ስለመኖሩ እርግጠኛ እንዳልሆኑ ነግረውናል። ቢቢሲ አማርኛ ኮ/ል ሪጃል ነኝ የሚሉትን ዕድሜ በተመለከተ የሚያቀርቧቸው የሰነድ መረጃዎችን በገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም።
news-52720407
https://www.bbc.com/amharic/news-52720407
የኮንቴነር ውስጥ ሰቆቃ፡ የ64 ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው የኮንቴነር ውስጥ ሞት የተረፈው ደጀኔ
የአስራ ስምንት ዓመቱ ደጀኔ ደገፋ በያዝነው ዓመት መባቻ በሞያሌ በኩል ኢትዮጵያን ትቶ ወደ ደቡብ አፍሪካ ጉዞ ሲጀምር ኪሱ ውስጥ ሦስት ሺህ ብር ገደማ ነበረው።
በሚቀጥሉት ሰባት ወራት አራት የአፍሪካ አገራትን ካቆራረጠ በኋላ ግን ካሰበበት ከመድረስ ይልቅ ስድሳ አራት የጉዞ አጋሮቹ በሞት ከተለዩት በኋላ በዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት እገዛ ወደ አገሩ ነብሱን ብቻ ይዞ ተመልሷል። የደጀኔን ታሪክ በጽሑፍ ለማንበብ፡ የ64 ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው የኮንቴነር ውስጥ ሞት የተረፈው ደጀኔ
48850572
https://www.bbc.com/amharic/48850572
በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች
ዘመናዊ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍን ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ላይ ካደረሱት ጎምቱ ጸሃፍት መካከል ቀላል የማይባሉት አፋቸውን የፈቱት በሌላ ቋንቋ ነው። ከስብኅት ገብረእግዚያብሔርና ከበዓሉ ግርማ ውጪ የአማርኛን ልብወለድ ማሰብ ከባድ ነው። ጸጋዬ ገብረመድኅንን ደግሞ ከተውኔቱና ከሥነ ግጥም አንፃር አለማውሳት አፍ ማበላሸት ነው። ግጥምንስ እንደ ሰለሞን ደሬሳ ማን አዘመነው ሊባል ነው?
አንዳንድ ምሁራን ደግሞ የአማርኛን ትርጉምን ከሳህለሥላሴ ብርሀነማርያም ውጪ ማሰብም አይቻልም በማለት ዘመናዊ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍን ከተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች የመጡ ሰዎች እንዳፋፉትና አሁን ያለውን ቅርፅ እንደሰጡት በመናገር "የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ነው" ይላሉ። • ኮሎኔል መንግሥቱን ትግል ለመግጠም ቤተ መንግሥት የሄደው ደራሲ • “ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጽሁፍ ውስጥ ደረጃ ቢወጣ እነዚህ አንቱ የተባሉ ደራሲያን ከአምባው አናት ላይ የሚቀመጡ መሆናቸውን የዘርፉ ምሁራን ይስማማሉ። እነዚህ ደራሲያን በሌሎች የዓለም ቋንቋዎች የመፃፍ እድል እያላቸው በአማርኛ የፃፉ፣ የራሳቸውን የሥነ ጽሁፍ ዘይቤ የገነቡ መሆናቸውን በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የውጪ ቋንቋዎችና ሥነ ሥሑፍ ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆነችው ፀደይ ወንድሙ ትናገራለች። እርግጥ ዘመናዊ የአማርኛ ሥነ ጽሁፍ ዘር ልቁጠር ካለች እርቃኗን እንደምትቀር የኮተቤው የሻው ተሰማ ያነሳል። ለዚህም በዓሉ ግርማ፣ ፀጋዬ ገብረመድኅ፣ ሠለሞን ደሬሳ፣ ገበየሁ አየለ፣ አማረ ማሞ፣ ሙሉጌታ ሉሌ፣ ታቦር ዋሚ እያለ መጥቀስ አማርኛ ሥነ ጽሁፍ በእነማን ጫንቃ ላይ ወድቆ እንደነበር ለመረዳት ይቻለናል ሲል ያብራራል። ታዲያ እነዚህን ስመ ገናና ደራሲያን ለዘመናዊ አማርኛ ሥነጽሑፍ ያላቸው አበርክቶ ምንድን ነው? ለዘመናዊ አማርኛ ሥነጽሑፍ ካስማ የሆኑ ደራሲያን ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ አማርኛ ከግራም ከቀኝም የተወጠረበት ካስማ አለው በማለት ከኮተቤ የሻው ሀሳብ ጋር ይስማማል። የመጀመሪያዎቹን የአማርኛ ደራሲያንን በተመለከተ "እውነት ነው አፋቸውን በአማርኛ የፈቱ ሰዎችን እናገኛለን" ብሎ እነ መኮንን እንዳልካቸው፣ ዮፍታሄ ንጉሴ ፣ ግርማቸው ተክለ ሐዋርያትን የሚጠቅሰው ዓለማየሁ፤ በተጨማሪ ግን የአማርኛ ልብ ወለድ ሥጋና ደም ነስቶ እስትንፋስ የዘራው አፋቸውን በአማርኛ በፈቱ ደራሲያን እንዳልሆ ይጠቅሳል። ለአማርኛ ሥነ ጽሁፍ ሁለተኛው ረድፍ ላይ ተሰልፈው የሚገኙት ከጣሊያን ወረራ በኋላ የተወለዱት፣ በተለይ ከ1928 ዓ.ም ወዲህ፣ ከመሰረተ ልማት መስፋፋት በኋላ የመጡት ደራሲያን መሆናቸውን ዓለማየሁ ያነሳል። • "ፍቅር እስከ መቃብር"ን በአይፎን 7? ጣሊያን በገነባው የጥርጊያ መንገድ ላይ በእግርም በበቅሎም ተጉዘው ወደ ያኔዋ አዲስ አበባ መምጣት የቻሉ እነዚህ ደራሲያን የአማርኛ ሥነ ጽሁፍን በዛሬው መልክና ልክ አሳደጉት ሲል ዓለማየሁ ያስረዳል። ከትግራይ ስብኅት፣ ከአምቦ ፀጋዬ፣ ሰለሞን ከወለጋ፣ አሰፋ ጫቦ ከጨንቻ በድርስቱም ሆነ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኀን ውስጥ በመሳተፍ አማርኛ ለሥነ ጽሑፍ ምቹ ቋንቋ እንዲሆን ያበረከቱት አስተዋጽኦ ቀላል አለመሆኑን ያሰምርበታል። ረዳት ፕሮፌሰር ፀደይም ዘመናዊ የአማርኛ ሥነ ጽሁፍን ዛሬ በምንነጋገርበት ደረጃ አጽንተው ያቆሙት ደራሲያን ወደ አዲስ አበባ የመጡት በልጅነታቸው መሆኑን በመጥቀስ አፋቸውን ከፈቱበት ቋንቋና ባህል በይበልጥ ከተሜነት ገኖ እንደሚታይባቸው ታስረዳለች። ነባሩን ባህል በመግሰስ የከተሜ ባህልን ማንገስ ሁሉንም በ1960ዎቹ አካባቢ የአማርኛን ዘመናዊ ድርሰት የጀመሩትን ደራሲያን በጅምላ ብንመለከት የሚለው ደራሲ ዓለማየሁ ነባሩን ባህል በማሻሻልና በዘመናዊ ባህል ውስጥ በማካተት የራሳቸውን አብዮት የመሩ ናቸው ይላል። ለዚህም አስረጂ ሲጠቅስ አማርኛ አፍ መፍቻቸው ያልሆኑ ደራሲያንን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹንም እንደ ዳኛቸው ወርቁ ያሉ ደራሲያንን መመልከት አስፈላጊ መሆኑን የሚያነሳው ዓለማየሁ "ዘላለም ውስጥ ለውስጥ የሚስለከለክ ባህልን በማደፍረስ ላይ የተመሰረተ ልብ ወለድ" በእንግሊዘኛም በአማርኛም በመፃፍ የዘመኑን መልክ ያሳየናል። ይህ አቤ ጉበኛንም ይጨምራል ሲል ይጠቅሳል። • "ወሎዬው" መንዙማ እነዚህ አፋቸውን በሌላ ቋንቋ የፈቱና ለዘመናዊ የአማርኛ ሥነ ጽሁፍ የአንበሳውን ድርሻ ያበረከቱ ደራሲያን የከተሜን አዲስ ባህልና ዘመናዊነትን በማምጣት በሥራዎቻቸው ውስጥ መታተራቸውን ያነጋገርናቸው በሙሉ ይጠቅሳሉ። የገጠሩን ባህል ወደ አዲስ አበባ ይዞ የመጣውን ማህበረሰብ ፈትሮ በመያዝ አዲስ ባህል፣ አዲስ አስተሳሰብ እንዲያዳብር የዘመናዊ ደራሲያኑ ፋና ወጊዎች በሥራዎቻቸው ማሳየታቸውን ይጠቅሳሉ። እነዚህ ደራሲያን ከተለያየ ባህልና ቋንቋ መምጣታቸውን ካየን የመጡበትን አካባቢ ባህል ወደ ሥራዎቻቸው አሻግረው ይሆን? መነሳቱ የማይቀር ጥያቄ ነው። ሦስቱም እንግዶቻችንን የሚያስማማው እነዚህ ደራሲያን መጥተው የገቡበት የከተሜነት ባህል የራሱ ቀለም ያለው መሆኑ ላይ ነው። ለረዳት ፕሮፌሰር ፀደይ ወንድሙ የእነዚህ ደራሲያን የሕይወትና የንባብ ተጋልጦ በራሱ ዘመናዊነትን የሚያሳይ እንደነበር በመጥቀስ "በዓሉ በእንግሊዘኛ የጻፋቸው ግጥሞች ነበሩት፤ ስብኅትም የዳኛቸው ወርቁን ሥራ አንብቦ በአማርኛ መጻፍ ከመጀመሩ በፊት በሌላ ቋንቋ መጻፉን በዘነበ ወላ 'ማስታወሻ' ውስጥ አንብበናል" ትላለች። አክላም እነዚህ ደራሲያን ዘመናዊነትን የተዋወቁትና ወደ ሥራዎቻቸው ያመጡት ከሕይወት ልምዳቸው መሆኑን በመጥቀስ በዘመናዊነት ውስጥ የሚጠቀሙበት ቋንቋ የአማርኛ ሥነ ጽሁፍ ቅልጡፍ እንዲሆን መጣራቸው ይታያል ትላለች። ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ስብኅት ከተሜነት፣ ሁሉን አቀፍ በሆነው የከተሜ ባህል፣ ዘመኑ የፈጠረውንና የሚያሳየውን በማስተጋባት አስተዋፅኦ እንደነበረው በማስታወስ፤ የተወለደበትንና ያደገበትን ባህል ወደ አማርኛ ሥነ ጽሁፍ የማሻገር ሀሳብ እንዳልነበረው ያሰምርበታል። የበዓሉ ግርማ ሥራዎችም ውስጥ ከተሜነት መንበሩን ተቆናጦ እንደሚታይ ሁለቱ ምሁራን ሲናገሩ ደራሲ ዓለማየሁ ደግሞ ከተሜነት ብቻ ሳይሆን ነባሩ ባህል ከአዲሱ መጤ ባህል ጋር ሲጣላ፣ ሲጋጭ፣ ሲናጭ ይታያል ይላል። በበዓሉ ድርሰት ውስጥ ነባሩን ባህል አዲሱ ሲያሸንፍ ይስተዋላል የሚለው ዓለማየሁ አዲስ አስተሳሰብን፣ አዲስ አበቤነትን በመመስረት፣ አዲስ አበቤነትን በማንፀባረቅ የተሻለ መሆኑን ይጠቅሳል። • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ የኮተቤው የሻው የእነዚህ ደራሲያን ከተሜነት ብቻ ሳይሆን ዘመናዊ ደራሲያን መሆናቸው በራሱ የተወለዱበትን ባህል ለማሻገር እድል እንዳልሰጣቸው ያስረዳል። ረዳት ፕሮፌሰር ፀደይ፤ የመረጡት ዘውግ ለዚህ ምቹ እንዳልነበር ከየሻው ጋር ትስማማለች። በርግጥ መቼታቸውን ከተማ ማድረጋቸው ባህልን ለማሻገር ከብዷቸዋል ብሎ ለመደምደም አስቸጋሪ ነው በማለት አብዛኞቹ ዘመናዊ ደራሲያን ወደ ከተማ የመጡት ገና በልጅነታቸው እንደሆነ ገልፃ ረጅም ጊዜ በንባብና በኑሮ ያሳለፉት በከተማ ውስጥ በመሆኑ ከተሜነት በሥራዎቻቸው ውስጥ እንደሚጎላ ታብራራለች። አክላም "ያኔ ትልቋ ከተማ አዲስ አበባ ብቻ ነበረች፤ እንደዛሬው ሌሎች ከተሞች ባለመኖራቸው አዲስ አበባና አዲስ አበቤነት ብቻ" መጉላቱን ታስረዳለች። ጋሽ ፀጋዬ ከሌሎቹ ደራሲያን ይለያል የሚሉት የኮተቤው የሻውና የመቀሌዋ ረዳት ፕሮፌሰር ፀደይ፣ በተለይ በግጥሞቹና መጣጥፎቹ ውስጥ የኦሮሞን ባህል ሲያስገባ እናያለን ይላሉ። ግን ይሄ የኦሮሞን ባህልና ቋንቋ ብቻ ሳይሆን ከዚያ ከፍ ባለና ደማቅ በሆነ መልኩ በሥራዎቹ ነባር ጀግኖችን በመፍጠር በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ አግዝፎ ማሳየት የፀጋዬ ሥራዎች ውስጥ የሚታዩ መሆናቸውን የሻው ያነሳል። "ጋሽ ፀጋዬ የሚያስብበት ጠገግ ሥነሰባዊ ስለሆነ፣ እኛን በጥንትነት ውስጥ የመፈለግ አዝማሚያ ስላለው ነው" በማለትም ሌሎቹ ግን አዲስ አበቤነት በሚያጠቃው የአስተሳሰብ ጠገግ ውስጥ ያሉ በመሆናቸው ለምን አፋቸውን የፈቱበትን ቋንቋና ባህል አላሻገሩም ብሎ እንደማይከሰሱም እንደማይወቀሱም ሁለቱም ይናገራል። • ጥበብን በወር-አበባና በአጽም ደራሲ ዓለማየሁ፤ የፀጋዬ ጥረት ኢትዮጵያን ዓለም አቀፋዊ ማድረግ ነው በማለት "በግብፅ በኩል አድርጎ ግብፅ ላይ ደግሞ በጥቁር ሥልጣኔ ውስጥ ኢትዮጵያ ያላትን ድርሻ ከፍ አድርጎ ማሳየት ነበር ሕልሙ" ይላል። ፀጋዬ ኢትዮጵያን ከፍ ከፍ በሚያደርግ ጥናት ላይ ተመስርቶ ነበር ሲሰራ የነበረው የሚለው ዓለማየሁ ወደ ኋላ 13 ሺህ ዓመታት ተጉዞ የአፍሪካዊያንን የፍልስፍና መሰረትና የሥልጣኔ ማማነት ለማሳየት መትጋቱን በማስታወስ የመጣበትን ባህል በአማርኛ ሥነ ጽሁፍ ላይ ለመጫን አለመሞከሩን ያስረዳል። ሠለሞን ደሬሳ የተለመዱ ሥራዎች ላይ አመጽ ያስነሳ፣ ያፈነገጠ ደራሲ ነው የሚለው ዓለማየሁ የተሻለ መንገድ በመቅደድ ያበረከተው አስተዋጽኦ እንደሚጎላ ይናገራል። ዓለማየሁ የሰለሞን ደሬሳን "ባህልና እኔ" የሚል አጭር መጣጥፍ በመጥቀስ የኖረውን ሥርዓት በማፍረስ አዲስ ጥርጊያ መንገድ በመቅደድ ረገድ ደፋርና የተሳካለት ደራሲ እንደነበር ያስታውሳል። ከመጡበት ማኅበረሰብ ወደ አማርኛ ቋንቋ ያሻገሩት ቃል፣ እሳቤ፣ ባህል አማርኛን ቋንቋ የዳበረው ከአረብኛና ከኦሮምኛ በወሰዳቸው በርካታ ቃላት ነው የሚለው ዓለማየሁ ገላጋይ አንዳንዴ እንደውም ቃላት ብቻ ሳይሆን እሳቤም ይወስዳል ሲል "ጉዲፈቻ"ን በምሳሌነት ያስረዳል። ስለዚህ እነዚህ ደራሲያን በስልትም ሆነ በቋንቋ ወደ አማርኛው በማጋባት በኩል እምብዛም መሆናቸውን በመግለፅ፤ ደራሲያኑ ከተሜነት ውስጥ ሲገቡና እዚያው ውስጥ በአማርኛ ሲጽፉ ይታያል እንጂ ከመጡበት ቋንቋ ወደ አማርኛ ሲያመጡ አይስተዋልመ ይላል። ረዳት ፕሮፌሰር ፀደይ እነዚህ ደራሲያን ከመምጣታቸውም በፊት ቋንቋዎቹ በራሳቸው መዋዋስ ጀምረዋል በማለት ባህልና ቋንቋ ማሻገሩን ከደራሲያኑ አንጻር ብቻ ማየት እንደማይገባ ትገልፃለች። በእርግጥ ዘመናዊ ደራሲያኑ ሥነ ጽሑፉን ሲያዘምኑ ቋንቋውን ለዚህ እንዲመች አድርጎ ቅልጡፍ ማድረግ ላይ መጨነቃቸው እንደማይቀር የምትናገረው ፀደይ ሠለሞንና ፀጋዬ በሥራዎቻቸው ውስጥ ከኦሮምኛ የወሰዷቸውን ቃላትና አንዳንድ አገላለፆች መጠቀማቸውን ትጠቅሳለች። • ''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" "እነዚህ ደራሲያን ከኦሮምኛ ቃላትን በመምጣት ከአማርኛ ጋር በመሸመን ሲጠቀሙ ቢስተዋልም ሌሎቹ ደራሲያን ግን የአማርኛ ቋንቋ ለሥነ ጽሁፍ ቅልጡፍ እንዲሆን በማድረግ ውስጥ ሚናቸው ይጎላል።" የኮተቤው የሻው ተሰማ ዘመናዊ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ደራሲያን የኖሩበትና የጻፉበት ዓለም በዙሪያው ከሚገኙ የተለያዩ ማኅበረሰቦች በተዋጣና በተዳቀለ ባህልና ወግ ውስጥ በመሆኑ የመጡበትን ማኅበረሰብ ባህል በተለየ ሁኔታ ለማሳየት እንዲጨነቁ አላደረጋቸውም ይላል። በእርግጥ ሰለሞን ደሬሳ አንዳንድ የኦሮምኛ ቃላትን አምጥቶ ለማስገባትና ወደ አማርኛ ለመለወጥ ሲሞክር ይታያል የሚለው ደራሲ ዓለማየሁ፤ ፀጋዬ ገብረመድኅንም አማርኛ ከአያቱ ግዕዝ ይልቅ ሊዳብርም ሊስፋፋም የሚችለው በወንድሞቹ ኦሮምኛ፣ ወላይትኛ ሲዳምኛ ያሉ ቋንቋዎች ነው ይል እንደነበር ይገልፃል። የአማርኛ ሥነ ጽሁፍ ከሌሎች ወንድም ቋንቋዎች እየተቀበለ በውስጡ ቢያካትት የውጪውን ቋንቋ ሊገዳደር በሚችል መልኩ ስፋቱም ይገዝፍ፣ ጥልቀቱም ይርቅ እንደነበር ያስረዳል። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ከተለያየ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ትርጉሙን፤ ቃላቱን ብቻ ሳይሆን እሳቤውንም ጭምር በማምጣት አማርኛን ማግዘፍ ይቻል እንደነበርም ሲያስረዳ ወላይታ "ሀይሲ" የሚሰኝ የአገጣጠም ስልት አለው በማለት ነው። ይህ የወላይታ አገጣጠም ስልት ከሰሜን በመጣው የቅኔ ባህልም ሆነ በዘመናዊ የአማርኛ የአገጣጠም ስልት አይሄድም በማለት አማርኛ ወደ ራሱ ለመውሰድ እንዳልቻለ በማንሳት በዚህ ረገድ በዘመናዊ ደራሲዎቹ ላይ የታየውን ክፍተት ያነሳል። የተጠቀሱት ዘመናዊ ደራሲያን ለአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ያበረከቱትን ውለታ መሠረት በማድረግ ከአማርኛ ቋንቋ ውጪ ያሉ የሌሎች ሀገርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ደራሲያን በአማርኛ የመጻፍ አስተዋጽኦ ቢያደርጉ የአማርኛ ሥነ ጽሁፍን የተሻለ ማድረግ ይቻል ይሆን?
news-49142489
https://www.bbc.com/amharic/news-49142489
ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ሊባል ይችላል?
አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር የለ ፍቃዷ ወሲብ ከፈጸመ፤ ይህ ያለአንዳች ጥርጥር በሕግ ፊት አስገድዶ መድፈር ነው። ተገላቢጦሹ ቢሆንስ? ሴት ልጅ ያለ ወንዱ ፍቃድ ወሲብ ብትፈጽምስ?
ይህ እንግሊዝን ጨምሮ በበርካታ ሃገራት ሕግ እንደ አስገድዶ መድፈር አይቆጠርም። ጾታዊ ግንኙነትን መሰረት ያደረጉ ጥናቶችን የሚያካሂዱት ተመራማሪ፤ ይህ በሕግ ፊት አስገድዶ መድፈር ተደርጎ መታየት ይኖርበታል ይላሉ። [ማሳሰቢያ፡ ይህ ጹሑፍ እንዳንድ አንባቢያንን ምቾች ሊነሳ ይችላል] ዶ/ር ሲኦብሃን ዊአር በላንካስተር ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት እአአ ከ2016-2017 ባሉ ጊዜያት በሴቶች ያለፍቃዳቸው ወሲብ እንዲፈጽሙ የተገደዱ ከ200 በላይ ወንዶችን አነጋግረው ጥናታዊ ምርምር አድርገዋል። በዚህ ሳምንት ይፍ የተደረገው ጥናት ከ30 በላይ ወንዶች ጋር ፊት ለፊት የተደረገ የቃለ መጠይቅ ውጤትም ተካቶበታል። ጥናቱ ወንዶች በምን አይነት ሁኔታ ያለፍቃዳቸው ወሲብ እንዲፈጽሙ እንደሚገደዱ፣ ይህ በደል የሚያስከትለው ተጽእኖ እና በሕግ የሚሰጠው ትርጓሜ ምን እንደሚመስል ዳሰሳውን አድርጓል። • የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት • ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን? በጥናቱ የተሳተፉት ወንዶች ማንነታቸው ይፋ አልተደረገም። ከተሳታፊዎቹ መካከል ግን አንዱን እንደምሳሌ እንውሰደው፤ ጆን ብለንም እንጥራው። ጆን እንደሚለው ከህይወት አጋሩ ጋር ሳለ ''ትክክል ያልሆኑ'' ነገሮች የሚላቸውን ምልክቶች አስተዋለ መጥፎ ነገሮችም መከሰት ጀመሩ። እንደ ጆን ከሆነ የህይወት አጋሩ በቅድሚያ እራሷን መጉዳት ጀመረች። አንዳንዴም እራሷ ላይ በምትወስዳቸው አደገኛ እርምጃዎች በመደናገጥ ወደ ህክምና ይዟት የሚሄድበት አጋጣሚዎች እንዳሉም ይናገራል። ጥንዶቹ ለሰዓታት የአዕምሮ ህክምና የምታገኝበትን ሁኔታ ተመካክረዋል። የሥነ ልቦና ባለሙያ ጋር ቀጠሮ ቢያዝላትም ፍቃደኛ ሳትሆን መቅረቷን ጆን ይናገራል። ይህ ነገር እያደር ሲመጣ እራሷ ላይ ጉዳት ማድረሱን አቁማ ፊቷን ወደ ጆን አዞረች። ''አንድ ቀን ሳሎን ቁጭ ብዬ ነበር። ምግብ ከምናበስልበት ስፍራ መጣችና አፍንጫዬን በኃይል በቡጢ መትታኝ ወደ መኝታ ቤት እየሳቀች ሮጣ ገባች" በማለት የህይወት አጋሩ ኃይለኝነት የጀመረበትን ሁኔታ ጆን ያስረዳል። እያደር በሄደ ቁጥርም ዱላው እና ጉንተላው እየበዛ ሄደ። "ከሥራ እንደተመለሰች ሁልጊዜም ወሲብ እንድናደርግ ትጠይቀኛለች" ይላል። "በጣም ኃይለኛ ትሆናለች። እንዳንዴም ከሥራ ቦታዋ ወደቤት ባትመለስ ብዬ የምመኝበት ጊዜያት አሉ።" አንድ ጠዋት ላይ ጆን ከእቅልፉ ሲነሳ የህይወት አጋሩ ቀኝ እጁን ከአልጋው ራስጌ ጋር አስረዋለች። ከዚያም ከአልጋው ጎን በነበረ ስፒከር አናቱን ትመታው ጀመር። ከዚያም ግራ እጁን በጨርቅ ከአልጋው ጋር ካሰረች በኋላ ከእርሷ ጋር ወሲብ እንዲፈጽም በኃይል ማስገደድ ጀመረች። በፍርሃት እና በድንጋጤ የተዋጠው ጆን ሰውነቱን ለእርሷ ጥያቄ ዝግጁ ማድረግ ተሳነው፤ በዚህ የተበሳጨቸው ሴት ደጋግማ ትመታው ያዘች። ከአልጋው ጋር የታሰሩ እጆቹን ከመፍታቷ በፊት ለሰዓታት ታስሮ ቆይቶ ነበር። ከዚህ ሁነት በኋላ ስለ ጉዳዩ ለመወያየት ጥረት ቢያደርግም እርሷ ፍቃደኛ ስላልነበረች እንደልተሳካ ጆን ያስረዳል። የጆን የህይወት አጋር ነብሰ ጡር መሆኗን ተከትሎ፤ ኃይለኝነቷ መቀነሱን ይናገራል። ልጃቸው ከተወለደች ጥቂት ወራት በኋላ ጆን አንድ ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ እጁ ከአልጋው ጋር ታስሮ ያገኛል። ከዚያም በኃይል ቫያግራ (የወሲብ ፍላጎትን የሚያነሳሳ እንክብል) እንዲወስድ ካደረገች በኋላ አፉን በጨርቅ አፍና ወሲብ እንደፈጸመች ጆን ይናገራል። ''በወቅቱ ምንም ማድረግ አልቻልኩም" ይላል ጆን። "ይህን ካደረገችኝ በኋላ ለምን ያክል ጊዜ እንደቆየሁ ባለውቅም ብቻ ለረዥም ሰዓት መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ውሃ እላዬ ላይ እያፈሰስኩ ቆየሁ. . . በስተመጨረሻም ወደ ሳሎን ሄድኩ። ይህን አድርጋ ስታበቃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረችው 'እራት ምንድነው የምንበላው?' ነበር።" • 100 ሺህ ብር፤ ብልትን ለማወፈር • ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው? ጆን ይህ ለሰዎች ለመናገር ጥረት ማድረጉን ይሁን እንጂ ሰዎች ስላማያምኑት እውነትነቱን በዝርዝር ማስረዳት ስለሚከብደው ብዙ ጊዜ እንደሚተወው ይናገራል። "አንዳንድ ሰዎች 'ለምን ቤቱን ጥለህ አትወጣም' ይሉኛል። ይህ ግን ቤቴ ነው። ቤቱን የገዛሁት ለልጆቼ ነው። በገንዘብም ረገድ ከእርሷ ጋር እንድኖር ግድ ሆኖብኛል። ይህም ብቻ አይደለም፤ 'ስትመታህ ለምን መልሰህ አትመታትም' ይሉኛል። ግን እሱ እንደመናገሩ ቀላል አይደለም። እንደው ድሮ ነበር ማምለጥ የነበረብኝ" በማለት ጆን ይተርካል። ይህን መሰል ታሪክ በርካታ በጥናቱ ተሳታፊ የሆኑ ወንዶች የሚጋሩት እውነታ ነው። የዶ/ር ሲኦብሃን ዊአር ጥናት ትኩረቱን ያደረገው በሴቶች ተገደው ወሲብ በሚፈጽሙ ወንዶች ላይ የሚከሰተው ተጽእኖ ስፋት እና መጠንን ለመለየት ሲሆን፤ ተገዶ ወሲብ መፈጸም ከሚደርሱ በደሎች አንዱ እንጂ ብቸኛው እንዳልሆነ ተመራማሪዋ ይናገራሉ። በጥናቱ ተሳታፊ ከሆኑ አንዱ ለበርከታ ዓመታት የደረሰበትን በደል ለፖሊስ ባስታወቀበት ወቅት "ይህ ነገር ባያስደስትህ ኖሮ ቀደም ብለህ ለፖሊስ ሪፖርት ታደርግ ነበር" እንደተባለ በጥናቱ ላይ ቃሉን ሰጥቷል። የጥናቱ ተሳታፊው ጆን እንዲህ ብሏል፡ "ስለጉዳዩ ማውራት ያስፈራል። ያሳፍራል። ደፍረን ስናወራ ደግሞ የሚያምነን የልም። ምክንያቱም ወንዶች ነና። 'እንዴት ወንድ ልጅ በሴት ልጅ ይበደላል? ወንድ ልጅ እኮ ነህ?' ይሉናል።" ጥናቱ ምን ይፋ አደረገ? በዶ/ር ሲኦብሃን ዊአር ጥናት ግልጽ ከተደረጉ ትክክለኛ ያልሆኑ አመለካከቶች መካከል፤ ወንዶች ከሴቶች በላይ ጠንካራ ስለሆኑ ሴቶች ወንዶችን አስገድደው ወሲብ መፈጸም ቸይችሉም፣ ወንዶች ፍቃደኛ ካልሆኑ ብልታቸው ስለማይቆም የሴቷ ብልት ውስጥ ሊገባ አይችልም የሚሉ የሚገኑበት ሲሆን፤ በተጨማሪም ከሴት ጋር የወሲብ ግንኙነት ማድረጊያ አጋጣሚዎች በሙሉ አዎንታዊ ናቸው የሚሉት ይገኙባቸዋል። ዶ/ር ሲኦብሃን እንደሚሉት ሌላው የተሳሳተው አመለካካት 'ወንዶች ብልታቸው ከቆመ ወሲብ ለማድረግ ፍላጎት አላቸው' የሚለው ነው ይላሉ። ተመራማሪዋ እንደሚሉት "ብልት የሚቆመው ለተነቃቃ የአዕምሮ ክፍል ምልሽ ሲሰጥ ነው።" "ወንዶች በፍርሃት፣ በንዴት፣ በጭንቀትም ውስጥ ሳሉ እንኳን የብልት መቆም ሊያጋጥማቸው ይችላል።" • እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ''ደካማ ነው'' ተባለ • የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? በጥናቱ ከተሳተፉ መከካል ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ወንዶች፤ በሴቶች ያለ ፍቃዳቸው ወሲብ እንዲፈጽሙ ከተገደዱባቸው ሁነቶች መካከል በአደንዛዥ እጽ እና አልኮል ጫና ስር ከወደቁ በኋላ መሆኑን ይጠቀሳሉ። ከዶ/ር ሲኦብሃን ዊአር ጋር ፊት ለፊት ቃለ ጠይቅ ካደረጉት አንዱ፤ ከአንዲት ሴት ጋር በምሽት ክለብ ሲዝናና ከቆየ በኋላ አታላ የሰጠችው እጽ እራሱን እንዲስት እንዳደረገው እና ያለ ፍቃዱ ወሲብ እንዲፍጽም እንዳስገደደችው ተናግሯል። ሌላ ወጣት ለዶ/ር ሲኦብሃን ሲናገር በአንድ ወቅት ለወንድ ጓደኛው የጻፈውን ደብዳቤ የተመለከተች የሥራ ባልደረባው ከእርሷ ጋር ወሲብ ካልፈጸመ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ነው ብላ እንደምታስወራበት በማስፈራራቷ ያለፍቃዱ ወሲብ መፈጸሙን አምኗል። ዶ/ር ሲኦብሃን ዊአር በጥናቶቻቸው የተሳተፉ ወንዶች ያለ ፍቃዳቸው ወሲብ እንዲፈጽሙ መደረጋቸውን ''ተገዶ መደፈር'' ሲሉ ይጠሩታል ይላሉ። ብዙዎቹም እንግሊዝን ጨምሮ በሌሎች ሃገራት ሕጎች ይህ በደል ''ተገዶ መደፍር'' ተብሎ አለመጠራቱ ያበሳጫቸዋል። በጥናቱ ላይ ከቀረቡ 8 የመፍትሄ ሃሳቦች መካከል አንዱ ወንዶች ያለ ፍቃዳቸው በሴቶች ወሲብ እንዲፈጽሙ ሲደረጉ በሕጎች ላይ ''አስገድዶ መደፈር'' ተበሎ እንዲፈረጅ አሳስቧል።
news-49541373
https://www.bbc.com/amharic/news-49541373
በመቀሌ የከተሙት ኤርትራውያን
ለሁለት አስርት አመታት ተፋጠው የነበሩት የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ሁኔታ ቤተሰብን በታትኗል፣ እንደወጡ የቀሩ አባትና ልጅ ተነፋፍቀው መገናኘት ሳይችሉ ቀርተዋል፤ እናት የናፈቀቻቸውን ልጆቿን አይን ለማየት እንደጓጓች አመታት የተቆጠሩባቸው፣ ብዙዎች ቤተሰቦቻቸውን ናፍቀው እምባ የነጠፋባቸውን ጊዜያት አሳልፈዋል።
በሁለቱ ሃገራት የተደረገው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህይወትን ከመቅጠፍ በተጨማሪ የሁለቱን እህትማማችና/ወንድማማች ህዝብም እንዳይገናኙና ተቆራርጠው እንዲቀሩ ምክንያት ሆኗል። •ኤርትራ በሳዋ ባደረገችው ወታደራዊ ትዕይንት ምን እያለች ይሆን? •በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል ከአንድ አመት በፊት የሁለቱ ሃገራት መንግሥታት ሰላም እናወርዳለን ማለታቸውን ተከትሎም ተቆራርጠው የነበሩ ቤተሰቦች ስሜታቸውን መግለፅ ከብዷቸው፤ እግራቸው ክዷቸው መሬት ላይ ሲንበረከኩ፤ ቃላት አጥሯቸው ሲያነቡ የነበሩና ሌላም ብዙ የብዙዎችን ስሜት የነኩ ሁኔታዎች ታይተዋል። ከቤተሰቦች መገናኘት በተጨማሪ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የነበረውም ንግድም እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል። ይሁን እንጂ እንጂ ሁለቱን ሃገራት በመንገድ የሚያገናኙት ዛላምበሳ ሰርሓ፣ ራማ ዓዲ ዃላ እንዲሁም ሑመራ ኦምሓጀር መስመሮች "ሕጋዊ አሰራር ሊበጅለት ነው" በሚል ምክንያት ደርቶ የነበረው የንግድ ግንኙነት እንዲቋረጥ ሆኗል። ሕጋዊ አሰራር ሊበጅለት ነው በሚል ምክንያት የተቋረጠው ግንኙነትም እስካሁን ተግባራዊ ባይሆንም የሁለቱም ሃገራት ህዝቦች ግንኙነታቸው እንደቀጠለ ነው። ኤርትራውያን በመቐለ ከተማ ተዘግተው የነበሩ ድንበሮች መከፈታቸውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ጎርፈዋል። ከትግራይ ነዳጅ ጨምሮ ዳቦ፣ እንጀራና ሌሎች የሸቀጥ አይነቶች ሲጓጓዙም እንደነበር ብዙዎች ይናገራሉ። በተለይም በዛላምበሳ በኩል ወደ ዓዲግራት ብሎም ወደ መቐለ ከተማ የገቡት ኤርትራውያን ቁጥራቸውን በትክክለ መንገር ባይቻልም በሺዎች እንደሚገመቱ ይነገራል። ወደ ትግራይ የመጡት ኤርትራውያን መቐለን ማእከል አድርገው በቋሚነት እየኖሩ ሲሆን በተለያዩ የስራ ዘርፎችም እንደተሰማሩ ቢቢሲ ለመገንዘብ ችሏል። ከነዚህ ውስጥ አርሴማ ሰመረ አንዷ ነች። ከኤርትራ መጥታ በከተማዋ እምብርት ሮማናት አደባባይ አካባቢ በፀጉር ስራ ተሰማርታለች። ከሃገር ወጥቶ ኑሮን መመስረት ቀላል ባይሆንም ለአርሴማ ብዙ አልከበዳትም። "መቐለ ለስራ ምቹ የሆነች ከተማ ነች፤ እንደ ሃገሬው ዜጎች ነው የምንስተናገደው እና በተጨማሪ የምጠየቀው ነገር የለንም" በማለት ትገልፀዋለች። አስመራ በነበረችበት ወቅት በዋነኝነት በአንድ የባህል ቡድን በድምፃዊነት እና በተወዛዋዥነት ትሰራ ነበር። መቐለም ከመጣች በኋላ ከፀጉር ስራው በተጨማሪ አልፎ አልፎ በምሽት ክበቦች እና ጭፈራ ቤቶች በተወዛዋዥነት ትሰራለች። በቅርቡም አንድ ነጠላ ዜማ ሰርታ ለመልቀቅ በዝግጅት ላይ እንደሆነች ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ገልፃለች። የሁለቱን ሃገራት እርቀ ሰላም ተከትሎ መቐለ የከተመው ሌላኛው ኪዳነ ገብረ ሚካኤል ነው። በተለምዶ 16 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢከም በፀጉር ስራ ተቀጥሮ በመስራት ይገኛል። "እዚህ ስንሰራ በመንግስት ይሁን ቀጣሪ ድርጅቶች የምጠየቀው ወረቀት ስለሌለ ምንም የምንቸገረው የለም" ይላል። •የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? የኑሮ ሁኔታ በትግራይ ክልል የተለየ የሕግ አሰራር ባይወጣም እንደ ሃገር ኤርትራውያን ከሌሎች ሃገራት ስደተኞች በተለየ ሁኔታ ሰርተው የሚለወጡበት እና ሀብት የሚያፈሩበት የሚደነግገው አዋጅ ተሻሽሎ ቀርቧል። የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ባለፈው አመት በትግራይ ስታድየም ባሰሙት ንግግር ኤርትራውያን ወደ ክልሉ መጥተው እንዲሰሩና ሃብት እንዲያፈሩ እንዲሁም በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ መንግሥታቸው አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ መናገራቸው የሚታወስ ነው። ምንም እንኳን ኤርትራውያን በነፃነት መንቀሳቀስ ቢፈቀድላቸውም ከስደተኞች መጠለያ ውጭ ከተማ ውስጥ ለሚኖሩ ኤርትራውያን ስደተኛ መሆናቸውን የሚገልፅ ወረቀት ይዞ መንቀሳቀስ ግዴታ እንደሆነ ኪዳነ ይናገራል። ከዚህም በተጨማሪ በአንዳንድ የስራ ዘርፎችም ለማሳተፍ እንዳማይችሉም ይገልፃል። •የኤርትራውን ሚኒስትር በጥይት ያቆሰለው መያዙ ተነገረ "የራሳችን ድርጅት እንድንከፍት አልተፈቀደልንም። በቅርቡ ይፈቀዳል የሚል መረጃ ስላለ ይፈቀድልናል ብለን በተስፋ እየጠበቅን ነው" ይላል። ምንም እንኳን ሁሉ አልጋ ባልጋ ባይሆንም የሁለቱ ሃገራት ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤ መመሳሰል ከሃገር ርቆ ሁለተኛ ሃገር የሆነላቸው አልታጡም፤ ከነዚህም መካከል ሰላም ብርሃነ አንዷ ናት። በአሁኑ ወቅት በአንድ መፅሃፍት ቤት ተቀጥራ ብትሰራም መጀመሪያ ስትመጣ የመቆየት ሃሳብ አልነበራትም። ተመሳሳይ ቋንቋ መናገራችው፣ የህዝቡ አኗኗር ዘዬ በአጠቃላይ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ትስስር በመረዳቷ መቀሌ ለመቆየት እንደወሰነች ትናገራለች። "መቀሌን ስለወደድኳት እዚሁ ቀረሁኝ፤ የትግራይና የኤርትራ ህዝቦች ግንኙነትም ከፍተኛ ትስስር እንዳለው ተረድቻለሁ"ትላለች። በመጀመሪያ ወደ መቀሌ ስትመጣ ለከተማዋም ሆነ ለህዝቡ ምንም አይነት ግምት ባይኖራትም በአሁኑ ወቅት ግን እንደ ሃገሬው ህዝብ ስለተቀበላትም ደስታዋ ከፍ ያለ ነው። ለረጅም ዓመታት ሰላምም ሆነ ጦርነት በሌለበት ሁኔታ ከመኖራቸው አንፃር ህዝቡ እንዲህ በቀላሉ ይወዳጃል ብላ እንዳልጠበቀችም ሰላም ትናገረለች "የትግራይ ህዝብ ሰው አክባሪ እና ለኤርትራውያን ትልቅ ክብር ያለው ህዝብ ሆኖ ይሰማኛል" በማለት ትዝብትዋን አካፍላናለች። በመቀሌም ብዙ ጓደኞችን አፍርታ ተስፋዋን ሰንቃ ሃገሬ ብላ እየኖረች ነው። •ኤርትራ በምሽት ድንበር ማቋረጥን ከለከለች ምንም እንኳን ስደተኛ መሆናቸውን የሚመሰክር ወረቀት ይዘው መንቀሳስ ቢችሉም የባንክ ሂሳብ ደብተር ለማውጣት የሚፈቅዱላቸው አንዳንዶች መሆናቸውን ይገልፃሉ። ኪዳነ በበኩሉ ምንም እንኳን ስደተኛ ቢሆነም ስደተኛነቱን ይህንን ያህል እንደማያስተውሰው ገልጿል። "ኤርትራዊ ሆነህ እዚሁ ሀገር ለመስራት ብዙ አስቸጋሪ አይደለም፤ ራስህን ከህብረተሰቡ ተለይተህ እንደ ስደተኛ አታስብም፤ ስደተኛ መሆኔን ትዝ ብሎኝ አያውቅም" ይላል። በግንኙነቱ እስካሁን ከተሰራው ይበልጥ ከተሰራበት ተስፋ ሰጪ ዕድሎች እንደሚታየውም ኪዳነ ይገልጻል። "ለስራም ብዙ አልቸገርም፤ እንደ ዜጋው ነው የምትኖረው። ስደተኛ በመሆንህ የሚፈጠር ልዩነት የለም፤የወረቀት ማስረጃ እና ዋስ አቅርበህ ስራ መቀጠር እንችላለን" በማለት አብራርታለች።
news-57067382
https://www.bbc.com/amharic/news-57067382
በትግራይ በመድፈር ወንጀል የተጠረጠሩ የመከላከያ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በትናንትናው ዕለት በትግራይ ከተማ ስለተፈፀሙ ግድያዎች እና መደፈሮች በሰጠው መግለጫ በወንጀሉ የተሳተፉ የፌደራል እና መከላከያ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፍቃዱ ጸጋ ጾታን መሰረት አድርጎ የሚፈጸም ወንጀል የመመርመር ስልጣን ያለው ክልሉ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተፈጸመውን ወንጀል እየመረመረ ያለው በክልሉ ፖሊስ አካላት መሆኑን ተናግረዋል። ከክልሉ ፖሊስ በተገኘው መረጃ መሠረት የመድፈር ጥቃት ደርሶብናል ብለው ሪፖርት ያደረጉ ሴቶች ቁጥር 116 መሆኑን ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ተናግረዋል። በወንጀል ድርጊቱ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት መኖራቸውን አቶ ፍቃዱ ጸጋ ተናግረዋል። አቶ ፍቃዱ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ድርጊቱን ፈጽመውታል የተባለው በግዳጅ ላይ እያሉ ስለሆነ ጉዳያቸው በጦር ፍርድ ቤት ይታያል ብለዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላትን በተመለከተ የክልሉ ፖሊስ ምርመራ አጠናቆ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይም ደግሞ ለፍትሕ ቢሮ መዝገቡ ተላልፎ ተሰጥቷል ሲሉ አስረድተዋል። እንደ እርሳቸው ገለፃ የፍትሕ ቢሮ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከሌሎች የፍትሕ አካላት ጋር በመተባበር የትኛውንም ወንጀል ፈጻሚ ሙያዊ ደረጃውን በጠበቀ መርምሮ ጥፋተኞችን ለሕግ ለማቅረብ ዝግጁነት አለው ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የካቲት ወር ላይ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 108 የመደፈር ጥቃቶች ለጤና ተቋማት ሪፓርት መደረጋቸውን ገልጿል ኮሚሽኑ በመቀለ ከሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ባገኘው መረጃ መሠረት፤ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ በመቀለ ሆስፒታል 52፣ በአይደር ሆስፒታል 27፣ በአዲግራት ሆስፒታል 22፣ በውቅሮ ሆስፒታል 7 በአጠቃላይ 108 የመደፈር ጥቃቶች ለጤና ተቋማት ሪፖርት ተደርገዋል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በግጭት ወቅት የሚከሰት ወሲባዊ ጥቃት ላይ አተኩሮ የሚሠራው ቡድን በትግራይ ክልል እየደረሰ ያለው ወሲባዊ ጥቃት እንዲገታ በማሳሰብ መግለጫ ያወጣው በጥር ወር ላይ ነው። የቡድኑ ልዩ ተወካይ ፕራምሊያ ፓተን ሁሉም አካላት ወሲባዊ ጥቃት እንዲገታ እንዲሁም ውጥረት እንዲረግብ የድርሻቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸው ይታወሳል ልዩ ተወካይዋ "በመቀለ ከተማ በርካታ ቁጥር ያለው ሰው የመደፈሩ ክስና በአጠቃላይ ከትግራይ ክልል የተሰሙት የወሲባዊ ጥቃት ክሶች እጅግ አሳስበውኛል" ብለዋል። ጨምረውም "ሰዎች የገዛ ቤተሰባቸውን እንዲደፍሩ እየተገደዱና ይህን ካላደረጉ ጥቃት እንደሚደርስባቸው የሚጠቁሙ በጣም የሚረብሹ ሪፖርቶች ተሰምተዋል" ብለዋል። ጥቅምት 24 2013 ዐዓ.ም በፌደራል መንግሥቱ እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል ግጭት ከተቀሰቀሱ ወዲህ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መድረሳቸውን የተለያዩ አለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እና ኢሰመኮ አስታውቋል። ኢሰመኮ እና አምነስቲ ባወጧቸው መግለቻዎች ላይም በሕዳር ወር አጋማሽ ላይ በአክሱም በንፁኀን ዜጎች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ ይገኝበታል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባካሄደው ምርመራ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የኤርትራ ወታደሮች በአክሱም ከተማ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን መሰብሰቡን ይፋ ባደረገው ሪፖርት ላይ አስታወቋል። አምነስቲ በሪፖርቱ ላይ የኤርትራ ወታደሮች በአክሱም ከተማ ከ200 በላይ ሰዎች መግደላቸውን ገልጾ ነበር። በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች በኅዳር ወር በሁለት ቀናት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደላቸውን በተመለከተ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የወጣውን ሪፖርት "ባልተሟላ መረጃና ውስን በሆነ የጥናት ዘዴ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው" ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ተችቷል። ኤርትራ ወታደሮቿ አክሱም ውስጥ ፈጸሙት የተባለውን ግድያ በተመለከተ የወጣውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት እንደማትቀበለው ገልጻለች። የፌደራል አቃቤ ሕግ በትናንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ በሕዳር ወር 2013 ዐዓ.ም የተፈፀሙ ወንጀሎችን እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል። በከተማዋ በተካሄደ ጦርነት የተተኮሰ መድፍ ዒላማውን ስቶ በመኖሪያ ቤት እና በዩኒቨርስቲው አካባቢ ወድቆ አምስት ሰዎች መሞታቸው በሪፖርቱ ላይ ተመልክቷል። በተጨማሪም በከተማዋየተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማስፈፀም በነበረ አለመግባባት በፖሊስ አባላት በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰው መገደሉን ሪፖርቱ ገልጿል። መግለጫው አክሎም የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ከህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሌላ ግዳጅ ከተማውን ለቆ እስከወጣበት እለት ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በአክሱም ከተማ መቆየቱን ያስረዳል። ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ሰራዊቱ ለተጨማሪ ግዳጅ ከተማዋን ለቆ ሲወጣ ቁጥሩ አነስተኛ የሆነ የኤርትራ ሰራዊት በሁለት ተሽከርካሪዎች በከተማዋ ተራራማ ቦታ ላይ መጥቶ መስፈሩንም ገልጿል። አቃቤ ህግ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከተውጣጡ አባላት በተቋቋመ የምርመራ ቡድን አማካኝነት በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ወታደሮች ተፈፅመዋል በሚሉ ለቀረቡለት ጥቆማዎች ምላሽ ለመስጠት በአካባቢው ተገኝቶ የወንጀል ፈፃሚዎቹን ማንነት ለመለየት የሚያስችል ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል። የኤርትራ ሰራዊት በአካባቢው ከሰፈረ በኋላ የህወሃት ኃይሎች የኤርትራ ሰራዊት ለመዋጋት ሳይሆን እጅ ለመስጠት ይፈልጋል በማለት ከአዴት የመጡ የህወሃት ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላትና በከተማዋ ውስጥ ካሉ 1500 የሚጠጉ የተኩስ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ጋር በመሆን ወደ አክሱም እንደገቡ መግለጫው አስፍሯል። መግለጫው አክሎም በበረሃ የነበሩት የቀድሞ የአክሱም ከንቲባ በአክሱም ከተማ ከህዳር 01-09 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ህወሃት የአንድ ቀን የመሳሪያ ተኩስ ስልጠና ለሰጣቸው 1 ሺህ 500 ወጣቶች መሳሪያ እንዲከፋፈል ትዕዛዝ ደብዳቤ በመፃፍ አስተላልፈዋል ብሏል። እነዚህ መሳሪያዎች "ከሰሜን እዝ ላይ የተሰረቁትን" ጨምሮ በአምስት ቦታዎች ላይ የተከማቹ የጦር መሳሪያዎች ናቸው ይላል የአቃቤ ህግ መግለጫ። እነዚህ አካካላት ተባብረው ከጥዋቲ 12 ሰዓት እስከ ቀኑ 8 ሰዓት ውጊያ ላይ ነበሩ የሚለው መግለጫው የመከላከያ ሰራዊቱ አጋዥ ኃይል በቦታው ሲደርስ ወደ ከተማዋ ሸሽተው መግባታቸውንም በምርመራ ማረጋገጡን አስፍሯል። አቃቤ ህግ እንደሚለው የምርመራ ቡድኑ የጦር መሳሪያ ከደረሳቸው እና ካልደረሳቸው ወጣቶች እንዲሁም ከልዩ ኃይል አባላት የምስክርነት ቃል ነው ይህንን ማረጋገጥ የቻልኩት ብሏል። የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት ቡድኑ የ95 ሰዎችን የምስክርነት ቃል መቀበሉን ጠቅሶ የ93 ሰዎች ህይወት ማለፉንም አስፍሯል። የሟቾቹን ማንነት በተመለከተ መግለጫው እንዳሰፈረው "ማቾቹምወታደራዊ የደንብ ልብስ ባይለብሱም በአብዛኛው በጦርነቱ የተሳተፉ ሰዎች ስለመሆናቸውም በምርመራው የተረጋገጠ ጉዳይ ነው" በማለት አትቷል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ መጋቢት ላይ ባወጣው መግለጫ በአክሱም ከተማ በኤርትራ ወታደሮች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀል ወይም የጦር ወንጀል ሊሆን ይችላል በማለት ገልጿል። ኮሚሽኑ በአክሱም ከተማ ውስጥ ስለተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ያካሄደው የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ ሪፖርቱ ላይ እንዳመለከተው የተፈጸሙት ድርጊቶች "ተራ ወንጀሎች ሳይሆኑ የዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችና መርሆዎችን የሚጥሱ ናቸው" በማለት በአጠቃላይ በክልሉ ውስጥ የተሟላ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ምርመራ ማካሄድ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል። በዚህም በኤርትራ ሠራዊት በአክሱም ከተማ ውስጥ የፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት "ምናልባት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ወይም የጦር ወንጀል ሊሆን ስለሚችል" ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያስፈልግ አመልክቷል። በከተማዋ በግጭቱ ተሳታፊ ያልነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ሆን ተብሎ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸሙን አመልክቶ በወታደራዊ ኢላማነት አስፈላጊነታቸው ሊገመገሙ የማይችሉ የሰላማዊ ሰዎች ንብረቶች፣ በሐይማኖት ተቋማትና በሆስፒታሎች ላይ ጭምር ሆን ተብሎ ዝርፊያና ጉዳት መድረሱን መግለፁ የሚታወስ ነው።
news-56648757
https://www.bbc.com/amharic/news-56648757
"ፈተና በማለፌ እንደ ሽልማት እንድገረዝ ተደረገ"
የተባበሩት መንግሥታት አካል የሆነው ዩኒሴፍ ያወጣው አንድ መረጃ እንደሚያመለክተው በግብጽ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 49 የሚገኙ ሴቶች 87 ከመቶ በሚሆኑት ላይ ግርዛት ተፈጽሞባቸዋል።
50 ከመቶ የሚሆኑት ግብጻዊያን ግርዛትን ሐይማኖታዊ ግዴታ አድርገው ይመለከቱታል። በግብጽ ጥብቅ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለይም በገጠሩ ክፍል የሚኖሩ ሴቶች ካልተገረዙ ንጹህ እንዳልሆኑ ይታሰባል። ለትዳርም ዝግጁ እንዳልሆኑ ነው የሚታመነው። እንደ አውሮፓውያኑ ከ2008 ወዲህ ግብጽ የሴት ልጅ ግርዛትን ከልክላለች። ሐኪሞች የሴት ልጅ ግርዛትን ከፈጸሙና ካስፈጸሙ እስከ 7 ዓመት በሚደርስ እስራት ሊቀጡም ይችላሉ። የግርዛት ጥያቄን የሚያቀርቡ ሴቶችም ሆኑ ቤተሰብ እስከ 3 ዓመት ድረስ እስር ሊጠብቃቸው ይችላል። ይሁን እንጂ ግብጻውያን አሁንም ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት እርግፍ አድርገው አልተዉትም። እንዲያው በዓለም ላይ በከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች ግርዛት ከሚፈጽሙባቸው አገሮች ተርታ ተሰልፋለች፤ ግብጽ። ሐኪም ቤቶችም "ፕላስቲክ ሰርጀሪ" በሚል ሽፋን የሴቶች ግርዛት አገልግሎትን በኅቡዕ ይሰጣሉ የሚሉ መረጃዎች አሉ። በዚህ ዘገባ የሦስት ሴት ግብጻውያንን ተሞክሮ እናስነብባችኋለን። "ፈተና በማለፌ ግርዛት ሸለሙኝ" ለይላ "እጄን ጥፍር አድርገው አሰሩኝ። ጭኔን ፈለቀቁት። እግሬን ግራና ቀኝ አንፈራጠው ያዙት። ይህ ሁሉ ለምን እንደሆነ አላውቅም ነበር። በሕይወቴ አሰቃቂው ነገር ነበር የተፈጸመብኝ። ምን እንዳስቀየምኳቸው እንጃ። እነዚህ የምወዳቸው ቤተሰቦቼ የኔን ስቃይ ለምን እንደናፈቁም አይገባኝም። ቆይ ግን፣ ጭኖቼ ውስጥ ስለት ይዘው ምን ይሠራሉ?" ይህን የምትናገረው ለይላ ገና የ11 ወይም የ12 ዓመት ልጃገረድ እያለች ነበር አሰቃቂ ግርዛቱ የተፈጸመባት። "ብዙውን ጊዜ ፕላስቲክ ሰርጀሪ በሚል የዳቦ ስም ነው ይህን ድርጊት የሚፈጽሙት" ይላሉ ሬዳ ኢልዳቡኩ። ኤልዳቡክ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ሲሆኑ ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች የነጻ የሕግ አገልግሎት የሚሰጡ ሰው ናቸው። መቀመጫውን ካይሮ ያደረገው የሴቶች መብት ንቅናቄ 3 ሺህ የፍርድ ቤት ፋይሎችን ከፍቶ 1 ሺህ 800ዎችን ማሸነፍ ችለዋል። ኢልዳንቡኪ ለቢቢሲ እንዳሉት ፖሊስና ፍርድ ቤት ብዙውን ጊዜ ግርዛት የሚፈጽሙ ሰዎችን ለመቅጣት ዳተኛ ናቸው። ለይላ ከአራት አስርታት በኋላ በ11 ዓመቷ የተፈጸመባትን አሰቃቂ ግርዛት አልረሳችውም። አሁንም ስታስበው ያንዘፈዝፋታል። ያን ጊዜ ገና የትምህርት ቤት ፈተና መጨረሷ ነበር። "ፈተናውን በማለፌ ይሸልሙኛል ስል ቤተሰቦቼ አዋላጅ አምጥተው፤ ከል ለብሰው ከበውኝ ግርዛትን ሸለሙኝ" ትላለች። ለይላ አሁን 44 ዓመቷ ሆኖ፤ አራት ልጆችን ወልዳ ታሳድጋለች። ያም ሆኖ ያን ጊዜ በ11 ዓመቷ ስለሆነው ነገር መናገር ትፈራለች። ግብጻዊያን ፊት ስለግርዛት መጥፎነት መናገርን ትፈራለች። ግርዛትን ማውገዝ ምን ያህል በዚያ ማኅብረሰብ ዘንድ አስፈሪ እንደሆነ ማሳያ ናት። አያቷ ሁለት ሴት ጎረቤቶች ነበሯቸው። ያኔ በ11 ዓመቷ ለግርዛት ከከበቧት ሰዎች መካከል እነሱ ይገኙበታል። ለይላ ሌላም የምታስታውሰው ነገር አለ፤ ጎረቤቶቿና አያቷ ከበው እግሯን ፈልቅቀው የብልቷን ጫፍ ከቆረጡ በኋላ የቆረጡትን ለወፎች ሲወረውሩላቸው። "በገጠር እንደመኖራችን ዶሮዎች ነበሩን። ልክ የቆረጡትን አካሌን ለወፎች ወረወሩላቸው። ወፎቹ ሊበሉት ተረባረቡ" ያን ጊዜ የበዓል ወቅት ነበር። ሰዎች በበዓል ስሜት ሲጫወቱ አስታውሳለሁ። እኔ ግን መራመድ እንኳ አልችልም ነበር። እግሬን አንፈራቅቄ ነበር በሰው እርዳታ ወዲያ ወዲህ የምለው። ለይላ በእሷ ላይ በትክክል ምን እንደደረሰባት ለመረዳት ረዥም ጊዜ ወስዶባታል። አድጋ ትዳር ስትመሠርት ነው የመገረዝ ጣጣውን ይበልጥ የተረዳችው። "ለእነዚያ የግብጽ የገጠር ሰዎች ያልተገረዘች ሴት ማለት ሃጥያትን ተሸክማ የምትዞር እንደማለት ነው። ለእነዚያ ገጠር ሰዎች የተገረዘች ሴት ንጽህት ናት። እኔ ግራ እኮ የሚገባኝ! እንዴት ግርዛት መልካም ሰው ከመሆንና ካለመሆን ጋር ይያያዘ? እንደገባኝ ያው እነሱም ላይ የተጫነና የማያውቁትን ባሕል ነው እየተከተሉ ያሉት። መቼስ ምን ማድረግ ይቻላል?" ለይላ የመጀመሪያ ልጇን ስትወልድ ሴት ሆነች። እሷ ያለፈችበትን ስቃይ ግን በልጇ ልትደግም አልፈቀደችም። ነገር ግን ይህን የግርዛት ሥነ ሥርዓት ባሏ ሲያሰናዳ ማስቆም አልቻለም። ለምን? ምክንያቱም ባሏ ቤተሰቦቹን ማስደሰት ይፈልጋል። የመጀመሪያ ልጇ እሷ ያየችውን መከራ አየች። የተቀሩት ልጆቿም እንዲያ ሊሆኑ ነበር። በዚህ ጊዜ አንድ አዲስ ዜና ተሰማ። ግርዛት በግብጽ ሕገ ወጥ ተግባር መሆኑ ታወጀ። ለይላ ከዚህ በኋላ ሴቶች መብት ተቆርቋሪዎችን ምክር መስማት ጀመረች። ትምህርት ተከታተለች። ግርዛት ለሞት ሊያበቃ እንደሚችል አወቀች። "ስለምን ብዬ ነው ሴት ልጄን ወደሞት የምነዳት? ለአንድ በድንቁርና ውስጥ ላለ ባሕል ለመገዛት ስል ልጄን ለስቃይ ልዳርጋት? አላደርገውም።" ሆኖም ግን ነገሩን ማስቆም አልቻለችም። "የመጀመሪያ ልጄን ለዚህ ስቃይ ስለዳረኳት ይጸጸተኛል። ሆኖም ማድረግ የምችለው ነገር አልነበረም። ባሌን ማስቆም አቃተኝ። እሱን ባስቆም ደግሞ የእሱ ቤተሰቦች አሉ። የእሱን ቤተሰቦች ባስቆም መላው የአካባቢው ሰው አለ። ልጄን አትገርዙብኝም ባልኳቸው ጊዜ አንቺ ማነሽና ነው ዓለምን ለትቀይር የምትሞክሪው? አሉኝ።" ለይላ የጾታ ትምህርት ከወሰደች በኋላ ግን ቆረጠች። ባሏን ማስጠንቀቂያ ሰጠችው። "የተቀሩት ሴት ልጆቼን የምታስገርዛቸው ከሆነ ፍቺ እፈልጋለሁ፤ አሁኑኑ" የምሯን ነበር። "የተቀሩትን ልጆቼን በዚህ መንገድ ባድንም የበኩር ልጄን ግን አሳልፌ ሰጠኋት። ደግሞ ብዙ ደም ነበር የፈሰሳት። በጣም ከመጨነቄ የተነሳ አጠገቧ እንኳ ለመሆን አቃተኝ።" "እናቴ መገረዜን ስትሰማ ራሷን ስታ ሆስፒታል ገባች" ሸሪፋ ሸሪፋ ያን ጊዜ 10 ዓመቷ ነበር። አባቷ አስገረዛት። "እናቴ መገረዜን አጥብቃ ትቃወም ነበር። አባቴ ግን የእሱን እናት ለማስደሰት ሲል ጨከነብኝ። የቤቱ አባወራና አዛዥ ናዛዥ እሱ እንደሆነ ለማስመስከርም ፈልጓል። ለእናቴ ሳይነግራት ሆስፒታል ሊያስገርዘኝ ይዞኝ ሄደ።" ሸሪፋ እንደምትገምተው ሐኪሙ ማደንዘዣ ወግቷት ነበር። "ሆኖም እያለቀስኩ ነበር። አባቴ ይህን እኔ ላይ ማድረግ ለምን እንደፈለገ አልገባኝም። ሐኪሙ ብልቴ ውስጥ ገብቶ ምን እንደሚሰራ አልተረዳሁም ነበር። የሆነ ትክክል ያልሆነ ነገር እየሆነ እንደሆነ ግን ገብቶኝ ነበር።" "ሐኪሙ የሆነ ሹል ነገር ተጠቅሞ ስለነበር ደሜ እንደ ጎርፍ መፍሰስ ጀመረ። ተደናገጡ። አባቴ በጣም ጥፋተኝነት ተሰማው። የሚያደርገው ሲጠፋው እናቴን ደውሎ ነገራት። እናቴ የእኔን መገረዝ ስትሰማ ራሷን ስታ ወደቀችና እኔ ወደነበርኩበት ሆስፒታል አመጧት። በዚያ ላይ ደም ግፊት ነበረባት። በዚያው በድንጋጤ ሞተች።" የሸሪፋ አባት አሁን ሌላ ሚስት አግብቶ ይኖራል። «ገንዘብ ይልክልኛል። ሕግ ማጥናት ነው የምፈልገው። በዚህ ጎጂ ልማድ ዙርያ ብዙ መሥራት እፈልጋለሁ።" "በወሲብ ተደስቼ አያውቅም" ጀሚላ ጀሚላ 39 ዓመቷ ነው። በዘጠኝ ዓመቷ ነበር የተገረዘችው። ታሪኳን አጋርታናለች። "ትዝ ይለኛል ክረምት ነበር። እናቴ አንዲት የሰፈር አዋላጅን ቤታችን ይዛ መጣች። ሁለቱ ጎረቤቶቻችንም ነበሩ። ሁሉንም ነገር አዘገጃጅታ ጥላኝ ወጣች። ውድ ልጇን ለአራጆች አሳልፋ ሰጠች። "ቀሚሴን አወለቁ። ሁለቱ ጎረቤቶቼ ሁለቱን እግሮቼን ግራና ቀኝ ጠፍረው ያዙ። የልምድ አዋላጇ የሆነ ስለት ያለው ነገር ይዛለች። በቃ ሁሉም ነገር ህመም ነበር። በእርግጥ እናቴ አብራኝ ያልሆነችው የሚደርስብኝን ስቃይ ማየት ስላቃተት ነበር።" ጀሚላ በልጅነቷ የደረሰባት ሕመም ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ አስተሳሰቧ ላይ ሥር ነቀል ለውጥ አመጣ። "አንድ ቀን ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ ይቺን የልምድ አዋላጅ መንገድ ላይ አገኘኋት። ቶሎ ብዬ መንገድ ቀየርኩ። ከእሷ ጋር አንድ መንገድ መጋራት ሁሉ አልፈለኩም ነበር።" ጀሚላ የጾታ ትምህርት ትከታተላለች። "ከዕለታት አንድ ቀን የግርዛትን አስከፊነት በምንማርበት ወቅት አንድ ሰውዬ ዘው ብሎ ገባና እንዲህ ተናገረ። ሴቶቻችንን ልክ እንደ አሜሪካ ሴቶች ሴተኛ አዳሪ ለማድረግ ነው አይደል አይገረዙ የምትሉት?" አሁንም ደረስ ጀሚላ ወሲብ በምትፈጽምበት ወቅት ሕመም ይሰማታል። ወሲብ አስደስደስቷት ሁሉ አያውቅም። "ሕይወት ራሱ አሰልቺ ናት፣ እንኳንስ ሕመም የተሞላበት ወሲብ ተጨምሮበት። ከባሌ ጋር የማደርገው ወሲብ የሕይወትን መከራ እንድረሳ የሚያደርግ ቢሆንልኝ እንኳ ምን ነበረበት?"
41157845
https://www.bbc.com/amharic/41157845
''ሙያችን መልክ ቢይዝ የትራፊክ አደጋን መቀነስ ይቻላል!'' የአዲስ አበባው ምርጥ ባርቴንደር።
የአዲስ አበባውን ምርጥ ባርቴንደር ይተዋወቁ !
የትራፊክ አደጋና የባርቴንዲግ ሙያ ምን ያገናኛቸዋል? መልከፃዲቅ ምትኩ ይባላል። በራዲሰን ብሉ ሆቴል ባር (መጠጥ ቤት) ስራ አስኪያጅ ነው። ከአራት ዓመታት በፊት ነበር በአስተናጋጅነት የሥራ ዘርፉን የተቀላቀለው። በቅርቡ በተካሄደ የባርቴንደሮች (የመጠጥ ቀማሚዎች) ውድድር መልከፃዲቅ ከብዙ ባለሙያዎች ልቆ 'የአዲስ አበባ ምርጥ ባርቴንደር' (መጠጥ ቀማሚ) ተብሎ ተሸልሟል። ባርቴንደር ማለት የመጠጥ ድብልቆችን በመፍጠር ወይም የተለመዱ የመጠጥ ደብልቆችን፣ ለስላሳና የታሸጉ መጠጦችን ከባንኮኒው ጀርባ በመሆን የሚያሰተናግድ ባለሙያ ማለት ነው። የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቅ የሆነው መልከፃዲቅ ወደዚህ ሙያ እንዴት እንደተሳበ ሲናገር ''አስተናጋጅ ሆኜ እሰራ በነበረበት ወቅት ባርቴንደሮችን የመርዳት ግዴታም ነበረብኝ። ይህም ሃላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡ ባርቴንደሮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን መልካም ግንኙነት አስተዋልኩ። እንደማስበው ደንበኞቻችን ለሥነ-አዕምሮ ሃኪሞቻቸው የሚያካፍሉትን መረጃ ዓይነት ለባርቴንደሮች ይነግራሉ። ባርቴንደሮች ከደንበኞቻቸው ጋር እጅግ ጥሩ የሚባል ግንኙነት ነው ያላቸው ይህም ወደ ሙያው እንደሳብ አድርጎኛል'' ይላል። ''ባርቴንደሮች ከደንበኞቻቸው ጋር እጅግ ጥሩ የሚባል ግንኙነት ነው ያላቸው ይህም ወደ ሙያው እንዽሳብ አድርጎኛል'' ሲል መልከፃዲቅ ይናገራል የትራፊክ አደጋና የባርቴንዲግ ሙያ መልከፃዲቅ የባርቴንዲንግ ሙያ የትራፊክ አደጋን ሊቀንስ እንደሚችል ያምናል። መልከፃዲቅ እንደሚለው ስራውን የሚያከብር ባርቴንደር ሙያው የሚለውን አጣምሮ ነው የሚሰራው። ይህም በምንም አይነት ሁኔታ ደንበኞች በመጠጥ ተፅዕኖ ውስጥ ሆነው አንዳያሽከረክሩ ጥንቃቄ ያደርጋል። ወደፊት መሠረታዊ የሆነ የባርቴንዲንግ ሙያን የሚያሰለጥን ተቋም በመክፍት በሃገራችን ጠጥቶ በማሽከርከር የሚከሰትን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ እንደሚፈልግ ይናገራል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያን ባህላዊ መጠጦች ከውጪ ሃገር መጠጦች ጋር በመቀላቀል ተወዳጅ ጣዕምን መፍጠር ከእቅዱ አንዱ ነው። አልፋ ሞሂቶ ''በበርካቶች የተወደደልኝ የራሴ የሆን አልፋ ሞሂቶ ብዬ የሰየምኩት የመጠጥ ድብልቅ አለኝ። ሞሂቶ በዓለም-አቀፍ ደረጃና በደንበኞቼ ዘንድ የተወደደ መጠጥ ነው። ይሁን እንጂ ይህ መጠጥ ጠንካራ አይደለም። ብዙዎቹ የእኔ ደንበኞች ደግሞ ጠንከር ያለ መጠጥን ይመርጣሉ። ሰለዚህ የእነሱን ፍላጎት ለሟሟላት ተኪላን በመጨመር የአልኮል መጠኑን ከፍ በማድረግና ሁሉም ግብዓቶች በትክክለኛ መጠን ላይ መሆናቸውን በማረጋገጥ የተወደደ ጣዕምን መፍጠር ችያለሁ'' ይላል። ''ከኔ ልምድ እንደተረዳሁት በሙያ ዘርፉ ብቁ ሆኖ ለመገኘት ዋናው ቁም-ነገር ለሙያው ጥልቅ የሆነ ፍላጎት መኖሩ ነው'' የሚለው መልከፃዲቅ፤ ከመጠጦች ጀርባ ላይ ያለውን ጽሁፍ በማንበብ ብቻ ስለ መጠጡ መሰረታዊ የሆኑ መረጃዎቹን ማግኘት ይቻላል። በተጨማሪም ከተለያዩ ድረ-ገፆች ላይ ብዙ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል" ሲል ይናገራል።
48482772
https://www.bbc.com/amharic/48482772
የሰሜን ኮርያው ባለሥልጣን እውን ተገድለዋል?
ሰሜን ኮርያ ከኒውክሌር ዘርፍ ተወካዮቿ አንዱን ገድላለች የሚል ዜና መናፈስ ቢጀምርም እውነተኛ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም። በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ዘገባ መሰረት፤ ሰሜን ኮርያ ከአሜሪካ ጋር ያደረገችው ውይይት ፍሬያማ ስላልሆነ፤ የውይይቱ አካል የነበሩ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው።
ኪም ኃይክ ኮል፤ በኪም ጆንግ ኡን እና ዶናልድ ትራምፕ ውይይት ወቅት መሰል ዜናዎች ከወደሰሜን ኮርያ ሲሰሙ ለማጣራት ስለሚከብድ፤ በአገሪቱ ውስጥ ስለሚፈጸሙ ተግባሮች በድፍረት መናገር ይከብዳል። በተለይም የመንግሥት ባለሥልጣኖች 'ተገድለዋል' ብሎ መዘገብ አስቸጋሪ ነው። • ኪም ጆንግ ኡን የጦርነት ልመና ጥሪ በማድረግ ተወቀሱ ከዚህ ቀደም የሰሜን ኮርያ ሚድያዎች ሳይቀር 'ተገድለዋል' ያሏቸው የመንግሥት ባለሥልጣኖች፤ ዘገባው ወጥቶ ብዙም ሳይቆይ ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ታይተዋል። ሰሜን ኮርያ በአሜሪካ ጉዳዮች ወክላው የነበረው ኪም ኃይክ ኮል መገደሉን ሱዑል ለሚገኝ ጋዜጣ የተናገረው አንድ ምንጭ ነው። ኪም ኃይክ ኮል፤ ኪም ጆንግ ኡን እና ዶናልድ ትራምፕ ባደረጉት ውይይት ከፍተኛ ሥልጣን ከነበራቸው አንዱ ነበር። ፒዮንግያንግ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ መገደሉም ተዘግቧል። የዜናውም ምንጭ እንደሚለው፤ ኪም ኃይክ ኮል ከሌሎች አራት የውጪ ጉዳይ ባለሥልጣኖች ጋር ተገድሏል። ባለሥልጣኖቹ ለአሜሪካ በመሰለል ተከሰው ነበር። በተጨማሪም የአሜሪካና የሰሜን ኮርያ ውይይት በተካሄደበት ወቅት የአሜሪካን ፍላጎት በግልጽ የሚያሳይ ሪፖርት አላቀረቡም ተብሏል። • ሰሜን ኮርያ የአሜሪካውያንን አጽም መለሰች በሌላ በኩል የኪም ጆንግ ኡን 'ቀኝ እጅ' የሚባለው ኪም ኃይክ ኮል፤ በቻይና ድንበር አካባቢ የሚገኝ የመልሶ ስልጠና ማዕከል ውስጥ ገብቷል የሚሉም አሉ። በአሜሪካና ሰሜን ኮርያ ውይይት እጃቸው የነበረ ባለሥልጣኖች ከውይይቱ ወዲህ ከሕዝብ እይታ ተሰውረዋል። ምናልባትም በዚህ ማዕከል የመግባቱ ወሬ እውነት ሊሆንም ይችላል። ኪም ጆንግ ኡን ከአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጋር ያደረጉት ውይይት አንዳችም ተስፋ አለማሳየቱ እጅግ ስላበሳጫቸው ተጠያቂ የሚያደርጉት ሰው ይፈልጋሉ። ኪም ጆንግ ኡን ከዚህ ቀደም ሰዎች ማስገደላቸውም ይታወቃል። ከዚህ ቀደም የኪም ጆንግ ኡን አጎት ጃንግ ሶንግ ቴክ አገር በመክዳት ተከሰው መገደላቸው ይታወሳል። 'ሲንሙን' የተባለው የመንግሥት ጋዜጣ በዚህ ሳምንት "ፀረ አብዮት ተግባር የፈጸሙ ሰዎች በአብዮቱ ይፈረድባቸዋል" የሚል ረርእሰ አንቀፅ አስነብቧል። የማንም ስም ባይጠቀስም ምን መልዕክት ለማስተላለፍ እንደተፈለገ ግልጽ ነው። • ኪምና ፑቲን ተገናኙ እንደጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2013 ላይ ኃዮን ሶንግ ውል የተባለች ዘፋኝ መገደሏ በዚሁ ጋዜጣ ቢዘገብም፤ ለክረምት ኦሎምፒክስ ወደሱዑል ካቀናው የልዑካን ቡድን ጋር ታይታለች። አሁን ሰሜን ኮርያ ውስጥ ሀያል ከሚባሉ አንዷም ናት። 2016 ላይ የቀድሞው የወታደር ኃላፊ ሪ ዮንግ ጊል በሙስና ተከሰው መገደላቸው ተዘግቦ ከጥቂት ወራት በኋላ ማዕረግ ተጨምሮላቸው በቴሌቭዥን ታይተዋል። እንደነዚህ አይነት አጋጣሚዎች ሰሜን ኮርያ ውስጥ አንድ ሰው ስለመገደሉ እርግጠኛ ሆኖ መናገር እንዳይቻል አድርጓል። የሱዑልና የአሜሪካ የደህንነት ሰዎች ኪም ኃይክ ኮል ተገድሏል ወይስ በሕይወት አለ የሚለውን ለማጣራት እየሞከሩ ነው። ሆኖም ከፒዮንግያንግ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ አፍ ሞልቶ አለ ወይም ሞቷል ማለት ይከብዳል።
news-56575784
https://www.bbc.com/amharic/news-56575784
በትግራዩ ግጭት እግሮቿን ያጣችው ታዳጊ አባት ጭንቀት
የሽረ ከተማ በየዕለቱ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ተፈናቃዮችን ታስተናግዳለች።
ከእነዚህም መካከል ከሽረ 50 ኪሎ ሜትር ርቃ ከምትገኘው አክሱም የመጣችው የስድስት ዓመቷ ቤተልሔም ተስፋዬ አንዷ ናት። ቤተልሔም በግጭቱ እናቷንና ሁለት እግሮቿን አጥታለች። አባቷ የቋጠረውን ጥሪትም ለእሷ ማሳከሚያ አውጥቶ ጨርሷል። አሁን ለቤተልሔም ሰው ሰራሽ እግር እንዲደረግላት የሚያስችለውን ገንዘብ ከየት እንደሚያገኝ ጨንቆታል።
50555257
https://www.bbc.com/amharic/50555257
ጃክ ማ እና ጃክ ዶርሲ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ምክንያት ምን ይሆን?
ሁለቱ ጃኮች በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ተገኝተዋል። የአሊባባው ጃክ ማ እና የትዊተሩ ጃክ ዶርሲ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከጃክ ማ ጋር በአንድነት ፓርክ ውስጥ የቻይናው አሊባባ የኤክትሮኒክስ መገበያያ ድርጅት እስያ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለው ግዙፍ ድርጅት ነው። ትዊተር ደግሞ በአራት አሜሪካዊያን ወጣቶች የተመሠረተ ግዙፍ የማሕበራዊ ትስስር መድረክ ነው። ጃክ ማ እና ጃክ ዶርሲ ቀጠሮ እንዳላቸው ወርሃ ኅዳር አጋማሽ ላይ አዲስ አበባ ተገኝተው የመገናኛ ብዙኀን ትኩረት አግኝተዋል። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ቻይናዊው ጉምቱ የቢዝነስ ሰው ጃክ ማ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር መክረዋል። አልፎም በአይሲቲ ፓርክ የተገኙት ጃካ ማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር በመሆን 'ኤሌክትሮኒክ ዎርልድ ትሬድ ፎረም' [ኢደብልዩቲፒ] የተሰኘ ፕሮጀክትን መርቀዋል። ፕሮጀክቱ በዓለም ዙሪያ ምርቶቻቸውን ማስተዋወቅ እና መገበያየት ለሚፈልጉ አነስተኛ የንግድ ተቋማት አመቺ ዕድል ይፈጥራል ተብሎለታል። በሌላ በኩል የትዊተር አጋር መሥራች የሆነው ወጣቱ ጃክ ዶርሲ ዓላማው ከናይጄሪያና ከኢትዮጵያ በአንዱ አገር ከሦስት እስከ ስድስት ወራት በመቆየት የኢንቨስትመንት አማራጩን ማየት ነው። ለምን ኢትዮጵያ? የፌርፋክስ አፍሪካ ግሎባል ሊቀ መንበር የሆኑት ዘመዴነህ ንጋቱ እኒህ የቴክኖሎጂ ባላባቶች ኢትዮጵያን የመረጡበት ዋነኛው ምክንያት የሕዝብ ብዛት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ምጣኔ ሃብቷ ከጊዜ ጊዜ እያደገ መምጣቱ ነው ይላሉ። «ከሰሃራ በታች ካሉ ኢኮኖሚዎች ኢትዮጵያ በጂዲፒ [በአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት] ሦስተኛ ነች። የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ብቻ ሳይሆኑ በምርትም ሆነ በመሠረተ ልማት ዝርጋት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ኢትዮጵያ ትኩረት እየሳበች ነው።» አክለውም «እነዚህ ሁለት ጃኮች ይህንን ተገንዝበው ነው የመጡት። በተለይ የአሊባባ ጃክ ማ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ግብዣ ነው የመጡት። አሊባባ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ800 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን የማስተናገድ አቅም አለው። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረቱ ምርቶችን ለዓለም ገበያ በቀላሉ ለማቅረብ የሚያስችል አንድ መድረክ ነው» ብለዋል። • ቻይናዊው ቢሊየነር በአዲስ አበባ አሊባባ የተሰኘው ኩባንያ 'አሊፔይ' የሚባል የመገበያያ መንገድ አለው። አቶ ዘመዴነህ ይህን የመገበያያ መንገድ እንደትልቅ አማራጭ ያዩታል። ስቴምፓወር የተሰኘውና በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በኢንጂነሪንግ ዘርፍ ላይ የተሠማራ ድርጅት ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ኢዮኤል ኃይሌም 'አሊፔይ' ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መምጣቱ ትልቅ እመርታ ነው ይላሉ። «የእነዚህ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ትልቁ ጥቅም የቴክኖሎጂ ሽግግር ነው። እኛ አገር ለምሳሌ የኢ-ኮሜርስ ሰርቪስ ገና ዳዴ እያለ ነው። ዲጂታል ቴክኖሎጂ እና ኢ-ኮሜርስ በጣም ብዙ የሰው ኃይልን መያዝ የሚቻልበት ዘርፍ ነው። ለምሳሌ እንደኛ ዓይነት ድርጅቶች ከእነ አሊባባ ልምድ መቅሰም ይችላሉ። የቴክኖሎጂ ባሕል ወደሃገራችን መግባቱ ትልቅ ጥቅም ነው።» የጃክ ማ አሊባባና የኢትዮጵያ መንግሥት በኤሌክትሮኒክስ የታገዘ ዓለም አቀፍ የንግድ መገናኛ ማዕከል ለመገንባት የፊርማ ስምምነት አድርገዋል። አቶ ዘመዴነህ እንደሚሉት ከዚህ ቀደም እነዚህን የሚመስሉ የግዙፍ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ እምብዛም አይስተዋልም ይላሉ። «ብዙ ጊዜ ሩዋንዳ ነው የሚሄዱት፤ ነገር ግን ሩዋንዳ ትንሽ ሃገር ነች። ኢትዮጵያ ግን ግዙፍ ናት። ይሄ ትልቅ አማራጭ ነው። ለምሳሌ ትዊተር በጣም ግዙፍ ሶሻል ሚድያ መድረክ ነው» በማለት የኢትዮጵያን ተፈላጊነት ይጠቅሳሉ። • ትዊተር 70 ሚሊዮን ሃሰተኛ ገጾችን ዘጋ «ጃክ ዶርሲ በግልም ይሁን በኩባንያ ደረጃ ኢንቨስት የማድረግ ሃሳብ አለው የሚል አዝማሚያ አለ እንደምንሰማው። ቀደም ሲል በዚህ በኩል ፍላጎት የያሳዩ የነበሩት ከምሥራቅ የሚመጡ ናቸው። በተለይ ባለፈው አንደ ዓመት ተኩል ግን ከምዕራቡ ዓለም ትልቅ ፍላጎት እየታየ ነው» ሲሉ የትዊተርን መምጣት ያነሳሉ። እንደ አቶ ዘመዴነህ ትንተና እነዚህ ግዙፍ ድርጀቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት በቴክኖሎጂ ብቻ ኢንቨስት ለማድረግ አይደለም፤ በሌሎችም የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሰማራት ፍላጎት አላቸው። «አውነት ለመናገር ሌላኛው ትኩረት ሳቢ ጉዳይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኖቤል ሽልማት ነው። ለምሳሌ እኔ በተሰማራሁበት የኢንቨስትመንት ማኅበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል። ለኢትዮጵያ 'ብራንዲንግም' [ገጽታ] ሽልማቱ ከፍተኛ ትርጉም አለው» በማለት ይናገራሉ። የአፍሮ ኤፍኤም፣ የቃና ቴሌቪዥና እና 251 ኮሚዩኒኬሽንስ መሥራች የሆነው አዲስ አለማየሁ «ሁለት ቢሊየነሮች መጡ ማለት እኮ ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ከካርታው ላይ አትፋቅም ማለት ነው» በማለት ጉብኝቶቹ ጠቃሚ ቦታ ለአገሪቱ እንደሚያስገኙላት ይገልጻል። • ከጥንት ሮማውያን እስከ ትዊተር የደረሰው የ# ምልክት «ለመጀመሪያ ጊዜ ይመስለኛል ቢሊየነሮች አገሩን ልይ ብለው ሲመጡ። ይህ ማለት አገራችን ከዚህ በኋላ ከቴክኖሎጂው ዓለም ርቃ የምትኖር አትሆንም» በማለት በዘርፉ ብዙ እምቅ ተሰጥዖ መኖሩን ጠቅሶ «በዚህ በኩል ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለም የሚሆን በጣም ብዙ ችሎታ ያላቸው ወጣቶች አሉን። እነዚህ ወጣቶች አሁን ተሻግረው ማየት ይጀምራሉ ማለት ነው። እነዚህ ሁለቱ መጡ ማለት ሌሎችም መከተላቸው አይቀርም።» ለዚህ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለውጥ በር ከፍቷል ይላል አዲስ፤ «ኢኮኖሚው እየተከፈተ ነው። አዳዲስ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ሊገቡ ነው። ኢንተርኔት ላይ ያለው ጭንቅንቅ የዛሬ ስድስት ወር፤ አንድ ዓመት ይቀረፋል ብዬ አምናለሁ። ሌላኛው ምክንያት 110 ሚሊዮን ሕዝብ ነው ያለን። አማካይ ዕድሜ 18 ዓመት ነው። የኢኮኖሚውም ዕድገት በጣም ፈጣን ነው።» ጃክ ዶርሲ የቴክ ባላባቶቹ ከመንግሥት ምን ይሻሉ? «አሊባባ ኢትዮጵያ ውስጥ ስኬታማ እንዲሆን አኔ 'ሴልስማን' [ሽያጭ ሠራተኛ] ሆኜ፤ ማኔጀርም ሆኜ አገለግላለሁ» ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለጃክ ማ ያሰሙት ንግግር ነበር። አቶ ዘመዴነህም ይህንን ንግግር ያወሳሉ። «መንግሥት ፈቃድ መስጠት ብቻ ሳይሆን በብዙ ጥረት የሚመጣው ኢንቨስተር ንቁ ተሳትፎ ሊያደርግ ስለሚገባ እሳቸው [ጠ/ሚ ዐብይ] ያሉት እውነታቸውን ነው። እነ አሊባባና ትዊተር ኢትዮጵያ ውስጥ መጥተው ስኬታማ ከሆኑ ውጤቱ ለአገራችን 'ብራንድ አምባሳደር' [የመልካም ገጽታ] ይሆኑናል።» ነገር ግን ከዚህ አንጻር የተጀመረውን መልካም ሂደት ለማስቀጠል አቶ ዘመዴነህም ሆኑ አዲስ የፖሊሲ ለውጥ እንደሚያሻ ይስማማሉ። • ኢትዮጵያ ወይስ ናይጄሪያ? የትዊተር አለቃ የፈጠረው ክርክር «መንግሥት የጀመረውን የለውጥ አጀንዳ መጨረስ አለበት። ለወጣቱ፤ በተለይ ደግሞ ለጀማሪ ኢንቨስተሮች ልዩ የሆነ ፖሊሲ መውጣት አለበት። አንድ ወጣት ሥራ ልሥራ ቢል ያለው ፈተና፤ ኩባንያውን ከማስመዝብ ጀምሮ እስከሚከፍለው ታክስ ድረስ እጅግ ከባድ ነው» የሚለው አዲስ ነው። አቶ ዘመዴነህም ቢሆን የፖሊሲ ለውጥ በአስቸኳይ መደረግ አለበት ከሚሉት ወገን ናቸው። «እርግጥ ነው ለአገር የሚጠቅም መሆን አለበት፤ ግን ደግሞ ኢንቨስተሮች እንዳይሸሹ የሚያደርግ ፖሊሲ ያሻል። ለምሳሌ የሞባይል ክፍያ አገልግሎት ከፋይናንስ ዘርፉ ጋር የተገናኘ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ሕጎች አሉ የውጭ ድርጅቶችን ከመሳተፍ የሚያግዱ። እነዚህ ፖሊሲዎች እንደገና መቃኘት አለባቸው።» ለአቶ እዮኤል ግን ዋናው ጉዳይ ለቴክኖሎጂ ያለው አመለካከትና የውጪ ምንዛሪ [ዶላር] ነው። «ያልተነካ ትለቅ ገበያ አለ። ነገር ግን ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድነው? ወይም ኢ-ኮሜርስ ምንድነው? ከቤተህ ቁጭ ብለህ እንዴት ትሸጣለህ? እነዚህ ሃሳቦች ብዙ አይታወቁም» ይላል እዮኤል። • የስልክዎን ባትሪ ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም ይህንን በምሳሌ ሲያስረዳም ኢትዮጵያ 'ሞባይል ባንኪንግ' ብዙ ተጠቃሚ ያለው ሶማሌ ክልል ውስጥ መሆኑና በቀን ውስጥም የብዙ ሚሊዮን ብር ልውውጥ እንደሚደረግ ጠቅሶ ለዚህም የቴክኖሎጂው መኖር ያለውን ጠቀሜታ ይናገራል። እዮኤል ከዚህ አንጻር የሚቀሩ ነገሮች እንዳሉ ሲናገር «አብዛኛው ሰው የሚገበያየው በደረቅ ኖት ነው። ኤቲኤም እንኳ በአግባቡ እየተጠቀምን አይደለም። ሌላውም ቦታ ብዙ ሥራ ይጠብቀናል የምንለው ለዚህ ነው።» በተጨማሪ ደግሞ ዶላር እንዴት ማነቆ ሊሆን እንደሚችል ሲያስረዳ «እኔ ኢትዮጵያ ሆኜ ከእንግሊዝ ወይም ከአሜሪካ አንድ ዕቃ መግዛት ብፈልግ አገሪቱ በቂ የሆነ 'ሃርድ ከረንሲ' [የውጭ ምንዛሪ] አላት ወይ? ምክንያቱም እኔ ከዚህ ለኢትዮጵያ መንግሥት የምከፍለው ብር ነው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የሚከፍልልኝ ዶላር ነው። በቂ ዶላር አለን ወይ ነው? የሚል ጥያቄ ቢነሳም አሊባባ በራሳቸው የመገበያያ መንገድ ይህንን ችግር ሊፈቱት ይችላሉ» ሲል ይናገራል። የቻይና ሀብታሙ ሰው ጃክ ማ ድርጅቱ ባዘጋጀው ድግስ ላይ እንደ ማይክል ጃክሰን አጊጦ መጥቷል የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥን በተመለከተም አቶ እዮኤል «አፍሪካ ውስጥ ትልቅ የፋይበር ገመድ ከተዘረጋባቸው አገራት ኢትዮጵያ አንዷ ነች። በእርግጥም የኢንተርኔት መቆራረጥ አለ። ነገር ግን ሁለት የቴሌኮም ኩባንያዎች ሊገቡ ነው» የሚባለው ችግሩን እንደሚቀርፉት ያምናል። የእነዚህ ኩብንያዎች መግባትም አሊባባን ለመሳሰሉ ትላልቅ ኩባንያዎች ሌላ ተጫማሪ አማራጭ እንደሚሆኑ ጠቅሶ «በእኔ ምልከታ ቴሌኮም በሞኖፖሊ የተያዘ ስለሆነና ፉክክር ስለሌበት ነው መቆራረጡ የሚያጋጥመው። እነዚህ ኩባንያዎች ግዙፍ ናቸው። የራሳቸውን 'ቪሳት' ተክለውም ቢሆን መጠቀም ይችላሉና ኢንትርኔት ብዙ ፈተና ይሆናል ብዬ አልጠበቅም» ይላል። የዚህ ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ በጀት 386.9 ቢሊዮን ብር ነው። የትዊተር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጃክ ዶርሲ የተጣራ ገቢ ደግሞ 4.2 ቢሊየን ዶላር [አሁን ባለው የምንዛሪ ገበያ ቢያንስ 126 ቢሊየን ብር ገደማ ነው]፣ የጃክ ማ የተጣራ ገቢ ደግሞ 36.6 ቢሊየን ዶላር [ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ] ነው። አዲስም ሆነ አቶ ዘመዴነህ፤ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ባለሙያው አቶ እዩኤል እነዚህ የናጠጡ ቢሊየነሮች ያላቸው አቅም በጣም ግዙፍ እንደሆነ ይስማማሉ። ጥያቄው ኢትዮጵያ ከእነዚህ ሰዎች ለመጠቀም ምን ያህል ዝግጁ ናት? የሚለው ነው።
news-53473459
https://www.bbc.com/amharic/news-53473459
ማኅበራዊ ሚዲያን ከጥላቻ መልዕክቶች የማጽዳት ዘመቻ
ከሳምንታት በፊት የተፈጸመውን የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተፈጸሙ ጥቃቶችና ባጋጠሙ ግጭቶች ሳቢያ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከፍተኛ መጠን የለው ንብረት በመውደሙ በርካቶች ቤት ንበረታቸውን አጥተው ለችግር ተጋልጠዋል።
ታዲያ ለእዚህና ለሌሎች መሰል ጥቃቶች በማኅበራዊ ሚዲያና በሌሎች መደበኛ መገናኛ ብዙሃን ላይ የሚሰራጩ ጥላቻንና ጥቃትን የሚያበረታቱ መልዕክቶች አስተዋጽኦ አላቸው ያሉ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እነዚህን ድርጊቶች ለማስቆም አንድ ኔትወርክ አቋቁመዋል። ነዋሪነታቸው በአሜሪካ የሆነውና የዚህ እንቅስቃሴ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ነአምን ዘለቀ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ኔትወርኩ በተለያዩ ዘርፎች የተዋቀሩ ኮሚቴዎችን የያዘ ነው። ኮሚቴዎቹ የሕግ፣ የሚዲያና ዲፕሎማሲ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ ዘርፍ የተዋቀሩ ናቸው። ይህ ኔትወርክ በአሜሪካ፣ በካናዳና በአውሮፓ አገራት ውስጥ ያሉ በርካታ የፖለቲካ ሰዎች፣ ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ ሲቪክ ማኅበረቦች የተሰባሰቡበት እንደሆነም አቶ ነአምን ጨምረው አስረድተዋል። ኔትወርኩ በአገር ውስጥ መረጋጋት እንዲመጣ የሕግ የበላይነት እንዲከበር፤ ወንጀለኞችና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ ለሕግ እንዲቀርቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስተባባሪው ገልፀውልናል። የማኅበራዊ ሚዲያው ኮሚቴ 'ተጋምደናል' (Interunited) የሚል ዘመቻ የጀመረ ሲሆን የጥላቻ ንግግሮችን በመሰብሰብና ሪፖርት በማድረግ እንዲሁም ባሉት ገፆች አማካይነትም መልዕክቶችን የማስተላለፍ ሥራ ይሰራል። የሕግ ኮሚቴውም እንዲህ ዓይነት መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ መገናኛ ብዙሃንና ግለሰቦች ባሉበት አገር ውስጥ ተጠያቂ እንዲሆኑና ለሕግ እንዲቀርቡ የሚሰራ ሲሆን መረጃዎችን በመሰብሰብ በማደራጀት የሚሰራው በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድኑ ይደገፋል ብለዋል። እስካሁንም በኔትወርኩ በተከፈተው የኢሜል አድራሻ በርካታ ማስረጃዎች እንደደረሷቸው አክለዋል። በሌላ በኩል "ከዚህ ቀደም በተለያዩ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በተዛባ መልኩ ዘገባዎች ተሰርተዋል" የሚሉት አቶ ነአምን፤ የሚዲያና ዲፕሎማሲ ኮሚቴው ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲደረጉ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። አቶ ነአምን "ከአገር ውጭ ሆነው በሕዝቡ ውስጥ መረጋጋትና ሰላም እንዳይኖር፤ ከባድ የጥላቻና ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ መልዕክቶችን የሚያሰራጩ ናቸው" ያሏቸው አካላት በአንድ ወገን ያሉ ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ ብሔሮችን እንወክላለን የሚሉ መሆናቸውንም ይናገራሉ። በተለያየ ጊዜ በአገሪቱ ተመሳሳይ ክስተቶች መፈጠራቸውን በማስተዋስ፤ አሁን ወደዚህ እንቅስቃሴ እንዲገቡ የገፋቸውን ምክንያት "የመጣው አደጋ በመግዘፉና ሕዝብን ለአመፅና ለሁከት የሚያነሳሱ መልዕክቶች በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም በተደራጀ መልኩ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በማየታችን ነው" ሲሉ አመልክተዋል። ኔትወርኩ ወገን ሳይለይ በሁሉም ብሔር ፅንፈኞች የሚደረጉ ጥላቻና፣ ግጭትና ጥቃትን የሚቀሰቅሱ እንቅስቃሴዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራም ተናግረዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ እንዲገነዘብ ማድረግ እና የጥላቻ ንግግሮችን የሚያራምዱ ሚዲያዎችና ግለሰቦችን በሕግ መጠየቅ የኔትወርኩ የአጭር ጊዜ እቅድ መሆኑን የገለፁት አቶ ነአምን፤ ወደ ፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። አቶ ነአምን ዘለቀ እና አቶ ዮሐንስ ሞላ "እኔም ሳፀዳ፤ ሌላውም ሲያፀዳ፤ አብረን እንፀዳለን" በሌላ በኩል በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችና ጥቃት ቀስቃሽ መልዕክቶችን ለፌስቡክ ሪፖርት የሚያደርግ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው። ይህንን እንቅስቃሴ የጀመረው ገጣሚና የማኅበራዊ ለውጥ አራማጁ ዮሐንስ ሞላ ነው። ከ10 ዓመታት በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚ እንደሆነ የሚናገረው ዮሐንስ፤ ከዚህ ቀደምም እንዲህ በዘመቻ አይጀምረው እንጂ ከፌስቡክ ሕግ ጋር የሚጣረሱ መልዕክቶችን ሲመለከት ሪፖርት እንደሚያደርግ ይናገራል። ዮሐንስ እንደሚለው ብሔር ተኮር ብቻ ሳይሆን ጾታዊ ትንኮሳ፣ ዛቻን፣ የህፃናት ጥቃትን እንዲሁም ሌሎች መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ፅሁፎችን፣ ፎቶዎችንና ቪዲዎችን ሲመለከት ለፌስቡክ የማሳወቅ ልምድ አለው። "የፌስቡክ አካውንት መክፈታቸውን እንጂ ማህበራዊ መድረኩን ሲቀላቀሉ፤ ሕጉ ምን እንደሆነ የማያውቁት ጥቂት አይደሉም" የሚለው ዮሐንስ፤ በዚህም የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን ባልተገባ መልኩ ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሆነ ያስረዳል ይላል። ከሰሞኑ ያጋጠመውን አለመረጋጋት ተከትሎም ይህንን በግሉ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ወደ ዘመቻ በመለወጥ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ በማሰብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ይገልጻል። "ፌስቡክ የፌስቡክ አካውንቶችን የሚዘጋው አሊያም የተላለፉ ይዘቶችን ከገፁ ላይ የሚያወርደው፤ የራሱን ሕግ ተከትሎ እንጂ ሪፖርት ባደረገ ሰው ብዛት አይደለም" የሚለው ዮሐንስ፤ ዘመቻውን መክፈቱ ሰዎችን ለማስተማርና እነርሱም ይህንን ማድረግ እንዲችሉ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ብሏል። ለእንደዚህ አይነት ሁከቶች የጥላቻ ንግግሮችና የጥቃት ቅስቀሳዎች ከፍተኛ የሆነ ድርሻ አላቸው በማለትም "ቀደም ብለን ብንጀምር፤ ምን አልባት ይሄ ቀን አይመጣም ነበር፤ ባለማድረጌም ቆጭቶኛል" ይላል። ዮሐንስ አሁን ላይ 'መንጥር' (Network Against Hate Speech) የሚል ኔትወርክ ተቋቁሞ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክቶ፤ ኔትወርኩ የቋንቋ፣ የብሔር፣ የፖለቲካ አቋም እንዲሁም የሙያ ስብጥር ያላቸው ሰዎች የተሳተፉበት እንደሆነም ያስረዳል። "ዘመቻው በአንድ ወገን ላይ ብቻ ያተኮረ ነው" የሚሉ ክሶች እንደሚቀርቡ ያነሳንለት ዮሐንስ፤ "በእኔ ፍላጎት ሳይሆን ፌስቡክ ይዘቱን ተመልክቶ በራሱ ሕግ ነው እርምጃ የሚወስደው" በማለት፤ ከየትኛውም በኩል የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮችንና የጥቃት መልዕክቶችን ሪፖርት ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይል ያስረዳል። ዮሐንስ አክሎም ይህን የሚሉ ወገኖችም በእነርሱ ገፅ የሚያዩት መሰል መልዕክቶች ካሉ ሪፖርት ያድርጉ በማለት ዋናው ሕግ መከበሩ በመሆኑ "እኔም ያገኘሁትን ሳፀዳ፤ ሌላውም ሲያፀዳ፤ አብረን እንፀዳለን" ብሏል። እስካሁን ባደረጉት እንቅስቃሴዎችም ውጤት ማየታቸውንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዮሐንስ ይናገራል። ይህ የበጎ ፈቃደኞች ስብስብ በፌስቡክ ላይ የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮችን ብቻ ሳይሆን እንደ ዩቲዩብና ትዊተር ባሉ ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የሚተላለፉትንም መሰል መልዕክቶችን ሪፖርት ያደርጋል።
news-53698695
https://www.bbc.com/amharic/news-53698695
ኮሮናቫይረስ ፡ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት ፖለቲካዊ ጦርነት ያጋጥም ይሆን?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለዓለም ስጋት ሆኖ በቀጠለበት በዚህ ወቅት የማንነካ ነን የሚሉ ታላላቅ አገራትን እያብረከረካቸው ይገኛል። የሰው ልጅ ደረስኩበት የሚለውን የሳይንስ ልህቀት ፈትኗል፤ እየፈተነም ይገኛል።
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እስካልተገታ ድረስ የዓለም ሕዝብ ወደቀደመው ህይወት መመለስ አይችልም። እናም ቀጣዩ እሽቅድምድም የኮቪድ-19 ክትባትን ማግኘት ሆኗል። በርካታ ኃያላን አገራት አሜሪካ፣ ቻይና ሩሲያና ዩናይትድ ኪንግደም ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ክትባቱ በማዞር ሳይንሳዊ ምርምሮቻቸውን እየፈተኑ ይገኛሉ። በርካታ ሳይንቲስቶቻቸውን በማሰማራትና የምርምር ማዕከላትም ላይ በርካታ መዋዕለ ንዋይም እያፈሰሱ ይገኛሉ። ምንም እንኳን በዚህ ሰዓት በሙከራ ላይ ካሉ ክትባቶች መካከል የትኛው ቀድሞ ይደርሳል የሚለውን መገመት ቢከብድም፤ የበለፀጉት አገራት በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች እያወጡ ከላብራቶሪዎች እነዚህን ክትባቶች እየገዙ ይገኛሉ። በዚያም መንገድ አቅርቦታቸውንም እየጨመሩ ነው። ለምሳሌ ዩናይትድ ኪንግደም የክትባት ሙከራውን ከሚያቀርቡት አስትራዜንካ፣ ፋይዘርና ባዮንቴክና ቫልኔቫ ከተባሉት ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ፈርማለች። እነዚህ ስምምነቶች ሁለት አገራትን ያካተቱ ሳይሆኑ በኩባንያዎችና በአገራት ወይም በግለሰቦች መካከል የሚፈፀሙ ክስተቶች በመሆናቸውም "የክትባት ብሔርተኝነትም" እየተባለ ነው። ለክትባቶች የሚደረገውን እሽቅድድም በተመለከተ ቢቢሲ ካውንስል ኦን ፎሬይን ሪሌሽንስ (የውጭ ግንኙነት ጉባኤ) ጥናት ማዕከል ፕሬዚዳንት የሆኑትን ሪቻርድ ኤን ሃስን አናግሯል። ግለሰቡ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮም በፖሊሲ አውጪ ዳይሬክተር እንዲሁም የአፍጋኒስታን እጣፈንታ ፕሮግራምና አየርላንድንም በተመለከተ ልዩ መልዕክተኛና አስተባባሪ ሆነው ሰርተዋል። በባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ እነዚህ ኃያላን አገራት የተለያዩ የክትባት ሙከራዎች ዕውቅና ከማግኘታቸው በፊት እየሸመቱ ይገኛሉ። እሽቅድምድም ይመስላል። ይህንንም በማስመልከት እርስዎም "የክትባት ብሔርተኝነት" እየታየ፣ እየጎላ ነው በሚል ፅፈዋል። እንዲሁም ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል አስፍረዋል። እንዴት እንዲህ ሊሉ ቻሉ? በርካታ አገራት የኮቪድ 19 ክትባትን የግላቸው ለማድረግ እየተሽቀዳደሙ ነው። አገራቱ ማንም እንዳይቀድማቸው በገፍ እየሸመቱም ይገኛሉ። ይሄ መቅረት የሚችል ብሔርተኝነት ነው። መንግሥታት ከሁሉ በፊት የራሳቸውን አገራት በማስቀደምም ላይ ይገኛሉ፤ ምክንያቱ ግልፅ ነው። እነዚህ መሪዎች ለዜጎቻቸው የኮሮናቫይረስን ወረርሸኝን በመግታትና ክትባቱንም አቅርቡ በሚል ከፍተኛ ጫና ደርሶባቸዋል። ችግሩ ግን እነዚህ አገራት ብቻ በበላይነት ክትባቶቹን ከያዟቸው ቢሊዮኖችን ያገላል፤ አይደርሳቸውም። በተለይም ተጋላጭ ለሆኑት ማኅበረሰብ አለመድረሱ ቀውስን የሚፈጥር ነው። ከዚህም በተጨማሪ ክትባት ብሔርተኝነትን ሙጭጭ ብለው ለያዙት ለእነዚህ አገራት መንግሥታትም ውጤቱ አሉታዊ ነው። በእነዚህ አገራት በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ቢኖራቸው በሽታው በዚያው አይገታም። ዓለም ካለችበት የግሎባላይዜሽን ሥርዓት በሽታው ይዛመታል፤ ወደ ሌሎች አገራትም መሰራጨቱ ስለማይቀር ነው። በአሁኑ ወቅት ከክትባቶቹ ጀርባ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ የሆነ የብልጦች አካሄድ ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ላይ ናቸው። በሆነ መንገድ ዓለም አቀፋዊ ስምምነት ላይ መደረስ ካልተቻለ ቀውስ ይፈጠራል። በአገራቱ ያለውን የፖለቲካ ጫና በተወሰነ መልኩ እረዳዋለሁ። ለአንድ መንግሥት ሌሎች አገራትን መርዳት አለብን እንዲሁም በተመሳሳይም ራሳችን መርዳት አለብን የሚለውን አብሮ ማስኬድ ፈታኝ ነው። የኮሮናቫይረስ ክትባት ፖለቲካዊ ጦርነት ላይ ነን ወይስ ሊገጥመን ይችላል? ጦርነት ባልለውም ለክትባት የሚደረግ ውድድርና እሽቅድምድም እለዋለሁ። ሁሉም ቀዳሚ መሆን ይፈልጋል። አንዳንዶች ለንግድና ትርፍን ለማጋበስ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ፖለቲካዊ ምክንያቶችን ከጀርባው ሰንቀዋል። ዋናው ችግሩ ከዚህ በበለጠ በርካቶች በቫይረሱ የሚያዙ ከሆነ መላው የዓለም ሕዝብም ተጋላጭ ነው። የዚህም በሽታ ዋነኛ አስተማሪነቱ ይሄ ነው። አንድ አገር ከሁሉ ቀድማ የኮሮናቫይረስ ክትባቱን ብታመርትም በሌሎች አገራት ላይ ጥገኛ መሆኗ አይቀርም። ምክንያቱም ምርቱን ለማምረት የተለያዩ ግብዓቶችን ከተለያዩ አገራት መፈለግ አይቀርም። የየትኛውንም አገር ድጋፍ ሳያስፈልገኝ መቶ በመቶ ራሴን የቻልኩኝ አገር ነኝ ማለት የሚችል ያለ አይመስለኝም። በክትባቱም እንደዚሁ ነው፤ ከሌሎች አገሮች ለክትባቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ሳልጠቀም መቶ በመቶ በራሴ ብቻ የኮሮናቫይረስ ክትባትን መስራት እችላለሁ የሚል የለም። ታዲያ መፍትሄው ምንድነው? አገራቱ ስምምነትስ ላይ እንዴት ሊደርሱ ይችላሉ? ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት ልክ እንደ ኢንሹራንስ ፖሊስ ስምምነት ላይ ለመድረስ ይሞክራል። ይሄ ስምምነትም ዋነኛው ነገር ምንድን ነው አንድ አገር የኮሮናቫይረስ ክትባትን ባያመርት የተለያዩ አገራት ከክትባቱ የሚጠቀሙበትን መንገድ መቀየስና ማከፋፈል ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ ዓለም አቀፋዊ ስምምነት ያሻዋል። ክትባቱ ከተገኘ በኋላ መንግሥታት ለመከፋፈል መንገድ ለማበጀት ስምምነት ላይ መድረስ አለባቸው። ለምሳሌ አንድ መንግሥት ግማሹን ክትባት ለራሱ ሕዝብ ካዋለ ግማሹን ለተቀረው ዓለም የሚሰጥበት መንገድን ማሰብ አለበት። በዚህም መንገድ ሁሉም ተጠቃሚነቱ ይረጋገጣል። እንደነዚህ አይነት ስምምነቶች ላይ መደረስ ከተቻለ የተለያዩ አገራት ክትባቱን ባያመርቱም እንኳን ለሕዝባቸው ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ ማለት ነው። እንደነዚህ አይነት ስምምነቶች ላይ የሚደረስ ይመስልዎታል? አይሆንም፤ የሚደረስ አይመስለኝም። በርግጠኝነት አሜሪካ፣ ቻይና የመሳሰሉት አገራት ክትባቱን በመጀመሪያ የሚያገኙት እነሱ እንደሆኑ ልበ ሙሉ ናቸው። እናም ከዚህ ክትባት ቅድሚያ መጠቀም ይፈልጋሉ፤ ይሄንንም ለዓለም ሕዝብ አሳልፈው መስጠት አይፈልጉም። ቅድሚያ ለሕዝባቸው እንደሚሉም እርግጠኛ ነኝ። በአሁኑ ሰዓት ብሔራዊ ስሜት በከፍተኛ ሁኔታ የጎለበተበት ወቅት ነው። ቅድሚያ ለእኔ! ለብቻዬ የሚሉ ሁኔታዎችም ይሰማሉ። መንግሥታት ከሌሎች አገራት ጋር የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለመከፋፈል ስምምነት ላይ ቢደርሱ በአገራቸው ፖለቲካዊ ክፍተት ይፈጠራል፤ እንዲሁም ጨና ይፈጠርብናል ብለው ያምናሉ፤ ሊሆንም ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ክትባትንም ለማግኘት የመጀመሪያ መሆን በራሱ ድል የማድረግ ስሜት አለው፤ ጠንካራ ምልክትም ነው፤ በተለይ የፖለቲካ ኃይልንን ለመቆጣጠር። ክትባቱን በመጀመሪያ ማግኘት የራሱ ጥቅሞች አሉት። ነገር ግን አሁን ያለውን አካሄድ ስንመለከተው በርካታ ክትባቶች ይፈጠራሉ እነዚህ ክትባቶች ደግሞ መፍትሄ አይሆኑም። ሁሉም ክትባቶች የራሳቸው ውስንነት አላቸው። ምን ያህል ሰዎችን መርዳት ይችላሉ እንዲሁም ከጎንዮሽ ጉዳቶችና ሌሎችም ነገሮች ተያይዞ ማለት ነው። ይህን ውይይታችንን የበለጠ አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ ሰዎች ክትባቱ ሲገኝ የወርቅ ሜዳልያ እንደተገኘ ያህል ሊቆጥሩት እንደሚችሉ ሳስብ ነው። ብዙዎች የክትባቱ መገኘት የኮቪድ-19 መፍትሄ ነው፤ አበቃ አከተመለትም ሊሉ ይችላሉ። ነገሩ ግን እንደዚያ አይደለም። የክትባቶችን ታሪክ ብናይ ለበሽታዎች ክትባት ሲገኙ የተወሰነውን ሰው ነው መርዳት የሚችሉት ሁሉንም አይደለም። ለተወሰነ ጊዜም የሆነውን ማኅበረሰብ ክፍል ይረዳሉ። ያልተፈለገ የጎንዮሽ ጉዳትም ያስከትላሉ ብዙዎች አንወስድም ብለው ያቆሙታል። የእኔ ግምት አንድም ይሁን ሌሎች ክትባቶች ቢገኙም የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት አሁን የምናደርጋቸውን ጥንቃቄዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ ጭምብል ማድረግ እንዲሁም እጅን በተደጋጋሚ መታጠብና በፀረ ተህዋሲያን ማፅዳቱን የምንቀጥልበት ይሆናል። በርካቶች ክትባቱ ሲገኝ የሚኖረውን ሚና ያገዝፉታል ወይም ያዳንቁታል። ክትባቱ ሁላችንንም አያድነንም። ክርክሩ በመርህ ደረጃ ልክ ነው። እውነታውን ካየነው በአሁኑ ሰዓት አገራት ክትባቶችን የራሳቸው ለማድረግ ነው እንጂ ለሌሎች ሲያስቡ አይታይም። በአገራቱ መካከል ስምምነቶች መደረስ ካልቻሉስ ዋናው አደጋ የሚሆነው ምንድን ነው? ዋናው አደጋማ የሰብዓዊ ቀውስ ይፈጠራል። በርካታ አገራት የምጣኔ ሃብትም ሆነ ለጤና ሥርዓቱ ምላሽ መስጠት አይችሉም። ክትባቶቹንም በብልህነት ካልተጋራናቸው ቫይረሱ ዓለማችንን ሊያጥለቀልቃት የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል። በርካቶችም ተጋላጭ ይሆናሉ።
news-52962667
https://www.bbc.com/amharic/news-52962667
ለጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይ ከምክር ቤት አባላት የቀረቡ ጥያቄዎችና የሰጡት መልስ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ ልዩ ስብሰባ በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት ተካሄዷል።
በዛሬው ልዩ ስብሰባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት መልስ፡ "መንግሥት ደካማ ነው" አሁን ያለው ጠቅላይ ሚስትሩ የሚመሩት መንግሥት ደካማ ነው የሚባለው የተሳሳተ ነው በማለት ምላሽ ሰጥተው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ "በደንብ የገረፈ ጥሩ አባት፤ ቁጫ አድርጎ የመከረ አባት እንደ አባት የማይታይበት የቆያ ብሂል አለ። ይህ ብሂል ትክክል አይደለም" ካሉ በኋላ "ኮሽ ባለ ቁጥር ሥልጣኔ ተወሰደ ብሎ የሚደናገጥ መንግሥት አይደለም" ሲሉ ስለአስተዳደራቸው ተናግረዋል። ከዚያ ይልቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገሪቱን ኢኮኖሚን ለማሻሻል እያደረገ ያለው ጥረትንና ያገኘውን ውጤት ኢትዮጵያ ከብድር አንጻር የነበረችበት ደረጃን በመለወጥ እንዲሁም የተሰሩ ፕሮጀክቶች ውጤት ላይ የተገኘውን ውጤት በመጥቀስ የመንግሥታቸውን ጥንካሬ ከኢኮኖሚና እድገት አንጻር ምላሽ ሰጥተዋል። ስለታገቱት ተማሪዎች ጉዳይ ከስድስት ወራት በፊት ታግተው የደረሱበት ስላልተወቁ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በተመለከተ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት ማብራሪያ መንግሥት ተማሪዎቹን ፈልጎ ለማግኘት ጊዜ እና ገንዘብ በማፍሰስ ሲያፈላልጋቸው መቆየቱን ጠቅሰው "ይሄ ግን ተራ እገታ" አይደለም ብለዋል። "መረጃ በደሰረን ቁጥር እየፈለግን ነው። አሁንም ተማሪዎቹን ካሉበት ለማግኘት የሚገኙ መረጃዎችን መሰረት አድርገን ፍለጋችንን ቀጥለናል" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ "እኛም ሴት ልጆች አሉን፤ ይሰማናል ይሁን እንጂ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚጽፉ ነገሮች" እንዳሉ አመልክተው መንግሥት ግን አሁንም ፍለጋ ላይ እንደሆነ ገልጸዋል። ትግራይን በሚመለከት "አንድ ሰው ወይም ሁለት ሰው ሲወቀስ ጉዳዩን ወደ ትግራይ አንወስደው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "በህውሓት እና በብልጽግና መካከል ረብ የሌላቸው ንግግሮች አሉ ይሄን መተው አለብን።" ጨምረውም "ለውጡ ከመጣ በኋላ የትግራይ ሕዝብ እንዳይጠቀም ተደርጓል የሚለው የተሳሳተ አመለካከት ነው" ብለው ጠቅላይ ሚንስትሩ "ባለፉት ሁለት ዓመታት እንኳ የትግራይ ክልል በጀት በ42 በመቶ አድጓል። በጀቱ ምን ያህል የሚፈለገው ቦታ ላይ ውሏል የሚለውን ግን የክልሉ ምክር ቤት ነው የሚገመግመው" ብለዋል። ትግራይን ሕዝብ ለመጉዳት ፍላጎት የለንም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ "ኮሮናቫይረስ ለመላከል 46 ሚሊዮን ብር ከበጀት ውጪ በጥሬ ገንዘብ እና በቁሳቀሱ ተረድቷል፤ ይሁን እንጂ ለኮሮናቫይረስ ለትግራይ ክልል ድጋፍ አልተደረገም የሚሉ አሉ። ማዳበሪያ ለገበሬው እንዳይቀር 445 ሚሊዮን ብር ተበድረን ለሌሎች ክልል ያልተደረገውን ማዳበሪያ ልከናል" ብለዋ ጠቅላይ ሚንሰትሩ። ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በትግራይ ውስጥ እየተካሄዱ በመሆኑ የፌደራል መንግሥት በትግራይ ላይ በደል ይፈጽማል መባሉ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። በሱዳን ድንበር ላይ ስላለ ጉዳይ "ከሱዳን ጋር ወድማማች ሕዝቦች ነን" ያሉት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ሕዝብ ብዙ ችግሮችን አብረው አልፈዋል። ከሱዳን ጋር ጦርነት አንሻም ግን "ሱዳን እና ኢትዮጵያን ለማዋጋት የሚፈልግ ኃይል የለም ማለት ግን አይቻልም" ብለዋል። ከሳምንታት በፊት በድንበር አካባቢ ተከሰተ ስለተባለው ችግርም ሁለቱ አገራት በሰላም ይፈቱታል በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ሰጥተዋል። የአምነስቲ ሪፖርት "የኢትዮጵያውያን መብት እየተጎዳ ነው ካለ ሪፖርቱ ፤ አይረባም ሳይሆን፤ የእኛም የጸዳ ተቋም ስላልሆነ ችግር ሊከሰት ይቻላል። እሱን ፈትሾ ማስተካከል ያስፈልጋል" በማለት ከሪፖርቱ ጋር የተለያዩ አላማዎች ቢኖሩም የሚስተካከለውን ለማረም ፈቃደኝነቱ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። "ካጠፋን መሸፈን አያስፈልግም፤ ስለዚህ መለስ ብሎ ለመፈተሽ ብዙ የሚያስጨንቀን ጉዳይ ግን አይደለም" ብለዋል። ሕዳሴ ግድበ ስድስት ዓመት በዘገየው ግድብ 6 ቢሊዮን ዶላር ኢትዮጵያ ማጣቷን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ ስምንት ኮንትራት 6 ተቋራጮች እንደሚሰሩት በማስታወስ አንዱ ተቋራጭ ከሥራ ቢዘገይ ለሌላው ተቋራጭ እንቅፋት እንደሚሆን አስታውሰዋል። ሥራ ሲሰራ ዲፕሎማሲው ይጠነክራል። ሥራ ሳይሰራ ሲቀር ዲፕሎማሲውም ቀላል ይሆናል። የሕዳሴ ፕሮጀክት ከጥንስሱ ጀምሮ የተወሰኑ ውሳኔዎችን ማጥናታቸውን እና በግድቡ ላይ ሜቴክ እንዲገባ መደረጉ ስህተት መሆኑን ተረድተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚንሰትሩ። ጠቅላይ ሚንስትሩ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራዎቹ እንደ አዲስ እንዲሰራ መደረጉን ተናግረዋል። በመጪው ክረምት ግድቡ 4.9 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዝ እንደሚቻል ተናግረዋል። ከለውጡ በኋላ ፕሮጅክቱ እንዴት እንደዳነ፤ "የምክር ቤት አባላት ሄዳችሁ ማየት ትችላላችሁ" ብለዋል ጠቅላይ ሚንሰትሩ። ዲፕሎማሲን በተመለከተ፤ የግብጽ የተሻለ የኤሌእከትሪክ እና የንጹሕ ውሃ አቅርቦት ለዜጎቿ ማቅረብ እንደምትችል ያስታወሱ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም ይህን ከማድረግ የሚከለክላትን አገር አትቀበልም ብለዋል። "እጅግ የሚያኮሩ ኢትዮጵያዊያን" ያሏቸው ግለሰቦች አሁንም የሕዳሴ ገድብ ጉዳይ እየተደራደሩ እንደሚገኙ አስታውሰዋል። ምርጫ ምርጫ ቦርድ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ምርጫ ማድረግ አልችልም የሚለው ሪፖርት ሲደርሰኝ፤ "ከወ/ሪት ብርቱኳን ጋር ባልተለመደ መልኩ ጠንከር ያለ ንግግር አድርገናል" በማለት ከምርጫ ቦርድ ውሳኔ ጋር ተስማምተው እንዳልነበረ ተናግረዋል። ፓርቲያቸው ምርጫው እንዲካሄድ ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበረው የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ "ብልጽግና ምርጫ የሚያስፈራው ፓርቲ እንዳለሆነ ለሁሉም ግልጽ ነው" ብለዋል። ወ/ሪት ብርቱኳን፤ "እስካሁን ከነበረው በማንም መስፈርት የማያሳፍር ምርጫ ለማካሄድ ነው ኃላፊነት የተቀበልኩት። ከዚህ ውጪ የሆነ ምርጫ ይደረገረ የሚሉ ከሆነ ሥራዬን እለቃለሁ። ምርጫ እንዲደረግ አታዙኝም ብለው ስልኩ ተዘጋ" ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ምርጫ መካሄድ የማይቻልበት ሁኔታ መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ የመንግሥትን የሥራ ዘመን በማራዘም ምርጫ ማካሄድ የሚቻልበትን አራት ሕገ-መንግሥታዊ አማራጮች መቅረባቸውን አስታውሰዋል። እምቦጭ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ሐይቁ በአካል ሄደው አረሙ ያለበትን ሁኔታ መመልከታቸውን አስታወሰው፤ አምቦጭ ሁለት አይነት መከላከያ መንገድ አለው ብለዋል። ይህም በሰው እና በማሽን በመጠቀም በጊዜያዊነት መከላከል መሆኑን ጠቁመው፤ መሠረታዊው መከላከያ ግን የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ነው። ከጉና ተራራ ስር የሚነሱ ተፋሰሶች ጣናን የሚመግቡ መሆኑን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ አካባቢው በሰው ልጆች ምክንያት እየተራቆተ መሆኑን አስረድተዋል። የተራራው መራቆት ለአካባቢው በጎርፍ መጥለቅለቅ እና የጣና ሐይቅ በአምቦጭ መወረር ምክንያት ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው ማሽን ብዙ ውጤታማ እንዳልነበረ እና 200 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ የተሻለ ማሽን ለመግዛት ጥረት እየተደረገ ነው። በቻይና የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን በተመለከተ ቻይና በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ተጠቅታ በነበረችበት ወቅት፤ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከቻይና ይውጡ የሚሉ አስተያየቶች እና እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፤ ነገር ግን "መሰል አስተያየቶች ሙሉ ምልከታ ያልነበራቸው ነበሩ" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት በቻይና የሚገኘ አንድም ኢትዮጵያዊ ተማሪ በቫይረሱ አልተያዘም። ከቻይና ፕሬዝደንት ጋር መነጋገራቸውን እና ተማሪዎቹ ለከፋ ችግር ሳይጋለጡ ማለፋቸውን ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ ለተማሪዎቹ ገንዘብ ተልኮ እንድነበረ እና የቻይና መንግሥት ለተማሪዎቹ ላደረገው እንክብካቤ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድን በተመለከተ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጨመረው እንዳሉት የቫይረሱ ስርጭት በቫይና ተስፋፍቶ በነበረበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የለበትም የሚለው ትችት ትክክል እንዳልነበረ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት፤ አየር መንገዱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለከፍተኛ ወጪ ቢዳረግም አንድም ሠራተኛ ሳይቀንስ ከመንግሥት ድጎማ ሳይጠይቅ ሥራውን እያስቀጠለ ይገኛል። በተጨማሪም አምስት የአየር መንገዱ ሠራተኞች ባቫይረሱ ተይዘው እንደነበረ አስታውሰው ሁሉም ማገገማቸውን ተናግረዋል። "የውጪ አገር መሪዎች ከእኔ ጋር በስልክ ሲነጋገሩ ቅድሚያ የሚያመሰግኑት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ "አስተዳደሩ እና ሠራተኞቹ ምስጋና ይገባቸዋል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ጨምረውም "ቻይና ለአየር መንገዱ በሳምንት 90 በረራን እንዲያደርግም ፈቅዳለች" ያሉ ሲሆን፤ ይህም የሆነው "በችግር ጊዜ ረድቶኛል [አየር መንገዱ] ብላ ነው ይህን ያደረገችው" ብለዋል። ችግኝ አምስት ሚሊዮን ችግኝ መትከል የምንችል ከሆነ ምርጫ ማካሄድ እንዴት ይሰነናል የሚል "ውሃ የማይቋጥር" ሐሳብ የሚያነሱ አሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚንሰትሩ። ምርጫን የሚያስፈጽሙ 100 ሺህ ሰዎች ማሰልጠን ስለማይቻል እንጂ፤ ድምጽ ሄዶ ለመስጠት ስለማይቻል አይደልም ምርጫው የተራዘመው ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። "ግለሰቦች ርቀት ጠብቀው ድምጽ ሊሰጡ ይቻላሉ ግን ለምርጫ ዝግጅት ማድረግ አይቻልም" ያሉት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ ከ5 ቢሊዮን በላይ ዝግጁ የተደረጉ ችግኞችን ግን በ90 ቀናት መትከል ከባድ እንደማይሆን ጠቅሰዋል። ኮሮናቫይረስና በድንበር አካባቢ ያለው እንቅስቃሴ ከአዋሳኝ ጎረቤት አገራት በአፋር፣ በአማራ ክልል መተማ እና ሶማሌ ክልል በኩል የሚገቡ ሰዎች በአከባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የጤና ስጋት ደቅነዋል። መንግሥት ይህን ለመቅረፍ ምን አስቧል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ "ኮሮናቫይረስ 213 በላይ አገራት ያጠቃ እና ትልቅ ትንሹን ያነጋገረ፤ የ21ኛ ክፍለ ዘመን ቴክኖሎጂ ሊመክተው ያልቻለ ክስተት ነው" በማለት ጀምረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ምንም እንኳ በሁሉም ክልሎች አና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቢኖሩም፤ ቫይረሱ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳትን የመናቅ እና የመዘናጋት ሁኔታ ይታያል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በስፓኒሽ ፍሉ ምክንያት ከ500 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ማጥቃቱን እና ወረርሽኙ በሦስት ዙር መከስቱን አስታውሰው፤ ከመጀመሪያው ይልቅ በሁለተኛው ዙር የተቀሰቀሰው ወረርሽኝ የገደለው ሰው ቁጥር የላቀ እንደነበረ በማስታወስ፤ ኮሮናቫይረስም በሁለተኛው ዙር ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል በማስጠንቀቅ ካለፈው ትምህርት ወስዶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። እያደጉ ባሉ አገራት የሚደርሰው ኢኮኖሚያዊ ጫና ከአደጉ አገራት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ እያደጉ ባሉ አገራት ላይ ከሚደርሰው ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመውጣት ግን ረዥም ጊዜ እንደሚወስድ ተናግረዋል። እንደ ተቀሩት አገራት ሁሉ የኢትዮጵያ የጤና ሥርዓትም በቫይረሱ መፈተኑን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ቫይረሱን ከተከሰተ ወዲህ ኮሮናቫይረስን የመመርምር 31 ላብራቶሪዎችን በማቋቋም በቀን 8ሺህ ሰው ናሙና መውሰድ የሚያስችል ደረጃ ላይ ኢትዮጵያ መድረሷን ተናግሯል። በመጪው ሐምሌ ወር ላይም በቀን ከ14 ሺህ ሰዎች ናሙና በመወሰድ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ የሚቻልበት አቅም ላይ እንደሚደረስ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ጨምረው እንደተናገሩት በአጭር ጊዜ ውስጥ መንግሥታቸው፤ በቫይረሱ የተያዙ 15 ሺህ ሰዎች ማከም የሚያስችል የጤና ሥርዓት መዘጋጀቱን፣ የቫይረሱ ምልክት የሚያሳዩ 30ሺህ ሰዎች ለይቶ ማቆያ እና ከውጪ ለሚመጡ 45 ሺህ ለይቶ ማቆያ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ክልሎችን እና የከተማ አስተዳደሮች በላብራቶሪ ማቋቋም እና የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል። "ኮሮናን በተመለከተ መንግሥት ከሕዝብ የደረቀው አንዳቸው ነገር የለም። ሁሉም መረጃ ለህዝብ በግልጽ ይነገር የሚል አቋም ይዘን ሁሉንም እየተናገርን ነው" በማለት መንግሥት የቫይረሱን ስርጭት የተመለከተ መረጃ እያቀበ አይደለም የሚባል ስህተት መሆኑን ጠቁመዋል። ኢኮኖሚ ጠቅላይ ሚንስትር በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት የ170 አገራት ኢኮኖሚ የእድገት መጠን ከዜሮ በታች እንደሚሆን የዓለም የገንዘብ ተቀወም (አይኤምኤፍን) በመጥቀስ ተናግተዋል። የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት 9 በመቶ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም እድገታችን እስከ 6 በመቶ ይሆናል። አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 3 በመቶ ያድጋል ሲል ተንበየዋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የዓለም ኢኮኖሚ እድገት ከዜሮ በታች ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አድገት አዎንታዊ የሆነበትን ምክንያት ሲያስረዱ፤ የበጀት ዓመት ሐምሌ መጀመሩ፣ የተለየ የጊዜ አቆጣጠር በኢትዮጵያ መኖሩ፣ ከኮረናቫይረስ በፊት ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ትልከው የነበረው ምርት እድገት እያሳየ እንደነበር የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የኢትዮጵያ የንግድ ሥርዓት ከተቀረው ዓለም ጋር የተሳሰረው ከ30 በመቶ በታች ነው ብለዋል። ይህም በመላው ዓለም ላይ የሚደርሰው ጫና ከፍተኛ ላይሆን እንደሚችል ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠቁመዋል።
news-53609387
https://www.bbc.com/amharic/news-53609387
ኦነግ፡ አቶ ዳውድ ኢብሳ ስለቆዩበት ሁኔታና ስለድርጅታቸው ይናገራሉ
ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ-መንበር የሆኑት የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፌደሬል ፖሊስ መከበቡንና ከቤታቸው መውጣትም ሆነ መግባት እንዳልቻሉ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መግለጻቸው ይታወሳል።
ለሁለት ሳምንታት ያህል ከቤታቸው ሳይወጡና የሰልክ ግንኙነት ለማድረግ ሳይችሉ እንደቆዩ የሚናገሩት አቶ ዳውድ ኢብሳ ከትናንት አርብ ጀምሮ ከቤታቸው መውጣት እንደቻሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ዳውድ ተጥሎባቸው ስለነበረው የእንቅስቃሴ እቀባና እርሳቸው በሌሉበት በፓርቲያቸው ከፍተኛ አመራር አባላት ስለተካሄደው ስብሰባ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ "ሐምሌ 10 ላይ የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ፤ እኔ የፌደራል ፖሊስ አባላት ናቸው ብዬ ነው የማምነው፤ መልዕክት ተቀብለው የመጡ ናቸው 'ለደኅነንትህ ሲባል ከቤት አትውጣ፤ በአካባቢውም ጥበቃ እናደርጋለን' ሲሉ በጥሞና ነገሩኝ" ሲሉ ሁኔታውን ያስታውሳሉ። አቶ ዳውድ ኢብሳም የጸጥታ ኃይሉ አባላት እንዳሉት የደኅንነት ጥበቃ ሊያደርጉላቸው እንደመጡ እንዳመኗቸውና የነገሯቸውንም እንደተቀበሉ ገልጸዋል። በተጨማሪም በሳምንቱ ሐምሌ 17 ላይ "ቤት ውስጥ ያሉትም ወደ ውጪ እንዳይወጡ" የሚል ትዕዛዝ እንደደረሳቸው የገለፁት አቶ ዳውድ፤ ይህንንም ለደኅንነት ጥበቃ ነው ብለው በማሰብ እንዳመኑ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ የዚያን ዕለት ከሰዓትና በማግስቱ የግል ስልካቸው መዘጋቱንና ግንኙነታቸው መቋረጡን በመግለጽ በደኅንነት ጥበቃ የተጀመረው ሁኔታ ወደ አሳሳቢ ሁኔታ መሻገሩን ጠቅሰዋል። "ለጥበቃ የመጣው የፖሊስ ኃይልና ስልኬን የዘጋው አካል ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው የማውቀው ነገር የለም። ግን ስልኬ ከሐምሌ 17 ጀምሮ ተዘጋ" የሚሉት አቶ ዳውድ፤ "ሐሙስ ዕለት ከአሁን በኋላ ለደኅንነትህ ጥንቃቄ እያደረክ መንቀሳቀስ ትችላለህ መባላቸውን" ያስረዳሉ። በዚህም መሠረት አርብ ዕለት ከቤታቸው ወጥተው ወደ የፓርቲያቸው ጽህፈት ቤት በመሄድ ጉዳያቸውን ከውነው እንደተመለሱ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የጽጥታ ኃይሎች በቤታቸው አካባቢ ተሰማርተው የደኅንነት ጥበቃ ማድረጋቸው ምናልባት አቶ ዳውድ እራሳቸው የሚያውቁት ስጋት ካለ በሚል ከቢቢሲ የተጠየቁት ሲሆን "ብዙ ጊዜ እየተደጋገሙ የሚመጡ ማስፈራሪያዎች፣ ማስረጃ መስሎ የሚመጣ ወሬ አለ። የዚህ ዓይነት መረጃ ተደጋግሞ ስለሚመጣ ትኩረት አልሰጠሁትም፤ ይህንን ፈርቼም ሥራዬን አላቆምኩም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ዳውድ ባለፈው ሰሞን ባጋጠማቸው ሁኔታ ላይ ጥያቄ እንዳላቸውም ገልጸዋል። "ስልኬ እንዲቋረጥ መደረጉን የደኅንነት ጉዳይ አድርጌ አልወሰድኩትም። ለሌላ ኦፕሬሽን እንደወሰዱት ነው የተረዳሁት። እነዚህ ሁለቱ ይገናኛሉ ብዬ ማመን ትንሽ ያስቸግረኛል፤ ነገር ግን ሊገናኙም ላይገናኙም ይችላሉ። ማወቅ አይቻልኩም" ያሉት አቶ ዳውድ፤ ቢቢሲ እስካናገራቸው ጊዜ ድረስ የእራሳቸው ስልክ እንደተዘጋ ሲሆን ለዚህ ቃለ ምልልስ እየተጠቀሙ ሌላ ቁጥር ነው። በደኅንነት በኩል ስጋት እንዳለ ያልሸሸጉት አቶ ዳውድ ኢብሳ "ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና ከድምፃዊ ሃጫሉ ግድያ በኋላ፤ የሆነ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ማንም የሚረዳው ነገር ነው" በማለት ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት እንደሚንቀሳቀሱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንዲህ ያለው ጥቃት በማንም ላይ ሊጋጥም ይችላል የሚሉት አቶ ዳውድ "ምክንያቱም መንግሥት የሕግ የበላይነትን አስከብራለሁ ብሎ ንፁሃን ዜጎችን ከማሰር ውጪ ለሕዝብ መረጃ አይሰጥም፤ የእነዚህ ሰዎች ገዳዮች እነማን ናቸው? የሚለውን ምርመራ አድርጎ ይፋ አያወጣም" በማለት "ስለዚህ ይህ በማንም ላይ በየትኛውም ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል ተረድተን ነው የምንንቀሳቀሰው" ብለዋል። አቶ ዳውድ ያልተገኙበት የፓርቲው ስብሰባ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ ተደርገዋል የሚለውን ዜና ተከትሎ፤ በግንባሩ ጽሕፈት ቤት የተካሄደው የድርጅቱ አመራሮች ስብሰባ "ሊቀ መንበሩን ለማንሳት ነው" የሚል መረጃ እንዲሰራጭ ምክንያት ሆኖ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም የግንባሩ አመራር ለሁለት የመከፈሉ ጉዳይ መነጋገሪያ ከመሆኑ በተጨማሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሊቀ መንበርነታቸው ተነስተው በአቶ አራርሶ ቢቂላ እንዲተኩ ተደርጓል የሚል ወሬም በስፋት ሲነገር ቆይቷል። ይሁን እንጂ አቶ ዳውድ ኢብሳን እንዲተኩ ተመርጠዋል የተባሉት አቶ አራርሶ ቢቂላ "ዜናው ፍጽም ሐሰት ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። አቶ አራርሶ በኦነግ ጽሕፈት ቤት የተካሄደው ስብሰባ የሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ እውቅና የነበረው መሆኑን በመናገር አሁንም የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። የግንባሩ ሊቀ መንበር በከተማው ውስጥ እያሉ በሚመሩት ድርጅት ስብሰባ ላይ ሳይገኙ ስብሰባው ስለመደረጉ አቶ ዳውድ የሚያውቁት ነገር ስለመኖሩ ከቢቢሲ ለተጠየቁት ጥያቄ፤ አቶ አራርሶ ቢቂላ በሰጡት መልስ "አቶ ዳውድ የተለየ ጉዳይ ስለገጠማቸው እየተንቀሳቀሱ የዕለተ ከዕለት ሥራቸውን ማከናወን አልቻሉም። ስለዚህም ስብሰባችን ላይ መገኘት አልቻሉም" በማለት ስለስብሰባው ከአቶ ዳውድ ጋር መነጋገራቸውን ገልጸው ነበር። አቶ አራርሶ ቢቂላ ይህንን ይበሉ እንጂ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ገዳ ኦልጅራ (ዶ/ር) ግን "በአቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ሰብሰባ የድርጅቱ እውቅና የለውም" በማለት ስብሰባው በግንባሩም ሆነ በሊቀ መንበሩ የማይታወቅ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ቢቢሲ ይህንኑ ውዝግብ ያነሳንላቸው አቶ ዳውድ፤ ስብሰባ መደረጉን እንደማያውቁ ገልፀው ከግንኙነት ውጪ ስለነበሩ ምን እንደተደረገ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል። "አሁን ገና ነው የማጣራው፤ የፓርቲውን አመራሮችም ሆነ አባላት የዕለት ተዕለት ሥራዎችን በጥሞና የሚከታተል በጉባዔ የተመረጠ የሕግ ቁጥጥር ኮሚቴ አለ። የእነሱን ውሳኔ ጠብቆ በእነሱ ትዕዛዝ መንቀሳቀስ የድርጅቱ ግዴታ በመሆኑ እርሱን እጠብቃለሁ" ብለዋል። ከሁለት ሳምንት በኋላ ትናንት አርብ ወደ ፓርቲያቸው ጽህፈት ቤት እንዳመሩ የገለፁት አቶ ዳውድ፤ ስለ ጉዳዩ የማጣራት ሥራ ውስጥ አለመግባታቸውን በመግለፅ "በሚዲያ የሚናፈሰውን መድገም አልፈልግም" ሲሉ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የአመራር ሹም ሽር ተካሂዷል ስለመባሉም "ስብሰባ አደረጉ የተባሉት አመራሮች፤ ጉዳዩ እዚያ ደረጃ እንዳልደረሰና እንዲህ ዓይነት እርምጃ እንዳልተወሰደ ነው የተናገሩት። ይህንንም ኮሚቴው ነው የሚያጣራው" በማለት ሹም ሽር እንዳልተካሄደ ግን ራሳቸው አቶ አራርሶ ቢቂላ ለመገናኛ ብዙሃን መናገራቸውን ጠቅሰዋል። የፓርቲው አመራሮችና አባላት እስር አቶ ዳውድ በየጊዜው የፓርቲው አመራሮችና አባላት እንደሚታሰሩባቸው ይናገራሉ። ይህንንም በተመለከተ ለምርጫ ቦርድ፣ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ለዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት በየጊዜው ማመልከቻና የእስረኞችን ዝርዝር ማስገባታቸውን ይገልፃሉ። ላቀረቡት ቅሬታ ምርጫ ቦርድ እንቅስቃሴ ያደረገ ቢሆንም "የሚጠበቅበትን ግዴታ ተወጥቷል ብለው እንደማያምኑ" ይናገራሉ። ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ሆነ ከሌሎች አካላት ግን ምላሽ አላገኘንም ብለዋል። ከድምፃዊ ሃጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞም የፓርቲው አመራሮችና አባላት መታሰራቸውን የሚገልፁት አቶ ዳውድ፤ የ103 አመራሮችና የቢሮ ኃላፊዎች ስም ዝርዝር ከታሰሩበት ቦታና የት እንደታሰሩ የሚያሳይ ማመልከቻ ለዐቃቤ ሕግና ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ማስገባታቸውን፤ የተቀሩት አባሎቻቸውም የት እንዳሉ እንዲጣራላቸው ለቀይ መስቀል ማሳወቃቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። በፓርቲያቸው ጽህፈት ቤት ላይም ጥቃት መፈፀሙን በመጥቀስ "ይህ ባህል እየሆነ ነው፤ መስዋዕትነት ቢኖርም አሁንም እንቀጥላለን" ሲሉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-46465368
https://www.bbc.com/amharic/news-46465368
ወገኖቹን ለመርዳት ከከተማ የራቀው ዶክተር ቴዎድሮስ
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል ለህሙማን የሚያቀርበውን ደም የሚያገኘው አምቡላንሶቹን በደርሶ መልስ ስምንት ሰዓት በሚፈጅ ጉዞ ወደ ጅማ ከተማ በመላክ ነው።
ኦክስጂን የሚያመላልሱለት መለስተኛ የጭነት መኪናዎች ደግሞ ከአምስት መቶ በላይ ኪሎ ሜትር አቆራርጠው ወደ አዲስ አበባ መጓዝ አለባቸው። ለወትሮውም ቢሆን በሆስፒታሉ እጥረት ተከስቶ የህሙማንን ህይወት ለከፋ አደጋ ከመጋለጡ በፊት ደም፣ ኦክስጂን እና መድኃኒት በተገቢው ጊዜ ማግኘቱ የራሱ ቢሮክራሲያዊ የራስ ምታቶች አሉት። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ሌላ ጋሬጣም ተጨምሮበታል - ፖለቲካዊ ያለመረጋጋት እና የመንገዶች መዘጋጋጋት። ሆስፒታሉ ካለበት ቦታ ወደ ጅማ የሚወስዱ ሁለት መንገዶች ሲኖሩ የቴፒ ከተማን አቋርጦ የሚያልፈውን ዘለግ ያለው መንገድ በስፍራው ባለ ፖለቲካዊ ያለመረጋጋት የማይደፈር ካደረገው ሰነባብቷል። በቦንጋ በኩል ጅማ የሚያደርሰው ሌላኛው መንገድ አማራጭ ሆኖ ቢቆይም እርሱም ቢሆን ያለፉትን ጥቂት ሳምንታት ሰላም አልነበረውም። የከፋ ዞን በመጀመሪያ ከቡና መገኛነት ጋር፤ ለጥቆም በክልል ደረጃ ራስን ከማስተዳደር ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያስተናግድ ይሄኛውም መንገድ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በድንጋይ፣ በተበላሹ መኪኖች እና በወደቁ ዛፎች ለቀናት ተዘጋግቷል። "መንገዱ ከተከፈተ በኋላ ስሄደበት ሰባ ሰባት ቦታ ላይ ተዘግቶ እንደነበር ቆጥሬያለሁ" የሚለው የሆስፒታሉ ዋና የህክምና ሥራ አስኪያጅ የሆነው ዶክተር ቴዎድሮስ ወርቁ ነው። በሌሎች ጊዜያት እንደዚህ ተቃውሞዎች እንቅስቃሴን በሚገቱበት ወቅት አምቡላንሶችን ማሳለፍ የተለመደ ቢሆንም፤ መንገዱ በዛፍና በመሳሰሉ ግዙፍ ቁሶች ከተዘጋ ግን የማለፍ ዕድል እንደማይኖር የሚያስረዳው ዶክተር ቴዎድሮስ፤ የከፋ ዞኑ ተቃውሞ ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በሄሌኮፕተር ለማስመጣት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር ንግግር ጀምሬ ነበር ይላል። • የ29 ዓመቷ የህክምና ዶክተርና ኢንጅነር ዕልልታ ጉዞ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል በያዝነው ዓመት ሰማንያ ሚሊዮን ብር አካባቢ በጀት ከመንግሥት ተመድቦለት፣ በ430 የህክምና እና የአስተዳደር ሠራተኞች ከሁለት ሚሊዮን ለሚልቁ የአካባቢው ነዋሪዎች የጤና ክብካቤ ግልጋሎት እንዲያቀርብ የሚጠበቅ ተቋም ነው። ዶክተር ቴዎድሮስ ሃያ ስድስተኛ ዓመቱን ሳያጋምስ ነው የሆስፒታሉን የህክምና ክፍል የማስተዳደር ኃላፊነትን የተረከበው። በኃላፊነት በቆየባቸው ያለፉት አምስት ወራት ቶሎ ቶሎ ከፍ ዝቅ የሚለው የፖለቲካ ትኩሳት ሥራው ላይ ጫና ማሳረፉን አይክድም። በተቃውሞ ምክንያት "የቴፒ ሆስፒታል ወደ ሁለት ሳምንት ሥራ አቋርጦ በመቆየቱ ወደእኛ የሚመጡ በሽተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ ነበር" እንዲሁም ከህክምና ቁሳቁሶች በተጨማሪ "ከፍ ያለ ህክምና የሚፈልጉ በሽተኞችን ወደሌላ ሆስፒታል ለመላክም ተቸግረን ነበር" ይላል። ፈተናን መጋፈጥ ዶክተር ቴዎድሮስ ሚዛን ቴፒ ያደረሰው የሥራ ህይወት ጎዳና ተግዳሮትን ለመጋፈጥ ካለው ዝንባሌ እንደሚነሳ ይናገራል። ከአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ ጥቁር አንበሳ ልዩ የህክምና ሆስፒታል ከሁለት ዓመት በፊት በህክምና እንደተመረቀ ቀጣይ ትምህርቱን እንዲከታትል የሚያስችለውን ውጤት ማስመዝገብ ችሎ ነበር። ለአንድ ዓመት ከአራት ወራት ያህል ከትምህርቱ ጋር በተያያዘ እንዲያሟላ የሚጠበቅበትን የጠቅላላ ህክምና ሥራ እያከናወነ እዚያው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ባለበት ጊዜ ነበር ከመዲናይቱ ወጣ ብሎ ኅበረተሰብን የማገልገል ውሳኔ ላይ የደረሰው። • በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው ቴዎድሮስ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሞላ ጎደል በሁሉም ቦታዎች ያለው የሐኪሞች ቁጥር ከታማሚው ፍላጎት ጋር የማይመጣጠን ቢሆንም ከከተሞች እየተራቀ በተሄደ ቁጥር የችግሩ አሳሳቢነት እንደሚበረታ ጠፍቶት አያውቅም። "በአብዛኛው የሚጎዱት ገጠር አካባቢ ያሉ [ታማሚዎች] ናቸው። በጠቅላላ ሐኪም ደረጃ ሊታከሙ የሚችሉ ብዙ ችግሮች፤ በርካታ ሰዎችን ለአደጋ እያጋለጡ፤ ለህልፈትም እያደረሱ ስለሆነ" ይህንን ለመጋፈጥ መፈለግ ተቀዳሚ ገፋፊ ምክንያቱ እንደሆነ ያወሳል። ቀድሞ አማን ሆስፒታል ተብሎ ይታወቅ ወደነበረው የአሁኑ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የማስተማሪያ ሆስፒታል እንደደረሰ በፅንስ ክትትል እና ማዋለድ ክፍል የጠቅላላ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ነው ሥራ የጀመረው። ምቾቱን በመተው ወደ ገጠር ያቀናው ዶክተር ቴዎድሮስ ከጥቁር አንበሳ የህክምና ትምህርት ቤት ቆይታው በተለየ ያለማንም ክትትል ሥራ መጀመሩ ፍርሃት እንዲሰማው ሳያደርገው አልቀረም። "ህይወትን ማዳን አልችል ይሆን የሚል ስጋት ገብቶኝ ነበር። ጥቁር አንበሳ እያለሁ በምሠራበት ወቅት ሁሌም የበላይ የሆነ ተቆጣጣሪ ክትትል ያደርግልኝ ነበር። እዚህ ግን ሁሉንም ነገር ብቻየን ነው የማደርገው" ይላል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። ይሁንና ተወልዶ ካደገባት ከመዲናይቱ አዲስ አበባ አንፃራዊ ምቾት ርቆ ሊሠራ ሲወስን፤ አንደኛው ምክንያቱ በፈተና ለመገራት መሻቱ ነበር። • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ አሁን ለሚያክመው ለእያንዳንዱ ታማሚ ኃላፊነቱ ከሞላ ጎደል እርሱ ላይ የሚወድቅ ነው።ይህም የሙያ ሥነ ምግባሩን ከወትሮም በላቀ የበረታ እንዲያደርግ፤ የኃላፊነት ስሜቱን የበለጠ እንዲጠነክር እንዳስገደደው እና በሒደቱም የተሻለ ሐኪም እያደረገው እንደሆነ ያምናል።በእርግጥም ለመላመድ ጊዜ አልፈጀበትም። እንዲያውም ከሁለት ወራት ቆይታ በኋላ 38 ሐኪሞችን ጨምሮ ሁለት መቶ ሰላሳ የህክምና ባለሞያዎችን የሚይዘውን የሆስፒታሉን የህክምና ክፍል በበላይነት እንዲመራ ታጨ። "ወደ ሃላፊነት ከመጣሁ በኋላ የተማርኩት ትልቁ ነገር" ይላል ዶክተር ቴዎድሮስ "በህክምናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮች ምን ያህል ውስብስብ እና ከሥርዓት ዝርጋታ ጋር የሚያያዙ መሆናቸው ነው።" የችግሮቹ መወሳሰብ በርካታ ወጣት ሐኪሞችን ከሐገር በብዛት እንዲፈልሱ እንዳደረጋቸው እገነዘባለሁ ይላል ዶክተር ቴዎድሮስ። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ድረ-ገፅ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ዝቅተኛ የህክምና ባለሞያዎች ካሉባቸው አገራት ተርታ የምትገኝ ናት ሲል ያስረዳል። የፍልሰቱ መንስዔዎች አንድም ምጣኔ ሃብታዊ በሌላም በኩል የተጨማሪ ዕውቀትን በመፈለግ የተሻለ ባለሞያ የመሆን ፍላጎቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምቱን አስቀምጦ አብረውት ከተመረቁ ወጣት ሐኪሞች መካከል ወደ ውጭ ያቀኑ ወይንም ወደ ውጭ ለመጓዝ ሒደት ላይ የሆኑ በርካቶችን እንደሚያውቅ ይናገራል። ዶክትር ቴዎድሮስ እነዚህን የህክምና ባለሙያዎች ወደዚያ የገፏቸውን ምክንያቶች እንደሚረዳ፤ ውሳኔያቸውንም እንደሚያከብር አፅንዖት ሰጥቶ ይገልፃል። "ውጭ አይሂዱ፣ አይማሩ፣ አይሻሻሉ አይባልም፤ ሆኖም "ከሐኪሞች ቁጥር ማነስ፣ ከሙያውም አስፈላጊነት ጋር በተገናኘ ለአገሪቷ በጣም ያስፈልጋሉና ተመልሰው መምጣት የሚችሉበት ዕድል ካለ መልካም ነው" ይላል። የተስፋ ፍንጣቂ እራሱን ከፍ ላሉ ኃላፊነቶች ለማጨት ባይታወር እንዳልሆነ የሚገልፀው ዶክተር ቴዎድሮስ፤ በተማሪነት ጊዜውም የህክምና ተማሪዎችን ማኅበር በአመራርነት በማገልገል እንዲሁም ከመጀመሪያ ዲግሪ የህክምና ተማሪ የማይጠበቅ ቢሆንም ምርምሮችን በመሥራት እና ለህትመት በማብቃት ራሱን መፈተኑን በአስረጅነት ያነሳል።ብዙዎች የማይደፍሩትን የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን ጋብ አድርጎ፤ ከአዲስ አበባ ርቆ በሐኪምነት ለመስራት ሲወስንም የሚያውቁት ያልተደነቁት ለዚህ ነው።በጠቅላላ ሐኪምነት በሠራባቸው ሁለት ወራት አስቀድሞም የጠበቀውን ያህል የህክምና ችግር ማስተዋሉ የውሳኔውን ትክክለኛነት እንዳሳመነውም ያስረዳል።ነገር ግን የሆስፒታሉን የህክምና ክፍል የመምራት ኃላፊነትን ከተቀበለ ወዲህ የዘርፉ ችግሮች "እስካሁ ከማውቀውና ከገመትኩትም በላይ የተወሳሰቡ መሆናቸውን ልብ ብያለሁ" ይላል። የህክምናው ዘርፍ ባለሞያዎችን ከሚያበቃበት መንገድ አንስቶ፣ መድኃኒቶችን እና ቁሳቁሶችን እንስሚያሰራጭበት ስልት ድረስ የሥርዓት ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው እያመነ መምጣቱን የሚናገረው ዶከትር ቴዎድሮስ "ጉዳዩ የሰዎች መቀያየር አይደለም" ይላል። ነገር ግን ባለፉት ጥቂት ወራት በአገሪቱ ውስጥ የታየው የፖለቲካ ለውጥ ወገግታውን ማሳረፉን ልብ ማለቱንም ይናገራል። "እንደዜጋ በአገሪቱ ያለው ለውጥ ተስፋ እንድትይዝ ያደርግሃል። በሐኪሞች ዘንድም ሌላ ቦታ ያለው ዓይነት መነቃቃት ያለ ይመስለኛል።"
46697206
https://www.bbc.com/amharic/46697206
በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ጃል መሮ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል?
በኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በመንግሥት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ውጥረትን አንግሷል። ይህን ብቻ አይደለም በቅርቡ በክልሉ ውስጥ ለሚፈጸሙ ግድያዎች እና ዘረፋዎች መንግሥት ኦነግን ተጠያቂ ሲያደርግ ቆይቷል።
በቅርቡ የክልሉ ፖሊስ እና ባለስልጣናት በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ኦነግን የአከባቢው አስተዳደሮችን ይገድላል፣ ጦር መሳሪያ ይዘርፋል እንዲሁም ሚሊሻዎችን ትጥቅ ያስፈታል ሲሉ ከሰዋል። ኩምሳ ዲሪባ ወይም በትግል ስሙ ጃል መሮ ተብሎ የሚታወቀው በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ጦር አዛዥ ነው። ጃል መሮ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚንቀሳቀሳው የኦነግ ሠራዊት ዘንድ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ እንደሆነ ይታመናል። ይህ ብቻም ሳይሆን አንዳንዶች ከሊቀመንበሩ ዳውድ ኢብሳ እዝ ነጻ ሆኖ በራሱ የሚንቀሳቀስ ቡድንን የሚመራ እንደሆነ ይነገርለታል። • በምዕራብ ኦሮሚያ በታጠቁ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱ ተገለፀ ቢቢሲም በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ሁኔታ እና ከኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ስላለው ግነኙነት ከጃል መሮ ቃለምልልስ አድርጓል። ቢቢሲ፡ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኘው የኦነግ ጦር ተልዕኮው ምንድነው? ጃል መሮ፡ ኦነግ የራሱ የሆነ ፍላጎት ወይም ተልዕኮ የለውም። ኦነግ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትን ነው የሚያስጠብቀው። ጦሩም የኦነግን ተልዕኮ ነው የሚወጣው። ይሄው ነው። ቢቢሲ፡ የኦነግን ጦር ወደ ካምፕ በማስገባቱ ጉዳይ ላይ የእርስዎ አቋም ምንድነው? ጃል መሮ፡ በቀላል ቋንቋ ላስረዳህ። በአንድ ቤተሰብ አባለት ውስጥ አባት፣ እናት እና ልጆች ይኖራሉ። በዚህ ቤተሰብ ውስጥ ወላጆች ማለትም እናት እና አባት እስካሉ ድረስ ቤተሰባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት የሚኖርባቸው እነርሱ ናቸው፤ ልጆች አይደሉም። የኦነግ ጦር ወደ ካምፕ ይግባ ወይም አይግባ በሚለው ላይም የኦነግ አጠቃላይ አመራሮች የሚወስኑትን ነው እኛ የምናስፈጽመው። ወደ ካምፕ እንገባለን ወይም አንገባም የሚለውን እኔ ልመልስ አልችልም። • ኦዲፒ፡ ኦነግ እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው ቢቢሲ፡ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ጦር ከሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ትዕዛዝ ውጪ ነው ይባላል። ከአቶ ዳውድ ቁጥጥር ውጪ ናችሁ? ጃል መሮ፡ በምዕራብ ዞን የሚገኘውም ይሁን በሌሎች ዞኖች ውስጥ የሚገኘው የኦነግ ሥራዊት በሙሉ ተጠሪነቱ፣ የሚመራውም፣ ትዕዛዝ የሚቀበለውም ከኦነግ ሊቀመንበር ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ነው። አቶ ዳውድ ኢብሳ የኦነግ ሊቀመንበር ናቸው። የኦነግ ጦር ደግሞ ካሉት የኦነግ ዘርፎች አንዱ ነው። ስለዚህ ተጠሪነቱም ለሊቀመንበሩ ነው። በአጭሩ ይሄው ነው። ከዚህ የተለየ ነገር የለም። • "በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው" የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ቢቢሲ፡ በቅርቡ ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር በምዕራብ ኦሮሚያ ተገናኝታችሁ እንደተወያያችሁ ተሰምቷል። የውይይታችሁ ርዕሰ ጉዳይ ምን ነበር? ጃል መሮ፡ አቶ ዳውድ ኢብሳ የኦነግ ሊቀመንበር እና የጦር የበላይ አዛዥ ናቸው። ከእሳቸው ጋር ብዙ ጉዳዮች ያገናኙናል። ብዙ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን። ውይይታችንም አንዴ ወይም ሁለት ጊዜ አይደለም። በቋሚነት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን። ይህ አዲስ ነገር አይደለም። የተወያየንበትን ርዕሰ ጉዳይ ማወቅ ካሻህ ግን እሳቸውን ደውለህ ጠይቅ። ቢቢሲ፡ ሰሞኑን እርሶ ለኦነግ ወታደሮች ያስተላለፉት መልዕክት እንደሆነ የተነገረ ደምጽ በርካቶች በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ሲቀባበሉት ነበረ። ድምፁ የእርስዎ ነው? ጃል መሮ፡ ስለ ጉዳዩ የማውቀው ጉዳይ የለም። እስቲ ነገረኝ፤ ምንድነው እሱ? ቢቢሲ፡ በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ሰዎች ሲጋሩት የነበረው ወደ 48 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው የእርስዎ ነው በተባለ ደምጽ፤ 'ትጥቅ ያስታጠቀንም ሆነ የሚያስፈታን የለም' የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ነው የተላለፈበት። ጃል መሮ፡ እንዲህ ባለ ጉዳይ ላይ ድምጽ ቀርጸን አናሰራጭም። ይህ የምትለው ድምጽ የት እንደተቀረጸ፣ ማን እንደቀረጸው እና እኔ መሆኔ መረጋገጥ አለበት። ቢቢሲ፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ አስተዳዳሪዎችም እንዲሁም በቅርቡ አቶ ለማ መገርሳ ለካማሼ ዞን አስተዳደሪዎች ግድያ ተጠያቂው የኦነግ ጦር ነው ብለዋል። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምነድነው? ጃል መሮ፡ በዚህ አካባቢ የታጠቀ ኃይል በርካታ ነው። የታጠቀ የመንግሥት አካል፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ታጣቂዎች እንዲሁም የኦነግ ታጣቂዎች በስፍራው ይንቀሳቀሳለሁ። ይህ ሁሉ ታጣቂ ቡድን ባለበት ኦነግ ላይ ብቻ ጣት መቀሰር አይቻልም፤ ትክክልም አይደለም። ገለልተኛ የሆነ አጣሪ አካል ወንጀሉን የፈጸመውን ማጣራት አለበት። ቢቢሲ፡የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኦነግ በምዕራብ ኦሮሚያ የመንግሥት ሥርዓትን ይንዳል፣ ጦር መሳሪያዎችን ይዘርፋል የሚሉ በርካታ ክሶችን ይሰነዝራል። እርስዎ ምን ይላሉ? ጃል መሮ፡ ከዚህ ቀደም ጦርነት ላይ ነበርን። ስንዋጋ ነበረ። የሚወጋንን ጦር አስተዳደራዊ ሥርዓቱን፣ ፖሊስን፣ ሚሊሻውን መበጣጠስ ደግሞ ግድ ነው። የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከደረስን በኋላ ኦነግ በራሱ ተነሳሽነት መንግሥት ላይ ተኩስ ከፍቶ አያውቅም፤ አጸፋዊ እርምጃ ካልወሰድን በቀር። • የኦነግ እና የመንግሥት እሰጣገባ ይህ ሁሉ ክስ ግን ሃሰተኛ ነው። መንግሥት ይህን ክስ የሚያቀርበው በዚህ አካባቢ ላይ ጦሩን በማዝመት ጦርነት ለመክፈት ቅድመ ዝግጅት ሲያከናውን ነው እንጂ ኦነግ ያፈረሰው የመንግሥት ሥርዓት የለም፤ የዘረፈውም የጦር መሳሪያ የለም። እንደውም የኦነግ ጦር ሥነ-ምግባር በተሞላበት መልኩ ተቆጣጥሮ ከያዘው ስፍራ አልተንቀሳቀሰም። ቢቢሲ፡ በምዕራብ ኦሮሚያ ኦነግ ተቆጣጥሬያለሁ የሚለው መሬት የትኛውን ነው? ጃል መሮ፡ እሱን የምዕራብ ኦሮሚያ ህዝብን መጠየቅ ትችላለህ። ቢቢሲ፡ ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ከተሰማራው የሃገር መከላከያ ጦር ጋር የተፈጠረውን ግጭት ይንገሩኝ እስቲ ጃል መሮ፡ የመጣብንን ጠላት መመከት እና ወደ መጣበት የመመለስ ችሎታውም ሆነ አቅሙ አለን። መስዋዕትነት ለመክፈልም ዝግጁ ነን። አሁንም ቢሆን የመጣብንን ኃይል እየተከላከልን እንገኛለን። በዚህ መካከል ግን ችግር ውስጥ እየገባ ያለው እና እየተሰቃየ ያለው የኦሮሞ ህዝብ ነው። የመንግሥት ጦር ውስጥም ያሉት ወታደሮች ህጻናት እና የደሃ እናት ልጆች ናቸው። ይህ ግጭት ግን ለሁለቱም [ኦነግ እና መንግሥት] ወገን የሚያስገኘው ጥቅም የለም። በዚያም ሆነ በዚህ እየተጎደ ያለው ኦሮሞው ነው። ቢቢሲ፡ ለዚህ መፍትሄው ምንድነው? ጃል መሮ፡ የግል የፖለቲካ ጥቅምን ለማስጠበቅ ከማሴር ይልቅ የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ብናስቀድም፤ ይህ ሁሉ ችግር በአንድ ለሊት መፍትሄ ያገኛል። የግል የፖለቲካ ጥቅም ከህዝብ ፍላጎት ካስቀደምን ግን ለዚህ ችግር መቼም ቢሆን መፍትሄ አይገኝም። ቢቢሲ፡ በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖች ውስጥ ኦነግ ሰላማዊ ትግል ለማካሄደ ወደ ሃገር ውስጥ ከገባ በኋላ ጦር እንደ አዲስ በመመልመል እያሰለጠነ ይገኛል ይባላል። ይህ ምን ያህል እውነት ነው? ጃል መሮ፡ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከታወጀ በኋላ የተካሄደ ምንም አይነት ስልጠና የለም። • ዐቢይ አሕመድ ለምን ወደ አምቦ አቀኑ? ቢቢሲ፡ ስለ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ምን ያስባሉ? ጃል መሮ፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት አልፈልግም። ቢቢሲ፡ ባለፉት ጥቂት ወራት በርካታ ለውጦች መጥተዋል። እርስዎ የኦሮሞ ህዝብ ነጻነቱን አግኝቷል ብለው ያምናሉ? ወይም ኦሮሞ ነጻነቱን የሚጎናጸፈው መቼ ነው? ጃል መሮ፡ እኔ እንደ አንድ ግለሰብ ነጻነቴን አላገኘሁም። ህዝቡም የእራሱን መልስ መስጠት ይችላል።
news-51270657
https://www.bbc.com/amharic/news-51270657
የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን እና የመንግሥት ዝምታ
የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን እና የመንግሥት ዝምታ።
ከሚማሩበት የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቀ ወጣቶች የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምላሽ አላገኘም። ተማሪዎቹ ከታገቱ 50 ቀናት አልፏቸዋል። ወላጆች ልጆቻቸው መታገታቸውን ከሰሙ አንስቶ ለሚመለከታቸው አካላት ልጆቻቸውን እንዲመለሱላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ አልሰጠም። የተማሪዎችን መታገት ተከትሎ ከቀናት በፊት ወደ አዲስ ዘመን ያቀናው የቢቢሲ ዘጋቢ ከተማዋ ሃዘን እንዳጠላባት ይናገራል። የታጋች ቤተሰቦች ፊታቸው ጠቁሮ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነው ነው ያገኘኋቸው የሚለው ዘጋቢያችን ቤተሰቦችን ማነጋገር እጅግ አሳዛኝ እንደነበረም ያስረዳል።
news-55730083
https://www.bbc.com/amharic/news-55730083
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካመላ ሐሪስ ማን ናቸው? የትስ ነው የሚኖሩት?
ካመላ ዛሬ አዲስ ታሪክ ጽፋለች፡፡ የመጀመርያዋ የአሜሪካ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆናለች፡፡
ለመሆኑ ማን ናት? ከየት መጣች? የት ነበረች? ምን ትወዳለች? ስለሷ ልናውቃቸው የሚገቡ ቁልፍ ጉዳዮች ከዚህ እንደሚከተለው ተከትበዋል፡፡ በዕድሜ 55 ብትደፍንም ለጊዜው አንቱታውን ትተን እንቀጥል፡፡ ካመላ ሐሪስ የተወለደችው በካሊፎርኒያ ግዛት ኦክላንድ ከተማ ነው፡፡ እናቷ ሻየመላ ጎፓላን ሕንዳዊት ናት፡፡ አባቷ ዶናልድ ሐሪስ ደግሞ ጃማይካዊ ነበሩ፡፡ አባትና እናቷ ሁለቱም በስደት ነው ወደ አሜሪካ የመጡት፡፡ ሁለቱም እንግሊዝ በቅኝ ከገዛቻቸው አገራት ነው የመጡት፡፡ ሁለቱም እንግሊዝ ሄደው እንዲማሩ ተጠይቀው አሜሪካንን የመረጡ ናቸው፡፡ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ በርክሌይ ካምፓስ ውስጥ ተማሪ ሆኑ፡፡ እሱ ኢኮኖሚክስ እሷ ሆም ሳይንስ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ የጥናት ቡድን ውስጥ ተያዩ፡፡ ያኔ አባቷ በካሊፎርኒያ በርክሌይ የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪ ነበር፡፡ በ1960ዎቹ መጀመርያ መሆኑ ነው፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ብሪቲሾች እንዴት አገሩ ጃማይካ ገብተው በቅኝ ግዛት ሕዝቡን እንዳሰቃዩ ንግግር ያደርግ ነበር አባቷ፡፡ ተማሪ እያለ ነው ይሄ ታሪክ፡፡ ንግግሩን ሲጨርስ አንዲት በጣም ደቃቃ ቀጭን ሴት፣ ነጠላ ጫማ የተጫማች፣ የሕንዶችን ነጠላ ከደረቷ ያጣፋች፣ ሄዳ ተዋወቀችው፡፡ ከሕንድ አገር እንደመጣችና እዚያም እንግሊዞች አገሬውን ፍዳውን ያበሉት እንደነበር ነገረችው፡፡ ተቀራረቡ፣ ተዋደዱ፣ ተጋቡ፡፡ መጀመርያ ካመላን ከዚያም ማያን ወለዱ፡፡ ካመላ ማያ የምትባል ታናሽ እህት አለቻት፡፡ አባቷ ዶናልድ ሐሪስ ከእናቷ ሻይመላ ጋር በኋላ ላይ በ1970ዎቹ መጀመርያ ተለያይተዋል፡፡ ያን ጊዜ ካመላ ገና የ7 ዓመት ሕጻን ነበረች፡፡ ካመላና ማያን በማሳደጉ ረገድ የእናቷ ሚና ትልቅ ነበር፡፡ ሆኖም አባቷ ከፍቺ በኋላ ለቤተሰቡ ቅርብ ሆኖ ነበር የቆየው፡፡ እናቷ በኋላ ላይ እንደ አባቷ 3ኛ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል፡፡ የሞቱት በ2009 ዓ.ም ሲሆን ለሞታቸው ምክንያት የደንዳኔ ካንሰር ነበር፡፡ አባቷ ዶናልድ አሁን የ82 ዓመት ዕውቅ የምጣኔ ሀብት "ኢምሬትስ ፕሮፌሰር" ሲሆኑ ከስታንፈርድ ዩኒቨርስቲ ጡረታ ወጥተው በራሳቸው የማማከር ሥራ ይሠራሉ፡፡ አባቷ በጃማይካ ቀልድ አያውቁም፡፡ ልጆቻቸው አገራቸውን እንዲወዱ፣ እንዳይረሱ ይፈልጋሉ፡፡ ሐሪስ በቅርቡ ጃማይካን ከእጸ ፋሪስ ጋር አገናኝታ በመቀለዷ ሽማግሌው አባቷ ቱግ ብለው ነበር፡፡ ካመላ ሐሪስ ባለትዳር ናት? የካመላ ሐሪስ ባል ዳግ ይባላል፡፡ ሁለት ለቁም ነገር የበቁ ወንድና ሴት ልጆች አሉት፡፡ ኮል እና ኢላ ይባላሉ፡፡ ከቀድሞ ባለቤቱ ከክሪስቲን ማኪን ነው የወለዳቸው፡፡ አሁን 26 እና 21 ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ የአባታቸውን ሚስት ‹እንጀራ እናት› ብለው መጥራት አልፈለጉም፡፡ ካመላን ቅጽል ስም አወጡላት፡፡ ‹ሞማላ› እያሉ ነው የሚያቆላምጧት፡፡ እንደ እናትም ናት ለማለትም ጭምር ነው፡፡ ካመላ ሐሪስ ከእንጀራ ልጆቿ ኮል እና ኢላ ጋር በጣም ቅርብ ናት፡፡ ባሏ ዳግ በአሜሪካ ታሪክ ሁለተኛው "ካልአዊ አባወራ" (ሰከንድ ጀንትለማን) ይሆናል ማለት ነው፡፡ ካመላ ጥቁር ኢሲያዊት አሜሪካዊት ናት፡፡ የብዙ ደም ቅልቅል መሆኗ እንደማይረብሻት፣ ራሷንም አንዲት ጠንካራ ሴት አሜሪካዊት አድርጋ እንደምትቆጥር ተናግራለች፡፡ ዳግና ሐሪስ የተጋቡት በ2014 ሳንታ ባርባራ ካሊፎርኒያ ውስጥ ነበር። ካመላ ኮሌጅ የተማረችው የብዙ ጥቁሮች ትምህርት ቤት በሆነው ሐዋርድ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡ ሐሪስ ለዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራቶች እጩ ለመሆን ሩጫ ጀምራ ኋላ ላይ በበቃኝ የወጣች ሴት ናት። በውድድሩ ወቅት አሁን የምርጫ ሸሪክ ካደረጓት ጆ ባይደን ጋር በተደጋጋሚ ተጋጭተዋል፣ ተከራክረዋል፣ አንድ ሁለት ተባብለዋል። በቀጥታ የክርክር ሥርጭት ወቅት ባይደንን አፋጣቸዋለች፡፡ የላይኛው ምክር ቤት አባል ሆና ካሊፎርኒያን ስትወክል በስብሰባዎች ላይ ትንፋሽ የሚያሳጥሩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ትታወቃለች፤ ሐሪስ፡፡ በካሊፎርኒያ ግዛት ዐቃቤ ሕግ ሆና ስትሰራ ስኬታማ አዳዲስ አሰራሮችን ዘርግታለች ተብላ ትሞካሻለች። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጆ ባይደን ሐሪስን የምርጫ ሸሪክ አድርገው ስለመምረጣቸው አስተያየት እንዲሰጡ በተጠየቁ ጊዜ፣ እንደመጣላቸው ስለሚናገሩ ይመስላል፣ "ባይደን አስቀያሚ ሴት ነው የመረጠው፤ ምን ነካው ባይደን? በምርጫው ተደንቂያለሁ" ብለው ነበር። ዛሬ ባይደንና ሐሪስ ትራምፕና ፔንስን አባረው ሥልጣኑን በይፋ ይረከባሉ፡፡ ሐሪስ በፊት የካሊፎርኒያ አቃቤ ሕግ ነበረች። በአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ካሊፎርኒያን በመወከል የተሳተፈችበት ዘመን ስኬታማ ነበር፤ ጠንካራ ሴት መሆኗን ያስመሰከረችበት ነበር፡፡ አሁን ያን ምክር ቤት በሊቀመንበርነት ትዘውረዋለች። ሐሪስ በፊት በሳንፍራንሲስኮም የአንድ ቀጠና አቃቢ ሕግ ሆና ሠርታለች። ሃሪስ ለባይደን በምርጫ ውስቀሳ ወቅት 2 ሚሊዮን ዶላር በበይነ መረብ ገንዘብ ማሰባሰብ ችላ ነበር፤ በግዛቷ ካሊፎርኒያ። ከጆርጅ ፍሎይድ የግፍ ግድያ ጋር በተያያዘ ደግሞ ሐሪስ በትላልቅ ሰልፎች የሕዝብ ትኩረት ያገኙ ንግግሮችን አድርጋ ነበር። የቀድሞዋ የካሊፎርኒያ ዐቃቤ ሕግ ሐሪስ በፀረ ዘረኝነት እንቅስቃሴ ውስጥ ድምጽ ስታሰማ ነው የኖረችው። ገና የ7 ዓመት ሕጻን ሳለች እናትና አባቷ የጸረ ዘረኝነት ሰልፎች ላይ ይዘዋት እየሄዱ መፈክር እንድታሰማ ያደርጓት ነበር፡፡ ያ አድጎ ዛሬ ለጥቁሮች አለኝታ ሆናለች፡፡ በተለይም ሐሪስ በአሜሪካ ውስጥ የፖሊስ ክንድ በጥቁሮች ላይ መበርታቱን በመቃወም የፖሊስ ማሻሻያ እንዲደረግ ስትቀሰቅስ ትታወቃለች። ካመላ ሐሪስ ዛሬ ታሪክ የምትጽፈው አንድ ብቻ አይደለም፡፡ የመጀመርያዋ ሴት፣ የመጀመርያዋ ጥቁር ሴት፣ የመጀመርያዋ ጥቁር እና ሴት እና ደቡብ ኢሲያዊት-አሜሪካዊት ሴት እያለ ይቀጥላል ዝርዝሩ፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንት ሥራው ምንድነው? በታሪክ እንደታየው የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሥራና ኃላፊነት ብዙ የሚባል አይደለም፡፡ ባርባራ ፔሪ የፕሬዝዳንታዊ ጥናት ተመራማሪ ናቸው፡፡ በቨርጂኒያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ፡፡ በአሜሪካ የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሥራ ምንድነው ሲባሉ በአጭሩ እንዲህ መልሰው ነበር፡- ‹‹የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሥራና ኃላፊነት የፕሬዝዳንቱን የልብ ትርታ ደረቱ ላይ ተለጥፎ እያዳመጡ መኖር ነው›› ባርባራ ማለት የፈለጉት ምንድነው? የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሚናና ጉልበት የሚገለጸው የፕሬዝዳንቱ ጤና ሲታወክ ወይም ደግሞ ሲሞት ብቻ ነው ማለታቸው ነው፡፡ በአሜሪካ ታሪክ ከ45 ፕሬዝዳንቶች ውስጥ ዘጠኙ የሥራ ዘመናቸውን ሳይጨርሱ ነጩን ቤተ መንግሥት ለቅቀዋል፡፡ ይህም ማለት ምክትሎቻቸው ትልቁን ሥልጣን ለመያዝና ለመሾፈር ዕድል አግኝተዋል ማለት ነው፡፡ ከዘጠኙ ታዲያ ስምንቱ በሞት ነው ከዋይት ሐውስ የወጡት፡፡ ባይደን 78 ዓመታቸው ነው፡፡ ሐሪስ በተጠንቀቅ መሆን አለባት ማለት ነው፡፡ አይበለውና አይቀሬው ሞት ቢመጣ የዓለም ትልቁ ሥልጣን ካመላ ሐሪስ እጅ ላይ ይወድቃል፡፡ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ምክትላቸው እንዲሆኑ የሚመርጧቸው ሰዎች እነሱ የሌላቸውን የሚያሟሉ እንዲሆኑ ይሻሉ፡፡ ይሄን ነገር ጂሚ ካርተር ናቸው በ1970ዎቹ የጀመሩት ይባላል፡፡ ጂሚ የጆርጂያ ገዥ ነበሩ፡፡ ፖለቲካውን ብዙም አያውቁትም ነበር፡፡ ዋሺንግተን ዲሲ ትርቃቸው ነበር፤ ለዓይንም ለልብም፡፡ ሲያሸንፉ ጊዜ ታዲያ ዎልተር ሞንዳሌ የሚባሉ ሴናተርን ምክትላቸው አደረጉ፡፡ ዋልተር የዲሲን ፖለቲካ ቀረጣጥፈው የበሉ ሰው ነበሩ፡፡ ምን ለማለት ነው፤ ፕሬዝዳንቶችና ምክትሎቻቸው በብዙ ነገር መለያየት የርዕዮተ ዓለምና አካባቢያዊ ሚዛንን ለማስጠበቅ ይረዳል፡፡ ለምሳሌ ኦባማ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ብዙም የካፒቶል ሒልን ፖለቲካ አያውቁም ነበር፡፡ ጆ ባይደን የ35 ዓመት የፖለቲካ ልምድ የነበራቸው ሴናተር ነበሩ፡፡ ምክትላቸው አደረጓቸው፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ይበልጥ ለመሳብ ኢቫንጀሊካል አጥባቂ ክርስቲያን ተከታይ የሆኑትን ማይክ ፔንስን አመጡ፡፡ ጆ ባይደን ደግሞ ጥቁሮችንና ሴቶችን ወደፊት ማምጣት ነበረባቸው፡፡ ደጋፊዎቻቸው ይህን እንዲያደርጉ ይጠብቁባቸዋል፡፡ በዚያ ላይ ከዕድሜያቸው ጋር ተያይዞ የሚነሳውን ቅሬታ በወጣቷ ካመላ ሐሪስ ለማካካስ ሞክረዋል፡፡ ስለዚህ ሐሪስ ለጆ ባይደን የጾታ፣ የቀለምና የዕድሜ ሚዛን አስጠባቂ ናት ማለት እንችላለን፡፡ ሌላው ሐሪስን ከምክትል ፕሬዝዳንቶች ፍዝ ሚና የተለየ ሚና እንዲኖራቸው የሚያደርጋት በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ያለው የቁጥር መመጣጠን ነው፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንቶች 100 አባላት ባሉት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ ሊቀመንበር ሆነው ስብሰባ ይመራሉ፡፡ ዘንድሮ ይህ ሚና መዶሻ መያዝ ብቻ አይሆንም፡፡ ወሳኙ ድምጽ የሚመጣው ከካመላ ሐሪስ ነው፡፡ ምክንያቱም በቁጥር ዲሞክራቶች 50፣ ሪፐብሊካኖችም 50 በመሆናቸው ነው፡፡ የመለያ የፍጹም ቅጣት ምቱን የሚመቱት ካሜላ ሐሪስ ናቸው፡፡ ካመላ ሐሪስ የት ነው የሚኖሩት? ጆ ባይደን ነጩ ቤተ መንግሥት ቢሮም መኝታም ይሆናቸዋል፡፡ ለመሆኑ ምክትላቸው ካመላ ሐሪስ የት ነው የሚኖሩት? ሐሪስና ባለቤታቸው ደግ ሌላ ቦታ ነው የሚኖሩት፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በተሰራ እጅግ ግዙፍና ውብ ቤት ውስጥ ነው መኖርያቸው የሚሆነው፡፡ ቤቱ የሚገኘው በሰሜን ምዕራብ ዋሺንግተን ሲሆን የአሜሪካ የናቫል አብዘርቫቶሪ ግቢ ውስጥ ነው የሚገኘው፡፡ ይሄ ግቢ ከዋይት ሐውስ ብዙም አይርቅም፡፡ የሐሪስ ቢሮ ደግሞ ዋይት ሐውስ ውስጥ ነው፡፡ ባለቤታቸው ሚስተር ዳግ የሚያስተምሩት በጆርጅታውን ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ቤት ነው፡፡ ጠበቃም ናቸው፡፡ ስለዚህ ለባልና ሚስቱ አዲሱ መኖርያ ቤታቸው ለሥራም ቅርብ ሆነ ማለት አይደል? ባልና ሚስቱ ልጆቻቸውን ይዘው ወዲያ ወዲህ ማለት ሲፈልጉ ኤይርፎርስ-2 እና ቦይንግ 757 በተጠንቀቅ ሁልጊዜም ይጠብቃቸዋል፡፡ 24 ሰዓት ሐሪስንና ባለቤታቸውን የሚጠብቅ ደኅንነት ለሰከንድ ዐይኑን አይጨፍንም፡፡ ሐሪስ እንደ ትራምፕ ጎልፍ የሚወዱ አይደሉም፡፡ ምግብ ማብሰል ግን ነፍሳቸው ነው፡፡ ምናልባት የጥቁር ነገር ሆኖ ሊሆን ይችላል ነገር ቀለል ማድረግ ይወዳሉ ይባላል፡፡ ጂንስና ኮንቨርስ ሸራ ጫማን ከታኮ ጫማ በበለጠ ታዘወትራለች ሐሪስ፡፡ እስከዛሬ ሦስት መጽሐፎችን ለኅመት ያበቃች ሲሆን አንዱ የልጆች መጽሐፍ ነው፡፡ ‹እናቴ በዚያ ዘመን ስትወልደኝ እዚህ ትደርሳለች ብላ አስባ የምታውቅ አይመስለኝም› የምትለው ካመላ ሐሪስ ምናልባት የመጀመርያዋ የአሜሪካ ሴት ፕሬዝዳንት ሆና ሌላ ታሪክ ትጽፍ ይሆን? ይህ እንዲሆን ደግሞ 4 ወይም 8 ዓመት መጠበቅ ላይኖርባት ይችላል፡፡ አይበለውና! ቀጣይዋ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ ማን ናቸው?
49930435
https://www.bbc.com/amharic/49930435
"የረሃብ አድማን የመረጥነው ከራሳችን የምንጀምረው ተቃውሞ ስለሆነ ነው" አቶ ገረሱ ገሳ
መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ፣ አንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲን ጨምሮ 70 የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫና ፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን በመቃወም የፊታችን ጥቅምት 5 እና 6 የረሀብ አድማ ለመምታት እንዳሰቡ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ ሰብሳቢ እና የ 70ዎቹ ፓርቲዎች አስተባባሪ ኮሚቴ ጸሀፊ አቶ ገረሱ ገሳ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቅርቡ በሰጣችሁት መግለጫ ላይ ለሁለት ቀንየረሃብ አድማ እናደርጋለን ብላችኋል። የረሃብ አድማ ለማድረግ የወሰናችሁት ለምንድን ነው? አቶ ገረሱ ገሳ፡ የረሃብ አድማውን ለማድረግ የተነሳንበት ምክንያት በምርጫና በፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ የተነሳ ነው። በአዋጁ ላይ ለመንግሥት፣ ለምርጫ ቦርድም አዋጁ ትክክለኛ ያልሆነና የሚያሰራ ስላይደለ እንዲሁም የፖለቲካ ስነ ምህዳሩን የሚያጠብ ስለሆነ፣ ተስተካክሎ መውጣት እንዳለበት በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበናል። ከዚህ በፊት ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከአንድም ሁለት ጊዜ የአዋጁ ረቂቅ ቀርቦ ተወያይተውበት ነበረ። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች • "ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ነገር ግን ፓርቲዎቹ የተወያዩበት ረቂቅ ተቀይሮ ሌላ ረቂቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ነው የፀደቀው። ስለዚህ ይኼ በአጠቃላይ በፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ማታለልም ጭምር ስለሆነ ይህንን በመቃወም ነው። ሕጉ እንዳይፀድቅ አስቀድመን ተቃውመናል። ለተለያዩ መንግሥታዊ አካላት አሳውቀናል። ግን ተቀባይነት አጥቶ አዋጁ ፀድቋል። አሁን ደግሞ የምንቃወመው አዋጁ ሥራ ላይ እንዳይውል ነው። ሙሉ አዋጁን ነው የምትቃወሙት ወይስ ለይታችሁ በመነጠል የምትቃወሟቸው አንቀጾች አሉ? አቶ ገረሱ ገሳ፡ አዋጁ ላይ የምንቃወማቸው በርካታ አንቀጾች አሉ። አሁን እኛ የምናስተባብረው የፖለቲካ ፓርቲ በአንድ ላይ ከ30 በላይ አንቀጾች ላይ፣ መሰረዝ፣ መሻሻል ያለባቸው አንቀጾችን እና ማስተካከያ መደረግ ያለባቸውን አንቀጾች ለይተን በዝርዝር ከነዝርዝር ሀሳቡ አቅርበናል። ለምርጫ ቦርድ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለሕግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ለፓርላማ አፈ ጉባዔ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩም፣ ለሀገሪቱ ፕሬዝደንትም፣ ለፌዴሬሽን አፈ ጉባዔ ጭምር ዝርዝሩን በሙሉ አቅርበናል። ሕጉ ላይ ያለውን እንከንና ችግር ማለት ነው። ያንን ሁሉ አድርገን የሚሰማን አካል ጠፋ። ከእኛ ከፖለቲካ ፓርቲዎች በተጨማሪ በተለያዩ አካላት በአዋጁ ላይ የቀረቡ ከ90 ባላነሱ አንቀጾች ላይ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማሻሻያ ጥያቄ ቀርቧል። ይህንን ሁሉ እንከን ይዞ ነው እንግዲህ አዋጁ የፀደቀው። ስለዚህ አዋጁ ላይ የማያሰሩ፣ የፖለቲካ ስነ ምህዳሩን የሚያጠቡ፣ የዜጎችን የመደራጀት መብት የሚገድቡ፣ እንዲሁም የመምረጥና የመመረጥ መብትን የሚያሳጡ፣ አንቀጾች ስላሉ እነዚህ አንቀጾች እንዲሻሻሉና እንዲቀየሩ ነው ተቃውሟችን። ለምን የረሃብ አድማን መረጣችሁ? አቶ ገረሱ ገሳ፡ የረሃብ አድማን የመረጥነው ከራሳችን የምንጀምረው ተቃውሞ ስለሆነ ነው። ከራሳችን ከአስተባባሪ ኮሚቴዎቹና፣ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ከራሳችን የሚጀምር ተቃውሞ ስለሆነ ነው። የረሃብ አድማው ላይ ጥሪ ያደረግነውም በመጀመሪያ ደረጃ ለሁሉም የፖለቲካ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም በዚህ ተቃውሞ ለተሳተፉ 70 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ አባላትና አመራሮች ነው። ከዚያ ውጪ ደግሞ ፈቃደኛ የሆነ የሕብረተሰብ አካል ተቃውሞውን መቀላቀል ይችላል። ስለዚህ ከራሳችን የምንጀምረው ተቃውሞ ስለሆነ ነው። መቼ ነው አድማውን ማካሄድ ያሰባችሁት? አቶ ገረሱ ገሳ፡ ጥቅምት አምስት እና ስድስት። ግን አንድ የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ አለ። ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ በመስከረም ወር ውስጥ ከአንድም ሁለት ሶስት የሥራ ቀናት አሉት። በእነዚህ ቀናት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ የሥራ ቀናት ማክሰኞና ሐሙስ እንደሆነ ይታወቃል፣ ስለዚህ በእነዚህ የስራ ቀናት ውስጥ አዋጁ ላይ ያለውን ችግር መልሶ የማያይና ይህንን የአስተባባሪ ኮሚቴ ጠርቶ የማያነጋግር ከሆነ ነው የረሃብ አድማውን የምናካሂደው። ነገር ግን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁን እንደገና ለማየትና ለማሻሻል የሚወስደው እርምጃ ካለ የረሃብ አድማው ላይቀጥል ይችላል ማለት ነው። ስለዚህ ይህንን አንድ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠናል። የረሃብ አድማው በመላ ሀገሪቱ ነው የሚካሄደው? ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሳተፋሉ? ለምን ያህል ሰዓትስ ይቆያል? አቶ ገረሱ ገሳ፡ የረሃብ አድማው በአዲስ አበባ ደረጃ፣ የአስተባባሪ ኮሚቴውና በሰባዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የታቀፉት አመራሮችና ተወካዮች በአንድ ቦታ ተሰብስበን ነው የረሃብ አድማውን የምናደርገው። በክልል ደረጃ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በያሉበት፣ በተደራጁበት አካባቢ ሆነው አመራሮቻቸው፣ ደጋፊዎቻቸውና አባሎቸቻቸው በረሃብ አድማው ይሳተፋሉ ማለት ነው። ከዚያ ውጪ በረሃብ አድማው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ዜጋ በየስራውም ቦታ በየቤቱም ሆኖ የረሃብ አድማውን መቀላቀል ይችላል። ይህ ማለት ለዲሞክራሲ፣ ለሰብዓዊ መብት፣ ለነፃነት፣ ለእኩልነት የሚደረግ፣ ለእኛም ለህዝብም የሚደረግ ትግል መስዋዕትነት ስለሆነ ማንኛውም ዜጋ የረሃብ አድማውን በተመቸው ስፍራ ሊቀላቀለን ይችላል። ለምሳሌ አዲስ አበባ የት ነው የረሃብ አድማው የሚካሄደው? አቶ ገረሱ ገሳ፡ በዋናነት ዋና አስተባባሪው የረሃብ አድማውን የሚያደርገው አዲስ አበባ ነው፤ ቦታውን ግን ከመስከረም 27 በኋላ ነው ይፋ የምናደርገው። ለ48 ሰዓታት የሚቆይ የረሃብ አድማ ነው የሚሆነው? አቶ ገረሱ ገሳ፡ አንዳንድ ታሳቢ የሆኑ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ በጤና እክል ምክንያት መድሃኒት በመውሰድ ላይ ያሉ፣ ምግብ በተወሰነ ሰዓት መመገብ ያለባቸው አመራሮችና ተወካዮች ሊኖሩ ይችላሉ፤ እነዚህ አካላት በዚህ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉበት ሁኔታ የተገደበ ነው። በተገደበና በተመጠነ መልኩ ነው የሚሳተፉት። ከዚያ ውጪ ጤናማ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ በሐኪም ልዩ ትዕዛዝ የሌላቸው 48 ሰዓት ከቻሉ ደግሞ መቀጠልም ይችላሉ። ውሃስ መጠጣት ይቻላል? አቶ ገረሱ ገሳ፡ ዝርዝር ሁኔታውን ውሃና መድሃኒትን በሚመለከት መስከረም 27 እና ከዚያ በኋላ ይፋ እናደርጋለን። በአድማው ላይ 48 ሰዓት መቆየት ሳይችሉ ቀርተው ተዝለፍልፈው ቢወድቁ ለእንደዚህ ዓይነት ድንገተኛ አደጋዎች ምን ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል? አቶ ገረሱ ገሳ፡ ለእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ቅድመ ሁኔታዎች እየተሰሩ ነው ያሉት። ምንድን ነው የምናደርገው? ምን ዓይነት ባለሙያዎች እናዘጋጃለን? የሚለው እየተሰራ ነው ያለው። የሕክምና ባለሙያዎችን፣ አስፈላጊ የምክር ባለሙያዎችንም፣ እያዘጋጀን ነው ያለነው። ይኼጉዳይሰባዎቹም የፖለቲካ ፓርቲዎች የተስማማችሁበትነው? አቶ ገረሱ ገሳ፡ አዎ። የተስማማንበት ጉዳይ ነው። ስምምነቱ ግን አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ነፃነትን ይከለክላል ማለት አይደለም። እስከዚያ ድረስ 'አይ እኔ በዚህ ስምምነት መቀጠል ያስቸግረኛል' የሚል ካለ ነፃነቱ የተጠበቀ ነው። መጀመሪያ እኛ ሂደቱን ስንጀምር በ33 ፓርቲዎች ነው የጀመርነው። ከዚያ በኋላ ሌሎች ፓርቲዎች ተቃውሞው ትክክል ነው ብለው እያመኑ ሲመጡና ሲቀላቀሉ ነው ቁጥሩ ጨምሮ ሰባ የደረሰው። • ምርጫ ፡ የተቃዋሚዎችና የመንግሥት ወግ? • ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ለሚካሄደው ምርጫ 3.7 ቢሊዮን ብር ጠየቀ ስለዚህ በፈቃዳቸው መጥተው እንደተቀላቀሉን በፈቃዳቸው ደግሞ አንሳተፍም ካሉ የምናስገድድበት ሁኔታ የለም። መቼ ነበር በ33 ፓርቲዎች ተቃውሞውን የጀመራችሁት? አቶ ገረሱ ገሳ፡ ተቃውሞውን ከጀመርን ሶስት ወር አካባቢ ይሆነናል። እነማን ናቸው ፓርቲዎቹ ለምሳሌ ቢጠቅሱልኝ? አቶ ገረሱ ገሳ፡ እኔ ሰብሳቢ የሆንኩበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ፣ መኢአድ፣ ኦብኮ፣ የገዳ ስርኣት አራማጅ ፓርቲ፣ ከኦሮሚያ ክልል ወደ ስድስት ፓርቲዎች፣ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ፣ የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር፣ እነዚህና አሁን ስማቸውን ዘርዝሬ የማልጨርሳቸው ፓርቲዎች አሉ። ከውጪ ከመጡ ፓርቲዎች መካከል አስር ፓርቲዎች ከእኛ ጋር በምናደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ አሉ። የረሃብ አድማ ግን ምን ያሕል አዋጭ ነው ለፖለቲካ ትግላችሁ? አቶ ገረሱ ገሳ፡ የረሃብ አድማ ምን ያህል አዋጭ ነው? የሚለው ሕሊና ያለው አካል፣ ለሕዝብ ደንታ ያለው አካል፣ የሕዝብ ብሶት፣ ሮሮ፥ ጥያቄ፣ ሊሰማና ሊደመጥ ይገባል የሚል መንግሥታዊ ሥልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ካለ፣ ከረሃብ አድማ በላይ አስከፊና አስነዋሪ ተቃውሞ የለም። በጣም አስከፊ ተቃውሞ ነው። መስማት፣ማዳመጥ የሚችል አካል ካለ። አንድ ሰው ራሴን ለረሃብ አጋልጣለሁ ሲል እሞታለሁ ከሚል በምንም አይተናነስም። ስለዚህ ወደዚህ ተቃውሞ የሚገቡ አካላት ለምንድን ነው ወደዚህ ተቃውሞ የሚገቡት ማለትና መስማት የሚችል ባለስልጣን በሀገራችን ካለ፣ ዲሞክራት መሪ ካለ ይኼ ተቃውሞ መንግስት ሊሰማውና ሊያዳምጠው የሚገባው ተቃውሞ ነው። ነገር ግን መንግሥት ላይ ድንጋይ እንደመወርወር፣ ጥይት እንደመተኮስ ወይንም የሆነ ተቋም እንደማቃጠል፣ አስደንጋጭ ላይሆን ይችላል። አምባገነን መንግሥታት ጥይት ሲተኮስባቸው፣ ድንጋይ ሲወረወርባቸውና የሆነ የሚፈነዳ፣ የሚያቃጥል ነገር ሲመጣ ነው የሚደነግጡት። ለእንደዚህ ዓይነት ሌላ ተቃውሞ ጆሮም ግድም አይሰጡም። ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ካለ ግን ከጥይት ጩኸትና ከቦምብ ፍንዳታ በላይ ይህ ትክክለኛ ተቃውሞ ነው። ለዚህ ነው እኛ እንደተቃዋሚ ይህንን የረሃብ አድማ መጀመሪያ በራሳችን የምንጀምረው። በመቀጠልም ደረጃ በደረጃ የምንሄድነበት መሆኑን አስበን ነው የገባነው። ለረሃብ አድማው ምላሽ ካልተሰጣችሁ ምንድን ነው የምታደርጉት? አቶ ገረሱ ገሳ፡ በመላ ሀገሪቱ የተቃውሞ ፊርማ የማሰባሰብ እርምጃ ነው የምንሰራው። ከዚያ ጎን ለጎን ደግሞ ከተፈቀደልን በተለያዩ ስፍራዎች ሕዝባዊ ስብሰባዎች እንጠራለን። በእነዚህ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ተቃውሞ የምናካሂድበትና አደባባይ ወጥተን ሰላማዊ ሰልፍ የምናካሄድበትን ሂደት እንከተላለን። ይኼ ደረጃ በደረጃ የምንከተለው ነው።
news-50894806
https://www.bbc.com/amharic/news-50894806
ገብርኤል ንጋቱ፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ ቁልፍ ሰው
አዲስ አበባ ውስጥ ተወልደው ያደጉት አቶ ገብርኤል ንጋቱ በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ ግዙፍ ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ ከሚገኙ ጥቂት ኢትዮጵያዊን መካከል አንዱ ናቸው።
በአፍረካ አገራት ውስጥ በሚካሄዱ የምጣኔ ሃብትና የልማት ተግባራት ላይ ቁልፍ ድርሻ ባለው የአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ ወሳኝ ከሚባሉ የባንኩ ባለስልጣናት አንዱ በመሆን ከ20 ዓመታት በላይ በ32 የአፍሪካ አገራት ውስጥ አገልግለዋል። አቶ ገብርኤል ከአርባ ዓመታት በፊት ደርግ ወደ ስልጣን ላይ በወጣበት ጊዜ ነበር ከኢትዮጵያ ወጥተው ለአጭር ጊዜ አውሮፓ ውስጥ ከቆዩ በኋላ አሜሪካ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ኖረዋል። • ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ አሜሪካ ውስጥ በስደት መኖር ሲጀምሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ሁኔታ አስቸጋሪ እንደነበር የሚያስታውሱት አቶ ገብርኤል፤ መጀመሪያ ላይ አሜሪካ ውስጥ ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት እንደተቸገሩና ትምህርት ሳይጀምሩ ለተወሰነ ጊዜ መቆየታቸውን ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ሁኔታ ሲባባስ ሕጋዊ የመኖሪያ ሰነድ ማግኘት ስለቻሉ ትምህርት ጀመሩ። ካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ውስጥ የመጀመሪያ ዲግሪ በፕላኒንግ፣ ሁለተኛ ዲግሪን ደግሞ ከፒትስበርግ ዩኒቨርስቲ፣ ከዚያም በኋላ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም እንግሊዝ አገር ማንቺስትር ዩኒቨርስቲና ሌሎችም ቦታዎች ተምረዋል። የስደት ፈተናና ጥረት በንጉሡ የስልጣን ዘመን ማብቂያ ላይ ወደ አሜሪካ የመጡት አቶ ገብርኤል ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ አሜሪካ ስላልገቡ "በስደት ውስጥ ኑሮን ማሸነፍ ፈታኝ ነበር" ይላሉ። የመኖሪያ ፈቃድ እኪያገኙ ድረስም በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ማለፋቸውንና የሥራ ፈቃድ ስላልነበራቸው የጽዳት ሥራን ተደብቀው ይሰሩ እንደነበርም ያስታውሳሉ። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት የንጉሡ ወዳጅ የነበሩት አሜሪካኖች ደርግ ስልጣኑን ይዞ ይወስዳቸው የነበሩትን እርምጃዎች ከተመለከቱ በኋላ ግን ለኢትዮጵያዊያን የመኖሪያ ፈቃድ መስጠት ሲጀምሩ በነጻነት የመኖርና የመስራት እድልን አገኙ። "ኢትዮጵያዊ በተለይ ከአገሩ ሲወጣ ጠንካራ ነው" የሚሉት አቶ ገብርኤል ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚችሉትን ሁሉ እየሰሩ ለመማርና የተሻለ ህይወት ለመኖር መጣር ነበረባቸው። ቢሆንም ግን ዝቅ ያለ ሥራ በመስራት የዕለት ተዕለት ወጪን ሸፍኖ ለመማር ከባድ እንደነበር የሚገልጹት አቶ ገብርኤል፤ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተዳብለው በአንድ ላይ ቤት በመከራየት ከዚያም የተለያዩ ሥራዎችን በፈረቃ በመስራት ዛሬ ለደረሱበት ደረጃ ያበቃቸውን ትምህርት በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ሆነው መማር ጀመሩ። የወጣትነት ፈተናዎች በአፍላ የወጣትነት ዕድሜያቸው ከአገር የወጡት አቶ ገብርኤል ንጋቱ፤ መጀመሪያ ጣሊያን ለተወሰኑ ወራት መቆየታቸውንና ከዚያም ወደ አሜሪካ ሲሄዱም ከቤተሰብ ቁጥጥር ነጻ መሆን ከእድሜ ጋር ተያይዞ የራሱ ፈተና አለው ይላሉ። ነጻነቱ እንዲሁም ቁጥጥር የማይደረግበት የተወሰነ ገንዘብ በእጅ መኖር ወደ ተለያዩ አላስፈላጊ ልማዶች ሊመሩ የሚችሉበት አጋጣሚዎች እንደነበሩና በዚያ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ራስን የመግዛት ጥንካሬ ያስፈልግ እንደነበር ያስታውሳሉ። • ዝነኞቹ ቮልስዋገኖችና ድንቅ ታሪኮቻቸው ነገር ግን የቤተሰባቸው አስተዳደግና በኃይማኖት ተቀርጸው እንዲያድጉ መደረጋቸው ከቤተሰብ ርቀው ባገኙት ነጻነት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይሄዱ እንዳደረጋቸውም ያምናሉ። አቶ ገብርኤል በወጣትነት ዘመናቸው ከትክክለኛው የሕይወት መስመር የሚያወጡ በርካታ ፈተናዎች የነበሩ ቢሆንም ወደዚያ ባለመሄዳቸው ለስኬት በቅተዋል። ነገር ግን ጥቂት የማይባሉ ጓደኞቻቸው ለፈተናዎቹ ተሸንፈው "ሕይወታቸው መመሳቀሉንና ለተለያዩ ችግሮች" መዳረጋቸውን ያስታውሳሉ። የአፍሪካ ልማት ባንክ አቶ ገብርኤል ጋብቻ መስርተው ልጆች ሲወልዱ ወደ ወጡበት አህጉር ተመልሰው ልጆቻቸውን የማሳደግ ፍላጎት እንዳደረባቸው፤ ለዚህም ከባለቤታቸው ጋር ተስማምተው ሥራ ሲያፈላልጉ፤ አፍሪካ ልማት ባንክ አይቮሪኮስት ውስጥ ዩኒሴፍ ደግሞ ኬንያ ውስጥ ላሏቸው ክፍት ቦታዎች ላወጡት ሥራ ተወዳደሩ። ሁለቱም ተቋማት አቶ ገብርኤል ለተወዳደሩበት ቦታ ከሌሎች ልቀው መገኘታቸውን በማመልከት አንዳቸው አንዳቸውን ተከትለው ሥራ እንዲጀምሩ ጋበዟቸው። አቶ ገብርኤልም ምርጫቸው አፍሪካ ልማት ባንክ ላይ አርፎ ቤተሰባቸውን ይዘው ከአሜሪካ ወደ ምዕራብ አፍሪካ አቀኑ። የአፍርካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአህጉሪቱ አገራት በባለቤትነት የሚያስተዳደሩት ሲሆን ከአፍሪካ ውጪ ደግሞ በተለያዩ አህጉራት የሚገኙ አገራትም በባንኩ ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ አላቸው። • "በጎጃም ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስጊድ 3ሺ ብር ረድታለች' ተባልኩኝ" ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አቶ ገብርኤል በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ ሥራ ሲጀምሩ ከዝቅተኛው የሙያተኛ ደረጃ የተነሱ ቢሆንም በየሁለትና በየሦስት ዓመቱ እየተወዳደሩ በማደግ በድርጅቱ ውስጥ ባሉ ኃላፊነት ቦታዎች ውስጥ አልፈው ዋና ዳይሬክተር ከሚባለው ከፍተኛ ቦታ ላይ ለመድረስ ችለዋል። አቶ ገብርኤል እንደሚሉት ባንኩ እርሳቸው በመሩት መልሶ የማዋቀር ሥራ በአምስት ቀጠናዎች ተከፋፍሎ እንዲሰራ የሚያስችለውን ሥራ አከናውነዋል። ከዘዚህ በኋላም አቶ ገብርኤል በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ ካሉ አምስት የዋና ዳይሬክተርነት ቦታዎች ውስጥ አንዱን በመምራት በባንኩ ታሪክ የመጀመሪያው ዋና ዳይሬክተር ለመሆን ከመብቃታቸው ባሻገር ለዚህ የኃላፊነት ቦታም በመብቃት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ናቸው። አቶ ገብርኤል በአፍሪካ ልማት ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ዋና ዳይሬክተር በመሆን ለበርካታ ዓመታት ከማገልገላቸው በፊት በሰላሳ ሁለት አገራት ውስጥ የሚሰራውን የባንኩን የመዋዕለ ነዋይ አስተዳደር ክፍልን በማቋቋምና ለበርካታ ዓመታት በመምራትም ጉልህ አሻራቸውን እንዳኖሩ ይነገርላቸዋል። ከባንኩ ዋና ዋና ክፍሎች አንዱ የሆነውና መቀመጫውን ኬንያ ውስጥ ያደረገውን የ13 አገራትን የሚከታተለው የባንኩን የምሥራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍን የመሰረቱት እንዲሁም ለረጅም ዓመታት የመሩት አቶ ገብርኤል ንጋቱ ናቸው። ባንኩ የአገራትን ሕዝብና የምጣኔ ሃብት ዕቅድን መሰረት በማድረግ የሚያማክር ሲሆን አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜም በብድርም ሆነ በዕርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ እንዲገኝና ዕቅዳቸው በተገቢው ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው። ፈተናና ስኬት አቶ ገብርኤል በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ የቆዩበት ጊዜ በስኬት ብቻ የተሞላ አልነበረም፤ የዛሬ 12 ዓመት ገደማ የዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ በተከሰተበት ጊዜ በአፍሪካ ሃብታም ከሚባሉ ጥቂት አገራት መካከል አንዷ የነበረችው ቦትስዋናን ለመደገፍ የተደረገው ጥረት እጅጉን በሥራ ሕይወታቸው ፈታኙ ነበር። እጅግ ውድ የነበረውና ቦትስዋና በስፋት የምትታወቅበት የአልማዝ ምርት ገበያ በወቅቱ በመውደቁ አገሪቱ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ በመውደቋ የአገሪቱ መንግሥት የአፍሪካ ልማት ባንክ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጥሪ አቀረበ። ለዚህ ሥራ ደግሞ በባንኩ ውስጥ ቀዳሚ ተመራጭ ሆነው የቀረቡት አቶ ገብርኤል ንጋቱ ነበሩ። ኃላፊነቱ እንደተሰጣቸው ለሥራው የሚያስፈልጋቸውን ቡድን አዋቅረው በመምራት ወደ ቦትስዋና ሄደው ድርድር በማድረግና ውድቀት አፋፍ ላይ የነበረውን የቦትስዋናን ኢኮኖሚ ለመታደግ የሚያስፈልጉ ፕሮጀክቶችን የመቅረጽ ሥራን ጀመሩ። • ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ? በወቅቱ አገሪቱ የገጠማት የኢኮኖሚ ቀውስ እጅግ አሳሳቢ ስለነበረ የሚያስፈልጋትን ድጋፍ ለይቶ በማወቅና መደረግ ያለባቸውን የማሻሻያ ዕርምጃዎች በማቅረብ በቶሎ እርምጃ ካልተወሰደ ፖለቲካዊ ቀውስ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ስለነበረ፤ በአቶ ገብርኤል የሚመራው ቡድን ለአንድ ወር ያህል ለ24 ሰዓታት ያለዕረፍት በመስራት ጥረት አድርጓል። ፕሮጀክት በማዘጋጀት፣ የፖሊሲ ሃሳቦችን በመቅረጽና ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር በመደራደር ቡድናቸው በቀንና በሌሊት ፈረቃ ተከፍሎ መፍትሄዎችን ለማምጣት ጥረት ማድረጋቸውን የሚናገሩት አቶ ገብርኤል "ሥራው እጅግ አስጨናቂና ውጥረት የተሞላበት ነበር" ይላሉ። ይህ ለአንድ ወር የተሰራው ሥራ በመጨረሻም የቦትስዋና መንግሥት ማድረግ የሚገባውን የማሻሻያ ሃሳቦች ለባንኩ ቦርድ ቀርቦ ከስምምነት ላይ በመደረሱ በአፍሪካ ልማት ባንክ ታሪክ በወቅቱ ለአንድ ፕሮጀክት የተሰጠ ከፍተኛው ገንዘብ ለመሆን ችሏል። ይህም ለቦትስዋና የተፈቀደ ከፍተኛው ብድር 1.5 ቢሊየን ዶላር ሲሆን አቶ ገብርኤልም ሐሳቦችን ከመቅረጽ አንስቶ ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር የሚደረገውን ድርድር በመምራት ወሳኝ ሚና ነበራቸው። ይህም በአቶ ገብርኤል የአፍሪካ ልማት ባንክ የሥራ ህይወታቸው ውስጥ "እጅግ የተጨነቅኩበትና ለስኬቱም አጥብቄ የጸለይኩበት ጉዳይ ነበር" ሲሉ ያስታውሱታል። በአፍሪካ ጠንካራ ኢኮኖሚ ካላቸው አገራት አንዷ የሆነችው ቦትስዋናም ከአሳሳቢው የውድቀት አፋፍ ተመልሳ አሁን የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲኖራት በማድረጋቸው አድናቆትን አግኝተዋል። ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ባንክ አቶ ገብርኤል ንጋቱ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በተያያዘ አገራቸው ኢትዮጵያን በሚመለከት ከፍ ያለ ፈተና ገጥሟቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ወቅቱ አወዛጋቢው የ1997 ዓ.ም ብሔራዊ ምርጫን ተከትሎ "በአገሪቱ ቀውስና አለመረጋጋት ያጋጠመበት ነበር" ይላሉ። በአገሪቱ በተከሰቱ ግድያዎች ሳቢያ የዓለም የገንዘብ ተቋማት ለኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ እንዳይሰጡ ግፊት በሚደረግበት ጊዜ ውሳኔው መንግሥትን ብቻ ሳይሆን ሕዝቡንም የሚጎዳ በመሆኑ ሌላ አማራጭ እንዲፈልግ ጥረት አድርገዋል። በዚህም አቶ ገብርኤል የሚሰጠው ድጋፍ ወደ መንግሥት እጅ ከመግባት ይልቅ ቁጥጥር እየተደረገበት ለሕዝቡ የሚቀርቡ 'መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለመጠበቅ' የሚያስችል ፕሮግራም በመንደፍ አሁን ድረስ የዘለቀ አማራጭን አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም አቶ ገብርኤል በባንኩ ድጋፍ ኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄዱ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ አቅርቦት ከጎረቤት አገራት ጋር ለማገናኘት እንዲሁም የመንገድ ግንባታዎችን በተመለከቱ ወሳኝ ፕሮጀክቶች ውስጥ ሚና ነበራቸው። • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ምንም እንኳን አቶ ገብርኤል ከነበሩበት ኃላፊነት አንጻር ሁሉም የአፍሪካ አገራት አገራቸው እንደሆኑ ቢናገሩም ኢትዮጵያን በሚመለከት ግን ልባቸው የሚደላባቸው አጋጣሚዎች እንዳሉ አይሸሽጉም። በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ የአገራቸውን ጥቅም የሚነካ ነገር ካለ በዝምታ አያልፉም ይባልላቸዋል። ባልደረቦቻቸውም ይህንን ስለሚያውቁ "ይህንን ገብርኤል አይቀበለውም" በማለት አስቀድመው እንደሚረዱ ገልጸው፤ ነገር ግን ይህ ድርጊታቸው ኢትዮጵያ ከሌሎች በተለየ እንድትጠቀም ሳይሆን "የኢትዮጵያ እንዳትበደልና የኢትዮጵያዊያን መብት እንዳይነካ የቻልኩትን ከማድረግ አንጻር ብቻ ነው" ይላሉ። ነገር ግን ከሌሎች ጋር ከሚያደርጉት በተለየ ለአገራቸው ባለስልጣናት ጠቃሚ መረጃዎችንና ምክሮችን በመስጠት አገራቸውና ሕዝቡ እንዲጠቀም ከሙያቸው ሥነ ምግባር ሳይወጡ ካላቸው ኃላፊነት አንጻር የሚችሉትን ሁሉ ባገኙት አጋጣሚ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ይናገራሉ። ኢትዮጵያዊያን በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ብትሆንም ዜጎቿ በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ተቋማት ውስጥ ያለቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑ "የሚያሳዝን ነው" ይላሉ አቶ ገብርኤል። እንደምሳሌም የምዕራብ አፍሪካ አገር የሆነችው ጋምቢያን ያነሳሉ፤ ጋምቢያ በጣም ትንሽ የሕዝብ ቁጥር ቢኖራትም በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ በሚሰሩ ዜጎቿ ቁጥር ኢትዮጵያን በብዙ ዕጥፍ ትበልጣለች ይላሉ። ለዚህም ከኃይለ ሥላሴ ሥርዓት መውደቅ በኋላ በነበሩት ጊዜያት ወደ ውጪ አገራት ሄዶ ለመማር የነበረው ዕድል መዘጋቱና ወደ ውጪ የሄዱትም ተምረው በትልልቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ከመግባት ይልቅ፤ የዕለት ኑሮን ለማሸነፍና ቤተሰብ ለመርዳት በተለያዩ ሥራዎች ላይ በመሰማራታቸው እንደሆነ ያስባሉ። ወደ ተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ለመግባት በዋናነት የሚያስፈልገው ብቃት መሆኑን የሚጠቅሱት አቶ ገብርኤል ከዚህ ባሻገር ግን የመንግሥት ድጋፍ ወሳኝ ነው። መንግሥት ዜጎቹ ለተወዳደሩበት ተቋማት ባሉት የግንኙነት መስመሮች ሁሉ ድጋፍ ከሰጠና ተጽዕኖ መፍጠር ከቻለ ተቀባይነት ለማግኘት ወሳኝ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ከዚህ አንጻር ግን ኢትዮጵያዊያን ብቃቱ ኖሯቸው ከመንግሥታቸው ድጋፍ ለማግኘት ስለሚቸገሩ የአገራቸውን ድጋፍ በሚያገኙ ሌሎች ተወዳዳሪዎች በመበለጥ ዕድሉን ያጣሉ። • ከ20 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? "ላለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት እንዲዚህ አይነቱን ድጋፍ ለዜጎቻቸው ለመስጠት ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻ በቂ አልነበረም፤ ነገሮች በፓርቲ አባልነት የሚወሰኑ ሆነው ቆይተዋል" የሚሉት አቶ ገብርኤል ይህ ግን አሁን እንደሚቀየር ያምናሉ። ብዙ ኢትዮጵያዊያን ተምረውና ሰርተው ውጤታማ መሆንን የሚያስቡት በአገራቸው ውስጥ ነው። "ከዚህ ወጥተን ራሳችንን በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንደምንችልና በብቃታችን የሚገባንንም ለማግኘት አስከመጨረሻው መጠየቅና ገፍቶ መሄድ መልመድ አለብን" ብለዋል። ለዚህ ደግሞ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሰሩ የተወሰኑ ኢትዮጵያዊያን በሥራቸው ብቁና የተመሰከረላቸው ስለሆኑ በችሎታ በኩል ኢትዮጵያዊያን ደፍረው መውጣት ከቻሉ ከማንም የሚያንሱበት የሥራ መስክ የለም ብለው ያምናሉ። ለዚህ ደግሞ ማበረታታትና ድጋፍ አስፈላጊ ነው። ከዚህ አንጻር ለዜጎቻቸው ድጋፍ የሚያደርጉ አገራትን ሲያነሱ ሴኔጋልን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ፤ በዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ለመስራት ለሚያመለክቱና ለሚሰሩ ዜጎቻቸው ድጋፍ የሚሰጥ ጽህፈት ቤት በአገሪቱ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ውስጥ አለ። ከዚህ በሻገርም አንድ ሴኔጋላዊ በየትኛውም ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ለመቀጠር አመልክቶ ድጋፍ ካስፈለገው ፕሬዝዳንቱ ሳይቀሩ ለተቋማቱ ኃላፊዎች በመደወል ዕድሉ እንዲሰጣቸው እስከመጠየቅ የሚደርስ ድጋፍ ያደርጋሉ። ይህም የሚሆነው በፖለቲካ አመለካከት፣ በዕምነት ወይም በብሔር ሳይሆን ዜጋ በመሆን የሚሰጥ ድጋፍ ነው ይላሉ አቶ ገብርኤል። ስንብት ለ35 ዓመታት ከዘለቀው ትዳራቸው የሦስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ገብርኤል ንጋቱ፤ ከሃያ ዓመታት በላይ በአፍሪካ ልማት ባንክ ውስጥ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ ቆይተው አክብሮትና ዝናን አትርፈዋል። የአቶ ገብርኤል ዕውቅና ባገለገሉበት ድርጅት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎችና ከፍተኛ ባለስልጣናት ዘንድም "ንጋቱ" እየተባሉ አክብሮትን አግኝተዋል። በዚህ ዓመት በጡረታ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ሲሰናበቱ አቶ ገብርኤል በተለያዩ አገራት መሪዎች እየተጋበዙ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፤ ድርጅታቸውም በአገልግሎት ዘመናቸው ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በክብር ነበር የሸኛቸው። "በቀጥታ ለአገሬና ለሕዝቧ ሰርቼ አላውቅም" የሚሉት አቶ ገብርኤል በውጪ አገር ለረጅም ዘመን ሰርተው ጡረታ ወጥተዋል። አሁን ባላቸው ዕውቀትና ልምድ አገራቸውን በሚጠቅሙ በተለያዩ መንገዶች ኢትዮጵያን ለማገልገል ፍላጎት እንዳላቸው ይናገራሉ። በዳያስፖራ ትረስት ፈንዱ ውስጥ የአማካሪ ምክር ቤት አባል ሲሆኑ፣ ከተወሰነ የዕረፍት ጊዜ በኋላ በተለያዩ መስኮች ላይ በመሰማራት አገራቸውንና ሕዝቡ የሚጠቅሙ ሥራዎችን ለማከናወን ዕቅድ አላቸው።
news-53148771
https://www.bbc.com/amharic/news-53148771
ታንዛኒያ፡ ኮሮናቫይረስንና ኢምፔሪያሊዝምን 'እንደመስሳለን' የሚሉት አወዛጋቢው ጆን ማጉፉሊ
የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ማን ይመስላቸዋል ከተባለ የብራዚሉ ጃይ ቦልሶናሮ፣ ወይም የፊሊፒንሱ ዲቶርቴ ወይም በትንሽ በትንሹ የአሜሪካው ትራምፕ?
ሁሉንም የሚያመሳስላቸው አወዛጋቢ መሪዎች መሆናቸው ነው። እንደመጣላቸው ይናገራሉ? ለጋዜጠኛ ይመቻሉ፤ የዜና ርዕስ ይሆናሉ፣ ተቺዎቻቸውን ከፍ ዝቅ አድርገው ይሳደባሉ። ጆን ማጉፉሊ ኢምፔሪያሊስቶችን መስደብ ቁርስ፣ ምሳ እራታቸው ነው። ኮሮናቫይረስ ከመጣ ወዲህ ደግሞ ሰውየው በዓለም ሚዲያ ጭምር ትኩረት አግኝተዋል። የሚናገሩት ከሳይንስ ጋር ይጣረሳል። "ኮሮናቫይረስ የሚባልን ነገር ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጸሎት ድምጥማጡን አጥፍተነዋል" ብለው ነበር። አሁን አሁን ማጉፉሊ ምንም ቢሉ ሕዝባቸው መገረም የተወ ይመስላል። ለነገሩ እርሳቸው ፕሬዝዳንት ከሆኑ እንደቀልድ 5 ዓመታት ሆናቸው። ራሳቸውን ብርቱ አፍሪካዊ ብሔርተኛ፣ ታንዛኒያዊ አርበኛና ጥብቅ የካቶሊክ አማኝ አድርገው ነው የሚያስቀምጡት። የውጭ ኃይሎችን እከሌ ከእከሌ ሳይለዩ የምሥራቅ አፍሪካ በዝባዦች ይሏቸዋል። "ታላቁ የታንዛኒያ ሕዝብ ሆይ! እንድትረዳልኝ የምፈልገው ታላቅ ፕሬዝዳንት፣ የማይናወጽ ፕሬዝዳንት ባለቤት እንደሆንክ ነው። እኔ መሪህ ማንንም አልፈራም፤ ለማንም አልንበረከክም" ብለው ነበር በመጋቢት 2018 (እ.ኤ.አ)። ማጉፉሊ የጤና ስጋት ባለበት በዚህ ወቅት ምዕመናን በአንድ ተሰብስበው አምልኮ እንዲያከናውኑ ያበረታታሉ ነጮችን በጥርጣሬ ማየት በመጪው ጥቅምት በመላው ታንዛኒያ ምርጫ ይካሄዳል። ማጉፉሊ ይኼ ጭራሽ የሚያሳስባቸው ጉዳይ አይደለም። መንበራቸው ተደላድሏል። ሁለተኛ ዙር አገራቸውን ይመራሉ ተብሎ ታምኗል። ይህ ማንም የሚጠራጠረው ጉዳይ አይመስልም። ምክንያቱም በርካታ ታንዛኒያዊያን መሪያቸው የአገራቸውን ጥቅም እያስከበሩላቸው የሚገኙ አርበኛ አድርገው ነው የሚመለከቷቸው። ለምሳሌ የማጉፉሊ አንዱ ፈተና ሆኖ የቆየው "ባሪክ ጎልድ ኮርፖሬሽን" የተሰኘ የካናዳ የማዕድን ድርጅት ነበር። ማጉፉሊ ድንገት ተነሱና የዚህ ማዕድን ቆፋሪ ድርጅት ከሦስት የወርቅ ማዕድን ቁፋሮዎች የሚያገኘው 70 ከመቶ ድርሻ ለታንዛኒያ መንግሥት ገቢ ካላደረገ ተጭበርብረናል አሉ። የኩባንያውን ኃላፊዎች "ያን ካላደረጋችሁ ታንዛኒያን እየበዘበዛችኋት እንደሆነ ነው የምቆጥረው" አሉ። ኩባንያው መጀመሪያ "እንዴት ተደርጎ፣ ሞቼ ነው ኖሬ!" አለ። በኋላ ግን ተለሳለሰ። ዘለግ ያለ ጊዜን ከወሰደ ድርድር በኋላ ድርጅቱና ማጉፉሊ ከስምምነት ደረሱ። መንግሥትም ከኮርፖሬሽኑ ድርሻ 16 ከመቶ ለመውሰድ ተስማማ። ማጉፉሊ ድርድሩ በአንዲት ላምና በአንዲት ጥንቸል መካከል የተደረገ ነበር ሲሉ ተናገሩ። በእርግጥም የድርድሩ ውጤት ከዚህ በኋላ የውጭ ድርጅቶች ታንዛንያን በኢንቨስትመንት ስም መበዝበዝ እንደማይችሉ ጥቆማ የሰጠ ነበር። ማጉፉሊ ድርድሩ እስኪሰምር ድረስ የዚህን ድርጅት ምርቶች ወደ ውጭ እንዳይላኩ አግደው ቆይተው ነበር። የባሪክ ወርቅ ማዕድን ሥራ አስኪያጅ ማርክ ብሪስቶ ስምምነቱን ሲፈረሙ የማጉፉሊን እጅ ከጨበጡ በኋላ እንደተናገሩት "አሁን የተፈራረምነው ነገር የማዕድን ኢንዱስትሪውን ወደፊት የሚፈትን ነው" አሉ። ማጉፉሊ በተራቸው ተነስተው ምላሽ ሰጡ፤ "ለዚህ ስምምነት መሳካት ታላቁን አምላኬን አመሰግነዋለሁ።" ማጉፉሊ ከዚህ የማዕድን ኩባንያ ጋር ብቻ አይደለም ጠብ ውስጥ የገቡት። ከቻይና ጋር በተመሳሳይ ሁለት ስምምነቶችን ሰርዘዋል። አንዱ የታንዛኒያ የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር ነው። ይህ መስመር የንግድ መናኸሪያዋን ዳሬሰላምን ከዋና ከተማዋ ዶዶማ የሚወስድ 500 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ነበር። ሁለተኛው በምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ ወደብ የባጋሞዮ ግንባታ ሲሆን ይህ ቦታ በአንድ ወቅት የጀርመን የምሥራቅ አፍሪካ ቅኝ የነበረው ግዛት ዋና መናኸሪያ ነበር። ይህ ፕሮጀክት 10 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ስምምነት የተደረገበት ነበር። ማጉፉሊ ከእርሳቸው ቀድመው ፕሬዝዳንት የነበሩት ጃካያ ኪክዌቴ ይህ ከቻይና ጋር ፈርመውት የነበረውን የወደብ ግንባታ ስምምነት "እብደት" ብለውታል። "እንዲህ ዓይነት ስምምነት የሚቀበለው እብድ ሰው ብቻ ነው።" ያን ስምምነት የፈረመውን አስተዳደር "ስግብግቦች" እንዲሁም "ታንዛኒያን ማስቀደም ያልቻሉና አገሪቱን ያሽመደመዱ" ሲሉ ነው የጠሯቸው። ማጉፉሊ ዋንኛ የታንዛኒያ ጠላት አድርገው የሚያስቀምጡት ምዕራባዊያንን ነው። ቀጥለው ደግሞ ለምዕራባዊያን የሚያጎበደዱ "አሻንጉሊቶች" የሚሏቸውን የአገራቸውን ሰዎች ነው። ቀጥለው መርማሪ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎችና ተቃዋሚዎቻቸውንም አይወዷቸውም። የነጭ አሽከር ይሏቸዋል። ማጉፉሊ ምዕራባዊያንን ብቻ ሳይሆን ቻይናንም ይተቻሉ የተግባር ሰው? ታንዛኒያዊው የፖለቲካ ተንታኝ ታቢት ጃኮብ ለቢቢሲ እንደተናገረው ማጉፉሊ ሥልጣኑን ሁሉ በእጃቸው አስገብተውም ቢሆን አንዳንድ ጊዜ የምዕራባዊያን ነገር ያባንናቸዋል። ብሔርተኝነታቸው መስመሩን ይስትና የሕዝበኝነት መስመርን ይይዛል። ተቃዋሚዎችን ማስጨነቅ፤ የፖለቲካ ምኅዳሩን ማጥበብ፣ ጋዜጠኞችን መከታተልና በደኅንነት ቅኝት ውስጥ እንዲቆዩ ማድረግ ማጉፉሊ የሚያሳዩት ባህሪ ነው። የሚመነጨውም ከፍርሃት ነው ይላሉ። ታንዛኒያዊው ጸሐፊ ኤልሲ ኢያኩዜ እንደሚለው ደግሞ ማጉፉሊ የሚመሩት በአንዳች እርሳቸው በሚያምኑት ርዕዮተ ዓለም የተቀኘ ቢሆንም ፍጹም የተግባር ሰው ናቸው። "ሰውየው ውይይት አይፈልግም ተግባር እንጂ" ይላል ኢያኩዜ። ወደ አውሮፓ የማይጓዘው ርዕሰ ብሔር በስዋሂሊ "በቡሩ" ማለት ወንድ ፍየል ማለት ነው። ይህን ቃል ዝነኛ ያደረጉት ማጉፉሊ ናቸው። ቃሉን የሚጠቀሙበት የምዕራቡን የኢምፔሪያሊስት ኃይል ለመጥራት ነው። "ወንድ ፍየሎች" እያሉ። ማጉፉሊ ወደ ሥልጣን ከመጡ አንድም ጊዜ ወደ ምዕራብ ዓለም ተጉዘው አያውቁም። አንድም ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ስብሰባ ታድመው አያውቁም። ይህ የሚገርም ነገር ነው። ሆኖም የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ ይገኛሉ። ጥቂት የአፍሪካ አገራትንም ጎብኝተው ያውቃሉ። ከእነዚህ መካከል ኡጋንዳና ሩዋንዳ ይገኙበታል። ሁለቱም አገራት እንደ ማጉፉሊ ሁሉ የምዕራቡን ዓለም የሚመለቱት በጥርጣሬ ነው። ማጉፉሊ በአካባቢው አገራት ስብሰባም አይገኙም። ከዛምቢያና ከኬንያ ጋር በኮሮናቫይረስ ምክንያት ድንበር ለምን ይዘጋል ሲሉ ተቃቅረው ነበር። ከኡጋንዳው ዩዌሪ ሙሴቬኒም ጋር እንዲሁ። አዛውንቱ ሙሴቬኒ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት በኮሮናቫይረስ ላይ በአንድነት መሥራት እንዳለባቸው ሲገልጹ "እኛ የምሥራቅ አፍሪካ አገር ሕዝቦች ከአንድ እናትና አባት የተወለድን ቤተሰብ" እንደማለት ነን ብለው ነበር። ስለዚህ ልክ እንደ ቤተሰብ እርስበርስ ትብብር ያሻናል ማለታቸው ነው። ማጉፉሊ ግን ይህን የሙሴቬኒን ሐሳብ በትወልድ አካባቢያቸው አንድ ቤተክርስቲያ ውስጥ ባደረጉት ንግግር ውደቅ አድርገውታል። "ትብብር ዕድገት ለማምጣት እንጂ በሽታው ለማስወገድ አይሆንም። በሽታ የማስወገድ ነገር የግል ጉዳይ ነው" ብለዋል። ኡጋንዳም ሆነች ሩዋንዳ ቫይረሱን ለመቆጣጠር የእንቅስቃሴ ገደብ አበጅተዋል። ከቤት አትውጡ ብለዋል፤ ይነስም ይብዛ። ማጉፉሊ በበኩላቸው "ከቤት ዉጡ" ነው የሚሉት። 'ብረቱ' ተብለው የሚታወቁት ማጉፉሊ ማጉፉሊ እየተገለሉ ይሆን? የማጉፉሊ ተቃዋሚዎች ታንዛኒያ የተጨናነቁ ከተሞች የእቅስቃሴ ገደብ ልታደርግባቸው ይገባ ነበር ብለው ይተቿቸዋል። ነገር ግን ማጉፉሊ የእንቅስቃሴ ገደብ ያላደረጉ ብቸኛው መሪ ተደርገው ነው የሚሳሉት። የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) ባወጣው አንድ ጥናት ግን እንደ ታንዛኒያ ሁሉ በርካታ አገራት የቤት ውስጥ መቀመጥን ግዳጅ አላደረጉም። እንዲያውም ከአፍሪካ አገራት ሲሶዎቹ ይህን አላደረጉም። ከእነዚህ መካከል ኢትዮጵያ ትጠቀሳለች። እርግጥ ነው ኮሮናቫይረስ በኅዳር አጋማሽ ሲከሰት ታንዛኒያ ትምሀርት ቤቶችን ዘግታለች። የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችንም አግዳ ነበር። እንዲያውም ማንም ሳይጀምረው ገና በትኩሱ ማጉፉሊ ሰው አልጨብጥም ብለው ነበር። ከተቃዋሚው መሪ ማአሊም ሰይፍ ሻሪፍ ሀማድ ጋር የእግር መጨባበጥ አድርገው ይኸው ዜና ሆኖ ነበር፤ ያኔ። ይህ የሆነው ብዙ ሰዎች ገና በእጅ መጨባበጥ ባላቆሙበት ጊዜ ነው። ያም ሆኖ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማሺዲሶ ሞዎቲ ታንዛኒያ ቫይረሱን ለመከላከል ያሳየችውን ዳተኝነት ተችተዋል። ማጉፉሊ ከሠሯቸው ስህተቶች ምናልባትም አንዱ የእምነት ቦታዎች እንዳይዘጉ ማድረጋቸው ሲሆን፤ በጸሎት ወቅትም ተገቢውን ማኅበራዊ ርቀት ለመጠበቅ መመሪያ አላስተላለፉም። ማጉፉሊ ግን ግድ የላቸውም፤ እንዲያውም "ኮሮናቫይረስ ሰይጣን ነው። በክርስቶስ መንፈስ ላይ ሊጸና አይችልም" ብለው ነበር። አንዲህ የሚሉት ማጉፉሊ በኬሚስትሪ ፒኤችዲ እንዳላቸው መዘንጋት አያሻም። ዶ/ር ማጉፉሊ ይባሉ ነበር እኛ ጋ ቢሆን። ጥብቅ የካቶሊክ እምነት ተከታይም ናቸው። በዚህ ወር ማጉፉሊ ለቤተክርስቲያን ምዕመናን ባደረጉት ቡራኬ "እንኳን ደስ ያላችሁ! ኮሮናቫይረስ ከአገራችን ጠፋላችሁ! ክብር ለጌታ!" ብለዋል። ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ ቫይረሱ አልጠፋም እጃችሁን በደንብ ታጠቡ ብለዋል። እንደገና ባለፈው ማክሰኞ ፓርላማው ከመበቱኑ በፊት "አምላካችን አገራችን ታንዛኒያን ከቫይረሱ ታድጓታል። አሁንም ሁሉም ትምህርት ቤቶች ይከፈታሉ፤ ሕይወት እንደ ቀድሞው ይቀጥላል" ብለዋል። ማጉፉሊ ላለመጨባበጥ በእግራቸው ሰላምታ ሲለዋወጡ በሴራ ያምኑ ይሆን? ጠቅላይ ሚኒስትር ቃሲም ማያሊማ የማጉፉሊን ንግግር በሚቃረን ሁኔታ በታንዛኒያ 66 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸውን ተናግረዋል። እንዲህ ግልጽ አሐዝ ይፋ ሲደረግ ከሚያዚያ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ነበር። ማጋፉሊ ከዚያ በፊት ባደረጉት ሌላ ንግግር ኮሮናቫይረስ ምዕራባዊያን የሸረቡት ሴራ ነው ብለው ነበር። ማጉፉሊ የምርመራ መሣሪዎች አስተማማኝነትም ላይ ጥያቄ አንስተው ያውቃሉ። "ብዙውን ጊዜ ሁሉም ከውጭ የሚገባ ነገር ትክክል ነው ብላችሁ መውሰድ አይኖባቸሁም። ብዙ መጨበርበር አለ፤ ብዙ መታለል አለ፤ ይህ ጦርነት ነው፣ የሴራ ጦርነት" ብለዋል ለሕዝባቸው። ማጉፉሊ ብረት ነው ማጉፉሊ አገር በቀል የባሕል መድኃኒቶች ፈውስ ስለመሆናቸው ብዙ ብለዋል። እንፋሎትን ጨምሮ ሌሎች ተክሎችም ይፈውሳሉ ሲሉ ተናግረዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ግን ይህን የሚያረጋግጥ ምንም መረጃ የለም ይላል። "ማጉፉሊ አብዛኛዎቹን የአፍሪካ አገራትን አጋር አድርጎ ነው የሚያያቸው፤ ለኮሮናቫይረስ መድኃኒት ከተገኘም ከአፍሪካ አገራት ቢሆን ነው የሚመርጠው፤ ከምዕራብ የሚመጣን ነገር አያምንም" ይላሉ የታንዛኒያ የፖለቲካ ተንታኝ ዳን ፓጄት። በርካታ የጤና ባለሞያዎች እንደሚያምኑት በርካታ የአፍሪካ መሪዎች ለሕዝባቸው ባዶ ተስፋን ይመግባሉ፤ ይህ ጆርጅ ዊሃን ይጨምራል። ነገር ግን የባህል መድኃኒትን በተመለከተ የብዙ አፍሪካዊያን የሕይወት ዘይቤ በመሆኑ በዚያ ላይ እምነት ማሳደራቸው የሚደንቅ አይደለም። የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያትተው 80 ከመቶ አፍሪካዊ የባሕል መድኃኒት ይጠቀማል። ዞሮ ዞሮ የማጉፉሊ ኮሮናቫይረስን ቸል የማለታቸው ነገር ይዞት የሚያመጣው ጣጣ ካለ የሚታወቀው በመጪዎቹ ወራት ነው። እስከዚያ ግን ማጉፉሊ እንዳወዛገቡ ይቀጥላሉ። በ2015 እንደ አውሮፓዊያኑ የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሥልጣን ለማጉፉሊ ሲያስረክቡ እንዲህ አሉ፤ "እኔስ እየሄድኩ ነው፤ እኔን የሚተካኝ ግን "ቹማ" ነው" ቹማ በስዋሂሊ ቅጥቅጥ ብረት ማለት ነው። ትክክለኛ አገላለጽ ይመስላል። ማጉፉሊ ለወዳጆቸው ብረት ሆነው ነው የሚታዩት፤ ለጠላቶቻቸው ግን ልምጭ።
news-47702786
https://www.bbc.com/amharic/news-47702786
አንዳንድ ጥያቄዎች ለ"108ኛው" የፖለቲካ ፓርቲ
አዲስ ፓርቲ እየመጣ ነው። የምሥረታ ጉባኤው ጠቅላላ ጉባኤው ባለበት ተካሄደል። ኦዲትና ኮሚሽን ተመርጧል። የሥራ ድልድ ተደርጓል። ማዕከላዊ ኮሚቴና ሥራ አስፈጻሚ ተመርጧል። ከምርጫ ቦርድ ሠርተፍኬት ለመውሰድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ለሚገኘው የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ መሥራችና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለወ/ሮ ነቢሃ መሐመድ አንዳንድ ጥያቄዎችን አንስተናል። ቢቢሲ፡ እንደው 108ኛ ፓርቲ መሆን ምን ዓይነት ስሜት ይሰጣል? ያሳፍራል ወይስ . . . ?
ወ/ሮ ነቢሃ፡ ሐሳብን በነጻነት መግለጽ እና የመደራጀት መብት ሀገሪቷ በሕገ መንግሥቱ ካጎናጸፈችን መብቶች አንዱና ዋንኛው ነው። ስለዚህ ዜጎች በርካታ ያልተፈቱላቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አሏቸው። ነጻነት አልተከበረም። ዜጋው በጠቅላላ እኩል ተጠቃሚ አይደለም። • "አጭሩ የሥልጣን ቆይታ የእኔ ነው" ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) ስለዚህ በእነዚህ ደረጃ ይሄንን ሊፈታ የሚችል የተደራጀ፣ ሁሉንም አካባቢ ያካተተ፣ በትምህርትም አጠቃላይ ክልሎችንም፣ ወረዳዎችንም፣ ቀበሌዎችንም፣ የጾታንም ስብጥር በጠበቀ፣ ወጣቱን ባካተተ...አገሪቱ ላይ የሚያወስፈልጋትን የነጻነት የፍትህ የእኩል ተጠቃሚነት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የተደራጀና የተጠናከረ አገራዊ ፓርቲ አለ ብለን በራሳችን በኩል ስለማናምን ያንን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅም አለን በሚል ነው [የመሠረትነው]። ቢቢሲ፡ አሁን ያነሷቸው የነጻነት፣ የእኩል ተጠቃሚነት ጉዳዮች እኮ የ107ቱ ፓርቲዎችበፕሮግራማቸው ላይ ያሉ ሐሳቦች ናቸው። 108ኛ መሆን ያስፈልጋል? ወ/ሮ ነቢሃ፡ በነገራችን ላይ በአብዛኛው 107 ፓርቲ እንበል እንጂ ዕውቅና የተሰጣቸው ፓርቲዎች 66ቱ ናቸው። የሁሉንም ብናይ ደግሞ በተወሰኑ አካባቢዎች የታጠሩ፣ ከተማ ላይ ብቻ የተወሰኑ፣ ወይንም ደግሞ የሆነን ብሔር መብት ለማስከበር የቆሙ ናቸው። ብዙዎቹ በአካባቢና በብሔረሰብ የተደራጁ ናቸው። ቢቢሲ፡ ግን እኮ አገራዊ ፓርቲዎችም ብዙ አሉ? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ቁጥራቸው የተወሰኑ ናቸው። ቢቢሲ፡ ሊሆን ይችላል።ግን አንሰዋል ይጨመር የሚያስብል አይደለም። ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ወደ ሁለት ሦስት ጠንካራ ፓርቲ ሰብሰብ ብላችሁ ገዢውን ፓርቲ ብትገዳደሩ ይሻላል ባሉ ማግስት 108ኛ ፓርቲ ይዞ መምጣት ግን... ወ/ሮ ነቢሃ፡ 108ኛ ፓርቲ ሆኖ አይደለም። አጠቃላይ 107 ከተመዘገቡት ውስጥ የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አለ። ምሥረታውን ነው ትናንትና ያካሄድነው እንጂ ከተመዘገቡት 107 ውስጥ 99ኛው የእኛ ነው። ያንን ማጣራት ትችላለህ። ቢቢሲ፡ ግዴለም ተራ ቁጥር አያጣላንም። ነጥቡ አሁን ለምን ፓርቲ መመሥረት አስፈለገ ነው? ወ/ሮ ነቢሃ፡ አስፈላጊነቱ አገራችን ከገጠሟት ወቅታዊም ሆኑ የረዥም ጊዜ ችግሮች ለመላቀቅ የሁሉም ዜጎች የተናጠልና የጋራ ርብርብ ይጠይቃል። ከዚህ ውስጥ በዋናነት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ኃይሎች ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው የሚሆነው። ቢቢሲ፡ ግን አሁን የፓርቲ እጥረት ኖሮ ነው እንዴ አገሪቱ እዚህ ችግር ውስጥ ያለችው? በፓርቲ ብዛት ችግር ይፈታል? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ፓርቲዎች መብዛታቸው ማነሳቸው ሳይሆን፤ ዋናው ሥራቸው ነው። አዲስ የተደራጁት ፓርቲዎች ቀርቶ አገሪቱን እየመራ ያለው ፓርቲ እንኳን የአገሪቱን ሕዝብ እኩል ተጠቃሚ እያደረገ አይደለም። ሁሉንም ክልሎች ሁሉንም ዜጎች እኩል ተጠቃሚ እያደረገ ስላይደለ የግድ ይሄ ፓርቲ መደራጀቱ ያስፈልጋል። ስለሆነም ይህ ፓርቲ የራሱ የሆነ የፖለቲካ ፕሮግራም ቀርጾ የራሱን የፖሊሲ ፕሮግራም ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ነው። ቢቢሲ፡ በሌሎች ፓርቲዎች ቸል የተባሉ፣ ያልተካተቱ ነገር ግን የእናንተ ፓርቲ በፖለቲካ ፕሮግራም የያዘው አንድ ጉዳይንይንገሩኝ እስኪ። ይሄ እኛን ልዩ የሚያደርገን ፕሮግራም ነው የምትሉት... ወ/ሮ ነቢሃ፡ እኛ ከፖለቲካ ፕሮግራማችን ውስጥ የመንግሥት አወቃቀር፣ የሥርዓተ መንግሥቱ ቅርጽ፣ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለማችንን በደንብ አርገን አሁን ካሉት ፓርቲዎች በተለየ ሁኔታ ተንተን አድርገን ያስቀመጥንበት ሁኔታ አለ። • "የሠራዊቱ ሁኔታ ከፍተኛ የህሊና መረበሽ ውስጥ ከቶኛል" አቶ ነአምን ዘለቀ ቢቢሲ፡ አሁን ያሉት ፓርቲዎች ተንተን አላደረጉትም? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ተንተን ሊያደርጉት ይችላሉ። ግን ደግሞ ማለት ነው። ይሄ ለይስሙላ የሚቋቋመ ፓርቲ አይደለም። ቢቢሲ፡ ሌሎች ፓርቲዎች ለይስሙላ ነው የተቋቋሙት? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ለምሳሌ አሁን እየመራ ያለውን ፓርቲ እያየን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው። [ለማንናውም] እኛ የራሳችንን አቋም ነው አስቀምጠን፣ ፖለቲካችን ይሄን ይሄን ይመስላል ብለን አስቀምጠን፣ አገሪቷን ካለችበት ድህነትና ኋላ ቀርነት [ለማውጣት] አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ከሚሆንበትን ሁኔታ ለማላቀቅ ነው፤ የምንሠራው የምንታገለው። ቢቢሲ፡ ግን'ኮ ማንኛውም ፓርቲ ስለ እኩልነትና ስለ ነጻነት እንጂ ጭቆናን ለማምጣት አይሠራም። በአደረጃጀት ደግሞ አገር አቀፍ ፓርቲዎች ይኖራሉ። ብሔር ተኮር ፓርቲዎች ይኖራሉ። እነዚህ ሁሉ ባሉበት አገር፣ በስም እንኳ የማናውቃቸው ፓርቲዎች ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ተጨማሪ ፓርቲ ይዞ መምጣት እንዴት ነው የሕዝብ ተቀባይነት ያስገኛል ብላችሁ ያሰባችሁት? ወ/ሮ ነቢሃ፡ በስም የማናውቃቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ ብለህ ስትል በስም የማታውቃቸው ፓርቲዎች ጭምር እንዳሉ እየገለጽክ ነው። ይህ የእኛን ፓርቲ ግን እያወቅከው ነው። ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በስም የሚታወቅ ነው። ሕገ መንግስቱ ደግሞ አትደራጁ ብሎ የሚያግድ የለም። 107 ፓርቲ በቂ ነው አይልም። [ፓርቲ አትመስርቱ] በቃ ብሎ የሚከለክለን የለም። ቢቢሲ፡ መደራጀቱን ጥያቄ ውስጥ አልከተትኩም'ኮ። ፋይዳው ላይ ነው ጥያቄዬ ወ/ሮ ነቢሃ፡ ፋይዳውን ነበር እኮ እኔም እየነገርኩህ የነበረው። ቢቢሲ፡ እስኪ በዚህ በዚህ ምክንያት ፓርቲዎች ይህንን ለሕዝብ ማድረስ ስላልቻሉ፤ ይህንን ክፍተት እንሸፍናለን ብላችሁ የምታነሱት የተለየ ነገር አለ? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ለምሳሌ የእኛ የፖለቲካ ርዕዮት ዓለም ከሌሎች ይለየናል ብለን የምንለው "ኮንሰርቫቲቭ ሊበራሊዝም" እናራምዳለን ብለን ነው የያዝነው፤ በዋናነት። ቢቢሲ፡ ምን ማለት ነው እሱ? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ቅይጥ ሊበራሊዝም ማለት ነው። • "በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ቢቢሲ፡ ምንድነው እሱ በቀላል ቋንቋ ያስረዱን እስኪ? ወ/ሮ ነቢሃ፡ አሁን በኢኮኖሚ ዘርፍ ያሉትን ጉዳዮች መንግሥት በበላይነት ነው እየመራ ያለው። በዓለም ደረጃ መንግሥት በበላይነት የሚመራበት ሁኔታ አይደለም ያለው። በግለሰብም በቡድንም በጋራም ሆኖ አቅም ያላቸው መሥራት የሚችሉ ማንኛውንም አካል አካታች አድርጎ በኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሳይኖር እንዲሠሩት የማድረግ ሂደት ነው በዋናነት። ቢቢሲ፡ ስለዚህ የምትከተሉት ቅይጥ ሊበራሊዝምያሉኝ ይህንንነው ማለት ነው? ወ/ሮ ነቢሃ፡ አዎ ግዙፍ የሆኑ ፕሮጀክቶች ሊኖሩ ይችላሉ። በግሉ ሊሠሩ የማይችሉ ካሉ እነሱን መንግሥት ይሠራል። በተጨማሪ ደግሞ ጥቅማቸው ጥቃቅን የሆኑ ነገሮች ላይ መንግሥት ሊሠራበት ይችላል። አብዛኛውን ግን ለግሉ ወይም በጋራ ለሚሠሩት የሚሰጥ ነው እንጂ እራሱ ሙሉ በሙሉ እየገባበት የሚያንቀሳቅሰው አይደለም። ቢቢሲ፡ ስለዚህ በኢኮኖሚ ውስጥ የመንግሥት እጅ ረዝሟል የሚል ቁጭት ነው ይህን ፓርቲ የፈጠረው? ወ/ሮ ነቢሃ፡ አንድም እሱ ነው። ሁለት ደግሞ ያልተሰሙ ድምጾች አሉ። የማን ከተባለ የዜጋው። እስከዛሬ የምናየው ነገር በገዢው ፓርቲ እየተመራ ያለው፤ አንድ አካባቢ የሆነ ሰው ብቻ ነው ተጠቃሚ እየሆነ ያለው። አገሪቷን እየመራ ያለውም ይኸው የአንድ አካባቢ ሰው ነው። ቢቢሲ፡ ይሄ አየተጠቀመ ነው የሚሉትን የአንድአካባቢ ሕዝብ መጥቀስ ይቻላል? ወ/ሮ ነቢሃ፡ የፖለቲካ መሪዎች፣ የፓርቲ መሪዎች ናቸው እየተጠቀሙ ያሉት። ሕዝቡን እየጠቀሙ አይደለም። የአንድ የፖለቲካ መሪ የበላይ ሆኖ ነው ያለው። ስለዚህ እኛ የሁሉም ክልሎች ሕዝብ ተወካይ አገሪቷን እየመራ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ነገር መመንጨት ያለበት ከሕዝብ ነው [ብለን እናምናለን]። እኔ አውቅልኸለሁ ከማለት ከሕዝብ መምጣት አለበት ብለን እናምናለን። ሲቀጥል ደግሞ ሥርዓተ መንግሥቱ በርዕሰ ብሔር የሚመራ፣ ቀጥታ በሕዝብ የሚመረጥ መሆን አለበት። ይሄን በተመለከተ የራሳችን የፖለቲካ ፕሮግራም አለን። ቢቢሲ፡ በቀጥታ ፕሬዚዳንትን መምረጥ ምን ለውጥ ያመጣል? ወ/ሮ ነቢሃ፡ አንድ አገር ሲመራ የራሱ የሆነ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ይኖሩታል። ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መመንጨት ያለባቸው ከሕዝብ ነው። እኔ አውቅልኸለሁ ብዬ ፖሊሲ መቅረጽ የለብኝም። የሚመለከተውን አካል ማሳተፍ አለብኝ። ኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጥሮ 86 የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች አሏት፤ የተለያየ እምነትና ባህል ያለበት አገር ነው። ስለዚህ እኔ እላይ ቁጭ ብዬ ታች ላለው ለጋምቤላው ለሶማሌው አውቅልኸለው ብዬ ልሠራለት አይገባም። አሳታፊ ሊሆን ይገባል። ቢቢሲ፡ ግን እኮ በመንግሥት ሥርዓት ውስጥ አሳታፊነት በተለያየ መንገድ ሊገለጽና ሊወከል ይችላል። የሕዝብ ድምጽ በእንደራሴዎች ሊወከል የሚችልበት አሰራርም አንዱ ነው። ወ/ሮ ነቢሃ፡ በሕዝብ ነው ምርጫ የሚደረገው እንጂ ፓርቲዎች ተሰባስበው መሆን የለበትም። የኢህአዴግን አወቃቀር አይተነዋል እኮ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአራቱም ብሔራዊ ድርጅቶች የበላይ የሆነው አንዱ በድምጽ ብልጫ ተወሰኖ ነው መሪ እንዲቀመጥ የሚደረገው እንጂ ከታች ሕዝቡ መርጦት አይደለም። ቀጥታ ከሕዝብ በኮሮጆ የሚመረጥ ነው መሆን ያለበት እንጂ አራት ፓርቲዎች የሚመርጡት መሆን የለበትም። ቢቢሲ፡ ምን ያህል ሰዎች ፈረሙላችሁ? ወ/ሮ ነቢሃ፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ የ1ሺህ 500 ሰው የፊርማ ናሙና ከተሰበሰበ ያ የመጨረሻው ደረጃ ነው። እኛ ግን ከ2500 በላይ ፊርማ የማሰባሰብ ሥራ ሠርተናል፤ ከሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች። ቢቢሲ፡ ሰዎች ምን ይሏችሁ ነበር ፊርማ ስትጠይቋቸው? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ምንድነው የተለየ ፕሮግራም ያላችሁ? የኢኮኖሚ ፕሮግራማችሁ ምንድነው ይሉን ነበር። ቢቢሲ፡ በዚህ ሰዓት ፓርቲ ልንመሠርት ነው ስትሏቸው ደስተኞች ናቸው? ወ/ሮ ነቢሃ፡ በጣም ደስተኞች ናቸው። እጅግ በጣም። አይደለም ከዛሬ 2 እና 3 ወር ይቅርና ትናንትና [እሑድ] የምስረታ ጉባኤውን ስናካሄድ በሚዲያ የተከታተሉ ሰዎች ይሄን ፓርቲ ዓላማውን በደንብ አሳውቁን በጣም ደስ ይላል ብለውናል፤ ከወዲሁ። ነጻነትና እኩልነት የሚለውን ሲሰሙ... ቢቢሲ፡ ፓርቲዎች ይመሠረታሉ፣ ልንዋሀድ ነው ይላሉ፣ ይፈርሳሉ ወይ ይሰነጠቃሉ፣ ይከስማሉ... ይሄ ነው ሕዝቡ ስለ ፓርቲዎች ያለው መረጃ። እንዴት ነው በእናንተ ሊደሰት የሚችለው? በስማችሁ ድምቀት ነው? ወይስ ሕዝቡ የፓርቲ ጥማቱን አልተወጣም ብላችሁ ነው የምታስቡት? ወ/ሮ ነቢሃ፡ የፓርቲ ጥማት ሳይሆን ትክክለኛ ምላሽ ሊሰጠው የሚችለውን ፓርቲ ከወዲሁ ፕሮግራሙ የያዘውን አይቶ ማወቅ ይፈልጋል። ፓርቲዎች ብዙ አሉ ግን ምንድነው ፕሮግራማቸው? ምንድነው ርዕዮተ ዓለማቸው? ምንድነው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው? የእኛ ይሄን ከመረዳት... ቢቢሲ፡ ሕዝብ ርዕዮተ ዓለማችንን ተረድቶ ነው ከወዲሁ የወደደን እያሉኝ ነው? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ያናገርናቸው ፕሮግራሙን ያስተዋወቅናቸው ሰዎች በጣም ደስተኞች ናቸው። በርዕዮተ ዓለማችን፣ በፕሮግራማችን። እንዲፈርሙልን አባል እንዲሆኑልን የጠየቅናቸው ሰዎች ማለቴ ነው፤ በጣም ደስተኞች ናቸው። ቢቢሲ፡ ይሄንን ፓርቲ ለመመሥረት ሐሳቡን ያመነጨው ማን ነው? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል አሁንም እየሠራ ያለ፣ ትናንትናም በተሰጠው የምስጢር ድምጽ አሰጣጥ በአጋጣሚ ሆኖ የፓርቲው ሊቀመንበር የኾነው ዶ/ር አብዱልቃድር ይባላል። ቢቢሲ፡ የፓርቲው መሪዎች እነማን ናቸው? ከዚህ በፊት ፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ናቸው? ወይስ ሁላችሁም አዲስ ናችሁ? ወ/ሮ ነቢሃ፡ በነገራችን ላይ ከዚህ በፊት በተለያየ ፓርቲ ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦች አብረውን አሉ። ከዚህ በፊት በነበሩ ፓርቲዎች አባል ሆነው፣ መሥራችም ሆነው ነገር ግን እዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተገኙ አሉ። የራሳቸውን ተሞክሮ እንዲሰጡ የተደረገበት ሁኔታ አለ። በአብዛኛው የተማረ ነው ምሁሮች ናቸው ያሉት፤ ወጣትም አለበት። ቢቢሲ፡ እነዚህ ሌላ ፓርቲ ውስጥ የነበሩት ከዚያ ወጥተው እናነት ጋ አመራር ሆኑ ማለት ነው? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ልምድ ያላቸው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነው የሆኑት። ቢቢሲ፡ ስለዚህ ከፓርቲ ፓርቲ የሚዘዋወሩ ሰዎች ናቸው የሚመሩት ፓርቲያችሁን? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ልምድ ሊሰጡን አንድ ሁለት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የገቡ አሉ እንጂ አብዛኛው ወጣት ነው። ቢቢሲ፡ ለልምድ ሲባል ነው እነሱ የገቡት? ወ/ሮ ነቢሃ፡ እነሱ ልምድ በሚል ነው እንጂ የገቡት ፓርቲው ውስጥ ያሉ ወጣቶች የተለያየ ዕውቀት ያላቸው፣ የፖለቲካ ልምድ ያላቸው፣ በጣም የተማሩ፣ አቅም ያላቸው ዶክተሮች፣ የፖለቲካ ልምድ ያላቸው ሰዎች ናቸው ያሉበት ፓርቲው ውስጥ። እና በዛ ላይ ከሁሉም አካባቢ የተውጣጣ ነው። ከጋምቤላ አለ፣ ከአፋር አለ፣ ከሐረር፣ ከሶማሌ ከደቡብ ከአማራም አካባቢ አለ፤ ከትግራይም አለ። ሁሉንም የአገሪቱን ህብረተሰብ ያካተተ ነው ስብጥሩ። ቢቢሲ፡ ስለዚህ ሁሉንም ብሔር ብሔረሶች ተወክለዋል ነው የሚሉት በሥራ አስፈጻሚው? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው ያልኩት። ሥራ አስፈጻሚማ 11 ነው ቁጥሩ። ቢቢሲ፡ ጠቅላላ ጉባኤ ስንት ናችሁ? ወ/ሮ ነቢሃ፡ 150 አባላት ቢቢሲ፡ ስለዚህ ሁሉም ብሔረሰቦች ተወክለዋላ? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ይህ አገር አቀፍ ፓርቲ ነው። ሁሉም አካባቢ መሥራት አለብን በሚለው እሳቤ አንደኛ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ነው። ፍላጎትን መሠረት አድርገን ስንሄድ ግን ደግሞ ሁሉንም የአገሪቷን አካባቢዎች ማካተት አለበት በሚል ከሁሉም በፍቃደኝነት፣ በሞራል፣ በተነሳሽነት፣ በአቅምም፣ ጾታንም ጭምር ታሳቢ ያደረገ [እንዲሆን ተደርጓል]። ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ሴቶች ፓርቲው ውስጥ ገብተዋል። ቢቢሲ፡ ብሔር ብሔረሰቦች ግን ሁሉም ተወክለዋል? ወ/ሮ ነቢሃ፡ አዎ ያልተወከለ የለም። ቢቢሲ፡ እንግዲያውስ አንድ ጥያቄ ላንሳ። ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ከተወከሉ ለመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ስንት ናቸው? ብዙውን ጊዜ በደፈናው ከ85 በላይ ናቸው ስለሚባል ነው... ወ/ሮ ነቢሃ፡ እ...ውክልና ሲባል ከሁሉም አካባቢ የተውጣጣ ነው እንጂ ለምሳሌ ኦሮሚያ ቁጥሩ ከፍተኛ ነው፤ ከአገሪቷ ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛል። እኛ ከሁሉም አካባቢ ወስደናል፣ ለሳምፕል የሚሆን ሰው ወስደናል። ሊሰራልን የሚችል ከሁሉም ብሔሮች... ቢቢሲ፡ ለናሙና ነው የወሰዳችሁት? ወ/ሮ ነቢሃ መሐመድ፡ መሥራት የሚችሉ አቅም ያላቸውን ወስደናል። እዚህ አዲስ አበባን ማዕከል አድርገን እዚህ ቁጭ ብለን ስለ አገሪቷ እናውቅልሀለን ማለት አንችልም።አንተ የምትለኝን ልናደርግ የምንችለው መንግሥት ስንመሠርት ነው። ቢቢሲ፡ የእናንተ የመሥራቾቹ ገቢ ወይም መተዳደሪያ ምንድነው? ወ/ሮ ነቢሃ፡ ሁላችንም በየራሳችንን የምንቀሳቀስ ነን። የግል ቢዝነስ የሚሠራ አለ፣ የመንግሥት ሠራተኛም አለ፣ ሥራ የሌለውም አለ። አብዛኛው ግን አቅም ያለው ነው፤ መንግሥት ቢሮም ተቀጥረው የሚሠሩ አሉ። ቢቢሲ፡ እንጂ ፓርቲን እንደ አንድ የገቢ ምንጭ በማሰብ ሕዝብንም በዚያው እያገዙ ኑሮን ለመደጎም የተሰባሰበ አይደለም? ወ/ሮ ነቢሃ፡ በፍጹም። በፍጹም። ቢቢሲ፡ መጪውን ምርጫ አሸንፋችሁ መንግሥት የምትመሰርቱ ይመስላችኋል? ወ/ሮ ነቢሃ፡ በሚገባ! እርግጠኝነት።
news-52252885
https://www.bbc.com/amharic/news-52252885
ኮሮናቫይረስ፡ የተፈጥሮ በሽታን የመከላከያ ሥርዓታችንና ኮሮናቫይረስ
በፈረንጆቹ 1918 የተከሰው ስፓኒሽ ፍሉ የተባለው ወረርሽኝ በወቅቱ ከነበረው የዓለም ሕዝብ አንድ አራተኛውን ማለትም ከ500 ሚሊዮን የሚሆኑትን ሲያጠቃ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን በመግደል በተመዘገበ ታሪክ ውስጥ በጣም ከፍተኛው መቅሰፍት ነበር።
በዚያ ዘመን ከወረርሽኙ ጋር በሚፈጠር ዕድል የእባብ ዘይት ሻጮች በከፍተኛ ሥራ ላይ ነበሩ፤ ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ማስታወቂያዎችን ይጠቀሙ ነበር። ማስታወቂያዎቻቸው በጋዜጣ ላይ በመደበኛነት ይወጡ የነበረ ሲሆን አስፈሪ ርዕሶችም ነበሯቸው። ወዳለንበት 2020 ስንመለስም ብዙ አልተለወጠም። ምንም እንኳን ኮቪ-19 ከስፓኒሽ ፍሉ ከመቶ ዓመታት ሳይንሳዊ ግኝቶች በኋላ ቢከሰትም አሁንም አጠያያቂ በሆኑ መድኃኒቶችና ባህላዊ መፍትሔዎች እንደተከበበ ነው። አሁን ግን ዋነኛው ማጠንጠኛ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም "ማጎልበት" የሚል ነው። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከሚያሰራጩት ያልተረጋገጡ መረጃዎች መካከል እንደማንኛውም ጊዜ ሁሉ የአመጋገብ ምክሮች በብዛት ይሰጣሉ። በፀረ-ተህዋሲያን እና በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦችን እንድንወስድ እየተበረታታን ነው። የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳትዎን ማጎልበት ክኒኖች፣ በብዛት የሚነግራለቸው ምርጥ ምግቦች ወይም የጤና አጠባበቅ ልምዶች በአቋራጭ ለጤነኛ የበሽታ መቋቋም ሥርዓት ያግዛሉ የሚለው አስተሳሰብ ያለተጨበጠ ነገር ነው ይላሉ ባለሙያዎች። አክለውም በእውነቱ በሽታን የመከላከል አቅምን "ከፍ ማድረግ" የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ ምንም አይነት ሳይንሳዊ ትርጉም የለውም። "በሽታን ለመከላከል ሦስት ነገሮች አሉ" ሲሉ የዬል ኢሙኖሎጂስት [የሰውነት በሽታን የመከላከል ሥርዓትን የሚያጠና ዘርፍ] የሆኑት አኪኮ ኢዋሳኪ ይገልጻሉ። "በመጀመሪያ ላይ በሽታን ለመከላከል ቆዳችንና የአየር መተላለፊ አካላችን አሉ። እነዚህ ለበሽታው እንቅፋት ይሆናሉ። ሆኖም ቫይረሱ እነዚህን መከላከያዎች ካለፈ በኋላ ተፈጥሮአዊው በሽታ መከላከያን ይነሳል" በዚህም ማንቂያውን ከፍ የሚያደርጉና ማንኛውንም መጤ ነገር መዋጋት የሚጀምሩ ኬሚካሎችንና ሴሎች ይካተታሉ። "ይህም በቂ ካልሆነ ሌላኛው በሽታን የመቋቋም ሥርዓታችን ወደ ሥራ ይገባል" ይላሉ። ይህም ጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት የሚወስድባቸው ሴሎችንና ፕሮቲኖችን ያካትታል። አብዛኞቹ ኢንፌክሽኖች በሽታ የመከላከል አቅምን ያነቃቃሉ። ሌላኛው መንገድ ደግሞ ክትባት ነው። አካልን በሕይወት ባሉ ወይም በሞቱ ረቂቅ ተህዋስያን ወይም ለእነሱ ክፍሎች በማጋለጥ ሰውነት ትክክለኛው በሽታ ሲመጣ እንዲለያቸው ማድረግ ነው። የሰውን በሽታ የመከላከል ሥርዓት "ከፍ ማድረግ" የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ ምናልባትም እነዚህን ምላሾች የበለጠ ንቁ ወይም ጠንካራ እንዲሆኑ ያደርግ ይሆናል። የሰውነታችን በሽታን የመከላከል ሥርዓት የጉንፋን ምልክቶችን ይውሰዱ የሰውነት ህመም፣ ትኩሳት፣ የጭንቅላት መክበድ፣ . . . ። እነዚህ ሁሉ በቫይረሱ የተከሰቱ አይደሉም። ይልቁንም አካልዎ በተፈጥሮአዊ መንገድ የሚያነቃቃቸው የበሽታ መከላከል ምላሽ ክፍሎች ናቸው። ከአፍንጫ የሚወጣው ፈሳሽ በሽታ አምጪ ተህዋስያንን ለማስወገድ ይረዳል። ትኩሳቱ በሽታው እንዳይባዛ የሚቸገርበትን ሞቃት አካባቢ እንዲኖር ይረዳል። ህመም እና አጠቃላይ ህመሙ የሚያስከትሉት ስሜት የሰውነት የበሽታ ተከላካይ ሴሎች ምን መሥራት እንዳለባቸውና ወዴት መሄድ እንዳለባቸው የሚነግራቸው ነው። ምልክቶቹ እንቅስቃሴ እንድንቀንስና ሰውነታችን እንዲሻለው ለአዕምሯችን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው። ሌላውን የበሽታ መከላከያ ገፅታ የመላመድ በሽታ ተከላካይ ሥርዓት ነው። ለምሳሌ አለርጂዎች የሚከሰቱት ሰውነት አይስማማኝም ብሎ በሚያስበው ነገር ላይ የሚሰጠው ምላሽ ነው። ነገር ግን የተወሰኑ የበሽታ ተከላካይ ህዋሳትን የሚያጎለብቱ ምርቶች "አጎልብተው" ባይሆንም የበሽታ መከላከያ ምላሽን ጠቃሚ በሆነ መንገድ ሊያሻሽሉ ይችላሉ ብለን እንገምታለን። "ችግሩ ብዙዎቹ ማስረጃ የላቸውም" ብለዋል ኢዋሳኪ፡፡ ስለዚህ በምን ላይ የተመሠረተ ነው? ጤናማ ከሆኑ ከቫይታሚን ዲ ውጭ ያሉ ተጨማሪ ነገሮችን ይርሱ። የቫይታሚኖች ሚና ብዙ መልቲቫይታሚኖች "የበሽታ መከላከል" ድጋፍ ይሰጣሉ ወይም "ጤናማ የበሽታ መከላከያ ተግባርን ጠብቆ ለማቆየት" ይረዳሉ ቢሉም ቢቢሲ ከአራት ዓመት በፊት እንደዘገበው ተጨማሪ ቫይታሚኖች ጤናማ ሰዎች ላይ አይሰሩም፤ አንዳንዶቹም ጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ። ቫይታሚን ሲን ይውሰዱ። ሆኖም የቪታሚን ሲን ጉንፋንን እና ሌሎች የመተንፈሻ አካላትን በሽታ ለመቋቋም እንድንችል በማገዝ ትልቅ ሚና እንዳለው የሚየሳይ ትንሽ ማስረጃ ብቻ ነው። ኮችሬን የተባለ ታዋቂ ድርጅት በፈረንጆቹ 2013 ባደረገው ምርምር አዋቂዎች ላይ "ከፍተኛ መጠን ያለው የቫይታሚን ሲ የበሽታ ምልክቶች መታየት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከተሰጠ በተለመደው የጉንፋን ምልክቶች ቆይታ ወይም ክብደት ላይ ምንም ለውጥ የማያመጣ መሆኑን ነው።" ባደጉት አገራት ያሉ ሰዎች ቫይታሚን ሲን ከምግባቸው ያገኛሉ። ይህም ጠቃሚ ነው ቢባልም በሌላ በኩል ደግሞ የዚህ ቪታሚን ከፍተኛ መጠን መገኘት የኩላሊት ጠጠርን ያስከትላል። "ጉድለት ከሌለዎት በስተቀር የቫይታሚን ምግቦች ለበሽታ መከላከያ ሥርዓትዎ ጠቃሚ አይደሉም" ብለዋል ኢዋዋኪ። በርካታ ጥናቶች ዝቅተኛ የቫይታሚን ዲ መጠንን ከመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች እና ከፍ ካለባቸው ከባድ ምልክቶች ጋር ያያይዙታል። በእርግጥ ብዙ በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ቫይታሚን ዲን በንቃት መገንዘብ ይችላሉ። እናም ምንም እንኳን በትክክል ምስጢር ሆኖ የሚቆይ ቢሆንም በነበረም ሆነ በተላላፊ በሽታ ምላሽ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይታሰባል። የቪታሚን ዲ እጥረት በብዙ አገራት (ሃብታም አገራትን ጨምሮ) ወረርሽኝ ነው። ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ በዓለም ዙሪያ አንድ ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በቂ ቫይታሚን ዲ እንዳላገኙ ይገመታል። ኮሮናቫይረስን ለመከላከል እራስን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ይረዳሉ በሚል በርካታ በተጨባጭ መረጃ ያልተደገፉ ነገሮች በስፋት ይሰማሉ። ነገር ግን እርስዎን የሚከላከል አንድ መንገድ አለ፤ ከሌሎች ሰዎች መራቅ። ፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶችን ማከማቸት አያስፈልግም። ነጭ የደም ሴሎች መርዛማ የኦክስጂን ውህዶችን ይለቃሉ። እነዚህም ባለ ሁለት መልክ ናቸው። በአንድ በኩል፣ ባክቴሪያዎችንና ቫይረሶችን እንዳይበዙም ያግዳቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ጤናማ ሴሎችን በመግደል ካንሰርና እርጅና እንዲከሰት እንዲሁም የሰውነትን በሽታ የመከላከል ሥርዓትን ሊያጠፉና ሊጎዱ ይችላሉ። ይህ እንዳይከሰት ለማስቆም ሰውነት በፀረ-ተህዋሲያን ላይ የተመሠረተ ነው። እነዚህ የማይታዘዙ የኦክስጂን ውህዶችን ለመቆጣጠርና ሴሎቻችንን ደህና ለማድረግ ይረዳሉ። እናም እነዚህን ከምግቦቻችን ውስጥ እናገኛለን። በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ማንኛውም ዓይነት መድኃኒትም ሆነ ቅመም ከኮቪድ-19 ሊከላከለን እንደሚችል የሚያመለክት ምንም መረጃ የለም። ስለዚህ ምን አንደሚሠራ ተረጋግጧል? ኢዋዋኪ እንደሚሉት አብዛኛዎቹ ታሪኮች በአንፃራዊነት የፈጠራ ሲሆኑ የተሳሳተ የደኅንነት ስሜት ይሰጥዎታል። "የማስጠነቅቀው ነገር ቢኖር ሰዎች የደኅንነት ስሜት ሲሰማቸው ወደ ውጭ በመሄድ በድግሶች ላይ እንዳይሳተፉ ነው" ይላሉ። የበሽታ መከላከያ ሥርዓትን የሚያጎለብቱ ዘዴዎች አሉ። የሚያማልሉ ወይም ታሽገው የሚሸጡ አይደሉም። ገንዘብዎንም አይጠይቁም፤ በቂ እንቅልፍ ያግኙ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ፣ የተመጣጠነ ምግብ ይመገቡና ጭንቀትን ለማስወገድ ይሞክሩ። ይህ ካልተሳካ ለተወሰኑ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን መከላከያ የሚሆን አንድ እርግጠኛ መንገድ አለ፤ ክትባት። ነገር ግን እስካሁን ለኮሮናቫይረስ መከላከያ የተገኘ ነገር የለም።
news-52649232
https://www.bbc.com/amharic/news-52649232
"ለሃያ አመታት ያህል ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስዘጋጅ ነበር" የንፅህና ሱሰኛው
የመፍራት ደረጃችን ቢለያይም፤ ብዙዎቻችን ጀርምን እንፈራለን። የቢቢሲው ጋዜጠኛ ፒተር ጎፊን ጀርሞችን በመፍራት፣ ጀርሞችን ከቤቱም ሆነ ከአካባቢው ሙሉ በሙሉ እንዲወገዱ ለሁለት አስርት አመታት ጥሯል።
ህይወቱ በሙሉ አካባቢውን በንፅህና ከመጠበቅ ጋር የተያያዘ ነው። ንፁህ ካልመሰለው ያስጨንቀዋል፤ ይሸበራል። ዓለም የምትገለበጥና መጥፎም ነገር የሚከሰት ይመስለዋል። ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ መታጠብ፣ ፀረ ተህዋሲያን (ዲስኢንፌክታንት) መጠቀም በሚመከርበትና ብዙዎች ብዙዎች ድግሞ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ በሚጥሩበት በዚህ ወቅት ነገሩ ለፒተር ግን የህይወቱ አካል ነው። ከሰሞኑ በማዕድ ቤት ቁጭ ብዬ የገዛኋቸውን የታሸጉ ጥራጥሬዎችን በፀረ-ተህዋሲያን እያፀዳሁ ነበር፤ እናም ለብዙዎች ይህ ምናልባት አዲስ ሊሆን ይችላል። ለእኔ ግን በባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያደረግኩት ነው። ድንገት አንድ ሃሳብ ብልጭ አለልኝ ፤ እሱም ላለፉት ሃያ ዓመታት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስዘጋጅ እንደነበር። ገና በአስራዎቹ እድሜ ነው ኦሲዲ (ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር) እንዳለብኝ የተረዳሁት። (ኦሲዲ የማይፈለግና ለመቆጣጠር የሚያስቸግር ሃሳብ በሰዎች እዝነ ህሊና እየተመላለሰ የሚያስጨንቅና፤ አንድን ነገርም ሱስ በሚባል ሁኔታ በተደጋጋሚ ከማድረግ ጋር ይገናኛል።) ሁለት ሦስተኛውንም የህይወት እድሜዬን ያሳለፍኩት ስለጀርሞች በመጨነቅ ነው፤ እንዴት ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ይተላለፋሉ? እንዴትስ ማጥፋት ይቻላል? የሚለው የዘወትር ጭንቀቴ ነበር። በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ስጋት የሆነውን የኮሮናቫይረስን መዛመት ለመከላከል የሚደረጉ ቅድመ ጥንቃቄዎችን ስሰማ ምን ያህል ቀድሜ እንደሄድኩም እረዳለሁ። በዘመናት የዳበረ ልምድ ከቤት ውጭ ያሉ ሰዎች ጋር አካላዊ ንክኪን ማስወገድ፣ ሌላ ሰው የነካውን ማንኛውንም ነገር ድንገት ብነካ መታጠብ፣ ከሱፐር ማርኬት የገዛኋቸውን ማንኛውንም እቃዎች በፀረ ተህዋሲያን (ዲስኢንፌክታንት) ማፅዳት አሁን በዚህ ወቅት ሳይሆን የህይወቴ አካል የሆኑ ተግባራት ናቸው። በዘመናትም በዚህ ረገድ ጠቢብ ሆኛለሁ ብል ማጋነን አይሆንም። በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮናቫይረስ በፈጠረው የአኗኗር ዘይቤና ባህልም የራሴን ባህርይ አይበታለሁ። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን በቫይረሱ ልጠቃ እችላለሁ ከሚል የመነጨ ፍራቻ የሚፈጥረው የፅዳት ሱስ ሙሉ በሙሉ አጥጋቢ ስለማይሆንም ጭንቀት ይፈጥራል። ሺህዎች ሳይሆኑ ሚሊዮኖች በአሁኑ ወቅት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተገናኘ "ሱፐርማርኬት ስገበያይ ያ ግለሰብ ተጠግቶኝ ይሆን?" እጄን በተገቢው መልኩ ታጥቤ ይሆን? ሳሙናው ጀርሞችን ይገላል? እናም በሌሎች ጥያቄዎች እየተረበሹ ነው። በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ስለ ኦሲዲ የምርምር ፅሁፋቸውን ያበረከቱ ዶክተሮች ይህንን ችግር "የጥርጣሬ እብደት" ብለውታል። እውነትም በጥርጣሬ ማበድ፤ በተለይም ጭንቀቴን መቆጣጠር ሲያቅተኝ ፤ መቼም ቢሆን እርግጠኛ አለመሆኔን ሳውቅ እውነትም ዶክተሮቹ እንዳሉት ነው። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ደግሞ አሁን ብዙዎች ይሄ ስሜት እየተሰማቸው ነው። አካላዊ ርቀታችንን መጠበቅ ከቻልን፣ በተደጋጋሚ እጃችንን ከታጠብን፣ አገራት ያሳለፏቸውን ቤት የመቀመጥ መሪያዎችን ከተከተልን በቫይረሱ እንደማንያዝ እርግጠኛ ነን። ነገር ግን አእምሯችንን የሚነዘንዘን ጥርጣሬና እርግጠኛ አለመሆን፤ ከዚያም ጋር ተያይዞ የሚመጣው ጭንቀት ህይወታችንን ሞልቶታል። የሚመላለሱት ሃሳቦች መጥፎ ስሜቶች ናቸው። ምናልባት ጭንቀቱ በትንሹም ቢሆን እንድንጠነቀቅ ያደርገን ነበር፤ ችግሩ ግን ከቁጥጥራችን ውጪ ይሆናሉ። በህይወቴ እንደማውቀው ጥርጣሬው የሚጀምረው "ንፁህ ነኝ" ከሚል ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ትንሽ ቆይቶ "ወደ ቀደመው ህይወቴ መመለስ እንዲሁም ኖርማል ልሆን እችል ይሆን" ወደሚለው ያመራል። ከዚያም በተደጋጋሚ መሞከሩ አድካሚ ያደርገዋል። መቼ ጀመረ? ያደግኩት ካናዳ ነው። ገና በአምስት ወይም ስድስት ዓመቴ ነው ጭንቀቴንና ፍርሃቴን መቆጣጠር የተሳነኝ። አስራ ሁለት ዓመቴ ሲሆን በአጠቃላይ ፍርሃቴ ከንፅህና ጋርና በጀርሞች መጠቃት ጋር የተያያዘ ሆነ። በተለይም ሰዎች ሲናገሩ ምራቃቸው መፈናጠሩና ሽንት ቤት ተፀዳድተው የማይታጠቡ ሰዎች መኖራቸውን ሳስብ ገዳይ የሆኑ ባክቴሪያዎች በሙሉ በሰውነቴ ላይ እየተርመሰመሱ እንደሆነ አስባለሁ። በር መዝጋት ስፈራ፣ መብራት ማጥፋትም ሆነ ማብራት ስጋት ሲሆንብኝ፤ እጄ እሲከቀላ ኧረ እንዳውም እስኪላጥ ስታጠብ ቤተሰቦቼ መመልከት ጀመሩ። እድለኛም ሆኜ ደጋፊና ችግሬን የሚቀበሉ ቤተሰቦች አሉኝ። ችግሬን ለመስማትም ሆነ ግራ ያጋባ በነበረው የጤና ሥርዓትም ውስጥ ህክምና እንዳገኝ ጥረት አድርገዋል። እናም ጭንቀቴን መቆጣጠር እንድችልም መድኃኒቶች ታዘዙልኝ። ከህክምናውም ጋር ሆነ ከንፅህና ሱስ ጋር መኖርን ተለማመድኩት። ሆኖም የንፅህና ሱሴ ታዳጊም ሆነ በ20ዎቹ እድሜዬ ላይ ህይወቴን አመሳቅሎታል። ሁለተኛ ደረጃም ሆነ ዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ ከጥናት በላይ ትኩረቴም ሆነ የሚያስጨንቀኝ ጀርሞችና ንፅህና ናቸው። አንዳንድ ጊዜም ሙሉ ሌሊት ልብሴን ሳጥብ፣ በደንብ ንፁህ ነኝ ብዬም ስለማስብ ሁለት ሦስት ጊዜ ገላዬን እታጠባለሁ። ጓደኞቼም ጋር የነበረኝ ግንኙነት የተገደበ ነበር፤ ይበክሉኛል ብዬም ስለማስብ ብቻ አይደለም። የተለየሁ መሆኑን ካወቁ ያገሉኛል የሚለው ሌላ ጭንቀቴ ነበር። ነገሮችን ለማሻሻል ጥረት በባለፉት አምስት ዓመታት ከኦሲዲ ጋር የተገናኘ ፍራቻዬን በተወሰነ ደረጃ መቆጣጠር ችያለሁ። ፍራቻዬንም መጋፈጥ መረጥኩኝ። በተቻለም መጠን ሊረዱኝ የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ እንዲሁም አላስፈላጊ የሚባሉና ከቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮችንም ላለማሰብ እሞክራለሁ። የትዳር አጋሬም ትዕግስተኛና የምትረዳኝ መሆኗ ህይወቴን አቅልሎታል። በሚገርም ሁኔታ ጀርምን ይፈሩና ጭንቀት የነበረባቸው ሰዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ መረጋጋት ታይቶባቸዋል። ምናልባትም የእነሱን የህይወት ዘይቤ ዓለም ስለተቀበለው፤ ዓለምን የሚመለከቱበት መነፅርን ብዙዎች መረዳት መቻላቸው እንዲሁም በርካቶች አስፈላጊ የሚባሉ ጥንቃቄዎች ከማድረጋቸው ጋር ተያይዞ ነው። ለእኔም ይህ ጉዳይ በተወሰነ መልኩ እውነታ አለው። ሆኖም ወረርሽኙም ደግሞ ፍንትው አድርጎ ያሳየኝም ጉዳይ አለ። በጎዳናዎች ላይ እንኳን ስንተላለፍ በቀላሉ ጀርሞች ከሰው ወደ ሰው መተላለለፍ መቻላቸው በተደጋጋሚ መነገሩ የምጨነቅበት ጉዳይ ምን ያህል እውነት እንደሆነም አሳይቶኛል። ድሮም ቢሆን ሱፐርማርኬት ሄጄ ስገዛ የሰው ንክኪን በመፍራት የታሸጉ ነገሮችን እመርጥ ነበር። ሆኖም ምግቦች ላይ የከፋ ስጋት አልነበረኝም። አሁን ግን በወረርሽኙ ምክንያት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ጀምሬያለሁ። አዕምሮዬ ታሞ ወደ ነበረበትና ከአስር ዓመት በፊት ወደነበረው ጥንቃቄም በተወሰነ መልኩ ተመልሻለሁ። የኮሮናቫይረስ ያጠናከረው ስጋት ከሱፐርማርኬት ስመለስ የገዛኋቸውን እቃዎች በሙሉ ቤቴ ውስጥ ገለል አድርጌ አስቀምጣቸዋለሁ። ጫማዬንም አውልቄ በሩ ላይ በጥንቃቄ አስቀምጣለሁ። እጄንም በደንብ እታጠባለሁ። የገዛኋቸውንም ነገሮች በሙሉ በውሃ፣ በፀረ ተህዋሲያን አፀዳለሁ። በተደጋጋሚም እጄን አታጠባለሁ። ከዚያም መደርደሪያ ወይም ፍሪጅ ውስጥ እከታለሁ። ይሄ አዲስ ልምድም ሆነ ባህርይ አይደለም ነገር ግን ለዓመታት ላስወግደው ያልቻልኩት የንፅህና ሱስ ነው። ምናልባት ብዙዎች እነዚህን ተግባራት ሊያከናውኑ ይችላሉ ሆኖም የእኔ ከባዱ ጭንቀትና የአዕምሮዬም ጤና እክልም እየገጠመኝ ነው። በኮሮናቫይረስ ምክንያት የአዕምሮ ጤና መቃወስም ችግሮች እየተፈጠሩ ነው። እርዳታን የሚሹ በርካታ ግለሰቦችም በየአገራቸው ያሉ የጥሪ ማዕከላትን እያጨናነቁ ነው። በአሁኑ ወቅት ሃገራት ጥለዋቸው የነበሩ አስገዳጅ የቤት መቀመጥም ሆነ የእንቅስቃሴ ገደቧችን መለላት አለባቸው የሚሉ ውይይቶች መበርታታቸውን ተከትሎ ብዙዎች መረጋጋት አልቻሉም። ትልልቅ መደብሮች፣ ቢሮዎችም ሆኑ ትምህርት ቤቶች የመከፈት እቅድና ሁኔታዎች ወደ ቀደመው ሁኔታ እንዲመለሱ እቅዶች ቢኖሩም ዓለም በኮሮናቫይረስ ከመጣባት ፍራቻና ጭንቀትም በቀላሉ አታገግምም። ለወራትም የሚቀጥል ይሆናል። በልምድ የዳበረ መፍትሔ ራሴን ከመፈተሽ እንዲሁም በዓመታት ውስጥ ካደረግኳቸው ህክምናዎች [ቴራፒዎች] የተማርኩት ነገር ቢሆን ፍራቻን መቆጣጠር እንደሚቻል ነው። ልምዴንም ለማካፈል ያህል፤ ከባለሙያዎች ወይም ከማምናቸውና ከምወዳቸው ሰዎች ጋር ጭንቀቴንና ስሜቴን በተረጋጋ ስሜት ማጋራቴ ብዙ ረድቶኛል። በህፃንነቴም ካናዳ እንዲሁም ትልቅ ሆኜ በእንግሊዝ የወሰድኩት ቴራፒ ብዙ ረድቶኛል፤ ምናልባት ባለሙያ እንኳን ማግኘት ካልተቻለ በራሳችሁ ማከናወን የምትችሏቸው ጉዳዮች አሉ። ለማንኛውም ሰው ሊጠቅሙም ይችላሉ። ለምሳሌም ያህል የሚያስጨንቋችሁን ጉዳዮች መዘርዘር፣ ለምን እንዳስጨነቃችሁና ምን እንደሚሰማችሁ መፃፍ። ከዚያም ዝርዝሮቹን በመመልከት ምክንያቶቹን መረጃዎችን በመጠቀም ማጤን፤ እናም ጭንቀታችሁ የተጋነነ፣ መሰረት የሌለው ወይም መፍትሄ ያለው መሆኑንም ትረዳላችሁ። በተለይም በአስገዳጅ ሁኔታ ቤት የተቀመጡ ሰዎች የጤና ስጋቶች፣ ሥራ ማጣት፣ ሥራዬን ላጣ እችላለሁ የሚል ስጋት፣ ብቸኝነት፣ መገለልና እንዲሁም ደስታ ማጣት ሊያጋጥም ይችላል። እናም እነዚህን ጭንቀቶች በደንብ በመርመር የተወሰነ ማቅለል ይቻል ይሆናል። ለምሳሌ ብቸኛ ላለመሆን በኣካል እንኳን ማግኘት ባትችሉ ከቤተሰብ ወይም ከጓደኞች ጋር በቪዲዮ ማውራት ሊሆን ይችላል። ሁኔታዎች ሲረጋጋጉ ደስ የሚል ስፍራ ለመሄድ ማቀድ፤ የባለሙያ ምክርም መስማት ይረዳል። በቫይረሱ የተጠቁ በርካታ ሰዎች አገግመዋል። እጅን በተደጋጋሚ መታጠብም ሆነ ልብስን ማጠብ ቫይረሱን እንደሚያስወግድ ሳይንሳዊ መረጃዎች መረዳት። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን በወረርሽኙ ብቻችንን አለመሆናችንን ልናውቅ ይገባል። ከዓለም ህዝብ ጋር አብረን እየተጋፈጥን ነው። ጭንቀቴና ፍርሃቴ በሚጨምርበት አንዳንዱ መጥፎ ቀን ለራሴ ያለኝ ስሜት ያሽቆለቁላል። ራሴን እንደ እንግዳና ሞኝ እንደሆንኩ እቆጥራለሁ። በዓለም ላይም እንደእኔ የሚሰማው ሰው እንደሌለም አስባለሁ። አሁን ግን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የኮሮናቫይረስ ጫና ሁላችንም ጫንቃ ላይ ነው። በዚህ ቀውስ ወቅት ራሳችንን ብናገልም፤ አንድ ላይ በሕብረት ነው የቆምነው።
news-53822257
https://www.bbc.com/amharic/news-53822257
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ እየጨመረ የመጣውን የብሔር ክፍፍል መመለስ ይችሉ ይሆን?
ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ ወደ ስልጣን ሲመጡ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ የዜጎች መፈናቀል እና ብሔር ተኮር ጥቃቶች መቋጫ ያገኛሉ የሚል እምነት ነበር።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በሁለት ዓመት የስልጣን ቆይታቸው ብዙ ለውጦችን አምጥተዋል። በተለይ ለሁለት አስርት ዓመታት ውጥረት የነበረበትን የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ እልባት በመስጠታቸው የዓለም የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ለመሆንም በቅተዋል። ግጭቶችና ተቃውሞዎች አሁንም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እንደቀጠሉ ናቸው። በሰኔ ወር መጨረሻ የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተነሳ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ እየጨመረ የመጣውን የብሔር ክፍፍል መመለስ ይችሉ ይሆን?
41855200
https://www.bbc.com/amharic/41855200
ጋሬጣ የተሞላበት የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ በኢትየጵያ
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የተደራጀ ተቃውሞ በሚነሳበት ወቅት የፊውዳላዊውን አገዛዝ ለመገርሰስ አስተዋፅኦ ያደረገው በጊዜው የነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ የአብዮቱ አንቀሳቃሽ ሞተር ተደርጎ ይታያል።
በአገሪቷ ውስጥ የነበሩ የባሌና የጎጃም ገበሬዎች አመፅ፣ የመምህራን ሀገር አቀፍ እንቅስቃሴ እንዲሁም በአጠቃላይ ማህበረሰቡ በተለይም ሴተኛ አዳሪዎች በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ቢኖራቸውም ታሪካቸው በተገቢው ሁኔታ አልሰፈረም። በዲላ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆነችው መስከረም አበራ በዚህ ላይ እንደ ምክንያት የምታያቸው የተወሰኑ ፅንሰ-ሀሳቦች አሏት። መስከረም እንደምትለው ብዙ ፅሁፎች የሚፃፉት በወንዶች ስለሆነ የሴቶችን ሚና ያለማጉላት ጉዳይ አለ። ከዚህም በተጨማሪ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ላይ የሴቶች ተሳትፏቸውም የተወሰነ ነበር። በተለይም በተማሩት መካከል የመሬት ለአራሹ እና የመደብ ጥያቄዎች በጠነከሩበት ወቅት ምንም እንኳን ሴቶች ቢኖሩበትም መስከረም እንደምትለው የእንቅስቃሴው መሪዎች አልነበሩም። የተወሰኑትም ተሳትፎ የነበራቸው የወንድ ጓደኞቻቸውን በመከተል እንደሆነ ትናገራለች። ፌሚኒዝም አገራዊ በሆነ መልኩ ውይይቶች እንዲፈጠሩና፤ የፆታ እኩልነት እንዲሰፍን የሚታገለው የሴታዊት እንቅስቃሴ አንደኛዋ መስራች የሆነችው ዶክተር ስሂን ተፈራ የሴቶች ቁጥር በሚያስደነግጥ ሁኔታ ከማነሱ በተጨማሪ በፖለቲካው ላይ የነበራቸው ተሳትፎ "በሚያሳፍር ሁኔታ" ቡና ማፍላት፣ የስብሰባ ቃለጉባኤ መያዝ፣ ወረቀት መበተን፣ መፈክር መያዝን የመሳሰሉ ሚናዎች ይሰጣቸው እንደነበር ትናገራለች። ከዚህም በተጨማሪ በወቅቱ ተሳታፊ የነበሩት ሴቶች እንደሚናገሩት ይቀልዱባቸው እንደነበር ስሂን ትናገራለች። ይህ ሁኔታ እየተለወጠ የመጣውም የፖለቲካ ንቃተ-ህሊናቸው ከፍ ባሉት እነዋለልኝ መኮንን የመሳሰሉት የሴቶች መብትንና እንቅስቃሴውን ስለተቀበሉት ነው። ከአስርት ዓመታትም በኋላ ብዙ ለውጥ እንደሌለ የምትናገረው መስከረም በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያሉ የሴቶች ቁጥር አነስተኛ ነው፤ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ ሴቶችም በጣም ጥቂት ናቸው። ጎልተው ከወጡት መካከል ብቅ ብላ የጠፋችውና የቅንጅት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር የነበረችውና ብርቱካን ሚደቅሳ ተጠቃሽ ናት። ከእርሷ በኋላም ሆነ ከሷ በፊት የነበሩት ሴቶች በስም ማጥፋት ዘመቻ ከፖለቲካው ምህዳርም ተገለዋል። በፖለቲካ ላይ ለምን መሳተፍ አስፈለገ? በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በመንግሥት ደረጃ የፖለቲካውን ስፍራ የተቆጣጠሩት ወንዶች ናቸው። ማህበረሰቡን ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ሴቶችን የሚመለከቱ ህጎችን የሚያረቁትም ሆነ የሚያስፈፅሙት ወንዶች ናቸው። አቶ ሺመልስ ካሳ "ቻለንጅስ ኤንድ ኦፖርቱኒቲስ ኦፍ ዉሜን ፖለቲካል ፓርቲሲፔሽን ኢን ኢትዮጵያ" በሚለው ፅሁፋቸው የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለምን አስፈለገ ለሚለው ጥያቄ እንደ ዋነኛ መልስ የሚያነሱትም የፍትህ ጥያቄን ነው። ግማሹን የህብረተሰቡን ክፍል እንደ መያዛቸው መጠን በውክልና ዲሞክራሲ ሴቶች በራሳቸው ለምን አይወከሉም የሚል ነው። ሌላኛው ደግሞ የሴቶችና የወንዶች የህይወት ልምድ በተለይም ከታሪካዊ ፆታዊ ኢ-ፍትሀዊነት ጋር ተያይዞ መስተካከል ያለባቸው ህግጋትንና አፈፃፀማቸውን ከሴቶች በላይ የሚያውቅ ስለሌለ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሴቶችና ወንዶች በእኩልነት መወከል አለባቸው የሚሉ ሐሳቦችንም ያነሳሉ። መስከረም አበራና የውብማር አስፋው መሰናክሎቹ ምንድን ናቸው? መስከረምም ሆነ ስሂን እንደ ምክንያትነት የሚጠቅሱት "አባታዊ ሥርዓት'" (ፓትሪያርኪ) ወንዶችን የበላይ በማድረግ ሴቶችን የደጋፊነት ሚና ሰጥቷቸዋል። በዚህም የፆታ የሥራ ክፍፍልና የሴቶችን ሚና በማዕድ ቤት ሥራዎች፣ ልጅ መውለድና መንከባከብ ነው። ሴቶች ወደ አደባባይ መውጣታቸው እንደ ነውርና ሥርዓቱን እንደ መጣስ ተደርጎ ነው የሚታየውም ትላለች መስከረም። ይህንን ሥርዓት ተላልፈው በፖለቲካው ላይ ተሳትፎ ያደርጉ የነበሩ ሴቶች ዘለፋ፣ ስድብ እንዲሁም "እዩኝ ባይ" የሚል ስም እንደሚያተርፉም ትናገራለች። በተለይም መሪ መሆን የወንድነት ሥራ ተደርጎ የሚታይ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የእምነት ተቋማት ሴቶች በብዙ መንገድ ከወንድ እንደሚያንሱ መስበካቸውም አስተዋፅኦ አድርጓል። የሀይማኖት ድርጅቶቹ የሴቶችን ቦታ ግልፅ አድርገው እንዳስቀመጡ አቶ ሽመልስ ይናገራሉ። ከሴቶች አለባባበሰ ጀምሮ፤ በምን መንገድ ወንዶችን መታዘዝ እንዳለባቸው እንዲሁም ከእምነት ቦታዎች አመራርም የተገለሉ መሆናቸው አስተዋፅኦ አድርጓል በማለት አቶ ሽመልስ በፅሁፋቸው አስፍረዋል። በተለይም የቤተሰብ መዋቅር ሲነሳ ይላሉ አቶ ሽመልስ "አባታዊ" በሆነ መንገድ የሚመራ ሲሆን የመንግሥት ሥርዓትም የቤተሰብ መዋቅርን ከመከተሉ አንፃር በቤት ውስጥ ያለውም የወንዶች የውሳኔም ይሁን የሌሎች ጉዳዮች የበላይነት በመንግሥት መዋቅሮች፤ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ወይም በቀን ተቀን ኑሮ ውስጥ ይንፀባረቃል። ብዙ ሴቶች ቢማሩም አሁንም ያለው "ያረጀ ያፈጀ" የሥራ ክፍፍል ሴቶች ቤት ውስጥ እንዲሰሩ ያስገድዳቸዋል። በሚገርም ሁኔታ ሁለቱም ተመሳሳይ ሥራ ሰርተው የገንዘብ አመንጪ ቢሆኑም ሴቷ የቤቱን ሥራ እንድትከውን ይጠበቅባታል። ይህም ሁኔታ ለመስከረም ጊዜያቸውን በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዳያተኩሩ እንደሚያደርጋቸው ትናገራለች። በተለያዩ መፅሄቶች የአገሪቷን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን ትንታኔ በመፃፍ የምትታወቀው መስከረም ለወንዶች ተብለው የተተዉ እንደ "ፓርላማ" መመልከት የእሷ ቦታ እንዳልሆነ የሚነግሯት አይታጡም። በተለይም ይህ "አባታዊ"ን ሥርዓት ምንም እንኳን ወንዶችን ቢጠቅምም ማህበረሰቡ እንደ ሥርዓት የተቀበለው በመሆኑና ሴቶችም ስለተቀበሉት ሥርዓቱን ለማፍረስ ውስብስብ ያደርገዋል። "ወንዶች የራሳቸው የሆነ የሚሰባሰቡበትና የሚወያዩበት ሴቶችን ያገለለ ቡድን አላቸው" የምትለው መስከረም ከዚህም ጋር ተያይዞ ሴቶች በፖለቲካው ወጣ ወጣ ሲሉ "ኩም" እንደሚደረጉ ትናገራለች። በአንድ መፅሄት ስትፅፍ በተመሳሳይ ዘርፍ ይፅፍ ከነበረ ወንድ በአራት እጥፍ ያነሰ ክፍያ እንዲሁም ፅሁፏን አውቀው እንዳላነበቡ የሚነግሯት ወንዶችም አልታጡም። " ጎበዝ ካለችና እነሱን የምትፈታተን ከመሰላቸው በተለያዩ ነገር ሊመቷት ይፈልጋሉ፤ የማሸማቀቅ ፖለቲካ የሰፈነበትና በአይን የሚታዩና የማይታዩ ጋሬጣዎች የተሞሉበት ነው" ትላለች። የፆታዊ ጥያቄዎችና መደራጀት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም ቦታው ግን አሁንም የአንድ ፓርቲን ሥራ ለማስፈፀም ካልሆነ ትክክለኛ ተሳትፎ አይደለም የሚሉት የህወሓት የቀድሞ ታጋይ የውብማር አስፋው ናቸው። የውብማር እንደሚናገሩት በንጉሡ አገዛዝ ዘመን ከ240 የፓርላማ አባለት 2 ሴቶች፤ በደርግ ጊዜ ከ835 የሸንጎ አባላት14 ሴቶች ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የሴት ፓርላማ አባላት 30 በመቶውን ይይዛሉ። ቁጥር መጨመሩን እንደ መልካም ነገር የሚያዩት ስሂንና የውብማር፤ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ የፓርቲውን ፕሮግራም ከማስፈፀም የዘለለ ባለመሆኑ ተሳትፎውን ሙሉ አያደርገውም ይላሉ። "በአሁኑ ወቅት ተሳትፏቸውን እንደ መሳሪያና የሴቶች ጥያቄ እንደተመለሰ ተደርጎ ነው እየተነገረ ያለው፤ ይሄ ግን ከወረቀት እየዘለለ አይደለም። ዋናው ጥያቄ ግን ነፃነት አላቸው ወይ? ምን ያህልስ የሀገሪቱን ፖሊሲ መቀየር ይችላሉ? ምንስ ያህል ተፅእኖ ፈጥረዋል" ብለው ወ/ሮ የውብማር ይጠይቃሉ ። ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘም በኋላ የነበሩት ሴቶች በአገሪቷ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መዋቅሮች ፖሊሲዎችን በማርቀቅና ህጎችን በማውጣት ተሳትፎ አልነበራቸውም። "ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለበት ትግል ቢሆንም፤ የመጣው ለውጥ ግን ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን አፋኝና ሰብአዊ መብቶችን የሚጥስ ድርጅት ነው" ይላሉ የውብማር። እነዚህ መሰናክሎች እያሉ በተደራጀ መልኩ የሴቶች እንቅስቃሴ ጎልቶ መውጣት ቢከብድም የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን የመሰለ ጠንካራ ድርጅትም መምጣት ችሏል። ከመንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ህግና ገቢ ከማግኘት ጋር ተያይዞ የድርጅቱ ሚና ቢቀንስም በሀገሪቱ ውስጥ የፆታ ግንኙነት ላይ ውይይቶችንና አከራካሪ ጉዳዮችን በመድረኩ ላይ በማምጣት አብዮት መፍጠር ችለዋል። የተነሱትንም ጥያቄዎች በማስቀጠልም፤ ብዙ ያልተደፈሩ አከራካሪ ጉዳዮችን በማንሳት ሴታዊት እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው። እስካሁን ድረስ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሁኑ የነፃነት እንቅስቃሴዎች የሥርዓተ-ፆታን ጥያቄ እንደ ፖለቲካ ጥያቄ አድርገው ይዘው መነሳት አልቻሉም። "ኃላፊነቱ የማን ነው? ማንነው ማንሳት ያለበት፤ ሴቶች ናቸው። የማንን ጥያቄ ማን ነው የሚያነሳው?" በማለት ስሂን ትጠይቃለች። "ፊኒክሷ ሞታም ትነሳለች፡ ያልተቋጨው የትግራይ ሴቶች ገድል" በሚል ርዕስ መፅሀፍ የፃፉት የውብማር በትግሉ ውስጥ የነበረው ሁኔታ ማህበረሰቡ ለሴቶች ዝቅተኛ ቦታ ያለው ነፀብራቅም ነው ይላሉ። በመጀመሪያው ዓመታት ሴቶች ፓርቲውን እንዲቀላቀሉ ያልተፈቀደ ሲሆን ከ1968 በኋላ ብዙ ሴቶች በሰራዊቱ እንዲሁም በሌሎች የትግሉ ዘርፍ ተሳታፊ ሆነዋል። የውብማር እንደሚናገሩት መጀመሪያ ላይ ከባድ መሳሪያዎችን ሴቶች መሸከም አይችሉም በማለት እኩልነትን ከጉልበት ጋር ማዛመድ፤ እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ የፆታዊ ግንኙነት ስለማይፈቀድ ሴቶችን እንደ ''አሳሳች'' ማየት፤ ይባስ ሲልም ፆታዊ ትንኮሳዎችም ነበሩ። ለችግሩም ምንጭ ወንዶችን ተጠያቂ የማያደርጉት የውብማር "ችግሩ የሰፈነው ሥርዓቱ ወንዶችን የበላይ ሲያደርግ ሴቶችን ተገዢና የበታች አድርጎ የሚያስቀምጡ ነው" በማለት ይናገራሉ። "በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው አቅምን አደራጅቶ መታገል እንጂ ማንም መብታችንን ሊሰጠን አይችልም። ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው፤ ስለሴቶች ጉዳይ ወንዶች እንዲታገሉ መማፀንም መጠበቅም የለብንም" በማለት ጨምረው ይናገራሉ። ለዚህ ግን የፖለቲካው ምህዳር መጥበብ የሰላማዊ ሰልፍን፣ የመናገር ነፃነትን መገደቡ ሴቶች ሊያደርጉት ከሚፈልጉት እንቅስቃሴ መገደብንም አምጥቷል ብለው ወ/ሮ የውብማር ያምናሉ።
news-56714416
https://www.bbc.com/amharic/news-56714416
ብራዚል በዓለም በቁመቱ ሦስተኛ የሆነ የክርሰቶስ ሐውልት እየገነባች ነው
በብራዚል ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ኤንካታዶ ከተማ የሚገነባው ባለ 43 ሜትር ቁመቱ የክርስቶስ ሐውልት በአገሪቷ ታዋቂውን የሪዮ ዴ ጄኒሮን ሐውልት ከመብለጡ ባሻገር በዓለም ላይ ሦስተኛው ረዥሙ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
የሐውልቱን ጭንቅላት እና የተዘረጉ እጆች የሚሳየው ክፍል ገጠማ ባለፈው ሳምንት ተጠናቋል። የግንባታው ሃሳብ ያመነጩት የከተማዋ ፖለቲከኛ አድሮአልዶ ኮናዛቲ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ነበር በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡት። በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ሐውልት 350 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በጀት ተይዞላታል። የክርስቶስ ወዳጆች የተሰኘው ማኅበር ለግንባታው የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከግለሰቦች እና ከድርጅቶች እያሰባሰበ እንደሚገኝም ገልጿል። ሐውልቱ ከአንደኛው እጅ ወደ ሌላኛው የእጅ ጫፍ ድረስ 36 ሜትር ሲረዝም ውስጥ ለውስጥ በሚገጠምለት የመጓጓዣ አሳንሰር ጎብኚዎችን እስከ ሐውልቱ ደረት ድረስ ይወስዳል። ይህም 40 ሜትር ከፍታ ሲኖረው ከተማዋን ለመጎብኘት ያስችላል ተብሏል። ይህንን ሐውልት የሚበልጡት ሁለት የክርስቶስ ሐውልቶች በኢንዶኔዢያ እና በሆላንድ ይገኛሉ። በኢንዶኔዢያ የሚገኘው 'ቡንቱ ቡራኬ' የተሰኘው የክርቶስ ሐውልት 52.55 ሜትር የሚረዝም ሲሆን የሆላንዱ 'ክራይስት ዘ ኪንግ' የተሰኘው ደግሞ 52.5 ሜትር ይረዝማል። በመላው ዓለም የድንግል ማሪያምን እና የቡድሃን ጨምሮ ከእነዚህ ሐውልቶች የሚረዝሙ በርካታ ሐይማኖታዊ ሐውልቶች ይገኛሉ።
news-43651648
https://www.bbc.com/amharic/news-43651648
አውስትራሊያ ሃሰተኛ የጋና ጋዜጠኞችን አባረረች
አውስትራሊያ የኮመንዌልዝ ስፖርታዊ ውድድርን ለመዘገብ ወደ አገሪቱ ያቀኑ 50 ሃሰተኛ ጋዜጠኞችን ልታባርር የቻለችው ግለሰቦቹ የቀረበላቸው ስፖርታዊ ጥያቄን መመለስ ባለመቻላቸው ነው።
እነዚህ ግለሰቦች ምንም እንኳ ሰነዶቻቸው እውነተኛ ቢሆን እንደ ስፖርት ጋዜጠኛ የቀረበላቸውንና በቀላሉ ሊመልሱት የሚገባቸውን ጥያቄ ባለመመለሳቸው ለጊዜው እንዲታሰሩ ከዚያም ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል። የጋና ምክትል ስፖርት ሚኒስትር ፒየስ ኢናም ሃዲዲዝ ጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ገልፀዋል። ነገር ግን በመጀመሪያ ደረጃም እነዚህ ግለሰቦች ቪዛ እንዲያገኙ ሚኒስቴር የመስሪያቤታቸው እጅ አለበት የሚለውን ውንጀላ አስተባብለዋል። ከተመላሾቹ መካከል ለአንድ የጋና ሬድዮ ጣቢያ ግለሰቦቹ ቪዛ እንዲያገኙ ለጋና ኦሊምፒክ ኮሚቴና ስፖርት ሚኒስቴር ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር መክፈላቸውን የተናገረ ግለሰብ አለም ተብሏል።
41862882
https://www.bbc.com/amharic/41862882
የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች
ባለፈው ግንቦት ከቦኮ ሃራም እገታ ከተለቀቁት ልጃገረዶች መካከል አንደኛዋ ለጋዜጠኛ አዳዎቢ ትሪሻ ንዋኡባኒ ለሶስት ዓመታት በታሰረችበት ወቅት ስላስቀመጠችው የማስታወሻ ደብተር አጫውታታለች።
የ24 ዓመቷ ናዖሚ አዳሙ አብረዋት ይማሩ ከነበሩት መካከል በእድሜ ትልቋ ነበረች። እ.አ.አ በ2014 እርሷን ጨምሮ በአብዛኛው ክርስቲያን የነበሩ ከ200 በላይ ሴት ተማሪዎች ታግተው በሰሜን ናይጄሪያ ወደሚገኘው ሳምቢሳ የተሰኘ የቦኮ ሃራም መደበቂያ ደን ተወሰዱ። በእስር በነበሩበት ጊዜ ሴቶቹ ቁርዓን እንዲቀሩ ይደረግ ስለነበር ማስታወሻ የሚይዙበት ደብተር ተሰጥቷቸው ነበር። ከመካከላቸው ግን አንዳንዶቹ ሴቶች የእገታውን ማስታወሻ ለመያዝ ተጠቀሙባቸው። ታጣቂዎቹ ባገኟቸውም ጊዜ ደብተሮቹን አቃጠሉባቸው። ናዖሚ ግን የራሷን መደበቅ ችላለች። አሁን 20 የሞላት የቅርብ ጓደኛዋ ሳራ ሳሙኤልና ሶስት ሌሎች ልጃገረዶችም እነዚህን ደብተሮች ገጠመኞቻቸውን ለመመዝገብ ተጠቀሙባቸው። ለማስታወሻ የተጠቀሙበት 2 ባለ 40 ገጽ ደብተሮች ተርፈዋል የተገኙትም ማስታወሻዎች በመለስተኛ እንግሊዘኛና በደካማ ሃውሳ የተጻፉ ሲሆኑ ያለ ቀናት የተመዘገቡ ቢሆንም በታገቱባቸው የመጀመሪያ ወራት አካባቢ የተጻፉ መሆናቸው ግልጽ ነው። ለማገት አላሰቡም ነበር በአውሮፓውያኑ ሚያዚያ 14, 2014 ዓ.ም የቺቦክ ትምህርት ቤት ላይ ጥቃት ያደረሱት ታጣቂዎች አመጣጣቸው ሞተር ለመስረቅ እንጂ ልጃገረዶቹን ለማገት አልነበረም ። የፈለጉትም ሞተር የትኛው እንደነበር ግልጽ ባይሆንም የመኪና ይሁን ሌላ ለማወቅ አዳጋች ሆኗል። ሆኖም በአካባቢው የግንባታ ሥራ እየተካሄደ ስለነበረ ድንገት ሲሚንቶ የሚያቦካውን ሞተር ፈልገው ሊሆን ይችላል፤ ይህም ሞተር ደረቅ መሣሪያዎችን ለመሥራት መጠቀም ስለሚቻል ሊሆን ይችላል። ሞተሩን በአካባቢው ማግኘት ሲያቅታቸው ግን ሰብሰበዋቸው የነበሩትን ልጃገረዶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲነጋገሩ ግን መስማማት አልቻሉም ነበር። ማስታወሻው እንዲህ ይላል "እርስ በርሳቸው መጣላት ጀመሩ። አንድ ትንሽ ልጅ ከመካከላቸው 'ማቃጠል አለብን' አላቸው። 'አይሆንም ወደ ሳምቢሳ መውሰድ አለብን' አለ ሁለተኛው። ሌላኛው ሰው ደግሞ 'አይ አይሆንም እንደሱ አናድርግ' አለና 'እንምራቸውና ከዚያ ወደ ቤተሰቦቻቸው ቤት እንሂድ' አለ። እየተከራከሩም ሳለ አንደኛው 'አይሆንም ባዶ መኪና ይዤ መጥቼ ባዶ መኪና ይዤ አልመለስም፣ ባይሆን ወደ [አቡባከር] ሼኮ [የቦኮ ሃራም መሪ] ይዘናቸው ከሄድን ምን ማድረግ እንዳለበን ያውቃሉ። " አንዳንዶቹ ሴቶች በታጣቂዎቹ መኪኖች ላይ ተጭነው ብዙዎቹ ደግሞ ሽጉጥ ተደቅኖባቸው ብዙ ኪሎሜትሮችን ከተራመዱ በኃላ የጭነት መኪኖች መጥተው አፈሷቸው። ማስታወሻ ደብተሮቹን ማን ጻፋቸው? ወደ ቦኮ ሃራም መደበቂያ ደን እያመሩ ሳለ አንዳንድ ተማሪዎች ከጭነት መኪኖቹ እየዘለሉ መውረድ ጀመሩ። አንደኛዋ ታጋች ግን ለአጋቹ ነገረችው። ድንገት ብቻዋን ትቀራለች ብላ ፈርታ ወይም ሥልጣንን ለማክበር ወይም ደግሞ በስቃይ ብቸኛ ላለመሆን ሊሆን ይችላል ትላለች ጸሃፊዋ። "መኪናው ውስጥ የነበረችው አንደኛዋ ልጅ 'ሹፌር አንዳንድ ሴቶች ለማምለጥ እየዘለሉ ነው' አለችው። ሹፌሩም በሩን ከፈተና በእጅ መብራት ቢፈልጋቸውም ማንንም ማየት አልቻለም። ስለዚህ አንድ ቦታ ሳይንቀሳቀሱ መቀመጥ እንዳለባቸው ተናገሩ። ካሁን ወዲህ እሷም ሆነች ማንም ሲዘል ቢያዝ በሽጉጥ እንገልሻለን'አሉ''። በቦኮሃራም የታገቱት ልጃገረዶች ከብዙ ስቃይ በኋላ ሳምቢሳ ደን ደርሰዋል። የክፋት ተንኮሎች ታጣቂዎቹ የታገቱት ሴቶች ላይ የተለያዩ የክፋት ዘዴዎችን በመጠቀም ያስፈራሯቸው ነበር። ምንም ውሸት ቢሆንም ወላጆቻቸው በቦኮ ሃራም ቁጥጥር ሥር እንደሆኑ ይነግሯቸው ነበር። በአንድ ወቅት ክርስቲያኖቹን ከሙስሊም ሴቶች ለይተው ኃይማኖታቸውን ወደ እስልምና ካልቀየሩ በቤንዚን እንደሚያቃጥሏቸው ነገሯቸው። "ወደኛ መጡና 'ሙስሊም ለሆናችሁ የጸሎት ሰዓት ደርሷል' አሉ። ከጸለዩ በኃላ 'ሙስሊም የሆናችሁ በአንድ በኩል ክርስቲያኖች ደግሞ በዚያኛው ማዶ ሁኑ'አሉን ፤ ከዚያ መኪናው ውስጥ ጄሪካን ስናይ ቤንዚን መሰለን፥ እነሱም 'ስንቶቻችሁ ወደ እስልምና ትቀየራላችሁ?' አሉን። ብዙዎቹ በፍራቻ ምክንያት ከመካከላችን ተነስተው ወደ ውስጥ ገቡ... እነሱም መልሰው 'የቀራችሁት በሙሉ መሞት ስላማራችሁ ነው ሙስሊም መሆን የማትፈልጉት? እናቃጥላችኋለን' አሉንና ቤንዚን የያዘ መስሎን የነበረውን ጄሪካን ሰጡን። ቤንዚን ግን አልነበረም ... ዉሃ ነበር።'' የሴቶቹ የ'መደፈር' ጉዳይ ከዚህ በፊት የቺቦክ ትምህርት ቤት ታጋች ልጃገረዶች ቃላቸውን ሲሰጡ አልፎ አልፎ የጋብቻ ጥያቄዎች ቢቀርቡላቸውም ወሲባዊ ጥቃትም እንዳልደረሰባቸውና ያለፍላጎታቸው እንዲያገቡ እንዳልተደረጉ ተናግረዋል። ልጃገረዶቹ ማስታዎሻዎቻቸውን በመቅበር ወይ በውስጥ ሱሪያቸው በመወሸቅ ይደብቋቸው ነብር እነዚህ ማስታወሻዎችም ልጃገረዶቹ እንደተደፈሩ ተደርጎ በተለያዩ ሚዲያዎች መወራቱ ታጣቂዎቹን በእጅጉ አስቆጥቷቸው እንደነበረ ይጠቅሳሉ። የታጣቂዎቹ አለቃ የሆነው አቡበካር ሼኮ በተደጋጋሚ ንዴቱን ግልጽ አድርጓል። እሱም በመጀመሪያ በተቀዳ መልዕክት ለልጃገረዶቹ መልዕክት አስተላልፏል። "ከዚያም በማታ አሰባሰቡንና የተቀዳ ካሴት አብርተው ይሰብኩልን ጀመር። ካሴቱ ከአለቃቸው ከአቡበከር ሼኮ መሆኑንም ገለጹልን... እሱም የፈጣሪን መንገድ ለማስተማር ብናግታችሁ ወላጆቻችሁ፣ ትምህርት ቤታችሁና መንግስታቸሁ እንደደፈርናቸሁና መጥፎ ነገር እንዳደርግናችሁ እየተናገሩ እያለቃቀሱ ነው። እኛ ግን የአላህን መንገድ ልናስተምራችሁ ነው ያመጣናችሁ። " የታጣቂዎችን ፍላጎት ላለማነሳሳት ሂጃብ መልበስ ታጣቂዎቹ ምንጊዜም ቢሆን ሴቶቹ ፍላጎታቸውን እንዳይፈታተኑ ይጠይቋቸው ነበር ፤ እናም ሰውነታቸውን በሂጃብ እንዲሸፍኑ ይነግሯቸዋል። '' ቁርዓን ከፍቶ ማንበብ ጀመረ፤ ከዚያም ከአንድ ቦታ ይህን አነበበልን 'ለጂሃድ ውጊያ የታያዘ ሰው ሁሉ የራሳችሁ ነው፤ በዛ ሰው ላይ የፈለጋችሁትን ነገር ሁሉ ማድረግ ትችላላችሁ'... ሆኖም እነሱ ሰውነታችንን በማየት በእኛ ላይ ኃጢዓት እንዳይሰሩ ወይም ሌላ ክፉ ነገር እንዳይፈጽሙ በማሰብ ሂጃብ ሰጡን'' የጋብቻ ጥያቄዎች ማስታወሻዎቹ ከታጣቂዎቹ የሚቀርቡት የጋብቻ ጥያቄዎች የሚደጋገሙና የሚያስገድዱ እንደነበሩ ይገልጻሉ። "አንደኛዋ ልጅ ዕቃ ፈልጋ ወደ ክፍል ስትገባ ማላም አህመድ የተሰኘው አንደኛው ታጣቂተከትሏት ገብቶ ለጋብቻ ቢጠይቃት እምቢ አለችው። መልሶ ግን "ስለ ጋብቻ የራስሽ ውሳኔ ምንድን ነው? አላት""እሷም በድጋሚ እምቢ አለችው። 'በቺቦክ እማርበት ከነበረ የሴቶች የመንግሥት ትምህርት ቤት ወደ ሳምቢሳ አመጣችሁኝ፤ አሁን ደግሞ ስለ ጋብቻ ትጠይቁኛላችሁ' አለች። እንዴት ልታገባ ትችላለች በዚያ ላይ እናቷ፣ አባቷ፣አክሰቶቿና ጓደኞቿ አያውቁም። ከዚያ 'አላገባም ብትልና ባለችበት አምላኳን ብቻዋን ብታመልክ ጥሩ አይደለም' ወይ ብላ ጠየቀችው። እሱም "መጥፎ ነው" ብሎ መለሰላት።" አንዳንዶች ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ ግፊት ተደርጎባቸዋል። "ሰዎቹ በሁለት ሃይሉክስ መኪኖች ሲመጡ አይተናቸዋል። እንደመጡም ከመካከላችን ማግባት የሚፈልጉ ካሉ ጠየቁ። ከዚያም እስልምናን የተቀበልነው በግድ ማግባት እንዳለብን ነገሩን፤ በተለይ ኃይማኖቱን በሙሉ ልብ የተቀበልን ከሆነ። ምላሽም እንድንሰጣቸውም ግማሽ ሰዓት ጠበቁን። ከዚያ አንድ ሙሉ ሰዓት ጠበቁን ማንም መልስ አልሰጣቸውም። " ጋዜጠኛዋ እንደምትለው ናዖሚ አዳሙ ለማግባት ፈቃደኛ ያልሆኑትን እንደ ባሪያ ነበር እንደሚመለከቷቸው ነግራታለች። "በየቀኑ ይደበድቡን ነበር፤ እንድናገባቸው ይጠይቁንና እምቢ ካልን ይደበድቡን ነበር። ልብስ እናጥባለን፣ ዉሃ ከወንዝ እንቀዳለን፣ ለሚስቶቻቸው ደግሞ ሁሉን ነገር እናደርግ ነበር። ባሪያዎቻቸው ነበርን።" ሴት ልጆቻችንን መልሱ' [ብሪንግ ባክ አወር ገርልስ] የተሰኘው በዓለም ዙሪያ የተደረገው እንደ ሚሼል ኦባማና ሌሎችንም ታዋቂ ሰዎችን ያሳተፈ እንቅስቃሴ ቢደረግም በደኑ አካባቢ የነበሩ ነዋሪዎች ግን ልጃገረዶቹን በመመለስ ጣልቃ መግባት ካለመፈለጋቸውም በላይ ጠፍተው ያገኟቸውን መልሰው ለቦኮ ሃራም አስረክበዋል። "አንዳንድ ሴቶች ሮጡ፤ ለማምለጥ ቢሞክሩም እንኳን ሊሳካላቸው አልቻሉም። አንዳንድ ሰዎችም አሰሯቸው።የተያዙበት መንገድ ደግሞ አምልጠው በአቅራቢያ ወደነበረ ሱቅ ውሃና ብስኩት ሲለምኑ ነው። 'ማን ናችሁ ከየት ነው የመጣችሁት? 'ብለው ሲጠይቋቸው በቦኮ ሃራም ከመንግሥት ሴቶች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ታግተው እንደነበር ነገሯቸው። ሰዎቹ ግን 'እነዚህ የሼኮ ልጆች አይደሉ እንዴ? ' ብለው ተጠያየቁ ፤ ከዚያም ምግብና የሚተኙበትን ቦታ ሰጧቸውና በማግስቱ ለቦኮ ሃራም አስረከቧቸው። በምሽት ነበር ወደ ሳምቢሳ ያመጧቸው... እነሱም አንገታቸውን እንደሚቆርጡ አስፈራሯቸውና ገረፏቸው።" የወቀሳው ጫወታ ከልጃገረዶቹ ማንም ሳይቀር ሁሉም እምነታቸውን ወደ እስልምና ለመቀየር ከተስማሙ ወደ ቤት ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀል እንደሚችሉ ተነግሯቸው ነበር። እናም በዚህ ኃሳብ የተስማሙት ልጃገረዶች እምቢታን መርጠው እገታውን ያስቀጠሉትን ልጃገረዶችን ተጠያቂ ያደርጉ ነበር። "እስልምናን የማይቀበሉት 'እንደ በግ፣ላምና ፍየል የሚቆጠሩ ናቸው' በሚል እንደሚገድሏቸው ይዝቱ ነበር። ከዚያም ከታጣቂዎቹ አንዱ የሆነው ማላም አባ እስልምናን ያልተቀበሉት በአንድ በኩል እንዲቆሙ ተናገረ።ለመቀበል ከተስማሙት ጋር እንዳይቀላቀሉም አዘዘ። 'ለእነርሱ ሌላ ቦታ ይዘጋጅላቸዋል' ቢልም ሌላኛው ደግሞ የእርሱን ሃሳብ በመቃወም አንድ ላይ መቆየት እንዳለብን ተናገረ። ከአንድ ሳምንት በኋላ ኃይማኖታችንን ለመቀየር ያልተስማማነው 'ወደቤታችን ከመሄድ እየገደብን ያለነው እኛው ራሳችን ነን' አልን'' የልጃገረዶቹ ፊት ደብዘዝ ተደርጓል ምክንያቱም የተወሰኑት የቦኮ ሃራም ታጣቂዎችን በማግባታቸው ከተፈቱ በኃላ መገለል ደርሶባቸዋል ቪድዮዎቹ እንዴት ተቀዱ? የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በየጊዜው ያገቷቸውን ልጃገረዶች በቪድዮ እየቀረጹ ይለቁ ነበር። ይህ ደግሞ ስለ ቀረጻው የውስጣዊ እይታ የሚሰጠን ክፍል ነው። " ከአንድ ቀን በፊት መጥተው ከመካከላችን 10 የሚሆኑትን ከዛፉ ሥር በቪድዮ ቀረጿቸው። አንድ በአንድ እየነጠሉ ስማቸውንና ስለቤተሰቦቻቸው ጥያቄ መጠየቅ ጀመሩ። ከዚያም 'ጉዳት አድርሰንባችኋል? 'ብለው ሲጠይቁን እኛም 'አይ' ብለን መለስን። ለቤተሰቦቻችንና ለመንግሥት ምን እያደረጉን እንደሆነ እንድንናገር ጠየቁን። ምክንያቱም መንግሥትና ቤተሰቦቻችን እየደፈሩንና እየረበሹን እንደሆነ ስለተናገሩ። '' "ከኛ መካከል አንደኛዋን ወስዶ 'ካገትንሽ ሰዓት አንስቶና እዚህ ቦታ ካመጣንሽ ጀምሮ ደፍረንሽም ሆነ አብረንሽ ተኝተን እናውቃለን?' ብሎ ሲጠይቃት እሷም 'አይ' ብላ መልስ ብትሰጠውም በድጋሚ ጠየቃት 'ለቤተሰቦችሽና ለመንግሥት ምን እያደረግንልሽ እንደሆነና እንዴት እየተንከባከብንሽ እንደሆነ አሳያቸው። '' ታጣቂዎቹ ዜና በጥሞና ይከታተሉ ነበር ብዙውን ጊዜ ቪድዮዎቹን ዜና ከተከታተሉ በኃላ ነበር የሚቀርጹት። "ትንሽ ቆይተው ቢቢሲ ሃውዛን [በናይጄሪያ ቋንቋ] ያዳምጡ ጀመር። ልክ ሬድዮ አዳምጠው እንደጨረሱ አንድ በአንድ ጠሩን። አንዳንዶቻችንን እንድንንበረከክ የተቀረነው ደግሞ እንድንቀመጥ አደረጉና የምናነበውን ሰጥተው መቅረጽ ጀመሩ። ከዚያ ከቁርዓን አነበብን።'' ማስታወሻ ደብተሮቹን የጻፏቸው ልጃገረዶች የት ደረሱ? ናኦሚ አዳሙና ሌሎች ሶስት ጸሃፊዎች ሮዳ ፒተር፣ ሳራቱ አዩባና ማርጋሬት ያማ ባለፈው ሚያዚያ ተፈትተዋል። መስከረም ላይ በናይጄሪያ በሚገኘው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ እንዲማሩ ተልከዋል። አዳሙ ለቤተሰቦቿ ከሰባቱ አንዷ ስትሆን ማስታወሻዎቹን የጻፈችው ቤተሰቦቿን በማሰብ እንደሆነ ለጋዜጠኛ አዳዎቢ አጫውታታለች። "ማስታወሻውን የጻፍኩት ወንድሞቼ፣ እህቶቼና ወላጆቼ እንዲያዩት ብዬ ነው" ትላለች የናኦሚ እናት የማስታወሻ ደብተሩን ይዘው የናኦሚ እናት ኮሎ ይባላሉ እሳቸው ማንበብ ባይችሉም ስለማስታወሻ ደብተሮቹ ይበልጥ ማወቅ እፈልጋለሁ ይላሉ። ብዙውን የማስታወሻ መልዕክቶች ሳራ ሳሙኤል ብትጽፋቸውም ገና ስላልተመለሰች ጓደኛዋ ናኦሚ አዝናለች። "እንደተጎዳሁ ይሰማኛል። እስካሁን እሷን ነው የማስበው። '' ሳራ በታገቱ በሁለተኛው ዓመት ነበር የናይጄሪያ ወታደራዊ ኃይል ሲከባቸውና የቦኮ ሃራም መተዳደሪያ አቅርቦት ሲዘጋባቸው በፍርሃት ለማግባት የተስማማችው። በማግባቷም ምክንያት የነበሩበትን ካምፕ ከባለቤቷ ጋር ምግብ ወደሚገኝበት አካባቢና የተሻለ ሕይወት ወደሚመሩበት ጥላ ለመሄድ ተገደደች። ከመካከላቸው ትዳር ከመሰረቱት ውስጥ እስካሁን አንዳቸውም አልተለቀቁም። የሳራ አባት አቶ ሳሙኤል ያጋ ለጋዜጠኛዋ የመጀመሪያ ልጁ መጽሃፏ ብዙም እንዳላስደነቀው አጫውቷታል። "ሁሌ እንዳነበበች ነበር። አንዳንዴ መጽሐፍ እንደያዘች እንቅልፍ ይዟት ይሄድ ነበር'' በለዋል ። በማስታወሻ ድብተሯ የመጨረሻው ገጽ ላይ የአምስት ወንድምና እህቶቿን ስሞች ጠቅሳለች በመጨረሻም " የአባቴ ስም ሳሙኤል ሲሆን እናቴ ደግሞ ርብቃ ትባላለች '' ብላ ጽፋለች። መርሳት የማትፈልግ ይመስል ነበር።
news-46835037
https://www.bbc.com/amharic/news-46835037
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስድሳ በላይ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችን ያገኛሉ
በሚቀጥለው ሰኞ ጥር 6ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች እና በዓለም ዙርያ በተለያዩ ሚሲዮኖች ኢትዮጵያን ከሚወክሉ ከስድሳ በላይ አምባሳደሮች እንደሚወያዩ ተገለፀ።
ውይይቱ በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን በተለይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እየተካሄደ ያለው የመዋቅር ማሻሻያ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ እንዲሁም ባለፉት አስር ወራት በውጭ ግንኙነት መስክ የተከናወኑ እርምጃዎች ይገመገማሉ ሲል ተሰናባቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ዛሬ ተናግረዋል። በቅርቡ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አቶ መለስ ከአስር በላይ የአገር መሪዎች ባለፉት አስር ወራት ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን አስታውሰዋል። •"የመከላከያ ሰራዊትን እንቅስቃሴ የሚያግድ ስራ አንቀበልም" ዶ/ር ደብረፅዮን •ኢትዮጵያ በዲፕሎማቶቿ ላይ ሽግሽግና ለውጥ ልታደርግ ነው ተሿሚው አምባሳደር ላለፉት ሁለት ዓመታት ያገለገሉበትን የቃል አቀባይነት የሥራ ኃላፊነት ለበርካታ ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ያገለገሉት አቶ ነብያት ጌታቸው ተረክበዋል። በተያያዘ የኢትዮጵያ ቀን መርኃ ግብር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ከተማዋን በማስጎብኘት ይከበራልም ተብሏል።
news-55089960
https://www.bbc.com/amharic/news-55089960
ለጭቁኖች ተቆርቋሪው የክፍለ ዘመኑ ታላቅ የእግር ኳስ ጥበበኛ ዲያጎ ማራዶና
አንፀባራቂ ስብዕና፣ ድንቅ ችሎታ፣ የላቀ አእምሮ፣ ተናዳጅ፣ ቁጡ፣ ለተጨቋኞች አዛኝ፣ እብሪተኛ ሌላም ሌላም. . .
በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የእግር ኳሱ ሊቅ ዲያጎ ማራዶና በህይወት እያለ ይሰጠው የነበሩ ስሞች ናቸው - የዓለማችን የእግር ኳስ ጀግና። ለእግር ኳስ የተፈጠረ ነው የሚባልለት አርጀንቲናዊው ማራዶና ለየት ያለ ድንቅ ችሎታን፣ ራዕይና ፍጥነትን ቀልብ ከመሳብ ጋር በማጣመር በርካታ አድናቂዎቹን አስደምሟል። "የአምላክ እጅ" ተብሎ በሚጠራው አወዛጋቢ ጎል፣ በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ መዘፈቁና ሌሎች ከግል ህይወቱ ጋር በተያያዘም ደጋፊዎቹ የተመሳቀለ እይታ እንዲኖራቸው አድርጓል። በአሁኑ ወቅት ጣልያንን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ያሉ አድናቂዎቹ እየዘከሩት ሲሆን በተለይም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ ታላቅ ቦታ አለው። በርካታ ጊዜያትም "ልቤም ሆነ ውስጤ ፍልስጥኤማዊ ነው" ሲል የተሰማው ማራዶና "ጭቆናን እናውቃለን" በማለትም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ለፍልስጥኤም ያለውን ድጋፍ አሳይቷል። አጭርና ጣፋጭ ህይወት- የእግር ኳሱ ሊቅ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና የተወለደው በአርጀንቲናዋ፣ ቦነስ አይረስ የድሆች መንደር ውስጥ ከዛሬ 60 ዓመት በፊት ነበር። የእግር ኳስ ፍላጎቱም የተጠነሰሰው ገና በታዳጊነቱ ሲሆን፤ በእግር ኳስ ታሪክ ታላቅ ቦታ ላይ መድረስ ችሏል። አንዳንዶችም ከታላቁ የብራዚል እግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ ያስበልጡታል። ማራዶና በ491 ጨዋታዎች 259 ጎሎችን በማስቆጠል የደቡብ አሜሪካ ተቀናቃኙን ፔሌን በመብለጥ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ ተጫዋች መሆን ቢችልም፤ ወደ በኋላ እግር ኳስን በበላይነት የሚያስተዳድረው ፊፋ የምርጫ ሕጉን በመቀየሩ ሁለቱም የክፍለ ዘመኑ ምርጥ በመሆን ተሰይመዋል። በእናቱ ማህፀን እግር ኳስን የለመደ ይመስል ማራዶና ገና በህፃንነቱ ነበር የላቀ ችሎታውን ማሳየት የጀመረው። ሎስ ሴቦሊታስ የተባለ የታዳጊዎች ቡድንን በመምራት በ136 ጨዋታዎች ባለመሸነፍ አይበገሬነቱን አሳይቷል። የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ህይወቱንም የጀመረው በ16 ዓመቱ አካባቢ ነው። አጠር ብሎ ደንደን ያለ ሰውነት ያለው ማራዶና ቁመቱም 1.65 ሜትር ነው። ሲታይ የተለመደው አይነት የስፖርተኛ ሰውነት የለውም። ነገር ግን ቀልጣፋነቱ፣ ነገሮችን ቀድሞ የመረዳት ችሎታው፣ የኳስ ቁጥጥሩ፣ ኳስ ማንቀርቀብና ቶሎ ማሳለፍ መቻሉ ላለመረጋጋቱና ብዙ ጊዜ የሚያጋጥመውን የክብደት ችግሩን አካክሶለታል። ምንም እንኳን የተቀናቃኝ ቡድንን ተከላካዮች በቀላሉ ማለፍ ቢችልም ማራዶና በግል ህይወቱ ራሱን በርካታ ጊዜ ችግር ውስጥ ተዘፍቆ አግኘቶታል። የአምላክ እጅና የክፍለ ዘመኑ ጎል ማራዶ ለአገሩ በተሰለፈባቸው 91 ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ላይ 34 ጎል አስቆጥሯል። ነገር ግን ይህ ምናልባት ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ጨዋታ ታሪኩ ውስጥ ከወንዝ ውሃን በማንኪያ እንደ መጨለፍ የሚቆጠር ነው። በጎሮጎሳውያኑ በ1986 ሜክሲኮ ላይ በተደረገው የዓለም ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኑን የመራው ማራዶና ከአራት ዓመታት በኋላም አገሩን ለመጨረሻ ዙር አደረሳት። በተለይም በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ የተከሰተው ውዝግብ የማራዶና መታወቂያ ሆነ። በወቅቱ አርጀንቲናና እንግሊዝ ያደርጉት ጨዋታ እግር ኳስ ብቻ አልነበረም፤ ፖለቲካም የተቀላቀለበት ነበር። ከውድድሩ ከዓመታት በፊት ለአስር ሳምንታት ያህል ፎክላንድስ ተብላ በምትጠራው ደሴት ምክንያት አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ጦርነት ገጥማ ነበር። በጨዋታው ላይ ሁለቱም የውጊያው መንፈስ ሳይለቃቸው ወደ ሜዳ ገብተው በእግር ኳሱም ላይ ይሄው የፀበኝነት ስሜት ነበር የተንፀባረቀው። ለ51 ደቂቃዎችም ያህል ያለ ምንም ጎል ጨዋታው ሲካሄድ ቆይቶ በድንገት ማራዶና ከግብ ጠባቂው ፒተር ሺልተን ጋር ዘሎ የተሻማትን ኳሷን በተቃራኒው መረብ አስቆጠረ። ማራዶና ከጨዋታው በኋላም ግቧ እንዴት እንደተቆጠችረ በተናገረበት ወቅት በጎሉ ውስጥ "ማራዶና ትንሽ ነበረበት፤ የአምላክም እጅ በትንሹ ነበረበት" በማለት ተናገረ። በዚሁ ጨዋታ ላይ ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ብዙዎች 'የክፍለ ዘመኑ ጎል' ብለው የጠሩትን ግብ አስቆጠረ። የተቀናቃኙን ቡድን አባላት እጥፍጥፍ አድርጎ፤ ሜዳው ላይ ብቻውን ያለ ሰው ይመስል፤ ጎሏን አስቆጠረ። "ድንቅ ጎል ነበረች። የእግር ኳስ እልቅና የታየበት፤ የሚገርም ነው" በማለት የቢቢሲው ዘጋቢ ቤሪ ዴቪስ ተናግሯል። በጨዋታው እንግሊዝ አንድ ጎል ብታስቆጥርም፤ አርጀንቲና 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። ለማራዶና ማሸነፉ ከጨዋታው፤ ከእግር ኳስም በላይ ነበር "እንግሊዞችን መዘረር" ፖለቲካዊ ድልም ነበረው። የናፖሊው ጀግና- በአደንዛዥ እፅ መዘፈቅ የዓለም አቀፍ የዝውውር ክብረ ወሰንን ማራዶና ሁለት ጊዜ መስበር ችሏል። በአገሩ ሲጫወትበት ከነበረው ቦካ ጁኒየርስ ወደ ስፔኑ ባርሴሎና በጎሮጎሳውያኑ 1982 ሲዛወር በ3 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ ወደ ጣልያኑ ክለብ ናፖሊም በ5 ሚሊዮን ፓውንድ ተዛወረ። በጣልያኗ ሳን ፓውሎ ስታዲየም በሄሊኮፕተር ሲያርፍም 80 ሺህ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ ተገኝተው ነበር- አዲሱን ጀግና ለመቀበል። ይህም በእግር ኳስ ታሪኩ ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገበት ወቅት ነው። ክለቡ በ1987 እና በ1990 የሊጉ አሸናፊ እንዲሆን እንዲሁም የአውሮፓ ሊግ ዋንጫን በ1989 እንዲያነሳም ቀዳሚውን ሚና የተጫወተው ማራዶና ነው። የመጀመሪያውን ድል በማስመልከት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች በጎዳናዎች ላይ በመውጣት ለአምስት ቀናት ያህል ደስታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ወቅት ማራዶና የሁሉንም ትኩረት ሳበ የሚጠበቅበትም ኃላፊነት ከፍተኛ ሆነ። ይህ ደግሞ ጫናንና መጨናነቅን አስከተለ። "ታላቅ ከተማ ናት ግን መተንፈስ እንኳን አልቻልኩም። ነፃ ሆኜ በመንገዶች ላይ መረማመድ እፈልጋለሁ። እኔም እንደ ሌላው ሰው ነኝ" ብሏል በወቅቱ። ከጣልያኑ የካሞራ ማፊያ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት አለው በሚል፣ የኮኬይን አደንዛዥ እፅ ሱስ ውስጥ መዘፈቅና ከልጅ ማደጎ ጋር በተፈጠረ እሰጣገባም ጋር ስሙ በተደጋጋሚ መነሳት ጀመረ። በጎርጎሳውያኑ በ1990 ጣልያን ላይ በተዘጋጀው የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በጀርመን 1 ለ 0 አገሩ አርጀንቲና መሸነፏን ተከትሎ እንዲሁም በቀጣዩ ዓመትም በተደረገለት ምርመራ አደንዛዥ እፅ መጠቀሙ በመታወቁ ለ15 ወራት እንዲታገድ ምክንያት ሆነ ። ከዚህ ሁሉ አገግሞና ራሱን አድሶ በጎሮጎሳውያኑ 1994 አሜሪካ ላይ ወደ ተካሄደው የዓለም ዋንጫ ቢመለስም ጎል አስቆጥሮ ደስታውን የገለፀበት መንገድ ያልተለመደና በርካቶችንም ያስደነገጠ ነበር። ማራዶና የታገደውን ኤፊድሪን የተባለ የተከለከለ አበረታች መድኃኒት ወስዶ በመገኘቱ ከውድድሩ እንዲወጣ ተደረገ። ህይወት ከጡረታ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ አበረታች እፅ በደሙ ውስጥ ከሦስት ዓመት በኋላ መገኘቱን ተከትሎ በ37 ዓመቱ ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ራሱን አገለለ። ነገር ግን ተጫዋቹን ችግሮች አልለቀቁትም። በጋዜጠኞች ላይ ተኩሷል በሚልም ሁለት ዓመት ከአስር ወራት እስር ቢፈረድበትም በማስጠንቀቂያ ታልፏል። የኮኬይንና የአልኮል መጠጡም የጤና እክል አስከትሎበታል ተብሏል። በከፍተኛ ሁኔታም ኪሎው የጨመረ ሲሆን፤ በአንድ ወቅት 128 ኪሎ ግራምም ይመዝን ነበር። በጎሮጎሳውያኑ 2004 በልብ ህመም ምክንያት ፅኑ የህሙማን ክፍል ውስጥ ገብቶም ነበር። ማራዶና ክብደቱን ለመቀነስ ቀዶ ህክምና ያደረገ ሲሆን ከአደንዛዥ ዕፅ ሱስም ለመላቀቅ ኩባ መኖር ጀመረ፤ የቀድሞውን የኩባ መሪና ሶሻሊስትና የነፃነት ታጋይ ፊደል ካስትሮንም አግኝቷቸው ነበር። ከዚህ ሁሉ በኋላ በጎሮጎሳውያኑ 2008 የአርጀንቲና ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣን ሆነ። በዚያው ዓመትም በነበረው የዓለም ዋንጫ አገሩ ለሩብ ፍፃሜ የበቃች ቢሆንም በጀርመን 4 ለ 0 ከተሸነፈ በኋላ ከቡድኑ ጋር የነበረው የሁለት ዓመት ቆይታ ተቋጫ። ውሻው ሻሪ ፔይ ከንፈሩን ነክሳው ቀዶ ህክምና ማድረጉ፣ ከትዳሩ ውጭ ለወለደው ለዲያጎ አርማንዶ ጁኒየር እውቅና መስጠቱም ስሙ ከየመድረኩ እንዳይጠፋ አደረገው። ከሁለት ዓመት በፊት ሩሲያ በተደረገው የዓለም ዋንጫ አርጀንቲናና ናይጄሪያ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተገኝቶ የነበረው ማራዶና የብዙዎች መነጋገሪያነት ሆኖ ነበር። ከናይጄሪያ ደጋፊ ጋር አብሮ መደነሱ፣ ከጨዋታው በፊት ወደ ሰማይ አንጋጦ ያደረገው ፀሎት፣ ሊዮነል ሜሲ ጎል ሲያስቆጥር በከፍተኛ ሁኔታ መደሰቱ፣ መሃል ላይ መተኛቱ እንዲሁም አርጀንቲና ሁለተኛ ጎል ስታስቆጥር የመሃል ጣቱን ሁለት ጊዜ ማሳየቱ ለሚዲያዎች ትኩስ ወሬ ነበር። ማራዶና ባለ ብዙ ስሙ፣ ለተጨቋኞች አዛኝ፣ አዝናኝ፣ ታላቅ፣ ቁጡ፣ የሚያዋርድና ሌሎች የተባለው ታላቁ እግር ኳሰ ተጨዋች ይህችን ዓለም ቢሰናበትም ህይወቱን የኖረበት መንገድ ለወደፊት ትውልድ የሚዘከረው፣ በእግር ኳስ ችሎታው የማይሞት ስምና አሻራ ትቶ አልፏል።
news-53737438
https://www.bbc.com/amharic/news-53737438
ካሽሚር፡ “መቃወም አንችልም፤ ከተቃወምን እንታሰራለን”
አምና ነሐሴ 5 ላይ ሕንድ የካሽሚርን ልዩ አስተዳደር አንስታ፤ ግዛቲቱን ለሁለት ከፍላለች። ጥብቅ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል። በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል። የግንኙነት መስመሮችም ተቋርጠዋል።
ገደቡ ሚያዝያ ላይ በመጠኑ ቢላላም፤ በኮቪድ-19 ምክንያት በድጋሚ ገደብ ተጥሏል። ቁጣና ፍርሀትን ያጫረው በካሽሚር ላይ የተጣለው ገደብ አንድ ዓመት አስቆጥሯል። ይህን ምክንያት በማድረግም 12 የካሽሚር ነዋሪዎችን ቢቢሲ አነጋግሯል። የጋዜጠኛዋ ሰንዓ ኢርሻድ ሞት ጋዜጠኛዋ ሰንዓ 26 ዓመቷ ነው። “በኛ ሙያ የግል ሕይወትና ሥራ መለየት አይቻልም” ትላለች። በሙያው አራት ዓመታት አስቆጥራለች። ባለፉት ዓመታት የእንቅስቃሴ ገደቦች ቢጣሉም የአምናው አስፈሪ እንደነበር ትናገራለች። “ምን እየተከናወነ እንደነበር ማወቅ አልቻልንም። እርስ በእርሳችን መረጃ የምንለዋወጥበት መንገድ ተቀይሯል። ሰሚ ለማግኘት አዳዲስ መንገዶች መፍጠር ነበረብን” በማለት ያሉበትን ሁኔታ ትገልጻለች። ለወትሮውም ከጋዜጠኞች ጋር የማይስማሙት የጸጥታ ኃይሎች፤ ካለፈው ዓመት ነሐሴ ጀምሮ የበለጠ ከፍተዋል። “አሁን ጋዜጠኞች ይታሰራሉ፣ የመረጃ ምንጫቸውን ይፋ እንዲያድጉ ይገደዳሉ። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማንኛውንም ነገር ከመጻፌ በፊት ቆም ብዬ ማሰብ ይጠበቅብኛል። ሁሌም እፈራለሁ።” ቤተሰቦቿ ስለ ደኅንነቷ እንደሚጨነቁ ትናገራለች። ስለ ሥራዋ ለቤሰቦቿ ምንም አትገልጽም። ልጁን ያጣው አልጣፍ ሁሴን የ55 ዓመቱ አልጣፍ ልጁን ያጣው የነሐሴ አምስቱን የመንግሥት ውሳኔ ተከትሎ ነው። የአልጣፍ ልጅ ኡሳይብ 17 ዓመቱ ነበር። ከጸጥታ ኃይሎች ለማምለጥ ሲሞክር ወንዝ ውስጥ ዘሎ ነው ሕይወቱን ያጣው። የጸጥታ ኃይሎች ይህን ድርጊታቸውን ክደዋል። ወጣቱ ከሞተ አንድ ዓመት ቢሞላም፤ የጤና ተቋም ለቤተሰቡ የሞት ማረጋገጫ ሰነድ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም። አባቱ አልጣፍ “ኳስ ሊጫወት ወጥቶ በሬሳ ሳጥን ተመለሰ። ፖሊሶች በዛን ቀን ማንም አልሞተም ይላሉ። እንደተገደለ ማመን አልፈለጉም። ምስክር ቢኖረኝም ጉዳዩን ለመከታተል ፍቃደኛ አይደሉም። ፖሊስ ጣቢያ፣ ፍርድ ቤት ብንሄድም ፍትሕ አላገኘንም” ይላል። ሙኒፋ ናዚፍ የስድስት ዓመቷ ሙኒፋ ናዚር የስድስት ዓመቷ ሙኒፋ በወንጭፍ ቀኝ አይኗን የተመታችው በተቃዋሚዎችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው። “ለብዙ ቀናት ሆስፒታል ነበርኩ። አሁን ብዙም ትዝ አይለኝም። ትምህርት ቤት የተማርኩትን ረስቻለሁ። መቶ ከመቶ እደፍን ነበር። አይኔ ከዳነ በኋላ ሐኪም መሆን እፈልጋለሁ። ሐኪሞች ስላዳኑኝ ደስ ይሉኛል” ትላለች ታዳጊዋ። ፎቶ ጋዜጠኛው አባቷ እንደሚለው የሙኒፋ አይን ዳግመኛ ማየት አይችልም። የትምህርት ቤት ክፍያ ከአቅሙ በላይ ስለሆነም ልጁን አስወጥቷታል። “የሚታየኝ ጭላንጭል ብቻ ነው። መጻሕፍት ማንበብ አልችልም። የትም አልሄድም። ሐኪሞች ከ15 ቀናት በኋላ ትምህርት ቤት መሄድ ትችያለሽ ቢሉኝም አንድ ዓመት አልፎኛል።” ባለ አውቶብሱ ፋሩቅ አህመድ ፋሩቅ 34 ዓመቱ ነው። ታዳጊ ሳለ ካሽሚር ውስጥ ከአውቶብስ ሹፌሮች ጋር ይሠራ ነበር። 2003 ላይ ያጠራቀመው ገንዘብ ላይ የባለቤቱን ወርቅ ሸጦ ገንዘብ ጨምሮበት የራሱ አውቶብስ ገዛ። አሁን የሰባት አውቶብስ ባለቤት ቢሆንም የትራንስፖርት ዘርፉ እንደቀድሞው እየተንቀሳቀሰ አይደለም። “400 ሺህ ሩፒ ከፍለን የመኪኖቹን ኢንሹራንስ አሳድሰናል። ግን ምንም ገቢ የለንም። ሰባት ሠራተኞቼ ለረሀብ ተጋልጠዋል። የራሴ ቤተሰብ መከራ ውስጥ ሆኖ እንዴት የነሱን ልረዳ እችላለሁ? እንደኔ አይነት ሰዎች ጥሪታችንን አሟጠን ነው ንግድ የምንጀምረው። ገቢ ከሌለን እንዴት እዳችንን መክፈል እንችላለን?” ፋሩቅ እዳዎቹን ለመክፈል ሲል የቀን ሥራ ጀምሯል። የፋሽን ዲዛይነሯ ኢቅራ አህመድ የ28 ዓመቷ ኢቅራ የራሷን የፋሽን ድርጅት የከፈተችው የማንም ተቀጣሪ ላለመሆን ነው። በድረገ ገጽ በምትሸጣቸው ሥራዎቿ የካሽሚርን ባህል ማስተዋወቅ እንደምትፈልግ ትናገራለች። “ኢንተርኔት መዘጋቱ ንግዴን አቀዝቅዞታል። 2ጂ ደግሞ ምንም ጥቅም የለውም። አሜሪካ፣ ዱባይና አውስትራሊያም ደንበኞች አሉኝ” ትላለች። 2ጂ ኢንተርኔት ደካማ ስለሆነ የምትሠራቸውን ልብሶች በድረ ገጽ ማስተዋወቅ አልቻለችም። ቀድሞ በሳምንት ከ100 እስከ 110 የሥራ ትዕዛዝ ታገኝ ነበር። አሁን ግን ቢበዛ ስድስት ልብስ እንድትሠራ ብትታዘዝ ነው። ዓለም አቀፍ ደንበኞቿ ያዘዙት ልብስ ሳይደርሳቸው ይዘገያል ብለው ይሰጋሉ። በቅርቡ አንድ ልብስ ለመላክ ስድስት ወር ወስዶባታል። “ንግዴ በዚህ ሁኔታ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ አይመስለኝም። ወርሀዊ ወጪዬ 200 ሺህ ሩፒ ነው። ምንም ገቢ ካላገኘው እንዴት ለሠራተኞቼ ደሞዝ እከፍላለሁ?” የፋሽን ዲዛይነሯ ኢቅራ አህመድ የሕግ ተማሪዋ ባድሩድ ዱጃ “ሕገ መንግሥቱን፣ ዴሞክራሲ ምን ማለት እንደሆነና ስለ መሠረታዊ መብት አጠናለሁ። እነዚህ ግን ከቃላት ያለፉ አይደሉም። የገነቡት ቤተ መንግሥት እየፈረሰ ነው። ነፃነታችንን እያጣን ነው። ለመምህራንም ይሁን ለተማሪዎች ሕግ መማር ቀልድ ሆኗል” ትላለች የ24 ዓመቷ የሕግ ተማሪ ባድሩድ። ባድሩድ የመረጠችው ዘርፍ ላይ ጥያቄ ማንሳት ጀምራለች። ጭቆናውንም እንዲህ ትገልጻለች. . . “መናገር ፈውስ ነበር። አሁን ግን ያሳስራል። ካሽሚር ውስጥ በሚገኝ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ውስጥ ስሠራ ከጋዜጠኞች ጋር በማውራቱ የታሰረ ሰው ገጥሞኛል። ተስፋችን ጨልሟል። ሕግ የተማርነው ሕግ እንዲያስከብሩ የሚከፈላቸው ሰዎች ሕግ ሲጥሱ ለማየት አይለም። ሌላ ሥራ መፈለግ ጀምሬያለሁ።” ፖለቲከኛው ማንዙር ባህት ማንዙር 29 ዓመቱ ነው። ሕንድን የሚያስተዳድረው ባህራታያ ጃናታ የተሰኘው ፓርቲ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊ ነው። ፓርቲውን በመቀላቀሉ ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ እንዳገለሉት ይናገራል። እሱ ግን የአካባቢውን ሰዎች እያገዘ እንደሆነ ነው የሚያምነው። “ህልሜ ስልጣን መያዝ ወይም ሀብት ማካበት ሳይሆን የሰዎችን ሕይወት መለወጥ ነው። ወጣቶች የሚያነሱት መሣሪያ መፍትሔ አይሆንም። በካሽሚር የሚሞቱት ወንድሞቼ ናቸው። ግጭት መልስ አይሆነንም።” አስጎብኚው ጃቪድ አህመድ የ35 ዓመቱ ጃቪድ ላለፉት ዓመታት በመርከብ ቱሪስቶችን እያጓጓዘ በቀን ወደ 500 ሩፒ ያገኝ ነበር። “አሁን ሕይወቴን የምገፋው አትክልት እየሸጥኩ ነው። ግን እንቅስቃሴ ስለተገደበ ገበያ የለም” ይላል። ጃቪድ ለልጆቹ ትምርት ቤት መክፈል አዳግቶታል። መንግሥት ለእያንዳንዱ መርከበኛ 1000 ሩፒ ለመስጠት ቃል ቢገባም፤ ገንዘቡ የመብራት ክፍያን እንኳ አይሸፍንም። “ነጋችን ጨምሟል። ቱሪስቶች ስለሚፈሩ አይመጡም። ያለንበት ወቅት ለካሽሚር ነዋሪዎች ከባድ ሆኗል። በተለይ ቱሪዝሙ በጣም ተቀዛቅዟል። ተስፋ ስለቆረጥኩ ለፈጣሪ ትቼዋለሁ።” ፋላህ ሳላህ ታዳጊዋ ፋላህ ሳላህ የ12 ዓመቷ ፋላህ “በተቀረው ሕንድ ታዳጊዎች የተሻለ የትምህርት እድል አላቸው። እኔ ግን መሠረታዊ ትምህርት ማግኘት አልቻልኩም። በዚህ እድሜ አስፈላጊውን እውቀት ካላገኘን በፈተና ተወዳዳሪ መሆን አንችልም” ትላለች። ፋላህ መሠረታዊ የሳይንስ እና ሒሳብ እውቀት እንደሌላት ትናገራለች። ኢንተርኔት በመቋረጡ ምክንያት ለጥያቄዎቿ መልስ ማግኘትም አልቻለችም። “አሁን ኢንተርኔት ቢመለስም በጣም ዝግ ያለ ነው። መጽሐፍ ላንብብ ብልም የተጻፈውን መገንዘብ አልችልም” የምትለው ፋላህ፤ ትምህርት ቤትና ጓደኞቿ እንደናፈቋት ትናገራለች። “ለዓመት ከቤት አልወጣሁም። ሌላ አገር ውስጥ ለአንድ ዓመት እንቅስቃሴ ቢቆም ተማሪዎች ተቃውሞ ይወጡ ነበር። እኛ ግን መቃወም አንችልም። ከተቃወምን እንታሰራለን።” የሆቴል አስተዳዳሪው ሳጂድ ፋሩቅ ሳጂድ ሆቴል አስተዳዳሪ ነው። አያቶቹና ቤተሰቦቹም ነጋዴ የነበሩት የ43 ዓመቱ ሳጂድ በካሽሚር ተስፋ ቆርጧል። በ1990ዎቹ የሕንድ አገዛዝን በመቃወም እንቅስቃሴዎች ከተጀመሩ ወዲህ ካሽሚር በግጭት እየተናጠች ሰዎች እየሞቱ መሆኑንም ይናገራል። “ይህ ሆቴል የተሠራው በሦስት ትውልድ ነው። ግን ከ1990ዎቹ ወዲህ እየተንገዳገድን ነው” ንግዱ አስተማማኝ እንዳልሆነ ሳጂድ ያስረዳል። ሆቴሉ መብራት ቢጠቀምም ባይጠቀምም 200 ሺህ ሩፒ ይከፍላል። “ነገሮች ይሻሻላሉ ብዬ አልጠብቅም። ካሽሚር ስታዝን የተቀረው አገር ይደሰታል። የተቀረው አገር ሲደሰት እኛ እናዝናለን። ሁሉም ነገር ፖለቲካ ሆኗል። ሁሉም ነገር ውስጥ ግጭት አለ። ታዲያ በዚህ ሁኔታ እንዴት ይነገዳል?” አርሶ አደሩቢላል አህመድ አርሶ አደሩቢላል አህመድ የ35 ዓመቱ አርሶ አደር ቢላል ፍራፍሬ ያመርታል። የአየር ሁኔታ መዛባት ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጨምሮበት አጣብቂኝ ውስጥ ስለገባ መሬቱን ለመሸጥ እያሰበ ነው። “ሥራ አጥ ከሆንን ዓመት ተቆጠረ። አፕል ከ100 ሺህ እስከ 150 ሺህ ሩፒ ገቢ ያስገባ ነበር። ዘንድሮ ግን 30 ሺህ ሩፒ ብቻ ነው ያገኘሁት። ወንድሜ 1200 ሳጥን አፕል ሰብስቦ ገዢ ስላጣ ምርቱን ጣለው። በዚሁ ከቀጠልኩ መሬቴን እሸጣለሁ።” ሸክላ ሠሪው መሐመድ ሳዲቅ መሐመድ 39 ዓመቱ ነው። አስፈላጊውን ግብዓት ማግኘት ስላልቻለ የሸክላ ሥራውን ለማቆም ተገዷል። መንግሥት በቅርቡ ከሌላ አካባቢ ለሄዱ ነጋዴዎች ፍቃድ ስለሰጠ እንደ መሐመድ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ተወላጆች ከሥራቸው ተፈናቅለዋል። “መንግሥት አፈር እንዳይቆፈር ወስኗል። የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነው ይላሉ። ለመሆኑ ፍርድ ቤቶች ይህን ሁሉ ዘመን የት ነበሩ? እንደኔ ያሉ ድሆች ቤተሰቦች ጉዳይ ፍርድ ቤቶችን አያሳስባቸውም? በረሀብ ሊገሉን ነው እንዴ? እንቅስቃሴ ስለተገታ የሠራሁትን መሸጥ አልቻልኩም። አዳዲስ የሸክላ ሥራ መሥራት አቁሜ የቀን ሠራተኛ ሆኛለሁ።”
53074945
https://www.bbc.com/amharic/53074945
የዲሞክራቲክ ኮንጎ ዳኛ ጭንቅላታቸው ላይ ተመትተው መሞታቸው ተረጋገጠ
በዲሞክራቲክ ኮንጎ የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከነበሩ ግለሰብ ጋር በተያያዘ የቀረበን የሙስና ክስ እያዩ የነበሩት ዳኛ በልብ ድካም መሞታቸው ከተገለፀ በኋላ በተደረገ ምርመራ ጭንቅላታቸው ላይ ተመትተው በደረሰባቸው ጉዳት መሞታቸውን የአገሪቱ ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ቫይታል ካሜሬ 50 ሚሊየን የሕዝብ ሃብት መዝብረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል የፍትህ ሚኒስትሩ፣ ሴሌስቲን ቱንዳ ያ ካሴንዴ ግድያውን የሚመረምር ቡድን መቋቋሙን አስታውቀዋል። በግንቦት ወር ዳኛ ራፋኤል ያኚ በልብ ድካም መሞታቸው ተገልጾ ነበር። እኚህ ግለሰብ ከፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጋር በተያያዘ የቀረበውን የሙስና ክስ እያዩ ነበር ተብሏል። ነገር ግን የአስከሬን ምርመራ ተደርጎ ጭንቅላታቸው ላይ ስለት ባለው መሳሪያ መመታታቸውንና የሞታቸው መንስኤም ይሄ መሆኑ ተረጋግጧል ሲሉ የፍትህ ሚኒስትሩ ሴሌስቴን ቱንዳ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ማክሰኞ እለት ተናግረዋል። የፍትህ ሚኒስትሩ አክለውም የሟች አስከሬን ላይ በተደረገው ምርመራ " መርዝ በአነስተኛ መጠን" መገኘቱን አስታውቀዋል። የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ካሜሬ፣ በአንድ ወቅት የፕሬዝዳንት ፍሌክስ ሺሴኬዲ መንግሥት ቁልፍ ሰው የነበሩ ሲሆን 50 ሚሊየን ዶላር የሕዝብ ሃብት በመመዝበር ክስ ቀርቦባቸዋል። ግለሰቡ ግን ምንም አይነት ወንጀል አልፈፀምኩም ሲሉ አስተባብለዋል። የካሜሬ ደጋፊዎች ክሱ ፖለቲካዊ ሴራ ነው ያሉ ሲሆን ይህም ግለሰቡ ወደፊት ለፕሬዝዳንትነት እንዳይወዳደሩ ያለመ ነው ሲሉ ይወቅሳሉ። በዲሞክራቲክ ኮንጎ በከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ላይ እንዲህ አይነት ክስ ሲቀርብ ካሜሬ የመጀመሪያው ሰው ናቸው። ይህንን የወንጀል ጉዳይ የሚከታተለው ችሎት ከዳኛው ሞት በኋላም መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል።
news-53004401
https://www.bbc.com/amharic/news-53004401
የጆርጅ ፍሎይድን ሞት የቀረጸችው ሴት ምን አለች?
ሰዎች ስለ ሟች ጆርጅ ፍሎይድ ያወራሉ። ሰዎች ስለ ጨካኙ ፖሊስ ዴሪክ ያወራሉ። ሰዎች ይህን ሁሉ ጉድ በስልኳ ቀርጻ ለዓለም ስላጋራችው አንዲት ትንሽ ልጅ ግን አያወሩም።
የፖሊሶችን ድርጊት በሞባይል ስልክ መቅረጽ አሜሪካ ውስጥ ተለምዷል የእርሷ የስልክ ቪዲዮ ባይኖር ዛሬ ስለ ጆርጅ ፍሎይድ የሚያወሩት ቤተሰቦቹ ብቻ በሆኑ ነበር። ማን ያውቃል? አንዳንድ ወንጀሎች ወንጀል የሚሆኑት ለአደባባይ ሲቀርቡ ነው። ስርቆት ሌብነት ሆኖ የሚያስከስሰው ሲደረስበት ብቻ ነው። በጆርጅ ፍሎይድ የደረሰው ሳይቀረጽ ቀርቶ ቢሆንስ? በዚህ ዘመን የማኅበራዊ ሚዲያ ጉልበት ኃያል ነው። ሰደድ እሳት ነው። ዓለምን ለማዳረስ ሰከንዶች ይበቁታል። አማዞን ጫካ ላይ የምትጫር ክብሪት…እንደማለት ነው። ዳርኔላ ፍሬዘር ገና 17 ዓመቷ ነው። ገና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መግባቷ ነው። የአክስቷን ልጅ ወደ ሰፈራቸው ምግብ ቤት ይዛት እየሄደች ነበር። የአክስቷ ልጅ ደግሞ ገና 9 ዓመቷ ነው፡። ልክ ምግብ ቤቱ አካባቢ ስትደርስ የሆነ ጥቁር ሰውዬ ፖሊሶች ሲያስጨንቁት አይታ ቆመች፤ ቆመችና እንደ ዋዛ ስልኳን ከኋላ ኪሷ መዘዝ አድርጋ አወጣች። 'ሪከርድ' የሚለውን ቀይ ምልክት ተጫነች። እርሷ መቅረጽ ስትጀምር ጆርጅ ፍሎይድ አየር አጥሮት ያቃስት ጀምሯል። "እባካችሁ! እባካችሁ" እያለ። የእርሱ እስትንፋስ እስከወዲያኛው ልትቋረጥ የመጨረሻ ቃሉ "I can't breathe," [መተንፍስ አልቻልኩም] ነበር። ይቺን "መተንፈስ አልቻልኩም" የምትለዋ ቃል ለመጨረሻ ጊዜ ከእስትንፋሱ ስትወጣ የዳርኔላ ስልክ ባትሪው አላለቀም። እርሷም መቅረጽ አላቆመችም። ከዚህ በኋላ ጆርጅ ፍሎይድ ምንም አላለም። እስከወዲያኛው አሸልቧል። የ44 ዓመቱ የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ቾቪን ግን እጁን ኪሱ አድርጎ በጉልበቱ የፍሎይድን አንገት እንደተጫነው ነበር። ከዴሪክ ጋር ሦስት ፖሊሶችም ለዚህ ተግባሩ ተባባሪ ነበሩ። የ17 ዓመቷ ዳርኔላ ስልኳ መቅረጹን እንዲያቆም ያደረገችው ፖሊስ ዴሪክ በእግሩ ወደ ግራ፣ ጆርጅ ፍሎይድ በቃሬዛ ወደ ቀኝ ሲሄዱ ነበር። በጆርጅ ፍⶀይድ ተጠያቂው ዴሪክ ቾቪን እናውግዛት ወይስ እናድንቃት? ዳርኔላ በድምሩ 10 ደቂቃ ከ9 ሰከንዶች ቀርጻለች። ድርጊቱን አጠናቃ ስልኳን ወደ ኪሷ ስትከት ግን በስልኳ ቋት ያኖረችው ተንቀሳቃሽ ምስል ዓለምን ሊንጥ እንደሚችል በፍጹም አልተከሰተላትም። በወቅቱ ምን እንዳደረገች፣ ምስሉ ከተሰራጨ በኋላ ምን እንደተሰማት ለቢቢሲ ለመናገር ፍቃደኛ አይደለችም። ለጊዜው ለቢቢሲም ሆነ ለሌላ ሚዲያ አስተያየት መስጠት ትታለች። ዕድሜዋም አንድ ምክንያት ይሆናል። የእርሷ ጠበቃ ሚስተር ኮቢን ግን ለምን ክስተቱን መቅረጽ እንደፈለገች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። "የዜግነት ግዴታዋን የመወጣት ስሜት ተሰምቷት ሊሆን ይችላል።" "ያም ሆነ ይህ በእርሷ ቪዲዮ የመብት ትግል እቅስቃሴ ድጋሚ ተወልዷል ብዬ አምናለሁ" ይላሉ ጠበቃዋ። የ2ኛ ደረጃ ተማሪዋ ዳርኔላ ከዚህ ክስተት በኋላ መጠነኛ የአእምሮ መታወክ ደርሶባት ሕክምና ጀምራለች። በሕይወቷ እንዲያ ያለ ሰቅጣጭ ነገር አይታ አታውቅም። ያን ቪዲዮ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ላይ ከሰቀለችው በኋላ የነበረው ምላሽ በእርሷ ዕድሜ ለመቋቋም የሚቻል አልነበረም። በፖሊስ ድርጊት የተቆጡ እንዳሉ ሁሉ በእርሷ ድርጊት የተቆጡም ቁጥራቸው ትንሽ አልነበረም። ያመሰገኗት እንዳሉ ሁሉ "ጫካኝ፣ አውሬ" ሲሉ የሞለጯትም ጥቂት አይደሉም። የጆርጅ ፍሎይድ አሰቃቂ ሞት በግንቦት 25 ነበር፤ እርሷ ወደ ፌስቡክ ገጽ ያመራቸው ግን ከ2 ቀናት በኋላ በግንቦት 27 ነው። ወዲያውኑ እሳት ተቀጣጠለ። ነደደ፣ ጨሰ…። የእርሷ ቪዲዮ የእርሷ መሆኑ ቀረ። ሚሊዮኖች ቤት ገባ። መጀመርያ አካባቢ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ስር ለተሰጧት አስተያየቶች ምላሽ ትሰጥ ነበር። አንዱ አስተያየት ሰጪ እርሷን ዝና ናፋቂ አድርጎ ይከሳታል። እንዲያ ባይሆን ኖሮ ሞባይልሽን አስቀምጠሸ የሚሞተውን ሰው ታድኚው ነበር ብሎ ይከሳታል። እርሷም ዝም አላለችም። የሚከተለውን መለሰችለት። "እኔ ያን ክስተት ባልቀርጽ ኖሮ፣ አራቱ ፖሊሶች ዛሬ በሥራ ላይ ነበሩ። ምናልባትም ሌላ ሰው እያነቁ…" ዳርኔላን 'ያን ያደረግሽው ዝና ፍለጋ ነው' የሚሏት ሰዎች ከምር ያበሳጯት። "ምን? ለዝና ነው ያደረግሽው ነው የምትሉኝ? ለገንዘብ ነው ያደረግሽ ነው የምትሉኝ? እናንተ ሰዎች ደደብና ደንቆሮዎች ሳትሆኑ አትቀሩም።" በዳርኔላ ላይ የደረሰው ትችት፤ አደጋ እየደረሰ ቪዲዮ መቅረጽ ጽድቅ ነው ኩነኔ የሚል ሌላ ዙር የክርክር ምዕራፍ ከፍቷል። ለመሆኑ እንዲህ ማድረግ ተገቢ ነው? በሞራል ሕግ እንዴት ይሰፈራል? ራስ ወደድነታችን ይሆን ሰው እየሞተ እኛ ቪዲዮ እንድንቀርጽ የሚያስችለን? በምንቀርጽበት ቅጽበት እየሞተ ላለው ሰው የምር ሐዘኔታ ይሰማናል? ነው ወይስ የሚያስጨንቀን በእኛ የሚቀረጸው የቪዲዮ ጥራትና ቀጥሎ የሚመጣው እውቅና? ፍሎይድ የተገደለበት ጎዳና ላይ የተቀመጠ መታሰቢያ የፖሊስን ግፍ የቀረጹ ሰዎች ምን ደረሰባቸው? ዳርኔላ በእርሷ የተቀረጸው ተንቀሳቃሽ ምስል ዓለምን ከናጠ በኋላ ሽልማት አልጠበቃትም። እንዲያውም ነገሩ ሕይወቷን ረብሾታል። አሁን የአእምሮ ሐኪም እየተንከባከባት የሚገኘው ያለምክንያት አይደለም። ከዚህ ቀደም ቪዲዮ በመቅረጽ ወንጀል ያጋለጡም ቢሆኑ ሽልማት አልጠበቃቸውም። ሕይወታቸው በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ተረባብሿል። 1.ዴኒስ ፍሎረስ ይሄን ቪዲዮ እየቀረጹ የፖሊስን ጭካኔ ማጋለጥ የጀመረው ሰው ዴኒስ ፍሎረስ ሳይሆን አይቀርም። የኒው ዮርክ ሰው ነው። የኒው ዮርክ ከተማ ፖሊስን እንደሱ የቀረጸ የለም። ፖሊስ 70 ጊዜ አስሮታል። ከ90ዎቹ ጀምሮ እንደቀረጻቸው ነው ያለው። ዛሬ 'ፖሊስ አደብ ይግዛ፣ ዘረኝነቱን ይተው' የሚሉ እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ ምክንያት የሆነው እርሱ ነው። ሞባይል ሳይጀመር እርሱ የፖሊስ ግፍ መቅረጽ ጀምሯል። ይህ ድርጊቱ ሕይወቱን እንዴት እንዳከበደው ወደኋላ ላይ ይነግረናል። ፍሎረስ የጀመረውን ተግባር ግን በብዙዎች ይተገበር ጀመር። ፍሎሪስ የኒው ዮርክ ፖሊሶችን በቪዲዮ ሲቀርጽ ከ70 ጊዜ በላእ ታስሯል 2.ቧንቧ ሠራተኛው ጆርጅ ሆሊዴይ ከፍሎረስ በኋላ በ1991 አካባቢ አንድ ጆርጅ ሆሊዴይ የሚባል የቧንቧ ሠራተኛ ከአፓርትመንቱ በርንዳ ላይ ሆኖ የቀረጸው ነገር ምናልባትም እንደ ወረርሽኝ የተዛመተ የመጀርመያ ቪዲዮ ሳይሆን አይቀርም። ያን ጊዜ እንደዛሬው ፌስቡክ የለ፣ ቅንጡ ሞባይል የለ! ምን የለ፣ ምን የለ! እርሱ ቀረጻ ያደረገውም በተለምዶ የልደት ካሜራ መቅረጫ በምንላት ትንሽ ሶኒ ቪዲዮ ካሜራ ነበር። ከበረንዳው ቀርጾ ያስቀረው ምስል ከባድ ውጤትን አስከተለ። በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ሮድኒ ኪንግ የሚባልን አንድ ጥቁር ወጣት በርከት ያሉ ነጭ ፖሊሶች ከበውት እየተቀባበሉ ሲያዳፉት የሚያሳይ አሰቃቂ ቪዲዮ ነበር። ጆርጅ ሆሊዴይ ያን ጊዜ ይህን ክስተት ሲቀርጽ ሞባይል አልነበረም ብለናል። 5ጂ ኢንተርኔትም አልተፈጠረም፤ ፌስቡክ የለም። ታዲያ እንዴት ተዛመተ? ይህንን የቀረጸውን አሰቃቂ የቪዲዮ ቴፕ ወስዶ እዚያ ሰፈሩ ለሚገኝ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰጠ። ጣቢያው ተንቀሳቃሽ ምስሉን በዜና እወጃ ሰዓት ላይ አስተላለፈው፤ አገሪቱም በተቃውሞ ተናጠች። ከዓመት በኋላ ያንን ድርጊት የፈጸሙ ፖሊሶች ፍርድ ቤት ነጻ ናችሁ ሲላቸው ደግሞ ደም አፋሳሽ ተቃወሞ በመላው አሜሪካ ዳግም ተከሰተ። "ይሄ ሰው የቀረጸው ምስል ነው በአሜሪካ ምድር የፖሊስን ግፍ መቅረጽ እንዲለመድ ምክንያት የሆነው" ይላል በዚህ ተግባር ጥርሱን የነቀለው የኒው ዮርኩ ፍሎርስ፣ ለቢቢሲ። በአሜሪካ ሕገ መንግሥት ዜጎች በፖሊስ የሚፈጸምን ተግባር ቆመው የመቅረጽ መብት አላቸው። ጆርጅ ሆሊዴይ ሮድኒ ኪንግ በፖሊሶች ሲደበደብ የቀረጸው ምስል 3.ራምሴ ኦርታ ከዚህ ክስተት በኋላ የመጣው የኤሪክ ጋርነር ጉዳይ ነው። ሚስተር ጋርነር የ43 ዓመት ጥቁር አሜሪካዊ ነበር። በኒው ዮርክ ከተማ በ2014 ልክ እንደ ጆርጅ ፍሎይድ ሁሉ በነጭ ፖሊሶች አንገቱን ታንቆ ነበር የሞተው። ፖሊሶቹ አንገቱን አንቀው የያዙት የምትሸጣቸው ሲጃራዎች ሕጋዊ አይደሉም በሚል ምክንያት ነበር። ልክ እንደ ጆርጅ ፍሎይድ ሁሉ ሚስተር ጋርነርም ፖሊሶቹ አንገቱን ጠምልለው ሲያስጨንቁት፤ 'እባካችሁ መተንፈስ አቃተኝ፣ እባካችሁ!' እያለ ይጮኽ ነበር። "I can't breath" የሚለው ንግግርም የትግል መፈክር መሆን የጀመረው ከእርሱ በኋላ ነበር። በእርሱ የደረሰው የሞት አደጋ ፍርድ ቤት የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ነው ቢልም ድርጊቱን የፈጸመው ፖሊስ ግን ነጻ ሆኗል። ያ ፖሊስ ስሙ ዳንኤል ፓንታሊዮ ይባል ነበር። ሟችና ገዳይን ለጊዜው ትተን ያን ድርጊት በቪዲዮ ስላስቀረው ሰው ትንሽ እናውራ። ራምሴ ኦርታ ይባላል። የእርሱ ጉዳይም እንደ ሌሎቹ ቀራጮች ሁሉ ሲያወዛግብ ነው የኖረው። "ይህን ክስተት ከቀረጽኩ በኋላ ፖሊሶች ሲከታተሉኝ ነው የኖርኩት" ብሏል ከዚህ በፊት በሰጠው አንድ ቃለ ምልልስ። በ2016 ራምሴ ኦርታ በአደገኛ እጽና በሕገ ወጥ መሳሪያ ዝውውር ክስ ተመሰረተበት። አራት ዓመትም ዘብጥያ ወረደ። እርግጥ ነው የተመሰረተበት ክስ የፖሊስን ድርጊት በቪዲዮ ከመቅረጽ ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር ባይኖርም ጓደኛው ሚስተር ፍሎረስ እንደሚያምነው ግን ፖሊስ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሲከታተለውና የሚታሰርበትን ሰበብ ሲፈልግለት፣ እንዲሁም ቀን ሲጠብቅለት ነበር። "ፖሊስን ማጋለጥ ለአደጋ መጋለጥ እንደሆነ ሊያስረዳ የሚችለው የራምሴ ኦርታ ጉዳይ ነው" ይላል ፍሎረስ። የሚገርመው ራምሴ ኦርታ ከእስሩ በኋላ ምነው ያን ጊዜ ፖሊስን ባልቀረጽኩ ኖሮ ሲል ተጸጽቷል። ያም ሆኖ ግፍ ሲፈጸም ዝም ብሎ ማለፍም ከባድ የሕሊና ጸጸት እንደሚተርፍ የፈይዲን ሳንታናን ታሪክ ማየት በቂ ነው። ራምሴ ኦርታ ጓደኛው ኤሪክ ጋርነር በፖሊሶች ሲገደል በቪዲዮ በመቅረጹ ፖሊሶች እንደሚያሳድዱት ይከሳል 4.ፈይዲን ሳንታና ፈይዲን ሳንታና በ2015 በሳውዝ ካሮላይና ግዛት፣ ቻርልስተን ከተማ ወደ ሥራ እየሄደ ነበር። አንድ ነጭ ፖሊስ ዋልተር ስኮት የሚባል አንድ ጥቁርን መኪናው ውስጥ ሳለ ሲያስቆመው ያያል። ነገሩ እንዲሁ ስላላማረው ወይም ልማድ ሆኖበት ይሆናል ስልኩን አውጥቶ መቅረጽ ይጀምራል። ፖሊሱ ትንሽ ዘወር ባለበት ቅጽበት ጥቁሩ ዋልተር ስኮት ድንገት ከመኪናው ወርዶ እግሬ አውጪኝ ይላል። ሳንታና ይህ ሁሉ ሲሆን በግማሽ ልብም ቢሆንም እየቀረጸው ነበር። በዚህ ቅጽበት ፖሊሱ ያደረገው ነገር ግን ፍጹም ያልጠበቀው ነበር። ፖሊሱ ሽጉጡን አውጥቶ እየሮጠ የነበረውን ጥቁሩን ዋልተር ስኮትን 8 ጥይቶችን ከጀርባ ለቀቀበት። አከታትሎ። ዋልተር ስኮት መሬት ላይ ወደቀ። ሳንታና እንደቀልድ የቀረጸው ነገር በኋላ ላይ ለከፍተኛ የአእምሮ መረበሽ ዳረገው። "ድንጋጤ ውስጥ የከተተኝ ምንም ያልታጠቀ አንድ ጥቁር ሰውዬ እንዲሁ ለማምለጥ ሲል ብቻ ስለሮጠ 8 ጥይት ከጀርባው ይዘንብበታል ብዬ አላሰብኩም ነበር" ብሏል ለቢቢሲ። ሳንታና ከዚህ ክስተት በኋላ ለሦሰት ቀናት ያህል ከቤት መውጣት አስጠላው። እርሱ ራሱ ስደተኛ ነው፣ በዚያ ላይ ከዶሚኒካን ሪፐብሊክ መጥቶ በፀጉር አስተካካይነት ነበር የሚተዳደረው። በስልኩ ያስቀረውን ነገር ለማንም አላሳየም። ለማንም አላጋራም። እንዲያ ቢያደርግ በኋላ ጣጣው ብዙ ነው ብሎ አሰበ። እንዲያውም ያስቀረውን ተንቀሳቃሽ ምስል እስከ ወዲያኛው ሊሰርዘውና ቻርለስተን ከተማን ጥሎ ለመሄድም አስቦ ነበር። በዚህ መወዛገብ ውስጥ ሳለ ታዲያ አንድ ቀን የፖሊስን ሪፖርት ተመለከተ። ያየውን ማመን አቅቶት ደርቆ ቀረ። በዚህ ሪፖርት 8 ጥይት በጥቁሩ ሰው ላይ ከጀርባው የለቀቀበት ራሱን ለማዳን ነው ይላል። "ፖሊስ ያን ያደረኩት ሰውየው መሳሪያ ይዞ ስለነበረ ሕይወቴ ላይ አደጋ እንዳያደርስ ፈርቼ ነው" የሚል ነገር ሳነብ ደነገጥኩ፤ "በዚህ ጊዜ ውሳኔዬን ቀለበስኩ" ይላል ሳንታና። "በዚያ ጊዜ ይህን ጭልጥ ያለ ውሸት ለማጋለጥ በምድር ላይ ያለሁት ብቸኛው ሰው እኔ እንደሆንኩ አውቃለሁ፤ ፍርሃቴን ለመጋፈጥ ወሰንኩ" ይላል ለቢቢሲ። ሳንታና ጨክኖ ያን ቪዲዮ ወስዶ ለሟች ቤተሰብ አስረከበ። ቪዲዮው ፖሊስ መዋሸቱን አጋለጠ። "እኔ የቀረጽኩት ቪዲዮ በቅጽበት እንደ ሰደድ እሳት ይዛመታል አላልኩም ነበር" ይላል ሳንታና። ከዚያ ቪዲዮ በኋላ የሳንታና ሕይወት እስከ ወዲያኛው ተቀየረ። "የእንገድልሀለን ዛቻ፣ ዘረኛ ስድቦች ሁሉ ይዘንቡብኝ ጀመር። ፍርሃቴን ለመጋፈጥ እኔም ነገሩን መጋፈጥ ፈለኩ…" ዕድሜ ለሳንታናና ለዚያ ቪዲዮ የፖሊስ መኮንንኑ ሚስተር ስላገር ክስ ተመሰረተበት። ፍርድም አገኘ። "አንዳንድ ጊዜ ዝም ማለት የወንጀል ተባባሪነት ነው። ላመንኩበት ነገር መታገል ጀመርኩ። ፍርሃቴንም እያሸነፍኩ መምጣት ጀመርኩ" ይላል ሳንታና፤ ለቢቢሲ በሰጠው አስተያየት። ፌይዲን ሳንታና ዋልተር ስኮት በጥይት ሲመታ የሚያሳየውን ቪዲዮ ለመዘረዝ አስቦ ነበር ፍትህን በእጃችን ይዞ መዞር ሞባይል ስልክና ኢንተርኔት በሌለበት ዘመን የተወለደው የፖሊስን ግፍ የማጋለጥ ተግባር ዛሬ ቀላል ሆኗል። በርካታ ሰዎች ግፍ የመሰላቸውን ተግባር በስልካቸው እየቀረጹ በማኅበራዊ ድረ አምባው ያጋራሉ። ይህም ወንጀሎች ቸል እንዳይባሉ፣ ማኅበረሰቡ በአካባቢው ለሚፈጠሩ ነገሮች ዐይኑን እንዲገልጥ ምክንያት ሆነዋል። ወንጀል ፈጻሚዎችም ግፍ ሲፈጽሙ ዓለም እየተመለከታቸው እንደሆነ ማገናዘብ ጀምረዋል። ለሀቀኛ መርማሪዎችም ነገሩ ሥራ አቅልሎላቸዋል። ለምሳሌ የጆርጅ ፍሎይድን ክስተት ከወጣቷ ዳርኔላ ስልክ ወስደው አስቀምጠውታል። "ወደፊት ደግሞ ዳርኔላ ፍርድ ቤት ቀርባ እንድትመሰክር መደረጉ አይቀርም" ይላሉ ጠበቃዋ ሚስተር ኮቢን። ምንም እንኳ ገና የ2ኛ ደረጃ ጀማሪ ተማሪ ብትሆንም ድርጊቱን በመቅረጽዋ ለአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ቃሏን ሰጥታለች። ቃሏን በምትሰጥበት ወቅት የነበራት ስሜት በዚህ ድርጊት ውስጥ መሳተፍ ተራ ተግባር እንዳልሆነ ማሳያ ነው። ጠበቃዋ ዳርኔላ ቃሏን ስትሰጥ የነበረውን ሁኔታ በዚህ መልኩ ገልጸውታል። "ያለማቋረጥ ታለቅስ ነበር። የደረሰባት ነገር ከባድ ነው። ለመርማሪዎች እንደገለጸቸው በማንኛው ሰዓት ዐይኗን ስትጨፍን የሚመጣባት ምስል ፖሊስ ጆርጅ ፍሎይድን አንቆ ሲገድለው ነው። የሚሰማት ድምጽ 'እርዱኝ መተንፈስ አልቻልኩም' የሚለው ነው። ጆርጅ ፍሎይድ እየሞተ ሳለ የነበረው ፊቱ ይመጣባታል። ዐይኗን ስትገልጥ ግን ምስሉ የለም። ዐይኗን ስትጨፍን ጆርጅ ፍሎይድ ነው የሚታያት።" ወጣቷ ዳርኔላ በዚህ ጉዳይ ፍርድ ቤት ቀርባ ባትመሰክር ምርጫዋ ነው። ይህን ቪዲዮ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ላይ ባትሰቅለው ትመርጥ ነበር። ምንም የመታወቅ ፍላጎት አልነበራትም። በዚህ ረገድ ጠበቃዋ ሚስተር ኮቢን ለቢቢሲ ያቀረበው የታሪክ ምስስሎሽ መጠቀስ የሚገባው ነው። "ዳርኔላ ልክ እንደ ሮዛ ፓርክስ ነው የሆነችው፤ ሮዛ ፓርክስ በ1955 ዓ.ም በአላባማ ባቡር ተሳፍራ ሳለ ወንበር ለነጭ እንድትለቅ ስትጠየቅ እምቢ አለች፡፡… ይህ ድርጊቷ በጥቁር መብት ትግል ታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡ ነገር ግን እርሷ ያን ስታደርግ ወደፊት ማን እንደምትሆን አላሰበችውም። ማርቲን ሉተር ኪንግን ወይም ማልኮም ኤክስን ለመሆን አልነበረም እምቢ አልነሳም ያለችው። በቃ በዚያ ሰዓትና ሁኔታ ለነጭ ወንበሯን መልቀቅ ትክክል እንዳልሆነ ተሰማት አደረገችውም፡፡ የእኔ ደንበኛ ዳርኔላም እንዲያ ናት። መጥፎ ተግባር አየች፤ ስልኳን አውጥታ ቀረጸች።" ዳርኔላስ ልጅ ናት፤ አንድ አዋቂ ሰው እየሞተ ያለን ሰው መርዳት ሲገባው ካሜራውን አውጥቶ ቢቀርጽ ድርጊቱ ጽድቅ ነው ኩነኔ?
news-55876984
https://www.bbc.com/amharic/news-55876984
ትግራይ፡ የዓይነ ሥውሩ ፖለቲከኛ ሞት ስለ ኢትዮጵያው ግጭት ምን ይነግረናል?
በስቃይ እና መከራ የተሞላው የአስመላሽ ወልደ ሥላሴ ሕይወት እና አሁን ደሞ ሕልፈታቸው በኢትዮጵያው በሰሜን ትግራይ ተራሮች እየተካሄደ ያለው ግጭት ምን ያህል አስቀያሚ እንደሆነ ማሳያ ነው፡፡
ሕወሓት ትጥቅ ትግል በጀመረበት እኤአ እንደ 1975 ዓ.ም ግድም ትግሉን የተቀላቀሉት ታጋይ አስመላሽ፣ የዐይን ብርሃናቸውን ያጡት በቦምብ ፍንዳታ በደረሰባቸው ጉዳት ነበር፡፡ በቦንብ ፍንጣሪ የተመቱት አምባላጌ ተራሮች ምሽግ ውስጥ ነበር፡፡ ያ የትጥቅ ትግል እንደ አውሮጳዊያኑ በ1991 ዓ.ም ዋና ከተማዋን አዲስ አበባ በመቆጣጠር እና ወታደራዊውን ሥርዓት በማስወገድ ተጠናቋል፡፡ ከዚያ በ1998 (እኤአ) ሕወሃት-መራሹ ኃይል ከኤርትራ ጋር ደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነት ሲያደርግ፣ አቶ አስመላሽ የግራ እጃቸውን አጡ፡፡ ያን ጊዜ በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለ ነበሩ፡፡ የግራ እጃቸውን ያሳጣቸው የኤርትራ የአየር ድብደባ ነበር፡፡ ሕወሃትን ወደ ሽምቅ ተዋጊነት በመለሰው ያሁኑ ጦርነት ደግሞ፣ ታጋይ አስመላሽ ተገደሉ፡፡ የሕወሃት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና ከፍተኛ አመራር የነበሩት አስመላሽ የተገደሉት ከቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሥዩም መስፍን እና ከቀድሞው የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር አባይ ጸሐዬ ጋር ነው፡፡ እነዚህ አመራሮች የተገደሉበትን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ያዘዙት የ44 ዐመቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ወደ ከፍተኛው የሥልጣን እርከን እስኪመጡ ድረስ በኢሕአዴግ-መራሹ መንግሥት ውስጥ እምብዛም የማይታወቁ አባል ነበሩ፡፡ አሁን እሳቸው እና ሕወሓት ጠላቶች ሆነዋል፡፡ ወደ ቀይ ባሕር መውጫ የሆነችውን ኤርትራንና ሱዳንን በመዋሰን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለውን ትግራይ ክልልን ለመቆጣጠርም እየተፋለሙ ነው የሚገኙት፡፡ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያን ሠራዊት ለማገዝ ወታደሮቻቸውን እንደላኩ ይነገራል፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት ኢሳያስ ወታደሮቻቸውን የላኩት እንደ አውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ከ1998 እስከ 2000 ዓ.ም በተደረገው የድንበር ጦርነት በሕወሃት ክንድ የደረሰባቸውን ውርደት ለመበቀል ነው፡፡ በዚያ ደም አፋሳሽ ጦርነት ያለቁት ሰዎች ብዛት እስከ 100 ሺህ ይደርሳል፡፡ ሁለቱም መንግሥታት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ መገኘታቸውን ያስተባብላሉ፡፡ ሆኖም ብዙ የትግራይ ዐይን እማኞች፣ ኤርትራዊያን እንዲሁም የአሜሪካ መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ምድር እንዳሉ ነው የሚናገሩት፡፡ ዐቢይ አሕመድ በህወሓት ላይ ድል መቀዳጀታቸውን ያወጁት የትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ በተያዘች ማግስት ነበር፡፡ ያንን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትሩ 250 ሺህ ተዋጊዎች እንደነበሩት የሚነገርለትን የሕወሃት አመራሮች አድኖ የመያዝ ዘመቻ እንደሚቀጥል ቃል ገቡ፡፡ እጅን ታስሮ እና ተጎሳቁሎ መታየት ሁሉም ከ60ዎቹ ዕድሜ በላይ ናቸው፤ አስመላሽ፣ ሥዩም እና አባይ፡፡ በምን አኳኋን እንደተገደሉ ግን በግልጽ አይታወቅም፡፡ አንዳንዶች ተይዘው እንደተረሸኑ ይገምታሉ፡፡ በመንግሥት በኩል የሚነገረው ግን በአንድ ዋሻ አቅራቢያ እጅ ስጡ ሲባሉ አሻፈረኝ በማለታቸው የተወሰደ ርምጃ እንደሆነ ነው፡፡ የእነዚህ ሦስት ታጋዮች መገደል የተሰማው የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ አቶ ስብሐት ነጋ አንዱ ናቸው፡፡ ስብሃት በካሜራ ፊት እጃቸው ታስሮ እና ተጎሳቁለው የታዩበት ሁኔታ፣ እኤአ በ2003 ሳዳም ሁሴን የተያዙበትን የሚያስታውስ ነው፡፡ አቶ ፈይሳል ሮቤል መቀመጫውን አሜሪካ ካደረገው የሆርን ኦፍ አፍሪካ ስተዲስ ባልደረባ ናቸው፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት የዐቢይ ደጋፊዎች ሀገሪቱን ለ3 ዐሥርት ዐመታት ያህል በጠንካራ ክንዱ የመራው የሕወሃት ባለሥልጣናት በገጠማቸው ዕጣ ፋንታ ደስተኞች ናቸው፡፡ ህወሓት መሪነቱን ያጣው በአገሪቱ ተቃዋሚዎች ሰልፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ በመጣ ለውጥ ነው፡፡ ለውጡ ዐቢይን ለሥልጣን አብቅቷቸዋል፡፡ "ህወሃትን አገኘነው፡፡ ከመድረ ገጽ እያጠፋነው ነው፡፡ ከእንግዲህ ተነስተው ሊጨቁኑን አይችሉም" የሚል ነው፡፡ ነገር ግን ህወሓትን የማይወዱት ትግራዋያን ጭምር እያሉ ያሉት ሌላ ነው፡፡ "ዓይነ ስውሩን አስመላሽን ገደላችሁ፡፡ የወገብ ቀዶ ጥገና አድርጎ ለመራመድ እንኳ የሚቸገረውን ሥዩምን ገደላችሁ፡፡ የልብ ቀዶ ጥገና ያደረገውን አባይን ገደላችሁ፡፡ ሁለት ፎቅ እንኳ ችለው የማይወጡትን አቦይ ስብሐትን አዋረዳችሁ፡፡ እነዚህ እኮ ለእኛ ጀግኖቻችን ናቸው" ነው የሚሉት፡፡ በስደት ላይ የሚገኙትና በሰብዓዊ መብቶች ዙርያ ዘመቻ በማድረግ የሚታወቁት አቶ ጳውሎስ ተስፋ ጊዮርጊስ እንደሚሉት፣ ጦርነቱ በተጀመረ በሦስተኛው ወር ግድም የህወሓት ሰራዊት በተፈጸመበት የድሮን ጥቃት ከባድ ኪሳራ እንደደረሰበት አጠያያቂ አልነበረም፡፡ ከድሮን በተጨማሪ በርካታ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወታደሮች ብሎም ከትግራይ ክልል ጋር በመሬት ይገባኛል ጥያቄ የሚወዛገበው አማራ ክልል ታጣቂዎች በጥቃቱ መሳተፋቸው ከባድ ጉዳት አድርሷል፡፡ ‹‹ህወሓት ሰፊ መሬቶችን፣ በርካታ ተዋጊዎችን፣ በርካታ መሪዎችን፣ በርካታ ከባድ መሣሪያዎችን በጦርነቱ አጥቷል፡፡ አሁን በእጁ ያሉት መካከለኛና ቀላል መሣሪያዎች ብቻ ናቸው፡፡ ኤርትራ በዚህ ደረጃ በዚህ ጦርነት ውስጥ ትገባለች ብሎ ሕወሃት በፍጹም የጠበቀ አይመስለኝም፡፡›› "ኢሳያስ የድሮ የጦርነት ዘዴያቸውን ነው የተጠቀሙት፡፡ ጠላትን በብዙ ታንክ፣ በብዙ ወታደሮች፣ በብዙ መሣሪያዎች እና በብዙ ቦምብ በአንድ ጊዜ የመጨፍለቅ ስትራቴጂ፡፡" አቶ ጳውሎስ በመቀጠልም፣ ‹‹ነገር ግን ህወሃት አሁንም አላበቃለትም፡፡ ከባድ ውጊያዎችን አድርጓል፡፡ አሁን ሽምቅ ውጊያ ለማድረግ፣ በደንብ ወደሚያውቀው ገጠራማዋ ትግራይ ማለትም ወደ ተራሮች እና ኮረብታዎች ተመልሷል፡፡›› የጎንደር ዩኒቨርስቲ አስተማሪው ምንይችል መሠረት ግን ሕወሃት ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጋር መጠነ ሰፊ ጦርነት ካደረገ በኋላ ወደ ደፈጣ ውጊያ መግባቱ የራሱ የሆነ አደጋ አለው ባይ ናቸው፡፡ ‹‹በደፈጣ ተዋጊ ድርጅት ውስጥ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ብዙ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡ ያው ሕወሃት የተረፉ ጥቂት ተዋጊዎች አሉት፡፡ በትግራይ አንዳንድ ተራራማ አካባቢዎችም ውጊያ እንዳለ ይሰማል፡፡ ሕወሃትም በአውራ ጎዳናዎች ላይ ደፈጣ ጥቃት ይፈጽማል፤ በዕርዳታ ካሚዮን ላይ ጭምር፡፡›› ያንዣበበው የርሃብ ስጋት እንደ አቶ ጳውሎስ ዕምነት ከሆነ፣ "መንግሥት ርሃብን እንደ መሳሪያ እየተጠቀመበት ነው፡፡ የመንግሥት ወታደሮች የአርሶ አደሩን ሰብል አቃጥለዋል፤ ጦርነቱ የተቀሰቀሰው በሰብል መሰብሰቢያ ወቅት ነው፡፡ ወታደሮች ከብቶችንም አርደዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው መንግሥት ትግራይን ሙሉ በሙሉ ዘግቶ በያዘበት ሁኔታ ነው፡፡ ምግብ እየገባ አልነበረም፡፡ አሁንም የምግብ ዕርዳታ ስርጭቱ የተገደበ ነው፡፡ "ሰዎች በምግብ ዕጥረት እየሞቱ ነው፡፡ ርሃብ ይከሰታል የሚል ስጋት አለ፡፡ ይሄ ጦርነት ርህራሄ የሌለበት ጦርነት ነው፡፡ እንዲያውም መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ባንድ ወቅት 'አሳውን ለማጥፋት፣ ባሕሩን አድርቅ' በማለት የተናገሩትን ያስታውሰኛል፡፡ የዐቢይ መንግሥት ሕወሃትን ለማዳከም፣ በርሃብ መቅጣትን ጨምሮ ሰላማዊውን የትግራይን ሕዝብ ማንበርከክ እንዳለበት አምኗል" ይላሉ አቶ ጳውሎስ። የረድዔት ድርጅቶች እንደሚሉት፣ ጦርነቱ በኮሮና ወረርሽኝና በአንበጣ ወረራ ወቅት በመቀስቀሱ ችግሩን የከፋ አድርጎታል፡፡ ቀውሱ በትግራይ ታሪክ ታይቶ እንደማይታወቅ በቅርቡ አንድ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሹም መናገራቸው በመገናኛ ብዙኀን ተዘግቧል፡፡ በባለሥልጣኑ ግምት፣ የክልሉ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ይፈልጋል፡፡ ይሄ ደግሞ የክልሉ አጠቃላይ ሕዝብ 75 መቶኛው ማለት ነው፡፡ ከቀዬው የተፈናቀለው ሕዝብ ደግሞ 2.5 ሚሊዮን እንደሆነ እና ሦስት ሕጻናትን ጨምሮ 13 ሰዎች በርሃብ ስለመሞታቸው ቢሯቸው ሪፖርት እንደደረሰው ባለሥልጣኑ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት በበኩሉ ርሃብን እንደ መሳሪያ ተጠቅሟል የሚለውን ውንጀላ ያስተባብላል፡፡ አቶ ምንይችልም እንዲህ ያሉት ውንጀላዎች "ሙሉ በሙሉ ስህተት ናቸው" ባይ ናቸው፡፡ "መንግሥት በቂ የምግብ ዕርዳታ ክምችት አለው፡፡ ሆኖም ርዳታውን በገጠራማው ክፍል እንዳያሰራጭ የሕወሃት ሃይሎች ሹፌሮችን ይገድላሉ፡፡ የዐለማቀፉን ኅብረተሰብ አስተያየት ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር እና ሐዘኔታ ለማግኘት በማሰብ፣ መንግሥት ርሃብን እንደ መሳሪያ እየተጠቀመ እንደሆነ ለማስመሰል ጥረት እያደረገ ያለው ሕወሃት ነው፡፡ "ሕወሃት ለአርሶ አደሮች ጠመንጃ አድሏል፤ አንዳንዶችም እንዲዋጉ አስገድዷቸዋል፡፡ የአርሶ አደሩ ሰብል የወደመው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ሕወሃት ከተሞችን ከመልቀቁ በፊት የመንግሥት ቢሮዎችን እና ሆስፒታሎችን ጭምር አውድሟል" ይላሉ አቶ ምንይችል፡፡ ከመንግሥት ጋር ትስስር ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቀደም ሲል ባወጣው ሪፖርት፣ በምዕራባዊ ትግራይ የሰፋፊ እርሻዎች ማዕከል በሆነችው ሑመራ፣ የአማራ ወጣት ቡድኖች፣ ሚሊሻ፣ ልዩ ሃይል እና የተወሰኑ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች የሕዝቡን ቤት ንብረት እንደዘረፉ ከነዋሪዎች መስማቱን ገልጧል፡፡ "ዘራፊዎቹ የምግብ እና ጥራጥሬ ማከማቻዎችን ባዶ አስቀርተዋቸዋል" በማለት የጠቀሰው ኮሚሽኑ፤ ሕዝቡን ለመርዳት የተላኩት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሃላፊዎችም በዘረፋው ስለመሳተፋቸው ባንድ የአካባቢው ነዋሪ ተነግሮኛል ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት እና የአማራ ታጣቂዎች በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች መንግሥት ዕርዳታ እንዳከፋፈል የዐለማቀፉ ግጭት አጥኝ ቡድን ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ተንታኝ ዊሊያም ዴቪድሰን ይናገራል፡፡ የህወሃት ሃይሎች የጸጥታ ስጋት በሚደቅኑባቸው አካባቢዎች ግን ሕወሃት ዕርዳታውን ወርሶ ለራሱ እንዳይጠቀምበት ወይም ነዳጅ እና ጦር መሳሪያ እንዳያስገባ በመስጋት መንግሥት ዕርዳታ እያደረሰ አይደለም፡፡ "ባብዛኛው ገጠራማ አካባቢ የፌደራሉ መንግሥት ቁጥጥር አነስተኛ በመሆኑ ወይም የጸጥታ ችግር በመኖሩ ዕርዳታ አልደረሰም፡፡ የፌደራል ኃይሎች በደንብ ወደሚቆጣጠሯቸው የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ እና ወደ ምዕራባዊ እና ማዕከላዊ ትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች ግን ዕርዳታ እየተጓጓዘ ነው" ይላል ዴቪድሰን፡፡ 'የኤርትራ ወታደሮች በቅድስቲቷ ከተማ' ዴቪድሰን እንደሚለው፣ የኤርትራ ወታደሮች በግጭት ተሳታፊ ስለመሆናቸው መንግሥትም ሆነ ኤርትራ ስላላመኑ፣ የኤርትራ ወታደሮች ወደሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ዕርዳታ መላክ ከሎጅስቲክም ሆነ ከፖለቲካ አንጻር አስቸጋሪ ሊሆን ችሏል፡፡ የኤርትራ ወታደሮች ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያች ቅድስት ስፍራ በሆነችው አክሱም እና ከመቀሌ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምተገኘው ውቅሮ ከተሞች እንደሚንቀሳቀሱ የአካባቢው ሰዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ ከሥልጣን የተወገዱት የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ደብረጺዮን ገብረ ሚካዔል የትውልድ ከተማ በሆነችው ሽረ ግን፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከገቡ በኋላ የኤርትራ ወታደሮች ወጥተዋል፡፡ ያም ሆኖ በከተማዋ አዋሳኝ የገጠር ቀበሌዎች አሁንም እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ የሱዳን ቁልፍ ሚና በሎንደን ዩኒቨርስቲ ኢንስቲትዩት ኦፍ ኮመንዌልዝ ስተዲስ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆነው ማርቲን ፕላውት እንደሚለው፣ መሬት መቆጣጠር የግድ የአሸናፊነት ማሳያ አይደለም፡፡ "ሕወሃት ትላልቅ እና ትናንሽ ከተሞችን ተቆጣጥሮ በመቆየት አያምንም ነበር፡፡ ጠላቶቹ እስከሚደላደሉ ይጠብቅና፣ ውጊያ የሚዋጋው ከኮረብታዎች እና ተራሮች ተነስቶ ነው፡፡ "ከዚያ ደፈጣ ጥሎ የመሰወር ስልት ነው የሚከተል፡፡ ጠላቱን በወራት ወይም ዐመታት ውስጥ ጨርሶ ያዳክማል፡፡ በቀደመው ሽምቅ ውጊያ ያደረገውም ይህንኑ ነው፡፡ ድጋሚ የተሳካ ሽምቅ ውጊያ ሊያደርግ የመቻሉ ነገር፣ የጦር መሳሪያ፣ ነዳጅ እና ምግብ አቅርቦት መስመሮችን በመቆጣጠሩ ወይም ባለመቆጣጠሩ የሚወሰን ይሆናል" ይላል ፕላውት፡፡ ድሮ ሕወሃት እነዚህን አቅርቦቶች የሚያገኘው ከሱዳን በኩል ነበር፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር የድንበር ውጥረት እና ግጭት ውስጥ የገባችው ሱዳን፣ ድጋሚ ይህን ትፈቅዳለች ወይ? የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ነው- ይላል ፕላውት ሃሳቡን ሲያጠቃልል፡፡ "ጦርነቱ አጭር ወይስ የተራዘመ ይሆናል የሚለውን የምትወስነው ሱዳን ናት፡፡''
news-56778227
https://www.bbc.com/amharic/news-56778227
በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው ተማሪ "ምን እንደምማር ግራ ገብቶኛል" ይላል
ከክፍል 1ኛ መውጣት ያለ ነው። ከ"ሴክሽን" 1ኛ መውጣትም ያለ ነው። ከትምህርት ቤት 1ኛ መውጣትም ይኖራል። ከ350ሺህ ተማሪ መካከል 1ኛ መውጣት ግን. . . ።
ብሩክ፣ እናቱ ዶ/ር ሄለን፣ እህቱ ኤፍራታ እና አባቱ ዶ/ር ባልካቸው ብሩክ ባልካቸው ይባላል። ብዙም ማውራት የሚወድ ዓይነት ልጅ አይመስልም። ለቢቢሲ የስልክ ጥያቄዎችን አሁን ለጊዜው ከሚገኝበት ሩዋንዳ፣ ኪጋሊ አጠር አጠር ያሉ መልሶችን ነበር የሚሰጠው። ቁጥሩም፣ ውጤቱም፣ ክስተቱም፣ ታሪኩም፣ ወደፊቱም ብዙ የገረመው ልጅ አይመስልም። የስክነት ምንጣፍ ላይ የሚራመድ ብስልና ብልህ ነው ብሩክ። ወይም እንደዚያ ይመስላል። ከብዙ ተማሪዎች ለየት የሚያደርጉት ባህሪዎች አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው። ለምሳሌ ብዙዎችን የሚፈታተነው ሒሳብ ትምህርት "የሚያዝናናኝ የትምህርት ዓይነት እሱ ነው" ሲል ይገልጸዋል። አንድ ተማሪ ከኳስ ቀጥሎ በሒሳብ ከተዝናና ያ ተማሪ የዋዛ እንዳልሆ መገመት ይቻላል። ብሩክ የአዲስ አበባ ወጣት ግልብጥ ብሎ ኳስ ከሚጫወትበት መስቀል አደባባይ ጀርባ በሚገኘው የቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው። ይሁን እንጂ ሰፈሩ ቤቴል ነው። እሱም እሑድ እሑድ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ሜዳ ይወጣል። ሜዳ ሲጠፋ አስፋልት ይወጣል። ኳስ ሊራገጥ። ኳስ መጫወት ብቻም ሳይሆን አዘውትሮ ይመለከታል። ከትልልቆቹ ቡድኖች የአርሴናል ደጋፊ ነው። እንዴት ሊሆን ቻለ? "አባቴ የአርሴናል ደጋፊ ስለሆነ እሱን ላግዘው ብዬ በዚያው የአርሴናል ደጋፊ ሆንኩ" ይላል። አባቱ ዶ/ር ባልካቸው ንጋቱ የማህፀን ስፔሻሊስት ናቸው። "በማተርናል ፌታል ሚዲስን" ደግሞ ሰብ ሰፔሻሊስት ናቸው። እናቱ ዶ/ር ሔለን ይፍጠርም ሐኪም ናቸው። የውስጥ ደዌ ሐኪም። የእርሳቸው ሰብ ስፔሻሊቲ ደግሞ ኢንዶክሪኖሎጂ ነው። ከእሳቸው ጋር ቆየት ብለን እናወጋለን። አሁን ወደ ብሩክ እንመለስ። ብሩክ መጀመሪያ ውጤቱን የሰማበትን ቅጽበት ለቢቢሲ ሲያስታውስ "አባቴ ነው እስኪ ውጤት ከወጣ እንይ ብሎ…" በማለት ይጀምራል። ረቡዕ ቀን ነበር። ከአባቱ ከዶ/ር ባልካቸው ጋር ሶፋ ላይ ሆነው እየተጫወቱ በየመሀሉ ኢንተርኔት ይሞክራሉ። ውጤት ለማየት። ኢንተርኔቱም ሲስተሙም አስቸገራቸው። ደጋግመው ሲሞክሩት ግን ሠራ። የውጤት ማወጂያ ድረገጹ የሁሉንም ትምህርት ጨምቆ ድምር ውጤት አይናገርም። ስለዚህ በተናጥል የየትምህርት ዓይነቶቹን ብቻ ነበር ማየት የቻሉት። ብሩክ በዚያ ማለዳ ምናልባትም የአባቱን የዶ/ር ባልካቸውን ያህል አልጓጓ ይሆናል። ሆኖም 7ቱን የትምህርት ዓይነቶች በቃል ደመሯቸው። 669 መጣ። ቁጥሩ በዝቶባቸው ይሆን? ወይም እርግጠኛ ለመሆን ብቻ ካልኩሌተር አስፈለጋቸው። የተለወጠ ነገር አልነበረም። 669! ይህ ቁጥር ለብሩክ አዲስ ቁጥር አይደለም። ለምን? ከዚያ ቀደም ብሎ ይህን ቁጥር ያውቀዋላ። የአገሪቱ ከፍተኛው ውጤት 669 ነው ተብሎ ሲወራ ሰምቷላ! የሚገርመው ግን ገና ውጤቱን ከማየቱም ቀደም ብሎ ይህ ትንግርቴ ቁጥር (magic number) የእሱ እንደሚሆንም ጠርጥሮ ነበር። እንዴት ሊሆን ይችላል? ቢቢሲ የብሩክ ልበ ሙሉነት እንደዋዛ ሊስማማ አልቻለም። ሞግቶታል። "ተው እንጂ ብሩክ! እንዴት ከ350ሺህ ተማሪ በላይ በተፈተነበት የአንድ አገር ብሔራዊ ፈተና ትልቁ ውጤት የእኔ ሊሆን ይችላል ብለህ ቀድመህ ልትገምት ትችላለህ?" ብሩክ ነገሩን ለማስረዳት ሞከረ። "አንደኛ ከዚያ በፊትም 'ውጤት ሳላይ ገና ጓደኞቼ ይሄ ትልቁ ውጤት ያንተ ሊሆን ይችላል' እያሉኝ ነበር"። ሁለተኛ ደግሞ ፈተናውን ስፈተን የከበደኝ አንድ የኬሚስትሪ ጥያቄ ብቻ ነበረች፤ ስለዚህ…" ይላል። "እውነት ለመናገር ፈተናው ቀሎኝ ነበር።" የሆነስ ሆኖ ብሩክን የፈተነችው የኬሚስትሪ ጥያቄ የቷ ትሆን? የቷስ ብትሆን ምን ትሰራልናለች? ብሩክ እንደሁ ዝሆኑን ውጤት ኪጋሊ ይዞት ገብቷል። ብሩክ "ጥያቄዋን ታስታውሳታለህ ብሩክ?" "የቷን?" "የከበደችህን!" "የሆነ ስለ ሳሙና አሰራር የቀረበ ጥያቄ ነው…" እንደ ሳሙና የተሙለጨለጨችበትን ጥያቄ አልረሳትም። ከእሷ ጥያቄ ሌላ ግን የከበደው አንድም ጥያቄ ትዝ አይለውም፤ ብሩክ። "እኛ አንድም ቀን አጥና ብለነው አናውቅም" እናቱ ዶ/ር ሔለን "ፈተናውን በደንብ ሠርቼ ስለነበር የአገሪቱ ከፍተኛ ውጤት የእኔ እንደሚሆን ገምቼ ነበር" የሚለው ልበ ሙሉ ተማሪ እናት ዶ/ር ሔለን ይፍጠር በልጃቸው ልበ ሙሉነት እሳቸውም ልበ ሙሉ ናቸው። "ብሩክ ከልጅነቱ ጀምሮ ትምህርት የሚወድ ልጅ ሆኖ ነው ያደገው፤ እንዲህ አድርግ፣ በዚህ ውጣ-በዚህ ግባ ብለነው ግን አናውቅም" ይላሉ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? "እውነቱን ንገሪኝ ካልከኝ ድሮ በልጅነቱ ካልሆነ እኔ አጥና፣ ፊልም አትይ፣ መሽቷል ኳስ አትመልከት፣ እንዲህ ሁን እንዲያ ሁን ስለው ትዝ አይለኝም። እኔም አባቱም።" ቆይ ግን! ወላጅ ልጁን እንዴት አጥና እያለ አይቆነጥጥም? አንድም ቀን አጥና ያልተባለ ልጅ እንዴት በአገሪቱ ትልቁን ብሔራዊ ውጤት ሊያመጣ ይችላል? ለዶ/ር ሔለን "ምስጢሩን ካልነገሩን አንላቀቅም" አልናቸው። ነገሩ አሳቃቸው። ከልብ አሳቃቸው…። "'ብሩክ ጎበዝ ልጅ ስለሆነ ነው' የሚለው መልስ አይሆንም ማለት ነው?" ብለው በድጋሚ ሳቁ። በአስጠኚ መምህራን ባይደገፍ እንኳ ላቅ ባለ ደረጃ የተማሩት ወላጆች እጁን ይዘው እንዴት አያስጠኑትም? "ዕድለኛ ሳንሆን አንቀርም" የሚሉት ዶ/ር ሔለን የልጃቸው ከትምህርት ጋር በፍቅር መውደቅ ምናልባት ብሩክ ልጅ እያለ እሳቸውና ባለቤታቸው የነበሩበት ሁኔታ ጋር ሊተሳሰር እንደሚችል ይገምታሉ። "ብሩክ የተወለደው እኔም አባቱም የሕክምና ተማሪ እያለን ነው። እኛ ስናጠና እያየ ስላደገ በዚያው ትምህርት ወዶ ሊሆን ይችላል።" ብሩክ የተፈተናቸውን ሰባት የትምህርት ዓይነቶች በሙሉ በአንጸባራቂ ውጤት ነው ያለፋቸው። ለምሳሌ ሲቪክ 98፣ ባዮሎጂ 97፣ ፊዚክስ 96፣ ሦስት ትምህርቶች ማለትም እንግሊዘኛ፣ ሒሳብና ኬሚስትሪን 95 እንዲሁም አፕቲቲዩድ 93 ከመቶ አስመዝግቧል። "ፌስቡክ ነበረኝ፣ ግን ብዙም ትዝ አይለኝም።" ተማሪ ብሩክ የትምህርት ዓይነቶችን መሠረት ያደረገ የአጠናን ዘዴን ይከተላል። ከሽምደዳ ይልቅ መረዳትን ያስቀድማል። የሚሸመደድ ነገር እምብዛምም አይማርከውም። ትምህርት እንደ ሒሳብ ሁሌ አዲስ ነገርን መፈለግ ሲሆን የበለጠ ዘለግ ላለ ሰዓት ለማንበብ ይበረታታል። "ካልገባኝ ዩቲዩብ ላይ ቪዲዮዎችን እመለከታለሁ። የመምህራንንም መምሪያንም እመለከታለው።" ማኅበራዊ ሚዲያውስ? ዩትዩብን ከፍቶ መዝጋት እንዲህ መጽሐፍ ገልጦ እንደ መክደን ነው እንዴ? ዩትዩብ ውቅያኖስ ነው። ኢንተርኔት ባሕር ነው። ጎርፍ ነው። ብሩክን እያሳሳቀ አይወስደውም? አንድ በርሱ ዕድሜ ያለ ተማሪ ቀርቶ… የማኅበራዊ ሚዲያ ሱስ ዓለም አቀፍ "ፈተና" የሆነው ዝም ብሎ አይደለም። ብሩክ ብሔራዊ ፈተናውንስ አጥንቶ አለፈው። ይህን የፌስቡክ ሱስ ፈተና እንዴት አለፈው? ደግሞም ኢንተርኔት እያሳሳቀ ይዞ የሚሄድ ወራጅ ውሃ የሆነው ለወጣቶች ብቻ አይደለም። በወጣቶች ቢብስም 3ኛ ዲግሪ ለሚሠሩም ፈተና ነው። ብሩክ በዚህ ጎርፍ እንዴት ሳትወሰድ ቀረህ ሲባል ጥያቄው ራሱ የገረመው በሚመስል ድምጽ፣ "ምንም አይመስለኝም" ይላል። ለምሳሌ "ፌስቡክ አለህ ወይ" ተብሎ ሲጠየቅ ብዙም እርግጠኛ ባልሆነ ድምጽ "አዎ፣ ነበረኝ፣ አለኝ፣ መሰለኝ…" ሲል ነው የመለሰው። "…ግን ብዙም ተጠቅሜበት አላውቅም፤ ከጓደኞቼ ጋር ለማውራት ቴሌግራም አለኝ።" በኢትዮጵያ ደረጃ ትልቁ ውጤት ያንተ ነው፤ ሌሎች ተማሪዎች የሌላቸው አንተ ያለህ ነገር ምንድነው ተብሎ ሲጠየቅ ደግሞ፣ "…እኔ ሌሎች የሌላቸውን እንዴት አውቃለሁ?" የሚል አጭር አፍ የሚያሲዝ መልስ ከሰጠ በኋላ፣ "እኔንጃ ብቻ፣ ዋናው ፍላጎት መሰለኝ…ፍላጎት ካለ በቃ…" ሲል ምስጢር የማይመስል የጉብዝና ምስጢርን ያጋራናል። "ሕይወት በትምህርት 1ኛ መውጣት ብቻ አይደለም" ዶ/ር ሔለን የብሩክ እናት ዶ/ር ሔለን ዕድለኝነታቸውንም ሳይሸሽጉ፣ የልጃቸውን ስክነት፣ ለትምህርት መሰጠትና በራሱ ምርጫ ነገሮችን እንዲያደርግ መፍቀድ፣ ጥሩ የአስተዳደግ መስመር እንደሆነ ፈራ ተባ እያሉ ለመምከር ባለመሻት ውስጥ ሆነው ይመክራሉ። "ልጅሽ ጎበዝ ስለሆነ መከረች አትበሉኝና በሚል ዓይነት ትሁት አንደበት ሲቀጥሉ፣ "ልጆችን እኛ ወደምንፈልገው፣ ወደእኛ፣ ወደ ወላጆች ፍላጎት መጎተት ልክ አይመስለኝም" ሲሉ ይሞግታሉ። ልጆችን በእኛ መንገድ ስንጎትታቸው አሉታዊ ስሜትም እናጋባባቸዋለን። ያ ጥሩ አይመጣም፤ አልህም አለ፤ ብዙ ጊዜ ልጆቹ ማድረግ፣ መሄድ የሚፈልጉበትን ዝንባሌ አይተን ማበረታታ፣ ማገዝ ነው የሚሻለው መሰለኝ። እኔንጃ ብቻ ወላጅ ሁሉም የራሱ አስተዳደግ ዘዴ ስላለው፤ ይሄ የግሌ አረዳድ ነው ብቻ…፡፡" ሁሉንም ተማሪ በትምህርቱ ጎበዝ ካልሆነ፣ 1ኛ ካልወጣ ብሎ ትንፋሽ ማሳጠርም ከዶ/ር ሔለን የአስተዳደግ ፍልስፍና የሚስማማ አይመስልም። ስፖርትም፣ ሙዚቃም ሥነ ጥበብን፣ የፈጠራ ሰው መሆንም ሌላ የሕይወት አማራጭ መንገዶች መሆናቸውን መዘንጋት አያሻም ባይ ናቸው። "በጣም ብዙ ዓይነት ሕይወት ነው ያለው እኮ፤ ምርጫችን ሰፊ ነው። ምንም ካለመማር ጀምሮ ምርጫ ነው። እርግጥ ነው ከዓለም ጋር ለመግባባት ፊደል መቁጠር አለብን። የግድ ነው፤ ከዚያ ግን ዓለም ላይ በጣም ብዙ ዓይነት ሙያ፣ ክህሎት አለ፤ ልጆች ራሳቸውን ፍላጎታቸውን ሊከተሉ ልንፈቅድ ይገባል" ሲሉ የሚያምኑበትን ይናገራሉ። ለዚህ ፍልስፍናቸው ተገዢ ለመሆን ይመስላል ዶ/ር ሔለን ልጃቸውን "ይህን ነው መማር ያለብህ፣ ያ ሙያ ይቅርብህ ተው" ብለውት አያውቁም። ማስረጃ? ይኸው ዩኒቨርስቲ ለመግባት ደጅ-ታዛ ሥር የቆመው ብሩክ ምን እንደሚማር አልወሰነም። እንዲያውም ግራ ገብቶታል። በዚህ ጊዜ ማንኛውም ወላጅ ልጁን በራሱ ጊዜ ይወስን ብሎ ይተዋል ተብሎ አይገመትም። በአንድም በሌላም መንገድ ወደ ወላጅ ምርጫ ለማምጣት ይሞከራል። ይመክራል፣ ያስመክራል። እነ ዶ/ር ሔለን ግን ሌላው ቀርቶ ወደ ሙያቸው ወደ ሕክምናው እንኳ ሊጎትቱት እየሞከሩ አይመስልም። "ዌል፣ ሙያችንን ቢወድልን አንጠላም ግን ይሄ የራሱ ውሳኔ ነው መሆን ያለበት" ይላሉ። ዶ/ር ሔለን አሁንም ያሰምሩበታል፤ የልጆችን ምርጫ ስለማክበር…። "እንደ ወላጅ ልጄ ተምሮ ይህን ካልሆነልኝ የምንለው ነገር አለ፤ ብዙውን ጊዜ ተምሮ ጥሩ ገቢ የሚያገኝበትን ነው የምናስበው። ልጄ ምን ፍላጎት አለው ብለን ማሰብ መቅደም አለበት።" ካሉ በኋላ "በማንኛውም ሙያ ፍላጎት ካለና ጥረት ካለ ለኑሯችን የሚሆን ነገር አይጠፋም። ስኬትም በዚያ መንገድ ቢሆን ነው ጥሩ። ደስተኛም የሚሆኑት ልጆች በፍላጎታቸው ሲሄዱና ሲኖሩ ነው" ብለው ይደመድማሉ። "ኪጋሊ ንጹሕ ከተማ ናት" ዶ/ር ሔለንና ዶ/ር ባልካቸው ርዋንዳ ለሥራ ነው የሄዱት። በቅርብ ነው የሄዱት። ብሩክም አብሯቸው ነው ያለው። ብሩክ ከዚህ የሚያኮራ ውጤት በኋላ ጓደኞቹንና መምህራኖቹን አላገኛቸውም። ምን ተሸለምክ ሲባል፣" ምንም!" ይላል፣ ብዙም ሳይከፋው። "ዘመዶቼ ግን በርታ ጎበዝ ብለው መርቀውኛል" ይላል። "ከቤተሰብ እስከሁን ምንም ዓይነት ሽልማት አልተሰጠውም።" እናት ዶ/ር ሔለን በልጃቸው ምላሽ ይስቃሉ። "ሽልማት አልለመድንም ይሆናል። አሁን እየተነጋገርን ነው። ሩዋንዳ የመጣነው በቅርቡ ነው። እዚህ የተዋወቅናቸው ኢትዮጵያዊያን ግን ኬክ ገዝተው እንኳን ደስ ያለህ ብለውታል" ካሉ በኋላ ድምጻቸውን ቀነስ አድርገው፣ "እኛም እያስብንበት ነው" ብለዋል። በልጃቸው ውጤት የተደሰቱት እናት ዶ/ር ሔለን ልጅዎ ስለራሱ ያልነገረን ነገር ካለ እርስዎ ቢነግሩን አልናቸው። "ብሩክ ልቡ ትልቅ ነው። ከትምህር ውጪም ልቡ ትልቅ ነው።" "የምን ልማር" ውልውል አጥና ተብሎ ታዞ የማያውቀው ብሩክ ከልጅነቱ ጀምሮ ከ1ኛ አስከ 3ኛ ነው እየወጣ ከስኬት ጋር ተለማምዶ ያለ ልጅ ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከጀመረ በኋላ ደግሞ አጥና የሚል ከወላጆቹ ስለመስማቱ ይጠራጠራል። "ወላጅ ካላስገደደህ ታዲያ ለምን ታጠናለህ? አይሰለችህም?" ሲባል "ባህሪዬም ስለሆነ ሊሆን ይችላል፣ አላውቅም፤ ብቻ ዝም ብዬ አጠናለሁ" ሲል መልሷል። ብሩክ ፈተናው አልቆም፣ ውጤቱን ወስዶም እያጠና ይሆን? "አይ አሁን እንኳ አሜሪካና ፈረንሳይ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ጋር እያመለከትኩ ነው" ይላል። የአሜሪካው ዩኒቨርስቲ ተስፋ ሰጥቶታል። ተጠባባቂ ሳያደርገው አልቀረም። ያ ካልተሳካ ግን አገር ቤት ተመልሶ ለመማር ቁርጠኛ ነው። እሱን የቸገረው ዩኒቨርስቲው መቼ ሆነና። ብሩክን የቸገረው ምን ዘርፍ ማጥናት እንዳለበት መወሰን ላይ ነው። ምሕንድስና? ሕክምና? ኮምፒውተር ሳይንስ? የሕዋ ሳይንስ? ለጊዜው አንዱም በአእምሮው ሽው አላለም። ለጊዜው ለየትኛውም ዘርፍ ልቡ አልደነግጠም። "የሚከብደኝ ትምህርት አለ ብዬ አላስብም ግን ምን እንደምማር ነው ግራ የገባኝ። አንድ ነገር ለመሆን አልፈለኩም። የሆነ ዘርፍ ላይ እንዳተኩር ያነሳሳኝ ነገር ደግሞ የለም መሰለኝ። ብቻ ገና ውሳኔ ላይ አልደረስኩም" ብሏል። የሚገርመው ብሩክ ከልጅነቱም ጀምሮ አውሮፕላን አበራለው፣ ኢንጂነር እሆናለው፤ ሰው አክማለው ሳይል ነው ያደገው። ሳድግ ይህን እሆናለው ሳይል ያደገ ልጅ ይኖራል? "ድሮም ይህን እሆናለሁ ብዬ እያሰብኩ አልተማርኩም። ምን እንደምሆን፣ ምን እንደምማር አስቤበትም አላውቅም። ለዚያ ይሆናል አሁን ግራ የገባኝ" ይላል። ምናልባት መማሩ በራሱ እያስደሰተው ስለቆየ ትምህርቱ የት እንደሚወስደው ለማሰብያ ጊዜ ነስቶት ይሆን? "ቤተሰቦችህ ይሄን ተማር አላሉህም?" "እነሱ ቀስ ብለህ አስብበትና ትወስናለህ ነው ያሉኝ።" ዶ/ር ሔለን በዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ። "እሱ የሚለን የመጀመርያ ዲግሪዬን በጠቅላላ ሳይንስ ሠርቼ ምን እንድምፈልግ ሳውቅ ብመርጥ ይሻላል ነው። እኛም ቸግሮናል። እሱም ግራ ገብቶታል።" ብሩክን የዛሬ ስንት ዓመት ምን ሙያ ላይ የት ደርሶ እናገኘው ይሆን?
44707901
https://www.bbc.com/amharic/44707901
እንወራረድ፡- የጦፈው የውርርድ ንግድ በአዲስ አበባ
ቀን ሲሰጥ ውርርድ ያልታሰበ ሲሳይ ያመጣል፡፡
ቀን ሲጥል ደግሞ በአንጻሩ ላልተፈለገ ዕዳ ይዳርጋል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ቤተኛ የነበረው ናትናኤል ተክሉ ልምድ የሚነግረንም ይሄንኑ ነው፡፡ "አራት መቶ ብር አስይዤ ፣11 የሚሆኑ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ውጤት ቀድሜ በመተንበይ 34ሺ ብር አሸንፌ አውቃለሁ፡፡"ሲል የፍስሃ ዘመኑን የሚያስታውሰው ናትናኤል በሌላ ጊዜ 5000ሺ ብር "የተበላበትን" ውርርድ ሲያስታውስ እንደሚቆጨው ድምጹ ያሳብቃል፡፡ ውርርድ እንዲህ ጽንፍ እና ጽንፍ ላይ ከቆሙ ስሜቶች ጋር በፍርርቅ የሚላተም "ጨዋታ" ነው፡፡ ያም ቢሆንም ቅሉ በዛሬዋ አዲስ አበባ ህጋዊ ንግድ ከመሆን አልገታውም፡፡ ከብሄራዊ ሎተሪ ፈቃድ አግኝተው የሚንቀሳቀሱ 10 ያህል የውርርድ ድርጅቶች በአዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ ሀበሻ ስፖርት ውርርድ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው፡፡ ከ20 በላይ ቅርንጫፎች ባሉት በዚህ ድርጅት ስር የስፖርት አፍቃሪያን ከሁለት ቡድኖች (ተፎካካሪዎች) መካካል የቱ እንደሚያሸንፍ፣በምን ያክል የጎል መጠን እንደሚረታ ፣እና የመሳሰሉ ሁነቶች ቀድመው በመገመት ብሎም ገንዘብ በማስያዝ ከድርጅቱ ጋር ይወራረዳሉ፡፡ ተጫዋቾች ከ10ብር ጀምረው መጫዎት እንደሚችሉ የሚናገሩት የድርጅቱ ሃላፊ አቶ የኔ ብልህ ባንተ አየሁ እስከ 350ሺ ብር ድረስ ደግሞ ማሸነፍ ይችላሉም ይላሉ። ብዙ ጊዜ ለውርርድ የሚመረጠው ስፖርት እግር ኳስ፤ ከእግር ኳስም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ስፖርታዊ ውርርድ ስሜታዊነት የሚያጅበው ጨዋታ ነው፡፡መጨረሻው ገንዘብ ማግኘት ወይ ገንዘብ ማጣትን የሚያስከትል እንደመሆኑ ለድርጅቶችም ለተጫዋቾችም የሚተወው ራስ ምታት አይናቅም፡፡ አቶ የኔ ብልህ እሳቸው ያዩዋቸውንም ሲገልጹ "ግጭቶች ይፈጠራሉ፡፡ማዘን ይፈጠራል፡፡የተለያዩ ውዥንብሮችም ይከተላሉ፡፡ተጫዎቾቹ ‹ብናሸንፍ ድርጅቱ ቃል የገባውን ገንዘብ ይሰጠናል ወይ!" የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ የተሸነፉ ተወራራጆች "ማስተዛዘኛ የሚሆን ነገር ልናገኝ ይገባል!'የሚል ጥያቄም ያቀርባሉ፡፡እኒህን ችግሮች የጨዋታውን ህግ እና ደንብ በማስረዳት ለመቅረፍ ሞክረናል፤" ይላሉ፡፡ በቅርቡ ከስፖርታዊ ውርርዶች ራሱን ያራቀው ናትናኤል ተክሉ ውርርድ የሚፈጥረው ስሜታዊነትን የሚገነዘበው ለተወራራጆች ከሚፈጥረው ጤናማ ያልሆነ ጥንዎት አንጻር ነው፡፡ ተወራራጆች ከጊዜያት በኋላ በረቡ ባልረቡ ጨዋታዎች ላይ ሳይቀር ተጠምደው ገንዘባቸውን ሲያፈሱ እንደሚያስተውል የሚነሳው ናትናኤል ፣ስሜቱ ልጓም ካልተበጀለት የተጨዋቾችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ህልውና ከማናጋት እንደማይመለስ ይጠቁማል ፤"እንደ ቁማር ሁሉ ሱስ ያስይዛል፡፡ አንድ ሱሰኛ ማናቸውም ነገሮችን በማድረግ ሱሱን ለማሟላት እንደሚጥረው ሁሉ ይሄንንም የውርርድ ሱስ በየትኛውም መንገድ ለማስታገስ (ብዙ ርቀት )የሚሄዱ ሰዎች እንዳሉም ይናገራሉ። የሀበሻ ስፖርት ውርርድ ድርጅት ሃላፊ አቶ የኔ ብልህ በበኩላቸው ውርርድ በመዝናኛ አማራጭነቱ እና እየፈጠረ ባለው የስራ ዕድል ላይ ያተኩራሉ፡፡ ለዋቢነት የሚያቀርቡት ደግሞ በድርጅታቸው ስር ተቀጥረው የሚሰሩ ከ70 በላይ ወጣት ሰራተኞችን ነው፡፡ የሆነው ሆነና አዲስ አበባ ስፖርታዊ ውርርድ ደርቶባታል፡፡ግዙፍ ቴሌቭዥኖችን ላይ ዐይናቸውን የተከሉ ተወራራጆች እዚህም እዚያም ማየት ብርቅነቱ ቀርቷል፡፡ በለስ የቀናቸው በደስታ ይፈነጥዛሉ፡፡ያልተሳካላቸው ጸጉራቸውን ይነጫሉ፡፡እንዲህ እንዲህ እያለ ውርርዱ ይቀጥላል፡፡
news-47176719
https://www.bbc.com/amharic/news-47176719
አምስት ነጥቦች ስለቀጣዩ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ
ኢትዮጵያ አራተኛውን አጠቃላይ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 ቀን 2011 ዓ.ም አንስቶ ልታካሂድ ሽር ጉድ ላይ ናት። የሕገ መንግሥቱ 103ኛ አንቀፅ ቆጠራው በየአስር ዓመቱ መከናወን እንዳለበት ይደነግጋል። ይሁንና በ1999 ዓ.ም እንደተካሄደው ሦስተኛው ቆጠራ ሁሉ ይሄኛውም አስቀድሞ ከተተለመለት ጊዜ ከአንድ ዓመት በላይ ተራዝሟል። 1. ሕዝብ እና ቤት ቆጠራው ለድብልቅ ማንነቶች እውቅና ይሰጣል?
ሦስተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ውጤት ይፋ በሆነበት ወቅት ከተለያዩ አካላት ነቀፌታዎችን ማስተናገዱ ይታወሳል። በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ እና የአማራ ክልል ሕዝቦች ቁጥሮች ጋር በተያያዘ የቆጥራውን ውጤት የመጠምዘዝ ሥራ ተከውኗል ሲሉ የሚያጣጥሉት አሉ። አራተኛው ቆጠራ የሚከናወነው ከፍ ባለ ጉጉት ከሚጠበቀው ከቀጣዩ ምርጫ አንድ ዓመት በፊት እንዲሁም በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ራስን የማስተዳደር ጥያቄዎች በተበራከቱበት ወቅት ነው። ቆጣሪዎች የሚመለመሉት ደግሞ በየአካባቢው ባለስልጣናት ነው። • በአንድ ቦታ የተሰበሰቡ ሰዎችን ቁጥር እንዴት ማወቅ ይቻላል? የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ እና የብሔራዊ ስታትስቲክስ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቢራቱ ይገዙ ቆጠራው ፖለቲካዊ ግብ ባይኖረውም፤ ለፖለቲካ ውሳኔዎች እና ፍላጎቶች ግብዓት መሆኑ ስለማይቀር የሚሰበሰበውን መረጃ ለራስ ፍላጎት እንደሚመች አድርጎ የመነካካት ዝንባሌ አንዱ ስጋታቸው መሆኑን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ይህን ለመቆጣጠር በዚህ ቆጠራ ላይ ተግባራዊ የሚደረጉ በቴክኖሎጂ የታገዙ አሠራሮች አንድ መላ እንደሚሆኑ ይናገራሉ። ለቆጣሪዎቻቸው ይህን የሚመለከት ስልጠና እንደሚሰጡ፤ ተጠያቂነት እንደሚኖርባቸውም አስረግጠው እንደሚያሳውቋቸውም አቶ ቢራቱ አክለው ያስረዳሉ። ከሚጠበቀው በተለየ የተጋነነ ለውጥ ካለ "በወረዳና በቀበሌ ያሉ የመስክ ታዛቢዎችን ለምን እንዲህ ያለ ልዩነት እንደመጣ ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፤ በጣም የተለየ ከሆነ ደግሞ ገለልተኛ ታዛቢ እንዲላክ ይደረጋል" ብለዋል። በምርጫ መጠይቅ ከሚሞሉ መረጃዎች አንደኛው የተቆጣሪዎቹ ብሔር ሲሆን፤ ድብልቅ የብሔር ማንነቶች ያሏቸው ተቆጣሪዎች አንደኛውን የመምረጥ ግዴታ እንደሌለባቸው የሚያስረዱት አቶ ቢራቱ "ብሔርን፣ ኃይማኖትን በተመለከተ መልስ ሰጭው የሰጠው ብቻ ነው የሚሞላው" ይላሉ። መረጃውን የሚሞላው ሰው በዚህ ጉዳይ ላይ የራሱን ብያኔ የመስጠት ስልጣን የለውም። ድብልቅ የብሔር ማንነት ያላቸውም ሆነ፤ የብሔር ማንነታቸውን መግለፅ የማይፈልጉ ሰዎች ይህንኑ ለቆጣሪያቸው ቢናገሩ፤ ቆጣሪያቸው የሚሞላው ወይንም የምትሞላው ኮድ አለ ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። 2. ለሕዝብ እና ቤት ቆጥራው ምን ያህል ዝግጅት ተደርጓል? ኢትዮጵያ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራውን ለመጀመሪያ ጊዜ በዲጂታል መሣሪያዎች የምታከናውን ሲሆን ለዚሁ ተግባር ያገለግላሉ የተባሉ 180 ሺህ ታብሌቶች ከአንድ ዓመት በፊት ተገዝተዋል። ታብሌቶቹ ከኃይል መቆራረጥ ጋር በተያያዘ ችግር እንዳይገጥማቸው ታስቦም በመጠባበቂያነት የሚያገለግሉ 126 ሺህ ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከማቻዎች (ፓወር ባንኮች) እንዲሁም 30 ሺህ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ የባትሪ አቅም መሙያዎች (ቻርጀሮች) ግዥ ተፈፅሟል። አቶ ቢራቱ ይገዙ ቆጠራውን በዲጂታል መሣርያዎች ማድረጉ "ለጥራት ቁጥጥርም፣ ለክትትልም፣ በጊዜ ለማድረስም፣ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍም" የተሻለ አማራጭ እንደሚሆን ታምኖበት የተወሰነ ነው ይላሉ። • በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? ሌላኛው የተከናወነው ሥራ የቆጠራ ክልል ማዘጋጀት ሲሆን እርሱም ሁለት ዓመታትን ወስዷል እንደ አቶ ቢራቱ ገለፃ። በዚህም መሠረት በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም ቀበሌዎች በቆጠራ ክልልነት ተሸንሽነዋል። በገጠር ቤቶች ዘርዘር ብለው እንደመገኘታቸው ከአንድ መቶ እስከ አንድ መቶ ሃምሳ ቤተሰቦች በአንድ የቆጠራ ክልል የተጠቀለሉ ሲሆን በከተማ ደግሞ የቤቶቹ ቁጥር ከአንድ መቶ ሃምሳ እስከ ሁለት መቶ ከፍ ይላል። የቆጠራ ክልሎቹ መገኛ በዓለም አቀፍ የአቀማመጥ ሥርዓት (ጂፒኤስ) ነጥባቸው ተወስዷል። እያንዳንዱ ቆጣሪ ከተሰጠው የቆጠራ ክልል ውጭ ቢንቀሳቀስ ዲጂታል መሣርያው አይሰራለትም ሲሉ አቶ ቢራቱ ገልፀዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አንደኛው ስጋት የሳይበር ጥቃት ሊፈፀም ይችላል የሚል እንደሆነ የተናገሩት አቶ ቢራቱ ይህን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራን ነው ብለዋል። 3. ውጤቱ መቼ ይፋ ይሆናል? በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች አልፎ አልፎ የሚስተዋለው ያለመረጋጋት የቆጥራውን ሒደት ሊያወከው ይችል እንደሆነ በቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ቢራቱ፤ ስጋቱ ቢኖርም ሥራችንን ሊያውከው ይችላል ብለን አንጠብቅም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በአስረጂነት የሚያነሱትም የቆጠራ ክልል ሲዘጋጅ በነበረበት በ2009 ዓ.ም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ተቃውሞ እና ያለመረጋጋት የነበረ ቢሆንም፤ ሥራቸው ላይ እንቅፋት የተፈጠረባቸው አጋጣሚዎች ያለመኖራቸውን ነው። • በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ አቶ ቢራቱ ቆጠራውን ለማካሄድ ከሰባት እስከ አስር ቀናት እንደሚወስድ ይገልፃሉ። ቆጠራው ከተከናወነ በኋላ የተሰበሰበውን መረጃ የመተንተን ሥራ የሚቀጥል ሲሆን፤ ውጤቱን ሕጉ የሚያስገድዳቸውን ሒደቶች አልፎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ ስድስት ወር ገደማ ያስፈልጋል ሲሉም አክለዋል። 4. ማን ምን ይጠየቃል? ለመጀመሪያ ጊዜ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራው መጠይቆች በአምስት ቋንቋዎች ተዘጋጅተዋል። ከአማርኛ በተጨማሪም ኦሮምኛ፣ ሶማሊኛ፣ ትግርኛ እና አፋርኛ መጠይቁ የተሰናዳባቸው ቋንቋዎች ናቸው። መሠረታዊ መረጃን ከሚያመላክቱ ዕድሜ፣ ፆታ፣ ኃይማኖት፣ ብሔር፣ የሥራ ስምሪትና የመሳሰሉ ጥያቄዎች በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ የአካል ጉዳት መረጃ እና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ደረጃ ማለትም የተንቀሳቃሽ ስልክ እና ኢንተርኔት ተጠቃሚነት መረጃዎችም ይጠየቃሉ። በኢትዮጵያ የሥነ ምድር ክልል ውስጥ የሚገኙ ዜጎችም ሆኑ ስደተኞች የሚቆጠሩ ሲሆን የሕግ ታራሚዎችን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን እና የጎዳና ተዳዳሪዎችን የሚመለከቱ ልዩ የመጠይቅ ዓይነቶችም አሉ ሲሉ የቆጠራ ኮሚሽኑ ዋና ጸሐፊ ይናገራሉ። • ኢትዮጵያዊያን ለምን ሥጋ አይመገቡም? ኢትዮጵያ ከዓለም ቀዳሚ ያደረጓትን ቁጥራቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ተፈናቃዮችን አስመልክተውም፤ መንግሥት በሚቀጥሉት ሁለት ወራት በተቻለ መጠን ወደቀያቸው "ለቆጠራውም፣ ለሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች ሲባል" እንዲመለሱ ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል። ይህ ሁሉ ተደርጎም ግን ፍልሰትን የተመለከተ "የአቆጣጠር ዘዴ አለ" ይላሉ። ተፈናቃዮቹ የቆጠራው ውጤት ይፋ ከመሆኑ በፊት ወደቀያቸው ለመመለሳቸው ማረጋገጫው ሲገኝም "መረጃውን ተከታትለን የምናስተካለው ነው የሚሆነው" ብለዋል ዳይሬክተሩ። ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቅቆ ወደውጭ አገር የሄደ የቤተሰብ አባል አለ ወይ? የሚለው ሌላኛው በአራተኛው የሕዝብ ቆጠራ ውስጥ የተካተተ አዲስ ጥያቄ ነው። 5. ቆጥራውን የሚያካሂዱት እነማን ናቸው? ቆጠራውን በበላይነት የመምራቱ እና የማስተባበሩ ስልጣን የሕዝብ ቆጥራ ኮሚሽን ነው። በሕገ መንግሥቱ መሠረት ኮሚሽኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ እጩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚፀድቁ አባላት ይኖሩታል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሚሽኑ የበላይ ሲሆኑ፤ ይመለከታቸዋል የሚባሉ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች እንዲሁም የክልል እና የከተማ መስተዳደር ኃላፊዎችን በአባልነት ያካትታል። አጠቃላይ ዕቅዶችን መገምገም፣ አቅጣጫዎችን መስጠት፣ በከፍተኛ ደረጃ መፍትሄ የሚፈልጉ ችግሮች በሚያጋጥሙበት ወቅት መፍትሄ መስጠት ከኮሚሽኑ ኃላፊነቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ሆኖም የቆጠራውን ቴክኒካዊ ሥራዎች የሚያከናውነው ቆጠራ በሚኖርበት ወቅት ተጠሪነቱ ለኮሚሽኑ የሚሆነው ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጄንሲ ነው። • እየከበዱ የመጡት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ችግሮች ኤጄንሲው የቆጠራ ካርታ የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት። የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ያቀርባል። ለተመለመሉ ቆጣሪዎች ስልጠና ይሰጣል። የቆጠራ መረጃውን ይሰበስባል። መረጃውን ይተነትናል። ከዚያም ለኮሚሽኑ ያቀርባል። ኮሚሽኑ መረጃውን ካፀደቀው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስፀድቃል። ኤጄንሲው በተጨማሪም የኮሚሽኑ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። ለቆጠራ የሚሰማሩ ሰራተኞችን መልምለው የሚያቀርቡት የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች ናቸው። ተመልማይ ቆጣሪዎቹ የመንግሥት ሰራተኞች ሲሆኑ በአብዛኛው መምህራን፣ የግብርና ልማት ሰራተኞችና የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ይሆናሉ።
news-56440712
https://www.bbc.com/amharic/news-56440712
የቦምብ ማስፈራሪያና ግድያ የከበባቸው የእስያው ቁንጮ ሃብታም
ታኅሣስ 18/2013 ዓ.ም ጥዋት በተቀጣጣይ ፈንጂዎች የተሞላ መኪና በእስያው ቁንጮ ሃብታም ቤት ሙኬሽ አምባኒ ቤት አጠገብ ተገኘ።
ሙኬሽ አምባኒ መኖሪያቸው ሕንድ ሙምባይ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት ደግሞ ቦምብና ተቀጣጣዮች ተሞልቶ ነበር የተባለው መኪና ባለቤት አስከሬን በባሕር ዳርቻ ላይ በውሃ ወደ ዳር ተገፍቶ ተገኘ። በሕንድ የንግድ መዲና አጠገብ በሚገኘው ባሕር ዳርቻ የተገኘው አስከሬን በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት የፌደራል ፖሊሶች ከዚህ ግድያ ጀርባ ያለውን እንቆቅልሽ ለመፍታት ተጠምደዋል። እንዴትስ ነው ከቱጃሩ ጋር ግንኙነትስ ያለው? እንዴት ተጀመረ? የሙምባይ ፖሊስ እንደሚለው 27 ፎቅ ያለውን የቱጃሩን ሙኬሽ አምባኒ ከሚጠብቁት የፀጥታ አካላት መካከል አንደኛው ግለሰብ አረንጓዴ ቀለም ያላትና ሕንድ ሰራሿን መኪና ቱጃሩ ቤት አጠገብ ቆማ አየ። መኪናዋ ላይ ተቀጣጣይ ነገሮችን ማየቱን ተከትሎ ፖሊስ ጠራ። ፖሊስም ቦምብ የሚያመክን ቡድኑን ይዞ መኪናዋን መመርመር ጀመረ። መኪናዋም ውስጥ 2.5 ኪሎግራም ክብደት ያለው ጌሊግናይት የተባለውን ተቀጣጣይ ቦምብ አገኙ። ይህ ጌሊግናይት የተሰኘው ፈንጂ በቅርፁ ዱላ መሳይና በስዊድናዊው የኬሚስትሪ ባለሙያ አልፍሬድ ኖቤል የተፈለሰፈውና በዋጋውም ረከስ ያለ ነው። ዱላ መሳይ ተቀጣጣዮቹ ከምንም መሳሪያ ጋር አልተገናኙም እንዲሁም እርስ በርሳቸው መደራረብ ቢጠበቅባቸውም እንዲሁ አልተደረገም። የቦምብና ተቀጣጣይ መሳሪያዎች ባለሙያ የሆኑ አንድ ግለሰብ ለኢንዲያ ቱደይ እንደተናገሩት ቦምቡ ቢፈናዳ ኖሮ ሙሉ በሙሉ መኪናዋን ያወድማት ነበር ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ መኪናው ውስጥ አምስት የመኪና ፈቃድና የሰሌዳ ቁጥር የተመዘገበባቸው ወረቀቶች፣ እንዲሁም ለሙኬሽ አምባኒና ባለቤታቸው ኒታ የተፃፈ ማስታወሻ ተገኝቷል። ማስታወሻውም "ይሄ በተወሰነ መልኩ ፍንጭ እንዲሆንህ ነው። አሁን ተቀጣጣዮቹን አላገናኘናቸውም። በሚቀጥለው ጊዜ ግን ሙሉ ቤተሰብህን ነው የምናፈነዳው" ይላል። ሙኬሽ አምባኒ ሙኬሽ አምባኒ ሪሊያንስ ኢንደስትሪስ የተባለው ኩባንያ ሊቀ መንበር ናቸው። አንጡራ ሃብታቸውም 76 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል። ዋነኛ የቱጃሩ ሃብትም ነዳጅ ማጣሪያ ቢሆንም ቴሌኮምን ጨምሮ ሌሎች ዘርፎች ላይ ኢንቨስትመንት አላቸው። ስለተተወችው መኪና ምን እናውቃለን? የሙምባይ ፖሊስ እንዳስታወቀው ይህቺ መኪና ያለቦታዋ የተገኘች ናት። የሙኬሽ አምባኒ ቤት የሚገኘው ካርማይክል ተብሎ በሚጠራው መንገድ ለመኖሪያ ተብሎ በተከለለው ስፍራ አፓርትመንት አካባቢም ነው። ፖሊስ በአካባቢው ያለ የደኅንት መቆጣተሪያ ካሜራን በማት ደረስኩበት ባለው መረጃ መኪናዋ የተነሳችው ከሙኬሽ አምባኒ መኖሪያ 15 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ካለ ስፍራ ነው። ስኮርፒዮ የተሰኘ ስያሜ ያላት ይህች መኪና ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ቆማ የነበረ ሲሆን ከዚያም አንድ ሌላ ቶዮታ መኪና ሲደርስ ተከታትለው ቱጃሩ ለባለፉት 10 ዓመታት ወደኖረበት ስፍራ አቀኑ። መኪኖቹ በስፍራው ሲደርሱ ከሌሊቱ 8፡30 ነበር። ከሙኬሽ ቤት 500 ሜትር ርቀት ሲደርሱ ቆሙ። ፖሊስ እንደሚለው ከስኮርፒዮዋ መኪና ጭምብል ያጠለቀ ግለሰብ ወረደና በቶዮታው ተሳፈረ። ከዚያም ቶዮታዋን እየነዱ ሄዱ። በተቀጣጣይ የተሞላችው መኪና ባለቤቷ ማን ነው? የስኮርፒዮዋ መኪና ባለቤትት ማንሹክ ሃይረን የተባለ የአካባቢው ነጋዴና የመኪና መለዋወጫ ግለሰብ ነው። ማንሹክ ከፖሊስ በቀረበለት ጥያቄ ሲመልስም መኪናው የእሱ እንዳልሆነችና የማደስ ሥራ ያልከፈለ ግለሰብ እንደሆነ ተናገረ። ግለሰቡ መክፈል ባለመቻሉ መኪናዋን በተያዥነት መያዙን ገለፀ። ማንሹክ ሂረን ይኼው የመኪናው ባለቤት ግለሰብ ለፖሊስ እንደተናገረው ከሙምባይ ወደ ሌላ ከተማ ለመሄድ ባቡር ጣቢያ በሄደበት ወቅት መኪናው በመበላሸቱ እዚያው አቁሟት እንደሄደ ነበር። በነጋታው መኪናውን ለመውሰድ ወደ ቦታው ሲሄድ ካቆመበት ሊያገኘው አልቻለም። በአቅራቢያው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ አምርቶ መኪናው እንደተሰረቀ አስታወቀ። መኪናው ከቱጃሩ ቤት አቅራቢያ በተቀጣጣዮች ተሞልቶ የመገኘቱ ዜና በሕንድ መነጋገሪያም ሆነ። የመኪናው ባለቤትም ብቸኛው እማኝ ስለሆነ ጥበቃ እንዲደረግለትም ጥሪ ቀረበ። ነገር ግን ከሰዓታት በኋላ የማንሹክ ሂረን አስከሬን በሙምባይ አቅራቢያ ከሚገኝ የባሕር ዳርቻ ተገኘ። ስለ ማንሹክ ሂረን ሞት ምን እናውቃለን? ፖሊስ እንደሚለው የካቲት 25 ምሽት ሱቁን ዘግቶ ወደቤቱ ሄደ። ቤቱም ከደረሰ በኋላ ታውዴ የሚባል ፖሊስ እንደደወለለትና ሊያገኘውም እንደሚወጣ ለቤተሰቦቹ ተናግሯል። ነገር ግን በዚያችው ምሽት አልተመለሰም። በነገታው ቤተሰቦቹ ጠፍቷል ብለው ለፖሊስ አመለከቱ። ፖሊስ በበኩሉ ሂረን ከቤቱ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ እንደወጣና ከሦስት ሰዓት በኋላም ስልኩ እንደተዘጋ ተናግሯል። በዚያችን ምሽት አገኘዋለሁ ብሎ የወጣው ፖሊስ ማንነት እስካሁን ድረስ አይታወቅም። ፖሊሶች ምርመራ በጀመሩበት ወቅት ድንገት አንድ አስከሬን ከባህሩ ወደ ዳርቻው ተገፍቶ ወጥቶ እንደተገኘ ተነገራቸው። በውሃ የተነፋው አስከሬን ከአራት- እስከ አምስት በሚሆኑ መሃረቦችም ፊቱ ተጠቅልሎ ነበር። በአሁኑ ወቅት የአስከሬኑ የመጀመሪያ ምርመራ ቢጠናቀቅም የግለሰቡ አሟሟት የሚታወቀው ሙሉው ሪፖርት ሲጠናቀቅ ነው። የሂረን አሟሟት ሴራ የተሞላበትና መረጃዎችንም ለማጥፋት ሙከራ ተደርጓል በማለት የሂረን ባለቤት ከሳለች። ከዚህም በተጨማሪ በተቀጣጣይ የተሞላው መኪናን በተመለከተም የብሔራዊ ምርመራ ኤጀንሲ የፀረ-ሽብር ዘርፍ በጥልቀት እየመረመርኩት ነው ብሏል። ፖሊስ ለምን ታሰረ? በቱጃሩ ቤት አጠገብ የተተወች መኪናን በተመለከተ መረጃ ከደረሳቸውና ወደ አካባቢው ከደረሱት መካከል ሳሺን ዌዝ የተባለ ፖሊስ አንዱ ነው። ፖሊሱ በሙምባይ ፖሊስ ውስጥ ታዋቂ የሆነ የወንጀል ምርመራ ቡድን ተባባሪ ኢንስክፔተር ነው። ሳቪን ዌዝ በቦታው የደረሰው የአካባቢው ፖሊስና ኃላፊዎች ከደረሱ ከሦስት ወይም ከአራት ሰዓታት በኋላ ነው ተብሏል። መጋቢት 4/2013 ዓ.ም የፌደራል መርማሪዎች ተባባሪ ኢንስፔክተሩን ለ12 ሰዓታት ያህል ከጠየቁት በኋላ በቁጥጥር ስር አዋሉት። ሳቺን ዌዝ ተባባሪ ኢንስፔክተሩ በቁጥጥር ስር በዋለበት በነገታው ጠፋች የተባለችው ቶዮታ መኪና በሙምባይ ፖሊስ የወንጀል ዘርፍ ጋራዥ ውስጥ ተገኘች። መርማሪዎች እንደሚሉት ተባባሪ ኢንስፔክተሩ ከቱጃሩ ቤት ተቀጣጣይ ቦምቦችን የያዘችውን መኪና ካቆሙ ሰዎች መካከል አንዱ ነው ይላሉ። የፖሊስ ኃላፊዎች ግን ይህንን ውንጀላ ነው በማለት አይቀበሉትም። ነገር ግን የፀረ-ሽብር ዘርፉ ኢንስፔክተሩን በሴራና ተቀጣጣይ ቦንቦቹን በተመለከተ የሰሩት ምርመራ ቸልተኝነት የተሞላ መሆኑንና ማስፈራሪያዎች የነበሩበት ነው በሚል ከሶታል። ፍርድ ቤቱም ሳቺን ዌዝ የጠየቀውን የዋስትና መብት ከልክሎታል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ የሂረን ባለቤት ለጋዜጠኞች እንደተናገረችው ተባባሪ ኢንስፔክተሩና ባለቤቷ በቅርበት ይተዋወቁ እንደነበር ነው። ስኮርፒዮ የተባለው መኪናም ለሁለት ዓመታት ያህል አብረው ይጠቀሙ እንደነበር ነው። በርካታ ጊዜያትም ይገናኙ እንደነበርም ተናግራለች። ሳቺን ዌዝ በበኩሉ ሂረንን እንደማያውቀውና ስለ ሞቱም ምንም እንደማያውቅ ተናግሯል። ሳቺን ዌዝ ማን ነው? ሳቺን ዌዝ የፖሊስን ኃይል የተቀላቀለው በአውሮፓውያኑ 1990 ነው። በሙምምባይ 'ኢንካውንተር ስፔሻሊስት' የሚባሉና በከተሞች ያሉ ወንጀሎችን ማፅዳት በሚል ያነጣጠረ ቡድን አባል ሆኖ ሰርቷል። ይህ ቡድን በወንጀለኞችና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ አወዛጋቢ ስም ነበረው። አንዳንድ ጊዜም በሕግ የማይመሩና ከወንጀለኞች ጋር የሚተባበሩ እየተባሉም ይከሰሳሉ። በአውሮፓውያኑ 2004 ሳቺን ዌዝ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለ ህይወቱ ካለፈው የ27 ዓመቱ የሶፍት ዌር መሃንዲስ ጋር ተያይዞ ከሥራ ታገደ። ክዋጃ ዩኑስ የተባለውን መሃንዲስ በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሳቺን ዌዝና የሥራ ባልደቦቹ ሲሆኑ ይህም ከተማዋ ውስጥ ከነበረ የቦንብ ፍንዳታ ጋር ተያይዞ ነው። ሳቺን ከመሃንዲሱ ሞት ጋር በተያያዘ እጄ የለም ሲል ክዷል። በአውሮፓውያኑ 2007 ከፖሊስ ኃላፊነቱ እለቃለሁ ቢልም ተቀባይነት አላገኘም። ወዲያው በቀጣዩ ዓመት በእግድ ላይ የነበረው ሳቺን ሺቭ ሴና የተባለ የቀኝ ክንፍ አክራሪ ፓርቲን ተቀላቀለ። ፓርቲው መዲናዋ የሙምባይ በምትገኝበት ማሃራሽትራ ግዛት የጥምር መንግሥት ከመሰረቱት መካከል አንዱ ነው። የፓርቲው አመራሮች ኢንስፔክተሩ የፖለቲካ ህይወቱ እምብዛም ነው ይላሉ። ባለፈው ዓመት ሰኔ እግዱ ተነስቶለት የወንጀል መርማሪ ቡድኑንም እንዲቀላለቀል ተደረገ። የፖሊስ ኃላፊዎች በኮቪድ-19 መመሪያዎች ምክንያት ባጋጠመ የፖሊስ እጥረት ምክንያት ወደ ሥራ እንደተመለሰ ይናገራሉ። ተችዎች በበኩላቸው የታገደ ፖሊስን የመለሱበት ምክንያት ፖለቲካዊ ነው ይላሉ። ባለፈው ሳምንት የሙምባይ ፖሊስ ተባባሪ ኢንስፔክተሩን ለሁለተኛ ጊዜ አግዶታል። ጠበቆቹ ደንበኛችን ከውንጀላው ነፃ ነው እያሉ ይከራከራሉ። ያልተመለሱ ጥያቄዎች ምንድን ናቸው? በርካታ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ፤ ለምሳሌም ያህል፦
news-56920410
https://www.bbc.com/amharic/news-56920410
'ገበሬው አምርቶ የማይጠቀምባት ኢትዮጵያ' የኑሮ ውድነቱን እንዴት መቀነስ ትችላለች?
በምጣኔ ሃብታዊ ቋንቋ የአቅርቦት ሰንሰለት ይባላል። በእንግሊዝኛው 'ሰፕላይ ቼይን' የሚባለው ማለት ነው።
የአቅርቦት ሰንሰለት ሸማቹ ወይም ተገልጋዩ የሚፈልገው ነገር ለገበያ እስኪቀርብ ድረስ ያለው ሂደት ነው። የምጣኔ ሃብት ሰዎች የአቅርቦት ሰንሰለት የአንዲት ሃገር ዕድገት ምሰሶ ወይም ከምሰሶዎች አንዱ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም ይላሉ። የአቅርቦት ሰንሰለትን በቀላል ቋንቋ ለማስረዳት ወደ አርባምንጭ እንሂድ። አርባምንጭ የፍራፍሬ ሃገር ናት። በተለይ ደግሞ ሙዝ። አንድ ፍሬ ሙዝ አርባምንጭ ላይ ያለው ዋጋ እና አዲስ አበባ ተመሳሳይ አይደለም። እንዲሆንም ላይጠበቅ ይችላል። ለምሳሌ አንድ ፍሬ አርባምንጭ ከተማ 20 ሳንቲም ተሸጠ እንበል፤ አዲስ አበባ ሲደርስ ደግሞ 1 ብር [ምሳሌ ነው]። ሙዝ አርባምንጭ በቅሎና አድጎ አዲስ አበባ አሊያም ሌሎች ከተሞች የሚደርሰው የአቅርቦት ሰንሰለትን ተሳፍሮ ነው። አምራች አለ። ከአምራች ተቀብሎ የሚያከፋፍል አለ። ከአከፋፋይ ተቀብሎ የሚቸረችር ይኖራል። ከዚያ ገዥ። ስለ አቅርቦት ሰንሰለት ይህን ካልን ከለት'ተዕለት ኑሯችን ጋር ያለውን ቁርኝት እንይ። አንድ የኢትዮጵያ ኑሮ ሁኔታ የሚያሳስባቸው ግለሰብ፣ አማራ ክልል ውስጥ ያለች አንድ ሽንኩርት አምራች ሥፍራ ያለው የሽንኩርት ዋጋና ከተማ ሲደርስ ያለው ዋጋ እጅግ የተለያየ መሆኑ ያሳስባል ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አሥፍረው ነበር። ለመሆኑ የአቅርቦት ሰንሰለትና የኑሮ ውድነት ግንኙነት አላቸው? የአቅርቦት ሰንሰለቱ የተቃና ቢሆን ኖሮ ለውጥ ይመጣል? "እርግጥ ነው ግንኙነት አላቸው። ነገር ግን ሌሎች ምክንያቶች የበለጠ ተፅዕኖ አላቸው" ይላሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ። "ያለፈውን አሥር ዓመት ብናይ ኢሕአዴግ በገጠርም በከተማም መንገድ ሠርቷል። ግን ከአሥር ዓመት በፊት ያለውን ንረትና አሁን ያለውን ስታየው የዛሬው በጣም ትልቅ ነው። ስለዚህ ሌሎች ገፊ ምክንያቶች ናቸው ለዋጋ ንረቱ ምክንያት የሆኑት እንጂ ሰንሰለቱ ብቻ አይደለም።" ፕሮፌሰር አለማየሁ እነዚህ 'ገፊ' ያሏቸውን ምክንያቶች ያስረዳሉ። ባደረግኩት ጥናት እነዚህ ምክንያቶች አራት ናቸው ይለሉ። "አንደኛው ምርታማነት ነው። ምርታማነታችን በሄክታር ሲሰላ በጣም የሞተ ነው። ለምሳሌ በአማካይ የእርሻ ምርታማነቱ የሚያድገው በዓመት በ2.5 ነው። ይህ ከሕዝብ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ዝቅ ያለ ነው። በእያንዳንዱ የሰብል ዓይነት ሊለያይ ይችላል። ነገር ግን በአጠቃላይ በቂ አይደለም። በጥናቴ መሠረት ቁጥር አንድ ምክንያት ይህ ነው። "ቁጥር ሁለት ያገኘሁት ምክንያት ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 12/13 ዓመታት ከተገቢው በላይ ብር ይታተም ነበር። ለምሳሌ 2000 ዓ.ም. ላይ የቁጠባ ሒሳብና የቼክ ሒሳብ ውስጥ ያለን ጨምሮ ጠቅላላ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ብር 67 ቢሊየን ነበር። አሁን 870 ቢሊየን ደርሷል። ይህ ማለት በአማካይ በ30 በመቶ ያድግ ነበር ማለት ነው ላለፉት 13 ዓመታት።" ፕሮፌሰር ዓለማየሁ የብር መጠኑ ከ4 እና 5 በመቶ መብለጥ አልነበረበትም ሲሉ ይሞግታሉ። ሶስተኛው ምክንያትም ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነው የሚሉት ምሁሩ የኢትዮጵያ ብር አቅም ከዓመት ዓመት እየተዳከመ መምጣቱ ሌላኛው ሰበብ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። "በተለይ አዲሱ መንግሥት ከመጣ በኋላ የገንዘባችን አቅም እየወረደ ወይም እየረከሰ መጥቷል። የቀደመው መንግሥት ብዙ ብር ያትም ነበር። አዲሱ መንግሥት ደግሞ ብሩን እያረከሰው ነው። 80 በመቶ የሚሆኑ ከውጭ የምንገዛቸው ነገሮች የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ነዳጅ የመሳሰሉ ናቸው። ስለዚህ ብሩ በረከሰ ቁጥር እነዚህ ዕቃዎች ይወደዳሉ። በ21 ብር የምትገዛው የነበረው አሁን በ40 ብር ነው የምትገዛው ማለት ነው።" ፕሮፌሰር አለማየሁ ወደ አራተኛው ምክንያት ሲመጡ ከላይ ካነሳነው የአቅርቦት ሰንሰለት ጋር የተያያዘ ርዕስ ያነሳሉ። "አራተኛው ምክንያት የነጋዴዎች አለአላግባብ ትርፍ ማጋበስ ነው። ለምሳሌ አንድ ሽንኩርት የሚያመርት ገበሬ የሚያገኘው ገቢና አዲስ አበባ ያንን ሽንኩርት የሚሸጠው ነጋዴ የሚያገኘው ሲነፃፀር ይዘገንናል። ገበሬው ምንም አያገኝም። ባደጉ ሃገራት አንድ ነጋዴ 20 በመቶ ካተረፈ ትልቅ ነገር ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እኮ መቶ ሁለት መቶ 'ፐርሰንት' ነው የምታተርፈው። መፍትሄውስ? ምሁሩ መፍትሄው ችግሮቹን 'መገልበጥ ነው' ይላሉ። እንዴት ማለት? በዝርዝር ያስረዳሉ። "ለምሳሌ የመጀመሪያው መፍትሄ የሚሆነው ምርታማነትን ማሳደግ ነው። ለምሳሌ ስንዴ ኢትዮጵያ ምን ያክል ታመርታለች? በቆሎስ? ደቡብ አፍሪካ በቆሎ የኛን እጥፍ ነው የምታመርተው። ስለዚህ ምርታማነት ላይ መሥራት ነው አንዱ መፍትሄ።" የምጣኔ ሃብት አስተማሪው ምርታማነት ማሳደግ ትልቅ 'ኢንቨስትመንት' ይጠይቃል ይላሉ። ነገር ግን በአጭር ጊዜ መፍትሄ ለማምጣት ሊደረግ የሚችለው በትናንሽ መስኖዎች ምርት ማምረት ነው ይላሉ። "ጠቅላላ ምርታማነት እንኳ ባይጨምር በዓመት ሁለቴ አመርትን ማለት ነው። ለምሳሌ 5 ኩንታል የምታመርት ከሆነ በዓመት፤ በመስኖ ሁለት ጊዜ አመርትክ ማለት 10 ኩንታል ሆነ ማለት ነው። ስለዚህ የአጭር ጊዜ መፍትሄ ሆኖ የሚታየኝ ይሄ ነው።" ፕሮፌሰር አለማየሁ ካለው የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር አንፃር ወጣቶች በዚህ መስክ ላይ እንዲሰማሩ ያሻል ይላሉ። እንደ ምሁሩ ከሆነ ሁለተኛው መፍትሄ ጥብቅ የሆነ የገንዘብ ፖሊሲ ማውጣት ነው። ካልሆነ ደግሞ የሚወሰደውን ብድር ከላይ ለተጠቀሰው መፍትሄ ማዋል ይገባል ይላሉ። "የሚታተመው ብር ባለፉት ሶስት ዓመታት እየቀነሰ መጥቷል። ይሄ ቆንጆ እርምጃ ነው። ግን ከዚህ በተጓዳኝ የሚታተመው ብር የት ነው የሚገባው የሚለው ነው። የሚታተመው ብር ምርታማነት ላይ ቢጠፋ ችግር አልነበረውም ነበር። የመጀመሪያውን ችግር በፈታ ነበር።" የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ከጠ/ሚ ኃይለማርያም ዘመን ጀምሮ ብር 'ዲቫሉዌት' አልያም አቅሙ መውረድ የለበትም በማለት ሲሞግቱ እንደነበር ይናገራሉ። "ፈረንጆቹ የሚነግሯቸው 'ኤክስፖርት' [የወጪ ንግድ] ይጨምራል፤ 'ኢምፖርትን' [የገቢ ንግድ] ይቀንሳል እያሉ ነው። ባለፉት ሶስት ዓመታት እኛ ማየት አንደቻልነው ኤክስፖርት አልጨመረም፤ ያው ባለፉት አስር ዓመታት በነበረበት [3 ቢሊዮን ዶላር] እንዳለ ነው። ኢምፖርቱ አይቀንስም [ወደ 17 ቢሊዮን ዶላር ነው]። ብርን የማርከስ ጎንዮሽ ጉዳት ከውጭ የሚመጣ ነገር በሙሉ ድሮ በ20 ብር የነበረው አሁን ወደ 40 ከፍ ማለቱ ነው። ይህ ለዋጋ ንረቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል።" ፕሮፌሰሩ ወደ አራተኛው መፍትሄ ሲመጡ የአቅርቦት ሰንሰለቱ የተስተካከለ ቢሆን ኖሮ የምርት ዋጋ እጅጉን ይቀንስ ነበር ይላሉ። "ያለው አማራጭ መቆጣጠር ነው። ነገር ግን ነጋዴን ተቆጣጥረህ አትዘልቀውም። አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ከ200 ሺህ በላይ ነጋዴዎች አሉ። ይሁንና ልቆጣጠር ብትል ችግር ሊፈጠር ይችላል። "ስለዚህ እኔ የሚታየኝ መፍትሄ ምንድነው፤ በግልና በመንግሥት ትብብር በየቀበሌው ገበያዎችን መመሥረት ነው። በተለይ መሠረታዊ ዕቃዎችን ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ። የአምራቾችና የሸማቾች ማሕበር የሚባሉ አሉ። ነገር ግን በሌብነትና በሙስና የተዘፈቁ ናቸው። ስለዚህ የትርፍ ህዳጉን ወስነህ 'ፕሮፌሽናል' የሆነ በግልና በመንግሥት የሚተዳደር [ፐብሊክ ኤንድ ፕራይቬት ፓርትነርሺፕ] ብትመሠርት አንድ መፍትሄ የሚሆን ይመስለኛል።" ምሁሩ እነዚህ ገበያዎች መሠረታዊ ለሆኑ ነገሮች ብቻ ነው መሆን ያለባቸው ይላሉ። "ለዚህ ቆንጆ ምሳሌ 40ና 50 ዓመታት ያገለገሉ ልብ የማንላቸው ተቋማት አሉ። ኢትፍሩትና ከነማ ፋርማሲ የሚባሉ። የእነዚህን ተቋማት 'ስትራክቸር' ማጥናትና በዚያ መሠረት ማቋቋም ይቻላል።" የአቅርቦት ሰንሰለት በኢትዮጵያና በጎረቤት ሃገራት ጎረቤት ሃገር ኬንያ ሁለተኛ ሃገሬ ናት የሚሉት ፕሮፌሰር አለማየሁ የኬንያ መንግሥት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ በገበሬውና በሸማቹ መካከል ያለውን የዋጋ ክፍተት በማጥበብ ትርፉን መልሶ ለገበሬ ማድረግ የሚያስችል ሥርዓት እየዘረጋ እንደሆነ ይናገራሉ። "ዓላማው ትርፉን ወስዶ ለገበሬው ጥቅም ማዋል ነው። ለምሳሌ የጤና ተቋማትን መገንባት፤ ትምህርት ቤት ማሠራት የመሳሰሉትን ለማቋቋም ነው የሚተልመው ይህ ሥርዓት።" ይህን እየቀረፁ ያሉት ኬንያዊ ባለሙያ ልክ እንደ ራይድ ወይም ኡበር ያለን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ እንዳሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። "ይህ 'ሲስተም' በኤሌክትሮኒክ አማካይነት ምርቶችንና ሸማቹን ማገናኘት ነው ዓላማው።" ኬንያ ከኛ የሚለያት ቁጥሩ አነስተኛ የሆነና የተደራጀ ነጋዴ መኖሩ ነው ይላሉ ምሁሩ። ስለዚህ ይህ ለቁጥጥር ይመቻል ሲሉ ልዩነቱን ያስረዳሉ። "እኛ አንድ 15-20 ዓመት አይቀረንም ብለህ ነው ኬንያ አሁን ያለችበት ለመድረስ?" የሚሉት ፕሮፌሰር አለማየሁ ኢትዮጵያ መወዳደር ያለባት ከነ ሩዋንዳና ማላዊ ጋር ነው ይላሉ። ምሁሩ ሐሳባቸውን ሲያጠቃልሉ 'ኋላ ቀር መሆናችን ገብቶን ወደ መፍትሄው በፍጥነት ማምራት አለብን' ይላሉ።
41411130
https://www.bbc.com/amharic/41411130
ቀጣዩ ኢትዮጵያዊ የማራቶን ባለተስፋ ጉዬ አዶላ ማነው?
በቅርቡ በርሊን ማራቶን በተደረገው ውድድር ላይ የጉዬ አዶላ ስም አልተጠቀሰም። ቀጣዩን የዓለም አለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ሬከርድ የሚሰብረው ማን ይሆን የሚለው መላ ምት ውስጥ ታላላቆቹ ሯጮች እነ ቀነኒሳ በቀለ፣ ዊልሰን ኪፕሳንግና ኢሉድ ኪፕቾጌ ነበሩ ግምት የተሰጣቸው።
ጉዬ አዶላ በበርሊን ማራቶን አሸንፎ በገባበት ወቅት ጉዬ እንኳን የማሸነፍ ግምት ሊሰጠው ይቅርና የማራቶን ውድድር ላይ ተወዳድሮ አያውቅም። ውድድሩ ሲያልቅ ግን ብዙዎች ስሙን አንስተውታል። ቀነኒሳ በቀለና ዊልሰን ኪፕሳንግ ሩጫውን መጨረስ ቢሳናቸውም፤ ጉዬ አዶላ እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ እልህ በሚያስጨርስ ሁኔታ ተወዳድሮ በጥቂት ሰከንዶች ተበልጦ ሁለተኛ ወጥቷል። ያስመዘገበውም ሰዓት በዓለም የማራቶን ሩጫ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት እንዲሁም ለኢትዮጵያም ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል። ጉዮ ማነው? ብዙ ያልተባለለት የ26 አመት እድሜ ያለው ጉዬ አዶላ ድንገት ከየት ተገኘ? በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ቢሉ በምትባል አካባቢ የተወለደው ጉዬ፤ እንደ ቀደሙት አትሌቶች ሩጫን የጀመረው በህፃንነቱ ትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት ነው። ዕድሜው 17 ሲሞላ ለቀጣይ ስልጠናዎች አዲስ አበባን መዳረሻው አደረገ። የአምቦ አትሌቲክስ ክለብ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ተፈሪ መኮንን በሩጫ ህይወቱ ላይ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ አበክሮ የሚናገረው ጉዬ፤ የሩጫ ህይወቱ ግን ማንሰራራት የጀመረው በኦሮሚያ የውሃ ሥራዎች ክለብ ቆይታው ነበር። ጉዬ ከውድድሩ በኋላ ሜዳልያውን አጥልቆ የመጀመሪያው ትልቅ ውድድር የነበረው ከሦስት ዓመታት በፊት ማራኬሽ ከተማ በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ነው። ይህም ለቀጣይ ውድድሮቹ ፈር የቀደደለት ሲሆን፤ በዚያው ዓመትም በተመሳሳይ ርቀት እንዲሁም በ10 ኪ.ሜ ብዙ ውድድሮችን አድርጓል። ነገር ግን ብዙ የሚያስደስት ውጤት ማምጣት አልቻለም። "የጤና እክል ደርሶብኝ ስለነበር ምግብ መመገብ ከብዶኝ ነበር" በማለት የሚናገረው ጉዬ፤ "ሰው ካልበላ ደግሞ መሮጥ ከባድ ነው፤ ከዚህ በተጨማሪም በወቅቱ ቀላል የማይባሉ የእግር ጉዳቶች ደርሰውብኝ ነበር" ይላል። ብዙዎች አትሌቶች ከድህነት በመውጣት የተሻለ ህይወትን ለማግኘት ሩጫን እንደ መውጫ መንገድ ያዩታል። የጉዬም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም። "ከገጠር የሚመጡ ሰዎች ምን አይነት ህይወት እንደሚመሩ ከዚያው የመጡ ያውቁታል። ከደሃ ቤተሰብ ነው የመጣሁት፤ ሩጫ ከጀመርኩ በኋላ ግን የቤተሰቦቼ ህይወት ላይ መሻሻል አለ" በማለት ይናገራል። ከእሱ በፊት የመጡ የሩጫ ጀግኖች የሚላቸውን የእነ ቀነኒሳ በቀለ እንዲሁም የጥሩነሽ ዲባባን ስኬት ማየቱ ትምህርቱን ዘጠነኛ ክፍል ላይ አቋርጦ ለሩጫ ሙሉ ትኩረቱን እንዲሰጥ አደረገው። የእሁድ ዕለቱ ድልም በሩጫ ዘመኑ ሁለተኛ የሚባለውን የ24 ሺህ ዶላር ሽልማትን አስገኝቶለታል። ከሦስት ዓመታት በፊት ከፍተኛ የሚባለውን ብር ያገኘው ህንድ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ሲሆን፤ ከማሸነፉ በተጨማሪ አዲስ ክብረ-ወሰንም አስመዝግቧል። በወቅቱ የተከፈለውም 35 ሺህ ዶላር ነበር። ከበርሊን ውድድር በኋላ ጣልያናዊው ማኔጀሩ ዝናውም ሆነ የሚያገኘው ብር ይቀየራል በማለትም አስተያየቱን ይሰጣል። "በዚህ ውድድር ላይ ያሸንፋል ተብሎ ስላልተጠበቀ፤ በአዘጋጆቹ የተሰጠው ክፍያ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።" በማለት የሚናገረው ጂያኒ ዲማዶና "ከዚህ በኋላ ግን ጠቀም ያለ ክፍያ ይሰጡታል" ይላል። ተጨማሪ የማራቶን ተስፋዎች ጉዬ የእራሱ ቤት የለውም፤ አላገባም። ነገር ግን በበርሊን ላይ ካሸነፈ በኋላ ብሩህ ተስፋ እንደሚታየው ተናግሯል። ጂያኒ ዲማዶናም የአሁኑን የጉዬን ድል እንደ ትልቅ ስኬት በማየት፤ ቀጣዩ ዝግጅታቸው በሚያዝያ ወር ላይ ለሚካሄደው ትልቁ የለንደን ማራቶን መሆኑን ይናገራል። ጉዬ አዶላ ከዚህ ቀደም ለምን በማራቶን ሩጫ አላሸነፈም? ምንም እንኳን በአሰልጣኞቹ አስተያየት ማራቶን ላይ እንዲሳተፍ ምክር ቢሰጠውም ጉዬ እንደሚለው ለማራቶን ሩጫ ምንም ፍላጎት አልነበረውም። በእድሜው ትንሽ መሆኑና እንዲህ አይነቱን ረዥም ርቀት ለመሮጥ ከባድ ነው በሚልም ይመልስላቸው ነበር። አሁን ግን ያለምንም ጥርጣሬ የማራቶን ሯጭ ነው። በበርሊን ያሸነፈበት ሰዓት ከአለም ሬከርድ በ49 ሰከንዶች ብቻ መለየቱ፤ በኢትዮጵያ ደረጃም ምርጥ የሚባል ሰዓት ማስመዝገብ አስችሎታል። ጂያኒ ዲማዶና እንደሚለው በስልጠናው ወቅት ጥሩ ሰዓትን ቢያስመዘግብም ይህ ግን "ታላቁ ህልማችን" ነው። "ባስመዘገብነው ሰዓት በጣም ነው የተደነቅነው። እየጠበቅን የነበረው 2፡05 ወይም ደግሞ 2፡06 ነበር። በጭራሽ 2፡03፡46 ግን አልነበረም" ይላል። የጉዬ ረዳት አሰልጣኝ የሆነው ከሊል አማን በበኩሉ፤ ጉዬ ለረዥም ርቀት ሩጫ ለየት ያለ ተሰጥኦ እንዳለው ይመሰክራል። "አሯሯጡ፤ እግሩን የሚያነሳበት መንገድ ጉልበቱን በብቃት እንደሚጠቀም የሚያሳይ ነው። ለዛም ነው የማይደክመው።" በማለት ሙያዊ አስተያየቱን ይሰጣል። ጉዬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሩጫ የህይወቱን 'ሀ' ብሎ የጀመረው ከሦስት ዓመታት በፊት ዴንማርክ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ሲሆን፤ በወቅቱም የነሐስ ሜዳሊያ ለማግኘት ችሏል።
news-50742407
https://www.bbc.com/amharic/news-50742407
ለሁለት ዓመታት የአስራ ሁለት ዓመት ልጁን በጓደኞቹ ያስደፈረው አባት ህንድን አስቆጣ
ቅዳሜና እሁድ ለሁለት ዓመታት ያህል የአስራ ሁለት ዓመቷ ህንዳዊቷ ታዳጊ በአባቷ ጓደኞች እንዲሁም አባቷ ባመጣቸው ሰዎች ተደፍራለች። [ ማስጠንቀቂያ፦ ፅሁፉ የሚሰቀጥጡና የሚረብሹ መረጃዎች ስላሉት ሲያነቡ ይህንን ከግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ]
ይሄ ሁሉ የተጀመረው በአንዲት ዕለት ነው፤ የታዳጊዋ አባት ጓደኞቹን ለመጠጥ ጋብዟቸው ነበር። በመጠጥ ኃይል የተገፋፉት ግለሰቦች ቤተሰቦቿ ፊት ይጎነታትሏት ጀመር። አንዳንዶቹም እናቷን ይዘዋት አንደኛው መኝታ ክፍል ውስጥ በተደጋጋሚ ይገቡ፣ ይወጡ ነበር። • የተነጠቀ ልጅነት በዚህ የተጀመረው መጎነታተል እዚያ ላይ አላቆመም። አንድ ዕለትም አባቷ ከአንደኛው ጓደኛው ጋር እንድትሆን አድርጎ የአንደኛውን መኝታ ቤት በር ከውጭ ቆለፈባት፤ ሰውየውም ደፈራት። የልጅነት ዓለሟም በዚህ ተቀጨ፤ ስቃይዋም አንድ ተብሎ ተጀመረ። አባቷ ጓደኞቹም የሆኑም ያልሆኑም ወንዶች ጋር በመደወል ቀጠሮ በመያዝ ገንዘብ እየተቀበል፤ ልጁን ማስደፈር ተያያዘው። ባለሙያዎች እንደሚያምኑት ህፃኗ ቢያንስ በሰላሳ የተለያዩ ወንዶች ተደፍራለች። • "በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" ከጥቂት ወራት በፊት ከመምህራን በደረሰ ጥቆማ በህፃናት ደህንነት ላይ የሚሰሩ ኃላፊዎች ታዳጊዋን ከትምህርት ቤቷ ወስደው በመጠለያ ቤት ውስጥ አስቀምጠዋታል። በተደረገላትም የህክምና ምርመራ በተደጋጋሚ እንደተደፈረች ማረጋገጥ ተችሏል። አባቷን ጨምሮ አራት ወንዶችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። እነሱም በመድፈር፣ ህፃናትን በወሲብ ንግድ በማሰማራትና በጥቃት ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ዋስም ተከልክለዋል። ከነዚህ ግለሰቦች በተጨማሪ ፖሊስ አባቷ ያውቃቸዋል ያላቸውና የመድፈርና አካላዊ ጥቃት አድርሰውባታል የተባሉ አምስት ግለሰቦችንም እየፈለገ ነው። መርማሪዎች ልጅቷን በመድፈር የተጠረጠሩ ሃያ አምስት ወንዶች ስምና ፎቶዎችን ይዘዋል። • ህንዳዊቷን ዶክተር በቡድን ደፍረው ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት በፖሊስ ተገደሉ "ፊታቸውን አላስታውስም፤ ብዙው ነገር ብዥ ብሎ ነው የሚታየኝ" ብላለች ታዳጊዋ ጥቃቱን ስለፈጸሙባት ሰዎች ስትጠየቅ። ቤተሰቦቿ በደቡባዊ ህንድ በምትገኝ ጥሩ አቅም ያላቸው ሰዎች በሚኖሩባት ከተማ ቢኖሩም፤ እነሱ ግን ኑሯቸው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በመስከረም ወር ላይ የታዳጊዋ ጎረቤቶች የሆኑ መምህራን ለትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች ልጅቷ ችግር ሊኖርባት እንደሚችል አሳውቀው ነበር። "ቤተሰቦቿ አንድ የሆነ ችግር ያለባቸው ይመስለናል፤ ቤቷም ውስጥ ምን እንደሆነ ባናውቅም የሆነ ግራ ግብት የሚል ጉዳይ እየተከናወነ ነው፤ እስቲ ህፃኗን አናግሯት" ብለው ተናገሩ። የትምህርት ቤቱ አስተዳደርም ከሴቶች ድጋፍ ቡድን አማካሪ በማምጣት ህፃኗን እንዲያናግሯት አደረጉ። በመምህራኑና ሰራተኞች ክፍል ውስጥም "እስቲ ስለ ራስሽና ስለ ቤተሰቦችሽ ትንሽ ንገሪን" አለቻት አማካሪዋ። ለሰዓታትም ከታዳጊዋ ባወሩበት ወቅት፤ አባቷ ሥራ ስሌለው ሁኔታዎች ፈታኝ እንደሆኑ ተናገረች። የቤት ኪራይም ስላልከፈሉ ከቤት ሊያስወጧቸውም እንደሚችሉ እያለቀሰች በልጅነት አንደበቷ አወራች። ትንሽ ቆይታም በዝምታ ተዋጠች። አማካሪዋ በክፍል ውስጥ ስለሚማሩት የሥርዓተ ፆታ ክፍለ ጊዜና ምን ያህል ህፃናትስ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ጠየቀቻት። • የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ደፍሮ የገደለን ተጠርጣሪ ስም ይፋ እንዲደረግ ወሰነ "እኛም ቤት ጥቃቶች ይደርሳሉ፤ አባቴ እናቴ ላይ ጥቃት ይፈፅማል" ብላ ምላሽ ሰጠች። አማካሪዋም "እስቲ ዘርዘር አድርገሽ ንገሪኝ" ብላ ጠየቀቻት። አንድ ቀን እናቷን ሊያይ የመጣ ግለሰብ ጥቃት እንዳደረሰባት ተናገረች። እናቷም በአፀፋው ግለሰቡን አስጠንቅቃዋለች አለች። ነገር ግን እሷ በሌለችበት ወቅት እናቷን ሊያዩ የሚመጡ ብዙ ወንዶች መኖራቸውንም አስረዳች። በተለይም ምሽት ላይ ጠጥተው የሚመጡና እናቷም ላይ ወሲባዊ ጥቃት የሚያደርሱ ወንዶች ቁጥር ብዙ ናቸው አለች። አማካሪዋም ስለ እርግዝና መከላከያ መድሃኒት ታውቅ እንደሆነ በጠየቀቻት ጊዜ "አይ እኛ ኮንዶም ነው የምንጠቀመው" የሚል ምላሽ ሰጠች ታዳጊዋ። ይሄ እንግዲህ በንግግራቸው መካከል ታዳጊዋ ወሲብ ፈፅማ እንደምታውቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር የጠቆመችው። ከዚህ በኋላ ነበር ስለተሰረቀው ልጅነቷ መናገር የጀመረችው። "ወንዶች እየመጡ እናቴን ወደ አንዱ መኝታ ክፍል ይወስዷታል። እኔ ይሄንን ያየሁት እንደተለመደ ነገር ነው። አንድ ቀን አባቴ እኔንም አንደኛው መኝታ ክፍል ውስጥ ገፍቶ አስገባኝና ከማላውቀው ሰው ጋር ቆለፈብኝ" ብላለች። አንዳንድ ጊዜም አባቷ አስገድዶ እርቃኗን ፎቶ ያነሳትና ለደፈሯት ወንዶች ፎቶ ይልክላቸዋል። የሆነ ወቅት ላይም ታዳጊዋ ለሦስት ወራት ያህል የወር አበባዋ በመዘግቱ ቤተሰቦቿን አስደንግጦ የነበረ ሲሆን፤ ህክምናም ወስደዋት መድኃኒት ታዞላት ነበር። በዚህ ወቅት አማካሪዋ በተደጋጋሚ የመደፈር ጥቃት እንደደረሰባት መረዳት ቻለች። አማካሪዋም በአፀፋው የህፃናት ደህንነት ኃላፊዎች ጋር ደወለችና ወደ መጠለያ እንደሚወስዷት ለታዳጊዋ ነገረቻት። • "የወሲብ ብዝበዛ ተጠቂ መሆኔን ለመረዳት ዓመታት ፈጅቶብኛል" ይህ ሁኔታ ታዳጊዋን ብዙ አልረበሻትም። እናቷ በተመሳሳይ ሰዓት ከመምህራን ጋር ውይይት እያደረገች የነበረ ሲሆን ስትወጣም ልጇ ወደ አንድ መኪና ስትገባ አይታ ጩኸቷን አቀለጠችው። "ልጄን የት ነው የምትወስዷት?" እያለች ነበር። አማካሪዋም ለእናቲቱ "አንዳንድ የባህርይ ችግሮች ስለተከሰቱባት የምክር አገልግሎት ስለሚያስፈልጋት ነው" የሚል ምላሽ ሰጠች። "ያለእኔ ፈቃድ ለልጄ የምክር አገልግሎት የምትሰጡት እነማን ናችሁ?" ነበር የእናቲቱ ጥያቄ። እናቷ እንደዚህ ብትልም ታዳጊዋ ወደ መጠለያ ተወሰደች። ላለፉት ሁለት ያህል ወራትም ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸው ታዳጊዎች ጋር እየኖረች ነው። በህንድ በሚያሳፍር መልኩ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ ታዳጊ ህፃናት ወሲባዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል። አብዛኛዎቹ ጥቃቶች የሚደርሱት ደግሞ ታዳጊዎቹ በሚያውቋቸው ሰዎች [በዘመዶች፣ በጎረቤቶች፣ በቤተሰብ] እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። ከሁለት ዓመት በፊት የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው ከ10 ሺህ በላይ ህፃናት እንደተደፈሩ ነው። በቅርብ ዓመታትም በህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን ነው። አማካሪዎቹ እንደሚሉት እንደእነዚህ አይነት አሰቃቂ ታሪኮችን መስማት አዲስ ነገር እንዳልሆነ ነው። መጠለያው ውስጥ ካሉ ታዳጊዎች መካከል በአስራ ሁለት እና በአስራ ስድስት ዓመት መካከል ያሉ ሦስት ታዳጊዎች ያሉ ሲሆን ሁሉም የተደፈሩት በአባቶቻቸው ነው። አንዷ አማካሪ እንደገለፀችውም በአባቷ የተደፈረች ነፍሰጡር የ15 ዓመት ታዳጊን ፈተና እንድትፈተን ወደ አዳራሹ እንዳደረሰቻት ነው። "ታዳጊዋን ከወለደች በኋላ ልጁን ስጭን ስንላት፤ ለምንድን ነው ልጄን የምሰጣችሁ? የአባቴ ልጅ እኮ ነው። ራሴ አሳድጋለሁ" ማለቷን አማካሪዋ ተናግራለች። የአስራ ሁለት ዓመቷ ታዳጊ መጠለያ በተወሰደችበት የመጀመሪያ ቀናቶች ውስጥ ሰላማዊ የሆነ እንቅልፍ ሊወስዳት ችሏል። ነገር ግን ከትንሽ ቀናት በኋላ እናቴ ናፈቀችኝ እያለች ግድግዳው ላይ መፃፍ ጀመረች። እናቷ በበኩሏ የልጇ ታሪክ የውሸት ነው "ከእኛ ጋር በተደጋጋሚ እየተጣላች ስለነበር እኛን ለማስተማር ስትል የፈጠረችው ታሪክ ነው" ብላለች። እናቷ እንደተናገረችው ባሏ ሥራውን ከማጣቱ በፊት በአንድ ወቅት ጥሩ ይከፈለው እንደነበር ነው። በአሁኑ ወቅት ባሏ እስር ቤት ሆኖ የፍርድ ሁኔታውን እየተጠባበቀ ሲሆን፤ ልጇም መጠለያ ውስጥ በመገኘቷ ቤቱ ውስጥ ብቻዋን ቀርታለች። "ለልጄ የማስብ እናት ነኝ፤ እናም ትፈልገኛለች" በማለት የታዳጊዋ እናት ለቢቢሲ ገልፃለች። . ...... በግድድዳው ላይ ትሞነጫችራቸው የነበሩ ስዕሎች በትዝታ እንድኖር አድርጎኛል የምትለው እናት "ሁሌም መሳል፣ መሞነጫጨር ነበር ሥራዋ፤ ያንን ብቻ ነበር የምታደርገው" በማለት እናቷ ትናገራለች። መኝታ ክፍሏ ውስጥም እናቷን እንደምትወዳት "ይቅርታ እማማ" የሚሉና ሌሎችም ስዕሎች አሉ ተብሏል።
news-48199195
https://www.bbc.com/amharic/news-48199195
በምስራቅ ጎጃም መነኩሴው ለምን በቁጥጥር ሥር ዋሉ?
ከትናንት በስቲያ ሚያዚያ 28 ቀን 2011 ዓ. ም. በምስራቅ ጎጃም ዞን፤ አዋበል ወረዳ በምትገኘው እነጋትራ ሐና ገዳም አስተዳዳሪ አባ ገ/ሥላሴ ሳሙኤል ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር የተፈጠረ ግጭትን ተከትሎ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የወረዳው ባለስልጣናት ለቢቢሲ አስታወቁ።
የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ይሄነው አበባው ከመነኩሴው ጋር 7 የጦር መሣሪያዎች የተያዙ ሲሆን፤ ስድስቱ ለገዳሙ መጠበቂያ ተብሎ ከመንግሥት ወጭ ተደርጎ የተሰጣቸው ነው ይላሉ፤ ይሁን እንጂ ሕጋዊ ያልሆነ አንድ ሽጉጥ የተገኘባቸው መሆኑን ገልፀዋል። • እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው "ስድስቱ መሣሪያዎች ከመንግሥት ወጭ ተደርገው ይሰጡ እንጂ በማን ሥም እንደተመዘገቡ ገና እየተጣራ ነው" ሲሉ ኃላፊው አክለዋል። ኃላፊው የገዳሙ አስተዳዳሪ ከዚህ ቀደምም ከኅብረተሰቡ ጋር ቅራኔ ነበራቸው ሲሉ ይገልፃሉ። "ሌላ የኃይማኖት መገልገያ ቦታ ባለመኖሩ ኅብረተሰቡ ማንኛውንም የኃይማኖት አገልግሎት የሚያገኙት እዚያ ነበር፤ እኚህ ግለሰብ ወደ ገዳሙ ከገቡ ጀምሮ ሕዝቡ ወደ ገዳሙ እንዳይገባ መከልከሉን ኅብረተሰቡ ቅሬታ ሲያሰማ ቆይቷል" ይላሉ የአስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊው አቶ ይሄነው። ለገዳሙ ተብሎ ከተፈቀደው መሬት ውጭ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ አስፋፍቶ ይዟል፤ በኃይል ነጥቆናል የሚሉ ቅሬታዎችንም ኅብረተሰቡ ሲያሰማ መቆየቱን ያክላሉ። ከትናንት በስቲያ የተፈጠረው ግጭትም መነሻው እነዚሁ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች መሆናቸውን አቶ ይሄነው ገልፀውልናል። ግጭቱ የተፈጠረበትን ምክንያት ሲናገሩም፤ "በኅብረተሰቡ ቅሬታ ያሳደረውን መሬት ለማረስ መነኩሴው በሬዎች ይጠምዳሉ፤ ከዚያ በኋላ መሬቱ አይታረስም ከሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ግጭት ተፈጠረ" ይላሉ። ሌላኛው ያነጋገርናቸው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ መንግሥት ቢጋርም በበኩላቸው ቦታው 'የወል መሬት' ሲሆን የአካባቢው ማኅበረሰብ ታቦት ሲወጣ የሚያከብሩበት እንደሆነ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደምም መነኩሴው ቦታውን አርሰው እንዳመረቱበት የሚናገሩት አስተዳዳሪው፤ ኅብረተሰቡ ቅሬታ በማሰማቱ ሰብሉን ለጋራ እንዳደረጉት ያስታውሳሉ። አቶ መንግስት እንደሚሉት መነኩሴው ከእምነት ውጭ የሚያከናውኗቸው ተግባራት አሉ ሲሉም ኃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ጥያቄዎችን ኅብረተሰቡ ሰንዝሯል። • ተዓምራዊቷ ቅድስት ማርያም ውቕሮ ገዳም እስካሁን ድረስ የኅብረተሰቡ ጥያቄ ለምን ምላሽ ሳይሰጠው ቆየ? ስንል የጠየቅናቸው አስተዳዳሪው፤ በአካባቢው ማኅበረሰብ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ባለፉት ወራት ከምስራቅ ጎጃም ዞን ሀገረ ስብከት ጋር እርሳቸው ባሉበት ውይይት እንደተደረገ ይናገራሉ። በዚህ ጊዜም መስተካከል አለባቸው ያሏቸው ስድስት ጉዳዮችን ከመነኩሴው ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል ሥርዓተ ቀብር እንዲካሄድ፣ ቅዳሴ እንዲፈፀም፣ ሰበካ ጉባዔ እንዲኖረው፣ ምክትል ሊቀመንበርና የገንዘቡን ፍሰት የሚያስተዳድር አካል እንዲኖረው እንዲሁም መነኩሳት ተቀጥረው እንዲቀድሱ የሚሉ ነበሩ። • ስለ ጠልሰም ወይም በተለምዶ የአስማት ጥበብ ተብሎ ስለሚጠራው ምን ያህል ያውቃሉ? ባሳለፍነው የካቲትና መጋቢት ወር ላይ ሕጉን በመከተል እንዲሠሩና ሕዝቡም አገልግሎቱን እንዲያገኝ ውሳኔ እንደተላለፈ ይገልፃሉ። መነኩሴው ለ28 ዓመታት በገዳሙ ውስጥ የኖሩ መሆናቸው የሚጠቅሱት የወረዳው የአስተዳደርና የፀጥታ ኃላፊ አቶ ይሄነው " መነኩሴው ገዳም ስለሆነ ማንኛውም ሰው ኃይማኖታዊ አገልግሎት ማግኘት አይችልም የሚል አቋም አላቸው" ይላሉ ። በሌላ በኩል ኅብረተሰቡ ሌላ የኃይማኖት ተቋም የለም፤ የት እንሂድ? አለበለዚያ ሌላ ቤተክርስቲያን ሊሠራልን ይገባል የሚል ጥያቄም ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ያክላሉ። በዚህ አለመግባባት ምክንያትም የአካባቢው ማኅበረሰብ ሰው ሲሞት ሌሎች አጎራባች ቀበሌዎች በመሄድ የቀብር ሥነ ሥርዓት እንደሚያስፈፅሙ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ከእሳቸው ጋር የሚቀራረቡና እሳቸውን የሚደግፉ ሰዎች በገዳሙ ውስጥ ኃይማኖታዊ አገልግሎት ያገኙ ነበር፤ ሲሞቱም የሚቀበሩት እዚያው ገዳሙ ውስጥ ነው፤ ይህም በኅብረተሰቡ መካከል መከፋፈልን ፈጥሯል ይላሉ አቶ ይሄነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ መነኩሴው ከሕዝቡ ጋር በሚያጨቃጭቃቸው መሬት ላይ ለማረስ በሬዎቻቸውን ጠመዱ ይላሉ። በዚህ ጊዜ ኅብረተሰቡ ማረስ የለባቸውም ሲል ተቃወመ፤ እንዲያውም 'አንፈልጋቸውም ይውጡልን' የሚል ጥያቄ ማሰማታቸውን ይገልፃሉ። በመሀል ከማን እንደሆነ ባልታወቀና ከገዳሙ ውስጥ በተተኮሰ ጥይት የአካባቢው ነዋሪ የሆነ የ22 ዓመት ወጣት እንደቆሰለ ያስረዳሉ። • ሰዎችን ከሲኖ ትራክ የገለበጠው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋለ በግጭቱ በገዳሙ ውስጥ ያሉት 10 በጭቃ የተሰሩ ቤቶችም የተቃጠሉ ሲሆን፤ አምስት ትንንሽ የዕቃ ማስቀመጫ ቤቶችም በከፊል ተቃጥለዋል። በገዳሙ ውስጥ በተቃጠሉ ቤቶችና በቆሰለው ልጅ ምክንያት ምርመራ ለማድረግ ሲባል መነኩሴው በቁጥጥር ሥር ውለው እየተጣራ መሆኑን ነግረውናል። 'ኅብረተሰቡ ከእኔ ጋር የማይስማማው ከሌላ ብሔር ስለመጣሁ ነው' የሚል ቅሬታ በመነኩሴው ይነሳ እንደነበር የጠየቅናቸው አቶ ይሄነው፤ "አስተዳደሩ ከየትም ይምጣ ከየት? ሕጋዊ ሆኖ መቆየት አለበት የሚል አቋም ነው ያለን" ይላሉ። ። ነገር ግን መነኩሴው ያለመግባባት ችግር ነበረባቸው የሚሉት ኃላፊው በዚህም ምክንያት ከኅብረተሰቡ ጋር በሚፈጠር ግጭት 'ከሌላ ብሔር ስለመጣሁ ነው' የሚል ቅሬታ ያሰማሉ" ብለዋል። አክለውም ግለሰቡ ለ28 ዓመታት በሠላም ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር የኖሩ ሲሆን፤ ከየት ብሔር እንደመጡም የሚታወቅ ነገር የለም ሲሉ ተናግረዋል። "በአሁኑ ሰዓት ገዳሙ ሌላ ችግር እንዳይደርስበት በፀጥታ ኃይሉ እየተጠበቀ ሲሆን፤ ከሚመለከታቸው የኃይማኖት አባቶች ጋርም እየተነጋገርን ነው፤ ባለቤት የሆነ አካል ንብረቶችን እንዲረከብ ጥረት እየተደረገ ነው" ሲሉ ገልፀዋል። በገዳሙ የዚያው አካባቢ የሆኑ ሦስት መነኮሳት የነበሩ ሲሆን እነርሱም ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቅለዋል ብለዋል። መነኩሴው የገዳሙ አስተዳዳሪ እንዴት ሆኑ? ቢቢሲ ያነጋገራቸው የምስራቅ ጎጃም ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀብርሃናት ካህሌ በቃሉ በገዳሙና በኅበረተሰቡ መካከል የሚነሳ የቆየ አለመግባባት ነበር ይላሉ። የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ የገዳሙ አባቶችንና የወረዳው ኃላፊዎችን አሰባስበው ይህንን አለመግባባት ለመፍታት እንደሞከሩ ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ገዳሙ ከዛሬ 30 ዓመት በፊት የተመሠረተ ሲሆን ሁሉም ሕዝብ ይገለገልበት የነበረ ቤተክርስቲያን ነበር። እኝህ አባት ከተመደቡ ጀምሮ ወደ ገዳምነት ተቀይሮ በአንድነት ገዳም እንዲተዳደር የሚል ውሳኔ አግኝቷል። ቤተ ክርስቲያኑ ወደ ገዳም ሲቀየር ሀገረ ስብከት ውሳኔ ያሳረፈበት ሳይሆን ከመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት በቀድሞ በነበሩ አባቶች ውሳኔ መነኩሴው እንደመጡ የሚያመለክት መረጃ እንዳገኙም ያስረዳሉ። ሊቀብርሃናት ካህሌም ይህንኑ ሀሳብ ሲያፀኑ "የዞንም ሆነ የወረዳ አስተዳዳሪዎች ከዚህ ቀደም ገዳሙ ይመራ የነበረው እዚህ አካባቢ ባሉ ባለሥልጣናት አለመሆኑን አያውቁም " ይላሉ። ሥራ አስኪያጁ ከዚህ ቀደም የአካባቢው ሰው በፍርሃት ወደ ገዳሙ ደፍሮ እንደማይገባ አስረድተው "ቦታው የሚታወቅበት፤ ነገር ግን አስተዳደሩ በውል የማይታወቅበት ደረጃ ላይ ነበር " ብለዋል። አሁን ግን ሕዝቡ ሲወያይ "የሠራነው ቤተክርስቲያን ነው፤ የፈለግነውን አገልግሎት ማግኘት አለብን፤ የገዳሙ አስተዳዳሪ ለሚፈልጉት ሰው አገልግሎት ይሰጣሉ፤ ሌላውን ያባርራሉ" ሲል ቅሬታ ማሰማታቸውን ይናገራሉ። ከውይይቱ በኋላ ሀገረ ስብከቱ ውሳኔዎችን አስተላለፈ። • በስህተት የተሰጣቸውን 1 ሚሊየን ብር የመለሱት መምህር ገዳሙ የአንድነት ገዳም ከሆነ መስፈርቱን ማሟላት አለበት፤ በርካታ መናኒያን መኖር አለባቸው፤ ገዳም ቢሆንም ለኅብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት አለበት የሚል ነበር ውሳኔው። በመሆኑም ይህም ገዳም ሰበካ ጉባዔ ተቋቁሞለት፤ የሰበካ ጉባዔ አባልነት ክፍያ እየተከፈለ፤ ህዝቡ የራሱን ተመራጮች አድርጎ እንዲገለገል ተወስኗል። ከዚህ በኋላ የወረዳው ቤተ ክህነት ሠራተኞች የሰበካ ጉባዔ ሊመሰርቱ በሚሄዱበት ጊዜ ምዕመኑ 'እኚህ አባት ካልተነሱ አንመርጥም' ሲሉ ተቃወሙ። "ግለሰቡ ራሳቸውን የቻለ ልዩ ባህሪ ሊኖርባቸው ይችል ይሆናል" የሚሉት ሥራ አስኪያጁ መነኩሴው የተለያዩ ቦታዎች እየሄዱ፣ እየለመኑ ገንዘብ በመሰብሰብ ገዳሙን እዚህ አድርሰውታል፤ ያስተዳድሩት ተብሎም ነበር። ሕዝቡ ግን አልተስማማም። ከትናንት በስቲያም በተነሳው ግጭት ሕዝቡ በጡሩምባ ተቀሳቅሶ በመውጣት በገዳሙ የሚገኙ የፀበልተኞችን ቤት እንዳቃጠሉና አንድ ሰውም በጥይት መቁሰሉን እንደሰሙ ነግረውናል። • እየሩሳሌም ለምን የኢትዮጵያዊያን ህልም ሆነች? ለጥበቃ የተሰጠ መሳሪያ እንዳለ እንደሚያውቁ የተናገሩት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መሳሪያዎቹ እውቅና እንደተሰጣቸውና በየዓመቱ ቆጠራ እንደሚያደርጉ ሰዎቹ ሲገልፁ እንደነበር እንደሰሙ አስረድተዋል። መነኩሴውም ከ30 ዓመታት በፊት በቦታው የተመደቡ ስለሆነ በሀገረ ስብከቱ ደረጃ የተመደቡበት ህጋዊ ደብዳቤ አላገኘንም ብለዋል። ይሁን እንጂ ከህብረተሰቡ ጋር ካላቸው ቅራኔ በስተቀር ቦታውን ለውጠውታል ሲሉ ይመሰክራሉ።
news-56333483
https://www.bbc.com/amharic/news-56333483
ቻይናና ሩሲያ በጨረቃ ላይ የጠፈር ጣቢያ ለመገንባት ተስማሙ
ቻይናና ሩሲያ በጨረቃ ላይ የጠፈር ጣቢያ ለመገንባት ተስማምተዋል።
የሩሲያ የጠፈር ኤጀንሲ ሮስኮሞስ እንዳስታወቀው ከቻይና ብሔራዊ የጠፈር አስተዳደር ጋር በጨረቃ ላይ፣ ወይም በዛቢያዋ ላይ የምርምር ማዕከል ለመገንባት ከስምምነት ላይ መደረሱን ነው። ይህንንም ሁለቱ ሃገራት በፊርማ ማፅደቃቸውን ነው። ከሁለቱም ሃገራት የጠፈር ኤጀንሲ የወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው ከግንባታው በኋላ ሁለቱ ሃገራት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ነው። ይኼ ዜና የወጣው ሩሲያ በጠፈር ላይ ያደረገችውን የመጀመሪያ በረራ 60ኛ አመት መታሰቢያ ክብረ በዓል በምታከብርበት ወቅት ነው። በጨረቃ ላይ የሚገነባው አለም አቀፉ የሳይንስ የጠፈር ጣቢያ በርካታ ሳይንሳዊ ምርምሮች ይካሄዱበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከነዚህም መካከል ጨረቃን መጠቀም የሚቻልበትን መንገዶች ያካተተም እንደሆነ ከሁለቱ አገራት ኤጀንሲዎች የወጡ መግለጫዎች ያሳያሉ። "ቻይናና ሩሲያ በጠፈር ሳይንስ፣ ምርምርና ልማት ላይ እንዲሁም በጠፈር ላይ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተመለከተ የተከማቸ ጥምር ልምዳቸውን በመጠቀም በጨረቃ ላይ አለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያን ለመገንባት ተስማምተዋል" በማለትም ከቻይና በማንዳሪን ቋንቋ የወጣው መግለጫ አትቷል። መግለጫው አክሎም ሁለቱ አገራት የምርምር ጣቢያውን በማቀድ፣ዲዛይን በማድረግ፣ በልማት እንዲሁም በቀን ተቀን ስራው ላይ እንደሚሳተፉ ይፋ አድርጓል። በቻይና የጠፈር ፕሮግራም ላይ ተንታኝ የሆኑት ቼን ሌን ይህ ፕሮጀክት ትልቅ ስፍራ ሊሰጠው እንደሚገባ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። "ለቻይና ይህ ፕሮጀክት በአለም አቀፉ የጠፈር ትብብር ትልቁ ነው፤ ስለዚህ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ነው" ብለዋል። በጠፈር አሰሳ ላይ ዘግየት ብላ የተቀላቀለችው ቻይና በታህሳስ ወር ላይ ከጨረቃ ላይ ድንጋይና አፈር ማምጣት መቻሏን አስታውቃለች። በወቅቱም ቻይና በጠፈር ላይ የምታደርገው ምርምር የላቀ ስፍራ ሊሰጠው እንደሚገባ ያሳየ ነው ተብሏል። በጠፈር አሰሳ ላይ የቀደምት ስፍራ የሚሰጣት ሩሲያ በበኩሏ በቅርቡ አሜሪካና ቻይና በሚያደርጉት እሽቅድምድም ወደኋላ ቀርታለች ተብሏል።
news-46970451
https://www.bbc.com/amharic/news-46970451
ወደ ካናዳ መሄድ አስበዋል? ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ
''. . . ማታለል እንደሆነ ግልጽ ነበረ። ጓደኛዬ በእርግጠኛነት ይሆናል ብትለኝም አጥብቄ አለመጠየቄ አሁንም ይቆጨኛል'' ይህን ያለችው ወደ ካናዳ እንልክሻለን በሚሉ አጭበርባሪዎች ከ30ሺህ በላይ ዶላር የተታለለችው ኑአሚን መኩሪያ ነች።
የካናዳ ሰንደቅ ዓላማ በቶሮንቶ ካናዳ ሰሜን አሜሪካዊቷ ሃገረ ካናዳ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ከተለያዩ ሃገራት እንደምትቀበል አስታውቃለች። ይህን እድል በመጠቀም ህይወታቸውን በካናዳ ለማደላደል ጥረት እያደረጉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል። የካናዳ መንግሥት ውሳኔን እና የሰዎች ፍላጎት ተከትሎ ወደ ካናዳ እንልካለን የሚሉ ሐሰተኛ የኢሚግሬሽን ባለሙያዎች የማጭበርበር ሥራን እያጧጧፉ ይገኛሉ። • ካናዳ ዕፀ ፋርስን ህጋዊ አደረገች • ከቤተሰቦቿ አምልጣ ካናዳ የገባችው የሳዑዲዋ ወጣት፡ 'ምንም የሚጎልብኝ የለም' ኑአሚን መኩሪያ በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ትገኛለች። የዛሬ ዓመት ገደማ ካናዳ እንወስድሻለን ያሉ ሰዎች ሰላሳ ሺህ ዶላር እንዳጭበርበሯት ትናገራለች። የጉዞ ሂደቱን የጀመረችላት ካናዳ የምትኖር ጓደኛዋ ነበረች። ጓደኛዋ ኑአሚንን ወደ ካናዳ እንወስዳለን ብለው የነበሩትን ሰዎች በአካል አግኝታቸው አታውቅም። እንደዚያም ሆኖ ኑአሚን እና ጓደኛዋ በሰዎቹ በተሰጣቸው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገንዘብ አስገብተው ነበር። ኑአሚንን እንወስዳታለን የሚሉት ሰዎች ግን እጥፍ ተጨማሪ ገንዘብ ሲጠይቁ፤ "ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት ገንዘብ አልጨምርም" በማለት ነገሩን በዚያው እንዳቆመች ኑአሚን ትናገራለች። በወቅቱ ሰላሳ ሺህ ዶላሩ የተከፈለው በተለያየ አገር ላሉ የባንክ ሂሳቦች እንደሆነ ኑአሚን ትናገራለች። እሷ አራት ሺህ ዶላር (በብር መንዝራ) ሃገር ውስጥ ባለ የባንክ ሂሳብ ስታስገባ ጓደኛዋ ደግሞ ካናዳ፣ ጣልያን፣ ዱባይና ኬንያ በሚገኙ የባንክ ሂሳቦች ቀሪውን ገንዘብ አስተላልፋለች። "ሂደቱ ማታለል እንደሆነ ግልጽ ነው። ጓደኛዬ በእርግጠኛነት ይሆናል ብትለኝም አጥብቄ አለመጠየቄ ይቆጨኛል" ትላለች። የኑአሚን እና የጓደኛዋን ታሪክ የሚጋሩ በርካቶች አሉ። በተሻለ ስፍራ የተሻለ ህይወት መመስረት የሁሉም ፍላጎት ነው ማለት ማጋነን ላይሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ይህን ፍላጎት በትክክለኛው መንገድ እንዴት ወደ እውነታ መለወጥ ይቻላል የሚለው ሊታሰብበት ይገባል። የካናዳ መንግሥት ይፋ ባደረገው ፕሮግራም መሰረት አንድ ሰው በየትኛው ዘርፍ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ጠንቅቆ ማወቁ፤ እራስን ከአጭበርባሪዎች ለመጠበቅ ያስችላል። በዚህም መሰረት በቋሚነት ወደ ካናዳ ሊኬድ የሚቻልባቸው ዋና ዋና አማራጮች ከዚህ በታች እንደሚከተለው ቀርበዋል። የቤተሰብ ስፖንስርሺፕ በካናዳ እድሜያቸው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ሆነው፤ የካናዳ ዜግነት ወይም የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች መስፈርቱን በሟሟላት የቅርብ የቤተሰብ አባላትን በዚህ ፕሮግራም ወደ ካናዳ ማምጣት ይችላሉ። የካናዳ የኢሚግሬሽን ይፋዊ ድረ-ገጽ እንደሚለው በዚህ ፕሮግራም የትዳር አጋር፣ ልጆች፣ ወላጆች፣ አያቶች እና የጉዲፈቻ ልጆች መካተት ይችላሉ። ከላይ የተጠቀሱት የቤተሰብ አባላት ዝርዝር ወደ ካናዳ ለማቅናት ማሟላት የሚኖርባቸው የየራሳቸው የሆነ መስፈርቶችን እና ልዩ የሆኑ ሥርዓት መከተል ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ የትዳር አጋሯን ወደ ካናዳ ለማምጣት የምታስብ አንዲት ሴት የካናዳ ዜጋ ወይም ነዋሪ መሆን ይኖርባታል። ከዚህ በተጨማሪም የመህበራዊ ድጋፍ ከመንግሥት የማትቀበል፣ ወደ ካናዳ ለምታመጣው የትዳር አጋር መሰረታዊ ፍላጎት ማሟላት የምትችል እና የገቢ መጠኗም በመንግሥት ዝቅተኛ ደረጃ ተብሎ ከተቀመጠው በላይ መሆን ይኖርበታል። • የቮልስ ዋገን መምጣት የመኪና ዋጋን ይቀንስ ይሆን? • ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ የነበረው እስረኛ ጥቃት ደረሰበት በሌላ መልኩ ወደ ካናዳ እንዲሄድ የሚፈለገው ሰው በካናዳ ተቀባይነት ያለው መሆን ይኖርበታል። ለሃገር ደህንነት አስጊ የሆኑ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተሳተፉ፣ በመንግሥት ስልጣን ላይ ያሉ ወይም ሳሉ ግፍ የፈጸሙ፣ በአልኮል እና በዕፅ ተጽእኖ ሥር ሆነው ያሽከረከሩ ወይም መሰል ወንጀል የፈጸሙ መሆን የለባቸውም። በተጨማሪም የጤና ሁኔታቸው ለሃገር አስጊ ከሆነ ወይም ከፍተኛ ህክምና እና ክትትል የሚያስፈልገው ህመም ያለባቸው እንዲሁም ወደ ካናዳ ለመግባት ሐሰተኛ መረጃ ያቀረቡ ሰዎች በካናዳ ተቀባይነት የሌላቸው ሰዎች ተብለው ይፈረጃሉ። ክህሎትን መሰረት ያደረገ ፕሮግራም (ኤክስፕረስ ኢንትሪ) ኤክስፕረስ ኢንትሪ ክህሎትን መሰረት ያደረገ ፕሮግራም ሲሆን እውቀት፣ ልምድ እና የቋንቋ ችሎታን በመጠቀም በቀጣሪዎች አማካኝነት ወደ ካናዳ የሚኬድበት መንገድ ነው። በሙያዬ በቂ ልምድ እና እውቀት አካብቻለሁ፤ በቋንቋ ችሎታዬም እተማመናለሁ የሚል እና ፍላጎት ያለው በኤክስፕረስ ኢንትሪው ተሳታፊ ሊሆን ይችላል። በቅድሚያ ወደ ይፋዊ ድረ-ገጹ በመሄድ የግል መረጃዎትን ያስገባሉ። በሰጡት መረጃ መሰረትም ነጥብ ያስመዘግባሉ። ከዚያም ባስመዘገቡት ነጥብ መሰረት ከተቀሩት አመልካቾች ጋር ይመዘናሉ። ያስመዘገቡት ውጤት፣ የሥራ ልምድዎ እና የቋንቋ ችሎታዎ የቀጣሪዎችን ቀልብ ከሳበ፤ በካናዳ ለመኖር የሚያስችል የጥሪ ድብዳቤ ይደርስዎታል። በዚህ ላይ በመመስራት የመኖሪያ ፍቃድ ይጠይቃሉ። በስደተኝነት በካናዳ ሕግ ስመሰረት ስደተኛ (ሪፊዩጂ) ማለት በፖለቲካ አመለካከት፣ በሐይማኖት፣ በብሔር ወይም በጾታ ግነኙነት ፍላጎታቸው ምክንያት የደረሰባቸውን ወይም የሚደርስባቸውን ክስ እና ጥቃት ሸሽተው ከሃገራቸው የወጡ ሆነው ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ወደ ሃገራቸው መመለስ የማይችሉ ሰዎች ማለት ነው። በስደተኛ ወይም 'ሪፊዩጂ' እና 'በኢሚግራንት' መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። ኢሚግራትን ማለት አንድ ሰው በውጫዊ ጫና ውስጥ ሳይወድቅ በራሱ ፍቃድ በቋሚነት በሌላ ሃገር መኖር የሚፈልግ ሰው ማለት ነው። ስደተኛ ወይም 'ሪፊዊጂ' ማለት ግን ተገዶ ከሃገሩ የወጣ ሰው ነው። ለምሳሌ አንድ ኢትዮጵያዊ በስደተኞች ፕሮግራም ወደ ካናዳ መሄድ ቢፈልግ ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ሃገራት ውስጥ ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞ ከፍተኛ ኮሚሽን 'ስደተኛ' ተብሎ መመዝገብ ይኖርበታል። ከዚያም ስደተኛ ተብሎ የተሰየመው ግለሰብ በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አማካኝነት ወደ ካናዳ ለመሄድ የሚያደርገውን ጥረት ይጀምራል ማለት ነው። ስደተኞች ወደ ካናዳ ለመሄድ ለካናዳ መንግሥት በቀጥታ ማመልከት አይችሉም። ጥያቄያቸው የሚያቀርቡት በተባበሩት መንግሥታት በኩል ብቻ ነው። በግል-ሥራ በመተዳደር (ሰልፍ-ኢምፕሎይድ ፐርሰንስ) ሰልፍ-ኢምፕሎይድ ፐርሰንስ ፕሮግራም መስፈርቱን የሚያሟሉ በግል-ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች ወደ ካናዳ በማቅናት ኗሯቸውን በቋሚነት እንዲመሰርቱ ያስችላል። በዚህ ፕሮግራም ውስጥ በተለይ በስፖርትና በጥበባት የሙያ መስኮች የተሰማሩ ሰዎች ጉዳይ በተለይ ይስተናገድበታል። በመስኮቹ ከሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ ልምድ ያላቸው፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች የተሳተፉ፣ ልምድ እና እውቀታቸውን ለካናዳ ለማበርከት ፍቃደኛ የሆኑ፣ የጤና እና የደህንነት መርመራዎችን ማለፍ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም እድሜ፣ ልምድ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የቋንቋ ችሎታ እና አዲስ ስፍራዎችን በቀላሉ የመላመድ ክህሎት ተጨማሪ ከግምት ውስጥ የሚገቡ መስፈርቶች ናቸው። ከላይ ከተዘረዘሩት ፕሮግራሞች ውጪ በካናዳ ኢንቨስት በማድረግ፣ በሥራ ፈጠራ፣ የእንክብካቤ አገልግሎቶችን በመስጥት (ካናዳ ውስጥ ልምድ ላላቸው ብቻ) የሚሉ እና ሌሎች ወደ ካናዳ ሊኬድባቸው የሚቻሉባቸው ፕሮግራሞች አሉ። ሐሰተኛ ማስረጃዎችን መጠቀም በሰዎች መታለልም ይሁን ሆን ተብሎ ቪዛ እና የመኖሪያ ፍቃድ ለማግኘት ሲባል ሐሰተኛ ማስረጃዎችን መጠቀም ወይም በቃለ መጠይቅ ወቅት የኢሚግሬሽን ኃላፊዎችን መዋሸት እንደ ከፍተኛ ወንጀል ይቆጠራል። ይህም ማመልከቻውን ውድቅ ከማድረግ አልፎ የወንጀል ክስ ሊያስመሰርት ይችላል። ሐሰተኛ ማስረጃ መጠቀማቸው የተረጋገጠባቸው እድሜ ልክ ወደ ካናዳ እንዳይገቡ እገዳ ሊጣልባቸው ይችላል። እራሳችንን እንዴት ከአጭበርባሪዎች መጠበቅ እንችላለን? የካናዳ ኢሚግሬሽን ድረ-ገጻ የትኛውም አካል የካናዳ ቪዛ ወይም ሥራ ለማስገኘት ቃል ሊገባልዎት አይችልም ይላል። የካናዳ መንግሥት የኢሚግሬሽን ኃላፊዎች፣ የካናዳ ኤምባሲዎች፣ ከፍተኛ ኮሚሽኖች እና ቆንስላዎች ብቻ ናቸው በቪዛ ጥያቄዎች ላይ ሊወስኑ የሚችሉት። በእርግጠኝነት የካናዳ ቪዛ እንደሚሰጥዎ የሚያስተዋውቁ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ሐሰተኛ የመሆናቸው እድል ከፍተኛ ነው ይላል ድረ-ገጹ። ገንዘብዎን ወይም የግል መረጃዎችን ለማግኘት ሲባል ሐሰተኛ የኢሚግሬሽን ባለሙያዎች የማጭበርበር ሥራዎችን ይሰራሉ። ጥንቃቄ ያድርጉ፤ ትክክለኛ የካናዳ መንግሥት የኢሚግሬሽን ባለሙያ በባንክ ገንዘብ ገቢ እንዲያደርጉ ወይም እንዲልኩ አይጠይቅም ወይም ለቅጽ ገንዘብ አያስከፍልም።
news-54830397
https://www.bbc.com/amharic/news-54830397
በኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ለምን ይፈራል?
የትግራይ ክልልና የፌደራል መንግሥት ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ከገቡ ሶስተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ ቢያደርግም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት በትግራይ ክልል የሚያደርገውን ወታደራዊ ጥቃት ለመቀጠል ቃል ገብቷል፡፡
በአንድ ወቅት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር በነበረው ግንባር ውስጥ አውራ ፓርቲ በነበረው በህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ለወራት ሞቅ ቀዝቀዝ ሲል ቆይቶ ጫፍ የደረሰው ህወሃት የፌደራሉን መንግሥት በመቃወም ክልላዊ ምርጫ ካካሄደ በኋላ ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ የመጣው የፌደራልና የትግራይ ክልል መንግሥት ግንኙነት የማይታረቅ ደረጃ የደረሰው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሆነ ፓርላማው ምርጫው በሕገ መንግሥት ትርጓሜ እንዲራዘም ያፀደቀ ቢሆንም የትግራይ ክልል ምርጫ ማድረጉ የበለጠ ነገሩን አክርሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በፌደራል ጦር ሰፈር ላይ በተፈፀመ ጥቃት "ብዙዎች ተሰውተው፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት" መከሰቱን ከተናገሩ በኋላ ወታደራዊ ኃይሉ በትግራይ ላይ ጥቃት እንዲሰነዝር አዘዙ ፡፡ ለዚህም የክልሉ ገዥ ፓርቲን ተጠያቂ አድርገዋል ፡፡ ውጥረቱ እንዴት መጣ? የፌደራል መንግስት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሃገራዊ ምርጫ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ መወሰኑንተከትሎ ባለፈው መስከረም በትግራይ ምርጫ መካሄዱ ለተፈጠረው ውጥረት መባባስ መንስኤ እንደሆነ ይወሰዳል፡፡ ሆኖም ውጥረቱ ረዘም ላለ ጊዜ እየጋለ ሲሄድ ነበር፡፡ ለአስርት ዓመታት በኢትዮጵያ አውራ የፖለቲካ ፓርቲ የነበረው ህወሃት ከሶስት አመት በፊት የዐብይ መንግስት ወደ ስልጣን መጥቶ ብዙም ሳይቆይ ነው ቅራኔ መፈጠር የጀመረው፡፡ "የለውጥ አራማጅ" የተባሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀደሙት መንግሥታት የነበሩትን ባለስልጣናት በሙስና እና በሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከመክሰስ ባለፈ ቁልፍ የህወሃት ሰዎችን ከማዕከላዊ መንግስት አስወገዱ፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆኑት የቀድሞው የደህንነት ኃላፊ እና የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ ከእስር በመሸሽ ወደ ትግራይ የተሰደዱ ሲሆን አሁንም በሽሽት ላይ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ባለፈው ዓመት ብሔርን መሠረት በማድረግ የተቋቋመውን እና ሃገሪቱን ሲያስተዳድር የነበረውን ኢህአዴግን በማፍረስ ብልጽግና ፓርቲን ለማቋቋም መወሰናቸው ውጥረቶቹ ላይ ነዳጅ ጨምሯል፡፡ ህወሃት ውሳኔው አገሪቱን ይከፋፍላል በማለት የተቃወመ ሲሆን ብልጽግናንም ለመቀላቀል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ የፌዴራሉ መንግስት ባለፈው ዓመት መጨረሻ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን ምርጫ ለሌላ ጊዜ ካስተላለፈ በኋላ አለመግባባቱ ይበልጥ እየሰፋ ሄደ፡፡ በትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ መወሰኑ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በፌዴራል መንግሥት ላይ የተደረገ የእምቢተኛ ድርጊት ነበር፡፡ የፌዴራሉ ፓርላማ ምርጫውን "ህገ ወጥ" ብሎታል፡፡ ከዚያን ጀምሮ ሁለቱም መንግሥታት አንዳቸው ሌላኛውን "ሕገ ወጥና ኢ-ሕገ መንግሥታዊ" ብለው ሲፈርጁ ቆይተዋል፡፡ ህወሃት ከዚህ በፊት በፌደራል ህገ-መንግስት ውስጥ "የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን" የሚፈቅደውን አንቀፅ በመጥቀስ እንደሚገነጠል ዲፋክቶ ስቴት እንደሚያቋቁም ሲዝት ነበር፡፡ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ነሐሴ ወር ላይ እንደተናገሩት "በከፍተኛ ትግል ያገኘነውን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እና በራስ የመመራት መብታችንን ለማፈን ለሚፈልግ ለማንም ወደ ኋላ አንልም" ብለዋል፡፡ በጥቅምት ወር ደግሞ የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚ አካላት ጋር ምንም ግንኙነት ላለማድረግም የወሰነ ሲሆን ፓርላማውም ለትግራይ የሚሰጠውን የበጀት ድጎማ እንዳይደረግም አግዷል። የህወሃት ወሳኝነት ሚና ግንቦት 20/1983 ዓ.ም የቀድሞው ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ እና እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ሕወሃት የፓርቲዎች ስብስብ በነበረው ገዢ ግንባር ውስጥ አውራ ከመሆኑም በላይ ትግራይንም እያስተዳደረ ነው፡፡ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ከስልጣን በማስወገድ ህወሃት ወሳኝ ሚና ከመጫወት ባለፈ የአገሪቱን ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚውንም መቆጣጠር ቻለ፡፡ የህወሃት ከዐብይ መንግስት ጋር አለመግባባቱ በአገሪቱ ውስጥ ባለው የኃይል ክፍል ውስጥ ትልቅ ስብራት ሆኗል፡፡ ደብረፅዮንን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የትግራይ ክልል አመራሮች ለረጅም ጊዜ በማዕከላዊ መንግሥት ውስጥ አገልግለዋል፡፡ አንጋፋው ታጋይ ደብረጽዮን በአንድ ወቅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እስከማገልገል ደርሰዋል፡፡ ጓዶቻቸው እና አማካሪዎቻቸው ዐብይ ወደ ስልጣን እስኪመጡ ድረስም በአገሪቱ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን ይዘው ነበር፡፡ የህወሃት ፍላጎት ምንድነው? የትግራይ አስተዳደር የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ማሻሻያ አሁን ያለውን የፌዴራል አደረጃጀት የሚያፈርስ እና አሃዳዊ የመንግሥት ሥርዓትን ለመገንባት እንደሚደረግ ሙከራ አድርጎ ይመለከተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያላቸውንም ወዳጅነት "መርህ አልባ" ነው ብሎ የሚጠራው። ዐብይ ለረጅም ጊዜ እንደጠላት ከምትታየው ከኤርትራ ጋር ሠላምን ለማምጣት ባደረጉት ጥረት እ.ኤ.አ. በ 2019 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡ ህወሃት ግን የትግራይ ፍላጎቶች ችላ እንደተባሉ እና ለወደፊቱም ቢሆን ከጎረቤት ሃገሯ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት የበለጠ ተሳትፎ እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው የህወሃት ባለስልጣናት ስልጣናቸውን ዝቅ አድርገው እየተመለከቱ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ኤርትራ በትግራይ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ ናት? በህወሃት እና ከትግራይ ክልል ጋር ረዥም ድንበር በሚጋራው በኤርትራ መንግሥት መካከል ለዓመታት የዘለቀ አለመግባባት አለ። ከ1990-1992 ባለው ጊዜ የተካሄደው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተጀመረው በሁለቱ መካከል ባለው የድንበር ውዝግብ ሲሆን በተለይም ደግሞ በባድመ ከተማ ይገባኛል ምክንያት ነው። የባድመ ሁኔታ እስካሁን እልባት ያላገኘ ሲሆን ኤርትራ በተባበሩት መንግሥታት በሚደገፈው የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ መሠረት ኢትዮጵያ ከተማዋን አሳልፋ እንድትሰጣት ትፈልጋለች ፡፡ ነገር ግን ይህ አካባቢውን ከሚያስተዳድረው የትግራይ መንግሥት ትብብር ውጭ ሊሳካ የሚችል አይመስልም፡፡ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጽህፈት ቤት በፌዴራል ጦር ሰፈር ላይ ስለተፈፀመው ጥቃት ሲገልጽ ህወሃት የጎረቤት ሃገር የኤርትራን ጦር የሚመስል መለዮ ጦሩን በማልበስ "በትግራይ ህዝብ ላይ በኤርትራ መንግስት የተፈፀመ ጥቃት ነው የሚል ሃሰተኛ መረጃ ለመፍጠር ሞክሯል" ሲል ይወነጅላል፡፡ ይህ ክስ በሦስተኛ ወገን ባይረጋገጥም ኤርትራ በትግራይ ለተፈጠረው ቀውስ ምን ዓይነት ምላሽ እንደምትሰጥ እና ወደ ጎረቤቷ የውስጥ ጉዳይ ትገባ ይሆን የሚል ስጋት አስከትሏል፡፡ ወደ መጠነ ሰፊ ጦርነት ምን ያህል ሊሸጋገር ይችላል? የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) "ለተቃዋሚዎች የቀብር ስፍራ" የሆነውን ክልል ለመከላከል መዘጋጀታቸውን ገልፀው የትግራይ ተወላጆች ሁኔታውን ተረድተው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ እንደ ደብረፅዮን ከሆነ "ሠራዊታችንን፣ ሚሊሻችንን እና ልዩ ኃይላችንን አዘጋጅተናል። ዝግጅታችን ጦርነትን ለማስወገድ ያለመ ቢሆንም ለመዋጋት ካስፈለገንም ለማሸነፍ ዝግጁ ነን" ብለዋል ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጽሕፈት ቤት የወታደራዊ ፍጥጫውን ትክክለኛነት ለማሳየት ህወሃትን "የማያባራ አመጽ እየቀሰቀሰ ነው" ሲል የከሰሰው ሲሆን "የመጨረሻውን ቀይ መስመርም አልፏል" ብለዋል፡፡ እነዚህ ንግግሮች ችግር አላቸው። በትግራይ ውስጥ ያለው ግጭት በሠላማዊ መንገድ ካልተፈታ በቀላሉ ሊፈነዳ የሚችል ሲሆን በተቀረው የአገሪቱ ክፍል በመዛመትም ውጥረቱን ሊያባብስ የሚችልባቸው አደጋዎች አሉ፡፡ በግጭቱ ያሉ ቁልፍ አካሎች በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መንግሥት ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ የኤርትና እና የሱዳንን ጉዳይ ማንሳት ይቻላል። የትግራይ ክልልን በሰሜን ኤርትራ፣ በሰሜን ምዕራብ ደግሞ ሱዳን ያዋስናል። ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ጋር ሽርክ የሆኑት ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ሕወሓት ለ1998ቱ የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ተጠያቂ ነው ብለው ያምናሉ። የሱዳን ወታደራዊ መሪ ሌ/ጀነራል አብደልፈታህ አልቡርሀም ከሳምንት በፊት ለሁለት ቀናት ኢትዮጵያ ውስጥ ይፋዊ ጉብኝት አድርገው ነበር። ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ጋር የሱዳን እና ኢትዮጵያን የድንበር ሰላም ለማስጠበቅ ተስማምተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በትግራይ ክልል ስላለው ወታደራዊ ተልዕኮ አላማ ባይናገሩም፤ ወታደራዊ ኃይል በመጠቀም ሕወሓትን ከጨዋታ ውጪ የማድረግ እቅድ እንዳላቸው ግልጽ ነው። በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ብሔር ተኮር ግጭቶች መቀስቀሳቸው ቀጥሏል። የአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ እንደሚጠቁመው፤ በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ሊያመራ ይችላል። ትግራይ ውስጥ ግጭት መነሳቱ፤ ውጥረት ውስጥ ካሉ እንደ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ያሉ አካባቢዎች መከላከያው ወደ ትግራይ እንዲያተኩር ያደርጋል። ይህም የደህንነት ስጋት ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ይታመናል። ግጭቱ ለጎረቤት አገር ኤርትራም ሊተርፍ ይችላል። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ደጋፊ መስከረም ድረ ገጽ ጥቅምት 4 እንዳስነበበው፤ ኢሳያስ አፈወርቂ ስለ ትግራይ ጦርነት ከከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣኖች ጋር ተነጋግረዋል። ግጭቱ 2018 ላይ የሰላም ስምምነት የተደረሰበት የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ክለላ ጉዳይን ሊያዘገይ ይችላል። በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግሥት ግጭት የተነሳው ኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ከግብፅ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ባለችበት ወቅትም ነው።
50931986
https://www.bbc.com/amharic/50931986
በሞቃዲሾ በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 76 ሰዎች ሞቱ
ከሰዓት በፊት በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃት በትንሹ 76 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። ዛሬ ጠዋት በርካታ ሰዎች ወደ ሥራ በሚሄዱበት ሰዓት ደረሰ በተባለው በዚህ የቦምብ ጥቃት ከሟቾች በተጨማሪ በርካቶች ቆስለዋል።
አደጋው የደረሰበት ይህ የሞቃዲሾ ክፍል ፍተሻ የሚደረግበትና በርካታ ሰዎች የሚንቀሳቀሱበት ነው። የፖሊስ መኮንኑ ኢብራሂም ሞሐመድ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ፍንዳታው እጅግ አደገኛ ነበር። የመዲና ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ሞሐመድ የሱፍ ለአሶሽየትድ ፕረስ እንደተናገሩት 73 አስክሬኖች ተቀብለዋል። ሳካሪ አብዱልቃድር የተባለ የአይንም ምስክር በበኩሉ "ማየት የቻልኩት እዛም እዚም የተበጣጠሰ የሰው አካል ነው፤ የአንዳንዱ ሰው ሬሳ በእሳት በመቃጠሉ መለየትም አይቻልም ነበር" ብሏል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም። ዘግይተው እየወጡ ባሉ መረጃዎች ደግሞ የሟቾች ቁጥር ከተገለጸውም እጥፍ ሊደርስ እንደሚችል ይጠቁማሉ። መሐመድ አብዱራዛቅ ተባሉ የምክር ቤት አባል የሟቾቹ ቁጥር 90 እንደደረሰ ያልተረጋገጠ አሀዝ እንደደረሳቸው ተናግረዋል። • የኤርትራና ኳታር ቅራኔ • ለፖለቲካ ፍላጎት የተጋጋለ ግጭት ነው፡ ሙስጠፋ ኡመር
news-43284748
https://www.bbc.com/amharic/news-43284748
'የወር አበባ ላይ ስለነበርኩ ለአያቴ ሐዘን መቀመጥ አልቻልኩም'
በብዙ የሕንድ ቤተሰቦች ውስጥ የማይዳሰስ ርዕስ ቢሆንም እንኳን የወር አበባ በሜጋ ቤተሰብ ውስጥ ግን ነውር አልነበረም። አንድ ቀን የዚህ እውነት ተቃራኒ በሁሉም ዕድሜ ክልል ያሉ ቤተሰቦቿ በተሰባሰቡት ወቅት ያለውን ልዩነት ገሃድ አወጣ።
የሜጋ ሞሃ አያት ከመታጠቢያ ቤት እየወጣች "ታምፖን (የወር አበባ መጠበቂያ አይነት) ያለው ሰው ይኖራል?" ብላ ጠየቀች። በትኩስ ሻይ ዙሪያ ጨዋታ ይዘው የነበሩት ብዙው የቤተሰቧ አባላት በአንድ ጊዜ ፀጥ አሉ። በሕንድ ደቡብ ያለችው ከታሚል ናዱ ወጣ ብላ የምትገኘው ራሜስዋራም የተሰኘችው ደሴት ላይ በአንድ የሆቴል ክፍል ነበር የታጨቁት። ተፈጠሯዊ ያልነበረው ፀጥታ በሁለት ምክንያቶች በጣም ያስታውቅ ነበር። አንደኛ ዝናቡ መስኮቱን ይደበድብ ስለነበርና ሁለተኛ ደግሞ በሦስት የተለያዩ አህጉራት ላይ የሚኖሩት ቤተሰቦቿ በየቀኑ ዋትሳፕም ላይ እየተገናኙ በአካል ሲገናኙ ግን መቼም ፀጥታ ባለመስፈኑ ነው። በሆቴሉ አልጋ ላይ ጋደም ብላ የነበረችው አክስቷ ተነስታ የእጅ ቦርሳዋን አነሳች። የወር አበባ መጠበቂያ አወጥታ አቀበለቻት። "ይህ ፋርማሲ እስክንሄድ ድረስ ይጠቅምሻል'' አልችና ባዘነ ፊት እያየቻት ''ይህ ምን ማለት እንደሆነ ታውቅያለሽ አይደል?'' ብላ ጠየቀቻት። ሜጋ ግን አላወቀችም ነበር። "ቤተ-መቅደስ መምጣት አትችይም ማለት ነው'' አለቻት። በራሜስዋራም ያለው የፀበል ገንዳዎች ሰዎች በመጠመቅ ለቅድመ ዘር አክብሮት የሚያቀርቡበት ነው ቤተሰባቸው ለእረፍት አልነበረም ወደ ራሜስዋራማ ያቀናው። ይህች ደሴት በጎብኚዎችና በዓሣ አስገሪዎቿ የታወቀች ብትሆንም እነርሱ ግን የተሰባሰቡት ለአሳዛኝ ጉዳይ ነው። ሜጋ የምትወዳት አያቷ ካረፈች ዓመት ሆኗት ነበር። እሷው ነበረች በተለያዩ አህጉራት ላይ ያሉትን የቤተሰቡ አባላትን የምታሰባስበው። ባለፈው ታህሳስ የህልፈቷ ዜና ሲደርሳቸው ሁሉም በፍጥነት አውሮፕላን ተሳፈሩ። እንደየአካባቢው ቢለያዩም በሒንዱ ባህል በሞት ዙሪያ ብዙ ወጎች አሉ። ሰው ሲሞት የሜጋ ቤተሰብ የሕንድ ደቡብ ሒንዱ ባህልን ነው የሚከተለው። አስክሬኗን ቤታቸው ወስደው በነጭ ጥጥ ከገነዙ በኋላ በትልቅ ኮባ ላይ አስተኝተው ተሰብስበው ፀለዩ። ወንዶቹ አስክሬኑን ለማቃጠል ሲወስዱ ሜጋም አብራ ብትሄድ ትወድ ነበር። ካረፈች በኋላ ለ15 ቀናት ሥጋ አልበሉም ነበር። ከ90 ቀናት በኋላ ደግሞ ልዩ ዝግጅት አደረጉ። ኤርፖርትም እርስ በርሳቸው ተሰነባበተው ለቀጣዩ የሞት ባህል በራሜስዋራም እንደሚገናኙ ቃል ገቡ። እዚያም ነበር የሜጋ ወንዱ አያት ከሴት አያቷ ቀድሞ የዛሬ 36 ዓመት ሲሞት አያቷ የመጨረሻዎቹን ሥነ-ሥርዓቶች ያስከበረችው። በቤንጋል ዉሃ ዳርቻ ላይ ያለው ራሜስዋራም ለታሪካዊ ቤተ-መቅደሶቹ የታወቀ ነው። አፈ ታሪኩ እንደሚለው 'ራማ' የተሰኘው የሒንዱ አምላክ እዚያ ነበር 'ሲታ' የተሰኘችውን ሚስቱን ከጠላፊዋ ለማስፈታት ድልድይ ወደ ሽሪላንካ የሠራው። በሦስቱ የአውሮፕላን ጉዞዎች መካከልና በሚያንገጨግጨው የመኪና ጉዞ እንዳነበበችው ራሜስዋራም በወሳኝ ጊዜያት ነበር የሚኬደው። ሜጋም እራሷን እንደ ሐይማኖታዊ ሰው ቆጥራ ባታውቅም ግን አሁን ከሚጓዙት ሰዎች መካከል አንዷ ሆና እራሷን አግኘችው። ታሚል ናዱ ታዋቂ የሐይማኖታዊ ጉዞ ስፍራ ነው አያቷ በሞተች በቀጣዮቹ ወራት በራሜስዋራም የሚደረገው የመሰናበቻው የመጨረሻ ምዕራፍ ምን እንደሚመስል ብዙ ታስብ ነበር። በአክስቷ የሆቴል ክፍል ውስጥ ሆነው ለሞተችው አያቷ የመሰናበቻ የመጨረሻው ክፍል ላይ መገኘት እንደማትችል ሲነገራት ሜጋ እራሷን የመከላከል ስሜት ውስጥ ገባች። ሜጋ በፍጥነት ''በወር አባበዬ ላይ ስላለሁኝ ነው ቤተ-መቅደስ መሄድ የማልችለው?'' ብላ ጠየቀች። አይኖቿን ቀስ ብላ በማጥበብ አክስቷ የሜጋ አነጋገር በወጣትነቷ ተቀባይነት እንዳልነበረውና አሁን ደግሞ ይበልጥ እንደሌለው በሚገባት መልኩ አየቻት። ሜጋም ወዲያውኑ ''ይቅርታ'' አለቻት። ''ግን እርግጠኛ ነን ይህንን አይደለም እያልሽኝ ያለሽው። ይህን ሁሉ ሃገር አቋርጬ አብሬያችሁ ቤተ-መቅደስ ላልገባ አይደለም መቼስ'' አለች። አክስቷም ''እኔ እኮ አይደለሁም ይህን የምልሽ። እንደዚያ ስለሆነ ነው'' አለቻት። ''ማን ስላለ'' ብላ ሜጋ አጥብቃ ጠየቀቻት። ''እንዲህ ነው በቃ። ትልቅ ነገርም ነው'' ብላ ሜጋን ለማገዝ ማንም ጣልቃ እንዳይገባ አድርጋ ንግግሩን ቋጨችው። ውሳኔውም ፀደቀ። ከሹፌሩ ጋር በቤተ-መቅደሱ ደጃፍ ትጠብቃለች። ልጅ እያለች የወር አበባዋ ሲመጣ የተለያዩ ምክንያቶች እየተነገሯት ቴምፕል ከመሄድ ትታቀብ ነበር። አንድ አክስቷ ይህ የመጣው በድሮ ጊዜ እንደዛሬ የወር አበባ መጠበቂያ ስላልነበራቸው ነው ብላ ነግራታለች። እናቷ ደግሞ በወር ውስጥ ይህን ቀን ብቻ ነው ሴት ልጅ ከሁሉም ሥራ የምትታቀበው፤ በዚህ ቀን ሙሉ እረፍት ስለሚገባት ነው ብላ አስረድታታለች። በቅርብ ጊዜ ደግሞ ምሁራንን ባነጋገረችበት ወቅት ሴቶች በወር አበባ ጊዜያቸው ቤተ-መቅደስ ምክንያት ማስረጃዎች የሚፃረሩ ሆነው ነበር ያገኘችው። አንደኛው ቻውፓዲ የተሰኘውን የሒንዱ ባህል በመጥቀስ ሴቶች በወር አበባቸው ንፅህና የተጓደላቸውና ዕድለቢስ መሆናቸውን አስረዳት። አንድ ቄስ ደግሞ በወር አበባቸው ጊዜ ሴቶች በጣም ንፁህ በመሆናቸው በሌሎች ሊቆሽሹ እንደሚችሉ አስረድቷታል። ዶ/ር አርቪንድ ሻርማ በሞንትሬያል መጊል ዩኒቨርሲቲ የሐይማኖት ፕሮፌሰር ሲሆኑ፤ እሳቸውም የሴቶችን ድርሻ በሒንዱዝም ውስጥ ነው በቅርብ ያጠኑት። እሳቸውም ይህ በባህላዊ አከባበር ወቅት ባለ ንፅህና ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል። '' ሰዎች ለባህላዊ አከባበር ንፁህ ወይም ብቁ የማይሆኑባቸው ጊዜያት አሉ። ለምሳሌ ከሬሳ ወይም ከአይነ-ምድር ጋር ከተነካኩ። ሴቶችም በወር አበባቸው ወቅት እንደዚያው ነው የሚቆጠሩት'' ብለዋል። ''የሃይማኖቱ መጻሕፍት ይህን ማስረጃ ለምን እንደማያስቀምጡ ማስራዳት ይከብዳል'' ብለው በመቀጠል '' ይህን የሒንዱዝም ሥርዓት የሚከተሉት ስማርታ ሒንዱዊም የተባሉት ናቸው። እነሱም በጥንት የስሚርቲስ የሒንዱ መጻሕፍት ላይ የሚገኙ ናቸው። በሻክታ ሒንዱዊዝም ግን የወር አበባ የሚያነፃ እንጂ እንደሚያቆሽሽ ተደርጎ አይታመንም'' ብለዋል። ከቅርብ ጊዜ አንስቶ ስለወር አበባ በጣም እየተወራ ነው። ለምሳሌ በክፍለ ሃገራት ላሉ ሴቶች የወር አበባ መጠበቂያ የመስጠት እቅዶችም ወጥተዋል። በሕንድ ሴቶች የማህበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም ''ሃፒ ቱ ብሊድ'' ወይም 'በመድማቴ ደስተኛ ነኝ' የሚሉ ሃሽታጎችን በመጠቀም በወር አበባ ዙሪያ ያለውን ነውር እየተገዳደሩ ይገኛሉ። 'ፓድ ማን' የተሰኘው የቅርብ ጊዜ የቦሊዉድም ፊልም የዓለማችን የመጀመሪያው የወር አበባ ፊልም በመባል ተሰይሟል። የራሜስዋራም ባለ 1000 አምድ መተላለፊያ ፊልሙ በአሩናቻላም ሙሩጋናንታም ሕይወት የሚያጠነጥን ሲሆን እሷም በታሚል ናዱ የምትገኝ አክቲቪስት ስትሆን በተለያዩ ክፍለ ሃገራት ላሉ ሴቶች በርካሽ የወር አበባ መጠበቂያ እንዲያገኙ የተሟገተች ናት። ዋናው ተዋናይ አክሻይ ኩማር እንዲህ ብሏል ''ሕይወቴን በሙሉ ከሴቶች ጋር ነው የኖርኩት። ሆኖም ግን ይህንን ፊልም ስሠራ በጣም ብዙ ነው የተማርኩት። ያለነው በድንጋይ ዘመን አይደልም የወር አበባ ደግሞ ተፈጥሮአዊ ነው።'' ሜጋ ቤተሰቧ ከቤተ-መቅደስ እስኪወጣ ድረስ ይህን ሁሉ በጭንቅላቷ ስታጠነጥን ነበር። ለመጨረሻው ሥነ-ሥርዓት መምጣት ያልቻለችውን ዘመዷን ለማነጋገር ስልኳን ከቦርሳዋ አወጣች። እሷም አዘነችላት። በመጨረሻም "የወር አበባሽ ላይ እንደነበርሽ መናገር አልነበረብሽም። አያውቁም ነበር'' በማለት ጻፈችላት። ሜጋ ''አንቺ በወር አበባሽ ጊዜ ቤተ-መቅደስ ገብተሽ ታውቂያለሽ?'' ብላ ጠየቀቻት። እሷም ቀስ ብላ ''በእኛ ዕድሜ ያሉ ሴቶች ይሄዳሉ። ማንም ካላወቀ ችግር የለውም'' ብላ ቀለል አድርጋ ነገረቻት።