id
stringlengths
4
5
url
stringlengths
39
537
title
stringlengths
2
65
text
stringlengths
2.5k
160k
45331
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%9B%E1%88%85%E1%88%99%E1%8B%B5%20%E1%8A%A0%E1%88%85%E1%88%98%E1%8B%B5
ማህሙድ አህመድ
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ አሻራቸውን መጣል ከቻሉ ስመ ጥሩ ዘፋኞች ውስጥ አንዱ ማህሙድ አህመድ ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተወዳጅነትን፣ ተደናቂነትን፣ ተፈቃሪነትን ማትረፍ የቻለ ፈርጥ እንደሆነ ብዙዎች ያምናሉ፡፡ ሙሉ ሕይወቱን በሙዚቃ ያሳለፈው ማህሙድ በሙዚቃው ይተነፍሳል፣ ይናገራል፣ ሰውን ያዝናናል፡፡ ከአርባ ዓመታት በላይ በቆየውም የሙዚቃ ሕይወቱ የተለያዩ ትውልድን በሙዚቃው አንድ ላይ ማምጣት የቻለ ትልቅ አርቲስት ነው፡፡ በተለያዩ ኮንሠርቶች በሚዘፍንበትም ወቅት በተለያዩ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ብሔራዊ መዝሙር በሚመስል መልኩ አብረውት በመዝፈንም በዘፈኑ አንድነትን ያሳያሉ፡፡ ማህሙድ የዝና ጣራ ላይ መድረስ ችሏል፡፡ በሕዝቡ ዘንድ ከመወደዱና ከመፈቀሩ በተጨማሪ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይም ዝናው ናኝቷል፡፡ የሰዎችን ልብ ከማሸነፉ በተጨማሪ ከኮንሠርቱ በፊት ቲኬቶቹ ተሸጦ የሚያልቅበት አጋጣሚም ተደጋጋሚም ነው፡፡ የተለያዩ ሽልማቶችንም ለማሸነፍም ችሏል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የቢቢሲ ወርልድ ሚዩዚክ አዋርድ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ምንም እንኳን ይሔን ያህል የጣራ ዝና ላይ ቢሆንም ትሁት፣ ሰዎችን የሚያከብርና በቀላሉም የሚግባባ ሰው ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ነበር የሰላም ዓለም አቀፍ ሙዚቃ ፌስቲቫል አካል ሆኖ ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር ሙዚቃ ሕይወቱን ያካፈለው፡፡ አዳራሹ በተማሪዎች ተሞልቶ የነበረ ሲሆን ለብዙዎች ማህሙድን ማየት ትልቅ ነገር ነው፡፡ በተለይም በአካል ተገኝቶ ከእነርሱ ጋር ማውራቱ እንደ ዕድልም ነው ያዩት፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ግን ማህሙድ በስሜት ተሞልቶ ከተማሪዎቹ በላይ ያለቀሰበት ሁኔታ ታይቷል፡፡ በሳግ በተቆራረጠ ድምፅም እዚህ ቦታ ላይ መገኘቱ ለእሱ ልዩ እንደሆነም ተናግሯል፡፡ ‹‹ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ከተማሪዎች ጋር ስለሙዚቃ ሕይወቴ ሳወራ፤ ዛሬ ብሞትም ምንም አይመስለኝም፡፡ በጣም ዕድለኛ ነኝ፡፡ እግዚአብሔርም በሕይወት ያቆየኝ ለዚህ ይመስለኛል፤›› ብሏል፡፡ ማህሙድ ከልጅነቱ ጀምሮ ያጋጠመውን ውጣ ውረድ በማስታወስ አሁን ያለበትን ደረጃም እግዚአብሔርን በማመስገን ተናግሯል፡፡ የተወለደው በ1933 ዓ.ም. አዲስ አበባ በአሜሪካን ግቢ አካባቢ ነው፡፡ ሥራንም ሆነ ሕይወትን በራሱ መጋፈጥ የጀመረው ገና በሕፃንነቱ ነው፡፡ አባቱ በሚሠራበት ግሪክ ክለብ አብሮ በመሔድ ቅርጫት ኳስና የቴኒስ ሜዳዎቹ ላይ ይሠራም ነበር፡፡ በስድስት ዓመቱም ሊስትሮ ሆኖ መሥራት ጀመረ፡፡ በትምህርት ቤት ቆይታው ብዙ ጐበዝ እንዳልነበር ፈገግ ብሎ የሚያወራው ማህሙድ ቤተሰቦቹንና ራሱን መርዳት እንዳለበትም የተረዳው ገና በሕፃንነቱ ነው፡፡ የሙዚቃ ሕይወቱ ሀ ብሎ የተጀመረው አንድ ክለብ ውስጥ ሳንድዊች እንዲያቀርብ በተቀጠረበት ጊዜ ነው፡፡ እንደ አጋጣሚም ሆኖ በዚያው ክለብ ውስጥ ጥላሁን ገሠሠ ይዘፍንበት የነበረ ቦታ ነበር፡፡ በአንድ አጋጣሚም ሁሉም ድምፃውያን ወደ ድሬዳዋ ሔደው ሙዚቀኞቹ ያለ ድምፃዊ እየተለማመዱ ነበር፡፡ የተፈራ ካሣን ‹‹አልጠላሽም ከቶ››ን የተዘራን ‹‹ይሔም አለ ለካ››ንና የጥላሁን ዘፈን እየተለማመዱ ነበር፡፡ በድምፅ መዝፈን እንደሚፈልግም ጠየቃቸው፡፡ ‹‹በጣም ቀጭን ነበርኩ እናም ‘ትችያለሽ? ወይ›› ብለው ጠየቁኝ፣ እናም እሞክራለሁ አልኩ›› በማለት ማህሙድ ይናገራል፡፡ ‹‹አልጠላሽም ከቶ›› የሚለውን ዘፈን በሚዘፍንበት ሰዓት የኮንጐ ዘማቾች በቦታው ነበሩ እናም አስደነቃቸው፡፡ እንደገናም እንዲዘፍን ተጠየቀ፡፡ የክለቡ ባለቤት በቦታው የነበረ ሲሆን አድናቆት በተሞላ ድምፅም ‹‹የአላህ ያለ መዝፈን ትችላለህ!›› እንዳለው ማህሙድ ያስታውሳል በዚህም አጋጣሚ ከአስተናጋጅነት ወደ ዘፋኝነት ተቀየረ፡፡ የቤቱ ባለቤትም ሙሉ ልብስ ገዛለት፡፡ ጥላሁንና ሌሎቹ ዘፋኞች በተመለሱበት ወቅት የእሱ መዝፈን በጣም ነው ያስገረማቸው፤ የግጥም ደብተርም ሰጡት፡፡ መዝፈን በጀመረበት ወቅት የተለያዩ ዘፋኞችን ሙዚቃ በመዝፈን ነበር፡፡ በዚህም ክለብ ነበር ‹‹አላወቅሽልኝም›› የሚለው የመጀመሪያው ዘፈኑ የሆነው ግጥም የተሰጠው፡፡ ክብር ዘበኛ መቀጠር ፍላጐቱ የነበረ ሲሆን መጀመሪያ ግን ፖሊስ ኦርኬስትራና ምድር ጦር ለመቀጠር ጠየቀ፡፡ በተለያዩ ምክንያቶችም እንደማይቀጥሩት ነገሩት፡፡ መቶ አለቃ ግርማ ሐድጉም (በኋላ ሻለቃ) ክብር ዘበኛ መቀጠር ይፈልግ እንደሆነ ጠየቁት፣ እሱም ተስማማ ከመቀጠሩ በፊት ግን በሕዝብ ፊት ዘፍኖ ማለፍ ነበረበት፡፡ የዚያን ጊዜ የነበረውን እያንዳንዷን ጥቃቅን ነገር በጥልቅ ያስታውሳል፤ የታምራት ሞላን ‹‹ተስፋ አትቁረጪ›› እንዲሁም ‹‹አላወቅሺልኝም››ን ሲዘፍን የተመልካቹ መልስ ለየት ያለ ነበር፡፡ ‹‹የኤልቪስ ፕሪስሊን ዳንስም እየደነስኩ ነበር፣ እናም የተመልካቹ መልስ የማይታመን ነበር፤›› በማለት ማህሙድ ይገልጻል፡፡ መቶ አለቃ ግርማም ወታደር ሆኖ እንዳይቀጠር መከሩት፣ የክብር ዘበኛ ሰዎችም በወታደርነትና ሙዚቀኝነት 120 ብር እንክፈልህ ብለው ጠየቁት፡፡ እሱ ግን ባለመስማማቱም በሙዚቀኝነት ብቻ በ1955 ዓ.ም. አካባቢ ተቀጠረ፡፡ ለአሥራ አንድ ዓመታትም ያህልም በዚህ ቦታ ሠርቷል፡፡ ‹‹ለዚህ ያበቃኝ፣ የማውቀውን ነገር ሁሉ ያስተማረኝ ለእኔ ወንድሜ ጥላሁን ገሠሠ ነው፡፡ ሌሎችም ሙዚቀኞች እንዲሁ በእኔ ላይ አሻራ ጥለዋል፤›› ይላል ማህሙድ፡፡ በዚያን ወቅት ሙዚቀኞች አንድ ላይ ይሰባሰቡበት የነበሩ ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ክብር ዘበኛ ይሠራ በነበረበት ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ይደረግ የነበረው የሙዚቀኞች ውድድር አንዱ ነው፡፡ የተለያዩ ባንዶች እንደ ምድር ጦር፣ ክብር ዘበኛና የፖሊስ ኦርኬስትራ ባንዶች ከድምፃውያኖቻቸው ጋር ይመጣሉ፡፡ እያንዳንዱም ድምፃዊ አንድ ወይም ሁለት ዘፈን ይዘፍናል፡፡ ይሔም ለሙዚቀኞች ጥሩ አጋጣሚ እንደነበር ይናገራል፡፡ ከአሥራ አንድ ዓመታት ቆይታም በኋላ በተለያዩ ክለቦች መሥራት ጀመረ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የነበረው ያገኘው የነበረው 60 ብር አምስት እህቶቹና ወንድሞቹ በአጠቃላይ ቤተሰቦቹን መደገፍ አልቻለም፡፡ በወቅቱ አባቱ ሥራ ያልነበራቸው ሲሆን እናቱ ብቻ ነበረች የምትሠራው፤ መጨረሻ ላይ ከክብር ዘበኛ በለቀቀበት ወቅት ደመወዙ 250 ብር ደርሶ ነበር፤ ከዚያም ከአይቤክስ ባንድ ጋር ተጠቃልሎ ራስ ሆቴል ተቀጥሮ መሥራት ጀመረ፡፡ በሙዚቃ ሕይወቱ ውስጥ ብዙ ውጣ ውረዶችን እንዳሳለፈ የሚናገረው ማህሙድ ዘመኑ ለሙዚቀኞችም ሆነ ለሙዚቃ ዕድገት የተመቻቸ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ እንደሚናገረው ከሆነ ይሔ ዕድገትም የተገኘውና እዚህ መድረስ የተቻለው በዱሮ ሙዚቀኞች መስዋዕትነት ነው፡፡ ‹‹እነዚህ ሙዚቀኞች አሻራቸውን ጥለው ማለፍ ችለዋል፤›› የሚለው ማህሙድ በዚያን ጊዜ የነበሩት ሙዚቀኞች ምንም እንኳን ችሎታው ቢኖራቸውም የሙዚቃ ትምህርት ቤት አልሔዱም፡፡ የዚያን ጊዜውንም በማስታወስ ለሙዚቀኞች እንዴት ከባድ እንደነበር ይናገራል፡፡ ሙያውም እንዴት ይናቅ እንደነበርም ያስታውሳል፡፡ በ1963 ከአይቤክስ ባንድ ጋር ራስ ሆቴል በሚሠራበት ወቅት ‹‹ኩሉን ማን ኳለሽ››፣ ‹‹አምባሰል››፣ ‹‹ችቦ አይሞላም ወገቧ›› እና ‹‹አልማዝ ምን ዕዳ ነው›› የመሳሰሉ ዘፈኖችን ይዘፍን ነበር፡፡ እነዚህ ዘፈኖች ከአንዳንድ ወገኖች ከፍተኛ ትችትም አጋጠመው፡፡ የዱሮ ዘፈኖችን በአዲስ መልክ ትጫወታለህ ለማለት አንድ ጋዜጠኛ ‹‹ፍራሽ አዳሽ›› ብሎ የጠራውን አጋጣሚም አሁንም አይረሳውም፡፡ ‹‹አላዘንኩም፡፡ የዱሮ ዘፈኖችን አዲስ ሕይወት በመስጠት ዘፍኛለሁ፡፡ ፍራሽም እንደ አዲስ ሲታደስ ይተኛበታል›› ይላል፡፡ ማህሙድ ከዚህም በተጨማሪ ‹‹ዓባይ ማዶ››፣ ‹‹ደኑን ጥሰሽ›› እና ‹‹የት ነበርሽ›› የሚሉት ዘፈኖቹም የተለየ ርዕዮተ ዓለም ያስተላልፋሉ በሚልም ተወቅሶ ነበር፡፡ የማህሙድ ዓለም አቀፍ ዕውቅና የመጣው ፍራንሲስ ፋልሴቶ ኢትዮጲክስ የሚለውን የሙዚቃ ስብስብ ካወጣ በኋላ ሲሆን ማህሙድም ውለታውን የረሳ አይመስልም፡፡ ፋልሴቶ ፈረንሣዊ ፕሮሞተር ሲሆን የማህሙድን ‹‹መላ መላ›› የሚለውን ዘፈን ሬዲዮ ላይ ሰምቶ አብረን እንሥራ ብሎ ጠየቀው፣ ማህሙድ መጀመሪያ ላይ ተጠራጥሮ እንደነበር ያስታውሳል፡፡ እየተደራደሩ ባሉበት በ1960ዎቹ አካባቢ ማህሙድ ወደ ፈረንሣይ አቅንቶ ሙላቱ አስታጥቄ ጋር አብሮ ዘፍኗል፡፡ በዚያችው ከተማም ማይክል ጃክሰን በዚያው ምሽት ዘፍኗል፡፡ ከተመለሰም በኋላ ነው ኢትዮጲክስ የወጣው፡፡ በዚሁ መድረክ ላይ አዲስ እየሠራው ያለውን ‹‹አብራኝ ናት›› ስለሚለው ዘፈኑም ተናግሯል፡፡ አዳራሽ ውስጥ እየጠቆመ ምን ያህል እንደሚያፈቅራትም ተናግሯል፡፡ ‹‹አብራኝ ናት ከልጅነት እስከ ዕውቀት አብራኝ ናት፡፡ እዚሁ አለች በመንፈስም በሥራዎቼም ውስጥ አብራኝ ናት፡፡ እዚህ ለመድረሴም ምክንያት እሷ ናት፡፡ ትመክረኛለች፤ ከዓመታት በፊት ‹‹አልማዝ አልማዝዬ›› ብዬ ዘፍኘላታለሁ፤ አሁን ደግሞ ‹‹አብራኝ ናት ብዬ›› እዘፍንላታለሁ፤›› ብሏል፤
9827
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A3%E1%89%A0%E1%88%AB%20%E1%88%9E%E1%88%8B
ኣበራ ሞላ
ዶ/ር አበራ ሞላ (መጋቢት ቀን ዓ.ም.) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ መናገሻ ኣውራጃ፣ ሰንዳፋ ከተማ የተወለዱ ኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች በግዕዝ ፊደል እንዲጽፉ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ናቸው። ዶክተር ኣበራ ሞላ የታወቁባቸው ዋናዎቹ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው። የመድንን ማነስ በማስወገድ ከዓለም የእንስሳት ሓኪሞች ኣንዱ ታዋቂ ምሁር፣ የግዕዝ ፊደልንና ሥነ ጽሑፍ በኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ውስጥ በኣለውም መጠቀም እንዲቻል የኣደረጉ ሰባት የዩናይትድ እስቴትስና ኢትዮጵያ ፓተንቶች ብቻቸውን የኣሏቸው የግኝት ሊቅና የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጣልያንን በማስገደድ ወሳኙን እርምጃ የወሰዱ ኣርበኛ ናቸው። ዶክተሩ የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ቀለሞችና የግዕዝ ኣሥር ቤት ኣኃዛዊ ቍጥሮች ፈጣሪም ናቸው። የግዕዝ ፊደል ሳይቆራረጥ፣ ሳይቀነስና ሳይበላለጥ ዩኒኮድ እንዲገባ የሰጡና ለመብቱ የተሟገቱለት ኣሸናፊ ናቸው። ዶ/ር ኣበራ ሞላ ከታዋቂ የዓለም ሳይንቲስቶች ኣንዱ ናቸው። ኢትዮጵያውያን ኢንተርኔት ላይ በዓማርኛ በነፃ ፒሲና ማክ ኮምፕዩተሮች ውስጥ እንዲከትቡ በድረገጽ ለግሰዋል። ግዕዝ በኮምፕዩተር ዶ/ር አበራ በኮምፕዩተር ግዕዝ ፊደልን መጠቀም እንዲቻል ያደረጉ ምሁር ናቸው። ይሀንንም ያደረጉት የዓማርኛውን የጽሕፈት መሣሪያ (ታይፕራይተር) ለሚያውቁት ቀላል እንዲሆን ”፣ ምትክ “ሀ”፣ “ጠ”፣ “ሸ”፣ “ዘ” እና እንግሊዝኛ ለሚያውቁ ”፣ ምትክ “አ”፣ “በ”፣ “ቸ”፣ “ደ” ቀለሞችን በመመደብ ዓይነት ሠላሳ ሰባቱን የግዕዝ ቤት ኆኄያት ለ፴፯ የኮምፕዩተር መርገጫዎች ስሞችም በማድረግ ነበር። ስምንቱን የፊደል ቤቶች ወይም እንዚራን ስምንት ፎንቶች ላይ በተኗቸው። በእዚህ ዘዴ በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይታተሙ የነበሩት የግዕዝ ፊደላት ለመጀመሪያ ጊዜ በኮምፕዩተር ተከተቡ። እ.ኤ.ኣ. በ1982 ከባለቤታቸው ወንድሞች ኣንዱ የሆነው ግሩም ከተማ ድህረ-ምረቃ ከሚማርበት ዴንቨር ዩኒቨርሲቲ መጥቶ ፊደል መሥሪያ ስለተለቀቀ ከኣንድ ዓረብ ጓደኛዬ ጋር ፊደሉን ለመሥራት ስንታገል ዋልን ብሎ ለዶ/ር ኣበራ ቢነግር ለዓማርኛ ፊደል ያላቸውን የልጅነት ፍቅር ቀስቅሶባቸው ፊደል መሥራት ከቻልክ ለምን የዓማርኛውን ኣትሞክርም ኣሉት። ሃያ ሰባት 27 የዓረብ ቀለሞችን በሚያስሠራው መሥራትን በመቶዎች የሚቆጠሩትን ፊደሎቻችንን መሥራት ኣንድ ኣይደለም ከተባባሉ በኋላ ወደፊት በዓማርኛ የሚሠራ ኮምፕዩተር እስኪሠራ ሺዎች ለእንግሊዝኛ የተሠሩን ፕሮግራሞችን ኢትዮጵያውያን እንድንጠቀምባቸው ቃላት ማተሚያዎችን በኣማራጭነት ማቅረብ እንዲቻል ዶክተሩ ኣብሻ የሚባለውን ኩባንያ ኣቋቋሙ። ፊደል መሥራት በመጀመር እ.ኤ.ኣ. ፍላጎታቸውን ኣሟሉ። መጀመሪያ መሥራት የሚቻለውም የኣማርኛ ታይፕራይተር ዓይነቱን ቅጥልጥል ፊደል እንደኣማርኛው ታይፕራይተር በኣንድ የላቲን ፊደል ምትክ መተካት ስለነበረ ያንን ስለኣልፈለጉ እንጂ ቅጥልጥሉንም ከማንም በፊትም ሊሠሩበት ይችሉ ነበር። ተሠርቶበታልም። እየኣንዳንዱ ቀለም ኣንድ-ወጥ የሆነውን የማተሚያ ቤቶች ዓይነት ትክክለኛ የግዕዝ ፊደላችንን ለመጀመሪያ ጊዜ በማቅረብና እየኣንዳንዱም በሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ በመፍጠር ግዕዝ ከማተሚያ ቤቶች ወደ ኮምፕዩተር እንዲገባ ኣደረጉ። ሞዴት በመባል የታወቀውን የቃላት ማተሚያ የማይክሮሶፍትን ዶስ በመጠቀም በ፲፱፻፹ ዓ.ም. ኣሜሪካ ውስጥ ለገበያ ኣቀረቡ። ጊዜውም ኮምፕዩተሮችና ማተሚያዎች በቂ ኃይል ማግኘት የጀመሩበት ነበር። ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲከተብ የፈጠሩበትን ዘዴ በዩናይትድ እስቴትስ ፓተንት መጠበቅ እንዲችሉ ቢያመለክቱም በእዚያን ጊዜ ኢትዮጵያ የፓተንት ሕግ ስለኣልነበራት የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል (ኢትዮጵያ) ሕጉ ሲወጣ ጉዳዩ ይታያል በማለት ስለወሰነ ፓተንት ኣልወጣለትም ነበር። ግዕዝ ድምጻዊ ፊደል ስለሆነ እያንዳድንዱን “ሀሁሂ” ቀለም ምትክ እየደረደሩ ማተም ከ፲፱፻ ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ የኣሉ ማተሚያ ቤቶች ሊጠቀሙበት ችለዋል። በቀለሞቹ ብዛት የተነሳ ግን የእንግሊዝኛውን የጽሕፈት መሣሪያ ለዓማርኛ እንኳን መጠቀም ኣልተቻለም። ከዳግማዊ ምኒልክ ጀምሮ ብዙ ኢትዮጵያውያን ሊቆች፣ ሚኒስትሮችና ደራስያን የእንግሊዝኛውን የታይፕ መጻፊያ ለዓማርኛ መክተቢያ እንዲያገለግል ወደ ሰማንያ ዓመታት ግድም ሲመራመሩ ቆይተው ባይሳካላቸውም ዶ/ር ኣበራ ጥረቶቻቸውን በኮምፕዩተር ኣሳክተዋል። ስለ ዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ምርምሩም የዋቢው ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት ኣባ ተክለ ማርያም ሰምሃራይ፣ ክቡር ዶ/ር ሃዲስ ኣለማየሁ፣ ኣቶ ዓለሙ ኃብተ ሚካኤል፣ ኢንጂነር ኣያና ብሩ፣ ዶ/ር ዓለመ ወርቅ፣ ኣለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ክቡር ኣቶ ኣበበ ኣረጋይ፣ ክቡር ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ፣ ዶ/ር ሉባክ፣ ኣቶ ዘውዴ ገብረ መድኅን፣ ብላታ መርስዔ ሃዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ፀሓፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣ ክቡር ኣቶ ሚሊዮን ነቅንቅ፣ ኣቶ ስይፉ ፈለቀ፣ ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል፣ ኣቶ ሳሙኤል ተረፈ፣ ሌላ እነ ኮሎኔል ታምራት ይገዙ፣ መንግስቱ ለማ፣ ኣቶ ብርሃኑ ድንቄ፣ ብላታ ዘውዴ በላይነህ፣ የኔታ ኣስረስ የኔሰው፣ ተክለማርያም ኃይሌ፣ ሼክ በክሪ ሳጳሎ እና ዶ/ር ፍቅሬ ዮሴፍንም ያጠቃልላል። ይህ ድካማቸው በመጨረሻ ሊሳካ የቻለው ግን ዶክተሩ ምንም ቀለም ሳይቀንሱ ወይም መልካቸውን ሳይቀይሩ የጥንቱንና ትክክለኛ የግዕዝ ቀለሞች በኮምፕዩተር ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲቀርቡ ስለኣደረጉ ነው። የእነዚህ ምሁራን በታይፕ መሣሪያ ሙከራዎች የመጠቀም ዓላማዎች ባይሳኩላቸውም ዶክተሩ በእዚያው የፊደል ገበታ ምኞታቸውን ኣሳክተውላቸዋል። በተጨማሪም የቢለን፣ ጉራጌ እና ሳሆ ምሁራን የቋንቋ ፊደሎቻቸውን እንዲጨምሩላቸው ናሙና ጽሑፎችን ልከውላቸዋል። ከእዚሁ ጋር በማያያዝ እያንዳንዱ ቀለም በሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ ኣዲስ የኣከታተብ ዘዴ ፈጥረው ኣዳዲስ የፊደል ገበታዎችን ኣቅርበዋል። ለእያንዳንዱ የግዕዝ ቤት ቀለምም እንደ እንግሊዝኛው ቍልፎች የእየእራሱ ቍልፍና የቍልፍ ስም መድበዋል። በእነዚህ የተነሳ የግዕዝን ፊደል የእንግሊዝኛው ወይም የኣማርኛ የታይፕ መጻፊያ መጻፍ ስለኣልቻለና ሳይጽፈው ኮምፕዩተር ለመጀመሪያ ጊዜ ደርሶለታል። ዶ/ር ኣበራ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት የግዕዝ ፊደል ኢትዮጵያውያን ለብዙ ሺህ ዓመታት በእጃቸው ሲጽፉትና ከ፲፱፻፬ ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ በማተሚያ መሣሪያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲጠቀሙብት የነበረውን ፊደል ነው። ግዕዝ በማተሚያ መሣሪያዎች ከኢትዮጵያ ውጪም ታትሟል። የግዕዝ ፊደል በብራናና የመሳሰሉት ላይ ሲጻፍ ቆይቶ በጉተንበርግ የፊደል መልቀሚያ ማተሚያ መሣሪያ ፈጠራ ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በማተሚያ መሣሪያ ሲጠቀም ቆይቶ ከ፲፱፻፹ ጀምሮ በዶክተሩ ግኝት በኮምፕዩተርና በኋላም በእጅ ስልክ መጠቀም ስለተቻለ ሕዝቡ በዓማርኛና ሌሎች ቋንቋዎች የእራሱ ኣታሚ ሆኗል። የግዕዝን ቀለም በኮምፕዩተር በቀላሉና በቀልጣፋ ዘዴ ማቅረብ ስለቻሉ ሕዝቡ ከማተሚያ ቤቶች በተሻለ ሁኔታ በፊደሉ መሥራት ችሏል። በእዚህም የተነሳ ሕዝቡ መጻሕፍትንና የመሳሰሉትን ለማሳተም በየማተሚያ ቤቶች ወረፋ ከመጠበቅና ከመንግሥት እገዳ ተርፎ የእራሱ ኣታሚ ሆኗል። ዘዴውም በዓማርኛ ሳይወሰን ለሁሉም የግዕዝ ቀለሞች መክተቢያና ማተሚያ ከሌሎች የዓለም ፊደላት እኩልና ጎን በሚገባ ሥራ ላይ እየዋለ ነው። ይህ የዓማርኛ ውክፔዲያ ገጽ እንደ ሌሎች ትክክለኛ የዓለም ባለ ፊደል ቋንቋዎች ገጾች የቀረበውም በእዚሁ በግዕዝ የዩኒኮድ መደብ ቀለሞች ነው። ሌላው የትግርኛ ውክፔዲያ ገጽ ነው። የዶ/ር ኣበራ ግኝቶች 16, 2009 ሕትመት) በግዕዝ ሳይወሰኑ ለኣያንዳንድ የዓለም ፊደሎች ኣዳዲስ ኣጠቃቀሞችና ግኝቶች ስለጠቀመ ስምንት የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንቶች ውስጥና ሦስት የፓተንት ማመልከቻዎች ውስጥ ተጠቅሷል። ቊጥሮቻቸውም 8645825፣ 8700653፣ 8706750፣ 8762356፣ 8812733፣ 9715111፣ 9723061፣ 9733724፣ 20110173558፣ 20160042059 እና 1 ናቸው። እነዚህ ኢትዮጵያን የሚያኮሩ ሥራዎችም ናቸው። ዶ/ር ኣበራ ሞላ ዩናይትድ እስቴትስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ስለ ኢትዮጵያ ፊደል ግኝታቸው ጉዳይ ፓተንት ማመልከቻ እ.ኤ.ኣ. ፌብሩዋሪ 15 1990 ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን የኣቀረቡት በኮምፕዩተር የተጻፈ የዓማርኛ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባይሆንም ታሪካዊ ነበር። ኮሚሽነር ኣበበ ሙሉነህ በዶ/ር ኣበራ በኮምፕዩተር ለተጻፈው ደብዳቤ መልሱን የጻፉት በአማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ በተጻፈ ደብዳቤ ነበር። ዶክተሩ ታህሳስ ቀን ዓ.ም. 19, 1988 ለኮሚሽነሩ የጻፉት ደብዳቤም ኣለ። በኣሁኑ ጊዜ በኮምፕዩተር፣ የእጅ ስልኮችና በመሳሰሉት በግዕዝ ፊደል እየቀረቡ የኣሉት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስለሆኑ የዶክተሩ ሕልምና ምኞት ከተሳኩ ቆይቷል። መጋቢት ቀን ዓ.ም. የዩናይትድ እስቴትስ መንግሥት ቊጥሩ 9,000,957 የሆነ የመጀመሪያውን የግዕዝ ፓተንት ወይም የግኝቱ ባለቤትነት መብት ማመልከቻውን ከኣስገቡበት ከሰባት ዓመታት በኋላ ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ሰጥቷል። ዕውቅናው እንዲታወቅ 9,000,957 የእሚል ማሳወቂያ ግኝቱን ከሚጠቀሙት ዘዴዎች ጋር መቅረብ እንደእሚገባው ሕጉ ይደነግጋል። የፓተንቱም መገኘት የግዕዝ ፊደል በትክክለኛ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እየተደገፈ የማደጉ ምስክርነት ነው። ይኸው የኢትዮጵያም ፓተንት ለዶክተሩ በሦስት ወራት ውስጥ እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ኣእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ጥቅምት ቀን ዓ.ም. ደብዳቤ ጽፏል። በቅርቡም ቍጥሩ 9,733,724 የሆነ ሁለተኛው ፓተንት ግዕዝን በእጅ ስልክ መጠቀም እንዲቻል በመፍጠራቸው በዩናይትድ እስቴትስ መንግሥት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ተሰጥቷል። የእነዚህ ፓተንቶች የኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት መሆኑ ጥቅሞች ለብዙዎቹ የኣልገባቸው ይመስላል። ዶ/ር ኣበራ ሞላ የፓተንትን ጥቅም ቀደም ብለው በኣሏቸው ፓተንቶች ምክንያት በማወቃቸው ግዕዝን ዲጂታይዝ በማድረግ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በቴክኖሎጂው እንዳይቀደሙ በማድረግ በፊደሉና እንደ ዓማርኛ በኣሉ ቋንቋዎቻቸው ላይ መብታቸው እንዳይወሰድ የኣደረጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለውለታ ሳይንቲስት ናቸው። እስከ ዓ.ም. ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ብቻቸውን የተሰጧቸው የግዕዝ ፓተንቶች ሰባት ደርሰዋል። ይኸንንም ሄዶ በመፈለግ ማጣራት በሳይንስ ዓለም የተለመደ ነው። ግዕዝን በኮምፕዩተር መክተብ ኣስቸጋሪ በመሆኑ በብቸኛው ምርምራቸው ገፍተውበት ተሳክቶላቸዋል። ሕዝቡ ስለእነዚህ እንዳያውቅም እዚህ ገጽ እየመጡ የሚሰርዙም ስለኣሉ የሚያዋጣ በሌሎች በኩል መፈለግ ነው። ምሳሌ የግዕዝ ቀለሞች ከልጃቸው ብሩክ ጋር የመጀመሪያውን የግዕዝ የእስክሪንና የማተሚያ ቀለሞች ለመሥራት ኣንድ ዓመት ግድም ነበር የወሰደው። የፊደሉም ችሎታ በማደግ መጀመሪያ ፖስትእስክሪፕት ከእዚያም በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ትሩታይፕ በኋላም ተንቀሳቃሽ ሆኗል። ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ የስምንት እንግሊዝኛ ሥፍራዎችን በማስለቀቅ ዓይነት ኣንዱኑ ቦታ በየተራ በመጋራት ነበር። በዩኒኮድ መፈጠር የተነሳ ዶ/ር ኣበራ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት እእያንዳንዱ ቀለም የእራሱን ስፍራ ኣግኝቷል። ከዓለም ፊደል ሠሪዎች ኣንዱ ናቸው። ብዙዎቹ የግዕዝ ቀለሞች በዓለም የፊደላት መደብ ዕውቅና ከኣገኙበት ከ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ግድም ወዲህ ግን የዕውቀት ክምችት እንዲስፋፋ በቀለሞቹ እንደመጠቀም ዛሬም ኋላቀር በሆነው የኣማርኛ የታይፕ መጻፊያው ዓይነት ቅጥልጥል የኣማርኛ ፊደላት እየጻፉ ኢትዮጵያንና እራሳቸውን ወደኋላ እየጎተቱ ያሉትን እየተቃወሙ ነው። ትክክለኛዎቹና ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች የዩኒኮድ መደብ ውስጥ እንዲገቡ ዶክተሩ ትልቅ ትግልና ኣስተዋጽዖም ኣድርገዋል። ለምሳሌ ያህል በመጀመሪያ ዙር ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት እንጂ የታይፕራይተሩ ፊደል ግዕዝ እንዳልሆነ ተገልጿል። ይኸን ግዕዝ የኣልሆነ ቊርጥራጭ የኣማርኛ ታይፕራተር ዓይነት ፊደል የግዕዝ ፊደል ስለኣልሆነ በሁለተኛ ዙር ተቃውመው ኣስጥለዋል። የዶክተሩ ሦስተኛ ዙር ተቃውሞ የዓማርኛውን የማተሚያ ቤት ፊደላት ለዩኒኮድ እ.ኤ.ኣ. በ1992 የቀነጠሱትን እና የኣናሳ ተጠቃሚዎች ፊደላት በቍርጥራጭ ፊደላት እንዲተኩ እ.ኤ.ኣ. በ1993 የፈለጉትንና የኣማርኛ ፊደላት ቅነሳ ውስጥ የገቡትንም ያጠቃላል። ዶክተሩ ዲጂታይዝ የኣደረጉት የግዕዝ ፊደል የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሲጠቀሙባቸው በነበሩት ፊደላት ሲታተሙ ስለነበሩና ስለሆኑ ዛሬ ወደ ፒ.ዲ.ኤፍ የተቀየሩትን ጭምር ያለ ችግር ማንበብ ተችሏል። ፊደሉንም ለማሟላትና ከሌሎች ፊደላት እኩል እንዲራመዱ በየጊዜው ጽፈዋል። ለምሳሌ ያህል እነ “ሀ”፣ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “አ”፣ እና “ዐ” የተሳሳቱ ድምፆች ተሰጣቸው እንጂ በዶ/ር ኣበራ ገለጻ የእየራዕቦቻቸው ሞክሼዎች ስለኣልሆኑ ለማጥፋት ማዘጋጀት ቀርቶ ድምፆቻቸውን ተረክበው መብታቸው መከበር ኣለበት ነው። ዕውቀቱም ከዩኒቨርሲቲ ወደ ሕዝቡ መድረስ ኣለበት። ይህ ትግርኛውንም ይመለከታል። ዓማርኛ፣ ቤንችና ጉሙዝ የቋንቋ ዋና ክፍሎች የ“ጨ” ቀለሞች፣ እንዚራንና ዘመዶች ቀለበቶች ሦስት ሳይሆኑ ሁለት ናቸው። የ“ሀ” ትክክለኛ ድምጽ ወደ “ኸ” የቀረበ ቢሆንም “ኸ”ም የዓማርኛ ሞክሼ የሚባለው ዓይነት ቀለም ስለኣልሆነ ነው ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝ ሲደረግ የምልክት መርገጫዎች ላይ የመርገጫ ስም የተሰጠው። የ“አ” ድምጽ በስሕተት “ኧረ” የሚለው ቃል ምሳሌ ውስጥ ስንጠቀምበት የነበረ ድምጽ ስለሆነ ለ“ኧ” ስምንተኛው የ“አ” ቤት ፊደል ድምፁን ዶክተሩ መልሰው ኣስረክበውታል። [“ኧረ”] መከተብ ያለበት በ“አረ” ነው። ምክንያቱም የስምንተኛው ድምጽ ቀለም የሚሠ'ራው ግዕዙ ወይም ራብዑ ላይ መስመር በመጨመር ስለሆነና የ“አ” ቤት ስምንተኛ ቀለም የማይኖርበት ምክንያት ስለሌለ ነው። ይህ የዓይኑ “ዐ” ባለመስመር “ዓ”ንም ሊመለከት ይችላል። “ኧ” የስምንተኛው የ“አ” ቤት ቀለም ስለሆነ ስምንተኛውን የ“አ” ቤት ድምጽ (ወደ “እዋ” የቀረበውን) ለ“ኧ” ፊደል መስጠቱ ተገቢ ይመስላል። የ“የ”ም ስምንተኛ ድምጽ ቀለም ኣለ። የ“ሀ”ም አንዲሁ። ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል ስለሆነ “ሀ” እና “ሃ” ወይም “አ” እና “ኣ” ድምጽ ስለማይጋሩ ነው ዶክተሩ ስማቸውን “ኣበራ” እንጂ “አበራ” በማለት የማይጽፉት። ከምክንያቶቹ ኣንዱ የግዕዝ ቤቶቹ ቅርሶች ሲጠሩ እንደራብዖቹ ኣፍ በሰፊው ስለማያስከፍቱ ነው። “ሰረቀ” እና “ሠረቀ” የሚባሉት ቃላት ከግዕዝ የተወረሱ ስለሆኑ ትርጕሞቻቸው ኣንድ ኣይደለም የሚሉ ኣሉ። ዓማርኛ የሚጠብቁና የሚላሉ ቃላት ኣሉት። “ምሥር” (“እህሉ”) እና “ምስር”ም (“ግብጽ”) ኣንድ ኣይደሉም። ንጉሡ “ሠ” የጠበቀ ስለሆነ ዓማርኛውን በእንደእዚህ ዓይነት መለየት ሳይጠቅም ኣይቀርም የሚሉ ኣሉ። ሞክሼ የተባሉትን ልዩነቶች ለስርወ ቃላት ስለሚጠቅሙ ኣለማወቅ ዕውቀቱን ኣያጠፋውም። “ጪ”፣ “ጬ” እና “ጯ” የተሠሩት ሦስተኛ ቀለበት በሌለው “ጨ” ላይ በሚቀጠሉ ቅርጾች ነው። እነዚህ “ጠ” ላይ እንደሚቀጠሉት “ጢ”፣ “ጤ” እና “ጧ” መሆኑ ነው። ስለዚህ እንደ “ጤ” ሦስተኛው እግር ላይ ኣንድ ቀለበት የኣለው “ጬ” እንጂ ሦስተኛው እግር ላይ ሁለት ቀለበቶች የኣሉት “ጬ” የተሳሳተ ነው። ለግዕዝ የሚያስፈልጉትን በመጨማመር ከፈጠሯቸው የግዕዝ ምልክቶች መካከል “መብት”፣ “ንግድ”፣ “ተመዝግቧል”፣ “ብር”፣ “ሣንቲም”፣ “ማጥበቂያ”፣ “ማላልያ” እና “ኣልቦ” ኣኃዝ ይገኙበታል። የማጥበቂያ ምልክትን ዓማርኛ ለጥቂት ምዕት ዓመታት የተጠቀመ ስለሆነ ዶክተሩ የኣቀረቡት ከኮምፕዩተሩ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲሄድ ኣዲስ ቅርጽና ስፍራ በመስጠት ነው። ዕውቅናም እንዲያገኙ ደራሲዎች እንዲጠቀሙባቸው ለዓመታት ከማቅረብ ሌላ ፓተንቶቻቸው ውስጥ ጽፈዋቸዋል። የኮምፕዩተር 42 እንግሊዝኛ ቁጥሮችና ምልክቶች ከግዕዙ ጋር ያቀረቡት ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ለግዕዝ ሥራ እንዲያገለግሉ ወስነው ከግዕዙ ቀለሞች ጋር በተመጣጠነ መልክ መሥራት ስለጀመሩ ኮምፕዩተር ገበታ ላይ ያሉት ኣጠቃቀም ለግዕዝም እንዲያገለግል ነው። ለምሳሌ ያህል “-”፣ እና የመደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛትና ማካፈል የግዕዝ የሢሳብ ምልክቶችና ማስሊያዎችም ናቸው። በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይቀርብ የነበረው የግዕዝ ፊደል ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ኣጠቃቀሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዓ.ም. ገደማ ለሕዝብ ቀርቧል። ከእዚያም ወዲህ ፊደሉ የዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ ስለገባ እእያንዳንዱ ቀለም የእራሱ ስፍራና ቍጥር (ኮድ) ኣለው። በእዚህም የተነሳ የግዕዝ ፊደል እንደሌሎች የዓለም ፊደላት የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ገብቷል። ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ስለ ኣገኘና ወደ የተለያዩ የቋንቋ ቀለሞች ስለኣሉት የሁሉም የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ብሔሮች መብቶች በእኩልነት መጠ'በቅ እንደኣለባቸው ዶክተሩ ያምናሉ። ስለዚህ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች የማያስተናግድ ወይንም ለማስተናገድ ችሎታ የሌለው ዘዴ መቅረብ ስለሌለበት ተጠያቂው ኣቅራቢው ብቻ ሳይሆን ተጠቃሚው ምሁርም ነው። በግዕዝ ቀለሞች ብዛት የተነሳ በግዕዝ መሥራት ቢያስቸግርም ከቴክኖሎጂው ጋር መጓዝ ስለቀጠለ ለእንግሊዝኛው የተሠሩትን ለግዕዝ መጠቀም እንዲቻልና ግዕዝ የሚፈልገውንም ለመሥራት መትጋት ይጠበቅብናል። የተሳሳቱ ነገሮችን ማስተካከልና በትክክል መጠቀም ጠቃሚ ናቸው። ዶክተሩ የተጠቀሙበት የሁለተኛው ፊደል መነሻ ተወዳጁና ለረዥም ዘመናት ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ኣንደኛው የሞኖታይፕ የፊደል መልቀሚያ መሥሪያ ፊደልና የተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት ዓ.ም. ቁምፊ ናቸው። የቀለማቱም መልኮች ከዩኒኮዱ ጋር ኣንድ ዓይነትና መደበኛ የኢትዮጵያ ፊደላት ናቸው። ውብ ቀለሞቻችንን በወጉና በማዕረጉ መጠቀም ተችሏል። ዶክተሩ ይኸን በመደበኛነት ከ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ጀምሮ እየተጠቀሙበት ነው። በማያምር፣ የተሳሳተና የከሳ ፊደል የተጻፈ ጽሑፍ ማንበብ ኣያጓጓም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነ ማይክሮሶፍት ጉግል )ና ኣፕል የተለያዩ የግዕዝ ፊደላት ማቅረብ ጀምረዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ቁምፊዎች መኖር ተፈላጊ ቢሆኑም ኣስቀያሚውንና የተሳሳቱትን በዝምታ ማሳለፍ ሕዝቡ ተስማምቶበታል ማለት ነው። በኣሁኑ ጊዜ ብዙ ደራስያን መጻሕፍትን በተሳሳቱ ፊደላት እያሳተሙ ስሕተቶችን እያስፋፉ ስለሆነ ሊነገራቸው ይገባል። ወደፊት በትክክለኛ የግዕዝ ፊደሎቻችን የተከተቡትን ጥንታዊ ቀለሞቻችንን ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ ወደኣደረጉት ትክክለኛ የዘመናዊው ማተሚያ ቤቶች ቀለሞች መቀየር ቢቻልም ዛሬ በኣለማወቅ በተሳሳቱ ቀለሞች ኣዳዲስ ስሕተቶችን ማስተዋወቅ ኣስፈላጊ ኣይደለም። የግዕዝ ፊደል ውስጥ ለሌሉ ድምጾች ኣዳዲስ ቀለሞች መፍጠር ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ይህ ፊደላችን ለሌሎች ቋንቋዎችም እንዲጠቅሙ ያስችላል። በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች ዘንድ ግዕዝ የኣዳም እና የሔዋን ቋንቋ ነበር፤ ፊደሉን የፈጠረው ከማየ ኣይኅ ኣስቀድሞ የሴት ልጅ ሄኖስ ነበረ፤ በሌላ በኩልም ኢትዮጵያዊው የግዕዝ ፊደል የዓለም ፊደላት ምንጭ ነው ይባላል። የኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝሮችና የግዛት ዓመታት እዚህ ኣሉ። ሌሎችም መረጃዎች ኣሉ። በግዕዝ ቋንቋ ብዙ እልፍ ድርሳናትና ምስጢራት ተከትበዋል። የግዕዙ ፊደል እድሜ ከላቲኑ የበለጠ ነው። (ጥንታዊቷ ግብጽ ከ5100 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያውያን የተቈረቈረች ናት ይባላል።) የግብፆችን ጽሑፍ ከኢትዮጵያ የተወሰደ መኾኑንና የሮማና የሌሎች ፈላስፎችም የተጠቀሙባቸው መጻሕፍት ከግብጽ መጽሓፎች የተወሰዱ እንደኾኑ ማረጋገጥ ተችሏል። በጽሑፍ ሰፍረው ከሚገኙ አንዳንድ መረጃዎችም በመመሥረት የጽሑፍ ፊደል በኢትዮጵያውያን የተጀመረ መኾኑን መገመት ይቻላል። የሥነ ፈለክ ጥናትን የጀመሩት ኢትዮጵያውያን ስለመኾናቸው ማስረጃዎች ይናገራሉ። ሌሎች ሃገራት የሓውልትንና የግንባታ ሥነ ጥበብን የተማሩት በጥንት ኢትዮጵያውያን ነው። ኢትዮጵያ የሥልጣኔ ምንጭ ነች የሚሉም ኣሉ። የላቲን ኤቢሲዲ ካፒታል ፊደላት የግዕዙን የመሰሉት እኛ ከግሪኮቹ ወስደን ኣይደለም። በኢትዮጵያ ታሪክ ጽሑፍ በግሃ ድንጋይ ተጠቅሞ በድጋይ ላይ ከመጻፍ ቅጠልን ቀጥቅጦ በመጭመቅ በብራና ላይ ወደ መጻፍ ሽግግር የተደረገው በንጉሥ ሰብታህ (2545-2515 ዓ.ዓ.?) ዘመነ መንግሥት መሆኑ ተጽፏል። ይህ ከ5000 ዓመታት ግድም በፊት መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ ከዛሬ ሰባት ሺህ አመታት በፊት በዳዕማት የፅሁፍ ትምህርት መስጠት መጀመሯን ለሚያውቅ ሰው በወቅቱ ኣገራችን ደርሳበት የነበረውን የሥልጣኔ ደረጃ መገመት ኣያዳግተውም፡፡ የግዕዝ ቍልፎች ምንም እንኳን እስከ የኣሉት የኮምፕዩተሩ መርገጫዎች ለእንግሊዝኛው ፊደላት ስምና መርገጫ እንዲሆኑ ቢሠሩም ፴፯ቱን መርገጫዎች ለ፴፯ቱ የግዕዝ ቤት ቀለሞች ማለትም ለ“ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ”፣ “ሠ”፣ “ረ”፣ “ሰ”፣ “ሸ”፣ “ቀ”፣ “ቐ”፣ “በ”፣ “ቨ”፣ “ተ”፣ “ቸ”፣ “ኀ”፣ “ነ”፣ “ኘ”፣ “አ”፣ “ከ’፣ “ኸ”፣ “ወ”፣ “ዐ”፣ “ዘ”፣ “ዠ”፣ “የ”፣ “ደ”፣ “ዸ”፣ “ጀ”፣ “ገ”፣ “ጘ”፣ “ጠ”፣ “ጨ”፣ “ጰ”፣ “ጸ”፣ “ፀ”፣ “ፈ” እና “ፐ” ስምና ቍልፎች እንዲሆኑ ኣድርገዋል። ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲጠቀም ሲፈጥሩ እያንዳንዱ ቀለም የሚከተበው በሁለት መርገጫዎች ነበር። ለሚፈልጉትም የቍልፍ መለጠፊያዎች ነበሩት። እያንዳንዱ የግዕዝ ቀለም ስም የሚከተበው እንደ እንግሊዝኛው ዝቅ መርገጫን በመጠቀም ነው። በኣሁኑ ጊዜ እያንዳንዱን ቀለም በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብ የሚያስችል ኣብሻ የሚባል ዘዴ ስለፈጠሩ ዓማርኛውን በእንግሊዝኛ ፎነቲክ እስፔሊንግ እንጽፋለን በማለትና ያም ስለኣልተሳካ እስከ ኣራት መርገጫዎች መጠቀም እንደማያስፈልግ ተደርሶበታል። ምክንያቱም ዓማርኛው በኣራት ቢከተብም የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎችን በእዚሁ እስፔሊንግ ዘዴ ለመክተብ እስከ ስምንት መርገጫዎችን መጠቀም ስለሚያስፈልግ ነው። እንግሊዝኛ የእራሱ ችግሮች የኣሉት ፊደል ነው። ላቲን “ቸ” ቀለምን የሚከትበው ሲሆን “ቸ” ቀለም ቢኖረው ኖሮ ትክክለኛ ኣጠቃቀም ስለሆነ ኣንድ መርገጫ ይሰ'ጠው ነበር። የላቲን ቊልፎች ለሃያ ስድስቱ ቀለሞች የተመደቡት ለእያንዳንዳቸው እንጂ በዋየልነትና ኮንሰናንትነት የሥራ ክፍፍል ኣይደለም። በሌላ ኣነጋገር መርገጫ የእንግሊዝኛ ፊደል የተመደበው ቀለም ስለሆነ እንጂ ዋየል ስለሆነ ኣይደለም። የዶክተር ኣበራ ግኝት ይኸን መሠረታዊ ኣጠቃቀም በማገናዘብ የላቲኑንና የግዕዙን ኣቀራረብ በማዋሃድ የዋየል መርገጫዎችን የፊደልነትና የዋየልነት ኣሠራር ለግዕዝ ተጠቅሞበታል። ምክንያቱም ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል ስለሆነ እንዚራኖቹን በዋየል መዘርዘር ሃያ ስድስቱን የላቲን ቀለሞች በዋየል ከመዘርዘር ጋር የተቀራረበ ስለሆነ ነው። በእዚሁ መሰረት 37ቱ የግዕዝ ቤቶች እንደ 26ቱ የላቲን ቤቶች የእየእራሳቸው መርገጫዎች ከተሰጣቸው በኋላ በዋየልነት እንዲያገለግሉ ለሁለተኛ ሥራ የተመደቡት የዋየል መርገጫዎችና ተጨማሪ መርገጫዎች የእንዚራን መቀየሪያዎች ሆነዋል። ግኝቱ ከእነዚህም ኣልፎ ለዋየል መርገጫዎች ሦስተኛ ኣዲስ ኣጠቃቀም ሥራ ላይ ኣውሏል። ለእንግሊዝኛው የኮምፕዩተር መርገጫና ኣከታተብ ዘዴ እንዲመች የግዕዝ ፊደላት እስከ ያሉት ቁልፎችን እንዲጋሩ ማድረግን ዶክተሩ ይቃወማሉ። ምክንያቱም ከ“ኤ” እስከ “ዚ” የኣሉት የላቲን ቍልፎችን ፊደሉ በኣንዳኣንድ መርገጫዎች በመጠቀም እንግሊዝኛውን እንዲከትብ የተሠራ እንጂ ከእዚያ በላይ ብዛት ከኣለው የግዕዝ ፊደል ኣጠቃቀም ጋር ግንኙነት ስለሌለው የግዕዙ ኣጠቃቀም ውስጥ ጣልቃ በመግባት ወሳኝ መሆን ስለማይገ'ባው ነው። ላቲን 26 ሳድሳን ሆህያቱን የሚከትበው ለእእያንዳንዱ ኣንድ መርገጫ በመጠቀም ሲሆን ለካፒታል ቀለሞቹ ሁለት መርገጫዎችን ይጠቀማል። የዶክተሩን ትክክለኛ ግኝትና ኣመዳደብ እናሻሽላለን ብለው የ"ዝቅ" መርገጫዎችን ከሳድሳኑ ጋር ግንኙነት ለሌላቸው የግዕዝ ኆኄያት (ምሳሌ፦ “ጥ” በ“ዝቅ” “ት” የመደቡ ግዕዙን ለእስፔሊንግ ጣጣ ለመዳረግ የሚፈልጉትንና ቀለማቱን በብዙ መርገጫዎች የሚከትቡትን ይቃወማሉ። ምክንያቱም ዶክተሩ በፈጠሩት ዘዴ ሁሉንም ቀለሞች ከኣንድ ገበታ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች መክተብ ስለተቻለና እየተሻሻለም ስለሆነ ነው። እነ “ዠ” እና “ጰ” ቀለሞች ራቅ የኣሉ መርገጫዎች ላይ የተመደቡት ብዙ ቃላትና ተጠቃሚዎች ስለሌሏቸው ነው። ግዕዙን በ26 የላቲን ፊደላት መጻፍ መሞከር ግዕዙ በላቲን መርገጫዎች እንዲጠቀም ማስገደድ ነው። የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶች ለግዕዝ የሚበጀውን መሥራትና መፍጠር እንጂ ሌላ ፊደል ላይ ማተኰር ኣስፈላጊ ኣይደለም። ምክንያቱም በዘዴው ዓማርኛውን እስከ ኣምስት መርገጫዎች በመጠቀም መክተብ ቢቻልም የሌሎች ቋንቋዎች ሲጨመሩ ከእዚያ በላይ መርገጫዎችን መጠቀም ስለሚያስከትሉ ነው። ዶክተሩ ለፊደላቱ መደበኛ ስፍራዎች ሲመድቡ ወደ ቀኝ ዳር የተመደቡት ብዙ ተጠቃሚዎች የሌላቸው ናቸው። እንዲህም ሆኖ በጥናት ላይ የተመረኰዘ ማሻሻል ማቅረብ ይቻላል። ለምሳሌ ያህል ኣንድ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት የግዕዝ መርገጫዎች መደብ ኣቅርቧል። መደብ የሚያወጡት ግን ሥራውን የፈጠሩት ናቸው። ግዕዝን በላቲን ፊደል ገበታ መክተብ ኣስቸጋሪነት የቀረበ ጽሑፍ ኣለ። ዩኒኮድ ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ የስምንት እንግሊዝኛ ሥፍራዎችን በማስለቀቅ ዓይነት ኣንድውኑ ቦታ በየተራ በመጋራት ነበር። በዩኒኮድ መፈጠር የተነሳ ግዕዝ ኣሥራ ሁለተኛው ገበታ ላይ ተመድቦ እእያንዳንዱ ቀለም የእራሱን ስፍራ ኣግኝቷል። ጥንትም ቢሆን እያንዳንዱ ቀለም የግሉ የሆነ ከ1 እስከ 5600 ቍጥር ነበረው። በተጨማሪም ትክክለኛዎቹና ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች ዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ እንዲገቡ በማቅረብና በመጻፍ ዶክተሩ ትልቅ ኣስተዋጽዖ ኣድርገዋል። ይህ ሊሆን የቻለውም የዓለም ፊደላትን ዩኒኮድ የተባለ የፊደላት መደብ ውስጥ ሁሉም የዓለም ቀለሞች ዕውቅና እንዲያገኙ በ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ለተቋቋመ ድርጅት ሁለተኛውን የግዕዝ ፊደል ከሠሩበት የኮሎራዶ ኩባንያ በኩል ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ ያደረጉትንና ያቀረቡትን ብዙ መቶዎች ትክክለኛ ቀለሞች በማስጣል ሌሎች ዓማርኛ ፊደል የኣልሆነውንና ዓማርኛን የማያስጽፈውን ኢንጂነር ኣያና ብሩ የሠሩትን ዓይነት የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ቅጥልጥል ፊደል ተሳስተው ዓማርኛና ግዕዝ ነው ብለው ስለኣቀረቡ ነበር። እነዚህ መቶ ሃያ ስምንት ስፍራዎች ይበቃሉ በማለት ለዩኒኮድ ኣቅርበው የነበረውን በመቃወምና ጽፈው በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ኣስጥለዋል። በኋላም 106 ፊደላትና 97 ቍርጥራጮችን የኣልሆኑትን ኢትዮፒክ እየኣሉ 256 የፊደል ስፍራዎች እንደማይበቋቸው እንኳን የኣልዓወቁትን ተቃውመዋል። ይኽንንም በማድረጋቸውና ኢትዮጵያውያን በፊደላቸውና ቋንቋዎቿቸው በኮምፕዩተር እንዲጠቀሙ ስለፈጠሩ ለግዕዝና ኢትዮጵያ ባለውለታ መሆናቸው ከመጻፉ ሌላ “የግዕዝ ኣባት” የሚል የቅጽል ስም ተሰጥቷቸዋል። በሁለተኛ ዙር ይህ የፊደል መቀጠል ጥፋት እንደገና ተደግሞ 364 ብቻ ግዕዝ፣ ዓማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮምኛ ቀለሞችን ያጠቃለለ ለዩኒኮድ በሌሎች ስለቀረቡ ዶክተሩ በድጋሚ ተቃውመዋል። ይኸንንም ተቃውመው የጻፉት ፊደል ስለበዛና የግዕዝ በቶቹ ወደ ስለደረሱ የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎች ቀለሞች በቅጥልጥሎች እንዲጻፉ ሌሎች ስለወሰኑ ነበር። በሦስተኛ ዙር ማሻሻያዎችም ከ55 በላይ የጉራጌ፣ ኣገው/ቢለንና የመሳሰሉት የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎች የግዕዝ ቀለሞች ዕውቅና እንዲያገኙ ቢጽፉምና በትብብር ቢሳካም ሌሎች በጀመሩት ጠንቅ ግዕዝ ኣራት ስፍራዎች ተበትኖ ለዩኒኮድ ቀርቧል። ዶ/ር ኣበራ ለግዕዝ መብት ባይቆሙለት ኖሮ የኣማርኛ መጻፊያው መኪና ኣስቸጋሪ ኣከታተብና የኣልተሟላ ቁርጥራጭ ፊደል ተሻሽሎም ቢሆን ስሕተቱ እንደሚቀጥል ጽፈውም የዩኒኮድ ፊደል ሆኖ ኢትዮጵያ ከማትወጣበት ዘላቂ ችግር ውስጥ ከመውደቅ ኣትድንም ነበር። ምንም እንኳን ዶክተሩ ሞዴት ውስጥ ጭምር ያቀረቧቸው ኣናሳ ቊጥር የኣላቸው ብሔሮች ቀለሞች ዩኒኮድ መደብ ውስጥ በመጨረሻው ቢገቡም ዶክተሩ ለግዕዝ ፊደል እንዲያገለግሉ የፈጠሯቸውና ብዙዎች ከ፳ ዓመታት በላይ የተጠቀሙባቸው የግዕዝ ኣልቦ፣ ቊጥራዊ ኣኃዞችና ኣዳዲስ ምልክቶች ገና ኣልገቡም። ለምሳሌ ያህል የሚፈልጉት የማጥበቂያ ምልክትና ሌሎችም ከፊደሉ በኋላ እንጂ ከላይ ብቻ እንዲገቡ ዶክተሩ ኣይፈልጉም። ያም ሆነ ይህ ዛሬ በኮምፕዩተር፣ የእጅ ስልክና የመሳሰሉት መሣሪያዎች ውስጥ የምንጠቀምበት የዩኒኮድ ፊደል ዶክተር ኣበራ ሞላ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉትም የግዕዝ ፊደላቸውና ፊደላችን ነው። ይህ ፊደል ኢትዮጵያውያን ለብዙ ዘመናት በብራናና በወረቀት ሲከትቡ የነበረውና ደራስያን በየማተሚያ ቤቶች ኣያሌ መጽሓፍትን የጻፉበት ነው። የኣማርኛ የታይፕርይተር ኣማርኛ እንዳልሆነ ዩኒኮድንና ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ኣሳምነው ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ የኣደርጉት የግዕዝ ፊደላቸው የዩኒኮድ ፊደል ሆኗል። እንዲህም ሆኖ የቅጥልጥል ፊደላቸው ውድቅ ከሆነባቸውና መጻፊያ ሠርተው ከተካሰሩት መካከል ኣንዱ ተቀይሞ ዛሬም የታይፕራይተሩን ፊደል ኮምፕዩተራይዝ ከኣደረጉት ኣንዱ ነው ተብሎ ዕውቅና ቢሰጠውም እንኳን በሓሰት ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣደረግሁ የሚል ኣለ። በሳይንስ ዓለም ውሸት ትልቅ ነውር ነው። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና በሚል ርዕስ ከእዚህ በታች የቀረቡትን ከ፴፭ በላይ እንከኖች ማንበብ ይቻላል። በኣሁኑ ጊዜ ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የቢለን፣ ባስኬቶ፣ ቤንች፣ ምኢን፣ ሙርሲ፣ ሱሪ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኣውንጂ፣ ኦሮምኛ፣ ዓማርኛ፣ ዲዚ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ ቋንቋዎች የሚጋሯቸውን ቀለሞችና ሌሎች ያጠቃልላል። ከእነዚህ መካከል የቢለን፣ ባስኬቶ፣ ምኢን፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኦሮምኛ፣ ዓማርኛ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ በዩኒኮድ የቋንቋዎች ፊደላት ስሞች አንዲሆኑ በዶክተሩ ተለይተዋል። በፊደሉ ከሚጠቀሙ ቋንቋዎች መካከል ሓረሪ ኣንዱ ነው። መጽሓፍ ቅዱስ ሙሉዉን ወይም በከፊል ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ ቤቶች ከታተሙባቸው ቋንቋዎች መካከል ሃዲያ፣ ሲዳሞ፣ ከንባታ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ይገኙበታል። የግዕዝ ፊደል ኢትዮጵያዊው ሊቅ ኦነሲሞስ ነሲብ የኦሮምኛውን መጫፈ ቁልቁሉ ሲጽፉ የፈጠሩትን "ዸ" ቀለምና እንዚራኖቹን ይጨምራል። ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ ያደረጉት ትክክለኛውና በሳይንሳዊ ግኝትና ኣርበኝነት ከኣጥፊዎች ያቆዩልንና የግዕዝ ቀለሞቻችን የተለያዩ መልኮች እዚህ ኣጓዳኝ መዝገበ ቃላት ማየት ይቻላል። እንደ ኤውሮጳ ኣቆጣጠር በ1991 የሚባል በ1934 ኣሜሪካ ውስጥ (በእነ ዶ/ር መላኩ በያን) የተቋቋመ ድርጅት ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ በማድረግና ለጀመሩት የግዕዝ ፊደል ሕዳሴ የዕውቅና ሽልማት ሰጥቷቸዋል። ሽልማቱም ይላል። ምንም እንኳን ለኣማርኛው የጽሕፈት መኪና ሲባል ቀለሞቹ እንዲቀነሱ የተለያዩ ሓሳቦች ቀደም ብለው ቢቀርቡም ትክክለኛዎቹ ፊደላት ወደ ኮምፕዩተርና ወደ ዩኒኮድ የዓለም መደብ በዶክተሩ ሲገቡ ሞክሼዎች እንዲቀሩ ስለኣልተባለ ትክክለኛ ሥራ ተሠርቷል። ምክንያቱም የዶክተሩ ዓላማ የግዕዝን ፊደል ወደ ኮምፕዩተር ማስገባት እንጂ የዓማርኛውን የታይፕራይተር ፊደል ወደ ኮምፕዩተር ማስገባት ስለኣልሆነና ሥራቸው የታይፕራይተሩን ችግር ከመፍታት ሌላ የማተሚያ ቤቶች ሠራተኞችንም ድካም የሚቀንስ መሆኑን ስለዓወቁ ነው። በኋላም ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው ግን በግማሽ የዓማርኛ ፊደል እንዲጻፍ መደብ ኣውጥተናል የኣሉትንና ፊደል ስለበዛ የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎች ቀለሞች ቅርጾቻቸውን እንደጠበቁ ማስገባት ቀርቶ በቅጥልጥል ነገሮች ይሥሩ የኣሉትን ጥቂት ኢትዮጵያውያን ዶክተሩ ከተቃወሙና ሁሉም ቀለሞች ቅርጾቻቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ ከኣሳመኑ በኋላ ነበር። እንዲህም ሆኖ ለድረገጽ መሥሪያ 225 ፊደሎችን ኣንድ የተራዘመ ለእንግሊዝኛ የተሠራ መደብ ስለሚችል በእዚያ ልክ የዓማርኛውን ቀለሞች መርጠው በቂ ናቸው በማለት ለኣንዱ ዕውቅና ስለሰጡ ዶክተሩ ለሦስተኛ ጊዜ ተቃውመው በማስጣል ኣሸንፈዋል። የሚያሳዝነው ግን እነዚሁ ሰዎች ግዕዝና ዩኒኮድ ምን እንደሆነ ዋቢ ኣድርገው እ.ኤ.ኣ. 1995 ሲጠቀሙበት የነበሩትን የዶክተሩን ቀለሞች እንኳን ያስገቡት ግዕዝን ኤክስቴንድድ ብለው ለኣራተኛ ጊዜ ከስሕተቶቻቸው ሲነቁ ነበር። እንዲህም ሆኖ ደራስያን በሚፈልጉት ቀለሞች ዓማርኛውን የመክተብ መብት ቢኖራቸውም ቀለማቱ በዩኒኮድ ዕውቅና ስለኣገኙ ፊደል መቀነስና መቀንጠስ ያስፈልጋል የሚባለው ክርክር በዶክተሩ ኣሸናፊነት ኣክትሟል። ቴክኖሎጂው በሁሉም የግዕዝ ቀለሞች እንድንጠቀም ችሎታ ስለሰጠን በተቀነሱ ወይም ሞክሼዎች በሌሏቸው መሥራትን ዶክተሩ ኣይደግፉም። ምክንያቱም ወደፊትም ኮምፕዩተሩ ትክክለኛዎቹን ኆኄያት መርጦ ስለሚያቀርብ ለመሳሳት ዕድሉ ስለማይኖር መቀነስ ደካማ ጊዜያዊ ኣማራጭ እንጂ ግዴታ መሆን ስለሌለበት ነው። በተጨማሪም ፊደል መቀነስ ከታይፕራይተር ጋር በተያያዘ የመጣ ደካማ አስተሳሰብ በዶክተሩ ግኝቶች የተነሳ ቀርተዋል። በግዕዝ ፊደል የሚጠቀሙ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ብዛት ወደ 45 ይደርሳል ይባላል። በቅርቡ መጠቀም ከጀመሩት መካከል ማሌ እና ዲሜ ቋንቋዎቻችን ይገኙበታል። ግዕዝ ወደ ዩኒኮድ ሲገባ ኣስተዋጽዖ ከኣደረጉት መካከል ዶ/ር ፒ. ማክክሉር፣ ኢ/ር ጆ. ቤከር፣ ኢ/ር ሎይድ ኣንድርሰን፣ ኢ/ር ግሌን ኣዳምስ፣ ዶ/ር በቀለ ሞላ፣ ጌታቸው ሞላ፣ ኢ/ር ፍሰሓ ኣጥላው፣ ኢ/ር ታከለ ኣድነው፣ ኢ/ር ፀሓይ ደመቀ፣ ዶ/ር ይጥና ፍርድይወቅ፣ ኢ/ር ግሩም ከተማ፣ ኢ/ር ቴዎድሮስ ኪዳኔ፣ ዶ/ር ሳሙኤል ክንዴ፣ ኢ/ር ተረፈ ራስወርቅ፣ ኢ/ር ተሻገር ተስፋዬ፣ ኢ/ር ታደሰ ፀጋዬ፡ ኢ/ር ማቲዎስ ወርቁ፣ ኢ/ር ኣባስ ዓለምነህ፣ ኢ/ር ዳንኤል ያዕቆብ፣ ኢ/ር ዮናስ ፍሰሓ፣ ዶ/ር ኣርዓያ ኣምሳሉ፣ ማይክል ኤቨርሰን፣ ኢ/ር ዳዊት ብርሃኑ፣ ኢ/ር ኤፍሬም ተክሌ፣ ኢ/ር እስክንድር ሳህሌ፣ ኢ/ር ዮናኤል ተክሉ እና የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ይገኙበታል። እነዚህ ውጭ ኣገር የኣሉ ኢትዮጵያውያን ኣገራቸው ችሎታውን በኣልነበራት ጊዜ ኃላፊነታችውን በትብብር የተወጡና ታሪክ የሠሩ ባለውለታ ጀግናዎች ናቸው። ይህ ዝርዝር ያላካተታቸውን ማሟላት ይቻላል። ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው ለዩኒኮድ ከኣቀረቡ በኋላ ችግር የፈጠሩባቸው የተለያዩ ዓይነቶች ሰዎች ነበሩ። ይህ የሚቀርበው ከረዥም ስሕቶቻችው መማር ኣቅቷቸው ዛሬም ሰውን ከማውናበድ በኣለመቆጠባቸው ሲሆን እንደኣስፈላጊነቱ ወደፊት ስማቸው ይዘረዘራል። ምሳሌ፦ የዩኒኮድ የዓለም ቀለሞች መደብ ውስጥ የግዕዝ ፊደላችን ፲፪ኛው (1200) መደብ ላይ ይጀምራል። የዩኒኮድ መደብ ውስጥ “ፘ” “ፙ”ን ስለቀደመ ማስተካከል ይኖርብናል። የኣሽሙር (ስላቅ፣ ቀልድ፣ ፌዝና መፀት) ምልክትም ተረስቶ የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ኣልገባም። በዶክተሩ ሳይንሳዊ ሥራ ተሸንፈው ፊደል መቀነስና መቀንጠስ ትተው በኋላ ተቆርቋሪ የሆኑ ኣሉ። ቀንና ደራሲ የሌሏቸው በተለይ በእንግሊዝኛ የቀረቡ ጽሑፎች ኣቀራረባቸው ግዕዙን ለማዳከም ስለሆነ ኣንባቢው መገንዘብ ይኖርበታል። ፊደሉ ለሌሎች ቋንቋዎች እንዲተርፍ መጨመር ያስፈልገው ይሆናል። ወደፊት ዩኒኮድ ውስጥ መግባት የኣለባቸው ወንበር የሌላቸውን ኣሥሩን የዶክተሩን ኣኃዞች፣ ሥዕላቸው እዚህ የቀረቡ የፈጠሯቸውን ስምንት ምልክቶችና ነቍጥን ይጨምራል። ዶ/ር ኣበራ ሞላ የግዕዝ ፊደል፣ ገበታና ኣከታተብ ፈጣሪ ከመሆናቸው ሌላ ፊደሉንም ወደ ትሩታይፕ በመቀየር የመጀመሪያው ናቸው። የሠሩትንም የግዕዝ ፊደል ለዩኒኮድም ሰጥተዋል። የፈጠሯቸው የተለያዩ የግዕዝ ፊደላት ሆኑ ኣከታተቦችና ገበታዎች ለተለያዩ ቍርጥራጮች፣ የግዕዝ ቀለሞችና የዩኒኮድ ፊደላት ጭምር ነው። ግዕዝ ኣረጋገጥ ዶ/ር ኣበራ ለመጀመሪያ ጊዜ ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲከተብ በሞዴት ሲፈጥሩ እያንዳንዱ ቀለም የትኛው ቍልፍ ላይ መመደብ እንዳለበትም ወስነዋል። ከእዚያም ወዲህ ኣመዳደቦቹ እንዳስፈላጊነታቸው በኢትዮወርድ እና ግዕዝኤዲት ተሻሽለው ቀርበዋል። ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገባ ወይንም ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲሠራ ሲፈጥሩ ኣዳዲስ ነገሮችን ፈጥረዋል። እነዚህም ኣንደኛ ፊደላቱ ኮምፕዩተር ላይ እንዲታዩና ሲታተሙም ወረቀት ላይ እንዲታዩ እያንዳንዱን ቀለም ለኮምፕዩተሩ እስክሪንና ለተለያዩ የማተሚያ መሣሪያዎች መሥራት። እያንዳንዱ የግዕዝ ቤት በፈንክሽን መርገጫ በኣንደኝነት እንዲቀርብ ሆኖ ቀለማቱ እንዚራን በሁለተኛው መርገጫ ኣማካኝነት ቀረቡ። ሁለተኛው ለፊደላቱ ገበታዎችና ገጽታ በመፍጠር የትኛው ቀለም የትኛው ቍልፍ ላይ እንደሚመደብ መወሰን። ሦስተኛው እያንዳንዱ ቀለም ከሁለት መርገጫዎች በላይ ሳያስፈገልገው እንዲከተብ የመክተቢያ ዘዴ መፍጠር። ለምሳሌ ያህል በሁለት መርገጫዎች የሚከተብ ቀለም የሚታየው ሁለተኛው መርገጫ ከተረገጠ በኋላ ሊሆን ይችላል። ኣራተኛው የግዕዝ ፊደል ለዘመናት ሲጠቀምበት እንደቆየው የፊደሉ ተጠቃሚ ቋንቋዎች የሚከተቡት በግዕዝ ፊደል ነው። (በሌላ ኣነጋገር ኣብዛኛው ፈረንጅ እንደሚመስለው ፊደሉ በላቲን ፊደል ተጽፎ ወደ ግዕዝ ኣይቀየርም ማለት ነው። የፊደሉ ዋና ጥቅሞች ለመጻፍና ኣንድን የግዕዝ ጽሑፍ ለማየት ነው።) ኣምስተኛው ግዕዝ መሣሪያውን በሚገባ እንዲጠቀም ኣስፈላጊ የሆኑትን ኣዳዲስ ነገሮች መጨመር፣ መፍጠር፣ ማስተዋወቅና መጠበቅ ነበሩ። ለምሳሌ ያህል ፊደላቱ ከተበተኑበት ስምንት ፎንቶች ሌላ ድርብርብ ሆነው ከቀረቡት ሌሎች ፊደላት ኣንዱ የሞዴት መጻፊያ ፎንት መነሻ ዓማርኛ በብዛት የሚጠቀምበት ሳድሳኑ በቀዳሚነትና በብዛት ሁለተኛ የሆኑት የግዕዝ ቤት ቀለሞች በዝቅ መርገጫዎች እንዲከተቡ ቀርበዋል። ለስድስተኛ ምሳሌ ያህል የኮምፕዩተር የእንግሊዝኛ ምልክቶች ኣጠቃቀም ለግዕዙም እንዲያገለግል በተመጣጣኝ ቀለሞች ቀርበዋል። የእንግሊዝኛው ኣመዳደብ የተመረጠው የቍልፎች መለጠፊያዎች በሰባተኛነት ቢሠ’ሩም ግዴታ በመሆን እንዳያስፈልጉና ኣከታተቡን ወደ እንግሊዝኛው (ቅውኽርትይ) ገበታ ለማቀራረብ ነበር። በኮምፕዩተር ዘመን ግዕዝን ብቻውን ማቅረብ በቂ ስለኣልሆነ ግዕዙ የቀረበው በዘጠኝነት ከእንግሊዝኛ ፊደሎች ጋር ነው። ስለዚህ እንደ ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ የኣሉት የሞዴት፣ ኢትዮወርድ እና ግዕዝኤዲት ፊደሎቻችን የእየእራሳቸው የእንግሊዝኛና የግዕዝ ፊደሎች ኣሏቸው። በዘጠኝነት ሕዝቡ እራሱን ኣከታተቦች እንዲያስተምር ጠቅሟል። በኣሥረኝነት የተጠቃሚዎች ቋንቋዎች ብዛት ተመጣጥነዋል፣ ስሕተቶችና ግድፈቶች እንዲታረሙና ወደ ዘመናዊ ኣሠራር እንዲሻሻሉ ሓሳቦች ቀርበዋል። በኣሥራ ኣንደኝነት ኣንድን ጽሑፍ በኣልተቀጠሉት የታይፕራይተር ገበታና በእንግሊዝኛ ዓይነት ኣቀማመጥ በሁለቱም ኣከታተብ መጻፍና ማሻሻል ቀርቶ በእንግሊዝኛው ዓይነት ብቻ እንዲሠራ ኣድርገዋል። በኣሥራ ሁለተኝነት ኣሠራሩም ለዘመናት የተለመዱትን የእንግሊዝኛ ዘዴዎችና ኣጠቃቀሞች ለግዕዙም በማድረግ ከኮምፕዩተር ወደ እጅ ስልኮች እንዲዘልቅ ሆኗል። የዶክተሩ ግኝት ለግዕዝ ብቻ ስለኣልሆነ እንግሊዝኛውንም ይመለከታል። በኣሥራ ሦስተኝነት ኣንድን ጽሑፍ ታይፕራይተርና በእንግሊዝኛው ኣጻጻፋቸው የተለያዩ ሰዎች እንዲከትቡና አንዲያሻሽሏቸው ኣስችለዋል። በመጨረሻም ዶክተሩ በፊደል ቅነሳ ባይስማሙም ለሚፈልጉት የተቀነሱትን የፊደል ገበታ ኣቅርበዋል። በኣሥራ ኣራተኛነት የዜሮ ኣኃዝ በሕንዶች ከሺህ ዓመታት ግድም ተገኝቶ ቀስ በቀስ ዓለም ሲጠቀምበት ኢትዮጵያውያን ምንም ሳያደርጉ ቆይተው በመጨረሻው የኣረቡን መጠቀም ስለጀመሩ ዶክተሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የግዕዝን ኣልቦዎች ፈጥረው ፊደሉ ከኮምፕዩተር ቴክኖሎጂ ጋር የሚሄድ ኣኃዛዊ ኣድርገውታል። እንዲህም ሆኖ ግዕዝን በኮምፕዩተር መጠቀም ፊደሉን ማቅረብ የሚመስሏቸው ኣሉ። የላቲንም ሆነ የግዕዙ ፊደል መሣሪያው ላይ ከሌለ ሳጥን የመሰሉ ነገሮች ይታያሉ። ፓተንት የሚሰጠውም ለፊደሉ ወይም ፊደሉን ለሠራው ኣይደለም። የዶክተሩን ፊደላት መርገጫዎች ስፍራ ቀይሮ ማቅረብ ሕዝቡን ለማወናበድ እንጂ ኣዲስ ግኝት ወይም ገበታ ኣይደለም። የዶክተሩን ፈር ቀዳጅ ሥራ በተለያዩ ደካማ ገልባጮች መተካት ቢሞከርም ብቸኛውና ትክክለኛ በመሆን ከ፴፪ ዓመታት በላይ ማገልገሉን ቀጥሏል። ዶክተሩ መክተቢያዎቹን ወደ ኣንድ ሲያሻሽሉት ገልባጮች ከሁለት በላይ መርገጫዎችን በመጠቀም ያልተሟሉና ያልተከተቡ ጽሑፎችን በማቀረብ ሕዝቡን በማጃጃል ገፍተውበታል። በኮምፕዩተር የግዕዝ ፊደል የመጀመሪያውን መብት ያገኘበት የዩናይትድ እስቴትስ ኮፒራይት ወይም መብት ምሳሌ ሞዴት (የኢትዮጵያ ቃላት ማተሚያ) በዶ/ር ኣበራ ሞላ፣ የመብት ቍጥር 0003337637 ዓ.ም. እዚህ ኣለ። ዶ/ር ኣበራ ሞላ እያንዳንዱ የግዕዝ ቀለም በሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ የፈጠሩትን ዘዴ በኢትዮጵያ ኋላ ቀርነት የተነሳ መብታቸውን ማስጠበቅ ስለኣልቻሉ የተለያዩ ኣከታተቦች መቅረብ ቢቀጥሉም ለዊንዶውስ እና ማክ ያቀረቡትንም በቅርቡ ወደ ኣይፎን እና ዓይፓድ ወስደውታል። የእንግሊዝኛው ኣመዳደብ የተመረጠው መለጠፊያ እንዳያስፈልግና ኣከታተቡን በፓተንት በተጠበቀው ወደ እንግሊዝኛው (ቅውኽርትይ) ገበታ ለማቀራረብ ነው። ሁለቱም ቋንቋዎች የሚጠቀሙበትን መርገጫዎች በመጋራት ሕዝቡ በሁለቱም ፊደላት በኣንድና ሁለት መርገጫዎች የተጠቀመው ለብዙ ዓመታት ሥራ ላይ ውሏል። በዶክተሩ ግኝት ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች ከኣንድ ገበታ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ መክተብ ተችሏል። ለላቲን ቀለሞች የተሠሩት መርገጫዎች ከኣሥር እጅ በላይ ብዛት ለኣላቸው የግዕዝ ቀለሞች ሥራ ላይ ውለዋል። በዶክተሩ ዲጂታይዝድ የሆነው የጥንቱ የግዕዝ ፊደል የውጭ ኣገሮችና የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ከመቶ ዓመታት በላይ የተጠቀሙበትም ፊደል ነው። መርገጫዎችን በጣቶች በመንካት መጻፍ ያስቻለውን የላቲን ቀለሞች የእጅ ጽሑፍ መሣሪያ ኣከታተብ ወደ ኮምፕዩተርና ጮሌ የእጅ ስልኮች በተሻሻለው ዓይነት ለግዕዝ ቀለምም ይኸው ትክክለኛና ሳይንሳዊ ኣጠቃቀም ለግዕዝ ሥን ጽሑፍ ሥራ ላይ ውሏል። የእዚህ ገጽ ኣንዱ ዓላማ ሕዝቡ ስለ ቴክኖሎጂው እንዲያውቅና እንዳይታለል ሲሆን ጥቂቱ በወሬ እየተፈታ ጊዜውን እንዳያባክን መረጃ መጠየቅም እንዲጀምር ነው። በሳይንስ ኣሠራር ኣንድ ነገር ተሻሻለ የሚባለው በሂሳብ ተመዝኖ ብልጫ ወይም ልዩነት ሲያሳይ እንጂ ኣንዳንዶቹ እንደሚፈልጉት በተራቀቀ መሣሪያ በመጠቀም ወደኋላ ለመመለስ ኣይደለም። በዶክተሩ ኣከታተብ "ህ" እንዲሁ በኣንድ መርገጫ ብቻ ይከተባል። "ሀ" በዝቅ ወይም መዝለያ" ሲጻፍ "ሁ" "ሂ" "ሃ" "ሄ" እና "ሆ" ይከተባሉ። የስምንተኛ ቤት ቀለሞች በ"\"፣ ወይም "8" ይከተባሉ። በኮምፕዩተር ኣከታተብ ወግ የመጀመሪያዎቹ የላቲን ቀለሞች ወይም ካፒታሎቹ የቁልፉም ስም ስለሆኑ የሚከተቡት በዝቅ መርገጫ ነው። በእንግሊዝኛው ኣያያዝ ("ኤች") የመርገጫው ስም የሆነው በዝቅ ("ኤች") እንደተከተበው የግዕዙም "ሀ" የመርገጫ ስም በዝቅ "ህ" ወይም "ሀ" እንዲከተብ ተደርጓል። ስለዚህ የ"ሀ" መርገጫ የ"ሀ" ቍልፍ ስምም ነው። በእዚሁ ኣያያዝ እንግሊዝኛ ለ94 ቀለሞቹ የሚጠቀምበትን ኣከታተብ የግዕዝ ፊደል ሁሉንም ቀለሞቹን እንዲጠቀምበት ሆኗል። ሠላሳ ሰባቱ የግዕዝ ቤት ቀለሞች እንደላቲኑ 26 የእራሳቸው ቁልፎች ስለኣሏቸው ለትምህትና ገለጻም ጠቀሜታ ኣላቸው። ስለዚህ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በማዳበል በሦስት መርገጫዎች መክተብ ጊዜና ጉልበት ማባከን ነው። ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በማዳበል በሦስት መርገጫዎች መክተብም ግዕዝ የእራሱ ገበታ እንዳይኖረው ነው። ማንኛውንም የዓማርኛ ቀለም በስድስት መርገጫዎች መክተብ ጊዜና ጉልበት ማባከን ነው። ምሳሌ "ፄ"። ዓማርኛውን በብዙ መርገጫዎች መክተብ ሌሎችን ከእዚያ በላይ መጠቀም ያስከትላል። ኣንዳንዶቹ በዘዴዎቻቸው የእራሳቸውን ቋንቋዎች በሦስት መርገጫዎች መክተብ እንጂ ፊደሉን ለሚጠቀሙ 80 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ዘዴዎቻቸው እንደማይጠቅሙ የተገነዘቡ ኣይመስልም። ኣመልካች ጣቶችን የ“ፈ” እና “ጀ” መርገጫዎች ላይ በማድረግ “ፋ” በትንሿ ጣትና “ፌ” በግራ ቀለበት ጣት ይከተባሉ። “ጁ” በቀኝ ኣመልካች፣ “ጂ” በመካከለው፣ “ጆ” በቀኝ ቀለበት እና “ጇ” በትንሿ ጣት ይከተባሉ። ይኸም በየተራ እንደ ”፣ ፣ እና እንደሚከተቡት መሆኑ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የግዕዝ ፊደል የእራሱ ገበታ ቢኖረው ስለማይጠቅመው በእንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ ወይም ኣረብኛ የፊደል ገበታ ቢጠቀም ይሻለዋል በማለት ግዕዝ በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ እንዲከተብ የሚፈልጉ ኣሉ። ላቲን ፊደሉን የሚከትበው በፊደሉ ነው። ግዕዝ ፊደሉን በላቲን ፊደል እስፔሊንግ እስከ በኣሉት ይከተብ ማለት ለፊደሉና ኢትዮጵያውያን ስድብ ነው። ምክንያቱም ለእያንዳንዱ የእንግሊዝኛ ቀለሙ የተሠሩት 26 መርገጫዎች ለ37 የግዕዝ ቀለሞች የተሠሩ ስለኣልሆኑ 26 መርገጫዎች ለላቲን መክተቢያዎች እንጂ ለግዕዙ ኣልተሠሩም። ግዕዝን በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ መክተብ እንግሊዝኛ ቋንቋዎችንንና ፊደሎቹን ለማዳበር ስለሚጠቅም ኣንዳንድ የውጭ ኣገር ሰዎችና ኢትዮጵያውያን ኣጎብጓቢዎች ይወዷቸዋል። በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ ዓማርኛና ግዕዝን መክተብ እንዳስቸገረ ቢጻፍም የማይቀየሩ ኣሉ። ግዕዝን በ26 መርገጫዎች መክተብ መሞከር ከእስፔሊንግ ጣጣ ኣልፎ ላቲን ውስጥ የሌለውን ፊደልን በእስፔሊንግ የመጻፍ ኣዲስ ችግር ግዕዝ ላይ ይፈጥራል። የላቲን ፊደል ተጠቃሚዎችን ለእስፔሊንግ ፊደል ችግር ውስጥ ከጣላቸው ኣንዱ ምክንያት የፊደላቱ ቍጥር ማነስ ነው። ግዕዝ ድምጻዊና የተስፋፋ ፊደል ስለሆነ የላቲንን ችግር ለግዕዝ ማካፈል ኣያስፈልግም። ለምሳሌ ያህል ትግርኛውን "ቜ" በስድስት መርገጫዎች የሚያስከትቡ ኣሉ። ከእዚህም ሌላ ያልተሟሉና ስለሆነ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች የማያስከትቡ ኣሉ። ወደ ኦሮምኛው የላቲን ቁቤ ኣከታተብ በቀረበ ኣንድን ድምጽ በብዙ መርገጫዎች የሚያስከትቡ ኣሉ። ግዕዝ ብዙ የድምጽ ቤቶች በኣሉት ቀለሞች ሲጠቀም እንግሊዝኛ ኣንድ ዓይነት ድምጽ ብቻ በኣለው ፊደል ነው የሚጠቀመው። የእንግሊዝኛው ፊደል ድምጽ በግዕዝ የሳድሱ ድምጽ ዓይነት ነው። በእንግሊዝኛ የኮምፕዩተር ገበታ ሳድሳኑ ድምጾች በኣንድ መርገጫ እንደሚከተቡት ሁሉ የግዕዙም ሳድሳን በኣንድ ይከተባሉ። በእንግሊዝኛ ካፒታል ፊደሎቹ የቁልፎቹ ስምም (ምሳሌ፦ ስለሆኑ በዝቅ መርገጫዎች እንደሚከተቡት በግዕዝም የመርገጫዎቹን ስሞች የግዕዝ ቤት ፊደላት (ምሳሌ፦ የግዕዝ ቤቱ “መ”) የቁልፎቹ ስምም በዝቅ መርገጫዎች እንዲከተቡ ዶክተሩ ወስነዋል። በተጨማሪም በዓማርኛ 40 በመቶ የሚሆኑት ቃላት ሳድሳኑ ስለሆኑና ይህ በብዛት ኣንደኛ ስለሚያደርጋቸው እነሱን አንደላቲኑ እያንዳቸውን በኣንድ መርገጫ መክተብ ተገቢ ነው። ሌሎቹ ሰባት እንዚራን ወደ 60 በመቶ ናቸው። በእንግሊዝኛው እንደሚደረገው የኮምፕዩተሩ ኣከታተብ ወደ እጅ ስልክ እንደዞረው ለግዕዙም ሆኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ወጉንና ሥርዓቱን ሳይጠብቁ የፊደሎቹን ቦታዎች እየቀያየሩ ለኮምፕዩተርና ለእጅ ስልክ የተለያዩ፣ የኣልተሟላና የማይጽፉ ኣከታተቦች በብዙ መርገጫዎች የሚያቀርቡ ኣሉ። ለምሳሌ ያህል ይህ የዊኪፔዲያ ገጽ “ቊ” እና “ቌ” የዓማርኛ ቀለሞችን ኣያስመርጥም። የዶክተሩን ሥራ መገልበጥ እንጂ ኣስተሳሰብ የኣልገባቸው ሳድሳኑን በሁለት መርገጫዎች የሚያስከትቡና የሚከትቡ እንዲሁም ኣንብበው ከመረዳት ይልቅ በወሬ የሚነዱ ተወናባጆች ኣሉ። በብዛት ኣንደኛ የሆኑትን የግዕዝ ሳድሳን ቀለሞች በዶክተሩ ፈጠራ በኣንድ መርገጫዎች ከመክተብ ይልቅ በሁለት መክተብ ጅልነት ነው። (ምሳሌ፦ "ጥ"ን በዝቅ የእንደዚህ ዓይነቶቹ ችግሮች መነሻዎች ስለጉዳዩ የሚያውቁት የዶክተሩን በፓተንቶች የተጠበትን ዘዴዎች ከመደገፍና እዚህ እንደሚደረገው ከማስተማር ይልቅ መገልበጥ፣ መስረቅ ወይም ዝምታን የመረጡ በብዛት ስለኣሉ ነው። እነዚህ እራሳቸውንና ግዕዝን መበደላቸውንም የማይገባቸውም ኣሉ። የዶክተሩ ግዕዝ ኣጠቃቀም ፊደላቱን ከኣንድ እስከ ስምንት በላይ ፎንቶች በመበታተንና እንዳሉ ከመጠቀም ሌላ በዋየሎች፣ ፈንክሽን፣ ኣኃዞችና ምልክቶች ቍልፎች ማቅለምንና መለዋወጥንም ይመለከታል። እንደታይፕራይተሩ ዘዴ ኣንድ የፊደል ገበታ ለግዕዝ ስለማይበቃ ከኣንድ በላይ ገበታዎች ላይ የተበተኑትን በኣንድ የተጻፈውን በሌላ መርገጫ ቀይሮ ማቅረብን ይጨምራል። ዶክተሩ የተጠቀሙበት ፕሮግራም ዓይነት ለገበያ የቀረበ ሲሆን (እ.ኤ.ኣ. በ1983) ዘዴዎቻቸው ከኢትዮጵያውያን ይልቅ የገልባጮችና የእውሸት የግዕዝ ሌጀንዶች ሲሳይ ሆኗል። ኢትዮጵያ የፓተንት ሕግ እንደሌላት ሳያውቁና ከዓወቁ በኋላ የዶክተሩን ዘዴዎች ገልብጠው የተለያዩ ፕሮግራሞች ውስጥ ሲሸጡና ሲበትኑ የነበሩ ከተጠቀሙባቸው ፕሮግራሞች መካከል ወርድእስታር፣ ወርድና ወርድፐርፌክት ይገኙበታል። የኢትዮወርድን ኢትዮፒክ ዶት ስም ቀይሮ ሲሸጥ ከነበረ ኣንስቶ ዘዴውን እንደኣዲስ ነገር ለኮምፕዩተር፣ ለእጅ ስልክና ፓተንት ማመልከቻ የኣቀረቡ ኣሉ። የዶክተሩ ፓተንት ግዕዝን በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብን ያጠቃልላል። የመድኅን ማነስ ከእዚህ ሌላ በእንስሳት ሕክምና ሙያቸውም በተለይ በኢምዩን ደፊሸንሲ ፓተንቶችና በኣበረከቱት 4,501,816 2,127,963 ፈውስ ይታወቃሉ። በኣደረጉት ምርምርና ውጤት ኢምዩን ደፊሸንሲን በማስወገድ በየዓመቱ ሲጠፉ የነበሩትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕይወትን እ.ኤ.ኣ. ከ፲፱፻፸፰ ወዲህ ማትረፍ ተችሏል። ከሰው ልጅ እናቶችና ከኣንዳንድ የጦጣና ውሻ ዝርያዎች በስተቀር የሌሎች እንስሳት ማህጸኖች ኢምዩኖግሎቡሊን የሚባለውን የበሽታ መከላከያ ፕሮቲን ለጽንሶቻቸው በእርግዝና ጊዜ ኣያስተላልፉም። ኣጥቢ እንስሳት በእርግዝና ጊዜ በኣካባቢው ለሚገኙት በሽታዎች መከላከያዎች በእንገርነት ያከማቹላቸውና ኣራሶቻቸው እንደተወለዱ ጡት ሲጠቡ የበሽታ መከላከያዎቹ ፕሮቲኖች ሳይለወጡ ከኣንጀት ወደ ደም በመግባት ለጥቂት ሳምንታት ከበሽታዎች ይከላከሉሏቸዋል። ኣራሶቹ እንገሩን ሳያገኙ ከቆዩ ግን ወደ ደም መግባታቸውና መከላከያነታቸው ቀርቶ እንደ ተራ ፕሮቲን ምግብ ብቻ ይሆናል። ስለዚህ እንደ ጥጆች የኣሉት ሲወለዱ የኤድስ ቫይረስ የበሽታ መከላከያቸውን እንደጨረሰ ሰው ምንም መከላከያ ስለሌላቸውና ኣካባቢው ያሉትን የበሽታ ጀርሞች እየቀማመሱ በተለያዩ በሽታዎች የእራሳቸውን መከላከያ መሥራት እስከሚጀምሩ ድረስ እየተጠቁ ኣብዛኛዎቹ ይታመማሉ፣ ወደ ኣሥር ከመቶም ይሞታሉ። ታክመው የሚድኑትም ኣይጠረቁም። በኮሎራዶ እሰቴት ዩኒቨርሲቲ የዶ/ር ኣበራ የድህረ ዶክትራል ምርምር ይኸን ችግር ለመቋቋም መፍትሔ ፍለጋ ጋር የተያያዘ ነበር። ከላይ እንደተገለጸው በዶ/ር ኣበራ ሞላ ግኝት እስከ 50 ከመቶ ለዘመናት ጠንቅ ሆኖ የቆየውን መድኃኒት የሌለውን የእንስሳትን ኤድስ ዓይነት ሁኔታ መቆጣጠርና ማስወገድ ተቻለ። ጥጆች የእናቶቻቸውን ጡት በመጥባት ወይም በጡጦ ከሚሰጣቸው እንገር በቂ የበሽታ መከላከያ ማግኘታቸው ኣስተማማኝ ኣይደለም። ኣንዱም ምክንያት የጥጃ ወተት ኣንጀት ይዘት ሁለት ሊትሮች ብቻ ስለሆነ ነው። በእዚህ የተነሳ እንደኣካባቢው ቆሻሻነት ለተቅማጥ፣ የሳንባ ምችና ሌሎች በሽታዎች እየተጋለጡ ገበሬውን የሚያካስሩት እንደተወለዱ በቂ መድኅን የኣላገኙት ዋናዎቹ ናቸው። እንገር ውስጥ የኣለውን የበሽታ መከላከያ ፕሮቲን ጥጃው እንደተወለደ ከተሰጠው እንገሩ ጨጓራ ሳይገባ ከወተት ኣንጀት ወደ እንጀት በመሄድ ሳይለወጥ ደም ውስጥ ይገባል። የእንቦሳ ጨጓራ እንደሚሠራና እንገር ውስጥ የኣሉት የበሽታ መከላከያዎች ወደ ደም እንደሚገቡ በምርምር በማረጋገጥ የመድኅን ማነስን ለመጀመሪያ ጊዜ ዶክተሩ ማስወገድ ቻሉ። ምርምራቸውን ጨርሰው ያቀረቡትን መፍትሔ ሁሉም ዓውቀውት ቢጠቀሙበት የመድኅን ማነስ ወደ ኣልቦ (ዜሮ) ከመቶ ግድም ሊወርድ ይችላል። ምክንያቱም ጥጃው እንደተወለደ እንገሩን ማግኘቱ የበሽታ መከላከያው ወደ ደም በብዛት የሚገባበት ጊዜ ከመሆኑም ሌላ የበሽታ መከላከሉን ሥራ ስለሚጀምርና ብዙ ደቂቃዎች ሳይወስድ እንገሩን በብዛት መስጠት ስለተቻለ ነው። እነዚህን ማሳካትና እንገሩ በቂ መከላከያ ፕሮቲን እንዳለው ማረጋገጥ ተጨማሪ ጥቅሞች ናቸው። ጥጆች እንደተውለዱ ወደ ጋለን የሚጠጋ ጥሩና ንፁህ እንገር እንደመጋት ባይጠቅምም ገበሬውም የእንገሩን ጥሩነት የሚያጣራበት የእንገር መመርመሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም ተወልዶ የተገኘ ጥጃ በቂ መድኅን እንዳገኘ የሚያጣራበት የደም መመርመሪያ ኣስፈላጊ ሆኖ ስለኣገኙት ኣዲስ የምርመራ ዘዴዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ፈጠሩለት። ኢምዩኖግሎቡሊን የሚባል ኣካል እራሱን የሚከላከልበት ፕሮቲን በብቃት መኖር ኣስፈላጊ ስለሆነ መ’መ’ርመር ኣለበት በማለት ኣዲስ ኣስተሳሰብ ከማስተዋውቅ ሌላ ለእንገርና ደም ቀላል መመዘኛዎች ፈጠሩ። በቂ የመከላከያ ፕሮቲን የኣለውን እንገር መጋት ፈውስ እንደሆነ በሳይንስ መጽሔቶችም ኣቀረቡ። የኣጋጋት ቪድዮዎች እዚህ ኣሉ። በዘዴው እየተጠቀሙ የኣሉት ቀስ በቀስ እየጨመሩ ስለሆነ በእየዓመቱ ብዙ ሚሊዮን ሕይወት ማዳን ቀጥሏል። በኣሁኑ ጊዜ የዶክተሩን ግኝት በመከተል በተለይ የዩናይትድ እስቴትስ ትላልቅ እርሻዎች ውስጥ ለእያንዳንዱ ጥጃ እንደተወለደ በቱቦው እንገር ይሰጣል። የእንገር ጥቅም በምርምር ከተረጋገጠበት እ.ኤ.ኣ. 1922 ወዲህ በመስኩ ትልቅ ኣስተዋጽዖ የዶክተሩ የ1977 ምርምራዊ ሥራ ሳይሆን ኣይቀርም። ምክንያቱም የእንገር ጥቅሙ ቢታወቅም ሁሉም ጥጃዎች እንዲያገኙት ስለኣልተቻለ ችግሩ ቀጥሎ ነበር። ከዶክተሩ ምርምር በፊት ጥጆች ሳር መቀንጠስ እስኪጀምሩ ድረስ ጨጓራ ስለማይሠራ በስሕተት እንኳን እንገር እዚያ ቢገባ ይጎዳቸዋል የሚባል ኣጉል እምነት በዓለም ላይ ነበር። ኣሜሪካ 65,000 የእንስሳት ሓኪሞችና 92 ሚሊዮን የቀንድ ከብቶች ኣሏት። የዶክተሩ ዘዴ ለተለያዩ ለማዳና የዱር እንስሳት ጥቅም ላይ መዋሉ ለኣርባ ዓመታት እያደገ ቀጥሏል። ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ በእየዓመቱ ከሚወለዱት 40 ሚሊዮን ጥጃዎች 4 ሚሊዮን የሚሆኑት በመድኅን ማነስ ሊሞቱ ይችሉ የነበሩት በዶክተሩ ግኝት በኣለፉት ኣርባ ዓመታት ሊተርፉ ችለዋል። በተጨማሪም በመቶ ጥጃዎች ሕክምና እንዳያስፈልጋቸው ሆኗል። በዓለም ላይ የኣሉ የቀንድ ከብቶች ኣንድ ቢሊዮን ስለሆኑ ቢያንስ ኣሥር በመቶ በዘዴያቸው ቢተርፍ ግምቱን ማስላት ይቻላል። ሌላው በረከታቸው ኣዲስ የሕክምና ዘዴ ሓኪሞችና ገበሬዎች እንዲጠቀሙባቸው የቱቦዎቹን ቀላልና ቀልጣፋ የሕክምና መንገድ ወይም ኣሰጣጥ (ጨጓራ ስለሚሠራ) ማግኘታቸው ነው። ከዶክተሩ ግኝት በፊት ጥጆች ሲታመሙ ሓኪም ቤት ተወስደው መድኃኒት የሚሰጣችው በመርፌ ነበር። በዶክተሩ ግኝት የተነሳ ገበሬው በቱቦው መድኃኒትና ፈሳሽ መስጠት ስለሚችል ወጪና ጊዜ ተቆጥበዋል። ዶክተሩ የመድኅንን ማነስ በማስወገድ ከዓለም የእንስሳት ሓኪሞች ኣንዱ ታዋቂ ምሁር ናቸው። የግዕዝ ፊደል በኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ውስጥ በኣለውም መጠቀም እንዲቻል የፈጠሩ ሊቅና የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጣልያንን በማስፈራራት ወሳኙን እርምጃ የወሰዱ ኣርበኛ ናቸው። ከእዚሁ ጋር የተያያዘ በኮምፕዩተር ኣዳዲስ ኣከታተቦችን፣ የፊደል ኣመዳደቦችና ገበታዎች ፈጥረዋል። ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት ፊደላቸውም የዩኒኮድ ፊደል ሆኗል። በተጨማሪም በሳይንቲስትነት፣ ተመራማሪነትና ሥራ ፈጣሪነት ለኣበረከቱት ዕውቅና የምንሰጠው በታላቅ ኩራት ነው። የኣበረከትነውም ዕውቅና በማሕበረሰቡ የዲሬክተሮች ቦርድና በሁሉም ኢትዮጵያውያን ስም ወሰን ከሌለው ምስጋና፣ ፍቅርና ኣድናቆት ጋር ነው። የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማሕበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ ዶክተሩን የበዓሉም የክብር እንግዳ ኣድርጓል።" ከእዚህ በላይ የቀረበውን የተናገሩት የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማሕበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ ፕሬዚደንት ኣቶ የሺጥላ ኣርኣያ ድርጅቱ ሰባተኛውን ዓመታዊ በዓል ኅዳር ቀን ዓ.ም. ሲልቨር እስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ ሲያከብር ስለዶክተሩ የተናገሩት ነበር። እንገር ጥጆች ወተት ሲጠቡ ወተቱ ትንሽ ይዘት የኣለው ወተት ኣንጀት ውስጥ በቀጥታ ስለሚገባ ወደ ሦስት ሳምንታት እድሜ ሞልቷቸው ሳር መቀንጠስ እስከሚጀምሩ ድረስ ጨጓራ ኣይነበጎ እና ሽንፍላ ሥራቸውን ኣይሠሩም የሚል እምነት በዓለም ስለነበረ ኣልጠባ ያሉትን እስቶማክ ቲዩብ በሚባል ቱቦ መጋትም ኣይጠቅምም የሚባል እምነት ነበር። ምክንያቱም እንቦሳዎች ወተት ሲጠቡ በተፈጥሮ ኢሶፋጂያል ግሩቭ የሚባል የጉሮሮ እጥፋት በኩል ወተቱ በኣቋራጭ ከጉሮሮ ወደ ወተት ኣንጀት ስለሚገባ ነው። በኣፍ በሚገባ የጨጓራ ቱቦ ውስጥ በደቂቃ ጨጓራ ውስጥ የተንቆረቆረ ኣንድ ጋለን ያህል እንገር ወደ ኣንጀት ሄዶ ደም እንደሚገባ በምርምር በማረጋገጥ በመድኅን ማነስ (ፓሲቭ ኢምዩን ደፊሸንሲ መነሻነት ሲከሰቱ የነበሩ ችግሮች (እ.ኤ.ኣ. በ፲፱፻፳፪ ቢደረስበትም) በዶ/ር ኣበራ ሞላ ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.ኣ. በ፲፱፻፸፯ ተወግደዋል። መረጃውም 182 ገጾች በኣለው መጽሓፋቸው በእንግሊዝኛ ቀርቧል። ከእዚያም ወዲህ ምርምራቸው በሌሎች ምርምሮች ተረጋግጠዋል። በእዚህ የተነሳ እንገር ባለማግኘት ሊሞቱና ሊታመሙ የሚችሉትን እስቶማክ ቲዩብ ወይም ኤሶፋጊያል ቲዩብ በሚባሉ ቱቦዎች በመጠቀም እንገሩን ጥጃው እንደተወለደ በመስጠት ሕይወቱን ማዳን ተችሏል። እንቦሳውም እንገሩን ቶሎ ከኣላገኘ ጀርሞችም ከሆድ እቃ በቀጥታ ወደ ደም ስለሚገቡ ኣደጋው ስለሚጨምር እንገሩን ጥጃው እንደተወለደ ከኣላገኘ ወደ ደም መግባቱም ቀስ በቀስ ስለሚቀር ጊዜና የእንገሩ መጠን ወሳኞች ናቸው። የእንቦሳ ጨጓራ እንደሚሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ በማረጋገጥ የጥጃውን ትብብር ሳይጠይቅ በምርምራቸው የእንገር መጠንንና ጊዜውን ሰው እንዲወስን ሆነ። ስለዚህ ኣልጠባ ያለን ጥጃ ዝም ብሎ መመልከትና መበሳጨት ቀርቶ ወተት ኣንጀት የማይችለውን እንገር ጨጓራ ውስጥ በማስቀመጥ ጥጃው እራሱን እንዲረዳ ኣደረጉ። ከብዙ ላሞች ተሰብስቦ ተደባልቆ የተፈረዘ እንገር በክብደት መጠን እየተለካ በቱቦ በኣንድ ደቂቃ ለጥጆች እንደተወልዱ የተሰጠው ኣንድ ጋለን ያህል እንገር በ፳፬ ሰዓታት ውስጥ በቂ መድኅን ደሙ ውስጥ እንዳስገኘና እንገሩን በፈቃዳቸው እያረፉ ብዙ ሰዓታት ሳይፈጁ ከጠቡት ጋር እኩል መሆኑን ኣረጋገጡ። የዶ/ር ኣበራ የምርምርው ውጤት ትልቅ ፈውስ ሊሆን የቻለው ጊዜ፣ ይዘትና መጠንን በኣንዴ በማካተት ስለገላገለ ነው። የጊዜ ጥቅም ጥጃው እንደተወለደ የተሰጠውን ወደ ደሙ ስለሚያስገባ ሲሆን በእዚህ ጊዜም ወደ ደም እንደመድኅኑ የሚገቡትን ጀርሞች ለመቅደምም ነው። እንገሩም ከኣንጀት ወደ ደም የሚገባው ጥጆች እንደተወለዱ ሲሆን ቀስ በቀስ እየቀነሰ በ24 ሰዓታት ውስጥ መተላለፉ ይዘጋበታል። በቱቦው ወደ ጋለን እንገር መስጠት ስለሚቻል በቂ መድኅን እንደተወለዱ መስጠቱ የበሽታ መከላከዎች በብዛት ወደ ደም ስለሚገቡ ነው። ስለዚህ ጥጃው እንደተወለደ መስጠቱ እንጂ መቆየቱ እንገር ማባከን ነው። ጥጃው ቢጠባም ወተት ኣንጀት በቂ ይዘት ስለሌለው የሚፈለገውን ያህል ሊጠባም ስለማይችል ጨጓራ እንደሚሠራ ስለኣረጋገጡ ኣንድ ጋለን እንደተወለደ በቱቦው መስጠት ስለቻሉ እንገሩ ውስጥ በቂ የመድኅን መጠን እንዳለ የሚጣራበት ኣስፈላጊ ነው በማለት ቀላል የምርመራ ዘዴ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈጠሩ። ምክንያቱም የሁሉም ላሞች እንገር የበሽታ መከላከያ ፕሮቲኖች መጠን እኩል ስለኣልሆነ ነው። በተጨማሪም ሬፍራክቶሜትር የሚባል መሣሪያ የእንገርን መድኅን መጠን ለመገመት እንደሚጠቅም የምርመራ ጽሑፍ ጻፉ። ግን ኣንድ ጥጃ በቂ መድኅን የሚኖረው እንደተወለደ ኣንድ ጋለን እንገር ስለኣገኘ ብቻ ሳይሆን በቂ ኢምዩኖግሎቡሊን ስለኣገኘ ስለሆነ እንገሩ ውስጥ በቂ እንዳለ ገበሬው ከላሟ ሳይለይ በኣንድ ደቂቃ እንገሩን መርምሮ የሚያጣራበት የምርመራ ዘዴ ፈጥረውና ኣስፈላጊነት ኣስተዋወቁ። የሥጋ ላሞች ግን ስለማይታለቡ ያንኑ የምርመራ ዘዴ የጥጆችን ደም በመውሰድ ገበሬው ሜዳ እንዳለ በኣንድ ደቂቃ ጥጃው በቂ መድኅን እንዳገኘ እንዲያጣራና ከኣላገኘ ቱቦውን በመጠቀም ማረም እንደሚቻል ኣቀረቡ። እንገሩን በሚገባ ለመጠቀም በኣካባቢው ለኣሉት በሽታዎች ላሞቹን በመክተብ ጥጆቹ ትክክለኛ መከላከያውን ከእንገሩ ያገኛሉ። (ዶክተሩ በተለይ የቫይረስ በሽታዎች ኣዳዲስና የተለመዱ መክተቢያዎችን የመሥራት የብዙ ዓመታት ልምድ ኣላቸው።) የምርምር ውጤቶቻቸውም ጥቅም በሌሎች ሲረጋገጡ ኣርባ ዓመታት ኣልፈዋል። በቂ መከለከያ ኣለማግኘት ይባላል። እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ግን መድኅን ስለሌለ የግዴታ ይሞ'ታል ማለት ኣለመሆኑንና (ኤድስ ያለበት ሁሉ እንደማይሞት ዓይነት) ሲጠባ የታየ ጥጃ ሁሉ በቂ መድኅን ኣገኘ ማለት ኣለመሆኑን ነው። የእንገሩ ጥቅም በኣካባቢው ቆሻሻነት፣ ጥጆቹ ጀርሞቹን ስለሚበሉና የበሽታዎች መኖር ናቸው። ሲጠባ የታየም ይሁን ያልታየ ጥጃ ጊዜ እንዳያልፍበት ደሙን በመመርመር የመድኅኑ መጠን እንዲጣራበት የእንገር መድኅን መመርመሪያ ኣዲሱን ዘዴያቸው ለጥጃውም ደም መመርመሪያ እንዲያገለግል ኣደረጉ። ምርመራዎቹም ኣስፈላጊ ሆነው ስለኣገኙዋቸው መፍትሔውን ፈጥረው ኣቀረቡ። ስለ ምርምር፣ ግኝቶቻቸውና ኣስተዋጽዖ ከታዋቂ የዓለም የእንስሳት ሓኪሞች ኣንዱ ከመሆናቸውም ሌላ በሽታን መከላከል ሲቻል በማከም ብቻ ስለማያምኑም የኣሜሪካና እንግሊዝ ፓተንቶች (የባለቤትነት መታወቂያ) ኣግኝተዋል። የግኝቶቻቸው ጥቅሞች እዚህ በተጠቃቀሱት የተወሰኑ ኣይደሉም፦ ምሳሌ 4,501,816 ፓተንታቸው ሌሎች ፓተንቶችን ጠቅሟል። በዶ/ር ኣበራ የምርምር ውጤት ዘዴ የተነሳ በኣሁኑ ጊዜ እያንዳንዱ ጥጃ እንደተወለደ እንገር በቱቦው የሚሰጠው ትላላቅ እርሻዎች ውስጥ ብቻ ኣይደለም። ብዙ ትላልቅ እርሻዎች ውስጥ ጥጆች በተወለዱ በሁለት ሰዓታት ውስጥ የሆድ ቱቦን በመጠቀም እንገር ይሰጣቸዋል። የእንገር ብዛት ብቻ ሳይሆን ጥራቱንም ማወቅ ኣስፈላጊ ሆኖ ስለኣገኙት መመርመሪያ ዘዴ ፈጥረውለት ዘዴውም ወደ መሣሪያ ተቀይሮ የእንገርን ኢምዩኖግሎቡሊን መጠን መገመት የገበሬዎች የዘወትር ሥራ ሆኗል። እንገር ሌሎች ጥቅሞችም ኣሉት። ለምሳሌ ያህል እንደተወለዱ በቂ መድኅን የኣገኙ ጥጆች ሲያድጉ ብዙ ወተት ይሰጣሉ። ኣሜሪካ ውስጥ ብቻ በእየዓመቱ ወደ 39 ሚሊዮን ጥጆች ስለሚወለዱ የተለያዩ እንስሳት ሳይቆጠሩ ምን ያህል ሕይወት እንደተረፈ ግምቱን ለኣንባቢ መተው ይሻላል። የዶክተሩን ዘዴ ዓለም እየተጠቀመበት ኣሜሪካ ውስጥ ብቻ ብዙ ቢሊየን ዶላሮች ሲይስተርፉ ኣርባ ዓመታት ሊሞሉ ነው። የኣንድ ጥጃ ዋጋ 70 ፓውንድ ቢሆንና በየዓመቱ በዓለም ላይ የሚያልቁትን ጥጃዎች ብቻ መቶ ሚሊዮን በማትረፍ የዶ/ሩ ምርምር ሥራ ዋጋ በኣለፉት 40 ዓመታት ብዙ ቢሊዮን ነው። ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስም ያህል የእንገር መድኅን መጠን ሬፍራክቶሜትር በሚባል መሣሪያ መገመት እንደሚቻል የጻፉትም ከ፴፮ ዓመታት በኋላ ዋቢ እየሆነና መጥቀሙ ነው። ዘዴዎቻቸውም እንደኣስፈላጊነታቸው ለተለያዩ ለማዳና የዱር እንስሳት ጥቅም ሥራ ላይ እየዋሉ ናቸው። ዶክተሩ በተማሩበት የሕክምና መስክ ብዙ ሚሊዮኖች ሕይወቶች ማትረፍ ስለቻሉ ፈጣሪናን የረዷቸውን ያልረሱ ደስተኛ ናቸው። የላም እንገር ለሰው ሕክምናም እየጠቀመ ነው። ሕክምና የምርምር ግኝታቸውም ጥጆች ሲታመሙም ኣዲስ የመድኃኒት፣ ምግብና ፈሳሽ መስጫ ዘዴ ሆኖ ተገኝቷል። ለምሳሌ ያህል የእንቦሳ ተቅማጥ እንደ ስው ኮለራ ብዙ ጥቃት የሚያደርሰው ከኣካል ውስጥ ውሃ እየተመጠጠ ስለሚያልቅ ስለሆነ ውሃውን ለመተካት ጥጆቹን ሓኪም ቤት መውሰድና ማሳከም ገበሬውን ብዙ ወጪ ያስወጣ ነበር። ከዶክተሩ ግኝት በኋላ ግን ትክክለኛውን የጨውና ስኳር መጠን ያለውን ንፁህ ውሃውን በቱቦው ማጠጣት ስለሚቻል ወጪ ቀንሷል። ዶክተሩ ለሕክምና ሞያቸው ካበረከቷቸው ኣንዱ ይኸን ኣዲስ የሕክምና ዘዴ ማቅረባቸው ነው። ከእዚያም ወዲህ ጥቅሙ ቢጋነንም የእንገር ንግድ ኣዳዲስ የዓለም ገበሬዎችና ኣምራቾቹ የገቢ ምንጭና የመድኅን የሕክምና ዘዴ ከመሆኑ ሌላ የሰው እናት እንገርና ወተትም ኣጠቃቀምም ተሻሽሏል። የምርምር ውጤታቸውም ጤናማ እንስሳትን ለማሳደግ መራዳትና ሓኪሞችንም ከመጥቀም ሌላ ለሌሎች እንስሳትም ሥራ ላይ ውሏል። ምሳሌ እንግሊዝን የ፲፮ ቢሊዮን ዶላር ያካሰረውን የላም ጉንፋን ወረርሽኝ ከኣስቆሙትና ከኣጠፉት ኣንዱ በመሆናቸው ዶክተሩ ሁለት የጀግንነት ሽልማት ከዩናይትድ እስቴትስ መንግሥት ተሰጥቷቸዋል። በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ኣለ። ኢትዮጵያውያን ሥጋ ለውጭ ኣገሮች በመሸጥ ብቻ ብዙ ቢሊዮን ብር ገቢ ሊያገኙ ስለሚችሉ መጀመሪያ ኣደገኛ የእንስሳት በሽታዎችን ማጥፋት ይጠበቅባቸዋል። እንደ በሽታውም ዓይነት ክትባት ትልቅ መሣሪያ ነው። የሰው ልጅ በመተባበር የሰውን ፈንጣጣ እና የቀንድ ከብትን ደስታ በሽታዎች ክትባትን በዋናነት በመጠቀም ከዓለም ኣጥፍቷል። ዶ/ር ኣበራ ኣዳዲስና የተለመዱ ክትባቶችን ኣምርተዋል፦ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው። የወፍ ኢንፍሉኤንዛና የመሳሰሉ በሽታዎች ሕዝቡ በሚገባ ማወቅና መዘጋጀት ይኖርበታል። ኤድስ ኤድስ ኣኳየርድ ኢምዩን ደፊሸንሲ ሲይንድሮም) በዓለም ላይ መሰራጨት እንደጀመረ ኤችኣይቪ )ን ክትባት እንደማይከላከለው በጊዜው ከሚያውቁት ሳይንቲስቶችና የበሽታ መከላከያ ክትባት ሠሪዎች ኣንዱ በመሆናቸው በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት ለመከላከል ሕዝቡን ለማስተማር ባለ ኣራት ገጾች የመጀመሪያው የሆነውን ገለጻ በዓማርኛ ስለ ኤድስ በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ተርጕመው እና ጽፈው በገዛ ገንዘባቸው እያባዙና እየኣደሉ ቆይተው በኋላም በኢትዮጵያ ሪቪው መጽሔት ኣትመዋል። በእዚያን ጊዜ ስለ ግብረሥጋ ግንኙነትና ኮንዶም የሚጠቅሰውና እንዲሁም የታመሙትን መርዳት ይገባል የሚለው ጽሑፋቸው ከጊዜው ደካማ ኣስተሳሰብ የቀደመ ስለሆነ ተገቢውን ተቀባይነት ሳያገኝ ቸል ተብሎ የታለፈበት ጊዜ ስለነበረ በሽታውን በምርምር በተረጋገጡ ዕውቀትና ትምህርት መከላከል ስለኣልተቻለ ከፍተኛ ጉዳት ኣድርሷል። ይኸንኑ ጽሑፍ ሕዝቡ እንዲያነብበት የሚባል የኮምፕዩተር ፊደላቸውን በ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. በነፃ የሰጡት ስጦታ ኣሁንም ኢንተርኔት ላይ ስለኣለ ኣንዳንዶቹ ኣልደረሱበትም እንጂ ደርሰውላቸው ነበር። ጽሑፉ ሲጻፍ ኤች ኣይ ቪ ቫይረስ የተገኘባቸው የዓለም ሕዝቦች ኣንድ ሚሊዮን ሆኖ ሳለ እስካሁን በበሽታው ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቍጥር ሚሊዮን ደርሷል። በ፳፻፰ ዓ.ም. 36 ሚሊዮን ያህል ሕዝቦች ቫይረሱ ኣለባቸው። ሰሞኑን ኃምሳ ሁለት ከመቶ ዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ የኣሉ ኢትዮጵያውያን ኤድስ ኣለባቸው የሚባል ወሬ እየተናፈሰ ነበር። ለምሳሌ ያህል መቶ ሰዎች ተመርምረው ኃምሳ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ውስጥ ኤድስ ቢኖርባቸው ዩናይትድ እስቴትስ ከኣለው ወደ ሚሊዮን ከሚጠጋ ሕዝብ ኣምስት መቶ ሃያ ሺህው ኤድስ ኣለው ማለት ኣይደለም። እነዚህ ሁለቱ ኣነጋገሮች የተለያዩ ናቸው። የወሬው ትክክል ኣለመሆንና መረጃው ከዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ ጋር በምናላቸው ስማቸው ቃለምልልስ እዚህ ቀርቧል። ኣንድ ሌላ ትንሽ ጥናትም እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል ከመቶው 28 እንዳለባቸው ኣያውቁም። ይህ ከመቶ 28 ኢትዮጵያውያን ውስጥ ቫይረሱ ኣለባቸው ማለት ኣይደለም። ነፃ መክተቢያ ከቅርብ በረከትም በግዕዝኤዲት ኦንላይን ዓማርኛ ሕዝቡ በነፃ በዓማርኛ ዊንዶውስ እና ማክ ኮምፕዩተሮች ውስጥ መጻፍና የዓለም ድረገጾችንና የመሳሰሉትን (ኢንተርኔት) በዓማርኛ መፈለግ እንዲችል ኣበርክተዋል። ጉግል በዓማርኛና እንግሊዝኛ፣ ያሁ እና ቢንግ በዓማርኛ መፈለጊያም ይገኙብታል። ቪድዮም እዚህ ኣለ። እነዚህ የኣንድ ሰው ብቻ ሥራዎች ስለኣልሆኑ ለሚመለከታቸው ሁሉ ምስጋና ይድረስልን። የድረገጹ ፩ኛ ጥቅም ሌላ መክተቢያና እንደ ማይክሮሶፍት ወርድ ወይም ፔጅስ የመሳሰሉ ፕሮግራሞችን (ተጠቃሚው ተመዝግቦ እያንዳንዱን በብዙ ሺህ ብር መግዛት ስለማይችል በእራሱ ፊደል መጠቀም እንዳይቸግረው) ኣማራጭ በማበርከት በዊንዶውስ እና ማክ ኮምፕዩተሮች በዓማርኛ ለመጻፍ ነው። ከእዚያ ጽሑፉ ኮፒ ተደርጎ ሌላ ሥፍራ ይለጠፋል። የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች ጽሑፎቻችንንና የመሳሰሉትን ወደ ኢንተርኔት ማስገባትና እነዚህኑ ፈልገን ማግኘት ካልቻልን የሚከተለው ኋላ ቀርነት ቀላል ላይሆን ይችላል። ፪ኛው ኢንተርኔትን በዓማርኛና እንግሊዝኛ ወይም ቀላቅሎ ለመፈለግ በኮምፕዩተር ያገኘነውን ኣዲስ ኣጠቃቀም በሚገባ እንድንጠቀምበት ነው። ይህ ቃላትን ጽሑፍ ውስጥ ለመፈለግና ለመተካትም ይጠቅማል። ሕዝቡ በቀላሉ መጻፍ ስለሚችል በሰለጠነበት የጽሑፍ ኣሠራር እንዲቀጥሉ ሲሆን ፫ኛው ጥቅም ኣንድ የዓማርኛ ጽሑፍ በቀለሙ የተጻፈ መሆኑን ለማረጋገጥና እንደኣስፈላጊነቱ ለማረም ነው። በግዕዝ ቀለም ያልተጻፈ ጽሑፍ ኮፒ ተደርጎ ገጹ ላይ ሲለጠፍ ዝብርቅርቅ እንግሊዝኛ ሆኖ ይታያል። ፬ተኛ ጥቅም ኣንዳንድ ምሁራን እንደ “ዝሆን”፣ “ኣኣ”፣ “ክኅሎት”፣ “ድድ የመሳሰሉትን የዓማርኛ ቃላት የማያስጽፉ ድረገጾችንና የመሳሰሉትን ለመጻፊያ ከማቅረብ እንዲቆጠቡ ነው። ኣንዳንዶቹ “ኵ”ን ኣጥፍተው በ“ክው” እንደ እንግሊዝኛ እስፔሊንግ መክተብና ወጪ መጨመር ቢፈልጉም “ኵ”ን መጻፍ የማይችሉ ኣሉ። "ሥዕል"ን በ"ሥእል" መተካትም ችግር ኣለው። ከእነዚሁ መካከል የእነ “ሐ” እና “ኀ” ቤቶች ቀለሞችን የ“ሀ” ሞክሼዎች ስለሆኑ መቀነስ እየፈለጉ ኣንዳንዶቹ “ትህትና”፣ “ትስስር”፣ “ግግር” እና “ትዝታ” የመሳሰሉትን ቃላት መክተብ ስለማይችሉ ዓማርኛውን በእንግሊዝኛ ለመክተብ ሲባል ቃላቱን ማጥፋት ይፈልጋሉ። እነዚህ ምሳሌዎች ያለተቃውሞ ለብዙ ዓመታት ኣሉ። ይህ ገጹን እየተጠቀሙ የኣሉ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ለዓማርኛ ፊደልና ቋንቋ መጥፋት ደንታ እንደሌላቸው የሚያሳይ ኣሳፋሪ መረጃ ነው። ኣንዳንዶቹ ግዕዝኤዲት በሁለት መርገጫዎች የሚያስከትበውን “ስስ” ቃል የሚከትቡት በሰባት መርገጫዎች ሲሆን “ፄ” ቀለምን ለመክተብ እስፔሊንጉን ማስታወስና ስድስት መርገጫዎች መጠቀም ቢያስፈልግም ሁሉንም የዓማርኛ ፊደላት ባዶ ስፍራ እየጨመሩ እንኳን ኣያስከትቡም። ዓማርኛውን መክተብ ሳይችሉ ሌሎች ቋንቋዎችን የጨመሩ ኣሉ። ምክንያቱም ከግዕዝ ቋንቋ ቀለሞች በሰተቀር ሌሎቹ ከዓማርኛው ቀለሞች በላይ ብዛት ስለኣላቸው ነው። ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና እንዳገኘ እያወቁ ዛሬም በእየዓይነቱ የፊደል ቁርጥራጭ የሚያቀርቡም ኣሉ። ፭ተኛው ጥቅም ሞክሼዎችን የማይወዱ ደራስያን ከሚወዷቸው ጋር እያምታቱ በተገኘው እንዳይጠቀሙ ይራዳል። “ሀ” የ“ሃ” እንዲሁም “አ” የ“ኣ” ሞክሼዎች የሚመስሏቸው ኣሉ። “ኳ” እራሱን የቻለ ሞክሼ የሌለው ቀለም ነውና ጊዜና ስፍራ ማባከን ስለሆነ በ“ኩዋ” ወይም “ክዋ” መዘርዘርም ፊደል ለመቀነስ በታይፕ መጻፊያ ዘመን በኣማራጭነት የቀረበና ያኔም ቢሆን ተቀባይነት የኣላገኘ ኣሁንም ቢሆን ጊዜው ያለፈበት ኋላ ቀር ኣስተሳሰብና የማያስፈልግ ግድፈት ነው። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና “ኳ”ን ሲከትብ የነበረው “ካ” ቀኝ እግር ስር መሥመር በመጨመር በኣሌለና የተሳሳተ ቀለም በመጠቀም ነበር። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና “ቋ”ን ሲከትብ የነበረው “ቀ” እግር ስር መሥመር በመጨመር በኣሌለና የተሳሳተ ቀለም በመጠቀም ነበር። በነፃ እየታደሉ በኣሉ የማያዛልቁ ኣከታተቦች ሕዝብ መታለሉ እንዳይቀጥልና እየተነገረውም እነዚያን ለምዶ በኋላ በትክክለኛ ሳይንሳዊ ኣከታተብ መጠቀም ተቸገርኩ እንዳይል ግዕዝኤዲት ይራዳል። ምክንያቱም በተገኘው መክተቢያ ተምሮ በኋላ በግዕዝኤዲት ለመሥራት ሲሞከር ሌላውን ኣጠቃቀም ለመተው ኣስቸጋሪ ስለሚሆንና ምንም ዓይነት ኣከታተብ ለማያውቅ ግዕዝኤዲትን መማር ቀላል ስለሆነ ነው። በተጨማሪም ዓማርኛውን በቍልፎቹ ብቻ መክተብ ስለኣልቻሉ ቀለሞቹን ከ“ሀ” እስከ “ፖ” ደርድረው በማውስ ቀስት በመጠቆም እንዲከተቡ ማድረግ ኣያስፈልግም። ዓማርኛውን በላቲን ቀለሞች መክተብ ኣስፈላጊ ሳይሆን በተገኘው የእንግሊዝኛ እስፔሊንግ እየጻፉ ያሉትን ኣንዳንድ ጉራማይሌ ምሁራን በሚገባ በሚያውቁት ዓማርኛ ፊደልና ቋንቋቸው እንዲጽፉና እንዲያነቡ ያገለግላል። እንግሊዝኛ እስፔሊንግ ከባድ ነገር በመሆኑ ዓማርኛ እንግሊዝኛውን ሊጠቅም ስለሚችል በእንግሊዝኛ ማድበስበስ የለብንም። ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል ስለሆነ ለመነበብም ሆነ ለመከተብ እስፔሊንግ ስለማያስፈልገው ሕዝቡ ዓማርኛውን በላቲን እስፔሊንግ እንዲከትብ በብዙ መርገጫዎች ማስቀጥቀጥም ሳይስፋፋ ዓማርኛውን በዓማርኛ ፊደል ለመክተብ ግዕዝኤዲት ይጠቅማል። ለምሳሌ ይህል “ያመት” የሚለውን ቃል እየጻፉ እንግለዝኛ ቃሉ በማወስ ቀስት እንዲመረጥ ወይም የባዶ ስፍራ ቍልፍ ሲነካ እንግሊዝኛውን ወደ ኣማርኛ በመቀየር “ያመት”ን እንድንጽፍ የሚገልጉ ፈረንጆች ኣሉ። እነሱ እንግሊዝኛውን የሚጽፉት ከኣንዱ ፊደል ወደ ሌላ በመቀየር ወይም ቃላትን በማውስ ቀስት በመልቀም ስለኣልሆነ ለዓማርኛ ተጠቃሚው እንዳልተጨነቁ ያሳያል። የ“ጰ” የዓማርኛ (ቁቤ) ኣነባበብና ኣከታተብ ካፒታል “ፒ” ነው ሲባል ተከርሞ በቅርቡ ወደ “ፒ” እና ነቍጥ ተቀይሯል ይባላል። ቴክኖሎጂውን ለዓማርኛ መፍጠር እንጂ ዓማርኛውን ለቴክኖሎጂው ኣያስፈልግም። ለላቲን ከተሠራ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲሄድና በዓማርኛው ኪሳራ ላቲኑን ለማዳበር ሲሞከር የላቲን ተናጋሪዎች ባይናገሩ ባይገርምም የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች በዝምታ እንደማይቀበሉት ዶክተሩ ኣሳይተዋል። ግዕዝኤዲት የዓማርኛና እንግሊዝኛ መክተቢያ ነው። ፈረንጆች ቋንቋዎቻቸውን በግዕዝ ፊደል እንዲከትቡ ኢትዮጵያውያን ኣልጠየቁም። ኢትዮጵያውያን ቋንቋዎቻቸውን በላቲን ፊደል እንዲከትቡ የሚፈልጉ ጥቂት ፈረንጆችና ኢትዮጵያውያን ግን ኣሉ። ኣንዳንድ ኢትዮጵያውያንም ነገር ስለተማታባቸው ቋንቋዎቹን መቀላቀልም ስለጀመሩ ዓማርኛውንም ሆነ እንግሊዝኛውን በሚገባ የማይናገርና የማይጽፍ ትውልድ እንዳይፈጥሩ ግዕዝኤዲት ይራዳል። ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዘመናት ከነፃነትዋ ጋር ጠብቃ ያቆየቻቸው ቋንቋዎችዋና የተሟሉት ቀለምዎችዋ ዛሬም በእኩልነት እያንዳንዱ ቀለምዋ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ እንዲከተብ ተደርጎ ተከባብሮና ተጋብቶ የኖረው ሕዝብ ፍላጎትና እኩልነት በኣብሻ ሥርዓት ቴክኖሎጂ ምሳሌ በግዕዝኤዲት ቀርቧል። የኣንዳንዶቹን ኣንድ ቋንቋ ቀለሞች በኣራት መርገጫዎች የሌላውን በስድስት መክተብ ወይም እንደሌሉ መርሳት የለም። የምሁራንና ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ሥራና ጥቅም ለኣለ ችግር መፍትሔ መፍጠር ነውና ዶ/ር ኣበራ ለእነዚያ የሚጠቅሙ ሠርተዋል። ኣንዳንድ የግዕዝ ተመራማሪዎች ግን በተሳሳተ ዓላማቸው ፊደሉ ለላቲን ፊደልና ገበታ እንዲስማማ መክተቢያ ሴራ መፍጠር ስለሆነ ግዕዝኤዲት ሳይንሳዊ ዓላማን በመሳት እንዳይቀጥሉ ትክክለኛውን ኣስተሳሰብ ያስገነዝባል። በቅርቡ ኣንድ የግኝታቸው ትክክለኛ ኣከታተብ የገባቸው ኢትዮጵያዊ “ዶ/ር አበራ ምሥጋና ይግባውና የአማርኛ ጽሑፍ ትየባ ፍጥነቴ ከእንግሊዝኛው አያንስም” በማለት ጽፈዋል። ግዕዝኤዲት በዓማርኛና እንግሊዝኛ ኣከታተብ ለመማር ይጠቅማል። በዓማርኛ በብዛት የምንጠቀምባቸው ቀለሞች ሳድሳን ስለሆኑ በኣንድ መርገጫ ይከተባሉ። ሳድሳን ዓማርኛ ጽሑፍ ውስጥ በብዛት ኣንደኛ ስለሆኑ ሳድሳንን በሁለት መርገጫዎች መክተብ በማያስፈልግ ድካም እራስን መበደል ነው። በብዛት ኣጠቃቀም ሁለተኛ የሆኑት ለሁለቱ ዝቅ መርገጫዎች ተመድበዋል። ለግዕዝ ተጠቃሚዎች ኢንተርኔት ላይ በነፃ ለመማርያ የቀረቡ እንግሊዝኛ ኣከታተብ መለማመጃዎችን በመጠቀም ያለኣስተማሪ በፍጥነት መክተብ መማር ይቻላል። “አ”፣ “ሰ”፣ “ደ” እና “ፈ” በግራ እጅ ጣቶች “ጀ”፣ “ከ”፣ “ለ” እና “ጠ” በቀኝ እጅ ጣቶች ይከተባሉ። ምሳሌ ዶ/ር ኣበራ ኮምፕዩተራይዝ ያደረጉትና የታገሉለት ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ስለኣገኘ የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ቅጥልጥል ፊደል እንዲቀር ቢጻፍም ዓማርኛ ነው ብለው ሲያቀርቡ የነበሩና ዛሬም የሚያቀርቡ ኣሉ። ግዕዝኤዲት የሚሠራው በትክክለኛ የግዕዝ ፊደላት ስለሆነ ልዩነቱን የማያውቁ እንዳይታለሉ ይጠቅማል። በትክክለኛ የግዕዝ ቀለሞች የተጻፉ ብዙ መጽሓፍት ምሳሌዎች እዚህ ኣሉ። የግዕዝና ላቲን ኣከታተብ ግንኙነት የላቸውም። በጥቂት የላቲን ቀለሞች እስፔሊንግ ብዙ የሆኑትን የግዕዝ ቀለሞች መክተብ መሞከር ላቲኑን ለመጥቀም ወይም ግዕዝን ለማዳከም ካልሆነ ጥቅም የለውም። ግዕዙን በላቲን እስፔሊንግ መክተብ ኣለባችሁ ብሎ ኢትዮጵያውያንን ያስገደደ የለም። በላቲን እና ሲረገጡ ይታያሉ። በግዕዝ ሲረገጡ “ቦ” ቀለምን ሊያስከትቡ ይችላሉ። ማለት “ቦ” ኣይደለም። እንዲሁም “ቦ” ኣይደለም። በ”ቦ” ምትክ እየጻፉ የዓማርኛውን ቀለም ትተው ዓማርኛውን በላቲን ፊደል የሚጽፉ ተጠቃሚዎች ቍጥር እየጨመረ ነው። ይህ የዓማርኛ ቁቤ ስለሆነ ፊደሉንና ቋንቋውን ሊያዳክማቸው ይችላል። በዓማርኛ “ቾ”ን በሁለት መርገጫዎች ከመክተብ በሦስት መክተብ ኣያፈጥንም። ተጨማሪ ምሳሌ ከኣስፈለገ ኣንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዓማርኛ በላቲን ፊደል እንዲጻፍና በኣጻጻፉም በግዕዝ ፊደል ምትክ በላቲን ፊደል ጽፎ ያቀረበው ጽሑፍ በዓማርኛው በዓማርኛና ዓማርኛው በእንግሊዝኛ እዚህ ኣለ። ዓማርኛን በላቲን ፊደል መጻፍና ማንበብ በኣንድ በኩል ዓማርኛንና ፊደሉን ማዳከም ሲሆን በሌላ በኩል ደካማና ኣክሳሪ የላቲንን ፊደል በዓማርኛው ፊደል መተካትን ለማስፋፋት ይመስላል። ይኸን ኣጠቃቀም ዶክተሩ ከሚቃወሙባቸው ምክንያቶች መካከል ዓማርኛን በላቲን ቀለሞች መክተብ ከዓማርኛው ቀለሞች የበዙ ቀለሞችን መጠቀምን ስለሚያስከትል ነው። የላቲን እስፔሊንግ ለቃላት እንጂ የግዕዝን ፊደላት ለመክተብ ኣይደለም። “የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር” የሚለውን ርዕስ በ15 የግዕዝ ቀለሞች ማስፈር ሲቻል በሚለው 28 መርገጫዎችን በመጠቀም በ24 የላቲን ቀለሞች መተካት ድርብርብ መካሰር ነው። (ይህ ዘዴ ባዶ ስፍራ ቃላት መካከል እያስገቡ በዓማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ የሌለ ኣከታተብን ማስተዋወቅን ቢያስከትልም ይኸንን ኣከታተብ የሚደግፉና እያስፋፉ ያሉ ጥቂት ኣይደሉም።) ግዕዝኤዲት የሚከትበውም ከእዚያ በኣነሱ መርገጫዎች ነው። ሙሉ ጽሑፉን በላቲን ፊደል ከመጻፍ ይልቅ በዓማርኛ ፊደል ማስፈር ብዛቱን ወደ 64.7 በመቶ ዝቅ ያደርገዋል። ይህ ውጤት በደካማ ኣከታተብ ዓማርኛና እንግሊዝኛውን ፊደላት ስናወዳድር ነው። በግዕዝኤዲት ኣከታተብ ይኸው ጽሑፍ በዓማርኛ የሚከተበው በኣነሱ መርገጫዎች ስለሆነ ከኣብሻ ኣከታተብ የተሻለ ኣከታተብ በኣሁኑ ጊዜ የለም። ይህ ለዓማርኛው ሲሆን ሌሎች የግዕዝ ፊደላት ሲጨመሩ ለእስፔሊንጉ ተጨማሪ መርገጫዎች ለሌላው ዘዴ ስለሚያስፈልጉ ግዕዝኤዲት ተወዳዳሪ የለውም። ለምሳሌ ያህል በሌላ ዘዴው እስፔሊንግ የዓማርኛው “ፄ” የሚከተበው በስድስት መርገጫዎች ስለሆነ ለጉሙዙ “ጼ” መክተቢያ ስምንት መርገጫዎችን መጠቀም ያስፈልጋል። ስለዚህ ትርፉ እጅ ማሳመም ነው። ግዕዝኤዲት የዓማርኛውን ሆነ የጉሙዙን የሚከትበው በሁለት መርገጫዎች ነው። በሁለት መርገጫዎች መከተብ የሚችልን ኣንድ የግዕዝ ቀለም ከሦስት እንከ ስምንት መርገጫዎች በመጠቀም መክተብ የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ እንዳንሆን ያሰጋል። በትክክለኛ ኣከታተብ ላይ ያልተመረኰዙ ኣዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ኣገሪቷን ወደኋላ ሊጎትቱ ይችላል። የተቆራረጡ የኣማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ ዓይነት ቀለሞችንና ያልተቆራረጡ ኣንድ የላቲን ፊደል የሚችለውን ቀለሞች እየመረጡና በሌሎች ዘዴዎች ሕዝቡን ሲያጉላሉ ከነበሩት ይገላግላል። ላቲን ለቀለሞቹ መክተቢያ የማይጠቀምበትን ከግዕዝ መጠየቅ ኣያስፈልግም፦ ምሳሌ በማውስ መክተብ። ምክንያቱም ግዕዝኤዲት ባይኖር ኖሮ ግዕዝ ሌሎች ችግሮች ውስጥ ሊወድቅ ይችል እንደነበረ ከእዚህ በላይ የተዘረዘሩት ሊቀሰቅሱን ይገባል። በእዚህ በተራቀቀው የኮምፕዩተር ዘመን የግዕዝ ፊደል በሳይንስና ቴክኖሎጂ ተደግፎ ማደግ ያለበት ጊዜ ነው። ለምሳሌ ያህል ነፃው የግዕዝኤዲት መክተቢያው ገጽ እንደሚሸጡት የዊንዶውስና የኣይፎን ኣከታተብ ዘዴዎች ቀላል ኣይደለም። ቴክኖሎጂውና ሳይንሱ ስለቀረበለት በተለይ ኣንዳኣዳንዱ ስለጉዳዩ በሚገባ ዓውቆ ኣልገባኝም ከእሚል የፊደሉን መብት እንዲያከብርና እንዲያስከብር ነው። የእንግሊዝኛው የቅውኽርትይ የኮምፕዩተር የፊደል ገበታ ወደ እጅ ስልክ ዞሯል። የግዕዙም እንደዚያው በግዕዝኤዲት ቀርበዋል። ኣዲስ ኣሠራር በእጅ ስልክ ማስተዋወቅ ስለተጀመር ሕዝቡ ሁለተኛ ዙር መታለል ውስጥ እንዳይገባ ግዕዝኤዲት ይራዳል። ፓተንት እየተጠበቀ ወይም የሚለው ማሳሰቢያ ነፃው ግዕዝኤዲት ላይ ያለውና እዚህም ስለሚሸጠው ዓይነት ገለጻም ውስጥ የተጠቀሰው ሌላ ሰው በተሰጠው ወይንም በተሸጠለት እንዲጠቀም እንጂ ዘዴውን መገልበጥ ትክክል እንዳልሆነና በሕጉ መሠረት እንደሚያስቀጣም ለማስጠንቀቅ ነው። የግኝታቸውን እንግሊዝኛ ገለጻ በቍጥሩ 20090179778 ወይም በሚከተለው ማያያዣ ማግኘት ይቻላል። ግኝቱ መጀመሪያ የቀረበውና የኣተመው የዩናይት እስቴትስ መንግሥት ስለሆነ ከኢትዮጵያው ቅድሚያ ኣለው። የነፃ መክተቢያውን ፊደል ወደ እንግሊዝኛ ቀይሮ ለእንግሊዝኛ ቃላት ማቀነባበሪያም መጠቀም ይቻላል። ኢትዮጵያ የእራሳቸው የጥንት ፊደላት ከኣላቸው ጥቂት ኣገሮች ኣንዷ በመሆንዋ ይህ ለሕዝብዋ ትልቅ ኩራት ነው። ዋጋው ውድ ነው ተብሎ ሶፍትዌር በሕገወጥ የኮፕ ቅጂ መጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ተስፋፍቷል ይባላል። ኣብዛኛው ኢትዮጵያዊ ልክ እንደእንግሊዝኛው ኮምፕዩተሩን የሚጠቀመብት ለተራ ጽሑፍ ነው። ሕዝቡ ኢንተርኔት እስከኣለው በነፃው ግዕዝኤዲት መጠቀም ስለሚችል መኃይምነት ሊኖር ኣይገባም። ግዕዝኤዲት በነፃ በዶክተሩ ስለተሰጠ ሕዝቡ ስፍትዌርም ከኣልፈለገ መግዛት ስለሌለበት እንደኣንዳንዶቹ የኣልከፈለበትን ሶፍትዌር ማባዛት የለባቸውም። ምክንያቱም በዓማርኛ ለመጻፍ የሚያስፈልጉት ኮምፕዩተርና ኢንተርኔት ብቻ ስለሆኑ ነው። በኣለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያን እየጎዱ የኣሉ ከመንደር ኣስተሳሰብ መላቀቅ ኣቅቷቸው የዶክተሩን ሥራዎች ማስተዋወቅ ሲገባቸው ሲደብቁ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ዋናዎቹ ናቸው። ምሳሌ በተሰረቀ ሶፍትዌር ስማቸውን በየዲስኩ የሚጽፉ የሚያተኩሩት ስለተሰረቁባው ዘፈኖች እንጂ ስሞቻቸውን ስለጻፉባቸው የተሰረቁ የዓማርኛ ሶፍርትዌር ማሰብ የማይችሉ በመሆናቸው ነው። የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር ስለ ኢትዮጵያ የዘመን ኣቈጣጠር ኢንተርኔት ላይ የተጻፈ ከጥቂት ዓረፍተ ነገሮች በስተቀር ስለኣልነበሩ ዶክተሩ በ፲፱፻፺፬ ያቀረቡት በተወዳጅነቱም ብዙ ድረገጾች ላይ ቀርቧል። ከእዚያም ወዲህ የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር ተገቢውን ዕውቅና ቢያገኝም ዛሬም በስሕተት የጁልያን ካለንደር ነው የእሚሉ ኣሉ። ኢትዮጵያውያን ስለ ሄኖክ ዘመን ኣቈጣጠርም ያውቃሉ። የሄኖክ ዓመት 364 ቀናት ነበሩት። የኢትዮጵያ መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ መጽሓፈ ሄኖክ ምዕራፍ ቍጥር ስለ 364 የዓመት ቀናት ይናገራል። ኢትዮጵያውያን ሲወርድ ሲወራረድ የመጣውን የነገሥታት የስም ዝርዝር ለብዙ ሺህ ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት 4,400 ዓመት በመጀመር ኣቆይተውልናል። ይህ ከ1,000 ዓመተ ዓለም ግድም ጀምሮ መሆኑ ነው። ይህ ኢትዮጵያውያን የእራሳቸው የዘመን መቍጠሪያ እንደነበራቸው የሚያመለክት ኣንድ ማስረጃ ነው። የግብጽና የሌሎችም እዚህ ኣለ። የጥንት ኢትዮጵያውያን የከዋክብትን ሳይንስ ፈጥረውና ስም ሰጥተዋቸው ለግብጻውያን ኣስተላለፉ ይባላል። የግሪክ ፊደል ከግብጹ ዴሞቲክ የተወሰደ ነው ይባላል። የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር የጁልያን ዘመን ኣቈጣጠር ኣይደለም። ጁልየስ ሲዘር ባለ 10 ወራትና 300 ቀናት የነበረውን የሮማውያን ካላንደር ትቶ 365.25 ቀናት የኣለውን ካለንደር ወስዷል። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያንና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ግን (2017) ልዩ ኣይደሉም። በ525 ዓ.ም. ዲኖስዮስ ኤክሲጅዮስ የሚባል የሩስያ መነኩሴ የሮማው ጳጳስ መልዕክተኛም በመሆን የፋሲካን በዓል ኣወሳሰን ከግብጻውያን እንዲማር ተልኮ ነበር። እንደሚመስለኝና ኣንዳንድ ፀሓፊዎችም እንደሚሉት ኤክሲጅዮስ በ525 ዓ.ም. 532 ዓመትን ሳይጠቀም ኣልቀረም። ዲኖስየስ ኣኖ ዶሚኒ ወይም ኤ.ዲ.) የሚባለውን ካለንደር በጃንዋሪ 1፣ 1 ኤ.ዲ. እንዲጀምር በ525 ቢወስንም በኋላም ፀሓፊዎች ጁልያን (ዩልዮስ) ካለንደር የኣሉት የግብጾችንና የኢትዮጵያን ዘመን መቊጠርያዎች ስለማይመለከት እራሱን የቻለ ካለንደር ሆኖ ቆይቷል። ኤክሲጅዮስ ወደኋላ በመቍጠር ሲጀምር ይመስለኛል ኣዲሱ ካለንደር ላይ ሰባት ዓመታት ግድም የጨመረበት ይላሉ ዶክተር ኣበራ ሞላ። የዓመታቱም ቍጥር ከግብጽ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የቀረበ ነው። ምክንያቱም የግብጻውያን ዓመተ ሰማዕታት ኣንድ ብሎ በ፪፻፸፮ ዓ.ም. የጀመረ ስለሆነ ነው። ጨረቃ መሬትን ስትዞርና መሬት ፀሓይን ስትዞር የሚወስዱት 532 ዓመታት (19 28) ተደጋጋሚነታቸው የታወቁ ናቸው በማለት ዶክተሩ ጽፈዋል። ኣሁን ያለነው ፲፭ኛው የ፭፻፴፪ ዓመታት ዙር ውስጥ ነው። የዲኖስዮስ ጁልያን ካላንደር ስሕተት እንደነበረው የቫቲካኑ ጳጳስ በቅርቡ በመጽሓፋቸው ስለኣሰፈሩ ዶክተሩም ኣመስግነዋቸዋል። ምክንያቱም የዩልዮስ ቀለንጦስ ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያው ላይ ሰባት ዓመታት ግድም ቢጨመሩም የእኛው ወደ ትክክለኛው የቀረበ ሳይሆን ኣልቀረም። ከግዕዙ ሲነጻጸር የጎርጎርዮስ ቀለንጦስ ተጠቃሚዎች የሦስተኛውን ሺህ መጀመሪያ የኣከበሩት ሰባት ዓመታት ግድም ቀድመው ነው። ኢትዮጵያውያን በዓላትንና ኣጽዋማትን ሲያከብሩ የቆዩት 532 ዓመታትን የሚሸፍነውን ኣንድ ትልቅ ጠንጠረዥ ደጋግሞ በመጠቀም ነው። ኢትዮጵያውያን ሚሌንየሙን ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ሲያከብሩ ዶክተሩ ተጋብዘው ይኽንኑ የቀለንጦስዎቹን ታሪክ ኣቅርበዋል። ከኣንድ ዓመተ ዓለም ጀምሮ መስከረም ኣንድ ቀን ምን ዕለት እንደዋለ ወይም እንደሚውል ማስላት ስለሚቻል የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር ለሌሎች ቀለንጦሶዎችም ማነጻጸሪያ ሊያገለግል ይችላል። ለምሳሌ ያህል በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. መስከረም ቀን ምን ዕለት እንደዋለ ለማወቅ 7494 ዓመተ ዓለም ላይ 1873 ደምሮ በሰባት ማካፈል ነው። ቀሪው ኣንድ ከሆነ ዕለቱ ማክሰኞ ነው። (1873 የተገኘው 5500 ዘመነ ብሉይንና 1994 ዓመተ ምሕረትን ደምሮ በኣራት በማካፈል ነው።) የኢትዮጵያና የጎርጎርዮስ ዘመን የዕለት ልዩነቶች በጥቂት ቀናት መለያየት እየጨመረ ይቀጥላል። ይህ በጎርጎርዮስ የሠግር ዓመታት ኣወሳሰን የተፈጠረ ልዩነት ነው። የጎርጎርሳውያን ሠግር በ፬፻ ዓመታት ብቻ እንዲሆን እ.ኤ.ኣ. በ፲፭፻፹፪ ስለወሰኑ የቀናቱ ኣመዳደብ በእየ ዓመታት ሦስት ሦስት ቀናት እየቀነሰ መለያየቱ ይቀጥላል። የጁልያን ካለንደር ላይ ዲኖስዮስ ሰባት ዓመታት ግድም ሲጨምር ጎርጎርዮስ ቀናት ቀንሷል። በእነዚህ የሮማውያን ለውጦችም ሳትስማማ ኢትዮጵያ ካለንደሯን እንደጠበቀች ቆይታለች። በኣሁኑ ጊዜ ኣንድ ዕለትን ከኢትዮጵያ ወደ ጎርጎርሳውያን ወይም ከጎርጎርሳውያን ወደ ኢትዮጵያ ኣቈጣጠር የሚመነዝሩ ድረገጾች ኣሉ። የቀለንጦስዎቹም ዕውቅና ጨምሯል። ዓለማችን ከኣንድ ስፍራ ጀምራ ፀሓይን እየዞረች ተመልሳ እዚያ ገደማ የምትደርሰው በተለያዩ ዕለታት ስለሆነ ካለንደሮች ትክክል ኣይደሉም። የኢትዮጵያ ዕለት የሚጀምረው ጠዋት ነው። ስለ ጵጉሜን 7 የሚጽፉም ኣሉ። ይህ በየስድስት መቶ ዓመታት የሚከሰተው በየዓመቱ የተጨመሩትን ደቂቃዎች ለመቀነስ ስለሚመስል ትክክል ሳይሆን ኣይቀርም ይላሉ ዶክተሩ። በዶክተሩ የጽሑፍ ገለጻና ምክንያት የተባበሩት መንግሥታት ማሕበር እና የኣፍሪቃ ሕብረት ከመስከረም ፳፻ ዓ.ም. እስከ መስከረም ፳፻፩ ዓ.ም. የኣለውን የኢትዮጵያ ዓመት ሚሌንየሙን በማክበር ዕውቅና ሰጥተዋል። ሦስተኛው የኢትዮጵያ ሺህ ዘመን የጀመረው መስከረም ቀን ዓ.ም. 11, 2008) ሲሆን መስከረም ቀን ዓ.ም. የሁለተኛው ሺህ የመጨረሻው የ2,000 ዓመት እንቁጣጣሽ እንጂ የሚሌንየሙ መጀመሪያ ኣልነበረም። ኢትዮጵያውያን ካለንደራቸውን እንዲተዉ የተሞከሩት ስለኣልሠሩ ጽሑፎቹ ደራሲና ቀናት ወደሌላቸው እየተቀየሩ ነው። የኢትዮጵያ ዕለት የሚጀምረው ጠዋት ሲሆን የዩሊዮሱ እኩለ ሌሊት ላይ ነው። ስለዚህ ልዩነቶቹን ለማስላት ስድስት ሰዓታት መጨመር ወይም መቀነስ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በ፲፱፻፺፪ ወይም 1999 የሚል ድረገጽ ያቀረበውን በመተርጐም ከእነካርታው በዶ/ር ኣበራ ቀርቦ ነበር። እነዚህም፦ 1. ኣሪ 2. ኣፋር 3. ኣላባ 4. ዐማርኛ 5. ኣንፊሎ 6. ኣኝዋክ 7. ኣርቦሬ 8. ኣርጎባ 9. ኣውንጅ 10. ባይሶ 11. ባምቤሺ 12. ባስኬቶ 14. ቤንች 15. በርታ 17. ቢራሌ 18. ኦሮምኛ (ቦረና-ኣርሲ-ጉጂ) 19. ቦሮ 20. ቡርጂ 21. ቡሳ 22. ጫራ 23. ደሳነች 24. ዲሜ 25. ደራሻ 26. ዲዚ 27. ዶርዜ 28. ጉራጌ 29. ጋሞ-ጎፋ-ዳውሮ 30. ጋንዛ 31. ጋዋዳ 32. ጌዴኦ 34. ጉሙዝ 35. ሃዲያ 36. ሃመር ባና 37. ሆዞ 38. ካቻማ-ጋርጁሌ 39. ካሲፖ-ባለሲ 40. ካፊቾ 41. ከንባታ 42. ካሮ 43. ኮሞ 44. ኮንሶ 45. ኩረት 47. ኩንፈል 48. ክዋማ 49. ክዌጉ 50. ሊቢዶ 51. ማጃንግ 52. ማሌ 53. ምኢን 54. ሜሎ 55. መስመስ 56. ሙርሌ 57. ሙርሲ 59. ናዪ 60. ጉራጌ (ሶዶ) 61. ኑአር 62. ንያንጋቶም 63. ኦፑኦ 64. ኦይዳ 65. ቆቱ (ኦሮምኛ) 66. ሳሆ 67. ሰዘ 68. ሻቦ 69. ሻካቾ 70. ሼኮ 71. ሲዳሞ 72. ሱማሌ 73. ሱሪ 75. ትግርኛ 76. ፃማይ 77. ኡዱክ 78. ጉራጌ (ምዕራብ) 79. ኦሮምኛ (ምዕራብ-መካከለኛ) 80. ኣገው (ምዕራብ) 81. ወላይታ 82. ጫምታንግ 83. የምሳ 84. ዛይ 85. ዛይሴ-ዘርጉላ ናቸው። በኣጭሩ ኢትዮጵያ ሰማንያ ቋንቋዎች ኣሏት ማለት ይቻላል። ሌሎች ዝርዝሮችም እዚህ ኣሉ። እዚህ ዝርዝር ውስጥ የግዕዝ ቋንቋ ኣልተካተተም። የግዕዝ ቋንቋና ግዕዝ ፊደል እንዳይምታቱ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እስከኣሁን በኣብዛኛዎቹ የግዕዝ ፊደል ቀለሞቻችን ተጠቃሚ ቋንቋዎች ብዙ ጽሑፎች ስለኣልተጻፉ ብዙ የቃላት ክምችቶችም የሉም። በኣሁኑ ጊዜ ውጪ ኣገር የኣሉ ኢትዮጵያውያንን በዓማርኛ ማስተናገድ ተጀምሯል። በዓማርኛ ለማንበብ የሚለውን መምረጥ ያስፈልጋል። ወደፊት በሌሎቹም የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ቋንቋዎች መስተናገድ እንዲጀመር በየቋንቋዎቹ መጻፍ መስፋፋት ጠቃሚ ሳይሆን ኣይቀርም። በሁሉም ቋንቋዎቻችን በግዕዝ ፊደል መክተብ እንዲቻል ቀለሞቹ ዩኒኮድ ውስጥ ገብተው መክተቢያዎቹ በዶክተሩ ስለተዘጋጁ ባለመጠቀም ለሚዳከሙ ቋንቋዎች ተጠያቂዎቹ የየቋንቋዎቹ ተጠቃሚዎች ናቸው። ዕውቀት እየበዛና እየገዘፈ ወደ ኢንተርኔት ስለገባ የሚፈለገውን በቀላሉ ማግኘት ተችሏል። ይህ በተለያዩ ቋንቋዎቻችንም እንዲኖር መጻፍ ያስፈልጋል። ቃላትና ጽሑፎች በብዛት ሲኖሩ ወደ መተርጐም ይኬዳል። በኢትዮጵያ ከ80 በላይ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች እንዳሉ፣ ከእነዚህም መካከል ወደ 51 የሚጠጉት ቋንቋዎች በመጀመርያ ደረጃና በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ለሚሰጡ ትምህርቶች በመማርያነት እንደሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ከተለያዩ የፊደል ዓይነቶች ዶክተሩ ስሙን ለጥቂቶቹ የሰጡት ሥራ ለማቅለል ነው። ለምሳሌ ያህል የቤንች ገበታ ሲመረጥ የሚጠቀሙበት ቋንቋዎች ብዙ ናቸው። ምሳሌ ኣዊንጊ። የ“ዸ” ፊደል እርባታዎች ለኦሮሞ የተሰጡት ዶክተሩ ፊደሉን ቀድመው ስለዓወቁና መረጃዎቹ ስለቀደሙ እንጂ ይኸው ፊደል የሳሆ ቋንቋን ድምጽ ስለሚወክልና የሳሆም ምሁራን ፊደሉን እንዲጨምሩላቸው ስለላኩላቸው ፊደሉ የሳሆም ነው። የኣንዳንድ የቦታዎች ስሞችም እየተለዋወጡ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ምሳሌ በረራ የቋንቋዎች ፊደላት ከግዕዝ በፊት የደኣማቱ ቅድመ-ግዕዝ ፊደል ነበር። ግዕዝ የሚለው ቃል ሁለት ትርጕሞች ኣሉት። ኣንደኛው የግዕዝ ቋንቋ ስም ሲሆን ሌላው የፊደሉ ነው። የግዕዝን ፊደል የሚጠቀሙት የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የእየራሳቸው የሆኑ ቀለሞች ኣሏቸው። የግዕዝ ቋንቋ ፊደሉን ብቻውን ሲጠቀም ቆይቶ ሌሎች ቋንቋዎች የእየራሳቸው የሆኑ ቀለማትን ጨምረውበት ተስፋፍቷል ይባላል። ዓማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮምኛ ብዙ ቀለሞች ከመቶ ዓመታት በላይ ቢጋሩም ሁሉም የእየራሳቸው ብቻ የሆኑ ቀለማት ኣሏቸው። ቢሆንም ግዕዝ የሁሉም ተጠቃሚ ቋንቋዎች የፊደል ስምም ነው። ከእነዚህም መካከል ብዙ ተጠቃሚዎች የኣሉት የዓማርኛ ፊደል ነው። የዓማርኛው ፊደልም በቅርቡ የተጨመረለትን የ“ቨ” ቤት ጨምሮ ከ፸ በላይ የግዕዝ ቋንቋ የሌለውን እነ “ሸ”፣ “ቸ”፣ “ኘ”፣ “ጀ”፣ “ጨ”፣ “ኸ”፣ “ዠ” እና ሌሎችንም ቀለማት ያካትታል። (ይህ ገለጻ ዓማርኛ የኣልሆነውን የታይፕራይተር ፊደል ስለማይመለከት ቅጥልጥል ፊደሉም ግዕዝ ኣይደለም።) ስለዚህ ዓማርኛ የሚጠቀመው በእራሱ ፊደል ነው። ይህ ኣገላለጽ የሌሎች ቋንቋዎች ፊደላትንም ይመለከታል። ለምሳሌ ያህል ሁሉም የዓማርኛ ቀለሞች የትግርኛው ውስጥ እንደሌሉት ሁሉም የትግርኛ ቀለሞች (ለምሳሌ “ቐ”) ዓማርኛው ውስጥ የሉም። ኣንዳንድ ሰዎች በስሕተት ዓማርኛ የእራሱ ፊደል የለውም ይላሉ። ዓማርኛ የእራሱ ፊደል የኣለው ቋንቋ ነው። የግዕዝም ቋንቋ የእራሱ ፊደል ኣለው። የግዕዝ ቋንቋ ፊደላት የዓማርኛው ውስጥ ሲኖሩ ሁሉም የዓማርኛ ፊደላት የግዕዙ ቋንቋ ፊደላት ውስጥ የሉም። የግዕዝ ወይም የተለያዩ ቋንቋዎች የሚጠቀሙበት የፊደሉም ስም ሲሆን ለተለያዩ ቋንቋዎች ተጨማሪ ቀለሞች ተጨምረዋል። ኦሮሞም የእራሱ የግዕዝ ፊደል ኣለው። እንዲሁም ሁሉም የኦሮሞ ፊደላት (ምሳሌ “ዸ”) የዓማርኛው ውስጥ የሉም። የኤርትራው ቢለንና የጎጃሙ ኣገው ቋንቋዎች ፊደላት ቀለሞች ኣንድ ዓይነት ናቸው። ጉራጌኛ ሰባቱንም ቤቶች ያጠቃልላል። የኣብዛኛዎቹ ኣዳዲስ ተጠቃሚ ቋንቋዎች ፊደሎች ዓማርኛው ላይ የተጨመሩ ናቸው። በእዚህም የተነሳ የቀለሞቹ መልኮች እየጨመሩ ቢሆንም ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆኑ ማወቁ እየቀለለ ነው። ተጠቃሚው የሚፈልገውን ቋንቋ በመምረጥ በቋንቋው ቀለሞች ብቻ መጠቀም ተችሏል። በላቲን ፊደል እንደሚጠቀሙት እንደእነ እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛና እስፓንኛ ፊደላት በመባል እንደሚታወቁት ሁሉ በግዕዝ ፊደል የሚጠቀሙትም የትግርኛ፣ ዓማርኛ፣ ግዕዝ፣ ኦሮምኛ ሌሎችም ፊደላት በመባል በፊደል ስማቸው ተከፋፍለዋል። ኣንዳንድ ምሁራን በስሕተት ዓማርኛና ትግርኛ የእራሳቸው ፊደላት የላቸውም ይላሉ። ይህ እንግሊዝኛና እስፓንኛ የእራሳቸው ፊደላት የላቸውም እንደማለት የተሳሳተ ነው። ከእዚህ ጎን የኣለው ሥዕል እንደሚያሳየው ፊደላቱን በቋንቋ ቀለሞች የመከፋፈሉ ጥቅም ኣጻጻፍ ለማቅለልም ሲሆን በሁሉም የግዕዝ ቀለሞች ለመጠቀም ግዕዝ” የሚለውን መምረጥ እንደሚቻል ለማሳየት ነው። (ኢትዮፒክ) በእንግሊዝኛ ግዕዝ ነው። በግዕዝ ቋንቋ ፊደላት ለመጠቀም "ግዕዝ ቋንቋ" የሚለውን መምረጥ ያስፈልጋል። በኣንድ ምሳሌ ቋንቋ የተሰየሙትንም ብዙ ቋንቋዎች ሊጠቀሙባቸውም ይችላሉ። ምሳሌ፦ ኣዊንጂ፣ ዲዚ። ወደፊትም ገበታውን በእያንዳንዱ ቋንቋ ለየብቻ ማቅረብ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ወደፊት እያንዳንዱ ቋንቋ በእራሱ ሰዋሰው፣ መዝገበ ቃላት፣ ማረሚያና የመሳሰሉት መጠቀም ስለኣለብን ሳይንሱንና ቴክኖሎጅውን በጀመርንበት በኣሁኑ ጊዜ ለየብቻቸው ማዳበር ስለሚያስፈልገን ነው። ይህ እንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ተቀላቅለው በላቲን ፊደላት እንደማይቀርቡት ዓይነት መሆኑ ነው። ለጥቂቶቹም መደበኛ ቅርጽ የተሰጣቸው ፊደላቱ በቋንቋ ስሞቻቸው ወደ ዩኒኮድ ሲገቡ ነበር። (በግዕዝኤዲት ኣጠቃቀም እንግሊዝኛ ለመቀላቀል የ“ቍጥጥር” እና “ኣማራጭ” ቁልፎች መጫን ያስፈልጋል።) በዶክተሩ ፓተንቶች የተጠቀሱት የግዕዝ ቀለሞች ብዛት ዊኪፔዲያ ውስጥ ከተጠቀሱት የበለጡ ናቸው። ዶክተሩ ግን በግላቸው በዓማርኛ ፊደል መቀነስ ከማይስማሙባቸው ምክንያቶች ኣንዱን ለመጥቀስ ያህል ኣንዳንድ የኣናሳ የግዕዝ ቀለሞች ተጠቃሚ ቋንቋዎች ቀለማት የተሠሩት ይቀነሱ የተባሉትን በመጠቀም ስለሆነ ነው። ሞክሼዎች ይቀነሱ የተባለው የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎች ፊደሉ በዛ ብለው ቅር እንዳይላቸው ነው የሚባልም ወሬ ኣለ። በእዚህ የተነሳ ጸሎቱ “ጸ” የፀሓዩ “ፀ” ሞክሼ ከሆነ የጉሙዙ “ꬨ” “ጸ” ሞክሼውን መመርኰዝ ኣልነበረበትም። “ጿ” ቀለም ያለውን ጸሎቱ “ጸ” ሞክሼ ነው ተብሎ ተዘልሎ የምኢኑ ዘጠነኛ እንዚር ፀሓዩ ላይ ስለቀረበ ዶክተሩ ለፀሓዩ ስምንተኛ ቀለም ኣቅርበዋል። ምክንያቱም በዶክተሩ ኣስተሳስብ ፊደል መቀነስ የሚፈልጉ ፊደል እንዳይቀነስ የሚፈልጉትን መብት መንካት የለባቸውም። “ኳ”ን ኣጥፍቶ “ክዋ” ወይም “ኩዋ” እንደ “ኳ” ይነበቡ ማለት ብቻ በቂ ኣይደለም። ምክንያቱም ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል ስለሆነ ነው። “ሀ” እና “አ” የእየራዕቦቻቸው ሞክሼዎች መስለዋቸው ከኣናሳ ቋንቋዎች ቀለሞች ውስጥ ሊያጠፏቸው የሚፈልጉም ኣሉ። ይኸን ልዩነት በኣለማወቅ የዩኒኮድ ፊደላችንም ላይ ችግር የፈጠሩ ኣሉ። ስለዚህ የሚሻሻሉ ነገሮች ጥናት ላይ ቢመረኰዙ ኣይከፉም። ሞክሼ የተባሉት ቀለሞች የእየእራሳቸው ጥቅሞች ኣሏቸው። ምሳሌ፦ መሳሳትና መሣሣትን በማጥበቂያ ወይም በማላልያ ምልክት ከመለየት የቃላቱን ኣመጣጦች ማወቅ ለዕውቀቱም ሆነ ለኮምፕዩተሩ ሳይበጅ ኣይቀርም። “መሣሣት” (“ትክክል ኣለመሆን”) እና “መሳሳት” (“ስስ መሆን”) ሁለት ቃላት በዓማርኛ ለመክተብ የሚወስዱት ሥፍራዎች ስምንት ሲሆኑ የሚከተቡት በ14 መርገጫዎች ነው። ላቲኖቹ የሚወስዱት እጥፍ ሥፍራዎችና 16 መርገጫዎች ስለሆኑ ሞክሼዎችን ማስወገድ ሥፍራዎችንና መርገጫዎችን ስለሚያስጨምር ለዓማርኛውም ጠቃሚ ኣይደለም። ምሳሌ፦ “መሳ'ሳ'ት”። ምክንያቱም የ“መሳሳት”ን ሁለት ኣጠቃቀሞች ከዓረፍተ ነገሩ መለየትም ይቻላል። እነዚህም እንደልብስ ያልጠነከረ “ስስ” መሆንና እንደሰው ርኅሩህ የሆነ “ስስ” መሆን ናቸው። በጊዜውም የኮምፕዩተር ክፍል ባይኖርም የሞዴት ፕሮግራሞች የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ለኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ (በፕሮፌሰር ዓለማየሁ በኩል) በ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. በነፃ ኣበርክቶ ነበር። ኦሮምኛን በግዕዝ ፊደሉ መክተብ ያስቸግራል በተባለበት ጊዜ ለቀረቡት ኣንዳንድ ምክንያቶች ዶክተሩ መፍትሔ ነበራቸው። ኦሮምኛን ከግዕዝ ይልቅ በላቲን ፊደል መጻፍ ይሻላል ተብሎ የቀረቡት ዘጠኝ ምክንያቶች ደካማዎች ነበሩ። ለምሳሌ ያህል በኣንደኝነት የቀረበው ምክንያት ላቲን 26 ቀለሞች ሲኖሩት የግዕዙ 189 ናቸው ይላል። የላቲን “ኤ” ፊደል ዓይነቶች 27 ሲሆኑ ከእነዚህ ስምንቱ ናቸው። “ብላ” በግዕዝ ፊደል “ኛዹ” ተብሎ በኦሮምኛ ሲጻፍ የሚወስደው ስፍራ ሁለት ብቻ ሲሆን እያንዳንዱን ቀለም ለመክተብ ኣንድ ስከንድ ቢወስድ በላቲን ፊደል በእንግሊዝኛ በፈረንሳይ እና በእስፓኝም ፊደል ኣያታርፉም። በሌላ በኩል ኣንዳንድ ኦሮሞዎች ወደ ላቲን የዞሩት በግዕዝ ፊደል እንዳይጠቀሙ ስለተከለከሉም ነው ይባላል። የግዕዝ ፊደልና ተጠቃሚ ቋንቋዎቹ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። ለምሳሌ ያህል ውክፔዲያ ስለ እንግሊዝኛ ፊደል ገጽ ሲኖረው ስለ ዓማርኛ ቋንቋ እንጂ በእንግሊዝኛ ስለ ዓማርኛ ፊደል ወይም የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ገጽ የለውም። በጽሑፍ የሌለ ነገር እንደሌለ ይቆጠራል ነው የሚባለው። በዓማርኛ ፊደል በነፃ መጻፊያ እዚህ ኣለ። የተሟሉ የዓማርኛ መክተቢያዎች ኣሉ። ስለዚህ ኣሁን በግዕዝ ፊደላችን በትክክለኛው ኣጠቃቀም በተለያዩ ቋንቋዎቻችን በሕጋዊ ሁኔታ በተገዙ ሶፍትዌር በመጻፍ ጽሑፎች ወደ ኮምፕዩተርና ኢንተርኔት የሚገቡበት ጊዜ ነው። በቅርቡም ሕዝብ ለብዙ ዘመናት የተጠቀመበት ዓማርኛ ብሔራዊነቱ ቀርቶ የሥራ ቋንቋ በመሆን በእንግሊዝኛ እንዲተካ ተደርጓል ይባላል። ኢትዮጵያ የእንግሊዝ ቅኝ ኣገር ስለኣልሆነች ባይሆን ዓማርኛው ላይ እንግሊዝኛን መጨመር እንጂ መተካቱን ዶክተሩ ይቃወማሉ። ተማረ የሚባለው ኣንድአንድ ኢትዮጵያዊ እያተኮር የኣለው ከጻፈልኝ ምን ኣለበት እየኣለ በተገኘው ሶፍትዌር ይጽፋል እንጂ ሁሉንም የዓማርኛ ቀለሞች እንኳን ከትቦ የሚጠቀምበት የመክተብ ችሎታ እንዳለው ማጣራቱ ኣጠራጣሪ ነው። “ባለፈው አንድ ዩኒቨርሲቲ ሄጄ አንድ ጓደኛዬ የነገረኝ አሳዛኝ ነገር ነበር። የአማርኛ መምህር ለመቅጠር የተሰጠው ፈተና ዩ፣ ዪ፣ ዬ እና ዮን መጻፍ ነበር። በጣም የሚገርመው ግን ከተፈተኑት ኣምስት የሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው መምህራን ኣንዱ ብቻ አሟልቶ ጽፏቸዋል። ወደፊት አማርኛን ማንበብና መጻፍ የሚችል ሰው ለማግኘት ሥዕለት ሳያስፈልግ አይቀርም።” ይላል እዚህ የኣለ ኣንድ ጽሑፍ። ለእዚህ ችግር የአማርኛ የጽሕፈት መኪናም ኣስተዋጽዖ ሳይኖረው እንዳልቀረ የኮሚሽነር ኣበበ ሙሉነህን የ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. ደብዳቤ ውስጥ የኣሉት የ“የ” እንዚራን መቀጠያዎች ያሳያሉ። (“ኢትዮጵያ”፣ “ዩናይትድ” እና “ኮምፒዩተር” የሚሉት ቃላት የተጻፉባቸው የ“የ” መቀጠያዎች መለየት ኣስቸጋሪ ነው። የአማርኛ የእጅ ጽሑፍ መጻፊያ “ዮ”ን መጻፍ የኣልቻለ ቢመስልም ስሕተቱ የፀሐፊው ሳይሆን ኣይቀርም። የትግርኛ ቀለሞቻችንን ለኣለመጠቀምና ቀስ በቀስ ለማጥፋት ያቀለሟቸውንም ዶክተሩ ተቃውመዋል። ለምሳሌም ያህል በአማርኛ የ“ሀ” ድምጽ ወደ “ኸ” የቀረበ ነው አንጂ “ሀ” የ“ሃ” ሞክሼ ኣይደለም። የ“ሀ” እና “ኸ” ድምፆች ኣንድ ባይሆኑም “ሀ” እና “ሃ” ኣንድ መሆን የለባቸውም። “ሐ”፣ “ኀ”፣ እና “ዀ”ም ኣሉ። የተለያዩ ቋንቋዎች ብቻ የሚጠቀሙባቸው ቀለሞችና ድምፆች ኣሉ። ምሳሌ የጉራግኛው “ⷐ”። ይኸ ለምሳሌ ያህል የቀረበ የጉራጌ ፊደል እንደ ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ዓይነት የተሟላ የግዕዝ ፊደል ለሌላቸው ኣይታይም። የሁሉም የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ቋንቋዎች ተለይተው መታወቅ እንደየፍላጎቱ ለማዳበር ይጠቅማል። ለምሳሌ ያህል ኦሮምኛ ከቴክኖሎጅው ጋር እንዲጓዝ እነኢትዮስዊትን ማዳበር ያስፈልጋል። ግዕዝ ትክክለኛ ፊደል ስለሆነ ወደፊት ሌሎች ዓለማት ስንሄድ ይዘናቸው የምንሄድ ስለሆኑና ከዋክብትን ስለሚጎበኙ በኣቋራጭ ኣንሸወድ። በግዕዝ በሚገባ ለመጠቀም ወጪ ማውጣትና ለመክፈል መዘጋጀት እንጂ ለላቲን የተሠሩ ፕሮግራሞችና መሣሪያዎች ሲባል ፊደል መቀነስ ላይ ማተኮርን ዶክተሩ ይቃወማሉ። የግዕዝ ፊደል መክተቢያዎች ሁሉንም ቀለሞች የማስተናገድ ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል። በዓማርኛ ብቻ የሚያስጽፈውን ግዕዝ ማለትም ተገቢ ኣይደለም። የዓማርኛ ከታቢም በሌሎች ፊደላት መኖር እንዳይዘናጋ ዓማርኛው ብቻ ተመርጦ እንዲከተብበት ኣማራጭ ሊኖር ይገባል። ፊደላትን በተለያዩ ቋንቋዎች ማቅረብ ለትርጕምና የተለያዩ ሥራዎች ማዳበር ይጠቅማል። ለምሳሌ ያህል ኦነሲሞስ ነሲብ በሁሉም የግዕዝ ቀለሞች ኣልተጠቀሙም። ጽሑፎች ኢትዮጵያንና ጠቅላላ ዕውቀት የሚመለከቱ ጉዳዮች በተለይ በእየጊዜው የቀረቡ ኣሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ስመ እጸዋት፣ የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር፣ ስመ በሽታ፣ የግዕዝ ፊደል፣ ስመ ኣኃዝ፣ የኢትዮጵያ እንስሳት ስመ አንሰሳት፣ የግዕዝ ስምና ኣኃዝ ስመ ምልክቶች፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች፣ ኣንዳንድ የፊደል ስሕተቶች፣ ግልጽ ደብዳቤ ለቫቲካን ጳጳስ ቤነዲክት ፲፮ተኛ እና ምሳሌዎች ናቸው። ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የኢትዮጵያ ሚሌንየም መከበር ያለበት መስከረም ቀን ዓ.ም. እንጂ መስከረም ቀን ዓ.ም. መሆን እንደኣሌለበት ኣንድ ድረገጽ ላይ ዶክተሩ ጽፈውና ኣሳምነው የኢትዮጵያ ምክር ቤት ከሰኔ ቀን ዓ.ም. እስከ መስከረም ቀን ዓ.ም. እንዲከበር የተደነገገው ስሕተት ተደርሶበት ሚሌንየሙ ዓመቱን ሙሉ እንዲከበር ተደርጓል። የኢትዮጵያ ስመ እጽዋት ምንጭ የዶ/ር ኣበራ ሞላ ሥራ ነው። በተጨማሪም ዶክተሩ በየጊዜው የሞዴት፣ ኢትዮወርድና ግዕዝኤዲት ኣማርኛና እንግሊዝኛ መመሪያዎችን ለመክተብና ማቀነባበሪያ ከተጠቀሙባቸውና የሌሎችም ሥራዎች ሌላ ብዙ መጽሓፍት ከ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ጀምሮ ከጻፉባቸው ታዋቂ ደራስያን መካከል ዶ/ር ዓለሙ ቢፍቱ እና ዶ/ር ለይኩን ብርሃኑ ይገኙበታል። እነዚህ በዓማርኛው ፊደል መጽሓፎቻቸውን ኣሜሪካ የጻፉና ያሳተሙ ደራስያን ዶክተሩን በመጥቀስ ኣመስግነዋል። ዶ/ር በቀለ ሞላ እና ጌታቸው ሞላ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ ፈጣን ማተሚያ ቤት የመጀመሪያው የሆነውን ግዕዝ ማተሚያ በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ኣቋቁመው ብዙ መጽሓፍትና ጽሑፍ-ነክ ሥራዎች በሶፍትዌር ታትመዋል። ዶ/ር በቀለም ተመስግነዋል። ዶክተር ኣበራም የግዕዝ ፊደል የረዥም ጊዜ ተጠቃሚ ናቸው። ለኣሥር ዓመታት ያህልም (ኤልያስ ክፍሌ) “ላንዳፍታ” (መኮንን ገሠሠ) መጽሔቶች ተባባሪ ኣዘጋጅ ነበሩ። ዶክተሩ ዲጂታይዝ በኣደረጉት ግዕዝ በተለያዩ ርዕሶች ኢንተርኔት ላይ የተለያዩ ጽሑፎችን ኣቅርበዋል። የዶክተሩ ሥራዎች የተለያዩ መጽሓፍትና መጽሔቶች ውስጥም ተጠቅሰዋል። ምሳሌ፦ 25 (ገጽ 526) (ገጽ 128) ዶክተሩንም ስለ ሥራዎቻቸው የኣመስገኑ ብዙዎች ናቸው። ቪድዮዎችና ሌሎችም ኣሉ። ይህ “ኣበራ ሞላ” የውክፔዲያ ገጽም በብዛት ከሚነበቡት ኣንዱ ነው። የዓማርኛና እንግሊዝኛ ቅልቅል ጽሑፎች ምሳሌ እዚህ ኣለ። ዶክተሩ ይኸን የዓማርኛ ዊኪፔዲያ ገጽ ከኣቀረቡት ፀሓፊዎች ኣራተኛ ናቸው። ገጹም በትልቅነት ኣንደኛ ነው። ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የአማርኛ ዊክፔዲያ ስመ እጽዋትና ስም አንስሳት መነሻዎች የዶክተሩ ጽሑፎች ናቸው። ዶክተሩ ከታዋቂ ሰዎች ኣንዱ ናቸው። በኣከናወኗቸው የተለያዩ ሥራዎች ጥቅሞቻቸው የተነኩ ጥቂት ሰዎች ስለእሳቸው የተጻፉ የእንግሊዝኛ ጽሑፍችን የሚሠርዙ ቢኖሩም ኣልተሳካላቸውም። ግዕዝ አከታተብ ዶክተሩ ከ564 በላይ የሆኑትን የግዕዝ ዩኒኮድ ቀለሞች ማንኛቸውንም በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ እንዲከተቡ ለፈጠሩት ቀልጣፋና ግሩም ኣዲስ ዘዴ መረጃ ፔንዲንግ ፓተንት እዚህ ወይም እዚህ ማንበብ ይቻላል። ኣብሻ በመባል በታወቀው በእዚህ ኣዲስ የመክተቢያ ዘዴ ወይም ሥርዓት ሕዝቡ በነፃ በአማርኛ መጻፍና የዓለም ድረገጾችንና የመሳሰሉትን (ኢንተርኔት) በአማርኛ መፈለግ እንዲችል (ፍሪታይፒንግ.ግዕዝኤዲት.ኮም) የሚባል ድረገጽ በ፳፻፪ ዓ.ም. ኣበርክተዋል። ከእዚያም ወዲህ ብዙ መቶ ሺህ ሰዎች ተጠቅመውበታል። በኣብሻ ሥርዓት ብዛቱ ከ፭፻ በላይ ከሆነው የግዕዝ ፊደል፣ ምልክት፣ ኣኃዝና ማዜሚያ ሌላ ኮምፕዩተሩ የሚጠቀምባቸውን የእንግሊዝኛ ቊጥሮችና ምልክቶችን ግዕዝ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ተጠቅሞባቸው መክተቢያዎቹ ተርፈዋል። በኣንድና ሁለት መርገጫዎች የእንግሊዝኛውን ቀለሞች እንዲከትብ የተሠራው የኮምፕዩተር የፊደል ገበታ ግዕዝን ወደ እንግሊዝኛው ዓይነት ኣከታተብ በቀረበ ዘዴ እንዲከትብ ሠርተዋል። በእዚህ ዘዴ ግዕዝ የእንግሊዝኛ እስፔሊንግ ጣጣ ውስጥ ሳይገባ የእንግሊዝኛውን የኮምፕዩተር ገበታ በመጋራት፣ በማዋሃድና ለብቻውም እንዲጠቀም ሆኗል። ይኸንንም ያደረጉት በፓተንት ማመልከቻቸው እንደጠቀሱት ግዕዝን በቀላሉና በቀለጠፈ ዘዴ መክተብ የሚያስችል ዘዴ ስለኣልነበረ ነው። ነፃውና የሚሸጠው ግዕዝኤዲት ሶፍትዌር የተሸፈኑት በኣንድ የባለቤትነት መታወቂያ ስለሆነ ማስጠንቀቂያው ለሁለቱም ነው። ፓተንቱ ቢኖርም ባይኖርም ከፈጠሩት ዘዴ የተሻለ በኣሁኑ ጊዜ ስለሌለ ማንኛውምን ቀለም በሁለት መርገጫዎች መክተብም ያስችላል። ለምሳሌ ያህል በፈጠሩት ኣዲስ ዘዴ ኮምፕዩተሩ በኣለው 47 መርገጫዎች የግዕዝ ሳድሳንና ኣኃዞች በኣንድ ኣንድ መርገጫዎች ሲከተቡ ሌሎች ከ400 በላይ የሆኑት የግዕዝ ቀለሞች እያንዳንዳቸው በሁለት መርገጫዎች ይከተባሉ። ስለዚህ በእዚህ ዘዴ መፈጠር የተነሳ ቀለሞችን በሁለትና ከእዚያ በላይ መርገጫዎች በመጠቀም ወይንም የግዕዝን ቀለም ላቲን በማይጠቀምበት ኣዲስና ኋላ ቀር ዘዴ እንደላቲን ቃላት በእስፔሊንግ መክተብ ኣያስፈልግም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዓማርኛውን በኣራት መርገጫዎች የሚያስከትቡ ዘዴዎችንና የኮምፕዩተር ፕሮግራሞች በነፃ በማደል እያዘናጉ በማለማመድ ላይ የኣሉም ኣሉ። ይህ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች በኣራት መርገጫዎች ስለማያስከትብና ሊያዛልቅ ስለማይችል ዓማርኛውንም ሆነ እንግሊዝኛውን ሳይጠቅም ሁለቱንም ከሌሎች የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች እንዳያጣላና እንዳያስተዛዝብ ዶክተሩ የፈጠሩት ይራዳል። ቸልተኝነት ከቀጠለ ግን የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች ኣናሳ እንዳይሆኑ ሳያስተውሉ በተገኘው በመጠቀም ይሀን ወሳኝ ጊዜ ከማባከን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ግዕዝኤዲት የሚከትበው እንደ እንግሊዝኛው ኣከታተብ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ቢመስልም ከእንግሊዝኛው በተሻለ፣ በረቀቀ፣ ኃይለኛና ኣዲስ ዘዴ ስለሆነ ፊደላችንን በዓለም ላይ ለማስፋፋትና በድምፃዊነቱ ጥቅም ላይ ለማዋል በሚገባ ተዘጋጅቷል። ሥራውም ሳይንስን የተመረኰዘ ነው። የግዕዝ ፊደል የረዥም ጊዜ ተናጋሪዎችና ጸሓፊዎች የኣሉት ሲሆን ድምጽን እንዲወክል የተሠራውን የእንግሊዝኛውን ዓለም-ኣቀፍ ድምፃዊ ፊደል ሊረዳ ይችላል። በኣሁኑ ጊዜ ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የቢለን፣ ቤንች፣ ምኢን፣ ሙርሲ፣ ሱሪ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኣውንጂ፣ ኦሮምኛ፣ ዓማርኛ፣ ዲዚ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ ቋንቋዎች የሚጋሯቸውን ቀለሞችና ሌሎችንም ያስከትባል። ይህ የውክፔዲያ ገጽም የተጻፈውና የቀረበው በግዕዝ ፊደል ነው። ግዕዝኤዲት.ኮም የኮሎራዶው ኣብሻ/የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ኩባንያ ሌላ የእሳቸውና ባለቤታቸው ወ/ሮ ሠናይት ከተማ ድረገጽ ነው። የሁሉም ስም ግዕዝኤዲት ቢሆንም የነፃው ኃይልና ኣጠቃቀም የተወሰነ ነው። ዶክተሩም እንዴት የግዕዝ ፊደል ለኮምፕዩተሮች፣ የእጅ ስልኮችና ለመሳሰሉት መቅረብ እንደሚቻል በሳይንሳዊ ምርምር የደረሱበትን ለገበያና በነፃ ከማድረስ ኣልፈው ለፊደሉ መብት ታግለው ስለተሳካላቸው በምርምሩ በመቀጠል ትክክለኛ መደብ ፈጥረዋል። እየተሻሻለም ነው። ስለዚህ እያንዳንዱን ቀለም በሁለት መርገጫዎች መክተብን ጨምሮ ከኣሁን ወዲያ መጠቀም ኣስፈላጊ ኣይደለም። ሕዝቡም ይሀን ተገንዝቦ ሳይንስ በፈጠረው የተራቀቀ መሣሪያ በሳይንሳዊ ወጉና በማዕረጉ መጠቀም እንጂ ለተለያዩ ዓላማዎችና በነፃ የሚቀርቡት ኋላቀር ኣከታተቦች ኣንዳንዱን እያበላሹት እንደሆነ መገንዘብ ይገባል። ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲሠራ ኣዲስ ግኝት ሲቀርብ በኮምፕዩተር ዘመን ብቻውን ማሠራት በቂ ስለኣልሆነ ሞዴት የግዕዝና የእንግሊዝኛ ማተሚያ ነበር። የኮምፕዩተር ኣጠቃቀም ከዶስ ወደ ዊንዶውስ ሲዞር ዶክተሩ ኢትዮወርድን በማቅረብ ለመጀመሪያ ጊዜ ግዕዝ ዊንዶውስን እንዲጠቀም ኃይል ኣገኘ። የኢትዮወርድ ኢትዮኤዲትም ሌሎች ጥቂት የዊንዶውስ ፕሮግራሞችም ውስጥ ይሠራ ነበር፦ ምሳሌ ወርድፐርፌክትና ኳርክኤክስፕሬስ። በግዕዝኤዲት ኮምፕዩተር በግዕዝ እንዲጠቀም ሆነ። ግዕዝ ወደ እጅ ስልክ ሲገባም የግሉ የማቀነባበሪያ (የግዕዝኤዲት) ገበታ ኖሮት ስልኩን በፊደሉና ከላቲን ጋር በመጋራት እንዲሠራ ኣደረጉ። የግዕዝኤዲት ኣከታተብ ትክክለኛና ሳይንሳዊ ከመሆኑም ሌላ ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች በእኩልነት ተስተናግደዋል። የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች ቀለሞቻቸውን በወጉና በቀላሉ እንዲጠቀሙ ኣስችሏል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዶክተሩ ፓተንት ማመልከቻ 20090179778 በሚከተሉት የኣሜሪካ ፓተንቶች ተጠቅሷል፦ 8,381,119 8,645,825 8,706,750 8,700,653 8,762,356 8,812,733 ከጠቃሾቹም የፓተንቶች ባለመብት ዋነኛው ጉግል ነው። ይህ ለኢትዮጵያም ክብር ነው። ስለ ዶክተሩ ሥራ የኣስተዋወቁና የኣመሰገኑ ከኢትዮጵያውያን ማሕበሮች እስከ ዩኒቨርሲቲ ዩኒየን የኣሉ ቢኖሩም ስለ ሥራዎቻቸው የኣልሰሙም ኣሉ። በቅርቡ ከኣንድ ኣንባቢ ስለ ዓማርኛና እንግሊዝኛ ኣጻጻፎች ጥያቄ ለግዕዝኤዲት ፌስቡክ ቀርቦ ነበር። [23] ጽሑፍን በግዕዝ ፊደል መጻፍ ያታርፋል። ኣንድን ገጽ በዓማርኛ ወይም እንግሊዝኛ ጽሑፎች ለመሙላት ዓማርኛውን የበለጠ ጊዜ ይወስድበታል። ምክንያቱም ዓማርኛ ቃላቱን ሲጽፍ ከእንግሊዝኛው በኣንድ ሦስተኛ ግድም በኣነሰ ስፍራ ስለሚያሰፍረው ነው። በእንግሊዝኛ ሦስት ገጾች ለሚያስፈልጉት በዓማርኛው ሁለት ገጾች ገደማ ይበቁታል። ይኸም የሆነበት ግዕዝ ድምፃዊ ፊደል ሲሆን ላቲን ፊደላዊ በመሆኑ ነው። እንግሊዝኛው የሚጻፈው በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ሲሆን ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ በሁለት መርገጫዎች ስለተከተበ እንግሊዝኛው ብልጫ የኣለው ይመስል ነበር። በቅርቡ ግን በዶ/ር ኣበራ ሞላ ግኝት ግዕዝን በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብ ስለተቻለ ኣከታተቡ ከእንግሊዝኛው ጋር እኩል ቢመስልም በላጭ ሆኗል። እንግሊዝኛ 47 መርገጫዎች የኣሉትን ኮምፕዩተር ከዝቅ መርገጫዎች ጋር በመጠቀም 94 ቀለሞችን ያስከትባል። ግዕዝኤዲት የዝቅ መርገጫዎችን ሳይጠቀም ወደ 500 የግዕዝ ቀለሞችን ያስከትባል። ከላይ በቀረቡት ምክንያቶች ስፍራዎች ስለሚያስቀንስ ኣንድን ጽሑፍ ወረቀት ላይና በኮምፕዩተሮች ለማቅረብ ዓማርኛው ያታርፋል ማለት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል “ዘ ኲክ ብራውን ፎክስ ጀምፕስ ኦቨር ዘ ሌይዚ ዶግ።” በዓማርኛ በ36 መርገጫዎች ተጽፎ 24 ስፍራዎች ይወስዳል። በእንግሊዝኛ በ37 መርገጫዎች ተጽፎ 36 ስፍራዎች ይወስዳል። [24] ይህ የእጅ ስልኮችንም ኣጠቃቀም ይመለከታል። ስለዚህ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ጊዜና ስፍራ ያስባክናል። ከላይ የኣሉት ሦስት ምሳሌዎች እንደሚያሳዩት በኣነሰ የኆኄያት ግድፈቶች አስፔሊንግ) እና ስፍራዎች ማስከተብ ብልጫዎች የነበረው የግዕዝ ፊደል በዶ/ር ኣበራ ግኝት የተነሳ የግዕዝ ፊደል ሓሳብን በኣነሰ ጊዜ መርገጫዎች እና ገበታ በማስከተብ ብልጫዎቹ ወደ ኣምስት ዓይነቶች ከፍ ብለዋል። ግዕዝ በእራሱ ፊደል እራሱን በዶክተሩ ግኝት ሲከትብ ከእንግሊዝኛው እስፔሊንግ ኣከታተብ የተሻለ ስለሆነ ግዕዝን በእንግሊዝኛ ፊደል እስፔሊንግ የሚያቀርቡትን ኣለመቃወም ሕዝቡን በማጃጃል ቀጥሎበታል። ግዕዝን ወደ ኮምፕዩተርና ጮሌ ስልክ ሲያስገቡ ፊደሉ የኣገኘውን ኣዲስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በሚገባ እንዲጠቀም ዶክተሩ አቅርበዋል፣ አስተምረዋልም። ይህ መሻሻል ስለኣለበት በየጊዜው መከታተል ያስፈልጋል። የአክሱም ሐውልት ስለ ዶ/ር አበራ ሞላ እና የአክሱም ሐውልት ከጣልያን ማስመለስ ጉዳይ ያውቁ ኖሯል? ጣልያኖች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከኣክሱም የዘረፉትን የኣክሱም ሓውልት እንዲመልሱ በ፲፱፻፵ ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ወስኖ ኢትዮጵያ እና ጣልያንም በጉዳዩ ተስማምተው ነበር። የተስማሙትም ጣልያን በኣሥራ ስምንት ወራት በወጪዋ ሓውልቱን ኢትዮጵያ መልሳ ኣክሱም እንድትተክል ነበር። ይህ ስለኣልተፈጸመ በፍርዱ መሠረትሓውልቱ እንዲመለስ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እና ኣቶ መለስ ዜናዊ ጠይቀው ጣልያን ለመመለስ ፈቃደኛ ኣልነበረችም። የሰውንም ልመና ስለኣልሰሙ ብስጭቱ ቀጠለ። በኋላም የተተከለበት ሮም ከተማ እንዳለ መብረቅ እንደመታው እንዲመለስ ኣቶ መለስ ዜናዊ ቢጠይቁም ሊያናግሯቸው እንኳን ፈቃደኞች ስለኣልሆኑና ጣልያኖች ስለኣልመለሱት የኢትዮጵያ ወዳጆች ሓውልቱ እንዲመለስ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ግንቦት ቀን ዓ.ም. በሮም ንግግራቸው መጠየቃቸው ይታወሳል። የሮም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞም ነበር። ቀደም ብሎም የኣንዳንድ ታዋቂ የዓለም ሰዎች፣ ኢትዮጵያውያንና የኣክሱም ሕዝብ የጥያቄ ፊርማ ጣልያኖችን ከኣለማስጨነቁም ሌላ ሓውልቱ ከተመለሰ ሥልጣኔን እለቃለሁ የኣሉም የጣልያን ባለሥልጣንም ነበሩ። ለኣለመመለስ ከቀረቡት ሰበቦች ሓውልቱ ጣልያን ኣገር ስለቆየ ጣልያናዊ ሆኗል፣ ቀደም ብሎ ፈቅዶት የነበረውን ገንዘብ የለንም በማለት፣ ሓውልቱ ስለኣረጀ ኢትዮጵያ ሲደርስ ይሰባበራል፣ በኣካባቢው ጦርነት ኣለ፣ በገንዘቡ ኣክሱም ያለውን ትልቁን የኣክሱም ሓውልት እንትከልበት፣ መመለስ የሚችለው ኣይሮፕላን ጦርነት ላይ ነው፣ ዓፄ ኃይለሥላሴ ሓውልቱን በስጦታ ለሮም ከተማ ሰጥተዋል ነበሩበት። ኢትዮጵያም ሓውልቱን ከፈለገች ለጣልያን መክፈል ኣለባት የኣሉም የጣልያን ኣክራሪ እንደነበሩ በኋላም ተደርሶበታል። ሓውልቱን መብረቅ ከመታው በኋላ ዶ/ር ኣበራም በግላቸው ለዩናይትድ እስቴትስ ፕሬዚደንት፣ ጥቂት ሴነተሮችና የኮንግረስ ወኪሎች እንዲረዱ የጻፉት ደብዳቤ መልስ ሳያገኝ ቀረ። በመጨረሻም ርዝመቱ 79 ጫማዎችና ክብደቱ 160 ቶን የሆነው ከ፲፯፻ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው የኣክሱም ሓውልት ሦስት ቁርጥራጮች ተደርጎ መጋዘን የተቀመጠው የትም ኣይሄድም ተብሎ በማዘናጋት ኣጀንዳ ቆየ። ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለስ ኣሜሪካ ኣውሮፕላንና ጣልያን ገንዝብ ከለከሉ የሚለውን የጦቢያ የካቲት ቀን ዓ.ም. 4, 2004) ጽሑፍ የዓዩትና የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክኸርስት በዩናይትድ እስቴትስ መማረር ያላስደሰታቸው ዶ/ር ኣበራ ሞላ ቅር ኣላቸው። በእዚህም የተነሳ ሓውልቱን በትናንሹ ኣስቆርጦ ገንዘብ ከዓለም ሕዝቦች ላይ በኢንተርኔት ማሰባሰብ እንደሚችሉ ኣዲስ ኣበባ ለሚገኘው የጣልያን ኤምባሲ በኢሜይል የካቲት ቀን ዓ.ም. ከዓሳወቁ በኋላ ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባው የጣልያን መንግሥት ወጪውን ከፍሎ ሓውልቱን እቦታው እንደሚተክለው ገለጸላቸው። በተጨማሪም ሌላ የጣልያን ኤምባሲ ባለሥልጣን የሆኑ ዶክተር ሰርቦ ሓውልቱን ለማስጫን ተስማሚ ኣውሮፕላን እያፈላለግን ነው ብለው መጋቢት ቀን ዓ.ም. 12, 2004) ለዶ/ር ኣበራ ኢሜይል ላኩ። ይኸንንም ለሓውልቱ መመለስ ለኣያሌ ዓመታት ሲታገሉ ለነበሩት ፕሮፌሰር ገልጸው ሓውልቱን መብረቅ ከመታው በኋላ ሊረዱዋቸው ስለጀመሩ በኢሜይል ይጻጻፉ ስለነበረ ላኩላቸው። ፕሮፌሰር ፓንክኸርስትም የዶክተሩን ሓሳብ ከሰሙ በኋላ የታችኛውን ሁለት ማስቆረጥም እንደሚያስፈልግና ገንዘብ ሊዋጣ እንደሚችል ጣልያኖችን ማሳወቅ እንዲከፍሉ ሊያስገድዳቸው ሳይችል እንደማይቀር ደግፈው ኣስታውቀዋቸው ነበር። ግንኙነት ስለኣልነበራቸው ለኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ግን ሳያሳውቁ ኣንዳንዶቹን ጽሑፎች ኢትዮፒክ.ኮም ድረገጻቸው ላይ ቢያስቀምጡም ብዙዎቹ ስለኣላነበቡት ጣልያን ወጪውን ለምን ለመክፈል እንደተስማማች ቢጻፍም በጊዜውና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሳይታወቅ የቆየ ይመስላል። ለኢትዮጵያ መንግሥት ግን ጣልያኖች ገንዘቡን እንደሚከፍሉ እስከ ሓምሌ ዓ.ም. ድረስ ያላሳወቁ ይመስላል። ጣልያኖች ቃላቸውን ደጋግመው ስለኣጠፉ እንደሚመልሱ የተስማሙበትንና የዶክተሩን ጉዳይ በሚገባ የሚያውቁት ፕሮፌሰር ፓንክኸርስትም ታግሰዋል። ስለ ገንዘብና ኣይሮፕላን መጥፋት ጣልያኖች ሲያወሩ መቆየታቸውን ዘ ጋርድያን ጋዜጣ 16, 2004) የኣተመው ኣንድ ምሳሌ ነው። በእዚህም ጊዜ (ሰኔ፣ ለሓውልቱ የብረት ማቀፊያ ተሠራለት። በመጨረሻም ሓውልቱ በ፺፰ ሲመለስ እንኳን ደስ ያለዎት የሚል የምስጋና ኢ.ሜይል ዶክተሩ ስለጉዳዩ ለዓመታት ለታገሉት ፕሮፌሰር ላኩ። ኤምባሲውም ዶ/ር ኣበራን ድንጋይ ከምታመላልስ ለረሃብተኛው ሕዝብ በገንዘቡ እህል ግዛበት ያለበትን ኢሜይል ኣስታውሰዋቸው ሓውልቱ ኢትዮጵያ ሲደርስ ፕሮፌሰሩ ደረሰኝ ብለው ከኣቀረቡት የእንግሊዝኛ ኢ.ሜይሎች መካከል የዶክተሩ ኣንዱ ነበር። ኣሜሪካኖችም የሓውልቱን ቁርጥራጮች ትክክለኛ መጠን ለማወቅ ተጠይቀው ያወጡትን ወጪና የኣክሱም ኣይሮፕላን ማረፊያ ችሎታ ያጠኑበትን ገንዘብ ጣልያኖች ኣልከፈሉንም ብለዋል። በእዚህ ኣኳኋን ወደ ስምንት ሚሊዮን ዶላር የጣልያን መንግሥት ወጪ ሓውልቱ በሩስያ ኣንቶኖቭ ኣይሮፕላን ከጣልያን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት መኃንዲሶች እርዳታና ሥራ (ኢንጂነር ክሮቺ) ኣክሱም ተተክሎ ነሓሴ ቀን ዓ.ም. ተመርቋል። ቪድዮዎችም እዚህ ኣሉ። ዓፄ ኃይለሥላሴ ሓውልቱን ጣልያኖች ከኣክሱም ሲወስዱትም ከመቃወማቸውም ሌላ ለብዙ ኣሥርት ዓመታት ሓውልቱ እንዲመለስ በሮም የኢትዮጵያ ኣምባሳደሮችና በየተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ወኪሎች ጠይቀዋል። የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኣክሱም እንዲመለስ በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግሥት የኢትዮጵያ ምክር ቤት ጠይቆ ነበር። ፕ/ር ፓንክኸርስት የኣክሱም ሓውልት ለኢትዮጵያ እንዳልተመለስ ለኣንድ የጣልያን ጋዜጣ በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. የጻፉትን የኣነበቡ ብሩኖ ኢምፔሪያሊ ለኣንድ ጋዜጣ የድጋፍ ደብዳቤ ጻፉ። የተጻፈውን የኣነበቡ ቪንሴንዞ ፍራንካቪግሊያ፣ ጁይሴፔ ኢንፍራንካ እና ኣልበርቶ ሮሲ የተባሉ ምሁራን ሓውልቱ እንዲመለስ ለጣልያን መንግሥት ደብዳቤ ከጻፉ በኋላ ፕሮፌሰሩም ይኸን ድጋፍ እንደሰሙ ኢትዮጵያውያን ፊርማ እንዲያሰባስቡ ጠየቁ። በእዚህም በመተባበር ከ500 ፊርማዎች በላይ በማሰባሰብ ከተሳተፉት መካከል ኣሰፋ ገብረማርያም፣ ልጅ ሚካኤል ዕምሩ፣ ሺፈራው በቀለ፣ ክሎውድ ሰምነር፣ ደኒስ ጀራርድ፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፣ ክቡር ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴ፣ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን፣ ተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ ተፈራ ደግፌ፣ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ ፕ/ር ኣቻምየለህ ደበላ፣ ፕ/ር ኣሸናፊ ከበደ፣ ካሳሁን ቸኮል፣ ሃሪ ችሃብራና ራስተፈሪያን ነበሩበት። በዓመቱም ፕሮፌሰሩን የጨመረ ሰዎች የኣሉት የኣስመላሽ ኮሚቴ ተቋቋመ። ፕ/ር ፓንክኸርስት ስለ ጉዳዩ ካነሱበትና ሌሎችም በእየጊዜው ሲጽፉ ሓውልቱን ለማስመለስ ከ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ጀምሮ የኣምስት ዓመታት የኣስተዋጽዖ ዝርዝር ውስጥ የሚከተሉት ኣሉበት። የኣዲስ ኣበባ ምክር ቤት፣ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጥያቄ ፊርማ፣ ፕ/ር እስቲቨን ሩበንሰን፣ ፕ/ር ደኒስ ማክ እስሚዝ፣ ኣቡነ ጳውሎስ ፭ተኛ፣ ዶ/ር ሳሊም ኣህመድ ሳሊም፣ ፕ/ር ፓስካል ጄ. ኢምፐራቶ፣ ፕ/ር ፍረደሪክ ጋምስት፣ ፕ/ር ኖርማ ኮምራዳ፣ ራጌሽዋር ሲንግ፣ ባማን ኣሊፍ፣ ዶ/ር ነቪል እስሚዝ፣ ሲይልቭያ ኤይሊንግ፣ ግለንዳ ጃክሰን፣ ኣቶ ገብሩ ኣሥራት፣ ፊታውራሪ ኣመዴ ለማ፣ ፊታውራሪ ኣበባየሁ ኣድማስ፣ ቀኛዝማች ቢያዝን ወንድወሰን፣ ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር፣ ሻለቃ ዻራርቱ ቱሉ፣ ዶ/ር ፈቃዱ ገዳሙ፣ ልዑልሥላሌ ተማሙ፣ ኢንጂነር ታደለ ብጡል፣ ተስፋዬ ዘለለው፣ ሚስስ ዊንዞፕ ቦዝወል፣ ኣንጀሎ ደል ቦካ፣ ዶናልድ ክረሜይ፣ ጆን እስፔንሰር፣ ዴቪድ በክስተን፣ ኣልበርቶ እስባክቺ፣ ሰይድ ሳማታር፣ ቪራጅ ጉፕታ፣ ፕ/ር ሃጋይ አርሊች፣ ሪቻርድ ግሪንፊልድ፣ ፒተር ጋረትሰን፣ ዩሪ ኮቢስቻኖቭ፣ ማርያ ራይት፣ ካትሱዮሺ ፋኩይ፣ ጃክ ጎትሌ፣ ፕ/ር ኢማኑኤል ሴሚ፣ ሮጀር ሽናይደር፣ ፕ/ር ክሪስቶፈር ክላፋም፣ ፕ/ር ፍረድሪክ ሃሊደይ፣ ፖውል ብሪትዝኪ፣ ኣሊ ማዝሩይ፣ ቶማስ ፓከንሃም፣ ኮህን ለጉም፣ ኬረን ዳልተን፣ ሆዜ ጃፊ፣ ፕ/ር ዊሊያም ዲያኪን፣ ዶ/ር ኪርስተን ፒደርሰን፣ ካትርይን ባርድ፣ ዶ/ር ረይደልፍ ሞልቬር፣ ኣይቫን ኣድለር፣ ዊልፍረድ ተሲገር፣ ግራሃም ሃንኮክ፣ ሰር በርናርድ ብሬይን፣ ሉትዝ ቤከር፣ ሮደሪክ ግሪየርሰን፣ ሪታ ማርሌይ፣ ጀርሜን ግሪር፣ ሲሮ ታደኦ፣ ኒኮላ ደማርኮ፣ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ፣ ፕ/ር ሥዩም ገብረእግዚኣብሔር፣ ዶ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ፕ/ር ኣሸናፊ ከበደ፣ ዶ/ር ካሳሁን ቸኮል፣ ዶ/ር ኣስፋወሰን ኣስራቴ፣ ልጅ ዘውዴ ኃይለማርያም፣ ሳሙኤል ፈረንጅ፣ ሪቻርድ ባልፍ፣ ሃሪ ካህን፣ ዶ/ር ካሳይ በጋሻው፣ ሪታ ፓንክኸርስት፣ ክቡር ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴ፣ ኣርቲስት ኣፈወርቅ ተክሌ፣ ሴጉን ኦሉሶላ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይገኙበታል። ሰለ ሓውልቱ ጉዳይ በየጊዜው በመጻፍ ከተራዱትም ውስጥ “ኢትዮፒያን ሪቪው” (ኤልያስ ክፍሌ)፣ “ኢትዮፕያን ሬጂስተር” (ግርማ በቀለ)፣ “ኢትዮፕያን ኮመንቴተር”፣ “ኣዲስ ትሪብዩን” እና “ቤዛ” ተጠቅሰዋል። ሓውልቱ እንዲመለስ እስከ ዓ.ም. እንቅስቃሴውን በመቀጠል ከተዘረዘሩት መካከል የሚከተሉት ኣሉበት። የኣክሱም ሓውልት ኣስመላሽ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ፣ ኣቶ ኃብተኣብ ባይሩ፣ ፕ/ር ሳሙኤል ኣሰፋ፣ ኣቶ ዳዊት ዮሓንስ፣ የኢትዮጵያ ፓርላማ፣ ፕ/ር ባሕሩ ዘውዴ፣ ማርኮ ቪጎኒ፣ የትግራይ ክልል ፓርላማ፣ ቶኒ ሂኬይ፣ ናፍታለም ኪሮስ፣ እስቲፈን ቤል፣ ኣልበርቶ ኢምፔሪያሊ፣ የሮም ኢትዮጵያውን፣ ጃራ ኃይለማርያም፣ ክቡር ኣቶ ወልደሚካኤል ጫሙ፣ ክቡር ኣቶ ሥዩም መስፍን፣ ፕ/ር ፍራንካቪግሊያ፣ በላይ ግደይ፣ ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ፣ ፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ፕ/ር ኣበበ ከበደ ክቡር ኣቶ ተሾመ ቶጋ፣ ጆርጅዮ ክሮቺ፣ የታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፊርማ፣ ፲፬ሺህ ፊርማ የፈረሙ የኣክሱም ሕዝብና ብዙ ሺህ ፊርማ ያለው በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያና ሌሎች የጥያቄ ፊርማ (ፔቲሽን)፣ የጥቂት ኣፍሪቃ ኣገሮች ኣምባሳደሮች ደብዳቤዎችና ሌሎችንም ጠቅሷል። ስለ ፊርማውም በማሰማት የቢቢሲ ሬድዮና ቴሌቪዥን፣ የካናዳ ሬድዮ፣ የእንንግሊዝ፣ የጣልያንና ኣንዳንድ የዓለም ጋዜጣዎች ትኩረት በመስጠት ረድተዋል። ኣንድ ቪድዮም ተሠርቶ ነበር። ለእዚህ ጉዳይ ከተረባረቡት መካከልም ብርሃኑ ተሰማ፣ ልዑልስገድ ተማሞ፣ ቢያዝን ወንድወሰን፣ ኣበባየሁ ኣዳማ፣ ኣፍሮሜት ኣሉላ ፓንክኸርስት፣ ታጋስ ኪንግ፣ ቶኒ ሂኪ፣ ሬናቶ ኢምፔሪያሊ፣ ጌይል ዋርደን እና ኣንድሩ ሎውረንስ ነበሩ። እዚህ የቀረበው በስም የተጠቀሱትን ብቻ ስለሆነ ወደፊት ማሟላትና ስለ እያንዳቸውም በስማቸው መጻፍ ይቻላል። ከእዚህ ሁሉ ድካም በኋላ ጣልያኖች ሓውልቱን እንደሚመልሱ ቃል ገብተው በ፲፱፻፺ ዓ.ም. ይመለሳል ተብሎ (ኢትዮጵያም ፕሮፌሰር ፓንክኸርስት የኣሉበት የኣክሱም ሓውልት ኣስመላሽ ኮሚቴ በ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ተቋቁሞም ስለነበረ (በ1988 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተጻፈ ደብዳቤ ለማስታወቂያና ባህል ሚኒስቴር ሐውልቱን ለማስመለስ የሚረዳ ብሔራዊ ኣስተባባሪ ኣካል እንዲቋቋም በተጠየቀው መሠረት፣ ሓውልት ኣስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴም ተቋቁሞ ነበር።) የጣልያን ፕሬዚደንት ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ይቅርታ ከጠየቁም በኋላ የመመለሱ ጉዳዩ በወሬ ቀረ። ይህ የኢትዮጵያና የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ስለ ሓውልቱ መመለስ ከተፈራረሙና ቴምብር ሁሉ ከተሠራ በኋላ ነበር። በመጨረሻም በዶ/ር ኣበበ ከበደ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ኔትወርክ በኩል ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስቴር በእንግሊዝኛና ጣልያንኛ የተጻፈው የልመና ደብዳቤ (14 2001) መልስ ሳያገኝ ቆይቶ በዓመቱ ግድም ሓውልቱን መብረቅ መታው። ሓውልቱን መብረቅ ሳይመታው ከስድስት ወራት ቀደም ብሎ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስርት ለጣልያኑ ኣቻቸው በነበሩት ውለታዎች መሠረት ሓውልቱ እንዲመለስ ደብዳቤ ጽፈው መልስ እንኳን ተነፈጋቸው። እንዲህም ሆኖ ሓውልቱ እንዲመለስ የደገፉ ጣልያኖች ነበሩ። የጣልያን መንግሥት ግን ለመመለስ ፈቃደኛ ስለኣልነበረ ተስፋ ተቆርጦ ነበር። የሓውልቱ መመለስ ጉዳይ እንደገና ያንሰራራው ጣልያኖች ሓውልቱን ሮም ሲተክሉት ብረት ኣስገቡበት እንጂ ከመብረቅ ስለኣልተከላከሉት ግንቦት ቀን ዓ.ም. 28, 2002) መብረቅ ከመታውና ከላይ በኩል ተሰብሮና ከተጎዳ በኋላ ነበር። ምክንያቱም ሌላ መብረቅ ቢመታው ሓውልት መሆኑ ቀርቶ የድንጋይ ክምር ሊሆን ስለሚችል ከልመና ያለፈ ኣስቸኳይ እርምጃ በኣንዳችን መወሰድ ስለነበረበት ነው ዶክተሩ በግላቸውና በብቸኝነት በጉዳዩ የገቡበት። የሚያሳዝነው ግን ሓውልቱን መብረቅ ከመታውም በኋላ እንኳን ለኢትዮጵያ እንዳይመለስ ተቋውሞ መቀጠል ነበር። ከእዚህ በላይ ለተዘረዘሩትና ሌሎችም ለኢትዮጵያ ስለ ኣደረጉት ኣስተዋጽዖ በተለይ ለፕሮፌሰር ፓንክኸርስት እግዜር ውለታቸውን ይመልስልን። ጣልያኖች የኣድዋን ድል ለመበቀልና ኢትዮጵያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጣልያንን ለሁለተኛ ጊዜ ስለ ኣሸነፈች ተበሳጭተው ሓውልቱ ላይ ቢንጠላጠሉም ከኣክሱም የወሰዱትን ሓውልት ሌላ ትውልድ ኣስመልሷል። ታሪኩ እንዳይጠፋ ኣንድ ቦታ መጻፍ ተገቢ ነው። ሓውልቱም ግዙፍ፣ ታዋቂና ተደናቂ በተባበሩት መንግሥታት የተመዘገበ የዓለም ቅርስ እንጂ ጉራም ኣይደለም። ይህ ሲደረግም በየተባበሩት መንግሥታት ስምምነት መሠረት ይኸን ትልቅ ቅርሷን ለማስመለስ ለዓመታት ስትታገል ኢትዮጵያን የረዳት መንግሥት ኣልነበረም። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት እንኳን ሓውልቱን መብረቅ ከመታው በኋላ ለኢትዮጵያ ይመለስ ኣላለም። ማንም ኣያስገድደንም ብለው የዓለም ሕዝቦች ላይ ሲቀልዱ የነበሩትን ጣልያኖች ኣንድ ሰው ሊያስመልሰውና እንደሚዋረዱ ኣስጠንቅቆ ሓውልቱን በማስገደድ ከማስመለስ በስተጀርባ ትምህርትነትም ኣሉት። ጣልያኖች የኣክሱምን ሓውልት ዘርፈው ከ፷፱ ዓመታት በኋላ በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. የመለሱት በዶክተሩ እንዳይዋረዱ ተገድደው እንጂ ወደ'ው ኣይደለም። ጣልያኖች በዶክተሩ ያለጉራ የተሰጣቸውን በጎ ፈቃድ ተጠቅመው ሓውልቱን ቢመልሱም በፈቃዳችን መለስን ብለው ሸንግለዋል። ምክንያቱም በፈቃድ ለመመለስ ብዙ ኣሥርት ዓመታት መፍጀት ባላስፈለገ ነበር። በፈቃድ ለመመለስ ቆራርጠው ድንጋያችሁን ውሰዱ በኣላሉ ነበር። በፈቃድ ለመመለስ ቆራርጠው ከኣስቀመጡበት ሮም ከተማ ለዘለዓለሙ የትም ኣይሄድም በኣላሉ ነበር። ከእዚያም ወዲህ ከዘረፏቸው መካከል እንኳን በፈቃዳቸው ተለምነውም ለኢትዮጵያ የመለሱት ሌላ ቅርስ የለም። የኢትዮጵያ መሪዎች ሥልጣን ላይ ሲያተኵሩ ግፍ የሠሩባት ለፍርድ ሳይቀርቡና በቢሊዮን ዶላሮች ሊቈጠር የሚችል ካሳ ጣልያንን ኣልኣስከፈሉም። (ሆኖም ሓውልቱ ሮም ሲነቀልና ኢትዮጵያም ሲተከል ጣልያኖች ከኢትዮጵያውያን ጋር ተባብረዋል።) ግን፤ ይባስ ብለው ጣልያኖች በ፳፻፬ ዓ.ም. ለግፈኛው ግራዚያኒ ሓውልት ስለሠሩ ከታሪክ መማር ሳይጠቅመን ኣይቀርም። የቫቲካን ካቶሊክ ጳጳሶችም ከፋሺስት ጋር በመተባበር ወረራውን ቄሶቻቸው ስለባረኩና ስለሌሎች ጥፋቶችም ይቅርታ መጠየቅ እንኳን ከብዷቸዋል። በእዚህ ጉዳይ ለሃገር በመቈርቈር ኢትዮጵያ ፍትሕ እንድታገኝ የሚታገሉ ኣሉ፦ ኪዳኔ ዓለማየሁ። የኣሁኖቹም መሪዎች ስልጣን ላይ እየኣሉ ጣልያን ለግራዚያኒን የሠራችውን ሓውልት እስክታፈርስ (እንደእነ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም የኣሉትን ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ከማሰር ይልቅ ዲፕሎማቲክ ግንኙነት ማቋረጥ ያንስባቸዋል። በ፳፻፮ ዓ.ም. ጄፍ ፒይርስ የሚባሉ ታዋቂ ካናዲያዊ ደራሲ ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግንነትና ጣልያንን በድጋሚ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በማሸነፍ ዓለምን እንደቀየሯት በጻፉት 978-1-62914-528-0 አና 978-1-63220-096-9) መጽሓፋቸው የኢትዮጵያን በደል የማይረሱ ዛሬም እንዳሉ በማሳሰብ ስለ ኣክሱም ሓውልት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ሲያሰፍሩ ዶክተሩን ገጽ 552 ላይ ጠቅሰዋል። በማለት ጽፈዋል። የፒይርስን መጽሓፍ መግቢያ የጻፉት ፓንክኸርስት ናቸው። ስለ ዶክተሩ ኣስተዋጽዖ የኣሰሙም ጥቂቶች ኣሉ። ኢትዮጵያን-ኣሜሪካን ፎረም ዶክተሩን የ2013 የዓመቱ ሰው በማለት ዕውቅና ሲሰጣቸው ከኣቀረባቸው ሥራዎቻቸው ኣንዱ ጣልያን የኣክሱምን ሓውልት በወጪዋ ስለኣልመለሰች እሳቸው ገንዘቡን ከዓለም ሕዝቦች በማሰባሰብ ሓውልቱን በትናንሹ ኣስቆርጠው ወደ ኢትዮጵያ ሊያስወስዱ እንደሚችሉ ከኣስፈራሩ በኋላ መሳካቱን ጠቅሷል። በሓምሌ ዓ.ም. ዶክተር ኣበራ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙበት የዝነኛው ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተቋም የግብዣ ደብዳቤ ትርጕም እንደሚከተለው ነበር። “ዓማርኛን ዲጂታይዝ በማድረግዎ ተወዳዳሪ የሌለው ዘመናዊ እድገት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖር ኣድርገዋል፣ እንዲሁም ተጽንእዎ ባህላዊ ቅርሶችን ወደ ማስጠበቅ ዘልቆ የኣክሱምን ሓውልት ወደ ትግራይ ሲያስመልሱ በጉዳዩ ባይገቡበት ኖሮ ይህ የኢትዮጵያ ቅርስ ላይመለስ ይችል ነበር” ይላል። የኢትዮጵያን ቅርሶች በማስከበርና በጥሩ ዓርዓያነት እ.ኤ.ኣ. በ2016 ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። በቅርቡም በፕሮፌሰር ፓንክኸርስት ከእዚህ ዓለም በሞት መለየት የተነሳ ሓውልቱን ኣስመልክቶ ከሰይፉ ብሻው ጋር የተደረገ ቃለምልልስ እዚህ ኣለ። ቀደም ብሎም ከኢሳት ሲሳይ ኣጌና ጋር በተደረገው ቃለ ምልልስ ስለ ኣክሱም ሓውልት ኣስተዋፅዖዋቸው እዚህ ነበር። ዶክተሩ ከብዙ ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ ሄደው ሳለ የኣክሱምን ሓውልት ጎብኝተዋል። በኅዳር የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማሕበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ የዕውቅና ሽልማት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ሲሰጥ ከጠቀሳቸው ኣንዱ የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጣልያንን በማስፈራራት ወሳኙን እርምጃ የወሰዱ ኣርበኛ መሆናቸውን ነበር። በግንቦት 2008 ዓ.ም. በኣገራዊ የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ኣዲስ ኣበባ ሲደረግ ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሌሎች 250 ሰዎችና ለሓውልቱ መመለስ ጥረት ያደረጉ የኣስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ አባላትና ባለሃብቶችን የኣካበተ ነበር። ለጥረቱ ሽልማት መሰጠት ያስፈለገው ኣንዳቸው ኣሜሪካ መጥተው ሓውልቱን ኣስመለስኩ ሲሉ ማን እንዳስመለሰ ከተነገራቸው በኋላ ነበር። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ስለ ዓማርኛ የጽሕፈት መኪና በዓማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ የተጻፉ ኢንተርኔት ላይ ብዙ የሉም። በእንግሊዝኛው እንደሚደረገው ኢትዮጵያውያን ፊደላቸውን በመጻፊያ መኪና መሣሪያ አማርኛ ታይፕራይተር) ለመጠቀም ተመራምረው ከደረሱበት ዘዴ ፊደላቱን ቆራርጦ መቀጠል የኢ/ር ኣያና ብሩ የ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. (እ..ኤ.ኣ. 1932) ገደማ ግኝት ሥራ ላይ ውሏል። በእዚህ የተነሳ ኢንጂነሩ ለኢትዮጵያ ባለውለታ ሊቅ ናቸው። ከመቶ በታች መርገጫዎች የኣሉት የእንግሊዝኛ የመጻፊያ መሣሪያ ከሁለት መቶ በላይ ለሆኑት የዓማርኛ ቀለሞች እንዲብቃቃ ፊደላቱን ቆራርጦ መቀጠል ኣስፈለገ። “ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ” እና “ሠ” ኣሉ እንጂ “ሁ”፣ “ሉ”፣ “ሑ”፣ “ሙ” እና “ሡ” ስለሌሉ የመቀነስ ምልክትን የመሰለ ከሌላ መርገጫ በመክተብ “ሀ”፣ “ለ”፣ “ሐ”፣ “መ” እና “ሠ” ጎን በማስቀመጥ ቅጥሎቹ ካዕቦቹን ስለሚመስሉ ተመልካቹ እንዲቀበላቸው ሆነ። ኣንዱን መቀጠያ ብዙ ቀለሞች ሊጋሩት ስለሚችሉ የሁሉም ቀለሞች በኣለመኖር የተነሳ መርገጫዎች መቆጠብ ተቻለ። “ሃ” እና “ማ’ እንጂ “ሂ”፣ “ሚ”፣ “ሄ” እና “ሜ” ስለሌሉ “ሃ” እና “ማ” እግሮች ጎን መስመር ወይም ቀለበት በማስቀመጥ እነዚያን በሚመስሉ ቅጥሎች እንድንጠቀም ሆነ። እነ “ቻ”ን የመሰሉ ቀለሞች ከታችና ከላይ ከሁለት መርገጫዎች “ተ” ላይ በሚቀጠሉ ነገሮች ስፍራው ወደኋላ እየተመለሰ ሦስት ነገሮች ኣንድ ፊደል እንዲመስል ተሠሩ። ስፍራ ስለኣነሰ እንደነ “ኳ” ያሉ ቀለሞች “ካ” ስር በተቀመጠ መስመር በሚሠሩ ኣዳዲስ ቀለሞች ተተኩ። የ“ላ”ን ግራ እግር ማሳጠር ስለኣልተቻለ “ለ” ቀኝ እግር ላይ ከመስመር በታች በወረደ መቀጠያ የ“ለ” ቀኝ እግር ረዝሞ ያልተለመደ መልክ ይዞ ቀረበ። በመቀጠል ሊሠሩ ለማይችሉ ቀለሞች የእራሳቸው ስፍራ ሲሰጣቸው ቦታ ስለኣልበቃ ካልገቡት መካከል የዓማርኛ ኣራት ነጥብ ኣሉበት። ስለዚህ የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና የተመረኮዘውና ኣከታተቡ የተንፏቀቀ ፊደል በኣንድ የእንግሊዝኛ ገበታ ምትክ መቀጠል ላይ ነው። የዓማርኛ ቀለም ግን እያንዳንዱ እራሱን የቻለ ስለሆነና ኣንድ የእንግሊዝኛ የፊደል ገበታ ስለማይበቃው የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ፊደል ዓማርኛ ኣይደለም። ፊደላት ለኮምፕዩተር ሲሠሩ ተለያይተው እንዲቀርቡ ሲደረግ የታይፕራይተሮቹ ግን እንዲነካኩ ተንፏቅቀው የተሠሩ ስለሆኑ ቦታዎቻቸውን የኣልጠበቁም ናቸው። ይህ ሁሉ ሲደረግ እንደእነ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የመሳሰሉት ሲጠቀሙ የነበሩት በትክክለኛዎቹ የግዕዝ ቀለሞች ነበር። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ተጀምሮ በደርግ ዘመን የኣበቃ የ፶ ዓመታት ግድም ዕድሜ የነበረው ቴክኖሎጂ ነው። የኣማርኛ ታይፕራይተር የሠሩ ሌሎችም ኣሉ። የኣማርኛ ታይፕራይተር ቴክኖሎጂ ያበቃለትም ዶክተር ኣበራ ሞላ የግዕዝን ፊደል ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው እ.ኤ.ኣ. በ1987 ሞዴትን ለገበያ ኣሜሪካ ውስጥ ስለኣቀረቡ ነበር። ስለዚሁ እውነታ ማቲው ሊንዳ በቅርቡ እንደጻፉት ዶ/ር ኣበራ ሞላ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ በማድረግ የዓማርኛውን ታይፕራይተር ሥራ ኣጥ ኣድርገውታል ይላል። 25 2, 2022, 425-442. .2022.0015. /872061 የዓማርኛ ፊደል የመክተቢያ ገበታና ዘዴ ስለ ኣልነበሩት ዶክተሩ ፊደሉን ወደ ኮምፕዩተር ሲያስገቡ ዘዴዎቹን ለመጀሪያ ጊዜ ከመፍጠር ሌላ የዓማርኛ የመጻፊያ መኪና ቅጥልጥል ፊደልና ኣከታተቡ ወደ ኮምፕዩተር እንዳይገባ ጽፈዋል። ኣንዳንዶቹም የቆዩና ኣዳዲስ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው። ፩ኛ. የዓማርኛ ፊደላት ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆኑ ዓማርኛ ያልሆኑ ፊደላት መኖር ዋጋ የለውም። በእንግሊዝኛው የጽሕፈት መኪና በዓማርኛ ለመጠቀም የተሠራው ዘዴ ጊዜው ያለፈበት ቴክኖሎጂ ነው። እንኳን ዓማርኛውን የማይጽፍ የጽሕፈት መኪና በሚገባ እንግሊዝኛውን የሚጽፈው የእንግሊኛ የጽሕፈት መኪና ዋጋ ኣጥቶ ሙዚየም ገብቷል። ስለዚህ የኮምፕዩተር ኣከታተብ ማሰልጠኛዎች የኣማርኛ ታይፕራይተር ኣከታተብ ማስተማር መተው ይጠበቅባቸዋል። ፪ኛ. የእንግሊዝኛው የመጻፊያ መኪና የተሠራው ለእያንዳንዱ የላቲን ፊደል መክተቢያና የመርገጫ ስም በመመደብ ሲሆን የዓማርኛው የመጻፊያ መኪና እነዚያን የሉትም። ዶክተሩ ለግዕዙ መክተቢያና የመርገጫ ስም ለመጀመሪያ ጊዜ ለኮምፕዩተር ፈጥረውለታል። ፫ኛ. የዓማርኛ የመኪና ፊደላት የሚሠሩት ለተወሰነ መጠን ተስተካክለው ወረቀት ላይ እንዲሰፍሩ ነው። በኮምፕዩተር ግን ኣንዱን መጠን መጨመርና መቀነስ ይቻላል። የመኪና ፊደላት ቁርጥራጮች መጠን ሲለወጥ ቅጥሎቹ ይደበቃሉ ወይም ክፍተታቸው ይጨምራል። የገጹ ስፋት ሲጠ'ብ ወይም ሲሰፋ ቅጥሎቹ ብቻቸውን ወደ ኣዲስ መስመር ሊዞሩ ይችላሉ። ቅጥሎቹ ስለሚበጣጠሱ ማሕተምን የመሳሰሉ ነገሮች ኣያሠሩም። ስለዚህ ቅጥልጥል የመኪና ቀለሞች የትክክለኛው ፊደል ተጠጊ እንጂ እራሳቸውን ችለው ሁሉንም ሥራዎች ስለማያሠሩ ኣስፈላጊ ኣይደሉም ብለው ዶክተሩ ጽፈዋል። በቅጥሎች ተንቀሳቃሽ የሚገላበጡ የሲኒማ፣ ቴሌቪዥና ቪድዮ ፊደላት ሊሠሩባቸው ኣይችልም። ፬ኛ. የላቲኑ የመጻፊያ መኪና እያንዳንዱን ቀለም የሚከትበው በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ሲሆን የዓማርኛው መኪና ከእዚያ በላይ መርጫዎችን ይጠይቃል። ስለዚህ ዓማርኛ ሳያስጽፍ ብዙ መርገጫዎችን መነካካት በሚያስፈልግ ዘዴ ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ከቀረበ ከ፴ ዓመታት በኋላ ዛሬም በ፳፻፱ ዓ.ም. መቀጣጠል ጥቅም የለውም። በኣብሻ ሥርዓት የተከተበውን ትክክለኛ ቀለም ለመሰረዝም ኣንድ መርገጫ በቂ ነው። ለኣስቀጣይና ተቀጣይ ግን ኣንድ መሰረዣ በቂ ኣይደለም። ፭ኛ. ወረቀት ላይ ሲሰፍሩም ሆነ የኮምፕዩተር እስክሪን ወይም መዝገብ ኣብዛኛዎቹ የዓማርኛ መኪና ፊደላት ከኣንድ በላይ ስፍራና ኮድ ይጠይቃሉ። ይህ ወጪ ያስጨምራል። የግዕዝና የላቲን የኮምፕዩተር ፊደላት እያንዳንዳቸው የሚያስፈልጓቸው ኣንድ ስፍራ ብቻ ነው። ፮ኛ. የፊደል ዋና ዓይነቶች ሁለት ናቸው። ኣንደኛው የሁሉም ቀለሞች ስፋት እኩል ሲሆን ሌላው የተለያዩ ስፋቶች ያለው ነው። በቅጥልጥል የዓማርኛ የመጻፊያ መኪና ቁርጥራጮች ስፋታቸው እኩል የሆኑ ቀለሞች መሥራት ኣይቻልም። በእንግሊዝኛና ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት ግዕዝ ቀለሞች ሁለቱንም ዓይነቶች መሥራት ይቻላል። ፯ኛ. ስፍራ ስለኣነሰ የግዕዝ ኣኃዞች ቀርተው የእንግሊዝኛው ቍጥሮች ብቻ የዓማርኛው ኣኃዛት ሆነው በዓማርኛው የጽሕፈት መኪና ቀርበዋል። ይህ ለግዕዙ ኣኃዞች መዳከም ኣንዱ ምክንያት ሆኗል። ግዕዝን ዲጂታይዝ ከማድረግ ሌላ ኣኃዞቹን ለማሟላት ዶክተሩ የግዕዝ ኣልቦ ሠርተው በማሰተዋወቅ ቊጥሮቹን ኣሟልተዋል። ስለዚህ በኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ድክመትና በግዕዝ ኣልቦ ኣለመኖር የተዳከሙት ኣኃዞቻችንን ኣሁን መጠቀም ይጠበቅብናል። በዶክተሩ ግኝት የተነሳ የግዕዝ ኣኃዞች ሠላሳ ናቸው። ፰ኛ. ለዓማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ እንዲስማማ ተብሎ ፊደል መቀነስና መቀንጠስ ተለምዶ ዶክተሩ ሁሉንም ቀለሞች ኮምፕዩተራይዝ ከኣደረጉ በኋላም መቀነስና መቀንጠስ እንደማያስፈልግ ግንዛቤ ማስጨበጥ ማስቸገሩ ቀጥሏል። ለምሳሌ ያህል “ኳ”ን በ“ኩዋ” ማንበብ የሚፈልጉ ሲኖሩ ፊደሉን ኣጥፍተው በ“ካ” እና መቀጠያው ሲጠቀሙ የከረሙ ስለኣላዋጣቸው የቆራረጡትን እንደመተው መልሰው በመቀጠል የኣሌለ መልከ-ጥፉ ኣዳዲስ ቀለሞች በመጨመር እያስለመዱ ናቸው። "ኳ" እራሱን የቻለ መስመር ላይ የሚያርፍ ቀለም ነው። "ካ" ላይ በተቀጠለ መስመር ተሠርቶ በኣዲስ ቅርጽነት የተሠራው የተሳሳተ ፊደል ነው። ለምሳሌ ያህል የ"ጡ"ን መቀጠያ ለ"ኩ" የሰጠ ኣለ። የማተሚያ ቤቶች መደበኛው ፊደል ተቆራርጦ ሲቀርብ ቅጥልጥል ዓማርኛ ያልሆነ ፊደል ይኸን ይመስላል። ለኣንዳንቹም ይኸን ፊደል ከኣልተቀጠሉት የማተሚያ ቤቶች ቀለሞች መለየት ስለተሳናቸው ኣሁንም እየተወናበዱ ነው። ምክንያቱም የዓማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ እንደ "ቋ" የኣሉትን ቀለሞች ስለሌሉት ከ"ቀ" እና መስመር በመቀጠል ሲያቀርቡ የነበሩትን እንደ ኣዲስ ፊደል የዩኒኮድ ፊደል መደብ እያቀረቡ ግዕዝ ያልሆኑ ነገሮችን በማሰራጨት ሰውን እያስቸገሩ ናቸው። የ"የ"ን እንዚራን ለማይለዩ ኣንዳኣንድ ምሁራን ሁለት ዓይነት "ቋ"፣ "ኋ"፣ "ኳ" እና "ጓ" ዓይነት ቀለሞች ማቅረብ የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም ኣይደለም። ትክክለኛዎቹ የግዕዝ "ቋ"፣ "ኋ"፣ "ኳ" እና "ጓ" የእየእራሳቸው መልኮች ያሏቸው መስመር ላይ የሚያርፉ ቀለሞች ናቸው። በተጨማሪም ትክክለኛዎቹን ቀለሞች የሚያዩት የዶክተሩን ፊደል ወይም ትክክለኛዎቹን ያሏቸው እንጂ በተሳሳቱ ቀለሞች የሚያዩት የተሳሳቱትን ስለሆነ መወናበዳቸውን ላይረዱ ይችላሉ። ፱ኛ. ከሚያስገርሙት ነገሮች መካከል ኣንዱን ለመጥቀስ ያህል 128 ስፍራዎች ይበቃሉ ብለው ሌሎች ለዩኒኮድ ሲያቀርቡ (ገልባጮች እንጂ) ከዶክተሩ በስተቀር ለዓማርኛ እንኳን እንደማይበቃ የሚያስተውሉና የሚጽፉ ምሁራን መጥፋት ነበር። በኋላም ቢሆን ቅጥልጥሎቹ እንደማያዋጡ ገባቸው እንጂ ሞዴት ፕሮግራም ውስጥ ጭምር የኣሉት የኣናሳ ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ቀለሞች በቅጥልጥል እንዲሠሩ ስለፈለጉ የዩኒኮድ መደብ ውስጥ እንዳይገቡ በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ሌሎች ኣስወግደዋቸው ነበር። ፲ኛ. የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና መሣሪያዎች ቁርጥራጮች፣ ኣከታተቦቻቸውና ኣመዳደቦች የተለያዩ ስለሆኑ ኣይናበቡም። ፲፩ኛ. የጽሕፈት መጻፊያ መሣሪያ ዓላማ በዓማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ ፊደል ለመክተብ ነበር። ዓማርኛ የሚያስጽፍ የጽሕፈት መሣሪያ ግን ስለሌለ የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ዓላማ ቁርጥራጮችን ለመቀጣጠል ነው። ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ መቀጣጠል ኣስፈላጊ ኣይደለም። ምክንያቱም እያንዳንዱ የግዕዝ ኆኄ እራሱን የቻለ ቀለም እንጂ ቅጥልጥል ፊደል ኣይደለም። ፲፪ኛ. ቁርጥራጮቹ የተመደቡባቸው ስፍራዎች መደበኛ ስለኣልሆኑ ፕሮግራም በተቀየረ ቍጥር ለደራሲው እንኳን ላይነበቡ ይችላሉ። ፲፫ኛ. ጽሑፉ የተጻፈበት ቁርጥራጮች ከሌሉ ጽሑፉ ኣይነበብም። በግዕዝ ዩኒኮድ የተጻፈ ጽሑፍ ኮምፕዩተሩ ወይም የእጅ ስልክ ላይ በኣለው ኣንዱ የዩኒኮድ ፊደል ይነበባል። ጽሑፉን ኣቅልሞ ወደ ሌላ የግዕዝ ፊደል መልክ መቀየር ይቻላል። የታይፕ ቈርጥራጮች ዓማርኛ እንኳን ስለኣልሆኑ ወደ ዩኒኮድ ፊደል ሲቀየሩ ዝብርቅርቅ የላቲን ፊደል ይሆናሉ። ፲፬ኛ. ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ የላቲን ምልክቶችንና ሌሎችንም ለግዕዝ ኣውርሰዋል። የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና መሣሪያዎች እንኳን ሌሎች የላቲን ምልክቶች መጨመር ሁሉንም ቀለሞች በመቀጣጠል በኣማርኛ እንኳን ኣያሠሩም። ፲፭ኛ. ኣንድን ጽሑፍ ለማረም ወይም ለማሻሻል የተጻፈበትን ኣከታተብ ዘዴ ዕውቅናና የመጻፊያው ኮምፕዩተሩ ላይ መኖርን ይጠይቃል። በነፃውና በሚሸጠው ግዕዝኤዲት ሲጻፍ የፊደል ገበታው እየታየ በመልቀም እንኳን መክተብ ይቻላል። በዩኒኮድ ፊደል የተጻፉትን በነፃው ግዕዝኤዲት ድረገጽ ላይ በመለጠፍ ማረምና ማሻሻል ይቻላል። በታይፕራይተር የተጻፉ ጽሑፎች ነፃው ግዕዝኤዲት ድረገጽ ላይ ሲለጠፉ ዝብርቅርቅ የእንግሊዝኛ ፊደል ሆነው ስለሚታዩ ማረምና ማሻሻል ኣይቻልም። ፲፮ኛ. የግዕዝ "ሀሁሂ" ቀለሞች እንደ እንግሊዝኛው ስለሆኑ ትክክለኛና የተወስኑ መልኮች ስለኣሏቸው ፊደል የቈጠረ ሁሉ ያውቃቸዋል። ከኣስቀያሚ ቆብ፣ ሠረዞችና ቀለበቶች ሲሠሩ የነበሩት የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ቀለሞች ቀርተው ትክክለኛውን የማተሚያ ቤት ቀለሞች ወይንም ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ ያደገረጉትን ቀለሞች መቆራረጥ ስለተጀመረ መለየት እያስቸገረ ነው። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ኣፍቃርያን በጀመሩት ሳይንሳዊ ያልሆነ ግትርነት ኣንድ ስፍራ የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ሊቀርብ ይችል የነበረው የግዕዝ ቀለም ኣራት የተለያዩ ስፍራዎች ተበትኗል። የዓማርኛ ሞክሼዎች ይቀነሱ የሚለው ኃሳብ የመጣው ለኣማርኛው የጽሕፈት መሣሪያ ሲባልም ስለነበረ ያልተቀነሱትን ቀለማት ብቻ ማስተማር የቆዩ ጽሑፎችን ማንበብ የማይችል ትውልድ ሊያስከትል ይችላል። የግዕዝ ኣኃዛት የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ውስጥ ስለኣልነበሩ በኣሁኑ ጊዜ የዓማርኛ ኣኃዞችን የማይለዩ ምሁራን ኣሉ። የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ኣጻጻፍ ኣንዳንዱን ቀለም ለመክተብ እስከ ኣራት መርገጫዎችን መጠቀም ስለሚያስከትል ትርፉ እጅ ማሳመም ነው ተብሎ ወደ ዓ.ም. ግድም ተጽፏል። የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና በኣንድ የእንግሊዝኛ የፊደል ገበታ ምትክ እንዲያገለግል የተሠራው ጊዜው ያለፈበት ቴክኖሎጂና ያልተሟላ ከመሆኑም ሌላ ሊሻሻልም የማይችል ስለሆነ ቀርቷል። ዩኒኮድ የተፈጠረው ብዙ መርገጫዎች ላይ የተበተኑትን ዶክተሩ ኮምፕዩተራዝ ያደረጉት የግዕዝ ቀለሞች የእየራሳቸው ኮዶች እንዲኖራቸው እንጂ ለቅጥልጥሎች ኣይደለም። ቅጥልጥልና ግማሽ ፊደሎችን ዩኒኮድ ኣያውቅም። የእንግሊዝኛ የመጻፊያ መሣሪያ እንግሊዝኛ ቀለሞችን ስለሚያጽፍ የእንግሊዝኛ የኮምፕዩተር ገበታ ሆኗል። የኣማርኛ የጽሕፈት መኪና ዓማርኛ ስለኣልጻፈና ስለማያጽፍ የዓማርኛ የኮምፕዩተር ገበታ መሆን የለበትም። ኣልሆነምም። ይህ የተዘረዘሩትንም ለማክ ኮምፕዩተሮች የቀረቡትንም ያጠቃልላል። የአማርኛ ታይፕራይተር ኮምፕዩተራይዝ ከተደረገ በኋላ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣደረግን ከኣሉት ኣንዳንዶቹ ጥፋታቸውን ማረም ስለተቸገሩ እንዳይዋረዱ ዝም ስለተባሉ ኤክስቴንድድ ኣስኪ የሚችለው ስፍራ ላይ ቁርጥራጮችን ኣቅርበው ተጠቃሚውን ከሃያ ዓመታት በኋላም ማታለል መቀጠላቸው በየቃለምልልሶቹ ቀርበዋል። ትክክለኛ የግዕዝ ፊደል መስለዋቸው በተቀጣጠሉ ፊደላት የተለያዩ ጽሑፎችና መጽሓፍት ሲጽፉ የከረሙ መታለላቸው ሲገባቸው የተበሳጩና እርዱን የኣሉን ኣሉ። በትክክለኛ ፊደላችን የተጻፉትን ወደፊት በተለያዩ ዓይነቶች ማቅረብ ስለሚቻል መጽሓፎችንም በኢንተርኔት መሸጥና ማንበብ ይቻላል፦ ምሳሌ ፳፫. በኣማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ ዓማርኛ ብሬል መጻፍ ኣስቸጋሪ ነው። ኢንጂነር ተረፈ ራስወርቅ በቅጥልቅል የዓማርኛ ፊደል የሚሠራ የመጀመሪያውን ቴሌክስ መሣሪያ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው። ዓማርኛ ያልሆነውን የቅጥልጥቅል ፊደልና የኢትዮጵያን ፊደላት የማይለዩ ኢንጂነሩ የኣልኣሠሩትን በፊደሉ ኣሠሩ የእሚል ጽሑፍ እዚህ ኣለ። ኣንዳንድ ደራስያን ስለ ሳይንስ ከመጻፋቸው በፊት መረጃዎችን መመልከት ቢጀምሩና ቢያቀርቡ ሳይጠቅም ኣይቀርም። ምክንያቱም ኮምፕዩተር የኢትዮጵያን ፊደላትና ኣኃዞች የተረከበው በኮምፕዩተር ዘመን ከማተሚያ ቤቶች እንጂ ችሎታውን ከኣልነበረው የቴሌክስ መሣሪያና ዘመን ኣልነበረም። አንዲሁም ኮምፕዩተር የኢትዮጵያን ፊደላትና ኣኃዞች የተረከበው በኮምፕዩተር ዘመን ከማተሚያ ቤቶች እንጂ ችሎታውን ከኣልነበረው የኣማርኛ የጽሕፈት መሣሪያና ዘመን ኣልነበረም። የኣማርኛ ታይፕራይተርና ለኮምፕዩተር የተሠራው ፊደሉ እንኳን ግዕዝን ኣማርኛ ቀለሞች ኣላስከተበም። በኣንድ የእንግሊዝኛ መደብ ምትክ የተሠራውን የኣማርኛ የጽሕፈት መኪናና የኮምፕዩተር ቅጥልጥል ፊደል በሓሰት ግዕዝ ነው በማለት ሰውን የሚያወናብዱ ኣሉ። ኣንድ የእንግሊዝኛ ፊደል ሥፍራ ለኣማርኛ ስለማይበቃ ሳይንስን ኣለመደገፍና እነዚህን ኣለመቃወም ግዕዙን እያበላሸው ነው። ግዕዝን ዲጂታይዝ ወይም ኮምፕዩተራይዝ ማድረግ ሳይንስ እንጂ ልብወለድ ኣይደለም። የኣማርኛውን ታይፕራይተር ፊደል ዲጂታይዝ ኣድርጎ ግዕዝን ዲጂታይዝ ኣደረግሁ የሚለውን በዝምታ ማሳለፍ ቦዘኔ ምሁራን ሳይንስን ወደ ልብወለድ እንዲቀይሩ እያበረታታ ነው። የታይፕራይተር ቁርጥራጮችን ኣቅርቦ ከማተሚያ ቤት ኣዲስ ዘመን ጋዜጣ ፊደላት ዓይነቶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው የሚለውን ወሬኛ ወይም "ሶ"ን ፊደል ለመጻፍ የ"ሰ" ግራ እግር ላይ መሰመር ጨምሮ የ"ሰ"ን ቀኝ እግር ኣሳጠርኩ የሚለውን ወይም የግዕዝ ፓተንት ሳይኖርው ኣለኝ የሚለውን የኣለመረጃ የሚያሳልፍ ጋዜጠኛ መተቸት ካልቻልን ፊደላችን ከኩራታችን ምንጭች ኣንዱ መሆኑ ቀርቶ የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ ሊያደርገን ይችላል። ይህ ለኢትዮጵያ የሚጠቅሙ ሥራዎች የሠሩ ኢትዮጵያውያን እንዳይታወቁ የሚሰርዙትን እያበተረታታ ነው። ሶፍትዌር የሚሠሩ ሠራተኞች እንደማንኛውም ሥራ ለጊዜዎቻቸውና ውጤቶቻቸው መከፈል ስለኣለባቸው ዶክተሩ በነፃ ማደል ኣልቻሉም። ገልባጮች ቀን፣ ፀሓፊና መረጃ በሌላቸው ልብ ወለዶች እና ተብለውበታል። የአማርኛ የታይፕራይተር ፊደል የግዕዝ ፊደል ኣይደለም። የማተሚያ ቤቶቻችን ፊደልም ኣይደለም። የእውሸት የዓማርኛ ፊደል እንጂ የዓማርኛም ፊደል ኣይደለም። መጽሓፍትም ሲታተሙ የነበሩት በግዕዝ ፊደል በማተሚያ ቤቶች ነበር። ኣሁንም ቢሆን በድሮው የማተሚያዎቹ ዓይነት ወይም ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት የዩኒኮድ የዓማርኛ ፊደል ነው። የታይፕራይተርንና በቅርቡም ተቈራርጠው ሲቀጣጠሉ የነበሩትን የማተሚያውን ፊደላት የማይለዩና ሁለቱ ኣንድ የሚመስሏቸው ኣሉ። የግዕዝ ዩኒኮድ ፊደል ከአማርኛው የታይፕራይተር ነገሮች ጋርም ግንኙነት የለውም። የአማርኛውን ታይፕራይተር ፊደል ግዕዝ እያሉ ስለጉዳዩ ያልሰሙትን ማታለልና ኣዳዲስ የታይፕራይተር ቁርጥራጮች ፊደላትን በመሥራት ጊዜዎቻቸው እየተባከነባቸው የኣሉ ኣሉ። ኦሮምኛም የእራሱ የግዕዝ ፊደል ስለኣለው ችግር ቢኖር እንኳን መፍትሔ ይፈጠርለታል እንጂ መቀጣጠል ኣስፈላጊ ኣይደለም። የኣማርኛ ታይፕራይተር እንደ ማተሚያ ቤቶች ፊደሎቻችን የግዕዝን ዜሮ ሳያውቁ የኣረብኛውን ኣልቦ በመውረስ እንዘልቅ ነበር። ከአማርኛ የጽሕፈት መኪና ኣጠቃቀምና ኣስተሳሰብ መላቀቅ ተቸግረው የግዕዝን ኣራት ነጥብ (ዓቢይ ነጥብ) በሁለት የላቲን ሁለት ነጥብ እየከተቡ የዓማርኛውን የዩኒኮድ ጽሑፍ እያበላሹ የኣሉት ደራስያን ቍጥር ብዙ ነው። የእዚህ ስሕተት ምንጭ የግዕዝን ኣራት ነጥብ የሌለው የአማርኛ የጽሕፍት መሣሪያ የአማርኛ ቁቤ ኣጠቃቀም ነው። በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ኣጠቃቀም ሁለት ባለ ሁለት ነጥቦች ጎን ለጎን ስለተቀመጡ የዓረፍተ ነገሮች መዝጊያ የሆነው የኣራት ነጥብ ምልክት ኣይደሉም። ለምሳሌ ያህል በግዕዝኤዲት ኣራት ነጥብ የሚከተበው በ“ዝቅ” እና (“3”) ቊልፎች መርገጫዎች ነው። ለተለያዩ የፊደል መጠኖች ለእየብቻቸው የሚገጣጠሙ ቀለሞችን መሥራት ኣድካሚና የማያዛልቅ ሥራ ነው። ለኣሥራ ሁለት ፖይንት የተሠራው ፊደል መጠን ሲለወጥ ፊደላቱ ይበላሻሉ። የአማርኛው ታይፕራይተር የእራሱ ፊደል ስለሌለው እንደግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ዓይነት የኣለውን ፊደል እየቆራረጡ በመቀጠል ሰዉን ሲያወንናብዱ ቆይተዋል። ምክንያቱም ገልባጮች ኣስቀያሚ መቀጣጠያዎቻቸውን መቀጣጠል ትተው ይኸን የማተሚያ ቤቱም ትክክለኛ ፊደል ቈራርጠው መቀጠል ስለጀመሩ ነው። የሚያቀርቡትም ጥቂት ዓይነቶች የፊደል መጠኖች ብቻ በመሆኑ ፊደላቱን ለማሳደግ ወይም ለማሳነስ ሲፈለግ ይዛነፋሉ። (ምሳሌ- ፊደል ሶፍትዌር) ለመቀጠል ሲባል ኣስቀጣዮች በወጉ ስለማይሠ'ሩ ስፍራዎቻቸውን የለቀቁ ቀለሞች ናቸው። በእዚህ የተነሳ የታይፕ ፊደላት የተዛነፉና ክፍተቶች የበዙባቸው ናቸው። እ.ኤ.ኣ. በ1987 በአማርኛ የእጅ ጽሑፍ ፊደል በኮምፕዩተር የተጻፉ ገጾች ምሳሌ እዚህ ሰምና ወርቅ መጽሔት የገጾቹ ሥዕሎች አሉ። የአማርኛን ታይፕራይተር የፈጠራ ቀለሞች ወይም ግዕዝ እያሉ የሚያወናብዱና የሚተባበሩዋቸው ጋዜጠኞች ኣሉ። ዶክተሩን የታይፕራይተር ኣፍቃርያን ኣሸንፈው ቢሆን ኖሮ ግዕዝን ኣንድ የፊደል ገበታ ላይ በኣሉት ሥፍራዎች መጠቀም ስለማይቻል ትርፉ ውርደት ይሆን ነበር። የአማርኛን ታይፕራይተር የፈጠራ ቀለሞች እንደ ዓማርኛው የኦሮሞውንም የግዕዝ ፊደል ስለኣልጻፉ ኣንዳንድ ኦሮሞዎች በላቲን ፊደል እንዲጠቀሙ ኣንዱ ምክንያት ሆኗል። በፊደል ቆራጮች ለዩኒኮድ እዚህ የቀረበው ሥራ ላይ ያልዋለው የማተሚያ ቤቱ ፊደል ኣቀራረብ ለይስሙላ ብቻ ነበር። ምክንያቱም ስምንት በኣሥራ ስድስት ማለትም 128 ሥፍራዎች በቂ ኣይደሉም። የኣማርኛ ታይፕራይተር ወደ ኮምፕዩተር የገባው በኣስቀያሚ ቀጫጭን ቁርጥራጮች እንጂ በእነዚህ የተቆራረጡ ትክክለኛ የግዕዝ ቀለሞች ቍርጥራጮች ኣልነበረም። የትክክለኛ የግዕዝ ቀለሞችን ቍርጥራጮችንም ግዕዝ ነው ማለትም ቅጥፈት እንጂ ሳይንስ ኣይደለም። በኣስቀያሚ ቀጫጭን ቁርጥራጮች አማርኛ የጽሕፈት መኪና ፊደሎች ምን አንደሚመስሉ አዚህ የኣለውን የኢትዮጵያ መዝሙር ገጽ ማየት ይቻላል። ሌላ ምሳሌ አዚህ ጎን የኣለው የ፲፱፻፹፪ ዓ. ም. የኣቶ ኣበበ ሙሉነህ ደብዳቤ ሥዕል ነው። ፊደል ቀናሾችና ቀንጣሾች ኣስቀያሚዎቹን የታይፕራይተር ፊደል ትተው የዶክተሩን ዓይነት ትክክለኛ ቀለሞች መቀንጠስ ጀምረው ሁሉንም የግዕዝ ፊደላትና መጻፊያ ስለሌላቸው ያልቀነጠሷቸውን ከሌላ በመውሰድ ኣንባቢውን በማታለል ቀጥለውበታል። ለምሳሌ ያህል የኣቶ ዘውዴ ረታ “የኤርትራ ጉዳይ” መጽሓፍ ርዕስ የውጭውና የውስጡ “ጉ” ቀለም መልኮች የተለያዩ ናቸው። ኣንዳንዶቹም ሲቀጥሉ የነበሩትን “ኳ”ን የመሰለ “ካ” እና መስመር ወይም “ቋ”ን የመሰለ “ቀ” እና መስመር መልሶ በቅርቡ በመቀጠል የዩኒኮድ ሥፍራ ላይ ጭምር በማቅረብ የተሳሳቱ ቀለሞችን በማስተዋወቅ ፊደሉን የማያስተውለውን ምሁር የሌለ ፊደልን ግዕዝ ነው እያሉት በማወናበዱ ገፍተውበታል። እንኳን 128 ቀርቶ 256 የኣንድ የእንግሊዝኛ ፊደል ተራዝሞም ስፍራዎቹ ስለማይበቁ በቅጥልጥል የግዕዝ ፊደላችንን መጻፍ ስለማይቻል ዶክተር ኣበራ ሞላ ባይኖሩ ኖሮ ኣንዳንድ ውሸታሞች የግዕዝ ፊደልን በተለመደው ሓሰታቸውና ዩኒኮድንም በመጠቀም ገድለውት ነበር። የኣማርኛ የታይፕራይተር ፊደል የተሠራውና በኮምፕዩተር የተሠራለትም ዓይነት በኣንድ የእንግሊዝኛ ፊደል ምትክ የቀረቡ የእውሸት ነገሮች ነው። ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት ለመጀመሪያ ጊዜ የግዕዝ ፊደላቱን በስምንት የእንግሊዝኛ ፊደላት ምትክ በመጠቀምና በመበተን ነው። የኣማርኛ ታይፕራይተር ትክክለኛዎቹን ፊደላት ስለሌሏቸው የሚቀጣጠለው ፊደል ትክክለኛ ላይሆን ይችል ነበር። ለምሳሌ ያህል የግዕዝ “ጯ” ፊደል ኣንድ ወጥ የግዕዝ ቤቱ ሦስተኛው እግር ላይ የተቀረጸ መስመር ያለው ሲሆን ፊደሉን በሚገባ የማያስተውሉ፣ ታይፕራይተር ተጠቃሚዎችና ተማሪዎቻቸው ፊደሉ የሚሠራው “ጫ” ስር መስመር በመጨመር የሚመስሏቸው ኣሉ። ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ እንደኣደረጉ የማያውቁ ዓዋቂዎችም ኣሉ። ኣንዳንዶቹም የታይፕራይተር ቅርጾች ወይም ሌሎችንም የሚከተቡት ከሁለት በላይ መርገጫዎችን በመጠቀም ነው። ኣንዳንድ ሰዎች ዶክተሩ የሠሯቸውን የተሟላውን የዓማርኛ የታይፕራይተር ፊደል መልክ ስላላሳዩ የሚገርማቸው ኣሉ። ዶክተሩ ፊደሉን የሠሩት ፊደል የሌላቸው ሰዎች ስለ ኤድስ የጻፉትን ዓይነት ጽሑፍ በነፃ እንዲያነቡበት የለቀቁት ሲሆን የሚል ስም የሰጡትን ያልተሟላ ወደ በመቀየር የሚያድሉ ሌባዎችም ስለበዙ ነው። ጥሬ ሥጋ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ዕድል በኣገኙ ቍጥር ችሎታቸውን ለሌሎች ከማስተማርና ስለሚያውቁት ከማስረዳት ኣይቆጠቡም። ለምሳሌ ያህል በ፳፻፭ ዓ.ም. ከኣንድ የዋሽንግተን ዲ.ሲ. የዓማርኛ ሬድዮ ጣቢያ ጋር ስለ ጥሬ ሥጋ ገለጻ ኣድርገው ነበር። ኢትዮጵያውያን ጥሬ ሥጋ ከሚበሉ ሕዝቦች መካከል ስለሆኑ ኣትብሉ ማለት ብቻ ትክክል ስለኣልሆነ የሚያዋጣው በምርምር የተደገፉ መረጃዎችን ማቅረብ ነው። በኣሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚደረገው ከብት በየቦታው እየታረደ ይበላ ስለነበረ ዩናይትድ እስቴትስ (ኣሜሪካ) ውስጥ እንዲቀር ተወስኖ በ፲፰፻፺፱ ዓ.ም. ፌዴራል ድንጋጌ የኣልተመረመረና ንጹህ ያልሆነ ሥጋ ለሕዝብ ማቅረብ ክልክል ነው። ሕጉን ኣለማወቅ መከላከያ ኣይደለም። ሥጋው የተመረመረ ለመሆኑ ማሕተሙን ማየት ያስፈልጋል። እንዲህም ሆኖ ኣንድ ሰው የእራሱን እንሰሳ ኣሳድጎና ኣርዶ ሳያስመረምር ቤተሰቡን ብቻ የማብላት መብት ኣለው። ጥሬ ሥጋ ጀርሞች ኣሉት። ስለዚህ የሚከተሉትንም ማወቅ ጠቃሚ ነው። ኣንድ እንሰሳ ሲታረድና ቆዳው ሲገፈፍ ጀርሞች በተለያዩ ሁኔታዎች ሥጋው ውጭ ላይ ስለሚቀሩ ያንን ማስወገድ ኣይቻልም። ቆዳ ሲገፈፍ ቢላው እንዲጸዳ ሙቅ ውሃ ውስጥ እየተነከረ ነው። እንደ ባክቴሪያ የኣሉ ጀርሞች በእየ20 ደቂቃዎች ሁለት በመሆን ይራባሉ። ይኸን እርባታ ቅዝቃዜ ያዘገየዋል። ስለዚህ እንሰሳው እንደታረደ ሥጋው ጥቅም ላይ ከኣልዋለ ሁልጊዜ መቀዝቀዝ ወይም መፈረጅ (ፍሪጅ ውስጥ መቀመጥ) ኣለበት። ለብዙ ጊዜ መቀመጥ ከኣለበት ሥጋው ከውሃ በረዶ ቅዝቃዜ በኣነሰ ወይም መፈረዝ (ፍሪዘር መግባት) ኣለበት። ኣንድ እንሰሳ ከመታረዱ በፊትና ከታረደ በኋላ በእንስሳት ሓኪም መታየት ኣለበት። ሓኪም ከሌለ ረዳት ሓኪሞች ወይም በሥጋ ምርመራ የሰለጠኑ ኣይተው ኣጠራጣሪውን ለእንስሳት ሓኪም የሚያቆዩበት መዘጋጀት ኣለበት። ምክንያቱም ሓኪሞች ብቻ የሚያውቋቸው ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ ብዙ በሽታዎች ስለኣሉ ነው። ሥጋ ውስጡ ንጹህ ነው። እንጨት ልሙጥ ስለኣልሆነ ለጀርሞች መደበቂያ ስለሚያገለግል ለብዙ ሰዎች የሚቀርብ ሥጋ ሲዘጋጅ መክተፊያ፣ የቢላው እጀታና ማቅረቢያው እንጨት ባይሆን ይመረጣል። የኮሶ በሽታ ሰውን የሚይዘው ያልተመረመረ ጥሬ ሥጋ በመብላት ነው። የኮሶ በሽታ ያለበት ሰው በየሜዳው ሰገራ ሲወጣ ከብቶች የኮሶውን እንቁላል ከሳር ጋር በመብላት ይበከላሉ። የኮሶ ትላምነት የኋላ-ቀር ሕዝብ የሰው በሽታ እንጂ የከብት በሽታ ኣይደለም። ሥጋ ጀርሞች ስለኣሉት ሲዘጋጅ ሳይበስሉ ከእሚበሉ እንደሰላጣ የኣሉ ምግቦች ጋር መነ'ካካት የለበትም። ፍሪጅ ውስጥም ሥጋን ከታች ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው። ሥጋ የኣለው የበሰለ ለብዙ ሰዎች የሚቀርብ ምግብ ጀርሞች እንዳያድጉበት እንደሞቀ እንዲቆይ ከኣልተደረገ በሁለት ሰዓታት ውስጥ ከኣልተበላ ወደ ማቀዝቀዣ ማግባት ጠቃሚ ነው። ማቀዝቀዣ ያልሞቀ ምግብ ማቀዝቀዣ ነው። የበሰሉ ሥጋ-ነክ ምግቦችን ማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ውስጥም በንጽሕና ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም እንደ ሊስቴሪያ የኣሉ ባክቴሪያዎች ማቀዝቀዣም ውስጥ ስለሚያድጉ ነው። ሥጋን ማብሰል የኮሶውን እንቁላል ይገድላል። የኮሶ ትል እንቁላል ያለበትን ጥሬ የከብት ሥጋ ለሁለት ሳምንታት ፍሪዝ ማድረግም ይገድላቸዋል። ኣልፎ ኣልፎ ሥጋ እየበሉ ስለታመሙ ሰዎች ይሰማል። ኣንድ ሰው በኮሶ በሽታ ከተያዘ በኣንድ ጊዜ የሚኖረው ኣንድ የኮሶ ትል ብቻ ነው። ጥሬ ሥጋ ውስጥ የኣሉ ጀርሞች ኣደገኝነት ሕጻናትና በቂ መድኅን የሌላቸው እንደኤድስ በሽተኞችና ኣዛውንት ላይ የበረቱ ናቸው። ለትላልቅ ድግሶች በስለው ፍሪዝ የተደረጉ ሥጋ-ነክ ምግቦችን ለማብሰል ከበረዶነታቸው እንዲሟሙ እንደ እቃው ትልቅነት እስከ ሦስት ዕለታት ሰዓታት) ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ጥሬ ሥጋን የተመለከተው ሕግ ሌሎች እንስሳትንም ይመለከታል። ኣንድ ከብት ለምግብነት እንዲያልፍ ወይም እንዲወድቅ የመወስን ሥልጣን የኣላቸው የእንስሳት ሓኪሞች ብቻ ናቸው። የሚሰራጭ ካንሰር የኣለበት እንሰሳ ለምግብነት ኣያልፍም። የኣልተሰራጨ ካንሰር በማየት የሚያውቁና የሚጠረጥሩ ሓኪሞች ናቸው። ጥሬ የኣሳማ ሥጋ ከመብላት ሰው የሚኖረው የኮሶ በሽታ ኣደገኝነት የከፋ ነው። ጥሬ ሥጋ መብላትና ጥሬ ኣሳ (ሱሺ) መብላት ኣንድ ኣይደለም። ኣንድ ጀርም ሰውና የተለያዩ እንስሳት ውስጥ የተለያዩ በሽታዎች ሊያመጣ ይችላል። ለምሳሌ ያህል ኣባሰንጋ ኣእዋፍን ኣይተናኰልም። ኮሮናቫይረስ ከጥሬ ሥጋ እንደሚተላለፍ ወይም እንደማይተላለፍ መረጃው ስለሌለ ሥጋን በጥንቃቄ መያዝና ኣብስሎ መብላት ይመከራል። በነገራችን ላይ ኮሮናቫይረስ እንጂ ኮሮና ወይም ኮሮና ቫይረስ የሚባል ቫይረስ የለም። በእንግሊዝኛም ስሙ ነው። ግዕዝኤዲት ለኣይፎን 4 እና በላይ እና ኣይፓድ የእጅ ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክ ለእንግሊዝኛ ኣጠቃቀም ከተሠራ ዓመታት ቢያልፉም ለዓማርኛ ሥራ ላይ ማዋል ይቻላል። ግዕዝኤዲት ለኣፕል ኣይፎን 6 6 ከኣፕሮባቲክስ ቀርቦላችኋል። በኣፕል ኣይፓድም ያስከትባል። ከኣይፎን 4ኤስ ወዲህ ለተሠሩትም ኣዲሱን የኣይኦኤስ 8 8) ሥርዓት በማስገባት ማሻሻል በዓማርኛው መጠቀም ያስችላል። ከኣፕ ሱቅ ወይም ኣይቲዩንስ ወደ ኣይፎን 6 የእጅ ስልካችን ስናስገባ የሚለው ከፊደል ገበታዎች ኃይል ጋር ያሉትን ልዩ ጥቅሞች ለመጠቀም የሚያስፈልግ ስለሆነ ለጊዜው መዝለል ይቻላል። እንዲህም ሆኖ ኣፕል እንጂ የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር የገዥዎችን ክሬዲት ካርድና ኣድራሻ ኣያውቅም። ይህ ለኣዲሱ የኣፕል የእጅ ስልክ የተለያዩ ቍሳቍሶች ውስጥ እንዲሠራ የቀረበው ቁስ ኣከታተብ የባለቤትነት መብቱ ለዶክተሩ ሊሰጥ እየተጠበቀ ባለው ኣብሻ ዘዴ ለዊዶውስና ማክ ኮምፕሩዩተሮች መክተቢያ በነፃ ከተሰጠውና ከሚሸጠው ግዕዝኤዲት ጋር ኣንድ ዓይነት ነው። ለተወስነ ጊዜ ዋጋው ዶላር (1.99) ነው። ቁሱ ተወዳጁን የግዕዝኤዲት ዩኒኮድ የዓማርኛውን ፊደል ይጨምራል። የግዕዝ ፊደል ያላቸው የኣንድሮይድ ስልኮችም ከኣይፎን የተላከላቸውን ማስነበብ ይችላሉ። የፊደል ገበታው ለጊዜው ለዓማርኛ ብቻ ቢሆንም ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች ማለትም ፣ እና ከኣንድ ገበታ እንዲያስከትብ የተሠራ ነው። እየተሻሻለ ስለሆነም የሌሎች ቋንቋዎቻችን መክተቢያዎች እንደኣስፈላጊነታቸው ወደፊት ይከፈታሉ። ከኣፕል ሱቅ ቁስ ከተገዛ በኋላ ኣዶው ስር የሚል ስሙ ይታያል። ከእዚያ ፣ በኩል ገበታውን መጫንና ወደ ከእዚያ ተመልሶ በኩል ፊደሉን ማስገባት ያስፈልጋል። ሲከፈት የሚታየው እንግሊዝኛ ስለሆነ ለዓማርኛው የዓለም ካርታ ያለበትን ኣዶ መጫን ነው። ተጭኖ መቆየትም “ኣማርኛ” የሚለው የፊደል ገበታ እንዲመረጥ ያቀርባል። ለኣጻጻፉ የሚለውን በኣማርኛ ወይም ማንበብ ይጠቅማል። ግዕዝኤዲት ኣንዴ ከተጫነ ጽሑፍ የሚያስፈልጉበት ቦታዎች ሁሉ ከእንግሊዝኛው ገበታ ስር በዓማርኛ ለመጻፍ ዝግጁ ስለሆነ የሚያስፈልገው ገበታውን መክፈት ብቻ ነው። የግዕዝኤዲት ገጽ ላይ ከትቦና ኮፒ ኣድርጎ ሌሎች ስፍራዎች መለጠፍ ሌላ ዘዴ ነው። በግዕዝኤዲት የተጻፈን የዓማርኛ ጽሑፍ በፋይል መልክ ለማስቀመጥ ወደ “ኖትስ” መገልበጥ ወይንም ኖትስ ውስጥ መክተብ ጠቃሚ ናቸው። ቀደም ብሎም ለእጅ ስልክ ዓማርኛውን ለመጀመሪያ ጊዜ ማቅረባቸው ቢታወስም ዓማርኛ ከዓለም ቋንቋዎች መደብ እንዲገባ ኣፕል ገበታችንን እንድናስገባ ስለወሰነና የመጀመሪያው ኩባንያ በመሆኑ ምስጋና ይገባዋል። የግዕዝኤዲት ቁስ የተለያዩ የኣይፎን 6 የእጅ ስልክ ፕሮግራሞች ውስጥ እንድንሠራ ኣዲስ ችሎታ ኣስገኝቷል። ቴክስት ኢ-ሜይል ትዊተር እና በመሳሰሉት ተደሰቱ። በኣሁኑ ጊዜ ኣንዳንድ ድረገጾችና ጽሑፎች ግን ላይነበቡ የሚችሉት በሌሎች ምክንያቶች ሲሆን ችግር የሌላቸው ድረገጾች ምሳሌ እዚህ ኣለ። ለምሳሌ ያህል እንደነፃው የግዕዝኤዲት ገጻችን የመሳሰሉት በኮምፕዩተር የሚነበቡት በኣዶቢ ፍላሽ ስለሆነና ኣፕል ፍላሽን ስለማያስገባ ድረገጹ ባይነበብ ችግሩ የግዕዝኤዲት ኣይደለም። ወጪና ጊዜ ያስጨምራል እንጂ ለኣንዳንዳቹም ተግዳሮት መፍቻ ዘዴዎች ኣሉ። ኣንዳንድ ፕሮግራሞችም በእንግሊዝኛ እንጂ በዩኒኮድ ፊደላት የመጠቀም ኃይል ገና የላቸውም። ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ፌስቡክን በድረገጽነት ማንበብ የዓማርኛውን ቀለሞች በኣለማቅረብ ሳጥን ስለሚያደርጋቸው በፌስቡክ ቁስ መጠቀም ያስፈልጋል። ኣይኦኤስ እነዚህን ችግሮች ስለኣስወገደ ግዕዝ ብዙ ፕሮግራሞች ውስጥ ይሠራል። ከጉግል፣ ቢንግ፣ ያሁ፣ ሳፋሪ የመሳሰሉት ሌላ ይኸን የዓማርኛ ውክፔድያ ገጽ ያስነብባል፣ ያስከትባልም። ለተጨማሪ መረጃ የግዕዝኤዲት ፌስብክ ገጽ መከታተል ይጠቅማል። የፌስቡክ ኣጓዳኙም እዚህ ኣለ። በኣይፓድና ኣይፎን ግዕዝኤዲትን ለመጠቀም ለጊዜው እንግሊዝኛውን በቋንቋነት በኩል ትቶ ኣማርኛን ኣንደኛ ማድረግ ይሻላል። ኣንዳንድ ፕሮግራሞች የተሠሩት ለእንግሊዝኛው ብቻ ስለሆነ በሚገባ ከኣልሠሩ ወደ እንግሊኛ መመለስ ያስፈልጋል። ኣይፎንና ኣይፓድ ለኣለው ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደል ጨምሮ የሚከፈለው $1.99 ለሦስቱም ነው። የኮምፕዩተሩና የስልኩ ግዕዝኤዲት ኣከታተብና ፋይሎች ኣንድ ከመሆናቸው ሌላ ይናበባሉ። ከእዚህ በፊት መጻፊያ ጠፍቶ በእንግሊዝኛ ፊደል ዓማርኛውን ፓልቶክ በመሳሰሉ ድረገጾች ውስጥ ሲጽፉ የነበሩትን ነፃው የግዕዝኤዲት ድረገጽ መገላገሉ ይታወሳል። ከእዚህ በፊት መጻፊያ ጠፍቶ በእንግሊዝኛ ፊደል ዓማርኛውን ሲጽፉ ወይም ለጄልብሬክ ሲከፍሉ የነበሩትን ግዕዝኤዲት ገላግሏል። ከእንግዲህ ወዲያ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብና ቴክኖሎጂን በሚ'ገባና ሳይንሳዊ ባልሆነ ዘዴ መጠቀም ኣስፈላጊ ኣይደለም። ይኸን በፔንዲንግ ፓተንት የተጠበቀ ትክክለኛ ቴክኖሎጂ ላልሰሙት እንድታሰሙና እንድታሳዩ እናበረታታለን። ስለ ቁሱ እዚህ የተጻፈው ጥቂት ሰዎች ግዕዝኤዲትን ከገዙ በኋላ ገበታውንና ፊደሉን ሳያስገቡ መጻፍ እየሞከሩ ስለተቸገሩም ነው። የሚለው ባለ ሰንደቅ ዓላማ ካርታችን ያለበት ኣዶ ከታየ በኋላ ያንን መንካት እንደተራ ቁስ ግዕዝኤዲትን ኣይከፍትም። በቁሱ ለመጠቀም የፊደል ገበታውና ፊደሉ በሴቲንግስ በኩል መግባት ኣለባቸው። የእንግሊዝኛው የፊደል ገበታ ከታየ በኋላ የዓለም ካርታው ያለበትን ኣዶ መንካት ወይም ተጭኖ መቆየት የዓማርኛውን የፊደል ገበታ ያቀርባል። በቅርቡ ወደ ኣይኦኤስ 10 ሲሻሻል የቁሱን ክፍል 1.3 በማድረግ ስሙም ተብሏል። ማሻሺያውም ነፃ ነው። የእጅ ስልክ ኣከታተብ የእንግሊዝኛው የኮምፕዩተር ኣከታተብ የእጅ ስልክ ኣጠቃቀምም ሆኗል። ግዕዝም ለኮምፕዩተር ሲጠቀምበት የነበረው ኣከታተብ ዓይነት ወደ እጅ ስልክ በዶ/ር ኣበራ ግኝት ገብቷል። የተለመደው የእንግሊዝኛና የግዕዙ ገበታ መርገጫዎች እየታዩ ለሁለቱም ፊደላት እንዲያገለግሉ የፈጠሩት ጥቅም ቀጥሏል። ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ የሚጠቀሙት የግዕዝ ዩኒኮዱን ፊደል ስለሆነ ውበቱን እንደጠበቀ ሁሉም መሣሪያዎች ይናበቡበታል። በእጅ ስልክ በኣንድ ጣት ከመክተብ ስልኩን ወደጎን ኣዙሮ በኣውራ ጣቶች መክተብ ያፈጥናል። በእዚህ የተነሳ ላቲን ለቀለሞቹ መክተቢያ የማይጠቀምበትን ከግዕዝ መጠየቅ ለእስማርት (ጮሌ) ስልኮችም ኣያስፈልግም። የግዕዝ ኣከታተብ ፈጣሪ ፓተንት (የግኝት ባለቤት) ከዶ/ር ኣበራ ሞላ ጋር ቃለ ምልልስ (ኢቢኤስ ቪድዮ እዚህ ኣለ። ለኮምፕዩተር የቀረቡት የላቲን ምልክቶችም ለግዕዝ ፊደል እንዲጠቅሙ በእጅ ስልክም ሥራ ላይ ውለዋል። የእጅ ስልኩ ገበታና ፊደል ከተበተነ በኋላ መክተብ ሲያስፈልግ የመጻፊያው ስፍራ ሲነካ የመክተቢያ ገበታ ይቀርባል። በዓማርኛ ለመክተብ የሚያስፈልገው የዓለም ካርታ ያለበትን በመንካት ገበታውን ወደ ዓማርኛ መለወጥ ነው። ለላቲን ኮምፕዩተር ኣከታተብ የተፈጠረው ገበታ ለላቲን የእጅ ስልክ እንደሆነው ሁሉ የግዕዙም "ቀወኸረተየ" የኮምፕዩተር መደበኛ ገበታ የእጅ ስልክም የግዕዝ ገበታ ሆኗል። ለስልክ የተገዛው ለኣይፓድም ጭምር ነው። ጽሑፍን ለማስቀመጥ ውስጥ መጻፍ ያስፈጋል። ዊንዶውስና ኣፕል የሚጠቀሙት በግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደል ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለኮምፕዩተር ለዓመታት ሲቀርቡ የነበሩት ዓይነት የማያዛልቁ ኣከታተቦች ለእጅ ስልኮች መቅረብ ስለጀመሩ ሕዝቡ በኣዲስ ዙር መታለል እንዳይቀጥል መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ለእዚህም የሚከተሉትን እንድንዘረዝር ተገድደናል። ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ እያንዳንዱ የግዕዝ ቀለም የተከተበው በሁለት መርገጫዎች ነበር። ይህ ተሻሽሎ በኣንድና በሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ ሆኗል። እንደእንግሊዝኛው የኮምፕዩተሩ ኣጠቃቀም ለእጅ ስልኩም ቀርቧል። ኣጠቃቀሞቹም ይቀጥላሉ። ይህ በሳይንስ የተደገፈ ኣጠቃቀም ይቀጥላል እንጂ ጥልቅ እየተባለ ለእጅ ስልክ ኣዲስ ኣጠቃቀም ኣይሠ'ራም ወይም ችግር ኣለበት ተብሎ ወደቀረው ኋላቀር ኣከታተብ መመለስ ኣስፈላጊ ኣይደለም። የኣማርኛ ታይፕ መቀጣጠያው ኣሠራር የትክክለኛ ኣማርኛ ፊደል መጻፊያ ኣልነበረም። የታይፕራይተሩ ኣጠቃቀም ሁለት ነጥብ ምልክት ለባዶ ስፍራነትና ሁለቱ፣ ሁለት ነጥቦችን በኣራት ነጥብ ምልክት ምትክነት መጠቀም ከመሣሪያው ኣጠቃቀም ችግሮች ጋር በተያያዙ የቁጠባ ኣሠራሮች የመጡ ነበሩ። ወረቀት ላይ ብቻ ሰፍረው የምናያቸው የጽሕፈት መሣሪያ ኣጠቃቀም ውጤቶች ከኮምዩተሩና የእጅ ስልክ ኣጠቃቀሞች ጋር ኣንድ ዓይነት ኣይደሉም። ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት የግዕዝ ፊደል ኣንዱን ምልክት ለሁለቱም ኣይጠቀምም፤ ኣልተጠቀመምም። የላቲንን የኮለን ሁለት ነጥብ ምልክት ዶክተሩ እንደሌሎቹ ለግዕዝ ኣጠቃቀም ቢያወርሱም ኣጠቃቀሞቻቸውን ማወቅ የተጠቃሚው ኃላፊነት ነው። ኮለን የግዕዝ ሁለት ነጥብ የባዶ ስፍራ ምልክት እንዳልሆነው ሁሉ የግዕዝ ሁለት ነጥብ ምልክትም ኮለን ኣይደለም። ሁለት፣ ሁለት ነጥቦችም ሆኑ ሁለት ኮለኖች የግዕዝ ኣራት ነጥብ ምልክት ኣይደሉም። የእዚህ ገጽ ኣንዱ ዓላማ ኣዳዲስ ጥፋቶች በቴክኖሎጂ እየተደገፉ እንዳይስፋፉ ነው። የዓማርኛን ጽሑፍ ለማስቀመጥ ኖትስ ቁስ ውስጥ መጻፍ ያስፈልጋል። የግዕዝ ፊደል የእጅ ስልክ ትክክለኛ ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂ ኣጠቃቀሞች ዘዴዎቹን ለፈጠሩት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ቍጥራቸው 9000957፣ 9733724፣ 10067574 እና 10133362 በሆኑ የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንቶች ተሰጥተዋል። ኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች የሚጠቀሙት ግዕዝኤዲት የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ፕሮግራሞች ኣንድ ዓይነት በሆነው የግዕዝ ፊደሉ ነው። ስለዚህ የቴክኖሎጅው ተጠቃሚዎች የተላኩላቸውን ኢሜይል የመሳሰሉ ጽሑፎች በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች የሚመለከቱት በግዕዝኤዲት ፊደል ነው። ፊደሉን ለሌላቸው ግን መሣሪያዎቹ ላይ በኣሉ ፊደላት ይቀርባሉ። ኣንዳንድ የግዕዝኤዲት ተጠቃሚዎች ፊደሉ በኣስቀያሚና የተሳሳተ የግዕዝ ፊደል ተቀየረብን የኣሉ ኣሉ። ይህ በቅርቡ ኣፕል መጠቀም በጀመረው ፊደሉ ኣጠቃቀም የመጣ ችግር ነው። የዓማርኛ ስሕተቶች በእዚህ ርዕስ ዶክተሩ ከዓመታት በፊት ያቀረቡትን ብዙ ኣንባቢዎች ስለኣላዩት ኣልታረሙም። እዚህ ውክፔዲያ ገጽ ላይ የቀረቡት ውጤት ማምጣት ስለጀመሩ ተሻሽለው ቀርበዋል። ወደፊት ኮምፕዩተሩ በግዕዝ ፊደል የቀረቡትን ያነባ'ል፣ ያሰማናል፣ ያርማል፣ ይተረጕማል፣ ወዘተርፈ። ስለዚህ ዶክተሩ ኣርቆ በማሰብ ስሕተቶችና ግድፈቶች ወደ ኮምፕዩተር ሳይገቡ እንዲታረሙ ከመጻፍ ኣልተቆጠቡም። እንደ ኤውሮጳ ኣቆጣጠር ማጠር ያለበት በ“እ.ኤ.ኣ.” እንጂ “እ.ኤ.ኣ” ማድረግ ከሚገባው በታች ማሳጠር ነው። ኣንድ ሰው በስሕተት የተጠቀመበትን ኣሠራር ሌሎቻችን በሚገባ ሳናስተውል መከተል የለብንም። “ኣ” ጎን ነጥብ ከኣሌለ “ኣ” ብቻውን እንዳለ ቃል መቆጠሩ ስለሆነና ኣጠቃቀሙም ትክክል ስለኣልሆነ ቋንቋ ሲበላሽ ዝም ብሎ መመልከት ተገቢ ነው? “ዓመተ ምሕረት” ማጠር ያለበት በ“ዓ.ም.” እንጂ “ዓ/ም” ያሳስታል። የእዝባር ጥቅም እንደ “ወይዘሮ” የሚጻፉትን ቃላት በ“ወ/ሮ" ለማሳጠር እንጂ ሁለት ቃላትን ለማሳጠር ኣይመስልም። የ“ሊቅ” ብዙ “ሊቆች” ወይም “ሊቃውንት” እንጂ “ሊቃውንቶች” የሉንም። እዚህ ላይ በተለይ ከግዕዝ የመጡ ቃላት ላይ መጠንቀቅ ሳይጠቅም ኣይቀርም። ኣባላት፣ መምህራን፣ መኳንንት የመሳሰሉ ቃላት የብዙ ቍጥሮች ናቸው። ስለዚህ ኣባላቶች፣ መምህራኖች፣ መኳንንቶች፣ ቃላቶች የሚባሉ የብዙ ብዙ ስለሆኑ እንዲህ የኣሉ የዓማርኛ ቃላት የሉም። ሞክሼ ቀለሞች የተለያዩ ጥቅሞች የኣሏቸው ለግዕዝ ቋንቋ እንጂ ለዓማርኛ ኣይደለም የሚባለው ትክክል ኣይደለም። ዌብ ድር፣ ዌብፔጅ ድረገጽ ወይም ገጸድር ነው። ድህረገጽ ከገጽ በኋላ ስለሆነ ትክክል ኣይደለም። ይህ ስሕተት ምን ያህል እንደተስፋፋ ለማስተዋል ድህረገጽ፣ ድኅረገጽ እና ድሕረገጽ ቃላትን ኢንተርኔት ላይ በመፈለግ ስህተቶቹን መመልከት ይቻላል። ድሕር ማለት ኋላ ነው። ድረገጽ ነው። ስለዚህ ድሕረገጽ ወይም ድኅረገጽ ኣይደለም። የ“ው” ድምጽ ሳድስ እንጂ ካዕቡ “ዉ” ስለኣልሆነ “ነው” መከተብ ያለበት በሳድሱ “ው” ነው። ዓማርኛ “ዉ” ቀለምን የሚጠቀምባቸው ብዙ ቃላት ስለሌሉት መጠንቀቅ ጠቃሚ ነው። በ“ዉ” ቀለም ከመጠቀም ልዩነቱ ላልገባቸው “ዉ”ን ኣለመጠቀም ያዋጣል። “ጊዜ” እንጂ “ግዜ” ዓማርኛ ኣይደለም። ኣንዳንድ ደራስያን “እ” ቀለምን መቀነስ ይወዳሉ። “ተእኛ” እና “ተኛ” እንዲሁም “የእርሷ” እና “የርሷ” የተለያዩ ናቸው። ኣራት ነጥብ እራሱን የቻለ ኣንድ የግዕዝ የምልክት ቀለም ነው። ኣንዳንድ ደራስያን ምልክቱን ከሁለት ባለሁለት ነጥቦች (ነቊጦች) ወይንም በእንግሊዝኛ ኮለን መክተብ ስለጀመሩ ይህ ትክክል ከኣለመሆኑም ሌላ ኣስፈላጊ ያልሆኑ ሁለት መርገጫዎች በማስጨመር ጊዜና ስፍራ የሚያስባክን ግድፈት ነው። ከሁለት ቀለሞች የተሠሩትን ለመሠረዝም ሁለት መሠረዣዎች ያስፈልጋሉ። ኣራት ነጥቦች የሌሉት ጽሑፍም ችግር ውስጥ ሊወድቅ ይችላል። ዶክተሩ የእንግሊዝኛው ኮለን ለግዕዝ እንዲጠቅም ያደረጉት በኮለንነት ስለሆነ የግሉ የዩኒኮድ ቊጥር ከኣለው ባለሁለት ነጥብ (ወይም ነቊጥ) የባዶ ስፍራ የግዕዝ ምልክታችን ጋርም ኣንድ ኣይደለም። ኣራት ነጥብን ከሁለት ባለ ሁለት ነጥቦች በኮምፕዩተር መክተብም ግድፈት ነው። ምክንያቱም ይህ ኣሠራር ኣራት ነጥቦች ከሌሉት የኣማርኛ የታይፕ መጻፊያ የመጣ የኣሠራር ችግር ስለሆነ እንጂ ሁለት ባለ ሁለት ነጥቦች ኣራት ነጥቦች የሚሆኑበት ኣከታተብ ወደ ኮምፕዩተር እንዳይገባ ዶክተሩ ከተከላከሉት ኣንዱ የጎደለ ኣጠቃቀም ነው። በሞዴት፣ ኢትዮወርድ፣ ግዕዝኤዲት በኮምፕዩተርና ግዕዝኤዲት በእጅ ስልክ የግዕዝ ኣራት ነጥብ ምልክት የተከተበውና እየተከተበ የኣለው በሁለት መርገጫዎች (“ዝቅ 3”) ነው። በግዕዝ ዩኒኮድ መደብ ውስጥ እንደሚታየው እና እዚህ ጎን ላይ የኣለው ሥዕል እንደሚያሳየው ሁለት ነጥብና ኣራት ነጥብ የተለያዩ ናቸው። ሁለት ሁለት ነጥብና ኣራት ነጥብ የተለያዩ ናቸው። ኢትዮጵያውያንም ኣራት ነጥብን በማያስከትብ ፕሮግራም መጠቀም የለባቸውም። የመጽሓፎች ይዘት እና ማውጫ የተለያዩ ናቸው። የኣንዳንዶች ስሕተቶች ምንጮች የተሳሳቱ ፊደላት ወይም መክተቢያዎች ናቸው፦ ምሳሌ “ቍጥር”ን በ“ቁጥር” መጻፍ። “ው”ን አንጂ “ዉ”ን የሚጠቀሙ ብዙ የዓማርኛ ቃላት የሉም። በቅርቡ ግን በኣለማወቅ በ“ው” ቀለም ምትክ “ዉ”ን በግድፈት የሚጠቀሙ ፀሓፊዎች እየበዙ ነውና ቢታሰብበት ኣይከፋም። መዝገበ ቃላትም ጠቃሚዎች ናቸው። (እንግሊዝኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት 1972)። “ው”ን በትክክል ከ40 በላይ ቃላት ውስጥ የተጠቀመ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ። “ው”ን በስሕተት ከ400 በላይ ቃላት ውስጥ የተጠቀመ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ። የግዕዙ “ሀ” ድምጽ ወደ “ኸ” የቀረበ ነው። “አ” እና “ኣ” ድምጽ ኣይጋሩም። ኣንዳንድ ፀሓፊዎች በነጠላ ሰረዝ ምትክ ኮማ በኣራት ነጥብ ምትክ ፔርየድ መጠቀም ስለጀመሩ ፊደሉንና ቋንቋውን እያበላሿቸው ናቸው። ኣንዳንድ ምሁራን ስለማያስተውሉ ሁሉንም የዓማርኛ ቃላት መክተብ በማይችሉ እየተጠቀሙ የሚያወሩትን መጻፍ ኣይችሉም። የግዕዝ ፊደል ታዋቂነት የኣለ እስፔሊንግ ስሕተት ድምጽን በማስፈር ትክክክለኛ ድምፃዊ ፊደል መሆኑ ነው። ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ጊዜና ጉልበት ማባከን ነው። ምክንያቱም የዶክተሩ ኣሠራር እንግሊዝኛውን ከኣጋጠመው ችግር ጭምር ለማላቀቅ እንጂ ለግዕዙ የእንግሊዝኛውን ችግር ለማካፈል ስለኣልሆነ ነው። ኣንዳንድ ፀሓፊዎች የተሳሳቱ ቅርጾች ያሏቸውን ቀለሞች እየተጠቀሙ ስሕተቶችን እያስፋፉ ናቸው። ለምሳሌ ያህል የ“ኩ” እና የ“ቡ” መቀጠያዎች ኣንድ ዓይነት ኣይደሉም። ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ላይ የኣሉ ፊደላት የተሳሳቱ ከሆኑ መሳሳቱ ስለማይታወቅ የተሳሳቱ ቀለሞች ተለምደው መቸገርና ማስቸገር ኣይቀርም። እነ “ቋ”፣ “ኋ”፣ “ኳ” እና “ጓ” እራሳቸውን የቻሉ መስመር ላይ የሚያርፉ ቀለሞች እንጂ እነ “ቀ”፣ “ኃ”፣ “ካ” እና “ጋ” ስር በተጋደሙ መስመሮች የሚቀርቡ ኣዳዲስ የታይፕራይተር የእውሸት ፈጠራዎች ተቀጣጥለው እንደ ኣዳዲስ ቀለሞች ማቅረብ ተገቢ ኣይደለም። የ"የ”ን እንዚራን መለየት ለኣቃታቸው ኣንዳንድ ምሁራን የኣሌሉ ቀለሞችን መልኮች ማስተዋወቅ ኣይበጅም። ስለዚህ የግዕዝን ፊደል ከመለገስ መለየቱ ቢቀድም ሳይሻል ኣይቀርም። መስከረምና ሰፕቴምበር ብዙ ቀናት ይጋራሉ እንጂ ኣንድ ኣይደሉም። መስከረም 1 ሰፕቴምበር 1 ወይም 1 ኣይደለም። ሁለት ዓመታት ወይም ዓመቶች እንጂ ሁለት ዓመት በማለት መጻፍ ስሕተት ነው። በግዕዝ ጽሑፍ ውስጥ ኣራት ነጥብና የመሳሰሉት (በቀለማት እንጂ) በባዶ ስፍራ መቀደም የለባቸውም። ምክንያቱም ግዕዝ ከእጅ ጽሑፍና የማተሚያ ቤቶች ኣጠቃቀም ወደ ኮምፕዩተር ሲሻሻል መለ'የት የሚገባቸውን ዶክተሩ ስለኣቀረቡ ነው። የግዕዝ ፊደል የኦሮምኛው ፊደል ውስጥ ያለውን የግዕዙን “ዸ” እና ሰባት እንዚራን ቀለሞቹን ያጠቃልላል። ስለዚህ እንደ “በዻዻ” የኣሉትን ቃላት በ“በዳዳ” ወይም “ዻራርቱ"ን በ“ደራርቱ” መክተብ ግድፈት ነው። የኦሮምኛው ፊደል የዶክተሩ ሞዴት፣ ኢትዮወርድ፣ ግዕዝኤዲትና ሌሎች ፕሮግራሞች ውስጥ ቀርበው የሚፈልጓቸው ተጠቅመውባቸዋል። ሁሉንም ቀለማት የሌሉት ወይም የማይከትቡ ዓማርኛ እየተባሉ ሲቀርቡ ኣለተቃውሞ መቀበል ነውር ነው። ምክንያቱም ይህ ለፊደሉና ለሰዋሰው የኣለመጨነቅን ስለሚያሳይና የፀሓፊዎችን ችሎታ ጥያቄ ውስጥ ስለሚያስገባ ነው። ዓማርኛ “መጠጥ” እና “መጠጥ ኣደረገ” የሚለውን በማጥበቅ መለየት ኣይችልም የሚሉ ኣሉ። “መጠጥ” እና “መጠጥ ኣደረገ” ሁለት ትርጕሞች ያሏቸው ቃላት እንጂ በማጥበቅ የሚለዩ ኣይደሉም። በኮምፕዩተር ሁለት ነጥብ የግዕዝ የባዶ ስፍራን ምልክት ነጥብ በሌለው የባዶ ስፍራ የእንግሊዝኛው ኣጠቃቀም ጋር ደርበው ዓማርኛውን የሚያቀርቡ ኣሉ። ከሁለቱ ዘዴዎች ኣንዱን መምረጥ እንጂ ሁለቱንም መውደድ ኣያዋጣም። ኣንዳንድ ሰዎች ዓማርኛ የእራሱ ፊደል የለውም ይላሉ። ዓማርኛ የእራሱ ፊደል የኣለው ቋንቋ ነው። የግዕዝም ቋንቋ የእራሱ ፊደል ኣለው። የግዕዝ ቋንቋ ፊደላት የዓማርኛው ውስጥ ሲኖሩ ሁሉም የዓማርኛ ፊደላት የግዕዙ ቋንቋ ፊደላት ውስጥ የሉም። ግዕዝ ወይም የተለያዩ ቋንቋዎች የሚጠቀሙበት የፊደሉም ስም ሲሆን ለተለያዩ ቋንቋዎች ተጨማሪ ቀለሞች ተጨምረዋል። የኣማርኛ የታይፕራይተር ፊደል የግዕዝ ፊደል ኣይደለም። የእውሸት ወይም የፈጠራ የዓማርኛ ፊደል እንጂ የዓማርኛም ፊደል ኣይደለም። መጽሓፍትም ሲታተሙ የነበሩት በግዕዝ ፊደል በማተሚያ ቤቶች ትክክለኛ ቀለሞች ነበር። ኣሁንም ቢሆን በድሮው ዓይነት ወይም ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት መነሻው ይህ ፊደል በሆነው የዩኒኮድ የግዕዝ ፊደል ዓይነት ነው። የታይፕራይተርንና የማተሚያውን ፊደላት የማይለዩና ሁለቱ ኣንድ የሚመስሏቸው ኣሉ። በወልጋዳ፣ የተሳሳቱና ከሲታ ቀለማት ተጽፈው የሚቀርቡ ጽሑፎችና መጻሕፍት እየበዙ ነው። የፊደል መልክ ከኣላማረ ለማንበብም ኣያጓጓም። ጥሩ የግዕዝ ፊደል ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት “ነጋሪት ጋዜጣ”ን ሲያትምበት የነበረው ፊደል ነው። ብዙ መጻሕፍትም ታትመውበታል። ግዕዝ ኮምፕዩተራይድ ስለሆነ በኮምፕዩተር የሚቀርቡት በዓለም ዙሪያ ሊታዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ዓማርኛውን በላቲን ፊደል የሚጽፉ ኣሉ። ግዕዝ ድምጻዊ ስለሆነ የተለያዩ ቋንቋዎችን ያስከትባል። እንግሊዝኛ ውስጥ የኣሉ ኣንዳንድ ችግሮችም የሉትም። ግዕዝን በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብ ስለተቻለ ኣከታተቡ ከእንግሊዝኛው ጋር እኩል ሆኗል። ስለዚህ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ያካስራል። ይህ የእጅ ስልኮችንም ኣጠቃቀም ይመለከታል። ከላይ የተጠቀሱት ስሕተቶች ጥቂቶቹ ትግርኛንም ያጠቃልላሉ። ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ለኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ቀርቧል። ወጉንና ሕጉን ጠብቆ መጠቀም የእራስንና የፈጣሪዎችን መብት መጠበቅ ነው። በተሰረቁ፣ በማይጽፉና የኣልተሟሉ ሶፍትዌሮች መጠቀም ለእራስና ለሌላው መብት ኣለመጨነቅን ያሳያል። ለጽሑፍ ጥቅም የሚያስፈልጉ ነፃ ሶፍትዌሮች ስለኣሉ ከእንደግዕዝኤዲት ዓይነት በስተቀር መግዛት ግዴታ ኣይደለም። ትክክለኛ ሰዋስው፣ የተሟሉ ቀለሞች፣ ትክክለኛ ቅርጾች እና የመሳሰሉትን በኣሌሏቸው መጠቀም ለቋንቋው መዳከም ምክንያቶች እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ኣስፈላጊዎች ናቸው። ስሕተቶች ሲደጋገሙ ሊለመዱ ይችላል። ዶክተሩ ከሰዋስው ተሳሳቶች ኣንዱ ናቸው። ስለ ግዕዝና ዓማርኛ ፊደላት ሲጻፍ ስለ ግዕዝ ቋንቋ የሚመስሏቸው ኣሉና ይታሰብበት። ፊደላችን ለኣፍሪቃውያንና ሌሎችም እንዲተርፍ በወጉ መጠቀምና መንከባከብ ይጠቅማል። "ዓማርኛ" በግዕዙ "ዐ" የማይጻ'ፈው ቀለሙ ድምጹን ስለማይወክል ነው። ብዙ ስሕተቶችና ግድፈቶች የኣሉትን ጽሑፍ በዋቢነት ለመጠቀም ኣያስተማምንም። ምክንያቱም ደራሲው ኣስፈላጊዎቹን ጥንቃቄዎች ኣለማድረጉን ስለሚያሳይ ኣለመግዛት ወይም መተቸት ሳይሻል ኣይቀርም። ለምሳሌ ያህል "ነው" እና "ነህ" የመሳሰሉትን ቃላት "ነዉ" እና "ነክ" የሚሉ ኣሉ። "ኢትዮጵያ"ን በትክክል መጻፍ የማይችሉ ፊደል በሚገባ ኣልቈጠሩም ወይም ረስተዋል ማለት ኣይደለምን? የኣንዳንዶቹ ስሕተቶች ምንጮች ማተሚያ ቤቶች ናቸው። ለምሳሌ ያህል ቀደም የኣሉ ጽሑፎች ውስጥ የ"ፏ" ፊደል መስመሩ የኣለው ከላይ ሆኖ ሳለ የኣዳዲሶቹ ከታች ነው። ቀደም የኣለውን ምልክት ዶክተሩ ሲጠቀሙ የተሳሳቱ የሚመስሏቸው ኣሉ። ይኸንኑ መቀጠያ ከግዕዝ ወግ ውጪ "ፍ" ላይ ተደርጎ በቅርቡ የቀረበ ፊደልም ኣለ። ማተሚያ ቤቶች በትክክለኛዎቹ ቀለሞች ከመቶ ዓመታት በላይ የተጠቀሙ ስለሆኑ መሪዎች እንጂ ተከታይ መሆን የለባቸውም። ዓማርኛ ማጥበቂያ ኣይጠቀምም የሚሉ ፈረንጆችም ኣሉ። በዓማርኛ ፊደል ሲደረብ እንደእንግሊዝኛው ኣይጠብቅም። ኣንዳንድ የዓማርኛ ተጠቃሚዎች ዓማርኛ ሞክሼዎ ድምጾች የሉትም የሚሉ ኣሉ። "ኣባይ"ና "ዓባይ" ኣንድ ኣለመሆናቸው በቅርቡ ከወንድሜ ጋር ስከራከር የዓባይ ጉዳይ የ"ባ" መጥበቅና ኣለመጥበቅ ነው በማለት ስላሳመነኝ ምርምሮች ኣስፈላጊ ናቸው። ዶክተሩ ለመንግሥት የኣቀረቡት የፓተንት ማመልከቻ በወጉ ጥበቃ ሳይደረግለት መንግሥትና ኣብዛኛው ሕዝብ ከዶክተሩ በተሰረቁ የግዕዝ ቴክኖሎጂ ሲጠቀም ቆይቷል። ኣሁን ለውጥ መጥቷል ስለተባለ ሁሉም ሌቦች መስረቅ ማቆም ይገባቸዋል። ሌብነት ተለምዶ የዶክተሩን ሥራዎች የሚደብቁም ኣሉ። ይህ ጽሑፍ ብዙ ዓይነት ግድፈቶች ኣሉት፦ ለምሳሌ ያህል ኣራት ነጥብ የለውም፣ በሳድሱ “ው” ምትክ ካዕቡን “ዉ” ተጠቅሟል፣ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ፣ ኢትዪጵያ እና ኢትዩጵያ በማለት ኣቅርቧል። ኣንድ ሰው ነዋሪነቱን ወይም እንጂ ዜግነቱን መቀየር ኣይችልም። ሞክሼ ኆኄያት የዓማርኛ ሞክሼ በተለያዩ ቀለሞች የተወከሉ ኣንድ ዓይነት ድምጽ ኣሏቸው የሚባሉ ኆኄያት ናቸው ይባላል። ሞክሼዎች ቢያንሱ ሁለት ሰዎች ስለሆኑ ስሞች ተጋሩ እንጂ ኣንድ ስለኣልሆኑ ኣንዱ ሞክሼ ሌላውን ሊሆን ኣይችልም። ስለዚህ የዓማርኛ ቀለሞች ሞክሼዎች ስለሆኑ ኣንዱን በሌላው መተካት ይቻላል የሚባለው ኣስተሳሰብ ትክክል ኣይደለም። የኣማርኛ ሞክሼዎች ናቸው የሚባሉት የእየእራሳቸው ቅርጾች፣ ድምፆችና ስሞች ስለኣሏቸው ሞክሼዎች ኣይደሉም። ምሳሌ “ዓይን” የሚጻፈው በዓይኑ “ዐ” ነው። የዓማርኛ ሞክሼዎችን ማስወገድ በሚከተሉት ምክንያቶች ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ሞክሼዎች ኣንድ ስለኣልሆኑ ኣንድ ናቸው ብሎ ኣንዱን ማንሳትና ሌላውን መጣል ከመነሻውም የተሳሳተ ኣስተሳሰብ ነው። የእነዚህ ሞክሼዎች ፊደላት ድምጾች እስከ ዓ.ም. ድረስ ማለትም እስከ ዓፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት ድረስ ተለይቶ ሲነገር ነበር። ሞክሼ ቀለሞች ይቀነሱ የተባለው ኃሳብ የመጣው በታይፕ መኪና ዘመን መርገጫዎቹ ስለኣነሱ ነበር። የኣማርኛ የጽሑፍ መሣሪያ ዓማርኛ ስለኣልጻፈና ግዕዝ በዶክተር ኣበራ ዲጂታይዝድ ስለሆነ የታይፕ መሣሪያውና ቅጥልጥል ቅርጾቹ ቀርተዋል። ኣሁን ሁሉም ቀለሞች ዲጂታይዝድ ስለሆኑ የዱሮ ችግሮችም መፍትሔ ኣግኝተዋል። መፍትሔ የፈጠሩትን ማመስገንና ሥራዎቻቸውን ማስተዋወቅ የጥቂቱ ብቻ መሆን የለበትም። የኣማርኛ ታይፕራይተር ፊደል የዩኒኮድ ፊደል እንዲሆን የሞከሩት በሳይንሳዊ መረጃ ተሸንፈው ቀርተው ትክክለኛዎቹ የግዕዝ ቀለሞች የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ገብተዋል። ይህ ከሆነ በኋላ ስዉ የሚያውቃቸው ቀለሞች ይቀነሱ ማለት የተማረውን ማስቸገር ስለሆነ ተገቢ ኣይደለም። ምክንያቱም የእያንዳንዱ ቀለም የሚከተበው በሁለት መርገጫዎች ስለሆነ በኋላም ከኣንድ መርገጫ የተረፉት ኣብላጫዎቹ የግዕዝ ቀለሞች የሚከተቡት በሁለት መርገጫዎች ስለሆነ የሞክሼዎች መኖር የፈጠረው ችግር የለም። ኣንዳንዶቹ ሞክሼዎችን የሚከትቡት ከኣንድ የመርገጫ ቍልፍ ስለሆነ እያንዳንዱን ሞክሼዎች የሚከትቡት ብዙ መርገጫዎችን በመጠቀም ነው። ሞክሼዎችን የሚጠሉት የማያዋጣው መክተቢያዎቻቸውን ለመጥቀም ሊሆን ይችላል። ይህ በተለይ የዓማርኛውን ቀለሞች በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ መክተብ የሚፈልጉትን ይመለከታል። በስመ ሞክሼና መሻሻል ሞክሼዎች የኣልሆኑትን መቀነስ የፈለጉ ኣሉ። ምሳሌ፦ “ጐ”ን በ“ግወ” መተካት። ይህ ድምፃዊ ፊደላችንን ወደ ኣክሳሪው ፊደላዊ ፊደል በመቀየር ያዳክመዋል። የፊደል ጥቅም ቋንቋን ለመግለጽ እንጂ ለፊደል ኣጠቃቀም ሲባል ቋንቋን መቀየር ወይም መቀነስ ኣይደለም። የሞክሼዎቹ ማንነት በጥናት ላይ የተመረኰዘ ኣይደለም። ለምሳሌ ያህል መንትያ እንጂ ሞክሼዎች ኣይደሉም የሚሉ ኣሉ። ሞክሼዎችን መቀነስ ጥቅም ቢኖረው ኖሮ የ“ከ" ቤት ድምጽን የሚጋሩትን (“ሲ”)፣ (“ኬ”) እና (“ኪው”) (ምሳሌ እና ወይም “ኬክ” እና “ኲን”) የላቲን ቀለሞች ተጠቃሚዎቻቸው ሊቀንሷቸውና ሦስቱንም ብቻ መጠቀም በመረጡ ነበር። ይህ ኣስቸጋሪነቱን ለማመልከት የቀረበ ምሳሌ ነው። ፈረንጆች ለእነዚህ ቀለሞቻቸው የተለያዩ መርገጫዎች ቢመድቡም ለእነ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “ኸ”፣ የግሎቻቸው መርገጫዎች መመደብ ኣይገባም የሚሉ ኣሉ። ዶክተሩ ይገ‘ባል በማለት ይኸን ኣይደግፉም። ሞክሼዎች እንዲጠፉ ከመቸኰል ልዩነታቸውንና ጥቅሞቻቸውን ማስተማር ከምሁራን ይጠበቃል። ምሳሌ፦ ኣለ። ሞክሼዎች የሌሉት ጽሑፍ ተለምዶ ሞክሼዎቹ ሊረሱ ይችላሉ። ሞክሼዎችን የማያውቋቸው ምሁራን የቆዩ ጽሑፎችን በሚገባ ላያውቁና ትርጕሞቻቸውን ላይረዱ ይችላሉ። ዶክተሩ የሠሩት የማጥበቂያና የማላልያ ቀለሞችም ላይጠቅሙ ይችላሉ። በቍጥሮቹ በኣለመጠቀም የተነሳ የግዕዝን ኣኃዞች የማይለዩ ምሁራን ኣሉ ይባላል። ምክሼዎችን የማይወዱ ጥቅሞቻቸውን መማር የማይፈልጉ ሊሆኑ ይችላሉ። የማይጽፉና ያልተሟሉ መክተቢያዎች የሚያቀርቡ ስለኣሉ ዘላቂ ችግሮችን ሲፈጥሩ ዛሬ መታገስ ኣስፈላጊ ኣይደለም። (የሞክሼዎች ኣለመኖር የፊደላቱን ቊጥሮች በማስቀነስ ኣከታተብ ቢያቀል'ም ኣማራጭ እንጂ ግዴታ መሆን የለበትም ባይ ናቸው ዶክተሩ። ምክንያቱም ኣማራጭነቱ አንደማያዋጣ ኣቅርቦ ማሳመን ስለሚቻል ነው።) ወደፊት በኮምፕዩተር እንድንራቀቅ ትክክለኛዎቹንና ሳይንሳዊ መሠረቶችን ስለፈጠርን ከሞክሼዎች መኖር ይልቅ ኣለመኖር ሊጎዳ ይችላል። ወደፊት ኮምፕዩተር ስለሚያስተካክለው የሞክሼዎች ኣጠቃቀም ችግር ስለማይሆን የሚያስቸግሩት ቀለሞቹን የማያውቁት ሊሆኑ ይችላሉ። ጥቂት የኣናሳ ተናጋሪዎች ቋንቋዎች ቀለሞች የተሠሩት ሞክሼዎች የተባሉትን በመጠቀም ስለሆነ ሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚያውቋቸውን የዓማርኛ ቀለሞች የማያውቁ ዓማርኛ ተናጋሪዎች መኖር ዓማርኛ ቋንቋንና ፊደሉን ይጎዷቸዋል እንጂ ኣይጠቅሙም። ስለዚህ በስመ ሞክሼ ዓማርኛውን ማዳከም ለዓለም ሕዝቦች ጭምር ጉዳት ነው። ኣንድ ጽሑፍ ሞክሼዎች በተባሉትም ይሁን በሌሎቹ ቢጻፍ ልዩነቶቻቸውን ለማያውቁ የሚፈጥሯቸው ችግሮች የሉም። ዓማርኛ የግዕዝ ቋንቋ ፊደል ላይ የሚያስፈልጉትን ኣዳዲስ ቀለሞች ጨመረ እንጂ የግዕዝን ፊደል ኣልቀነሰም። የግዕዝ ፊደል መክተቢያ ሁሉንም ቀለሞቹን ማስተናገድ የቴክኖሎጂው መጀመሪያ ነው። የኮምፕዩተር ቴክኖሎጂው የገላገለው የግዕዝን ቀለም ለዘመናት ሲለቅሙ የነበሩትን የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሠራተኞች ጭምር ነው። ይህ ጉዳይ የአማርኛ የታይፕ መጻፊያውን ኣይመለከትም። የትግርኛ ቀለሞች በዓማርኛው ላይ ተጨማሪ ኣሏቸው እንጂ የተቀራረቡ ናቸው። የትግርኛ ፊደል ውስጥ የሌሉ ጥቂት የዓማርኛ ቀለሞች ኣሉ። ኣንዳንድ ፀሓፊዎች ግን ከትግርኛ ቀለሞች ውስጥ እነ “ሀ”፣ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “አ” እና “ዐ” የራብኦቻቸው ሞክሼዎች መስለዋቸው ተሳስተው ሊቀንሷቸው ኣጥቊረዋቸዋል። እንደ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ገለጻ ግን ኆኄያቱ ሞክሼዎች ስለኣልሆኑ መብታቸው መከበር ኣለበት ነው። ይኸንንምና የ“ሠ"ንና የ“ፀ" እንዚራን የኣጠቃለለውን ሞክሼነት በዓማርኛና በእንግሊዝኛ ተቃውመዋል። ሞክሼነት ልብወለድ እንጂ ሳይንስ ኣይደለም። ዶክተሩ ዲጂታይዝ ያደረጉትና የእያንዳንዱ ግዕዝ ቀለም መብት ተጠብቆ ዩኒኮድ ውስጥ እንዲገባ የታገሉት ሳይንስንና ታሪክን በመመርኰዝ ነው። የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች በፊደላቸው ሲጠቀሙ ብዛቱ ኣላስቸገራቸውም። ብዛት ችግር የሆነው መርገጫዎች ስለኣነሱ ስለሆነ የምሁራን ዓላማ ለችግሮቹ መፍትሔ መፍጠር እንጂ ለጊዜያዊ ችግርና መርገጫዎች ሲባል ፊደል መቀነስ መፍትሔ ኣይደለም። የታይፕራይተር ፊደል ቀናሾችና ቀንጣሾች ቢሳካላቸው ኖሮ ሞክሼዎቹ ስለማይኖሩ ዶክተሩ መፍትሔ ለመፍጠር ይቸገሩ ነበር። እንዲህም ሆኖ የታይፕራይተሩን ቍርጥራጮች ኣንዱ ግዕዝ ነው ብሎ ሲያወናብድ ዶክተሩን በመደገፍ የተማሩበት የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲም ይሁን የፊደሉ መብት ተከራካሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኣለፉት ዓመታት ስለ ዶክተሩ ሥራዎችም ይሁን ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች ዩኒኮድ እንዲገቡ ስለታገሉት ትንፍሽ ኣላሉም። ስር የሰደደን ነገር መቀየር ኣስቸጋሪ ነው። በስመ ሞክሼ ቋንቋው እየተበላሸ ነው። ለምሳሌ ያህል “ቍጥር”፣ “ሽኵቻ”፣ “ጫጕላ”፣ “ጓጕቷል”ን የመሳሰሉ ትክክለኛ ቃላት እንዳይኖሩ ሊሆን ነው። ያም ካልሆነ እንደላቲኑ ኣስተሳሰብ ሁለት ቀለሞች በኣንድነት ኣንዲነበብ የማድረግን ባዕድ ኣጠቃቀም ያስከትላል። “ጸ” እና እንዚራኖቹ የ“ፀ” እና እንዚራኖቹ ሞክሼዎች ናቸው ተብለው ቀርተው ዩኒኮድ የሚያውቀው “ጿ” በሞክሼ ስም እንዲወገድ ተፈልጓል። ስምንተኛው የ“ፀ” ድምጽ በስሕተት ስለሌለና ዩኒኮድ ስለማያውቀው ዩኒኮድ ውስጥ እንደማስገባት ዝም ማለት በስመ ሞክሼ ፊደሉን ለማበላሸት እንጂ ለመቀነስ ብቻ እንዳልሆነ ያመለክታል። ምክንያቱም ለኣንዳንዶቹ ሁለቱም “ጿ"ዎች ሞክሼዎች ስለሆኑ ነው። “ጸሎት” እና “ፀሓይ” ውስጥ “ጸ” እና “ፀ” ሲነገሩ ኣፋችን ውስጥ ምላስ የሚያርፈው በተለያዩ ስፍራዎች ነው። ትግርኛ እንደ ዓማርኛው የግዕዝ ቋንቋ ፊደል ላይ የሚያስፈልጉትን ኣዳዲስ ቀለሞች ጨምሯል። ግዕዝና ትግርኛ የሞክሼ ችግር የለባቸውም ይባላል። የሞክሼዎችን ችግር ዓማርኛ ላይ ማጥበቅ ለምን ኣስፈለገ? ኣንዳንድ ሰዎች ሞክሼዎች የግዕዙን ድምጽ በዓማርኛ ኣጥተዋል ይላሉ። የሞክሼዎች ጉዳይ ግን የቃላት ኣመጣጥንና በቀለም የትርጕማንን መለያየት ጭምር ያመለክታል። ምሳሌ፦ ዓይኑ “ዐ” የጠበቀ ነው ትክክለኛ ኣጠቃቀሞችንም ለመከተል መዝገበ ቃላት ኣሉ። “ፀ”ም የጠበቀ ነው። ትክክለኛዎቹን የኣማርኛ ኆኄያት የተከተለው ኣፄ ኃይለ ሥላሴ በ፲፱፻፷፪ ዓ.ም. የኣሳተሙት መጽሓፍ ቅዱስ ኣስተማማኝ ነው ይባላል። ቅዱስ ኦነሲሞስ ነሲብ “መጫፈ ቁልቁሉ”ን በግዕዝ ፊደል በ፲፰፻፺፪ በኦሮምኛ ጽፈው ሲያሳትሙ በኋላ ሞክሼዎች ከተባሉት ኣንዳንዶቹን ኣስወግደዋል። “ፍቅር እስከ መቃብር” 67 ሞክሼዎች ቀለሞች በሌሉት አማርኛ በክቡር ዶ/ር ሓዲስ ዓለማየሁ በ፲፱፻፶፪ ታትሟል። (ይህ የሆነው የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሞክሼ የተባሉትን ቀለሞች እየኣሉት ነው።) የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ከሆነ በኋላ በታይፕራይተር ዓይነት ቅጥልጥል ፊደል “ኣማርኛ መዝገበ ቃላት” ሞክሼዎች የተባሉትን በሌሉት ቀለሞች በ፲፱፻፺፫ ኣትሟል። ስለ ሞክሼዎች በምሳሌ ቀረቡ እንጂ ደራሲዎቹ በሥራዎቻቸው ታላላቅ የኣገር ባለውለታዎች ናቸው። ዶ/ር ኣበራ ሞላ “ኧ” ስምንተኛው የ“አ” ቤት ፊደል መሆኑን በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ጽሑፋቸው እስከኣመለከቱበት ጊዜ ድረስ ብዙዎቹ የኣላወቁት ይመስላል። ሓዲስ ዓለማየሁ “ኧ” የእራሱ እንዚራን እንዳለው ቈጥረው በስሕተት ስድስት እንዚራኑን ጭምር ቀንሼዋለሁ ብለዋል። የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲም "ኧ”ን ጥቅም ላይ ኣላዋልኩም ቢልም “ኧ”ን በስምንተኝነት ሳይጠቀምበት ጥሎታል። “አ” እና “ኧ” ሞክሼዎች ስለኣልሆኑ መጽሓፎቻቸው ውስጥ የማይመለከታቸው የሞክሼዎች ኣጠቃቀምና ውይይት ውስጥ ሁለቱም በስሕተት ጣልቃ ኣስገብተዋቸዋል። እነዚህ የኣለ በቂ ምርምር በስመ ሞክሼ የቀረቡ ጉዳዮች የኣለፉትን ችግሮች እያስወገዱ የኣሉትን የዶክተሩን ሥራዎች ኣክብደዋቸዋል። ሓዲስ የ“ኧ”ን ግዕዞች ብቻ ይዤ እርባታቸውን ጥያለሁ ቢሉም “ኧ” የግዕዝ ቤት ቀለም ኣይደለም። የ“ኸ”ን ግዕዝ ብቻ ይዤ እርባታቸውን ጥያለሁ ቢሉም “ኸ”ን ከእንዚራኖቹ ጋር ጥለዋል ማለት ይቻላል። ምክንያቱም ሓዲስ “ኹ”ን የጣሉት የ“ሁ” ሞክሼያቸው በመሆኑ "ኸ"ም የ"ሀ" ሞክሼያቸው ስለሆነ እንደሌሎቹ መጣ'ል ነበረበት። ዩኒቨርሲቲውም ነባር የፊደል ገበታው ውስጥ “ኧ”ን እንደ ግዕዝ ቤት ወስዶ እርባታዎቹን በጥያቄ ምልክቶች ኣቅርቧቸዋል። “ሀ” እና “ሃ” እንዲሁም “አ” እና “ኣ” ሞክሼዎች ኣይደሉም። እነዚህን ቀለሞች በስመ ሞክሼ ተሳስቶ በማስወገድ ማግደፍና ኣንዱን ቀለም ጥሎ ሌላውን ማንሳት ትክክል ኣይደለም። ይህ በስመ ሞክሼ ፊደል መቀነሰ ሳይሆን ፊደል ማስወገድ ነው። ለምሳሌ ያህል የሓዲስ መጽሓፍ ውስጥ ራብዖቹ “ሃ” እና “ኣ” የሉም። ሓዲስ መጽሓፋቸው ውስጥ በ“ሃ” ምትክ “ሀ”ን እና በ“ኣ” ቀለም ምትክ “አ”ን በስሕተት ተጠቅመዋል። እነዚህን ስሕተቶች ለማስወገድ በኣሁኑ ጊዜም አንደኣስፈላጊነቱ በ“ሀ” ምትክ “ሃ” እና በ“አ” ምትክ “ኣ”ን መጻፍ ትክክል መሆኑን ለኣንዳንዶቹ ማስገንዘብ ኣስቸግሯል። ምክንያቱም መመራመር በማይችሉባቸው ጊዜያት የተማሯቸውን ስሕተቶች ከኣደጉም በኋላ በምርምር ለማሳመንና ለማስተካከል ሲሞከር የሚያስቸግሩ ስለኣሉ ነው። ምሳሌ፦ “ኣበራ” አንጂ “አበራ” ትክክል ኣይደለም። በተጨማሪም ፊደል ቀናሾችና ቀንጣሾች ወደዱም ኣልወደዱም ዶክተሩ ኣሸንፈው ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች የዩኒኮድ መደብ ውስጥ ስለገቡ በእነዚህ ስሕተቶችና ግድፈቶች መቀጠል ኣስፈላጊ ኣይደሉም። ወደፊት ኮምፕዩተር ትክክለኛዎቹን ስለሚያቀረብ ዛሬ ሥራ ከማበላሸት ይልቅ መማር ሳይጠቅም ኣይቀርም። ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ የምልክት መርገጫ ላይ ወደዳር ከመደቧቸው መካከል “ኸ” ኣንዱ ነበር። ሓዲስ የ“ኸ” እና “ኧ” ግዕዞቻቸውን ብቻ ይዤ እርባታዎቹን ጥያለሁ ሲሉ “ኸ” ወደ ግዕዙ “ሀ” ድምጽ የቀረበና “ኧ” (እንደ “አርዝ”) የግዕዙ “አ” ድምጽ መሆኑን የተገነዘቡ ኣይመስልም። በሌላ በኩል ስማቸውን “ሀዲስ” እንጂ “ሃዲስ” ኣለማለታቸውና “ኸ” ኣራተኛ የ“ሀ” ሞክሼያቸው መሆኑን ስለኣልጠቀሱም የተቸገሩበት ይመስላል። ስለዚህ በሓዲስ ኣስተሳሰብ “ኸ” እና “ኧ” ለየት የኣሉ ቀለሞች ብቻ ተደርገው በስሕተት የተወሰዱ ናቸው ማለትም ይቻላል። የ“ኸ” ጉዳይ ኣንዳንድ ፈረንጆችንም ግራ ያጋባ ይመስላል። ለምሳሌ ያህል የ“ኧ” ድምጽ ወደ “እዋ” የቀረበ ስምንተኛ የ“አ” ቤት ቀለም በመሆኑ በተለምዶ “ኧረ” የሚለው ቃል ኣጻጻፍና ኣነባብ የተሳሳቱ ስለሆኑ ትክክለኛው “አረ” ነው። ስሕተቱ የ“አ”ን ድምጽ እንጂ የፊደሉን መልክ ኣይመለከትም። ምሳሌም እዚህ ኣለ። የስሕተቱ ምንጭ “አ” እና “ኣ” እንደሞክሼ ተወስደው የግዕዙ “አ” ሥራ ስለጐደለ ለ“ኧ” የተሰጠው ሳይሆን ኣይቀርም ይላሉ ዶክተሩ። ቢሳካላቸው ሓዲስ “ኣ”ን የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ “አ”ን እያጠፉ ፊደላቱ ላይኖሩን ሲደረግ የሚቈረቈር እየጠፋ ነውና ትውልዱን ምን እንደነካው ማወቅ ኣስቸግሯል። ሊቁ ኣለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ ኣንዳንድ ፀሓፊዎች ሲጠነቀቁ ብዙዎቹ አዐ፣ ሀሐኀ፣ ሰሠ፣ እና ጸፀ እና የሆኑበት ምክንያት ምን እንደሆነ ኣያስቡም ብለው የጥንቱ “አበገደ” ፊደል ኣኃዛዊ ስለሆነ “ጐ” ሰባ ቍጥርን ይወክላል ይላሉ። ሞክሼዎችን ለማስወገድ በተጀመረው ዘመቻ ሳቢያ የማያስፈልጉ ቀለሞች ዓማርኛ ቃላት ውስጥ ብቅ እያሉ የቋንቋውን የኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ጽሑፎች ማበላሸት ቀጥሏል። የዓማርኛ ፊደልን መጻፍ የኣልቻለው የጽሕፈት መሣሪያ ሳይጽፈው ተዘልሎ ኮምፕዩተር ደርሶለታል። ትክክለኛዎቹን ኆኄያት ከመማር ይልቅ መቀነስ የሚፈልጉትን ቴክኖሎጂ ስለሚደርስላቸው የሞክሼዎች ተግዳሮት ዘላቂ ኣይደሉም። በፊደሉ ብዛት የተነሳ መጻፍ ያስቸግራል ሲሉ የነበሩት መፍትሔ ከተፈጠረለት ዓመታት እንደኣለፉ የኣልሰሙ ይመስላል። የሚለውን የእንግሊዝኛ ዓረፍተ ነገር “ዘ ኲክ ብራውን ፎክስ ጀምፕስ ኦቨር ዘ ሌይዚ ዶግ።” ብሎ ሞክሼውን ሳይቀንሱ ጭምር በዓማርኛ መጻፍ ያታርፋል። ለምሳሌ ያህልም የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲው ማዕከል ሞክሼዎች እንዲቀነሱ ስለወሰነና “ኲ” በ“ኩ” አንዲተካ ስለፈለገ ቀለሙ ስለማይኖር “ኲክ” የሚለው ቃል በዓማርኛ እንዲጻፍ የሚፈልገው “ኩክ” በማለት ነው። ከላይ የቀረበውን 36 ሥፍራዎች የወሰደውን የእንግሊዝኛ ዓረፍተ ነገር በግዕዝ 24 ሥፍራዎች መጻፍ ስለሚቻል ሞክሼዎችን የማስቀረት ጉዳት አንጂ ጥቅም ኣያሳይም። ጽሑፍን በፊደላዊ ፊደል ከመጻፍ ይልቅ በግዕዙ ድምጻዊ ፊደል መጻፍ የወረቀትንና የኮምፕዩተር ጽሑፎች ማስቀመጫ ስፍራዎችን ስለሚቆጥብ ጽሑፎችን በላቲን ፊደል ለሚጽፉ ኢትዮጵያውያንም ትምህርት ነው። ምክንያቱም ዓረፍተ ነገሩን በኦሮምኛ ቁቤም ሆነ በአማርኛ ቁቤ መክተብም ኣያታርፍም። ዕውቀትን መቀነስ ሞክሼዎችን እንደመቀነስ ስንፍና እንጂ ጉብዝና ኣይደለም። ኢትዮጵያውያን ሞክሼ የተባሉትን ሳይቀንሱ ለረዥም ዘመናት በእጃቸውና ማተሚያ ቤቶች ሲጠቀሙ ቆይተው ታይፕራይተርን የኣዩ ለመቀነስ ታግለው ኣልተሳካላቸውም። ነገር በቀለለበት በእዚህ ዘመን እያንዳንዱ ፀሓፊ በቀላሉ ኣታሚ በሆነበት ጊዜ ስለ ፊደል ማስተማር እንጂ መቀነስ ምሁራዊ ተግባር ኣይደለም። “መሳሳት” (“ርህሩህ ወይም ስስ መሆን”) እና “መሣሣት” (“ትክክል ኣለመሆን”) ኣንድ የኣልሆኑት በዓማርኛ ድምጽ መጥፋት ኣይደለም። ኣንዳንዶቹ ፊደል መቀነስ የሚፈልጉት ለዓማርኛው ከኣላቸው ጥላቻ ወይም ኣጎብጋቢነት ሊሆን ይችላል። የፊደላቱን መልኮች ከመቀየር ኣንስቶ ግዕዙን በላቲን ፊደል መተካት የሚፈልጉ ኣሉ። “ተደጋግሞ የሚነሳውም የቱርክ (ኣረብኛ) ፊደሏን ትታ የላቲን ፊደልን መቀበሏና የጃፓን ፊደሏን ሳትቀይር በሥልጣኔ የመገስገሷ ታሪካዊ ተሞክሮ ነው። የእኛ ኣገር የብሔር ፖለቲከኞችና ኣመራራቸው የቱርኩ ልምድ ይሻለናል ብሎ ከወሰነ፣ ይኼው ሁለት አሥርት ዓመታት ገደማ ተቆጠሩ” ይላል ይህ ጽሑፍ። የዓማርኛውን ፊደል ትተው ቋንቋውን በላቲን ፊደል የሚጽፉ ባይጠፉም፤ ግኝቶቻቸው ከግዕዝ ኣልፈው ለላቲኑ ስለጠቀሙ ዶክተሩ በሥራና ተቃውሞ ቀድመዋቸዋል። ግዕዝ በማተሚያ፣ የኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ቴክኖሎጂዎች በሚገባ እየተጠቀመ ነው። እንደሰዉ ብዛት ግን ብዙ ጽሑፎች በኮምፕዩተርና የእጅ ስልኮች ተጽፈው ኣልተቀመጡም። በኣንድ የፊደል ዓይነት መጻፍ የኣልቻለን ሕዝብ ሞክሼዎች በኣሉትና በሌሉት ጻፍ ማለት ተገቢ ኣይመስልም። ምክንያቱም ኣዲስ ነገር ከጥንቱ ጋር ይቀርባል እንጂ ስለማይተካው ነው። የግዕዝ ቋንቋ ቀለሞች የዓማርኛ ቋንቋ ፊደል መነሻ ቢሆኑም የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ቀለሞችን ሞክሼዎች ናቸው በማለት ከዓማርኛ ሲቀንሷቸው ተስተውሏል። እነሱ የኣሰቡት ቢሳካላቸው እነ ”፣ ”፣ ”ን የመሳሰሉት ቃላት በእንግሊዝኛ እንጂ በዓማርኛ መጻፍ ላይቻል ነው። እንደእነዚህ ዓይነት ምሁራን ለማያውቋቸው የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ቋንቋዎች ቀርቶ ለሚያውቁት ዓማርኛ ደንታ የሌላቸው ሳይሆኑ ኣይቀሩም። በስመ ሞክሼ ፊደሉን መቀነስ የጀመሩት ጥቂት ዓማርኛ ተጠቃሚዎች ናቸው። የግዕዝ ፊደል ኣንዱ ትልቅ ችሎታ ለኣዳዲስ ድምጾች ኣዳዲስ ቀለሞች መፍጠር መቻሉ ነው። ዓማርኛ ፊደላቱን ከግዕዝ ቢወስድም ለቋንቋው የማያስፈልጉትን ሞክሼዎች መጣል ነበረበት የሚሉ ኣሉ። ዓማርኛ የሚጥላቸው ሞክሼዎች የሉም። እንግሊዞች ፊደላቸውን ለማሻሻል ሞክረው ኣልተሳካላቸውም እየተባለ ዓማርኛው መሻሻል ኣለበት ማለት ምንድን ነው? የግዕዝ ፊደል ውስጥ ለሌሉ ድምጾች ኣዳዲስ ቀለሞች መፍጠር ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ይህ ፊደላችን ለሌሎች ቋንቋዎችና ፊደላትም እንዲጠቅም ያስችላል። ዓማርኛ ከግዕዝ የወረሳቸውን ቃላት እየተጠቀመ እየኣደገ ነው። ፊደላቱ እንዳይቀነሱ ከሚፈልጉት ኣንዱ ዶ/ር ኣምሳሉ ኣክሊሉ ናቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግዕዝ ውስጥ የኣሉት በተናጠል እየቀጠሉ ሞክሼዎች የሚሆኑት ዓማርኛ ስለሆኑ የሚመስላቸው ኣሉ። ይህ እውነት ኣይደለም። ኢትዮጵያውያን ቀለሞቻቸውን ሳይቀንሱ በብራናና ማተሚያ ቤቶች ብዙ ደክመው በሚገባ ተጠቅመውባቸው ኣቆይተውናል። ይኸንኑ ፍላጎት ዶክተሩ በኮምፕዩተር ከማሳካት ሌላ ለዩኒኮድ ኣቅርበው የፊደሉ ፍላጎት ተሟልቷል። የግዕዝን ፊደል ሳይጽፍ የእንግሊዝኛውን የታይፕ መሣሪያ ዓማርኛን እንደጻፈ መቍጠርና ይኸንኑ በኮምፕዩተር መጠቀም እራስን ማታለል ነው። ፊደል መቀነስና መቀንጠስ ከታይራይተር ጋር ጊዜው የኣለፈበት ኣስተሳሰብ ነው። በኣንድ በኩል ፊደል በዛ እያሉ በሌላ በኩል የሚጠብቅና የሚላሉ ቃላት ችግር ፈጥረዋል የሚሉ ኣሉ። የፊደል ቀናሾች ስንፍና ወደ ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ስለገባና ኣንዳንዱን ሰው ከሚገባው በላይ ቸልተኝነት ስለተጠናወተው መቀስቀስ ኣስቸግራል። ስለ ቴክኖሎጂ ኣንብቦ ከመረዳት ይልቅ በወሬ የተገኘውን ሶፍትዌር እየተጠቀመ ፊደል ሲጎድልበት መጠየቅ የማይችል ሆኗል። በተቀነሱ ቀለሞች የሚጠቀሙ ደራስያን ጽሑፎች ኢንተርኔት ላይ ተፈልገው ላይገኙ ስለሚችሉ እራሳቸውና ሥራዎቻቸውን ከጥቅም ውጪ እያደረጉ ናቸው። ሁለተኛው የሞክሼዎች ጥቅም ዓማርኛ ከሌሎች ሴማዊ ቋንቋዎች ጋር ያለውን ዝምድና ስለሚያመላክቱ ነው። የዓማርኛ ሞክሼዎችን ለመለየት ከቃላቱ ብቻ ፍንጭ ማግኘት ስለሚቻል ምሳሌዎችን ከመሸምደድ ይልቅ መረዳት ሳይጠቅም ኣይቀርም ይላሉ ዶክተሩ። ለምሳሌ ያህል “ፀሓይ" የሚለ ቃል ውስጥ “ፀ" የጠበቀ ስለሆነ ፀሓዩን “ፀ" መጠቀም ይጠቅማል። “ንሥር"ና “ንስር"ን ለመለየት የቋንቋው ተናጋሪ በድምጽ ስለሚለያቸው “ንስር"ን ከእሳቱ “ሰ" ጋር በማያያዝ ኣገባቡን መለየት ይቻላል። ሌላ ምሳሌ “ምሥር" እና “ምስር" ሲሆን የጠበቀው እንደንጉሡ “ሠ” ባለ ንጉሡ “ሠ” “ምሥር" መሆኑ ነው። “ምሥር”ን ኣጥፍቶ እንደ “ምስ'ር” መጻፍ ሥፍራና መርገጫዎች በማስጨመር ያካስራል። “ምስር” እንዲሁ ወይም ያልጠበቀ ሲሆን “ምሥር” እንደ ዓይኑ “ዐ” የጠበቀ ስለሆነ ኣነጋገሩን ከፊደሉ ማገናኘት ሳይጠቅም ኣይቀርም። የሞክሼዎች ኣጠቃቀም ኃይማኖታዊ ነው የሚሉም ኣሉ። "ዓይን"ና "ዓመት" የጠበቁ ናቸው ቢባል የወንዙን ስም በ"ኣባይ" የሚጽፉ ኣሉ። ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ጥናት ያስፈልጋቸዋል። ለምሳሌ ያህል "ኣባይ" እና "ዓባይ"ን በድምጽ መለየት ይቻላል እንዳይባል የሚጠብቀውና የሚላላው "ባ" ቀለም ስለሆነ ነው። የሞክሼ ተብዬዎቹ መኖር ዓማርኛውን ኣዳበረው እንጂ ኣልጎዳውም። ይህ ፊደሉን የሚጠቀሙ ሌሎች ቋንቋዎችንም ሊመለከት ይችላል። የላቲን ፊደል ስለኣስቸገረ ፈረንጆች ኣዳዲስ ፊደላት እየፈጠሩ እያሻሻሉት ነው። የሞክሼ ፊደል ጉዳይ ጊዜው የኣለፈበት ክርክር ነው። በኮምፕዩተር ዘመን ቴክኖሎጅው ችግሮቻችንን ስለሚፈታ ፊደል ለመቀነስ መከራከር ግዕዛዊ ኣይደለም። ትክክለኛዎች ቀለሞች ከሌሉ ወደፊት ኮምፕዩተሩን ማናገር ቀላል ኣይሆንም። ሞክሼዎችን በሚፈልጉና በማይፈልጉ መካከል የሚፈጠሩት ችግሮች ሰዉ ላይ ሥራ ያበዛሉ። ኆኄያትን መጠበቅ ቅኔ ላይ ትንሽ ችግር ሊፈጥር ይችላል። በቅርቡ በግዕዝ ፊደል መብዛት የተነሳ መዝገበ ቃላትን መጠቀም ኣስቸገረ በማለት ፊደል እንዲቀነስ የሚል መጽሓፍ ተጽፏል። ይህ ጊዜው ያለፈበት ኣስተያየት ነው። ወደፊት ኣንድ የሚፈለግን ቃል ጽፎ ኮምፕዩተር ካለበት ያወጣዋል እንጂ መጽሓፍ ማገላበጥ ኣያስፈልግም። መጥበቅና ኣለመጥበቅ ከሞክሼዎች ጋር እንዳይምታቱ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በሌላ በኩል የዓማርኛን ሞክሼዎች መወገድ የሚፈልጉ ምክንያቶች ቢኖሯቸውም ኣንዳንዶቹ ከላይ ተጠቃቅሰዋል። ስድስት ዓይነቶች “ሀ”ዎች ቢኖሩም በሃሌታው “ሀ” እና እንዚራኖቹ ብንጠቀም የእነ “ሐ”፣ “ኀ”፣ “ኈ”፣ “ኸ” እና “ዀ” እንዚራኖች ጭምር ድምፆች ኣንድ ዓይነት በመሆናቸውና ዓማርኛ ውስጥ ስለጠፉም ስለማያስፈልጉ የቀለሞች ቍጥር ይቀንሳል ነው። ሞክሼዎች ቢቀነሱ ግዕዝን ለመክተብ በሁሉም ቍልፎች መጠቀም ኣያስፈልግም የሚሉ ኣይጠፉም። የኣለነው ዓለም እየሰለጠነና ነገሮች እየቀለሉ በኣሉበት ዘመን ስለሆነ መቀነስ የምንችላቸው ስለኣሉ መጓተት ኣያስፈልግም የሚሉ ኣሉ። በግዕዝ ፊደል የሚጠቀሙ የተለያዩ ቋንቋዎች ድምፆችን የሚወክሉት ኣዳዲስ ቀለሞች ተሠርተው ሥራ ላይ ስለዋሉ የማያስፈልጓቸውን ሞክሼዎች ማስወገጃ ጊዜው ኣሁን ነው የሚሉ ኣይጠፉም። ፓተንት ፓተንት ኣንድ ሰው ጥቅም ያለው ኣዲስ ነገር ወይም ግኝት ሲያቀርብ ከመንግሥት ለተወሰነ ጊዜ የሚሰጥ የባለቤትነት መታወቂያ ነው። በፓተንት የተጠበቀን ግኝት ያለባለቤቱ ፈቃድ መሥራት፣ መጠቀምና መሸጥ ክልክል ነው። ምሳሌ፦ እ.ኤ.ኣ. በ1878 የ“ቅውኽርትይ”ን የእንግሊዝኛ የታይፕ መሣሪያ ለፈጠረው ክሪስቶፈር ሾልስ ቍጥሩ 207,559 የሆነ የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንት ሲሰጠው የእጅ ስልክ በ1973 ለፈጠረው ማርቲን ኩፐር ቍጥሩ 3,906,166 የሆነ የኣሜሪካ ፓተንት ተሰጥቷል። በ2015 ግዕዝ በኮምፕዩተር ለተከተበበት ግኝት ቍጥሩ 9,000,957 የሆነ ለዶክተር ኣበራ ሞላ በዩናይትድ እስቴትስ መንግሥት የባለቤትነት መታወቂያ መጋቢት ቀን ዓ.ም. ተሰጥቷል። የፓተንቱ ስም፣ ቍጥር፣ ፈጣሪና የተሰጠበት ቀን ይታተማል። (የኢትዮጵያም ፓተንት ለዶክተሩ በሦስት ወራት ውስጥ እንደሚሰጥ ጥቅምት ቀን ዓ.ም. ተጽፏል።) ይህ ኣብሻ በሚል ስም የታወቀው ግኝት ግዕዝ በኮምፕዩተርና ከመሳሰሉት ከኣንድ ገበታ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች እንዲከተብ የኣስቻለ መደብ ነው። ለግዕዝ ፊደልም የመጀመሪያው ፓተንት ነው። ፓተንት ለፈጣሪው የሚሰጠው ዕውቀቱን ለሕዝብ ስለኣሳወቀ ሌሎች ያለፈጣሪው ፈቃድ እንዳይጠቀሙበት መከላከያ ሲሆን የመለያ ቊጥር ይሰጠዋል። ኣንድ ሰው ፓተንት ኣለኝ ሲል በስሙ ወይንም በፓተንቱ ቍጥር በመፈለግ ማረጋገጥ ይቻላል። ምሳሌ እዚህ፦ የግዕዝ ፓተንት ተሰጠ ማለትም ኣሜሪካ ግኝቱን ኣጣርቶ ለዓለም በማሳወቅ ስለግኝቱ ኣተመ እንጂ ፊደሉ ለኣሜሪካ ተሰጠ ማለት ኣይደለም። የግዕዝ ፊደል ቴክኖሎጂ በፓተንት የተጠበቀ ስለሆነ የግኝቱን ፈጣሪ መብት ማክበርና ማስከበር ከሕዝቡና መንግሥት ይጠበቃል። የግዕዝ ፊደል ሁለተኛ የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት ማሳወቂያ በቅርቡ ኣግኝቷል። ዶክተር ኣበራ ሞላ ቍጥሩ ዘጠኝ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰላሳ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ሁለት የሆነ ኣዲስ የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት ማሳወቂያ (ፓተንት) ሚያዝያ ቀን ዓ.ም. ተሰጣቸው። ይህ ኮምፕዩተሮች፣ የእጅ ስልኮችና ተመሳሳይ መሣሪያዎች ውስጥ የእንግሊዝኛ ፊደላት ከሚከትቡበት ኣንዳንድ ዘዴዎች ጋር የተቀራረበ ነው። በቅርቡ ኣንድ የኤውሮጳ ኩባንያ ከጤፍ ኣጠቃቀም ጋር የተያያዘ ፓተንት ስለኣገኘ ኢትዮጵያውያን ኣልተደሰቱም። ዶ/ር ኣበራ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው በፓተንቶች ባይጠብቋቸው ኖሮ ኢትዮጵያ ከማትወጣበት ጣጣ ትገባ እንደነበረ በሚገባ የተረዱ ምሁራን ኣሉ። የዶክተሩን ግዙፍ ውለታዎች ከግማሽ ደርዘን በላይ የሆኑ ድርጅቶች በሽልማት ሲያበረታቷቸው የኢትዮጵያን ቅርስ፣ ፊደልና ቋንቋዎች በኣዳዲስ ቴክኖሎጂ እንደጠበቁ ዛሬም ያልተገነዘቡ ኣሉ። የዶክተሩ ድካም ኣንዱ ምክንያት የኢትዮጵያውያን በፊደላቸው የመጠቀም መብት እንዳይወሰድባቸው ነው። ኣንድ ፓተንት የኣለው ፈጣሪ በፈጠራው ላይጠቀም ወይም ውጤቱን ላይሸጥ ይችላል። ቴክኖሎጂ ዓለምን ስለኣቀራረበና በፍጥንት እያደገ ስለሆነ ፓተንት ማግኘት ቀላል ነገር ኣይደለም። በፓተንት የሚጠበቅ ግኝት መጀመሪያ ለመንግሥት እንጂ ለሕዝብ መቅረብ የለበትም። በግዕዝ ፊደል ለብዙ ሺህ ዓመታት ስንጠቀም ስለነበረ ኣጠቃቀሙም ሆነ ፊደሉ ኣዲስ ነገር ኣይደለም። ዶክተሩ የፓተንትን ጥቅም ቀደም ብለው ያውቁ ስለነበረ ቴክኖሎጂው እንደጀመረ በመረዳትና በማበልጸግ የሠሩት በሌሎች እንዳንቀደም ነበር። ቴክኖሎጂውንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንደሚጋሩም በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ለመንግሥት በጽሑፍ ቢገለጽም ስላልተባበሩ መብታቸውን ለማስጠብቅ ወደ ኣሜሪካ መንግሥት ስለተመለሱ ኣሜሪካም የኢትዮጵያ ባለውለታ ናት። ዶ/ር ኣበራ የግዕዝ ፓተንት ኣገኙ ማለት ሰዉ በፊደሉ እንዳይጠቀም ተደረገ ማለት ኣይደለም። ሌላ የፓተንት ጥቅም ሌሎች ዓዋቂዎች ቀደም የኣሉትን እየጠቃቀሱ በማሻሻል ኣዳዲስ ፈጠራዎችን እንዲፈጥሩ ነው። የፓተንቶች በሌሎች መጠቀስ ለግኝቱ ፈጣሪ፣ ኩባንያና ኣገርም ክብር ነው። ለምሳሌ ያህል የዶ/ር ኣበራ ፈጠራዎች ከደርዘን በላይ የዓለም ፓተንቶችና ማመልከቻዎች ውስጥ ተጠቅሰዋል። የፓተንት መረጃዎችም ውስጥ ከግኝቱ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ሥራዎች በፈጣሪዎቹና መርማሪዎች ይጠቀሳሉ። በዶ/ር ኣበራ ሞላ ስምና በብቸኝነት እስከኣሁን (እ.ኤ.ኣ. 2018) የተሰጡዋቸው ፓተንቶች ቍጥር 9 ደርሰዋል። በኣሜሪካ ፓተንት የሚሰጠው ሰው ነዋሪነት እንጂ ዜግነት ኣይመዘገብም። ቍጥሩ 10,067,574 የሆነ ሦስተኛ የዩናይትድ እስቴትስ የግዕዝ ፓተንት በቅርቡ ለዶክተሩ ተሰጥቷል። በቅርቡም ኣራተኛ የዩናይትድ እስቴትስና ሦስት የኢትዮጵያ ፓተንቶች ለዶክተሩ ተስጥተዋል። ዶክተር ኣበራ ሌሎች ፓተንቶች እንዳሏቸው ቀደም ብሎ ተጠቅሷል። እንዶድ ትላትልን እንደሚገድል በደረሱበት ትልቅ ኣስተዋጽዖዋቸው የኣሜሪካ ፓተንት በማግኘት የታወቁት ሌላው ኢትዮጵያዊ ዶ/ር ኣክሊሉ ለማ ናቸው። የኣሜሪካ ፓተንቶች ያሏቸው ኢትዮጵያውያንም እነዚህ ብቻ ኣይደሉም። የመጀመሪያው የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንት ከተሰጠበት 1790 ኤ.ዲ. ጀምሮ የኣሉት ኢንተርኔት ላይ ይገኛሉ። ፓተንቶቹ ለቀለሞቹ ስለሆኑ ዶክተሩ መብቱን ያስከበሩት ለኢትዮጵያና ኤርትራ ፊደላት ነው። የዶ/ር ኣበራ ሞላ ፓተንቶች የኣማርኛ ታይፕራይተርን ስለማይመለከቱ ከእነሱ ጋር ግንኙነት የላቸውም። የፓተንትና ኮፒራይት መብቶች የተለያዩ ናቸው። ለምሳሌ ያህል የዶክተሩ የሞዴት የዩናይትድ እስቴትስ ኮፒራይት መብት እዚህ ኣለ። የግዕዝ ፊደል ከተለያዩ መብቶች ጋር በተያያዙ ተጠቃሚዎቹ እንዲጠቀሙ የመብት ንግድ ምልክት ተመዝግቧል ምልክት የመሳሰሉትን ፈጥረው በፓተንታቸውም ስለኣስተዋወቁ በዓማርኛ መጠቀም ተጀምሯል። የግዕዝ ፊደል የእጅ ስልክ ትክክለኛ ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂ ኣጠቃቀሞች ዘዴዎቹን ለፈጠሩት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ቍጥራቸው 9000957፣ 9733724፣ 10067574 እና 10133362 በሆኑ የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንቶች ተሰጥተዋል። ይቀጥላል...። የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ምልክት ግዕዝን ዲጂታይዝ ሲያደርጉ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ለዓለም ከኣበረከቷቸው ግኝቶች መካከል የግዕዝ ኣልቦ ወይም ዜሮ ቍጥር ምልክት መፍጠር ኣንዱ ነበር። በእዚህ ግኝት የተነሳ አንደጥቂት ባለ ኣኃዝ የዓለም ፊደላት ግዕዝ ኣዲስ ባለ ኣሥር ቤት የኣኃዝ ቀለሞች ኣሉት። እነዚህም ኣዲሱ የኣልቦ ኣኃዝ ምልክትና የሚከተሉት ከኣንድ እስከ ዘጠኝ የኣሉት የግዕዝ ቍጥራዊ ኣኃዞች ናቸው። የዘጠኙ ቍጥሮች መልኮች ከፊደላውያኑ ጋር ኣንድ ዓይነቶች ቢሆኑም የኣሥሮቹ ቍጥራዊ ኣኃዞች ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጓቸውን ሃያ የግዕዝ ቍጥሮችና በኋላም በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የእነዚህኑ ሃያ ፊደላዊ ቍጥሮቻችን መብቶችና ኣጠቃቀሞች ኣይመለከትም። ኣዲሶቹ ኣሥር ቍጥራዊ ኣኃዞች የዱሮዎቹ ሃያ ቍጥሮች ላይ የተጨመሩ ሆነው በኣጠቃቀማቸው የተለያዩ ናቸው። ግዕዝ ወደ ዩኒኮድ ከመግባቱ በፊት ዘጠኞቹና ኣልቦ በቊጥራዊ ኣኃዝነት ከኣራተኛው ፊደል በዶክተሩ የግዕዝ መክተቢያዎች ሥራ ላይ ውለዋል። የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ከሞዴት 480 ቀለሞች ኣንዱ መሆኑና መርገጫው እዚህ ኣሉ። የኣልቦ ኣኃዝ ዋና ጥቅሞች ሁለት ናቸው። ኣንደኛው በቍጥርነት ሲሆን ሌላው ስፍራ በመያዝ ነው። የግዕዝ ኣልቦና ቍጥሮች ኣስፈላጊ ናቸው። ኣልቦ የታወቀ ቍጥር ስለሆነ የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች በፊደላቸው የማያውቁበት ምክንያት የለም። የኣልቦ ስፍራ መያዝ ጥቅም በእንግሊዝኛው ዜሮ ለማስረዳት ያህል 2016 እና 201 ሲጻፉ በየተራ ምዕትና ዓሠርቱ ቤቶች ውስጥ ቍጥሮች እንደሌሉ ለማሳየት ነው። 2016 ከ201 የሚለየው በዜሮ ስፍራ ኣያያዝም ነው። እንደ ግዕዝ የኣሉ የጥንት ፊደላት የኣልቦ ጉዳይ በሚገባ ስለኣልገባቸው የቍጥር ምልክቶችን ከኣንድ ጀምረዋል። የዜሮ ምልክት ጥቅም በሕንዶች ተደርሶበት ከሺህ ዓመታት በላይ ሥራ ላይ ቢውልም ኢትዮጵያውያን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሳይጠቀሙበት ቆይተዋል። የማተሚያ መሣሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለግዕዝ ጥቅም ላይ በዋለባቸው መቶ ዓመታት ውስጥና ከአዚያ በፊትም የእንግሊዝኛውን (ኣረብኛ) ዜሮ ተጠቅመዋል። ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ እያንዳንዶቹ ቍጥሮቹ የቀረቡት በፊደልነት ስለሆነ ኮምፕዩተር ሁሉንም የግዕዝን ቍጥሮች በኣኃዝነት ኣያውቃቸውም። ፊደሉ በኮምፕዩተሮችንና ተመሳሳይ መሣሪያዎች በሚገባ እንዲጠቀም የጎደለበት የኣልቦ ኣኃዝ ተሠርቶ ከዘጠኞቹ ኣኃዞች ጋር ተገቢ ሥፍራዎች ውስጥ መቅረብ ይኖርባቸዋል። ስለዚህ ኣዲስ ኣሥር ቍጥሮች ስለተጨመሩ ፊደሉ ሠላሳ ኣኃዞች ኣሉት። ዶክተሩ የኣልቦን ቍጥር መልክ የኣቀረቡትም ኣሁን ኣይደለም። የግዕዝ ኣልቦ ሞዴት፣ ኢትዮወርድና ግዕዝኤዲት ፕሮግራሞች ኣራተኛው ፊደል ውስጥ ቀርበዋል። ኣዲሶቹ ኣሥር የግዕዝ ኣኃዛት ሥራ ላይ የሚውሉት በተግባር የእንግሊዝኛው ኣሥር ቍጥሮች ኣማራጭ በመሆን ነው። የኣዲሶቹ ኣሥር ቍጥሮች ኣጠቃቀም ከሃያዎቹ የተለየ ስለሆነ መለየት እንዲቻል ኣዲሶቹን “ኣበራ” ማለት ይቻላል። ኣዲሶቹን በቅርጽም መለየት እንዲቻል ትንሽ ለውጥ ማድረግ ሳይጠቅም ኣይቀርም፦ ምሳሌ ወንበሮቻቸውን ማንሳት። ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሲገባ ከዶ/ሩ ኣሥር ኣኃዛት በስተቀር ኣሥራ ኣንዶቹ የቀረቡት በፊደልነት ነበር። ከኣሥር እስከ መቶ የኣሉትንም የመደቡት የሰባተኛው ፊደል ኣኃዞች መርገጫዎች ላይ በፊደልነት ነበር። ይህ ስንጠቀምባቸው የነበሩትን የግዕዝ ቊጥሮች ኣጠቃቀሞችንም ኣልቀየረም። በኋላም ሃያዎቹ ወደ ዩኒኮድ የገቡት በፊደልነት ነበር። የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ሥፍራው የቍጥሮች መካከል በመሆን ነው። ከዜሮው በላይ በኣሉት ቍጥሮች ልክ ከዜሮ በታችም ኣሉ። ዶክተሩ የግዕዝን ዜሮ ፈጥረው የጨመሩት ቍጥሮቹ ኣልቦን ስለሌላቸው እንደሮማ ኣኃዛት ለሂሳብ ሥራ ኣይጠቅሙም ተብለው እንዳይዳከሙም ነው። ኮምፕዩተር የሂሳብና የጽሕፈት መሣሪያ በመሆኑ ግዕዝ ዜሮ ቍጥርን ስለሌለው ፈጥረውለት ዶክተሩና ሞዴት፣ ኢትዮወርድና ግዕዝኤዲት ፕሮግራሞቻቸውን የገዙ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። የቍጥሮችን ስፍራዎች ዩኒኮድ ለእንግሊዝኛ ስለመደበ ግዕዝ ወደ ዩኒኮድ ሲገባ የግዕዝን ኣኃዞች ከላቲኑ ጋር መጠቀም ስለኣልተቻለ የፊደላት ስፍራዎች ተሰጥተዋቸዋል። የግዕዝን ኣልቦ የኣለው የግዕዝ ኣሥር ቊጥራዊ ኣኃዛት ስፍራዎቹን ከእንግሊዝኛ ጋር መጋራት ይችላሉ። የግዕዝ ዜሮ ስለሌለ የጥንት ኢትዮጵያውያን ሂሳብ ኣያውቁም ወይም ኣይችሉም ማለትም ኣይደለም። የመደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛትና ማካፈል ዘዴዎች ምሳሌዎች እዚህ ኣሉ። የግዕዝ ፊደል ኣልቦ ቍጥርን ኣልነበረውም እንጂ ኣስተሳሰቡን ኣልተጠቀምበትም ማለት ኣይደለም። ኣንድ ስንዝር ሲለካ የመነሻው የኣውራ ጣት ስፍራ በቍጥር ሲገለጽ ኣልቦ ነው። የኣልቦ ኣጠቃቀሞች ዘመን መቍጠሪያችን፣ ኮከብ ቆጠራና ሌሎችም ውስጥ ኣሉ። በግዕዝ ኣልቦ ምልክት መፈጠር የተነሳ ኢትዮጵያ ለዓለም ኣዲስ የቍጥር ኣኃዝ ኣበርክታለች። በግኝቱ መጠቀምና ማስተዋወቅ የኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው። ከሠላሳ ዓመታት በላይ ሥራ ላይ የዋለ ኣኃዝና ፓተንቶችም ውስጥ የቀረበ በመሆኑ ከማተሚያ ቤት ጎደሎ ፊደሉና የታይፕራተር ቅነሳ ኣስተሳሰብ መላቀቅ ያስፈልጋል። ዶ/ሩ የግዕዝን ኣልቦ ምልክትና ኣጠቃቀም ስለኣቀረቡ የግዕዝን ሃያ ኣኃዞች የኣጠፉ የሚመስሏቸው ኣሉ። ኣንዳንድ ሰዎች ፊደሉ እንከን የሌለው የእግዚኣብሔር ስጦታ ነውና ኣትነካኩት ይላሉ። የዶክተሩ ገለጻ ሳይንስ እንጂ እምነት ኣይደለም። ዶክተሩ የግዕዝን ኣልቦ ከኣቀረቡ ከኣሥር ዓመታት በኋላ ለእኔም ታየኝ የእሚል ኣንድ ኢትዮጵያዊ ዩናይትድ እስቴትስ ኣለ። በኣሁኑ ጊዜ ነፃው፣ የሚሸጠውና የቁሱ ግዕዝኤዲት ውስጥ የኣሉት የግዕዝ ኣልቦና ቍጥሮች በኣኃዝነት ኣይሠሩም። የኣልቦውም ኣቀማመጥ ጊዜያዊ ነው። ኣልቦ ለረቀቁ የሂሳብ ሥራዎችም ኣስፈላጊ ነው። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፊዚክስ ስማር ኣልቦ ኣልቦ መሆኑን ማረጋገጤን ኣስታውሳለሁ። ግዕዝ ኣገር በቀል ፊደል ሆኖ ሳለ ለቅኝ ተገዥዎቻው ተሰጥተዋል። ግዕዝ የኣልቦን ኣኃዝ የኣልነበረው ከኣምስት ግኝቶቹ ኣንዱ ኣኃዝነት ስለነበረ ሳይሆን ኣይቀርም። የጥንት ግብጻውያን በኣኃዞቻቸው ማባዛትን ከኢትዮጵያውያን ሳያገኙ ኣልቀሩም። ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣደረግን የሚሉትን ኣንዳንድ ዋሾዎች ከኣሳጧቸው መካከል የግዕዝ ኣልቦ ኣለመኖሯቸው ኣንዱ ነው። ምክንያቱም በታይፕራይተር ኣጠቃቀም ሥራ ላይ ማዋል የሚቻለው የላቲኑን ኣኃዞች ብቻ ስለሆነ የዶክተሩን የኣልቦ ኣኃዝ ኣስተሳሰብ ኣልደገፉም። በነገራችን ላይ የመጀመሪያዎቹ የላቲን ካፒታል ቀለሞች የግዕዙን ኣኃዞች የመሰሉት እያንዳንዶቹ ቀንና ደራሲ በሌለው ጽሑፍ ሊያሳምኑን በመፈለግ ምንጩ የግሪክ ሳይሆን ኣይቀርም እንደሚሉት ሳይሆን ገልባጮቹ ግሪኮች ሳይሆኑ እንዳልቀረ መረጃ ኣለ። እዚሁ ጽሑፍ ውስጥ መጨረሻ ላይ መቀየሪያ ተብለው የቀረቡ ኣሉ። ሥራው ጥሩ ሆኖ ሳለ የቀረበው የኣረብኛን የኮምፕዩተር ቍጥሮች ወደ ግዕዝና ግዕዙን ወደ ኣረብኛው ያስቀይራል ተብሎ ነው። ዩኒኮድ ውስጥ የኣሉት የግዕዝ ቍጥሮች ፊደል እንጂ በኮምፕዩተር ወግና ኣሠራር ቍጥሮች ስለኣልሆኑ ለኮምፕዩተር ሂሳብ ሥራ የተዘጋጀ ኣለመሆኑ መታወቅ ኣለበት። ኣሁን በኣለው ወግና ኣሠራር ኮምፕዩተር በግዕዝ ኣኃዞች እንዲጠቀም ዶክተሩ ከብዙ ዓመታት በፊት የፈጠሩት የተሻለና ዘለቄታ የኣለው ዘዴ ነው። ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝ ከተደረገ በኋላ ለትላልቆቹ ኣኋዞች የተለያዩ ቀለሞች መፍጠር የሞከሩ ኣሉ። ምሳሌ ቍጥሮችን ከኣልቦ እስከ ዘጠኝ በኣሉ ቀለሞች መጠቀም ሳይንሳዊ ነው። ስለዚህ ኣዲስ ተጨማሪ የግዕዝ ኣኋዞችን መፍጠርን ዶክተሩ ኣያበረታቱም። በእዚህ ኣጋጣሚ ዶክተሩ ማሳሰብ የሚፈልጉት ኣንዳንድ ፀሓፊዎች ከሌሎች የኣገኙትን ዋቢ ኣድርጎ የማቅረብ ጥቅምና ኣስፈላጊነት መገንዘብ ነው። ዋቢ የሌለውን ጽሑፍ በዋቢነት መጠቀም ኣስቸጋሪ ነው። ኣልቦን ጨምሮ የእንግሊዝኛውን የኣኃዞች ኣጠቃቀም በተለይም ኣኃዞች በቃላት ሲገለጹ ጠንቅቆ ማወቅ ለትርጕም ጠቃሚ ነው። በዓማርኛ የጽሕፈት ሥርዓት ውስጥ የሒሳብ ምልክቶች ኣለመገኘታቸው ችግር ነው የሚሉ ኣሉ። ከሒሳብ ምልክቶቹ ይልቅ የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ምልክት ኣለመኖር ነበር ችግሩ። ምንም እንኳ የዜሮ ምልክት በቊጥሩ ስርዓት ውስጥ ባይኖርም፣ የዜሮ ጽንሰ ሐሳብ ግን ለብዙ መቶ ዓመታት አልቦ በሚለው ቃል ውስጥ ተካቶ እናያለን፣ በተለይ የማካፈል ስሌት ውጤቶች ውስጥ። የዶክተሩ ኣሥር ኣዳዲስ የግዕዝ ቍጥራዊ ኣኃዞች ከኣንድ እስከ ዘጠኝ ከኣሉት የዩኒኮድ መደብ ውስጥ የገቡት ዘጠኙ ጥንታዊ ፊደላዊ ኣኃዞች እንዲለዩ በቅርቡ ዶክተሩ መቀመጫዎቻቸውን ኣንስተዋል። ይህ ከግዕዝ ቀለሞች ጠባይም ጋር የሚሄድ ነው። ምክንያቱም ቍጥራዊና ፊደላዊ ኣኃዞች ቅርጾች መጋራት ስለሌለባቸውም ነው። ኣልቦው ጥቅም ላይ እንዲውል ዶክተሩ ከ"1" እስከ "9" ተጨማሪም ኣኃዞች በመጨመር የግዕዝን ቍጥሮች ብዛት ከ፳ ወደ ከፍ ቢያደርጉም ኣሥሮቹን በቊጥርኝት በመቀጠል አንድንጠቀም ኣድርገዋቸዋል። ዶክተሩ ከዩኒኮድ በፊት የፈጠሩት የኣልቦ ቍጥራዊ ኣኃዝ መቀመጫ የኣለው ቀለም ሲሆን ከዩኒኮድ በኋላ በቅርቡ የጨመሯቸው ከኣልቦ እስከ ዘጠኝ የኣሉት መቀመጫ የሌላቸው ኣዳዲስ ኣሥር ቍጥራዊ ኣኃዛት ናቸው። ስለዚህ የዶክተሩ ኣልቦ ኣኃዞች ሁለት ዓይነቶች ናቸው። ሕዝቡ በኣማራጭነት እንዲጠቀምበት የሚፈልጉትም በኣዲሶቹ ኣሥሮቹ ቊጥራዊ ኣኃዞች ነው። እነዚህ ግኝቶችና ኣጠቃቀሞቻቸው በፓተንት ማመልከቻቸውም ተጠቅሰዋል። ዶ/ሩ ፊደል ውስጥ የኣቀረቡት የግዕዝ ኣልቦ ዩኒኮዱ ውስጥ እንደኣሉት ኣኃዞች ፊደላዊ ነው። ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ዶክተሩ ከኣረቡ ሌላ ለኣሥሩ ኣኃዛዊ ቍጥሮች ከሰባት በላይ ምርጫዎች ሲኖራቸው ታይፕራይተሩ በኣንድ የእንግሊዝኛ ፊደል ምትክ የቀረበ ቴክኖሎጂ ስለሆነ ለኣንድም ግዕዛዊ ኣኃዝ ስፍራ ኣልነበነውም። የኣማርኛ ታይፕራይተር ኮምፕዩተራይዝድ ሲደረግ ለፊደላት የነበረው 128 ስፍራዎች ብቻ ስለነበሩና ለኣማርኛም በቂ ቦታዎች ስለኣልነበሩት ግዕዝን በታይፕራተር ዲጂታይዝ ኣደረግን የሚሉት ፊደሉንና መጻፊያውን የኣልነበራቸው ዋሾዎች ጭምር ናቸው። ለግዕዙ ግኝት ቀለም ቅርፅ የተጠቀሙት በእንግሊዝኛ እዝባራዊ ኣልቦ የሚባለውን ነው። ከላቲኑ (“ኦ”) ቀለም እንዲለይ የላቲኑም ኣልቦ ጠበብና ረዘም የተደረገ ስለሆነ ቅርፁ ወደ የግዕዝ ኣራት ቍጥር ዓይኑ “ዐ” እና ፀሓዩ “ፀ” የቀረበ ስለሆነ እንዳያምታቱ ነው። ስለ ዶክተሩ ኣልቦ ኣኃዝ ፈጠራ እስከኣሁንም ከኣልሰሙት መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይገኙበታል። የግዕዝ ቍጥሮች ዩኒኮድ ውስጥ የኣሉት በፊደልነት ቢሆንም እንጠቀምባቸው። ሃያዎቹ የግዕዝ ኣኃዞች ፩/1 ፪/2 ፫/3 ፬/4 ፭/5 ፮/6 ፯/7 ፰/8 ፱/9 ፲/10 ፳/20 ፴/30 ፵/40 ፶/50 ፷/60 ፸/70 ፹/80 ፺/90 ፻/100 ፼/10,000 ናቸው። ምሳሌ፦ ሰኔ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ሰኔ ቀን ዓ.ም.። የግዕዝ ምልክቶች የግዕዝ ፊደል ምልክቶቹንም ያጠቃልላል። በኮምፕዩተር ዘመንም ግዕዝ መሣሪያዎቹንና የእጅ ስልክ የመሳሰሉትን በሚገባ እንዲጠቀም ዶክተሩ የላቲኑን ምልክቶች በማውረስ ተጠቅመውባቸዋል። ከእነዚህም ዋናዎቹ ቍልፎች የኣሏቸው 32 ምልክቶች ናቸው። የኮምፕዩተር 42 እንግሊዝኛ ቁጥሮችና ምልክቶች ከግዕዙ ጋር ያቀረቡት ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ለግዕዝ ሥራ እንዲያገለግሉ ወስነው ከግዕዙ ቀለሞች ጋር በተመጣጠነ መልክ መሥራት ስለጀመሩ ኮምፕዩተር ገበታ ላይ ያሉት ኣጠቃቀሞች ለግዕዝም እንዲያገለግሉ ነው። ለምሳሌ ያህል “-”፣ እና የመደመር፣ መቀነስ፣ ማባዛትና ማካፈል የግዕዝ የሂሳብ ምልክቶችና ማስሊያዎችም ናቸው። የግዕዝ ምልክቶች ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የፈጠሯቸውን ኣሥር የዜማ ምልክቶች ያጠቃልላል። ምልክቶቹን ከቀለሞች በላይ መክተብ ከኣስቸገረ ከቀኝ ጎኖቻቸው መክተብ ይቻላል። እንዲህም ሆኖ የላቲኑን ምልክቶች በግዕዝነት ስንጠቀምባቸው መከተል የኣለብን ኣጠቃቀሞች ኣሉ። የእንግሊዝኛው የፊደል ገበታ ላይ የኣለው የላቲንን የኮለን ምልክት ኮምፕዩተሩ የሚያውቀው በኮለንነት እንጂ መልኩ የግዕዝን ሁለት ነጥብ ምልክት ስለመሰለ በነጥብነት ኣይደለም። ግዕዝ የእራሱ ኮድ የኣለው በኣለ ሁለት ነጥብ የባዶ ስፍራ ምልክት ስለኣለው ኮለንን በባዶ ስፍራ ምትክ መጠቀም ትክክል ኣይደለም። ሁለት፣ ሁለት ነጥቦች የኣራት ነጥብ ምልክት ኣይደሉም። ስለዚህ ሁለት፣ ሁለት ነጥቦች በኣራት ነጥብ ምትክ መጠቀም ትክክል ኣይደለም። ሁለት ኮለኖችም የኣራት ነጥብ ምልክት ኣይደሉም። ስለዚህ ሁለት ኮለኖችም በኣራት ነጥብ ምትክ መጠቀም ትክክል ኣይደለም። ሁለት፣ ሁለት ነጥቦች በዓማርኛ የመኪና መጻፊያ (ታይፕራይተር) ዘመን በኣራት ነጥብነት ስንጠቀምባቸው የነበረው ዓላማው ጽሑፉን ወረቀት ላይ ኣስፍሮ ማንበብ ብቻ ስለነበረ ነው። በኮምፕዩተር ግን የቀለሙ ኮድ ወይም ቍጥር ስለሚሰፍር ኣጠቃቀሞቹ የተለያዩ ናቸው። ይህን ኣጠቃቀም ኣለማወቅ ኣራት ነጥብ የሌላቸው ጽሑፎችን ያስከትላል። ኣራት ነጥብ የሌሏቸው ጽሑፎችን መተርጐምም ያስቸግራል። ሌሎች የተግዳሮት ምንጮች የዶክተሩን የመርገጫዎች ኣመዳደብ እናሻሽላለን ብለው የላቲኑን የምልክት መርገጫዎች ለግዕዝም ተመሳሳይ ኣጠቃቀሞች የኣቀረቡትንም በመጠኑ ይመለከታል። ስለዚህ ኣንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዓማርኛውን ኣራት ነጥብ በሌለው ከመጻፍ እንዲቆጠቡና ኣራት ነጥብ በሌለውም መጻፊያ እየጻፉ ጊዜያቸውን ከማባከን ቢቆጠቡ ይጠቅማል። ስለ ኣራት ነጥብ የተሳሳተ ኣጠቃቀም ተጨማሪ መረጃ የሁለት ነጥቦቹ ሁለት እየተከፈሉ ግማሾቹ ወደ ኣዲስ መስመር መዞር ነው። በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ኣጠቃቀም ምልክቶች በቀለማት እንጂ በባዶ ስፍራዎች መቀደም የለባቸውም። ዶክተሩ በእንግሊዝኛው የንግድ ምልክት ምትክ የግዕዝ የንግድ ምልክት (“ንም”) ምልክት ፈጥረው ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። ጮሌ ስልኮችን ወደጎን ኣዙሮ መጠቀም ያፈጥናል። በተለይ ይኸን ኣጠቃቀም እንደእንግሊዝኛው ለማቀላጠፍ ለሳድሳን መዝጊያ ዶክተሩ የ”ዠ“ን መርገጫ ለግራ ኣውራ ጣት እንዲጠቅምም ኣድርገዋል። የግዕዝ የነቁጥ ምልክት ተረስቶ ዩኒኮድ ውስጥ ስለኣልገባ መጨመር ይኖርብናል። ምክንያቱም ምልክቱ ከሌሎች የቁምፊው ቀለሞች ጋር እንዲሄድ መሠራት ስለኣለበት ነው። ኣሥሩ የያሬድ ምልክቶች ብዙ ሰዎች ከኣሏቸው የዶክተሩ ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደል ውስጥ ኣሉ። እያንዳንዱም የሚከተበው በሁለት መርገጫዎች ነው። በተሳሳቱ ኣራት ነጥቦች የተጻፉ ኣስተማማኝ የኣልሆነ ጽሑፎች ኣሉ። ከእዚህ ጽሑፍ ኣንድ ሁለት ኣንቀጾችን ኮፒ ተደርገው ገጽ ላይ ቢለጠፉ ችግሮቹን መመልከት ይቻላል። ግዕዝና ኦሮምኛ ግዕዝ በዶክተር ኣበራ ሞላ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ለዓማርኛ ተመድበው ከተረፉት ሦስት መርገጫዎች ኣንዱ ለኦሮሞ ሲሆን ሌላው ለትግርኛ ተሰጥቶ የቀረው ለኣገው/ቢለን ሥራ ላይ ውለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ጊዜ የኣንድ ድርጅት ኦሮሞ ምሁራን ተሰብስበው ከግዕዙ ይልቅ ላቲን ይበጀናል በማለት ግዕዙን ስለተዉት የሚከተሉትን መጋራት ሳይጠቅም ኣይቀርም። (ለኦሮሞው “ዸ” ፊደል የላቲኑ የመቀነስ ምልክት መርገጫ በዶክተሩ መመደቡን እዚህ ከቀኝ ጎን ከኣሉት ሥዕሎች 1989 ሞዴት የፊደል ገበታ ፲፱፻፹፪ ዓ.ም.” የሚለውን ማስተዋል ይጠቅማል። ቁቤ ኦሮምኛን በላቲን ፊደል የመክተቢያ ዘዴ ነው። ጥንትም ቢሆን ፊደላት በእጅ ጽሑፍ ሲጻፉ ላቲን ከግዕዙ በፍጥነት የተከተበበት ጊዜ ኣልነበረም። ምክንያቱም ግዕዝ ኣንድን ድምጽ በኣንድ ቀለም ሲያሰፍር ለኣብዛኛው የላቲን ድምጾች ሁለት ቀለሞች ስለሚያስፈልጉት ነው። የላቲንና ግዕዝ ቀለሞች (ኦሮምኛውን ግዕዝ ጨምሮ) በማተሚያ መሣሪያዎች ሲከተቡ የሁለቱም ቀለሞች መረጣዎች ኣጠቃቀሞች እኩል ነበር። በእዚህ ዘዴ በግዕዝ ቋንቋ በ1513፣ 1/0/] ኦሮምኛ ዓማርኛ መተርጐሚያ በ1850 ግድም በኣቶ ሓብተ ሥላሴ ታትሟል። መጽሓፍ ቅዱስን ወደ ኦሮምኛ የመተርጐሙንም ሥራ በማስፋፋት ከሌሎች የቋንቋው ተናጋሪዎች ጋር (ዋሬ፣ ሩፎ፣ ሾለን፣ ጀገን እና ገብረሚካኤል) በመተባበር ሙሉውን ኣዲስ ኪዳን ወደ ኦሮምኛ ተርጕመው በሰኔ 1862 ዓ.ም. ኣገባደዱ። ይህም ትርጕማቸው ለኦሮምኛ ሥነጽሑፍ የመጀመሪያው ኣዲስ ኪዳን መሆኑ ነው። ከጥቂት ዓመታት በኋላም ሚስዮኑ ክራጵፍ በ፲፰፻፸፩ ዓ.ም. በራሱ ስም ያሳተመው ይህንኑ የነኣለቃ ዘነብን ዓ.ም. ሥራ “ቁልቁሎታ መጻፎታ ከኩ ሐረዋ” ነበር። ኣለቃ ዘነብ ወደ ዓ.ም. ግድም የ“ኦሮምኛና ኣገውኛ መዝገበ ቃላት” ጽፈዋል ይባላል። የኣስቴር ጋኖን የትርጕም መጽሓፍ በመጠቀም በ፲፰፻፹፯ ዓ.ም. የታተመም የኦሮምኛ ሓዲስ ኪዳን፣ መጫፈ ቁልቁሉ በ፲፰፻፺፱ እ.ኤ.ኣ. ዓ.ም.) በቅዱስ ኦነሲሞስ ነሲብ፣ እና ከእዚያም ወዲህ እንደነ በሪሳ የኣሉ ጋዜጣዎች በግዕዝ ፊደል በኦሮምኛ ታትመዋል። መጫፈ ቁልቁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ፊደል በኦሮምኛ ቋንቋ የተጻፈ የምዕራብያኑ መጽሓፍ ቅዱስ ትርጕም ነው። ቀደም ብሎም በግዕዝ ፊደል በኦሮምኛ ከቀረቡት መረጃዎች ኣንዱ ጀምስ ብሩስ የወሰደው የ1790 የኦሮምኛ ትርጕምና የኢዘንበርግ ጽሑፍም ኣሉ። በዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝድ የሆነው ግዕዝ እ.ኤ.ኣ. በ1987 ለገበያ ቀርቦ በማተሚያ ቤቶች ፊደላት (ሞዴት ፕሮግራም) መክተብ ስለተጀመረ ምሁራን ደስ ሊላቸውና ሳይንሱንና ቴክኖሎጅውን ማወቅና ማስተዋወቅ በተገባ ነበር። ይህ በኣለመደረጉ እ.ኤ.ኣ. በ1992 በፕሮፌሰር ጥላሁን ጋሜታ ወደ ላቲን ለማዞር ከቀረቡት የኣማርኛ የጽሕፈት መኪናን የሚመለከቱት ጊዜ ለኣለፈባቸውና ኮምፕዩተርን የማይመለከቱ ምክንያቶች መልሶችም ነበሩ። ስለዚህ በግዕዝ ፊደል በማተሚያ ፊደላት ሲጻፉ የነበሩት በኮምፕዩተር ስለቀረቡ ቴክኖሎጂው ስለተሻሻለና ስለቀለለ ጉዳዩ ይመለከተናል የኣሉት የኦሮሞ ምሁራን ሊደሰቱ የሚገባ እንጂ ወደ ላቲን የሚያስዞር ኣዲስ ምክንያት ኣልነበረም። በጊዜውም በፕሮፌሰር ባዬ ይማም በዓማርኛ መልስ ቀርቦ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽና ፕሮፌሰር ሳሙኤል ክንዴ ወደ እንግሊዝኛ ተርጕመውታል። ለምሳሌ ያህል ወደ ላቲን የተዞረው ብዙ የግዕዝ ፊደላትን ከማስተማር የኣነሱትን ላቲን ማስተማር ይቀልላል የሚሉ ኣሉ። የላቲኑ ፊደል በቍጥር ማነስ ዕድሜ ልክ እስፔሊንግ ማጥናትንና ኣለመጨረስን ኣስከትሏል። የግዕዝ ፊደላት ቤቶች፣ ቅርጾችና ድምጾች በወጉ የተሠሩ ውብና ግሩም ፈጠራዎች ናቸው። ለምሳሌ ያህል የካዕብ ቤት ፊደላትን ድምጾች ለማሰማት ከንፈሮችን ማሞጥሞጥ ሲያስፈልግ በቅርጽ ከግዕዙ የሚለዩት ከቀኝ ጎን መሥመር በማስጨመር ነው። የስምንተኛው ቤት ድምጾች የሚጻፉት ከግዕዙ ወይም ራብዕ ግርጌ ወይም ኣናት ላይ መስመር በመጨመር ዓይነት ነው። ላቲን የእራሱ ችግሮች የኣሉት ፊደል ነው። በዶክተሩ ግኝት እያንዳንዱን የግዕዝ ቀለም በሁለት መርገጫዎች መክተብ ተችሏል። ላቲን ይኸን እየኣንዳንዱን የግዕዝ ቀለም በሁለት መርገጫዎች የመክተብ ችሎታ ስለሌለው ግዕዝን በግዕዝ ፊደል መክተብ ብልጫ ኣገኘ። ስለዚህ ኦሮምኛን በላቲን ፊደል መክተብ (ቁቤ) መሻሻል ኣይደለም። የኦሮምኛው የግዕዝ ፊደል ከሌሎቹ የግዕዝ ቀለሞች ጋር በዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ለኣለፉት ዓመታት በኮምፕዩተር ቀርቦ በኋላም በዩኒኮድ ዕውቅና ቢያገኝም ሁሉም ባይሆኑ ኦሮሞዎች ግዕዙን እርግፍ ኣድርገው ጥለው ወደ ላቲኑ ስለዞሩ የተፈጠሩት ችግሮች ቀጥለዋል። ለምሳሌ ያህል ላቲን እራሱን የሚገልጸው የኮምፕዩተሩ ገበታ ላይ በኣሉት ቀለሞች ብቻ ኣይደለም። በእጅ የጽሕፈት መሣሪያ ዘመን ታይፕራይተር ዓማርኛንና ኦሮምኛን ለማስጻፍ ስለኣልቻለ ላቲን ብልጫ ነበረው። የዶክተሩ ግኝት ለእውሸቱ (የፈጠራ) የታይፕራይተር የኣማርኛ ነገሮችና ለትክክለኛዎቹ የማተሚያ ቤቶች ፊደላት ኣጠቃቀሞች እጅግ ትልቅ ፈውስ ነበር። የታይፕራይተር ፊደል ለታይፕራይተር ሲባል የተሠራ በፍፁም ትክክለኛ በኣለመሆኑና ለብዙ ምዕት ዓመታትም በእጅ ስንጽፈው የነበረው ከኣለመሆኑም ሌላ የማተሚያ ቤት ፊደላችንም ስለኣልሆነ ከቁርጥራጮች የሚሠራውን ብጥስጥስ ዶ/ር ኣበራ የእውሸት ፊደል ይሉታል። ስለ ታይፕራይተሩ ድክመት ዶክተሩ እ.ኤ.ኣ. በ1991 ስለኣቀረቡ መሣሪያው ወደ ቁቤ ለመዞር ምክንያት መሆን ኣልነበረበትም። በታይፕራይተር በመቀጣጠል “ዸ”ን እና እርባታዎቹን መጻፍም ከአማርኛው የተለየ ችግር ኣልነበረውም። ቀደም ብሎም የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሲጠቀሙቸው የነበሩት የኦሮሞ የግዕዝ ቀለሞች እየኣሉና ከእዚያም ወዲህ በኮምፕዩተር የኦሮምኛው የግዕዝ ፊደል በዶክተሩ መከተብ መቻልና የተጠቃሚዎች መኖር ግንዛቤ ውስጥ ሳይገቡ በንቀት ብዙ ዓመታት ባክነዋል። ቴክኖሎጂ የችግር መፍቻ እንጂ ከችግር መሸሽያ ኣይደለም። ለቴክኖሎጂ ተብሎ ፊደል መቀየርና መቀነስም ነውር ነው። ለምሳሌ ያህል እንደ እንግሊዝኛው ላቲን ዓይነቶቹ የተጻፉት ቃላት የማይነበቡበት (ለምሳሌ ይህል ሳይቀነሱ ኣሉ። ቁቤ በላቲን ዋየሎች ከሚጠቀምባቸው በተሻለ ኦሮምኛ በግዕዙ ሊጠቀም ይችላል። ኦሮምኛን በፊደል ለመክተብ ከላቲኑ ቁቤ የግዕዝ ፊደል ይጠቅማል። መጽሓፍ ቅዱስ በከፊል እ.ኤ.ኣ. በ1841 በኦሮሞ ቋንቋ በግዕዝ ፊደል ተጽፏል። እንዲሁም እ.ኤ.ኣ. በ1875 የኦሮሞ ሓዲስ ኪዳን በግዕዝ ፊደል ታትሟል። በልሳነ ግእዝና በኣፋን ኦሮሞ (ግእዚፊ ኣፋን ኦሮሞቲን የተዘጋጀው መጽሓፈ ቅዳሴ ክታበ ቅዳሴ መጋቢት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢሊሌ ሆቴል ተመርቋል። የትርጐማና የኣርትኦት ሥራው 10 ዓመታት የወሰደው ባለ ሦስት ዓምዱ ክታበ ቅዳሴ፦ የመጀመርያው ረድፍ በግእዝ ቋንቋ፣ ሁለተኛው ረድፍ በኦሮምኛ ሆኖ በግእዝ ፊደል፣ ሦስተኛው ረድፍ በኦሮምኛ ሆኖ በቁቤ ፊደል ተጽፏል ይላል ሪፖርተር ጋዜጣ። ይህ የግዕዝ ፊደል ኦሮምኛን ኣይጽፍም ለሚሉት ማፈሪያ ነው። ስለዚህ ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን ግዕዝ ኦሮምኛን ኣይጽፍም በማለት ከጀመሩት የእውሸት ዘመቻዎቻቸውና ሕዝቡን ከማጣላትና ከመለያየት መቆጠብ ይኖርባቸዋል። ከእነዚህ ተርጓሚዎች ሌላ ለግዕዝ እድገት የሠሩ የኦሮሞ ሊቃውንት ኣሉን። መጽሓፍ ቅዱስ ሙሉዉን ወይም በከፊል ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ ቤቶች ከታተሙባቸው ቋንቋዎች መካከል የግዕዝ ቋንቋ (ግዕዝኛ)፣ ዓማርኛ፣ ትግርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሃዲያ፣ ሲዳሞ፣ ከንባታ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ይገኙበታል። መጽሓፍ ቅዱስ በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎችም ተተርጕሟል። ለምሳሌ ጋሞ ጎፋና ዳውሮ። ስለዚህ ለዓመታት በማተሚያ ቤቶች የግዕዝ ፊደላት ሲከተብ የነበረው ኦሮምኛ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ዛሬ ሥራ ላይ እየዋለ ግዕዝ ኦሮምኛን ኣይጽፍም ማለት ሳይንስ ኣይደለም። በኣነሱ የኆኄያት ግድፈቶች እስፔሊንጎች) እና ስፍራዎች ማስከተብ ብልጫዎች የነበረው የግዕዝ ፊደል በዶ/ር ኣበራ ግኝቶች የተነሳ የግዕዝ ፊደል ሓሳብን በኣነሱ ጊዜያት መርገጫዎች እና ገበታዎች በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች በማስከተብ ብልጫዎቹ ወደ ኣምስት ዓይነቶች ከፍ ብለዋል። ለምሳሌ ያህል “ዘ ኲክ ብራውን ፎክስ ጃምፕስ ኦቨር ዘ ሌይዚ ዶግ።” የሚለውን ዓረፍተ ነገር ላቲን በ36 ቀለሞችና በቁቤ በ45 ቀለሞች ከመክተብ ይልቅ በግዕዝ ፊደል በ24 ቀለሞች መክተብ የተሻለ ነው። ስለዚህ ግዕዝ እንኳን ከላቲኑ ቁቤ ከላቲኑ እንግሊዝኛ የተሻለ ነው። የቁቤ ሥርዓት እ.ኤ.ኣ. በ1992 ገደማ የተመሠረተው ኣንዱ ቀለም ኣንድን ድምጽ በመወከል ነው ተብሏል። የላቲንም ሆነ የቁቤ ቀለሞች ኣንድን ድምጽ በኣንድ ቀለም ከሚወክለው የግዕዝ ፊደል ጋር የመወዳደር ችሎታ የላቸውም። ላቲን ኣንዳንድ ድምጾችን የሚከትበው በሁለት ቀለሞች ስለሆነ ሁሉም ቀለሞች ለየብቻቸው ኣንድ ድምጽ እንዲወክሉ እንኳን ተደርጎ መጠቀም ኣይቻልም። ለምሳሌ ያህል እና የ“ዽ” እስፔሊንግ ስለሆኑ “ዲ” እና “ኤች”ን በሁለት ቀለምነት ጎን ለጎን ኣስቀምጦ እና ድምጽ ሰጪነት መጠቀም ኣይቻልም። ይህ ምሳሌ የሚያሳየው ቁቤ የተመሠረተው በጥቂት የኦሮሞ ምሁራን ማምታታትም ላይ መመርኰዙን ነው። ሌላ ምሳሌ ግዕዝ ዋየልና ማጥበቂያ የለውም የሚባለው ነው። ለግዕዝ ዋየል ስለማያስፈልገውና ስለሌለው ዋየል ባያስፈልገውም መዘርዘር ይቻላል። ኣንድ ቀለም የሚበቃውን የግዕዝ ማጥበቂያ ትቶ ለኣልተሟላ ማጥበቅ ሲባል ወደ ላቲን ዋየሎች መዞር ኣያታርፍም። ለላቲን የሚያስፈልጉትን ረዣዥም ዋየሎች ግዕዝ ስለሌለው ኦሮምኛን በላቲን ለመክተብ መረጥን ለሚሉት ሰበቡ ሳይንሳዊ ስለኣልሆነና ግዕዝ ሥርዓተ ንባብ (ማንሳት፣ መጣል፣ ማጥበቅ፣ ማላላት፣ ማናበብ፣ አለማናበብ፣ መዋጥና መቍጠር) ስለኣለው ሊታሰብበት ይገባል ይላሉ ዶክተር ኣበራ። የግዕዝ ፊደል በብዛቱ እየተወቀሰ ከእዚያ በበዙ ቀለምች መተካት ትክክል አይደለም። ቁቤ ሁሉንም የላቲን ዋየሎችንና እንዚራን ኣልተጠቀመም። ጥናት ላይ ተመርኵዞም ኦሮምኛ ሁሉንም የዓማርኛ ቀለሞች የኣለመጠቀምም መብት ኣለው። የተለያዩ ምክንያቶች በማቅረብ የግዕዝ ፊደል ኦሮምኛን ኣይጽፍም የኣሉትን እንደተሳሳቱ ሳይጠቅሱ ኣሁንም መጥቀስ ስለጉዳዩ ኣሁንም የሚጽፉት ጥቂት ምሁራን እራሳቸውን ማረም እንዳልቻሉ ያሳያል። የ“መ” እና “ማ”ን እስፔሊንግ እና ማድረግ መካሰር ነው። ወደ ላቲን የተዞረው ያለበቂ ጥናትና ሕዝቡ ሳያውቅና ሳይመርጥ በእውሸት ሕዝብ መረጠው ተብሎ ነው። ማንኛውንም የኦሮሞ ፊደል በሦስት መርገጫዎች መክተብ ነውር ነው። ማንኛውንም የኦሮምኛ ድምጽ በሦስት መርገጫዎች መክተብ ነውር ነው። ምክንያቱም ግዕዝ በኮምፕዩተር ኣይጻፍም ተብሎ የኣማርኛ ታይፕራይተር ማጓጓዝ እንደችግር በቀረበበት ጊዜ እያንዳንዱ የኦሮምኛ የግዕዝ ቀለም በኮምፕዩተር በሁለት መርገጫዎች በዶክተሩ እየተከተበ ነበር። ምንም እንኳን ግዕዝ እንከን የማይወጣለት ፊደል ነው ማለት ባይቻልም ለኣንድ ድምጽ ኣንድ ቀለም ለመመደብና ኣንድን ቀለም ለኣንድ ድምጽ ለመመደብ የተፈጠረ ነው ማለት ይቻላል። ግዕዝ በኮምፕዩተር እየተጻፈ በፊደላዊ ፊደል በላቲን ኦሮምኛውን በበዙ መርገጫዎች መክተብ ኣሁንም ሳይንሳዊና የተሻለ ነው ማለት ለቴክኖሎጂ ሲባል እራስን ዝቅ ማድረግና ኣርቆ ኣለማስተዋል ነው። ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን ዓማርኛ የማጥበቂያ ምልክት የለውም የሚሏቸውን ስሕተቶች ቀጥለውበታል። ዓማርኛ መጥበቅ የኣለበትን ቃል ከማይጠብቀው የሚለይበት ዘዴዎች ኣሉት። ከእነዚህ ኣንዱ ከሚጠብቀው ቀለም ኣናት በላይ ኣንድ ነጥብ መክተብ ሲሆን ምሳሌውም በ፲፮፻፺ ዓ.ም. ላቲንና ዓማርኛ መተርጐሚያ መጽሓፍ ውስጥ ታትሟል። ለምሳሌ ያህል “ላላ‘” እና “አላላ‘” ገጽ 1 እና “መነ‘ሣት” ገጽ 50 ላይ ቀርበዋል። ይኸንንም ኣጠቃቀም ሓዲስ ዓለማየሁ [በ“ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሓፋቸው ኣስፋፍተውታል። በኣዲስ ቅርጽ ለኮምፕዩተር እንዲስማማ መጥበቅ ከኣለበት ቀለም ኋላም እንዲከተብ ተደርጎ ማጥበቂያና ማላልያ በዶክተር ኣበራ ፓተንትም ውስጥ ኣ.ኤ.ኣ. በ2009 ተጠቅሰዋል። የቁቤ ዋየሎች “ኤ”፣ “ኢ”፣ “ኣይ”፣ “ኦ” እና “ዩ” ”፣ እና ስለሆኑ በቁቤ “ክታበ”ን ከ“ኪታባ” የመለየትና ማጥበቅ/ማላላት ችግሮች ቢኖሩትም ስለ ቁቤ ማጥበቅ፣ ማላላት፣ ማስረዘምና ማሳጠር የሚጽፉም ኣሉ። ይህ በኣዲስ ፊደልነት የቀረበውንም በብዛት ከግዕዝ ፊደል የበለጠውንም ይመለከታል። ግዕዝ ሰባት እንዚራን ሲኖረው ኦሮምኛ 10 ያስፈልጉታል የተባለው ትክክል ከኣለመሆኑም ሌላ ቍጥሩን ወደ 13 መጨመርም ስለኣላዋጣም ኣልቀጠለም። ትክክለኛው የግዕዝ ኣጻጻፍ “ኣፋን” እንጂ “አፋን“ ኣይደለም። ኣንዳንዱ “ድ“ን ሌላው ይጽፋል። ይህ ግዕዝና ኦሮምኛ ሳይንሳዊ ጽሑፍ ስለ ፊደላቱ እንጂ ቋንቋዎቹን ኣይመለከትም። የኦሮሞ ቋንቋችን መዳከም ስለሌለበት ስለ ፊደል ስንወያይ ሰለ ቋንቋና ሰለኣልፈጠርናቸው ኦሮሞነት መቀላቀል ሳይንስ ኣይደለም። የኦሮምኛው የግዕዝ ፊደል ከሌሎቹ የግዕዝ ቀለሞች ጋር በዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ለኣለፉት ዓመታት በኮምፕዩተር ቀርቦ በኋላም በዩኒኮድ፣ ዩናይትድ እስቴትስና የኢትዮጵያ መንግሥታት ዕውቅና ቢያገኝም ዛሬም ሶፍትዌር ውስጥ የሉም ብለው የሚጽፉ ኣሉ። ምሳሌ፦ “በዻኔ” እነ “ሸ”፣ “ቸ”፣ “ኘ”፣ “ዸ”፣ “ጠ”፣ “ጨ”፣ “ጰ”፣ እንዚራኖቹንና ሌሎች ቀለሞች የኣሉትን ለኦሮምኛ የሚያስፈልጉትን ቀለሞች ትቶ እነዚህን ወደ የሌሉት የላቲን ፊደል መዞር ሳይንስ ኣይደለም። የእነ“ጨ”፣ “ⶸ” እና “ꬠ” እንዚራን በቁቤ መለየት ቀላል ኣይሆንም። የኦሮምኛ ድምጾችንና እርባታዎችን የሚወክል የፊደል ገበታ (ከኣማርኛ ታይፕራይተር፣ ዓረብኛና ላቲን) ለጊዜው የተሻለው ላቲን ነው በማለት በስሕተት የቁቤ ኣጻጻፍ ሥራ ላይ ዋለ። ይህ ለዓማርኛው በኣለመደረጉ ዶክተሩ በመፍትሔው የደረሱለት ለኦሮምኛው ፊደል ጭምርም ነበርና ነውም። ምክንያቱም ዓማርኛና ኦሮምኛ በትክክለኛው የግዕዝ ፊደል ለብዙ ምዕት ዓመታት ተጠቅመውበታል። የጄምስ ብሩስና ሌሎች መረጃዎችም ኣሉ። ስለዚህ ዓማርኛውንም ሆነ ሌሎችን ቋንቋዎቻችንን ለማይጽፈው የዓማርኛ ታይፕራይተር ሲባል ፊደሉን የተዉት ቋንቋዎች በኣንዳንድ ተናጋሪዎች ስሕተት እንጂ በግዕዝ ፊደል ሲጠቀሙ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ስሕተት ኣልነበረም። በዶክተሩ ግኝቶች ከ“አ” እና “ኸ” መርገጫዎች የግዕዝ ቀለሞች እየተከተቡ ናቸው። ቁቤ ”፣ እና በተጠቀመው ዓይነት በ“ኣ”፣ “ኤ”፣ “ኢ”፣ “ኦ” እና “ኡ” የግዕዝ ቀለሞች መጠቀም ይችል ነበር። ኣንዳንድ ኦሮሞዎች “ቢራ” በላቲን ኦሮምኛ ተብሎ የሚጻፈው ግዕዝ ስለማይችለውም ነው ይላሉ። ምትክ “ብኢኢርርኣኣ” ተብሎ በግዕዝ ፊደል መጻፍ ይቻላል። ስለዚህ ቁቤ የተመሠረተው ሳይንሳዊ ጥቅም ላይ ኣይደለም። “ቢ” እና “ራ” ቀለሞችን ዓማርኛ በኣራት ዓይነቶች ማለትም “ቢራ”፣ “ቢ'ራ”፣ “ቢራ'” እና “ቢ'ራ'” መጠቀም ይችላል። “ብኢርኣ” ወይም “ቢርራ”ም ኣለ። ለምሳሌ ያህል “ለቆ” የሚለውን ቃል “ለቅቆ” ወይም “ለቆ'” ዓይነቶች መክተብና ማላልያና ማጥበቂያዎች መጨመርም ይቻላል። ቁቤ ዋየሎችን ከመደራረብ በ“ዓ”፣ “ዔ”፣ “ዒ”፣ “ዖ” እና “ዑ” የግዕዝ ቀለሞች ኣጠቃቀም ምሳሌዎች ጊዜ፣ ሥፍራና ጉልበት መቆጠብ ይችል ነበር። ከኣምስት የላቲን ዋየሎች የግዕዙ “አ”፣ “ዐ” እና ሰባት እንዚራኖቻቸው የተሻለ ገላጮችና ሥፍራ ቆጣቢዎች ናችው። እዚህ የቀረቡትም መረጃዎች ዋሾ የኦሮሞ ምሁሮችን ስለሚያሳፍሩ ዝም እያሉ የተጃጃሉት እነዚያኑ ጥያቄዎች ደጋግመው ይጠይቃሉ። ኣንዳንድ የኦሮሞ ምሁራን ግዕዝ የኦሮምኛ ቃላትን ኣይጽፍም በማለቱ በኣለማወቅ በስሕተቱ ገፍተውበታል። ጎዸቱ፣ ቶኮፋዸ፣ ዹፌ፣ ዹጉማ፣ ጀዺ፣ ዻባ፣ ዻራርቱ፣ ባዻዻ፣ ዻዻ፣ ጄዼ፣ ዼራ፣ ዽባፍ፣ ዽባ፣ ነንዾከዼስ፣ ዿ የእንዚራኑ ምሳሌዎች ናቸው። ዓማርኛው ላይ የተጨመሩት ስምንቱ የኦሮሞ ቀለሞች “ዸ”፣ “ዹ”፣ “ዺ”፣ “ዻ”፣ “ዼ”፣ “ዽ”፣ “ዾ” እና “ዿ” ናቸው። የኦሮሞውም ላይ የተጨመረ የምኢን የግዕዝ “ⶍ” ቀለምም ኣለ። ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን “ዻ” የግዕዝ ኦሮምኛ ቀለም በኣንድ ቀለም በሁለት መርገጫዎች ከመክተብ ይልቅ በማለት በሦስት ቀለሞችና በሦስት መርገጫዎች በኦሮምኛ መክተብ የተሻለ ሳይንስ ይመስላቸዋል። ኣንዳንድ የግዕዝ ቀለሞችን በላቲን ለመለየት ሦስትና ከሦስት በላይ ቀለሞችን መደርደር ያስፈልጋል። ግዕዝ ለኣዳዲስ ድምጾች ፊደል ሲፈጥር ቁቤ ለኣለው ፊደል ሌላ ድምጽና እስፔሊንግ በመጨመር መሻሻል ስለሚፈልግ ችግሩን ያባብሳል። ግዕዝን በላቲን እስፔሊንግ ለመጻፍ የሞከሩትም ጥቂቶቹን እስከኣሁን የኣዋጣቸው የሕዝቡ ስለቴክኖሎጂው በሚገ'ባ ኣለመረዳት ነው። በሚገባ ሳይታሰብበት የግዕዝ ቀለሞች በላጭነትና ጥቅሞች ሳይገለጹ ታልፈዋል። ምሳሌ፦ ግዕዝ ችግር የለውም ማለት ሳይሆን የላቲንን ቃላት እስፔሊንጎች ዕድሜ ልክ ቢማሩትም ማስታወስ ኣይቻልም። በእዚህ ላይ “ኦሮሞ” የሚለው ቃል እስፔሊንግ በላቲን በኦሮምኛ ቁቤ የኣለ በቂ ምክንያት ነው። የቁቤ ላቲንና የላቲንን እንግሊዝኛ ተደራራቢ እስፔሊንጎች ማስታወስ ኣስቸጋሪነት የተነሳ ትክክለኛዎቹን ማስተማርና ማስታወስ ሳያስቸግር ኣይቀርም። ግዕዝ ኣዳዲስ ቀለሞችን እየፈጠረ ሲያድግ ቁቤ በኣሉት የላቲን ቀለሞች ላይ እስፔሊንግ መጨመር ስለኣለበት ለሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እየጠቀመ ማደጉ ኣጠራጣሪ ነው። ምክንያቱም በሁሉም የግዕዝ ቀለሞቻችን ለመክተብ ከቁቤው የበዙ ልዩ የፊደል መክተቢያ እስፔሊንጎች መማር ሊያስፈልግ ነው። ስለዚህ ቁቤ የኣናሳ ተጠቃሚዎች በመሆን ኦሮምኛን፣ ኦሮሞውንና ኢትዮጵያን ሊያቈረቍዝ ይችላል። በኣጠቃቀም የላቲን ፊደል ከግዕዝ ሳድሳን ቀለሞች ጋር ኣንድ ዓይነት ነው። ግዕዝ እንዚራኑን በኣንዳንድ ቀለሞች ሲወክል ላቲን ዋየሎቹን ሳድሳኑ ጎን ማስከተብ ስለኣለበት ከሰባት ጊዜ በላይ እጥፍ ስፍራዎችን ያስባክናል። ይኸንን የግዕዝ ምሳሌ የ“ገ” 11 እንዚራን በላቲን ጠብቆና ሳይጠብቅ በመክተብ ልዩነቱን መመልከት ይቻላል። ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን በስሕተት ኦሮምኛ 10 እንዚራን ሲያስፈልገው ግዕዝ ሰባት ብቻ ኣለው ይላሉ። ላቲን ኣምስት ዋየሎች ኣሉት ተብሎ ኣምስቱኑ ዋየሎች እየደራረቡ ኦሮምኛ ኣሥር ዋየሎች ኣሉት ማለት ኦሮምኛውን መሳደብ ነው። ዋየል መደራረብም ትርፉ ስፍራ ማባከን ነው። የላቲን ዋየሎች ኣምስት ናቸው ቢባል እንኳን ለኦሮምኛ ኣምስት ዋየሎች በቂ ኣይደሉም። የቁቤ ዋየሎች ኣምስት ከሆኑ ከኣምስት በላይ እንዚራን ለኣላቸው የግዕዝ ቀለሞች ለመጠቀም ከላቲኑ ቁቤ የበዙ የእስፔሊንግ ችግሮች ይፈጥራሉ። ለምሳሌ ያህል “ዸ”ን በስምንት ዋየሎቹ ለመክተብ ለቁቤ ላቲን ከ20 በላይ ቀለሞች ሲያስፈልጉት ለግዕዙ በቂ ናቸው። ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን በስሕተት ላቲን 26 ቀለሞች ሲኖሩት የግዕዙ ብዙ ናቸው ይላሉ። የላቲን ዓይነቶች ከ26 በላይ ናቸው። ዋናዎቹ 26 የላቲን ቀለሞች እንደግዕዙ 37 የተሟሉ ኣይደሉም። የግዕዝ ፊደላት በ37 የግዕዝ ቤት ተከፋፍለው እንዚራኖቹ በድምጽና በቅርጽ በወጉ የተደረደሩ ስለሆነ ሕጻናትን ማስተማር እንደ ቢሆንም የግዕዝ ተማሪ የሚማረው እስፔሊንግ እንዳያስታውስ እንጂ ዕድሜ ልኩን እስፔሊንጎች እንዲፈልግ ኣይደለም። ለምሳሌ ያህል የካዕብ ቤቶቹ ቀለሞች የሚከተቡት በግዕዞቹ ላይ ከቀኝ ጎን መስመር በመጨመር ሲሆን ድምጾቻቸው እንዲሰሙ ከንፈሮችን ማሞጥሞጥ ያስፈልጋል። ላቲን እራሱን ለማሻሻል ኣዳዲስ ፊደላትን እየቀረጸ ሲሆን ቁቤ ሊጠቀምባቸው ኣልተዘጋጀም። የቻይና ሥዕላዊ ፊደላት ብዙ ሺህ ናቸው። ግዕዝ በእጅ ኣይጻፍ ይመስል ስለላቲኑ የእጅ ጽሑፍ የሚያነሱም ኣሉ። ዶክተሩ ኦሮምኛን በግዕዝ ፊደል በኮምፕዩተር ለመክተብ የሚያስፈልጉትን ከሠሩ በኋላ ለ24 ተነባቢና 10 ዋየሎቹ የኦሮምኛ ፊደላቱ 34 ቀለሞችን መፍጠር ስለሚያስቸግርና ኣስፈላጊ ኣይደለም ተብሎ ወደ ላቲን ዞርን ከቀረቡት ምክንያቶች ኣንዱ ነበር። ግዕዝ እንደኦሮምኛና ሲዳምኛ የኣሉትን (ኩሻዊ) ቋንቋዎችን ጥሩ ኣድርጎ ኣይጽፍም የሚለው ወይም የግዕዝ ኣንድን ድምጽ በኣንድ ቀለም መወከል እንደችግር ተቆጥሮ ወደ ላቲን ለመዞር የቀረቡት ምክንያቶች ወደ እውነት የተጠጉ ኣልነበሩም። ግዕዝ ለኣንድ ድምጽ ኣንድ ቀለምና ኣንድን ቀለም ለኣንድ ድምጽ በማድረግ የተራቀቀ ፊደል ነው። በግዕዝና በላቲን የሚጠቀሙ ኢትዮጵያውያን ስለማይግባቡ በየእለቱ እየተራራቁ ናቸው። ኣንድ ሕዝብ በተለያዩ ፊደላትና ቋንቋዎች እንዲጠቀም ማስገደድ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነበር። ኦሮሞው ዓማርኛና ፊደሉን እንዳይማር ተወስኖ የፌዴራል ሥራ እንዳያገኝ ሆኗል። እንደኦሮሞው ኣያያዝ በላቲን ፊደል የሚጠቀሙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ኣሉ። ኣይርላንዳዊው በርናርድ ሿው ግዕዝን ዓውቆ ቢሆን ኖሮ ላቲን ቦታ ኣይኖረውም ነበር የሚል ጽሑፍ በሰይፉ ኣዳነች ቢሻው እዚህ ቀርቧል። የላቲን ፊደል ለእያንዳንዱ ድምጽ ኣንድ ቀለም እንዲኖረው ተመኝተው ነበር። ላቲን የኣልተሟላና ኣክሳሪ ፊደል መሆኑንም ሿው ገልጸዋል። ስለዚህ ባለቤቱ የጠላውን ኦሮሞው ኣዲስ ኣግበስባሽ መሆን የለበትም። ላቲን ማወቅ ኦሮሞዎችን ከፊደሉ ተጠቃሚዎች ያቀራርባል ተብሎ እንደምክንያት ቀርቧል። ኢትዮጵያውያን የላቲንን ፊደል ስለሚማሩ ኣልተጎዱም። በግዕዝ እንደኣስፈላጊነቱ መጠቀም እንዲቻል የማላልያ ምልክት ለመጀመሪያ ጊዜ ስለፈጠሩ የዶክተሩ ፓተንትም ውስጥ ተጠቅሷል። የዩኒኮድ ግዕዝ መደብም ውስጥ ኣለ። ግዕዝ ኣንድን ቀለም ባለማጥብቅ፣ በማጥበቅና በማላላት ያስከትባል ይላሉ ዶክተሩ። ቁቤ የሚረዝሙ ድምጸ ልሳናትን የሚወክልበት ምልክት የለውም። ኤ ሾርት ዋየል እና ኤኤ ሎንግ ዋየል ናቸው ተብለው ዋየል፣ ማጥበቂያና ማላሊያም ሊሆኑ ኣይችሉም። ስለዚህ ላቲን ከግዕዙ ጋር ሲወዳደር ለቋንቋው የሚያስፈልጉትን እንዚራን በመቀነስ ኦሮምኛውን ጎዳው እንጂ ኣልጠቀመውም። የኦሮምኛን “ዽ” ድምጽ እንጂ ግዕዝ ኣይጽፈውም በማለት ማታለል የኦሮሞው ትግል ምክንያትም ይሁን ውጤት ኣይደለም። ኣንዳኣንድ የኦሮሞ ምሁራን ላቲንም ሆነ ቁቤ ከውጪ የተገኙ ናቸው በማለት ግዕዝ የሳባ ፊደል ነው ማለቱን ኣክርረውበታል። ግዕዝ ኢትዮጵያዊ ፊደል ነው። ዶክተሩ ለግዕዝና እንግሊዝኛ ፊደል የሚጠቅሙ ግኝቶችን በማቅረቡ ገፍተውበታል። የቁቤ ተከታዮች የኦሮሞ ምሁራን ላቲን እራሱን የኣሻሻለበትን ዘዴዎች እንኳን ሳይጠቀሙ ከግዕዙ ኣጠቃቀም እራሳቸውን ስለኣገለሉ ኢትዮጵያንና ዓለምን በመስኩ እንዳይጠቅሙ እየተደረገ ነው። በዓማርኛ “መሣሣት"ና “መሳሳት" እንዲሁም “ዓለማቀፍ"ና “ኣለማቀፍ" የመሳሰሉት ኣንድ ኣይደሉም። የግዕዝ ፊደል የኦሮምኛው ፊደል ውስጥ ያለውን “ዸ” እና ሰባት እንዚራን ቀለሞቹን ያጠቃልላል። ስለዚህ እንደ “በዻዻ” የኣሉትን ቃላት በ“በዳዳ” ወይም “ዻራርቱ"ን በ“ደራርቱ” መክተብ ግድፈት ነው። የ“ዸ” እንዚራን የግዕዝ ፊደላት ውስጥ መኖርን በመካድ ኣንዳንድ የኦሮሞ ምሁራን ኦሮሞውን ሲያጃጅሉት ዓመታት ኣልፈዋል። ለምሳሌ ያህል “በዻዻ” የሚለውን ሦስት ድምጾች የኣሉትን ቃል በሦስት ቀለሞች በስድስት መርገጫዎች በግዕዝ ከመክተብ ይልቅ በላቲን በስምንት ቀለሞች በዘጠኝ መርገጫዎች መክተብ ዓይነት የተሻለ መሆኑን ሕዝቡ መርጧል የሚሉ ኣሉ። ኦሮምኛን በግዕዝ ፊደል ማስተማር እንዲጀመር ሓሳብ ቀርቧል። ይህ ሌሎች ኦሮምኛውን እንዲማሩም ያበረታታል። ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን በምክንያቶች ስለተሸነፉ ስሕተቶቹን ተቀብለው እንደመታረም ኣዳዲስ ምክንያቶችን እያቀረቡ በማወናበዱ ቀጥለውብታል። ለምሳሌ ያህል የኣማርኛ ታይፕራይተርም ይሁን የግዕዝ ማተሚያ ቤቶች የኣረቡን ኣኃዞች ሲጠቀሙባቸው ስለነበረ እንደኣዲስ ነገር ግዕዝ የኣልቦ ኣኃዝ ስለሌለው ፊደሉ ለሂሳብ ኣይጠቅምም ብለው ወደ ላቲን ለመዞር እንደምክንያት ማቅረብ የሚሞክሩ ኣሉ። ቁቤ ወደ ላቲን የዞረው በኣኃዞቹ ምክንያት ስለኣልነበረና ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ የግዕዝ ዜሮ ቀለምን ፈጥረው ስለነበረ ቁቤ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሊመሠረት የሚፈለ'ገው በኣዲስ ቅጥፈት ላይ መሆን የለበትም። በቅርቡ በኣንድ ፀሓፊ “ተማሪ” የሚለውን ቃል በግዕዝ ቀለሞች ለማስቀመጥ ኣሥራ ሁለት ባይትስ ሲያስፈልገው በቁቤ ስምንት ባይትስ ይበቃዋል በማለት የላቲንን ብልጫ ለማሳየት ተሞክሯል። ሁለቱም የሚወስዱት ስምንት ባይትስ ነው። (ይህ ቀለሞቹ ፊታችን በኮምፕዩተር እስክሪን ወይም ወረቀት ላይ ሲታዩ ማለት ኣይደለም።) ግዕዙ ላይ ከተጨመሩት የተለዩ የእራሳቸው ፊደላት ከኣሏቸው 13 የፊደል ዓይነቶች ሌላ ወደፊት ለኣፍሪቃና ሌሎች ቋንቋዎች ኣዳዲስ ፊደላት ሲጨመሩ በየስሞቻቸው ይቀርባሉ። በፊደሉ መጠቀምንና ኣለመጠቀምን ዶክተሩ ኣያስገድዱም። “የኦሮሞ ሊቃውንት ባደረጉት ጥናት መሠረት ለኦሮምኛ የሚስማማውን ፊደል (ላቲንን) መርጠውለታል፤ ይህ ያለቀ፥ የደቀቀ ጉዳይ ነው፤ ኦሮሞ ያልሆኑትን የሚገዳቸው ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩ የሚገድደው ኦሮሞዎችን ብቻ ከሆነና ኦሮሞዎች ከተስማሙበት በጥላቻ ላይ የተመሠረተ ምርጫ ሊያደርጉ ይችላሉ። ኦሮምኛ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን ከታሰበ ግን፥ ጉዳዩ ብሔራዊ እንጂ ኦሮሞዎች ብቻቸውን የሚወስኑበት የኦሮሞዎች ጉልማ ሊሆን አይችልም። ጥያቄውም ከሌሎቹ ቋንቋዎች ይልቅ በኦሮምኛ ላይ የሚነሣው በዚህ ምክንያት ነው።” ይላሉ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ። ግዕዝ ለኦሮምኛ እንደሚበጅ የሚቀርቡ ጽሑፎች ቀጥለዋል። የፖለቲካን ችግር ሳይንስ ማድረግ መሞከር ተገቢ ኣይደለም። ኣንዳንድ ሰዎች “ዱ” ፊደል ሆኖ ቀለበቱ መካከል መስመር የኣለውን ቀለም (“ꬉ”) የኦሮምኛው የግዕዝ ፊደል ነው ይላሉ። ይህ ስሕተት ነው። እነ“ꬉ” የጋሞ ጎፋ፣ ዳውሮና ባስኬቶ ፊደላት ናቸው። በግዕዝ ፊደል ድምጽን ከፍና ዝቅ ማድረግ ለመለየት የሚያስችሉ ምልክቶችን መፍጠር ይቻላል። ይህ ለኦሮምኛው ኣስፈላጊ ኣይደለም። ዶ/ር ኣማረ ተግባሩ ኃይሌ ፊዳ በሚለው በ፳፻፲ ዓ.ም. በታተመው መጽሓፋቸው ገጽ 101 ላይ "የግዕዙ ፊደል ድክመቶቹን ለማስወገድ የሚያስችል ቅጥያዎች ከተደረጉለት ኣፋን ኦሮሞውን በግዕዝ ፊደል መጻፍ እንደሚቻል ዶ/ር ኃይሌ መናገራቸውን መመስከር እችላለሁ" ይላሉ። ግዕዝና ዓማርኛ ይህ ጽሑፍ ዓማርኛን የተመለከተ ስለ ፊደሉ (እንደ ኦሮምኛው) የዶክተሩ ኣስተዋጽዖ እንጂ ስለ ቋንቋው ኣይደለም። ስለ ቋንቋው በየሺሓሳብ ኣበራ እዚህ ጥሩ ቀርቧል። የግዕዝን ፊደል በኮምፕዩተር መጠቀም ኣዲስ ቴክኖሎጂ ስለሆነ የተጠቃሚው መሠረታዊ ሕጎችንና ወጎችን ማወቅ ኣስፍላጊ ናቸው። ቴክኖሎጂ ጠቃሚ ነው። እነዚህ ታውቀው በኢትዮጵያውያን ትጋት ብዙ ሚሊዮን ጽሑፎች በኣለፉት ዓመታት ቀርበዋል። የፊደሉ እድገት ለወዳጆቹ ትልቅ እርካታ ነው። ለምሳሌ ያህል ዶ/ር ዓለሙ ቢፍቱ በሞዴት፣ ዶ/ር ለይኩን ብርሃኑ በኢትዮወርድ መጽሓፎች ጽፈው ኣሳትመዋል። በቅርቡም ዶ/ር ኣክሊሉ ሃብቴ ግዕዝኤዲትንና ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደሉን ተጠቅመዋል። የመጀመሪያው የግዕዝ ትሩታይፕ ፊደላችን እንደኣስፈላጊነቱ እየታረመ የዩኒኮድ ፊደል የሆነው ትክክከኛ ቅርጾች እዚህ ጎን ከኣለው የኣቶ ኣብርሃም ያየህ የ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. መጽሓፍ ማሳሰቢያ ገጽ ሥዕል መመልከት ይቻላል። በዶክተሩ ፈጠራ ምክንያት መጽሓፎቻቸውን ጽፈው ለማሳተም የቻሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን ኣሉ። ከእነዚህም መካከል እ.ኤ.ኣ. በ1994 የዶክተሩን ፕሮግራም በመጠቀም ከ25 ዓመታት በኋላ ምስጋና የለገሷቸው ኣንዱ ዶ/ር ኣማረ ተግባሩ ናቸው። የዶ/ር ኣበራ ሞላ እና ጋሼ አበራ ሞላ (ስለሺ ደምሴ) ግንኙነትም እዚህ ኣለ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኣለማወቅ በተለይ ዓማርኛ ላይ ብዙ ችግሮች የኣደረሱ ኣሉ። ከግዕዝ ፊደል ተጠቃሚዎች ዓማርኛ ዋነኛውና ወሳኝ ነው። የኮምፕዩተር፣ እጅ ስልክና የመሳሰሉት የቴክኖሎጂ ግኝቶች በብዙ ቢሊዮን ዶላር ወጪ፣ በብዙ ሰዎች ድካም፣ ፓተንቶችና ምርምሮች የተገኙ ስለሆኑ ሶፍትዌር እንደማንኛውም ነገር የሚገዙ እንጂ ኣንዳንዶቹ እንደሚያደርጉት ሰርቆ መጠቀም ነውር ነው። ብዙ ኢትዮጵያውን እነዚህን ሁሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሳንከፍልባቸው በማግኘታችን እንደማመስገንና ለግዕዝ የሚያስፈልጉትን ገዝቶ ከመጠቀም ይልቅ ፊደሉ የእራሱ ገበታ እንዳይኖረው የሚፈልጉትን ጭምር ዓውቀውም ሆነ ሳያውቁ እየረዱ ናቸው። የግዕዝ መክተቢያ ሁሉንም ተጠቃሚ ቋንቋዎች ለማስተናገድ የሚችል መሆን ይኖርበታል። ችሎታውን ከኣለው ለዓማርኛው ብቻ ማቅረብ ሲቻል ዓማርኛ ብቻ የሚያስጽፍ ግን ዓማርኛውን ኣደጋ ላይ የሚጥል ነው። ለምሳሌ ያህል “ቜ”ን በ6 መርገጫዎች የሚከትብና “ⷄ”ን ለመክተብ ከ6 በላይ ተጨማሪ መርገጫዎች የሚያስፈልጉት ኣለ። እየኣንኣንዱን ቀለም በሁለት መርገጫዎች መክተብ ሲቻል የ“ጬ”፣ “ⶼ”፣ “ꬤ” እና “ⶐ” ኣከታተብ ለመለየት የመክተቢያ እስፔሊንግ ማስታወስ ወይም መዝገብ (መዝገበ ፊደል) ያስፈልጋል። ዓማርኛ የማያስጽፍ መጻፊያ ይጽፋል ተብሎ ኢንተርኔት ላይ ለዓመታት ተቀምጧል። በዶክተሩም የፓተንት ማመልከቻዎች ቀርበዋል። ይኸን የሚያስተውልና የሚቃወም የተማረ ኢትዮጵያዊ ኣለመኖር የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ነውና ይታሰብበት። ምሳሌ፦ “ትዝታ”፣ “ድድ”፣ “ህህ”፣ እና “ሏ”ን የማያስጽፉ ኣሉ። ምክንያቱም ሕዝቡ ትናንሽ ችግሮችን እየተመለከተ መቃወም ከኣልቻለ እራሱን ከከባድ ችግሮች ለመከላከል ኣለመዘጋጀቱን ስለሚያሳይ ነው። ይኸን ኣጻጻፍ የወደዱ ከመቶ ሺህ በላይ ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያንን ምን እንደነካቸው ማስገረም ቀጥሏል። ምክንያቱም ጥቂት የኦሮሞ ምሁራን ግዕዙን ለመጥላት መጥላት ምክንያት ሊሆን ሲችል የኣንዳንድ የዓማርኛ ፊደል ተጠቃሚዎች በኣምታታቾች መጃጃል ምክንያቱ ኣልተገኘም። ላቲን እስፔሊንግ የሚጠቀመው ለቃላት ሲሆን የኣንዳንድ ኢትዮጵያውያን ፊደሎቻቸው ቃላት ይመስሉ በላቲን እስፔሊንግ መክተብ ምን ይባላል? ኣንዳንድ ኢትዮጵያውያን ለብዙ ዓመታት ዓማርኛውን በእንግሊዝኛ ፊደል በተገኘው እስፔሊንግ ሲጽፉ ቆይተዋል። እንደ ፓልቶክ የኣሉ ፕሮግራሞች ምሳሌዎች ናቸው። በፓልቶክ ለመሳተፍ ከተቻለ እንደ ግዕዝኤዲት የኣሉትንም የዓማርኛ መክተቢያ መጠቀም ስለሚቻል ኣንዳንድ ዓማርኛ ተናጋሪዎች ዓማርኛውን በኣለመጠቀም እያዳከሙት ናቸው። በዓማርኛ እያወሩ በላቲን መጻፍ ከቀጠለ ነገ ዓማርኛውን መጻፍ የሚችሉ ላይኖሩ ይችላሉ። ይህ የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክ ከኣለው ሕዝብ ትውልድ ኣይጠበቅም። ኣንድ የዓማርኛ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ሲጀመር ኣስተያየት በእንግሊዝኛ የሚሰጡ ኣሉ። በእንግሊዝኛ የሚጽፉት ዓማርኛውን ለማዳከም ሊሆን ስለሚችል በተለይ ስማቸውን እየደበቁና እየተሳደቡ የኣሉትን የድረገጾቹ ኣቅራቢዎች ማንሳት ይገባቸዋል። ኣንድ የዓማርኛ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ሲጀመር ኣስተያየት በእንግሊዝኛ የሚሰጡ ምሁራን ኣሉ። በዓማርኛ መጻፍ የማይችሉት ስለጉዳዮቹም ላይገባቸው ስለሚችል በኣለማስተዋል ዓማርኛውን እያዳከሙ ናቸው። ዓማርኛ የሚያነቡ እንጂ የማይጽፉ የቋንቋው ምሁራን በእንግሊዝኛ ሲጽፉ ኣንባቢዎቹንም ላይገባቸው ይችላል። ኣንዳንድ ምሁራን ዶክተሩ እየተጠቀሙበት የኣለውን ፊደል ስለሌላቸው ስለቅርጾቹ የሚያነቡትን ባይረ'ዱ ኣያስገርምም። ምክንያቱም ጽሑፉን የሚጽፉትና የሚያነቡት መሣሪያው ላይ በኣለ ፊደል ስለሆነ ነው። ለምሳሌ ያህል ሦስት ቀለበቶች የኣሉት ኃምሱ እንጂ ግዕዙ “ጨ” ኣይደለም። ስለዚህ ኣንድ ኣንባቢ ወይም ፀሓፊ ሦስት ቀለበቶች የኣለውን ግዕዝ “ጨ” ከኣየ የሚጠቀመው በተሳሳተ ፊደል ነው። በኮምፕዩተር ዘመን ስለኣለን ጽሑፎችን ለማቅረብ ወርቃማ ጊዜ ውስጥ ነን። ሶፍትዌራችንን እየገዙ የኣሉት ዓማርኛ ተናጋሪዎች ስለሆኑ እናመሰግናለን። በግዕዝ ኮምፕዩተር መክተቢያ ከኮምፕዩተሩ ጋር ስለማይመጣ መክተቢያ መግዛት ያስፈልጋል። የኮምፕዩተርም ዋና ጥቅም የተጻፈን ነገር ማስቀመጥ ስለሆነ ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም ኣንድን ጽሑፍ እንደፌስቡክ ከኣሉ ገጾች ውስጥ ወስዶ ማስቀመጥ ብቻ በቂ ኣይደለም። በቋንቋዎቻችን የተጻፉ መረጃዎች እንደሌሎች ቋንቋዎች በብዛት እንዲኖሩ በእጥፍ ብዛት መጻፍና ማስቀመጥ ይጠበቅብናል። በኣለፉት ጥቂት ዓመታት ብዙ ጽሑፎች በኢትዮጵያውያን ትጋት ስለቀረቡ በኮምፕዩተር እንግሊዝኛውን ወደ ዓማርኛና ዓማርኛውን ወደ እንግሊዝኛ መተርጐም ተጀምሯል። የዓማርኛ ትክክለኛዎቹ ኆኄያት "ዓማርኛ" ናቸው። ሌሎች ምሳሌዎችም “ኃይል”፣ “ሕዝብ” እና “ዓቢይ” ናቸው። ለምሳሌ ያህል “አቢይ”፣ “ኣቢይ”፣ “ዐቢይ”፣ ወይም “ዓብይ” ትክክል ኣይመስለኝም ይላሉ ዶክተሩ። ምሳሌ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ባሕረ ሓሳብ መጽሓፍ ገጽ 47 እና 48 ስለ ዓቢይ ጾምና ዓቢይ ቀመር ቀርበዋል። በኣጠቃላይ በኣለፉት 45 ዓመታት የኢትዮጵያውያን የዕውቀትና የዓማርኛ ቋንቋዎች ችሎታዎች ኣቆልቍለዋል። በተለይ በእዚህ ዕድሜ ክልል ውስጥ የኣሉ ምሁራን ዓማርኛ ሲናገሩ እንግሊዝኛ እንዳይቀላቅሉ ሊያስተውሉ ይገባል። ኣንዳንድ ዓማርኛ ተናጋሪዎች በሚለው ቃል ምትክ የሚለውን ይጠቀማሉ። መዝገበ ቃላት መጠቀም ሳይጠቅም ኣይቀርም። ፊደል በሚገባ ስለ ኣልቆጠሩ በ“ነው” ምትክ “ነዉ" ይጠቀማሉ። ኣንዳንድ ዓማርኛ ፀሓፊዎች በነጠላ ሰረዝ ምትክ የላቲኑን ኮማ እንዲሁም በድርብ ሰረዝ ምትክ የላቲኑን ሰሚ ኮለን መጠቀም ስለጀመሩ ዶክተሩ እየተቃወሙ ናቸው። ኣንዳንድ ዓማርኛ ፀሓፊዎች መጽሓፎች ሲያሳትሙ ገጾቹን ለየብቻቸው እያተሙ ይጠርዛሉ። የመጽሓፍና መጽሔት ገጾች ሲታጠፉ ቍጥሮቹና ርዕሶቹ መሣሣም ይገባቸዋል። ለምሳሌ ያህል ገጽ ኣንድ ከግራ ግርጌ ግራ ማዕዘን ላይ ከሆነ ገጽ ሁለት ከቀኝ ግርጌ ቀኝ ማዕዘን ላይ መሆን ይኖርበታል። ኣንዳንድ ምሁራን ለዓማርኛ ቃለ ምልልስ ሲቀርቡ በዓማርኛ መናገር እንዳለባቸው ኣስቀድሞ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል። እንግሊዝኛ እየቀላቀሉ የሚያስቸግሩትን በማረም የኣሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጥሩ ሥራ ይዟል። ኣንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዓማርኛውን ኣራት ነጥብ በሌለው ከመጻፍ እንዲቆጠቡና ኣራት ነጥብ በሌለውም መጻፊያ እየጻፉ ጊዜያቸውን ከማባከን ቢቆጠቡ ይጠቅማል። ኣንዳንድ ፀሓፊዎች ሞክሼዎች የሚሏቸውን ቀለሞች በሌሏቸው ዓማርኛውን እየጻፉ ችግሮች እየፈጠሩ ናቸው። ለምሳሌ ያህል “መሳሳት“ና “መሣሣት" ኣንድ ኣይደሉም። “ምሥር“ አና “ምስር“ ኣንድ ኣይደሉም። ኣንድ የግዕዝ ፊደል በሁለት መርገጫዎች እንደተከተበ ከዶክተሩ ፈጠራ ጋር ከነማስረጃዎቹ ከቀረቡ ዓመታት ኣልፈዋል። ማንኛውንም የግዕዝ ፊደል ዛሬ በሦስትና ከእዚያ በላይ መርገጫዎች መክተብ ከተማረ ሕዝብ ኣይጠበቅም። ኣንድን የዓማርኛ ቀለም በ5 መርገጫዎች መክተብ ኣንዳንዶቹን የሌሎች ቋንቋዎች ቀለሞች ለመክተብ እስከ ስምንት መርገጫዎች መጠቀም ያስፈልጋል። ፊደል ለመክተብ ቃላት ይመስል እስፔሊንግ ማስታወስ የለብንም። ኣንድ የግዕዝ ፊደል በኣንድ ወይም ሁለት መርገጫዎች ከተከተበ በኋላ ልክ እንደላቲኑ ሌላ ፊደል ኣጠገቡ ስለተከተበ ኣይቀየርም። ሌላ ፊደል ወይም መርገጫ የሚቀይረው ከሆነ መጀመሪያውኑ ቀለሙ ኣልተከተበም ማለት ነው። እነዚህ ከነማስረጃዎቹ ከቀረቡ በኋላ በእንደዚህ ዓይነት መክተቢያዎች መጠቀምና የኣልተጻፉትን ማንበብ ሊያበቃ ይገባል። ኢትዮጵያ የእራሳቸው ፊደል ከኣሏቸው ጥንታዊ ጥቂት ኣገራት ኣንዷ ሆና ሳለ እንደሌሎቹ ቴክኖሎጅውን ማሳደግ ሲገባ የሶፍትዌር መብት በሚገባ የማይከበርባት ኣገር ሆናለች። ይህ የኢትዮጵያን እድገት ማቀጨጩን ይቀጥላል። የሌላውን መብት የማያከብርን መንግሥትና ሕዝብ ማሰልጠንና መብት ማስጠበቅ ኣስቸጋሪ ነው። ዓማርኛ የተናጋሪዎቹ የነበረና የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጽሑፍ ቋንቋ የሆነ ነው። በኣሁኑ ጊዜ ዓማርኛ ኢንተርኔት ላይ ብዙ እድገት እያሳየ ነው። እንደነ ጉግልና ፌስቡክ የኣሉ ድርጅቶች ሥራዎቻቸውን በዓማርኛ ሲያቀርቡ ኢትዮጵያውያን እየተራዱ ከኣሉት መካከል ናቸው። ይህ ጥሩ ሥራ ሆኖ ሳለ በቂ ዕውቀት የሌሏቸው እየገቡበት ስሕተቶችን እያስፋፉ ናቸው። ለምሳሌ ያህል የሚለውን ቃል “ቀናቶች” በማለት የሚያቀርቡ ኣሉ። ትርጕሙ “ቀናት” ወይም “ቀኖች” እንጂ “ቀናቶች” የሚባል ነገር የለም። ግዕዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮምፕዩተር በዶ/ር ኣበራ ግኝት እስከሚቀርብ ድረስ ቴክኖሎጂው ስለኣልነበረም ከእርሳቸው ዘዴም ውጪ በግዕዝ መጻፍ ኣይቻልም ነበር። ዝምታው ስለቀጠለ ቴክኖሎጅውን ቀድመው ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣደረግን የሚሉ ዋሾዎችም ኣሉ። የግዕዝ ፊደል ሌሎች እንዲጠቀሙበት ቀለሞች እንደመጨመር በስሕተት ዓማርኛው ኣይፈልጋቸውም እያሉ በተቀነሱ ፊደላት የሚጠቀሙ ኣሉ። ባለቤቱ የኣላከበረውን ፊደል ጎረቤት ኣይፈልገውም። የግዕዝ ፊደል ለሁሉም ተጠቃሚ ቋንቋዎች የሚያስፈልጉትን በኣንድና ሁለት መርገጫዎች በዶክተሩ ግኝት መክተብ ተችሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተቀነሱ የዓማርኛ ፊደላትን እንኳን ከሦስትና ከእዚያም በላይ መርገጫዎች የሚከትቡ የእንግሊዝኛ እስፔሊንግ የመክተቢያ ዘዴዎች የኣለተቃውሞ እየተስፋፉ ናቸው። እነዚህ ኣከታተቦች ሌሎች የኣናሳ ተጠቃሚዎች ቋንቋዎች ቀለሞች በበዙ መርገጫዎች እንዲከተቡ ያስገድዳሉ። ዓማርኛ በበዙ መርገጫዎች በሌሎቹ ቋንቋዎች ምትክ ለመጠቀም ከኣልተዘጋጀ በዘዴዎቹ መጠቀም የለበትም። ኦሮምኛን በላቲን መክተብ (ቁቤ) ከኣሰከተሉት ችግሮች ኣንዱ የማያስፈልጉ ብዙ መርገጫዎችን መነካካት ነው። ዓማርኛን በላቲን እስፔሊንግ መክተብ ተቀራራቢ ችግሮችን ስለሚፈጥር የዘዴው የግዕዝ ተጠቃሚዎች ሌሎችን በእዚህ ለመውቀስ ብቃት የላቸውም። የግዕዝ ፊደል አንዲቀነስ የሚያቀነቅኑ ኣሉ። ኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ የኣላት ኣገር መሆኗ እየተረሳ ወሬና ፖለቲካ ላይ ማተኰር በዝቷል። በግዕዝ እንዲከትብ የኣደረገለትን ለማመስገንም የማያውቅ ሕዝብ ወደመሆኑ ስለተጠጋ ፈጣሪን ማመስገን ኣይጎዳም። ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ በኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች እየተጠቀምንበት ይህን ግኝት የፈጠሩልን ዶ/ር ኣበራ ሞላ መሆናቸውን የማያውቁ ብዙ ናቸው። ፈረንጁ ኣዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ፈጥረው ዓለምን በቴክኖሎጂ የቀየሩትን ፓተንቶች የኣሏቸውን እነ ቶማስ ኤዲሶን፣ ግራሃም ቤል እስቲቭ ጆብስ ቢል ጌትስ የመሳሰሉትን ሲያከብርና ሲያበረታታ ኢትዮጵያዊውን ሳይንቲስት ሶፍትዌሩን በፓተንቶች ጠብቀው ሲያቀርቡ ለመግዛትና ሥራውን ለማስተዋወቅ እንኳን የሚፈልጉ ብዙ ኣይደሉም። በኮምፕዩተር መጻፍ ኣለመቻል የዘመኑ መኃይምነት ነው። ኣንድ ደራሲ ስለኣንድ ነገር ሲጽፍ የእራሱ ሥራ ከኣልሆነ ዋቢ ማቅረብ ተገቢ ነው። ዋቢ የሌለው ሥራ የደራሲው ብቻ ነው ማለት ነው። ኣንድ ደራሲ ትክክለኛ የቃላት ቀለሞችን ከዘነጋ መዝገበ ቃላት መመልከት ጠቃሚ ነው። ምሳሌ፦ መዝገበ ቃላት እያሉ ፊደል በሚገባ የኣልቈጠሩ ጸፀሓፊዎችን በመከተል በ “ው” እንጂ በ “ዉ” የማይጻፉትን እየጻፉ ቋንቋ ማበላሸት ከኣንዳንድ የተማሩ ሰዎች ኣይጠበቅም። መኃይም የማይሠራውን ስሕተት የተማረው ሲሠራው ኣሳፋሪ ነው። ለምሳሌ ያህል እዚህ ጽሑፍ ውስጥ ከ፬፻ በላይ ግድፈቶች ኣሉ። አዚህ ውስጥ የለም። “ፊደላቱ የሚሰጡትን ድምጽና ትርጉም ኣውቆ የኣንዱ ፊደል መውጣት መሻሻል ለረዥም ዘመናት የተጻፉ መጻሕፍት የሓሳብ፣ የትርጕም፣ የቅርስ ጥፋት እንደሚያመጡ ማወቅ ይሻል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ዳግም ጥያቄ በማያስነሳ መልኩ ትክክለኛውን ነገር ሊያስቀምጡና ጥናት በማጥናት ምላሻቸውን ሊሰጡ ይገባል። ከእዚህም በላይ ደግሞ ባለድርሻ የሆነችው ቅደስት ቤተ ክርስትያን ምላሿን ማሳወቅ እንደሚገባት የጥያቄው መብዛት ኣፋጣኝ እንደሆነ ያመላክታል” ይላል ማኅበረ ቅዱሳን። እንዲህም ሆኖ ጽሑፋቸውን በዓማርኛ እንዲጽፉ ያስቻላቸውን እግዜር ይስጥልኝ ለማለት እንኳን የዶክተሩን ስም ሰምተው ላያውቁ ይችላሉ። በተሳሳተ መክተቢያ የተጻፈ በመሆኑ ኣስተማማኝ የኣልሆነ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ። ከእዚህ ጽሑፍ ኣንድ ሁለት ኣንቀጾችን ኮፒ ተደርገው ወይም ገጽ ላይ ቢለጠፉ ችግሮቹን መመልከት ይቻላል። ግዕዝ በዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝድ ሆኖ ተገቢውን ዕውቅና ኣግኝቷል። የማይጽፉና የኣልተሟሉ መክተቢያዎች እየተጠቀሙ ኣንዳንድ የዓማርኛ ምሁራን እራሳቸውን እያዋረዱ ናቸው። ለምሳሌ ያህል ያልተሟሉ የመክተቢያ ዘዴዎች ኣሉ። ሕዝቡን እያወናበዱ የኣሉት ወደ ኦሮምኛው የላቲን ቁቤ ኣከታተብ ዓይነት በብዙ መርገጫዎች የሚያስከትቡ ኣሉ። ኣንዳንድ የዓማርኛ ደራስያን በተሳሳቱ መጻፊያዎችና ፊደላት እየተጠቀሙ እራሳቸውን እየጎዱ ናቸው። በጊዜ መንቃት ስለኣልቻሉ ኣንዳንዶቹ እንደኦሮሞዎቹ መጃጃልን እያስፋፉ ናቸው። በቂ የኢንተርኔት ኣገልግሎት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሌለ የዶክተሩን ሥራዎች የማያውቁ በተወሰነው ዕውቀታቸው የሚያቀርቧቸው ኢትዮጵያን እየጎዱ ስለሆነ ኣንባቢው ይሀን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል። ምሳሌዎች፦ ይህ ስለ እና ያልሰማ ይመስላል። ስለ ጋብርኤላ፣ ስለ ዶ/ር ኣየለና ካማራ የዶ/ሩ ሥራዎች ውስጥ ተጠቅሰው ስለኣሉ ከሁሉም ቀድሞ የነበሩትን ሥራዎች ኣንዳቸውም ኣልጠቀሱም። በዶክተሩ በተፈጠረው ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ የማያመስግነው ቍጥር ስፍር ስለሌለው ከተለመደው መደበቅ ታልፎ ስድብ ተጀምሯል። የዓማርኛውን ፊደል ከ“ሀ” እስከ “ፐ” በቃል የማይደረድሩ ምሁራን ኣሉ ይባላል። ይህ ኣሳፋሪ ነውና ይታሰብበት። ፊደል ቅነሳ ስለ ፊደል ቅነሳ እዚህ ገጽ በየቦታው የቀረቡ ቢኖሩም እንደገና ማንሳቱ ኣይጎዳም። የግዕዝ ፊደል ከ1513 ዓ.ም. ጀምሮ እስከኣሁን ድረስ በማተሚያ መሣሪያዎች በሚገባ እየተጠቀመ ስለሆነ የብቃት ችግር የለውም። መጽሓፍት በማተሚያ ቤቶች ሲታተሙ ስሕተቶቹ ብዙ ኣልነበሩም። ፊደል መቀነስ የተጀመውረው በሚሲዮናውያን ነው። በዐፄ በካፋ ዘመነ መንግሥት ሃሌታውን “ሀ” ከሐመሩ “ሐ” ንጉሡን “ሠ” ከእሳቱ “ሰ” ጻድቁን “ጸ” ከፀሐዩ “ፀ” ለይቶ በሥፍራቸው ያልጻፈ፤ ፊደል አዛውሮ የተገኘ ጸሐፊ እጁን ይቆረጥ እንደ ነበረ የጽሑፍ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የመቀነሱም ነገር ብዙዎቹ ሲከራከሩ እንደነበሩት ዓማርኛውን ብቻ የተመለከተ ኣይደለም። ከዳግማዊ ምኒልክ ጀምሮ ብዙ ኢትዮጵያውያን ሊቆች፣ ሚኒስትሮችና ደራስያን የእንግሊዝኛውን የታይፕ መጻፊያ ለዓማርኛ መክተቢያ እንዲያገለግል ወደ ሰማንያ ዓመታት ግድም ሲመራመሩ ቆይተው ኣልተሳካላቸውም። ኢ/ር ኣያና ብሩና ኢ/ር ተረፈ ራስወርቅ የዓማርኛውን ፊደላት በመቀነስና ቆርጦ በመቀጠል ኣማርኛ በመሰሉ የፈጠራ ቅርጾች የኣቀረቧቸው ሥራ ላይ ውለዋል። እነዚህ ቍርጥራጮች ግን የዓማርኛ ፊደሎች ኣይደሉም። ለእነዚህ ከመቶ በኣነሱ መቀጣጠያዎች የሚሠሩ የፈጠራ የኣማርኛ ነገሮች የሚያስፈልጋቸው ኣንድ የእንግሊዝኛ የፊደል ገበታ ስለሆነ በኣንዱ ገበታ ምትክ ብቻ የቀረቡ ናቸው። የዓማርኛ ቀለሞች ብዛት ከ200 በላይ ስለሆነ 100 ስፍራዎች ኣይበቁትም። ኆኄያቸውን የጠበቁ የግዕዝና ዓማርኛ ጽሑፎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለብዙ ዘመናት ተጽፈዋል። በእጅ ጽሑፍም ወረቀት ላይ መክተብ ለኢትዮጵያ ሕዝብና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጠቅሟል። ፊደል መቀነስ ትኩረት የኣገኘው “ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሓፍ በተቀነሱ ፊደላት በ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. ከታተመ በኋላ ነበር። እዚህ ላይ ተደርቦ ለታይፕራይተር ቴክኖሎጂ እንዲመች የፊደል ቅነሳ ክርክር ተጀምሮ በመጨረሻው ውድቅ ሆነ። የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መርሐ ልሳን [ኣካዴሚ] በ1973 ዓ.ም. ካወጣው የአጻጻፍ ሥርዓት ውሳኔ በስተቀር ሌላ ወሳኝ ጥናት ባለመደረጉ፣ ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ሊሆን የሚችሉ መምህራንንም ስለዚህ ጉዳይ ሆን ብሎ ያስተማራቸው ሰው ባለመኖሩ እነሱ ራሳቸው በዘፈቀደ ስለሚጽፉ ተማሪዎቻቸውም የነሱን ፈለግ በመከተል በዘፈቀደ ይጽፋሉ፤ የሚሉት ዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ "የአማርኛን ሞክሼን ሆሄያት ጠንቅቆ ያለመጻፍ ችግርና መፍትሔ" የሚባል መጽሓፍም ጽፈዋል። ሃሌታው “ሀ”፣ ሓመሩ “ሐ”፣ ብዙኃኑ “ኀ”፣ ንጉሡ “ሠ”፣ እሳቱ “ሰ”፣ ኣልፋው “አ”፣ “ዓይኑ” “ዐ”፣ ጸሎቱ “ጸ”፣ ፀሐዩ “ፀ” የተባሉትን በማጥበቅና በማላላት ብቻ ለመግለጽ ኣስቸጋሪ ነው። እንደ ዶ/ር ኣምሳሉ ተፈራ ኣገላለጽ "ከፊደላት ጋር የሚከሰቱ ችግሮችን ኣስመልክቶም በዓማርኛ ፊደል ገበታ ላይ ተመሳሳይ ድምጽ ያላቸው ስለሚገኙ፤ በኣጻጻፍ ረገድ በርካታ ልዩነቶች መኖራቸው፤ ራብዕ ድምፅ ያላቸው ከግዕዙ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ፊደላት መኖራቸው፤ ሳድስና ሳልስን እያቀያየሩ መጠቀም፣ ዲቃላዎችንና ፍንጽቅ ፈደላትን በዝርዝር የመጠቀም ዝንባሌ፣ በመሠረታዊ ቃሉ ላይ የሌለውን ቃል መጨመር፣ የኣናባቢዎች ቅጥል ኣለመለየት ችግሩን ይበልጥ እንዳሰፋው ጠቁመዋል። (የእነዚህም ምሳሌዎች በቅደም ተከተል “ሀ" እና “ኀ"፤ “ሃገር" እና “ኣገር"፣ “አ" እና “ኣ"፣ “ግዜ" እና “ጊዜ"፣ “ፏፏቴን"ን በ“ፍዋፍዋቴ"፣ “ኈ"ን በ“ሆ"፣ “መምህራንን" በ“መምህራኖች" እና “ዮ"ን በ“ዬ" ዓይነቶች ናቸው በማለት በኣጠቃላይ ግን ችግሩ ከፊደሉ ሳይሆን ከተጠቃሚው ነው ይላሉ ዶ/ር ኣበራ።) ይህ ችግር በምሁራን ዘንድ ሞክሼ ቃላት ይቀነሱ፤ አይቀነሱ የሚለው ሐሳብ ዛሬም ድረስ እያከራከረ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ኣማራጮችንም በተመለከተ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ኣካዳሚ በ1973 ዓ.ም. ተመሳሳይ ድምፅ ያላቸው ፊደሎች ከገበታው ላይ ተቀንሰው በኣንድ ፊደል ብቻ ይወከሉ የሚል ሲሆን፣ የቤተ ክሕነት ሊቃውንት ኣቋም ደግሞ ፊደላት የፈጣሪን ቸርነት የሚገልጹ እና ከእሱ የተገኙ ስለሆኑ ሁሉም ጠንቅቆ ሊጽፋቸው ይገባል እንጂ በፍጹም ሊቀነሱ አይገባም ነው። ፊደላቱ በሙሉ መንፈሳዊ፣ ተፈጥሯዊና ሙያዊ ትርጓሜ ስላላቸው ያንን ያጣሉ በማለት" ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ ይገልጻሉ። የኣብነት (ቄስ) ትምህርት ቤቶች ትኩርት መነፈግንም የሚጠቅሱ ኣሉ። ከ1980 ዓ.ም. ወዲህም እነዚሁ ቀለሞች በዶ/ር ኣበራ ወደ ኮምፕዩተር ስለገቡ የግዕዝ ፊደላችንን የኣጋጠመው ችግር የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በተቀነሱና በተቀነጠሱ ፊደላት “ኣማርኛ መዝገበ ቃላት” በ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. እንዲሁም “ክብረ ነገስት ግእዝና ኣማርኛ” መጽሓፍት በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. ኣትሟል። በመጽሓፎቹ ርዕሶች “ኣማርኛ”፣ “ነገስት”ና “ግእዝ” ተብለው የቀረቡት “ዓ”፣ “ሥ” እና “ዕ” ከተቀነሱት ቀለሞቻቸው ውስጥ የተካተቱ በመሆናቸው ነው። እነዚህ ቍርጥራጮች ግን የዓማርኛ ፊደሎች ኣይደሉም። ክርክሩ በኣይቀነስ ባዮች ምክንያታዊ ኣሸናፊነት ማለቅ ሲገባው እንደቀጠለ ኣለ። ይህ ሁሉ ሲደረግ የዩኒኮድ ዓማርኛ ቀለሞች ኣልተቀነሱም። ለብዙ መቶ ዓመታት በውጭ ኣገራትና ኢትዮጵያ ውስጥ በግዕዝ ፊደላችን ሲጠቀሙ የነበሩ ማተሚያ ቤቶች ፊደል ሲቀንሱ ኣልሰማንም። ይህ የተዛባ የቅነሳ ኣጠቃቀም የመንግሥትም ፍላጎት ይመስላል። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዓይነት ተቋማት ፊደል መቀጠሉን ተዉት እንጂ በመቀነሱ ስለቀጠሉበት ነው። የግዕዝ ፊደል ትክክለኛ ኣጠቃቀም እያለ በተቀነሱና በተቈራረጡ ነገሮች መጠቀም መቀጠል በኮምፕዩተር ዘመን የሚያስከትለው ኪሳራ ቀላል ኣይደለም። ለምሳሌ ያህል በታይፕራይተር ዘመንና ይኸንኑ መሣሪያ ኮምፕዩተራይዝ የኣደረጉት ኣራት ነጥብን ሲከትቡ የነበሩት ሁለት ባለ ሁለት ነጥቦችን በመጠቀም ነበር። ዶ/ር ኣበራ ግን ለኣራት ነጥብ ከመነሻውም ኣንድ ስፍራ ስለመደቡለት ከዩኒኮድ በፊትም ይሁን በኋላ ፊደሉ የእራሱ የኮምፕዩተር ቍጥር ወይም ኮድ ኣለው። ጥቂት ኣዳዲስ ፊደል ቀናሾች ወይም የግዕዝ መክተቢያ ኣቅራቢዎች ኣራት ነጥብን ከሁለት ባለ ሁለት ቀለሞች ማስከተብ ስለጀመሩ ጽሑፎቹ ኣራት ነጥብ የላቸውም። በኣሁኑ ጊዜ በብዙ ሚሊዮን የሚቈጠሩ ኢንተርኔት ላይ የኣሉ ኣራት ነጥብ የሌላቸው ጽሑፎች ማለቂያ የሌላቸው ናቸው። (የማለቂያን ቅኔነት የሚገባቸው ያውቁታል።) እነዚህን ስሕተቶች እየተከታተሉ ማረም ኣስቸጋሪ ስለሆነ ስሕተቶቹ እንዳይቀጥሉ ሁላችንም መረባረብ ይኖርብናል። ሁለት ነጥቦች መካክል ተገብቶ ሁለቱን ብቻ በኣንድ መርገጫ መሰረዝ ከተቻለ መክተቢያውን ሆነ ፊደሉን ኣለመጠቀም ያዋጣል። ኣራት ነጥብ በሌላቸው ቀለሞች የተጻፉ ብዙ መጽሓፍትም ስለኣሉ ሰዉ በኣወናባጆች ወደኋላ እየተመለሰ ነው። ይህ የምልክት ቅነሳ ያስከተለው ችግር ነው። የግዕዝ ፊደላችን እንደ ቻይናው ሥዕሎች የሚሳሉበት ስለኣልሆነ በሺዎች የሚቈጠሩ ኣይደለም። ፊደል መቀነስ ፊደላችን ላይ የተቃጣ ዘመቻ ነው። ቀደም ብለው በዶክተሩ ለዩኒኮድ የተለገሰውን ፊደል ኣስጥለው የተቈራረጡ የአማርኛ ፊደል ለዩኒኮድ የኣቀረቡት ተሸንፈዋል። ቀደም ብለው በዶክተሩ ለዩኒኮድ የተለገሰውን ፊደል ኣስጥለው የተቀነሱ ፊደላትን ለመቀጣጠል ለዩኒኮድ ለማቅረብ የኣቀዱት በሁለተኛ ዙር ጥፋት የኣቀዱትም ተሸንፈዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ቀደም ብሎ ለአማርኛ ታይፕራይተር ሲባል ፊደል ይቀነስ የተባለውን ክርክር የቀጠሉበት ስለ ዶክተር ኣበራ ሥራ ያልሰሙት እንደእነ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ተቋም የኣሉት ነበሩ። ወደፊት ኮምፕዩተሩ ዓረፍተ ነገርን በማረም ትክክለኛውን ሆኄ እንዲያስቀምጥ እናደርጋለን። መጻፍ የማይፈግጉ ለኮምፕዩተሩ ነግረውት ይጽፋል። "ቋንቋ"ን በ"ቁዋንቁዋ" መጻፍ ኮምፕዩተሩ ቀለሞቹን የሚያስቀምጥባቸውን ሥፍራዎች ከማስጨመር ሌላ ወረቀትንና ጊዜ ያስባክናል። "ቋንቋ"ን "ቁዋንቁዋ" በሚመስል ድምጽ ማንበብ እንኳን የፊደሉና የዓማርኛ ቋንቋ ሥርዓት ኣይደሉም። "ቁዋ" እንደ "ቋ" እንዲጻፍና እንዲነበብ ማስገድድ የኣምባገነኖች ፍላጎት እንጂ የፊደሉና የቋንቋው ኣይደሉም። ዶክተር ኣበራ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው ፓተንቶች ሲያገኙባቸው ቴክኖሎጅው በዓዋቂዎች ተጠንቶና ተፈትሾ ነው። ከእዚሁ ጋር የተያያዙ ኣዳዲስ ኣጠቃቀሞች ለግዕዙ ቀርበዋል። ለምሳሌ ያህል "ቋንቋ" የሚለው ቃል እንዲፈለግ ለኢንተርኔት ሲቀርብ ብዙ ቃላቱን የያዙ ጽሑፎችን ማግኘት ሲቻል ቃሉን በ"ቁዋንቁዋ" የሚጽፉ ከኣሉ ፍለጋው ሁለቴ እንዲደረግ ያስገድዳል። ስለዚህ ለታይፕራይተር ሲባል የቀረበ ክርክር ከኋላቀር መሣሪያው ጋር መቅረት ኣለበት። ዶ/ር ኣበራ ሞላ ከታዋቂ የዓለም ሳይንቲስቶች ኣንዱ ናቸው። የግዕዝ ቁምፊዎች ቁምፊ ኣንድ ዓይነት ቅርጽ የኣሏቸው የፊደል ቀለም ቤተሰብ ነው። ድንጋይ፣ ብራናና ወረቀት ላይ በእጅ ሲጻፉ የነበሩት የግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ መሣሪያዎች እ.ኤ.ኣ. ከ1513 ጀምሮ ሲጠቀሙ ቆይተዋል። በ፲፱፻፳፭ ዓ. ም. ግድም የጽሕፈት መሣሪያ ተፈጥሮ ለቢሮ ሥራዎች ጠቅሟል። ግዕዝ ወደ ኮምፕዩተር ሳይገባ ለኢትዮጵያ ጽሑፍ መበልጸግ ትልቁን ድርሻ የኣበረከተው የማተሚያ መሣሪያ ሳይሆን ኣልቀረም። የግዕዝ ወደ ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ በፊደሉ መግባት በተለይ የዓማርኛ ጽሑፎችን እንዲስፋፉ ጠቅሟል። ፊደሉ ከቴክኖሎጅው ጋር እንዲራመድ መገንዘብ ስለኣለብን ኣንዳንድ ነጥቦች ከእዚህ በታች ቀርበዋል። ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ዶክተሩ የቁምፊውን መጠን በግምት ኣስቀመጡት እንጂ መደብ ኣላወጡለትም። በኣሁኑ ጊዜ ሕዝቡ በግዕዝ ፊደል በብዛት መጽሓፍት እየጻፈ ስለሆነ እየተደሰትን ነው። ሆኖም ጽሑፎች እየታተሙባቸው የኣሉት ቁምፊዎች መልኮች የተለያዩና ኣብዛኛዎቹ የተሳሳቱ ስለሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ከግዕዝኤዲት ፕሮግራሞች ጋር እየተሸጠ የኣለው የዶ/ር ኣበራ ሞላ ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ቁምፊ ወደ ትክክለኛው የቀረበ ነው። ይኸን ቁምፊ ከተጠቀሙበት መካከል ዶ/ር ኣክሊሉ ሃብቴ በ፳፻፱ ዓ.ም. ያሳተሙት ባለ 629 ገጾች "የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ" መጽሓፍ ኣንዱ ነው። በፊደሉ ለብዙ ዓመታት እየተጠቀሙበት የኣሉት የኣቶ ኣብርሃ በላይ ኢትዮሚዲያ ገጾችም ኣሉ። በ፳፻፲፩ ዓ.ም. ሰይፉ ኣዳነች ብሻው በግዕዝኤዲት ፕሮግራም በመጠቀም "የምኒልክ ጥላ" መጽሓፍ ጽፈዋል። በጽሑፋቸውም ዶክተር ኣበራ ስለ ሆኄያት መልኮች በተለይ የ"ጨ" ባለሁለት እግርነት እውነታ ተቀብለዋል። መጽሓፍ በኮምፕዩተር ሲታተም ቁምፊውን ኣስቀድሞ መወሰን ይጠቅማል። ምክንያቱም በኣንዳንድ ኣስቀያሚና የተሳሳቱ የፊደል መልኮች የተጻፉ ጽሑፎች ማንበብ ኣያጓጓም። ኣንድ የግዕዝ ዩኒኮድ ቁምፊ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች እንደኣሉት ማጣራት የደራሲው ሥራ ነው። ምክንያቱም ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው የማተሚያ ቤቶቹን ኃላፊነት ለደራሲዎች ስለሰጡ ኣዲሱን ቴክኖሎጂ መማር ኣስፈላጊ ስለሆነ ነው። ኣንድ በግዕዝ ዩኒኮድ ቁምፊ የሚጠቀም ደራሲ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች መክተብ መቻሉን ማጣራት የደራሲ ሥራ ነው። ምክንያቱም ዶክተሩ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው የማተሚያ ቤቶቹን ኃላፊነት ለደራሲዎች ስለሰጡ ኣዲሱን ቴክኖሎጂ መማር ኣስፈላጊ ስለሆነ ነው። ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ዶክተሩ በመደበኛነት የተጠቀሙት የኢትዮጵያ ቍጥር ፊደል ነው። እ.ኤ.ኣ. በ1988 በዶክተሩ ከፖስትእስክሪፕት ፊደላቸው የተሠራ የመጀመሪያው ትሩታይፕ የግዕዝ ፊደልና ፊደላቸው ነው። ለሥራቸው መሳካት የኮሎራዶው ኩባንያዎች ከዶክተሩ ባለውለታዎች ዋነኞቹ ናቸው። ይህ እነ ብርሃንና ሰላምና የመሰሉ የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ሲጠቀሙበት የነበረው ቁምፊ ወደ ታይምስ ሮማን የእንግሊዝኛ ቁምፊ የቀረበና ተመሳሳይ ቢሆንም ከላቲኑ ጋር ሲወዳደር የግዕዝ ፊደል ተለቅና ደመቅ የኣለ ነው። ኣብዛኛዎቹ የዓማርኛና እንግሊዝኛ መጽሓፍት ሲጻፉ የነበሩት በእነዚህ ቁምፊዎች ነበር። ይህ የግዕዝ ቁምፊ መልክ ወደጎን ቀጠን ብሎ ወደታች የወፈረ ነው። በማተሚያ ቤቶቹና ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ሲታተሙ የነበሩት መጽሓፎች የፊደል መጠን ከ10 እስከ 12 ነበር። ኣንድ የግዕዝ ቁምፊ ቢያንስ ከኣንድ ተመጣጣኝ የእንግሊዝኛ ቁምፊ ጋር መቅረብ ይኖርበታል። ኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች ላይ በቀላሉ ማየት እንዲቻል የሚቀርቡ ጽሑፎች ደቦልቦል በኣሉ ቁምፊዎች ነው። እነዚህን ለመጽሓፎችና ለመሳሰሉት መጠቀም ኣስፈላጊ ኣይደለም። ምክንያቱም ትላልቅ ስለሆኑ በዛ የኣሉ ስፍራዎችንና ወረቀቶችን ስለሚያስባክኑና ጥቅማቸው ለኅትመት ስለኣልሆነ ነው። ኣንዳኣንድ ሰዎች ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ማድረግ ፊደሉን መሥራትና ማቅረብ ይመስላቸዋል። ይህ ከኣለማወቅ የመጣ ስሕተት ነው። በፓተንት የሚጠበቀው ኣዲስ የሆነውና ፊደሉን በኮምፕዩተር መጠቀም የኣስቻለውን ቀደም ብሎ ያልነበረውን ዘዴ ነው እንጂ ከዘዴው ጋር ለሚቀርቡት ፊደላት ኣይደለም። ኣንዳኣንድ ሰዎች ግዕዝን ኣሜሪካ ፓተንት ማድረግ ፓተንቱን ወይም ፊደሉን ለኣሜሪካ መስጠት ይመስላቸዋል። ይህ ከኣለማወቅ የመጣ የፈጠራ ወሬ ነው። ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገው ከትክክለኛው ቁምፊ ጋር ዶክተሩ ከኣቀረቡ በኋላ ከአማርኛው ቅጥልጥል ፊደል እስከኣልተሟሉና የተሳሳቱ ቀለሞች የኣሉዋቸውን ቁምፊዎች በነፃና በሽያጭ የሚያቀርቡ ኣሉ። ይኸንን መረዳትና ማስተዋል የተጠቃሚው ኃላፊነት ሲሆን ኣንባቢው ስሕተቶችን እያየ ዝም ማለቱ ደረጃቸው ለኣዘቀጡ በኮምፕዩተር ለቀረቡ ጽሑፎች ኣስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። ኣንድ ኣንባቢ ኮምፕዩተር፣ የእጅ ስልክና የመሳሰሉት ላይ የሚመለከተው የግዕዝ ዩኒኮድ ፊደል መሣሪያው ላይ በኣለው ፊደል ነው። ፊደሉ ትክክል ከኣልሆነ ትክክል ኣለመሆኑንንም ላይረዳ ይችላል። ለምሳሌ ያህል የ"ጨ" ቀለበቶች ሁለት ናቸው ሲባልና ቢያነብ ባለ ሁለት ቀለበቶች ትክክለኛ ፊደል ከሌለው ፊደሉን የሚያነበው ሦስት ቀለበቶች በኣሉት የተሳሳተ ፊደል ነው። የዶክተሩ የግዕዝ ቁምፊ ከኣሥር ዓመታት በላይ እዚህ የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንትና ማመልከቻው ውስጥ ኣሉ። ኣንድ በቅርቡ የተለቀቀ ቁምፊ ውስጥ የዓይኑ "ዓ" ፊደል መልክ ወደ ኣረቡ ዘጠኝ (9) የቀረበ ሲሆን የሌላው "ፃ" መስመሩ የኣለው በ"ዓ" ክብ ውስጥ ነው። ዶክተር ኣበራ ሞላ ከዓለም ፊደል ሠሪዎች ኣንዱ ናቸው። በማተሚያ ቤቶች ከታተሙ የግዕዝ ቁምፊዎች የሚከተሉት ይገኙበታል። በተሳሳተ ፊደል የተጻፈ በመሆኑ ኣስተማማኝ የኣልሆነ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ። ከእዚህ ጽሑፍ ኣንድ ሁለት ኣንቀጾች ኮፒ ተደርገው ገጽ ላይ ቢለጠፉ ችግሮቹን መመልከት ይቻላል። ኣንድ ቆንጆ የቁም ፊደል አጣጣል እዚህ ኣለ። በግዕዝ ፊደል ወግ ስምንተኛው ፊደል የሚቀርበው ግዕዙ ወይም ራብዑ ላይ መስመር በመጨመር ነው "ፏ" የተሠራው መስመሩን "ፋ" ኣንገት ላይ በመጨመር ነው። በኣሁኑ ጊዜ ብዙዎቹ ቅጣዩን በስሕተት ከታች ሲያቀርቡ ኣንዱ በቅርቡ "ፍ" ላይ ኣድርጎታል። መሳሳታቸውን ከቆዩ ጽሑፎች ውስጥ ማየት ይቻላል። እንዲህ ዓይነቶችን ስሕተቶች ስር ሳይሰዱ ማረም ከኣልተቻለ ዛሬ "ኣበበ"ን እሞታታለሁ እንጂ በ"አበበ" ከኣልሆነ ኣልጽፍም እንደሚሉት ጥቂቶቹ በኋላ በትምህርት ማቃናት ሊያስቸግር ይችላል። ኣንድ የግዕዝ ቁምፊ ቢያንስ ኣንድ ኣብሮት የኣለ የእንግሊዝኛ ፊደል ጋር መቅረብ ይኖርበታል። ስለዚህ ለሰው የሚቀርበው የላቲን ፊደልም እንደግዕዙ የፊደል ሠሪው መሆን ይገባዋል። የግዕዙና የላቲኑም ፊደላት ቅርጾች የተቀራረቡ መሆን ይኖርባቸዋል። ዩኒኮድ ለፊደላቱ መደብ ሰጠ እንጂ ፊደል ኣላቀረበም። የግዕዙ ፊደል ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ላይ ከሌለ የግዕዝ ፊደል ኣይታይም። የሚታየውም እንደፊደሉ ሊለያይ ይችላል። ስለዚህ ኣንድ ተጠቃሚ የሚጠቀምበትን መሣሪያ ላይ ያለውን የፊደል ስምና መልክ ማወቅ ኣለበት። ኣንድ የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች ቅርጾች ማወቅ ይጠበቅበታል። በኣሁኑ ጊዜ ግን ሁሉንም የዓማርኛ ቀለሞች እንኳን የማይለዩ ኣሉ። ከእዚህ በፊት ተዉ እያልናቸው በታይፕራይተር ዓይነት ፊደል ተታልለው መጽሓፍት ሲጽፉ ከርመው የተበሳጩ ኣሉ። ኣሁንም በተሣሣቱ የዩኒኮድ ፊደሎችና የዓማርኛ መጻፊያዎች እየተጠቀሙ እራሳቸውንና ዓማርኛውን እየጎዱ የኣሉ ኣሉና ይታሰብበት። የግዕዝ ፊደል ቅርጾችና ምንነት ምሳሌዎች የሚከተሉት ናቸው። የግዕዝ ኣኃዞች እያንዳንዳቸው ከላይና ከታች ሰረዞች ኣሏቸው። የኮምፕዩተሩ እስክሪን ላይ የሚታየውና የሚታተመው ኣንድ ፊደል ነው። የፊደሉ መጠን በኣነሰ ቍጥር ጥራቱ እየቀነሰ መስመሮቹ ኣንድ መስለው ይታያሉ። ፊደሉ የዶክተሩ ከሆነ ጽሑፉን ከእዚህ ወስዶ ወርድ ላይ ለጥፎ በማሳደግ ማረጋገጥ ይቻላል። እንዲህም ሆኖ ቍጥሮቹ ጎን ለጎን ሲሆኑ ሰረዞቹ እንዲገናኙ የተሠሩና የሚቀጣጠሉ በነፃ የሚታደሉ የተሣሣቱ ፊደሎች ኣሉ። ለእዚህ ነው በነፃ የሚታደሉትን ሁሉ መጠቀም የማያዋጣው። ኣንድን የግዕዝ ፊደል ጽሑፍ እንደወርድ የኣሉ ቁሶች ውስጥ ኣቅልሞ የሚለውን ፊደል በመምረጥ ወደ ፊደሉ መቀየር ይቻላል። ይህ እንግሊዝኛውንም ወደ ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደል ያስቀይራል። ለዊንደውስንና ኣይፎን የሚሸጡት ግዕዝኤዲት ፕሮግራሞች የሚጠቀሙት ኣንድ ዓይነት በሆነው ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ ፊደል ነው። ይህ ፊደል እ.ኤ.ኣ. በ1989 ግድም ለዩኒኮድ የተለገሰው የመጀመሪያ የግዕዝ ትሩታይፕ ፊደል ነው። የግዕዝ ሳልስ፣ ኃምስና ስምንተኛ ቀለሞች ቅጥያዎች የ"ጨ" ሦስተኛው ባዶ እግር ላይ ይቀጠላሉ እንጂ የሌሉትን ቀለበቶች ኣያስፈቱም። የ"ጠ" እና "ጨ" ቤቶች እርባታ ቀለሞች ልዩነቶች በሁለት ቀለበቶች መኖር ብቻ ነው። ትርጕሞች የውጭ መያያዣዎች 2007-09-15. ግዕዝ በኮምፕዩተር በአበራ ሞላ ዓ.ም ግዕዝ በኮምፕዩተር 1991 ኤልያስ ክፍሌ ዶክተር ኣበራ ሞላ ቴክኖሎጂ ኤድስ በ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ዶክተር ኣበራ ሞላ ኤድስ ኤችአይቪ ኤችኣይቪ ዶ/ር ኣበራ ከኣሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጋር፣ ማክሰኞ ሰኔ ፲፱፻፹፩ ዓ.ም.፣ ትዝታ በላቸው ፒዲኤፍ 15) 2 1, 1993, 5 1998 1991. ኤድስ በዶ/ር ኣበራ ሞላ ዓ.ም. (1991) ግዕዝና ኮምፕዩተር በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. (1991) ሞዴት ኮፒራይት (የቅጂ መብት) ዶ/ር ኣበራ ሞላ) ዶ/ር ኣበራ ሞላ) እናስተዋውቅዎ ደምሴ ኣጎናፍር የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር ዶ/ር ፀዳይ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ስመ እጸዋት ስመ እጸዋት ዶ/ር ዓለሙ ቢፍቱ 1992 ጤፍ 1996 የኢትዮጵያ እጽዋት ዓማርኛ ዊኪ የውሻ እብደት፣ 1974 ስመ በሽታ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች 1999 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዶ/ር ኣበራ ሞላ ሰይፉ ኣብዲ ሰይፉ ኣብዲ ሚሌንየም ግዕዝኤዲት ኦንላይን ዓማርኛ ግዕዝኤዲት ኮምፕዩተር ማስታወሻ፣ ሮዝ መጽሔት ዋሽንግተን ዲ.ሲ.፣ ዶ/ር በቀለ ሞላ 1996 ሞዴት ዶ/ር ኣበራ ሞላ ያሁ እና ቢንግ በዓማርኛ መፈለጊያ የአማርኛ የጽሕፈት መኪና ግዕዝኤዲት ዜናዊ መግለጫ ግዕዝኤዲት ዜናዊ መግለጫ ጉግል በዓማርኛ ግዕዝ ስምና ኣኃዝ ኣበራ ሞላ] ዓማርኛ በጉግል ኣፈላለግ የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶች ሳይንቲስቶች የፊደላት ምንጭ ፊደል ሠሪ የአክሱም ሐውልት የግዕዝ ቀለንጦስ የግዕዝ ፊደል ግዕዝኤዲት ሚሌንየም የግዕዝ ኣልቦ ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እውቀት መለዋወጫ መረብ ግዕዝኤዲት በነፃው ግዕዝኤዲት ዓማርኛ ኣከታተብ፣ አማርኛ በነፃው ግዕዝኤዲት አማርኛ ኣከታተብ፣ እንግሊዝኛ የኣክሱም ሓውልት የኣክሱም ሓውልት የግዕዝ ፊደል ኣባት የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶች ኢትዮወርድ ፊደል ኢምዩንደፊሸንሲ የኣሜሪካ ፓተንት 4,501,816 ኢምዩንደፊሸንሲ የኣሜሪካ ፓተንት ሞዴት የኢትዮጵያ ቃላት ማተሚያ ኮፒ መብት የኢትዮጵያ ፓተንት ማመልከቻ፣ ግዕዝ በኮምፕዩተር ዓ.ም. የኣሜሪካ ፓተንት ፔንዲንግ፣ ግዕዝ በኮምፕዩተር 2127963 የእንግሊዝ ፓተንት ሰባት ቤት ጉራጌ አማርኛ አፈላለግ የእጅ ስልክ የእጅ ስልክ ኑግ ማሽላ ጤፍ የኢትዮጵያ እጽዋት የግዕዝ ኣከታተብ ኣዲስ ግኝት። መላኩ ወረደ ግዕዝኤዲት ከዶከተር አበራ ሞላ ጋር በኮሎራዶ የተደረገ ውይይት ክፍል ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. 1992 እ.ኤ.ኣ.። 1992 እንዳለ ጌታሁን ከዶከተር አበራ ሞላ ጋር በኮሎራዶ የተደረገ ውይይት ክፍል ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. 1992 እ.ኤ.ኣ.። 1992, 1 ከዶክተር አበራ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ሙሉ ክፍል ያድምጡ በቪ.ኦ.ኤ. መለስካቸው አመሀ፣ 26.09.2012 11/28/12 ግልጽ ደብዳቤ ለቫቲካን ጳጳስ ግዕዝኤዲት ቪዲዮ ዓ.ም.፣ 9/26/2012 ስለ ግዕዝ ቴክኖሎጂ ከዶቸ ቨለ ሬድዮ ተክሌ የኋላእሸት ጋር የዶ/ር ኣበራ ቃለ ምልልስ (መጋቢት ቀን ዓ.ም.) ፈውስ ግኝት 8381119 2, ሺና ታዋቂ የዓለም የእንስሳት ሐኪሞች የኢንሳይድ ኢትዮጵያ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶች ኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የእጅ ስልክ ግዕዝኤዲት ፌስቡክ በኮምፕዩተር የዓለም ፊደል ሠሪዎች 2000 ኢንጅነር ኣያና ብሩ ነቢዩ ኣስፋው ኤልያስ ክፍሌ 25 ግዕዝ ግዕዝ ግዕዝ ግዕዝ ዓማርኛ አማርኛ አማርኛ ኣማርኛ ፊደላት አማርኛ ትግርኛ ትግርኛ ትግርኛ ፊደል ኣገው ቢለን ኣገው ቢለን ጉራጌ ጉራጌ ዳግማዊ በለጠ ሀሁ ቪድዮ ነዓምን ዘለቀ ሞዴት ኢትዮወርድ 365 ግዕዝኤዲት ውክፐዲያ የዶ/ር ኣበራ ሞላ ኣዲስ ፓተንት ማመልከቻ ግዕዝኤዲት ቪድዮ አማርኛ ኣከታተብ በዶ/ር ኣበራ ሞላ አራጌ ምስጋና ምስጋና በረከት ኪሮስ የዶ/ር ኣበራ ሞላ ውክፔዲያ ገጽ ኣንባቢ ብዛት የውክፔድያ ጽሁፎች ከረጅሙ ተደርድረው ያሁኑ የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር የጠፋው ሰው ግዕዝኤዲት ኣከታተብ በዶ/ር ኣበራ ሞላ በበፍቃዱ... ጌታቸው ወልደሥላሴ አክሱም ኢትዮ ሰርክል ጋሻው ገብረኣብ ስመ ኣኃዝ የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር 3,350 ኢንጂነር ተረፈ ራስወርቅ ትዊተር ፀዳይ ኣብራሃ በላይ 1947 1982-2008... ዮሓንስ ግሸን 2011 1996 ኣበበ በለው ደቸ ቨለ ሠዓሊ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን ኣርጋው ዓቢይ ሞላ ሓውልታችንን ኣሁን መልሱ! ሻምበል በላይነህ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ኢትዮጵያዊ ሥዕሎች፣ ኣቤን ኤዘር 20090179778 1 (2010-2014) 2013 ዶ/ር እምነት ታደሰ ዶ/ር በቀለ ሞላ 1935–1941 2014 ጀፍ ፒይርስ ኣቢይ ጌታቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢብኮ) ዶ/ር ፀዳይ መክብብ ዶ/ር ፀዳይ መክብብ ተክሌ የኋላእሸት 1 ቃለ ምልልስ ክፍል 2 ቃለ ምልልስ ክፍል 3 ቃለ ምልልስ ክፍል ወንድወሰን ፍቅሬ ምስጋና ኢሳት የሳምንቱ አንግዳ ኢሳት የሳምንቱ አንግዳ ስለ ግዕዝና ኣክሱም ሓውልት ከሲሳይ ኣጌና ጋር ዳንኤል ክብረት ኪዳኔ ዓለማየሁ ዘርማንዘር 1997, ዶ/ር ቲም ካርማይክል ኢትዮጵያ 25 ስመ ኣኃዝ 6 ግዕዝኤዲት ፌስቡክ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ፎቶዎች ምስጋና፣ ዶክተር ኣበራ (አበራ) ሞላ በኮምፕዩተር ግዕዝ ፊደልን ለመጀመሪያ ጊዜ መጠቀም እንዲቻል ስለኣደረጉ። የኢትዮጵያ ሙዚቃ ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ ኢትዮጵያን ዲጄ ግዕዝኤዲት ቁስ (ኣፕ) ለኣይፎን እና ኣይፓድ 20090179778 1 (2010-2014) 20090179778 6 የንግድ ምልክት ኢትዮጵያ'ዬ ኢትዮጵያ'ዬ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ምን ያህል ያውቃሉ? ሞክሼ ፊደላት ሸገር ብሎግ 1906 መጽሓፈ ሄኖክ በእንግሊዝኛ የእንስሳት ሕክምና መጋቢት ደብረ ብርሃን ስለ ነፃው ግዕዝኤዲት ቪድዮ በዶ/ር ኣበራ ሞላ፣ የኮምፕዩተር ጥገና ባለሙያ እልፍነሽ ኃይለመስቀል እና የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ዮርዳኖስ ኣዳነ፣ ኣሸናፊ ዘለቀ እና ኤፍሬም ፀጋየ ጋር የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን 2013, ያሬድ በቀለ መኮንን ግዕዝኤዲት አማርኛ ለአይፎንና አይፓድ ግዕዝኤዲት ለኣይፎን 5 6 8 ግዕዝኤዲት ለኣይፎን 6 8 6 የኢሳት የሳምንቱ እንግዳ ዶ/ር ኣበራ ሞላ 8, 2015) ሲሳይ ኣጌና የግዕዝኤዲት ፊደል (ቁምፊ) ኢትዮሚድያ ኣዲስ ነገር፣ የግዕዝ ኣከታተብ ግኝት ፓተንት (የግኝት ባለቤት) ከዶ/ር ኣበራ ሞላ ጋር (ኢቢኤስ ቃለ ምልልስ ቪድዮ አማርኛን ከቴክኖሎጂ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቁ ምሁር... .ዶክተር አበራ ሞላ አማርኛ እና ቴክኖሎጂ እንተዋወቅ በየሺ ሀሳብ አበራ ዶክተር አበራ ሞላ በየሺ ሀሳብ አበራ ስለ ሁለተኛው የግዕዝ ኣከታተብ ግኝት አማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት የግዕዝ ፊደል የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት መብት ኣገኘ። ቋጠሮ ማንተጋፍቶት ስለሺ እና ነጋሽ መሐመድ 1 ስለ ግዕዝና የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኣክሱም ኣመላለስ የዶክተር ኣበራ ሞላ ቃለምልልስ ከኢሳት ሲሳይ ኣጌና ጋር፣ ሚያዝያ ቀን ዓ.ም. የዶ/ር ኣበራ ሞላ ግዕዝ ኣከታተብ የተራዘመና የመጀመሪያው የኣሜሪካ ፓተንት ቍጥር 9,000,957 =114125298610656] 7, 2015 የግዕዝ ፊደል የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት መብት ኣገኘ። የግዕዝ ፊደል የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት መብት ኣገኘ። ኣብርሃም ቀጄላ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ በኣበበ በለው የኣዲስ ድምጽ ሬድዮ ቃለ መጠይቅ። ከፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ ዶ/ር ኣበራ ሞላ እና ጋዜጠኛ ኣብርሃም ቀጄላ ጋር፣ ኅዳር ቀን ዓ.ም. 27, 2016) "ለኦሮምኛ ከላቲኑ ቁቤ የግዕዝ ፊደል ይጠቅማል" ዶ/ር ኣበራ ሞላ፣ ሠይፉ ኣዳነች ብሻው በኣያልቅበት ተሾመ ሬዲዮ ኣቢሲኒያ ከዶ/ር ኣበራ ሞላ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ፣ ሁለት ክፍሎች ኣብርሃም ቀጄላ የዶ/ር ኣበራ ሞላ ቃለምልልስ ከሳምሶን ውብሸት ሕሊና ሬድዮ ቬጋስ ጋር የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኣክሱም ኣመላለስ የዶክተር ኣበራ ሞላ ኣስተዋፅዖና ታሪክ፤ ከማሕደረ ኣንድነት ሬድዮ ሰይፉ ብሻው ጋር (ኣትላንታ፣ ሚያዝያ ቀን ዓ.ም.) "ለኦሮምኝ ከላቲኑ ቁቤ የግዕዝ ፊደል ይጠቅማል" የዶክተር ኣበራ ሞላ ቃለመጠይቅ፤ ከማሕደረ ኣንድነት ሬድዮ ሰይፉ ብሻው ጋር (ኣትላንታ፣ ዓ.ም.) የሺሓሳብ አበራ ወንድወሰን ዘለቀ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ የዶክተር ኣበራ ሞላ ቃለመጠይቅ ከሻለቃ ኣብርሃም ታከለ ጋር ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ዶክተር አበራ ሞላ እና የኢትዮጵያ ፊደል 2017 2017 የግዕዝ ፊደል እውነታዎች፣ ቅርሶችና ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ዶክተር አበራ ሞላ በየሺሀሳብ አበራ አፋን ኦሮሞ የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ የመሆን ግዴታነትና የእራሱ በሆነው በኢትዮጵያ ፊደል የመገልገል ተገቢነት ኣብርሃም ቀጄላ ልሣነ ዐማራ የሺሀሳብ አበራ የኢትዮጵያ ሓኪሞች የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ሁለተኛ ደብዳቤ ለለማ መገርሳ የግዕዝ ፊደል እውነታዎች፣ ቅርሶችና ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ዶክተር አበራ ሞላ 23 24, 2017 ግዕዝ ከላቲን ለምን እንደሚሻል የሚያመላክቱ ነጥቦች የዶ/ር ኣበራ ሞላ ኢሳት/ራዕይ ስብሰባ ዓ.ም.፣ ክፍል 2 ዛጎል ደረጀ ነጋሽ 2017 (የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማሕበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ) 2017 የዕውቅና ሽልማት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ተሰጠ የዕውቅና ሽልማት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ተሰጠ፣ የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማሕበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ የእንስሳት መድኅንና ጥሬ ሥጋ ዶ/ር ኣበራ ሞላ 1 የግዕዝ ፊደልና የኣክሱም ሓውልት ዶ/ር ኣበራ ሞላ 2 የዶ/ር ኣበራ ሞላ ሥራዎችና ትሩፋቶች ከካሳሁን ሰቦቃ ቃለምልልስ ከዶ/ር ኣበራ ሞላ ጋር የዓባይ ሚዲያ ቃለምልልስ “የግዕዝ ፊደላችን የኦሮምኛ ቋንቋን መተየብ አይችልም ተብሎ ወደ ላቲን መሔድ ስሕተት ነው። እንዲያውም የኦሮምኛ ቋንቋችን እንዳይዳከም፤ ኦሮምኛን ተጨማሪ የአገሪቱ የሥራ ቋንቋ ብናደርግ የተሻለ ይመስለኛል።” ዶ/ር አበራ ሞላ የኢትዮጵያ ሓኪሞች ሳይንቲስቶች ግዕዝ ለኦሮምኛ ሙሉ ብቃት እንዳለው የቀረቡ ሳይንሳዊ ነጥቦች ዶ/ር አበራ ሞላ ምሁራን/አክቲቪስቶች ኦሮምኛ በአማራ ክልል በግእዝ ፊደል እንደ ትምህርት እንዲሰጥ ጠየቁ። ግርማ ካሳ ኦሮምኛን በአማራው ክልል በግዕዝ ስለማስተማር 13, 2018) 13, 2018) "ትኩረት" የዶ/ር ኣበራ ሞላ ቃለምልልስ ከኢሳት ምናላቸው ስማቸው ጋር። ግንቦት ፳፻፲ ዓ.ም. 14, 2018 ምሁራን/አክቲቪስቶች ኦሮምኛ በኦሮሞ ክልል በግእዝ ፊደል እንደ ትምህርት እንዲሰጥ ጠየቁ። ምሁራን/አክቲቪስቶች ኦሮምኛ በኦሮሞ ክልል በግእዝ ፊደል እንደ ትምህርት እንዲሰጥ ጠየቁ። ትኩረት 23 2018 ኢሮብ 11, 2018 የግዕዝ ፊደል ሁለተኛ የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት ማሳወቂያ ኣገኘ ጌታቸው ሞላ የግዕዝ ፊደል ሁለተኛ የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት ማሳወቂያ ኣገኘ ጌታቸው ሞላ ዘ-ሐበሻ 10,067,574 4, 2018. ኢትዮጵያ የስነ-ጽሑፍ ቅርሶች ሲዳሞኛ በግዕዝ ፊደል (የዮሓንስ ወንጌል) የግዕዝ ፊደል የዩናይትድ ስቴትስ የባለቤትነት መብት ኣገኘ። ዶ/ር ኣበራ ሞላ እና ፍሬው ተገኝ የግዕዝ ፊደላትን በኮምፒተር እና በተንቀሳቃሽ ስልክ መከተብ... 1/31/2019 ከግርማ ካሳ ጋር 1 4, የ፬ ክፍል አንድን ከብት የመጣል ሥልጣን ያለው የእንስሳት ሃኪም ብቻ ነው ዶ/ር አበራ ሞላ ከዮሰፍ ገብሬ ጋር፣ የ፬ ክፍል የግዕዝ ፊደላትና የኮምፕዩተር እንዲሁም የሞባይል ስልኮች ትውውቅ ዶ/ር አበራ ሞላ ከዮሰፍ ገብሬ ጋር፣ የ፬ ክፍል እውን ግዕዝ የአዳም እና የሄዋን ቋንቋ ነው? ዶ/ር አበራ ሞላ ከዮሰፍ ገብሬ ጋር፣ የ፬ ክፍል እስክንድር ነጋ ትንቢቶች አንድ በአንድ እየተፈጸሙ ነው!!! (ዘመድኩን በቀለ) የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ሁሉ በግእዝ ፊደል እንዲጠቀሙ ማግባባት ያስፈልጋል ያሬድ ጥበቡ መረጃ ዋሜራ ቲቪ፣ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ከግርማ ካሳ ጋር 2018 ግዕዝ ኦሮምኛ ጨምሮ ለሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ብቃት እንዳለው ዶ/ር አበራ ይናገራሉ። አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ የካቲት 10/2011 ዓ.ም. ግዕዝ ኦሮምኛ ጨምሮ ለሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ብቃት እንዳለው ዶ/ር አበራ ይናገራሉ። አዲስ ዘመን ጋዘጣ፣ ጽጌረዳ ጫንያለው ግዕዝኤዲት ፌስቡክ “አገርኛ ቋንቋን ከኮምፒዩተር ያዋሃዱ ሳይንቲስት!” አዲስ ዘመን ጋዘጣ፣ ጽጌረዳ ጫንያለው የእጽዋት ሥዕሎች የኢትዮጵያ ፊደል በፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ሳይንቲስቶች በኩር መጽሔት ገጽ 3 መስከረም 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ዕትም እንግዳ ዶክተር አበራ ሞላ፣ ሰሎሞን አሰፌ አሥራት እንግዳ:- በኮምፕዩተር ግዕዝ ፊደልን መጠቀም እንዲቻል ያደረጉት ምሁር ዶ/ር አበራ ሞላ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ታሪክ እና የኦሮሞ ቤተክህነት ጽ/ቤት ይቋቋምልን ጥያቄን በጨረፍታ (በተረፈ ወርቁ) ዶ/ር ኣበራ ሞላ ከሕብር ሬዲዮ ኃብታሙ ኣሰፋ ጋር። ዶ/ር ኣበራ ሞላ ከሕብር ሬዲዮ ኃብታሙ ኣሰፋ ጋር። ኦሮምኛን የፌደራልና የኣዲስ ኣበባ የሥራ ቋንቋ የማድረግ ዕድሎችና ችግሮች፤ (ዶ/ር ኣብርሃም ዓለሙ) ኦሮምኛን የፌደራልና የኣዲስ ኣበባ የሥራ ቋንቋ የማድረግ ዕድሎችና ችግሮች፤ (ዶ/ር ኣብርሃም ዓለሙ) “ምስጋናና ሕያው ምስክርነት ለኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ለዶ/ር ኣበራ ሞላ ባሉበት" ዶ/ር አማረ ተግባሩ ግዕዝ በኮምፕዩተር ያስተዋወቁት ኢትዮጵያዊ፣ 19.03.2020 አዜብ ታደሰ እና እሸቴ በቀለ ደቸ ቨለ 10,133,362 የፊደል ሓዋርያ ቦርድ ጋዜጣዊ መግለጫ (ዶ/ር ኣበራ ሞላ) መስተጋህደ ዜና ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታን በሚመለከት የአቋም መግለጫ፤ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኮቪድ-19 አማካሪዎች ምክር ቤት (ሕዳር ፳፻፲፫ ዓ.ም.) (11/22/2020) ዓለምፀሐይ ወዳጆ የጥበብ መድረክ 1/23/2021 (2009) 127-129. 2022 ዋቢ የኢትዮጵያ ሀኪሞች ሳይንቲስቶች
30895
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%20%E1%88%98%E1%88%8B%E1%8A%AD%E1%89%B0%E1%8A%9E%E1%89%BD%20%E1%89%A0%E1%89%A5%E1%88%AA%E1%89%B3%E1%8A%92%E1%8B%AB
የኢትዮጵያ መላክተኞች በብሪታኒያ
የታላቋ ብሪታኒያ መንግሥት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ጉዳዩን የሚያስፈጽምለት ወኪል እና የብሔራዊ ምሥጢራዊ ጉዳይ ባለሙያ (‘አምባሳዶር’)፤ በጊዜያዊነትም ኾነ በቋሚ ሹመት ወደኢትዮጵያ መላክ የጀመረው በ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው። ከዚያ በፊት በተለያዩ ጊዜያት መላክተኞችን የሰደደ ቢሆንም የነዚያ ተልዕኮ ግን ወደተለያዩት የክፍለ አገራት መሳፍንት እና ገዚዎች ነበር። የኢትዮጵያም ነገሥታት ከዓፄ ቴዎድሮስ ጀምሮ እስከ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ድረስ አልፎ አልፎ ጊዜያዊ መላክተኞቻቸውን ወደ ታላቋ ብሪታኒያ ልከዋል። ዳሩ ግን ከእነዚህ ልዑካን አብዛኞቹ የውጭ ዜጎች ነበሩ። ከነዚህ አንዱ ዓፄ ቴዎድሮስን ወክሎ ወደ ሎንዶን ያመራው ሚሲዮናዊው ማርቲን ፍላድ ሲሆን ከኢትዮጵያውያን ደግሞ የዓፄ ዮሐንስ ልዑክ መርጫ ወርቄ፣ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክን ወክለው ለንጉሥ ኤድዋርድ ፯ኛ የንግሥ በዓል የተላኩት ልዑል ራስ መኮንን እና ከንቲባ ገብሩ፤ እንዲሁም ንግሥት ነገሥታት ዘውዲቱን ወክለው በንጉሥ ጆርጅ አምስተኛ የንግሥ በዓል ላይ የተገኙት ደጃዝማች (በኋላ ልዑል ራስ) ካሣ ኃይሉ በዋቢነት ይጠቀሳሉ። በቋሚነትም በ፲፰፻፷፭ ዓ/ም የዓፄ ዮሐንስ ቆንስላ ሄንሪ ሳሙኤል ኪንግ በሎንዶን የኢትዮጵያን ጉዳይ እንዲይስፈጽም ተሹሞ እንደነበር ታሪክ ይዘግባል። በዚሁ በንግሥት ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመን አልጋ ወራሽ እና ባለምሉ ሥልጣን እንደራሴው ራስ ተፈሪ መኮንን ከመሳፍንትና መኳንንቶቻቸው ጋር በብሪታኒያ እና ሌሎችም የአውሮፓ አገራት ያደረኡት ጉብኝት በዓይነቱ የመጀመሪያው ከመሆኑም ባሻገር፣ ዘመናዊት ኢትዮጵያ በአጽናፋዊ ትሥሥር ሂደት ለመሳተፍ ያላትን ፍላጎት ያበሥራል። በዚህ ጉብኝት የተከፈተውንም ግንኙነት ለማጠናከርና የኢትዮጵያን ጉዳይና ጥቅም ለማስከበር ቋሚ መላክተኞችን በጊዜው ከነበሩት ከተማሩ ኢትዮጵያውያን መኻል እየተመለመሉ ወደሎንዶን፤ ፓሪስ፤ ሮማ እና ዠኔቭ ተላኩ። በብሪታኒያ የኢትዮጵያ ቋሚ መላክተኞች በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመን የተሾሙ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቋሚ መላክተኛ ነጋድራስ (በኋላ ራስ ቢትወደድ) መኮንን እንዳልካቸው ሲሆኑ፣ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለብሪታኒያው ንጉሥ ጆርጅ አምስተኛ ስም ኅዳር ቀን ዓ/ም በባኪንግሃም ቤተ መንግሥት የተረከቧቸው አልጋ ወራሹ የዌልስ መስፍን (የወደፊቱ ንጉሥ ኤድዋርድ ስምንተኛ) ነበሩ። ነጋድራስ መኮንን በዚህ መደባቸው ሁለት ዓመት አገልግለዋል። በብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚያዝያ ቀን ዓ/ም ያወጣው “የኢትዮጵያ ትላልቅ ሰዎች ዝርዝር” ላይ በተራ ቁጥር ስለይነጋድራስ መኮንን እንዳልካቸው ሲተነትን፤ በጥቅምት ወር ዓ/ም ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ሲገቡ፣ ያጋጠማቸው አዲስ አበባ ከተማ እንዳይገቡ የመታገድ ትዕዛዝ እንደነበረና ምክንያቱም ፓሪስ ላይ በወቅቱ የራስ ጉግሳ አርአያ ሚስት ከነበሩት የንጉሠ ነገሥቱ ታላቅ ወንድም ልጅ፣ ልዕልት የሻሸወርቅ ይልማ ጋር ባልገዋል በሚል እንደነበር፤ ራስ ጉግሳም በኋላ በዚሁ ምክንያት ሚስታቸውን እንደፈቱ እና ነጋድራስ የአሥር ሺ የኢትዮጵያ ብር ቅጣት እንደተጣለባቸው ዘግቧል። ወደሎንዶን ሥራቸውም ሳይመለሱ በዚያው እንደቀሩና በታኅሣሥ ወር ዓ/ም ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ ኾነው ተሾሙ። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የተሾሙ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ቋሚ መላክተኛ ኾነው የተሾሙት ባለ ሥልጣን ደግሞ በጅሮንድ ዘለቀ አግደው ሲሆኑ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለብሪታኒያው ንጉሥ ጆርጅ አምስተኛ ሐምሌ ቀን ዓ/ም በባኪንግሃም ቤተ መንግሥት አስረክበው፣ በዚሁ ሥልጣን ላይ እስከ ግንቦት ቀን ዓ/ም ቆዩ። በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት የተማሩት በጅሮንድ ዘለቀ፣ የዋና መላክተኛነት ሥልጣናቸው በሎንዶን፤ በፓሪስእና ዠኔቭ በሚገኘው የዓለም መንግሥታት ማኅበር ነበር። ይኼንን ተልዕኮ አጠናቀው ወደኢትዮጵያ ሲመለሱ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የእርሻ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። በሦስተኛ ተራ ለዚህ ሥልጣን የተመደቡት ደግሞ በጅሮንድ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም (ፊታውራሪ ነበሩ። እኒህ ሰው ሹመታችው በአንድነት ለፈረንሳይ፣ ብሪታኒያ እና የዓለም መንግሥታት ማኅበር እንደነበር እና ሹመቱን እንዳልፈለጉት “ኦቶባዮግራፊ” (የሕይወቴ ታሪክ) በተባለው መጽሐፋቸው (ገጽ 416-419) ላይ በሰፊው ተንትነውታል። በጅሮንድ ተክለ ሐዋርያት የሹመት ደብዳቤያቸውን መጀመሪያ ለፈረንሳይ ፕሬዚደንት ካቀረቡ በኋላ ወደሎንዶን ተጉዘው በባኪንግሃም ቤተ መንግሥት ለብሪታኒያው ንጉሥ ጆርጅ አምስተኛ ግንቦት ቀን ዓ/ም አቅርበዋል። በሎንዶን ወደፊት በዋና መላክተኛነት የሚሾሙትን አቶ (በኋላ ብላታ) ኤፍሬም ተወልደ መድኅንን፤ በፓሪስ ደግሞ ዋና ጸሐፊውን አቶ ተስፋዬ ተገኝን ቋሚ ወኪሎች በማድረግ እሳቸው ሥራቸውን በሎንዶን፤ ፓሪስ እና በዠኔቭ በማፈራረቅ ሲሠሩ ቆዩ። በ፲፱፻፳፯ ዓ/ም የወልወል ግጭት ስለተነሳ እና በዓለም መንግሥታት ማኅበር ኃላፊነታቸው ብዙ ስለተወጠሩ በሰኔ ወር ላይ የሎንዶኑን ዋና መላክተኛነት እንዲለቁ ተደረገ። በጅሮንድ ተክለ ሐዋርያትን ተከትለው በአራተኛ ተራ የተሾሙት መላክተኛ፣ አዛዥ ወርቅነህ ነበሩ። አዛዥ ወርቅነህ/ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ የመቅደላ ጦርነት ጊዜ በእንግሊዝ የጦር መኮንን በሕጻንነታቸው ወደሕንድ አገር ተወስደው እዚያው ያደጉ፤ የኖሩ እና በቀዶ ጥገና ሙያ የተሠማሩ ሰው ሲሆኑ አሳዳጊ አባቶቻቸው በሰጧቸው ስሞች ቻርልስ (በወሰዳቸው መኮንን ስም)፤ ማርቲን (ባሳዳጊያቸው ሐኪም ስም) ይባሉ ነበር። አዛዥ ወርቅነህ በሎንዶን የኢትዮጵያ ዋና መላክተኛነቱን ሥልጣን ሲሾሙ የሹመት ማስረጃቸውን መጀመሪያ ለንጉሥ ጆርጅ አምስተኛ ሐምሌ ቀን ዓ/ም፤ በኋላ ደግሞ ለንጉሥ ኤድዋርድ ስምንተኛ ጥር ቀን ዓ/ም አቅርበዋል። በዚህ ዕለት የኢትዮጵያን ግዛት ከ ግንቦት ቀን ዓ/ም ጀምሮ የምወክለው እኔ ነኝ ያለችው የኢጣሊያ መላክተኛም የሹመት ማስረጃውን አብሮ አቅርቧል። በሎንዶን ‘ፕሪንስስ ጌት’ (17 የሚገኘውን የኢትዮጵያ መላከተኞች መኖሪያ እና መሥሪያ ቤትን በአገራቸው ስም የገዙትም ዋና መላክተኛ አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ ናቸው። አምሥተኛው ዋና መላክተኛ የኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆች የፋሺስት ኢጣልያን ቀንበር ከአምሥት ዓመት ትግል በኋላ በ፲፱፻፴፫ ዓ/ም ሲያስወግዱ፤ ወደሎንዶን የታላኩት ብላታ አየለ ገብሬ ነበሩ። ብላታ አየለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለንጉሥ ጆርጅ ስድስተኛ መስከረም ቀን ዓ/ም አቅርበዋል። ስድስተኛው ዋና መላክተኛ፤ የኤርትራው ተወላጅ ብላታ ኤፍሬም ተወልደ መድኅን ነበሩ። ብላታ ኤፍሬም በሎንዶን እና በፓሪስ የኢትዮጵያ መላክተኞች መሥሪያ ቤቶች በዋና ፀሐፊነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፤ በዋሺንግቶን የኢትዮጵያን ቢሮ በዋና መላክተኛነት የመጀመሪያው ሹም ሆነው ጥቅምት ቀን ዓ/ም የከፈቱ ሲሆኑ፤ የሎንዶኑን ዋና መላክተኛነት ከብላታ አየለ ገብሬ ተረክበው የሹመት ደብዳቤያቸውን ለንጉሥ ጆርጅ ስድስተኛ ጥቅምት ቀን ዓ/ም አቅርበዋል። ብላታ ኤፍሬም በቤይሩት የአሜሪካ ኮሌጅ የተማሩ ሲኾን በአዲስ አበባየተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪም ነበሩ። ከዚያም በ ዓ/ም በፓሪስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ሆነው ተሾሙ። ከሁለት ዓመትም በኋላ በሎንዶን የኢትዮጵያ ጉዳይ አስፈጻሚ ኾነው አገልግለዋል። ብላታ ኤፍሬምን የተከተሉት ሰባተኛው መላክተኛ በሎንዶን ለሰባት ዓመታት ያገለገሉት አቶ አበበ ረታነበሩ። አቶ አበበ የሹመት ደብዳቤያቸውን መጀመሪያ፣ ጥቅምት ቀን ዓ/ም ለንጉሥ ጆርጅ ስድስተኛ፤ ወዲያው ግንቦት ቀን ዓ/ም ለዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ አቅርበዋል። አቶ አበበ አንድ ዓመት በዋና መላክተኛነት ካገለገሉ በኋላ ጥቅምት ቀን ዓ/ም በሹመት ዕድገት አምባሳዶርነት ተሹመዋል። በስምንተኛ ተራ ከአቶ አበበ ረታ የአምባሳዶርነት ሥልጣኑን በ፲፱፻፵፰ ዓ/ም የተረከቡት አቶ አማኑኤል አብርሐም ሲሆኑ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ጥር ቀን ዓ/ም አቅርበው በሎንዶን አራት ዓመታት አገልግለዋል። አቶ አማኑኤል የአዛዥ ወርቅነህ ደቀ-መዝሙር ሲሆኑ፣ አዛዥ ወርቅነህ ወደሎንዶን የተላኩ ጊዜ ይዘዋቸው ሲመጡ ያለደመወዝ ለቀለባቸው ብቻ በጸሐፊነት እየሠሩ እንዲትዳደሩ አስማምተው እንዳመጧቸው ስለህይወት ታሪካቸው በተጻፈ ዘገባ ላይ ተተንትኗል። አቶ አማኑኤል በጠላት ወረራ ዘመናት አዛዥ ወርቅነህ ሥልጣናቸውን ለቅቀው ወደሕንድ አገር ሲሄዱ የኢትዮጵያን ሥራ በስደት ላይ በነበሩት ንጉሠ ነገሥት እና ተከታዮቻቸው አመራር መሠረት በሎንዶን ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ዘጠነኛው የኢትዮጵያ አምባሳዶር፤ አባታቸው ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው ቢሮውን በቀዳሚነት በከፈቱ በ ዓመቱ የተሾሙት ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ነበሩ። ልጅ እንዳልካቸው የሹመት ደብዳቤያቸውን ለዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ መጋቢት ቀን ዓ/ም ካቀረቡ በኋላ በዚህ ሥልጣን ለአንድ ዓመት ከ ስምንት ወራት አገልግለዋል። ልጅ እንዳልካቸው የሎንዶኑን አምባሳዶርነት ያስረከቡት ለተከታያቸው፣ በአሥረኛ ተራ ቁጥር ለተመዘገቡት እና በደራሲነታቸው ለሚታወቁት አቶ ሀዲስ ዓለማየሁ ነበር። አቶ ሀዲስ የሹመታቸውን ደብዳቤ ጥቅምት ቀን አቅርበው በጠቅላላው ለአምሥት ዓመታት አገልግለዋል። አቶ ሀዲስ ከሥነ ጽሑፍ ሙያቸው ከደረሷቸው መጻሕፍት በተለየ ትልቅ ዝና ያተረፈላቸው ‘ፍቅር እስከ መቃብር’ አዲስ አበባ በታተመበት ጊዜ እሳቸው ኑሯቸው ሎንዶን እንደነበረና “አብሮ አደጋቸው” አቶ መሀሪ ካሣ እንዳሳተሙላቸው በመጽሐፉ የምስጋና ገጽ ላይ አስፍረውታል። አቶ ሀዲስ በሎንዶን ቆይታቸውን ጨርሰው ሥልጣኑን ሲለቁ በአሥራ አንደኛ መደብ የተከተሏቸው አምባሳዶር ጥቅምት ቀን ዓ/ም ሹመታቸውን ለንግሥት ኤልሳቤጥ ያቀረቡት አቶ ገብረ መስቀል ክፍለእግዚ ናቸው። በ፲፪ኛ ተራ ቁጥር ሚያዝያ ቀን ዓ/ም በባኪንግሃም ቤተ መንግሥት ሥነ ሥርዓት ላይ ንግሥት ኤልሳቤጥን በመወከል የንግሥቲቱ እናት እና እህት የሹመት ደብዳቤያቸውን የተቀበሏቸው አምባሳዶር ሌተና ጄነራል ኢያሱ መንገሻ ነበሩ። ለብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኤድዋርድ ሂዝ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለ ሥልጣናት ሰኔ ቀን ዓ/ም የተዘጋጀ አጭር መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ሌተና ጄነራል ኢያሱ ከኢትዮጵያ መንግሥት የመከላከያ ሚኒስትር ጋር እንደማይግባቡ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ፀሐፊ-ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድን የግልጽ ተቃዋሚ መሆናቸውን ይዘግባል። ወደ እንግሊዝ አገር በአምባሳዶርነት መላካቸውንም በአገር ቤት ከነበረው አለመግባባት እና ግጭት እንደተገላገሉ ይቆጥሩታል በማለት ይደመደመዋል። በደርግ ዘመን የተሾሙ ሌተና ጄነራል ኢያሱ ወደአገራቸው ሲመለሱ ሎንዶን በአምባሳዶርነት የተኳቸው አቶ ዘውዴ መኩሪያ ሲሆኑ የሥልጣን ደብዳቤያቸውን ልንግሥት ኤልሳቤጥ ያቀረቡት ሰኔ ቀን ዓ/ም ነበር። አቶ ዘውዴ የደርግ መንግሥት የመጀመሪያው ሹም ቢሆኑም ቦሎንዶን የኢትዮጵያ ዋና መላክተኛነት ተራ ቁጥር ፲፫ኛው መሆናቸው ነው። በ፲፬ኛ መደብ የተመዘገቡት አምባሳዶር አቶ አያሌው ወልደ ጊዮርጊስ ደግሞ የሹመት ማስረጃቸውን ያቀረቡት ታኅሣሥ ቀን ነው። ::ከአቶ አያሌው እስከ ዶ/ር በየነ ነገዎ ያሉትን አምባሳደሮች ዝርዝር የምታውቁ እባካችሁ ሙሉት በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የተሾሙ የካቲት ቀን ዓ/ም የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡት አምባሳዶር ዶ/ር በየነ ነገዎ ሲሆኑ እስከ ሚያዝያ ቀን ዓ/ም ለሦሥት ዓመታት አገልግለዋል። ዶ/ር በየነን የተከተሉት መላክተኛ ደግሞ ከታኅሣሥ ቀን በሎንዶን የኢትዮጵያ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ፍስሐ አዱኛ ናቸው። አቶ ፍስሐ ማዕርጋቸው ወደአምባሳዶርነት የካቲት ቀን ዓ/ም ተሻሽሎላቸው የሹመት ደብዳቤያቸውን ለዳግማዊት ንግሥት ኤልሣቤጥ ሚያዝያ ቀን ዓ/ም ባኪንግሃም ቤተ መንግሥት ቀርበው አስረክበዋል። አቶ ፍስሐ በየካቲት ወር ዓ/ም የደረሳቸውን ወደአገር ቤት የመመለስ ጥሪ ሲደርሳቸው በሥራቸው ይሰሩ ከነበሩ ሌሎች ዲፕሎማቶች ጋር ወደ አሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው ለቀዋል። መጋቢት ፲፱፻፺፰ ዓ/ም የአምባሳዶርነት ሥልጣኑን የተረከቡትና ለዳግማዊት ንግሥት ኤልሣቤጥ የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡት አቶ ብርሃኑ ከበደ ሲሆኑ ወደሎንዶን ከመዛወራቸው በፊት በስዊድን፤ ኖርዌይ፤ ዴንማርክ እና ፊንላንድ አምባሳዶር ሆነው ሲሠሩ ቆይተዋል። ዋቢ ምንጮች 7532, 4940, 3281, 4909, 889, 4123, 5535, 5532, 5079, 2652, 566, 2365, 8031, 12047, 4759, 9295, 16165 2157/2157/1] 54 18, 1937; 4); 8 ሀዲስ ዓለማየሁ፣ “ፍቅር እስከ መቃብር”፣ ፲ኛ እትም፣ ሜጋ አሳታሚ እና ማከፋፈያ ኃ/የት/የግ/ማህበር ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም (ፊታውራሪ “ኦቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የኢትዮጵያ ሰዎች የኢትዮጵያ
50491
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%89%A1%E1%8A%90%20%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%8A%95%E1%8D%8B%E1%88%B0%20%E1%8A%AD%E1%88%AD%E1%88%B5%E1%89%B6%E1%88%B5
አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ የስማቸው ትርጓሜ የክርስቶስ፣ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ማለት ነው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊታቸው ላይ እፍ ብሎ ጸጋውን፣ በረከቱን ስላሳደረባቸው በዚህ ስም ይጠራሉ የጻድቁ፣ የአባታቸው ስም መልአከ ምክሩ ሲሆን የእናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ የትውልድ ቦታቸው በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዳውንት ዐወን ዓባይ የተባለ አካባቢ ነው የተፀነሱት ሚያዝያ የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ ቀን ነው የሕይወት ታሪካቸው በተወለዱ ዕለት በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ‹‹ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ›› በማለት እግዚአብሔርን አመሰግነዋል፡፡ የሕፃናትን አንደበት ለሚያናግሩ፣ ለሥላሴ እና ለእመቤታችን እንደዚሁም ለክርስቶስ መስቀል ዘጠኝ ጊዜ ሰግደዋል፡፡ በልጅነታቸው፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትገለጽላቸው ነበር፡፡ ያደጉትም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸው ነው፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜም የመጻሕፍት ዂሉ ርእስ የሚኾን ፊደልንና የሐዋርያው ዮሐንስን መልእክት ደብረ ድባ በሚባል ቦታ ከመምህር ኪራኮስ ተምረዋል፡፡ የሐዋርያትን ሥራ፣ የቅዱስ ጳውሎስን መልእክት፣ የዳዊትን መዝሙር፣ እንደዚሁም ትርጓሜ መጻሕፍትን ተምረዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በዘመኑ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የዲቁና መዓርግ ተቀበሉ፡፡ ከዚያም በሐይቅ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም መነኰሱ፡፡ ከዚያም ወደ ሕንጻ ደብረ ድባ ሔደው የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት፣ የገዳማት አለቃ፣ የመነኮሳት አባት ከሚኾን ከአባ ሙሴ መዓርገ ቅስና፣ ቍምስና እና ኤጲስ ቆጶስነት በቅደም ተከተል ተቀብለዋል፡፡ ተጋድሎዋቸውና ታመራቸው አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፣ ዐቢይ ጾምን ዐርባ ሌሊትና ዐርባ ቀን እኽልን ውኃ ሳይቀምሱ ይጾሙ ነበር፡፡ እግሮቻቸው እስኪያብጡ ድረስ ቆመው ይጸልዩ ነበር፡፡ ለሽፋሽፍቶቻቸውም ዕረፍትን አይሰጡአቸውም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም ሲሔዱ ወደ ገዳሙ ለመግባት ሐይቁን የሚያሻግራቸው ቢያጡ ተንበርክከው ሲጸልዩ በቅዱስ ሚካኤል እጅ ደንገል (ታንኳ) ቀርቦላቸው ሐይቁን ተሻግረዋል፡፡ ዘጠኝ ዓመት ዓባይ ባሕር ውስጥ በራሳቸው ተዘቅዝቀው በመቆም ለኢትዮጵያ ሲጸልዩ ከቆዩ በኋላ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሳቸው መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ዂሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ፥ ኢትዮጵያን ምሬልሃለሁና ከዚህ ባሕር ውጣ›› ብሏቸዋል፡፡ ከዚያም ማረፊያቸው ወደ ኾነች ዳውንት (ደብረ አስጋጅ) በመመለስ ዐሥራ ሰባት ገዳማትን መሥርተዋል፡፡ ወደ ደብረ ዳሞ በሔዱ ጊዜም በትእምርተ መስቀል አማትበው ያለ ገመድ ከደብረ ዳሞ ተራራ ላይ በመውጣት ከአቡነ አረጋዊ ጋር (ከተሰወሩበት ቦት መጥተው) ተገናኝተዋል፡፡ በየገዳማቱ ሲዘዋወሩ ከሞላ ውኃ በደረሱ ጊዜ በመስቀል ምልክት አማትበው በእግራቸው እንደ ደረቅ መሬት እየረገጡ ይሻገሩ ነበር፡፡ አምስት አንበሶችና አምስት ነብሮች ይከተሏቸው ነበር፤ እነዚያም አንበሶችና ነብሮች የሚመገቡትን ባጡ ጊዜ ድንጋዩን ባርከው ሥጋ ያደረጉላቸው ነበር እነሱም ያንን ይመገቡ ነበር፡፡ የትግራይን አድባራትና ገዳማትን ለመጐብኘት ወደ ቅዱስ ያሬድ ደብር ሲደርሱ እመቤታችን ከቅዱስ ያሬድ (ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ) እና ከልጅዋ ጋር ወደ እርሳቸው መጥታ ብዙ ተአምራትን አድርጋላቸዋለች፤ ከቅዱስ ያሬድም ተምረዋል፤ ቡራኬ ተቀብለዋል፡፡ የመጨረሻዎቻቸው ጊዜያት የጻድቁ የዕረፍታቸው ቀን በደረሰ ጊዜ እንደ ነጋሪት ቃልና እንደ ነጎድጓድ ያለ ድምፅ በሰማይ ተሰማ፤ እንደ ፀሐይ እና እንደ ጨረቃ እንደ ከዋክብት የሚያበሩ የተለያዩ መብራቶች ታዩ፡፡ መሬትም አራት ጊዜ ተንቀጠቀጠች፡፡ ተራሮችና ኮረብቶች እጅግ ተነዋወጡ፡፡ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በምትለይበት ሰዓት እንደ መብረቅ የሚጮኽ ታላቅ ድምፅ ከሰማይ ተሰማ፡፡ ያን ጊዜ ሰው ዂሉ፣ እንስሳት፣ አራዊት፣ ዛፎችና ቅጠሎች፣ ተራሮች፣ ኮረብቶች፣ ወፎችም በየወገናቸው አለቀሱ፡፡ ፀሐይና ጨረቃ ጨለሙ፤ ከዋክብትም ረገፉ፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በታላቅ ግርማ፣ በአንድነትና በሦስትነት እየተመሰገኑ መጡ፡፡ ኪሩቤል፣ ሱራፌል ከነማዕጥንታቸው፣ ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት፣ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት፣ ዐሥራ አምስቱ ነቢያት፣ ሰማዕታት ከቅዱስ እስጢፋኖስ እስከ ተፈጻሜተ ሰማዕት ሊቀ ጳጳስ ዼጥሮስ ድረስ ያሉት፣ ቅዱሳን መነኮሳት ከአባታቸው ከእንጦንስ ጋር መጡ የሰማዕታት እናታቸው፣ የመነኮሳትና የደናግል አክሊላቸው፣ ክብራቸው፣ መመኪያቸው፣ የሐዋርያት ስብከታቸው፣ የነቢያት ትንቢታቸው፣ የመላእክት እኅታቸው፣ የኃጥኣን ተስፋቸው፣ የፍጥረት ሁሉ አማላጃቸው፣ የምሕረት እናት፣ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደናግላንን አስከትላ መጣች፡፡ ጻድቁ አባታችን ከጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ለዚህ ክብር ያበቃቸውን እግዚአብሔርን አመስግነው በሰላም ዐረፉ፡፡ ዕረፍታቸውም ሚያዚያ ዘጠኝ ቀን ሲኾን፣ ያረፉበት ቦታም ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዳውንት ከተማ ደብረ አስጋጅ ገዳም ነው፡፡ ከተቀበሉት ቃልኪዳን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከተቀበሉት ቃል ኪዳን ጥቂቱ ዝክራቸውን የዘከረ፣ መታሰቢያቸውን ያደረገ፣ ስማቸውን የጠራ፣ ገድላቸውን የጻፈ፣ ያጻፈ፣ ያነበበ፣ የተረጐመ፣ የሰማ፤ በፍጹም ልቡና ‹‹አምላከ እስትንፋሰ ክርስቶስ (የእስትንፋሰ ክርስቶስ አምላክ) ኀጢአቴን ይቅር በለኝ›› ብሎ የጸለየ ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ይጻፍለታል፡፡ ለቤተ ክርስቲያናቸው መባዕ፣ ስንዴ፣ ዘይት፣ ዕጣን፣ ጧፍ የሰጠ ኀጢአቱ ይደመሰስለታል፤ በገነት፣ በመንግሥተ ሰማያት በደስታ ይኖራል፡፡ በስማቸው የተራቆተውን ያለበሰ፣ የተራበውን ያበላ፣ ያዘነውን ያረጋጋ፣ በመታሰበያቸው ዕለት ለአገልግሎት የሚፈለገውን መልካሙን ነገር ያደረገ ኀጢአቱ ይሰረይለታል፡፡ በየዓመቱ ሚያዚያ ቀን እና በየወሩ የዕረፍታቸውን መታሰቢያ በዓል ያከበረ፣ ዝክራቸውን የዘከረ ሰማያዊ ክብር ያገኛል፡፡ በስማቸው የጽዋ ማኅበር የሚጠጡ ሰዎች ቢኖሩ በመካከላቸው የጻድቁ አምላክ ይገኛል፡፡ ዝክራቸውን የዘከሩ፣ መታሰቢያቸውን ያደረጉ፣ በስማቸው የተማጸኑ፣ በገድላቸው የተሻሹ፣ በጠበላቸው የተጠመቁና የጠጡ መካኖች ልጅ ይወልዳሉ፡፡ ችግር ደርሶበት ስማቸውን የጠራ፣ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በስማቸው የሰየመ፣ በበዓላቸው ቀን ቁራሽ እንጀራና ቀዝቃዛ ውኃ ለነዳያን የሰጠ ኀጢአቱ ይሰረይለታል ካደረጉአቸው ተአምራት መካከል ከፊሉ ከደቀ መዝሙራቸው ከልብሰ ክርስቶስ ጋር በጎዳና ሲሔዱ የደረቀ የሰው አጥንት አግኝተው ፈጽሞ ወደ እግዚአብሔር ሲለምኑ ያን ጊዜ በጸሎታቸው ኃይል ያ የሞተውና የደረቀው አጥንት ነፍስ ዘርቶ ተነሥቷል፡፡ የቀትር ጋኔን ለክፏት ልቧን ሰውሮአት የአገኘችውን ሰው እና እንስሳ በጥርሷ ትነክስ የነበረች አንዲት ሴት ሕመሟ ጸንቶባት ሞታ ሰዎች ሊቀብሯት ሲሉ የእስትንፋሰ ክርስቶስን መስቀልና መታጠቂያውን በአስከሬኑ ላይ ሲያስቀምጡት በእግዚአብሔር ኃይል ተነሥታለች፡፡ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ በብርሃን ሠረገላ ወደ ሰማይ ሲያርጉ ዓይኑ የጠፋ፣ እግሮቹ ልምሾ የኾኑ ሰው ዐይቷቸው ‹‹አባቴ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ፥ በጸሎትዎ ፈውሱኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስም ያንን ሰው አዝነውለት በእጃቸው ያለውን መሐረብ ወረወሩለት፡፡ በዚያን ጊዜ ልምሾ የነበሩ እግሮቹ ዳኑ፤ ዓይኑም በራለት፡፡ ስንዴ ዘርተው፣ ወይን፣ ጽድንም፣ ወይራን፣ ግራርንም ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ስንዴውን ለመሥዋዕት፣ ወይኑን ለቍርባን ዕለቱን በተአምራት አድርሰዋቸዋል ካረፉ በኋላ (በዐጸደ ነፍስ) ካደረጉአቸው ተአምራት መካከል ጥቂቶቹ በልጃቸው ዐይነ ሥውር መኾን ተጨንቀው የነበሩ አንዲት እናት እስትንፋሰ ክርስቶስ ልጃቸውን ቢፈውሱላቸው እንደሚመነኵሱ ስእለት ተስለው ጠበሉን ሲያስጠምቁት የልጃቸው ዐይኑ በራለት፡፡ ኾኖም ግን ተስለው የነበረውን ምንኵስና እንዳያደርጉ ዘመዶቻቸው ስለ ከለከሏቸው ልጃቸው ተመልሶ ዐይነ ሥውር ኾኗል፡፡ ወለተ ማርያም የተባሉ እናት ትዳር መሥርተው ለዐሥራ ሁለት ዓመታት ልጅ ሳይወልዱ ሲኖሩ የጻድቁን ገድል አዝለው በስማቸው ስም ቢማጸኑ ልጅ ለመውለድ በቅተዋል፡፡ ሊበተን የነበረውም ትዳራቸውም ተቃንቶላቸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር በጻድቁ አማላጅነት ከጡት ካንሰር በሽታ እንደ ተፈወሱ፣ ጤንነታቸው እንደ ተመለሰላቸው እኒህ እናት ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ የጻድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን በዓል ይዘክሩ የነበሩ ሰዎች ላም አካለ ጎደሎ ጥጃ ትወልዳለች፡፡ ከቤተሰቡ መካከል በእምነቷ ጠንካራ የነበረችው እኅታቸው ጥጃዋን በእስትንፋሰ ክርስቶስ ገድል ብታሻት በእግሯ ቆማ ሔዳለች፡፡ የእናቷንም ጡት ተንቀሳቅሳ ለመጥባት ችላለች፡፡ ለአምስት ዓመታት ሆዱ አብጦ የነበረ አንድ ዲያቆን የጻድቁ ገድል የተደገመበትን ጠበል ሲጠጣ ከሕመሙ ተፈውሷል፡፡ ወደ ደብሩ ለመሄድ በአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ስም እየተማጸኑ በገድላቸው በመጸለይና ሰውነታቸውን በማሻሸት፣ እንደዚሁም በገዳማቸው በሚገኘው በጠበላቸው በመጠመቅ፣ በእምነታቸው በመቀባት ብዙ ምእመናን አሁንም ከሕመማቸው እየተፈወሱ ናቸው፡፡ የጻድቁ ገዳም (ደብረ አስጋጅ) በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዳውንት ከተማ አካባቢ ይገኛል፡፡ በረከት ለመቀበል ወደ ገዳሙ ለመሔድ ከወልድያ እስከ ዳውንት በመኪና የስምንት ሰዓታት መንገድ ይወስዳል፡፡ ከዳውንት ከተማ ወደ ገዳሙ አቅራቢያ የሚያደርሱ አነስተኛ ተሸከርካሪዎችም ይገኛሉ፡፡ ወደ ገዳሙ ለመግባት ለጠነከሩ የአንድ ሰዓት ያህል የእግር ጕዞ ይኖረዋል፡፡ የጻድቁ በዓለ ዕረፍት በሚከበርበት ዕለት (ሚያዝያ ዘጠኝ ቀን) ከወልድያ እስከ ገዳሙ የሚያደርሱ መጓጓዣዎች ስለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያኑ ወደ ገዳሙ በመሔድ ከበረከቱ ተሳታፊ እንዲኾኑ ገዳሙ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ የጻድቁ ጸሎታቸው በረከታቸውና አማላጅነታቸው ከዂላችን ጋር ይኹን ወስብሐት ለእግዚአብሔር የበለጠ ለመረዳት እዚህ ላይ
13521
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%8A%9D%20%E1%8A%A0%E1%88%85%E1%88%98%E1%8B%B5
ግራኝ አህመድ
በተለምዶው ግራኝ አሕመድ ተብሎ የሚታወቀው የጦር መሪ ሙሉ ስሙ ኢማም አሕመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ ሲኾን የኖረውም ከ1507 እስክ ታህሳስ 21፣ 1543 (እ.ኤ.አ) ነበር። [1]) በዘመኑ በእስልምና ሃይማኖት የኢማምነት ደረጃ የደረሰ ሲኾን የአዳል ግዛት ተብሎ ይታወቅ የነበረውን የጥንቱን የኢትዮጵያ ክፍል በመምራት እንዲሁም በዘመኑ የነበሩትን ነገሥታት ከመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል እንዲያፈገፍጉ በማድረግ በታሪክ ይታወቃል። በዚህ የተነሳ 3/4ኛ የሚኾነውን የኢትዮጵያ ክፍል ለተወሰነ ጊዜ መቆጣጠር ችሏል። አንድ አንድ የታሪክ ተመራማሪዎችም የግራኝ አሕመድ ሰራዊት ከሞላ ጎደል በሱማሌ ጎሳ ሰዎች የተድሎችን በመቀዳጀቱ ምክኒያት በዚህ ስያሜ እንደጠሩት ይነገራል። ይህ መሪ ከ1529 እስከ 1543 ከነበሩት የመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል ነገስታት ጋር ጦርነት እንዳረገ ታሪክ ይዘግባል። የኢማም አሕመድ ጎሳ ጻሃፊዎች ዘንድ እንደሚታመነው ግራኝ አረብ እንደነበር ሲሆን በሌሎች ታሪክ ተመራማሪወች ዘንድ ግን ሱማሌ እንደሆነ ነው። እንደ እስራኤላዊው የታሪክ ተመራማሪ ሃጋይ ኽልሪች ግን ግራኝ አህመድ ሱማሊኛ ቋንቋን እንደማይናገር አትቷል። በሌላ ሁኔታ ብዙ የታሪክ ጸሃፍት እና መረጃዎች ግራኝ አህመድ የሐረር ተወላጅ መሆኑን ጠቅሰዋል:: ለግራኝ አህመድ እንቅስቃሴ አስተዋጾ ያደረጉ ነገዶች እንደ ኢሳቅ፣ ዳሩድ እና ማረሃን የተሰኙት የሱማሌ ጎሳወች ሲሆኑ ጎሳወቹ ግን በዘር ምክንያት ሳይሆን ያብሩ የነበሩት በሃይማኖት ተመሳሳይነት ነበር። የኢማሙ ዳግም ድል በኖራ ሀመድ ሁመድ የኢማሙን በ18 ዓመት እድሜ የተገኘ ድል ሰምቶና ደንግጦ መናገሻ ከተማውን ሀረርን ጥሎ ወደ ሶማሊያ የሸሸው ሱልጣን አቡበክር ኪዳር (ኪዳድ) በምትባል ቦታ ተደበቀ። ኢማሙም በነካ እጁ በሙስሊሙ መካከል ፈሳድ እንዲስፋፋና ሙስሊሙ የአንድነት ሀይልና ወኔው እንዲነጥፍ ምክነያት የሆነውን ሱልጣን አቡበክር ለማጥቃት ወደተደበቀበት ከተማ ተጓዘ። ኢማሙ ቦታው ላይ ሲደርሱም ሱልጣኑ ጦሩን አሰልፎ ጠበቃቸው። ሁለቱ ጦሮችም ዝሁር ወቅት ላይ ተገናኙ ኢማሙና ጓዶቻቸውም በኢስላማዊ ህብረትና ሙሐመዳዊ ወኔ ማጥቃት ጀመሩ። በርካታው የሱልጣኑ ሰራዊት ተገደለ። ከፊሉም ሱልጣኑን ጨምሮ ሸሸ። ኢማሙ 20 አመት ሳይሞላቸው ሁለተኛውን ጦርነታቸውን በፍፁም ድል አድራጊነት ተወጡ። የሱልጣኑን መሸሸጊያ አወደሙ። በዚህ ጦርነትም ኢማሙ 30 ፈረስና ሌሎች ቁሳቁሶችን ማረኩ። ነገር ግን ኢማሙ ሐረር ገብተው ብዙ ሳይቆዩ ሱልጣኑ ለቁጥር የሚያዳግት ሰራዊት እዛው ሶማሌያ ላይ ሰበሰበና ኢማሙን ለማጥቃት ወደ ሐረር ተመመ። የሱልጣኑ ጦር በርካታ ፈረሰኞችን ያካተተ ስለነበር ኢማሙ የሱልጣኑን መቃረብ ሲሰሙ ስልታዊ ማፈግፈግን መረጡ። ከነጦራቸውም ወደ ሁበት ተጉዘው ጋረሙለታ ተራራ ላይ መሸጉ። ሱልጣኑም ሐረር ገባ። ኢማም አሕመድ በጋሪሙለታ ተራራ ላይ መስፈራቸውን የሰማው ሱልጣን ጦሩን ይዞ ሁበት ገባ። ተራራውንም ለቁጥር ባዳገተው ሰራዊት አስከበበው። ከፍተኛ ጥበቃም አደረገ። የኢማሙ ጦር ከተራራው መውረድና ለህይወት መሠረታዊ የሆኑትን ምግብና የመጠጥ ውሀ ማግኘት አልቻሉም። ሱልጣኑ በዚህ ሁኔታ ለሁለት ሳምንታት ያህል ከበባውን አጠናክሮ ቀጠለ። በስተመጨረሻ ግን የኢማሙ ጦር ተዳከመና ተስፋ መቁረጥ ታየ። ስለሆነም በለሊት የኢማሙ ጦር ወርዶ ከሱልጣኑ ጋር ጦርነት ገጠሙ። ዳሩ ግን የኢማሙ ጦር ለ2 ሳምንት ታግቶ የቆየ በመሆኑ ውጊያው ላይ ቀልጣፋ መሆን አልቻለም። በመሆኑም የኢማሙ ጦር በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃ። ከአንጋፋ የኢማሙ የጦር አዝማቾች መካከል አንዱ ዑመረዲንም ተገደለ። ኢማሙና ጥቂት ጓዶቻቸው ግን አመለጡ። የኋላ ኋላ ግን በዘመኑ ዑለማኦች ከፍተኛ ጥረት በሁለቱ አሚሮች መካከል ስምምነት እንዲኖር ተደረገ። ስምምነቱም ሱልጣኑ ሸሪዓን ሊጠብቅና በፍትህ ሊያስተዳድር ኢማሙና ጦራቸው ደግሞ መሸፈቱን አቁሞ ለሱልጣኑ ታዛዥ ሆኖ በሰላም እንዲኖር የሚያግባባ ነበር። ስምምነቱም መተግበር ተጀመረ። ኢማሙም ጥማታቸው የስልጣን ሳይሆን የሸሪዓ መጠበቅ መሆኑን ሰጥ ለጥ ብለው ለሱልጣኑ በመታዘዝ አሳዩ። በኋላ ግን ሱልጣኑ ስምምነቱን አፈረሰ። ቀደምት ዓመታት ኢማም ግራኝ አህመድ የተወለደው ዘይላ ተብላ ትታወቅ በነበረው የባህር በር አካባቢ በሰሜናዊ ምዕራብ አዳል በአሁኑ ዘመን ሶማሊያ) ነበር። ይህ ታሪካዊ አዳል (ሶማሊያ) የእስልምና ሃይማኖትን የሚከተል መንግስት ይሁን እንጂ በጊዜ ለነበረ የክርስትና ተከታይ ኢትዮጵያው መካከለኛ መንግስት ግብር ይከፍል ነበር። ግራኝም በጎለመሰ ጊዜ ማህፉዝ የተባለን የዘይላ አስተዳዳሪን ልጅ ባቲ ድል ወምበሬ አገባ።. ነገር ግን ማህፉዝ ከመካከለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ተጣልቶ በአጼ ልብነ ድንግል ላይ ጥቃት አድርሶ ሲመለስ በ1517 ተገደለ። በአዳል እርስ በርስ ጦርነት ተነሳ። ግራኝ አህመድም ከተወሰኑ የትግል ዓመታት በኋላ በስልጣን የሚሻኮቱትን በማሸነፍ ሐረርን ተቆጣጠረ። በዚህ ጊዜ የአዳል መሪ ሆነ። ዘመቻዎች በ1527፣ የአዳል መሪ ከሆነ በኋላ፣ ከአዳል ከትሞች የሚጠበቀውን ግብር ለመካከለኛው የኢትዮጵያ መንገስት እንዳይከፈል አገደ። አጼ ልብነ ድንግልም የባሌ ጦር አዛዡን ደግላን ግብሩን እንዲያስከፍል ላከ። ደግላን ግን በአዲር ጦርነት ተሸነፈ። ከዚህ ቀጥሎ ግራኝ ወደ ምስራቅ በመዝመት ሱማሌውችን በጦርነት ግዛቱ አደረገ። ቀስ ብሎም ወደ ምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ብዙ ዘመቻወችን በማካሄድ ስፍር ቁጥር የሌላችቸው ባሪያወችን በመፈንገል በደቡብ አረቢያ፣ ለዘቢድ አስተዳዳሪ በስጦታ መልክ በመላክ በተራው የብዙ ጠመንጃወች ባለቤት ሆነ። በ1528 የልብነ ድንግል ሰራዊት በአዳል ላይ ጥቃት ስላደረሰ፣ ይህን ለመበቀል በ1529 በክርስትያኑ ንጉስ ላይ ኢማም አህመድ ዘመቻውን የኢትዮጵያና አዳል ጦርነት ጀመረ። መሰረታዊው የኢማም አህመድ አላማ ግን "ጅሃድ" ወይም "በሃይማኖት መታገል" ነበር በዚህ ጊዜ የአጼ ልብነ ድንግልን ሰራዊት መምጣት የሰሙት የግራኝ ወታደሮች በፍርሃት ተውጠው ለመሸሽ ሲሞክሩ፣ ግራኝ ግን በጽናትና ቆራጥነት አብዛኞቹ ባሉበት እንዲቆሙ በማድረግ የልብነ ድንግልን ሰራዊት ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ደቡብ ምስራቅ በምትገኘው በሽምብራ ቁሬ ጦርነት መጋቢት 1529 አሸነፈ ጦርነቱን ያሸንፍ እንጂ ብዙ ወታደሮች ስላለቁበት ቀሪው ሰራዊቱ ወደሃገሩ ተመልሶ ከንደገና መታገል ሰጋ። በዚህ መሃል ከአረብ አገር 70 ሙሉ ትጥቅ ያላቸው ወታደሮችና ብዙ ጠብመንጃወች እና 7 መድፎች ከኦቶማን ቱርኮች አገኘ። በ1531፣ የግራኝ ጦር የልብነ ድንግልን ሰራዊት አምባሰል አንጾኪያ ላይ ገጥሞ እንደገና ድል አደረገ። ለዚህ ድል መሰረቱ በዕርዳታ ያገኘው መድፍ እንደነበር ሉዶልፍ ሲያትት ከግራኝ ወገን የተተኮሰ መድፍ ጥይት በአጋጣሚ ልብነ ድንግል ሰራዊት መካከል ወደቀ፣ ይህ እንግዳ መሳሪያ የሚያሰክትለውን ቁስል እንኳ እንዴት ማዳን እንደሚቻል የማያውቁጥ ኢትዮጵያውያን በድንጋጤ ተበታተኑ ከዚህ በኋላ የኢማሙ ሰራዊት ወደሰሜን በመዝመት በሃይቅ፣ ወሎ ደሴቶች ላይ የነበሩትን አካባቢዎችን ተቆጣጠረ። ቀጥሎም ትግራይ ውስጥ ይጠብቀው የነበረውን ሰራዊት በማሸነፍ አክሱም ከተማ ተቆጣጠረ። ይህ ከመሆኑ በፊት አስቀድማ ንግስት እሌኒ የተባለችው የሃድያ ንግስት የዘርዓ ያዕቆብ ሚስት)፣ ለፖርቱጋሎች የወታደር እርዳታ እንዲያረጉ መልዕክት ልካ ኖሮ፣ ታህሳስ 10፣ 1541 400 ጠመንጃ ያነገቱ የፕርቱጋል ሰራዊት ምጽዋ ላይ አረፉ። በዚህ ጊዜ አጼ ልብነ ድንግል በስደት እያለ በ1540 ሲሞት እሱን ተክቶ አጼ ገላውዲወስ ንጉሰ ነገስት ሆኖ ነበር። በ ክሪስታቮ ደጋማ የሚመራው የፖርቹጋሎቹ ሰራዊትና ኢትዮጵያውያን ሚያዚያ 1፣ 1542 በጃርቴ ጦርነት (ጃርቴ በሌላ ስሙ አናሳ ሲባል በአምባላጌ እና በአሻንጌ ሃይቅ መካከል የሚገኝ ቦታ ነው) ከ ግራኝ ሰራዊት ጋር የመጀምሪያ ፍልሚያ አደረገ። በዚህ ጊዜ ፖርቱጋሎቹ ግራኝን ለመጀመሪያ ጊዜ ማየታቸው ሲሆን በጊዜው የነበረው ፖርቹጋላዊው ካስታንሶ ክሩቅ ሆኖ ስላየው ስለግራኝ እንዲህ ይላል፦ በሱ በኩል ያለውን የጦር አውድማ በሚዘጋጅበት ጊዜ፣ የዘይላው ንጉስ ኢማም አህመድ ኮረብታው ላይ ወጣ። በዚህ ጊዜ ብዙ ፈረሰኞች አብረው ተከትለውት ነበር፣ እግረኞችም እንዲሁ። የእኛን የጦር ቀጠና ለመመርመር፣ እኮረብታው ጫፍ ሲደረስ ከ300 ፈረሶች እና ሶስት ግዙፍ ባንዲራወች ጋር ቆመ። አርማዎቹም ሁለቱ ነጭና መካከላቸው ላይ ቀይ ጨረቃ ምልክት ሲኖራቸው አንዱ ደግሞ ቀይና መሃሉ ላይ ነጭ ጨረቃ ያሉባቸው ከንጉሱ ዘንድ ምንጊዜም የማይለዩ ነበሩ ይላል። በዚህ ሁኔታ ለ4 ቀናት በመፋጠጥና መልዕክት በመለዋወጥ እኒህ የማይተዋወቁ ሁለት ሰራዊት ጊዜያቸውን ካሳለፉ በኋላ ክሪስታቮ ደጋማ እግረኛ ወታደሮቹን (ኢትዮጵያኖችንም ይጨምራል) በአራት ማዕዘን ቅርጽ በማደራጀት ወደ ኢማሙ ሰራዊት ዘመተ። የእስላሙ ሰራዊት፣ ብዙ ጊዜ እየደጋገመ ጥቃት ቢያደረስም በመድፍና በጠመንጃ የታጠረ አራት ማዕዘኑ ሊሸነፍ አልቻለም። በዚህ ጦርነት መካከል በድንገት በተተኮሰ ጥይት ግራኝ አህመድ እግሩ ላይ ቆሰለ። ስለሆነም የኢማሙ ሰራዊት መሸሽ መጀመሩን ያዩት የኢትዮጵያና የፖርቹጋል ሰራዊት ተበታትኖ የሚሮጠውን ሰራዊት በማጥቃት ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ። ይሁንና የቀሩት ወታደሮች ከእንደገና በማደራጀት ኢማሙ ጦርነት ከተካሄደብት ወንዝ ራቅ ብሎ ሰፈረ። በሚቀጥሉት ጥቂት የግራኙ ጎራ አዳዲስ ወታደሮች በማስመጣት በከፍተኛ ሁኔታ መጠናከር ጀመረ። ይህ ነገር ያላማረው ደጋማ ቶሎ ብሎ ጦርነት መግጠም አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ መጋቢት 16 ላይ አሁንም አራት ማዕዘን በመስራት ዘመተ። ምንም እንኳ የኢማሙ ጦር ከበፊቱ በበለጠ ቁርጠኝነት ቢዋጉም፣ በድንገት በፈነዳ የጥይት ቀልህ ምክንያት ፈረሶቹ በመደናገጣቸው አራቱ ማዕዘን አሁንም አሸነፈ። በዚህ ጊዜ የኢማሙ ሰራዊት በዕውር ደንብስ እያመለጠ ሸሸ። ክሳታንሶ የተባለው ፖርቱጋላዊም በጸጸት እንዲህ ብሎ መዘገበ፡ መቶ የሚሆኑ ፈረሶች ቢኖሩን ኑሮ የዛሬው ቀን ድል የተሟላ ይሆን ነበረ ምክንያቱም ንጉሱ እራሱ በቃሬዛ አራት ሰወች ተሸክመውት ነው ያመለጠው። ቀሪው ሰራዊትም የሸሸው በተረጋጋ ሁኔታ ሳይሆን በእውር ድንብስ ነበር። የመረብ ምላሽ (አሁኑ ኤርትራ) አስተዳዳሪ ባህር ንጉስ ይስሃቅ ከተደባለቀ በኋላ፣ አጠቃላዩ ሰራዊ ወደ ደቡብ በመነቀሳቀስ በ10ኛው ቀን ከግራኙ ጦር ፊት ለፊት አረፈ። በዚህ መሃል ክረምት ስለገባ በዝናቡ ምክንያት ደጋማ ለሶስተኛ ጊዜ ግራኝን ሊገጥመው ፈልጎ ግን ሳይችል ቀረ። በንግስት ሰብለ ወንጌል ጎትጓችነት ደጋማ በወፍላ፣ ከአሻንጌ ሃይቅ ፊት ለፊት፣ ከግራኝ ጦር ብዙም ሳይርቅ ክረምቱን አሳለፈ። በዚህ ትይዩ ኢማሙ ደግሞ በ ዞብል ተራራወች ላይ ሰራዊቱን አስፈረ። ድል በጦር መሳሪያ ብዛት እንደሚወሰን የተገነዘበው ግራኝ ለእስላሙ አለም የድረሱልኝ ጥሪ አቀረበ። አረቦችም 2000 ጠመንጃወችና መድፎች እንዲሁም ከቱርክ 900 የተመረጡ ወታደሮች ተላኩለት። ባንጻሩ የፖርቹጋሎቹ ወታደሮች ብዛት በተለያዩ ግዴታወችና በጦርነት ላይ በደረሰው ሞት ምክንያት ከ400 ወደ 300 ዝቅ ብሎ ነበር። ይህ በዚህ እንዳለ ክረምት አልፎ በጋ ሲሆን በሃይል የተጠናከረው ግራኝ አህመድ በፖርቹጋሎቹ የጦር ቀጠና ላይ ጥቃት በማድረስ ቁጥራቸውን ወደ 140 አመናመነው። ክርስታቮ ደጋማም ቆስሎ 10 ከሚሆኑ ወታደሮቹ ጋር ተማረከ። በዚህ ጊዜ በሃይማኖቱ ከጸና እንደሚገደል ከሰለመ ግን እንደማይገደል ተነግሮት ሃይማኖቴን አልቀይርም በማለቱ በተማረክበት ተገደለ። ከዚህ ጥቃት የተረፉትና የአጼ ገላውዲወስ ሰራዊት በመጨረሻ ተገናኝተው ሃይላቸውን በማጠናከር የካቲት 21፣ 1543 የወይና ደጋ ጦርነት ተብሎ በሚታወቀው ጥቃት አደረሱ። በዚህ ጦርነት 8560 የሚሆኑት የኢትዮጵያና ፖርቱጋል ሰራዊት 15,200 የሚሆነውን የኢማሙን ሰራዊት አሸነፈ። ኢማሙ በጥይት ተመትቶ ለማምለጥ ሲሞክር ካልአይ የተባለ ወጣት የፈረሰኛው ጦር መሪ ተከታትሎ ሄዶ አንገቱን ቀልቶ ገደለው። የግራኝ ሚስት፣ ባቲ ድል ወምበሬም ከተራረፉ የቱርክ ወታደሮች ጋር አምልጣ ሐረር ገባች። ተከታዮቿንም በማስተባበር የባሏን ሞት ለመበቀል የባሏን እህት ልጅ ኑር ኢብን ሙጃሂድን በማግባት ተነሳች። ፈጠገር ውስጥ የኑር ኢብን ሙጃሂድወታደሮች ጋር ሲዋጋ አጼ ገላውዲወስ እንደተገደለ እና አስከሬኑ ተፈልጎ አንገቱ ተቆርጦ ወደ ሐረር እንደተላከ አንዳንድ የታሪክ ጸሓፊያን ይዘግባሉ:: አቤቶ ሀመልማል የተባለው የአፄ ገላውዴዎስ አጎት ልጅ ሰራዊቱን እየመራ ሀረር ከተማ ገብቶ ከተማይቱን ከዘረፈ እና ካወደመ በኋላ ሱልጣን በረከትን ማርኮ አንገቱን ቀልቶ እደገደለውም ተፅፏል። የኢትዮጵያ ታሪክ ግራኝ አህመድ ማጣቀሻወች ፉቱሑል ሐበሻ ሺሃቡዲን ኣረብ ፈቂህ ሷሊሕ አስታጥቄ የፌስ ቡክ ገፅ
50954
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%8B%E1%89%85%E1%88%8B%E1%88%9A
ዋቅላሚ
የቃሉ መሰረታዊ አመጣጥ ዋቅላሚ የሚለው ቃል የተገኘው “ውሃ” እና “አቅላሚ” ከተሰኙ ሁለት የአማርኛ ቃላት ሲሆን ለሚለው የላቲን ቃል የአማርኛ አቻ ቃል ነው። ስያሜው እንደሚያመለክተው በዚህ መደብ ስር ያሉ ፍጡራን ውሃን የማቅለም ባህርይ አላቸው። ነጠላቁጥር የሆነውና አልጋ የተሰኘው ቃል በላቲን የባህር አረም ማለት ሲሆን በእንግሊዝኛም ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ የባህር አረም 'የሚለው ቃል በጥንታዊ ግሪክ ፋይኮስ ይባል የነበረ ሲሆን ትርጓሜውም የባህር አረም(ምናልባትም ቀይ ዋቅላሚ) ወይም ከቀይ ዋቅላሚ የሚገኝ ቀለም ማለት እንደነበር ይታመናል፡፡ የዋቅላሚ ጥናት ፋይኮሎጂ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን አልጎሎጂ የተሰኘው ቃል ከአገልግሎት ውጭ እየሆነ የመጣ ቃል ነው። መግለጫ ዋቅላሚ የሚለው ቃል ከተለያዩ ስርወዘራዊ ቡድኖች የተገኙ እና በተለያዩ የሥርዓተ ምደባ ዘርፎች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ሕይወት ያላቸው ፍጡራንን የሚወክል ሰፊ ቡድን ነው። በአጠቃላይ ዋቅላሚዎች ስንል እያልን ያለነው፦ በአብዛኛው እውነተኛ ስር፣ግንድ፣ ቅጠል እና ሥርአተሸንዳ የሌላቸው ባለ ቀላል የመራቢያ መዋቅር የሆኑ እና ምግብሰሪ የሆኑ የውሃውስጥ ዕፅዋትመሰል ፍጡራንን ነው። በመላው ዓለም ማለትም፦ በባሕር፣ በጨው አልባ ዉሃማ አካላት እና እርጥበታማ የየብስ ክፍሎች ተሰራጭተው ይገኛሉ። አብዛኛዎቹ ሚክሮስኮፓዊ ሲሆኑ ጥቂቶች ግን በጣም ግዙፎች ናቸው። ለምሳሌ አንዳንድ የባሕር ውስጥ አረሞች እስከ ሜትር ያህል ሊረዝሙ ይችላሉ። በውሃ ላይ የሚንሳፈፉ ዋቅላሚዎች ፋይቶፕላንክተን ይባላሉ፡፡ ዋቅላሚዎች ብዙ የመራቢያ ስልቶች አሏቸው፤ ክለኤ ቁርሰት ከተሰኘው ተራ ኢ-ጾታዊ የመራቢያ ስልት ውስብስብ እስከሆኑ ጾታዊ የመራቢያ ስልቶች ይታይባቸዋል፡፡ ስርዓተ ምደባ የአለምአቀፉ የእፅዋት ስያሜ ኮድ ኮሚቴ ለዋቅላሚ ስርዓተምደባ የሚያገለግሉ የተወሰኑ ቅጥያዎችን ለመጠቀም ምክረሃሳብ አቅርቧል፡፡ እነዚህም ቅጥያዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ )ለክፍለሰፍን፣ ለመደብ፣ )ለንዑስ መደብ፣ አለስ ለክፍለመደብ፣ )ለንዑስ ክፍለመደብ፣ )ለአስተኔ፣ ኦይዲስ )ለንዑስ አስተኔ፣ የግሪክ መሰረት ያለው ስያሜ ለ ወገን፣ የላቲን መሰረት ያለው ስያሜ ለዝርያ ናቸው፡፡ ከ 800 በላይ የዋቅላሚ ወገኖች ሲኖሩ እያንዳንዱ የዋቅላሚ ወገን በስሩ የተለያዩ ዝርያዎችን ይይዛል። ለመጀመሪያ ደረጃ ምደባ መሰረት የሆኑ የዋቅላሚዎች ባህሪያት የዋቅላሚዎች የመጀመሪያ ደረጃ ምደባ የተወሰኑ የስነቅርፅ ገፅታዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ከነዚህ ገፅታዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ፡- (ሀ) የህዋስ የቀለም ተዋፅኦ፣ (ለ) የተከማቸ ምግብ ኬሚካላዊ ተፈጥሮ፣ (ሐ)የተንቀሳቃሽ ህዋሳት ልምጭት አይነት፣ ቁጥር፣ የመጋጠሚያ ነጥብ እና አንፃራዊ ርዝመት (መ)የህዋስ ግንብ መዋቅር እና (ሠ) በህዋሱ ውስጥ በትክክል የተደራጀ ኒውክለስ የመኖርና ያለመኖር ሁኔታ ወይም በተለየ ሁኔታ ጉልህ የሆነ የህዋስ መዋቅር ናቸው። ዋና ዋናዎቹ የዋቅላሚ ስርወዘራዊ ቡድኖች የሚከተሉት ናቸው አረንጓዴ ዋቅላሚዎች ባልጩት ዋቅላሚዎች ወርቃማ ዋቅላሚዎች ኢዩግሊኖፋይታ ዳይኖፍላጅላታ ቡናማ ዋቅላሚዎች ቀይ ዋቅላሚዎች ሰማያዊ አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች ስነ ቅርፅ ዋቅላሚዎች አስገራሚ የስነቅርፅ ተለያይነት የሚታይባቸው ፍጥረቶች ናቸው፡፡ ስነ ቅርፃቸው ላይ በመመስረት ዋቅላሚዎች አንድህዋሴ ዋቅላሚዎች፣ ኩይዋሳዊ ዋቅላሚዎች፣ዘሃዊ ዋቅላሚዎች፣ መቆ ዋቅላሚዎች እና ዥንቃዊ ዋቅላሚዎች በሚባሉ መደቦች ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ 1. አንድ-ህዋሴ ዋቅላሚዎች ህዋስግንብ ያላቸው የማይንቀሳቀሱ ነጠላ ህዋሳት ወይም በሚያጣብቅ ነገር ውስጥ ያሉ የማይንቀሳቀሱ ህዋሳት ናቸው። 2. ኩይዋሳዊ የትናንሽ ተንቀሳቃሽ ህዋሳት መደበኛ ቡድኖች። 3. ዘሃዊ እንደ ጨሌ ገመድ ሰንሰለት ሰርተው የተደረደሩ ህዋሳት ህዋሳት ናቸው። እንደ ስፓይሮጋይራ ያሉ ዝርያዎች ቅርንጫፍ ይሌላቸው ሲሆኑ እንደ ስቲጎኔማ ያሉት ደግሞ ቅርንጫፍ አላቸው። 4. መቆ መቆ ዋቅላሚዎች የሚባሉት በአንድ ህዋስ ውስጥ ብዙ ኒውክለሶች ያሏቸው ማለትም በህዋስ ግንቦች ባልተከፋፈለ አንድ ቤተህዋስ ውስጥ ብዙ ኒውክለሶች የሚገኙበት የዋቅላሚ አይነት ነው፡፡ 5. ዥንቃዊ ህብረህዋስ መሰል የሆነ ብቃይ አካል ያላቸው ዋቅላሚዎች ናቸው። ለምሳሌ በብዙ ሜትር የሚለካ ርዝመት ያለው ማክሮሲስቲስ ከዥንቃዊ ዋቅላሚዎች አንዱ ነው። ስነ ምሕዳር ዋቅላሚዎቸ በውሃ አካላት ውስጥ በስፋት ይገኛሉ፤ በየብስ ላይም በተለመደ መልኩ ይገኛሉ እንዲሁም በበረዶ አካላት ላይና ባልተለመዱ ቦታዎች ይገኛሉ። የባሕር ውስጥ አረሞች የሚባሉት ከ100 ሜትር በላይ ጥልቀት በሌላቸው የውሃ አካላት ውስጥ ይገኛሉ። ነገርግን እንደ ናቪኩላ ፔናታ ያሉ ዝርያዎች እስከ 360 ሜትር ጥልቀት ድረስ እንደሚገኙ ተመዝግቧል። የተለያዩ የዋቅላሚ ዝርያዎች ለውሃ ስነ ምህዳር ወሳኝ ሚና አላቸው። በውሃማ አካላት ውስጥ ተንሳፍፈው የሚገኙ ዋቅላሚዎች (ፋይቶፕላንክተኖች) ለአብዛኛው የባህር ውስጥ የምግብ ሰንሰለት መሰረት ሆነው ያገለግላሉ።በሳይንቲስቶች ግምት መሰረት በከባቢ አየር ውስጥ ከሚገኘው ኦክሲጅን ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነው የሚመረተው የብርሃን አስተፃምሮ በሚያካሂዱ ዋቅላሚዎች ነው፡፡ ጥቅም ለምግብነት በተፈጥሮ የሚያድጉ ዋቅላሚዎች በጣም ጠቃሚ የምግብ ምንጭ ናቸው። በተለይ በእስያ አህጉር በአንዳንዶች እጅግ በጣም ጠቃሚ ተብለው የተለዩ አሉ። ቫይታሚን 1, 2, 3, 6, እና ቪታሚን ይዘው ይገኛሉ። በአዮዲን፣ ፖታሲየም፣ ብረት፣ማግኒዥየም እና ካልስየም የበለፀጉ ናቸው። በተጨማሪም ለገበያ የሚመረቱ ደቂቅዋቅላሚዎቸ ሲያኖባክቴሪያዎችን ጨምሮ እንደ ስፓይሩሊና እና ክሎሬላ ያሉት ለስርዓተ-ምግብ ማሟያ ተብለው ይሸጣሉ። በቤታ ካሮቲን ከበለፀገው ዱናሌላ የቪታሚን ማሟያ ይመረታል። ዋቅላሚዎች በብዙ አገራት ብሔራዊ ምግብ ናቸው። በቻይና ፋት ቾይን ጨምሮ ከ70 በላይ የዋቅላሚ ዝርያዎች ለብግብነት ይውላሉ። በጃፓን ኖሪ እና አውኖሪን ጨምሮ ከ20 በላይ የዋቅላሚ ዝርያዎች ለምግብነት ይውላሉ። በአየርላንድ ደልስ፣ በቺሊ ኮካዩዮ ለምግብነት የሚውሉ የዋቅላሚ አይነቶች ናቸው። በዌልስ የሌቨርዳቦ ወይም ባረ ለውር የሚባለውን ምግብ ለማዘጋጀት ሌቨር የሚባል ዋቅላሚ ጥቅም ላይ ይውላል፤ በኮሪያ ደግሞ ጂም የሚሰኝ ዋቅላሚ ለምግብነት ያግለግላል። በስኮትላንድ፣ አየርላንድ፣ ግሪንላንድ እና አይስላንድ የባህር እና ባደርሎክ የሰላጣ ግብዓቶች ናቸው። በአሁኑ ሰዓት ዋቅላሚዎች የአለምን የምግብ ችግር ለመፍታት እምቅ አቅም ያላቸው አማራጭ መሆናቸው ከግምት ውስጥ እየገባ ነው። ለምግብ ዝግጅት የሚያገለግሉ ሁለት ታዋቂ የዋቅላሚ ዝርያዎች አሉ፡ ክሎሬላ፦ ይህ የዋቅላሚ ዝርያ በጨው እልባ የውሃ አካላት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአረንጓቀፉ ውስጥ ለፎቶሲንተሲስ የሚያግለግሉ ቀለማት አሉት። በብረት፣ ዚንክ፣ ማግኒዥየም፣ 2 እና ኦሜጋ-3 ፋቲአሲድ የበለፀገ ነው። በተጨማሪም ሰውነታችን በራሱ ያማያመርታቸውን ዘጠኙንም አሚኖ አሲዶች ይዞ ይገኛል። ስፓይሩሊና፦ የሲያኖባክቴረያ ዝርያ ሲሆን በፕሮቲን ይዘቱ በ10% ከክሎሬላ የላቀ ነው፤ እንዲሁም ከክሎሬላ የተሻለ የመዳብ እና የቪታሚን 1 ይዘት አለው። አጋር አጋር ከቀይ ዋቅላሚ የሚዘጋጅ ወፍሮ የመጋገር ባህሪይ ያለው ሲሆን በንግዱ አለም ከፍተኛ ተፈላጊነት አለው። አብዛኛዎቹ ደቂቅ አካላት አጋርን ማብላላት የማይችሉ በመሆናቸው በላዩ ላይ ባክቴሪያ እና ፈንገስ ለማሳደግ ምቹ ማሳደጊያ ነው። አርጂኔቶች አርጂኒክ አሲድ ወይም አርጂኔት ከቡናማ ዋቅላሚዎች የሚገኝ ውህድ ነው። ጥቅሞቹ ለምግብ ማወፈሪያ ከመዋል አንስቶ ለቁስል መሸፈኛነት ጭምር ነው። በባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ ሰፊ አገልግሎት አለው። በኒውሜክሲኮ አርጂኔት ለማዘጋጀት እና ለአበሎኒ ምግብነት በኣመት ከ100,000 እስከ 170,000 ቶን የሚደርስ ማክሮሲስቲስ ይመረታል። የሀይል ምንጭ ለወደፊቱ ተወዳዳሪ ለመሆን እና በየጊዜው ከሚቀያየረው የሀገርውስጥ ፖሊሲ ባለፈ ራስን ለመቻል የባዮፊውል ዋጋ ከተፈጥሮ ነዳጅ ዋጋ ማንስ አለበት ካልሆነም እኩል መሆን ይኖርበታል። እዚህ ጋ ዋቅላሚን መሰረት ያደረጉ የነዳጅ ውጤቶች ትልቅ ተስፋ ሰጪ ቦታ ይይዛሉ፤ ይህም በቀጥታ የሚያያዘው በተወሰነ ቦታ ላይ በአንድ አመት ውስጥዋ ቅላሚዎች ባላቸው ከፍተኛ ምርት የመስጠት አቅም ላይ ነው። ለብክለት ቁጥጥር ፍሳሽ ቆሻሻ በዋቅላሚዎች ሊታከም ይችላል፤ ይህም ለፍሳሽ ቆሻሻ ማከሚያ የሚውሉ ከፍተኛ መጠን ያላቸው መርዛማ ኬሚካሎችን ለመቀነስ አይነተኛ መፍትሔ ነው። ዋቅላሚዎች ከእርሻ በጎርፍ ታጥበው የሚሄዱ ማዳበሪያዎችን ለማጥመድ ይጠቅማሉ፤ በቀጣይነት በማዳበሪያ የበለጸገውን ዋቅላሚ እንደማዳበሪያ መጠቀም ይቻላል። የውሃ ማቆሪያዎችን ወይም ኩሬዎችን በዋቅላሚ አማካኝነት ማጽዳት ይቻላል፤ ይህም የሚሆነው ወይም የሚባል መሳርያ ባለብት ዋቅላሚዎች በውሃ ውስጥ ያለውን ንጥረነገር እንዲመጡ በማድርግ ነው። የግብርና ምርምር አገልግሎት ተመራማሪዎች በጎርፍ ታጥቦ ከሚሄደው ናይትሮጅን ከ60–90%የሚሆነው እንዲሁም ከ70–100% የሚሆነው ፎስፈረስ አማካኝነት ከፍግ ፍሳሾች ውስጥ መሰብሰብ እንደሚቻል ደርሰውበታል። ዋቢ ምንጭ አትክልት ሥነ
1631
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%88%88%E1%88%B5%20%E1%8B%9C%E1%8A%93%E1%8B%8A
መለስ ዜናዊ
መለሰ ዜናዊ (የትውልድ ስማቸው ለገሠ ዜናዊ አስረስ) (ሚያዝያ ቀን ዓ/ም ነሐሴ ቀን ዓ/ም) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰው ነበሩ። በአድዋ ትግራይ የተወለዱ ሲሆን ከ፲፱፻፹፯ ዓ/ም አንስተው እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን በከፍተኛው የአመራር ቦታ ላይ ነበሩ። የኢህአዴግና የሕውሓት ሊቀመንበር በመሆን ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ ቆይተዋል። አቶ መለስ ዜናዊ አባታቸው (አቶ ዜናዊ አስረስ ከጎዣም አገው ቤተሰባዊ ትስስር እንዳላቸው ይታመናል) የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ፣ በእናታቸው በኩል ደግሞ ኤርትራዊ ናቸው። መለስ በታወቀው ጀነራል ዊንጌት 2ኛ ደረጃ ተምህርት ቤት የተማሩና ከአጼ አህለስላሴ የኮከብ ተማሪዎች ሽልማት የተሸለሙ፣ ከዛም ወደ በረሃ ወርደው በታጋይነት ከመሰለፍቸው በፊት፤ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሜዲካል ፋክልቲ ተማሪ ነበሩ። ትግርኛ፣አማርኛና፡ እንግሊዝኛ አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ። መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዜያት ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ባደረጓቸው አስተዋፅኦዎች የኢትዮጵያ ባለውለታ ናቸው ይባላሉ፡፡ ኢትዮጵያም እንደ እርሳቸው ያለ መሪ አግኝታ እንደማታውቅ በሰፊው ይነገራል፡፡ ወደ ስልጣን አመጣጥ አቶ መለስ የሚመሩት ሕውሓት የኮሎኔል መንግስቱ ኅይለ ማርያምን አምባገነናዊ መንግስት በትጥቅ ትግል ሲታገሉ ከነበሩ ድርጅቶች አንዱ ነበር። አቶ መለስ የሕወሓት አመራር ኮሚቴ መሪ ሆነው በ1971 ተመረጡ፤ ቀጥሎም በ1975 የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኑ። የደርግ መንግሥት ከወደቀም ጀምሮ የሕወሓትና የኢህአዴግ ሊቀ-መንበርም ሆነው አገልግለዋል። ኢህአዴግ የአራቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የኦሮሞ ህዝቦች ዲሞከራሲያዊ ድርጅት፣ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ውህደት ነው። ወደ ስልጣን ሲመጡ በጊዜው ላቋቋሙት ጊዜያዊ መንግስት ፕረዚዳንት ሆነው ካገለገሉ በሗላ 1985 ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተመረጡ። በጊዜው የፕረዚደንትነቱን ቦታ የተረከቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ናችው። የሽግግር መንግስታቸው የአምባገነኑ የመንግስቱ ኃይለ ማርያም አስተዳደር እንደ ወደቀ አዲስ አበባን የተቆጣጠረው ኢአሓዴግ በሕዝብ ምርጫ ሳይሆን ብሔረሰቦችን መሰረት ባደረገ በጥቂት ግለሰቦች የሽግግር መንግሥቱ በመቋቋሙና በተለይም የአማራን ሕዝብ(የአማራን የፖለቲካ አስተሳሰብ) ያለው ፖርቲ ሳይወከል መቅረቱ አብዛኛውን ሕዝብና ምሁራንን በጣም አስቆጣ። የኢህአዴግ ደጋፊዎች በወቅቱ በአምባ ገነኑ ደርግ ስር ተጨቁኖ ለነበረው ድሃ ኢትዮጵያዊ የኢህአደግ ወደ ስልጣን መምጣት ሌላ አማራጭ ስላልነበር የኢሕአዴግን መንግስት ሕዝቡ ለመቀበል ስለ ተገደደ በጊዜው ኢህአዴግ ይህ ነው የተባለ ተቃውሞ አልገጠመውም። በአንጻሩ ከጅምሩ በትጥቅ ትግል ኢሕአዴግን ሲረዱ የነበሩ የአረብና የምዕራባውያን መንግስታት ከጎንህ አለን በማለት በሁለት እግሩ አንዲቆም አስችለውታል። ይሁን እንጂ እያደር ሲመጣ የአቶ መለሰ ዚናዊ መንግስት የታገለለትን ዓላማ ስቶ ዲሞክራሲን በማፈን የነጻ ፕሬስ አፈና በማካሄድና የብአዊ መብት ረገጣ ስላበዛ ብዙ የምዕራባዊያን ድጋፍና ከማጣቱም በላይ የብዙ ሺ ኢትዮጵያዊያን ለስደት ዳርጎአል። ሆኖም ዓለም አቀፉን ሽብርተኛ ለመታገል በሚል ሽንገላ ሱማሌን በመውረሩ ምክንያት በጆርጅ ቡሽ የምትመራ አሜሪካ ቀንደኛና ዋነኛ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆና ቀርታለች። ቀጣዩ የአሜሪካ መሪ ባራክ ኦባማም የአገራቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ካላቸው ፍላጎት አልቃይዳንና አልሸባብ የተባሉ የአክራሪ እስላም ቡድኖችን እየታገልኩ ነው ላለው ኢሕአዴግን ድጋፋቸውን ቀጥለዋል። የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች ምንም እንኳ በደርግ የግፍ አገዛዝ የተማረረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኢህአዴግን ለመቀበልና አብሮ ለመስራት ወደ ኋላ ባይልም ውሎ ሲያድር ግን በኢህአዴግ የአገር ውስጥ ፖሊሲ መከፋቱ አልቀረም። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ብሎ ራሱን የስየመው ቡድን ከኢህአዴግ ጋር በመቃቃሩ ራሱን ከፓርላማውና ከካቢኔው አግልሎ ወደ ትጥቅ ትግሉ ተመለሰ። ጠ.ሚ. መለስ የኤርትራን የመገንጠል ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር መፍቀዳቸው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ብሔረሰብ እንዲገነጠል የሚያስችለውን አንቀጽ በሕገ መንግስታቸው በማካተታቸው በተለይ በምሁራን ዘንድ የከረረ ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። ሁሉም በክልሉ በቋንቋው ይማር የተሰኘው ፖሊሲያቸውም በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬና መከፋፈልን በመፍጠሩ በሀገርና ከሀገር ውጭ በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂዶባቸዋል። በ1997 ዓ.ም. አጋማሽ ጠቅላላ ምርጫ ሲደረግ ከተለያዩ የፖለቲካ ህቡዕ ፓርቲዎች የተውጣጣ ቅንጅት የተሰኘ ጥምር የፖለቲካ ፓርቲ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ተወዳደረ። በውጤቱም የዓለም ታዛቢዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ከመቶ 97 እጁ መራጭ የተቃዋሚውን ፓርቲ ቅንጅትን መረጠ። በውጤቱ የተደናገጠው የአቶ መለስ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የአዲስ አበባን ፖሊስ በፌዴራል ቁጥጥር ስር አዞረ። የአዲስ አበባ ምክር ቤትንም በኦሮሚያ መስተዳደር ስር እንዲተዳደር አዲስ ድንጋጌ አወጣ። ይሁን እንጂ ብዙም ገለልተኛ ታዛቢ በሌለበት ከአዲስ አበባ ውጪ ኢሕአዴግ 90 በመቶ ማሸነፉ ስለታወጀ ተቃዋሚዎች አድልዎ ተደርጎብናልና ምርጫው እንደገና ይጣራ ብለው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የክስ ማመልከቻ በማስገባታቸው ማጣሪያ ተካሄደ። ተቃዎሚዎች በጠቅላላው የምርጫ ውጤት ባለመስማማታቸው ያሸነፉበትን የፓርላማ ወንበር ባለመቀበል የገዢው ፓርቲ በበላይነት ከተቆጣጠረው ፓርላማ ራሳቸውን አገለሉ። ሚሥስ አና ጎሜዝ የተባሉ የአውሮፓ ታዛቢ ቡድን መሪ ምርጫው አድልዎና ጫና እንደነበረበት ለዓለም ሕዝብ ምስክርነታቸውን ተናገሩ። አብዛኛዎቹ ታዛቢዎች (አፍሪካ ሕብረት አና የጂሚ ካርተርማእከል) ምርጫው በኢትዮጲያ ከተካሄዱ ምርጫዎች በጣም የተሻለ መሆኑን መሰከሩ። በሺ የሚቆጠሩ የቅንጅት ደጋፊዎች በዋና ዋና ከተማዎች በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ በቁጣ በሚገልጹበት ጊዜ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሕዝብ በፖሊስ በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱን አጥቶአል። የአቶ መለስ መንግስት አብዛኛዎችን በህዝብ የተመረጡ የቅንጅት ፓርቲ አባላትንና በሺህ የሚቆጠሩ አባላትን ባገር ክህደት አና መንግስትን ለመገልበጥ በመሞከር ከሰሳቸው። ሁለት ዓመት በፈጀ የፍርድ ሂደትም ፍርድ ቤቱ የቅንጅት መሪዎችን አገርን በመክዳት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው አገኛቸው። ይሁን እንጂ ሁሉም የ ቅንጅት መሪዎችና አብዛኛው ደጋፊ አባላት ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ በመጠየቃቸው ከእስር ነጻ
51091
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%9B%E1%8C%94%20%E1%88%A5%E1%88%AD%E1%8B%88-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%A5%E1%89%B5
ዛጔ ሥርወ-መንግሥት
የአማራ ሥርወ-መንግሥት እና ነገድ በኢትዮጵያ አማራ ማለት በቋንቋው አማርኛ እና ግዕዝ ሲኾን ትርጉሙም ነጻ ህዝብ ማለት ነው፡፡ የአማራ ሥርወ መንግሥት እና ነገድ በጥንታዊት ኢትዮጵያ ከአክሱም መንግስት በፊት የዳማት ስርዎ መንግስት አንስቶ እስከ 1975 አ ም በኢትዮጵያን በመንገሥ ለተከታታይ ከ3000 ዓመታት በላይ አስተዳድሯል፡፡ ከታወቁ ታላላቅ የአማራ ነገስታት መካከል (ቅዱስና ንጉሥ) በመኾን በተከታታይ የነገሡት አራት ቅዱሳን፡ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ቅዱስ ሐርቤ (ገብረ ማረያም) ቅዱስ ላሊበላ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሥታት ዕድሜ ዘመናቸውን ሙሉ ሀገራቸው ኢትዮጵያን በሃይማኖታዊ፤ ማኅበራዊ፤ ትምህርታዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ናቸው፡፡ በሀገራችን ታዋቂ የቱሪስት መስህብ ከሆኑት ቅርሶች መካከል የታላቁ የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናትን የገነቡት እነዚህ ታላላቅ ቅዱሳን ነገሥታት ናቸው፡፡ እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት የተሰሩት ከአንድወጥ ትልቅ ዐለት ላይ መሆኑ ዓለምን ያስደነቀ ቅርስ ነው፡፡ ስለእነዚህና ሌሎችም ነገሥታት ታሪክና ሥራ ቀጥሎ በስፋት እናቀርባለን፡፡ የአማራ ነገድ እና ታሪክ አገው ልቡ ዘጠኝ ስምንቱን አኑሮ በአንዱ አጫወተኝ የተባለበት ታሪክና ምክንያት አለው፡፡ አማራ ማለት እንደ እግዚአብሔር ልበ ሰፊ ነገር አላፊ ነው ማለት ነው፡፡ ወልደ እግዚአብሔር መድኀኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ (ኩኑ ጠቢባነ ከመ እባብ ወየዋህ ከመ አርዌ ርግብ) እንደ እባብ ልባሞች አንደ ርግብ የዋሆች ኹኑ ብሎ አዝዞናል እንጂ ከአህዛብ እና ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ ሂዱ ኑሩ ተደባለቁ አላለንም፡፡ ምንጭ፡ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ 2000 ዓ.ም ገፅ-136) አባ አውግስጢኖስም ይህንን የክርስትና ሕይወት በአጽንኦት ሲገልጹትና ሲመክሩን በክርስትና ህይወት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የምድር ጨው እና የዓለም ብርሐን ሆኖ በሃይማኖትና ምግባር መኖር ነው እንጂ በአሕዛብ ማኅብራዊ ጣጣ ውስጥ ገብተን መደባለቅ የለብንም ብለዋል፡፡ ከታሪክ ስንነሳ የአገው ህዝብ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሐይማኖቱ ጠንካራ አማኝ ና በሐይማኖት ጉዳዮች ላይ በፅናት በመቆም ሚስጥራትን የሚጠብቅ ነው፡፡ በሐይማኖት ጉዳዮች ላይ ቀልድና ዋዛ ፈዛዛ አይወድም፡፡ ከእንግዳ ሰዎች ወይም ከባዕድ ጋር ሲገናኝ ደግሞ በቶሎ ተግናኝቶ አይመሳሰልም አይደባለቅም ነገር ግን እንግዳውን በአግባቡ እያስተናገደ በልቡ ግን ይመረምረዋል፡ ያጠናዋል፡ የምን እምነት ተከታይ እንደሆነ ኑሮው አና ባህሉ አንዴት እንደሆነ ለማዎቅና ለመጠንቀቅ ይሞክራል፡፡ ወዲያውም እውነተኛ አማኝና ክርስቲያን መሆኑን ሲያረጋግጥ እንደ ርግብ የዋህ ይሆንለታል ማለት ነው፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዘመነ ዛጉዌ ሥርወ-መንግስት ዛጔ የሚለዉ ስያሜ የሥርወ-መንግሥቱ ተዋናዮች የነገደ አገው ተወላጆች ስለኾኑ የአገው መንግሥት ለማለት ’’ዘአገው’’ ከሚለው ቃል የተወሰደ ነው፡፡ ለዛጔ ሥርወ መንግሥት ነገሥታት የዘር ግንድ መሰረት የኾነው መራ ተክለሃይማኖት የአክሱም መንግሥት ካከተመ በኋላ በትረ መንግሥቱን ጨብጦ መናገሻ ከተማዉን ወደ ላስታ በማዛወር በኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እነዲጀመር ምክንያት ኾኗል፡፡ ከመራ ተክለሃይማኖት ዠምሮ ከሦስት መቶ ዓመታት በላይ ዐሥራ አንድ የዛጔ ነገሥታት ኢትዮጲያን እንደ አስተዳደሩ ትውፊታዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከነዚህም መካል አራቱ ክህነትን ከንግሥና ጋር አስተባብረው የያዙ እና በቤተክርስቲያን ቅድስናቸዉ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ካህናት ነገሥታት የሚባሉት ከአስራአንዱ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ነገሥታት መካከል ቀደም ብለን እንደገለፅናቸው፣ ካህናት ነገሥታት በመባል የሚታወቁት አራት ናቸው፡ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ቅዱስ ሐርቤ(ገብረ ማረያም) ቅዱስ ላሊበላ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሥታት ለክርስትና እምነታቸዉ የነበራቸዉ ፍቅር፣ያደረጉት መስዋዕትነትና ውለታ ማንነታቸዉን ይገልፃቸዋል፡፡ በርግጥ ኹሉም የዛጔ ነገሥታት ክርስቲያኖች ስለነበሩ በዮዲት ጉዲት የጥፋት ዘመቻ ምክንያት፡ -ተመናምኖ የነበረዉን ክርስትና እንደገና እንዲያንሠራራ ማድረጋቸው -ተስፋ የቆረጠዉን ሕዝበ-ክርስቲያን እንዲፅናና፣ማድረጋቸው -የተቃጠሉ መጽሐፍት እንደገና እንዲፃፉና ማድረጋቸው እና -የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናት እንደገና እንዲሰሩ ያደረጉት ጥረት፤ በኢትዮጲያ ቤተክርስቲያን ታሪክ የሚረሳ አይደለም፡፡ ከሁሉም በበለጠ እነዚህ አራቱ ነገሥታት ሙሉ ሕይወታቸውን ለመንፈሳዊ ነገር አዉለዉ አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ፣ በፅድቅ ሥራቸዉ ኹሉ ለሕዝበ ክርስቲያኑ አራያ በመሆን የክርስትና ሃይማኖት እንዲከበር፣ እንዲስፋፋና እንዲጠናቀር በማድረግ በፍፁም ተጋድሎ ቤተክርስቲያንን ያገለግሉ ስለሆነ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዉለታቸዉን ባለመዘንጋት የቅድስና ማዕረግ ሰጥታ ትጠራቸዋለች፡፡ ስለነዚህ ቅዱሳን ነገስታት በገድላቸዉ፣በታሪክ ነገስታቸዉና በስንክሳር ከተዘገበዉ ሌላ ትተውልን የኼዱት አስደናቂ ቅርሶቻቸዉ ማንነታቸውን ይነግሩናል፡፡ በይተለይ በነዚህ ቅዱሳን የታነፁ አብያተ ክርስቲያናት ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና ያገኙና መንፈሳዊ ምግባራቸዉንና የቅድስና ሕይወታቸውን አጉልተዉ በማሳየት አራያ የሚሆኑን ናቸዉ፡፡ (የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ ክፍል-2 ገጽ 43) ''የአራቱን ቅዱሳን ነገስታት ዘመነ መንግሥት ልዩ የሚያደርገዉ ከሁሉም በላይ ቤተክርስቲያን የነበራት ክብርና ድጋፍነበር፡፡ ነገስታቱ ራሳቸዉ ካህናት ፍፁም መንፈሳዊያን ስለነበሩ ለቤተክርስቲያን በነበራቸዉ ታላቅ ፍቅር ሌላዉም ህዝበ ክርስቲያን አርአያነቱን በመከተል ለቤተክርስቲያን ትልቅ ድጋፍ ነበረዉ፡፡እነዚህ ነገስታት አብያተ ክርስቲያናትን ከማሳነጽ ሌላ ለበርካታ ገዳማትና አድባራት ተጨማሪ
4226
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8D%8D%E1%88%AB%E1%8A%95%E1%8A%AD%E1%88%8A%E1%8A%95%20%E1%88%AE%E1%8B%98%E1%89%A8%E1%88%8D%E1%89%B5
ፍራንክሊን ሮዘቨልት
ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት ጥር 30, 1882 ኤፕሪል 12, 1945), ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል. በመጀመርያ ፊደላቸው አሜሪካዊ ፖለቲከኛ እና ጠበቃ ከ1933 እስከ እለተ ሞቱ በ1945 ድረስ የዩናይትድ ስቴትስ 32ኛው ፕሬዚደንት ሆነው ያገለገሉ ሲሆን የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባል በመሆን ሪከርድ በሆነ አራት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዎች አሸንፈው የሀገሪቱ ማዕከላዊ ሰው ሆነዋል። በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ የዓለም ክስተቶች። ሩዝቬልት በዩኤስ ታሪክ ውስጥ ለከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ምላሽ በመስጠት የኒው ድርድርን የሀገር ውስጥ አጀንዳ በመተግበር በአብዛኛዎቹ የታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት ወቅት የፌደራል መንግስትን መርቷል። የፓርቲያቸው ዋና መሪ እንደመሆናቸው መጠን በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ሶስተኛው በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ዘመናዊ ሊበራሊዝምን የሚገልጸውን አዲስ ስምምነት ጥምረት ገነቡ። ሦስተኛው እና አራተኛው የስልጣን ዘመን በ2ኛው የዓለም ጦርነት የተቆጣጠረው ሲሆን በስልጣን ላይ ከሞተ በኋላ ብዙም ሳይቆይ አብቅቷል። የተወለደው ከሮዝቬልት ቤተሰብ በሃይድ ፓርክ ኒው ዮርክ ከግሮተን ትምህርት ቤት እና ከሃርቫርድ ኮሌጅ የተመረቀ ሲሆን በኮሎምቢያ የሕግ ትምህርት ቤት ገብቷል በኒው ዮርክ ከተማ የሕግ ልምምድ ለማድረግ ባር ፈተናውን ካለፈ በኋላ ወጣ እ.ኤ.አ. በ 1905 አምስተኛውን የአጎቱን ልጅ ኤሌኖር ሩዝቬልትን አገባ። ስድስት ልጆችን የወለዱ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አምስቱ እስከ ጉልምስና ደርሰዋል። እ.ኤ.አ. በ 1910 ለኒውዮርክ ግዛት ሴኔት ምርጫ አሸንፈዋል እና በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በፕሬዝዳንት ውድሮው ዊልሰን ስር የባህር ኃይል ረዳት ፀሀፊ ሆኖ አገልግሏል ሩዝቬልት በዲሞክራቲክ ፓርቲ 1920 የብሔራዊ ትኬት የጄምስ ኤም ኮክስ ተወዳዳሪ ነበር ግን ኮክስ ተሸንፏል። በሪፐብሊካን ዋረን ጂ ሃርዲንግ. እ.ኤ.አ. በ 1921 ሩዝቬልት በፓራላይቲክ በሽታ ያዘ በወቅቱ ፖሊዮ ተብሎ የሚታመን ሲሆን እግሮቹም በቋሚነት ሽባ ሆነዋል። ሩዝቬልት ከህመሙ ለማገገም ሲሞክር በዋርም ስፕሪንግስ፣ ጆርጂያ የፖሊዮ ማገገሚያ ማዕከል አቋቋመ። በ1928 የኒውዮርክ ገዥ ሆኖ ከተመረጠ በኋላ ሩዝቬልት ሳይታደግ መራመድ ባይችልም ከ1929 እስከ 1933 በገዥነት አገልግሏል፣ በዩናይትድ ስቴትስ እየከበበ ያለውን የኢኮኖሚ ቀውስ ለመቋቋም ፕሮግራሞችን አቅርቧል። እ.ኤ.አ. በ 1932 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሩዝቬልት በዩኤስ ታሪክ ውስጥ ከታዩት የመሬት መንሸራተት ድሎች በአንዱ የሪፐብሊካን ፓርቲ ስልጣንን ኸርበርት ሁቨርን አሸንፏል። የሩዝቬልት ፕሬዝደንት የጀመረው በታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት መካከል ሲሆን በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ በ73ኛው የአሜሪካ ኮንግረስ ታይቶ የማይታወቅ የፌደራል ህግ አውጪ ምርታማነትን መርቷል። ሩዝቬልት እፎይታን፣ ማገገሚያ እና ማሻሻያ ለማድረግ የተነደፉ ፕሮግራሞችን እንዲፈጠር ጠይቋል። በመጀመሪያው አመት ውስጥ እነዚህን ፖሊሲዎች በተከታታይ በሚወጡ የአስፈፃሚ ትዕዛዞች እና አዲስ ስምምነት ተብሎ በሚጠራው የፌደራል ህግ መተግበር ጀመረ። ብዙ የአዲስ ስምምነት ፕሮግራሞች እንደ ብሔራዊ የማገገም አስተዳደር ላሉ ሥራ አጦች እፎይታ ሰጥተዋል። በርካታ የአዲስ ስምምነት ፕሮግራሞች እና የፌዴራል ህጎች እንደ የግብርና ማስተካከያ ህግ ለገበሬዎች እፎይታ ሰጥተዋል። ሩዝቬልት ከፋይናንስ፣ ግንኙነት እና ጉልበት ጋር የተያያዙ ዋና ዋና የቁጥጥር ማሻሻያዎችን አቋቋመ። ከኢኮኖሚው በተጨማሪ፣ ሩዝቬልት በክልከላ ምክንያት እየጨመረ የመጣውን ወንጀል ለመግታት ሞክሯል። ለመሻር በመድረክ ላይ ዘመቻ ካደረጉ በኋላ፣ ሩዝቬልት የ1933 የቢራ ፍቃድ ህግን ተግባራዊ በማድረግ 21ኛውን ማሻሻያ ተግባራዊ አደረገ። ከአልኮል ሽያጭ የሚሰበሰበው የታክስ ገቢ እንደ አዲስ ስምምነት አካል ለሕዝብ ሥራዎች ይሆናል። ሩዝቬልት በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው 30 "የፋየርሳይድ ቻት" የሬዲዮ አድራሻዎችን በመስጠት ለአሜሪካን ህዝብ በቀጥታ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ሬዲዮን ይጠቀም ነበር እና በቴሌቪዥን የተላለፈ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነዋል። ከ1933 እስከ 1936 ባለው ጊዜ ውስጥ ኢኮኖሚው በፍጥነት ተሻሽሏል፣ እና ሩዝቬልት በ1936 እንደገና በምርጫ አሸንፏል። የኒው ድርድር ታዋቂነት ቢኖርም ብዙዎቹ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወግ አጥባቂ አቋም ይዘው የቆዩ ሲሆን አዲስ ስምምነትን በተደጋጋሚ ይገድሉ ነበር። በድጋሚ መመረጡን ተከትሎ፣ ሩዝቬልት በ1937 የፍትህ ሂደቶች ማሻሻያ ህግ (ወይም "የፍርድ ቤት ማሸግ እቅድ") በመጠየቅ ይህንን ለመቃወም ፈለገ፣ ይህም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን መጠን ያሰፋ ነበር። ሂሳቡ አዲስ በተቋቋመው የሁለትዮሽ ወግ አጥባቂ ጥምረት ታግዶ የነበረ ሲሆን ይህም ተጨማሪ የአዲስ ስምምነት ህግን ለመከላከል ፈልጎ ነበር። በውጤቱም, ኢኮኖሚው ማሽቆልቆል ጀመረ, ይህም የ 1937-1938 ውድቀትን አስከተለ. በሮዝቬልት ስር የተተገበሩ ሌሎች ዋና ዋና የ1930ዎቹ ህግጋቶች እና ኤጀንሲዎች የሴኩሪቲስ እና ልውውጥ ኮሚሽን፣ የብሄራዊ የሰራተኛ ግንኙነት ህግ፣ የፌደራል የተቀማጭ ገንዘብ መድን ድርጅት፣ የማህበራዊ ዋስትና እና የፍትሃዊ የስራ ደረጃዎች ህግን ያካትታሉ። ሩዝቬልት እ.ኤ.አ. በ 1940 በድጋሚ ለሦስተኛ የስልጣን ዘመናቸው ተመረጡ፣ ከሁለት የምርጫ ዘመን በላይ ያገለገሉ ብቸኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አድርገውታል። እ.ኤ.አ. በ 1939 ሌላ የዓለም ጦርነት በአድማስ ላይ ነበር ይህም ዩናይትድ ስቴትስ ገለልተኛነትን የሚያረጋግጡ ተከታታይ ህጎችን በማውጣት እና ጣልቃ ገብነትን ውድቅ በማድረግ ምላሽ እንድትሰጥ አነሳሳው። ይህም ሆኖ ፕሬዚዳንት ሩዝቬልት ለቻይና፣ ለእንግሊዝ እና በመጨረሻም ለሶቪየት ኅብረት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ እና የገንዘብ ድጋፍ ሰጡ። እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 7 ቀን 1941 የጃፓን ጥቃት በፐርል ሃርበር ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ሩዝቬልት በጃፓን ላይ የጦርነት አዋጅ ተናገረ። በታኅሣሥ 11 የጃፓን አጋሮች፣ ናዚ ጀርመን እና ፋሺስት ኢጣሊያ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ጦርነት አውጀዋል። በምላሹ ዩኤስ ከአሊያንስ ጋር በመተባበር ወደ አውሮፓ ጦርነት ቲያትር ገባ። በከፍተኛ ረዳታቸው ሃሪ ሆፕኪንስ በመታገዝ እና በጠንካራ ሀገራዊ ድጋፍ ከእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊንስተን ቸርችል፣ የሶቪየት ዋና ፀሀፊ ጆሴፍ ስታሊን እና ከቻይናው ጄኔራሊሲሞ ቺያንግ ካይ-ሼክ ጋር በቅርበት በመስራት የተባበሩት መንግስታትን በአክሲስ ሀይሎች ላይ በመምራት ላይ ናቸው። ሩዝቬልት የጦርነቱን ጥረት ለመደገፍ የአሜሪካን ኢኮኖሚ ማሰባሰብን በበላይነት በመቆጣጠር የአውሮፓን የመጀመሪያ ስትራቴጂ በመተግበር የብድር-ሊዝ ፕሮግራምን በማነሳሳት እና የጀርመንን ሽንፈት ከጃፓን የበለጠ ቅድሚያ ሰጥቷል። የእሱ አስተዳደር የፔንታጎንን ግንባታ በበላይነት ይቆጣጠር ነበር፣ በዓለም የመጀመሪያውን የአቶሚክ ቦምብ ልማት አነሳስቷል እና ከሌሎች የህብረት መሪዎች ጋር በመሆን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ከጦርነቱ በኋላ ሌሎች ተቋማትን መሠረት ለመጣል። ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም መድረክ ልዕለ ኃያል የሆነችው በጦርነቱ መሪነት ነው። ሩዝቬልት እ.ኤ.አ. በ 1944 በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከጦርነቱ በኋላ ማገገሚያ መድረክ ላይ በድጋሚ ተወዳድሮ አሸንፏል። በኋለኞቹ የጦርነት ዓመታት አካላዊ ጤንነቱ ማሽቆልቆል ጀመረ እና ለአራተኛው የስልጣን ዘመን ከሶስት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሩዝቬልት ኤፕሪል 12, 1945 ሞተ። ምክትል ፕሬዝዳንት ሃሪ ኤስ. ትሩማን በፕሬዚዳንትነት ስልጣን ያዙ እና በአክሲስ ሀይሎች እጅ መስጠትን በበላይነት ተቆጣጠሩ። እሱ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ፣ በርካታ የሩዝቬልት ድርጊቶች እንደ ጃፓን አሜሪካውያን በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ ወደ ሌላ ቦታ መዛወር እና መመልመል በመሳሰሉት ከፍተኛ ትችቶች ደርሰዋል። ቢሆንም፣ እሱ በተከታታይ በምሁራን፣ በፖለቲካ ሳይንቲስቶች እና በታሪክ ተመራማሪዎች በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ከታላላቅ ፕሬዚዳንቶች አንዱ ሆኖ ተመድቧል። የአሜሪካ
35758
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%AD%20%E1%8A%A4%E1%88%8D%20%E1%88%B2%20%E1%8B%91%E1%8B%B0%E1%89%B5
አር ኤል ሲ ዑደት
አር ኤል ሲ (አልሲ) ዑደት እሚባለው እንቅፋት (ሬዚዝስተር)ን፣ አቃቤን(ካፓሲተር) እና እቃቤን(ኢንዳክተር) ያቀፈ የኤሌክትሪክ ዑደትን ነው። እኒህ የኤሌክትሪክ አባላቶች በትይዩ ወይንም በቅጥልጥል ተያይዘው ሊገኙ ይችላሉ። ይህ ዑደት እጅግ ብዙ ጥቅም ያለውና በብዙ የኤሌክትሮኒክ ቁሳቁሶች ውስጥ ሰርጾ የሚገኝ ነው። አንድ የአልሲ ዑደት በርሱ ትይዩ የሆነ ድግግም (ፍሪኪዮንሲ) ያለው መልዕክት (ሲግናል) ሲያጋጥመው ከርሱ ጋር አብሮ ስለሚከንፍ፣ በራዲዮን ውስጥ ጣቢያ ለመቀየር ያገልገላል። እንዲሁም ዥዋዥዌ የሚጫወቱ የኤሌክትሪክ ዑደቶችን ለመፍጠር በጣም ጠቃሚ ነው። በተረፈ የአልሲ ዑደት የተለያየ ክፍሎች በውስጣቸው ለሚያልፍ ድግግም ኤሌክትሪክ የተለያየ ጸባይ ያሳያሉ። ለምሳሌ ኢንዳክተር ከፍተኛ ድግግም ሞገዶችን አሳልፎ ዝቅተኛ ድግግም ሞገዶችን ሲገድል፣ ካፓሲተር በተራው ከፍተኛ ሞገዶችን ገድሎ ዝቅተኞችን ያሳልፋል። ስለሆነም በቴፕ ስፒከር ውስጥ ጎርናና ድምጽን ወይንም የቀጠነ ድምጽን ለመምረጥ ያገለግላል። ቅጥልጥል አልሲ ዑደት ይህን ዑደት የሚገዛው የለውጥ እኩልዮሽ ከየኪርኮች ቮልቴጅ ህግ በመነሳት ማግኘት ይቻላል። ይሄውም እያንዳንዳቸውን ቮልቴጆች ተክተን ስናስቀምጣቸውና፣ አልፎም ስናወዳድራቸው የሚከተለውን እኩልዮሽ ይሰጡናል፦ ይህን እንግዲህ ከሁለተኛ ደረጃ የውድድር እኩልዮሽ ጋር ተመሳሳይነት አለው። ስለሆነም ከሁለተኛ ደርጃ ውድድር እኩልዮሽ አጠቃላይ ጠባያዊ ቀመር ጋር እንዲህ ማመሳስል ይቻላል፦ እዚህ ላይ እና በማዕዘናዊ ድግግሞሽ መስፈርት ነው የተመጡት። ኔፐር ድግግሞሽ ተብሎ ሲታወቅ የሚለካውም በዑደቱ ውስጥ የሚፈጠረው ዥዋዥዌ የሚቀንስበትን መጠን ነው። በሌላ ጠራር ዲኬይ ፍሪኩዌንሲም ይባላል። በአንጻሩ ያልተጫነ አብሮ የመክነፍ ድግግም (አንጉላር ሬዞናንስ ፍሪኮንሲ) ይባላል። የሚለካውም፣ በዑደቱ ውስጥ ሬዚዝተር (እንቅፋት) ባይኖር ዑደቱ የሚጫወተን የተፈጥሮ ዥዋዥዌ መጠን ነው። አንድ ሰው የራዲዮ ጣቢያ ሲፈልግ፣ ይህን ፍሪኮንሲ በመቀያየር ራዲዮው ከራዲዮ ጣቢያ ጋር አብሮ እንዲከንፍ በማድረግ ነው። ለተቀጣጣል አልሲ ዑደት፣ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት ዕኩልዮሾች በማመሳሰል፣ የመበስበስ (ኔፐር) ድግግሞሹ መጠን እንዲህ ይቀመራል፦ እና ከፍተኛ አልፋ ያለው ዑደት በቶሎ ይሞታል፣በአንጻሩ ዝቅተኛ አልፋ ያለው ለብዙ ጊዜ ዥዋዥዌ ይጫዎታል። ሌላው ጠቃሚ ቀመር ፋክተር ሲሰኝ ከላይ እንደተገኙት ቀመሮች ከአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ የውድድር እኩልዮሽ ይመነጫል። ኪው ፋክተር ኪው ፋክተር ወይንም ኳሊቲ ፋክተር፣ አብረው የሚከንፉ ነገሮችን ለመለካትና ለማወዳደር በጣም ጠቃሚ የሆነ ስሌት ነው። በሚገርም ሁኔታም ብዙ ትርጓሜ አለው፣ እንዲሁም በብዙ አይነት መንገድ ሊቀመር ይችላል። ኪው ፋክተር፣ በአንድ ዑደት ውስጥ የሚገኝ የተጠራቀመ ከፍተኛ አቅም ሲካፈል በአብሮ መክነፍ ጊዜ ለሚጠፋው የእያንዳንዱ ድግግም አቅም ጋር እኩል ነው። ስለሆነም ትልቅ ኪው ያላቸው ዑደቶች በቶሎ የማይረግቡ ዥዋዥዎች ሲሆኑ፣ ትንሽ ኪው ያላቸው ደግሞ የረገቡና አቅማቸውን ይሚያባክኑ ናችው። ኪው ፋክተር፡ እንዲሁ ከላይ ከተሰጠው የውድድር እኩልዮሽ አንጻር እንዲህ ሊሰላ ይችላል፦ ትርጓሜውም፣ የአንድ ዑደት አብሮ የመክነፍ ድግግም ለዥዋዥዌ የመበስበስ ፍጥነት ሲካፈል ማለት ነው። ስለሆነም ትልቅ ሲሆን (>0.5) ዑደቱ ዥዋዥዌ ያካሂዳል። ትንሽ ሲሆን (<0.5) ደግሞ በቶሎ ይከስማል። ስለዚህ ዑደቱ ረግቧል ይባላል። በመሃል (=0.5) ሲሆን አንድ ጊዜ ዥው ይልና ይከስማል። ኪው ፋክተር ሌላም ትርጓሜ አለው፣ ይሄውም ከባንድ ስፋት ጋር ይገናኛል፦ አንስተኛ ያላቸው ዑደቶች ሰፊ ባንድ ሲኖራቸው፣ ትልቅ ያላቸው ባንጻሩ ባንዳቸው ጠባብ ነው። ስለሆነም ኪው ፋክተር የአንድ ኤሌክትሮኒክስ የመምረጥ ብቃቱ ጋር ቀጥተኛ ዝምድና አለው። በሌላ ጎን፣ አንድ ያልረገበ ዑደት፣ ዥዋዥዌ ሲጫዎት ከከፍተኛ መጠኑ እስከ 4% ድረስ የሚርገበገብበትን ብዛት ይለካል። በሌላ አነጋግር ከደወል ፍሪኮንሲ ጋር ይገናኛል ማለት ነው። ከላይ የተቀመጡትን ቀመሮች በመጠቀም የባንድ ስፋት እንዲህ ይሰላል የአልሲ ዑደት አላፊ ውጤት የአልሲ ዑደት አጠቃላይ አላፊ ባህርይ ከሚከተለው የውድድር እኩልዮሽ ይፈልቃል፡ የዚህ ኳድራቲክ እኩልዮሽ ሲፈታ የሚከተሉትን ዋጋዎች ይሰጣል፦ ከዚህ ተነስተን፣ የኡደቱን አጠቃላይ አላፊ ጠባይ በሚከተለው እኩልዮሽ መፍታት እንችላለን፡ ይህ እኩልዮሽ እንደ አልፋ (የመዳከም ፍጥነት) እና እንደ ኦሜጋ (የአብሮ መክነፍ ፍጥነት) ዋጋ 3 የተለያዩ ውጤቶችን ይሰጠናል። እነርሱም፣ በጣም የረገበ፣ መካከል የረገበ፣ እና በትንሹ የረገበ ናቸው። በጣም የረገበ ውጤት በጣም የረገበ ውጤት እምንለው የዑደቱ አላፊ የኤሌክትሪክ ጅረት ዥዋዥዌ ሳይጫወት የሆነ ዋጋ ላይ ከደረሰ በኋላ በዚያ ሲረጋ ነው። ይህን ለማድረግ ከሚከተሉት አንዱ ዕውነት መሆን ግድ ነው። በትንሹ የረገበ ውጤት በትንሹ የረገበ ውጤት እምንለው የዑደቱ አላፊ የኤሌክትሪክ ጅረት ጊዜ ዥዋዥዌ ከተጫወተ በኋላ ወደ አንድ ዋጋ እየረጋ ሲሄድ ነው። ይህን ለማድረግ ከሚከተሉት አንዱ ዕውነት መሆን ግድ ነው። ከላይ የተጠቀሰው የኤሌክትሪክ ጅረት ቀመር በትሪጎኖሜትሪ ህግጋት ሲሰላ የሚከተለውን የተጨመቀ ቀመር ይሰጠናል፦ ይህ ቀመር እሚያሳየው በትንሹ የረገበ ዑደት፣ እየተዳከመ የሚሄድ ጅዋጅዌ እንደሚጫዎት ነው። የተዳከመው ዥዋዥዌ ድግግሞሽ እንዲህ ይሰላል ነው። የዥዋዥዌው መጠን የሚደክምበት ፍጥነት ሲሆን በ የተቀመረው ንሴት አጠቃላይ ዥዋዥዌው የሚከናወንብበትን ኤንቨሎፕ ያሰላል። የድግግሞሽ መጠን ቀመር ከአልፋና ከኦሜጋ-ኦ እንዲህ ይሰላል ይሄ እንግዲህ የረገበው ዑደት አብሮ-የመክነፍ ድግግም ይባላል። ወይንም የረገበ ዑደት ተፈጥሯዊ ድግግም ይባላል። ከውጭ ሆኖ ይህን ዑደት እሚገፋ ኅይል ከሌለ ዑደቱ የሚርገበገብበት ፍሪኮንሲ መጠን ነው። በአንጻሩ የአብሮ መክነፍ ድግግም (ያልረገበ ድግግም), ከዚህ ይለያል። በመጀመሪያ ደረጃ አልሲ ዑደቱ ምንም ሬዚስተር ባይኖረው የሚርገበገብበት ድግግም ሲሆን፣ ኋላ ደግሞ፣ ምንም እንኳ ዑደቱ ውስጥ ሬዚስተር ቢገባም፣ አጠቃላይ ዑደቱን ከውጭ ሆኖ አብሮ ለማክነፍ የሚያገለግል ድግግም ነው። ማለት አንድ የተሰጠን አልሲ ዑደት ከዉጭ በሚፈልቅ ቮልቴጅ ለማክነፍ ቢፈለግ የውጭው ኃይል በ ፍሪኮንሲ ነው መርገብገብ ያለበት። መካከል የረገበ ውጤት መካከል የረገበ ውጤት እምንለው የዑደቱ አላፊ የኤሌክትሪክ ጅረት ምንም ዥዋዥዌ ሳይጭወት ቶሎ ተዳክሞ የረጋ ዋጋ የሚደርስበትን ሁኔታ ነው። ይህን ለማድረግ ከሚከተሉት አንዱ ዕውነት መሆን ግድ ነው። ትይዩ አልሲ ዑደት ተጨማሪ ንባቦች (እንግሊዝኛ) 2005 1-55860-735-8. 2002 90-5809-245-3. 2006 7-302-13021-3. 2004 0-8493-2087-9. 2008 0-13-198925-1. ኤሌክትሪክ
12795
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%88%83%E1%8A%95
ብርሃን
ብርሃን ነገሮች በዓይን እንዲታዩ የሚያደርግ የተፈጥሮ ሞገድ ነው። የብርሃን ሞገድ ከኤሌክትሪክ እና ከመግነጢስ የተሰራ ስለሆነ ሞገዱ የ ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ይባላል። ይሁንና፣ የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ብርሃንን ብቻ ሳይሆን የብርሃንን ታናናሽና ታላላቅ ወንድሞች ሳይቀር ያፈልቃል። ከብርሃን ታናናሽ ወንድሞች፣ ሬዲዮ፣ ራዳር እና ታህታይ ቀይ ይገኙበታል። ታላላቅ ወንድሞቹ ቢባል፣ ላዕላይ ወይን ጠጅ፣ ኤክስ ሬይ፣ ጋማ ጨረር ይገኛሉ። እነዚህ የብርሃን ወንድሞች በተፈጥሯቸው ከብርሃን ጋር አንድ ቢሆኑም የሰው ዓይን ሊያያቸው ስለማይችል ብርሃን አይባሉም። ሆኖም ግን አንድ አንድ እንስሳት እነዚህን ሞገዶች መመልከት ይችላላሉ። ለምሳሌ ታህታይ ቀይ የሚባለው የብርሃን ታናሽ ወንድም፣ ለሰዎች እንደ ሙቀት ሆኖ ይሰማል። ለምሳሌ የፀሐይ መሞቅ ከምትተፋው የታህታይ ቀይ ጨረራ ይመነጫል። በበረሃ የሚንከላዎሱ እባቦች ይህን ሞገድ በአይናቸው መመልከት ስለሚችሉ፣ ሙቀት ያለውን ማንኛውንም ነገር በጭለማ ሳይቀር ማየት ይችላሉ። ንቦች በተቃራኒ፣ የሰው ልጅ እማያየውን ላዕላይ ወይን ጠጅ ሞገድ በዓይናቸው ማየት ስለሚችሉ፣ አበቦች ለንቦች ከሰው ልጅ የተለየ መልክና መልዕክት ያስተላልፋሉ። ብርሃን ሞገድ ብቻ ሳይሆን፣ እንደሌሎቹ ጨረራዎች የሞገድና እኑስ ሁለትዮሽተፈጥሮን አዋህዶ የያዘ ነው። ስለዚህና ስለመሳሰሉት መሰረታዊ የብርሃን ባህርያት የሚያጠናው የዕውቀት ዘርፍ ሥነ ብርሃን (ኦፕቲክስ) በመባል ይታወቃል። የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት (ፊዚክስ) ምርምር ዋና ክፍል ነው። የብርሃን ጸባዮች፣ ምንጮችና ፋይዳዎች የብርሃን ፍጥነት የብርሃን ፍጥነት ብርሃን በመቅጽበት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ አይጓዝም። ይልቁኑ ብርሃን የሚጓዘው በከፍተኛ፣ ነገር ግን ውሱን ፍጥነት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የብርሃንን ፍጥነት በተሳካ ሁኔታ የለካው ሮመር የተባለ የዴንማርክ ሰው ሲሆን ይህም በ1676 ዓ.ም. ነበር። ከርሱ በኋላ የተነሱ ሳይንቲስቶች፣ በተሻሻለ መንገድ ፍጥነቱን ለክተዋል። በአሁኑ ዘመን የሚሰራበት የብርሃን የኦና ውስጥ ፍጥነት 299,792,458 ሜትር በሰከንድ 2000, 15, 3, በሌላ አነጋገር አንድ የብርሃን ጨረር በያንዳንዷ ሰከንድ ወደ ሶስት መቶ ሚሊዮን ሜትር የሚጠጋ ርቀት ይጓዛል። ይህ የጠፈር ውስጥ ፍጥነት በ ምልከት ሲወከል፣ ለተፈጥሮ ህግጋት ጥናት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው የተፈጥሮ ቋሚ ቁጥር ነው። ብርሃን፣ ከኦና ወጥቶ በቁስ አካል ውስጥ (ለምሳሌ በአየር ውስጥ) ሲጓዝ ፍጥነቱ ይቀንሳል። የዚህ ቀስተኛ ፍጥነት መጠን በቁሱ ዳይኤሌክትሪክ ባህርይና በብርሃኑ አቅም ይወሰናል። ብርሃን ኦና ውስጥ ያለው ፍጥነት በአንድ ቁስ ውስጥ ላለው ፍጥነቱ ሲካፈል ውጤቱ የዚያ ቁስ የስብራት ውድር ይባላል። በሒሳብ ቋንቋ ሲጻፍ፦ እዚህ ላይ የቁሱ የስብራት ውድር ሲሆን፣ ደግሞ በቁሱ ውስጥ ያለው የብርሃን ፍጥነት ነው። የብርሃን የጉዞ አቅጣጫ መቀየር ብርሃን በቀጥተኛ መንገድ እንደሚጓዝ ከጥንት ጀምሮ የታዎቀ ሃቅ ነው። ደግሞም የብርሃን ቀጥተኛ ጉዞ አልፎ አልፎ ሊስተጓጎል እንደሚችል ሌላው የሚታዎቅ ሃቅ ነው። ብርሃን የሚጓዝበትን አቅጣጫ በሦስት መንገዶች ይቀይራል፦ እነርሱም በመንጸባረቅ፣ በመሰበር እና በመወላገድ ናቸው። መንጸባረቅ (ሪፍሌክሽን) የብርሃን ነጸብራቅ ብርሃን አንድ ቁስን ሲመታ የቁሱ አተሞች የተወሰነውን ብርሃን ውጠው የተቀረውን መልሰው በተለያየ አቅጣጫ ወደ ውጭ ይረጫሉ። ይህ ጉዳይ የብርሃን መበተን ይሰኛል። ቁስ ነገሮች የመታየታቸው ምስጢር ከዚህ የብርሃናዊ መፍካት አንጻር ነው። ከነዚህ ቁሶች በተለየ መልኩ፣ እንደ መስታውት ያሉ፣ ገጽታቸው ልስልስ የሆኑ አካላት፣ ብርሃን ከገጽታቸው ሲንጸባረቅ በሚነሳው የሞገድ መጠላለፍ ምክንያት አብዛኛው የሚፈካው ጨረራ እርስ በርሱ ይጣፋል። በዚህ መጠፋፋት ወቅት ጸንቶ የሚቀረው፣ ብርሃኑ በአረፈበት ማዕዘን ትክክል ተገልብጦ ያለው የሞገድ ስብስብ ብቻ ነው፣ ይኸውም የብርሃን ነፀብራቅ ይሰኛል። በሌላ አባባል፣ ብርሃን አንድ ገጽታ ላይ ሲያርፍ እና ሲንጸባረቅ በነጸብራቁና በመጤው ጨረር መካከል ያለው ማዕዘን ከሁለት እኩል ቦታ ይከፈላል፣ የሚያካፍላቸውም የገጽታው ቀጤ ነክ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በብርሃን ስብረት አማካይነት ብርሃን ሊንጸባረቅ ይችላል። ይህ የሚሆነው አንድ የብርሃን ጨረር ያለበትን አካል ለማምለጥ ያለው ፍጥነት በቂ ሆኖ ሳይገኝ ሲቀር ነው። ጨረሩ የቁሱን ድንበር ከተወሰነ ማዕዘን በላይ በሆነ አቅጣጫ ሲመታ በጣም ከመሰበሩ የተነሳ ተመልሶ ወደ ቁሱ ይንጸባረቃል። ይህም አጠቃላይ ውስጣዊ ነጸብራቅ እሚባለው ነው። የአልማዝ ፈርጦች መጭለቅለቅ ከዚህ የተነሳ ነው። ብርሃን በዘፈቀደ ሲንጸባረቅ ተበተነይባላል። እንደ መስታዎት ነጸብራቅ አቅጣጫን የተከተለ ሳይሆን እንደ ግድግዳ መፍካት ወይንም እንደብርሃን ጸዳል በሚተን ውሃ ውስጥ መፍካት ነው። የሰማይ ሰማያዊ ቀለም የሚመነጨው ብርሃን በከባቢ አየር ስለሚበተን ነው። የደመና እና ወተት ነጭነት እንዲሁ ብርሃን በውሃ እና በካልሲየም ስለተበተነ ነው። ስብረት (ሬፍራክሽን) የብርሃን ስብረት የብርሃን ስብረት እምንለው የብርሃን ጨረር ካንድ ብርሃን አሳላፊ ወደ ሌላ አሳላፊ አካል ሲጓዝ የሚገጥመውን ፈጣን የአቅጣጫ መቀየር ሁኔታ ነው። ይህ የመጉበጥ ሁናቴ በስኔል ህግ እንዲህ ሲባል በሒሳብ ቋንቋ ይገለጻል፦ እዚህ ላይ በብርሃኑ ጨረርና በአንደኛው ብርሃን አስተላላፊ አካል ቀጤ ነክ መካከል ያለውን ማዕዘን ሲዎክል ደግሞ በሁለተኛው አካል ቀጤ ነክና በብርሃኑ ጨረር መካከል ያለውን ማዕዘን ይወክላል። 1 እና 2 የብርሃን አስተላላፊዎቹ የስብራት ውድር ናቸው፣ 1 ለጠፈር ሲሆን 1 ደግሞ ለማናቸው ብርሃን አስተላላፊና በከፊል አስተላላፊ ቁስ አካሎች የሚሆን ነው። አንድ ጨረር ከአንድ አካል ወጥቶ ወደሌላ አካል ሲገባ የጨረሩ የሞገድ ርዝመትና ፍጥነት ይቀየራል። ሆኖም ግን ድግግሞሹ ባለበት ይጸናል። ያ ጨረር ለሚገባበት አካል ገላ ቀጤ ነክ ካልሆነ የሞገድ ርዝመቱ ወይም ፍጥነቱ መቀየር ብርሃኑ እንዲጎብጥ ወይም አቅጣጭ እንዲቀይር ያደርገዋል። አንድ መኪና አንድ ጎን ጎማዎቹ ቀጥ ቢሉና ሌሎች ጎን ጎማዎቹ ቢሽከረከሩ ሳይወድ በግድ እንደሚታጠፍ ነው። የብርሃን አቅጣጫ መቀየር የብርሃን ስብረት በመባል ይታወቃል። የተለያዩ የብርሃን ቀለማት እኩል አይሰበሩም። ቀይ ብርሃን ቀስ ብሎ ሲሰበር ወይን ጸጅ ደግሞ በከፍተኛ ሁናቴ ይሰበራል። ስለሆነም ከሁሉም ቀለም የተሰራ ነጭ ብርሃን በብርሃን ሰባሪ አካላት፣ ለምሳሌ ፕሪዝም ወይንም የእስክርፒቶ ቀፎ ውስጥ ሲያልፍ ይበተንና ኅብረ ቀለማትን ይፈጥራል። የቀስተ ደመና መፈጠር ብርሃን በከባቢ አየር ባሉ የውሃ ሞለኪሎች መሰበር ምክንያት ነው። መወላገድ (ዲፍራክሽን) የብርሃን መወላገድ ሞገዶች እንቅፋት ወይም ጠባብ ክፍተት ሲያጋጥማቸው በእንቅፋቱ ዙርያ የመጠምዘም ባህርይ ያሳያሉ። ለምሳሌ ከአንድ ክፍል ሆኖ ከሌላ ክፍል የሚወራን ወሬ ማዳመጥ መቻሉ የድምጽ ሞገድ በግድግዳወችና በሮች ዙሪያ መጠማዘዝ በመቻሉ ነው። ከዚህ በተጻራሪ የዕለት ተለት ተመክሯችን እንደሚያረጋግጥልን ብርሃን በቀጥተኛ መንገድ እንደሚጓዝ ነው፣ ሰሆነም አንድ ክፍል ሆነን ሌላ ክፍል የሚሆነውን ማየት አንችልም። ነገር ግን በጥንቃቄ ስናስተውል ይሄ ሙሉ በሙሉ እውነት ሆኖ አናገኘውም። ለምሳሌ በጣም ስል የሆኑ ጠርዞች የሚያሳርፉትን ጥላ በጥንቃቄ ስንመረምር አንድ ወጥ ከመሆን ይልቅ በፈርጅ በፈርጁ የደመቀና የጨለመ ሆኖ እናገኛለን። ብርሃን በቀጥታ እሚጓዝ ከሆነ ለምን ይሄ ሆነ? አንድ ክፍል ሆነን ሌላ ክፍል የሚሆነውን የማናይበት ምክንያት የብርሃን ሞገድ ርዝመት ከድምጽ ሞገድ ርዝመት በጣም ስለሚያን የድምጽን ያህል መጠማዘዝ ስለማይችል ነው። ብርሃን ሁል ጊዜ በቀጥታ መንገድ አይጓዝም። ይልቁኑ የብርሃን ጨረር እንቅፋት ሲያጋጥመው ወይም ጠባብ ክፍተት ውስጥ ሲገባ ይጎብጣል። ይህ ኩነት የብርሃን መወላገድ ይሰኛል። በጠባብ ቀዳዳዎች አጮልቀን ስንመለከት ነገሮች ተንጋደው የሚታዩት ስለዚህ ምክንያት ነው። ከብርሃን መንጸባረቅና መሰበር ውጭ የብርሃንን አቅጣጫ የሚቀይረው ይሄ መወላገድ ነው። መጠላለፍ (ኢንተርፌረንስ) የብርሃን መጠላለፍ የብርሃን መጠላለፍ እንደማንኛውም ሞገድ መጠላለፍ ነው እንጂ ልዩ አይደለም። ለምሳሌ አንድ የረጋ ውሃ ላይ ሁለት ልጆች የተለያየ ቦታ ላይ ጠጠር ቢጥሉ፣ ከጠጠሮቹ እየከበቡ የሚሰፉት ሞገዶች የሚሰሩት መጠላለፍ አንድ ቦታ በሃይል እንዲጎብጡ፣ ሌላ ቦታ እንዲያንሱ እያደረገ ለአይን የሚስብ የመጠላለፍ ቅርጾች በውሃው ገጽታ ላይ ይሰራሉ። ብርሃንም እንዲህ አይነት የመጠላለፍ ባህርይ ያሳያል። ጉዳዩን በቀላሉ ለማየት የያንግን ሙከራ ማካሄድ ይረዳል። የያንግ ሙከራ ምንድን ነው፣ አንድ አይነት ቀለም ያለው ብርሃን አንድ በቀጭኑ የተሸነተረ ካርድ ላይ ይበራል። ከዚህ ሽንትር ካርድ ብርሃኑ እየተወላገደ ይሄድና ሌላ ሁለት ቦታ ላይ የተሸነተረ ካርድ ላይ እንዲያርፍ ይደረጋል። ከኒህ ሁለት ሽንትሮች ያመለጠው ሁለት ጊዜ የተወላገደ ብርሃን ንጹህ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ ይደረጋል። የብርሃንን መጠላለፍ በደንብ በሚያሳይ መልኩ ይህ የሚያርፈው ብርሃን ብዙ ደማቅና ጨለማ ሸንተረሮች በግድግዳው ላይ ይፈጥራል። ከዚህ በተረፈ የብርሃን መጠላለፍ በተፈጥሮም እንዳለ ለማስተዋል ይቻልል። ለምሳሌ ሥሥ የዘይት ወይም ቤንዚን እድፍ በውሃ ላይ ተንጣሎ ሲገኝ የሚፈጥረው ኅብረ ቀለም ከብርሃን መጠላለፍ የሚመጣ ነው። የሲዲ ገጽታም ኅብረ ቀለም ማሳየቱ ብርሃን መጠላለፍ የሚመነጭ ነው። መዋልት (ፖላራይዜሽን) የብርሃን መዋልት የብርሃን ሞገድ ልከ አንድን ገመደ ወደላይ ወደታች ስናደርግ እንደምናገኘው ሞገድ ነው። ማለት የሞገዱ ጉዞ ወደፊት ሲሆን ሞገዱ የሚርገበገበው ወደ ላይ-ወደ ታች ነው። ሞገዱ የሚርገበገብበት አቅጣጫ የሞገዱ ዋልታ ይሰኛል። የሞገዱ የጉዞ አቅጣጫና የሞገዱ ዋልታ አንድ ወጥ አይደሉም። ይልቁኑ ሞገዱ በአንድ አቅጣጫ እየተጓዘ እያለ የሞገዱ ዋልታ ሊቀየር ይችላል። ለምሳሌ የአንድ ሞገድ ዋልታ ወደ ላይ ወደታች ከሆነ፣ ይህን ቀይሮ ወ ጎንና ወደ ጎን ሊርገበገብ ይችላል። ይህ የብርሃን ባህርይ መዋልት ይባላል። ጉዳዩን በገሃዱ አለም ማየት ይቻላል። ብዙ የጸሐይ መነጽሮች የሚሰሩት ብርሃንን ዋልታ ከሚለዩ ንጥር ነገሮች ነው። ስለሆነም የመነጽሮቹ መስታወቶች የሚያሳልፉት ከነርሱ ዋልታ ጋር የሚስማማውን ክፍል ብቻ ነው። ስለዚህ ሁለት የጸሓይ መነጽሮችን በተለያየ ማዕዘን በማስቀመጥ ከአንዱ ያለፈውን የዋለታ ብርሃን በሌላው መነጽር እንደገና በማጥራት የተለያየ የብርሃን መጠን እንዲያልፍ ማድረግ ይቻላል። በርግጥ ሁለቱ መነጽሮች ደርቦ በማስቀመጥና አንዱን ከሌላው አንጻር በማዞር ከከፍተኛ ብርሃን እስከ ሙሉ በሙሉ ጨለማ እንዲያስተላልፉ ማድረግ ይቻላል። የብርሃን ግፊት ብርሃን በተጨባጭ ግፊት ማድረግ ይችላል። ይህን የሚያደርገው ፎቶኖች የተሰኙት የብርሃን እኑሶች የቁስን ገጽታ በመደብደብ ግፊታቸውን በማሳረፍ ነው። የብርሃን ግፊት እሚለካው የአንድን ብርሃን ጨረር ሃይል ለብርሃን ፍጥነት በማካፈል ነው። የብርሃን ፍጥነት እጅግ ግዙፍ ስለሆነ ክብርሃን የሚገኘው ግፊት በጣም አንስተኛ ነው። ስለዚህ አንዲት ሳንቲም በብርሃን ለማንሳት 30 ቢሊዮን የ1 ዋት ሌዘር ፖይነተሮች በአንድ ላይ መሳተፍ አለባቸው፡፡ የሆኖ ሆኖ የብርሃን ግፊት በናኖ ሜትር ደረጃ ባለው አንስተኛው አለም ውስጥ የማይናቅ ሚና ይቻወታል። ስለሆነም ጥቃቅን የናኖ ሜትር ማብሪያ ማጥፊያወችን በብርሃን ግፊት ለመቆጣጠር ጥናት ይካሄዳል። ብርሃንና የኬሚካል ፋይዳው ፎቶኬሚስትሪ አንድ አንድ ቅመሞች (ኬሚካልስ) ብርሃን ሲያርፍባቸው ጠባያቸው ይቀየራል። ግማሾቹ የብርሃኑን አቅም ገንዘብ በማድረግ ከፍተኛ አቅም ገዝተው ከሌላ ቁስ ጋር የኬሚካል ግንኙነት ያደርጋሉ፣ ገሚሶቹ ያላቸውን ግንኙነት አቋርጠው ለብቻቸው ይሆናሉ። የተክሎች ምግብ ዝግጅት (ፎቶ ሲንቴሲስ) ከዚህ ወገን ነው። እፅዋት የተለያዩ የስኳር አይነቶች የሚሰሩት ከውሃ፣ የተቃጠለ አየርና ከብርሃን ነው። የሰው ልጅ ቆዳ እንዲሁ ቫይታሚን ዲ የሚፈጥረው የብርሃንን አቅም በመጠቀም ነው። ዓይንም ብርሃንን የሚመለከተው ከአይን ውስጥ ያሉ ኬሚካሎችን በብርሃን የመቀየር ጠባይ በመጠቀም ነው። የፎቶ ፊልም እንዲሁ ከብርና-ናይትሮጅን ኬሚካል የተሰራ ሲሆን ብርሃን ሲያርፍበት ጠባዩን ስለሚቀያይር ፎቶ ለማንሳት ያስችላል። የብርሃን ምንጮች ብዙ የብርሃን ምንጮች በአለም ላይ ይገኛሉ። ብዙ ጊዜ የብርሃን ምንጮች በመጋል የፋሙ ነገሮች ናቸው። ማናቸውም ሙቀት ያላቸው ነገሮች የጥቁር አካል ጨረራ ያመነጫል። ለምሳሌ የፀሐይ አካል ገጽታ ሙቀት መጠን 6,000 ኬልቪን ሲደሰርስ በዚህ ምክንያት ከገጽታው የሚመነጨው የፀሐይ ጨረራ ለአይን የሚታይ ብርሃንንም ይጨምራል። ብስሌት እንደተደረሰበት ከፀሐይ ጨራራ ወደ 40% ይሚጠጋው በአይን የሚታይ ብርሃን ነው። በዚህ ትይዩ የቤት አምፑል ከሚወስደው የኤሌክትሪክ አቅም በብርሃን መልኩ የሚረጨው 10% ብቻ ነው፣ የተቀረውን ወደ ግለት ቀይሮ በታህታይ ቀይ ጨረራ ይረጫል። የሚግም የፋመ ብረትም ብርሃን ክሚያመነጩ ወገን ነው። መለስተኛ ሙቀት ያላቸው ነገሮች፣ ለምሳሌ የሰው ልጅ፣ ለአይን የማይታይ የጥቁር አካል ጨረራ በአካባቢው ይረጫል፣ ሆኖም ይሄ በታህታይ ቀይ ደረጃ ስለሆነ ለአይን አይታይም። ሙቀቱ እየጨመረ ሲሄድ ከታህታይ ቀይ የሞገድ ርዘመቱ ቀንሶ ወደ ቀይ ቀለም እያደላ ይሄዳል። የጋመው ቀይ የበለጠ ሲግል ወደ ነጭ ቀለም ይቀየርና ሙቀቱ እየባሰ ሲሄድ ወደ በጣም አጭር የሞገድ እርዝመተ እያደላ ይሄዳል፣ ይሄውም ወደ ሰማያዊ ቀለም መሆኑ ነው። ከዚህ ይብስ ከጋለ አንድኛውን ላይን ይሰወርና የላዕላይ ወይነ ጸጅ ጨረር ባህሪን ይይዛል። እኒህን ቀለማት በሚንቀለቀል እሳት ውስጥ የሚፍሙ ብረታ ብርቶችም ሊስተዋሉ ይችላሉ። አተሞች ብርሃንን አመንጭተው መርጨት ወይም ውጠው ማስቀረት ይችላሉ። ይህን እሚያረጉት እንዲሁ በደፈናው ሳይሆን ለጠባያቸው በሚስማማ አቅም ውስጥ ያለን ብርሃን ነው። ይህ ሲሆን አተሞቹ የመርጨት መስመር በአተሞቹ ብትን ላይ እንዲፈጥር ያደርጋል። ሁለት አይነት የኤሌክትሮማግኔቲክ ምርጨት አለ። ፩ኛው ድንገተኛ መርጨት ሲባል ይህ አይነት ብርሃን በብርሃን ረጪ ዳዮድ፣ ጋዝ ርጭት፣ ኒዖን አምፑል፣ ሜርኩሪ አምፑልና በ እሳትነበልባል ለሚመነጨው ብርሃን ተጠያቂ ነው። ፪ኛው የተነሳሳ መርጨት ሲባል በሌዘር እና ሜዘር ለሚመነጨው ብርሃን ተጠያቂ ነው። የኤሌክትሪክ ቻርጅ ተሸካሚ አካላት (ለምሳሌ ኤሌክትሮን የሚጓዙበት ፍጥነት ሲቀንስ ጨረራ ይረጫሉ፣ በዚህ አኳኋን የምታይ ብርሃን ሊፈጥሩ ይችላሉ፡ ሳይክሎትሮን ጨራራ፣ ሲንክሮትሮን ጨራራ እና ብሬምስትራንግ ጨራራ የዚህ ምሳሌወች ናቸው። አንድ አንድ እኑሶች (ፓርቲክልስ) በቁስ አካል ውስጥ ከብርሃን ፍጥነት በላይ ከተጓዙ ቼርንኮቭ ጨረራ የተሰኘን በአይን ሊታይ የሚጭል ጨረር ይፈጥራሉ። አንድ አንድ ቅመሞች (ኬሚካሎች) ብርሃን የመፍጠር ችሎታ አላቸው። ህይወት ባላቸው ነገሮች፣ በተለይ በአንድ አንድ ትንኞች፣ ዘንድ ብልጭ-ድርግም የሚል ብርሃን እንዲያመነጩ የሚያግዛቸው ይሄው ነው። አንድ አንድ ቁስ አካላት ከፍተኛ አቅም ባለው ጨረራ ሲደበደቡ የመጋምና የመፍካት ሁኔታ ያሳያሉ። ይህ ጉዳይ ፍሎሮሰንስ ይሰኛል፣ የሸምበቆ መብራት የዚህ አይነት ነው። ሌሎች ደግሞ ቶሎ ከመፍካት ይልቅ ቀስ ብለው ብርሃን መርጨት ያደርጋሉ፣ እኒህ ፎስፎረሰንስ ይሰኛል። ፎስፎረሰንስ ቁሶች በጥቃቅን የአተም ንዑስ አካላት ሲደበደብ እንዲሁ ብርሃን ይሰጣል። በዚህ መንገድ ብርሃን ከሚሰጡት ውገን የቴሌቪዥን፣ ኮምፒውተር እና ካቶድ ጨረር ቱቦ ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች የብርሃን ማመንጫ መንገዶች አሉ ግን ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋናወቹ ናቸው። ለመሆኑ ብርሃን ምንድን ነው?? ስለብርሃን የተሰነዘሩ ኅልዮቶች በየዘመኑ ጥንታዊት ሕንድ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ6-5ኛ ክፍለ ዝመን የነበሩ ህንዶች ስለብርሃን ብዙ ተፈላስፈዋል። አንድ አንዶቹ ብርሃን ያልተቆራረጠ ነገር ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ የተቆራረጠ እኑስ ነገር ሲሆን ከከፍተኛ ፍጥነት ካላቸው የእሳት እኑሶች የሚፈጠር ነው ብለው አስፍረዋል። ሌሎች በተራቸው ብርሃን የአቅም አይነት ነው ሲሉ የአሁኑን አይነት የፎቶን ግንዛቤ አስፍረዋል። ጥንታዊት ግሪክ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ5ኛው ክፍለ ዝመን ይኖር የነበር ኢምፐዶክልስ እንዳስተማረ የሰው ልጅ አይን ከአራቱ ንጥረ ነገሮች (እሳት፣ አየር፣ መሬትና ውሃ) የተሰራ ሲሆን ጣዖቷ አፍሮዳይት የሰውን ልጅ እሳት በአይኑ ውስጥ እንዳቀጣጠለች፣ ስለዚህም የሰው ልጅ አይን የብርሃን ምንጭ እንደንበር አስተምሯል። ሆኖም የሰው ልጅ ማታ ላይ ስለማያይ ይህ አስተሳሰቡ እንደማያዋጣው በመገንዘብ በርግጥም የሰው ልጅ እሚያየው ከራሱ በሚያመነጨው ብርሃንና ከጸሃይ በሚያገኘው ጨረር ግንኙነት ነው ለማለት ችሏል። ዩክሊድ በበኩሉ የኢምፐዶክልስን ኅልዮት ጥያቄ ውስጥ በመጣል ብርሃን ከአይን ይመነጫል የሚለውን ሃሳብ አልተቀበለም። በተጨማሪ ብርሃን በቀጥተኛ መስመር እንደሚጓዝና ከገጽታ ላይ ሲንጸባረቅ የሚከተለውን የጂዎሜትሪ ህግ አስቀምጧል። ሉክሪተስ በበኩሉ ብርሃን የእኑስ አካላት ውጤት ነው የሚለውን ሃሳብ አስተጋብቷል። ቶሎሚ ደግሞ ስለ ብርሃን መሳበር ጽፏል። አካላዊ ኅልዮት (ዘመናዊ) ከጥንቶቹ በኋላ የአረቡ አል ሃዘን፣ ፈረንሳዩ ደካርት እንዲሁም እንግሊዙ ቤከን እርስ በርሳቸው በሂደት እየተተራረሙ የብርሃንን ምንነት ለማወቅ ሞክረዋል። ሆኖም ደካርት የብርሃንን ጸባይ በአካላዊ መንገድ (ያለ መንፈሳዊ መንገድ) ለመግልጽ ስለቻለ የዘመናዊ የብርሃን ትምህርት አባት በመባል ይታወቃል። የዘመናዊው የብርሃን ኅልዮት ከሁለት የብርሃን ተፈጥሮ ደጋፊወች ቅራኔ ያደገ ነው። አንደኛው ወገን ብርሃን እኑስ (ጠጣር፣ ደቂቅ፣ ፓርቲክል) ነው ሲል፣ ሌላኛው ደግሞ ብርሃን ሞገድ (ዌቭ፣ ፈሳሽ ዓይነት፣ የማይቆራረጥ) ነው የሚል ነበር። እኑስ ኅልዮት እኑስ ስንል እዚህ ላይ ደቂቅ ጠጣር አንስተኛ ነገር እንደማለት ነው። ከነደካርት ቀጥሎ ከፍተኛውን እርምጃ ወደፊት የወሰደው ፒር ጋሲንዲ (1592–1655) ብርሃን በጣም ጥቃቅን እኑሶች ክምችት ነው በማለት አስረዳ። ኢሳቅ ኒውተን ገና በወጣትነቱ የጋሲንዲን ጥናት በማንበቡ እርሱም የብራሃንን እኑስነት መሰረት በማድረግ ጥናት አቅርቧል። ለዚህ ምክንያቱን ሲያቀርብ ሞገዶች፣ ለምሳሌ የድምጽ ሞገድ በቀጥታ ከመሄድ ይልቅ በእንቅፋት ዙሪያ መጓዝ ይችላሉ። ነገር ግን ብርሃን በቀጥታ እንጂ እንቅፋትን የመዞር ችሎታ የለውም። ኒውተን የብርሃን ነጸብራቅንና ጥላን በዚሁ ኅልዮቱ ለመግለጽ ችሏል። የብርሃን ስብረትንም በተሳሳተ መልኩ በዚሁ ኅልዮቱ ገልጿል። ኢሳቅ ኒውተን በነበረው የገነነ ክብር ምክንያት 18ኛው ክፍለ ዘመን የርሱን የብርሃን እኑስ ኅልዮት በመከተል ተጠናቀቀ። ይሁንና በ19ኛው ክፍለ ዘመን ይህን አስተሳሰብ የሚቃወሙና የብርሃንን ሞገደኝነት የሚያስተምሩ ጥናቶች መታየት ጀመሩ። ሞገዳዊ ኅልዮት በኒውተን ዘመን የተነሱት ሮበርት ሁክ እና ክርስቲያን ሁይገንስ የብርሃንን ሞገዳዊነት የሚያስረግጡ ጥናቶችን አሳተመው ነበር። ነገር ግን ኒውተን ከነበረው ክብር አኳያ ብዙወች ችላ ብለዋቸው ነበር። የብርሃን ሞገዳዊ ኅልዮት ብርሃን ልክ እንደ ድምፅ እንደሚጠላለፍ የተነበየ ነበር። በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳው ቶማስ ያንግ ይህን ጉዳይ በሙከራ ለማሳየት ቻለ። በተረፈ እንደማንኛውም ተራማጅ ሞገድ እንደሚዋልት በዚህ ወቅት በሙከራ ተረጋገጠ። ያንግ በዚህ ሳይወሰን ብርሃን እንደሚወላገድ በሁለትዮሽ ሽንትር ካርድ ሙከራ ለማሳየት ቻለ። የተለያዩ ቀለማት መፈጠር ምክንያቱ በተለያዩት የብርሃን ሞገዶች ውስጥ ባለ የሞገድ ርዝመት ምክንያት እንደሆነ በጥናቱ አቀረበ። ይህ ሁሉ የብርሃንን ሞገዳዊነት ያጠናከረ ጥናትና የብርሃንን እኑስ አለመሆን ለጊዜው ሳይንቲስቶች ያሳመነ ነበር። ላዮናርድ ኦይለር፣ ኦግስቲን ፍሬስነል፣ ሲሞን ፖይሰን የብርሃንን ሞገድ የሂሳብ ቀመሮች ሊጠረጠር በማይችል ሁኔታ መሰረት ሰጡት። ፍሬስነል በ1821 የብርሃን ዋልታዊነት በሞገድ ኅልዮት ብቻና ብቻ የሚገለጽ እና እንዲሁም ብርሃን ተራማጅ ሞገድ እንጂ ፊት-ኋላ የሚል ሞገድ ቅንብር እንዳልሆነ በሂሳብ ቀመሩ ለማስረገጥ ቻለ። ይህ እንግዲህ የኒውተንን የእኑስ ኅልዮት ጥያቄ ውስጥ የጣለ ሂደት ነበር። እንደ ኒውተን ኅልዮት፣ የብርሃን ጨረር ከቀላል ነገር ወደ ጭፍግ (ዴንስ) ያለ ነገር ሲሻገር በግስበት ምክንያት ፍጥነቱ ይጨምራል። ሆኖም ግን ላዮን ፎካልት በ1850 ባደረገው ጥንቃቄ የተመላበት የፍጥነት ልኬት፣ ብርሃን እንዲያውም ጭፍግ ያለ አካል ውስጥ ሲጓዝ ቀስ እንደሚል አረጋገጠ ይህ እንግዲህ የኒውተን እኑስ ኅልዮት ሙሉ በሙሎ እንዲጣልና የሞገድ ኅልዮቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ያደረገ ሁናቴ ነበር። የሞገድ ኅልዮት በራሱ ድክመት ነበረው። ድምጽ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለመጓዝ በመሃከሉ ሞግዱን ተሸካሚ አካል ያስፈልገዋል። ለምሳሌ አንድ ሰው በጠፈር ውስጥ ቢናገር በሌሎች አይሰማም ምክንያቱም የድምጹን ሞገድ የሚያስተላልፍ አየር የለምና። ልክ እንዲሁ ብርሃንን አስተላላፊ አካል ያስፈልጋል። ነገር ግን ብርሃን በባዶ ጠፈር ውስጥ ከፀሐይ መንጭቶ መሬት ይደርሳል። ስለሆነም የጥንቶቹ ሳይንቲስቶች ጠፈር ውስጥ የሚኖር ኤተር የተባለ በአይን የማይታይ ነገር ሞገዱን እንደሚያስተላልፍ መላ ምት አደርጉ። ኮረንቲና መግነጢስ (ኤሌክትሮማግኔቲክ) ኅልዮት ሚካኤል ፋራዳይ በ1845 ዓ.ም. የብርሃንን ዋልታ በመግነጢስ መቀየር እንደሚቻል አስተዋለ። ይህ እንግዲህ ብርሃን ከኮረንቲና መግነጢስ ጋር ግንኙነት እንዳለው ያሳየ የመጀመሪያው መረጃ ነበር። ይሄው ፋራዳይ ከ2 አመት በኋላ ብርሃን በጣም ከፍተኛ ድግግሞሽ ያለው ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ረብሻ እንደሆነ ጻፈ። በፋራዳይ ስራ ተመስጦ ቀጣዩን ጥናት ያካሄደው ጄምስ ክላርክ ማክስዌውል በ1862 ዓ.ም. ባወጣው ጥናቱ፣ የኤሌክትሮማግኔቲክ ሞገዶች (ማዕበሎች) አንዴ ከተፈጠሩ በኋላ ያለምንም እርዳታ በኅዋ ውስጥ በቋሚ ፍጥነት መጓዝ እንዲችሉ አሳየ። በሂሳብ ቀመሩ እንዳሰላ ይህ የኤሌክትሮመግነጢሳዊ ሞገድ ፍጥነት ሌሎች ሳይንቲስቶች በሙከራ ካገኙት የብርሃን ፍጥነት ጋር አንድ ሆነ። ከዚህ ተነስቶ፣ ማክስዌል፣ ብርሃን የኤሌክትሮማግኔቲክ ሞገድ እንደሆነ አስረዳ። በ1873ዓ.ም. ማክስዌል የብርሃንና የኤሌክትሮማግኔትን ባህርይ እንዲሁም የመግነጢስ መስክንና የኤሌክትሪክ መስክን ጠባይ በሂሳብ ቀመር ግልጽ አድርጎ አስቀመጠ። ሄኔሪክ ኸርዝ በበኩሎ የማክስዌልን ሂሳብ በመጠቀም የራዲዮ ሞገድን ላብሯረተሩ ውስጥ በመፍጠርና በመጥለፍ እንዲሁም ልክ እንደ ብርሃን ሞገዶቹ የመንጸባረቅ፣ መሳበር፣ መወላገድና መጠላለፍ ባህርያትን እንደሚያሳዩ በተጨባጭ በማረጋገጥ የብርሃንን ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ሞገድነት ሙሉ በሙሉ አሳማኝ በሆነ መልኩ አረጋገጠ። በአውሁኑ ወቅት እንደሚታወቀው የኤሌክትሮመግነጢሳዊ ማዕበል ከኤሌክትሪክና መግነጢስመስኮች የተሰራ ሲሆን እኒህ መስኮች እርስ በርሳቸው ቀጤ ነክ ናቸው። የማክስዌል ኅልዮትና የኸርዝ ሙከራወች ራዲዮ፣ ራዳር፣ ቴሌቪዥን፣ ገመድ አልባ ግንኙነት እንዲፈጠሩ አደርጉ። ልዩ አንጻርዊ ኅልዮት ልዩ አንጻርዊ ኅልዮት የሞገድ ኅልዮቱ በጣም የተሳካ ከመሆኑ የተነሳ አብዛኛውን የብርሃን እይታዊና ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ባህርይ ለመተንተን ያስቻለ ነበር። ይህም የ19ኛው ክፍለ ዘመን ፊዚክስ ታላቁ ድል ተደርጎ ይቆጠራል። ነገር ግን በክፍለ ዘመኑ መዝጊያ ወራት ልዩ ልዩ፣ በሙከራ የተጋለጡ ተቃርኖወችና በኅልዮቱ አጥጋቢ ሁናቴ ሊተነተኑ የማይችሉ የብርሃን ክስተቶች ብቅ ማለት ጀመሩ። አንደኛውና ዋና እራስ ምታት የነበረው የብርሃን ፍጥነት ነበር። የጥንቱ ሳይንቲስት ጋሊልዮ ጋሊሊ እንዳስረዳ ማናቸውም ፍጥነት አንጻራዊ ነው። ስለሆነም አንድ ሰው የሚንቀሳቀስ መኪና ላይ ቢረማመድ ፍጥነቱ የርሱ የመራመድ ፍጥነት ሲደመር የመኪናው ፍጥነት ነው። ነገር ግን የማክስዌል ቀመር ያስረዳ እንደነበር የብርሃን ፍጥነት ምንጊዜም ቋሚና አንድ ነው። ለምሳሌ በሚነዳ መኪና ፊት ያሉ መብራቶች የሚያመነጩት ብርሃን ፍጥነት ከቆመ መኪና ብርሃን ጋር እኩል ነው። ይህ እንግዳ ውጤት በሚኬልሰን ሞርሌ ሙከራ የተረጋገጠ የውኑ አለም ባህርይ ነበር። በ1905 አልበርት አይንስታይን ይህን እንቆቅልሽ እስከፈታ ድረስ እንቆቅልሽ ሆኖ ቆይቶ ነብር። አይንስታይን እንዳስረዳ፣ ኅዋና ጊዜ ቋሚ ነገር ሳይሆኑ የሚለጠጡና የሚኮማተሩ ነገሮች ናቸው። ስለዚህ የብርሃን ፍጥነት (በጠፈር) ምንጊዜም ቋሚ የመሆኑ ምስጢር የኅዋና ጊዜ መኮማተር እንደሆነ አስረዳ። በዚያውም አይንስትያን ከዚይ በፊት የማይታወቀውን የግዝፈት እና የአቅምን ተመጣጣኘት በሚከተለው ቀመሩ አስረገጠ ማለቱ አቅም ሲሆን፣ የዕረፍት ግዝፈት እና ደግሞ የብርሃን ፍጥነት በጠፈር ውስጥ ናቸው። የእኑስ ኅልዮት እንደገና ማንሰራራት በሙከራ ከተደረሰበት ሌላ እንግዳ ጠባይ በአሁኑ ዘመን የፎቶኤሌክትሪክ ተጽዕኖ የሚባለው የብርሃን ፀባይ ነበር። ብርሃን ከብረታ ብረቶች ገጽታ ጋር ሲገናኝ የገጽታውን ኤሌክትሮኖች ከአተሞቻቸው በማፈናጠር የኤሌክትሪክ ጅረት(ከረንት) እንዲፈጠር ያደርጋል። በጥንቃቄ በተደረጉ ሙከራወች መሰረት የተፈናጣሪወቹ ኤሌክትሮኖች አቅም በሚያርፍባቸው የብርሃን ድምቀት (ኢንተንስቲ) ሳይሆን የሚወሰነው በብርሃኑ ድግግሞሽ መጠን ነበር። እያንዳንዱ አይነት ብረታብረት ከተወሰነ የድግግሞሽ መጠን በታች ያለ ብርሃን ካረፈበት ከነጭርሱኑ ኤሌክትሮኖቹ አይንቀሳቀሱም (የፈለገ ብርሃኑ የደመቀ ቢሆንም)። እኒህ ተስተውሎወች (የሙከራ ውጤቶች) የብርሃንን የሞገድነት ተፈጥሮ የሚቃረኑ ነበሩ። ለብዙ አመታት ሳይንቲስቶች እኒህን ተቃርኖወች ከሞገድ ኅልዮት ጋር ለማስታረቅ ሞክረዋል፣ ነገር ግን አልተሳካላቸውም። አልበርት አይንስታይን በ1905 ዓ.ም. ለችግሩ መፍትሔ አቀረበ። ይህን ያደረገው የብርሃንን እኑስ ኅልዮት እንደገና እንዲንሰራራ በማድረግ ነበር። ሆኖም ግን ለሞገድ ኅልዮት እጅግ ብዙ መረጃ ስለነበር በመጀመሪያ የአይንስታይን መፍትሔ በዘመኑ በነበሩ ሳይንቲስቶች ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም። ነገር ግን የ የፎቶኤሌክትሪክ ተጽዕኖን የአይንስታን ትንታኔ በበቂ ሁኔታ ስለገለጸ ቀስ በቀስ ተቀባይነትን አገኘ፣ ስለሆነም አይንትስታን ለዚህ ስራው የኖቤል ሽልማትን አገኘ። ይህ የአንስታይን የፎቶኤሌክትሪክ ኅልዮት ለቀጣዩ የኳንተም ኅልዮት መሰረትና አሁን ተቀባይነት ላለው የብርሃን ሁለት ጸባይነት መሰረት የጣለ ነበር። ኳንተም ኅልዮት ኳንተም ኅልዮት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከተደረጉ ሙከራወች የተነሳ ሌላ ቀውስ ተፈጠረ፣ ይኸውም የኤሌክትሮማግኔቲክ ኅልዮት በሚለውና በተጨባጭ ሙከራወች ውጤት መካከል የነበር ልዩነት ነው። ማናቸውም ሙቀት ያላቸው ቁሶች የሙቀት ጨረራ ይረጫሉ፣ ነገር ግን ጨረራቸው ያልተቆራረጠ አልነበርም። በ1900፣ ማክስ ፕላንክ የተሰኘው ጀርመናዊ ተማሪ የዚህን ጉዳይ ስረ መሰረት ለማወቅ ባደረገው ጥናት ማናቸውም ነገሮች (ጥቁር አካላት) ኤሌክትሮማግኔት ጨረራ የሚረጩት በጠጣር በጠጣር ቁርጥራጭ እንጂ በተቀጣጣይ እንደፈሳሽ አለነበረም። እኒህ ጠጣር የኤሌክትሮማግኔት ጨረራ ቁራጭ መሰረቶች ፎቶን ተባሉ። የሚይዙት ጠጣር ቁራጭ አቅም ኳንታ እንዲባል አንስታይን አሳወቀ። ፎቶን መባሉ በዚሁ ዘመን ኤሌክትሮኖች እና ፕሮቶኖች የታወቁበት ዘመን ስለነበር ለመለየት ነበር። ፎቶን አቅም ሲኖረው, መጠኑም ከአለው ድግግሞሽ, ,ጋር ቀጥተኛ ውድር አለው። በሒሳብ ሲቀመጥ ማለቱ፦ የ ፕላንክ ቋሚ ቁጥር, የሞገድ ርዝመት፣ እና ደግሞ የብርሃን ፍጥነት ናቸው። ልክ እንዲሁ፣ የፎቶን እንድርድሪት (ሞመንተም) ከሞገዱ ድግግሞሽና ጋር ቀጥተኛ ውድር ሲኖረው ከየሞገዱ ርዝመት ጋር ግን ተገልባጭ ውድር አለው። ወደሒሳብ ቋንቋ ሲተረጎም፦ ይሁንና ይህ የፕላንክ ጥናት የፎቶንን ጠጣር የሚመስል ባህርይ በአጥጋቢ ሁኔታ የገለጸ አልነበረም። የእኑስ ሞገድ ሁለትዮሽ የብርሃንን ተፈጥሮ የሚገልጸው የአሁኑ ዘመናዊ ኅልዮት በአልበርት አይንስታይን የፎቶኤሌክትሪክ ተጽዕኖ ኅልዮትና በማክስ ፕላንክ የፎቶን ጥናት ላይ የተመሰረት ነው። የአይንስታን ትንታኔ በእኑስነት ላይ ያተኮረ ሲሆን የፕላንክ ደግሞ በሞገድነት ላይ ያተኮረ ነበር። የዘመናዊው ኅልዮት እሚለው ብርሃን የሞገድ-እኑስ ሁለትዮሽ ተፈጥሮ አለው ይላል። ማለቱ ብርሃን፣ ሞገድም፣ እኑስም ነው። አይንስታይን እንዳስተማረ፡ የፎቶን አቅም ከፎቶኑ ድግግሞሽ ጋር ቀጥተኛ ውድር አለው ማለት ድግግሞሹ ሲበዛ፣ አቅሙም ይበዛል፣ ሲያንስ ያንሳል)። ይህ ሃልዮት ሲሰፋ ማናቸውም የአለም አካላት እኑስም ሞገድም ናቸው ብሎ ያስቀምጣል። ብርሃን ብቻ ሳይሆን፣ ማንኛውም ነገር የእኑስነቱን ወይም ደግሞ የሞገድነቱን ባህርይ ለይቶ ሊያወጣ የሚችል ሙከራ ሊካሄድበት ይችላል። አንድ ነገር ግዝፈቱ ትልቅ ከሆነ የእኑስነቱ ባህርይ ገኖ ይወጣል። ስለሆነም የአለምን ሞገዳዊነት በዘልማድ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። ሉዊ ደ ብሮይ በ1924 አፍረጥርጦ የኤሌክትሮንን የእኑስና ሞገድ ሁለትዮሽ ፀባይን እስከተነተነ የሁለቱ ጸባይን የያዘ ብርሃን ብቻ ነው ብሎ ሳይንቲስቶች ያስቡ ነበር። የኤሌክትሮን ሞገዳዊ ባህርይ በ1927 ዓ.ም. በዳቪሰንና ገርመር በተጨባጭ ተመክሮ ተረጋገጠ። ኳንተም ሥነ ኤሌክትሮ-እንቅስቃሴ (ኤሌክትሮዳይናሚክስ) የኳንተም መካኒካል ኅልዮት በብርሃንና ኤሌክትሮማግኔቲካዊ ጨረራ ያለው አስተሳሰብ ቀስ በቀስ እየተቀየረ 1920ወቹ አልቀው 1930ዎቹ ተደግሙ። በ1940ወቹ ይህ ኅልዮት አብቦ አሁን የሚታወቀውን የኳንተም ኤለክትሮዳይናሚክስ ወይንም በሌላ ስሙ የኳንተም መስክ ኅልዮት ወለደ። ይህ አዲሱ ኅልዮት በብዙ ሙከራወች የተፈተነና ጸንቶ የቆመ ሲሆን በሌላ ጎን ስፋት ያላቸውን የተፈጥሮ ክስተቶች በአጥጋቢ ሁኔታ መተንተን የሚያስች ሆኖ እስካሁን ጸንቶ ይገኛል። ኳንተም ኤሌክትሮዲናሚክስን ያቋቋሙት ሳይንቲስቶች ሪቻርድ ፌይማን፣ ፍሪማን ዴይሰን፣ ጁሊያን ሽዊንገር፣ እና ሽን-ኢችሮ ቶሞናጋ ናቸው። ፌይማን፣ ሽዊንገር እና ቶሞናጋ የ1965 ኖቤል ሽልማት ስለዚህ ስራቸው አሸንፈዋል።
13066
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%89%E1%8A%AD%E1%88%B0%E1%88%9D%E1%89%A0%E1%88%AD%E1%8C%8D
ሉክሰምበርግ
ሉክሰምበርግ: በኅዳር ዓ/ም ዛቪዬ በተል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆኑ ሉክሳምቡርግ ከቤልጅግና አይስላንድ በኋላ ሦስተኛው ሰዶማዊ የመንግሥት መሪ ያለው አገር ሆነ። በይፋ ሉክሰምበርግ በምእራብ አውሮፓ የምትገኝ በመሬት ተከበበች ሀገር ናት፡፡ በምእራብ እና ሰሜን ከቤልጂየም፣ በምስራቅ ከጀርመን፣ እና በደቡብ ከፈረንሳይ ጋራ ትዋሰናለች፡፡ መዲናዋ ሉክምበርግ ሲቲ ከብሩሰልስ እና ስትራስቦርግ ጋር የአውሮፓ ህብረት፣ የምስራቅ አውሮፓ የፍትህ ፍርድ ቤት፣ የኢዩ ከፍተኛ የህግ አውጪ ባለስልጣን መቀመጫዎች ናቸው፡፡ ባሕሏ፣ ህዝቦቿ እና ቋንቋዋ በከፍተኛ ሁኔታ ከአጎራባች ሐገራት ጋራ በመወራረሱ የተነሳ በዋነኛነት የፈረንሳይ እና የጀርመን ባሕሎች ቅይጥ ሐገር ሆናለች፡፡ ይሄም በሐገሪቱ በሚነገሩ ሶስት አበይት ቋንቋዎች ጉልህ ሆኖ ይቀርባል እነዚህም ሉክሰምበርጊሽ፣ ፈረንሳይኛ፣ እና ጀርመንኛ ናቸው፡፡ በአጎራባች ሐገራት በተለይም በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ተደጋግሞ የደረሰባት ወረራ የተነሳ ሐገሪቱ በፈረንሳይ እና ጀርመን ድርድር ፈቋዷ እንዲወሰን የሆነ ሲሆን ከብዙ በጥቂቱ የአውሮፓ ሕብረት እንዲመሰረት መሰረቱን ጥሏል፡፡ ስፋቷ 2,586 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ሲሆን (998 ስኩ.ማይልስ) በአውሮፓ ውስጥ ካሉ ሉዐላዊ ሐገራት ውስጥ ትን ግዛት ስትሆን የዩኤስ የሮዴ ደሴትን ያህል ስፋት ወይም የእንግሊዟን ኖርዛምፕተንሻየር ታህላለች፡፡ በ2016 በአውሮፓ ውስጥ በእጅጉ ዝቅተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ሐገር የሚያደርጋት 576,429 ህዝብ ያላት ሲሆን ነገር ግን እስካሁን ከፍተኛው የህዝብ ቁጥር እድገት ምጣኔ ያላት ሐገር ናት፡፡ በህገመንግስታዊ የዘውድ ስርዐት የተወካይ ዴሞክራሲ እነደመኖሩ በከፍተኛው የሉክሰምበርግ መስፍን ከፍተኛ መስፍን ሄነሪ የምትመራ ሲሆን በአለማችን ላይ በመሳፍንት አገዛዛ ስር ያለች ብቸኛ ቀሪዋ ሐገር ናት፡፡ እንደተባበሩት መንግስታት የ2014 መግለጫ ከሆነ ሉክሰምበርግ ያደገች ሐገር ስትሆን ኢኮኖሚዋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በአለማችንም ከፍተኛው የነፍስ ወከፍ ምጣኔ ሐብት ያላት ሐገር ናት፡፡ የሉክሰምብግ ሲቲ እድሜ ጠገብ የከተማ ክፍሎቿ እና ምሽጎቿ በ1994 ከፍተኛ ምሽጎችን እና እድሜ ጠገብ ከተማ በልዩ ብቃት ጠብቃ በማቆየቷ የዩኔስኮ የአለም ቅርስ በመሆን ተመዝግባለች፡፡ የሉክሰምበርግ ታሪክ ጀምሯ ተብሎ የሚታሰበው በ963 ባላበት ሲግፍሬድ ባሕረ ሰላጤውን ኮረብታማ መሬት ሲወስድ እና ሉሲሊንቡርሁክ፣ “ትንሽ ግንብ” በመባል የሚታወቀውን የሮማውያን ዘመን ምሽግ፣ እና አካባቢው በቅርቡ ከሚገኘው የንጉሳዊ የቅይዱስ ማክሲሚን ገዳም ከወሰደ በኋላ ጀምሯል፡፡ የሴግፍሬድ ዘሮች ግዛታቸውን በጋብቻ፣ በጦርነት እና በጭሰኛ እና ጌታ ግንኙነት አስፋፍተውታል፡፡ የሉክሰምርግ ባላባቶች በ13ኛው ክፍለዘመን ፍፃሜ ላይ ከፍተኛ ግዛት ላይ መንሰራፋት እና መግዛት ችለዋል፡፡ በ1308 የሉክሰምበርግ ባላባት የሆነው ሄነሪ የጀርመኖች እና የቅዱስ ሮማውያን ንጉሰ ነገስት ንጉስ ሆነ፡፡ የሉክሰምበርግ ተወካዮች ምክር ቤት በመካከለኛው ዘመን አራት ቅዱስ የሮማውያን ንጉሰ ነገስቶችን ሾሟል፡፡ በ1354 ቻርልስ መስተዳድሩን ወደ መሳፍንት ሉክሰምበርግ ቀይሮታል፡፡ ሲጊስሙንድ ወንድ ወራሽ ስላልነበረው መሳፍንቱ ከቡርጉንዲያን በከፊል ሆነዋል እንዲሁም የሐብስቡርግ፣ ኔዘርላንድስ አስራሰባት ግዛተቶች መካከል ሆኗል፡፡ ባለፉት ምዕተ አመታት በፈረንሳይ ንጉሳዊ መንግስት እና በሐብስቡርግ ግዛቶች መካከል የሚገኙት ከፍተኛ ስትራቴጂክ አስፈላጊነት ያላቸው የሉክሰምበርግ ከተማ እና ምሽጎቿ በአውሮፓ ውስጥ በእጅጉ ዝናን ካተረፉ ምሽጎች አንዱ ለመሆን እንዲችሉ ተደርገው የተገነቡ ናቸው፡፡ የፈረንሳዩ ሉዊስ እና የኦስትሪያዋ ማሪያ ቴሬዛ ከተቆጣጠሯት በኋላ ሉክሰምበርግ የመጀመሪያው የፈረንሳይ ሪፐብሊክ እና በናፖሊዎን ስር የነበረው ንጉሳዊ አገዛዝ አካል ሆናለች፡፡ የአሁኗ ሉክሰምበርግ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሐገር ብቅ ያለችው በ1815 በቪዬና ኮንግረስ ወቅት ነበር፡፡ ከሐይለኛ ምሽጎቹ ጋር ከፍተኛው መስፍን ከተማዋን በፈረንሳይ ከሚሰነዘርባት ሌላ ወረራ ለመከላከል ከፕሩሲያን ሽምቅ ተዋጊዎች ጋራ በኔዘርላንድሱ ዊሊያም የግል ቁጥጥር ስር በመሆን ነጻ እና ገለልተኛ ሐገር ሆናለች፡፡ በ1839 ከቤልጂየም አብዮት መፈንዳት በኋላ ፈረንሳይኛ ብቻ የሚናገረው የሰሉክሰምበርግ አካል ወደቤልጂየም ተቀላቅሏል እና ሉክሰምበርጊሽ ተናጋሪው ክፍል የአሁኗን ሉክምሰምበርግ መስርተዋታል፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የቀዩን ምድር የበለፀገ ብረታዘል መሬት የብረት ኢንዱስትሪው ፍለጋ ባደረገበት ወቅት ሐገሪቱን ወደኢንዱስትሪ ግስጋሴ ውስጥ አስገብቷቷል፡፡ ዋና መስሪያ ቤቱን በሉክሰምበርግ ከተማ ያደረገው የአለማችን ታላቁ የብረት አምራች የሆነው አርሴሎርሚታል አሁንም እነዚህን ወቅቶች የሚያስታውሰን ነው፡፡ በ1960ዎቹ የብረት ኢንዱስትሪው ውድቀት ካስመዘገበ በኋላ የአለማችን የገንዘብ ማዕከል ፣ለመሆን ሐገሪቱ ራሷን በማደራጀቱ ላይ ትኩረቷን በማድረግ አሁን የታወቀችበትን የባንክ ማዕከል ለመገንባት ችላለች፡፡ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ጅማሬ አንስቶ መንግስቶቿ ሐገሪቱን በእውቀት ወደታነጸ ኢኮኖሚ ልማት ውስጥ በማስገባቱ ላይ ያተከረች ሲሆን ከዚህም ጋራ ተያይዞ የሉሰምበርግ ዩንቨርስቲ እና ብሔራዊ የህዋ ፕሮግራም በ2020 ወደጨረቃ በሚደረግ ሰው አልባ ጉዞ ላይ የመጀመሪያ ተሳትፎዋን ለማድረግ በማቀድ መስርታለች፡፡ ሉክሰምበርግ የአውሮፓ ህብረት፣ ኦኢሲዲ፣ የተባበሩት መንግስታት፣ ናቶ፣ እና ቤኔሉክስ መስራች አባል ስትሆን የፖለቲካ ስምምነቷን በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ውህደት ላይ መስርታለች፡፡ የሐገሪቱ መዲና እና ትልቋ ከተማ የሆነችው የሉክሰምበርግ ሲቲ የአውሮፓ ህብረት በርካታ ተቋማት እና ኤጀንሲዎች መቀመጫ ናት፡፡ የሐገሪቱ የመጀመሪያው ታሪክ ሆኖ በተመዘገበው ሉክሰምበርግ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በ2005 እና 2006 አገልግላለች፡፡ በ2016 የሉክሰምበርግ ዜጎች ወደ 172 ሐገራት እና ግዛቶች ነጻ ቪዛ ወይም በደረሱበት ቪዛ እንዲሰጣቸው ሆኖ የነበረ ሲሆን ካናዳ እና ስዊትዘርላንድ ከመሳሰሉ ሐገራት ጋራ በተያያዘ የሉክሰምበርጋዊን ፓስፖርት በአለም 6ኛው በመሆን ደረጃ ተሰጥቶታል፡፡ ታሪክ ሐገር የሉክሰምበርግ ታሪክ መመዝገብ የጀመረው በሲግፍሪድ፣በአርዴኔስ ኮርት የሚገኘው እድሜ ጠገብ ቋጥኝ ያለው ሉሲሊንቡሩህክ (የዛሬው የሉክሰምበርግ የንጉሳዊያን መኖሪያ) በመያዝ፣ የንጉሳዊው የቅይዱስ ማክሲሚን ገዳም ልውውጥ በ1955 እ.ኤ.አ. በማድረግ ነው፡፡ በዚህ ምሽግ አካባቢ ከተማ በሂደት መመስረቱን በመቀጠል ከፍተኛ ስትራቴጂክ ጠቀሜታ ያለው ማዕከል መሆን ችሏል፡፡ የመሳፍንት ግዛት በ14ኛው እና 15ኛው ክፍለ ዘመናት ሶስት የሉክሰምበርግ ምክር ቤት አባላት የሮማ ቅዱሳት ነገስታት በመሆን ነገሱ፡፡ በ1437 እ.ኤ.አ. የሉክሰምበርግ ምክር ቤት በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ወንድ በማጣት የአልጋ ወራሽ ችግር ገጥሞት ነበር፣ ይኸውም ግዛቶች በደቿ ኤልሳቤጥ ለቡርገንዲው ፊሊፕ እንዲሸጥ አድርጓል፡፡ በሚከተሉት ምዕተ አመቶች የሉክምበርግ ምሽግ ተከታትለው በመጡ ሰፋሪዎቿ፣ ቦርቦኖች፣ ሐብስበርጎች፣ ሆሄንዞለርንስ እና ፈረንሳዮች ከጊዜ ወደጊዜ ሰፍቷል እንዲሁም ተጠናክሯል፡፡ አስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ናፖሊዎን በ1815 እ.ኤ.አ. ከተሸነፈ በኋላ፣ ሉክሰምበርግ በፕሩሺያ እና በኔዛርላንድስ መካከል ክርክር እንዲፈጠርባት ምክንያት ሆናለች፡፡ ከኔዘርላንድስ ጋራ በሕብረት በመሆን በጀርመን ኮንፌዴሬሽን ውስጥ የቪዬና ኮንግረስ ሉክሰምበርግን እንደትልቅ መሳፍንት አመራር በማድረግ የመሰረታት ሲሆን፣ በዚሁ ጊዜ የኔዘርለንድስ አካል በመሆን እና እንደአንድ ግዛቷ በመሆን እየተመራች የሉክሰምበርግ ምሽጎች በፕሩሺያ ጦር ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ይሄ ስምምነት በለንደኑ የ1839 እ.ኤ.አ. የመጀመሪያው ስምምነት የተከለሰ ሲሆን ከዚሁ እለት በኋላ የሉክሰምበርግ ሙሉ ነጻነት ከ1830-1839 እ.ኤ.አ. የቤልጂየም አብዮት በተነሳበት ወቅት ዕውን የሆነ ሲሆን እና በ1839 እ.ኤ.አ. ስምምነት ሙኑ ነፃነቷን ተቀዳጅታለች፣ የሉክሰምበርግ ግዛት ከግማሽ በላይ የተቀነሰ ሲሆን፣ በብዛት የፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆነው ምዕራባዊው የሐገሪቱ ክፍል ወደቤልጂየም ተዛውሯል፡፡ በ1842 እ.ኤ.አ. ሉክሰምበርግ የጀርመንን የጉምሩክ ሕብረት (ዞልቨሬይን) ተቀላቅላለች፡፡ ይኸውም የጀርመን ገበያ እንዲከፈት፣ የሉክሰምበርግ የብረት ኢንዱስትሪ እንዲያድግ፣ እና የሉክሰምበርግ የምድር ባቡር ኔትወርክ ከ1855 እስከ 1875 እ.ኤ.አ. ድረስ እንዲስፋፋ፣ በተለይም ከዚህ አንስቶ የአውሮፓውያንን የኢንዱስትሪ ክልሎች የሚያገናኘው የሉክሰምበርግ-ቲዎንቪል የባቡር ሐዲድ እንዲገነባ አድርጓል፡፡ አሁንም የፕሩሺያ የጦር ሰራዊት ምሽጎቹን ተቆጣጥረዋቸው ስለነበር በ1861 እ.ኤ.አ. ፓሰሬል ተከፈተ፣ ቪል ሆትን እና በቦክ የሚገኙትን ዋና ምሽጎች ከሉክሰምበርግ የምድር ባቡር ጣቢያ ጋር የሚያገናኘው የፔትሩስ ወንዝ ሸለቆን የሚያቋርጠው የመጀመሪያው የመንገድ ላይ ድልድይ፤በደቡብ አቅጣጫ በሚገኘው በዚያ ወቅት በተመሸገው ቡርቦን ሜዳማ ክፍል ላይ በ1959 እ.ኤ.አ. ተከፈተ፡፡ በ1866 ከተከሰተው የሉክሰምበርግ ችግር በኋላ በፕሩሺያ እና ፈረንሳይ መካከል ጦርነት የተፈጠረ ሲሆን፣ ከፍተኛው የመሳፍንት ነጻነት እና ገለልተኝነት በ1867ቱ እ.ኤ.አ. በለንደኑ ሁለተኛው ስምምነት በድጋሚ ተረጋግጧል፣ የፕሩሺያ የጦር ሰራዊት ከሉክሰምበርግ ምሽጎች በመውጣት ቦክ እና በአቅራቢያው የሚገኙ ምሽጎች ፈራርሰዋል፡፡ የኔዘርላንድስ ንጉስ የሉክሰምበርክ ከፍተኛ መስፍን ርዕሰ ብሔር በመሆን የቀጠለ ሲሆን፣ እስከ 1890 እ.ኤ.አ. ድረስ በሁለቱ ሐገራት መካከል ያለውን የሁለቱን ሐገራት ግንኙነት አስቀጥሏል፡፡ ዊሊያም ከዚህ አለም በሞት ሲለይ የኔዘርላንድስ ዙፋን ወደሴት ልጁ ዊልሔልሚና ተላለፈ፣ በዚህም ሁኔታ ሉክሰምበርግ (በናሱ ቤተሰብ ፓክት በወንድ ወራሾች ብቻ ተወስኖ የነበረው) ወደናሱ-ዌይልበርጉ አዶልፍ ተላልፏል፡፡ በ1870 እ.ኤ.አ. በፍራንኮ-ፕሩሺያን ጦርነት ጊዜ ወታደሮችን ከሜትዝ (በመቀጠል ጠፈረንሳይ ክፍል የሆነችው) በመሳፍንቱ ሐገር እንዲያልፉ ፈረንሳይ የባቡር ሐዲዱን መጠቀሟን አስመልክተቶ እና ወደቲዎንቪል አቅርቦቶችን ለማቅረብ ምንም እንኳን ክርክሮች የነበሩ ቢሆንም፣ የሉክሰምበርግ ገለልተኛነት በጀርመን አክብሮት ተቸሮታል፣ እና ጀርመንም ሆነች ፈረንሳይ ሀገሪቱን ወረዋት አያውቁም፡፡ ነገር ግን በ1871እ.ኤ.አ. ጀርመን በፈረንሳይ ላይ ድል በመቀዳጀቷ ሜትዝ እና ቲዎንቪልን ጨምሮ ሉክሰምበርግ ከሎሬን ጋራ ያላት ድንበር ከፈረንሳይ ጋራ ከመጎራበት ይልቅ በፍራክፈርት ስምምነት መሰረት እንደአልሴስ-ሎሬን ከጀርመን ንጉሳዊ መንግስት ጋራ ወደተያያዘችው ተለውጧል፡፡ ይሄም ጀርመን የባቡር ሐዲዶችን የመቆጣጠር እና የማስፋፋት ወታደራዊ ጥቅም እንድታገኝ አስችሏታል፡፡ ሐያኛው ክፍለ ዘመን ኦገስት 1914 እ.ኤ.አ. ንጉሳዊቷ ጀርመን ከፈረንሳይ ጋራ ባደረገችው ጦርነት በሉክሰምበርግ ላይ ወረራ በማካሄድ የሉክሰምበርግን ገለልተኝነት ጥሳለች፡፡ ይሄ ሁኔታ ጀርመን የባቡር ሐዲዱን መጠቀም እንድትችል አድርጓቷል፡፡ በዚሁ ሁኔታ ከፈረንሳይ ነጥቃዋለች፡፡ ይሁንና ከጀርመን ሰፈራ ባሻገር ሉክሰምበርግ አብዛኛውን ነጻነቷን እና የፖለቲካ ስልቶቿን እንድታስቀጥል ሁኔታዎች ተመቻችተውላታል፡፡ በ1940 እ.ኤ.አ. ኛው የአለም ጦርነት ከተነሳ በኋላ የናዚ ጀርመን ዌህርማችት ወደሐገሰሪቱ በገባ ጊዜ የሉክሰምበርግ ገለልተኛነት በድጋሚ “ሙሉ ለሙሉ ያለማብራሪያ” ተጣሰ፡፡ ከመጀመሪያው የአለም ጦርነት በተቃርኖ በሆነ መንገድ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ጀርመን በሉክሰምበርግ መስፈሯ ሐገሪቱን የጀርመን ግዛት ተደርጋ እንድትቆጠር አድርጓታል እና ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ በትይዩ ከምትገኘው ከሶስተኛዋ ሬይች አውራጃ ጋር እንድትያያዝ አድርጓታል፡፡ መቀመጫውን በለንደን አድርጎ የነበረው በስደት ላይ የነበረው መንግስት አጋሮችን በመደገፍ በኖርማንዲ ወረራ ላይ ተሳታፊ የሆኑ በጎ ፈቃደኛ አናሳ ቡድኖችን ልኮ ነበር፡፡ ሉክሰምበርግ በሴፕቴምበር 1944 እ.ኤ.አ. ነጻ የወጣች ሲሆን በ1945 እ.ኤ.አ. የተባበሩት መንግስታት መስራች አባል ሆናለች፡፡ በህገመንግስቱ የሉክሰምበርግ ገለልተኛ አቋም በ1948 ያበቃ ሲሆን በ1949 እ.ኤ.አ. የናቶ መስራች አባል ሐገር ሆናለች፡፡ በ1951 ከስድስቱ የአውሮፓውያን የድንጋይ ከሰል እና የብረት ማሕበረሰብ አንዷ የሆነች ሲሆን ይኸውም ማሕበረሰብ በ1957 እ.ኤ.አ. የአውሮፓውያን የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ የሆነው እና በ1993 እ.ኤ.አ. የአውሮፓ ሕብረት የሆነው ሕብረት ሲሆን እንዲሁም በ1999 እ.ኤ.አ. ሉክሰምበርግ የዩሮ መገበያያ አካባቢን ተቀላቅላለች፡፡ በ2005 እ.ኤ.አ. ለአውሮፓ ህገመንግስት በሚመሰርተው የአሕ ስምምነት ላይ ህዝበ ውሳኔ ተካሂዷል፡፡ ፖለቲካ ሉክሰምበርግ በህገመንግስታዊ የዘውድ አገዛዝ የሚመራ የፓርላማ ዲሞክራሲ ያላት ሐገር ናት፡፡በ1868ቱ እ.ኤ.አ. ህገመንግስት የህግ አስፈጻሚነት ስልጣን በከፍተኛው መስፍን እና በርካታ ሌሎች ሚኒስቴሮችን በያዘው ካቢኔው ተይዞ ነበር፡፡ ከፍተኛው መስፍን የህግ ረቂቅን የማፍረስ አቅም የነበረው ሲሆን በዚህ ሁኔታ አዲስ ምርጫ በሶስት ወራት ጊዜ መከናወን ነበረበት፡፡ ይሁንና ከ1919 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሐገሪቷ ሉዐላዊነት ሰፈነ፣ በህገመንግስቱ እና በህጉ መሰረት በከፍተኛ መስፍኑ ይተገበራል፡፡ የህግ ማውጣት ስልጣን ለዲኤታው ምክር ቤት፣ ከአራት የመራጮች አካላት ለአምስት አመት የስልጣን ዘመን ለተመረጡ ስልሳ አባላት ላሉት በአንድ የህግ አውጭው አካል ለተዋቀረው የህግ አውጪ ተሰጥቷል፡፡ ሁለተኛው አካል፣ የሐገሪቱ ምክር ቤት (ኮንሴይል ድኢታት) በከፍተኛው መስፍን የተመረጡ ሐያ አንድ መደበኛ ዜጎችን የያዘ ሲሆን የህግ ረቂቆችን በማርቀቁ ሂደት የዲኤታዎችን ምክር ቤት ያማክራል፡፡ ከፍተኛው መስፍን ሶስት የስር ፍርድ ቤቶች ያሉት ሲሆን (ጀስቲስ ደ ፔይክስ፣ በኢስች-ሱር-አልዜቴ፣ የሉክሰምበርግ ከተማ እና ዲየኪርች)፣ ሁለት አውራጃ ፍርድ ቤቶች (ሉክሰምበርግ እና ዲየኪርች) እና የፍትህ ከፍተኛ ፍርድ ቤት (ሉክሰምበርግ)፣የአቤቱታ ፍርድ ቤቱን እና የሰበር ሰሚ ችሎትን ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም አስደተዳደራዊ ችሎት እና አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ያለ ሲሆን እንዲሁም የህገመንግስቱ ፍድ ቤት ሁሉም በመዲናዋ ይገኛሉ፡፡ አስተዳደራዊ መምሪያዎች ሉክሰምበርግ በ12 የአስተዳደር ክፍሎች የተከፈለች ሲሆን በ105 ትንንሽ የአስተዳደር ክፍሎች በተጨማሪም ተከፍለዋል፡፡ አስራሁለቱ ትንንሽ አስተዳደሮች የከተማ ደረጃ ያላቸው ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሉክሰምበርግ ከተማ ትልቋ ነች፡፡ የውጭ ግንኙነት ሉክሰምበርግ ለረጅም ዘመን የአውሮፓ ፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚ ውሕደትን በዋነኛነት ስትደግፍ ቆይታለች፡፡ የአውሮፓን ውሕደት በሚተነብየው ጥረታቸው ሉክሰምበርግ እና ቤልጂየም በ1921 እ.ኤ.አ. የቤልጂየም-ሉክሰምበርግ የኢኮኖሚክ ሕብረትን የመሰረቱ ሲሆን ይሄም ልውውጥ የሚደረግበት መገበያያ ገንዘብ ለመፍጠር እና የጋራ እሴት እንዲኖር ያለመ ነበር፡፡ ሉክሰምበርግ የቤኔሉክስ የኢኮኖሚ ሕብረት አባል እና የአውሮፓ ኢኮኖሚ ማሕበረሰብ (አሁን የአውሮፓ ሕብረት) አባል ናት፡፡ በተጨማሪም በሸንጀን ቡድን ውስጥ (ስምምነቱ በተፈረመባት የሉክሰምበርግ መንደር ስም የተሰየመ) የተሳተፈች ሲሆን፣ ግቡም በአባል ሐገራት መካከል የሚደረግ ነፃ ዝውውር ማለት ነው፡፡ በዚሁ ጊዜ አብዛኛው የሉክሰምበርግ ዜጎች የአውሮፓ ሕብረት ስሜት የሚኖረው በፍተኛ የትራንስ አትላንቲክ ግንኙነት ግንዛቤ ውስጥ እና ፕሮ-ናቶ፣ ፕሮ-ዩኤስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን የሚከተል ይሆናል፡፡ ሉክሰምበርግ የአውሮፓውያን የፍትህ ፍርድ ቤት፣ የአውሮፓ አዲተሮች ፍርድ ቤት፣ የአውሮፓ ሕብረተሰብ የስታቲስቲክ ጽ/ቤት (“ዩሮስታት”) እና ሌሎች አስፈላጊ የኢዩ አካላት መቀመጫ ናት፡፡ የአውሮፓ ፓርላማ ሴክሬተሪያት በሉክሰምበርግ የሚገኝ ሲሆን ነገር ግን ፓርላማው በአብዛኛው የሚሰበሰበው በብሩሰልስ እና አልፎ አልፎም በስትራስቡርግ ነው፡፡ ወታደር ሉክሰምበርግ በመከላከያ ሐይሉ እና በናቶ ውስጥ በጅጉ አነስተኛ የሆነ የጦር ሰራዊት ያላት ሲሆን እስከ 800 የሚጠጉ ወታደሮች እና 100 የመንግስት ሰራተኞች ናቸው፡፡ በየብስ የተከበበች ሐገር እንደመሆኗ የባሕር ሐይል የላትም፡፡ ሉክሰምበርግ በተጨማሪም የአየር ሐይል የሌላት ሲሆን፣ ይሁንና የናቶ 17 ኤደብሊውኤሲኤስ አውሮፕላኖች እንደሁኔታዉ የሉክሰምበርግ አውሮፕላኖች ሆነው ተመዝግበዋል፡፡ ከቤልጂየም ጋራ ባደረገችው የጣምራ ስምምነት ሁለቱም ሀገራት ለአንድ ኤ400ኤም ወታደራዊ ካርጎ አውሮፕላን የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ መልክዐ ምድር ሉክሰምበርግ በአውሮፓ አንዷ እጅግ ትንሽ ሐገር ናት እንዲሁም የአለማችን 194 ነጻ ሐገራት በስፋቷ 179ኛ በመሆን ተቀምጣለች፡፡ ሐገሪቱ በስፋቷ 2,586 ስኩዌር ኪሎሜትር (998 ስኩ. ማ) ስትሆን እንዲሁም ርዝመቷ 82 ኪሜ (51 ማይ) እና 57 ኪሜ (35 ማ) ወርድ አላት፡፡ በ490 እና 510 ሰ ላቲቲውድ እና 50 እና 70 ምስ ሎንግቲውድ መካከል ትገኛለች፡፡ በምስራቅ ሉክሰምበርግን የጀርመን የቡንደስላንድ ሪኔላንድ-ፓላቲኔት እና ሳርላንድ ሲያዋስናት እና በስተደቡብ የፈረንሳይዋ ክልል ሎሬይን ታዋስናታለች፡፡ ታላቋ የመስፍን ሐገር የቤልጂየሟ ዋሉን ክልል የምትዋሰን ሲሆን፣ በተለይ ኋላ የተመለከተችው የሉክሰምበርግ ግዛት እና ሊዬጅ፣ ከፊሎቹ ጀርመንኛ ተናጋሪ የቤልጂየም ማሕበረሰብን ያቀፈ ሲሆን፣ በምዕራብ እና በሰሜን በተከታታይ ናቸው፡፡ የሐገሪቱ ሰሜናዌ ሩብ ክፍል “ኦዬስሊንግ” በመባል የሚታወቁ ሲሆን እና የአርዴኔስ ግማሽ ክፍል ናቸው፡፡ ኮረብታማ እና ዝቅተና ተራሮችን የያዘ ሲሆን የክኔይፍ አቅራቢያ ዊልዌርዴጅ፣ ከፍታ ላይ የሚገኘውን ነጥብ፣ በ560 ሜ (1,837 ጫማ) ነው፡፡ ሌሎች ተራሮች “ቡርግፕላዝ” 559 ሜትሮች ሁልዳንጅ አካባቢ እና “ናፖሌዎንስጋርድ” በ 554 ሜትሮች ራምብሮች አካባቢ ናቸው፡፡ ክልሉ በተራራቀ መልኩ ህዝብ የሰፈረበት ሲሆን አራት ሺህ በላይ በሚደርስ ህዝብ ባለበት አንድ ከተማ ብቻ ይገኛል (ዊልትዝ)፡፡ የሐገሪቱ ደቡባዊ ሁለት ሶስተኛ ክፍል “ጉትላንድ” በመባል የሚጠራ ሲሆን ከኦየስሊግ ይልቅ ህዝብ ተጠጋግቶ የሚኖርባት አካባቢ ናት፡፡ በተጫሪም ይበልጥ ብዝሐነር ያላት እና በአምስት የመልክዐምድር ክፍሎች የምትከፈል ናት፡፡ የሉክሰምበርግ አምባ በደቡብ ማዕከላዊ ሉክሰምበርግ ሰፊ፣ ዝርግ፣ አሸዋማ ድንጋ የሚበዛባት ቦታ እንዲሁም የሉክሰምበርግ ከተማ ሳይት ናት፡፡ ከሉክሰምበርግ ምስራቅ አቅጣጫ ትንሷ ስዊትዘርላንድ ኮረብታማ ገፅታ እና ጥቅቅ ያሉ ደኖች ያሉበት ስፍራ ነው፡፡ የሞሴል ሸለቆ ዝቅተኛው ቦታ ሲሆን በደቡባዊው ምስራቅ ድንበር ታኮ የሚሄድ ቦታ ነው፡፡ ሬድ ላንድስ በደቡባዊው ጫፍ እና በደቡባዊው ምዕራብ የሉክሰምበርግ የኢንዱስትሪ ልብ እና የሉክሰምበርግ ትልልቅ ከተሞች መገኛ ቦታ ነው፡፡ የሉክሰምበርግ እና የጀርመን ድንበር ላይ ሶስት ወንዞች ያሉ ሲሆን እነዚህም ሞሴል፣ ሳውየር፣እና ኦውር ናቸው፡፡ ሌሎች አበይት ወንዞች አልዜት፣ ክሌርቭ፣ እና ዊልትዝ ናቸው፡፡ የሳውር መካከል እና አተርት ሸለቆ በጉትላንድ እና ኦዬስሊንግ ድንበር መካከል ነው፡፡ በ2012 እ.ኤ.አ. የአካባቢ ደረጃ መጣኝ መሰረት ሉክሰምበርግ በአካባቢ ጥበቃ ምዘና ከተደረገባቸው 132 ሐገራት መካከል በደረጃ አራተኛዋ የተሻለች ፈጻመሚ ናት፡፡ በሜርሰርስ ከወጡት ለመኖ የሚመቹ ምርጥ 10 ሐገራት መካከል ሉክሰምበርግ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ አየር ንብረት ሉክሰምበርግ የባሕር አይነት የአየር ንብረት ያላት ሲሆን (ኮፐን፡ ሲኤፍቢ)፣ በተለይ በክረምት መገባደጃ ከፍተኛ ዝናብ ይኖራታል፡፡ ክረምቶች ዋቃት እና በጋዎች ቀዝቃዛ ናቸው፡፡ ትራንስፖርት ሉክሰምበርግ አመቺ የሆነ የመንገድ፣ የባቡር እና የአየር ትራንስፖር ፋሲሊቲዎች እና አገልግሎቶች አሏት፡፡ የመንገድ ኔትወርክ በቅርብ አመታት በጉልህ ዘመናዊ ሲሆን 147 ኪሜ (91ማይ) የሞተር መንገዶች መዲናዋን ከአጎራባች ሐገራት ጋራ ያገናኟታል፡፡ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ፓሪስ ድረስ የሚያገናኘው የቲጂቪ አገናኝ መምጣት የከተማዋ የባቡር ጣቢያ እንዲታደስ ያደረገ ሲሆን እና በ2008 እ.ኤ.አ. በሉክሰምበርግ አየር ማረፊያ አዲስ የተሳፋሪዎች ተርሚናል ተከፍቷል፡፡ በመዲናዋ የከተማ የኤሌክትሪክ ባቡር እንዲሁም ቀላል ባቡር በአቅራቢያ አካባቢ ዎች በቀጣይ ጥቂት አመታት የማስተዋወቅ እቅድ አለ፡፡ በሉክሰምበርግ በ1000 ሰዎች 680.1 ተሽከርካሪዎች አሉ ይኸውም ከሁለቱ የሞናኮ መስተዳድር እና የብሪቲሽ የውጭ ግዛት ከሆነችው ጂብራልታር በስተቀር ከሁሉም በላይ ነው፡፡ ግንኙነቶች በሉክሰምበርግ የቴሌኮሙኒኬሽን ኢንዱስትሪ ከፓለቲካ ተፅዕኖ ነጻ ሲሆን እና የኤሌክትሮኒክ ኔትወርኮች በጉልህ ደረጃ አድገዋል፡፡ በተለያዩ ኦፕሬተሮች መካከል ያለው ውድድር በ2011እ.ኤ.አ. በወጣው ፓኩዌት ቴሌኮም የመንግስት የህግ ረቂቅ ማዕቀፍ ዋስትና ተሰጥቷቸዋል ይኸውም የአውሮፓውያንን የቴሌኮም መመሪያዎች ወደሉክሰምበርግ ህግ የተለወጠ ነው፡፡ ይኸውም የኔትወርክ እና አገልግሎቶችን ኢንቨስትመንት ያበረታታል፡፡ ተቆጣጣሪው አይኤልአር- ኢንስቲቱት ሉክሰምቦርጂስደ ሬጉሌሽን ለማሕበራቱ በእነዚህን ደንቦች ተገዢ እንዲሆኑ ማረጋገጫ ያቀርባል፡፡ ስነ-ህዝብ ዘር የሉክሰምበርግ ህዝብ ሉክሰምበርጋዊያን በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከቤልጂየም ፣ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ጀርመን እና ፖርቱጋል አብዛኞቹ በኋላ ላይ ከተጠቀሰው መጡ ሆነው በመበራከታቸው የተነሳ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ስደተኛ ህዝብ በቅጥር እድገት አሳይቷል፡፡ በ2013 እ.ኤ.አ. የፖርቱጋል ዜግነት ያላቸው 88,000 ነዋሪዎች ነበሩ፡፡ በተጨማሪም ጥቂት የሚባሉ የሮማኒ (ጂፕሲ) እና የአይሁድ ህዝቦች አሉ፡፡ ሁለቱ በሉክሰምበርግ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ከፍተኛ ጭፍጨፋ ደርሶባቸው ከሉክሰምበርግ እንዲወጡ ሆኗል፡፡ ከዩጎዝላቭ ጦርነት ጅማሬ አንስቶ ሉክሰምበርግ ከቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና፣ ሞንቴኔግሮ፣ እና ሰርቢያ በርካታ ስደተኞችን አስተናግዳለች፡፡ በአመት ከ10,000 በላይ አዳዲስ ስደተኞች ወደሉክሰምበርግ ይደርሳሉ፣ አብዛኞቹም ከአሕ ሐገራ ናቸው እንዲሁም አምስራቅ አውሮፓ ናቸው፡፡ በ2000 እ.ኤ.አ. በሉክሰምበርግ 162,000 ስደተኞች በሉክሰምበርግ ነበሩ እነዚህም የህዝብ ቁጥሩን 37 በመቶ ይሆናሉ፡፡ በሉክሰምበርግ በግምት 5,000 ህገወጥ ስደተኞች በ1999 ነበሩ፡፡ ቋንቋ በሉክሰምበርግ ሶስት ቋንቋዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡ እነዚህም ፈረንሳይኛ፣ ጀርመን፣ እ ሉክሰምበርጊሽ ሲሆኑ የሞስሌ ክልል ፍራንኮኒያን ቋንቋ በቤልጂየም፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን አጎራባች ክፍሎች ይነገራል፡፡ ምንም እንኳን ሉክሰምበርጊሽ የጀርመን ምዕራብ ማዕከላዊ ከፍተኛ የጀርመን ቋንቋዎች ቡድን ቢሆንም ከ5000 በላይ የሆኑ የቋንቋው ቃላት መሰረታቸው ከፈረንሳይኛ ነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ የታተሙ የሉክሰምበርጊሽ አረፍተ ነገሮች በሳምንታዊው “ሉክሰምበርገር ዎቼንብላት” ጋዜጣ ሁለተኛው እትም በአፕሪል 14 1821 እ.ኤ.አ. ላይ ይታሉ፡፡ ከሶስቱ አንዱ ይፋዊ ቋንቋ እንደመሆኑ ሉክሰምበርጊሽ የከፍተኛው መስፍን ብሔራዊ ቋንቋ እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ እያንዳንዳቸው ሶስቱ እንደዋነኛ ቋንቋ በመሆን በተወሰኑ ሁኔታዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ የሉክሰምበርግ የትምህርት ስርአት በሶስት ቋንቋ የተዘጋጀ ነው፡ የመጀመሪያዎቹ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት አመታት በሉክሰምበርጊሽ ሲሆኑ፣ ወደጀርመን የሚቀየር ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ የመማር ማስተማሩ ቋንቋ ወደፈረንሳይኛ ይለወጣል፡፡ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ በሶስቱ ቋንቋዎች ብቁ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል፡፡ በትምህርት ቤት እንግሊዝኛ ትምህርት የሚሰጥ በመሆኑ በተለይ በሉክሰምበርግ ሲቲ ሰዎች እንግሊዝኛ መናገር ይችላሉ፡፡ ፈረንሳይኛ የመንግስት ተመራጭ ቋንቋ ነው፡፡ ሐይማኖት ሉክሰምበርግ ሐይማኖትን የማትቀበል ሐገር ናት ሆኖም ሐገሪቱ የተወሰኑ ሐይማኖቶችን በይፋ ሁሉም ሊከሉት የሚገባ ሐይማኖት በማድረግ እውቅና ይሰጣል፡፡ ይሄ ሐገሪቱ በሐይማኖት ላይ የማስተዳደር እና ካሕናትን በመምረጡ ረገድ ሚና እንዲኖራት ያስችላል፣ ለዚህም በተለዋጭ የተወሰኑ የስራ ማስኬጃ ወጪዎችን እና ምንዳ ይከፍላል፡፡ ከ1980 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግስት በሐይማኖታዊ እምነቶች ወይም ልማዶች ላይ ስታቲስቲክስ መሰብሰቡ ህገወጥ ነገር ሆኖ ቆይቷል፡፡ በሲአይኤ ፋክትቡክ ግምት መሰረት በ2000 እ.ኤ.አ. ዓመት 87% ሉክሰምበርጎች የንጉሳዊያን ቤተሰቦችን ጨምሮ ካቶሊኮች ሲሆ፣ ቀሪዎቹ 13% ሙስሊሞች፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች፣ አይሁዶች፣ እና ሐይማኖት የለሾች ናቸው፡፡ በ2010 ፒው የምርምር ማዕከል ጥናት መሰረት 70.4% ክርስቲያኖች፣ 2.3% ሙስሊሞች፣ 26.8% ምንም ዝንባሌ የሌላቸው፣እና 0.5% ሌሎች ሐይማኖቶች ናቸው፡፡ ትምህርት የሉክሰምበርግ ዩንቨርሲቲ እና የሉክሰምበርግ ሚያሚ ዩንቨርሲቲ ግቢዎች ሉክሰምበርግ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ዩንቨርሲቲዎች ናቸው፡፡ ጤና ሉክሰምበርግ በአውሮፓ ውስጥ በነፍስ ወከገፍ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን አልኮል ትሸጣለች፡፡ ይሁንና ከአጎራባች ሐገራት ደንበኞች የሚገዛው ከፍተኛ ቁጥር ያለው አልኮል በስታቲስቲክስ በነፍስወከፍ ከፍተኛ የአልኮል ሽያጭ ሲሆን ይሄ የአልኮል ሽያጭ ደረጃ የሉክሰምበርግ ህዝብን ትክክለኛ የአልኮል ሽያጭ አይወክልም፡፡ ባሕል ሉክሰምበርግ በጎረቤቶቿ ባሕል ተሸፍና ቆይታለች፡፡ በርካታ ባሕሎች አሏት በርካታዉ ሕብረተሰብ በገጠራማው ክፍል የሚኖር ነው፡፡ በአብዛኛው በመዲናዋ የሚገኙ በርካታ ታዋቂ ሙዚየሞች አሏት፡፡ እነዚህም የታሪክ እና ስነ-ጥበብ ብሄራዊ ሙዚየም፣ የሉክሰምበርግ ከተማ ታሪክ ሙዚየም፣ እና አዲሱ ከፍተኛው መስፍን ጂን የዘመናዊ የስነ-ጥበብ ሙዚየም (ሙዳም) ናቸው፡፡ በዲየኪርች የሚገኘው የብሔራዊ ወታደራዊ ታሪክ ሙዚየም የቡልጅ ታሪክን በመወከሉ በልዩ ሁኔታ ይታወቃል፡፡ የሉክሰምበርግ ከተማ ራሷ በምሽጎቿ ታሪካዊ አስፈላጊነት ረገድ በዩኔስኮ የአልም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ገብታለች፡፡ ሐገሪቱ የተወሰኑ በአለማቀፍ ደረጃ የታወቁ ከያኔያን ያሏት ሲሆን እነዚህም ሰዐሊው ቴዎ ኬርግ፣ ጆሴፍ ኩተር እና ሚሼል ማጄሩስ እና በዩኔስኮው የአለም መዝገብ ትውስታ ላይ የሰው ዝርያ በሚል የተቀመጠለት የፎቶግራፍ ባለሞያው ኤድዋርድ ስቴይቼን እና አሁን በክሌርቫውክስ በቋሚነት የሚገኘው ነው፡፡ የፊልም ኮከብ የሆኑት ሎሬታ ያንግ የሉክሰምበርጊሽ ዝርያ ያላቸው ግለሰብ ናቸው፡፡ ሁለት ጊዜ የአውሮፓ የባሕል መዲና በመባል የተሰየመች ጀየመጀመሪያዋ ከተማ ናት፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1995 እ.ኤ.አ. ነው፡፡ በ2007 የአውሮፓ የባህል መዲና የሉክሰምበርግን ከፍተኛ መስፍን ሬይንላንድ-ፕፋልዝ እና በጀርመን የምትገኘውን ሳርላንድ፣ የዋሉን ክልልን እና ጀርመንኛ ተናጋሪ የሆነውን የቤልጂየም ክፍል እና በፈረንሳይ የሚገኘውን ሎሬን ክልል አካታ ድንበር ተሻጋሪ ሆናለች፡፡ ስፖርት በአውሮፓ ካሉት በርካታ ሐገራት በተለየ መልኩ የሉክሰምበርግ ስፖርት በአንድ ብሔራዊ ስፖርት ላይ የተወሰነ አይደለም ነገር ግን ቡድን እና በግል በርካታ ስፒርቶችን ያካትታል፡፡ ከ521,353 ሕዝቧ 10,000 የአንደኛው ወይም የሌላኛው ስፖርት ፌዴሬሽን ፈቃድ ለው አባ ነው፡፡ ትልቁ የሐገሪቱ የስፖርት ማዕከል ድኮክ የሚሰኘው በሉክሰምበርግ ሰሜናዊ ምስራቅ አቅጣጫ በኪርችበርግ የሚገኘው የቤት ውስጥ ሜዳ እና የኦሎምፒክ መዋኛ ገንዳ ሲሆን 8300 ሰዎችን መያዝ ይችላል፡፡ ሜዳው ለቅርጫት ኳስ፣ ለእጅ ኳስ፣ ጂምናስቲክ፣ እና የመረብ ኳስ ሜዳዎችን የሚያካትት ነሲሆን የ2007 እ.ኤ.አ. የአውሮፓ የሴቶች መረን ኳስ የፍጻሜ ጨዋታን ጨምሮ አ ስተናግዷል፡፡ ታዋቂ የስፖርቱ ሰዎች፡ አልፓይን ስኪየር ማርክ ጊራርዴሊ ከ1985 እና 1993 እ.ኤ.አ. መካከል ለአምስት ጊዜ የአለም ዋንቻ አጠቃላይ ሻምፒዮና ሳይክሊስት ኒኮላስ ፍራንትዝ፣ የ1927 እና 1928 እ.ኤ.አ. ቱር ደ ፍራንስ አሸናፊ፣ ቻርሊ ጋውል የ1956 እና 1959 እ.ኤ.አ. ጊሮ ደኢታሊያን እና በ1959 እ.ኤ.አ. የቱር ደ ፍራንስ አሸናፊ፣ ኤልሲ ጃኮብስ፣ በ1958 እ.ኤ.አ. የመጀመሪያዋ የሴት የመንገድ የአለም ሻምፒዮን፣ እና አንዲ ሽሌክ የ2010 ቱር ደ ፍራንስ አሸናፊ፡፡ የመካከለኛ ርቀት ሯጭ ጆሲ ባርቴል፣ በ1952 እ.ኤ.አ. የክረምት ኦሎምፒክ የወንዶች 1500 ሜትር አሸናፊ፡፡ 1961 እ.ኤ.አ. የአለም የውሐ ስኪ ሻምፒዮን ሳይልቪ ሁልሴማን የቴኒስ ተጫዋች ጊልስ ሙለር፣ አን ክሬመር እና ማንዲ ሚኔላ ምግብ የሉክሰምበርግ ምግብ በላቲን እና በጀርመን አለማት መካከል ያለውን ድንበር የሚያንጸባርቅ ሲሆን በአጎራባች ፈረንሳይ እና ጀርመን ምግቦች በከፍተኛ ሁኔታ ተፅዕኖ አድሮበታል፡፡ መገናኛ የሉክሰምበርግ ሚዲያ አበይት ቋንቋዎች ፈረንሳይኛ እና ጀርመንኛ ነቸው፡፡ ሰፊ ስርጭት ያለው ጋዜጣ በጀርመን ቋንቋ የሚወጣው የዕለት ሉክሰምበርግ ወርት ነው፡፡ ፖርቱጊውዝ እና እንግሊዝኛ የራዲዮ እና ብሔራዊ የህትመት ሚዲያዎች አሉ፡፡ ሉክሰምበርግ በራዲዮ እና በቴሌቪዥን ጣቢያዎቿ በመላው አውሮፓ ትታወቃለች፡፡ ሉክሰምበርግ በሚስተር ሁብሎት አማካኝነት አኒሜትድ ፊልም ዘውግ በ2014 እ.ኤ.አ. የኦስካር አሸናፊ ሆናለች፡፡ በተጨማሪም የሚከተሉትን ይመልከቱ የሉክሰምበርግ ማውጫ የሉክሰምበርግ አርክቴክቸር በሉክሰምበርግ የንጉሳውያን መኖሪያዎች ዝርዝር የሉክሰምበርግ ሐይቆች የውጭ ዕዳ ያለባቸው ሐገራ ዝርዝር የአውሮፓ
52442
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A2%E1%88%8E%E1%8A%95%20%E1%88%9B%E1%88%B5%E1%8A%AD
ኢሎን ማስክ
ይህ መጣጥፍ ስለ ቴስላ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ነው አንባቢዎች በአንቀጹ ውስጥ ያሉትን የሰዓት ቀናት ከአውሮፓውያን የቀን መቁጠሪያ በተለየ በጽሑፉ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር እንዳያዩ ይመከራል ይህ ጽሑፍ በከፍተኛ ሁኔታ ሊስተካከል ነው። ኢሎን ሪቭ ማስክ ሰኔ 28፣ 1971 ተወለደ) ሥራ ፈጣሪ፣ ባለሀብት እና የንግድ ታላቅ ሰው ነው። እሱ በ መስራች፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና ዋና መሐንዲስ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ባለሀብት፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የ የቦሪንግ ኩባንያ መስራች; እና የ እና ተባባሪ መስራች. እ.ኤ.አ. እስከ ኤፕሪል 2022 ድረስ ወደ 273 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት ያለው፣ በብሉምበርግ ቢሊየነሮች መረጃ ጠቋሚ እና በፎርብስ የእውነተኛ ጊዜ ቢሊየነሮች ዝርዝር መሠረት ማስክ በዓለም ላይ እጅግ ሀብታም ሰው ነው። ማስክ ከካናዳ እናት እና ደቡብ አፍሪካዊ አባት ተወልዶ ያደገው በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ነው። በ17 አመቱ ወደ ካናዳ ከመውጣቱ በፊት የፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲን ለአጭር ጊዜ ተከታትሏል በኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ ተመዝግበው ከሁለት አመት በኋላ ወደ ፔንስልቬንያ ዩኒቨርሲቲ ተዛውረው በኢኮኖሚክስ እና ፊዚክስ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። እ.ኤ.አ. ጅምር በኮምፓክ በ 307 ሚሊዮን ዶላር በ1999 ተገዛ። በዚሁ አመት ማስክ የኦንላይን ባንክ ኤክስ.ኮምን በጋራ መስርቷል፣ እ.ኤ.አ. በ2000 ጋር በመዋሃድ ፈጠረ። ኩባንያው በ 2002 በ የተገዛው በ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ነው. እ.ኤ.አ. በ 2002 ማስክ ስፔስኤክስን የኤሮስፔስ አምራች እና የጠፈር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅትን አቋቋመ እሱም ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ዋና መሀንዲስ ነው። እ.ኤ.አ. ቴስላ እና ቴስላ ኢነርጂ ሆነ። እ.ኤ.አ. በ2015፣ ወዳጃዊ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን የሚያበረታታውን የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ የምርምር ኩባንያ በጋራ አቋቋመ። እ.ኤ.አ. በ 2016 ኒውራሊንክን በአንጎል-ኮምፒዩተር ኢንተርፕራይዞች ልማት ላይ ያተኮረ የኒውሮቴክኖሎጂ ኩባንያ አቋቋመ እና የተሰኘውን ዋሻ ግንባታ ኩባንያ አቋቋመ። ማስክ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የክትባት ማጓጓዣ ዘዴን ሃይፐርሉፕን አቅርቧል። ማስክ ላልተለመዱ እና ሳይንሳዊ ያልሆኑ አቋሞች እና በጣም ይፋ በሆነ አወዛጋቢ መግለጫዎች ተችቷል። እ.ኤ.አ. በ 2018 ቴስላን በግል ለመቆጣጠር የገንዘብ ድጋፍ እንዳገኘ በውሸት በትዊተር በመላክ በዩኤስ ሴኩሪቲስ እና ልውውጥ ኮሚሽን ተከሷል። በጊዜያዊነት ከሊቀመንበርነቱ በመልቀቅ እና በትዊተር አጠቃቀሙ ላይ ገደቦችን በመስማማት ከ ጋር ተስማማ። እ.ኤ.አ. በ2019፣ በታም ሉአንግ ዋሻ ማዳን ውስጥ ምክር በሰጠው የእንግሊዝ ዋሻ የቀረበለትን የስም ማጥፋት ችሎት አሸንፏል። ማስክ ስለ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨቱ እና እንደ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ክሪፕቶፕ እና የህዝብ ማመላለሻ ባሉ ጉዳዮች ላይ ስላለው ሌሎች አስተያየቶቹ ተችተዋል። የመጀመሪያ ህይወት ልጅነት እና ቤተሰብ ኢሎን ሪቭ ማስክ ሰኔ 28 ቀን 1971 በፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ ተወለደ።[9] እናቱ በሳስካችዋን፣ ካናዳ የተወለደ፣ ነገር ግን በደቡብ አፍሪካ ያደገው ሞዴል እና የአመጋገብ ባለሙያ ማዬ ማስክ ኔኤ ሃልዴማን) ትባላለች። አባቱ ኤሮል ማስክ በደቡብ አፍሪካ የኤሌክትሮ መካኒካል መሐንዲስ፣ ፓይለት፣ መርከበኛ፣ አማካሪ እና የንብረት ገንቢ በአንድ ወቅት በታንጋኒካ ሀይቅ አቅራቢያ የሚገኘው የዛምቢያ ኤመራልድ ማዕድን ማውጫ ግማሽ ባለቤት ነበር። ማስክ ታናሽ ወንድም ኪምባል (የተወለደው 1972) እና ታናሽ እህት ቶስካ (የተወለደው 1974) አለው። የእናቱ አያት ኢያሱ ሃልዴማን በነጠላ ሞተር ቤላንካ አውሮፕላን ወደ አፍሪካ እና አውስትራሊያ አውሮፕላን ውስጥ መዝገብ ሰባሪ ጉዞዎችን በማድረግ ቤተሰቡን የወሰደ ጀብደኛ አሜሪካዊ-የተወለደ ካናዳዊ ነበር። እና ማስክ የብሪቲሽ እና የፔንስልቬንያ ደች ዝርያ አለው። ማስክ ገና ልጅ እያለ ዶክተሮች መስማት የተሳነው መሆኑን ስለጠረጠሩ አዴኖይድስ ተወግዶ ነበር ነገር ግን እናቱ በኋላ ላይ "በሌላ ዓለም" እያሰበ እንደሆነ ወሰነች. ቤተሰቡ በኤሎን ወጣትነት በጣም ሀብታም ነበር; ኤሮል ማስክ በአንድ ወቅት “ብዙ ገንዘብ ነበረን አንዳንድ ጊዜ ደህንነታችንን እንኳን መዝጋት አንችልም” ብሏል። እ.ኤ.አ. ልታስበው የምትችለውን ክፉ ነገር ሁሉ ማለት ይቻላል እርሱ አድርጓል። በአባቱ በኩል ግማሽ እህት እና ግማሽ ወንድም አለው. ኢሎን በወጣትነቱ የአንግሊካን ሰንበት ትምህርት ቤት ገብቷል። በ10 ዓመቱ ማስክ የኮምፒዩተር እና የቪዲዮ ጨዋታዎችን ፍላጎት አዳበረ እና -20 አግኝቷል። የኮምፒዩተር ፕሮግራሚግን በማኑዋል የተማረ ሲሆን በ12 ዓመቱ የተሰኘውን ላይ የተመሰረተ የቪዲዮ ጌም ኮድ ለ እና መፅሄት በ500 ዶላር ሸጠ። ግራ የሚያጋባ እና አስተዋይ ልጅ፣ ማስክ በልጅነቱ ሁሉ ጉልበተኛ ነበር እና አንድ ጊዜ የወንዶች ቡድን ደረጃ ላይ ከጣሉት በኋላ ሆስፒታል ገብቷል። ከፕሪቶሪያ ቦይስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከመመረቁ በፊት የ መሰናዶ ትምህርት ቤት እና ብራያንስተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቷል ትምህርት ከካናዳ ወደ አሜሪካ መግባት ቀላል እንደሚሆን የተረዳው ማስክ በካናዳ በተወለደችው እናቱ በኩል የካናዳ ፓስፖርት ጠየቀ። ሰነዶቹን በመጠባበቅ ላይ እያለ ለአምስት ወራት በፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ ገብቷል; ይህ በደቡብ አፍሪካ ወታደራዊ አገልግሎት ውስጥ የግዴታ አገልግሎት እንዳይሰጥ አስችሎታል. ማስክ በሰኔ 1989 ካናዳ ደረሰ፣ እና በሳስካችዋን ውስጥ ከአንድ ሁለተኛ የአጎት ልጅ ጋር ለአንድ ዓመት ያህል በእርሻ እና በእንጨት ወፍጮ ውስጥ ያልተለመዱ ስራዎችን ኖረ። እ.ኤ.አ. በ 1990 በኪንግስተን ኦንታሪዮ ወደሚገኘው ኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ ገባ። ከሁለት አመት በኋላ ወደ ፔንስልቬንያ ዩኒቨርሲቲ ተዛውሮ በ1995 በፊዚክስ ባችለር ኦፍ አርትስ ዲግሪ እና በኢኮኖሚክስ የሳይንስ ባችለር ዲግሪ አግኝቷል። እ.ኤ.አ. በ 1994 ሙክ በበጋው ወቅት በሲሊኮን ቫሊ ውስጥ ሁለት ልምምዶችን አካሂዷል-በኃይል ማከማቻ ጅምር ፒናክል ምርምር ኢንስቲትዩት ለኃይል ማከማቻ ኤሌክትሮይቲክ አልትራካፓሲተሮችን ያጠናል እና በፓሎ አልቶ ላይ የተመሠረተ ጅምር የሮኬት ሳይንስ ጨዋታዎች። እ.ኤ.አ. በ 1995 በካሊፎርኒያ ውስጥ በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ በቁሳቁስ ሳይንስ የዶክተር ኦፍ ፍልስፍና (ፒኤችዲ) ፕሮግራም ተቀበለ ማስክ በኔትስኬፕ ሥራ ለማግኘት ሞክሮ ነበር ነገርግን ለጥያቄዎቹ ምንም ምላሽ አላገኘም። ከሁለት ቀናት በኋላ ስታንፎርድን አቋርጦ የኢንተርኔት እድገትን ለመቀላቀል እና የኢንተርኔት ጅምር ለመጀመር ወሰነ። የንግድ ሥራ ዚፕ2 እ.ኤ.አ. በ1995 ማስክ፣ ኪምባል እና ግሬግ ኩሪ ከመልአክ ባለሀብቶች በተገኘ ገንዘብ ዚፕ2ን የድር ሶፍትዌር ኩባንያ መሰረቱ። ሥራውን በፓሎ አልቶ ውስጥ በሚገኝ አነስተኛ የተከራይ ቢሮ ውስጥ አስቀመጡት። ኩባንያው የኢንተርኔት ከተማ መመሪያን አዘጋጅቶ ለጋዜጣ አሳታሚ ኢንዱስትሪ፣ ካርታዎች፣ አቅጣጫዎች እና ቢጫ ገፆች አቅርቧል። ማስክ ኩባንያው ውጤታማ ከመሆኑ በፊት አፓርታማ መግዛት ስላልቻለ ቢሮ ተከራይቶ ሶፋ ላይ ተኝቶ ውስጥ ሻወር ማድረጉን እና አንድ ኮምፒዩተር ከወንድሙ ጋር እንደሚጋራ ተናግሯል። እሱ እና ኪምባል በንግድ ውሳኔዎች ላይ መስማማት በማይችሉበት ጊዜ ልዩነቶቻቸውን በትግል መፍታት እንደቻሉ ማስክ “ድረ-ገጹ በቀን ውስጥ ነበር እና እኔ ማታ ማታ በሳምንት ሰባት ቀን ሁል ጊዜ ኮድ እያደረግሁ ነበር” ብለዋል የማስክ ወንድሞች ከኒውዮርክ ታይምስ እና ከቺካጎ ትሪቡን ጋር ውል ወስደዋል እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ጋር የመዋሃድ ዕቅዶችን እንዲተው አሳምነው።ሙስክ በሊቀመንበሩ ሪች ሶርኪን የተያዘው ዋና ስራ አስፈፃሚ ለመሆን ያደረገው ሙከራ በቦርዱ ከሽፏል። ኮምፓክ በየካቲት 1999 ዚፕ2ን በ307 ሚሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ ገዙ እና ማስክ ለ7 በመቶ ድርሻው 22 ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል። እና እ.ኤ.አ. በ 1999 ማስክ በመስመር ላይ የፋይናንስ አገልግሎት እና የኢሜይል ክፍያ ኩባንያ ን በጋራ አቋቋመ። ጅምር በፌዴራል ኢንሹራንስ ከገቡት የመስመር ላይ ባንኮች አንዱ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ የስራ ወራት ከ200,000 በላይ ደንበኞች አገልግሎቱን ተቀላቅለዋል። የኩባንያው ባለሀብቶች ማስክን ልምድ እንደሌለው አድርገው በመቁጠር በዓመቱ መጨረሻ በኢንቱይት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቢል ሃሪስ እንዲተኩ አድርገውታል። በሚቀጥለው አመት፣ ውድድርን ለማስቀረት ከኦንላይን ባንክ ኮንፊኒቲ ጋር ተዋህዷል። በማክስ ሌቭቺን እና በፒተር ቲኤል የተመሰረተው ኮንፊኒቲ ከኤክስ.ኮም አገልግሎት የበለጠ ታዋቂ የነበረው ፒፓል የገንዘብ ማስተላለፊያ አገልግሎት ነበረው ።በተዋሃደው ኩባንያ ውስጥ ማስክ እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተመለሰ። ሙክ የማይክሮሶፍት ሶፍትዌሮችን ከሊኑክስ መመረጡ በድርጅቱ ውስጥ አለመግባባት ፈጠረ እና ቲኤል ስራውን እንዲለቅ አድርጎታል። በቴክኖሎጂ ጉዳዮች እና የተቀናጀ የቢዝነስ ሞዴል ባለመኖሩ ቦርዱ ማስክን በማስወገድ በሴፕቴምበር 2000 በቲኤል ተክቷል። ኢቤይ በ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ክምችት፣ ከዚህ ውስጥ ሙክ 11.72% የአክሲዮን ትልቁ ባለድርሻ -175.8 ሚሊዮን ዶላር አግኝቷል። እ.ኤ.አ. በ 2017 ማስክ ስሜታዊ እሴት እንዳለው በማብራራት የ ን ጎራ ከ ላይ ላልታወቀ መጠን ገዝቷል
15768
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%9B%E1%8A%95%E1%8B%B4%E1%88%8D%E1%89%A5%E1%88%AE%E1%89%B5
ማንዴልብሮት
ቤንዋ ማንዴልብሮት (20 ህዳር 1924 14 ጥቅምት 2010 እ.ኤ.አ) ታዋቂ የ20 ና የ21ኛው ክፍለዘመን ሒሳብ ፈልሳፊና ተመራማሪ ነበር። የፍርክስክስ ጂዖሜትሪ አባት ተብሎ የሚታወቀው ይህ ሰው በዚህ በፈጠረው የሂሳብ ጥናት ዘርፍ ቅጥ የለሽና የተፈረካከሱ የጂዖሜትሪ ቅርጾችን በተለይ ባጎላናቸው (ቀረብ ብለን ባየናቸው ጊዜ ሁሉ) ከራሳቸው ጋር ተመሣሣይነት ያላቸውን ክስተቶችን በሂሳብ እኩልዮሽ ለመግለጽ ችሏል።ማንድልብሮት ፖላንድ አገር ተወልዶ በህጻንነቱ ፈራንሳይ አደገ ኋላም ቀሪ ዘመኑን በአሜሪካን አገር አሳለፈ። የአሜሪካና ፈረንሳይ ዜጋ ነበር። የፍርክስክስ ጂዖሜትሪ መፈጠር ከማንዴል ብሮት መነሳት በፊት የነበረው የሂሳብ ተማሪወች አስተሳሰብ እንዲህ ነበር፡ «በአለማችን ላይ የሚገኙ ቅርጾች እጅግ ውስብስብ፣ የጎረበጡ ፍርክስክስ ያሉና ቅጥ የሌላቸው ስለሆኑ በሂሳብ ቀመር ሙሉ ለሙሉ ለመግለጽ አይቻልም» በዚህ ምክንያት ሂሳብ ተማሪወች ትኩረት ሰጥተው ያጠኑት የነበረው በምናባቸው አስተካክለው ለፈጠሩዋቸው ቅርጾች፣ ለምሳሌ ለክብ፣ ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማዕዘን፣ ፓራቦላ ወዘተ ነበር። እኒህ እንግዲህ በጣም የተስተካከሉ የምናባዊ አለም ፍጥረቶች እንጂ በርግጥም በተፈጥሮ የማይገኙ ናቸው። የማንዴልብሮት ትልቁ ግኝት እንግዲህ ከዚህ ከምናባዊ አለም ወጥተን ወደ ገሃዱ አለም ስንገባ የምናገኛቸውን የተወሳሰቡ ቅርጾችን፣ ለምሳሌ ደመናን፣ ተራሮችን፣ የባህር ወደብን፣ ዛፎችን በሂሳብ ቀመር ማስቀመጫ ዘዴን ማግኘቱና በሂደት ማስተካከሉ ነበር። ይህ ስራው ለዘመናዊው የኬዖስ ጥናት መሰረት ሆነ። የፍርክስክስ ጂዖሜትሪ ጥናት መሰረት ማንዴልብሮት በ1960ወቹ በተሰኘው የአሜሪካን የኮምፒውተር አምራች ኩባንያ ተቀጥሮ ይሰራ ናበር። በዚህ ወቅት ኮምፒውተሮች በሚያደርጉት የመረጃ ልውውጥ ወቅት የሚነሱ ኤሌክትሪክ ረብሻወች ምክንያት አንዱ ኮምፒዩተር ወደ ሌላው የላከው መልዕክት ስህተት ሆኖ ይገኝ ነበር። ምንም እንኳ የስህተቶቹ ተፈጥሮ በጊዜው በሳይንቲስቶች ባይታወቅም ስህተቶቹ ግን ሁልጊዜ የሚፈጠሩ ሳይሆኑ እየተጠራቀሙ በየተወሰኑ የጊዜ ክፍሎች የሚፈጠሩ መሆኑ ተደረሰበት፣ ማለት ለተወሰነ ጊዜ ስህተት የሌለበት ስራ ይሰራና ብዙ ስህተት ያለበት ስራ ደግሞ ለቀጣዩ ጊዜ ይፈጠራል። እኒህን ጥርቅም ስህተቶች በቅርበት ሲመረምር በርግጥም ቅጥ አልባ ከመሆን ይልቅ ንድፍ እንዳላቸው ተገነዘበ። ንድፋቸውም እንዲህ ነበር፡ ሁለት ሰዓት የኮምፒውተሮቹን ልውውጥ ብናስተውል፣ አንዱ ስዓት ምንም ስህተት ሳይኖር ካለፈ መጪው አንድ ሰዓት ደግሞ ስህተት ይኖረዋል። በተጨማሪ ስህተት የተገኘበትን ሰዓት በ20 በ20 ደቂቃ ብንከፍለው እና ብንመለከት፣ አንዱ 20 ደቂቃ ያለ ስህተት ሲያልፍ ቀጣዩ 20 ደቂቃ ስህተት ይይዛል። እንግዲህ ሰዓቶቹን እየከፋፈለ ባጎላ ቁጥር በሁሉም የማጉሊያ ዘርፍ የስህተት አቃፊው ሰዓት መጠን ከስህተት አልባው ይጊዜ መጠን ጋር ያለው ውድር ምንጊዜም ቋሚ እንደሆነ ተገነዘበ። በሌላ አነገጋር የኤሌክትሪኩ ረብሻ በፈለግነው መጠን ባጎላነው ቁጥር እራሱን ደጋሚ መሆኑን አሳየ፣ ማለት እያንዳንዷ ትንሽ ክፍል በጎላች ቁጥር ከሷ በላይ ያለውን የትልቁን ክፍል መልክ/ይዘት/ቅርጽ ትደግማለች። ማንዴልብሮት ይህ "እራስን የመድገም" ባህርይ በሌሎች የተፈጥሮ ክስተቶች እንደሚታይ ማስተዋል ጀመረ። ለምሳሌ የጥጥ ዋጋን በጥንቃቄ ሲመረመር፣ የየቀኑ፣ የየወሩና የየአመቱ የጥጥ ዋጋ ቅጥ አልባ ቢሆንም ነገር ግን የየቀኑ ዋጋ ለውጥ ከየየወሩ የዋጋ ለውጥ እንዲሁም ከየየአመቱ ለውጥ ጋር አንድ አይነት እንደሆነ ለማወቅ ቻለ። የዛፎች ቅጠሎችም ልክ እንዳንጠለጠላቸው ዛፍ ተመሳሳይ ቅርንጫፍ እንዳላቸው በሌላ ወገን ደግሞ የባህር ጠረፎች ላይ የሚስተዋሉት ገባ ብለው ያሉ ሰላጤወች (ወደ ዋናው ምድር ገባ ያሉ ወደቦች) ቀረብ ተብለው ሲታዩ በራሳቸው ላይ እንደገና ገባ ያለ አንስተኛ ሰላጤ ይኖራል ሆኖም እኒህ አንስተኛ ሰላጤወች ቀርበው ሲታዩ ሌሎች አንስተኛ ስላጤወች አሏቸው፣ ወዘተ...። በ1967 ባሳተመው "የብሪታንያ የባህር ጠረፍ ርዝመት ስንት ነው?" በሚለው መጽሃፉ በርግጥም የእንግሊዝ ጠረፍ ህልቁ መሳፍርት ሰላጤወች ያሉትና ርዝመቱ እንደ አትኩረታችን እንደሚለያይ አሳይቷል። የዚህ ምክንያቱ ከላይ ከላዩ እንይ ከተባል ጠረፉን መለካት ቀላል ቢሆንም ቀረብ እያልን ስንሄድ በወደቡ ውስጥ ሰላጤወች እናገኛለን ከዚያ ስንቀርብ በበሰላጤው ውስጥ ሰላጤ እና እያለ ሄዶ በድንጋይ ውስጥ ድንጋይ እናገኛለን በድንጋዩ ውስጥ አሸዋ እያለ ህልቁ መሳፍርት ይጠጋል። ርዝመቱ እንግዲህ በተለምዶ ቢታወቅም በትክክል ግን አይታወቅም። እነዚህን እራሳቸውን የሚደግሙ ክስተቶች እና ሌሎች ተመሳሳይ ንድፎች በነበረው ሂሳብ መግለጽ እንደማይቻል ስላወቀ በቀጣዮቹ አመታት የፍርክስክስ ጂዖሜትሪን ለዚህ ተግባር ፈጠረ። ፍራክታል የሚለውንም የሂሳብ ቃል በ1975 ሰየመ። የዚህ ጥናቱ ውጤት በአንዲት የሂሳብ ቀመር ተጠናቀቀ፣ ይቺ ቀመር የ ማንዴልብሮት ስብስብ በመባል ትታወቃለች። መጽሃፉ ታተመ በ1982 ዓ.ም፣ ከሌሎች የከፍተኛ ሂሳብ ጥናት መጽሃፎች በላይ የተሸጠውን (የተፈጥሮ ፍርክስክስ ጂዖሜትሪ የተባለውን መጽሃፉን አሳተመ። በዚህ መጽሐፉ «ደመና የኳስ ቅርጽ አይደለም፣ ተራሮች የአሎ አሎ ቅርጽ የላቸውም፣ የባህር ጠረፎች ክብ አይደሉም፣ የዛፍ ቅርፊት ለስላሳ ሳይሆን ሸካራ ነው፣ መብረቅ በቀጥተኛ መንገድ አይጓዝም» በማለት በጊዜው የነበረውን የሂሳብና ሳይንስ አስተያየት ተቸ። የድሮው ጂዖሜትሪ ለተፈጥሮ ክስተቶች ምንም ተስማሚ እንዳልነበር ያሳመነው ማንዴልብሮት በመጽሃፉ እንዴት ከላይ የተገለጹት ክስተቶችና የስቶክ ገበያ ዋጋ ልውውጥ፣ የፈሳሾች ንቅንቅ፣ የመሬት እንቅስቃሴወች፣ ምህዋሮች፣ የእንስሣቶች የቡድን ባህርይና ሙዚቃ ሳይቀር በፍርክስክስ ጂዖሜትሪ ናሙናቸው እንዴት እንዲሰራ አስረዳ። ይህ እጅግ ሃይለኛ የሆነ ሂሳብ በአለንበት የኮምፒውተሮች ዘመን የበለጠ ሃይልን ሊጎናጸፍ ቻለ። በአሁኑ ዘመን ፍርክስክስ ጂዖሜትሪን በመጠቀም እውነተኛ ተራሮችን፣ የባህር ወደቦችን፣ ዛፎችን፣ ደመናወችንና የሴል እድግትን በማስመሰል በኮምፒውተር ስዕልና ተንቀሳቃሽ ምስል መስራት ይቻላል። ከዚህ ሌላ የዲጂታል ምስልን ለመጭመቅ፣ ለመኪና ጎማወች በጣም ጥሩ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ለመመራመር፣ ለአውሮፕላን ክንፍ አቅድ ለማውጣት፣ ሃኪም ቤት ሄዶ የሰውነትን ክፍል በራጅ ለማስነሳት ወዘተ... ከፍተኛ ግልጋሎት ይሰጣል። የፈረንሳይ ሰዎች ሒሳብ
13259
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%89%83%20%E1%8C%88%E1%89%A5%E1%88%A8%20%E1%88%90%E1%8A%93
አለቃ ገብረ ሐና
ከህይወት ታሪካቸው ስንጀምር አንዳንዶች የአባታቸው ስም ደስታ ተገኝ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ገብረ ማርያም ነው ይላሉ። ምናልባት አንዱ የአለም ሌላው ደግሞ የክርስትና ስማቸው ሊሆን ይችላል። የተወለዱት በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በድሮው የደብረታቦር አውራጃ ፎገራ ወረዳ፤ ናብጋ ጊዮርጊስ በተባለው ቦታ በ1814 ዓ.ም. ነው። የመጀመርያ ትምህርታቸውን በአካባቢው ከቀሰሙ በኋላ ወደ ጎጃም ተሻግረው ቅኔን ተቀኙ። ከዚያም ወደ ጎንደር ከተማ ተመልሰው ከመምሕር ወደ አብ ወልደ ማርያም ጽዋትወ ዜማ፤ ከባሕታዊ ገብረ አምላክ አቋቋም፤ ከዐቃቤ ስብሃት ገብረ መድሕን ትርጓሜ መጽሐፍትን እንዲሁም ድጓን ተምረዋል። በእዚህ የሰፋ እውቀታቸው የተነሣ በ26 ዓመታቸው ጎንደር ሊቀካህናትነት ተሾመው ነበር። በዚህም ሹመት ለሰባት ዓመት ማገልገላቸው ይነገራል። በፍትሐ ነገሥት ሊቅነታቸው ደግሞ በዳኝነት እየተሰየሙ አገልግለዋል። አለቃ ገብረ ሐና ጨዋታ አዋቂነታቸው እየታወቀ የመጣው በዚህ ወቅት ነበር። በዚህም እውቀታቸው የትንሹ ዓሊ አጫዋች ሆኑ። አጼ ቴዎድሮስ ሥልጣኑን ሲይዙ አለቃን በቤተ መንግሥት አገኟቸው። አለቃ የቤተ መንግሥቱን ሰዎች በቀልዳቸው ሸንቆጥ ስለሚያደርጉ መስማማት አልቻሉም ነበር። እንዲያውም ዐጼ ቴዎድሮስ «ገብረ ሐና ፍትሐ ነገስቱን ጻፍ፤ ፍርድ ስጥ ገንዘብ ያውልህ፤ ቀልድህን ግን ተወኝ።» ሲሉ ተናግረዋቸው ነበር ይባላል። አለቃ ግን አላቆሙም። በተለይም ደግሞ በንጉሡ ባለሟል በብላታ አድጎ ላይ «አድግ በግእዝ አህያ ማለት ነው እያሉ በሚሰነዝሩት ትችት በተደጋጋሚ ተከሰው ዐጼ ቴዎድሮስ ዘንድ ቀርበዋል። በመጨረሻ ቴዎድሮስ ክስ ሲሰለቻቸው ምላስ ቀርቶ ታገሉና ተሸናነፉ ብለው ፈረዱ። በዚህም ትግል ምሁሩ አለቃ ተሸነፉ። ንጉሡም እንግዲህ ምን ይበጅህ? ሲሉ ጠየቋቸው አለቃም «ድሮስ ትግል የአህያ ሥራ አይደል» ብለው በመመለሣቸው ከአካባቢያቸው ለማራቅ ሲሉ ንጉሡ ገብረ ሐናን ለትግራይ ጨለቆት ሥላሴ አለቃ አድርገው በመሾም ወደ ትግራይ ላኳቸው። ወደካቶሊክነት የተቀየረውና ከአንቷን ዳባዲ ጋር በዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን ስለሆነው ሁሉ ደብዳቤ ይለዋወጥ የነበረው የዋድላው ሰው ደብተራ አሰጋኽኝ ጥር 1858 ዓ.ም. ለአንቷን ዳባዲ በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ በማለት ይህን ሁኔታ ገልጦት ነበር «አለቃ ገብረ ሐናን ንጉሥ መቱዋቸው። ወደ ትግሬ ወደ ላስታ ተሰደዱ። እጅግ ተዋረዱ እኔም በዋድላ አገኘኋቸው ወደ ቆራጣም ሄዱ» ሲል ጽፏል። ደስታ እንዳለ ሁሉ መከራም ያለ ስለሆነ ሁለቱንም በጸጋ መቀበል የሰው ልጅ ሁሉ ግዴታ ነው። ካህናት በአጼ ቴዎድሮስ ላይ ባመጹ ጊዜ በአድማው ካሉበት ካህናት መካከል አንዱ ገብረ ሐና መሆናቸው ስለታወቀ ዐጼ ቴዎድሮስ በአለቃ ገብረ ሐና ላይ አምርረው ሊቀጧቸው ዛቱ። አለቃም ሸሽተው ጣና ሐይቅ ሬማ መድኃኔዓለም ገዳም ገቡ። በዚያም ባሕታዊ ጸዐዳ ገብረ ሥላሴ የተባሉ የአቋቋም ሊቅ አገኙ። ሁለቱም ተወያይተው በጎንደር አቋቋም ስልት የመቋሚያውን የአካል እንቅስቃሴ ጨምረው ዝማሜውን አዘጋጁት (በኋላ ተክሌ አቋቋም እየተባለ የሚታወቀው ነው)። ባህታዊ ጸዐዳ «ከእንግዲህ እኔ ወደ ዓለም አልመለስም፤ አንተ ይህንን ስልት አስተምር» ብለው አለቃ ገብረሐናን አደራ አሏቸው። ከዐጼ ቴዎድሮስ ሞት በዃላ በ1864 ዓ.ም. ዐጼ ዮሐንስ ሲነግሡ ከገዳም ወጥተው ወደ ትግራይ አቀኑ። በመቀጠልም በቴዎድሮስ ቤተመንግሥት ሳሉ የሚያውቋቸው ምኒልክ በሸዋ መንገሣቸውን ተከትለው ሸዋ መጡ። ዓፄ ምኒልክ በዓፄ ቴዎድሮስ ቤተመንግሥት ሳሉ አለቃ ገብረ ሐናን ስለሚያውቋቸው በደቡብ ጎንደር የሚገኘውን የአቡነ ሐራን ገዳም ሾሟቸው። በዚያም ጊዜ በአካባቢው ከባድ ርሃብ በመከሠቱ አለቃ ከገዳሙ ብር አንድ ሺ አውጥተው ለገበሬዎች አከፋፈሏቸው። በዚህም ተግባራቸው ተከስሰው ወደ አዲስ አበባ መጡ። የፍርድ ሚኒስቴር የነበሩት አፈ ንጉሥ ነሲቡ ስሕተት ነው ብለው ፈርደውባቸው ነበር። ነገር ግን ጉዳዩ በምኒልክ ዘንድ ስለተሰማ ወደ ዙፋኑ ችሎት ተሻገረ። ዐጼ ምኒልክም ይህ ተግባር ያሸልማል እንጂ አያስቀጣም ብለው በመፍረዳቸው አለቃ ነጻ ወጡ። ንጉሥ ምኒልክ አለቃን የእንጦጦ ራጉኤል አለቃ አድርገው ሾሟቸው። እርሳቸውም ትርጓሜ መጻሕፍትን ያስተምሩ ነበር። ጥቂት ጊዜ በአዲስ አበባ እንደ ተቀመጡ እንደገና ወደ ጎንደር ተመልሰው፤ ድንግልናቸውን አፍርሰው ወይዘሮ ማዘንጊያን አገቡና ተክሌ የተባለ አንድ ወንድ ልጅና በፍታ የተባለች ሴት ልጅ ወለዱ። አንዳንድ ሊቃውንት አለቃ ገብረ ሐና ሊቅ፤ መልከመልካምና የነገሥታቱ ወዳጅ በመሆናቸው በዚያ ዘመን የነበሩ ሴቶች ወዳጅነት ለማበጀት ይሻሙባቸው ነበር ይላሉ። አለቃ ድንግልናቸውን ያፈረሱት ሆን ብለው ሳይሆን እኔ አስፈርሰዋለሁ በሚል የወይዛዝርት ውድድር የተነሣ ነው ይባላል። የአለቃ መንፈሳዊ ሕይወት የተናጋው ከዚያ በዃላ ነው ይባላል። ተክሌ ለትምህርት ሲደርስ ከሌላው የቤተክርስቲያን ትምህርት ጋር እርሳቸው ከባሕታዊ ጸዐዳ ገብረ ሥላሴ ጋር ሆነው ያዘጋጁትን ዝማሜ አስተማሩት። አለቃ ገብረ ሐና ደርቡሽ ጎንደርን ሲወርር ልጃቸውን ወደ ወሎ ልከው እርሳቸው ጎጃም ውስጥ ዘጌ ገዳም ገቡ። በዃላም ዐጼ ምኒልክ ደርቡሽን ለመውጋት ወደ ፎገራ መምጣታቸውን ሲሰሙ፤ ከተደበቁበት ወጥተው ንጉሡን ተከትለው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ምኒልክም እንደገና የራጉኤል አለቃ አድርገው ሾሟቸው። ልጃቸው አለቃ ተክሌ ወሎ ንጉሥ ሚካኤል ዘንድ እያሉ የተንታ ሚካኤል በዓል ሲከበር ከአባታቸው የተማሩትን ዝማሜ በተመስጦ አቀረቡት። ንጉሥ ሚካኤልም በዚህ ተደንቀው በዚያው በተንታ እንዲያገለግሉ አደረጉ። የተክሌ ዝማሜ በይፋ የተጀመረው ያኔ ነው ይባላል። በዃላ ራስ ጉግሣ የአለቃ ተክሌን ዝና ሰምተው ንጉሥ ሚካኤልን በማስፈቀድ ወደ ደብረ ታቦር አምጥተው የኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሾሟቸው። አለቃ በአዲስ አበባ እያሉ ከመኳንንቱ ከመሳፍንቱ ጋር ያላስማሟቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ። የመጀመርያው ትንባሆ ይጠጣሉ ተብሎ የተነገረው ሐሜት አንድ ቀን በቅኔ ማኅሌት ፒፓቸው ወድቆ በመጋለጣቸው ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአድዋ ጦርነት ታላቅ ጀብዱ ለፈጸሙት ለደጃዝማች ባልቻ ዐጼ ምኒልክ የሚወዷትን ጎራዴያቸውን ሲሸልሟቸው «ወይ ጎራዴ ወይ ጎራዴ ከቤቷ ገባች» በማለት በሽሙጥ በመናገራቸው ባልቻ እገላለሁ ብለው ተነሡ። ይህም አልበቃ ብሏቸው ከእቴጌ ጣይቱ ጋር በነገር ተኳረፉና መላ የቤተመንግሥቱ ሰው አደመባቸው። ዐጼ ምኒልክ አለቃን ምን ቢወዷቸው በተለይ ከደጃች ባልቻና እቴጌ ጣይቱ ጋር የፈጠሩትን ጠብ አልወደዱላቸውም። በዚህ ምክንያት አለቃ ገብረ ሐና ከአዲስ አበባ ለቅቀው እንዲወጡ ተወሰነባቸው። በጎንደርና በወሎ ጥቂት ጊዜ ከሰነበቱ በዃላ ልጃቸውን ገብረ ሐና ሞተ ብለህ ተናገር ብለው አዲስ አበባ ላኩት። አለቃ ተክሌ ይህንን መርዶ በቤተመንግሥቱ ሲያረዱ ምንም እንኳ ገብረ ሐና ከብዙዎቹ ጋር ቢኳረፉም ታላቅ ሐዘን ሆነ። ከተወሰኑ ቀናት በዃላ አለቃ ራሳቸው አዲስ አበባ ገቡና ጉድ አሰኙ። ምኒልክም አስጠርተው ሞቱ ከተባለው በዃላ ከየት መጡ ቢባሉ «በሰማይ ጣይቱ የለች፤ ምኒልክ የለ፤ ጠጅ የለ፤ ጮማ የለ፤ ባዶ ቤት ቢሆንብኝ ለጠባቂው ጉቦ ሰጥቼ መጣሁ።» ብለው ሁሉንም አሳቋቸው። ጣይቱም መኳንንቱም ይቅር አሏቸው። አለቃ ገብረ ሐና እድሜያቸው እየገፋ አደብም እየገዙ መጡ አዲስ አበባ ተቀምጠውም ትርጓሜ መጽሐፍት ማስተማር ቀጠሉ። ዐጼ ምኒልክ የአብያተ ክርስቲያናቱን የግብዝና መሬት ለመኳንንቱ በመስጠታቸው ካህናቱ ምንም ባለ ማግኘታቸው የተቆጡት አለቃ ገብረ ሐና ተቃውሟቸውን በቀልድ ለዐጼ ምኒልክ አቀረቡ። ይህም ከወይዛዝርቱና ከመኳንንቱ ጋር መልሶ አጋጫቸው። ከዚህ በዃላ አዲስ አበባ መቀመጥ ስላልቻሉ ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ደብረ ታቦር ተመለሱ። ያኔ ልጃቸው አለቃ ተክሌ ደብረ ታቦር ኢየሱስን እልቅና ተሾመው ነበር። ለጥቂት ቀናት ደብረ ታቦር ከልጃቸው ጋር ሰንብተው ወደ ትውልድ ቦታቸው ናባጋ ጊዮርጊስ መጡ። በእድሜያቸው መጨረሻ ዝምተኛ ሆነው ነበር ቀድሞ በሠሩት ሥራ እየተጸጸቱ አንደበታቸውን ከነገር ዘርቅ ከለከሉ። ከጥሩ ምግብና ከጥሩ መጠጥ ተቆጠቡ። ቅዱሳን መጻሕፍትን ሰብስበው «መሳቂያና መሳለቂያ አደረግዃችሁ» እያሉ ይቅርታ ይጠይቁ ነበር ይባላል። በዚህ ሁኔታ ከሰነበቱ በዃላ በ84 ዓመታቸው የካቲት 1898 ዓ.ም. ዐረፉ። አለቃ ገብረ ሐና በብዙ ሰዎች ዘንድ በቀልደኝነታቸው ይታወቁ እንጂ በቤተክርስቲያን ታሪክ ወደር ከማይገኝላቸው ሊቃውንት አንዱ ነበሩ። አለቃ ለማ ኃይሉ (የደራሲ መንግስቱ ለማ አባት) ሰለ አለቃ ገብረ ሃና ሊቅነት ሲናገሩ የሞያ መጨረሻ እርሳቸው አይደሉም ወይ የሐዲስ መምህር ናቸው። የፍትሐ ነገስት መምህር ናቸው። መርሐ እውሩን፤ አቡሻሩን የሚያውቁ ባለሙያ ናቸው። ለዚህ ለዝማሜ እሚባለው ለመቋሚያ እገሌ ይመስለዋል አይባልም። ከገብረ ሐና ፊት የሚዘም የለም።» ብለዋል። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴም «አለቃ ገብረ ሐና እጅግ የተማሩ የጎንደር ሊቅ ነበሩ። በዚህም በላይ ኃይለ ቃልና ጨዋታ ያውቁ ነበር» በማለት ይገልጿቸዋል። (ምንጭ (ዚና ሰኔ 1999)) ።በ1998 ዚና እንዳጻፈው ደግሞ አለቃ ገብረ ሃና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቅ ሲሆኑ አቋቋምና ዜማ ቅኔ ከእነ አግባቡ የሚያውቁ እንደነበሩ ታሪካቸው ያስረዳል። አለቃ ባልሳሳት የነበሩበት በአጼ ምንይልክ ዘመን ይመስለኛል። በቅርቡ የሳቸውንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሊቃውንት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ የታተመ ስለኆነ ስለሳቸውም ኆነ ስለሌሎች ባለ ታሪኮች ጥሩ ግንዛቤ ይኖረናል እላለሁ። አሳታሚው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ (ዳንኤል አበራ፣ 2000 ዓ.ም.) ኢትዮጵያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ
15803
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%AD%E1%88%B0%E1%8A%93%E1%88%8D%20%E1%8B%A8%E1%8A%A5%E1%8C%8D%E1%88%AD%20%E1%8A%B3%E1%88%B5%20%E1%8A%AD%E1%88%88%E1%89%A5
አርሰናል የእግር ኳስ ክለብ
አርሰናል በሆሎ መንገድ፤ ሰሜን ለንደን ውስጥ የሚገኝ አለም አቀፍ ክለብ ነው። ይህ ክለብ በእንግሊዝ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን በዚህም 13 የፕሪሚየር ሊግ እና 14 የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎችን አግኝቷል።ይህ መጣጥፍ መቀመጫውን እንግሊዝ ስላለው የወንዶች እግር ኳስ ክለብ ነው። ለሴቶች ቡድን አርሴናል ደብሊውኤፍ.ሲ. አርሴናል ለሚባሉ ሌሎች ቡድኖች፣ አርሴናል (ዲሳምቢጉሽን) የማህበር እግር ኳስን ይመልከቱ። አርሰናል ሙሉ ስም አርሰናል እግር ኳስ ክለብ[1] ቅጽል ስም (ዎች) አጭር ስም አርሴናል ኦክቶበር 1886 ተመሠረተ። ከ136 ዓመታት በፊት፣ እንደ የምድር ኤሚሬትስ ስታዲየም አቅም 60,704 ባለቤት ስፖርት እና መዝናኛ ስራ አስኪያጁ ማይክል አርቴታ ሊግ ፕሪሚየር ሊግ 2021–22 ፕሪሚየር ሊግ፣ 5ኛ ከ20 የድር ጣቢያ ክለብ ድር ጣቢያ የቤት ቀለሞች የርቀት ቀለሞች ሦስተኛው ቀለሞች የአሁኑ ወቅት የአርሴናል መምሪያዎች የወንዶች እግር ኳስ የሴቶች እግር ኳስ የወንዶች አካዳሚ የሴቶች አካዳሚ የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ በኢስሊንግተን፣ ለንደን የሚገኝ የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ክለብ ነው። አርሰናል የሚጫወተው በእንግሊዝ እግር ኳስ ከፍተኛ ሊግ በሆነው በፕሪምየር ሊግ ነው። ክለቡ 13 የሊግ ዋንጫዎችን (አንድ ያለመሸነፍ ዋንጫን ጨምሮ)፣ ሪከርድ 14 የኤፍኤ ካፕ፣ ሁለት ሊግ ካፕ፣ 16 ኤፍኤ ኮሚኒቲሺልድ፣ አንድ የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዎች ዋንጫ እና አንድ የኢንተር-ሲቲዎች ትርኢት ዋንጫዎችን አንስቷል። ዋንጫ በማሸነፍ ረገድ በእንግሊዝ እግር ኳስ ሶስተኛው ክለብ ነው። እ.ኤ.አ. በ1893 ከደቡብ እንግሊዝ የመጣ የመጀመሪያው ክለብ አርሰናል ሲሆን በ1904 አንደኛ ዲቪዚዮን ደረሰ። አንድ ጊዜ ብቻ ሲወርድ በ1913 በከፍተኛ ዲቪዚዮን ረጅሙን ጉዞ ቀጥሏል [2] አሸንፏል። በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ሁለተኛው ከፍተኛ በረራዎች።[3] እ.ኤ.አ. በ1930ዎቹ አርሰናል አምስት የሊግ ሻምፒዮና እና ሁለት የኤፍኤ ካፕ እና ሌላ የኤፍኤ ካፕ እና ሁለት ሻምፒዮናዎችን ከጦርነቱ በኋላ አሸንፏል። በ1970–71 የመጀመሪያውን ሊግ እና የኤፍኤ ካፕ ድርብ አሸንፈዋል። በ1989 እና 2005 መካከል፣ ሁለት ተጨማሪ ድርብ ዋንጫዎችን ጨምሮ አምስት የሊግ ዋንጫዎችን እና አምስት የኤፍኤ ዋንጫዎችን አሸንፈዋል። 20ኛውን ክፍለ ዘመን በከፍተኛ አማካይ የሊግ ቦታ አጠናቀዋል።[4] በ1998 እና 2017 መካከል አርሰናል ለአስራ ዘጠኝ ተከታታይ የውድድር ዘመናት ቻምፒየንስ ሊግ ማለፍ ችሏል። ኸርበርት ቻፕማን የአርሰናልን ሀብት ለዘለአለም የለወጠው ክለቡን የመጀመሪያውን የብር ዕቃ አሸንፏል እና ትሩፋቱ ክለቡን በ1930ዎቹ አስርት አመታት እንዲቆጣጠር አድርጎታል። ነገር ግን ቻፕማን በ1934 በሳንባ ምች ህይወቱ አለፈ። በ55 ዓመቱ የደብሊውኤም ምስረታን፣ የጎርፍ መብራቶችን እና የሸሚዝ ቁጥሮችን ለማስተዋወቅ ረድቷል፣ [5] በተጨማሪም ነጭ እጀ እና ቀይ ቀዩን በክለቡ ማሊያ ላይ ጨመረ።[6] አርሰን ቬንገር ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ አሰልጣኝ ሲሆኑ ብዙ ዋንጫዎችንም አሸንፈዋል። ሰባት የኤፍኤ ካፕ ዋንጫዎችን በማንሳት ሪከርድ ያስመዘገበ ሲሆን የዋንጫ አሸናፊ ቡድኑ በ2003 እና 2004 መካከል በተደረጉ 49 ጨዋታዎች ያለ ሽንፈት በእንግሊዝ ሪከርድ አስመዝግቧል፤ ይህ የማይበገር ቅፅል ስም አግኝቷል። እ.ኤ.አ. በ 1886 በዎልዊች ውስጥ በሚገኘው የሮያል አርሴናል ውስጥ የጦር መሳሪያ ሰራተኞች ክለቡን እንደ መሰረቱት። እ.ኤ.አ. በ 1913 ክለቡ ከተማዋን አቋርጦ ወደ አርሰናል ስታዲየም ሀይበሪ በመሄድ የቶተንሃም ሆትስፐር የቅርብ ጎረቤት በመሆን የሰሜን ለንደን ደርቢን ፈጠረ። እ.ኤ.አ. በ 2006 በአቅራቢያው ወደሚገኘው ኤሚሬትስ ስታዲየም ተዛውረዋል። በ2019–20 የውድድር ዘመን በ አመታዊ ገቢ፣[7] አርሰናል በፎርብስ 2.68 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው ተገምቷል፣ይህም ከአለም ስምንተኛው እጅግ ውድ ክለብ ያደርገዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ። የክለቡ መሪ ቃል ቪክቶሪያ ኮንኮርዲያ ክሬሲት በላቲን "በሃርሞኒ ድል" ነው።ታሪክ ተጨማሪ መረጃ፡ የአርሰናል ኤፍ.ሲ ታሪክ (1886–1966)፣ የአርሰናል ኤፍ.ሲ. ታሪክ (1966-አሁን) እና የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ሙዚየም 1886–1919፡ ከዲያል አደባባይ ወደ አርሰናል የሮያል አርሰናል ቡድን በ1888 ኦሪጅናል ካፒቴን ዴቪድ ዳንስኪን በአግዳሚ ወንበር በስተቀኝ ተቀምጧል። በጥቅምት 1886 ስኮትላንዳዊው ዴቪድ ዳንስኪን እና በዎልዊች ውስጥ አስራ አምስት የጦር መሳሪያ ሰራተኞች በሮያል አርሴናል ኮምፕሌክስ እምብርት ላይ ባለው አውደ ጥናት የተሰየመውን የዲያል ስኩዌር እግር ኳስ ክለብ አቋቋሙ። እያንዳንዱ አባል ስድስት ሳንቲም አበርክቷል እና ዳንስኪን ክለቡን ለመመስረትም ሶስት ሽልንግ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በታህሳስ 11 ቀን 1886 ከምስራቃዊ ዋንደርደርስ ጋር ተጫውተው 6–0 አሸንፈዋል።[14] ክለቡ ከአንድ ወር በኋላ ወደ ሮያል አርሰናል ተቀየረ፣[13][15] እና የመጀመሪያ መኖሪያው ፕሉምስቴድ ኮመን ነበር፣[13] አብዛኛውን ጊዜያቸውን በማኖር ግራውንድ በመጫወት ያሳለፉ ቢሆንም። የመጀመሪያዎቹ ዋንጫዎቻቸው የኬንት ሲኒየር ካፕ እና የለንደን በጎ አድራጎት ዋንጫ በ1889–90 እና በ1890–91 የለንደን ሲኒየር ካፕ ነበሩ። በደቡብ ምስራቅ ለንደን አርሴናል ያሸነፈባቸው የካውንቲ ማህበር ብቸኛ ዋንጫዎች እነዚህ ነበሩ።[16][17] በ1891 ሮያል አርሰናል ወደ ፕሮፌሽናልነት የተለወጠ የመጀመሪያው የለንደን ክለብ ሆነ።[18] ሮያል አርሰናል እ.ኤ.አ. የመጀመርያው የደቡብ እግር ኳስ ሊግ አባል ከሁለተኛ ዲቪዚዮን ጀምሮ ወደ አንደኛ ዲቪዚዮን በ1904 ዓ.ም ደረሰ።በጦር መሣሪያ ሰራተኞች መካከል ባለው የገንዘብ ችግር እና በከተማው ውስጥ ሌሎች ተደራሽ የእግር ኳስ ክለቦች በመምጣታቸው ምክንያት የተሰብሳቢዎች ውድቀት ክለቡን መርቷል። በ1910 ለኪሳራ ተቃርቧል።[21][20]፡ 112–149 ነጋዴዎች ሄንሪ ኖሪስ እና ዊልያም ሆል በክለቡ ውስጥ ተሳታፊ ሆኑ እና ወደ ሌላ ቦታ ሊዘዋወሩ ፈለጉ።[22][20]፡ 22–42 እ.ኤ.አ. በ1913 ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ከተመለሰ ብዙም ሳይቆይ ክለቡ ወንዙን ተሻግሮ ወደ አዲሱ የአርሰናል ስታዲየም ሀይበሪ ተዛወረ።[23][24][25] እ.ኤ.አ. በ1919 እግር ኳስ ሊግ አርሰናልን ከ 1914–15 ከጦርነት በፊት በነበረው የመጨረሻ የውድድር ዘመን አምስተኛ ደረጃን ቢይዝም ወደ ቀድሞው የሀገር ውስጥ ተቀናቃኝ ቶተንሃም ሆትስፑርን ወደ አዲስ ትልቅ ዲቪዚዮን እንዲቀላቀሉ ለማድረግ ድምጽ ሰጥቷል። በዚያው አመት በኋላ አርሰናል ዛሬ በአጠቃላይ እንደሚታወቀው ቀስ በቀስ ስሙን ወደ አርሰናል ለመጨረሻ ጊዜ ን በኦፊሴላዊ ሰነዶች መጣል ጀመረ።[26] 1919–1953፡ የእንግሊዝ ባንክ ክለብ የሄርበርት ቻፕማን የነሐስ ጡጫ በኤምሬትስ ስታዲየም ውስጥ ቆሟል። በአዲስ ቤት እና አንደኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ፣ የተሰብሳቢዎች ብዛት በማኖር ግራውንድ ከእጥፍ በላይ ነበር፣ እና የአርሰናል በጀት በፍጥነት አድጓል።[27][28] ቦታቸው እና ሪከርድ የሰበረ ደሞዝ እ.ኤ.አ. በሚቀጥሉት አምስት አመታት ቻፕማን አዲስ አርሰናል ገነባ። ዘላቂ የሆነ አዲስ አሰልጣኝ ቶም ዊትታከርን ሾመ፣[31] የቻርሊ ቡቻንን አዲስ ጅምር ምስረታ ላይ ተግባራዊ አድርጓል፣[32][33] እንደ ክሊፍ ባስቲን እና ኤዲ ሃፕጉድ ያሉ ወጣት ተጫዋቾችን ማረከ እና የሃይቤሪን ገቢ እንደ ዴቪድ ጃክ እና አሌክስ ባሉ ኮከቦች ላይ አወድሷል። ጄምስ ሪከርድ በመስበር ወጪ እና የበር ደረሰኞች አርሰናል በፍጥነት የእንግሊዝ ባንክ ክለብ በመባል ይታወቃል።[34][35] የቻፕማን አርሰናል በ1930 የኤፍኤ ዋንጫ እና የሊግ ሻምፒዮና በ1930–31 እና 1932–33 አሸንፏል።[36] ቻፕማን ከሜዳው ውጪ የሆኑ ለውጦችን መርቷል፡ ነጭ እጅጌዎች እና የሸሚዝ ቁጥሮች በመሳሪያው ላይ የቲዩብ ጣቢያ በክለቡ ስም ተሰይሟል፡[40][41] እና ከሁለቱ ባለጸጋዎች የመጀመሪያው የአርት ዲኮ ማቆሚያዎች ተጠናቀቀ። በእንግሊዝ እግር ኳስ ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ የጎርፍ መብራቶች ጋር።[28] በ1933–34 የውድድር ዘመን አጋማሽ ላይ ቻፕማን በሳንባ ምች ሞተ።[42] ስራው በ1933–34 እና 1934–35 አርእስቶች ባርኔጣ ላዩ እና ከዚያም የ1936 ኤፍኤ ዋንጫ እና 1937–38 ዋንጫን ላዩት ለጆ ሻው እና ለጆርጅ አሊሰን ተወ። ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማለት የእግር ኳስ ሊግ ለሰባት ዓመታት ታግዷል፣ አርሰናል ግን ከጦርነቱ በኋላ በሁለተኛው የውድድር ዘመን፣ 1947–48 አሸንፎ ተመለሰ። ይህ የቶም ዊትከር አሰልጣኝ ሆኖ የመጀመርያው የውድድር ዘመን ነበር፣ አሊሰንን ለመተካት ካደገ በኋላ፣ እና ክለቡ የእንግሊዝ ሻምፒዮንነቱን ሪከርድ አቻ አድርጓል። እ.ኤ.አ. በ1950 ሶስተኛ የኤፍኤ ዋንጫን አሸንፈዋል እና በ1952–53 ሪከርድ የሰበረ ሰባተኛ ሻምፒዮና አሸንፈዋል።[43] ሆኖም ጦርነቱ በአርሰናል ላይ ጉዳት አድርሷል። ክለቡ ከየትኛውም ከፍተኛ የበረራ ክለብ የበለጠ ተጫዋቾች ተገድለዋል፣[44] እና የሰሜን ባንክ ስታንድ እንደገና በመገንባት እዳ የአርሴናልን ሃብት አበላሽቷል።[45][28] 1953–1986፡ መካከለኛነት፣ ሚ እና ኒል አላን ቦል (በስተግራ) እና በርቲ ሚ (እ.ኤ.አ. በ 1971 አርሴናልን የመጀመሪያውን ድርብ የመሩት) በ1972 ፎቶ አርሰናል ለተጨማሪ 18 አመታት የሊጉን እና የኤፍኤ ዋንጫን ማሸነፍ አልነበረበትም። የ 53 ቻምፒዮንስ ቡድን አርጅቶ ነበር እና ክለቡ ጠንካራ ተተኪዎችን ማምጣት አልቻለም።[46] ምንም እንኳን አርሰናል በእነዚህ አመታት ውስጥ ተፎካካሪ የነበረ ቢሆንም ሀብታቸው እየቀነሰ ነበር; ክለቡ አብዛኛውን የ1950ዎቹ እና 1960ዎቹን በመካከለኛው የጠረጴዛ መካከለኛነት አሳልፏል።[47] የቀድሞ የእንግሊዝ ካፒቴን ቢሊ ራይት እንኳን ክለቡን ማምጣት አልቻለምአርሰናል ለተጨማሪ 18 አመታት የሊጉን እና የኤፍኤ ዋንጫን ማሸነፍ አልነበረበትም። የ 53 ቻምፒዮንስ ቡድን አርጅቶ ነበር እና ክለቡ ጠንካራ ተተኪዎችን ማምጣት አልቻለም።[46] ምንም እንኳን አርሰናል በእነዚህ አመታት ውስጥ ተፎካካሪ የነበረ ቢሆንም ሀብታቸው እየቀነሰ ነበር; ክለቡ አብዛኛውን የ1950ዎቹ እና 1960ዎቹን በመካከለኛው የጠረጴዛ መካከለኛነት አሳልፏል።[47] በ1962 እና 1966 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ የቀድሞ የእንግሊዝ ካፒቴን ቢሊ ራይት ክለቡን በአሰልጣኝነት ምንም አይነት ስኬት ማምጣት አልቻለም።[48] አርሰናል በ1966 የክለብ ፊዚዮቴራፒስት በርቲ ሚ ተጠባባቂ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ።[49][50] ከአዲሱ ረዳት ዶን ሃው እና እንደ ቦብ ማክናብ እና ጆርጅ ግርሃም ካሉ አዳዲስ ተጫዋቾች ጋር ሜ አርሰናልን በ1967–68 እና 1968–69 የመጀመሪያውን የሊግ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታቸውን አሳትፏል። የሚቀጥለው የውድድር ዘመን ጥሩ ውጤት አስመዝግቧል፣ በአርሰናል የመጀመሪያ ፉክክር የአውሮፓ ዋንጫ፣ የ1969–70 የኢንተር ከተማ ትርኢት ዋንጫ። በዚህ የውድድር ዘመን፣ አርሰናል በመጀመሪያው ሊግ እና ኤፍኤ ካፕ ድርብ እና አዲስ የእንግሊዝ ሻምፒዮንነት ክብረወሰን በማስመዝገብ የበለጠ ድል አስመዝግቧል።[51] ይህ አስርት ዓመታት ያለጊዜው ከፍተኛ ነጥብ አመልክቷል; ድርብ አሸናፊው ቡድን ብዙም ሳይቆይ ተበተነ እና ቀሪዎቹ አስርት አመታት በተከታታይ ናፍቆት ተቃርበዋል፣ አርሰናል በ1972 የኤፍኤ ካፕ 2ኛ በመሆን ያጠናቀቀ ሲሆን በ1972–73 አንደኛ ዲቪዚዮን በመሆን አጠናቋል።[50] በ1976 የቀድሞ ተጫዋች ቴሪ ኒል ሚይን ተክቶ በ34 አመቱ እስከ ዛሬ ትንሹ የአርሰናል አሰልጣኝ ሆነ።[52] እንደ ማልኮም ማክዶናልድ እና ፓት ጄኒንዝ ባሉ አዳዲስ ፈራሚዎች እና በጎን እንደ ሊም ብራዲ እና ፍራንክ ስታፕልተን ያሉ ተሰጥኦዎችን በማፍራት ክለቡ ሶስት የኤፍኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታዎችን (1978 ኤፍኤ ካፕ 1979 የኤፍኤ ዋንጫ እና 1980 ኤፍኤ ካፕ) ተሸንፏል። የ1980 የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዎች ዋንጫ ፍፃሜ በቅጣት። በዚህ ወቅት የክለቡ ብቸኛው ዋንጫ የ1979 የኤፍኤ ዋንጫ ሲሆን በመጨረሻ ደቂቃ ማንቸስተር ዩናይትድን 3–2 በማሸነፍ የፍፃሜ ውድድር በብዙዎች ዘንድ እንደ ክላሲክ ተወስዷል።[53][54] 1986–1996፡ የጆርጅ ግርሃም ቶኒ አዳምስ ሃውልት ከኤምሬትስ ስታዲየም ውጪ ከሜ ድርብ አሸናፊዎች አንዱ የሆነው ጆርጅ ግራሃም በ1986 ወደ አሰልጣኝነት ተመለሰ፣ አርሰናል በ1987 የግራሃምን የመጀመርያ የውድድር ዘመን የመጀመርያውን የሊግ ዋንጫ በማንሳት ተመለሰ። አዲስ ፈራሚዎቹ ኒጄል ዊንተርበርን፣ ሊ ዲክሰን እና ስቲቭ ቦውልድ በ1988 ክለቡን የተቀላቀሉት በሃገሩ ተጫዋች ቶኒ አዳምስ የሚመራው “ታዋቂውን የኋላ ፎር” ለማጠናቀቅ ነበር።[55] ወዲያውኑ የ1988ቱን የእግር ኳስ ሊግ የመቶ አመት ዋንጫ አሸንፈዋል እና በ1988–89 የእግር ኳስ ሊግ ዋንጫን ተከትለው በመጨረሻው ደቂቃ ጎል ነጥቀው በአቻው የዋንጫ ተፎካካሪዎች ሊቨርፑል ላይ በተደረገው የውድድር ዘመን የመጨረሻ ጨዋታ።[56] የግራሃም አርሰናል በ1990-91 ሌላ ዋንጫ አሸንፏል፣ በአንድ ጨዋታ ብቻ ተሸንፏል፣ በ1993 የኤፍኤ ካፕ እና የሊግ ካፕ ዋንጫን እንዲሁም የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዎች ዋንጫን በ1994 አሸንፏል። የግራሃም ስም ከተወካዩ ኳሶችን ሲወስድ ሲታወቅ ስሙ ወድቋል። የተወሰኑ ተጫዋቾችን በማስፈረሙ እና በ1995 ተሰናብቷል።[57][58] የእሱ ምትክ ብሩስ ሪዮክ ለአንድ የውድድር ዘመን ብቻ የቆየ ሲሆን ከዳይሬክተሮች ቦርድ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ክለቡን ለቋል።[59] 1996–2018፡ ቬንገር ብቸኛውን ያልተሸነፍንበትን የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ካጠናቀቁ በኋላ ልዩ የሆነ የወርቅ ዋንጫ ለአርሴናል ተሰጥቷል። እ.ኤ.አ. በ1996 በተሾሙት የፈረንሳዩ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር የስልጣን ዘመን ሜታሞርፎስ የተደረገው ክለብ እግር ኳስን ማጥቃት [60] የአመጋገብ እና የአካል ብቃት ልምምዶችን ማሻሻያ እና በገንዘብ [መ] ቅልጥፍና የስልጣን ዘመናቸውን ገልፀውታል። እንደ ፓትሪክ ቪየራ እና ቲየሪ ሄንሪ ያሉ ቁልፍ ተጫዋቾችን ከቬንገር በመሰብሰብ አርሰናል በ1997–98 ሁለተኛ ሊግ እና ካፕ ዋንጫን በ2001–02 ሶስተኛውን አሸንፏል። በተጨማሪም ክለቡ የ1999-2000 የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ መድረሱን በ2003 እና 2005 የኤፍኤ ካፕ ፍፃሜዎች በማሸነፍ በ2003-04 ፕሪሚየር ሊግን አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ በማሸነፍ ቡድኑን ቅፅል ስም አስገኝቶለታል። "የማይበገሩ" [69] ይህ ድል የተገኘው ከግንቦት 7 ቀን 2003 እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2004 ባሉት 49 የሊግ ጨዋታዎች ያልተሸነፉ ሲሆን ይህም ብሔራዊ ሪከርድ ነው።[70] አርሰናል በሊጉ አንደኛ ወይም ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ቬንገር በ8ኛው የመጀመርያ 9 የውድድር ዘመን በ ነው። የእንግሊዝ እግር ኳስ ክለቦች
52407
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A0%E1%88%BD%E1%88%AD%20%E1%8A%A0%E1%88%8D%20%E1%8A%A0%E1%88%B3%E1%8B%B5
በሽር አል አሳድ
ባሻር ሃፌዝ አል-አሳድ (እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 1965 ተወለደ) ከጁላይ 17 ቀን 2000 ጀምሮ የሶሪያ 19ኛው የሶሪያ ፕሬዝዳንት የሆነ የሶሪያ ፖለቲከኛ ነው። በተጨማሪም እሱ የሶሪያ ጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ እና ፀሃፊ ነው። የዓረብ ሶሻሊስት ባአት ፓርቲ ማዕከላዊ ዕዝ ጀነራል አባቱ ሃፌዝ አል አሳድ ከ 1971 እስከ 2000 ድረስ ሲያገለግል የሶሪያ ፕሬዝዳንት ነበር በደማስቆ ተወልዶ ያደገው በሽር አል አሳድ ከደማስቆ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት በ1988 ተመርቆ በሶሪያ ጦር ውስጥ በዶክተርነት መሥራት ጀመረ። ከአራት ዓመታት በኋላ በለንደን በሚገኘው የዌስተርን ዓይን ሆስፒታል የድህረ ምረቃ ትምህርትን በዐይን ህክምና ተምሯል። እ.ኤ.አ. በ1994፣ ታላቅ ወንድሙ ባሴል በመኪና አደጋ ከሞተ በኋላ፣ ባሻር የባስልን አልጋ ወራሽነት ሚና ለመረከብ ወደ ሶሪያ ተጠራ። እ.ኤ.አ. በ1998 በሊባኖስ የሶሪያን ወታደራዊ ይዞታ በመምራት ወደ ወታደራዊ አካዳሚ ገባ። የፖለቲካ ሳይንቲስቶች የሶሪያን የአሳድ ቤተሰብ አገዛዝ እንደ ግላዊ አምባገነናዊ አገዛዝ ገልጸውታል። በ2000 እና 2007 ምርጫዎች 97.29% እና 97.6% ድጋፍ አግኝቻለሁ። እ.ኤ.አ. ጁላይ 16 ቀን 2014 አሳድ ሌላ ምርጫ 88.7% ድምጽ ከሰጠ በኋላ ለሌላ ሰባት ዓመታት ቃለ መሃላ ፈጸመ። ምርጫው የተካሄደው በሶሪያ መንግስት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ብቻ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቃውሞ ቀርቦበታል። አሳድ እ.ኤ.አ. በ2021 ከ95% በላይ ድምጽ በማግኘት ሌላ ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ ብሄራዊ ምርጫ በድጋሚ ተመርጧል። በእርሳቸው አመራር ጊዜ ሁሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሶሪያን የሰብአዊ መብት ሁኔታ ድሃ አድርገው ይገልጹታል። የአሳድ መንግስት ራሱን ሴኩላር ነው ሲል ሲገልጽ አንዳንድ የፖለቲካ ሳይንቲስቶች ግን አገዛዙ በሀገሪቱ ያለውን የኑፋቄ ግጭት እንደሚጠቀም ይጽፋሉ። በአንድ ወቅት በብዙ ግዛቶች የለውጥ አራማጅ ሆነው ይታዩ የነበሩት አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት እና አብዛኛው የአረብ ሊግ አሳድ በ2011 በአረብ ጸደይ ተቃዋሚዎች ላይ የሃይል እርምጃ እንዲወስድ ካዘዘ በኋላ ከፕሬዚዳንትነት ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀው ነበር፣ ይህም ወደ ሶሪያ እንዲመራ አድርጓል። የእርስ በእርስ ጦርነት. እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2013 የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ናቪ ፒላ እንደተናገሩት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባደረገው ምርመራ የተገኘው ውጤት አሳድን በጦር ወንጀሎች ውስጥ እንደሚያሳትፍ ተናግሯል። የ የጋራ የምርመራ ዘዴ በጥቅምት 2017 የአሳድ መንግስት ለካን ሼክሁን ኬሚካላዊ ጥቃት ተጠያቂ እንደሆነ ደምድሟል። በሰኔ 2014 የአሜሪካ የሶሪያ ተጠያቂነት ፕሮጀክት አሳድን ለአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በላካቸው የመንግስት ባለስልጣናት እና አማፂዎች የጦር ወንጀል ክስ ዝርዝር ውስጥ አካቷል። አሳድ የጦር ወንጀሎችን ውንጀላ ውድቅ በማድረግ በአሜሪካ የሚመራው የሶሪያ ጣልቃ ገብነት የአገዛዙን ለውጥ በመሞከር ተችቷል። የመጀመሪያ ህይወት ባሻር ሃፌዝ አል-አሳድ በሴፕቴምበር 11 ቀን 1965 በደማስቆ ተወለደ፣ የአኒሳ ማክሎፍ እና የሃፌዝ አል-አሳድ ሁለተኛ ወንድ ልጅ እና ሶስተኛ ልጅ። አል አሳድ በአረብኛ "አንበሳ" ማለት ነው። የአሳድ አባት አያት አሊ ሱለይማን አል-አሳድ ከገበሬነት ወደ አናሳ ታዋቂነት መቀየር ችለዋል እና ይህንንም ለማንፀባረቅ በ1927 የቤተሰቡን ስም ዋህሽ (“አሰቃቂ” ማለት ነው) ወደ አል-አሳድ ቀይሮታል። የአሳድ አባት ሃፌዝ በድህነት ከሚኖር ከአላውያን የገጠር ቤተሰብ ተወልዶ በባአት ፓርቲ ማዕረግ በማደግ በ1970 የእርምት አብዮት የሶሪያን የፓርቲውን ቅርንጫፍ ተቆጣጥሮ ወደ ሶሪያ ፕሬዝዳንትነት በወጣበት ጊዜ ተጠናቀቀ። ሃፌዝ ደጋፊዎቹን በባአት ፓርቲ ውስጥ አስተዋወቀ፣ ብዙዎቹም የአላዊት ታሪክ ነበሩ። ከአብዮቱ በኋላ፣ ሱኒ፣ ድሩዝ እና ኢስማኢሊስ ከሠራዊቱ እና ከበአት ፓርቲ ተወግደዋል። ታናሹ አሳድ አምስት ወንድሞችና እህቶች ያሉት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ሞተዋል። ቡሽራ የምትባል እህት ገና በህፃንነቷ ሞተች። የአሳድ ታናሽ ወንድም ማጅድ የህዝብ ሰው አልነበረም እና ብዙም የሚያውቀው የአእምሮ ጉድለት ካለበት በቀር በ2009 በ"ረጅም ህመም" ከዚህ አለም በሞት ተለየ።ከወንድሞቹ ባሴል እና ማሄር እና ሁለተኛዋ እህት ቡሽራ ትባላለች በተለየ መልኩ ባሻር ጸጥ ያለ፣ የተከለለ እና ለፖለቲካም ሆነ ለውትድርና ፍላጎት አልነበረውም። የአሳድ ልጆች አባታቸውን የሚያዩት እምብዛም እንዳልነበር የተነገረ ሲሆን ባሽር በኋላ ወደ አባታቸው ቢሮ የገቡት እሱ ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ተናግሯል። “ለስላሳ ተናጋሪ” ተብሎ የተገለፀ ሲሆን አንድ የዩንቨርስቲው ጓደኛ እንዳለው ዓይናፋር ነበር፣ የአይን ንክኪ የራቀ እና ዝቅ ባለ ድምፅ ይናገር ነበር። አሳድ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን የተማረው በደማስቆ በሚገኘው አረብ-ፈረንሣይ አል ሁሪያ ትምህርት ቤት ነው። በ1982 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ካጠናቀቅኩ በኋላ በደማስቆ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ተምሬያለሁእ.ኤ.አ. በ 1988 አሳድ ከህክምና ትምህርት ቤት ተመርቆ በደማስቆ ዳርቻ በሚገኘው ቲሽሪን ወታደራዊ ሆስፒታል በወታደራዊ ዶክተርነት መሥራት ጀመረ ከአራት አመታት በኋላ በሎንዶን መኖር ጀመረ በዌስተርን አይን ሆስፒታል የዓይን ህክምና የድህረ ምረቃ ስልጠና ጀመረ። በለንደን በነበረበት ጊዜ እንደ "ጂኪ አይቲ ሰው" ተገልጿል. ባሻር ጥቂት የፖለቲካ ምኞቶች ነበሩት እና አባቱ የባሻርን ታላቅ ወንድም ባሴልን እንደ የወደፊት ፕሬዝደንት ሲያዘጋጅ ነበር። ሆኖም ባሴል በ1994 በመኪና አደጋ ሞተ እና ባሻር ብዙም ሳይቆይ ወደ ሶሪያ ጦር ተጠራ። ወደ ስልጣን መነሳት፡ 1994–2000 (አውሮፓዊ) ባሴል ከሞተ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሃፌዝ አል አሳድ ባሽርን አዲሱን አልጋ ወራሽ ለማድረግ ወሰነ። በቀጣዮቹ ስድስት ዓመታት ተኩል ውስጥ፣ እ.ኤ.አ. በ2000 እስኪሞት ድረስ ሃፌዝ ባሻርን ስልጣኑን እንዲረከብ አዘጋጀ። ለስላሳ ሽግግር ዝግጅት በሶስት ደረጃዎች ተዘጋጅቷል. በመጀመሪያ ለባሽር በወታደራዊ እና በደህንነት መዋቅር ውስጥ ድጋፍ ተዘጋጅቷል. ሁለተኛ የባሽር ምስል ከህዝብ ጋር ተመስርቷል። እና በመጨረሻም ባሻር አገሪቱን የማስተዳደር ዘዴዎችን ጠንቅቆ ያውቅ ነበር። ባሻር በውትድርና ውስጥ ምስክርነቱን ለማረጋገጥ በ1994 በሆምስ ወደሚገኘው ወታደራዊ አካዳሚ ገባ እና በማዕረጉ ተገፋፍቶ በጥር 1999 የከፍተኛ የሶሪያ ሪፐብሊካን የጥበቃ ኮሎኔል ሆነ። አዛዦች ወደ ጡረታ ተገፍተው ነበር፣ እና አዲስ፣ ወጣት፣ ለእርሱ ታማኝ የሆኑ የአላውያን መኮንኖች ቦታቸውን ያዙ። እ.ኤ.አ. በ 1998 ባሻር የሶሪያን ሊባኖስ ፋይል ሀላፊ ወሰደ ከ 1970 ዎቹ ጀምሮ በምክትል ፕሬዝዳንት አብዱል ሀሊም ካዳም ይመራ የነበረ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ለፕሬዝዳንትነት እጩ ተወዳዳሪ ነበር። በሊባኖስ የሶሪያን ጉዳይ በመምራት፣ ባሻር ካዳምን ወደ ጎን ገፍቶ በሊባኖስ ውስጥ የራሱን የስልጣን ጣቢያ መመስረት ችሏል። በዚሁ አመት ከሊባኖስ ፖለቲከኞች ጋር መጠነኛ ምክክር ካደረጉ በኋላ ባሻር ታማኝ አጋር የነበሩትን ኤሚል ላሁድን የሊባኖስ ፕሬዝዳንት አድርጎ በመሾም የቀድሞ የሊባኖሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ራፊች ሃሪሪን ወደ ጎን ገትረው በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሾሙ በኋላ የፖለቲካ ክብደታቸውን ባለማስቀመጥ በሊባኖስ የነበረውን የድሮውን የሶሪያ ሥርዓት የበለጠ ለማዳከም ባሻር የሊባኖሱን የሶሪያ ከፍተኛ ኮሚሽነር ጋዚ ካናንን በሩስተም ጋዛሌህ ተክቷል። ባሻር ከወታደራዊ ህይወቱ ጋር ትይዩ በህዝብ ጉዳዮች ላይ ተሰማርቶ ነበር። ሰፊ ሥልጣን ተሰጥቶት ከዜጎች ቅሬታና አቤቱታ ለመቀበል የቢሮ ኃላፊ ሆኖ በሙስና ላይ ዘመቻ መርቷል። በዚህ ዘመቻ ምክንያት የበሽር ተፎካካሪ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙዎቹ በሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል። ባሻር የሶሪያ ኮምፒዩተር ሶሳይቲ ፕሬዝዳንት ሆነ እና በሶሪያ ውስጥ ኢንተርኔትን ለማስተዋወቅ ረድተዋል ፣ይህም እንደ ዘመናዊ እና ተሀድሶ ምስሉን ረድቷል። ፕሬዚዳንትነት የደማስቆ ጸደይ እና የእርስ በርስ ጦርነት በፊት፡ 2000–2011 (አውሮፓዊ) ሰኔ 10 ቀን 2000 ሃፌዝ አል አሳድ ከሞተ በኋላ የሶሪያ ሕገ መንግሥት ተሻሽሏል። ለፕሬዚዳንትነት ዝቅተኛው የእድሜ መስፈርት ከ40 ወደ 34 ዝቅ ብሏል ይህም በወቅቱ የበሽር እድሜ ነበር። ከዚያ በኋላ አሳድ እ.ኤ.አ. በጁላይ 10 ቀን 2000 በፕሬዚዳንትነት የተረጋገጠ ሲሆን 97.29% ለአመራሩ ድጋፍ አግኝቷል። የሶሪያ ፕሬዚደንት ሆነው በነበራቸው ሚና መሰረት፣ የሶሪያ ጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ እና የባአት ፓርቲ ክልላዊ ፀሃፊ ሆነው ተሾሙ። ስልጣኑን ከተረከበ በኋላ የተሃድሶ እንቅስቃሴ በደማስቆ የፀደይ ወቅት ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ ወስዷል፣ ይህም የመዝህ እስረኞች እንዲዘጉ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የሙስሊም ወንድማማችነት ፖሊሲዎችን ለመልቀቅ ሰፊ የምህረት አዋጅ ታውጆ ነበር።ነገር ግን የጸጥታ ሃይሎች በውስጥም እንደገና ጀመሩ። ዓመቱ. ብዙ ተንታኞች በአሳድ የስልጣን ዘመናቸው የተሃድሶ ለውጥ በ"አሮጌው ዘበኛ" ታግዶ እንደነበር ይገልጻሉ፣ ለሟች አባቱ ታማኝ በሆኑ የመንግስት አባላት። በአሸባሪነት ጦርነት ወቅት አሳድ አገራቸውን ከምዕራቡ ዓለም ጋር ተባበሩ። ሶሪያ በአልቃይዳ ተጠርጣሪዎች በሶሪያ እስር ቤቶች ሲጠየቁ በሲአይኤ ያልተለመደ የስርጭት ቦታ ነበረች። አሳድ ስልጣን ከያዘ በኋላ ብዙም ሳይቆይ "የሶሪያን ግንኙነት ከሂዝቦላህ እና በቴህራን የሚገኙ ደጋፊዎቿን የደህንነት አስተምህሮው ዋና አካል አድርጎታል" እና በውጭ ፖሊሲው አሳድ አሜሪካን፣ እስራኤልን፣ ሳዑዲ አረቢያን በግልፅ ተቺ ነው። እና ቱርክ. እ.ኤ.አ. በ 2005 የሊባኖስ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራፊች ሃሪሪ ተገድለዋል የክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተር እንደዘገበው "ሶሪያ ለሃሪሪ ግድያ በሰፊው ተወቅሳለች፡ ግድያው ወደ ተፈጸመባቸው ወራትም በሃሪሪ እና በሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ መካከል ያለው ግንኙነት ዛቻ እና ማስፈራሪያ ውስጥ ወድቆ ነበር" ሲል ዘግቧል። ቢቢሲ በታህሳስ 2005 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጊዜያዊ ሪፖርት "የሶሪያ ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርጓል" ሲል ዘግቧል, "ደማስቆ በየካቲት ወር ሃሪሪን በገደለው የመኪና ቦምብ ውስጥ እጃቸው እንዳለበት አጥብቋል." እ.ኤ.አ. ግንቦት 27 ቀን 2007 አሳድ በፕሬዝዳንትነታቸው በተደረገ ህዝበ ውሳኔ 97.6% ድምጽ በማግኘቱ ለተጨማሪ የሰባት አመታት የስልጣን ዘመን ፀድቋል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሀገሪቱ ውስጥ እንዲገቡ አልተፈቀዱም እና አሳድ በሪፈረንደም ብቸኛው እጩ ነበሩ። በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት በጥር 26 ቀን 2011 በሶሪያ ህዝባዊ ተቃውሞ ተጀመረ። ተቃዋሚዎች የፖለቲካ ማሻሻያ እና የዜጎች መብቶች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ እንዲሁም ከ1963 ጀምሮ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲቆም ጠይቀዋል። አንድ "የቁጣ ቀን" ሙከራ ነበር። ለየካቲት 4-5 ተቀምጧል፣ ምንም እንኳን ሳይታሰብ ቢጠናቀቅም። በመጋቢት 18-19 የተካሄደው ተቃውሞ በሶሪያ ውስጥ ለአስርት አመታት ከተካሄደው ትልቁ ነበር፣ እና የሶሪያ ባለስልጣን ተቃውሞ ባሰሙ ዜጎቹ ላይ የኃይል እርምጃ ወሰደ።የዩ.ኤስ. በሚያዝያ 2011 በአሳድ መንግስት ላይ የተወሰነ ማዕቀብ የጣለ ሲሆን በመቀጠልም ባራክ ኦባማ በግንቦት 18 ቀን 2011 ባሻር አሳድን እና ሌሎች 6 ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠረ የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ። ግንቦት 23 ቀን 2011 የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአሳድ እና በጉዞ እገዳ እና በንብረት እግድ የተጎዱትን ዝርዝር ውስጥ ለመጨመር ብራሰልስ ላይ ባደረጉት ስብሰባ ተስማምተዋል።ግንቦት 24 ቀን 2011 ካናዳ አሳድን ጨምሮ በሶሪያ መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች። ሰኔ 20፣ ለተቃዋሚዎች ጥያቄ እና የውጭ ግፊት ምላሽ፣ አሳድ ወደ ተሀድሶ፣ አዲስ የፓርላማ ምርጫ እና የበለጠ ነጻነቶችን የሚያካትት ብሄራዊ ውይይት ለማድረግ ቃል ገባ። ስደተኞቹ ከቱርክ ወደ አገራቸው እንዲመለሱም አሳስበዋል፣ ምህረት እንደሚደረግላቸው እና ሁከቱንም በጥቂቱ አጥፊዎች ተጠያቂ አድርገዋል። አሳድ ሁከቱን በ"ሴራዎች" የከሰሱ ሲሆን የሶሪያ ተቃዋሚዎችን እና ተቃዋሚዎችን "ፊቲና" ሲሉ ከሰዋቸዋል፣ የሶሪያ ባአት ፓርቲ ጥብቅ ሴኩላሪዝም ባህልን ጥሰዋል።በጁላይ 2011 ዩኤስ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን አሳድ የፕሬዚዳንትነት መብታቸውን አጥተዋል ብለዋል። እ.ኤ.አ. ነሐሴ 18 ቀን 2011 ባራክ ኦባማ አሳድ “ወደ ጎን እንዲሄድ” የሚያሳስብ የጽሁፍ መግለጫ አውጥቷል። በነሀሴ ወር የአሳድ መንግስት ተቺ የሆነው ካርቱኒስት አሊ ፋርዛት ጥቃት ደርሶበታል። የቀልደኛው ዘመዶች ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት አጥቂዎቹ የፋርዛትን አጥንት ለመስበር የዛቱት ሲሆን ይህም የመንግስት ባለስልጣናትን በተለይም የአሳድን ካርቱን መሳል እንዲያቆም ለማስጠንቀቅ ነው። ፋርዛት በሁለቱም እጆቹ ስብራት እና በጭንቅላቱ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል ገብቷል።እ.ኤ.አ ከጥቅምት 2011 ጀምሮ ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል ሆና በምዕራባውያን ደጋፊነት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ የቀረቡትን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳቦች ደጋግማ በመቃወም የተባበሩት መንግስታት ማዕቀብ አልፎ ተርፎም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በአሳድ መንግስት ላይ ሊፈጠር ይችላል። እ.ኤ.አ. በጥር 2012 መጨረሻ ላይ ከ5,000 የሚበልጡ ሰላማዊ ዜጎች እና ተቃዋሚዎች (ታጣቂ ታጣቂዎችን ጨምሮ) በሶሪያ ጦር፣ በደህንነት ወኪሎች እና ሚሊሻዎች (ሻቢሃ) እንደተገደሉ እና 1,100 ሰዎች በ"አሸባሪ ታጣቂ ሀይሎች መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 10 ቀን 2012 አሳድ ህዝባዊ አመፁ በውጭ ሀገራት የተቀነባበረ መሆኑን እና “ድል [በቅርብ ነበር]” በማለት አወጀ። በተጨማሪም የአረብ ሊግ ሶሪያን በማገድ አረብ መሆኗን ገልጿል። ይሁን እንጂ አሳድ “የብሔራዊ ሉዓላዊነት” ከተከበረ ሀገሪቱ በአረቦች መካከል ያለውን መፍትሄ “በሯን አትዘጋም” ብለዋል። በመጋቢት ወር በአዲስ ህገ መንግስት ላይ ህዝበ ውሳኔ ሊደረግ እንደሚችልም ተናግረዋል።እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. ህዝበ ውሳኔው ለሶሪያ ፕሬዝዳንት የአስራ አራት አመት ድምር ጊዜ ገደብ አስተዋውቋል። ህዝበ ውሳኔው ዩኤስን ጨምሮ በውጪ ሀገራት ትርጉም የለሽ ተብሏል። እና ቱርክ; በጁላይ 2012 የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ አድርጓል ሲሉ የምዕራባውያን ኃያላን መንግስታትን አውግዘዋል። እ.ኤ.አ. ጁላይ 15 ቀን 2012 ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ሶሪያ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መሆኗን አወጀ በአገር አቀፍ ደረጃ የሁሉም ወገኖች ሞት ወደ 20,000 መቃረቡ ተዘግቧል። እ.ኤ.አ. ጥር 6 ቀን 2013 አሳድ ከሰኔ ወር ጀምሮ ባደረጉት የመጀመሪያ ትልቅ ንግግር በአገራቸው የተፈጠረው ግጭት ከሶሪያ ውጭ ባሉ “ጠላቶች” የተነሳ “ወደ ገሃነም” በሚሄዱት እና “ትምህርት እንደሚሰጣቸው” ተናግረዋል ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ለመፍትሄው የተደረጉ ሙከራዎች ያልተሳኩ "የፖለቲካዊ መፍትሄ ፍላጎት የለንም ማለት አይደለም" በማለት አሁንም ለፖለቲካዊ መፍትሄ ክፍት እንደሆነ ተናግረዋል. በሴፕቴምበር 2014 በራቃ ጠቅላይ ግዛት የመጨረሻው የመንግስት መሬቶች የነበሩት አራት ወታደራዊ ካምፖች ከወደቁ በኋላ አሳድ ከአላውያን የድጋፍ መሰረቱ ከፍተኛ ትችት ደርሶበታል። ይህም የበሽር አል አሳድ የአጎት ልጅ የሆነው ዱራይድ አል-አሳድ የሶሪያ መከላከያ ሚኒስትር ፋህድ ጃሴም አል ፍሪጅ ስልጣን እንዲለቁ የጠየቁትን የኢራቅ እስላማዊ መንግስት እና ሌቫንት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ወታደሮች መማረክን ተከትሎ የተናገረውን ይጨምራል። በታብቃ ኤር ቤዝ ከ ድል በኋላ። ይህን ተከትሎ ብዙም ሳይቆይ አላዊት በሆምስ ገዢው ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ተቃውሞዎች እና የአሳድ የአጎት ልጅ ሃፌዝ ማክሉፍ ከደህንነት ቦታው በማሰናበት ወደ ቤላሩስ እንዲሰደዱ አድርጓል። በአላውያን መካከል በአሳድ ላይ ያለው ምሬት እየጨመረ የመጣው ከአላውያን አካባቢዎች በመጡ ጦርነቶች የተገደሉት ወታደሮች ቁጥር ተመጣጣኝ አለመሆኑ፣ የአሳድ መንግስት ጥሏቸዋል በሚል ስሜት እንዲሁም የኢኮኖሚው ውድቀት ተባብሷል። ለአሳድ ቅርበት ያላቸው ሰዎች የመዳን እድልን በተመለከተ ስጋታቸውን መግለጽ የጀመሩ ሲሆን አንደኛው እ.ኤ.አ. በ2014 መጨረሻ ላይ; "አሁን ያለው ሁኔታ ዘላቂ ነው ብዬ አላየውም... ደማስቆ የሆነ ጊዜ ትፈርሳለች ብዬ አስባለሁ።" እ.ኤ.አ. በ2015፣ በርካታ የአሳድ ቤተሰብ አባላት ግልፅ ባልሆኑ ሁኔታዎች በላታኪያ ሞተዋል። እ.ኤ.አ. ማርች 14፣ የአሳድ የአጎት ልጅ እና የሻቢያ መስራች መሀመድ ቱፊች አል-አሳድ፣ የአሳድ ቤተሰብ ቅድመ አያት በሆነው በቀርዳሃ በተፈጠረው አለመግባባት በአምስት ጥይቶች ጭንቅላቱ ላይ ተገደለ። በሚያዝያ 2015፣ አሳድ በአልዚራ፣ ላታኪያ የአጎቱን ልጅ ሙንዘር አል-አሳድን እንዲታሰር አዘዘ። የታሰሩት በተጨባጭ ወንጀሎች ምክንያት ይሁን አይሁን ግልጽ የሆነ ነገር የለም። በሰሜን እና በደቡባዊ ሶሪያ ከተከታታይ የመንግስት ሽንፈት በኋላ፣ የመንግስት አለመረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ለአሳድ መንግስት የሚሰጠው ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ከመጣው የአላውያን ድጋፍ መካከል፣ እና የአሳድ ዘመዶች፣ አላውያን እና ነጋዴዎች ደማስቆን እየሸሹ ስለመሆኑ እየጨመሩ መምጣታቸውን ተንታኞች ገልጸዋል። ለላታኪያ እና ለውጭ ሀገራት. የኢንተለጀንስ ሃላፊ አሊ ማምሉክ በኤፕሪል ወር ላይ በቁም እስር ላይ የነበሩ ሲሆን ከአሳድ አጎት ሪፋት አል አሳድ ጋር ባሽርን በፕሬዚዳንትነት ለመተካት በማሴር ተከሰው ነበር። በፓልሚራ ጥቃት ከአሳድ ጋር ዝምድና ያላቸው ሁለት መኮንኖችን ገድለዋል የተባሉት የአራተኛው ታጣቂ ክፍለ ጦር አዛዦች፣ የቤሊ ወታደራዊ አየር ማረፊያ፣ የሰራዊቱ ልዩ ሃይል እና የአንደኛ ታጣቂ ክፍል አዛዦች በከፍተኛ ደረጃ የተገደሉ ናቸው። ከሴፕቴምበር 2015 (እ.ኤ.አ.) ከሩሲያ ጣልቃ ገብነት ጀምሮ (አውሮፓውያን) እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 4 ቀን 2015 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ለአሳድ መንግስት በበቂ ሁኔታ “ከባድ” እርዳታ እየሰጠች ነው ብለዋል-በሎጅስቲክ እና በወታደራዊ ድጋፍ። እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 30 ቀን 2015 በሩሲያ ቀጥተኛ ወታደራዊ ጣልቃገብነት ከጀመረ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በሶሪያ መንግሥት መደበኛ ጥያቄ ፑቲን ወታደራዊ ዘመቻው አስቀድሞ በደንብ መዘጋጀቱን ገልፀው የሩሲያን ዓላማ በሶሪያ ውስጥ “በሶሪያ ውስጥ ያለውን ህጋዊ ኃይል ማረጋጋት እና መፍጠር” ሲል ገልፀዋል የፖለቲካ ስምምነት ሁኔታዎች" እ.ኤ.አ. በህዳር 2015 አሳድ የሀገሪቱን የእርስ በርስ ጦርነት ወደ ፍጻሜው ለማድረስ ዲፕሎማሲያዊ ሂደት በ"አሸባሪዎች በተያዘችበት ጊዜ ሊጀመር እንደማይችል ቢቢሲ ኒውስ ቢቢሲ ዘግቧል አመጸኞችም እንዲሁ። እ.ኤ.አ ኖቬምበር 22፣ አሳድ በአየር ዘመቻው በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ሩሲያ ከ ጋር ባደረገችው ውጊያ በአሜሪካ የሚመራው ጥምረት በአንድ አመት ካስመዘገበችው የበለጠ ውጤት እንዳገኘች ተናግሯል። በታህሳስ 1 ቀን ከ ቼስካ ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ መልቀቂያ የጠየቁ መሪዎች ለእሱ ምንም ፍላጎት እንዳልነበራቸው ተናግሯል ማንም ማንም በቁም ነገር አይመለከታቸውም ምክንያቱም እነሱ “ጥልቅ ያልሆኑ” እና በዩኤስኤ ቁጥጥር ስር በታህሳስ 2015 መጨረሻ ከፍተኛ ባለሥልጣናቱ ሩሲያ ሶሪያን የማረጋጋት ማዕከላዊ ግቡን ማሳካት መቻሏን እና በአንጻራዊ ሁኔታ ዝቅተኛ ወጭዎች በዚህ ደረጃ ለዓመታት እንደሚቆይ አምነዋል እ.ኤ.አ በጥር 2016 ፑቲን ሩሲያ የአሳድ ጦርን እንደምትደግፍ እና ፀረ-አሳድ አማፂያን ን እስከወጉ ድረስ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ተናግረው ነበር። ባሽር አል አሳድ በሶሪያ ጉዳይ የኢራን ተወካይ አሊ አክባር ቬላያቲ ጋር ተገናኙ 6 ሜይ 2016 እ.ኤ.አ. ጥር 22 ቀን 2016 የፋይናንሺያል ታይምስ ስም-አልባ "የምዕራብ የስለላ ባለስልጣኖችን" በመጥቀስ የሩሲያ ጄኔራል ኢጎር ሰርጉን የ ዳይሬክተር የሩሲያ ፌዴሬሽን የጦር ኃይሎች አጠቃላይ ሰራተኛ ዋና ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ከጥቂት ጊዜ በፊት እንደነበረ ተናግሯል ጃንዋሪ 3 2016 ድንገተኛ ሞት ወደ ደማስቆ ተልኳል ከቭላድሚር ፑቲን ፕሬዝደንት አሳድ ከስልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ። የፋይናንሺያል ታይምስ ዘገባ በፑቲን ቃል አቀባይ ውድቅ ተደርጓል። እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2016 የአሳድ ጦር በአማፅያን ቁጥጥር ስር የሚገኘውን አሌፖን ግማሹን መልሶ እንደወሰደ እና በከተማዋ ለ6 ዓመታት የቆየውን አለመግባባት እንዳበቃ ተዘግቧል። እ.ኤ.አ. በታህሳስ 15፣ የመንግስት ሃይሎች የእርስ በርስ ጦርነት የሆነውን ሀሌፖን በሙሉ ለመንጠቅ አፋፍ ላይ እንዳሉ ሲነገር፣ አሳድ የከተማዋን “ነጻነት” አክብሯል፣ እና “ታሪክ በሁሉም ሰው እየተጻፈ ነው የሶሪያ ዜጋ" ከዶናልድ ትራምፕ ምርጫ በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ቅድሚያ ለአሳድ ከኦባማ አስተዳደር ቅድሚያ የተለየ ነበር እና በመጋቢት 2017 በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኒኪ ሃሌይ የዩ.ኤስ. በ2017 የካን ሼክሁን ኬሚካላዊ ጥቃት ምክንያት ይህ አቋም በ"አሳድን መውጣት" ላይ ትኩረት አላደረገም። በፕሬዚዳንት ትራምፕ ትእዛዝ የሶሪያ አየር ማረፊያ ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የአሳድ ቃል አቀባይ የዩናይትድ ስቴትስን ባህሪ ኢፍትሃዊ እና እብሪተኛ ጥቃት ሲሉ ገልፀው የሚሳኤል ጥቃቱ የሶሪያ መንግስትን ጥልቅ ፖሊሲዎች አይለውጥም ብለዋል። ፕሬዚደንት አሳድ በተጨማሪም የሶሪያ ጦር እ.ኤ.አ. በ2013 ሁሉንም ኬሚካላዊ የጦር መሳሪያ ትቶ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት መሳሪያ ቢይዝ ሊጠቀምበት እንደማይችል ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል ለእኛ የአየር ድብደባ. እ.ኤ.አ ሰኔ 2017 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን “አሳድ [የኬሚካል ጦር መሳሪያዎችን] አልተጠቀመም” እና የኬሚካላዊ ጥቃቱ የተፈፀመው “ለዚህ እሱን ተጠያቂ ለማድረግ በሚፈልጉ ሰዎች ነው” ብለዋል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አለምአቀፍ የኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ተቆጣጣሪዎች ጥቃቱ የአሳድ መንግስት ተግባር መሆኑን አረጋግጠዋል። እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 7 2017 የሶሪያ መንግስት የፓሪስን የአየር ንብረት ስምምነት መፈረሙን አስታውቋል። እ.ኤ.አ. ኦገስት 30 2020 አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ያካተተ የመጀመሪያው ሁሴን አርኖስ መንግስት ተፈጠረ። እ.ኤ.አ. ኦገስት 10 ቀን 2021 የሁለተኛው ሁሴን አርኖስ መንግስት ተፈጠረ የፖለቲካ ሥራ ኢኮኖሚ እንደ ኤቢሲ ኒውስ ዘገባ፣ በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት "በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለችው ሶሪያ በመጠን ተቆርጣለች፣ ተደበደበች እና ደሃ ነች"። የኢኮኖሚ ማዕቀብ (የሶሪያ ተጠያቂነት ህግ) ከሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ተግባራዊ ሲሆን የእርስ በርስ ጦርነት ሲቀሰቀስ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመቀላቀል የሶሪያን ኢኮኖሚ መበታተን ፈጠረ። እነዚህ ማዕቀቦች በጥቅምት 2014 በአውሮፓ ህብረት እና በዩ.ኤስ. አሁንም በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉ የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ ኢንዱስትሪዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር ናቸው፣ አሁን ባለው ግጭት ኢኮኖሚያዊ ነፃነት እየተቀየረ ነው። የለንደኑ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በሶሪያ የጦርነት ኢኮኖሚ መፈጠሩን ገልጿል። እ.ኤ.አ. በ 2014 የአውሮፓ የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት ሪፖርት የጦርነት ኢኮኖሚ መፈጠሩን ገልጿል። ከሁለቱም ወገኖች ቢያንስ 140,000 ሰዎችን እንደገደለ የሚገመተው ግጭት ከሶስት ዓመታት በኋላ አብዛኛው የሶሪያ ኢኮኖሚ ፈርሷል። ሁከቱ እየሰፋና ማዕቀብ በመጣ ቁጥር ሀብትና መሰረተ ልማቶች ወድመዋል፣የኢኮኖሚው ውጤት ወድቋል፣ባለሀብቶችም አገር ጥለው ተሰደዋል። በአሁኑ ወቅት ስራ አጥነት ከ50 በመቶ በላይ ሲሆን ግማሹ የህብረተሰብ ክፍል ከድህነት ወለል በታች ነው የሚኖረው።...ከዚህ ዳራ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ ውስጥ እየከተቱ ያሉትን ሁከት፣ ብጥብጥ እና ስርዓት አልበኝነት የሚመገቡ ጉልህ የሆኑ አዳዲስ የኢኮኖሚ አውታሮችን እና የንግድ እንቅስቃሴዎችን እየፈጠረ ያለው የጦርነት ኢኮኖሚ እየተፈጠረ ነው። ይህ የጦርነት ኢኮኖሚ የምዕራባውያን ማዕቀቦች ሳያውቁት አስተዋፅዖ ያበረከቱት ለአንዳንድ ሶሪያውያን ግጭቱን ለማራዘም ማበረታቻ እየፈጠረ እና ችግሩን ለማስወገድ አስቸጋሪ ያደርገዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሶሪያ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ባወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው ከሶሪያ ህዝብ ውስጥ 2/3ኛው በአሁኑ ጊዜ “በከፋ ድህነት” ውስጥ ይኖራሉ። ሥራ አጥነት 50 በመቶ ደርሷል። እ.ኤ.አ ኦክቶበር 2014፣ በታርቱስ የ50 ሚሊዮን ዶላር የገበያ አዳራሽ ተከፈተ ይህም የመንግስት ደጋፊዎች ትችትን የቀሰቀሰ እና እንደ የአሳድ መንግስት ፖሊሲ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የመደበኛነት ስሜትን ለመፍጠር የሚሞክር አካል ሆኖ ታይቷል። በሙስና የተከሰሱ ውንጀላዎች ተቃውሞን አስከትለው ብጥብጥ ከፈጠሩ በኋላ ለተገደሉ ወታደሮች ቤተሰቦች ቅድሚያ መስጠት የሚለው የመንግስት ፖሊሲ ተሰርዟል። እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2014 የአውሮፓ ህብረት የአውሮፕላን ነዳጅ ለአሳድ መንግስት መሸጥ ከልክሏል ፣ይህም መንግስት ለወደፊቱ የበለጠ ውድ የሆነ ኢንሹራንስ አልባ የጄት ነዳጅ ጭነቶች እንዲገዛ አስገድዶታል። ሰብዓዊ መብቶች እ.ኤ.አ. በ 2007 የወጣው ህግ የበይነመረብ ካፌዎች ተጠቃሚዎች በቻት መድረኮች ላይ የሚለጥፉትን ሁሉንም አስተያየቶች እንዲመዘግቡ ያስገድዳል። እንደ አረብኛ ዊኪፔዲያ፣ ዩቲዩብ እና ፌስቡክ ያሉ ድረ-ገጾች ከ2008 እስከ የካቲት 2011 ድረስ ያለማቋረጥ ተዘግተዋል። እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የአሳድ መንግስት ሚስጥራዊ ፖሊሶች የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ሲያሰቃዩ፣ ሲያስሩ እና ሲገድሉ እንዲሁም መንግስትን የሚቃወሙ አካላትን ዘርዝረዋል። በተጨማሪም ሶሪያ ሊባኖስን ከያዘች በኋላ ወደ 600 የሚጠጉ የሊባኖስ የፖለቲካ እስረኞች በመንግስት እስር ቤቶች እንደሚገኙ የሚታሰበ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ ከ30 ዓመታት በላይ በእስር ላይ ይገኛሉ። ከ2006 ጀምሮ የአሳድ መንግስት በፖለቲካ ተቃዋሚዎች ላይ የጉዞ እገዳን አስፋፋ። እ.ኤ.አ. በ2007 ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ አሳድ “እኛ የፖለቲካ እስረኞች የሉንም” በማለት ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ በታህሳስ 2007 የጋራ ተቃዋሚ ግንባርን ሲያደራጁ የነበሩ 30 የሶሪያ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች መታሰራቸውን ዘግቧል። በዚህ ቡድን ውስጥ 3 የተቃዋሚ መሪዎች ናቸው የተባሉት በእስር ላይ ይገኛሉ። እ.ኤ.አ. በ 2010 ሶሪያ የፊት መሸፈኛዎችን በዩኒቨርሲቲዎች ከለከለች እ.ኤ.አ. በ 2011 የሶሪያን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ፣ አሳድ የመጋረጃ እገዳውን በከፊል ዘና አድርጎታል። የውጭ ፖሊሲ መጽሔት እ.ኤ.አ. በ 2011 ተቃውሞን ተከትሎ ስለ አሳድ አቋም መግለጫ አዘጋጅቷል በአስርት አመታት የግዛት ዘመናቸው... የአሳድ ቤተሰብ ወታደሩን ከመንግስት ጋር በጥብቅ በማዋሃድ ጠንካራ የፖለቲካ ደህንነት መረብ ፈጠረ። እ.ኤ.አ. በ 1970 የበሽር አባት ሃፌዝ አል-አሳድ በሶሪያ የጦር ሃይሎች ማዕረግ ካደጉ በኋላ ስልጣናቸውን ተቆጣጠሩ ፣በዚያን ጊዜም ታማኝ አላውያንን ቁልፍ ቦታዎች ላይ በመትከል የታማኝ አላውያን መረብ አቋቋመ። እንደውም ወታደራዊው፣ ገዥው ልሂቃን እና ጨካኝ ሚስጥራዊ ፖሊሶች እርስ በርስ የተሳሰሩ በመሆናቸው አሁን የአሳድን መንግስት ከደህንነት ተቋሙ መለየት አልተቻለም።...ስለዚህ...መንግስትና ታማኝ ሃይሎች ሁሉንም መከላከል ችለዋል። ግን በጣም ቆራጥ እና የማይፈሩ ተቃዋሚ አክቲቪስቶች። ከዚህ አንፃር፣ የሶሪያ ሁኔታ በተወሰነ ደረጃ ከሳዳም ሁሴን በኢራቅ ውስጥ ከነበረው ጠንካራ የሱኒ አናሳ አገዛዝ ጋር የሚወዳደር
19140
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B5%E1%89%A5%E1%88%B5%E1%89%A5
ስብስብ
ስብስብ ሲባል ተለይተው ሊዘርዘሩ የሚችሉ ነገሮች ክምችት ማለት ነው። ሥነ ስብስብ የሒሳብ ጥናት መሰረት ከመሆኑ የተነሳ በአሁኑ ወቅት በሁሉም የሂሳብ ዘርፎች ሰርጾ ይገኛል። ስለሆነም ከመዋዕለ ህጻናት እስከ ዩኒቨርስቲወች ድረስ የስብስብ ጥናት እንደ ትምህርት ይሰጣል። ትርጓሜወች ከላይ እንደተጠቀሰው ስብስብ ማለቱ ጥርት ብለው የተለዩ ነገሮች (የየቅል ነገሮች) ክምችት ማለት ነው። እኒህ የተከማቹ ነገሮች፣ እያንዳንዳቸው፣ የስብስቡ አባል ይሰኛሉ። የአንድ ስብስብ አባላት ማናቸውም አይነት ነገር ሊሆኑ ይችላሉ ሰወች፣ ቁጥሮች፣ ፊደሎች፣ ሌሎች ስብስቦች፣ ወዘተ... ስብስቦች፣ በእንግሊዝኛ ፊደላት ካፒታል ሌተር ይሰየማሉ። ስብስብ እና ስብስብ እኩል ናቸው የሚባሉት ሁለቱም ስብስቦች አንድ አይነትና አንድ አይነት ብቻ ስብስብ ሲኖራቸው ነው። ስብስብን የመግለጫ መንገዶች ስብስብን በሁለት አይነት መንገድ መግልጽ ይቻላል። አንደኛው ቃላትን በመጠቀም የስብስቡን አባላት በመወሰን ነው። ምሳሌ፡- ማለት የመጀመሪያዎቹ አራት መቁጠሪያ ቁጥሮች ስብስብ ነው ማለት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ቀለማት ስብስብ ነው ሁለተኛው መንገድ የስብስቡን አባላት አንድ-ባንድ በመዘርዘር ይሆናል። ለዚህ ተግባር እንዲጠቅም አባላቱን በብራኬት መክበብና የእንግሊዝኛ ኮማ በአባላቱ መካከል በማስቀመጥ ነው። ለምሳሌ {4, 2, 1, 3} {ቀይ, ቢጫ, አረንጓዴ} የስብስብ አባላት፣ እያንዳዳቸው በጠራ ሁኔታ የተለያዩ (የየቅል) መሆን አለባቸው። አባላቱ ቢደጋገሙ ምንም ለውጥ አያመጡም። በሌላ አነጋገር የአንድ ሰብስብ ሁለት አባላቱ አንድ አይነት ሊሆኑ አይችሉም። የስብስብ አባላት አደራደር ቅደም-ተከተል የለውም። እንደፈለገ ሊደረደር ይችላል። እንዲህ የሆነበት ምክንያት የስብስብ ጽንሰ ሐሳብ ዋና አላም ማን/ምን የሰብስቡ አባል ነው የሚለውን ጥያቄ ለመመልስ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የሚከተሉት ስብስቦች እኩል ናቸው። {6, 11} {11, 6} {11, 11, 6, 11} የአንድ ስብስብ አባላት ብዙ ከሆኑና የአባላቱ ይዘት ግልጽ ከሆነ ሁሉንም አባላት መጻፍ አያስፈልግም። ለዚህ ተግባር መጠቀም ይቻላል። {1, 2, 3, 1000}, በብራኬት መንገድ እያንዳንዱን አባላት ሳይዘረዝሩ ስብስቡን መግለጽም ይቻላል። ለምሳሌ {የካርታ ጨዋታ ምልክቶች} ማለቱ እኒህ ምልክቶች አባላቱ የሆነ ስብስብ ማለቱ ነው። በአጠቃላይ መልኩ ስብስብ መስሪያ አጻጻፍ የሚባለውን ዘዴ በመጠቀም ስብስቦችን በብራኬት ተጠቀመን እንዲህ መስራት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ 2 4 መቁጠሪያ ቁጥር ሲሆን; 0 19} እዚህ ላይ የ(":") ምልክት ትርጓሜው "ሆኖ ሲያበቃ" እንደማለት ነው። ከላይ የተጠቀሰው ምሳሌ ሲነበብ የሁሉም ቁጥሮች 2 4, ስብስብ ሆኖ ሲያበቃ ደግሞ በ0 እና 19 መካከል ያለ መቁጠሪያ ቁጥር ነው"። አባልነት ነገር የስብስብ አባል ከሆነ ይህ ኩነት እንዲህ ይወከላል በሌላ በኩል የስብስብ አባል ካልሆነ እንዲህ ይወከላል ሌላ ከበድ ያለ ምሳሌ ለመውሰድ ያክል {1,2,3,4}, {ቀይ, ቢጫ አረንጓዴ}, እና 2 4 መቁጠሪያ ቁጥር ነው; እና 0 19} 4 እና 285 ነገር ግን 9 እና ሰማያዊ ታህታይ ስብስብ ማናቸውም የስብስብ አባላት የስብስብ አባላት ከሆኑ፣ የ ታህታይ ስብስብ ነው እንላለን። ሲጻፍ ሲነበበ ስብስብ ውስጥ ይገኛል)። በዚህ ትይዩ እንዲህ በለንም መጻፍ እንችላለን ላዕላይ ስብስብ ነው ወይም ስብስብ ን ይጠቀልላል። ታህታይ ስብስብ ሆኖ ነገር ግን ሁለቱ ስብስቦች እኩል ካልሆኑ ደንበኛ ታህታይ ስብስብ ይሰኛል፣ በሒሳብ ምልክት ሲጻፍ ሌሎች ደራሲያን ይህን ምልከት ይጠቀማሉ። ታህታይ ስብስብ ነው ምሳሌ፡ የሁሉ ወንዶች ስብስብ የሁሉ ሰወች ስብስብ ታህታይ ስብስብነው። {1, 3} {1, 2, 3, 4}. {1, 2, 3, 4} {1, 2, 3, 4}. ባዶ ስብስብ የማናቸውም ስብስብ ታህታይ ስብስብ ነው። ሁሉም ስብስብ በበኩሉ የራሱ ስብስብ ታህታይ ስብስብ ነው። ሁለት ስብስቦች እኩል እንደሆኑ ለማረጋገጥ የሚያገለግል መምሪያ ሐሳብ ይኼ ነው፦ ሁለት ስብስቦች እኩል የሚሆኑት እና ሲሆኑና ሲሆኑ ብቻ ነው። የስብስብ ብዛት የስብስብ ብዛት የምንለው የአንድ ስብስብ አባላትን ብዛት ነው። ለምሳሌ የስብስብ ብዛት በሒሳብ ምልክት እንዲህ ይወከላል፡ ለምሳሌ፡ ስብስብ የፈረንሳይ ባንዲራ ቀለሞች ስብስብ ቢሆን፣ የ ብዛት ሲሰላ ነው፣ ምክንያቱም የፈረንሳይ ባንዲራ ቀለሞች 3 ናቸውና። ባዶ ስብስብ የምንለው ልዩ ስብስብ በውስጡ ምንም አባላት የሉትም ስለሆነም ብዛቱ ዜሮ ነው እንላለን። ምልክቱም ይሄ ነው፡ ወይም ለምሳሌ ጎናቸው አራት የሆኑ ሶስት ማዕዘኖች ስብስብ ዜሮ አባላት ስላሉት ባዶ ስብስብ ይባላል። በተጻራሪ አንድ አንድ ስብስቦች አእላፍ ብዛት አሏቸው። ለምሳሌ የቁጥሮች ስብስብን ብንወሰድ አእላፍ አባላት አሉት። አንድ አንድ አእላፋት ከሌሎች አእላፋት የሚበልጡበት ሁኔታ ይገኛል። ለምሳሌ የውኑ ቁጥር ብዛት ከመቁጠሪያ ቁጥር ብዛት ይበልጣል፣ ምንም እንኳ ሁለቱም ብዛታቸው አእላፍ ቢሆንም። በተጻራሪ አንድ አንድ እኩል የማይመስሉ አዕላፎች እኩል ሆነው ይገኛሉ። ለምሳሌ የመስመር ቁራጭ ና የተቆረጠበት መስመር እኩል ብዛት አላቸው፣ ማለት እኩል የነጥብ ብዛት አላቸው። እኒህንና እኒህ የመሰሉ እንግዳ የአእላፍ ጠባዮች የተጠኑት በጆርጅ ካንተር ነበር። ርቢ ስብስቦች(ፓወር ሴት) የስብስብ ርቢ ስብስብ የምንለው ማናቸውንም የስብስብ ታህታይ ስብስቦች አቅፎ የሚይዝን ስብስብ ነው። ማለት ከ አባላት የሚሰሩ ማናቸውንም ስብስቦችና ባዶ ስብስብን ይይዛል። አንድ ብዛቱ አእላፍ ያልሆነ (አባላቱ የሚያልቁ) ስብስብ ብዛቱ ቢሆነ የርቢ ስብስቡ ብዛት ነው። የርቢ ስብስብ እንዲህ ይወከላል ለምሳሌ፡ {1, 2, 3} ስብስብ ቢሰጠን፣ ርቢ ስብስቡ ይሄ ነው {{1, 2, 3}, {1, 2}, {1, 3}, {2, 3}, {1}, {2}, {3}, የመጀመሪያው ስብስብ ብዛት 3 ሲሆን የርቢ ስብስቡ ብዛት 23 8 ነው። መሰረታዊ የስብስብ መተግበሪያወች ከተሰጠ ስብስብ ወይም ስብስቦች ሌሎች ስብስቦች ለመፍጠር የተለያዩ መተግበራዊያወች ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ እኒህ ናቸው ውሁድ ስብስብ ሁለት ስብስቦች "ሊደመሩ" ይችላሉ። መደመርን መተግብሪያ ውህድ ስብስብ ሲሆን፣ እና ውህድ እንዲህ ይጻፋል ትርጓሜውም በ ወይም በ የሚገኙ ሁሉም አባላት ስብስብ ማለት ነው። ምሳሌ: አንድ አንድ መሰረታዊ የውህድ ስብስብ ጸባዮች: የጋራ ስብስብ የሁለት ስብስቦችን የጋራ አባላት በመውሰድ እንዲሁ አዲስ ስብስብ መፍጠር ይቻላል። እና የጋራ ስብስብ እንዲህ ይወከላል ትርጓሜውም በ እና በ ውስጥ የሚገኙ የጋራ አባላቶች ስብስብ ማለት ነው። ከሆነ እና የየቅል ስብስብ ይሰኛሉ። ምሳሌዎች: የጋራ ስብስብ መሰረታዊ ጸባዮች: የሚሆነው ከሆነና ከሆነ ብቻ ነው። የስብስብ ውጭ ሁለት ስብስቦች ሊቀናነሱ ይችላሉ። (ወይም ማለቱ ማናቸውም ውስጥ ኖረው ነገር ግን በ የማይገኙ አባላት ስብስብ ማለቱ ነው። በአንድ አንድ ስሌቶች ማናቸውም ስብስቦች የአቃፊያቸው አለም አቀፍ ስብስብ አባል እንደሆኑ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ። ይህ ሁሉን አቃፊ ስብስብ እንዲህ ይወከላል፡ በዚህ ጊዜ የ ውጭ ወይንም የ ተቃርኖ ይሰኛል። ምሳሌ: አለም አቀፉ ስብስብ የመቁጠሪያ ቁጥሮችን ቢወክል, ደግሞ ተጋማሽ ቁጥሮችን, ኢተጋማሽ ቁጥሮችን ቢወክል, መሰረታዊ የውጭ ስብስብ ጸባዮች: እና ሚዛናዊ ውጭ ስብስብ እንዲህ ይተረጎማል። ለምሳሌ የ {7,8,9,10} እና {9,10,11,12} ሚዛናዊ ውጭ ስብስብ {7,8,11,12} ነው። ካርቴዣን ብዜት እያንዳንዷን የአንድ ስብስብ አባላት ከሌላው ስብስብ አባላት ጋር በማያያዝ አዲስ ስብስብ መፍጠር ይቻላል። የ ስብስብ እና ካርቴዥያዊ ብዜት እንዲህ ይወከላል ትርጓሜውም የቅደም ተከተል ስብስብ ሆኖ ሲያበቃ፣ እዚህ ላይ የስብስብ አባል ሲሆን ደግሞ የስብስብ አባል ነው ማለት ነው።ብብ ምሳሌ: መሰርታዊ የካርቴዢያዊ ብዜት ጸባዮች: እና አላቂ ስብስቦች ቢሆኑ የብዛታቸው ጸባይ እንዲህ ነው የስነ ስብስብ ቦታ በሂሳብ ጥናት የስብስብ ኅልዮት (ትምህርት) ለሁሉ የሒሳብ ትምህርት መሰረት እንደሆነ ይታመናል። ለምሳሌ አልጀብራ፣ ቡድን ሂሳብ፣ መስክ ሂሳብ፣ ቀለበት ሂሳብ በሙሉ አንድ አይነት ወም ሌላ አይነት ስብስቦች ሲሆኑ የሚለያዩትም በአንድ ወይም በሌላ መተግብሪያ (ኦፕሬሽን) ስር መዘጋታቸው ብቻ ነው። በሌላ ጎን የስብስብ ኅልዮት ለዝምድና ሂሳብ መሰረት ነው። ይሄም ለፈንክሽንና ሌሎች ጽንሰ ሃሳቦች አስፈላጊ ነው። ተጨማሪ ንባብ (1979) 978-0-691-02447-9. (1960) 0-387-90092-6. (1979) 0-486-63829-4. (2006) 978-0-521-67599-4 የውጭ ድረ ገጾች 2 ሥነ ስብስብ ሥነ
46301
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8C%8C%E1%88%8B%E1%8B%8D%E1%8B%AB%E1%8A%95%20%E1%89%A0%E1%88%B5%E1%88%8D%E1%8C%A4
ወንጌላውያን በስልጤ
1ኛ. ሀይደር ይባላል የአልከሶ አከባቢ ተወለጅ ነው። በአሁኑ ሰዓት በወራቤ ከተማ በሐጂ ፈድሉ ህንጻ ስር አንድ ክፍል ተከራይቶ የመድሐኒት መሸጫ መደብር ከፍቶ ይሸጣል(የገንዘብ ምንጩ ባይታወቅም)፤ይህ ግለሰብ ለረጅም ጊዜ በአልከሶ ሀድራ ውስጥ ሲካድም እንደነበረና ሙሉ ጊዜውን ጫት ሲቅም (ሲፈጭ ቢባል ይሻላል ላሉ በቅርበት የሚያውቁት) የኖረ ገሪባ ነገር እንደነበር በቅርበት የሚያውቁት ይናገራሉ በዚሁ አጋጣሚ ነበር በጴንጤዎች መረብ ተጠልፎ ገብቶ በሂደት ሱሱን አስትተው የኢኮኖሚ አቅሙን አሻሽለው ወደ ወራቤ መልሰውት በአሁኑ ሰዓት የአክፍሮት ስራውን በጥንቃቄ እየሰራ ይገኛል፡፡ እሱ መድኃኒት ለመግዛት የሚመጡ የገጠር ሰዎችን በተለይም መድኃኒት የመግዛት አቅም የሌላቸውን እንደሚያጠምድ ይነገራል፡፡ 2ኛ. ሁሴን ቃዲ ይባላል፤ ወጣት ነው። በወራቤ መሰናዶ ትምህርት ቤት በመምህርነት እየሰራ ይገኛል። ይህ ግለሰብ አስተዳደጉ ወላጅ አጥ የሆኑ ህጻናት በሚያድግበት የህጻናት አምባ እንደሆነ ይገራል። ከሙስሊም ቤተሰብ ቢወለድም ምንም ዓይነት ኢስላማዊ መሰረት እንዳልነበረው ቢያንስ ይህ አስተዳደጉ አብነት ይሆናል። ይህ ወጣት ወንጌላዊ ከመሰል ከሌላ አከባቢ ከመጡ ወጣት ፕሮቴስታንቶች ጋር በመሆን ሴቶችን እየጋበዙ እንደሚያጠምዱ ይነገራል፡፡ 3ኛ. ኪያር ይባላል የአልከሶ አከባቢ ተወላጅ እንደሆነ (አልከሶዎች ምን ነካቸው?) እና አስተዳደጉ ዝዋይ እንደሆነ ይነገራል። ከግንበኝት ተነስቶ በአጭር ጊዜ እንዴት ኮንትራከተር እንደሆነ እና የመኪና ባለቤት እንደሆነ አላህ ይወቀው ብቻ በአሁኑ ሰዓት በዞኑ ውስጥ በርካታ የግንባታ ጨረታዎችን ‹እያሸነፈ› ጴንጤ ባለሙያዎችን እያስመጣ ከእኛ የቀን ሰራተኛ ሴቶች ጋር እየቀላቀለ እያሰራ እንደሆነ የይዓን ምስክሮች ያናገራሉ። በአሁኑ ሰዓት በበተለይ በወራቤ በሚካሄዱ ግንባታዎች ላይ ከባለሙያ እስከ የቀን ሰራተኛ ሆነው የሚሰሩ ጴንጤዎችን ታያቸዋለህ አንድ እንኩዋን ቢሆን መዝሙሩን እያስጮሀ ነው የሚሰራው፣የእኛዎቹ ደግሞ የትግርኛ ወይም የስልጠኛ ዘፈን ከፍተው ሲያዳምጡ ታያቸዋለህ፡፡ (ሴኩላሪዝ በጣም ስለገባን ነው መሰለኝ) 4ኛ. ገነት ተክሌ ትባላለች ስልጤ ባትሆንም አባቷ ተክሌ ለረጅም ጊዜ በወራቤ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር እና የምርጫ(ቅርጫ) ቦርድ ሆኖ እያገለገለ ነው። ልጅትም እዚሁ ስለተወለደች ስልኛንም ስልጤንም በደንብ ታውቃቸዋለች፡፡ የማትሪክ ውጤቷ ከፍተኛ ትምህር ተቋም ባያስገባትም በአሁኑ ሰዓት ግን በሚሽነሪዎች(ምናልባትም በቤንጃሚን) አማካኝነት እስከ ውጭ ሀገር ተልካ ዲግሪ፣ሁለተኛ ዲግሪ እስከ ዶክትሬት ሊያስምሯት እንደሆነ ሰምተናል። ይህ ምን ችግር አለው ትሉኝ ይሆናል የእኛ ልጆች በባትሪ እየተፈለጉ በአክራሪነት እተፈረጁ ዞኑን ብሎም ሀገር ለቀው እንዲወጡ እየተደረገ ነገ ደግሞ ይህን ከፈተኛውን የዞን ሹመት መያዝ ያለባቸው ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ብቻ ናቸው የሚል ህግ ቢያመጡ ማን ይሆን በቦታው የሚቀመጠው? አትጠራጠሩ ገነት ተክሌ ናት፡፡ ከዚያስ?ከዚያማ…..የእኛ በምንለው ሰማን ሽፋ እንኳን ካደረሰብን የሞራል ውድቀት፣ ፍራቻ፣ ውርደት እስካሁን ማንሰራራት አልቻልንም። መስጂድ ውስጥ እንኩዋን ኖርማል ዳዕዋ ማድረግ እየፈራን ያለንበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል። አላህ ይድረስልን፡፡ ይህች ገነት በአሁኑ ሰዓት(የገንዘቡ ምንጭ ባይታወቅም) ወራቤ ከተማ ላይ በርካታ መሬቶችን በሊዝ አሸንፋለች መቼም ለምን ይሆን ብሎ የሚጠይቅ ካለ እርግጠኛ ሁኑ ለቸርች አገልግሎት ነው የሚሆነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጴንጤዎች ለሚበትኑት በራሪ ወረቀት እንኳን መልስ ወረቀት መበተን አልቻልንም፡፡ አንዱ ወንድሜ ወራቤ ገበያ ላይ አጋጠመኝ ብሎ የነገረኝ ደግሞ ምን መሰላቹ? የገጠር ሴቶች ናቸው ሲገበያዩ ‹‹ቢሳ ሱም›› ሲሉ ሰምቼ በጣም ደነገጥኩኝ አለኝ። እዚህም ተደርሷል፡፡ ስለዚህ….. ስለዚህማ ስልጤ 100 ሙስሊም ነው የሚለውን ያረጀ ተረታችንን ትተን ቢያንስ ቢያንስ ለቤተሰባችን ስንል እንንቀሳቀስ፣ እንደራጅ፤ ተቸገሩትን እንርዳ፤ ጧሪ ያጡ በርካታ አረጋዊያን አሉ ፤በርካታ አይታሞች(ወላጅ አጥ ህጻናት) አሉ፤ ቤታቸው የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው በርካታ ሚስኪኖች አሉ፤ አይደለም ስለመንሃጅ አርካኑል ኢስላም አርካኑል ኢማንን የማያውቁ ፤ስለጠሃራ፣ ስለሂጃብ፣ የማያውቁ በርካታ ወገናችን አለ። እነ እንትና መስጂድ እነ እንትና መስጂድ ከሚለው ዝቅታ ከፍ ብለን ስለ ህዝባች እንኑር። እኛ መስጂድ ውስጥ መስጂድ ከገባው ወንድማችን ጋር በመንሃጅ ጉዳይ ለመጋደል እንፈላለጋለን እነሱ(ጰንጤዎች ደግሞ የመስጂዱን አቅጣጫ የማያውቀውን ሙስሊም ነኝ እያለ ብቻ የሚኖረውን እየነጠቀን ነው። እንንቃ እርስ በርስ ከመተቻቸት በዘለለ እኔ ለህዝቤ ምን ሰራሁ እንበል እና ራሳችንን እንጠይቅ። አበቃሁ እኔንም እናንተንም የስራ ሰዎች ያድረገን። ቸር ያሰማን ክርስትና
15918
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%8B%E1%8D%95%E1%88%8B%E1%88%B5%20%E1%88%BD%E1%8C%8D%E1%8C%8D%E1%88%AD
ላፕላስ ሽግግር
በሒሳብ ጥናት ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ስራ ላይ የሚውል የመደመራዊ ሽግግር ቢኖር ይሄው ላፕላስ ሽግግር የሚባለው ነው። ይህ ሽግግር በፊዚክስ፣ሒሳብ፣ በምህንድስናና በእድል ጥናት የዕውቀት ዘርፎች በከፍተኛ ስራ ላይ ይውላል። ሎጋሪዝም ማባዛትን ወደ መደመር እንደሚቀይርና ማባዛትን እንደሚያቃልል ሁሉ የላፕላስት ትራንስፎርም የካልኩለስን ሥነ ለውጥና ሥነ ማጎር ወደ ማባዛትና ማካፈል በማሻገር የካልኩለስን ተግባር ያቃልላል። የላፕላስ ሽግግር ከፎሪየር ሽግግር ጋር ተዛማጅ ቢሆንም ቅሉ የፎሪየር ሽግግር ፈንክሽኖችን ወይም መልእክትን ወደ መስረታዊ የርግብግብ ክፍላቸው ሲበትናቸው የላፕላስ ሽግግር ግን ወደ መሰረታዊ ቅርጻቸው ይበትናቸዋል። ሁለቱም ግን የውድድር እኩልዮሽን (ዲፈረንሺያል ኢኮዥን) ጥያቄወችን ለመፍታት የሚጠቅሙ ሂሳባዊ መሳሪያወች ናቸው። የላፕላስ ሽግግር በፊዚክስና በ ምህንድስና ከፍተኛ ጥቅም ያላቸው ጊዜ-የማይለውጣቸው ቀጥተኛ (ሊኒያር ታይም ኢንቫሪያንት) ሥርዓቶችን ለመፍታት ሲሆን ይህ ጉዳይ የኤሌክትሪክ ምህንድስናን፣ ብርሃናዊ መሳሪያወች ምህንድስናን ሌሎች ተነቀሳቃሽ እቃወችን በቀላሉ ለመተለም ይረዳል። በዚህ የትንታኔ ሥርዓት በጊዜ ግዛት ውስጥ ተቀምጠው ያሉ ጥያቄወችን ወደ ድግግሞሽ ግዛት ጣይቄዎች በማሻገር የሚደረገውን የስሌት ሂደት መቀነስ ነው። በጊዜ ውስጥ ያለ ስርዓት ሲሆን በድግግሞሽ ግዛት ያለ ሥርዓት የላፕላስ ሽግግር ምልክት ይሄን ይመስላል ቀጥተኛ ኦፕሬተር ሲሆን )ን 0) ወደ እንግዲህ ድግግሞሽ ያቅጣጫ ቁጥር ነው ይቀይራል። ታሪክ የላፕላስ ሽግግር በእውቁ የሒሳብና ከዋክብት ሊቅ ፒየ-ስሞን ላፕላስ ስም የተሰየመ ሲሆን፣ ይሄው አጥኝ የሽግግሩን ግኝት የተጠቀመበት የዕድል ጥናቱን በቀላሉ ለማካሄድ ነበር። ከላፕላስ በፊት እርግጥ ነው ኦይለር የሚከተለውን አይነት ጥረዛ(ኢንቴግራል) አጥንቷል፦ ይህንም ያጠናው የአንድ አንድ ውድድር እኩልዮሾችን መፍትሔ ለማግኘት ነበር፤ ነገር ግን ነግሩን ጠለቅ ብሎ የማየት ዝንባሌ አላሳየም። ዮሴፍ ሉዊ ላግራንግ የተሰኘው የፈረንሳይ የሂሳብ ሊቅም በበኩሉ የኦይለር አድናቂ እንደሞሆኑ መጠን የእድል ችፍገትን ለማስላት ተመሳሳይ ፎርሙላ ተጠቅሟል፦ ይህ ስሌት አሁን ካለንበት የላፕላስ ሽግግር ቀመር ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ዳሩ ግን ያሁን እውቀት አካል እንጂ ሙሉ በሙሉ የላፕላስ ሽግግርን እንደማይወክል ስምምነት ላይ ተደርሷል። ላፕላስ በ1782አካባቢ ከላይ የተጠቀሰውን የኦይለርን ቀመር ለለውድድር እኩልዮሽ መፍትሔነት ቢመረምርም ቅሉ በ1785 በጣም ወሳኝ ርምጃ ወስደ። ይሄውም ከላይ የተጻፉትን ሥነ-ጠረዛ እንደ የዲፈረንሻል ጥያቄ ከማየት ይልቅ እራሳቸውን የቻሉ የፈንክሽን አሻጋሪወች መሆናቸውን ተገነዘበ። ለዚህም ስራው እንዲረዳው ይህን የመሰለ የጥረዛ ቀመር መጠቀም ጀመረ፦ አንዳንድ የሂሳብ ታሪክ አጥኘወች ይህን ፈንክሽን የዘመናዊው ላፕላስ ሽግግር ኅልዮት አካል አድርገው ያዩታል። ተግባሩም አጠቃላይ የውድድር እኩልዮሾችን ከከባድ ወደ ቀላል በማሻገር ምፍትሔያቸውን በተሻገረው ቅርጽ መፈለግ ነበር። ቀጥሎም አሁን የሚታወቀውን የላፕላስ ሽግግር በመመርመር ጥልቅ የሆነ እምቅ ጥቅሙን ለመገንዘብ ቻለ። ላፕላስ የዮሴፍ ፎሪየርን የሙቀት ሥርፀት ጥናትና የፎሪየር ዝርዝር መፍትሔውን ውሱን ኃይል በመተቸት በአዲሱ ቀመሩ ፎርየር ከፈታቸው ጥያቄወች የሰፉ ጥያቄወችን መልስ ለማግኘት ቻለ። የላፕላስ ሽግግር ደንበኛ ትርጓሜ ግዛቱ ማናቸውም የውን ቁጥር 0፣ የሆነ አስረካቢ ቢሰጠን፣ የዚህ አስረክቢ የላፕላስ ሽግግር ትርጓሜ እንዲህ ነው: ፓራሜትር እዚህ ላይ የአቅጣጫ ቁጥር ናት፣ ማለት እና የውኑ ቁጥር ናቸው። የሥነ ጥረዛው (ኢንቴገራሉ) ምንነት እንደ አጠቃቀማችን ይለያያል። ለጥራዙ ህልውና የአስረካቢን በ[0,∞) መጠረዝ መቻል አስፈላጊ ነው።. ሁለት ጎን ላፕላስ ሽግግር ላፕላስ ሽግግር ሲባል አብላጫውን ጊዜ ትርጓሜው አንድ ጎን ላፕላስ ሽግግር ማለት ነው (0 እና ከ0 በላይ) ነገር ግን የላፕላስ ሽግግር ሁሎንም የውን ቁጥሮች እንዲያሳትፍ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል፣ ማለት የማጎሪያው መነሻና መድረሻ ከነጌቲቭ አዕላፍ እስከ ፖዚቲቭ አዕላፍ ማለት ነው። ሁለት ጎን የላፕላስ ሽግግር እንዲህ ይቀመራል፡ የላፕላስ ሽግግር ግልብጥ የላፕላስ ሽግግር ግልብጥ በእንዲህ መልኩ በአቅጣጫ ቁጥር ሥነ ጥረዛ ይጻፋል፡ እዚህ ላይ የውኑ ቁጥር ነው። የሽግግሩ ሥነ ጥረዛ ውሱን የሚሆንበት አካባቢ በየቦታው መጠረዝ የሚችል ከሆነ ላፕላስ ሽግግር ውሱን ነው የሚባለው የሚከተለው ጥገት ኅልው ሲሆን ነው። እንግዲህ ይህ እንዲሆን ቀላል መፈተኛው ዘዴ ኅልው ከሆነ የዚያ ፈንክሽን ላፕላስ ሽግግር ውሱን ነው፣ ስለሆነም አለ (ኅልው ነው)። የሽግግሩ ፀባዮችኛ እርጉጦች የላፕላስ ሽግግር ፀባዮች ሊኒያር የእንቅስቃሴ ስርዓቶችን ተንትኖ ለመረዳት የሚያስችሉ ብዙ ጥሩ ጸባዮች አሉት። በተለይ ዋናው ለዚህ ጉዳይ የሚጠቅመው ፀባዩ ውድድርን ወደ ማባዛት እና ጥረዛን ወደማካፈል በመቀየር ሂሳብን ማቃለሉ ነው። ይህ እንግዲህ ሎጋሪዝም ማባዛትን ወደ ሎጋሪዝም መደመር እና ማካፈልን ወደ ሎጋሪዝም መቀነስ እንደሚቀይረው አይነት ባህርይ ነው። ስለሆነም የላፕላስ ሽግግር የውድድር እኩልዮሽና የጥረዛ እኩልዮሽን ወደ ፖሊኖሚያል እኩልዮሽ በመቀየር ስራን ከማቀላጠፍ በላይ እጅግ ያቃልላል። በዚህ ወቅት በጊዜ ግዛት ውስጥ የነበሩት እኩልዮሾች ወደ ግዛት ስለሚሻገሩ፣ የተገኘውን የላፕላስ ሽግግር መፍትሔ ወደ ጊዜ ግዛት እንደገና መቀየር ግድ ይላል። ይሔውም የሚከናወነው በ መገልበጥ ነው። ሁለት ፈንክሽኖች እና ቢሰጡንና የላፕላስ ተሻጋሪዎቻቸው እና ቢሆኑ: ይህን ልብ በማለት፣ የላፕላስ ሽግግር ዋና ዋና ጠባዮች ከታች ይቀርባሉ የመጀመሪያ ዋጋ እርጉጥ: የመጨረሻ ዋጋ እርጉጥ: ማናቸውም ዋልታወች (የ በቁጥር ጠለል ግራ ጎን ላይ ከተገኙ በጊዜ ውስጥ ያለ የኤሌክትሪክ ኡደት -ግዛት ተመጣጣኙና እግዶሹ የላፕላስ ሽግግር ብዙውን ጊዜ በኤሌክትሪክ ኡደት (ሰርኪዩት) ትንታኔ ላይ ተጠቃሚነትን ያገኛል። አብዛኛውን ጊዜ የተሰጠን ዑደት ወደ -ግዛት ተመጣጣኙ ማሻገር ቀላል ነው። የዑደቱ አባላት በቀላሉ ወደ ተመጣጣኝ ተቃውሞአቸው (ኢምፔዳንስ) ይቀየራል፣ ይኼውም ፌዘር እንደሚገኝበት ስሌት ነው እንጅ ልዩ አይደለም። የሚከተለው ምስል ይህን ተግባር ባጭሩ ያሳያል እዚህ ላይ እንቅፋት(ሬዚዝስተር) በጊዜም ሆነ በኤስ-ግዛት አንድ አይነት ዋጋ አለው። የኤሌክትሪክ ምንጮች በዚህ ትንታኔ ውስጥ እንዳይወጡ የሚሆኑት ትንታኔ በሚጀመርበት ወቅት ዋጋ ካላቸው ነው። ለምሳሌ አቃቤው (ካፓሲተሩ) ሲጀመር ቮልቴጅ ካለው ወይንም የኤሌክትሪክ እልከኛው (ኢንደክተሩ) በውስጡ የኤሌክትሪክ ጅረት ካለው፣ በ -ግዛት ሆነው ያሉት ምንጮች በተሻጋሪው ዑደት ውስጥ መግባት ግድ ይላል። ማጣቀሻ ኤሌክትሪካል ኢንጂኔሪንግ አልጀብራ
52436
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B5%E1%89%B2%E1%89%A8%E1%8A%95%20%E1%88%83%E1%8B%8D%E1%8A%AA%E1%8A%95%E1%8C%8D
ስቲቨን ሃውኪንግ
እስጢፋኖስ ዊሊያም ሃውኪንግ (እ.ኤ.አ. ጥር 8 ቀን 1942 መጋቢት 14 ቀን 2018) እንግሊዛዊ የቲዎሬቲካል የፊዚክስ ሊቅ የኮስሞሎጂ ባለሙያ እና ደራሲ ሲሆን በሞቱ ጊዜ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የቲዎሬቲካል ኮስሞሎጂ ማእከል የምርምር ዳይሬክተር ነበሩ በ 1979 እና 2009 መካከል በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሉሲያን የሂሳብ ፕሮፌሰር ነበሩ። ሃውኪንግ በኦክስፎርድ ውስጥ ከዶክተሮች ቤተሰብ ተወለደ። በጥቅምት 1959 በ 17 አመቱ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጀመረ እና በፊዚክስ የመጀመሪያ ክፍል ዲግሪ አግኝቷል። በጥቅምት 1962 የድህረ ምረቃ ስራውን በካምብሪጅ ትሪኒቲ አዳራሽ የጀመረ ሲሆን እ.ኤ.አ. መጋቢት 1966 የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን በተግባራዊ ሂሳብ እና በቲዎሬቲካል ፊዚክስ በአጠቃላይ አንፃራዊነት እና ኮስሞሎጂ ስፔሻላይዝድ አግኝተዋል። እ.ኤ.አ. በ 1963 ሃውኪንግ ቀደም ብሎ የጀመረው ቀስ በቀስ እየተሻሻለ የመጣው የሞተር ነርቭ በሽታ (አሚዮትሮፊክ ላተራል ስክለሮሲስ ኤ ኤል ኤስ ለአጭር ጊዜ) ቀስ በቀስ በአስርተ ዓመታት ውስጥ ሽባ እንዳደረገው ታወቀ። ንግግሩን ካጣ በኋላ በመጀመሪያ የእጅ ማብሪያ ማጥፊያን በመጠቀም እና በመጨረሻም አንድ ነጠላ የጉንጭ ጡንቻን በመጠቀም ንግግርን በሚፈጥር መሳሪያ በኩል ተናገረ። የሃውኪንግ ሳይንሳዊ ስራዎች ከሮጀር ፔንሮዝ ጋር በጠቅላላ አንፃራዊነት ማዕቀፍ ውስጥ በስበት ነጠላ ንድፈ ሀሳቦች ላይ ትብብርን እና ጥቁር ቀዳዳዎች ጨረሮችን እንደሚያመነጩ የንድፈ ሃሳባዊ ትንበያ፣ ብዙ ጊዜ ሃውኪንግ ጨረር ይባላል። መጀመሪያ ላይ የሃውኪንግ ጨረር አወዛጋቢ ነበር። እ.ኤ.አ. በ 1970 ዎቹ መገባደጃ ላይ እና ተጨማሪ ምርምር ከታተመ በኋላ ግኝቱ በቲዎሬቲካል ፊዚክስ ውስጥ እንደ ትልቅ ግኝት በሰፊው ተቀባይነት አግኝቷል። ሃውኪንግ የአጠቃላይ አንፃራዊነት እና የኳንተም ሜካኒክስ ፅንሰ-ሀሳብ በህብረት የተብራራ የኮስሞሎጂ ፅንሰ-ሀሳብን ለማዘጋጀት የመጀመሪያው ነው። እሱ የኳንተም ሜካኒክስ የብዙ-ዓለማት ትርጓሜ ጠንካራ ደጋፊ ነበር። ሃውኪንግ በብዙ የታወቁ የሳይንስ ስራዎች የንግድ ስኬትን አስመዝግቧል በዚህም ፅንሰ-ሀሳቦቹን እና ኮስሞሎጂን በአጠቃላይ ተወያይቷል። የተሰኘው መጽሃፉ በእሁድ ታይምስ የባለሞያዎች ዝርዝር ላይ ለ237 ሳምንታት ሪከርድ ሰበረ። ሃውኪንግ የሮያል ሶሳይቲ ባልደረባ፣ የህይወት ዘመን የጳጳሳዊ ሳይንስ አካዳሚ አባል እና የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛው የሲቪል ሽልማት የፕሬዝዳንት የነፃነት ሜዳሊያ ተሸላሚ ነበር። እ.ኤ.አ. በ 2002 ሃውኪንግ በቢቢሲ የ100 ታላቋ ብሪታንያ ህዝብ ምርጫ 25 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ከ 50 ዓመታት በላይ በሞተር ነርቭ በሽታ ከኖረ በኋላ በ 76 ዓመቱ በ 14 2018 ሞተ. የመጀመሪያ ህይወት ቤተሰብ ሃውኪንግ የተወለደው እ.ኤ.አ. ጥር 8 ቀን 1942 በኦክስፎርድ ከአባታቸው ፍራንክ እና ኢሶቤል ኢሊን ሃውኪንግ (ከተወለደው ዎከር) ነው። የሃውኪንግ እናት በግላስጎው ስኮትላንድ ውስጥ ከዶክተሮች ቤተሰብ ተወለደች። ከዮርክሻየር የመጣው ባለጸጋ አባቱ ቅድመ አያቱ የእርሻ መሬት በመግዛት እራሱን ከመጠን በላይ ማራዘሙ እና ከዚያም በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በታላቅ የግብርና ጭንቀት ውስጥ ወድቋል። የአባታቸው ቅድመ አያት በቤታቸው ትምህርት ቤት በመክፈት ቤተሰቡን ከገንዘብ ውድመት ታደጉት። የቤተሰቦቻቸው የገንዘብ ችግር ቢኖርባቸውም፣ ሁለቱም ወላጆች በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ነበር፣ ፍራንክ ህክምናን ሲያነብ ኢሶቤል ደግሞ ፍልስፍናን፣ ፖለቲካን እና ኢኮኖሚክስን አንብቧል። ኢሶቤል ለህክምና ምርምር ተቋም ፀሃፊ ሆኖ ሰርቷል፣ ፍራንክ ደግሞ የህክምና ተመራማሪ ነበር። ሃውኪንግ ፊሊፕ እና ሜሪ የተባሉ ሁለት ታናናሽ እህቶች ነበሩት እና የማደጎ ወንድም ኤድዋርድ ፍራንክ ዴቪድ (1955–2003)። እ.ኤ.አ. በ 1950 የሃውኪንግ አባት በብሔራዊ የህክምና ምርምር ተቋም የፓራሲቶሎጂ ክፍል ኃላፊ በሆነ ጊዜ ቤተሰቡ ወደ ሴንት አልባንስ ሄርትፎርድሻየር ተዛወረ። በሴንት አልባንስ፣ ቤተሰቡ በጣም አስተዋይ እና በተወሰነ መልኩ ወጣ ገባ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፣ ምግቦች ብዙ ጊዜ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር መጽሃፍ በማንበብ ያሳልፋሉ። በትልቅ፣ በተዝረከረከ እና በደንብ ባልተጠበቀ ቤት ውስጥ ቆጣቢ ኑሮ ኖረዋል እና በለንደን ታክሲ ውስጥ ተጓዙ። የሃውኪንግ አባት በአፍሪካ ውስጥ ብዙ ጊዜ በማይሠራበት ወቅት፣ የተቀረው ቤተሰብ በማሎርካ አራት ወራትን ያሳለፈው የእናቱን ጓደኛ በርልን እና ባለቤቷን ገጣሚውን ሮበርት ግሬቭስን ለመጠየቅ ነው። የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ዓመታት ሴንት አልባንስ ለሴቶች ልጆች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለጥቂት ወራት ተምሯል። በዚያን ጊዜ ትናንሽ ወንዶች ልጆች በአንዱ ቤት መገኘት ይችላሉ. ሃውኪንግ በአንድ አመት መጀመሪያ ላይ አስራ አንድ -ፕላስ ካለፈ በኋላ በመጀመሪያ የራድልት ትምህርት ቤት እና ከሴፕቴምበር 1952 ጀምሮ በሴንት አልባንስ ትምህርት ቤት በሁለት ገለልተኛ (ማለትም ክፍያ የሚከፈል) ትምህርት ቤቶችን ተምሯል። ቤተሰቡ ለትምህርት ከፍተኛ ዋጋ ሰጥቷል. የሃውኪንግ አባት ልጁ በደንብ በሚታወቀው የዌስትሚኒስተር ትምህርት ቤት እንዲማር ፈልጎ ነበር ነገርግን የ13 አመቱ ሃውኪንግ የስኮላርሺፕ ፈተና በወጣበት ቀን ታሞ ነበር። ቤተሰቦቹ ያለ ስኮላርሺፕ የገንዘብ ድጋፍ የትምህርት ቤቱን ክፍያ መግዛት አልቻሉም፣ ስለዚህ ሃውኪንግ በሴንት አልባንስ ቀረ። አወንታዊ ውጤቱ ሃውኪንግ በቦርድ ጨዋታዎች፣ ርችቶች ማምረት፣ ሞዴል አውሮፕላኖች እና ጀልባዎች፣ እና ስለ ክርስትና እና ስለ ክርስትና ረጅም ውይይቶች ከሚወዳቸው የጓደኞቹ ቡድን ጋር መቀራረቡ ነበር። ከ1958 ዓ.ም ጀምሮ በሂሳብ መምህር ዲክራን ታህታ አማካኝነት ኮምፒውተር ከሰአት ክፍሎች፣ አሮጌ የስልክ መቀየሪያ ሰሌዳ እና ሌሎች እንደገና ጥቅም ላይ የዋሉ አካላት ገነቡ። ምንም እንኳን በትምህርት ቤት "አንስታይን" ተብሎ ቢታወቅም, ሃውኪንግ በመጀመሪያ በአካዳሚክ ስኬታማ አልነበረም. ከጊዜ በኋላ ለሳይንሳዊ ትምህርቶች ከፍተኛ ችሎታ ማሳየት ጀመረ እና በታህታ ተመስጦ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሂሳብ ለማንበብ ወሰነ። የሃውኪንግ አባት ለሂሳብ ተመራቂዎች ጥቂት ስራዎች ስለሌለባቸው ህክምና እንዲያጠና መከረው። ልጁም የራሱን አልማ ተማሪ በሆነው በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እንዲማር ፈለገ። በዚያን ጊዜ ሂሳብ ማንበብ ስለማይቻል ሃውኪንግ ፊዚክስ እና ኬሚስትሪ ለማጥናት ወሰነ። ርእሰ መምህሩ እስከሚቀጥለው አመት እንዲቆይ ቢመክሩም ሃውኪንግ በመጋቢት 1959 ፈተናውን ከወሰደ በኋላ የነፃ ትምህርት ዕድል አግኝቷል። የመጀመሪያ ዲግሪ ዓመታት ሃውኪንግ በጥቅምት 1959 በ17 ዓመቱ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ኦክስፎርድ ጀመረ። በመጀመሪያዎቹ አስራ ስምንት ወራት ውስጥ አሰልቺ እና ብቸኛ ነበር የአካዳሚክ ስራውን "በሚያስቅ ቀላል" አገኘው። የፊዚክስ አስተማሪው ሮበርት በርማን በኋላ ላይ "አንድ ነገር ማድረግ እንደሚቻል ማወቅ ለእሱ ብቻ አስፈላጊ ነበር, እና ሌሎች ሰዎች እንዴት እንዳደረጉት ሳያይ ማድረግ ይችላል." እንደ በርማን አባባል ሃውኪንግ "ከልጆች አንዱ ለመሆን" የበለጠ ጥረት ባደረገበት በሁለተኛውና በሦስተኛው አመቱ ለውጥ ተፈጠረ። ወደ ታዋቂ፣ ሕያው እና ብልህ የኮሌጅ አባል፣ ወደ ክላሲካል ሙዚቃ እና ሳይንሳዊ ልብ ወለድ አደገ። የለውጡ ከፊሉ የኮሌጁ ጀልባ ክለብ የሆነውን የዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጀልባ ክለብን ለመቀላቀል ባደረገው ውሳኔ የቀዘፋ ቡድን አባላትን ደግፏል። በወቅቱ የቀዘፋው አሰልጣኝ ሃውኪንግ ደፋር ምስል በማዳበር መርከበኞቹን ወደ ተበላሹ ጀልባዎች የሚያደርሱ ኮርሶችን በመምራት 1,000 ሰዓታት ያህል እንዳጠና ገልጿል። እነዚህ የማያስደስት የጥናት ልማዶች የመጨረሻ ውድድሩን መቀመጥ ፈታኝ አድርገውታል፣ እና እውነተኛ እውቀት ከሚጠይቁት ይልቅ የቲዎሬቲካል ፊዚክስ ጥያቄዎችን ብቻ ለመመለስ ወሰነ። የአንደኛ ደረጃ ዲግሪ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ በኮስሞሎጂ ላቀደው የድህረ ምረቃ ጥናት የመቀበል ቅድመ ሁኔታ ነበር። ተጨንቆ፣ ከፈተናው በፊት በነበረው ምሽት ጥሩ እንቅልፍ ተኝቷል፣ እና የመጨረሻው ውጤት በአንደኛ እና በሁለተኛ ደረጃ በክብር መካከል ባለው ድንበር ላይ ነበር ይህም ከኦክስፎርድ ፈታኞች ጋር ቪቫ (የአፍ ምርመራ) አደረገ። ሃውኪንግ እንደ ሰነፍ እና አስቸጋሪ ተማሪ መቆጠሩ አሳስቦት ነበር። ስለዚህ እቅዱን እንዲገልጽ በቪቫ ሲጠየቅ፣ “አንደኛ ከሸልሙኝ፣ ወደ ካምብሪጅ እሄዳለሁ፣ ሁለተኛ ከተቀበልኩ በኦክስፎርድ እቆያለሁ፣ ስለዚህ መጀመሪያ እንደምትሰጡኝ እጠብቃለሁ። እሱ ከሚያምነው በላይ ከፍ ያለ ግምት ተይዞ ነበር; በርማን እንደተናገረው፣ ፈታሾቹ “ከራሳቸው በጣም ብልህ ከሆነ ሰው ጋር እንደሚነጋገሩ ለመገንዘብ በቂ አስተዋዮች ነበሩ”። በፊዚክስ የመጀመሪያ ክፍል ቢኤ ዲግሪ ተቀብሎ ከጓደኛው ጋር ወደ ኢራን ያደረጉትን ጉዞ ካጠናቀቀ በኋላ በጥቅምት 1962 በካምብሪጅ ትሪኒቲ አዳራሽ የድህረ ምረቃ ስራውን ጀመረ። የድህረ ምረቃ ዓመታት የሃውኪንግ የዶክትሬት ተማሪ ሆኖ የመጀመሪያ አመት አስቸጋሪ ነበር። ከታዋቂው የስነ ፈለክ ተመራማሪ ፍሬድ ሆዬል ይልቅ የዘመናዊ ኮስሞሎጂ መስራቾች አንዱ የሆነውን ዴኒስ ዊልያም ን እንደ ተቆጣጣሪ መመደቡ መጀመሪያ ላይ ቅር ብሎት ነበር፣ እና የሒሳብ ትምህርት በአጠቃላይ አንፃራዊነት እና ኮስሞሎጂ ውስጥ ለስራ በቂ እንዳልሆነ ተገንዝቦ ነበር። የሞተር ነርቭ በሽታ እንዳለበት ከታወቀ በኋላ, ሃውኪንግ በመንፈስ ጭንቀት ውስጥ ወደቀ ምንም እንኳን ዶክተሮቹ ትምህርቱን እንዲቀጥል ቢመከሩም, ምንም እንኳን ትንሽ ጥቅም እንደሌለው ተሰማው. ዶክተሮቹ ከተነበዩት በላይ በሽታው በዝግታ እያደገ ሄዷል። ምንም እንኳን ሃውኪንግ ሳይደገፍ መራመድ ቢከብደውም፣ ንግግሩም ሊታወቅ የማይችል ቢሆንም፣ ሁለት ዓመት ብቻ እንደቀረው በመጀመርያ ምርመራው መሠረተ ቢስ ሆኖ ተገኝቷል። በ ማበረታቻ ወደ ስራው ተመለሰ። ሃውኪንግ በጁን 1964 በነበረው ንግግር የፍሬድ ሆይል እና የተማሪውን ጃያንት ናርሊካርን ስራ በይፋ ሲቃወም የብሩህነት እና የድፍረት ስም ማዳበር ጀመረ። ሃውኪንግ የዶክትሬት ትምህርቱን ሲጀምር በፊዚክስ ማህበረሰብ ውስጥ ስለ አጽናፈ ሰማይ አፈጣጠር ወቅታዊ ላይ ብዙ ክርክር ነበር። በጥቁር ጉድጓዶች መሃል ላይ ያለው የጠፈር ጊዜ ነጠላነት በሮጀር ፔንሮዝ ቲዎሪ በመነሳሳት ሃውኪንግ ተመሳሳይ አስተሳሰብን ለጽንፈ ዓለሙ ሁሉ ተግባራዊ አደረገ። እና በ 1965 ውስጥ, በዚህ ርዕስ ላይ የመመረቂያ ጽሁፎችን ጻፈ. የሃውኪንግ ተሲስ በ 1966 ጸድቋል. ሌሎች አዎንታዊ እድገቶች ነበሩ: ሃውኪንግ በካምብሪጅ ውስጥ በጎንቪል እና በካዩስ ኮሌጅ የምርምር ህብረት አግኝቷል. የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በተግባራዊ ሂሳብ እና በቲዎሬቲካል ፊዚክስ፣ በጠቅላላ አንፃራዊነት እና ኮስሞሎጂ ስፔሻላይዝድ በመጋቢት 1966 ዓ.ም. እና ድርሰቱ ከፔንሮዝ ጋር የዚያን አመት የተከበረውን የአዳም ሽልማትን በማሸነፍ ከፍተኛ ሽልማቶችን አጋርቷል። ሙያ ከ1966-1975 ዓ.ም በስራው እና ከፔንሮዝ ጋር በመተባበር ሃውኪንግ በዶክትሬት ዲግሪው ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳሰሰውን ነጠላ ንድፈ ሃሳቦችን አራዘመ። ይህ የነጠላ አካላት መኖርን ብቻ ሳይሆን አጽናፈ ሰማይ እንደ ነጠላነት ሊጀምር ይችላል የሚለውን ንድፈ ሃሳብም ይጨምራል። የጋራ ድርሰታቸው በ1968ቱ የስበት ምርምር ፋውንዴሽን ውድድር አንደኛ ሆኖ የወጣው። እ.ኤ.አ. በ1970 አጽናፈ ዓለማት ለአጠቃላይ የአንፃራዊነት ፅንሰ-ሀሳብ የሚታዘዝ ከሆነ እና በአሌክሳንደር ፍሪድማን ከተዘጋጁት የፊዚካል ኮስሞሎጂ ሞዴሎች ጋር የሚስማማ ከሆነ፣ እንደ ነጠላነት መጀመሩን የሚያሳይ ማረጋገጫ አሳትመዋል። እ.ኤ.አ. በ1969 ሃውኪንግ በካይየስ ለመቆየት በልዩ ሁኔታ የተፈጠረውን የሳይንስ ልዩነት ህብረት ተቀበለ። እ.ኤ.አ. በ 1970 ሃውኪንግ የጥቁር ጉድጓድ ተለዋዋጭነት ሁለተኛ ህግ ተብሎ የሚታወቀውን የጥቁር ጉድጓድ ክስተት አድማስ በጭራሽ ሊቀንስ እንደማይችል አውጥቷል። ከጄምስ ኤም ባርዲን እና ብራንደን ካርተር ጋር፣ ከቴርሞዳይናሚክስ ጋር ተመሳሳይነት በመሳል አራቱን የብላክ ሆል ሜካኒኮች ህግጋትን አቅርቧል።ለሃውኪንግ ብስጭት፣የጆን ዊለር ተመራቂ ተማሪ የሆነው ጃኮብ ቤከንስታይን በመቀጠል ቴርሞዳይናሚክ ፅንሰ ሀሳቦችን ተግባራዊ ለማድረግ እና በመጨረሻም በትክክል ሄደ። በጥሬው. እ.ኤ.አ. በ 1970 ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሃውኪንግ ሥራ ከካርተር ቨርነር እስራኤል እና ዴቪድ ሲ ሮቢንሰን ጋር የዊለርን ያለፀጉር ንድፈ ሃሳብ አጥብቆ ደግፎ ነበር ይህም አንድ ጥቁር ቀዳዳ ከየትኛውም የመጀመሪያው ቁሳቁስ ቢፈጠር ሙሉ በሙሉ ሊገለጽ እንደሚችል ይናገራል የጅምላ, የኤሌክትሪክ ክፍያ እና የማሽከርከር ባህሪያት. “ጥቁር ሆልስ” በሚል ርዕስ የጻፈው ድርሰቱ በጥር 1971 የስበት ምርምር ፋውንዴሽን ሽልማት አሸንፏል።የሃውኪንግ የመጀመሪያ መጽሃፍ፣ ከጆርጅ ኤሊስ ጋር የተጻፈው በ1973 ታትሟል። ከ 1973 ጀምሮ ሃውኪንግ ወደ ኳንተም ስበት እና የኳንተም መካኒኮች ጥናት ገባ። በዚህ አካባቢ ያከናወነው ሥራ ወደ ሞስኮ በመጎብኘት እና ከያኮቭ ቦሪሶቪች ዜልዶቪች እና አሌክሲ ስታሮቢንስኪ ጋር ባደረጉት ውይይት ተነሳስተው ሥራው በእርግጠኝነት ባልታወቀ መርህ መሠረት የሚሽከረከሩ ጥቁር ቀዳዳዎች ቅንጣቶችን እንደሚለቁ አሳይቷል ለሃውኪንግ ብስጭት ብዙ የተፈተሸ ስሌት ጥቁር ጉድጓዶች በጭራሽ ሊቀንሱ አይችሉም ከሚለው ሁለተኛው ህግ ጋር የሚቃረኑ ግኝቶችን አቅርቧል እና የቤከንስታይን ስለ ኢንትሮፒያቸው ያለውን ምክንያት ይደግፋል። ሃውኪንግ እ.ኤ.አ. ከ1974 ጀምሮ ያቀረበው ውጤቶቹ እንደሚያሳየው ዛሬ ሃውኪንግ ጨረር በመባል የሚታወቀው ጥቁር ቀዳዳዎች ጨረሮችን እንደሚያመነጩ እና ጉልበታቸውን እስኪጨርሱ እና እስኪተን ድረስ ሊቀጥል ይችላል. መጀመሪያ ላይ የሃውኪንግ ጨረር አወዛጋቢ ነበር። እ.ኤ.አ. በ 1970 ዎቹ መገባደጃ ላይ እና ተጨማሪ ምርምር ከታተመ በኋላ ግኝቱ በቲዎሬቲካል ፊዚክስ ውስጥ ትልቅ ግኝት ሆኖ በሰፊው ተቀባይነት አግኝቷል ሃውኪንግ የሃውኪንግ ጨረር ከታወጀ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በ 1974 የሮያል ሶሳይቲ ባልደረባ ተመረጠ በዛን ጊዜ እሱ ከታናሽ የሳይንስ ሊቃውንት አንዱ ነበር. ሃውኪንግ እ.ኤ.አ. 1 ጥቁር ጉድጓድ ነበር. ውርዱ ጥቁር ቀዳዳዎች የሉም የሚለውን ሃሳብ በመቃወም "የኢንሹራንስ ፖሊሲ" ነበር. ሃውኪንግ በ1990 ውድድሩን እንዳጣ አምኗል።ይህ ውርርድ ከብዙዎቹ መካከል የመጀመሪያው የሆነው ከቶርን እና ከሌሎች ጋር ነው።ሃውኪንግ ከካልቴክ ጋር ያለውን ግንኙነት ጠብቆ ነበር፣ከዚህ የመጀመሪያ ጉብኝት ጀምሮ በየአመቱ ማለት ይቻላል አንድ ወር አሳልፏል። 1975-1990 (አውሮፓ) ሃውኪንግ በ1975 ወደ ካምብሪጅ ተመለሰ በስበት ፊዚክስ አንባቢ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ። እ.ኤ.አ. በ 1970 ዎቹ አጋማሽ እና መገባደጃ ላይ ህዝባዊ ፍላጎት በጥቁር ጉድጓዶች እና እነሱን በማጥናት ላይ የነበሩት የፊዚክስ ሊቃውንት እያደገ የመጣበት ወቅት ነበር። ሃውኪንግ ለህትመት እና ለቴሌቭዥን በመደበኛነት ቃለ መጠይቅ ይደረግለት ነበር።በተጨማሪም ለስራው ከፍተኛ የአካዳሚክ እውቅና አግኝቷል። እ.ኤ.አ. በ 1975 ሁለቱም የኤዲንግተን ሜዳሊያ እና ፒየስ የወርቅ ሜዳሊያ እና በ 1976 የዳኒ ሄኔማን ሽልማት የማክስዌል ሜዳሊያ እና ሽልማት እና የሂዩዝ ሜዳሊያ ተሸልመዋል እ.ኤ.አ. በ1977 በስበት ፊዚክስ ወንበር ፕሮፌሰር ሆነው ተሾሙ። በሚቀጥለው ዓመት የአልበርት አንስታይን ሜዳሊያ እና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት አግኝተዋል። እ.ኤ.አ. በ 1979 ሃውኪንግ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሉሲያን የሂሳብ ፕሮፌሰር ተመረጠ። በዚህ ሚና የመክፈቻ ንግግራቸው፡ “መጨረሻው በቲዎሬቲካል ፊዚክስ እይታ ላይ ነውን?” የሚል ርዕስ ነበረው። እና የፊዚክስ ሊቃውንት እያጠኗቸው ያሉትን በርካታ አስደናቂ ችግሮችን ለመፍታት =8 ን እንደ መሪ ሃሳብ አቅርቧል። የእሱ ማስተዋወቅ ከጤና-ቀውስ ጋር የተገጣጠመ ሲሆን ይህም ምንም እንኳን ሳይወድ በቤት ውስጥ አንዳንድ የነርሲንግ አገልግሎቶችን እንዲቀበል አድርጓል። ከዚሁ ጋር በሒሳብ ማስረጃዎች ላይ አጥብቆ ከመናገር ይልቅ በፊዚክስ አካሄዱ ላይ ሽግግር እያደረገ ነበር። ለኪፕ ቶርን "ከጠንካራነት ትክክል መሆንን እመርጣለሁ" ሲል ተናግሯል። እ.ኤ.አ. በ 1981 በጥቁር ጉድጓድ ውስጥ ያለው መረጃ ጥቁር ጉድጓድ በሚተንበት ጊዜ ሊጠፋ በማይችል ሁኔታ ይጠፋል የሚል ሀሳብ አቀረበ ይህ የመረጃ አያዎ (ፓራዶክስ) የኳንተም ሜካኒክስ መሰረታዊ መርሆችን ይጥሳል፣ እና "የጥቁር ሆል ጦርነት" ከሊዮናርድ ሱስኪንድ እና ከጄራርድ 'ት ሁፍት ጋር ጨምሮ ለዓመታት ክርክር መርቷል።የኮስሞሎጂካል የዋጋ ግሽበት ከቢግ ባንግ በኋላ አጽናፈ ዓለሙ መጀመሪያ ላይ በሚያስደንቅ ፍጥነት መስፋፋቱን የሚጠቁም ፅንሰ-ሀሳብ ወደ ቀርፋፋ መስፋፋት ከመምጣቱ በፊት በአላን ጉት ሀሳብ የቀረበ እና እንዲሁም በአንድሬ ሊንዴ የተሰራ ነው። እ.ኤ.አ. በጥቅምት 1981 በሞስኮ ከተካሄደው ኮንፈረንስ በኋላ ሃውኪንግ እና ጋሪ ጊቦንስ በ1982 የበጋ ወቅት የኑፍፊልድ አውደ ጥናት በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ በዋናነት ያተኮረው አውደ ጥናት በኑፍፊልድ ወርክሾፕ አዘጋጁ። ወደ አጽናፈ ሰማይ አመጣጥ የኳንተም-ቲዎሪ ምርምር መስመር። እ.ኤ.አ. በ 1981 በቫቲካን ኮንፈረንስ ወደ አጽናፈ ሰማይ ወይም መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ድንበር ላይኖር እንደሚችል የሚጠቁሙ ስራዎችን አቅርበዋል በመቀጠል ሃውኪንግ ከጂም ሃርትል ጋር በመተባበር ጥናቱን ያዳበረ ሲሆን በ1983 ደግሞ ሃርትል-ሃውኪንግ ግዛት በመባል የሚታወቅ ሞዴል አሳትመዋል። ከፕላንክ ዘመን በፊት አጽናፈ ሰማይ በቦታ-ጊዜ ውስጥ ምንም ወሰን እንደሌለው ሀሳብ አቀረበ። ከቢግ ባንግ በፊት ጊዜ አልነበረውም እና የአጽናፈ ሰማይ መጀመሪያ ጽንሰ-ሀሳብ ትርጉም የለሽ ነው የጥንታዊው ቢግ ባንግ ሞዴሎች የመጀመሪያ ነጠላነት ከሰሜን ዋልታ ጋር በሚመሳሰል ክልል ተተካ። አንድ ሰው ከሰሜን ዋልታ ወደ ሰሜን መሄድ አይችልም, ነገር ግን ምንም ወሰን የለም በቀላሉ ሁሉም የሰሜን መስመሮች የሚገናኙበት እና የሚያልቁበት ነጥብ ነው. መጀመሪያ ላይ፣ ድንበር የለሽ ፕሮፖዛል የተዘጋውን አጽናፈ ሰማይ ይተነብያል፣ እሱም በእግዚአብሔር መኖር ላይ አንድምታ ነበረው። ሃውኪንግ እንዳብራራው፣ "ዩኒቨርስ ድንበሮች ባይኖሩት ግን ራሱን የቻለ ከሆነ...እግዚአብሔር አጽናፈ ሰማይ እንዴት እንደጀመረ የመምረጥ ነፃነት አይኖረውም ነበር።" ሃውኪንግ የፈጣሪን መኖር አልከለከለም ፣በጊዜ አጭር ታሪክ ውስጥ “የተዋሃደ ንድፈ ሃሳብ የራሱን ህልውና የሚያመጣ ነውን?” ሲል ጠይቋል ፣እንዲሁም “ሙሉ ንድፈ-ሀሳብ ካገኘን የመጨረሻው ይሆናል” ብሏል። የሰውን ምክንያት ማሸነፍ ለዚያ የእግዚአብሔርን ሀሳብ ማወቅ አለብን"; በመጀመሪያ ሥራው፣ ሃውኪንግ ስለ እግዚአብሔር በምሳሌያዊ አነጋገር ተናግሯል። በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ የአጽናፈ ሰማይን አመጣጥ ለማብራራት የእግዚአብሔር መኖር አስፈላጊ እንዳልሆነ ጠቁሟል. ከጊዜ በኋላ ከኒይል ቱሮክ ጋር የተደረገው ውይይት የእግዚአብሔር ሕልውና ክፍት ከሆነው አጽናፈ ዓለም ጋር የሚስማማ መሆኑን እንዲገነዘቡ አድርጓል። በጊዜ ቀስቶች አካባቢ በሃውኪንግ የተደረገ ተጨማሪ ስራ እ.ኤ.አ. በ 1985 የወረቀት ንድፈ ሀሳብ ታትሟል ድንበር የለሽ ሀሳብ ትክክል ከሆነ ያኔ አጽናፈ ሰማይ መስፋፋቱን ሲያቆም እና በመጨረሻ ሲወድቅ ጊዜው ወደ ኋላ ይመለሳል በዶን ፔጅ የተፃፈው ወረቀት እና በሬይመንድ ላፍላሜ የተፃፈው ገለልተኛ ስሌቶች ሃውኪንግ ይህንን ፅንሰ-ሀሳብ እንዲያነሳ አድርጓቸዋል። ክብር መሰጠቱን ቀጥሏል፡ እ.ኤ.አ. በ1981 የአሜሪካ ፍራንክሊን ሜዳሊያ ተሸልሟል እና በ1982 አዲስ አመት ክብር የብሪቲሽ ኢምፓየር ትዕዛዝ አዛዥ ሾመ። እነዚህ ሽልማቶች የሃውኪንግን የፋይናንሺያል ሁኔታ ጉልህ ለውጥ አላደረጉም እና የልጆቹን ትምህርት እና የቤት ወጪዎችን ፋይናንስ ለማድረግ በማነሳሳት በ 1982 ስለ አጽናፈ ሰማይ ለሰፊው ህዝብ ተደራሽ የሆነ ታዋቂ መጽሐፍ ለመጻፍ ወሰነ በአካዳሚክ ፕሬስ ከማተም ይልቅ የጅምላ ገበያ አሳታሚ ከሆነው ባንተም ቡክስ ጋር ውል ተፈራረመ እና ለመጽሃፉ ትልቅ እድገት አግኝቷል። የጊዜ አጭር ታሪክ ተብሎ የሚጠራው የመጽሐፉ የመጀመሪያ ረቂቅ በ1984 ተጠናቀቀ።ሃውኪንግ በንግግር መፍጠሪያ መሳሪያው ካሰራቸው የመጀመሪያ መልእክቶች አንዱ ረዳቱ የታይም አጭር ታሪክ ፅፎ እንዲጨርስ ያቀረበው ጥያቄ ነው። በባንታም የሚገኘው የሱ አርታኢ ፒተር ጉዛርዲ ሃሳቦቹን በግልፅ ቴክኒካል ባልሆነ ቋንቋ እንዲያብራራ ገፋፍቶታል ይህ ሂደት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከሚሄደው ተናዳፊ ሃውኪንግ ብዙ ክለሳዎችን የሚያስፈልገው። መጽሐፉ በኤፕሪል 1988 በዩኤስ እና በሰኔ ወር በእንግሊዝ ታትሟል እና ያልተለመደ ስኬት ሆኖ ተገኝቷል በፍጥነት በሁለቱም ሀገራት ከፍተኛ የተሸጠው ዝርዝር ውስጥ በመውጣት እና እዚያ ለወራት ቆየ። መጽሐፉ ወደ ብዙ ቋንቋዎች ተተርጉሟል, እና በመጨረሻም ወደ 9 ሚሊዮን የሚገመቱ ቅጂዎች ተሽጧል. የሚዲያ ትኩረት ከፍተኛ ነበር፣ እና ኒውስዊክ መጽሔት ሽፋን እና የቴሌቭዥን ልዩ ሁለቱም “የዩኒቨርስ ጌታ” ሲሉ ገልፀውታል። ስኬት ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማቶችን አስገኝቷል፣ ነገር ግን የታዋቂነት ሁኔታ ተግዳሮቶችም ጭምር። ሃውኪንግ ስራውን ለማስተዋወቅ ብዙ ተጉዟል፣ እና በትናንሽ ሰአታት ድግስ እና መደነስ ይወድ ነበር። ግብዣውን እና ጎብኝዎችን አለመቀበል መቸገሩ ለስራ እና ለተማሪዎቹ የተወሰነ ጊዜ እንዲቆይ አድርጎታል። አንዳንድ ባልደረቦች ሃውኪንግ በአካለ ጎደሎነቱ ምክንያት ስለተሰማው ትኩረት ተቆጥተው ነበር። አምስት ተጨማሪ የክብር ዲግሪዎችን፣ የሮያል አስትሮኖሚካል ሶሳይቲ የወርቅ ሜዳሊያ (1985)፣ የፖል ዲራክ ሜዳሊያ (1987) እና፣ ከፔንሮዝ፣ ከታዋቂው (1988) ጋር በጋራ ጨምሮ ተጨማሪ የትምህርት እውቅና አግኝቷል። እ.ኤ.አ. በ 1989 የልደት ክብር የክብር ጓደኛ ተሾመ በ 1990 ዎቹ መገባደጃ ላይ የእንግሊዝ የሳይንስ የገንዘብ ድጋፍ ፖሊሲን በመቃወም የ ውድቅ እንዳደረገ ተዘግቧል 1990-2000 (አውሮፓዊ) ሃውኪንግ በፊዚክስ ውስጥ ስራውን ቀጠለ፡ እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. በ1994 በካምብሪጅ ኒውተን ኢንስቲትዩት ሃውኪንግ እና ፔንሮዝ በ1996 "የህዋ እና የጊዜ ተፈጥሮ" በሚል የታተሙ ተከታታይ ስድስት ትምህርቶችን ሰጥተዋል። እ.ኤ.አ. በ1997 ከኪፕ ቶርን እና ከካልቴክ ባልደረባ ጆን ፕሬስኪል ጋር የተደረገውን የ1991 የህዝብ ሳይንሳዊ ውርርድ አምኗል። ሃውኪንግ የፔንሮዝ የ"ኮስሚክ ሳንሱር ግምት" ሀሳብ በአድማስ ውስጥ ያልታሸጉ "ራቁት ነጠላ ነገሮች" ሊኖሩ እንደማይችሉ ትክክል መሆኑን ተወራርዶ ነበር። የእሱ ስምምነት ያለጊዜው ሊሆን እንደሚችል ካወቀ በኋላ፣ አዲስ እና የበለጠ የተጣራ ውርርድ ተደረገ። ይህ እንደዚህ ያሉ ነጠላ ነገሮች ያለ ተጨማሪ ሁኔታዎች እንደሚከሰቱ ገልጿል። በዚያው ዓመት፣ ቶርን፣ ሃውኪንግ እና ፕረስኪል ሌላ ውርርድ አደረጉ፣ በዚህ ጊዜ ስለ ጥቁር ጉድጓድ መረጃ አያዎ (ፓራዶክስ)። ቶርን እና ሃውኪንግ አጠቃላይ አንፃራዊነት ለጥቁር ጉድጓዶች መፈልፈያ እና መረጃ ማጣት የማይቻል ስላደረገው በሃውኪንግ ጨረር የተሸከመው የጅምላ ሃይል እና መረጃ “አዲስ” መሆን አለበት እንጂ ከጥቁር ቀዳዳ ክስተት አድማስ መሆን የለበትም ሲሉ ተከራክረዋል። ይህ የጥቃቅን ምክንያት የኳንተም መካኒኮችን ስለሚቃረን፣ የኳንተም ሜካኒክስ ንድፈ ሐሳብ እንደገና መፃፍ ይኖርበታል። ፕሬስኪል በተቃራኒው ተከራክሯል፣ ኳንተም ሜካኒክስ በጥቁር ጉድጓድ የሚለቀቀው መረጃ ቀደም ሲል ከወደቀው መረጃ ጋር ስለሚገናኝ በአጠቃላይ አንፃራዊነት የተሰጠው የጥቁር ጉድጓዶች ጽንሰ-ሀሳብ በተወሰነ መንገድ መሻሻል አለበት ብሏል። ሳይንስን ለብዙ ተመልካቾች ማምጣትን ጨምሮ ሃውኪንግ ይፋዊ መገለጫውን ጠብቋል። በኤሮል ሞሪስ ዳይሬክት የተደረገ እና በስቲቨን ስፒልበርግ ፕሮዲዩስ የሆነ የፊልም እትም በ1992 ታየ። ሃውኪንግ ፊልሙ ባዮግራፊያዊ ሳይሆን ሳይንሳዊ እንዲሆን ፈልጎ ነበር፣ ነገር ግን እሱ በሌላ መልኩ አሳምኖታል። ፊልሙ, ወሳኝ ስኬት ቢሆንም, በሰፊው አልተለቀቀም. በ1993 ብላክ ሆልስ እና ቤቢ ዩኒቨርስ እና ሌሎች ድርሰቶች በሚል ርዕስ የታዋቂ-ደረጃ ድርሰቶች፣ ቃለመጠይቆች እና ንግግሮች ታትመዋል እና ስድስት ክፍሎች ያሉት ተከታታይ የቴሌቭዥን ስቴፈን ሃውኪንግ ዩኒቨርስ እና ተጓዳኝ መጽሃፍ በ1997 ታየ። ሃውኪንግ እንደጸና በዚህ ጊዜ ትኩረቱ ሙሉ በሙሉ በሳይንስ ላይ ነበር 2000–2018 (አውሮፓዊ) ሃውኪንግ ለታዋቂ ተመልካቾች ጽሑፎቹን በመቀጠል በ2001 ዘ ዩኒቨርስ በአጭሩ አሳተመ እና በ2005 ከሊዮናርድ ሎዲኖው ጋር የፃፉትን የቀድሞ ስራዎቹን ለብዙ ተመልካቾች ተደራሽ ለማድረግ በማለም የፃፉትን እና አምላክ ኢንቲጀርን ፈጠረ፣ በ 2006 ታየ። ከቶማስ ሄርቶግ በ እና ጂም ሃርትል ከ2006 ጀምሮ ሃውኪንግ የኮስሞሎጂን ከላይ ወደ ታች ያዘጋጀው ፅንሰ-ሀሳብ ፈጠረ። ስለዚህም የአጽናፈ ዓለሙን ውቅር የሚተነብይ ንድፈ ሐሳብ ከአንድ የተለየ የመነሻ ሁኔታ መቅረጽ ተገቢ አይደለም ይላል። ይህን ሲያደርጉ፣ ንድፈ ሃሳቡ ጥሩ የማስተካከል ጥያቄን ሊፈታ የሚችልበትን ሁኔታ ይጠቁማል። ሃውኪንግ ወደ ቺሊ፣ ኢስተር ደሴት፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስፔን (የፎንሴካ ሽልማትን በ2008 ለመቀበል)፣ ካናዳ እና በርካታ ወደ አሜሪካ የተደረጉ ጉዞዎችን ጨምሮ በሰፊው መጓዙን ቀጠለ። ከአካል ጉዳቱ ጋር በተያያዙ ተጨባጭ ምክንያቶች፣ ሃውኪንግ ከጊዜ ወደ ጊዜ በግል ጄት ይጓዛል፣ እና እ.ኤ.አ. በ2011 የአለምአቀፍ ጉዞ ብቸኛው መንገድ
15726
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%9D%E1%88%B5%E1%8A%AB%E1%8B%AC%20%E1%8A%85%E1%8B%99%E1%8A%93%E1%8A%95%20%E1%88%98%E1%8B%B5%E1%8A%80%E1%8A%94%20%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9D
ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም
ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን፣ አዲስ አበባ የዚህ ቤተ ክርስቲያን ጽላት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገራችን ኢትዮጵያ በፋሺስት ኢጣልያ በተወረረች ጊዜ በስደት እንግሊዝ አገር ባዝ በተባለ ከተማ ሲኖሩ፣ ጥር ቀን ዓ/ም በጊዜው በስደት ኢየሩሳሌም ለነበሩት ወደ ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ (በኋላ አቡነ ባስልዮስ) አንድ ፅላትና ለአገልግሎት የሚበቁ አምስት መነኮሳትን ወደእንግሊዝ አገር እንዲልኩላቸው በአባ ሐና ጅማ በላኩት ደብዳቤ መሠረት ተልኮ በስደት የኖረ ፅላት ነበር። ጃንሆይ]] የስደት መልእክት== “ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ይድረስ ከብፁዕ አባቴ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ እንደምን ሰንብተዋል እኛ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነን። እስካሁን ባለነው አኳኋን የምናስበው ለናንተ ነው እንጂ ወደኛ ምንም የሚያሳስብ የለም። ይልቁንም የኛ እዚህ መሆንና በየጊዜው ጀኔቭ በሚደረገው ስብሰባ ቢፈቀድልን የኛ መሄድ ባይፈቀድልንም መላክተኛችንን መላክ ለመጣንበት ጉዳይ ዋና ረዳታችን ስለሆነ የፈጣሪያችን ፍርድ የኢትዮጵያን ጉዳይ እስካጠቃለልን ድረስ እዚሁ ሆኖ ማዳመጥ የሚያስፈልግ መሆኑን ስለተረዳነው የፈጣሪያችንን ቁርጥ እስክናውቅ ድረስ በዚሁ በእንግሊዝ አገር ለመቆየት ቆርጠናል። የእግዚአብሔር ቸርነት ፈቅዶልንና አሰናብቶን ወደ ኢየሩሳሌም እስከምንመጣበት ቀን ድረስ የሃይማኖት ችግር እንዳያገኘን የሚያድጉትም ልጆቻችን የሃይማኖታቸውን መሠረት እንዳያጡት አስበን አንድ ጽላትና አምስት መነኮሳት የሚያስፈልጉትን ንዋየ ቅድሳትና መጻሕፍት ሰጥተውት ይዞ እንዲመጣ አባ ሐናን ልኬዋለሁና ከመምህር ገሪማ ጋራ ተማክራችሁ ዐቢይ ጾም ሳይገባ እንዲደርስ አድርጋችሁ እንድትልኩልን ይሁን። በየጠረፋችንም ተሰደው በሰው ግዛት ላሉትም ሰዎቻችን እንደዚሁ ሰው መላክ አስፈላጊ ሳይሆን አይቀርምና እየተመካከራችሁበትና ፈቃዱ የሚሆን መነኩሴ እየመረጣችሁ እስክናስታውቃችሁ ድረስ መጠበቅ ነው። ጥር ቀን ዓ/ም ሎንዶን” እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስም ይሄ መልእክት እንደደረሳቸው በኢየሩሳሌም ዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ገዳም የነበረውን፣ በስመ መድኀኔ ዓለም የተጠራ ጽላት ለቁርባንና ለጸሎት የሚያስፈልጉትን ንዋየ ቅድሳት እና መጻሕፍት ጭምር በአምስት መነኮሳት እጅ አስይዘው በፍጥነት ወደእንግሊዝ አገር ላኩ። የተላኩትም መነኮሳት፦ ፩ኛ/ መምህር ገብረ ኢየሱስ መነኮስ ወቆሞስ ፪ኛ/ አባ ሐና ጅማ መነኮስ ፫ኛ/ አባ ማርቆስ መነኮስ ፬ኛ/ አባ ኃይሌ ብሩክ መነኮስ ፭ኛ/ አባ ገብረ ማርያም መነኮስ ናቸው። እነዚህ መነኮሳትም እንግሊዝ አገር እንደደረሱ፣ ሚያዝያ ቀን ዓ/ም አንድ መካነ ጸሎት ባርከው እንደ ቤተ ክርስቲያን ሕግ የጸሎትና የቁርባን ሥርዓት ያደርጉ ጀመር። ከዚያም የተነሳ ያች ቤተ ክርስቲያን በስደት ያለች ኦርቶዶክሳዊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተብላ ትጠራ ጀመር። የፋሺስት ኢጣልያ ኃይል ተደምስሶ የኢትዮጵያ ነጻነት ሲመለስ ይሄ በስደት እንግሊዝ አገር የነበረው የመድኀኔ ዓለም ጽላትም ከግርማዊት እቴጌ መነን ጋር ነሐሴ ቀን ዓ/ም ተመልሶ አገሩ ገባ። ከዚያም በኋላ ሚያዝያ ቀን ዓ/ም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሆስፒታል ቅጽር ግቢ በታነፀው ቤተ ክርስቲያን “ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም” ተብሎ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ። በስደት በነበሩበት ዘመናት ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተለመደው በግዕዝ ሲዘመር፣ በሥርዓቱ ውስጥ የተካተቱት ጸሎቶችም ሆኑ የቅዱስ ወንጌል ምንባብ፣ ወዘተ. ግን በአማርኛ ቋንቋ ነበር የሚነበቡት። አሁንም ይሄ ታቦት ተመልሶ ከገባ በኋላ በአባ ሐና ጅማ እና በአባ ኃይሌ ብሩክ መሪነት ሥርዓቱ ቀጠለ። በአገሪቱም ይሄ አዲስና ምእመኑን የሚያሳትፍ ተራማጅ ሥርዓት በኢትዮጵያ በጊዜው ያልተለመደ ቢሆንም የከተማው ምእመናን ጧት እና ማታ የምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለምን ቤተ ክርስቲያን ማዘውተር ልምድ ሆነ። በተጨማሪም፣ የአጥቢያው ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት እና እቴጌ መነን ትምህርት ቤት ተማሪዎች እሑድ እሑድ የማይለዩ አስቀዳሾች ነበሩ። በዚህ ዓይነት እስከ ዓ/ም ቆይቶ በጊዜው የነበረበት የቅዳሴ ቤት መጥበብ ግልጽ ስለሆነ ንጉሠ ነገሥቱ አሁን ቤተ ክርስቲያኑ የሚገኝበትን ቦታ ለአዲስ ቤተ ክርስቲያን ግንባት እንዲሆን አዘዙ። የቤተ ክርስቲያን ግንባታ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የአዲሱን የምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን መሠረት ድንጋይ ሚያዝያ ቀን ዓ/ም ሲያስቀምጡ አትኩሮታቸው ወጣቱ ትውልድ ላይ እንደነበር ያደረጉት ንግግር ያመለክታል። በተፈሪ መኮንን ተማሪ ቤት ክበብ ውስጥ ይህን የአዲሱን ቤተ ክርስቲያን መሠረት ስንመሠርት በዚህ ተማሪ ቤት የሚማሩት ክርስቲያናውያን ወጣቶች የኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖታቸውን ሥርዓት እንዲጠቀሙበት አስበን ነው። የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ሃይማኖቱን የማያከብር ሃይማኖት የሌለው፣ እርሱም የሚያምነው ደገፋ የሌለው፣ እርሱንም ማንም የማያምነው የሁለት ዓለም ስደተኛ ነው። ፍሬውን ለማየት ተስፋችን እርሱ ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ነው።” የቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃ ግንባታ በሚካሄድበት ጊዜ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በቅርብ እንደተረዳው፣ ንጉሠ ነገሥቱ፣ ልዑላን እና ልዑላት ቤተ ሰቦቻቸው፤ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ የሕንፃውን መገንቢያ ድንጋይ በትከሻቸው እያቀረቡ እንደተሳተፉ ተገንዝቧል። በዚህ ዓይነት እርምጃ ተገንብቶ፣ ልክ በሁለት ዓመቱ በ፲፱፻፵፪ ዓ/ም ግንባታው ተፈጽሞ ቤተ ቅዳሴው ሚያዝያ ቀን ተመረቀ። ዋቢ ምንጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐዋርያዊ ድርጅት፣ “ትንሣኤ፡ የሃያ አምስት ዓመታት መንፈሳዊ እርምጃ” ዓ/ም) ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት። አብያተ
9595
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B0%E1%88%A8%E1%89%B5%20%E1%8A%90
ተረት ነ
ነቅናቂ ሳለ ማን ጥሩ ይጠጣል ነበረ እንጂ ይኖራል የሚባል ፍጡር የለም ነበርንበት አትኩሩበት ነቢያት በመደመዱ ሀዋርያት ገደገዱ ነቢያት በቀየሱ ሀዋርያት ገሰገሱ ነቢይ ቢኖር በከበረ ነበር ነቢይ ባገሩ አይከበርም ነብር ቢያንቀላፋ ዝንጀሮ ጎበኘው ነብር ባየለበት ዘመን ድመት ይበረታል ነብር ባየለበት ዘመን ድመት ይኮርታል ነብር ሳይገድል ቆዳውን ያስማማል ነብር አየኝ በል ነብር አይኑን ታመመ ፍየል መሪ ሆነ ነብር የሞተ እለት ፍየል ልጅዋን ትድራለች ነዋሪ ለዘላለም አለ አምላክ የለም ነውር ለባለቤቱ እንግዳ ነው ነገረኛ ሰው ከቤቱ አይሞትም ነገረኛ ታሞ አይተኛ ነገረኛ ናቸው አርቃችሁ ቅበሩዋቸው ነገረኛ ናቸው አጥልቃችሁ ቅበሩዋቸው የተነሱ እንደሆን ብዙ ነው ጣጣቸው ነገረኛ ዝንጀሮ ውሻ ታረባለች ነገሩ ነገር ነው ውስጡ ጥቅንጥቅ ነው ነገሩ ነገር ነው ውስጡ ጉራንጉር ነው ነገሩ ነው እንጅ ቢላዋ ሰው አይጎዳም ነገሩ ነው እንጅ ጩቤ ሰው አይጎዳም ነገሬ በሆዴ መንገዴ ባመዴ ነገሬ በከንፈሬ ነገር ለበለጠ ውድማ ለመለጠ ነገር ለበለጥ ውድማ ለመለጥ ነገር ለሰሚ ውሀ ለሎሚ ነገር ለጀማሪው እሳት ለጫሪው ነገር ሲበዛ ይሆናል ዋዛ ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም ነገር ሲያመልጥ እራስ ሲመልጥ አይታወቅም ነገር ሲጀመር እህል ሲከመር ነገር ሳያውቁ ሙግት ሳይጎለብቱ ትእቢት ነገር ሳያውቁ ሙግት አቅም ሳይኖር ትእቢት ነገር ስንት ነው ሁለት ምን ያበዛዋል ውሸት ነገር በሆዴ መንገድ በአመዴ ነገር በሆዴ እየተመኘሁ ቢከፍቱት ተልባ ሆኜ ተገኘሁ ነገር በለዛው ጥሬ በለዛዛው ነገር በልክ ሙያ በልብ ነገር በመልከኛ ጠላ በመክደኛ ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ መዝሙር በሀሌ ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ዜማ በሀሌ ነገር በቀጠሮ ዘፈን በከበሮ ነገር በትኩሱ ጨዋታ በወዙ ነገር በነገር ይጠቀሳል እሾህ በእሾህ ይነቀሳል ነገር በእርቅ መንገድ በድርቅ ነገር በእርቅ ወይፈንን በድርቅ ነገር በወቀሳ በደል በካሳ ነገር በዋስ እህል በነፋስ ነገር በዋና ሚዶ በእረኛ ነገር በዋና ሜዳ በእረና ነገር በዋና ዘፈን በገና ነገር በዋናው ንብ በአውራው ነገር በዳኛ ሚዶ በእረኛ ነገር ቢሳሳት ከጥንቱ ሰይፍ ቢመዘዝ ካፎቱ ነገር ቢሳሳት ከጠዋቱ ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ ነገር ቢበዛ ባህያ አይጫንም ነገር ባዋቂ ብረት በጠራቂ ነገር አለኝ ከማለት ስራ አለኝ ማለት ነገርን አድምጦ እህልን አላምጦ ነገር እንደዛፉ ዛፉ እንደቅርንጫፉ ነገር ከመጀመሪያው እህል ከመከመሪያው ነገር ከመጀመሪያ ፍለጋ ከመሻገሪያ ነገር ከመጀመሪያው ውሀ ከመሻገሪያው ነገር ከስነበተ ቅራሪ ከሆመጠጠ ነገር ካምጩ ውሀ ከምንጩ ነገር ከስሩ ውሀ ከጥሩ ነገርን ከስሩ ውሀን ከጥሩ ነገር ከእብድ ይገኛል ነገር ከእጅ ይገኛል ነገር ከዋስ ምላስ ከጥርስ ነገር ከዋስ ምላስ ከጥርስ አያልፍም ነገር ከውሉ ጋሻ ከንግቡ ነገር ከግቡ ጋሻ ከእንግቡ ነገር ከፊቱ ዱቄት ከወንፊቱ ነገር ካንሹ ስጋ ከጠባሹ ነገር ካንሺው ስጋ ከጠባሺው ነገር ካጀማመሩ እሀ ል ካከማመሩ ነገር ወዳድ ሰው ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ ይላል ነገር ወዳጅ ሰው ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ ይላል ነገር ወዳጅ ከቤቱ አይሞትም ነገር ወዴት ትሄዳለህ ጎንደር መጨረሻህ ታገር ነገር ያለዳኛ ትብትብ ያለመጫኛ ነገር የሚከረው ጎንጓኙን ሲያገኝ ነው ነገር የሻ ዳኛ አምጡ ይላል የዶሮ ሻኛ ነገር የዋለበት ዳኛ ያውቃል ከብት የዋለበት እረኛ ያውቃል ነገር የፈራ ይቃጠራል አውሬ የፈራ ያጥራል ነገር ያለዳኛ ተረት ሰማይ ያለ ደመና ብረት ነገር ፈጣሪውን እሾህ አጣሪውን ነገር ነገርን ያነሳል ጥጋብ ሞትን ያስረሳል ነገርህና ነገሬ ልክ ነው ሰው መስማቱ ትርፍ ነው ነገር ነገርን ያመጣል ድግር አፈር(ን) ያወጣል ነገርህን በጠጄ ርስትህን በልጄ ነገር በነገር ይወቀሳል እሾህ በሾህ ይነቀሳል ነገርም ይበረክታል ባለጋራም ይታክታል ነገርኩት መስዬ እንዲመስለው ብዬ ነገር መጫኛ እንዳሳጠሩት ወይም እንዳስረዘሙት ነው ነገርና ገመድ አለውሉ አይፈታም ነገርን በእርቅ ወይፈንን በድርቅ ነገር እንዲጠፋ ዳኛውን ግደል ነገር ነገርን ይወልዳል ነጋሪ የሌለው ይታማ አይመስለው ነጋዴ ወረቱን ዘላን ከብቱን ገበሬ ምርቱን ነጋዴን ተዘማች ምን አቀላቀለው ነጻነት ያኮራል ስራ ያስከብራል ነጭ ሽንኩርት በመሽተቱ እራሱን ቀብሮ ይኖራል ነጭ ድሀ ነጭ ማር ይከፍላል ነጭ እንደሸማ ትክል እንደትርሽማ ነጭ እንደሸማ ትክል እንደአክርማ ነፋስ በተነሳበት ጊዜ እሳት አይጭሩም ነፋስ ሲነሳ እሳት አይጫርም ነፍጥ ቢያጓራ የጌታውን ጎን ይሰብር ነፍጥ ቢያጓር የጌታውን ጎን ይሰብር ነፍስ በፈጣሪዋ ሴት ባሳዳሪዋ ኑር ባገር ጥፋ ካገር ኑሮ በዘዴ አቶ ዘወልዴ ኑሮ በዘዴ ጾም በሁዳዴ ኑሮ በደጋ መተኛት ባልጋ ኑሮ ቢያምርህ ችላ ጥጋብ ቢያምርህ ባቄላ ኑሮ ከማናደድ ሄዶ መመስገን ኑሮ ከማናደድ ሄዶ መናፈቅ ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል ኑሮ ካሉት የጤፍ ቅጠል ሁለት ሰው ያስተኛል ኑሮ ካሉት ፍሪጅ ይሞቃል ኑሮ ካሉት ፍሪጅ ይሞቃል አለ የቢራ ጠርሙስ ኑ ባይ ከባሪ እንቢ ባይ ቀላይ ኑሮ ኑሮ ከመሬት ዙሮ ዙሮ ከቤት ኑሮ ኑሮ ከመሬት ዙሮ ዙሮ ከቤት አይቀርም ኑሮ ያኗኑራል ህግ ያከባብራል ናቂ ወዳቂ ና ብላ ሳይሉት ከወጡ አውጡልኝ ና ያሉት እንግዳ እራቱ ፍሪዳ ናዳ መጣልህ ቢሉት ተከናንቤአለሁ አለ ናዳ መጣልህ ቢሉት ተከናንቤአለሁ ልቀቀው አለ ንቡን አባሮ ማሩን ንብ ላጥር ሳያረዳ አይሄድም ንብ ሲሰማራ አጥሩን ተመልከት ንብ ቢሄድ ካጥር ሰው ቢሄድ ካገር ንብ ቢሄድ ካጥር ሰው ቢሰደድ ካገር ንብ ባውራው ገበሬ ባዝመራው ንብን አይተህ ተገዛ ብሎዋል እግዜር ንካ ያለው አይቀርም ንዳማ ቢአጭዱት ክምር አይሞላም ንጉሱ በድንኳናቸው እኔ በጎጆዬ ንጉሱ በድንኳናቸው እኔ በጎጆዬ ንጉስ ነን አለ ድሀ ንገስ ቢሉት ሳልዋጋ አልነግስ አለ ንጉስ ለብያኔ አቡን ለኩነኔ ንጉስ በመንግስቱ እግዜር በመለኮቱ ጎልማሳ በሚስቱ ንጉስ በመንግስቱ ጎልማሳ በሚስቱ አምላክ ባምላክነቱ ንጉስ በግንቡ ይታማል ንጉስ በግንቡ ገበሬ በርስቱ ቢገቡባቸው ቀናተኞች ናቸው ንጉስ ከግንቡ ውጭ ይታማል ንጉስ በዘውዱ ድሀ ባመዱ ንጉስ ቢቆጣቀስ ብለህ ውጣ ንጉስ ሲቆጡ ቀስ ብላችሁ ውጡ ንጉሱ ቢሞቱ ከማን ይሟገቱ ንጉስ ቢያተርፍ ሁሉ ይተርፍ ንጉስ ሲሞት ግንቡን ብልህ ሲሞት ልቡን ንጉስ አንጋሹን ቤተክርስቲያን ቀዳሹን ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ አባት አይወቀስ ንጉሱ ከሾመው ማረሻ የሾመው ንጉስ ከተነፈሰ አይን ከፈሰሰ ንጉስ ከተነፈሰ ውሀ ከፈሰሰ ንጉስ ይተክላል ንጉስ ይነቅላል ንጉስ የቆረጠው እጅ ካለ ይቆጠራል ንጉስ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት ንጉስ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት (አንድ ነው) ንጋትን ዶሮ ያውቃል ወፍ ያረጋግጣል ንጋትን አውራ ዶሮ ያውቃል ወፍ ያረጋግጣል ንጋትና ጥራት እያደር ይታያል ንጉስ የሰቀለው አንበሳ የሰበረው ንፉግ ለግሶ ቢሰጥ እጁ ይንቀጠቀጥ ንጉስ የወደደው ዘመን የወለደው ንጉስ ያላቸው ንቦች ማር ይበላሉ ንጉስ የሌላቸው ዝንቦች ጥንብን ይልሳሉ ንጉስ ይሞግትልህ ንጉስ አይሞግትህ ንግግር ሲበዛ ይጠፋል ማር ሲበዛ ያስተፋል ንፍጥ ለባለቤቱ ቅቤ ነው ኖረሽ አልጠቀምሽን ሞተሽ አለቀቅሽን ኖሮ ኖሮ ከሞት ዞሮ ዞሮ ከቤት]]
39218
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%89%A1%E1%8A%90%20%E1%89%A3%E1%88%B5%E1%88%8D%E1%8B%AE%E1%88%B5
አቡነ ባስልዮስ
ቀዳማዊ አቡነ ባስልዮስ (፲፰፻፹፬ዓ/ም (ሚዳ ሚካኤል) ዓ/ም (አዲስ አበባ)) የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ ነበሩ። አቡነ ባስልዮስ ሲወለዱ የተሰጣቸው ስም ገብረ ጊዮርጊስ ሲሆን መጋቢት ቀን ዓ/ም ከደብተራ ወልደጻድቅ ሰሎሞንና ከወይዘሮ (በኋላ እማሆይ) ወለተማርያም ባዩ በሸዋ አውራጃ ሚዳ ሚካኤል ተወለዱ። ደብተራ ወልደጻድቅ የይፋት ቀውትጌስ ማርያም ተወላጅ ሲሆኑ፣ እማሆይ ወለተማርያም ደግሞ በመንዝ ላሎ ምድር የተወለዱ ነበር። በሕጻንነታቸው ዘመን መንፈሳዊ ትምህርትን እየተማሩና የኮሶ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን እያገለገሉ አድገዋል። አቡነ ባስልዮስ የአሥራ-አራት ታዳጊ ወጣት እያሉ በ፲፰፻፺፱ ዓ/ም ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብተው ትምህርታቸውን ከመምህር ገብረ ኢየሱስ ሲከታተሉ ቆይተው በዚያው ገዳም መዓርገ-ምንኩስናቸውን እስከተቀበሉበት ድረስ ለሦስት ዓመታት በእርድና አገልግለዋል። በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመን በ፲፱፻፱ ዓ/ም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ትዕዛዝ በመናገሻ ግርጌ ለሚሠራው የማርያም ቤተ ክርስቲያን ለሚጠጉ መነኮሳትና ባሕታውያን የሚሠሩትን መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደር ረዳት እንዲሆኑ በተጠየቁት መሠረት፣ እያገለገሉና ቅዳሴ እያስተማሩ ለሦስት ዓመታት በመናገሻ ማርያም ደብር ቆዩ። እዚሁም ገዳም መምህር (አበ ምኔት) ሆነው ሲኖሩ ወደሐዋርያዊነት ሥራ በመሠማራት ቆዩ። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የመናገሻ አምባ ማርያምን ገዳም እያስተዳደሩ ሳሉ፤ ከዚህ ሥልጣናቸው በተጨማሪ የአዲስ አበባ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መምህርነት በየካቲት ቀን ዓ/ም ተሰጣቸው። ከዚያም ቀጥሎ መጋቢት ቀን ፲፱፻፳፭ዓ/ም በኢየሩሳሌም ያሉ የኢትዮጵያን ገዳማት በመንፈሳዊ መሪነት አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ለሁለት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ ወደአገራቸው ተመለሱ። የካቲት ቀን ዓ/ም በአቡነ ተክለ ሃይማኖት መንበር፥ ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ዘነበረ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተብለው፥ አምሣ-ዘጠነኛው ዕጨጌ ሆነውተሽሙ። በዚሁ በዕጨጌነታቸው ዘመን የፋሺስት ወረራ ኢትዮጵያን ባጠቃ ጊዜ፣ በጦርነቱ ግምባር ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ተሰልፈው አብያተ ክርስቲያናትንና መጻሕፍትን የሚያቃጥል የምእመናንን ዘር የሚያጠፋ ጠላት መጥቷልና በሃይማኖት፤ በጸሎት፣ በምህላ በርታ እያሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያጽናኑ ቆዩ። በጦርነቱም ጊዜ የተቀመጡበት በቅሎ በአረር ተመቶ እስኪወድቅና የለበሱትም ካባ አምስት ላይ በጥይት እስኪበሳሳ ድረስ ከንጉሠ ነገሥቱ ሳይለዩ የቆራጥነት ሥራ ሠርተዋል። ሠራዊቱም ድል ህኖ በተፈታ ጊዜ ክንጉሠ ነገሥቱ ጋር በስደት ወደኢየሩሳሌም አቅንተው እስከ ድል ጊዜ ድረስ በስደት ቆይተዋል። በዚሁ በስደት ዘመናቸውም ሳሉ በርካታ ሐዋሪያዊ መልእክቶችን ለአርበኞችም፤ ለሕዝቡም በመላክ የማጽናናትና የሃይማኖታዊ ጣምሮችን ያስተላልፉ ነበር። ንጉሠ ነገሥቱ በስደት ከነበሩበት ከ’ባዝ’ (ብሪታንያ) ጥር ቀን ዓ/ም በጊዜው በስደት ኢየሩሳሌም ለነበሩት ወደ ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ አንድ ፅላትና ለአገልግሎት የሚበቁ አምስት መነኮሳትን ወደ እንግሊዝ አገር እንዲልኩላቸው በአባ ሐና ጅማ በላኩት ደብዳቤ መሠረት፣ ዛሬ ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም የተባለውን የመድኀኔ ዓለምን ጽላት ወደንጉሠ ነገሥቱ ወዳሉበት ባዝ የላኩት እሳቸው ነበሩ፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፥ ጥር ቀን ዓ/ም በኢትዮጵያ ጠረፍ በኡም-ኢድላ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ-ዓላማ ሲተክሉ ዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስም አብረዋቸው ነበሩ። ከዚያም ንጉሠ ነገሥቱ በምድረ [[ጎጃም]፤ በቡሬ፤ በደብረ ማርቆስ፤ በደብረ ሊባኖስ እና በእንጦጦ በኩል አድርገው ሚያዝያ ቀን ዓ/ም አዲስ አበባ ሲገቡ ዕጨጌው ሳይለዩ አብረው ነበሩ። ከዕጨጌነት ወደ ጵጵስና ወደ ፕትርክና ከድል በኋላም ከእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ጋር በጠላት ወረራ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት እንዲታደስና እንዲቀጥል ለማድረግ በየካቲት ወር ዓ/ም ንግግር ተጀመረ። ሆኖም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የጵጵስና ማዕርግ የመስጠትን ልምዳዊ መብቷን ለኢትዮጵያውያን አልለቅም በማለቷ በድርድሩ ስምምነት እስከተደረሰበት እስከ ሐምሌ ቀን ቆይቶ፤ በቀድሞው ሥልጣናቸው ሲያገለግሉ የቆዩት ዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ አቡነ ባስልዮስ ተብለው ከአቡነ ቴዎፍልስ፤ አቡነ ሚካኤል፤ አቡነ ያዕቆብ እና አቡነ ጢሞቴዎስ ጋር በእስክንድርያው ፓትርያርክ አቡነ ዮሳብ እጅ ተቀቡ። ግብጻዊው አቡነ ቄርሎስም ካይሮ ላይ ስላረፉ ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ጥር ቀን ዓ/ም ካይሮ ላይ በአቡነ ዮሳብ እጅ ተቀብተው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሊቀ-ጳጳሳት ሆኑ። የፓትርያርኩንም ፈቃድ ካገኙ በኋላ በሚቀጥለው ነሐሴ ወር ላይ አምሥት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳትን ሾሙ። ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመራር ላይ ብዙ ጊዜ የወሰደ ድርድር ከተደረገ በኋላ ስምምነት ተደርጎ፥ እሑድ፣ ሰኔ ቀን ዓ/ም፤ ንጉሠ ነገሥቱም በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ፓፓው አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ላይ የሢመቱን ሥርዓተ-ጸሎት አድርሰው፤ የፓትርያርክነቱን ዘውድ ባርከው ደፉላቸው። ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አቡነ ባስልዮስ በግብጽ ፓትርያርክ እጅ በዚህ ማዕርግ ሲቀቡ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ነው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ እስከ ዓ/ም ድርሰ አርባ ሁለት አብያተ-ክርስቲያነትን እንዳሠሩና አስራ ሁለት ትምህርት ቤቶችንም እንዳለሙ አዲስ ዘመን ጋዜጣ፤ የፓትርያርኩን ሞት ተከትል ባወጣው የሐዘን ዘገባ ላይ ገልጾታል። ከነዚህም መኻል በተለይም፣ በደብረ ጽጌ ያለውን የእብነት ትምህርት ቤት በግል ገንዘባቸው ነበር የሚያስተዳድሩት (አዲስ ዘመን፣ ጥቅምት 3/1963 ዓ.ም.)። ፓትርያርኩ በተወለዱ በ፸፱ ዓመት ዕድሜያቸው ጥቅምት ቀን ዓ/ም አርፈው ጥቅምት ቀን በደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ። አቡነ ቴዎፍሎስ ተተክተው ሁለተኛው ፓትርያርክ ሆኑ። ማጣቀሻ ዋቢ ምንጮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐዋርያዊ ድርጅት፣ «ትንሣኤ፡ የሃያ አምስት ዓመታት መንፈሳዊ እርምጃ» ፤ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ዓ/ም) ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ «የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ»፤ ብርሃንና ሰላም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ማተሚያ ቤት ዓ/ም) «ዜና ባስልዮስ ሊቀ ጳጳሳት ኢትዮጵያዊ»፤ ትንሳዔ ዘጉባዔ ማተሚያ ቤት ዓ/ም)
4273
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%89%A0%E1%88%B3
አንበሳ
አንበሳ ጡት አጥቢ የእንስሶች መደብ ውስጥ ተብሎ የሚታወቀው ቤተሰብ አባል ሲሆን ግዙፍ ድመቶች ከሚባሉት 4 አራዊት አንዱ ነው። ከነዚህም መካከል ነብር ከሚባለው ግሥላ መሳይ አውሬ ቀጥሎ በቁመቱና ክብደቱ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። አንበሳ ዛሬ በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ) እና በህንድ ብቻ የሚገኝ ሲሆን በታሪክ እስያና በደቡብ አውሮፓ እንደነበርና እንደጠፋ ይታወቃል። ቀልብ የሚስብ አስደናቂ ፍጡር አንበሶች በጣም ቁጡ ሊሆኑ ይችላሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሙጭሊትን ያህል ገራምና ተጫዋች ይሆናሉ። ሲጠግቡ በዝግታ የሚያንኮራፉ ቢሆንም እንኳ እስከ ስምንት ኪሎ ሜትር ድረስ ሊሰማ በሚችል ኃይለኛ ድምፅ ሊያገሡ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ሰነፎችና ልፍስፍሶች ይመስሉ ይሆናል፤ ሆኖም በሚያስገርም ፍጥነት የመንቀሳቀስ ችሎታ አላቸው። የሰው ልጅ፣ አንበሳ ባለው ድፍረት ለዘላለም ሲወሳ እንዲኖር አድርጓል፤ በመሆኑም ደፋር ሰው አንበሳ ተብሎ ይጠራል። ሲምባ*—በማኅበር የሚኖር እንስሳ አንበሶች በማኅበር ከሚኖሩት የድመት ወገን የሆኑ እንስሶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በትልልቅ መንጋ ተከፋፍለው የሚኖሩ ሲሆን እያንዳንዱ መንጋ ከጥቂት አባሎች አንስቶ ከ30 በላይ ሊደርስ ይችላል። አንድ መንጋ የጠበቀ ዝምድና ያላቸው በርከት ያሉ ሴት አንበሶች ይኖሩታል። አንድ ላይ ይኖራሉ፣ ያድናሉ እንዲሁም ይወልዳሉ። ዕድሜ ልካቸውን ሊዘልቅ የሚችለው ይህ የጠበቀ ትስስር ለመንጋው ጠንካራ መሠረት የሚጥል ከመሆኑም በላይ ለመንጋው ሕልውና ጥሩ ዋስትና ይሆናል። እያንዳንዱ መንጋ እየተዘዋወሩ የሚጠብቁና የመንጋውን የክልል ወሰን የሚያወጡ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ለአካለ መጠን የደረሱ ወንድ አንበሶች ይኖሩታል። እነዚህ ዕጹብ ድንቅ የሆኑ አውሬዎች ከጥቁሩ የአፍንጫቸው ጫፍ አንስቶ እስከ ጭራቸው ጫፍ ድረስ ከሦስት ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሲሆን ከ225 ኪሎ ግራም በላይ ሊመዝኑ ይችላሉ። ቤተሰቡን በበላይነት የሚቆጣጠሩት ወንዶቹ ቢሆኑም አመራር የሚሰጡት ግን ሴቶቹ ናቸው። ወደ ጥላ ሥፍራ መሄድን ወይም አደን መጀመርን በመሳሰሉት ሁኔታዎች ብዙውን ጊዜ መንጋውን ለአንድ ዓይነት እንቅስቃሴ የሚያነሳሱት ሴቶቹ አንበሶች ናቸው። ሴት አንበሶች በአብዛኛው በየሁለት ዓመቱ ይወልዳሉ። ግልገሎቹ በሚወለዱበት ጊዜ ምንም ዓይነት አቅም አይኖራቸውም። ግልገሎችን ማሳደግ የሁሉም የጋራ ሥራ ነው፤ በመሆኑም ሴቶቹ አንበሶች በሙሉ በመንጋው ውስጥ ያሉትን ግልገሎች ይጠብቃሉ እንዲሁም ያጠባሉ። የግልገሎቹ ዕድገት ፈጣን ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ መሮጥና መቦረቅ ይጀምራሉ። ልክ እንደ ሙጭሊቶች እየተንደባለሉ ይጫወታሉ፤ ከሚያጫውቷቸው ጋር ይታገላሉ፤ እንዲሁም በረጃጅሙ ሣር ውስጥ ወዲያና ወዲህ ይዘላሉ። እያንዳንዱ የሚንቀሳቀስ ነገር ሁሉ ስሜታቸውን ይማርከዋል፤ ቢራቢሮዎችን ለመያዝ ይዘላሉ፣ ትናንሽ ነፍሳትን ያሳድዳሉ፣ ከየጭራሮና ከየሐረጉ ጋር ይታገላሉ። ይበልጥ ስሜታቸውን የሚማርከው ግን እነርሱን ለማጫወት እናታቸው ወዲያና ወዲህ የምታወናጭፈው ጭራዋ ነው። እያንዳንዱ መንጋ የሚኖርበት በደንብ የተከለለ ቦታ ያለው ሲሆን ይህ መኖሪያ ብዙ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ሊኖረው ይችላል። አንበሶች ውኃ እንደ ልብ ባለበትና ከቀትር ሐሩር የሚከላከል ጥላ በሚያገኙበት ከፍ ያለ ቦታ ላይ መኖር ይመርጣሉ። በእንዲህ ዓይነቱ ሥፍራ ከዝሆኖች፣ ከቀጭኔዎች፣ ከጎሽና ከሌሎች ሜዳማ በሆኑ ሥፍራዎች ከሚኖሩ እንስሶች ጋር በአንድነት ይኖራሉ። አንበሳ አብዛኛውን ጊዜውን በእንቅልፍ ጥቂቱን ጊዜ ደግሞ በአደንና በተዋስቦ ያሳልፋል። እንዲያውም አንበሶች በቀን ውስጥ ወደ 20 የሚጠጋውን ሰዓት የሚያሳልፉት በዕረፍት፣ በመተኛት ወይም በመቀመጥ ነው። ከባድ እንቅልፍ ተኝተው ሲታዩ ሰላማዊና ለማዳ ይመስላሉ። ይሁን እንጂ በዚህ መታለል የለብህም፤ አንበሳ እጅግ ቁጡ ከሆኑት አራዊት መካከል አንዱ ነው! አዳኝ አንበሶች በጣም ቀልጣፋና ፈጣን ቢሆኑም እንኳ በአደን ጊዜ የሚሳካላቸው 30 በመቶ ብቻ ነው። በመሆኑም አንበሶች ከተደቀኑባቸው ትልልቅ አደጋዎች አንዱ ረኃብ ነው። ለአካለ መጠን የደረሰ አንድ አንበሳ ያለው ጥንካሬ እጅግ የሚያስገርም ነው። በቤተሰብ ደረጃ የሚያድኑ እንደ መሆናቸው መጠን ከ1,300 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ያላቸውን እንስሳት የመጣልና የመግደል አቅም እንዳላቸው ይነገራል። አንበሶች በመጀመሪያ ላይ በሰዓት እስከ 59 ኪሎ ሜትር ድረስ ሊሮጡ ይችላሉ፤ ሆኖም ይህ ፍጥነታቸው እስከ መጨረሻ አይዘልቅም። በዚህ ምክንያት ቀለባቸውን ለማግኘት አድብቶ የመያዝ ዘዴ ይጠቀማሉ። የማደኑን ተግባር 90 በመቶ የሚያከናውኑት ሴቶቹ አንበሶች ቢሆኑም በሚበሉበት ጊዜ ትልቁን ድርሻ የሚያገኙት ትልልቆቹ ወንድ አንበሶች ናቸው። አደን በሚጠፋበት ጊዜ አንዳንዴ አንበሶች በጣም ስለሚርባቸው ያገኙትን መብል ለራሳቸው ግልገሎች እንኳ ለማካፈል ፈቃደኛ አይሆኑም። ታዳኝ ከብዙ ዓመታት በፊት ባለ ግርማ ሞገሱ አንበሳ በመላው የአፍሪካ አህጉር እንዲሁም በእስያ፣ በአውሮፓ፣ በህንድና በፍልስጤም አንዳንድ ቦታዎች ይገኝ ነበር። አዳኝ እንደመሆኑ መጠን ሰውን እየተቀናቀነ የሚኖር እንስሳ ነው። በከብቶች ላይ አደጋ የሚጥልና በሰዎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ አንበሳ ገና እንደታየ በጥይት የሚገደል ፍጡር ሆነ። የሕዝብ ቁጥር ፍንዳታ የአንበሳን መኖሪያ በእጅጉ አመናምኖታል። ዛሬ ከአፍሪካ ውጪ ባለው የዓለም ክፍል በዱር የሚኖሩት አንበሶች በጥቂት መቶዎች ብቻ የሚቆጠሩ ሆነዋል። በአሁኑ ጊዜ አንበሶች ሰው ከሚያደርስባቸው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ተጠብቀው መኖር የሚችሉት ጥበቃ በሚደረግባቸው ክልሎች ውስጥና በዱር አራዊት መጠበቂያ ቦታዎች ብቻ ሆኗል። አንበሳ ሲያገሣ አንበሶች በሚያገሡበት ጊዜ በብዙ ኪሎ ሜትር ርቀት ሊሰማ የሚችል ከፍተኛ ድምፅ የማውጣት ልዩ ችሎታ አላቸው። አንበሳ ሲያገሣ የሚያሰማው ድምፅ “እጅግ ማራኪ ከሆኑት የተፈጥሮ ድምፆች” አንዱ እንደሆነ ይነገራል። ብዙውን ጊዜ አንበሶች በጨለማ ሰዓትና ንጋት ላይ ያገሣሉ። ወንዶቹም ሆኑ ሴቶቹ አንበሶች የሚያገሡ ሲሆን አንዳንዴም የመንጋው አባላት በአንድነት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያገሣሉ። በአንበሶች ላይ ጥናት የሚያካሂዱ ሳይንቲስቶች አንበሶች የሚያገሡባቸው የተወሰኑ ምክንያቶች እንዳሉ ይናገራሉ። ወንዶቹ አንበሶች የሚኖሩበትን ክልል ድንበር ለማሳወቅ እንዲሁም ሌሎች ወንድ አንበሶች ወደ ክልላቸው እንዳይገቡ ለማስጠንቀቅ ሲሉ ያገሣሉ። በርቀት ወይም በጨለማ ተነጣጥለው ያሉ የአንድ መንጋ አባላት ያሉበትን ቦታ ለመጠቆም ያገሣሉ። በተጨማሪም አንድ እንስሳ ከገደሉ በኋላ ለሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት ምግቡ ያለበትን ቦታ ለማሳወቅ ያገሣሉ። አንበሶች በሚያድኑበት ጊዜ የሚያድኗቸውን እንስሳት ለማስደንበር ብለው አያገሡም። ሪቻርድ ኤስቲዝ ዘ ቢሄቭየር ጋይድ ቱ አፍሪካን ማማልስ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ “አንበሶች የሚያድኑትን እንስሳ ለማጥመድ ሲሉ ሆን ብለው እንደሚያገሡ የሚጠቁም ምንም ነገር የለም (በተሞክሮዬ እንዳየሁት በአንበሳ የሚታደኑ እንስሳት አንበሳ ለሚያሰማው የግሣት ድምፅ ብዙም ትኩረት አይሰጡም)።” የግርጌ ማስታወሻ ሲምባ በስዋሂሊ “አንበሳ” ማለት ነው። የዱር አራዊት ታላላቅ ድመቶች የኢትዮጵያ አጥቢ
13860
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%8B%B3%E1%88%8D
አዳል
የአዳል ሱልጣኔት ተብሎ ይታወቅ የነበረው ግዛት በመካከለኛው ዘመን (ከ1415 1577 ዓ.ም.) የነበረ በመጀመሪያዎቹ ከ1415–1559 መሪዎቹ የወላስማ ሱልጣኖች የአርጎባዎች እና የብዙ እስልምና ተከታይ ጎሳዎች ድብልቅ የነበረ ግዛት ነው። አንዳንድ ተመራማሪወች አብዛኛው አዳል የአፋር ጎሳዎች ተዋጾ ነበረበት ሲሉ አንዳንዶች ደግሞ ባብዛኛው ከዲር እና ዳሩድ የሶማሌ ነገዶች የተውጣጣ ነበር ይላሉ። የአዳልን ሱልጣኔት አብዛኛ ጎሳ ስብጥር ክርክር ይውደቅ እንጂ በርግጥም ሱልጥኔቱ የብዙ ጎሳዎች ስብስብ እንደነበር ግን ክርክር የለም። ስለ አዳል ሱልጣኔት በትንሹ (ከ1415- 1577 ዓ.ል.) በአብዱ እንድሪስ (ከሚሴ) አስራ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ሰለሞናዊ ነጋሲ የነበረው ወጣቱ አጼ ዳዊት በ1413 ዓ.ል. በአጠገቡ በነበረው የኢፋት ሱልጣኔት ላይ ሀይለኛ ጥቃት ከፈተ። የሱልጣኔቱ ገዠ የነበረውን ሱልጣን ሰዓደዲንን በዜይላ ከተማ ከገደለው በኋላም ኢፋትን ከአጼው ግዛተ መንግስት ጋር ቀላቀለው። ሆኖም አጼ ዳዊት በቁጥጥር ስር ካዋለው የኢፋት ግዛት በሙሉ ሀይሉ ለመግዛት የቻለው ከአዋሽ ወንዝ በስተምዕራብ ያለውን ብቻ ነው። ከወንዙ በስተ-ምስራቅ ያለውና እስከ ዘይላ ድረስ የተንጣለለው ምድር ወዲያውኑ ነበር ከእጁ ያፈተለከው። አባታቸው በዘይላ ሲገደል በስደተኝነት ወደ የመን የሸሹት አስራ አንዱ የሰዓደዲን ልጆች በ1415 ዓ.ል. ከስደት ተመልሰው በምስራቃዊው የኢፋት ግዛት ላይ አዲስ ሱልጣኔት መሰረቱ። ዋና ከተማቸውን ከሀረር አጠገብ በነበረችውና “ደከር” በምትባለው መሬት ላይ ቆረቆሩ። ዳግማዊ ሰብረዲን የሚባለውን የሰዓደዲን ልጅ በወላስማው ወንበር ላይ ካስቀመጡ በኋላ ህልውናቸውን በይፋ አበሰሩ። ከእንግዲህ ወዲያም ለማንም እንደማይገብሩና ሀገራቸውንም ከጥቃት እንደሚከላከሉ በይፋ አወጁ። ለአዲሱ ሱልጣኔትም “አዳል” የሚል ስያሜ ሰጡ። የኢማም ኣህመድ ኢብን ኢብራሂም ኣል ጋዚ ዘመን ታዋቂው ገዥ ኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል ጋዚ በሱልጣኔቱ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ነበረው። ከ በለው ጎሳ የተወለደው አህመድ ግራኝ እንደ ማህፉዝ ባሉ ሌሎች የሙስሊም ገዥዎች ስር ብዙ ቦታዎችን ካገለገለ በኋላ በ1527 ወደ ስልጣን መጣ። ግራኝ በተለምዶ በኢትዮጵያ ታሪክ አብያተ ክርስቲያናትን በማፍረስ እና ለክርስቲያኖች የማይራራ ሰው ሆኖ ይገለጻል። ይህን ለመደገፍ አንዳንድ ማስረጃዎች ሊኖሩ ቢችሉም፣ አህመድ ግራኝ እስካሁን ድረስ በሀገሪቱ ላይ ተጽእኖ ያላቸውን በርካታ ስኬቶችን ኣስመዝግብዋል። እንደ መሪ፣ በክርስቲያን ግዛት ላይ ብዙ ዘመቻዎችን መርቷል፣ እና ብዙ ጦርነቶች ላይ ልብነ ድንግልን እና ሌሎች ገዥዎችን አሸንፏል። በእርሳቸው አገዛዝ ወቅት ንግድ ለክልሎች ኢኮኖሚ ህልውና ቁልፍ ነገር ነበር እናም አዳል ከተለያዩ ሀገራት በተለይም ከኦቶማን ቱርክ ጋር ጠንካራ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ነበረው። የእስልምና ሀይማኖት እንዲስፋፋም የጊዜው ነጋዴዎች ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በኣካባቢው ለሚኖሩ ሙስሊሞች መብዛት ምክንያት እንደሆነ ይታመናል። የአዳል ሱልጣኔት የተወለደው ከላይ በተገለጸው ሁኔታ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ከታዩት ሱልጣኔታዊ መንግስታት ውስጥ እጅግ-ገናና ስም የነበረው ይኸው የአዳል ሱልጣኔት ነው። ይህ ሱልጣኔታዊ መንግስት የኢትዮጵያን ታሪክ ለመቀየር የቻሉትን እንደ አሚር ማሕፉዝ ሙሐመድ፣ ኢማም አሕመድ ኢብራሂም አል-ጛዚ (አሕመድ ግራኝ) እና አሚር ኑር ሙጃሂድን የመሳሰሉ ታላላቅ መሪዎችን አፍርቷል። በርካታ ጸሀፍት ስለርሱ ከትበዋል። በልዩ ልዩ ህዝቦች ስነ-ቃል ውስጥ እስካሁን ድረስ ያልቀዘቀዙ ወጎች እንዲከሰቱ ምክንያት ሆኗል። አሁንም ስለርሱ ታሪክ የሚያወሱ በርካታ ድርሳናት እየተጻፉ ነው። ከዚህ እልፍ ሲል ደግሞ “አዳል” የሚለው የሱልጣኔቱ መጠሪያ የሰው ስም ሆኖ ይገኛል። በተለይ የሚያስደንቀው ደግሞ በዚህ ስያሜ የሚጠሩት ከሙስሊሞች ይልቅ ክርስቲያኖች መሆናቸው ነው። ለዚህም ብዙዎች የሚያስታውሷቸውን እንደ ጋሻው አዳል፣ ዘሪኹን አዳልና ራስ አዳል ተሰማ (በኋላ ንጉስ ተክለ ሀይማኖት ተብለው በጎጃም የተሾሙት) የመሳሰሉ ስሞችን መጥቀስ ይቻላል። በሌላ በኩል የሰለሞናዊው አጼ መንግስት ከአዳል ሱልጣኔት ጋር በጦር ሜዳ እየተላለቀ ከነበሩት ክፍለ ጦሮች መካከል አንዱን “አዳል መብረቅ” በሚል ስያሜ ይጠራው ነበር። እርሱም በበኩሉ አዳልን እየጠላው ያደንቀው ነበር ማለት ነው። ከዚህ መረዳት እንደሚቻለው የሱልጣኔቱ ስመ-ገናናት በሁሉም ወገኖችና ህዝቦች ዘንድ ተደናቂነት ነበረው። “አዳል” የሚለው ስም ምንጭ በትክክል አይታወቅም። አንዳንዶች “አዳ አሊ” (በአፋርኛ የአሊ ቤት ለማለት ነው) ከሚል ሥርወ-ቃል እንደተገኘ ይገምታሉ። አንዳንዶች ደግሞ ጥንት የሀረር አሚር ከነበረው “አሚር ኢዳል” ስም የተገኘ እንደሆነ ይናገራሉ። ሆኖም እርግጠኛው ነገር ላይ አልተደረሰም። የስያሜው ጥንታዊነት ግን በብዙ ምንጮች የተረጋገጠ ነው። ለምሳሌ አቡ ፈድሉላህ አል-ዑመሪ የሚባለው ግብጻዊ ምሁር በ1349 ዓ.ል. በጻፈውና “መሳሊከል አብሳር ፊ መማሊከል መሳር” በሚባለው ዝነኛ መጽሀፍ ውስጥ አዳል ተደጋግሞ የተጠቀሰ ስም ነው። ከ1415 ዓ.ል. በፊት “አዳል” በኢፋት ሱልጣኔት ስር የነበረ የአንድ አውራጃ ስም ነበር። የዐጼ ዐምደ ጽዮን (1314-1344 ዓ.ል) ዜና መዋዕል ዘጋቢ እንደጻፈው ከሆነ የዚህ አውራጃ ዋና ከተማ “ተላቅ” የሚል ስያሜ ነበረው። “ፉቱሕ አል- ሐበሽ” የተሰኘው መጽሀፍ ደራሲ ሱልጣኔቱን “አዳል” ከሚለው ስም በተጨማሪ “በሪ ሰዓደዲን” (የሰዓደዲን በር) እና “ዳር ሰዓደዲን” (የሰዓደዲን ሀገር) በሚሉ ስሞችም ይጠራዋል። ይህም ሱልጣኔቱን ያቋቋሙት የሱልጣን ሰዓደዲን ልጆች እንደ ሰማዕት በሚያዩት አባታቸው ስም ያወጡለት የክብር ስያሜ ነው። የግዕዝ ምንጮችም ስለኢትዮጵያ ኢስላማዊ ግዛቶች በሚጽፉበት ጊዜ “አዳል” የሚለውን ስም በእጅጉ ይደጋግሙታል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ስያሜው ከግዛት መጠሪያነት ያልፍና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በሙሉ በወል የሚጠሩበት ስም ሆኖ ይገኛል። በኢትዮጵያ ምድር ከታዩት ሱልጣኔቶች እምብዛም በማያደናግር ሁኔታ ታሪኩ የተጻፈለት “አዳል” ብቻ ነው (ከአንዳንድ አሻሚ ነጥቦች በስተቀር)። እጅግ ሰፊ ግዛት የሚያካልለውም “አዳል” ነው። ከሀረር ከተማ ታሪክ ጋር በእጅጉ የተቆራኘውም “አዳል” ነው። አዳል በስፋቱም ሆነ በሕዝቦቹ ብዛት በኢትዮጵያ ምድር ከታዩት ሱልጣኔታዊ ግዛቶች በእጅጉ ይልቃል። በፕሮፌሰር ኡልሪች ብራውኬምፐር ጥናት እንደተገለጸው አዳል በስተምዕራብ በኩል ከባሊ፣ ደዋሮና ፈጠጋር(የአሁኗ ቢሾፍቱ) ጋር ይዋሰናል። በስተሰሜን በኩል ደግሞ እስከ አውሳ በረሃ መጨረሻ ድረስ ይደርሳል። በምስራቅ እስከ ኤደን ባህረ ሰላጤ የሚደርስ ሲሆን በደቡብ ደግሞ ከህንድ ውቅያኖስ ጋር ይዋሰናል። በአዳል ግዛት ውስጥ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የሶማሊ፣ የሀረላ (ሀረሪ) እና የአርጎባ ህዝቦች ይኖሩ የነበረ ሲሆን በዘመናችን በውል የማይታወቁ ሌሎች ህዝቦችም ነበሩበት። ዘይላ፡ አራ፣ በርበራ፣ ዳርዱራ፣ ሳሊራ፣ ሆበት፣ ጊዳያ፣ ሐርጋያ፣ ሀረር እና ኩሰም ከአዳል ከተሞች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። “ደከር” የሱልጣኔቱ የመጀመሪያ መዲና ነበረች፤ ከዚያም በዜይላ ተተካች፤ በስተመጨረሻም ሀረር የግዛተ መንግስቱ ዋና ከተማ ሆነች። አዳል የአዋሽ ወንዝ በሚፈስበት ክፍሉ እጅግ ለምና ለእርሻ ተስማሚ የሆነ መሬት ነበረው። አብዛኛው የሱልጣኔቱ ነዋሪ በግብርና ይተዳደር የነበረ ሲሆን ይህም የሰብል ማምረትንና የከብት እርባታን ያካተተ ነበር። በሌላ በኩል ሱልጣኔቱ የህንድ ውቅያኖስና የኤደን ባህረ ሰላጤ ተጎራባች መሆኑ ንግድ በክልሉ እንዲስፋፋ በእጅጉ ረድቷል። ዘይላ ሱልጣኔቱ ከውጪው ዓለም ጋር የሚገናኝበት ዋነኛ ወደብ ነበረች። የታጁራ፡ በርበራና መርካ ወደቦችም የሱልጣኔቱ አካላት ነበሩ። ከደቡብ፣ ከምዕራብና ከደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚመጡት የግብርና ውጤቶች፣ የዝሆን ጥርስ፣ ዝባድ ዘወተ.. ወደ ውጪ የሚላኩት በነዚሁ ወደቦች በኩል ሲሆን ከውጪው ዓለም የሚገቡ ሸቀጦችም ወደ ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገቡት በሱልጣኔቱ ምድር ነው። ሰፊው የአዳል ሱልጣኔት በስሩ ያሉትን ክልሎች ሁሉ አንድ ወጥ በሆነ መንገድ አይደለም ያስተዳደረው። በስሩ ካሉት አካባቢዎች አንዳንዶቹ የራስ ገዝ አይነት አስተዳደር ነበራቸው። እነዚህ አስተዳደሮች “አሚር” የሚል ማዕረግ በነበራቸው ገዥዎች ይተዳደሩ ነበር። በአሚር ከሚተዳደሩት የአዳል ክፍለ ሀገራት በጣም ጎልተው የሚታዩት ዘይላ፣ ሁበትና ሀረር ናቸው። “አዳል” ሱልጣኔቱ በታሪክ የሚታወቅበት ትክክለኛ ስም ነው። ይህም ከላይ እንደገለጽኩት በበርካታ የጥንት ሰነዶች ውስጥ የተመዘገበ ስያሜ ከመሆኑም በላይ የሱልጣኔቱ ገዥዎችና የሀገሬውም ህዝብ በመጠሪያነት ይጠቀሙበት ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አንዳንድ ጸሀፍት ስያሜውን ከታሪክ ሰነዶች የማውጣት አዝማሚያ እየታየባቸው ነው። ምክንያቱን ባይነግሩንም ከሁኔታዎች መገመት የሚቻል ይመስለኛል። ይኸውም የ“አፋር ህዝብ ስያሜውን እንደ ስድብ ያየዋል” በሚል ሰበብ ነው። በርግጥም የአፋር ህዝብ “አፋር” ተብሎ ነው መጠራት ያለበት። ይህንንም በ1969 ዓ.ል. በገዋኔ ከተማ በተደረገው ታላቅ ጉባኤ ባሳለፈው ውሳኔ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች አስታውቋል። እኛም ውሳኔውን በሙሉ ልባችን እናከብረዋለን። ስለዚህ “አዳል” የሚለው ስም የ“አፋር” ህዝብ መጠሪያ ሆኖ መቅረብ የለበትም። ነገር ግን በታሪክ ድርሳናት የሰፈረው “አዳል” የመንግስት ስም ከመሆኑ ውጪ የአፋር ህዝብን በተናጠል የሚመለከት ስያሜ አይደለም። ደግሞም ስያሜውን ለመንግስታቸው ያወጡት የጥንቱ ወላስማዎችና የሱልጣኔቱ ህዝቦች በዚህ ስም መጠራቱን ይወዱት ነበር። ዛሬ እኛ ተነስተን ጥንት “አዳል” ሲባል የነበረውን የሱልጣኔታዊ መንግስቱን ስያሜ “አፋር” ወደሚለው ከቀየርነው ታሪክ በጣም ይፋለሳል። ሱልጣኔቱ የበርካታ ህዝቦች ግዛት ሆኖ ሳለ የአንድ ህዝብ ብቻ አድርጎ ማቅረቡም ከባድ ስህተት ነው። ስለሆነም የጥንቱን ሱልጣኔት “አዳል” በሚለው ትክክለኛ ስሙ መጥራት ይገባል። ከዚህ ጋር መጠቀስ ያለበት ሌላ ጉዳይ ደግሞ በ“አዳል” ታሪክ ላይ የሚደረገው የታሪክ ሽሚያ ነው። በዘመናችን የተለቀቁ በርካታ የኢንተርኔት ገጾች “አዳል” የሶማሊዎች ሱልጣኔት እንደነበረና ግዛቱም ሶማሊዎች የሰፈሩበትን አካባቢ (ሶማሊያ፣ ሶማሊላንድ፣ ኦጋዴን ወዘተ...) ብቻ እንደሚያጠቃልል አድርገው ነው የሚጽፉት። እነኝህ የኢንተርኔት ጽሁፎች አንድ የማያስተባብሉት ነገር ቢኖር “ሀረር የአዳል ዋና ከተማ ነበረች” የሚለው ብቻ ነው (ይህንንም ማስተባበል ያልቻሉት በፉቱሑል ሐበሽ ውስጥ የተጻፈ ሀቅ ስለሆነ ነው)። የሶማሊያው ጄኔራል ሙሐመድ ዚያድ በሬ በ1970 ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜም ይህንን የአዳል ሱልጣኔት ታሪክ እንደ ባለቤትነት ማረጋገጫ በማቅረብ “ከአዋሽና ዋቤ ሸበሌ ወንዞች በስተምስራቅና ደቡብ ያለው ግዛት በሙሉ የሶማሊያ ህጋዊ መሬት ነው” የሚል ፕሮፓጋንዳ ነዝቶ ነበር። ይሁንና ይህ ሁሉ ዐይን ያወጣ የታሪክ ዘረፋ ነው። በአዳል ግዛት ውስጥ ሶማሊዎች መኖራቸው እርግጠኛ ነገር ቢሆንም አዳልና የዛሬዋ ሶማሊያ በአፈጣጠራቸው፣ በማህበረ ህዝብ ተዋጾኦዋቸውና በታሪካዊ ጉዞአቸው በጭራሽ አይመሳሰሉም። አዳል የጥንታዊው የኢፋት ሱልጣኔት ቀጥተኛ ወራሽ ሆኖ ነው የተቋቋመው። የሱልጣኔቱ መሪዎችም በኢፋት (የዛሬው ሰሜን ምስራቅ ሸዋ አካባቢ ማዕከላቸውን ከቆረቆሩት የጥንቱ የወላስማ ሱልጣኖች የዘር ሀረግ ነው የተገኙት። የሱልጣኔቱ ዋና መስራች የሚባሉት ህዝቦች የሚኖሩትም በአሁኑ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ነው። በአንድ ዘመን “አዳል” ሲባል የነበረው ስፍራ የተጠቃለለው በአሁኑ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ነው (“አዳል እና ኢሳ” እና “ጨርጨር፣ አዳልና ጋራ ጉራቻ” የሚባሉትን አውራጃዎች ታስታውሱ የለም?)። የዛሬዋ ሶማሊያ አብዛኛው ክፍል በአዳል ሱልጣኔት ስር የነበረ ግዛት ቢሆንም ሱልጣኔቱ ታሪክ ሲሰራ የነበረውም ሆነ ታሪኩ የተቀበረው አሁን በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ባለው ዋነኛ መሬቱ ላይ ነው። በአጭር አነጋገር የ“አዳል” መነሻም ሆነ እምብርቱ የነበረው በአሁኑ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ነው። በሌላ በኩል አዳል በዘመኑ (ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን) የነበሩት የኢትዮጵያ ሱልጣኔታዊ ግዛቶች ሁሉ (ሀዲያ፣ባሌ፣ ደዋሮ፣ ሻርካ፣ ደራ፣ አራባባኒ ወዘተ..) የፖለቲካዊና መንፈሳዊ መሪ እንደነበረም የታሪክ ድርሳናት ያረጋግጣሉ። ዛሬ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ 45 በመቶ ያህል የሚሸፍኑት ሙስሊም አማኞች መነሻም በነዚያ የጥንት ሱልጣኔታዊ ግዛቶች የሚኖሩት ሙስሊሞች ናቸው። በዚህ አንጻር ሲታይም የሱልጣኔቱ ታሪክ ህጋዊ ባለቤቶች መላው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንጂ በ1960 ዓ.ል የተወለደው የሶማሊያ መንግስትና የ“ታላቋ ሶማሊያ” መፈክር አቀንቃኞች አይደሉም። (ምንጭ፡- አፈንዲ ሙተቂ፣ “ሀረር ጌይ-2”- የሀረርና የአዳል ታሪካዊ ወጎች፡ ገጽ 33-35) ማጣቀሻ (ምንጭ፡- አፈንዲ ሙተቂ፣ “ሀረር ጌይ-2”- የሀረርና የአዳል ታሪካዊ ወጎች፡ ገጽ 33-35) አዳል የምለው ስም የጉሣ ስም ይምሰልናል አፋር ውስጥ አዳአል ይምባል ጐሣ አለ ና አዳል የሚለው ስም የጐሣ ስም የምሰልናል የኢትዮጵያ ታሪክ ታሪካዊ
52411
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A4%E1%88%8D%E1%8B%9B%E1%89%A4%E1%89%B5%20I
ኤልዛቤት I
ኤልዛቤት (ሴፕቴምበር 7 1533 መጋቢት 24 ቀን 1603) [ሀ] የእንግሊዝ እና የአየርላንድ ንግስት ከህዳር 17 ቀን 1558 በ1603 እስከሞተችበት ጊዜ ድረስ የእንግሊዝ እና የአየርላንድ ንግስት ነበረች። አንዳንድ ጊዜ ድንግል ንግሥት እየተባለች የምትጠራው ኤልዛቤት ከአምስቱ የንጉሠ ነገሥታት ቤት የመጨረሻዋ ነበረች። ቱዶር. ኤልዛቤት የ21⁄2 አመት ልጅ እያለች የተገደለችው የሄንሪ ስምንተኛ እና ሁለተኛ ሚስቱ አን ቦሊን ልጅ ነበረች። የአን ከሄንሪ ጋር የነበራት ጋብቻ ፈርሷል፣ እና ኤልዛቤት ህጋዊ እንዳልሆነ ተነገረች። ግማሽ ወንድሟ ኤድዋርድ ስድስተኛ እ.ኤ.አ. በ 1553 እስኪሞት ድረስ ገዝቷል ዘውዱን ለሴት ጄን ግሬይ ውርስ በመስጠት እና የሁለቱን ግማሽ እህቶቹ የሮማ ካቶሊክ ማርያም እና የታናሽቷ ኤልዛቤትን የይገባኛል ጥያቄ ችላ በማለት ምንም እንኳን በተቃራኒው የሕግ ሕግ ቢኖርም የኤድዋርድ ኑዛዜ ወደ ጎን ቀረበ እና ማርያም ንግሥት ሆና ሌዲ ጄን ግሬይን ከስልጣን አወረደች። በማርያም የግዛት ዘመን ኤልዛቤት የፕሮቴስታንት አማፂያንን ትረዳለች ተብላ ተጠርጥራ ለአንድ ዓመት ያህል ታስራለች። እ.ኤ.አ. ንግሥት ሆና ካደረገችው የመጀመሪያ ተግባሯ አንዱ የእንግሊዝ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን መመስረት ሲሆን ለዚህም ዋና አስተዳዳሪ ሆነች። ይህ የኤልዛቤት ሃይማኖታዊ ሰፈራ ወደ እንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን መቀየር ነበረበት። ኤልዛቤት አግብታ ወራሽ ታፈራለች ተብሎ ይጠበቅ ነበር; ይሁን እንጂ ብዙ መጠናናት ቢያደርግም እሷ ግን ፈጽሞ አላደረገችም። እሷ በመጨረሻ የመጀመሪያ የአጎቷ ልጅ ሁለት ጊዜ ተወግዷል, ጄምስ ስድስተኛ የስኮትላንድ; ይህም የታላቋ ብሪታንያ መንግሥት መሠረት ጥሏል። እሷ ቀደም ሲል የጄምስ እናት ማርያም፣ የስኮትላንድ ንግሥት ለእስር እና ግድያ ተጠያቂ ሆና ነበር። በመንግስት ውስጥ ኤልዛቤት ከአባቷ እና ከፊል ወንድሞቿ እና እህቶቿ የበለጠ ልከኛ ነበረች። አንዱ መፈክሯ "ቪዲዮ እና ታይኦ" ("አየሁ እና ዝም አልኩ") ነበር። በሃይማኖት በአንጻራዊ ሁኔታ ታጋሽ ነበረች እና ስልታዊ ስደትን አስወግዳለች። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በ1570 ዓ.ም ሕገ-ወጥ መሆኗን ካወጁ በኋላ ተገዢዎቿን ከመታዘዝ ከለቀቀች በኋላ፣ በርካታ ሴራዎች ሕይወቷን አደጋ ላይ ጥለውታል፣ ይህ ሁሉ በፍራንሲስ ዋልሲንግሃም በሚመራው የአገልጋዮቿ ሚስጥራዊ አገልግሎት ተሸነፈ። ኤልዛቤት በፈረንሳይ እና በስፔን ዋና ዋና ኃያላን መንግስታት መካከል በመቀያየር በውጭ ጉዳይ ላይ ጠንቃቃ ነበረች። በኔዘርላንድ፣ ፈረንሣይ እና አየርላንድ ውስጥ በርካታ ውጤታማ ያልሆኑ፣ በቂ ሀብት የሌላቸውን ወታደራዊ ዘመቻዎችን በግማሽ ልብ ብቻ ደግፋለች። በ1580ዎቹ አጋማሽ እንግሊዝ ከስፔን ጋር ጦርነትን ማስወገድ አልቻለችም። እያደገች ስትሄድ ኤልዛቤት በድንግልናዋ ተከበረች። በጊዜው በስዕሎች፣በገጸ-ባህሪያት እና በስነ-ጽሁፍ ይከበር የነበረው የስብዕና አምልኮ በዙሪያዋ ወጣ። የኤልዛቤት ንግስና የኤልዛቤት ዘመን በመባል ይታወቃል። ወቅቱ እንደ ዊልያም ሼክስፒር እና ክሪስቶፈር ማርሎው ባሉ ፀሀፊ ፀሃፊዎች የሚመራ የእንግሊዝ ድራማ በማበብ እና እንደ ፍራንሲስ ድሬክ እና ዋልተር ራሌይ ባሉ የእንግሊዝ የባህር ላይ ጀብደኞች ብቃቶች ታዋቂ ነው። አንዳንድ የታሪክ ተመራማሪዎች ኤልዛቤትን እንደ አጭር ግልፍተኛ፣ አንዳንዴም ቆራጥ የሆነች ገዥ አድርገው ይገልጻሉ፣ ከእርስዋ ትክክለኛ የዕድል ድርሻ በላይ የምትደሰት። በንግሥናዋ መገባደጃ አካባቢ፣ ተከታታይ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ችግሮች ተወዳጅነቷን አዳከሙ። ነገር ግን፣ ኤልዛቤት እንደ ገሪዝማቲክ ተዋናይ እና ውሾች በህይወት የተረፈች በነበረበት ዘመን መንግስት በተጨናነቀ እና ውስን በሆነበት እና በአጎራባች ሀገራት ያሉ ነገስታት ዙፋኖቻቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ የውስጥ ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ነው። ከግማሽ ወንድሞቿ እና እህቶቿ አጭር የግዛት ዘመን በኋላ፣ በዙፋኑ ላይ ያሳለፉት 44 ዓመታት ለመንግሥቱ መረጋጋትን አስገኝተው ብሔራዊ ማንነት እንዲገነዘቡ ረድተዋል። የመጀመሪያ ህይወት ኤልዛቤት በሴፕቴምበር 7 1533 በግሪንዊች ቤተመንግስት የተወለደች ሲሆን በአያቶቿ በዮርክ ኤልዛቤት እና በሌዲ ኤልዛቤት ሃዋርድ ስም ተሰየመች። እሷ ከልጅነቷ ለመዳን በጋብቻ የተወለደችው የእንግሊዙ ሄንሪ ስምንተኛ ሁለተኛ ልጅ ነበረች። እናቷ የሄንሪ ሁለተኛ ሚስት አን ቦሊን ነበረች። ስትወለድ ኤልዛቤት የእንግሊዝ ዙፋን ወራሽ ነበረች። ሄንሪ ወንድ ወራሽ ለመምሰል እና የቱዶርን ተተኪነት ለማረጋገጥ በማሰብ ከማርያም እናት ካትሪን ከአራጎን ጋር ትዳሩን ሲያፈርስ ታላቅ እህቷ ማርያም የሕጋዊ ወራሽነት ቦታ አጥታ ነበር። ሴፕቴምበር 1533 እና የእርሷ አምላክ ወላጆች የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ቶማስ ክራንመር ነበሩ; ሄንሪ ኮርቴናይ, 1 ኛ ማርከስ ኦቭ ኤክሰተር; ኤልዛቤት ስታፎርድ, የኖርፎልክ ዱቼዝ; እና ማርጋሬት ዎቶን፣ ዶዋገር ማርሽዮነስ ኦፍ ዶርሴት። በአጎቷ ጆርጅ ቦሊን ቪስካውንት ሮችፎርድ በሕፃኑ ላይ በተከበረው ሥነ ሥርዓት ላይ አንድ ሽፋን ተደረገ ጆን የስሌፎርድ 1 ኛ ባሮን ሁሴ; ጌታ ቶማስ ሃዋርድ; እና ዊልያም ሃዋርድ፣ 1ኛ ባሮን ሃዋርድ የኤፊንጋም። የአራጎን ካትሪን በተፈጥሮ ምክንያት ከሞተች ከአራት ወራት በኋላ እናቷ በግንቦት 19 ቀን 1536 አንገቷ ተቆርጦ ኤልዛቤት የሁለት አመት ከስምንት ወር ልጅ ነበረች። ኤልዛቤት ህጋዊ እንዳልሆነ ተፈርጆ ነበር እና በንጉሣዊው ተተኪነት ቦታዋን ተነፍጓል። ንግሥት ጄን የዙፋኑ አልጋ ወራሽ የሆነው ልጃቸው ኤድዋርድ በተወለደ ብዙም ሳይቆይ በሚቀጥለው ዓመት ሞተች። ኤልሳቤጥ በጥምቀት በዓል ወቅት ክርስቶስን ወይም የጥምቀትን ጨርቅ ይዛ በወንድሟ ቤተሰብ ውስጥ ትቀመጥ ነበር።የኤልዛቤት የመጀመሪያዋ አስተዳዳሪ ማርጋሬት ብራያን “በህይወቴ ውስጥ የማውቀውን ያህል ለሕፃን እና ለሁኔታዎች ጨዋ ነች” በማለት ጽፋለች። ካትሪን ቻምፐርኖውኔ በኋላ በእሷ የምትታወቅ ካትሪን “ካት” አሽሊ ያገባች በ 1537 የኤልዛቤት አስተዳዳሪ ሆና ተሾመች እና በ 1565 እስክትሞት ድረስ የኤልዛቤት ጓደኛ ሆና ቆይታለች። በ1544 ዊልያም ግሪንዳል ሞግዚቷ በሆነበት ጊዜ ኤልዛቤት እንግሊዘኛ፣ ላቲን እና ጣሊያንኛ መጻፍ ችላለች። ጎበዝ እና ጎበዝ ሞግዚት በሆነችው ስር እሷም በፈረንሳይኛ እና በግሪክኛ እድገት አሳይታለች። በ12 ዓመቷ የእንጀራ እናቷን ካትሪን ፓረርን የሃይማኖት ሥራ ጸሎቶችን ወይም ሜዲቴሽን ከእንግሊዝኛ ወደ ጣሊያንኛ፣ ላቲን እና ፈረንሳይኛ መተርጎም ችላለች፣ ይህም ለአባቷ እንደ አዲስ ዓመት ስጦታ ያቀረበችለትን ነው። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ከነበረችበት ጊዜ ጀምሮ እና በህይወቷ ሙሉ በላቲን እና በግሪክ የበርካታ ክላሲካል ደራሲያን ስራዎችን ተርጉማለች፣የሲሴሮ ፕሮ ማርሴሎ፣ የቦይቲየስ ደ መጽናኛ ፍልስፍና፣ የፕሉታርክ ድርሰት እና የታሲተስ አናልስን ጨምሮ። በዘመናዊው ዘመን ከነበሩት አራት የእንግሊዝኛ ትርጉሞች መካከል አንዱ የሆነው ከላምቢት ቤተ መንግሥት ቤተ መፃህፍት የታሲተስ ትርጉም በ2019 የኤልዛቤት የራሷ እንደሆነ ተረጋግጧል፣ የእጅ ጽሁፍ እና ወረቀት ላይ ዝርዝር ትንታኔ ከተሰጠ በኋላ። በ1548 ግሪንዳል ከሞተች በኋላ፣ ኤልዛቤት ትምህርቷን በወንድሟ ኤድዋርድ አስተማሪ ሮጀር አስቻም መማር መሳተፊያ መሆን እንዳለበት በማመን አዛኝ አስተማሪ ተቀበለች። አሁን ያለው የኤልዛቤት ትምህርት እና ቅድመ-ትምህርት እውቀት በአብዛኛው የመጣው ከአስቻም ትውስታዎች ነው። በ1550 መደበኛ ትምህርቷ ሲያልቅ፣ ኤልዛቤት በትውልዷ ውስጥ ካሉት ምርጥ የተማሩ ሴቶች አንዷ ነበረች። በህይወቷ መጨረሻ ላይ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ የዌልስ፣ ኮርኒሽ፣ ስኮትላንዳዊ እና አይሪሽ ቋንቋዎችን እንደምትናገር ታምኖ ነበር። የቬኒስ አምባሳደር በ1603 “[እነዚህን] ቋንቋዎች በሚገባ ስለያዘች እያንዳንዳቸው የአፍ መፍቻ ቋንቋዋ እስኪመስሉ ድረስ” ተናግራለች። የታሪክ ምሁሩ ማርክ ስቶይል ምናልባት ኮርኒሽኛን በዊልያም ኪሊግሬው፣ የፕራይቪ ቻምበር ሙሽራ እና በኋላም ቻምበርሊን ኦቭ ዘ ኤክስቼከር እንዳስተማራት ጠቁመዋል።የኤልዛቤት የመጀመሪያዋ አስተዳዳሪ ማርጋሬት ብራያን “በህይወቴ ውስጥ የማውቀውን ያህል ለሕፃን እና ለሁኔታዎች ጨዋ ነች” በማለት ጽፋለች። ካትሪን ቻምፐርኖውኔ በኋላ በእሷ የምትታወቅ ካትሪን “ካት” አሽሊ ያገባች በ 1537 የኤልዛቤት አስተዳዳሪ ሆና ተሾመች እና በ 1565 እስክትሞት ድረስ የኤልዛቤት ጓደኛ ሆና ቆይታለች። በ1544 ዊልያም ግሪንዳል ሞግዚቷ በሆነበት ጊዜ ኤልዛቤት እንግሊዘኛ፣ ላቲን እና ጣሊያንኛ መጻፍ ችላለች። ጎበዝ እና ጎበዝ ሞግዚት በሆነችው ስር እሷም በፈረንሳይኛ እና በግሪክኛ እድገት አሳይታለች። በ12 ዓመቷ የእንጀራ እናቷን ካትሪን ፓረርን የሃይማኖት ሥራ ጸሎቶችን ወይም ሜዲቴሽን ከእንግሊዝኛ ወደ ጣሊያንኛ፣ ላቲን እና ፈረንሳይኛ መተርጎም ችላለች፣ ይህም ለአባቷ እንደ አዲስ ዓመት ስጦታ ያቀረበችለትን ነው። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ከነበረችበት ጊዜ ጀምሮ እና በህይወቷ ሙሉ በላቲን እና በግሪክ የበርካታ ክላሲካል ደራሲያን ስራዎችን ተርጉማለች፣የሲሴሮ ፕሮ ማርሴሎ፣ የቦይቲየስ ደ መጽናኛ ፍልስፍና፣ የፕሉታርክ ድርሰት እና የታሲተስ አናልስን ጨምሮ። በዘመናዊው ዘመን ከነበሩት አራት የእንግሊዝኛ ትርጉሞች መካከል አንዱ የሆነው ከላምቢት ቤተ መንግሥት ቤተ መፃህፍት የታሲተስ ትርጉም በ2019 የኤልዛቤት የራሷ እንደሆነ ተረጋግጧል፣ የእጅ ጽሁፍ እና ወረቀት ላይ ዝርዝር ትንታኔ ከተሰጠ በኋላ። በ1548 ግሪንዳል ከሞተች በኋላ፣ ኤልዛቤት ትምህርቷን በወንድሟ ኤድዋርድ አስተማሪ ሮጀር አስቻም መማር መሳተፊያ መሆን እንዳለበት በማመን አዛኝ አስተማሪ ተቀበለች። አሁን ያለው የኤልዛቤት ትምህርት እና ቅድመ-ትምህርት እውቀት በአብዛኛው የመጣው ከአስቻም ትውስታዎች ነው። በ1550 መደበኛ ትምህርቷ ሲያልቅ፣ ኤልዛቤት በትውልዷ ውስጥ ካሉት ምርጥ የተማሩ ሴቶች አንዷ ነበረች። በህይወቷ መጨረሻ ላይ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ የዌልስ፣ ኮርኒሽ፣ ስኮትላንዳዊ እና አይሪሽ ቋንቋዎችን እንደምትናገር ታምኖ ነበር። የቬኒስ አምባሳደር በ1603 “[እነዚህን] ቋንቋዎች በሚገባ ስለያዘች እያንዳንዳቸው የአፍ መፍቻ ቋንቋዋ እስኪመስሉ ድረስ” ተናግራለች። የታሪክ ምሁሩ ማርክ ስቶይል ምናልባት ኮርኒሽኛን በዊልያም ኪሊግሬው፣ የፕራይቪ ቻምበር ሙሽራ እና በኋላም ቻምበርሊን ኦቭ ዘ ኤክስቼከር እንዳስተማራት ጠቁመዋል። ቶማስ ሲይሞር ሄንሪ ስምንተኛ በ1547 ሞተ እና የኤልዛቤት ግማሽ ወንድም ኤድዋርድ ስድስተኛ በ9 ዓመቱ ንጉስ ሆነ። የሄንሪ መበለት ካትሪን ፓር ብዙም ሳይቆይ ቶማስ ሲይሞርን፣ የሱዴሊ 1ኛ ባሮን ሲይሞርን፣ የኤድዋርድ ስድስተኛ አጎት እና የሎርድ ጠበቃ ኤድዋርድ ሲይሞርን ወንድም፣ የሱመርሴት 1 መስፍንን አገባች። ጥንዶቹ ኤልዛቤትን ወደ ቼልሲ ቤታቸው ወሰዱ። እዚያም ኤልዛቤት አንዳንድ የታሪክ ተመራማሪዎች በቀሪው ሕይወቷ እንደነካት የሚያምኑትን የስሜት ቀውስ አጋጥሟታል። ቶማስ ሲሞር ከ14 ዓመቷ ኤልዛቤት ጋር በፈረስ ግልቢያ እና የሌሊት ልብሱን ለብሳ ወደ መኝታ ቤቷ መግባቱን፣ መኳኳትን እና ቂጥ ላይ በጥፊ መምታት ጨምሮ ነበር። ኤልዛቤት በማለዳ ተነሳች እና ያልተፈለገ የጠዋት ጉብኝቶችን ለማስቀረት እራሷን በገረዶች ከበበች። ፓር ባሏን ተገቢ ባልሆነ እንቅስቃሴው ከመጋፈጥ ይልቅ ተቀላቀለች። ሁለት ጊዜ ኤልዛቤትን ስትመታ አብራው ነበር፣ እና አንድ ጊዜ ጥቁር ጋዋንዋን "በሺህ ቁርጥራጮች" ቆርጦ ያዘቻት። ሆኖም፣ ፓር ጥንዶቹን በእቅፍ ካገኛት በኋላ፣ ይህንን ሁኔታ ጨርሳለች። በግንቦት 1548 ኤልዛቤት ተባረረች። ቶማስ ሲይሞር ግን የንጉሣዊ ቤተሰብን ለመቆጣጠር ማሴሩን ቀጠለ እና የንጉሱን ሰው ገዥ ለመሾም ሞከረ። ፓር በሴፕቴምበር 5 1548 ከወሊድ በኋላ ሲሞት፣ እሷን ለማግባት በማሰብ ትኩረቱን ወደ ኤልዛቤት አድሷል። ሴይሞርን የምትወደው አስተዳዳሪዋ ካት አሽሊ ኤልዛቤት እሱን እንደ ባሏ እንድትወስድ ለማሳመን ፈለገች። እሷም ኤልዛቤትን ለሴይሞር እንድትጽፍ እና “በሀዘኑም እንድታጽናናው” ለማሳመን ሞክራለች፣ ነገር ግን ኤልዛቤት ቶማስ በእንጀራ እናቷ ሞት እንዳሳዘነች ተናግራ መጽናኛ እንደፈለገች ተናግራለች። በጥር 1549 ሲይሞር ወንድሙን ሱመርሴትን ከተከላካይነት ለማውረድ፣ ሌዲ ጄን ግሬይን ለንጉስ ኤድዋርድ 6ኛ ለማግባት እና ኤልዛቤትን እንደ ራሷ ሚስት ለማድረግ በማሴር ተጠርጥሮ ተይዞ በግንቡ ውስጥ ታስሯል። በ ሃትፊልድ ሃውስ የምትኖረው ኤልዛቤት ምንም አትቀበልም። ግትርነቷ ጠያቂዋን ሰር ሮበርት ቲርዊትን “ጥፋተኛ መሆኗን በፊቷ አይቻለሁ” ሲሉ ዘግበውታል። ሲይሞር መጋቢት 20 ቀን 1549 አንገቱ ተቆረጠ ንግስና ማርያም ኤድዋርድ ስድስተኛ በጁላይ 6 1553 በ15 ዓመቱ አረፈ። ኑዛዜው የ1543 የዘውድ ሥልጣንን ቸል በማለት ማርያምን እና ኤልዛቤትን ተተኪነት አገለለ እና በምትኩ የሄንሪ ስምንተኛ ታናሽ እህት የማርያም የልጅ ልጅ የሆነችውን ሌዲ ጄን ግሬይ ወራሽ አድርጎ ገልጿል። ጄን በፕራይቪ ካውንስል ንግሥት ተባለች፣ ነገር ግን ድጋፏ በፍጥነት ፈራረሰ፣ እና ከዘጠኝ ቀናት በኋላ ከስልጣን ተባረረች። እ.ኤ.አ. ኦገስት 3 1553 ማርያም በድል አድራጊነት ወደ ለንደን ገባች፣ ኤልዛቤትም ከጎኗ ነበር።በእህቶች መካከል ያለው የአብሮነት ትርኢት ብዙም አልዘለቀም። አጥባቂ ካቶሊክ የነበረችው ሜሪ ኤልዛቤት የተማረችበትን የፕሮቴስታንት እምነት ለማጥፋት ቆርጣ ተነስታ ሁሉም ሰው በካቶሊክ ቅዳሴ ላይ እንዲገኝ አዘዘች። ኤልዛቤት በውጫዊ ሁኔታ መስማማት ነበረባት። የማርያም የመጀመሪያ ተወዳጅነት በ 1554 የቅዱስ ሮማዊው ንጉሠ ነገሥት ቻርልስ አምስተኛ ልጅ እና ንቁ የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆነውን ስፔናዊውን ፊሊፕ ለማግባት ማቀዷን ስታስታውቅ ነበር። ብስጭት በአገሪቱ በፍጥነት ተሰራጭቷል፣ እና ብዙዎች የማርያምን ሃይማኖታዊ ፖሊሲዎች በመቃወም ኤልዛቤትን እንደ ትኩረት አድርገው ይመለከቱ ነበር። በጥር እና በፌብሩዋሪ 1554 የዋይት አመጽ ተነሳ; ብዙም ሳይቆይ ታፍኗል። ኤልዛቤት ፍርድ ቤት ቀርቦ ስለእሷ ሚና ተጠይቃለች፣ እና በመጋቢት 18፣ በለንደን ግንብ ውስጥ ታስራለች። ኤልዛቤት ንፁህነቷን አጥብቃ ተቃወመች። ምንም እንኳን ከዓመፀኞቹ ጋር ማሴር ባትችልም አንዳንዶቹ ወደ እርሷ እንደቀረቡ ይታወቃል። የማርያም የቅርብ ታማኝ፣ የቻርልስ አምስተኛ አምባሳደር ሲሞን ሬናርድ፣ ኤልዛቤት በምትኖርበት ጊዜ ዙፋኗ መቼም ቢሆን ደህና አይሆንም ሲል ተከራከረ። እና ሎርድ ቻንስለር እስጢፋኖስ ጋርዲነር፣ ኤልዛቤት ለፍርድ እንድትቀርብ ሠርተዋል። በመንግስት ውስጥ ያሉ የኤልዛቤት ደጋፊዎች፣ ዊልያም ፔጅን፣ 1ኛ ባሮን ፔጅትን ጨምሮ፣ በእሷ ላይ ጠንካራ ማስረጃ በሌለበት ማርያም እህቷን እንድትታደግ አሳመኗት። በምትኩ፣ በግንቦት 22፣ ኤልዛቤት ከግንቡ ወደ ዉድስቶክ ተዛወረች፣ እዚያም በሰር ሄንሪ ቤዲንግፌልድ ክስ ውስጥ ለአንድ አመት ያህል በቤት እስራት ልታሳልፍ ነበር። ህዝቡ በመንገዱ ሁሉ ደስ አሰኝቷታል።እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 17 ቀን 1555 ኤልዛቤት የማርያምን ግልፅ እርግዝና የመጨረሻ ደረጃ ላይ ለመገኘት ወደ ፍርድ ቤት ተጠራች። ማርያምና ልጇ ቢሞቱ ኤልሳቤጥ ንግሥት ትሆናለች፣ነገር ግን ማርያም ጤናማ ልጅ ከወለደች፣ የኤልሳቤጥ ንግሥት የመሆን እድሏ በጣም እያሽቆለቆለ ይሄዳል። ማርያም እንዳልፀነሰች ሲታወቅ ልጅ መውለድ እንደምትችል ማንም አላመነም። የኤልዛቤት ተተኪነት የተረጋገጠ ይመስላል። በ1556 የስፔን ዙፋን ላይ የወጣው ንጉስ ፊሊፕ አዲሱን የፖለቲካ እውነታ አምኖ አማቱን አሳደገ። በፈረንሳይ ያደገችው እና ከፈረንሳይ ዳፊን ጋር ከታጨችው ከዋነኛው አማራጭ ሜሪ፣ የስኮትላንዳዊቷ ንግሥት የተሻለ አጋር ነበረች። በ1558 ሚስቱ ስትታመም ንጉስ ፊልጶስ ከኤልሳቤጥ ጋር ለመመካከር የፌሪያን ግዛት ላከ። ይህ ቃለ ምልልስ የተካሄደው በጥቅምት 1555 ለመኖር በተመለሰችው ሃትፊልድ ሃውስ ነው። በጥቅምት 1558 ኤልዛቤት ለመንግሥቷ እቅድ አውጥታ ነበር። ማርያም ህዳር 6 ቀን 1558 ኤልዛቤትን እንደ ወራሽ አወቀች፣ እና ኤልሳቤጥ ንግሥት ሆና በኖቬምበር 17 ማርያም ስትሞት መግባት ኤልሳቤጥ በ25 ዓመቷ ንግሥት ሆነች፣ እና ፍላጎቷን ለምክር ቤትዋ እና ሌሎች ጓደኞቿን ታማኝ ለመሆን ወደ ሃትፊልድ ለመጡት ተናገረች። ንግግሩ የሉዓላዊውን "ሁለት አካላት" የመካከለኛው ዘመን የፖለቲካ ሥነ-መለኮትን የተቀበለችበትን የመጀመሪያ ዘገባ ይዟል፡ አካል ተፈጥሯዊ እና ፖለቲካዊ፡ ጌቶቼ፣ የተፈጥሮ ህግ ለእህቴ እንዳዝን ያነሳሳኛል; በእኔ ላይ የወረደው ሸክም አስገረመኝ፣ ነገር ግን እኔ የእግዚአብሔር ፍጡር እንደ ሆንኩ በመቁጠር፣ ሹመቱን እንድፈጽም የተሾምኩ፣ ለዚያም እሺ እሆናለሁ፣ አገልጋይ ለመሆን የጸጋውን እርዳታ ለማግኘት ከልቤ እመኛለሁ። በዚህ ቢሮ ውስጥ ስላለው ሰማያዊ ፈቃዱ አሁን ለእኔ የተሰጠኝ። እኔ በተፈጥሮ አንድ አካል እንደ ሆንሁ፥ ምንም እንኳን በእርሱ ፈቃድ አንድ የፖለቲካ አካል ለመምራት፥ ሁላችሁንም በእኔ ፍርድ እናንተም ከእናንተ አገልግሎት ጋር በመልካም ሒሳብ እንድትሰጡኝ ረዳቱ ትሆኑ ዘንድ እፈቅዳለሁ። ለልዑል እግዚአብሔር እና በምድር ላይ ላሉ ዘመዶቻችን አንዳንድ መጽናናትን ይተውልን። ሁሉንም ድርጊቶቼን በጥሩ ምክር እና ምክር መምራት ማለቴ ነው። በዘውድ ሥርዓቱ ዋዜማ የድል ግስጋሴዋ በከተማዋ ሲታመስ፣ በዜጎች በሙሉ ልቧ የተቀበሏት እና በንግግሮች እና ትርኢቶች የተቀበሏት እጅግ በጣም ጠንካራ የፕሮቴስታንት ጣእም ያለው ነው። የኤልዛቤት ግልጽ እና የጸጋ ምላሽ ሰጪዎች “በድንቅ የተደፈሩ” ተመልካቾችን እንድትወድ አድርጓታል። በማግስቱ፣ ጥር 15 ቀን 1559፣ በኮከብ ቆጣሪዋ ጆን ዲ፣ ኤልዛቤት የተመረጠችበት ቀን በዌስትሚኒስተር አቢ በካርሊል የካቶሊክ ጳጳስ ኦወን ኦግሌቶርፕ ዘውድ ተቀዳጀች። ከዚያም ሰዎቹ እንዲቀበሏት ቀረበች፣ በሚሰሙት የአካል ክፍሎች፣ ፊፋ፣ ጥሩምባ፣ ከበሮ እና ደወሎች መካከል። ምንም እንኳን ኤልዛቤት በእንግሊዝ ንግሥት ሆና እንኳን ደህና መጣችሁ ብትልም፣ ሀገሪቱ አሁንም በሃገር ውስጥ እና በባህር ማዶ የሚደርሰው የካቶሊክ ስጋት፣ እንዲሁም ማንን እንደምታገባ በመምረጡ ስጋት ላይ ነች። የቤተክርስቲያን ሰፈር የኤልዛቤት የግል ሃይማኖታዊ እምነቶች በሊቃውንት ብዙ ክርክር ተደርጎባቸዋል። እሷ ፕሮቴስታንት ነበረች፣ ነገር ግን የካቶሊክ ምልክቶችን (እንደ ስቅለት ያሉ) ትይዛለች፣ እና የፕሮቴስታንት ቁልፍ የሆነውን እምነት በመቃወም የስብከትን ሚና አሳንሳለች። ኤልዛቤት እና አማካሪዎቿ በመናፍቃን እንግሊዝ ላይ የካቶሊክ የመስቀል ጦርነት እንደሚያስፈራራ ተገነዘቡ። ስለዚህ ንግስቲቱ የእንግሊዝ ፕሮቴስታንቶችን ፍላጎት እየተናገረች ካቶሊኮችን በእጅጉ የማያስከፋ ፕሮቴስታንት መፍትሄ ፈለገች፣ነገር ግን ሰፊ ተሃድሶ እንዲደረግ የሚገፋፉትን ፒዩሪታኖችን አትታገስም። በዚህ ምክንያት የ1559 ፓርላማ በኤድዋርድ ስድስተኛ ፕሮቴስታንት ሰፈር ላይ የተመሰረተ ቤተክርስትያን ንጉሱ ራስ ሆኖ ነገር ግን እንደ አልባሳት ያሉ ብዙ የካቶሊክ አካላት ላሉት ቤተክርስቲያን ህግ ማውጣት ጀመረ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሀሳቦቹን አጥብቆ ደግፏል፣ ነገር ግን የላዕላይነት ረቂቅ ህግ በጌቶች ምክር ቤት በተለይም ከጳጳሳት ተቃውሞ ገጠመው። የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ጨምሮ ብዙ ጳጳሳት በወቅቱ ክፍት በመሆናቸው ኤልዛቤት እድለኛ ነበረች። ቢሆንም፣ ብዙዎች አንዲት ሴት ለመሸከም ተቀባይነት እንደሌለው በማሰብ ኤልዛቤት ይበልጥ አከራካሪ ከሆነው የበላይ አለቃ ይልቅ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን የበላይ ገዥ የሚለውን ማዕረግ ለመቀበል ተገድዳለች። በግንቦት 8 ቀን 1559 አዲሱ የበላይነት ህግ ህግ ሆነ። ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናት ለንጉሱ የበላይ ገዥ በመሆን ታማኝነታቸውን መማል ወይም ከስልጣን መባረር አለባቸው። በማርያም ይፈጸም የነበረው ተቃዋሚዎች ስደት እንዳይደገም የኑፋቄ ሕጎቹ ተሽረዋል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ቤተ ክርስቲያን መገኘትን እና የ1552 የጋራ ጸሎት መጽሐፍን በተሻሻለው እትም መጠቀምን የሚያስገድድ አዲስ የወጥነት ሕግ ወጣ፣ ምንም እንኳን በዳግም መቀበል ወይም አለመገኘት እና አለመከተል ቅጣቶች ጽንፍ ባይሆኑም የጋብቻ ጥያቄ ከኤሊዛቤት ንግሥና መጀመሪያ ጀምሮ ታገባለች ተብሎ ይጠበቅ ነበር, እና ጥያቄው ለማን ተነሳ. ብዙ ቅናሾችን ብታገኝም አላገባችም እና ልጅ አልባ ሆና ቀረች; ለዚህ ምክንያቱ ግልጽ አይደለም. የታሪክ ተመራማሪዎች ቶማስ ሲሞር ከፆታዊ ግንኙነት እንዳቋረጠ ይገምታሉ። ሃምሳ እስክትሆን ድረስ ብዙ ፈላጊዎችን አስባለች። የመጨረሻ የፍቅር ጓደኝነት የ22 ዓመቷ የአንጁው መስፍን ፍራንሲስ ጋር ነበር። በስፔናዊው ንጉስ ፊሊፕ 2ኛ እጅ እንደተጫወተችው እህቷ ስልጣኗን ሊያጣ እንደሚችል ስጋት ውስጥ ገብታለች፣ ትዳር ወራሽ የመሆን እድል ፈጠረላት። ሆኖም የባል ምርጫ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት አልፎ ተርፎም ዓመፅ ያስነሳል። ሮበርት ዱድሊ በ1559 የጸደይ ወራት፣ ኤልዛቤት ከልጅነት ጓደኛዋ ከሮበርት ዱድሊ ጋር ፍቅር እንደነበራት ግልጽ ሆነ። ሚስቱ ኤሚ ሮብሳርት "በአንደኛው ጡቷ ላይ በሚታመም በሽታ" እየተሰቃየች እንደነበረ እና ንግስቲቱ ሚስቱ ብትሞት ዱድሊን ማግባት እንደምትፈልግ ተነግሯል። እጅ; ትዕግሥት የለሽ መልእክቶቻቸው ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አሳፋሪ ንግግር ውስጥ ተሰማርተው እና ከምትወደው ጋር ጋብቻ በእንግሊዝ ውስጥ ተቀባይነት እንደሌለው ዘግበዋል: “በእሱ እና በእሷ ላይ በቁጣ የማይጮህ ሰው የለም… እሷ ከተወደዱ በስተቀር ማንንም አታገባም ሮበርት." ኤሚ ዱድሊ በሴፕቴምበር 1560 ከደረጃ በረራ ላይ በመውደቁ ሞተች እና ምንም እንኳን የምርመራ ተቆጣጣሪው የአደጋ ምርመራ ቢያገኝም ብዙ ሰዎች ባሏ ንግሥቲቱን እንዲያገባ ሲል ሞቷን አመቻችቷል ብለው ጠረጠሩት። ኤልዛቤት ዱድሊንን ለተወሰነ ጊዜ ለማግባት አስባ ነበር። ሆኖም ዊልያም ሴሲል፣ ኒኮላስ ትሮክሞርተን እና አንዳንድ ወግ አጥባቂ እኩዮቻቸው አለመስማማታቸውን በማያሻማ መልኩ ግልጽ አድርገዋል። ጋብቻው ከተፈጸመ ባላባቶች እንደሚነሱ የሚነገር ወሬም ነበር። ሮበርት ዱድሊ ለንግስት ተብለው ከሚታሰቡ ሌሎች የጋብቻ እጩዎች መካከል፣ ለሌላ አስርት ዓመታት ያህል እንደ እጩ መቆጠር ቀጠለ። ኤልዛቤት በፍቅሩ በጣም ትቀና ነበር፣ ምንም እንኳን እሷ ራሷ ልታገባው ባትፈልግም ነበር። እ.ኤ.አ. በ1564 ዱድሊንን እንደ የሌስተር አርል አሳደገችው። በመጨረሻም በ 1578 እንደገና አገባ, ንግሥቲቱ ለባለቤቱ ሌቲስ ኖሊስ ተደጋጋሚ ብስጭት እና የዕድሜ ልክ ጥላቻ ምላሽ ሰጥታለች. አሁንም፣ ዱድሊ የታሪክ ምሁር የሆኑት ሱዛን ዶራን ሁኔታውን እንደገለፁት ሁል ጊዜ “[የኤልዛቤት] ስሜታዊ ሕይወት መሃል ላይ ይቆዩ ነበር። እ.ኤ.አ. በ1588 የስፔን ጦር ከተሸነፈ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሞተ። ኤልዛቤት ከሞተች በኋላ፣ በጣም ከግል ንብረቶቿ መካከል ከእርሱ የተላከ ማስታወሻ ተገኘች፤ በእጇ በጻፈችው ጽሑፍ ላይ “የመጨረሻው ደብዳቤ” የውጭ አገር እጩዎች የጋብቻ ድርድር በኤልዛቤት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ ቁልፍ አካል ነበር። በ1559 መጀመሪያ ላይ የግማሽ እህቷ ሚስት የነበረችውን የፊሊፕን እጅ አልተቀበለችም ግን ለብዙ ዓመታት የስዊድን ንጉስ ኤሪክ አሥራ አራተኛውን ሀሳብ አቀረበች። ቀደም ሲል በኤልዛቤት ሕይወት ውስጥ ለእሷ የዴንማርክ ግጥሚያ ውይይት ተደርጎበታል ሄንሪ ስምንተኛ በ1545 ከዴንማርክ ልዑል አዶልፍ ፣የሆልስታይን-ጎቶርፕ መስፍን ጋር እና ኤድዋርድ ሲይሞር ፣የሱመርሴት መስፍን ከፕሪንስ ፍሬድሪክ (በኋላ ፍሬደሪክ 2) ከበርካታ አመታት በኋላ እንዲጋቡ ሀሳብ አቅርበው ነበር ፣ነገር ግን ድርድሩ በ1551 ቀነሰ እ.ኤ.አ. በ1559 አካባቢ የዳኖ-እንግሊዘኛ ፕሮቴስታንት ህብረት ታሳቢ ተደርጎ ነበር፣ እና የስዊድንን ሃሳብ ለመቃወም ንጉስ ፍሬድሪክ በ1559 መጨረሻ ላይ ለኤልዛቤት ጥያቄ አቀረበ።ለብዙ አመታት እሷም የፊሊፕን የአጎት ልጅ ቻርልስ የኦስትሪያውን አርክዱክን ለማግባት በቁም ነገር ተደራድራለች። እ.ኤ.አ. በ 1569 ከሀብስበርግ ጋር ያለው ግንኙነት ተበላሽቷል ኤልዛቤት በተራው ከሁለት የፈረንሣይ ቫሎይስ መኳንንት ጋር ጋብቻን አስባ ነበር በመጀመሪያ ሄንሪ የአንጁዱ መስፍን እና ከ 1572 እስከ 1581 ወንድሙ ፍራንሲስ የአንጁው መስፍን የቀድሞ የአሌንኮን መስፍን። ይህ የመጨረሻው ሀሳብ በደቡባዊ ኔዘርላንድ የስፔን ቁጥጥር ላይ ከታቀደው ጥምረት ጋር የተያያዘ ነው። ኤልዛቤት የፍቅር ጓደኝነትን ለተወሰነ ጊዜ በቁም ነገር የወሰደችው እና ፍራንሲስ የላከላትን የእንቁራሪት ቅርጽ ያለው የጆሮ ጌጥ ለብሳለች። እ.ኤ.አ. በ 1563 ኤልዛቤት የንጉሠ ነገሥቱን ልዑክ “የተፈጥሮዬን ዝንባሌ ከተከተልኩ ይህ ነው-ለማኝ ሴት እና ነጠላ ከንግሥት እና ከጋብቻ ይልቅ። በዓመቱ በኋላ፣ ኤልዛቤት በፈንጣጣ መታመሟን ተከትሎ፣ የመተካካት ጥያቄ በፓርላማ ውስጥ የጦፈ ጉዳይ ሆነ። አባላት ንግስቲቱ እንድትጋባ ወይም ወራሽ እንድትሰይም አሳስቧታል፣ ስትሞት የእርስ በርስ ጦርነትን ለመከላከል። እሷም ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነችም። በ 1566 ታክስ ለመጨመር ድጋፉን እስክትፈልግ ድረስ እንደገና ያልተሰበሰበውን ፓርላማ በኤፕሪል አነሳች ከዚህ ቀደም ለማግባት ቃል ገብታ፣ ሥርዓት ለሌለው ቤት እንዲህ አለች፡-ለክብር ስል በአደባባይ የተነገረውን የልዑል ቃል በፍጹም አላፈርስም። ስለዚህም ደግሜ እላለሁ፣ በተመቸኝ መጠን አገባለሁ፣ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ላገባው የምፈልገውን ወይም ራሴን ካልወሰደው፣ ወይም ሌላ ታላቅ ነገር ቢፈጠር። እ.ኤ.አ. በ 1570 በመንግስት ውስጥ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኤልዛቤት በጭራሽ አታገባም ወይም ተተኪ አትሰይም ብለው በግል ተቀበሉ። ዊልያም ሴሲል ቀድሞውንም ለተከታታይ ችግር መፍትሄዎችን እየፈለገ ነበር። ኤልዛቤት ባለማግባቷ ብዙ ጊዜ በኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ትከሰሳለች። ዝምታዋ ግን የራሷን የፖለቲካ ደህንነት አጠንክሯል፡ ወራሽ ብትሰይም ዙፋንዋ ለየግል ግልበጣ እንደሚጋለጥ ታውቃለች። "እንደ እኔ ሁለተኛ ሰው" በቀድሞዋ ላይ የሴራዎች ትኩረት የተደረገበትን መንገድ አስታውሳለች. ድንግልና የኤልዛቤት ያላገባች ሁኔታ ከድንግል ማርያም ጋር የተያያዘ የድንግልና አምልኮን አነሳሳ። በግጥም እና በቁም ሥዕላዊ መግለጫ፣ እርሷ በድንግልና፣ አምላክ ወይም ሁለቱም ተመስላለች እንጂ እንደ መደበኛ ሴት አይታይም። መጀመሪያ ላይ ኤልሳቤጥ ብቻ የድንግልናዋን መልካም ነገር አደረገች፡ በ1559 ለጋራ ማህበረሰብ እንዲህ አለች፡- “እናም፣ በመጨረሻ፣ ይህ ይበቃኛል፣ የእብነበረድ ድንጋይ ንግሥት እንዲህ ያለ ጊዜ እንደነገሠች ያስታውቃል። በድንግልና ኖረች ሞተችም። በኋላ፣ ገጣሚዎች እና ጸሃፊዎች ጭብጡን አነሱ እና ኤልዛቤትን ከፍ ያደረገችውን ምስል አዘጋጁ። እ.ኤ.አ. በ 1578 ለድንግል የተሰጡ የህዝብ ውለታዎች ንግሥቲቱ ከአሌንኮን መስፍን ጋር ባደረገችው የጋብቻ ድርድር ላይ የተቃውሞ ኮድ ማረጋገጫ ሆኖ አገልግሏል። በመጨረሻ፣ ኤልዛቤት በመለኮታዊ ጥበቃ ስር ከግዛቷ እና ከተገዥዎቿ ጋር እንዳገባች አጥብቃ ትጠይቃለች። በ 1599 ስለ "ባሎቼ ሁሉ, የእኔ ጥሩ ሰዎች" ተናገረች.ይህ የድንግልና ይገባኛል ጥያቄ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት አላገኘም። ካቶሊኮች ኤልዛቤትን ከሰውነቷ ጋር በምሳሌያዊ ሁኔታ የሚያረክሰውን “ርኩስ ፍትወት” ውስጥ ገብታለች ሲሉ ከሰሷት። ፈረንሳዊው ሄንሪ አራተኛ የአውሮፓ ታላላቅ ጥያቄዎች አንዱ "ንግሥት ኤልሳቤጥ ገረድ ነበረች ወይስ አይደለም" የሚለው ነው። የኤልዛቤት ድንግልና ጥያቄን በተመለከተ ዋናው ጉዳይ ንግስቲቱ ከሮበርት ዱድሊ ጋር የነበራትን የፍቅር ግንኙነት ፈጽማለች ወይ የሚለው ነበር። እ.ኤ.አ. በ 1559 የዱድሊ መኝታ ቤቶች ከራሷ አፓርታማዎች አጠገብ እንዲዛወሩ አደረገች። እ.ኤ.አ. በ1561 ሰውነቷ እንዲያብጥ ባደረገው ህመም ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ የአልጋ ቁራኛ ሆናለች። በ1587 ራሱን አርተር ዱድሌይ ብሎ የሚጠራ ወጣት በስፔን የባህር ዳርቻ በሰላዩ ተጠርጥሮ ተይዟል። ሰውዬው የኤልዛቤት እና የሮበርት ዱድሌይ ህገወጥ ልጅ ነኝ ሲል በ1561 በህመም ወቅት ከልደቱ ጋር የሚስማማ እድሜው ነበር። ለምርመራ ወደ ማድሪድ ተወሰደ፣ እዚያም ወደ ስፔን በግዞት በተወሰደው የካቶሊክ መኳንንት እና የንጉስ ፊሊፕ 2ኛ ፀሃፊ በሆነው ፍራንሲስ ኢንግልፊልድ ተመርምሯል። አርተር በንጉሣዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ ወደ ስፔን እስከሚደርስበት ጊዜ ድረስ የሕይወቱ ታሪክ መሆኑን የሚገልጹ ሦስት ደብዳቤዎች ቃለ-መጠይቁን የሚገልጹ ሦስት ደብዳቤዎች ዛሬ አሉ። ሆኖም ይህ ስፔናዊውን ማሳመን አልቻለም፡ ኢንግፊልድ የአርተር “አሁን ያለው የይገባኛል ጥያቄ ምንም አይደለም” ሲል ለንጉስ ፊሊፕ አምኗል፣ ነገር ግን “እንዲሸሽ መፍቀድ የለበትም፣ ነገር ግን በጣም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው” ሲል ጠቁሟል። ንጉሱ ተስማምተው ነበር፣ እና አርተር ከአሁን በኋላ አልተሰማም። የዘመናችን ስኮላርሺፕ የታሪኩን መሰረታዊ መነሻ “የማይቻል” በማለት ውድቅ አድርጎታል እና የኤልዛቤት ህይወት በዘመኗ በነበሩ ሰዎች በጣም በቅርብ ይታይ ስለነበር እርግዝናን መደበቅ አልቻለችም ሲል ተናግሯል። የስኮትስ ንግሥት ማርያም በስኮትላንድ ላይ የኤሊዛቤት የመጀመሪያ ፖሊሲ የፈረንሳይን መኖር መቃወም ነበር። ፈረንሳዮች እንግሊዝን ለመውረር እንዳቀዱ እና የካቶሊክ ዘመድ የሆነችውን የስኮትላንድ ንግሥት ማርያምን በዙፋኑ ላይ እንዳስቀምጧት ፈራች። ሜሪ የሄንሪ ስምንተኛ ታላቅ እህት ማርጋሬት የልጅ ልጅ በመሆኗ የእንግሊዝ ዘውድ ወራሽ እንደሆነች ብዙዎች ይቆጠሩ ነበር። ማርያም “የቅርብ ዘመድ ያላት ሴት” በመሆኗ በኩራት ተናግራለች። ኤልዛቤት የፕሮቴስታንት አማፂያንን ለመርዳት ወደ ስኮትላንድ ጦር እንድትልክ ተገፋፍታ ነበር፣ እና ዘመቻው የተሳሳተ ቢሆንም፣ በጁላይ 1560 የወጣው የኤድንበርግ ስምምነት የፈረንሳይን ስጋት በሰሜን በኩል ሜሪ በ1561 ወደ ስኮትላንድ ስትመለስ በስልጣን ላይ ሀገሪቱ የተመሰረተች የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን ነበራት እና የምትመራው በኤሊዛቤት ድጋፍ በፕሮቴስታንት መኳንንት ምክር ቤት ነበር። ማርያም ስምምነቱን ለማጽደቅ ፈቃደኛ አልሆነችም። እ.ኤ.አ. በ 1563 ኤልዛቤት የራሷን ፈላጊ ሮበርት ዱድሊን ለማርያም ባል እንድትሆን አቀረበች የሚመለከታቸውን ሁለት ሰዎች ሳትጠይቅ ሁለቱም ደስተኞች አልነበሩም እና በ 1565 ሜሪ ሄንሪ ስቱዋርትን ጌታ ዳርንሌይን አገባች, እሱም የራሱን የእንግሊዝ ዙፋን ይዞ ነበር. ጋብቻው ድሉን ለስኮትላንድ ፕሮቴስታንቶች እና ለኤልዛቤት ካስረከበው በማርያም ከተከሰቱት ተከታታይ የፍርድ ስህተቶች የመጀመሪያው ነው። ዳርንሌይ በፍጥነት ተወዳጅነት አጥቷል እና በየካቲት 1567 በሴረኞች ተገደለ፣ በእርግጠኝነት በጄምስ ሄፕበርን 4ኛ አርል የ ብዙም ሳይቆይ፣ በሜይ 15፣ 1567፣ ሜሪ ቦዝዌልን አገባች፣ ይህም ባሏን በመግደል ላይ ተካፋይ እንደነበረች ጥርጣሬን አስነስቷል። ኤልሳቤጥ ማርያምን ስለ ጋብቻ ነገረቻት፣ እንዲህ በማለት ጻፈቻት። እንደዚህ አይነት ጉዳይ ለማግባት ከመቸኮል ይልቅ ለክብርሽ ከዚህ የከፋ ምርጫ እንዴት ሊደረግ ቻለ። እኛ በውሸት እናምናለን። እነዚህ ክስተቶች በሎክ ሌቨን ካስት ለማርያም ሽንፈት እና እስራት በፍጥነት አመሩ። የስኮትላንድ ጌቶች በሰኔ 1566 የተወለደውን ልጇን ጄምስ ስድስተኛን እንድትገልፅ አስገደዷት። ጄምስ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሆኖ እንዲያድግ ወደ ስተርሊንግ ካስል ተወሰደ። ሜሪ በ1568 ከሎክ ሌቨን አመለጠች ነገርግን ሌላ ሽንፈት ካደረገች በኋላ ድንበሩን አቋርጣ ወደ እንግሊዝ ሸሸች። የኤልዛቤት የመጀመሪያዋ ደመ ነፍስ አብረዋት የነበሩትን ንጉሣዊቷን መመለስ ነበር; ግን እሷ እና ምክር ቤቷ በምትኩ በደህና መጫወትን መረጡ። ማርያምን ከእንግሊዝ ጦር ጋር ወደ ስኮትላንድ ከመመለስ ወይም ወደ ፈረንሣይና የእንግሊዝ ካቶሊካዊ ጠላቶች ከመላክ ይልቅ እንግሊዝ ውስጥ አስሯት ለቀጣዮቹ አሥራ ዘጠኝ ዓመታት ታስራለች። የካቶሊክ ምክንያት ማርያም ብዙም ሳይቆይ የአመፅ ትኩረት ሆነች። በ 1569 በሰሜን ውስጥ ትልቅ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነበር; ግቡ ማርያምን ነፃ ማውጣት፣ የኖርፎልክ 4ኛ መስፍን ከቶማስ ሃዋርድ ጋር ማግባት እና በእንግሊዝ ዙፋን ላይ ማስቀመጥ ነበር። አማፂዎቹ ከተሸነፉ በኋላ ከ750 በላይ የሚሆኑት በኤልዛቤት ትእዛዝ ተገድለዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ አምስተኛ በ1570 ዓ.ም ረጅናንስ በኤክሴልሲስ የተሰኘ በሬ አወጡ፣ እሱም “ኤልዛቤት፣ የመሰለችው የእንግሊዝ ንግሥት እና የወንጀል አገልጋይ” እንድትገለል እና መናፍቅ እንደሆነች በማወጅ ሁሉንም ፈታለች። ለእሷ ከማንኛውም ታማኝነት ተገዢዎች ትእዛዞቿን የሚታዘዙ ካቶሊኮች የመገለል ዛቻ ደርሶባቸዋል። የጳጳሱ በሬ በፓርላማ በካቶሊኮች ላይ የሕግ አውጭ እርምጃዎችን ቀስቅሷል፣ ሆኖም ግን በኤልዛቤት ጣልቃ ገብነት የተቀነሰው። እ.ኤ.አ. በ 1581 የእንግሊዘኛ ትምህርቶችን ወደ ኤልዛቤት ያላቸውን ታማኝነት ለማንሳት "ዓላማ" ወደ ካቶሊካዊነት መለወጥ የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ክህደት ፈፅሞ ነበር. ከ 1570 ዎቹ ጀምሮ ከአህጉራዊ ሴሚናሮች የተውጣጡ ሚስዮናውያን ካህናት በድብቅ ወደ እንግሊዝ ሄዱ "የእንግሊዝ ዳግመኛ መመለሻ" ምክንያት. ብዙዎች ተገድለዋል፣ የሰማዕትነት አምልኮን በመፍጠር። በኤክሴልሲስ የሚገኘው ሬጋንስ እንግሊዛዊ ካቶሊኮች ማርያምን እንደ ህጋዊ የእንግሊዝ ሉዓላዊ ገዢ እንድትመለከቱ ጠንካራ ማበረታቻ ሰጥቷቸዋል። ማርያም እሷን በእንግሊዝ ዙፋን ላይ ለማስቀመጥ ስለ እያንዳንዱ የካቶሊክ ሴራ አልተነገራቸውም ግን በ 1571 ከሪዶልፊ ሴራ (የማርያም ፈላጊ የኖርፎልክ መስፍን ጭንቅላቱን እንዲያጣ ያደረገው) በ 1586 ወደ ባቢንግተን ሴራ የኤልዛቤት የስለላ አስተዳዳሪ ሰር ፍራንሲስ ዋልሲንግሃም እና የንጉሣዊው ምክር ቤት በእሷ ላይ ክስ አሰባሰቡ። በመጀመሪያ ኤልሳቤጥ የማርያምን ሞት ጥሪ ተቃወመች። እ.ኤ.አ. በ 1586 መገባደጃ ላይ በባቢንግተን ሴራ ወቅት በተፃፉ ደብዳቤዎች ማስረጃ ላይ የማርያምን ችሎት እና ግድያ እንድትቀበል ተገፋፍታለች። የኤልዛቤት የቅጣት አዋጅ ማወጁ “የተነገረላት ማርያም፣ የአንድ ዘውድ ባለቤት መስሎ፣ በዛው ግዛት ውስጥ የተለያዩ ነገሮችን ዞራ በንጉሣዊው ሰውነታችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት፣ ሞት እና ጥፋት አስባ ነበር። እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ኤልዛቤት የተፈረመውን የግድያ ማዘዣ እንዲላክ አላሰበችም ስትል ፀሐፊዋን ዊልያም ዴቪሰንን ሳታውቅ ተግባራዊ አድርጋለች በማለት ወቅሳለች። የኤልዛቤት ፀፀት ቅንነት እና የፍርድ ቤት ማዘዣውን ለማዘግየት ፈለገች ወይስ አልፈለገችም በዘመኗም ሆነ በኋላ የታሪክ ፀሃፊዎች ጥያቄ ውስጥ ገብተዋል። ጦርነቶች እና የባህር ማዶ ንግድ የኤልዛቤት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በአብዛኛው መከላከያ ነበር። ለየት ያለ ሁኔታ ከጥቅምት 1562 እስከ ሰኔ 1563 ድረስ የእንግሊዝ የሌሃቭር ይዞታ ነበር፣ ይህ የሆነው የኤልዛቤት ሁጉኖት አጋሮች ከካቶሊኮች ጋር በመተባበር ወደቡን መልሶ ለመያዝ ባደረገ ጊዜ ሳይሳካ ቀርቷል። የኤልዛቤት አላማ በጥር 1558 በፈረንሣይ የተሸነፈችውን ሌሃቭርን ወደ ካሌ መቀየር ነበር። ይህ ከስፔን ጋር በተደረገው ጦርነት ፍሬያማ የሆነ ሲሆን 80 በመቶው የተካሄደው በባህር ላይ ነው። እ.ኤ.አ. ከ1577 እስከ 1580 ድረስ ፍራንሲስ ድሬክን ከዞረ በኋላ ፈረሰች እና በስፔን ወደቦች እና መርከቦች ላይ ባደረገው ወረራ ታዋቂነትን አገኘ። የባህር ላይ ዝርፊያ እና ራስን ማበልጸግ ንግሥቲቱ ብዙም ቁጥጥር ያልነበራቸው የኤሊዛቤት የባህር ተጓዦችን አባረራቸው። ኔዜሪላንድ በ1562-1563 ሌሃቭር ከተያዘች እና ከጠፋች በኋላ ኤልዛቤት እስከ 1585 ድረስ የእንግሊዝ ጦር በላከችበት ወቅት በአህጉሪቱ ወታደራዊ ጉዞዎችን ከማድረግ ተቆጥባ የፕሮቴስታንት ደች ሆላንድን በፊሊፕ ላይ ያመፀው ።ይህም በ 1584 የንግስቲቱ አጋሮች ዊልያም ሞትን ተከትሎ ነበር ዝምተኛው፣ የብርቱካን ልዑል፣ እና የአንጁው መስፍን፣ እና ተከታታይ የደች ከተማዎች ለስፔን ኔዘርላንድስ የፊልጶስ ገዥ የፓርማ መስፍን አሌክሳንደር ፋርኔስ መሰጠታቸው። በታህሳስ 1584 በፊሊፕ እና በፈረንሣይ ካቶሊካዊ ሊግ በጆይንቪል መካከል የተደረገ ጥምረት የአንጁ ወንድም ፈረንሣዊው ሄንሪ ሳልሳዊ የስፔን የኔዘርላንድን የበላይነት ለመቃወም ያለውን አቅም አሳጣው። በተጨማሪም የካቶሊክ ሊግ ጠንካራ በሆነበት በፈረንሳይ የባህር ዳርቻ ላይ የስፓኒሽ ተጽእኖን አስፋፍቷል እና እንግሊዝን ለወረራ አጋልጧል። እ.ኤ.አ. በ1585 የበጋው ወቅት አንትወርፕ የፓርማ መስፍን ከበባ በእንግሊዘኛ እና በ ደች. ውጤቱም ኤልዛቤት ለደች ወታደራዊ ድጋፍ ለመስጠት ቃል የገባችበት የነሀሴ 1585 የኖንሱች ስምምነት ነበር። ስምምነቱ እ.ኤ.አ. በ 1604 እስከ ለንደን ስምምነት ድረስ የዘለቀውን የአንግሎ-ስፓኒሽ ጦርነት መጀመሪያ ያመላክታል ጉዞውን የተመራው በኤልዛቤት የቀድሞ ፈላጊ፣ የሌስተር አርል ነው። ኤልዛቤት ከጅምሩ ይህን ተግባር አልደገፈችም። ሌስተር ሆላንድ በገባ በቀናት ውስጥ ከስፔን ጋር ሚስጥራዊ የሰላም ድርድር ስትጀምር ላዩን ላይ ያሉትን ደች በእንግሊዝ ጦር ለመደገፍ የነበራት ስልቷ ከሌስተር ጋር ግጭት ውስጥ መግባት ነበረበት። ንቁ ዘመቻ. ኤልዛቤት በበኩሏ "ከጠላት ጋር ምንም አይነት ወሳኝ እርምጃ እንዳይወስድ" ትፈልጋለች። ከኔዘርላንድስ ጄኔራል የጠቅላይ ገዥነት ቦታ በመቀበል ኤልዛቤትን አስቆጣች። ኤልዛቤት ይህንን የኔዘርላንድስ ሉዓላዊነት እንድትቀበል ለማስገደድ የተደረገ የደች ተንኮል አድርጋ ተመለከተች፣ይህም እስካሁን ድረስ ሁሌም ውድቅ አድርጋ ነበር። ለሌስተር ጻፈች፡- ከዚች ምድር ርዕሰ ጉዳይ በላይ የሆነ ሰው በራሳችን ተነሥቶ በእኛ እጅግ የተወደደ፣ በንቀት ምክንያት ትእዛዛችንን ይጥሳል ብለን ልንገምት አንችልም ነበር (በልምምድ ሲወድቅ ባናውቅ ኖሮ)። በአክብሮት እጅግ በጣም የሚነካን እና ስለዚህ የእኛ ግልጽ ደስታ እና ትዕዛዛት ሁሉም መዘግየቶች እና ማመካኛዎች ተለያይተው በታማኝነትዎ ግዴታ ላይ ወዲያውኑ ታዘዙ እና የዚህ ተሸካሚው በእኛ ውስጥ እንዲያደርጉ የሚዘዙትን ሁሉ እንዲፈጽሙ ነው። ስም ስለዚህም አትሳቱ፣ በተቻለ መጠን ተቃራኒውን መልስ እንደምትሰጥ። የኤልዛቤት “ትዕዛዝ” መልእክተኛዋ የተቃውሞ ደብዳቤዋን በሆላንድ ምክር ቤት ፊት በይፋ በማንበብ ሌስተር በአቅራቢያው መቆም ነበረባት። ይህ የ"ሌተናል ጄኔራል" ህዝባዊ ውርደት ከስፔን ጋር የተለየ ሰላም ለመፍጠር ከቀጠለችበት ንግግር ጋር ተዳምሮ ሌስተር በኔዘርላንድስ መካከል ያለውን አቋም በማያዳግም ሁኔታ አሳፈረ። ኤልዛቤት በረሃብ ለተቸገሩ ወታደሮቿ ቃል የተገባለትን ገንዘብ ለመላክ ደጋግማ በመቅረቷ ወታደራዊ ዘመቻው ክፉኛ ተስተጓጎለ። ለጉዳዩ እራሷን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኗ፣ እንደ ፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪ የሌስተር ድክመቷ፣ እና በቡድን የተሞላው እና የተመሰቃቀለው የኔዘርላንድ ፖለቲካ ሁኔታ የዘመቻውን ውድቀት አስከትሏል። በመጨረሻም ሌስተር ትእዛዙን በታህሳስ 1587 ለቀቀ። የስፔን አርማዳ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሰር ፍራንሲስ ድሬክ በ1585 እና በ1586 በካሪቢያን ባህር በሚገኙ የስፔን ወደቦች እና መርከቦች ላይ ትልቅ ጉዞ አድርጓል። ጦርነቱን ወደ እንግሊዝ ለመውሰድ ወስኗል እ.ኤ.አ. ሐምሌ 12 ቀን 1588 የስፔን አርማዳ ታላቅ የመርከብ መርከቦች የስፔን ወረራ ኃይልን በፓርማ መስፍን ስር ከኔዘርላንድ ወደ ደቡብ ምስራቅ እንግሊዝ የባህር ዳርቻ ለማጓጓዝ በማቀድ ወደ ጣቢያው ተጓዙ የስፔን መርከቦችን ወደ ሰሜናዊ ምስራቅ የበተነው የተሳሳተ ስሌት፣ መጥፎ ዕድል እና የእንግሊዝ የእሳት አደጋ መርከቦች በጁላይ 29 ከግሬቪላይን ላይ የተደረገ ጥቃት፣ አርማዳውን አሸንፏል። የአየርላንድ የባህር ዳርቻ (አንዳንድ መርከቦች በሰሜን ባህር በኩል ወደ ስፔን ለመመለስ ከሞከሩ በኋላ እና በአየርላንድ ምዕራባዊ የባህር ጠረፍ በኩል ወደ ደቡብ ይመለሱ)። የአርማዳውን እጣ ፈንታ ሳያውቁ የእንግሊዝ ሚሊሻዎች በሌስተር ኦፍ ሌስተር ትእዛዝ ሀገሪቱን ለመከላከል ተሰበሰቡ። ሌስተር ኤልዛቤት ወታደሮቿን በኤሴክስ በቲልበሪ እንድትመረምር ነሐሴ 8 ጋብዟታል። በነጭ ቬልቬት ቀሚስ ላይ የብር ጡት ለብሳ በጣም ዝነኛ በሆነው ንግግሯ ላይ እንዲህ ብላ ተናግራቸዋለች። አፍቃሪ ወገኖቼ፣ ለደህንነታችን በሚጠነቀቁ አንዳንድ ሰዎች አሳምነናል፣ ክህደትን በመፍራት ራሳችንን ለታጠቁ ሰዎች እንዴት እንደምንሰጥ እንጠንቀቅ። ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፥ ታማኝና አፍቃሪ ሕዝቤን ሳልታመን ልኖር አልወድም... ደካማና ደካማ ሴት አካል እንዳለኝ አውቃለሁ፥ ነገር ግን የንጉሥና የንጉሥ ልብና ሆድ አለኝ። የእንግሊዝ አገር፣ እና ፓርማ ወይም ስፔን፣ ወይም ማንኛውም የአውሮፓ ልዑል የግዛቴን ድንበሮች ሊደፍሩ ይገባል ብለው መጥፎ ንቀት ያስቡ።ወረራ ሳይመጣ ህዝቡ ተደሰተ። በቅዱስ ጳውሎስ ካቴድራል ለምስጋና አገልግሎት የኤልሳቤጥ ሰልፍ የዘውድ ንግዷን እንደ ትርኢት ተቀናቃኙ። የአርማዳ ሽንፈት ለኤልዛቤትም ሆነ ለፕሮቴስታንት እንግሊዝ ጠንካራ የፕሮፓጋንዳ ድል ነበር። እንግሊዛውያን በድንግል ንግሥት ሥር የእግዚአብሔርን ሞገስ እና ሀገሪቱን የማይደፈርስ ምልክት አድርገው ይወስዱታል። ይሁን እንጂ ድሉ በጦርነቱ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ማምጣት አልቻለም, ይህም ቀጥሏል እና ብዙ ጊዜ ለስፔን ይጠቅማል. ስፔናውያን የኔዘርላንድን ደቡባዊ ግዛቶች አሁንም ይቆጣጠሩ ነበር, እናም የወረራ ስጋት አሁንም አለ. ሰር ዋልተር ራሌይ ከሞተች በኋላ የኤልዛቤት ማስጠንቀቂያ ከስፔን ጋር የሚደረገውን ጦርነት እንዳደናቀፈ ተናግሯል፡- ሟች ንግሥት እንደ ጸሐፍዎቿ ሁሉ ተዋጊዎቿን ብታምን ኖሮ፣ እኛ በሷ ጊዜ ያን ታላቅ ግዛት ጨፍጭፈን ንጉሣቸውን በሾላና በብርቱካን አደረግን እንደ ቀድሞው ዘመን። ነገር ግን ግርማዊነቷ ሁሉንም ነገር በግማሽ ያደረጉ ሲሆን በጥቃቅን ወረራዎች ስፔናዊውን እራሱን እንዴት መከላከል እንዳለበት እና የራሱን ድክመት እንዲያይ አስተምሮታል። ምንም እንኳን አንዳንድ የታሪክ ምሁራን ኤልዛቤትን በተመሳሳይ ምክንያቶች ቢተቹም፣ የራሌይ ብይን ብዙ ጊዜ ኢ-ፍትሃዊ ነው ተብሏል። ኤልዛቤት እራሷ እንዳስቀመጠችው በአንድ ወቅት በተግባር ባሳዩት አዛዦቿ ላይ ብዙ እምነት እንዳትጥል በቂ ምክንያት ነበራት። እ.ኤ.አ. በ1589፣ ከስፔን አርማዳ በኋላ፣ ኤልዛቤት የእንግሊዙን አርማዳ ወይም ከ23,375 ሰዎች እና 150 መርከቦች ጋር፣ በሰር ፍራንሲስ ድራክ እንደ አድሚራል እና ሰር ጆን ኖሬይስ በጄኔራልነት ወደ ስፔን ላከች። የእንግሊዝ መርከቦች ከ11,000–15,000 ሰዎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል ወይም በበሽታ ሞቱ እና 40 መርከቦች በመስጠም ወይም በመማረክ አስከፊ ሽንፈት ደርሶባቸዋል። እንግሊዝ በስፔን አርማዳ ላይ ያሸነፈችው ጥቅም ጠፋ፣ እና የስፔን ድል በሚቀጥሉት አስርት አመታት ውስጥ የፊሊፕ 2ኛ የባህር ሃይል መነቃቃትን አሳይቷል። ፈረንሳይ በ 1589 የፕሮቴስታንት ሄንሪ አራተኛ የፈረንሳይን ዙፋን ሲወርስ, ኤልዛቤት ወታደራዊ ድጋፍ ላከችው. በ1563 ከሌ ሃቭር ካፈገፈገች በኋላ ወደ ፈረንሳይ የመግባት የመጀመሪያዋ የመጀመሪያዋ ነበር።የሄንሪ ርስት በካቶሊክ ሊግ እና በፊሊፕ 2ኛ ከፍተኛ ክርክር ነበረበት።እና ኤልዛቤት የስፔን የቻናል ወደቦችን እንዳይቆጣጠር ፈራች። በፈረንሳይ ተከታዩ የእንግሊዝኛ ዘመቻዎች ግን ያልተደራጁ እና ውጤታማ አልነበሩም። ፔሬግሪን በርቲ፣ 13ኛ ባሮን ዊሎቢ ደ ኤሬስቢ፣ በአብዛኛው የኤልዛቤትን ትእዛዝ ችላ በማለት፣ በሰሜን ፈረንሳይ ብዙም ሳይቆይ 4,000 ሰራዊት ይዞ ዞረ። በታህሳስ 1589 ግማሹን ወታደሮቹን በማጣቱ በችግር ውስጥ ወድቋል። በ1591፣ 3,000 ሰዎችን ወደ ብሪታኒ የመራው የጆን ኖሬይስ ዘመቻ የበለጠ ጥፋት ነበር። እንደነዚህ ያሉትን ጉዞዎች በተመለከተ፣ ኤልዛቤት አዛዦቹ በጠየቁት አቅርቦቶች እና ማጠናከሪያዎች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፈቃደኛ አልነበራትም። ኖርሬስ ለበለጠ ድጋፍ በአካል ለመማፀን ወደ ለንደን ሄደ። እሱ በሌለበት ጊዜ፣ አንድ የካቶሊክ ሊግ ጦር በግንቦት 1591 በሰሜን ምዕራብ ፈረንሳይ ክራኦን የሠራዊቱን አጽም ለማጥፋት ተቃርቧል። በሐምሌ ወር ኤልዛቤት ሄንሪ አራተኛን እንዲከበብ ለመርዳት በሮበርት ዴቬሬክስ፣ የኤሴክስ 2ኛ አርል የሚመራ ሌላ ጦር ላከች። ሩዋን ውጤቱም እንዲሁ አስከፊ ነበር። ኤሴክስ ምንም ነገር አላደረገም እና በጥር 1592 ወደ ቤት ተመለሰ። ሄንሪ በሚያዝያ ወር ከበባውን ተወ። እንደተለመደው ኤልዛቤት ከአዛዦቿ ውጭ አገር ከነበሩ በኋላ መቆጣጠር አልቻለችም። ስለ ኤሴክስ “እሱ ባለበት፣ ወይም የሚያደርገው፣ ወይም ምን ማድረግ እንዳለበት፣ እኛ አላዋቂዎች ነን” ስትል ጽፋለች። አይርላድ አየርላንድ ከሁለቱ መንግሥቶቿ አንዷ ብትሆንም፣ ኤልዛቤት በጠላትነት ፈርጆ ነበር፣ እና በራስ ገዝ በምትሆን ቦታ፣ የአየርላንድ ሕዝብ የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆነች እና ሥልጣኗን ለመቃወም እና ከጠላቶቿ ጋር ለማሴር ፈቃደኛ ነበረች። በዚያ የነበራት ፖሊሲ ለአሽከሮችዎቿን መሬት መስጠት እና አማፂያኑ ስፔንን እንግሊዝን የምታጠቁበት መሰረት እንዳይሰጡ ማድረግ ነበር። በተከታታይ ህዝባዊ አመጽ የዘውዱ ሃይሎች መሬቱን በማቃጠል ወንድ፣ ሴትና ህጻን ጨፍጭፈዋል። እ.ኤ.አ. ገጣሚው እና ቅኝ ገጣሚው ኤድመንድ ስፔንሰር ተጎጂዎቹ "ማንኛውም የድንጋይ ልብ እንዲሁ ያበላሸው ነበር" ሲል ጽፏል። ኤልዛቤት አዛዦቿን አይሪሽ፣ “ያ ጨዋና አረመኔያዊ ሕዝብ” በደንብ እንዲያዙ መከረቻቸው። ነገር ግን እሷ ወይም አዛዦቿ ኃይል እና ደም መፋሰስ ፈላጭ ቆራጭ አላማቸውን ሲፈጽሙ ምንም አይነት ጸጸት አላሳዩም። እ.ኤ.አ. በ 1594 እና 1603 መካከል ኤልዛቤት በአየርላንድ በዘጠኝ ዓመታት ጦርነት ወቅት እጅግ በጣም ከባድ ፈተና ገጠማት ከስፔን ጋር በተደረገው ከፍተኛ ጦርነት የአመፅ መሪውን ሂዩ ኦኔል የታይሮናዊውን አርል ደግፋለች። በ 1599 ጸደይ, ኤልዛቤት አመፁን ለማጥፋት ሮበርት ዴቬሬክስ, 2 ኛ አርል ኦቭ ኤሴክስ ላከ. ለብስጭቷ፣ ትንሽ እድገት አላደረገም እና ትእዛዟን በመጣስ ወደ እንግሊዝ ተመለሰ። እሱ በቻርልስ ብሎንት ተተካ፣ ሎርድ ሞንጆይ፣ አመጸኞቹን ለማሸነፍ ሦስት ዓመታት ፈጅቷል። ኦኔል በመጨረሻ ኤልዛቤት ከሞተች ከጥቂት ቀናት በኋላ በ1603 እጁን ሰጠ። ብዙም ሳይቆይ በእንግሊዝ እና በስፔን መካከል የሰላም ስምምነት ተፈረመ። ራሽያ ኤልዛቤት በመጀመሪያ በግማሽ ወንድሟ በኤድዋርድ ስድስተኛ የተቋቋመውን ከሩሲያው ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቀጠለች ብዙ ጊዜ ለኢቫን ዘሪብል በትህትና ትጽፍ ነበር፣ ምንም እንኳን ዛር ብዙ ጊዜ በወታደራዊ ህብረት ላይ ከማተኮር ይልቅ በንግድ ላይ ባላት ትኩረት ተበሳጭታ ነበር። ዛር እንኳን አንድ ጊዜ ሀሳብ አቀረበላት እና በኋለኛው የግዛት ዘመን ግዛቱ አደጋ ላይ ከወደቀ በእንግሊዝ ጥገኝነት እንዲሰጥ ዋስትና ጠየቀ።የሙስኮቪ ኩባንያ ተወካይ ሆኖ ስራውን የጀመረው እንግሊዛዊው ነጋዴ እና አሳሽ አንቶኒ ጄንኪንሰን ሆነ። በኢቫን ዘሪብል ፍርድ ቤት የንግሥቲቱ ልዩ አምባሳደር በ1584 ኢቫን ሲሞት፣ ብዙም ፍላጎት የሌለው ልጁ ፌዮዶር ተተካ። እንደ አባቱ ሳይሆን ፌዮዶር ከእንግሊዝ ጋር ልዩ የንግድ መብቶችን ለማስጠበቅ ምንም ቅንዓት አልነበረውም። ፌዮዶር መንግስቱን ለሁሉም የውጭ ዜጎች ክፍት መሆኑን አውጇል እና ኢቫን በቸልታ የታገሉትን የእንግሊዝ አምባሳደር ሰር ጀሮም ቦውስን አሰናበተ። ኤልዛቤት አዲስ አምባሳደርን ዶክተር ጊልስ ፍሌቸርን ላከች ከገዢው ቦሪስ ጎዱኖቭ ዛርን እንደገና እንዲያጤነው እንዲያሳምንለት ለመጠየቅ። ድርድሩ ከሽፏል፣ ፍሌቸር ፌዮዶርን ከበርካታ ርዕሶች ሁለቱን በማውጣቱ ምክንያት። ኤልዛቤት በግማሽ ማራኪ፣ ግማሽ የሚያንቋሽሽ ደብዳቤዎች ለፌዮዶር ይግባኝ ማለቷን ቀጠለች። ኅብረት እንዲመሠርት ሐሳብ አቀረበች፣ ከፌዮዶር አባት ሲቀርብላት ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆነችውን ነገር ግን ውድቅ ተደረገች። የሙስሊም ግዛቶች በኤልዛቤት የግዛት ዘመን በእንግሊዝ እና በባርበሪ ግዛቶች መካከል የንግድ እና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ተፈጠረ። እንግሊዝ ከስፔን ጋር በመቃወም ከሞሮኮ ጋር የንግድ ግንኙነት መስርታ የጦር ትጥቅ፣ ጥይቶች፣ እንጨትና ብረት በመሸጥ የሞሮኮ ስኳር በመሸጥ ላይ ነበር፣ ምንም እንኳን የፓፓል እገዳ ቢኖርበትም። በ1600 የሞሮኮ ገዥ ሙላይ አህመድ አል ማንሱር ዋና ፀሀፊ አብዱል ኦዋህድ ቤን መስኡድ በንግሥት ኤልሳቤጥ ቀዳማዊ ፍርድ ቤት አምባሳደር በመሆን እንግሊዝን ጎበኘ፣ የአንግሎ-ሞሮኮ ኅብረትን በስፔን ላይ ለመደራደር። ኤልዛቤት “ተስማማች። የጦር መሳሪያ ቁሳቁሶችን ለሞሮኮ ለመሸጥ እና እሷ እና ሙላይ አህመድ አል-ማንሱር በስፔን ላይ የጋራ ዘመቻ ስለመጀመር ተነጋገሩ። ይሁን እንጂ ውይይቶቹ ያልተቋረጡ ሲሆን ሁለቱም ገዥዎች ከኤምባሲው በሁለት ዓመታት ውስጥ ሞተዋል. ከኦቶማን ኢምፓየር ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትም በሌቫንት ካምፓኒ ቻርተር እና የመጀመሪያውን የእንግሊዝ አምባሳደር ወደ ፖርቴ በመላክ በ1578 ዓ.ም. በሁለቱም አቅጣጫዎች ተልከዋል እና በኤሊዛቤት እና በሱልጣን ሙራድ መካከል የኤፒስቶላር ልውውጥ ተደረገ። በአንድ የደብዳቤ ልውውጡ ላይ፣ ሙራድ እስልምና እና ፕሮቴስታንት “ከሮማ ካቶሊክ ጋር ካደረጉት የበለጠ የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፣ ሁለቱም የጣዖት አምልኮን አይቀበሉም” የሚለውን አስተሳሰብ አስተናግዶ በእንግሊዝ እና በኦቶማን ኢምፓየር መካከል ህብረት ለመፍጠር ተከራክሯል። ካቶሊካዊ አውሮፓ፣ እንግሊዝ ቆርቆሮ እና እርሳስ (ለመድፍ ለመወርወር) እና ጥይቶችን ወደ ኦቶማን ኢምፓየር ላከች እና ኤልዛቤት በ1585 ከስፔን ጋር ጦርነት በተቀሰቀሰበት ወቅት ፍራንሲስ ዋልሲንግሃም በቀጥታ ኦቶማን እንዲመራ ሲጠይቅ ከሙራድ ጋር በጋራ ወታደራዊ ዘመቻ ላይ በቁም ነገር ተወያይታለች። የጋራ የስፔን ጠላት ላይ ወታደራዊ ተሳትፎ አሜሪካ በ1583፣ ሰር ሃምፍሬይ ጊልበርት በኒውፋውንድላንድ ላይ ቅኝ ግዛት ለመመስረት ወደ ምዕራብ ተጓዙ። ወደ እንግሊዝ አልተመለሰም። የጊልበርት ዘመድ ሰር ዋልተር ራሌይ የአትላንቲክ ውቅያኖስን ቃኝተው የቨርጂኒያ ግዛት ይገባኛል፣ ምናልባት ለኤልዛቤት፣ “ድንግል ንግሥት” ክብር የተሰየመ ሊሆን ይችላል። ይህ ግዛት ከኒው ኢንግላንድ እስከ ካሮላይና ድረስ ካለው ከአሁኑ የቨርጂኒያ ግዛት በጣም ትልቅ ነበር። በ1585 ራሌይ ከጥቂት ሰዎች ጋር ወደ ቨርጂኒያ ተመለሰ። ከአሁኑ ሰሜን ካሮላይና ወጣ ብላ በምትገኘው በሮአኖክ ደሴት አረፉ። ከመጀመሪያው ቅኝ ግዛት ውድቀት በኋላ ራሌይ ሌላ ቡድን መለመለ እና ጆን ዋይትን አዛዥ አደረገው። ራሌይ በ1590 ሲመለስ የተወው የሮአኖክ ቅኝ ግዛት ምንም ዱካ አልተገኘም ነገር ግን በሰሜን አሜሪካ የመጀመሪያው የእንግሊዝ ሰፈራ ነበር። የምስራቅ ህንድ ኩባንያ የምስራቅ ህንድ ኩባንያ በህንድ ውቅያኖስ ክልል እና በቻይና ለመገበያየት የተቋቋመ ሲሆን በታህሳስ 31 ቀን 1600 ቻርተሩን ከንግሥት ኤልዛቤት ተቀበለ ለ 15 ዓመታት ኩባንያው በምስራቅ ምስራቅ ካሉ አገሮች ጋር በእንግሊዝ ንግድ ላይ በሞኖፖል ተሸልሟል የጥሩ ተስፋ ኬፕ እና የማጅላን የባህር ዳርቻዎች ምዕራብ። ሰር ጀምስ ላንካስተር በ1601 የመጀመሪያውን ጉዞ አዘዙ። ኩባንያው በ18ኛው እና በ19ኛው ክፍለ ዘመን በህንድ ውስጥ ግማሹን የአለም ንግድ እና ጠቃሚ ግዛት ተቆጣጠረ። የግርማዊቷ ንግስና መጨረሻ መምጣት እ.ኤ.አ. በ 1588 የስፔን አርማዳ ከተሸነፈ በኋላ ያለው ጊዜ ለኤልዛቤት እስከ ንግሥናዋ መጨረሻ ድረስ አዲስ ችግሮች አምጥቷል ከስፔን እና አየርላንድ ጋር የነበረው ግጭት እየገፋ ሲሄድ የግብር ሸክሙ እየከበደ ሄዶ ኢኮኖሚው ደካማ በሆነ ምርት ተመታ። የጦርነት ዋጋ. ዋጋ ጨምሯል እና የኑሮ ደረጃው ቀንሷል። በዚህ ጊዜ የካቶሊኮች ጭቆና ተባብሷል እና ኤልዛቤት በ1591 የካቶሊክን ሰዎች እንዲጠይቁ እና እንዲከታተሉ ኮሚሽኖችን ሰጠች። የሰላም እና የብልጽግናን ቅዠት ለማስቀጠል በውስጣዊ ሰላዮች እና ፕሮፓጋንዳ ላይ ትተማመናለች። በመጨረሻዎቹ ዓመታት ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ትችት ህዝቡ ለእሷ ያለው ፍቅር ማሽቆልቆሉን ያሳያል።ለዚህ “ሁለተኛው የግዛት ዘመን” የኤልዛቤት አንዱ መንስኤ፣ አንዳንድ ጊዜ ተብሎ እንደሚጠራው፣ በ1590ዎቹ ውስጥ የነበረው የግላዊነት ምክር ቤት የኤልዛቤት አስተዳደር አካል የተለወጠ ባህሪ ነው። አዲስ ትውልድ በስልጣን ላይ ነበር። ከሎርድ በርግሌይ በስተቀር፣ በ1590 አካባቢ በጣም አስፈላጊዎቹ ፖለቲከኞች ሞተዋል፡ የሌስተር አርል በ1588 ዓ.ም. ሰር ፍራንሲስ ዋልሲንግሃም በ1590 ዓ.ም. እና ሰር ክሪስቶፈር ሃቶን በ1591። ከ1590ዎቹ በፊት በመንግስት ውስጥ ከፋፋይ ግጭትና ግጭት አሁን መለያው ሆነ በሎርድ በርግሌይ ልጅ በሮበርት ሴሲል እና በሎርድ ቡርግሌይ ልጅ መካከል መራራ ፉክክር ተፈጠረ። እና በግዛቱ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ለመያዝ የተደረገው ትግል ፖለቲካውን አበላሽቷል። በ1594 ታማኝ በሆነው ዶክተር ሎፔዝ ጉዳይ ላይ እንደሚታየው የንግሥቲቱ የግል ሥልጣን እየቀነሰ ነበር። በኤርል ኦፍ ኤሴክስ በአገር ክህደት በስህተት በተከሰሰበት ወቅት፣ በመታሰሩ የተናደደች እና ጥፋቱን ያላመነች ቢመስልም ከመገደሉ ማስቀረት አልቻለችም። በመጨረሻዎቹ የንግሥና ዓመታት ኤልዛቤት በጦርነት ጊዜ ተጨማሪ ድጎማዎችን ለፓርላማ ከመጠየቅ ይልቅ ሞኖፖሊዎችን ከዋጋ ነፃ የሆነ የደጋፊነት ስርዓት በመስጠቱ ላይ ትተማመን ነበር። በሕዝብ ወጪ የቤተ መንግሥት አባላትን ማበልጸግ እና ቂም መብዛት። ይህ በ 1601 ፓርላማ ውስጥ በኮመንስ ሃውስ ውስጥ ቅስቀሳ አብቅቷል እ.ኤ.አ. ህዳር 30 ቀን 1601 በታዋቂው “ወርቃማው ንግግር” በኋይትሆል ቤተመንግስት 140 አባላትን ለተወካዩት ኤልዛቤት በደሉን እንደማታውቅ ተናግራ አባላቱን በተስፋ ቃል አሸንፋለች። እና ለስሜቶች የተለመደው ይግባኝሉዓላዊነታቸውን ከስህተቱ ሂደት የሚጠብቃቸው፣ በድንቁርና ሳይሆን በዐላማ ወድቀው ሊሆን ይችላል፣ ምን ምስጋና ይገባቸዋል፣ ቢገምቱትም እናውቃለን። እናም የዜጎቻችንን ልብ በፍቅር ከመጠበቅ የበለጠ ውድ ነገር ስላልሆነ፣ የነጻነታችንን ተሳዳቢዎች፣ የህዝባችን አራማጆች፣ የድሆች ጠላፊዎች ባይነገሩን ኖሮ ምንኛ ያልተገባ ጥርጣሬ ፈጠርን ነበር። !በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ አለመረጋጋት የታየበት ተመሳሳይ ወቅት ግን በእንግሊዝ ታይቶ የማይታወቅ የስነ-ጽሁፍ አበባ አፍርቷል። በ1578 ከጆን ሊሊ ኢፉዌስ እና ከኤድመንድ ስፔንሰር ዘ ሼፐርድስ ካላንደር ጋር በ1578 ዓ.ም. በ1590ዎቹ የእንግሊዝ ሥነ-ጽሑፍ ታዋቂ የሆኑ አንዳንድ ታዋቂዎች በኤልዛቤት የግዛት ዘመን በሁለተኛው አስርት ዓመታት መጨረሻ ላይ የአዲሱ ሥነ-ጽሑፍ እንቅስቃሴ የመጀመሪያ ምልክቶች ታይተዋል። ዊልያም ሼክስፒር እና ክሪስቶፈር ማርሎዌን ጨምሮ። በያቆብ ዘመን በመቀጠል፣ የእንግሊዝ ቲያትር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይደርሳል።የታላቅ የኤልዛቤት ዘመን አስተሳሰብ በአብዛኛው የተመካው በኤልሳቤጥ የግዛት ዘመን ንቁ ተሳትፎ በነበሩት ግንበኞች፣ ድራማ ባለሙያዎች፣ ገጣሚዎች እና ሙዚቀኞች ላይ ነው። የኪነ ጥበብ ዋና ደጋፊ ላልሆነችው ንግሥቲቱ በቀጥታ የተበደሩት ትንሽ ነው። ኤልዛቤት ሲያረጅ ምስሏ ቀስ በቀስ ተለወጠ። እሷ እንደ ቤልፎቤ ወይም አስትሪያ፣ እና ከአርማዳ በኋላ፣ እንደ ግሎሪያና፣ የኤድመንድ ስፔንሰር ግጥም ዘላለማዊ ወጣት ፌሪ ኩዊን ተመሰለች። ኤልዛቤት ለኤድመንድ ስፔንሰር የጡረታ አበል ሰጠች; ይህ ለእሷ ያልተለመደ ስለነበር ሥራውን እንደወደደች ያሳያል። የተሳሉት የቁም ሥዕሎቿ ከእውነታው የራቁ ሆኑ እና ከእርሷ በጣም እንድታንስ ያደረጓት የእንቆቅልሽ አዶዎች ስብስብ ሆኑ። እንዲያውም ቆዳዋ በ1562 በፈንጣጣ ተጎድቶ ነበር፣ ግማሹ ራሰ በራዋን ትቶ በዊግ እና በመዋቢያዎች ላይ ጥገኛ ነች። ጣፋጮች መውደዷ እና የጥርስ ሀኪሞችን መፍራት ለከባድ የጥርስ መበስበስ እና ኪሳራ አስተዋጽኦ አድርጓል በዚህም መጠን የውጪ ሀገራት አምባሳደሮች ንግግሯን ለመረዳት እስኪቸገሩ ድረስ የፈረንሳዩ ሄንሪ አራተኛ ልዩ አምባሳደር አንድሬ ሁራልት ደ ማይሴ ከንግስቲቱ ጋር ተገኝተው ነበር በዚህ ጊዜ "ጥርሶቿ በጣም ቢጫ እና እኩል አይደሉም በግራ በኩል ደግሞ ከቀኝ ያነሱ ናቸው. ብዙዎቹ ጠፍተዋል, ስለዚህም በፍጥነት ስትናገር ሰው በቀላሉ ሊረዳት አይችልም." እሱ ግን አክሎም፣ “መልክዋ ፍትሃዊ እና ረጅም እና በምታደርገው ነገር ሁሉ የተዋበች ናት፤ እስከሆነ ድረስ ክብሯን ትጠብቃለች፣ ነገር ግን በትህትና እና በጸጋ። ሰር ዋልተር ራሌይ "ጊዜ ያስገረማት ሴት" ብሏታል።የኤልዛቤት ውበቷ እየደበዘዘ በሄደ ቁጥር አሽከሮችዎቿ ያወድሱታል። ኤልዛቤት ይህን ሚና በመጫወት ደስተኛ ነበረች፣ነገር ግን በህይወቷ የመጨረሻ አስር አመታት ውስጥ የራሷን አፈጻጸም ማመን ጀምራለች። የሌስተር የእንጀራ ልጅ የሆነችውን እና እሷን ይቅር ያለችለትን የማራኪውን ወጣት ሮበርት ዴቬሬክስን፣ አርል ኦቭ ኤሴክስን ትወዳለች እና ትወደዋለች። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄደው ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ቢሆንም፣ እሷም ለወታደርነት ሾመችው። እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. በየካቲት 1601 ጆርጅ በለንደን አመጽ ለማነሳሳት ሞከረ። ንግሥቲቱን ሊይዝ አስቦ ነበር ነገር ግን ጥቂቶች ለድጋፉ ተሰበሰቡ እና በየካቲት 25 አንገቱ ተቆርጧል። ኤልዛቤት ለዚህ ክስተት በከፊል ተጠያቂው የራሷ የተሳሳተ ፍርድ እንደሆነ ታውቃለች። አንድ ታዛቢ በ1602 እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ደስታዋ በጨለማ ውስጥ መቀመጥ እና አንዳንድ ጊዜ እንባ በማፍሰስ ኤሴክስን ለማልቀስ ነው። ሞት የኤልዛቤት ከፍተኛ አማካሪ ዊልያም ሴሲል 1ኛ ባሮን በርግሌይ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 4 ቀን 1598 ሞተ። የፖለቲካ ካባው ለልጁ ሮበርት ሴሲል ተላለፈ፣ እሱም ብዙም ሳይቆይ የመንግስት መሪ ሆነ። ለስላሳ ቅደም ተከተል. ኤልዛቤት ተተኪዋን በፍፁም ስለማትጠራት፣ ሲሲል በድብቅ የመቀጠል ግዴታ ]ስለዚህ ከስኮትላንዳዊው ጄምስ ስድስተኛ ጋር በኮድ ድርድር ውስጥ ገባ፣ እሱም ጠንካራ ነገር ግን እውቅና የሌለው የይገባኛል ጥያቄ ነበረው። ኤልዛቤት እና "የከፍተኛውን ሰው ልብ ጠብቅ፣ ወሲብ እና ጥራት ምንም ነገር ትክክል ያልሆነው እንደ አላስፈላጊ ማብራሪያዎች ወይም በራሷ ድርጊት ብዙ ጉጉ" ነው። ምክሩ ሰራ። የጄምስ ቃና ኤልዛቤትን አስደስቷታል፣ እሷም ምላሽ ሰጥታለች፡- “እንግዲህ እንደማትጠራጠር አምናለሁ፣ ነገር ግን የመጨረሻ ደብዳቤዎችሽ ተቀባይነት ባለው መልኩ ተወስደዋል ምክንያቱም የእኔ ምስጋና የሚጎድላቸው ስላልሆኑ፣ ነገር ግን በአመስጋኝነት መንፈስ አቅርቡልኝ። በታሪክ ምሁር ጄ.ኢ.ኔል እይታ ኤልዛቤት ምኞቷን ለያዕቆብ በግልፅ ተናግራ ላትሆን ትችላለች፣ነገር ግን “የተሸፈኑ ሐረጎች ከሆነ የማይታለሉ” በማለት አሳውቃቸዋለች።በጓደኞቿ መካከል ተከታታይ ሞት እስከ 1602 መኸር ድረስ የንግስት ጤንነት ጤናማ ነበር እ.ኤ.አ. በመጋቢት ወር ኤልዛቤት ታመመች እና "በተቀመጠ እና ሊወገድ በማይችል የጭንቀት ስሜት" ውስጥ ቆየች እና ለሰዓታት መጨረሻ ላይ ትራስ ላይ ሳትነቃነቅ ተቀመጠች። ሮበርት ሴሲል መተኛት እንዳለባት ሲነግራት፣ “ትንሽ ሰው ለመኳንንት የምትጠቀምበት ቃል መሆን የለበትም” ብላ ተናገረች። ማርች 24 ቀን 1603 በሪችመንድ ቤተመንግስት ከጠዋቱ ሁለት እና ሶስት መካከል ሞተች። ከጥቂት ሰአታት በኋላ ሴሲል እና ምክር ቤቱ እቅዳቸውን አውጥተው የእንግሊዝ ንጉስ ጀምስ አወጁ። እ.ኤ.አ. በ1750ዎቹ የእንግሊዝ ካላንደር ማሻሻያ ተከትሎ የንግሥቲቱን ሞት በ1603 መመዝገብ የተለመደ ቢሆንም፣ እንግሊዝ መጋቢት 25 ቀን አዲስ ዓመትን ታከብራለች፣ በተለምዶ ሌዲ ቀን በመባል ይታወቃል። ስለዚህም ኤልዛቤት በአሮጌው አቆጣጠር በ1602 የመጨረሻ ቀን ሞተች። ዘመናዊው ኮንቬንሽን አዲሱን ለዓመት ሲጠቀሙ አሮጌውን የቀን መቁጠሪያ ለቀን እና ለወሩ መጠቀም ነው.የኤልዛቤት የሬሳ ሣጥን በምሽት ከወንዙ ወርዶ ወደ ኋይትሃል፣ ችቦ በበራ ጀልባ ላይ ተወሰደ። በኤፕሪል 28 የቀብር ሥነ-ሥርዓቷ ላይ የሬሳ ሳጥኑ በጥቁር ቬልቬት በተሰቀለ በአራት ፈረሶች በተሳለ መኪና ላይ ወደ ዌስትሚኒስተር አቢ ተወሰደ። ታሪክ ጸሐፊው ዮሐንስ ስቶው እንዳሉት፡- ዌስትሚኒስተር በጎዳናዎቻቸው፣በቤታቸው፣በመስኮቶቻቸው፣በመሪዎቻቸው እና በገንዳዎቻቸው ላይ ብዙ አይነት ሰዎች ተጭነው ነበር፣ይህን ለማየት በወጡት፣እናም የእርሷን ምስል በሬሳ ሣጥን ላይ ተዘርግቶ ሲያዩ፣እንዲህ አይነት አጠቃላይ ማልቀስ፣ማቃሰት እና በሰው ትዝታ ውስጥ እንዳልታየ ወይም እንዳልታወቀ ማልቀስ። ኤልሳቤጥ በዌስትሚኒስተር አቢ ውስጥ ታስራለች፣ ከግማሽ እህቷ ሜሪ 1 ጋር በተጋራው መቃብር ውስጥ። በመቃብራቸው ላይ የላቲን ፅሁፍ ተባባሪዎች ወደ ተተርጉሟል። መንግሥትና መቃብር፣ እንተኛለን፣ ኤልሳቤጥ እና ማርያም፣ እህቶች፣ በትንሣኤ ተስፋ። ቅርስ ኤልዛቤት በብዙ ተገዢዎቿ አዘነች፣ ሌሎች በመሞቷ ግን እፎይታ አግኝተዋል። የንጉሥ ጄምስ የሚጠበቀው ነገር በጣም ተጀመረ ነገር ግን ውድቅ አደረገ። በ1620ዎቹ የኤልዛቤት አምልኮ ናፍቆት መነቃቃት ነበር። ኤልሳቤጥ የፕሮቴስታንቶች ጀግንነት እና የወርቅ ዘመን ገዥ ተብላ ተወድሳለች። ጄምስ የተበላሸ ፍርድ ቤትን ሲመራ የካቶሊክ ደጋፊ ሆኖ ተሣልፏል። ኤልዛቤት በንግሥና ዘመኗ መጨረሻ ላይ ያዳበረችው የድል አድራጊ ምስል፣ ከቡድንተኝነት እና ከወታደራዊ እና ከኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዳራ አንፃር፣ ከጥቅም ውጪ የሆነች እና ስሟ ከፍ ከፍ አለ። የጎልፍሬይ ጉድማን የግሎስተር ኤጲስ ቆጶስ፣ “የስኮትላንድ መንግሥት ልምድ ባገኘን ጊዜ ንግሥቲቱ ሕያው የሆነች ትመስላለች። ከዚያ በኋላ የማስታወስ ችሎታዋ በጣም ከፍ ያለ ነበር።” የኤልዛቤት መንግሥት ዘውድ፣ ቤተ ክርስቲያን እና ፓርላማ በሠሩበት ጊዜ ተስማሚ ሆነ። ሕገ መንግሥታዊ ሚዛን. በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በፕሮቴስታንት አድናቂዎቿ የተሳለችው የኤልዛቤት ምስል ዘላቂ እና ተደማጭነት ነበረው። የማስታወስ ችሎታዋም በናፖሊዮን ጦርነት ወቅት እንደገና ታደሰ፣ ሀገሪቱ እንደገና በወረራ አፋፍ ላይ ስትገኝ። በቪክቶሪያ ዘመን የኤልዛቤት አፈ ታሪክ በጊዜው ከነበረው የንጉሠ ነገሥታዊ ርዕዮተ ዓለም ጋር ተስተካክሎ ነበር, እና በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ኤልዛቤት ለውጭ ስጋቶች ብሔራዊ ተቃውሞ የፍቅር ምልክት ነበረች. የዚያን ጊዜ ታሪክ ጸሐፊዎች እንደ ጄ.ኢ.ኔል (1934) እና ኤ.ኤል. እና ደግሞ በግል ንግሥቲቱን ሃሳባዊ: እሷ ሁልጊዜ ትክክል ሁሉንም ነገር አደረገ; የእሷ ይበልጥ ደስ የማይሉ ባህሪያት ችላ ተብለዋል ወይም እንደ ጭንቀት ምልክቶች ተብራርተዋል. ይሁን እንጂ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ጸሐፊዎች ስለ ኤልዛቤት የበለጠ የተወሳሰበ አመለካከት ወስደዋል. የግዛት ዘመኗ በ1587 እና 1596 በካዲዝ ላይ በተካሄደው ጦርነት በስፓኒሽ ላይ በተሳካ ሁኔታ ወረራ በመፈጸሙ ታዋቂ ነው፣ ነገር ግን አንዳንድ የታሪክ ተመራማሪዎች በየብስ እና በባህር ላይ ወታደራዊ ውድቀቶችን ያመለክታሉ። በአየርላንድ የኤልዛቤት ጦር በመጨረሻ አሸንፏል። ነገር ግን ስልታቸው መዝገብዋን ያበላሻል። የፕሮቴስታንት ብሔራትን በስፔንና በሐብስበርግ ላይ ደፋር ተሟጋች ከመሆን ይልቅ በውጭ ፖሊሲዎቿ ውስጥ ጠንቃቃ ትሆናለች። ለውጭ ፕሮቴስታንቶች በጣም የተገደበ እርዳታ ሰጥታለች እና አዛዦቿ በውጭ ሀገር ለውጥ ለማምጣት ገንዘብ ሳትሰጥ ቀርታለች። ኤልዛቤት ብሄራዊ ማንነትን ለመቅረፅ የሚረዳ የእንግሊዝ ቤተክርስትያን መስርታ ዛሬም በቦታው ይገኛል። በኋላ የፕሮቴስታንት ጀግና ብለው ያመሰገኗት ሰዎች ሁሉንም የካቶሊክ እምነት ልማዶች ከእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ለማቋረጥ ፈቃደኛ አለመሆኖን ችላ ብለውታል። በእሷ ዘመን ጥብቅ ፕሮቴስታንቶች በ1559 የተካሄደውን የሰፈራ እና የአንድነት ድርጊት እንደ ስምምነት አድርገው ይመለከቱት እንደነበር የታሪክ ተመራማሪዎች አስታውሰዋል። እንዲያውም ኤልዛቤት እምነት የግል እንደሆነ ታምናለች እና ፍራንሲስ ቤከን እንዳሉት “በሰዎች ልብ ውስጥ መስኮቶችን እና ምስጢራዊ ሀሳቦችን መሥራት” አልፈለገችም። ኤልዛቤት በአብዛኛው የመከላከያ የውጭ ፖሊሲን ብትከተልም, የግዛቷ ዘመን የእንግሊዝን የውጭ አገር ደረጃ ከፍ አድርጎታል. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲክስተስ አምስተኛ “ሴት ብቻ ነች፣ የግማሽ ደሴት እመቤት ብቻ ነች፣ ሆኖም ግን እራሷን በስፔን፣ በፈረንሳይ፣ በግዛቱ፣ በሁሉም እንድትፈራ ታደርጋለች። በኤልዛቤት ዘመን፣ ሕዝበ ክርስትና እንደተበታተነች ብሔሩ አዲስ በራስ የመተማመን እና የሉዓላዊነት ስሜት አገኘ። ኤልዛቤት አንድ ንጉስ በሕዝብ ፈቃድ እንደሚገዛ የተገነዘበች የመጀመሪያዋ ቱዶር ነበረች። ስለዚህ ሁል ጊዜ ከፓርላማ እና ከአማካሪዎቿ ጋር ትሰራለች እውነቱን ይነግሯታል—የእሷ ስቱዋርት ተተኪዎቿ ሊከተሉት ያልቻሉትን የመንግስት ዘይቤ። አንዳንድ የታሪክ ተመራማሪዎች እድለኛ ብለው ይጠሩታል; አምላክ እንደሚጠብቃት አምናለች። ኤልዛቤት "ብቻ እንግሊዘኛ" በመሆኗ እራሷን በመታበይ በእግዚአብሔር ታምናለች፣ እውነተኛ ምክር እና የተገዥዎቿ ፍቅር ለአገዛዟ ስኬት። በጸሎቷ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡- ጦርነቶች እና ብጥብጦች በአስከፊ ስደት በዙሪያዬ ያሉትን ሁሉንም ነገስታት እና ሀገራት ባናደዱበት ጊዜ፣ የእኔ ንግሥና ሰላማዊ ነበር፣ እና የእኔ ግዛት ለተሰቃየች ቤተክርስቲያንሽ መቀበያ ነው። የሕዝቤ ፍቅር ጸንቶ ታየ የጠላቶቼም አሳብ ከሸፈ።
13476
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%8D%E1%89%A0%E1%88%AD%E1%89%B5%20%E1%8A%A0%E1%8B%AD%E1%8A%95%E1%88%B5%E1%89%B3%E1%8B%AD%E1%8A%95
አልበርት አይንስታይን
አልበርት አይንስታይን በ1895 ዓ.ም ነበር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ገብቶ በድግሪ ለመረቅ በስዊስ (ዙሪክ ከተማ) የምዝገባ ማመልከቻውን ያስገባው። ለአንስታይን ብቸኛ ማስረጃው በጀርመን ሙኒክ ከተማ የተማረበት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውጤቱ ብቻ ነበር። አባቱ በሙኒክ ከተማ የከፈተው ንግድ ለኪሳራ በመዳረጉና ወደ ጣሊያን ሀገር በመሰደዱ የተነሳ ጀርመን ሀገር ብቻውን የቀረው አይንስታይን እንደ ድሮው ለትምህርቱ ትኩረት መስጠት አልሆነለትም። በዚህ ወቅት ነበር አይንስታይን ትምህርቱን አቋርጦ በሚላን ከሚገኙት ቤተሰቦቹ ጋር የተቀላቀለው። ከጣሊያን ወደ ስዊስ በመሄድ በኮሌጅ ደረጃ ገብቶ ለመመረቅ ያመላከተበት የስዊስ «ዙሪክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጂ» ምንም እንኳን አይንስታይን ትምህርቱን ያላጠናቀቀ ቢሆንም የመግቢያ ፈተናውን ካለፈ ሊማር እንደሚችል ተፈቀደለት። አይንስታይንም በታላቅ ወኔ በማትሪክ ውጤታቸው ከፍተኛ ነጥብ ካመጡና በዕድሜ ከሜበልጡት ተማሪዎች ጋር ወደፈተና አዳራሹ ገባ። የፈተናው አይነት አለም አቀፍ ይዘት ያላቸው እንደ «ፈረንሳይኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ታሪክ፣ ጆግራፊ፣ ሙዚቃ» ይገኙበታል። የመግቢያ ፈተናዎቹም ለኢንጅነሪንግ ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎችን ብቃት በሚገባ አብጠርጥረው ሊፈትኑ የሚችሉ ጥያቄዎችን ያካተተ ነበር። ይህን ከባድ ፈተና ነበር አይንስታይን የተጋፈጠው። አንድ ሳምንት የፈጀው ይህ የመግቢያ ፈተናም በሶሥተኛው ሳምንት ነበር ውጤቱ የተገለጨው። ከ300 ተማሪዎች ውስጥም በዲግሪ ፕሮግራም እንዲታቀፉ የሚፈቀድላቸው ከመቶ ለማይበልጡት በመሆኑ ፍክክሩ እጅግ ከባድ ነበር። የተፈታኝ ተማሪዎችም ውጤት አንድ አንድ እያል መለጠፍ ተጀመረ ከማትስና ከፊዚክስ የሰቃዮች ሰቃይ የነበረው አንስታይን ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያቋረጠው፣ የማትሪክ ፈተና ያልወሰደው አንስታይን በማትሪክ ውጤታቸው አንቱታን ያተረፉ የሲውዘር ላንድ ተማሪዎችን ከእግሩ ስር አሰልፏቸዋል። ይሁን እንጂ ይህን መሰሉ የሰቀላ ውጤት በሌሎች የትምህርት አይነቶች ላይ ሊደግም ግን አልተቻለውም ነበር። አልበርት አንስታይን ተወልዶ ያደገው በጀርመን ነው ፈረንሳይኛን ቋንቋ መሆኑን ከማወቅ የዘለለ እውቀት አልነበረውም። በሰዎች ትልቅ ግምት የሚሰጣቸው አለባበስና ፀጉር አበጣጠር በእርሱ ዘንድ ተራ ነገሮች ናቸው። ፀጉሩም ቢሆን ሁሌም ጨፍራራ ነበር። ብሎም የምርምር ስራዎቹን ወደ እንግሊዘኛ የሚለውጡለት ጓደኞቹ ነበሩ። ብሎም ልታሪክ ትምህርትና ለጂኦግራፊ ትምህርት ንቁ ስላልነበር ወደ ኮሌጅ ለመግባት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀረ። በፈተና መውደቁን የሰሙት አባቱ ሄርማን እና እናቱ ፓውሊን አንስታይንን በቶሎ ወደ ሚላን እንዲመጣ አደረጉት። በአንድ በኩል ልጃቸው ትምህርቱን እንዲያጠናቅቅ ቢመክሩትም አሻፈረኝ ብሏችው ነበርና ብዚህ ሁኔታ መቆየቱ አሳስቧችዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከዙሪክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰናበቱ አሳዝኗቸዋል። በመጨረሻ አንስታይን ጉዞውን ከሲውዘር ላንድ ወደ ጣሊያኗ ሚላን አደረገ። ከወላጆቹም ጋር ተገናኘ። ወላጆቹም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሚላን እንዲያጠናቅቅ ቢመክሩትም እሱግን አሻፈረኝ አለ። አሁንም ምኞቱ ያለው በታላቁ የዚውዘርላንድ ኮሌጅ (ዙሪክ ፖሊ ቴክኒክ) ላይ እንደሆነ በጠንካራ አንደበቱ ገለፀላቸው። አንስታይንን እንደገና ወደ ሲውዘርላንድ ላኩት። አንስታይን አሁን አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት አላጣውም። በዚህ ኮሌጅ ገብቶ ለመማር የመግቢያ ፈተናውን ማለፍ ይጠበቅበታል። ፈተናውን በሚገባ ለማለፍ ደግሞ የሁለተኛ ድረጃ ትምህርቱን ማጠናቅቅ እንዳለበርት ተገንዝቧል። በመሆኑም ከዙሪክ ከተማ ብዙም ወደማትርቀው አይራው ከተማ አመራ። በአይራው ከተማ ውስጥ በምትገኘው የካንቶሊክ ት/ቤት ተመዝግቦ ያቃረጠውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ቀጠለ። በዚህ ት/ቤት ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ስኬት ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ትምህርቱን አጠናቀቀ። በ1986 አንስታይን በዙሪክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ገብቶ ለመማር የሚያስችለውን ፈተና እንደገና ወሰደ። "ከትላንት እንማራለን፣ ዛሬን እንኖራለን፣ ስለነገም ተስፋ እናደርጋለን" የሚለው አንስታይን በመጨረሻ ህልሙን እውን አድርጎ በኮሌጁ ለመታቀፍ በቃ። የኮሌጅ ቆይታው በጣም አስገራሚ የነበረ ሲሆን ብዙ ጊዜውንም ክፍል ገብቶ ከመማር ይልቅ በቤተ-ሙከራ ጅፍሎች ውስጥ ማሳለፍ ይመርጥ ነበር። ገና ኮሌጅ በገባ በመጀመሪያው ሴሜስተር ላይ ሳይንሳዊ ጥናት በማካሄድ አድናቆትን ያገኘው አንስታይን የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርትን የሚያፈቀረው ለንድፈ ሃሳብ (ቴዮሪ) ሳይሆን ለተግባራዊ አጠቃቀም ነበር። በርግጥ አንድ ተግባራዊ ውጤት ያለውን ሳይንሳዊ ጥናት ላማካሄድ ቲዮሪ መሰረታዊ መነሻ ማሆኑ አይካድም አንስታይን ግን 10 በመቶ ጊዜውን ለጥናት 90 በመቶውን ደግሞ ለተግባራዊ ምርምር ነበር የሚያውለው። የ16 አመት ልጅ ግሩም የሳይንስ ምርምር አደረገ ሲባል ቢደመጥ ማን ያምናል። ነገሩ ግን እውነት ነው አንስታይን በ16 አመቱ ነበር ኢተር በማግኔት መግነጢሳዊ ሃይል ውስጥ ሲያልፍ የሚኖረውን ባህሪይ ያጠናው። በዚያው ኮሌጅ ውስጥ የተለያዩ ሽልማቶን የተቸረው አንስታይን ነበር። በ1890 የኮሌጁ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን የኤልክትሪክ ምህንድስና ድግሪውን ጫነ። በመረቃው ወቅት የደስታው ተካፋይ በመሆን ከሚላን ተነስተው ዙሪክ የደረሱት እናቱ ፓውሊን አባቱ ሄርማን ደስታቸው እጅግ ሀያል ነበር። አብራው ደግሞ አንዲት የሲውዘርላንድ ዜግነት ያላት ተመራቂ ትገኛለች። ሜሊቫ ሜሪክ በመባል የምትጠራው ይህቺ ወጣት ከአንስታይን ጋር ስትማር የነበረችና ትምህርት ያገናኛቸው ፍቅረኛሞች ናቸው። የአንስታይን የእድሜ ልክ ጓደኛ የነበረው ኢንጂነር ማይክል ቢሶ የተገኘው ከዚሁ ኮሌጅ ነው። የምረቃ ስነ-ስርአቱ አምሮና ደምቆ ኢንጂነር አልበርት አንስታይንም ካባና ወርቁን አጥልቆ ነበር የተጠናቀቀው። ቀሪው ምርቃት ደግሞ የተካሄደው በሜሊቫ ሜሪክ ቤተሰቦች ውስጥ ነበር። ፊዚሲስቶች የጀርመን
9181
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%B0%E1%88%AD%E1%8C%8D
ደርግ
ደርግ ከሰኔ 21፣ 1966 እስከ 1983ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰፍኖ የነበር የወታደራዊ አገዛዝ ስርዓት አይነት ነበር። ደርግ የሚለው ቃል ከግዕዝ የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም ቡድን ወይንም ኮሚቴ ማለት ነው። ይህን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ለስርዓቱ መገለጫነት የተጠቀመው ግለሰብ ሻለቃ ናደው ዘካሪያስ ሲባል ይሄውም ሰኔ 21፣ 1966 ዓ.ም. ነበር። በዚህ ወቅት፣ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የአራተኛ እግረኛ ክፍለ ጦር መምሪያ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ መለዮ ለባሾች በየካቲት ወር ስለፈነዳው አብዮት ከሰኔ 19 ጀምሮ ውይይት የሚያካሂዱበት ጊዜ የነበር ሲሆን፤ ሻለቃ ናደው የዚህ ኮሚቴ ማስታወቂያ ጉዳይ ሠራተኛ ነበር። ደርግ በዚህ ሁኔታ በዝቅተኛ መኮንኖች (ከኮሎኔል ማዕረግ በታች) ከተመሰረተ በኋላ በዚያው ቀን ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም የደርግ ሊቀመንበር በመሆን ተመርጦ እስከ ስርዓቱ ማብቂያ (1979) ድረስ በዚያ ስልጣን አገልግሏል። የአብዮቱ ዋዜማ የታኅሣሥ ግርግር ተብሎ በሚታወቀውና በ1953 ዓ.ም. የተካሄደው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ከከሸፈ በኋላ የቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘውዳዊ መንግስት የተለያዩ ማሻሻያ ለውጦችን ለስርዓቱ አስተዋወቀ። አብዛኛዎቹ ማሻሻያዎች መፈንቅለ መንግስቱን እንዲደግፉ ለሚጠረጠሩ የጦርና የፖሊስ ሃይሎች የመሬት ስጦታ በማድረግ ላይ ያተኮረ ነበር። ስለሆነም የአገሪቱ መሰረታዊ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሁኔታ በቋሚ ሁኔታ ሊሻሻል አልቻለም። በ1958ዓ.ም. የባለ ርስቱን መደብ ጉልበት ለመቀነስ በማሰብ የዘውዱ ሥርዓት አዲስ አይነት የመሬት ግብር ለማስተዋወቅ ሞከረ። ሆኖም ፓርላማው ሙሉ በሙሉ ውድቅ አደረገው። በምትኩ፣ በሚቀጥለው ዓመት የእርሻ ውጤቶች ግብር ለፓርላማ ቀርቦ ጸደቀ። ምንም እንኳ የጸደቀው ግብር መንግስት ካቀረበው በጣም የተለወጠ ቢሆንም፣ በባለርስቱ መደብ አመጽ ማስነሳቱ አልቀረም። በተለይ በጎጃም ባለርስቶች በተነሳ አመጽ ምክንያት የሁለት አመት ወታደራዊ ዘመቻ በጎጃም ተደርጎ አመጹን ለማሸነፍ ስላልተቻለ መንግስት ወታደሩን ከጎጃም በማውጣት ግብሩን ሙሉ በሙሉ መሰርዝ ግድ አለው። እንዲያውም ወደኋላ፣ እስከ 1932ዓ.ም. የነበር የግብር እዳ በሙሉ ተሰረዘ። የጎጃሙ ሽንፈት ሌሎች ለውጥን የሚቃወሙ ክፍሎች እንዲያምጹ ከማበረታቱም በላይ ስርዓቱን ለሌላ አጣብቂኝ ዳረገው። ለውጥን እሚቃወሙ ኃይሎች በሚያምጹበት በዚያው ወቅት፣ በተቃራኒው ለውጥን የሚፈልጉ ተማሪዎች፣ ገበሬዎችና፣ የሰራተኞች ማህበራት ባንጻሩ የኑሮ ውድነትን፣ ጉቦንና፣ የመሬት ሥርዓቱን በመቃዎም ማደም ጀመሩ። ይህ የተወሳሰበ ሁኔታ በእድሜ እየገፉ የሄዱት ንጉሱ ፊታቸውን ወደ ውጭ ጉዳይ እንዲያዞሩና የአገሪቱን የውስጥ ጉዳይ በጠቅላይ ሚንስትራቸው አክሊሉ ሃብተወልድ ጫንቃ ላይ እንዲያስቀምጡ አደረጋቸው። ሥርዓቱ በሁለት ተጻራሪ አጣብቂኞች ውስጥ ገብቶ ባለበት በዚህ ወቅት በተፈጠረ የርሃብ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስናና አጠቃላይ ቅሬታ የ1966ቱ አብዮት እንዲፈነዳ ግድ ሆነ። አብዮቱን ሀ ብሎ የጀመረው የወታደሩ መደብ ሲሆን፣ ጥር፣1966 ዓ.ም. ነገሌ፣ ሲዳሞ ላይ ሰፍሮ የነበረው የምድር ጦር ሠራዊት አዛዥ መኮንኖቻቸውን ሲያግቱ ይጀምራል። ጉዳዩ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚኖሩ የሰራዊቱ ክፍሎች ድጋፍን በማግኘቱ በወታደሩ መደብ ከመዛመቱም ባሻገር ወደ ተቀረው ዜጋም በመዝለል በመጋባቱ በብዙ ከተማዎች አመጽ መነሳት ጀመረ። የዘውዱ መንግስት ለዚህ መልስ ይሆናል ብሎ ያስበውን ብዙ ጥቃቅን ለውጦችን አድርጓል፤ ለምሳሌ አክሊሉ ሃብተወልድን አንስቶ እንዳልካቸው መኮንንን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓል፣ ለወታደሩ ልዩ ደመዎዝ ጭማሪ አድርጓል፣ ሊተገበር የነበር የትምህርት ስርዓት ማሻሻያ ለውጥን በተነሳበት ተቃውሞ ምክንያት አስቁሟል፣ የካቲት ወር ላይ እንዲሁ የመልስቱን ሕገ መንግስት ለማሻሻል ሞክሯል። ምንም እንኳ እኒህ ለውጦች ውጥረቱን ቢያረግቡም፣ በኋላ ላይ በኮሎኔል አለም ዘውድ የሚመራ የዘውዱ ተቆርቋሪ ቡድን የእንዳልካቸውን አስተዳደር ለመጥቀም በማሰብ ብዙ የአየር ኃይል መኮንኖችን ለእስር ዳረገ። በዚህ ሁኔታ የተበሳጨውና ተከፋፍሎ የነበረው የጦር ሠራዊቱ ክፍል፣ ኮ/ል አለም ዘውድ ከሚመራው ቡድን በማፈንገጥ በአንድ ልብ አመጽ ጀመረ። ሻለቃና ከሻለቃ በታች የሆኑት እነዚህ መኮንኖች በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የአገሪቱ ሰራዊት ሶስት ሶስት ተወካዮች ወደ አዲስ አበባ እንዲልኩ በማድረግ፣እርስ በርሳቸው በመሰባሰብ፣ ደርግን መሰረቱ። የደርግ አመሰራረት ኮ/ል አለም ዘውድ የዘውዱ ተቆርቋሪ እንደሆነ ከታመነበት በኋላ በኮ/ል አጥናፉ አባተ የሚመራ፣ ባብዛኛው ከሆለታ ጦር ማሰልጠኛ የተመረቀ ቡድንና ጥቂት የሐረር መኮንኖች ማስለጠኛ ምሩቆች ሁነው አክራሪ አብዮተኛ ቡድን መስርተው ከአለም ዘውድ ቡድን ተገንጥለው ወጡ። ይህ ቡድን በኮሚቴ በመዋቀር በአገሪቱ ከሚገኙ 42 የጦር ክፍሎች ሦስት ሦስት ወኪሎች ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ካደረገ በኋላ ከሰኔ '66 ጀምሮ መደበኛ ስብስባ በማድረግ ደርግ' እንዲቋቋም አደረገ። በአነጋገር ጥንካሬው፣ ውሳኔ ለመወሰን ባለምፍራቱና ባለማመንታቱ ታዋቂነት ያተረፈው መንግስቱ ኃይለማርያም ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን መፈክር ካስተዋወቀ በኋላ በጣም ተቀባይነትን በማግኘቱ የዚሁ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ። ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን መፈክር ባስተዋወቀበት ንግግሩ ኮሚቴው ኢትዮጵያን ከመበታተን አደጋ ለማዳን የቆመ ኃይል አድርጎ በማቅረብ ለተዘበራረቀው አብዮት አቅጣጫ ከመስጠቱም በተጨማሪ የአገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅ የሚችል ሃይል ይሄው ኮሚቴ እንደሆነ በማሳየት ለኮሚቴው የሃገር ጠባቂነትን አላማ ለማሰጠት ችሎ ነበር። መንግስቱ፣ ምንም እንኳ በወታደሩ ዘንድ ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በመላው ሃገሪቱ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነትን ማግኘት እንደማይችል ስለተረዳ ለዚህ ተግባር እንዲረዳው ጄኔራል አማን አንዶምን የስርዓቱ መሪ እንዲሆን በመጋበዝ የጊዜያዊው አስተዳደር ደርግ መሪ እንዲሆን አደረገ። ቀጥሎም ለዓፄ ኃይለሥላሴ 5 ጥያቄዎችን በማቅረብ ንጉሱ አምስቱንም ስለፈቀዱ የደርግ ሃይል በቅጽበት እንዲያድግ አደረገ። በመቀጠል፣ በሃይል የጎለበተው ደርግ ጠቅላይ ሚንስትር እንዳልካቸው ከስልጣን እንዲነሱ አድርጎ ሚካኤል እምሩን ተካ። አማን አንዶም መከላከያ ሚንስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ እንዳልካቸውና የርሳቸው ደጋፊዎች እንዲታሰሩ ተደረገ። በዚህ መልኩ ቀስ ብሎ ይካሄድ የነበረው ለውጥ ፍጥነት ጨመረ። መንግስቱ፣ ንጉሱ እራሳቸውን በቀጥታ መጋፈጥ ስላልፈለገ ቀስ በቀስ የኃይላቻውን መዋቅር በማፈራረስ፣ የክብር ዘበኛን መሪ በማሳሰር፣ በኋላም የጆናታን ዲምብሊን የወሎ ረሃብ ቪዲዮ በቴሌቪዥን በማቅረብ ንጉሱ ተጠያቂ መሆናቸውን በማሳየት፣ ሙሉው ስራ ከተሰራ በኋላ ያለምንም ችግር ንጉሱን ከስልጣን ማስወገድ ቻለ። የጊዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ንጉሱ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ጄኔራል አማን አንዶም የጊዚያዊ ወታደራዊ ደርግ ዋና ሊቀመንበር ሆኖ በመሾም፣ አዲሱ ስርዓት መስከረም፣ 1967 ተጀመረ። ደርግ በዚህ አኳሃን ስልጣን ላይ እንደወጣ አዲስ ረቆ የነብረውን ሕገ መንግሥት እና የነበረውን ፓርላማ ወዲያው ሰረዘ። የአማን ተግባር በተለይ ለአለም ፈገግ የሚል መልክ ማሳየትና እጅ መጨበጥ ነበርና ከሁለት ወር በኋላ መንግስቱ አስገድሎት ሌላ አሻንጉሊት መሪ ተፈሪ በንቲ በሥፍራው አስቆመ። አመሠራረት እና ዕድገት የመንግስቱ አመራር መረሳ በ1982 የ1977 ረሃብ ዕርዳታና ውዝግቡ የደርግ ማብቂያ የተመሰረተው በጥቂት ዝቅተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ሲሆን ደርግ የአጼ ኃይለ ስላሴ መንግስትን ገርሦ በምትኩ ወታደራዊ ጁንታ በመመስረት ስሙን በመቀያየር አገዛዙ ለ17 ዓመታት ኢትዮጵያን አስተዳድሮአል። የተመሠረተበትም ቀን ሰኔ 20 1966 ነው ደግሞ ይዩ፦ 1974 እ.ኤ.አ. 1987 እ.ኤ.አ. 1991 እ.ኤ.አ. መንግስቱ ኃይለ ማርያም ማጣቀሻ የኢትዮጵያ ታሪክ ፓርቲዎች
15387
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%B0%E1%8C%83%E1%8B%9D%E1%88%9B%E1%89%BD%20%E1%8A%83%E1%89%A5%E1%89%B0%20%E1%88%A5%E1%88%8B%E1%88%B4%20%E1%89%A0%E1%88%8B%E1%8B%AD%E1%8A%90%E1%88%85
ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በላይነህ
=100084732863752 ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በላይነህ በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በከሰም ወረዳ ልዩ ሰሙ ውቢት በሚባለው ሥፍራ፣ ከታወቁት አባታቸው ከአቶ በላይነህ ቢተውልኝ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ማናለብሽ በድሉ መስከረም ቀን ዓ.ም ተወለዱ። በተወለዱ በአሥራ አምስት ዓመታቸው በቤተ መንግሥት የዕልፍኝ አሽከር ሆነው ሲያግለግሉ ከቆዩ በኋላ ጥንታዊ የክብር ዘበኛ ሲቋቋም በወታደርነት ተዛውረው አግልግሎታችውን አበረከቱ። አርበኝነት በመጋቢት ወር ዓ.ም ማይጨው ላይ በተደረገው ታላቁ ጦርነት ከክብር ዘበኞች ጋደኞቻቸው ጋር ሆነው ከፍ ባለ ጀግንነት ከጠላት ጋር በመዋጋት አገራቸውንና ንጉሠ ነግሥታቸውን አግልግለዋል። ከዚያም እንደተመለሱ በንጉሠ ነግሥታቸው መሪ ትእዛዝ መሠረት የጦርነት ትግላቸውን በመቀጠል አምስት ዓመት ሙሉ በአርበኝነት የጦር መሪ በመሆን እጅግ ከፍ ባለ ጀግንነት ሌት ከቀን ያለ አንዳች አረፍት በየጦር ሜዳው የጠላትን ኃይል ያንበረከኩ ታላቅ ጀግና ነበሩ የገደሏቸውንም የጠላት መኮንኖች ለመጥቀስ ያህል፣ በሐምሌ ወር ዓ.ም አሌልቱ ላይ የጠላት የጦር ከባድ መኪናዎች(ካሚዮን)በተቃጠሉ ጊዜ የጦር መሪ የነበሩት አርበኞች ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በላይነህና ፊታውራሪ ጂማ ሰንበቴ ነበሩ። ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በዚሁ ጦርነት ላይ ሁለት የጠላት ከፍተኛ መኮንኖች ግድለዋል። ፪.ክቡር ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በላይነህ በአሌልቱ ሜዳ ላይ ከኅዳር ቀን ዓ.ም ጀምሮ ሦስት ቀን ሙሉ የፈጀውን ጦርነት ባደረጉ ጊዜ ከጠላት በኩል የኢጣሊያ ፋሽስቶች ብቻ መኮንኖችና ወታደሮች ተግድለዋል። ፫.በ፲፱፻፳፱ ዓ.ም ሸንኮራ አራራቲ ላይ በተደረገው ኃይለኛ ጦርነት ጄኔራል አውጎስቲኒን ግድለዋል። ፬.በ፲፱፻፴ ዓ.ም ቡልጋ ውስጥ ጨመሪ በተባለ ቦታ በተደረገው ከባድ ጦርነት ክቡር ራስ ደስታ ዳምጠውን እና እነደጃዝማች አበራ ካሳን የገደለውን ከፍተኛ የጠላት የጦር መሪ ገድለዋል። ፭.በግንቦት ወር ዓ.ም በቡልጋ የጉንጭ በተባለ ሥፍራ በተደረገው ብርቱ ጦርነት ጄኔራል ጋሊያኒን ገድለዋል። ጀኔራል ጋሊያኒ በተገደለ ማግስት ስቻት በተባለው ሥፍራ የጠላት አውሮፕላኖች ብዙ ስንቅና ጥይት ለደጃዝማች ጦር ጥለዋል። ይህም ሊደረግ የቻለው ከጄኔራል ጋሊያኒ ላይ ብዙ የጦር መሣሪያና የአውሮፕላን ምልክት የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ስለማረኩ ነው። ከነዚህም ከገደሏቸው የጠላት መኮንኖች ላይ ብዙ ኒሻን ማርከው አሁን በቤተ መጻሕፍት መወዘክር ለመታሰቢያ ሰጥተዋቸው ይገኛሉ። የሰሜን ዘመቻ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በእንግሊዝ ሠራዊት እርዳታ ሚያዝያ ቀን አዲስ አበባ ሲገቡ በራስ አበበ አረጋይ የሚመራው የሸዋ የአርበኛ ሠራዊት በሰሜን ኢትዮጵያ መሽጎ የተቀመጠውን የጣልያን ጦር ከ እንግግሊዙ "ጊዲዮን ፎርስ" ሠራዊት ጋር ለማስለቀቅ ሲላኩ፣ ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ አርበኞቻቸውን ይዘው ዘመቱ። ከሸዋ ተነስተው ከ አርበኞች ጋር በ እንግሊዙ 'ቢምባሺ ጋይ ካምቤል' መሪነት በመጀመሪያ ደሴ ላይ የ'ዱካ ዳዎስታ'ን ጦር ድል ካደረጉ በኋላ ጉዟችውን ወደ ጎንደር በመቀጠል በ ፯ሺ የ 'ዳግላስ ፎርስ' ጋር ተቀላቀለው አስከ ጎንደር ድረስ የነበሩትን ታላላቅ የጠላት የጦር ምሽጎች በተለይም ቁልቋል በር እና ፍርቃ በር የተባሉትን ምሽጎች ከነ ፊታውራሪ ከበደ ካሳ እና ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን አርበኞች ጋር በመተባበር ደመሰሱ። ነሐሴ ቀን ዓ/ም በጣልያኑ ኮሎኔል አድርያኖ ቶሬሊ የሚመራው ሠራዊት ቁልቋል በር ላይ ለመሸገው ሠራዊት በአምሳ ስምንት የጭነት መኪና ስንቅ አቀብሎ ወደጎንደርሲመለስ አርበኞቹና እንግሊዞች በጣሉበት አደጋ ላይ ከወገን ሠራዊት ሰዎች ሲሞቱ ከቆሰሉት ሰዎች መሃል እግራቸውን በጥይት የቆሰሉት አንዱ ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ ነበሩ። በመጨረሻም ጎንደር ላይ የሠፈረውን የጀኔራል ጉልዬልሞ ናሲን ሠራዊት በጦር ኃይል የጦር ምሽጉን በመጣስ ከተማው ውስጥ ገቡ። ኅዳር ቀን ዓ.ም አዲስ አበባ ነጻ በወጣች በ ፯ኛው ወር፣ የጄነራል ጉልዬልሞ ናሲ ሠራዊት ድል ሆኖ የፋሺስት ኢጣልያ ወረራ ጎንደር ላይ አከተመ። በነጻነት ዘመን ከዚህ ድል በኋላ፣ ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ ከነሠራዊታቸው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው የካቲት ቀን ዓ/ም በታላቅ ሰልፍና ሥነ ሥርዓት ስድስት ዓመት ከተለዩዋቸው ንጉሠ ነግሥታችው ፊት ቀርበው ቆርጠጥ ቆርጠጥ ጎርደድ ጎርደድ አንዳንዴም በርከክ እያሉ ኃብቴ ኃብተ ሥላሴ የጠቅል አሽከር የንጉስ ተፈሪ ለሃይማኖቱ ተከራካሪ ጄኔራል ገዳይ ኒሻን ያሠረ ማጆር ማራኪ የተከበረ ያንተ አሽከር ያንተ ወታደር በዘመተበት የማያሳፍር ዘው ዘው ባይ ከጦሩ ማህል ጄኔራል ናዚ አቤት አቤት ሲል እያሉ ይህንንና ይህን የመሳሰለውን የፉከራ ቃል እየተናገሩ ከማይጨው ጀምረው እስካሁን ድረስ የሠሩትን ጀብዱ ሲቆጥሩ እንኳን ከዚህ በፊት ሥራ የሰራውን ቀርቶ ያልሰራውንም ዘራፍ ለገናው ለማለት ወኔውን ይቀሰቅሰው ነበር ።ከዚህ በኋላ የማረኳቸውን ከባድና ቀላል መትረየሶች በማበርከት ያደረጓቸውን አግልግሎቶች ጠቅሰው «እኔ አገልጋይዎ እንኩዋን አይነዎን አይቼ ከፊትዎ ቀርቤ ድካሜንና ሙያዬን ተናግርኩ እንጂ እንግዲህ እኔ ይህንን እድል ካግኘሁ በኋላ እውነተኛ ባሪያዎ ነኝና ምንም አላሳስብምብለው ቢናገሩ» ግርማዊ ጃንሆይ «ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ከመውደዱ የተነሣ እንግዲህ እናንተ ጌቶች ናችሁ እንጂ ባሮች አይደላችሁም እንዳላቸው ተወዳጅ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም ሥራህም በማንም አፍ የተመሰገነ ባንዲራችን ጋዜጣ ፩ኛ ዓመት፣ ቁጥር የካቲት ቀን ብለው ሞገሳዊ ቃል ሰጥተዋቸዋል። በዚሁ ዕለት የደጃዝማችነት ማዓረግ ተሰጣቸው። ከዚያም ወዲህ ፩/የክብር ዘበኛ ከፍተኛ መኮንን ሆነው በአስፈላጊው ቦታ እየተዘዋወሩ ፀጥታ ነሺዎችን የጦር ኃይል እያዘዙ ፀጥታ አስከብረዋል። ፪/በ፲፱፻፴፱ ዓ.ም ክፍለ ጦራቸውን እያዘዙ የጉርሱምና የጊሪ አውራጃ ገዥ ሆነው ተሹመዋል። ፫/በ፲፱፻፵፯ ዓ.ም በግርማዊ ንጉሠ ነግሥት መልካም ፈቃድ የጨቦና ጉራጌ አውራጃ ገዥ ሆነው ተሹመዋል። ፬/በ፲፱፻፶፪ ዓ.ም የምሥራቅ ሸዋ ብሔራዊ ጦር አዛዥ ሆነው ተሹመዋል። ፭/በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል ሆነው በመሾም እስከ ዕለተ ሞታቸው ጊዜ ድረስ አግልግለዋል። የተሸለሟቸው ኒሻኖችና ሜዳዮች የቅዱስ ጊዮርጊስ የጀብዱ ሜዳይ ባለ ዘንባባ የአርበኝንት ሜዳይ የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ ኮማንደር ያለ ፕላክ የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ ከነ ፕላኩ ከእንግሊዝ መንግሥት፦ የአፍሪቃ ኮከብ እና የአፍሪቃ የድል ኮከብ ሜዳዮች የኢትዮጵያ የድል ኮከብ ሜዳይ ናቸው። ክቡር ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በላይነህ ፈጣሪያቸውን ፈሪ፤ ሀገራቸውንና ንጉሠ ነገሥታቸውን አፍቃሪ ድኅ መጋቢና አሳዳሪ ሽማግሌዎችን ጧሪ ጓደኞቻቸውን አክባሪ ነበሩ። ብዙ ጊዜ ያማቸው በነበረው የጉበትና የልብ ድካም ህመም ሚያዝያ ቀን ዓ.ም በተወለዱ በ፷ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ የተከበሩ ልዑላውያን ቤተሰቦች፤ የተከበሩ ሚንስትሮችና ከፍተኛ የጦር ባለስልጣኖች በተገኙበት በከፍተኛ ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ለሀገራችው ታላላቅ አገልግሎት ለፈጸሙ ጀግኖች አርበኞች በተዘጋጀው ሥፍራ በክብር አርፈዋል። ምንጭ ባንዲራችን ጋዜጣ ኛ አመት ቁጥር የካቲት ፲፱፻፴፬ ዓ.ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ሚያዝያ ዓ.ም 1941), (እንግሊዝኛ) (1995),
50747
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0/%E1%89%85%E1%8B%B3%E1%88%9D
አ/ቅዳም
አ/ቅዳም የአዲስ ቅዳም ከተማ አመሰራረት አጭር ታሪክ አዲስ ቅዳም በድሮው ጎጃም አጠቃላይ ግዛት አገው ምድር አውራጃ ፣በባንጃ ወረዳ፣በባንጃ ለኮማ ምክትል ወረዳነት ከ1936-1987 ዓ.ም የቆየች ስትሆን ከ1987 ዓ.ም ወዲህ አዊ ብሔረሰብ ዞን ራሱን ችሎ ሲቋቋም ወረዳዎች ውስጥ የፋግታ ለኮማ ወረዳ ዋና ከተማ ነች አንዳንድ አፈታሪኮች ለኮማ የባንጃ ልጅ ሲሆን ፋግታ ደግሞ የአንከሻ ልጅ ነው ይላሉ ፡፡ከተማዋ ከመዲናችን አዲስ አበባ 470 ኪ.ሜ ፣ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህርዳር 104 ኪ.ሜ እንዲሁም ከብሔስብ ዞን ርዕሰ ከተማ እንጅባራ 18 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከአዲስ አበባ -ጎንደር በሚወስደው አገር አቋራጭ መንገድ ግራና ቀኝ ደጋማ ቦታ ላይ የተመሰረተች ናት ፡፡ሰባቱ የአገው አባቶች ዛሬ አዲስ ቅዳም እየተባለ የሚጠራውን ቦታ በድሮ ጊዜ “አጂስ ክዳሜ” ብለው ሰይመውት ቅዳሜ ቀን ለመወያያትና ለገቢያ ማዕከልነት(ኩሰጝፂ፣ዙሚትጝፂ፣ እንክርጝፂ ኧኧኮ) ይጠቀሙበት እንደነበር የአካባቢው ቀደምት አባቶችና አፈ ታሪኮች ያስረዳሉ በ1903 ዓ.ም ጎጃም ገዥ የነበረው ንጉስ ተ/ሃይማኖት ሲሞት በጊዜው የነበሩት የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ምኒልክ ጎጃምን ምስራቅ ፣ዳሞትና አገው ምድር ብለው ሲከፋፍሉ ለእነዚህ ግዛቶችም አስተዳዳሪ/ገዢ/ ሲመርጡ ራስ መንገሻ አቲከም አገው ምድርንና ደሞትን ገዢ ሆነው ተሾሙ፡፡ ከዚያ በፊት የነሩበት አዛዥ ገዛኻኝ ከወሰኑት ቦታ ባንግ ታራራ(አመዳይ ደን) ላይ ሆነው የጥንቱን ገበያ ስባቱ አባቶች ካስቀመጡት አንስተው ወደ አቅራቢያቸው አዛማች ኪዳነ ምህረት ወደ “ጉቢቺሊ” በመውሰዳቸው በመሰራቾቹ ተቃውሞ ብዙም ሳይቆይ ተመልሶ አሁን ካለንበት ከጥንቱ ቦታ ገበያው ተቋቁሟል ወደ ቦታው ሲመለሱ ግን የድሮ መጠሪያ “አጂስ ቅዳሜ” በመቀየር አዲስ ቅዳም ተብሎ ተጠርቷል ይህም ሊሆን የቻለው የአውጚ ቋንቋ በአማረኛ እየተወረስ በመሄዱ ነው ይላሉ አባቶች የአዲስ ቅዳም ጦርነት የኢጣሊያን ጦርነት ሽንፈት በኃላ በኢትዮጵያ አርበኞች ላይ ለመቀበል ከ40 አመታት በኋላ እደገትና ተነሳስተው ክብራቸውንም ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ ላይ በኦጋዴን አካባቢ ድንበር ጥስው በመግባት አደጋን አድርሰዋል ፡፡ምንም እንኳ ያስቡት ባይሳካለቸውም የኢትዮጵያ አርበኞች ተጋድሏቸውን በየጫካውና በየሽንተረሩ ተያይዘውታል ለአምስት አመታት ያህል ከተካሄዱ ጦርቶች መካከል በድሮው አገው ምድር አውራጃ በአሁኑ አዊ አስ/ዞን ውስጥ አንዱ በጦርነት የአዲስ ቅዳም ጦርነት ነበር፡፡ ይህ ጦርነት የተካሄደው የኢጣሊያን የዳፈጣ ጦር ግንቦት 24/1932 ዓ.ም በሁለት አቅጣጫ ማለትም የእንጅባራው በደቡብና የዳንግላው በስተ ሰሜን የእንጅባራው አድጓሚ ተራራ እንዲሁም የዳንግላው ከአ/ቅዳም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ መትረይስ በመቀየስ ለገበያ የመጣውን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ሲዘጋጅ ጀግኖች የአገው ምድር አባት አርበኞች የተለመደ ሽንፈት አከናንበው መልሰውታል አዲሲቅዳም ከተማ ምንም አይነት ቤት ስላልነበረው ቅዳሜ ቀን ለገቢያ ብዙ ህዝብ ይሰብሰብ ነበር፡፡ይህን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ነበር የጣሊያን ፋሽስት ጦር ቋምጦ የተነሳው በዕለቱም ህዝብ በቦታው የተለያዩ መሳሪያዎችን ለመሸጥና ለመግዛት የመጡ የአገውምድር አባትአርበኞች፣ራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ፣ ፊታውራሪ የኔው አባዲት፣ ፊትአውራሪ ደስታወርቄ፣ቀኝ አዝማች በቀለ ወንድምና ቀኝ አዝማች አባ ደስታ የተሳተፉ ሲሆን በተለይ እና ፊት አውራሪ የኔው አባዲና ከማሳው በመመስግ ፣ራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ከኳሽኒ መሽገው የፋሺስት ነጭ ደጋአመድ አድርገዋል፡፡ ጦርነቱ ከዕለቱ በግምት 4 ስዓት የተጀመረው ቀኑን ሙሉ ውሎ ጽሀይ ግባት ላይ በአገውምድር አርበኞች ድልአድራጊት ተፈፅሟል፡፡በዕለቱ በዱርገ ደሉ የነበሩ ሴቶች ፊታውራሪ ተብለው የተሸለሙ ሲሆን ከጣላትም ሆነ ከአባት አርበኞች የሞተ እንዳለ ሆኖ ብዙ መሳሪያዎችን ማለትም 500 ያህል አልቢን ምኒሽር ፣50 ሽጉጦች ፣8 የእጅ መትረይስ ከጠላት እጅ ተማርከዋል፡፡በማለት በወቅቱ ተሳታፊ የነበሩት አባት አርበኞች በትውስት ይናገራሉ የከተማዋ ገበሬዎች የአዲስ ቅዳም ከተማን ጥንታዊ የገቢያ ማዕከልነት ሲገልፁት በጃን ሆይ ጊዜ አዲስ ቅዳሜ ቀን የገቢያ ማዕከል በመሆንዋ ሀይለኛ የሆነ የገቢያ ምርት የገቢያ ግብዓት ለነበራትየዳንግላ ገበያን ቅዳሜ ቀን በተመሳሳይ ይውል ስለነበር ዳንግላ የገበያ ግብአት በመቀነሱ ወደ ረዕቡ ቀን እንደቀየሩ በጊዜው የነበረው ታሪክ አዋቂ አውራጃ ገዥ ግራ አዝማች አየሁ ጀንበሬያስረዳሉ ሆኖም ግን የደርግ መንግስት ከገባ በኃላ የገብያተኛውን የስራ ቀን እንዲውል ማለትም ቅዳሜ በማህበረሰዱ ዘምድ ስንበት ውይምሀጥማኖታዊ በዓል ተብሎ ስለሚከበር ነው ይህ አዲስ ቅዳም የገበያ ማዕከል በትልቅ ሾላ ዛፍ ስራ ስለነበር በዚህ ጥላ በመጠለል ጠላ፣ አረቄ፣ዳቦና የተለያዩ ነገሮች በተጨማሪ ይሸጥበት እንደነበር ይነገራሉ ገበያው ሰፊና ጥንታዊ በመሆኑ እንስሳት፣ እህል፣ማር፣ቅቤ ፣ሸቀጣ ሸቀጥ ፣ቡናና ሌሎችም ይገበያዩበታል የከተማው አመሰራረት ከተማዋ የተመሰረተችው በሁለት አጥቢያ ዳኛ በሚተዳደር የሽንኩሪ ሚካኤል እና በዚምብሪ ኪዳነ ምህረት ባለአባቶች መሬት ሲሆን ይህቦታ 1936 በፊት የባለአባቶች መሬት እንጂ ምንም አይነት ቤቶች ያልነበሩበት ፣ለከማነትም ያልታቀደ አልፎ አልፎ ቆባ ዛፍ ያለበት እንዲሁም ገበያተኛው የሚገበያይበት ትልቅ የሾላ ዛፍ እንደነበር የቦታው ነዋሪ አባቶች ያስተውሳሉ፡፡ ከጣሊያን ሽንፈት ወረራ በኃላ ፣ጃንሆይ ከውጭ ሀገር ከተመለሱ በኃላ /ማለትም 1936 ዓ.ም/ የአዲስ ቅዳም ከተማ ለገበያ ቦታ ሰፋትና ድምቀት በማመን በወቅቱ የነበሩ አገው ምድር አውራጃ አስተዳዳሪ ደጅ አዝማች ያረጋል እረታ ሰብሳቢነት በባንጃ ወረዳ አስረዳዳሪ ቀኝ አዝማች ቸኮል ጀንበሬ ፣በለኮማ ባንጃ ምክትል አስተዳዳሪነት ፣በፊት አውራሪ ደስታ ወርቄ በተገኙበት ገበያ ቦታ በአካባቢው ህዝብና የመሬት ባለይዞታዎች ፈቃደኝነት የገቢያው ስፋት በመከለሉ ከዚያው በመነሳት ምክትል አስተዳደሩና ወረዳ ቤተ ክህነት እንዲሆነ ተወሰነ፡፡ በ1951 በገቢያው ዙሪያ በአካባቢው ቤት በሰረቱት ከተማዋ መቆርቆር ጀመረች ከዚያ በፊት ለምክትል ወረዳ እናቤተ ክህነት ቢሮ በስተቀር ምንም አይነት ቤት ያልነበረ ሲሆን ከ1951 ጀምሮ ግንወ/ሮ የዝብነሽ ታመነ የተባለች ሴት የመሸታ መሸጫ የዳስ ጎጆ በጊዜው ከነበሩ መሬት ባለአባቶች ጠይቃ ስራች በኋላም እና ወ/ሮ ቦጌ ብዙነህ፣ነጋድራስ ቢረስ፣ አቶ አያሌው ፈንቴ እና ሌሎችም የመሬት ባለአባቶችና ሌላ አካባቢ የመጡ ከባለአባቶች መሬት እየገዙ የሳር ጎጆዎችን መስራት ጀመሩ፡፡ ነጋድራስ ቢረስ ወርቅነህ የከተማዋ ቆርቆሮ ነጋዴ ነበሩ ሲሆን ከአዲስ አበባ በበቅሎ በመጫን አምጥተው ከተማዋን ከሳር ቤት ወደ ቆርቆሮ ቤት በመቀየር ከተማዋም ከገጠር ወደ ከተማ በሚደረገው የነጋዴዎችና ሴተኛ አዳሪዎች ፍልሰት እየሰፋች መምጣቷን የከተማዋ ነዋሪዎች ያበስራሉ ወ/ሮ የዝብነሽ ታመነ የመጀመሪያ መሽታ ቤት/ጠላ እና አረቄ ስትከፍት ወ/ሮ ቦጌ ብዙነሽ መጀመሪያ ከተማ ጠጅ ቤት እንደነበራቸው አባቶች ያወሳሉ መጀመሪያው ሰፈር የዶሮ ማነቂያ ሰፈር ይባላል ስያሜ የተሰጠውም ትንሽ አጣብቂኝ መንገድ ዛሬ ቴሌ ከመሰራቱ በፊት እንደነበር የሰፈሩ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ምንጭ፡- ፋግታ ለኮማ ወረዳ ባህልናቱሪዝም ጽ/ቤት
50476
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%8D%E1%89%A0%E1%88%AD%E1%89%B5%20%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%88%BD%E1%89%B3%E1%8B%AD%E1%8A%95
አልበርት አንሽታይን
በረር እነሆ አልበርት አንሽታይን በማንኛውም ጊዜ ከኖሩት ታላላቅ እና በጣም የታወቁ ሳይንቲስቶች እንደ አንዱ ይቆጠራል። እ.ኤ.አ. በ 1905 ለዶክትሬት ማሟያ ያቀረባቸው ሦስት ፔፐሮች በ20ኛውክ/ዘመን የፋዚክስ እድገት ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበራቸው እና የምእራቡን አስተሳሰብ ወደ ላቀ ደረጃም አሸጋግረዋል እነዚህ ፔፐሮች የብርሃንን ተፈጠሮአዊ ቅንጣትን ያወያዩ በሞለኪውላዊ እንቅስቃሴ ላይ መግለጫ የሰጡ እና የአንፃራዊነት ልዩ ንድፈ ሃሳብን ያስተዋወቁ ናቸው፡፡ አንስታይን ባህላዊ ሳይንሳዊና ግምቶችን በመገምገም ማንም ጋር ያልደረሰበትን ድምዳሜ በማምጣት ዝነኛ ሆኗል ምንም እንኳን የሰላም እና የጽዮናዊነት ጠንካራ ደጋፊ የነበረ ቢሆንም በማህበራዊ ተሳትፎው አምበዛም አይደለም። እዚህ ስለ ጋንዲ ተወያይቶ እዛ አመፅን ያወድሳል ይሉታል አንዳንድ ነቃፊዎቹ፡፡ ትወልደ ጀርመን አሜሪካዊ የፊዚክስ ሊቅ የኖቤል ተሸላሚ የአንፃራዊነት ንድፈ ሀሳብ ፈጣሪና የብርሃን ቅንጣት ባህሪይ በተመለከተ ደፋር መላምት ያስቀመጠ። ምናልባትም የ20 ኛው ክፍለዘመን እውቅ ሳይንቲስት አንሽታይን እ.ኤ.አ. ማርች 14 ቀን 1879 በኡልም ተወለደ የኤሌክትሪክ ማሽን የሚያመርት አነስተኛ ሱቅ ባላቸው ቤተሰብ ጋር ሙኒክ ውስጥ አደገ እስከ ሦስት ዓመቱ ድረስ መናገር የማይችል ቢሆንም፣ በወጣትነቱ ግን ስለ ተፈጥሮ የማወቅ ጉጉት እንዳለው እና ከባድ የሂሳብ ፅንሰ ሀሳቦችን የመረዳት ችሎታውን አሳይቷል በ 12 ዓመቱ እራሱን የኢሊሲዲያን ጂኦሜትሪ አስተማረ አንሽታይን ሙኒክ ውስጥ የሚገኝ ትምህርት ቤት ሪስትረክሽን የበዛበትንና ኢሀሳባዊ መንፈስ ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት በእጅጉይጠላ ነበር ቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ በደረሰባቸው ኪሳራ ምክንያት ጀርመንን ለቀው ወደ ሚላን ሲያቀኑ በዚያን ጊዜ የ 15 ዓመት ወጣት የሆነው አንስታይን የሚጠላውን ትምህርት ለማቆም ሰበብ አገኘ በዚች አለም ውስጥ የራሱን መንገድ መከተል እንዳለበት ግልጽ ሆነ ከሚላን የአንድ ዓመት የጥሞና ቆይታ በኋላ ወደ ስዊዘርላንድ በማምራት በአራኡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቅቆ ዙሪክ በሚገኘው የስዊስ ፌዴራል የቴክኖሎጂ ተቋም ገባ። አንስታይን እዚህም በነበረው የመማሪያ ዘዴዎች አልተደሰተም። ብዙውን ጊዜ ትምህርቱን ያቌርጣል ጊዜውንም ራሱን ፊዚክስ በማስተማር ወይም የሚወደውን ቫዮሊን ለመጫወት ይጠቀምበት ነበር። ፈተናዎቹን የሚያልፈውም የክፍል ጓደኛው ኖት በመውሰድና በማጥናት በመሆኑና በዚሁ መንገድ ከተቌሙ ሊመረቅ በመቻሉ ፕሮፌሰሮቹ በሱ ብዙም ደስተኞች አልነበሩም ሪኮሜንዴሽን ላለመጻፍ አስከመወሰን አድርሶአቸዋል፡፡ አንስታይን ለሁለት ዓመታት ያህል ቱቶርና እና ተተኪ መምህር ሆኖ አገልግሏል እ.ኤ.አ. በ 1902 በርን ውስጥ በሚገኘው የስዊስ የፈጠራ ባለቤትነት ጽ የምርመራ ኃላፊ ሆኖም አገለገለ አንስታይን በ 1905 ለዶክተሬት ማሟያ በሞለኪውሎች ስፋት ላይ ሥነ-ፅሁፋዊ ጥናት አቅርቦ ከዙሪክ ዩኒቨርሲቲ ዶክትሬቱን ከተቀበለ በኋላ ለ20 ኛው ክፍለዘመን የፊዚክስ እድገት እድገት ማዕከላዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ሶስት የስነ-ፅሁፍ ወረቀቶችም አሳተመ የመጀመሪያው በብሮናዊያን ሞሽን ጽሁፍ ላይ በፈሳሽ ውስጥ ስለሚሰራጩ ቅንጣቶች እንቅስቃሴ ትርጉም ያለው ትንበያዎችን አድርጓል እነዚህ ግምቶች ም በኋላ ላይ በሙከራ ተረጋገጡ ሁለተኛውና የኖቤል ሽልማት ያስገኘለት የፎቶ ኤሌክትሪክ ተፅእኖ ይባላል የብርሃንን በህርይ በተመለከተ አብዮታዊ መላምት የያዘ ድንቅ ተዎሪ-፡፡ አንስታይን ሀሳብ ሲያቀርብ በተወሰኑ ሁኔታዎች ስር ብርሃን ቅንጣቶች እንደሆኑ ተደርገው ሊቆጠሩ ይችላሉ የሚለውን ብቻ ሳይሆን፣የማንኛውም የብርሃን ክፍል የተሸከመው ኃይል ፎቶን ተብለው የሚጠሩና ከጨረር ድግግሞሽ ጋር ተመጣጣኝ መሆናቸውን ገምቷል የዚህ ቀመር ነው የጨረራ ኃይል ፕላክ ኮንስታነት ተብሎ የሚታወቀው ዩኒቨርሳል ኮንስታንት ደግሞ የጨረሩ ድግግሞሽ ነው በብርሃን ሞገድ ውስጥ ያለው ኃይል በኢንዲቪጅዋል ዩኒት ወይም በኳንታ ውስጥ ይተላለፋል የሚለው ምክረ ሀሳብ የብርሃን ሀይል ቀጣይነት ያለው ሂደት መገለጫ ነው ከሚለው የመቶ ዓመት ባህልና አስተሳሰብ ጋር ይጋጫል። እንደ እውነቱ ከሆነ አንስታይን ያቀረበውን ሃሳብ ማንም አልተቀበለም ነበር በሂሳብ ቀመር ያሸበረቀ የሃሰት ክምር ነው እስከማለት የደረሱ ሰዎችም ነበሩ በእርግጥ የአሜሪካው የፊዚክስ ሊቅ ሮበርት አንድዬይ ሚልኪን ከአስር አመት በኋላ ፅንሰ-ሀሳቡን በተከታታይ ሲያረጋግጥ በውጤቱ በጣም ተገርመ፤ ተደመመ፤ ምህታትም መሰለው በተወሰነ ደረጃም ተጨንቀ የኤሌክትሮኒካላዊ ጨረር ተፈጥሮን መረዳትን ዋና ትኩረቱ የነበረው አንስታይን በመቀጠልም የብርሃን ሞገድ እና ቅንጣቶች ሞዴሎች ስብስብ የሆነ ፅንሰ-ሀሳብ እንዲፈጠር አጥብቆ አሳስቧል እንደገናም በጣም ጥቂት የፊዚክስ ሊቃውንት የተረዱት ወይም ለእነዚህ ሀሳቦች ፍለጎት ያላቸው ሰዎችንም አገኘ አንስታይን በ 1905 ሦስተኛው ዋና ጽሑፍ “ኤሌክትሮማዳይናሚክስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ” የአንፃራዊነት ልዩ ጽንሰ-ሀሳብ ተብሎ የሚያካትት ከእንግሊዛዊው የሂሣብ እና የፊዚክስ ሊቅ ሰር ይስሐቅ ኒውተን ተፈጥሮአዊ ፈላስፋ ጀምሮ (የፊዚክስ ሊቃውንት እና ኬሚስቶች የቁስ እና ጨረር ምንነት እና በአንድ በተዋሃደ የዓለም ስዕል ላይ እንዴት እንደተገናኙ ለማወቅ ሞክረዋል። ሜካኒካል ህጎች መሠረታዊ የሆኑት ስፍራው መካኒካዊ የዓለም እይታ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የኤሌክትሪክ ህጎች መሠረታዊ መሆናቸውም የኤሌክትሮማግኔቲክ የዓለም እይታ በመባል ይታወቃል ሆኖም ማንኛውም አቀራረብ ለጨረር (ለምሳሌ መብራት) እና ከተለያዩ የማመሳከሪያ ክፈፎች ሲታይ በተመሳሳይ ጊዜ መስተጋብር እና ታዛቢ በእያንቀሳቀሱ መስተጋብራዊ ምልከታዎች ላይ አንድ ወጥ የሆነ ማብራሪያ መስጠት አልተቻልም አንስታይን እነዚህን ችግሮች ለአስር ዓመታት ካሰላሰለ በኋላ እ.ኤ.አ. በ 1905 የፀደይ ወቅት የችግሩ ማዕቀፍ በቁሳዊ ፅንሰ-ሀሳብ ሳይሆን በመለካት ፅንሰ-ሀሳብ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ተገነዘበ የሁለት ርቀት እና በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ጊዜ የሚከናወኑ መሆናቸውን በሚመለከት በፍርድ ውሳኔዎች ላይ የሚመረኮዝ የሁሉም የጊዜ እና የቦታ መለኪያዎች በፍርድ ላይ እንደሚወሰኑ መገንዘቡ በልዩነት ጽንሰ-ሃሳቡ እምብርት ላይ ነበር ይህ በሁለት ድህረ-ገፅታዎች ላይ የተመሠረተ ፅንሰ-ሀሳብ እንዲያዳብር አነሳሳው-የግንኙነት መርህ የአካል ህጎች በሁሉም የውስጥ ውስጥ ባሉ የማጣቀሻ ስርዓቶች ውስጥ አንድ አይነት ናቸው የብርሃን ፍጥነት ቋሚነት የተንተራሰ ነበር። አንስታይን እንደበየነው በጠረፍ ውስጥ የብርሃን ፍጥነት ባማናቸውም ተመልካቾች (ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ) ዘንድ አንድ ነው፣ በዚህ ምክንያት በተንቀሳቃሽ ሳጥን ውስጥ የሚፈጠር ኩነት የሚወስደው የጊዜ ቆይታ ከሳጥኑ ውስጥ ላለ ተመልካችና ከሳጥኑ ውስጥ ላለ ተመልካች አንድ አይደለም ብሏል የአንሽታይንን ሥራዎችን አስቸጋሪ ያደርገው የተወሳሰበ ሂሳብ ወይም ቴክኒካዊ ምስጢሮች ስለነበሩት አይደለም ችግሩ የመነጨው ሃሳብና ዕምነት ላይ ይወድቃል፡፡ በጥሩ ጽንሰ ሃሳብ ባህሪይ ላይ ባለው አምነት እንዲሁም በልምድ እና በንድፈ ሀሳብ መካከል ስላለው ግንኙነት የተናሳ ነው። አናሽታይን ብቸኛው የእውቀት ምንጭ ተሞክሮ ነው የሚል ትልቅ ዕምነት አለው፣ የሳይንሳዊ ፅንሰ-ሀሳቦች የተስተካከለ አካላዊ አስተሳሰብ ነፃ ፈጠራዎች እንደሆኑና ጽንሰ-ሀሳቦች የተመሠረቱባቸው ትምህርቶች ከሙከራ ጋር በምንም መንገድ መገናኘት እንደማይችሉ ያምን ነበር። ስለሆነም ጥሩው ጽንሰ-ሐሳብ ለአካላዊው ማስረጃ ተጠያቂነት ቢያንስ ጥቂት ድውረቶች ከሚያስፈልጉበት አንዱ ነው ይህ ሁሉምን የአንስታይን ሥራ ባህሪ የሆነው ይህ የፖላቲስ ድንገተኛ ስራ የእርሱ ባልደረቦች ድጋፍ እስኪያደርጉ ድረስ ስራው በጣም ከባድ እንዲሆን ያደረገው አንስታይን ወሳኝ የሆኑ ደጋፊዎች ነበሩት የእሱ ዋና ደጋፊ ደግሞ የጀርመን የፊዚክስ ሊቅ ማክስ ፕላክ ነበር ኮከቡ በፊዚክስ ማህበረሰብ ውስጥ መነሳት ከጀመረ በኋላ ለአራት ዓመታት በፓተንት ቢሮው ውስጥ ቆይቷል ከዚያ በጀርመን ተናጋሪ አካዳሚ ዓለም በፍጥነት ወደ ላይ ወጣ የመጀመሪያዎቹ የትምህርት ቀጠሮውም በ 1909 በዙሪክ ዩኒቨርሲቲ ነበር በ 1911 በፕራግ ወደ ጀርመንኛ ተናጋሪ ዩኒቨርስቲ ተዛወረ እና በ 1912 በዛርሪክ ውስጥ ወደ ስዊስ ብሔራዊ ፖሊቴክኒክ ተመለሰ በመጨረሻም በ 1914 በርሊን በሚገኘው የኪኪ ዊልሄልም የፊዚክስ ተቋም ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል፡፡ አንሽታይን እ.ኤ.አ. በ 1907 የፈጠራ ባለቤትነት መስሪያ ቤትን ለቆ ከመሄዱ በፊት የአንጻራዊነት ጽንሰ ሃሳብን ማስፋትና ከሁሉም አስተባባሪ ስርዓቶችጋር አሰናስሎ የማጠቃለል ሥራ ጀመረ የሚዛናዊነት መርሆን ጠቅሶ ሲያስረዳ ግራቪቴሽናል ፊልድ ከማጣቀሻ ፍሬም ፍጥነት ጋር ተመጣጣኝ በሚል ነው ለምሳሌ በሚንቀሳቀስ ሊፍት ላይ ያሉ ሰዎች በመርህ ደረጃ የሚያንቀሳቅሳቸው ኃይል በስበት ኃይል ወይም ቌሚ ሊፍቱ ፍጥነት እንደሆነ መወሰን አይችሉም። የአንጻራዊነት አጠቃላይ ፅንሰ-ሀሳብ እስከ 1916 ድረስ አልታተመም በዚህ ፅንሰ-ሀሳብ ውስጥ ከዚህ በፊት ተለውጦ የነበረው የአካላት መስተጋብር የቦታ-ጊዜ ጂኦሜትሪ ተፅእኖ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጿል (ሶስት-ልኬት ስፋት የሂሳብ አገባብ ሶስት አቅጣጫዎችን ከኢሉሲዲያናን ቦታ እና ጊዜ እንደ አራተኛው ልኬት))። አንስታይን በአጠቃላይ የተዛመደ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅንሰ-ሀሳብ መሠረት ቀደም ሲል ባልተገለፁት የፕላኔቶች የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ላሉ ያልተለመዱ ልዩነቶችን በመጥቀስ እንደ ፀሐይ ያለ ትልቅ አካል ባለው የከዋክብት ብርሃን መታጠፍን ተንብዮ ነበር የዚህ የመጨረሻ ክስተት ማረጋገጫ በ 1919 የታየው የፀሐይ ግርዶሽ ነው አንሽታይንም የሚዲያን ትኩረት ሳበ ዝናውም በዓለም ዙሪያ ናኘ ቤሄደበት ፎቶግራፍ መነሳት፤ የክብር ተጋባዥ የአለም ዜጋ መሆን ሆነ ሥራው ስፔሻል እ.ኤ.አ. በ 1905 አልበርት ባሳተመው የአንጻራዊነትን ልዩ ፅንሰ-ሀሳብ ላይ በዚህ ጽንሰ-ሀሳብ መሠረት በማስና በኃይል መካከል ያለው ግንኙነት የሚገለጠው በ 2 ሲሆን የተወሰነ መጠን ካለው ኃይል ይያያዛል )ይህ ማስ በብረሀን ፍጥነት ስኩዬር ከተባዛ ኃይል ጋር እኩል ነው )። በጣም ትንሽ የሆነ ቁስ ከፍተኛ መጠን ካለው ኃይል ጋር እኩል ነው። ለምሳሌ 1 ኪ.ግ ቁስ ሙሉ በሙሉ ወደ ኃይል ከተቀየረ ሲፈነዳ ከሚለቀው 22 ሜጋ ዋት ኃይል ጋር እኩል ይሆናል። በአጭሩ አንድ ቁስ ሲታመቅ በከፍተኛ ኃይል ይፈነዳል፡፡በአለማየሁ
52659
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%8B%B4%E1%88%8B%20%E1%8A%93%E1%89%AB%E1%88%AE%20%E1%89%A4%E1%88%8E
አዴላ ናቫሮ ቤሎ
አዴላ ናቫሮ ቤሎ 1968 ተወለደ ቲጁአና, ባጃ ካሊፎርኒያ የሜክሲኮ ዜግነት ሞያ ጋዜጠኛ ድርጅት የ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት (2007) ድፍረት በጋዜጠኝነት ሽልማት (2011) አዴላ ናቫሮ ቤሎ (እ.ኤ.አ. በ 1968 በቲጁአና ባጃ ካሊፎርኒያ ሜክሲኮ ተወለደ) የሜክሲኮ ጋዜጠኛ እና የቲጁዋና ሳምንታዊ መጽሔት ዜታ ዋና ዳይሬክተር ነው። በ1980 የተመሰረተው በሜክሲኮ የድንበር ከተሞች ስለተደራጁ ወንጀሎች፣ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እና ሙስና በተደጋጋሚ ከሚዘግቡ ጥቂት ህትመቶች አንዱ ነው። ለዜታ የሚሰሩ ብዙ አርታኢዎች እና ዘጋቢዎች ተገድለዋል, ሄክተር ፌሊክስ ሚራንዳ, የዜታ መስራች እና ተባባሪ አርታኢ ፍራንሲስኮ ኦርቲዝ ፍራንኮን ጨምሮ. የመጀመሪያ ህይወት የናቫሮ የመጻፍ ፍላጎት ከልጅነቷ ጀምሮ ነበር፣ በመጽሐፍ በተሞላ ቤት ውስጥ አሳለፈች። ምንጣፍ ሻጭ አባቷ በቀን ቢያንስ አራት ጋዜጦችን ያነብ ነበር። በኮሌጅ ውስጥ በኮሙኒኬሽን ተምራለች። እዚያ በነበረችበት ጊዜ፣ ኢየሱስ ብላንኮርነላስ ታዋቂው የቲጁአና የምርመራ ጋዜጠኛ፣ ወደ ንግግር መጣ፣ እና ናቫሮ ለዜታ መጽሔት ፖለቲካን የሚሸፍን ሥራ እንዲሰጠው ጠየቀው። ናቫሮ በ1990 ተቀጠረች፣ እና ብላንኮርንላስ አማካሪዋ ሆነች። የጋዜጠኝነት ሙያ የዜታ ዳይሬክተርነትን ከመውሰዱ በፊት ናቫሮ ለመጽሔቱ ዘጋቢ ሆኖ ሰርቷል, በ 1994 የቺያፓስን ግጭት ይሸፍናል. እሷም ለተሰኘው መጽሔት አንድ አምድ አበርክታለች. የመጀመሪያ ዘገባዋ ያተኮረው በሜክሲኮ የረዥም ጊዜ ገዥው ተቋማዊ አብዮታዊ ፓርቲ ላይ ቢሆንም፣ አባላቶቹ ቢሮ ከያዙ በኋላ በብሔራዊ የድርጊት ፓርቲ ውስጥ ስላለው ሙስና ሪፖርት ማድረግ ጀምራለች። እ.ኤ.አ. በ 1994 ናቫሮ በወረቀቱ አምስት ሰው የአርትዖት ሰራተኛ ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች ብላንኮርኔላስ በ2006 በካንሰር ህይወቱ አለፈ፣የመጽሔቱን ቁጥጥር ለናቫሮ እና ለልጁ ሴሳር ሬኔ ብላንኮ ቪላሎን ትቶ ነበር። በበርካታ አዘጋጆቹ ሞት የተዳከመው ብላንኮርንላስ የዜታ ለውጥን የማበረታታት ችሎታውን መጠራጠር ጀመረ እና መጽሔቱን በሞት ለመዝጋት አስቦ ነበር፣ ነገር ግን ናቫሮ እና ብላንኮ መጽሔቱ እንዲቀጥል እንዲፈቅድ ገፋፉት። የመጽሔቱ አዲስ ዳይሬክተር እንደመሆኑ ናቫሮ "ጋዜጠኛ እራሱን ሳንሱር ባደረገ ቁጥር መላው ህብረተሰብ ይሸነፋል" በማለት የብላንኮርንላስን የተደራጁ ወንጀሎች ከፍተኛ ስጋት የመዝገቡን ባህል ቀጠለ። ጠባቂዎቹ የዜታ አምደኛ እና ተባባሪ መስራች ሄክተር ፌሊክስ ሚራንዳ የገደሉትን የቀድሞ የቲጁአና ከንቲባ ጆርጅ ሃንክ ሮን ምርመራን ተቆጣጠረች። እ.ኤ.አ. በ 2011 ሃንክ በህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ክስ መታሰሩን ተከትሎ መጽሔቱ በቤቱ ውስጥ የተገኙትን 88 ሽጉጦች ዝርዝር እና ተከታታይ ቁጥሮች አሳትሟል ጉዳዩ ተሸጧል፣ እና የገጽ እይታዎች ብዛት የመጽሔቱ ድረ-ገጽ እንዲበላሽ አድርጎታል። ሃንክ በማስረጃ እጦት ቢፈታም ናቫሮ በፊሊክስ ግድያ ውስጥ ተሳትፏል ተብሎ እንዲታሰር ግፊት ማድረጉን ቀጠለ። ዘታ በ 2009 እና 2010 ለሜክሲኮ ጦር በጣም አዛኝ በመሆን እና የተጠረጠረውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ለመሸፈን ባለመቻሉ ተወቅሷል; መጽሔቱ የጦር ጄኔራሎችን በየአመቱ "የአመቱ ምርጥ ሰው" ብሎ ሰይሟል። በጃንዋሪ 2010 የዩኤስ ህግ አስከባሪዎች ከቲጁአና ካርቴል የሞት ዛቻ ለናቫሮ አሳውቀዋል፣ ይህም የሜክሲኮ መንግስት ሰባት ወታደሮቿን ጠባቂ አድርጎ እንዲመድብ አድርጓል። ከአንድ ወር በኋላ፣ በዜታ ቢሮዎች ላይ የእጅ ቦምብ ጥቃት ሲያደርሱ የነበሩ አስር ሰዎች ታሰሩ። ሽልማቶች እና እውቅና እ.ኤ.አ. በ 2007 ናቫሮ ጋዜጠኞችን ለመከላከል ከኮሚቴው ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት አሸንፏል ሽልማቱ የሚሰጠው ጥቃት፣ ዛቻ ወይም እስራት ሲደርስ የፕሬስ ነፃነትን በመጠበቅ ድፍረት ያሳዩ ጋዜጠኞች ነው። ሲፒጄ ስለ ናቫሮ ቤሎ እና ዜታ አጭር ቪዲዮ አዘጋጅቷል። የ2011 አለም አቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን ድፍረት በጋዜጠኝነት ሽልማት ተሸላሚ ነች። እ.ኤ.አ. በ1999 ናቫሮ “ፍልሰት” በሚል መሪ ቃል በስድስት ከተማ የአሜሪካ ጉብኝት እንዲያደርግ በዩኤስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ተሰጠው። እሷም በስፔን ሀገር የተሰጠውን የ 2008 ሽልማት ኦርቴጋ ተሸልሟል በኤዲቶሪያል ፐርፊል, አርጀንቲና የተሰጠው የ 2009 ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት; እና በ2009. እ.ኤ.አ. በ2010፣ የሚዙሪ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት ለሚዙሪ የክብር ሜዳሊያ ለጋዜጠኝነት ልዩ አገልግሎት ሰጥቷታል። እ.ኤ.አ. በ 2012 በውጭ ፖሊሲ መጽሔት 100 ሆና ተሰየመች። በሚቀጥለው ዓመት በፎርብስ መጽሔት "በሜክሲኮ ውስጥ 50 በጣም ኃይለኛ ሴቶች" ውስጥ ተዘርዝራለች. ናቫሮ እና ዜታ በ በርናርዶ ሩይዝ ዘጋቢ ፊልም ውስጥ ተዘርዝረዋል በታዋቂው ባህል ውስጥ የአንድሪያ ኑኔዝ ባህሪ፣ በናርኮስ፡ ሜክሲኮ ሲዝን ሶስት በሉዊሳ ሩቢኖ የተጫወተው፣ በናቫሮ ላይ የተመሰረተ ነው። ዋቢዎች "አዴላ ናቫሮ ቤሎ". (በጣሊያንኛ)። 2009. ኦክቶበር 4 2015 ከዋናው የተመዘገበ. ነሐሴ 26 ቀን 2012 ተገኝቷል። "ሲፒጄ አምስት ጋዜጠኞችን ሊያከብር" የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ. 2007. ከዋናው የተመዘገበ በሴፕቴምበር 3 ቀን 2012. ነሐሴ 26 ቀን 2012 ተገኝቷል። ፒተር ሮው (ነሐሴ 26 ቀን 2012)። "የሜክሲኮ ጋዜጠኛ በመስቀል ላይ" ዩ-ቲ ሳን ዲዬጎ በታህሳስ 23 ቀን 2015 ከዋናው የተመዘገበ። ነሐሴ 26 ቀን 2012 የተገኘ። አን-ማሪ ኦኮኖር (ጥቅምት 26 ቀን 2011)። "በአታላይ ቲጁአና፣ አዴላ ናቫሮ ቤሎ የሚያሰጋቸው አደጋዎች ሕይወት ወይም ሞት ናቸው።" ዋሽንግተን ፖስት የካቲት 10 ቀን 2012 ተመልሷል። ቢል ማንሰን (መስከረም 23 ቀን 1999)። "አዴላ አሜሪካ" የሳን ዲዬጎ አንባቢ። ኤፕሪል 10 ቀን 2012 ተመልሷል። አድሪያን ፍሎሪዶ (መጋቢት 16 ቀን 2012) "የሪፖርተሮ ፊልም በሜክሲኮ ውስጥ ለጋዜጠኞች አደገኛነትን ያሳያል" ፍሮንቴራስ። በሴፕቴምበር 17 ቀን 2012 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ነሐሴ 26 ቀን 2012 የተገኘ። ሄክተር ቶባር (ህዳር 24 ቀን 2006)። "ኢየሱስ ብላንኮርንላስ፣ 70፤ ደራሲ የአደንዛዥ እፅ ጋሪዎችን ድርጊት አጋልጧል።" ሎስ አንጀለስ ታይምስ. ነሐሴ 25 ቀን 2012 ተመልሷል። "የአለም አቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን ድፍረት በጋዜጠኝነት ሽልማቶች" 2011. ከዋናው የተመዘገበ ጁላይ 20 ቀን 2012. ነሐሴ 26 ቀን 2012 ተገኝቷል። "ቲጁአና ጋዜጣ በአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች አልተወደደም" ዜና 4 ማርች 2012. ኦገስት 27 ቀን 2012 ተገኝቷል። "የጥቅም ቪዲዮዎች አዴላ ናቫሮ ቤሎ". የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ. ኤፕሪል 10 ቀን 2012 ተመልሷል። "አዴላ ናቫሮ ቤሎ". የዓለም የፍትህ መድረክ. በጁን 21 ቀን 2013 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። በኤፕሪል 10 ቀን 2012 የተገኘ። "የ ምርጥ 100 ዓለም አቀፍ አስተሳሰቦች". የውጭ ፖሊሲ. ህዳር 28 ቀን 2012 ከዋናው የተመዘገበው በኖቬምበር 30 ቀን 2012 ነው። ህዳር 28 ቀን 2012 የተገኘ። "አዴላ ናቫሮ በሜክሲኮ ውስጥ ካሉ 50 በጣም ኃይለኛ ሴቶች መካከል". ዘታ(በስፓኒሽ)። 25 ሴፕቴምበር 2013. ኦክቶበር 10 2013 ከዋናው የተመዘገበ። ኦክቶበር 10 ቀን 2013 የተገኘ። "ሪፖርተሮ". ፒ.ቢ.ኤስ. 2012. በጥር 17 ቀን 2013 ከመጀመሪያው የተመዘገበ። ነሐሴ 25 ቀን 2012 የተገኘ።አዴላ ናቫሮ ቤሎ አዴላ ናቫሮ ቤሎ ውጫዊ አገናኞች ኦፊሴላዊ ድር ጣቢያ አዴላ ናቫሮ ቤሎ በትዊተር ላይ አዴላ ናቫሮ ቤሎ በፌስቡክ አዴላ ናቫሮ ቤሎ ጋዜጠኞችን ለመከላከል በኮሚቴ ሪፖርተሮ በዜታ ታሪክ ላይ የ ዘጋቢ ፊልም ምድቦች:የሲፒጄ አለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት አሸናፊዎች የሜክሲኮ ሴት ጋዜጠኞች የሜክሲኮ ዝርያ ያላቸው ጣሊያናዊ 1968 ልደት ከባጃ ካሊፎርኒያ የመጡ ፀሐፊዎች ከቲጁአና የመጡ
16106
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8B%9E%E1%88%AB%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%88%AD%20%E1%8D%8D%E1%8A%AB%E1%88%AC%20%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%88%8D%20%E1%8D%AB
የዞራስተር ፍካሬ ክፍል ፫
ክፍል "ከትልቁ ተራራየ ፊት ቆምኩ፣ ከሩቁም መዋተቴ እንዲሁ። ለዛም ስል መጀመሪያ ወደ ጥልቁ ገደሌ፣ ወደ የሚያመኝ ስፍራ፣ ወደጥቁሩ ጎርፌ መውርድ አለብኝ" በማለት ዞራስተር ከተከታዮቹ ተለይቶ ከባዱን ስራውን ለመፈጸም ባዘነ። ግቡም የ"በላይ ሰው"ን ማስተማር አቁሞ እራሱ የበላይ ሰው ለመሆን ነበር። "መሰላል ከሌላችሁ በራሳችሁ ጭንቅላት ላይ መወጣጣትን ልመዱ፤ በሌላስ በምን መንገድ ወደላይ ለመውጣት ትሻላችሁ? በጭንቅላታችሁ፣ ከልባችሁ እርቃችሁ... ከዋክብቶቻችሁ ሳይቀሩ ከግራችሁ በታች እስኪሆኑ ወደ ላይ ተወጣጡ!" ዞራስተር በከተሞችና በባህር ጠረፎች በሚዋትትበት ዘመን መንፈሱን ወደታች ስለሚጎትተው የስበት ሃይል ማውጣት ማውረድ ጀመረ። ይህ ሃሳቡን ወደታች የሚጎትተው መንፈስ ባለፈው ክፍል አዋቂው የነገርው የ«ሁሉ ነገር ከንቱነት ነበር። ሁሉም ወደ ላይ የተወረወረ ነገር ወደ መሬት መልሶ ይወድቃል፣ ስለሆነም ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው!» ዞራስተር ይህን ወደታች የሚጎትት የስበት ሃይል ለማሸነፍ የሁሉ ነገር ዘላለማዊ መመላለስን ሃሳብ ማውጣት ማውረድ ጀመረ። በአለም ላይ ያለው የቁስ ብዛት የተወሰነ ሲሆን ጊዜ ግን የማያልቅ ጅረት ነው። ስለሆነም በቁስ ውስጥ ያሉት እያንዳንዱ አተሞች የሚደረደሩበት መንገድ ስፍር ቁጥር ባይኖርውም... ከጊዜ ወሰን የለሽ የትየለሌንት አንጻር እያንዳንዱ የአቶም አደራደር ዘዴ ተመልሶ ይመጣል። እያንዳንዱ ቁስ ያለፈበትን አደራደር በዘመናት ይደግማል። ሁሉም ነገር ተመልሶ ይመጣል። ሁሉም ኅልው ነገር ካሁን በፊት ኅልው ነበር ስለዚህ መጭው ዘመን እንደ በፊቱ ነው። "ኦ! ዞራስተር" አሉ እንስሳቶቹ "ሁሉም ነገር ይሄዳል፣ ሁሉም ነገር ተመልሶ ይመጣል፣ ለዘላለም የህልውና ጎማ ይሽከረከራል። ሁሉም ይሞታል፣ ሁሉም እንደገና ያብባል፣ የህይወት ቀለበት በንዲህ መልኩ ለዘላለም ይቀጥላል። ሁሉም ይሰበራል፣ ሁሉም እንደገና ይጋጠማል፣ ላለም እስከ ዘላለም አንድ አይነት የኅልውና ቤት ይገነባል። ሁሉም ይለያያል፣ ሁሉም ከሁሉ ጋር እንደገና ይገናኛል፣ ለዘለዓለም የኅልውና ቀለበት በራሱ ላይ እንዲህ ይሽከረከራል።" ጊዜ እንደ መስመር ቀጥ ብሎ የተሰመረ ሳይሆን፣ ላለም እስከ ዘላለም ክብ ሰርቶ በራሱ ላይ የሚሽከረከር እንጂ። "ቀጥ ያለ ሁሉ ውሸት ነው፣ ሁሉም እውነት የተንጋደደ ነው! ጊዜ ራሱ ክብ ነው!" ነገር ግን የዘላለም መመላስ ዞራስተርን ከማስደስተ ይልቅ በጣም በጠበጠው። በዚህ ፍልስፍና መሰረት ሁሉ የሰው ልጅ የበላይ-ሰው ለመሆን የሚያደርገው ጥረት መና ሆነ እንደገና ወደ ነበረበት ዝቅተኛ ስብእና ጊዜውን ጠብቆ ይመለሳል። የበላይ ሰው ማለት የሰው ልጅ በትግል የወጣው ተራራና ከዚህም ተራራ ተነስቶ ወደ የበለጠ ከፍታ የሚወጣጣበት ሳይሆን በአዙሪት ውስጥ ያለ አንድ አልባሌ ነጥብ ሆነ። ሃሳቡ ዞራስትራን ክፉኛ አውኮት ሲቆዝም የአንድ ወጣት እረኛ ታሪክ በራዕይ መልኩ ታየው። እረኛው ጉሮሮ ውስጥ ጥቁር እባብ ተሰንቅሮ መተንፈሻ አሳጣው። እባቡንም ከጉሮሮው መንግሎ ለማውጣት የማይቻል ሆነ። በዚህ ጊዜ ዞራስተር ድምጹን ከፍ አድርጎ "እራሱን ግመጠው!" ብሎ ለዕረኛው ጮኽ። ዕረኛውም የተባለውን በማድረግ የእባቡን እራስ ቱፍ ሲል የነጻነትን ሳቅ ያቀልጠው ጀመር። ከዚህ ጀምሮ ዞራስተር አንድና አንድ አላማ ብቻ ህይወቱን ገዛ፣ እርሱም ወደታች የሚጎትተውን መንፈስ በማሸነፍ ልክ እንደ እረኛው የነጻነቱን ሳቅ መሳቅ። ዞራስተር ከብዙ ጉዞ በኋላ ከተራራው ዋሻ ደረስ። በዚህ ክፍል መጨረሻ ዞራስተር ያወከውን ወደታች የሚጎትተውን መንፈስ ሲያሸንፍ እናነባለን። የዘላለም መመላስን ተስፋ አስቆራጭ ሃሳብ ያሸነፈው እንዲህ ነበር፡ ጊዜ ክብ ከሆነ፣ እክቡ የትኛው ላይ ኅልው እንደሆን (የት ላይ እንደምንኖር) ምንም ለውጥ አያመጣም፣ በየትኛው የዕድገት ደረጃ ላይ ኅልው መሆናችንም ምንም ለውጥ አያመጣም፣ "ሁሉም ቅጽበት ላይ ኅልውና ይጀመራል... መካከሉ ሁሉም ቦታ ነው።" ብዙ ሰወች ባለፈው ዘመን ይኖራሉ (ማለት በትውፊት፣ ባህል፣ ካለፉት ዘመናት በተወረሱ የግብረገብ ህግጋት፣ ወዘተ...ስር)። ዞራስተር ደግሞ ወደፊት በሚመጣው፣ ባልተፈጠረው አለም ባህል ይኖር ነበር። ሆኖም ግን ዞራስተር እንደተገነዘበ ያለፈውና መጭው ዘመን ምንም ዋጋ የላቸውም፣ ህይወትን መኖር በአሁኗ ቅጽበት ነው። የህይወት ትግል የሚካሄደው በዚች ቅጽበት ሲሆን ህይወትም የሚገለጸው ኗሪው በትግሉ ውስጥ በሚያሳየው ብርታት ነው። ከዚህ አንጻር የዘላለም ምልልስ ተስፋ የሚያስቆርጥ ጽንሰ ሃሳብ ሳይሆን ከሃይማኖት ውጭ የሆነ አዲስ አይነት የሚያሰደስት ዘላለማዊነት ሆነ። ስለሆነም ዞራስተር ከነበረበት ተውከት ዳነ። ለዚህም ሲል መዝፈንና መደነስ ጀመረ። መዝፈንና መደነስ ከመናገር አንጻር የበለጠ ሃይል አላቸው፡ መናገር ከሰውነታችን የተቆረጠ፣ የንቃተ ኅሊና ስራ ሲሆን መዝፈንና መደንስ ግን ከሰውነታችን ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴወች ስለሆኑ ንቃተ-ኅሊናንና አካላታችንን አንድ ላይ የሚያሳትፉ ስራወች ናቸው። መዝፈንና መደነስ የሚችል ሰው ሙሉ ስለሆነ ህይወቱም ከአዋቂ አስተማሪወች ይልቅ በአሁኗ ቅጽበት የሚካሄድ ነው። ዞራስተር አስተማሪ በነበረበት ጊዜ የተሰማው ጎደሎነት ከዚህ አንጻር ነው። መዝፈንና መደነስ ባለመቻሉ ጎድሎ ነበር። ለማጠቃለል ያክል፣ የመጽሃፉ የመጀመሪያ ክፍል የ"በላይ ሰውን" መምጣት የሚሰብክ ሲሆን፣ እጅግ በለመለሙና ጣፋጭ በሆኑ እይታወች የታጀበ ነበር። ክፍሉ ከተዘበራረቀው የባህል ፍርክስካሽ የተስተካከለ ስልጣኔን ለመገንባት የሚጥር ነው። ሆኖም ሁሉም የተስተካከለ ነገር የተሸሸገ ዝብርቅርቅ አስከፊ ነገር ስላለው፣ ይህም አስከፊ ነገር ዞሮ ዞሮ እራሱን የበላይ ስለሚያደርግ፣ ይህን መጋፈጥ ግድ ይላል። የአፖሎ ቀን ያለ ዳዮኒስ ጭለማ ኅልው አይሆንም። ማታው እንዳውም ከቀኑ በጣም ሃይለኛ ነው። እኒህ ጭለማ የሆኑ የህይወት ኃይሎች እጅግ ሃይለኛ ስለሆኑ ሰወች ብዙ ጊዜ ከህይወት መራቅ ይመርጣሉ፣ ስለዚህም በብዙወች አስተያየት ህይወት እጅግ ስቃይ የበዛበትና መጥፎ ሲሆን፣ ኑሮ መሸነፍ ያለበት ነገር ነው ብለው ያምናሉ። የዞራስተር አላማ እንግዲህ ምንም እንኳ ህይወት ብዙ ጊዜ ሽብር ቢኖረውም፣ መጥፎውም ቢበዛም ህይወት መኖር ያለበትና መደገፍ ያለበት እንደሆነ ማሳየት ነው። የመጽሃፉ የመጨረሻ ክፍል የዋናወቹ ገጸ ባህርያት ወደ ህይወትን ከነሽብሩና ጭለማው መውደድን ሽግግር ይተርካል። ከብዙ ማሰብና ማስተማር በኋላ ህይወትን መኖር፣ ህይወትን ማፍቀር። የሚያይ፣ የሚሰማው፣ የሚያውቅ ፍቅር። ከዘላለም መመላለስ በተጨማሪ ኒሼ ስለ አዳዲስ ህግጋት/ዋጋወች ማውጣት በዚሁ ክፍል አጥብቆ አስተምሯል። "በተሰባበሩና ግማሽ ድረስ በተጻፈባቸው ጽላቶች ተከብቤ ተቀምጨ እጠባበቃለሁ። ከቶ መቼ ይሆን የኔስ ጊዜ?" መደብ :የዞራስተር
15084
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A0%E1%88%AC
በሬ
በሬ የትልቁ ለማዳ፤ ወንድ የቀንድ ከብት የጎልማሳነት ደረጃ መጠሪያ ነው። እነዚህም በሮማይስጥ ከሚባሉት ዝርያዎች እጅግ በከፍተኛ መጠን ከተስፋፉት ዋነኞቹ ናቸው። ይህ እንሥሳ ለእርሻ፣ ለምግብነት እንዲሁም በአንዳንድ ቦታዎች ለመጓጓዣነት ያገለግላል። የዚሁ ዝርያ የሴት ፆታ ላም ትባላለች። የበሬ ዝርያዎች የመጨረሻ ምርጥ ተብለው የሚመለከቱት የበሬ ዝርያዎች የእንግሊዝ ነጭ በሬ፣ አንኮሌ ዋቱሲ፣ አንገስ፣ ሳንታ ገርትሩደስ፣ ገርንሲ፣ ሆልስታይን፣ ኤርሺየር፣ ብራንገስ፣ ብራህማን፣ ቺያኒና፣ ሄረፎርድ፣ ቻሮላዪስ፣ እና ጋሎዌይ የበሬ ዝርያ ናቸው። የበሬ ሥጋ የበሬ ሥጋ በብዛት በተመሳይ ሁኔታ ተበልቶ፡ ባክቴርያ በማስወገድ ረገድ ግን በአንጻራዊ ሁኔታዎች ተቀምጦ በጥቅም ላይ የሚውል የሙሉ ፕሮቲን ምንጭ ነው። ሊንና ኤክስትራ ሊን የሚባሉት የሥጋ ደረጃዎች ቀይ ሥጋ ውስጥ በሚገኝ የስብ መጠን ነው የሚወሰኑት። ከስብ መጠን አንጻር ሲታይ፤ ኤክስትራ ሊን ለጤና ተስማሚነቱ ቀዳሚ ነው። በአብዛኛው የመጨረሻ ሊን ተብሎ የሚታየው አይን ራውንድ የበሬ ሥጋና ማንኛውም 4 ግራም ስብና 1.4 ግራም ሳቹሬትድ ስብ በሰርቪንግ ያለው የበሬ ሥጋ ነው። ሌሎች ኤክስትራ ሊን ተብለው የሚታወቁ የበሬ ስጋ ብልቶች ሰርሎይን ቲፕ ሳይድ የበሬ ሥጋ፣ ቶፕ ራውንድ የበሬ ሥጋ፣ ቦተም ራውንድ የበሬ ሥጋና ሰር ሎይን የበሬ ስጋ ናቸው። ከሁሉም በላይ በሊንነት ወይንም ደግሞ በስብ አልባነቱ ወደር የሌለው ግን የበሬ ልብ ነው። የጥጃ ሥጋ ከበሬ ሥጋ ጋር ሲነፃፀር ደግሞ በአጠቃላይ ወደ ግማሽ አካባቢ የስብ ይዞታ እንደሚኖረው ይመለከታል። ሊን ተብለው የሚመደቡት የበሬ ሥጋ ክፍሎች ረድፍ በርከት ያለ ምርጫ ሲኖር፤ ከሊን ወደ ስብ የበዛበት ተደርገው ሲደረደሩ፦ ብሪስኬት፣ ራውንድ ቶፕ፣ ራውንድ፣ ሻንክ፣ ስርሎይን ቲፕ፣ ቸክና ቦተም ራውንድ የበሬ ሥጋ ናቸው። ሌሎች ሊን ሥጋ የሚገኝባቸው የበሬ ሥጋ ብልቶች፦ ቶፕሎይን፤ የትከሻ ፕቲት መዳሊዮን ቁርጦች፣ ፍላንክ፣ የትከሻ መሃል፣ ትራይ ቲፕ፣ ተንደርሎይንና ቲ-የጎድን አጥንት የበሬ ሥጋ ናቸው። አጭር ሎይን የበሬ ሥጋ ባለሰባት ጎድን የጎድን አጥንት የሆነው የአጭር ሎይን ሰብ ፕራይማል ቁርጦች፡ ማለት ስትሪፕ ሎይንና ቴንደርሎይን፡ በሸፍ ኮናርድ ዌይንቢች የሚበለተው ኒው ዮርክ ስትሪፕ፣ ፊሌት፣ እና ሜዳሊዮን ቁርጥ ተደርጎ ሲሆን፤እስከነ የጎድን አጥንቱ ደግሞ ፖርተርሀውስ ስቴክ፣ ቲ-ቦን ስቴክ፣ እና እንደ ባለአጥንት ኒው ዮርክ ስትሪፕ ስቴክ ተደርጎ ይበለታል። ፒስሞ ቁርጥ ቴንደርሎይን፦ ፒስሞ ቁርጥ ሙሉ ቴንደርሎይን፡ ማለት የአጭር ሎይንና የሰርሎይን ክፍል ተደርጎ ያልተቆረጠ ቴንደርሎይን ነው። ቶፕ ሎይን የበሬ ሥጋ ኒው ዮርክ ስትሪፕ ስቴክ የግሪል ጥብስ፣ ሩላድ በመጥበሻ ጥብስ፣ አሮስቶ፣ በመጥበሻ ለብልቦ በኦቨን የተጨረሰ ሱ ቪድ መንሀተን ስቴክ (ወፈር ያለ ቁርጥ) የመንሀተን ስቴክ ጥብስ ምንቸት አብሽ ቴንደርሎይን የበሬ ሥጋ ሻቶብሪዮን የተጨሰ ስንግ ቴንደርሎይን ፒንዊል ስንግ ቴንደርሎይን ፒንዊል አሮስቶ ፕቲት ፍሌ ምኞን ከተጠበሰ ፖርቶበሎ ጋር ፊሌት የበሬ ሥጋ ሱ ቪድ ፊሌት አሜሪኬን የበሬ ሥጋ ካርፓቺዮ ሻቶብሪዮን ክላሲክ ሻቶብሪዮን ፍሌ ምኞን የበሬ ሥጋ ኦስካር የበሬ ሥጋ ዌሊንግቶን ስቲር ፍራይድ የበሬ ጥብስ ካርፓቺዎ በትልልቅ ሜዳልየን ተቆርጦ ጎረድ-ጎረድ ተደርጎ የበሬ ጥብስ ስትሮገኖፍ ተከትፎ ክትፎ የሸዋ ክትፎ ስቴክ ታርታር ሺግ ኮፍቴ እስከነ ጎድኑ ፖርተርሀውስ ስቴክ፦ ይህ ቁርጥ ከአጭር ሎይን የሰር ሎይን ጫፍ የምሚቆረጥ በመሆኑ ከቴንደር ሎይን በበዛትና ከኒው ዮርክ ስትሪፕ ሎይን ደግሞ በመጠኑ የሆነ ይዞታ አለው፡፤ በመጥበሻ ለብልቦ በኦቨን መጨረስ ቲ-ቦን ስቴክ በመጥበሻ ለብልቦ በኦቨን መጨረስ የካንሳስ ከተማ ስትሪፕ ስቴክ ሰርሎይን የበሬ ሥጋ ቶፕ ሰርሎይን ስቴክ (ኤክስትራ ሊን የበሬ ስጋ) የበሬ ሥጋ ታርታር ኮርኔቶ የበሬ ሥጋ ታታኪ ቦ ታይ ቸን የበሬ ሥጋ የታታኪ ሱሺ ቅመማም የበሬ ሥጋ ሰላጣ ጀነራል ሶ የበሬ የበሬ ሥጋ ሽዋርማ ቺዝ ስቴክ በግሪድል መጥበሻ መጥበስ፣ በመጥበሻ አብስሎ በድስት መጨረስ ሰርሎይን ቲፕ ሳይድ (ኤክስትራ ሊን የበሬ ስጋ) ሰርሎይን ቲፕ አሮስቶ በት ቴንደር ትራይ ቲፕ ስንግ አሮስቶ ፔፐርኮርን አሮስቶ ትርይ ቲፕ የግሪል ጥብስ ትራይ ቲፕ የመጥበሻ ጥብስ ቦል ቲፕ ረምፕ የበሬ ሥጋ ጀርኪ ረምፕ ስቴክ የረምፕ ስቴክ የግሪል ጥብስ ራውንድ የበሬ ሥጋ ቶፕ ሳይድ/ከውስጥ በኩል (ኤክስትራ ሊን የበሬ ሥጋ) ቋንጣ ቋንጣ ፍርፍር የቋንጣ ወጥ የበሬ ሥጋ ጀርኪ ተሪያኪ የበሬ ሥጋ ጀርኪ ቶፕ ራውንድ ስቴክ የመጥበሻ ጥብስ ሳወርብራትን ቦተም ራውንድ/ቦተም ፍላት (ኤክስትራ ሊን የበሬ ሥጋ) ነክል የሥጋ ወጥ ጉስ ኔክ የራውንድ አይን (ሊን የበሬ ስጋ) ዝልዝል አልጫ ወጥ የጣልያን ብረሳኦላ ቦተም ራውንድ (ሊን የበሬ ስጋ) ሂል ታላቅና ታናሽ የበሬ ስጋ ከነቅልጥም አጥንቱ በወርዱ ተሸንሽኖ ኦሶ ቡኮ በመጥበሻ ጀምሮ በድስት መጨረስ የድስት ወጥ ሺን የበሬ ሥጋ ፍላንክ የበሬ ሥጋ ፍላንክ ስቴክ ዩኴ የበሬ ሥጋ ጀርኪ ቢርቤኪው ስንግ ፍላንክ ስቴክ ፒንዊል ለንደን ብሮይል የፈረንሳይ ስቴክ ጥብስ ካባብ ፍላፕ የበሬ ሥጋ (ሰርሎይን ፍላፕ) የፍላፕ ስቴክ የግሪል ጥብስ ስከርት የበሬ ሥጋ (ዳያፍራም) ስከርት ስቴክ የመጥበሻ ጥብስ ስንግ ስከርት የበሬ ሥጋ ፒንዊል በመጥበሻ ለብልቦ በኦቨን መጨረስ ፈሂታስ ብሪስኬት የበሬ ሥጋ አጥንት የሌለው ፓከር ቁርጥ ብሪስኬት የካንሳስ ሲቲ ባርቤኪው ሳንድዊች ሹሉ ግማሽ የካንሳስ ሲቲ ባርቤኪው ሳንድዊች የተጨሰበት ብሪስኬት ጠፍጣፋንው ግማሽ ሱ ቪድ ፐስትራሚ ስሞክሀውስ ብሪስኬት ሳንድዊች ጥቅል ብሪስኬት ብሮይል በክሮክፖት እስከነ አጥንቱ ቸክ የበሬ ሥጋ ተፈጭቶ የበሬ ሥጋ ጀርኪ የአዲስ አበባ ቢግ ማክ ሱ ቪድ በርገር ኦሰንዎርስት ቺሊ ፍላት አይረን ስቴክ (ስለት ቁርጥ) በግሪል ለመጥበስ ቸክ ቴንደር አንደር ብሌድ ሮስት የበሬ ሥጋ ቶፕ ብሌድ፡ ከጡንቻ ልስላሴ አንፃር ሲታይ፡ ከቴንደር ሎይን ሁለተኛ ነው። በግሪል አሮስቶ ቸክ ሮስት የበሬ ሥጋ ጉላዥ የበሬ እና ጊነስ (በድንች) ስትሮጋኖፍ በመጥበሻ ለብልቦ በድስት መጨረስ ጎድን እስከነ ጎድን አጥንቱ ቶማሀክ ስቴክ የበሬ ሥጋ ቶማሀክ ስቴክ ቁርጥ ጎድን ሮስት የበሬ ሥጋ (ፕራይም ጎድን) ፍሬንችድ ጎድን ሮስት ጥብስ ባለአጥንት የጎድን-አይን ስቴክ የበሬ ሥጋ (ፕራይም ጎድን) ባለአጥንት የጎድን-አይን ስቴክ ጥብስ አጭር ጎድን ሱ ቪድ እንግሊዝ ቁርጥ ብሮይልድ የበሬ ጎድን (ከደረት) ስቲኪ የበሬ ጎድን አሮስቶ ፍላንከን ቁርጥ የበሬ የጀርባ ጎድን (ቤቢ ባክ ጎድን) የግሪል ባርቤኪው የተጨሰበት የኦቨን አሮስቶ ካልቢ በግሪል መጥበስ የጎድን አሮስቶ የጎድን ስቴክ በመጥበሻ ለብልቦ በኦቨን መጨረስ አጥንት የሌለው ደልማንኮ ስቴክ በመጥበሻ መጥበስ የጎድን-አይን የበሬ ስጋ ግዩዶን የጎድን-አይን አሮስቶ ፊሊ ቺዝ ስቴክ የጎድን አይን ስቴክ (ስኮች ፊሌት) የበሬ ኩላሊት የበሬ ስጋና ኩላሊት ፓይ ዱለት የበሬ ጨጓራ ትሪፓ ዱለት ምላስና ሰምበር ስቲር ፍራይድ ትሪፓ የሮማ ስታይል ትሪፓ ጨጓራ ጥብስ ጨጓራ ወጥ የበሬ ምላስ ምላስና ሰምበር ምላስ ቅቅል የበሬ የሮኪ ተራራ ኦይስተርስ ፍራይድ የሮኪ ተራራ ኦይስተርስ የኢስያ የሮኪ ተራራ ኦይስተር ታኮ የበሬ ልብ (ኤክስትራ ሊን) ዱለት የበሬ ልብ ታርታር የበሬ ልብ የመጥበሻ ጥብስ የበሬ ልብ ወጥ የበሬ ልብ የግሪል ጥብስ የበሬ ልብ ካባብ ደግሞ ይዩ የከብት ስጋ የጥጃ ሥጋ አበሳሰል በር:ኑሮዘዴ ለማዳ እንስሶች የቶራ
9952
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%8B%AB
እስያ
እስያ በዋነኛነት በምስራቅ እና ሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ የምትገኝ የምድር ትልቁ እና በሕዝብ ብዛት የምትገኝ ናት። የዩራሺያን አህጉራዊ መሬት ከአውሮፓ አህጉር ጋር ትጋራለች፣ እና የአፍሮ-ኢውራሺያ አህጉራዊ መሬት ከአፍሪካ እና አውሮፓ ጋር ትጋራለች። እስያ 44,579,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር (17,212,000 ስኩዌር ማይልስ)፣ ከምድር አጠቃላይ ስፋት 30 በመቶው እና ከምድር አጠቃላይ የገጽታ ስፋት 8.7% ያህሉን ይሸፍናል።ለብዙ የሰው ዘር መኖሪያ የሆነችው አህጉር ከረጅም ጊዜ በፊት የኖረችው የብዙዎቹ የመጀመሪያ ስልጣኔዎች ቦታ፡ 4.7 ቢሊዮን ህዝብዋ ከአለም ህዝብ 60% ገደማ ነው። በአጠቃላይ እስያ በምስራቅ በፓስፊክ ውቅያኖስ፣ በደቡብ በህንድ ውቅያኖስ እና በሰሜን በአርክቲክ ውቅያኖስ የተከበበ ነው። በመካከላቸው ግልጽ የሆነ አካላዊ እና ጂኦግራፊያዊ መለያየት ስለሌለ የእስያ ድንበር ከአውሮፓ ጋር ታሪካዊ እና ባህላዊ ግንባታ ነው። በተወሰነ ደረጃ የዘፈቀደ ነው እና በጥንታዊ ጥንታዊነት ከመጀመሪያው ፅንሰ-ሀሳብ ጀምሮ ተንቀሳቅሷል። የዩራሺያ በሁለት አህጉራት መከፋፈል የምስራቅ ምዕራብ የባህል፣ የቋንቋ እና የጎሳ ልዩነቶችን ያንፀባርቃል፣ አንዳንዶቹ በሰላማዊ መስመር ሳይሆን በስፔክትረም ይለያያሉ። በብዛት ተቀባይነት ያለው ድንበሮች እስያ ከሱዌዝ ካናል በስተምስራቅ ከአፍሪካ ይለያታል; እና ከቱርክ ስትሬት በስተ ምሥራቅ የኡራል ተራሮች እና የኡራል ወንዝ እና ከካውካሰስ ተራሮች በስተደቡብ እና በካስፒያን እና ጥቁር ባህሮች ከአውሮፓ ይለያሉ. ቻይና እና ህንድ ከ1 እስከ 1800 ዓ.ም. በዓለም ላይ ትልቁ ኢኮኖሚ በመሆን ተፈራርቀዋል። ቻይና ትልቅ የኤኮኖሚ ሃይል ነበረች እና ብዙዎችን ወደ ምስራቃዊ ስቧል እና ለብዙዎች የህንድ ጥንታዊ ባህሎች አፈ ታሪክ ሀብት እና ብልጽግና ኤዥያንን በመምሰል የአውሮፓ ንግድን ፍለጋን እና ቅኝ ግዛትን ይስባል። ከአውሮፓ ወደ አሜሪካ የሚወስደውን የአትላንቲክ ተሻጋሪ መንገድ ኮሎምበስ ወደ ህንድ የሚወስደውን መንገድ ሲፈልግ በአጋጣሚ ማግኘቱ ይህን ጥልቅ መማረክ ያሳያል። የሐር መንገድ በኤሽያ ኋለኛ አገሮች ውስጥ ዋናው የምስራቅ-ምዕራብ የንግድ መስመር ሆነ የማላካ የባህር ዳርቻ እንደ ዋና የባህር መስመር ነው። እስያ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን (በተለይ የምስራቅ እስያ) እና ጠንካራ የህዝብ እድገት አሳይታለች፣ ነገር ግን አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር እድገት ቀንሷል። እስያ የሂንዱይዝም፣ የዞራስተሪያኒዝም፣ የአይሁድ እምነት፣ የጃይኒዝም፣ የቡድሂዝም እምነት፣ የኮንፊሺያኒዝም፣ ታኦይዝም፣ ክርስትና፣ እስልምና፣ ሲክሂዝም እና ሌሎች በርካታ ሃይማኖቶች ጨምሮ የአብዛኛው የአለም ዋና ዋና ሃይማኖቶች መገኛ ነበረች። ከግዙፉና ከልዩነቱ አንፃር የኤዥያ ጽንሰ-ሐሳብ-ከጥንታዊው ጥንታዊነት ጀምሮ ያለው ስም-ከሥጋዊ ጂኦግራፊ ይልቅ ከሰው ልጅ ጂኦግራፊ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። ባህሎች, አከባቢዎች, ኢኮኖሚክስ, ታሪካዊ ግንኙነቶች እና የመንግስት ስርዓቶች. በተጨማሪም ከምድር ወገብ ደቡብ በመካከለኛው ምስራቅ በሞቃታማው በረሃ፣ በምስራቅ ደጋማ አካባቢዎች እና በአህጉራዊው ማእከል እስከ ሳይቤሪያ ውስጥ ያሉ ሰፊ የከርሰ ምድር እና የዋልታ አካባቢዎች ያሉ በርካታ የተለያዩ የአየር ንብረት ሁኔታዎች አሏት። ፍቺ እና ድንበሮች እስያ-አፍሪካ ድንበር በእስያ እና በአፍሪካ መካከል ያለው ድንበር ቀይ ባህር፣ የስዊዝ ባሕረ ሰላጤ እና የስዊዝ ካናል ነው። ይህ ግብፅን አህጉር ተሻጋሪ ሀገር ያደርጋታል፣ የሲና ባሕረ ገብ መሬት በእስያ እና የተቀረው የሀገሪቱ ክፍል በአፍሪካ ነው። እስያ አውሮፓ ድንበር የብሉይ ዓለም የሶስትዮሽ ክፍፍል ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ጥቅም ላይ የዋለው እንደ አናክሲማንደር እና ሄካቴየስ ባሉ የግሪክ ጂኦግራፊዎች ምክንያት ነው። ዘመናዊው የሪዮኒ ወንዝ) በካውካሰስ ጆርጂያ (ከአፉ በፖቲ በጥቁር ባህር ዳርቻ በሱራሚ ማለፊያ እና በኩራ ወንዝ በኩል እስከ ካስፒያን ባህር ድረስ) አሁንም በሄሮዶተስ በ 5 ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. በሄለናዊው ዘመን፣ ይህ የአውራጃ ስብሰባ ተሻሽሎ ነበር፣ እናም በአውሮፓ እና በእስያ መካከል ያለው ድንበር አሁን ታኒስ (የዘመናዊው ዶን ወንዝ) ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ይህ እንደ ፖሲዶኒየስ፣ ስትራቦ እና ቶለሚ ባሉ የሮማውያን ዘመን ደራሲያን የተጠቀሙበት ስምምነት ነው። በእስያ እና በአውሮፓ መካከል ያለው ድንበር በታሪክ በአውሮፓውያን ምሁራን ይገለጻል።የሩሲያ የዛርዶም ንጉስ ታላቁ ፒተር ታላቁ ፒተር የስዊድን እና የኦቶማን ኢምፓየር ተቀናቃኝ የይገባኛል ጥያቄዎችን ወደ ምስራቃዊ አገሮች በማሸነፍ እና የታጠቁ ተቃውሞዎችን ሲያሸንፍ የዶን ወንዝ ለሰሜን አውሮፓውያን አጥጋቢ አልነበረም። በሳይቤሪያ ነገዶች በ 1721 የተመሰረተው በ 1721 ወደ ኡራል ተራሮች እና ከዚያም በላይ የሚደርስ አዲስ የሩሲያ ኢምፓየር አቋቋመ የግዛቱ ዋና ጂኦግራፊያዊ ቲዎሪስት የቀድሞ የስዊድን እስረኛ ነበር በ 1709 በፖልታቫ ጦርነት ተወሰደ እና ተመድቧል ወደ ቶቦልስክ, ከፒተር የሳይቤሪያ ባለስልጣን ቫሲሊ ታቲሽቼቭ ጋር የተገናኘ እና ለወደፊት መጽሐፍ ለመዘጋጀት የጂኦግራፊያዊ እና አንትሮፖሎጂ ጥናቶችን ለማካሄድ ነፃነት ተፈቅዶለታል. በስዊድን፣ ፒተር ከሞተ ከአምስት ዓመታት በኋላ፣ በ1730 ፊሊፕ ጆሃን ቮን ስትራለንበርግ የኡራል ተራሮችን የእስያ ድንበር አድርጎ የሚያሳይ አዲስ አትላስ አሳተመ። ታቲሽቼቭ ሀሳቡን ለቮን ስትራለንበርግ እንዳቀረበ አስታወቀ። የኋለኛው ደግሞ የኢምባ ወንዝን የታችኛው ወሰን አድርጎ ጠቁሟል። በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ የኡራል ወንዝ እስኪያሸንፍ ድረስ በሚቀጥለው ክፍለ ዘመን የተለያዩ ሀሳቦች ቀርበዋል. ድንበሩ የኡራል ወንዝ ወደ ሚሰራበት ከጥቁር ባህር ወደ ካስፒያን ባህር ተወስዷል። በጥቁር ባህር እና በካስፒያን መካከል ያለው ድንበር ብዙውን ጊዜ በካውካሰስ ተራሮች ጫፍ ላይ ይደረጋል ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ ወደ ሰሜን ቢቀመጥም የእስያ-ውቅያኖስ ድንበር በእስያ እና በኦሽንያ ክልል መካከል ያለው ድንበር ብዙውን ጊዜ በማላይ ደሴቶች ውስጥ አንድ ቦታ ላይ ይደረጋል። በኢንዶኔዥያ የሚገኙት የማሉኩ ደሴቶች ብዙውን ጊዜ በደቡብ ምስራቅ እስያ ድንበር ላይ ከኒው ጊኒ ጋር ከደሴቶቹ በስተምስራቅ ሙሉ በሙሉ የኦሺኒያ አካል እንደሆኑ ይታሰባል። በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነደፉት ደቡብ ምስራቅ እስያ እና ኦሺኒያ የሚሉት ቃላት፣ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ የተለያዩ መልክዓ ምድራዊ ትርጉሞች ነበሯቸው። የትኛዎቹ የማሌይ ደሴቶች ደሴቶች እስያ እንደሆኑ ለመወሰን ዋናው ምክንያት በዚያ የሚገኙት የተለያዩ ኢምፓየሮች (ሁሉም አውሮፓውያን አይደሉም) የቅኝ ግዛት ይዞታዎች መገኛ ነው። ሉዊስ እና ዊገን "የደቡብ ምስራቅ እስያ" ወደ አሁን ድንበሮች መጥበብ ቀስ በቀስ ሂደት ነበር ይላሉ። ቀጣይነት ያለው ትርጉም ጂኦግራፊያዊ እስያ ከጥንት ግሪኮች ጀምሮ በሌሎች ባህሎች ላይ ተጭኖ በዓለም ላይ የአውሮፓ ፅንሰ-ሀሳቦች ባህላዊ ቅርስ ነው ትርጉሙ ምን ማለት እንደሆነ ትክክለኛ ያልሆነ ጽንሰ-ሀሳብ ነው። እስያ ከተለያዩ አይነት አካላት ባህላዊ ድንበሮች ጋር በትክክል አይዛመድም። ከሄሮዶተስ ዘመን ጀምሮ ጥቂት የማይባሉ የጂኦግራፊ ባለሙያዎች የሶስት አህጉር ስርዓትን (አውሮፓ, አፍሪካ, እስያ) በመካከላቸው ምንም አይነት ተጨባጭ አካላዊ መለያየት የለም ብለው ውድቅ አድርገዋል. ለምሳሌ፣ በኦክስፎርድ የአውሮፓ የአርኪዮሎጂ ኤመርቲስ ፕሮፌሰር የሆኑት ሰር ባሪ ኩንሊፍ፣ አውሮፓ በጂኦግራፊያዊ እና በባህል ብቻ "የምዕራባዊው የእስያ አህጉር የላቀ" እንደነበረች ይከራከራሉ። በጂኦግራፊያዊ አገላለጽ፣ እስያ የዩራሲያ አህጉር ዋና ዋና ምስራቃዊ አካል ነች አውሮፓ የመሬቱ ሰሜናዊ ምዕራብ ባሕረ ገብ መሬት ነች። እስያ፣ አውሮፓ እና አፍሪካ አንድ ነጠላ ቀጣይነት ያለው መሬት-አፍሮ-ኤውራሲያ (ከሱዌዝ ካናል በስተቀር) እና አንድ የጋራ አህጉራዊ መደርደሪያን ይጋራሉ። ሁሉም ማለት ይቻላል አውሮፓ እና የእስያ ዋና ክፍል በዩራሺያን ፕላት ላይ ተቀምጠዋል በደቡብ በኩል በአረብ እና በህንድ ሳህን እና በሳይቤሪያ ምስራቃዊ ክፍል (ከቼርስኪ ክልል ምስራቅ) በሰሜን አሜሪካ ጠፍጣፋ ላይ። ሥርወ ቃል "እስያ" የሚባል ቦታ ሀሳብ በመጀመሪያ የግሪክ ሥልጣኔ ጽንሰ-ሐሳብ ነበር, ምንም እንኳን ይህ በአሁኑ ጊዜ በዚህ ስም ከሚታወቀው አህጉር ጋር ላይስማማ ይችላል. የእንግሊዘኛው ቃል የመጣው ከላቲን ስነ-ጽሑፍ ነው, እሱም ተመሳሳይ ቅርጽ አለው, "እስያ". በሌሎች ቋንቋዎች "እስያ" ከሮማን ኢምፓየር ከላቲን የመጣ ስለመሆኑ ብዙም እርግጠኛ አይደለም፣ እና የላቲን ቃል የመጨረሻው ምንጭ በእርግጠኝነት አይታወቅም ምንም እንኳን በርካታ ንድፈ ሐሳቦች ታትመዋል። እስያ የመላው አህጉር ስም አድርገው ከተጠቀሙባቸው የመጀመሪያዎቹ ክላሲካል ጸሐፊዎች አንዱ ፕሊኒ ነው። ይህ ዘይቤያዊ የትርጉም ለውጥ የተለመደ ነው እና በአንዳንድ ሌሎች የጂኦግራፊያዊ ስሞች ለምሳሌ እንደ ስካንዲኔቪያ (ከስካኒያ) ይታያል። የነሐስ ዘመን ከግሪክ ቅኔ በፊት የኤጂያን ባህር አካባቢ በግሪክ የጨለማ ዘመን ነበር፣ በዚህ መጀመሪያ ላይ የቃላት አጻጻፍ ጠፋ እና የፊደል አጻጻፍ አልተጀመረም። ከዚያ በፊት በነሐስ ዘመን የአሦር ኢምፓየር፣ የኬጢያውያን ግዛት እና የግሪክ የተለያዩ የሜይሴኒያ ግዛቶች መዛግብት እስያ እንደሚገኝ ጥርጥር የለውም፣ በእርግጠኝነት አናቶሊያ ውስጥ፣ ከሊዲያ ጋር ተመሳሳይ ካልሆነ ጨምሮ። እነዚህ መዝገቦች አስተዳደራዊ ናቸው እና ግጥም አያካትቱም. የማሴኔያን ግዛቶች በ1200 ዓክልበ አካባቢ ባልታወቁ ወኪሎች ወድመዋል፣ ምንም እንኳን አንድ የአስተሳሰብ ትምህርት ቤት የዶሪያን ወረራ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ቢመደብም። የቤተ መንግሥቶቹ መቃጠላቸው የማይሴኔያን የአስተዳደር መዛግብት የያዙ የሸክላ ጽላቶች በመጋገር እንዲጠበቁ አድርጓቸዋል። እነዚህ ጽላቶች የተጻፉት ሊኒያር ቢ በተባለው የግሪክ ሲላቢክ ስክሪፕት ነው። ይህ ስክሪፕት የተፈታው በብዙ ፍላጎት ባላቸው አካላት ነው፣ በተለይም በወጣቱ የዓለም ጦርነት ጸሐፊ ሚካኤል ቬንተሪስ፣ በመቀጠልም በሊቁ ጆን ቻድዊክ ተረድቷል። በጥንታዊው ፓይሎስ ቦታ በካርል ብሌገን የተገኘው ዋና መሸጎጫ በመቶዎች የሚቆጠሩ የወንድ እና የሴት ስሞች በተለያዩ ዘዴዎች የተፈጠሩ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በባርነት የተያዙ ሴቶች ናቸው (የህብረተሰቡ ጥናት በይዘቱ እንደሚያሳየው)። እንደ ልብስ ሥራ ባሉ ንግዶች ውስጥ ያገለግሉ ነበር እና አብዛኛውን ጊዜ ከልጆች ጋር ይመጡ ነበር። ከአንዳንዶቹ ጋር የተቆራኘው “የምርኮ ምርኮኞች” ኤፒሄት መነሻቸውን ያሳያል። አንዳንዶቹ የብሔር ስሞች ናቸው። በተለይም አንዱ፣ “የእስያ ሴቶችን” ይለያል።ምናልባት በእስያ ተይዘው ሊሆን ይችላል፣ነገር ግን ሌሎች ሚልጢያ፣ሚሊጢስ፣የግሪክ ቅኝ ግዛት የሆነችው፣በግሪኮች ለባሪያነት ያልተወረረች የሚሊጢን ይመስሉ ነበር። ቻድዊክ ስሞቹ እነዚህ የውጭ አገር ሴቶች የተገዙባቸውን ቦታዎች እንደሚመዘግቡ ይጠቁማል።ስሙም በነጠላ አስዊያ ነው፣ እሱም የአገሩን ስም እና ከዚያ የመጣች ሴትን ያመለክታል። የወንድነት ቅርጽ አለ, ይህ አስዊያ በኬጢያውያን ዘንድ አሱዋ ተብሎ የሚጠራው፣ ልድያን ወይም "የሮማን እስያ"ን ያማከለ ክልል የተረፈ ይመስላል። ይህ ስም፣ አሱዋ፣ ለአህጉሪቱ “እስያ” መጠሪያ መነሻ ሆኖ ተጠቁሟል። የአሱዋ ሊግ በ1400 ዓክልበ አካባቢ በ1400 ዓ.ዓ አካባቢ በኬጢያውያን በቱድሃሊያ የተሸነፈ በምእራብ አናቶሊያ የግዛት ኮንፌዴሬሽን ነበር። ክላሲካል ጥንታዊነት የላቲን እስያ እና የግሪክ ተመሳሳይ ቃል ይመስላል። የሮማውያን ደራሲዎች እንደ እስያ ተርጉመዋል። ሮማውያን በምዕራብ አናቶሊያ (በአሁኗ ቱርክ) የምትገኝ እስያ ግዛት ብለው ሰየሙት። በዘመናዊቷ ኢራቅ ውስጥ ትንሽ እስያ እና እስያ ሜጀር ነበሩ። የስሙ የመጀመሪያ ማስረጃ ግሪክ እንደመሆኑ መጠን እስያ የመጣው መሆኗ ሳይሆን አይቀርም፣ ነገር ግን ጥንታዊ ሽግግሮች፣ በሥነ-ጽሑፋዊ አውዶች እጥረት ምክንያት፣ በድርጊቱ ውስጥ ለመያዝ አስቸጋሪ ናቸው። በጣም የሚገመቱት ተሽከርካሪዎች እንደ ሄሮዶተስ ያሉ የጥንት ጂኦግራፊዎች እና የታሪክ ተመራማሪዎች ነበሩ ሁሉም ግሪክ ናቸው። የጥንት ግሪክ ቀደምት እና የበለጸገ የስሙን አጠቃቀም ያረጋግጣል። የመጀመሪያው የእስያ አህጉራዊ አጠቃቀም ለሄሮዶቱስ (በ440 ዓክልበ. አካባቢ) የተነገረለት እሱ ስላፈለሰ ሳይሆን፣ ታሪኮቹ በማንኛውም ዝርዝር ሁኔታ ሊገልጹት ከቀደሙት ንባብ በመሆናቸው ነው። በጥንቃቄ ገልጾታል፣ ያነበበቸውን፣ አሁን ግን ሥራቸው የጠፋባቸውን የቀድሞ የጂኦግራፊ ባለሙያዎችን ጠቅሷል። በርሱም ከግሪክ እና ከግብፅ በተቃራኒ አናቶሊያ እና የፋርስ ኢምፓየር ማለት ነው። ሄሮዶተስ የሦስት ሴቶች ስም “በተጨባጭ አንድ ለሆነ ትራክት የተሰጠ” (ኤውሮፓ፣ ኤዥያ እና ሊቢያ አፍሪካን በመጥቀስ) ለምን ሦስት የሴቶች ስሞች እንደተሰጡት ግራ እንዳጋባው ተናግሯል፣ አብዛኞቹ ግሪኮች እስያ የተሰየመችው በባለቤቱ ሚስት ስም እንደሆነ ገልጿል። ፕሮሜቴየስ (ማለትም ሄሲዮን)፣ ነገር ግን ልድያውያን ይህ ስም በሰርዴስ ላለው ነገድ ያስተላለፈው በኮቲስ ልጅ አሲየስ ነው ይላሉ። በግሪክ አፈ ታሪክ፣ “ኤዥያ” ወይም “ኤሲ” “የኒምፍ ወይም ታይታን የልድያ አምላክ” ስም ነበር። በጥንቷ ግሪክ ሃይማኖት ቦታዎች ከጠባቂ መላእክት ጋር ተመሳሳይነት ባለው የሴት መለኮት ጥበቃ ሥር ነበሩ። ገጣሚዎቹ ተግባራቸውን እና ትውልዳቸውን በአምሳያ ቋንቋ ጨምረው በአስደሳች ታሪኮች ዘረዘሩ።ይህም ተከትሎ ተውኔት ደራሲያን ወደ ክላሲካል የግሪክ ድራማ ተለውጠው "የግሪክ አፈ ታሪክ" ሆነዋል። ለምሳሌ፣ ሄሲኦድ የቴቲስ እና የውቅያኖስን ሴት ልጆች ጠቅሷል፣ ከእነዚህም መካከል "ቅዱስ ኩባንያ"፣ "ከጌታ አፖሎ እና ወንዞች ጋር ወጣቶች በእጃቸው ያሉ" አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ጂኦግራፊያዊ ናቸው-ዶሪስ, ሮዳ, ዩሮፓ, እስያ. ሄሲኦድ ያብራራል፡- ሦስት ሺህ ንጹሕ ቁርጭምጭም የሌላቸው የውቅያኖስ ሴቶች ልጆች በሩቅና በሰፊ ተበታትነው ይገኛሉና፥ በየቦታውም ለምድርና ለጥልቁ ውኃ ያገለግላሉ። ኢሊያድ (በጥንቶቹ ግሪኮች በሆሜር የተነገረው) በትሮጃን ጦርነት አሲዮስ በተባለው ጦርነት ሁለት ፍርጂያውያን (በሉቪያውያን የተካውን ነገድ) ጠቅሷል። እንዲሁም በሊዲያ ውስጥ ማርሽ እንደ የያዘ ማርሽ ወይም ቆላማ። ብዙ ሙስሊሞች እንደሚሉት፣ ይህ ቃል የመጣው የሙሴ አሳዳጊ እናት ከሆነችው ከጥንቷ ግብፅ ንግሥት እስያ ነው። ታሪክ የእስያ ታሪክ እንደ የተለያዩ የባህር ዳርቻ ዳርቻዎች ታሪክ ሊታይ ይችላል-ምስራቅ እስያ ደቡብ እስያ ደቡብ ምስራቅ እስያ እና መካከለኛው ምስራቅ በመካከለኛው እስያ ረግረጋማ ውስጠኛ ክፍል የተገናኘ። የባህር ዳርቻው አካባቢ ለአንዳንድ የአለም ቀደምት የታወቁ ስልጣኔዎች መኖሪያ ነበር ፣እያንዳንዳቸውም ለም በሆነ የወንዝ ሸለቆዎች ዙሪያ ያደጉ። በሜሶጶጣሚያ፣ በኢንዱስ ሸለቆ እና በቢጫ ወንዝ የነበሩት ስልጣኔዎች ብዙ ተመሳሳይነት አላቸው። እነዚህ ስልጣኔዎች እንደ ሂሳብ እና ጎማ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን እና ሀሳቦችን ተለዋውጠው ሊሆን ይችላል። እንደ ጽሑፍ ያሉ ሌሎች ፈጠራዎች በየአካባቢው በግለሰብ ደረጃ የተገነቡ ይመስላሉ. በእነዚህ ቆላማ አካባቢዎች የተገነቡ ከተሞች፣ ግዛቶች እና ኢምፓየሮች። የመካከለኛው ስቴፕ ክልል ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በሁሉም የእስያ አካባቢዎች በፈረስ ላይ በተቀመጡ ዘላኖች ይኖሩ ነበር ከደረጃው ውስጥ በጣም ቀደምት የተለጠፈው መስፋፋት ኢንዶ-አውሮፓውያን ቋንቋቸውን ወደ መካከለኛው ምስራቅ፣ ደቡብ እስያ እና ቶቻሪያውያን ወደሚኖሩበት የቻይና ድንበሮች ያሰራጩ ናቸው። ሰሜናዊው የእስያ ክፍል፣ አብዛኛው ሳይቤሪያን ጨምሮ፣ ጥቅጥቅ ባለው ደኖች፣ የአየር ንብረት እና ታንድራ ምክንያት ለዳካ ዘላኖች በአብዛኛው ተደራሽ አልነበረም። እነዚህ አካባቢዎች በጣም ጥቂት ሰዎች አልነበሩም። ማዕከሉ እና አከባቢዎቹ በአብዛኛው በተራሮች እና በረሃዎች ተለያይተዋል. የካውካሰስ እና የሂማላያ ተራሮች እንዲሁም የካራኩም እና የጎቢ በረሃዎች የእንጀራ ፈረሰኞች በጭንቅ ብቻ የሚሻገሩትን መሰናክሎች ፈጠሩ። የከተማው ነዋሪዎች በቴክኖሎጂ እና በማህበራዊ ደረጃ የላቀ ደረጃ ላይ የደረሱ ቢሆኑም፣ በብዙ አጋጣሚዎች የተጫኑትን የእግረኛ መንጋዎች ለመከላከል በወታደራዊ ዘርፍ ምንም ማድረግ አልቻሉም። ይሁን እንጂ ቆላማው አካባቢ ብዙ የፈረስ ጉልበትን የሚደግፍ በቂ ክፍት የሣር ሜዳዎች አልነበራቸውም; በዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች በቻይና፣ ህንድ እና መካከለኛው ምስራቅ ያሉትን ግዛቶች ያሸነፉ ዘላኖች ብዙውን ጊዜ ከአካባቢው እና ከበለጸጉ ማህበረሰቦች ጋር መላመድን አግኝተዋል። የእስልምና ኸሊፋቶች የባይዛንታይን እና የፋርስ ግዛቶች ሽንፈት ወደ ምዕራብ እስያ እና የመካከለኛው እስያ ደቡባዊ ክፍሎች እና የደቡብ እስያ ምዕራባዊ ክፍሎች በ7ኛው ክፍለ ዘመን ወረራዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓቸዋል። የሞንጎሊያ ኢምፓየር በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሰፊውን የእስያ ክፍል አሸንፎ ከቻይና እስከ አውሮፓ ድረስ ያለውን አካባቢ ያዘ። ከሞንጎል ወረራ በፊት የሶንግ ሥርወ መንግሥት ወደ 120 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች እንደነበሩ ይነገራል። ወረራውን ተከትሎ በተካሄደው 1300 የህዝብ ቆጠራ ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ሪፖርት አድርጓል። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስከፊ ከሆኑት ወረርሽኞች አንዱ የሆነው ጥቁር ሞት በመካከለኛው እስያ በረሃማ ሜዳ ላይ እንደመጣ ይገመታል፣ ከዚያም በሃር መንገድ ተጉዟል። የሩስያ ኢምፓየር ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ወደ እስያ መስፋፋት የጀመረ ሲሆን በመጨረሻም በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ሁሉንም ሳይቤሪያ እና አብዛኛው የመካከለኛው እስያ ክፍል ይቆጣጠራል። የኦቶማን ኢምፓየር አናቶሊያን፣ አብዛኛው መካከለኛው ምስራቅን፣ ሰሜን አፍሪካንና ባልካንን ከ16ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ ተቆጣጠረ። በ 17 ኛው ክፍለ ዘመን ማንቹ ቻይናን ድል በማድረግ የኪንግ ሥርወ መንግሥት አቋቋመ። እስላማዊው የሙጋል ኢምፓየር እና የሂንዱ ማራታ ኢምፓየር በ16ኛው እና በ18ኛው ክፍለ ዘመን እንደቅደም ተከተላቸው ህንድን በብዛት ተቆጣጠሩ። የጃፓን ኢምፓየር አብዛኛውን የምስራቅ እስያ እና አብዛኛው ደቡብ ምስራቅ እስያ፣ ኒው ጊኒ እና የፓሲፊክ ደሴቶችን እስከ ሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ድረስ ተቆጣጠረ። የቻልኮሊቲክ ዘመን (ወይም የመዳብ ዘመን) የጀመረው በ4500 ዓ.ዓ ገደማ ነው፣ ከዚያም የነሐስ ዘመን በ3500 ዓክልበ ገደማ ጀመረ፣ የኒዮሊቲክ ባህሎችን በመተካት። የኢንዱስ ሸለቆ ሥልጣኔ (አይቪሲ) የነሐስ ዘመን ሥልጣኔ ነበር (3300-1300 ዓክልበ. በሳል ጊዜ 2600-1900 ዓክልበ.) በዚህ ስልጣኔ ውስጥ ቀደምት የሂንዱይዝም አይነት እንደተደረገ ይቆጠራል። ከእነዚህ የስልጣኔ ታላላቅ ከተሞች መካከል ከፍተኛ የከተማ ፕላን እና ጥበባት የነበራቸው ሃራፓ እና ሞሄንጆ-ዳሮ ይገኙበታል። በ1700 ዓክልበ. አካባቢ የእነዚህ ክልሎች ውድመት መንስኤ አከራካሪ ነው፣ ምንም እንኳን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በተፈጥሮ አደጋዎች (በተለይ በጎርፍ) ነው። ይህ ዘመን በህንድ ውስጥ ከ1500 እስከ 500 ዓ.ዓ. አካባቢ ያለውን የቬዲክ ዘመንን ያመለክታል። በዚህ ጊዜ ውስጥ የሳንስክሪት ቋንቋ አዳብሯል እና ቬዳስ ተጽፏል, ስለ አማልክት እና ስለ ጦርነቶች ተረቶች የሚናገሩ ድንቅ ዝማሬዎች. ይህ የቬዲክ ሃይማኖት መሠረት ነበር፣ እሱም በመጨረሻ የተራቀቀ እና ወደ ሂንዱይዝም የሚያድግ። ቻይና እና ቬትናም የብረታ ብረት ሥራ ማዕከላት ነበሩ። ከኒዮሊቲክ ዘመን ጀምሮ፣ ዶንግ ሶን ከበሮ የሚባሉት የመጀመሪያዎቹ የነሐስ ከበሮዎች በ ትናም እና በደቡብ ቻይና በቀይ ወንዝ ዴልታ ክልሎች እና አከባቢዎች ተገኝተዋል። እነዚህ ከቬትናም ቅድመ ታሪክ ዶንግ ልጅ ባህል ጋር ይዛመዳሉ። ዘፈን ዳ የነሐስ ከበሮ ገጽ፣ ዶንግ ሶን ባህል፣ ቬትናም በባን ቺያንግ፣ ታይላንድ (ደቡብ ምስራቅ እስያ) ከ2100 ዓክልበ. ጀምሮ የነሐስ ቅርሶች ተገኝተዋል። በኒያንጋን የበርማ የነሐስ መሳሪያዎች ከሴራሚክስ እና ከድንጋይ የተሰሩ ቅርሶች ጋር ተቆፍረዋል። የፍቅር ጓደኝነት በአሁኑ ጊዜ ሰፊ ነው (3500-500 ዓክልበ.) ጂኦግራፊ እና የአየር ንብረት እስያ በምድር ላይ ትልቁ አህጉር ነው። ከምድር አጠቃላይ ስፋት 9 በመቶውን ይሸፍናል (ወይም ከመሬት ስፋቱ 30 በመቶው) እና ረጅሙ የባህር ዳርቻ ያለው ሲሆን በ62,800 ኪሎ ሜትር (39,022 ማይል)። እስያ በአጠቃላይ የዩራሺያን ምሥራቃዊ አራት-አምስተኛውን እንደያዘ ይገለጻል። ከሱዌዝ ካናል እና ከኡራል ተራሮች በስተምስራቅ እና ከካውካሰስ ተራሮች በስተደቡብ (ወይም ኩማ-ማኒች ዲፕሬሽን) እና ካስፒያን እና ጥቁር ባህሮች ይገኛሉ። በምስራቅ በፓስፊክ ውቅያኖስ በደቡብ በህንድ ውቅያኖስ እና በሰሜን በአርክቲክ ውቅያኖስ የተከበበ ነው። እስያ በ 49 አገሮች የተከፋፈለ ነው, ከእነዚህ ውስጥ አምስቱ (ጆርጂያ, አዘርባጃን, ሩሲያ, ካዛኪስታን እና ቱርክ) አቋራጭ አገሮች በከፊል በአውሮፓ ውስጥ ይገኛሉ. በጂኦግራፊያዊ አገላለጽ ሩሲያ በከፊል በእስያ ውስጥ ትገኛለች, ነገር ግን በባህላዊ እና በፖለቲካዊ መልኩ እንደ አውሮፓውያን ሀገር ይቆጠራል. የጎቢ በረሃ ሞንጎሊያ ውስጥ ሲሆን የአረብ በረሃ አብዛኛውን የመካከለኛው ምስራቅን ክፍል ያቋርጣል። በቻይና የሚገኘው ያንግትዜ ወንዝ በአህጉሪቱ ረጅሙ ነው። በኔፓል እና በቻይና መካከል ያለው ሂማላያ በዓለም ላይ ካሉት የተራራ ሰንሰለቶች ሁሉ ረጅሙ ነው። ሞቃታማው የዝናብ ደኖች በአብዛኛው የደቡባዊ እስያ ክፍል ላይ ተዘርግተው የተንሰራፋ ሲሆን ሾጣጣ እና ደረቅ ደኖች በሰሜን በኩል ይገኛሉ. የአየር ንብረት እስያ በጣም የተለያየ የአየር ንብረት ባህሪያት አላት. የአየር ንብረት በሳይቤሪያ ከአርክቲክ እና ከሱባርክቲክ እስከ ደቡባዊ ህንድ እና ደቡብ ምስራቅ እስያ ሞቃታማ የአየር ጠባይ ይደርሳል። በደቡብ ምስራቅ ክፍሎች ላይ እርጥብ ነው እና በብዙ የውስጥ ክፍል ውስጥ ደረቅ ነው። በምድር ላይ ካሉት ትላልቅ የቀን ሙቀት ክልሎች መካከል አንዳንዶቹ በምዕራባዊ እስያ ክፍሎች ውስጥ ይከሰታሉ። የዝናብ ስርጭት በደቡባዊ እና ምስራቃዊ ክፍሎች ላይ የበላይነት አለው፣ ምክንያቱም ሂማላያ በመኖሩ በበጋ ወቅት እርጥበትን የሚስብ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን እንዲፈጠር ያስገድዳል። የአህጉሪቱ ደቡብ ምዕራብ ክፍሎች ሞቃት ናቸው። ሳይቤሪያ በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ ውስጥ በጣም ቀዝቃዛ ከሆኑት ቦታዎች አንዱ ነው, እና ለሰሜን አሜሪካ የአርክቲክ የአየር ብዛት ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል. ለትሮፒካል አውሎ ንፋስ እንቅስቃሴ በምድር ላይ በጣም ንቁው ቦታ ከፊሊፒንስ ሰሜናዊ ምስራቅ እና ከጃፓን ደቡብ ይገኛል። እ.ኤ.አ. በ 2010 በአለምአቀፍ ስጋት ትንተና ፋርም ማፕሌክሮፍት የተደረገ ጥናት 16 ለአየር ንብረት ለውጥ በጣም የተጋለጡ ሀገራትን ለይቷል የእያንዳንዱ ሀገር ተጋላጭነት የሚሰላው በሚቀጥሉት 30 ዓመታት ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖ ያላቸውን 42 ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ አመልካቾችን በመጠቀም ነው። የእስያ አገሮች ባንግላዲሽ፣ህንድ፣ፊሊፒንስ፣ቬትናም፣ታይላንድ፣ፓኪስታን፣ቻይና እና ሲሪላንካ በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ስጋት ካጋጠማቸው 16 አገሮች መካከል ይገኙበታል።አንዳንድ ለውጦች እየታዩ ነው። ለምሳሌ፣ በህንድ ሞቃታማ አካባቢዎች ከፊል ደረቃማ የአየር ጠባይ ባለባቸው አካባቢዎች፣ ከ1901 እስከ 2003 ባለው ጊዜ ውስጥ የሙቀት መጠኑ በ0.4 ዲግሪ ሴልሲየስ ጨምሯል። እ.ኤ.አ. በ2013 በአለም አቀፉ የሰብል ምርምር ኢንስቲትዩት ለከፊል-በረሃማ ትሮፒክስ የተደረገ ጥናት ሳይንስን ለማግኘት ያለመ- የእስያ የግብርና ሥርዓቶች የአየር ንብረት ለውጥን እንዲቋቋሙ የሚያስችላቸው፣ ድሆችን እና አቅመ ደካሞችን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ድሆችን የሚደግፉ አቀራረቦች እና ቴክኒኮች። የጥናቱ ምክረ ሃሳቦች የአየር ንብረት መረጃ አጠቃቀምን ከማሻሻል እና የአየር ንብረትን መሰረት ያደረጉ የግብርና ምክር አገልግሎቶችን ከማጠናከር፣ የገጠር ቤተሰብን ገቢ ብዝሃነትን ከማበረታታት እና አርሶ አደሩ የደን ሽፋንን ለማሳደግ፣ የከርሰ ምድር ውሃን ለመሙላት የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ርምጃዎችን እንዲወስድ ማበረታቻ መስጠት ነው። ታዳሽ ኃይልን ይጠቀሙ. የደቡብ ምስራቅ እስያ መንግስታት አሥሩ አገሮች ብሩኒ ካምቦዲያ ኢንዶኔዥያ ላኦስ ማሌዥያ ምያንማር ፊሊፒንስ ሲንጋፖር ታይላንድ እና ቬትናም በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖዎች በጣም የተጋለጡ ናቸው ሆኖም የኤኤስያን የአየር ንብረት ቅነሳ ጥረቶች ከተጋረጡበት የአየር ንብረት አደጋዎች እና አደጋዎች ጋር የተመጣጠኑ
50373
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%88%90%E1%8B%8B%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%89%B5%20%E1%88%A5%E1%88%AB%20%E1%8D%B0
የሐዋርያት ሥራ ፰
የሐዋርያት ሥራ በአዲስ ኪዳን ፭ኛ መጽሐፍ "የሐዋርያት ሥራ" ውስጥ የሚገኝ ሲሆን "ስምንተኛው ምዕራፍ" ነው የሚያተኩረውም በፊሊጶስ (አርድዕት) ሰባኪነት የተከናወኑ ሥራዎችና በተለይ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ማመንና መጠመቅ (ቁ፣፳፮) ምስክር ላይ ነው ይህም በ፵ ንዑስ ክፍሎች ይካተታል የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ቁጥር ፲ 1፤በዚያን፡ቀንም፡በኢየሩሳሌም፡ባለች፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ላይ፡ታላቅ፡ስደት፡ኾነ፤ዅሉም፡ከሐዋርያትም፡ በቀር፡ወደ፡ይሁዳና፡ወደሰማርያ፡አገሮች፡ተበተኑ። 2፤በጸሎትም፡የተጉ፡ሰዎች፡እስጢፋኖስን፡ቀበሩት፡ታላቅ፡ልቅሶም፡አለቀሱለት። 3፤ሳውል፡ግን፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ያፈርስ፡ነበር፤ወደዅሉም፡ቤት፡እየገባ፡ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡እየጐተተ፡ ወደ፡ወህኒ፡አሳልፎ፡ይሰጥ፡ነበር። 4፤የተበተኑትም፡ቃሉን፡እየሰበኩ፡ዞሩ። 5፤ፊልጶስም፡ወደሰማርያ፡ከተማ፡ወርዶ፡ክርስቶስን፡ሰበከላቸው። 6፤ሕዝቡም፡የፊልጶስን፡ቃል፡በሰሙ፡ጊዜ፡ያደርጋት፡የነበረውንም፡ምልክት፡ባዩ፡ጊዜ፥የተናገረውን፡ባንድ፡ልብ፡አደመጡ። 7፤ርኩሳን፡መናፍስት፡በታላቅ፡ድምፅ፡እየጮኹ፡ከብዙ፡ሰዎች፡ይወጡ፡ነበርና፤ብዙም፡ሽባዎችና፡ ዐንካሳዎች፡ተፈወሱ፤ 8፤በዚያችም፡ከተማ፡ታላቅ፡ደስታ፡ኾነ። 9፤ሲሞን፡የሚሉት፡አንድ፡ሰው፡ግን፦እኔ፡ታላቅ፡ነኝ፡ብሎ፥እየጠነቈለ፡የሰማርያንም፡ወገን፡እያስገረመ፡ ቀድሞ፡በከተማ፡ነበረ። 10፤ከታናናሾችም፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላላቆቹ፡ድረስ፦ታላቁ፡የእግዚአብሔር፡ኀይል፡ይህ፡ነው፡እያሉ፡ዅሉ፡ ያደምጡት፡ነበር። ቁጥር ፳ 11፤ከብዙ፡ዘመንም፡ዠምሮ፡በጥንቈላ፡ስላስገረማቸው፡ያደምጡት፡ነበር። 12፤ነገር፡ግን፥ስለእግዚአብሔር፡መንግሥትና፡ስለኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ስም፡እየሰበከላቸው፡ፊልጶስን፡ባመኑት፡ ጊዜ፥ወንዶችም፡ሴቶችም፡ተጠመቁ። 13፤ሲሞንም፡ደግሞ፡ራሱ፡አመነ፤ተጠምቆም፡ከፊልጶስ፡ጋራ፡ይተባበር፡ነበር፤የሚደረገውንም፡ምልክትና፡ ታላቅ፡ተኣምራት፡ባየ፡ጊዜ፡ተገረመ። 14፤በኢየሩሳሌምም፡የነበሩት፡ሐዋርያት፡የሰማርያ፡ሰዎች፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡እንደተቀበሉ፡ሰምተው፡ ጴጥሮስንና፡ዮሐንስን፡ሰደዱላቸው። 15፤እነርሱም፡በወረዱ፡ጊዜ፡መንፈስ፡ቅዱስን፡ይቀበሉ፡ዘንድ፡ጸለዩላቸው፤ 16፤በጌታ፡በኢየሱስ፡ስም፡ብቻ፡ተጠምቀው፡ነበር፡እንጂ፡ከነርሱ፡ባንዱ፡ላይ፡ስንኳ፡ገና፡አልወረደም፡ ነበርና። 17፤በዚያን፡ጊዜ፡እጃቸውን፡ጫኑባቸው፡መንፈስ፡ቅዱስንም፡ተቀበሉ። 18፤ሲሞንም፡በሐዋርያት፡እጅ፡መጫን፡መንፈስ፡ቅዱስ፡እንዲሰጥ፡ባየ፡ጊዜ፥ገንዘብ፡አመጣላቸውና፦ 19፤እጄን፡የምጭንበት፡ዅሉ፡መንፈስ፡ቅዱስን፡ይቀበል፡ዘንድ፡ለእኔ፡ደግሞ፡ይህን፡ሥልጣን፡ስጡኝ፡አለ። 20፤ጴጥሮስ፡ግን፡እንዲህ፡አለው፦የእግዚአብሔርን፡ስጦታ፡በገንዘብ፡እንድታገኝ፡ዐስበኻልና፥ብርኽ፡ ከአንተ፡ጋራ፡ይጥፋ። ቁጥር ፴ 21፤ልብኽ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡የቀና፡አይደለምና፡ከዚህ፡ነገር፡ዕድል፡ወይም፡ፈንታ፡የለኽም። 22፤እንግዲህ፡ስለዚህ፡ክፋትኽ፡ንስሓ፡ግባ፥ምናልባትም፡የልብኽን፡ዐሳብ፡ይቅር፡ይልኽ፡እንደ፡ኾነ፡ወደ፡ እግዚአብሔር፡ለምን፤ 23፤በመራራ፡መርዝና፡በዐመፅ፡እስራት፡እንዳለኽ፡አይኻለኹና። 24፤ሲሞንም፡መልሶ፦ካላችኹት፡አንዳች፡እንዳይደርስብኝ፡እናንተው፡ወደ፡ጌታ፡ለምኑልኝ፡አላቸው። 25፤እነርሱም፡ከመሰከሩና፡የጌታን፡ቃል፡ከተናገሩ፡በዃላ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ ተመለሱ፤በሳምራውያን፡በብዙ፡መንደሮችም፡ወንጌልን፡ሰበኩ። 26፤የጌታም፡መልአክ፡ፊልጶስን፦ተነሥተኽ፡በደቡብ፡በኩል፡ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ጋዛ፡ወደሚያወርደው፡ ምድረ፡በዳ፡ወደ፡ኾነ፡መንገድ፡ኺድ፡አለው። 27፤ተነሥቶም፡ኼደ።እንሆም፥ህንደኬ፡የተባለች፡የኢትዮጵያ፡ንግሥት፡አዛዥና፡ጃን፡ደረባ፡የነበረ፡ በገንዘቧም፡ዅሉ፡የሠለጠነ፡አንድ፡የኢትዮጵያ፡ሰው፡ሊሰግድ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጥቶ፡ነበር፤ 28፤ሲመለስም፡በሠረገላ፡ተቀምጦ፡የነቢዩን፡የኢሳይያስን፡መጽሐፍ፡ያነብ፡ነበር። 29፤መንፈስም፡ፊልጶስን፦ወደዚህ፡ሠረገላ፡ቅረብና፡ተገናኝ፡አለው። 30፤ፊልጶስም፡ሮጦ፡የነቢዩን፡የኢሳይያስን፡መጽሐፍ፡ሲያነብ፡ሰማና፦በእውኑ፡የምታነበውን፡ ታስተውለዋለኽን፧አለው። ቁጥር ፵ 31፤ርሱም፦የሚመራኝ፡ሳይኖር፡ይህ፡እንዴት፡ይቻለኛል፧አለው።ወጥቶም፡ከርሱ፡ጋራ፡ይቀመጥ፡ዘንድ፡ ፊልጶስን፡ለመነው። 32፤ያነበውም፡የነበረ፡የመጽሐፉ፡ክፍል፡ይህ፡ነበረ፤እንደ፡በግ፡ወደ፡መታረድ፡ተነዳ፥የበግ፡ጠቦትም፡ በሸላቹ፡ፊት፡ዝም፡እንደሚል፥እንዲሁ፡አፉን፡አልከፈተም። 33፤በውርደቱ፡ፍርዱ፡ተወገደ፤ሕይወቱ፡ከምድር፡ተወግዳለችና፡ትውልዱንስ፡ማን፡ይናገራል፧ 34፤ጃን፡ደረባውም፡ለፊልጶስ፡መልሶ፦እባክኽ፥ነቢዩ፡ይህን፡ስለ፡ማን፡ይናገራል፧ስለ፡ራሱ፡ነውን፡ ወይስ፡ስለ፡ሌላ፧አለው። 35፤ፊልጶስም፡አፉን፡ከፈተ፥ከዚህም፡መጽሐፍ፡ዠምሮ፡ስለ፡ኢየሱስ፡ወንጌልን፡ሰበከለት። 36፤በመንገድም፡ሲኼዱ፡ወደ፡ውሃ፡ደረሱ፤ጃን፡ደረባውም፦እንሆ፥ውሃ፤እንዳልጠመቅ፡የሚከለክለኝ፡ምንድር፡ነው፧አለው። 37፤ፊልጶስም፦በፍጹም፡ልብኽ፡ብታምን፥ተፈቅዷል፡አለው።መልሶም፦ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡የእግዚአብሔር፡ ልጅ፡እንደ፡ኾነ፡አምናለኹ፡አለ። 38፤ሠረገላውም፡ይቆም፡ዘንድ፡አዘዘ፥ፊልጶስና፡ጃን፡ደረባው፡ኹለቱም፡ወደ፡ውሃ፡ወረዱ፥አጠመቀውም። 39፤ከውሃውም፡ከወጡ፡በዃላ፡የጌታ፡መንፈስ፡ፊልጶስን፡ነጠቀው፤ጃን፡ደረባውም፡ኹለተኛ፡ አላየውም፥ደስ፡ብሎት፡መንገዱን፡ይኼድ፡ነበርና። 40፤ፊልጶስ፡ግን፡በአዛጦን፡ተገኘ፥ወደ፡ቂሳርያም፡እስኪመጣ፡ድረስ፡እየዞረ፡በከተማዎች፡ዅሉ፡ወንጌልን፡
13958
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%89%B3%E1%8A%85%E1%88%A3%E1%88%A5%20%E1%8C%8D%E1%88%AD%E1%8C%8D%E1%88%AD
የታኅሣሥ ግርግር
የታኅሣሥ ግርግር በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ዓመቱ በገባ በአራተኛው ወር ላይ የተከሰተው የታኅሣሥ ፲፱፻፶፫ቱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ፤ የአገሪቷ መጭው ዕድሏ ፊቱን ገለጥ ያደረገብት ሁኔታ ነበር። ለምን? ከ፲፱፻፷፮ቱ አብዮት በፊት ዙፋኑን ክፉኛ ያናጋ ተቃውሞ ቢኖር፤ እንዲያውም የአብዮቱ ምሥረታ፣ በኢትዮጵያ “ዘመናዊ” ታሪክ ውስጥ ወሳኝ የሆነ የፖለቲካ ተቃውሞ ምዕራፍ መክፈቻ ሊባል የሚገባው ይኼው የአምሳ ሦስቱ ሙከራ ስለሆነ ነው። ከዚያ በፊት ዙፋኑ “የማይደፈር፣ የማይሞከር”፤ ንጉሠ ነገሥቱ የማይፈተን መለኮታዊ ሥልጣን እና እንደ ሥርወ መንግሥታቸው አመጣጥ “ሰሎሞናዊ ጥበብ”ን የተቀዳጁ ናቸው የሚባለውን ዕምነት እውን እንዳልሆነ የተገነዘብንበት የታሪክ ምዕራፍ ስለሆነ ነው። ከዚህም አልፎ በአፍሪቃ አኅጉር ከንስር ወይም ግብጽ ስኬታማ መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የተጸነሰው ሁለተኛው ሙከራ ነበር። በሌላ አመለካከት ደግሞ ሙከራውን በጥምር ያቀነባበሩት ሁለቱ ወንድማማቾች ተምሳሌት የስድሳ ስድስቱን አብዮት በወታደርዊና የሲቪል ገጽታዎች መንታ ጥምርነቱ፣ የሚያንጸባርቅም ፈር ቀዳጅ ድርጊት ሆኖ እናገኘዋለን። «የዓድመኞቹ ዓላማ መንግሥቱን ገልብጠው አንድ መንግሥት ለማቋቋም፣ አልጋ ወራሻችንን ምክንያት አድርጎ ለመስበክ የተቻላቸውን ያህል በብዙ መንገድ ሠርተዋል። ግን ዓላማው የሚበልጠው የነሱን አምቢሲዮን መሙላት፣ የቀረውን የሕዝቡን ያታለሉበት ነገር ሁሉ እኛ ከፈራነው ነገር የወጣ አንድም ነገር የለም።»ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ ከግርግሩ ክሽፈት በኋላ ለውጭ ጋዜጠኞች ከሰጡት ቃለ ምልልስ። የ፲፱፻፵፰ ዓ/ም ሕገ መንግሥት በ ፲፮ኛው ክፍለ ዘመን የጣልያን ተወላጁ ኒኮሎ ማክያቬሊ ሲጽፍ፣ “መገንዘብ ያለብን፣ አዲስ ስርዓትን በመሪነት ማስተዋወቅ ከሁሉም የበለጠ ፈታኝ ሥራ፤ የምሥረታው ተግባርም እጅግ አድካሚ የሆነ እና ውጤቱ ያልተረጋገጠ በመሆኑ የሚወዳደረው ነገር የሌለው ነው” ይላል፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በድሮው ስልት አዲስ ስርዓትን ለማስተዋወቅ ሞከሩ። እሳቸው ባለፈው ምዕተ ዓመት የተወለዱና ባለፈ ስርዓት ያደጉ ሲሆኑ “በስልጣኔ እርምጃ” ላይ ጉዞዋን የጀመረችው የኢትዮጵያ ልጆች ግን አብዛኛዎቹ ከጣልያን ወረራ በኋላ የተወለዱ ነበሩ። “ለአገራችሁ የሥልጣኔ እርምጃ ተግታችሁ ሥሩ፣ አገልግሉ!” ይሏቸው አልነበረም? ታዲያ “ወጣቱ ትውልድ” “ለአገር አንድነትና ብልጽግና” ብሎ ቢነሳ ያው አይደለም? ከ ፲፱፻፵፰ቱ “ሕገ መንግሥት” በኋላ ግን ወጣቱ ትውልድ ንጉሠ ነገሥቱን እንኳን በ“አዲስ ስርዓት” እና ሂደት ሊያሻሽሉ ቀርቶ እንዲያውም ለሥልጣኔ ሳንካ/ ጋሬጣ/ እንቅፋት ናቸው ብሎ አመነ። የአርባ ስምንቱማ ሕገ መንግሥት የተሻሻለ፤ ኢትዮጵያን ከዘመኑ ጋር የሚያጣምር ተብሎ ነበር የታወጀው። በውስጡ የተደነገጉት ሕጎች ግን ቁጥራቸው ከሢሶ በላይ የሚሆኑት ስለ ንጉሠ ነገሥታዊው ቤተሰብና የዘውዱን አወራረስ የሚመለከት እንጂ ወጣቱ እና የተማረው ወገን እንደጓጓው ኢትዮጵያን እንደነ ብሪታንያ እና እንደነ ጃፓን ወደ ሕገ መንግሥታዊ ንጉዛት የሚቀይር አልነበረም። ንጉሠ ነገሥቱ ፍጹም የሆነ ሥልጣን እንደያዙ የሚቆዩበት መሣሪያ ነበር። ይባስ ብሎ ይኸው ሕገ መንግሥት እንኳን የንጉሠ ነገሥቱን ሥልጣን ቀንሶ ለሕዝብ ሊያስረክብ ቀርቶ እንዲያውም የንጉሠ ነገሥቱ ሥልጣን “መለኮታዊነቱን” በማስረገጥ የእንደራሴው ምክር ቤት አባላት እንደተለመደው በሹመት እንጂ በሕዝብ ምርጫ እንደማይሰየሙ አረጋገጠ። ወጣቱ ትውልድ በሚያየው የኤሊ እርምጃ እና ለዚህም ምክንያት ናቸው ብሎ ባመነባቸው በንጉሠ ነገሥቱና አስተዳደራቸው እጅግ ተደናገረ። እነዚህ ወጣት መሪዎች፣ አንዳንዶቹም ውጭ የተማሩ የጥንታዊው ስርዓት ባለሥልጣናት ልጆች ቢሆኑም እርምጃው እንዲፋጠን፤ ዘመናዊ አዲስ ስርዓት እንዲመሠረት ያላቸውን ምኞትና ዓላማ ለማራመድ ሲሹ በግድ የንጉሠ ነገሥቱና የስርዓታቸው ተቃራኒ ኃይሎች መሆናቸው አልቀረም። እውነትም ከዚህ በፊት እነ ቢትወደድ ነጋሽ በዛብህ፣ ብላታ ታከለ ወልደሐዋርያት፤ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ እና የመሳሰሉ የንጉሠ ነገሥቱን ሥልጣንና ስርዓት ተፈታትነዋል። ነገር ግን ከሞት በስተቀር ያተረፉት ነገር ወይም ያመጡት ለውጥ አልነበረም። አሁን ግን በተማሩና “ተራማጅ” በተባሉ ወጣት ትውልድ የመሚመራው ቅራኔ ልዩ እና ዘላቂ መሆን ይኖርበታል ብለው ተማምነዋል። ወንድማማቾቹ መንግሥቱ ንዋይ በ ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ አራዳ ጊዮርጊስ ገዳም ሠፈር አካባቢ ተወለዱ። አባታቸው ዓለቃ ንዋይ የደብሩ ዓለቃ ነበሩ። መንግሥቱ በተወለዱ በስምንት ዓመታቸው በ፲፱፻፲፮ ዓ/ም ታናሽዬው ገርማሜ ንዋይ ተወለዱ። ሁለቱም ትምሕርታቸውን በ ተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ተከታትለው አዲሱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ሲመሰረት ወደዚያ ተዛውሩ። የገነት ጦር ትምሕርት ቤት ሲከፈት ደግሞ፣ መንግሥቱ ንዋይ ተመልምለው ከገቡት ዕጩ መኮንኖች አንዱ ነበሩ። ሌሎች (በኋላ ጄነራሎች) እንደነ አቢይ አበበ፣ አሰፋ አያና፣ ኢሳያስ ገብረሥላሴና ከበደ ገብሬ በዚሁ ትምሕርት ቤት ከመንግሥቱ ጋር የነበሩ ዕጩ መኮንኖች ናቸው። መንግሥቱ ከዚያው የጦር ትምሕርት ቤት በመቶ አለቃ ማዕረግ ተመርቀው ሲወጡ ወዲያው የጠላት ኢጣልያ ጦር አገሪቱን ይወርና እሳቸው ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር ወደማይጨው ዘምተው ግዴታቸውን ተውጥተዋል። ጠላትም ድሉን ሲቀዳጅ እና ንጉሠ ነገሥቱ ሲሰደዱ መቶ አለቃ መንግሥቱ በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደሸሸበት ነቀምት ሄደው እዚያ “ጥቁር አንበሳ” የሚባለውን ማኅበር መሥራች አባል ናቸው። ከጥቂት ጊዜም በኋላ ከጓደኞቻቸው ጋር ወደጅቡቲ ተሰደዱ። በ፲፱፻፴፪ ዓ/ም ንጉሠ ነገሥቱ ተመልሰው ካርቱም ሲገቡ እነኚህን ስደተኛ መኮንኖች ከጅቡቲ ወደካርቱም እንዲመጡ ይደረግና መንግሥቱ ንዋይ ከነ ሙሉጌታ ቡሊ፣ ነገሠ ወልደሐና፣ ወልደማርያም ኃይሌ፣ ዘውዴ ገበሳ እና ታምራት ዘገየ ጋር ሆነው ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ተቀላቀሉ። ወዲያውም ከእሳቸው ጋር በ፲፱፻፴፫ ዓ/ም አብረው ወደኢትዮጵያ በድል ሲገቡ በክብር ዘበኛ ውስጥ በጄኔራል ሙሉጌታ ሥር ሻምበል ሆነው ቆዩ። በመስከረም ወር ዓ/ም ኮሎኔል መንግሥቱ ብርጋዴር ጄኔራል ተብለው የክብር ዘበኛ ጠቅላይ አዛዥነትን ተሾሙ። ተራማጅ እና የክብር ዘበኛን ሠራዊት በሰገላዊ ውትድርና ንቃተ ሕሊናውን ለማዳበር ብዙ የጣሩ መኮንን እንደነበሩ ተመስክሮላቸዋል። ገርማሜ የስምንት ዓመት ታናሽ ቢሆንም ከሁለቱ የበለጠ የተፈጥሮ ኮስታራ፣ ትጉሕ ተማሪ እና ስፖርተኛ (በተለይም በእግር ኳስ) እንደነበር ይነገርለታል። ታላቅ ወንድሙንም ተከትሎ አንደኛ ደረጃ ትምሕርቱን በተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በኮተቤው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትምሕርት ቤት ካጠናቀቀ በኋላ በ፲፱፻፴፭ ዓ/ም ገደማ በልዑል አልጋ ወራሽ መርድ አዝማች አስፋ ወሰን ከሁለት ዘመዶቹ ገርማሜ እና አምዴ ወንዳፍራሽ፣ ሙሉጌታ ስነጊዮርጊስ፣ ሙላቱ ደበበ እና ምናሴ ኃይሌ (በኋላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩት) ጋር ወደአሜሪካ ለትምሕርት ተላኩ። በዚህ ጊዜ ሌሎቹ ለጉዟቸው ሱፍ ልብስ ሲያሰፉ፣ ገርማሜ (ንዋይ) ግን በርኖስ ይገዛና ይሄንኑ ኮት እና ሱሪ አሰፍቶ ለብሶ ወደ ዊስኮንሲን ዩኒቨርሲቲ ይጓዛል። ከዊስኮንሲን የመጀመሪያ ጉላፑን ይቀበልና ሊቀኪን ጉላፑን ደግሞ ከ ኮለምቢያ ዩኒቨርሲቲ በ ደቦሰብ ሰገል ይቀበላል። አሜሪካ በነበረበት ጊዜም በ”ሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር” ፕሬዚደንት ነበረ። ለሊቀኪን ጉላፑ መመረቂያ ያቀረበው የጥናት ጽሑፍ “የነጮች የሠፈራ ፖሊሲ በኬንያ ላይ ያለው ተጽእኖ 1954)) በሚል ርዕስ ሲሆን በጭቆና ቀንበር ሥር የሚኖሩ አፍሪቃውያንን ዕሮሮ የሚያስተጋባ ጽሑፍ ነው። ትምሕርቱን እስከ ዲበሲን ጉላፕ ደረጃ ለመከታተል ቢፈልግም ወደኢትዮጵያ እንዲመለስ በተደረገለት ጥሪ መሠረት በ፲፱፻፵፮ ዓ/ም አገሩ ተመልሶ ሲገባ መጀመሪያ በአገር ግዛት ሚኒስትር ውስጥ የደጃዝማች (በኋላ ራስ መስፍን ስለሺ በኋላም የሚኒስቴሩ የራስ አበበ አረጋይ ዋና ጸሐፊ ሆኖ ሲያገለግል ቆየ። እዚሁ አገር ግዛት ሚኒስቴር ውስጥ በነበረበት ጊዜ በአፍሪቃ አኅጉር የመጀመሪያው መፈንቅለ መንግሥት በንስር የተሳካበት ጊዜ ነበር። ገርማሜም ለኮሎኔል ናስር መንግሥት በድብቅ “እባካችሁ ስለመንግሥታችሁ አቋም እና አመሠራረት ማብራሪያ ላኩልን” የሚል ደብዳቤ መላኩ ሲደረስበት በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት እና በጊዜው ባለሥልጣኖች ላይ ምን ያህል ሽብር እና የእምነት ጉድለት እንደጣለ መገመት ይቻላል። አለባበሱ ሁሌም በካኪ ልብስና ቀይ ክራባት ስለነበረም “ወልፈናኝ” የሚል ቅጽል ስም ከማትረፉም በላይ ለአብዮታዊ መንግሥቶች ከጻፈው ደብዳቤ ጋር በትንሹ የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት ጥርጣሬ፣ በተጨባጭ ሁኔታ ግን ታላቅ ትኩረት እንዲሰጠውና በ”እንግልት ሥፍራ” መንፈሱ መሰበር እና ሎሌነቱ መፈተን እንዳለበት ወሰኑ። ስለዚህም በተከታታይ በስውር ግዞት የሩቅና ፈታኝ ግዛቶች አስተዳዳድሪ እየተደረገ ይሾማል። የገርማሜ ንዋይ የመጀመሪያው መፈተኛ የወላይታ አውራጃ ገዥነት ነበር። እሱ ግን ይሄንን የግዞት ቦታ የፍትሓዊ አስተዳደር ሙከራ ጣቢያ በማድረግ ብዙ “ፍሬያማ” ሥራዎችን ሠርቷል። ለምሳሌ፦ በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች የሚማሩበትን ትምሕርት ቤቶች በመሥራት የሥፍራ ዕቅድ በመጀመርና የጭሰኝነትም ውልም በጽሑፍ በመደንገግ የጭሰኛውን መከራ ከፈለለት በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በኩል ግን፣ እንኳን መንፈሱ ሊሰበር ቀርቶ እንዲያውም በአውራጃው ሕዝብ የተወደደ ሲሆን እንግልቱ አንሷል እንደማለት ያህል ይመስላል፣ በዘመኑ የእንግሊዝ መንግሥት የኢጣልያ ሶማልያን እና በጊዜው በሞግዚትነት ያስተዳድር የነበረውን የኦጋዴንን ግዛት አጣምሮ “ታላቋ ሶማልያ” በሚል አንድ አድርጎ ከኢትዮጵያ እጅ ለመፈልቀቅ በሚዶልትበት ፈታኝ ጊዜ፣ ገርማሜን የጅጅጋ አውራጃ ገዥ ያደርጉታል። እሱ ግን የኢትዮጵያ ሱማሌዎችን ሕይወት ለማሻሻል በወሰዳቸው እርምጃዎች ተወዳጅነትን አገኘ እንጂ እንደተገመተው መንፈሱም አልተሰበረ፣ ሥራው አልከሸፈም። መንግሥት በዚህም በጠረፍ አስተዳደሩም ላይ ጣልቃ እየገባበት ሊያደንቅፈው መሞከሩን አልተወውም። ያንጊዜ ነው ማዕበሉን መለወጥ አማራጭ የሌለው ተግባር መሆኑን የተረዳው። ወንድሙንም ለዚሁ ዓላማ ማነሳሳት የጀመረው ያኔ ነው። የሙከራው ጥንሰሳ መንግሥቱ ንዋይ ለፖሊስም ሆነ በሕይወታቸው ላይ ለፈረደባቸው ችሎት እንደገለጹት፣ ከ ዓ/ም ጀምሮ ንጉሠ ነገሥቱን እየተከተሉ በየከተማው፣ በየአውራጃውና በየወረዳው ሲዘዋወሩ የአቤቱታ አቅራቢው ሕዝብ ብዛትና በአዋጅ የሚነገረው ሁሉ ተግባር ላይ አለመዋሉ ያሳስባቸው እንደነበር ተንትነዋል። የመፈንቅለ መንግሥቱም ሦስተኛ አባል የነበሩት የንጉሠ ነገሥቱ ልዩ ካቢኔ ጸጥታ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ሌተና ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁም እንዲሁ በፍትሕ ዕጥረት ምክንያት ብሶት እንደተሰማቸው ይነገራል። አራተኛው አባል ብርጋዴር ጄነራል ጽጌ ዲቡ የብርጋዴር መንግሥቱ የቅርብ ወዳጅ ከመሆናቸውም ሌላ የፖሊስ ሠራዊቱ ዋና አዛዥ ነበሩ። ጽጌና መንግሥቱ አብረው ይውላሉ አብረው ያመሻሉ። በፖሊስ ሠራዊት ፈጥኖ ደራሽ ግቢ መኮንኖች ክበብ ነው የሚውሉት የሚያመሹት። ወንድማማቾቹ አባታቸው ዓለቃ ንዋይ በሞቱ በሁለተኛው ወር በአንድ ድግስ፤ መንግሥቱ ከወይዘሪት ከፋይ ታፈረ ጋር ገርማሜ ደግሞ ከወይዘሪት አያልነሽ ዘውዴ ጋር የካቲት ቀን ዓ/ም ተዳሩ። በሚቀጥለው ዓመትም ሚያዝያ ቀን ዓ/ም በሱሉልታ የተካሄደው የክብር ዘበኛ ሠራዊት የጦር ታክቲክ ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደውል መሆኑን እና መፈንቅለ መንግሥቱ የዚያን ዕለት እንደተጀመረ እነ አቶ መኮንን ሀብተወልድ ገምተዋል ይባላል። ለማንኛውም የሙከራው ጥንሰሳ ተደርሶበት ነበ፤። አልፎ ተርፎም ንጉሠ ነገሥቱን የጸጥታና ስለላ ክፍል ሃላዊዎቻቸው አስጠንቅቀዋቸው ነበር ቢባልም፣ “አያደርጉትም” በሚል ንቀትም ይሁን ወይም ደግሞ በዕርግጥ የሚከሰት ተግባር ከሆነ ደግሞ እራሳቸውን ከጥቃት አግጣጫ ለማስወገድ ያቀዱትም የ”ሰሎሞናዊ ጥበብ” ሊሆን ይችላል፤ ብቻ ንጉሠ ነገሥቱ ኅዳር ቀን ለጉብኝት መጀመሪያ ወደምዕራብ አፍሪቃ ቀጥሎም ወደብራዚል በረሩ። ለእድምተኞቹ ይሄ እንከን ወይም ተወዳዳሪ የሌለው አመቺ ሁኔታን ፈጠረላቸው። የታኅሣሡ ጉሽ ሙከራው ማክሰኞ ታኅሣሥ ቀን ተጀመረ። ለትላልቅ መሳፍንት፣ መኳንንቶችና ዋና ሚኒስቴሮች “እቴጌ ታመዋልና በአስቸኳይ ወደቤተ መንግሥት ይምጡ” የሚል የስልክ ጥሪ መልክት ተላለፈ። እነ ራስ ስዩም መንገሻ፣ ራስ አበበ አረጋይ፣ አባ ሐና ጅማ፣ መኮንን ሀብተወልድ እና ሌሎችም በተቀበሉት ጥሪ መሠረት ቤተ መንግሥቱ ሲደርሱ ከእቴጌይቱ እና ከአልጋ ወራሽ ጋር ቁጥጥር ስር ዋሉ። የጦር ሠራዊቱ ኤታ ማጆር ሹም ሜጀር ጄነራል መርድ መንገሻ እና የምድር ጦር አዛዡ ሜጀር ጄነራል ከበደ ገብሬ ግን በተደጋጋሚ ቢጠሩም አሻፈረኝ ብለው አፈንግጠው ቀሩ። ዕሮብ ታኅሣሥ ቀን ወንድማማቾቹ መፈንቅለ መንግሥቱን ለሕዝብ ሲያስተዋውቁ፣ ለማስተላለፍ የፈለጉት ዐቢይ መልእክት ኢትዮጵያ በቅርብ ነጻ ከወጡት የአፍሪቃ አገሮች እንኳን ስትነጻጸር ምን ያህል ወደኋላ እንደቀረችና የመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ የሀገሪቱን የቀድሞ ዝናና ክብር ለማደስ መሆኑን ነው። የሰፊው ሕዝብ ብሶት የቆረቆራቸው መሆኑን በመግለጽ፣ ፋብሪካዎች ለማቋቋምና ትምሕርት ቤቶች ለመክፈት ቃል ገቡ። የለውጥ ፈላጊ ናቸው የሚባሉትን ልዑል ራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾማቸውንና አልጋ ወራሹን አስፋ ወሰንን (“አስገድደው”) በማስማማትም መንግሥት በቆረጠላቸው ደመወዝ እየተዳደሩ ለሕገ መንግሥት የሚገዙ ንጉሥ ሆነው እንደሚያገለግሉ እራሳቸው ለሕዝቡ በራዲዮ እንዲያስተላልፉ አደረጉ። ይሄ የአልጋ ወራሹ መልዕክት በገርማሜ ንዋይ፣ በሌተና ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁና ባልደረቦቻቸው የተዘጋጀ ንግግር ሲሆን በከፊል እንደዚህ ነበር፦ “…ድንቁርናን ከመካከላቸው አጥፍተው በአእምሯቸው መራቀቅና በኑሮ ደረጃው እየገፉ የሚሄዱ የዓለም ሕዝቦች ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሊያደርሰው የሚችል የማይፈጸም የቃል ተስፋ መስማት ሳይሆን እውነተኛ ተግባር ላይ የዋለ የሕዝብ የአእምሮና የኑሮ እድገት የሀገር ኃብት ልማት ፕሮግራም እስከዛሬ ድረስ ተዘርግቶ ካለማየቱም በላይ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ነጻነታቸውን ያገኙ የአፍሪቃ አገሮች እንኳን ሳይቀሩ በሚፈጽሙት የስልጣኔ እርምጃዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ እየቀደሙና ወደኋላ እየጣሉ ወደፊት የሚገሰግሱ መሆናቸው ለኢትዮጵያ ዕለት በዕለት ገሃድ እየሆነለት ሄደ። ይሄም ሁኔታ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያን ሕዝብ የረጅም ተስፋ መጨረሻ ላይ አላደረሰውም። ይህም ከመሆኑ የተነሳ ከጥቂት ጊዜ ወዲህ የተጀመረው የሕዝብ እንቅስቃሴ እነሆ ዛሬ ሥልጣንን ጨብጦ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለሀገሪቱም መድኅን ከመሆን ደረጃ ላይ መድረሱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ልገልጽላችሁ ዕድል በማግኘቴ ደስታዬ ፍጹም ነው።…….” ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋና ተቃራኒዎቹ፤ አንደኛው ከሻለቃነት ማዕረግ በአንድ ጊዜ ወደ ብርጋዴር ጄነራልነት የተተኮሱት ሜጀር ጄነራል መርዕድ መንገሻ ሲሆኑ ሌላው ደግሞ ሜጀር ጄነራል ከበደ ገብሬ ያለመያዛቸው ለተቃራኒው ኃይል ጊዜ የሰጠና በመጨረሻም የሙከራውን መክሸፍ ምክንያት ሆኑት ከሚባሉት ዐቢይ ጉዳዮች ዋናው ነው። ከመኳንንቱ መኃል ደግሞ የሕዝብ እንደራሴዎች ሸንጎ ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩት ዳጃዝማች (በኋላ ልዑል ራስ) አሥራተ ካሳ ነበሩ፡ እነኚህ ሁለት ጄነራሎችን እና የመሳሰሉ ተቃራኒዎችን መንግሥቱ ንዋይ ሌሎቹን በቁጥጥር ሥር ባዋሉበት ስልት እንዲመጡ ቢጠይቋቸውም አሻፈረን ብለው መቅረታቸው እጅግ በጣም በጅቷቸዋል። ሌተና ኮሎነል ወርቅነህ ገበየሁ ለመፈንቅለ መንግሥቱ ስኬታማነት እነዚህን ሁለት ጄኔራሎች በአስቸኳይ ቁጥጥር ላይ ማዋል ወሳኝ መሆኑን ደጋግመው ቢያስታውሱም ጄነራል መንግሥቱ ግን “ደም መፋሰስን ያስከትላል” በሚል ዕምነት ውድቅ አደረጉባቸው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስም “ክርስቲያን የሆናችሁ ልጆቼ እንዲሁም የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ…..ትናንትና አንዳንድ የክብር ዘበኛ ሠራዊት አባላት….ሀገራቸውን ክደዋል።….እነኚህን ከሃዲዎች አትመኑ አትከተሏቸው። በተሰጠኝ ሥልጣን አውግዣችኋለሁ…” የሚለውን መልክታቸው በሠፊው ተሰራጨ/ተበተነ። አቶ ጌታቸው በቀለ በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ፣ ኮሎነል ወርቅነህ "ስለ መፈንቅለ መንግሥቱ መጠንሰስ የሰማሁት ከተጀመረ በኋላ ነው። አሁን ተቃዋሚ ብሆን ጠንሳሾቹ ይገሉኛል። ከነሱ ጋር ሆኜ ለለውጥ ስዋጋ ብሞት ይሻለኛል ብዬ ወስኛለሁ።" አሉኝ ብለዋል መንግሥቱ ንዋይና ሁለቱ ጓደኞቻቸው ስላልተያዙት ሁለት ጄነራሎች የነበራቸው ግምት በጣም አነስተኛ ሲሆን ጄነራል መርድ የተገመቱት በአዲሱ መንግሥት ውስጥ ስለሚኖራቸው የሥልጣን ክፍያ ዋስትና ለማግኘት ፍላጎት እንዳላቸው ሲሆን፤ በጥሩ ኢትዮጵያውነት የተወሱት ከበደ ገብሬ ደግሞ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደህንነት ባላጋራ እንደማይሆኑና ከመርዕድ መንገሻ ጋር እንዳልተስማሙ በተጨባጭ መግለጫ የተደገፈ ነበር። ሆኖም የነኚህን አፈንጋጭ ጄነራሎች ከሥልጣን መሻር በራዲዮ አስነገሩ። ሐሙስ ታኅሣሥ ቀን የነጄነራል መርድ ተቃራኒ ኃይል ዝግጅቱን ጨርሶ በዚያው ዕለት ከቀትር በኋላ በዓየር እና በታንክ ጭምር የተፋፋመ ውጊያ ሲጀምር መንግሥቱ ንዋይ መምሪያ ክፍላቸውን ወደ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ያዛውራሉ። ዓርብ ታኅሣሥ ቀን የሙከራው ኃይል እየተዳከመ በአንጻሩ ደግሞ ተቃዋሚዎቻቸው እያደር እየጎለመሱ መሄዳቸውን የተገነዘቡት ሽብርተኞች በቁጥጥራቸው ላይ የነበሩትን ሃያ መሳፍንት፣ መኳንንት፣ ሚኒስትሮችንና መኮንኖችን ወደ አረንጓዴ ሳሎን ያዛውሩና አልጋወራሹንና አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ለብቻቸው እንዲጠበቁ ያደርጋሉ። ጄነራል ጽጌ ዲቡ ወዲያው ከተቃራኒ ወገን በተተኮሰ ጥይት ሲገደሉ፣ እነ ጄነራል መንግሥቱ የያዟቸውን እስረኞት ረሽነው ለማምለጥ ወሰኑ። ከነዚህ እስረኞች መሃል የነበሩት ብርጋዴር ጄነራል መኮንን ደነቀ “እኔ አውቆ ይሆን ሳያውቅ እንደሆነ አላውቅም፣ ነገር ግን መጀመሪያ ጥይት የተተኮሰው በሙሉጌታ ላይ ነው።” “መንግሥቱ ንዋይ ውጡ ሲል ሲወጡ ከጀርባቸው ተኩስባቸው ብሎ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር መንግሥቱ። በኋላ ተነሱና ውጡ አሉ፡ አባ ሐና እኔ ቤቱን አውቀዋለሁ ከዚህ የተሻለ ቦታ የለም ሲሉ መንግሥቱ “ታዲያ አትሏቸውም?” ሲል ተኩሱ ተከፈተ።” ይላሉ። መንግሥቱ ንዋይ ግን በ የካቲት ወር ዓ/ም ለፍርድ ቤት በሰጡት ቃል “እኔ ግደሉም አላልኩም እራሴም አልተኮስኩም” ብለዋል። ያም ሆነ ይህ፣ ከሀያዎቹ መኻል እነ ሙሉጌታ ቡሊ፤ ራስ ሥዩም መንገሻ፤ ራስ አበበ አረጋይ፤ አቶ መኮንን ሀብተወልድ፤ አባ ሐና ጅማ፤ አቶ አምደሚካኤል ደሳለኝ፤ ብላታ ዳዊት ዕቁበ እግዚ፤ አቶ ገብረ ወልድ እንግዳ ወርቅ፣ ብላታ አየለ ገብሬ፤አቶ ታደሰ ነጋሽ፤ በጠቅላላው አሥራ አምስቱ ሲገደሉ፣ ሦስቱ ቆስለው ራስ አንዳርጋቸው መሳይ እና አንድ ሌላ ሰው ደግሞ ምንም ሳይነካቸው ተርፈዋል። ተቆሰሉትም አንዱ በአሥራ ሁለት ጥይት ተመተው የተረፉት ብርጋዴር ጄነራል መኮንን ደነቀ ናቸው። ጽጌ ዲቡ ከጦር ሠራዊት ኃይሎች ጋር ሲታኮሱ ቀደም ብለው ሲሞቱ፣ ኮሎኔል ወርቅነህ ደግሞ በተከበቡ ጊዜ “እጄን አልሰጥም ብለው” ራሳቸውን አጠፉ። መንግሥቱና ገርማሜ ግን በቤተ መንግሥቱ ጋራዥ በኩል ሾልከው ወደቀጨኔ መድሃኔ ዓለም በኩል ጫካ ለጫካ ኮበለሉ። ከሙከራው በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ በማግስቱ ቅዳሜ ታኅሣሥ ቀን በአስመራ በኩል አድርገው ብዙም ወደአልተረጋጋችው አዲስ አበባ ከተማ ሲገቡ ወዲያው የወንድማማቾቹን ፎቶግራፍ የያዘ ማስታወቂያ በሠፊው ተሰራጨ። “የብዙዎችን ደም በግፍ ያፈሰሱት ከሐዲዎች የመንግሥቱ ንዋይና የገርማሜ ንዋይ ፎቶግራፎች እነዚህ ናቸው። ……..ጢማቸውን በመላጨት ወይም በማሳደግ ወይም በሌላ ዘዴ ይጠቀሙ ይሆናል። እነሱን ይዞ ለመጣ ታማኝ፣ በእያንዳንዳቸው አሥር ሺህ ብር/$ 10000 እና ልዩ ሽልማት ይሰጠዋል።” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ታኅሣሥ ቀን ወንድማማቾቹና ባልደረባቸው ሻምበል ባየ ጥላሁን ከአዲስ አበባ ድሬ ጨለባ በሚባል ሥፍራ ወደሚገኝ የዘመዳቸው እርስት በማምራት ላይ ሳሉ ነው የተከበቡት። እዚሁ ሥፍራ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ሻምበል ባየ እና ገርማሜ ሲገደሉ መንግሥቱ ነዋይ ግን ክፉኛ ቆስለው ይያዛሉ። የሁለቱ ሟቾች አስከሬን አዲስ አበባ ቤተ መንግሥቱ ደጃፍ ላይ ካደረ በኋላ በማግሥቱ ከኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ አስከሬን ጋራ ምኒልክ አደባባይ ላይ ተሰቅሎ ዋለ። መንግሥቱ ንዋይ ቆስለው ከተያዙ በኋላ ከወር በላይ በህክምና ቆይተዋል። ከህክምናውም በኋላ የካቲት ቀን ለፍርድ ሲቀረቡ አንድ ዓይናቸው ድሬ ጨለባ ላይ የጠፋ ከመሆኑም በላይ ሁለተኛውም አስተማማኝ አልነበረም፡፡ በዚሁ ችሎት ላይ “መጀመሪያ ላይ አንድ ደረጃ ባላቸው የተያያዘ፤ በተማሩና አዲስ መንፈስ ባላቸው ኢትዮጵያውያኖች መንግሥት ለማቋቋም ነው ያሰብኩት። ከዚያ በኋላ ጃንሆይ ይጠየቃሉ። ጃንሆይ ይጠየቁና በእንግሊዝ መንግሥት ደረጃ ወይም ፖሊሲ መሠረት በመንግሥት ጉዳይ ውስጥ አጠቃላይ ሳይገቡ ፓርላማው ራሱ ነው የሚገዛው። ቤተ መንግሥቱን የሚያዘው ፓርላማ ነው።” ብለዋል ፍርድ ቤቱ መጋቢት ቀን ውሳኔውን ሰጠ። ጄነራሉ ይግባኝ ይሉ እንደሁ ሲጠየቁ ከዚህ የሚከተለውን እንደትንቢት የሚቆጠር ምላሽ ሰጡ። ”እናንተ ዳኞች! የበየናችሁብኝን የሞት ፍርድ ያለይግባኝ ተቀብያለሁ። ይግባኝ ብዬ የሚመለከትልኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቢሆን ኖሮ ይግባኝ ማለት በፈልኩ ነበር። ነገር ግን ይህ እንደማይሆን አውቃለሁና የዓፄ ኃይለ ሥላሴን ፊት ለማየት አልፈቅድም። በእግዚአብሔር ስም በተቀመጣችሁበት የፍርድ ወንበር ላይ ከመቀመጣችሁ በፊት በእኔ ላይ የምትሰጡትን ፍርድ ታውቁት እንደነበር ሳስበውና ፍርድ እስከዚህ መድረሱን ስታዘብ ኀዘኔ ይብሳል። ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት፣ ነጻነትና እርምጃ የተነሳሁ ወንጀለኛ ነኝ እንጂ ላፋጀው የተነሳሁ ወንበዴ አይደለሁም። ይህን ማድረግ ፈልጌ ቢሆን ኖሮ ማንም የማይወዳደረው ሠራዊትና መሣሪያ ሳላጣ ዛሬ ከእናንተ ፊት ለመቆም ባልበቃሁ ነበር። እኔ ከዓፄ ኃይለ ሥላሴ ድንክ ውሾች ያነሰ ደመወዝ የሚያገኙ ሁለት የተራ ወታደሮችን አጣልቼ ለማደባደብና ሀገር ለማፍረስ አለመነሳሳቴን የሚያረጋግጥልኝ ከእናንተ በትዕዛዝ ያገኘሁትን ፍርድ ለመቀበል እዚህ መቆሜ ነው። ከእኔ በፊት በግፍ የፈሰሰው ንፁህ የኢትዮጵያዊያን ደም ብዙ ነው፡፡ በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ግፍ ሽልማት በመሆኑ እኔ ለመሞት የመጀመሪያው ሰው አልሆንም፡፡ ሥልጣን አላፊ ነው፡፡ እናንተ ዛሬ ከጨበጣችሁት የበለጠ ሥልጣን ነበረኝ፡፡ ሀብትም አላጣሁም፡፡ ነገር ግን ሕዝብ የሚበደልበት ሥልጣንና ድሃ የማይካፈለው ሀብት ስላልፈለግሁ ሁሉንም ንቄ ተነሳሁ። አሁንም እሞታለሁ፡፡ ሰው ሞትን ይሸሻል እኔ ግን በደስታ ወደሞት እሄዳለሁ፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅነት ቀድመውኝ መስዋዕት የሆኑትን አብረውኝ ተነስተው የነበሩትን ጀግኖች ወንድሞቼን ለመገናኝት ናፍቄአለሁ፡፡ የጀመርኩት ሥራ ቀላል አይደለም። ነገር ግን አልተሸነፍኩም። ወገኔ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጀመርኩትን ሥራ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ፈጽሞ እራሱን እንደሚጠቅምበት አልጠራጠርም። ከሁሉ በበለጠ የሚያስደስተኝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ልሠራለት ካሰብኳቸው ሥራዎች አንዱ የኢትዮጵያን ወታደር ዋጋና ክብር ከፍ ማድረግ ሲሆን ይህ ኀሳቤ ሕይወቴ ከማለፉ በፊት ሲፈፀም ማየቴ ነው፡፡ ዛሬ መኖራችሁን በማየቴ ነገ መሞታችሁን ረስታችሁ አሜን ብላችሁ ቀናችሁን በማስተላለፍ በመገደዳችሁ በእኔ ላይ ሳትፈርዱ በራሳችሁ ላይ የፈረዳችሁ መሆናችሁን አላስተዋላችሁም፡፡ እኔ የተነሳሁት ከትክክለኛ ህግና ከህሊናችሁ ውጭ ለመፍረድ እንዳትገደዱ ለማድረግ ነበር፡፡ ባጭሩ በእኔ ላይ ለመፍረድ የቸኮላችሁትን ያህል አሥር እና አሥራ አምስት ዓመት የምታጉላሉት የድሀውን ሕዝብ ጉዳይ እንደዚህ አፋጥናችሁ ብትሠሩትና ብትሸኙት ኖሮ የእኔ መነሳት ባላስፈለገ ነበር። ከእናንተ ከዳኞችና የሞት ፍርድ እንድትበይኑብኝ ካዘዛችሁ ሰው ይልቅ ፍርድ ተቀባይ የዛሬው ወንጀለኛ የነገው ባለታሪክ ነኝ። የኔ ከጓደኞቼ መካከል ለጊዜው በሕይወት መቆየትና ለእናንተ ፍርድ መብቃት የመመዘኑን ፍርድ ለመጭው ትውልድ የሚያሳይ ይሆናል፡፡ ዋ ዋ ዋ ለእናንተና ለገዢአችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃሳቤ በዝርዝር ገብቶት በአንድነት በሚነሳበት ጊዜ የሚወርድባችሁ መዓት አሰቃቂ ይሆናል፡፡ በተለይ የአፄ ኃ/ስላሴ የግፍ መንግስት ባላደራዎች ሆነው ድሀውን የኢትዮጵያ ህዝብ ሲገሸልጡት ከነበሩት መኮንን ሀ/ወልድና ገ/ወልድ እንግዳወርቅን ከመሳሰሉት በመንፈስ የታሰሩ በስጋ የኮሰሱ መዠገሮች መካከል ጥቂቶቹን ገለል ማድረጌን ሳስታውስና የተረፉትም ፍፃሜያቸውን በሚበድሉት በኢትዮጵያ ህዝብ እጅ ላይ መውደቅ ሲሰማኝ ደስ ይለኛል፡ በዚሁም መሠረት ጄነራሉ መጋቢት ቀን ዓ/ም በስቅላት ተቀጡ። መንግሥቱ ንዋይ በተከተሉት ጥቂት ዓመታት የንጉሠ ነገሥቱን ስርዓት በመቃወም ለቀጠለው ትግል እና ከአሥራ ሁለት ዓመት በኋላም ስርዓቱን ላወደመው አብዮት ዋና ፈር ቀዳጅና አርአያ ሲሆኑ በወንድማቸው እና በአባታቸው ስም የሰየሟቸው የሁለት ወንድ ልጆች አባትም ነበሩ። ማጣቀሻ ዋቢ ምንጮች (1994) ጦቢያ መጽሔት፣ አራተኛ ዓመት ቁጥር 2፣ ጥቅምት 1988 ዓ/ም ጥቁር ደም ጋዜጣ፣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር 64፣ መስከረም 23 ቀን 1992 ዓ/ም 1960 =-7449873047253848654# (1993) የኢትዮጵያ
9004
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A4%E1%89%BD%E1%8A%A0%E1%8B%AD%E1%89%AA
ኤችአይቪ
ኤችአይቪ ቫይረስ የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ የነጭ ደም ሴሎችን (ህዋሳትን) በማጥቃት በቀላሉ ሰውነት ለበሽታ እንዲጋለጥ የሚያደርግ ቫይረስ ነው። ኤችአይቪ ያለባቸው ሰዎች የበሽታው ምልክት ሳይታይባቸው ለብዙ ዓመታት መኖር ይችላሉ። ቫይረሱ በሰውነታ ውስጥ እስከ አስር ዓመት በመቆየት ምንም ሳይታውቅ እና ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይታይበት በመኖር እና አለማውቅ ከአንድ ሰው ወደሌላ ሰው ሊተላለፍ የሚችል አደገኛ ቫይረስ ነው። ኤችአይቪ የሚያጠቃው ኤችአይቪ የሚያጠቃው የሰውነት የነጭ የደም ሴሎችን የሰውነት የበሽታ የመከላከያ ተቁዋማትን ነው። የሲዲፎር በመባል የሚታውቀውን የሰውነት የነጭ የደም ሴል ቁጥሩን 4 ከ 200 በታች በማድረግ የቫይረሱ መጠን በደም ውስጥ እንዲጨምር በማድረግ ለሕይወት ኣደገኛ እና ምቹ ጊዜ ተባቂ በመባል የሚታውቁትን በሸታዎች (ኦፓርቹንስቲክ ኢንፈክሽስ በመፍጠር ኤድስ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደርጋል። ኤድስ ኤድስ ማለትም ኣኳየርድ ኢምዩኖደፊሸንሲ ሲንድረም ሲሆን ኤድስ ኤችእይቪ የማያማጣው የመጨረሻ ደረጃ ነው። ኤችአይቪ ያለበት ሰው ኤድስ ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ ዓመታት ይወስድበታል። እንዲሁም መድኃኒቱንም ሳይጅምር ኤድስ ደረጃ ሳይደርስ ብዙ ዓመታት ሊቆይ ይችላል። አንድ ሰው የኤድስ ደረጃ ላይ ደረሰ ማለት የኤችአይቪ ቫይርስ የበሽታ መከላከያ ሃይል ተቁዋማትን ደምስሶ እና ሰውነታችን ከማንኛውም በሽታ የመቋቋም ኃይሉን በማሳጣት ለተለያዩ ኢንፈክሽኖች ይጋለጣል። አንድ ሰው አንድ ወይም ሁለት ኢንፌክሽኖች ሲኖሩበት እና በጣም ዝቅያለ የቲ-ሴል ቁጥር ሲኖረው ያሰው የኤድስ ደረጃ ደረሰ ሊያስብለው ይችላል። የኤችአይቪ አመጣጥ ሳይንቲስቶች የኤችአይቪን ቫይረስ አመጣጥ እንደጠቆሙት ከሆነ ከዌስት አፍሪካ ከሚገኝው ቺፓንዝ ዝርያ የመጣ መሆኑን አሳወቀዋል። ይህውም ሊሆን የቻለው የሰው ልጅ ቺፓንዚን ለምግብነት በሚይድንበት ጊዜ በሚደረገው የደም ንክኪ መሰርት ቫይርሱ ሊተላለፈ እንደቻለና። ከብዙ አመት በሃላም ቀስ በቀስ ወደ መላው አለም ሊስፋፋ እንደቻለ ገልጽዋል ኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 ዓ.ም.) ወዲህ ነው። በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤችአይቪ ቫይርስ ጋር አብረው ይኖራሉ። በዓለም ላይም ከ 25 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኤድስ በሚመጣ በሸታ ተይዘው ሞተዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዬጵያ ውስጥ የኤድስ ታማሚዎች መኖራችው የተረጋገጠው በ1978 ዓ/ም ነው። በ2006ዓ/ም ወደ 2.9 ሚሊዮን የሚጠጉ ወንዶች፤ ሴቶች እና ሕጻናትም ሕይወታቸውን አተዋል። ኤችአይቪ ከተያዙት ውስጥ ከግማሸ በላይ የሚገምቱት ሲሞቱ 39.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ከቫይርሱ ጋር በመኖር ይገኛሉ። በቅርቡ እንደተዘገበው 4.3 ሚሊዮን የሚጠጉ አዲስ ሰዎች በኤችአይቪ እንደተያዙ ይገልጻል። ኤችአይቪ መተላለፊያ መንገዶች የኤች አይቪ ቫይረስ ከሰውንት ከውጣ በሃላ በጣም ደካማ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ አይቆይም ወድያውኑ ይሞታል። በዛ የተነሳ ነው ኤችአይቪ ከማንም ሰው ጋር በምናደርጋቸው የዕለት ተለት እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ፣ እንደ እጅ መጨባበጥ፣ መተቃቅፍ፣ እና መሳሳም ሊያስተላልፉ እንደማይችሉና። በተጨማሪም ኤች አይቪ በመጸዳጃ ቤት መቀመጫ፣ በበር መኽፈቻ፣ በብርጭቆ መጠጫ፣ በምግብ ወይም በማንኛውም አይነት እንስሳ እንደ ቢንቢ ንክሻ በመሳሰሉት ሊይዝ አይችልም። ኤችአይቪ ለመያዝም ሆነ ለማስተላለፍ የሚችሉበት መንገዶች የተለያዩ ናቸው፣ መንገዶቹ ምን እንደሆኑ ማወቁ በጣም ጠቀሜታ አለው። ስለ ኤችአይቪ ዕውቀት ያለውን ሰው ማነጋገር ተገቢ ሆኖ ሳለ ይህንንም ከታች የተዘርዘረውን በተግባር ላይ ቢያውሉት መልካም ነው፣ ኤችአይቪ በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊተላለፍ ይችላል ቫይረሱ ያለበት ሰው የተጠቀመበትን የድረግ መርፌ ሌላ ሰው ቢጠቀምበት ቫይረሱ ሊተላለፍ ይችል። ቫይረሱ ካለበት ማንኛውም ሰው (ወንድ ወይም ሴት) ጋር የግብረ ሰዶም ግንኙነት በማድረግ በሽታው ሊይዝ ይችላል። ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር በሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ኤችአይቪ ያለባት እናት ቫይረሱን (ማህፀን ውስጥና በወሊድ ጊዜም) ለሕፃንዋ ማስተላለፍ ትችላለች። ቫይረሱ የለባት እመጫትን ጡት ወተት ካጠባች ቫይረሱን ሊተላለፍ ይችላል። መከላከያ እርምጃዎች 4ቱ መ" ዎችይ መታቀብ መወሰን መጠቀም መመርመር ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ በጣም ጠቃሚ ነው ከኤችአይቪ ቫይረስ ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይጠቅማል ከማንኛውም ዓይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት (ከተቻለ) መቆጠብ፣ ካልተቻለ ኣንድ ታማኝ የፍቅር ጓደኛ ጋር በመወሰን ኮንዶም መጠቀም ለረዥም ጊዜ ተማምነው ኣብረው የቆዩ ባልና ሚስት በመስጋትና ለኤችአይቪ ይይዘኛል በሚል ፍራቻ በኮንዶም መጠቀም የለባቸውም። ታማኝነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ኣስፈላጊ ስለሆነ ባለትዳሮች ታማኝንታችውን ማጎልበት ይጠበቅባቸዋል የሚወጉ ድራጎች (እየተደበቁ ተሰባስበው ባልፀዱ መሣሪያዎች ከሚወስዱ ጋር) አለመውሰድ ማለት መርፌና ሲሪንጋ ኣለመጋራት ከማያውቁት ሰው ወይም ከብዙ ሰዎች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ካደረጉ ከሌላ ሰው ጋር ምንም አይንት ግንኙንት ከመፈጽም በፊት መመርመራ ያድርጉ ለገንዘብ ብለው ከማያቁት ሰው ጋር ማንኛውንም ዓይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ኣለማድረግ ኤችአይቪ ለመያዝ የሚያስችሉ ባህሪዎች ዋነኞቹ -በጣም አስጊ ደረጃ ላይ ሊሆኑ የሚችሉ የሚወጉ ድራጎች (እየተደበቁ ተሰባስበው ባልፀዱ መሣሪያዎች ከሚወስዱ ብዙ ሰዎች ጋር) መርፌና ሲሪንጋ ከተጋሩ ልቅ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት፣ የግብረ ሰዶም ግንኙነት ከፈጸሙ ለገንዘብ ብለው የግብር ሥጋ ግንኙንት ወይም የግብረ ሰዶም ግንኙነት ከፈጸሙ ለአባላዘር በሽታ ተጋለጠው የሚያቁ ከሆነና ወይም ከላይ የተዘርዘሩትን ከፈጸመ ግለሰብ ጋር የወሲባዊ ግኑኘንት ከፈጸሙ የኤችአይቪ ምርመራ እርግጠኛ ዕራስን ለማወቅ ግዴታ መልሱ የሚገኘው የኤችአይቪ ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ ዕራሶን የሚጠራጠሩ ከሆነ ተመርመሩ። ተመርምረው ውጤቶን ከቫይረሱ ነፃ መሆኖ ቢነገሮትም የውሽት ውጤት የሚባል (ዊንዶ ፔሬድ የሚባል) ነገር ስላለ ከ 3-6 ወር በሃላ እርግጠኛ ለመሆን ደግመው መመርመር ይገባል። ይህን ሲያረጉ ግን አሁንም ኮንዶም መጠቀሞን አይርሱ። ኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 ዓ.ም.) ወዲህ ሲሆን እስከ 1985 ድረስ የተበከለ ደም ናሙና በመወጋትና በመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ይዚህ ሰለባ በመሆን ብዙ ሰዎች ተይዘዋል። ከ1988 ወዲህ ግን ኤችአይቪ ሲኖር ደም ውስጥ ነጭ ሴል የሚሠራውን ኣንቲቦዲ በመመርመር ኤችአይቪ ቫይረስ እንዳለ እና እንደሌለ የሚጣራበት ፈጣን የምርመራ ዘዴ ስለተሠራ በሆስፒታል ከሚሰጠን ደም መተላለፉ ቀርትዋል። ከአካል የሚወጡ ፈሳሾች ላይ ሁሉ ኤችአይቪን ማግኝት የሚቻል ቢሆንም መደበኛ የኤችአይቪ ምርመራ በደም ናሙና ላይ የሚደረግ የኤችአይቪ-1/2 አንቲ ባዲ ምርመራ ነው። እስታሁን የተሰሩትን የአንቲባዲ ምርመራ አይነቶችን በሁለት ከፍል ማየት ይቻላል። ኤላይዛ መሰረት አርገው የሚከናወኑ ኤላይዛ አይ.ኤፍ.ኤ ኤላይዛ-ዌስተርን ቦሎት ፈጣን ምርመራዎች የሚባሉት ተመርተው በገበያላይ የቀርቡ ወደ 60 የሚቆጠሩ መመርመሪያዎች ሲኖሩ በሶስት ዋና ዋና ቴክኒኮች ላይ የተመረኮዙ ናችው። ፓርዲክል አጉሌሽን ላተራል ፍሎ ፍሎ ትሩ እነዚህ መመርመሪያዎች እያንዳንዳቸው ለምርመራ ማከናወኛነት በምንጠቀምበት ጊዜ ምንም አይነት ተጨማሪ ኪሚካል አያስፈልጋቸውም። ለመጠቀምም ጊዜ የማይፈጅና ዋጋውም ተመጣጣኝ ነው። አስተማማጝነታቸውም ከኤላይዛር ጋር የሚስተካከል ነው። ፈጣን የኤችአይቪ ምርመራ ማለት ለቫይረሱ የተዘጋጀ አንቲ ቦዲ በደም ውስጥ መኖሩንና አለመኖሩን የሚያመልክት የምርመራ አይነት ነው። በፈጣን የምርመራ ዘዴ ውጤቱን ከ10-60 ደቂቃዎች ውስጥ ማውቅ የሚያስችል የመመርመሪያ ዘዴ ነው። ተመርምረው ውጤቶዎ ኤችአይቪ ፖዘቲቨ ከሆነስ በአሁኑ ጊዘ በኤችአይቪ ዙሪያ ላይ በዙ መረጃዎች የሚገኘበት ግዘ ስለሆነ ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርይቻላል። በአሁን ሰአት ኤችአይቪን እንደማንኛውም አይንት ቫይረስ አይቶ ጤናን እየጠበኩና መንፈስን ሳያስጨንቁ ተረጋግቶ መኖር ይቻላሉ። ኤችአይቪ እንዳይዘን የምንከላከልበት ክትባት በአሁኑ ሰአት የለም። ኤችአይቪ ከያዘም በኋላ የሚፈውስ መድኃኒት የለም። ነገር ግን ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖር የቻላለ። በአሁኑ ጊዜ ፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች ከፈተኛውን አስታውጾ በማድረግ ላይ የገኛሉ። ኤችአይቪ ያለበት ሰው በትክክል የፀረ-የኤችአይቪ መዳኒቶቹን በመውሰድ እንደማንኛውም ሰው መኖር ይችላል። ቫይርሱ ያለባቸው ሰዎች መውለድ ሲፈልጉ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ከጤና ባለሙያቸው ጋር በመነጋገር ጤነኛ ልጀ መውለስ ይችላሉ። ኤችአይቪ ያለባት እናትከማርገዝዋ በፊት ማወቅ የሚገባትን ቅድመ ተከተሎች መከተል ይኖርባታል። ኤችአይቪ እንዴት እንደሚተላለፍ መረጃዎችን በመከታተል ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ትክክለኛዎቹን ጥንቃቄዎች መከተልና ለሌሎችም ማስተማር የያንዳንዳችን ኃላፊነት መሆን አለበት። ኤችአይቪ እንዴት እንደሚተላለፈ ግንዛቤዎች እንዴት እንደምንከላከል መረዳትና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለብን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው። እንዳይስፋፋ መከላከል መታቀብ (ከማንኛውም አይነት የገብረስጋ ግንኙነት መቆጠብ) እንድ የትዳር ጛደኛ እስከሚያገኙ ድረስ ወይም ደሞ ኤችአይቪ እንዳለባችሁ ካወቃችሁ ሁለት ኤችአይቪ እንዳለባቸው ያወቁ ባለትዳሮች ወይም አበረው ያሉ ጉዋድኞች በግብረ-ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶም መጠቀም አለባቸው ምክንያቱም ከተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች ለመከላከል እና ከተለያዩ የኤችአይቪ ንዑስ ዝርያዎች ላለመያዝ ከሁለት አንዳቸው ብቻ ከሆኑ ኤችአይቪ ያለበት ሁልጊዜ ኮንዶም መጠቀም እና ቅባት ያለው ኮንዶም መጠቀም ወይ ደሞ ከአንድ ሰው በላይ ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙንት የሚፈጸሙ ከነበሩ ወይም ከሆኑ፦ የኤችአይቪ ምርመራ ያድርጉ ወንድ ከሆኑ እና ከወንድ ጋር የግብረ-ሰዶም ግንኙነት ፈጸመው ከሆነ ቢያንስ ቢያንስ በአመት አንዴ ይመርመሩ ሴት ከሆኑ እና ለማርገዝ እቅድ ካሎት ወይም ካርገዙ በአስቸኩዋይ ይመርምሩ (ጤነኛ ልጅ ለመውለድ ሲባል) የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ከመፈጸሞ በፊት ስለ ኤችአይቪ እና ሰለ ተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች ከወንድ/ከሴት ጛድኛ ጋር በግልጽ ማውራት ልምድ ማረግ አለብን በደንብ ተጠናኑ፣ ተወያዩ ስለ ሁለታችሁም ስለ አለፈው የወሲብ ሕይውታችሁ ውይም ድራግ ትጠቀሙ ከነበረ መጠጥ፣ ጫት ሱሰኝነት) ሌሎችም ከዚህ በፊት የኤችአይቪ ምርመራ አርገው እንደሚያቁና እንደማያቁ መጠያየቅ ምንም እንኩዋን የኤችአይቪ እያዛለሁ ብለው ምንም ጥርጣሬ ባይኖሮትም ሁሌ ለጠቅላላ ምርመራ በሚሄዱበት ጊዜ የኤችአይቪ ምርመራ ቢያረጉ በጣም ጠቃሚ ነው የውጭ መያያዣዎች አበሻ ኬር የበጎ እድራጊ ድርጅት 20, 2008 ትርጉም በአበሻ ኬር ትርጉም በአበሻ ኬር የኢትዮጲያ ኤድስ መረጃ ማእከል ኣበራ ሞላ 1991. ዶ/ር ኣበራ ሞላ 1991 1988
52821
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%8A%AD%E1%88%B1%E1%88%9D%20%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%A5%E1%89%B5
አክሱም መንግሥት
የአክሱም መንግሥት (ኤርትሪያ) መንግሥተ አክሱም (ግዕዝ) በ1ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ–ሐ. በ960 ዓ.ም የአክሱም ወይም የአክሱም ንጉስ ኢንዱቢስን የሚያሳይ የአክሱማይት ገንዘብ ንጉሥ የሚያሳይ ምንዛሬ የአክሱም መንግሥት በከፍተኛ ደረጃ በ6ኛው ክፍለ ዘመን የአክሱም መንግሥት በከፍተኛ ደረጃ በ6ኛው ክፍለ ዘመን ካፒታል ኤርትራ አክሱም ኩባር/ጃርማ (ከ800 ዓ.ም. በኋላ) የተለመዱ ቋንቋዎች ግእዝ ሳቢክ ግሪክ[1] (ከ1ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ)[2] ሃይማኖት ክርስትና (ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፤ ከ4ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በኋላ በይፋ) አክሱማይት አምልኮተ አምልኮ (ከ350 በፊት ይፋ የሆነ)[3] የአጋንንት ስም(ዎች) አክሱማይት፣ ኢትዮጵያዊ፣ አቢሲኒያ የመንግስት ንጉሳዊ አገዛዝ ሐ. 100 ዛ ሃቃላ (በመጀመሪያ የታወቀው) ሐ. 940 ዲል ናኦድ (የመጨረሻ) ታሪካዊ ዘመን ክላሲካል ጥንታዊነት እስከ መጀመሪያው የመካከለኛው ዘመን የተቋቋመ በ 1 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ቀደምት የደቡብ አረቢያ ተሳትፎ 3 ኛው ክፍለ ዘመን የሜሮን ድል 330 የኢዛና ወደ ክርስትና መቀየሩ 333 የሂሚያራይት መንግሥት ወረራ 520 ቀደምት የሙስሊም ወረራዎች 7 ኛው ክፍለ ዘመን በንግስት ጉዲት ተደምስሷል ሐ. በ960 ዓ.ም አካባቢ 1,250,000 ኪሜ2 (480,000 ካሬ ማይል) ምንዛሬ ምንዛሬ የቀደመው በ ተሳክቷል። ዲኤም የዛግዌ ሥርወ መንግሥት የሲሚን መንግሥት የሸዋ ሱልጣኔት ዛሬ በከፊል ኤርትሪያ ጅቡቲ ሱዳን የመን የአክሱም መንግሥት (ግእዝ፡ መንግሥተ አክሱም፣ እንዲሁም የአክሱም መንግሥት ወይም የአክሱም ኢምፓየር በመባል የሚታወቀው፣ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ እና በደቡብ አረቢያ ላይ ያተኮረ መንግሥት ከጥንት ጀምሮ እስከ መካከለኛው ዘመን መጀመሪያ ድረስ ያለ መንግሥት ነበር። የአሁኗ ኤርትራን፣ ሰሜናዊ ጅቡቲን እና ምስራቃዊ ሱዳንን የሚሸፍን ሲሆን በንጉሥ ካሌብ ዘመነ መንግስት ወደ ደቡብ አረቢያ አብዛኛው ክፍል ዘልቋል። አክሱም ለብዙ መቶ ዘመናት የመንግሥቱ ዋና ከተማ ሆና ስታገለግል በ9ኛው ክፍለ ዘመን ግን የንግድ ትስስር በመቀነሱ እና በተደጋጋሚ የውጭ ወረራ ምክንያት ወደ ጃርማ [4] ተዛወረ።[5][6] ከቀደምት የዲኤምቲ ስልጣኔ በመነሳት መንግስቱ የተመሰረተው በ1ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ሳይሆን አይቀርም።[7] የቅድመ-አክሱማዊ ባህል በከፊል የዳበረው በደቡብ አረቢያ ተጽዕኖ ምክንያት ነው፣ በጥንቷ ደቡብ አረቢያ ስክሪፕት አጠቃቀም እና በጥንታዊ ሴማዊ ሀይማኖት ልምምዶች ላይ ይታያል።[8] ነገር ግን የግእዝ ፊደል በ4ኛው ክፍለ ዘመን ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን መንግሥቱ በሮም እና በህንድ መካከል ባለው የንግድ መስመር ላይ ዋና ኃይል እየሆነ ሲመጣ ወደ ግሪኮ-ሮማን የባህል ሉል በመግባት ግሪክን እንደ ቋንቋ መጠቀም ጀመረ።[9] የአክሱም መንግሥት በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ በአክሱም ኢዛና ሥር ክርስትናን የመንግሥት ሃይማኖት አድርጎ የወሰደው በዚህ ነው።[10] አክሱማውያን ወደ ክርስትና መምጣታቸውን ተከትሎ የሃውልት ግንባታ አቆሙ።[5] የአክሱም መንግሥት በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበሩት አራት ታላላቅ ኃያላን መንግስታት ከፋርስ፣ ሮም እና ቻይና ጋር በመሆን በፋርስ ነቢይ ማኒ ነበር።[11] ከኢንዱቢስ የግዛት ዘመን ጀምሮ አክሱም እስከ ቂሳርያ እና ደቡባዊ ህንድ ባሉ ቦታዎች የተቆፈሩትን የራሱን ሳንቲሞች ያወጣል።[12] ግዛቱ በጥንት ዘመን መስፋፋቱን ቀጠለ፣ ሜሮንን በመቆጣጠር በጣም አጭር ጊዜ ወሰደ፣ ከርሱም "ኢትዮጵያ" የሚለውን የግሪክ አገላለጽ የወረሰ ነው።[13] የአክሱማውያን የቀይ ባህር የበላይነት ያበቃው በአክሱም ካሌብ ዘመነ መንግስት ሲሆን በባይዛንታይን ንጉሠ ነገሥት ጀስቲን ቀዳማዊ ትዕዛዝ የአይሁድ ንጉሥ በዱ ኑዋስ በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለውን ስደት ለማስቆም በየመን የሚገኘውን የሂሚያራይት መንግሥት ወረረ። ከሂያር ጋር በመቀላቀል፣ የአክሱም መንግሥት በግዛቱ ትልቁ ነበር። ሆኖም ግዛቱ በአክሱማይት-ፋርስ ጦርነቶች ጠፍቷል።[14] የመንግሥቱ አዝጋሚ ማሽቆልቆል የጀመረው በ7ኛው ክፍለ ዘመን ነው፣ በዚህ ጊዜ ምንዛሪ ማውጣት አቆመ። የፋርስ (በኋላም ሙስሊሞች) በቀይ ባህር ውስጥ መገኘታቸው አክሱምን በኢኮኖሚ እንዲሰቃይ አድርጓቸዋል፣ እናም የአክሱም ከተማ ነዋሪ ቁጥር ቀንሷል። ከአካባቢያዊ እና ውስጣዊ ሁኔታዎች ጎን ለጎን, ይህ የመቀነስ ምክንያት ነው. የአክሱም የመጨረሻዎቹ ሶስት መቶ ዘመናት እንደ ጨለማ ዘመን ተቆጥረዋል፣ እናም እርግጠኛ ባልሆኑ ሁኔታዎች መንግስቱ በ960 አካባቢ ፈራረሰ።[10] በጥንት ዘመን ከነበሩት ዋና ዋና ግዛቶች መካከል አንዱ ቢሆንም፣ የአክሱም መንግሥት በመካከለኛው ዘመን ሁሉ ኢትዮጵያ ተገልላ በነበረችበት ጊዜ ጨለማ ውስጥ ወደቀች።[15]ሀ ኢምፓየር የኢዛና ድንጋይ ኢዛና ወደ ክርስትና መግባቱን እና ሜሮንን ጨምሮ በአካባቢው ያሉትን የተለያዩ ህዝቦች መገዛቱን መዝግቧል። አክሱማዊት መንህር በባላው ካላው (መተራ) ሰናፌ አቅራቢያ የአክሱም መንግሥት በኤርትራና የሚገኝ የንግድ ግዛት ነበር።[19] ከ100-940 ዓ.ም ገደማ ነበረ፣ ከአይረን ዘመን ፕሮቶ-አክሱማይት ዘመን ሐ. ከክርስቶስ ልደት በፊት በአራተኛው ክፍለ ዘመን ታዋቂነትን ለማግኘት በአንደኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. በአክሱም መጽሃፍ መሰረት የግዛቱ የመጀመሪያ ዋና ከተማ ማዛብር የኩሽ ልጅ ኢቲዮጲስ ነው የተሰራችው[20] ዋና ከተማዋ በኋላ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ወደ አክሱም ተዛወረች። መንግሥቱ በአራተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ "ኢትዮጵያ" የሚለውን ስም ይጠቀም ነበር.[16][21] የአክሱም ኢምፓየር በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛዎቹ የኤርትራ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በምእራብ የመን የግብፅን ጀልባ ዲዛይን በመጠቀም የወረረውን [22] እና አንዳንድ የምስራቅ ሱዳን ክፍሎች ይስፋፋ ነበር።[21] የግዛቱ ዋና ከተማ አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኝ አክሱም ነበረች። ዛሬ ትንሽ ማህበረሰብ፣ አክሱም ከተማ በአንድ ወቅት የተጨናነቀች ዋና ከተማ፣ የባህል እና የኢኮኖሚ ማዕከል ነበረች። ሁለት ኮረብታዎች እና ሁለት ጅረቶች በከተማይቱ ምስራቅ እና ምዕራብ ይገኛሉ; ምናልባት ይህንን አካባቢ ለማስተካከል የመነሻ ተነሳሽነት ሊሆን ይችላል። ከከተማው ውጭ ባሉት ኮረብታዎች እና ሜዳዎች ላይ የአክሱማውያን መቃብር ስቴሊ ወይም ሐውልት የሚባሉ የተንቆጠቆጡ የመቃብር ድንጋዮች ነበሯቸው። ሌሎች ጠቃሚ ከተሞች የሃ፣ ሃውልቲ-መላዞ፣ ማታራ፣ አዱሊስ እና ቆሃይቶ፣ የመጨረሻዎቹ ሶስት ከተሞች አሁን በኤርትራ ይገኛሉ። በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በኤንዱቢስ የግዛት ዘመን፣ የራሷን ገንዘብ ማውጣት የጀመረች ሲሆን በማኒ ከሳሳንያን ኢምፓየር፣ ከሮማ ኢምፓየር እና ከቻይና "ሶስት መንግስታት" ጋር በዘመኑ ከነበሩት አራት ታላላቅ ኃያላን መንግስታት አንዱ ተብሎ ተሰየመ። አክሱማውያን በ325 ወይም 328 ዓ.ም በንጉሥ ኢዛና ክርስትናን እንደ መንግሥታዊ ሃይማኖት የወሰዱ ሲሆን አክሱም የመስቀልን ምስል በሳንቲሞቹ ላይ የተጠቀመች የመጀመሪያዋ ሀገር ነች።[23][24] በ3ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ (ምናልባትም ከ240-260 ዓ.ም.) አካባቢ፣ በሴምብሮውተስ የሚመሩት አክሱማውያን ሴሴይን አሸነፉ፣ ሴሴያ የአክሱም መንግሥት ገባር ሆነ።[25][26] በ330 አካባቢ፣ የአክሱም ኢዛና ሠራዊቱን እየመራ ወደ ሜሮ ግዛት በመግባት ከተማዋን ራሷን ወረረች። አንድ ትልቅ የድንጋይ ሐውልት እዚያው ቀርቷል፣ ወረራውም በኢዛና ድንጋይ ላይ የተያያዘ
16043
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A0%E1%88%8B%E1%8B%AD%20%E1%8B%98%E1%88%88%E1%89%80
በላይ ዘለቀ
በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ በላይ ዘለቀ የተወለደው በጎጃም ክ/ሀገር በቢቸና አውራጃ፣ ለምጨን በተባለው ቦታ ነው። ዘለቀ ላቀው (የበላይ ዘለቀ አባት) የልጅ እያሱ አንጋች ነበሩ ልጅ እያሱ ሲገለበጡ ዘለቀ ላቀው ወደሚስታቸው አገር ወደ ለምጨን ሄደው ልጆቻቸውን ይዘው ወደአገራቸው ወደ ለምጨን (ቢቸና ወረዳ ተሻገሩ። (ቢቸና ጎጃም ውስጥ ጫቀታ ወሎ ውስጥ ከአባይ ወንዝ ማዶ ለማዶ ናቸው። ይገበያያሉም፡ ይጋባሉም።) በ1916 አ.ም. ማለት በላይ ዘለቀ የ14 አመት ልጅ ሳለ ፊታውራሪ እምቢ አለ የተባለ የራስ ሀይሉ ሌባ አዳኝ (ጸጥታ አስከባሪ ዘለቀ ላቀውን ከበባቸው። ዘለቀ ላቀው እጄን አልሰጥም ስላሉ ተኩስ ተከፈተ። ዘለቀ ላቀውና አብረዋቸው የነበረ አለሙ መርሻ የተባሉ ወንድማቸው ከአስር ሰው በላይ ገድለው ብዙ ሰው አቆሰሉ። «እኛ ልጆች ተኩስ ካባራ በህዋላ ተየጫካው ስንመለስ ሁለቱም ሞተዋል። የዘለቀ ላቀው ሬሳ እበቱ በራፍ ላይ ተሰቅሎዋል።» አሉ ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ። እንግዲህ በላይ ዘለቀና ተሻለ አለሙ እኩል አባቶቻቸውን አጡ አብረው የሀዘንን ጽዋ ቀመሱ እኩል በቀልን እያሰላሰሉ አደጉ በሁዋላም አብረው ጠላትን ተዋጉ። ዘለቀ ላቀው ሲሞቱ ልጆቻቸው ወደእናታቸው አገር ወደ ጫቀታ ተመለሱ። በላይ ዘለቀ ያባቱን ደም ለመመለስ ተኩስ እየተማረ አደገ። አደገና ያባቱን «ናስ ማሰር» (ባለ ነሐስ ማሰርያ ውጅግራ ጠመንጃ ይዞ ወደ አባቱ አገር ወደ ለምጨን (ቢቸና)ተሻገረ። አባቶቻቸው የተገደሉባቸው ጎረምሶች ዳኝነት እንዳይሹ ዳኛው ራስ ሀይሉ ሆኑባቸው የቀራቸው ምርጫ በቀል ነው መሳርያ እየገዙ እየተዘጋጁ ለምጨን ቀንጦ ማርያም እያረሱ ቀን ይጠብቁ ጀመር። ...እንዲህ ሲል ጥልያን መጣ ...በሚያዝያ 28 ቀን (1928 አ.ም.) ለቀኛዝማች መሸሻ ጥልያን መሳርያ በአየር አወረደላቸው (ለጥልያን ገቡ ካለው ሰበካ ያዙ በረንታ ወረዳ (ቢቸና አውራጃ ደረሱ። የዱሀ ከተማ ሰፍረው ህዝቡን መሳርያ እየነጠቁ (ጥልያንን እንዳይወጋ ጥልያን ደግ መንግስት ነውና እንገዛለን እያሉ ይሰብካሉ (እንዲሾማቸው። «ልጅ በላይ ዘለቀ ግን እዋጋለሁ እንዋጋ እያለ እኛን ወንድሞቹን አነሳሳን» አሉ ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ «ቀሰቀሰን ከሰላሳ እስከ ሀብሳ ለምንደርስ ያንድ አያት ልጆች ...የገልገል ላቀው ልጆች ...ታጥቀን ተነሳን ከቀኛዝማች በላይ መሸሻ ሰዎች መሳርያ እየነጠቅን በረሃ ገባን።» «ጦር ሲያሳድደን ...ስንሸሽ ...ቤት ሲያቃጥልብን ...ከሁዋላው ወይም ከጎኑ በድንገት እየመታነው መሳርያ ነጥቀን ስናመልጥ .....እንዲህ ስንል አንድ ቀን የማናልፈው ጉዳይ መጣ። ግንባር መግጠም ግድ ሆነ። ጠላት መሸሻ አሳጣና።» «የዛሬን ጦር ማን ይምራው አለን ልጅ በላይ «አንተን መርጠናል ...እስከ መጨረሻው» አልነው። "ሁላችሁም ወንድማማች ናችሁ።" ፊታውራሪ ተሻለን "በላይ ዘለቀን እርስዎ እንኳን በ4 አመት እበልጠዋለሁ ብለዋል። እንግዲያው በምኑ ነው አለቃችሁ እንዲሆን የመረጣችሁት?" "እንዴ! በደግነቱ በጀግንነቱ! ጠባየ መልካም በመሆኑ! እኔ ይቅርብኝ ብሎ ለሌላው ስለሚያዝን!" (ያን ጊዜ 1928 አ.ም. ልጅ በላይ 3 ወልደዋል። ልጅ ተሻለ ግን ገና በታህሳስ ነው ያገቡ።) ወይዘሮ ድንቅነሽ ሀይሉ (የራስ ሀይሉ ልጅ ጥልያን ሾመዋቸው የለም ጨጉ ጉልተ ገዥ ሆነው ሄዱ። ህዝቡን መሳርያ አግባ ብለው አሰባሰቡ። በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ በድንገት ገብተው መሳርያዎቹን ነትቀው ሴትየዋን ሳይጎዱ ሳያጎሳቁሉ ወደመጡበት መልሰው ላኩዋቸው። የነጠቁዋቸውን መሳርያ 35 ያህል ጠመንጃ ዋሻ ደበቁት። ለራሳቸው በቂ መሳርያ ይዘዋላ። ከዚህ በሁዋላ ደብረ ማርቆስን ጥልያን እየያዘ በላይ ዘለቀን ያሳድነው ጀመር። ከ'28 አ.ም. ሚያዝያ እስከ ግንቦት 29 ቀን ድረስ ሁኔታው ተመሳሳይና ተደጋጋሚ ነበር ጦር ይመጣል ...ያስሳል .....እነ በላይ ዘለቀ ይሸሻሉ ...በሁዋላ ቀስ ብለው መጥተው ጥቂቱን ገድለው መሳርያ ነጥቀው ....እልም መሳርያ በየዋሸው ያከማቻሉ እንደዚህ ብዙ አሰሳ ተሞከረ ባንዱ አሰሳ የበላይ ዘለቀ በትና የለምጨን ቤቶች በሙሉ ተቃጠሉ። ከብቱም ተዘረፈ። ጠላት ለምጨን 3 ጊዘ ነው ያቃጠለ። "እስከ ታህሳስ 29 ቀን ድረስ አሰሳው የሚካሄደው በባንዳ ነበር።" በታህሳስ 8 ቀን 1929 ግብጣን ደቡብ የተባለ ጥልያን ቢቸና ገባ ቢሉን ከዱማ ገስግሰን ቢቸና አደጋ ልንጥል ስንል ካህናት ጽላት ይዘው ስእል መስቀል ይዘው "አገሩንና ታቦቱን ያቃጥልብናልና አትውጉት እሱን እኛ ተመለስ እንለዋለን።" ብለው መለሱን። ግብጣን ደበቡም በላይ ዘለቀ መጣብህ ቢሉት ወደማርቆስ ተመለሰ።" በየካቲት 29 ጥልያን አገሩን አስነስቶ ወረረን። ከያውራጃው ግብጣን ደበቡ አስከተተ። ጦር ሲመጣባቸው እነ በላይ ዘለቀ ሸሹ። አጥቷቸው ሲመለሱ እያደፈጠ በጎን አደጋ እየጣሉ ብዙ መሳርያ ነጠቁት። "የግንቦት እርገት ለት ..በ29 ነበር የዋለ ..ጥልያን ራሱ መጣ" የበላይ ዘለቀን ዘመዶች ከለምጨን እየደበደቡ ወደ አርበኞቹ እንዲመሩዋቸው አስገደዱዋቸው። "ጦሩ ሲመጣ አሳለፍነው። ከጎን አደጋ ጣልንበት። በላይ ዘለቀ አንዱን ትሊንቲ ገድለው ኩረኔሉን አቆሰለው። ብዙ ባንዳዎች ሞቱ።" ታስሮ እየተደበደበ ሲመራ የነበረው አዛዥ ቢያዝን ዱብዳ የተባለው የበላይ ዘለቀ ዘመድም ቆሰለ። በሰኔ 29 (1929) ጠላት በቅምቧት በደጀን በገበያ በሽበል በበረንታ የነበረውን "ደንበኛ" በሙሉ አከተተው። (ደንበኛ የሚባለው "የመንግስት የደንብ ብረት የያዘ ነፍጠኛ ነው ቀኛዝማች ስማ ነገዎ አዝማች ሆኖ ይህን ሁሉ አስከትቶ አባይ ወረደና አባራ ጂወርጂስ ሰፈረ። ሀሳቡ እነ በላይ ዘለቀ ወደ ጫቀታ እንዳይሻገሩ በር በሩን ለመዝጋት ነበር። "እንውጋው" አለ በላይ ዘለቀ "ጦሩ በጣም ብዙ ነው አንችለውም" አሉት ሌሎቹ "ግድ የለም። ጦሩ በየመንደሩ ይመራል። አዝማቹ ላይ አደጋ እንጣልበት።" እነ በላይ ዘለቀ ቀኛዝማች ለማ ነገዎ ያደረበትን በለሊት ከበቡት። ሲነጋ ለማ ነገኦን ከነወንድሞቹ ደመሰሱት። ጦሩ በሙሉ እጁን ሰጠ። መሳሪያውንና በቅሎውን ሁሉ አስረከበ። ድል አድራጊዎቹ መሳርያውን ዋሻ ውስጥ ደበቁት። በቅሎዎቹን ወደ ጫቀታ ልከው በጥይት ለወጡዋቸው።" ይሄ የሆነው ሰኔ 10 ነበር። ሰኔ 12 በአውሮፕላን ይደበድቡን ጀመር። በረንታ ጎይ ጂወርጂስ ላይ 12 ሰው ሞተብን። እኛም ተመልሰን ወደ በረሃችን ሸሸን።" ፊታውራሪ ለማ ሞገስ የጣልያን የጦር እንደራሴ ሆኖ ከማርቆስ ተልኮ ወጥቶ ዲማ አጠገብ ገድ ወንዝ ዋሻ ውስጥ እንዳለ ከበባቸው። ወጥተው ገጠሙ። ድል ነሱት። ብዙ ሰው ሞተበት። እሱ ግን አመለጠ። በላይ ዘለቀ 60 ያህል ምንሽርና አልቤን ማረከ። ምንሽርና አልቤን ሲያገኙ የመጀመርያ ጊዜያቸው ነበር። እስካሁን ግን ሲዋጉ በናስማስር በውጅግራ በለበን ብቻ ነበር። "ድፍን ሀምሌን ተከበብን። ለምጨን አንድ ዋሻ ገብተን ተደበቅን። ኤኛን ሲያጣን ጊዜ የጎይ ጂወርጂስና ያካባቢውን ህዝብ ጎይ ላይ ሰብስቦ በላይ ዘለቀን ካላመጣችሁ ብሎ በመትረየስ ፈጃቸው።" በላይ ዘለቀ የቶክሱ እለት ሞቶ ተቀብሯል ተብሎ ለጥልያኖች ተነገራቸው። ሰው ሰደው መቃብሩን ቢያስመረምሩት ሴት ሆና ተገኘች። አንዱ አሳባቂ በላይ ዘለቀ ወደ እነብሰ አውራጃ ነው የሄደው ብሎ ለጥልያኖች ጠቆማቸው። የጥልያን ጦር ወደ እነብሴ ዘመተ። የእነብሴና የጎንቻ ህዝብ ገጠመውና ጨረሰው። አንድ ጥልያን ብቻ አመለጠ። በላይ ዘለቀና አገሬው እስከ ነሀሴ 1929 ድረስ የበላይ ዘለቀ ተከታዮች ከ30 እንከ 50 የሚደርሱ ወንድሞቹ ብቻ ነበሩ። "ነሀሴ ጂወርጂስ በላይ ዘለቀ በረንታ ላይ አዋጅ አስነገረ። ኤኛን ምሰሉ እርዱን። አለዚያ ግን ይህ የጦር ሜዳ ነውና እንዳትጎዱ ሂዱ ልቀቁ "እናርጅ እናውጋ (የደብረወርቅ ወረዳ በረንታና ሸበል ጉበያ (ደጀን አጠገብ እነማይ (ቢቸና አውራጃ ...ይሄ ሁሉ አመነ ተባበረን። "ከህዳር ማርያም (1930) እስከ መጋቢት ውድማትን አዋባልን ቅምብዋትን ሊበንን ባስን አነድድን ደጀንን ...እነዚህን ያዝን።" "በየካቲት ትሊንቲ ከጫቀታ ዘመተብን አባይ ደረሰ። አገድነው። ብዙ ውጊያ ተደረገ። 80 ብረት (ከነሰው ማረክን። መለስነው። ወደደጀን ተመለስን።" "ከሸዋ ሲዘምትብን አባይ ላይ አገድነው። ወር ካስራምስት ቀን ተዋጋነው። 3 መኪናዎች ሰበርን። ውስጣቸው የነበሩ ጥልያኖች ሞቱ። "ጥልያን ሀይሉን አጠናክሮ በደጀን በኩል ከሸዋ መጣብን። 12 በጦለኔ በጀኔራል ማሊን አዝማችነት መጣ። "መጋቢት 19 ቀን (1930) ውጊያው ማለዳ የጀመረ በአስራአንድ ተኩል አበቃ። መትረየስና መድፍ ከታች ፈረሰኛ በሻምላ (በጎራዴ ተጨምሮበት ከላይ አሮብላ ወንድሞቻችን አለቁ። የጦር አዝማች የነበረው የበላይ ዘለቀ ወንድም ደጃዝማች ታደለ ላወቅ ወደቀ። ተሰማ ላቀው ቆስሎ አመለጠ። 300 ያህል አለቅን። የተቀረውን ጨለማ ገላገለን። "ጠላት ፆን ማርቆስ ገባ። እኛ ወደ በረሀችን ገባን። "ሚያዝያ 4 (1930) እበረሀችን አፋፍ ላይ እንደሰፈርን ጠላት ባራት ረድፍ ቢቸና ገባ። ሚያዝያ 6 ጦሩን ባራት ማእዘን አቀነባብሮ በረሀችንን በሙሉ ከበበው። በመካከሉ ደግሞ በግንባር እልፍ አእላፋት ጦር ይዞ ተሰለፈ።" "ባለው ሀይላችን ገጠምነው።" "ሊያፍነን ሞከረ በብዛቱ።" "የቆላ ጫካ ነው ....እሳት ለቀቅንበት" "ይገርማል እኮ የቀን ነገር !ልፋሱ እሳቱን እያንቦገቦገ ወደነሱ ወሰደው። ብዙዎቹን እሳት በላቸው። ብዙዎቹ አመለጡ። "የበላይ ዘለቀ ሚስት ወይዘሮ ሸክሚቱ አለማየሁ በመትረየስ ሞቱ (እንደወንድ ለብሰው ነበር ልጅ የሻሸወርቅ በላይ ተማረከች። የናትየዋ እናትም ተማረከች። "ከዚህ በሁዋላ አባይን ተሻግረን ጫቀታ ገባን። ያጌ ከተማ ግዛው ሰብስቤ የተባለው የጥልያን እንደራሴ ገድለን አገሩን አቃትለን የጎበዝ አለቃ ሾመን ፊታውራሪንና ቀኛዝማች እያሱ ልጅ በላይ ሾመው ...ተመልሰን ወደ ለምጨን በረሀ ገባን "ክረምቱን ከረምን።" (ያን ጊዜ ወንዞች ስለሚሞሉ እነ በላይ ዘለቀም ያርሳሉ ጥልያንም በየካምቦው ይከርማል በህዳር 27 1931 ጥልያን የዴንሳ አማኑኤልን ክልክል ሸንበቆ ሊቆርጥ (ሰፈር ሊሰራበት ይመጣል ማለትን ሰማን አርበኞቹ። ደፈጣ አድርገው መሽገው አደሩ። ማለዳ ሲመጣ ገጠሙት። "ብዙ ባንዳ ገደልን። ብዙ መሳርያ ማረክን። ጥልያን ግን አመለጠ።" በሶስተኛው ቀኑ ለምጨን ወዳዳ በሚባል ቀበሌ ኮረነል አጎረኔ አውግስቶ የተባለ ጥልያን ሁለት መድፍ ጠምዶ ገጠማቸው። ሰቀላ ገብሬልን አቃጠለ። ከሁለቱም በኩል ብዙ ሰው አለቀ። በዘጠኝ ሰአት ኮረነሉ ድል ሆኖ ወደ ካምቦ ተመለሰ። "ይህ ሁሉ ሲሆን ለምጨን ውስት ፈላው በሚባል ቦታ ላይ ከትመን ከዚያ እየወጣን ነው ጦርነት የምናደርገው ፈላው ነበር ዋናው ምሽጋችን ከ30 እስከ 1933 እ.ም ድል ሆነን አናውቅም።" ሰኔ 1931 እነ በላይ ዘለቀ ወደ ማርቆስ ልንዘምት ነው ክተት ብለው አወጁ። ጦሩ ከተተ። መነሻቸውን ወደ ደብረ ማርቆስ አስመስለው ለሊት አባይን ተሻግረው ወደ ጫቃታ ገቡ። ሲነጋ ደጋው ደርሰዋል። "ሀይሌ ረዳ የተባለ የጥልያን እንደራሴ ያገ ላይ ገጠመን። ተሸንፎ ሸሸ። አመለጠ። ከተማውን አቃጠልን። ሽቅብ ወደ ወጊዲ አፋፍ ቀጠልን። "በማግስቱ ወጊዲ ላይ ያለውን ካምፕ (ምሽግ በቦምብና በእሳት አቃጠልነው። ያልተተኮሰበት አዳዲስ አልቤንና ምንሽር በጭነት ወሰድን። የኛ ሰው እየገባ አራት አምስት ምንሽር አንግቶ አንዱን የደስ ደስ ወደ ላይ እየተኮሰ ወጣ አገሩን ሹም ሽር አድርገነው ወደ ፈላው ተመለስን።" ይህን ጊዜ ባንዳዎች የነበላይ ዘለቀ ይዞታ የሆነውን አገር መልሰው ለማሳመን ጥረት ያደርጉ ጀመር። በድለንታ መጀመራቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለበላይ ዘለቀ ከታማኞቹ ደረሰው እነ በላይ ዘለቀም በፍጥነት ሄደው ባንዳዎቹን ከድለንታ አስወጡዋቸው። እስከ ደብረ ማርቆስ ድረስ አባረሩዋቸው እከተማው ዳር ቤቶች ተቃጠሉ።" ኦ ሮማ ተቃጠለች! አለ ጥልያን ሲዘብት። እነ በላይ ዘለቀ ይዞታቸውን ከባንዳ ለማጽዳት አገሩን እያሰሱ ደብረ ወርቅ አካባቢ ደረሱ።" ሰኔ 1ቀን /፲፱፻፴፪ዓ/ም። በዚህን ጊዜ እንደአጋጣሚ ጥልያን ከደብረ ወርቅ ብዙ ጉዋዝና መሳርያ (ስንቅና ትጥቅ ይዞ ወደ ቢቸና ይጉዋዛል። እነ በላይ ዘለቀ ይህን አላወቁም። ማለዳ እንደተነሱ ጅብ ሲያዩ ጊዜ ብዙዎች ተኮሱበት። የተኩሱን እሩምታ ወደ ቢቸና የሚጉዋዘው ጥልያን ሰማውና ቃፊር ቢልክ እነ በላይ ዘለቀ ናቸው። አዙር እንወጋቸዋለን አለ። ጦር ወደአርበኞቹ በኩል ሲሄድ የአዛዥ በቅሎ ሶስት ጊዜ ጣለችው። አጠገቡ ያሉት ባንዳዎች "ምልኪው መጥፎ ነውና ዛሬ ጦርነት ባናደርግ ይሻላል" አሉት። እሱ ግን በቅሎይቱን ገረፋት ለቅጣት ጥይት ጫነባትና በለላ በቅሎ ተቀመጠ። አርበኞቹን አያልፋሽ እተባለ ተራራ ላይ ገጠማቸው። ውጊያው ሲጀመር አርበኞቹ ከላይ በኩል ጠላት ከታች በኩል ናቸው። በላይ ዘለቀ አርበኞቹን "ጎበዝ ጥልያን ጥይቱን የሚያመጣው ከፋብሪካ ነው። እኛ ግን ገዝተን ነው። ስለዚህ ጥይት መለዋወጥ አያዋጣምና በጨበጣ እንግባበት "አላቸውና በመጀመርያ ዘሎ እየጮኸ ከጠላት መሀል ገባ። "ይህ የደብረወርቁ ጦርነት ለኛ የመጨረሻው ትልቅ ውጊያ ነበር። ድል አደረግን። ዘጠኝ የውሀ መትረየስ (ከባድ በከብት የሚጫን ቁጥር የለለው ቀላል መትረየስ ጥይትና ጠመንጃ ለማንሳት እስኪያቅተን እና አስራ ሁለት ባንዲራዎች ማረክን። አስራ አንዱን ባንዲራ በላይ ዘለቀ በሁዋላ ለንጉሱ አስረከበ። አንዱ ባንዲራ አሁን የጎላ ጂወርጂስ (ደብረቀርቅ አጠገብ ይገኛል። "የደብረ ወርቁ ጦርነት የተደረገው ሰኔ 1/1932 አ.ም. ነበር። በበነጋው አስራ ሁለት አሮብላ መጥቶ የተዋጋንበትን አካባቢ ደበደበው። እኛ ግን ያን ጊዜ ፈላው ምሽጋችን ገብተናል። በላያችን አልፎዋል እኮ ታድያ። በላይ ዘለቀ "ጂወርጂስ ያውቃል አይዟችሁ" አለን። "እንዳትነቃነቁ ሰውም በቅሎም ባለበት ቀጥ ብሎ ቆመ። አሮብላን በሙሉ አልፎን ሄደ።" ክረምቱን አርበኞቹ በምችጋቸው ከረሙ። ታህሳስ 1933። አርበኖቹ የቢቸናውን ካምቦ (ምሽግ ለመክበብ ሲዘጋጁ ራስ ሀይሉ በላይ ዘለቀን መጥቼ ላነጋግርኽ ብለው ላኩበት እሺ ግን ከጠላት ጋር የነበረ ባንዳ እንዳይከተልዎ ፎቶ አንሺም እንዳይመጣ ብሎ ላከባቸው ሰቀላ ገብሬል ድረስ መጥተው አነጋገሩት። "ከተዋጋችሁ አገሩም ይጠፋል ትልያንም እኔን ላያምነኝ ነው። ካልወጋኸው ግን እራሱ አገሩን ይለቃል "እሺ ይሁን "ጃንሆይም መጥተዋል "አሉት። "እንግዲያው እሱንም አፍነን እናስቀረው። እሱስ ይዞት የመጣው እንግሊዝ ያው ነጭ አይደለምን አላቸው "አይሆንም "አሉት ተቀየመ ግን መውጋቱን ተወ "ነጭ እዚህ ግድም እንዳላይ" አላቸው ራስ ሀይሉን "እርስዎንም እንዳልደፍርዎት ቶሎ ይዘውልኝ ይውጡ ሌሊቱን ተነስተው ሄዱ ጥልያንም ቢቸናን ለቆ ሄደ (ራስ ሀይሉ ደብረወርቅ ሲደርሱ ራስ ተመስገን ፈንታ ወግቶ ጉዋዛቸውን ብዙ ጠገራም አገኘ እሳቸው ግን አመለጡ በላይ ዘለቀና ምቀኞቹ መጋቢት 1933 አ.ም. ከበደ ተሰማ (ደጃዝማች )ወዳገራቸው ለመመለስ መንገድ ላይ ከነበሩት ንጉስ ተልከው መጡ ::ከሳቸው ጋር የነበረው ጀኔራል ሳንፎርድ በላይ ዘለቀን ለመጨበጥ እጁን ሲዘረጋ በላይ ዘለቀ "ለፈረንጅ እጄን አልሰጥም "ብለው ሳንፎርድን አግባቡት በሁዋላ ልጅ መርድ መንገሻና እንግሊዞች ወደ ደጀን መቱ ::ወደበላይ ዘለቀ ላኩባቸው ::ሄዱ ::"የደጀንን ምሽግ ለመስበር ተባበሩን "ተባለ "መድፍ ይዛችሁዋል ?ኤሮቢላ ይዛችሁዋል ?"አላቸው በላይ ዘለቀ "አልያዝንም ግን መክበብ ይበቃል "አሉት "አይበቃም "አላቸው ::"ከዚህ በፊት ወር ካስራ አምስት ቀን ሙሉ ሞክረን ብዙ ወንድሞቼ አልቀዋል ::መድፍና ኤሮብላ አምጡና ምቱት ሌላውን ለኛ ተዉልን ::አለዚያ ግን እኔ ወንድሞቼን በከንቱ አላስፈጅም ሳይስማሙ ተለያዩ ንጉሱ ደብረ ማርቆስ ሲገቡ አርባ አራት ሺህ የበላይ ዘለቀ ሰራዊት በፊታቸው በሰልፍ አለፈ ::ያውም ባንድ ቀን ጥሪ የደረሰው ነው እንጂ ሰራዊቱ በሙሉ አይደለም በላይ ዘለቀ እንግዲህ በሰላም አርሼ እበላለሁ ብሎ ንጉሱን "አገሩንም ሰራዊቱን ይረከቡኝ "አላቸው "የሰላም ጊዜ ስራ አለ ::አገርን ማስተዳደር አለ "አሉት "እኔ ተራ ሰው ነኝ ::ሀረግ የሚቆጥሩት ሰዎች አያሰሩኝም ::ከርስዎ ጋር ያጣሉኛል "አላቸው "እኛ የማንንም ወሬ አልሰማም ::እንደአባትህ ቁጠረን ::እነዚህ ልጆቻችንም ወንድሞች ናቸው ንጉስ ሹም ሽር አደረጉ ::በላይ ዘለቀ ከወንድሞቹ ጋር ሆኖ በሁዋላም ከአገሬው ጋር ሆኖ ጠላትን ተዋግቶ ነጻ ያወጣው ጠቅላይ ግዛት ለራስ ሀይሉ ተሰጠ በላይ ዘለቀ ወዳዲሳባ ተጠርቶ ደጃዝማች ተብሎ የቢቸና አውራጃ ገዥ ሆኖ ተሾመ የቢቸና አውራዣ ገዥ ሆኖም ሊሰራ አልቻለም ::ከደብረ ማርቆስ ትእዛዝ እየመጣ ወረዳዎቹ ሁሉ ቀድሞ ባንዳ የነበሩ ሰዎች ተሾሙባቸው። ብስጭት በዛበት በላይ ዘለቀ። "ሊወጋን ነው ....እምቢ አለ ..."እያሉ ማስወራት ጀመሩ። በቂ ካስወሩ በሁዋላ ከራያ ኦሮሞዎች ጦር አስዘመቱበት። (ጎጃመማ በላይ ዘለቀን ወይ ይወደዋል ወይ ይፈራዋል።) በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ ከጥቂት ታማኝ ተከታዮቹ ጋር ሆነው ወደ ሳማ አምባ ሸሹ ::በላይ ዘለቀ ሸፈተ ተባለ ሳማ አምባ ያለ ሁለት በር የላትም ሁለቱንም በር ይዘው ሀያ አምስት ቀን ሌትና ቀን ተዋጉ "ምረነዋል ልቀቁት ይምጣ "የሚል መልእክት ከንጉሱ መጣ ከሳማ አምባ ከወረዱ በሁዋላ ተከበቡና መሳሪያቸውን ተነጥቀው እንደ እስረኞች ወደ አዲስ አበባ ተወሰዱ በላይ ዘለቀ ሞት ተፈረደበት ::ንጉሱ "ምህረት አደረጉለትና ቅጣቱ ወደ እስራት ተለወጠለት መስከረም 1936 አ .ም በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ በያገሩ ተበትነው ታሰሩ በላይ ዘለቀና ወንድሙ እጅጉ ዘለቀ ወሊሶ በበቀለ ወያ ጠባቂነት ታሰሩ የበላይ ዘለቀ ምቀኖች አሁንም አላረፉለትም ::በላይ ዘለቀ ከዳ ;አመለጠ ጠፋ እየተባለ ይወራ ጀመር ::በቀለ ወያ ተያዘና "ምን ቢሰጥህ ነው የለቀከው ?"ተባለ ::"እረ እኔ አልለቀኩትም አለ በላይ ዘለቀና እጅጉ ዘለቀን ወደ አዲስ አበባ አመጡዋቸውና ከአንድ ሌላ ሰው ጋር አሰሩዋቸው :.ያ ሰው እናምልጥ እያለ እነ በላይ ዘለቀን ይጎተጉታቸው ጀመር አንድ ቀን "ጠባቂዎቻችንን የኛ ወዳጆች ገዝተዋቸዋልና እናምልጥ ::በንዲህ ያለ ስፍራ እነ እገሌ መኪና ይዘው እየጠበቁን ናቸው ::"አል "ወንድሞቸ በየቦታው ተበታትነው ታስረው እኔ ማምለጥ ምን ያረግልኛል አለ በላይ ዘለቀ "ፈራህ እንዴ በላይ ዘለቀ ?"አለው "እኔ የዘለቀ ልጅ በላይ ዘለቀ ወንድሙን ላከው መኪናው እተባለበት ስፍራ መኖሩን ለማረጋገጥ ::ወንድምየው በተባለበት ስፍራ መኪና አየ ::እስረኞቹና ጠባቂዎቻቸው አብረው አመለጡ ::እመኪናው ቦታ ሲደርሱ መኪናው የለም ::እንግሊዝም የለም ጠባቂዎቻቸው ከዚያ ሮጠው አጠገባቸው ከነበረው ጫካ ገቡና ደጋግመው ተኮሱ ::ምልክት ነው በላይ ዘለቀ እጠላቶቹ ወጥመድ ውስጥ መግባቱን አወቀ በላይ ዘለቀና እጅጉ ዘለቀ ከዚያ እሮጠው አመለጡ ሰላሌ ደርሰው በቅሎ ለመከራየት ሲነጋገሩ ተከበቡ በላይ ዘለቀ በጦር ፍርድ ቤት ሞት ተፈረደበት ::ንጉሱ ፍርዱን አጸደቁት ጥር 1937:.በላይ ዘለቀ በስቅላት ሞተ ::እድሜው ሰላሳ አምስት አመት ነበር ጥልያንን በመድፍ በመትረየስ በአውሮፕላን ሊገድለው ያልቻለውን ጀግና በቅናት የተነሳሱ መቀኞች የሸረቡት ገመድ ገደለው ::ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ ሰላሳ አምስት አመት ታስረው በለውጡ ተፈቱ በላይ ዘለቀ ፎቶ ተነስቶ አያውቅም ::መልኩን ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ እንዲህ ብለው ይገልሱታል "አፍንጫው ሰተት ብሎ ወርዶ ቅጠሉ ነፋ ነፋ ይላል ::ከንፈሩ ከበድ ይላል ::ጠጉሩ ክርክም ጎፈሬ ጺሙ ሙሉ ለስላሳ ረጅም ጣቱ መልካም ወተት የተነከረ ነው የሚመስለው ጣቱ ::እግረ ቀጭን በላይ ዘለቀ ደጃዝማች ተብሎ ካዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ እንደተመለሰ ከባለስልጣኖች ጋር ለመገናኘት ወደ "ጠቅላይ ግዛቱ ጽህፈት ቤት ሄደ ::ዘበኞቹም አጋፋሪውም ሲያዩት ጊዜ ሽሽታቸውን ለቀቁ ::ስምና ግርማው ያን ያህል ያስፈራ ነበር ከጽህፈት ቤቱ ወጥቶ ወደ ሚያርፍበት ቤት ሲገባ ወሬው ከተማውን ከመቼው እንዳደረሰው አይታወቅም ::ማርቆስ ያለ ሰው ሁሉ እንጀራውን ወጡን ጠላውን ጠጁን አረቄውን እየያዘ መጣ ::በላይ ዘለቀን ህዝቡ ሲወደው ያን ያህል ነበር ::ምግብና መጠጡ ከመብዛቱ የተነሳ ሰዎች ወደውጭ ተላኩና አላፊ አግዳሚውን "የራበኽ ስንቅ የለለኽ ና ብላ !በበላይ አምላክ ና ግባ "እያሉ ጋበዙት በበላይ ዘለቀ ሰራዊት ውስጥ መሪና ተከታይ አለቃና ጭፍራ ያለው በውጊያ ሰአት ነው እንጂ በምግብ ሰአት ሁሉም እኩል ነው ::ለሰራዊቱ የሚበቃ ምግብ ከሌለ ያለው ተቆራርሶ ለሁሉም እኩል ይደርሰዋል በላይ ዘለቀ መሶብ ሲቀርብለት "ሁሉም በልቷል ይላል "አይ ዛሬ እጥረት አለ "ካሉት "እንግዲህ መልሱ ::እኔ አልበላም "ይልና ጦሙን ያድራል (አንዳንድ ጊዜ ሁሉም ባይበላም ውሸታቸውን ሁሉም በልቷል ይሉና ያበሉታል "አንድ ጊዜ ሁለት ቀን ጦም አድረን በላይ ዘለቀ ዛሬ ሶስት ድርብ (ሁለት ቁና ሽምብራ ላመጣልኝ ጠመንጃ እሰጠዋለሁ አለ ::አንድ ገበሬ ሽምብራውን አመጣ ;ጠመንጃውን ወሰደ ::ሽምብራውን በልተን አደርን በላይ ዘለቀ የገንዘብ ፍቅር የለበትም ::እንዲያውም ብር በእጁ አያድርም "ራስ ጌታ አታርጉብኝ ...ይጠቀጥቀኛል "ይላል ያቃዠኛል ማለቱ ነው በጎጃምኛ። ንጉሱ ደብረማርቆስ የመጡ ጊዜ አስራ ሁለት ሺህ ብር ሰጥተውት ሄዱ። በላይ ዘለቀ ከማርቆስ ወደ ቢቸና ሲጉዋዝ አንዱ መጥቶ "ቤቴ ተቃጠለ "ገንዘብ ሲሰጠው ;ሌላው መጥቶ "ከብቴ ተዘረፈ ሲል ገንዘብ ሲሰጠው እንዲህ ሲል ገና ቢቸና ሳይገባ አስራ ሁለት ሺ ብሩ አለቀ። "ጊዮርጊስ ያውቃል "ይላል በላይ ዘለቀ። በጊዮርጊስ በጣም ያምናል። ፍልሰታ ሲሆን ሁል ጊዜ ሱባኤ ይገባል። "እኔ የዘለቀ ልጅ !"ይላል ሲቆጣ። "በምድር በሰማይ የሚያስጉዘው !በላይ የወንዶች ቁና "ይላል ሲፎክር። በላይ ዘለቀ ተኩሶ አይስትም። ፍጥነቱ ደሞ ሲደግንና ሲተኩስ እኩል ነው። ውጊያ ሊጀምር ሲል "እኔ ሳልተኩስ እንዳትተኩሱ "ብሎ ያዛል። አንዳንድ ጊዜ በውጊያ ሰአት "እርስዎ እዚህ ይቆዩን ሲሉት "ምን ይላል ቁጣ እየጀመረው። "እርስዎ ከወደቁ መሪ የለንም" ሲሉት "ወይድ! እኔ አሮጌ ነፍጠኛ ነኝ።"ይልና ግንባር ይጋፈጣል። በላይ ዘለቀ እራሱ ሲዋጋ "ገምባው" ይተበባለው ጥሩንባው ይነፋል። "ገምባው "ባንዳን ያስበረግጋል። ጥልያንን ያብረከርካል። በላይ ዘለቀ የዘመኑን አስተሳሰብ በማወቁ ህዝቡን ለማስተባበር "ትልቅ ሰው" ማስፈለጉን በመገንዘቡ እሱ እራሱ ግን ተራ ሰው በመሆኑ የንጉስ ተክለሀይማኖት ሀረግ ለሆኑት ለልጅ ሀይሉ በለው ደብዳቤ ጻፈላቸው። የደብዳቤው ሀሳብ ባጭሩ "ህዝቡን ለማስተባበር እርስዎ የበላይ ሆነው እነን የጎበዝ አለቃ ይሹሙኝና ጠላትን እንቋቋመው። እኔም እዋጋለሁ። እርስዎ ወደጦር ግንባር መድረስ አይኖርብዎትም።" የሚል ነበር። ደጋግሞ ደብዳቤ ጻፈላቸው። ገጸበረከትም ላከላቸው።...ጠመንጃ ሽጉጥ ዝናር ከነጥይቱ ሶስት መቶ ብርና ካባ። ልጅ ሀይሉ በለው ለደብዳቤዎቹ አንድም መልስ ሳይሰቱ አንድ ቀን አንድ የትእዛዝ ደብዳቤ ላኩበት። "ደብረወርቅ ገበያችንን ያለአግባብ ቀረጡብን ብለዋልና ከንግዲህ ቆቅ የሰገረ ወፍ የበረረ እንዳይደርስባቸው። የተወሰደባቸውም ቀረጥ እንዲመለስላቸው።" በላይ ዘለቀ ተናደደ። አብረውት የነበሩትን "ጎበዝ እግዚአብሄር የወለደው ሰው አለ?" ሲል ጠየቀ። "እግዚአብሄር ይፈጥራል እንጂ አይወልድም አሉት። "ንጉስስ?" "ንጉስም እግዚአብሄር ይቀባዋል እንጂ አይወልድም። ይፈጥረዋል እንደሌላሰው" "እኔንም ፈጥሮኛል። ሊቀባኝ አይችልም?" "የሱ ሀይል ካደረብዎ የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ።" "እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ ለማንም አልታጠቅም።" ተመስገን ፈንታ የበላይ ዘለቀ የቅርብ ጉዋደኛው ነበር። አንድ ቀን ከጠላት በፊት ተመስገን ፈንታ በላይ ዘለቀን "ሸዋ ሄደን ለትልቅ ሰው እንደር። እንሾማለን ;እንሸለማለን "አለው። "እኔ ሰው ሆኜ ለሰው አላድርም "አለ በላይ ዘለቀ። "ባንተ ተኩስ ;ባንተ ወኔ፤ ባንዳፍታ ትሾማለኽ። "ጀግንነት እደጃችን ድረስ ይመጣ እንደሆነ ማን ያውቃል?" አለው በላይ ዘለቀ። አመታት አለፉ። ሞረድ እጀ ጠባብ ካስመራ እሚመጣ አፈ ሾሌ ሱሪና ተመሳሳይ ኮኮት ጥንግ ድርብ ጥበብ ኩታ በቅሎ እንደተጫነች ጠመንጃ ከነሙሉ ዝናር ጥይት ...በላይ ዘለቀ ይህንን ሁሉ አዘጋጀና ተመስገን ፈንታን ጠርቶ፥ "ያ የጌታ አዳር ሄደን እንሸለማለን ያልከው ይኸውና "ብሎ ሸለመው። በአርበኝነት ዘመን ጉዋደኛሞቹ አልተለያዩም። በላይ ዘለቀ መጀመርያ "ራስ ብሎ የሾመው ተመስገን ፈንታን ነበር። "እኔንስ ራስ አልከኝ። አንተ ማን ልትባል ነው?" አለው ተመስገን ፈንታ። "እኔንማ እናቴ አንደዜ በላይ ብላኛለች አለ በላይ ዘለቀ ዋቢ ጽሁፍ
49628
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%89%86%E1%88%B5%20%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8C%8C%E1%88%8D
የማርቆስ ወንጌል
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ማርቆስ እንደ ጻፈው። ቅዱስ ማርቆስ ወንግልን ለመስበክ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ወደ ሮም ተጉዞ ቀዳሚ የወንጌል ፀሐፊ ሆነ (፩ኛ ጴጥ ም፡፭ ቁ፡፲፪- ከጌታ የሰማውንና የተማረውን ጽፎአል። ወንጌልንም የጻፈበት ዘመን ጌታ ከዐረገ አሥራ አንደኛው ተፈፅሞ አሥራ ሁለተኛው ሲጀምር፣ ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በአራተኛው ዓመት ሲሆን ወንጌል ተብሎ ይፋ የወጣበት ቋንቋ ሮማይስጥ ነው ማለት ቅዱስ ጴጥሮስ በሮማይስጥ አስተርጉሞ የሮማ ሰዎችን ለማስተማር ተጠቅሞበታል ወንጌሉም ቅዱስ ማርቆስ ካለፈ በኋላ በስሙ ተጠርቷል። ቀጥሎም በመንፈስ ቅዱስ''' መሪነት በግብፅ አገር ተልኮውን ማኪያሄድ እንዳለበት ተረድቶ እዚሁ አገር ላይ የአንበሳ ጣዖቶችን በማጥፋት የነገደ ይሁዳ የሆነውን አንበሳ ክርስቶስን በመስበክ ከዚያም የመጀመሪያው ጳጳስ ሆኖ በመናፍቃን ተገድሎ በሰማዕትነት ያለፈ ቅዱስ ነው። ይህ ክርስቲያናዊ ተጋድሎ ነው የአንበሳ ምልክት እንዲሰጠው ዋና ምክኒያት የሆነው። በተጨማሪ በራዕዪ ዮሐንስ ጌታች መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አሸናፊ የይሁዳ አንበሳ ተብሎ ተሰይሟል በነብዩ በሆሴዕ አንበሳ ተብሎ መጠራቱን እናያለን የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 1፤የእግዚአብሔር፡ልጅ፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ወንጌል፡መዠመሪያ። 2-3፤እንሆ፥መንገድኽን፡የሚጠርግ፡መልክተኛዬን፡በፊትኽ፡እልካለኹ፡የጌታን፡መንገድ፡ አዘጋጁ፡ጥርጊያውንም፡አቅኑ፡እያለ፡በምድረ፡በዳ፡የሚጮኽ፡ሰው፡ድምፅ፡ተብሎ፡ በነቢዩ፡በኢሳይያስ፡እንደ፡ተጻፈ፥ 4፤ዮሐንስ፡በምድረ፡በዳ፡እያጠመቀ፡የንስሓንም፡ጥምቀት፡ለኀጢአት፡ ስርየት፡እየሰበከ፡መጣ። 5፤የይሁዳም፡አገር፡ዅሉ፡የኢየሩሳሌምም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ ርሱ፡ይወጡ፡ነበር፥ ኀጢአታቸውንም፡እየተናዘዙ፡በዮርዳኖስ፡ወንዝ፡ከርሱ፡ይጠመቁ፡ነበር። 6፤ዮሐንስም፡የግመል፡ጠጕር፡ለብሶ፡በወገቡ፡ጠፍር፡ይታጠቅ፡አንበጣና፡የበረሓ፡ ማርም፡ይበላ፡ነበር። 7፤ተጐንብሼ፡የጫማውን፡ጠፍር፡መፍታት፡የማይገ፟ባ፟ኝ፡ ከእኔ፡የሚበረታ፡በዃላዬ፡ይመጣል። 8፤እኔ፡በውሃ፡አጠመቅዃችኹ፡ርሱ፡ግን፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ያጠምቃችዃል፡እያለ፡ ይሰብክ፡ነበር። 9፤በዚያ፡ወራትም፡ኢየሱስ፡ከገሊላ፡ናዝሬት፡መጥቶ፡ከዮሐንስ፡በዮርዳኖስ፡ወንዝ፡ተጠመቀ። 10፤ወዲያውም፡ከውሃው፡በወጣ፡ጊዜ፡ሰማያት፡ሲቀደዱ፡መንፈስም፡እንደ፡ርግብ፡ሲወርድበት፡ አየና፦የምወድኽ፡ልጄ፡አንተ፡ነኽ፥ 11፤ባንተ፡ደስ፡ይለኛል፡የሚል፡ድምፅ፡ከሰማያት፡መጣ። 12፤ወዲያውም፡መንፈስ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡አወጣው። 13፤በምድረ፡በዳም፡ከሰይጣን፡እየተፈተነ፡ አርባ፡ቀን፡ሰነበተ፡ከአራዊትም፡ጋራ፡ነበረ፥ መላእክቱም፡አገለገሉት። 14-15፤ዮሐንስም፡ዐልፎ፡ከተሰጠ፡በዃላ፡ኢየሱስ፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ወንጌል፡ እየሰበከና፦ዘመኑ፡ተፈጸመ፡የእግዚአብሔርም፡መንግሥት፡ቀርባለች፡ንስሓ፡ግቡ፡ በወንጌልም፡እመኑ፡እያለ፡ወደ፡ገሊላ፡መጣ። 16፤በገሊላ፡ባሕርም፡አጠገብ፡ሲያልፍ፡ስምዖንን፡ወንድሙንም፡እንድርያስን፡መረባቸውን፡ ወደ፡ባሕር፡ሲጥሉ፡አየ፥ዓሣ፡አጥማጆች፡ነበሩና። 17፤ኢየሱስም፦በዃላዬ፡ኑና፡ሰዎችን፡አጥማጆች፡እንድትኾኑ፡አደርጋችዃለኹ፡አላቸው። 18፤ወዲያውም፡መረባቸውን፡ትተው፡ተከተሉት። 19፤ከዚያም፡ጥቂት፡እልፍ፡ብሎ፡የዘብዴዎስን፡ልጅ፡ያዕቆብን፡ወንድሙንም፡ዮሐንስን፡ደግሞ፡በታንኳ፡ ላይ፡መረባቸውን፡ሲያበጁ፡አየ። 20፤ወዲያውም፡ጠራቸው፡አባታቸውንም፡ዘብዴዎስን፡ከሞያተኛዎቹ፡ጋራ፡በታንኳ፡ላይ፡ ትተው፡ተከትለውት፡ኼዱ። 21፤ወደ፡ቅፍርናሖምም፡ገቡ፤ወዲያውም፡በሰንበት፡ወደ፡ምኵራብ፡ገብቶ፡አስተማረ። 22፤እንደ፡ባለሥልጣን፡ያስተምራቸው፡ነበር፡እንጂ፡እንደ፡ጻፊዎች፡አይደለምና፡በትምህርቱ፡ ተገረሙ። 23፤በዚያን፡ጊዜም፡በምኵራባቸው፡ርኩስ፡መንፈስ፡ያለው፡ሰው፡ነበረ፤ 24፤ርሱም፦የናዝሬቱ፡ኢየሱስ፡ሆይ፥ከአንተ፡ጋራ፡ምን፡አለን፧ልታጠፋን፡መጣኽን፧ማን፡እንደ፡ ኾንኽ፡ዐውቄያለኹ፥የእግዚአብሔር፡ቅዱሱ፡ብሎ፡ጮኸ። 25፤ኢየሱስም፦ዝም፡በል፡ከርሱም፡ውጣ፡ብሎ፡ገሠጸው። 26፤ርኩሱም፡መንፈስ፡አንፈራገጠውና፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኾ፡ከርሱ፡ወጣ። 27፤ዅሉም፦ይህ፡ምንድር፡ነው፧በሥልጣን፡ርኩሳን፡መናፍስትን፡ያዛ፟ል፤እነርሱም፡ ይታዘዙለታልና፥ይህ፡ዐዲስ፡ትምህርት፡ምንድር፡ነው፧ብለው፡እስኪጠያየቁ፡ድረስ፡አደነቁ። 28፤ዝናውም፡ወዲያው፡በየስፍራው፡ወደገሊላ፡ዙሪያ፡ዅሉ፡ወጣ። 29፤ወዲያውም፡ከምኵራብ፡ወጥቶ፡ከያዕቆብና፡ከዮሐንስ፡ጋራ፡ወደስምዖንና፡ወደእንድርያስ፡ቤት፡ገባ። 30፤የስምዖንም፡ዐማት፡በንዳድ፡ታማ፡ተኝታ፡ነበር፥ስለ፡ርሷም፡ወዲያው፡ነገሩት። 31፤ቀርቦም፡እጇን፡ይዞ፡አስነሣት፡ንዳዱም፡ወዲያው፡ለቀቃትና፡አገለገለቻቸው። 32፤ፀሓይም፡ገብቶ፡በመሸ፡ጊዜ፥የታመሙትንና፡አጋንንት፡ያደረባቸውን፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፤ 33፤ከተማዪቱም፡ዅላ፡በደጅ፡ተሰብስባ፡ነበር። 34፤በልዩ፡ልዩ፡ደዌም፡የታመሙትን፡ብዙዎችን፡ፈወሰ፥ብዙዎችንም፡አጋንንት፡አወጣ፥ አጋንንትም፡ክርስቶስ፡መኾኑን፡ዐውቀው፡ነበርና፥ሊናገሩ፡አልፈቀደላቸውም። 35፤ማለዳም፡ተነሥቶ፡ገና፡ሌሊት፡ሳለ፡ወጣ፡ወደ፡ምድረ፡በዳም፡ኼዶ፡በዚያ፡ጸለየ። 36፤ስምዖንና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩትም፡ገሥግሠው፡ተከተሉት፥ 37፤ባገኙትም፡ጊዜ፦ዅሉ፡ይፈልጉኻል፡አሉት። 38፤ርሱም፦በዚያ፡ደግሞ፡ልሰብክ፡ወደ፡ሌላ፡ስፍራ፡በቅርብ፡ወዳሉ፡መንደሮች፡እንኺድ፡ስለዚህ፡ወጥቻለኹና፡አላቸው። 39፤በምኵራባቸውም፡እየሰበከ፡አጋንንትንም፡እያወጣ፡ወደ፡ገሊላ፡ዅሉ፡መጣ። 40፤ለምጻምም፡ወደ፡ርሱ፡መጥቶ፡ተንበረከከና፦ብትወድስ፡ልታነጻኝ፡ትችላለኽ፡ብሎ፡ለመነው። 41፤ኢየሱስም፡ዐዘነለት፡እጁንም፡ዘርግቶ፡ዳሰሰውና፦እወዳ፟ለኹ፤ንጻ፡አለው። 42፤በተናገረም፡ጊዜ፡ለምጹ፡ወዲያው፡ለቀቀውና፡ነጻ። 43፤በብርቱም፡ተናግሮ፡ወዲያው፡አወጣው፤ 44፤ለማንም፡አንዳች፡እንዳትናገር፡ተጠንቀቅ፥ነገር፡ግን፥ኼደኽ፡ራስኽን፡ለካህን፡አሳይ፡ለእነርሱም፡ምስክር፡እንዲኾን፡ ስለ፡መንጻትኽ፡ሙሴ፡ያዘዘውን፡አቅርብ፡አለው። 45፤ርሱ፡ግን፡ሲወጣ፡ብዙ፡ሊሰብክና፡ነገሩን፡ሊያወራ፡ዠመረ፥ስለዚህም፡ኢየሱስ፡ተገልጦ፡ወደ፡ከተማ፡መግባት፡ወደ፡ ፊት፡ተሳነው፥ነገር፡ግን፥በውጭ፡በምድረ፡በዳ፡ይኖር፡ነበር፤ከየስፍራውም፡ወደ፡ርሱ፡ይመጡ፡ነበር። ምዕራፍ 1፤ከጥቂት፡ቀን፡በዃላ፡ወደ፡ቅፍርናሖም፡ደግሞ፡ገብቶ፡በቤት፡እንደ፡ኾነ፡ተሰማ። 2፤በደጅ፡ያለው፡ስፍራም፡እስኪጠባ፟ቸው፡ድረስ፡ብዙ፡ሰዎች፡ተሰበሰቡ፤ቃሉንም፡ይነግራቸው፡ነበር። 3፤አራት፡ሰዎችም፡የተሸከሙትን፡ሽባ፡አመጡለት። 4፤ስለሕዝቡም፡ብዛት፡ወደ፡ርሱ፡ማቅረብ፡ቢያቅታቸው፡ርሱ፡ያለበትን፡የቤቱን፡ጣራ፡አነሡ፥ነድለውም፡ ሽባው፡የተኛበትን፡ዐልጋ፡አወረዱ።5፤ኢየሱስም፡እምነታቸውን፡አይቶ፡ሽባውን፦አንተ፡ልጅ፥ኀጢአትኽ፡ተሰረየችልኽ፡አለው። 6፤ከጻፊዎችም፡አንዳንዶቹ፡በዚያ፡ተቀምጠው፡ነበር፡በልባቸውም፦ይህ፡ሰው፡ስለ፡ምን፡እንደዚህ፡ያለ፡ ስድብ፡ይናገራል፧ 7፤ከአንዱ፡ከእግዚአብሔር፡በቀር፡ኀጢአት፡ሊያስተሰርይ፡ማን፡ይችላል፧ብለው፡ዐሰቡ። 8፤ወዲያውም፡ኢየሱስ፡በልባቸው፡እንዲህ፡እንዳሰቡ፡በመንፈስ፡ዐውቆ፡እንዲህ፡አላቸው፦በልባችኹ፡ይህን፡ ስለ፡ምን፡ታስባላችኹ፧ 9፤ሽባውን፦ኀጢአትኽ፡ተሰረየችልኽ፡ከማለት፡ወይስ 1 ተነሣ፡ዐልጋኽንም፡ተሸከምና፡ኺድ፡ከማለት፡ ማናቸው፡ይቀላል፧ 10፤ነገር፡ግን፥ለሰው፡ልጅ፡በምድር፡ላይ፡ኀጢአትን፡ሊያስተሰርይ፡ሥልጣን፡እንዳለው፡እንድታውቁ፤ 11፤ሽባውን፦አንተን፡እልኻለኹ፥ተነሣ፥ዐልጋኽን፡ተሸከምና፡ወደ፡ቤትኽ፡ኺድ፡አለው። 12፤ተነሥቶም፡ወዲያው፡ዐልጋውን፡ተሸክሞ፡በዅሉ፡ፊት፡ወጣ፥ስለዚህም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ ተገረሙና፦እንዲህ፡ያለ፡ከቶ፡አላየንም፡ብለው፡እግዚአብሔርን፡አከበሩ። 13፤ደግሞም፡በባሕር፡አጠገብ፡ወጣ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡መጡና፡አስተማራቸው። 14፤ሲያልፍም፡በመቅረጫው፡ተቀምጦ፡የነበረውን፡የእልፍዮስን፡ልጅ፡ሌዊን፡አየና፦ተከተለኝ፡ አለው።ተነሥቶም፡ተከተለው። 15፤በቤቱም፡በማእዱ፡ተቀምጦ፡ሳለ፥ብዙ፡ቀራጮችና፡ኀጢአተኛዎች፡ከኢየሱስና፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ ተቀመጡ፤ብዙ፡ነበሩ፡ይከተሉትም፡ነበር። 16፤ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያንም፥ከቀራጮችና፡ከኀጢአተኛዎች፡ጋራ፡ሲበላ፡አይተው፡ለደቀ፡ መዛሙርቱ፦ከቀራጮችና፡ከኀጢአተኛዎች፡ጋራ፡የሚበላና፡የሚጠጣ፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧አሉ። 17፤ኢየሱስም፡ሰምቶ፦ሕመምተኛዎች፡እንጂ፡ብርቱዎች፡ባለመድኀኒት፡አያስፈልጋቸውም፤ኀጢአተኛዎችን፡ እንጂ፡ጻድቃንን፡ልጠራ፡አልመጣኹም፡አላቸው። 18፤የዮሐንስ፡ደቀ፡መዛሙርትና፡ፈሪሳውያን፡ይጦሙ፡ነበር።መጥተውም፦የዮሐንስና፡የፈሪሳውያን፡ደቀ፡ መዛሙርት፡የሚጦሙት፡የአንተ፡ደቀ፡መዛሙርት፡ግን፡የማይጦሙት፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧አሉት። 19፤ኢየሱስም፡አላቸው፦ሙሽራው፡ከነርሱ፡ጋራ፡ሳለ፡ሚዜዎች፡ሊጦሙ፡ይችላሉን፧ሙሽራው፡ከነርሱ፡ ጋራ፡ሳለ፡ሊጦሙ፡አይችሉም። 20፤ነገር፡ግን፥ሙሽራው፡ከነርሱ፡የሚወሰድበት፡ወራት፡ይመጣል፥በዚያ፡ወራትም፡ይጦማሉ። 21፤በአረጀ፡ልብስ፡ዐዲስ፡ዕራፊ፡የሚጥፍ፡የለም፤ቢደረግ፡ግን፥ዐዲሱ፡መጣፊያ፡አሮጌውን፡ ይቦጭቀዋል፥መቀደዱም፡የባሰ፡ይኾናል። 22፤በአረጀ፡አቍማዳም፡ዐዲስ፡የወይን፡ጠጅ፡የሚያኖር፡የለም፤ቢደረግ፡ግን፥የወይን፡ጠጁ፡አቍማዳውን፡ ያፈነዳል፡የወይኑም፡ጠጅ፡ይፈሳል፡አቍማዳውም፡ይጠፋል፡ዐዲሱን፡የወይን፡ጠጅ፡ግን፡በዐዲስ፡አቍማዳ፡ ያኖራሉ። 23፤በሰንበትም፡በዕርሻ፡መካከል፡ሲያልፍ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡እየኼዱ፡እሸት፡ይቀጥፉ፡ዠመር። 24፤ፈሪሳውያንም፦እንሆ፥በሰንበት፡ያልተፈቀደውን፡ስለ፡ምን፡ያደርጋሉ፧አሉት። 25፤ርሱም፦ዳዊት፡ባስፈለገውና፡በተራበ፡ጊዜ፥ርሱ፡ዐብረውት፡ከነበሩት፡ጋራ፡ያደረገውን፥ 26፤አብያተር፡ሊቀ፡ካህናት፡በነበረ፡ጊዜ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እንደ፡ገባ፥ከካህናት፡በቀር፡መብላት፡ ያልተፈቀደውን፡የመሥዋዕትን፡እንጀራ፡እንደ፡በላ፥ከርሱም፡ጋራ፡ለነበሩት፡እንደ፡ሰጣቸው፡ከቶ፡ አላነበባችኹምን፧አላቸው። 27፤ደግሞ፦ሰንበት፡ስለ፡ሰው፡ተፈጥሯል፡እንጂ፡ሰው፡ስለ፡ሰንበት፡አልተፈጠረም፤ 28፤እንዲሁም፡የሰው፡ልጅ፡ለሰንበት፡እንኳ፡ጌታዋ፡ነው፡አላቸው። ምዕራፍ 1፤ደግሞም፡ወደ፡ምኵራብ፡ገባ፥በዚያም፡እጁ፡የሰለለች፡ሰው፡ነበር፤ 2፤ሊከሱትም፥በሰንበት፡ይፈውሰው፡እንደ፡ኾነ፡ይጠባበቁት፡ነበር። 3፤እጁ፡የሰለለችውንም፡ሰው፦ተነሥተኽ፡ወደ፡መካከል፡ና፡አለው። 4፤በሰንበት፡በጎ፡ማድረግ፡ተፈቅዷልን፧ወይስ፡ክፉ፧ነፍስ፡ማዳን፡ወይስ፡መግደል፧አላቸው፤እነርሱም፡ ዝም፡አሉ። 5፤ስለልባቸውም፡ድንዛዜ፡ዐዝኖ፡ዙሪያውን፡እየተመለከተ፡በቍጣ፡አያቸው፥ሰውየውንም፦እጅኽን፡ዘርጋ፡ አለው። 6፤ዘረጋትም፥እጁም፡ዳነች።ፈሪሳውያንም፡ወጥተው፡ወዲያው፡እንዴት፡አድርገው፡እንዲያጠፉት፡ከሄሮድስ፡ ወገን፡ጋራ፡ተማከሩበት። 7፤ኢየሱስም፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ወደ፡ባሕር፡ፈቀቅ፡አለ፤ከገሊላ፡የመጡም፡ብዙ፡ሰዎች፡ተከተሉት፤ 8፤እንዴት፡ትልቅ፡ነገርም፡እንዳደረገው፡ሰምተው፡ብዙ፡ሰዎች፡ከይሁዳ፡ከኢየሩሳሌምም፡ከኤዶምያስም፡ ከዮርዳኖስ፡ማዶም፡ከጢሮስና፡ከሲዶና፡ምድርም፡ወደ፡ርሱ፡መጡ። 9፤ሰዎቹም፡እንዳያጋፉት፡ታንኳን፡ያቈዩለት፡ዘንድ፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡አዘዛቸው፤ 10፤ብዙ፡ሰዎችን፡አድኖ፡ነበርና፥ስለዚህም፡ሥቃይ፡ያለባቸው፡ዅሉ፡እንዲዳስሱት፡ይወድቁበት፡ነበር። 11፤ርኩሳን፡መናፍስትም፡ባዩት፡ጊዜ፡በፊቱ፡ተደፍተው፦አንተ፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኽ፡እያሉ፡ጮኹ። 12፤እንዳይገልጡትም፡በጣም፡አዘዛቸው። 13፤ወደ፡ተራራም፡ወጣ፥ራሱም፡የወደዳቸውን፡ወደ፡ርሱ፡ጠራ፥ወደ፡ርሱም፡ኼዱ። 14፤ከርሱም፡ጋራ፡እንዲኖሩና፡ለመስበክ፡እንዲልካቸው፥ 15፤ድውዮችንም፡ሊፈውሱ፡አጋንንትንም፡ሊያወጡ፡ሥልጣን፡ይኾንላቸው፡ዘንድ፡ዐሥራ፡ኹለት፡አደረገ፤ 16፤ስምዖንንም፡ጴጥሮስ፡ብሎ፡ሰየመው፤ 17፤የዘብዴዎስንም፡ልጅ፡ያዕቆብን፡የያዕቆብንም፡ወንድም፡ዮሐንስን፡ቦአኔርጌስ፡ብሎ፡ሰየማቸው፥የነጐድጓድ፡ ልጆች፡ማለት፡ነው፤ 18፤እንድርያስንም፡ፊልጶስንም፡በርተሎሜውስንም፡ማቴዎስንም፡ቶማስንም፡የእልፍዮስን፡ልጅ፡ያዕቆብንም፡ ታዴዎስንም፡ቀነናዊውንም፡ስምዖንን፥ 19፤አሳልፎ፡የሰጠውንም፡የአስቆሮቱን፡ይሁዳን። 20፤ወደ፡ቤትም፡መጡ፤እንጀራም፡መብላት፡ስንኳ፡እስኪሳናቸው፡ድረስ፡እንደ፡ገና፡ብዙ፡ሰዎች፡ተሰበሰቡ። 21፤ዘመዶቹም፡ሰምተው፦አበደ፡ብለዋልና፥ሊይዙት፡ወጡ። 22፤ከኢየሩሳሌም፡የወረዱ፡ጻፊዎችም፦ብዔል፡ዜቡል፡አለበት፤ደግሞ፦በአጋንንት፡አለቃ፡አጋንንትን፡ያወጣል፡ብለው፡ተናገሩ። 23፤እነርሱንም፡ወደ፡ርሱ፡ጠርቶ፡በምሳሌ፡አላቸው፦ሰይጣን፡ሰይጣንን፡ሊያወጣው፡እንዴት፡ይችላል፧ 24፤መንግሥትም፡ርስ፡በርሷ፡ከተለያየች፡ያች፡መንግሥት፡ልትቆም፡አትችልም፤ 25፤ቤትም፡ርስ፡በርሱ፡ከተለያየ፡ያ፡ቤት፡ሊቆም፡አይችልም። 26፤ሰይጣንም፡ራሱን፡ተቃውሞ፡ከተለያየ፥መጨረሻ፡ይኾንበታል፡እንጂ፡ሊቆም፡አይችልም። 27፤ነገር፡ግን፥አስቀድሞ፡ኀይለኛውን፡ሳያስር፡ወደኀይለኛው፡ቤት፡ገብቶ፡ዕቃውን፡ሊበዘብዝ፡የሚችል፡ የለም፥ከዚያም፡ወዲያ፡ቤቱን፡ይበዘብዛል። 28፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ለሰው፡ልጆች፡ኀጢአት፡ዅሉ፡የሚሳደቡትም፡ስድብ፡ዅሉ፡ይሰረይላቸዋል፤ 29፤በመንፈስ፡ቅዱስ፡ላይ፡የሚሳደብ፡ዅሉ፡ግን፡የዘለዓለም፡ኀጢአት፡ዕዳ፡ይኾንበታል፡እንጂ፡ለዘለዓለም፡ አይሰረይለትም። 30፤ርኩስ፡መንፈስ፡አለበት፡ይሉ፡ነበርና። 31፤እናቱና፡ወንድሞቹም፡መጡ፥በውጭም፡ቆመው፡ወደ፡ርሱ፡ልከው፡አስጠሩት። 32፤ብዙ፡ሰዎችም፡በዙሪያው፡ተቀምጠው፡ነበሩና፦እንሆ፥እናትኽ፡ወንድሞችኽም፡በውጭ፡ቆመው፡ ይፈልጉኻል፡አሉት። 33፤መልሶም፦እናቴ፡ማን፡ናት፧ወንድሞቼስ፡እነ፡ማን፡ናቸው፧አላቸው። 34፤በዙሪያው፡ተቀምጠው፡ወደነበሩትም፡ተመለከተና፦እንሆ፥እናቴ፡ወንድሞቼም። 35፤የእግዚአብሔርን፡ፈቃድ፡የሚያደርግ፡ዅሉ፥ርሱ፡ወንድሜ፡ነው፡እኅቴም፡እናቴም፡አለ። ምዕራፍ 1፤ደግሞም፡በባሕር፡ዳር፡ሊያስተምር፡ዠመረ።እጅግ፡ብዙ፡ሰዎችም፡ወደ፡ርሱ፡ስለ፡ተሰበሰቡ፡ርሱ፡ በታንኳ፡ገብቶ፡በባሕር፡ላይ፡ተቀመጠ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡በባሕር፡ዳር፡በምድር፡ላይ፡ነበሩ። 2፤በምሳሌም፡ብዙ፡ያስተምራቸው፡ነበር፥በትምህርቱም፡አላቸው፦ስሙ፤ 3-4፤እንሆ፥ዘሪ፡ሊዘራ፡ወጣ።ሲዘራም፡አንዳንዱ፡በመንገድ፡ዳር፡ወደቀና፡ወፎች፡መጥተው፡በሉት። 5፤ሌላውም፡ብዙ፡መሬት፡በሌለበት፡በጭንጫ፡ላይ፡ወደቀና፡ጥልቅ፡መሬት፡ስላልነበረው፡ ወዲያው፡በቀለ፤ 6፤ፀሓይም፡ሲወጣ፡ጠወለገ፥ሥርም፡ስላልነበረው፡ደረቀ። 7፤ሌላውም፡በሾኽ፡መካከል፡ ወደቀ፥ሾኽም፡ ወጣና፡ዐነቀው፥ፍሬም፡አልሰጠም። 8፤ሌላውም፡በመልካም፡መሬት፡ላይ፡ወደቀና፡ወጥቶ፡አድጎ፡ፍሬ፡ ሰጠ፥አንዱም፡ሠላሳ፡ አንዱም፡ስድሳ፡ አንዱም፡መቶ፡አፈራ። 9፤የሚሰማ፡ዦሮ፡ያለው፡ይስማ፡አለ። 10፤ብቻውንም፡በኾነ፡ጊዜ፥በዙሪያው፡የነበሩት፡ከዐሥራ፡ ኹለቱ፡ጋራ፡ስለ፡ምሳሌው፡ጠየቁት። 11-12፤እንዲህም፡አላቸው፦ለእናንተ፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ምስጢር፡ማወቅ፡ተሰጥቷችዃል፤ በውጭ፡ላሉት፡ግን፥አይተው፡እንዲያዩ፡እንዳይመለከቱም፥ሰምተውም፡እንዲሰሙ፡ እንዳያስተውሉም፥እንዳይመለሱ፡ኀጢአታቸውም፡እንዳይሰረይላቸው፡ነገር፡ዅሉ፡በምሳሌ፡ ይኾንባቸዋል። 13፤አላቸውም፦ይህን፡ምሳሌ፡አታውቁምን፧እንዴትስ፡ምሳሌዎቹን፡ዅሉ፡ታውቃላችኹ፧ 14፤ዘሪው፡ቃሉን፡ይዘራል።ቃልም፡በተዘራበት፡በመንገድ፡ዳር፡የኾኑት፡እነዚህ፡ናቸው፥ 15፤በሰሙት፡ጊዜም፡ሰይጣን፡ወዲያው፡መጥቶ፡በልባቸው፡የተዘራውን፡ቃል፡ይወስዳል። 16፤እንዲሁም፡በጭንጫ፡ላይ፡የተዘሩት፡እነዚህ፡ናቸው፥ቃሉንም፡ሰምተው፡ወዲያው፡በደስታ፡ ይቀበሉታል፥ 17፤ለጊዜውም፡ነው፡እንጂ፡በእነርሱ፡ሥር፡የላቸውም፥ዃላም፡በቃሉ፡ምክንያት፡መከራ፡ወይም፡ስደት፡ በኾነ፡ጊዜ፡ወዲያው፡ይሰናከላሉ። 18፤በሾኽም፡የተዘሩት፡ሌላዎች፡ናቸው፥ቃሉን፡የሰሙት፡ እነዚህ፡ናቸው፥ 19፤የዚህም፡ዓለም፡ዐሳብና፡የባለጠግነት፡ማታለል፡የሌላውም፡ነገር፡ምኞት፡ገብተው፡ቃሉን፡ ያንቃሉ፥የማያፈራም፡ይኾናል። 20፤በመልካምም፡መሬት፡የተዘሩት፡ቃሉን፡ሰምተው፡የሚቀበሉት፡ አንዱም፡ሠላሳ፡አንዱም፡ስድሳ፡አንዱም፡መቶ፡ፍሬ፡የሚያፈሩት፡እነዚህ፡ናቸው። 21፤እንዲህም፡አላቸው፦መብራትን፡ከእንቅብ፡ወይስ፡ከዐልጋ፡በታች፡ሊያኖሩት፡ያመጡታልን፧በመቅረዝ፡ ላይ፡ሊያኖሩት፡አይደለምን፧ 22፤እንዲገለጥ፡ባይኾን፡የተሰወረ፡የለምና፤ወደ፡ግልጥ፡እንዲመጣ፡እንጂ፡ የተሸሸገ፡የለም። 23፤የሚሰማ፡ዦሮ፡ያለው፡ቢኖር፡ይስማ። 24፤አላቸውም፦ምን፡እንድትሰሙ፡ተጠበቁ።በምትሰፍሩበት፡መስፈሪያ፡ይሰፈርላችዃል፡ለእናንተም፡ ይጨመርላችዃል። 25፤ላለው፡ይሰጠዋልና፤ከሌለውም፡ያው፡ያለው፡እንኳ፡ይወሰድበታል። 26፤ርሱም፡አለ፦በምድር፡ዘርን፡እንደሚዘራ፡ሰው፡የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡እንደዚህ፡ናት፡ሌሊትና፡ ቀን፡ይተኛልም፡ይነሣልም፥ 27፤ርሱም፡እንዴት፡እንደሚኾን፡ሳያውቅ፡ዘሩ፡ይበቅላል፡ያድግማል። 28፤ምድሪቱም፡ዐውቃ፡በመዠመሪያ፡ቡቃያ፡ዃላም፡ዛላ፡ዃላም፡በዛላው፡ፍጹም፡ሰብል፡ታፈራለች። 29፤ፍሬ፡ግን፡ሲበስል፡መከር፡ደርሷልና፥ወዲያው፡ማጭድ፡ይልካል። 30፤ርሱም፡አለ፦የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡በምን፡እናስመስላታለን፧ወይስ፡በምን፡ምሳሌ፡እንመስላታለን፧ 31፤እንደ፡ሰናፍጭ፡ቅንጣት፡ናት፥ርሷም፡በምድር፡በተዘራች፡ጊዜ፡በምድር፡ካለ፡ዘር፡ዅሉ፡ ታንሳለች፤በተዘራችም፡ጊዜ፡ትወጣለች፡ከአትክልትም፡ዅሉ፡የምትበልጥ፡ትኾናለች፥ 32፤የሰማይ፡ወፎችም፡በጥላዋ፡ሊሰፍሩ፡እስኪችሉ፡ታላላቅ፡ቅርንጫፎች፡ታደርጋለች። 33፤መስማትም፡በሚችሉበት፡መጠን፡እነዚህን፡በሚመስል፡በብዙ፡ምሳሌ፡ቃሉን፡ይነግራቸው፡ ነበር፤ያለምሳሌ፡ግን፡አልነገራቸውም፥ 34፤ለብቻቸውም፡ሲኾኑ፡ነገሩን፡ዅሉ፡ለገዛ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ ይፈታላቸው፡ነበር። 35፤በዚያም፡ቀን፡በመሸ፡ጊዜ፦ወደ፡ማዶ፡እንሻገር፡አላቸው። 36፤ሕዝቡንም፡ትተው፡በታንኳ፡እንዲያው፡ወሰዱት፥ሌላዎች፡ታንኳዎችም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበሩ። 37፤ብርቱ፡ዐውሎ፡ነፋስም፡ተነሣና፡ውሃ፡በታንኳዪቱ፡እስኪሞላ፡ድረስ፡ማዕበሉ፡በታንኳዪቱ፡ይገባ፡ነበር። 38፤ርሱም፡በስተዃላዋ፡ትራስ፡ተንተርሶ፡ተኝቶነበር፤አንቅተውም፣ መምህርሆይ፥ስንጠፋ አይገድኽምን፡አሉት። 39፤ነቅቶም፡ነፋሱን፡ገሠጸው፡ባሕሩንም፦ዝም፡በል፥ጸጥ፡በል፡አለው።ነፋሱም፡ተወ፥ታላቅ፡ጸጥታምኾነ። 40፤እንዲህ፡የምትፈሩ፡ስለ፡ምን፡ነው፧እንዴትስ፡እምነት፡የላችኹም፧አላቸው። 41፤ እጅግም ፈሩና፡እንግዲህ፡ነፋስም፡ባሕርም፡የሚታዘዙለት፡ይህ፡ማን፡ነው፧ተባባሉ። ምዕራፍ 1፤ወደባሕር፡ማዶም፡ወደጌርጌሴኖን፡አገር፡መጡ። 2፤ከታንኳዪቱም፡በወጣ፡ጊዜ፥ርኩስ፡መንፈስ፡የያዘው፡ሰው፡ከመቃብር፡ወጥቶ፡ወዲያው፡ተገናኘው፤ 3፤ርሱም፡በመቃብር፡ይኖር፡ነበር፥በሰንሰለትም፡ስንኳ፡ማንም፡ሊያስረው፡በዚያን፡ጊዜ፡አይችልም፡ነበር፤ 4፤ብዙ፡ጊዜ፡በእግር፡ብረትና፡በሰንሰለት፡ይታሰር፡ነበርና፥ዳሩ፡ግን፡ሰንሰለቱን፡ይበጣጥስ፡እግር፡ብረቱንም፡ ይሰባብር፡ነበር፥ሊያሸንፈውም፡የሚችል፡አልነበረም፤ 5፤ዅልጊዜም፡ሌሊትና፡ቀን፡በመቃብርና፡በተራራ፡ኾኖ፡ይጮኽ፡ነበር፡ሰውነቱንም፡በድንጋይ፡ይቧጭር፡ ነበር። 6፤ኢየሱስንም፡ከሩቅ፡ባየ፡ጊዜ፡ሮጦ፡ሰገደለት፥ 7፤በታላቅ፡ድምፅም፡እየጮኸ፦የልዑል፡እግዚአብሔር፡ልጅ፡ኢየሱስ፡ሆይ፥ከአንተ፡ጋራ፡ምን፡ አለኝ፧እንዳታሠቃየኝ፡በእግዚአብሔር፡አምልኻለኹ፡አለ፤ 8፤አንተ፡ርኩስ፡መንፈስ፥ከዚህ፡ሰው፡ውጣ፡ብሎት፡ነበርና፦ 9፤ስምኽ፡ማን፡ነው፧ብሎ፡ጠየቀው፦ብዙዎች፡ነንና፡ስሜ፡ሌጌዎን278፡ነው፡አለው፥ 10፤ከአገርም፡ውጭ፡እንዳይሰዳቸው፡አጥብቆ፡ለመነው። 11፤በዚያም፡በተራራ፡ጥግ፡ብዙ፡የዕሪያ፡መንጋ፡ይሰማራ፡ነበርና፦ 12፤ወደ፡ዕሪያዎቹ፡እንድንገባ፡ስደደን፡ብለው፡ለመኑት። 13፤ኢየሱስም፡ፈቀደላቸው።ርኩሳን፡መናፍስቱም፡ወጥተው፡ወደ፡ዕሪያዎቹ፡ገቡ፥ኹለት፡ሺሕም፡የሚያኽል፡ መንጋ፡ከአፋፉ፡ወደ፡ባሕር፡ተጣደፉና፡በባሕር፡ሰጠሙ። 14፤እረኛዎቹም፡ሸሽተው፡በከተማውና፡በአገሩ፡አወሩ፤ነገሩም፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ለማየት፡መጡ። 15፤ወደ፡ኢየሱስም፡መጡ፥አጋንንትም፡ያደሩበትን፡ሌጌዎንም፡የነበረበትን፡ሰው፡ተቀምጦ፡ለብሶም፡ልቡም፡ ተመልሶ፡አዩና፡ፈሩ። 16፤ያዩት፡ሰዎችም፡አጋንንት፡ላደሩበት፡ሰው፡የኾነውንና፡ስለ፡ዕሪያዎቹ፡ተረኩላቸው። 17፤ከአገራቸውም፡እንዲኼድላቸው፡ይለምኑት፡ዠመር። 18፤ወደ፡ታንኳዪቱም፡በገባ፡ጊዜ፡አጋንንት፡ዐድረውበት፡የነበረው፡ሰው፡ከርሱ፡ጋራ፡እንዲኖር፡ለመነው። 19፤ኢየሱስም፡አልፈቀደለትም፥ነገር፡ግን፦ወደ፡ቤትኽ፡በቤተ፡ሰዎችኽ፡ዘንድ፡ኼደኽ፡ጌታ፡እንዴት፡ያለ፡ ታላቅ፡ነገር፡እንዳደረገልኽ፡እንዴትስ፡እንደ፡ማረኽ፡አውራላቸው፡አለው። 20፤ኼዶም፡ኢየሱስ፡እንዴት፡ያለ፡ታላቅ፡ነገር፡እንዳደረገለት፡ዐሥር፡ከተማ፡በሚባል፡አገር፡ይሰብክ፡ ዠመር፤ዅሉም፡ተደነቁ። 21፤ኢየሱስም፡ደግሞ፡በታንኳዪቱ፡ወደ፡ማዶ፡ከተሻገረ፡በዃላ፥ብዙ፡ሰዎች፡ወደ፡ርሱ፡ ተሰበሰቡ፥በባሕርም፡አጠገብ፡ነበረ። 22፤ኢያኢሮስ፡የተባለ፡ከምኵራብ፡አለቃዎች፡አንዱ፡መጣ፤ባየውም፡ጊዜ፡በእግሩ፡ላይ፡ወደቀና፦ 23፤ታናሺቱ፡ልጄ፡ልትሞት፡ቀርባለችና፡እንድትድንና፡በሕይወት፡እንድትኖር፡መጥተኽ፡እጅኽን፡ጫንባት፡ ብሎ፡አጥብቆ፡ለመነው። 24፤ከርሱም፡ጋራ፡ኼደ።ብዙ፡ሕዝብም፡ተከተሉት፡አጋፉትም። 25፤ከዐሥራ፡ኹለት፡ዓመትም፡ዠምሮ፡ደም፡የሚፈሳ፟ት፡ሴት፡ነበረች፥ 26፤ከብዙ፡ባለመድኀኒቶችም፡ብዙ፡ተሠቃየች፤ገንዘቧንም፡ዅሉ፡ከስራ፡ባሰባት፡እንጂ፡ምንም፡ አልተጠቀመችም፤ 27፤የኢየሱስንም፡ወሬ፡ሰምታ፡በስተዃላው፡በሰዎች፡መካከል፡መጥታ፡ልብሱን፡ዳሰሰች። 28፤ልብሱን፡ብቻ፡የዳሰስኹ፡እንደ፡ኾነ፡እድናለኹ፡ብላለችና። 29፤ወዲያውም፡የደሟ፡ምንጭ፡ደረቀ፡ከሥቃይዋም፡እንደ፡ዳነች፡በሰውነቷ፡ዐወቀች። 30፤ወዲያውም፡ኢየሱስ፡ከርሱ፡ኀይል፡እንደ፡ወጣ፡በገዛ፡ራሱ፡ዐውቆ፡በሕዝቡ፡መካከል፡ዘወር፡ ብሎ፦ልብሴን፡የዳሰሰ፡ማን፡ነው፧አለ። 31፤ደቀ፡መዛሙርቱም፦ሕዝቡ፡ሲያጋፉኽ፡እያየኽ፦ማን፡ዳሰሰኝ፡ትላለኽን፧አሉት። 32፤ይህንም፡ያደረገችውን፡ለማየት፡ዘወር፡ብሎ፡ይመለከት፡ነበር። 33፤ሴቲቱ፡ግን፡የተደረገላትን፡ስላወቀች፥እየፈራች፡እየተንቀጠቀጠችም፥መጥታ፡በፊቱ፡ተደፋች፡ እውነቱንም፡ዅሉ፡ነገረችው። 34፤ርሱም፦ልጄ፡ሆይ፥እምነትሽ፡አድኖሻል፤በሰላም፡ኺጂ፡ከሥቃይሽም፡ተፈወሽ፡አላት። 35፤ርሱም፡ገና፡ሲናገር፡ከምኵራብ፡አለቃው፡ቤት፡ዘንድ፡የመጡት፦ልጅኽ፡ሞታለች፤ስለ፡ምን፡ መምህሩን፡አኹን፡ታደክመዋለኽ፧አሉት። 36፤ኢየሱስ፡ግን፡የተናገሩትን፡ቃል፡አድምጦ፡ለምኵራቡ፡አለቃ፦እመን፡ብቻ፡እንጂ፡አትፍራ፡አለው። 37፤ከጴጥሮስም፡ከያዕቆብም፡ከያዕቆብም፡ወንድም፡ከዮሐንስ፡በቀር፡ማንም፡እንዲከተለው፡አልፈቀደም። 38፤ወደምኵራቡ፡አለቃ፡ቤትም፡መጥቶ፡ሰዎች፡ሲንጫጩና፡ሲያለቅሱ፡ዋይታም፡ሲያበዙ፡አየ፤ 39፤ገብቶም፦ስለ፡ምን፡ትንጫጫላችኹ፥ታለቅሳላችኹም፧ብላቴናዪቱ፡ተኝታለች፡እንጂ፡አልሞተችም፡ አላቸው። 40፤በጣምም፡ሣቁበት።ርሱ፡ግን፡ዅሉን፡አስወጥቶ፡የብላቴናዪቱን፡አባትና፡እናትም፡ከርሱ፡ጋራ፡ የነበሩትንም፡ይዞ፡ብላቴናዪቱ፡ወዳለችበት፡ገባ። 41፤የብላቴናዪቱንም፡እጅ፡ይዞ፦ጣሊታ279፡ቁሚ፡አላት፤ፍችውም፡አንቺ፡ብላቴና፡ተነሽ፡እልሻለኹ፡ነው። 42፤ብላቴናዪቱም፡የዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረችና፡ወዲያው፡ቆማ፡ተመላለሰች።ወዲያውም፡ታላቅ፡ መገረም፡ተገረሙ። 43፤ይህንም፡ማንም፡እንዳያውቅ፡አጥብቆ፡አዟቸው።የምትበላውን፡ስጧት፡አላቸው። ሮማ.፥ሌጌዎን፡(ሰራዊት፥ጭፍራ፤6000፡ጭፍራ፡ከናለቃው፡አንድ፡ሌጌዎን፡ይባላል።ኪ.ወ.ክ.፥ገ.558)። ምዕራፍ 1፤ከዚያም፡ወጥቶ፡ወደገዛ፡አገሩ፡መጣ፡ደቀ፡መዛሙርቱም፡ተከተሉት። 2፤ሰንበትም፡በኾነ፡ጊዜ፡በምኵራብ፡ያስተምር፡ዠመር፤ብዙዎችም፡ሰምተው፡ተገረሙና፦እነዚህን፡ነገሮች፡ ይህ፡ከወዴት፡አገኛቸው፧ለዚህ፡የተሰጠችው፡ጥበብ፡ምንድር፡ናት፧በእጁም፡የሚደረጉ፡እንደነዚህ፡ያሉ፡ ተኣምራት፡ምንድር፡ናቸው፧ 3፤ይህስ፡ጸራቢው፡የማርያም፡ልጅ፡የያዕቆብም፡የዮሳም፡የይሁዳም፡የስምዖንም፡ወንድም፡ አይደለምን፧እኅቶቹስ፡በዚህ፡በእኛ፡ዘንድ፡አይደሉምን፧አሉ፤ይሰናከሉበትም፡ነበር። 4፤ኢየሱስም፦ነቢይ፡ከገዛ፡አገሩና፡ከገዛ፡ዘመዶቹ፡ከገዛ፡ቤቱም፡በቀር፡ሳይከበር፡አይቀርም፡አላቸው። 5፤በዚያም፡በጥቂቶች፡ድውዮች፡ላይ፡እጁን፡ጭኖ፡ከመፈወስ፡በቀር፥ተኣምር፡ሊያደርግ፡ምንም፡አልቻለም። 6፤ስላለማመናቸውም፡ተደነቀ።በመንደሮችም፡እያስተማረ፡ይዞር፡ነበር። 7፤አስራ፡ኹለቱንም፡ወደ፡ርሱ፡ጠራ፥ኹለት፡ኹለቱንም፡ይልካቸው፡ዠመር፥በርኩሳን፡መናፍስትም፡ላይ፡ ሥልጣን፡ሰጣቸው፥ 8፤ለመንገድም፡ከበትር፡በቀር፡እንጀራም፡ቢኾን፡ከረጢትም፡ቢኾን፡መሐለቅም፡በመቀነታቸው፡ቢኾን፡ እንዳይዙ፡አዘዛቸው። 9፤በእግራችኹ፡ጫማ፡አድርጉ፡እንጂ፡ኹለት፡እጀ፡ጠባብ፡አትልበሱ፡አለ። 10፤በማናቸውም፡ስፍራ፡ወደ፡ቤት፡ብትገቡ፡ከዚያ፡እስክትወጡ፡ድረስ፡በዚያው፡ተቀመጡ። 11፤ከማይቀበሏችኹና፡ከማይሰሟችኹ፡ስፍራ፡ዅሉ፥ከዚያ፡ወጥታችኹ፡ምስክር፡ይኾንባቸው፡ዘንድ፡ ከእግራችኹ፡በታች፡ያለውን፡ትቢያ፡አራግፉ።እውነት፡እላችዃለኹ፥ከዚያች፡ከተማ፡ይልቅ፡ለሰዶምና፡ ለገሞራ፡በፍርድ፡ቀን፡ይቀልላቸዋል፡አላቸው። 12፤ወጥተውም፡ንስሓ፡እንዲገቡ፡ሰበኩ፥ብዙ፡አጋንንትንም፡አወጡ፥ 13፤ብዙ፡ድውዮችንም፡ዘይት፡እየቀቡ፡ፈወሷቸው። 14፤ስሙም፡ተገልጧልና፥ንጉሡ፡ሄሮድስ፡በሰማ፡ጊዜ፦መጥምቁ፡ዮሐንስ፡ከሙታን፡ተነሥቷል፡ ስለዚህም፡ኀይል፡በርሱ፡ይደረጋል፡አለ። 15፤ሌላዎችም፦ኤልያስ፡ነው፡አሉ፤ሌላዎችም፦ከነቢያት፡እንደ፡አንዱ፡ነቢይ፡ነው፡አሉ። 16፤ሄሮድስ፡ግን፡ሰምቶ፦እኔ፡ራሱን፡ያስቈረጥኹት፡ዮሐንስ፡ይህ፡ነው፡ርሱ፡ከሙታን፡ተነሥቷል፡አለ። 17፤ሄሮድስ፡የወንድሙን፡የፊልጶስን፡ሚስት፡ሄሮድያዳን፡አግብቶ፡ነበርና፥በርሷ፡ምክንያት፡ራሱ፡ልኮ፡ ዮሐንስን፡አስይዞ፡በወህኒ፡አሳስሮት፡ነበር፤ 18፤ዮሐንስ፡ሄሮድስን፦የወንድምኽ፡ሚስት፡ለአንተ፡ልትኾን፡አልተፈቀደም፡ይለው፡ነበርና። 19፤ሄሮድያዳ፡ግን፡ተቃውማው፡ልትገድለው፡ትፈልግ፡ነበር፡አልቻለችም፤ 20፤ሄሮድስ፡ዮሐንስ፡ጻድቅና፡ቅዱስ፡ሰው፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቆ፡ይፈራውና፡ይጠባበቀው፡ነበር፤ርሱንም፡ ሰምቶ፡በብዙ፡ነገር፡ያመነታ፡ነበር፤ 21፤በደስታም፡ይሰማው፡ነበር።ሄሮድስም፡በተወለደበት፡ቀን፡ለመኳንንቱና፡ለሻለቃዎቹ፡ለገሊላም፡ሹማምንት፡ ግብር፡ባደረገ፡ጊዜ፡ምቹ፡ቀን፡ኾነላትና፡ 22፤የሄሮድያዳ፡ልጅ፡ገብታ፡ስትዘፍን፡ሄሮድስንና፡ከርሱ፡ጋራ፡የተቀመጡትን፡ደስ፡አሠኘቻቸው።ንጉሡም፡ ብላቴናዪቱን፦የምትወጂውን፡ዅሉ፡ለምኚኝ፡እሰጥሽማለኹ፡አላት፤ 23፤የመንግሥቴ፡እኩሌታ፡ስንኳ፡ቢኾን፡የምትለምኚውን፡ዅሉ፡እሰጥሻለኹ፡ብሎ፡ማለላት። 24፤ወጥታም፡ለእናቷ፦ምን፡ልለምነው፧አለች።ርሷም፦የመጥምቁን፡የዮሐንስን፡ራስ፡አለች። 25፤ወዲያውም፡ፈጥና፡ወደ፡ንጉሡ፡ገብታ፦የመጥምቁን፡የዮሐንስን፡ራስ፡በወጭት፡አኹን፡ልትሰጠኝ፡ እወዳለኹ፡ብላ፡ለመነችው። 26፤ንጉሡም፡እጅግ፡ዐዝኖ፡ስለ፡መሐላው፡ከርሱም፡ጋራ፡ስለተቀመጡት፡ሊነሣት፡አልወደደም። 27፤ወዲያውም፡ንጉሡ፡ባለወግ፡ልኮ፡ራሱን፡እንዲያመጣ፡አዘዘው።ኼዶም፡በወህኒ፡ራሱን፡ቈረጠ፥ 28፤ራሱንም፡በወጭት፡አምጥቶ፡ለብላቴናዪቱ፡ሰጣት፥ብላቴናዪቱም፡ለእናቷ፡ሰጠች። 29፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ሰምተው፡መጡ፡በድኑንም፡ወስደው፡ቀበሩት። 30፤ሐዋርያትም፡ወደ፡ኢየሱስ፡ተሰብስበው፡ያደረጉትንና፡ያስተማሩትን፡ዅሉ፡ነገሩት። 31፤እናንት፡ራሳችኹ፡ብቻችኹን፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ኑና፡ጥቂት፡ዕረፉ፡አላቸው፤የሚመጡና፡የሚኼዱ፡ ብዙዎች፡ነበሩና፥ለመብላት፡እንኳ፡ጊዜ፡ዐጡ። 32፤በታንኳውም፡ብቻቸውን፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ኼዱ። 33፤ሰዎችም፡ሲኼዱ፡አይዋቸው፡ብዙዎችም፡ዐወቋቸውና፡ከከተማዎች፡ዅሉ፡በእግር፡እየሮጡ፡ወዲያ፡ ቀደሟቸው፡ወደ፡ርሱም፡ተሰበሰቡ። 34፤ኢየሱስም፡ወጥቶ፡ብዙ፡ሕዝብ፡አየና፡እረኛ፡እንደሌላቸው፡በጎች፡ስለ፡ነበሩ፡ዐዘነላቸው፥ብዙም፡ ነገር፡ያስተምራቸው፡ዠመር። 35፤በዚያን፡ጊዜም፡ብዙ፡ሰዓት፡ካለፈ፡በዃላ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ወደ፡ርሱ፡ቀርበው፦ቦታው፡ምድረ፡በዳ፡ ነው፡አኹንም፡መሽቷል፤ 36፤የሚበሉት፡የላቸውምና፡በዙሪያ፡ወዳሉ፡ገጠሮችና፡መንደሮች፡ኼደው፡እንጀራ፡ለራሳቸው፡እንዲገዙ፡ አሰናብታቸው፡አሉት። 37፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፦እናንተ፡የሚበሉትን፡ስጧቸው፡አላቸው፦ኼደን፡እንጀራ፡በኹለት፡መቶ፡ዲናር፡ እንግዛላቸውን፧እንዲበሉም፡እንስጣቸውን፧አሉት። 38፤ርሱም፦ስንት፡እንጀራ፡አላችኹ፧ኺዱና፡እዩ፡አላቸው።ባወቁም፡ጊዜ፦ዐምስት፥ኹለትም፡ዓሣ፡ አሉት። 39፤ዅሉንም፡በየክፍሉ፡በለመለመ፡ሣር፡ላይ፡እንዲያስቀምጧቸው፡አዘዛቸው። 40፤መቶ፡መቶውና፡ዐምሳ፡ዐምሳው፡እየኾኑ፡በተራ፡በተራ፡ተቀመጡ። 41፤ዐምስቱንም፡እንጀራ፡ኹለቱንም፡ዓሣ፡ይዞ፡ወደ፡ሰማይ፡አሻቅቦ፡አየና፡ባረከ፥እንጀራውንም፡ቈርሶ፡ እንዲያቀርቡላቸው፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ሰጠ፥ 42፤ኹለቱን፡ዓሣ፡ደግሞ፡ለዅሉ፡ከፈለ።ዅሉም፡በልተው፡ጠገቡ፤ 43፤ከቍርስራሹም፡ዐሥራ፡ኹለት፡መሶብ፡የሞላ፡አነሡ፥ከዓሣውም፡ደግሞ። 44፤እንጀራውንም፡የበሉት፡ወንዶቹ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ነበሩ። 45፤ወዲያውም፡ሕዝቡን፡ሲያሰናብት፡ሳለ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡በታንኳ፡ገብተው፡ወደ፡ማዶ፡ወደ፡ቤተ፡ ሳይዳ፡እንዲቀድሙት፡ግድ፡አላቸው። 46፤ካሰናበታቸውም፡በዃላ፡ሊጸልይ፡ወደ፡ተራራ፡ወጣ። 47፤በመሸም፡ጊዜ፡ታንኳዪቱ፡በባሕር፡መካከል፡ሳለች፡ርሱ፡ብቻውን፡በምድር፡ላይ፡ነበረ። 48፤ነፋስ፡ወደ፡ፊታቸው፡ነበረና፡እየቀዘፉ፡ሲጨነቁ፡አይቶ፥ከሌሊቱ፡በአራተኛው፡ክፍል፡በባሕር፡ላይ፡ እየኼደ፡ወደ፡እነርሱ፡መጣ፤ሊያልፋቸውም፡ይወድ፡ነበር። 49፤እነርሱ፡ግን፡በባሕር፡ላይ፡ሲኼድ፡ባዩት፡ጊዜ፡ምትሀት፡መሰላቸውና፡ጮኹ፥ 50፤ዅሉ፡አይተውታልና፥ታወኩም።ወዲያውም፡ተናገራቸውና፦አይዟችኹ፤እኔ፡ነኝ፥አትፍሩ፡አላቸው። 51፤ወደ፡እነርሱም፡ወደ፡ታንኳዪቱ፡ገባ፥ነፋሱም፡ተወ፤በራሳቸውም፡ያለመጠን፡እጅግ፡ተገረሙ፤ 52፤ስለ፡እንጀራው፡አላስተዋሉምና፤ነገር፡ግን፥ልባቸው፡ደንዝዞ፡ነበር። 53፤ተሻግረውም፡ወደ፡ምድር፡ወደ፡ጌንሴሬጥ፡ደረሱ፡ታንኳዪቱንም፡አስጠጉ። 54፤ከታንኳዪቱም፡ሲወጡ፡ወዲያው፡ዐውቀውት፡ 55፤በዚያች፡አገር፡ዅሉ፡ዙሪያ፡ሮጡና፡ርሱ፡እንዳለ፡ወደሰሙበት፡ስፍራ፡ሕመምተኛዎችን፡በዐልጋ፡ላይ፡ ያመጡ፡ዠመር። 56፤በገባበትም፡ስፍራ፡ዅሉ፥መንደርም፡ከተማም፡ገጠርም፡ቢኾን፥በገበያ፡ድውዮችን፡ያኖሩ፡ ነበር፤የልብሱንም፡ጫፍ፡እንኳ፡ሊዳስሱ፡ይለምኑት፡ነበር፡የዳሰሱትም፡ዅሉ፡ዳኑ። (ጣልያታ፡ወይም፡ጣሊታ፡ማለት=ሴት፡ልጅ፥ቈንዦ፥ገና፡አካለ፡መጠን፡ያልሞላች)። ምዕራፍ 1፤ፈሪሳውያንና፡ከጻፊዎች፡ወገን፡ከኢየሩሳሌም፡የመጡትም፡ወደ፡ርሱ፡ተሰበሰቡ። 2፤ከደቀ፡መዛሙርቱም፡አንዳንድ፡በርኩስ፡ማለት፡ባልታጠበ፡እጅ፡እንጀራ፡ሲበሉ፡አዩ። 3፤ፈሪሳውያንና፡አይሁድም፡ዅሉ፡የሽማግሌዎችን፡ወግ፡ሲጠብቁ፡እጃቸውን፡ደኅና፡አድርገው፡ሳይታጠቡ፡ አይበሉምና፥ 4፤ከገበያም፡ተመልሰው፡ካልታጠቡ፡አይበሉም፥ጽዋንም፡ማድጋንም፡የናስ፡ዕቃንም፡ዐልጋንም፡እንደ፡ ማጠብ፡ሌላ፡ነገር፡ሊጠብቁት፡የተቀበሉት፡ብዙ፡አለ። 5፤ፈሪሳውያንም፡ጻፊዎችም፦ደቀ፡መዛሙርትኽ፡እንደ፡ሽማግሌዎች፡ወግ፡ስለ፡ምን፡አይኼዱም፧ነገር፡ ግን፡እጃቸውን፡ሳይታጠቡ፡እንጀራ፡ይበላሉ፡ብለው፡ጠየቁት። 6፤ርሱ፡ግን፡እንዲህ፡አላቸው፦ኢሳይያስ፡ስለ፡እናንተ፡ስለ፡ግብዞች፦ይህ፡ሕዝብ፡በከንፈሩ፡ያከብረኛል፡ ልቡ፡ግን፡ከእኔ፡በጣም፡የራቀ፡ነው፤ 7፤የሰውም፡ሥርዐት፡የኾነ፡ትምህርት፡እያስተማሩ፡በከንቱ፡ያመልኩኛል፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡በእውነት፡ ትንቢት፡ተናገረ። 8፤የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ትታችኹ፡ጽዋን፡ማድጋንም፡እንደ፡ማጠብ፡የሰውን፡ወግ፡ ትጠብቃላችኹ፥ይህንም፡የመሰለ፡ብዙ፡ሌላ፡ነገር፡ታደርጋላችኹ። 9፤እንዲህም፡አላቸው፦ወጋችኹን፡ትጠብቁ፡ዘንድ፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡እጅግ፡ንቃችዃል። 10፤ሙሴ፦አባትኽንና፡እናትኽን፡አክብር፤ደግሞ፦አባቱን፡ወይም፡እናቱን፡የሰደበ፡ፈጽሞ፡ይሙት፡ ብሏልና። 11፤እናንተ፡ግን፡ትላላችኹ፦ሰው፡አባቱን፡ወይም፡እናቱን፦ከእኔ፡የምትጠቀምበት፡ነገር፡ዅሉ፡ቍርባን፡ ማለት፡መባ፡ነው፡ቢል፥ 12፤ለአባቱና፡ለእናቱ፡ምንም፡እንኳ፡ሊያደርግ፡ወደ፡ፊት፡አትፈቅዱለትም፤ 13፤ባስተላለፋችኹትም፡ወግ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ትሽራላችኹ፤እንደዚሁም፡ይህን፡የሚመስል፡ብዙ፡ነገር፡ ታደርጋላችኹ። 14፤ደግሞም፡ሕዝቡን፡ጠርቶ፦ዅላችኹ፡እኔን፡ስሙ፥አስተውሉም። 15፤ከሰው፡የሚወጡት፡ሰውን፡የሚያረክሱ፡ናቸው፡እንጂ፥ከሰው፡ውጭ፡የሚገባውስ፡ሊያረክሰው፡የሚችል፡ ምንም፡የለም። 16፤የሚሰማ፡ዦሮ፡ያለው፡ቢኖር፡ይስማ፡አላቸው። 17፤ከሕዝቡ፡ዘንድ፡ወደ፡ቤት፡ከገባ፡በዃላ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ምሳሌውን፡ጠየቁት። 18፤ርሱም፦እናንተ፡ደግሞ፡እንደዚህ፡የማታስተውሉ፡ናችኹን፧ከውጭ፡ወደ፡ሰው፡የሚገባ፡ሊያረክሰው፡ ምንም፡እንዳይችል፡አትመለከቱምን፧ 19፤ወደ፡ሆድ፡ገብቶ፡ወደ፡እዳሪ፡ይወጣል፡እንጂ፡ወደ፡ልብ፡አይገባምና፤መብልን፡ዅሉ፡እያጠራ፡ አላቸው። 20፤ርሱም፡አለ፦ከሰው፡የሚወጣው፡ሰውን፡የሚያረክስ፡ያ፡ነው።21፤ከውስጥ፡ከሰው፡ልብ፡የሚወጣ፡ክፉ፡ዐሳብ፥ 22፤ዝሙት፥መስረቅ፥መግደል፥ምንዝርነት፥መጐምዠት፥ክፋት፥ተንኰል፥መዳራት፥ምቀኝነት፥ስድብ፥ት ዕቢት፥ስንፍና፡ናቸውና፤ 23፤ይህ፡ክፉው፡ዅሉ፡ከውስጥ፡ይወጣል፡ሰውን፡ያረክሰዋል። 24፤ከዚያም፡ተነሥቶ፡ወደ፡ጢሮስና፡ወደሲዶና፡አገር፡ኼደ።ወደ፡ቤትም፡ገብቶ፡ማንም፡እንዳያውቅበት፡ ወደደ፡ሊሰወርም፡አልተቻለውም፤ 25፤ወዲያው፡ግን፡ታናሺቱ፡ልጇ፡ርኩስ፡መንፈስ፡ያደረባት፡አንዲት፡ሴት፡ስለ፡ርሱ፡ሰምታ፡መጣችና፡ በእግሩ፡ላይ፡ተደፋች፡ 26፤ሴቲቱም፡ግሪክ፥ትውልዷም፡ሲሮፊኒቃዊት፡ነበረች፤ከልጇ፡ጋኔን፡ያወጣላት፡ዘንድ፡ለመነችው። 27፤ኢየሱስ፡ግን፦ልጆቹ፡በፊት፡ይጠግቡ፡ዘንድ፡ተዪ፡የልጆቹን፡እንጀራ፡ይዞ፡ለቡችሎች፡መጣል፡ አይገ፟ባ፟ምና፥አላት። 28፤ርሷም፡መልሳ፦አዎን፥ጌታ፡ሆይ፥ቡችሎች፡እንኳ፡ከማእዱ፡በታች፡ኾነው፡የልጆችን፡ፍርፋሪ፡ ይበላሉ፡አለችው። 29፤ርሱም፦ስለዚህ፡ቃልሽ፡ኺጂ፡ጋኔኑ፡ከልጅሽ፡ወጥቷል፡አላት። 30፤ወደ፡ቤቷም፡ኼዳ፡ጋኔኑ፡ወጥቶ፡ልጇም፡በዐልጋ፡ላይ፡ተኝታ፡አገኘች። 31፤ደግሞም፡ከጢሮስ፡አገር፡ወጥቶ፡በሲዶና፡ዐልፎ፡ዐሥር፡ከተማ፡በሚባል፡አገር፡መካከል፡ወደገሊላ፡ ባሕር፡መጣ። 32፤ደንቈሮና፡ኰልታፋም፡የኾነ፡ሰው፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፥ 33፤እጁንም፡ይጭንበት፡ዘንድ፡ለመኑት።ከሕዝቡም፡ለይቶ፡ለብቻው፡ወሰደው፥ጣቶቹንም፡በዦሮዎቹ፡አገባ፡ እንትፍም፡ብሎ፡ምላሱን፡ዳሰሰ፤ 34፤ወደ፡ሰማይም፡አሻቅቦ፡አይቶ፡ቃተተና፦ኤፍታሕ፡አለው፥ርሱም፡ተከፈት፡ማለት፡ነው። 35፤ወዲያውም፡ዦሮዎቹ፡ተከፈቱ፡የምላሱም፡እስራት፡ተፈታ፡አጥርቶም፡ተናገረ። 36፤ለማንም፡አትንገሩ፡ብሎ፡አዘዛቸው፡እነርሱ፡ግን፡ባዘዛቸውም፡መጠን፡ይልቅ፡እጅግ፡አወሩት። 37፤ያለመጠንም፡ተገረሙና፦ዅሉን፡ደኅና፡አድርጓል፤ደንቈሮዎችም፡እንዲሰሙ፡ዲዳዎችም፡እንዲናገሩ፡ ያደርጋል፡አሉ። ምዕራፍ 1፤በዚያ፡ወራት፡ደግሞ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ነበረ፡የሚበሉትም፡ስለሌላቸው፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ጠርቶ፦ 2፤ሕዝቡ፡ከእኔ፡ጋራ፡እስካኹን፡ሦስት፡ቀን፡ውለዋልና፥የሚበሉት፡ስለሌላቸው፡አዝንላቸዋለኹ፤ 3፤ከነርሱም፡አንዳንዶቹ፡ከሩቅ፡መጥተዋልና፥ጦማቸውን፡ወደ፡ቤታቸው፡ባሰናብታቸው፡በመንገድ፡ይዝላሉ፡ አላቸው። 4፤ደቀ፡መዛሙርቱም፦በዚህ፡በምድረ፡በዳ፡እንጀራ፡ከየት፡አግኝቶ፡ሰው፡እነዚህን፡ማጥገብ፡ ይችላል፧ብለው፡መለሱለት። 5፤ርሱም፦ስንት፡እንጀራ፡አላችኹ፧ብሎ፡ጠየቃቸው፥እነርሱም፦ሰባት፡አሉት። 6፤ሕዝቡም፡በምድር፡እንዲቀመጡ፡አዘዘ።ሰባቱንም፡እንጀራ፡ይዞ፡አመሰገነ፥ቈርሶም፡እንዲያቀርቡላቸው፡ ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ሰጠ፥ለሕዝቡም፡አቀረቡ። 7፤ጥቂትም፡ትንሽ፡ዓሣ፡ነበራቸው፤ባረከውም፡ይህንም፡ደግሞ፡እንዲያቀርቡላቸው፡አዘዘ። 8፤በሉም፡ጠገቡም፥የተረፈውንም፡ቍርስራሽ፡ሰባት፡ቅርጫት፡አነሡ። 9፤የበሉትም፡አራት፡ሺሕ፡ያኽል፡ነበሩ። 10፤አሰናበታቸውም።ወዲያውም፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ወደ፡ታንኳዪቱ፡ገብቶ፡ወደዳልማኑታ፡አገር፡ መጣ። 11፤ፈሪሳውያንም፡ወጡና፡ሊፈትኑት፡ከሰማይ፡ምልክት፡ከርሱ፡ፈልገው፡ከርሱ፡ጋራ፡ይከራከሩ፡ዠመር። 12፤በመንፈሱም፡እጅግ፡ቃተተና፦ይህ፡ትውልድ፡ስለ፡ምን፡ምልክት፡ይፈልጋል፧እውነት፡ እላችዃለኹ፥ለዚህ፡ትውልድ፡ምልክት፡አይሰጠውም፡አለ። 13፤ትቷቸውም፡እንደ፡ገና፡ወደ፡ታንኳዪቱ፡ገብቶ፡ወደ፡ማዶ፡ኼደ። 14፤እንጀራ፡መያዝም፡ረሱ፥ለእነርሱም፡ካንድ፡እንጀራ፡በቀር፡በታንኳዪቱ፡አልነበራቸውም። 15፤ርሱም፦ተጠንቀቁ፤ከፈሪሳውያንና፡ከሄሮድስ፡ርሾ፡ተጠበቁ፡ብሎ፡አዘዛቸው። 16፤ርስ፡በርሳቸውም፦እንጀራ፡ስለሌለን፡ይኾናል፡ብለው፡ተነጋገሩ። 17፤ኢየሱስም፡ዐውቆ፡እንዲህ፡አላቸው፦እንጀራ፡ስለሌላችኹ፡ስለ፡ምን፡ትነጋገራላችኹ፧ገና፡ አልተመለከታችኹምን፧አላስተዋላችኹምን፧ 18፤ልባችኹስ፡ደንዝዟልን፧ዐይን፡ሳላችኹ፡አታዩምን፧ዦሮስ፡ሳላችኹ፡አትሰሙምን፧ትዝስ፡አይላችኹምን፧ 19፤ዐምስቱን፡እንጀራ፡ለዐምስት፡ሺሕ፡በቈረስኹ፡ጊዜ፥ቍርስራሹ፡የሞላ፡ስንት፡መሶብ፡ አነሣችኹ፧እነርሱም፦ዐሥራ፡ኹለት፡አሉት። 20፤ሰባቱን፡እንጀራስ፡ለአራት፡ሺሕ፡በቈረስኹ፡ጊዜ፥ቍርስራሹ፡የሞላ፡ስንት፡ቅርጫት፡ አነሣችኹ፧እነርሱም፦ሰባት፡አሉት። 21፤ገና፡አላስተዋላችኹምን፧አላቸው። 22፤ወደ፡ቤተ፡ሳይዳም፡መጡ።ዕውርም፡አመጡለት፥እንዲዳስሰውም፡ለመኑት። 23፤ዕውሩንም፡እጁን፡ይዞ፡ከመንደር፡ውጭ፡አወጣው፥በዐይኑም፡ተፍቶበት፡እጁንም፡ጭኖበት።አንዳች፡ ታያለኽን፡ብሎ፡ጠየቀው። 24፤አሻቅቦም፦ሰዎች፡እንደ፡ዛፍ፡ሲመላለሱ፡አያለኹ፡አለ። 25፤ከዚህም፡በዃላ፡ደግሞ፡እጁን፡በዐይኑ፡ላይ፡ጫነበት፡አጥርቶም፡አየና፡ዳነም፡ከሩቅም፡ሳይቀር፡ዅሉን፡ ተመለከተ። 26፤ወደ፡ቤቱም፡ሰደደውና፦ወደ፡መንደሩ፡አትግባ፡በመንደሩም፡ለማንም፡አንዳች፡አትናገር፡አለው። 27፤ኢየሱስና፡ደቀ፡መዛሙርቱም፡በፊልጶስ፡ቂሳርያ፡ወዳሉ፡መንደሮች፡ወጡ፡በመንገድም፦ሰዎች፡እኔ፡ ማን፡እንደ፡ኾንኹ፡ይላሉ፧ብሎ፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ጠየቃቸው። 28፤እነርሱም፦መጥምቁ፡ዮሐንስ፥ሌላዎችም፡ኤልያስ፥ሌላዎችም፡ከነቢያት፡አንዱ፡ብለው፡ነገሩት። 29፤እናንተስ፡እኔ፡ማን፡እንደ፡ኾንኹ፡ትላላችኹ፧ብሎ፡ጠየቃቸው።ጴጥሮስም፦አንተ፡ክርስቶስ፡ነኽ፡ ብሎ፡መለሰለት። 30፤ስለ፡ርሱም፡ለማንም፡እንዳይናገሩ፡አዘዛቸው። 31፤የሰው፡ልጅ፡ብዙ፡መከራ፡ሊቀበል፥ከሽማግሌዎችም፡ከካህናት፡አለቃዎችም፡ከጻፊዎችም፡ ሊጣል፥ሊገደልም፡ከሦስት፡ቀንም፡በዃላ፡ሊነሣ፡እንዲገባው፡ያስተምራቸው፡ዠመር፤ቃሉንም፡ገልጦ፡ ይናገር፡ነበር። 32፤ጴጥሮስም፡ወደ፡ርሱ፡ወስዶ፡ይገሥጸው፡ዠመር። 33፤ርሱ፡ግን፡ዘወር፡አለ፡ደቀ፡መዛሙርቱንም፡አይቶ፡ጴጥሮስን፡ገሠጸውና፦ወደ፡ዃላዬ፡ኺድ፥አንተ፡ ሰይጣን፤የሰውን፡እንጂ፡የእግዚአብሔርን፡ነገር፡አታስብምና፡አለው። 34፤ሕዝቡንም፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ጠርቶ፡እንዲህ፡አላቸው፦በዃላዬ፡ሊመጣ፡የሚወድ፡ ቢኖር፥ራሱን፡ይካድ፡መስቀሉንም፡ተሸክሞ፡ይከተለኝ። 35፤ነፍሱን፡ሊያድን፡የሚወድ፡ዅሉ፡ያጠፋታልና፥ስለ፡እኔና፡ስለ፡ወንጌል፡ነፍሱን፡የሚያጠፋ፡ዅሉ፡ግን፡ ያድናታል። 36፤ሰው፡ዓለምን፡ዅሉ፡ቢያተርፍ፡ነፍሱንም፡ቢያጐድል፡ምን፡ይጠቅመዋል፧ 37፤ሰውስ፡ስለነፍሱ፡ቤዛ፡ምን፡ይሰጣል፧ 38፤በዚህም፡በዘማዊና፡በኀጢአተኛ፡ትውልድ፡መካከል፡በእኔና፡በቃሌ፡የሚያፍር፡ዅሉ፥የሰው፡ልጅ፡ ደግሞ፡በአባቱ፡ክብር፡ከቅዱሳን፡መላእክት፡ጋራ፡በመጣ፡ጊዜ፡በርሱ፡ያፍርበታል። ምዕራፍ 1፤እውነት፡እላችዃለኹ፥በዚህ፡ከቆሙት፡ሰዎች፡የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡በኀይል፡ስትመጣ፡እስኪያዩ፡ ድረስ፥ሞትን፡የማይቀምሱ፡አንዳንዶች፡አሉ፡አላቸው። 2፤ከስድስት፡ቀንም፡በዃላ፡ኢየሱስ፡ጴጥሮስንና፡ያዕቆብን፡ዮሐንስንም፡ይዞ፡ወደ፡ረዥም፡ተራራ፡ብቻቸውን፡ አወጣቸው።በፊታቸውም፡ተለወጠ፥ልብሱም፡አንጸባረቀ፤ 3፤ዐጣቢም፡በምድር፡ላይ፡እንደዚያ፡ሊያነጣው፡እስከማይችል፡በጣም፡ነጭ፡ኾነ። 4፤ኤልያስና፡ሙሴም፡ታዩዋቸው፥ከኢየሱስም፡ጋራ፡ይነጋገሩ፡ነበር። 5፤ጴጥሮስም፡መልሶ፡ኢየሱስን፦መምህር፡ሆይ፥በዚህ፡መኾን፡ለእኛ፡መልካም፡ነውና፥አንድ፡ለአንተ፡ አንድም፡ለሙሴ፡አንድም፡ለኤልያስ፡ሦስት፡ዳሶች፡እንሥራ፡አለው። 6፤እጅግ፡ስለ፡ፈሩ፡የሚለውን፡አያውቅም፡ነበር። 7፤ደመናም፡መጥቶ፡ጋረዳቸው፥ከደመናውም፦የምወደ፟ው፡ልጄ፡ይህ፡ነው፥ርሱን፡ስሙት፡የሚል፡ድምፅ፡ መጣ።8፤ድንገትም፡ዞረው፡ሲመለከቱ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ከኢየሱስ፡ብቻ፡በቀር፡ማንንም፡አላዩም። 9፤ከተራራውም፡ሲወርዱ፡የሰው፡ልጅ፡ከሙታን፡እስኪነሣ፡ድረስ፡ያዩትን፡ለማንም፡እንዳይነግሩ፡አዘዛቸው። 10፤ቃሉንም፡ይዘው፦ከሙታን፡መነሣት፡ምንድር፡ነው፧እያሉ፡ርስ፡በርሳቸው፡ተጠያየቁ። 11፤እነርሱም፦ኤልያስ፡አስቀድሞ፡ሊመጣ፡እንዲገባው፡ጻፊዎች፡ስለ፡ምን፡ይላሉ፧ብለው፡ጠየቁት። 12፤ርሱም፡መልሶ፦ኤልያስማ፡አስቀድሞ፡ይመጣል፥ዅሉንም፡ያቀናናል፤ስለ፡ሰው፡ልጅም፡እንዴት፡ ተብሎ፡ተጽፏል፧ብዙ፡መከራ፡እንዲቀበል፡እንዲናቅም። 13፤ነገር፡ግን፥እላችዃለኹ፥ኤልያስ፡ደግሞ፡መጥቷል፥ስለ፡ርሱም፡እንደ፡ተጸፈ፡የወደዱትን፡ዅሉ፡ አደረጉበት፡አላቸው። 14፤ወደ፡ደቀ፡መዛሙርቱም፡በመጣ፡ጊዜ፥ብዙ፡ሕዝብ፡ሲከቧ፟ቸው፥ጻፊዎችም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ሲከራከሩ፡ አየ። 15፤ወዲያውም፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ባዩት፡ጊዜ፡ደነገጡ፥ወደ፡ርሱም፡ሮጠው፡እጅ፡ነሡት። 16፤ጻፊዎችንም፦ስለ፡ምን፡ከነርሱ፡ጋራ፡ትከራከራላችኹ፧ብሎ፡ጠየቃቸው። 17፤ከሕዝቡ፡አንዱ፡መልሶ፦መምህር፡ሆይ፥ዲዳ፡መንፈስ፡ያደረበትን፡ልጄን፡ወዳንተ፡አምጥቻለኹ፤ 18፤በያዘውም፡ስፍራ፡ዅሉ፡ይጥለዋል፤ዐረፋም፡ይደፍቃል፥ጥርሱንም፡ያፋጫል፡ ይደርቃልም፤እንዲያወጡለትም፡ለደቀ፡መዛሙርትኽ፡ነገርዃቸው፥አልቻሉምም፡አለው። 19፤ርሱም፡መልሶ፦የማታምን፡ትውልድ፡ሆይ፥እስከ፡መቼ፡ከእናንተ፡ጋራ፡እኖራለኹ፧እስከ፡መቼስ፡ እታገሣችዃለኹ፧ወደ፡እኔ፡አምጡት፡አላቸው። 20፤ወደ፡ርሱም፡አመጡት።ርሱንም፡ባየ፡ጊዜ፡ያ፡መንፈስ፡ወዲያው፡አንፈራገጠው፤ወደ፡ምድርም፡ ወድቆ፡ዐረፋ፡እየደፈቀ፡ተንፈራፈረ። 21፤አባቱንም፦ይህ፡ከያዘው፡ስንት፡ዘመን፡ነው፧ብሎ፡ጠየቀው።ርሱም፦ከሕፃንነቱ፡ዠምሮ፡ነው፤ 22፤ብዙ፡ጊዜም፡ሊያጠፋው፡ወደ፡እሳትም፡ወደ፡ውሃም፡ጣለው፤ቢቻልኽ፡ግን፡ዕዘንልን፥ርዳንም፡አለው። 23፤ኢየሱስም፦ቢቻልኽ፡ትላለኽ፤ለሚያምን፡ዅሉ፡ይቻላል፡አለው። 24፤ወዲያውም፡የብላቴናው፡አባት፡ጮኾ፦አምናለኹ፤አለማመኔን፡ርዳው፡አለ። 25፤ኢየሱስም፡ሕዝቡ፡እንደ፡ገና፡ሲራወጥ፡አይቶ፡ርኩሱን፡መንፈስ፡ገሠጸና፦አንተ፡ዲዳ፡ደንቈሮም፡ መንፈስ፥እኔ፡አዝኻለኹ፥ከርሱ፡ውጣ፡እንግዲህም፡አትግባበት፡አለው። 26፤ጮኾም፡እጅግም፡አንፈራግጦት፡ወጣ፤ብዙዎችም፦ሞተ፡እስኪሉ፡ድረስ፡እንደ፡ሙት፡ኾነ። 27፤ኢየሱስ፡ግን፡እጁን፡ይዞ፡አስነሣው፡ቆመም። 28፤ወደ፡ቤትም፡ከገባ፡በዃላ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፦እኛ፡ልናወጣው፡ያልቻልን፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧ብለው፡ ብቻውን፡ጠየቁት። 29፤ይህ፡ወገን፡በጸሎትና፡በጦም፡ካልኾነ፡በምንም፡ሊወጣ፡አይችልም፡አላቸው። 30-31፤ከዚያም፡ወጥተው፡በገሊላ፡በኩል፡ዐለፉ፤ደቀ፡መዛሙርቱንም፡ያስተምር፡ስለ፡ነበር፡ማንም፡ያውቅ፡ ዘንድ፡አልወደደም፤ለእነርሱም፦የሰው፡ልጅ፡በሰዎች፡እጅ፡ዐልፎ፡ይሰጣል፥ይገድሉትማል፥ተገድሎም፡ በሦስተኛው፡ቀን፡ይነሣል፡ይላቸው፡ነበር። 32፤እነርሱም፡ነገሩን፡አላስተዋሉም፥እንዳይጠይቁትም፡ፈሩ። 33፤ወደ፡ቅፍርናሖምም፡መጣ።በቤትም፡ኾኖ፦በመንገድ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ምን፡ተነጋገራችኹ፧ብሎ፡ ጠየቃቸው። 34፤እነርሱ፡ግን፡በመንገድ፦ከዅሉ፡የሚበልጥ፡ማን፡ይኾን፧ተባብለው፡ነበርና፥ዝም፡አሉ። 35፤ተቀምጦም፡ዐሥራ፡ኹለቱን፡ጠርቶ፦ሰው፡ፊተኛ፡ሊኾን፡ቢወድ፡ከዅሉ፡በዃላ፡የዅሉም፡አገልጋይ፡ ይኹን፡አላቸው። 36፤ሕፃንም፡ይዞ፡በመካከላቸው፡አቆመው፡ዐቅፎም። 37፤እንደዚህ፡ካሉ፡ሕፃናት፡አንዱን፡በስሜ፡የሚቀበል፡ዅሉ፡እኔን፡ይቀበላል፤የሚቀበለኝም፡ዅሉ፡የላከኝን፡ እንጂ፡እኔን፡አይቀበልም፡አላቸው። 38፤ዮሐንስ፡መልሶ፦መምህር፡ሆይ፥አንድ፡ሰው፡በስምኽ፡አጋንንትን፡ሲያወጣ፡አየነው፥ 39፤ስለማይከተለንም፡ከለከልነው፡አለው።ኢየሱስ፡ግን፡አለ፦በስሜ፡ተኣምር፡ሠርቶ፡በቶሎ፡በእኔ፡ላይ፡ ክፉ፡መናገር፡የሚችል፡ማንም፡የለምና፡አትከልክሉት፤ 40፤የማይቃወመን፡ርሱ፡ከእኛ፡ጋራ፡ነውና። 41፤የክርስቶስ፡ስለ፡ኾናችኹ፡በስሜ፡ጽዋ፡ውሃ፡የሚያጠጣችኹ፡ዅሉ፥ዋጋው፡እንዳይጠፋበት፡እውነት፡ እላችዃለኹ። 42፤በእኔም፡ከሚያምኑት፡ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡አንዱን፡የሚያሰናክል፡ዅሉ፡ትልቅ፡የወፍጮ፡ድንጋይ፡ በዐንገቱ፡ታስሮ፡ወደ፡ባሕር፡ቢጣል፡ይሻለው፡ነበር። 43-44፤እጅኽ፡ብታሰናክልኽ፡ቍረጣት፤ኹለት፡እጅ፡ኖሮኽ፡ትላቸው፡ወደማይሞትበት፡እሳቱም፡ ወደማይጠፋበት፡ወደ፡ገሃነም፡ወደማይጠፋ፡እሳት፡ከመኼድ፡ጕንድሽ፡ኾነኽ፡ወደ፡ሕይወት፡መግባት፡ ይሻላል። 45-46፤እግርኽ፡ብታሰናክልኽ፡ቍረጣት፤ኹለት፡እግር፡ኖሮኽ፡ትላቸው፡ወደማይሞትበት፡እሳቱም፡ ወደማይጠፋበት፡ወደ፡ገሃነም፡ወደማይጠፋ፡እሳት፡ከመጣል፡ዐንካሳ፡ኾነኽ፡ወደ፡ሕይወት፡መግባት፡ ይሻልኻል። 47-48፤ዐይንኽ፡ብታሰናክልኽ፡አውጣት፤ኹለት፡ዐይን፡ኖሮኽ፡ትላቸው፡ወደማይሞትበት፡እሳቱም፡ ወደማይጠፋበት፡ወደ፡ገሃነመ፡እሳት፡ከመጣል፡አንዲት፡ዐይን፡ኖራኽ፡ወደእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ መግባት፡ይሻልኻል። 49፤ሰው፡ዅሉ፡በእሳት፡ይቀመማልና፥መሥዋዕትም፡ዅሉ፡በጨው፡ይቀመማል። 50፤ጨው፡መልካም፡ነው፤ጨው፡ግን፡ዐልጫ፡ቢኾን፡በምን፡ታጣፍጡታላችኹ፧በነፍሳችኹ፡ጨው፡ ይኑርባችኹ፥ርስ፡በርሳችኹም፡ተስማሙ። ምዕራፍ 1፤ከዚያም፡ተነሥቶ፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡ወደይሁዳ፡አገር፡መጣ፥ደግሞም፡ብዙ፡ሰዎች፡ወደ፡ርሱ፡ተሰበሰቡ፡ እንደ፡ልማዱም፡ደግሞ፡ያስተምራቸው፡ነበር። 2፤ፈሪሳውያንም፡ቀርበው፦ሰው፡ሚስቱን፡ሊፈታ፡ተፈቅዶለታልን፧ብለው፡ሊፈትኑት፡ጠየቁት። 3፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፦ሙሴ፡ምን፡አዘዛችኹ፧አላቸው። 4፤እነርሱም፦ሙሴስ፡የፍቿን፡ጽሕፈት፡ጽፎ፡እንዲፈታት፡ፈቀደ፡አሉ። 5፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦ስለልባችኹ፡ጥንካሬ፡ይህችን፡ትእዛዝ፡ጻፈላችኹ። 6፤ከፍጥረት፡መዠመሪያ፡ግን፡እግዚአብሔር፡ወንድና፡ሴት፡አደረጋቸው፤ 7፤ስለዚህ፥ሰው፡አባቱንና፡እናቱን፡ይተዋል፥ከሚስቱም፡ጋራ፡ይተባበራል፥ 8፤ኹለቱም፡አንድ፡ሥጋ፡ይኾናሉ፤ስለዚህ፥አንድ፡ሥጋ፡ናቸው፡እንጂ፡ወደ፡ፊት፡ኹለት፡አይደሉም። 9፤እግዚአብሔር፡ያጣመረውን፡እንግዲህ፡ሰው፡አይለየው። 10፤በቤትም፡ደግሞ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ስለዚህ፡ነገር፡ጠየቁት። 11፤ርሱም፦ሚስቱን፡ፈቶ፟፡ሌላ፡የሚያገባ፡ዅሉ፡በርሷ፡ላይ፡ያመነዝራል፤ 12፤ርሷም፡ባሏን፡ፈታ፟፡ሌላ፡ብታገባ፡ታመነዝራለች፡አላቸው። 13፤እንዲዳስሳቸውም፡ሕፃናትን፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ያመጧቸውን፡ገሠጿቸው። 14፤ኢየሱስ፡ግን፡አይቶ፡ተቈጣና፦ሕፃናትን፡ወደ፡እኔ፡ይመጡ፡ዘንድ፡ ተዉ፥አትከልክሏቸው፤የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡እንደነዚህ፡ላሉት፡ናትና። 15፤እውነት፡እላችዃለኹ፤የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡እንደ፡ሕፃን፡የማይቀበላት፡ዅሉ፡ከቶ፡አይገባባትም፡ አላቸው። 16፤ዐቀፋቸውም፡እጁንም፡ጭኖ፡ባረካቸው። 17፤ርሱም፡በመንገድ፡ሲወጣ፡አንድ፡ሰው፡ወደ፡ርሱ፡ሮጦ፡ተንበረከከለትና፦ቸር፡መምህር፡ሆይ፥የዘለዓለም፡ሕይወትን፡እወርስ፡ዘንድ፡ምን፡ላድርግ፧ብሎ፡ጠየቀው። 18፤ኢየሱስም፦ስለ፡ምን፡ቸር፡ትለኛለኽ፧ከአንዱ፡ከእግዚአብሔር፡በቀር፡ቸር፡ማንም፡የለም። 19፤ትእዛዛትን፡ታውቃለኽ፤አታመንዝር፥አትግደል፥አትስረቅ፥በሐሰት፡አትመስክር፥አታታል፟፥አባትኽንና፡ እናትኽን፡አክብር፡አለው። 20፤ርሱም፡መልሶ፦መምህር፡ሆይ፥ይህን፡ዅሉ፡ከሕፃንነቴ፡ዠምሬ፡ጠብቄያለኹ፡አለው። 21፤ኢየሱስም፡ወደ፡ርሱ፡ተመልክቶ፡ወደደውና፦አንድ፡ነገር፡ጐደለኽ፤ኺድ፥ያለኽን፡ዅሉ፡ሽጠኽ፡ ለድኻዎች፡ስጥ፥በሰማይም፡መዝገብ፡ታገኛለኽ፥መስቀሉንም፡ተሸክመኽ፡ና፥ተከተለኝ፡አለው። 22፤ነገር፡ግን፥ስለዚህ፡ነገር፡ፊቱ፡ጠቈረ፥ብዙ፡ንብረት፡ነበረውና፡እያዘነም፡ኼደ። 23፤ኢየሱስም፡ዘወር፡ብሎ፡አይቶ፡ደቀ፡መዛሙርቱን፦ገንዘብ፡ላላቸው፡ወደእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ መግባት፡እንዴት፡ጭንቅ፡ይኾናል፡አላቸው። 24፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡እነዚህን፡ቃሎች፡አደነቁ።ኢየሱስም፡ደግሞ፡መልሶ፦ልጆች፡ሆይ፥በገንዘብ፡ ለሚታመኑ፡ወደእግዚአብሔር፡መንግሥት፡መግባት፡እንዴት፡ጭንቅ፡ነው። 25፤ባለጠጋ፡ወደእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ከሚገባ፡ግመል፡በመርፌ፡ቀዳዳ፡ቢያልፍ፡ይቀላል፡አላቸው። 26፤እነርሱም፡ያለመጠን፡ተገረሙና፡ርስ፡በርሳቸው፦እንግዲያ፡ማን፡ሊድን፡ይችላል፧ተባባሉ። 27፤ኢየሱስም፡ተመለከታቸውና፦ይህ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡እንጂ፡በሰው፡ዘንድ፡ አይቻልም፤በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ዅሉ፡ይቻላልና፥አለ። 28፤ጴጥሮስም፦እንሆ፥እኛ፡ዅሉን፡ትተን፡ተከተልንኽ፡ይለው፡ዠመር። 29፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥ስለ፡እኔና፡ስለ፡ወንጌል፡ቤትን፡ወይም፡ ወንድሞችን፡ወይም፡እኅቶችን፡ወይም፡አባትን፡ወይም፡እናትን፡ወይም፡ሚስትን፡ወይም፡ልጆችን፡ወይም፡ ዕርሻን፡የተወ፥ 30፤አኹን፡በዚህ፡ዘመን፡ከስደት፡ጋራ፡ቤቶችን፡ወንድሞችንና፡እኅቶችንም፡እናቶችንም፡ልጆችንም፡ ዕርሻንም፡መቶ፡ዕጥፍ፥በሚመጣውም፡ዓለም፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡የማይቀበል፡ማንም፡የለም። 31፤ግን፡ብዙ፡ፊተኛዎች፡ዃለኛዎች፡ዃለኛዎችም፡ፊተኛዎች፡ይኾናሉ። 32፤ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ሊወጡ፡በመንገድ፡ነበሩ፥ኢየሱስም፡ይቀድማቸው፡ነበርና፥ተደነቁ፤የተከተሉትም፡ ይፈሩ፡ነበር።ደግሞም፡ዐሥራ፡ኹለቱን፡ወደ፡ርሱ፡አቅርቦ፡ይደርስበት፡ዘንድ፡ያለውን፡ይነግራቸው፡ዠመር። 33፤እንሆ፥ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እንወጣለን፥የሰው፡ልጅም፡ለካህናት፡አለቃዎችና፡ለጻፊዎች፡ዐልፎ፡ ይሰጣል፥የሞት፡ፍርድም፡ይፈርዱበታል፥ለአሕዛብም፡አሳልፈው፡ይሰጡታል፥ 34፤ይዘብቱበትማል፡ይተፉበትማል፡ይገርፉትማል፡ይገድሉትማል፥በሦስተኛውም፡ቀን፡ይነሣል፡አላቸው። 35፤የዘብዴዎስ፡ልጆች፡ያዕቆብና፡ዮሐንስም፡ወደ፡ርሱ፡ቀርበው፦መምህር፡ሆይ፥የምንለምንኽን፡ዅሉ፡ እንድታደርግልን፡እንወዳለን፡አሉት። 36፤ርሱም፦ምን፡ላደርግላችኹ፡ትወዳላችኹ፧አላቸው። 37፤እነርሱም፦በክብርኽ፡ጊዜ፡አንዳችን፡በቀኝ፡አንዳችንም፡በግራኽ፡መቀመጥን፡ስጠን፡አሉት። 38፤ኢየሱስ፡ግን፦የምትለምኑትን፡አታውቁም።እኔ፡የምጠጣውን፡ጽዋ፡ልትጠጡ፥እኔ፡የምጠመቀውንስ፡ ጥምቀት፡ልትጠመቁ፡ትችላላችኹን፧አላቸው። 39፤እነርሱም፦እንችላለን፡አሉት።ኢየሱስም፦እኔ፡የምጠጣውን፡ጽዋ፡ትጠጣላችኹ፥እኔ፡የምጠመቀውንም፡ ጥምቀት፡ትጠመቃላችኹ፤ 40፤በቀኝና፡በግራ፡መቀመጥ፡ግን፡ለተዘጋጀላቸው፡ነው፡እንጂ፡የምሰጥ፡እኔ፡አይደለኹም፡አላቸው። 41፤ዐሥሩም፡ሰምተው፡በያዕቆብና፡በዮሐንስ፡ይቈጡ፡ዠመር። 42፤ኢየሱስም፡ወደ፡ርሱ፡ጠርቶ፡እንዲህ፡አላቸው፦የአሕዛብ፡አለቃዎች፡ተብሎ፡የምታስቡት፡ እንዲገዟቸው፡ታላላቆቻቸውም፡በላያቸው፡እንዲሠለጥኑ፡ታውቃላችኹ። 43፤በእናንተስ፡እንዲህ፡አይደለም፤ነገር፡ግን፥ማንም፡ከእናንተ፡ታላቅ፡ሊኾን፡የሚወድ፡የእናንተ፡አገልጋይ፡ ይኹን፥ 44፤ከእናንተም፡ማንም፡ፊተኛ፡ሊኾን፡የሚወድ፡የዅሉ፡ባሪያ፡ይኹን፤ 45፤እንዲሁ፡የሰው፡ልጅም፡ሊያገለግልና፡ነፍሱን፡ለብዙዎች፡ቤዛ፡ሊሰጥ፡እንጂ፡እንዲያገለግሉት፡አልመጣም። 46፤ወደ፡ኢያሪኮም፡መጡ።ከደቀ፡መዛሙርቱና፡ከብዙ፡ሕዝብ፡ጋራ፡ከኢያሪኮ፡ሲወጣ፡የጤሜዎስ፡ልጅ፡ ዕውሩ፡በርጤሜዎስ፡እየለመነ፡በመንገድ፡ዳር፡ተቀምጦ፡ነበር። 47፤የናዝሬቱ፡ኢየሱስም፡እንደ፡ኾነ፡በሰማ፡ጊዜ፦የዳዊት፡ልጅ፡ኢየሱስ፡ሆይ፥ማረኝ፡እያለ፡ይጮኽ፡ ዠመር። 48፤ብዙዎችም፡ዝም፡እንዲል፡ገሠጹት፤ርሱ፡ግን፦የዳዊት፡ልጅ፡ሆይ፥ማረኝ፡እያለ፡አብዝቶ፡ጮኸ። 49፤ኢየሱስም፡ቆመና፦ጥሩት፡አለ።ዕውሩንም፦አይዞኽ፥ተነሣ፥ይጠራኻል፡ብለው፡ጠሩት። 50፤ርሱም፡እየዘለለ፡ተነሣና፡ልብሱን፡ጥሎ፡ወደ፡ኢየሱስ፡መጣ። 51፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ምን፡ላደርግልኽ፡ትወዳለኽ፧አለው።ዕውሩም፦መምህር፡ሆይ፥አይ፡ዘንድ፡ አለው። 52፤ኢየሱስም፦ኺድ፤እምነትኽ፡አድኖኻል፡አለው።ወዲያውም፡አየ፡በመንገድም፡ተከተለው። ምዕራፍ 1፤ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ከደብረ፡ዘይት፡አጠገብ፡ወዳሉቱ፡ወደ፡ቤተ፡ፋጌና፡ወደ፡ቢታንያ፡በቀረቡ፡ ጊዜ፥ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ኹለቱን፡ልኮ። 2፤በፊታችኹ፡ወዳለችው፡መንደር፡ኺዱ፥ወዲያውም፡ወደ፡ርሷ፡ገብታችኹ፡ከሰው፡ማንም፡ገና፡ ያልተቀመጠበት፡ውርንጫ፡ታስሮ፡ታገኛላችኹ፤ፈታ፟ችኹ፡አምጡልኝ። 3፤ማንም፦ስለ፡ምን፡እንዲህ፡ታደርጋላችኹ፧ቢላችኹ።ለጌታ፡ያስፈልገዋል፡በሉት፥ወዲያውም፡ደግሞ፡ ወደዚህ፡ይሰደዋል፡አላቸው። 4፤ኼዱም፡ውርንጫውንም፡በመንገድ፡መተላለፊያ፡በደጅ፡ውጭ፡ታስሮ፡አገኙት፥ፈቱትም፦ 5፤በዚያም፡ከቆሙት፡አንዳንዶቹ፦ውርንጫውን፡የምትፈቱት፡ምን፡ልታደርጉት፡ነው፡አሏቸው። 6፤እነርሱም፡ኢየሱስ፡እንዳዘዘ፡አሏቸው፤ተዉአቸውም፦ 7፤ውርንጫውንም፡ወደ፡ኢየሱስ፡አመጡት፥ልብሳቸውንም፡በላዩ፡ጣሉ፥ተቀመጠበትም። 8፤ብዙ፡ሰዎችም፡ልብሳቸውን፡በመንገድ፡ላይ፡አነጠፉ፥ሌላዎችም፡ከዛፍ፡ቅጠሎችን፡እየቈረጡ፡ያነጥፉ፡ ነበር። 9፤የሚቀድሙትም፡የሚከተሉትም፦ሆሣዕና፤በጌታ፡ስም፡የሚመጣ፡የተባረከ፡ነው፤ 10፤በጌታ፡ስም፡የምትመጣ፡የአባታችን፡የዳዊት፡መንግሥት፡የተባረከች፡ናት፤ሆሣዕና፡በአርያም፡እያሉ፡ ይጮኹ፡ነበር። 11፤ኢየሱስም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወደ፡መቅደስ፡ገባ፤ዘወር፡ብሎም፡ዅሉን፡ከተመለከተ፡በዃላ፥ጊዜው፡መሽቶ፡ስለ፡ነበር፥ከዐሥራ፡ኹለቱ፡ጋራ፡ወደ፡ቢታንያ፡ወጣ። 12፤በማግስቱም፡ከቢታንያ፡ሲወጡ፡ተራበ። 13፤ቅጠልም፡ያላት፡በለስ፡ከሩቅ፡አይቶ፡ምናልባት፡አንዳች፡ይገኝባት፡እንደ፡ኾነ፡ብሎ፡መጣ፥ነገር፡ ግን፥የበለስ፡ወራት፡አልነበረምና፡መጥቶ፡ከቅጠል፡በቀር፡ምንም፡አላገኘባትም። 14፤መልሶም፦ካኹን፡ዠምሮ፡ለዘለዓለም፡ማንም፡ከአንቺ፡ፍሬ፡አይብላ፡አላት።ደቀ፡መዛሙርቱም፡ሰሙ። 15፤ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡መጡ።ወደ፡መቅደስም፡ገብቶ፡በመቅደስ፡የሚሸጡትንና፡የሚገዙትን፡ያወጣ፡ ዠመር፥የገንዘብ፡ለዋጮችንም፡ገበታዎች፡የርግብ፡ሻጪዎችንም፡ወንበሮች፡ገለበጠ፤ 16፤ዕቃም፡ተሸክሞ፡ማንም፡በመቅደስ፡ሊያልፍ፡አልፈቀደም። 17፤አስተማራቸውም፦ቤቴ፡ለአሕዛብ፡ዅሉ፡የጸሎት፡ቤት፡ትባላለች፡ተብሎ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧እናንተ፡ ግን፡የወንበዴዎች፡ዋሻ፡አደረጋችዃት፡አላቸው። 18፤የካህናት፡አለቃዎችም፡ጻፊዎችም፡ሰምተው፥ሕዝቡ፡ዅሉ፡በትምህርቱ፡ይገረሙ፡ስለ፡ነበር፡ይፈሩት፡ነበርና፥እንዴት፡አድርገው፡እንዲያጠፉት፡ፈለጉ። 19፤ማታ፡ማታም፡ከከተማ፡ወደ፡ውጭ፡ይወጣ፡ነበር። 20፤ማለዳም፡ሲያልፉ፡በለሲቱን፡ከሥሯ፡ደርቃ፡አይዋት። 21፤ጴጥሮስም፡ትዝ፡ብሎት።መምህር፡ሆይ፥እንሆ፥የረገምኻት፡በለስ፡ደርቃለች፡አለው። 22፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦በእግዚአብሔር፡እመኑ። 23፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ማንም፡ያለው፡ነገር፡እንዲደረግለት፡ቢያምን፡በልቡ፡ሳይጠራጠር፥ይህን፡ ተራራ፦ተነቅለኽ፡ወደ፡ባሕር፡ተወርወር፡ቢል፡ይኾንለታል። 24፤ስለዚህ፥እላችዃለኹ፥የጸለያችኹትን፡የለመናችኹትንም፡ዅሉ፡እንዳገኛችኹት፡እመኑ፥ይኾንላችኹማል። 25፤ለጸሎትም፡በቆማችኹ፡ጊዜ፥በሰማያት፡ያለው፡አባታችኹ፡ደግሞ፡ኀጢአታችኹን፡ይቅር፡ እንዲላችኹ፥በማንም፡ላይ፡አንዳች፡ቢኖርባችኹ፡ይቅር፡በሉት። 26፤እናንተ፡ግን፡ይቅር፡ባትሉ፡በሰማያት፡ያለው፡አባታችኹም፡ኀጢአታችኹን፡ይቅር፡አይላችኹም። 27፤ደግሞም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ።ርሱም፡በመቅደስ፡ሲመላለስ፥የካህናት፡አለቃዎችና፡ጻፊዎች፡ ሽማግሌዎችም፡ወደ፡ርሱ፡መጥተው፦ 28፤እነዚህን፡በምን፡ሥልጣን፡ታደርጋለኽ፧ወይስ፡እነዚህን፡ለማድረግ፡ይህን፡ሥልጣን፡ማን፡ ሰጠኽ፧አሉት። 29፤ኢየሱስም፦እኔም፡አንዲት፡ነገር፡እጠይቃችዃለኹ፥እናንተም፡መልሱልኝ፥እኔም፡በምን፡ሥልጣን፡ እነዚህን፡እንዳደርግ፡እነግራችዃለኹ። 30፤የዮሐንስ፡ጥምቀት፡ከሰማይ፡ነበረችን፡ወይስ፡ከሰው፧መልሱልኝ፡አላቸው። 31፤ርስ፡በርሳቸውም፡ሲነጋገሩ፦ከሰማይ፡ነው፡ብንል፦እንግዲያውስ፡ስለ፡ምን፡ አላመናችኹበትም፧ይለናል፤ 32፤ነገር፡ግን፦ከሰው፡ነው፡እንበልን፧አሉ፤ዅሉ፡ዮሐንስን፡በእውነት፡እንደ፡ነቢይ፡ያዩት፡ ነበርና፥ሕዝቡን፡ፈሩ። 33፤ለኢየሱስም፡መልሰው፦አናውቅም፡አሉት፡ኢየሱስም፦እኔም፡በምን፡ሥልጣን፡እነዚህን፡እንዳደርግ፡ አልነግራችኹም፡አላቸው። ምዕራፍ 1፤በምሳሌም ይነግራቸው ጀመር። አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፥ ቅጥርም ቀጠረለት፥ መጥመቂያም ማሰለት፥ ግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። 2፤በጊዜውም ከወይን አትክልት ፍሬ ከገበሬዎቹ እንዲቀበል አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፤ 3፤ይዘውም ደበደቡት ባዶውንም ሰደዱት። 4፤ዳግመኛም ሌላውን ባሪያ ወደ እነርሱ ላከ እርሱንም ወግረው ራሱን አቈሰሉት አዋርደውም ሰደዱት። 5፤ሌላውንም ላከ፤ እርሱንም ገደሉት፥ ከሌሎችም ከብዙዎች አንዳንዱን ደበደቡ አንዳንዱንም ገደሉ። 6፤የሚወደው አንድ ልጅ ገና ነበረው፤ ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ እርሱን ከሁሉ በኋላ ወደ እነርሱ ላከ። 7፤እነዚያ ገበሬዎች ግን እርስ በርሳቸው፦ ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለው፥ ርስቱም ለኛ ይሆናል ተባባሉ። 8፤ይዘውም ገደሉት፥ ከወይኑም አትክልት ወደ ውጭ ጣሉት። 9፤እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋል? ይመጣል ገበሬዎቹንም ያጠፋል፥ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል። 10-11፤ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው። የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን? 12፤ምሳሌውንም ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አውቀዋልና ሊይዙት ፈለጉ፥ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። ትተውትም ሄዱ። 13፤በንግግርም ሊያጠምዱት ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑትን ወደ እርሱ ላኩ። 14፤መጥተውም፦ መምህር ሆይ፥ የሰውን ፊት ሳትመለከት በእውነት የእግዚአብሔር መንገድ ታስተምራለህና እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንምም እንዳታደላ እናውቃለን፤ ለቄሣር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? እንስጥን ወይስ አንስጥ? አሉት። 15፤እርሱ ግን ግብዝነታቸውን አውቆ፦ ለምን ትፈትኑኛላችሁ? አየው ዘንድ አንድ ዲናር አምጡልኝ አላቸው። 16፤እነርሱም አመጡለት። ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት? አላቸው፤ እነርሱም፦ የቄሣር ናት አሉት። 17፤ኢየሱስም መልሶ፦ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው። በእርሱም ተደነቁ። 18፤ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው ጠየቁት እንዲህም አሉት፦ 19፤መምህር ሆይ፥ ሙሴ፦ የአንድ ሰው ወንድም ሚስቱን ትቶ ልጅ ሳያስቀር ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ ብሎ ጻፈልን። 20፤ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፤ ፊተኛውም ሚስት አግብቶ ዘር ሳያስቀር ሞተ፤ 21፤ሁለተኛውም አገባት፥ ዘርም ሳይተው ሞተ፤ ሦስተኛውም እንዲሁ፤ 22ሰባቱም አገቡአት፥ ዘርም አላስቀሩም። ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ደግሞ ሞተች። 23፤ሰባቱ አግብተዋታልና በትንሣኤ ቀን ሲነሡ ከእነርሱ ለማናቸው ሚስት ትሆናለች? 24፤ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ስለዚህ የምትስቱ አይደለምን? 25፤ከሙታንስ ሲነሡ በሰማያት እንዳሉ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፥ አይጋቡምም። 26፤ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔር፦ እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን? 27፤የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም። እንግዲህ እጅግ ትስታላችሁ። 28፤ከጻፎችም አንዱ ቀርቦ ሲከራከሩ ሰማና መልካም አድርጎ እንደ መለሰላቸው አስተውሎ፦ ከሁሉ ፊተኛይቱ ትእዛዝ ማናቸይቱ ናት? ብሎ ጠየቀው። 29፤ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥ 30፤አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። 31፤ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም። 32፤ጻፊውም፦ መልካም ነው፥ መምህር ሆይ፤ አንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም ብለህ በእውነት ተናገርህ፤ 33፤በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው። 34፤ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ፦ አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም። 35፤ኢየሱስም በመቅደስ ሲያስተምር መልሶ እንዲህ አለ፦ ጻፎች ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ? 36፤ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ፦ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው አለ። 37፤ዳዊትም ራሱ ጌታ አለው፤ እንዴትስ ልጁ ይሆናል? ብዙ ሕዝብም በደስታ ይሰሙት ነበር። 38-39፤ሲያስተምርም እንዲህ አለ፦ ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤ 40፤የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ። 41፤ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበር፤ ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር፤ 42፤አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች። 43፤ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች፤ 44፤ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፥ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አላቸው። ምዕራፍ 1 እርሱም ከመቅደስ ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ መምህር ሆይ፥ እንዴት ያሉ ድንጋይዎችና እንዴት ያሉ ሕንጻዎች እንደ ሆኑ እይ አለው። 2 ኢየሱስም መልሶ፦ እነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህን? ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አለው።3 በመቅደስም ትይዩ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ጴጥሮስና ያዕቆብ ዮሐንስም እንድርያስም፦ 4 ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ለብቻቸው ጠየቁት። 5 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። 6 ብዙዎች፦ እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ። 7 ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው። 8 ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። 9 እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። 10 አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል። 11 ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። 12 ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤ 13 በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። 14 ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፥ 15 በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፥ 16 በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ። 17 በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። 18 ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤ 19 በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና። 20 ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ። 21 በዚያን ጊዜም ማንም፦ እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፥ ወይም፦ እነሆ፥ ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤ 22 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ። 23 እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ። 24 በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ 25 ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። 26 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። 27 በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል። 28 ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤ 29 እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ መሆኑን ስታዩ ቀርቦ በደጅ እንደ ሆነ እወቁ። 30 እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። 31 ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም። 32 ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም። 33 ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም። 34 ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፥ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ። 35 እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና 36 ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ። 37 ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ። ምዕራፍ 1 ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር። 2 የሕዝብ ሁከት እንዳይሆን በበዓል አይሁን ይሉ ነበርና። 3 እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው። 4 አንዳንዶችም፦ ይህ የሽቱ ጥፋት ለምንድር ነው? 5 ይህ ሽቱ ከሦስት መቶ ዲናር በሚበልጥ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና ብለው በራሳቸው ይቈጡ ነበር፤ እርስዋንም ነቀፉአት። 6 ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች። 7 ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፥ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም። 8 የተቻላትን አደረገች፤ አስቀድማ ለመቃብሬ ሥጋዬን ቀባችው። 9 እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለሙ ሁሉ በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራ፥ እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ ሊሆን ይነገራል። 10 ከአሥራ ሁለቱም አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ። 11 ሲሰሙም ደስ አላቸው ብርም ይሰጡት ዘንድ ተስፋ ሰጡት። በሚመች ጊዜም እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈልግ ነበር። 12 ፋሲካን በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ፦ ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ? አሉት። 13 ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ላከ እንዲህም አላቸው፦ ወደ ከተማ ሂዱ፥ ማድጋ ውኃ የተሸከመ ሰውም ይገናኛችኋል፤ 14 ተከተሉት፥ የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ፦ መምህሩ፦ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው? ይላል በሉት። 15 እርሱም በደርብ ላይ ያለውን የተሰናዳና የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፤ 16 በዚያም አሰናዱልን። ደቀ መዛሙርቱም ወጡ ወደ ከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙ፥ ፋሲካንም አሰናዱ። 17 በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ጋር መጣ። 18 ተቀምጠውም ሲበሉ ኢየሱስ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ፥ እርሱም ከእኔ ጋር የሚበላው አሳልፎ ይሰጠኛል አለ። 19 እነርሱም ያዝኑ፥ እያንዳንዳቸውም፦ እኔ እሆንን? ይሉት ጀመር። 20 እርሱም መልሶ፦ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ከእኔ ጋር ወደ ወጭቱ እጁን የሚያጠልቀው ነው። 21 የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር አላቸው። 22 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ሰጣቸውና፦ እንካችሁ፤ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። 23 ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፥ ሁሉም ከእርሱ ጠጡ። 24 እርሱም፦ ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው። 25 እውነት እላችኋለሁ፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ከወይኑ ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ደግሞ አልጠጣውም አላቸው። 26 መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ። 27 ኢየሱስም፦ በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ እረኛዉን እመታለሁ በጎችም ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና። 28 ነገር ግን ከተነሣሁ በኋላ ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው። 29 ጴጥሮስም፦ ሁሉም ቢሰናከሉ እኔ ግን ከቶ አልሰናከልም አለው። 30 ኢየሱስም፦ እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽሦስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው። 31 እርሱም ቃሉን አበርትቶ፦ ከአንተ ጋር የምሞት እንኳ ቢሆን ከቶ አልክድህም አለ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ። 32 ጌቴሴማኒ ወደምትባልም ስፍራ መጡ፥ ደቀ መዛሙርቱንም፦ ስጸልይ ሳለሁ፥ በዚህ ተቀመጡ አላቸው። 33 ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ሊደነግጥም ሊተክዝም ጀመረና። 34 ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቈዩ ትጉም አላቸው። 35 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በምድርም ወድቆ፥ ይቻልስ ቢሆን ሰዓቲቱ ከእርሱ እንድታልፍ ጸለየና፦ 36 አባ አባት ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ። 37 መጣም ተኝተውም አገኛቸው፥ ጴጥሮስንም፦ ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን? 38 ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ ጸልዩም፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች፥ ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው። 39 ደግሞም ሄዶ ያንኑ ቃል ጸለየ። 40 ደግሞም መጥቶ ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፥ የሚመልሱለትንም አላወቁም። 41 ሦስተኛም መጥቶ፦ እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፤ ይበቃል፤ ሰዓቲቱ ደረሰች፤ እነሆ፥ የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል። 42 ተነሡ፥ እንሂድ፤ እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል አላቸው። 43 ወዲያውም ገና ሲናገር ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፥ ከእርሱም ጋር ብዙ ሰዎች ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ከሽማግሌዎችም ዘንድ መጡ። በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል። 44 አሳልፎ የሚሰጠውም፦ የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር። 45 መጥቶም ወዲያው ወደ እርሱ ቀረበና፦ መምህር ሆይ፥ መምህር ሆይ፥ ብሎ ሳመው፤ 46 እነርሱም እጃቸውን በእርሱ ላይ ጭነው ያዙት። 47 በአጠገብ ከቆሙት ግን አንዱ ሰይፉን መዞ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መታ ጆሮውንም ቈረጠ። 48 ኢየሱስም መልሶ፦ ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን? 49 በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስኖር አልያዛችሁኝም፤ ነገር ግን መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ይህ ሆነ አላቸው። 50 ሁሉም ትተውት ሸሹ። 51 ዕርቃኑን በነጠላ የሸፈነ አንድ ጎበዝ ይከተለው ነበር፥ 52 ጎበዛዝቱም ያዙት፤ እርሱ ግን ነጠላውን ትቶ ዕራቁቱን ሸሸ። 53 ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወሰዱት፥ የካህናት አለቆችም ሁሉ ሽማግሌዎችም ጻፎችም ተሰበሰቡ። 54 ጴጥሮስም እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ በሩቁ ተከተለው፥ ከሎሌዎችም ጋር ተቀምጦ እሳት ይሞቅ ነበር። 55 የካህናት አለቆችም ሸንጎውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ ምስክር ይፈልጉ ነበር፥ አላገኙምም፤ 56 ብዙዎች በሐሰት ይመሰክሩበት ነበርና፥ ምስክርነታቸው ግን አልተሰማማም። 57-58 ሰዎችም ተነሥተው፦ እኔ ይህን በእጅ የተሠራውን ቤተ መቅደስ አፈርሰዋለሁ በሦስት ቀንም ሌላውን በእጅ ያልተሠራውን እሠራለሁ ሲል ሰማነው ብለው በሐሰት መሰከሩበት። 59 ምስክርነታቸውም እንዲሁ እንኳ አልተሰማማም። 60 ሊቀ ካህናቱም በመካከላቸው ተነሥቶ፦ አንዳች አትመልስምን? እነዚህስ በአንተ ላይ የሚመሰክሩብህ ምንድር ነው? ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው። 61 እርሱ ግን ዝም አለ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና፦ የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው። 62 ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ። 63 ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና፦ ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል? 64 ስድቡን ሰማችሁ፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እነርሱም ሁሉ፦ ሞት ይገባዋል ብለው ፈረዱበት። 65 አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትና፦ ትንቢት ተናገር ይሉት ጀመር፤ ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት። 66 ጴጥሮስም በግቢ ውስጥ ወደ ታች ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ገረዶች አንዲቱ መጣች፥ 67 ጴጥሮስም እሳት ሲሞቅ አይታ ተመለከተችውና፦ አንተ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበርህ አለችው። 68 እርሱ ግን፦ የምትዪውን አላውቅም አላስተውልምም ብሎ ካደ። ወደ ውጭም ወደ ደጅ ወጣ፤ ዶሮም ጮኸ። 69 ገረዲቱም አይታው በዚያ ለቆሙት፦ ይህም ከእነርሱ ወገን ነው ስትል ሁለተኛ ትነግራቸው ጀመር። 70 እርሱም ደግሞ ካደ። ጥቂት ቈይተውም በዚያ የቆሙት ዳግመኛ ጴጥሮስን፦ የገሊላ ሰው ነህና ከእነርሱ ወገን በእውነት ነህ አሉት። 71 እርሱ ግን፦ ይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም ብሎ ይረገምና ይምል ጀመር። ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ። 72 ጴጥሮስንም ኢየሱስ፦ ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው ቃል ትዝ አለው፤ ነገሩንም አስቦ አለቀሰ። ምዕራፍ 1፤ወዲያውም፡ማለዳ፡የካህናት፡አለቃዎች፡ከሽማግሌዎችና፡ከጻፊዎች፡ከሸንጎውም፡ዅሉ፡ጋራ፡ከተማከሩ፡ በዃላ፥ኢየሱስን፡አሳስረው፡ወሰዱትና፡ለጲላጦስ፡አሳልፈው፡ሰጡት። 2፤ጲላጦስም፦አንተ፡የአይሁድ፡ንጉሥ፡ነኽን፧ብሎ፡ጠየቀው።ርሱም፦አንተ፡አልኽ፡ብሎ፡መለሰለት። 3፤የካህናት፡አለቃዎችም፡ብዙ፡ያሳጡት፡ነበር፤ርሱ፡ግን፡ምንም፡አልመለሰም። 4፤ጲላጦስም፡ደግሞ፦አንዳች፡አትመልስምን፧እንሆ፥በስንት፡ነገር፡ያሳጡኻል፡ብሎ፡ጠየቀው። 5፤ኢየሱስም፡ከዚያ፡በዃላ፡ጲላጦስ፡እስኪደነቅ፡ድረስ፡ምንም፡አልመለሰም። 6፤በዚያም፡በዓል፡የለመኑትን፡አንድ፡እስረኛ፡ይፈታላቸው፡ነበር። 7፤በዐመፅም፡ነፍስ፡ከገደሉት፡ከዐመፀኛዎች፡ጋራ፡የታሰረ፡በርባን፡የተባለ፡ነበረ። 8፤ሕዝቡም፡ወጥተው፡እንደ፡ልማዱ፡ያደርግላቸው፡ዘንድ፡እየጮኹ፡ይለምኑት፡ዠመር። 9፤ጲላጦስም፦የአይሁድን፡ንጉሥ፡እፈታላችኹ፡ዘንድ፡ትወዳላችኹን፧ብሎ፡መለሰላቸው፤ 10፤የካህናት፡አለቃዎች፡በቅንአት፡አሳልፈው፡እንደ፡ሰጡት፡ያውቅ፡ነበርና። 11፤የካህናት፡አለቃዎች፡ግን፡በርባንን፡በርሱ፡ፈንታ፡ይፈታላቸው፡ዘንድ፡ሕዝቡን፡አወኳቸው። 12፤ጲላጦስም፡ዳግመኛ፡መልሶ፦እንግዲህ፡የአይሁድ፡ንጉሥ፡የምትሉትን፡ምን፡ላደርገው፡ትወዳላችኹ፧አላቸው። 13፤እነርሱም፡ዳግመኛ፦ስቀለው፡እያሉ፡ጮኹ። 14፤ጲላጦስም፦ምን፡ነው፧ያደረገው፡ክፋት፡ምንድር፡ነው፧አላቸው።እነርሱ፡ግን፦ስቀለው፡እያሉ፡ ጩኸት፡አበዙ። 15፤ጲላጦስም፡የሕዝቡን፡ፈቃድ፡ሊያደርግ፡ወዶ፡በርባንን፡ፈታላቸው፥ኢየሱስንም፡ገርፎ፡እንዲሰቀል፡ አሳልፎ፡ሰጠ። 16፤ወታደሮችም፡ፕራይቶሪዮን፡ወደሚባል፡ግቢ፡ውስጥ፡ወሰዱት፥ጭፍራውንም፡ዅሉ፡በአንድነት፡ጠሩ። 17፤ቀይ፡ልብስም፡አለበሱት፥የሾኽ፡አክሊልም፡ጐንጉነው፡ደፉበት፤ 18፤የአይሁድ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን፡እያሉ፡እጅ፡ይነሡት፡ዠመር፤ 19፤ራሱንም፡በመቃ፡መቱት፡ተፉበትም፥ተንበርክከውም፡ሰገዱለት። 20፤ከተዘባበቱበትም፡በዃላ፡ቀዩን፡ልብስ፡ገፈፉት፥ልብሱንም፡አለበሱት፥ሊሰቅሉትም፡ወሰዱት። 21፤አንድ፡መንገድ፡ዐላፊም፡የአሌክስንድሮስና፡የሩፎስ፡አባት፡ስምዖን፡የተባለ፡የቀሬና፡ሰው፡ከገጠር፡ ሲመጣ፡መስቀሉን፡ይሸከም፡ዘንድ፡አስገደዱት። 22፤ትርጓሜውም፡የራስ፡ቅል፡ስፍራ፡ወደሚኾን፡ጎልጎታ፡ወደተባለ፡ስፍራ፡ወሰዱት። 23፤ከርቤም፡የተቀላቀለበትን፡የወይን፡ጠጅ፡እንዲጠጣ፡ሰጡት፤ርሱ፡ግን፡አልተቀበለም። 24፤ሰቀሉትም፥ልብሱንም፡ማን፡ማን፡እንዲወስድ፡ዕጣ፡ተጣጥለው፡ተካፈሉ። 25፤በሰቀሉትም፡ጊዜ፡ሦስት፡ሰዓት፡ነበረ። 26፤የክሱ፡ጽሕፈትም፦የአይሁድ፡ንጉሥ፡የሚል፡ተጽፎ፡ነበር። 27፤ከርሱም፡ጋራ፡ኹለት፡ወንበዴዎች፡አንዱን፡በቀኙ፡አንዱንም፡በግራው፡ሰቀሉ። 28፤መጽሐፍም፦ከዐመፀኛዎች፡ጋራ፡ተቈጠረ፡ያለው፡ተፈጸመ። 29፤የሚያልፉትም፡ራሳቸውን፡እየነቀነቁ፡ይሰድቡት፡ነበርና፦ዋ፥ቤተ፡መቅደስን፡የምታፈርስ፡በሦስት፡ቀንም፡ የምትሠራ፥ 30፤ከመስቀል፡ወርደኽ፡ራስኽን፡አድን፡አሉ። 31፤እንዲሁም፡የካህናት፡አለቃዎች፡ደግሞ፡ከጻፊዎች፡ጋራ፡ርስ፡በርሳቸው፡እየተዘባበቱ፦ሌላዎችን፡ አዳነ፤ራሱን፡ሊያድን፡አይችልም፤ 32፤አይተን፡እናምን፡ዘንድ፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ክርስቶስ፡አኹን፡ከመስቀል፡ይውረድ፡አሉ።ከርሱም፡ጋራ፡ የተሰቀሉት፡ይነቅፉት፡ነበር። 33፤ስድስት፡ሰዓትም፡በኾነ፡ጊዜ፥እስከ፡ዘጠኝ፡ሰዓት፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ጨለማ፡ኾነ። 34፤በዘጠኝ፡ሰዓትም፡ኢየሱስ፦ኤሎሄ፥ኤሎሄ፥ላማ፡ሰበቅታኒ፧ብሎ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኸ፤ትርጓሜውም፡ አምላኬ፥አምላኬ፥ለምን፡ተውኸኝ፧ማለት፡ነው። 35፤በዚያም፡ከቆሙት፡ሰዎች፡ሰምተው፦እንሆ፥ኤልያስን፡ይጠራል፡አሉ። 36፤አንዱም፡ሮጦ፡ሖምጣጤ፡በሰፍነግ፡ሞላ፡በመቃም፡አድርጎ።ተዉ፤ኤልያስ፡ሊያወርደው፡ይመጣ፡እንደ፡ ኾነ፡እንይ፡እያለ፡አጠጣው። 37፤ኢየሱስም፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኸ፡ነፍሱንም፡ሰጠ። 38፤የቤተ፡መቅደስም፡መጋረጃ፡ከላይ፡እስከ፡ታች፡ከኹለት፡ተቀደደ። 39፤በዚያም፡በአንጻሩ፡የቆመ፡የመቶ፡አለቃ፡እንደዚህ፡ጮኾ፡ነፍሱን፡እንደ፡ሰጠ፡ባየ፡ጊዜ፦ይህ፡ሰው፡ በእውነት፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነበረ፡አለ። 40-41፤ሴቶችም፡ደግሞ፡በሩቅ፡ኾነው፡ይመለከቱ፡ነበር፤ከነርሱም፡በገሊላ፡ሳለ፡ይከተሉትና፡ያገለግሉት፡ የነበሩ፡መግደላዊት፡ማርያም፡የታናሹ፡ያዕቆብና፡የዮሳም፡እናት፡ማርያም፡ሰሎሜም፡ነበሩ፥ከርሱም፡ጋራ፡ ወደ፡ኢየሩሳሌም፡የወጡ፡ሌላዎች፡ብዙዎች፡ሴቶች፡ነበሩ። 42፤አኹንም፡በመሸ፡ጊዜ፡የሰንበት፡ዋዜማ፡የኾነ፡የማዘጋጀት፡ቀን፡ስለ፡ነበረ፥የከበረ፡አማካሪ፡የኾነ፡ የአርማትያስ፡ዮሴፍ፡መጣ፥ 43፤ርሱም፡ደግሞ፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ይጠባበቅ፡ነበር፤ደፍሮም፡ወደ፡ጲላጦስ፡ገባና፡የኢየሱስን፡ ሥጋ፡ለመነው። 44፤ጲላጦስም፡አኹኑን፡እንዴት፡ሞተ፡ብሎ፡ተደነቀ፥የመቶ፡አለቃውንም፡ጠርቶ፡ከሞተ፡ቈይቷልን፧ብሎ፡ ጠየቀው፤ 45፤ከመቶ፡አለቃውም፡ተረድቶ፡በድኑን፡ለዮሴፍ፡ሰጠው። 46፤በፍታም፡ገዝቶ፡አውርዶም፡በበፍታ፡ከፈነው፡ከአለትም፡በተወቀረ፡መቃብር፡አኖረው፥በመቃብሩ፡ ደጃፍም፡ድንጋይ፡አንከባለለ። 47፤መግደላዊትም፡ማርያም፡የዮሳም፡እናት፡ማርያም፡ወዴት፡እንዳኖሩት፡ይመለከቱ፡ነበር። ምዕራፍ 1፤ሰንበትም፡ካለፈ፡በዃላ፡መግደላዊት፡ማርያም፡የያዕቆብም፡እናት፡ማርያም፡ሰሎሜም፡መጥተው፡ሊቀቡት፡ ሽቱ፡ገዙ። 2፤ከሳምንቱም፡በፊተኛው፡ቀን፡እጅግ፡በማለዳ፡ፀሓይ፡ከወጣ፡በዃላ፡ወደ፡መቃብር፡መጡ። 3፤ርስ፡በርሳቸውም፦ድንጋዩን፡ከመቃብር፡ደጃፍ፡ማን፡ያንከባልልልናል፧ይባባሉ፡ነበር፤ 4፤ድንጋዩ፡እጅግ፡ትልቅ፡ነበርና፤አሻቅበውም፡አይተው፡ድንጋዩ፡ተንከባሎ፡እንደ፡ነበር፡ተመለከቱ።5፤ወደ፡መቃብሩም፡ገብተው፡ነጭ፡ልብስ፡የተጐናጸፈ፡ጕልማሳ፡በቀኝ፡በኩል፡ተቀምጦ፡አዩና፡ደነገጡ። 6፤ርሱ፡ግን፦አትደንግጡ፤የተሰቀለውን፡የናዝሬቱን፡ኢየሱስን፡ትፈልጋላችኹ፤ተነሥቷል፥በዚህ፡ የለም፤እንሆ፥ርሱን፡ያኖሩበት፡ስፍራ። 7፤ነገር፡ግን፥ኼዳችኹ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ለጴጥሮስም፦ወደ፡ገሊላ፡ይቀድማችዃል፤እንደ፡ነገራችኹ፡ በዚያ፡ታዩታላችኹ፡ብላችኹ፡ንገሯቸው፡አላቸው። 8፤መንቀጥቀጥና፡መደንገጥ፡ይዟቸው፡ነበርና፥ወጥተው፡ከመቃብር፡ሸሹ፤ይፈሩ፡ነበርና፥ለማንም፡አንዳች፡ አልነገሩም።እነርሱም፡ያዘዛቸውን፡ዅሉ፡ለጴጥሮስና፡ከርሱ፡ጋራ፡ላሉት፡በዐጪሩ፡ተናገሩ።ከዚህም፡በዃላ፡ ኢየሱስ፡ራሱ፡ለዘለዓለም፡ድኅነት፡የኾነውን፡የማይለወጠውን፡ቅዱስ፡ወንጌል፡ከፀሓይ፡መውጫ፡እስከ፡ መጥለቂያው፡ድረስ፡በእጃቸው፡ላከው። 9፤ከሳምንቱም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ማልዶ፡በተነሣ፡ጊዜ፥አስቀድሞ፡ሰባት፡አጋንንት፡ላወጣላት፡ ለመግደላዊት፡ማርያም፡ታየ። 10፤ርሷ፡ኼዳ፡ከርሱ፡ጋራ፡ኾነው፡ለነበሩት፡ሲያዝኑና፡ሲያለቅሱ፡ሳሉ፡አወራችላቸው፤ 11፤እነርሱም፡ሕያው፡እንደ፡ኾነ፡ለርሷም፡እንደ፡ታያት፡ሲሰሙ፡አላመኑም። 12፤ከዚህም፡በዃላ፡ከነርሱ፡ለኹለቱ፡ወደ፡ባላገር፡ሲኼዱ፡በመንገድ፡በሌላ፡መልክ፡ተገለጠ፤ 13፤እነርሱም፡ኼደው፡ለሌላዎቹ፡አወሩ፤እነዚያንም፡ደግሞ፡አላመኗቸውም። 14፤ዃላም፡በማእዱ፡ተቀምጠው፡ሳሉ፡ለዐሥራ፡አንዱ፡ተገለጠ፥ተነሥቶም፡ያዩትን፡ስላላመኗቸው፡ አለማመናቸውንና፡የልባቸውን፡ጥንካሬ፡ነቀፈ። 15፤እንዲህም፡አላቸው፦ወደ፡ዓለም፡ዅሉ፡ኺዱ፥ወንጌልንም፡ለፍጥረት፡ዅሉ፡ስበኩ። 16፤ያመነ፡የተጠመቀም፡ይድናል፥ያላመነ፡ግን፡ይፈረድበታል። 17፤ያመኑትንም፡እነዚህ፡ምልክቶች፡ይከተሏቸዋል፤በስሜ፡አጋንንትን፡ያወጣሉ፤በዐዲስ፡ቋንቋ፡ ይናገራሉ፤እባቦችን፡ይይዛሉ፥ 18፤የሚገድልም፡ነገር፡ቢጠጡ፡አይጐዳቸውም፤እጃቸውን፡በድውዮች፡ላይ፡ይጭናሉ፡እነርሱም፡ይድናሉ። 19፤ጌታ፡ኢየሱስም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ከተናገረ፡በዃላ፡ወደ፡ሰማይ፡ዐረገ፡በእግዚአብሔርም፡ ቀኝ፡ተቀመጠ። 20፤እነርሱም፡ወጥተው፡በየስፍራው፡ዅሉ፡ሰበኩ፥ጌታም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ይሠራ፡ነበር፥በሚከተሉትም፡ ምልክቶች፡ቃሉን፡ያጸና፡ነበር፨ መጽሐፍ
48333
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%80%E1%88%AB%E1%8A%95%E1%8B%AE%20%E1%88%98%E1%8B%B5%E1%8A%85%E1%8A%94%20%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9D
ቀራንዮ መድኅኔ ዓለም
ደብረ ቀራንዮ መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ደብሩ ለመጀመርያ ጊዜ የተመሠረተው በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ በ1826 ዓም ሲሆን ከአዲስ አበባ ቤተክርስቲያኖች በዕድሜ ትልቁ ነው። አሁን ያለውን ቤተክርስቲያን ያሠሩት ደግሞ አፄ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ናቸው።የደብረ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ዳግማዊ ቀራንዮ ዘኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አንዱና ቀዳሚው የሆነው ይህ ደብር የተመሰረተው በ1826 ዓ/ም በንጉስ ሳህለስላሴ ሲሆነ አመሰራረቱም ንጉስ ሳህለ ስላሴ በሸዋ ግዛታቸው ውስጥ እየተዘዋወሩ አንድነትን ለማስተማር ባላቸው ጽኑ ዓላማ መሰረት ሰራዊታቸውን አስከትለው 1826 ዓ/ም ወደ ደቡብ ተጒዋዙ በዚህ ጉዙአቸው በወሊሶ በኩል አልፈው የጉራጌን ህዝብ ሀገር አስተማሩ ጉዞአቸውንም በማራዘም በአርሲ አካባቢ የሰሜኑን ክልል እነዲማር አድርገው በግራኝ ምክንያት ተለያይቶ የነበረውን ህዝብና ክልል አንድ ካደረጉ በኋላ ከጉዞአቸው ሲመለሱ ዛሬ ቀራንዮ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያነ ከተመሰረተበት ቦታ ደርሰው ጥቂት ዕረፍት ቆይታ አደረጉ፡፡ በዚህም ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ አመልክቷቸው በዚህ ቦታ እግዚአብሔር እንዲመለክበት በቦታውም ፅላተ መድኃኔዓለም ከእቲሳ መጥቶ በመረጡበት ቦታ እንዲተከል ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ ታቦቱ በንጉሱ ትዕዛዝ መጥቶ በመረጡት በተዘጋጀለት መቃኞ ውስጥ ቢያርፍም ቦታው ደን ለበስ ስለነበረና ብዙ ኢአማንያን እንዲሁም ሽፍቶች ስለነበሩ መቃኞ ከአንድም ሶስት ጊዜ ሊቃጠል ችሎአል ሆኖም የንጉሱ አላማ ዕውቀትን ማበልጸግ ቤተክርስትያንን ማነጽ ስለነበር የሽፍቶቹን ኃይል በእግዚአብሔር አጋዥነት አሸንፈዋቸዋል ቤተክርስትያኑንም አጠገቡ ከሚገኘው አቃቂ ወንዝ ጋር በማጣመር አቃቂ መድኃዓለም ተብሎ ይጠራም ነበር የመድኃነኔዓለም ጽላት አመጣጥ በሚወሳበት ወቅት መምህር ተክለወልድና አባ ደጀን ተጠቃሽ ናቸው መምህር ተክለወልድ ከእቲሳ አምጥተው በዚህ ቦታበተሰራውመቃኞ ውስጥ እንዳስቀመጡት በአገልግሎታቸውም ወቅት ከባድ ፈተና እንዳጋጠማቸው ይነገራል በሌላ በኩል ደግሞ በሁለተኝነነት የጠቀስናቸው አባደጀን እንዳመጡት ይነገራል፡፡ከንጉስ ሳህለ ስላሴ ትዕዛዝ ተቀብለው ጽላቱም ከእቲሳ አስይዘውየላኳቸው አባ ዘወልደማርያም የተባሉ አባት እንደነበሩ ይታወሳል አባ ዘወልደማርያም በዚህም ቦታ ቦታ ሀገር በቀል እጽዋትን ተክለዋል አባ ደጀንም ከጽላቱ ጋር ድርሳነ ማህየዊ የተባለ በዚህቤተክርስትያን ብቻ የሚገኝ መጽሀፍ አምጥተዋል ደብሩ በዚህ አይነት ሁኔታ ከቀጠለ በኋላ 1899 ዓ/ም አጼ ምንሊክ ባወጁት አዋጅ የአብያተ ክርስትያናያ ምስረታና ዕደሳ መሰረት ቤተክርስትያኑ በሶስት አመት ውስጥ ተጠናቆ 1901 አጼው ባሰሩት አዲስ የሳር ክዳን ትልቅ ቤተክርስትያን ውስጥ ሊገባ ችሏል አጼ ምንሊክም በዚያው ዓመት በጃን ሜዳ መኳንንቱንና መሳፍንቱ ህዝቡ በተሰበሰበበት አቃቂ መድኃኔዓለም እንዳይባል እንዲህም ብሎ የጠራ ይቀጣል ከአሁን በኋላ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ይባል እንጅ ብለው በአዋጅ ተናግረው አጸደቁ ቀራንዮ የሚለው ስያሜ ምንም እንኳን ለቤተመቅደሱ የተሰጠው ስያሜ ቢሆንም ለክልሉ ለአካባቢው እስከ አሁን ድረስ መጠሪያ በመሆን ያገለግላል፡፡ አፄ ምንሊክም ጌታችን ከተሰቀለበት ከኢየሩሳሌም ቀራንዮ አፈር በማስመጣት በግቢው ውስጥ ካስፈሰሱ ብኋላ ዳግማዊ ቀራንዮ ብለው መሰየማቸውን ታሪክ ይናገራል አዲሱን የሳር ክዳን ቤተክርስትያን ከንጉሱ ትዕዛዝ ተቀብለው ከነሰራተኞቻቸው ያሰሩት ኋላም የደብሩ የመጀመሪያ ገበዝ በመሆን ደብሩም ለብዙ አመታት የመሩት ደጃዝማች ወልደገብርኤል ነበሩ ደጃዝማች ወልደገብርኤል የቤተመንግሰቱንና የቤተክርስትያኑን ስራ በትጋት በመስራት ለቤተክርስትያኑ ታላቅ ሰው ነበሩ ኋላም ደጃዝማች ወልደገብርኤል የቤተመንግስቱ ስራ ፋታስላልሰጣቸው የደብሩን ቅርስና ሀብት ለህይወታቸው ሳይሳሱ ለጠበቁት ለቄሰገበዝ አስራት ሀብተሚካኤል አስረከቧቸው 1901 የተሰራው አዲሱ ቤተመቅደስ የምዕመናን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዛበ መምጣቱ የተነሳና ለአገልግሎት አይመችም ነበር ይህንንም የተመለከቱት ንግስት ዘውዲቱ ሌላ ዘመናዊና ሰፊ ቤተክርስትያን ለማሰራት ያቅዳሉ ነገር ግን ሀሳባቸውን እውን ሳያደርጉ 1922 ዓ/ም ያርፋሉ ከዚህም በኋላ 1922 በዚያው ዓመት በግርማዊ ጃንሆይ እንደነገሱ የንግስት ዘውዲቱ ዕቅድና አላማ የነበረውና ታላቁን ቤተመቅደስ አሰሩ የቤተመቅደሱም ስራ 1922 ተጃምሮ 1925 በግርማዊ ጃንሆይ በነገሱ በሶስተኛ ዘመነ መንግስታቸው ተጠናቀቀ በዚሁ ዓመትም በታላቅ ድምቀት በአዲሱ ቤተክርስትያን በደመቀ ሁኔታ ተከበረ አሁን የሚገኘው ቤተክርስትያነ ግንባታው ተሰርቶ እስኪያልቅ ድረስ ደጃዝማች ወልደገብርኤል ለአፅማቸው ማረፊያ ባሰሩት ባለአንድ ፎቅ የቆርቆሮ ክዳን ቤት ውስጥ ነበር በዚህም ፅላቱ ሳለ ቅዳሴው በፎቁ ማህሌቱ በታች ይስተናገድ ነበር፡፡ አሁን የሚገኘው ህንጻ ቤተክርስትያን ምን ያህል ገንዘብ እንደፈጀ የሚገልጽ ሰነድ የለም ነገር ግን በግርማዊ ጃንሆይ በግል ገንዘባቸው እንዳሰሩት ታሪክ ይናገራል ህንጻውን የሰሩት ሁለት የጣልያን ዜግነት የነበራቸው በዚያም ዘመን በህንጻ ስራ ታዋቂ በነበሩት ሙሴ ፓፓጀማና ኩኞስ ነበሩ በደብሩም ብዙ የተለያዩ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን በአሁኑም ሰዓት ከ350 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ እጽዋት ሲገኙ ከዚህም በተጨማሪም ደብሩ ከተለያዩ ነገስታት የተሰጡትና በአንዳንድ አባቶች የተሰጡት ጥንታዊ የብርሃና መጽሃፍት አልባሳት የተለያዩ ውድ የወርቅ የብር የነሀስ መስቀሎች ጥላዎች በንግስት ቪክቶርያ ለሳህለ ስላሴ የተሰጡ የተለያዩ ውድ ስጦታዎችና የባላብዙ ታሪከና ቅርስ ባለቤት ደብር ነው ደብረ ቀራንዮ በአጥቢያው ለሚገኙ ደብራትና አብያተክርስትያናት ብሎም ለአዲስ አበባ ከተማ መመስረት መነሻም ነው፡፡ የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት አዲስ
22330
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%8E%E1%8D%8B
ጎፋ
ቋንቋ የጌዞ ብሔረሰብ ቋንቋ ‹ጌዞኛ› ሲሆን፣ ቋንቋው ከማዕከላዊ ኦማዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ይመደባል። ሕዝብ ቁጥር በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት የብሔረሰቡ ሕዝብ ብዛት 363ሺ9 ነው፡፡ መልክዓ ምድር ታሪክ የዑባ ካቲ (ንጉሥ) ግዛት የዑባ አካባቢ ነፃ የተደራጀ ባህላዊ የፖለቲካ አስተዳደር የተፈጠረው ከአሪ ግዛት ተነጥሎ ዑባ ነፃ አስተዳደር ግዛት ከሆነበት ዘመን ወዲህ ነበር የዑባ ጥንታዊ ግዛት በሰሜን ዜንቲ ወንዝ በደቡብ ምስራቅ የማዜ ወንዝ ይዞ እስከ ዛላና ዑባ መካከል ያለው ሸለቆ አልፎ ዘቃ ዛልቶ እና ጋላዳ ቀበለያትን ያካትታል በደቡብ ማሌ ወረዳ በደቡብ ምዕራብ የአሪ ግዛት: በምዕራብ ሙሉ በሙሉ በአሪ ግዛት ይዋስናል ።የካቲው (የንጉሱ) አስተዳደር ሥርዓት ለብቻ የተዘረጋው ከአሪ ማዕከል የመጣው ንጉስ ሾዴ ከነገሰበት ጊዜ ጀምሮ ሲሆን ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን አካባቢ ይገዛ የነበረው የዚህ ትውልድ ነበር መጀመሪያ ከአሪ ወደ ዑባ አካባቢ የመጣው ሰው የተቀመጠው በዑባ ተራራማ አካባቢ አምፖ በሚል ስም በሚታወቅበት ቦታ ነበር ከዚህ በመነሳት የጎሳው ዝሪያዎች ቀስ በቀስ ግዛት አስፋፍተው ሊቆጣጠሩ እንደቻሉ ይገለፃል በአካባቢው የካቲ አስተዳደር ከተመሠረተ በኋላ ሰሜናዊ የግዛት ክፍል ማለትም መላና አካባቢውን ጋልጣና አካባቢውን በመልቀቅ ወደ ደቡብ ምሥራቅ በማስፋፋት ጥንት የባዮ ግዛት የነበረውን ዙዛና አካባቢውን ጋላዳና አካባቢውን ያዘ በሰሜናዊ ግዛት የጎፋ እና የዛላ ካቲ አይለው በነበሩ ጊዜ ዑባን በኃይል አስለቅቀው ወደ ደቡብ እንድዞር አደረገዋል ይባላል የጎፋ እና የዛላ ካቲታይ(ንጉሶች) ፍላጎት ከፍ እያለ በመጣበት ወቅት የዑባ ካቲ ላይ በጦርነት እነዚህን ቀበሌያትንና አካባቢውን በኃይል አስለቅቀው እንደያዘ ይነገራል ወደ ዑባ ተሻግረው ከነገሰው ነጥቀው በትውልድ ሀረግ ቆጠራ መሠረት የሚቀጥሉ ካቲዎች በዑባ ነግሰዋል:: 1. ጋልታይዛ 8. አይሳ 2. ሾጴ 9. ታንጋ 3. ፖሻ 10. ሉፀ 4. ቱጫ 11. ኦፈ 5. ቶልባ 12. ኩንሳ 6. ቦላ 13. ዲቻ ናቸው 7. ካንሳ ነበሩ እነዚህ ነገስታት ዑባን ከዳር እስከ ዳር ያስተዳደሩ የነበሩት አከባቢው ወደ ማዕከላዊ መንግስት አስተደደር ሥር እስከሚሆን ድረስ ነበር ዑባን ከገዙት ካቲዎች ውስጥ ድንበር ከማስከበር አልፎ ጦርነቶችን አካሄዶ የተወሰኑ ግዛት ክፍሎችን በኃይል እንደያዘ የሚነገረው ካቲ ቦላ ነበር ካቲ ቦላ በጣም ጦረኛ ስለነበረ ህዝብን አሰልፎ ከጎፋ እና ከዛላ ጋር በሚዋስኑ አካባቢዎች ድንበሮችን ለማካለል የበቃ ካቲ ነበር ከአሪ ግዛት ጋር ያለውን ውስጣዊ የዝምድና ትስስር በመበጠስ ወደ ጦርነት ገብቶ ድንበሩ እንድካለል ያደረገው እሱ እንደነበረ ይነገራል የዑባ ካቲ አስተዳደር ሥርዓት የጀመረው ከዑባ ዣላ ከፍ ብሎ በሚገኘው አምፖ በሚባለው ቦታ ነው እዚሁ መጀመሪያ መጥቶ የነገሰው ካቲው ሾዴ ሲሆን ሶስት የአምልኮ የአስተዳደር ማዕከል እና የመኖሪያ ቦታዎችን በማበጀት ማስተዳደር ጀመረ በዚሁ መሠረት ዶጃ የነጋሲያን የአምልኮ ሥፍራ እና አምፖ የአስተዳደር ማዕከል ካምባ የመኖሪያ ቦታ አድርጎ በዚሁ ተራራ ላይ አዘጋጀ ከዚያን በኋላ ጥንታዊ የዑባ ግዛት ተብሎ የሚታወቀውን አካባቢ ይገዙ የነበሩ ካቲዎች ዋና መኖሪያቸውና የአስተዳደር ማዕከላቸውን እዚሁ አድርገዋል። ሆኖም ከኋላ አስተዳዳሩ እየተጠናከረ ሲሄድ ዣላ ቡኔ ጋልፃ እና በሌሎች ቦታዎች መቀመጫቻውን ያደረጉት የበታች ተሿሚዎችን ተጠርነቱን ለካቲው ሆኖ ሲያስተዳድሩ ቆይቷል ከላይ በተጠቀሱት የአስተዳደር አካበቢዎች ኃላፊነት ይዘው ያስተዳደሩት የነበሩ ማይጫ ዳና የሚል ማዕረግ ስም የያዙት ነበሩ በዚህ አቅጣጫ ካቲዎች ህዝብንና መሬትን በበላይነት ይመሩ እንደነበሩ የዕድሜ ባለፀጎች መረጃዎች ያስረዳሉ ሌላው ደግሞ ማይጫ ዳና ሥር የአስተዳደር ሥራዎችን ከመሥራት አኳያ ትልቅ አስተዋፆኦ እንደነበራቸው የሚነገርላቸው የሚባሉ ሳጋ እንደ ቃልቻ ያሉ ረግመውና መርቀው የሚያደርሱ ይገኙ ነበር ሥራቸውንም ሊያከናወኑ ህዝብ የከበረታ ሥፍራ ይሰጣቸው ነበር ሌሎች ደግሞ በህዝብ ውስጥ የሚሠሩ ባህላዊ አምልኮ አስፈፃሚዎች ብታንቴ የሚባሉት በየቀበሌያት ይገኙ ነበር በነፃ ግዛት ይኖር የነበረው ህዝብ በአዋሳኝ ከሚገኘው ህዝብ ጋር ተቀላቅሎ በጎሳ ሥርጭት በባህል አንድ ሆኖ ኖረዋል ይሁንና የካቲ አስተዳደር እየተጠናከረ በሄደበት ወቅት ከጎፋም ከዛላና ከሌሎች ደቡባዊ አቅጣጫ ከሚገኙት ጋር ጦርነቶችን አካሂደዋል ከዛላ ካቲ ግዛት ጋር መሀላ ፈጽመው የውል ስምምነቱን ጨርሰው የኖሩት ዑባ ዙማ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በተደረገው እርቅና ስምምነት ነበር በጎ ፋ ካቲ ካንሳና በዑባ ካቲ አይሳ መካከል ከፍተኛ ጦርነት በተካሄደበት ጊዜ በዑባ ጋይላ ላይ በተደረገው ውጊያ የመራውን ካቲ ካንሳን ወግቶ ካቆሰለ በኋላ እንደሞተ ይነገራል፡፡ በዚያን ዘመን በነዚህ አካባቢዎች ጦርነቶች ሲከፈቱ አንዱ ከሌላው ወገን ጋር ለማስታረቅ ጥረት የሚያደርጉት ራሳቸው ካቲዎች ነበሩ፡፡ ይህንን ሚና ካቲዎች የሚጫወቱት የሠላም ምልክት አድርገው በሚወስዱት የመልዕክት ልውውጥ ነበር፡፡ ይኽውም ቀድሞ ሰላም ፈላጊ ካቲው የራሱን መርኩዝ ለሌላኛው ካቲ በመላክና የዚያኛውንምርኩዝ የላከው መልዕክተኛ ይዞ ሲመጣ ነበር፡፡ ይህንን መጀመሪያ በመስጠትና ምላሽ የማግኘት ሥርዓት በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ሁኔታ ሁለቱም ወገኖች ወደ እርቅ ድርድር ይገቡ ነበር፡፡ ካቲዎች ትልቅ አክብሮት ከህዝብ የሚሰጣቸው ሲሆን ሥልጣናቸውም ከመለኮታው ኃይል እንደሆነ አድርገው ይወስዱ ነበር፡፡ ስለዝህም ካቲው በዑባ በጣም ይከበራል፤ ህዝቡም ይታዘዝለት ነበር፡፡ የአነጋገስ ሥነ-ሥርዓትም በተመለከተ ለአጎራባች ካቲዎች እንደሚደረግላቸው ዓይነት ነው፡፡ ይኸውም ለካቲዎች የሚደረግ ክብር መለክያ ዕቃዎች ተመሳሳይነት እና ካቲው ሲሞት የሚተካው የካቲው ታላቅ ልጅ መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ሳጋ የሚባሉት ከሌሎች አንጋሾች ጋር በመሆን ካቲው በሚነግስበት ወቀት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱት ክፍል እንደሆነ ይነገራል፡፡በዑባ የካቲ አስተዳደር መጀመር ተከትሎ በአጎራባች ከሚገኙት ካቲ ግዛቶች ጋር ያለው ግንኙት መልክ እየያዘ መጥቷል፡፡ቀደም ሲል በአከባቢው እንደነበሩ የሚነገሩ ጎሳው ተቋዋሚዎች ፈርሰው የአሪ ግዛት እየተጠናከረ እንደመጣ ብዛት ያላቸው ማህበረሰቦች በየቦታው በአይካ መንግሰት ሥር ሆነው ሲተዳደሩ ቆይቷል ብሔረሰብ በጋሞጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ብሔረሰቡ በዋናነነት በጎፋ ዙሪያ፣ ዛላ፣ ዑባ፣ ደብረፀሐይ እና መሎካዛ በሚባሉ ወረዳዎች ይገኛል፡፡ የብሔረሰቡ ዋና የሀብት መሠረት ጥምር ግብርና ሲሆን፤ የገቢ ምንጭ በሚያስገኙ ምርቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የጎፋ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ ነባር ባህላዊ አስተዳደር አለው፡፡ ጥንት በጎፋ ግዛት ክልል ሥር የነበሩ አካባቢዎች በሰባት የካዎ (ነጉሥ) ግዛቶች ተከፋፍለው የተደራደሩ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ከአዎ የአስተዳደር ማዕከል ቤተ-መንግሥት(ጋዶ) ነበረው፡፡ ማዕከላዊ አስተዳደሩ የተለየ ሥልጣንና የሥራ ድርሻ ያላቸውን አስፈፃሚ አካላትን የያዘ ነበር፡፡ ካዎ (ንጉሥ)- የባህላዊ አስተዳደሩ ቁንጮና ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሲሆን፤ ከእርሱ ቀጥሎ የሚገኙትን የሥልጣን አካላትንና አማካሪዎችን የመሾምና የመሻር ሥልጣን ነበረው። ጠንከር ያለ ውሳኔን የሚሹ ጉዳዮች የመጨረሻ ብይን የሚያገኙትም በካዎ ነበር፡፡ ብሔረሰቡ ጋብቻ የሚፈጸመው የጎሣ አቻነትን፣ የሀብት ደረጃ በማስተያየትና የሥጋ ዝምድና አለመኖርን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ወንዶች ከ17-25፤ ሴቶች ደግሞ ከ14-19 ባለው የዕድሜ ክልል ጋብቻ ይፈጽማሉ፡፡ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት ይገረዛሉ፡፡ ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት ሴቷ ጥጥ ፈትላ አልባሳት ስታዘጋጅ ወንድም በፊናው የመኖሪያ ቤትና የራሱን የእርሻ ቦታ ያደራጃል፡፡ በብሔረሰቡ የተለያዩ የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች አሉት፡፡ በቤተሰብ ስምምነት፣ በጠለፋ የሚፈጸሙ ጋብቻዎች ኣሉት። በተጋቢዎችም ሆነ በቤተሰብ መካከል ያለመግባባት ሲከሰት ወይም የአግቢው ገቢ ሀብት አቅም ውሱንነት ሲከሰት ተጋቢዎቹ ሳይተዋወቁ የወንዱ አባት ሽማግሌ ይዞ የልጅቷን ቤተሰብ ከ1-2 ቀን ደጅ በመጥናት የሚፈጸም የሽምግልና ጋብቻም ኣለው። የምትክ ጋብቻ የሚባለው ደግሞ፤ ሚስት ከሞተች እህቷ ወይም የቅርብ ዘመዷ በምትክ ሚስትነት የምትሰጥበት የጋብቻ ኣይነት ነው፡፡ ወዶ ገብ ጋብቻ ደሞ ሌላው በብሔረሰቡ የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ ይኸውም፤ ሳታገባ የቆየች ሴት የራሷን ንብረት በመያዝ ወደ ወንዱ ቤት በፈቃዷ ሄዳ በመግባት የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ በብሔረሰቡ በበዓላት ቀናት ከሚዘጋጁት ምግቦች መካከል ሸንዴራ ይገኝበታል፡፡ ከበቆሎና ከገብስ ዱቄት የሚሠራ ሆኖ ቅመማቅመምና ቅቤ በማጣፈጫነት ገብቶበት የሚበላ ጥሩ ምግባቸው ነው፡፡ ቡላ በአይብ ጎመንና ቅቤ ገብቶበት የማሠራው ‹‹ባጭራ›› የተባለው ምግባቸውና ‹‹ቅንጬ›› በበዓላት ቀን ከሚያዘጋጇቸው ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ጐፋዎች በነባሩ ባህላቸው ከቆፋ፣ ከሌጦና ከጥጥ የተሠሩ አልባሳትን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ‹‹ኢቴ›› የማባለው ከቆዳና ከሌጦ የሚሠራውን ልብስ ወጣቶችና አዋቂዎች በጀርባቸው ላይ ጣል በማድረግ ከወገባቸው ብቻ ‹‹አሣራ›› (ዲታ) የሚባለውን ከጥጥ የሚሠራ ግልድም ያገለድማሉ፡፡ ማንቾ (ማሽኮ) ዕድሜያቸው ከ1-8 የማሆናቸው ሴት ሕፃናት ደሞ ከድርና ማግ አልፎ አልፎም ከቆዳ ተገምዶ ጫፉ ላይ በዛጎል ያጌጠን ልብስ ለብልታቸው መሸፈኛ ይታጠቁታል፡፡ በባህላዊ ሽመና የሚሠሩ ቡልኮ፣ጋቢ፣ነጠላ፣መቀነት ወዘተ… በብሔረሰቡ በብዛት የሚዘወተሩ አልባሳት ናቸው፡፡ የብሔረሰቡ አባል ሲሞት ለባህላዊ መዎች፣ ለአዛውንቶች፣ ለጎልማሶችም ሆነ ለወጣቶች ‹‹ዘዬና›› ‹‹ዳርበ›› የሚባለውን የሙዚቃ መሣሪያ በመምታት የአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሰበሰብ ይደረጋል፡፡ የሞተው ንጉሡ ከሆነ ሁሉም ሰው ግንባሩን ጥላሸት ወይም ጭቃ በመቀባት በፀጉሩ ላይ ደግሞ አመድ በመነስነስ ‹‹ሰማይ ተናደ›› በማለት ያለቀሳል፡፡ የለቅሶው ርዝማኔ እንደሟች ክብርና ዝና ከ4-7 ቀናት ይቆያል፡፡ ታዋቂ ሰዎች ጎፋ የኢትዮጵያ ብሔር ነው። የኢትዮጵያ
52615
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B0%E1%88%8E%E1%88%9E%E1%8A%95%20%E1%8B%B4%E1%88%AC%E1%88%B3
ሰሎሞን ዴሬሳ
በ1995 ዋሽንግተን ዲሲ ሰለ ቀጣዩ ዓለም ወይም ከሞት ቡሃላ ስላለው ህይዎት ተጠይቆ የሰጠው ምላሽ ነበር። ሲመለከቱት ይበልጥ ጥያቄ የሚያጭር ማንነት ያለው፣ በዘመናዊ የኢትዮጲያ ስነ-ፁሑፍ ውስጥ አማፂ ሊባል የሚችል ስብዕና ያለው ሙግትና ተጠየቅን የሚወድ እንዲሁም ግጥም ማለት ቤት ሲመታ ብቻ ሳይሆን ቤት ሳይመታ ጭምር መሆኑን ከኦረምኛ ቋንቋ ወለሎን በመውሰድና ለአማረኛው የግጥም ስልት የሰተዋወቀና ያረጋገጠ ታላቅ የስነ-ፁሑፍ ሰው ጋሽ ሰለሞን ደሬሳ። የዘርፈ ብዙ ሙያ ባለቤቶች ስለሆነው ጋሽ ሰሎሞን ደሬሳ ከወለጋ እስክ አዲስ አበባ፣ ከዚያም ከፈረንሳይ እስክ አሜሪካ ያሳለፋቸውን የሂዎት ተሞክሮ ላስቃኛችሁ። ጋሽ ሰሎሞን ደሬሳን ለመግለፅ ደራሲ፣ገጣሚ፣ጋዜጠኛ፣የስነ-ጥበብ ሃያሲ፣ተፈላሳፊ፣መምህር፣አማካሪ….እያልን መቀጠል እንችላለን።በ1964 ባወጣዉ “ልጅነት” በተሰኘው አፈንጋጭ ዘይቤ በነበረው የግጥም መድብሉ ምክኒያት ለበርካቶች ገጣሚነቱ ይጎላል።ይህ ስሙን የተከለበት መድብሉ ብዙ የወዛገበና ትችት የዘነበበት ቢሆንም ባልታሰበ መንገድ ለደራሲው የገጣሚነት ማረጋገጫ ቡራኬዎች ነበሩ።ከዚያ በፊት በጋዜጠኝነቱ የሚታዎቀዉ ጋሽ ሰሎሞን የአዲስ የግጥም ስልት መሪ ለመሆን በቅቷል። ጋሽ ሰሎሞን የተወለደው በምዕራብ ወለጋ ዞን መናገሻ ከሆነቺው ጊምቢ ብዙም በማትርቀው ጬታ በተባለች መንደር ነበር። ወደ ቡሃለዉ ግጥም የፃፈላትን የትውልድ መንደሩን የለቀቀው ገና በአራት ዓመቱ ሲሆን አዲስ አበባ ካመጡት ቡሃላ ምንምንኳን ዘመዶቹ ትምህርት ቢያስገቡትም ትምህርት አለገባ ስላለው ተፈሪ መኮንን፣መደሃኒያለም እንዲሁም ዊንጌት የመሳሰሉ ትምህርት ቤቶችን አዳርሷል።ሰነፍ የተባለው ተማሪ ግን ገና በ16 ዓመቱ ቀ.ኃ.ሰ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅን እንደተቀለቀለ ይናገራል። ጋሽ ሰለሞን በዩኒቪርሲቲ ቆይታው የስነ-ፁሑፍና ፍልስፍና ትምህርቱን ቢጀምርም ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ በኢትዮጰያ ሬድዮ የእንግሊዘኛ ዜና አንባቢ ሆኖ ለ 3ወራት እንዳገለገለ የነፃ ትምህት እድል አግኝቶ ወደ ፈረንሳይ አቀና።ምናልባትም የወደፊት ሂዎቱና አስተሳሰቡ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ካሳደሩበት መካከል ይህ የፈረንሣይ ኑሮው አንዱ ነው። ቱሉዝ በተባለች በደቡብ ፈረንሳይ በምትገኝ ከተማ ይማር የነበረው ጋሽ ሰለሞን ብዙን ጊዜ አውሮፓና ፓሪስን በመጎብኘት ያሳልፍ ነበር። ፈረንሳይ ውስጥ እነ ጀምስ ቦልደዊንና ቸሰተር ሃይምስን ከመሳሰሉ ታላላቅ የአሜሪካ ደራሲያን ጋር መዋሉ፣ከጃዝ ሙዚቀኞችና ከሰዓሊያን ጋር ሃሳብ መለዋወጡ፣የተለያዩ ሙዚየሞችና ጋለሪዎችን መጎብኘቱ የስነ-ጥበብ ግንዛቤውን በማዳበር በኩል እገዛ አድረገውለታል።ከገጣሚነቱ ባሻገር በሀገራችን ከሞቱ የስነ-ጥበብ ሃያሲ ሰዩም ወልዴ ሌላ የሚጠቀስ የዘርፉ ድንቅ ባለሙያ መሆኑ ይነገርለታል። ጋሽ ሰለሞን ፈረንሳይን የለቀቀው ሰዓሊ ጓደኛው እስክንድር በጎሲያን አሜሪካ ውስጥ ሊየገባ በመሆኑ ሚዜ ሆኖ አሜሪካ በማቅናቱ ነበር።የፈረንሳይ ትምህርቱን አቋርጦ አሜሪካ የገባው ጋሽ ሰለሞን ለመጨረሻ ጊዜ አውሮፓን ቢሰናበትም ፓሪስ ላይ በፈረንሳይኛ ግጥሞች ፅፎ የተወሰኑት ታትመውለት ነበር።ለመጀመሪያ ለአንዲት የአዲስ አበባ ኮርዳ አፍቃሪ 10 ሳንቲም ተከፍሎት የግጥም ስንኞችን ሀ ብሎ መደርደር የጀመረው ጋሽ ሰለሞን “ኪነጥበብ ለኪነጥበብነቱ” የሚለዉን የኪነጥበብ መርህ እንደሚከተል ይነገርለታል። በአሜሪካ ቆይታው በቅድሚያ ወደ ካሊፎርኒያ በማቅናት ከጌታሁን አምባቸው ጋር በጋራ በመሆን በቴፕ እየቀረፁ አማረኛ ማስተማር ጀመሩ። ይህ በንዲህ እንዳለ እሱን ጨምሮ 11 ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት “ኢትየጵያን ዲክሽነሪ” ላይ አሻራዉን አሳርፏል። ምን ይሄ ብቻ ከሉካንዳ ጀምሮ እስከ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባሉት ቦታዎች ሰርቷል።እዚያ እያለ ለኢትዮዮጵያ ሬድዮ ለወጣው ክፍት የስራ ቦታ ተወዳድሮ በማለፉ ወደ ሀገሩ ተመልሶ በድጋሚ ኢትዮጵያ ሬድዮ ተቀጥሯል። እንዲሁም የኢትዮጲያ ሬድዮንና ቴለቪዥን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆኖም አገልግሏል። ጋሽ ሰለሞን የጋዜጠኝነትና የስነ-ፅሑፍ ችሎታውን ይበልጥ ያስመሰከረው ከ1950ዎቹ ጀምሮ አዲስ ሪፖርተርና በተባለው የእንገሊዘኛ መፀሄቶችና መነን በመሳሰሉ የአማረኛና የእንግሊዘኛ ህትመቶች ላይ በሚያሰፍራቸው መጣጥፎች ነበር። እነዚህ የፅሁፍ ተሞክሮቹና የአፃፃፍ ልምዶቹ ወደቡሃላው የታዎቀበትን የግጥም ስልት ለመሞከርም መንደርደሪያ ሆነውታል። ጋሽ ሰለሞን በ1965ዓ.ም ወደ አሜሪካ እንደተጓዘ በሃገራችን የመንግስት ለውጥ በመደረጉ በነበረበት መቅረትን መርጧል። በደርግ ስረዓት ወቅት ስለኢትዮጵያ ከመገናኛ ብዙኃን ከሚሰማው በስተቀር ሀገሩን አይቶ የማያቀው ጋሽ ሰለሞን ደርግ ከወደቀ ቡሃላ ሀገሩን ከመጎብኘቱም በላይ በ1991በቤህራዊ ቴያትር አዳራሽ ለአድናቂዎቹ ግጥሞቹን አንብቧል።ጋሽ ሰለሞን በአሜሪካን ኑሮው ከስነ-ፁሁፍ ይልቅ ወደ መምህርነቱ አድልቶ ነበር። እንደገና ዩኒቨርሲቲ በመግባትም በምስራቃዊያን ፍልስፍናና አሜሪካን ስነ-ፀሁፍ የመጀመሪያ ድግሪውን አግኝቷል። እሱ የመጀመሪያ ድግሪ ብቻ ቢኖረውም ከሚያስተምራቸውና ከሚያማክራቸው መካከል የድህረ ምረቃ ተማሪዎችም ይገኙበት ነበር።ተማሪዎቹ የክፍሉ ጓደኞቹ ብቻ ሳይሆኑ በተለያየ የስራ መስክም ተሰማርተው የጠበቀ ወዳጂነት ነበረው። ጋሽ ሰለሞን ከ19 ዓመታት በፊት መስከረም 1991ዓ.ም ከሪፓርተር መፀሄት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ስለትምህርቱ፣ ስለጓደኞቹ፣ሰለግጥሞቹ፣ስለኢትዮጲየ ስነፅሁፍ፣ስለመንፍሳዊነት፣ስለኢትዮጲያዊያንና ቤሄረሰቦቿ እንዲሁም ስለጋዜጠኝነት ሰፋ ያል ሐተታ ሰጥቶ ነበር።ለትውስታችን ይረዳን ዘንድ ስለመንፈሳዊነት፣ ሰለግጥሞቹ እንዲሁም ስለጋዜጠኝነት ያሰፈራቸውን ላሰዳሳችሁ። ከ1000 በላይ የሃይማኖት መፀሃፍትን ብቻ ያነበበዉ ጋሽ ሰለሞን መንፈሳዊው እሳቤው ከኢትዮጲያዊያን እሳቤ ጋር እጅጉን ከመቃረኑም በላይ ለሱ እስልምናና ክርስትና እንደ ሀይማኖት አይቆጥራቸውም ይልቁንም እሱ መንፈሳዊነት ሰለሚለዉና አንደ ለዩ ሰለሞንን ስለመፍጠር ትረጉም ስለሚሰጠው እሳቤው የደላል።በ1995 ከያሬድ ጥበቡ ጋር ባደረገው ቆይታ እግዛብሔር የሚውደውን እንደሚቀጣ እንዲሁም አብዛህኛው ኢትዮጵያዊ ሰለሚየምንበትና ፈጣሪ ስለሚዎደን ይቀጣናል ስለሚሉት እምነት ሲጠይቀው ጋሽ ሰለሞን የሰጠው መልስ እንዲህ በማለት ነበር። “እንደኔ አስተሳሰብ ስለተዎደድን ነው የምንረገጠው የሚለው በተለይ ከአይሁዶች የዎረስነው ብሉይ ኪዳንባንቀበል፤ ከወደድከኝ የኔ ወንድም አትርገጠኝ፣ ጌታዬ ከዎደድከኝ አትርገጠኝ፣ ከረገጥከኝ ካጉላላሀኝ አልወድህም ብዬ እኔ ለራሴ ቆርጫለሁ።” እንደ ጋሽ ሰለሞን እይታ ግጥም ለመፃፍ ትንሽ ጥጋብ፣ ልበ ደንዳናነት እንዲሁም እብደት ያስፈልጋል።እንደሱ እሳቤ አንድ ፀሐፊ አንድ ደህና ነገር ከፃፈ ቡሃላ ህይዎቱ ካለተለዎጠ ድግግሞሽ ነው የሚፅፈው።አክሎም የሱ ግጥም ለማንበብ የሱን ድምፅ እንደሚሹ እንዲሁም መነሻው እሱ እንደሆነ ገልፆ በግርድፉ ለሱ ግጥም ማለት በግጥም የተፃፈፈ እንዲሰማን መሆኑን ይገልፃል። “በአጭሩ ለኔ እንደሚመስለኝ በስድ ንባብ የተፃፈ እንዲገባህ፣ በግጥም የተፃፈው እንዲሰማህ ነው።ገባህ አልገባህ ሁለተኛ ነገረ ይመስለኛል።ግጥምን የማነበው እንዲገባኝ ሳይሆን እንዲሰማኝ ነው።”በአጭሩ ለኔ እንደሚመስለኝ በስድ ንባብ የተፃፈ እንዲገባህ፣ በግጥም የተፃፈው እንዲሰማህ ነው።ገባህ አልገባህ ሁለተኛ ነገረ ይመስለኛል።ግጥምን የማነበው እንዲገባኝ ሳይሆን እንድመሠጥበት ነው” ጋሽ ሰለሞን የጋዜጠኝነት ተሞክሮውንና በወቅቱ የለውን የጋዜጠኞቹ እውነትን ለማወቅ ከቢሮክራሲዉ ጋር የሚያደረጉትን ትግል ገልፆ ባሁኑ ወቅት የሉት ድፍረት ይጎላቸዋል ሲልም ምልከታውን ጣል አድርጎል። ጋሽ ሰለሞን ከገዳሙ አብረሃ ጋር በመቀናጀት በአቢዎቱ ዋዜማ የነበረውን የፖለቲካ፣ኢኮኖማያዊ እንዲሁም መሃበራዊ አለመረጋጋት አስመልክቶ በ1961ዓ.ም በአዲስ ሪፖርተር ዘ ሀይፈኔትድ ኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በሁለት ክፍል ታትሞ በዎጣዉ አምድ በሁለት ዓለም ውስጥ ስለተፈጠረው ውጥረት ለመመርመር ሞክረዋል።ይህ ፅሁፍ እስካሁንም አግራሞትን ከማጫሩም በላይ ጋሽ ሰለሞን የተዋጣለት ሃያሲ መሆኑን ይመሰክራል።ባጠቃላይ ጋሽ ሰለሞን ደሬሳን የህይዎት ተሞክሮና የሚከተለውን ፍልስፍና ለመግለፅ እስካሁን የተጠቀሱት ባህርን በጭልፋ እንደመጭለፍ ይሆናልና በዚሁ መቋጨት አሰብኩ። የጋሽ ስበኃት አምቻ፣የነይልማ ደሬሳ ባለስጋ ብኩኑ ፈላስፋ ስደተኛው ገጣሚ ሰለሞን ደሬሳ በአሜሪካ ግዛት ሚኔሶታ ከተማ ሂዎቱን እየመራ ሳለ ባደረበት ፅኑ ህመም ሳቢያ ለ7 ወራት ሲታከም ቆይቶ ባሳለፍነው ጥቅምት 23,2010 በ80 አመቱ ላይመለስ አሸለበ።የአልጋ ቁራኛ እስከሆነበት ድረስ በሚኔሶታ ዩኒቨርሲቲ የሀይማኖት ንፅፅር መምህር የነበረው ጋሽ ሰለሞን የአንድ ሴት ልጅ አባት ሲሆን 3መፀሐፍትን ለአንባቢያን አበርክቷል። ስረዓተ ቀብሩም በኑዛዜው መሰረት በሚኔሶታ ከተማ በሚገኘው የባህር ዳርቻ ልጁ ፣ባለቤቱ እንዲሁም ወዳጆቹ በተገኙበት በግባዓተ ዕሳት ተፈፅሟልበዛሬው መሰናዷችን የንባብ ሰው ስለሆነው፣ግልፅ በሆነ አገላለፅ የተሰማውን የሚናገር፣ከፍተኛ የማድመጥ ክህሎት ስላለውና ምንም አይነት ቢሮክራሲ የማይዋጥለት እንዲሁም ከተሞክሮውና እውቀቱ ሳንቋደሰ የመለጠን ድንቅ ባለታሪክ ጋሽ ሰለሞን ደሬሳ ለመዳሰስ ሞክረናል።መሰናዶውን በማዘጋጀት ያቀረብኩላችሁ እኔ ኑሩ ሀሰን ስሆን እንደመረጃነት መፀሄት,ዋዜማ ሬዲዮ እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ከተለያየ ሰው ጋር የደረገውን ቃለምልልስ በማሰባሰብ ነበር። ሳምንት ከተረኛ አዘጋጅ በአዲስ ታሪክ እስክንገናኝ ሰናይ ዕለተ ቅዳሜ ተመኘሁ ሰላም። በወለጋ ክፍለ አገር ጩታ በተባለች መንደር በ1929 ወይም በ1930 ዓ.ም. [1937] ተወለድኩ፡፡ በጣሊያን ጊዜ፡፡ አራት ዓመት ሲሞላኝ ዘመዶቼ ወደ አዲስ አበባ ይዘውኝ ስለመጡ አገሬ አዲስ አበባ ነው ማለት ይቀለኛል፡፡ ትምህርት አልገባ ብሎታል ተብዬ ያልገባሁበት ትምህርት ቤት የለም፡፡ በመጨረሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በ16 ዓመቴ ገባሁ፡፡ እዚያም ከትምህርቱ ይልቅ ልጅ ሁሉ እንደሚያደርገው ጨዋታና መበጥበጥ ይበልጥብኝ ነበር፡፡ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ትምህርት አላጠናቅኩትም፡፡ ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከሚገኙት ልጆች መጻሕፍት ቤቱን እንደኔ የተጠቀመበት ብዙ ተማሪ ያለ አይመስለኝም፡፡ ከዚያ ለሦስት ወራት የእንግሊዝኛ ዜና አንባቢ ሆኜ በአሁኑ ራዲዮ ኢትዮጵያ በቀድሞው ራዲዮ አዲስ አበባ ተቀጠርኩ፡፡ ከአለቃዩ ጋር በልጅነቴ የተነሳ አልተስማማንም፡፡ ወዲያው እንዳጋጣሚ ፈረንሣይ አገር ስኮላርሺፕ አገኘሁ፡፡ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ በፈረንሣይኛ ቋንቋ ትምህርት የጅማሪ ክፍሎን ሦስት ጊዜ በተደጋጋሚ የወደቀ ቢኖር እኔ ብቻ ሳልሆን አልቀርም፡፡ ፈረንሣይኛ ይህን ያህል አላስቸገረኝም፡፡ ተማሪ ቤት ተመዘገብኩ፡፡ ፈረንሣይ አገር የዩኒቨርሲቲ ፈተና በዓመት አንድ ጊዜ ነው የምትፈተነው፡፡ የምማረው ቱሉዝ ነበርና እኔ አውሮፓ ውስጥ ስዞር ከርሜ አንድ ሦስት ወር ሲቀረው መጥቼ አጥንቼ አልፋለሁ፡፡ በኋላ ሰዓሊው እስክንድር በጎስያን ጥቁር አሜሪካዊት አላባማ ሊያገባ ስለነበር ለሱ ሚዜ ሆኜ አሜሪካ ሄድኩኝ፡፡ ሁለተኛ ወደ አውሮፓ አልተመለስኩም፡፡ ወደ ካሊፎርኒያ ሄጄ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አገኘሁ፡፡ በቴፕ እየቀረፁ ቋንቋ ማስተማር የመጀመሪያውን ክፍላቸውን ከጌታሁን አምባቸው ጋር እኔ ነበርኩ ያቋቋምኩት፡፡ ያላየሁት ገንዘብ እጄ ገባ፡፡ አማርኛ አስተምር ነበር፣ ይህን አሠራ ነበር፣ በኋላ ላይ ደግሞ ዎልፍ ሌስላው ‹‹ኢትዮጵያን ዲክሽነሪ›› ብሎ ያወጣትን አንድ አሥራ አንድ ኢትዮጵያውያን ሆነን ስንሠራ እሱ ሱፐርቫይዘር ነበር፤ በዚህ ሁሉ የማገኘው ገንዘብብ ኪሴን ሞላው፡፡ ከዚያ ወደ ኒዮርክ ሄድሁና ለአንድ ለሁለት ቀን ሉካንዳ ውስጥ ሥራ እሠራለሁ ብዬ ገባሁ፡፡ ገንዘቡ ጥሩ ነበር፤ ግን የሥጋው ሽታ ስለበዛ እሱን ጥዬ ወጣሁ፡፡ ግራና ቀኝ ስል በተባበሩት መንግሥታት ሥራ አገኘሁ፡፡ እዚያ እየሠራሁ አንድ ማስታወቂያ አየሁ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ሠራተኛ ይፈልጋል›› የሚል ሲሆን፣ አሜሪካኖችም ሌሎችም ሲያመለክቱ እኔም አመለከትኩ፡፡ በቋንቋ ማወቅ ስለሆነ እኔ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ፈረንሣይኛ፣ እንግሊዝኛ እናገራለሁ፡፡ ትግርኛም ትንሽ ትንሽ እሰማ ነበር፡፡ በዚህ አሜሪካኖቹን አሸንፌ ተቀጥሬ መጣሁ፡፡ በእውነት ያደግሁት ራዲዮ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፤ ነፍሴን ያወቅሁት፡፡ ወደ መጨረሻ ከዚያ ስወጣ የራዲዮ የቴሌቪዥን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ነበርኩ፤ ለአዲስ ሪፖርተር እንግሊዝኛ መጽሔት እሠራ ነበር ግጥም እፃፅፍ ነበር፡፡ እውነቱን ለመናገር እኔ ገጣሚ ነኝ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ እንዲሁ በየቦታው እየተጻፈ (አሁንም እንዲሁ ነው) የጠፋው ጠፍቶ የተገኘውን ባለቤት ስብሰባ ካስቀመጣቸው ውስጥ ‹‹ልጅነት›› ወጣች፡፡ የቀሩትን እዚሁ ትቻቸው ሄድኩኝ፡፡ እንደ ሦስት ጅምር ተውኔቶች፣ የአጫጭር ልቦለድ ስብስቦችና ግጥሞች እዚሁ ቀረሁ፡፡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ጽሑፍ አስተምር ስነበር ለብዙ ጊዜ አልጽፍም ነበር፡፡ ለእኔ ሁለቱ አንድ ላይ አልሄደም፤ አስቸገረ፡፡ የማስተምረው እና አንድ ላይ በማንኛውም አቅጣጫ ነው፡፡ አስተምር ነበር፡፡ ለማስተማር ኳሊፊኬሽን ኖሮኝ አያውቅም፡፡ ሳመለክት እንዳጋጣሚ እቀጠራለሁ ከዚያ ከተማሪዎቹ ጋር እየተማርኩ ነው የማስተምረው፡፡ የዛሬ አምስት ነው ስድስት ዓመት ገደማ ከዩኒቨርሲቲ ወጣሁ፡፡ ምክንያቱም የተማሪዎቼን ጽሑፍ ማረም ስለሰለቸኝ ነበር፡፡ ከዚያ ጀመርኩኝ፡፡ አሁንም የምሠራው ይህንኑ ነው፡፡ ከየትኛውም ተቋም ጋር ግንኙነት የለኝም፡፡ የማስተምረው በአንድ ቦታ ሳይሆን እየተዘዋወርኩ ነው፡፡ ተማሪዎቼን የማሰባስበው በአፍ ማስታወቂያና እርስ በርሱ እየተስማማ ከሚመጣው ነው፡፡ ያለኝ የባችለር ዲግሪ ነው የመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ነገር ግን የድህረ ምረቃ ተማሪዎችንም አስተምር ነበር፡፡ መጀመሪያ በዩኒቨርሲቲው ፕብሊክ ሄልዝ ኮሌጅ ውስጥ ከዚያ ደግሞ ገሽታልት ኢንስቲትዩት (የሳይኮሎጂ) ውስጥ በሳይኮሎጂ ለፒኤችዲ የሚሠሩትንም፣ ሶሻል ወርከሮችንም፣ ሳይካትሪስቶችንም አስተምር ነበር፡፡ አሁንም እንደዚህ ያሉ የግል ተሪማዎች አሉኝ፡፡ የባችለር ዲግሪዬን አዲስ አበባ ሳልጨርሰው ነው የሄድኩት፡፡ አሜሪካ ሄጄ የጨረስኩት ነው፡፡ እዚህ ዩኒቨርሲቲ ሳልጨርሰው ሳይሆን ዲግሬዬን ሳላገኝ የወጣሁት ነበረ፡፡ የምዕራባውያን ፍልስፍናን ክፍል ውስጥ በመማር ሳይሆን በማንበብ ምናልባት ኮሌጅ ለማስተርስ ከሚሠሩት ጋር እኩል ሳላነብ የቀረሁ አይመስለኝ፡፡ ስላልተፈተንኩበት ሳለማር ልል አልችልም፡፡ እዚያ ብሄድ አዲስ ነገር ካጋጠመኝ ብዬ በአንድ ስምንት ወር ውስጥ ጨረስኳት፡፡ ከሦስት ወር በኋላ እዚያው ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ መልሰው ለማስተማር ቀጠሩኝ፡፡ መጀመሪያ ስቀጠር ሳስተምረው የነበረ ኮርስ ‹‹ሥነ ጥበብና ቴክኖሎጂ›› የሚል የራስ ፈጠራ የሆነ ነበር፡፡ ቴክኖሎጂው እየተሻሻለ ሲሄድ ሥነ ጥበቡን ይለውጠዋል፡፡ ሥነ ጥበቡ ደግሞ እየተሻሻለ ሲሄድ ለቴክኖሎጂው አዲስ መንገድ ይከፍታል፡፡ እና በዓለም ታሪክ ውስጥ ሥነ ጥበብና ቴክኖሎጂ የት የት ቦታ ነው የተገናኙት የሚለውን ማስተማር ጀመርሁ፡፡ የፈረንሳይ ሥነጽሑፍና እኔ[ለማስተካከል ኮድ አርም] የፈረንሳይን ሥነ ጽሑፍ አነብም አጠናም ነበር፡፡ የደረሱበትን አላውቅም እንጂ በፈረንሣይኛ የጻፍኳቸው፣ ታትመው የወጡም ግጥሞች ነበሩኝ፡፡ አሁን ፈረንሣይኛው እየጠፋ ሄዷል፡፡ የቀሩኝ አማርኛ፣ እንግሊዝኛ ኦሮምኛ ናቸው፡፡ በኦሮምኛ እስካሁን አልጻፍኩም፡፡ በኔ ላይ ተፅዕኖ ያሳደረብኝ የፈረንሳይ ሥነ ጽሑፍ ሳይሆን ፓሪስ መኖሬ ነው፡፡ ፓሪስ ስደርስ 20 ዓመቴ ነበር፡፡ ፓሪስ ነፃ ክፍት ከተማ ስለነበርና ልጅ ስለበርኩ ቁልፉን የከተማው ከንቲባ እንደሰጠኝ ነው ያየሁት፡፡ በኋላ ትልልቅ የሆኑ ጸሐፊዎች፣ የሙዚቃ ሰዎች ሠዓሊዎች ነበሩ፡፡ እንዲያውም ላንድ አቫን ጋርድ የፈረንሣይ ጋለሪ ማንም ሳይሾመኝ ሥዕል አውቃለሁ ብዬ ገብቼ አንድ አማካሪ ሆኜ ያኔ የመረጥኳቸው ሠዓሊዎች አሁን በዓለም የታወቁ አሉ፤ ኢትዮጵያውያን ማለቴ አይደለም፡፡ ዋናው ተፅዕኖ ከነሱ ጋር መዋል መቻሌ ነው፡፡ ከጥቁር አሜሪካዎች ጋርም በጣም በጣም ቅርብ ነበርኩኝ በተለይ ከጃዝ ሙዚቀኞች ጋር፡፡ አሁንም በብዛት የምሰማው ሙዚቃ የኢትዮጵያ፣ ጃዝና ክላሲካል ሙዚቃ ነው፡፡ ከፈረንሣይ ጸሐፊዎች ጋርም ያለ ዕድሜዬና ያለ ዕውቀቴ እኩል ገብቼ ዋልኩኝ፡፡ በማንበብ ሳይሆን አብሮ በመዋል እንዳባቶች ሆነው አሳድገውኛል፡፡ ከፈረንሣይ፣ ከእንግሊዝ ከአሜሪካን ጸሐፊዎች ውስጥ ሪቻርድ ሪይት ለትንሽ አመለጠኝ፡፡ ግን የእሱ ጓደኞች ከሚውሉበት ነበር የምውለው፡፡ እነ ቸስተር ሃየምስ፣ ጀምስ ቦልድዊንና ስማቸውን ከማላስታውሳቸው ጸሐፊዎች ጋር አብሮ መዋል እኔንም ጸሐፊ ያደረገኝ መስሎኝ ነበር፡፡ ያሳደጉኝ እነሱ እንጂ የፈረንሣይ ዩኒቨርሲቲ አይደለም፡፡ በተጨማሪም ፓሪስ ከተማ አለች ከኢትዮጵያውያን ጓደኞቼ ጋር እየዋልኩኝ ወደ ሙዚየም፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ቲያትር ቤት፣ ኮንሰርት እሄድ ነበር፡፡ ገንዘብ ብዙ አልነበረበኝም፡፡ በተለይ መጨረሻው ላይ ምንም አልነበረኝም፡፡ ከትሬንታ ላይ ሌሊት ሌሊት አትክልት እያወረድኩ ነበረ የምኖረው፡፡ ግን አንድ ሳንቲም ኪሴ ሳይኖር እንደ ሚሊየነር ልጅ ነው ፓሪስን የኖርኩባት፡፡ ከአዲስ አበባ ቀጥላ የትውልድ ከተማዬ የምትመስለኝ ፓሪስ ነች፡፡ የሥነ ጽሑፍ አቋም[ለማስተካከል ኮድ አርም] ከብዙ ወጣት ደራስያን ጋር ከዮሐንስ አድማሱ፣ ብርሃኑ ዘርይሁን ጋር የተለየ አቋም ነበረኝ፡፡ ከዮሐንስ ጋር ከሥነ ጽሑፍ ይልቅ የጓደኝነት ግንኙነት ነበረን፡፡ በጣም በጣም አደንቀው የነበረና አሁንም የማደንቀው የአማርኛ ባለቅኔ ብዬ የምገምተው ገብረክርስቶስ ደስታ ነው የተረሳ፡፡ የተረሳ ስል ግጥሞቹ ተሰብስበው በመጽሐፍ መልክ አልወጡም፡፡ ከአቶ መንግሥቱ ለማ ጋርም ጓደኞች ነን፡፡ አንዳንዶቹን ግጥሞቹን በጣም አደንቃቸው ነበር፡፡ እሱ እኔ ላይ ተፅዕኖ ሳይኖረው አይቀርም ብዬ እገምታለሁ፡፡ ምክንያቱም መጻፍ ሳልጀምር ነው የሱን ግጥም እሱ ሲያነብ መስማት የጀመርኩት፡፡ እንዲያውም ልጅነት ውስጥ ‹‹ቱሉዝ ገምቤላ›› የምትል አንድ ግጥም አለች፡፡ እሷ ያለጥርጥር የመንግሥቱ ተፅዕኖ አለባት፡፡ አንዳንድ ጸሐፊዎች ወይም ገጣሚዎች አካባቢያቸው ያለውን የሰው ሕይወት ሆነ፣ የማኅበራዊ ሆነ፣ የመሬት አቀማመጥ፣ ቅጠላ ቅጠሉን ይጽፋሉ፡፡ አንዳንድ ደግሞ ከሐሳብ ነው የሚጽፉት ግብ አላቸው፡፡ ወይ የማስተማር ወይ የመቀስቀስ (እንደ ፉከራ) ወይ ሕይወት ከበደኝ ብሎ እሮሮ የማሰማት ዓለማ አለው፡፡ ሌላው መንገድ የሰው ልጅ ውጪው ብቻ ሳይሆን ውስጡም ሕይወት አለውና የውስጡ ብዙ ጊዜ እውጪ አንፀባርቆ አይታይም፡፡ እኔን በተለይ የሚስበኝ ይኼ ነው፡፡ ነገር ግን ወስኜ ‹‹ጥበብ ለጥበብነቱ ሲባል›› ብዬ ተነስቼ አላውቅም፡፡ ልጅም ሆኜ ወደዚያ ይስበኝ ነበር፡፡ እንዳጋጣሚ በልጅነቴ የመጀመሪያዬን ግጥም 10 ሳንቲም ነበር ሸጥኳት፡፡ ጎረቤታችን የነበረች አንድ ወጣት ሴት ከአንድ ወጣት ጋር ፍቅር ይዟት 10 ሳንቲም ከፍላ እሷ ናት ግጥም ያጻፈችኝ፡፡ የግጥሙም አለመወደድ ይሁን ወይም የሷ የትም አልደረሰም፡፡ እና እሱ ተፅዕኖ አሳደረብኝ፣ ግብ ለማጣት አይለም፡፡ ግብ መጀመሪያ ላይ ወስኜ እንዲህ ይሁን ብዬ አልነበረም የምጽፈው፡፡ ውስጤ ያለውን እንደመጣም ነበር የምጽፈው፡፡ አሁን ደግሞ ለኔ እንደሚመስለኝ ዛሬ የምጽፈው ግጥም ሳየው ግጥሙን አንብቤ የሚለው ሁሉ ዛሬ ካወቅሁት ባይታተም ግዴለኝም፡፡ አሜሪካ እንድ አሥራ ሦስት ግጥሞች አንድ የግጥም መድበል ውስጥ ወጥተዋል፡፡ እንግሊዝ አገርም አንድ ሁለት ወጥተዋል፡፡ ካናዳም ወጥተዋል፡፡ እና እንዳጋጣሚ ወዳጅ አግኝቷቸው ፎቶ ኮፒ ልኮልኝ ሳያቸው ያኔ ምን እንደሆኑ አላውቃቸውም ነበር፡፡ አሁን ነው የምረዳቸው፡፡ አንብቤው ግጥሙ በሙሉ ለራሴ ግልጽ ሆኖ ከታየኝ የትናንትናውን፣ ያለፈውን እንደማወራ መስሎ ስለሚሰማኝ አላስቀምጣቸውም፡፡ ግጥም እንደዚህ መጻፍ ጥሩ አይደለም ማለቴ አይደለም፡፡ እያንዳንዱ አናፂ ሆነ ጸሐፊ የየራሱ ባህርይ ስላለው የኔ ባህርይ ወደ ውጭው አይደለም ማለቴ ነው፡፡ ግብ በሚመለከት ግን እኔ ባልወስነውም ያገኛል፡፡ ጓደኛሞች[ለማስተካከል ኮድ አርም] ከስብሐት ገብረእግዚአብሔርና ከተስፋዬ ገሰሰ ጋር አብሮ አደጎች ነበርን፤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፡፡ ውጭ ሁላችንም የራስ የራሳችን ጓደኞች ነበርን፡፡ ሲመሽ ሁላችንም አንድ ሰፈር ነበር የምንሄደው ውቤ በረሃ፡፡ አንዳንዴ አብረን እንሄዳለን እንጂ የውቤ በረሃ ጓደኞቼ እነስብሐት አልነበሩም፡፡ ሦስታችን ስንገናኝ ሥነ ጽሑፍ በብዛት እናነብ ነበር፡፡ ስብሐት ያን ጊዜም ቢሆን ግጥም አልነበረም የሚጽፈው፣ አጫጭር ልቦለዶች ነው፡፡ ተስፋዬ ግጥምም ይሞካክር ነበር፡፡ እኔ ወደ ግጥም ነበር የማደላው፡፡ ስብሐት መጀመሪያ ጽፎ አስደንቆኝ ያየሁት ኤክስ አን ፕሮቫንስ ሆኖ የጻፈውን ነው፡፡ እኔ ፓሪስ ነበርኩ፡፡ ላየው ስለፈለኩ መንገድ ላይ መኪና እየለመንኩ ደረስኩ፡፡ ይች ትኩሳት ተብላ የወጣችው ያኔ ስትጻፍ ነበረች አጀማመሯን አየሁት፡፡ ከዚያ ደግሞ እዚህ መጥቼ በእጅ ተገልብጠው ቀበና በላይ እንግሊዝ ተማሪ ቤት በታች ሲኖር አስነበበኝ፡፡ የኔንም አብረን እናነብ ነበር፡፡ በኋላ ደግሞ እህቴን አገባ፤ ሃና ይልማን፡፡ ከመንገድ ወዲህና ከመንገድ ወዲያ ስለምንኖር ሁልጊዜ ማታ ማታ እንገናኝ ነበር፡፡ ስብሐትና ተስፋዬ በወንድምነትም በጓደኝነትም እንደ ወንድሞቼ የሚቀርቡኝ ናቸው፡፡ ከነገብረክርስቶስ ደስታ፣ መንግሥቱ ለማ፣ ዳኛቸው ወርቁ፣ ዮሐንስ አድማሱ ጋር ያገናኘን ሥነ ጽሑፍ ነው፡፡ ከዚያ ተነስቶ ነው ጓደኞች የሆነው፡፡ ከዮሐንስ ጋር ትንሽ እንዳንቀራረብ ያደረገን የሥነ ሐሳብ መለያየት ሳይሆን ሐረር ሊያስተምር መሄዱ ነው፤ የምንገናኘው ሲመጣ ነበር፡፡ የሚገርመኝ ነገር እኔ የሱን ግጥም ሳነብ በሐሳብ ተለያየን ብዬ አልነበረም የማስበው፤ ‹‹ይኼ ዮሐንስ አድማሱ ነው›› ነው የምለው እሱም አንስቶት በዚህ ስንከራከር አላውቅም፡፡ ሲያነብ ግን ይኼ ሰሎሞን ነው ይላል፡፡ ሳናነብበት መለያየታችንን ተቀብለን የምንናበብ ይመስለኛል፡፡ ገብረክርስቶስ ዊንጌት አብረን ስንማር እሱ ሥዕል ነበር የሚሠራው፤ ጀርመን አገር ሲማርም ሄጄ ጎብኜቸዋለሁ፤ ከእስክንድር ጋር፡፡ መጀመሪያ ግጥም ያነበበልኝ እዚያ ነው፤ ኮለን አጠገብ ይኖር ነበር፡፡ ምንም እንኳ ሥዕሎቹ ቆንጆ ቢሆኑም የሚያስደንቁኝ የአማርኛ ግጥሞቹ ነበሩ፡፡ ከዚያ መጥተን እዚህ ቀጠልን፡፡ ያን ጊዜ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም ይጻጽፍ ነበር፤ አሁን ትቶ እንደሆነ አላውቅም፡፡ እሱም አንዱ ባለጠበል ነበር፡፡ ዳኛቸው አይመጣም፡፡ ተጎትቶ ካልሆነ ከሰው አይቀርብም ነበር፡፡ ከኔ ጋር ግን ውጭም ወዳጆች ነበርን፡፡ ‹‹ልጅነት›› ታትማ ስትወጣ በመጠኑ ቁጣ ወረደባት፡፡ የኢትዮጵያን የግጥም አወራረድ አበላሽ፤ ከፈረንጅ ያመጣው ነው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ሱሪያሊስቶቹን ገልብጦ ነው ምናምን ይባል ነበር፡፡ የማስታውሰው የምስጋና ጽሑፍ ያገኙሁት ከዳኛቸው ወርቁ ብቻ ነው፡፡ የደረሰኝ የምስጋና ጽሑፍ የቄስ ጽሕፈት ይመስል ነበርና የሱ መሆኑን ያወቅሁት በኋላ ስንቀራረብ ነው፤ አልፈረመባትም ነበር፡፡ እንደ አጋጣሚ ደግሞ እኔ ‹‹አደፍርስ››ን አግኝቼ ሳነብ ‹‹ማነው ልጅነትን የጻፈው?›› ብሎ ሲፈልግ ነው የተገናኘነው፡፡ በጣም በጣም ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን የትም ቦታ ከማደንቃቸው ጸሐፊዎች ዳኛቸው አንዱ ነው፡፡ በሁሉም ሳይሆን በአደፍርስና በ በአጠቃላይ ግን አንድ ጸሐፊ አንደ ደህና ነገር ከጻፈ በኋላ ሕይወቱ ካልተለወጠ ድግግሞሽ ነው የሚጽፈው፡፡ እነ ዳኛቸው ለአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ያደረጉት አስተዋፅኦ ከሁሉ የበለጠ ስታይል (አማርኛ ምን እንደምለው አላውቅም) ይመስለኛል፡፡ ይኸውም የስብሐትን የአማርኛ አጻጻፍ የትም ባየውና ባይፈርምበትም የስብሐት መሆኑን አውቃለሁ፡፡ መጀመሪያ መቅለሏ፣ የአረፍተ ነገሩ ማጠር፣ ቁጭ ብለህ የምትነጋገር ነው የሚመስልህ፡፡ አማርኛ አሁንም ብሶበታል፤ ገመድ ሆኗል፡፡ የዳኛቸው ደግሞ የስብሐት ተቃራኒ የሆነ ነው፡፡ ግን ገመድ አለበትም፡፡ የመንግሥቱ ለማ ሌላው ቢቀር ‹‹ማን ያውቃል›› የምትል ግጥም አለች፡፡ የመስቀል ወፍና የአደይ አበባ ቀጠሮ እንዳላቸው መስከረም ሲጠባ ማን ያውቃል? የምትል፡፡ አንድ ጸሐፊ ሁልጊዜ ተነባ የምትታወስና የሰውን መንፈስ ፍላጎት የምትቀሰቅስ ከጻፈ ዕድለኛ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ እና የመንግሥቱ ለማ ይኼ ግጥም አለ፤ ሌሎችም አሉት፡፡ ትያትሮችም አሉ፡፡ መንግሥቱ ለማ ፌዘኛና ተሰጥኦ ነበረው፡፡ ሌላ እንደሱ ተሰጥኦ የነበረውም አቶ ነጋሽ ገብረማርያም ነው፤ አሁንም ይጽፍ እንደሆነ አላውቅም፡፡ በጣም ለማሳቅ ስጦታ ያለው፡፡ እስክንድር አሁን በቅርብ በሚል መጽሔት አንድ ረዘም ያለ ድርሰት ስለሱ በእንግሊዝኛ ጽፌ ነበር፡፡ ያው እዚያ ያልኩትን ነው የምደግመው፡፡ እስክንድር በኢትዮጵያ ሥነ ሥዕል ውስጥ የተለየ ቦታ ያለው ይመስለኛል፡፡ የተለየ ቦታ ያለው ስል ከሌሎቹ ሁሉ ይልቃል ለማለት ሳይሆን ጨክኖ መንገድ ክፍቷል ብዬ ነው የምገምተው፡፡ መንገድ ሲከፍት ደግሞ ፓሪስና ሎንደን አሥር ዓመት ከተማረ በኋላ (እውነቱን ለመናገር አልተማረም ከሠዓሊዎች ጋር በመዋል፤ ሙዚየሙም ውስጥ ጊዜ ከማሳለፍ፣ ከማጠንጠን ተነስቶ) ከፈረንጆቹ ተፈናቅሎ ወደ አፍሪካ ትራዲሽን በጠቅላላው፣ በተለይ ደግሞ የምዕራብ አፍሪካ ቅርፆች ተፅዕኖ አሳደሩበት፡፡ የነ ኤምስጋርቱቶላ ጽሑፍ ተፅዕኖ አሳደረበት፡፡ ከዚያ ተላቆ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ1966 እንደገና መንገድ ለመለወጥ በጣም ዝግጁ ሆኖ መጣ፡፡ መጥቶ የአክሱምን፣ የጎንደርን፣ የላሊበላን፣ የወላይታ ቅርፃ ቅርፆችን፣ ኦሮሞ መቃብር ላይ የሚቆሙትን፣ ሐረር ዋሻ ውስጥ ያሉትን አየና አንድ ጊዜ ጭንቅላጹን በረገደው፡፡ ተመልሶ ያንን ሊሠራ ሲችል ተላቀቀና ወደዚህ ዞረ፡፡ አሁን የኢትዮጵያን ሥዕሎች ዞሬ አላሁም እንጂ ለብዙ ጊዜ ተፅዕኖው ይታይ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ሰንፈው ነው፡፡ ባትሰንፍም የአንዳንድ ሰው ሥዕል አንድ ጊዜ ካየኸው አይለቅህም፡፡ የእስክንድር ሥዕሎች ሲታዩ አዲስ ነገር ይመስላሉ፤ ደግመህ ስታየው አብረኸው ያደግኸው ይመስላል፡፡ የኢትዮጵያን ሥዕሎች ጥንት የነበሩት ጎንደር ደብረብረሃን ሥላሴ ያሉት ሥዕሎች የሚያስደንቁ ናቸው፡፡ ከዚያ ወዲህ ጨክኖ ዓይኑን ወደዚህ ዞር ያደረገና ታይቶት የሠራ ነው፡፡ በቅርብ ካሉት ውስጥ በጣም የማደንቀው ሠዓሊ እሱ ነው፡፡ ይልቃል አይደለም አደንቀዋለሁ ነው
17742
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A5%E1%89%B4%E1%8C%8C%20%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%89%B5%E1%8B%8B%E1%89%A5
እቴጌ ምንትዋብ
እቴጌ ምንትዋብ በዙፋን ስሟ ብርሃን ሞገስ በ1698 ዓ.ም. ከአባቷ ደጅአዝማች መንበር እና እናቷ ልዕልት እንኮይ በቋራ፣ ጎንደር ስትወለድ የክርስትና ስሟ ወለተ ጊዮርጊስ ነበር። እናቷ ልዕልት እንኮይ ከዓፄ ሚናስ ዘር የምትወለድ እንደነበረች ይጠቀሳል። ምንትዋብ በ18ኛው ክፍልዘመን ኢትዮጵያ ላይ ብዙ አሻራ ትታ የለፈች ንቁ፣ ሃይለኛና ተራማጅ መሪ ነበረች። ከባሏ ዓፄ በካፋ ዘመን ጀምሮ እስከ ልጇ ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ እና ልጅ ልጇ ዓፄ እዮዋስ ዘመን ድረስ ለ40 አመታት የአገሪቱ እኩል መሪ የነበረች ናት። በዚህች መሪ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ የህንጻዎች ግንባታና የቤተክርስቲያን ድረሰት፣ እንዲሁም ስነ ጥበብ እድገት ታይቷል። በፋሲል ግቢ የመጨረሻውን ግንብ ያስገነባችው ምንትዋብ ነበረች። ከልጆቿ የእድሜ አናሳነትና እራሷም በሰራቻቸው አንድ አንድ ስህተቶች ምክንያት በስልጣን በነበረችበት ዘመን የነበረው እድገትና ሰላም እርሷ ስታልፍ አብሮ አለፏል። እንግዴህ አገሪቱ ወደ ዘመነ መሳፍንት የተሻገረችው ልክ እርሷ እንዳለፈች ነበር። ዐፄ በካፋ ከዐፄ በካፋ ጋር ስለመገናኘቷ ዐፄ በካፋ በህዝብ ዘንድ ክብርን ካስገኘለት ስራው አንዱ ብዙ ጊዜውን በመሰዋት፣ እራሱን ደብቆ በግዛቱ ሁሉ እየተዘዋወረ ስህተት የተሰራውን ማቃናቱ ነበር። በዚህ ሁኔታ አንድ ቀን ተደብቆ ከጣና ሃይቅ በስተ ምዕራብ ሲጓዝ ቋራ ላይ ወባ ታመመና ከአንድ ገበሬ ቤት አረፈ። የስኮትላንዱ ተጓዥ ሐኪም ይጋቤ ሲተርክ "ወጣቷ ምንትዋብ ከመጠን በላይ ቆንጆ፣ ተግባቢና ልዝብ" የነበረች ሲሆን በካፋ ታሞ ያረፈበት ቤት ባለቤት ልጅ ነበረች። ምንትዋብ ታማሚውን ንጉሥ ተንክባክባ ለጤንነት ስላበቃችው ጳጉሜ5፣ 1716 (እ.ኤ.አ) ላይ ወደ ጎንደር ከተማእንዳስመጣትና እንዳገባት ይዘግባል። በ1717 ዳግማዊ አጼ ኢያሱን ወለደች። ከዚህ በኋላ ለ2 አመት ጎንደር ከተማ ተቀምጣ በመካከሉ በ1718 ወደ ወልቃይት እንድትሄድ ተደረገ። ምንም እንኳ ከሁለት ወር በኋላ ብትመለስም ልጇ ግን ወደ ሰሜን ሽሬ፣ ትግሬ ተልኮ በዚያ እስከ 1730 መኖር ቀጠለ። የአጼ በካፋ መሞትና የምንትዋብ መንገሥ አጼ በካፋ በ1722 ዓ.ም. ሲሞት የከተማው ህዝብ ሞቱን ሊቀበል አልቻለም። ለዚህ ምክንያቱ ከአሁን በፊት ንጉሱ ሳይሞት የሞተ በማስመሰል ህዝቡ ላይ ሽብር በመፍጠሩ ነበር። ምንትዋብም ባሏ ሲሞት የህዝቡን ጥርጣሬ በመጠቀም ውስጥ በማስገባትና ከቋራ አምስት ወንድሞቿ መጥተው የቤተመንግስት ስልጣን እስኪጨብጡና እስኪያረጋጉ ድረስ የንጉሱን ሞት ደብቃ ቆየች። ከወንድሞቿ መምጣት በኋላ እርሷና ዘመዶቿ ሆነው የ7 አመት ልጇን ኢያሱን ለማንገስ ቻሉ። ከ2 ወር በኋላ ታህሳስ 15፣ 1722 ላይ የልጇን ህጻን መሆን በማስታከክ እራሷ ላይ ዘውድ በመጫን በንግሥት ሥልጣን እንደራሴነቷን አሳወጀች። ለሚቀጥሉት 40 አመታት እርሷና ወንድሟ ወልደ ልዑል ከንጉሥ ልጇና ልጅ ልጇ ጋር እኩል ተሰሚነት ኑሯቸው አገሪቱን ለማስተዳደር በቁ፡፡ አንዳንዶች ይህ በዝምድና የተተበተበ አመራርና ያስከተለው የዘር ፉክክር አገሪቱን ለዘመነ መሳፍንት ያበቃ ተግባር ነበር ሲሉ ይታዘባሉ። የምንትዋብ አስተዳደር ምንትዋብና ልጇ ይከተሉት የነበረው ፖሊሲ ፊት ለፊት መጋፈጥ ሳይሆን እርቅንና መስማማትን ነበር። ለዚህ ተግባር እንዲረዳት፣ በጣም ቆንጆ የሚባሉ ሶስት ሴት ልጆቿን (ከበካፋ ሞት በኋላ ካገባችው ምልምል ኢያሱ የተወለዱ) በዘመኑ ኃይለኛ ለተባሉ የጎጥ መሪወች በመዳር (ወለተ እስራኤልን ለጎጃም ጦረኛ ደጃች ዮሴዴቅ ወልደ ሃቢብ (1751)፣ ወይዘሮ አልጣሽን ለሰሜን ባላባት ወልደ ሃዋርያት (የራስ ሥዑል ሚካኤል ልጅ)1747 እና ወይዘሮ አስቴርን ለትግሬ መሪ ራስማርያም ባሪያው1761) በመዳር በግዛቷ ስላም አስፍና ነበር። ንግስቲቱ በማዕከላዊው መንግስት ሹም ሽረት ብታደርግም ራቅ ብለው የሚገኙት ክፍሎች ግን በራሳቸው እንዲተዳደሩ አድርጋ ነበር። የኦሮሞ ቡድኖች ወደ ሰሜን የሚያረጉትን ዘመቻ ስላቋረጡ በደቡብ በኩል መረጋጋት ተከስቶ ነበር። በሌላ ጎን፣ በደቡብ የተወሰዱ መሬቶችን ለማስመለስ ምንም አይነት ዘመቻ በዚህ ዘመን አልተካሄደም። ስለሆነም ከጊዜ ወደጊዜ ራቅ ያሉ ስፍራወች ኢ-ጥገኝነታቸው እየጎላ ሄደ። ከነበረው አጠቃላይ ሰላም አንጻር ልጇ እያሱ ወደ ሰሜን የሚያደርገው ዘመቻ የፖለቲካ ሳይሆን ለአደንና መሰል ክንውኖች ነበር። ምንትዋብና ያከናወነቻቸው ስራዎቿ በልጇና በልጅ ልጇ ዘመናት ለ40 ዓመት ስትነግስ ያከናወናቸቻው ስራወች ብዙ ነበሩ። ምንትዋብ በባህሪዋ ተራማጅና ንቁ ነበረች። በቤተክርስቲያን ተነስቶ በነበረው የቅባት እና ተዋህዶ ክርክር ለማስታረቅ ያደረገችው ጥረት የተሳካ ነበር። ስለሆነም ከሞላ ጎደል በአስተዳደሯ ወቅት ሃይማኖታዊ ስላም ነግሶ ነበር። ከሌሎች መንፈሳዊ ስራዎቿ ውስጥ ብዙ አብያተ-ክርስቲያናትንና ግንቦችን በማነጽ እንዲሁም በግሏ እየተከታተለች ድርሰቶችን በማስደረስ ስሟ ይጠቀሳል። ቁስቋምን በደብረ ፀሐይ ስለመመስረቷ እቴጌ ምንትዋብ በተለያዩ ምክንያቶች እራሷን ከጎንደር ከተማ ለማራቅ ጥረት አድርጋለች። የዚህ ጥረት ውጤት ከጎንደር ከተማ 3 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ በሚገኘውደብረ ፀሐይ (ቁስቋም) ያሰራቻቸው ህንጻወች ናቸው። የስኮትላንድ ተጓዥጄምስ ብሩስ (ሃኪም ይጋቤ) በኒህ ህንጻወች አንድ ክፍል ተሰጥቶት ይኖር ነበርና ስለቁስቋም ሲጽፍ 3 ፎቅ የሆነ ቤተመንግስት፣ ክብ የሆነ ቤተክርስቲያንና ብዙ የተለያዩ የሰራተኞችና ዘበኞች ቤቶች እንዲሁም ግብዣ ቤት በአንድ ማይል ዙርያ በታጠረ ግቢ ይኖር እንደነበር አስፍሯል። እነዚህን ቤተመንግስቶችና ቤተክርስቲያኖች ከ1723 ጀምራ በማሰራት በ1732 ነበር ያስመረቀቻቸው። በግቢው ውስጥ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን፣ ደብረ ፀሐይ ማርያም ይባላል። በጄምስ ብሩስ ግምት፣ ኢትዮጵያ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሃብታም የነበረና ብዙ ምርጥ ምስላትንና በወርቅና በብር የተሰሩ የቤተክርስቲያን መገልገያ ዕቃወችን የተመላ ነበር። የተገነባውም በአናጢዎችመሪ በጅሮንድ ኢሳያስ እና አዛዥ ማሞ፣ አዛዥ ህርያቆሳና አዛዥ ናቡተ መሪነት ነበር። ቤተክርስቲያኑ በቀይ ሃር አሸብርቆ በዙሪያው 380 መስታውቶች ተተክለውት ብርቅርቅታው ጎንደር ከተማ ድረስ ይታይ ነበር። ነገር ግን ቤተክርስቲያኑና ሌሎች በግቢው የነበሩ ህንጻወች በሱዳን ወራሪ መሃዲስቶች፣ በ1880 ተቃጠሉ። አሁን በጊቢው የሚገኘው ቤተክርስቲያን በዚህ ፍርስራሽ ላይ የተሰራ ነው። ጛርጋ ስላሴና ሌሎች ህንጻዎች ስለማሰራቷ የአቡነ እውስጣጢዎስን ቤተክርስቲያን ሐምሌ 1729 ላይ አሰርታ ለማስመረቅ ችላለች።ጣና ሃይቅ በሚገኘው ደጋ ደሴት እንዲሁ የራሷ የሆነ ቪላ የነበራት ሲሆን በዚሁ ደሴት ለቅዱስ እስጢፋኖስ መታሰቢያ ያሰራችውን ቤተ ክርስቲያን በ1739 ለማስመረቅ ችላለች። በተረፈም በርሷ ዘመን በስዕል ያጌጡ ድርሳናትና አጠቃላይ ስነ ጥበብ የሚበረታቱ ስለነበር ከዚሁ ዘመን የሚመነጩ የስነ ጥበብ ውጤቶች እጅግ ብዙ ናቸው። ኪነትን ስለማሳደጓ እና በዘመኗ ስለተፈጠረው የስነ ስዕል አብዮት ምንትዋብ እጅግ መንፈሳዊ ነበረች። ለዚህ ስትል ብዙ መንፈሳዊ ስራወችን በገንዘብ ትደጉም ነበር። ብዙ መጻህፍት በዚህ ዘመን ተጽፈዋል፣ ከአረብኛም ተተርጉመው ወደ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የተሰራጩት ብዛት ስፍር ቁጥር የለውም። ለስነጥበብ ከነበራት ትኩረትና ከምታደርገው ድጎማ የተነሳ በዚሁ ዘመን በድንገት የተፈጠረ ልዩ አይነት የሥነ-ስዕል ስራ ተጀመረ። ይህ እንግዲህ በውጭ ሃገር የኪነት አጥኝወች ዘንድ ሁለተኛው የጎንደሪን የስነስዕል ስልት የሚባለው ነው። በአዲሱ ስልት ሥነ ሰዕል የቀጥተኛ መስመሮች ጥንቅር መሆኑ ቀርቶ በጎባጣ መስመሮች ጥንቅር የሚሰራና በህብረ ቀለማት የደመቀ ሆነ። የእውነተኛ ሰወች የሚመስሉ ምስሎችም መታየት ጀመሩ። በዚህ ሁኔታ በጣና ሃይቅ በአሰራችው ናርጋ ስላሴ ቤተክርስቲያን እና በቁስቋሙ ደብረፀሐይ ማርያም ግድግዳወች ላይ አይን የሚስቡ ምስሎች ተሰርተው ነበር። ሆኖም ብዙወቹ በመሃዲስት ሱዳኖች ሲወድሙ ንግስቲቱ በራሷ ክትትል ያስደረሰችው መጽሐፈ ራዕይ የትሰኘው በምስል ያሸበረቀ መጽሓፍ አሁን እንግሊዝ አገር ስለሚገኝ የአዲሱ የሥነ ሥዕል ስርዓት ቅርስ ከጥፋት ድኖ አሁን ቅርሱን መዝግቦ ይገኛል። በጊዜው ትታማባቸው የነበሩ ጉዳዮች አጼ በካፋ ከሞቱ በኋላ ከተወሰኑ ወንዶች ጋር ለአጫጭር ጊዜያት ትወጣ ነበር ተብላ ትታማ ነበር። በመጨረሻ፣ ምንም እንኳ ግራዝማች እያሱን ብታገባም የአማቷ ልጅ ከሞሆኑም በላይ ከእርሷ በድሜ ስለሚያንስ "ምልምል እያሱ" በሚል የሽሙጥ ስም ይታወቅ ነበር። ከዚህ ምልምል እያሱ 3 ሴት ልጆችን ስታተርፍ እነርሱም ልዕልት አስቴር፣ ልዕልት ወለተ እስራኤልና ልዕልት አልጣሽ ይባሉ ነበር። ልጇ ዐፄ እያሱ ይህን ምልማል እያሱን ይጠላው ነበር፤ ስለሆነም አንድ ቀን ለሽርሽር እንውጣ ብሎት ጣና ሃይቅ አካባቢ በአሽከሮቹ ተገፍትሮ ገደል ውስጥ እንዲሞት እንዳደረገ ይጠቀሳል። ታሪክ ፀሐፊው ተክለ ጻድቅ መኩርያ እንደዘገበ፣ ሺህ ነዋ የሚለው ቀልድ ከምንትዋብ የግብዣ አዳራሽ ነበር የፈለቀው። በተረፈ ንግስቲቱ በአንዱ ቅድም አያቷ ፖርቱጋላዊ ነበረች ተብላ ስለምትታማ ለካቶሊኮች ታደላለች የሚል ግንዛቤ በጊዜው ነበር የዘመነ መሳፍንት አጀማመር በኢትዮጵያ ታሪክ፣ በተደጋጋሚ እንደሚታየው፣ የህጻናት ስልጣን ላይ መውጣት አገሪቱን ከጥንት ጀምሮ ለውድቀት የዳረገ ነበር። የዳግማዊ አጼ ኢያሱና የልጁ የኢዮዋስ በህጻንነታቸው መንገስ ከዚሁ እውነታ የተለየ አልነበረም። አጼ በካፋ ሲሞት ልጁ ኢያሱ መንገሱ ህጋዊ ቢሆንም ህጻን ስለነበር ሃይል ለማግኘት የግዴታ ከሌላ ቦታ የፖለቲካ መሰረት ማግኘት ነበረበት። ስለሆነም እናቱ እቴጌ ምንትዋብ የምትተማመንባቸው የቋራ ዘመዶቿን በቤተ መንግስት ሾመች። ለምሳሌ፡ ወንድሟ ወልደ ልዑልን በራስ ማዕረግ። በዚህ ስራዋ ቀደምት በጎንደር ከትማ ስልጣን የነበራቸው ባላባቶች በጣም ጠሏት። ስለሆነም ከ1735-1736 እርሷንና ልጇን ከስልጣን ለማስወገድ ባላባቱ ሞከርው አመጹ ስለከሸፈ ይብሱኑ የቋራ ዘመዶቿን በከፍተኛ ስልጣንና በሰራዊቱ ላይ ሾመች ስልጣኗ እንዳይናጋ፣ የባላባቱን ኃይል በየጁወች ሃይል ለማጣፋት በማሰብ ልጇ አጼ ኢያሱን ለየጁ ባላባት ልጅ የሆነችውን ውቢት ክርስትና ከተነሳች በኋላ ወለተ ቤርሳቤሕ) ዳረች። ሆኖም ግን ንጉሱ ክርስቲያን ያልሆነች የየጁ ሴት አገባ ተብሎ ይታማ ስለነበር ጋብቻው በከተማው እርሱን ያስጠላና ድብቅ እንጂ በግልጽ የሚካሄድ አለነበረም። በመካከሉ ቤርሳቤሕ ቀስ በቀስ የየጁ ዘመዶቿን ልክ ምንትዋብ የቋራ ዘመዶቿን በቤተመንግስት እንደሰገሰገች ታደርግ ነበር። በዚህ ሁኔታ በየጁዎችና በቋራዎች የለሆሳስ ፉክክር ተጀመረ። ዳግማዊ አጼ ኢያሱ በ1747 ሲሞትና ከቤርሳቤሕ የወለደው ልጁ እዮዋስ ሲነግስ ምንትዋብ መልሳ እንደራሴነቷን አጸናች። ቤርሳቤሕ በበኩሏ ልክ ምንትዋብ የኢያሱ ሞግዚት እቴጌ እንደነበረች፣ እርሷ በተራዋ ለእዮዋስ እንደራሴነት(እቴጌነት) ይገባኛል በማለቷ በሁለቱ ጥል ተነሳ። በዚህ ወቅት አጼ እዮዋስ አያቱን ምንትዋብን ከመደገፍ ይልቅ የቤርሳቤህና የየጁዎች ወገን ሆነ። ውዝግቡ በ1759ዓ.ም. ወደ የርስ በርስ ጦርነት አመራ። በዚህ ጦርነት፣ የየጁም ሆነ የቋራ ክፍሎች ሃይላቸው ስለተዳከመ፣ ከትግሬ ገዢ ራስ ሥዑል ሚካኤል እገዛ ፈለጉ። ሥዑል ሚካኤል መጀመሪያ የንጉሱና የጁወች ደጋፊ የሆነ ቢሆንም በምንትዋብ የዲፖሎማሲ ስራ ኋላ የርሷ አጋር በመሆን አቋሙን ቀየረ። በስተመጨረሻ 1769 ላይ ሥዑል ሚካኤል፣ አጼ እዮዋስ የጁወችን በጦርነት ደግፏል በሚል ክስ እንዲገደል አደረገ። የንጉሱ መገደል በአገሪቱ ሲሰራበት የነበረውን ትውፊት የቀየረ እንግዳ ስራ ነበር። እንግዲህ እስከ ብዙ ዘመን ድረስ የነበረውን የንጉስ ክብር የነካ ስለነበር የሚፈራ አንድ ሃይል በመታጣቱ አገሪቱ ወደ ዘመነ መሳፍንት ሁሉ በሁሉ ጦርነት ገባች። ምንትዋብ፣ ምንም እንኳ የየጁዎች ዋና ተቃዋሚ የነበርች ብትሆንም፣ የልጅ ልጇን መገደልና የሥዑል ሚካኤልን መግነን በመጥላት 1762 ላይ ወደ ጎጃም ሸሽታ ከሄደች በኋላ 1763 ተመልሳ ከጎንደር 3 ኪሎ ሜትር ሰሜን-ምዕራብ በሚገኘው ቁስቋም ባሰራችው ቤተ መንግስት ኑሮ ጀመረች። ከዚህ በኋላ ሃይሏ በመዳከሙ አገሪቱ ቀስ በቀስ እየተከፋፈለች ወደ ዘመነ መሳፍንት ስትሻገርና በስልጣን ትሥሥር ያስቀመጠቻቸው ዘመዶቿ ሲዋረዱ ከማየት በስተቀር ምንም ማድረግ አቅቷት ግንቦት ቀን ዓ/ም አረፈች። የእቴጌ ምንትዋብ ትውልድ =አቤቶ ዋክሶስ የቡላው| ወይዘሮ ዮልያና}} ማጣቀሻ ዋቢ መጻሕፍት 1965), 81 1994 1813 ,''1997, ተክለጻድቅ መኩሪያ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፡ ከዐፄ ልብነ ድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ ታሪክ ወንግሥት ብርሃን ሞገሳ ወይንም የእቴጌ ምንትዋብ ዜና መዋዕል ከዚሁ ዘመን የሚመነጩ ቀሪ ምስሎች መደብ :የኢትዮጵያ ታሪክ መደብ
49119
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%90%E1%89%A2%E1%8B%AD%20%E1%8A%A0%E1%88%85%E1%88%98%E1%8B%B5
ዐቢይ አህመድ
አብይ አህመድ አሊ (በኦሮምኛ፡ በእንግሊዝኛ የተወለዱት ነሐሴ 9 ቀን 1968 ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛ ሲሆኑ ከመጋቢት 24 2010 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 4ኛ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያን ለ28 ዓመታት የገዛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 3ተኛ ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆኑ በዚያ ቦታ ላይ የመጀመሪያው የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጅ ናቸው። አብይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሲሆኑ በ2011 ዓ.ም ኢህአዴግ ፈርሶ የብልጽግና ፓርቲ እስኪመሰርት ድረስ ከኢህአዴግ አራት ጥምር ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አባል ነበሩ። ለ20 አመታት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የነበረውን ግጭትና አለመግባባት ለማስቆም በሰሩት ስራ የኤ.አ 2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸንፈዋል። አቶ አብይ በ2012 ዓ.ም ሰኔ ወር በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር ሊካሄድ የታቀደውን የፓርላማ ምርጫ ለማራዘም ወስነዋል። ይህ እርምጃ በተለይ ከተቃዋሚዎች በኩል ትችት የፈጠረ ሲሆን ህገ መንግስታዊ ሕጋዊነት ጥያቄ አስነስቷል። በጥቅምት 2013 በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት የመከላከያ ሰራዊት እና የኤርትራ ጦር ከህወሓት ሃይሎች ጋር ላደረጉት የትግራይ ጦርነት መነሻ ነበር የግል ሕይወት ልጅነት አብይ አህመድ የተወለዱት በትንሿ በሻሻ ከተማ ነው። ሟች አባታቸው አቶ አህመድ አሊ ሙስሊም ኦሮሞ ሟች እናታቸው ወይዘሮ ትዘታ ወልዴ ክርስቲያን ኦሮሞ ሲሆኑ አንዳንድ ምንጮች እናታቸው የአማራ ተወላጅ ናቸው ቢሉም ጠ/ሚ አብይ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ቃለ ምልልስ ላይ ሁለቱም ወላጆቻቸው ኦሮሞ እንደሆኑ "ማንም ኦሮሙማዬን አይሰጠኘም አይወስደብኝም" በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። የአብይ አባት ኦሮምኛ ብቻ የሚናገር መደበኛ የኦሮሞ ገበሬ ነበር፣ ትዘታ ግን አማርኛም ሆነ ኦሮምኛን አቀላጥፋ ትናገር ነበር። አብይ ለአባታቸው አስራ ሶስተኛ ልጅ እና ለእናታቸው ስድስተኛ እና የመጨረሻ ልጅ ሲሆኑ ከአባታቸው አራቱ ሚስቶች የአራተኛዋ ልጅ ናቸው። የልጅነት ስማቸው አብዮት ይባል ነበር። ይህ ስም በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ በነበረው የኢትዮጵያ አብዮት ምክንያት አንዳንድ ጊዜ ለህፃናት ይሰጥ ነበር። የወቅቱ አብዮት በአካባቢው ወደሚገኝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማረ በኋላ በአጋሮ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቱን ቀጠለ። ብዙ የግል ዘገባዎች እንደሚያሳዩት አቢይ ሁልጊዜም በትምህርቱ ያለው ፍላጎት ከፍተኛ ሲሆን በኋላም ሌሎች እንዲማሩ እና እንዲሻሻሉ ያበረታታ ነበር። አቶ አብይ የጎንደር አማራ ተወላጅ የሆኑትን ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸውን ሁለቱም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በማገልገል ላይ እያሉ አግበተዋል። የሶስት ሴት ልጆች እና የአንድ ማደጎ ወንድ ልጅ አባት ናቸው። አብይ ኦሮምኛ፣አማርኛ፣ትግርኛ እና እንግሊዘኛ ይናገራሉ። የአካል ብቃት አዘውታሪ ሲሆኑ የአካል ጤና ከአእምሮ ጤና ጋር አብሮ እንደሚሄድ ተናግረዋል ፣በዚህም በአዲስ አበባ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ያዘወትራሉ። ሃይማኖት አቶ አብይ የፕሮቴስታንት ክርስትና እምነት ተከታይ ናቸው። ከሙስሊም አባት እና ከኦርቶዶክስ ክርስቲያን እናት የተወለዱ ሲሆን ያደጉት በሃይማኖተ ብዙ ቤተሰብ ውስጥ ነው። አብይ እና ቤተሰቡ የዘወትር ምእመናን ሲሆኑ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን አልፎ አልፎ ወንጌልን በመስበክ እና በማስተማር አገልግለዋል። ባለቤታቸው ዝናሽ ታያቸው በቤተክርስቲያኗ የወንጌል ዘማሪ ሆነው ያገለግላሉ። ትምህርት በ2001 ዓ.ም ዶ/ር አቢይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በማገልገል ላይ በነበሩበት ወቅት በአዲስ አበባ ከማይክሮሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ አግኝተዋል። የትምህርት ዝግጅታቸውን በተለይም የመጀመርያ ዲግሪ ትምህርታቸውን በተመለከተ ብዙ ጥያቄ የሚያጭሩ ሁኔታዎች አሉ። በ2003 ዶ/ር አቢይ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በትራንስፎርሜሽናል አመራር በለንደን ከሚገኝው ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ትምህርት ቤት ከአለም አቀፍ ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት አዲስ አበባ ጋር በመተባበር አግኝተዋል በተጨማሪም 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከአሽላንድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሊድስታር ማኔጅመንት እና አመራር ኮሌጅ ባዘጋጀው መርሃግብር የቢዝነስ አስተዳደር ማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። በ2009 የዶክትሬት ዲግሪያቸውን መመረቂያ ጽሁፍ "ማህበራዊ ካፒታል እና ሚናው በባህላዊ ግጭት አፈታት ኢትዮጵያ፡ የሃይማኖት ግጭት ጉዳይ በጅማ ዞን ክልል" በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ጥናት ተቋም አጠናቀዋል። ሆኖም የአለም የሰላም ፋውንዴሽን የተባለ ተቋም ግን በዶክትሬት ዲግሪያቸው ላይ የተገቢነት ትችት ሰንዝሯል። ውትድርና ታዳጊው አብይ በ1983 መጀመሪያ ላይ በ14 አመቱ ታላቅ ወንድሙ ከሞተ በኋላ የመንግስቱ ሀይለማርያምን የማርክሲስት ሌኒኒስት መንግስት በመቃወም የትጥቅ ትግሉን ተቀላቀለ። በዚያን ጊዜ 200 የሚጠጉ ታጋዮችን ብቻ ያቀፈ አነስተኛ ድርጅት የነበረው ኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ)ን በመቀላቀል የህጻን ወታደር ሆነ። ወደ 90,000 የሚጠጉ የትግራይ ተወላጅ ታጋዮች ባሉበት ጦር ውስጥ የኦህዴድ ታጋዮች ጥቂት ስለነበሩ አብይ በፍጥነት የትግርኛ ቋንቋ መማር ቻለ። በትግራይ ተወላጆች በሚተዳደረው ንቅናቄ ውስጥ ትግርኛ ተናጋሪ በመሆኑ በወታደራዊ ስራው ወደፊት ለመሄድ አስችሎታል። ከደርግ ውድቀት በኋላ በምዕራብ ወለጋ ከሚገኘው አሰፋ ብርጌድ መደበኛ ወታደራዊ ሥልጠና ከወሰደ በኋላ በ1985 ዓ.ም ወታደር በመሆን በአሁኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በመረጃና ኮሙኒኬሽን ክፍል ውስጥ ሰርቷል። እ.ኤ.አ. በ 1987 ከሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ በኋላ የተባበሩት መንግስታት የሩዋንዳ እርዳታ ተልዕኮ አባል በመሆን በሀገሪቱ ዋና ከተማ ኪጋሊ ውስጥ ተሰማርቷል እ.ኤ.አ. ከ1990 እስከ 1992 በነበረው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የስለላ ቡድን መርቷል። ከዚህ በኋላም አብይ ወደ ትውልድ ከተማው በሻሻ ተመልሶ፣ የመከላከያ ሰራዊት መኮንን በመሆን በሙስሊም እና በክርስቲያኑ ማህበረሰብ መካከል የተፈጠረውን ግጭትና በርካታ ሰዎች ሲሞቱበት የነበረውን አሳሳቢ ሁኔታ መፍታት በመፍታት መረጋጋትን እና ሰላምን አምጥቷል። በኋለኞቹ ዓመታት፣ የፓርላማ አባል ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ፣ የሃይማኖት መድረክ በመፍጠር በሃይማኖቶች መካከል እርቅ ለማውረድ እነዚህን ጥረቶች ቀጥሏል። እ.ኤ.አ. በ2006 ዓ.ም አብይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን (ኢንሳ) ከመሰረቱት መስራች አባላት አንዱ ሲሆን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግሏል። ለሁለት ዓመታት ያህል በዳይሬክተሩ የሥራ ፈቃድ ምክንያት የኢንሳ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ነበር። በዚህ ተያይዞም እንደ ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ባሉ በመረጃና ኮሙዩኒኬሽን ላይ የሚሰሩ የበርካታ የመንግስት ኤጀንሲዎች የቦርድ አባል ነበሩ። እ.ኤ.አ. በ2010 ከወታደርነት እና የኢንሳ (የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ) ምክትል ዋና ዳይሬክተርነትን ከመተውና ፖለቲከኛ ለመሆን ከመወሰኑ በፊት የሌተናል ኮሎኔልነት ማዕረግን አግኝቷል። ፖለቲካ የፓርላማ አባልነት አብይ የፖለቲካ ስራውን የጀመረው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አባል በመሆን ነው። ኦህዴድ ከ1983 ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ገዥ ፓርቲ የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ውስጥ ከነበሩት አራት ጥምር ፓርቲዎች አንዱ ነበር።አብይ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመሆን በቅልጥፍና የፖለቲካ መሰላሉን ወጥተዋል። በ2010 ዓ.ም በተካሄደው አገራዊ ምርጫ አብይ የአጋሮ ወረዳን በመወከል የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል በመሆን ተመርጠዋል። በጅማ ዞን ከፓርላማ አባልነታቸው በፊትም ሆነ በነበሩበት ወቅት በእስልምና እምነት ተከታዮችና ክርስቲያኖች መካከል በርካታ ሃይማኖታዊ ግጭቶች ነበሩ። ከእነዚህ ግጭቶች መካከል ጥቂቶቹ ወደ ሁከት ተቀይረው ለሰው ህይወት እና ንብረት መውደም ምክንያት ሆነዋል። በዞኑ ዕርቀ ሰላም እንዲወርድ ከበርካታ የሀይማኖት ተቋማትና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመተባበር አብይ የፓርላማ አባል እንደመሆናቸው ንቁ ሚና ነበራቸው። በክልሉ የሙስሊሙና የክርስቲያኑ ማህበረሰብ ሰላማዊ መስተጋብር ወደነበረበት እንዲመለስ ዘላቂ የመፍታት ዘዴ በመቅረጽ "የሀይማኖት መድረክ ለሰላም" የተሰኘ መድረክ በማዘጋጀት አግዘዋል። አቢይ በ2006፣ በፓርላማ ቆይታቸው ወቅት የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል የተሰኘ የመንግስት የምርምር ተቋም ዋና ዳይሬክተር ሆነዋል። በሚቀጥለው አመት የኦህዴድ ስራ አስፈፃሚ አባል በመሆን በዚያው አመት ለትውልድ ወረዳው ለጎማ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ለሁለተኛ ጊዜ ተመረጡ። ወደ ስልጣን መውጣት ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል እና በተለይም በአዲስ አበባ ዙሪያ ህገ-ወጥ የመሬት ወረራዎችን ለመከላከል በሚደረገው ንቅናቄ አብይ ማዕከላዊ ከሆኑት መካከል አንዱ ነበር። የመሬት ቅርምቱ መነሻ የሆነው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ቢቆምም፣ ግጭቱ በመቀጠሉ የአካል ጉዳትና ሞት አስከትሏል። በስተመጨረሻም የአብይ አህመድን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያሳደገው፣ ትኩረት እንዲሰጠው ያደረጋቸው እና የፖለቲካ መሰላል እንዲወጣ ያደረገው ይህ ከመሬት ወረራ ጋር የተያያዘ ትግል ነው። አብይ በ2008 ዓ.ም ከ12 ወራት በኋላ የተወውን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እያለ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ ካቢኔ አባል በመሆን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው አገልግለዋል። በተጨማሪም የኦሮሚያ ከተማ ልማትና ፕላን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነዋል። አብይ በዚህ ቢሮ በኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዮት ፣በኦሮሚያ መሬትና ኢንቨስትመንት ማሻሻያ ፣የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የተንሰራፋውን የመሬት ወረራ ለመቋቋም ዋና አንቀሳቃሽ ሃይል ይሆናል ተብሎ ተጠብቋል። ከስራዎቹ የሚጠቀሰው በ2009 በተፈጠረው ግጭት ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉትን አንድ ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጆችን መንከባከብ ነበር። ከጥቅምት 2009 ዓ.ም ጀምሮ የኦዲፒ ሴክሬታሪያት ሃላፊ በመሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለት ሶስተኛውን የሚያካትቱትን የኦሮሞና የአማራ ብሔረሰቦች መካከል በተለምዶ "ኦሮማራ" የተባለውን አዲስ ጥምረት እንዲፈጠር አመቻችቷል። በ2010 መጀመሪያ አካባቢ ብዙ የፖለቲካ ታዛቢዎችና ህዝብ አብይ እና ለማ መገርሳን በኦሮሞ ብሔረሰብ ውስጥ በጣም ተወዳጅ አድርገው ቆጥረዋቸው ነበር። ነገር ግን በኦሮሚያ ክልልና በኢትዮጵያ ስርነቀል ለውጥ እና ነፃነት ለማምጣት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ይህ ካልሆነ ግን ንቅናቄው እንደሚቀጥል የኦሮሞ ወጣቶች ጠይቀዋል። እስከ 2010 መጀመሪያ ድረስ አብይ የኦዲፒ ሴክሬታሪያት እና የኦሮሚያ ቤቶችና ከተማ ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል። የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ከተመረጡ በኋላ ግን እነዚህን ሁሉ ኃላፊነቶች ትተዋል። የኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ የወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት አቶ ሀይለማርያም ከጠቅላይ ሚንስትርነቱም ሆነ ከኢህአዴግ ሊቀመንበርነቱ ለመልቀቅ የስልጣን መልቀቂያ አስገቡ። የአቶ ኃይለማርያም የስልጣን መልቀቂያ ማስገባት በኢህአዴግ ጥምር አባላት መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ የአመራር ሽኩቻ ምክንያት ሆኗል። ብዙ የፖለቲካ ታዛቢዎች አቶ ለማ መገርሳንና አብይ አህመድን ግንባር ቀደም እጩዎች አድርገው መላምት ሰንዝረዋል። አቶ ለማ መገርሳ የብዙሀኑ ተወዳጆች ቢሆኑም የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በሚፈቅደው መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የሚያስፈልገው መስፈርት ማለትም የፓርላማ አባል አልነበሩም። ስለዚህም ከውድድር ውጪ ሆነዋል። አንዳንድ ታዛቢዎች እንደሚተቹት ኦህዴድ አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚኒስትር ማድረጉ በጥምረቱ ውስጥ ያለውን የመሪነት ሚና ለማስቀጠል የወሰደው ስልታዊ እርምጃ ነው። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የፓርቲውን መሪ ለመምረጥ ስብሰባቸውን በመጋቢት 1 ቀን 2010 ጀመሩ። አራቱ ፓርቲዎች እያንዳንዳቸው 45 አባላት ልከዋል። ተፎካካሪዎቹ ከኦህዴድ ዓብይ አህመድ፣ ከአዴፓ የወቅቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሽፈራው ሽጉጤ የደኢህዴን ሊቀመንበር እና ደብረፂዮን ገብረሚካኤል የህወሓት ሊቀመንበር ነበሩ። አብይ አህመድ በብዙሃኑ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተወዳጅ የነበረ ቢሆንም በአመራር ውይይቶቹ ወቅት ከህወሓት እና ደኢህዴን አባላት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። መጋቢት 27/2010 የሊቀመንበሩ ምርጫ ሊጀመር ጥቂት ሰአታት ሲቀረው የአብይ አህመድ ቀንደኛ ተፎካካሪ ሆነው ይታዩ የነበሩት አቶ ደመቀ መኮንን ከምርጫው ራሳቸውን አግልለዋል። ብዙ ታዛቢዎች ይህንን የአብይ አህመድ ደጋፊነት አድርገው ይመለከቱት ነበር። ከዚያም አቶ ደመቀ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲቀጥሉ ተወሰነ። አቶ ደመቀ መውጣቱን ተከትሎ አብይ አህመድ ከአዴፓ እና ከኦዴፓ ስራ አስፈፃሚ አባላት ሙሉ ድምፅ ያገኘ ሲሆን 18 ተጨማሪ ድምፅ ከሌላ ቦታ በምስጢር ድምጽ አግኝቷል። እኩለ ሌሊት ላይ አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙ ሲሆን 108 ድምፅ በማግኘት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተደረጉ ሲሆን ሽፈራው ሽጉጤ 58 እና ደብረፂዮን ገብረሚካኤል 2 ድምፅ አግኝተዋል። በ2010 ዓ.ም አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርጠው ቃለ መሃላ ፈጸሙ። ጠቅላይ ሚኒስትርነት መጋቢት 24 ፣2010 ዓ.ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 3ኛ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰየመ፡፡ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሰየሙ በኋላም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። የስልጣን ሽግግሩ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ መጀመሪያ በመሆኑ መንግስት በአዲስ እይታ እድሉን ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡ በአገሪቱ በተፈጠረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት የተፈጠረውን ኢኮኖሚያዊ መቀዛቀዝን ለማካካስ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ በመስራት ጭምር ጥረት ይደረጋል፣ ለዚህም ሁሉም ሊተባበር ይገባል ብለዋል፡፡ የወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት፣ ጥራት ያለው የትምህርት ስርዓት ማረጋገጥ፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው ጉዳይ ከመንግስት ጋር ተቀራርበው እንዲሰሩ ትኩረት መሰጠቱንና ሌሎች ጉዳዮችንም በንግግራቸው አንስተዋል፡፡ ተፎካካሪ የፖለቲካ ኃይሎችም የተሻለች ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ገንቢ ሀሳብ እያቀረቡ ከመንግስት ጋር ከመቸውም ጊዜ በላይ በጋራ እንዲሰሩ ፍላጎት መኖሩንም አመልክተዋል፡፡ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ለዓመታት የነበረው አለመግባባት መቋጫ እንዲያገኝ መንግስት አበክሮ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል፡፡ የጠቅላዩ ንግግር የብዙሃኑን ስሜት የኮረኮረ ነበር። ፖሊሲ የአብይ መንግስት ስልጣን ከያዘበት 2010 ጀምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን ከኢትዮጵያ እስር ቤቶች እንዲፈቱ እና የሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር በፍጥነት እንዲከፈት አድርገዋል። በግንቦት 2018 ብቻ የኦሮሚያ ክልል ከ7,600 በላይ የህግ ታራሚዎችን ይቅርታ አድርጓል። በሽብርተኝነት ተከሰው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው የግንቦት 7 መሪ አቶ አንዳርጋቸው ፀጌ በፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ እና ከሌሎች 575 እስረኞች ጋር በይቅርታ ተፈትተዋል። በዚያው እለት በአንዳርጋቸው ባልደረባ ብርሃኑ ነጋ እና በኦሮሞ ተቃዋሚው እና የህዝብ ምሁር ጃዋር መሀመድ ላይ እንዲሁም በአሜሪካ በሚገኙት ኢሳት እና የሳተላይት ቴሌቭዥን አውታሮች ላይ የነበረው ክስ ተቋርጧል። ብዙም ሳይቆይ አብይ ከሀያ አራት ሰአት በፊት የሞት ፍርደኛ የነበረውን አቶ አንዳርጋቸውን በጽህፈት ቤታቸው አግኝተው በማነጋገር "ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ" እርምጃ ወሰዱ። የገዥውን ፓርቲ ተቺዎች ሳይቀር “ደፋር እና አስደናቂ” ያስባለ እርምጃ ነበር። ዶ/ር አብይ ከዚህ ቀደም ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፖለቲካው ሂደት ሰላማዊ ተሳትፎ ለማድረግ ቁርጠኛ የሆኑትን መስራች ሌንጮ ለታን ጨምሮ የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮችን አቀባበል አድርገው ነበር። ገዥው ፓርቲ በሰፊው የፖለቲካ ጭቆና መሳሪያ የነበረውን የሀገሪቱን የጸረ-ሽብር ህግ እንደሚያሻሽል ታውጇል። አቢይ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስቆም ከሁለት ወራት ቀደም ብሎ የስድስት ወር የስልጣን ዘመኑን እንደሚያጠናቅቅ አስታውቋል ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማቆም አስፈላጊውን ህግ አጽድቋል። በጁን 2010 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት የመጀመሪያ መግለጫ፣ መንግስታቸው የተፈረደባቸውን "አሸባሪዎች" ከእስር ሲፈታ የተሰነዘረውን ትችት በመቃወም ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ኢህአዴግ አንድ አካል ከሆንክ አልፎ ተርፎም ብታሟሉ የሚሰጣችሁ ስም ነው። ተቃውሞ" የዘፈቀደ እስራትን እና እራሳቸው ማሰቃየትን የሚደግፉ ፖሊሲዎች ተቃዋሚዎችን ለመጨፍለቅ ከህገ መንግስታዊ ዉጭ የሽብር ድርጊቶች መሆናቸውን ተከራክረዋል። ይህም በሰኔ 15 ቀን ለ304 እስረኞች (289ኙ ከሽብርተኝነት ጋር በተገናኘ የተከሰሱ) ተጨማሪ ይቅርታ መደረጉን ተከትሎ ነው። የተሀድሶው ፍጥነት በገዢው ፓርቲ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት የገለጠ ሲሆን በወታደራዊ ሃይሉ ውስጥ ያሉ ጠንካራ ሃይሎች እና እስካሁን ገዢው ህወሓት "አስጨናቂ" ናቸው ተብሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማብቂያ ላይ እና የፖለቲካ እስረኞችን ይፈታሉ ተብሏል። ቀደም ሲል በትግራይ ኦንላይን የመንግስት ደጋፊ ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ኤዲቶሪያል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መጠበቅ እንዳለበት በመሟገት አብይ "በጣም በፍጥነት እየሰራ ነው" ሲል ተናግሯል።የፖለቲካ እስረኞችን መፈታት የሚመለከት ሌላ ጽሁፍም የኢትዮጵያን መንግስት ጠቁሟል። የወንጀል ፍትህ ስርዓት ተዘዋዋሪ በር ሆኖ ነበር እናም የአብይ አስተዳደር በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ይቅር ለማለት እና ለመፍታት በማይቻል ሁኔታ ሲጣደፍ የነበረ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ብዙ ገዳይ ወንጀለኞች እና አደገኛ ቃጠሎዎች እ.ኤ.አ. ሰኔ 13 ቀን 2010 የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባድሜን ተረክቦ ወደ ግል ለማዘዋወር የተላለፈውን ውሳኔ "መሰረታዊ ጉድለት ያለበት" ሲል አውግዟል። ግልጽነት እ.ኤ.አ. በ2018 ነፃ ፕሬስን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት አብይ በስደት የሚገኙ ሚዲያዎችን ወደ መጡበት እንዲመለሱ ጋብዟል። እንዲመለሱ ከተጋበዙት የመገናኛ ብዙኃን አንዱ ኢሳት (በኢትዮጵያ ትግራውያን ላይ የዘር ማጥፋት እንዲፈጸም ጥሪ ያቀረበው) ነው።ነገር ግን አቢይ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2018 ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ.ም አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው እ.ኤ.አ. ሥራውን ከጀመረ ከአምስት ወራት በኋላ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። እ.ኤ.አ. ከማርች 21 ቀን 2019 ጀምሮ ከጋዜጠኞች ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልነበረበት ሌላ ጋዜጣዊ መግለጫ አልሰጠም (የተዘጋጁ መግለጫዎችን ከማንበብ ይልቅ)። መንግሥታዊ ያልሆኑት ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደገለፁት የአብይ መንግስት እ.ኤ.አ. ከ2019 አጋማሽ ጀምሮ የኢትዮጵያን ጋዜጠኞች እያሰረ እና የሚዲያ ተቋማትን እየዘጋ ነው (ከኢሳት-ቲቪ በስተቀር)። ከአለም አቀፍ ሚዲያዎች መንግስታቸው የሮይተርስን ዘጋቢ የፕሬስ ፍቃድ አግዶ የነበረ ሲሆን ለቢቢሲ እና ለዶይቸ ቬለ ዘጋቢዎችም መንግስት "የመገናኛ ብዙሃን ስርጭት ህግን በመጣስ" ሲል የገለፀውን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አስተላልፏል። የኢኮኖሚ ማሻሻያ እ.ኤ.አ ሰኔ 2018 ገዥው ጥምረት በመንግስት ባለቤትነት የተያዙ ድርጅቶችን ወደ ግል የማዞር እና ከወሰን ውጪ ተብለው የሚታሰቡ በርካታ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ነፃ የማውጣት ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል። በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በአቪዬሽን፣ በኤሌትሪክ እና በሎጅስቲክስ ዘርፍ ያሉ የመንግስት ሞኖፖሊዎች እንዲቆሙ እና እነዚያ ኢንዱስትሪዎች ለግሉ ዘርፍ ውድድር ክፍት ይሆናሉ። በአፍሪካ ትልቁ እና ከፍተኛ ትርፋማ የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ ድርጅቶች አክሲዮኖች ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች ሊገዙ ነው ምንም እንኳን መንግስት በእነዚህ ኩባንያዎች ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ መያዙን የሚቀጥል ቢሆንም በዚህ መንገድ ይቀጥላል የኢኮኖሚውን ከፍተኛ ደረጃ መቆጣጠር፣ አነስተኛ ወሳኝ ተብለው በሚገመቱ ዘርፎች የመንግስት ኢንተርፕራይዞች የባቡር ኦፕሬተሮችን፣ ስኳርን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ ሆቴሎችን እና የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶችን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ግል ሊዘዋወሩ ይችላሉ። መንግስት በኢኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር ደረጃ በተመለከተ የርዕዮተ ዓለም ለውጥን ከመወከል በተጨማሪ፣ እርምጃው በ2017 የበጀት ዓመት መጨረሻ ላይ ያለውን የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ክምችት ለማሻሻል ያለመ ተግባራዊ እርምጃ ተደርጎ ታይቷል። ከሁለት ወር በታች ዋጋ ያለው ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች፣ እንዲሁም እያደገ የመጣውን የሉዓላዊ ዕዳ ጫና በማቃለል። እ.ኤ.አ ሰኔ 2018 ዓ.ም አብይ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ከማዘዋወሩ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ስቶክ ልውውጥ ለማቋቋም ያለውን ፍላጎት አስታውቋል። እ.ኤ.አ. በ2015 ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛትም ሆነ በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የአክሲዮን ልውውጥ ሳታገኝ ከዓለም ትልቁ ሀገር ነበረች። የውጭ ፖሊሲ እ.ኤ.አ. በግንቦት 2018 አብይ ሳውዲ አረቢያን ጎበኘ፣የ2017ቱን የሳዑዲ አረቢያ ጽዳት ተከትሎ ለእስር የተዳረጉት ቢሊየነር ስራ ፈጣሪ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን እስረኞች እንዲፈቱ ዋስትና አግኝቷል። እ.ኤ.አ ሰኔ 2018 ከግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ ጋር በካይሮ ተገናኝተው በተናጥል በአዲስ አበባ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና የአማፅያኑ መሪ ሪያክ ማቻር የሰላም ድርድርን ለማበረታታት ሞክረዋል የጅቡቲ እና የወደብ ስምምነት አብይ ስልጣን ከያዙ በኋላ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የባህር በር የሌላትን የኢትዮጵያን የወደብ ተጠቃሚነት የማስፋት ፖሊሲ ተከተለ። ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው ጥቂት ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ መንግስት ከዲፒ ወርልድ ጋር በመተባበር እውቅና በሌለው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ በርበራ ወደብ 19 በመቶ ድርሻ እንደሚወስድ ይፋ ሆነ። እ.ኤ.አ በግንቦት 2018 ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ ላይ ፍትሃዊ ይዞታ እንዲኖራት ከጅቡቲ መንግስት ጋር ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ በወደቡ ልማት እና የወደብ አያያዝ ክፍያ ላይ የበኩሏን ድርሻ እንድትይዝ ያስችላታል። ከሁለት ቀናት በኋላ ተመሳሳይ ስምምነት ከሱዳን መንግስት ጋር ኢትዮጵያ በፖርት ሱዳን የባለቤትነት ድርሻ እንድትኖራት ተፈራረመ። የኢትዮ-ጅቡቲ ስምምነት ለጅቡቲ መንግስት በመንግስት ባለቤትነት የተያዙ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችን እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ ቴሌኮምን በመሳሰሉት ኩባንያዎች ላይ ድርሻ እንዲወስድ አማራጭ ይሰጣል። ይህን ተከትሎም ብዙም ሳይቆይ አብይ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በላሙ ወደብ የኢትዮጵያ ሎጅስቲክስ ተቋም በላሙ ወደብ እና በላሙ-ደቡብ ሱዳን-ኢትዮጵያ ትራንስፖርት ኮሪደር ለመገንባት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ፕሮጀክት. የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት ወደ መደበኛው መቀየሩም ኢትዮጵያ ከኢትዮ-ኤርትራ ግጭት በፊት ዋና ወደቦቿ የነበሩትን የማሳዋ እና አሰብ ወደቦችን መጠቀም እንድትቀጥል እድል ይከፍታል ይህም ለሰሜናዊው ክልል ልዩ ጥቅም ይኖረዋል። ትግራይ። እ.ኤ.አ. ከ1998 ጀምሮ የኢትዮጵያ የባህር ላይ ትራፊክን ከሞላ ጎደል ያስተናገደውን ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል። ኤርትሪያ አብይ ስልጣን እንደተረከበ የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት እንዲቆም ለመደራደር ፈቃደኛ መሆናቸውን ገለፁ። እ.ኤ.አ ሰኔ 2018 በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማስቆም መንግስት አጨቃጫቂውን የድንበር ከተማ ባድሜን ለኤርትራ ለማስረከብ በ2000 የአልጀርሱ ስምምነት መሰረት መስማማቱን ይፋ አድርጓል። በኢትዮጵያና በኤርትራ ጦርነት ወቅት ጦርነቱ ቢያበቃም። ኢትዮጵያ ባድሜን ለኤርትራ እንድትሰጥ የሰጠውን የአለም አቀፍ የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ እስከዚያው ድረስ ውድቅ አድርጋ ነበር፣ በዚህም የተነሳ በሁለቱ መንግስታት መካከል የቀዘቀዘ ግጭት (በሕዝብ ዘንድ “ጦርነት የለም፣ ግን ሰላም የለሽ ፖሊሲ ነው”)። እ.ኤ.አ. ሰኔ 20 ቀን 2010 በተከበረው ብሔራዊ በዓል ላይ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአቢይ የቀረበውን የሰላም ተነሳሽነት ተቀብለው የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንዲልኩ ሀሳብ አቅርበዋል። እ.ኤ.አ. ሰኔ 26 ቀን 2018 የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ መሀመድ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ወደ ኢትዮጵያ ባደረገው የመጀመሪያው የኤርትራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባን ጎብኝተዋል። አብይ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመጋቢት 2019 በአስመራ፣ በጁላይ 8፣ 2018፣ በ2018 የኤርትራ እና ኢትዮጵያ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ከኤርትራ አቻ ጋር የተገናኘው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መሪ ሆነ። በማግስቱ ሁለቱ ውጥረቱ እንዲቆም እና ከሌሎች ጉዳዮች መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን እንደገና ለመመስረት “የሰላም እና የወዳጅነት የጋራ መግለጫ” ተፈራርመዋል። የቀጥታ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ የመንገድ እና የአቪዬሽን ግንኙነቶችን እንደገና መክፈት፤ እና ኢትዮጵያ የማሳዋ እና አሰብ ወደቦችን እንድትጠቀም ማመቻቸት። አቢይ በ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት የተሸለመው ጦርነቱን ለማስቆም ባደረገው ጥረት ነው። በተግባር ግን ስምምነቱ "በአብዛኛው ተግባራዊ ያልሆነ" ተብሎ ተገልጿል. ተቺዎች በሁለቱ ሀገራት መካከል ብዙም ለውጥ አላመጣም ይላሉ። ከኤርትራ ዲያስፖራዎች መካከል፣ በተግባር ብዙም ያልተቀየረ ቢሆንም፣ ከኤርትራ ጋር በተደረገው ስምምነት ላይ በማተኮር ለኖቤል የሰላም ሽልማት ብዙዎች እንደማይቀበሉት ገልጸዋል። እ.ኤ.አ. በጁላይ 2020 የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር “የሰላሙ ስምምነት ከተፈረመ ከሁለት ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሉዓላዊ ግዛታችን ውስጥ መገኘታቸውን ቀጥለዋል፣ የሁለቱም ሀገራት ንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በሚፈለገው መጠንና መጠን አልቀጠለም። የኖቤል የሰላም ሽልማትን የመሻር ጥሪ እ.ኤ.አ. በጥር 2019 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ አምባሳደሮች በተሰበሰቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር በጦርነት ወቅት የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን አስመልክቶ ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል። እ.ኤ.አ. በ1896 በአዱዋ ጦርነት እና በኋላም በኤርትራ ጦርነት ወቅት የወታደሮችን ሚና በመጥቀስ አብይ “ይህ አልተመረመረም ግን ግልጽ ነው። በአጼ ምኒልክ ጊዜ ከአድዋ ጦርነት ጀምሮ እስከ ኋለኞቹ ጦርነቶች ድረስ ብዙ ከመሃል ኢትዮጵያ ኦሮሞዎች፣ አማሮች ወደ ትግራይ ሄደው ለመታገል ቆይተዋል። ከኤርትራ ጋር ለነበረው ጦርነት እዛ ነበሩ እና ትግራይ ውስጥ ለ30 አመታት ወታደራዊ ሰልፉ ነበረ። ስለዚህ ኦሮሞ በትግራይ ያለው ድርሻ ምን ያህል እንደሆነ እያሰቡ ከሆነ ለማወቅ ተዉት። (የታዳሚው ታዳሚዎች) ይህን መናገሩ ስህተት ሊሆን ይችላል፡ ግን፡ ወደ አድዋ ለውጊያ የሄዱት ብቻ ሄደው አልተመለሱም። እያንዳንዳቸው 10 ያህል ልጆች ነበሯቸው። [የታዳሚው ከፍተኛ ሳቅ እና ጭብጨባ]። ጃን ኒሰን እና ባልደረቦቻቸው ይህንን እንደ “ግልጽ እውቅና፣ ወታደራዊ ስልቶችን እና ስትራቴጂን እንደ ማእከላዊ አምድ የሚይዝ፣ በጦርነት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር አጠቃቀምን እንደ ማረጋገጫ” አድርገው ይቆጥሩታል። እ.ኤ.አ ሰኔ 2021 የበርካታ ሀገራት ተወካዮች በትግራይ በተፈፀሙ የጦር ወንጀሎች ምክንያት ለአብይ የኖቤል የሰላም ሽልማት በድጋሚ እንዲታይ ጠይቀዋል። በአንድ ወቅት ዘ ጋርዲያን የተባለው የውጪ ጉዳይ አዘጋጅ ሲሞን ቲስዳል በሰጠው አስተያየት አብይ “በተለየው ክልል ስላደረገው ተግባር የኖቤል የሰላም ሽልማቱን መስጠት አለበት” ሲል ጽፏል። በተባለው የፔቲሽን ድርጅት ውስጥ ያለ ሰው የሰላም ሽልማቱን በመሻር 35,000 ፊርማዎችን ለመሰብሰብ ዘመቻ ከፍቷል። ከሴፕቴምበር 2021 ጀምሮ ወደ 30,000 የሚጠጉ ተገኝተዋል። ግብጽ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ያለው አለመግባባት በሁለቱም ሀገራት ብሔራዊ ስጋት ሆኗል። "ኢትዮጵያን ግድብ ከመስራቷ የሚከለክለው ምንም አይነት ሃይል የለም፣ ጦርነት ካስፈለገ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን እናዘጋጅ ነበር" ሲሉ ዶ/ር አብይ አስጠንቅቀዋል። አክቲቪስቱ፣ ዘፋኙ እና የፖለቲካው ታዋቂው የሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ብጥብጥ ከቀሰቀሰ በኋላ አብይ ፍንጭ የሰጠው ለግድያው ግልፅ የሆነ ተጠርጣሪ እና ግልጽ ምክንያት ሳይኖር፣ ሁንዴሳ በካይሮ ትእዛዝ በሚሰሩ የግብፅ የደህንነት አባላት ተገድሎ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል። ችግር ለመቀስቀስ. አንድ የግብፅ ዲፕሎማት ግብፅ አሁን ካለችበት ውጥረት ጋር ምንም ግንኙነት የላትም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ኢያን ብሬመር በታይም መጽሄት መጣጥፍ ላይ ጠ/ሚኒስትር አብይ "ኢትዮጵያውያንን በጋራ ጠላት ላይ አንድ ለማድረግ የሚያስችል ፍየል እየፈለጉ ሊሆን ይችላል" ሲል ጽፏል። የሃይማኖት ስምምነት ኢትዮጵያ የተለያዩ የሀይማኖት ቡድኖች በዋናነት የክርስቲያን እና የሙስሊም ማህበረሰቦች ሀገር ነች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ የኢትዮጵያ እስልምና ምክር ቤት የሃይማኖትና የአስተዳደር መከፋፈልና ግጭቶች የገጠሟቸው በሃይማኖትና በሃይማኖት መካከል ያሉ ልዩነቶችና ግጭቶች ዋነኛ አሳሳቢ ጉዳዮች ነበሩ። እ.ኤ.አ. በ 2018 በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ያሉ ተቀናቃኞችን በማስታረቅ ላከናወኑት ተግባር በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልዩ "የሰላምና እርቅ" ሽልማት ተሰጥቷቸዋል። የደህንነት ሴክተር ማሻሻያ የጸጥታው ሴክተር ማሻሻያ ሰኔ 2010 ዓ.ም አቢይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦችን ባነጋገረበት ወቅት በፖለቲካ ውስጥ ያለውን ሚና ለመገደብ በማሰብ ሰራዊቱን ውጤታማነቱን እና ሙያዊ ብቃቱን ለማጠናከር ማሻሻያ ለማድረግ እንደሚፈልግ አስታውቋል። ይህ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ማለትም ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ከፍተኛ አወዛጋቢ የሆኑትን እንደ ሊዩ ሃይል ያሉ የክልል ታጣቂዎችን ለመበተን በድጋሚ የቀረበ ጥሪ ተከትሎ ነበር። ይህ እርምጃ አብዛኛውን የወታደራዊ ከፍተኛ አዛዥን ከሚቆጣጠሩት የህወሓት ጠንካራ ሃይሎች ተቃውሞ ሊገጥመው ይችላል ተብሎ ይታሰባል። በተለይም በ1996 ኤርትራ መገንጠልን ተከትሎ በጅቡቲ ከግዛት ውጭ የሚደረግ ጉዞን ተከትሎ የተበተነው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል በመጨረሻ እንዲዋቀር ጥሪ አቅርበዋል "ወደፊት የባህር ሃይላችንን አቅማችንን መገንባት አለብን። ይህ እርምጃ አገሪቱ ከ25 ዓመታት በፊት በባሕር ዳርቻዋ ላይ በደረሰባት ኪሳራ አሁንም ብልህ የሆኑ ብሔርተኞችን እንደሚስብ ተዘግቧል። ኢትዮጵያ በጣና ሀይቅ ላይ የባህር ማሰልጠኛ ተቋም እና የሀገር አቀፍ የባህር ማጓጓዣ መስመር ቀድሞውኑ አላት። እ.ኤ.አ. ሰኔ 7 ቀን 2007 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ የ ዋና ኢታማዦር ሹም ሳሞራ ዮኒስን በሌተናል ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጌታቸው አሰፋን በሌ/ጄኔራል አደም መሐመድ በመተካት ሰፊ የድጋፍ ማሻሻያ አድርጓል። የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪና የቀድሞ የጦር አዛዥ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ከሕወሓት መስራቾች አንዱና የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ስብሃት ነጋ ጡረታ መውጣታቸው ቀደም ሲል በግንቦት ወር ይፋ መደረጉ ይታወሳል። የእጅ ቦምብ ጥቃት ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ድጋፍ ለማሳየት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። አብይ ለተሰበሰበው ህዝብ ንግግር እንደጨረሰ እሳቸውና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ከተቀመጡበት በ17 ሜትር ርቀት ላይ የእጅ ቦምብ ተወርውሮ አረፈ። ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ከ165 በላይ ቆስለዋል። ጥቃቱን ተከትሎም የፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ 9 የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ወዲያው ከስራ የተባረሩ ናቸው። አጥቂዎችን የጫነች የፖሊስ መኪና እንዴት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደተቃረበ እና ወዲያው መኪናው አጥፊ መረጃዎችን እንደበራች የሚሉ ጥያቄዎች ተጠይቀዋል። ከጥቃቱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍንዳታው ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በብሔራዊ ቲቪ ቀርበው ጉዳዩን “ኢትዮጵያን አንድነቷን ለማየት የማይፈልጉ ኃይሎች ያደረጉት ያልተሳካ ሙከራ” ሲሉ ገልጸውታል። በዕለቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎችን ለማግኘት በጥቁር አንበሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል። የካቢኔ ለውጥ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተካሄደው የፓርላማ ስብሰባ፣ በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው የመንግስት ሚኒስትሮች ቁጥር ከ28 ወደ 20 የካቢኔ አባላት ግማሹን የሴት ሚኒስትሮችን ቦታ እንዲይዝ አቢይ ሀሳብ አቅርቧል። በአዲሱ የካቢኔ መዋቅር ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ; የመጀመሪያዋ ሴት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ሙሳ; የአዲሱ የሰላም ሚኒስቴር የመጀመሪያዋ ሴት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና የስለላ ኤጀንሲዎች ኃላፊነት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬስ ሴክሬታሪ ወይዘሮ ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ የበይነመረብ መዘጋት እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች እና ኔትብሎክስ ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንደሚገልጹት፣ አገሪቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ፈጣን ዲጂታላይዜሽንና በሴሉላር የኢንተርኔት ግንኙነት ላይ ብትተማመንም በዐብይ አህመድ መሪነት በፖለቲካ ምክንያት የሚደረጉ የኢንተርኔት መዘጋት በከባድና በከባድ ሁኔታ ተባብሰዋል። እ.ኤ.አ. በ2020 በኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት መዘጋት “በተደጋጋሚ የሚሰማራ” ተብሎ ተገልጿል:: አክሰስ አሁን እንደተናገረው መዝጋት “ባለሥልጣናት ብጥብጥ እና እንቅስቃሴን ለመደበቅ የሚያስችል መሣሪያ” ሆኗል ብሏል። መንግስታቸው ‹ውሃም አየርም አይደለም› እንዳሉት እና መቼ ኢንተርኔት ይቆርጣል። የፖለቲካ ፓርቲ ማሻሻያ እ.ኤ.አ. ህዳር 21 ቀን 2011 የኢህአዴግ ገዢ ጥምረት ከፀደቀ በኋላ፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እና ሌሎች አምስት አጋር ፓርቲዎችን ከመሰረቱት አራቱ ፓርቲዎች ሦስቱን በማዋሃድ ብልጽግና ፓርቲ የተሰኘ አዲስ ፓርቲ ተቋቁሟል። ፓርቲዎቹ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ)፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን)፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ)፣ የሐረሪ ብሄራዊ ሊግ (ሀብሊግ)፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ)፣ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ይገኙበታል። ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ)፣ የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ (ጋህአፓ) እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) አዲስ የተዋሃደ ፓርቲ መርሃ ግብሮች እና መተዳደሪያ ደንቦቹ በመጀመሪያ የጸደቁት በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ነው። "የብልጽግና ፓርቲ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ብዝሃነት እና አስተዋጾ እውቅና የሚሰጥ እውነተኛ ፌዴራላዊ ስርዓትን ለማጠናከር እና ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው" ብለው ያምናሉ። የእርስ በርስ ግጭቶች አወል አሎ በ2018 አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ ሁለት የማይታረቁ እና ፓራዶክሲካል የወደፊት ራዕይ ተፈጥሯል ሲል ይሞግታል። የእነዚህ ርዕዮተ ዓለም እይታዎች ማዕከላዊ የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪካዊ ትርክትን ይቃረናሉ። አቢይ በሀገሪቱ ትልቅ ማሻሻያ አደረገ እና ከህወሀት አባላት ጋር ያለውን ግንኙነት ያበላሻል ተብሎ የሚጠረጠረው የነጻነት እርምጃ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የእርስ በርስ ግጭቶች እና የአብይ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ጊዜ በዝርዝር ይዘረዝራል። የአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ሙከራ እ.ኤ.አ. መኮነን የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ረዳታቸው ሜጀር ጀነራል ግዛቸው አበራ የአማራ ክልል የጸጥታ ሃይል ሃላፊ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌን ወንጀሉን በመምራት ላይ ናቸው ሲል ከሰሰ። እና ፅጌ ሰኔ 24 ቀን በባህር ዳር አካባቢ በፖሊስ በጥይት ተመትተዋል። የመተከል ግጭት እ.ኤ.አ. ከሰኔ 2010 ጀምሮ በኢትዮጵያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተደረገው ጦርነት የጉሙዝ ተወላጆች ሚሊሻዎችን ያሳተፈ ነው ተብሏል። ጉሙዝ እንደ ቡአዲን እና የጉሙዝ ነፃ አውጪ ግንባር የመሳሰሉ ሚሊሻዎችን በማቋቋም ጥቃት ፈጽሟል ተብሏል። እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘገባ ከታህሳስ 22 እስከ 23 ቀን 2020 የጉሙዝ ጥቃት በአማራ፣ በኦሮሞ እና በሺናሻ ላይ የተፈጸመ ሲሆን የጉሙዝ ብሄረተኞች “ሰፋሪ” ብለው ይመለከቷቸዋል። ኦክቶበር 2012 የኢትዮጵያ ግጭቶች እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2019 ኢትዮጵያዊው አክቲቪስት እና የሚዲያ ባለቤት ጃዋር መሀመድ ጥቅምት 23 ቀን ምሽት ላይ በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት የደህንነት ዝርዝሩን በአዲስ አበባ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤቱን ግቢ ለቀው እንዲወጡ ለማድረግ ሞክረዋል ሲል ተናግሯል ስለዚህ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትእዛዝ። ባለፈው ቀን አብይ በፓርላማ ንግግር ሲያደርግ "የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው የሚዲያ ባለቤቶች "በሁለቱም መንገድ እየተጫወቱ ነው" ሲሉ ክስ ሰንዝረው ነበር፤ ይህ ደግሞ ከጃዋር ጋር የተያያዘ ከሆነ ነው። የኢትዮጵያን ሰላምና ህልውና የሚያናጋ... እርምጃ እንወስዳለን። ሀጫሉ ሁንዴሳ አመጽ የኦሮሞ ዘፋኝ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ከጁን 30 እስከ ጁላይ 2 ቀን 2020 በኦሮሚያ ክልል፣ አዲስ አበባ እና ጅማ ላይ ከፍተኛ ብጥብጥ አስከትሏል፣ በሁከቱ ቢያንስ 239 ሰዎች መሞታቸውን የፖሊስ የመጀመሪያ ዘገባ ያሳያል። ማጣቀሻዎች የኢትዮጵያ
11738
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%8A%AD%E1%88%8A%E1%88%89%20%E1%88%80%E1%89%A5%E1%89%B0-%E1%8B%88%E1%88%8D%E1%8B%B5
አክሊሉ ሀብተ-ወልድ
ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰው ሲሆኑ በ ጣልያን ወረራ ጊዜ አምስቱን ዓመት ሙሉ በፓሪስ የኢትዮጵያ ጉዳይ ፈጻሚ፤ በዠኔቭ በዓለም መንግሥታት ማኅበር የኢትዮጵያ ዋና ጸሐፊ ከድል በኋላም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት እና እስከ አብዮት ፍንዳታ ድረስም በዓፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴር ነበሩ። ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ አቃቂ ታስረው ከቆዩ በኋላ ያለፍርድ ኅዳር ቀን ዓ/ም ከስልሳ ሰዎች ጋር በደርግ ተረሽነው ሞቱ። የተማሪነት ዘመናት አክሊሉ መጋቢት ቀን ዓ/ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ቡልጋ ከተወለዱት አለቃ ሀብተወልድ ካብትነህ እና ከወይዘሮ ያደግድጉ ፍልፈሉ ተወልደው የአማርኛ ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው የራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አጠናቀቁ። ከዚያም በዳግማዊ ምኒልክ ትምሕርት ቤት ለሦስት ዓመታት ዘመናዊ ትምሕርት ከተከታተሉ በኋላ በ፲፱፻፲፯ ዓ/ም ወደ እስክንድርያ ትምሕርታቸውን እዚያ በሚገኘው የፈረንሳይ “ሊሴ” ትምህርት ቤት እንዲቀጥሉ በአልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መኮንን ተላኩ። እስክንድርያም እስከ ዓ/ም ከተማሩ በኋላ የሊሴ ትምሕርታቸውን አጠናቀው ለከፍተኛ ትምሕርት ወደ ፓሪስ እና ታዋቂው ሶርቦን ዩኒቨርሲቲ አምርተው የከፍተኛ የንግድ ሕግ እና ሽከታኪን ትምሕርት ጀመሩ። ሶርቦን እስከ ዓ/ም ድረስ ተምረው የመጀመሪያ ሲማክቶ ጉላፕ በሸከታኪን እንዲሁም የ ሲማሕግ ጉላፕ ተመርቀው ወጡ። ወዲያው ፋሽሽት ኢጣልያ ሀገራችንን ይወርና ወጣቱ አክሊሉ ሀብተወልድ ለውድ አገራቸው ነጻነት የአርበኝነት ትግላቸውን በቶፍካ እና በገቢ ሰብሳቢነት እዚያው ፈረንሳይ አገር ተሰማሩ። በዓለም መንግሥታት ማኅበር የኢትዮጵያ ዋና ፀሐፊ በጦርነቱ ዋዜማ ኢትዮጵያ በዓለም መንግሥታት ማኅበር ሸንጎ ጣልያን በግፍ ልትወራት መነሳቷን እና በማኅበሩ ‘የጋራ ደህንነት’ ዋስትና መሠረት አባላት አገሮች መሃል ገብተው ጣልያንን እንዲያስታግሱ በምትከረከርበት ጊዜ አክሊሉ በፈረንሳይ አገር ውስጥ ተማሪ ሆነው ሳሉ ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ትግል በመመልከት ንጉሠ ነገሥቱ፤ በዠኔቭ የኢትዮጵያ ልዑካን መሪ ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም ሥር ዋና ፀሐፊ አደረጓቸው። ፊታውራሪው ያንጊዜ በፈረንሳይ፣ በብሪታንያ እና በዠኔቭ የኢትዮጵያ ዋና ልዑክ ነበሩ። ጦርነቱ በይፋ ከመጀመሩ በፊት ወደዠኔቭ እየሄዱ በኢትዮጵያ ስም ከጣልያን ጋር በዓለም መንግሥታት ማኅበር ሸንጎ ይሟገቱ የነበሩት እነዚህ ሁለቱ ስዎች ነበሩ። ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ወደአገራቸው ሲመለሱና ብላቴንጌታ ወልደ ማርያም በፓሪስ የኢትዮጵያ አምባሳዶር ሲሆኑ አክሊሉ የ”ፕሬስ አታሼ” ሆነው እንዲሠሩ ንጉሠ ነገሥቱ ቢያዟቸውም አምባሳደሩ “እምቢ ብለው አላስገባም አሉኝ። ቢሆንም እውጭ ሆቴል ቁጭ ብዬ እንደፕሬስ አታሼ ሆኜ ሥሠራ ነበር።” መስከረም ቀን ዓ/ም ለደርግ የምርመራ ኮሚሽን ‘ዓለም በቃኝ’ እስር ቤት ሆነው በላኩት የታሪክ ማስተወሻተው) የሚሉን አክሊሉ ሀብተወልድ በዚሁ ሥራ አፈ ቀላጤ ሆነው ለጋዜጠኞች ማብራሪያ እና ቃለ ምልልስ በመስጠት የኢትዮጵያን አቋም እና የተሰነዘረባትን ግፈኛ ድርጊት ማስተዋወቃቸውን ቀጠሉ። ለመሆኑ ብላቴንጌታ ወልደ ማርያም ለምን ይሆን አክሊሉን አላስገባም ያሉት። ምናልባት ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ “ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ሁለተኛ መጽሐፍ” በተባለው መጽሐፋቸው ላይ “በፓሪስ የኛ ሚኒስቴር የነበረው ብላቴንጌታ ወልደማርያም አየለ እኛን ከድቶ ለጣልያኖች በገባ ጊዜ በዓለም መንግሥታት ማኅበር የኢትዮጵያ ጸሐፊ አቶ አክሊሉ ሀብተወልድ በፓሪስ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ አገልግሎናል።” ብለው ያሠፈሩት ምክንያቱን ይጠቁም ይሆናል። በወቅቱ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበረው ፒዬር ላቫል እና የብሪታንያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሙኤል ሆር በ ታኅሣሥ ወር ዓ/ም በምስጢር ዶልተው አዘጋጅተውት የነበረውን፤ ኢትዮጵያን የሚበልጠውን አገር (ሐረርን፣ ሲዳሞን፣ ባሌን) ለጣልያን ሰጥታ ጎጃምን፣ ጎንደርን እና ትግሬን አስቀርታ ተጣልያን ጋር እንድትታረቅ የሚደነግገውን የ”ሆር-ላቫል” ስምምነት የሚባለውን ለጃንሆይ መስጠታቸው ሲሰማ አክሊሉ ሀብተወልድ ማዳም ታቡዴስ ለምትባለው የ”ራዲካል ፓርቲ” ጋዜጣ ኃላፊ ለነበረችው ታዋቂ ጋዜጠኛ በምስጢር ይገልጹላትና እሷ ሎንዶን ላይ በጋዜጣና በራዲዮ ይፋ አደረገችው። ጉዳዩ በብሪታንያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትልቅ ውዝግብና ሙግት ተደርጎበት ሆርም ምክር ቤቱን ይቅርታ እንዲጠይቅና ስምምነቱም እንዲወድቅ አድርጎታል። የጠላት ዘመን በሚያዝያ ወር ዓ/ም መደምደሚያ የፈረንሳይ የሕግ አውጪዎች ምክር ቤት አባላት ምርጫ በሚካሄድበት ጊዜ ወጣቱ አክሊሉ ለሦስቱ ዋና ፓርቲዎች የወቅቱ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንስቴር የነበሩት ፒዬር ላቫል ሙሶሊኒን ለማስደሰት ሲል ኢትዮጵያን በመሸጥ “የጋራ ደህንነት” የተባለውን የዓለም ጸጥታው ምክር ቤትን ዓላማ ማድከሙን፤ የኢትዮጵያ አቤቱታ እንዳይታይ እያደረገ እንደነ ሙሶሊኒና ሂትለርን እንዳበራታ በዚህም የዓለም ጦርነትን እንዲፋጠን ማድረጉን በዝርዝር ማስረዳትና ለፓርቲዎቹም የላቫልን መንግሥት ለመገልበጥ መሣሪያ መስጠት ለኢትዮጵያ ታላቅ ጥቅም እንደሚሰጥ በመገንዘብ በነዚህ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብሰባ እየተገኙ የኢትዮጵያን እሮሮ ማሰማት ጀመሩ። የፈረንሳይም ጋዜጦች እነኚህን ስብሰባዎች በሚዘግቡ ጊዜ የአክሊሉ ሀብተወልድን ንግግርም ጨምረው ሲያትሙ ሀገራቸው የደረሰባትን የግፍ ወረራ ለመላው የፈረንሳይ ሕዝብ ሲያስተዋውቁ ቆዩ። አዲስ የተመረጠውን የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊዮን ብሎምን አነጋግረው ፈረንሳይ የሙሶሊኒ ፋሽሽት ኢጣልያ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ያላትን ይዞታ መቼም ቢሆን እንደማያውቅ አረጋግጦላቸዋል። ወዲያው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በስደት ወደብሪታንያ ሲመጡ አክሊሉም በዚያው በፓሪስ የኢትዮጵያ ጉዳይ ፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆዩ። መስከረም ቀን ዓ/ም ለደርግ የምርመራ ኮሚሽን ‘ዓለም በቃኝ’ እስር ቤት ሆነው በላኩት የታሪክ ማስተወሻተው እንደነገሩን፤ “በ፲፱፻፴ ዓ/ም የእንግሊዝ ንጉሥና ንግሥት በግብዣ ለጉብኝት ፓሪስ በመጡ ጊዜ ተሌሎች አምባሳደሮች ጋር እኔም ተጠርቼ ሄጄ ነበር። በፕሮቶኮሉ ደንብ የኢትዮጵያና የጣልያን ጉዳይ ፈጻሚዎች አቀማመጣቸው ጎን ለጎን ስለነበር አጠገቡ በምሆንበት ጊዜያት ጣልያኑ በጣም ሲቆጣ እኔም ኃይለኛ ቃል ስለተናገርኩት ጠቡን ሁሉም ሰምተው የፕሮቶኮሉ ሹም በመካከላችን የሌላ አገር ጉዳይ ፈጻሚ አስቀመጠ።” ይላሉ በወቅቱ ጣልያኖች በኢትዮጵያ ላይ “ኋላቀር፤ ባርያ ሻጭ፤ አውሬዎች…. የኛ ተልዕኮ ኢትዮጵያን ማሰልጠን ነው….” እያሉ ፕሮፓጋዳቸውን ያዛምቱ ስለነበር የፈረንሳይ ሕዝብ ስሜቱን ለኛ ስሞታውን ወደነሱ አዙሮ ነበር። ይሄንን በዘለቄታማና ስኬታማ መንገድ ለመከላከል አክሊሉ (ሀ) ከልዩ ልዩ ጋዜጮች ጋር በመገናኘት እውነቱን በማስረዳት (ለ) ተነ ሙሴ ጃንጉል (በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሥር የፈረንሳይኛ ጋዜጣ ያቋቋመ) እና ከሌሎች ፈረንሳዮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን የሚረዱ ሁለት ኮሚቴዎች እና በማቋቋምና በነዚህ ኮሚቴዎች በኩል የኢትዮጵያን ጉዳይ በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ ፈረንሳዮች በማሰራጨት የሕዝብ ዕርዳታ ለማስገኘት ችለዋል። (ሐ) በነዚሁ ኮሚቴዎች ዕርዳታና መሥራችነት የኢትዮጵያን አቋምና የጣልያንን ግፍ በየጊዜው የሚያስረዳ “ኑቬል ደ ኤትዮፒ” (የኢትዮጵያ ዜና) የሚባል ጋዜጣ ተመሠርቶ እሳቸውም በየጊዜው በጋዜጣው ይጽፉ ነበር። ከድል በኋላ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲያከትም የተሸናፊዎቹን የጀርመንን እና የጣልያንን ይዞታ፤ የካሳ ጉዳይ እና በድል ጊዜ ከጣልያን ወደ እንግሊዝ አስተዳደር ተላልፈው የነበሩትን የኤርትራን እና የኦጋዴንን ጉዳይ ለመወሰን በየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሪነት “የሰላም ጉባዔ” በሚካሄድበት ጊዜ አቶ አክሊሉ ሀብተወልድ መጀመሪያ በፓሪሱ ጉባዔ በታዛቢነት በመጨረሻም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተመሠረተበት በሳን ፍራንሲስኮ ከተማ የኢትዮጵያን ልዑካን በመምራት ተሳትፈዋል። አክሊሉ ሀብተወልድን ትልቅ የዲፕሎማሲ ሰው መሆናቸውንና በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረኮች ለኢትዮጵያ ብዙ መታገላቸውን የሚያስመሰክርላቸው ዘመን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካከተመበት ጊዜ ጀምሮ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ በኅብረታዊ መንግሥት የመዋሐድ ጉዳይ እስከተፈረመበት ኅዳር ወር ዓ/ም ድረስ የነበረው ዘመን ነው። አክሊሉ በእንግሊዝና በኢጣሊያ ተሸንሽና የነበርቸውን አገራቸውን ረጅም ዓመት የፈጀ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በማድረግ አንድ ያደረጉ ታላቅ ዲፕሎማት እንደነበሩ ስለሳቸው ብዙም የተጻፈ መረጃ ማግኘት ቢያስቸግርም በአምባሳደር ዘውዴ ረታ የተጻፈው ‘የኤርትራ ጉዳይ’ የተባለው መጽሐፍ ስለኚህ ሰው ታላቅ ተጋድሎ በሰፊው ተዘርዝሮ ይገኛል አምባሳዶር ዘውዴ የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተው በዓለም መድረክ ላይ ይካሄድ ስለነበረው ትግል ሲጽፉ በዚያን ጊዜ በአካባቢ ቡድን ብዛት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃይል የነበራቸው የላቲን አሜሪካ አገሮች የጣልያን ወገን በመሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩን አክሊሉ ሀብተወልድን እጅግ በጣም ቢያናድዷቸው የተከተለውን ትንቢታዊ ንግግር ከማኅበሩ መድረክ ላይ አደርጉ፦ «በዚህ አጋጣሚ ለባልደረቦቼ የላቲን አሜሪካ አገሮች ተወካዮች፣ በተለይም ለአርጀንቲናው ልዑክ እጅግ በጣም ከባድ ፋይዳ ስላለው ጉዳይ የማስተላልፈው መልዕክት አለኝ። ዛሬ አገሬ ከግብጽ እና ከላይቤሪያ ጋር ሆና እናንተ ከጣልያን ጋር በማደም የአፍሪቃን ሕዝቦች ለመጨቆን የምትጫወቱትን ሚና በጥንቃቄ እየተመለከትን ነው። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ግን እዚህ ያለነው ሦስት አፍሪቃውያን አገሮች በአስር እጥፍ በዝተን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ተገቢ መቀመጫችንን እንይዛለን። ያን ጊዜ እኛ እንደናንተ ሳይሆን፣ ለዓለም ሰላም ድጋፍ እና ፍትሐዊ ፍርድ ድምጻችንን እንደምናሰማ ጥርጣሬ የለኝም።» ሲሉ ስሜታዊ ንግግራቸውን አሰምተዋል። እውነትም ይሄንን በተናገሩ በአሥር ዐመታት ውስጥ አፍሪቃውያን አገሮች በማኅበሩ ውስጥ ትልቁ አኅጉራዊ ቡድን ለመሆን በቁ። ረዥሙ የስደት ዘመን ተጠናቀቀ በ፲፱፻፲፯ ዓ/ም መጀመሪያ ለትምሕርት ከአገራቸው፣ ከትምሕርታቸውም በኋላ በጣልያን የግፍ ወረራ ምክንያት አምስቱን ዓመታት አውሮፓ ቆይተው በተቻላቸውና በተሰጣቸውም መመሪያ ስለአገራቸው ሲታገሉ የኖሩት አክሊሉ፤ ከጠላትም ድል መደረግ በኋላ የሳቸው ዲፕሎማሲያዊ የትግል ሥራ እስከሚገባደድ ድረስ በድካም፤ በጭንቀት እና በህመምም ለብዙ ዓመታት በፓሪስ እና ኒው ዮርክ የኖሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጥቂት የሥራ ጋደኞቻቸው ጋር በ፲፱፻፵፬ ዓ/ም ወደናፈቋት አገራቸው ተመለሱ። የኤርትራን ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስፈጽመው የተመለሱትን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገራቸው ሕዝብ በተለይም ኤርትራውያን በጣም ሞቅ ባለ ሁኔታ ተቀበሏቸው። ቀደም ብሎ ንጉሠ ነገሥቱ፣ እቴጌ መነን፣ ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣ አቶ ይልማ ደሬሳ እና የወለጋ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ የነበሩት ደጃዝማች መኮንን ደስታ የደስታ ቴሌግራም ተልኮላቸው ነበር። ሆኖም ንጉሠ ነገሥቱ መስከረም ቀን ዓ/ም የኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር በኅብረት መንግሥት መዋሐድ አስመልክተው ባደረጉት ንግግር አንዳንድ ኤርትራውያንን በስም ጠርተው ሲያመሰግኑ፤ ለዚህ ውጤት እጅግ ከፍ ያለ ትግል ያካሄዱትንና ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ መስዋዕትነትን ላበረከቱት አክሊሉ ሀብተወልድ ግን በሕዝብ ፊት ምስጋና ያለማቅረባቸው ያሳዝናል። በሚያዝያ ወር ዓ/ም የአክሊሉ ዋና ደጋፊ የነበሩት እና እስከዚያ ጊዜ ድረስ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ትልቅ ሥልጣን እና በንጉሠ ነገሥቱም ታማኝነትና ተሰሚነት የነበራቸው ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ትክክለኛ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከዚህ ቁልፍ ቦታ ተነስተው መጀመሪያ የአሩሲ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ ቀጥሎም የጋሙ ጎፋ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳድሪ ተደርጉ። አምባሳዶር ዘውዴ ረታ በመጽሐፋቸው ስለዚህ ጉዳይ ሲያወሱ፣ የኤርትራ ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚካሄድበት ጊዜ አክሊሉ ሀብተወልድ የብሪታንያን የኤርትራ አቋም ነቅፈው በመዝለፋቸው የንጉሠ ነገሥቱ የግል ፀሐፊ የነበሩት እና የብሪታንያ ደጋፊ የሚባሉት አቶ ተፈራ ወርቅ (በኋላ ፀሐፊ ትዕዛዝ) ‘የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አክሊሉ ለብሪታንያ ይቅርታ ይጠይቅ ሲሉ ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ግን ያደረገው አግባብ ነው ይቅርታ መጠየቅ የለበትም በሚል ጉዳይ ተከራክረዋል ሲሉን የፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ከሥልጣን መወገድ ምክንያት ዕውን ይሄ ይሆን ወይ? ሊያስብለን ይችላል። ባህሩ ዘውዴ ደግሞ 1855-1991) በተባለው መጽሐፉ ላይ የፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ከሥልጣን መወገድ ዋና ምክኛት የነበሩት የግል ምስጢራዊ የስለላ ድር የዳበሩት እና በዚህም የሚያገኙትን መረጃዎች ለንጉሠ ነገሥቱ በማካፈል ይወደዱ የነበሩት የአክሊሉ ታላቅ ወንድም መኮንን ሀብተወልድ ናቸው ይለናል። እንዴት የፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ የመውደቅ ምክንያት እንደሆኑ ባያብራራልንም ምናልባት በዚሁ የምስጢራዊ ስለላ ድራቸው ‘ትልቅ ምስጢር አግኝተውባቸው ይሆን? ለማለት ያበቃናል። ትክክለኛ ምክንያቱ ይህም ይሁን ያ፣ የፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ መወገድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አቶ አክሊሉን ግን ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር የሚያቀራርበውን በፀሀፊ ትዕዛዝ ማዕረግ የፅህፈት ሚኒስቴርና እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርነትን አፍርቶላቸዋል። የታኅሣሥ ግርግር በክብር ዘበኛ ሠራዊት አዛዥ ጄነራል መንግሥቱ ንዋይ እና በታናሽ ወንድማቸው አቶ ገርማሜ ንዋይ የተጸነሰሰውና ታኅሣሥ ቀን ዓ/ም ተጀምሮ ዓርብ ታኅሣሥ ቀን አሥራ አምስት መኳንንት፣ ሚኒስቴሮች እና የጦር መኮንኖች መረሸን ያከተመው የታኅሣሥ ግርግር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ፣ ለፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ በታላቅ ወንድማቸው አቶ መኮንን ሀብተወልድ መገደል ትልቅ የግል ሀዘን ላይ ቢጥላቸውም፤ በጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት ይመሩ የነበሩት የራስ አበበ አረጋይ በአመጸኞቹ እጅ መገደል ለሳቸው የጠላይ ሚኒስቴርነቱን ማዕርግ እና ሥልጣን አስገኝቶላቸዋል። በጠቅላይ ሚኒስቴርነት እና በፅሕፈት ሚኒስቴርነት በጥምር ሲያገለግሉ ዘመናዊውንና ጥንታዊውን ሥልጣናት በጃቸው በማግባት ለንጉሠ ነገሥቱ ቀርበው በተሰሚነት አብዮቱ እስከፈነዳ ድረስ ሠሩ። የአብዮት ፍንዳታ በ፲፱፻፷፭ ዓ/ም የተቀጣጠለው አብዮታዊ ሽብር በተማሪዎች ሰልፍ፣ የወታደሮች እንቅስቃሴ እንዲሁም የዓለምን ዱኛ ያናጋው የነዳጅ ማዕቀብ ሲለኮሱ የደርግ ሥልጣንም እየጎለመሰ መጣ። ወታደሮቹም መኮንኖችን ብቻ ሳይሆን የ መንግሥት ባለሥልጣናትንም ጭምር የማሠር ስልጣን እንደሚኖራቸው ንጉሠ ነገሥቱን አሳመኑ። በየካቲት ወር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አክሊሉ ሀብተወልድ ከነ ሚኒስቴሮቻቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ። ‘ተንፏቃቂው አብዮት’ ወዲያው ተተክተው የተሾሙትንም አዲስ ጠቅላይ ሚኒስቴር ልጅ እንዳልካቸው መኮንንም ከሥልጣን አውርዶ ከነ አክሊሉ ሀብተወልድ ጋር ከርቸሌ ከከተተ በኋላ መስከረም ቀን ዓ/ም ባለቤቱን እራሳቸውን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ከሥልጣን አወረደ። ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ከንጉሠ ነገሥቱ አዝማድ እና ቤተሰቦች፤ መሳፍንት እና መኳንንት፤ ባለሥልጣናትና ወታደራዊ መኮንኖች ጋር በእስራት ከቆዩ በኋላ ያለክስም ያለፍርድ በኅዳር ወር ዓ/ም በተወለዱ በ ስድሳ ሦስት ዓመታቸው ከስልሳ ሰዎች ጋር ተረሽነው ሞቱ። የአክሊሉ ሀብተወልድ ጥቅሶች "የደረሰው ይድረስ ደካማ ሆኜ መታየት አልፈልግም የሀገሬን ጥቅምና መብት የሚነካ መስሎ ከታየኝ መናገሬን አልተውም "…ሀገሬ ኢትዮጵያ በዓለም ሸንጎ ላይ ፍርድ ተነፍጓት ስታዝን የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።…..ኢትዮጵያ ያለፉት ታሪኮቿ በትክክል እንዳስረዱት፤ለነፃነቷና ለመንቷ፤በኮሎኒያሊስቶች ጣሊአን ጋር በየጊዜዉ ስተዋጋ፤ያሸነፈችዉ ብቻዋን ነዉ። የተጠቃቺዉም ብቻዋን ስለሆነ፤አገሬ መቸዉንም ለሚደርስባት አደጋ ከማንም እርዳታ አገኛለሁ ብላ አትጠብቅም።ዛሬም ሆነ ነፃነቷን ለመጠበቅ፤ታሪኳን ለማስከበር አስፈላጊዉን ዝግጅት ማድረግ ያለባት፤እሷ ራሷ ብቻ ነች።…" “በዚህ አጋጣሚ ለባልደረቦቼ የላቲን አሜሪካ አገሮች ተወካዮች፣ በተለይም ለአርጀንቲናው ልዑክ እጅግ በጣም ከባድ ፋይዳ ስላለው ጉዳይ የማስተላልፈው መልዕክት አለኝ። ዛሬ አገሬ ከግብጽ እና ከላይቤሪያ ጋር ሆና እናንተ ከጣልያን ጋር በማደም የአፍሪቃን ሕዝቦች ለመጨቆን የምትጫወቱትን ሚና በጥንቃቄ እየተመለከትን ነው። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ግን እዚህ ያለነው ሦስት አፍሪቃውያን አገሮች በአስር እጥፍ በዝተን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ተገቢ መቀመጫችንን እንይዛለን። ያን ጊዜ እኛ እንደናንተ ሳይሆን፣ ለዓለም ሰላም ድጋፍ እና ፍትሐዊ ፍርድ ድምጻችንን እንደምናሰማ ጥርጣሬ የለኝም።” ማመዛገቢያ ዋቢ ምንጮች ጦብያ መጽሔት ፪ኛ ዓመት ቁጥር መስከረም ዓ/ም (እንግሊዝኛ) (1941-1963) (እንግሊዝኛ) 1855-1991), (2001) የኢትዮጵያ ካቢኔ አባላት
48361
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%98%E1%88%98%E1%8A%90%20%E1%88%85%E1%8B%B3%E1%88%B4
ዘመነ ህዳሴ
ዘመነ ህዳሴ ረኔሳንስ በተለይ በአውሮፓ ታሪክ እንደሚወሰን ከ1445 እስከ 1640 ዓም ድረስ ያህል ያለው ጊዜ ነው። በተለይ በዚህ ዘመን የተከሠተው የሥነ ጥበብ ተሃድሶ ማለት ነው። ይህም ቁስጥንጥንያ ለኦቶማን ቱርኮች ከወደቀበት ዓመት ከ1445 ዓም ጀምሮ አካባቢ ይቆጠራል። በዚያን ጊዜ ቢዛንታይን መንግሥት ስለ ወደቀ የአውሮፓ ሥነ ጥበብ ማዕከል ወደ ጣልያን ሊዛወር ጀመረ። ከዚህም በኋላ የሥነ ጥበብ «ዘመነ ህዳሴ» ከጣልያን ወደ ሌሎቹ አውሮፓ አገራት ይስፋፋ ነበር። «የፕሮቴስታንት ተሃድሶ» ንቅናቄ ደግሞ በዚህ ዘመን ያህል ውስጥ (ከ1509 እስከ 1640 ዓም ድረስ) ተከሠተ። በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ ከመካከለኛው ዘመን ወደ ዘመናዊነት የተሸጋገረበት እና የ 15 ኛውን እና 16 ኛውን ክፍለ ዘመን የሚሸፍንበት ወቅት ነው እሱም የጥንታዊ ጥንታዊ ሀሳቦችን እና ግኝቶችን ለማነቃቃትና ለመብለጥ በሚደረገው ጥረት ይታወቃል። የተከሰተው ከመካከለኛው ዘመን መጨረሻ ቀውስ በኋላ እና ከትልቅ ማህበራዊ ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው. ከመደበኛው ወቅታዊነት በተጨማሪ የ"ረዥም ህዳሴ" ደጋፊዎች በ 14 ኛው ክፍለ ዘመን እና መጨረሻውን በ 17 ኛው ክፍለ ዘመን ያስቀመጡት ይሆናል. ባህላዊው አመለካከት በይበልጥ የሚያተኩረው በህዳሴው ቀደምት ዘመናዊ ገፅታዎች ላይ ነው እና ካለፈው ጊዜ የራቀ ነው በማለት ይከራከራሉ፣ ነገር ግን ዛሬ ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎች በመካከለኛው ዘመን ገፅታው ላይ ያተኩራሉ እና የመካከለኛው ዘመን ማራዘሚያ ነበር ብለው ይከራከራሉ። ሆኖም የዘመኑ ጅምር የ15ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ህዳሴ እና የጣሊያን ፕሮቶ-ህዳሴ ከ1250 ወይም 1300 አካባቢ ከኋለኛው መካከለኛው ዘመን፣ በተለምዶ እስከ ሲ. 1250-1500፣ እና የመካከለኛው ዘመን እራሳቸው እንደ ዘመናዊው ዘመን ባሉ ቀስ በቀስ ለውጦች የተሞላ ረጅም ጊዜ ነበሩ። እና በሁለቱም መካከል እንደ መሸጋገሪያ ጊዜ፣ ህዳሴ ከሁለቱም ጋር ተመሳሳይነት አለው፣ በተለይም የሁለቱም የመጨረሻ እና የመጀመሪያ ንዑስ ወቅቶች። የህዳሴው ምሁራዊ መሰረት ከሮማን ሰብአዊታስ ጽንሰ-ሀሳብ የተገኘ እና "ሰው የሁሉም ነገር መለኪያ ነው" ከሚለው እንደ ፕሮታጎራስ ያለ የጥንታዊ የግሪክ ፍልስፍና እንደገና የተገኘ የሰብአዊነት ስሪት ነው። ይህ አዲስ አስተሳሰብ በኪነጥበብ፣ በሥነ ሕንፃ፣ በፖለቲካ፣ በሳይንስ እና በሥነ ጽሑፍ ውስጥ ተገለጠ። ቀደምት ምሳሌዎች በዘይት ሥዕል ላይ የአመለካከት እድገት እና ኮንክሪት እንዴት መሥራት እንደሚቻል እንደገና መታደስ ናቸው። ምንም እንኳን የብረት ተንቀሳቃሽ ዓይነት መፈልሰፍ ከ 15 ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ሀሳቦችን ለማሰራጨት ቢያፋጥንም የሕዳሴው ለውጦች በመላው አውሮፓ አንድ ወጥ አልነበሩም የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች በጣሊያን በ 13 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ታይተዋል በተለይም በዳንቴ ጽሑፎች። እና የጊዮቶ ሥዕሎች። እንደ ባህላዊ እንቅስቃሴ ህዳሴው የላቲን እና የቋንቋ ሥነ-ጽሑፍ ፈጠራዎችን ያቀፈ ነበር በ 14 ኛው ክፍለ ዘመን በጥንታዊ ምንጮች ላይ የተመሠረተ የመማር ትንሳኤ ጀምሮ በዘመኑ የነበሩት ለፔትራች ይመሰክራሉ በሥዕል ውስጥ የበለጠ ተፈጥሯዊ እውነታን የመስመራዊ እይታ እና ሌሎች ዘዴዎችን ማዳበር; እና ቀስ በቀስ ግን ሰፊ የትምህርት ማሻሻያ። በፖለቲካ ውስጥ ህዳሴ ለዲፕሎማሲ ልማዶች እና ስምምነቶች እድገት አስተዋጽኦ አድርጓል በሳይንስ ደግሞ በታዛቢነት እና በመረጃ አመክንዮ ላይ የበለጠ ጥገኛ እንዲኖር አድርጓል። ምንም እንኳን ህዳሴ በብዙ ምሁራዊ እና ማህበራዊ ሳይንሳዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አብዮቶች ቢያዩም እንዲሁም ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት እና የሂሳብ አያያዝ መስክ ምናልባት በሥነ-ጥበባዊ እድገቶቹ እና እንደ ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ እና ማይክል አንጄሎ ባሉ ፖሊማቶች አስተዋፅዎ ይታወቃል። "የህዳሴ ሰው" የሚለውን ቃል አነሳስቷል. ህዳሴ የጀመረው ከብዙዎቹ የኢጣሊያ ግዛቶች አንዷ በሆነችው በፍሎረንስ ነው። በጊዜው የፍሎረንስን ማህበራዊ እና ህዝባዊ ባህሪያትን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ላይ በማተኮር ስለ አመጣጡ እና ባህሪያቱ የተለያዩ ንድፈ ሀሳቦች ቀርበዋል-የፖለቲካ አወቃቀሯ የበላይ ቤተሰቡ ፣የሜዲቺ እና የግሪክ ፍልሰት። የቁስጥንጥንያ የኦቶማን ቱርኮች ውድቀትን ተከትሎ ወደ ኢጣሊያ የመጡ ምሁራን እና ጽሑፎቻቸው። ሌሎች ዋና ዋና ማዕከላት ቬኒስ፣ ጄኖዋ፣ ሚላን፣ ሮም በህዳሴው ፓፓሲ እና ኔፕልስ ነበሩ። ከጣሊያን ጀምሮ ህዳሴ በመላው አውሮፓ በፍላንደርዝ፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታኒያ፣ አየርላንድ፣ ስፔን፣ ፖርቱጋል፣ ጀርመን፣ ፖላንድ፣ ሃንጋሪ (ከኔፕልስ ቢያትሪስ ጋር) እና ሌሎችም ተስፋፋ። የህዳሴው ዘመን ረጅምና ውስብስብ የሆነ የታሪክ አጻጻፍ አለው፤ ከአጠቃላይ የልዩነት ጊዜያዊ ጥርጣሬዎች ጋር ተያይዞ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የ‹‹ሕዳሴ›› ክብርና የግለሰብ የባህል ጀግኖች ‹‹የሕዳሴ ሰዎች›› በማለት ምላሽ በሚሰጡ የታሪክ ተመራማሪዎች መካከል ብዙ ክርክር ተካሂዷል። የህዳሴ ጥቅም እንደ ቃል እና እንደ ታሪካዊ መግለጫ። አንዳንድ ታዛቢዎች ህዳሴ ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ የተፈጠረ የባህል “ግስጋሴ” ነው ወይ የሚለውን ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ሲሆን ይልቁንም ዘመኑን ለጥንታዊው ዘመን አፍራሽነት እና ናፍቆት ያዩታል፣ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ የታሪክ ተመራማሪዎች በተለይም የሎንጌ ዱሬዬ በምትኩ ላይ ያተኩራሉ። በሁለቱ ዘመናት መካከል ያለው ቀጣይነት, ተያያዥነት ያላቸው, ፓንፍስኪ እንደተመለከተው, "በሺህ ትስስር". ሪናሲታ ('ዳግም መወለድ') የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ በጆርጂዮ ቫሳሪ የአርቲስቶች ህይወት 1550) ላይ ታየ፣ በ1830ዎቹ ውስጥ እንደ ህዳሴ ተብሎ ተጠርቷል። ቃሉ እንደ ካሮሊንግያን ህዳሴ (8ኛው እና 9ኛው ክፍለ ዘመን)፣ የኦቶኒያ ህዳሴ (10ኛው እና 11ኛው ክፍለ ዘመን) እና የ12ኛው ክፍለ ዘመን ህዳሴ ላሉ ሌሎች ታሪካዊ እና ባህላዊ እንቅስቃሴዎችም ተዘርግቷል። የአውሮፓ
35140
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9B%E1%8B%A8%E1%88%81%20%E1%89%B4%E1%8B%8E%E1%8B%B5%E1%88%AE%E1%88%B5
ዓለማየሁ ቴዎድሮስ
ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የ ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የወይዘሮ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ ነበር። በ1860 ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት ጦርነት ልጃቸው ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝ ሀገር ተወስዶ ነበር፡፡ በዛሬው የኛ አምዳችንም የዚህን ልዑል ባዕድ ሀገር ኑሮ ልናስቃኛችሁ ወደድን፡፡ ልዑል አለማየሁ ሚያዚያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም በደብተረ ታቦር ከተማ ነበር ውልደቱ፡፡ በልዑሉ ውልደት የተደሰቱት አፄ ቴዎድሮስም በእለቱ መድፍ ያስተኮሱ ሲሆን 500 ያህል እስረኞችንም ፈትተዋል፡፡ ከልዑሉ ጋር ሲጫወቱ መዋል አፄውን እጅግ የሚያስደስት ነገር ነበር፡፡ ተናደው እና ተበሳጭተው ከነበር እንኳን አለማየሁን ታቅፈው ሲስሙ ንዴታቸው ይበርድ ነበር ይባላል፡፡ ልዑል አለማየሁ እንግሊዞች እጅ ከገባ ቡሀላ ከእድሜው ለጋነት የተነሳ የሚጠብቀው እና የሚንከባከበው ሰው ሊኖር ግድ ነበር፡፡ ይህንን የተረዳው ጀነራል ናፔር ካፕቴን ስፒዲ የተባለን ሰው የአለማየሁ ጠባቂ እንዲሆን መደበው፡ ምክንያቱ ደግሞ ካፕቴኑ የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገሩ ነበር፡፡ በተጨማሪም አለቃ ዝርዓት እና አቶ ገብረመድህን የተባሉ ሁለት ኢትዮጵዊያን ሞዚቶች እና አጫዋቾች¬ ተመረጡለት፡፡ አለማየሁ ከጠባቂው ስፒዲ ጋር ፌሬዝ በተባለችው መርከብ ተሳፍሮ በ1860 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ አቀና፡፡ በመርከቢቱ ላይ በነበራቸውም ቆይታ ስፒዲ እና አለማሁ እጅግ የጠበቀ ወዳጅነትን መስርተው ነበር፡፡ ስፒዲ በሄደበት ቦታ ሁሉ አለማየሁን ማስከተል ያዘወትር ነበር፡፡ ይህንን የሁለቱን ፍቅር ያየው ጀነራል ናፒየርም ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ይልቁንም የአለማየሁን ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ካፕቴን ስፒዲ እንዲረከብ ስለወሰነ ሁለቱ ሞግዚቶች ጉዞው ተጠናቆ እንግሊዝ ሀገር ሳይደርሱ ከስዊዝ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ፡፡ ምንም እንኳን የእንግሊዛውያኑ የታሪክ ድርሳናት ይህንን ቢሉም ልዑሉ ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹን በተባለው መጠን አምርሮ ይጠላቸው እና ባያቸውም ቁጥር በብስጭት ያለቅስ እንደነበር ማረጋገጫ የለንም፡፡ ከሶስት ወራት የመክረብ ላይ ጉዞ በኃላ አለማየሁ እንግሊዝ ሀገር ደረሰ፡፡ እዛ አንደደረሰም የወቅቱ የእንግሊዝ ንግስት ከነበረችው ንግስት ቪክቶሪያ ጋር ተገናኘ፡፡ ንግስቲቱም ልዑሉ የፈለገው እና ያሻው ይደረግለት ዘንድ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡ ልዑሉ በመቀደላ የነበረውን እልቂት በመጠኑም ቢሆን በማየቱ እና የአባቱ እና የእናቱ ተከታታይ ሞትም በልጅ አዕምሮው ሊቀበለው ከሚችው በላይ ስለነበር እጅግ ታውኮ እንደነበር በተደጋጋሚ ተፅፎ እናገኛለን፡፡ አንድ እንግሊዝ ሀገር ውስጥ በሚገኝ ሙዚየም ውስጥ ባለ የንግስት ቪክቶሪያ የእለት ማስወሻ ላይም ንግስቲቱ፡ “ምስኪኑ ልጅ አሁንም ፍርሀቱ አለቀቀውም፡፡ መቅደላ የነበረው እልቂት እና የአባቱን ሞት ስላየ ያ ነገር በአዕምሮው ይመጣበታል፡፡ የሚል ቃል ፅፋ እናገኛለን፡፡ ልዑሉ እንግሊዝ ሀገር ከደረሰ በኃላ ጠባቂው የነበረው ካፕቴን ስፒዲ የእንግሊዘኛ ቋንቋን ያስተምረው ጀመር፡ ንግስቲቱም የልዑሉን ሁኔታ በቅርበት ትከታተል ነበር፡፡ ስፒዲ ልጁን እንዳይጎዳው በማሰብም በስፒዲ ላይ የልዑሉን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተል ተቆጣጣሪ አስቀምጠውበት ነበር ይባላል፡፡ አንድ ግዜ ንግስት ቪክቶሪያ ስለ ልዑሉ በእለት ውሎ መመዝገቢያዋ ላይ ከመዘገበችው መሀል “ልጁ ጨዋ እና ውብ ልጅ ነው፡፡ ኬክ መብላት ደግሞ ይወዳል፡ የሰጠሁትንም ኬክ ሁሉ ጨርሶ በላ፡፡” የሚል አረፍተ ነገር ተፅፎ እናገኛለን፡፡ ንግስቲቱ በተደጋጋሚ ለዚህ እናት ለሌለው ልጅ እናቱ እኔ ነኝ ስትል ትደመጣለች፡፡ ለልዑሉም የተለየ አክብሮት እና ፍቅር ልዩ ትኩረትም እንደነበራት ድርሳናት ዘግበውታል፡፡ ምንም እንኳን ከንግስቲቱ ጋር የነበራቸው ወዳጅነት ከግዜ ወደ ግዜ እየበረታ ቢመጣም ከሀገሩ ሲወጣ አብሮት የነበረውን ካፕቴን ስፒዲን ግን ለአፍታም አልዘነጋውም ነበር፡፡ በየትኘውም ስፍራ ሲሄድ ስፒዲ አብሮት እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ ግብዣም ሲሄድ ሆነ ከልዑላን ልጆች ጋር እንዲጫወት ሲጋበዝ ስፒዲን ትቶ መሄድ አይሆንለትም፡ ቤተ-መንግስት ሲገባ እንኳን ስፒዲን አስከትሎ ነው፡፡ ስፒዲ እና አለማየሁ አብረው ይበላሉ አብረውም ደግሞ ይተኛሉ፡፡ አለማየሁን ለብቻው ማሳደግ የከበደው ስፒዲ ልጁን በማሳደግ ትረዳው ዘንድ ሚስት ለማግባት ወሰነ፡፡ ከዛም ወ/ሮ ኮታንን አገኘ እና አገባት፡፡ አለማየሁ እና ወ/ሮ ኮታንም ለመዋደድ ግዜ አልወሰደባቸውም ነበር፡፡ በ1861 ዓ.ም ስፒዲ ህንድ ሀገር በምትገኝ አንዲት ከተማ አዛዥ ሆኖ ስለተሾመ የ8 ዓመቱን አለማየሁን እና ሚስቱን ይዞ ወደዛው አቀና፡፡ በሄዱበት ሀገርም አለማየሁ ትምህርቱን መከታተሉን ቀጥሎ የነበረ ሲሆን ከመደበኛው ትምህርት በዘለለም ፈረስ ግልቢያ እና ሌሎች ስፖርቶችንም ያዘወትር ነበር፡፡ ልዑሉ በዚህ አይነት ከቆየ በኃላ ቻንስለር ሮበርት ሉዊ ልዑሉ የቀለም ትምህርት ላይ ከሚያዘወትር ይልቅ የወታደር ትምህርት ቤት ገብቶ የፈረስ ውትድርናን እንዲማር መደረግ አለበት ሲሉ ያቀረቡት ሀሳብ የልዑሉን ህይወት እስከወዲያኛው የለወጠ ነበር፡፡ ይህም ሀሳብ ተቀባይነትን ስላገኘ አለማየሁን ከስፒዲ ነጥሎ በመንግስት ቁጥጥር ስር ለማድረግ እና የውትድርና ትምህርቱን እንዲከታተል ተወሰነ፡፡ ይህ ውሳኔ ግን ለአለማየሁም ሆነ ለስፒዲ ከባድ ግዜ ነበር፡፡ ስፒዲ እና ሚስቱ አለማየሁን ላለመስጠት ከባድ ትግልን አደረጉ፡፡ ነገር ግን ትግላቸው ውጤትን አላስገኘላቸውም፡፡ ይልቁኑም አለማየሁ ወደ እንግሊዝ ሀገር እንዲመለስ ተወሰነ፡፡ ስፒዲም አለማየሁን ይዞ ወደ እንግሊዝ መጣ፡፡ የአለማየሁ አዲሱ አስተማሪ እና ጠባቂ እንዲሁኑ የተመረጡትም በአስተማሪነታቸው የተመሰከረላቸው እና በደግነታቸው የታወቁት ቄስ ብሌክ ነበሩ፡፡ ንግስት ቪክቶሪያም የአለማየሁን እና የስፒዲን ፍቅር ያውቁ ስለነበር ሁለቱን ቶሎ መነጣጠል አልፈለጉም፡፡ ይልቁኑም አለማየሁ ከቄስ ብሌክ ጋር እስኪላመድ ድረስ ስፒዲ አብሮት ይቆይ ስትል ፈቀደች፡፡ አዲሶቹ የአለማየሁ ጠባቂዎች አለማየሁ ስራ እንዲሰራ ወሰኑ፡፡ በወጣለትም ፈረቃ መሰረት በሳምንት ለ 31 ሰዓት ተኩል ያህል ማንኛውንም አይነት ስራ እንዲሰራ ተወሰነ፡ የስፒዲ ሚስትም ይህንን በመቃወም ጠባቂው ለነበሩት በቢዶልፍ ደብዳቤ ላከች፡፡ ቢዶልፍም ለሉዊ አለማየሁ አንዳንድ ግዜ እየሄደ ከስፒዲ ሚስት ጋር ግዜ እንዲያሳልፍ ሲሉ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ በትዕዛዙም መሰረት የስፒዲ ሚስት ከአለማየሁ ጋር እንድትውል ተፈቀደላት፡፡ ሚስቱም አብራ ውላ ያየችውን እንዲህ ስትል በደብዳቤ ገልጣለች፡ “ማደጉን ቁመቱ አድጓል፡፡ መልኩ ግን ገርጥቷል፡፡ አካላቱም ከስቷል፡፡ ዝምተኛ እና ጭምትም ሆኗል፡፡ ከወንዶች ልጆች ጋር እንዳይገናኝ እና ከእኩዮቹም ጋር እንዳይገናኝ ተደርጓል፡ ውጪ እየወጣም እንዳይዘል ታግዷል፡፡ እየደጋገመም ‘አብረውኝ የሚጫወቱ ልጆች አጣሁ፡፡ ቅዳሜ እና እሁድ ብቻ ከሁለት ልጆች ጋር አንድጫወት ይፈቀድልኛል፡፡ ሊያጫውቱኝ የሚመጡትም እነዚህ ልጆች ሁልግዜ እነሱ ብቻ በመሆናቸው ተሰላችተናል፡፡ በሌላ ቀን ግን የሌሎች ልጆችን እጅ አንኳን ጨብጬ አላውቅም’ ብሎኛል፡ ይህንን የመሰሉት ነገሮች ያበሳጩታል፡፡ እኔም ብሆን ይህን የሚበሳጭበትን ጉዳይ ለማስተው ጓደኛ ልፈጥርለት አልቻልኩም፡፡ እየደጋገመ የነገረኝም ‘ወንዶች ልጆች እፈልጋለሁ፡፡ የበለጠ እንድንዛመድም እፈልጋለሁ’ እያለ ነው፡፡ በምግብ አበላሉ በኩልስ እንዴት ነህ ብዬ ብጠይቀው ‘ምግብ አሁን አይበላልኝም፡፡ ምክንያቱም ውጪ ወጥቼ ስለማልዛለል እና ስለማልጫወት አይርበኝም፡፡ የምበላው በትንሹ ነው’ ብሎ መለሰልኝ፡፡ እኔ እንደማስበው አለማየሁ ደስተኛ እና በሚደረግለት የረካ ልጅ አይደለም፡፡” የስፒዲ ሚስት የፃፈችው ይህ ደብዳቤ ከንግስት ቪክቶሪያ ዘንድ ደረሰ፡፡ ንግስቲቱም ትንሹ ልዑል አብሮአቸው ሊጫወት የሚችሉ ጓደኞች እንዲፈለጉለት አዘዘች፡፡ እንደተባለውም ተደረገ፡፡ 1867 ዓ.ም አለማየሁ ወደ ራግቢ ትምህርት ቤት ተዛወረ፡ በዚህም ከቄስ ብሌክ ቤት ወጥቶ ወደ ሊው ዋርነር ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በዚህ ግን ደስተኛ ስላልነበር በቀጣዩ አመት ሚስተር ድራፐር ቤት እንዲኖር ተደረገ፡፡ ቄስ ብሌክም ካዩት የልዑሉ ባህሪ በመነሳት ልዑሉ ወታደርነት ላይ ቢያተኩር የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ተናገሩ፡፡ በዚህም ንግግር መሰረት የወታደር ትምህርት ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በአንድ ወቅት አለማየሁ ወደ ሊድስ በመሄድ በሰር ራምሰን ቤት ተቀምጦ በነበረበት ወቅት በመርዝ ተመረዘ። መርዙ ህዳር 5 ቀን 1872 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3 ሰዓት ከሩብ በተወለደ በ19 ዓመቱ ከዚህ አለም እንዲሰናት አደረገው፡፡ አስከሬኑም ዊንድሶር ባለው የነገስታት መቀበርያ በክብር አረፈ፡፡ በመቃብሩም ላይ “የሀበሻው ልዑል አለማየሁ” የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበት እስካሁን በእንግሊዝ ሀገር ይገኛል፡፡ አጼ
52840
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B5%E1%8D%93%E1%8B%AD%E1%88%A9%E1%88%8A%E1%8A%93
ስፓይሩሊና
የስፓይሩሊና ምንነትና ጥቅሞች ስፓይሩሊና ምንድነው? ስፓይሩሊና የሚለው ስም የተወሰደው ከላቲን ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ቀጭን ጥምዝምዝ ማለት ነው፡፡ ስፓይሩሊና በዋነኛነት ከሁለት የሲያኖባክቴሪያ ዓይነቴዎች ማለትም ከአርትሮስፒራ ፕላተንሲስና አርትሮስፒራ ማክሲማ የሚዘጋጁ የሰው ምግብና የእንስሳት ተጨማሪ ምግቦች የሚታወቁበት ስም ነው፡፡ ሌሎች የአርትሮስፒራ ዓይነቴዎች በስፓይሩሊና ዝርያ ስር ተመድበው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተደረገ ስምምነት ሁለቱም (ስፓይሩሊናና አርትሮስፒራ) ልዩነት ያላቸው ዝርያዎች በመሆናቸው፣ ለምግብነት ጥቅም ላይ የሚውሉት ዓይነቴዎች በአርትሮስፒራ ስር እንዲጠቃለሉ ሆነዋል፡፡ ይሁን እንጂ ትክክለኛም ባይሆን ስፓይሩሊና የሚለው ስም ይበልጥ ታዋቂነት አለው፡፡ አርትሮስፒራ ስፓይሩሊና በመባል ለምግብነት በገበያ የዋሉ የሲያኖባክቴሪያ ዝርያዎችን ይይዛል ማለት ነው፡፡ አርትሮስፒራ ግራም ኔጌቲቭ፣ ሰማያዊ-አረንጓዴ፣ የፀሀይ ብርሃንንና ካርቦንዳይኦክሳይድን እንዲሁም ከኢ-ኢርጋኒክ ውህዶች ኤሌክትሮንን የሚጠቀሙ፣ ቀጫጭን፣ እንድና ከአንድ በላይ የተያያዙ ህዋሳት ያሏቸው፤ በብዙ ወይም በጥቂቱ ጥምዝ የሆኑ የሲያኖባክቴሪያ ዝርያ ናቸው፡፡ የተለያየ የርዝመት መጠን (ከ100-200 ማይክሮን) እና ከ8-10 ማይክሮን የሚደርስ ስፋት አላቸው፡፡ አርትሮስፒራን ከሌሎች ሲያኖባክቴሪያ የተለየ የሚያደርገው የሚኖርበት ስርዓተ ምህዳር ሲሆ ይኸውም ደቂቅ አካሉ በጣም ማእድን በበዛበት፣ ጨዋማና ሞቃት ውሃ መባዛቱ/ማደጉ ነው፡፡ ሌሎች ህይወት ያላቸው አካላት በዚህ አይነቱ ስርዓተ ምህዳር ለመኖር ይከብዳቸዋል፡፡ በዚህ ስርዓተ ምህዳር የሚኖረው አርትሮስፒራ ሌሎችን የሚያስወግድበት መንገድ፡ አርትሮስፒራ የሚኖርበት ስፍራ ያለውን ሶዳ ጨው(ካርቦኔትና ባይካርቦኔት) በመመገብ የውሃውን ጨዋማነት ከፍ ስለሚያደርግ (እስከ 12.5 ፒኤች ስለሚያደርሰው) የአርትሮስፒራ ጥምዝምዞች ደማቅ ቀለማማና በአብዛኛው በውሃ ላይ የሚንሳፈፉ በመኖናቸውና በብቃት የፀሀይ ብርሃንን ስሚከላከሉ፣ ሌሎች ዋቅላሚዎች እንዳይኖሩ ያደርጋሉ፡፡ መቼ ታወቀ? በመጀመሪያ የታወቀው በ1940 (እኤአ) ዴንጊርድ በተባለ ፈረንሳዊ ፋይኮሎጂስት ሲሆን ለጥናቱ መነሻ የሆነውን ናሙና ያገኘው ክሪች ከተባለና በመካከለኛው አፍሪካ በዛሬዋ ቻድ አጠገብ በነበረ በፈረንሳይ ሰራዊት ውስጥ በፋርማሲስትነት ከሚሰራ ጓደኛው ነበር፡፡ ክሪች በአካባቢው የገበያ ስፍራ በትናንሽ ብሽኩጽ መልክ የሚሸጠውን ደረቅ የባክቴሪያ ጥፍጥፍ አግኝቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ ስለአርትሮስፒራ ፕላተንሲስ ሳይታወቅ 25 ዓመታት ያለፈ ሲሆን እንደገናም ወደ እውቅና የመጣው ጄ.ሌዎናርድ በተባለው ቤልጄማዊ ቦታኒስት ነው፡፡ ለእውቅና መነሻ የሆነውም በቻድ ሀይቅ አካባባ ያሉት ካኔምቡዎች በየመንደሩ ባሉ የሜዳ ላይ ገበያዎች ሰማያዊ-አረንጓዴ ከኬኮችን ለሽያጭ ማቅረባቸው ነበር፡፡ የት ይገኛል? አርትሮስፒራ ፐላተንሲስ የተበለው ዓይነቴ በአፍሪካ፣ በእስያ በደቡብ አሜሪካ የሚገኝ ሲሆ አርትሮስፒራ ማክሲማ ደግሞ በመካከለኛው አሜሪካ ይገኛል፡፡ አርትሮስፒራ ፕላተንሲስ ጥልቅ ባልሆ ጨዋማ ጉድጓዶችና በሶዳ ሃይቆች የፒኤች መጠኑ ከ9-11 በሚደርስና 38.3 ግራም በሊት በሆነ በጣም ከፍተኛ ጨውነት ባለው፣ አብዛኞቹ አካላት ሲኖሩ በማይችሉበት ቦታ ተደላድሎ ይኖራል፡፡ የእሳተገሞራ አፈር አካል የሆኑት ሶድየም ካርቦኔትና ባይካርቦኔት የተባሉት ዋነኛዎቹ የጨዋማነት ማዕድኖች ናቸው፡፡ ከብርሃናዊ አስተፃምሮ አንፃር ደግሞ አርትሮስፒራ ፕላተንሲስ በሚያስደንቅ ሁኔታ ከፍተኛ የኦክሲጅን መጠን አምራች በመሆን ይታወቃል፡፡ ይጠቅማልን? የሰው ልጅ ሰውነት የሚፈልገውን ሁሉ በተሟላ ሁኔታ ሊሰጥ የሚችል አንድም ፍራፍሬ፣ ቅጠላቅጠል ወይም የስጋ አይነት የለም፡፡ ስፓይሩሊና ግን ይህን ያሟላል፡፡ ስፓይሩሊና እስከአሁን ከታወቁት ምግቦች ይልቅ እጅግ የበለፀገ ነው፡፡ ስፓይሩሊና በ9ኛው ክፍለ ዘመን በቻድ በነበረው የካኔምብ ግዛት እንኳን ይታወቅ ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ የደረቀና በኬክ መልክ የተዘጋጀ አልፎም በሽያጭ የሚቀርበውን “ዲሄ” የሚባለውን በየቀኑ ለምግብነት ይጠቀማሉ፡፡ ዲሄ በትናንሽ ሃይቆ ወይም ጉድጓዶች ላይ የሚንሳፈፍን የአርትሮስፒራ ፕላተንሲስ ግግር በመልምና በማድረቅ ተቆራርጦም ለሽያጭ ይቀርባል፡፡ በተመሳሳይ በ16ኛው ክፍለዘመን በሜክሲኮ ይኖሩ የነበሩ አዚቴክሶች ከቴኮኮ ሃይቅ በመልቀም ስፓይሩሊናን ለምግብነት ይጠቀሙት እንደነበር ይነገራል፡፡ ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠር የዓለም ህዝብ ስፓይሩሊናን ይመገባል፡፡ የሰው ልጅ ሰውነት ለመኖር ከሚያስፈልጉት ንፁህ አየርና ውሃ ባሻገር አስፈላጊ የሆኑ የንጥረ ምግብ ዓይነቶች ይፈልጋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ደግሞ በተሟላ ሁኔታ በስፓይሩሊና ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የንጥረ ምግብ ዓይነቶች ገንቢ/ጠጋኝ፣ ሀይልና ሙቀት ሰጪ፣ ቫይታሚን መዕድናት፣ ኤንዛይምና የሰውነት ቀለም ንጥሮች ናቸው፡፡ ስፓይሩሊና ያለውን የጤና ጥቅም ስናይ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን፣ ካንሰርን፣ በደቂቅ አካላት አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችንና ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡ ከነዚህም ባሻገር በደም ውስጥ ያለ የስብ መጠንን፣ የስኳር በሽታን፣ የአይን፣ የደምግፊት በሽታን ለመቆጣጠርና የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ እንዲሁም ቁስልን ለማዳን ይጠቅማል፡፡ እንዴት ጥቅም ላይ ይውላል? ስፓይሩሊና በዱቄት፣ በእንክብል፣ በኬክ፣ በብስኩትና በጁስ መልክ እየተዘጋጀ ለሰው ልጅ በዋነ ምግብነትና በተጨማሪ ምግብነት ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ለአሳ፣ ለዶሮና ለሌሎች በተጨማሪ ምግብነት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የስፓይሩሊና ምርት ውዳቂም ተመራጭ የሆነውን ባዮፕላስቲክ ለማምረት
49963
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%B3%E1%88%AA%E1%8B%8E%E1%88%B5%20%E1%88%9E%E1%8B%B2
ዳሪዎስ ሞዲ
ከፐርሺያ የሚሳብ የዘር ግንድ ያላቸው በዜግነት እንግሊዛዊ በትውልድ ሕንዳዊ አባቱና ከኢትዮጵያዊት እናቱ በአዲስ አበባ ከተማ ራስ መኰንን ድልድይ አካባቢ በ1938 ዓ.ም.የተወለደው ዳርዮስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ነበር፡፡ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ትምህርቱን መከታተል ቢጀምርም በወቅቱ በነበረው የተማሪዎች ንቅናቄ ሳቢያ የቅርብ ጓደኛውና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት የነበረው ጥላሁን ግዛው መገደልን ተከትሎ ትምሕርቱን አቋርጦ ወጣ፥ በመካነየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሥር የነበረውና በዓለም ሉተራን ፌዴሬሽን በሚረዳው የዘመኑ ታዋቂ የሬዲዮ ጣቢያ ብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ በ1964 ዓ.ም. በመቀጠር ጣቢያውን ደርግ እስከ ወረሰበት ጊዜ ድረስ ሠርቷል፡፡ ድኅረ አብዮት በአብዮታዊት ኢትዮጵያ ድምፅና በብሔራዊ ሬዲዮ እስከ 1980ዎቹ መገባደጃ ድረስ በዜና አንባቢነት፣ በፕሮግራም አዘጋጅነት የሠራ ሲሆን፣ ጡረታ እስከወጣበት 1994 ዓ.ም. ድረስ ያገለገለው በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የውጭ ቋንቋ ዴስክ ነበር፡፡ የሚለውን ቃል ሕዝብ ሊረዳው በሚችለው ቃል በራሱ መንገድ ተርጉሞ "ቅስመ ተፈጥሮ መከላከያ ሰባሪ በሽታ" ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ሕዝብን ስለ በሽታው ያስተማረውም ይሄው ሙያተኛ ነበር፥ ለዚህ ውለታው ግን ሽልማት ቀርቶ ምሥጋና ሊደርሠው ቀርቶ ይብሱን "ያልተገቡ ቃላትን በመጠቀም" በሚል ከደመወዙ ሠማንያ ብር ተቀጥቷል። የሚባሉትን ያለ ተፈጥሯዊ የግንኙነት መንገድ በጽንሳቸው ልጅ የሚታቀፉ (ማሕጸን የሚያከራዩ ሴቶች) ጉዲፈቻ የሚል ኦሮሚፋ ቃል እና ጽንስ የሚለውን በማዋሃድ "ጽንሰ-ፈቻ" ብሎ የሰየመውም ዳርዮስ ነበር። ዳርዮስ ከቀደሙ የሙያ አባቶቹ አሃዱ ሳቡሬ፡ አሠፋ ይርጉ ብዙ እንደተማረ በዚህም ለንደን ሳይሆን ሎንዶን፡ ዋሺንግተን ሳይሆን ዋሽንግቶን ብሎ በመዘገብም ይታወቅ ነበር። ጋዜጠኛው ከሙያ አባቶቹ ያገኘውን ለራሱ ሳያስቀር ለተተኪዎቹ በማስተማር ብንያም ከበደ፡ ነጋሽ መሃመድ፡ ብርቱኳን ሐረገወይን፡ ሳምሶን ማሞ ዓይነቶቹን ሙያተኞች ምሳሌ ሆኗቸዋል። ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ ሠኔ 13 ቀን 2007 በ68 ዓመቱ ሕይወቱ አልፏል፥ ዳርዮስ ሞዲ ባለትዳርና የሠባት ልጆች አባትም ነበር። ሠኔ 14 ቀን ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት በፈረንሳይ ጉራራ ጊዮርጊስ ቤተክርሥትያን የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ሲፈጸም የሙያ ልጁ ጋዜጠኛና የማስታወቂያ ባለሙያ ብንያም ከበደ እንዲህ የሕይወት ታሪኩን አንብቦታል፡- “ጋሽ ዳሪዮስ ጋዜጠኛ ብቻ ሳይሆን የጋዜጠኞች አባትም ነበረ። ይሄ ታሪክ ብቻ ሊሆን ይችላል። ነበር ቅርብ ነው። ነበር እያልን ዳርዮስን ብቻ ሳይሆን ሙያውንም አብረን እንቅበረው። በፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ፎቶ ቤት ሞሪስ እልቪስን የከፈቱት የሚስተር ሞዲ ጉስታቭ ልጅ ነው፤ ዳሪዮስ ሞዲ። በትውልድ ፐርሺያዊ በዜግነት እንግሊዛዊ ከሆኑት ከሚስተር ጉስታቭ እና ከወ/ሮ አማረች መኩሪያ ታህሳስ 12 ቀን 1939 ዓ.ም እዚያው ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ ተወለደ። የድርሰትና የግጥም ዝንባሌ የነበረው ዳሪዮስ ሞዲ ማንበብ፣ ሁኔታዎችን በጥልቀት ማስተዋልና መመርመር የጀመረው ከልጅነቱ ጀምሮ ነው። በኢትዮጵያ ስር ነቀል ለውጥ እንዲመጣ ሲታገሉ ከነበሩት ተማሪዎች በተለይም ከጥላሁን ግዛው ጋር ለአንድ አላማ ተሰልፈው በእውቀት ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ላይ ቢቆይም የጥላሁን ግዛውን መገደል ተከትሎ ድርጊቱን በፅኑ ካወገዙት አስር ጓደኞቹ ጋር የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ጥሎ ወጥቷል። ዘመኑም 1962 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ በነበረው መንግሥት አመለካከቱ ያልተወደደለት ዳሪዮስ፣ ድፍን ሁለት ዓመት ሙሉ ስራ የሚቀጥረው አላገኘም ነበር። ይሁንና በግሉ የትርጉም ስራዎችን ይሰራ ስለነበር በ1964 ዓ.ም በብስራት ወንጌል ራዲዮ ጣቢያ ለመቀጠር ምክንያት ሆነው። ህይወቱ መስመር ያዘ፡- በመልካም ፀባይ እና ባህሪዋ የቁንጅና ጣሪያ ከሆነችው መሰረት ኃይሌ /መሳይ/ ጋር ትዳር መሰረተ። ትዳሩም ፀንቶ አራት ወንድ ልጆችን እና ሶስት ሴት ልጆችን አፈራ። ዳሪዮስ ሞዲ ለሬዲዮ የተፈጠረ ምሉዕ በኩልዔ የሆነ ጋዜጠኛ ነበረ። ተስምቶ የማይጠገብ፣ እያነበበ የሚስረቀረቅ የሬዲዮ ሞገድን የሚገዛ ባለግርማ ድምፅ የታደለው ዳሪዮስ ሞዲ፣ ከዜና ባህሪው ተነስቶ አነባነቡን የሚከተል እንከን አልባም ዜና አንባቢ ነበር። መንግሥታት በተለዋወጡ ቁጥር የሚሉት ጎልቶ ይደመጥላቸው ዘንድ የሚዲያው ልሳንና የድምፅ ሞገድ ዳሪዮስ ነበር። እንደየጊዜው የአዳዲስ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ድልድይ ድምፅ ሆኖም አገልግሏል። እስከ ዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ ሚዲያ ስራ ውስጥ እንደ ዳሪዮስ አይነት የትርጉም ጌታ አልተገኘም። ዳሪዮስ ዘንድ በይመስለኛል እና ይሆናል በሚል አቻ ትርጉም አይገኝም። የቀደምት አባቶቹን መዝገብ እየፈተሸ፣ ለዘመናዊው አለምም እንዲስማማ የራሱንም የትርጉም መንገድ እየፈለገ የሚማስን የቃላት ዲታ እና ታላቅ ሙያተኛ ነበር። የራሱን ትርጉም የሕዝብ ቋንቋ ማድረግ የቻለ፣ የቋንቋ ምሁራንም ደግመው ደጋግመው የሚመሰክሩለት የትርጉም መምህር ነበር። አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጣሊያኒኛ የመተርጎም ብቃት የመነጨው ካልተቋረጠ የንባብ ብቃቱ ነው። ስራው ላይ እንዳቀረቀረ እስከወዲያኛው ያንቀላፋው ይህ ሰው በቁሙ አስታውሶ፣ ሙያዊ ልቀቱን መዝኖ መሸለም ባልተለመደበት ሀገር እንደዋዛ ኖሮ ማለፉን ለምናውቅ ለኛ የእግር እሳት ነው። በብስራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያ የጀመረው የሬዲዮ ጋዜጠኝነት ሕይወቱ በኢትዮጵያ ሬዲዮ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለ30 ዓመታት ቢቀጥልም ይከፈለው የነበረው ደሞዝ የሰውየውን አስደናቂ ችሎታና የሙያ ልቀት የሚመጥን ቀርቶ ለወር አስቤዛ የማይበቃ ነበር። እንዲህም ሆኖ ህይወት ለዳሪዮስ ሬዲዮ ነው። ጡረታም ወጥቶ የናፈቀውን ሬዲዮ ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን በሸገር እና በሬዲዮ ፋና ቀጥሎበት ቆይቷል። ዳሪዮስ ሞዲ ወር ጠብቆ ከሚያገኘው ከሶስት አሃዝ ባልበለጠ ደሞዝ ራሱን እና ቤተሰቡን ለማስተዳደር ቢቸገርም ያን ወርቃማ ድምፁን ግን ለማስታወቂያ ለማዋል፣ ማስታወቂያ ሊሰራበት ግን ፈቃደኛ አልነበረም። ዜና ላይ የሚሰማ ድምፅ እንዴት ሆኖ ሸቀጥ ይተዋወቅበታል ሲል ይሞግታል። ይህ በራሱ የሙያውን ሥነ-ምግባር መጣስ ነው ሲል ለሙያው መርህ እና ልዕልና አጥብቆ ይከራከራል። የመጨረሻዎቹ ሶስት ዓመታት ለዳሪዮስ ጥሩ አልነበሩም። ለዘመናት ማልዶ ከስራው ገበታው የማይታጣው ዳሪዮስ ህመም ደጋገመው። እንደ ልብ መተንፈስ ተሳነው። በኦክሲጅን እየተረዳ ቆየ። ዳሪዮስ የልብ ትርታው ቀጥ የምትል የምትመስለው ኦክሲጅን ሲያጣ ብቻ አልነበረም። ካላነበበና ዜና ካልሰማ እስትንፋሱ ያለ አይመስለውም። ጋሽ ዳሪዮስ ሰውን ቶሎ የማይቀርብና ከቀረበም የእድሜ ልክ እውነተኛ ወዳጅ የሚሆን፣ ትሁት ደግ እና እውቀቱን ያለ ስስት የሚሰጥ ታማኝ ሰው ነበር። እንደው በቀዝቃዛው በክረምቱ ሰሞን እንከተላለን አንድ ጎበዝ ቀድሞን አይ ጉድ መፈጠር ለመሰነባበት ዳሪዮስን መቼም ማንም አይደርስበት ሮጥን ሮጥን የትም አልደረስንም ማን ይከተለዋል ውድ ዳርዮስን ብለን ለመሰነባበት ከእግዚአብሔር አስገራሚ ስራ አንዱን እንደ ማሳረጊያ እንይ። ለ43 ዓመታት ከጎኑ ያልተለየችው፣ ለትዳሯም ለልጆቿም ህልውና የደከመችው፣ ልጆቿ እንኳን አይተዋት ስሟ ሲጠራ የሚንሰፈሰፉላት መሳይ፣ ልክ የዛሬ አራት ወር ከሁለት ቀናት ታማ አርብ እለት ሆስፒታል ገባች። ዳሪዮስም ለመጨረሻ ጊዜ ሆስፒታል የገባው በዕለተ አርብ ነበር። አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ከሌሊቱ 11 ሰዓት በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ባለትዳሮቹ ነፍሳቸው ተለየች። ልክ እንደዛሬው በዚህ ስፍራ መሳይን ሸኘናት። ዳሪዮስ ተከተላት። አርብ፣ ቅዳሜ እሁድ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይህችን አለም ተለዩ።” መደብ :የኢትዮጵያ
12916
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8B%95%E1%89%A5%E1%88%AB%E1%8B%8D%E1%8B%AB%E1%8A%95%20%E1%89%B3%E1%88%AA%E1%8A%AD
የዕብራውያን ታሪክ
በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የዕብራውያን ታሪክ በዔቦር ተወላጅ በአብርሃም (መጀመርያ አብራም ተብሎ) ይጀምራል። ከአብርሃም እስከ ሙሴ እንደ ብሉይና ሐዲስ ኪዳን አቆጣጠር አብርሃም (አብራም) ለአዳም ፳፩ኛ ትውልድ ነው። የተወለደውም ከአርፋክስድ ወገን በከለዳውያን ከተማ በከላውዴዎን ዑር ነው። ኦሪት ዘፍጥረት 11፡31 እንደሚለው፣ ይህ አብራም ከአባቱ ከታራ ቤተሠብ ጋራ ከዑር ተነሥተው ወደ ከነዓን ይሄዱ ዘንድ በካራን አገር ተቀመጡ። ስለዚህ ዑርና ካራን የተለያዩ ቦታዎች ናቸው። የከለዳውያን ዑር የሚባለው ስፍራ በአርፋክስድ ርስት ሲሆን፣ አብርሃም የደረሰበት ሥፍራ ካራን ግን በአራም ርስት በፓዳን-አራም ወይም አራም-ናሓራይም (አራም በሁለቱ ወንዞች መካከል ወይም መስጴጦምያ) ተገኘ። አብርሃም በዚህ ስፍራ በልማድም በዝምድናም ተሳስሮ አብሮ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር ተገለጠለትና እንዲህ ሲል አዘዘው። «ካገርህ ውጣ፤ ከዘመዶችህም ካባትህም ቤት ተለይ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ፤ ታላቅም ሕዝብ አደርግኻለሁ። ለበረከትም ትሆናለህ» (ዘፍ፡ ም፡ ቁ፡ ይህ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት ምናልባት 2119 ዓመት ግድም ነው። እንግዲህ አብርሃም በአንዱ እግዚአብሔር በቻ ለማምለክና እሱና ዘሩ ለእግዚአብሔር የተመረጡ እንዲሆኑ የተጠራበት ዘመን ነበር። ከዚህም ዘመን አስቀድሞ፣ ኦሪት ዘፍጥረትና መጽሐፈ ኩፋሌ እንደሚተርኩት፣ አሕዛብ ሁሉ እንደየኖኅ ልጆች ወገኖች ከባቢሎን ግንብ ሥፍራ ከሰናዖር ወደየአገራቸው ተበትነው ነበር። የካም ልጅ ከነዓን ግን የኩፋሌ ውላቸውን ፈርሶ ወደ ማዶ ባሕር በመርከብ ለመጓዝ ፈቃደኛ ሳይሆን በአርፋክስድ (በሴም) ርስት ተቀመጠና በልጁ ሲዶና ስም ከተማ ሠራ። በዚያው ዘመን አሕዛብ ሁሉ በስኅተት ተመርተው ወደ ጣኦት ቢዞሩም በከነዓን የተነሡት ሕዝቦች ልማድ በተለይ እግዚአብሔርን እንዳስጠላው ይላል። አብርሃም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ታዘዘ ከወገኖቹ ከከለዳውያን ተለይቶ ቤተሰቡን ይዞ ወንድሙን ሎጥን፤ ከነቤተሰቡ አስከትሎ ወደ ከነዓን አገር (ዛሬ ኢየሩሳሌም ወይም ፓለስቲን ወደሚባለው) ሄዶ ተቀመጠ። በዚያም ሲኖር ከሸመገለ በኋላ ይስሐቅን ከሚስቱ ከሳራ፤ እስማኤልን ከገረዱ ከአጋር ወለደ። ነገር ግን ከገረዱ የተወለደው ወደ ፊት ለአብርሃምና ለዘሩ የተመደበውን አገርና ዕድል አይወርስም ተብሎ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ እስማኤልን ከነናቱ አስወጥቶ ወደ ፋራን በረሓ (ዐረብ) ሰደዳቸው። ዛሬ እስላሞች ሁሉ ዓረቦች በእስማኤል በኩል የአብርሃም ልጆችና ወራሾች ናቸው ይላሉ። በተለይ ፳ኤሎች ግን በአብርሃም ልጅነት የሚመኩት በደንበኛው ልጁ በይስሐቅ በኩል የመጣውን ትውልድ በመከተል ነው። አንዳንድ ክርስቲያን ደግሞ እንደ ዮሐንስ ምጥምቁ ቃል መዳን በአብርሃም ተወላጅነት የሚሰጥ አይደለም ባዮች ናቸው። (ማቴ 3፡9፤ ሉቃስ 3፡8) ይስሐቅም ከሚስቱ ከርብቃ ኤሳውንና ያዕቆብን ወለደ። ያዕቆብ የኤሳው ታናሽ ሆኖ ሳለ ብኵርናን በምስር ወጥ ከኤሳው ከገበየ በኋላ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤልን የነገድ አባቶች ወለደ። ከዐሥራ ሁለቱም አንዱ ከብንያም በላይ የመጨረሻው ልጅ ዮሴፍ ነው። በዛሬ አባቶች ዘንድ እንደ ተለመደ ትንሹን ዮሴፍን አባቱ ያዕቆብ ከሌሎቹ አብልጦ ይወደው ነበርና በዚሁ ቅናት የያዛቸው ወንድሞቹ ከምድያም በከነዓን በኩል ወደ ግብፅ ለሚሔድ ነጋዴ ዮሴፍን ሸጡት። ገዥውም ዮሴፍን ይዞ ወደ አገሩ ወደ ግብፅ ከገባ በኋላ ለጶጢፋር ሸጠው። ጶጢፋርም በቤቱ እንደ አሽከር አድርጎ አስቀመጠው። ጌታውም ለጉዳዩ ወደ ውጭ በሔደበት ሰዓት የጌታው ሚስት ለሥጋ ፈቃድ ተመኘችውና ጠየቀችው። እሱም «ጌታዬ ባያይ እግዚአብሔር ያያል» የሚል የሚያስደነግጥ መልስ ሰጠና እንቢ አላት። እሷ ግን ሳታፍር ሳትደነግጥ ለማስገደድ ልብሱን ብትይዘው ልብሱን ተወላትና ወደ ውጭ ሸሸ። ከዚህ በኋላ ጌትዮው ከመንገድ ሲገባ «ይኸ ለአሽከርነት ያመጣኸው ዕብራዊ ካላነቅሁሽ ብሎ ስንተናነቅ ብጮኽበት ልብሱን ጥሎኝ ሔደ» ብላ አሳየችው። ጌትዮም ነገሩን ሳይመረምር የሚስቱን ቃል ብቻ በማመን ጻድቁን እንደ ኅጢአተኛ እወህኒ ቤት አገባው። ከዚህ ከወህኒ ቤት በሕልም አፈታት ምክንያት ወጥቶ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ጋራ ተዋወቀና ባለሟል ሆነ። ቀጥሎም ዮሴፍ የንጉሡ የፈርዖን እንደራሴ ለመሆን በቃ። በዚህ ዘመን ግብፅን ይገዙ የነበሩት የመካከለኛው መንግሥት ፈርዖኖች ነበሩ። በዚህ ዘመን በከነዓን አገር ረኃብ ተነሥቶ ነበርና፤ የሚሸመት እኽል ለመፈለግ የሸጡት ወንድሞቹ ከከነዓን ወደ ግብፅ መጡ። እሱም ወንድሞቹን ዐወቃቸው፤ የሚፈልጉትንም እኽል ሰጣቸው። የአባቱንም ሕይወት ጠይቆ ከተረዳ በኋላም ከአባታቸው ከያዕቆብና ከሚስቶቻቸው ጋራ ከከነዓን ወደ ግብፅ መጥተው እንዲቀመጡ ነገራቸው። ከዚህ በኋላ ከእግዚአብሔር ለአባታቸው ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጣቸውን አገራቸውን ከነዓንን ትተው ያዕቆብና ልጆቹ በድምሩ ነፍስ ሆነው ግብፅ መጥተው ተቀመጡ። ወደ ግብጽ የወረዱበት ጊዜ፣ በመጽሐፈ ኩፋሌ ሲቆጠሩ፣ ከፍጥረት 2172 ዓመታት አለፉ፣ ይህም ከክርስቶስ ልደት በፊት 1900 ዓመታት ያህል ነው። ዮሴፍ ካለፈ በኋላ፣ በአባይ ወንዝ አፍ ወይም በጌሤም ለትንሽ ጊዜ ለእጭታዊ (ለ13ኛው ሥርወ መንግሥት) ተገዥ 14ኛ ሥርወ መንግሥት ተነሣ፤ እነዚህ ከከነዓን የደረሱ ሴማዊ እረኞችና ነጋዴዎች ሲባሉ የዕብራውያን ዘመን በግብጽ ሊያብራራ ይችላል። ከሙሴ እስከ ዳዊት በግብፅ ዓመት ያኽል እንደ ተቀመጡ ዘራቸው በረከተና የግብፅን መንግሥት እማሥጋት ደረሱ። ስለዚህ በበረከቱበት በመጨረሻ ጊዜ የነበረው የግብፅ ንጉሥ በእስራኤሎች ላይ በኃዘን እስኪጮሁ ድረስ አገዛዝ አጸናባቸው። ይህ ጭቆና ሙሴ በተወለደበት ሰዓት ያህል ጀመረ። እግዚአብሔር ግን ለበረከት ትሆናላችው ብሎ ለራሱ አምልኮ የመረጣቸው ሕዝቦች ናቸውና ሥቃያቸውን ተመልክቶ አዘነላቸው። ሙሴም አድጎ ወደ ምድያም ሸሽቶ የያህዌን ራዕይ በደብረ ሲና ላይ አይቶ ሕዝቡ ከግብጽ እንዲያመልጡ ታዘዘ። በሙሴም አማካይነት በልዮ ልዮ ተአምራት ከግብፅ አወጣቸው። ፈርዖኑም ከግብጽ በር ስያባርራቸው ሥራዊቱ በታላቅ ተዓምር በቀይ ባሕር ጠፋ። የዚህ ፈርዖን መታወቂያ በሰፊ ተከረክሯል። ለምሳሌ ዳግማዊ ራምሴስ እንደ ነበር የሚያስቡ ብዙ አሉ። ሆኖም ይህ ፈርዖን የገዛ በ1200 ዓክልበ. ግድም ስለ ሆነ፣ ከዳዊት ዘመን በፊት ለእስራኤል ዘመነ መሳፍንት (በመጽሐፈ መሳፍንት) ከዘጸዓት በኋላ ጊዜው አይበቃም። በመጽሐፈ ኩፋሌ ቁጥጥር ከግብጽ ታሪክ ጋር ሲስማማ፣ ዘጸዓት የሆነው በ1661 ዓክልበ. ስለ ሆነ የጠፋው ፈርዖን መርነፍሬ አይ (ከ13ኛው ሥርወ መንግሥት) ይመስላል። በመርነፍሬ አይ ዘመን መጨረሻ፣ ዕብራውያን የወጡበት ዓመት፣ የግብጽ ኃይል እጅግ ደክሞ አንድ አሞራዊ ወገን «ሂክሶስ» ወይም 15ናው ሥርወ መንግሥት ወደ ግብጽ ስሜን ወረረ፤ እነዚህ ከከነዓን ስለ ደረሱ ብዙ ጊዜ ከእብራውያን ጋር ተደናግረዋል። ኢያሱ ወልደ ነዌ ከነዓንን እያሸነፈው፣ ሂክሶስ መላውን ግብጽ ያሸነፉ ተዋጊዎች ነበሩ፣ በ1548 ዓክልበ. ፈርዖኑ አህሞስ ሂክሶስን ከግብጽ አባረራቸው እንጂ ይህ የእብራውያን ዘጸአት አልነበረም። ለእስራኤል ወደ ፊትም የሚተዳደሩበትን ሕግ በሙሴ አማካይነት ሰጣቸው። ከዚያም በኢያሱ መሪነት የከነዓንን ነገሥታት አሸንፈው ለአባታቸው ወደ ተሰጠው ወደ ከነዓን አገር ገቡ። በአብርሃምና በያዕቆብ ጊዜ ያንድ የትልቅ ሰው ቤተሰብ ብቻ የነበሩት አሁን ግን ከያዕቆብ እስከ ሳሙኤል ድረስ ዓመት በሚያኽል ጊዜ ውስጥ በርክተው በበረቱባቸው ጊዜዎች መንግሥት ለማቆም በቁ። መጽሐፈ መሳፍንት እንደሚተርክ፣ በሌሎች ወቅቶች በአረመኔ ጎረቤታቸው በአሕዛብ ጣኦታት ከተሳሳቱ በኋላ፣ አይሁዶች ለጊዜ ተገዥ ይሆኑ ነበር። በየተራ ለሶርያ፣ ለሞአብ፣ ለአሞን፣ ለምድያም ወዘተ. ይገዙ ነበር፣ እያንዳንዱም ጊዜ ዕብራውያን ወደ እግዜር በተመለሱበት ወቅት የሚያድናቸው ፈራጅ ወይም አለቃ ይልካቸው ነበር። ጎቶንያል፣ ናዖድ፣ ዲቦራና ባራክ፣ ጌዴዎንም በዚህ አይነት ነበሩ፣ የአረመኔ ሃይሎችን ያሸንፉ ነበር። በነዚህም ክፍለዘመናት በሥነ ቅርስ በተገኙት በሌሎች ታሪካዊ ሰነዶች እንደሚታወቅ፣ «ሃቢሩ» ወይም «አፒሩ» የተባለ ብርቱ ወገን ከከነዓናዊ ጎረቤቶቻቸው ጋራ ይታገሉ ነበር፤ ሆኖም የነዚህ «ሃቢሩ» መታወቂያ ለዘመናዊ ምዕራባውያንና አይሁዳውያን ሊቃውንት የ«ሚኒማሊስም» (ክህደት) ፍልስፍና ተከታዮች ስለ ሆኑ አጠያያቂ ጉዳይ ሆኗል። ከጌዴዎን ቀጥሎ አቢሚለክ ለሦስት ዓመታት (1252-1249 ዓክልበ. ያህል) የእስራኤላውያን አምባገነን በሴኬም ተደረገ። በእርሱ አስተዳደር ግን ሃይማኖታቸው የአረመኔ ጣኦት በአልብሪት አምልኮት ሆነ። መጨረሻውም በእርስ በርስ ጦርነት ደረሰ (መሳፍንት 9)። በሚከተሉት ፈራጆች ዘመን ዕብራውያን በተለይ በገለዓድና ኤፍሬም ሠፈሮች ይጠቀሳሉ እንጂ መላውን አገር እንዳልያዙ ይመስላል። በ1155 ዓክልበ. ግን እንደገና ፍልስጥኤም በርቶ እስራኤልን ይገዛ ጀመር። በ1135 ዓክልበ. በፍልስጥኤማውያን ሥር እየቆዩ ሶምሶን የእስራኤላውያን አለቃ ሆነ። በ1115 ዓክልበ. ኤሊ የእስራኤል ፈራጅ ሆነ። በ1076 ዓክልበ. ፍልስጥኤማውያን ታቦትን ማረኩ፤ በሚከተለው አመት ግን ሳሙኤል አስመለሰው። ስለዚህ በመጀመሪያ ጊዜ በነጌዴዎን፤ በነሶምሶን በመሳፍንቱ፤ ከዚያም በነኤሊ፤ በነሳሙኤል በካህናቱ ሲተዳደሩ ቆይተው በመጨረሻ እንደ ጎረቤቶቻቸው እንደ ፍልስጥኤማውያን፤ እንደ ሞዓባውያንና እንደ አሶራውያን «ንጉሥ» ይደረግልን ብለው ጠየቁና በእግዚአብሔር ፈቃድ በ1055 ዓክልበ. ሳሙኤል ሳኦል የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን አደረገ። ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ከዚያም ዳዊት ቀጥሎም ልጁ ሰሎሞን ነገሠ። በዳዊትና በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት የእስራኤል ልጆች መንግሥታቸው ታላቅ መሆኑ በሁሉ ዘንድ ታወቀ። እነዚህ የእስራኤል ዘሮች ምንም እንኳን ቀድሞ በግብፅና በሲና በረሓ በኋላም በአገራቸው በከነዓን ሳሉ አንዳንድ ጊዜ አብረው በአሉት ሕዝብ ልማድና አምልኮ እየተዋጡ ጣዖት ማምለካቸው ባይቀር ከአብርሃም ጀምሮ እስከዚህ እስከ ሰሎሞን መንግሥት ድረስ፤ ከሰሎሞን ጀምሮም እስከ ዛሬ ድረስ በአንዱ በእግዚአብሔር ያመልካሉ። በሰሎሞንም ጊዜ ለእግዚአብሔር ትልቅ ቤተ መቅደስ ተሠራ። ስለዚህ የእውነተኛው እግዚአብሔርና የነሱም የዳዊትና ይልቁንም የሰሎሞን ስም በዓለም ታወቀ። ከክርስቶስ ልደት በፊት በሺ ዓመት ላይ ንግሥታችን ንግሥተ ሳባ የሰሎሞንን ጥበብ ለማየት ወደ ይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም የሔደቸው በዚህ ምክንያት ነው። ነገር ግን ከዚያ ወዲህ የተነሡት የሰሎሞን ተከታዮች አንዳንድ ነገሥታት የጎረቤቶቻቸውን የጢሮስንና የሲዶናን የባቢሎንንም አማልክት ብኤልንና ሞሎክን እያመለኩ እግዚአብሔርን አሳዘኑት። አንዱ ንጉሥ ተነሥቶ ለጣዖት አትስገድ አታምልክ፤ የሰገድህ አንደ ሆነ በአሕዛብ እጅ ትወድቃለህ የሚለውን የኦሪትን ቃል በካህናቱና በነቢያቱ አፍ ለሕዝቡ እያስነበበ ጣዖታቱን እንዲያጠፉና ሕዝቡ እውነተኛውን እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ ሲያደርግ፤ አንዱ ንጉሥ ደግሞ የማይታየውን እውነተኛውን እግዚአብሔርን ከማምለክ የሚታየውን ሐሰተኛውን ጣዖት ማምለክ ስለ መረጠና ሕዝቡም ስለ ተከተለው እስራኤል ከአምላካቸው ከእግዚአብሔር ተጣሉ። የውድቀታቸውም ዋዜማ ሲሆን ወደ ሁለት መከፈል ጀመሩ። ከሙሴ ጀምሮ እስከ ሰሎሞን ድረስ በ፩ መሪ ይተዳደሩ የነበሩት አሁን በሮብዓም ዘመን ወደ ሁለት ተከፈሉና ዐሥሩ ነገዶች ከኢየሩሳሌም በሰሜን በኩል ያለውን ሰማርያን ያዙ። የመጀመሪያውም ንጉሣቸው ኢዮርብዓም ሆነ። ሁለቱ የይሁዳና የብንያም ወገኖች በታችኛው በዚሁ በኢየሩሳሌም ቀርተው ለየብቻ ይተዳደሩ ጀመር። ስማቸውም የላይኛው የእስራኤል መንግሥት የታችኛው የይሁዳ መንግሥት ይባል ጀመር። እነዚህ ወደ ሁለት የተከፈሉት መንግሥታት አንዳንድ ጊዜ እየተጣሉ እርስ በራሳቸው ሲዋጉ፤ አንዳንድ ጊዜ እየተፋቀሩ አንድ ሆነው የእስራኤልን መንግሥት ጠላት አሶርን የይሁዳን መንግሥት ጠላት ባቢሎንን ሲወጉ ብዙ ዘመን በነጻነት ቆዩ። ከዚህ ቀጥሎ ግን ነፃነታቸው በአሶርና በባቢሎን ተደምስሶ በሰማርያ ከነገሡት ነገሥታት እነአክዓብ (አሐብ) በይሁዳ ከነገሡት እነሮብዓም፤ እነምናሴ «እኔ ነኝ አምላካችሁ ከባርነት ቤት ከምድረ ግብፅ ያወጣኋችሁ፤ ከኔ በቀር ለሌሎች አማልክት አትስገዱ» ያለውን ችላ እያሉ ሞሎክንና ብዔልን እያመለኩ ስለ አስቸገሩት፤ በወሰናቸው ያሉት በእርሱ የማያመልኩት የአሶርና የባቢሎን መንግሥታት እንዲያይሉባቸው አደረገ። ስለዚህ በሰሜን ያለውን የእስራኤልን መንግሥት አሶራውያን፤ በደቡብ በኩል ያለውን የይሁዳን መንግሥት ባቢሎናውያን በጦርነት ደመሰሱት። በሰሎሞን ጊዜ አምሮ የተሠራውም ቤተ መቅደስ ፈረሰ። የዚህ ቤተ መቅደስና የነገሥታቱም መሣሪያ ከነገሥታቱና ከሕዝቡ ጋራ በምርኮ ወደ ባቢሎን ተጋዘ። ወደ ኢየሩሳሌምም ከባቢሎን ከአሶር ከሰማሪያ ድብልቅ ዘሮች ከሰሜን፤ የኤዶምያስ ሰዎች ከደቡብ እየመጡ በየቀኑ ተሰደዱበት። ከባቢሎን ምርኮ እስከ ኢየሱስ ልደት እንግዲህ እሰከ አሁን ድረስ ምንም እንኳን በየስፍራቸው የሰዎቹ መኖር የታወቀ ቢሆን ፋርሶችም ግሪኮችም ሮማውያንም ታናሽ እስያንና የአፍሪካን ሰሜን ወረው ገና በገናንነት አልተነሡም። ነገር ግን ከኋላ ከረጅም ጊዜ በግምት ከ፬ ሺሕ ዓመት ጀምሮ እስከ አሁን እስከ ፮ኛው መቶ ዓመት ድረስ ከክርስቶስ ልደት በፊት የታወቁም ሥልጣኔም ኃይልም ያላቸው ግብፅ፤ አሶር፤ ባቢሎን፤ ኢትዮጵያ (ናፓታ)፤ ህንድ፤ ቻይና ናቸው። ነገር ግን በኋላ የታናሽ እስያን አገሮችና ግብፅን እስራኤሎችን ጭምር ቀጥቅጦ የገዛውን በነናቡከደነጾር ጊዜ የገነነውን የባቢሎንን መንግሥት የሚጥል የፋርስ መንግሥት ተነሣ። ከፋርስ በፊት ጎረቤቱ የሜዶን (ሚድያ) መንግሥት ለጥቂት ዘመን አይሎ ነበር። እስከ ባቢሎንና እስከ አሶር እስከ ኢየሩሳሌምም ደርሶ ነበር። ፋርስንም የራሱ ግዛት አድርጎት ነበር። ነገር ግን ፋርሶች ጊዜ ሲመቻቸው ከውስጣቸው ቂሮስ የሚባለውን ብልኅ ንጉሥ ባነገሡ ጊዜ የሜዶንም የአሶርም የባቢሎንም ትልቅነት ወደ ውድቀት ማዘንበል ጀመረ። ቂሮስ ከክርስትና በፊት በ፭፻፶ ዓመት በፋርስ ላይ ነገሠና መጀመሪያ የሜዶንን ቀጥሎ የልድያን መንግሥት አሸንፎ ያዘ። ከዚያም በናቡናኢድ ዘመነ መንግሥት ትልቁን የባቢሎንን ከተማ በ፭፻፴፰ ዓመት ከቦ አስጨነቀ። በመጨረሻም በጦር ኃይል አሸንፎ ያዘና ትልቁን የባቢሎንን ግዛት የፋርስ የአውራጃ ግዛቱ አደረገው። ከዚህ በኋላ በናቡከደናጾር ጊዜ በምርኮ የሄዱት የኢየሩሳሌም (የእስራኤል) ሹማምንት ተፈትተው ሁሉም ተሰብስበው ድል አድራጊው ቂሮስ ፊት በቀረቡና ባያቸው ጊዜ አዘነላቸው። ስለዚህ ምርኮኞቹ ፳ኤሎች አለቆቻቸውን ዕዝራን ነሕምያን ዘሩባቤልን ይዘው በነፃነት ወደ አገራቸው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ ፈቀደላቸው። ከኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥትና ከቤተ መቅደስም ተዘርፎ በባቢሎን ከተማ ለጊዜው የተገኘውን ንዋየ ቅድሳት ይዘው ሄደው የፈረሰውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መልሰው እንዲሠሩ አዘዛቸው። ከራሱም እርዳታ ጨመረላቸው። እስራኤሎችም ቂሮስን ተሰናብተው በሹማምንት በነዘሩባቤል በሊቀ ካህናቱም እየተመሩ በደስታ ወደ አገራቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው የከተማውንና የቤተ መቅደሱን ሥራ ጀመሩ። ሥራውንም እጅ በእጅ ብለው ቅጥሩን ሠርተው አዳረሱት። ዳሩ ግን በመካከሉ የሚያሳዝን ነገር መጣ። «እነዚህ ሰዎች ከተማቸውንና ቅጥራቸውን ሠርተው ከፈጸሙ በኋላ አይታዘዙልህም፤ የቀድሞ ታሪካቸውንም ስንመረምር አዋኪ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተናል» ብለው ነገረ ሠሪዎችና የፋርስ መንግሥት ተመልካቾች ለንጉሡ ላኩ። ንጉሡም ምንም ደግና ብልኅ ቢሆን በእንደዚህ ያለ ዘውዱንና ገዥነቱን በሚያሠጋ ነገር መገንገኑ አይቀርምና ሥራው ይቁም የሚል ትእዛዝ አስተላለፈ። ቢሆንም በቂሮስም በዳርዮስም ጊዜ ሲከለከልም ሲፈቀድም በቀን ብዛት የኢየሩሳሌም ከተማና ቤተ መቅደስ ተሠርቶ አለቀ። ይህ ሁሉ በብሉይ ኪዳን በመጽሐፈ ነገሥትና በመጽሐፈ ዕዝራ በመጽሐፈ ዜና መዋዕል፤ በመጽሐፈ መቃያንና በዜና አይሁድም ተጽፏል። የፋርስ መንግሥት በቂሮስና በነዳርዮስ ዘመን ቅልቅ የንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሆኖ እስከ ዓመት ድረስ ከቆየ በኋላ በዚህ ዘመን ከመቄዶንያ (ግሪክ) ትልቁ እስክንድር ተነሥቶ ጦሩን ይዞ ከመጨረሻው ከፋርስ ንጉሥ ከዳርዮስ ፫ኛ ጋራ ተጋጥሞ አሸንፏል። እስክንድርም የዳርዮስን ጦር ካሸነፈ በኋላ የፋርስና የግዛቱ የባቢሎን የአሶር የፓለስቲን የግብፅ ባለቤት ሆኖ፤ እስከ ህንድ ወንዝ ድረስ ገፍቷል። እስክንድር በነገሠ በ፲፫ በተወለደ በ፴፫ ዓመቱ ስለ ሞተ ግዛቱን «ዲያዶክ» የሚባሉት የጦር አለቆች ተከፋፍለው እስከ ሮማውያን መምጣት ድረስ ገዝተዋል። በፓለስቲን ያሉት እስራኤሎች ከባቢሎን ወደ ፋርስ፤ ከፋርስ ወደ ግሪክ (ከገዥ ወደ ገዥ) ከዚያም ወዲህ ቶሎሜውስ (በጥሊሞስ) በሚባሉት በግብፅ ገዥዎች ቀጥሎ ደግሞ ሴሌውሲድ በሚባሉት በሶርያ ነገሥታት ውስጥ ጥገኛም ተገዥም እየሆኑ ከክርስቶስ ልደት በፊት የሁለቱንና የአንደኛውን መቶ ዓመት ጊዜያቸውን አሳለፉ። ቶሎሜውስና ሴሌውኩስ የሚባሉት የትልቁ እስክንድር የጦር አለቆች ነበሩ። እስክንድር ከሞተ በኋላ ቶሎሜውስ በግብፅ ነገሠና ቶሎሜይ የተባለውን፤ ሴሌውኩስ በአሶርና በባቢሎን ነግሦ ሴሌውሲድ የተባለውን ቤተ መንግሥት (ዲናስቲ) የመሠረቱ ናቸው። ከዚህ በኋላ ሮማውያን ከኢጣሊያ ተነሥተው እነሺፒዮኔ የአፍሪካን፤ ሰሜን፤ እነማሪዮ እነቼዛሬ ኦታቪያኖ የፈረንሳዊን የኤስፓኝን የእንግሊዝን (ጋልያና ብሪታንያን ኤስጳንያን)፤ እነሲላ እነፓምፔዎ የባልካንን አገሮችና የታናሽ እስያን መንግሥታት ሲወሩ ፓምፔዎ (ዮሐንስ መደብር ፉምፍዮስ የሚለው) እንደ ኤውሮፓ አቆጣጠር በ፷፪ ዓመት ላይ ድል አድርጎ ፓለስቲንን ያዘ። ከዚህ በኋላ በ፳፱ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ሮማውያንን ካዩ ጁሊዎ ቼዛሬ አታቪያኖ የሚሉት በኋላ ግርማ ያለው ጠቅላይ አለቃ ለማለት «አውግስጦስ» የሚባል የማዕረግ ስም የተጨመረለት፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በዚሁ ይዞታ አውግስጦስ ቄሳር የምንለው በሮማ ነገሠ። ከአውግስጦስ ቄሳር ንጉሥ ቀደም ብሎ በዮልዩስ ቄሳር ጊዜ በሮማ የበላይ ገዥነት ውስጥ ትልቁ ሄሮድስ የሚባለው ንጉሥ ተብሎ ከሮማ ምክር ቤት በአርባ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ተፈቅዶ በይሁዳ (ፓለስቲን) ተሾሟል። ሄሮድስ የኤዶምያስ ተወላጅ ነው። የኤዶምያስም ዘር ከያዕቆብ ታላቅ ወንድም ከኤሳው ትውልድ የመጣ ነው ይባላል። ሄሮድስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ የግሪክና የሮማን ሥልጣኔ በአገሩ ለማስገባት ፈቃደኛ ሆነ። በሮማ የነገሠውን አውግስጦስ ቄሳርንም ከልቡ ይወደው ነበርና በቀያፉ በታች በባሕር ዳር የምትገኘዋን ከተማ አሠርቶ ለእርሱ ስም መታሰቢያ እንድትሆን ቂሳርያ ብሎ ሰየማት። በዚህ ሁሉ ምክንያት ሄሮድስ በሮማውያን ዘንድ የታመነና የተወደደ ሆኖ በፓለስቲን በንጉሥነት ብዙ ጊዜ ቆየ። እንዲሁም ምንም እንኳን ባህሪዮና ምግባሩ እንደ ወገኖቹ እንደ ኤዶምያስ ቢሆን፤ ሃይማኖቱ ወደ እስራኤል የሚያደላ ስለነበር የአይሁድን ሃይማኖትና ልማድ ያከብርና ነበርና እነሱም እርሱን ይፈሩትና ያከብሩት ነበር። ዛሬ ግን በክርስቲያኖች ዘንድ ጌታችን የተወለደ ጊዜ ንጉሥ የሚሆን ሕፃን ተወለደ ማለትን ሰምቶ ከኔ በቀር ማን ንጉሥ ሊሆን ነው ብሎ ጌታችንን አብሮ ያገኘ መስሎት ብዙ ሕፃናት በማስፈጀቱ ለወዳጁ ለሄሮድያዳ ሲል የዮሐንስ መጥምቁን ራስ በማስቆረጡ እንደ ትልቅ ጨካኝና አመፀኛ የተቆጠረ ሰው ነው። ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኘው የ፳ኤሎች ታሪክ ነው። የእስያ ታሪክ አይሁድ እስራኤል መጽሐፍ
10280
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%8C%BD%E1%88%90%E1%8D%8D%20%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5
መጽሐፍ ቅዱስ
መጽሐፍ ቅዱስ ነብያት እና ታሪካውያን የጻፉት የክርስቲያኖች እምነት መጽሓፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን ተከፍሎ 81 መጻሕፍት ያሉት ሲሆን በአንዳንድ እምነቶች ደግሞ 73 እና 66 ክፍል ብቻ ነው አሉት ብለው ያምናሉ። ከነዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍትም ጋራ የመጻሕፍት ቁጥር 81 ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ከመቶ 25% የአምላክ ንግግር፣ ከመቶ 25 የነብያት ንግግር እና ከመቶ 50 የታሪክ ጽሐፍያን ንግግር ይዟል። ነገር ግን በነብያት ውስጥም በቃሉም በታሪክም ተነገረ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ነው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንነት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተለመደው «ባይብል» የሚለው ቃል ከጥንቱ የኮይነ ግሪክኛ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ቃሉ የተገኘበት /ታ ቢብሊያ/ የሚለው ሀረግ «መጽሐፍቱ» ወይም «ትንንሽ መጽሐፍት» ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። የዚሁም ቃል መነሻ ከግሪኩ ስም /ቢውብሎስ/ (ፓፒሩስ ወይም ቄጠማ፣ የወረቀት ተክል) ሲሆን ይሄ ቃል «ፓፒሩስ» ከተነገደበት ከተማ ጌባል ቢውብሎስ ስም መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ ለአይሁድና ክርስትና እምነት የእምነት መሰረት የሆኑ ትናንሽ መጽሐፍትን የያዘ አንድ ጥራዝ ነው። በተለምዶ «ብሉይ ኪዳን» በመባል የሚጠራውና በአይሁዳውያን በ24 እና በክርስቲያኖች በ39 መጽሐፍት የሚከፈለው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ክፍል በመጀመሪያ በአብዛኛው የተጻፈው በጥንታዊው የዕብራይስጥ ቋንቋ ሲሆን የተጻፉበት ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የተወሰኑ መቶ አመታት ቀደም ብሎ እንደሆነ ይነገራል። እነዚህን መጽሐፍት የጻፉት በወቅቱ የነበሩ የታመኑ አይሁዳውያን ወይም እስራኤላውያን ናቸው። የመጨረሻዎቹን 27 መጻሕፍት በግሪክኛ የጻፏቸው ክርስቲያኖች ሲሆኑ «አዲስ ኪዳን» በመባል በሰፊው ይታወቃሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ማስረጃም ሆነ በጣም ጥንታዊ የሆኑት ወጎች እንደሚጠቁሙት እነዚህ 66 መጻህፍት የተጻፉት ግብጽ ኃያል ከነበረችበት ጊዜ አንስቶ ሮም የዓለም ኃያል መንግስት እስከ ነበረችበት ዘመን ባሉት 1600 ዓመታት ውስጥ ነው። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት መሰረት ከ66ቱ መጽሐፍት በተጨማሪ የተካተቱ የተወሰኑ መጽሐፍት ሲኖሩ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እነዚህ ተጨማሪ መጻሕፍት (ዲዩቴሮካኖኒካል በመባልም ይታወቃሉ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱትን መጻሕፍት ቁጥር ወደ 81 ያደርሱታል።በ እና የተፃፈው 66 ነው:: ከክርስቶስ ስብከት ቀጥሎ ምዕመናን የሆኑት ለረጅም ዘመን ተጨማሪ መጻሕፍቱን ከነመጽሐፈ ሄኖክና ኩፋሌ ያንብቡ ነበር። በግሪኩ «ሴፕቱዋጊንት» ትርጉም እንዲሁም በሞት ባሕር ጥቅል ብራናዎች (50 ዓመት ከክርስቶስ በፊት) በዕብራይስጥ መጻሕፍት መኃል ይገኙ ነበር። የአይሁድ ሰንሄድሪን ረቢዎች በ100 ዓ.ም. አካባቢ በተለይም ረቢ አኪቫ በን ዮሴፍ እነዚህን ተጨማሪ መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ቅጂ አጠፉ። እስካሁንም ድረስ በዕብራይስጥ ትርጉም አይታወቁም። አዲስ ኪዳን ከተጻፈ በኋላ፣ ብዙ አጠያያቂ ወንጌሎችና የሌሎች እምነቶች ጽሑፎች ደግሞ ሊሠራጩ ጀመር። ግኖስቲክ የተባለው እምነት ተከታዮች በተለይ ብዙ ሥነ ጽሑፍ ፈጠሩ፣ ይህ ግን ከኦርቶዶክስ ወንጌል የተዛቡ ትምህርቶች ነበር። በ170 ዓ.ም. በክርስትያኖች ዘንድ የቱ መጻሕፍት ትክክለኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ናቸው? የሚል ጥያቄ ይነሣ ጀመር። መሊቶ ዘሳርዲስ የተባለ ጳጳስ በዚያን ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም መጻሕፍት ቤት ጉዞ አድርጎ የ ዕብራውያን መጻሕፍት ምን ምን እንደ ነበሩ ዘገበ። ተጨማሪ መጻሕፍቱ ከዚያ በፊት ስለ ጠፉ አልተዘገቡም። ስለዚህ ከዚህ በቀር ምንም ያልተዘረዘሩት ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ትክክለኛ አይሆኑም የሚል ሀሣብ በሮሜ መንግሥት ክርስቲያኖች ተነሣ። ይህም የአይሁዶች ቀኖና በንቅያ ጉባኤ (317 ዓ.ም.) በሮሜ መንግሥት ለክርስቲያኖች ጸና። የመጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ባህርያት መጽሐፍ ቅዱስ የስነምግባር ጉዳዮችን በሚመለከት መመሪያ የሚሰጥ ከመሆኑም ሌላ እንደ ወንጀል፣ ረሃብና የአካባቢ መበከል ያሉት ችግሮች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሔ የሚያገኙበትን መንገድ ይገልጻል። ችግሩ ግን፣ መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ጉዳዮች አስመልክቶ የሚናገረውን ነገር ብዙ ሰዎች በቁም ነገር መመልከት ትተዋል። ከዚህ ቀደም ይህ መጽሐፍ ቢያንስ በምዕራቡ ዓለም እንኳ ትልቅ ተሰሚነት ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በሰዎች አማካኝነት ቢሆንም እንኳ ቀደም ባሉት ጊዜያት በሕዝበ ክርስትና ውስጥ የነበሩት አብዛኞቹ ሰዎች የአምላክ ቃል መሆኑንና መልእክቱም አምላክ በመንፈስ አነሳሽነት ያስጻፈው እንደሆነ ያምኑ ነበር። ይሁን እንጂ ዛሬ እያንዳንዱን ነገር መጠራጠር የተለመደ ነገር ሆኗል። ሰዎች ባህላቸውን፣ የተለያዩ ጽንሰ ሐሳቦችን፣ የስነምግባር ደንቦችንና የአምላክን መኖር እንኳ ሳይቀር የጠራጠራሉ። በተለይ የመጽሐፍ ቅዱስን ጠቃሚነት በተመለከተ ጥርጣሬ ገብቷቸዋል። አብዛኞቹ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ጊዜ ያለፈበትና አላስፈላጊ እንደሆነ አድርገው የሚያዩት ይመስላል። ከዘመናችን ምሁራን መካከል መጽሐፍ ቅዱስን እንደ አምላክ ቃል አድርገው የሚመለከቱት በጣም ጥቂት ናቸው። እንዲያውም አብዛኞቹ ሰዎች ከምሁሩ ጄምስ ባር አባባል ጋር ይስማማሉ፡- "ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልማዶች ያለኝ አመለካከት የሰው ልጅ የፈጠራ ውጤት ናቸው የሚል ነው። የሰው ልጅ የራሱን እምነት ያሰፈረበት መጽሐፍ ነው።" ይህ አመለካከት ወደ አንድ ነጥብ ያመራል፦ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች የጻፉት ተራ መጽሐፍ ከሆነ ለሰው ልጅ ችግሮች ምንም ዓይነት ግልጽ የሆነ መልስ አይገኝም ማለት ነው። የሰው ልጆች በገዛ እጃቸው በሚያመጡት ጣጣ ከህልውና ውጭ እንዳይሆኑ ወይም በኑክሊየር ጦርነት እንዳያልቁ አቅማቸው የፈቀደውን ያህል በጭፍን መዳከር ይኖርባቸዋል ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ከሆነ ግን ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ የሚያስፈልገን ዋነኛው ነገር እርሱ ይሆናል። የታሪክ መዝገቦች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላሉ? በብዛት በመሸጥ አቻ ያልተገኘለት መጽሐፍ ቅዱስ በብዛት ታትሞ በመሸጥና በሰፊው በመሰራጨት ረገድ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል። ጊነስ ቡክ ኦቭ ወርልድ ሬኮርድስ የተባለው መጽሐፍ በ1988 እትሙ እንደገለጸው ከ1815 እስከ 1975 ባሉት ዓመታት ውስጥ ብቻ ወደ 2.5 ቢልዮን የሚገመቱ ቅጂዎች ታትመዋል። ይህ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ሊሰራጭ ይቅርና ወደዚያ ቁጥር የተጠጋ አንድም መጽሐፍ በታሪክ አልታየም። ከዚህም በተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል በብዙ ቋንቋዎች የተተረጎመ መጽሐፍ አይገኝም። ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ከ1800 በሚበልጡ የተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛል። በኢትዮጵያ እንኳን በአማርኛ፣ ትግሪኛ፣ ኦሮምኛ፣ ወላይትኛ፣ ጉራግኛና ሌሎች ቋንቋዎች መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉም ሆነ በከፊል ተተርጎሞ ይገናል። በአጠቃላይ ዛሬ 98 በመቶ ገደማ የሚሆነው የምድራችን ነዋሪ መጽሐፍ ቅዱስን በቋንቋው ማግኘት ይችላል። ተደማጭነት ያለው መጽሐፍ ዘ ኒው ኢንሳይክለፒዲያ ብሪታኒካ መጽሐፍ ቅዱስን "በታሪክ ዘመናት ከታዩት ጽሑፎች ሁሉ ይበልጥ ተደማጭነት ያለው የመጻህፍት ስብስብ" ሲል ጠርቶታል። የ19ኛው ጀርመናዊ ባለቅኔ ሄንሪክ ሃይነ እንዲህ ብለዋል፦ "ይህን ሁሉ ማስተዋል ያገኘሁት ከአንድ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ። ቅዱስ መጽሐፍ መባሉ ይገባዋል። አምላኩን ያጣ ሰው ካለ በዚህ መጽሐፍ አማካኝነት ሊያገኘው ይችላል።" በዚሁ መቶ ዘመን የኖረውና የጸረ-ባርነት እንቅስቃሴ አራማጅ የነበረው ዊልያም ኤች ሴዋርድ እንዲህ ብሏል፦ "የሰው ልጅ የመሻሻል ተስፋ የተመካው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በሚሄደው የመጽሐፍ ቅዱስ ተደማጭነት ላይ ነው።" የዩናይትድ ስቴትስ 16ኛ ፕሬዚዳንት የነበሩት አብርሃም ሊንከን መጽሐፍ ቅዱስን በሚመለከት እንዲህ ብለዋል፦ "አምላክ ለሰው ልጆች ከሰጠው ስጦታ ሁሉ የላቀ ስጦታ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ባይኖር ኖሮ መልካሙንና ክፉውን ለይተን ማወቅ ባልቻልን ነበር።" የብሪታንያው የህግ ሰው ሰር ዊልያም ብላክስተን "ሁሉም ሰብዓዊ ሕጎች የተመሰረቱት በእነዚህ ሁለት ሕጎች ማለትም በተፈጥሮ ሕግና አምላክ ለሰው ልጆች በሰጠው ሕግ [በመጽሐፍ ቅዱስ] ላይ ነው፤ እንግዲያው ሰብዓዊ ሕጎች ከእነዚህ ሕጎች ጋር እንዲጋጩ ማድረግ አይገባም ማለት ነው።" ብለው ሲናገሩ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ተደማጭነት እንዳለው ጎላ አድርገው መግለጻቸው ነበር። የተጠላና የተወደደ በአንጻሩ ደግሞ በታሪክ ዘመናት ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል የከረረ ተቃውሞ የገጠመው መጽሐፍ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ ከመካከለኛው ዘመን አንስቶ እስከ 20ኛው መቶ ዘመን ድረስ በአደባባይ ተቆልሎ እንዲቃጠል ተደርጓል። በዛሬው ዘመን እንኳ ሳይቀር መጽሐፍ ቅዱስን በማንበባቸው ወይም በማሰራጨታቸው ምክንያት የገንዘብ ቅጣት የተጣለባቸው ወይም በእስራት የተቀጡ ሰዎች አሉ። ባለፉት መቶ ዘመናት እንዲህ ያለው "ወንጀል" ብዙውን ጊዜ አሰቃቂ ለሆነ ድብደባ አልፎ ተርፎም ለሞት የሚዳርግ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ውስጥ ያሳደረው ፍቅር ከዚሁ ጎን ለጎን የሚታይ ነው። ብዙዎች የማያቋርጥ ስደት ቢደርስባቸውም መጽሐፍ ቅዱስን ማንበባቸውን ገፍተውበታል። ለምሳሌ ያህል በ16ኛው መቶ ዘመን የኖረውንና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተምሮ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው አስተማሪ የነበረውን ዊልያም ቲንደልን እንመልከት። ቲንደል ለመጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ ፍቅር ነበረው። ይሁን እንጂ በዘመኑ የነበሩት ሃይማኖታዊ ባለ ሥልጣናት መጽሐፍ ቅዱስ ሙት በነበረው በላቲን ቋንቋ ተወስኖ እንዲቀር ሽንጣቸውን ገትረው የሟገቱ ነበር። ቲንደል ግን የአገሩ ሶዎች መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ አጋጣሚ እንዲኖራቸው በማሰብ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመተርጎም ቆርጦ ተነሳ። ይህ ተግባሩ ከሕጉ ጋር የሚቃረን ስለነበር ቲንደል ጥሩ የማስተማር ስራውን ትቶ መሰደድ ግድ ሆነበት። የግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎችን ("አዲስ ኪዳን") እና አንዳንዶቹን የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ("ብሉይ ኪዳን") ወደ አገሩ ቋንቋ ተርጉሞ እስኪጨርስ ኑሮውን በስደት ለመግፋት ተገዷል። ይሁን እንጂ በመጨረሻ በመያዙና መናፍቅ ነው ተብሎ በመወንጀሉ ተሰቅሎ እንዲሞትና በድኑም በእሳት እንዲቃጠል ተደርጓል። ቲንደል፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ወይም ለሌሎች ሰዎች እንዲዳረስ ለማድረግ ሲሉ ብዙ መሥዋዕትነት ከከፈሉት በርካታ ሰዎች መካከል አንዱ ብቻ ነው። ከሌላው ሰው የተለየ ምንም ነገር ያልነበራቸውን ብዙ ወንዶችና ሴቶች ይህን ያህል ድፍረት እንዲኖራቸው ያነሳሳ ሌላ መጽሐፍ በታሪክ ውስጥ አልታየም። ከዚህ አንጻር መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥም አቻ አይገኝለትም። ማመዛገቢያ ውጫዊ መያያዣ መጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ድምፅ መጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ
22397
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A4%E1%8A%95%E1%89%BD
ቤንች
ቋንቋ የቤንች ብሔረሰብ ቋንቋ ‹‹ቤንችኛ›› ሲሆን ከምዕራብ ኦሞአዊ የቋንቋ ቤተሰብ ይመደባል። የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ አማርኛ፣ ካፊኖኖ እና ሸኮኛ ቋንቋዎችን ይናገራሉ። ሕዝብ ቁጥር መልክዓ ምድር የቤንች ብሔረሰብ አባላት በዋናነነት በዞኑ በሰሜን ቤንች እና በደቡብ ቤንች፣በሸዋ ቤንች ወረዳዎች እንዲሁም በሸኮ እና ጉራፈርዳ ወረዳዎች ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ከዞኑ ውጭም የብሔረሰቡ አባላት ኩታ ገጠም በሆኑት በከፋ ዞን በጨና እና ዳቻ ወረዳዎች፣ በሻካ ዞን በየኪ ወረዳ እንዲሁም በአዲስ አበባ ‹‹ጊሚራ›› ሰፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ይገኛሉ፡፡ ብሔረሰቡ የሚገኝበት አቀማመጥ ሜዳማ፣ ተራራማ እና ሸለቋማ ሲሆን፤ ደጋማ፣ ቆላማ እና ወይና ደጋ የአየር ንብረት አለው፡፡ የብሔረሰቡ ዋነኛ መተዳደሪያ ጥምር ግብርና ነው፡፡ ከተክሎች፣ ከሥራሥር፣ ከጥራጥሬ፣ ከቅመማቅመም ከአገዳ እህል የሚገኙ ምርቶች ያመርታል፡፡ ቡና ዋና የገቢ ምንጭ ሲሆን፤ ቅመማቅመም፣ ቆዳ እና ሌጦ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ናቸው፡፡ ታሪክ ቤንች ብሔረሰብ በቤንች ማጅ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ስድስት ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ የብሔረሰቡ አሰያየም ‹‹ቤንችቲያት›› ከተባለው ጥንታዊ የብሔረሰቡ መሪ እንደተወለደ ይነገራል፡፡ ‹‹ታት›› የሚባለው ቃል ‹‹ጌታ›› ማለት ሲሆን ለብሔረሰቡና ለቋንቋው መጠሪያ ነው፡፡ በቤንች ብሔረሰብ በርካታ ጐሳዎች ቢገኙም ከምት፣ ቃም፣ ማንጃ(ባንድ) እና ማኖ(ፋቂ) ዋና ዋናዎቹ ናቸው በሐረሰቡ የራሱ የሆነ ባህላዊ አስተዳደር እና የዳኝነት ሥርዓት ያለው ሲሆን፤ ባህላዊ አስተዳደሩ የሥልጣን እርከን እና የሥራ ኃላፊነት የሚወሰነው በእርከኑ ባሉ ሽማግለዎችና በጎሳ መሪዎች ምርጫ ነው፡፡ ‹‹ከምት›› ከፍተኛ ከበሬታ የሚሰጠው መሪ ነው፡፡ ማንኛውንም ፖለቲካዊ ማኀበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮችን በበላይነት ይመራል፡፡ የባህላዊ አስተዳደሩ ቁንጮ ከእዚህ ጎሣ የሚሾም ሲሆን ‹‹ቤንችያት›› (ከምት) ባላባት ይባላል፡፡ የሚመረጠውም ‹‹ከባይከስ›› ጎሳ ነው፡፡ የሥልጣን ሽግግሩም የዘር ሀረግን የተከተከለ ሲሆን የመሪዎቹ ወይም የ‹‹ቲያቶት›› ሥልጣን የሚተላለፈው ከ‹‹ቲያቶች›› የመጠሪያ ሚስት ለተወለደ የበኩር ልጅ ነው፡፡ መሪው ልጅ ሳይተካ ከሞተ ወንድሙ ሥልጣኑን ይወርሳል፡፡ ለ‹‹ቲያትነት›› የሚመረጠው ልጅ ወይም ወንድም በቂ ችሎታ ያለው እና ከሌለ ወገን ያልተከቀላቀለ ቤንች መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ብሔረሰቡ ግጭቶችን የሚፈታበት የተለያዩ መንገዶች ያሉት ሲሆን፤ ግድያ ከተፈፀመ ወንጀሉ አፈፃፀም ከተጣራ በኋላ በሁለቱ ደመኞች ድንበር ላይ በሬ ታርዶ በደም ይታረቃሉ፡፡ ልጃገረድም ከገዳይ ወገን በካሳ ትሰጣለች፡፡ በብሔረሰቡ መዋሸት፣መሥረቅ፣ዝሙት መፈጸም አጥብቆ የተከለከለ ነው፡፡ ይህን ተግባር የፈጸመ ለቃልቻ ወይፈን ወይም ጊደር ይሰጣል፡፡ ከ1ዐ እስከ 3ዐ ጅራፍም ይገረፋል፤ በእግረሙቅ ይታሠራል፤ ለተወሰኑ ወራትም ለባላባቱ እንዲያደርስ ይደረጋል፡፡ በቤንች ብሔረሰብ የጋብቻ ሥርዓት በቤተሰብ ስምምነት፣በጠለፋ፣በማስኮብለል እና በውርስ ይፈጸማል፡፡ በብሔረሰቡ ሴት ልጅ 15 ዓመት ወንድ ልጅ ደግሞ 2ዐ ዓመት ሲሞላው የጋብቻ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ ባላባቱ እስከ 4ዐ ሚስቶችን ማግባት ሲችል አንጋፋዋ ሚስት ‹‹ጌን›› ትባላለች፡፡ በብሔረሰቡ ከወቅቶች ጋር ተያይዞ ምርት እንዲሰጥ፣ በሽታ እንዲጠፋ፣ ሰላም እንዲሰፍን በዓመት 3 ጊዜ የሚከበሩ በዓላት አሉ፡፡ በዓላቶቹ በቃልቻዎችና በባለአባቱ የሚመሩ ሲሆን፤ቦርዴ ተጠምቆ ልዩ ልዩ መልክ ያላቸው ዶሮዎች እና ከ5ዐ እስከ 6ዐ ያህል ከብቶች ታርደው እንዲከበር ይደረጋል፡፡ ቤንቾች በዓላትን፣ የዘመንና የወቅት አቆጣጠርን የጨረቃ መውጣትና መግባትን ተከትለው ከአዝመራ ወቅቶች ጋር በማዛመደ ያከብራል፡፡ ብሔረሰቡ ባህላዊ ቤቶችን ከእንጨት፣ ከጭቃ እና ከሣር የሚሠራ ሲሆን፤ጣራቸው በጭቃ የተሸፈነው ነው፡፡ የጎሣ መሪዎቹ ቤቶች ከፍታ ያላቸውና ሰፊ ናቸው፡፡ በብሔረሰቡ ከበቆሎ ወይም ከጤፍ የተሠራ ዳቦ፣ እንሰት(አምቾ)፣ ጎደሬ፣ እና የጎደሬ ገንፎ ይበላል፡፡ የቆጮ ቅቅል፣በቆሎ ተቆልቶ ከተፈጨ በኋላ የተዘጋጀ ጎመን ተጨምሮ በገንፎ መልክ ተዘጋጅቶ ይበላል፡፡ በብሔረሰቡ ወንዶች ሆዳቸውን በቀኝ እና በግራ ክንዳቸው አማካኝነት ቀጠን ያለ ‹‹ጋሱ›› የተባለ መስመር በመሥራት ያስውቡታል፡፡ ወንዶቹም ሆነ ሴቶቹ ለጉትቻ ጆሮአቸውን ይበሳሉ፡፡ አዛውንቶቹ ቁምጣ ሱሪ አንዳንዴም በላሌ፣ኩታ፣ ሹራብና ረጃጅም ልብሶችን ይለብሳሉ፡፡ ጦር መያዝም ልምዳቸው ነው፡፡ በብሔረሰቡ የለቅሶና የሀዘን ሥርዓት መሠረት ባለውቃቢ(ቃልቻ) ሲሞት አስከሬኑ ከመቀበሩ በፊት ውቃቢው በልጁ ወይም በዘመዱ ላይ እንዲወርድ በሚል በዋናው ቃልቻ ይለመናል፡፡ ባለአባቱ ወይም መሪ ሲሞት የሟች የቤተሰብ ቀብርን ከፈጸመ ከወር በኋላ መልዕክቱ ይተላለፋል፡፡ እየተደገሰ ሁለት ወር ይለቀሳል፡፡ ወጣት ሲሞት ለሳምንት ተለቅሶ በሦስተኛው ወሩ ልብሶቹ መቃብሩ ላይ ይጣላሉ፡፡ ንብረቱም እንዲወድም ይደረጋል፡፡ ታዋቂ ሰዎች ቤንች የኢትዮጵያ ብሔር ነው። የኢትዮጵያ ብሔሮች
47663
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A3%E1%88%88%E1%88%99%E1%8B%AB%20%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%8D%8D
ባለሙያ ንድፍ
«ባለሙያ ንድፍ» (እንግሊዝኛ፦ በተለይ በአሜሪካ አገር የጀመረ የዝግመተ ለውጥ አከራካሪ አስተያየት ነው። በዚህም አስተሳሰብ የ«ዝግመተ ለውጥ» እና የ«ተዓምር» (የእግዚአብሔር ሥራ) ትርጉም አንድ ነው። ታሪክ ዓለሙ በ«ባለሙያ ንድፈኛ» መፈጠሩ ለእግዚአብሔር ሕልውና ማስረጃ ያህል መሆኑ በእርግጥ ጥንታዊ አስተያየት ነው። እንዲህ ያለ ሃሣብ እንኳ በሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ እንደ ተጠቀሱ በጅሮንድ ተክለ ሐዋርያት «ፈጣሪ መኖሩንና የበላይ ገዥነቱን የሚያሳምነን ዓለምን በሙሉ በማይፈርስና በጽኑ ሕግ ለዘላለም ወስኖ በመፍጠሩ ነው» ብለዋል። ጃንሆይም በራሳቸው በኩል እጅግ ብዙ ተመሳሳይ አስተያየቶች ይናገሩ ነበር። በአሜሪካ አገር የሕዝቡን መብቶች ለመጠብቅ፣ በ1783 ዓም የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ፩ኛ መለወጫ እንዳለ በከፊል፦ «ስለ ሃይማኖት መመሥረት የነካ፣ ወይንም የእርሱን ነጻ ተግባር የከለከለ ሕግ ምክር ቤቱ አይሠራም...።» የዚህ ላይኛ ሕግ አሣብ ምንም የመንግሥት ሃይማኖት እንዳይመሠረት፣ እንዲሁም መንግሥት በሃይማኖታዊ ጉዳይ ጥልቅ ከማለት ለመከልከል እንዲደረግ ነበር። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ቻርለስ ዳርዊን የዝግመተ ለውጥ ሃልዮ ባሳተመ ወቅት በመጀመርያ በሃይማኖታዊ ሰዎች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት አላገኘም ነበር፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዘንድ እግዚአብሔር ከ6 ሺ ዓመት በፊት ዓለሙን በ፮ ቀናት ውስጥ እንደ ፈጠረ ይመስላልና። እስካሁን ድረስ ይህ ክርክር ባይፈታም ለከሃዲዎች ወገን ብዙ ተስፋ ሰጣቸው፤ «መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ የተሳተ ቢሆንስ ዓለሙ ፈቃዶቻችንም ምናልባት ያለምንም ፈጣሪ ዝም ብለው እንዳጋጣሚ ከአንዳችም ታይተዋል» በማለት ገመቱ። ይህ አይነት ጥርጣሬ አስተያየት በጣም ረቂቅ ግሩም ዓለማችን ወይም ነጻ ፈቃዳችን ለምን ወይም እንዴት ከአንዳችም እንደ ደረሱ ግን አይገልጽልንም፤ ብዙ የማይፈቱ ጥያቄዎች ከመተዉ በላይ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ በማስተዋል የተሳተ ነው በጭራሽ ለማለት እንዲህ ቀላል አይሆንም። ኦሪት ዘፍጥረት እንደሚለው፣ ከመጀመርያው ቀን በኋለ ምንም ጠፈር ወይም ፀሐይ ገና አልነበሩም፤ የነበረው ውሃ፣ ብርሃን፣ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ናቸው። መሬት በዚህ ቀን ከተገኘች፣ በውኃው ውስጥ መሆን ነበረበት እንጂ ጠፈር ወይም ፀሓይ ገና ሳይኖሩ የ«ቀን» ትርጉም እዚህ የመሬት 24 ሰዓታት መዞር ሊባል እንደ ቻለ አይመስልም። በእግዚአብሔር አስተያየት አንድ ቀን መባሉ ብርሃኑ ከውሃ ዙሪያ ለመጓዝ የፈጀበት ጊዜ ሊሆን ይቻላል። ከሳይንሳዊ ግመት በመተንተን እንግዲህ ይህ መጀመርያ «ቀን» ምናልባት 9 ቢሊዮን የኛ የምድር ዓመታት እንደ ሆነ ይቻላል። ከ፪ኛ ቀን በኋላ፣ አብዛኛው ውኃ ደርቆ ጠፈር ተፈጠረ፣ የቀረው ውኃ ተለይቶ ለምድርና ለአንዳንድ ሌላ ዓለም ይጠብቅ ነበር። ይህ «ቀን» ደግሞ ያለ ፀሓይ ብዙ ቢሊዮን አመታት ሊሆን ይችላል። ከ፫ኛ ቀን በኋላ፣ ውኃው በምድር በይበልጥ ደርቆ የብስ ተገለጠ፣ የብስም የአትክልት ወገን አስገኘ። በሳይንሳዊ ግመት ደግሞ ምንም እንስሳ ሳይኖር አትክልት በመላው የብስ ላይ ተስፋፍቶ ነበር። በዚህ አስተያየት ይህ «ቀን» ምናልባት ብዙ መቶ ሚሊዮን ዓመታት ቆየ። ከ፬ኛው ቀን በኋላ፣ ጸሐይ እና ጣቢያው በሙሉ በሥፍራ ተገኝቶ ነበር። ዳሩ ግን በሳይንሳዊ ግመት አትክልት የብሱን ከመሸፈኑና ጉንደ እንስሳ ከመታየቱ መካከል ብዙ መቶ ሚሊዮን ዓመታት ስላሉ፣ ይህም ቀን እንደኛ ቀን ዛሬ ነበር ማለት ያስቸግራል። ከ፭ኛው ቀን በኋላ፣ የባሕር እንስሳትና ተሳቢ አራዊት እስከ አዕዋፍ ድረስ ተፈጥረዋል። ባለፈው ቀን አትክልት የተገኙ ከየብስ ሲሆን፣ አሁን ግን የእንስሶችን ወገን ያስገኘው ውኃው ይባላል። አጥቢ እንስሳትና በመጨረሻ የሰው ልጅ ግን በሚከተለው ፮ኛው ቀን የተፈጠሩ ነው። የሰው ልጅም በተረፈው ዓለም ላይና በእንስሶች ላይ ላዕላይነትና ገዥነት ተሰጠ። ይህም ሁሉ ከሳይንሳዊው አስተሳሰብ በቅድመ ተከተል ረገድ እጅግ አይለይም፤ ቀኖቹ ግን ብዙ መቶ ሚሊዮን ዓመታት እንደ ፈጁ ይላል። እግዚአብሔር የአብርሃም ልጆችን ከድንጋይ በኃይሉ ማምጣት ከቻለ (ማቴ. 3:9)፣ በእርግጥ የበራሂ ኮድ ዐውቆአል ማለት ነው፤ ከጦጣ በራሂ አራያ ለውጦ የሰው ልጅን አራያ በራሂ ፈጥሮ 2) አዳም ግን ከጦጣ መወለዱ አስፈላጊ አልነበረም ማለት ነው፤ ከጦጣ ተወለደ ብንል ኖሮ ግን «ምድር ያስገኘው ፍጥረት» መባሉ እንኳ ውሸት አይሆንም ነበር። ከዚያ በኋላ ሰብአዊ ነፍስና አዕምሮ ተቀብሎ በዚያን ጊዜ ሰው «እግዜር ከመሬተ ምድር ያስገኘው ፍጥረት» ሆነና እግዜር ሰዎችን መፍጠሩ «መልካም እንደ ሆነ አየ» መባሉ ቁም ነገር ነው። ያም ሆነ ይህ ይህን ሁሉ ቸል ብለው «መጽሐፍ ቅዱስ ተሳተና ስለዚህ ይህ ሁሉ አለምና ሕያው ነፍስ ሕይወትም እንዳጋጣሚ ከአንዳችም ታዩ» የሚል የከሃዲ ወገን በየጥቂቱ ተቀባይነቱን ያስፋፋ ጀመር። የዝግመተ ለውጥ ትምህርት በመጨረሻ በአሜሪካ መንግሥት ትምህርት ቤቶች እንዲገባ ከተፈቀደ በኋላ፣ ጥቂት ዓመታት አልፈው የሥነ ፍጥረት ትምህርት ለማስወገድ የጣረ እንቅስቃሴ ተነሣ። በ1979 ዓም የአሜሪካ ላይኛ ችሎት ፈራጆች ይን ሃሣብ ተረድተው የሥነ ፍጥረተኛ ትምህርት ከአሜሪካ መንግሥት ትምህርት ቤቶች እንዲከለከል በየኑ። ለዚያው ብያኔ መሠረት፣ ሕገ መንግሥቱ የመንግሥት ሃይማኖትን ስለማይፈቅድ፣ የአገሩ ምክር ቤት ይቅርና ትምህርት ቤት ስንኳ ምንምን ሃይማኖት ለመደግፍ አይፈቀድምና ዝግመተ ለውጥ ከከሃዲነት ጋራ ማስተምር ተገደዱ አሉ። ከዚህ ቀጥሎ የ«ባለሙያ ንድፍ» ሃሣብ ዘመናዊነት አገኘ። በተለይ በአሜሪካ ሰፊ ሕዝብ መካከል፣ ላይኛ ችሎቱ ሥነ ፍጥረት ከትምህርት ቤት ምንም ቢያስወግድም፣ ከግማሽ በላይ የክርስትናንና የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች ናቸው። ነገር ግን የ«ባለሙያ ንድፍ» ክርክር እንደገና በ1998 ዓም በአንድ የአሜሪካ ችሎት ቀርቦ፣ ፈራጁ የከሃዲነትን ወገን ደግፎ አለሙ በማናችም «ባለሙያ ንድፈኛ» ከቶ አልተነደፈም በማለት በየነ፤ ወይም ይህ አስተሳሰብ ሳይንሳዊ ስለማይሆን በትምህርት ቤት አይፈቀድም፤ በመንግሥት ትምህርት ቤት ከሃዲነት ብቻ ይታገሣል ማለት ነው። በአውሮፓ ኅብረት መንግሥት ደግሞ ከከሃዲነት በቀር ይህ አሣብ ምንም ሳይታገስ በፍጹም ይከለከላል። በእስልምናና በሂንዱኢዝም አገራት ዘንድ ግን፣ ዓለም የ«ባለሙያ ንድፍ» ነው የሚል ሃሣብ ለትምህርት ሳይንሳዊ መሆኑ ትኩረትና ተቀባይነት አገኝቷል። 'ባለሙያነት' ምን ማለት ነው? በክርስቲያናዊ ፍልስፍናና አስተያየት ብልሃት ከሰው ልጆች የሚወጣ ሲሆን ጥበብ ሁሉ ከፈጣሪ ይወጣል። የሰው ልጅ ብልሃት ሲዳከም የፈጣሪ ጥበብ ሊረዳን የሚቻለው ነው። «ባለሙያ» ለሮማይስጡ ሲተረጎም በዚሁ ረገድ ይህ ባለሙያነት የፈጣሪ ጥበብ እንጂ የሰው ልጅ አይነት ብልሃት አይሆንም። እግዚአብሔር እኛን ከጡት አጥቢዎች የሠራን ከድሮ ጀምሮ ቢታወቅም፣ ይህ የሆነው ምድሪቱ «የእግዚአብሔር መረገጫ» እንዲል (ኢሳ. ማቴ ለመፈጸም በማሠብ ሆን ብሎ ተደረገ ማለቱ ነው። ሳይንስ ሃይማኖት የፖለቲካ
47199
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%88%AE%E1%88%9B%20%E1%8A%AB%E1%89%B6%E1%88%8A%E1%8A%AD%20%E1%89%A4%E1%89%B0%20%E1%8A%AD%E1%88%AD%E1%88%B5%E1%89%B2%E1%8B%AB%E1%8A%95
የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን
የካቶሊክ እምነት እውነተኛ መነሻ በክርስትና ታሪክ ስለ ካቶሊክ መነሻ እና የክርስትና መከፋፈል በስፋት ማወቅ ከፈለጉ ይህንን ጽሑፍ በእርጋታ ያንብቡ! አውጣኪ፣ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ እና የኬልቄዶን ጉባኤ በቀሲስ ዶ/ር ምክረ ሥላሴ ገ/አማኑኤል መግቢያ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በመካከለኛው ምሥራቅ በተለይ በአንጾኪያና በግብጽ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ያወከና ታላቅ ብጥብጥ የፈጠረ በምሥጢረ ሥላሴ እምነት ላይ የተነሣ የተሳሳተ ትምህርት ነበር፡፡ ይኸውም አርዮስ ከእስክንድርያዊው መምህሩ ከአርጌኒስ በቀሰመው ትምህርት በዘዴ ‹‹ክብር ምስጋና ይግባውና እግዚአብሔር ወልድን ፍጡር ነው፤ አምላክም አይደለም፤›› ለማለት ‹‹ሀሎ አመ ኢሃሎ ወልድ›› (ወልድ ያልነበረበት ጊዜ ነበር) በግሪክኛ፡- ‹‹ኢን ፖቴ ኦቴ ኡክ ኢን›› ብሎ የክሕደት ትምህርት በማስተማሩ መላው የክርስትናው ዓለም ታውኮ ነበር፡፡ ይህ በ325 ዓ.ም. በኒቂያ ጉባኤ አርዮስና ኑፋቄው በመወገዙ ችግሩ መፍትሔ አግኝቶ ነበር፡፡ ከ106 ዓመታት በኋላ ደግሞ ንስጥሮስ ከአንጾኪያ በአገኘው ትምህርት በቊስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያን በምሥጢረ ሥጋዌ እምነት ላይ ስለ ክርስቶስ የተሳሳተ ትምህርት ያስተምር ጀመር፡፡ ይኸውም ንስጥሮስ 1ኛ ክርስቶስ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ አለው፤ 2ኛ/ ክርስቶስ ፍጹም ሰው እንጂ ፍጹም አምላክ አይደለም፤ እንዲሁም 3ኛ/ እመቤታችን ሰውን እንጂ አምላክን አልወለደችም፤ ስለዚህ እመቤታችን ወላዲተ ሰብእ እንጂ ወላዲተ አምላክ ልትባል አይገባትም (ሕስወኬ ትሰመይ ወላዲተ አምላክ፣ በአማን ትሰመይ ወላዲተ ሰብእ) ብሎ በማስተማሩ ይህ ኑፋቄ በ431 ዓ.ም. ላይ በታላቁ መምህር በእስክንድርያው ፓትርያርክ በቅዱስ ቄርሎስ አማካኝነት በኤፌሶን ጉባኤ ተወግዞ ችግሩ ተወግዶ ነበር፡፡ ሆኖም የንስጥሮስ የክህደት እምነት ጨርሶ ሳይጠፋ በዚያው በመካከ ለኛው ምሥራቅ በተለይ በፋርስና በባቢሎን እንዲሁም በኤዴሳ ሲስፋፋ ቆይቷል፡፡ እንዲሁም ንስጥሮሳውያን በኤፌሶንና በቊስጥንጥንያ በብዛት ይገኙ ነበር፡፡ አውጣኪና ትምህርቱ የንስጥሮስን ትምህርት በጥብቅ ይቃወሙ የነበሩት የግብጽ መነኰሳትና ካህናት ነበሩ፡፡ በቊስጥንጥንያም ቢሆን አያሌ የንስጥሮስ ተቃዋሚዎች ነበሩ፡፡ የንስጥሮስን ትምህርት አጥብቆ ይቃወም የነበረና ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት እጅግ ቀናኢ የነበረ አውጣኪ የተባለ በቊስጥንጥንያ የአንድ ትልቅ ገዳም አበምኔት (መምህር) ነበር፡፡ አውጣኪ ‹‹ክርስቶስ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ አለው›› የሚለውን የንስጥሮሳውያንን ትምህርት አጥብቆ በመቃወም እሱ ወደ ተቃራኒው የባሰ ክህደት ውስጥ ገባ፡፡ አውጣኪ በቊስጥንጥንያ ‹‹ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ብቻ አለው፤›› እያለ ያስተምር ጀመር፡፡ አባባሉ የቅዱስ ቄርሎስን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ይመስላል፡፡ አውጣኪ ግን ‹‹አንድ ባሕርይ›› ሲል የክርስቶስን መለኮታዊ ባሕርይ ብቻ ማለቱ ነበር፡፡ በአውጣኪ አባባል ‹‹ሁለቱ ባሕርያት ማለት የሥጋና የመለኮት ባሕርያት በተዋሐዱ ጊዜ የመለኮት ባሕርይ የሥጋን ባሕርይ ውጦታል፤ አጥፍቶታል፡፡ ሥጋና መለኮት ከተዋሐዱ በኋላ በክርስቶስ ላይ የሚታየው የመለኮት ባሕርይ ብቻ ነው፡፡ በክርስቶስ የሥጋ ባሕርይ ተውጦ የመለኮት ባሕርይ ብቻ ነው የሚታየው፤›› ይል ነበር፡፡ ይህ አባባል በእኛም ቤተ ክርስቲያን ማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተወገዘ ነው፡፡ አውጣኪ በተጨማሪ ከሥጋዌ በኋላ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ነው ለማለት ‹‹ክርስቶስ ዘዕሩይ ምስሌነ በትስብእቱ›› ማለት ‹‹ክርስቶስ በትስብእቱ (በሥጋው) ከእኛ ጋር አንድ ነው›› የሚለውን ኦርቶዶክሳዊ አነጋገር አይቀበልም ነበር፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት መሠረት ‹‹ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው፡፡›› ነገር ግን ፍጹም ሰው ካልሆነና እኛን ወክሎ በመስቀል ላይ በሥጋው መከራን ካልተቀበለ፣ የእኛ የሰዎች ድኅነት አስተማማኝ አይሆንም፡፡ በክርስቶስ የሥጋና የመለኮት ባሕርያት ተዋሕደው በመስቀል ላይ በአንድነት ባሕርዩ በተቀበለው መከራ ድኅነትን አግኝተናል፡፡ ‹‹በክርስቶስ የሥጋ ባሕርይ ተውጦ ወይም ጠፍቶ የመለኮት ባሕርይ ብቻ ነው የሚታየው›› የሚለውን የአውጣኪን የኑፋቄ (የክህደት) ትምህርት የሰማው የቊስጥንጥንያ ፓትርያርክ ፍላብያኖስ ወዲያውኑ ደብዳቤ ጽፎ ስሕተቱን በማስረዳት አውጣኪ ከስሕተቱ እንዲታረምና ይህን ትምህርት እንዳያሰራጭ አስጠነ ቀቀው፡፡ አውጣኪ ግን የኑፋቄ ትምህርቱን አላቆመም፡፡ ከዚህ ላይ አንድ ነገር ማስታወስ አለብን፤ ይኸውም አውጣኪ ክሪሳፍዮስ ለተባለው ለንጉሠ ነገሥቱ ለዳግማዊ ቴዎዶስዮስ ኃይለኛ ጠቅላይ ሚኒስትር የንስሓ አባት ስለነበር የልብ-ልብ የተሰማው ይመስላል፡፡ ፓትርያርክ ፍላብያኖስም ይህንን ስለሚያውቅ ይመስላል አውጣኪን በጣም ሊጫነው አልፈለገም፡፡ ሆኖም ኃይለኛ የነበረ የዶሪሊያም ሊቀ ጳጳስ የነበረው አውሳብዮስ አውጣኪን አጥብቆ ስለ ተቃወመውና ስለ ከሰሰው፣ የቊስጥንጥንያው ፓትርያርክ ፍላብያኖስ እንደተለመደው የመላው አብያተ ክርስቲያናት ጳጳሳት ተጠርተው ጉባኤ በማድረግ ፈንታ፣ በእርሱ ስር የሚተዳደሩትን ሃያ ዘጠኝ ጳጳሳትንና ሠላሳ ሦስት የገዳማት አበምኔቶችን ብቻ ሰብስቦ በእርሱ ሰብሳቢነት በ448 ዓ.ም. በቊስጥንጥንያ አህጉራዊ ሲኖዶስ አድርጎ የአውጣኪን የክሕደት ትምህርት መመርመር ጀመረ፡፡ አውጣኪ በጉባኤው ላይ እንዲቀርብ ሁለት ጊዜ ተጠርቶ ለመቅረብ አልፈለገም፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ ሲጠራ ብቻ ቀርቦ ስለ ኑፋቄ ትምህርቱ ሲጠየቅ ግልጽ ያልሆነ የሃይማኖት መግለጫ በጽሑፍ አቀረበ፡፡ መግለጫው ግን ስለተከሰሰበት የክህደት ትምህርት ምንም አይገልጥም፡፡ ሆኖም የዶሪሊያም ጳጳስ አውሳብዮስ ግልጥ አድርጎ ‹‹ክርስቶስ በትስብእቱ ከእኛ ጋር አንድ ነው?›› ብሎ በጠየቀው ጊዜ አውጣኪ አንድ አይደለም በማለት ካደ፡፡ ከክህደቱም እንዲመለስ ቢጠየቅ አሻፈረኝ አለ፡፡ ስለዚህ ጉባኤው አውጣኪን አወገዘው፡፡ ከአበምኔት ሹመቱና ከክህነት ሥልጣኑም ሽሮ ተራ ሰው አደረገው፡፡ የሮሙ ፖፕ ለቊስጥንጥንያው ፓትርያርክ ፍላብያኖስ ‹‹ክርስቶስ ሁለት ባሕርያት አንድ አካል አለው›› የሚል የሃይማኖት ፎርሙላ የያዘ ደብዳቤ ልኮለት ስለነበረ፤ አውጣኪ ይህንንም ነበር እንዲቀበል የተጠየቀው፡፡ ይህ ደግሞ ከንስጥሮስ ኑፋቄ ጋር የተዛመደ ስለነበረ (ይህ አባባል መንፈቀ ንስጥሮሳዊ ይባላል) አውጣኪ አልቀበልም አለ፡፡ ስለዚህ አውጣኪ ‹‹የቅዱስ ቄርሎስን ሃይማኖት ስለመሰ ከርኩ እንጂ አንዳች የሃይማኖት ስሕተት ሳይኖርብኝ ያለ አግባብ ተወገዝኩ፤›› ብሎ ለንጉሠ ነገሥቱ ለዳግማዊ ቴዎዶስዮስ አመለከተ፡፡ እንዲሁም ለሮም ፖፕ ለልዮን ቀዳማዊና ለእስክን ድርያው መንበረ ፓትርያርክ ለዲዮስቆሮስ ለሌሎችም ጳጳሳት ደብዳቤ ላከ፡፡ የቊስጥንጥንያው ፓትርያርክ ፍላብያኖስም በበኩሉ የአውጣኪን ኑፋቄና ጉባኤው ስለ እርሱ የወሰነውን ውሳኔ ለፖፕ ልዮን ላከለት፡፡ ፖፑም የጉባኤውን ውሳኔ በማጽደቅ ምሥጢረ ሥጋዌን የያዘ ደብዳቤ ለፍላብያኖስ በድጋሚ ላከለት፡፡ በደብዳቤውም ውስጥ ክርስቶስ ሁለት ባሕርያትና አንድ አካል እንዳለው በግልጽ አስፍሯል፡፡ ይህም አባባል ከላይ እንደተገለጸው መንፈቀ ንስጥሮሳዊ ነው፡፡ ሁለተኛው የኤፌሶን ሲኖዶስ (449) አውጣኪ በቊስጥንጥንያ እጅግ የተከበረ ሰው ስለነበረና ብዙም ደጋፊዎች ስለነበሩት የእርሱ በ448 ዓ.ም. ጉባኤ መወገዝ ብዙዎችን አስቆጥቶ ነበር፡፡ እንደውም ያወገዘው ፓትርያርክ ፍላብያኖስ ንስጥሮሳዊ ነው እየተባለ ይወራና ይወቀስ ጀመር፡፡ ንጉሠ ነገሥቱም የነገሩን ክብደት ተመልክቶ ምናልባትም በአውጣኪ ንስሓ-ልጅ በጠቅላይ ምኒስትሩ ተጽእኖ ይሆናል ዓለም-አቀፍ የአብያተ ክርስቲያናት ጳጳሳት ሲኖዶስ በኤፌሶን እንዲደረግ ለጳጳሳቱ ሁሉ ጥሪ አስተላለፈ፡፡ ስብሰባውም በነሐሴ ወር 449 ዓ.ም. በኤፌሶን እንዲሆን ተወሰነ፡፡ ባለፉት ሲኖዶሶች እንደተደረገው ሁሉ የእስክንድርያው ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ሰብሳቢ እንዲሆን ንጉሠ ነገሥቱ ወሰነ፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሰብሳቢ በመሆኑ ሃያ ሦስት ከሚሆኑ ከግብጽ ጳጳሳት ጋር ቀደም ብሎ ኤፌሶን ደረሰ፡፡ ፖፕ ልዮን ግን ይህ ስብሰባ እንዲደረግ አልፈለገም ነበር፡፡ እንደውም ለንጉሠ ነገሥቱ ታላቅ እኅት ለብርክልያ ንጉሡ ጉባኤውን እንዳይጠራ እንድታግባባው ጠይቋት ነበር፡፡ ሆኖም ንጉሠ ነገሥቱ በሐሳቡ ጸንቶ ጉባኤውን ስለጠራ ፖፑም ሦስት መልእክተኞች ላከ፡፡ በጉባኤው ላይ አንድ መቶ ሠላሳ አምስት ጳጳሳት ተሰብስበው ነበር፡፡ ምንም እንኳ ጉባኤው ስብሰባውን የጀመረው አንድ ሳምንት ዘግይቶ ቢሆንም የሮሙ ፖፕ እንደራሴዎች በዚህ ጊዜ ሊገኙ አልቻሉም፡፡ የቊስጥንጥንያው ፓትርያርክ ፍላብያኖስም በጉባኤው ላይ እንዲገኝ ተጠርቶ አልመጣም፡፡ የቀረበትንም ምክንያት አልገለጠም፡፡ ምናልባትም በእሱ ሰብሳቢነት የተሰበሰበው አህጉራዊ ሲኖዶስ ያወገዘው የአውጣኪ ጉዳይ እንደገና እንዲታይ በመደረጉ ቅር ብሎት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ አዲስ ነገር አልነበረም፡፡ ከዚህ በፊትም ብዙ መናፍቃን አርዮስም ጭምር መጀመሪያ በአህጉራዊ ሲኖዶሶች ከተወገዙ በኋላ ነበር ጉዳያቸው እንደገና በዓለም-አቀፍ ሲኖዶሶች እንዲታዩ የተደረገው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ጳጳሳት ተጠብቀው ባይመጡም ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ የተገኙትን አንድ መቶ ሠላሳ አምስት ጳጳሳት ይዞ በነሐሴ ወር 449 ዓ.ም. ስብሰባውን ጀመረ፡፡ ጉባኤው የተደረገው እንደበፊቱ በኤፌሶን በቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ ጉባኤውም እንደተጀመረ አውጣኪ ተጠርቶ ስለተከሰሰበት ጉዳይ መልስ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ አውጣኪ በቊስጥንጥንያ ሕዝብ እጅግ የተወደደና የተደነቀ ከመሆኑም በላይ በቃላት የሚጫወት ቅንነት የጐደለው ሰው ነበር፡፡ አውጣኪ በጉባኤው ፊት ቀርቦ በራሱ እጅ የተጻፈና የፈረመበት የእምነት መግለጫ አቀረበ፡፡ መግለጫውም ከመነበቡ በፊት ራሱ እንዲህ ሲል ጮኾ ተናገረ፡- ‹‹ከልጅነቴ ጀምሮ በግልጥ በምነና (በብሕትውና) ለመኖር ነበር የምፈልገው፡፡ ዛሬ በሕዝብ መካከል በመገኘቴ ታላቅ ሐዘን ይሰማኛል፡፡ ሆኖም እምነቴን ለመመስከር ስለሆነ ደስታ ይሰማኛል፡፡ በኒቅያ ጉባኤ የተወሰነውንና አባታችን የእስክንድርያው ፓትርያርክ ቅዱስ ቄርሎስ ያስተማረውን እምነት በትክክል እቀበላለሁ፤›› አለ፡፡ ከዚህ በኋላ የጉባኤው ጸሓፊ የሚከተለውን የአውጣኪ የእምነት መግለጫ ማንበብ ጀመረ፤ መግለጫውም እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሁሉን በያዘ፣ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ አምናለሁ፡፡ በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ በሚሆን በአንድ ልጁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ፤ ለእኛ ለሰዎች ሲል ለድኅነታችን ከሰማይ ወረደ፡፡ ሥጋ ለበሰ፤ ሰውም ሆነ፡፡ ታመመ፤ ሞተ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ ይመጣል፡፡ እርሱ ያልነበረበት ጊዜ ነበረ የሚሉ፣ ከመወለዱም በፊት አልነበረም፤ ካለምንም ተፈጠረ የሚሉት፣ ከአብ ጋር በባሕርዩ የተለየ ነው የሚሉት፣ የእርሱ ሁለቱ ባሕርያት ተቀላቅለዋል ወይም ተዋውጠዋል የሚሉት፣ እነዚህ ሁሉ በአንዲት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን የተወገዙ ናቸው፡፡ እኔም የምከተለው እምነት ይህ ነው፡፡ በዚህ እምነት እስካሁን ኖሬአለሁ፤ ወደፊትም እስክሞት ድረስ በዚሁ እኖራለሁ፡፡›› የሚል ነበር፡፡ አውጣኪ ይህንን ለጉባኤው ሲያስረዳ ተከትለዉት የመጡትም መነኰሳት አውጣኪ ያቀረበውና የተናገረው ትክክል መሆኑን ከዚያው በጉባኤው ፊት አረጋገጡ፡፡ ስለዚህ ይህን የሃይማኖት መግለጫ ከአዩና ከሰሙ በኋላ አራት ሊቃነ ጳጳሳት ማለት የኢየሩሳሌሙ፣ የአንጾኪያው፣ የኤፌሶኑና የቂሣርው ዘቀጰዶቅያ አውጣኪ በእምነቱ ኦርቶዶክስ ነው በማለት ለጉባኤው አጽንተው ሲናገሩ ሁሉም አውጣኪ ከተከሰሰበት ኑፋቄ ንጹሕ መሆኑን በአንድ ድምፅ ወሰኑ፡፡ ከተላለፈበትም ውግዘት ፈቱት፡፡ ሥልጣነ ክህነቱንም መልሰውለት ወደ ቀድሞው የሓላፊነት ሥራው እንዲመለስ ውሳኔ አስተላለፉ፡፡ የሁለት ባሕርይን ሐሳብ ይቀበል የነበረው የዶሪሊያም ጳጳስ አውሳብዮስ አውጣኪን በመወንጀል መግለጫ ሲያቀርብ በዚያ የተሰበሰቡት መነኰሳትና ምእመናን በታላቅ ድምፅ ‹‹አውሳብዮስ ይቃጠል! አውሳብዮስ በሕይወቱ ይውደም! ክርስቶስን ለሁለት እንደ ከፈለ እሱም ለሁለት ይከፈል!›› እያሉ ይጮኹ ጀመር፡፡ የቊስጥንጥንያን ፓትርያርክ ፍላብያኖስንና አውጣኪን ያወገዙትን ጳጳሳት የሮሙን ፖፕ ልዮን 1ኛን ጭምር አውጣኪን ያለ አግባብ በማውገዛቸውና ሥልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀማቸው ጉባኤው ካወገዛቸው በኋላ፣ የሚከተለውን አጭር መግለጫ አወጣ፡- ‹‹ከኒቅያ እስከ ኤፌሶን አባቶቻችን በጉባኤ ተሰብስበው ከወሰኑት ሃይማኖት ሌላ የሚጨምር፣ የሚቀንስ ወይም የሚያሻሽል ቢኖር የተወገዘ ይሁን፡፡›› ዘግይተው የደረሱት የፖፑ መልእከተኞች ዩልዮስና ሬናቱስ የተባሉት ጳጳሳትና ዲያቆን ሂላሩስ ከፖፑ የተላከውን የሃይማኖት መግለጫ ደብዳቤ እንዲነበብ ጠይቀው ነበር፡፡ ነገር ግን ደብዳቤው ‹‹ክርስቶስ ሁለት ባሕርያት አንድ አካል አለው›› ስለሚልና ይህም ከንስጥሮስ ኑፋቄ ጋር ስለሚመሳሰል ጉባኤው እንዲነበብ አልፈቀደም፡፡ በዚህም ምክንያት የፖፑ መልእከተኞች ተቀይመው ወዲያውኑ በድብቅ ከጉባኤው ወጥተው ወደመጡበት ተመለሱ፡፡ የጉባኤውም ውሳኔ በንጉሠ ነገሥቱ በዳግማዊ ቴዎዶስዮስ ጸደቀ፡፡ የቊስጥንጥንያ ፓትርያርክ ፍላብያኖስ በኤፌሶን 2ኛ ጉባኤ እንደተወገዘ ወዲያውኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ የዚህን ጉባኤ ውሳኔ ሲሰማ የሮሙ ፖፕ ልዮን ቀዳማዊ እጅግ ተናዶ ጉባኤውን ‹‹ጉባኤ ፈያት (የወንበዴዎች ጉባኤ)›› ብሎ ጠራው፡፡ የጉባኤውንም ሊቀ መንበር ቅዱስ ዲዮስቆሮስን አወገዘው፡፡ ከእስክንድርያ ጋር የነበረውንም ግንኙነት ጨርሶ አቋረጠ፡፡ ፖፑ ይህን ሁሉ ያደረገው እሱ የላከው የሃይማኖት ነክ ደብዳቤ በጉባኤው ላይ ስላልተነበበና የእርሱም መልእክተኞች በጉባኤው ላይ በሙሉ ባለመካፈላቸው ነበር፡፡ በተጨማሪም ፖፑ ለንጉሠ ነገሥቱ ለዳግማዊ ቴዎዶስዮስ የኤፌሶኑን ጉባኤ የዲዮስቆሮስ ጉባኤ ብሎ በመጥራት በጉባኤው ላይ ያለውን ቅሬታ ከገለጸ በኋላ፣ ሌላ ዓለም አቀፍ ሲኖዶስ (ጉባኤ) እንዲጠራ ጥብቅ ሐሳብ አቀረበ፡፡ እንዲረዳውም የምዕራቡን ክፍል ገዥ (ንጉሥ) የነበረውን ሣልሳዊ ዋሌንቲኒያኖስን እና ሚስቱን ንግሥት አውዶቅሲያን አጥብቆ ለምኖ ነበር፡፡ እነዚህም ባለሥልጣኖች እያንዳንዳቸው ሐሳቡን በመደገፍ ለንጉሠ ነገሥቱ ለዳግማዊ ቴዎዶስዮስ ደብዳቤ ጽፈው ነበር፡፡ ዳግማዊ ቴዎዶስዮስ ግን ሁለተኛው የኤፌሶን ጉባኤ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላቸው የቅዱሳን አባቶች ጉባኤ መሆኑን ገልጦ በመጻፍ ስለ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ምንም የሚያሳስብ ነገር አለመኖሩን ገልጦ አሳስቧቸዋል፡፡ በተጨማሪም የምዕራቡን ንጉሥና ንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡ መክሯቸው ነበር፡፡ ፖፕ ልዮን ግን ሌላ ዓለም-አቀፍ ሲኖዶስ እንዲደረግ ዳግማዊ ቴዎዶስዮስን አጥብቆ መጠየቁን ቀጠለ፡፡ ሆኖም የፖፑ ጥረት ሁሉ ውጤት አላስገኘም፡፡ ምክንያቱም ዳግማዊ ቴዎዶስዮስ ለ2ኛው የኤፌሶን ጉባኤ ታላቅ አክብሮት ስለነበረውና ውሳኔውንም በሚገባ ስላጸደቀው ነበር፡፡ የኬልቄዶን ጉባኤ ሁለተኛው የኤፌሶን ጉባኤ ከአለፈ ከአንድ ዓመት በኋላ በሐምሌ ወር 450 ዓ.ም. ዳግማዊ ቴዎዶስዮስ በድንገት ከፈረስ ላይ ወድቆ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ ቴዎዶስዮስ ወራሽ ስላልነበረው ለአልጋው ቅርብ የነበረች ታላቅ እኅቱ ብርክልያ ነበረች፡፡ ብርክልያ ግን በድንግልና መንኵሳ ነበር የምትኖረው፡፡ ሆኖም ብርክልያ ለሥልጣን ስለጓጓች ምንኵስናዋን አፍርሳ የሮም መንግሥት የጦር አዛዥ ጄኔራል የነበረውን መርቅያን አግብታ በነሐሴ ወር 450 ዓ.ም. እሱ ንጉሠ ነገሥት እሷ ንግሥት ሆነው የሮምን ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ማስተዳደር ጀመሩ፡፡ ይህ የብርክልያ ምንኵስናን ማፍረስ በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በተለይም በግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም ነበር፡፡ የሮሙ ፖፕ ግን ከአዲሶቹ የሮም መንግሥት ንግሥትና ንጉሠ ነገሥት ዘንድ ተወዳጅነትን ለማግኘት ሲል ጋብቻቸውን በማወደስ አጸደቀላቸው፤ ቡራኬውንም ላከላቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ፖፕ ልዮን ከቊስጥንጥንያ ንጉሣዊ ቤተሰብ ጋር ወዳጅነትን መሠረተ፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ ብሎም በጻፈው ደብዳቤ መጨረሻ ላይ እሱ የፈለገው ዓለም አቀፍ ሲኖዶስ እንዲሰበሰብ አሳሰበ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ ነገሥቱ በመርቅያንና በፖፕ ልዮን መካከል ብዙ የወዳጅነት ደብዳቤዎች ተጻጽፈዋል፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ መርቅያን በሥልጣኑ በ2ኛው በኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘው የፍላብያኖስ አስከሬን ፈልሶ በቊስጥንጥንያ በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ክብር እንዲቀበር አደረገ፡፡ የተጋዙት ጳጳሳትም ከግዞት ወጥተው ወደየሥራቸው እንዲመለሱ አደረገ፡፡ በመሠረቱ በሲኖዶስ የተወገዙት ወደ ቀድሞ ሥራቸው መመለስ የሚችሉት በንጉሥ ትእዛዝ ሳይሆን በጳጳሳት ሲኖዶስ መሆን ስለነበረበት ንጉሡ ያደረገው ሕገ-ወጥ ሥራ ነበር:: ፖፑም የሱ ፍላጎት ስለነበረ ይህንን አልተቃወመም፡፡ በተቃራኒው ንጉሡ የተወገዙት ጳጳሳት ወደየሀገረ ስብከታቸው እንዲመለሱ የፍላብያኖስም አስከሬን ወደ ቊስጥንጥንያ ፈልሶ በክብር እንዲቀበር በማድረጉ ፖፕ ልዮን ለንጉሠ ነገሥቱ ልባዊ ምስጋና አቅርቧል፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ መርቅ ያንና ንግሥቲቱ ብርክልያ 2ኛው የኤፌሶን ሲኖዶስ ባቀረበው የሃይማኖት መግለጫ መሠረት ነፃ ያደረገውን አውጣኪንም ያለ ሲኖዶስ ውሳኔ ወደ ሰሜን ሶርያ እንዲጋዝ አደረጉ፡፡ ፖፕ ልዮን በአሳሰበው መሠረት ንጉሥ መርቅያን ጥቅምት 8 ቀን 451 ዓ.ም. ዓለም-አቀፍ ሲኖዶስ እንዲደረግ ለጳጳሳት ሁሉ ጥሪ አስተላለፈ፡፡ ጉባኤውም እንዲደረግ የታሰበው ከቊስጥንጥንያ 96 ኪሎ ሜትር ያህል ርቃ በምትገኝ በኒቅያ ነበር፡፡ ነገር ግን በጸጥታ ምክንያት ከቊስጥንጥንያ 3 ኪሎ ሜትር ብቻ ርቃ በምትገኘው በኬልቄዶን እንዲሆን ንጉሡ ስለ ወሰነ ጉባኤው በኬልቄዶን ሆነ፡፡ ንጉሥ መርቅያንና ንግሥት ብርክልያ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ተገኝተዋል፡፡ ጉባኤው በሥነ ሥርዓት መካሄዱን የሚቆጣጠሩ 18 ዳኞች በንጉሡ ተሠይመው ነበር፡፡ እነዚህ ሁሉ ዳኞች መሠየማቸው መንግሥት ሲኖዶሱን ምን ያህል እንደተቈጣጠረው ያመለክታል፡፡ የጉባኤው አባላት አቀማመጥ እንደሚከተለው ነበር፤ ዳኞቹ በመኻል ከዳኞቹ በስተግራ የፖፑ መልእክተኞች፣ ቀጥሎ የቊስጥንጥንያው አናቶልያስ፣ የአንጾኪያው ማክሲሙስ፣ የቂሣርያውና የኤፌሶኑ ጳጳሳትና ሌሎች የምሥራቅና የመካከለኛው ምሥራቅ አህጉር ጳጳሳት ሲሆኑ፣ በቀኝ በኩል ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የኢየሩሳሌም፣ የተሰሎንቄ፣ የቆሮንቶስ፣ የግብጽ፣ የኢሊሪኩም፣ የፍልስጥኤም ጳጳሳትና ሌሎች ጳጳሳት ተቀምጠዋል፡፡ በኤፌሶን ጉባኤ የተወገ ዙትን ንስጥሮሳውያን መናፍቃንን የቂሮስ ኤጲስቆጶስ ቴዎዶሪጦስንና የኤዴሳን ኤጲስቆጶስ ኢባንን የዚህ ጉባኤ አባላት አድርገው ተቀበሏቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ብዙ ብጥብጥ ተነሣ፤ የግብጽ ጳጳሳት በኤፌሶን ጉባኤ የተወገዙትን ንስጥሮሳውያን ቴዎዶሪጦስንና ኢባንን ጉባኤው በአባልነት በመቀበሉ ‹‹አይሁዶችን፣ የክርስቶስን ጠላቶች ከዚህ አስወጡ!›› እያሉ በመጮኽ ተቃውሟቸውን አሰሙ፡፡ ጉባኤው ግን የእነሱን ጩኸት ከቁም ነገር አልቈጠረውም፡፡ ጉባኤውን በሊቀ መንበርነት በተራ የመሩት ከመንግሥት የተሠየሙት ዳኞችና የሮሙ ፖፕ መልእከተኞች ነበሩ፡፡ የሮሙ ተወካዮች ጉባኤውን ሲመሩ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር፡፡ ከአሁኑ በስተቀር ባለፉት ዓለም-አቀፍ ሲኖዶሶች ሁሉ የእስክንድርያው ፓትርያርክ ከሊቃነ መናብርቱ ዋናው ነበር፡፡ አሁን ግን የእስክን ድርያውን ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስን ለመኰነን የተሰበሰበ ሲኖዶስ ስለሆነ ዲዮስቆሮስ ከሊቃነ መናብርቱ አንዱ አልሆነም፡፡ የጉባኤው አባላት ቦታቸውን ይዘው እንደተቀመጡ የሮሙ ፖፕ ተወካይ ፓስካሲኑስ ተነሥቶ ለዳኞቹ ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ከተቀመጠበት ቦታ ማለት ከጉባኤው እንዲነሣና ሌላ ቦታ እንዲቀመጥ አመለከተ፡፡ የመንግሥቱ ዳኞች ለምን ይነሣል ብለው በጠየቁ ጊዜ፣ ሌላው የፖፑ መልእክተኛ ሊሴንቲያስ የተባለው ዲዮስቆሮስ ከዚህ በፊት የሮሙ ፖፕ ሳይፈቅድ በሥልጣኑ ሲኖዶስ (የ449 ሲኖዶስን ማለቱ ነው) እንዲካሄድ አድርጓል በማለት ክስ አቀረበ፡፡ ይህ ግን መሠረት የሌለው ክስ ነበር፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት የተደረጉት ሲኖዶሶች ሁሉ የተጠሩትና የተካሄዱት በሮም ንጉሠ ነገሥት ፈቃድና ትእዛዝ እንጂ በሮሙ ፖፕ ፈቃድ አልነበረም፡፡ ያለፈውም የሁለተኛው የኤፌሶን ሲኖዶስ የተጠራው በዳግማዊ ቴዎዶስዮስ ትእዛዝ እንጂ በፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ሥልጣን አልነበረም፡፡ ስለዚህ የቀረበው ክስ ዳኞቹን አላረካ ቸውም፡፡ በዚህ ጉዳይ ብዙ ጭቅጭቅ ስለተፈጠረ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በፈቃዱ ቦታውን ለቆ ተከሳሾች በሚቀመጡበት ቦታ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ የሮሙ ፖፕ ተወካዮች በሁለተኛው የኤፌሶን ጉባኤ ፓትር ያርክ ዲዮስቆሮስ የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና አፍርሷል ሲሉ ከሰሱ፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሲመልስ እሱ በንጉሠ ነገሥቱ በቴዎ ዶስዮስ ትእዛዝና ጥያቄ መሠረት ነው ጉባኤውን የመራው፡፡ እሱ ቀኖናን አፈረሰ? ወይስ በኤፌሶን ጉባኤ የተወገዙትን ንስጥሮሳውያን መናፍቃንን የቂሮስ ኤጲስ ቆጶስ ቴዎዶሪጦስንና የኤዴሳን ኤጲስቆጶስ ኢባንን የዚህ ጉባኤ አባላት አድርገው የተቀበሉት እነሱ ናቸው ቀኖና አፍራሾች? ብሎ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ሆኖም ይህ የፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ጥያቄ ምንም መልስ ሳይሰጠው በዝምታ ታለፈ፡፡ ቀጥሎ በ2ኛው የኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘው የዶሪሌኡም ኤጲስቀጶስ አውሳብዮስ ተነሥቶ ዲዮስቆሮስ እሱንና የቊስጥንጥንያውን ፍላብያኖስን ‹‹ምንም የሃይማኖት ጕድለት ሳይገኝብን ያለ አግባብ አውግዞናል ጥቃትም አድርሶብናል፡፡ በተጨማሪም አውጣኪን ከግዝቱ በመፍታት የኦርቶዶክስ እምነትን አበላሽቷል፤›› በማለት ክስ አቀረበ፡፡ ይህ ተመሳሳይ ክስ በሮሙ ፖፕ ተወካዮችም ቀርቧል፡፡ በመሠረቱ ይህ ክስ እውነት እንኳ ቢሆን የሚመለከተው ሲኖዶሱን እንጂ የሲኖዶሱን ሊቀ መንበር ዲዮስቆሮስን አልነበረም፡፡ ከዚህ ላይ ልንገነዘበው የሚገባው የሮሙ ፖፕ ተወካዮችም ሆኑ ከሳሹ አውሳብዮስ በአጠቃላይ የኬልቄዶን ጉባኤም ቢሆን ዲዮስቆሮስን በእምነት ክህደት አልከሰሱትም፡፡ ሆኖም መናፍቅ ነው ተብሎ የታሰበውን አውጣኪን የ449 ዓ.ም. ሲኖዶስ ነጻ አድርጎ ከውግዘቱ ስለፈታው ብቻ ዲዮስቆሮስን የአውጣኪን የኑፋቄ ትምህርት ተቀብሏል ብለው በጭፍኑ ደምድመዋል፡፡ አውጣኪ ግን በፊት ያስተምር የነበረውን የኑፋቄ ትምህርት ትቶ በቃልም በጽሑፍም ኦርቶዶክሳዊ የእምነት መግለጫ በማቅረቡ በዚህ መሠረት ነው 2ኛው የኤፌሶን (የ449) ሲኖዶስ ነጻ ያደረገው፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ አውጣኪ ያቀረበው የእምነት መግለጫ የሚገኝበት የ449 ሲኖዶስ ቃለ ጉባኤ እንዲነበብ ጠየቀ፡፡ የ449 ሲኖዶስ ቃለ ጉባኤ የመጀመሪያው ክፍል ከተነበበ በኋላ ጉባኤውን የጠራው ንጉሡ ዳግማዊ ቴዎዶስዮስ መሆኑና አውጣኪንም ነጻ ያደረጉት በጉባኤው የነበሩት ጳጳሳት በሙሉ ተስማምተው በፊርማቸው ያጸደቁት መሆኑ ተነበበ፡፡ በ449 ዓ.ም. በ2ኛው የኤፌሶን ሲኖዶስ ላይ የነበሩት ጳጳሳት ግን የ449 ሲኖዶስን ውሳኔ ፈጽሞ እንደማያውቁት የፈረሙትም በወታደሮች ተገደው በባዶ ወረቀት ላይ መሆኑን አጥብቀው ተናገሩ:: የግብጽ ጳጳሳት ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ‹‹የክርስቶስ ወታደር የዚህን ዓለም ባለሥልጣን ፈጽሞ አይፈራም፡፡ እሳት አንድዱ አንድ ሰማዕት እንዴት እንደሚሞት እናሳያችሁ!›› ብለው በጉባኤው ፊት ተናገሩ፡፡ ባዶ ወረቀት ላይ ነው የፈረምነው ካሉት አንዱ የኤፌሶኑ ኤጲስ ቆጶስ እስጢፋኖስ ነበር፡፡ ይህ ሰው አውጣኪ ነጻ እንዲደረግ ተነሥተው ከተናገሩት ሰዎች ሁለተኛው ነበር፡፡ አውሳብዮስና ፍላብያኖስም እንዲወገዙ ከተናገሩት 5ኛው ተናጋሪ እሱ ነበር፡፡ የሲኖዶሱ ጸሓፊ በ449 ሲኖዶስ ቃለ ጉባኤ ላይ የአውጣኪን የሃይማኖት መግለጫ ሲያነብ አንዳንድ አባቶች ይህን መግለጫ እንዳላዩትና ፊርማቸውም አስመስሎ የተፈረመ ነው በማለት ካዱ፡፡ ከዚህ በኋላ በጉባኤው ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ እምነቱን እንዲገልጽ ተጠይቆ ሁለቱ ባሕርያት (የመለኮትና የሥጋ) ያለ መቀላቀልና ያለ ትድምርት፣ ያለ መለወጥና ያለ መለያየት በአንድ አካል እንደተዋሐዱ በሚገባ አስረዳ፡፡ እንዲሁም በቅዱስ ቄርሎስ ትምህርት መሠረት ‹‹አአምን በአሐዱ ባሕርይ (ህላዌ) ዘቃለ እግዚአብሔር ሥግው፤›› ብሎ አስረዳ፡፡ ጉባኤውም በዚህ በዲዮስቆሮስ እምነት ላይ ምንም እንከን፣ ምንም ስሕተት አላገኘም፡፡ ጉባኤው በሌላ መንገድ ‹‹አውጣኪ በጽሑፍ ካቀረበው የተለየ በቃል ቢናገር ምን ትፈርድ ነበር?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ፣ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ‹‹አውጣኪ የጻፈውን ትቶ ሌላ የክህደት ነገር ቢናገር፣ እሱን ማውገዝ ብቻ ሳይሆን በእሳትም እንዲቃጠል እፈርድበት ነበር፤›› ብሎ መለሰ፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በእንደዚህ ያለ ነጐድጓዳዊ አነጋገር ሁሉን ግልጥልጥ አድርጎ በተናገረ ጊዜ፣ ኬልቄዶናውያን ጸጥ አሉ፡፡ ዲዮስቆሮስን በመቃወም የተናገሩ የምሥራቅ አህጉር ጳጳሳት ግን ንግግሩ ልባቸውን ነክቶት ‹‹በድለናል፤ ይቅርታ እንጠይቃለን!›› በማለት ጮኹ፡፡ የመንግሥቱ ዳኞች በባዶ ወረቀት ላይ ነው የፈረምነው ስላሉት እንደገና ሲጠይቋቸው ‹‹በድለናል፤ ይቅርታ እንጠይቃለን፤›› ሲሉ መለሱ፡፡ እንደገና ፍላብያኖስን ዲዮስቆሮስ ነው ያስገደለው ስላሉት ቢጠየቁ አሁንም ‹‹በድለናል፤ ይቅርታ እንጠይቃለን፤›› ሲሉ መለሱ፡፡ በዚህ ሁኔታ እነዚህ ጳጳሳት 1ኛ/ በሐሰት በባዶ ወረቀት ላይ ፈርመናል በማለታቸውና፣ 2ኛ/ ፍላብያኖስንና አውሳብዮስን ያለ አግባብ በማውገዛቸው ይቅርታ ጠየቁ፡፡ የመንግሥቱ ዳኞች ፍላብያኖስ ኦርቶዶክስ መሆኑን አጥብቀው በጠየቁ ጊዜ፣ የሮሙ ተወካዮችና አብዛኞቹ አባላት በ449 ሲኖዶስ ጊዜ የነበሩትም ጭምር ፍላብያኖስ ኦርቶዶክስ እንደነበረ ተናገሩ፤ ‹‹ታዲያ ለምን ተወገዘ?›› ሲሉ ዳኞቹ ጠየቁ፡፡ በዚህ ጊዜ ዲዮስቆሮስ ፍላብያኖስ ‹‹ክርስቶስ ከሥጋዌ በኋላ ሁለት ባሕርያት እንዳለው አጥብቆ ይናገር ነበር፤›› ብሎ ተናገረ፡፡ የዚህም እውነት እንዲወጣ ብሎ የ449 ሲኖዶስ ቃለ ጉባኤ ቀርቦ እንዲነበብ አበክሮ ጠየቀ፡፡ ለዚህ ምንም መልስ አልተሰጠውም፡፡ ሁሉም ዳኞቹም ጭምር ቃለ ጉባኤው እንዳይነበብ ስለፈለጉ ጸጥ አሉ፡፡ ሁሉም ዝም ቢሉም ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ንግግሩን በመቀጠል ፍላብያኖስ ‹‹ክርስቶስ ከሥጋዌ በኋላ ሁለት ባሕርያት አለው፤›› እያለ እንደሚናገር መልሶ መላልሶ አስረዳ፡፡ የቀድሞ አባቶች ግን ለምሳሌ አትናቴዎስ፣ ጎርጎርዮስና ቄርሎስ ‹‹አሐዱ ባሕርይ ዘእግዚአብሔር ቃል ሥግው›› እንጂ ከተዋሕዶ በኋላ ‹‹ሁለት ባሕርያት›› ፈጽሞ እንደማይሉ በመጻሕፍቶቻቸው ሁሉ ለማንበብ እንደሚቻል አስረዳ፡፡ የቀረቡትን ማስረጃዎች ሁሉ ከቁም ነገር ሳያስገቡ ጉባኤውም በሚገባ ሳይወያይበት ዳኞቹ በጭፍን ፍላብያኖስና አውሳብዮስ ያላግባብ ነው የተወገዙት በማለት ውሳኔ አሳለፉ፡፡ በተጨማሪም አውጣኪ ቀርቦ ሳይጠየቅ ለ449 ጉባኤ ያቀረበውንም የሃይማኖት መግለጫ ሳይመለከቱ፣ በጭፍን በ449 ሲኖዶስ ላይ ያለ አግባብ ነው ነጻ ሆኖ ከግዝቱ የተፈታው ብለው ዳኞቹ፣ የፖፑ ተወካዮችና ሌሎቹ የጉባኤው አባላት ወሰኑ፡፡ ይህ በግልጥ የሚያመለክተው የኬልቄዶን ጉባኤ የተጠራው ዲዮስቆሮስንና አውጣኪን ለማውገዝና ፍላብያኖስንና አውሳብዮስን ነጻ ለማድረግ መሆኑን ነው፡፡ ከላይ ለቀረቡት ጥብቅ ማስረጃዎች ምንም መልስ ሳይሰጡ የመንግሥቱ ዳኞችና የሮሙ ፖፕ እንደራሴዎች የፖፑን የዶግማ ደብዳቤ አስተያየቱን እንዲገልጥ ለፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ሰጡት፡፡ ዲዮስቆሮስም ለጥቂት ጊዜ ከአነበበው በኋላ፣ ደብዳቤው ኦርቶዶክሳዊ ሳይሆን ንስጥሮሳዊ መሆኑን ገልጦ ደብዳቤውንና ደራሲውን ያለ አንዳች ማመንታት አወገዘ፡፡ ከተሰበሰቡት ጳጳሳት ብዙዎቹ ስለ ልዮን ደብዳቤ የዲዮስቆሮስን አስተያየትና ስሜት ተጋርተዋል፡፡ ነገር ግን አስተያታቸውን በይፋ ለመግለጥ ድፍረት አልነበራቸውም፡፡ ሌሎች ደግሞ ስለዚሁ ደብዳቤ ታላቅ ጥርጣሬና መደናበር እንዳደረባቸው በፊታቸው ላይ ይነበብ ነበር፡፡ ይህን የአባላቱን ሁኔታ የተመለ ከቱት ዳኞች በደብዳቤው ውስጥ የሚያውክና የሚያስቸግር ነገር እንዳለ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አንዳንድ ጳጳሳት ምንም ችግር አለመኖሩን ገልጠው፣ ሆኖም አንዳንድ የላቲን ቃላትንና አባባሎችን በደንብ ለመመርመር ጊዜ ለማግኘት ስብሰባው ለአምስት ቀናት እንዲበተን ጠየቁ፡፡ ጥያቄአቸውም ወዲያውኑ ተቀባይነት አግኝቶ ስብሰባው ተበተነ፡፡ ነገር ግን ከሦስት ቀናት በኋላ ጳጳሳቱ የመንግሥቱ ዳኞች በሌሉበት ለነሱም ሳይነግሩ ይፋዊ ስብሰባቸውን በፖፑ እንደራሴ ፓስካሲኑስ ሊቀ መንበርነት ቀጠሉ፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ የግብጽ ጳጳሳትና ሌሎች ብዙ ጳጳሳት አልተገኙም፡፡ ስብሰባውን እንደጀመሩ የፖፑ እንደራሴና የስብሰባው ሊቀ መንበር ‹‹የፖፑ ደብዳቤ መከበር አለበት፡፡ ሁሉም ደብዳቤውን መቀበል አለባቸው፡፡ ይህን ደብዳቤ የሚቃወም ተከሶ በጉባኤው ፊት መቅረብ አለበት፤›› ሲል አወጀ፡፡ ወዲያውኑ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወደ ስብሰባው እንዲመጣ ወደ ማረፊያ ቦታው ሦስት ጳጳሳትና አንድ ዲያቆን ተላኩ፡፡ በዚያን ጊዜ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ከቤት እንዳይወጣ ንግሥት ብርክልያ ባዘዘቻቸው ወታደሮች ይጠበቅ ነበር፡፡ መልእክተኞቹም ዲዮስቆሮስን ወደ ጉባኤው እንዲመጣ በጠየቁት ጊዜ፣ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ‹‹ጉባኤው የተበተነው ለአምስት ቀናት ሲሆን አሁን ገና ሦስት ቀናት ነው ያለፉት፡፡ አሁን እንዴት ለመሰብሰብ እንችላለን? ለመሆኑ የመንግሥቱ ተወካዮች ዳኞች ተነግሯቸዋል?›› ብሎ ጠየቀ፡፡ ለመጀመሪያው ጥያቄ መልስ አልተሰጠውም፡፡ ለሁለተኛው ጥያቄ ግን ‹‹ለቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ምእመናን አያስፈልጉም፤›› ሲሉ መለሱለት፡፡ ቀጥሎ ከቤት ወጥቶ ወደ ስብሰባው ለመሄድ ይፈቅዱለት እንደሆነ ወታደሮቹን ማስፈቀዳቸውን መልእክተኞቹን ጠየቀ፡፡ እነርሱም በበኩላቸው ‹‹እኛ የተላክነው አንተን እንድንጠራ ነው እንጂ ወታደሮችን እንድንጠይቅ እይደለም፤›› ሲሉ መለሱና ተመልሰው ሄዱ፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞች ለዲዮስቆሮስ ሌላ ጥሪ አቀረቡ፡፡ እሱም የመንግሥት ተወካዮች ዳኞች ከሌሉ እንደማይ መጣ ነግሯቸው ተመለሱ፡፡ ይህ ሁሉ የተደረገው በሲኖዶስ ሕግ መሠረት አንድ ሰው ሦስት ጊዜ ተጠርቶ ካልመጣ እንደሚወገዝ ስለሚያውቁ በዚሁ መሠረት ዲዮስቆሮስን በሌለበት ለማውገዝና የፖፕ ልዮንን የዶግማ ደብዳቤ ሁሉም እንዲቀበሉት ለማድረግ ነበር፡፡ ይህም የታቀደው በፖፑ ወኪሎች ነበር፡፡ በዚህ መካከል ሌሎች ከሳሾች ቀርበው በፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ላይ የተለያዩ እምነትን የማይመለከቱ የሐሰት ክሶችን እንዲያቀርቡ ተደረገ፡፡ በመጨረሻም ዲዮስቆሮስ ወደ ጉባኤው እንዲመጣ ለሦስተኛ ጊዜ መልእክተኞች ላኩበት፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ የኬልቄዶን ጉባኤ ሤራ በደንብ ስለገባው የሃይማኖት መልእክቱን ቀደም አድርጎ ያስተላለፈ መሆኑን ገልጾ በሕመም ምክንያት ወደ ጉባኤው ለመሄድ አለመቻሉን ስለገለጠላቸው መልእክተኞቹ ተመልሰው ሄዱ፡፡ የፖፑ ተወካዮችና አንዳንድ የእነርሱ ደጋፊዎች ዲዮስቆሮስን ለማውገዝ ይህንኑ ነበር የፈለጉት፡፡ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ በኬልቄዶናውያን መወገዝ የሮሙ ፖፕ ልዮን፣ የሮም የምሥራቁ ክፍል ንጉሠ ነገሥት የመርቅያንና የንግሥቲቱ የብርክልያ ታላቅ ተጽእኖ የነበረበት ይህ የኬልቄዶን ጉባኤ መጀመ ሪያም የተሰበሰበው ዲዮስቆሮስን ለማው ገዝና ከሥልጣኑ ለማውረድ ስለነበረ፣ እሱን ለማውገዝ ብዙ ምክንያቶች ይፈልጉ ነበር፡፡ በሃይማኖት በኩል ምንም ስሕተት ስላላገኙበት የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና አፍርሷል በማለት እሱን ወንጀለኛ ለማድረግ አስበው ሕጉን የሚያስከብሩት የመንግሥት ዳኞች ለአምስት ቀናት ጉባኤውን በበተኑበት ጊዜ ከግማሽ ያነሱ አባላት ተሰብስበው ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በጉባኤው ላይ እንዲገኝ ሦስት ጊዜ ደጋግመው ጥሪ እንዲደርሰው አደረጉ፡፡ ዲዮስቆሮስም ከላይ እንደተገለጸው ሕግ አስከባሪዎቹ ዳኞችና ሌሎች ከእርሱ ጋር የተከሰሱት በሌሉበት ለመገኘት ስላልፈለገ በጉባኤው ላይ አልተገኘም፡፡ ይህን ምክንያት አድርገው ‹ሲያሻኝ ጭስ ወጋኝ› እንደሚሉት ቀኖና አፍርሷል በማለት የተሰበሰቡት በአንድ ድምፅ አወገዙት፡፡ ሲያወግዙትም ሦስት ምክንያቶች ዘርዝረዋል፤ 1ኛ/ በመናፍቅነት የተከሰሰውንና የተወገዘውን አውጣኪን ነጻ አድርጎ ወደ ቤተ ክርስቲያን አንድነት መልሶታል፡፡ ከዚህ ላይ አውጣኪ በጽሑፍ ያቀረ በውንና በቃልም ያረጋገጠውን ኦርቶዶክሳዊ የሃይማኖት መግለጫ ሊመለከ ቱት አልፈለጉም፡፡ 2ኛ/ የሮሙ ፖፕ ልዮን የላከውን የሃይማኖት መግለጫ ደብዳቤ ባለመ ቀበል ደብዳቤውንም ፖፕ ልዮንንም አውግዟል የሚል ነው፡፡ 3ኛ/ በጉባኤው ላይ እንዲገኝ ሦስት ጊዜ ተጠርቶ አልተገኘም የሚል ነበር፡፡ ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ከተወገዘና ከሥልጣን እንዲወርድ ከተወሰነበት በኋላ ንግሥት ብርክልያ በግል አስጠርታ ሐሳቡን ለውጦ በልዮን ጦማር ላይ እንዲስማማና እንዲፈርም ትእዛዝ አዘል ምክር ሰጥታው ነበር ይባላል፡፡ እሱ ግን መንፈሰ ጠንካራ ስለነበር የንግሥቲቱን ትእዛዝና ምክር አልተቀበለም፡፡ በዚህ ተናዳ ንግሥቲቱ ቅዱስ ዲዮስቆሮስን በወታደሮች በሚያሰቅቅ ሁኔታ አስደበደበችው፡፡ በዚህም ድብደባ ጥርሶቹ ወላልቀው ጽሕሙም ተነጫጭቶ ነበር፡፡ እሱም የተነጨ ጽሕሙንና የወለቁትን ጥርሶች በአንድ ላይ ቋጥሮ ‹‹ይህ የሃይማኖት ፍሬ ነው፤›› የሚል ጽፎበት ለግብጽ ምእመናን ልኮላቸዋል ይባላል፡፡ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወደ ግዞት መላክ እጅግ የሚገርመው የኬልቄዶን ጉባኤ ስብሰባውን ሳይፈጽም የጉባኤውም ዘገባ ገና ሳይደርሰው የቊስጥ ንጥንያ ንጉሠ ነገሥት መርቅያን የጉባኤውን ውሳኔዎች ሁሉ የሚያጸድቅ ጽሑፍ ለጉባኤው ላከ፡፡ እንዲሁም ንጉሡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ (ጋንግራ) ወደሚባል ደሴት እንዲጋዝ ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወደተጋዘበት ወደ ደሴተ ጋግራ በሄደ ጊዜ በፈቃዳቸው ሁለት ጳጳሳትና ሁለት ዲያቆናት ተከትለዉት ሄደው ነበር፡፡ ሦስተኛው ጻድቅ የነበረ መቃርዮስ የተባለ የኤድኮ ጳጳስ አብሮት ለመሄድ በመንገድ ላይ ሳለ ‹‹ቅዱስ ማርቆስ ደሙን ባፈሰሰበት ከተማ የሰማዕትነት አክሊል ስለሚጠብቅህ ቶሎ ብለህ ሂድ እንዳያመልጥህ፤›› ብሎ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ስለነገረው ወዲያውኑ ወደ ግብጽ ሄደ፡፡ ንጉሠ ነገሥት መርቅያን ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስን ወደ ግዞት እንዲላክ ከአደረገ በኋላ የጉባኤው ውሳኔ በመንግሥት መጽደ ቁን በመግለጽ ለእስክንድርያና ለመላዋ የግብጽ ሕዝብና ለግብጽ ቤተ ክርስቲያን መልእክት ላከ፡፡ ወዲያውኑም በዲዮስቆሮስ ምትክ ፕሮቴሪዮስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ በቊስጥ ንጥንያ ሹሞ ወደ እስክንድርያ በብዙ ወታደሮች ታጅቦ እንዲሄድ አደረገ፡፡ ወታደሮቹም ለአዲሱ ፓትርያርክ የማይታዘዙትንና የማይገዙትን ከባድ ቅጣት እንዲቀጡ በጥብቅ ታዝዘው ነበር፡፡ የግብጽ ክርስቲያኖች ግን ለዲዮስቆሮስ ታማኝነታቸውን በመግለጥ ንጉሡ ለላከው ፓትርያርክ አንገዛም አሉ፡፡ የግብጽ ጳጳሳትም አስቸኳይ ስብሰባ አድርገው ለፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ ታማኝነታቸውን በአንድ ድምፅ ገልጠው፣ ፖፕ ልዮንንና የልዮንን ጦማር እንዲሁም የኬልቄዶንን ጉባኤን ጉባዔ ከለባት ብለው በመጥራት አወገዙት፡፡ ፓትርያርክ አንዲሆን የተላከባቸውንም ፕሮቴሪዮስን አወገዙ፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ መርቅያንም ይህን እንደሰማ አጸፋውን ለመመለስ ጳጳሳቱ በሙሉ በኬልቄዶን ጉባኤ ውሳኔና በልዮን ጦማር ላይ እንዲ ፈርሙ በግብጽ ለነበሩት የጦር ሹማም ንቱና መኰንኖቹ ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡ መኰንኖቹም በትእዛዙ መሠረት ጽሑፎቹን ለማስፈረም ወደየጳጳሳቱ ሲሄዱ መጀመሪያ የተገኘው ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወደ ግዞት ሊከተለው ሲል ‹‹ወደ እስክን ድርያ ሂድ፤ በዚያ የሰማዕትነት አክሊል ይጠብቅሃል፤›› ያለው የኤድኮ ጳጳስ አባ መቃርዮስ ነበር፡፡ ወታደሮቹ ጽሑፎቹን አልፈርምም በማለቱ ከዚያው ደብድበው ገድለውታል፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው በመጽናታቸውና የኬልቄዶንን ጉባኤ ባለመቀበላቸው ሠላሳ ሺሕ (30,000) የሚሆኑ ካህናትና ምእመናን ተገድለዋል፡፡ ከጥቂት የሰበካ አብያተ ክርስቲያናት በስተቀር አብዛኞቹ የአብያተ ክርስቲያናት ሕንጻዎች የኬልቄዶንን ጉባኤ ለሚደግፉ ጥቂት ክርስቲያኖች በንጉሠ ነገሥቱ ትእዛዝ እንዲሰጣቸው ተደረገ፡፡ ፓትርያርክ ዲዮስቆሮስ አምስት ዓመት በግዞት ግፍና ሥቃይ እየተቀበለ ከቆየ በኋላ በ456 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ መላው የግብጽ ካህናትና ምእመናን የአባታቸውን ማረፍ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ሐዘን ተሰማቸው፡፡ ወዲያውኑ ካህናቱና ሕዝበ ክርስቲያኑ ተሰብስበው የዲዮስቆሮስ ዋና ጸሓፊ የነበረውን ጢሞቴዎስ የተባለውን አባት በአንድ ድምፅ መርጠው በዲዮስቆሮስ ፋንታ ዳግማዊ ጢሞቴዎስ ተብሎ የእስክን ድርያ 26ኛው ፓትርያርክ ሆኖ እንዲሾም አደረጉ፡፡ ይህ ምርጫ በሚካሄድበት ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ የመርቅያን ዋና እንደራሴ አገረ ገዥው በእስክንድርያ አልነበረም፡፡ ገዥው ሲመለስ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን አዲስ ፓትርያርክ መርጠው መሾማቸውን በሰማ ጊዜ እጅግ ተናደደ፡፡ አገረገ ዥውም ግብጻውያን ፓትርያርክ የመምረጥ መብት እንዳልነ በራቸው ነገራቸው፡፡ ለማናቸውም እርሱ እስከሚመለስ ድረስ መጠበቅ ነበረባቸው በማለት ምርጫውን እንደማይቀበለው በግልጥ ነገራቸው፡፡ ለእነሱ የተሾመላቸ ውንና መንግሥትም የሚቀበለውን ፕሮቴሪዮስን የግድ መቀበልና ለእርሱ መታዘዝ እንዳለባቸው ነግሮአቸው ሌላ ፓትርያርክ መምረጥ በመንግሥት ላይ እንደማመፅ የሚያስቆጥርና ከባድ ቅጣት የሚያስከትል ነው በማለት አስጠነቀቃቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አዲሱ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ዳግማዊ ጢሞቴዎስ ጳጳሳቱን በሙሉ ጠርተው ሲኖዶስ አደረጉና የኬልቄዶንን ጉባኤና የጉባኤውን ደጋፊዎች እንደገና አወገዟ ቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ዲዮኒስዮስ የሚባል አንድ የመንግሥት ወታደራዊ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከቊስጥንጥንያ ተልኮ መጣ፡፡ የመጣውም የግብጽ ክርስቲያኖች በሙሉ መንግሥት የሾመውን ፕሮቴሪ ዮስን እንዲቀበሉ ለማድረግ ነበር፡፡ ለእርሱም የማይታዘዙትን ከባድ ቅጣት እንዲቀጣቸው ሥልጣን ተሰጥቶት ነበር የመጣው፡፡ ይህ ባለሥልጣን በመጣ ጊዜ ፓትርያርክ ዳግማዊ ጢሞቴዎስ ከእስክንድርያ ወጥተው የተለያዩ ሀገረ ስብከቶችን በመጐብኘት ላይ ነበሩ፡፡ ፓትርያርኩ በተመለሱ ጊዜ መንበረ ሊቀ ጵጵስናቸው ውጭውም ውስጡም በመንግሥት ቊልፍ ተቈልፎ አገኙት፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ በዚህ እጅግ ተናደው መንግሥት ወደሾመው ፓትርያርክ ወደ ፕሮቴሪዮስ ሄደው በንጉሡ የተሾመውን ፓትርያርክ ከተደበቀበት አውጥተው ገደሉት፡፡ ይህ ዓመፅ መንግሥትን ስላሳሰበ በሕዝብ ላይ አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ አልተፈለገም፡፡ ሆኖም ንጉሥ መርቅያን ግብጻውያን የመረጡት ፓትርያርክ ጢሞቴዎስና ወንድሙ ተይዘው ዲዮስቆሮስ ታስሮበት በነበረበት በደሴተ ጋግራ እንዲጋዙ አደረገ፡፡ ይህንም ያደረገው የሕዝቡን መንፈስ ለመስበርና ተስፋ ለማስቈረጥ ነበር፡፡ የሕዝቡ መንፈስ ግን ፈጽሞ አልተለወጠም፡፡ የቊስጥንጥንያ መንግሥት ደጋግሞ ፓትርያርክ ቢልክም ግብጻውያን ግን መንግሥት የሚልካቸውን ፈጽሞ አይቀበሉም ነበር፡፡ እስከ ኬልቄዶን ጉባኤ ድረስ በግብጽ የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በቅዳሴና በሌሎች የጸሎት አገልግሎት ጊዜ በግሪክኛ ቋንቋ ነበር የሚጠቀሙት፡፡ ከዚህ በኋላ ግን በቅብጥ ቋንቋ መጠቀም ጀመሩ፡፡ ከ451 ዓ.ም. ጀምሮ ማለት ከኬልቄዶን ጉባዔ በኋላ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ተከፈለች፡፡ በአንድ በኩል የሮም ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሙሉ ድጋፍ የነበራቸው እኛ መለካውያን ብለን የምንጠራቸው የምዕራቡ አብያተ ክርስቲያናት የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች የሆኑ ሁሉ ሲሆኑ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የምሥራቅ ወይም የኦርየንታል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ማለት የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የሶርያ፣ የአርመንና የሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡ የፖፕ ልዮን ቀዳማዊ የሃይማኖት መግለጫ ጦማር የልዮን የሃይማኖት መግለጫ ጦማር (ደብዳቤ) የሚከተሉት ነጥቦች ነበሩት፡- 1ኛ/በክርስቶስ ውስጥ የመለኮት ባሕርይና የትስብእት ባሕርይ በአንድ አካል አንድ ሆኑ፤ ያለ መቀላቀል፣ ያለ መለያየትና ያለ መለወጥ፡፡ 2ኛ/ እያንዳንዱ ባሕርይ የግብር ክልሉን ጠብቆ ይኖራል፡፡ ይህም ማለት መለኮት የመለኮትን ሥራ ይሠራል፤ ትስብእትም የትስብእትን ሥራ ይሠራል፡፡ 3ኛ/ ‹‹ከመዋሐድ በፊት ሁለት ነበሩ፤ ከተዋሐዱ በኋላ ግን አንድ ባሕርይ ነው ማለት ሞኝነት ነው፤›› የሚል ኃይለ ቃል ይገኝበታል፡፡ ከልዮን ጦማር ውስጥ ከዚህ በላይ የገለጥናቸው አንድ አካል ከማለቱ በስተቀር የንስጥሮስን ትምህርት ነው የሚገልጡት፡፡ ሁለቱ ባሕርያት አንድ ሆኑ ሲሉ እንደ ኀዳሪና ማኅደር፣ ጽምረትን እንጂ ተዋሕዶን አይገልጡም፡፡ ተዋሕዶ ግን እንደ ነፍስና ሥጋ ነው፡፡ ‹‹እያንዳንዱ ባሕርይ የግብር ክልሉን ጠብቆ ይኖራል›› የሚለው በተዋሕዶ የቃል ገንዘብ ለሥጋ፣ የሥጋ ገንዘብ ለቃል መሆኑንና መገናዘቡን መወራረሱንም የሚጻረር ነው፤ ቅዱስ ቄርሎስ እንዲህ ይላል ‹‹እንቲአሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲአሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል፡፡›› ይህም ማለት ‹‹የቃል ገንዘብ ለሥጋ ሆነ፤ የሥጋም ገንዘብ ለቃል ሆነ፤›› ማለት ነው፡፡ ይህ ፍጹም ተዋሕዶን የሚያመለክት ነው፡፡ ስለዚህ ነው ሥግው ቃል በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው የምንለው፡፡ የልዮንን ጦማርና የኬልቄዶንን ጉባኤ ውሳኔ በመከተል የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና የግሪክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ‹‹ክርስቶስ ሁለት ባሕርያት አንድ አካል አለው›› ይላሉ፡፡ በአገላለጽም ሁለቱ ባሕርያት የተዋሐዱት ያለ መቀላቀል፣ ያለ መለያየትና ያለ መለወጥ ነው ይላሉ፡፡ አንድ ባሕርይ ለማለት የፈሩት ወደ አውጣኪ ትምህርት ይወስደናል ብለው በመፍራት ነው፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ሁለቱ ባሕርያት (የሥጋና የመለኮት) ተዋሐዱ ስንል ‹‹ወረሰዮ አሐደ ምስለ መለኮቱ ዘእንበለ ቱስሕት ወኢትድምርት፣ ዘእንበለ ፍልጠት ወኢውላጤ›› (ያለ መቀላቀልና ያለ መጨመር፣ ያለ መለየትና ያለ መለወጥ ከመለኮቱ ጋር አንድ አደረገው፤) እንላለን፡፡ አባቶቻችን ያስተማሯት ርትዕት ሃይማኖታችንም ይህች ናት፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ ማስገንዘቢያ የተወደዳችሁ የማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ተከታታዮች፣ ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ ለማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል መቅረቡንና በታኅሣሥ ወር ዓ.ም በታተመው ፳፬ኛ ዓመት ቍጥር ሐመር መጽሔት፣ ከገጽ ፲፭ ለንባብ መብቃቱን ለማስገንዘብ
14117
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%88%E1%88%8D%E1%8B%B0%20%E1%8C%8A%E1%8B%AE%E1%88%AD%E1%8C%8A%E1%88%B5%20%E1%8B%88%E1%88%8D%E1%8B%B0%20%E1%8B%AE%E1%88%90%E1%8A%95%E1%88%B5
ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ
ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ዓ/ም ዓ/ም) በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት በተላለያዩ ጊዜያት የፅሕፈት፤ የእርሻ፤ የአገር ግዛት እና ገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሁም የጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ በመሆን አገልግለዋል። በትውልድ አገራቸው ቡልጋ ቤተ ክርስቲያን ያሠሩ ትልቅ ሁለ ገብ ሰው ነበሩ። ወደፊት የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት የሚደመድመው የስድሳ ስድስቱ አብዮት በተፋፋመበት ወቅት፣ እኚህ ሰው ለሕክምና ወደ ሎንዶን መጥተው ሲታከሙ ቆይተው ሐምሌ ቀን ዓ/ም እዚያው አርፈው ኬንሳል ግሪን (እንግሊዝኛ፦ በሚባል የመቃብር ሥፍራ ተቀበሩ። የወጣትነት ዘመናት ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በሞረትና ጅሩ ወረዳ ጎበላ ሚካኤል በሚባል ስፍራ ከተወለዱት ከአባታቸው አቶ ወልደዮሐንስ ናዳቸው እና ከመንዝ ተወላጅዋ እናታቸው ወይዘሮ ወደርየለሽ ወልደገብሬል፣ አዲስ አበባ 'አባታችን ሠፈር'፣ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በ፲፰፻፺፫ ዓ/ም ተወለዱ። በዘመኑ ስርዓት የግዕዝ እና አማርኛ ትምህርታቸውን በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ትምህርት ቤት የአማርኛን ጽሕፈትና ንባብ አጠናቀቁ። ከዚያ ቀጥሎ መቼ፣ እንዴትና ለምን ለሚሉት ጥያቄዎች መረጃ ባይገኝም ሆኔም ቀሬ በንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ ዘመን መሆኑ ነው፣ አዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒልክ ትምሕርት ቤት ፈረንሳይኛ ቋንቋ አጥንተዋል። በዚህም የቋንቋ ዕውቀት በአስተርጓሚነት ሲያገለግሉ ቆይተው ኢትዮጵያ የዓለም መንግሥታት ማኅበር አባል ስትሆን በ ዓ/ም ወደ ማኅበሩ ፅሕፈት ቤት ዠኔቭ ይላካሉ። ከዠኔቭ ሲመለሱ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ ጣልያን፣ ቤልጅግ እና ጀርመን ክፍል ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ በ፲፱፻፳፫ ዓ/ም በዚያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዲሬክቶርነት ማዕርግ ለሦስት ዓመት አገልግለዋል። በ፲፱፻፳፮ ዓ/ም በፅሕፈት ሚኒስቴር ጠቅላይ ዲረክቶር ተብለው ለጥቀውም የንጉሠ ነገሥቱ የግል ፀሐፊ ሆነው እስከ ጠላት ወረራ ድረስ ሲያገለግሉ ቆዩ። ከንጉሠ ነገሥቱም ጋር የቅርብ ግንኙነታቸውና ወደፊት የሚይዙትም የ’ፈላጭ ቆራጭነት’ ሥልጣን የተመሠረተው በዚህ ጊዜ እንደሆነ ይገመታል። የጠላት ወረራና ያስከተለው ስደት የንጉሠ ነገሥቱ የግል ፀሐፊ አቶ ወልደ ጊዮርጊስ ፋሽሽት ኢጣልያ አገራችንን በወረረ ጊዜ ክንጉሠ ነገሥቱ ሳይለዩ፣ በማይጨው ዘመቻ ከአዲስ አበባ ወደደሴ አብረው ኅዳር ቀን ዓ/ም ይጓዛሉ በኋላም ግንቦት ወር ዓ/ም በጂቡቲ እና በኢየሩሳሌም በኩል አድርገው ከሐይፋ ወደብ እስከ ጅብራልታር በእንግሊዝ የጦር መርከብ፣ ከጅብራልታር እስከ "ሳውዝሃምፕቶን" (እንግሊዝኛ የእንግሊዝ ወደብ በመንገደኛ መርከብ ተጉዘው የአምስት ዓመት የስደታቸውን ዘመን አብረው ተሳትፈዋል። በስደት ዘመን ንጉሠ ነገሥቱ ከቤተሰባቸው ጋር በባዝ ከተማ “ፌየርፊልድ ሃውስ” (እንግሊዝኛ )የስደት ዘመን እንዳሳለፉ ብዙ ተጽፏል። ከቤተ ሰቡም ጋር አብረው የነበሩ (ሠራተኞች፣ አገልጋዮች፣ መነኮሳት) ሌሎች ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንደነበሩ ‘ሉትዝ ሄበር’ “ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በባዝ ከ 1928 1932 ዓ.ም” 1936 1940) በሚል ጽሑፉ በሰፊው አስፍሮታል። በዚያ የስደት ዘመን ግን ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ የት እንደኖሩ መረጃ ማግኘት ባይቻልም የንጉሠ ነገሥቱ የግል ጸሐፊ ስለነበሩ እምብዛም እንድማይርቋቸው ይገመታል። ሆኔም ቀሬ በታኅሣሥ ዓ/ም የፈረንጆች ገና ዕለት ንጉሠ ነገሥቱ በቢቢሲ ራዲዮ ለአሜሪካውያን ደጋፊዎቻቸው መልዕክት ሲያስተላልፉ፣ በስደት የዲፕሎማሲ ትግል ሲያካሂዱና ከዓለም መንግሥታት ማኅበር ጋር ‘የአእምሯዊ ግብግብ’ በገጠሙበት ጊዜ አጠገባቸው ሆነው ከሚያማክሯቸው ሰዎች አንዱ አቶ ወልደ ጊዮርጊስ እንደነበሩ ንጉሥ ነገሥቱ “ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ፪ኛ መጽሐፍ” ላይ ጠቅሰውታል። ከድል እስከ ግዞት «የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሥልጣን በግዛቱ ውስጥ ያልተወሰነ ነው። ሥልጣኑ ሃይማኖታዊም ሆነ ሥጋዊ ጉዳዮችን ያጠቃልላል። በሥልጣኑ ይሾማል፣ ይሽራል መውሰድም፣ መስጠትም፤ ማሰርም፣ መፍታትም፤ መግደልም፣ መስቀልም ይችላል። ትንሹም ትልቁም ንጉሠ ነገሥቱ የእግዚአብሔር ተወካይ ነው ብሎ ስለሚያምን የእርሱን ትዕዛዝ ያለአንዳችም ሰበብ ወይም ማመካኘት በደስታ ይቀበላል።» “ዝክረ ነገር” ከ ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል «በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የአስተዳደር ስልት፤ ለሥልጣን የብቃተ ቢስነት ወንጀል ወይም የማይካድ የሙስና ድርጊት ሲታይ የተለመደው ቅጣት ወደሌላ ሥራ መዛወር ሲሆን፤ ለንጉሠ ነገሥቱ ታማኝ አለመሆን ግን ያለምንም ጥርጣሬ በፈጣን ፍርድ በግዞት ዓለም መጥፋትን ያስከትላል።» ጆን ማርካኪስ “ኢትዮጵያ፥ የባህላዊ ሽከታ ሥነ አካል” እዚህ አስተያየት ላይ ደግሞ ‘የንጉሠ ነገሥቱን ስም እና ተወዳጅነት የሚሻማ/የሚያሳማ ዝናም ያተረፈ ‘ባለ ሥልጣን’ የሚጠብቀው እንዲሁ ተመሳሳይ ቅጣት ነበር’ ብንል ከእውነቱ አንርቅም። ስለፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ እምብዛም የተጻፈ ባይኖርም ያሉት ቅንጥብጣቢዎች ከሞላ ጎደል የሚያሳዩን በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ከላይ የሠፈሩትን ሁለቱንም ገጽታዎች መጀመሪያ በ”እንደራሴ” መልክ የተጠቀሙበትና በመጨረሻውም የግዞት ዓለምን የቀመሱባቸው ገጽታዎች መሆናቸውን ነው። ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር አብረው በስደት በነበሩባቸው ዘመናት በታማኝነታቸው የንጉሠ ነገሥቱን እምነት አስገኘላቸው። የግል ጸሐፊነታቸው በኋላም የጽሕፈት ሚኒስቴርነታቸው ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ከማንም የላቀ አቀራረብ (ስለዚህም ተሰሚነትን) ስለሰጣቸው እንዲሁም የራሳቸው የዱኛ ችሎታ ከንጉሠ ነገሥቱ ቀጥሎ ሌላ ማንም ያልነበረውን የሥልጣን መብት ሰጥቷቸዋል። (ባህሩ ዘውዴ የዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክ ከ 1847 እስከ 1983) ከስደት ሲመለሱ ‘ፀሐፌ ትዕዛዝ’ ተብለው የጽሕፈት ሚንስቴር ሆነው ይሾማሉ። በተለምዶው ስርዓት የጽሕፈት ሚኒስቴሩ የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥታዊ መዝገቦች ጸሐፊ እና ጠባቂ ሲሆን፣ ዐዋጆች፤ ትዕዛዛት እና መንግሥታዊ ሰነዶችም በዚሁ ሰው በኩል ያልፋሉ። ይሄ ማለት ደግሞ ከላይ እንደሠፈረው፣ ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደመስቀል በ”ዝክረ ነገር” ላይ “ትንሹም ትልቁም ንጉሠ ነገሥቱ የእግዚአብሔር ተወካይ ነው ብሎ ስለሚያምን የእርሱን (የንጉሠ ነገሥቱን) ትዕዛዝ ያለአንዳችም ሰበብ ወይም ማመካኘት በደስታ ይቀበላል።>> ብለው ያስረዱንን ስርዓት ለዚህ ማዕርግ የበቃ ሰው የቱን ያህል ሥልጣን እንደነበረውና ዝንባሌው የራሱን ሥልጣን የማዳበርም ከሆነ ይሀንን ዓይነት መሠረት ይዞ የዝንባሌውን ዓላማ ስኬታማ ማድረግ እንዴት ቀላል እንደሆነ ይገነዘቧል። በ፲፱፻፴፭ ዓ/ም ድል በተገኘ በሁለት ዓመቱ፣ ንጉሠ ነገሥቱ “የመንግሥታችንን ሚኒስቴሮች ሥልጣንና ግዴታዎች ለማብራራት” በሚል ዐዋጅ በራሳቸው ሰብሳቢነት የሚመራ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት እና “ቃለ መሐላ” የሰጡ ሚኒስቴሮች መሾማቸውን ሲይስታውቁ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት በፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ እንደሚመራና ምክር ቤቱም በኒሁ ሰው ‘ቁጥጥር’ ስር እንደሚሆን ታወጀ። እኒህ ሚኒስቴር በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ውስጥ “ከማናቸውም ባለሥልጣን ጋር በቀጥታ የመገናኘት ሥልጣን” እንደተሰጣቸው ዐዋጁ ለጥቆ አስታወቀ። እንግዲህ በዚህ አዋጅ መሠረት ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ በንጉሠ ነገሥቱ ፍላጎት እና ዐዋጅ የዘውዱን የበላይነት ለማስከበር ሙሉ ሥልጣን ‘እንደራሴ’ መሆናቸው ተረጋግጧል። በሌላ መልክ ሲተረጎም፤ ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ በንጉሠ ነገሥቱ እውቀትም ይሁን ፍላጎት ‘በማስመሰል’ም ይሁን በትክክል የንጉሠ ነገሥት መንግሥቱን ዓላማ በማራመድ ኢትዮጵያን ለማልማት፤ በዘመናዊ መንገድ ለመምራት፤ ‘ለመፍለጥ ለመቁረጥ’፤ የራሳቸውን ባለሟሎች እና ወገኖች በማንኛውም ረገድ ለማዳበር፤ የራሳቸውን የሥልጣን መሠረት ለማስፋፍትም ሆነ የዘውድ ስርዓቱን ዘላለማዊ ለማድረግ ልዩና ቁልፋዊ ቦታ እንደነበራቸው እንገነዘባለን። ምስጢራዊና የሥልጣን አያያዝ፣ አጠቃቀም እና ‘ከመለኮት የተሠጠ’ መብታቸውን ከማንም ጋር መሻማት የማይፈልጉትስ ንጉሠ ነገሥት እንደዚህ ዓይነት ዐዋጅ ሲያስተላልፉ፣ ምን አስበው ኖሯል? በጊዜው አገራችንን ከፋሽሽት ጣልያን ለማላቀቅ አባቶቻችን እና እናቶቻችን የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለመደገፍ ገብተው የነበሩት እንግሊዞች፤ ከድል በኋላ ኢትዮጵያን ቢያንስ በሥራቸው እንደቅኝ ግዛት ለማስተዳደር፤ ይሄ ባይሳካላቸው ደግሞ ሕዝቦቿንና ግዛቷን ከፋፍለው ለመበተን የሚጥሩበት ጊዜ ነበር። ታዲያ ለንጉሠ ነገሥቱ የዚህ አዋጅ መነሻ ምናልባት እንግሊዞች በዓላማቸው የቀናቸው እንደሆነ የሚያሳብቡበት የዋህ ሰው ማዘጋጀታቸው ኖሯል? የፀሐፌ ትእዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ አነሳስ፣ እድገት፣ ይሄን ያህልም ሥልጣን እስከመያዝ መብቃትና በመጨረሻውም ውስጡ ከተበላ በኋላ እንደሚወረወር የሙዝ ልጣጭ መደረግ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በአንባቢ እና የኢትዮጵያን የቅርብ ታሪክ በሚያጠና ሰው ጭንቅላት ላይ ያስነሳሉ። በሥልጣን ዘመን በ፲፱፻፴፬ ዓ/ም የ”አንግሎ-ኢትዮጵያ ስምምነት” (እንግሊዝኛ 1941-42) ድርድር ወሳኝና ቁልፍ የሆነ ሚና ተጫውተዋል። በተለይም በጊዜው ኦጋዴንን በእንግሊዝ መንግሥት ሥር ለማስተዳደር የሚካሄደውን ሴራ በመቃወም ያደረጉት ትግል በአንዳንድ የብሪታንያ ባለ ሥልጣናት አመለካከት እሳቸውን ያለአግባብ ‘ጸረ-ብሪታንያ’ እንዳስባላቸው ትልቁ የኢትዮጵያ ታሪክ ምሑር ሪቻርድ ፓንክኸርስት ገልጾታል። ይሄንን በተመለከተ እሳቸው “እኔ ለኢትዮጵያ የቆምኩ እንጂ ጸረ ማንም አይደለሁም።” ብለዋል። በ ዓ/ም የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት በአውራጃዎቹና በጠቅላይ ግዛቶቹ ላይ ‘ለማጠንከር’ በወሰዱት እርምጃ የአገር ግዛት ሚኒስቴርነትን ሥልጣን ከጽሕፈት ሚኒስቴር ጋር በመለጠቅ ያዙ። ይሔ ሚኒስቴር በአገሪቱ አጠቃላይ የጸጥታን ጉዳይ የሚቆጣጠርም ስለነበር ፀሐፌ ትዕዛዝን የበለጠ አስከባሪና ተፈሪነትን አስገኝቶላቸዋል። ሆኖም የአገር ግዛት ሚኒስቴርን በ፲፱፻፵፩ ዓ/ም ለቀው የፍትሕ ሚኒስቴርነትን ያዙ። የራሳቸውን ባለሟሎችም በየሚኒስትሩና በየ መንግሥት መሥሪያ ቦታዎች አሠማሩ። የ ዓመተ ምሕረቱን የሕገ መንግሥት ረቂቅ ከሦስት አሜሪካውያን እና ከጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ ጋር አዘጋጅተዋል። በንጉሠ ነገሥቱ የሳቸው ልዩ እና አቻ የሌለው ተሰሚነት እንዲሁም የያዙት ቆራጣዊ ሥልጣን የሚያስፈራቸውና የሚያሳስባቸው መሳፍንት፣ መኳንንትና ባለ ሥልጣኖች ቁጥር እያደር እይጨመረ መምጣቱ አልቀረም። ለጊዜው በንጉሠ ነገሥቱ አመለካከት (እንደዚህ የተጠላ ባለ ሥልጣን በንጉሠ ነገሥቱ ላይ ለማመጽ አይፈልግም እንዲያውም ጥላቻን ከንጉሠ ነገሥቱ ላይ ይመክታል) እና ግምገማ የዚህ ዓይነት ጥላቻ ፀሐፌ ትዕዛዝን እስከነአካቴው ጠቀመቸው እንጂ አልጎዳቸውም። ግዞት ሆኖም የውጭ ጋዜጠኖች ፀሐፌ ትዕዛዝን ‘የኢትዮጵያ አምባ ገነን’ ሲሉ ማንሳታቸው ለንጉሠ ነገሥቱ የሳቸው የዝና ተወዳዳሪ ሆኖ መታየት የፀሐፌ ትዕዛዝን ውድቀት ካስጀመሩት ምክንያቶች አንዱ ነው ተብሉ ይገመታል። ሌላው ደግሞ ምክንያት የኤርትራን እና የኢትዮጵያን ‘ማኅበራዊ’ መንግሥት ይመለከታል። አምባሳዶር ዘውዴ ረታ፣ “የኤርትራ ጉዳይ” በተባለው መጽሐፋቸው እንደገለጹልን በመጋቢት ወር ዓ/ም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤርትራን በተመለከተ ጉዳይ ክርክር ሲደረግ የእንግሊዙ ልዑክ ያቀረበውን የመከፋፈል ኃሳብ በመቃወም የጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ መልስ ሲሰጡ ይሄንን በመቃወም ስለተናገሩት ንግግርና የእንግሊዝን መንግሥት ‘አስቀይመው’ ከሆነ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ምን ዓይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ለመምከር ንጉሠ ነገሥቱ በሰበሰቡት ጉባዔ ላይ በጊዜው የግል ጸሐፊያቸው የነበሩት እና ዬንግሊዝ ደጋፊ የሚባሉት አቶ (በኋላ ፀሐፌ ትዕዛዝ) ተፈራ ወርቅ ኪዳነ ወልድ አክሊሉ ለብሪታንያ መንግሥት ልዑክ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ደጋፊ ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ደግሞ የአክሊሉ እርምጃ ትክክል መሆኑን እና ምንም ዓይነት ይቅርታ መደረግ እንደሌለበት ተከራከሩ። በዚሁ መጽሐፍ ላይ ኤርትራና ኢትዮጵያ በ’ኅብረት መንግሥት’ አስተዳደር በተዋሃዱ ዓመት ባልሞላው ጊዜ በተነሳው የ’ኅብረት መንግሥት’ አለማስፈለግ ጉዳይ በ መስከረም ወር ዓ/ም በተደረገው የንጉሠ ነገሥቱ ውስጣዊ ጉባዔ ላይ ልዑል ራስ ካሳ በአንድ አገር ውስጥ ሁለት ዓይነት አመራር ሊኖር ስለማይችል በአንድ ሕጋዊ አስተዳደር ሁሉንም የኢትዮጵያ አካላት ማስተዳደር እንደሚያስፈልግ ሲያስረዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አክሊሉ ሀብተ ወልድ ደግሞ ኢትዮጵያ ወዳም ሆነ ጠልታ ይሄንን ዓይነት አስተዳደር በሕግ የተቀበለችው ስለሆነ ይሄንን በጥንቃቄ መተግበር ግዴታዋ እንደሆነና ኅብረታዊ መንግሥቱን መለወጥ ካስፈለገም ሕጋዊ በሆነ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ታዛቢዎች የሚመሰከር የ’ውሳኔ ሕዝብ’ ድምጽ መሆን እንዳለበት ሲያስገነዝቡ፣ ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ አክሊሉን በመደገፍ ኢትዮጵያ የኅብረታዊ መንግሥትን ለመደምሰስ እንዳልተዘጋጀችና እርምጃው የሚያስከትላቸውንም ክስተቶች በቅጡ ለማጥናት ጊዜ ያስፈልጋል።’ ብለው ካስረዱ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ይሄንን ግምገማ እሳቸው ያስጀመሩት እና የሚገፋፉት ጉዳይ ነው በሚል ተርጉመው ፀሐፌ ትዕዛዙን በመቆጣት ‘’ለ እንደራሴያችን ራስ አንዳርጌ ወይም ለምክትሉ ደጃዝማች አስፍሃ የኅብረት መንግሥቱን መውደቅ የሚያፋጥን ምንም ዓይነት ትዕዛዝ እንዳልሰጠን ከሁሉ የበለጠ አንተ ታውቃለህ።” በማለት ገሰጿቸው ይሉናል። እንግዲህ ባንድ በኩል ፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ከንጉሠ ነገሥቱ በዐዋጅ በተሰጣቸው ሙሉ ሥልጣን ብዙ የሚፈሯቸውና የተከፉ መሳፍንት፣ መኳንንትና ባለሥልጣናት እንደጠሏቸውና የሳቸውን ከሥልጣን መውረድ በጉጉት ይጠባበቁ እንደነበር ተመልክተናል። ቀጥሎም የንጉሠ ነገሥቱ የግል ፀሐፊ (ማለትም ለንጉሠ ነገሥቱ ቅርብነትና ተሰሚነትን እያገኙ የመጡት) እንዲሁም የ’እንግሊዝ ደጋፊ’ ይባሉ የነበሩት ፀሐፌ ትዕዛዝ ተፈራ ወርቅ ኪዳነ ወልድ ከወልደ ጊዮርጊስ ጋር ያደርጉትን ሙግት ተመልክተን ምናልባት የጽሕፈት ሚኒስቴሩ ዘላቂና ኃይለኛ ባላጋራ አጋጥሟቸው ይሆን ለማለት እንችላለን። በሦስተና ደረጃ የኤርትራን የኅብረት መንግሥት በተመለከት የንጉሠ ነገሥቱ ተግሳጽ በሌሎች (ተቃዋሚዎቻቸው) ፊት ሲደርሳቸው ጆን ማርካኪስ “በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የአስተዳደር ስልት፤ ለሥልጣን የብቃተ ቢስነት ወንጀል ወይም የማይካድ የሙስና ድርጊት ሲታይ የተለመደው ቅጣት ወደሌላ ሥራ መዛወር ሲሆን፤ ለንጉሠ ነገሥቱ ታማኝ አለመሆን ግን ያለምንም ጥርጣሬ በፈጣን ፍርድ በግዞት ዓለም መጥፋትን ያስከትላል።” ያለን በፀሐፌ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ ላይ እየተተገበረ መሆኑን እንገነዘባለን። ወዲያውኑ ፀሐፌ ትዕዛዝ ከጽሕፈት ሚኒስቴርነታቸው ተሽረው መጀመሪያ የአሩሲ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ ሆነው እስከ ዓ/ም ከቆዩ በኋላ ወደ ገሙ ጎፋ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳድሪ ሆነው ተዛወሩ። የስድሳ ስድስቱ አብዮት ኃይለ ሥላሴን ከሥልጣን ከማውርዱ ከጥቂት ጊዜ ቀደም ብሎ ለሕክምና ወደ እንግሊዝ አገር ይሄዱና ሁለተኛውንና የመጨረሻውን የስደት ዘመን ጀምረው በተወለዱ በሰባ አምስት ዓመታቸው እዚያው እንግሊዝ አገር አርፈው ተቀበሩ። ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ በአባታቸው የትውልድ አገር በቡልጋ ውስጥ የቅድስጌ ማርያምን ቤተ ክርስቲያን በግል አሠርተዋል። ማጣቀሻ ዋቢ ምንጮች ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ፣ አንደኛ መጽሐፍ ዓ/ም (1941-1963) (1993) (2006) (2003) (2001) (1994) የኢትዮጵያ ካቢኔ
35205
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%99%E1%88%B4
ሙሴ
ሙሴ (ዕብራይስጥ፡ /ሞሼህ/) በብሉይ ኪዳን ከሚጠቀሱት ታላላቅ ነብያት አንዱ ነው። ሙሴ በተወለደበት ዘመን የእስራኤል ልጆች በግብጽ ውስጥ በባርነት ተገዝተው የነበርበት ሆኖም ግን ቁጥራቸው እየበዛና እየተጠናከሩ የነበርበት ጊዜ ነበር። በዚህ ዘመን ግብፅን ያስተዳድር የነበር፣ ስሙ በብሉይ ኪዳን ያልተጠቀሰው የግብፅ ፈርዖን፣ የእስራኤል ልጆች ከውጭ የግብፅ ጠላቶች አግዘው ሊወጉን ይችሉ ይሆናል በሚል ፍራቻ ማናቸው የእስራኤል ወገን የሆኑ ወንድ ልጆች በተወለዱ ጊዜ እንዲገደሉ አዘዘ። ሆኖም የሙሴ እናት፣ ዮካብድ፣ ልጇን ደብቃ ታኖር ነበር። ከሶስት ወር ድበቃ በኋላ ልጁን በደንገል ሳጥን አድርጋ በአባይ (ናይል) ወንዝ አጠገብ አስቀመጠችው። ሳጥኑ እየተንሳፈፈ የፈርዖን ልጅ እምትታጠብበት ስፍራ ደረሰ፣ የፈርዖንም ልጅ ለህጻኑ ስላዘነች በፈርዖን ቤት አደገ። ከስደቱ እስከ እረፍቱ ባጭሩ ካደገ በኋላ አንድ የግብፅ ባሪያ አሳዳሪ እስራኤላዊ አሽከሩን ሲደበድብ አይቶ ሙሴ ግብጻዊውን ገደለው። ሆኖም ይህ ጉዳይ በግብጽ ባለስልጣኖች ዘንድ እየተሰማ ስለሄደ ሙሴ ወደ ምድያም አገር ተሰደደ። በዚያ ለ40 አመት ያክል ሲቀመጥ የካህኑን ዮቶርን በጎች ይጠብቅ ነበር። በዚህ ጊዜ የድሮው ፈርዖን ሞቶ አዲስ ፈርዖን በግብፅ ነግሶ ነበር። በአዲሱ ፈርዖን ዘመን የእስራኤላዊያኑ ጭቆና ባሰ እንጅ አልቀነሰም። ከኮሬብ ተራራ በሚገኝ ቁጥቋጦ ውስጥ በተገለጠለት መልዕክት መሰረት ሙሴ እድሜው 80 ከሞላ በኋላ ወደ ግብፅ ተመለሰ የመመለሱም ዋና ዓላማ እስራኤላውያኑ ግብፅን ለቀው እንዲወጡ አዲሱን ፈርዖን ለማስፈቀድ ነበር። አዲሱ ፈርዖን እምቢ ስላለ ሙሴ 10 መቅሰፍቶችን በግብፅ ላይ ከፈፀመ በኋላ ንጉሱ ስለተስማማ እስራኤላውያንን እየመራ ቀይ ባሕርን በእግዚአብሔር ኃይል ከፍሎ በደረቅ ምድር ላይ አሳልፏቸው ከተገዙበት ግብፅ አውጥቶ በሲናይ (ሲና) በረሃ ብዙ ታአምራትን እያደረገ ውሀ ከዲንጋይ እያፈለቀ ከፀሐይ በደመና እየጋረደ በሌሊት ብርሃን እያደረገ መና ከሰማይ እያወረደ ሌላም ብዙ ተአምር የሠራ መርቷቸዋል በዚህ ወቅት እስራኤላውያኑ በኮሬብ ተራራ ተመስርተው የኤዶምን ደንበሮች ያስሱ ነበር አሥርቱ ትዕዛዛትን ሙሴ የተቀበለው በዚህ ወቅት ነበር። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ሙሴና ህዝቡ ለ40 ዓመት በበረሃው ውስጥ ከዋተቱ በኋላ ሙሴም ወደ ተስፋይቱ ምድር ወደ ከነዓን ሳይገባ እሱን እንዲተካው እያሱን መርጦ በዚሁ በስደት ወራት እድሜው 120 ሲሆን አልፏል። የኖረበት ዘመን አጭር መረጃ በታሪክ አጥኝዎች ዘንድ፣ ሙሴ መቼ እንደኖረ በዕርግጥ አይታወቅም። አንድ አንድ ተመራማሪዎች የኖረበትን ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት በ13ኛው ክፍለዘመን ሲያደርጉ ሌሎች ከዛ በፊት ነው ይላሉ። ይህም ግመት በዚያው ክፍለ ዘመን መጨረሻ የገዛው ፈርዖን መርነፕታህ በጽላቱ የእስራኤል ስም መጀመርያው ስለ ጠቀሰው ነው፤ እንዲሁም የአባቱም ስም ራምሴ በኦሪት ዘጸአት የከተማ ስም ሆኖ ስለ ታየ ነው። ንጉሥ ዳዊት ግን በእስራኤል በ1000 ዓክልበ. ያህል ስለ ገዛ፣ ጸአቱ በመርነፕታህ ዘመን ሆነ ማለቱ ለእብራውያን ዘመነ መሳፍንት አይበቃም። በፈርዖኑ ራምሴ ሥር የተገነባው ፒ-ራምሴስ በጥንቱ አቫሪስ ሥፍራ ስለ ሆነ፣ የከተማው ኋለኛው ስም በተቀበለው ጽሑፍ እንደ ተገኘ መስሏል። ሌላው የተሰየመው ከተማ ፊቶም (ፒጦት በኩፋሌ) በግብጽኛ ፐር-አቱም ተብሎ ከአቫሪስ ዘመን መኖሩ ታውቋል። በኩፋሌ በመጽሐፈ ኩፋሌ ዘንድ የእግዚአብሔር መላእክት ለሙሴ በደብረ ሲና ላይ ያቀረቡት ቃል ነው። ይህ የሆነበት ዓመተ ዓለም አዳምና ሕይዋን ከኤዶም ገነት ከወጡ 2,410 ዓመታት በኋላ እንደ ነበር በኢዮቤልዩና በሱባዔ አቆጣጠር ያመለክታል። ዕብራውያንን ከግብጽ ባርነት ወደ ደብረ ሲና የመሩዋቸውም በ2410 ዓ.ዓ. እንደ ሆነ ይነግረናል። የመጽሐፈ ኩፋሌ ዜና መዋዕል አከፋፈል በጠቅላላ ከሥነ ቅርሳዊ መዝገቦች ጋር ሊነጻጽር ይችላል። በዚህ አከፋፈል 2410 ዓ.ዓ. ማለት ከክርስቶስ ልደት በፊት (እንደ ኢትዮጵያዊ አቆጣጠር) 1661 ዓመታት አካባቢ እንደ ነበር ሊገመት ይቻላል። 2149 ዓ.ዓ. (1922 ዓክልበ. ግ.) የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ ወደ ግብጽ ባርነት ተሸጠ። 2164 ዓ.ዓ. (1907 ዓክልበ. ግ. ዮሴፍ የፈርዖን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ። 2171 ዓ.ዓ. (1900 ዓክልበ. ግ.) የ፯ አመት ታላቅ ረሃብ በመካከለኛው ምሥራቅ ጀመረ 2172 ዓ.ዓ. (1899 ዓክልበ. ግ.) የተረፉት የእስራኤል ልጆች ከከነዓን ወደ ጌሤም አገር (በአባይ ወንዛፍ) ፈለሱ። 2242 ዓ.ዓ. (1829 ዓክልበ. ግ.) ዮሴፍ በግብጽ ዓረፈ። 2263 ዓ.ዓ. (1808 ዓክልበ. ግ.) ዕብራውያን የወንድሞቹን ሬሳዎች ወደ ከነዓን አድርሰው ብዙዎችም ወደ ግብጽ ተመልሰው ጥቂቶቹ ግን ከነሙሴ አባት ዕብራን (ወይም እንበረም እንደ ኦሪት ዘጸአት) በኬብሮን ቀሩ። የከነዓን ንጉሥ መምከሮን ከግብጽ ፈርዖን ጋር ስለ ተዋጋ የግብጽ በር ተዘጋ። 2303 ዓ.ዓ. (1768 ዓክልበ. ግ.) የሙሴ አባት ዕብራን ከከነዓን ወደ ጌሤም ተመለሰ። 2330 ዓ.ዓ. (1741 ዓክልበ. ግ.) የዕብራውያን መከራ ዘመን በጨካኝ ፈርዖን ተጀመረ። ሙሴ በጌሤም ተወለደ። 2372 ዓ.ዓ. (1699 ዓክልበ. ግ.) ሙሴ ከግብጽ ወደ ምድያም ሸሸ። 2410 ዓ.ዓ. (1661 ዓክልበ. ግ.) ሙሴ ከምድያም ወደ ግብጽ ይመልሳል፣ የግብጽ መቅሰፍቶች፣ ዕብራውያን ወደ ሲና በረሃ አመለጡ፣ ሕገ ሙሴን በደብረ ሲና ይቀበላሉ። በዚህ አከፋፈል፣ እስራኤል ከነዓንን የወረረበት ወቅት ከ፵ ዓመት በኋላ (2450 ዓ.ዓ. ወይም 1621 ዓክልበ.) ጀመረ፣ ሙሴም ከዮርዳኖስ ወንዝ ምሥራቅ አንዳንድ አሞራዊ አገር አሸንፎ ወንዙን ሳይሻገር ግን በዚያው ዓመት እንዳረፈ በኦሪት ይዘገባል። በ1661 ዓክልበ. የግብጽ ሃይል እጅግ ተደከመ፣ ከመርነፈሬ አይ በኋላ የተከተሉት ፈርዖኖች ከዋና ከተማቸው ከጤቤስ ውጭ ሥልጣን አልነበራቸውም። በዚያም ጊዜ ሂክሶስ የተባለው የአሞራውያን ብሔር ጌሤምን ወረሩ፣ ከግብጻውያንም ጋራ ይዋጉ ጀመር። እነዚህ ሂክሶስ (ወይም «15ኛው ሥርወ መንግሥት») በመጨረሻ በ1548 ዓክልበ. ከግብጽ ተባረሩ፣ የታሪክ ጸሐፊዎች ግን ብዙ ጊዜ ይህን ድርጊት ከጸአቱ ጋራ ይደናገሩ ነበር። ሆኖም በጌሤም የገዛው «14ኛው ሥርወ መንግሥት» (1821-1742 ዓክልበ. ግ.) የተባሉት ነጋዴዎችና እረኞች ለሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ደግሞ ይዩ የዕብራውያን ታሪክ ሙሳ (አ.ሰ) ሙሴ በእስልምና የብሉይ ኪዳን ሰዎች መጽሐፍ
46315
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B4%E1%88%8C%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%8D%8D
ቴሌግራፍ
ቴሌግራፍ የመልእክት ግኑኝነት የፅሁፍ ህትመት ማተሚያ መሳሪያ ቀደም ብሎ ዋና የመገናኛ መንገድ ነበር፤ ቀጥሎም ቴሌግራፍ ፈጣን ግኑኝነትን ከሩቅ ስፍራ ድረስ አስቻለ፤ የራዲዮ ስርጭት መጀመርም የቴሌግራፍን ዝና ቀነሰው እናም ሽቦ አልባ ቴሌግራፍ ብሎም ስልክ የቀጥታ እንድ ለአንድ ግኑኝነት መቻል ደረጃ ሲደረስ ፤መገናኛ ብዝኋን በቴሌቪዥን መስኮት ዋናው የግኑኝነት መንገድ ሆነ፡፡ በኢንተርኔት ዘመን ቴሌግረፊክ ወይንም የመልእክት ግኑኝነት በሽቦ መስመር ላይ በዘዴው እና በአጠቃቀሙ ጎልብቶ እና ቀሎ እነ ጋዜጣ፤ ራዲዮ፤ ቴሌቪዥን ስልክንም ጨምሮ በመጠቅለል ላይ ይገኛል። የቴሌግራፍ ታሪክ ቴልግራፊ(ከግሪክ «ቴሌ» ማለት ከርቀት፤ «ገራፋይን» ማለት መፃፍ) ሲሆን የረዥም ርቀት የፅሁፍ ወይንም የምልክት መልእክቶች ማስተላለፍን የሚወክል ሲሆን ይህም መልእክቱን የሚሸከም ወይንም የሚያደርስ አካልን አያካትትም፡፡ የኤኬክትሪክ ቴሌግራፍ፤ የኤሌክትሪክ ቴሌግራፍ የኤሌክትሪክ ሲግናልን በተዘጋጀ የሽቦ መስመር ወይንም በራዲዮ ሞገድ መልክ መላክን ይገልፃል፤ ይህም አዲስ የተገኘውን የኤሌክትሪሲቲ ከስተት ማለትም ኃይሉን ማምረት፤ መቆጣጠር ሲቻል አብረው ያሉትንም እንደ፡ የኬሚካል ለውጦች፤ ብልጫታዎቹን፤ የማይለዋወጡ ቻረጆች የስበት ሀይል፤ የኤሌክትሪክ ንዝረት እና የማግኔቲዝም ጠባዩ ላይ ምርምር እና ክትትል ሲቀጥል የቴሌግራፍ አይነቶች እና ዕድገቱ በጀርመኖቹ ፊዚሺያኖች የኤሌክትሮኬሚካል ቴሌግራፍ ዘዴ የሚጠቀመው በአንድ ወገን ብዙ ሽቦዎች እያንዳንዳቸው ልዩ የሆነ ስም ወይንም ፊደል የሚወክሉ አንድበአንድ በኤሌክትሪክ ቻረጅ ሲደረጉ በሌላኛው በኩል እነዚህ ሽቦዎች ጫፋቸው የኬሚካል እቃ ውስጥ ተነክረው ቻርጅ በተደረገው ሽቦ መስመር ያለው ኬሚካል በሚፈጥረው እንፋሎት መሰል ምልክት ወይንም በብል ትርጉም መስጠትን ይመስላል ዴቪስ ሪሌይ በማበል የሚታወቀውም ትንሽ ከረንት ፍሰት ትልቅ የኤሌክትሮማግኔት እንቅስቃሴን በማስነሰቱ ይህም የኤሌክትሪክ ሲገናል ማስተላለፍ ወይንም ቴሌግራፍ፤የኤሌክትሮማግኔትም መታወቅ እናም ጥቅል ሽቦዎችን በማብዛት ኢነሱሌትድ በሆነ ብረት ዙሪያ የመፈጠረውን የማገኔቲክ ኃይል ከፍ በማድረግ ሳይንቲስቱ ሃንስ ክ. በ1820 እ.ኤ.አ. የኤሌክትሪክ ዥረት የማግኔቲዝም ኃይል እንደሚፈጥር እና ይህም የደቡባዊ ዋልታ የሚያመለክት አመልካችን እንደሚያንቀሳቅስ፤ ቀጥሎም ጆ. የተባለው ጋልቫኖሜትር ወይንም የኤሌክትሪክ ዝረትን ፍሰት አመልካች መሳሪያ በመፈልሰፉ፤ አ.ማ. ጋልቫኖሜትሮችን በማሰባሰብ ልከ እንደ ኤሌክትሮኬሚካሎቹ ዎች በእያንዳንዱ ሽቦ ላይ የሚመጣውን የኤሌክትሪክ ፍሰት በማመልከት የቴሌግራፍ ጥቅም እንደሚገኝ ሳሙኤል ሞርስ የሞርስ ኮድም የሚባለውን ለእያንዳንዱ ፊደሎች የተለየ ድምፅ በመቀጠል በቴሌግራፍ ታዋቂ የጋውስ ጋልቫኖሜትርም በዘዴው ተሸሽሎ ኮሚውታቶር በመጠቀም ፤ከቮልታይክ ፒል ወይንም ከባትሪ መሰል ይልቅ የኢንዳክሽን የኤሌክትሪክ ኃይል (ፐልስ) በማድረግ በኮሚውታቶሩ አማካኝነት የዝረት አመልካች ቀስቷን በፖዘቲቭ እና በኔጌቲቭ አቅጣጫ በማንቀሳቀስ በዚሁ ኮድ የተሰጠውን ፊደሎች ማስተላለፍ መቻሉ ሲሆን እነዚህ ፖሰቲቭ እና ኔጋቲቭ መጠኖችም ሊገኙ የቻሉት ጥቅል ሽቦዎችን በማግኔቱ ዙሪያ ወደ ላይ ችና ወደታች በማንቀሳቀስ ነበር፤ በዚህም ሰባት 7 ፊደሎችን በደቂቃ ማስተላለፍ ተችሎ 0 የቻርልስ ቴሌግራፍ አመለካች ቀስትን እንደ ሰዐት ቆጣሪ ገበታ ላይ መልእክቱን እንዲያመለክት ማድረግ ነበር ይህም የቴሌግራፍ መልእክቶችንም ከኮዳቸው ወደ ግልፅ ትርጎሜ ለማምጣት የሰለጠኑ ሰዋች ፍላጎት ያስቀረ ነበር እንዲሁም መልእክቱ በሚመጣበት ወቅት ተርጎሚዎች መኖር ነበረባቸው እናም በ1846 አሌክአንደር የኬሚካል ቴሌግራፍን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ዥረት ሲግናል የብረት ጠቆሚን በወረቀት ላይ የቀለም ምልክት እንዲያደርግ በማድረግ ከዛም እነዚህን ምልክቶችንም በሌላ ጊዜ መተርጎም ያመለክታል፤ ቀጥሎም የፊደል ገበታ ያላቸው መሳሪያዎች (ኪ-ቦርድ) መልእክት የሚልኩ ቴሌግራፎችን በመጠቀም ፊደሎቹን ሲቀበሉ ወዲያውኑ በሞርስ ኮድ ማተም ተጀመር፤ ሌላውም በሞርስ ኮዶች መሰረት የኤሌክትሪክ ሲግናሉ ሲመጣ በታመቀ አየር በመጠቀም ቀዳዳዎችን በወረቀት ላይ በመብሳት ቀጥሎም መተርጎም ይከተላል ተግዳሮቶች የሽባውች የመጠነ አቃቢነት ወይንም ካፓሲታንስ እና ሽቦው በረዘመ ቁጥር የኃይሉ መጠን እንቅፋት ወይንም ረዚስታንስ እየጨመረ በመሄዱ የሚገኘውን የመልእክት ፍጥነት ላይ ተፅእኖ አስድሯል ለዚህም ሲፎን የሚባ መሳሪያ በ…… የሚሰራ ፍጥነቱን ወደ 20 ፊደሎች በደቂቃ አድርሷታል ኦሊቨር ሄቪሳይድም የማስተላለፊያ መስመሩን የሲግናል መዛባት ለማጥፋት በሽቦው ላይ የዥረት አቃቢነት ወይንም ኢንደክታንስ ቢጨመርበት የሚለውን ሀሳብ አፈለቀ እነደዚሁም ይህ ኢንሱሌትድ ሽቦ የኤሌክትሮማግኔት ፀባዩን ከፍ በማድረግ ረዚስታንሱ የሚያመጣውን ጉድለት ቀንሶታል፤ ይህ ኢነሱሌተር ወይንም ኤልክትሪክ የማያስተላለፍ ፕላስቲክ መሰል ከኢሴያ ከ/አለም ከሚገኝ ዛፍ ጉታ ፐርቻ እነደሚገኝ ታውቆ በስኮትላንድ ሀኪም ታውቆ ነበር እናም ይህ በእነ ፋራዳይ ለኤሌክትሪክ ኢነሱሌተርነት እንዲውል አደረጉት ሌላው የቴሌግራፍ ተግዳሮት የነበረው የመላኪያ ፍጥነቱን መጨመር ነበር(ፊደሎች/በደቂቃ) ይህም በሰው የሚሰር እጅ ስራን ማስቀረት ይጨምራል፤ ለዚህም የድምፅ ሰራተኞችን በመዝግቦ በመተንተን… ሞርስ ኦፐሬተር የተበላው መሳሪያ ዶት እና ዳሽ ኮዶችን በመለየት በሚጠቀመው ዘዴ……… የቶማስ ኤዲሰንም መልቲፕሌክ ቴሌግፍ ሢግናሎችን በጊዜ በፍጥነት በመከፋፈል የሚገኘውን እስከ ቤል ቴሌፎን ዕያለ መሻሻል አሳይቷል የአጠቃቀሙ ዕድገቱ ጋውስ በ1835 በጀርመን የባቡር መስመር ጣቢያ የቴሌግራፍ መስመር ለትግበራ ውሎ ነበር በ1840 ሞርስ የኤሌክትሪክ ቴሌግራፉን ለዕይታ ባቀረበበት ወቅት የታላከው መልእክት ፈጣሪ በመጀመሪያ ምን አለ የሚል ትርጎሜ ይመስላል፤ እናም ለአሜሪካው ምክርቤት በፃፈው ማስታወሻ ሞርስ እንዲህ ብሎ ነበር ይህን መሰሉ የፈጣን ግኑኝነት መሳሬያ ትልቅ ወጤት ያለው ስለሚሆን ስለዚህም ልክ እንደ አያያዛችን ለጥሩም ለመጥፎም ሊውል ኮክ እና ዊትስቶን የኤሌክትሪክ ቴሌግራፍ መስርተው በ13ኪሜ ርዝመት ያለው ለንግድ ያዋለውን የቴሌግፍ መስመር በግሬት ዌስተርን ሬይልዌይ አካባቢ ዘረጉ ይህም ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሲሰጥ ነበር በ1850ወቹ በእንግሊዝ እና በ ፈረንሳይ መካከል የቴሌግራፍ መስመር ሲዘረጋ በመጀመሪያ ባይሳካም በሁለተኛ ሙከራ ግኑኘነት ማድረግ ተችሎል ቀጥሎም በ1860ዎቹ አትላንቲክ ውቂያኖስን ያቆረጠ የትሌግራፍ መስመር መዘርጋት ተችሎ በአሁጉራት መካከል ያለውን የጊዜ እና የቦታ ርቀት ከበደትን ያሳጣው ሆኗል፤ ዌስተርን ዩኒየን የመሳሰሉ ድርጅቶች ዋና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ነበሩ፤ እነደዚህም እያለ በፓሲፊክ ላይ የቴሌግራፍ ግኑኝነት በ 1902 ሲጠናቀቅ የቢሪቲሽ የባህር ውስጥ መስመር ዝርጋታ አብዛኛውን የወከለ ነበር፤ የዌስተርን ዩኒየን የቴሌግራፍ ግልጋሎት እስከ 2006 ድረስ ሲሰራ የነበረ ሲሆን የህንድም ተልግራፍ አገልግሎት እስከ 2013 ድረስ ጥቅም ላይ ውሎ ነበር፡፡ ኮክ እና ዊትስቶን የኤሌክትሪክ ቴሌግራፍ መስርተው በ13ኪሜ ርዝመት ያለው ለንግድ ያዋለውን የቴሌግፍ መስመር በግሬት ዌስተርን ሬይልዌይ አካባቢ ዘረጉ ይህም ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሲሰጥ ነበር ↵-➞በ1850ወቹ በእንግሊዝ እና በ ፈረንሳይ መካከል የቴሌግራፍ መስመር ሲዘረጋ በመጀመሪያ ባይሳካም በሁለተኛ ሙከራ ግኑኘነት ማድረግ ተችሎል ቀጥሎም በ1860ዎቹ አትላንቲክ ውቂያኖስን ያቆረጠ የትሌግራፍ መስመር መዘርጋት ተችሎ በአሁጉራት መካከል ያለውን የጊዜ እና የቦታ ርቀት ከበደትን ያሳጣው ሆኗል፤ ዌስተርን ዩኒየን የመሳሰሉ ድርጅቶች ዋና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ነበሩ፤ እነደዚህም እያለ በፓሲፊክ ላይ የቴሌግራፍ ግኑኝነት በ 1902 ሲጠናቀቅ የቢሪቲሽ የባህር ውስጥ መስመር ዝርጋታ አብዛኛውን የወከለ ነበር፤ የዌስተርን ዩኒየን የቴሌግራፍ ግልጋሎት እስከ 2006 ድረስ ሲሰራ የነበረ ሲሆን የህንድም ተልግራፍ አገልግሎት እስከ 2013 ድረስ ጥቅም ላይ ውሎ ነበር፡፡ ፈጠራዎች
49842
https://am.wikipedia.org/wiki/3%20%E1%89%B1%E1%89%B5%E1%88%9E%E1%88%B5
3 ቱትሞስ
መንኸፐሬ 3 ቱትሞስ በጥንታዊ ግብጽ የግብጽ አዲስ መንግሥትና የ18ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖን ሲሆን ምናልባት 1466-1433 ዓክልበ. የገዛ ነበረ። የአባቱ 2 ቱትሞስ ቁባት ንግሥት ኢሰት ተባለች፣ እርሷም የ3 ቱትሞስ እናት ሆነች። የ፪ ቱትሞስ ተከታይ በይፋ ልጁ ቱትሞስ ሲሆን፣ እሱ ግን ገና የ 2 ዓመት ሕጻን ልጅ ሆኖ በ1487 ዓክልበ. የ፪ ቱትሞስ ሌላ ንግሥት ሃትሸፕሱት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴው፣ በቅርብም ጊዜ ውስጥ በራስዋ መብት ፈርዖን ተባለች። በአንድ ጽላት ሃትሸፕሱት በየካቲት 10 ቀን፣ 22ኛ ዘመነ መንግሥትዋ (1466 ዓክልበ. ግ.) አረፈች የሚል ነው። ይህም መንኸፐሬ ቱትሞስ ፈርዖን የሆነበት ቀን ነበር፣ ሆኖም በተመሳሳይ እንደ 22ኛ ዘመነ መንግሥቱ ይቆጥሩት ነበር። ስለ፫ ቱትሞስ ዘመቻዎች የሚገልጹ ከዘመኑም የሆኑ በርካታ ምንጮች ተገኝተዋል። ግዛቱን ከናፓታ በደቡብ (የኩሽ መንግሥት መርዌ ዋና ከተማ) እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ በስሜን ድረስ በ17 ዘመቻዎች አስፋፋው። በየካቲት 10 ቀን 1466 ዓክልበ. ብቸኛው ፈርዖን እንደ ሆነ ወዲያው ሥራዊቱን ይዞ በመርከብ በሶርያ ደርሶ ዘመተ። ይህ ሶርያዊ ዘመቻ ከመጊዶ ውጊያው ዘመቻ ወር በፊት እንደ ሆነ በአርማንትና በናፓታ በተገኙት ጽላቶች ይገለጻል፤ በመካከሉ ወደ ግብጽ ቢመለስም ሁለቱም ግን «መጀመርያው ዘመቻው» ይባላሉ። በናፓታ ጽላቱ ላይ ቱትሞስ እንዲህ ይላል፦ «ግርማዊነቴ ወደ ስሜን ወደ እስያ ዳርቻ በመርከብ ሄድኩ። በጌባልም ግርማዊነቴም ብዙ የአርዘ ሊባኖስ መርከቦች ወደ ጋሪዎች ታስረው በበሬዎች ተስበው ከኔ በፊት ወደ ናሓሪን ወንዝ ተጓዙ፣ ወንዙን እንዲሻገሩ።» የቱትሞስም ሥራዊት ኤፍራጥስ ወንዝን ተሻግሮ ወደ ሚታኒ ግዛት ገብተው የሚታኒ ኃያላት ሸሹ ይላል። ከዚያ ቱትሞስ ለግብጽ ይግባኝ የሚል ሐውልት እዚያ በኤፍራጥስ ዳር አቆመ። የአርማንትም ጽላት ደግሞ ይህን ይጠቅሳል። ሁለቱም ጽሁፎች ደግሞ ቱትሞስ በኒያ አገር ሲመለስ 120 ዝሆኖችን አድኖ ገደላቸው በማለት ይስማማሉ። በአርማንት ጽላትም ዘንድ ሰባት አናብስትና 12 ጎሽ ደግሞ እንደ ገደላቸው ይጨምራል። ይሄው «ኒያ አገር» ያንጊዜ በኢድሪሚ ግዛት (ሙኪሽ)፣ ሚታኒም የባራታርና ግዛት እንደ ነበሩ ይታሥባል። የኢድሪሚም ሆነ የባራታርና መዝገቦች ስለ ግብጽ ቢጥቀሱ ገና አልተገኙም። አንዳንድ ሥፍራዎች ከማቃጠልና ከመዝረፍ በቀር፣ የቱትሞስ ሥራዊት በዚህ ጉዞ ላይ ትልቅ ውጊያ እንዳላገኙ ይመስላል። በሚቀጥለው ዓመት ግን ኢድሪሚ የባራታርና ጥገኛ ተባባሪ እንደ ሆነ ይታወቃል። በ፫ ቱትሞስ መዝገቦች ዘንድ በኤፍራጥስ ላይ ሳለ የኬጥያውያን መንግሥት፣ የአሦርና የባቢሎን (ካሣዊ) ነገሥታት ሁላቸው የግብጽ የበላይነት ተቀብለው የግብር ስጦታዎች ላኩለት ይባላል። «ዘጠኙ ቀስቶች» ወይም ክግብጽ ስሜን ባሉት ደሴቶች (እነ ቆጵሮስ?) ደግሞ በቱትሞስ ግዛት ውስጥ ነበሩ ብሎ ይግባኝ አለ። ሚታኒ ብቻ ለግብጽ የማይገብረው ኃይል ቀረ ማለት ነው። ቱትሞስም ከዚህ በኋላ ከኒያ አገር ወድ ግብጽ ገሥግሦ ተመለሰ። በከነዓን ምድር (ግብጽኛ፦ ጃሂ) ሲያልፍ፣ ኗሪዎቹ ባብዛኛው ፈርተው እቤቶቻቸው ውስጥ ተደበቁና ቱትሞስ የግብጽ ይግባኝ ማለቱን በዚህም ጣለ ይላል። ሆኖም በመጊዶና በተለይ በቃዴስ (ግብጽኛ፦ ረጨኑ) የተገኙት ከነዓናውያን ተሰብስበው እንደ ተቃወሙት ተመለከተ። በመጽሐፈ መሳፍንት መሠረት ዕብራውያን በዚህ ዘመን በጎቶንያል ፈራጅነት ነበሩ፤ በጎቶንያል ሥር አርባ አመት ሰላም አገኙ ከማለት በቀር ስለ ግብጾች ይሁንና ምንም ሌላ መረጃ አይሰጥም። ከጊዜ በኋላ በፈራጆቹ ዘመን የዕብራውያን ማዕከል በገለዓድ ወይም ከዮርዳኖስ ወንዝ ምሥራቅ ሙሴም ባሸነፈው ምድር መሆኑ ይመስላል፤ ምናልባት በጎቶንያል ዘመን ደግሞ የእስራኤላውያን ቅሬታ የተገኘው በተለይ በዚያ በገለዓድ አገር እንደ ሆነ ይቻላል። የሻሱ ወይም ሱቱ ሕዝብ በኤዶምና ሞአብ ብቻ ሳይሆን ከዮርዳኖስ ምዕራብ ደግሞ ይጠቀሳሉ። መጽሐፈ መሳፍንትም እንደሚለን የከነዓን ወገን በባሕር ዳር ላይና በተለይ በመጊዶ አካባቢ ቀርተው ነበር። ወደ ግብጽ ተመልሶ ወዲያው በሚያዝያ 25 ቀን ቱትሞስ ዞር ብሎ ከ10 ወይም 20 ሺህ ጭፍሮች ጋር ወደ ስሜኑ ገሠገሠ። «እንዲህም ሆኖ ነበር፤ በሻሩሄን የነበሩት ነገዶችና ሕዝቦች፣ ከያራዛ (ኢየሩሳሌም?) እስከ ዓለሙ አሮንቃ (ኤፍራጥስ) ድረስ በጊርማዊነቱ ዓምጸው ነበር።» በግንቦት 4 ቀን ወደ ጋዛ ደረሰ፣ ይህም ከዚያ በፊት የግብጽ ከተማ ነበር። በግንቦት 5 ቀን ከጋዛ ለዘመቻ ወደ ረጨኑ ወጣ። በመንገዱ ላይ ወደ ኢዮጴ ከተማ መጣ። በአንዱ ጽሑፍ ዘንድ፣ ኢዮጴ ለፈርዖን ጠላት ሆኖ የግብጽ የጦር አለቃው ጀሁቲ 200 ሰዎች በማቅ ውስጥ ደብቆ እንደ ስጦታ አስመስሎ የኢዮጴም ሰዎች በከተማው ግድግዶች ውስጥ አስገብተዋቸው ከተማውን መያዝ ተቻሉ። የዛሬው ታሪክ መምኅሮች ይህንን ጽሑፍ ልቦለድ ብለውታል፤ ሆኖም የጦር አለቃው ጀሁቲ መቃብርና ቅርሶች ከ1816 ዓም ጀምሮ ለሥነ ቅርስ ታወቀዋል። በባሕር ዳር መንገድ ተቀጥሎ በግንቦት 16 ቀን በየሄም ደረሰ፣ የሄምን ከመጊዶ የሚለዩም ተራሮች አሉ። በግንቦት 19 ቀን ሥራዊቱ በመጊዶ አጠገብ ባለው ሜዳ ደረሰ። የረጨኑም ሥራዊት በቃዴስና በመጊዶ ነገሥታት ተመራ። በግንቦት 21 በረጨኑ ሥራዊት ላይ ጥቃት ጥለው ግብጻውያን በመጊዶ ውግያ አሸነፉዋቸው፤ የረጨኑ ቅሬታ ግን ወደ መጊዶ ከተማ መሸሽ ቻሉ። የረጨኑ ሰዎች እጅ እስከሚስጡ ድረስ ግብጻውያንም ለሰባት ወር ከበቡዋቸው። ከተማረከው ሀብት ብዙ ብር፣ ወርቅ፣ ዕንቁ፣ እኅል፣ ወይን ጠጅ፣ 340 ምርከኞች፣ 2041 ባዝራዎች፣ 191 ፈረስ ግልገሎች፣ 6 ድንጉላ ፈረሶች፣ 2 የወርቅ ሠረገሎች (የነገሥታት) 924 ሠረገሎች ባጠቃላይ፣ 2 የነሓስ ጥሩሮች (የነገሥታት)፣ 200 ጥሩሮች፣ 502 ቀስቶች፣ 7 የብር ድንኳን ዓምዶች፣ 1929 ትልልቅ ከብት፣ 2000 ትንንሽ ከብት፣ 20500 ነጭ ትንንሽ ከብት (በግ) ወሰዱ። ከዚህ በኋላ ቱትሞስ ወደ ደቡብ ሊባኖስ ገሥግሦ ሦስት ከተሞች ይዞ በዚያ መካከል የግብጻውያን አምባ አሠራ፤ ከዚህም አገር የዘረፈው ዝርዝር 2503 ሰዎች፣ ብዙ የድንጋይና የወርቅ ዕቃዎች፣ የሐቢሩ ዕደ ጥበቦች፣ 3 ትልልቅ ጀበናዎች፣ 87 ቢላዋዎች፣ ብዙ የወርቅና የብር ቀለበቶች፣ የብርና የወርቅ ሐውልቶች፣ ከወርቅ፣ ዝሆን ጥርስ፣ ዞጲ፣ እና ካራቦ ዕንጨት የተሠሩ ስድስት ወምበሮች፣ 6 የግርም መቀመጮቻቸው፣ የዞጲ፣ ወርቅና ዕንቁ ሐውልት፣ የነሐስ ዕቃዎች፣ ብዙ ልብስም ነው። የሚከተሉት ጥቃቅን «ዘመቻዎች» ግብር ለመቀበል ብቻ ነበሩ። በ1463 ዓክልበ. በከነዓን ምድር የተገኙት እንስሶችና ዕጽዋት ተዘረዘሩ። በ1459 ዓክልበ በአምስተኛው ዘመቻ በፊንቄ በመርከብ ደርሶ ኡላዛን ወደብ ከቱኒፕ፣ እንዲሁም አርዳታን ያዘ። የሐቢሩም ወገን ሰዎች በኡላዛ ውስጥ እንደተገኙ ግብጾቹ ዘገቡ። በ1458 ዓክልበ. በቃዴስ ላይ ዘምቶ ጹሙሩን (ሰማሪዎን) ወደብና እንደገና አርዳታን ያዘ። በ1455 ዓክልበ. በ8ኛው ዘመቻ እንደገና በሚታኒ ላይ ተዋጋ። በ1454 ዓክልበ. ቱትሞስ ኑሐሼን (በሙኪሽ ግዛት) ዘረፈ። ልዑል ታኩ የኑሐሼ አገረ ገዥ እንዲሆን አደረገው። በ1453 ዓክልበ. የግብጽና የሚታኒ ሥራዊቶች ከሐለብ ስሜን ተጋጥመው ቱትሞስ በአርዓና ውጊያ አሸነፋቸው። በ1452-1450 ዓክልበ ቱትሞስ በኑሐሼ ዙሪያ ይዘምት ነበር፣ አላላኽም (ሙኪሽ) እንኳን ገበረለት። በ1449 ዓክልበ. ቱትሞስ በሻሱ ብሔር ላይ ዘመተ። ይህም እስራኤላውያን ለሞአብ ንጉሥ ኤግሎም የተገዙበት ዘመን ይመስላል። በ1446 ዓክልበ. ሚታኒ እንደገና በሶርያ ግዛቶቹ መሃል አመጽ አነሳስቶ፣ ቱትሞስ ተመልሶ አርቃን ወደብ፣ ቱኒፕንም ከተማ ያዘ፣ በቃዴስም ዙሪያ የሚታኒ አምባዎች አጠፍቶ ወደ ግብጽ ተመለሰ። ከዚህ በኋላ በኖቢያ ዘመተና ናፓታን በ1436 ዓክልበ. ያዘ። የቱትሞስ ዘመቻዎች በካርናክ «የዜና መዋዕል አዳራሽ» በተባለ ሕንጻ በግብጽኛ እንዲህ ተቀርጸዋል፦ ወደ ቱትሞስ ዘመን መጨረሻ፣ ልጁ 2 አመንሆተፕ የጋራ ፈርዖን በሆነበት ጊዜ (1435 ዓክልበ.) ወደያው ብዙ የሃትሸፕሱት ምስሎችና ካርቱሾች ከቅርሶቿ ለመደምሰስ እንደ ጣረ ይመስላል። አመንሆተፕ የዘመንዋን ትዝታ ከታሪክ ለማጥፋት እንዳሠበ ይመስላል። ከተረፉት ምስሎቿ ብዛት የተነሣ ግን ዘመንዋን ማጥፋቱ ስኬታም እንዳልሆነ ግልጽ ነው። የአዲስ መንግሥት
39424
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%B8%E1%8A%93%E1%8D%8A%20%E1%8A%A8%E1%89%A0%E1%8B%B0
አሸናፊ ከበደ
አስተዳደግና የትምህርት ዘመናት ፕሮፌሶር አሸናፊ ከበደ አዲስ አበባ ግንቦት ቀን ዓ/ም ተወለዱ።አባታቸው ግራዝማች ከበደ አድነው ሲሆኑ ክልጅነታቸው ጀምሮ የሙዚቃ ስሜትንና ፍቅር ያሳደሩባቸው እናታቸው ወይዘሮ ፋንታዬ ነከሬ ነበሩ። አያታቸው ሊቀመኳስ አድነው ጎሹ ደግሞ የአድዋ አርበኛ እናየንግሥት ዘውዲቱም ታማኝ አማካሪ እንደነበሩ ይነገራል። የሙዚቃ ፍቅርን ገና በልጅነታቸው ያሳደሩባቸው እናታቸው ሲሆኑ ታዳጊው አሸናፊ ገና የዘጠኝ ዓመት ልጅ ሳሉ እኒህ የሚያፈቅሯቸውና ዕድሜ ልካቸውን በኀዘን የሚስታውሷቸው እናታቸው ሞተውባቸዋል። መሠረታዊ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ኮከበ ጽባሕ) ካጠናቀቁ በኋላ በሐረር የመምህራን ማሠልጠኛ ኮሌጅ ተመርቀዋል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በኒው ዮርክ ክፍለ-ሀገር ከሚገኘው የሮቼስተር ዩኒቨርሲቲ፣ “ኢስትማን የሙዚቃ ትምህርት ቤት” በ፲፱፻፶፬ ዓ/ም በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ ወደኢትዮጵያ ተመልሰው፤ የያሬድ ሙዚቃ ትምሕርት ቤትን መሠረቱ። የዚሁ ትምህርት ቤትም የመጀመሪያው ዳይሬክቶር ከመሆናቸውም ባሻገር በአዲስ አበባው የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር (ወ.ወ.ክ.ማ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት መርሓ-ዕውራን ትምህርት ቤት እና በመሳሰሉ የወጣቶች ማኅበራት እየተገኙ የሙዚቃ ትምህርት ይሰጡ ነበር። በኢትዮጵያ የሥራ አገልግሎት የያሬድ ትምህርት ቤት ዲሬክቶር ሆነው ከ ፲፱፻፶፭ዓ/ም እስከ ዓ/ም ድረስ ባገለገሉበት ወቅት በንጉሠ ነገሥቱ “ብሔራዊ የሙዚቃ አቀናባሪ” ተብለው ከመሠያማቸውም ሌላ ለባሕላዊ ጉዳዮች ላደረጉት የላቀ ተዋጽዖ በ፲፱፻፶፱ ዓ/ም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት ተሸላሚ ሆነዋል። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የ፸፭ኛ የልደት በዓል በተከበረበት በዚሁ ዓመተ ምኅረት በሁንጋሪያ መንግሥት ተጋብዘው ወደ ቡዳፔስት በመጓዝ ታዋቂውን «እረኛው ባለዋሽንት» እና «የኢትዮጵያ ሲንፎኒያ” የተባሉትን ሁለት ድርሰቶቻቸውን በአቀናባሪነትና በኦርኬስትራ መሪነት አቅርበው፤ በሸክላ አሳትመዋል። መታሰቢያነቱንም ለጃንሆይ የልደት በዓል አበርክተዋል። ከሸክላው የሚገኘውን ገቢ በወቅቱ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሥር ይተዳደር ለነበረው የመርሐ-ዕውራን ትምህርት ቤት ለግሠዋል። ፕሮፌሶር አሸናፊ ከበደ ‘ጥቁሩ ኮዳሊ’ የሚለውን ማቆላመጫም ያገኙት የረቂቅ ሙዚቃ ድርሰታቸውን በሁንጋሪያ ውስጥ ከ’ፊልሃርሞኒክ ኦርኬስትራ’ው ጋር በሳቸው ሙዚቃ መሪነት ባቀረቡበት ጊዜ ነበር። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለተመልካቾች ባቀረበው፣ የሕይወት ታሪክ ዳሰሳ ቅንብር ላይ አብሮ አደግ ጓደኛና ሚዜያቸውም የነበሩት፣ ደራሲው አቶ አስፋው ዳምጤ፤ ፕሮፌሶር አሸናፊን ከያሬድ ትምህርት ቤት መልቀቅና ወዲያውም ከአገራቸው ለመሰደድ ያበቃቸው ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ሲሰጡ የተማሪዎች የረቂቅ ሙዚቃ ቅንብር በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ አዘጋጅተው፣ ንጉሠ ነገሥቱ እንዲገኙ በሚኒስትሩ በኩል ያቀረቡት ጥሪ እንደሚደርስ ባለመተማመን በሌላ መንገድ አድርሰው ንጉሠ ነገሥቱ በተገኙበት ለሕዝብ ቀርቧል። ሆኖም በዚህ የተቀየሙት ሚኒስትሮችና የቀጥታ ዓለቆቻቸው በያዙት ቂም እሳቸውን ከዲሬክተርነት አውርደው በምትካቸው አንድ ተራ የክቡር ዘበኛ ባንድ ተጫዋች የነበረ የውጭ ዜጋ አስገቡ። “አገር ትቶ ሲሄድ፤ አይ! እኔ መቼም በገዛ አገሬ ሁለተኛ ዜጋ አልሆንም!” ብሎኛል ይላሉ። በስደት ዘመናት ለከፍተኛ ትምህርት ወደአሜሪካ በተመለሱ ጊዜ የሙዚቃ ጥናታቸውን አጠናቀው፣ የ’ማስተሬት ዲግሪ’ በ፲፱፻፷፩ ዓ/ም፤ በ’ዶክቶር’ነት ደግሞ በ፲፱፻፷፫ ዓ/ም ከ’ዌስሊያን ዩኒቨርሲቲ’ ተመረቁ። ከ ዓ/ም እስከ ዓ/ም ድረስ በኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ፣ ‘ክዊንስ ኮሌጅ’ እና በማሳቹሴትስ ብራንዲስ ዩኒቨርሲቲ በረዳት ፕሮፌሶርነት ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ለአሥራ ዘጠኝ ዓመታት በፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ፤ መጀመሪያ በፕሮፌሶርነትና በኋላም የዩኒቨርሲቲው “የጥቁር አሜሪካውያን የባህል ማዕከል” ዲሬክቶር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። በተጨማሪም የዶ/ር መላኩ በያን የአዕምሮ ጥንሥስ የነበረውን “የኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር ድርጅት” ዳይሬክቶር በመሆን አገልግለዋል። ፕሮፌሶር አሸናፊ ከመጀመሪያ ሚስታቸው ወይዘሮ ዕሌኒ ገብረመስቀል ጋር ያፈሯቸው ኒና እና ሰናይት የተባሉ የሁለት ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ ሰናይት አሸናፊ በአሜሪካ የታወቀች የትዕይንተ-መስኮት ተዋናይ ናት። ሦስተኛ ልጃቸው ያሬድ አሸናፊ ደግሞ ከአሜሪካዊታ ሁለተኛ ሚስታቸው የተወለደ ነው። የሕይወት ፍጻሜ ፕሮፌሶር አሸናፊ ከበደ የ፷ኛ የልደት በዓላቸው ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ሞተው የተገኙ ሲሆን፤ ምናልባት የራሳቸውን ሕይወት ሳያጠፉ እንዳልቀሩ ብዙዎች ይገምታሉ። አቶ አበራ ሞልቶት የተባሉት ወዳጃቸው ለኢትዮጵያ ቴለቪዥን ቅንጅት በሰጡት ቃለ-ምልልስ ላይ ከዕለተ ሞታቸው በፊት ጽፈውላቸው እንደነበረና ደብዳቤውንም በመጥቀስ፦ «ጋሽ አበራ፤ ስለዚህ ወረቀት ምን ትላለህ? ይህ አዲሱ ሙከራዬ ነው። ግን እንደራዕይ የሚታየኝ ከመጪው ሐምሌ በፊት ወደሌላ አኅጉር እሄዳለሁ። ሞቼ፣ ሥጋዬን ትቼ ከዚህ ወደኒርቫና እሸጋገራለሁ።» እንደሚል አስረድተዋል። ዘመዳቸው አቶ በቀለ አሳምነው ደግሞ በዚሁ የቴሌቪዥን ቅንብር ላይ ስለዚህ ጉዳይ ሲያብራሩ፦ «“ባባቱ በኩል ታናሽ ወንድም አለው፤ ታዲያ አሸናፊ ወንድሙ ጋ ደውሎ “ከሣምንት በኋላ የለሁም…. ለሰው ልጅ ከስልሳ ዓመት በላይ መኖር ምንድነው ጥቅሙ?» ብሎት ነበር ይሉና ፖሊሶች ከምናየው ሁኔታ የራስን ነፍስ የማጥፋት ድርጊት ይመስላል ማለታቸውን ገልጸዋል። ፕሮፌሶር አሸናፊ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ድርጅት ከተቀበሉት ሽልማት ባሻገር የሱዳንን የዳንስ እና የድራማ ኢንስቲቱተ በማቋቋማቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሳይንስና የባሕል ድርጅት ሽልማትም ተቀብለዋል። ድርሰቶች ፕሮፌሶር አሸናፊ ከሙዚቃ ድርሰቶቻቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነትና ተወዳጅነትን ያተረፈው ‘እረኛው ባለዋሽንት’ ብቻ ሳይሆን ከሌሎቹም አንዳንዱን ለመጥቀስ፦ ‘ሰላም ለኢትዮጵያ’፤ ‘የአገራችን ሕይወት’፤ ‘የተማሪ ፍቅር’፤ ‘እሳት እራት’፤ ‘ኮቱሬዥያ’ እና ‘ኒርቫኒክ ፋንታሲ’ የሚባሉት ድርሰቶች የሚጠቀሱ ናቸው። በሥነ-ጽሑፍ ረገድ ደግሞ በተማሪነታቸው ዘመን በ፲፱፻፶፮ ዓ/ም የደረሱት እና ያሳተሙት “ንስሐ” ወይም የተባለው መጽሐፍ እና “የሙዚቃ ሰዋሰው” እንዲሁም በርካታ የጥናትና ምርምር ድርሰቶች ይጠቀሳሉ። ማጣቀሻዎች ዋቢ ምንጮች (1938-1998); 43, 2 1999), 322-334; /852737 ፕሮፌሰር ኣሸናፊ ከበደ የጽሑፎቻቸው ማውጫ የኢትዮጵያ ቴሌቪዝን፤ “የሙዚቃ ሰዎችና ሥራዎቻቸው” ክፍል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር ድርጅት የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች የኢትዮጵያ
18982
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%20%E1%8A%A0%E1%8B%A8%E1%88%AD%20%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%88%E1%8B%B5%20%E1%8A%A0%E1%8B%B0%E1%8C%8B%E1%8B%8E%E1%89%BD
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋዎች
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተመሠረተበት ከታኅሣሥ ቀን ዓ/ም ጀምሮ በ፷፭ ዓመት ዕድሜው እስከ ዓ/ም ድረስ በጠለፋ፤ በብልሽት ወይም በአብራሪ ጥፋት ምክንያት አደጋዎችን አስመዝግቧል። በነዚህ አደጋዎች የ ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ በዓቢይነት የተመዘገቡት ጥፋቶች በ፳፻፪ ዓ/ም በሜድትራኒያን ባሕር ውስጥ የተከሰከሰውና የ፺ ሰዎች ሕይወት የጠፋበት የበረራ ቁጥር እና ሰዎችን ለሞት የዳረገው የየበረራ ቁጥር በሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ መከስከስ ናቸው። የብልሽት እና አብራሪ ጥፋት አደጋዎች ሐምሌ ቀን ዓ/ም ጎሬ፤ ኢሉባቦር አየር መንገዱ በተመሠረተ በሁለት ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመዘገበው አደጋ፣ በዚህ ዕለት በክረምት ዝናብ ረጥቦ በነበረው የጎሬ አየር ዠበብ ማረፊያ ላይ ሲያርፍ ተንሸራቶ የተከሰከሰው ዲ-ሲ አየር ዠበብ (ሰሌዳ ቁጥር -5) ነበር። ማኮብኮቢያውን ስቶ ደንጊያ ላይ ሲከሰከስ የደረሰበት ጉዳት አየር ዠበቡን ከበረራ ጥቅም ውጭ አውሎታል። ሆኖም ከዚህ አደጋ በኋላ የአየር መንገዱ የጎሬ ቢሮ ሆኖ አገልግሏል። ሐምሌ ቀን ዓ/ም ሱዳን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር (የሰሌዳ ቁጥር -35) ከግሪክ ርዕሰ ከተማ አቴና ስድስት አየር-ዠበብተኞችንና አሥራ አራት መንገድኞችን ጭኖ በካርቱም በኩል ወደአዲስ አበባ ለመጓዝ ከአቴና ከምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል ላይ ተነሳ። ካርቱም በሰላም ደርሶ ሐምሌ ቀን ሲነጋጋ የአዲስ አበባ በረራውን በጀመረ በአሥራ አምስት ደቂቃው ከጧቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ሲሆን ሁለተኛው ሞተሩ በእሳት ተያያዘ። አብራሪዎቹ ይኼንን እሳት በመከላከያ ሊያጠፉ ሲሞክሩ ሞተሩ ፈነዳ። በዚህ ጊዜ አብራሪዎቹ በአስቸኳይ ማረፊያ ጎማዎቹን ሳያወርዱ፤ ከካርቱም ከተማ ኪ.ሜ. እርቀት በርሻ መሬት ላይ አሳረፉ። አየር ዠበቡ ለማረፍ ፩ሺ ጫማ ሲቀረው ሁለተኛው ሞተር ተገንጥሎ ሲወድቅ ያስከተለው መናጋት የአየር ዠበቡን የግራ ክንፍ ቁልቁል አዛብቶታል። አደጋው ያደረሰበት ጉዳት አየርዠበቡን ከጥቅም ውጭ ሲያውለው በተዓምር ግን ሁሉም ተሳፋሪዎች ተርፈዋል። ካፕቴን መኮንን ስለዚህ አደጋ ባሠፈሩት ትንተና ላይ፤ «አይሮፕላኑ ገና በረሃው ላይ ለማረፍ ሲጠጋ አስተናጋጆቹ የአደጋ ጊዘ መውጫዎቹን መስኮቶች ከፍተዋቸው ስለነበረ፤ እንደቆመ በጣም አጭር በሆነ ጊዜ ማለትም በ ሴኮንድ ውስጥ መንገደኞችና ዘጠኝ ሠራተኞች ምንም ሳይነካቸው ከሚቃጠለው አይሮፕላን ወጥተዋል። እንደ ዕድል ሆኖ ነፋሱ መንገደኞች ወደወጡበት በኩል ይነፍስ ስለነበረ የእሳቱ ወላፈን ሳይነካቸው ከአይሮፕላኑ ለመራቅ ቻሉ» በሚል አስፍረውታል። የአደጋው ምክንያት፣ አየር ዠበቡ ሲያርፍና ሲነሳ በ’ፍሬኖቹ’ መጋል ምክንያት እና የፍሬን ዘይት መፍሰስ ጎማው በመፈንዳቱ በሁለተኛው ሞተር ማዕቀፍ ውስጥ የተቀጣጠለው እሳት እንደሆነ ባለሙያዎች ገምተዋል። ካፕቴን መኮንን ደግሞ በመጽሐፋቸው ላይ ስለአደጋው የምርመራ ውጤት ባሠፈሩት መሠረት «ከካርቱም ሲነሳ የእግሮቹ ፍሬኖች እንደሞቁ ታጥፈው ኑሮ ጎማው ታፍኖ ስለቆየ ፈንድቶ ብዙ ነገሮች ስለጎዳ፣ ከፈሳች ነዳጅ ጋር ተገናኝቶ እሳት ስለተነሳ የአደጋው መነሾ መሆኑ ታወቀ።» በማለት አብራርተውታል። ሐምሌ ቀን ዓ/ም ቡልቂ በረራ ቁጥር (የሰሌዳ ቁጥር -18) የነበረው የ’ዳግላስ ሲ-፫ አየር ዠበብ የአየር መንገዱ የመጀመሪያው የሰው ሕይወት ጥፋት የተመዘገበበት በረራ ነው። ከአዲስ አበባ ፭መቶ ፳ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ክልል ጋሞጎፋ ዞን ጎፋ ወረዳ ውስጥ ከምትገኘው ቡልቂ አየር-ዠበብ ማረፊያ ሦስት ዠበብተኞት እና ስምንት መንገደኞች እንዲሁም የቡና ምርት ጭኖ ወደጅማ ለመብረር ከጧቱ ሦስት ሰዓት ላይ ከተነሳ በኋላ ከአየር-ዠበቡ የተላለፈው ድምጽ ሦስት ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ላይ አብራሪው ቶማስ ሃሎክ የጅማ የራዲዮ ማስተላለፊያ እንዲከፍተለት ያስተላለፈው ጥያቄ ነበር። አየር ዠበቡ መድረሻውን በ፳፯ ተኩል ኪሎ ሜትር አልፎት ከጅማ በስተደቡብ ከሚገኝ ተራራ ጋር ፱ሺ ፬መቶ ጫማ ከፍታ ላይ ተጋጭቶ ተገኘ። በተዓምር ከዠበብተኞቹ አብራሪው ሃሎክ ብቻ ሲሞት ሌሎች አሥር ተሣፋሪዎች ተርፈዋል። አየር ዠበቡ በደረሰበት አደጋ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። የአደጋው ምክንያት (ሀ) አብራሪው፣ አሜሪካዊው ቶማስ ፒ ሃሎክ የአካባቢውን ዓየር ሁኔታ መጥፎ ቢሆንም አቃልሎ በመገመቱ እና (ለ) የአየር ዠበቡን ሽቅብ የመውጣት ችሎታ ባለማወቅ በቂ ፍጥነት ሳያገኝ የአለአቅሙ ሽቅብ ለማስወጣት መሞከሩ እንደሆነ የአደጋው ጥናት ደምድሟል። ነሐሴ ቀን ዓ/ም -ሰንዳፋ በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ቲ-፲፮ ተመዝግቦ የነበረው አየር ዠበብ ለአየር መንገዱ ሁለተኛው የነፍስ ጥፋት አደጋ የተከሰተበት በረራ ሲሆን፣ በግል ኪራይ ለዳሰሳ ጥናት ሦስት ዠበብተኞችንና አሥራ ስድስት መንገድኞችን ጭኖ ከአዲስ አበባ ልደታ ማረፊያ ተነሥቶ ወደ አስመራ በረራ ጀምሮ ነበር። ነገር ግን ሰንዳፋ አካባቢ ላይ የሞተሩ ተሽከርካሪ ሲያቆም አብራሪው ወደልደታ ለመመለስ ሞክሮ ነበር። ዳሩ ግን አየር ዠበቡ ወደመሬት ተከሰከሰና አስተናጋጇና አራት መንገደኞች ሕይወታቸው አልፏል። ጥር ቀን ዓ/ም -ቴፒ በከፋ ጠቅላይ ግዛት (የአሁኑ ከፊቾ ሸኪቾ ዞን) ውስጥ ከሚገኘው የቴፒ አየር-ዠበብ ማረፊያ ተነስቶ ወደ ጅማ ለመሄድ ሦስት ዠበብተኞችንና አሥራ አምስት መንገደኞችን ጭኖ የነበረው ዲ-ሲ የሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ቲ-፩ አየር ዠበብ ከማኮብኮቢያው ሊነሳ ሲንደረደር ባልታወቀ ምክንያት በአቅራቢያው ከነበረ ወፍጮ ቤት ላይ ተላግቷል። በዚህ አደጋ አንዲት ወጣት ስትሞት ሦስት እግረኞች ደግሞ ክፉኛ ቀስለዋል። ኅዳር ቀን ዓ.ም አዲስ አበባ ሰሌዳ ቁጥሩ ኢቲ-ኤ ኤ ቲ የነበረው ዲ-ሲ ከጥገና በኋላ በሦስት አብራሪዎች ለፈተና ከአዲስ አበባ ልደታ አየር-ዠበብ ማረፊያ ሊነሳ ሲንደረደር ወደግራ በመሳብ ከማኮብኮቢያው ጥሶ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በጥገናው ሥርዓት ላይ የግራ እና የቀኝ መጠምዘዣ መሪዎቹ በስኅተት ተለዋውጠው መገጠማቸው የአደጋው ምክንያት ሆነዋል። መስከረም ቀን ዓ/ም ጎሬ ዠበብተኞችንና ተሣፋሪዎችን አጠቃሎ አሥራ ሰባት ተሣፋሪዎችን ጭኖ ጎሬ አየር ዠበብ ማረፊያ ላይ በማረፍ አደጋ የጠፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢቲ-ኤቢ አይ አየር ዠበብ አሥራ ሰባቱም ተሳፋሪዎችና አብራሪዎች ሕይወታቸውን ያጡበት በረራ ነበር። መጋቢት ቀን ዓ/ም አስመራ ከአዲስ አበባ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሦስት አብራሪዎችና አንድ መንገደኛ ጭኖ ወደአስመራ የበረረው ዲ-ሲ- -6 )የጭነት በረራ ሲሆን አስመራ ላይ ሲያርፍ የፊትም ዋናዎቹም ጎማዎች ሲገነጠሉ አየር-ዠበቡ በእሳት ተያይዞ ከማኮብኮቢያው አልፎ ሜዳ ላይ ተቀጣጥሎ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ኤ ኤ ዋይ የተመዘገበው ይኽ ዲ-ሲ- አየር-ዠበብ በአደጋው ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ ሲሆን አየር መንገዱ ዋና አብራሪውን ካፕቴን መኩሪያ በለጠን ሲያሳርፉ በስህተት/አውቀው የዓየር መግቻዎቹን አልተጠቀሙም ብሎ ስለፈረደባቸው ከማዕረጋቸው በሁለት ደረጃ ዝቅ ከማድረጉም በላይ ከአገልግሎታቸውም የሁለት ዓመት ቅነሳ እንዲደረግ በይኖባቸዋል። ካፕቴን መኩሪያ በ፲፱፻፹፰ ዓ/ም በጠላፊዎች ማስገደድ በቆሞሮስ ደሴቶች አጥቢያ ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ የወደቀው የዓየር መንገዱ በረራ ቁጥር ፱መቶ ምክትል አብራሪ የካፕቴን ዮናስ መኩሪያ አባት ነበሩ። ጳጉሜ ቀን ዓ/ም- ጎንደር በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ኤቢኪው የተመዘገበው ዲ-ሲ አየር ዠበብ ከአስመራ ተነስቶ በአክሱም፤ ጎንደር እና ባሕር-ዳር በኩል ወደአዲስ አበባ ሊሄድ የተነሳው በረራ ከአክሱም በተነሳ በ ደቂቃው ከጧቱ አራት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ ላይ የቀኝ ክንፉ ተገንጥሎ ሲወድቅ ተሣፍረው የነበሩት አሥራ አንዱም ሰዎች ሞተዋል። አየር ዠበቡም ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ሐምሌ ቀን ዓ/ም ሞጣ በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ኤቢኢ የተመዘገበው ዲ-ሲ ሞጣ አየር-ዠበብ ማረፊያ ላይ ሲያርፍ ማኮብኮቢያውን ስቶ ሲከሰከስ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በዚህ በረራ ላይ ስንት ሰዎች እንደነበሩ፤አደጋው በሰው አካል ወይም ነፍስ ላይ ያደረሰው ክስተት ምን እንደነበር መረጃ አልተገኘም። ኅዳር ቀን ዓ/ም ወላይታ ሶዶ በዚህ ዕለት ከወላይታ ሶዶ ተነስቶ በምዕራብ ወለጋ ዞን ወደምትገኘው በጊ ለመብረር ሦስት ዠበብተኞችንና ሃያ አንድ መንገደኞችን የጫነው ዲ-ሲ ለመነሳት ሲያኮበክብ ተከስክሶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በዚህ አደጋ የዋናውና የምክትል አብራሪዎቹ ሕይወት ሲያልፍ አሥሩ መንገደኞች ቀላል የአካል ጉዳይ ደርሶባቸዋል። አስተናጋጇና የቀሩት አሥራ አንድ መንገደኞች ምንም ሳይሆኑ ተርፈዋል። በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ኤ ኤ አር የተመዘገበው ይህ አየር-ዠበብ በዚህ አደጋ ጊዜ የ፴፩ ዓምት ዕድሜ የነበረው ሲሆን በጠቃላላው ፳፯ሺ ሰዓታት የበረረ አሮጌ አየር-ዠበብ ነበር። ጳጉሜ ቀን ዓ/ም ጮቄ ተራራ ይህ በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ኤቢ ኤክስ የተመዘገበው ዲ-ሲ ከባሕር-ዳር ወደ ደብረ ማርቆስ ስድስት መንገደኞች፤ አንድ አስተናጋጅ፤ ዋና እና ምክትል አብራሪውን ጭኖ ሲበር ከዳመና ሽፋን ውስጥ ብቅ ሲል ከፊቱ በቅርቡ ተራራ ያጋጠማቸው አብራሪዎች በሽቅብ እና ዙር በረራ ለማምለጥ በሚሞክሩበት ጊዜ የአየር-ዠበቡ ጭራ ዛፎችን ስለመታ አብራሪዎቹ ለመቆጣጠር አልቻሉም። በዚህ ጊዜ በረራው ጮቄ ተራራ ላይ በጀርባው ተከሰከሰ። ተሳፈሩትም ዘጠኝ ሰዎች መኻል አንድ መንገደኛ ብቻ ሲሞት ሌሎቹ ተርፈዋል። ኢቲ-ኤቢ ኤክስ ለ፴፫ ዓመታት በጠቅላላው ለ፳፫ሺ ሰዓት የበረራ አገልግሎት ከሰጠ በኋላ በዚህ አደጋ ከጥቅም ውጭ ሆነ። ሚያዝያ ቀን ዓ/ም ምጽዋ በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ኤ ኤ ኤስ ተመዝግቦ የነበረው ይህ ዲ-ሲ አየር ዠበብ በተሠራ በ ሠላሳ ሁለት ዓመት ዕድሜው፤ ከ፴፫ሺ፻፸፪ ሰዓት የበረራ አገልግሎት በኋላ ምጽዋ አየር ዠበብ ማረፊያ ላይ በእሳት አደጋ ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል። ግንቦት ቀን ዓ/ም ምጽዋ በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ኤ ዲ ሲ ተመዝግቦ የነበረው ይህ ዲ-ሲ አየር ዠበብ በተሠራ በ ሠላሳ ሁለት ዓመት ዕድሜው፤ ከ፴፪ሺ፮፻፹፪ ሰዓት የበረራ አገልግሎት በኋላ ምጽዋ አየር ዠበብ ማረፊያ ላይ ለመነሣት ስያኮበክብ በፍንዳታ የተነሳ ተቃጥሎ ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል። ጥቅምት ቀን ዓ/ም አስመራ ከአስመራ አየር ዠበብ ማረፊያ ሊነሳ በማኮበኮብ ላይ ሳለ የቀኝ ጎማዎች ተገንጥለው በመውደቃቸው ከአገልግሎት ውጭ የሆነው ዲ-ሲ )፤ ሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ኤ ኤ ዜድ አየር ዠበብ በአደጋው ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ታኅሣሥ ቀን ዓ/ም አቦርሶ በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ኤኢጄ ተመዝግቦ የነበረው ዲ-ሲ አየር ዠበብ አምሥት መንገደኞች፤ አንድ አስተናጋጅ እና ሁለት አብራሪዎችን ጭኖ በባሌ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ኦቦርሶ ላይ ሲያርፍ ጎማዎቹ ተገንጥለው በመውደቃቸው ከጥቅም ውጭ ሆኗል። አየር ዠበቡ ያለጎማ በሆዱ አርፎ ከንተሸራተተ በኋላ ከምስጥ ክምር ጋር ተጋጭቶ ቆመ። ሰኔ ቀን ዓ/ም ቀብሪዳር ኢቲ-ኤ ኤ ፒ 0) ዲሲ አየር ዠበብ በኦጋዴን ውስጥ ቀብሪዳር ላይ ሲያርፍ ዋናው የግራ ጎን ማረፊያ ጎማ በመሰበሩ ከጥቅም ውጭ ውሏል። ሐምሌ ቀን ዓ/ም ጅማ ሰሌዳ ቁጥሩ ኢቲ-ኤቢኤፍ የነበረው ዲ-ሲ -3 -1)) የተገዛው በየካቲት ወር ዓ/ም ሲሆን፤ ሁለት መንገደኞችንና ሦስት ዠበብተኞችን ጭኖ ከቲፒ ቀን ለአሥራ አንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ላይ ተነስቶ የአርባ ደቂቃ በረራውን ወደ ጅማ ጀመረ። የዓየሩ ሁኔታ በዝቅተኛ ጉም የተሸፈነ ዝናባማ እና የሩቅ እይታም የተወሰነበት ነበር። አሥራ አንድ ሰዓት ከሃያ ላይ የጅማ አየር ዠበብ ማረፊያ ስለዓየር ሁኔታ ለአብራሪው የራዲዮ መልዕክት ካስተላለፈለት በኋላ ከበረራው ምንም የተሰማ ነገር አልነበረም። አየር ዠበቡ በስምንት ሺ ጫማ ከፍታ ላይ ከተራራ ጋር ተጋጭቶ አምስቱም ሰዎች ሕይወታቸው አልፎ ተግኝቷል። ኅዳር ቀን ዓ/ም ሚያዝያ ቀን ዓ/ም አገልግሎት ላይ የዋለው ኢቲ-ኤሲዲ የመጀመሪያው የአየር መንገዱ ‘ቦይንግ’ ፯መቶ፯ ነበር። በአደጋው ዕለት ሦስት ዠበብተኞችንና ሁለት መንገደኞችን ይዞ በጭነት በረራ ከሮማ ‘ፊዩሚቺኖ’ ማረፊያ ተነስቶ ሲያሸቅብ፣ ሰባት እና ስምንት ሜትር ከፍታ ላይ የዛፍ ቅርንጫፎችን በመምታቱ ወድቆ ተሰባብሮ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ጥቅምት ቀን ዓ/ም ወላይታ ሶዶ በሰሌዳ ቁጥር ኢት-ኤጂኬ የተመዘገበው ዲ-ሲ አየር ዠበብ ሦስት ዠበብተኞችንና ሃያ ዘጠኝ መንገደኞችን ጭኖ በበረራ ላይ ሳለ የዠበቡ የሃይድሮሊክ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ በመክሸፉ አብራሪዎቹ በአስቸኳይ ለማረፍ ወደወላይታ ሶዶ አምርተው ሞተሩችን ካተፉ በኋላ ሲያርፉ አየር ዠበቡ ለሺ ሁለት መቶ ሜትር ከተንሸራተተ በኋላ የውሐ ቦይ ውስጥ ገብቶ ቆመ። ዳሩ ግን በዚህ ክስተት በተሳፋሪዎቹ ላይ ክፉ ጉዳት ባይደርስም አየር ዠበቡ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ጥቅምት ቀን ዓ/ም ደገሀቡር ኢቲ-ኤጂኪው በሰኔ ወር ዓ/ም ከሌላ አየር መንገድ የተገዛ ዲ-ሲ- ነበር። ከነአብራሪዎቹ አሥራ ሦስት ሰዎችን ጭኖ በረዳት አብራሪው ቁጥጥር በሰሜን ኦጋዴን ደገሀቡር ላይ ሲያርፍ ያልተጠበቀ የነፋስ ኃይል መታው። በዚህ ጊዜ ዋናው አብራሪ አየር ዠበቡን ከምክትሉ ተቀብሎ ለማቆም ቢጥርም ማኮብኮቢያውን ስቶ የውሐ ቦይ ውስጥ ሲወረወር ማረፊያ ጎማዎቹ ተገንጥለው ወደቁ። በዚህ አደጋ በሰው ላይ የደረሰ ክፉ ጉዳት ባይኖርም አየር ዠበቡ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ጥር ቀን ዓ/ም የሰሌዳ ቁጥሩ ኢቲ-ኤጂፒ የነበረው ዲሲ ለአየር መንገዱ አገልግሎት ላይ የዋለው በ፷ዎቹ ማገባደጃ ሁለት አመታት ውስጥ ሲሆን በአደጋው ዕለት ከአስመራ በስተ-ምዕራብ ባልታወቀ ምክንያት ወድቆ ሲከሰከስ ሦስቱም የአየር መንገዱ ሠራተኞች ሞተዋል። አየር ዠበቡም ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ሚያዝያ ቀን ዓ/ም ኦቦርሶ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢቲ-ኤጂዩ የነበረው ይህ ዲ-ሲ -47 አየር ዠበብ ዋናውንና ምክትል አብራሪውን፤ አንድ አስተናጋጅ እንዲሁም አራት መንገደኞችን ጭኖኦቦርሶ ማረፊያ ላይ ሲያርፍ የማኮብኮቢያው ድንበር ላይ የተተከሉትን ድንጋዮች በመምታት የቀኝ ማረፊያ ጎማዎቹ በመሰበራቸው የጥገና ሥራ ከተደረገለት በኋላ ለጥቂት ወራት ወደአገልግሎት ተመልሶ ነበር። ዳሩ ግን በሌላ አደጋ ከጥቅም ውጭ ውሏል፡፡ በዚህ ኦቦርሶ ማረፊያ ላይ ኢቲ-ኤ-ኤ-ጄ ታኅሣሥ ቀን ዓ/ም በተመሳሳይ የጎማዎች መገንጠል አደጋ ከምስጥ ክምር ጋር ተጋጭቶ ከጥቅም ውጭ እንደዋለ ተዘግቧል። መስከረም ቀን ዓ/ም ባረንቱ ሚያዝያ ቀን ዓ/ም ኦቦርሶ ላይ በደረሰበት አደጋ ሰፊ ጥገና ተደርጎለት ወደአገልግሎት የተመለሰው ኢቲ-ኤጂዩ የነበረው ይህ ዲ-ሲ -47 አየር ዠበብ በደቡብ-ምዕራብ ኤርትራ፣ ከባረንቱ ማረፊያ ሊነሳ ሲያኮበኩብ በአፍንጫው ተደፍቶ ሲከሰከስ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ሐምሌ ቀን ዓ/ም ሎንዶን 'ሂዝሮው'' ጥያራ ጣቢያ በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ- ኤ ኦ ፒ የተመዘገበው እና ልዩ ስሙ "ንግሥት ሣባ" የተባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አየር ዠበብ በዛሬው ዕለት በሎንዶን 'ሂዝሮው' ጥያራ ጣቢያ እንደቆመ የእሳት አደጋ ደረሰበት። ይኽ አደጋ የተከሰተው ጥያራው መንገደኞችን አሣፍሮ ከአዲስ አበባ ከገባ ከስምንት ሰዓታት በኋላ ነው። አየር መንገዱ ይኽንን ዠበብ ከቦይንግ ኩባንያ ተረክቦ አገልግሎት ላይ ያዋለው ከስምንት ወራት በፊት ኅዳር ቀን ዓ/ም ነው። የአየር ጠለፋ እና የአመጽ ጉዳቶች መጋቢት ቀን ዓ/ም የሰሌዳ ቁጥሩ ኢቲ-ኤሲ ኪው የነበረው የቦይንግ ፯መቶ፯ አየር ዠበብ በአየር መንገዱ ታሪክ በሽብርተኞች የአየር ጠለፋ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰለባ የደረሰብት አየር ዠበብ ነበር። ከግሪክ ርዕሰ ከተማ አቴና ተነስቶ ፍራንክፈርት ዓለም አቀፍ የአየር ዠበብ ማረፊያ የደረሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አየር ዠበብ በቆመበት ሥፍራ ላይ በአውሮፕላኑ የቱሪስት ማዕርግ ክፍል ላይ ሁለት ፈንጂዎች ጉዳት አድርሰዋል። አየር ዠበቡን በማጸዳዳት ላይ የነበሩም ሴቶች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጉዳቱን ያደረሰው ‘ለኤርትራ ነጻነት-የአረባዊ ሶርያ እንቅስቃሴ’ የሚባለው ቡድን ነው ሲል የኤርትራ ነጻነት ግንባር ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የገጠር ነዋሪ ኤርትራውያንን ለማጥቃት የሚላኩትን ወታደሮች ወደኤርትራ ስለሚያጓጉዝ የበቀል ጥቃት ያካሄዱት እነሱ እንደሆኑ አረጋግጧል። ሰኔ ቀን ዓ/ም ፓኪስታን ካራቺ አየር ዠበብ ማረፊያ ላይ ሦስት የኤርትራ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች፣ በሰሌዳ ቁጥር ኢ.ቲ. ኤ.ሲ.ዲ. የተመዘገበውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ ፫፻፷ ሲ አየር ዠበብ ላይ ፈንጂ ወርውረው ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበታል። ኦኖም አየር ዠበቡ ተጠግኖ አገልግሎት ላይ ውሏል። መሐመድ ኢድሪስ፣ ፍስሐዬ አብርሃምና ዓሊ አብደላ የተባሉት ሦስቱም ታጣቂ አመጸኞች ሲያዙ በሰጡት መግለጫ፣ በኤርትራ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስተዳደር ተቃዋሚ መሆናቸውን ለማሳወቅ የወሰዱት የሸፍጥ ድርጊት እንደሆነ ገልጸዋል። ሦስቱም ሸፍጠኞት በድርጊታቸው ምክንያት ለፍርድ ቀርበው የአንድ ዓመት ጽኑ እሥራት ተፈርዶባቸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የኤርትራ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባዮች ሐምሌ ቀን ዓ/ም ይፋ ባደረጉት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ ኤርትራውያን ላይ ለሚያካሂደው የአየር ድብደባ በቀላቸውን በአየር መንገዱ ላይ ለመወጣት ሙከራቸውን ስለሚቀጥሉ በዚሁ ብሔራዊ አየር መንገድ የሚሣፈሩ መንገደኞች ለሕይወታቸው አስጊና አደገኛ እንደሚሆን በመጠቆም የአየር መንገዱን የገቢ ምንጭ ከማዳከም እንደማይመለሱ አስታውቀዋል። ነሐሴ ቀን ዓ/ም በተማሪው ንቅናቄ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተው፣ አንደበተ ርቱዕ የነበረው ብርሃነ መስቀል ረዳ፤ የሕግ ተማሪ የነበረው ኢያሱ ዓለማየሁ፤ ኃይለ ኢየሱስ ወልደ ሰማያት፤ ገዛኸኝ እንዳለ፤ አማኑኤል ገብረ ኢየሱስ፤ የመንግሥት ሠራተኛ የነበረው አ.አ.፤ በጠቅላላው ሰባት ሆነው ከ ባሕር-ዳር ተነስቶ ወደአዲስ አበባ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዓለም አቀፍ አየር-ዠበብ ማረፊያ (ቦሌ) ሊበር የታቀደውን ዲ-ሲ -3) ወደ ካርቱም እንዲያመራ አስገደዱት። እነኚህ ጠላፊዎች የካርቱም ቆይታቸው ለደህንነታቸው ዋስትና እንደሌለው በመገንዘብ፤ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ ወደ አልጄሪያ መዲና አልጄርስ አመሩ። መስከረም ቀን ዓ/ም ከአዲስ አበባ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዓለም-አቀፍ ማረፊያ መንገደኞችንና ዠበብተኞችን አሳፈሮ ወደ ጂቡቲ በመማራት ላይ የነበረው ዲ-ሲ- -6) በረራ በሦስት ኤርትራውያን ተጠልፎ ወደ አደን እንዲበር ተገድዶ ወደዚያው ሲበር የአየር መንገዱ የጸጥታ ታጣቂ አንዱን አመጸኛ ተኩሶ አቁስሎታል። አደን ሲያርፉም የአገሪቱ የፖሊስ ኃይል ሦስቱንም ጠላፊዎች በቁጥጥር ሥር አዋላቸው። ጠላፊዎቹ የኤርትራ ነጻነት ግንባር አባላት እንደሆኑ ታውቋል። ታኅሣሥ ቀን ዓ/ም ከእስፓኝ ርዕሰ ከተማ ማድሪድ ዘጠኝ ዠበተኞችንና አሥራ አራት መንገደኞችን ጭኖ በሮማ በኩል ወደአዲስ አበባ ጉዞውን የጀመረው ቦይንግ ፯መቶ፯ 707) በረራ የየመን ተወላጅ የሆነ ጠላፊ ሽጉጡን መዝዞ በረራ ክፍል ውስጥ ከገባ በኋላ አብራሪውን ወደአደን እንዲያመራ ቢያዘውም ቅሉ፣ አብራሪው ለነዳጅ ሮማ ማረፍ ግድ እንደሚሆንበት አስረድቶ ነበር። የአየር መንገዱ የጸጥታ አስከባሪ በረራ ክፍል ውስጥ ገብቶ ጠላፊውን በሽጉጥ ገድሎታል። በዚህ ጊዜ ሁለተኛው ጠላፊ ጩቤውን ጨብጦ ወደበረራ ክፍሉ ሲሮጥ ሁለተኛው የአየር መንገዱ የጸጥታ አስከባሪ እርሱንም በሽጉጥ ተኩሶ ገድሎታል። ከዚህ ክስተት በኋላ በረራው በሰላም አቴና ላይ አርፏል። የኤርትራ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ ደማስቆ ላይ ገለጻ ሲሰጥ ሁለቱ የግንባሩ አባላት ቢሆኑም ዓላማቸው አየር-ዠበቡን ለምጥለፍ ሳይሆን ስለድርጅቱ በራሪ ማስታወቂያዎችን ለማደል ነበር ብሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የ[[እስፓኝ ፖሊስ ታኅሣሥ ቀን ማድሪድ ዓለም አቀፍ ማረፊያ ላይ ሦሥተኛው አባል ነው ብለው የገመቱትን ሰው ፈንጂ ይዞ ሲገባ በቁጥጥር ስር አውለውታል። ጥር ቀን ዓ/ም አራት የኤርትራ ነጻነት ግንባር ሸፍጠኞች ከባሕር-ዳር ወጎንደር፣ ከነዠበብተኞቹ ሃያ ሰዎችን የጫነውን ዲ-ሲ፫ አየር ዠበብ በኃይል ወደ ቱኒዚያ ዋ ሁለተኛ ከተማ በንጋዚ እንዲበር ካስገደዱት በኋላ ለነዳጅ ቅጅ ካርቱም ላይ አረፈ። ኅዳር ቀን ዓ/ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ፯መቶ፰ ከአዲስ አበባ ተነስቶ አስመራ፤ አቴና፤ ሮማ እና ፓሪስ ለመሄድ ከነዠበብተኞቹ ዘጠና አራት ሰዎች ጭኖ በተነሳ በአሥራ ሦስት ደቂቃዎች ከመንገደኞቹ መኻል ወንዶችና ሴቶች ሽጉጥ መዝዘው በአማርኛ ትዕዛዛቸውን ሲጮኹ የአየር መንገዱ የጸጥታ ሰራተኞች ተኩስ ከፍተው ስድስቱን ጠላፊዎች ሲገድሉ ሰባተኛው በኋላ ሆስፒታል ገብቶ ሞቷል። በተኩሱ ጊዜ ከጠላፊዎቹ አንዱ የያዘውን የእጅ ቦምብ ነቅሎ ሲጥለው ከመንገደኞቹ አንዱ ብድግ አድርጎ ሰው ወደሌለበት ሥፍራ ጥሎት ፈነዳ። ይኽ ፍንዳታ አንድ ሞተር እና የአቅጣጫ መቆጣጠሪያ ከጥቅም ውጭ ሲያደርገው የአየር ዠበቡን የመንገደኞች ክፍል በጢስ አፍኖት ነበር። ኣብራሪው ካፕቴን ቀጸላ ኃይሌ ያለምንም ድንጋጣ አየር-ዠበቡን ወደአዲስ አበባመልሰው በሰላም አሳርፈውታል። ካፕቴኑ ለዚህ ተግባራቸው ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የጀግንነት ሜዳይ ከመሸለማቸውም ባሻገር በአየር ዠበቡ ተሣፍሮ የነበረውና ከእንግሊዝ ለወፎች ጥናት ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው ቡድን፤ ከዚህ አደጋ ላተረፏቸው ለኚህ ካፕቴን ሎንዶን ከተማ ውስጥ ከፍ ያለ ግብዣ አድርገውላቸዋል። ጠላፊዎቹ የኤርትራ ነጻነት ግንባር አባላት ሲሆኑ መሪያቸውም በዚሁ ድርጊት የተገደለችው ማርታ መብርሃቴ ነበረች። መጋቢት ቀን ዓ/ም ላሊበላ ሲያርፍ በአመጸኞች የጥይት እሩምታ የተመታው ዲ-ሲ አየር ዠበብ ሰሌዳ ቁጥር ኢቲ- ኤቢአር ከጥቅም ውጭ ሲሆን የአንድ ሰውም ሕይወት ጠፍቷል። አየር ዠበቡ በዚህ አደጋ ጊዜ የ፴፫ ዓመት ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን ለ ፴፫ሺ፮፻፳፮ ሰዓት በረራ አገልግሏል። ሚያዝያ ቀን ዓ/ም ከመቀሌ ወደ ጎንደር ሲበር ሁለት ሰዎች የከሸፈ የጠለፋ ሙከራ ያደረጉበት ዲ-ሲ አየር ዠበብ ጎንደር ላይ በሰላም አርፏል። ዳሩ ግን ሁለቱን ጠላፊዎች አጠቃሎ የሦስት ሰዎች ሕይወት አልፎበታል። የካቲት ቀን ዓ/ም ባረንቱ ኢቲ-ኤ-ኤፍ ደብልዩ ዲሲ ለአየር መንገዱ አገልግሎት ላይ የዋለው በ፷ዎቹ ማገባደጃ ሁለት አመታት ውስጥ ሲሆን፤ በደቡብ-ምዕራብ ኤርትራ በምትገኘው ባረንቱ ላይ በቦምብ ፍንዳታ ተከስክሶ ሲወድቅ አምስቱም ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። አየር ዠበቡም ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ዋቢ ምንጮች ክፍሉ ታደሰ፤ ያ ትውልድ፤ ቦሌ ማተሚያ ድርጅት (ዓ/ም የለውም) 18, 1972) 15, 1969 (1968-1974) =19690311-0 11 2011.] 1992 የኢትዮጵያ አየር
13975
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%89%A1%E1%8A%90%20%E1%88%B0%E1%88%8B%E1%88%9B
አቡነ ሰላማ
አቡነ ሰላማ በአጼ ቴወድሮስ ዘመን የነበሩ ፓትሪያርክ ናቸው። የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን አጭር ታሪክ “ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጒድጓድ ተቅበዘበዙ።” ዕብ. 11፥38። በእርግጥ ዓለም ለእገሌ ይገባል ለእገሌ አይገባም የምትባል አይደለችም። ቅዱሳን መናንያን ግን በራሳቸው ፈቃደ ዓለምን አንፈልግሽም ስላሏት ዓለም አልተገባቸውም ተባሉ። እንደ ማንኛውም ሰው በዓለም መኖር ሲችሉ ዓለምን ንቀው መኖሪያቸውን በተራራና በዋሻ አደረጉ። ያላቸውን ንቀው እንደ ሌላቸው በመሆን ስለ ሰማያዊ ፍቅር መከራን ተቀበሉ። “ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ” ዕብ. 11፥37 ወዳጄ ሆይ! ለመሆኑ ቅዱሳን አባቶቻችን የሞቀ ቤታቸውን ጥለው በዱር በጫካ ከአራዊት ጋራ መኖርን መምረጣቸው እንደ ሞኝነት ይቆጠር ይሆን? ወይስ እውቀት ያነሳቸው ይመስልሃል? አይደለም። በሳይንሱ ዓለም ትምህርት ተምረው ዲፕሎም፣ ዲግሪ፣ ማስትሬት የጨረሱ ዶክትሬትም ጨብጠው ወደ ገዳም የገቡ ብዙዎች ናቸው። እነዚህ ቅዱሳን በዓለም ላይ ሳሉ ብዙ ነገር ቢኖራቸውም እንኳን የሚበልጠውን ሰማያዊ ፍቅር ፈልገው ሁሉንም ትተው ወደ ምናኔ ገቡ። “እውነት እላችኋለሁ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።” ማቴ. 19፥28። ወዳጄ ሆይ! የቅዱሳን ገዳማውያን ገድል የሕይወታቸው ኑሮ ለሁሉም መልካም ምሳሌና አርአያ ሊሆን ይችላል። ከምንም በላይ ደግሞ እምነታችን ለማጠንከርም ይረዳናል። ምክንያቱም ጠንካራ እምነት ማምጣት የምንችለው የእምነት ጀግኖች አባቶቻችንን የሰሩትን አብነት በማድረግ ነው። አዎ! የቅዱሳንን ሕይወት ማጥናት ለእኛም ከይስሙላ ወይም ከታይታ ኑሮ ወጥተን በትክክል የተቀየረ ሕይወት እንዲኖረን ያግዘናል። ስለሆነም ቅዱሳን በየዕለቱ ሥራቸውን እንድናስታውስና ሕይወታቸው የመንፈስ ምግብ ማድረግ ይገባናል። እንግዲህ ወዳጄ የቅዱሳን ገዳማውያን በረከታቸው ለማግኘትና ከሕይወታቸው ተምረን ብርሃን የሆነውን መንገዳቸውን እንድንከተል ወደ ታሪካቸው እንሻገር። “የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው።” ምሳ. 4፥18 ወዳጄ ሆይ! ˝ባሕርን በጭልፋ˝ እንደሚባለው በዚህች ብጣሽ ወረቀት የሁሉንም ቅዱሳን መናንያን ታሪክ መዘርዘር ባይቻልም ከቅዱሳን ታሪክ የዚሁ ቅዱስ ጻድቅ ራሱ እንደ ሻማ እየቀለጠ ለእኛ ብርሃን የሆነ የታላቁ አባታችን አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ፍቅሩን እንመልከት። አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን በሦስተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በሕዳር 26/ 245 ዓ.ም ከአባቱ ቅዱስ ምናጦስና ከእናቱ ቅድስት ማርያም ሰናይት በጢሮስ /ግሪክ/ ተወለደ። የመጀመሪያ ስሙ ፍሬምናጦስ ይባላል። አባታችን አቡነ ሰላማ የ12 ዓመት ልጅ እያለ ሜሮጵዮስ የተባለ ነጋዴ /ፈላስፋ/ ይዞት ወደ አገራችን በእግዚአብሔር ፈቃድ መጣ። ከእርሱም ጋር ኤድስዮስ የተባለም አብሮት እንደነበረ ይታወቃል። እነዚህን ሁለት ወጣቶች አስከትሎ የመጣው ሜሮጵዮስ በቀይ ባሕር አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በጣሉለት አደጋ በዚሁ እንደ ሞተ ታሪክ ይነግረናል። ፍሬምናጦስና ኤድስዮስ ግን በወቅቱ የአክሱም ንጉሥ የነበረው ንጉሥ ታዜር ጋር አድገዋል። ንጉሡ በአእምሮ መብሰላቸውን ተመልክቶ ፍሬምናጦስ በጅሮንድ ኤድስዮስም ጋሻ ጃግሬው አድርጎ ሾማቸው። ከዚያ በኋላ ንጉሥ ታዜር ሲያርፍ ወደ ፈለጉበት እንድሄዱ ነፃ ስለተለቀቁ ኤድስዮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ሄዷል። አባታችን አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ግን በጨለማ የሚኖረውን ሕዝብ ትቼ ወደ አገሬ አልመለስም በማለት እኛን በማፍቀር እንደቀረ ታሪክ ያስረዳናል። ወዳጄ! የቅዱሳን ፍቅራቸው እውነትም ልብ ይነካል። በዚያን ጊዜ በአገራችን ኢትዮጵያ ስርዓተ ንስሐ፣ ስርዓተ ጥምቀት፣ ስርዓተ ቅዳሴ፣ ስርዓተ ቅዱስ ቁርባን የሚያከናውን ጳጳስ ስላልነበረ ይህን የተመለከቱ ነገስታት ኢዛናና ሳይዛና ጵጵስና እንዲያመጣ አባታችን አቡነ ሰላማን ወደ ግብጽ ላኩት። አባታችንም ወደ ግብጽ በመሄድ ስርዓቶቹን በመማር በቅዱስ አትናትዮስ አንብሮተ እድ ˝ኤዽስ ቆጶስ ዘአክሱም ወዘኩላ ኢትዮጵያ” ተብሎ ጵጵስና ተቀበለ። ወደ አገራችን ከተመለሰ በኋላ መጀመሪያ ነገስታት ኢዛናና ሳይዛናን አጥምቆና አቁርቦ አብርሃ ወአጽበሃ በማለት ስመ ክርስትና ሰጣቸው። በመቀጠልም በመላው አገራችን እየተዘዋወረ በማስተማር ስርዓቱን ፈጽሟል። ከዚህም የተነሳ ጨለማን አስወግዶ ብርሃንን የገለጠ ቀዳሚ የምድረ ሐበሻ ታላቅ ሐዋርያ ነው። የቀናች ሃይማኖትን በማስተማር ጨለማውን ብርሃን በማድረጉ “ብርሃን ገላጭ ሰላማ” ተብሏል። የሓምሌ ወር ስንክሳር። አባታችን አቡነ ሰላማ በኢትዮጵያና ኤርትራ በመላው ምድረ ሓበሻ በኪደተ እግሩ ተመላለሶ ወንጌል እንዳስተማረና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ድውያንን ፈውሶ ሙታንን እንዳስነሳ ገድሉ ያስረዳናል። በተለያዩ ባዕድ አምልኮ ያመልክ የነበረ ሕዝብም በጣፋጭ ስብከቱ እግዚአብሔርን ወደ ማመን መልሶታል በጸሎቱ አጋንንትን ጠራርጎ ከአገራችን በማስወጣት ሰላም የሰጠን የሰላም አባት ነው። ˝ሰላማ˝ ማለት ˝ሰውና እግዚአብሔርን የሚያስታርቅ˝ ማለት ነው። ወዳጄ ሆይ! አባታችን አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን በ 350 ዓ.ም ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ እንዲታወጅ አድርጓል። ˝አቡነ /አባታችን/ የሚለውን ማዕረግ ለመጀመሪያ የተሰጠው ለርሱ ነው። ጻድቁ አባታችን በዕድሜም በጸጋም ትልቅ አባት በመሆኑ ከኋላው ለመጡት ብዙዎች ቅዱሳን መምህራቸውና አባታቸው ነው። ለዚህም ነው አባታችን ቅዱስ ያሬድ “ዝንቱ ብእሲ መምህርነ ዘተፈነወ ውስተ ምድርነ ይከሰተ ብርሃነ” በማለት አመስግኖታል። ብርሃንን ለመግለጥ ወደ አገራችን የተላከ መምህራችን ማለቱ ነው። ወዳጄ ሆይ! በልጅነታቸው የመጡት አባታችን አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የአገራችን ፍቅር አስገድዷቸው እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው በአገራችን የኖሩ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያቶች ውስጥ ከሰሯቸው የተለያዩ ድንቅ ሥራዎች ውስጥ በጥቂቱ እንደሚከተለው ይሆናል። ወንጌል የሚያስተምሩ፣ የሚያጠምቁና የሚያቆርቡ ካህናትና ዲያቆናት ሾመዋል። ለምእመናን መካሪ የንስሐ አባት እንዲኖራቸው አድርገዋል። ከአብርሃ ወአጽብሃ ጋር በመሆን አብያተ ክርስቲያን አንጸዋል። ቅዱሳት መጻሕፍት ከሱርስት፣ ከዕብራይስጥና ከግሪክ ወደ ግእዝ ቋንቋ እንዲተረጎሙ አድርገዋል። የሳባውያን ፊደል አቀማመጥ በማስተካከል ከግራ ወደ ቀኝ የመጻፍንና የማንበብን ዘዴ በማስተማር ብዙ ውለታ የዋሉ ታላቅ አባት ናቸው። የኢትዮጵያ ሰዎች ኢትዮጵያ በ19ኛው ክፍለ
18891
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B6%E1%89%A4%E1%88%8D
ቶቤል
ቶቤል፣ ዕብራይስጥ፦ /ቱባል/፣ በኦሪት ዘፍጥረት 10 መሠረት የያፌት ልጅና የኖኅ ልጅ-ልጅ ነበረ። ከዚህ በላይ በትንቢተ ሕዝቅኤል 38፡2-3፣ 39፡1 ቶቤል ይጠቀሳል። የተለያዩ ልማዶች ስለ ቶቤል መታወቂያ በ1ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. የአይሁድ ሊቅ ፍላቪዩስ ዮሴፉስ እንዲህ ብሎ ጻፈ፦ «ቶቤል የቶቤላውያን (ጦቤሌስ) አባት ሆነ፤ አሁንም ኢቤራውያን (ኢቤሬስ) ይባላሉ።» ይህ በአናቶሊያና በኋላ በካውካሶስ ተራሮች የተገኘ ሕዝብ ነበር። የካውካሶስ ኢቤራውያን ሕዝብ ከዛሬው ጂዮርጂያ ወላጆች መካከል ነበሩ። የክርስትና ጳጳሳት አውስታጥዮስ ዘአንጥዮኪያ (330 ዓ.ም. ግድም) እና ቴዎዶሬቶስ (450 ዓ.ም. ግድም) ደግሞ ይህንን ታሪክ ተቀበሉ። ዳሩ ግን ጀሮም (400 ዓ.ም. ግድም)፣ ኢሲዶር (635 ዓ.ም. ግድም) እና ነኒዩስ (830 ዓ.ም. ግድም) እንዳሉት፣ የቶቤል ተወላጆች ኢቤራውያን ብቻ ከመሆናቸው በላይ፣ ጣልያውያን (የጥንት ጣልያን ኗሪዎች) እና እስፓንያውያን ከቶቤል ተወለዱ። (የድሮ እስፓንያ ሰዎች ደግሞ «ኢቤራውያን» ተባሉ።) ቅዱስ አቡሊድስ ሌላ ልማድ ዘገበ፤ የቶቤል ዘሮች «ሄታሊ» (ወይም በአንዳንድ ቅጂ ተሰላውያን) እንደ ሆኑ ጻፉ። የሱርስጥ ጽሑፍ መጽሐፈ ንብ (1214 ዓ.ም. ግድም) ቶቤል የቢታንያ ሰዎች አባት እንደ ነበር ይላል። የኬጥያውያን መንግሥት ከወደቀ በኋላ (1190 ዓክልበ. ግድም) በአናቶሊያ ታባል የተባለ መንግሥት ተገኘ፤ ከቶቤል ልጆች እንደ ወጣ የሚያምኑ አሉ። እንዲሁም ጎረቤቶቻቸው ሙሽካውያን ከሞሳሕ እንደ ወጡ ይታመናል። ከዚህም ዘመን በኋላ ግሪኮች ቲባሬኒ የሚባል ሕዝብ በአናቶሊያ ያውቁ ነበር። ልማዶች ስለ ቶቤል መንግሥት በእስፓንያና በፖርቱጋል ዙሪያ በአንድ ካታሎኒያ (ምሥራቅ እስፓንያ) ተውፊት ዘንድ፣ የያፌት ልጅ ቶቤል ከኢዮጴ (አሁን ተል አቪቭ) ከቤተሠቡ ጋር በመርከብ ወደ እስፓንያ ፍራንኮሊ ወንዝ ከባቢሎን ግንብ ውድቀት በኋላ 12 ዓመት ደረሰ፤ በዚያም ስለ ልጁ «ታራሆ» ስም ከተማ መሠረተ (የአሁን ታራጎና)። ከዚያ ወደ ኤብሮ ወንዝ ወጣ፤ ይህም የሁለተኛው ልጅ «ኢቤር» ስም አለው፣ አምፖስታን እዚያ ሠራ። የሦስተኛው ልጁ ስም «ሰምፕቶፋይል» ይባላል። ኖህ (ወይም የኖህ 4ኛው ልጅ ያኑስ) ከመቶ አመት በኋላ እዚህ እንደ ጎበኛቸው ይጨምራል። በዚህ ተውፊት፣ ቶቤል ለ155 አመት በእስፓንያ ነገሠ፣ ወደ ማውሬታኒያም (አሁን ሞሮኮ) ለመስፋፋት ሲል ሞተና ልጁ ኢቤር ተከተለው። ከዚህ በላይ ራቬና በጣልያ፣ ሴቱባል በፖርቱጋል፣ ቶሌዶ እና ብዙ ሌሎች ከተሞች በእስፓንያ ሁላቸው በቶቤል ያፌት እንደ ተመሠረቱ የሚሉ ልማዶች አሉ። በተጨማሪ፣ የቶቤል ሚስት ስም «ኖያ» እንደ ነበር፣ በሳን ቪንሴንቴ ርእሰ ምድር ፖርቱጋል እንደ ተቀበረ፣ ወይም በመሞቱ 65፣000 ተወላጆች እንደ ነበሩት የሚሉ ልማዶች አሉ። ንጉስ ቶቤል ሕግጋቱን በከላውዴዎን ቋንቋ አወጣ፤ የ1ዱ አመት ልክ በ365 ቀኖች እና 6 ሰዓቶች አደረገው፤ የቤትንም አሠራር፣ እህልንም ወደ ዳቦ መጋገር፣ ወዘተርፈ ኑሮ ዘዴ ለሕዝቡ እንዳስተማረ ይባላል። የነዚህ ትውፊቶች ምንጭ አኒዮ ዳ ቪቴርቦ በ1490 ዓ.ም. ያሳተመው ሀሣዊ ቤሮሦስ የተባለው ሰነድ ይመስላል፤ ይህ ጽሑፍ ግን ባብዛናው እንደ እውነተኛ ታሪክ አይቆጠረም። ነገር ግን ከዚያ በፊት በአራጎን መምህር-ንጉስ 4 ፔድሮ (1360 ዓ.ም. ግድም) መሠረት ቶቤል መጀመርያ በእስፓንያ የሰፈረ ሰው ነበር፣ ጀሮምና ኢሲዶርም እንደ ጻፉ እቤራውያን ከርሱ ተወለዱ፣ በቀድሞ «ሴቱባሌስ» ተብለው በኤብሮ ወንዝ ሠፈሩ፣ በኋላም ስለዚያ ወንዝ ስማቸውን ወደ «ኢቤራውያን» ቀየሩ። እንዲሁም በ1270 ዓ.ም. ግድም የጻፉት የካስቲል መምህር-ንጉሥ 10 አልፎንሶ ተመሳሳይ አፈ ታሪክ አቀረቡ፤ በርሳቸው ጽሁፍ ግን ቶቤል በፒሬኔስ ተራሮች ውስጥ በአስፓ ተራራ ሠፈረ፤ «ሴቱባሌስ» የሚል ስም መጀመርያ ክፍል ከ«ሴቱስ» መጥቶ ትርጉሙ ነገድ ማለት መሆኑን ጨመሩ። በሳቸው ዘንድ ስማቸው በኋላ «ሴልቲቤራውያን» (ቄልቲቤራውያን) ሆነ። ከዚህም በፊት በ740 ዓ.ም. ያህል የጻፈው ታሪክ ጸሐፊ አቡልቃሲም ታሪፍ አበንታሪክ እንዳለው፣ የያፌት ልጅ ቶቤል (ወይም «ሴም ቶፋይል») እስፓንያን በ3 ልጆቹ መካከል አካፈለው፤ በኲሩ ታራሆ ወደ ስሜን-ምሥራቅ ያለውን ክፍል (ታራሆን፣ በኋላ አራጎን) ተቀበለው። ሁለተኛው ልጅ፣ ዳግማዊ ሴም ቶፋይል፣ በምዕራብ በውቅያኖስ አጠገብ ያለውን ክፍል (ሴቱባል) ወረሰ፤ ታናሹም ኢቤር በምሥራቅ በሜድትራኔአን አጠገብ ያለውን ክፍል (ኢቤሪያ) ተቀበለ። ከዚያ ቶቤል ለራሱ «ሞራር» የተባለ ከተማ ሠራ፣ ይህም አሁን ሜሪዳ፣ እስፓንያ ነው። አበንታሪክ ይህን ዝርዝር ከከተማው ዋና መግቢያ በር በላይ ከተገኘው ድንጊያ ተቀርጾ እንዳነበበው ወደ አረብኛም እንዳስተረጎመው ይለናል። በስሜን እስፓንያ በሚገኘው ባስክ ብሔር በኩል ደግሞ የባስክ ሊቅ ፖዛ (15ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም.) የጻፈው ቶቤል የባስኮች (የኢቤራውያንም) አባት እንደ ነበር ነው። የፈረንሳይ ባስክ ጸሐፊ ኦጉስተን ቻሆ (19ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም.) «የአይቶር ተውፊት» አሳተመ፤ የባስኮች አባት አይቶር ከቶቤል ዘር እንደ ነበር ይላል። የእስፓንያ አፈታሪካዊ ነገሥታት የአይሁድ ረቢዎች ልማዶች ስለ ቶቤል በጣልያን በአይሁድ ረቢዎች ምንጮች የቶቤል ልጆች ስሞች ይለያያሉ። በሀሣዊ ፊሎ (62 ዓ.ም. ግድም) ልጆቹ «ፓናቶባ» እና «ኤቴባ» ሲሆኑ፣ «ፔዔድ» የሚባል አገር ለርስታቸው ተሰጡ። በመካከለኛ ዘመን የታየው የይራሕሜል ዜና መዋዕል ልጆቹን «ፋንቶንያ» እና «አቲፓ» አገራቸውም «ፓሃጥ» ይላቸዋል። በሌላ ሥፍራ ይህ መጽሐፍ ከጀሮም የመጣ መረጃ አለው፤ የቶቤል ልጆች በኢቤርያና እስፓንያ ሠፈሩ ይላል። በሌላ ሥፍራ እንደገና ከዮሲፖን (950 ዓ.ም. ግድም) የወረደ ትውፊት አል። በዚህ ትውፊት የቶቤል ልጆች በቶስካና (የጣልያን ክፍል) ሠፈሩ፤ «ሳቢኖ» የተባለ ከተማ ሠሩ። የኪቲም (ያዋን) ልጆች ግን በዚህ አጠገብ በካምፓንያ ክፍላገር ከተማቸውን «ፖሶማንጋ» ሠሩ። ቲቤር ወንዝ በመካከላቸው ጠረፋቸው ሆነ። ኪቲሞች ግን የሳቢኖ ሴቶች በግድ ከያዙ በኋላ ወደ ጦርነት ሔዱ። ኪቲሞች ለቶቤል ልጆች የጋራ ክልሶቻቸውን ባሳያቸው ጊዜ ጦርነቱ ተጨረሰ። ይህም ትውፊት በአጭሩ በሠፈር ሀያሻር ይገኛል፤ በዚያም የቶቤል ልጆች «አሪፒ»፣ «ኬሴድ»ና «ታዓሪ» ይባላሉ። የቶቤል ተወላጆች ካዝሮችና ስላቮች ሆኑ የሚለው ሌላ የእስላም ሃልዮ የአረብኛ መዝገበ ቃላት «ታጅ አል-አሩስ» (በአል-ዙባይዲ፣ 1782 ዓ.ም.) እንደ ዘገበው፣ አንዳንድ የእስላም ደራሲ ካዛሮች (በአሁኑ ሩስያ የኖሩ) ከሞሳሕ እንደ ተወለዱ ሲያምኑ፣ ሌሎች ግን ካዛሮችና ስላቮች ከወንድሙ ቶቤል እንደ ተወለዱ ይላሉ። ነጥቦች ዋቢ መጽሐፍ የኖህ
50825
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B0%E1%89%A3%E1%8A%A0%E1%8B%8A%20%E1%88%98%E1%89%A5%E1%89%B6%E1%89%BD
ሰባአዊ መብቶች
አለም አቀፍ የሰብእዊ መብቶች ድንጋጌ መንደርደሪያ የመላውን የሰው ዘር ተፈጥሮእዊ ክብር እንዲሁም የማይገሰሱ እና እኩል የሆኑ መብቶች ማክበርና እውቅና መስጠት ለዓላማችን ሰላም ፍትህና ነጻነት ዋና መሰረት በመሆኑ፤ የሰብእዊ መብቶች ጥሰትና አለመከበር አሰቃቂ ለሆኑና ለህሊናም ዘግናኝ ለሆኑ ተግባራት መንሰኤ ሆኖአል። ይህንንም ተከትሎ ሁሉም የሰው ልጆች የንግግርና የዕምነት ነጻነቶችን በሚቀዳጁበት እንዲሁም ከፍርሃት ነጻ ሆነው የሚኖሩበት የአለም አኗኗር ስርእት አሙን መሆን የአያንዳንዱ ሰው ተቀዳሚ ምኞት በመሆኑ፤ የሰው ልጅ አምባገነናዊነትንና ጭቆናን ለማስወገድ አመጽን እንደ እማራጭ እንዳይወስድ ሰብእዊ መብቶች በህግ የበላይነት መጠበቅ ስለሚገባቸው፤ 1. በሃገራትም መካከል መልካም ግንኙነቶችን ማዳበርና ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት በመሰረታዊ ሰብእዊ መብቶች፤ በሰው ልጅ ክብርና ዋጋ፤ በወንዶችና በሴቶች የአኩልነት መብቶች እንዲሁም በማህበራዊ መሻሻልና የኑሮ ደረጃ አድገት ላይ ያላቸውን ጽኑ እምነት በጋራ መተዳደሪያ ሰነዳቸው ላይ በማረጋገጣቸው፤ አባል ሃገራት በራሳቸውና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ለሰብእዊ መብቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች መከበርና መስፋፋት ዕውን መሆን ቃል ኪዳን በመግባታቸው፤ በነዚህ መብቶችና ነጻነቶች ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ መፍጠሩ ለቃል ኪዳኑ ገሃዳዊ ተግበራዊነት ከፍተኛ ጠቀሜታ አና አስተዋጽኦ በመኖሩ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ይህንን እለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ እያንዳንዱ ግለሰብ እና የማህበረሰብ አካል እነዚህን መብቶችና ነጻነቶች ለማስከበር፤ በዕለት ተዕለት በማስታወስ በማስተማርና በማስገንዘብ እንዲሁም ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ሂደታዊ አርምጃዎችን በመውሰድ የስኬታማነት የጋራ መስፈርት ሆኖ የተቀመጠውን የሰብእዊ መብቶችና ነጻነቶች ውጤታማ አለም አቀፋዊ እውቅናና መከበር በአባል ሃገራት ህዝቦችና በመላው አስተዳደራዊ ግዛቶቻቸው ይሰፍን ዘንድ ይህንን አዋጅ አስተላልፏል/አጽድቋል። አንቀጽ 1 የሰው ልጅ በተፈጥሮው ነፃ ነው። በክብርና በመብትም አኩል ነው። የሚያስተውል ህሊናም በተፈጥሮ የተለገሰ በመሆኑ አንዱ ከሌላው ጋር በወንድማማችነት መንፈስ ሊኖር ይገባዋል አንቀጽ 2፤ ሁሉም ሰው በዚህ ድንጋጌ ውስጥ የሰፈሩትን ሁሉንም መብቶችና ነፃነቶች ያለምንም ዓይነት የዘር የቀለም የፆታ የቋንቋ የሃይማኖት የፖለቲካ ወይም ሌላ አይነት አስተሳሰብ የብሄራዊ ወይም ማህበራዊ ታሪክ የሃብት የትውልድ ወይም ሌላ አይነት ሁኔታዎች ልዩነት ሳይደረግበት የመጠቀም መብት አለው:: አንቀጽ 3፤ ሁሉም ሰው በነፃነትና በሰላም የመኖር መብት አለው:: አንቀጽ 4፤ ማንም ሰው በባርነትና በባርነት ቀንበር መያዝ የለበትም ባርነትና የባሪያ ንግድ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ ነው:: አንቀጽ 5 ማንም ሰው በስቃይ ወይም በጭካኔ እንዲሁም ኢሰብአዊና ክብረ ነክ ወይም አዋራጅ በሆነ አያያዝ መያዝ ወይም መቀጣት የለበትም አንቀጽ 6 ሁሉም ሰው በየትኛውም ቦታ በህግ ፊት እንደሰው የመታየት መብት አለው:: አንቀጽ 7 ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው ሁሉም ሰዎች ያለምንም ልዩነት እኩል የሆነ ህጋዊ ከለላ እና ጥበቃ የማግኘት መብት አለው:: አንቀጽ 8 እያንዳንዱ ሰው በህግ ወይም በህገ መንግስት የተሰጡት መሰረታዊ መብቶች ላይ ጥሰት በሚደርስበት ጊዜ ችሎታ ባላቸው ብሄራዊ የፍትህ ተቋማት ውጤታማ የሆነ ፍትህ የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ነው አንቀጽ 9 ማንም ሰው ያለፍርድ በግዞት መያዝ ወይም መታሰር የለበትም አንቀጽ 10 እያንዳንዱ ሰው በመብቶቹ ና በግዴታዎቹ አፈፃፀም እንዲሁም በሚከሰስበት ማንኛውም አይነት የወንጀል ክስ ጉዳዩ ነፃ በሆነና በማያዳላ እንዲሁም ትክክለኛና ፍታዊ በሆነ የፍርድ ሸንጎ እንዲታይለት የማድረግ ሙሉ መብት አለው:: አንቀጽ 11 1. በወንጀል ክስ የተከሰሰ ማንኛውም ሰው ለመከላከያው አስፈላጊ የሆኑትን ሁሉ አቅርቦ በሚከራከርበት የይፋ የፍርድ ሸንጎ ወይም ችሎት ወንጀለኛ መሆኑ በህግ እስከሚረጋገጥበት ድረስ ከወንጀል ነፃ እንደሆነ የመቆጠር መብት አለው:: 2.ማንም ሰው በብሄራዊ ወይም አለምዓቀፍ ህግ መሰረት ወንጀል ሆኖ ያልተደነገገን ተግባር በመፈፀሙ በጊዜው ወንጀለኛ ተብሎ ሊከሰስ አይችልም እንዲሁም ወንጀሉ በተፈፅመበት ጊዜ ከተደነገገው ቅጣት ይበልጥ አይፈረድበትም:: አንቀጽ 12 ማንም ሰው በግል ኑሮው በቤተሰቡ በቤቱ ውስጥ ወይም በሚፃፃፈው ደብዳቤ ላይ ከፍርድ ውጭ ከሚደረግ ጣልቃገብነት ነፃ ነው:: እንዲሁም ክብርና ዝናን ከሚነኩት ማንኝቸውም አይነት ጥቃቶች የተጠበቀ ነው:: እያንዳንዱ ሰው እነዚህን ከመሰሉ ጣልቃ ገብነትና ጥቃቶች ህጋዊ ከለላ የማግኘት መብት አለው:: አንቀጽ 13 1 እያንዳንዱ ሰው በሃገሩውስጥ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስና የመኖር መብት አለው:: 2 እያንዳንዱ ሰው የራሱን ወይም የየትኛውንም አገር ለቆ የመሄድ እንዲሁም ወደራሱም አገር የመመለስ መብት አለው:: አንቀጽ 14 1 እያንዳንዱ ሰው ከጭቆና ሸሽቶ በሌሎች ዓገሮች ጥገኝነት የመጠየቅና በደህና የመኖር መብት አለው 2 ፖለቲካዊ ካልሆኑ ወንጀሎች ወይም የተባብሩት መንግስታት ድርጅትን ዋና ዓላማዎችን ከሚቃረኑ ስራዎች የተነሳ በሚደርሱ ክሶች ምክንያት ከሆነ ይህ መብት ሊያገለግል አይችልም:: አንቀጽ 15 1 ሁሉም ሰው የዜግነት መብት አለው 2 ማንም ሰው ያለፍርድ ዜግነቱ አይወሰድበትም ወይም ዜግነቱን የመለወጥ መብት አይነፍገውም:: አንቀጽ 16 1 ለአካለ መጠን የደረሱ ወንዶችና ሴቶች በዘር በብሄርና በሃይማኖት ልዩነት ሳይወሰኑ ጋብቻን የመፈፀምና ቤተሰብን የመመስረት መብት አላቸው።ጋብቻ በመፈጸም በት ጊዜና ጋብቻ በሚፈርስበትም ጊዜ እኩል መብት አላቸው 2 ጋብቻ የሚፈፀመው ሁለቱም ተጋቢዎች በሚያደርጉት ነፃና ሙሉ ስምምነት መሰረት ብቻ ነው:: 3 ቤተሰብ የማህበረሰብ ተፈጥሮአዊና መሰረታዊ ክፍል በመሆኑ በህብረተሰቡና በመንግስት ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል አንቀጽ 17 1 ሁሉም ሰው በግል ወይም በጋራ ንብረት የማፍራትና የንብረት ባለቤት የመሆን መብት አለው 2 ማንም ሰው ያለፍርድ ንብረቱን ሊነጠቅ አይችልም አንቀጽ 18 ሁሉም ሰው የሃሳብ የህሊናና የሀይማኖት ነፃነት መብት አለው:: ይህም መብት ሀይማኖቱን ወይም እምነቱን የመለወጥ ነፃነትንና ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር ሆኖ በይፋ የማስተማር በተግባር የመግለፅ የማምለክና የማክበር ነፃነትን ይጨምራል:: አንቀጽ 19 ሁሉም ሰው የሀሳብና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አለው ይህ መብት ሀሳብንና መረጃን ያለምንም ገደብ የማግኘትን የመቀበልን የማካፈልንና ያለምንም ጣልቃ ገብነት በሀሳብ የመፅናትን ያጠቃልላል:: አንቀጽ 20 1 ሁሉም ሰው በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብና የመደራጀት መብት አለው:: 2 ማንም ሰው የየትኛውም ማህበር አባል እንዲሆን ሊገደድ አይችልም:: አንቀጽ 21 1 ሁሉም ሰው በሀገሩ የመንግስት አስትዳደር ውስጥ በቀጥታ ወይም ነፃ በሆነ ሂደት በተመረጡ ተወካዮች አማካኝነት ተሳትፎ የማድረግ መብት አለው 2 ሁሉም ሰው የሀገሩን ህዝባዊ አገልግሎቶች የመጠቀም እኩል የሆነ መብት አለው:: 3 የመንግስት ስልጣን በህዝብ ፍላጎጎትና ስምምነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት:: ይህም የህዝብ ፍላጎተና ስምምነት አለም አቀፍና ለሁሉም እኩል ቢሆን እንዲሁም በምስጢር በሚደረግ የድምፅ መስጠት ምርጫ ወይም ተመጣጣኝ በሆነ ድምፅን የመግለፅ ሁኔታ በየጊዜውና በትክክል በሚፈፀሙ ምርጫዎች የሚረጋገጥ መሆን አለበት:: አንቀጽ 22 እያንዳንዱ ሰው የህብረተሰብ አካል እንደመሆኑ መጠን ማህበራዊ ደህንነቱ የመጠበቅ መብት አለው:: በተጨማሪም በብሄራዊና አለም አቀፍ ጥረትና ትብብር እንዲሁም በመንግስታዊ ድርጅቶችና የሀብት ምንጬች ለክብሩና ለሰብዓዊ ነፃ እድገቱ አስፈላጊ የሆኑ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና የባህል መብቶች በተግባር እንዲረጋገጡለት የመጠየቅ መብት አለው:: አንቀጽ 23 1 ሁሉም ሰው ስራ የመስራትና ከስራ አጥነት የመጠበቅ መብት አለው:: እንዲሁም ነፃ የስራ ምርጫና ፍትሀዊና ተስማሚ የሆነ የስራ ሁኔታ የማግኘት መብት አለው:: 2 ሁሉም ሰው ያለምንም አድልዎ ለተመሳሳይ ስራ ተመሳሳይ ክፍያ የማግኘት መብት አለው 3 በስራ ላ ይ ያለ ሰው ለራሱና ለቤተሰቡ ሰብአዊ ክብር ተገቢ ደህንነት መጠበቂያ ዘዴዎች የተደገፈ ትክክለኛና ተስማሚ ዋጋን የማግኘት መብት አለው 4 እያንዳንዱ ሰው ጥቅሞቹን ለማስከበር የሙያ ማህበሮችን የማቋቋምና አባልም የመሆን መብት አለው አንቀጽ 24 እያንዳንዱ ሰው እረፍት የማግኘትና የመዝናናት መብት አለው እንዲሁም በአግባብ የተወሰኑ የስራ ሰዓቶችና በየጊዜው የእረፍት ጊዜያትን ከደሞዝ ጋር የማግኘት መብት አለው አንቀጽ 25 1 እያንዳንዱ ሰው ለእራሱና ለቤተሰቡ ጤንነትና ደህንነት ምግብ ልብስ ቤትና ህክምና አስፍላጊ የማህበራዊ ኑሮ አገልግሎቶችም ጭምር የሚበቃ የኑሮ ደረጃ ለማግኘት መብት አለው ስራ ሳይቀጠር ቢቀር ቢታመም ለመስራት ባይችል ባል ወይም ሚስት ቢሞት ቢያረጅ ወይም ከቁጥጥሩ ውጭ በሆኑ ምክንያቶች መሰናክል ቢገጥመው ደህንነቱ እንዲጠበቅለት መብት አለው:: 2 ወላድነትና ህፃንነት ልዩ ጥንቃቄና እርዳታ የማግኘት መብት አላቸው በጋብቻ ወይም ያለጋብቻ የሚወለዱ ህፃናትም በተመሳሳይ ደህንነታቸው የመጠበቅ መብት አላቸው:: አንቀጽ 26 1.እያንዳንዱ ሰው የመማር መብት አለው። ትምህርት ቢያንስ ቢያንስ በመሰረታዊና በአንደኛ ደረጃ በነፃ መቅረብ ይገባዋል:: የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መማር ግዴታ ነው:: የቴክኒክና የልዩ ልዩ ሙያ ትምህርት በጠቅላላው የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ደግሞ በችሎታ መሰረት ለሁሉም እኩል መቅረብ አለበት 2.ትምህርት ለእያንዳነዱ ሰው ሁኔታ ማሻሻያና ለሰብአዊ መብቶችም እንዲሁም ለመሰረታዊ ነፃነቶች ክብር ማዳበርያ የሚውል መሆን አለበት:: እንዲሁም የተለያየ ዘር ወይም ሀይማኖት ባሏቸው ህዝቦች መካከል ሁሉ መግባባትን ተቻችሎ የመኖርንና የመተባበርን መንፈስ የሚያጠናክርና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላምን ለመጠበቅ የሚፈፅማቸው ተግባራት እንዲስፋፋ የሚደረግ እና የሚያበረታታ መሆን አለበት 3.ወላጆች ለልጆቻቸው ለመሰጠት የሚፈልጉትን ትምህርት ለመምረጥ ቅድሚያ መብት አላቸው አንቀጽ 27 1 እያንዳንዱ ሰው በህብረተሰቡ የባህል ሕይወት በነፃ መካፈልና በኪነ ጥበብ ለመጠቀም በሳይንስ እርምጃና በጥቅሞቹም ለመሳተፍ መብት አለው:: 2 እያንዳንዱ ሰው ከደረሰው ማንኛውም የሳይንስ የድርሰትና የኪነጥበብ ስራ የሚያገኘው የሞራልና የሀብት ጥቅሞች እንዲከበሩለት መብት አለው አንቀጽ 28 ሁሉም ሰው በዚህ ድንጋጌ ውስጥ የሰፈሩት መብቶችና ነፃነቶች ሙሉ በሙሉ በተገባር ሊውሉ የሚችሉበት ማህበራዊና አለም አቀፋዊ የኑሮ ስርአት አባል የመሆን መብቱ የተጠበቀ ነው አንቀጽ 29 1 እያንዳንዱ ሰው ለስብእናው ነፃና ሙሉ እድገት ብቸኛ መሰረት ለሆነው ለሚኖርበት ማህበረሰብ ሊፈፅማቸው የሚገቡ ግዴታዎች አሉት:: 2 እያንዳንዱ ሰው በመብቶቹና በንፃነቶቹ በሚጠቀምበት ጊዜ ገደብ የሚያ ጋጥመው የዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ መሰረታዊ መስፈርቶች የሆኑትን ግብረገብነትን ስርዓተ ማህበርና የጋራ ደሀንነትን ለማረጋገጥ እና የሌሎችን መብቶችና ነፃነቶች ለማሳወቅና ለማክበር በህግ የተቀመጡ ገደቦችን እንዳይተላለፍ ብቻ ነው 3 እነዚህ መበቶችና ነፃነቶች በማንኛውም ሁኔታ የተባበሩት መንግስትታት መሰረታዊ አላማዎች በሚቃረን መንገድ ሊፈፀሙ አይገባቸውም አንቀጽ 30 በዚህ ውሳኔ ላይ የተዘረዘረውን ሁሉ በዚሁ ውስጥ የተጠቀሱትን ማናቸውንም መብቶች ወይም ነፃነቶች የመጣስ ድርጊትን ለመፈፀም ለማንኛውም መንግስት ወይም ድርጅት ወይም ሰው የተከለከለ ነው
13483
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%93%E1%8D%84%20%E1%88%B1%E1%88%B0%E1%8A%92%E1%8B%AE%E1%88%B5
ዓፄ ሱሰኒዮስ
ዓፄ ሱስኒዩስ በዙፋን ስማቸው "መልአክ ሰገድ" ተብለው ሲታወቁ በ1572 ተወልደው በ1632 (እ.ኤ.አ)አርፈዋል። ከ1606–1632 እ.ኤ.አ. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ሲሆን፣ አባታቸው የአፄ ልብነ ድንግል የልጅ ልጅ የሆኑት አቤቶ ፋሲለደስ እና ልጃቸው ደግሞ ዓፄ ፋሲለደስ ነበሩ። እናታቸው ወይዘሮ ሐመልማለ-ወርቅ የተሰኙ የጎጃም አስተዳዳሪ ልጅ ነበሩ። በሱሰንዮስ ዘመን የነበረው የጀስዩት ሚስዩን አልሜዳ ሱሰንዩስ "ረጅም፣ ወንዳወንድ፣ ትላልቅ አይኖች ያሉት፣ አፍንጫው ቀጥ ያለና ጢሙም በጥንቃቄ የተከረከመ ነው" ካለ በኋላ አለባበሱን ሲገልፅ [በጊዜው የአውሮጳውያን ፋሽን የነበረውን አይነት] እስከ ጉልበቱ የሚደርስ ከደማቅ ቀይ ሐር የተሰራ በፍታ በስስ ጥብቅ ያለ ሱሪ እና በትላልቅ ወርቅ ያጌጠ ቀበቶ ለብሶ ከላዩ ላይ በተለያየ ቅርጻቅርጽ ያጌጠ ካባ ይደርባል። የህይወት ታሪክ በህጻንነቱ ሱሰኒዩስ የተወለደው የአህመድ ግራኝ ሰራዊት ከተሸነፈ በኋላ ሲሆን በዚህ ጊዜ የህዝብ ንቅናቄ ይታይ ነበር። የሱሰኒዮስ ዜና መዋዕል እንደሚያትተው በህፃንነቱ ከአባቱ ጋር ጎጃም ውስጥ ይኖሩበት የነበረው ከተማ በአንድ ተንቀሳቃሽ የኦሮሞ ቡድን ስር ወደቀ አባቱና ቀሪው የከተማው ሰው ሲገደል እሱ ግን ለአንድ አመት ከግማሽ በምርኮ ከኦሮሞው ቡድን መሪ ጋር ተቀመጠ። ከዚያ በኋላ የኦሮሞው ቡድን በዳሞት ከደጅ አዝማች አስቦ ጋር ጦርነት ለመግጠም ሞክሮ በመሸነፉ ወደአካባቢው ዋሻወች በመግባት ለመሸሸግ ሞከረ። የደጃአዝማች አስቦ ሰራዊት የተሸሸጉትን ቡድኖች አባላት እዋሻው ድረስ በመግባት ከነመሪያቸው በሰንሰለት አሰሩዋቸውና "ህጻኑን ሱሰኒዮስ ካመጣችሁ ትለቀቃላችሁ ካላመጣችሁ ግን ትገደላላችሁ" አላቸው። ሱሰኒዮስ በዚህ መንገድ ሲለቀቅ፣ ደጃች አስቦ ህጻኑን መንገዱ ለተባለ የአቤቶ ፋሲለደስ ወዳጅ በአደራ ሰጡት። መንገዱም የንግስት አድማስ ሞገሴ (የአፄ ሰርፀ ድንግል እናት) ቤተኛ ስለነበር ህጻኑ ከንግስቲቱ ዘንድ አደገ ወህኒና አጼ ያዕቆብ በ1590ወቹ የአፄ ሰርፀ ድንግል ልጆች እድሜያቸው ገና ጨቅላ ስለነበር አጼው የወንድማቸውን ልጅ ዘድንግልን ለተተኪ ንጉስነት አጭተውት ነበር። ንግስት ማርያም ሰናና የወቅቱ መሳፍንት (ለምሳሌ ራስ አትናቲወስ) የ 7 ዓመት ህጻን የነበረው የሰርፀ ድንግል ልጅ ያዕቆብ እንዲነገስ የአባቱን ሃሳብ አስቀየሩ። ህጻኑም የነገሰበት ጊዜ ከ1597 እስከ 1603 ነበር። በዚህ ጊዜ የርስ በርስ ጦርነት እንዳይነሳ ለህጻኑ ስልጣን ተቀናቃኝ ሊሆን ይችላል የተባለውና በህዝቡ ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈውን ዘድንግልን በግዞት ወደ ጣና ሃይቅ እንዲባረር አደረጉ። ሱሰኒዮስም ከዘድንግል ጋር አብሮ ከማደጉ በተጨማሪ ይዋደዱ ስለነበር እንዲሁም ልክ እንደ ዘድንግል ለያዕቆብ ስልጣን አስጊ ሆነ ስለተገኘ) በማምለጥ በጎጃምና ሸዋ ገዳማት እንዲሁም በኋላ ከተንቀሳቃሽ ኦሮሞወች ጋር ኑሮውን አደረገ። አብረውት ከነበሩት ኦሮሞወች ሠራዊት በመመልመል ሸዋ ውስጥ በተለይ ይፋትን፣ መርሃ ቤቴንና ቢዛሞን በጦርነት ተቆጣጠረ። ወጣቱ ንጉስ ያዕቆብ የጊዜው መኳንንቶች ስልጣን ያለገደብ መሆኑን በመቃወም ስልጣናቸው እንዲገደብ በመሞከሩና በእድሜው ምክናያት በሱ ቦታ ሆኖ አገሪቱን የሚያስተዳድረውን ራስ አትናቲወስን ስልጣን መጋፋት ሲጀምር ከዘመኑ ባለስልጣኖች ጋር ጥል ገባ። በዚህ ጊዜ መኳንንቶቹ "ሃይማኖት የለሽ አረመኔ" እና "ጠንቋይ" ነው የሚል የፈጠራ ወሬ በንጉሱ ላይ በመንዛት በግዞት ከስልጣን እንዲባረርና በእንራያ በስደት እንዲኖር አደረጉት። አጼ ዘድንግልን በ 1603 የጉራጌው ራስዘስላሴ አቀነባባሪነት ንጉሰ ነገስት አደረጉት። ዘድንግል፣ ምንም እንኳ አይምሮው ብሩህ የነበረ መሪ ቢሆንም ወደ ካቶሊክ ሃይማኖት በማዘንበሉ ምክንያት አመጽና ጦርነት ተነስቶበት በ1604 በላባርት ጦርነት ሞተ። ንግስና ዘድንግል ባለፈ ጊዜ ሱሰኒዮስ በምስራቅ ጎጃም በምተገኘው ጥንታዊቷ መርጡለማሪያም ቤ/ክርስቲያን የዙፋን አክሊል ደፋ (ህዳር 1604 እ.ኤ.አ)። ነገር ግን ራስ ዘስላሴና አንዳንድ መኳንንት ቀደምት የተባረረውን ንጉስ ያዕቆብን በመደገፍ አቋም ያዙ፣ እንዲሁም መልሰው አነገሱት በአንድ አገር ሁለት አጼ መኖር ስለማይችል፣ ሱሰኒዮስ፣ ራስዘስላሴን ጦርነት ገጥሞ ከማረካቸው በኋላ አጼ ያዕቆብን በ1607 ደቡብ ጎጃም ውስጥ የጎል ጦርነት ተብሎ በሚታወቀው ገጥሞ አሸነፈው። ከዚህ ጦርነት በኋላ ሱሰኒዮስ ብቸኛው የአገሪቱ መሪ ሆነ። ራስ ዘስላሴም ከምርኮ በኋላ ሱሰኒዩስን ይደግፉ እንጂ ቆይተው፣ ንጉሱ ወደ ካቶሊክ ሃይማኖት በማድላቱ፣ መጣላታቸው አልቀረም በዚህ ምክንያት በምስራቅ ጎጃም በሚገኝው አምባ ጉዛምን ለእስር ተዳረጉ። አምባው ላይ አመት ከቆዩ በኋላ በማምለጥ በሽፍትነት እያሉ አንድ ገበሬ ገድሎ እራሳቸውን ለንጉሱ ሱሰኒዮስ እንደላከ ጄምስ ብሩስ ይተርካል። አሰምሳዮቹ አጼ ያዕቆቦች በጎል ጦርነት ጊዜ የአጼ ያዕቆብ ሰራዊት ሽንፈት ይድረስበት እንጂ የንጉሱ ሬሳ በጦር ሜዳው ስላልተገኘ በጦርነቱ መሞቱ አጠራጣሪ ሆነ። በዚህ ምክንያት ብዙ "አጼ ያዕቆብ እኔ ነኝ" የሚሉ የአመጽ መሪወች በሱሰኒዮስ ንግስና ዘመን ተነሱ። ለምሳሌ ሱሰኒዩስ ከነገሰ በኋላ በ1608 ደብረ ቢዘን (ያሁኑ ኤርትራ ውስጥ አጼ ያዕቆብ ነኝ የሚል ብዙ ተከታይ ያለው መሪ ተነሳ። ይህ አሰምሳይ ንጉስ ሁል ጊዜ ፊቱን ተሸፋፍኖ ነበር ሰው ፊት የሚቀርበው። ለዚህ እንግዳ ጸባዩም የሚሰጠው ምክንያት "በጦርነት ፊቴ ላይ ጠባሳና ቁስል ስለደረሰ ሰውን ላለማስቀየም" ነው ይል ነበር የትግራይ ገዢ የነበረው ሰዕለ ክርስቶስ የአመጹን መነሳት በሰማ ጊዜ የራሱንና የፖርቱጋል ወታደሮችን አሰልፎ በአስመሳዩ ንጉስ ላይ ዘመተ፡፡ አመጸኛው ሶስት ጊዜ በጦርነት ቢሸነፍም ሳይማረክ በማምለጥ በሐማሴን ተራራወች ለመደበቅ ቻለ። ይህ በዚህ እንዳለ፣ የስዕለ ክርስቶስ ሰራዊት ወደ ሰሜን መክተቱን የሰሙት የኦሮሞ ቡድኖች ትግራይን በመወረር ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ በዚህ ምክንያት ንጉሱ ወደ ትግራይ ለመሄድ መሰናዶ ጀመረ። በመሃል ግን በርብ ወንዝ ተፋሰስ አካባቢ የመረዋ ኦሮሞ ተብለው የሚታወቁ ቡድኖች ገጥመው በመጀመሪያው ዙር ስላላሸነፈ ለሁለተኛ ጊዜ ሃይሉን አጠናክሮ በመግጠም አሸንፎ እንዲበታተኑ አደረገ። የተበተኑት መረዋወች ከሌሎች ኦሮሞወች ጋር ሃይላቸውን አጠናክረው በማበር ለብቀላ እንደገና ወደ በጌ ምድር ወረራ አደረጉ። በዚህ ጊዜ ሱሰኒዩስ ከቀኛዝማች ጁሊየስ እና ክፍለ ክርስቶስ ጋር በመሆን ጥር17፣ 1608 የእብናት ጦርነት ተብሎ በሚታወቀው ድል አድረጉ። ጀምስ ብሩስ፣ የነገስታቱን ዜና መዋዕል ዋቢ አድርጎ እንደዘገበ፣ በ እብናት ጦርነት ወቅት ከንጉሱ ወገን 400 ሲሞቱ ከወራሪወቹ ዘንድ 12000 ሞተዋል ይላል። የዚህ ጉዳይ በንዲህ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ባለ ድሉ ሱሰኒዮስ፣ ወደ ትግራይ በሊማሊሞገደል እና ዋልድባ አድርጎ አቀና። በዚያውም የንጉሰ ነገስትነቱን ማዕረግ ታህሳስ 18፣ 1608 በአክሱም አጸና። በትግራይ ውስጥ ተነስቶ የነበረውንም አመጽና የኦሮሞ ቡድን ጥቃት በማሸነፍ ጸጥታ አሰፈነ። ይሁንና አሰመሳዩን ያዕቆብን ለመያዝ ያደረገው ጥረት ፍሬ ስላላፈራ ስራውን መልሶ ለወንድሙ ስዕለ ክርስቶስ ተወለትና ወደ ቤተ መንግስቱ ደንካዝ ተመለሰ። ትንሽ ቆይቶም በስዕለ ክርስቶስ ገፋፊነት ሁለት የአስመሳዩ ያዕቆብ ተከታዮች መሪያቸውን በመግድል አንገቱን ቆርጠው ለሱሰኒዩስ ላኩ። ስኮቱ ጄምስ ብሩስ እንደመዘገበ "የአስመሳዩ እራስ ስላልተሸፋፈነ፣ አሰመሳዩ ፊት ላይ ምንም ጠባሳ፣ ምንም ቁስል፣ ምንም ችግር እንደሌለ አስተዋልን። ይልቁኑ ይሸፋፈን የነበረው ከእውነተኛው ንጉስ ያዕቆብ ጋር ምንም ምሥሥል እንዳልነበረው ለመደበቅ እንደነበር ተገነዘብን" በማለት የደብረ ቢዘኑ አጼ ያዕቆብ ታሪክ በንዲህ መልክ ተቋጨ። ሱሰኒዮስና የካቶሊክ እምነት ሱሰኒዮስ በርግጥ ረጅም ጊዜ አገሪቱን ይምራት እንጂ አስተዳደሩ የሚታወቀው የኢትዮጵያን መንግስት ሃይማኖት ከተዋህዶ ወደ ካቶሊክ በመቀየሩ ነው። ሱሰኒዮስ ካቶሊክ ሃይማኖትን የተቀበለበት ምክንያት በሁለት ምክንያት ነበር፦ አንደኛው ፔድሮ ፔዝ የተባለው የጀስዩት ሰባኪ ስላግባባው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከፖርቹጋል እና ስፔን ወታደራዊ ድጋፍ ለማግኘት ነበር። በ ታህሳስ 10፣1607 ለፖርቹጋሉ ንጉስ እና ጥቅምት 14 1607 ለ ሮማው ፓፓ በጻፈው ደብዳቤው (አሁን ድረስ ይገኛል) ወታደሮች እንደሚፈልግ ሲገልጽ ነገር ግን ሃይማኖቱን መቀየሩን በሁለቱም ደብዳቤወች አይገልጽም፤ ይልቁኑ በሁለቱም ደብዳቤወቹ ሙሉ ትጥቅ ያደርጉ የአውሮጳ ወታደሮች እንዲልኩለት ይጠይቃል። የዚህም ጥያቄ መነሻው የማያቋርጥ አመጽ አንዴ በሃይማኖት፣ ሌላ ጊዜ በ"አሰምሳይ ያዕቆቦች" በተረፈም በተንቀሳቃሽ የኦሮሞ ቡድኖች ስለተነሳበት ነበር። ሱሰኒዮስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለካቶሊኮች ብዙ እርዳት አድርጓል፣ ለምሳሌ በግዛቱ መጀምሪያ ለካቶሊክ ጀስዊቶች በጎርጎራ ሰፋፊ መሬት ሰጥቷቸው ነበር። ቆይቶም በ1622 የነበሩትን ብዙ ሚስቶች (ከመጀመሪያየቱ ሚስቱ በቀር) በመፍታት፣ የካቶሊክ እምነት መቀበሉን በአደባባይ አስታወቀ። ሆኖም ግን ፔድሮ ፔዝ ይባል የነበረው ለዘብተኛው የካቶሊኩ ቄስ በበሽታ በመሞቱ ከስፔን አልፎንሶ ሜንዴስ የተባለ ጳጳስ በኢትዮጵያ ላይ ተሹሞ በ1624 መጣ። አዲሱ ጳጳስ በጣም ግትር፣ እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚል፣ ጠባብ አይምሮ የነበረውና መቻቻል የማያውቅ ነበር ቶሎ ብሎም የቅዳሜን ሰንበትነት ሻረ፣ ብዙ አጽዋማትንም አስወጣ፣ ከዚያም በህዝብ ፊት የሮማው ፓፓን የበላይነት በኢትዮጵያ ላይ አወጀ። በዚህ ምክንያት አመጽ ተነሳ። የሱሰኒዩስ ወንድም የማነ ክርስቶስ፣ ጃንደረባው ክፍለ ዋህድ ና ጁሊየስ ሦስቱ ሆነው ሱሰኒዮስን ሊገድሉት ሞከሩ ግን ሱሰኒዮስ አመለጠ። መልሰውም ጦርነት ጎጃም ውስጥ ከፈቱበት ግን ተሸነፉ የሃይማኖት አመጽ በሃይማኖት የተነሳው አመጽ እየጨመረ እንጂ እየበረደ ሊሄድ አልቻለም። በተለይ በወንድሙ መልክዐ ክርስቶስ ይመራ የነበረው የላስታ አመጽ ሊሸነፍ አልቻለም። በ1629 ወደ 30 ሺ ወታደሮች አስከትሎ የላስታውን አመጽ ለመቆጣጠር ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀረ። እንዲያውም መሪ የነበረው የሚስቱ ወንድም ልጅ በጦርነቱ ተገደለ ለሁለተኛ ጊዜ መልክዓ ክርስቶስን ለመግጠም ያደረገው ሙከራ ከሁሉ ሁሉ የራሱ ወታደሮች ወኔ መኮስመኑን አስገነዘበው። በዚህ ምክንያት የወታደሮቹን ወኔ ለመገንባት የሃይማኖት ነጻነት በመፍቀድ የ"ዕሮብን ጾም" እንዲጾሙ ፈቀደ። ይሁንና አሁንም እንደበፊቱ የመልዐከ ክርስቶስ ጦር ሊበገር አልቻለም። ሱሰኒዮስ ያለምንም ፍሬ ወደ ቤ/መንግስቱ ዳንካዝ ባዶ እጁን ተመለ። ለሶስተኛ ዙር ጦር ለመግጠም በሚዘጋጅበት ጊዜ የሰራዊቱ ወኔ ከመዝቀጡ የተነሳ ለመዝመት እንደማይፈልጉ ተገነዘበ። ላስታ ውስጥ የሚካሄደው የማያባራ ጦርነት ምንም ለውጥ እንዳላመጣ፣ የአገሪቱን ግዛት እንደማይጨምር፣ የሚዋጉዋቸውም ሰወች ጠላት እንዳልሆኑና፣ በሃይማኖት ምክንያት የነበረው ሰቆቃ እንዲያቆም በልጁ በፋሲለደስ አድርገው ወታደሮቹ ምክንያታቸውን ገለጹለት። ሱሰንዮስም መልሶ በዚህ በሶስተኛው ዙር የላስታውን አመጽ ድል ካደረጉለት የቀደመውን የኢትዮጵያ ሃይማኖት እንደሚመልስ በልጁ ላከባቸው። የፋሲለደስ ንግግር የሱሰኒዮስን ቃል ኪዳን ገንዘብ በማድረግ ሰራዊቱ ወደ ላስታ ተመመ። በዚህ መካከል 25፣000 የሚሆኑ የመልክዐ ክርስቶስ ሰራዊት ላስታን ለቀው መሃል መንገድ ላይ ሊገናኙት ሰልፍ እንደጀመሩ መረጃ አገኘ። ሐምሌ 26፣ 1631 ሰራዊቶች ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ሱሰኒዮስ ከጥቂት ፈረሰኞቹ ጋር በመሆን በድፍረት ቀደም ብለው የመጡትን የመልዐክ ክርስቶስ ወታደሮች በማጥቃት እግረኛው ሳይቀላቀላቸው አሽመደመዱት። በዚህ ጊዜ ሌላው የላስታ ሰራዊት በፍርሃት ተበተነ፣ የንጉሱም ፈረሰኛ ጦር ብዙውን ገደለ። በዚህ ሁኔታ አመጸኞቹ ሲሸነፉ መሪያቸው የንጉሱ ወንድም ግን በፈረሱ ፍጥነት ምክንያት ሊያመልጥ ቻለ። በሚቀጥለው ቀን አጼ ሱሰኒዮስ ከልጁ ፋሲለደስ ጋር ያለፈውን ቀን የጦር ውሎ ለመገምገም ወደሜዳ ወጡ። 8000 የሚሆኑ የመልክዐ ክርስቶስ ሰራዊት መሞታቸውን ባየ ጊዜ ፋሲለደስ ለአባቱ እንዲህ ሲል መናገሩን ጄምስ ብሮስ ያትታል እነዚህ በሜዳ ላይ ታርደው የምታያቸው ወይም አረመኔ ወይም መሃመዳውያን አይደሉም። ሞታቸውም ምንም ደስታ አያመጣም። ክርስቲያን እና የራስህ ሰወች ናቸው፣ አንዳንዶቹም የስጋ ዘመዶችህ። ምንም ጥቅም የማይገኝበት ይሄ ድል አይደለም! እነዚህን በገደልክ ቁጥር እራስክን በጎራዴ ወግተህ እንደገደልክ ቁጥር ነው። ስንት ሰው አረድክ? ስንት ተጨማሪ መግደል ተፈልጋህ? መዘባበቻ ሆንን እኮ! በአረመኔወቹና በአረቦች ሳይቀር የእናት አባታቸውን ሃይማኖት ትተው እርስ በርሳቸው የሚተላለቁ እየተባልን የሰው መሳለቂያ ሆንን። የልጁ ወቀሳ ውሸት እንደሌለውና ድሉ በኢትዮጵያን ዘንድ የበለጠ መጠላትን እንጂ መፈቀርን እንዳላተረፈለት ተረዳ። የሃይማኖት ነጻነት ከዚህ ድል በኋላ አመት ባልሞላ ጊዜ ስኔ 14፣ 1632 ካቶሊክ ሃይማኖትን የሚከተል መከተል እንደሚችል፣ ግን ያን ሃይማኖት ማንም በግድ መከተል እንደሌለበት ከቤተ መንግስቱ ደንቀዝ አዋጅ አሳወጀ። በዚህ ጊዜ የካቶሊክ ቤ/ክርስቲያን የአገሪቱ መንግስት ቤ/ክርስቲያን መሆኑ አከተመለት። ስልጣን ርክክብ የሃይማኖት ነጻነትን ካወጀ በኋላ ሃገሪቱን የመምራት ሃይሉ እንደሌለው ሲገነዘብ ቀስ በቀስ ለልጁ ስልጣኑን አስረከበ። ሐምሌ 1632 ፋሲለደስ ንጉሰ ነገስት ሲሆን ሱሰንዮስ ሙሉ በሙሉ ከስልጣን ወረደ። ወዲያውም የማይደን በሽታ ሱሰንዮስን ያዘውና በተወለደ በ61 አመቱ እ.ኤ.አ መስከረም 7፣ 1632 ከዚህ አለም በሞት ተለየ። በትልቅ ክብርና ስነስርዓት ልጁ በተገኘበተ በ ገነተ እየሱስ ቤ/ክርስቲያን ተቀበረ። የአጼ ሱሰንዮስ ዜና መዋዕል ማጣቀሻ የኢትዮጵያ ነገሥታት መደብ
2855
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8A%AE%E1%88%AD%E1%8B%AB%20%E1%8C%A6%E1%88%AD%E1%8A%90%E1%89%B5
የኮርያ ጦርነት
{{የጦርነት መረጃ ጦርነት_ስም የኮርያ ጦርነት ክፍል ቀዝቃዛው ጦርነት ስዕል የስዕል_መግለጫ ከላይ በቀኝ ዙሪያ፦ የተባበሩት መንግሥታት ኃይሎች 38ኛው ፓራለል ጋር ሲደርሱ፣ ኤፍ 86 ሴበር ተዋጊ አውሮፕላን በኮሪያ ውግያ ጊዜ፣ ኢንቾን የመርከብ መጠሊያ፤ የኢንቾን ውጊያ መጀመሪያ፣ የቻይና ወታደሮች አቀባበል ሲደረግላቸው፣ የአሜሪካ ሠራዊት በኢንቾን መከላከያ ግድግዳ ሲወጡ ቀን ከሰኔ ቀን ዓ.ም. እስከ ዛሬ የተኩስ ማቆም የተፈረመው ሐምሌ ቀን ዓ.ም. ቦታ የኮሪያ ልሳነ ምድር ውጤት የተኩስ ማቆም ስምምነት ተፈረመ የደቡብ ኮሪያ ወረራ በሰሜን ኮሪያ መክሸፍ የሰሜን ኮሪያ ወረራ በተባበሩት መንግሥታት መክሸፍ የደቡብ ኮሪያ ወረራ በቻይና መክሸፍ የኮሪያ ጦር የለሽ ክልል መቋቋም፣ ሁለቱም ወገኖች 38ኛው ፓራለል አካባቢ ትንሽ መሬት አገኙ ወገን1 (ውሳኔ ፈረንሳይ የሕክምና ዕርዳታ፦ ወገን2 ሰሜን ኮሪያና አጋሮች፦ የሕክምና ዕርዳታ፦ ፖላንድ ሁንጋሪ ቡልጋሪያ ሮማንያ መሪ1 መሪ2 አቅም1 አቅም2 ጉዳት1 የሞቱ፦የቆሰሉ፦የጠፉ፦ጠቅላላ፦| ጉዳት2 የሞቱ፦የቆሰሉ፦የጠፉ፦ጠቅላላ፦ }}የኮርያ ጦርነት በኮርያ ከሰኔ 18 1942 እስከ ኃምሌ 20 1945 የተዋገ ጦርነት ነበር።የኮሪያ ዘማቾች ትውስታሬሳ እንኳ አልተማረከብንም” “አለመማረክ የጀግንነት ጉዳይ አይደለም” በአምስት ዙር ኮርያ ከዘመቱት 6037 ኢትዮጵያውያን መካከል 122ቱ በጦርነቱ ሞተዋል፡፡ አንዳቸውም አልተማረኩም ሳይማረኩ ግዳጃቸውን ፈጽመው ከተመለሱት 350ው የዛሬ 20 ዓመት የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበርን መስርተው ሰሞኑን የዘመቻውን 61ኛ ዓመት አክብረዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መልካሙ ተክሌ ከአስር አለቃ ዘነበወርቅ በላይነህ እና ከየኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር ፕሬዝደንት ኮሎኔል መለሰ ተሰማ ጋር አጭር ቃለምልልስ አድርጓል፡፡''' ለኮሪያ ዘመቻ እንዴት ነው የተመረጡት? በመሠረቱ የገበሬ ልጅ ነኝ፡፡ ለኮሪያ ዘመቻ ተብዬ አይደለም ወደ ወታደራዊ ዘመቻ የገባሁት፡፡ በጣልያን ወረራ ወቅት በሕፃንነቴ ከአባቴ ጋር ጫካ ለጫካ ተንከራትቻለሁ፡፡ በ1939 ዓ.ም ወታደርነት ተቀጠርኩ፡፡ የተወለድኩት በ1922 ዓ.ም ነው፡፡ ወታደር በሆንኩ በአምስት ወይ በስድስት ዓመት ኮርያ ዘመትኩ፡፡ እውነቱን ለመናገር ስዘምት ማንበብና መፃፍ አልችልም ነበር፡፡ አሁንም ድረስ? አይደለም፡፡ እዚያው ኮርያ እያለሁ ዘመድ ደብዳቤ ፃፈልኝ፡፡ ሃምሳ አለቃ ንጉሤ ወልደሚካኤል የሚባል ጓደኛዬን ፃፍልኝ ስለው ሂድ አልጽፍም አለኝ፡፡ ንዴት ያዘኝና ወንጌሌ ቆስጣ ለሚባሉ አለቃዬ ጋዜጣ ስጡኝና ፊደል ልማርበት አልኳቸው፡፡ ፊደል ጭምር ሰጡኝ፡፡ በዚያው በጓደኞቼ አጋዥነት ተለማምጄ ስሜን መፃፍ ቻልኩ፡፡ በሦስት ወር ደብዳቤ ለቤተሰብ ጽፌ ደብዳቤዬ እንደደረሳቸው ቤተሰቦቼ ሌላ ደብዳቤ ላኩልኝ፡፡ ጥሩ አለቆች ስለነበሩኝም እዚህ ስመለስ ጫካ ወስደው ጥቁር ሰሌዳ በማሸከም ያስተምሩን ነበር፡፡ የማታ ትምህርትም ገብቼ ነበር፡፡ ዘመቻውን ከሦስተኛው ቃኘው ጋር በኮሎኔል ወልደዮሐንስ ሽታ አዝማችነት ነበር የዘመትኩት፡፡ እዚያ ሲደርሱ ከነበረው ምን ያስታውሳሉ? የመጀመሪያውን ቅኝት ስንወጣ በእኔ መቶ አዛዥነት ነበር፡፡ የመጀመርያው ተኩስ ሞትና መቁሰልም የደረሰው በእኛ ላይ ነው፡፡ የዘመትነው በግንቦት ወር 1945 ዓ.ም ነበር፡፡ የመጀመሪያው ቃኘው የዘመተው በ1943 ዓ.ም ነበር፡፡ አንድ ሞቶብን ሁለት ቆሰሉ፡፡ አንደኛው ቁስለኛ እጁ ተቆረጠ፡፡ የሞተውንና ቁስለኞቹን ይዘን ወደ ወገን ጦር ተቀላቀልን፡፡ ሁለተኛው የጦር ግንባር ከፍተኛው የቲቮ ተራራ ነው፡፡ እዚያ ላይ በመከላከል ላይ ነበርን፡፡ ጓደኛዬ እዚህ ውስጥ አለ (በጦርነቱ የተሰውትን ሃውልት እያሳዩ) በዳኔ ነገዎ ይባላል፡፡ መከላከያ ውስጥ አንድ ላይ ነበርን፡፡ ባንከር አለ፡፡ ድንገት ቢተኮስ እዚያ እንግባ ስለው እምቢ አለ፡፡ እየጐተትኩት እያለሁ ጥይት ተተኮሰ፡፡ እሱን በጣጥሶ ሲጥል እኔን አፈር ከአንገት በታች ቀበረኝ፡፡ ጥይቱ እያበራ ሲመጣ እኔ ዘልዬ ስወድቅ እሱን በጣጠሰው፡፡ ከ45 ደቂቃ ቁፋሮ በኋላ ነው ያወጡኝ፡፡ ከዚያ የጓደኛዬን ሰውነት በዳበሳ ፈልገን በራሱ ሸራ አድርገን ለመቃብር አበቃነው፡፡ ጦርነቱ ባይቆም ያ ሁሉ ሠራዊት ያልቅ ነበር፡፡ ግን አንድም አልተማረከም? አንድም አልተማረከም፡፡ ዘማቹ ይፋቀራል፡፡ ይከባበራል፡፡ ጓደኛህ ቢሞት እንኳ ሬሳውን ጥለህ አትሄድም፡፡ ሬሳ እንኳ አልተማረከብንም፡፡ አመት ከሰባት ወር እዚያ ቆይቻለሁ፡፡ ጦርነቱም የቆመው እዚያ እያለን ነው፡፡ ከዚያም በኋላ በየቀጠናው ጥበቃ እናደርግ ነበር፡፡ አሁን በእርቁ ለሰሜን ኮርያ ተሰጠ እንጂ ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ሰሜን ዘልቀናል፡፡ ብዙ ምሽግ መቆፈራችን ነው አንድም እዚያ ብዙ ያቆየን፡፡ ሀገሩም የራሱን ጦር እስኪያደራጅ መቆየቱ የግድ ነበር፡፡ ነሐሴ 29/1946 ዓ.ም ተመልሰን አዲስ አበባ ገባን፡፡ ሌሎቹ የተማረኩት ምን አልባት በምቾት ብቻ መኖር ስለለመዱ ይመስለኛል፡፡ እኔ ከወገኔ ተለይቼ እጄን የምሰጥበት ምክንያት የለም፡፡ ሄጄ ማን እጅ ነው የምገባው? ጠላት እጅ፡፡ ስም ያለው ሞት መሞት እንጂ ሁለት ሞት አልሞትም፡፡ የመጀመሪያው ቃኘው ሻለቃ ሲሄድ እርስዎ የት ነበሩ? ሠራዊት ውስጥ ነበርኩ፤ ሐረር የልዑል መኮንን ቤተመንግስት ጥበቃ ላይ ነበርን፡፡ በ1944 ወደ አዲስ አበባ ተዛውረን መጣን፡፡ ከዚያ ተመልምዬ ነው ወደ ኮርያ ለመሄድ የበቃሁት፡፡ እንዴት እንደተመለመልን አላውቅም፡፡ ይኼን የሚያውቁት መልማዮቹ ናቸው፡፡ የታዘዘውን ፈፃሚ ጠንካራ ሞራል ያለው ሠራዊት ተመርጧል፡፡ ከማን ጋር የምትዋጉት? የውጊያ ብቃታቸውስ ምን ይመስላል? እነዚያ ሰሜን ኮርያ፣ ሶቭየት ሕብረት፣ ቻይናና ተባባሪዎቻቸው ናቸው፡፡ ብርቱ ስልት አላቸው፡፡ በጨበጣ ውጊያ የወደቀልህ መስሎ መትቶ ይጥልሃል፡፡ የእኛዎቹ በተለይ አሜሪካኖች እጅግ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ታንክ፣ መድፍ… ታንክ ላይ የሚጠመደው ጀነራል መድፋቸውማ የተለየ ነው፡፡ ይኼ መድፍ በጣም በርቀት መምታት የሚችል ነው፡፡ እዚህ ሲተኮስ እዚያ ፈንድቶ ርቀቱን ይጨምራል፡፡ አውሮፕላኖችም አሉት የኛ ወገን፡፡ አንድ ጦር ከተከበበ በአየር ይመታል አካባቢው፡፡ በዚህ መልኩ 70ሺህ ያህል የተቀናቃኝ ጦር ተደምስሷል፡፡ ከእኛ ግን 18 ብቻ ነው የሞተው፤ ተከቦ ከነበረው፡፡ የቋንቋና የባህል ችግር አልገጠማችሁም? እኛ ከማንም ጋር ግንኙነት የለንም፡፡ ግንኙነት ያለው ከዋናው መምሪያ ነው፡፡ አገናኝ መኮንኖች እዚያ የተባለውን ይነግሩናል እንጂ ከሕዝብ ጋር በፍፁም አንገናኝም፡፡ ስንገናኝም በጥቅሻ ነው፡፡ ያለነው እልም ያለ ገጠር ውስጥ በመሆኑ ከተማ ወጥቶ በእረፍት ጊዜ መዝናናት የሚባል ነገር የለም፡፡ ብንታመም ሻምበላችን ውስጥ ሕክምና አለ፡፡ አንድ ጊዜ ታምሜ ነበር፡፡ እዚያ ታክሜ ከአቅም በላይ ስለሆነባቸው ሌላ ሀኪም ቤት ተላኩ፤ ወዲያውኑ በሄሊኮፕተር ፑዛን ከተማ ሄድኩ፡፡ ለ20 ቀን ያህል ታክሜ ተመልሻለሁ፡፡ ሕክምናቸው በጣም ጥሩ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከዚያ ሀገር ሴት ጋር በፍቅር መውደቅ ጋብቻ እና የመሳሰሉት አይኖሩም? ጋብቻ ሳይሆን ከጋብቻ ውጪ ከዚያ ሀገር ሴቶች ልጅ የወለዱ ወታደሮቻችን አሉ፤ ከኮሪያ ሳይሆን ከጃፓን ፍቃድ ስንወጣ ጃፓን ነበር የምንሄደው፡፡ ፍቅር ይዟቸው ሲለያዩ የተላቀሱም አሉ፡፡ እርስዎስ? እንዲህ አይነት ጣጣ ውስጥ አልገባሁም፡፡ ጃፓን ፍቃድ ሄጃለሁ፡፡ ግን ልጅነትም አለ፡፡ ሀኪም ቤት ውስጥ በተኛሁ ጊዜ ግን አንድ ችግር ገጥሞኛል፡፡ ምን አይነት ችግር? አንዲት ነጭ አሜከካዊት ሻምበል የሕክምና ባለሙያ ነበረች፡፡ ፑዛን ጋውን ለብሳ መጣች፡፡ አልኮል የፈሰሰበት ሙቅ ውሃ እና ፎጣ ይዛ ገላህን ልጠበው ልሸው አለችኝ፡፡ በፍፁም እንዴት ተደርጐ አልኳት፡፡ በኋላ አሁን ስሙን የረሳሁት አስተርጓሚ ጠራች፡፡ ለምን እምቢ ትላለህ ገላህን ልጠብህ እኮ ነው ያለችህ አለኝ፡፡ ከዚህ ስሄድ እንኳን ላገባ ሴት አላውቅም፡፡ ራሴ መታጠብ ስችል ሴት እንዴት ያጥበኛል አልኩ፡፡ ሳቀብኝና ነግሯት ለኔ ችግር የለውም አለኝ፡፡ በኋላ ስታጥበኝ የሷንም ፍላጐት በማየቴ ሰውነቴ ጋለ፤ ፍላጐቴ ተነሳሳ፡፡ ይኼኔ “ኧረ ባክህ” ብዬ ስነግረው ሳቀና ነገራት፡፡ ችግር የለውም ብላ አንድም የሰውነቴ ክፍል ሳይቀር አገላብጣ አጠበችኝ፡፡ ትንሽ ቆይታ ልብሷን ለውጣ ለእኔም ልብስ ይዛ መጣች፡፡ ይዛኝ ሄደች፡፡ የዚያኑ እለት ግንኙነት አደረግን፡፡ የመጀመሪያዬ እሱ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ለምን እንደሆነ ጠላኋት፡፡ ተመልሼ ሀኪም ቤት ተኛሁ፡፡ ሳያት ሁሉ እሸፋፈን ነበር፤ ከጥላቻዬ የተነሳ፡፡ ሳልቆይ ለአለቃዬ ለአስተርጓሚው ነገርኩት፡፡ ድኛለሁ ይላል ይውጣ ተባለ፡፡ እሷ አይወጣም ብላ እንደገና ስምንት ቀን አቆየችኝ፡፡ ከአንዴ በላይ አብረን አልወጣንም፤ እምቢ አልኩ፡፡ በዚሁ መንስኤ ለ15 ቀን ታምሜአለሁ፡፡ ሕክምና ሳይጨርሱ ነው ከሻምበሏ ጋር የወጣችሁት? ሕክምናማ ጨርሼ እኮ ነው መታጠቡ የመጣው፡፡ ጥሬ ስጋ ስትበሉ የውጭ ዜጐች አይተው ይሸሹዋችሁ ነበር የሚባለው እውነት ነው? ይኼንን እኔም እንዳንተው ነው የሰማሁት፡፡ ይህንን አደረገ የተባለው ሻለቃ ተፈራ ወልደትንሣኤ ነው ይባላል፡፡ ከመጀመሪያ ዙር ዘማቾች፡፡ እንደዘመተ መንጉሱ በማቀዝቀዣ ታሽጐ ቁርጥ ሥጋ ይላካል ለጦሩ ንጉሱ የላኩላችሁን ተመገቡ ተብሎ ምግብ ቤት (ሚንስ ቤት) ይመገባሉ፡፡ የጦሩ አባላት ተመግበው የተረፈውን የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ የምንሰጥበት እቃ አለ፡፡ ያን ሥጋ በላስቲክ ጠቅልሎ ይዟል መሠለኝ፡፡ በልቶ ሲጠግብ ጦርነት ይታዘዛል፡፡ ከውጊያ በኋላ ድል አድርገው ሲጨረሱ በድካምና በረሃብ ቁጭ ይላሉ፡፡ በያዘው ሴንጢ እየቆረጠ ያንን ሥጋ ይበላል፡፡ ይህንን አንዲት ቻይናዊት ፈርታ ተደብቃ አይታዋለች፡፡ ደንግጣ ሰው የሚበሉ እንግዳ ሰዎች መጡ ብላ አስወራች፡፡ ከዚያን ወዲህ ነው እንዲህ መወራት የጀመረው፡፡ ሰው በላ መጣ አሉን፡፡ እርስዎ በስንት የጦር ግንባሮት ተሳትፈዋል? ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ዮክ ተራራ የጦር ግንባር ነው፡፡ ሁለተኛው ችቦ ነው፡፡ ከነዚህ ውጪ የለም፡፡ በጣም የሚያስታውሱት የኢትዮጵያም ሆነ የሌላ ሀገር ወታደር? አንድ ግዳጅ ላይ አንድ የመቶ አዛዥ ማንደፍሮ የማነህ ይባላሉ፡፡ ቅኝት ይወጣሉ፡፡ የኛ ሰራዊት ቅኝት ከመውጣቱ በፊት አሜሪካ የማረከቻቸውን የቻይና ወታደሮች አሰልጥና በስለላ ታሰማራ ነበር፡፡ ለእነሱና ለእኛ የተሰጠው ቦታ የተለያየ ነው፡፡ ለመቶ አለቃው ተነግሯል፡፡ ቻይናዎቹ የኛን ይዞታ ይዘው ይጠብቋቸዋል፡፡ የኛዎቹ ሊይዙ ሲሉ ተኩስ ከፈቱባቸው፡፡ የሞቱት ሞቱ፡፡ ቁስለኞችን ውሰዱ ተባልን፡፡ በዚያን ጊዜ እኔ ተመለመልኩና ሂድ ቁስለኛ አምጣ ተብዬ ተላኩኝ፡፡ በሸክም ነው የምናመጣው፤ ያውም ተራራ እና ጨለማ ነው፡፡ ተሸክሜ ሳንጃ ሰክቻለሁ፣ ጠመንጃዬ እንደጎረሰ ነው፡፡ ተሸክሜ ዳገት እየወጣሁ ትንሽ ሲቀረን አንሸራቶኝ ስወድቅ ሰውየውም ወደቀ፡፡ እኔን አጥፍቶ ሊያመልጥ ሲያስብ ቻይናዊው ቀና ብሎ ይቃኛል፣ ቶሎ ብዬ ርምጃ ወሰድኩ፡፡ አሁን ኑሮ እንዴት ነዉ? የቀበሌ ቤት ተከራይቼ ነው የምኖረው፡፡ እዚህ የኢትዮጵያ ኮርያ ዘማቾች ማህበር በጥበቃ ሰራተኝነት አገለግላለሁ፡፡ ፍላጎት ያለው ያገልግል ሲባል ተቀጠርኩ፡፡ ከምኖርባት ሽሮሜዳ አፍንጮ በር በእግር መንቀሳቀሱን ወድጄዋለሁ፡፡ ደመወዙ ግን አይወራም አይጠቅምም፡፡ ዘጠኝ ልጆች አሉኝ፡፡ ሦስቱ አግብተዋል፡፡ ሌሎቹ ገና ናቸው፡፡ አንደኛው ልዴ መለሰ ዘነበወርቅ ይባላል ደቡብ ኮርያ ለትምህርት ቢሄድም ከእኔ ጋር እንዳለ ነው የሚቆጠረው፡፡ 249 ብር ነበር የሚከፈለኝ በብዙ ጭቅጭቅ ለቀን እንሄዳለን ስንል ነው መሠለኝ 294 ብር ሆኗል፡፡ የጡረታ አበሉ 310 ብር ነው፡፡ በፊት ደመወዛችን 15 ብር ነበር፡፡ ያውም አምስቱ ብር ተያዥ ነው፡፡ 10 ብር እንቀበላለን፡፡ ሦስት ኪሎ ስንዴም ይሰፈርልናል፡፡ ቤተሰብና ትዳር ስለሌለን ብር ከሃምሳ ሸጠናት ከሰልና ሳሙና እንገዛበት ነበር፡፡ ትዳርስ እንዴት መሠረቱ? በ1957 ዓ.ም በ32 ዓመቴ ነው ያገባሁት፡፡ እናት አባቴ ናቸው የዳሩኝ፡፡ ከሰራዊቱ ወጥቼ በሲቪል ስራ ላይ ነበርኩ አየር መንገድ ውስጥ፡፡ አባቴን ከሀገር መውጣቴ ካልቀረ አልመለሥም ዳረኝ ስለው እሺ አለ፡፡ አግኝቼልሃለሁና ናና እያት አለኝ፤ ሰሜን ሸዋ ደብረሊባኖስ አካባቢ ነው የቤተሰቦቼ ቤት፤ ሄድኩ፡፡ አይንህ አይኔ፣ አንደበትህ አንደበቴ ነው፤ ማየቴ ምን ጥቅምና ትርፍ አለው፤ አንተ ባየኻት እስማማለሁ አልኩት፡፡ ያየሁአት የሰርጉ እለት ነው፡፡ የሰርጉ እለት ስገባ ሴቶቹ በሀገራችን ባህል መሠረት ተሸፋፍነዋል፡፡ እናት አባቷንም አላውቅም፡፡ ወላጅ አባቷ ማነው አልኩ? እኔ ነኝ አሉ፡፡ እርስዎ ነዎት? ስል አዎ አሉ፡፡ ያውቁኛል ስል ኧረ ልጄ አላውቅህም አሉኝ፡፡ ዘነበወርቅ በላይነህ እባላለሁ አልኳቸው፡፡ አንተ ነህ ሲሉኝ አዎ ልጅም ፈቅደውልኛል ሲላቸው አዎ አሉኝ፡፡ በሉ ስለማላውቃት ይስጡኝ አልኳቸው፡፡ ገልጠው ይቺ ነች ልጄ አሉ፡፡ ተሞሽራ ከተቀመጠችበት፡፡ ወ/ሮ አሥራት አለሙ፣ የልጆቼን እናት፣ ባለቤቴን እንደዚህ ነው ያገባኋት፡፡ አገር ቤት ተጋባንና አዲስ አበባ ሽሮሜዳ መኖር ጀመርን፡፡ ማህበራችሁ እንዴት ተመሠረተ? ማህበሩ የተመሠረተው በ1994 ዓ.ም ነው፡፡ ከዚያ በፊት በነበሩት መንግስታት ድጋፍ ማጣት ማህበሩ አልተቋቋመም ነበር፡፡ በሁለት ትልልቅ ምክንያቶች ነው የተቋቋመው፡፡ አንደኛው:- ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘመኑ ከሰለጠኑት መንግስታት አንፃር ምን ቦታ እንደነበራት ለማሳየት ነው፡፡ ሌላው ሀገራችን የሰጠችንን መወጣታችንንና ታሪክ መስራታችንን ለትውልድ ለማስተላለፍ ነው፡፡ ኮርያ ለመዝመት እንዴት ተመረጡ፣ እድሜዎ ስንት ነው? እንዴት እንደተመረጥን አናውቀውም፡፡ መኮንኖች ስለሆንን ማን ይሂድ ማን ይቅር የሚለውን የሚያውቁት አለቆቻችን ናቸው፡፡ ሚሊተሪ አካዳሚ ስንገባ ወታደር እንደምንሆን እናውቃለን፡፡ አካዳሚው የንጉሠ ነገሥቱ የክብር ዘበኛ ጦር አካዳሚ ነው፡፡ ቪላ ሳህለሥላሴ ይባላል የሠለጠንበት ቦታ፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ነው፡፡ ሦስተኛ ኮርሰኞች ነን፡፡ ትምህርታችንን ከሌሎቹ በሰባት ወር ቀድመን ነው የፈፀምነው፡፡ በዚያን ጊዜ የነበረው ከፍተኛ ክፍል ስምንተኛ ስለነበር ከስምንተኛ ክፍል ነው የገባሁት፡፡ የጦር አካዳሚውን ትምህርት እንደጨረስን የኮርያ ዘመቻ ወሬ ተሰማ፡፡ እኛ ሚያዝያ 3 ተመርቀን በማግስቱ ሚያዝያ 4 ጓደኞቻችን ዘመቱ፤ በመጀመሪያ ቃኘው፡፡ እኔ በሁለተኛው ቃኘው የሄድኩት በ1944 ዓ.ም ነው፡፡ ስትሄዱ እንዴት ነበረ ጉዞው? ወደ ለገሃር ማክ በሚባል ወታደራዊ መኪና ሄድን ከጃንሜዳ፡፡ ከዚያ በባቡር ወደ ጅቡቲ፤ ከዚያም በመርከብ ደቡብ ኮርያ፡፡ ደቡባዊ የወደብ ከተማ የሆነችው ፑዛን ከሃያ ሁለት ቀን የባህር ላይ ጉዞ በኋላ ገባን፡፡ ከዚያም እንደገና በመኪና ተሳፍረን እዚያው አካባቢ ከአየር ፀባዩ እና ከጦር መሣሪያው ጋር ተለማመድን፡፡ በሌላ ባቡር ሁለት ቀን ተጉዘን ገባን፡፡ እንደገና በአሜሪካ መኪና ተጭነን ግንባር ደረስን፡፡ ያኔ ኮርያ ስደርስ የ21 ዓመት ከሰባት ወር ልጅ ነበርኩ፡፡ ሚስት ሳያገቡ ነበር የሄዱት? ኡ…እንኳን ላገባ የሴት ጓደኛ አልነበረኝም፡፡ እንደዛሬው ልጆች አልነበርንም፡፡ እዚያስ አንዷን ደቡብ ኮርያዊት የመተዋወቅ ነገር? የሄድነው ለጦርነት ነው እንጂ ለሽርሽር አይደለም፡፡ ከነሱ ጋር የምንገናኘው በሦስት ወር አንድ ጊዜ ከጦር ግንባር እረፍት ለማድረግ ስንመለስ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ አቅራቢያችን ወዳሉ ከተሞች እንሄዳለን፤ ጃፓንም ድረስ፡፡ በእንደዚህ አይነት አጋጣሚ ተጠቃቅሶ መግባባትና መጫወት አይቀርም፡፡ ጦርነት ውስጥ ሆነህ እጮኛ ለመያዝ ሚስት ለማግባት መመኘቱ ጥሩ ነው፡፡ እድሉ ግን ይገኛል ወይ ነው ጥያቄው፡፡ መቀባበጡ ግን እድሜአችን ስለነበር አልቀረም፡፡ እንዴት ትግባቡ ነበር? በጫወታ ለመግባባት እኮ ምልክት ይበቃል፡፡ ለእረፍት ስንመለስ ጦር ሜዳ መኖራችንንም እንረሳዋለን፡፡ ምክንያቱም ዘመናዊ አቅርቦት ነበር፡፡ ከመከላከያ መስመር እንኳ ከቻልክ በየአምስቱ ቀን ሻወር አለ፡፡ እዚያ እየታጠብክ የለበስከውን ጥለህ አዲስ ልብስ ትለብሳለህ፡፡ ተግባብቶ ትዳር የያዘ ወይ ፍቅረኛ የነበረውና የወለደ አልነበረም? ይኖራል፡፡ ከኛ በላይ ያሉት ይኖራሉ፡፡ እኛ የመቶ አዛዦች ነን፡፡ ከፍተኛ መኮንኖችና አዛዦቻችን ማለት ነው፡፡ ጠና ያሉ ናቸው፡፡ አራት አምስት ልጅ ከወለዱ በኋላ የዘመቱ ይገኙባቸዋል፡፡ ያላየሁትን አልመሠክርም ሲያደርጉ አላየሁም፡፡ እኛ ብንቀብጥ ብንቀብጥ ከጓደኞቼ ጋር ነው፡፡ ከአዛዦቼ ጋር ሆኜ ደግሞ መቅበጥም አልችልም፡፡ የባህልና የቋንቋ ግጭትስ? ትክክለኛውን ለመናገር ከነሱ ጋር የባህል ልውውጥ የለንም፡፡ ምክንያቱም በሄድንበት ቦታ ሁሉ የሚቀርብልን ምግብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አንድ አይነት ምግብ ነው፤ የጦር ግንባር መዘርዘረ ምግብ፡፡ ወደ ሕዝብ የሚያቀርብ የለንም፡፡ በጦሩ ወረዳም ሕዝቡ የለም፡፡ ጥሬ ሥጋ በመብላታችሁ “ሰው በሎች” ብለው ሲሸሿችሁ ነበር የሚባለውስ? ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ በነበርኩበት ጊዜ ይኼ አልተፈፀመም፡፡ ወሬውን ሰምቼዋለሁ፡፡ በዐይኔ ያየሁት ነገር የለም፡፡ በዘመትኩበት ጊዜ እንዲህ አልተደረገም፡፡ ኮርያዎች ከዚያ በፊት ጥሬ ሥጋ አልበሉ ይሆናል፡፡ ተቀቅሎ የሚበላ ጥሬ ሥጋ ግን ይቀርብልሃል፡፡ ሃበሾች ያ ደስ ብሏቸው በልተው ሊሆን ይችላል፡፡ ለምንድነው አንድም ሰው ያልተማረከው? አለመማረክ የጀግንነትና የጉብዝና ጉዳይ አይደለም፡፡ አለመማረክ የአመራር ውጤት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የት እንዳለ የት እንደወደቀ ዝርዝር ቁጥጥር በምታደርግበት ጊዜ የቆሰለውን፣ የወደቀውን ሰው ታውቃለህ፡፡ አንድ ሰው ከጓደኞቹ መሃል ሲጠፋ የት እንደወደቀ ትፈልጋለህ፡፡ ይኼ ለእኛ መሠረታዊ ትምህርታችን ነው፡፡ አጥቅተህም ቦታ ከያዝክ በኋላ ሰዎችህን ትቆጣጠራለህ፡፡ እዚያ ስታጣው የት እንደደረሰ ትፈልገዋለህ፡፡ አንድም ቀን አልሸሸንም፡፡ ምናልባት ሽሽት ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰዎችን ለመቆጣጠር ሲያቅትህ ነፍስህን ብቻ ለማውጣት ስትሸሽ ያን ጊዜ ሰዎችህ ሊማረኩ ይችላሉ፡፡ በስንት ውጊያዎች ተሳትፈዋል? ሻለቃው በተዋጋባቸው ውጊያዎች ሁሉ ተሳትፌአለሁ፡፡ አምስት ዋና ዋና ውጊያዎች ነበሩ፡፡ ከዚያ በተረፈ የሽምቅ፣ የደፈጣ ውጊያዎች አሉ፡፡ በነዚህ ሁሉ ተካፍያለሁ፡፡ ስለዚህ መቁጠር ያስቸግራል፡፡ ውጊያ ላይም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ትዝ የሚልዎት ሰው ካለ? የሰማሁትን ሳይሆን ያየሁትን ልንገርህ፡፡ በነበርኩበት ግንባር እንደ ጥላዬ ወንድም አገኘሁ ያሉትን አስታውሳለሁ፡፡ እንደ ሞገሥ አልዩ ያሉትንም አስታውሳለሁ፡፡ በጦር ሜዳ ውስጥ ገብተው ሙያ እየሰሩ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ጓደኛዬ በቀለ ገብረ ኪዳን ደግሞ አብረን ቅኝት ወጣን፡፡ ሁላችም በያለንበት ተከበብን፡፡ በኋላ እንደምንም አድርገን ከዚያ ሰብረን ወጣን፡፡ ጠላት በሚሸሽበት ጊዜ እሱ ከጎኔ ወድቋል፡፡ እሱን አንስቼ አንድ ቦታ ላይ አስቀምጬ ረርዳታ ጠየኩ፡፡ ክፉኛ ቆስሎ ነበር፡፡ መማረክ የሚመጣው እንዲህ አይነቱ ቦታ ላይ ነበር፡፡ ያን ጊዜ እንኳን አልተማረክንም፤ ሦስት አራት ቦታ ላይ ተከበን በነበርንበት ጊዜ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ አንድ ጓደኛዬ ከፊቴ ቀድሞ ይኼዳል፡፡ ቁርስ ሰዓት ላይ ነው እኔ ከኋላ ነኝ፡፡ ቁርሳችንን በልተን ስንመጣ ከኋላ ተተኮሰብን፡፡ ጥይቱ ልክ እሱ ላይ ያርፋል፡፡ ሲፈነዳ በጭሱ ተሸፈነ፡፡ ሞተ ብዬ ሳስብ ጭሱ ፈገግ ሲል ቆሞ አየሁት፡፡ ሮጬ ስሄድ ሰውነቱ በሙሉ ደም ነው፡፡ “ሞገሴ” ስለው “እ…” አለኝ፡፡ “ደህና ነህ?” ስለው “ደህና ነኝ አንተስ?” አለኝ፡፡ “ደህና ነኝ ይኸ የምን ደም ነው?” ስለው ደሙን አይቶ ወደቀ፡፡ ያ ትንሽ አስደነገጠኝ፡፡ ሳልነግረው ብደግፈው ሮኖ ምናልባት አይወድቅም ነበር፡፡ ወዲያው አምቡላንስ ጠየቅን፡፡ ታክሞ ዳነ፡፡ መለሰ ዘርይሁን ደግሞ ነበር፡፡ ኮርያኖች መከላከያ መሥመራችንን በሽቦ ያጥራሉ፡፡ በጠላት መድፍ ተደብድቦ የሳሳ አለ፡፡ ያ ጠላት እንዲያጠቃ መከላከያ ነው ቀድሞውኑ፡፡ ያንን ለማሳጠር ጠይቀን የኮርያ ሰርቪስ ቡድን የሚባል አለ፡፡ እሾሃም ሽቦውን ያጥራሉ፡፡ ብረቱን ለመትከል ድምፅ ሲያሰሙ ያንን የሰማ ጠላት ከባድ መሣርያ ይተኩሳል፡፡ ሲመጣ መሃከላቸው ያርፋል፡፡ ብዙዎቹ ቆሰሉ፡፡ አንዳንዶቹ ሞቱ፡፡ አንድ ወታደር እርዱኝ ብሎ ጮኸ፤ ቆስሎ፡፡ በኃይል ጮኸ፡፡ ወታደሮቻችን ያለ ትዕዛዝ ከዚያ መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ መለሰ ዘርይሁን ግን አላስችል ብሎት ከሁለት ሦስት ወታደሮች ጋር ዘሎ ይወጣና ሁሉም ቁስለኞች ተሸክመው የቆሰሉትን ወደ መስመር ሲመልሱ፣ ሁለተኛውን ሰው ሲታደግ ሌላ ፈንጂ መጣና ሁለቱንም አብሮ ገደላቸው፡፡ በደም የተሳሰረ ወዳጅነት የምንለው አሁን ያ ነው፡፡ አንድ ሰውም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ አንድ ሰውም ቢሆን ኮርያዊ ነው፡፡ የሁለቱ ደም ተቀላሏልና በደም የተሳሰረ ወዳጅነት እንላለን፡፡ የአሁን ኑሮዎ እንዴት ነው? ጃንሆይ የሰጡን አንድ ነገር ነው፡፡ ወደ ኮርያ ስንሄድ አንድ ሰንደቅ ዓላማ ሰጥተውናል፡፡ ይኼን ሰንደቅ ዓላማ መመርያ አድርጋችሁ እንድትዘምቱ፣ በተሰማራችሁበት ቦታ ጀግንነት ሠርታችሁ በደረታችሁ ላይ ልዩ ምልክት አድርጋችሁ በኩራት ስትመለሱ በአደራ የሰጠናችሁን አርማ መልሳችሁ እንድታስረክቡን ነው ያሉት፡፡ ያንን መልሰን አስረክበናቸዋል፡፡ ጃንሆይ ስለወታደርነት የተናገሩት አንደ ነገር አለ፡፡ “ወታደርና ጊዜው” የሚለው የክብር ዘበኛ የመጀመርያው የወታደር ጋዜጣ አለ፡፡ እዚያ ላይ ያሰፈሩት ምንድነው.. “የጦር ሰው ፖለቲካን መልመድ ወላዋይነትን ያስከትላል፡፡ ሲታዘዝም ለምን ማለት ሃፍረት ነው” ብለዋል፡፡ የሄድነው ታዘን ነው፡፡ ስንመለስ ይህን አድርጉልን አላለንም፤ እሳቸውም አላደረጉልንም፡፡ ኮንጎም ዘምቻለሁ፡፡ ከዚያ ስመለስ ትንሽ ፍራንክ ተጠራቅማ ጠብቃኝ ነበር፡፡ በዚያች ፍራንክ ቦታ ገዛሁኝ፡፡ በቦታዋ በደርግ ጊዜ ቤት ሰራሁባት፤ ሳትወረስ ጠብቃኝ ነበር፡፡ ከሰራሁም በኋላ አልተወረሰችም፡፡ ትንንሽ ትንንሽ ቤቶች ሠርቻለሁ፡፡ ያንን እያከራየሁ ስለምኖር በጣም ጥሩ ኑሮ ነው የምኖረው፤ ከጓደኞቼ አንፃር ስመለከተው፡፡ እንዴት ገዙ? ልጆቼ ይረዱኛል፡፡ የመኪና ዋጋም የዋጋ ግሽበቱም እንዲህ አልነበረም፤ እኔ መኪና ስገዛ፡፡ ሦስት ወንድ ሦስት ሴት ልጆች አሉኝ፡፡ ኢንጂነሮች፣ የሕግ ባለሙያዎች ወዘተ ናቸው፡፡ በባህላችን ልጅ አይቆጠርም፡፡ የደቡብ ኮርያ መንግስት ለማህበራችሁ ስላደረገው ድጋፍ ቢያብራሩልኝ? የተለየ ነገር አላደረገም፡፡ ነገር ግን ለኮርያ ዘማች ልጆች የነፃ ትምህርት እድል ሰጥቷል፡፡ ለዘማቹ ያደረገው የጎላ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ኮርያኖች መጀመርያ በተሰለፍንበት የጦር ግንባር አካባቢ ለምቶ ከተማ ካደረጉ በኋላ፣ በተለይ ቹንቾን በተባለ አካባቢ የማህበራችንን ሕንፃና ሐውልት በከንቲባ አርከበ እቁባይ ጊዜ ሠርቶልናል፡፡ ሌላው የኮርያ ወርልድ ቪዥን፤ በሰባት ሚሊዮን ብር መዝናኛ ማዕከል ለመሥራት ቃል ገብተዋል፡፡ ምስጋናውን ከቻልክ በኮርያንኛ አስተላልፍልን፡፡ ሕንፃውን ቶሎ እንዲጀምሩ አስታውስልን፡፡ የእስያ ታሪክ ኮሪያ
44928
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%88%92%E1%88%B3%E1%89%A5%20%E1%89%B3%E1%88%AA%E1%8A%AD
የሒሳብ ታሪክ
የሒሳብ ታሪክ ተብሎ በመጠራት የሚታወቀዉ የጥናት ክፍል በዋናነት የሚያተኩረዉ ስለ ቀድሞ የሂሳብ ግኝቶች ሲሆን ስለ ሂሳባዊ አሰራሮች እና በቀድሞ ጊዜ የነበረዉን የሂሳብ አመለካከቶች ነዉ። ጥንታዊ የሂሳብ ጽሁፎች በተወሰነ ቦታዎች ብቻ መታወቅ ችለዉ ጥቅም ላይ ዉለዉ ነበረ ከነዚህም ውስጥ የባቢሎን 322የባቢሎናውያን (1900 ክ.ል.በ.)የሸክላ ፅሁፎች በቅርፃ ቅርፅ መልክ የጥንታዊ ግብጽጥንታዊ ግብፅ ዕውቅና ያለው ማህደር (1200 1800 ክ.ል.በ.) ይጠቀሳሉ እነዚህም በጥንት እና በስፋት ከታወቁት የስነ ቁጥር እና የስፋት፤ የትልቅነት የቅርፅ ሂሳቦች ቀጥሎ የታወቀውን የፋይታጎሪአን እርጉጥ ያትታሉ። የሒሳብ ጥናት ይሄ የሒሳብ ጥናት እንደ አንድ የትምህርት ክፍል (የፓይታጎረስ ደቀመዝሙራን) እንደተጀመረ ይታውቃል፣ ስሙንም ከግሪክኛ ቃል ተወስዶ ትርጎሜዉም የመመሪያዎች ትምህርት እንደ ማለት ነዉ። ግሪኮች የሂሳብን አሠራር በፅሁፍ ሲያስፋፉ፤ቻይናዎች የቁጥር ዲጂቶችን ቦታ አቀማመጥ ዘዴ አሳይተዋል፡ ህንዳዊ አረቦችም በቁጥር ህግ እና ኦፐሬተር ጥቅም ሲያሳዩ እስከ አሁንም በጥቅም ላይ ውሎል፤ በታዋቂዎቹ ዐረቦችም በእስልምና ሒሳብ የሚታወቅ አሠራር ወደ አውሮፓ አስፋፍቷል፤ እንዲሁም ከዘመናት በኋላ በአዲሲቱ ኢጣሊያህዳሴ ማበቡን ቀጥሎል። ሒሳባዊ አስተሳሰብ ምንጩ ከቁጥሮች ከመጠን እና ከቅርጾች ነዉ ነ። አንድ ሁለት እና ብዙ፤ ነገር ግን ከዚህ በላይ ለይተዉ በማያዉቁ ቋንቋዎች መኖ ለቁጥር በጊዜ ኂደት ለቁጥር በጊዜ ሂደት እየተለወጠ መምጣት ማሳመኛ ነዉ። ከስዋዚላንድ የሌቦምቦ፤ ከኮንጎ ወንዝ ናይል ወንዝ አካባቢ ኢሻንጎ የአጥንት ላይ ምልክቶች የእንግሊዝ ትላልቅ የድንጋይ አቀማመጦች ጥንታዊ የሒሳብ ቀመሮችን ሳይዙ እንደማይቀር ታምኖል። ይሁንና አሳማኝነት ያላቸዉ የባቢሎን፤ የግብጽ እናም ከዛ ቀጥሎ ያሉት የባቢሎን ከመስጴጦምያ የአሁኑ ኢራቅ ከሱመር እስከ ሄለናዊያን ያለዉን ጊዜ ያመለክታል የግብጽ ሒሳብ በግብጻዊያን ቋንቋ የተጻፈን ያመለክታል፤ የግሪኮች -ሄለናውያን ሂሳብ ከፍልስፍናው ሰው ሚለተስ ቴልስ ጊዜ ጀምሮ እሰከ አቴንስ የትምህርት መዐከል መዘጋት ድረስ ያለውን ጊዜ ያመለክታል። የቻይናዎች የአረቦች ከዚያም የመካከለኛዉ ዘመን አዉሮፓ የሒሳብ እዉቀት በልጽጎ ለህዋ ሳይንስ ለምህንድስና፤ ለንግድ እናም በኮምፒውተር ሳይንስ በዲጂታል ጨዋታዎች በስታቲስቲክ እና በመሳሰሉት እየተጠቀምንበት ይገኛል። በዚህም ሒሳብ እንደ የስድስት ወር የጨረቃ የጊዜ መቁጠሪያየብቸኛ ቁጥሮች የተካታታይነታቸው ስርዐት የክብ 360 ከፍታዎች360 (60 6) የ60 ደቂቃ የአንድ ሰአት አከፋፈል፤የአየር ትንበያ ዘዴ የስፋት ቀመሮች፤ የቃላት እንቆቅልሾች የቁጥሮች ብዜት ሰንጠረዥ ከሂሳባዊ ቅርፆች ጋር ያላቸው ዝምድና እና ከክፍፍሎች ጋር፤ የዜሮ ምልክት እንደ የባዶ ዲጂት ቦታ መያዣ፤ ከግምቶች፤ድግግሞሽ፤ ከማረጋገጫዎች እይታ በመነሳት እርጉጦች ላይ መድረስ ከላይ ወደ ታች በመውረድ የመድረሻ ሀሳብ ላይ መድረስ እነዚህንም በመጠቀም ለጥያቄዎች መልስ ለሚሆኑ ገለፃዎች እና ማረጋጫ እርጉጦቸቸ ላይ መድረስ ችለው በአሁን ጊዜም በልዩ ሁኔታ ቀጥሎል። ሂሳብ እና ማህበረሰቡ በጥቂቱ ከታዋቂ እና የሒሳብን አሰራር ካስፋፉ ሒሳባዉያን መካከልም፡የሳሞሱ ፣የፐርሺያው መሀመድ ኢብን ሙሳ የመጀመሪያው እውነተኛ የሂሳብ ሰው የተባለው ቴልስ ሳሞስ፤ ፕላቶ፤ ኡዋዶከስ፤ አርስቶትል፤ ኢኩሊድ፤ የሳይራከሱ አርኬሚድስ፤ ኤራስተሄንስ፤ ሂፕራከስ፤ ፕቶለሚ፤ ፊቦናኪ፣ ኒዉተን፤ ሌይበንዝ፤ ኡለር፤ ላግራንጀ፤ ላፕላስ፤ ጋዉስ ተጠቃሽ ናቸዉ። -እንደ መላ ምት ከሆነ ፋይታጎራ ስለ ሂሳብ፤ ስለ ቅርፃች፤ ስለ ህዋ ለመማር ወደ ግብፅ ሀገር ቄሶች ጋር ቆይታ አድርጎ ቀጥሎም ፋይታጎሪአን ትምህርት ቤቶችን መስርቶ ነበር፤ የፍልስፍናውም መሰረት ሂሳብ አለማትን ይገዛል የሚል ሆኖ (ሁሉሙ ነገር ቁጥር ነው) ብሎም የሚለውን ቃል መስጠቱ ነው፤ የ90 ዲገሪ አንግል ያለው ሶስት መዐዘን እርጉጥ ታዋቂው ነው፡፡ የግሪኩ የፍልስፍና ሰውም ቴልስ የፒራሚዶችን ከፍታ፤ የመርከቦችን ርቀት ከወደብ፤ ለማወቅ የጂኦሜትሪን ጥበብ የተጠቀመ ሲሆን፤ -ፕላቶ በሂሳብ አለም ውስጥ ጠቃሚ ስው ነው ተብሏል እሱም (መስመር ማለት ውፍረት የሌለው ርዝመት ነው) ብሎ ገልፆል፣ ከ300 ከ.ክ.በ. የኖረው ይህ ሰው የፕላቶኒክ አካዳሚውም በአቴንስ ታዋቂ ነበረ፡፡ አሪስቶትልም ለሂሳብ ዕድገት ሎጂክ ወይንም ስነ አመንክዩ፤ የትክክለኛ አስተሳሰብ የሂሳብ ትርጉሞችን መሠረት የጣለ ነው፡፡ -ኢዩከሊድም በሶስተኛው ክፍለ ዘመን የሂሳብ ትምህርት የምርምር መዐከል በነበረው የአሌክሳንድሪያ ኤለመንትስ( የተባለውን የመማሪያ መፅሀፉን ያስተማረውን እና የፃፈው፤ -አርኬሜደስም የሉልን የስፋት መጠን እና በፓራቦላ ወይንምበእሩብ ክብ ስር የሚኖረውን ስፋት እና የፓይን- የተሻለ የቁጥር መጠን(310/71 310/70 )በማግኘቱ ይታወቀል ከዚህም ጋር ተያይዞ ለአንድ ንጉስ በቀረበለት የመዐድን ጥሬ እቃ ትክክልኝነት ለማረጋገጥ በተጠቀመው የቦያንስ እና የዴንሲቲ ቀመር በአፈ ታሪክ ተያይዞ ይታወቃል፤ -የኒቂያው ሂፓረከስ የትሪግኖሜትሪ ሰንጠረዥንም በማጠናቀሩ ታወቃል የክብን 360 ድግሪ ወይንም ከፍታዎች፤ -ከቻይና ሀገር ውጭ ካሉ ሰዎችም የፓይን ቁጥር በተሸለ የገመተው እንደ ጊዜው ሂሳባውያን ስምምነት መሠረት ከሆነ ነው፤ -የአሌክሳንድሪያዋ ታዋቂ የመጀመሪያዋ ሴት የሂሳብ ሰው ነች እሶም የአባቷን ቤተ-መፅሀፍት ውስጥ ስራ በመተካት በተግባራዊ ሂሳብ ላይ ብዙ መፅሀፍ መፃፍ ችላለች፡፡ -በሂሳባዊ ጥበብ ዘጠኙ ምዕራፎች የተባለው ፅሁፍም ከቻይናዎች ቀደም ካሉ የሂሳብ ፅሁፎች መካከል ናቸው እነዚህም በእርሻ፤ በንግድ፤ በቻይናዎቹ የፓጎዳ ማማዎች፤ በምህንድስና፤ በቅርፆች ጥናት ላይ ባተኮሩ 246 የቃላት እንቆቅልሾችን አካቷል፤ እንዲሁም የቁጥሮች አፃፃፍ እንደ 123 1 (የ100 ምልክት) 2 (የ10 ምልክት) 3) በዚህ መሠረት እናም የቅርንጫፍ ቁጥሮች አሰያየም ተብሎ በአለም ላይ በጊዜው የታወቀውን፤ ሌላም የአራቱ ዋና ዋና አካሎች ውዱ ነፀብራቅ ተብሎ የሚታወቀውንም ሂሳብ ስሌት መልሶችንም -የህንዱ ሱልባ ሱትራ አሰራርም ክብን ለመስራት ልክ ከአንድ እኩል ጎን ካለው አራት መዐዘን አቀራረብን ይከተላል ይህም ሌላኛው የፓይ ቁጥር ግምትን ለማምጣት የተጠቀሙበት ዘዴ ነው፤ ሳይን እና ኮሳይን የሚባሉትም ቃላቶች የመጡት ከሳንስክሪቱ ጂያ እና ኮጂያ ትርጎሜ ነው፡፡ -በእስልምና አገዛዝ በነበሩት እንደ መካከለኛው ምስራቅ፣ሰሜን አፍሪካ፣ የተወሰነው የህንድ ክፍል በኤሺያ በዚህም ጊዜ ከአልጎሪዝም፣ አልጌብራ፣ ጋር የላቲን ቋንቋ ትርጎሜ ምስስል ያለው አል ክዋሪዝምም ብዙ መፅሀፎችን ፅፎል ከነዚህም ውስጥ የማጠናቀቅ እና የማቻቻል ስሌቶች የፅሁፍ ጥንቅር -በመካከለኛው ዘመን አውሮፓም የሂሳብ ጥናት ፍላጎት ነበር፤ ለዚህም ዋናው ምክንያት ስለተፈጥሮ አሰራር ስለሚያስረዳ ነው፣ በፕላቶ እንደተነገረው እና በመፅሀፍ ቅዱስ እንደተጠቀሰውም እግዚአብሄር ሁሉንም በመጠን፣በልክ እና በስፋት እንዲሆን አዘዘ በሚለውም ነበር፡፡ የባህር ሀሳብ የሚባለው የዘመን አቆጣጠር ቀመር በመንበረ እስክንድርያ አስራ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ በነበረው በቅዱስ ድሜጥሮስ እንደተደረሰ ተገልፆል እናም ይህ በኢትዮጵያም በቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሙሁሮች በዘመን መለወጫ የበዓላትን እና የአጽዋማትን ወቅት ለመወሰን እና ለማውጣት ይጠቀሙበታል፡፡ የአይዛክ ኒውተን (የተፈጥሮ ፍልስፍና የሂሳብ መመሪያ- የሚለው መፅኀፉ ሜካኒክስ ለሚባለው የትምህርት ክፍልን ለማስረዳት እንደ ቅመም አገልግሏል፤ የባይኖሚያል እርጉጥም ፅንሰ ሀሳብም የሱ ነው፡፡ የአለን ቱሪንግ ዝና እንደ ሂሳባዊያን የመጣውም የአልጎሪዝሞች እና የስሌቶች ብቃቱ ለኮምፒውተር ባገለገለው መሰረት፤ የቱሪንግ መሳሪያ- በሚባለውም ይታወቃል፡፡ ቤንጃሚን (1731-1806) የተባለውም አፍሪካ አሜሪካዊም በግሉ ባካበተው የ ሂሳብ አስተሳሰብ የፀሀይን ግርዶሽ መከሰቻ እና ሎከስት የሚባሉትን በራሪ ነፍሳት የ17 አመት የህይወት ኡደት ድግግሞሽ መተንበይ ችሎ ነበር፡፡ የጆን ቮን ኒውማን የሂሳብ እውቀቶችም የዲ.ኤን. ኤ. ትንታኔን፤ የኩዋንተም ሜካኒክስ፤ የኢኮኖሚክስ ሂሳብ የመሰሰሉትን ያጠቃልላሉ፡፡ ጆረጅ (1815-1864) ቡሊአን የተባውን የአልጌብራ ክፍል ደርሷል፤ የዳንኤል (1700-1782) ሄይድሮዳይናሚካ የሂሳብ መመሪያ መፅሀፍም በሌሎች የሳይንስ ክፍሎች ጥቅም ላይ ውሏል፤ ሉካ (1445-1517) ጣሊያናዊው የሂሳብ መዝገብ አያያዝ መንገድን በመጥረጉ የአካውንቲንግ ተብሎም ይታወቃል፤ እንግሊዛዊቷም አዳ ላቭሌስም- የአለማችን የመጀመሪያዋ የኮምፒውተር መመሪያ ሰጪ ወይንም ፐሮገራመር ተብላ ትታወቃች፤ ለሬኔ (1596-1650) የካርቴዢያን ኮኦርዲኔት ዘዴ ተሰጥቶታል፡፡
19871
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B6%E1%89%85%E1%88%AB%E1%8C%A0%E1%88%B5
ሶቅራጠስ
ሶቅራጠስ (470 ዓ.ዓ. 399 ዓ.ዓ.) የነበረ ዋና የጥንት ግሪክ ፈላስፋ እና አስተማሪ እንዲሁም የምዕራቡ አለም ፍልስፍና መስራች ነበር። ሶቅራጥስ በግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ ይኖር ነበር። የሶቅራጥስ ጥናት የሰው ልጆች እንዴት ያስባሉ? በሚለው ጥያቄ ላይ ያጠነጠነ ነበር። በሌላ ጎን የሶቅራጠስ ዘዴ የሚባለውን አይነት የምርምር መንገድ በመፍጠሩም ይጠቀሳል። ማለት ከአንድ ጥያቄ ተነሰቶ ወደ ጠለቅ ያለ ጥያቄ በመሻገር ነገሮችን ከስረ መሰረታቸው ለመረዳት መሞከሪያ ዘዴ ሲሆን በዘመኑ እንግዳና የራሱ የፈላስፋው ዋና ፈጠራ ነበር። አንድ ሰው እንዴት ሰናይ (ጥሩ) ሊባል ይቻላል በሚለው ጥያቄም ዙሪያ አስተዋጽዖ በማድረግ የሥነ ምግባር መስራችም ነው። የሶቅራጠስ አስተሳሰብ ዘዴወች ለምዕራቡ አለም ማደግ ባደረጉት አስተዋጽዖ እንዲሁም በፕላቶ እና አሪስጣጣሊስ ሰርጾ የምዕራቡን አለም አስተሳሰብ በመቀየራቸው፣ በአሁኑ ዘመን ይሄ ፈላስፋ የምዕራቡ አለም ፍልስፍና አባት በመባል ይታወቃል። የህይወት ታሪክ ሶቅራጠስ በዘመኑ ምንም አልጻፈም፣ ስለሆነም የህይወት ታሪኩ ብዙ አይታወቅም። ይልቁኑ የርሱ ተማሪወች የነበሩት ፕላቶ እና ዜኖፎን ስለርሱ በመመዝገባቸው አንድ አንድ ነገሮችን ለማወቅ ተችሏል። ፕላቶ በተለይ አስተማሪው ያደረጋቸውን ዋና ዋና ቃለ ምልልሶች በመመዝገቡ የሶቅራጥስ አስተሳሰቦች ከሞላ ጎደል ለቀሪው ትውልድ ተላልፈዋል። ሶቅራጠስን ይጠላ የነበረው የዚያው ዘመን ተውኔት ደራሲ አሪስቶፋነስ በበኩሉ ስለሶቅራጠስ ጉሞቹ የተሰኘ ተውኔት ጽፎ ነበር። በዚህ ተውኔቱ ፈላስፋው እብድ እና የሰወችን ገንዘብ ሆን ብሎ የሚዘርፍ አጭበርባሪ አድርጎ አቅርቦታል። ፕላቶ በበኩሉ አስተማሪው በነጻ ያስተምር እንደንበር ሳይዘግብ አላለፈም። እንደ ፕላቶ ዘገባ፣ የሶቅራጠስ እናት ፌናርት የተሰኘች አዋላጅ ነበረች። ሶቅራጠስ እናቱ ሴቶች ልጅ እንዲወልዱ እንደምትረዳ ሁሉ እርሱ ደግሞ ሰዎች አዳዲስ አሳቦችን እንዲወልዱ ለመርዳት እንደሚሞክር መናገሩ ይጠቀሳል። የሶቅራጠስ አባት ድንጋይ አናጢ የነበረው ሶፍሮኒስከስ እንደነበር ይጠቀሳል። ሶቅራጠስ በዘመኑ ድሃ የነበረ ሲሆን ለዚህ ምክንያቱ ከገንዘብ ይልቅ እውቀት ይበልጣል ብሎ ስለሚያምን ነበር። ሶቅራጠስ ስራ እንደማይሰራና በፍልስፍና ሃሳብና ክርክር ጊዜውን እንደሚያሳልፍ ፕላቶ ዘግቦት ይገኛል። ዛንቲፕ የተሰኘች ከርሱ በዕድሜ በጣም የምታንስ ሴትን አግብቶ ሶስት ልጆች እንደነበሩት ፕላቶ ጽፏል። ሶቅራጠስ ብዙ ጊዜ ወደ ገበያ በመውጣት ውይይት መክፈት ደስታው ነበር። ብዙ ሰወች ስለሚናገረው ነገር ለመስማት ይጓጉ ነበር። ከነዚህ ሰወች መካከል ጥቂት የማይባሉት የራሱ ተማሪወች ሲሆኑ በሚሄድበት ሁሉ እየተከተክሉ ከሚያስተምረው ለመረዳት ይሞክሩ ነበር። እርሱም ሆን ብሎ ከባድ ጥያቄወችን በመጠየቅ ምንም እንደማያውቁ ለማሳየት ይጥር ነበር። ስለሆነም ብዙ ሰወች በሚጓጉት ልክ ይናደዱበት ነበር። ማነው ጠቢቡ? ሶቅራጠስ ይኖርበት የነበረው ዘመን የአቴናኃይል እየተዳከመ በስፓርታ ሊጠቃና ሊወድቅ ባለበት ነበር። ስለሆነም ሶቅራጠስ የአቴናን ውድቀት ለማቆም አቴናን እንደተናዳፊ ዝንብ ያጠቃ ነበር። በዚህ መካከል ነበር የሶቅራጠስ ጓደኛ የሆነው ቼረፎን የደልፊውን ጠንቋይ እንዲህ ሲል የጠየቀው፡ "ከሰወች ልጆች ሁሉ በጥበቡ ከሶቅራጥስ የሚበልጥ አለን?" የጠንቋዩም መል "ማንም ከርሱ የሚበልጥ የለም" የሚል ነበር። ይህ መልስ ለሶቅራጠስ እንቆቅልሽ ነበር፣ ምክንያቱም ሶቅራጠስ በራሱ ምንም ጥበብ እንደሌለው ያምን ነበርና። ስለሆነም የዕንቆቅልሹን ፍቺ ለማግኘት በአቴናውያን ዘንድ አዋቂ ናቸው ሚባሉ ግለሰቦችን፣ ገጣሚወችን፣ ኪነ ጥበበኞችን፣ መሪወችን እየሄደ ጥያቄ መጠየቅ ጀመረ። ከዚህ ተመክሮው እኒህ በህዝቡ ዘንድ አዋቂ የተባሉ ሰወች ምንም እንኳ ለራሳቸው ብዙ የሚያውቁና እና ጠቢብ የሆኑ ቢመስላቸውም ሲመረመሩ ግን እምብዛም የማያውቁና ጥበብ የጎደላቸው መሆኑን አረጋገጠ። ስለሆነም ሶቅራጠስ የጠንቋዩን እንቆቅልሽ እንደፈታ አመነ። በእርሱ አስተያየት ህዝቡ አዋቂ ናቸው የሚላቸው ሰወች ምንም እንኳ ለራሳቸው አዋቂ የሆኑ ቢመስላቸውም፣ ሲፈተኑ ግን አላዋቂ ናቸው። በዚህ ትይዩ ሶቅራጠስ አላዋቂ እና ጥበብም የጎደለው መሆኑን እራሱ ስለሚያውቅ በዚህች ምክንያት እርሱ ከሌሎቹ የተሻለ ሆኖ ተገኘ። በሌላ አነጋገር አለማወቁን ማወቁ ከሌሎቹ በተሻለ ጠቢብ አደረገው። ይህ እንግዴህ የሶቅራጥስ እንቆቅልሽ ተብሎ የሚታወቀው ነው። በአቴናውያዊን ባለስልጣናት ዘንድ ጥላቻ ያስነሳበት ይሄው ጉዳይ ነበር። የሶቅራጠስ ሞት ሶቅራጠስ 70 ዓመት በሞላው ጊዜ የአቴና መንግስት እንዲያዝና ለፍርድ እንዲቀርብ አደረገ። በወቅቱ ሁለት ክሶች ሲቀርቡበት አንደኛው "በትምህርትህ ወጣቱን አበላሽተሃል" የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ለግሪክ ጣዖታት አልተገዛህም" የሚል ነበር። እንደ ፕላቶ ዘገባ ግን ሶቅራጠስ የግሪክ ጣኦታት አምላኪ ነበር። በአንድ አንድ ተመራማርወች ዘንድ የአቴንስ መንግስት ያቀረባቸው ክሶች በውሸት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የሆኖ ሆኖ፣ ክሪቶ የተሰኘው የፈላስፋው ጓደኛ ለጠባቂወቹ ጉቦ በመስጠት እንዲያመልጥ ሁኔታውን አመቻችቶ ነበር። ሶቅራጠስ ግን እምቢ በማለት ቀረ እንጂ አላመለጠም። ሶቅራጠስ ለፍርድ በቀረበ ጊዜ ሰፊ የሆነ የመከላከያ ክርክር በማቅረብ የአቴናን መንግስት ክስ ውድቅ ለማደርግ ሞክሯል። ከዚህ በኋላ ዳኞቹ ምን አይነት ቅጣት እንዲበይኑበት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት፣ ለአቴና ህብረተሰብ ካበረከተው ጥሩ ተግባራቱ አንጻር በቀሪው ዘመኑ ሁሉ ነጻ እራት እንዲያመጡለት ተናገረ። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ወይ በቅጣት እንዲለቀቅ ወይንም ደግሞ እንዲገደል የእጅ ምርጫ አደረገ። ውጤቱም ሶቅራጠስ እንዲገደል የሚል ሆነ። ይሁንና ሶቅራጠስ ሞትን አይፈራም ነበር። ሞቱን ለማስቀረት ይቅርታም ሆነ ሌላ ማባበያ አላቀረበም። በርሱ ሥነ ምግባር መሰረት ላመነበት ነገር እስከመጨረሻ መቆሙ ሰናይ ድርጊት ነበር። ስለሆነም ሄምሎክ የተሰኘ መርዝ ጠጥቶ እንዲሞት ስለታዘዘ፣ መርዙን በመጠጣት አለፈ። የሶቅራጠስ ሃሳቦች ሶቅራጠስ የሰወችን ስህተት ለማሳየት ወደ ኋላ አይልም ነበር። እራሱም እንደማያውቅ ያስተምር ነበር። አለማወቄን አውቃለሁ የሚለው ጥቅስ ከዚህ ፈላስፋ ይመነጫል። ስለሆነም ሶቅራጠስ የዕውቀቱን ድንበር እና ልክ ያውቅ ነበር። ከስነ ምግባር አንጻር ሶቅራጠስ ያምን የነበረው የሰው ልጆች ዕኩይ ተግባር የሚፈጽሙት የተሻለ ነበር ስለማያውቁ ነው። ሶቅራጠስ እንደሚለው "ያልተመረመረ ህይወት ምንም ዋጋ የሌለው ህይወት ነው"። ማለቱ እያንዳንዱ ሰው ስለራሱ ህይወት አላማና ተግባር እንዲመረምር መልካም ነው የሚል ነው። ብዙው ሰው የሚያየውን ነገር ከልብ እንደማይመለከት/እንደማይገነዘብ ያምን ነበር። በተረፈ ሶቅራጠስ ስለ ህይወት ትርጉም እና ስለሰናይ ተግባራት ብዙ ጥይቄወችን በማቅረቡ ይጠቀሳል። እኒህ ጥያቄወች እስከ አሁኑ ዘመን የፍልስፍና ዋና ጥያቄና አነሳሽ ሃሳቦች ናቸው። ከሶቅራጠስ በፊት ፍላስፍና ማለት የሂሳብ ጥያቄወችን ለመመለስ የሚጥርና ስለ ተፈጥሮ አለም ጥያቄወችን የሚያቀርብ ነበር። እርሱ ግን ሥነ እውቀትን ሥነ ምግባርንና ፖለቲካን በመመርመር የፍልስፋናን አድማስ በጣም አስፍቶታል። ስለሆነም የምዕራቡ አለም ፈላስፋ በመባል ይታወቃል። ፈላስፋዎች የግሪክ
41647
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B3%E1%88%8B%E1%89%81%20%E1%88%B3%E1%88%AD%E1%8C%8E%E1%8A%95
ታላቁ ሳርጎን
ታላቁ ሳርጎን (አካድኛ፦ ሻሩ-ኪን «ዕውነተኛ ንጉሥ») ከ2077 እስከ 2064 ዓክልበ. ግድም ድረስ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) የአካድ ንጉሥ ነበረ። የሱመር ነገሥታት ዝርዝር ቅጂዎች ለ56፥ 55 ወይም 54 ዓመታት እንደ ገዛ ቢሉንም፣ በሥነ ቅርስ ከዘመኑ የተገኙት ሰነዶች ለአራት ልዩ ልዩ ዓመቶች ብቻ ተገኝተዋል። ስለዚህ በጣም ረጅም ዘመን እንደ ገዛ አጠራጣሪ ነው። የታወቁት 4 ዓመት ስሞች እንዲህ ናቸው፦ «ሳርጎን ወደ ሲሙሩም የሄደበት ዓመት»፣ «ሳርጎን ኡሩአን ያጠፋበት ዓመት»፣ «ሳርጎን ኤላምን ያጠፋበት ዓመት»፣ እና «ማሪ የጠፋበት ዓመት» ናቸው። ይህ የዓመት ስሞች አቆጣጠር ዘዴ የሚታወቀው በዋናነት ከሳርጎን ዘመን ጀምሮ ነው። ንጉሥ ከመሆኑ በፊት የሳርጎን ትውፊት በተባለው ሱመርኛ ጽላት የአባቱ ስም ላዕቡም ይሰጣል። የነገሥታት ዝርዝር የሳርጎን አባት የአጸድ ጠባቂ እንደ ነበር ይለናል። በኋላ ዘመን (7ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) በአሦርኛ በተጻፈ ትውፊት ዘንድ፣ ሳርጎን «እናቴ ዝቅተኛ ነበረች፤ አባቴንም አላወቅሁም፣ የአባቴም ወንድም በተራራ ይኖራል» ይላል። ግልጽ የሚሆነው ከንጉሣዊ መነሻ አለመሆኑ ነው። የአሦርኛው ሰነድ ደግሞ እንዳለው እናቱ ዲቃላ ማሳደግ ባለመቻሏ በሸምበቆ ቅርጫት ውስጥ በወንዙ ላይ አስቀመጠችውና የመስኖ ቆፋሪ የሆነ ሰው አኪ አገኝቶት አሳደገው። ሳርጎን ያደገበት መንደር «አዙፒራኑ» በኤፍራጥስ ዳር ሲሆን አኪ የአጸዱ ጠባቂ እንዲሆን እንዳስተማረው ይጨምራል። ከተራ ክፍል በመወለዱ ምናልባት ሻሩ-ኪን፥ «ዕውነተኛ ንጉሥ»፥ የልደት ስሙ ሳይሆን ዘውድ ከተጫነው የወሰደው ስያሜ ይሆናል የሚያስቡ ሊቃውንት አሉ። በአካድኛው ስሙ ሻሩ-ኪን ሲሆን «ሳርጎን» የሚለው አጻጻፍ በትንቢተ ኢሳይያስ ሞክሼው የአሦር ንጉሥ 2 ሳርጎን በዕብራይስጡ እንዲህ ስለሚባል ነው። ሱመርኛው የሳርጎን ትውፊት ንጉሥ ከመሆኑ በፊት ያለውን ታሪክ እንዲህ ይሰጣል። ሳርጎን ከኪሽ ንጉሥ ኡር-ዛባባ ሎሌዎች መካከል የቤተ መንግሥት አስረካቢ ሲሆን፣ ንጉሡ ኡር-ዛባባ ሕልምን አይቶ ሳርጎንን የ«ዋንጫ ተሸካሚ» ማዕረግ ሾመው፣ ይህም በመጠጦች (ጠጅ) ሳጥን ላይ ሓላፊነቱን ያለው ማለት ነው። ከዚያ ሳርጎን በራሱ ሕልም ኡር-ዛባባ በደም ወንዝ ውስጥ ሲሰመጥ ያያል። ስለዚህ ኡር-ዛባባ ሰምቶ እጅግ ተቸግሮ ሳርጎንን በተንኮል ለመግደል ያቅዳል። ሳርጎን የንጉሥ ተልዕኮ ሆኖ አንድ መልዕክት በሸክላ ጽላት ለኡሩክ ንጉሥ ሉጋል-ዛገሢ እንዲወስደው ታዘዘ። መልዕክቱ ግን መልዕክተኛውን ስለ መግደል የሚል ልመና ነበር። ሰነዱ ተሰብሮ ከዚያ በኋላ ምን እንደ ሆነ ቢያጣም፣ ሳርጎን የአካድ መንግሥት መሥራች ለመሆን ስለ በቃ ሴራው እንዳልተከናወነ መገመት እንችላለን። የነገሥታት ዝርዝሩና የባቢሎን መቅደስ ዜና መዋዕል (ወይም «የቫይድነር ዜና መዋዕል» የተባለው ጽላት ሳርጎን የኡር-ዛባባ «ዋንጫ ተሸካሚ» በማድረጋቸው ከሱመርኛው ሳርጎን ትውፊት ጋራ ይስማማሉ። ዜና መዋዕሉ እንዲህ አለው፦ ኡር-ዛባባ ዋንጫ ተሸካሚውን ሳርጎንን የመቅደሱን ወይን ጠጅ መሥዋዕት እንዲቀይር አዘዘው። አልቀየረም ግን ለመቅደሱ ቶሎ እንዲሠዋ ጠነቀቀ። ከዚህ በኋላ በአረመኔው ጣኦት ሜሮዳክ ሞገስ የዓለም 4 ሩቦች ግዛት እንዳገኘው በማለት ይጨምራል። ይህ ማለት በኒፑር የነበሩት ቄሳውንት ንጉሥነቱን እንዳዳገፉት ይሆናል። የሳርጎን መንግሥት ስለ ሳርጎን መንግሥት በአካድ የተለያዩ ምንጮች አሉ። የሚከተለው ታላቅ የጽላት መዝገብ ስለ ሳርጎን መንግሥት ብዙ መረጃ ይሰጣል፦ «ሳርጎን የዓለም ንጉሥ ከ9 የአካድ ሥራዊቶች ጋር ኡሩክን አሸነፈ። እርሱ እራሱ ሀምሳ ከንቲቦችንና ንጉሡን ማረከ። በናጉርዛም ደግሞ በውግያ ተዋገና አሸነፈ። እንደገና ለ3ኛ ጊዜ ሁለቱ ተዋጉና እርሱ አሸነፈ። ኡሩክ ከተማ አጠፋ፣ ከዚያም ግድግዶቹን አፈራረሰ። የጦር መሳርያዎቹን ከኡሩካዊው ሰው ጋር አጋጨ፣ ድልም አደረገው። ከሉጋል-ዛገ-ሲ የኡሩክ ንጉሥ ጋር የጦር መሳርያዎቹን አጋጨ፣ ከዚያም ያዘው። በአንገት ብረት ወደ መቅደሱ በር አመጣው። ሳርጎን የአካድ ንጉሥ ከዑር ሰው ጋር የጦር መሳርያዎቹን አጋጨ፣ ድልም አደረገው። ከተማውን አጠፋ፣ ከዚያም ግድግዶቹን አፈራረሰ። የጨረቃ ጣኦት መስጊድ አጠፋ፣ ከዚያም ግድግዶቹን አፈራረሰ። ከላጋሽ እስከ ባሕር ድረስ ያሉትን አገሮች ሁሉ አጠፋቸው፣ መሣሪያዎቹንም በባሕር አጠባቸው። ደግሞ በኡማ ከተማ ላይ በውግያ ድል አደረገ። ለአገሩ ንጉሥ ለሳርጎን ኤንሊል ጠላትን አልሰጠውም። ከላይኛው ባሕር እስከ ታችኛው ባሕር ድረስ ያለውን ግዛት ኤንሊል ሰጠው። በተጨማሪ ከታችኛው ባሕር እስከ ላይኛው ባሕር ድረስ የአካድ ዜጋዎች ብቻ አገረ-ገዥነትን ያዙ። የማሪ ሰው እና የኤላም ሰው በአገሩ ንጉሥ ሳርጎን ፊት ለማገልገል ቆሙ። ያገሩ ንጉሥ ሳርጎን ኪሽን ወደ ቀድሞ ሥፍራዋ መለሳት፤ ከተሞቿም ለእርሱ ጣቢያ ሆነው ተመደቡ። ሳርጎን የዓለም ንጉሥ በ34 ውግያዎች አሸናፊ ሆነ፤ እስከ ባህር ዳርቻ ድረስ የከተሞችን ግድግዶች አፈራረሰ። የሜሉሓ መርከቦች፣ የማጋን መርከቦች፣ የድልሙን መርከቦች በአካድ ወደብ አሠረ። ላይኛው አገራት ተሰጠ፦ ማሪ፣ ያርሙቲ፣ ኤብላ፣ እስከ አርዘ ሊባኖስ ደን፣ እስከ ብር ተራሮች ድረስ። ሳርጎን ኤንሊል ተፎካካሪ ያልፈቀደለት ንጉሥ፣ ቀን በቀን በፊቱ 5400 ሰዎች ዳቦ እንዲበሉ አደረገ። ሳርጎን የዓለም ንጉሥ ኤላምንና ፓራሕሱምን አሸነፈ። የሉሒሻን ልጅ ሂሸፕራሺኒ፥ የኤላምን ንጉሥ፥ ማረከው።» በኋላ ዘመን በተጻፈ ሌላ ሰነድ እንደሚለው የሳርጎን መንግሥት ከላይኛ ባሕር (ሜዲቴራኒያን) ማዶ እስከ አናኪና ካፕታራ (ቆጵሮስና ቀርጤስ) ድረስ፣ ከታችኛው ባሕር (የፋርስ ወሽመጥ) ማዶ እስከ ድልሙንና ማጋን (ባሕሬንና ኦማን) ድረስ ተዘረጋ። ሆኖም ከድልሙን በቀር እነዚህ ፉከራዎች በሌላ ምንጭ አልተገኙምና ኣጠራጣሪ ይሆናሉ። ከሳርጎን በፊት የሱመር ይፋዊ እና መደበኛ ቋንቋ ሱመርኛ ሲሆን፣ በአካድ መንግሥት ከሳርጎን ጀምሮ አካድኛ ይፋዊ ሆነ። ይህ የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ነው። ከዚህ በላይ ለጊዜው በኤላም አካድኛ ይፋዊ ሆኖ እንዳደረገው ይመስላል። የቀድሞ ነገሥታት ዜና መዋዕል 20) ስለ ሳርጎን እንዲህ ይላል፦ «ባሕሩን በምሥራቅ ተሻገረ፣ በ11ኛው ዓመት ምዕራቡን አገር እስከ ሩቅ ጫፉ ድረስ አሸነፈ። በአንድ ሥልጣን ሥር አመጣው፣ ሐውልቶችን በዚያ አቆመ፣ የምዕራቡም ምርኮ በጀልባዎች አዛወረ። የችሎቱ ሹሞች የ10 ሰዓት ቀን እንዲቀመጡ አደረገና የአገራት ወገኖችን በአንድነት ገዛ። ወደ ካዛሉ ገሥግሦ ካዛሉ የፍርስራሽ ቁልል አደረገው፣ የወፍ መሥፈሪያ ቦታ ስንኳ አልቀረም። በኋላ፣ በእርጅናው፣ አገራት ሁሉ እንደገና አመጹና በአካድ ከበቡት። ሳርጎን ለመውጋት ወጥቶ ድል አደረጋቸው። ገለበጣቸው፣ ሰፊ ሥራዊታቸውን በተናቸው። በኋላ፣ ሱባርቱ በመላው ሓያላት ሳርጎንን አጠቃ፣ ወደ ጦሩ ጠራው። ሳርጎን ደፈጣ አዘጋጅቶ በፍጹም ድል አደረጋቸው። ሰፊ ሥራዊታቸውን በተናቸው፣ ንብረታቸውንም ወደ አካድ ላከው። የባቢሎን ጒድጓድ አፈር ቆፍሮ አዲስ ባቢሎን በአካድ ፊት ሠራ። ስላደረገው በደል ታላቅ ጌታ ሜሮዳክ ተቆጥቶ ቤቱን በረሃብ አጠፋ። ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ተገዦቹ አመጹበት፣ ሜሮዳክም በመናወዝ ቀሠፈው።» የቫይድነር ዜና መዋዕል ስለ ሳርጎን ዘመን ተመሳሳይ ታሪክ ይገልጻል፦ «ቤተ መቅደሱን ጠበቀው። በዙፋን የቀመጡት ሁሉ ግብራቸውን ወደ ባቢሎን አመጡ። ነገር ግን ቤል (ሜሮዳክ) የሰጠውን ትዕዛዝ ቸል አለ። ከጒድጓዱ አፈር ቆፍሮ በአካድ ፊት ከተማ ሠራ፣ ስሙንም 'ባቢሎን' አለው። ኤንሊል (ሜሮዳክ) የሰጠውን ትዕዛዝ ለወጠና ሰዎች ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ድረስ (ሳርጎንን) ተቃወሙት። እንቁልፉን አጣ።» ከነዚህ ምንጮች፣ የሱመር ዋና ቤተ መቅደስ ከኒፑር ወደ ባቢሎን አዲስ ሥፍራ ስላዛወረው ሕዝቡና ቄሳውንቱ እንዳመጹበት ይመስላል። ከዚህ ዘመን አስቀድሞ «ባቢሎን» ማለት የኤሪዱ መጠሪያ እንደ ነበር የሚል ማስረጃ አለ። ወደ ምዕራብ ስላደረጉት ዘመቻዎች ሌሎች መዝገቦች ይታወቃሉ። በአንዳንድ ጽላት ዘንድ፣ ሳርጎን የ40 ሺህ ወታደሮች ሠራዊት ነበረው። ከሥራዊቱ ጋር ደብረ አማናን ተሻገረ፣ ወደ አርዘ ሊባኖስ ደን ደረሱ። ወደ ማርዳማን አገር (ከስሜን ጤግሮስ ምዕራብ የነበረ የሑራውያን ክፍላገር) ለመውረር ያቅዳል። ከዚያ አገር የመጣ ተልእኮ ግን እንዲህ ይጠይቃል፦ «በዳርቻው ክፋቶች የሚያድቡበት የአሙሩ አገር አይደለምን?» ነገር ግን ሳርጎን አይመልስም፣ የሲሙሩም ሰዎችና ከብቶች ሁሉ ይዘው ከተማውን አፈራረሰ። ይህ በስሜን መስጴጦምያ የተገኘ የሆራውያን ከተማ-አገር ነበር። አሙሩ እና ሱባርቱ አገሮች እንደ ያዙ ይላል። በኬጥኛ የተጻፈው ግጥም የውግያ ንጉሥ ስለ ሳርጎን ምዕራብ ዘመቻ ነው። ይህ ጽሑፍ በአካድኛ ትርጉም ደግሞ በአሦርና በአማርና ደብዳቤዎች መካከል (በግብጽ) ተገኝቷል። ሳርጎን በጥልቅ በሐቲ አገር (አናቶሊያ) እንደ ዘመተ ይናገራሉ። ጽሁፉ እንደሚተርከው፣ በሐቲ በካነሽ የኖሩት አካዳዊ ነጋዴዎች በቡሩሻንዳ ንጉሥ ኑርዳጋል ስለ ተበደሉ ሳርጎን በሩቅ መንገድ ከሠራዊቱ ጋር መጥቶ ኑርዳጋልን እንዲቀጣው በሚል ልመና ልከው አስረዱት። የኑርዳጋል ሰዎች በጸጥታቸው እየኮሩ ዝም ብሎ የሳርጎን ሥራዊት ደረሰና ቶሎ አሸነፋቸው። ሦስት ዓመት በቡሩሻንዳ ቆይተው የከተማውን ግድግዶች ሰበሩ። በአሦርኛው ሳርጎን ትውፊት እንደሚለው፣ «ለ[...]4 ዓመታት መንግሥቴን ገዛሁት። የጥቁር ራስ ሕዝብ ላይ ገዛሁት፣ ነገሥኩት፤ ታላላቅ ተራሮች በነሐስ መጥረቢያዎች አጠፋሁ። በላይኛ ተራሮች ወጣሁ፣ በታችኛ ተራሮች በኩል ፈነዳሁ። የባሕሩን አገር ሦስት ጊዜ ወረርሁት፣ ድልሙንን ያዝኩ። ወደ ታላቅ ዱር-ኢሉ ወጣሁ። ከኔ በኋላ የሚከበር ማናቸውንም ንጉሥ... የጥቁር ራስ ሕዝብ ላይ ይግዛ፣ ይነግስ። ታላላቅ ተራሮች በነሐስ መጥረቢያዎች ያጥፋቸው፤ በላይኛ ተራሮች ይውጣ፣ በታችኛው ተራሮች በኩል ይፈነዳ፤ የባሕሩን አገር ሦስት ጊዜ ይውረር፤ ድልሙንን ይይዝ፣ ወደ ታላቅ ዱር-ኢሉ ይውጣ።» ቤተሠብ በሳርጎን ዘመን ከተቀረጹ ሰነዶች፣ የሳርጎን ንግሥት ታሽሉልቱም እንደ ነበረች፣ ወንድ ልጆቻቸውም ሪሙሽ፣ ማኒሽቱሹ፣ ሹ-ኤንሊል (ኢባሩም) እና ኢላባኢሽ-ታካል እንደ ነበሩ ይታወቃል። ከነዚህም ሪሙሽና ማኒሽቱሹ በአካድ ዙፋን ተከተሉ። ሴት ልጃቸው ኤንሄዱአና የመቅደሱ ዋና ሴት ካህን ሆና በራስዋ በኩል ዝነኛ የማሕሌት ጸሐፊ ሆነች። ብዙ የጻፈች መዝሙሮች በሥነ ቅርስ ተገኝተዋል። ዋቢ መጽሐፍት የአካድ
52435
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8B%93%E1%89%A3%E1%8B%AD%20%E1%88%8D%E1%8C%85
የዓባይ ልጅ
የዓባይ ልጅ የጣልቃ ገብነት መሳሪያው በኢትዮጵያ እስሌማን [ቃል በገባሁት መሰረት፡ አንድ የሀገራችን ተቋም ታብሌት መረከቡ፤ እንዲሁም በተያያዥ የሚመጣ ስውር አጀንዳ የፅሁፉ ትኩረት ይሆናል። ከተቋሙ አመራሮች ጋር ስለ ስጋቱ በመነጋገራችን ስሙን ባለመጥቀስ አቅርቤዋለሁ። መስሪያ ቤቱ ታብሌቶቹን የተቀበለው የባሰ ከሆነው የፔንታጎን ቅርንጫፍ መሆኑ ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል። ይህ ቅርንጫፍ የሽግግር ኢኒሼቲቭ ቢሮ ይባላል፣ ወይም የሚሉት። የውጭ ተልዕኮ ከሌሎች ዘመናት በተለየ እንዲሆን ባይደን ማዘዛቸው ይታወሳል። ይኸውም በሳማንታ ፓወር እየተመራ ከመቼውም በበለጠ ቀኝ እጅ እንዲሆን ነበር የተደረገው። ለኢትዮጵያው ተቋም ታብሌቶች ያቀረበው አደገኛው ክንፍ ሲሆን በውጭ አገራት እንደ ጦርነት አይነት ቀውስ ሲከሰት የሚቋቋም ነው። ምን ሲያደርግ ነበር? ብለን ስንጠይቅ ምላሹ በምንገምታቸውም በማንገምታቸውም ተንኮሎች የተሞላ ታሪኩን እንሰማለን። ልብ በሉ ስጋተለ የኛው ተቋም ታብሌት ከመቀበሉ በላይ በሶስቱ ክልሎች ካቀረበው የርዳታ ገንዘብ ጋር አብሮ የሚመጣ ጣጣ ነው። መሰል ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ከውጭ አገራት መቀበላችን አይቀሬ ነውና የሳይበር ጥበቃ አቅም መገንባት የመፍትሄ አንዱ ርምጃ ነው። ይሁንና ቁልፍ መረጃዎችና የመረጃ ሰዎች ጋር ልውውጥ የሚያደርግ የአገራችን መስሪያ ቤት ከተቀበለው የታብሌት ርዳታ ከጥቅሙ አሉታዊ ጉዳቱ እጅጉን አሳሳቢ ይሆናል። ከ33 ታብሌቶች ድጋፍ በተጨማሪ ባለፈው አመት የትብብር ስምምነት አድርገው አራት አማካሪዎችን ወጪ ሸፍኖ አስመድቧል። ሰባት ተለማማጅ ባለሙያዎች ቅጥርና የቁሳቁስ ግዢ በአጠቃላይ 100 ሺህ ዶላር/3.8 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉን በድረ ገፁ አስፍሯል። ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ፣ መሳሪያውን እሺ ብሎ የተቀበለው መስሪያ ቤት በመሰል ስጋቶችን በተመለከተ ጥናታዊ ምክረ-ሐሳቦች እንዲያቀርብ የተመሰረተ መሆኑ ነው። ማነው? የዛሬን አያርገውና ጉድ ይፋ የሆነው በአሶሼትድ ፕሬስ የምርመራ ዘገባ ነበር። አሶሼትድ ፕሬስ መረጃውን ደልቶታል፤ ኮፒዎችን ግን ማግኘት ችያለሁ። በወቅቱ ሶስት ጋዜጠኞች በአሜሪካ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ እኛ በዩኤስኤአይዲ በኩል በተከፈተ የሽግግር ተነሳሽነት ቢሮ በሚል ግልጽ ያልሆነ ቢሮ በኩባ የሞባይል ስልኮች ትዊተርን የመሰለ የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያ አላማ ማስፈፀሚያነት ስለማዘጋጀቱ ምርመራ ዘገባው ፀሀይ ላይ አስጥቶት አልፏል። የኩባ ወጣቶች መተግብሪያው በአሜሪካ የስለላ ድርጅቶች እንደሚሾር፣ ግላዊ መረጃቸው እየተቀዳ መሆኑን አልጠረጠሩም ነበር ይላል ዘገባው። በማለት በኩባ ብሄራዊ ወፍ የተሰየመ መተግበሪያ የኩባዊያንን የግል መረጃ ይሰበስባል፣ በሚፈጥሩት መስተጋብርም የፖለቲካ ዝንባሌዎቻቸውን በደረጃ ያስቀምጣል። "የኩባ መንግስትን የሚቃወሙ ባንዶች በ..ኮንሰርቱ ላይ እንዲጫወቱ መፍቀድ ተገቢ ነበር ወይ?" የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው እንደነበር የምርመራ ዘገባው በአብነት ተጠቅሶታል። ስትራቴጂ በወጣቱ የሚወደዱ መረጃዎችን መጀመሪያ ላይ በስፋት በማቅረብ፣ በሂደት የተመዝጋቢውንና የተሳትፎ መጠኑን መገንባት፣ ቀስ በቀስ ደግሞ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ጉዳዮችን በማቅረብ ኋላ ላይም ወደ ፖለቲካዊ ንቅናቄ እንዲገቡ ማነሳሳት ነበር። በዚህም በመንግስትና ህብረተሰቡ መሀል ያለውን የሃይል ሚዛን መናድና በሚፈለገው መንገድ እንደገና ለማዋቀር ያለመ ነበር። እንደ ምርመራ ሪፖርቱ። አብዛኛዎቹ የዩኤስኤአይዲ የጣልቃ ገብነት ፕሮጄክቶች “ሽግግር” ብለው በሚጠሩት ስያሜ በኩል ነው ተፈፃሚ የሚሆኑት። በ1994 የተመሰረተው በራሷ በአሜሪካ ከሚገኙ የባንዳ ኔትወርኮች፣ የልማት ድርጅቶችና “መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት” ተብዬዎች ጋር ውል ገብቷል በሚል ተወግዟል። ጋር ሲሰራ ከሲአይኤ በስተቀር ከየትኛውም የልማት ድርጅቱ ክንፍ ወይም የመንግስት አካል የተነጠለ አካሄድ ያለው ነው። ልዩ የአስተዳደር ዘይቤ ያለውና እንደ የውጭ ዘመቻ በተለየ የተቋቋመ ቢሮ ተደርጎ ሊገለጽ ይችላል። ይህ የአስተዳደር ዘይቤ በኦቲአይ እና በኮንትራክተሩ መካከል በሚኖር ጠንካራ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ይሆናል”። "ዓላማው...የሽግግር ተነሳሽነት ቢሮ (ኦቲአይ) ለአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ አላማ ቀውስ የገባችው ሀገር ውስጥ የሚገኙ አጋሮችን በመርዳት... የሽግግርና የማረጋጊያ ፍላጎቶች ላይ ያነጣጠረ ፈጣን፣ ተለዋዋጭ፣ የአጭር ጊዜ ርዳታ በመስጠት ይሰራል። "በሽግግር፣ በግጭት ወይም ከግጭት ወደ ሰላም እንዲሁም መሰል ወሳኝ የፖለቲካ ክንውኖች ሲከሰቱ የእድል መስኮቱን የሚታወቅበትን የአጭር ጊዜ ፕሮጀክት ይጀምራል። አብዛኛውን ጊዜ እስከ ሶስት አመት የጊዜ ቆይታ ያለው ነው” ወደ አንድ ሀገር ከመግባታቸው በፊት ተከታዮቹን መመዘኛዎች ይጠቀማል፡- አገሪቱ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አስፈላጊ ናት? አሜሪካን የሚጠቅም የእድል መስኮት አለ? የኦቲአይ መሳተፍ ለአሜሪካ ጥቅም የመሳካቱን እድል በከፍተኛ ደረጃ መጨምር ይችላል? ይኸው ቢሮ የመጀመሪያውን መስፈርቱን እንደሚከተለው ያብራራል። አገሪቱ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም ጠቃሚ ናት? ሰብአዊ ርዳታ የሚከፋፈለው በተረጂ መንግስታት ፍላጎት ላይ ብቻ ቢሆንም፣ የሽግግር/ቀውስ ርዳታ የሚመደበው የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲ ዓላማዎችና አንገብጋቢ ጉዳዮች ለማራመድ በማሰብ ነው”። በተጨማሪም ዩኤስኤአይዲ ሰራተኞች ለመሄድ በማይደፍሩባቸው አካባቢዎች ኦቲአይ ልክ እምደ ሲአይኤ ተጎዞ ጉዳዩን ይፈፅማል። ጋር በኮንሰልታንትነት ለመስራት ከፍተኛ የደህንነት ማረጋገጫ የሚጠይቅ ሲሆን ከ"ልማት ድርጅቶች" የሚያደርጋቸው ውሎችም ብዙ ጊዜ ከፔንታጎን "የኮንትራት ደህንነት ምደባ ዝርዝር" የሚል አባሪ የሚሰጣቸው ናቸው። ይህ ጉድ የምርመራ ዘገባ ከተጋለጠ በኋላ በኤፕሪል 8 2014፣ አሜሪካዊው ሴናተር ፓትሪክ ሌሂ ፕሮጀክቱን “ደደብ፣ ደደብ፣ ደደብ” ብለው ነበር የገለፁት። ለማሰተባበል ለሞከረው ስራ ሀላፊ ከሌላኛው ባለስልጣን የተሰጠው ምላሽ “ሁሉንም የዩኤስኤአይዲ ሰራተኞች ሰላይ ብሎ ለመፈረጅ አያስችልም' የተባለው ተራ ማስተባበያ ነው።" ያሉ ሲሆን "በሁሉም ሀገር የተመደቡ ሰራተኞች ለኛ ለሴናተሮች በሚልኩት አንድ አይነት የቅሬታ ኢሜይላቸው 'እንዴት እንዲህ አይነት አደጋ ላይ ይጥሉናል?” ነው የሚሉት.." በማለት ድርጊቱ ድሮም በበጎ የማይነሳውን የአሜሪካ ስም ይበልጥ የሚያጠለሽ ድርጊት ነው..በማለት አፍረንባችኋል ብለዋቸዋል። ተቀጥረው የሚገኙ የሀገራችን ዜጎች ከተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው እየፈለግኩ ተመለከትኳቸው። ምናልባትም እነሱ ሳያውቁት መጠቀሚያ እየተደረጉ ይመስለኛል። ዋናው ነጥብ፣ የዚህ ዋና ኢላማ ታብሌት የተቀበለው ተቋም አይደለም። ለተለያዩ ክልሎች ካቀረበው የቢሊዮን ብሮች የልማትና ስራ ፈጠራ ርዳታ ውስጥ ግማሹ አጀንዳዎችን የሚመለከቱ መሆናቸውን አንብቤያለሁ።
51061
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%89%B5%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%8B%AD%20%E1%88%BD%E1%8C%8D%E1%8C%8D%E1%88%AD%20%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%A5%E1%89%B5
የትግራይ ሽግግር መንግሥት
የትግራይ ሽግግር መንግስት በትግራይ ክልል ስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና በፌደራል መንግሥት መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክኒያት በኢትዮጵያ ፌደሬሽን ም ቤት በይፋ የታወጀ አስተዳደር ነው። ዳራ በመጋቢት 2018 (እ.ኤ.አ.) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሌተናል ኮ ል አብይ አህመድ ለሚመራው መንግስት ስልጣኑን በመስጠት ዘላቂ ሰላም እና ዴሞክራሲን ለማምጣት የታቀደውን ማሻሻያ በመደገፍ ስልጣናቸውን ለቀቁ። አብይ ሁሉንም የክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንድ የተማከለ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ለማገናኘት ሞክሯል በኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) አውራ ፓርቲ የሆነው ህወሃት ፈቃደኛ ባለመሆኑ እና የብልጽግና ፓርቲው ሌሎች ሶስት የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ውህደት ሆኖ ተፈጥሯል። በ2020 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክኒያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለነሐሴ ወር 2020 የታቀደውን የፌዴራል ምርጫ በፌዴሬሽን ምከር ቤት ውሳኔ መሰረት ከኮሮና ስርጭት መቀነስ በኋላ ከስድስት ወይም ዘጣኝ ወር ጊዜ ዝግጅት በኋላ እንድደረግ ላልተወሰነ ጊዜ መርጫውን አስተላልፏል። ነገር ግን የፌዴሬሽን ምክር ቤት በመቃወም የትግራይን ክልል ምርጫ ለማካሄድ የራሱ የሆነ የክልል ምርጫ ቦርድ አቋቋመ። ይህንን ተከትሎ የትግራይ ክልላዊ ምርጫ የተካሄደው መስከረም 9 ቀን 2020 (እ.አ.አ.) ሲሆን ህወሓት ሙሉ መቀመጫ አሸንፍለውም ብሏል። 98.2% ያሸነፈው ህወሃት ነበር። እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2020 የትግራይ ክልል መንግሥት ከፌደራል መንግስት ስር ያሉ ባለስልጣናት ስልጣናቸውን እንዲለቁ እና ወደ ትግራዩ መንግስት እንዲቀላቀሉ አሳስበዋል፤ ይህ ተከትሎ አብዛኞቹ የትግራይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ስልጣናቸውን ለቀዋል። እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2020 የፌደራሉ መንግስት ከትግራይ ክልል ምክር ቤት እና ከክልሉ ከፍተኛ የስራ አስፈፃሚ አካል ጋር ያለውን ማንኛውንም ግንኙነት ለማቆም ወስነ፣ የፌዴሬሽን ምከር ቤት ለክልሉ የበጀት ድጎማዎችን አቋርጧል ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ደብዳቤዎችን እና መረጃዎችን ወደ ትግራይ ከፍተኛ የሥራ አስፈፃሚ አካላት እንዳይልኩ ወይም ለተቋሞቻቸው ድጋፍ እንዳያደርጉ አግዶ ክልሉ በአገር አቀፍ መድረኮች እንዳይሳተፍም ውሳኔ አሳለፈ። የትግራይ መንግስትም ይህንን በክልሉ ላይ ጦርነት የማወጅ መግለጫ አድርጎ ገልፆታል። እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2020 በፌደራል እና በትግራይ ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረው ግጭት ወታደራዊ ግጭት ሆኖ የፌደራል ኃይሎች እስከ ህዳር 2020 መጨረሻ ድረስ ባደረጉት "ሕግ የማሰከበር ዘመቻ" የክልሉን ዋና ከተማ መቐለን ተቆጣጥረዋል። ሕገ-መንግስታዊ አውድ የ1995 ቱ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ “ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ ያለገደብ የተጠበቀ ነው” ይላል። በአንቀፅ 62 ንኡስ አንቀጽ 9 የ1995 ቱ ሕገ መንግሥት ለፌዴሬሽን ምከር ቤት “ማንኛውም ክልል ይህን ህገ መንግሥት በመጣስ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌዴራሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ” የማዘዝ ስልጣን ሰጥቶታል። የሽግግር መንግሥት ፍጥረት ጠ ሚ አብይ አህመድ በመቀሌ አካባቢ ሰፍሮ የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ልዩ ሀይል ጥቃት መሰንዘሩን ህዳር 4 ቀን 2020 ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስመለስ ያለመ ነው ሲል የገለጸውን እርምጃ በመጀመር በትግራይ ክልል ውስጥ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት የክልሉን ገዥ አነሳ፤ ከዚያ የፌዴሬሽን ምከር ቤት መንግሥት በትግራይ ክልል ጣልቃ እንዲገባ ፈቅዶ የትግራይ የሽግግር መንግሥት አቋቋመ። አመራር እና መዋቅር እንደ ጥቅምት 21፣ 2020 (እ.ኤ.አ) የመንግሥት መግለጫ፣ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የትግራይ የሽግግር መንግሥት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ተሹመዋል። እንደ ጥቅምት 28፣ 2020 (እ.ኤ.አ) የአስተዳደሩ አወቃቀር የሚመራው በአምስት ሰዎች ነው። ቦርከና የተባለ የኢትዮጵያ ዜና ጠንቃሪ ዌብሳይት በጥቅምት ወር ማገባደጃ እንደገለጸው የሽግግር መንገስቱን የሚመሩት ትግራዋይ ብቻ ይሆናሉ። የሽግግር መንግስቱ አወቃቀር በዲሴምበር 2020 ተጠናቆ በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚፀድቅ ቻርተር እንደሚተላለፍ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ገልፀዋል። እስከ ህዳር 28 ድረስ ዕቅዱ በክልል ደረጃ እና በዞን ደረጃ አመራር እንዲለወጥ የታቀደ ሲሆን የወረዳና የቀበሌ አስተዳደሮችን ሙሉ በሙሉ ጠብቆ ማቆየት” የሚል ነበር፤ “ተቋማትን ለመምራት የተሾሙ ባለሥልጣናትን መምረጥ” ውስጥ የሕዝብ ምክክርና የሕዝብ ተሳትፎ ታቅዶ ነበር። እ.ኤ.አ. ታህሳስ 15 ቀን 2020 ዓረና ትግራይ የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እና አሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አዴፓ ጨምሮ የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት “በክልሉ ካቢኔ ውስጥ የአመራር ቦታዎች እና በተለያዩ የከፍተኛ ደረጃ ቦታዎች እንደሚሾሙ ሙሉ አስታውቋል፤ የክልል አስተዳደር በዚህ መሠረት የአረና ትግራይ ሊቀመንበር አበራ ደስታ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ አድርጎ ሾመዋል። በታህሳስ 16 ቀን 2020 የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መካኒካል ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል መምህር አሰፋ በቀለ በክልሉ የሽግግር መንግስት የመንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሾሙ። ስልጣናት ሙሉ ነጋ የሽግግር አስተዳደሩ አራት ዋና ዋና ስልጣን እንደሚኖሩት ገልፀዋል የክልል አስፈፃሚ ተቋማትን እንደገና መፍጠር፤ በሕዝብ ምክክር የሚመሩ የክልል እና የዞን አመራሮችን መሾም እንጂ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮችን አለመሾም፤ "ህግና ስርዓትን ማረጋገጥ"፤ የ 2021 የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተደነገገው መሠረት ማካሄድ፤ አስተዳደሩም እንዲሁ በፌዴራል መንግሥት የተሰጣቸውን ሥራዎች “በንቃት [ተግባራዊ ለማድረግ]” ሥልጣን ተሰጥቶታል የተገለሉ ስልጣናት እ.ኤ.አ ጥቅምት 28 ቀን 2020 በ “ራያ ጠለምትና ወልቃይት አከባቢዎች” በታሪካዊ ምክንያቶች የሚጠበቀው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ አለመግባባቶች ከሽግግር አስተዳደሩ ከታቀዱት ኃይሎች እንዲገለሉ ተደርጓል። የግዛት ቁጥጥር ምዕራባዊ ዞን ከኖቬምበር 23 ቀን 2020 ጀምሮ በምዕራባዊ ዞን (ምዕራባዊ ትግራይ) ከቁጥጥር ስር የሆኑ የትግራይ ከተማ ሁመራ ከአማራ ክልል በተውጣጡ ባለስልጣናት እና የፀጥታ ኃይሎች ይተዳደር ነበር፤ እንደ ሁመራ እና ጎሹ ስደተኞች መሠረት ፋኖ የተባለ የአማራ የወጣት ቡድን የሁመራ ፍርድ ቤት መቆጣጠሩን አረጋግጦ ነበር። ሰሜን ምዕራባዊ ዞን ታህሳስ 2፣ 2020 (እ.ኤ.አ) ላይ፣ ዶ/ር ሙሉ እንዳሉት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ስር የሚገኝ ሽሬ እንደ ስላሴ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ቀበሊያት ነዋሪዎች፣ እያንዳንዱ ቀበሌ 20 ተወካይ ያደራጁ ሲሆን እነዚህም አንድ ላይ 25 የወረዳ ምክር ቤት አባላትን ምክር ቤቱ አምስት አባላቱን ካቢኔ አድርጎም ሾሟል። የወረዳው አስተዳዳሪም መመረጣቸውን ዶ/ር ሙሉ ጨምሮ ገልፀዋል። ታህሳስ 15 ቀን ስማቸው ያልተጠቀሰ የመቀሌ ከንቲባ መሾም በሙሉ ተገለፀ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 16 ቀን 2020 (እ.አ.አ.) እ.ኤ.አ. የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ኦፊሴላዊ የፌስ ቡክ ገጽን የጠቀሰው የኢትዮጵያ ቃና ቴሌቪዥን አዲሱ ከንቲባ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህርና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ ናቸው። ደቡባዊ ዞን እ.ኤ.አ. ታህሳስ 16 ቀን 2020 የትግራይ የሽግግር መንግስት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሙሉ ሚሊዮን አበራን የደቡባዊ ዞን ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርገው ሾሙ። እነዚህንም ይመልከቱ የትግራይ ግጭት 2020 በኢትዮጵያ ዋቢ የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር መንግሥታት በኢትዮጵያ የትግራይ
1549
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%8D%E1%89%A5%E1%8D%85
ግብፅ
ግብፅ ወይም ምጽር፣ ምሥር (አረብኛ በሰሜን ምስራቅ ኣፍሪካ የምትገኝ አገር ናት። 77 ሚሊዮን ከሚሆነው ህዝቧ አብዛኛው ከናይል ወንዝ ዳርቻ በአንድ ኪሎሜትር ክልል ውስጥ ይገኛል። የግብፅ አብዛኛው መሬት በሰሃራ በረሃ ክልል ውስጥ ይገኛል። ዋና ከተማዋ ካይሮ ስትሆን ከአፍሪካም ትልቋ ከተማ ናት። ሌላ ትኩረት የሚሰጣት ከተማ አሌክሳንድሪያ (እስክንድርያ) ናት። አሌክሳንድሪያ የአገሪቱ ዋና ወደብ ስትሆን በህዝብ ብዛት ከአገሪቱ ሁለተኛ ናት። ግብፅ በሰሜን ከሜዴቴራኒያን ባሕር በምሥራቅ ከቀይ ባሕር፤ በደቡብ ከኖብያ፤ በምዕራብ ከምድረ በዳው አገር ይዋሰናል። ነጭ አባይ በግብፅ መካከል ያደርግና ከደቡብ ወደ ምሥራቅ ይሄዳል። የአባይ ወንዝ የሚሞላው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። በግብፅ የሚዘንበው አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ስለ ሆነ ግብፅ በአባይ ለምቶ ይኖራል። ግብፅ የመጀመሪያ ቀደምት ስልጣኔ ያላት ሀገር ናት። ከ3000 ዓዓ የተነሳው ጥንታዊ የግብፅ ስልጣኔ፣ በስነ ቅርፅ፣ ኪነጥበብ፣ ምህንድስናና ቴክኖሎጂ የላቀ ሲሆን በቡዙ ስነ ቅሪትና ሳይንሳዊ ምርምር ላይ የዋለ ነው። በተጨማሪም ግብፅ ለሶስት ሺህ አመት በዘውዳዊ ግዛት ስትመራ ነበር። በ3150 ዓዓ ንጉስ ሜኔስ የግብፅ የተዋሀደ ስልጣኔ አስጀመረ። የታላቁ ጊዛው ፒራሚድ በ2600 ዓዓ በአራተኛው የግብዕ ስርወ መንግስት ፈርኦን በነበረው ኩፉ የተገነባ ሲሆን፣ በአለም አንደኛ የሆነ የቱሪስት መስህብነት ያለው ሀውልት ነው። ነገር ግን ይህ ፒራሚድ በወቅቱ የነበሩት የፈርኦኖች ሰይጣንን ማምለኪያ እና መናፍስት የመጥሪያም ሀውልት መሆኑም ይታውቃል። ይህ ሀውልት ለተጓዳኝ የሮማ ወይም የአሁኑ ምዕራብያውያን ስልጣኔ ተረፈ ምርት ሆኖ እያገለገለ ነው። በተጨማሪም የምዕራብያውያን አጋንንታዊ ማምለኪያ ምልክት ሊሆን ችሏል። ኢሉሚናቲ እና አሜሪካ በማህተሟ ላይ በመጠቀም የሚመጣውን ሰይጣናዊው አምባገነናዊው የአለም መንግስት የሚመኙበትን ዘዴ ያሳያል። ግብፅ በጥንት ዘመን የክርስትና ቁንጮ የሆነች ሀገር ነበረች፣ ነገር ግን በ7ተኛው ክፍለ ዘመን እስልምና ሲስፋፋ ወዲያውኑ የእስላም ሀገር ሆናለች። ግብፅ በ1922 ዓም ከእንግሊዝ ቀኝ ግዛት ስትወጣ፣ ከእስራኤል ጋር ብዙ የድንበር ጦርነት አድርጋልች። በ1978 ዓም፣ ግብፅ የጋዛን ግዛት በመተው እስራኤል እንደሀገር እንደሆነች ተገነዘበች። ከዛም በኋላም ግብፅ በብዙ የፓለቲካ አለመረጋጋት አሳልፋለች። ከ2011 ዓም አብዮት ጀምሮ ግብፅ በግማሽ የርዕሰ ብሄር አስተዳደር ትመራለች። የግብፅ ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ ኢል ሲዝ በብዙ ሀያሲያን አምባገነናዊ አመራር እንዳለው ተናግሯል። ግብፅ የክልል ሀያላን የሆነች ሀገር ናት። የግብፅ ህዝቦች ምንም እንኳን ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረባቸው ሀይማኖተኛ ቢሆኑም፣ ከምዕራብያውያን ጋር በመተባበር አዲሱን አምባገነናዊ የአለም መንግስት ለመመስረት እየነደፉበት ይገኛሉ። በተጨማሪም ግብፅ የሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አጠቃላይ ፓለቲካ ለመቆጣጠርና ሀያልነቷን ለማጠናከር ከአሜሪካ ጋር እየሰራችበት ይገኛል። ግብፅ በታሪክ ታዋቂ ጥንታዊ ሀይማኖት የነበራት ሲሆን ይህም ሀይማኖት ከጥንቆላና፣ መናፍስትን ከመሳብ ጋር ተያያዥነት አለው። ስለሆነም የግብፅ ሀይማኖት በምዕራብያውያን ዘንድ እጅግ ተወዳጅነት ያገኘ ሆኗል። ፍሪሜሰንሪ የተባለው ሰይጣናዊው ድርጅት የጥንታዊቷን ግብፅ ስልጣኔ በመጠቀም እንደራሱ ጥበብ በማዋል ታላቋን የሮማ (ምዕራብያውያን) ስልጣኔ አስነስቷል። ይህም ለሚያመጡት አምባገነናዊው የሰይጣን መንግስት ለመመስረት ሲባል ነው። ግብፅ የኒው ወርልድ ኦርደር፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአረብ ሊግ አባል ናት። ታሪክ ጥንታውያን የግብጽ ባለሥልጣኖች በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ከማየ አይኅ ቀጥሎ መጀመሪያ የአፍሪካ ሕዝብ የኖኅ ልጅ የካም ዘሮች ናቸው፤ ይህ አገር ሰናዖር ለሚሉት ቅርብ ስለ ነበር የባብል ግንብ ከተሠራ በኋላ ከዚህ ተነስተው ወደ ግብፅ ወረዱ። የግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት ዋና ጥንታዊ ነው፤ የመሠረተውም ፈርዖን ሜኒስ የተባለው ነው። ጸሓፊው ጊዮርጊስ ስንቄሎስ ዓ.ም. አካባቢ የጻፈው) ይህ ፈርዖን ሜኒስ በዕውነት የካም ልጅ ምጽራይም እንደ ነበረ ገመተ። ዳሩ ግን አባ አውሳብዮስ በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ ዓ.ም. ተጽፎ)፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ ማኔጦን (፫ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከማየ አይህ አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በእስላም ጸሐፊዎች በግብጻዊው እብን አብድ ኤል-ሀከም እና በፋርሳውያን አል-ታባሪና ሙሐመድ ቈንዳሚር መጻሕፍት ሲገኝ፣ ፒራሚዶች፣ እስፊንክስ ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋት ውኃ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ ግን አገሩ ለካም ተወላጅ ለምጽራይም ('ማሣር' ወይም 'መሥር') ተሠጠ ብለው ጻፉ። በግሪኩ ጸሐፊ ሄሮዶቶስ ዘንድ፣ የግብፅ ቀድሞ ዘመን የመጀመሪያው ፈርዖን ሜኒስ ነጭ አባይን ከመነሻው ወደ ጎን መለሰና ውሃው ይፈስበት በነበረው ላይ ሜምፊስ የተባለውን ከተማ ቆረቆረ። ታላቅ ንጉሥም ስለ ነበረ ከሞተ በኋላ ሕዝቡ እንደ አምላክ አድርገው አመለኩት። በዘመናዊ አስተሳስብ፣ ይህ ላይኛ ግብጽና ታችኛ ግብጽ ያዋሐደው መጀመርያው ፈርዖን መታወቂያ ለሥነ ቅርስ ከሚታወቀው ፈርዖን «ናርመር» ከተባለው ጋር አንድ ነው። ናርመር (ሜኒስ) አገሩን ካዋሐደ አስቀድሞ ሌሎችም ነገሥታት (ለምሳሌ ንጉሥ ጊንጥ) በአገሩ ክፍሎች ብቻ ላይ እንደ ነገሡ ከተገኙት ቅርሶች (የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ ወይም የጊንጥ ዱላ እንደሚያሳይ) ይታወቃል። የሃይሮግሊፍ ቅርሶችና መዝገቦች ለማንበብ ችሎታው አሁን ስላለ፣ ሜኒስ ከነገሠ በኋላ የግብፅ ታሪክ በጥቂት መጠን ተገልጾአል። መጀመርያው ሥርወ መንግሥታት (፩ኛው እስከ ፮ኛው ድረስ) የቀድሞ ዘመን መንግሥት ይባላሉ። በ፩ኛው ሥርወ መንግሥት ሰባአዊ መስዋዕት በሰፊ ይደረግ ነበርና ከፈርዖኖቹ ጋራ ብዙ ሎሌዎች አብረው ይቀበሩ ነበር። የሔሩ ወገን በሴት ወገን ላይ ይበረታ ነበር። በ፪ኛው ሥርወ መንግሥት የፈርዖኖች መቃብር ከተማ ከላይኛ ግብጽ ወደ ታችኛ ግብጽ (ስሜኑ) ተዛወረ። በኋለኛ 2ኛው ሥርወ መንግሥት ዘመን የሴት ወገን ወኪል ፈርዖን ፐሪብሰን ተነሣና ያንጊዜ ትግሎች እንደ በዙ ይመስላል። በ፫ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ የሔሩ ወገን ለሥልጣን ተመልሶ፣ ነጨሪኸት የተባለው ፈርዖን የመጀመርያውን ሀረም (ፒራሚድ) አሠራ። ከርሱም በኋላ የተነሡት ታላላቅ ፈርዖኖች በጊዛ ሜዳ ላይ ፒራሚዶቻቸውን እንዲሁም የጊዛ ታላቅ እስፊንክስን ሠሩ። በ፬ኛውም ሥርወ መንግሥት የፈርዖኖች ዝሙት የገዛ እኅቶቻቸውን እስከሚያግቡ ድረስ ደረሰ። በ፭ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ፈርዖኖች በሀረሞቻቸው ውስጥ የሀረም ጽሕፈቶች ያስቀረጹ ጀመር፤ እነኚህ ጽሕፈቶች የሔሩ ተከታዮች ወገን (ወይም «ደቂቃ ሔሩ») በሴት ተከታዮች ወገን ላይ የፈጸሙትን ጨካኝ የጭራቅነት ሥነ ስርዓት ይመሰክራሉ። ይህም አስጨናቂ ሁኔታ በ፮ኛው ሥርወ መንግሥት እየተቀጠለ ፈርዖኖቹ ዓለማቸውን ሁሉ ከነጎረቤቶቻቸውም ጋር በጽናት ይገዙ ነበር። ፮ኛው ሥርወ መንግሥት ከነገሠ በኋላ የግብፅ ታሪክ እጅግ ግልጽ ሆኖ አይታይም። በታሪክ ጸሐፍት እንደ ማኔጦን ዝርዝሮች በኩል፣ ለ፯ኛው-፰ኛው ሥርወ መንግሥታት በርካታ ስሞች ቢመዘገቡም፣ ከጥቂቶቹ ብቻ በስተቀር አንዳችም ሥነ ቅርሳዊ ማስረጃ ከቶ ስላልተገኘላቸው፣ ስሞች ብቻ ቀርተው በእውነት እንደ ኖሩ ወይም ዝም ብለው በማስመስል እንደ ተፈጠሩ አይታወቀም። ከቀድሞውም ዘመን በኋላ በእርግጥኛነት የነገሡት መጀመርያ ፈርዖኖች የግብጽ መካከለኛውን ዘመን መንግሥት የመሠረቱት በስማቸውም ውስጥ «ታ-ዊ» (ሁለቱ አገራት ወይም በዕብራይስጥ ምስራይም) የተባሉት ናቸው። የግሪክ ጸሐፍት አፈ ታሪክ በ6ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ኒቶክሪስ የተባለች ሴት የአገሩ ንግሥት እንደ ሆነች የሄሮዶቶስና የማኔጦን ታሪኮች ይነግራሉ። ሄሮዶቶስ እንደሚለው፣ ወንድሙዋን ግብፆች ስለ ገደሉባት እሷም ልትበቀልለት አሰበች። ለዚሁ ጉዳይ ከመሬት ውስጥ አንድ ታላቅ አዳራሽ አሠራች። ከዚያም ታላቅ ግብር አዘጋጅታ የወንድሙዋን ገዳዮች ወደዚሁ ግብር ጠራቻቸው። የተጠሩትም በግብፅ ግዛት የታወቁ ክቡራን ነበሩ። እንዲሁ ሆኖ ሳለ በድንገት ከውጪ በራሳቸው ላይ ውካታና ፍጅት ጩኸትም ተነሳ። የጥፋት ውሃ አዳራሹን ሰብሮ ገባ። ንግሥት ኒቶክሪስ አስቀድማ የወንዙን ውሃ በሚስጥር ወደ አዳራሹ እንዲገባ አድርጋ ነበርና ውሃው በዚያ ታላቅ ግብር ላይ እንዲለቀቅ አደረገች። በዚያም የገቡ ሁሉ ሰጥመው ቀሩ። ይህ የኒቶክሪስ ታሪክ በሄሮዶቶስም ሆነ በማኔጦን ቢገኝም፣ በዘመናዊ ሥነ ቅርስ አስተያየት ለዘመንዋ ምንም ማስረጃ ስላልተገኘ አሁን እንደ አፈ ታሪካዊ ንግሥት ብቻ ትቆጠራለች። በግሪኮች የታሪክ ጸሐፍት ዘንድ ሌላ ስመ ጥሩ ፈርዖን ሲሶስትሪስ ነበር። ይህ ንጉሥ ዓለምን ለማሸነፍ አስቦ ከግብፅ ሲነሣ የሚሊዮን እኩሌታ የሚሆኑ እግረኛ ወታደሮች፣ ሺህ ፈረሰኞች፤ ሺህ የተሰናዱ ሠረገሎች እንደ ነበሩት ይተረኩ ነበር። ዝና ፈላጊነቱ በክብር ተፈጸመለትና ትልቅ ድል አገኘ። በየሄደበት ስፍራ ሁሉ ከእብነ በረድ የተሠራ ሐውልት አቆመ። የሚመጣው ትውልድ እንዳይረሳው ባቆመው ሐውልት ላይ ጽሕፈት እንዲቀረጽበት አደረገ። በብዝዎቹ ሐውልት ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎአል። «ንጉሠ ነገሥት ሲሶስትሪስ በጦር ሠራዊቱ ኅይሉ ይህን አገር አሸንፎዋል» ነገር ግን ዘመናዊ የታሪክ ጸሓፊዎች እንደዚህ አላደረገም ብለው ይጠራጠራሉ። በማኔጦን ነገሥታት ዝርዝር «ሴሶስትሪስ» የሚባል ፈርዖን በ12ኛው ሥርወ መንግሥት በፈርዖን 3 ሰኑስረት (ሰንዎስረት) ፋንታ ይታያል። ስለዚህ የሴሶስትሪስ አፈ ታሪክ ከሰንዎስረት ትዝታ እንደ ተወረደ ይታመናል። ጵቶልሚዮስና ንግሥት ክሌዎፓትራ ሺሻክ የተባለ የግብፅ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን ስለ ያዛት የሰሎሞን ቤተ መቅደስ በዝብዞ ንዋየ ቅድሳቱን ሁሉ ጠርጉ ወሰደው። አሚኖፌስ የተባለ ስመ ጥሩ የግብፅ ንጉሥ ነበር፤ ይህም ምናልባት ለስሙ መጥሪያ (ለመታሰቢያው) ብሎ አንድ ትልቅ መቅደስና ምስል ያቆመ ሜምኖን የተባለው ንጉሥ ሳይሆን አይቀርም። የዚህም ፍራሽ እስከ ዛሬ በቴቤስ ይታያል። ያቆመውም የድንጋይ ምስል ፀሓይ ስትወጣ ደስ የሚያሰኝ ቃል ፀሓይ ስትጠልቅ የኅዘን ቃል ያሰማል ይባላል። ዛሬም በዚያ የሚያልፉ መንገደኞች ድምፁን የሚሰሙ ይመስላቸዋል። ዓመት ከዘመነ ክርስትና በፊት ካምቢሲስ ንጉሠ ፋርስ ግብፅን ድል አድርጎ ነበረና ሳሜኒቱስ የተባለውን የግብፅን ንጉሥ የወይፈን ደም በግድ ስለ አስጠጣው እንደ መርዝ ሆነበትና በዚሁ ጠንቅ ሞተ። ዓመት ከዘመነ ክርስትና በፊት የመቄዶንያው ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ግብፅን ድል አድርጎት ነበር። በዚህ ስፍራ እስክንድሪያ የተባለ አንድ ስመ ጥሩ ከተማ ሠራ። ይህም ከተማ በዓለም ከታወቁት ከተሞች እጅግ ጥሩ ሆኖ የተሠራና መሰል የሌለው አያል መቶ ዓመት የቆየ ቤተ መንግሥት መሆኑ ታውቆዋል። የጥንቱ ሥራው ፈራርሶ ዛሬ የሚታየው እስክንድሪያ ከጥንቱ በጣም ያነሰ ነው። እስክንድር ሲሞት በዚሁ በእስክንድርያ ተቀበረ። ይኸው ከተማ ስመ ጥሩ በመሆኑ እስከ ዛሬ በግብፅ ዋና የንግድ ሁለተኛ ከተማ ተብሎ ይጠራል። እስክንድር የሱ ጀኔራል የነበረውን ጵቶልሚዎስን አገሩን እንዲገዛ ሾመው። ከጵቶልሚዎስ ጀምሮ ተወላጆቹ ሁሉ የንጉሥ ዘር ተብለው ሁሉም ጵቶልሚዎስ ተብለዋል። ዓመት ገዝተዋል። ከነዚህም በመጨረሻ የነገሠው ጵቶልሚዎስ ዲዮናስዮስ ይባላል። በላዮ የገዛ ሚስቱ ተነሥታ ሸፈተችበትና ተዋጋችው። ጵቶልሚዎስ ዲዮናስዮስ በመጨረሻ ድል ሆነና ለማምለጥ የማይሆንበት ቢሆን በነጭ ዐባይ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ። ሚስቱ ክሌዎፓትራ የተባለች የግብፅ ዋና ገዢ ሆነች። አሉ ተብለው ከሚጠሩት ቆነጃጅት አንዲቱ እርስዋ ነበረች። ስጦታዋና ተፈጥሮዋ ከውበትዋ ጋር የተካከሉ ነበሩ። ዳሩ ግን ክፉ ነበረች። ከሠራችው ሁሉ እጅግ የሚያሰቅቀው ነገር ያሥራ አንድ ዓመት ሕፃን የነበረውን የገዛ ወንድምዋን በመርዝ ማስገደልዋ ነው። ምንም ክፋትዋን ዓለም ቢያውቀው እኔ ነኝ ያለ ጀግና የውበት ማጥመጃዋን ሊቃወም የሚችል አልተገኘም። ማርክ አንቶኒ የተባለ የሮማ ጀኔራል በግሪክ አገር ፊሊጵ በተባለች አውራጃ ብሩተስንና ካሲውስን ድል ባደረገ ጊዜ ከሜዴቴራኒያን ባሕር በሰሜን ምሥራቅ ወደምትሆን ወደ ሲሲሊያ እንድትመጣ ክሌዎፓትራን አስጠራት። ምክንያቱም ለብሩተስ ረድታ ነበርና ሊቀጣት አስቦ ነበር። ክሌዎፓትራ ጥሪው እንደ ደረሳት እሺ ብላ በፍጥነት ተነሥታ በተለይ በወርቅ ባጌጠ ታንኳ ገባች። ታንኳው በሽራው ፈንታ ዋጋው የበዛ የከበረ ሐር ነበረው። ታንኳውን በብር መቅዘፊያ የሚቀዝፉት የተወደዱ ቆነጃጅት ነበሩ። ንግሥት ክሌዎፓትራ ሐር ተጋርዶላት በመርከቡ ተደግፋ ተቀምጣ ነበረች። እንደዚህ ሁና ሲድኑስ በተባለው ወንዝ ተንሳፈፈች። ያለችበትም ታንኳ እጅግ ያማረ ነበር። እርስዋም ራስዋ የተወደደች ነበረች። የሚታየው ሁለመናዋ ሕልም ይመስል ነበር። ከታንኳው መጋረጃ ነፋስ እየጠቀሰ የሚወስደው ሽቶ እያወደ ክሌዎፓትራ እንደ ተቃረበች ማርክ አንቶኒን አስጠነቀቀው። ከሩቅ ልብ የሚነካ የሙዚቃ ድምፅ ይሰማ ነበር። ቀጥሎ የብር መቅዘፊያው ሲብለጨለጭ ከሩቅ ይታይ ነበር። ነገር ግን አንቶኒ የግብፆችን ንግሥት በተመለከተ ጊዜ ምንም አላሰበም። ማርክ አንቶኒ ከክሌዎፓትራ እስኪገናኝ ድረስ ክቡር ሰውና ጀግና መሆኑን አሳየ እንጂ ከዚያ በኋላ ግን ፍጹም እንደ ባሪያዋ ሆነ። ከክሌዎፓትራና ከርሱ ክፉ አካሄድ የተነሣ ኦክታቢዎስ ከተባለ ከሌላ የሮማ ጀኔራል ጋር በግሪክ አገር አክቲውም በተባለች አውራጃ ላይ ተዋግተው አንቶኒ ድል ሆነና በገዛ ሰይፉ ወድቆ ሞተ። ክሌዎፓትራም ኦክታቢዎስ በሕይወትዋ ወደ ሮማ የወሰዳት እንደ ሆነ በሕዝብ መኻከል እንደሚያጋልጣት ተረዳችው። ስለዚህ ለመታገሥ የማይችል ሲሆንባት ጊዜ በግብፅ አገር አንድ ዐይነት በተናከሰ ጊዜ ሕመሙ የማይሰማ መርዛም እባብ ስላለ ክሌዎፓትራ ከንደዚህ ያለ መርዛም እባብ አንዱን አሲዛ አስመጥታ ሰውነቷን አስነከሰች። ትንሽ ቆይታ ሁለመናዋ ደነዘዘ አበጠ ወዲያው ልቡዋ መምታቱን አቆመ። ውበት የነበራት ክፋዩቱ የግብፅ ንግሥት ክሌዎፓትራ እንደዚህ ሆና ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ሞተች። ተከታይ ታሪክ ከንግሥት ክሌዎፓትራ ሞት በኋላ ግብፅ ለሮማ መንግሥት ተገዛና እስከ ዘመነ ክርስትና ዓመት ድረስ የምሥራቅ መንግሥት እየተባለ ለሮማ እንደ ተገዛ ቆየ። ከዚህ በኋላ ሳራሲኖች ድል አደረጉትና እስከ ዓመት ቆየ። የሳራሲን ገዦች ያሠለጠኗቸው ማምሉኮች የተባሉት የገዛ ዘበኞቻቸው ሳራሲኖችን ከዙፋናቸው ዘርጥጠው አወረዷቸው። ቱርክ መጥቶ ድል እስኪያደርጋቸው ድረስ ማምሉኮች ግብፅን እስከ ገዝተዋል። ቱርኮችም ግብፅን እስከ ዓመት ገዝተዋል። ከዚህ በኋላ ናፖሊዮን ቦናፓርቲ አርባ ሺህ የሚሆን የጦር ሠራዊት ከፈረንሳይ አገር አምጥቶ፤ ግብፅን ወረረ። ቱርኮችም ግብፅን ከያዙ ወዲህ ማምሉክ የተባለውን ጭፍራ ወደ ሥራቸው አግብተው ጠብቀውት ነበርና እነዚህ ተስፋ እስኪቆርጡ ድረስ ተከላከሉ። ጦርነቱን የሚዋጉበት ስፍራ በፒራሚዱ አጠገብ ነበር። በዚያ ሲዋጉ ሳሉ እኩሌቶቹ እዚያው ታረዱ። ሌሎቹም እየዘለሉ ወደ ነጭ ዐባይ ወንዝ ባሕር ሰጠሙ። ከዚህ ጦርነነት በኋላ ናፖሊዮን ቶሎ ብሎ ወዲያው ወደ ፈረንሳይ አገር ተመለሰ እንጂ በዚህ አልዘገየም። ሲሄድም ጀኔራል ክሌበር የተባለውን ለፈረንሳይ ጦር ጠቅላይ አድርጎት ሄደ። ጀኔራል ክሌበር ጀግና ሰው ነበር። ዳሩ ግን ጨካኝ ነበርና ጨካኝነቱ ሕይወቱን እስከ ማጣት አደረሰው። ይኸው ጨካኙ ጀኔራል አንድ ቀን ሼህ ሳዳ የሚባል አንድ ሽማግሌ እስላም አገኘና ውስጥ እግሩን በከዘራ አስደበደበው። ወዲያው ትንሽ እንደ ቆየ ጀኔራሉ ወደ መስጊድ ገብቶ ሳለ አንድ የተናደደ እስላም ገሠገሠና በጩቤ ቢሽጥበት ያን ጊዜውኑ ሞተ። በ፲፰፻፩ ዓመት እንግሊዝ ፈርንሳዮችን ከግብፅ ለማስወጣት ከብዙ ጦር ጋራ ሰር ራልፍ አቤሮክሮምቢን ሰደደው። ጀኔራል መኑ የፈረንሳይ ኮማንደር ነበር። አቡኬር ላይ ተዋጉና ሰር ራልፍ አቤሮክሮምቢ ድል አደረገው። ዳሩ ግን እርሱም ራሱ ክፉኛ ቆስሎ ነበር። በዚያው ዓመት የፈርንሳይ ጦር ተሸነፈና ከግብፅ ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ወደ ፈረንሳይ አገር ተመለሰ። ዳሩ ግን ባላገሮቹ ከፊተኞቹ ገዢዎቻቸው ከቱርኮች ይልቅ የፈረንሳይ ጀኔራል ቅን ፍርድ እየፈረደ በመልካም አገዛዝ በደንብና በሕግ ይገዛቸው ነበርና በመሄዱ እጅግ አዝነው ተላቀሱ። የዛሬው የግብፅ ዋና ከተማ ትልቁ ካይሮ ነው። ቀድሞ ከነበረው ይልቅ የዛሬው በጣም ትንሽ ነው። ነገር ግን ሺህ ሰዎች ይኖሩበታል። ባህል የቤት ሥራ አሠራር ዕውቀትና የድንጋይ መውቀር ብልሀት ከሦስትና ከአራት ሺሕ ዓመት በፊት ብዙ ሚሊዮን ሕዝብ እንደ ነበረ እጅግ ለዐይን ያማሩ ታላላቅና ሰፋፊ የነበሩ የከተሞቻቸው ፍራሽ በመገኘታቸው እንረዳለን። በጥንቱም ሆነ ወይም በዛሬው አስተያየት ስንገምተው እጅግ ደምቆ የሚታይ ከተማ እንደ ቴቤስ ያለ አይገኝም። ባለመቶ በር ከተማ ይሉታል። በጦር ጊዜ ከዚህ ከተማ በያንዳንዱ በር የሚወጣው የጦር ሠራዊት እንደሚከተለው ነው። መሣሪያቸው የተሰናዳ ሠረገሎችና ሺሕ ወታደሮች ናቸው። ከ፳፬፻ ዓመት በፊት የነበረ ካምቢሲስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ በነበረበት ዘመን ቴቤስ ፈርሶ ነበር። የከተማው ፍራሽ ከነጭ ዐባይ ወንዝ ግራና ቀኝ ማይል ርቀት ተበታትኖ እስከ ዛሬ ይታያል። ከሐውልቱም ያያሎቹ ውፍረት ጫማ (ፊት) ይሆናል። ከግብፆች ነገሥታት አንደኛው ዙሪያው አርባ አምስት ማይል የሚሆን ትልቅ ጉድጓድ ቆፍራችሁ ወደታች ጥልቅነት ያለው ባሕር ይሁን ብሎ ሕዝቡን አዘዛቸው። አንደኛው ንጉሥ ደግሞ ከመሬት ውስጥ አስቆፍሮ ከዕብነ በረድ የታነጸ ሦስት ሺሕ ጓዳ ያለው አዳራሽ አሠራ። ለዚህም ዘወርዋራ መንገድ ነበረው። ከፍ ባለው ጓዳ አንዲት የተቀደሰች አዞና ግብፆችም የሚያመልኩዋቸው ሌሎች አራዊት ነበሩ። ከምድር በታች ባለው ጓዳ የግብፃውያን ነገሥታት ዐፅም ተጋድሞአል። ደግሞ አንደ የሚያስደንቀው ሥራ መሬቱን ወደ ውስጥ ቆፍረው አለቱ ሲወጣ ያንን ወቅረው የድንጋይ ምሰሶ ያደርጉታል። ውስጥ ለውስጥ ጋሌሪ የደርብ መንገድ እያደረጉ ይሠሩታል። በዚህ ውስጥ ከሺሕ ዓመት በፊት የሞተውን ሰው ሬሳ አጋድመውት ይገኛል። ሳይለወጥ ልክ እንደ ተቀበረ ጊዜ ሆኖ ይታያል። ይህንንም ሙሚስ ይሉታል። የግብፅ ፒራሚድ በነጭ ዐባይ ወንዝ ዳር ይገኛል። ታላቁ ፒራሚድ ከፍታው ጫማ (ፊት) ነው። የግብፅ ፒራሚዶች የተሠሩበትን ዘመን የሠራቸውንም ሰው ማን እንደሆነ ከቶ አይታወቅም። ለመሆኑ ግን ለመቃብራቸውና ለዘለዓለም መታሰቢያ እንዲሆኑዋቸው ጥንታውያን የግብፅ ነገሥታት አሠርተቀቸዋል ይባላል። ነገር ግን ፒራሚዱ ሳይፈርስና ሳይናድ ምንም ብዙ ዘመን ቢቆይ የሠሩት ነገሥታት እነማን እንደ ሆኑ ስማቸው ተረስቷል። በቴቤስ አጠገብ ባንድ ሜዳ ላይ ወንድና ሴት ሆነው የሰው መልክ የሚመስሉ ሁሉ ታላላቅ ሐውልቶች አሉ፤ ቁመታቸውም ጫማ (ፊት) ይሆናል። በግብፆች መኻከል ከሚገኘው ከቀድሞ ሥራ ሁሉ በጣም የሚያስደንቅ ሲፊክስ የሚሉት ነገር ነው። ይኸውም ከታች አካሉ የአንበሳ ሆኖ ከላይ ከራሱ ትልቅ የሴት መልክ ነው። ዛሬ እንደሚታየው ከታች ያለው አካሉ በአሸዋ ውስጥ ተቀብሯል። የላይኛው ክፍል ከምድር በላይ የሚታየው ራሱና አንገቱ ነው። ይኸውም ቁመቱ ጫማ (ፊት) ነው። የተጠረበው ከአለት ድንጋይ ነው። በሩቁ ለተመለከተው ሰው አፍንጫዋ ደፍጣጣ የሆነች ሴት ከአሸዋ ውስጥ ብቅ ያለች ይመስላል። በጥንት ቴቤስ አጠገብ ያለው ሉክሶር የተባለው ከተማ ፍራሽ ለተመልካቹ የሚያስደንቅ ሁኖ ያለመጠን ትልቅ ነው። ከመቅደሶቹ አንዱ የጥንት ሥራ ስመ ጥሩ ይመስላል። ግብፃውያን ይህን የሚያስደንቅ ሥራ ሲሠሩበት በነበሩ ዘመን ከዛሬ ይልቅ የዚያን ጊዜ ብዙ ጥበብ ዐዋቂዎችና የተማሩ ሰዎች እንደነበሩ ይታያል። ጥበባቸውንና ዕውቀታቸው ከፍ ያለ እንደ ነበረ ተመልክተው የሌሎች አገር ሰዎች እንደ አስማተኞች ይገምቱዋቸው ነበር። ግብፆች ልማደ አገር ከንቱ አምልኮት ነበራቸው። ዋናዩቱም ጣዖታቸው ኢሲስ ትባላለች፤ ባልዋም ኦሲሪስ ይባላል። ምስላቸውን ሠርተው ለነዚህ ይሰግዱላቸዋል። ኢሲስ በጣም የተከበረች ጣዖት ናት፤ ሕዝቡም አያሎች መቅደሶች ሠርተውላታል፤ በዚህም ያመልኩዋታል። ግብፅ ስሜን
2049
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A5%E1%88%AB%E1%8B%9A%E1%88%8D
ብራዚል
ብራዚል በደቡብ አሜሪካ በመሬት ስፋትም ሆነ በሕዝብ ብዛት አንደኛዋ ትልቅ አገር ነች። በአለም አንደኛ ቡድን በእግር ኳስ አላት። ስነ-ሕዝብ ቋንቋዎች ይፋዊ ቋንቋ ፖርቱጊዝ ሲሆን መነጋገሪያው ግን በፖርቱጋል ከሚነገረው መደበኛ ፖርቱጊዝ እንደ ቀበሌኛ ትንሽ ይለያል። ከዚያ በቀር ብዙ የጥንታዊ ኗሪዎች ልሳናት የሚችሉ ጎሣዎች ይገኛሉ። አንዳንድ ማህበረሠብ ደግሞ ጀርመንኛን ወይንም ጣልኛን ይናገራል። ሃይማኖት ሃይማኖት በብራዚል (2010) ሃይማኖት መቶኛ ካቶሊካዊነት 64.6% ፕሮቴስታንት 22.2% አግኖስቲስቲዝም ኤቲዝም ሃይማኖት የለውም 8% ሌሎች እምነቶች 3.2% መናፍስታዊ እምነት 2% ሕገ-መንግሥቱ የአምልኮ ነፃነትን እና የቤተክርስቲያን-መገንጠልን የመለያየት ነፃነት ያወጣል ብራዚል በይፋዊ ዓለማዊ መንግስት ያደርገዋል ምንም እንኳን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የበለጠ ልዩ መብት ብትኖራትም ማንኛውንም አይነት የሃይማኖት መቻቻል ይከለክላል.398 ከላይ የተጠቀሰው የካቶሊክ እምነት በአገሪቱ ውስጥ ትልቁ እምነት መሆኑን ነው ስለሆነም ብራዚል በዓለም ውስጥ ትልቁ የካቶሊክ ብዛት አላት እ.ኤ.አ. በ 2010 በተደረገው ቆጠራ መሠረት በብራዚል ውስጥ በጣም ተከታዮች ያሉባቸው ሃይማኖቶች የካቶሊክ እምነት ናቸው ይህም የህዝብ ብዛት 64.6% (123 ሚሊዮን) ይወክላል የፕሮቴስታንት እምነትም በተለያዩ ገጽታዎች (በታሪካዊ እና በ ንጠቆስጤ) በ 22.2 (42.3 ሚሊዮን) እና መናፍስታዊነት 2% (3.8 ሚሊዮን) ተከትለዋል 8% (15.3 ሚሊዮን) ማንኛውንም ሃይማኖት አይከተሉም (ኤቲስት ፕሮሞሽን ፕሮቲኖች ወዘተ) ትምህርት የፌዴራል መንግሥት የክልሎች ወይም የፌዴራል አውራጃ እንዲሁም መዘጋጃ ቤቶች የየራሳቸውን የትምህርት ሥርዓቶች ማስተዳደርና ማደራጀት እንዳለባቸው የፌዴራል ሕገ መንግሥትና የመመሪያ መመሪያዎች እና ብሔራዊ ትምህርት (ኤል.ኤስ.ቢ.) ይወስናል እያንዳንዳቸው እነዚህ የሕዝብ ትምህርት ሥርዓቶች ገንዘብ የሚያመነጭ የራሱ የሆነ የጥገና ሥራ ኃላፊነት አለባቸው አዲሱ ህገ-መንግስት 25% የስቴቱን በጀት እና 18% የፌዴራል ግብር እና የማዘጋጃ ቤት ክፍያዎችን ይይዛል። መረጃ መሠረት እ.ኤ.አ. በ 2007 የመማሪያ ብዛቱ 90% ነበር ይህ ማለት 14.1 ሚሊዮን ብራዚላዊያን ማንበብና መጻፍ አልቻሉም ተግባራዊ ማንበብና መጻፍ ወደ 21.6% አድጓል ከ 6 እስከ 14 ዓመት ባለው ቡድን ውስጥ 97% እና ከ 15 እስከ 17 ዓመት ባለው ሰዎች ውስጥ 82.1% ነበር ዕድሜያቸው ከ 10 ዓመት በላይ ለሆኑት አማካይ የጥናት ጊዜ 6.9 ዓመታት ነበር ከፍተኛ ትምህርት የሚጀምረው ከሁለተኛ ደረጃ በሚመረቅበት ጊዜ ሲሆን በልዩ ልዩ አካዴሚያዊ ወይም ሙያዊ የሥራ መስክ ልዩ ችሎታዎችን ሊሰጡ የሚችሉ አማራጮችን ሊሰጥ ይችላል በትምህርት ቤቱ ላይ በመመርኮዝ ተማሪዎች በድህረ-ምረቃ ኮርሶች ወይም ትምህርታቸውን (ዳራ) ማሻሻል ይችላሉ ከፍተኛ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመከታተል በሕግ መመሪያዎች እና የትምህርት ማዕከላት ሁሉም ደረጃዎች ማጠናቀቅ ግዴታ ነው ተማሪው አካላዊ አእምሯዊ የእይታ ወይም የኦዲት ክፍል ቢሆን ምንም ዓይነት የአካል ጉዳት የማያደርስበት እስከሆነ ድረስ ቅድመ-ትምህርት ቤት መሠረታዊና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያስተምራል ጤና የብራዚል የህዝብ ጤና ስርዓት-ሲቲማ ኒያኒ ዴ ሳኡዴ-በሁሉም የመንግስት ደረጃዎች የሚተዳደር ሲሆን የግል የጤና ሥርዓቶች ደግሞ ተጓዳኝ ሚና ይጫወታሉ የህዝብ ጤና አገልግሎቶች ለሁሉም ብራዚላዊያን እንደሚሰጡ ሁለንተናዊ ናቸው ነዋሪዎችን በነፃ ሆኖም የጤና ማዕከላትና ሆስፒታሎች ግንባታና ጥገና በግብር የተደገፈ በመሆኑ አገሪቱ በየዓመቱ ከ 9 በመቶው ን በጤና ወጭዎች ታወጣለች በ 1000 ነዋሪ ሐኪሞች እና 2.4 የሆስፒታል አልጋዎች እ.ኤ.አ. በ 1988 ሁለንተናዊ የጤና ስርዓት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ የተሻሻሉ መሻሻል ቢኖርም በብራዚል በሕዝባዊ ጤና ላይ አሁንም ብዙ ችግሮች አሉ መፍትሄ ለማግኘት ከ 2006 ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የሕፃናቱ ከፍተኛ መጠን (2.51%) እና የእናቶች ሞት (በ 1000 የወሊድ ሞት 73,7 ሰዎች) ናቸው ተላላፊ ባልሆኑ ተላላፊ በሽታዎች ምክንያት እንደ የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች (151,00 በአንድ 100,000 ነዋሪ ሞት) እና ካንሰር (ከ 100,000 ነዋሪዎች 72.7 ሰዎች ሞት) በብራዚል ህዝብ ጤና ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ በመጨረሻም እንደ አንዳንድ የመኪና አደጋዎች አመፅ እና ራስን ማጥፋትን ያሉ አንዳንድ ውጫዊ ግን መከላከል ምክንያቶች በአገሪቱ ውስጥ ከሞቱት የ 14.9% ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነዋል ባሕል አርት የብራዚል ሥነ ጥበብ ከ 19 ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ በፊት በብራዚል ውስጥ ዋነኛው ዘይቤ በብራዚልነት በዘመናዊነት አገላለፅነት ኪዩቢዝም እስከ ግብረ-ሰዋዊነት ድረስ በተለያዩ ዘይቤዎች ተዳሷል ሆኖም የብራዚል የመጀመሪያዎቹ የጥበብ ምሳሌዎች ከ 15,000 ዓመታት ወዲህ ባለው በሴራ ዴ ካቪቫራ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ዋሻ ሥዕሎች ናቸው እንደ ቅድመ-ሀፓናዊ ጊዜዎች ካሉ ትናንሽ የሴራሚክ እና የድንጋይ ቅርፃ ቅርጾች ብቻ የተወሰዱት ዋና የኪነ ጥበባዊ መግለጫዎች በኋላ በዚህ ደረጃ በተደረጉት ሥዕሎች ቅርፃ ቅርጾች እና ሕንፃዎች መሠረት እንደተመለከተው በብራዚል ሥነጥበብ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ የሥነጥበብ እንቅስቃሴ ባሮክ ነበር ብሄራዊ ነፃነት ከመጀመሩ ጥቂት ቀደም ብሎ የኪነ-ጥበባዊ ኢምፔሪያል አካዳሚ ተመሠረተ ከአስርተ ዓመታት በኋላ በሀገሪቱ ውስጥ የ 19 ኛው ክፍለዘመን ዋና የኪነ-ጥበብ እንቅስቃሴ ብቅ እያለ የብራዚል ሮማንቲዝም በዚህ ወቅት የአካዳሚክ ጥበብ ወደ “ወርቃማ ዘመን” ደርሷል እንደ ቪክቶር ሜይለሌስ እና ፔድሮ አሜሪክ ተወካዮች ከአውሮፓ አቻው የሚለዩት እንቅስቃሴዎችን በመፍጠር እንቅስቃሴን ከፈጠሩ እ.ኤ.አ. በ 1922 “ዘመናዊው የጥበብ ሳምንት” ተካሄደ ሳኦ ፓውሎ ውስጥ የብራዚላዊው ዘመናዊነት መጀመሪያ ምልክት የሆነ ክስተት እንደ አኒታ ማልፋቲቲ ታርላሻ አምባ አማኤል ኤሚሊኖ ዲ ካልቫካናቲ ቪሲቴ ዶ ሬጎ ሞንቴሮ ቪክቶር ሲንዲዶ ፖርትዋንሪ እና ኦስካር ኒየሜር ያሉ አርቲስቶች በተመሳሳይ ጊዜ በብራዚል ውስጥ የኪነጥበብ ጥበባት እድገትና እድገትን እንደረዱት ብራዚል ካቴድራል በብራዚል የሥነ ሕንፃ ኦስካር ኒዬየር የተነደፈው እ.ኤ.አ. በ 1987 የዓለም ቅርስ ጣቢያ መሆኑ ተገለጸ በአገሪቱ ታሪክ ውስጥ ከታዩት እጅግ ግዙፍ ወንበዴዎች አንዱ የሆነው ዕረፍቱ የብራዚል ሲኒማ ሥነ ጥበብ በ 19 ኛው መቶ ዘመን መገባደጃ ላይ እንደ ገና የተወለደ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለምርትዎቻቸው አዲስ ዓለም አቀፍ ዕውቅና እየሰፋ ነበር በርካታ የብራዚል ፊልሞች የአለምአቀፍ ሃያሲያን ዕውቅና ያገኙ እና በምድባቸው ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሽልማቶችን አግኝተዋል ለምሳሌ ኒኒስ (በዮሴ ፓዳልታ) ቲማቲሞች መሠረት በአሜሪካ ውስጥ ምርጥ ግምገማዎች ያለው የውጭ ፊልም ነው የ ተስፋ ሰጪዎች (በ በካኒስ ፊልም ፌስቲቫል የፓልሜ ዲ ኦርን አሸነፈ። ኒዲድ ደ ዲዮስ (በፈርሬስ ሜየርሌል) ታይምስ መጽሔት ከተመረጡት 100 ምርጥ ፊልሞች መካከል አንዱ ሆኖ ተመረጠ። በተቃራኒው ምንም እንኳን ቲያትር ከቅኝ ግዛት ዘመን ጀምሮ በጄይስቶቹ ወደ አገሪቱ ያስተዋወቀ ቢሆንም ይህ ጥበብ እስከ 19 ኛው ክፍለዘመን ድረስ በብራዚል ህዝብ ዘንድ ፍላጎት አልፈጠረም ሆኖም በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን አምባገነናዊ አገዛዞች ውስጥ ቲያትሩ በመንግሥት ሳንሱር ቁጥጥር ስር የነበረ ሲሆን በአገሪቱ ውስጥ ሊታዩ የሚችሉትን የሥራ ዓይነቶች እና ዓይነቶች ይገድባል በመጨረሻው የወታደራዊ ስርዓት ውድቀት ወቅት በርካታ ብራዚላዊያን ተዋናዮች እንደ ጌራል ቶማስ ኡልሲስ ክሩዝ ወዘተ የመሳሰሉትን በሚሰማሩበት መስክ በዓለም ዙሪያ ጎልቶ ወጥተዋል የብራዚል ሙዚቃ በአፍሪካ በአውሮፓ እና በአሜሪኒያን ቅር ች ተፅእኖ ያላቸውን የተለያዩ የክልል ዘይቤዎችን ይ ል ከጊዜ በኋላ ሳባ ብራዚላዊ ዝነኛ ሙዚቃ ቾሮ ሴርታንጆ ቢርጋ ፎሮ ፣ ማራካታ ቦሳ ኖቫ የብራዚል ዓለት እና አዜኤልን ጨምሮ በብዙ የተለያዩ ዓይነቶች ውስጥ ብሔራዊ ሙዚቃ ተፈልሷል አንቶኒዮ ካርሎስ ኢዮብም ሄሪ እና በውጭ አገር በጣም የታወቁ ሙዚቀኞች በመሆናቸው የዓለም አቀፋዊ ዕውቅና አግኝተዋል የብራዚል ሥነ ጽሑፍ የተጀመረው በ 16 ኛው ክፍለዘመን ብራዚል ከተገኘ በኋላ በዬይቶች ከተበረታቱት የስነፅሁፍ እንቅስቃሴ የተነሱ ናቸው፡፡በመጀመሪያው ጊዜ ከፖርቹጋላዊ ሥነ ጽሑፍ ጋር የተቆራኘ ቢሆንም የነፃነት ጊዜ እና እስከ ምዕተ ዓመቱ ድረስ ነበር እንደ ሮማንቲሲዝም እና እውነታዊነት ባሉ እንቅስቃሴዎች ተጽዕኖ ነበር የብራዚል ሥነ ጽሑፍ እ.ኤ.አ. በ 1922 ከሌሎች ሀገራት ስራዎች ጋር የተጣራ ዕረፍትን ያሳለፈውን የዘመናዊ ስነ-ጥበባት ሳምንት (እ.አ.አ.) የራሱ የሆነ ትምህርት ቤቶቻቸውን ወደ ዘመናዊው እና የመጀመሪያዎቹ ትውልዶቻቸው እንዲመሰረት መጣ በእውነት ነፃ አውጪ ፀሐፊዎች። እንደ ማኑዌል ባንደራ ካርሎስ ዶርሞንድ ደ አንድሬስ ጆዋ ጉዋማዌስ ሮሳ ክላሲስ ሊሴሰር እና ሴሲሊያ ሜይሌስ ያሉ በርካታ ታዋቂ ብራዚላዊ ጸሐፊዎች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የተገኙ ናቸው። ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የብራዚል ሳይንሳዊ ምርት የተጀመረው በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹ አስርት ዓመታት ውስጥ ሲሆን በፖርቱጋል ልዑል ገዥ ጁዋን ስድስተኛ የሚመራው የንጉሣዊው ቤተሰብ እና የፖርቹጋላዊው መኳንንት በሪዮ ዲ ጃኔሮ የፖርቹጋልን ናፖሊዮን ጦር ወረራ በመሸሽ በደረሰ ጊዜ ነበር እስከዚያ ጊዜ ድረስ ብራዚል ዩኒቨርሲቲዎች ወይም ሳይንሳዊ ድርጅቶች በሌሉበት የፖርቹጋላዊ ቅኝ ግዛት ነበረች ከስፔን ግዛት የአሜሪካ ቅኝ ግዛቶች በተቃራኒ ምንም እንኳን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ማንበብና መጻፍ ያልቻሉ ሰዎች ቢኖሩም ከ 16 ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ነበረው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ልማት ብሔራዊ ምክር ቤት (ሲ.ሲ.ፒ.) የሳይንሳዊ እና የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎችን እድገትና እድገትን የመመራት የማስተዳደር እና የማስፋፋት የመንግስት ኤጀንሲ ነው ።30 ነገር ግን በብራዚል የቴክኖሎጂ ምርምር በአብዛኛው የሚከናወነው በ የሕዝብ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ተቋማት ከታወቁት የብራዚል ቴክኖሎጅያዊ ልማት ማዕከላት መካከል ኦስዋርዶ ክሩዝ ፣ የአየር ማቀፊያ ቴክኖሎጂ አጠቃላይ ትዕዛዝ እቴሬዛ ብራናርራራ ደ ፓስሲሳ አግሮፔኩሲያ እና ተቋማት ናቸው ብራዚል በላቲን አሜሪካ ውስጥ ለማስነሻ ተሽከርካሪዎች እና ሳተላይቶች ለማምረት ትልቅ ሀብትን ስለሚመደብ በላቲን አሜሪካ ውስጥ በጣም ከተሻሻሉ የቦታ ፕሮግራሞች አንዱ ነው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 14 ቀን 1997 የብራዚል የጠፈር ኤጄንሲ ክፍሎቹን ለማቅረብ ከናሳ ጋር ስምምነት ተፈራረመ ይህ ስምምነት በሶዩዝ ተሽከርካሪ ላይ ለነበረው ማርኮ ፖንቴስ በማርች 2006 ፕላኔቷን ለመዞር የመጀመሪያዋ የብራዚል ተመራማሪ እንድትሆን የሚያስችል አጋጣሚ ፈጠረ ብሔራዊ ካንቺቶሮን ብርሃን ላብራቶሪ በካምፓስሳ ሳኦ ፓውሎ እስከአሁንም ድረስ በላቲን አሜሪካ ውስጥ ብቸኛው የመቧጠጫ ፍጥነት ያለው ብቸኛው ሰው ነው በሪዮ ዴ ጄኔሮ ግዛት ሬ ዴኑ የኑክሌር ነዳጅ ፋብሪካ የበለፀገው ዩራኒየም የሀገሪቱን የኃይል ፍላጎት ያሟላል ለአገሪቱ የመጀመሪያ የኑክሌር ባህር ሰርጓጅ ግንባታ እቅዶች አሉ፡፡ብራዚል እንዲሁ ከሦስት የላቲን አሜሪካ አገራት አን ናት ብራዚል እንዲሁ እንደ አባቶች ሮቤርቶ ላሊ ዴ ሞራ እና ፍራንሲስ ጆአኦ ዴ ዶ አልቤርቶ ሳንቶስ ዱምቦንግ ኮሎራ ሰል ማርዮ ንበርግ ዮሴ ሊዬስ ሎፔስ ሊዮፖልድ ፓውሎ ሪቢቦይም ካሳ ላቲስ አንድሪያ ል ኔሊዮ ጆሴ ኒኮላይ ኔልሰን ቤርዲን ቫል ብሬል ካርሎስ ቻግስ ኦስዋዋሮ ክሩዝ ሄሪኬክ ዴ ሮቻ ሊማ ሞሪኮዮ ሮቻ ኢ ሲልቫ እና ዩሪሲሊሌስ ዘሪቢኒ ናቸው። የጨጓራ በሽታ የብራዚል ምግብ የአገሬው ተወላጅ እና የስደተኛ ሕዝብ ድብልቅን የሚያንፀባርቅ ከክልል ወደ ክልል በጣም ይለያያል ይህ የክልላዊ ልዩነቶችን ጠብቆ ለማቆየት ብሔራዊ ን ገል ል ከእነዚህ መካከል በጣም ጥሩ ከሆኑት መካከል ብሄራዊ ምግብ ነው ፣ እና ብራዚል እንደ ብጊጋሬሮ እና ቤይጂንሆ ያሉ ብዙ የተለያዩ ጣፋጮች አሏት ብሄራዊ መጠጦች ቡናማ እና ካካዋ ናቸው በመጀመሪያ ከብራዚል የመጣ ሩቅ መጠጥ ይህ መጠጥ ከስኳር ዘንግ ይርቃል እናም የብሔራዊ ኮክቴል የካያፊሪንሃ ዋና ንጥረ ነገር ነው። የተለያዩ ምግቦች ቢኖሩም አንድ የተለመደው የብራዚል ምግብ ከበቆሎ ጋር ከበሰለ ባቄላ ጋር የበሬ ወይም የአሳማ ሥጋ እንዲሁም ሰላጣ ወይንም የተቀቀለ ወይንም የተጠበሰ እንቁላል የፈረንሣይ ፍሬዎች ወይም ከፋራ የተሰራ ዱቄት ካሳቫ እና ጨው ያለበት ሲሆን በመሠረቱ እሱ ኦርጋንኖ የተጠበሰ ሽንኩርት እና የተጠበሰ በርሜል ሊኖረው ይችላል፡፡በአብዛኛው ክልል ውስጥ ለሚኖረው ሞቃታማ የአየር ጠባይ ምስጋና ይግባቸው እንደ ‹ማንጎ› ያሉ በርካታ ፍራፍሬዎች ይበቅላሉ ፣ ፓፓያ አራኪ ኩባያ ብርቱካናማ ኮኮዋ ፣ ጉዋቫ የፍሬ ፍራፍሬ እና አናናስ። ከእነዚህ ፍራፍሬዎች ሁሉ ጭማቂዎች እና ቅመማ ቅመሞች ለቾኮሌት ለሻማ ለ አይስክሬም እና ለሌሎች ጣውላዎች ለማምረት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡በኢንዱስትሪ በበለፀጉ አገራት ሁሉ ፈጣን ምግብ የሚሰጡ ብዙ ኩባንያዎች መገኘታቸው እየጨመረ ነው በተለይም በከተሞች ውስጥ የብራዚል ህዝብ አመጋገብ እና የአመጋገብ ስርዓት ለውጦችን ያስከትላል ፓውሎ ሪቢቦይም ካሳ ላቲስ አንድሪያ ል ኔሊዮ ጆሴ ኒኮላይ ኔልሰን ቤርዲን ቫል ብሬል ካርሎስ ቻግስ ኦስዋዋሮ ክሩዝ ሄሪኬክ ዴ ሮቻ ሊማ ሞሪኮዮ ሮቻ ኢ ሲልቫ እና ዩሪሲሊሌስ ዘሪቢኒ ናቸው። ስፖርት ኗሪዎቹ ለእግር ኳስ ያላቸው ፍቅር አይበለጠም። ብዙ ሚሊዮን አድናቂዎች አሉት። የማወቅ ጉጉቶች ሊግ ኦፍ አፈ ታሪክ ተጫዋቾች ከህዝብ ቦታዎች በህጋዊ መንገድ ታግደዋል።
10170
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%93%E1%8D%84%20%E1%89%B4%E1%8B%8E%E1%8B%B5%E1%88%AE%E1%88%B5
ዓፄ ቴዎድሮስ
ጀግናዉ ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ (ጥር ቀን ዓ.ም. ሚያዝያ ቀን፲፰፻፷ ዓ.ም.) ከ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታችው ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። በትውልድ ስማቸው ካሳ ኀይሉ ሲባሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳ እና እንዲሁም አንድ ለናቱ ተብለው የሚታወቁ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ወታደርና ፖለቲከኛ ነበሩ። ቴዎድሮስ ጥር ቀን ዓ.ም. ሻርጌ በተባለ ቦታ ቋራ ውስጥ፣ ከጎንደር ከተማበስተ ምዕራብ ተወለዱ። የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት-ዘመነ መሳፍንት በሚባለው ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ። ዓፄ ቴዎድሮስ በህጻንነታቸው የቄስ ትምህርት ከቀሰሙ በኋላ፣ የአጎታቸውንና በኋላም ለጥቂት ጊዜ የጎጃሙን ጦር መሪ የጎሹ ዘውዴን ጦር ተቀላቀሉ። በዚሁ የውትድርና ዘመናቸው ከፍተኛ ችሎታን ማስመዝገብ ስለጀመሩና ዝናቸው ስለተስፋፋ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. በወይዘሮ መነን ሊበን አምዴ አነሳሽነት የልጇን የራስ አሊ አሉላን ልጅ፣ ተዋበች አሊን ተዳሩ፤ እንዲሁም በደጃዝማችነት ማዕረግ የቋራ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ። ቴዎድሮስ ግን በ፲፰፻፵፬ ዓ.ም. አጠቃላይ የዘመነ መሳፍንት ሥርዓትን በመቃወም በሰሜናዊ ባላባቶች ላይ ዘመቻ ጀመሩ። በኒህ ተከታታይ ዘመቻወች የገጠሟቸውን ባላባቶች ስላሸነፉ፣ መጀመሪያ የራስ ማዕረግን በኋላም የንጉሥ ማዕረግን በአንድ ዓመት ውስጥ ተቀዳጁ። በየጊዜው በሚያደርጉት የተሳካ ዘመቻ የዘመኑን ባላባቶች ኃይል በመሰባበር የካቲት ቀን ዓ.ም ንጉሥ ካሳ ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆኑ። ሥርዓተ ንግሡ የዘመነ መሳፍንት መቃብር በመሆን የዘመናዊ ኢትዮጵያን ታሪክ "ሀ" በማለት ጀመረ። ዓፄ ኃይለ ስላሴ እስከ ፈጸሙት ድረስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ሥራም በዚሁ ወቅት ተጀመረ። ዓፄ ቴዎድሮስ ሰሜናዊ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አንድ ለማድረግ የሞከሩት፣ አጠቃላይ በታሪክ የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ክፍል ነበር ለዚህም ዋቢ ወደ ወሎና ወደ ሸዋ ያደረጓቸው ዘመቻወች ይጠቀሳሉ። በዘመነ ንግሣቸው ዓፄ ቴዎድሮስ አገሪቱን የሚያሻሽሉ ሥርዓቶችን ለአገራቸው አስተዋውቀዋል። ከነዚህም ውስጥ፡ ባርነትን የሚያግድ አዋጅ፣ የመጀመሪያው መንገድ ግንባታ፣ የሥርዓተ ንዋይና የፖለቲካ ሥርዓቱን በማዕከላዊ መንገድ ማዋቀር፣ የባላባት የተከፋፈለ "ሁሉ-በሁሉ-ጦርነት ሥርዓት"ን በማስቀረት ብሔራዊ ውትድርናን ማስተዋወቅ ይጠቀሳሉ። በዘመነ መሳፍንት እንደልባቸው ይፈልጡ ይቆርጡ በነበሩ ባላባቶች ዘንድ እኒህ ለውጦች እጅግ የተጠሉ ሆኑ። በ፲፰፻፶ ዓ.ም. ብዙወቹ ባላባቶች አመጽ ማነሳሳት ጀመሩ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም ንጉሠ ነገሥቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርስት የነበረውን መሬት ለገበሬወች በማከፋፈላቸው ከሃይማኖት መሪወች ጋር ተጣሉ። ይህን ተከተሎ በየቦታው አመጽ በሚነሳበት መካከል አውሮፓውያን ሚሲዮኖችም ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር በተነሳሳ አለመግባባት ምክንያት በዓፄው ታሰሩ። በመጋቢት ወር ዓ.ም ላይ የእንግሊዝ መንግሥት በሮበርት ናፒየር የሚመራ፣ በጊዜው እጅግ ግዙፍ የተባለ ኃይልን አሰናድቶ አውሮፓውያን እስረኞችን ለማስፈታት ጦር ላከ። መጋቢት ቀን ዓ.ም ይህ ጦር በመቅደላ ምሽግ ላይ በሚገኘው፣ በአመጽ በተዳከመ የንጉሱ ጦር ላይ ጥቃት አደረሰ። በውጊያው መሃል ንጉሠ ነገሥቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁ እስከመጨረሻው አሻፈረኝ በማለት በሽጉጣቸው እራሳቸውን ገድለው በጀግንነት አለፉ። ዓፄ ቴዎድሮስ ያሰቡትን ለውጦች በሙሉ በተግባር ቢፈጽሙ ኖሮ በእርግጥም ታላቅና የሰለጠነ ሀገር መሪ ሊሆኑ ይችሉ እንደነበር ታሪክ ተመራማሪወች ይስማማሉ። ዕቅዳቸው በዚህ መልኩ ቢሰናከልም፣ እጅግ ድንቅ መሪ፣ የተዋጣላቸው ወታደርና የተባበረች ዘመናዊ አገር ራዕይ አብሳሪ እንደነበሩ ያሰሯቸው አውሮጳውያን ሳይቀር ሳይመሰክሩ አላለፉም። የዙፋን ስማቸው «ቴዎድሮስ»ን የወሰዱት ከፍካሬ ኢየሱስ ከተገኘ ትንቢት ነበረ። በዚያው ትንቢት በኩል፣ በዓለም መጨረሻው ክፍለ ዘመን፣ ተወዳጁ፣ የጥንቱ ዘመን ንጉስ ቀዳማዊ ቴዎድሮስ እንደገና ተነስቶ አገሪቱን ለ፵ ዓመታት ይገዛል የሚል ነበር። "ቴዎድሮስ" የሚለው ስም ከግሪክ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም «ጤዎስ ዶሮስ»፣ 'የአምላክ ስጦታ' ማለት ነው። ታሪክ ዓጼ ቴወድሮስ የቋራ አስተዳዳሪ የነበሩት ደጃዝማች ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ጊዮርጊስ (ባጭሩ ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ) ልጅ ናቸው። እናታቸው ወይዘሮ አትጠገብ ወንድበወሰን ሲባሉ አመጣጣቸውም ከጎንደር ከተማ ባላባቶች ነበር። የወይዘሮ አትጠገብ እናት ወይዘሮ ትሻል ስትባል የበጌምድር ክፍል መሳፍንት ዘር ነበረች፣ በአባቷ በኩል አያቷ ራስ ወዳጆ በዘመናቸው ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ባላባት ነበሩ። የወይዘሮ አትጠገብ ድህነት በታሪክ መጻህፍት በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ቢሆንም አመጣጡ እንዲህ ነበር፡ የህጻኑ ቴወድሮስ አባት ደጃች ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ከሱዳኖች ጋር በተነሳ ጦርነት በጀግንነት ሲወድቁ እናት ገና ሁለት አመት የሆነውን ልጇን ይዛ ከቋራ ወደ ጎንደር ከተማ ሄደች። በዚህ ወቅት ሁለተኛ ላታገባ በመቁረብ ልጇን ብቻዋን ማሳደግ ግድ አላት። አንዳንዶች በዚህ ምክንያት እራሷን ለማስተዳደር ኮሶ ትሸጥ ነበር ሲሉ ጸሃፊው ጳውሎስ ኞኞ ወይዘሮ አትጠገብ መቼውንም ኮሶ አትሸጥም ነበር ይላል (ኮሶ ትሸጥ ነበር የሚለው የልጁ ጠላቶች ፈጠራ ወሬ ነበር በማለት ያስረዳል)። ሆኖም ቀረ ህጻኑ ቴወድሮስ በድህነት እንዳላደገ ሁሉም የታሪክ ጸሃፊያን ይስማማሉ።አንድ ለናቱ ቴወድሮስ በእናቱ በኩል እህትም ሆነ ወንድም አልነበረውም። የወደፊቱ አጼ ቴዎድሮስ በ፲፰፻፴፱ ዓ.ም. ተዋበች አሊ የተባለችውን የዘመነ መሳፍንት ታላቅ ባላባት፣ የራስ አሊ አሉላን፣ ልጅ አገባ። ተዋበች በጊዜው የ፲፭ ዓመት ወጣት የነበረች ሲሆን ቁንጅናዋና አስተሳሰቡዋ በጊዜው በነበሩ ሰወች ዘንድ የተደነቀ ነበር። ሁለቱ በፍቅር በመውደቃቸው ቴወድሮስ በአባቷ ራስ አሊና በአያቷ እቴጌ መነን ላይ ሲያምጽ ባሏን ትደግፍ ነበር። አጼ ቴወድሮስ የሚስታቸውን መታመም ከዘመቻ መልስ በ፲፰፻፵፰ ዓ.ም ላይ ከሰሙ በኋላ እቴጌ ተዋበች በ፲፰፻፶ አረፉ። በኃዘኑ ወቅት እስቲ ጠይቁልኝ እርቃ ሳትሄድ እትጌ ተዋበች ሚስት እናት ገረድ? ብለው እንደተቀኙ በታሪክ መዛግብት ሰፍሮ ይገኛል። ከሁለት ዓመት ሀዘን በኋላ በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም ዓፄ ቴዎድሮስ ከሁለተኛ ሚስታቸው ጋር ተገናኙ። «ደራስጌ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀምጠው ሳለ አንድ ወታደራቸው ወደ ርሳቸው ቀረበና «ጌታየ፣ አንዲት ሴት አገኘሁ፣ ፊቷም እንደ ፀሐይ የሚያበራ ነው።» ልጅቱም በኋላ ወደ ቤተመንግሥት ቀረበች፣ ስሟም ጥሩነሽ ውቤ፣ የደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ልጅ ነበረች። ንጉሱም አይተዋት "እውነትም ወርቅ ናት" በማለት አገቧት። በዚህ ወቅት ንጉሠ ነገሥቱ አባቷን ራስ ውቤን አስረዋቸው ነበር። ራስ ውቤ የሰሜን፣ወልቃይት ፣ፀገዴ፣ትግራይ፣ ሰራየ፣ ሐማሴንና አንጎት (ሰሜን ወሎ) አስተዳዳሪ ሲሆኑ ከዓፄ ፋሲለደስ የሚወለዱ ስለነበሩ ለንጉሥነት የሚገዳደሩ ነበሩ። የጥሩወርቅ (ጥሩነሽ) እናት ደግሞ ወይዘሮ ላቂያየ የተባሉ የትግራይ መሳፍንት ዘር ነበሩ። ከኒህ ሚስታቸው ደጃዝማች ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የተባለውን ከሁሉ በላይ የሚወዱትን፣ እርሳቸውን እንዲተካ ያጩትን ልጅ ወለዱ። ዓፄ ቴዎድሮስ በአጠቃላይ ጊዜ ሲያገቡ ወንድና ሴት ልጆች ነበሯቸው፣ እነርሱም፦ ወጣቱ ኀይሉ ካሳ ውልደትና ትምህርት ቤት ካሳ ኃይሉ በ1811 ዓ.ም. አባታቸው ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ በሚያስተዳድሩት ቋራ፣ ከእናታቸው ወይዘሮ አትጠገብ ተወለዱ። ቋራ በምዕራቡ ኢትዮጵያ ከሱዳን ድንበር የሚገኝ ሲሆን በዘመኑ ከሱዳኖችና ክግብፆች ዘንድ ብዙ ወረራ ይደርስበት የነበር ክፍል ነው። ደጅ አዝማች ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ከሱዳን ጋር በተደረገ ጦርነት ሲያልፉ፣ በ1813 ዓ.ም ወይዘሮ አትጠገብ ህጻኑን ቴወድሮስ ይዘው ወደተወለዱበት ጎንደር ከተማ ተመለሱ። ወይዘሮ አትጠገብ በነበራቸው ገቢ መጠን ልጃቸውን በጥሩ ሁኔታ ማሳደግ ስላልቻሉ ክንፉ ሃይሉ ህጻኑን ቴወድሮስ በጎንደርና በጣና ሃይቅ መካከል በሚገኘው ቸንከር በተባለ ቦታ የተክለ ሃይማኖት ገዳም ለትምህርት ላኩት። ቀጥሎ የሆነውን በጊዜው የነበር ደብተራ ዘነበ እንዲህ ሲል ይዘግባል፡ በልጅነትዎ፡ቸንከር፡ትምርት፡ሲማሩ፡ከገዳሙ።ደጃች፡ማሩ፡በደምቢያ፡ሸፈቱ።ያነ፡ጊዜ፡የቤጌ፡ምድር፡ሁሉ፡ገዢ፡እራስ፡ይማም፡ነበሩ። ደጃች፡ማሩን፡ለማሳደድ፡በመጡ፡ጊዜ፡ገዳሙን፡ሰበሩት። አብረው፡የሚማሩዋቸውን፡፵፰አሽከሮች፡ሰልቦ፡ልጅ፡ካሳን፡ትቷቸው፡ሄደ፡በውስጥ፡ሳሉ። ይህም በህጻኑ ላይ የማይጠፋ የአይምሮ ጠባሳ ትቶ ያለፈ ኩነት ነበር። ህጻኑ ወደ አጎቱ ወደ ደጃዝማች ክንፉ ቤት ተመልሶ በአጎቱ ቤት የአስተዳደርን፣ የወታደራዊ ዘዴንና ስልትን ተማረ። ማንበብና መጻፍን በዚሁ ወቅት በሚገባ ተለማመደ። የወደፊቱ ቴወድሮስ እጅግ ማንበብን የሚወድ ሰው ነበር፣ የኢትዮጵያን ጥንታዊና ጊዜያዊ ድርሳናትን፣ የአውሮጳን ጥንታዊ እና ጊዚያዊ ታሪክ በደንብ እንዳጠና መረጃ አለ። የሼክስፒርን ስራወችና መጽሃፍ ቅዱስን ሳይቀር እንዳጠና በጊዜው የነበሩ አውሮጳውያን ሳይመዘግቡ አላለፉም። ለነበረበት ዘመን በደንብ የተማረ ሰው ነበር። በሽፍትነት ወራት የደምቢያ አስተዳዳሪ የነበሩት ደጃዝማች ክንፉ ምንም እንኳ ቴወድሮስን ለዘመቻ ይዘውት ቢውጡም ግዛታቸውን ከካሳ ይልቅ መኮንን ለተባለ ልጃቸው ለማውረስ በመፈለጋቸው ግንኙነታቸው የሻከረ ሆነ። በ1839 ደጃች ክንፉ ካረፉ በኋላ የክንፉ ሁለት ልጆችና ካሳ ሆነው የዳሞትና ጎጃም ገዢ በነበሩትን ደጅ አዝማች ጎሹ ዘውዴን ጦርነት ገጥመው ተሸነፉ። ልጅ ካሳ በጦርነቱ ባይማረክም ብዙ ወራት በሽሽት ከቆየ በኋላ የአሸናፊውን ደጃች ጎሹን ጦር በመጨረሻ ተቀላቀለ። ምንም እንኳ የውትድርና ብቃትን ቢያሳይም በደጃች ጎሹ ሰራዊት ውስጥ እድገትን ስላላገኘ ወደ ቋራ ተመለሰ።። ሆኖም ወይዘሮ መነን ሊበን አምዴ አጠቃላይ ደምቢያን የግሏ ርስት አድርጋ ነበር። በዚህ ምክንያት የመነን ሊብን ተወካይ ገዢወች ወጣቱን ካሳ ከቋራ እንዲለቅ ይወተውቱት ነበር። ካሳም የተነጠቀውን የአባቱን ርስት ለማስለመስ ያለው አማራጭ አመጽ በመሆኑ ወደቆላ ወርዶ ሸፈተ። ካሳ እንደሌሎች ሽፍቶች ሳይሆን በደግነቱና በፍርድ አዋቂነቱ እራሱን ለየ። ለምሳሌ በሽፍትነት የሚያገኘውን ገንዘብ ለገበሬወች እያከፋፈለ ሞፈርና ቀንበር እንዲገዙ ይረዳ ነበር። ይህ አይዞህ ባይነትና ደግነት ለወጣቱ የፖለቲካ መሰረት ሲያስገኘው ከጊዜ ወደጊዜ ደጋፊወቹ እንዲበራከቱ አደረገ። በ12 ሰወች የተጀመረው አመጽ በጥቂት ጊዜ 300 ጦረኞችን ሰበሰበ። ተከታዮቹ እየበዙ ሲሄድ በጣም የተሳካ የጦር ስልት መከተል ጀመረ፣ ስልቱም እንዲህ ነበር፡ ያልተጠበቀ ዘመቻውን ቀን ላይ ካወጀ በኋላ ከ5 እስከ 600 ፈረሰኞቹ ጋር ሆኖ ሌሊቱን ሲጓዝ ያድርና ጠዋት ላይ ጠላቶቹ ላይ በድንገት ይደርሳል። ዱብዳው ጦርነትም በካሳ አሸናፊነት ይፈጸማል። በዚህ ሁኔታ በ1829 ዓ.ም. የካሳ ጦር ሱዳን ጠረፍ ደረሰ። የፖለቲካ ሰው የካሳ ሽፍቶች በነጋዴወች ላይ የሚያካሂዱት ጥቃት በተዘዋዋሪ የእቴጌ መነንን (በጊዜው የሳልሳዊ አጼ ዮሃንስ ባለቤት) የቀረጥ ገቢ ቀነሰ። በዚህና እየጎላ በመጣው የካሳ ዝና ምክንያት የየጁ ባላባት ምን እንዲያደረጉ ግራ ገባቸው። ችላ እንዳይሉት ችሎታ አለው፣ እንዳይወጉት ጥሩ ተዋጊ ነው። 134 ስለሆነም ወይዘሮ መነን ለቴወድሮስ በመስፍን ማዕረግ የልጇን የራስአሊ አሉላን ጦር እንዲቀላቀል ጋበዘችው። ካሳም ያለውን ጥንካሬ ግምት ውስጥ በማስገባት ለመነን ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የራሱን ሰራዊት እንደያዘ የቋራ አስተዳዳሪ ሆኖ ተሰየመ። በዚያውም የራስ አሊን ልጅ ተዋበች አሊን በ1839ዓ.ም. አገባ። አዲስ ማዕረግ የተጎናጸፈውን የልጁን ባል ራስ አሊና እናቱ ወይዘሮ መነን ድሃ አደግነቱን አስመልክተው ንቀት በተሞላው መልኩ ያስተናግዱት ነበር። ከዚህ በተረፈ የመነን ርስት የሆነ ደምቢያም የቋራን ክፍሎች ስለያዘ የቋራ ገቢ በጣም አንስተኛ ነበር። በዚህና መስል ምክንያቶች በሚስቱ ድጋፍ በመነን ላይ አመፀ፣ ስሙንም አባ ታጠቅ በማለት ደምቢያን ወረረ። የቴወድሮስን ወርራ አድገኛነት ያልተረዳችው ወይዘሮ መነን በደጅ አዝማች ወንድይራድ የሚመራ አንስተኛ ሃይል አድርጋ ጦር ላከችበት። ይህ ጦር ሁለት ጊዜ በቴወድሮስ ተሸነፈ። በምስራቅ፣ በጎጃም መነንና ልጇ አሊ በጦርነት ተጠምደው ስለነበር የጎንደር ከተማን ለቀው ወደጎጃም ጦራቸውን ይዘው ዘመቱ። የተገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም ጥር 1840 ላይ የጎንደር ከተማን ቴወድሮስ ተቆጣጠረ። የራሱን ባለስልጣኖች በከተማው ላይ ከሾመ በኋላ ለአሊ ይገባው የነበርውን ግብር ሰበሰበ፣ ቀጥሎም ከነገስታቱ ጎተራና ከከባቢውም መንደሮች እህልን መዘበረ። ከጎጃም መልስ፣ በጣና ሃይቅ በስተሰሜን በተደረገ ጦርነት እቴጌ መነን ጭኗ ላይ ቆስላ ከባሏ ከሳልሳዊ አጼ ዮሃንስ ጋር በቴወድሮስ ታሰረች። እኒህ እሰርኞችን ለማስለቀቅ በተደረገ ውይይት ቴወድሮስ የደጅ አዝማችነትን ማዕረግ ከራስ አሊ አገኝ። እንዲሁም ደምቢያ ለቋራ ተመልሰ። በአንጻሩ ቴወድሮስ የአሊን ሰራዊት ልዋሃድ ተስማማ። ቴወድሮስ የመጀመሪያው የዘመናዊ ጦር መሳሪያ ውጊያ የገጠመው በዚሁ በደጅ አዝማችነት ወራት ነበር። ደባርቅ ላይ ሰፍሮ የነበረውን በሙሃመድ አሊ የሚመራ የግብጽ ወራሪ ሃይል ለማጥቃት ከ16፣000 ሰራዊት ጋር መጋቢት 1840 ላይ ዘመቻ አድርጎ፣ ምንም እንኳ የርሱ ሃይሎች ቁጥር ከግብጾቹ ቢበልጥም በግብጾቹ ዲሲፕሊንና ዘመናዊ ጦር መሳሪያ ምክንያት ተሸነፈ። ይህ ጉዳይ ቴወድሮስን እጅጉን ያስደነቀ ኩነት ነበር። ከዚህ በኋላ ነበር ቴወድሮስ ዘመናዊ ጦር መሳሪያን ለማግኘትና ዘመናዊ የጦር ስልትን ለመማር ከፍተኛ ፍላጎት ያደረበት። ጦርነትና ንግሥና ከትንሹ አሊ ጋር ጥል ከሱዳን ጋር ለጦርነት በወጣበት ወቅት ቋራ ላይ ይዘርፉ የነበሩትን አማጺወች ሲመለስ ቀጣ። በዚህ መንገድ የቋራ ግዛቱን ካጸና እኋላ ከከባቢው ተገዳዳሪወች ይበልጥ ጠነከረ። ጥር 1840 ላይ ራስ አሊ ቴወድሮስ ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጣ ለሁለተኛ ጊዜ ቢልኩበትም ባለመሄዱ በሁለቱ መካከል የመጀመሪያው ጥል ታየ። ከ1841- 42 ለተወሰነ ጊዜ በአገው ምድር ዘመቻ ካደረገ በኋላ ወደ ቋራ ተመለሰ። 1844 ላይ ከራስ አሊ ጋር ፊት ለፊት በመጋፈጥ ወደ ዙፋን የሚያደርገውን ጉዞ ጀመረ። ከዚህ ዓመት በኋላ ታላላቅ የዘመነ መሳፍንት ባላባቶችን ተራ በተራ በመውጋት አሸነፋቸው። በኒህ ጦርነቶች "የላቀ የውጊያ ስልትንና ጥበብን" በማሳየት ወታደራዊ ብቃቱን አስመዘገበ። በ1844 መጨረሻ አካባቢ ከራስ አሊ ጋር የገባውን ውል ሙሉ በሙሉ በማፍረስ ራስ አሊ ወደ ጎጃም ሊያደርገው በነበርው ዘመቻ እንደማይሳተፍ አስታወቀ። ራስ አሊም ለብዙ ወራት ጦር በመላክ ቴወድሮስን በቋራ ውጊያ ገጠመው 7። በስተመጨረዣ መስከረም 1845 ላይ አሊ ጎሹን የቋራ ገዢ አድርጎ በቴወድሮስ ላይ ሾመበት። ይህ አዲሱ ሹም ቴወድሮስን ለመግጠም ወደቋራ ከሰራዊቱ ጋር ተመመ። በዘመነ መሳፍንት ላይ ጦር ስለመክፈቱ ጥቅምት 27፣ 1845 ላይ ቴወድሮስ የድሮ አለቃውን የጎጃም ባላባት ደጅ አዝማች ጎሹ ዘውዴን በጉር አምባ ጦርነት ገጥሞ አንድ ቀን ሙሉ በተደረገ ውጊያ ደጅ አዝማች ጎሹ ስለወደቁ በቴወድሮስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ይህ በጊዜው እንደ ታላቅ ድል የታየ ሲሆን ጉር አምባ ለጎንደር ከተማ በጣም የቀረበ ቦታ ስለነበር የቴወድሮስን የወደፊት ምኞት ያመላከተ ጦርነት ነበር። በዚህ ድል የተደናገጠው ራስ አሊ ምንም እንኳ ከቴወድሮስ የዕርቅን መልዕክት ቢላክለትም የጎንደር ከተማን ለቆ ወደ ደብረ ታቦር አመራ። ቴወድሮስ ብዙም ሳይቆይ የጎንደር ከተማን ያዘ። ራስ አሊ ደብረ ታቦር ላይ ሆኖ የየጁን፣ የወሎና የትግራይን ጦር አንድ አድርጎ ቴወድሮስን ለመውጋት ለ3ቱም ክፍሎች ጥሪ አደረገ። ጥር 1945 ላይ የትግራዩ ባላባት ደጅ አዝማች ውቤ ከራስ አሊ ጋር ትብብር እንደፈጠሩ ሰማ፡ ይህ በዘመኑ የሁለት ታላላቅ የተባሉ ሰራዊቶች ቅንጅት ነበር። መጋቢት ላይ የጠላት ጦር ወደርሱ እየመጣ እንደሆነ መረጃ በማግኘቱ ከጎንደር ከተማ 3ሰዓት የእግር ጉዞ ላይ ባለው በ ጎርጎራ ቢሸን ላይ ሰራዊቱን አሰፈረ። ሚያዚያ12፣ 1845 ላይ በዚሁ ቦታ በተደረገ ጦርነት በየጁው ደጅአዝማች ብሩ አሊጋዝ የሚመራው ጦር እንዳለ ተደመሰሰ። በዘመነ መሳፍንት ላይ ጦርነት የከፈተው ካሳ በጦርነቱ የራስ አሊንና የደጅ አዝማች ውቤን ሶስት ደጅ አዝማቾች ገደለ። ከዚህ ድል በኋላ ወደ ጎንደር ከተማ ተመልሶ የተቀሩትን ሁለቱን መሪዎች ውቤንና አሊን፣ ለመደምሰስ ይዘጋጅ ጀመር። ግንቦት 1845 ላይ ደብረ ታቦር ላይ ዘመቻ አድርጎ ከተማይቱን መዘበረ። አማቱን ራስ አሊንም ቢያሳድደው ጎጃም ላይ መሸገ። ቀጥሎም በሰኔ29፣ 1845 ላይ አይሻል በተባለ ቦታ ጦርነት ገጥመው ቴወድሮስ ራስ አሊን አሸነፈ፣ እቴጌ መነን ሊበንንም ማረከ። የአይሻል ጦርነት በዘመኑ እጅግ በደም የጨቀየ አስክፊ ጦርነት ነበር። ብዙ ታሪክ አጥኝወች ይህ የአይሻል ጦርነት የዘመነ መሳፍንት ማብቂያ እንደሆነ ይስማማሉ። 3 ከዚህ በኋላ ሁሉ በሁሉ ጦርነት የሚከፍትበትና ሃይለኛ ባላባቶች ተቀራምተው አገሪቱን የሚያስተዳድሩበት ዘመነ መሳፍንት አበቃለት። በዚህ ወቅት እንደ ጥንቱ አንድ ጠንካራ ሰው ከሌሎች ልቆ አገሪቱን የሚያስተዳድርበት ሁኔታ ተፈጠረ። ከአይሻል ጦርነት በኋላ ራስ አሊ ወደ የጁ ሸሹ፣ 1848 ላይ በዚያው በየጁ አረፉ። ከ18ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀመሮ የገነነው የየጁ ሃይልና የራስ አሊ ጥንካሬ አይሻል ላይ አበቃ። ከዚህ ድል በኋላ ቴወድሮስ የመላው ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ መሪ ቢሆንም ቅሉ አጠቃላይ መሪ ለመሆን የተቀሩትን የሰሜን ባላባቶች ማሸነፍ ነበረበት። ግንቦት 1846 አምባ ጄበል ላይ ከጎርጎራ ቢሸን ጦርነት አምልጦ የነበረውን ብሩ ጎሹን ተዋግቶ በመማረክ ለሚለቀጥሉት 14 አመታት እስረኛው አደረገው። ትንሽ ቆይቶም ቴወድሮስ የላስታውን ፋሪስ አሊን ደመሰሰ። ከአቡነ ሰላማ ጋር ስምምነት፣ የደራስጌ ጦርነት በወቅቱ ዙፋን ላይ ለመውጣት አንድ ቀሪ እንቅፋት በቴዎድሮስ ላይ ተጋረጠ፣ እርሱም የሰሜኑ ደጃዝማች ውቤ ነበር። ከአይሻል ጦርነት በኋላ ራሱ ውቤ ከቴወድሮስ ጋር እርቅን በመሻት የተለያዩ ስጦታን ላከለት። ቴዎድሮስ በላስታና በጎጃም ቀሪ ዘመቻወችን ሲያደርግ ከኋላው በሰሜውን ውቤ ጦር እንዳይከፍትበት ሲል የውቤን ስጦታወች ተቀበለ። በዚህ ስምምነት መሰረት የቴዎድሮስ ሰራዊት ትግራይን መልቀቅ ጀመረ ሆኖም ግን አቡነ ሰላማ ከትግራይ ወደ ጎንደር እንዲመጡ አደረገ። አቡነ ሰላማ ከግብጽ የመጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ፓትሪያርክ ነበሩ። ደጅአዝማች ውቤ እራሳቸውን ለማንገስ ከግብጽ ያስመጧቸው ነበሩ። የቴወድሮስ አላማ አቡነ ሰላማን ከርሱ ዘንድ በማድረግ የቤተክርስቲያኗን ፈቃድ ለማግኘትና አገሪቷን እንደገና ለመገንባት ነበር። ወዲያውም ቴወድሮንና አቡነ ሰላማን የሚያግባባ አንድ አላማ ተገኘ አንዲት ጠንካራ ቤ/ክርስቲያን በአገሪቱ እንዲኖር ማድረግ። በዘመኑ ሶስት ልደት የሚባል ትምህርት ተነስቶ ይህን ሃሳብ በሚያነሱና በተዋህዶ ተከታዮች መካከል ከፍተኛ ክርክር ነበር። ይህን ክፍፍል ለማስወገድ ሐምሌ 1846 ላይ በቴዎድሮስ የሚመራ የአምባ ጫራ ጉባኤ ተጠራ። ለተዋህዶ ተቃዋሚወች ቴወድሮስ ጠየቃቸው፡ "አቡነስ ሰላማን እንደመሪያችሁ ታውቁታላችሁ?" እነርሱም ለስወ "አዎ" አሉት። ያን ጊዜ መልሶ ጠየቃቸው፡ "እንኪያስ ልጆቼ ከአቡኑ የተለየ የሚያስተምሩ መናፍቅ ናቸው ከዚህ በኋላ ለ3 ቀን ያለምግብና መጠጥ ትቷቸው ሄደ፣ ከዚህ በኋላ ጥፋታቸውን አመኑ። ከዚህ ስምምነት በኋላ የሶስት ልደት ትምህርት ኑፋቄ ተባለና የተዋህዶ ትምህርት የአገሪቱ ብቸኛ ትምህርት ሆነ እኒህን ለውጦች በመፈጸሙ ከአቡነ ሰላማ ጋር ያለው ግንኙነት እጅግ ጥሩ ሆነ። በ1846 መጨረሻወቹ ቴዎድሮስ ንጉስ ተብሎ በአቡነ ስላማ ተቀባ። ቴዎድሮስና ተዋበችም ጋብቻቸውን ህጋዊ በማድረግ ቆረቡ። የቴዎድሮስን ንጉስ መሆን ደጅአዝማች ውቤ ሊቀበለው አልቻለም። ስለሆነም ቴወድሮስን ለመውጋት ዝግጅት ማደርግ ጀመረ። በዚህ ምክንያት ቴዎድሮስ ያለመንም ችግር ሰሜንን በመውረር ከትግራይ የካቲት 9፣ 1847 የተነሳውን ውቤን ደራስጌ ላይ ገጠመው። ደራስጌ የደጅ አዝማች ውቤ ዋና ከተማ የነበር ቢሆንም በዚህ ጦርነት ተሸነፈና ተማረከ። ከሁለት ቀን በኋላ ቴወድሮስ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ተብሎ አክሊል ጫነ። በደራስጌ ማርያም ዘውድ ስለመጫናቸው ከብዙ መራራ ትግል በኋላ የሰሜን ተፎካካሪወቹን ያስወገደው። ንጉስ ካሳ ሃይሉ የካቲት 11፣ 1847 ዓ.ም. ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው ዘውድ ጫኑ፣ ስማቸውም ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ተባለ። ስርአተ ንግሱ የተከናወነው በደራስጌ ማርያም ቤተክርስቲያን ሲሆን የዓለምን ተገልባጭ ዘይቤ በሚያሳይ መልኩ ይኸው ቤ/ክርስቲያን ደጃዝማች ውቤ ለራሳቸው ስርዓተ ንግስ ሲሉ ያስሩት ነበር፣ ስርዓተ ንግሱንም የፈጸሙት አቡነ ሰላማ ሲሆኑ እኒሁ ጳጳስ ከግብጽ በደጅ አዝማች ውቤ ለራሳቸው ንግስና የመጡ ነበሩ። አጼ ቴዎድሮስ በመጀመሪያወቹ የአገዛዝ ዘመናቸው ራሳቸውን ከሰሎሞናዊው ስርወ መንግስት የተለዩ እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል ይህም በዘመነ መሳፍንት የደረሰው የግብረገብና ፖለቲካ መላሸቅ ምክንያት ስርወ መንግስቱ በህዝቡ ዘንድ ዋጋው ረክሶ ነበር በዚህ ምክንያት የአጼ ቴወድሮስ የመጀመሪያወቹ የአገዛዝ ዘመናት ከ1270ዓ.ም. ይኩኖ አምላክ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋርድ የመጣውን የአገሪቱን አሰራር በጭንቅላቱ የደፋ ነበር። ሆኖም ግን በኋላ ላይ አጼ ቴዎድሮስ በእናታቸው የአጼፋሲለደስ ዘር እንደሆኑ ለማሳየት ሞክረዋል፣ ስለሆነም በአጠቃላይ መልኩ በአሁኑ ዘመን የሰለሞናዊ ስርወ መንግስት አካል እንደሆኑ ይጠቀሳል የአጼ ቴዎድሮስ ዙፋን ላይ መውጣት በ1845 በአይሻል ጦርነት ተጀምሮ የነበረውን የዘመነ መሳፍንት ስርዓተ ቀብር አጠናቋል። ብዙ ታሪክ ተመራማሪወች የካቲት11፣ 1847 የዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ጅማሬ እንደሆነ ይስማማሉ 2። ሪቻርድ ፐንኸርስት እንደጻፈ፡"የካሳ ሃይሉ ከፍ ማለት አዲሱን የኢትዮጵያ ታሪክ የከፈተ ክስተት ነበር 3"። አጼ ቴዎድሮስ የዙፋን ስማቸውን የመረጡት ከፍካሬ እየሱስ ሲሆን ይህ መጽሃፍ የሚያትተው ስለሚመጣው አለምና በ15ኛው ክፍለ ዘመን ስለነበረው በዘመኑ ኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስለነበር ንጉስ ቀዳማዊ አጼ ቴወድሮስ ስርዓት እንደገና በኢትዮጵያ መንሰራፋት ነበር። ይሄው የጥንቱ ንጉስ፣ ምንም እንኳ የአገዛዙ ዘመን እጅግ አጭር ቢሆንም፣ የፈጸመውም ጥሩ ተግባራት በታሪክ ጅረት ተሽርሽሮ ቢጠፋም በጥንቶቹ ኢትዮጵያውን ዘንድ ምንጊዜም የማይረሳ ተወዳጅ ንጉስ ነበር። ከሰራቸው ስራወች አንዱ ከይኩኖ አምላክ ጀምሮ ለቤተክርስቲያን ሲወርድ ሲዋርድ የመጣውን የቤተክርስቲያን መሬት ለገበሬወች ማከፋፈሉ ነበር። በፍካሬ እየሱስ መሰረት፣ ቀዳማዊ ቴዎድሮስ እንደገና ከሞት ይነሳና ፍትህና ሰላም አስፍኖ "ሁሉም ከሚፈጠረው ደስታና ሰላም ተካፋይ" የሚሆንበት ግዛት ያንሰራፋል የሚል ነበር 132። በ1830ዎቹ የዘመነ መሳፍንት ጦርነቶች በተሰቃየው ህዝብ ዘንድ ይህ የፍካሬ እየሱስ ትንቢት ከመንደር መንደር የገነነ ነበር። አጼ ቴዎድሮስ፣ ይህ "የአገሪቱን የታሪክ አቅጣጫ የሚቀይር" የሚመጣው ንጉስ ነኝ ብለው ያምኑ እንደነበር ለማመን አይከብድም 7። በስርዓተ ንግሳቸው ላይ ባደርጉት ንግግር አገሪቷን አንድ ለማድረግና እንደገና ለመገንባት ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት ገልጸዋል። የቴወድሮስን የህይወት ታሪክ የጻፈው ስቬን ሩቤንሰን አፄ ቴወድሮስ ስልጣን ላይ ሲወጡ በአይምሮአቸው ውስጥ የነበረውን ዕቅድ እንዲህ ሲል ይዘግባል፡ "የቴዎድሮስ ስሜት እንደቀደሙት ነገስታት ሳይሆን የተለየ ነበር፡ ለእርሱ የባላባቶች ትርምስ፣ የግብረገብ መላሸቅ፣ የቴክኖሎጂ ኋላቀርነት የአገሪቱን መኖር ጥያቄ ውስጥ የጣሉ ጉዳዮች ነበሩ። ያወጃቸው ለውጦች፣ የተከተላቸውና ሊተገብራቸው የፈለጋቸው ፖሊሲወች፣ እያንዳንዱን ችግር ለመፍታት ያሳየው እልከኝነት፣ የሚያሳዩት የንጉሱ አላማ ብሔራዊ ተሃድሶና አገሪቱን ወደ ዘመናዊ አገር ማሻገር እንደነበር ነው የቴወድሮስ መንግስት፡ አንድነትና ሥልጣኔ ዘመቻ ወደ ወሎና ሸዋ ከሁለት አመት የማያቋርጥ ዘመቻ በኋላ የነገሱት አጼ ቴወድሮስ ለማረፍ አልፈለጉም፣ እንዲያውም ዋናዋና ታላቁ ግባቸውን እውን ለማድረግ ወደ ደቡቡ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ክፍል መዝመት ግድ አላቸው 9። የሰሜኖቹን ባላባቶች በማሸነፍ ብቻ አለመታቀባቸው በታሪክ ጸሃፊው ባህሩ ዘውዴ ዘንድ ንጉሱ "ሰፋ ያለ ራዕይ" እንደነበራቸው የሚያሳይ ሆኖ ተገኝቷል። የደራስጌው ስርዓተ ንግስ የዘመነ መሳፍንትን ማብቃት ሲያሳይ የሸዋውና የወሎው ዘመቻ በአንጻሩ በአጼ ምንሊክ የተጠናቀቀውን የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ማዕከል ወደ ደቡብ ማምራት አመላካች ነበር። የወሎና የሸዋ በራስ መተዳደር በርግጥም ንጉሱ የነበራቸውን የማዕከላዊ አንድ ኢትዮጵያ ራዕይ አደጋ የጣለ ስለሆነ ዘመቻው ግድ የሚል ነበር በመጋቢት ዓ.ም በፆም ወቅት አጼ ቴዎድሮስ ወደ ወሎ ዘመቻ አደረጉ። ምንም እንኳ ይህን ዘመቻ ወሎ ውስጥ ይገኙ የነበሩት ጎሳወች ተባብረው ለማሸነፍ ቢሞክሩም የቴዎድሮስ ሰራዊት በመስከረም ቀን ዓ/ም መቅደላን በመቆጣጠር ድል አደርጋቸው። መቅደላ እንግዴ በኋላው ዘመን የአጼ ቴወድሮስ የመንግስት ማዕከልና ዋና ምሽግ የሆነ ነው የወሎ ዋና ዋና መሪወች ከተማረኩ በኋላ አመጽ እንዳያስነሱ በቴወድሮስ መቅደላ ላይ ታሰሩ። የወሎው ድል ለአጼ ቴወድሮስ ትልቅ ስልታዊ ጠቀሜታ ነበረው ምክንያቱም ወደ ሸዋ በሚያደርጉት ዘመቻ የኋላቸው ለጥቃት አይጋለጥምና። ሸዋ በዚህ ወቅት ከዘመነ መሳፍንት ትርምስ የተገላገለ ክፍል ስለነበር ከሰሜኑ ኢትዮጵያ በተለየ መልኩ ሰላም የሰፈነበትና ሃብታም ነበር። ጥቅምት 1848 ላይ በድንገት የአጼ ቴዎድሮስ ሰራዊት ከወሎ ተነስቶ ሸዋ ገባ። የንጉሰ ነገሥቱ ሰራዊት ድንገተኛ አመጣጥ የሸዋን ሰራዊት ስለከፋፈለው በጥቅምት አጋማሽ ላይ በአጼ ቴዎድሮስና ንጉሥኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ ሠራዊት መካከል በተደረገ ጦርነት የአጼው ጦር የባለወርቅ ጦርነት ተብሎ የሚታወቀውን ውጊያ ድል አደረገ። ዘመቻው ባጠቃላይ ወር የፈጀ ነበር። መንዝ ግድምና ኤፍራታ በቴዎድሮስ ስር ሲወድቁ ሌሎች የሸዋ ክፍሎች ግን በሰይፉ ሣህለ ሥላሴ፣ የንጉሥ ኃይለ መለኮት ወንድም መሪነት የቴዎድሮስን ጦር በመከላከል ቆዩ በራስ ዳርጌ የሚመራው የንጉሠ ነገሥቱ ጦር ህዳር 1848 ላይ በበረከት ጦርነት አሸነፈ በመካከሉ ኅዳር ቀን፣ ንጉሥ ኃይለ መለኮት በሕመም አረፉ። በዚህ ምክንያት የሸዋ ወታደሮች ዓላማ የንጉሡን ልጅ ምኒልክን ከቴዎድሮስ እጅ ተከላክሎ ማዳን ሆነ። ሆኖም ግን ልጅ ምኒልክ በቴዎድሮስ እጅ በመውደቁና ቴዎድሮስም እንደልጃቸው ሊያሳድጉት ቃል በመግባታቸው የካቲት ዓ/ም ላይ አንኮበር ሲገቡ በቀሳውስትና አንኮበር መሪወች ዘንድ ተቀባይነትን አገኙ። ቀጥሎም ንጉሰ ነገስቱ በጊዜው የነበረውን የሸዋ አስተዳደር በመቀየረ መርድ አዝማች በሚለው የጥንት ማዕረግ የንጉሥ ኃይለ መለኮት ወንድም የነበሩትን ኃይለ ሚካኤል የሸዋ አስተዳዳሪ አድርገው ሾሙ። ለ፪ መቶ ክፍለ ዘመን ተከፋፍሎ የነበረውን የኢትዮጵያ ግዛት አጼ ቴዎድሮስ በ፫ አመት ዘመቻ በንዲህ መልኩ አንድ አደረጉ 11። በ፲፰፻፵፰ ዓ/ም አጋማሽ ላይ ሸዋን ጎጃምን ወሎን ትግራይንና ጎንደርን አንድ ላይ በመግዛት፣ በ፵፯ ዓመታቸው፣ የዘመነ መሳፍንት የመጨረሻ ባላባትና የአዲሱ ዘመናዊ አገር የመጀመሪያ ንጉሠ ነገሥት ለመሆን በቁ። በዚህ ወቅት የአገሪቱ ዋና ከተማ ከጎንደር ወደ ደብረ ታቦር ተዛውሮ ነበር 9። የአዲሱ ንጉሠ ነገሥት የመጀመሪያ ስራዎች የቴዎድሮስ መነሳት የዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክ መጀመሪያ ነው፣ ለዚህም ምክንያቱ የፈጸሟቸው ለውጦች ናቸው ከርሳቸው በፊት ከነበሩ ነገሥታት በተለየ መልኩ ቴዎድሮስ አገሪቱን ወደ ዘመናዊ አገር ለማሻገር ያሳዩት ፍላጎት ንግሰ ነገሥት በነበሩበት ወቅት የነበራቸው ወጣትነትና። ከአደጉበት ከቋራ ነባራዊ ሁኔታ የመነጫል። ቋራ በዘመኑ ከሱዳን የማያቋርጥ ውጊያ የሚደረግበትና በዚያ የሚኖረው ህዝብ ከመካከለኛው መንግስት የሚያገኘው ምንም እርዳታ ስላልነበር ህዝቡ እጅግ የተሰቃየበት ነበር። ቀሳውስቱም ቢሆን በጎጥ ተከፋፍለው የየራሳቸው ሃይማኖታዊ ስርዓት በመተለም የተዋህዶ ቤተክርስቲያናን ከብዙ ቦታ ለመክፈል የሚገዳደሩበት ዘመን ነበር። የገጠሩም ክፍል በባላባቶች የርስ በርስ ጦርነት የተሰቃየ ነበር። የአገሪቱ ሁኔታ ንጉሰ ነገስቱ ዘመነ መሳፍንትን ለማጥፋት እንዲነንሳሱ አደረገ። በጊዜው የነበረው የእንግሊልዙ ቆንጽላ ዋልተር ፕላውዴን ንጉሰ ነገሥቱ የኢትዮጵያን ቀደምት ታላቅነት ለመመለስ ዋና አላማ እንዳላቸው ሳይመዘግብ አላለፈም፣ በፕላውዴን አስተሳሰብ ይሄ የንጉሰ ነገስቱ ዋና አነሳሽ አላማ ነበር። ከዚህ አንጻር የቴዎድሮስ የንግስና መጀመሪያ አመታቶች በብሄራዊ ፍትሕ፣ ርህራሄና የደሃ አደጎችን ህይወት በማሻሻል ላይ ያተኮረ 2002, 65 ቴዎድሮስ ቀደምት የአገሪቱ መንገድ ሰሪ ነበር። በዜና መዋዕሎችና የውጭ አይን እማኞች መሰረት ቴዎድሮስ በራሱ በእጁ መንገድ በመስራት ሌሎች እንዲከተሉት ይመራ ነበር። ንጉሱ ከ"ሌት እስከ ምሸት በራሳቸው እጅ ድንጋይ ይፈነቅሉ እንዲሁም ጎርባጣውን ክፍል ያቃኑ" ነበር። በምሳሌ የሚመራው ቴዎድሮስ እርሱ እየሰራ ሌሎች ተከታዮቹ ሊበሉም ሆነ ሊያርፉ አይደፍሩም ነበር። ሌሎች መንገድ ሰሪወችንም እጅግ ይረዳ ነበር። ደብተራ ዘነብ እንዲህ ሲል ይዘግባል፡ >ያነግዜም፡ንጉሱ፡ወደ፡ዋድላ፡ሄዱ። የንምሳ፡ሰው፡አቶ፡ሰንደል፡የቤተ፡ሐርን፡መንገድ፡ያበጁ፡ነበር። ከንጉሥ፡ቴዎድሮስም፡በተገናኙ፡ጊዜ። አቶ፡ሰንደል፡የሚረዳኝ፡አጣሁ።ብቻዬን፡ሆንኁ፡አሉ። ንጉሡም፡እጅግ፡ተቆጡ፡ይኽ፡ከሩቅ፡አገር፡መጥቶ፡ሲገዛ።ያገሬ፡ሰው፡እምቢ፡ሊል፡ብለው፡የዋድላውን፡ምስለኔ፡ይመር፡ጎዳናን፡ገርፈው፡አሰሩዋቸው። ለአቶ፡ሰንደልም፡ንጉሥ፡የሚቀመጡበትን፡በቅሎ፡መጣምር፡ኮርቻ፡የተጫነ፡ከነስራቱ፡ቀሚስዎን፡ሱሪዎን፡ሺ፡ብር፡አድርገው፡ሰጧቸው። ለአቶ፡ቡላዴ፡ለእንግሊዙ፡ሶስት፡መቶ፡ብር፡ሰጡ። ለንምሳ፡ሰዎች፡ለበንደርና፡ለኪንጽሌን፡ለማየር፡፮፻ብር፡ሰጧቸው። ቀሚስ፡ድርብ፡እያለበሱ፡የጨጨሆን፡ ቴዎድሮስ ቀደምት የተንሰራፋውን የባሪያ ንግድ ስርዓት ያጠቃ ንጉስ ነበር በዚህ ወቅት ባሪያ መሸጥም ሆነ መለወጥ እንዲሁም ማጓጓዝን የሚያግዱ ብዙ ድንጋጌወችን ንጉሱ በማወጅ ቀደምት የባርነት ስርዓት ተቃዋሚ ንጉስ ሆነ። ለምሳሌ ጎጃም፣ ባሶ ውስጥ ባደረገው ዘመቻ በገበያው የተገኙ ባሪያወችን በነጻ ለቋል። ወሎ ውስጥ የተማረኩ ባሪያወች እንዳይሸጡ አግዷል። ሆኖም ግን ከህጉ ውጭ በኮንትሮባንድ ውስጥ ለውስጥ በአገሪቷ ዳርቻወች ባሪያ መሸጡና መለወጡ አላቆመም። ከባህል አንጻር የአማርኛ ስነ ጽሁፍ በኒሁን ንጉሥ ዘመን ማደግና መሻሻል አሳይቷል። ከፍተኛው የመንግስት ስራ በአማርኛ ይካሄድ ነበር። ዜና መዋእላቸውን በአማርኛ ለመጀሚርያ ጊዜ ያስጻፉ ንጉሥ ነበሩ።፣ ከዚህ በፊት በግዕዝ ነበር። ከዚህ በኋላ አማርኛ የአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ሆነ።።ቴዎድሮስ ከግዕዝ ይልቅ ሰወች በሚረዱት አማርኛ መጽሃፍ ቅዱስ እንዲተረጎም አደርጉ። የመጀመሪያው የጂዖግራፊያ መጽሃፍ በአማርኛ የታተመውም በኒሁ ንጉስ ዘመን ነበር። ህዝቡ ለጋብቻ ከፍተኛ ዋጋ እንዲሰጥም በጣም ጥረት አድርገዋል፣ እራሳቸውም በአንድ ሴት በመወሰን መሪ ምሳሌ ለመሆን ሞክረዋል። ከቴዎድሮስ በፊት ይሰራበት የነበረውን ከወገብ በላይ እራቁት መሆን የአለባበስ ዘዴን በማስቀረት ሹሞች በጥሩ ሁኔታ እንዲለብሱ አድርገዋል። በአጠቃላይ ህዝቡ የሃይማኖትና የባህል ህጎችን አጥብቆ እንዲከተል ጥረት አድርገዋል። ከአስተዳደር ስልት አንጻር ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ እስከፈጸሙት ድረስ የነበረውን አገሪቱን በማዕከላዊ ሃይል የማስተዳደር ስራ ጀምረዋል። በአዲሱ ስርዓት መሰረት የግብር እና የፍርድ ባለስልጣናት ከማዕከላዊ መንግስት ደመወዛቸውን እንዲያገኙ ተደረገ፣ ይህም በየቦታው የነበሩ ባላባቶችን የመፍለጥ የመቁረጥ ሃይል የቀነሰ ተግባር ነበር። የሆኖ ሆኖ ንጉሡ የገዥውን መደብ ሙሉ በሙሉ አልቀየሩም፣ አንድ አንድ ገዥወች በነበሩበት እንዲቀጥሉ አድርገዋል። ለምሳሌ የትግራይ ገዥ የነበሩት ደጅ አዝማች ሰባጋዲስ ዘር የሆኑትን ካሳ ምርጫን በትግራይ ሾሙ፣ እንዲሁም የንጉስ ሳህለ ስላሴ ዘር የሆኑትን ሃይለ ሚካኤልን በመሾም በየቦታው የነበሩትን የሃይል ማዕከላት በነበሩበት እንዲጸኑ አድርገዋል። በአንዳንድ ክፍሎች የራሳቸውን ዘመዶች ስልጣን ያወጡበት ሁኔታ ይገኛል፣ ለምሳሌ ራስ እንግዳን በጎጃም። ይህ ስርዓት በመጀመሪያ እጅግ የተሳካ ነበር ምክንያቱም በዘመነ መሳፍንት እንኳ ሳይቀር ጠንካራ ባላባቶች ለንጉሳዊው ስልጣን የመገዛት ባህርይ ያሳዩ ነበርና። ከሸዋ መርዕድ አዝማች ሃይለ ሚካኤል በየጊዜው ወደ ንጉሱ የጓዙ ነበር። ትግራይ ደግሞ ለንጉሱ ዋና የገቢ ምንጭ ነበር (200፣000 ማሪያ ቴሬሳ በአመት)፣ ከበጌምድር የሚያገኙት 50፣000 ማሪያ ቴሬሳ ብቻ ነበር። ሆኖም ግን አንድ አንድ ጥቃቅን ባላባቶች አመጽ ለማስነሳት መመኮራቸው አልቀረም፣ ስለሆነም ንጉሱ ሰራዊቱን ማሻሻል እንዳለባቸው ተገነዘቡ። ዘመናዊ ሠራዊት ሠራዊቱ በፖለቲካው ውስጥ ባለው መሰረታዊ ተፅዕኖ ምክንያት ንጉስ ቴዎድሮስ በዚህ ክፍል ላይ ብዙ ትኩረት አድርገዋል። እራሳቸውን ከስሎሞኑ ስርወ መንግስት በመጀመሪያ የአገዛዛቸው ዘመን በማራቃቸው ብቸኛው ወደላይ የሚያወጣቸው መሰላል የውትድርና ብቃት እንደሆነ ጠንቅቀው ተረዱ። አገራዊ ሠራዊቱን ለማጠናከርና ብሔራዊ አንድነትን እውን ለማድረግ፣ ዋልተር ፕላውዴን "ታላቁ ለውጥ" ያለውን አጼ ቴዎድሮስ አከናወኑ 9። ይህ ታላቅ ለውጥ በ3 አብይ ክፍሎች ላይ ያተኮረ ነበር፡ ፩.መዋቅር ፪.ዲሲፕሊንና ፫.ትጥቅ ናቸው። እኒህ ለውጦች ከሞላ ጎደል የተወደዱና ለብዙ ድሎች ያበቃቸው ሲሆን ስልጣናቸውንም ለማንሰራፋት አይነተኛ ምክንያት ናቸው። እኒህ ለውጦች የአገሪቱ ዜጎች በ"አንጻራዊ ደህነነት" እንዲኖሩ ረድተዋል 9። ከመዋቅር አንጻር ከዘመነ መሳፍንት ሲወርድ የመጣውን የተከፋፈለ የባላባቶች ሰራዊትን በአንድ ብሔራዊ ሰራዊት ቀይረዋል። ከተለያዩ ክፍለ ሃገሮች የመጡት ወታደሮች በንጉሠ ነገሥቱ በተዋቀረ አንድ የጦር ክፍል ስር ተደራጁ። እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ሰራዊት የሚሰራበት የአስር አለቃ፣ የሀምሳ አለቃና መሰል ማዕረጎች የተፈጠሩት በዚሁ ዘመን ነበር። ንጉሡን የሚያጅቡትን ወታደሮች ቁጥር በመቀነስ፣ የዚህን ክፍል እዳተኝነትን ቀነሱ። ወታደሮች ከዚህ በኋላ ቋሚ ደሞዝ ተቆርጦላቸው ስለሚተዳደሩ የሰፈሩበትን ቦታ መበዝበዝ በህግ ተከለከሉ። በፊውዳሉ ስርዓት ወታደሮች በረገጡበት ቦታ ያሉ ገበሬወች ምግብና መኝታ እንዲያቀርቡ ይገደደዱ ነበር። ይህ ሁኔታ በንጉሠ ነገሥቱ አጥብቆ የተከለከለ ነበር። ይህን በሚያሳይ መልኩ ለምሳሌ አንድ ገበሬ የ12 ጫጩት እናት የሆነችን ዶሮ እንዲያርድ በንጉሱ ወታደር ይገደዳል። ድርጊቱ ንጉሱ ድረስ ቀርቦ በዳኝነት ከታየ በኋላ ወታደሩ በሞት ሲቀጣ ገብሬው ላም ተሰጥቶት እንዲሄድ ተደረገ። በዚህ ዘመን ወታደሮች ቀለብ የሚባል ገቢ ከንጉሱ የሚሰፈርላቸው ሲሆን ከዚህ ውጭ ማንም ገበሬውን ያስገደደ ወታደር ከፍተኛ ቅጣት ይቀጣ ነበር። ንጉሡ በሠራዊቱ ዘንድ እንደ ብረት የጠነከረ ዲሲፕሊን ለማቋቋም ሞክረዋል። ለምሳሌ ወደ ወሎ ባደረጉት ዘመቻ ያለትዕዛዝ ጦርነት የሚገቡ ወታደሮች ያለርህራሄ ይገደሉ ነበር። በሸዋው ዘመቻ እርስ በርስ ሽኩቻ ያሳዩ ወታደሮች በሙሉ በጥይት ተደብድበዋል። ባህሩ ዘውዴ እኒህ ድርጊቶች ደም መፋሰሱ እንዲባባስ በማድረግ ብዙ ጥቅም አላመጡም ያላል። ሆኖም ወታደሩ በራሱ ፈቃድ ብዙ ጥፋት እንዳያደርግ ረድቷል። አብዛኛው የአጼ ቴዎድሮስ ሰራዊት ጦር መሳሪያ ከጦር ሜዳ የተማረከ ነበር ቆይተው ግን ከአውሮጳ ቴክኖሎጂ በማስመጣት በኢትዮጵያ ምድር ላይ የመሳሪያ ማምረቻ ለማቋቋም ሞክረዋል። ለዚህ ተግባራቸው እንዲረዳ የአውሮጳ ሚስዮኖችን በጋፋት፣ ደብረታቦር ሰብስበው መሳሪያ እንዲሰሩ አደርጉ ከዚህ ትይዩ ትምህርት ቤት በማቋቋም ጥበቡን ተማሪወች እንዲቀስሙ አደረጉ። የመጀመሪያው ትክክለኛ የመሳሪያ ዝርዝር የተገኘው ከመቅደላ በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን ነበር፡ 15 መድፎች፣ 7 አዳፍኔዎች፣ 11፣063 ጠመንጃዎች፣ 875ሽጉጦች፣ 481 ሳንጃዎችና ጥይቶችን ያጠቃልላል። ውስጣዊ ተቃውሞና ግርግር አስቸጋሪው የኢትዮጵያ ቤ/ክርስቲያንን ሽግግር አጼ ቴዎድሮስ ያሰቡትን ለውጥ በተግባር ለመፈጸም ቋሚ የተረጋጋ የመዋዕለ ንዋይ መሰረት እንደሚያስፈልጋቸው ተገነዘቡ በዘመኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ከሁሉ ግምባር ቀደም ሃብታም ድርጅት ነበር። አጼ ቴዎድሮስ የተዋህዶን ትምህርት ስለደገፉና አቡነ ሰላማም ይህ ጉዳይ ስላስደስታቸው በቴዎድሮስና በቤተክርስቲያን መካከል የነበረው ግንኙነት በመጀመሪያው የንጉሱ ዘመን መልካም ነበር። 17፣። በፖለቲካው አንድነት እንደሚፈልጉ ሁሉ በሃይማኖቱም አንድነትን ማየት ይፈልጉ ነበር። በዘመኑ ቴዎድሮስ እጅግ ሃይማኖተኛና የጋብቻን አንድ ለአንድ መጽናት የሚያክብሩ፣ የቤተክርስቲያን ክፍፍልን የሚቃወሙና እንዲሁም "ከክርስቶስ ውጭ እኔ ባዶ ነኝ" የሚሉ መሪ ነበሩ። በዚህ ምክንያት ከቤተ ከርስቲያን ጋር የነበረው የመጀመሪያ ግንኙነት ጥሩ የነበር ቢሆንም የቴዎድሮስና የአቡነ ሰላማ (እንዲሁም መላው የቤተክርስቲያኒቱ ቀሳውስት) ግንኙነት ቀስ እያለ እየተበላሸ ሄደ፣ ለዚህም ምክንያቱ ቤተክርስቲያኒቱን ለመለወጥ ያደረጉት አንድ አንድ ተግባር ነበር። ከቤተክርስቲያን ጋር ያለው ጥል በተለይ ፈጦ የወጣው የመሬት ይዞታን ለማሻሻል ያቀዱትን ሃሳብ ባሰውቁ ጊዜ ነበር። ለምሳሌ በ1848 ዓ.ም. ቀሳውስቱን ሰብስበው እንዲህ አሏቸው፡" እኔስ ምን ልብላ፣ ወታደሮቸስ? ግማሹን መሬት የመስቀል መሬት ብላችሁ ትወስዳላችሁ፣ ግማጩን ደግሞ ሪምና ገዳም 19፣"። መሬቱን ለግብር ከፋይ ገብሬወች በማከፋፈል አገሪቱ ላይ ሊያካሂዱት ላሰቡት መሻሻል ወጭ ቋሚ ገቢ ለማግኘት ነበር። 1852 ላይ የመሬት የዞታ ማሻሻሉ ስራ በከፊልም ቢሆን ተከናወነ በዚህ ወቅት የቤ/ክርስቲያን መሬት በከፊል ለገበሬወች አከፈፋሉ። ይህም በፍካሬ እየሱስ ላይ እንደተጠቀሰውና በእውን እንደነበረው ቀዳማዊ ቴዎድሮስ ስራ ነበር። በዚሁ አመት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከሁለት ቄሶችና ሶስት ዲያቆኖች በላይ እንዳይሆን 96 ከዚህም በላይ ደብተራነትን ከነአካቴው ለማጥፋት እንዳሰቡ ገለጹ። ብዙ ደብሮች ከአስፈላጊ በላይ የሰው ሃይል ሲኖራቸው ነገር ግን ከግብር ነጻ ስለሆኑ የአገሪቱን ሃብት በከንቱ ያባክናሉ፣ ይህም አጼ ቴዎድሮስ አጥብቀው የተቃወሙት ስርዓት ነበር። ንጉሱ በወግ አጥባቂ ቀሳውስት ላይ ያላቸውን መጸታዊ ንቀት ሲገልጹ "ዱላቸውን ከመንደር መንደር እየጎተቱ ያለ ምንም ስራ የሚያውደለድሉ ይሏቸው ነበር። ሆኖም ቀሳውስቱ አርፈው የንጉሱ ተጠቂ መሆን አልቻሉም። በ1856 ዓ.ም. አቡነ ሰላማ እስከታሰሩ ድረስ ቤተክርስቲያኗ በአቡኑ መሪነት በንጉሱ ላይ ተቃውሞ አነሳች። የቀሳውስቱ ዋና ማጥቂያ ስልት የንጉሱን "ነጣቂ"እንጂ "ህጋዊ ንጉስ" አለመሆን ማስታወስ ነበር። ውስጣዊ ግርግር የጎጥ አመጾች አስተዳደሩ ማዕከላዊ እየሆነ በሄደ ቁጥር የሃይላቸውን መሸርሸር የተረዱት የየጎጡ ባላባቶች ጦር ማንሳት ጀመሩ። የጎጃሙ ተዳላ ጓሉ፣ የወልቃይቱ ጢሶ ጎበዜ፣ የሸዋወቹ ሰይፉ ሳህለስላሴና በዛብህ፣ የወሎዎቹ ደጃዝማች ሊበን አምዴ አመጽ አስነሱ። በዋግሹም ጎበዜ የሚመራው የላስታ ጦር ጭራሽ ጎንደርን ለጥቂት ጊዜ ለመቆጣጠር ቻለ፣ ሰሜንና ወገራም እንዲሁ ለአመጽ ተነሳሱ። በመጀመሪያዎቹ የቴዎድሮስ ዘመናት የትግራዩ ደጃዝማች ካሳ ምርጫ ከሌሎቹ ባላባቶች በተለየ መልኩ ለአዲሱ ንጉስ ክብርና ታማኝነት ያሳይ ነበር። በዚህ ወቅት የንጉሠ ነገሥቱ ጦር ሰራዊት ከሁሉ የተሻለ ስለነበር ሁሉኑም አመጽ በሃይል ለመቆጣጠር ቻለ። የንጉሱን ሰራዊት መመገብ የሰለቻቸው ገበሬወች ግን ባንጻሩ ለአመጹ መበረታታት አስተዋጾ አደረጉ። በየጊዜው የሚካሄደው ዘመቻም ለድህነትና ለህዝብ ማለቅ ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገ መጣ። በዚህ መካከል የአገሪቱን ብሄራዊ መከላከያ ለማጠናከር አጼው ያወጡት የግብር ስልት አዲሱን ስርዓት ከገበሬወች ዘንድ ሙሉ በሙሉ ለየው እኒህ ተቃውሞወች ከተራ ሰውነት ተነስተው አገሪቱን ለማሳደግና ፍትሃዊ ስርዓት ለማስፈን በሞከሩት አጼው ዘንድ አሳዛኝ ነበሩ። በ1850ወቹ ንግሡ በዛ ያሉ አመጾችን በትግሬና በበጌምድር ለማፈን ቻሉ። ታህሳስ 1852 የሰሜኑ ክፍል አመጽ ዋና አዛዥ የነበረውን አገው ንጉሴን ወግተው ገደሉ። በ1857 መቅደላ ያደገው ወጣቱ ምኒሊክ ምንም እንኳ ንጉሱን ቢወድም ከመቅደላ አምልጦ ሸዋ በመግባት የግዛቱን ኢ-ጥገኝነት አወጀ። ጎበዝ የተሰኘው የድሮው የላስታ መሪ ልጅ የላስታ መሪ በመሆን ስልጣኑን አወጀ፣ ትግራይም እንዲሁ በካሳ ምርጫ ስር ወደቀ። ከ1858-59 ንጉሱ የጢሶ ጎበዜን ጦር በጎንደርና የተድላ ጓሉን ሃይሎች በጎጃም ለመቆጣጠር ብዙ ዘመቻወን አካሄዱ። በነዚህ ዘመቻወች ብዙ ወታደሮች ከንጉሱ እየከዱ አመለጡ። በ1859 በንጉሱ ሙሉ ቁጥጥር ስር የነበረ አካባቢ ቢኖር በጌምድር ነበር 72። ጥቅምት 1860 ላይ ቴዎድሮስ ደብረታቦርን አቃጥለው ወደ መቅደላ በመሄድ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ ኑሮአቸውን በዚያ አደረጉ። አጼ ቴዎድሮስ ያቀዱት እና ለመተግብረ የፈለጉት አገር በተግባር መስራት አልቻለም። ንጉሱ የሃገራቸውን ህዝብ ምንጊዜም ላለመበደል ቢፈልጉም የፖለቲካውንና የፍትሃዊ ስርዓቱን ቅጥ ለማስተካከል አይነተኛ አማራጭ የወታደራዊ ሃይል በመሆኑ ብቻ ጦር መክፈት ግድ እንዳላቸው ሳይናገሩ አላለፉም። ከባህር ጠረፍ በርቀት የመሰረቱት መቅደላም እንደ ትግራይና ሸዋ በፍጥነት ዘመናዊ ጦር መሳሪያን ሊያገኝ አልቻለም። የንጉሱ በጣም ጠንካራ ወታደራዊ ዲሲፕሊን(ግብረ ገብ) ብዙዎቹ ወታደሮች እንዲከዱ አደረገ። ባንድ ወቅት የአጼው ሰራዊት ከመቶ ሺህ በላይ የነበር ሲሆን በ1858 ከአስር ሺህ ብዙ አይበልጥም ነበር። በቁም እስር የነበሩት አቡነ ሰላማ በ1859 ሲሞቱ አጠቃላይ ክርስቲያኑ ክፍል በቴዎድሮስ ላይ ከፍተኛ ጥላቻን አሳየ። በአገሪቱ የነበረው የተቃውሞ መጠን ከማየሉ የተነሳ አጼ ቴዎድሮስ ከደብረታቦር መቅደላ ባሰሩት መንገድ እንኳ ሳይቀር በሰላም መንቀሳቀስ አልቻሉም። በ1859 መጨረሻ ይሄው መንገድ እጅግ አደገኛ እየሆነ በመምጣቱ ንጉሰ ነገስቱ በመቅደላ ሙሉ በሙሉ ተወሰኑ። የሃይማኖት ግርግር በንጉሱና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን መካከል የነበረው ግንኙነት እየተበላሸ ቢሄድም ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር የነበርው ግንኙነት የከፋ ነበር። በመጀመሪያ፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ካቶሊኮች፣ እስላሞች፣ እና ፈላሻወች የሃይማኖት ነጻነት ተፈቅዶላቸው ይኖሩ ነበር። ሆኖም የአገሪቱ ውስጣዊ ሁኔታን መበላሸት ተከተሎ ሚሲዮኖችና ሌሎች ሃይማኖቶች ጫና እየበዛባቸው ሄደ። ንጉሰ ነገሥቱ ለአገሪቱ አዲስ አይነት ቴክኖሎጂን ለማስተዋወቅ ከነበራቸው ፍላጎት አንጻር በንግሱና በፕሮቴስታንት ሚሲዮኖች የነገረው የመጀመሪያ ግንኙነት መልካም ነበር። እንደ ካቶሊኮች የግለሰቦችን ሃይማኖት ለመቀየር ሳይሆን የቤተክርስቲያኒቱን ውስጣዊ አሰራር ለመቀየር ስለሚፈልጉ ፕሮቴስታንቶች በንጉሱ ዘንድ በጥሩ አይን ይታዩ ነበር። በ1847 ከስዊዘርላንድ የተላኩ ወጣት እጅ ጥበብ አዋቂ የፕሮቴስታንት ሚስዮኖችን ለማስተናገድ ንጉሱ ቃል ገቡ። እኒህ ሚስዮኖች በአማርኛ የታተሙ የሃይማኖት መጽሃፍትን ይዘው የመጡ ሲሆን፣ ቴዎድሮስ ግን የፈለጉት የጦር መሳሪያወችን ነበር፣ ሆኖም ቀረ ግን ንጉሱ ለኒህ ሚሲዮኖች ጥሩ አቀባበል አደረጉላቸው። በንጉሱ ፈቃድ መሰረት እኒህ ሚሲዮኖች የሰበካ ስራቸው ክርስቲያን ባልሆነው ክፍል ብቻ እንዲወስኑ ሲደረግ፣ የእጅ ጥበብ ስራቸው ግን ንጉሱ በፈለጉት መጠን ጥራት አልነበረውም። ሚሲዮኖቹ የእጅ ጥበብ አዋቂ ቢሆኑም ንጉሱ ላሰማራቸው ስራ ግን የተለማመዱ አልነበሩም። በ1853 አካባቢ በንጉሱ አግባቢነት አንስተኛ አዳፍኔ ሰርተው ሲያቀርቡ ወዲያው መድፍ እንዲሰሩ ከንጉሱ ዘንድ ጥያቄ ቀረበላቸው። ምንም እንኳ እኒህ ነገሮች ንጉሱን ቢያስደስቱም ፕሮቴስታንቶች ሌሎች አውሮጳውያን ላይ ይደርስ ከነበረው ጭቆና ተቋዳሽ ከመሆን አልተረፉም። ለዚህ ምክንያቱ ለምሳሌ የፕሮቴስታንት ሰባኪ የነበረውን ሄንሪ ስተርን ንግሱ ላይ የሚናገራቸው በጊዜው የሚያስቆጣ ንግግር ይጠቀሳል። ለምሳሌ ሄነሪ ስተርን ባሳተመው መጽሃፉ ላይ የንጉሱ እናት በጣም ደሃ ከመሆኗ የተነሳ "ኮሶ ትሸጥ ነበር" ይህም በንጉሱ ዘንድ እጅግ የሚያስቆጣ ነበር። ስለሆነም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብዙዎቹ ሚሲዮኖች (ከሄንሪ ስተርን ጨምሮ) በመቅደላ ታሰሩ። በአንጻሩ ከካቶሊኮች ጋር የነበረው ግንኙነት ምንጊዜም ብልሹ ነበር፣ ለዚህም ምክንያቱ ሁለት ነበር፦ ካቶሊኮች በስሜኑ በኩል የነበራቸው ተጽዕኖ የንጉሱን ስልጣን የሚገዳደር ነበር ከፈረንሳይ ሃይል ጋር የነበራቸው የጠበቀ ግንኙነት ነበር ጃኮቢና ጉስቲኖ የተሰኙ ካቶሊኮች በአንድ ወገን አቡነ ሰላማ በሌላ ወገን ባስነሱት የግል ጥል ምክንያት አጼ ቴዎድሮስ ካቶሊኮቹን በ1846 ከአገር ሲያባርሩ ኢትዮጵያዊ ደጋፊወቻቸውን እንዲታሰሩ አደርጉ። በዚህ ምክንያት ካቶሊኮች፣ በተለይ ፈረንሳይ ንጉሱን ከስልጣን ለማሰወገድ መዘጋጀት ጀመሩ። አገው ንጉሴ የተሰኘው የሰሜን መሪ ንጉሱን ለመውጋት እና ዘመናዊ ጦር መሳሪያ በተለዋጭ ለማግኘት እንደሚፈልግ ሲሰማ በፓሪስ ደስታ 135 አገው ንጉሴ ከካቶሊኮችና ከፈረንሳይ ባገኘው ድጋፍ መሰረት ሃይሉን በትግራይ ማጠናክር ጀመረ። ሆኖም በ1852 ላይ በጦርነት ተሸንፎ ተገደለ። አጼ ቴዎድሮስ ከመስሊሞች ጋር የነበራቸው ግንኙነት ለየት ያለ ነበር። ምንም እንኳ ሙስሊሞች ሃይማኖታቸውን በነጻነት እንዲያካሂዱ ንጉሱ ቢፈቅዱም ወደ ኦሮቶዶክስ ክርስትና እንዲለወጡ ግን ይደግፉ ነበር። የአጼ ቴዎድሮስ አባት የተገደሉት በሱዳን መስሊሞች ቢሆንም ቅሉ የሃይማኖት ነጻነታቸው ግን እንደተጠበቀ እንዲቀጥል ፍላጎታቸው ነበር። ሆኖም በአገዛዛቸው መጨረሻ ከሙስሊሞች ጋር የነበረው ግንኙነት የሻከረ ነበር፣ ለዚህ ምክንያቱ ሁለት ነበር፤ አንደኛው የኦቶማን ግዛት በቀይ ባህር መንሰራፋትና የሙስሊም ነጋዴወች ባሪያ ንግድ ነበር። ባሪያ ንግድ በንጉሠ ነገሥቱ አዋጅ መሰረት ወንጀል ነበር። ስለሆነም በሚያዚያ 1856 ዓ.ም. እስልምና በግዛቱ ሲከለከል፣ ይህን ጉዳይ በመቃወም ስራ ያቆሙ ሙስሊሞችኑን ንጉሱ ይቀጡ ነበር። ዲፕሎማሲና የአውሮጳውያን መታሰር የክርስቲያን ትብብር ህልም የንጉሰ ነገስቱን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በ፫ ዋና ኩነቶች ተጽዕኖ ደርሶበታል፦ በቴዎድሮስ ዘመን አገሪቱ በቱርክና ግብጽ ሃይሎች የተከበበች ስለነበር ከዚህ መከበብ እራስን ለማዳን ከአውሮጳውያን ጋር የክርስትና ትብብር ለመፍጠር ንጉሰ ነገሥቱ ፈቃድ ማሳየት ከአውሮጳ የመጡ መናኛ/ሰነፍ ዲፕሎማቶች በንጉሱ ዲፕሎማሳዊ ጥረት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማድረግ በተለይ በብሪታኒያ ዲፕሎማቶች የተሰሩ «ማመን የሚያስቸግሩ ስህተቶችና መልዕክት አለማድረስ» ናቸው። አጼ ቴዎድሮስ በግል ደረጃ ከነበራቸው የጠበቀ ሃይማኖታዊ እይታ ውጭ ስለ ዘመኑ የአውሮጳ እርስ በርስ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረትና ግንኙነት የጠለቀ መረጃ አልነበራቸውም። የአጼ ቴዎድሮስ የዲፕሎማሲ ደብዳቤወች እንደሚያሳዩት ለንጉሱ የሃይማኖት ጉዳይ ለዲፕሎማሲው ጥረት ዋና ጉዳይ ነበር፣ ከአውሮጳውያን ጋር ትብብር በመፍጠር የግብጽን እስላማዊ ሃይል ለመመከት የነበራቸውን ፍላጎት የዚሁ ሃይማኖታዊ ዲፕሎማሲ አካል ነበር። ስለሆነም ክርስቲያን እንግሊዝ ከሙስሊም ቱርክ ጋር ወግና ክርስቲያን ሩሲያን በክሪሚያ ጦርነት እንደወጋች ሲሰሙ ለንጉሱ እጅግ እንግዳ ሁኔታ ነበር። በተረፈ የዘመኑ የአውሮጳ ቤተመንግስቶች በዘረኛነት የተሸበቡ ስለነበር ለነሱ «አንድ የአፍሪቃ ንጉስ ከተራ የጎሳ አለቃነት ባለፈ አይታይም ነበር»፤ ይህም እውነታ ለንጉሱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የተደበቀ ነበር። ከውጫዊ አደጋ በተረፈ ውስጣዊ አመጽ ሲነሳም እንዲሁ ዲፕሎማሲን በመጠቀም ብሄራዊ ድጋፍ ለማግኝገት ንጉሱ ሞክረዋል4። ከአውሮጳ አገሮች የቴክኖሎጂ እና የወታደራዊ ድጋፍን መጠየቅ የዚህ ዲፕሎማሲ አካል ነበር። የፈረንሳዮች መልስ ንጉሱ የካቶሊክ ሚሲዮኖች በአገሪቱ እንዲዘዋወሩ ከፈቀዱ ድጋፉን እንደሚሰጡ ነበር፣ ሆኖም ግን ይህን ጉዳይ ንጉሱ እንደማይፈቅዱ አስቀድሞ የታወቀ ስለነበር «ድጋፍ ከመከልከል» ጋር ምንም ልዩነት አልነበረውም። ሩሲያኖች በክሪሚያ ጦርነት ተዳክመው ስለነበር ለንጉሱ ድጋፍ መላክ አልቻሉም። በዚህ ምክንያት በክሪሚያው ጦርነት መነሳት የተበሳጩት ቴዎድሮስ። በኋላ ያሰሩትን መድፍ ሴባስቶፖል በማለት ለሩሲያኖቹ ጦር ሜዳ ማስታወሻ ሰየሙ። በዚህ ትይዩ ከሙስሊም አገሮች ጋር፣ በተለይ ከግብጽ ጋር፣ የነበረው ግንኙነት እየተበላሸ ሄደ። በ1848፣ የአሌክሳንድሪያ ፓትሪያርክ ቄርሎስ ለጥየቃ ወደኢትዮጵያ በመጡበት ጊዜ አቡነ ሰላማ፣ በንጉሱ ስም፣ ግብጽ ወታደራዊ እርዳታ እንድታደርግ ጠየቁ። የቆብጡ ፓትሪያርክም የንጉሰ ነገሥቱ አምባሳደር በካይሮ ለመሆንና ጥያቄውን ለማቅረብ ተስማሙ። ሆኖም ይህ ጉዳይ ንጉሱ ሳይሰሙ በሁለቱ የሃይማኖት መሪወች መካከል የተከናወነ ስለነበር ንጉሰ ነገሥቱ የተደረገውን ጉዳይ ሲሰሙ ሁለቱንም ግብጻውያን እስር ቤት ከተቷቸው። በዚ ሁኔታ ነገሮች ቀጥለው ፓትሪያርክ ቄርሎስ ህዳር 1849 ላይ ሲፈቱ አቡነ ሰላማ በታሰሩበት 1859 አረፉ። ከዚህ ጎን ዋድ ንምር ለተሰኘው ሱዳናዊ የማክ ንምርልጅ ንጉሰ ነገስቱ እርዳታ ያደርጉ ነበር። ይሄ ሰውና አባቱ በግብጾች ላይ የሚካሄድ ሱዳናዊ አመጽ መሪ ነበሩ። ስለሆነም የአጼ ቴዎድሮስ ድጋፍ በአካባቢው የነበርውን የግብጽን ሃይል ለመነቅነቅ ከነበረ አቅድ የመነጨ ነበር። ይሁንና ከምዕራቡ የአገሪቱ ክፍል ከሚመጣው የግብጾች ጸብ ይልቅ ቴዎድሮስን ከአውሮጳውያን ጋር ለመስራት የገፋፋቸው በምስራቅ ከቀይ ባህር የሚመነጨው የቱርኮች አደጋ ነበር። የቴዎድሮስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በአብዛኞቹ አውሮጳውያን ሃይሎች ዘንድ አወንታዊ ምላሽ አለማግኘቱን ተከትሉ ንጉሱ ከእንግሊዞች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር ፈቀዱ። በተለይ ለዚህ ፍላጎት ዋና መንስኤ የነበረው ሊቀ መኩዋስ ብለው ከሰየሙት ሊቀመኳስ ጆህን ቤል እና የእንግሊዝ የመጀመሪያ ቆንጽላ በኢትዮጵያ ዋልተር ፕላውዴን ጋር የነበራቸው ቅርበት ነበር። በኒህ ሁለት ሰወች ምክንያት ንጉሱ ለብሪታንያ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የነበራቸው ሲሆን ነገር ግን ከእንግሊዞች ዘንድ ተገልባጭ ፍቅርና አድናቆት አልነበረም። የሆነው ሆኖ በመጨረሻ ንጉሱ የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር የፈለጉት አገር ዋና ጠላታቸውና የመውደቃቸው ምክንያት ሆኖ አረፈው። የእንግሊዝ ዲፕሎማሲ መበላሸት ጥቅምት 29፣ 1854 ላይ አጼ ቴዎድሮስ ሁለት ተመሳሳይ ደብዳቤወችን ለእንግሊዟ ንግስት ቪክቶሪያና ለፈረንሳዩ ናፖሊዮን ሳልሳዊ ላኩ። የደብዳቤያቸው ፍሬ ነገር የቱርኮች በኢትዮጵያ ግዛት መኖርን የሚቃወምና እነርሱን ከኢትዮጵያ ምድር ለማባረር ድጋፍ እንዲሰጡ ነበር። ደብዳቤው በ1854 የእንግሊዝ ቆንጽላ በኢትዮጵያ ተብሎ በተሾመው ካፕቴን ካሜሮን አማካኘት የተላከ ነበር። በዚሁ ደብዳቤ ንጉሠ ነገሥቱ ጆን ቤልና ዋልተር ፕላውዴን ለንጉሱ የገቡትን ቃል አስታውሶ ንግስት ቪክቶሪያ የንጉስ "ታላቅ ንግስት" እንደሆነችና "የክርስቲያኖች ወዳጅ" እንደሆነች ያስታውሳል። በዚህ ምክንያት እንግሊዝን እንደሚወዱ በደብዳቤው አስፍረዋል። ከዚህ በተጨማሪ የቱርኮች በኢትዮጵያ ባህር ወደብ ላይ መንሰራፋት በቀይ ባህርል ላይ ጉዞ እንዳያደርጉ የሚከለክልና አምባሳደርም እንዳይልኩ ያደረጋቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። ጥር 12፣ 1854 ላይ የቴዎድሮስ ደብዳቤ ለንድን ቢደረሰም። የታቀደውን አላማ አልፈጸመም። ለዚህ ምክንያቱ ሩሲያውያን የእንግሊዝን የህንድ ግዛት መገዳደራቸው ነበር። ስለሆነም እንግሊዝ ሩሲያን በጠላትነት ፈርጃ ክሩሲያ ጠላቶች -ከቱርኮች ጋር የጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማድረግ ሩሲያን አንድ ላይ የሚታገሉበት ወቅት ነበር። ስለሆነም የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መሰሪያ ቤት ለቴዎድሮስ ደብዳቤ መልስ እንኳ ሳይጽፍ እንዲሁ በተመላሽ ደብዳቤውን ለእንግሊዝ ወኪል በህንድ ላከ። የህንዱም መስሪያ ቤት ደብዳቤውን ወደ ጎን ከማስቀመጥ ውጭ መልስ አልላከም ነበር። በዚያው አመት ሚያዚያ 1854 ካፒቴን ካሜሮን ክእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ጸሃፊ ኸርል ረስል በደረሰው ደብዳቤ የእንግሊዝ መንግስት የኢትዮጵያን የድጋፍ ጥያቄወች ውድቅ እንዳደረገ ተረዳ። ካሜሮን ወደ ምጽዋ በመሄድ በዚያ እንዲወስን መልዕክቱ ያዝ ነበር። በዚህ መካከል ንጉሱ ከእንግሊዝ መልስ ባለማግኘታቸው የእንግሊዝ መንግስት ሆን ብሎ ችላ እንዳላቸው እምነት 156 በታሪክ አጥኝው ሪቻርድ ፐንክኽርስት አስተሳሰብ የዚህ እምነት ምክንያት የቴዎድሮስ "እንግሊዝ ግብጽን ትደግፋለች" የሚል "የተሳሳተ እምነት" ነው ይበል እንጂ። በእርግጥም እንግሊዞች ከግብስ ጋር የንግድ ግንኙነት ለመፍጠር ሞክረው ነበር። በ1856፣ በግብጽ ቁጥጥር ስር በነበረው የሱዳን ክፍል የጥጥ ተክልን ለመትከል የሚያስችል እቅድ ለመንደፍ የእንግሊዙ ካፒቴን ካሜሮን ተጉዞ ነበር። እኒህን ነገሮች የሚከታተሉት ንጉሱ፣ ካሜሮን የግብጾቹን በሱዳን ወረራ ዕውቅና እንደሚሰጥና በግልጽም ለነሱ እንደሚያደላ ተረዱ። ህዳር 1856 ላይ ከኸርል ሩስል ጸሃፊ ጄምስ መሪይ በመጣ ደብዳቤ መሰረት ካፒቴን ካሜሮን በምጽዋ ላይ እንጂ በኢትዮጵያ እንዳልተሾመ ማስታወሻ ደረስው። ነገር ግን ይሄ ደብዳቤ ስህተት ነበር ምክንያቱም የካፒቴን ካሜሮን ሹመት የንግስቲቷ ቆንጽላ በኢትዮጵያ የሚል ነበርና።።. እንኒህ ለውጦችን በጥሞና የሚከታተሉት አጼ ቴዎድሮስ ይህ የብሪታኒያ መንግስት ፖሊሲ በጊዜው ምጽዋን ይቆጣጠር የነበረውን የኦቶማን/ቱርክ ግዛት የሚደግፍ ሆነው አገኙት። ለቴዎድሮስ ትልቅ ትርጉም በነበረባት እየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያንና መኖሪያቸው በእንግሊዞች ጥበቃ ያገኝ የነበር ቢሆንም አዲስ የተሾመው የብሪታንያ ቆንጽላ ግን የኦቶማን ቱርኮች ኢትዮጵያውያንን ከሚኖሩበት ሲያባርሩ እንግሊዞቹ አልተቃወሙም ነበር። የእንግሊዝ መንግስት ኦቶማን ቱርክን ለመደገፍ መምረጡ በንጉሰ ነገስቱና በእንግሊዝ መንግስት መካከል ለተፈጠረው ጥል ዋና መነሻ ነበር። ንጉሡ ለጻፉት ደብዳቤ አንድ አመት ሙሉ መልሱን ሲጠባበቁ ቢቆዩም ምንም መልስ ባለማግኘታቸው ትዕግስታቸው ተሟጦ ጥር 4፣ 1856 ላይ ካፒቴን ካሜሮንና ሌሎች የዲፕሎማሲው አካሎች በመቅደላ ታሰሩ። እስክዚያው ድረስ መልስ ሳይሰጡ ዝምታን የፈቀዱት እንግሊዞች በርግጥም በዚህ ጊዜ ከዝምታቸው ነቁ ወዲያውም ወደ ጎን የተጣለው የንጉሱ ደብዳቤ ተፈልጎ ተገኘ፣ ብዙም ሳይቆይ እንግሊዞች ደብዳቤ ላኩ "አስቸኳይ" ደብዳቤ ተጽፎ በሆሙዝ ራሳም አማክይነት ጥር 26፣ 1858 ጣና ሃይቅ አጠገብ ለንጉሱ ደረሰ። በዚሁ ደብዳቤ የእንግሊዝ መንግስት እስረኞቹ እንዲፈቱና ይህ ሲሆን እርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቀ። በዚህ መልስ ያልረኩት ቴዎድሮስ ራሳምን እንዲሁ በመቅደላ እስር ቤት ከተቱት ለሰላም መውረድ የመጨረሻው ተስፋ ነው የተባለው ሚሲዮኑ ማርትን ፍላድ በሐምሌ 1858 ከቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝ ተላከ። ጥር 1859 ላይ ንጉሰ ነገሥቱ እስረኞቹን ፈተው ወደ ምጽዋ ከተወሰዱ በምትኩ የእንግሊዝ መንግስት ወታደራዊ እርዳታ እንደሚያደርግ ደብዳቤ ከእንግሊዝ መንግስት ደረሳቸው። በመካከሉ፣ ኢትዮጵያው ውስጥ የነበረቸው የማርቲን ፍላድ ሚስት፣ አውሮጳውያኑ እንደገና እንደታሰሩ ለባሏ አሳወቀች። ታህሳስ 185 ላይ እስረኞቹ ተፈተው ወደ ምጽዋ እንዲላኩ ፍላጎቱን አስታወቀ። በዚህ ወቅት ንጉሰ ነገሥቱ በማያባራ ዘመቻና የማያቋርጥ አመጽ ተጠምደው ስለነበር ከመቅደላ ምጽዋ ያለውን መንገድ መቆጣጠር አይችሉም ነበር። ስለሆነም ሚያዚያ 1859 ከእንግሊዝ የደረሳቸውን ዛቻ መልስ ባለመስጠት ችላ አሉት በዚህ ሁኔታ የእንግሊዝ መንግስት እስረኞቹን ለማስፈታት ዘመቻ ለማድረግ ወሰነ። የቴዎድሮስ መሞት የእንግሊዞች ዘመቻ በመረጃ ልውውጥ ላይ በተነሳው ችግርና እንዲሁም እንግሊዞች ለንጉሱ የላኩት ዛቻ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት ነሐሴ 1859 እንግሊዞች በሮበርት ናፒየር የሚመራ 32፣000 ጦር ሰራዊት አዘመቱ። እንግሊዞቹ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ስለሚሆነው ጉዳይ ጥልቅ መረጃ የነበራቸው ሲሆን በየአካባቢው እየተነሳ ስለነበር አመጽ ሙሉ ግንዛቤ ነበራቸው። የቴዎድሮስ ሰራዊት በድሮ ጊዜ ወደ 100፣000 የሚጠጋ የነበር ሲሆን በ1859 ከ5 እስከ 10፣000 በላይ አይሆንም ነበር። ንጉሰ ነገሥቱ የመጨረሻ ዘመቻቸውን ፈጽመው በጥቅምት 1860 ላይ መቅደላ ደረሱ፣ ይሄውም ከናፒየር ሰራዊት 2 ሳምንት ቀድሞ ነበር። የእንግሊዝ ሠራዊት ያለምንም ችግር ምጽዋ ላይ ካረፈ በኋላ ከሌሎች የኢትዮጵያ ኃይሎች ለምሳሌ ካሳ ምርጫ ድጋፍ በማግኘት፣ ከተክለ ጊዮርጊስ ሐዘን በማግኘት፣ ከዳግማዊ ምኒልክ ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ ሳይደርስበት ያለ ችግር ወደ መቅደላ 1969, 112 የብሪታንያ ሠራዊት በተለይ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘው ከካሳ ምርጫ ሲሆን፣ በቂ የመጓጓዣና የምግብ እርዳታ ያገኙት ከኒሁ ሹም ነበር። ሚያዚያ ቀን ዓ/ም ላይ የመጀመሪያውና የመጨረሻው የፊት ለፊት ጦርነት በቴዎድሮስ ሰራዊትና በናፒየር ሰራዊት መካከል ተካሄደ70። ይህ ጦርነት በታሪክ የአሮጌ ጦርነት ተብሎ ሲታወቅ ከመቅደላ እግርጌ የተደረገ ውጊያ ሲሆን በዚሁ ጦርነት የኢትዮጵያ ሰራዊት ተሸንፎ አፈገፈገ 12። በሚቀጥለው ቀን፣ ሚያዚያ11 ላይ፣ ናፒየር ለቴዎድሮስ በጻፈው ደብዳቤ ንጉሡ እስረኞቹን ከፈቱና ለ"እንግሊዟ ንግሥት እጅ ከሰጡ" "በክብር እንደሚያዙ" አሳወቃቸው። ሆኖም ንጉሰ ነገሥቱ ከኩራታቸው አንጻር ይህን አይነት መዋረድ እንደማይቀበሉ አሳወቁ። በዚህ ሁኔታ ንጉሱ አቋማቸውን በደምብ የሚያሳውቅ፣ በጊዜው "ድንቅ" የተባለ፣ ማንነታቸውንም በርግጥ የሚይሳይ ደብዳቤ ጻፉ። ለናፒርየር የተጻፈው ይህ ደብዳቤ አጠቃላይ የጊዜውን የኢትዮጵያ ሁኔታ የዳሰሰና ለኢትዮጵያ ህዝብ የገቡት የመጨረሻ ኪዳን ነበር። "በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ፡ አንድ አምላክ፡ በሥላሴ፣ በክርስቶስ፡ የሚያምነው ካሳ ለአገሬ ሕዝብ "ግብርን ተቀበሉ፣ ስርዓትንም ተማሩ" ብየ፡ብነገር፡ እነርሱ ግን፡ ይህን በመቃወም፡ ከኔ ጋር ጥል ጀመሩ። አንተ ግን በስራት፡ በሚመሩ፡ ወታደሮች፡ ታሸንፋለህ። አልባሌ የብረት፡ ኳስ፡ ፈርተው፡ የሚወዱኝና የሚከተሉኝ ሰወች ጥለውኝ ጠፉ። አንተ ፡ጥቃት፡ ስታደረስ፡ ከነርሱ፡ ጋር አልነበርኩም። እኔማ፡ እራሴን፡ ትልቅ አድርጌ፡ ቆጥሬ፡ ዋጋ በሌለው፡ መድፍ ተዋጋሁ። እግዚአብሔር ቢፈቅድ፡ ሁሉን ፡ለመመራት፡ ነበር፡ ሃሳቤ፣ አምላክ ይሄን፡ ከከለከለኝ ሞቴን እጠብቃለሁ እራስክን ፡ትላንት ፡ያስደሰትክ ሆይ፣ አምላክ እንደኔ አያድርግህ፣ በተለይ ደግሞ አምላክ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ጠላቶቸን አያድርግህ። እኔማ እየሩሳሌም ሂጄ ቱርኮችን ለማባረር ነበር ሃሳቤ። ወንዶችን የማረከ፣ በሌሎች ሊማረክ አይችልም። እኒህን "የጀግንነት ቃላት" ካስጻፉ በኋላ ንጉሱ እራሳቸውን ሊያጠፉ ቢሞክሩም ወታደሮቻቸው ሽጉጣቸውን ከጃቸው ነጥቀው አዳኗቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን ከእንግሊዞች ጋር የሚደረገው ድርድር አላቋረጠም፣ ንጉሰ ነገሥቱም ጥሉን በሰላም ለመፍታት ከመሞከር አልተቆጠቡም። ለፋሲካ በዓል ማክበሪያ ብለው ንጉሱ ለናፒየር ብዙ ከብቶች በስጦታ ላኩ። የእንግሊዙ ጦር አዛዥ ግን የከብት ስጦታውን አልቀበልም በማለት መልሶ ላከ። የስጦታውን አለመቀበል ንጉሱ ሲሰሙ ከመቅደላ ለመውጣት ሞከሩ ሆኖም ግን መቅደላ በእንግሊዞች ተከቦ ነበር። በዚህ ወቅት ለብዙ ወቅት የታሰሩት ሚሲዮኖችና የፖለቲከኛ እስረኞች ተፈቱ። የተፈቱትን እስረኞች ያዩ ገለልተኛ ተመልካቾች፣ በፈረንሳይ፣ በሩሲያ፣ በሳውዲ አረቢያ፣ በሆላንድ፣ አውስትራሊያና ስፔን በእስረኞቹ መልካም ጤና በጣም ይደነቁ ነበር፣ ከእስረኞቹ አንዱም «በታስርነበት ወቅት ጥሩ ቤትና ምግብ ነበረን የምንፈራው የንጉሱን ቁጣ ነበር»። ሚያዚያ ቀን ሦስት ሰዓት ላይ እንግሊዞች በመቅደላ ምሽግ ላይ የመጨረሻ ጥቃት አደረሱ። ንጉሱ፣ የሃይል ሚዛኑ ወደ እንግሊዞቹ ሙሉ በሙሉ አንዳጋደለ ስለተረዱ ለወታደሮቻቸው እንዲህ በማለተ ተለይተው ሄዱ "ተፈጽሟል! ከርሱ እጅ ከምወድቅ ብሞት ይሻለኛል"። ወዲያውም ከንግስት ቪክቶሪያ የተላከላቸውን ሽጉጥ መዘው በመጉረስ በጀግንነት አለፉ። እንግሊዞቹ 9 ሚሊዮን ፓውንድ አውጥተው ዘመቻውን ሲያቅዱ የመቅደላን ምሽግ አፍርሰው ንጉሱን ለመማረክ ነበር። ሆኖም ምሽጉ ሲሰበር ንጉሱ ሞተው ስልተገኘ ናፒየር እጅጉን በመናደዱ ሙሉውን መቅደላ እንዲመዘብርና የተረፈው በእሳት እንዲጋይ አደረገ። ሚያዚያ 18 ላይ እንግሊዞቹ የተከፋፈለች አገር ትተው ሄዱ፣ ወዲያም ግንቦት 1860 ላይ የላስታው ዋግሹም ጎበዜ በ60፣000 ጠንካራ ወታደሮቹ በመታገዝ ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጼ ተክለ ጊዮርጊስ በመባል ስልጣን ላይ ወጣ። ውርስና ትዝታ እንደ ባህሩ ዘውዴ አስተያየት የቴዎድሮስ ህይወት በ3 ቦታወች ይጠቃለላል፡ ቋራ፣ ጋፋትና መቅደላ። የመጀመሪያው የፖለቲካና ውታደራዊ መሰረትን ሲወክል፣ ሁለተኛው የዘመናዊነትን ፍላጎት ይወክላል፣ ሶስተኛው ደግሞ መጠለያንና፣ የሞት ቦታን ይወክላል። አጠቃላዩ የቴዎድሮስ ውጤት ቅይጥ ነው፣ የሚለው ባህሩ ዘውዴ፣ ለውጡ "ስልትና ጭብጥ" ይጎለዋል ሲል። ብዙው ለውጥ ሙሉ በሙሉ "ያልተተገበረ ሙከራ" ነበር ይላል። በአጠቃላይ መልኩ፣ ለውጡቹ ሊተገበሩ የሚችሉ የነበሩ በሂንም 60 ላለመተግበራቸው የተወሰኑ ምክንያቶች ነበሩ 68።የመጀመሪያው ምክንያት የኢትዮጵያ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ሲሆን ተራራማው ምልክዓ ምድር ተገቢ የሆነ የርስ በርስ መርጃ ልውውጥን ስለሚያግድ ለውጦቹን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለማስተዋወቅ አስቸጋሪ ነበር። ሌላው ደግሞ ታላቅ የወታደራዊ መዋቅራቸውን ወደ ፖለቲካዊ የበላይነት ለመተርጎም አለመቻላቸው ነበር። አንድ ክፍለ ዘመን ሙሉ ያለምንም መካከለኛ መንግስት የነበረን አገር በንጉሰ ነገሥቱ መልካም ፈቃድ ብቻ ለማስተካከል የማይቻል ነው። በ"ፖለቲካ ሹመት" አዲስ የገዢ መደብ ለመፍጠር የሞከሩትም ሁኔታ ከነባር ጥንታዊ ገዥወች ጋር ያጣላቸው ነበር60። ፓውል ሄንዝ እንደጻፈ ግን "ምን አልባትም የተዋቀረ መንግስት እና አንስተኛ አስተዳዳሪወች ቢኖራቸው፣ ንጉሱ ያሰቡትን ለውጥና ተሃድሶ ማድረግ ይችሉ ነበር"። የንጉሱ ተራማጅ ግቦች በቂ ስልትና አስፍላጊ ጥሬ ሃብት አልነበረውም 47፤ እንዲሁም ለነበሩበት ጊዜ የሚፈጥንና የሚጋጭ ነበር። ታሪክ ጸሃፊወች ቴዎድሮስ ከፈጸሙት ተግባራት ይልቅ ባሳዩት አርቆ አሳቢነትና ሊፈጽሙት በሞከሩት ተግባራት ሲያነሱ 60 ሺፈራው የተባለው የታሪክ ተመራማሪ ብዙ ጊዜ ታሪክ ጸሃፊወች ከዚህ ጎን ለጎን የቴዎድሮስን ህጋዊ መሪነት ጥያቄ ስር ሲጥሉ ይታያሉ ብሏል። ታሪክ አጥኝው ፓውል ሄንዝ እንደመዘገበ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያን ዘንድ "በጣም ታዋቂው መሪ ሆነ"። ንጉሱ ከሞቱ በኋላ በትውልዶች ዘንድ ለየት ያሉ ሰው መሆናቸው እየታመነ ሄደ፣ አንድ አንድ ጊዜም በተጋነነ ሁኔታ በተለይ ንጉሱ እስካሁን የሚታወሱበት ዋና ምክንያት ከጊዜይቸው ቀደም ብሎ በነበራቸው የተለያዩ እቅዶች ነበር። በኢትዮጵያኖች አይን ቴዎድሮስ የዘመናዊ ስልጣኔን በር ከፋች ሲሆኑ "እንደገና አንድ የሆነችና ጠንካራ ኢትዮጵያም" ምልክት ናቸው። የአገሪቱን ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አንድነት ለመመለስ ታላቁ ምኖታቸው ነበር፣ ያገሪቱን ጥንታዊ ድንበርም ለማስመለስ እንዲሁ 60። ምንም እንኳ በጊዜያቸው ብዙወች ባይረዷቸውም አገራቸውን ለማሰልጠንም ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል60። በፖውል ሄንዝ አስተሳሰብ ንጉሱ ለአንድ ክፍለ ዘመን ሲበሰብስ የነበረውን መንግስት በመቅጨት ተራማጅነትን፣ አንድነትንና ስልጣኔን አስተዋውቀዋል፣ ስለሆነም የመጀመሪያው ዘመናዊና ማዕከላዊ መሪ ነበሩ። የብሄራዊ አንድነት መፍጠርን ሂደት ንጉሱ ዙፋን ላይ ከወጡ ጀምሮ አካሂደዋል። በሞቱ ጊዜ ብዙውን ህዝብ ከእንቅልፍ በመቀስቀሳቸው፣ የርሳቸው ተከታዮች ንጉሱ የጀመሩትን ስራ ሊያስፈጽሙ ችለዋል። እንደ ታሪክ አጥኝው ሃሮልድ ማርከስአስተያየት የዳግማዊ አጼ ምንሊክ ግዛት በቴዎድሮስ የተጠነሰሰውና በአጼ ዮሓንስ የታደሰውን የማዕከላዊ ግዛትን ሃሳብ ድል ያበሰረ ነበር። በመጨርሻም ሌላው አጼ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚታወሱበት ምክንያት በ"ከፍተኛ ጀብዱዋቸው"ና ከርሳቸው በላይ ከፍ ባሉ ሰራዊቶች ላይ በተቀዳጇቸው አስገራሚ ድሎች ምክንያት ነበር ከሌሎች ታላላቅ መሪወች ይልቅ የአጼ ቴዎድሮስ አሟሟት በኢትዮጵያን ዘንድ የማይረሳ ነው 39። በጀግንነት፣ እጅ አልሰጥም ብለው ማለፋቸው ለህዝቡ "ቅቤ ያጠጣ" ተግባር እንደነበር ታሪክ አጥኝው ብርሃኑ አበበ ይገልጻል። ስለሆነም ንጉሱ በሞቱ ጊዜ የተገጠሙት ግጥሞች እስካሁን ድረስ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይታወቃሉ። መቅደላ አፋፉ ላይ ጩኸት በረከተ የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ የቴዎድሮስ እራሳቸውን ማጥፋት በጊዜው ለነበሩና አሁን ድረስ ላሉ ሰዓሊያን ስእሎች ጥሩ ርዕስ ሆነ። የንጉሱ ሞት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአውሮጳ ሳይቀር ለቴዎድሮስ ከፍተኛ ሃዘንና አድናቆትን አተረፈ። «ማርከው ሊወስዷቸው አቅደው የመጡትን እንግሊዞች ግብ በማኮላሸት »ቴዎድሮስም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቦታን አገኙ። ብዙ የልቦለድ ጸሃፊያን እና ቲያትር አዘጋጆች ለቴዎድሮስ እስካሁን ድረስ ይደርሳሉ ይጽፋሉ፣ ምሁራንም ቢሆን አሁን ድረስ ልጆቻቸውን በንጉሱ ስም ይሰይማሉ። የኢትዮጵያ ዘፋኞች፣ ዘመናዊ ዘፋኞች ሳይቀሩ የንጉሱን ስም ይጠቅሳሉ። እንደ ብርሃኑ አበበ አስተሳስብ "የምርኮን ውርደት አሻፈረኝ በማለት በመሞታቸው" በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ግምትን ንጉሱ እንዲያገኙ አድርጓል። ጳውሎስ ኞኞ፣ አጤ ቴዎድሮስ፤ ዓ.ም. 2001 |0631224939 ገጽ131-161 2002, ገጽ. 48-73 |0520224795 1969 1855-1868 ገጽ103-115 2004 ገጽ 376-377 |0810849100 1998 |2-7068-1340-7 ገጽ 87-104 1970, ገጽ 84-89 2004, 123-143 |2-84586-537-6 መጽሐፎች 1855-1991, 2002, 64-111 0-8214-1440-2) 1855 1896 ገጽ 27-42 ,1966 1867-68, 1979 2007, 440 978-2-84586-736-9) (1855-1868) 92-97 ታሪካዊ መዝገቦች 1868 በኢንተርኔት 1870 በኢንተርኔት 1869 በኢንተርኔት 1888 በኢንተርኔት (አማርኛ ደብዳቤ) በኢንተርኔት ልብ ወለዶች የታንጉት ምስጢር ስዕሎች ከአጼ ቴዎድሮስ ዘመን የሚመነጩና ሌሎች ከንጉሱ ጋር የተያያዙ ስዕሎችና ፎቶግራፎች ንጉሱ በፍርድ ወምበር, 1920 1950 የተሳለ, የብሪታኒያ ቤተ መዘክር 'የቴዎድሮስ ሞት], 1960, የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት ቤተ መዘክር በቲያትር አማርኛ፡ ተጨማሪ የውጭ ድረ ገጾች በገላውዲዎስ አርአያ 1855-89 ዜና መዋዕሎች ማመዛገቢያ ዋቢ መጻሕፍት 1998 1979 1768, 1769, 1770, 1771, 1772 1773, 1790, 64 2004 1844-1913, 1995 2002, ገጽ. 48-73 |0520224795 2001 1855-1991, 2002, 64-111 0-8214-1440-2) 1855 1896 ገጽ 27-42 አጼ
1832
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%88%95%E1%8C%88%20%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%A5%E1%89%B5%20%E1%89%B3%E1%88%AA%E1%8A%AD
የሕገ መንግሥት ታሪክ
የሱመር ከተማ ላጋሽ አለቃ ኡሩካጊና በ2093 ዓክልበ. ያሕል ያዋጀ ሕገ ፍትሕ በታሪካዊ መዝገብ እስከምናውቀው ድረስ መጀመርያ የሕገ መንግሥት ሰነድ ነው። ሰነዱ እራሱ ገና አልተገኘም፤ ነገር ግን ለዜጎቹ አንዳንድ መብት እንደ ፈቀደላቸው ይታወቃል። ለምሳሌ ለመበለትና ለደሀ አደጎች ቀረጥ እንዳስቀረላቸው ድሆችንም ከሃብታሞች አራጣ እንደጠበቃቸው ይታወቃል። ከዚህ በኋላ ብዙ መንግሥታት በተጻፈ ሕግ እንዲገዙ ልዩ ስርዓት ነበራቸው። ከተገኙት ሕግጋት ሁሉ ጥንታዊ የሆነው በ1983 ዓክልበ. የገዙ የኡር ንጉሥ የኡር-ናሙ ሕግጋት ነው። በተለይ ዕውቅ የሆኑ የጥንት መንግሥት ሕጎች የኢሲን ንጉሥ ሊፒት-እሽታር ሕግጋት (1832 ዓክልበ.) የኤሽኑና ሕግጋት (ምናልባት 1775 ዓክልበ. ግድም)፤ የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ሕግጋት (1704 ዓክልበ.) እና፤ ሕገ ሙሴ ለእስራኤል (1661 ዓክልበ.) ናቸው። ሕገ ሙሴ በተለይ በኦሪት ዘጸአት 21 እና 22 ያህዌ አስተካክሎ ከነዚህ ሁሉ የተሻሸሉት ብያኔዎች ይጠቅልላል። በኋላ ኬጢያውያን (1488 ዓክልበ. ግድም) እና አሦር (1080 ዓክልበ. ግድም) በበኩላቸው ለራሳቸው ሕግጋት አወጡ። በ628 ዓክልበ.፣ ድራኮ የሚባል ጸሃፊ የአቴና ከተማ ሕግጋት ጻፈ፤ ይህም ሕግ እጅግ ጨካኝ ሆኖ ይሙት በቃ ለማንኛውም ጥፋት ወሰነ። በ600 ዓክልበ.፣ የአቴና አለቃ ሶሎን አዲስ ሕገ መንግሥት ፈጠረ። የሰራተኞች ሸክም አቀለለ፣ ነገር ግን ባላባትነት በልደት ሳይሆን በንብረት ብዛት እንዲቈጠር አስደረገ። ክሊስቴኔስ እንደገና በ516 ዓክልበ. በዴሞክራሲያዊ መሠረት የተሻሸለ ለአቴና ሕገ መንግሥት አወጣ። የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ በ350 ዓክልበ. ግድም የሕገ መንግሥት ሀሣብ ለይቶ ዐወቀ። በጽሑፎቹ የአቴና፣ የስፓርታና የካርታግና ሕገ መንግሥቶች ያነጻጽራል። በመደምደሚያው የተሻለው ሕገ መንግሥት ከንጉሣዊ፣ ከመኳንንታዊና ከሕዝባዊ ወገኖች የተደባለቀ መሆኑን ገመተ። በሀሣቡ በመንግሥት የሚከፋፈሉ ዜጎች ከማይከፋፈሉ ከባርዮችና ዜጎች ካልሆኑ ሰዎች ልዩነት አደረገ። ሮማውያን መጀመርያ «12ቱ ሰንተረዦች» የተባለውን ሕገ መንግሥት ያወጡ በ457 ዓክልበ. ነበር። ከዚያ በኋላ አንዳንዴ የተለያዩ ሕጎችና ትእዛዛት ይጨምሩበት ነበር እንጂ እስከ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስ ድረስ (430 ዓ.ም.) ሌላ ክምቹ ሕገ መንግሥት አልኖረም ነበር። በኋላም በምሥራቁ መንግሥት (ቢዛንታይን) በኩል መጽሐፈ ዩስጢኒያኖስ (526 ዓ.ም.) ለአውሮፓ ከፍ ያለ ተጽእኖ ነበረው። ይህም በምስራቁ ነገሥታት 3ኛ ሌዎን ኢሳውራዊ «ኤክሎጋ» (732 ዓ.ም.) እና በ1ኛ ባሲሌዎስ «ባሲሊካ» (870 ዓ.ም.) በተባሉት ሕገ ፍትሐን ተከተለ። በሕንድ ንጉሥ አሾካ መንግሥት የአሾካ አዋጆች ሕግጋት በ264 አክልበ. መሠረቱ። ከምዕራቡ ሮማ መንግሥት ውድቀት ደግሞ ወደ ተረፈው ሕዋእ ውስጥ ከፈለሱት ጀርመናውያን ወገኖች አብዛኛው የራሳቸውን ሕጎች ዝርዝር በጽሑፍ አወጡ። በተለይ የሚታወቁም የቪዚጎቶች አለቃ ዩሪክ ሕግ (463 ዓ.ም.)፣ የቡርጎንዳውያን ሕግጋት (እኚህ ለጀርመናውያንና ለሮማውያን የተለያየ ፍትሕ ነበራቸው)፣ የአላማናውያን ሕግጋትና፣ የፍራንኮች ሕግጋት ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የተጻፉት ከ492 ዓ.ም. ጀምሮ ነው። በ498 ዓ.ም. የቪዚጎቶች አለቃ 2ኛ አላሪክ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስና አንዳንድ የተለያዩ የቀድሞ ሮማ ሐገጋት አከማችተው አዋጁአቸው። ከዚህም በኋላ የታዩ ሕጎች የሎምባርዶች ሕግጋት (635 ዓ.ም.)፣ የቪዚጎቶች አዳዲስ ሕግጋት (646 ዓ.ም.)፣ የአላማናውያን አዳዲስ ሕግጋት (722 ዓ.ም.) እና የፍሪዝያውያን ሕግጋት (777 ዓ.ም.) አሉ። በአውሮፓ አኅጉር ላይ የተጻፉት እነኚህ ፍትሖች ሁሉ በሮማይስጥ ቢጻፉም፣ በእንግሊዝ አገር ግን የተጠቀሙት ሕጎች ከኬንት ንጉሥ ኤጠልቤርት ሕጎች (594 ዓ.ም.) ጀምሮ በጥንታዊ እንግሊዝኛ የተቀነባበሩ ነበሩ። በ885 ዓ.ም. ታላቁ አልፍሬድ ይህንንና ሁለት የድሮ ፍትሖች ከሕገ ሙሴና ከሕገ ወንጌል ጋራ አጋጥመው የእንግሊዝ ሕገ መንግሥት ዶም ቦክ ሠርተዋል። በ596 ዓ.ም. በጃፓን 17 አንቀጽ ያለ ሕገ መንግሥት በልዑል ሾታኩ እንደተጻፈ ይታመናል። እንዲሁም በ614 ዓ.ም. ከነቢዩ መሐመድ የወጣው የመዲና ሕገ መንግሥት ዕጅግ ጥንታዊ ምሳሌ ነው። በዌልስ በ940 ዓ.ም. አካባቢ ንጉስ ህወል ዳ ሕጎቹን ጻፉ። በዛሬው ሩሲያ ደግሞ የክዬቭ ታላቅ መስፍን ያሮስላቭ ጥበበኛው ፕራቭዳ ያሮስላቫ የተባለውን ሕገ መንግሥት በ1009 ዓ.ም. ያህል ሠሩ። ይህ ሕግ በ1046 ታድሶ በኪዬቭ ሩስ በሙሉ ህጝ ሆነ። በስሜን አሜሪካ የኖሩ ኗሪ ጎሣ ሆደነሾኒ 'የአፈ ቃል' ሕገ መንግሥት «ጋያነሸጎዋ» የነበራችው ከ1080-1140 ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ እንደሆነ ይታመናል። ይህ ሕግ በከፊል ለአሜሪካ ሕገ መንግሥት ተጽእኖ እንደነበረው ይታመናልና የአሜሪካ ምክር ቤት በ1981 ዓ.ም. ይህንን ግንዛቤ አስታወቀ። በእንግሊዝ አገር በ1092 ዓ.ም. ንጉስ 1 ሄንሪ የነጻነት ሥርአት የተባለውን ሰነድ አዋጀ። ይህ መጀመርያ የንጉሱን ሥልጣን ወሰኖ ንጉሡ ለቤተ ካህናትና ለቤተ መሳፍንት ወገኖች የሚገባውን እንቅብቃቤ ገለጸ። ይህም መሰረት በመኳንንቱ ሲዘረጋ በ1207 ዓ.ም. የእንግሊዝ ንጉሱን ዮሃንስ (ጆን) ማግና ካርታ («ታላቅ ሥርዓት») የሚባለውን ሰነድ እንዲፈርሙት አስገደዱዋቸው። ከዚሁ መሃል ቁም ነገር የሆነው ንጉሡ ያለ ሕጋዊ ሂደት ማንንም ሰው እንዳይገድሉ፣ ከአገር እንዳያሳደዱ፣ ወይም እስር ቤት እንዳያስገቡ ከለከላቸው። በዚያ ወቅት ያ ሰነድ በእንግሊዝ አገር የነጻነት መሠረት ሆነ። በ1212 እና 1222 ዓ.ም. መካከል አንድ የሳቅሰን አስተዳዳሪ አይከ ቮን ረፕጎቭ ያቀነባበረው ሕግጋት ሳቅሰንሽፒግል በአንዳንድ ጀርመን ክፍላገር እስከ 1892 ዓ.ም. ድረስ ላይኛ ሕገ መንግሥት ሆነ። በ1228 ዓ.ም. ሱንዲያታ ከይታ ማሊ መንግሥትን ለማወሐድ የ'አፈ ቃል' ሕገ መንግሥት አወጡ። ይህ ሕግ 'ኩሩካን ፉጋ' ተብሎ ነበር። በ1240 አካባቢ በግብጽ አገር ቅብጡ አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል ፍትሐ ነገሥት በአረብኛ ጻፉ። እብን አል-አሣል ሕጎቹን የወሰዱት በከፊል ከሃዋርያት ጽህፈቶችና ከሕገ ሙሴ፤ በከፊልም ከድሮ ቢዛንታይን ነገስታት ሕጎች ነበር። መጽሐፉ በግዕዝ ተተርጉሞ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ወቅት በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በ1450 አከባቢ እንደነበር የሚል ታሪካዊ መዝገብ አለ። ቢሆንም መጀመርያ እንደ ሕገ ምንግሥት መጠቀሙን የተመዘገበው በዓፄ ሠርፀ ድንግል ዘመን (ከ1555 ጀምሮ) ነው። ፍትሐ ነገስት እስከ 1923 ዓ.ም. የብሄሩን ዋና ሕግ ሆኖ ቆየ። በ1904 ዓ.ም. ዐጼ 2 ምኒልክ የዘመናዊ ሕገ መንግሥት ፅንሰ ሀሳብ ተረድተው በጸሀፊው መምሬ ብስራት አንድ ሕገ መንግሥት የሚመስል ሰነድ ታተመ፤ ይህ ግን በውነት ሕገ መንግሥት አይባልም። «በምኒሊክ ስለተቋቋሙት ሚኒስቴሮች በምሳሌ የቀረበ ጽሑፍ» በምሳሌና በትርጓሜ የእያንዳንዱን ሚኒስቴር ሥራ እንደ ሰውነት አካላት አስመሰለ። ለምሳሌ፦ «የራስ ሥራ በነፍስና በስጋ ባጥንትና በዥማት ተዋደው በሚኖሩ አካላት ሁሉ አለቃና የውቀት መሰብሰቢያ ሳጥን ነው... የዦሮ ሥራ ዦሮ በትምህርት የሚገኘውን ጥበብና ዕውቀት ሁሉ ከራስና ከልብ ለማዋሐድ የድምጽ ኃይል የሚስብ መኪናነት አለው። ዦሮ ባይኖር ዕውቀትና ፍሬ ያለው ንግግር ባልተገኘም ነበር... ያይን ሥራ ዓይን ለማየት ከብርሃን ጋራ ተስማምቶ የተፈጠረ ያካላት ሁሉ መብራት ነው። በጅና በግር ለሚሠራ ሥራ በትምህርት ለሚገኝ ጥበብ ሁሉ መሪ ነው። ግዙፍ ሆኖ የተፈጠረውን ፍጥረት ሁሉ ለማየት ይችላል... የልብ ሥራ ልብ የደግና የክፉ ሃሳብ መብቀያ ነው... የጅ ሥራ እጅ በጥበብ ለተገኘ ሥራ ሁሉ የብረትና የናስ የወርቅ ፋብሪካና መኪና በያይነቱ፤ የርሻ የጽሀፈት የስፌት የቤት ሥራ በያይነቱ፤ ይህን ለመሰለ ሁሉ ሠራተኛ ነው... የግር ሥራ እግር ለነዚህ ለተቆጠሩት ሁሉ መቆሚያ ጉልበትና ብርታት ልብ ወደ አስበበትና ወደ ታዘዘበት መሄጃ ነው...» የሚመስል ቋንቋ በውስጡ አለበት። ኢትዮጵያ መጀመርያ ዘመናዊ ሕገ መንግሥት የተቀበለችው በ1923 አመተ ምኅረት በአጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የታወጀ ሲሆን የሕግ አማካሪ ቤቶች በሁለት ያስከፈለ ነው። ይህ የመንግሥታቸው ዋና መሠረት ሆኖ እስከ 1948 አ.ም. አገለገለ፤ በዚያ አመት ተሻሽሎ በወጣ ሕገ መንግሥት ሕዝቦች በመንግሥት ሥራ የሚጫወቱት ሚና እንደገና ተስፋፋ። ይህ ብቻ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሆኖ እስከ 1967 አ.ም. ቆየ፤ የዛኔ በደርግ በግፍ (በሕገ መንግስት እራሱ ባልሆነ ሂደት) ተሰረዘ።
13869
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%A5%E1%88%A9%E1%8A%90%E1%88%BD%20%E1%8B%B2%E1%89%A3%E1%89%A3
ጥሩነሽ ዲባባ
ጥሩነሽ ዲዲባባ በ 1978 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በአርሲ ክፍለ ሀገር በቼፋ ወረዳ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ነው። ጥሩነሽ ለቤተሰብዋ ከአምስት 3 ናት። የጥሩነሽ አስተዳደግ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነው። ነገር ግን የጥሩነሽ ቤተሰቦች የረጅም ርቀት አትሌቶች ናቸው። አክስቷ ደራርቱ ቱሉ ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ እና አንድ ጊዜ ደግሞ የ 10000 ሜትር አሸናፊ እና የብዙ አገር አቋራጭ ውድድር አሸናፊ ነበረች። ሌላ አክስቷም በቀሉ ዲባባ ጥሩ ሯጭ ነበረች ጥሩነሽ ልጅ እያለች በበቆጂ ስትኖር። ሌላዋ እህትዋ እጅጋየሁ ዲባባ ከጥሩነሽ ቀደም ብላ መሮጥ ጀምራ ነበር። ጥሩነሽ ዲባባ የቤተሰብዋን ፈለግ መከተል የጀመረችው እድሜዋ ከፍ ካለ በኋላ ነው። ጥሩነሽ ዲባባ ከ ሯጭ ቤተሰብ ብትፈጠርም ለመሮጥ ግን ምንም ፍላጎት አልነበራትም። ቱሉ በባርሴሎና ኦሎምፒክ በ 10000 ሜትር ባሸነፈች በሰባት አመቱ ጥሩነሽ ወደ አዲስ አበባ በ 2000 ዓ/ም መንገድ ጀመረች። ነገር ግን በቀሉ ዲባባ አባል ከሆነችበት ከእስረኞች ማረሚያ ፖሊስ ቡድን ስፖርት መስሪያ ክበብ ውስጥ አስመዝግባት ልምምድ ቀጠለች። ጥሩነሽ ዲባባ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጮች አንዷ ለመሆን በቃች። ጥሩነሽ ዲባባ በ 14 አመት እድሜዋ በጣም ወጣት እና ሰውነትዋም ተሰባሪ ይመስል ነበር። ብዙዎችም በሩጫ ምንም ተስፋ እንደሌላት እና ሩጫው የሚጠይቀውን ጠንካራ ሰውነት የላትም ብለው ያምኑ ነበር። ጥሩነሽ ዲባባ የኢትዮጵያ የረጅም ርቀት ተወዳዳሪ አትሌት ናት። በ 5000ሜትር የአለም ክብረ ወስን ባለቤት ስትሆን በ5000 ሜትር እና በ10000 ሜትር የኦሎምፒክ ውድድር አሸናፊ ናት። ጥሩነሽ አራት የአለም አቀፍ ውድድር እና አምስት የአገር አቋራጭ ውድድር አሸነፊ ናት። በቅጽል ስም “የሕጻን ፊት ያላት ደምሳሽ” በማለት ይጠሩዋታል። ውድድር ጥሩነሽ ዲባባ የመጀመሪያ አለም አቀፍ የውጪ ውድድር ያደረገችው በ 2001 በአለም አቀፍ አትሌቶች ውድድር ላይ ነው። ውድድሩን ስታካሂድ የ 15 አመት ልጅ ነበረች በዚህ ውድድር አምስተኛ በመሆን ጨርሳለች። በ 2003 በተደረገው የአፍሮ ኤሽያ ውድድር ላይ በ 5000 ሜትር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። የጥሩነሽ ዲባባ አስደናቂ ውጤቶች ማምጣት የጀመረችው በአለም አቀፍ አትሌቶች ውድድር ላይ በ 2003 2005 እና 2007 ላይ ነው። ጥሩነሽ በ 2003 በ 5000 ሜትር ተስፈንጥራ በመውጣት የስፔይኗን ማርታ ዶሚኒጌዝ እና የኬንያዋን ኤዲት ማሳያ ቀድማ በመግባት ነው። በወቅቱ የታወቀች አትሌት ባለመሆኗ ውድድሩን ያስተላልፉ የነበሩት እንግሊዛዊ ስቲቭ ክራም እና ብሬንዳን ፎስተር ውድድሩ 100 ሜትር እስኪቀረው አንድም ጊዜ ስሟን ሳይጠሩ ቀርተዋል። በ 2005 ውድድር ላይ ተስፈንጥራ በመውጣት ብርሀኔ አደሬን እና እህታዋን እጅጋየሁን ቀድማ በመግባት የመጀመሪያዋ 5000 10000 ሜትር የወርቅ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች። በ2007 ኦሳካ ላይ በተካሄደው የ 10000 ሜትር ውድድር የቱርክዋን ኤልቫን አቢይ ለገስን ተስፈንጥራ በመቅደም በ 31:55.41 አሽናፊ ሆናለች። በ 2004 በ አቴንስ ኦሎምፒክ በ 5000ሜትር ጥሩነሽ ሶስተኛ ወጥታለች በመሰረት ደፋር እና በ ኢሳቤላ ኦቺቺ በመሸነፍ። በሁኔታው ብዙ ሰዎች ቢበሳጩም የ 19 አመትዋ ጥሩነሽ የመጀመሪያዋ ወጣት ባለ ኦሎምፒክ ሜዳል ኢትዮጵያዊ አትሌት አሸናፊ አድርጓታል። በ2006 በወርቃማው ማህበር ውድድር ከስድስት የወርቅ ሜዳሊያ አምስቱን አሸናፊ ሆናለች (5,000 ሜ) በዚህም $83,333 ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች። የጥሩነሽ ዲባባ ሀይለኛ ተፎካካሪ መሰረት ደፋር ናት። ሁለቱንም በአንድ ውድድር ላይ ለማሳተፍ ታስቧል ነገር ግን ብዙ ጊዜ የሚሳካው በውድድር ላይ ብቻ ነው። የጥሩነሽ ዲባባ የአሯሯጥ ዘዴ በመጨረሻው ዙር ላይ ተስፈንጥሮ በመውጣት ማሸነፍ ነው። በመጨረሻው የ 10000 ሜትር ውድድር ላይ በ 2005 ዓ/ም የመጨረሻውን 400 ሜትር በ 58.33 ሴኮንድስ ነው የጨረሰችው። ጥሩነሽ ዲባባ በአገር አቋራጭ ሩጫም የተሳካ ውጤት አምጥታለች። ጥሩነሽ ዲባባ አለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድር ባሰናዳው አለም አቀፍ የአገር አቋራጭ ውድድር አምስት የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ነች። ውድድሩም የወጣቶች (በላውሳኔ 2003) አንድ አጭር ርቀት (በ ሴይንት ጋልሚየር 2005) እና ሌሎች ሁለት ረጅም ርቀት (በ ሴይንት ጋልሚየር 2005 እና በፉኩኦካ 2006 ከ2007 ጀምሮ በየምድቡ አንድ ውድድር ብቻ ይካሄዳል። ጥሩነሽ ዲባባ ሞምባሳ በተካሄደው ውድድር የብር ሜዳሊያ ተሸልማለች። በ ኤዲንበርግ ላይ በተካሄደው የወርቅ ሜዳሊያ በ 2008 ተሸላሚ ናት። የወርቅ ሜዳሊያ በኦሎምፒክ ጥሩነሽ ዲባባ በ 2008 ኦስሎ በተካሄደው የ 5000 ሜትር በ14 ደቂቃ 11.15ሴኮንድስ በመግባት በውድድሩ አንደኛ በመውጣት የአዲስ ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን በቅታለች። ጥሩነሽ ዲባባ በ ነሐሴ 15 2008 በቤጂንግ ኦሎምፒክ በተደረገው የ 10 000 ሜትር ውድድር በ 29:54.66 በመግባት በውድድሩ አንደኛ በመውጣት የአዲስ ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን በቅታለች። አሮጌው ሰአት 30:17.49 ነበር። የክብረ ወሰኑም ባለቤት የነበረችው የጥሩነሽ ዲባብ አክስት ደራርቱ ቱሉ ነበረች። ይህም ሰአት የተመዘገበው በሲድኔ ኦሎምፒክ በ2000ዓ/ም ነበር። አዲሱ የጥሩነሽ ዲባባ ክብረ ወስን ሁለተኛው ፈጣኑ የ 10000 ሜትር ሰአት ሲሆን ለአፍሪካ ደግሞ ፈጣኑ ክብረ ወሰን ነው። የቀድሞው የአፍሪካ ክብረ ወሰን (30:04.18) ነበር በ 2003 አለም አቀፍ ውድድር ላይ በ ብርሃኔ አደሬ የተመዘገበ። ከአንድ ሳምንት በኋላ በነሐሴ 22 2008 በ 5000 ሜትር መሰረት ደፋርን ቀድማ በመግባት በ 15:41.40 የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ለመሆን በቅታለች። በዚህ ኦሎምፒክ በሁለት ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘቷ በአለም የመጀመሪያዋ የሴት አትሌት ሆናለች። በ 5000 እና በ10000 ሜትር በአንድ ኦሎምፒክ አሸናፊ በመሆኗ። በ 2008 የቤት ውስጥ እና የሜዳ ዜና የአመቱ ታላቅ አትሌት በማለት ሸልሟታል። በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽንም አስደናቂ የሴት አትሌት በማለት ሽልማት አበርክቶላታል። ተመሳሳይ ሽልማት በ 2005 ቀደም ብሎ ተበርክቶላታል። በ 2009 በጤና ችግር ምክንያት በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ባዘጋጀው አገር አቋራጭ ውድድር በአማን ተሳታፊ ሳትሆን ቀርታለች። እንዲሁም በ 2009 በበርሊን በተካሄደው የአለም አቀፍ ውድድርም አልተሳተፈችም። በህዳር 15 2009 በዜቬኡቬሌንሉፕ(ሰባት ኮረብታ) በተካሄደው የ15 ኪሎ ሜትር ርቀት ውድድር በኔዘርላንድ ኒጄምገን የካዮኮ ፉኩሺን የ15 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰን በግማሽ ደቂቃ በመስበር በ 46:28 አሸናፊ ለመሆን በቅታለች። ከ 2005 በኋላ ይህ ውድድር የመጀመሪያዋ ነበር። ይህንንም አገር አቋራጭ የውጭ ውድድር እንደወደደችው ተናግራለች። ነገር ግን በቤት ውስጥ ውድድር እንደምትቆይ ተናግራለች። በሃምሌ 27 2012 እ.ኤ.አ በለንደን በተካሄደው የ10000 ሜትር የኦሎምፒክ ውድድር 30 ደቂቃ ከ20.75 ሰከንድ ገብታ ውድድሩን በማሸነፍ በኦሎምፒክ ያገኘችውን የወርቅ ሜዳሊያ ቁጥር ወደ ሶስት ከፍ አድርጋለች። በመሆኑም በኢትዮጲያ ውስጥ እጅግ ውጤታማ የሆነ አትሌትነትን ቦታ ከቀነኒሳ በቀለ ጋር ተጋርታለች። በጋጠማት ጉዳት ምክንያት ለ16 ወራት ከውድድር ተገልላ ታህሳስ 2012 ወደ ውድድር የተመለሰችው ጥሩነሽ ውድድሩ ሊጠናቀቅ አንድ ዙር ሊቀረው አካባቢ አፈትልካ በማምለጥ በረጅም ርቀት አሸንፋለች። የግል ሕይወት ጥሩነሽ ዲባባ ስለሺ ስህንን አግብታለች። ስለሺ ስህን በ2004 እና 2008 የ 10000 ሜትር ኦሎምፒክ ውድድር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ አትሌት ነው። ጥሩነሽ ዲባባ ከቤጂንግ ኦሎምፒክ በኋላም የእስረኞች ማረሚያ ፖሊስ ለቡድኑ እና ለሀገርዋ ላደረገችው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የ ሌ/ኮለኔልነት ማዕርግ ተሰጥቷታል። በስሟም በአዲስ አበባ ውጭ ሆስፒታል ተሰይሞላታል። የአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ውድድር ውጤት የአልማዝ ማህበር የአልማዝ ማህበር በየአመቱ የሚካሄድ የቤት ውስጥ እና የሜዳ ውድድር ነው። ውድድሩም የሚዘጋጀው በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ነው የተጀመረውም በ 2010 ነው። የአለም አትሌቲክስ መጨረሻ የአለም አትሌቲክስ መጨረሻ በየአመቱ የሚካሄድ የቤት ውስጥ እና የሜዳ ውድድር ነው። ውድድሩም የሚዘጋጀው በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ነው የተጀመረውም በ 2003 እስከ 2009. የወርቅ ማህበር የወርቅ ማህበር በየአመቱ የሚካሄድ የቤት ውስጥ እና የሜዳ ውድድር ነው። ውድድሩም የሚዘጋጀው በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ነው የተጀመረውም በ 1998 እስከ 2009. የውጭ ውድድር በቤት ውስጥ ውድድር የቪዲዮ ቃለ መጠይቅ 2007 ማጣቀሻዎች ወደ ውጭ የሚያገናኙ 2008 10000 2008 5000 የኢትዮጵያ
11610
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%83%E1%8D%93%E1%8A%95
ጃፓን
ጃፓን (ጃፓንኛ፡ ኒፖን ወይም ኒሆን፣ እና በመደበኛነት በምስራቅ እስያ የምትገኝ ደሴት ሀገር ናት። በሰሜን ምዕራብ የፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ የምትገኝ ሲሆን በምዕራብ በኩል በጃፓን ባህር ትዋሰናለች፣ በሰሜን ከኦክሆትስክ ባህር ወደ ምስራቅ ቻይና ባህር እና በደቡብ ታይዋን ይዘልቃል። ጃፓን የእሳት ቀለበት አካል ነች እና 377,975 ስኩዌር ኪሎ ሜትር (145,937 ካሬ ማይል) የሚሸፍኑ 6852 ደሴቶችን ያቀፈ ደሴት ነው። አምስቱ ዋና ደሴቶች ሆካይዶ፣ ሆንሹ (ዋናው መሬት)፣ ሺኮኩ፣ ኪዩሹ እና ኦኪናዋ ናቸው። ቶኪዮ የሀገሪቱ ዋና ከተማ እና ትልቁ ከተማ ናት; ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ዮኮሃማ፣ ኦሳካ፣ ናጎያ፣ ሳፖሮ፣ ፉኩኦካ፣ ኮቤ እና ኪዮቶ ያካትታሉ። ጃፓን በዓለም ላይ በሕዝብ ብዛት አስራ አንደኛው፣እንዲሁም በጣም በብዛት ከሚኖሩባቸው እና ከተሜዎች መካከል አንዷ ነች። ከአገሪቱ ሦስት አራተኛው የመሬት አቀማመጥ ተራራማ ሲሆን 125.44 ሚሊዮን ህዝቧን በጠባብ የባህር ዳርቻዎች ላይ ያቀፈ ነው። ጃፓን በ 47 የአስተዳደር ክልሎች እና በስምንት ባህላዊ ክልሎች የተከፋፈለ ነው. የታላቋ ቶኪዮ አካባቢ ከ37.4 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ያሉት የዓለማችን በሕዝብ ብዛት ያለው የሜትሮፖሊታን አካባቢ ነው። ጃፓን የምትኖረው ከላኛው ፓሊዮሊቲክ ዘመን (ከ30,000 ዓክልበ. ግድም) ጀምሮ ቢሆንም፣ ስለ ደሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በጽሑፍ የተጠቀሰው በቻይንኛ ዜና መዋዕል (የሃን መጽሐፍ) በ2ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. በ 4 ኛው እና 9 ኛው ክፍለ ዘመን መካከል የጃፓን መንግስታት በንጉሠ ነገሥት እና በሄያን-ኪዮ በሚገኘው የንጉሠ ነገሥት ፍርድ ቤት ሥር አንድ ሆነዋል። ከ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ፣ የፖለቲካ ስልጣን በተከታታይ ወታደራዊ አምባገነኖች (ሾጉን) እና ፊውዳል ገዥዎች (ዳይሚዮ) የተያዘ እና በተዋጊ ባላባቶች (ሳሙራይ) ክፍል ተፈጻሚ ነበር። ከመቶ አመት የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ ሀገሪቱ በ1603 በቶኩጋዋ ሾጉናቴ ስር አንድ ሆነች፣ ይህ ደግሞ ገለልተኛ የውጭ ፖሊሲ አወጣ። እ.ኤ.አ. በ 1854 የዩናይትድ ስቴትስ መርከቦች ጃፓንን ለምዕራቡ ዓለም ንግድ እንድትከፍት አስገደዷት ይህም የሾጉናቴው መጨረሻ እና የንጉሠ ነገሥቱ ኃይል በ 1868 እንደገና እንዲመለስ አድርጓል በሜጂ ዘመን የጃፓን ኢምፓየር በምዕራባውያን ሞዴል የተሠራ ሕገ መንግሥት አጽድቆ ተከታትሏል። የኢንዱስትሪ እና የዘመናዊነት ፕሮግራም. በወታደራዊ ኃይል እና በባህር ማዶ ቅኝ ግዛት ውስጥ ጃፓን በ 1937 ቻይናን ወረረች እና በ 1941 ወደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት እንደ አክሰስ ኃይል ገባች በፓስፊክ ጦርነት እና በሁለት የአቶሚክ ቦምቦች ሽንፈት ከደረሰባት በኋላ ጃፓን በ 1945 እጇን ሰጠች እና በሰባት ዓመታት አጋርነት ስር ወደቀች። ሥራ አዲስ ሕገ መንግሥት ባፀደቀበት ወቅት። እ.ኤ.አ. በ 1947 ሕገ መንግሥት መሠረት ጃፓን አሃዳዊ የፓርላማ ሕገ መንግሥታዊ ንጉሣዊ አገዛዝን ከሁለት ምክር ቤቶች የሕግ አውጭ አካል ጋር ጠብቋል ብሔራዊ አመጋገብ። ጃፓን የተባበሩት መንግስታት (ከ1956 ጀምሮ)፣ 20 እና የቡድን ሰባትን ጨምሮ የበርካታ አለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ነች። ምንም እንኳን ሀገሪቱ ጦርነት የማወጅ መብቷን ብታጣም ከዓለም ጠንካራ ወታደራዊ ሃይሎች ተርታ የሚመደበውን የራስ መከላከያ ሃይል አላት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጃፓን በኢኮኖሚያዊ ተአምር ሪከርድ የሆነ እድገት አግኝታለች በ1972 በዓለም ሁለተኛዋ ትልቅ ኢኮኖሚ ሆና ነበር ነገር ግን ከ1995 ጀምሮ የጠፉ አስርት ዓመታት እየተባለ በሚጠራው ጊዜ ቆሞ ነበር። እ.ኤ.አ. ከ2021 ጀምሮ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ያለው በስመ እና አራተኛው ትልቁ ነው። በሰብአዊ ልማት መረጃ ጠቋሚ "በጣም ከፍተኛ" ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ጃፓን ምንም እንኳን የህዝብ ቁጥር እየቀነሰች ቢሆንም ከአለም ከፍተኛ የህይወት ተስፋዎች አንዷ ነች። በአውቶሞቲቭ፣ በሮቦቲክስና በኤሌክትሮኒክስ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ዓለም አቀፋዊ መሪ የሆነችው ጃፓን ለሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ አስተዋጾ አበርክታለች። የጃፓን ባህል ታዋቂ የኮሚክ፣ አኒሜሽን እና የቪዲዮ ጌም ኢንዱስትሪዎችን የሚያጠቃልለው ጥበቡን፣ ምግብ ቤቱን፣ ሙዚቃውን እና ታዋቂ ባህሉን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ በሰፊው ይታወቃል። ሥርወ ቃል የጃፓን የጃፓን ስም ካንጂ በመጠቀም የተጻፈ ሲሆን ኒፖን ወይም ኒዮን በ 8 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ጉዲፈቻ ከመውሰዷ በፊት ሀገሪቱ በቻይና ዋ በጃፓን በ 757 ወደ ተቀይሯል) እና በጃፓን ውስጥ ያማቶ በሚለው ስም ትታወቅ ነበር። የመጀመሪያው የሲኖ-ጃፓን የገጸ ባህሪያቱ ንባብ ኒፖን በባንክ ኖቶች እና በፖስታ ቴምብሮች ላይ ጨምሮ ለኦፊሴላዊ አገልግሎት ተመራጭ ነው። ኒዮን በተለምዶ በዕለት ተዕለት ንግግር ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል እና በኤዶ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የጃፓን ፎኖሎጂ ለውጦችን ገፀ ባህሪያቱ “የፀሀይ ምንጭ” ማለት ነው፣[9] እሱም የታዋቂው የምዕራቡ ዓለም “የፀሐይ መውጫ ምድር” ምንጭ ነው። "ጃፓን" የሚለው ስም በቻይንኛ አጠራር ላይ የተመሰረተ እና ከአውሮፓ ቋንቋዎች ጋር የተዋወቀው በጥንት ንግድ ነው። በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማርኮ ፖሎ ገፀ-ባህሪያትን ሲፓንጉ በማለት የቀደመውን ማንዳሪን ወይም ዉ ቻይንኛ አጠራር መዝግቧል። የድሮው ማላይኛ የጃፓን ጃፓንግ ወይም ጃፑን ስም ከደቡባዊ የባህር ዳርቻ የቻይና ቀበሌኛ ተወስዶ በደቡብ ምስራቅ እስያ የፖርቹጋል ነጋዴዎች አጋጥሟቸዋል ቃሉን በ 16 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ወደ አውሮፓ ያመጡት በእንግሊዘኛ የመጀመሪያው የስሙ እትም በ1577 በታተመ መጽሐፍ ላይ የተገኘ ሲሆን ስሙን በ1565 የፖርቹጋልኛ ፊደላት ተተርጉሞ ጂያፓን ብሎ ጻፈ። ታሪክ ክላሲካል ታሪክ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ1000 ዓክልበ. ጀምሮ፣ የያዮ ሰዎች ከከዩሹ ወደ ደሴቶች መግባት ጀመሩ፣ ከጆሞን ጋር እየተጣመሩ; በያዮ ዘመን እርጥበታማ የሩዝ እርባታ፣ አዲስ ዓይነት የሸክላ ስራ እና ከቻይና እና ኮሪያ የብረታ ብረት ስራዎችን ጨምሮ ልምምዶችን ማስተዋወቅ ታየ። በአፈ ታሪክ መሰረት፣ ንጉሠ ነገሥት ጂሙ (የአማተራሱ የልጅ ልጅ) በ660 ዓክልበ ጃፓን ውስጥ ቀጣይነት ያለው የንጉሠ ነገሥት መስመር የጀመረ መንግሥት መሠረተ። ጃፓን በ 111 ዓ.ም በተጠናቀቀው የሃን ቻይንኛ መጽሐፍ ውስጥ በጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ታየ። ቡድሂዝም በ 552 ከባኬጄ (የኮሪያ መንግሥት) ወደ ጃፓን ገባ ግን የጃፓን ቡድሂዝም እድገት በዋነኝነት በቻይና ተጽዕኖ ነበረው። ቀደምት ተቃውሞ ቢኖርም ቡድሂዝም በገዢው መደብ ተስፋፋ፣ እንደ ልዑል ሾቶኩ ያሉ ምስሎችን ጨምሮ፣ እና በአሱካ ጊዜ (592-710) ጀምሮ ሰፊ ተቀባይነትን አግኝቷል። እ.ኤ.አ. በ 645 የተካሄደው የታይካ ሪፎርም በጃፓን ያሉትን ሁሉንም መሬት በብሔራዊ ደረጃ በማውጣት በአርኪዎች መካከል እኩል እንዲከፋፈል እና የቤተሰብ መዝገብ እንዲጠናቀር ትእዛዝ ሰጠ ለአዲሱ የግብር ስርዓት መሠረት። የ672 የጂንሺን ጦርነት፣ በልዑል ኦማማ እና በእህቱ ልጅ በልዑል ኦቶሞ መካከል የተደረገው ደም አፋሳሽ ግጭት፣ ለቀጣይ አስተዳደራዊ ማሻሻያ ትልቅ መንስዔ ሆነ። እነዚህ ማሻሻያዎች የተጠናቀቁት የታይሆ ኮድን በማወጅ ሲሆን ይህም ያሉትን ህጎች በማጠናከር የማዕከላዊ እና የበታች የአካባቢ መንግስታትን መዋቅር አቋቋመ። እነዚህ የህግ ማሻሻያዎች የሪትሱሪዮ ግዛትን ፈጠሩ፣ የቻይና አይነት የተማከለ የመንግስት ስርዓት ለግማሽ ሺህ ዓመት በቦታው ላይ ቆይቷል። የናራ ጊዜ (710–784) በሄይጆ-ኪዮ (በአሁኑ ናራ) የሚገኘውን ኢምፔሪያል ፍርድ ቤት ያማከለ የጃፓን መንግስት መፈጠሩን ያመለክታል። ወቅቱ የኮጂኪ (712) እና ኒዮን ሾኪ (720) መጠናቀቅ፣ እንዲሁም በቡዲስት አነሳሽነት የጥበብ ስራ እና ስነ-ህንፃ በማዳበር አዲስ የስነ-ፅሁፍ ባህል በመታየቱ ይታወቃል። እ.ኤ.አ. በ 735-737 የተከሰተው የፈንጣጣ ወረርሽኝ ከጃፓን ህዝብ አንድ ሶስተኛውን እንደገደለ ይታመናል። እ.ኤ.አ. በ 784 ንጉሠ ነገሥት ካንሙ ዋና ከተማውን አዛውሮ በ 794 በሄያን-ኪዮ (በዛሬዋ ኪዮቶ) ላይ ሰፈረ። የሙራሳኪ ሺኪቡ የጄንጂ ተረት እና የጃፓን ብሔራዊ መዝሙር "ኪሚጋዮ" ግጥሞች የተጻፉት በዚህ ጊዜ ነው የፊውዳል ዘመን የጃፓን ፊውዳል ዘመን የሳሙራይ ተዋጊዎች ገዥ መደብ ብቅ ማለት እና የበላይነት ይታወቅ ነበር። እ.ኤ.አ. በ 1185 በጄንፔ ጦርነት የታይራ ጎሳ ሽንፈትን ተከትሎ ሳሙራይ ሚናሞቶ ኖ ዮሪቶሞ በካማኩራ ወታደራዊ መንግስት አቋቋመ። ዮሪቶሞ ከሞተ በኋላ፣ የሆጆ ጎሳ ለሾጉን ገዥዎች ሆነው ወደ ስልጣን መጡ። የዜን የቡድሂዝም ትምህርት ቤት በካማኩራ ጊዜ (1185-1333) ከቻይና ተዋወቀ እና በሳሙራይ ክፍል ዘንድ ታዋቂ ሆነ። የካማኩራ ጦር በ 1274 እና 1281 የሞንጎሊያውያን ወረራዎችን ከለከለ በኋላ ግን በንጉሠ ነገሥት ጎ-ዳይጎ ተወገደ። በሙሮማቺ ዘመን (1336-1573) ጀምሮ ጎ-ዳይጎ በ1336 በአሺካጋ ታካውጂ ተሸንፏል።የተተካው አሺካጋ ሾጉናቴ የፊውዳል የጦር አበጋዞችን (ዳይሚዮ) መቆጣጠር ተስኖት በ1467 የእርስ በርስ ጦርነት ተጀመረ፣ የመቶ አመት የዘለቀው የሴንጎኩ ዘመን (የተከፈተ)። "ጦርነት ግዛቶች"). በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የፖርቹጋል ነጋዴዎች እና የየየሱሳውያን ሚስዮናውያን ጃፓን ለመጀመሪያ ጊዜ በጃፓን እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ቀጥተኛ የንግድ እና የባህል ልውውጥ ጀመሩ። ኦዳ ኖቡናጋ ብዙ ሌሎች ዳይሚዮዎችን ለማሸነፍ የአውሮፓ ቴክኖሎጂን እና የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅሟል፤ የስልጣን መጠናከር የጀመረው የአዙቺ–ሞሞያማ ጊዜ ተብሎ ይጠራ ነበር። እ.ኤ.አ. በ 1582 ኖቡናጋ ከሞተ በኋላ ተተኪው ቶዮቶሚ ሂዴዮሺ በ 1590 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሀገሪቱን አንድ በማድረግ በ 1592 እና 1597 ሁለት ያልተሳካ የኮሪያ ወረራዎችን ጀመረ ቶኩጋዋ ኢያሱ የሂዴዮሺ ልጅ ቶዮቶሚ ሂዲዮሪ አስተዳዳሪ ሆኖ አገልግሏል እና ቦታውን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ድጋፍ ለማግኘት ተጠቅሞበታል። ግልጽ ጦርነት በፈነዳበት ጊዜ ኢያሱ በሴኪጋሃራ ጦርነት በ1600 ተቀናቃኝ የሆኑትን ጎሳዎችን ድል አደረገ። በ1603 በንጉሠ ነገሥት ጎ ዮዚ ተሾመ ሾጉን ተሾመ እና በኤዶ (በአሁኑ ቶኪዮ) የቶኩጋዋ ሾጉናቴ አቋቋመ። ሾጉናቴው ቡክ ሾሃቶን ጨምሮ እርምጃዎችን አውጥቷል፣ ራሱን ችሎ የሚመራውን ዳይሚዮ ለመቆጣጠር እንደ የሥነ ምግባር ደንብ እና በ1639 የገለልተኛ ሳኮኩ (“የተዘጋ አገር”) ፖሊሲ ለሁለት ተኩል ምዕተ-አመታት የዘለቀው የኢዶ ዘመን (ኤዶ ዘመን) ተብሎ የሚታወቀውን አስጨናቂ የፖለቲካ አንድነት 1603-1868) የዘመናዊው የጃፓን ኢኮኖሚ እድገት የጀመረው በዚህ ጊዜ ውስጥ ሲሆን መንገዶችን እና የውሃ ማጓጓዣ መስመሮችን እንዲሁም የፋይናንስ መሳሪያዎችን እንደ የወደፊት ኮንትራቶች, የባንክ እና የኦሳካ ሩዝ ደላሎች መድን. የምዕራባውያን ሳይንሶች (ራንጋኩ) ጥናት በናጋሳኪ ውስጥ ከደች ግዛት ጋር በመገናኘት ቀጥሏል. የኢዶ ክፍለ ጊዜ ኮኩጋኩ ("ብሔራዊ ጥናቶች") በጃፓኖች የጃፓን ጥናት ፈጠረ ዘመናዊው ዘመን በ 1854 ኮሞዶር ማቲው ሲ ፔሪ እና የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል "ጥቁር መርከቦች" ጃፓን በካናጋዋ ስምምነት ለውጭው ዓለም እንዲከፈት አስገደዱ. ከዚያ በኋላ ከሌሎች ምዕራባውያን አገሮች ጋር የተደረጉ ተመሳሳይ ስምምነቶች ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶችን አስከትለዋል. የሹጉን መልቀቂያ የቦሺን ጦርነት እና በንጉሠ ነገሥቱ ሥር (የሜጂ ተሐድሶ) ሥር የተዋሃደ የተማከለ መንግሥት እንዲቋቋም አድርጓል። የምዕራባውያን የፖለቲካ፣ የፍትህ እና ወታደራዊ ተቋማትን በመቀበል፣ ካቢኔው የፕራይቪ ካውንስልን አደራጅቷል፣ የሜጂ ህገ መንግስት አስተዋወቀ እና የኢምፔሪያል አመጋገብን አሰባስቧል። በሜጂ ዘመን (1868-1912) የጃፓን ኢምፓየር በእስያ እጅግ የበለፀገች ሀገር ሆና እና በኢንዱስትሪ የበለፀገች የአለም ኃያል ሆና ወታደራዊ ግጭትን በመከተል የተፅዕኖ ግዛቷን አስፋች። በአንደኛው የሲኖ-ጃፓን ጦርነት (1894-1895) እና የሩስያ-ጃፓን ጦርነት (1904-1905) ጃፓን ታይዋንን፣ ኮሪያን እና የሳክሃሊን ደቡባዊ አጋማሽን ተቆጣጠረች የጃፓን ህዝብ በ1873 ከ35 ሚሊዮን በእጥፍ አድጓል። እ.ኤ.አ. በ1935 ሚሊዮን ወደ ከተማ መስፋፋት ትልቅ ለውጥ አምጥቷል።በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የታይሾ ዲሞክራሲ (1912–1926) በመስፋፋት እና በወታደራዊ ሃይል የተጋረደበት ወቅት ታይቷል። አንደኛው የዓለም ጦርነት ከድል አድራጊዎቹ አጋሮች ጎን የተቀላቀለችው ጃፓን በፓስፊክ ውቅያኖስ እና በቻይና የሚገኙ የጀርመን ንብረቶችን እንድትይዝ አስችሏታል። እ.ኤ.አ. በ1920ዎቹ ወደ ስታቲዝም የፖለቲካ ለውጥ የ1923 ታላቁን የቶኪዮ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ህገ-ወጥነት የታየበት ወቅት፣ የፖለቲካ ተቃውሞን የሚቃወሙ ህጎች መውጣታቸውን እና ተከታታይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎችን ተመልክተዋል። ይህ ሂደት እ.ኤ.አ. በ1930ዎቹ የተፋጠነ ሲሆን ይህም ለሊበራል ዴሞክራሲ ጠላትነት እና በእስያ ውስጥ ለመስፋፋት የሚተጉ በርካታ አክራሪ ብሔርተኛ ቡድኖችን ፈጠረ። በ 1931 ጃፓን ማንቹሪያን ወረረች እና ተቆጣጠረች; ወረራውን ዓለም አቀፍ ውግዘት ተከትሎ ከሁለት ዓመት በኋላ ከሊግ ኦፍ ኔሽን አባልነት ለቀቀ። እ.ኤ.አ. በ 1936 ጃፓን ከናዚ ጀርመን ጋር የፀረ-ኮንተርን ስምምነት ፈረመ እ.ኤ.አ. የ 1940 የሶስትዮሽ ስምምነት ከአክሲስ ሀይሎች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል።የጃፓን ኢምፓየር ሁለተኛውን የሲኖ-ጃፓን ጦርነት (1937-1945) በማባባስ ሌሎች የቻይናን ክፍሎች በ1937 ወረረ። እ.ኤ.አ. በ 1940 ኢምፓየር የፈረንሳይ ኢንዶቺናን ወረረ ከዚያ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ በጃፓን ላይ የነዳጅ ማዕቀብ ጣለች። እ.ኤ.አ. በታህሳስ 7-8፣ 1941 የጃፓን ጦር በፐርል ሃርበር እንዲሁም በእንግሊዝ ጦር በማላያ፣ ሲንጋፖር እና ሆንግ ኮንግ እና ሌሎችም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ ድንገተኛ ጥቃቶችን ፈጽሟል። በጦርነቱ ወቅት በጃፓን በተያዘችባቸው አካባቢዎች፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በርካታ ጥቃቶች ተፈጽመዋል፣ ብዙዎቹም ወደ ወሲባዊ ባርነት ተገደዋል። በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ የተባበሩት መንግስታት ድሎች በሶቪየት ወረራ የማንቹሪያ እና በ 1945 በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ የአቶሚክ ቦምብ ፍንዳታ ከተጠናቀቁ በኋላ ጃፓን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እጅ ለመስጠት ተስማማች። ጦርነቱ ጃፓን ቅኝ ግዛቶቿን እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህይወቶቿን አስከፍሏታል። የተባበሩት መንግስታት (በዩናይትድ ስቴትስ የሚመራው) በሚሊዮን የሚቆጠሩ የጃፓን ሰፋሪዎች ከቀድሞ ቅኝ ግዛቶቻቸው እና ወታደራዊ ካምፖች በመላው እስያ በመመለስ የጃፓን ኢምፓየርን እና በወረራቸዉ ግዛቶች ላይ ያለውን ተጽእኖ በማጥፋት ነበር። አጋሮቹ የጃፓን መሪዎች በጦር ወንጀሎች ክስ ለመመስረት ዓለም አቀፍ የሩቅ ምስራቅ ወታደራዊ ፍርድ ቤትን ጠሩ። እ.ኤ.አ. በ 1947 ጃፓን የሊበራል ዲሞክራሲያዊ አሠራሮችን የሚያጎላ አዲስ ሕገ መንግሥት አፀደቀች። በ1952 የተባበሩት መንግስታት የሳን ፍራንሲስኮ ስምምነት አብቅቷል እና ጃፓን በ1956 የተባበሩት መንግስታት አባል እንድትሆን ተፈቀደላት። ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበችበት ወቅት ጃፓን በዓለም ሁለተኛዋ ትልቁ ኢኮኖሚ እንድትሆን አድርጓታል። ይህ በ1990ዎቹ አጋማሽ ላይ የንብረት ዋጋ አረፋ ብቅ ካለ በኋላ፣ “የጠፋው አስርት ዓመት” ላይ አብቅቷል። እ.ኤ.አ. መጋቢት 11 ቀን 2011 ጃፓን በታሪኳ ከታዩት የመሬት መንቀጥቀጦች አንዱ የሆነውን የፉኩሺማ ዳይቺ የኒውክሌር አደጋ አስከትሏል። እ.ኤ.አ. ግንቦት 1 ቀን 2019 አፄ አኪሂቶ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ልጁ ናሩሂቶ ንጉሠ ነገሥት ሆነ የሪዋ ዘመን ጀምሮ የመሬት አቀማመጥ ጃፓን 6,852 ደሴቶችን ያቀፈች ሲሆን በእስያ ፓሲፊክ የባህር ዳርቻ ላይ ይገኛሉ። ከ3,000 ኪሎ ሜትር በላይ (1,900 ማይል) በሰሜን ምስራቅ ደቡብ ምዕራብ ከኦክሆትስክ ባህር እስከ ምስራቅ ቻይና ባህር ይዘልቃል። ከሰሜን እስከ ደቡብ ያሉት አምስት ዋና ዋና ደሴቶች ሆካይዶ፣ ሆንሹ፣ ሺኮኩ፣ ኪዩሹ እና ኦኪናዋ ናቸው። ኦኪናዋን የሚያካትቱት የሪዩኩ ደሴቶች ከኪዩሹ በስተደቡብ የሚገኙ ሰንሰለት ናቸው። የናንፖ ደሴቶች ከጃፓን ዋና ደሴቶች በስተደቡብ እና በምስራቅ ይገኛሉ። አንድ ላይ ሆነው ብዙውን ጊዜ የጃፓን ደሴቶች በመባል ይታወቃሉ. ከ 2019 ጀምሮ የጃፓን ግዛት 377,975.24 ኪ.ሜ. (145,937.06 ካሬ ማይል) ነው። ጃፓን በ29,751 ኪሜ (18,486 ማይል) ላይ በዓለም ላይ ስድስተኛው ረጅሙ የባህር ዳርቻ አላት። ራቅ ካሉ ደሴቶችዋ የተነሳ ጃፓን 4,470,000 ኪሜ2 (1,730,000 ስኩዌር ማይል) የሚሸፍን ከዓለም ስምንተኛ ትልቅ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አላት። የጃፓን ደሴቶች 66.4% ደኖች 12.8% ግብርና እና 4.8% የመኖሪያ (2002) ናቸው። በዋነኛነት ወጣ ገባ እና ተራራማ መሬት ለመኖሪያ የተገደበ ነው። ስለዚህ ለመኖሪያ ምቹ የሆኑ ዞኖች፣ በተለይም በባሕር ዳርቻዎች፣ በጣም ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት አላቸው፡ ጃፓን በሕዝብ ብዛት 40ኛዋ ነች። ሆንሹ እ.ኤ.አ. ከ2010 ጀምሮ በ450 2 (1,200/ስኩዌር ማይል) ከፍተኛውን የህዝብ ጥግግት ያላት ሲሆን ሆካይዶ ከ2016 ጀምሮ ዝቅተኛው የ64.5 2 ነው። መሬት (ኡሜትቴቺ). የቢዋ ሀይቅ ጥንታዊ ሀይቅ እና የሀገሪቱ ትልቁ የንፁህ ውሃ ሀይቅ ነው። ጃፓን በፓሲፊክ የእሳት አደጋ ቀለበት አጠገብ ስላለች ለመሬት መንቀጥቀጥ፣ ሱናሚ እና የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ በጣም የተጋለጠች ነች። በ2016 የአለም ስጋት መረጃ ጠቋሚ ሲመዘን 17ኛው ከፍተኛ የተፈጥሮ አደጋ ስጋት አላት። ጃፓን 111 ንቁ እሳተ ገሞራዎች አሏት። አውዳሚ የመሬት መንቀጥቀጦች, ብዙውን ጊዜ ሱናሚ ያስከትላሉ, በእያንዳንዱ ክፍለ ዘመን ብዙ ጊዜ ይከሰታሉ; እ.ኤ.አ. በ 1923 የቶኪዮ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ 140,000 በላይ ሰዎችን ገድሏል የቅርብ ጊዜ ዋና ዋና መንቀጥቀጦች እ.ኤ.አ. የ1995 ታላቁ የሃንሺን የመሬት መንቀጥቀጥ እና የ2011 የቶሆኩ የመሬት መንቀጥቀጥ ትልቅ ሱናሚ የቀሰቀሰ ነው። የአየር ንብረት የጃፓን የአየር ንብረት በአብዛኛው ሞቃታማ ነው ነገር ግን ከሰሜን ወደ ደቡብ በጣም ይለያያል. ሰሜናዊው ጫፍ ሆካይዶ እርጥበታማ አህጉራዊ የአየር ንብረት አለው ረጅም፣ ቀዝቃዛ ክረምት እና በጣም ሞቃታማ እና ቀዝቃዛ የበጋ። የዝናብ መጠን ከባድ አይደለም, ነገር ግን ደሴቶቹ ብዙውን ጊዜ በክረምት ውስጥ ጥልቅ የበረዶ ዳርቻዎች ይገነባሉ. በሆንሹ ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ ላይ ባለው የጃፓን ባህር ውስጥ የሰሜን ምዕራብ የክረምት ነፋሶች በክረምት ወቅት ከባድ በረዶ ያመጣሉ በበጋ ወቅት ክልሉ አንዳንድ ጊዜ በጠላት ምክንያት ከፍተኛ ሙቀት ያጋጥመዋል. የመካከለኛው ሃይላንድ ዓይነተኛ የውስጥ እርጥበታማ አህጉራዊ የአየር ንብረት አለው፣ በበጋ እና በክረምት መካከል ትልቅ የሙቀት ልዩነት አለው። የቹጎኩ እና የሺኮኩ ክልሎች ተራሮች የሴቶ ኢንላንድ ባህርን ከወቅታዊ ንፋስ ይከላከላሉ፣ ይህም አመቱን ሙሉ ቀላል የአየር ሁኔታን ያመጣል። የፓስፊክ የባህር ዳርቻ በደቡብ ምስራቅ ወቅታዊ ንፋስ ምክንያት መለስተኛ ክረምት የሚያጋጥመው እርጥበት አዘል ሞቃታማ የአየር ጠባይ አለው። የሪዩኪዩ እና የናንፖ ደሴቶች ሞቃታማ የአየር ጠባይ ያላቸው፣ ሞቃታማ ክረምት እና ሞቃታማ በጋ አላቸው። በተለይም በዝናብ ወቅት የዝናብ መጠን በጣም ከባድ ነው። ዋናው የዝናብ ወቅት በኦኪናዋ በግንቦት መጀመሪያ ላይ ይጀምራል, እና የዝናብ ፊት ቀስ በቀስ ወደ ሰሜን ይንቀሳቀሳል. በበጋ መጨረሻ እና በመጸው መጀመሪያ ላይ, አውሎ ነፋሶች ብዙውን ጊዜ ከባድ ዝናብ ያመጣሉ. የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር እንደገለጸው የዝናብ መጠን መጨመር እና የአየር ሙቀት መጨመር በግብርና ኢንዱስትሪ እና በሌሎች አካባቢዎች ላይ ችግር ፈጥሯል. በጃፓን እስካሁን የተለካው ከፍተኛው የሙቀት መጠን በጁላይ 23፣ 2018 ተመዝግቧል እና በነሐሴ 17፣ 2020 ተደግሟል። ብዝሃ ህይወት ጃፓን የደሴቶቹን የአየር ንብረት እና ጂኦግራፊ የሚያንፀባርቁ ዘጠኝ የደን አከባቢዎች አሏት። በሪዩኪዩ እና ቦኒን ደሴቶች ውስጥ ከሚገኙት ከንዑስትሮፒካል እርጥበታማ ሰፊ ቅጠል ደኖች እስከ መካከለኛው ሰፊ ቅጠል እና ድብልቅ ደኖች በዋና ደሴቶች መለስተኛ የአየር ጠባይ ክልሎች እስከ ሰሜናዊ ደሴቶች ቅዝቃዜና የክረምት ክፍሎች ድረስ መካከለኛ ሾጣጣ ደኖች ይገኛሉ። ጃፓን ከ90,000 በላይ የዱር አራዊት ዝርያዎች እንዳሏት እ.ኤ.አ. በ2019 ቡናማ ድብ፣ የጃፓን ማካክ፣ የጃፓን ራኩን ውሻ፣ ትንሹ የጃፓን የመስክ አይጥ እና የጃፓን ግዙፉ ሳላማንደርን ጨምሮ። ጠቃሚ የሆኑ የእፅዋት እና የእንስሳት አካባቢዎችን እንዲሁም 52 ራምሳር ረግረጋማ ቦታዎችን ለመጠበቅ ትልቅ የብሔራዊ ፓርኮች መረብ ተቋቁሟል። አራት ቅርሶች በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መዝገብ ውስጥ ገብተው አስደናቂ የተፈጥሮ እሴታቸው ተመዝግቧል አካባቢ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት በነበረበት ወቅት የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲዎች በመንግስት እና በኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽኖች ዝቅተኛ ነበሩ; በውጤቱም, በ 1950 ዎቹ እና 1960 ዎቹ ውስጥ የአካባቢ ብክለት በስፋት ተስፋፍቷል. እየጨመረ ለሚሄደው ስጋት ምላሽ በመስጠት፣ በ1970 መንግሥት የአካባቢ ጥበቃ ሕጎችን አስተዋወቀ። በ1973 የተከሰተው የነዳጅ ቀውስ ጃፓን ባላት የተፈጥሮ ሀብት እጥረት ምክንያት የኃይል አጠቃቀምን አበረታቷል። ጃፓን አንድ ሀገር ለአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት ያለውን ቁርጠኝነት በሚለካው በ2018 የአካባቢ አፈፃፀም መረጃ ጠቋሚ 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ጃፓን በአለም አምስተኛዋ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት ነች። የ1997 የኪዮቶ ፕሮቶኮል አዘጋጅ እና ፈራሚ ጃፓን የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀትን የመቀነስ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ የስምምነት ግዴታ አለባት። እ.ኤ.አ. በ 2020 የጃፓን መንግስት በ 2050 የካርቦን-ገለልተኛነት ኢላማ መሆኑን አስታውቋል የአካባቢ ጉዳዮች የከተማ አየር ብክለትን የታገዱ ጥቃቅን እና መርዛማ ንጥረነገሮች) የቆሻሻ አያያዝ የውሃ መውጣቱን የተፈጥሮ ጥበቃን የአየር ንብረት ለውጥን የኬሚካል አስተዳደርን እና ዓለም አቀፍ ኮርፖሬሽንን ያጠቃልላል ለጥበቃ ሥራ። ፖለቲካ ጃፓን የንጉሠ ነገሥቱ ሥልጣን በሥነ ሥርዓት ሚና የተገደበበት አሃዳዊ መንግሥት እና ሕገ መንግሥታዊ ንግሥና ነው። በምትኩ የአስፈፃሚ ስልጣኑ በጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሉዓላዊነታቸው የጃፓን ህዝብ በሆነው ካቢኔያቸው ነው። ናሩሂቶ የጃፓን ንጉሠ ነገሥት ነው፣ አባቱን አኪሂቶን በ2019 የ ዙፋን ሲይዝ ተተኩ።የጃፓን የሕግ አውጭ አካል ብሔራዊ አመጋገብ፣ የሁለት ምክር ቤት ፓርላማ ነው። በየአራት ዓመቱ በሕዝብ ድምፅ የሚመረጥ ወይም ሲፈርስ 465 ወንበሮች ያሉት የታችኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና 245 መቀመጫዎች ያሉት ከፍተኛ የምክር ቤት አባላት ያሉት ሲሆን በሕዝብ የተመረጡ አባላቱ ለስድስት ዓመታት ያገለግላሉ። ከ 18 ዓመት በላይ ለሆኑ አዋቂዎች ሁሉን አቀፍ ምርጫ አለ, ለሁሉም የተመረጡ ቢሮዎች በሚስጥር ድምጽ መስጠት. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የመሾም እና የማሰናበት ስልጣን ያለው ሲሆን ከአመጋገብ አባላት መካከል ከተሰየመ በኋላ በንጉሠ ነገሥቱ ይሾማል። ፉሚዮ ኪሺዳ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር; እ.ኤ.አ. በ 2021 የሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ አመራር ምርጫን በማሸነፍ ሥራውን ጀመሩ በታሪክ በቻይና ህግ ተጽእኖ ስር የነበረው የጃፓን የህግ ስርዓት በኤዶ ዘመን ራሱን ችሎ እንደ ኩጂካታ ኦሳዳሜጋኪ ባሉ ፅሁፎች አደገ። ከ 19 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ጀምሮ የፍትህ ስርዓቱ በአውሮፓ የሲቪል ህግ ላይ በተለይም በጀርመን ላይ የተመሰረተ ነው. እ.ኤ.አ. በ 1896 ጃፓን በጀርመን ቡርገርሊች ጌሴትዝቡች ላይ የተመሠረተ የሲቪል ኮድ አቋቁማለች እሱም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ማሻሻያዎችን አድርጓል እ.ኤ.አ. በሕግ የተደነገገው ሕግ የሚመነጨው ከሕግ አውጪው ነው፣ ሕገ መንግሥቱም ንጉሠ ነገሥቱ ሕግን የመቃወም ሥልጣን ሳይሰጡ በአመጋገብ የወጡትን ሕግ እንዲያውጁ ይደነግጋል። የጃፓን ሕግ ዋና አካል ስድስት ኮዶች ይባላል። የጃፓን የፍርድ ቤት ሥርዓት በአራት መሠረታዊ ደረጃዎች የተከፈለ ነው፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ሦስት የሥር ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ክፍሎች የውጭ ግንኙነት እ.ኤ.አ. ከ1956 ጀምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገር የሆነችው ጃፓን የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ከሚፈልጉት 4 ሀገራት አንዷ ነች። ጃፓን የ 7፣ እና አባል ስትሆን በምስራቅ እስያ የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊ ነች። እ.ኤ.አ. በ2014 9.2 ቢሊዮን ዶላር በመለገስ ከአለም አምስተኛዋ ትልቅ ለጋሽ ናት። ጃፓን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጠበቀ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ግንኙነት ያላት ሲሆን ከሱ ጋር የጸጥታ አጋርነትን ትጠብቃለች። ዩናይትድ ስቴትስ ለጃፓን የወጪ ንግድ ዋና ገበያ እና የጃፓን የውጭ ምርቶች ዋና ምንጭ ናት እናም ሀገሪቱን ለመከላከል ቁርጠኛ ነች በጃፓን ወታደራዊ ሰፈሮች ጃፓን የኳድሪተራል ሴኪዩሪቲ ውይይት (በተለምዶ “ኳድ”) አባል ነች፣ እ.ኤ.አ. በ2017 የተሻሻለው የባለብዙ ወገን የደህንነት ትብብር የቻይናን ተፅእኖ በህንድ-ፓሲፊክ ክልል ውስጥ ለመገደብ ከአሜሪካ ፣አውስትራሊያ እና ህንድ ጋር በመሆን ነባሩን የሚያንፀባርቅ ነው። ግንኙነቶች እና የትብብር ቅጦች. ጃፓን ከደቡብ ኮሪያ ጋር የነበራት ግንኙነት በታሪክ የሻከረ ነበር ምክንያቱም ጃፓን በጃፓን ቅኝ ግዛት ወቅት በኮሪያውያን ላይ ባደረገችው አያያዝ በተለይም በሴቶች ምቾት ጉዳይ። እ.ኤ.አ. በ2015 ጃፓን ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያለውን የምቾት የሴቶች አለመግባባት ለመፍታት መደበኛ ይቅርታ በመጠየቅ እና በህይወት ላሉ አጽናኝ ሴቶች ገንዘብ በመክፈል ተስማምታለች። ከ2019 ጀምሮ ጃፓን የኮሪያ ሙዚቃ ቴሌቪዥን (ኬ-ድራማስ) እና ሌሎች የባህል ምርቶች ዋና አስመጪ ናት። ጃፓን ከጎረቤቶቿ ጋር በተለያዩ የግዛት ውዝግብ ውስጥ ትገኛለች። ጃፓን እ.ኤ.አ. በ 1945 በሶቪየት ዩኒየን የተያዙትን የደቡባዊ ኩሪል ደሴቶችን ሩሲያ ለመቆጣጠር ትወዳደራለች ደቡብ ኮሪያ የሊያንኮርት ሮክስን መቆጣጠሩ በጃፓን እንደተነገረው ተቀባይነት አላገኘም ጃፓን በሴንካኩ ደሴቶች እና በኦኪኖቶሪሺማ ሁኔታ ላይ ከቻይና እና ታይዋን ጋር ያለውን ግንኙነት አሻከረ። እ.ኤ.አ. በ 2022 ጃፓን ከታይላንድ እና ከታላቋ ብሪታንያ እና ሰሜን አየርላንድ ጋር ለመከላከያ ስምምነቶች ተስማምታለች። ወታደራዊ ጃፓን በአለም አቀፍ የሰላም መረጃ ጠቋሚ 2020 ሁለተኛዋ ከፍተኛ ደረጃ ያለው የእስያ ሀገር ነች።ጃፓን በዓለም ላይ ካሉት ከማንኛውም ሀገር ወታደራዊ በጀቶች አንዷን ትይዛለች። የሀገሪቱ ጦር (የጃፓን የራስ መከላከያ ሃይሎች) በጃፓን ህገ መንግስት አንቀፅ 9 የተገደበ ሲሆን ይህም ጃፓን በአለም አቀፍ አለመግባባቶች ጦርነት የማወጅ ወይም ወታደራዊ ሃይል የመጠቀም መብቷን ይጥላል። ወታደሩ የሚተዳደረው በመከላከያ ሚኒስቴር ሲሆን በዋናነት የጃፓን ምድር መከላከያ ሃይል፣ የጃፓን የባህር ሃይል ራስን የመከላከል ሃይል እና የጃፓን አየር መከላከያ ሃይልን ያቀፈ ነው። ወታደሮቹን ወደ ኢራቅ እና አፍጋኒስታን ማሰማራቱ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የጃፓን ጦር ወደ ባህር ማዶ ሲጠቀም የመጀመሪያው ነው። የጃፓን መንግስት በፀጥታ ፖሊሲው ላይ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት መመስረትን፣ የብሄራዊ ደህንነት ስትራቴጂን ማፅደቅ እና የብሄራዊ መከላከያ መርሃ ግብር መመሪያዎችን ጨምሮ ለውጦችን ሲያደርግ ቆይቷል። በግንቦት 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጃፓን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ ያቆየችውን ስሜታዊነት ለመተው እና ለክልላዊ ደህንነት የበለጠ ሀላፊነት ለመውሰድ ትፈልጋለች ብለዋል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም ከሰሜን ኮሪያ እና ከቻይና ጋር ያለው ውጥረት በጄኤስዲኤፍ ሁኔታ እና ከጃፓን ማህበረሰብ ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ክርክሩን ቀጥሏል። የሀገር ውስጥ ህግ አስከባሪ በጃፓን ውስጥ የአገር ውስጥ ደህንነት በዋናነት በፕሬፌክተራል ፖሊስ መምሪያዎች በብሔራዊ ፖሊስ ኤጀንሲ ቁጥጥር ስር ይሰጣል። ለፕሬፌክራል ፖሊስ መምሪያዎች ማዕከላዊ አስተባባሪ አካል እንደመሆኑ የብሔራዊ ፖሊስ ኤጀንሲ በብሔራዊ የህዝብ ደህንነት ኮሚሽን ነው የሚተዳደረው። የልዩ ጥቃት ቡድኑ ከግዛት-ደረጃ ፀረ-ሽጉጥ ጓዶች እና ከኤንቢሲ የሽብር ቡድኖች ጋር የሚተባበሩ ብሄራዊ ደረጃ የፀረ-ሽብርተኝነት ታክቲክ ክፍሎችን ያካትታል። የጃፓን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በጃፓን ዙሪያ ያሉ የግዛት ውሀዎችን ይጠብቃሉ እና በኮንትሮባንድ በባህር ውስጥ የአካባቢ ወንጀሎች አደን የባህር ላይ ወንበዴዎች የስለላ መርከቦች ያልተፈቀደ የውጭ አሳ ማጥመጃ መርከቦች እና ህገ-ወጥ ስደት ላይ ክትትል እና ቁጥጥር እርምጃዎችን ይጠቀማል። የጦር መሳሪያ እና ሰይፍ ይዞታ ቁጥጥር ህግ የሲቪል ሽጉጥ፣ ጎራዴ እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ባለቤትነትን በጥብቅ ይቆጣጠራል። እንደ የተባበሩት መንግስታት የአደንዛዥ ዕፅ እና የወንጀል ፅህፈት ቤት እ.ኤ.አ. በ 2018 ስታቲስቲክስን ሪፖርት ካደረጉት የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት መካከል እንደ ግድያ ጠለፋ ወሲባዊ ጥቃት እና ዘረፋ ያሉ የጥቃት ወንጀሎች በጃፓን በጣም ዝቅተኛ ናቸው። ኢኮኖሚ ጃፓን በአለም አቀፍ ደረጃ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች, ከአሜሪካ እና ከቻይና በመቀጠል, በስም እና በአለም አራተኛ ትልቅ ብሄራዊ ኢኮኖሚ ከዩናይትድ ስቴትስ, ቻይና እና ህንድ በመግዛት አቅምን በመግዛት እኩልነት እንደ 2019. ከ 2019 ጀምሮ የጃፓን የሠራተኛ ኃይል 67 ሚሊዮን ሠራተኞችን ያቀፈ ነበር። ጃፓን 2.4 በመቶ አካባቢ ዝቅተኛ የስራ አጥ ቁጥር አላት። እ.ኤ.አ. በ2017 16 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ ከድህነት ወለል በታች ነበር።ጃፓን ዛሬ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከፍተኛው የህዝብ እዳ ጥምርታ ያላት ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2017 ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አንፃር ብሄራዊ ዕዳ 236 በመቶ ደርሷል። የጃፓን የን ከአለም ሶስተኛው ነው። ትልቁ የመጠባበቂያ ገንዘብ (ከአሜሪካ ዶላር እና ከዩሮ በኋላ)። የጃፓን የወጪ ንግድ በ2018 ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 18.5% ደርሷል። እ.ኤ.አ. በ2019 የጃፓን ዋና የወጪ ገበያዎች ዩናይትድ ስቴትስ (19.8 በመቶ) እና ቻይና (19.1 በመቶ) ነበሩ። ዋና ወደ ውጭ የሚላከው የሞተር ተሽከርካሪዎች፣ የብረትና የብረት ውጤቶች፣ ሴሚኮንዳክተሮች እና የመኪና መለዋወጫዎች ናቸው። እ.ኤ.አ. በ2019 የጃፓን ዋና የማስመጫ ገበያዎች ቻይና (23.5 በመቶ)፣ ዩናይትድ ስቴትስ (11 በመቶ) እና አውስትራሊያ (6.3 በመቶ) ነበሩ። የጃፓን ዋና ምርቶች ማሽነሪዎች እና መሳሪያዎች፣ የቅሪተ አካል ነዳጆች፣ የምግብ እቃዎች፣ ኬሚካሎች እና ለኢንዱስትሪዎቿ የሚውሉ ጥሬ እቃዎች ናቸው። የጃፓን የካፒታሊዝም ልዩነት ብዙ የተለያዩ ገፅታዎች አሉት፡ የ ኢንተርፕራይዞች ተፅእኖ ፈጣሪ ናቸው፣ እና የህይወት ዘመን ስራ እና ከፍተኛ ደረጃ ላይ የተመሰረተ የስራ እድገት በጃፓን የስራ አካባቢ የተለመደ ነው። ጃፓን ትልቅ የትብብር ዘርፍ ያላት ሲሆን በዓለም ላይ ካሉት አስር ትላልቅ የህብረት ስራ ማህበራት ሦስቱ ያሉት ሲሆን ይህም ትልቁ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበር እና በአለም ላይ ትልቁ የግብርና ህብረት ስራ ማህበርን ጨምሮ እ.ኤ.አ. ለ2015–2016 በአለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ሪፖርት ውስጥ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ግብርና እና አሳ እ.ኤ.አ. በ2018 የጃፓን የግብርና ዘርፍ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ውስጥ 1.2 በመቶውን ይይዛል።[የጃፓን መሬት 11.5% ብቻ ለእርሻ ተስማሚ ነው። በዚህ የእርሻ መሬት እጦት ምክንያት የእርከን ስርዓት በአነስተኛ ቦታዎች ላይ ለማርባት ያገለግላል. ይህ በዩኒት አካባቢ ከአለም ከፍተኛ የሰብል ምርት ደረጃ አንዱን ያስገኛል፣ እ.ኤ.አ. በ2018 የግብርና ራስን የመቻል መጠን 50% ገደማ ነው። የጃፓን አነስተኛ የግብርና ዘርፍ ከፍተኛ ድጎማ እና ጥበቃ የሚደረግለት ነው። አርሶ አደሮች ተተኪ ለማግኘት አስቸጋሪ በሆነበት ወቅት እያረጁ በመሆናቸው በግብርና ላይ ስጋት እየጨመረ መጥቷል። ጃፓን በ2016 ከተያዙ እና 3,167,610 ሜትሪክ ቶን አሳ በመያዝ ከአለም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፤ ይህም ካለፉት አስር አመታት አማካይ ዓመታዊ አማካይ 4,000,000 ቶን ቀንስ ነበር። ጃፓን በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ የዓሣ ማጥመጃ መርከቦች አንዷን ትይዛለች እና 15% የሚጠጋውን የዓለም አቀፉ ተሳፋሪዎችን ይሸፍናል ይህም የጃፓን ማጥመድ እንደ ቱና ያሉ የዓሣ ክምችቶችን እያሟጠጠ ነው የሚል ትችት አስከትሏል። ጃፓን የንግድ አሳ ነባሪዎችን በመደገፍ ውዝግብ አስነስቷል። ኢንዱስትሪ ጃፓን ትልቅ የኢንዱስትሪ አቅም ያላት ሲሆን ለአንዳንድ "ትልቁ እና በቴክኖሎጂ የላቁ የሞተር ተሽከርካሪዎች፣ የማሽን መሳሪያዎች፣ ብረት እና ብረት ያልሆኑ ብረቶች፣ መርከቦች፣ ኬሚካል ንጥረ ነገሮች፣ ጨርቃ ጨርቅ እና የተሻሻሉ ምግቦች አምራቾች መኖሪያ ነች" የጃፓን የኢንዱስትሪ ዘርፍ በግምት ይይዛል። ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ውስጥ 27.5% የሀገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ምርት እ.ኤ.አ. በ2019 ከአለም ሶስተኛው ከፍተኛ ነው። ጃፓን እ.ኤ.አ. በ 2017 በዓለም ላይ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ አውቶሞቢሎችን በማምረት ላይ ትገኛለች እና የዓለማችን ትልቁ የመኪና ኩባንያ ቶዮታ መኖሪያ ነች። የጃፓን የመርከብ ግንባታ ኢንዱስትሪ ከደቡብ ኮሪያ እና ከቻይና ውድድር ያጋጥመዋል; እ.ኤ.አ. በ 2020 የመንግስት ተነሳሽነት ይህንን ዘርፍ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማሳደግ ግብ አድርጎ ለይቷል። አገልግሎቶች እና ቱሪዝም የጃፓን የአገልግሎት ዘርፍ እ.ኤ.አ. በ 2019 ከጠቅላላው የኢኮኖሚ ውጤት 70 በመቶውን ይይዛል ባንክ ችርቻሮ ትራንስፖርት እና ቴሌኮሙኒኬሽን ሁሉም ዋና ዋና ኢንዱስትሪዎች ናቸው እንደ ቶዮታ ሚትሱቢሺ ፣ ፣ እና ካሉ ኩባንያዎች ጋር በዓለም ላይ ካሉት ታላላቅ መካከል ተዘርዝሯል። ጃፓን በ2019 31.9 ሚሊዮን አለም አቀፍ ቱሪስቶችን ስቧል።ለገቢ ቱሪዝም ጃፓን በ2019 ከአለም 11ኛ ሆናለች።የ2017ቱ የጉዞ እና ቱሪዝም ተወዳዳሪነት ሪፖርት ጃፓንን ከ141 ሀገራት 4ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፣ይህም በእስያ ከፍተኛው ነበር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጃፓን በሳይንሳዊ ምርምር በተለይም በተፈጥሮ ሳይንስ እና ምህንድስና ግንባር ቀደም ሀገር ነች። ሀገሪቱ በ2020 ብሉምበርግ ኢኖቬሽን ኢንዴክስ 12ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች እና በ2021 በአለምአቀፍ ኢኖቬሽን ኢንዴክስ 13ኛ ሆና በ2019 ከ 15ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንፃር የጃፓን የምርምር እና ልማት በጀት ከአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ከ867,000 ተመራማሪዎች ጋር እ.ኤ.አ. በ2017 የ19 ትሪሊዮን የን የምርምር እና ልማት በጀትን በመጋራት ሀገሪቱ በፊዚክስ፣ በኬሚስትሪ ወይም በህክምና፣ እና በሶስት የፊልድ ሜዳሊያ ተሸላሚዎችን ሀያ ሁለት የኖቤል ተሸላሚዎችን አፍርታለች። ጃፓን በሮቦቲክስ ምርት እና አጠቃቀም ከአለም ቀዳሚ ስትሆን ከአለም የ2017 አጠቃላይ 55% ያቀረበች ናት። ጃፓን በነፍስ ወከፍ በሳይንስና በቴክኖሎጂ የተመራማሪዎች ቁጥር ከ1000 14 ያህሉ በአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። እንደ ደቡብ ኮሪያ እና ቻይና ባሉ ሀገራት ፉክክር ሲነሳ የጃፓን የሸማቾች ኤሌክትሮኒክስ ኢንዱስትሪ በአንድ ወቅት በዓለም ላይ ጠንካራው ተብሎ ይገመታል ይሁን እንጂ በጃፓን ውስጥ የቪዲዮ ጨዋታዎች ዋነኛ ኢንዱስትሪዎች ናቸው. እ.ኤ.አ. በ 2014 የጃፓን የሸማቾች ቪዲዮ ጌም ገበያ 9.6 ቢሊዮን ዶላር አስመዝግቧል በሞባይል ጌም 5.8 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል እ.ኤ.አ. በ2015 ጃፓን ከቻይና፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ ብቻ በመቀጠል አራተኛዋ ትልቁ የፒሲ ጨዋታ ገበያ ሆናለች። የጃፓን ኤሮስፔስ ፍለጋ ኤጀንሲ የጃፓን ብሔራዊ የጠፈር ኤጀንሲ ነው; የጠፈር፣ የፕላኔቶች እና የአቪዬሽን ጥናቶችን ያካሂዳል እንዲሁም የሮኬቶችን እና ሳተላይቶችን እድገት ይመራል። በአለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ተሳታፊ ነው፡ የጃፓን የሙከራ ሞጁል (ኪቦ) በስፔስ ሹትል ስብሰባ በረራዎች ወቅት ወደ ጣቢያው ተጨምሯል እ.ኤ.አ. አሰሳ የጨረቃ መሰረት መገንባት እና በ2030 የጠፈር ተመራማሪዎችን ማረፍን ያጠቃልላል። በ2007፣ የጨረቃ አሳሽ (ሴሌኖሎጂካል እና ኢንጂነሪንግ ኤክስፕሎረር) ከታንጋሺማ የጠፈር ማዕከል አስጀመረ። ከአፖሎ ፕሮግራም በኋላ ትልቁ የጨረቃ ተልዕኮ ዓላማው ስለ ጨረቃ አመጣጥ እና ዝግመተ ለውጥ መረጃ መሰብሰብ ነበር። አሳሹ በጥቅምት 4 ቀን 2007 የጨረቃ ምህዋር ውስጥ ገባ እና ሆን ብሎ ሰኔ 11 ቀን 2009 ጨረቃ ላይ ተከሰከሰ። መሠረተ ልማት መጓጓዣ ጃፓን በትራንስፖርት መሠረተ ልማት ላይ ብዙ ኢንቨስት አድርጋለች። አገሪቱ በግምት 1,200,000 ኪሎ ሜትር (750,000 ማይል) መንገድ ከ1,000,000 ኪሎ ሜትር (620,000 ማይል) የከተማ፣ የከተማ እና የመንደር መንገዶች፣ 130,000 ኪሎ ሜትር (81,000 ማይል) የፕሪፌክተራል መንገዶች እና አጠቃላይ ብሄራዊ አውራ ጎዳናዎች፣ 54,73401 ኪሎሜትር እ.ኤ.አ. ከ2017 ጀምሮ 7641 ኪሎ ሜትር (4748 ማይል) ብሔራዊ የፍጥነት መንገዶች። እ.ኤ.አ. በ 1987 ወደ ፕራይቬታይዜሽን ከተዛወረ ወዲህ በደርዘን የሚቆጠሩ የጃፓን የባቡር ኩባንያዎች በክልል እና በአካባቢው የመንገደኞች የትራንስፖርት ገበያዎች ይወዳደራሉ ዋና ዋና ኩባንያዎች ሰባት የጄአር ኢንተርፕራይዞችን፣ ኪንቴሱ፣ ሴይቡ ባቡር እና ኬዮ ኮርፖሬሽን ያካትታሉ። ዋና ዋና ከተሞችን የሚያገናኙት ባለከፍተኛ ፍጥነት ሺንካንሰን (ጥይት ባቡሮች) በደህንነታቸው እና በሰዓታቸው ይታወቃሉ። እ.ኤ.አ. በ 2013 በጃፓን ውስጥ 175 አውሮፕላን ማረፊያዎች አሉ ትልቁ የሀገር ውስጥ አውሮፕላን ማረፊያ በቶኪዮ ሃኔዳ አውሮፕላን ማረፊያ በ 2019 የእስያ ሁለተኛው በጣም የተጨናነቀ አውሮፕላን ማረፊያ ነበር የኪሂን እና የሃንሺን ሱፐርፖርት ማዕከሎች በ 7.98 እና 5.22 ሚሊዮን በቅደም ተከተል በዓለም ላይ ካሉት ትልቁ አውሮፕላን ማረፊያዎች ናቸው ከ 2017 ጀምሮ ጉልበት እ.ኤ.አ. ከ 2019 ጀምሮ በጃፓን 37.1% የኃይል ምንጭ ከፔትሮሊየም 25.1% ከድንጋይ ከሰል 22.4% ከተፈጥሮ ጋዝ 3.5% ከውሃ ኃይል እና 2.8% ከኒውክሌር ኃይል ከሌሎች ምንጮች ጋር። እ.ኤ.አ. በ2010 የኑክሌር ኃይል ከ11.2 በመቶ ቀንሷል። በግንቦት 2012 ሁሉም የሀገሪቱ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ከመስመር ውጭ ተወስደዋል ምክንያቱም በመጋቢት 2011 የፉኩሺማ ዳይቺ የኒውክሌር አደጋ ተከትሎ በቀጠለው ህዝባዊ ተቃውሞ፣ ምንም እንኳን የመንግስት ባለስልጣናት የህዝብን አስተያየት ለማዛባት ቢሞክሩም ቢያንስ አንዳንዶቹን ወደ አገልግሎት የመመለስ ሞገስ. የሰንዳይ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ በ2015 እንደገና ጀምሯል፣ እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሌሎች በርካታ የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች እንደገና ተጀምረዋል። ጃፓን ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ክምችት የላትም እና ከውጭ በሚገቡ የኃይል ምንጮች ላይ ከፍተኛ ጥገኛ አላት። ስለዚህ ሀገሪቱ ምንጮቿን ለማብዛት እና ከፍተኛ የሃይል ቆጣቢነትን ለመጠበቅ አላማ አድርጋለች። የውሃ አቅርቦት እና የንፅህና አጠባበቅ የውሃ እና የአካባቢ ጽዳትና ንፅህና ዘርፍ ኃላፊነት በጤና በሠራተኛ እና ደህንነት ጥበቃ ሚኒስቴር ለቤት ውስጥ አገልግሎት የውሃ አቅርቦትን የሚቆጣጠር የመሬት፣ የመሠረተ ልማት፣ የትራንስፖርትና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የውኃ ሀብት ልማት እንዲሁም የንፅህና አጠባበቅ፣ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር, የአካባቢ የውሃ ጥራት እና የአካባቢ ጥበቃ; እና የውስጥ ጉዳይ እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር, የመገልገያዎችን የአፈፃፀም መለኪያዎችን ይቆጣጠራል. የተሻሻለ የውሃ ምንጭ ማግኘት በጃፓን ሁለንተናዊ ነው። 98% የሚሆነው ህዝብ የቧንቧ ውሃ አቅርቦትን ከህዝብ አገልግሎቶች ይቀበላል ባህል የጃፓን ሥዕል ታሪክ በአገሬው የጃፓን ውበት እና ከውጭ በሚገቡ ሀሳቦች መካከል ውህደት እና ውድድር ያሳያል። በጃፓን እና አውሮፓውያን ስነ-ጥበብ መካከል ያለው መስተጋብር ከፍተኛ ነበር፡ ለምሳሌ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ጃፖኒዝም ተብሎ በሚታወቀው እንቅስቃሴ ወደ ውጭ መላክ የጀመረው ህትመቶች በምዕራቡ ዓለም የዘመናዊ ጥበብ እድገት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል፣ በተለይም በድህረ-ኢምፕሬሽን. የጃፓን አርክቴክቸር በአካባቢያዊ እና በሌሎች ተጽእኖዎች መካከል ጥምረት ነው. በተለምዶ ከእንጨት ወይም ከጭቃ ፕላስተር መዋቅሮች, ከመሬት ላይ ትንሽ ከፍ ብሎ, በቆርቆሮ ወይም በሳር የተሸፈነ ጣሪያዎች ተመስሏል. የአይሴ መቅደስ የጃፓን አርኪቴክቸር ምሳሌ በመሆን ተከብሯል። ባህላዊ መኖሪያ ቤቶች እና ብዙ የቤተመቅደሶች ሕንፃዎች በክፍሎች እና በቤት ውስጥ እና ከቤት ውጭ ክፍተት መካከል ያለውን ልዩነት የሚያበላሹ የታታሚ ምንጣፎችን እና ተንሸራታች በሮች መጠቀምን ይመለከታሉ። ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ጃፓን አብዛኛዎቹን የምዕራባውያን ዘመናዊ አርክቴክቶችን በግንባታ እና ዲዛይን ውስጥ አካታለች። የጃፓን አርክቴክቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በመጀመሪያ እንደ ኬንዞ ታንግ ባሉ አርክቴክቶች እና ከዚያም እንደ ሜታቦሊዝም ያሉ እንቅስቃሴዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ነበር። ሥነ ጽሑፍ እና ፍልስፍና የመጀመሪያዎቹ የጃፓን ሥነ-ጽሑፍ ሥራዎች ኮጂኪ እና ኒሆን ሾኪ ዜና መዋዕል እና የማንዮሹ የግጥም ሥነ-ሥርዓት ሁሉም ከ 8 ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እና በቻይንኛ ገጸ-ባህሪያት የተፃፉ ያካትታሉ። በሄያን ዘመን መጀመሪያ ላይ ካና (ሂራጋና እና ካታካና) በመባል የሚታወቁት የፎኖግራሞች ስርዓት ተፈጠረ። የቀርከሃ ቆራጭ ታሪክ እጅግ ጥንታዊው የጃፓን ትረካ ተደርጎ ይቆጠራል። የፍርድ ቤት ህይወት ታሪክ በሴይ ሾናጎን ትራስ መፅሃፍ ውስጥ ተሰጥቷል የገንጂ ታሪክ በሙራሳኪ ሺኪቡ ብዙ ጊዜ የአለም የመጀመሪያ ልቦለድ ተብሎ ይገለጻል። በኤዶ ዘመን፣ ቾኒን ("የከተማ ሰዎች") የሳሙራይ ባላባቶችን እንደ ስነ-ጽሁፍ አዘጋጆች እና ሸማቾች ያዙ። የሳይካኩ ስራዎች ተወዳጅነት ለምሳሌ ይህንን የአንባቢነት እና የደራሲነት ለውጥ ያሳያል፡ ባሾ ደግሞ የኮኪንሹን የግጥም ወግ በሃካይ (ሃይኩ) በማደስ ኦኩ ኖ ሆሶሚቺ የተባለውን የግጥም ማስታወሻ ጻፈ። የሜጂ ዘመን የጃፓን ስነ-ጽሁፍ የምዕራባውያን ተጽእኖዎችን በማቀናጀት የባህላዊ ስነ-ጽሁፍ ቅርጾችን ማሽቆልቆሉን ተመልክቷል. ናትሱሜ ሶሴኪ እና ሞሪ ኦጋይ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ጉልህ ልብወለድ ደራሲዎች ነበሩ፣ በመቀጠልም ፣ እና፣ በቅርቡ ደግሞ ሃሩኪ ሙራካሚ እና ኬንጂ ናካጋሚ። ጃፓን ሁለት የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ደራሲዎች አሏት ያሱናሪ ካዋባታ (1968) እና ኬንዛቡሮ ኦ (1994)። የጃፓን ፍልስፍና በታሪክ የሁለቱም የውጭ፣ በተለይም የቻይና እና የምዕራባውያን እና ልዩ የጃፓን አካላት ውህደት ነው። በሥነ-ጽሑፋዊ ቅርጾች, የጃፓን ፍልስፍና የጀመረው ከአሥራ አራት መቶ ዓመታት በፊት ነው. በጃፓን የህብረተሰብ እና የራስነት ፅንሰ-ሀሳብ እና በመንግስት አደረጃጀት እና በህብረተሰቡ መዋቅር ውስጥ የኮንፊሽያውያን ሀሳቦች በግልጽ ይታያሉ። ቡድሂዝም የጃፓን ሳይኮሎጂ፣ ሜታፊዚክስ እና ውበት ላይ በጥልቅ ተጽዕኖ አሳድሯል። ጥበቦችን ማከናወን የጃፓን ሙዚቃ ሁለገብ እና የተለያየ ነው። በ9ኛው እና በ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደ ኮቶ ያሉ ብዙ መሣሪያዎች ተዋወቁ። ታዋቂው ህዝባዊ ሙዚቃ፣ ጊታር ከሚመስለው ሻሚሰን ጋር፣ የተጀመረው በ16ኛው ክፍለ ዘመን ነው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ የገባው የምዕራባውያን ክላሲካል ሙዚቃ የጃፓን ባህል ዋነኛ አካል ነው። ኩሚ-ዳይኮ (የስብስብ ከበሮ) የተገነባው በድህረ-ጦርነት ጃፓን ሲሆን በሰሜን አሜሪካ በጣም ተወዳጅ ሆነ። ከጦርነቱ በኋላ በጃፓን ታዋቂ የሆኑ ሙዚቃዎች በአሜሪካ እና አውሮፓውያን አዝማሚያዎች ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል, ይህም የጄ-ፖፕ እድገትን አስከትሏል. ካራኦኬ ጠቃሚ ባህላዊ እንቅስቃሴ ነው። ከጃፓን ያሉት አራቱ ባህላዊ ቲያትሮች ኖህ፣ ኪዮገን፣ ካቡኪ እና ቡራኩ ናቸው። ኖህ በዓለም ላይ ካሉት ተከታታይ የቲያትር ወጎች አንዱ ነው። በዓላት በይፋ፣ ጃፓን 16 ብሄራዊ፣ በመንግስት እውቅና የተሰጣቸው በዓላት አሏት። በጃፓን ውስጥ ያሉ ህዝባዊ በዓላት በ1948 በህዝባዊ የበዓል ህግ በ1948 የተደነገገ ነው። ከ2000 ጀምሮ ጃፓን የበአል ቀንን ወደ ሰኞ ሀገራዊ ትእዛዝ ተቀብላለች። ረጅም ቅዳሜና እሁድ ለማግኘት. በጃፓን ያሉት ብሄራዊ በዓላት በጥር 1 አዲስ አመት በጥር ሁለተኛ ሰኞ የእድሜ ቀን መምጣት የካቲት 11 ብሔራዊ የመሠረት ቀን የንጉሠ ነገሥቱ ልደት በየካቲት 23 የቨርናል ኢኩዊኖክስ ቀን በመጋቢት 20 ወይም 21 የሾዋ ቀን በ ኤፕሪል 29 በግንቦት 3 ሕገ መንግሥት መታሰቢያ ቀን በግንቦት 4 የሕፃናት ቀን በግንቦት 5 በሐምሌ ሦስተኛው ሰኞ ላይ የባህር ቀን በነሐሴ 11 የተራራ ቀን በሴፕቴምበር ሦስተኛው ሰኞ ላይ ለአረጋውያን ቀን አክብሮት መጸው በሴፕቴምበር 23 ወይም 24 ኢኩኖክስ፣ በጥቅምት ሁለተኛ ሰኞ የጤና እና የስፖርት ቀን፣ የባህል ቀን ህዳር 3 እና የሰራተኛ የምስጋና ቀን ህዳር 23 ምግብ የጃፓን ምግብ ባህላዊ የምግብ አዘገጃጀቶችን እና የአካባቢ ቁሳቁሶችን የሚጠቀሙ እጅግ በጣም ብዙ የክልል ልዩ ምግቦችን ያቀርባል የባህር ምግብ እና የጃፓን ሩዝ ወይም ኑድል ባህላዊ ምግቦች ናቸው. የጃፓን ካሪ ከብሪቲሽ ህንድ ወደ ጃፓን ከገባ ጀምሮ በሰፊው ጥቅም ላይ ስለሚውል ከራመን እና ሱሺ ጎን ለጎን ብሄራዊ ምግብ ተብሎ ሊጠራ ይችላል። ባህላዊ የጃፓን ጣፋጮች ዋጋሺ በመባል ይታወቃሉ። እንደ ቀይ ባቄላ ጥፍጥፍ እና ሞቺ የመሳሰሉ ንጥረ ነገሮች ጥቅም ላይ ይውላሉ. ተጨማሪ ዘመናዊ ጣዕም አረንጓዴ ሻይ አይስ ክሬምን ያካትታል. ታዋቂ የጃፓን መጠጦች ሴክን ያጠቃልላሉ፣ እሱ በተለምዶ ከ14-17% አልኮሆል ያለው እና በብዙ ሩዝ መፍላት የሚዘጋጅ የሩዝ መጠጥ ነው ቢራ በጃፓን ከ 17 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ጀምሮ ተዘጋጅቷል። አረንጓዴ ሻይ በጃፓን ይመረታል እና በጃፓን ሻይ ሥነ ሥርዓት ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው እንደ ባሉ ቅርጾች ተዘጋጅቷል ሚዲያ እ.ኤ.አ. በ 2015 በጃፓን በቴሌቪዥን እይታ ላይ ባደረገው ጥናት 79 በመቶው የጃፓን ቴሌቪዥን በየቀኑ ይመለከታሉ። የጃፓን የቴሌቭዥን ድራማዎች በጃፓን እና በአለም አቀፍ ደረጃ ይታያሉ፤ ሌሎች ታዋቂ ትርኢቶች በተለያዩ ትዕይንቶች፣ አስቂኝ እና የዜና ፕሮግራሞች ዘውጎች ናቸው። እ.ኤ.አ. በ2016 በዓለም ላይ በብዛት ከተሰራጩት የጃፓን ጋዜጦች መካከል ይጠቀሳሉ። ማንጋ በመባል የሚታወቁት የጃፓን ኮሜዲዎች በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ የተገነቡ እና በዓለም ዙሪያ ተወዳጅ እየሆኑ መጥተዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የማንጋ ተከታታዮች የአሜሪካን የኮሚክስ ኢንደስትሪን የሚወዳደሩ የሁሉም ጊዜ በጣም የተሸጡ የኮሚክስ ተከታታይ ጥቂቶቹ ሆነዋል። ጃፓን በዓለም ላይ ካሉት ጥንታዊ እና ትልቁ የፊልም ኢንዱስትሪዎች አንዱ ነው ያለው።የኢሺሮ ሆንዳ ጎዲዚላ የጃፓን ዓለም አቀፍ አዶ ሆነ እና አጠቃላይ የካይጁ ፊልሞችን ንዑስ ዘውግ እንዲሁም በታሪክ ውስጥ ረጅሙ የፊልም ፍራንቻይዝ ፈጠረ። አኒም በመባል የሚታወቁት የጃፓን አኒሜሽን ፊልሞች እና የቴሌቭዥን ተከታታዮች በአብዛኛው በጃፓን ማንጋ ተጽዕኖ ሥር ውለው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅ እየሆኑ መጥተዋል። እንደ ዘንዶ ኳስ፣ አንድ ቁራጭ፣ ሲመጣ እና ጋኔን ገዳይ ያሉ ብዙ የጃፓን የሚዲያ ፍራንቻዎች ትልቅ ተወዳጅነትን አግኝተዋል፣ እና ከአለም ከፍተኛ ገቢ ከሚያስገኙ የሚዲያ ፍራንቺሶች መካከል ናቸው። ፖክሞን በሁሉም ጊዜያት ከፍተኛ ገቢ ያስገኘ የሚዲያ ፍራንቻይዝ እንደሆነ
47836
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8B%94%E1%8B%B5%E1%8A%95%20%E1%8C%88%E1%8A%90%E1%89%B5
የዔድን ገነት
የዔድን ገነት (ዕብራይስጥ፦ /ገን ዐድን/) በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት እግዚአብሔር በሰው ልጅ መጀመርያ ቅድመ ታሪክ በምድር የተከለ ገነት ነበረ። ይህ ገነት በተለይ የሚገለጸው በኦሪት ዘፍጥረት 2 እና 3፣ እንዲሁም በመጽሐፈ ኩፋሌ 4 እና 5 ነው፤ ደግሞ በትንቢተ ሕዝቅያስ 28 ይጠቀሳል። አንዳንዴ በመሳሳት «ዔድን» ሳይሆን የ«ኤዶም» ገነት ተብሏል፤ ኤዶም ግን በትክክል የያዕቆብ ወንድም ዔሳው የመሠረተው ሀገር ነበረ። መጽሐፈ ኩፋሌ 4:14, 16 እንደሚያብራራልን፣ መጀመርዮቹ ሰዎች አዳም እና ሔዋን በገነት የቆዩበት ዘመን ሰባት አመታት ያህል ነበር። በመጽሐፈ ኩፋሌ አቆጣጠር አስርቱ ቃላት እስከ ተሰጡበት ዓመት ድረስ 2410 ዓመታት ስለሚቆጠር፣ እነዚህ ቅድመ ታሪካዊ ሰባት አመታት ከ4071 እስከ 4064 ዓክልበ. ያህል እንደ ነበሩ መረዳት ይቻላል። ሌሎች ግን በሌሎች ዘዴዎች በኩል ሌሎችን ፍቾች አገኝተዋል። አዳም ከተፈጠረበት ከሥነ-ፍጥረት 6ኛው ቀን ጀምሮ በአዳም 40ኛው ቀን ወደ ገነት እንደ ገባ፣ ሚስቱም ሔዋን በ80ኛው ቀን እንደ ገባች ይለናል (4:9, 12)። ወደ ገነትም ሳይገቡ በተወለዱበት አገር በኤልዳ እየቆየ አዳም መጀመርያው ሳምንት እንስሶችን ያሰይማቸው ነበር፣ ከ፪ኛውም ሳምንት ጀምሮ ሔዋንን ያውቃት ነበር። አዳም ከተፈጠረበት ከዓለም 6ኛው «ቀን» አስቀድሞ ዓለሙ፣ ምድሩ፣ አትክልቱና እንስሶች ሁሉ ወዘተ. ተፈጥረው ነበር፤ እነዚህ 6ቱ «ቀኖች» ግን እንደ አሁን የ24 ሰዓት ቀኖች እንደ ነበሩ አይመስልም። በሥነ ቅርስ መጀመርያው የምናውቀው ታሪካዊ ሰነድ «የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ» 3125-3100 ዓክልበ.ግ. ይመስላል፤ ከዚያ አስቀድሞ ለነበረው ዘመን የሰው ልጅ ታሪካዊ መዝገቦች (ሰነዶች) በፍጹም ባለመኖራቸው፣ ይህ ስለ «ቅድመ ታሪክ» አንድ ቅድመ-ታሪካዊ አስተያየት ሲሆን፣ በሰፊ በአብርሃማዊ ሃይማኖቶች (በተለይ ክርስትና፣ እስልምና፣ አይሁድና) የሚገኝ አስተያየት ነው። (ደግሞ ባለሙያ ንድፍን ይዩ።) በዚሁም አጭር የገነት ወቅት ከአሁን በጣም የተለዩ ሁናቴዎች እንደ ነበሩ የሚል አሣብ ይፈጠራል። አዳም እና ሔዋን በኤድን ሲቆዩ መዋቲ መሆናቸው እንደ ታሠበ አይመስልም። ሞት ለሰው ልጆች የመጣበት ምክንያት አዳም እና ሔዋን በዓመፃ ጸባይ የተከለከለውን ፍሬ ተመግበው ከዔድን ገነት ስለ ተሰደዱ እንደ ሆነ ይመስላል። የእንስሶች ጉዳይ በግልጽ ባይብራራልንም ከአዳም ጋር ለመናገር በዚሁ ወቅት ችሎታው እንደ ነበራቸው በኩፋሌ 5:2 ይጻፋል። እባብ በዚህ ሰዓት እግሮቹን ገና ስላላጣ ባለ እግር ፍጡር እንደ ነበር ይመስላል። የእግዚአብሔር መላእክት ለአዳምና ሔዋን የገነት አጠባበቅ በነዚህ 7 አመቶች ያስተምራቸው ነበር (ኩፋሌ 4:14)። «የአዳምና ሔዋን ትግል ከሠይጣን ጋራ» የአዳምና ሔዋን ትግል ከሠይጣን ጋራ ሌላ ቀኖናዊ ያልሆነ በተለይ በአረብኛና ግዕዝ የታወቀ ጥንታዊ ጽሑፍ ነው። በዚህ ጽሑፍ ዘንድ ግን አዳምና ሔዋን ሳይበድሉ በገነት የቆዩበት ወቅት ጥቂት ሰዓቶች ብቻ ነበር፤ ከገነትም በወጡ በ223ኛው ቀን (ወይም ከ7 ወርና 13 ቀናት በኋላ) አዳም ሔዋንን በጋብቻ ያገባት ነው። ይህ መረጃ ከኩፋሌ ጋር አይስማማም። ይኸውም መጽሐፍ ስለ ዔድን ገነት ተጨማሪ ዝርዝርዎች ይሰጣል። ከነዚህም መሃል፦ አዳም በገነት እያለ ሌሊትን አላወቀም ነበር። (እንደ ክፋሌ ለ፯ አመት እንዲህ ከሆነ የምድር ምኋር ከአሁን እንደ ተለየ መስሎ በገነት ምንጊዜም መዓልት ነበር ማለት ነው።) የገነት ፍሬ ከአሁን ትልቅ ነበር፤ በገነት ውስጥ አንድ የበለስ ፍሬ ክብደት እንደ አንድ ሃብሃብ ነበር። ጻዕሙም እንደ ጣፋጭ ሥጋ ወጥ ነበር። ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤም በገነት መኖራቸውም ይጠቀሳል። የተከለከለው ፍሬ እነዚህ ምንጮች የተከለከለውን ፍሬ መታወቂያ አይወስኑም። ብዙዎች እንደሚገመቱ የቱፋሕ ወይም የበለስ ዛፍ ነበረ። አንድ ሰነድ በጥንታዊ ስላቭኛ የተጠበቀው መጽሐፍ 3 ባሮክ እንዳለው፣ የተከለከለው ፍሬ ወይን ነበር። እግዚአብሐር የእባቡን ባሕርይ እንደ ለወጠ ሁሉ የወይኑንም ባሕርይ በቅጣቱ ከዛፍ ወደ ሐረግ ብቻ ለወጠ ይላል። ሆኖም በእቅዱ ወደፊት የመድኃኔ አለም ደም በመሆኑ ከእርጉም ወደ በረከት ይለውጠዋል በማለት ተጨመረ። ሥፍራ በመጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች ምንጮች ስለ ገነቱ ሥፍራ አንዳንድ ፍንጭ ይሰጣል፤ ስለ ፍንጮቹ ትርጓሜ ግን አስተሳሰቦች ተለይተዋል። «እግዚአብሔር አምላክ በምሥራቅ በኤድን ገነትን ተከለ... ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር። የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፤ ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኛል። የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል። የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው። አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው።» (ዘፍ. 2:8, 10-14) በዚህ ጥንታዊ ወቅት የነበረው መልክዓምድር ከአሁኑ እንደ ተለየ ይመስላል። ከተጠቀሱት ወንዞች፣ የጤግሮስና የኤፍራጥስ መታወቂያዎች ያለ ክርክር ታውቀዋል። «ግዮን» የአባይ (ናይል) ስም ሲሆን ኢትዮጵያንም ይከብባል። የ«ፊሶን» ሥፍራ በተለይ አጠያያቂ ሆኗል፣ ኤውላጥ ግን በኋላ የኖህ ልጆች ዘመን ስሙን ለአገሩ ሰጠ፤ በአረቢያ በቀይ ባሕር አጠገብ እንደ ተገኘ ይታስባል። ቀይ ባሕሩ በዚህ ወቅት ወንዝ ብቻ ከሆነ፣ እሱ የፊሶን መታወቂያ ሊሆን ይቻላል፤ ወይም የሕንድ ሥፍራ ያንጊዜ በአፍሪካና በአረቢያ አጠገብ ከሆነ፣ የፊሶን መታወቂያ ሌሎች እንደሚሉ ሕንዱስ ወንዝ ሊሆን ይቻላል። አባይ ደግሞ ወደ ሜድትራኔያን ባህር ሳይፈስ ወደ ዔድን ለመድረስ በሲናና ዮርዳኖስ በኩል እንደ ተዛወረ ይመስላል። በዕብራይስጥ ትርጉሙ፣ በኢትዮጵያ ሥፍራ «ኩሽ» አለው፤ በአንዳንድ ምዕራባውያን ሊቃውንት ሃልዮ ዘንድ ይህ «ኩሽ» ኢትዮጵያ ሳይሆን በ1500-1100 ዓክልበ. ግድም ባቢሎንን የገዙት ብሔር «ካሣውያን» ይሆናሉ ብለዋል። በኩፋሌ 9፣ የገነቱ ሥፍራ በሴም ርስት ውስጥ፣ ለካም ርስት ቅርብ መገኘቱ ይመስላል። በተለይም በ9:8 ዘንድ ገነት፣ ደብረ ሲናና ደብረ ጽዮን ሦስቱ ቅዱስ ቦታዎች «አንዱ በአንዱ አንጻር ለምስጋና ተፈጠሩ» ይለናል። ሄኖክ ሳይሞት መላእክት ወደ ገነት እንዲመለስ ፈቀዱ በምዕራፍ ሲለን፣ አራተኛው የተቀደሠ ቦታ «የምሥራቁ ደብር» ይባላል፤ ይህ ደብረ አራራት መሆኑ ይታስባል። በተቀበልነው ትርጉም በዘፍጥረት ዘንድ አዳምና ሔዋን ከኤድን ወደ ምሥራቅ ተሰደዱ፤ በኩፋሌ ወደ ተፈጠሩበት ወደ ኤልዳ (ወይም «ሞኤልዳ») ተመለሱ፤ ባብዛኞች ጥንታዊ ምንጮች ይህ ከገነት ወደ ምዕራቡ ተገኘ። ወንዞቹ ሁሉ በዚያን ጊዜ የተጋጠሙበት ምድር አሁን የአረብ በረሃ ቢመስልም፣ በመስጴጦምያ ወይም በአፍሪካ እንደ ነበር የሚሉ ብዙ አሉ። እንዲሁም ሌሎች በጣም ልዩ ልዩ አስተሳስቦች አሉ። ለምሳሌ በሞርሞኒስም ዘንድ፣ የዔድን ገነትና የአዳምና ሔዋን ዕውነተኛ መገኛ በሚዙሪ ክፍላገር አሜሪካ ነበረ። መጽሐፍ
50108
https://am.wikipedia.org/wiki/Love%2C%20Simon
Love, Simon
(እንግሊዝኛ)(በአማርኛ "ከፍቅር ጋር፣ ሳይመን") 2018 እ.አ.አ የተለቀቀ በተጻፈው በተባለው መጽሐፍ መሰረት የተዘጋጀ አሜሪካዊ የፍቅርና ወጣት ኮሜዲ-ድራማ ፊልም ነው። ዋና ዋና ተዋናዮቹ እና ናቸው። የፊልሙ ጭብጥ የሚያጠነጥነው ሳይመን ስፒየር በተባለ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ላይ ነው። ሳይመን እራሱን ይፋ ያላወጣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ሲሆን ይህም እንዳይታወቀብት ሚስጥሩን ከቤተሰቡና ጓደኞቹ እንዲሁም ማንነቱን ለትምሕርት ቤት ሊያጋልጥው ካስፈራራው ሰው ጋር የሚያደርገውን ትግል ያሳያል። በተጨማሪም በበይነ መረብ ከተዋወቀው እና ፍቅር ካስያዘው ነገር ግን ማንነቱን የማያውቀውን የክፍል ጓደኛው ማን እንደሆን ለማወቅ የሚያደርገውንም ጥረት ያሳያል። መጀመሪያ የታየው ፌብሪወሪ 27፣ 2018 እ.አ.አ ሲሆን በይፋ የተለቀቀው በዩናይትድ ስቴትስ ማርች 16 2018 እ.አ.አ ነው። የፊልም ተቺዎች በበኩላቸው ፊልሙ ባሉት "ደማቅ የፍቅር ስሜት፣ ለየት ለየት ያለ የተዋናዮች ቡድንና አብዮታዊ መደበኛነት" አሞግሰውታል። በተጨማሪም ፊልሙን "አስደሳችና ልብ የሚነካ" መሆኑን ገለጸዋል። በስመ ጥር የሆሊውድ ስቱዲዮ የተሰራ የመጀመሪያው በተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወጣት የፍቅር ሕይወት ታሪክ ላይ ያተኮረው ፊልም በዓለም ዙሪያ $65 ሚሊዮን ብር ገቢ አስገኝቷል። ታሪክ ሳይመን ስፒየር በአትላንታ፣ ጆርጂያ ክፍለ ከተማ የሚኖር የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነቱን ያልገለጸ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ነው። ከቤተሰቡ ጋር ጠንካራና በፍቅር የተሞላ ግንኙነት አለው። አስቀድሞ የሚያውቃቸው ኒክ እና ሊያ እንዲሁም ቅርብ ጊዜ ከተዋወቃት አቢ ጋር ጥብቅ ጓደኝነት መስርቷል። አንድ ቀን ሊያ ሳይመንን የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች የምስጢር መስጫ ድረ ገጹ ላይ በድብቅ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ስለሆነው አንድ የትምህርት ቤታቸው ተማሪ ጽፎ ስላየችው ጽሁፍ ትነገረዋለች። ስለተማሪው የሚታወቀው በኦንላይን ስሙ (ብሉ) መባሉ ብቻ ነው። ሳይመን በኢሜይል ከብሉ ጋር መጻጻፍ ይጀምራል፣ እርሱም ለኢሜይሉ (ዣክ) የሚል ስም ይጠቀማል። ሁለቱም ስለራሳቸው ግላዊ መረጃ በመለዋወጥ ግንኙነት ይፈጠራሉ። ይሁን እንጂ እርስ በእርሳቸው የተላላኳቸው ኢሜይሎች በስህተት በሌላ ተማሪ እጅ ይገባል። የሳይመንን ሚሰጢር በእጁ ያስገባው ማርቲን የሚባለው ተማሪ አቢን የሳይመን ጓደኛ በጣም ይወዳታል ነገር ግን ጓደኛ ሊያደርጋት አልቻለም። የሳይመንን ምስጢር እንደ ማስፈራሪያ በመጠቀም አቢን ጓደኛው እንድትሆን እንዲረዳው ይህን ካላደረገ ግን ምስጢሩን ለመላው ትምህርት ቤት እንደሚነግርበት አስፈራራው፡፡ ሳይመን በዚህ መሃል የክፍል ጓደኛው የሆነው ብራም "ብሉ" ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ይጀምራል። በሃሎዊን ግብዣ ላይ ሳይመን ከብራም ጋር ለመነጋገር ቢሞክርም ከሴት ተማሪ ጋር ሲሳሳም ያየዋል። ሳይመን ለኒክ አቢን የሚወድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነ የፍቅር ጓደኛ እንዳላት በመንገር ይዋሸዋል። ከግብዣው በኋላ ሊያ ለሳይመን አንድን ሰው እስከ ሕይወቷ መጨረሻ የምታፈቅር ሆኖ እንደሚሰማት ትነግረዋለች። ሳይመን ይህ የምታፈቅረው ሰው ኒክ ነው ብሎ ያምናል። በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ ሳይመን ከአቢና ከማርቲን ጋር ተገናኝቶ ለሚያሳዩት የቲያትር ትዕይንት ይለማመዳሉ። ከሳይመንና ከአስተናጋጃቸው፣ ላይል በመሃል ጥሩ ግንኙነት ይፈጠራል። ሳይመን እርሱ "ብሉ" ሊሆን ይችላል ብሎ ያምናል። በኋላ በሌሊት ሳይመን ለአቢ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነቱን ይነግራታል። እርሷም በአዎንታዊ ስሜት ትቀበለዋለች። በትምህርት ቤት የኳስ ጨዋታ ላይ ሆነው ሳይመን ላይልን ያየዋል። ላይል "ብሉ" መሆኑን ሊጠይቅ እያሰበ ሳለ ግን ላይል አቢን እንደሚወድ ይደርስበታል። በዚህም የተናደደው ሳይመንን ማርቲን ምክር እንዲሰጠው ሲጠይቅ ሳይመን አዝወትሮ መነዝነዙ አበሳጭቶት "ደፍረህ የፈለግከውን አድርግ ወይም ተወው" ይለዋል። በዚህ መሰረት ማርቲን ያቀደውን ለማድረግ ይወስናል። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት ተሳታፊዎች ሁሉ ብሔራዊ መዝሙር መዘመራቸውን ማርቲን ያስቆማና ለአቢና ለተሳታፊዎች ሁሉ አቢን እንደሚወድ ይነግራቸዋል። አቢ ግን ለእርሱ እንደዚያ ዓይነት ስሜት እንደሌላት ትነግረዋለች። ይህንንም ተከትሎ ማርቲንን ሌሎቹ ተማሪዎቹ ያላገጡበታል። ማርቲን በተፈጠረው ነገር ሰዎች እርሱ ላይ ማላገጣቸውን እንዲያቆሙና በበቀል ስሜት በገና ዋዜማ የሳይመን ኢሜይሎችን በምስጢር ድረ ገጹ ላይ በመለጠፍ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነቱን ለመላው ትምህርት ቤት ያሳውቅበታል። የሳይመን እህት ኖራ ወንድሟን ልታጽናናው ብትሞክርም ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረት የመኝታ ቤቱ በር ይዘጋባታል በዚህም ብቻ ሳያበቃ ከትምህርት ቤት ጓደኞቹ ለሚደርሱት መልዕክቶች ምላሽ መስጠት ያቆማል። በዕለተ ገና ሳይመን የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነቱን ለወላጆቹ ይነግራቸዋል። ምንም እንኳ ቢገርማቸውም ይቀበሉታል። ከበዓል ዕረፍት በኋላ ፍቅረኛሞች የሆኑት ኒክ እና አቢ ተበሳጭተው ሳይመንን ስለ ነገራቸው ውሸቶች ያፋጥጡታል። እርሱም ያደረጋቸውን ነገሮች በሙሉ ማርቲን እያስፈራራው የሰራቸው ጥፋቶች መሆኑን ይነግራቸዋል። ሊያ የምትወደው ኒክን ሳይሆን ሳይመን መሆኑን ትነግረዋለች። ጓደኞቹ ከተጣሉት በኋላ ሳይመን ከብሉ የመጨረሻ ኢሜይል ይደርሰዋል። በኢሜይሉ ውይይታቸው ብሉ ይፋ በመውጣቱ ማዘኑን ይገልፃል። ከዚያህ በኋላም መጻጻፋቸውን መቀጠል እንደማይፈልግ ነግሮ የኢሜይል መለያውን ያስወግዳል። ሳይመን ጓደኞቹን ብቻ ሳይሆን ፍቅር ያስያዘው ምስጢራዊውን ሰው ስላጣ በጣም ያዝናል። በትምህርት ቤት መመገቢያ ክፍል ውስጥ ሳይመንን እና ግልጽ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ የሆነ ኢታን በተባለ ሌላ ተማሪ ላይ ሁለት ተማሪዎች ያላገጣሉ። በሳይመን እና በኢታን መካከል የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነታቸውን መግለጻቸውን ተከትሎ ያጋጠሟቸውን ችግሮች በመወያየት ጥሩ ግንኙነት ይፈጠራሉ። ሳይመን ሊያን ይቅርታ ይጠይቃታል። በምስጢር መስጫ ድረ ገጹ ላይ ጓደኞቹን በይፋ ይቅርታ ይጠይቃቸዋል እንዲሁም ብሉ ከእርሱ ጋር የትምህርት ቤት ካርነቫል በዓል ላይ እንዲገናኙ ይጠይቀዋል። ከትምህርት ቤቱ የሙዚቃ ዝግጅት በኋላ ሊያ፣ ኒክ እና አቢ ከሳይመን ጋር እርቅ ያወርዱና ከእነርሱ ጋር ወደ ካርነቫሉ እንዲሄድ ይጋብዙታል። ሳይመን ብሉን ለመጠበቀ ፌሪስ መንኩራኮሩ ላይ ይቀመጣል። ሳይመን የፌሪስ መንኩራኮር ላይ ለመቆየት የገዛቸው ትኬቶች በሙሉ ሲያለቁ ማርቲን ላጥፋው ጠፋት ካሳ ሌላ አንድ ዙር ትኬት ለሳይመን ይገዛለታል። ዙሩ ከመጀመር በፊት ብራም ከሳይመን ጎን በመቀመጡ ብሉ እርሱ መሆኑን ለሁሉም ግልጽ ያደርጋል። ሳይመን ከሴት ተማሪ ሲሳሳም ያየው በስካር መንፈስ የተሰራ ስህተት እንደነበረ ይነግረዋል። አንድ ላይ ፌሪስ መንኩራኮሩ ላይ ተቀምጠው ይሳሳማሉ ይሄንንም ክስተት ቆመው ሲመለከቱ የነበሩት ጓደኞቻቸው ደስታቸውን በጨብጨባ ይገልጣሉ። የሳይመን ሕይወት ቀስ በቀስ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ይመለሳል። እርሱና ብራም ፍቅረኛሞች ይሆናሉ። የአሜሪካ
49168
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A5%E1%8C%8D%E1%88%AD%20%E1%8A%B3%E1%88%B5%20%E1%88%88%E1%8B%88%E1%8B%B3%E1%8C%85%E1%8A%90%E1%89%B5
እግር ኳስ ለወዳጅነት
እግር ኳስ ለወዳጅነት በ የሚተገበር ዓመታዊ የአለምአቀፍ የልጆች ማህበራዊ ፕሮግራም ነው። የፕሮግራሙ ግብ በወጣቱ ትውልድ ላይ በእግር ኳስ በኩል የጤናማ አኗኗር አስፈላጊ እሴቶችን እና ፍላጎትን ማስረጽ ነው። በፕሮግራሙ መዋቅር ውስጥ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ዕድሜያቸው 12 ዓመት የሆኑ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በዓመታዊ የአለምአቀፍ ልጆች መድረክ፣ የ«እግር ኳስ ለወዳጅነት» አለም ዋንጫ፣ አለምአቀፍ የእግር ኳስ ቀን እና የጓደኝነት ላይ ይሳተፋሉ የ ዓለምአቀፍ ፕሮግራሙ አስተባባሪ (ሩሲያ) ታሪክ እግር ኳስ ለወዳጅነት 2013 የመጀመሪያው የአለምአቀፍ የልጆች የእግር ኳስ ለወዳጅነት መድረክ እ.ኤ.አ. ሜይ 25፣ 2013 ለንደን ውስጥ ከ8 አገሮች የመጡ 670 ልጆች ተሳትፈውበታል፦ ከቡልጋሪያ፣ ታላቋ ብሪታኒያ፣ ሃንጋሪ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ሩሲያ፣ ሰርቢያ እና ስሎቬኒያ ሩሲያ በ2018 ዓ.ም. ላይ የፊፋ አለም ዋንጫ ግጥሚያዎችን ከሚያስተናግዱ 11 የሩሲያ ከተማዎች በተውጣጡ 11 የእግር ኳስ ቡድኖች ተወክላ ነበር። እንዲሁም የዜኒት፣ ቼልሲ፣ ሻልክ 04፣ ክርቨና ዝቨዝዳ ክለቦች የሕጻናት ቡድኖች፤ የልጆች ስፖርት ቀን አሸናፊዎች፤ እና አሸናፊዎች የእርሱ ፌስቲቫል አሸናፊዎችም በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል። በመድረኩ ጊዜ ልጆቹ ከሌሎች አገሮች ከመጡ አቻዎቻቸው እና ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ተወያይተዋል፣ እና እንዲሁም በዌምብሌይ ስቴዲዮም 2012/2013 ላይ ሻምፒዮንሽ ሊግ ፍጻሜን ተከታትለዋል። የመድረኩ ውጤት ልጆቹ የሚከተሉት የፕሮግራሙ ስምንት እሴቶችን ቀምረው ያስቀመጡበት ክፍት ደብዳቤ ነው፦ ወዳጅነት፣ እኩልነት፣ ፍትሕ፣ ጤና፣ ሠላም፣ ታማኝነት፣ ድል እና ባህሎች። በኋላ ላይ ደብዳቤው ወደ የዩዌፋ፣ ፊፋ እና አይኦሲ መሪዎች ተልኳል]። ሴፕቴምበር 2013 ላይ ከቭላዲሚር ፑቲን እና በተደረገ ስብሰባ ላይ ሴፕ ብላተር ደብዳቤውን መቀበላቸውንና እግር ኳስ ለወዳጅነትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2014 የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ ሁለተኛ ምዕራፍ እ.እ.አ. ሜይ 23-25፣ 2014 ዓ.ም. ላይ በሊዝበን ላይ የተካሄደ ሲሆን ከ16 አገሮች የመጡ 450 ታዳጊዎችን ያቀፈ ነበር፦ ቤላሩስ፣ ቡልጋሪያ፣ ታላቋ ብሪታኒያ፣ ሃንጋሪ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖላንድ፣ ፖርቱጋል፣ ሩሲያ፣ ሰርቢያ፣ ስሎቬኒያ፣ ቱርክ፣ ዩክሬን፣ ፈረንሳይ እና ክሮሽያ። ወጣቶቹ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በአለምአቀፉ የእግር ኳስ ለወዳጅነት መድረክ ላይ ተሳትፈዋል፣ በጎዳና እግር ኳስ ላይ ተሳትፈዋል፣ እና 2013/2014 ላይ የዩዌፋ ሻምፒዮና ሊግ ፍጻሜን ተከታትለዋል የ2014 የአለምአቀፍ ጎዳና እግር ኳስ ውድድሩ አሸናፊ ቤንፊካ ታዳጊ ቡድን (ፖርቱጋል) ነው። የፕሮግራሙ ሁለተኛ ምዕራፍ ውጤት የእግር ኳስ ለወዳጅነት ንቅናቄ መሪ ምርጫ ነው። የተመረጠው የፖርቱጋሉ ፌሊፕ ሷሬዝ ነበር ጁን 2014 ላይ እንደ የንቅናቄው መሪ ዩሪ አንድሬየቪች ሞሮዞቭን ለመዘከር ዘጠነኛውን የአለምአቀፍ ወጣት እግር ኳስ ውድድርን ጎብኝቶ ነበር። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2015 የአለምአቀፍ ማህበራዊ ፕሮግራሙ እግር ኳስ ለወዳጅነት ሶስተኛ ምዕራፍ ጁን 2015 በበርሊን ላይ ነው የተካሄደው። ከእስያ አህጉር የመጡ ወጣት ተሳታፊዎች ከጃፓን፣ ቻይና እና ካዛክስታን የመጡ የልጆች እግር ኳስ ቡድኖች ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሮግራሙ ላይ ተሳትፈዋል። በጠቅላላ ከ24 አገሮች የመጡ የ24 እግር ኳስ ክለቦች ታዳጊ ቡድኖች በሶስተኛው ምዕራፍ ላይ ተሳትርፈዋል። ወጣት ተጫዋቾቹ ከሌሎች አገሮች ከመጡ አቻዎቻቸው እና የዓለም እግር ኳስ ኮከቦች፣ የፕሮግራሙ አለምአቀፍ አምባሳደር ፍራንዝ ቤከንባወር ጨምሮ፣ ጋር ተወያይተዋል፣ እንዲሁም የታዳጊ ቡድኖች አለምአቀፍ የጎዳና እግር ኳስ ውድድር ላይም ተሳትፈዋል። የ2015 አለምአቀፍ የጎዳና እግር ኳስ ውድድር አሸናፊ የራፒድ አነስተኛ ቡድን (ኦስትሪያ) ነው። የሶስተኛው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ምዕራፍ ክስተቶች ከቀዳሚ የዓለም መገናኛ ብዙሃን በመጡ 200 አካባቢ ጋዜጠኛዎችና እንዲሁም ከአውሮፓ እና ከእስያ በመጡ የአለምአቀፍ የልጆች ፕሬስ ማዕከል አባል በሆኑ 24 ወጣት ሪፖርተሮች ተሸፍነዋል። የ2015 ዋናው ክስተት የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫ ሽልማት ነበር፣ የተሸለመውም የባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ (ስፔን) ነበር። አሸናፊው የተመረጠው በመድረኩ ዋዜማ ላይ በሁሉም 24 ተሳታፊ አገሮች ውስጥ በነበረው አለምአቀፍ ድምጽ አሰጣጥ ላይ በተሳተፉ ልጆች ነው። በመድረኩ መጨረሻ ላይ ሁሉም ተሳታፊዎች በወጉ መሠረት የ2014/2015 ሻምፒዮና ሊግ ፍጻሜውን በበርሊን ውስጥ ባለው የኦሊምፒክ ስታዲየም ላይ ተከታትለዋል እግር ኳስ ለወዳጅነት 2016 በ 2016 ለጓደኝነት የሚጀምሩ ዓለማቀፍ የልጆች ማህበራዊ መርሃ ግብር በኦንላይን አብሮ መሆን ተጫን ጉባኤ እንደ አንድ ክፍል ተሰጥቶ ነበር መጋቢት 24 ሙኒክ ውስጥ ተካሂዷል ተካሂዷል የአለምአቀፍ አምባሳደር የተሳተፈበት። በፕሮግራሙ አራተኛ ምዕራፍ ላይ ከአዘርባይጃን፣8 አዲሱ ወጣት ቡድን አልጄሪያ፣ አርሜኒያ፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ቪዬትናም፣ ኪርጊዝታን እና ሶርያ ተቀላቅለውበታል፣ ስለዚህ ጠቅላላው የተሳታፊ አገሮች ብዛት 32 ላይ ደረሰ። እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 5፣ 2016 ዓ.ም. ላይ ልዩ የሆነው የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫ ምርጫ ተጀመረ በመላው ዓለም ያሉ አድናቂዎች አሸናፊውን መምረጥ ላይ ተሳትፈዋል፣ ነገር ግን የመጨረሻው ውሳኔ የተሰጠው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ተሳታፊዎች ባካሄዱት ምርጫ ነው። ዋንጫው ያሸነፈው የባየርን እግር ኳስ ክለብ (ሙኒክ) ነው። የእግር ኳስ ለወዳጅነት ተሳታፊዎች ክለቡ ልዩ ፍላጎቶች ያላቸው ልጆችን ለመደገፍ ያደረጋቸው እንቅስቃሴዎችንና እንዲሁም በተለያዩ አገሮች ውስጥ ላሉ ልጆች ሕክምና ማቅረብና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ልጆች ለመርዳት ያደረጋቸው ጅማሮዎችን አውስተዋል። አራተኛው የአለምአቀፍ ልጆች መድረክ እግር ኳስ ለወዳጅነት እና የልጆቹ አለምአቀፍ የጎዳና እግር ኳስ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ እ.ኤ.አ. ሜይ 27-28፣ 2016 ዓ.ም. በሚላን ውስጥ ተካሂዷል። የውድድሩ አሸናፊ የስሎቬኒያው የማሪቦር ቡድን ነው። በመድረኩ መጨረሻ ላይ ተሳታፊዎቹ በወጉ መሠረት የዩዌፋ ሻምፒዮና ሊግ ፍጻሜውን ተከታትለዋል የመድረኩ ክስተቶች ከቀደምት መገናኛ ብዙሃን በመጡ 200 ጋዜጠኛዎችና እንዲሁም ከተሳታፊ አገሮች በመጡ ወጣት ጋዜጠኛዎችን ባካተተው የልጆች አለምአቀፍ ፕሬስ ማዕከል ተሸፍኗል። ከሶርያ ክለብ አልዋህዳ የመጡ ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾች በአራተኛው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ምዕራፍ ላይ ተካፍለው ነበር፣ ይህም ከዚህ በፊት ያልተደረገ ነው። የሶርያው ቡድን ከፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ውስጥ መካተቱ እና የሶርያ ልጆች በሚላን ውስጥ የነበሩ ክስተቶችን መጎብኘታቸው በአገሪቷ ውስጥ የነገሰውን ሰብዓዊ ቀውስ መወጫ አንድ አስፈላጊ እርምጃ ነበር። የአለምአቀፍ ቴሌቪዥን ጣቢያው ራሽያ ቱዴይ የአረብኛው የስፖርት እትም ቦርዱ በሶርያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ድጋፍ ልጆቹ በፕሮጀክቱ ላይ መሳተፋቸውን የሚያሳይ «ሶስት ቀናት ያለጦርነት» የሚል ጥናታዊ ፊልም ሰርቷል። እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 14፣ 2016 ዓ.ም. ላይ ከ7,000 በላይ ሰዎች ፊልሙን በደማስቆ ላይ ሲመረቅ ተመልክተውታል። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2017 በ2017 የአለምአቀፍ ልጆች ማህበራዊ ፕሮጀክቱ እግር ኳስ ለወዳጅነት የተዘጋጀው በሴንት ፒተርስበርግ (ሩሲያ) ሲሆን የመጨረሻዎቹ ክስተቶች ከጁን 26 እስከ ጁላይ 3 ድረስ እዚሁ የተካሄዱ ናቸው። 2017 ላይ የተሳታፊ አገሮች ብዛት ከ32 ወደ 64 አድጓል። ለመጀመሪያ ጊዜ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ ከሜክሲኮ [31] እና ከአሜሪካ የመጡ ልጆች ተከታትለውታል። በዚህም ፕሮጀክቱ የአራት አህጉራት አፍሪካ፣ ዩሬዥያ፣ ሰሜን አሜሪካ እና ደቡብ አሜሪካ ወጣት ተጫዋቾችን አገናኝቶ አንድ አድርጓቸዋል። በአምስተኛው ምዕራፍ ላይ ፕሮግራሙ በአዲስ ጽንሰ-ሐሳብ መሠረት ነው የተተገበረው፦ ከእያንዳንዱ አገር አንድ ወጣት ተጫዋች አገሩ/ሯን እንዲወክሉ ተመርጠዋል። አካል ጉዳት ያላቸው ጨምሮ ልጆቹ 12 ዓመት በሆናቸው ወንድ እና ሴት ልጆች በተመሠረቱ አለምአቀፍ የወዳጅነት ቡድኖች ላይ አንድነት አሳይተዋል። በተደረገ ግልጽ የዕጣ ስነ-ስርዓት የቡድኖቹ የአገር ጥንቅር እና የተሳታፊ አገሮች ተወካዮች የጨዋታ ቦታዎች ተወስኗል። ዕጣው በበይነመረብ ጉባዔ ሁነታ ላይ ነው የተካሄደው። ስምንቱ የወዳጅነት ቡድኖችን የመሩት ወጣት አሰልጣኞች ናቸው፦ (ስሎቬኒያ)፣ ስቴፋን ማክሲሞቪች (ሰርቢያ)፣ ብራንደን ሻባኒ (ታላቋ ብሪታኒያ)፣ ቻርሊ ሱዊ (ቻይና)፣ (ሩሲያ)፣ ቦግዳን ክሮለቨትስኪ (ሩሲያ)፣ አንቶን ኢቫኖቭ (ሩሲያ)፣ (ኔዘርላንድስ)። የእግር ኳስ ለወዳጅነት አለምአቀፍ ፕሬስ ማዕከል ተወካይየሆኑት ሊሊያ ማትሱሞቶ (ጃፓን) እንዲሁም በዕጣው ስነ-ስርዓቱ ላይም ተካፍለዋል። የእግር ኳስ ለወዳጅነት 2017 አለም ዋንጫ አሸናፊ «ብርቱካናማ» ቡድኑ ነበር፣ ይህም ከዘጠኝ አገሮች ወጣት አሰልጣኝ እና ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾችን ያካተተ ነበር፦ (ስሎቬኒያ)፣ ሆንግ ጁን ማርቪን ቱ (ሲንጋፖር)፣ ፖል ፑዊግ ኢ ሞንታና (ስፔን)፣ ጋብሪየል ሜንዶዛ (ቦሊቪያ)፣ ራቫን ካዚሞቭ (አዘርባይጃን)፣ ክሪሲሚር ስታኒሚሮቭ (ቡልጋሪያ)፣ ኢቫን አጉስቲን ካስኮ (አርጀንቲና)፣ ሮማን ሆራክ (ቼክ ሪፐብሊክ)፣ ሃምዛህ ዩሱፍ ኑሪ አልሃቫት (ሊብያ)። ቁልፍ የሰብዓዊ እሴቶች በወጣቱ ትውልድ ላይ እንዲሰርጽ ጥሪ ያቀረቡ ቪክቶር ዙብኮቭ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበር)፣ ፋትማ ሳሙራ (የፊፋ ዋና ሴክረተሪ)፣ ፊሊፕ ለ ፍሎክ (የፊፋ ዋና የንግድ ዳይሬክተር)፣ ጂዩሊዮ ባፕቲሳ (የብራዚል እግር ኳስ ተጫዋች)፣ ኢቫን ዛሞራኖ (የቺሊ አጥቂ)፣ አሌክሳንደር ከርዛኮቭ (የሩሲያ እግር ኳስ ተጫዋች) እና ሌሎች እንግዳዎች የአለምአቀፍ ልጆች መድረኩን እግር ኳስ ለወዳጅነት ተከታትለውታል። 2017 ላይ ፕሮጀክቱ ከ600,000 በላይ ሰዎችን አንድ ላይ ያሰባሰበ ሲሆን ከ64 አገሮች የተውጣጡ ከ1,000 በላይ ልጆችና አዋቂዎች የመጨረሻዎቹን ክስተቶች በሴንት ፒተርስበርግ ላይ ተከታትለዋል። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2018 2018 ላይ ስድስተኛው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ በሩሲያ ውስጥ ከፌብሩዋሪ 15 እስከ ጁን 15 እንዲካሄድ ተወስኗል። የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች 211 አገሮችን እና የዓለም ክፍሎችን የሚወክሉ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾችን እና ጋዜጠኛዎችን ያካትታል። የ2018 ፕሮግራሙ ኦፊሴላዊ ጅምር በአየር ላይ በግልጽ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ዕጣ የተሰጠ ሲሆን በውጤቶቹ መሠረት 32 የአለምአቀፍ እግር ኳስ ቡድኖች የወዳጅነት ቡድኖች ተመስርተዋል። አዲሱ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ክፍል የአካባቢ ጥበቃ ተልዕኮ ነው 2018 ላይ የአለምአቀፍ እግር ኳስ ወዳጅነት ቡድኖች በብርቅዬ እና አደጋ ላይ ያሉ የእንስሳት ዝርያዎች ነው የተሰየሙት፦ በ2018 ዓ.ም. የተፈጥሮ ጥበቃ ተልእኮ መሠረት የሚል መጠሪያ የተሰጠው የዓለም ማህበረሰብ በመጥፋት ላይ የሚገኙ እንሠሣትን ለማዳን የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል። የሩሲያ የዓሜሪካ የኔፓልና የታላቋ ብሪታኒያ የእንሠሣት ጥበቃ ክልሎች በእንቅስቃሴው ላይ ተካፋዮች ሆነዋል። ሞስኮ ውስጥ በተደረገው የእግር ኳስ ለወዳጅነት የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ወቅት ተካፋዮቹ በተፈጥሮ ጋዝ የሚንቀሳቀሱ በኤኮ ወዳጅ አውቶቡሶች ተጉዘዋል። በ2018 ውስጥ በእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፉ አገሮች እና ክልሎች፦ 1. የአውስትራሊያ ኮመንዌልዝ 2. የኦስትሪያ ሪፐብሊክ 3. የአዘርባይጃን ሪፐብሊክ 4. የአልጄሪያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5. ዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂን ደሴቶች 6. የአሜሪካ ሳሞአ 7. አንጉላ 8. አንቲጓ እና ባርቡዳ 9. የግብጽ አረብ ሪፐብሊክ 10. አርጀንቲና ሪፐብሊክ 11. አሩባ 12. ባርቤዶስ 13. ቤሊዝ 14. የቤርሙዳ ደሴቶች 15. የቬነዝዌላ ቦሊቫሪያዊ ሪፐብሊክ 16. ቦስኒያ እና ሄርዘጎቪና 17. የብሪታኒያ ቨርጂን ደሴቶች 18. ቡርኪና ፋሶ 19. የሉክዘምበርግ ታላቅ ግዛት 20. ሃንጋሪ 21. የኡራጓይ ኦሪየንታል ሪፐብሊክ 22. ጋቦን ሪፐብሊክ 23. የጊኒ ሪፐብሊክ 24. ጂብራልታር 25. ብሩነይ ዳሩሳላም 26. እስራኤል 27. ኳታር 28. ኩዌት 29. ሊብያ 30. ፍልስጥኤም 31. ግረናዳ 32. ግሪክ 33. ጂዮርጂያ 34. የቲሞር-ሌስተ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 35. የኮንጎ ዲምክራሲያዊ ሪፐብሊክ 36. የሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፕ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 37. የሽሪላንካ ዲሞክራሲያዊ ሶሻሊስት ሪፐብሊክ 38. የዶሚኒካ ሪፐብሊክ 39. ዮርዳኖስ 40. የአፍጋኒስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ 41. የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ 42. የማውሪታኒያ እስላማዊ ሪፐብሊክ 43. የጣልያን ሪፐብሊክ 44. የየመን ሪፐብሊክ 45. የካይማን ደሴቶች 46. ካናዳ 47. የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ 48. የቻይና ታይፔይ (ታይዋን) 49. አንዶራ 50. ሊችተንስታይን 51. የጉያና ትብብራዊ ሪፐብሊክ 52. የኮሪያ ዲሞክራሲያዊ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ 53. ባህሬን መንግሥት 54. ቤልጂየም መንግሥት 55. ቡታን መንግሥት 56. ዴንማርክ መንግሥት 57. ስፔንመንግሥት 58. ካምቦዲያመንግሥት 59. ሌሶቶ መንግሥት 60. ሞሮኮ መንግሥት 61. ኔዘርላንድስ መንግሥት 62. ኖርዌይ መንግሥት 63. ሳውዲ አረቢያመንግሥት 64. ስዋዚላንድመንግሥት 65. ታይላንድ መንግሥት 66. ቶንጋ መንግሥት 67. ስዊድንመንግሥት 68. ኪርጊዝ ሪፐብሊክ 69. 70. የላዎ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 71. የላትቪያ ሪፐብሊክ 72. የሊባኖስ ሪፐብሊክ 73. የሊቱዌኒያ ሪፐብሊክ 74. ማሌይዥያ 75. የማልዲቭስ ሪፐብሊክ 76. ሜክሲኮ 77. ቦሊቪያ 78. ሞንጎሊያ 79. ሞንትሴራት 80. የባንግላዴሽ ሕዝብ ሪፐብሊክ 81. የፓፑዋ ኒው ጊኒ ነጻ ግዛት 82. የሳሞአ ነጻ ግዛት 83. ኒው ዚላንድ 84. ኒው ካሌዶኒያ 85. ታንዛኒያ 86. የተባበሩት አረብ ኢመሬቶች 87. የኩክ ደሴቶች 88. የቱርክ እና ካይኮስ ደሴቶች 89. የአልባኒያ ሪፐብሊክ 90. የአንጎላ ሪፐብሊክ 91. የአርሜኒያ ሪፐብሊክ 92. የቤላሩስ ሪፐብሊክ 93. የቤኒን ሪፐብሊክ 94. የቡልጋሪያ ሪፐብሊክ 95. የቦትስዋና ሪፐብሊክ 96. የቡሩንዲ ሪፐብሊክ 97. የቫኗቱ ሪፐብሊክ 98. የሃይቲ ሪፐብሊክ 99. የጋምቢያ ሪፐብሊክ 100. የጋና ሪፐብሊክ 101. የጓቴማላ ሪፐብሊክ 102. የጊኒ-ቢሳው ሪፐብሊክ 103. የሆንዱራስ ሪፐብሊክ 104. የጅቡቲ ሪፐብሊክ 105. የዛምቢያ ሪፐብሊክ 106. የዚምባብዌ ሪፐብሊክ 107. የህንድ ሪፐብሊክ 108. የኢንዶኔዥያ ሪፐብሊክ 109. የኢራቅ ሪፐብሊክ 110. የአየርላንድ ሪፐብሊክ 111. የአይስላንድ ሪፐብሊክ 112. የካዛክስታን ሪፐብሊክ 113. የኬንያ ሪፐብሊክ 114. የቆጵሮስ ሪፐብሊክ 115. የኮሎምቢያ ሪፐብሊክ 116. የኮንጎ ሪፐብሊክ 117. የኮሪያ ሪፐብሊክ 118. የኮሶቮ ሪፐብሊክ 119. የኮስታ ሪካ ሪፐብሊክ 120. የኮት ዲቯር ሪፐብሊክ 121. የኩባ ሪፐብሊክ 122. የላይቤሪያ ሪፐብሊክ 123. የማውሪሸስ ሪፐብሊክ 124. የማዳጋስካር ሪፐብሊክ 125. የመቄዶንያ ሪፐብሊክ 126. የማላዊ ሪፐብሊክ 127. የማሊ ሪፐብሊክ 128. የማልታ ሪፐብሊክ 129. የሞዛምቢክ ሪፐብሊክ 130. የሞልዶቫ ሪፐብሊክ 131. የናሚቢያ ሪፐብሊክ 132. የኒጀር ሪፐብሊክ 133. የኒካራጓ ሪፐብሊክ 134. የኬፕ ቨርዴ ሪፐብሊክ 135. የፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ 136. የፓናማ ሪፐብሊክ 137. የፓራጓይ ሪፐብሊክ 138. የፔሩ ሪፐብሊክ 139. የፖላንድ ሪፐብሊክ 140. የፖርቱጋል ሪፐብሊክ 141. የርዋንዳ ሪፐብሊክ 142. የሳን ማሪኖ ሪፐብሊክ 143. የሲሸልስ ሪፐብሊክ 144. የሴነጋል ሪፐብሊክ 145. የሰርቢያ ሪፐብሊክ 146. የሲንጋፖር ሪፐብሊክ 147. የስሎቬኒያ ሪፐብሊክ 148. የሚያንማር ህብረት ሪፐብሊክ 149. የሱዳን ሪፐብሊክ 150. የሱሪናም ሪፐብሊክ 151. የሴራ ሊዮን ሪፐብሊክ 152. የታጂኪስታን ሪፐብሊክ 153. የትሪኒዳድ እና ቶቤጎ ሪፐብሊክ 154. የቱርክሜኒስታን ሪፐብሊክ 155. የኡጋንዳ ሪፐብሊክ 156. የኡዝቤኪስታን ሪፐብሊክ 157. የፊጂ ሪፐብሊክ 158. የፊሊፒንስ ሪፐብሊክ 159. የክሮሽያ ሪፐብሊክ 160. የቻድ ሪፐብሊክ 161. የሞንተኔግሮ ሪፐብሊክ 162. የቺሊ ሪፐብሊክ 163. የኢኳዶር ሪፐብሊክ 164. የኢኳቶሪያል ጊኒ ሪፐብሊክ 165. የኤል ሳልቫዶር ሪፐብሊክ 166. የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ 167. የካሜሮን ሪፐብሊክ 168. የሩሲያ ፌደሬሽን 169. ሮማኒያ 170. የሕዝባዊ ሪፐብሊክ ቻይና የሆንግ ኮንግ ልዩ አስተዳደራዊ ክልል 171. የፖርቶ ሪኮ ነጻ ተጓዳኝ ግዛት 172. ሰሜናዊ አየርላንድ 173. ሴንት ቪንሰንት እና ግረናዲንስ 174. ሴንት ሉሲያ 175. የሶርያ አረብ ሪፐብሊክ 176. የስሎቫክ ሪፐብሊክ 177. የባሃማስ የጋራ ብልጽግና 178. የዶሚኒካ የጋራ ብልጽግና 179. የታላቋ ብሪታኒያ እና የሰሜናዊ አየርላንድ የተባበረ ንጉሳዊ ግዛት 180. አሜሪካ 181. የሰለሞን ደሴቶች 182. የቪዬትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ 183. የኮሞሮስ ህብረት 184. የሕዝባዊ ሪፐብሊክ ቻይና የማካዎ ልዩ አስተዳደራዊ ክልል 185. የኦማን ሱልታኔት 186. ታሂቲ 187. የጓም ግዛት 188. የቶጎ ሪፐብሊክ 189. የቱኒዚያ ሪፐብሊክ 190. የቱርክ ሪፐብሊክ 191. ዩክሬን 192. ዌልስ 193. የፋሮዌ ደሴቶች 194. የኔፓል ፌዴራል ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 195. የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 196. የብራዚል ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ 197. የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ 198. የናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ 199. የሶማልያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ 200. የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ ፌዴሬሽን 201. የፊንላንድ ሪፐብሊክ 202. የፈረንሳይ ሪፐብሊክ 203. የመካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ 204. የቼክ ሪፐብሊክ 205. የስዊስ ኮንፌዴሬሽን 206. ስኮትላንድ 207. ኤርትራ 208. የኤስቶኒያ ሪፐብሊክ 209. የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ 210. ጃማይካ 211. ጃፓን በ2018 ዓ.ም. በተደረገው የዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ሻምፒዮና ላይ 32 የዓለም አቀፍ ቡድኖች «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ቡድኖችተካፋይሆነዋል። የፍጻሜው ውድድር ዘጋቢም ሶሪያዊው ወጣት ዘጋቢ ያዝን ጣኃ ነበር። የፍጻሜው ውድድርም ዋና ዳኛም ወጣቱ ሩሲያዊው ቦግዳን ባታሊን ነበር። የ2018 «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ውድድር አሸናፊም «የሺምፓንዜ» ቡድን ሲኾን ተጫዋቾቹም ከዶሚኒካ ከሴንት ኪትስና ኔቪስ ማላዊ ኮሎምቢያ ቤኒንና ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ የተውጣጡ ነበሩ። የቡድኑም አልጣኝ ከሣራንስክ (ሩሲያ የመጣው ተሣታፊ ቭላዲስላቭ ፐሊኮቭ ነበር። የስድስተኛው «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት የህፃናት ጉባኤ ሰኔ 13 ቀን «በሞስ አኳረም» የውቂያኖስና የሥነ ተፈጥሮ ምርምር ማእከል ነበር። በሥነ ሥርዓቱም ላይ ቪክተር ዙብኮቭ (የጋዝፕሮም ሕዝባዊ አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ምክር ቤት ሊቀ መበር) ኦልጋ ገለዴትስ የሩሲያ ፌዴሬሽን መንግሥት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢከር ካሲሊ ስታዋቂው የእስፓኝ የእግር ኳስ ተጫዋችና የብሔራዊ ቡድን ካፒቴን አሌክሳንድር ከርዣኮቭ የሩሲያ የእግር ኳስ ተጫዋችና የወጣቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝና የ54 ሀገሮች አምባሰደሮችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። በመዝጊያ ሥነ ሥርአቱም ላይ የስድስተኛው ዙር ምርጥ ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሽልማት አግኝተዋል። ዴኦ ካሌንጋ ምቬንዜ ከዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ (ምርጥ አጥቂ) ያሚሩ ኦኡሩ ከቤኒን (ምርጥ በረኛ) ጉስታቮ ሰንትራ ሮቻ ከብራዚል (እጅግ ጠቃሚ ተጫዋች) በመኾን ልዩ ተሸላሚዎች ሆነዋል። የ2018 ዓ. ም. «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ምርጥ ወጣት ጋዜኛ አሩባዊቷ ሼይካሊ አሰንሲዮን በብሎጓ አማካይነት ወጣት የኦኪያኒያ ነዋሪዎች ለስነተፈጥሮ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስባለች። በሥነ ሥርአቱም ላይ የቀዳሚው «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ዙር ተካፋይ የነበረችው የህንዳዊቷ የአናኒ ካምቦጅ መጽሐፍ ተመርቋል። በ2017 ዓ. ም. አምስተኛው «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ውድድር ከተጠናቀ በኋላ አናኒ እንደ ወጣት ጋዜጠኛ በውድድሩ ወቅት ያገኘችውን ልምድ የሚዘግብ «ጉዞዬ ከሞሃይ እስከ ቅዱስ ፒተርቡርግ» የሚል መጽሐፍ ለአንባቢያን አቅርባለች። በመጽሐፉም ውስጥ ለዓለም መለወጥ እገዛ የሚያደርጉ ዘጠኝ እሴቶችን አስቀምጣለች። ሰኔ 14 ቀን «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ዓለም አቀፍ የልጆች ጉባኤ ከተጠናቀቀ በኋላ ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾችና ጋዜጠኞች በዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) በ 2018 ዓ. ም. በሞስኮ ከተማ በተዘጋጀው የዓለም የእግር ኳስ ሻምፒዮና መክፈቻ ሥነ ሥርት ላይ ተካፍዋል። ሰኔ 14 ቀን «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ዓለም አቀፍ የልጆች ጉባኤ ከተጠናቀቀ በኋላ ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾችና ጋዜጠኞች በዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) በ 2018 ዓ. ም. በሞስኮ ከተማ በተዘጋጀው የዓለም የእግር ኳስ ሻምፒዮና መክፈቻ ሥነ ሥርት ላይ ተካፍዋል። ልጆቹም በሉዥኒኪይ ስታዲየም በመክፈቻው ሥነ ሥርአት ላይ ተካፋይ የኾኑትን የ211 ሀገሮችን የሰንደቅ ዓላማዎች በታላቅ ክብር ሰቅለዋል። ከዚያም በሩሲያሲያና በሳኡዲ አረቢያ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የተደረገውን የመክፈቻ ጨዋታ ተመልክተዋል። በመክፈቻው ሥነ ሥርአት ላይ የተገኙት ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን የሩሲያሲያውን ወጣት «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» አምባሳደር አልበርት ዚናቶቭን ወደ መንበራቸው በመጋበዝ የመክፈቻ ውድድሩን ተመልክተዋል። ወጣቱ አምባሳደርም ከብራዚላዊው የዓለም የእግር ኳስ ሻምፒዮን ሮቤርቶ ካርሎስና ከእስፓኙ የእግር ኳስ ተጫዋች ከኢከር ካሲሊያስ ጋር ሀሣብ ተለዋውጧል። በፍጻሜ ሥነ ሥርአቶች ላይም ከ211 ሀገሮች የተውጣጡ ከ1500 በላይ ልጆች ተካፍለዋል። በጠቅላላው በስድስተኛው ዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተደረጉት ከ180 በላይ ዝግጅቶች ላይ ከ240 ሺ በላይ ልጆች ተካፋይ ኾነዋል። የ2018 ዓ.ም ፕሮጀክቱም በከፍተኛ የሩሲያ ባለሥልጣናት በኩል ድጋፍ አግኝቷል። በዝግጅቱ መክፈቻ ሥነ ሥርአት ላይ የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦልጋ ገለዴትስ የፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲንን የመልካም ምኞት መግለጪያ አንብበዋል። የሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ድሚትሪ ሜድቬደቭም በበኩላቸው ለስድስተኛው የዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ተሳታፊዎችና እንግዶች የመልካም ምኞት ቴሌግራም አስተላልፈዋል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አፈ ቀላጤ ማሪያ ዛኃሮቫ ግንቦት 23 ቀን ባደረገችው አጭር መግለጪያ የዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» በዓለም ማህበረሰብዕ ዘንድ ዋነኛ ከኾኑት የሀገሪቷ ሰብአዊ ተኮር ፖሊሲዎች አንዱ እንደኾነ ገልጻለች። የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ን እንደሚደግፍ የገለጸ ሲኾን በሞስኮ የ2018 ዓ.ም. በተካሄደው ዝግጅት ላይ የተሣታፊዎችና የእንግዶች ቁጥር ወደ 5000 እንደሚጠጋ አስታውቋል። እግር ኳስ ለወዳጅነት 2019 እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን 2019 ሰባተኛው ዙር የዓለም አቀፍ የህፃናት ማህበራዊ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም የተከናወነ ሲሆን የፍጻሜው ፕሮግራምም ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 2 ድረስ በማድሪድ ከተማ ተካሂደዋል ሚያዝያ 25 ቀን የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ እና ወዳጅነት ቀን ከ 50 በላይ በሆኑ የአውሮፓ የእስያ የአፍሪካ የሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ ሀገሮች የተከበረ ሲሆን የሩሲያ የእግር ኳስ ህብረትም የበዓሉ ተካፋይ ሆኗል፡፡ /እ.ኤ.አ. ግንቦት 30 ቀን በማድሪድ ከተማ የተካሄደው የዓለም አቀፍ የህፃናት ማህበራዊ ጉባኤ መድረክላይ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ባለሙያዎች የእግር ኳስ አሰልጣኞች የህፃናት ቡድን ሐኪሞች ኮከቦች መሪ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች የዓለም የእግር ኳስ አካዳሚዎች ተወካዮችና ፌዴሬሽኖች ተካፍለዋል። ግንቦት 31 ቀን ሁሉን አቀፍ የዓለም እግር ኳስ ሥልጠና በማድሪድ ተካሂዷል «የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት የ ኦፊሴላዊ የምስክር ወረቀት ተቀብሏል በሰባተኛው ዙር የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ውድድር ከአውሮፓ ከአፍሪካ ከእስያ ከሰሜን እና ከደቡብ አሜሪካ የተውጣጡ 32 ወጣት ጋዜጠኞች ዓለም አቀፍ የህፃናት ፕሬስ ማዕከልን በማዋቀር የዝግጅቱን ዜናዎች ከዓለም አቀፍ እና ከብሔራዊ መገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር አቀናብረው አቅርበዋል። የሰባተኛው ዙር የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ተሳታፊዎች «የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫ» (የዓለም አቀፍ የህፃናት ማህበራዊ ፕሮግራም እግር ኳስ ለወዳጅነት ሽልማት) ለሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ እጅግ ማህበራዊ ኃላፊነት ያለው ቡድን በማለት አበርክተዋል እ.ኤ.አ. ሰኔ 1 የሰባተኛው ዙር ፍፃሜ በማድሪድ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበራት ህብረት ፒች እግር ኳስ ሜዳ ተካሄዷል በፍጻሜ ውድሩ ላይ የአንቲጉዋ እባብ ብሔራዊ ቡድንና የታስማኒያ ዲያብሎስ በመደበኛው ሰዓት 1: 1 ተለያይተው ነበር።የአንቲጉዋ እባብ በቅጣት ምት አሸናፊ በመሆን ዋናውን ሽልማት አግኝቷል እግር ኳስ ለወዳጅነት 2020 ስምንተኛው የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ውድድር እ.ኤ.አ. በ 2020 (እ.ኤ.አ.) ከህዳር 27 እስከ ታህሣስ 9 ቀን 2020 በዲጂታል መሥመር ላይ ተካሂዷል። ከ 100 በላይ ሀገሮች የተውጣጡ ከ 10,000 በላይ ተሳታፊዎች ቁልፍ በሆኑ ዝግጅቶች ላይ ተካፍለዋል ለስምንተኛው ዙር ውድድር ሲባል አንድ ባለብዙ ተተጠቃሚዎችየእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ተዘጋጅቷል በዚህ ፕሮግራምመሠረት የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት 2020 ሻምፒዮና ተካሂዷል። ጨዋታውን ከታህሣስ 10 ቀን 2020 ጀምሮ- የዓለም እግር ኳስ ቀን መጫን ይቻላል ተጠቃሚዎች በዓለም አቀፍ ቡድኖች ውስጥ አንድ ላይ በመሆን በእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ህጎች መሠረት በጨዋታዎች የመሳተፍ ዕድልን አግኝተዋል ይህ የባለብዙ አውታረ መረብ ተጠቃሚዎች ጨዋታ እንደ ወዳጅነት ሰላም እና እኩልነት ባሉ የፕሮግራሙ ዋና እሴቶች ላይ የተመሠረተ ነው። እ.ኤ.አ. ኅዳር 27 የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት የዓለም አቀፍ ሻምፒዮና 2020 የመስመር ላይ የእጣ አጣጣል ሥነሥርዓት ተካሂዷል ከኅዳር 28 እስከ ታህሳስ 6 ድረስ ለህፃናት የሰብአዊ እና የስፖርት ትምህርታዊ መርሃግብሮች ያለው ዓለም አቀፍ የመስመር ላይ የወዳጅነት ስብሰባ ተካሄደ ከኅዳር 30 እስከ ታህሳስ 4 ቀን ድረስ የልጆች ስፖርቶች ማሳደጊያ ፕሮጀክቶች የቀረቡበት “እግር ኳስ ለወዳጅኝነት” የተሰኘው ዓለም አቀፍ የመስመር ላይ መድረክ ስብሰባ ተካሄዷል ባለሙያዎች “እግር ኳስ ለጓደኝነት” ለዓለም አቀፍ ሽልማት የሚያበቁ ፕሮጀክቶች በማቅረባቸው አድናቆታቸውን ገልጸዋል ከታህሳስ 7-8 (እ.ኤ.አ.) የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት የመስመር ላይ የዓለም ሻምፒዮና ተካሄደ የዘንድሮው ሻምፒዮና በዲጂታል መድረክ በመስመር ላይ የተካሄደ ሲሆን የባለብዙ ተጫዋች እግር ኳስ አስመሳይ እግር ኳስ ለጓደኝነት በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል ታህሳስ 9 ቀን ታላቁ የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ፍፃሜ ተካሂዷል የተባበሩት መንግስታት 75 ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመደገፍ ከተለያዩ ሀገራት ለሕጻናት የተዘጋጁ ተከታታይ ድህረ-ገፆች በፕሮግራሙ ስምንተኛው ዙር ላይ ቀርበዋል በስምንተኛው ዙር ወቅት ሳምንታዊው “ስታዲየም እኔ የምገኝበት ሥፍራ” የሚል ትርኢት በዓለም ዙሪያ ካሉ ነጻ ወጥ የእግር ኳስ ጋር በመሆን ተጀምሯል በእያንዳንዱ ትዕይንት ውስጥ ነጻ ወጥ የእግር ኳስ ባለሙያዎች ወጣት አምባሳደሮችን የጨዋታን ብልሃት ያስተማሯቸው ሲሆን በእያንዳንዱ ክፍል መጨረሺያ ተካፋዮቹ የምርጥ ብልሃት ውድድር ላይ እንዲቀርቡ ይነገር ነበር ትርኢቱ በዓለምአቀፍ የመስመር ላይ ማስተር ክላስ ተጠናቅቋል በዚህም የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ፕሮግራም በተሳተፉት ተሳታፊዎች ቁጥር ለሁለተኛ ጊዜ የጊነስ ዓለም አቀፍ ክብረ ወሰን ባለቤት ሆነ (እ.ኤ.አ. ታህሳስ 6 ቀን 2020) የመልካም ዜና አርታኢ የእግር ኳስ ለወዳጅኝነት ልጆች ከዓለም ዙሪያ የተገኙ አዎንታዊ ዜናዎችን ለተመልካቾች ያካፈሉበት በወጣት ጋዜጠኞች የተጀመረው ሳምንታዊ ትርዒት የእግር ኳስ ለወዳጅነት አለም ሻምፒዮና አለምአቀፍ የልጆች እግር ኳስ ውድድሩ በእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ መዋቅር ውስጥ ነው የሚካሄደው። በሻምፒዮናው ላይ የሚሳተፉ ቡድኖች የወዳጅነት ቡድኖች በግልጽ ዕጣው ስነ-ስርዓት ጊዜ ነው የሚመሠረቱት ቡድኖቹ በእግር ኳስ ለወዳጅነት መርሕ መሠረት የተደራጁ ናቸው፤ የተለያዩ አገራት፣ ጾታዎች እና አካላዊ ብቃት አትሌቶች ያላቸው በተመሳሳዩ ቡድን ውስጥ ነው የሚጫወቱት። የአለምአቀፍ ልጆች መድረክ እግር ኳስ ለወዳጅነት በዓመታዊው የአለምአቀፍ ልጆች መድረክ እግር ኳስ ለወዳጅነት ላይ የፕሮጀክቱ ወጣት ተሳታፊዎች ከአዋቂዎች ጋር በመሆን የፕሮግራሙ እሴቶችን በመላው ዓለም ላይ ማስተዋወቅና መገንባት ላይ ተወያይተዋል። በመድረኩ ጊዜ ልጆች ከሌሎች አገሮች ከመጡ አቻዎቻቸው፣ ታዋቂ እግር ኳስ ተጫዋቾች፣ ጋዜጠኛዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ፣ እና በዚህም ለወደፊት ሁለገብ እሴቶችን አቻዎቻቸው ጋር ለማስተዋወቅ በራሳቸው የሚሰሩ አምባሳደሮች ይሆናሉ። አለምአቀፍ የልጆች ፕሬስ ማዕከል አንድ ልዩ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ አካል የራሱ የአለምአቀፍ ልጆች ፕሬስ ማዕከል ነው። መጀመሪያ በ2014 ላይ በተካሄደው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ላይ ነበር የተደራጀው። በፕሬስ ማዕከሉ ውስጥ ያሉ ወጣት ጋዜጠኛዎች የፕሮግራሙን ክስተቶች በየአገሮቻቸው ይሸፍናሉ፦ ለብሔራዊ እና ለአለምአቀፍ የስፖርት ሚዲያ ዜና ያዘጋጃሉ፤ ለእግር ኳስ ለወዳጅነት ቴሌቪዥን ጣቢያ፣ ለአለምአቀፍ የልጆች እግር ኳስ ለወዳጅነት ጋዜጣ እና ለፕሮግራሙ ኦፊሴላዊ የሬዲዮ ጣቢያ ይዘት መፍጠር ላይ ይሳተፋሉ። የአለምአቀፍ ልጆች ፕሬስ ማዕከል የምርጥ ወጣት ጋዜጠኛ ብሔራዊ ውድድሮች አሸናፊዎችን፣ ወጣት ጦማሪያንን፣ ፎቶ አንሺዎችን እና ጸሐፊያንን ያገናኛል። ከፕሬስ ማዕከሉ የመጡ ወጣት ጋዜጠኛዎች ከፕሮግራሙ ውስጥ ሆነው እይታቸውን ያቀርባሉ፣ «ልጆች ስለልጆች» የሚለውን አሰራር በመተግበር። የእግር ኳስ እና የወዳጅነት አለምአቀፍ ቀን በእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ ስር የእግር ኳስ እና ወዳጅነት አለምአቀፍ ቀን ኤፕሪል 25 ላይ ይከበራል። ይህ በዓል 2014 ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በ16 አገሮች ውስጥ ተከብሯል። በዚህ ቀን ላይ የወዳጅነት ግጥሚያዎች፣ ድንገተኛ ሕዝባዊ ትርዒቶች፣ ክፍት የስልጠና ክፍለ-ጊዜዎች፣ ወዘተ ተካሂደዋል። ከ50,000 በላይ ሰዎች በክብረ-በዓሉ ላይ ተካፍለውበታል። 2015 ላይ የእግር ኳስ እና ወዳጅነት ቀን በ24 አገሮች ውስጥ ተከብሯል። በፌስቲቫሉ ጊዜ የወዳጅነት ግጥሚያዎች እና ሌሎች ክስተቶች ነበሩ። ጀርመን ውስጥ የሻልክ 04 እግር ኳስ ተጫዋቾች ክፍት የስልጠና ክፍለ-ጊዜ አዘጋጅተው ነበር፣ ሰርቢያ የቴሌቪዥን ትርዒት አስተናግዳለች፣ ዩክሬን በታዳጊ የቮሊን ኤፍሲ ቡድን እና በሉትስክ ከተማ የቤተሰቦች፣ ልጆች እና ወጣቶች ማዕከል የተመዘገቡ ልጆች መካከል ግጥሚያ ነበር። ሩሲያ ውስጥ የእግር ኳስ እና ወዳጅነት ቀን ኤፕሪል 25 ላይ በ11 ከተማዎች ላይ ተከብሯል። የፕሮግራሙን ቁልፍ እሴቶችን ለማስታወስ የወዳጅነት ግጥሚያዎች በቭላዲቮስቶክ፣ ኖቮሲቢርስክ፣ የካተሪንበርግ፣ ክራስኖያርስክ፣ ባርናውል፣ ሴንት ፒተርስበርግ እና ሳራንስክ ላይ ተካሂደው ነበር። በክራስኖያርስክ፣ ሶቺ እና ሮስቶቭ-ኦን-ዶን ውስጥ የወዳጅነት ቅብብል በኦሊምፒክ 2014 ችቦ ያዥዎች ተሳትፎ ተካሂዷል። በሞስኮ ውስጥ የእኩል ዕድል ውድድር በማየት የተሳናቸው ስፖርት ፌዴሬሽን ድጋፍ ተደራጅቷል። ሜይ 5 ላይ የእግር ኳስ እና የወዳጅነት ቀን በኒዝኒ ኖቭጎሮድ እና ካዛን ውስጥ ተከብሯል። 2015 ላይ የእግር ኳስ እና ወዳጅነት ቀን በ32 አገሮች ውስጥ ተከብሯል። ሩሲያ ውስጥ በዘጠኝ ከተማዎች ውስጥ ተከብሯል፦ ሞስኮ፣ ሴንት ፒተርስበርግ፣ ኖቮሲቢርክስ፣ ባርናውል፣ ቢሮቢድዛን፣ ኢርኩትስክ፣ ክራስኖዳር፣ ኖዝኒ ኖቭጎሮድ እና ሮስቶቭ-ኦን-ዶን። ኖዝኒ ኖቭጎሮድ ከቮልጋ ኤፍሲ ለመጡ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች የወዳጅነት ግጥሚያ አስተናግዳለች፣ እና የክለቡ አዋቂ ተጫዋቾች ለልጆቹ የማሟቂያ እና ስልጠና ስራዎችን አካሂዷል። በኖቮሲቢርስክ ውስጥ በተደረገ የወዳጅነት ግጥሚያ ላይ አካል ጉዳተኛ የሆኑ ልጆች ተሳትፈውበታል የኖቮሲቢርስክ ክልል ቡድን የርማክ-ሲቢር። 2017 ላይ የእግር ኳስ እና ወዳጅነት ቀን በ64 አገሮች ውስጥ ተከብሯል። የሰርቢያው ተከላካይ ብራኒስላቭ ኢቫኖቪች እና የኔዘርላንድስ አጥቂው ዲርክ ኩይት ጨምሮ ታዋቂ እግር ኳስ ተጫዋቾች በመላው ዓለም ውስጥ በነበሩ ክስተቶች ላይ ተሳትፈዋል። ግሪክ ውስጥ ከአገሩ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመሆን የአውሮፓ እግር ኳስ ሻምፒዮና 2004ን ያሸነፈው ቲዮዶራስ ዛጎራኪስ ክስተቱን ተከታትሏል። ሩሲያ ውስጥ ዜኒት ኤፍሲ የ2017 የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም ወጣት አምባሳደር ለሆነው ዛካር ባዲዩክ ልዩ የስልጠና ክፍለ-ጊዜ አዘጋጅቷል። ስልጠና ላይ የዜኒት ኤፍሲ በረኛው ዩሪ ሎዲጊን የዛካር ችሎታን ከፍተኛ ግምት የሰጠው ሲሆን የበረኛ ሚስጥሮችን አጋርቶታል። «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» ዘጠኝ እሴቶች ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በተካሄደው የጀመሪያው ዓለም አቀፍ የልጆች ጉባኤ ላይ ከዩናይትድ ኪንግደም ከጀርመን ከስሎቬንያ ከሃንጋሪ ከሰርቢያ ከቡልጋሪያ ከግሪክ እና ከሩስያ የተውጣጡ ወጣት አምባሳደሮች የመጀመሪያዎቹን ስምንት እሴቶች አቀነባበሩ። እነሱም ጓደኝነት፣ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ጤና፣ ሰላም፣ ታማኝነት፣ ድል እና መልካም ልማዶች ናቸው። እሴቶቹም በግልጽ ደብዳቤ ይፋ ሆነዋል። ደብዳቤውም ለዓለም አቀፍ «የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ)፣ ለአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እና ለዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መሪዎች ተልኳል። በመስከረም ወር 2013 ዓ. ም. ዮሴፍ ብላተር ከቭላድሚር ፑቲንና ቪታሊሙትኮ ጋር በተገናኘ ጊዜ ደብዳቤውን እንዳገኘና «የእግር ኳስ ለወዳጅነት»ን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። እ.ኤ.አ በ 2015 ዓ.ም. ቻይና፣ ጃፓንና ካዛክስታን ከ «የእግር ኳስ ለወዳጅነት» መርሀ ግብር ጋር በመተባበር ዘጠነኛ እሴት ለመጨመር ወሰኑ። እሱም «ክብር» ነበር። የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫ የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫ የአለምአቀፍ ልጆች ማህበራዊ ፕሮግራም የእግር ኳስ ለወዳጅነት ሽልማት ነው። በየዓመቱ ዋንጫው ለፕሮጀክቱ እሴቶቹ ከፍተኛ ጽናት ላሳየ ይሸለማል፦ ውዳጅነት፣ እኩልነት፣ ፍትሕ፣ ጤና፣ ሠላም፣ ታማኝነት፣ ድል፣ ባህሎች እና ክብር። በመላው ዓለም ያሉ አድናቂዎች አሸናፊውን መምረጥ ላይ ይሳተፋሉ፣ ነገር ግን የመጨረሻው ውሳኔ የሚሰጠው የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮጀክት ተሳታፊዎች ባካሄዱት ምርጫ ነው። የዘጠኝ እሴቶች ዋንጫው የያዙ የእግር ኳስ ክለቦች፦ ባርሴሎና (2015)፣ ባየርን ሙኒክ (2016)፣ አል ዋህዳ (ልዩ ሽልማት)፣ ሪያል ማድሪድ (2017)። የወዳጅነት አምባር ሁሉም የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም እንቅስቃሴዎች የእኩልነት እና ጤናማ አኗኗር ምልክት የሆኑ የወዳጅነት አምባሮች በመለዋወጥ የሚጀመር ነው። አምባሩ ሁለት ሰማያዊ እና አረንጓዴ ክሮችን የያዘ ሲሆን የፕሮግራሙን እሴቶች በሚጋራ ማንኛውም ሰው መደረግ ይችላል። እንደ መሠረት ከሆነ «የእንቅስቃሴው ምልክት ባለሁለት ቀለም አምባር ነው፣ ልክ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ ውስጣዊ እሴቶች ያህል ቀላል እና መረዳት የሚቻል ነው። የፕሮግራሙ ወጣት ተሳታፊዎች የወዳጅነት አምባሮችን በታዋቂ ስፖርተኛዎች እና ግለሰቦች አንጓ ላይ አስረዋል፣ ከእነሱ ውስጥ እነዚህ ይገኙበታል፦ ዲክ አድቮካት፣ አናቶሊ ቲሞሹክ እና ሉዊስ ኔቱ፣ ፍራንዝ ቤከንባወር ሉዊስ ፌርናንዴቭ፣ ዲዲየር ድሮግባ፣ ማክስ ሜየር፣ ፋትማ ሳሙራ፣ ሊዮን ጎረካ፣ ዶመኒኮ ክሪሺቶ፣ ሚሸል ሳልጋዶ፣ አለክሳንደር ከርዛኮቭ፣ ዲማስ ፒሮስ፣ ሚዮድራግ ቦዞቪች፣ አደሊና ሶትኒኮቫ፣ ዩሪ ካመነትስ። በክፍለ-ጊዜዎች መካከል የነበረው የተሳታፊዎች እንቅስቃሴ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች ከኦፊሴላዊ ክፍለ-ጊዜው ውጭ በተለያዩ ክስተቶች ላይ ይሳተፋሉ። ሜይ 2013 ላይ የማሪቦር ታዳጊ እግር ኳስ ክለብ (ስሎቬኒያ) ተጫዋቾች ከካምቦዲያ ልጆች ጋር የበጎ-አድራጎት ወዳጅነት ግጥሚያ አድርገው ነበር እ.ኤ.አ. ሴፕቴምበር 14፣ 2014 ዓ.ም. ላይ በሶቺ፣ ሩሲያ ውስጥ የሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ከፊፋ ፕሬዚዳንት ሴፕ ብላተር ጋር ስብሰባ ባደረጉበት ጊዜ የፕሮግራሙ ሩሲያዊያን ተሳታፊዎች ከቭላዲሚር ፑቲን ጋር ተነጋግረዋል። ጁን 2014 ላይ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ሆላንድ የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራሙ አባል የሆነውን የታቨርኒ ቡድን በፈረንሳይ እና ናይጄሪያ መካከል የተደረገውን የ2014 ፊፋ አለም ዋንጫ ግጥሚያ እንዲከታተሉ ወደ ኤሊሲ ቤተ-መንግስት ጋብዘዋል። ኤፕሪል 2016 ላይ የ2015 የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም አምባሳደር በፕሮጀክቱ ላይ ስለነበራቸው የተሳትፎ ልምድ ለመጋራት ከጠንካራው የቤላሩስ ሰው ከኪሪል ሺምኮ እና ከቤት ኤፍሲ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ተገናኝቶ ነበር። ዩሪ ቫሽቹክ ተምሳሌታዊው የወዳጅነት አምባር ለኪሪል ሺምኮ ሰጥቷል፣ በዚህም የፕሮጀክቱን ዓላማዎች የማስተዋወቅ ኃላፊነቱን አብሮ ሰጥቷል፦ ወዳጅነት፣ ፍትህ፣ ጤናማ አኗኗር። ሽልማቶችና እና ስጦታዎች የእግር ኳስ ለወዳጅነት ፕሮግራም የተለያዩ ውድድሮችን ያሸነፈ ሲሆን የተወሰኑ የሩሲያ እና አለምአቀፍ ሽልማቶችን የያዘ ነው። ከእነሱ ውስጥ እነዚህ ይገኙበታል፦ በ«የአለምአቀፍ ትብብር ግንባታ» ምድብ ውስጥ «ምርጥ የሩሲያ ማህበራዊ ፕሮጀክቶች»፣ በ«የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት» ምድብ ውስጥ የአለምአቀፍ የንግድ ተግባቢዎች ማህበር የወርቅ መቃ ብዕር ሽልማቶች (2016)፣ በ«ምርጥ የፕላኔቱ ማህበራዊ ፕሮጀክት» ምድብ ውስጥ የሳቤር ሽልማቶች (2016)፣ በ«ምርጥ የአለምአቀፍ ስትራቴጂ» ምድብ ውስጥ የድራም ማህበራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ሽልማቶች (2017)፣ በ«ምርጥ የሚዲያ ስትራቴጂ» ምድብ ውስጥ የፈጠራ ዲጂታል ገበያ መፍትሔዎች አለምአቀፋዊ ሽልማቶች (2017)፣ «በምርጥ የሩሲያ ማህበራዊ ፕሮጀክት» ምድብ ውስጥ «ብራማ ቀስተኛ» እና የግራንድ ፕሪክሽ «ብራማ ቀስተኛ» (2018)። እግር
2065
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%A3%E1%8A%93%20%E1%88%90%E1%8B%AD%E1%89%85
ጣና ሐይቅ
ጣና ሐይቅ (ቀደምት ባሕረ ጎጃም) በጎጃም ክፍለሃገር ውስጥ ሲገኝ ቅዱሱ ሐይቅም ይባላል።ጣና ሃይቅ በጥንታዊ ቋንቋ (ግእዝ) አገላለጽ ‹‹ጻና ሐይቅ›› ይባላል፡፡ድንግል ማርያም በገዳሙ የነበራትን ቆይታ አጠናቃ ስትመለስ “ፀአና በደመና” በደመና ጫናት የተባለው በጊዜ ብዛት ለአሁኑ የሐይቁ መጠሪያ ስም “ጣና” መሠረት ሆኖታል ነው የሚባለው።በክርስቶስ ልደት ገደማ ስለግብጽ ብዙ ምርምር ያደረገው ስትራቦ ዓባይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኝ ትልቅ ሐይቅ እንደሚነሳ ያውቅ ነበር ይባላል፡፡ የሐይቁን ስምም ስትራቦ “ሴቦ” ብሎታል፡፡ የሁለተኛው ዘመን የግብጽ መልክዓ ምድር ተመራማሪ ገላውዲዮስ ፕቶሎሚ ደግሞ “ኮሎ” ይለዋል፡፡ የአቴናው ድራማ ጸሐፊ አስክለስ “መዳብ የተቀባው ሐይቅ የኢትዮጵያ ጌጥ” ብሎታል፡፡ ባለቅኔው ሆሜርም “ከሌሎች የተለየና ጥርት ያለ የውኃ ባለቤት ነው” ብሎ ጠርቶታል፡፡ ከኢትዮጵያ አንደኛ እና ትልቁ ሐይቅ ነው። 84 ከ.ሜ. ረጅም እና 66 ኪ.ሜ. ሰፊ ነው። ባጠቃላይ 3,500 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል። ጣና በአጠቃላይ በውስጡ ከ37 በላይ ደሴቶች ሲኖሩት 27 ገዳማትን አቅፎ ይዟል።ገዳማቶች በ14ኛ ምእት ዓመት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ባመነኮሷቸው ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› ተብለው በሚጠሩት ቅዱሳን አባቶች የተመሠረቱ ናቸው።ከገዳማቶች መካከል፦ •••ደብረ ማርያም •••ክብራን ገብርኤል •••ዑራ ኪዳነምህረት •••መሀል ዘጌ ጊዮርጊስ •••አቡነ በትረ ማርያም •••አዝዋ ማርያም •••ዳጋ ኢስጢፋኖስ •••ይጋንዳ ተለሃይማኖት •••ናርጋ ስላሴ •••ደብረ ሲና ማርያም •••ማንድባ መድኃኒዓለም •••ጣና ቂርቆስ •••ክርስቶስ ሳምራ ገዳም •••ራማ መድሕኒ ዓለም •••ኮታ ማርያም…እና ሌሎችም ገዳማቶች ይገኙበታል። ሰባቱ ከዋክብት የሚባሉት አኩስም አቅራቢያ የሚገኘው የደብረ በንኮል ገዳም መሥራች አቡነ መድኅነ እግዚእ ደቀ መዛሙርት ናቸው።እነርሱም፦ 1.አቡነ ታዴዎስ~ደብረ ማርያም መሥራች 2.አቡነ ዘዮሐንስ~የክብራን እና የእንጦስ ገዳም መሥራች 3. አቡነ በትረማርያም~የዘጌ ጊዮርጊስ መሥራች 4. አቡነ ኂሩተ አምላክ~የዳጋ እስጢፋኖስ መሥራች 5.አቡነ ኢሳይ~የመንዳባ መድኃኔዓለም መሥራች 6.አቡነ ዘካርያስ~ደብረ ገሊላ መሥራች 7.አቡነ ፍቁረዮሐንስ~ጣና ቂርቆስ መሥራች ናቸው። ታሪካዊ የጣና ክፍሎች ጣና ቂርቆስ ጣና ቂርቆስ በጣና ሀይቅ ውስጥከሚገኙት ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት አንዱና ቀዳማዊዉ ሢሆን የተመሠረተው ከክርስቶሥ ልደት በፊት 982 ሲሆን የንጉስ ሰለሞን ልጅ ቀዳማዊ ምኒልክ ከእሥራየል ታቦተ ጽዮንን አጅበው በታቦተ ጽዮን መሪነት በፈቃደ እግዚአብሔር የመኳንንት ልጆችና ታቦተ ጽዮንን የሚያገለግሉ ካህናት እዲሁም ከሌዋዉያን በጠቅላላ ብዙ ሽህ ህዝብ አሥከትሎ ወደ ደሤቱ በመምጣት ይህንን ታላቅ ገዳም መሠረተው፡፡ የቦታውንም ስም ሳፍ ጽዮን መካነ ሣህል በማለት ሠይመውታል፡፡ እስራኤላውያን ካህናት ታቦተ ጽዮንን ከዚህ ገዳም ሲያሥቀምጡ አብሮ የመጣውን ህዝብ ከባህር ውጭ ባለው ሥፍራ ሥላሠፈሩት እስከ ዛሬ ድረስ አከባቢው ነገደ እስራኤል በመባል ይታወቃል፡፡ ከመጡት እስራኤላውያን ካህናት መካከል የሊቀ ካህኑ የሣዶቅ ልጅ አዛርያሥ ይገኝበታል፡፡ ካህኑ አዛርያስ አምልኮተ እግዚአብሔርንና መሠዋተ ኦሪትን ካስፋፋ በሇላ ከዚህ አለም በሞት ሲለይ በጣና ቂርቆስ ደሴት ነበር መካነ መቃብሩ ያረፈው፡፡ መካነ መቃብሩ የቃል ኪዳኑ ታቦት ድንኳን ካረፈበት ምስራቅ አቅጣጫ በሁለት የድንጋይ ቋጥኞች መካከል ይገኛል፡፡ የጣና ቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያን ከገዳሙ ከፋተኛ ቦታ ላይ የተሰራ ሁኖ የቃል ኪዳኑ ታቦት (ጽላተ ሙሴ) ካረፈችበት ቦታ ምዕራብ አቅጣጫ በቅርብ እርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የቤተ-ክርስቲያኑ ቅርጽ አራት ማዕዘን የሆነበት ምክኒያት የቃል ኪዳኑ ታቦት ድንኳን አምሳያ እንደሆነ መነኮሣት ይገልፃሉ፡፡ ህገ ኦሪትናአዲስ ኪዳን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰበከበትና የጽላተ ሙሴ ማደሪያ የሆነው ሣፋ ጽዮን ደብረ ሣህል ወይም የዛሬው ጣና ቂርቆስ አንድነት ገዳም እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስደት ዘመኗ አረጋዊ ዮሴፋንና ቅድስት ሶሎሜን አስከትላ በመላኩ ዑራኤል መሪነት ከዚህ ታላቅ ገዳም 3ወር ከ10 ቀን ከልጇ ጋር ተቀምጣበታለች፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ታላቅ ገዳም ሳለች ይመራ የነበረዉ መላዕክ ለዮሴፍ በህልሙ "ሄሮድሥ ስለሞተ ህፃኑንና እናቱን ይዘህ ተመለስ" በማለት ሲነግረው ዮሴፍም ወደ ህፃኑ በመቅረብ /ፀአና በደመና/ በደመና ጫናት በማለቱ የገዳሙና የሀይቁ መጠሪያ ስም ጣና በመባል እደቀረ ይነገራል፡፡ የኢትዮጵያ ብርሀን ተብለው የሚጠሩት አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሀንከነገሥታቱ ጋር ወደ ዚህ ቦታ በመምጣት የመጀመሪያውን የክርስትና እምነት ግዝረትን ሽረው ጥምቀትን፡ መሠዋዕተ ኦሪትን ሽረዉ አማናዊዉንየክርስቶስ ስጋና ደም በመሠዋት የክርስትና እምነትን አፅንተውበታል፡፡ አቡነ ሰላማ ጥምቀትን ብቻ ሳይሆንአምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈፀምበትንታቦተ ህግ በቦታው አራት ጽላት በመቅረፅ በዛን ጊዜ እምነቱ ይስፍፍባቸው ወደ ነበሩት ሀገራት በትግራይ አክሱም ፅዮን፡ በጎጃም መርጦ ለማርያም እና ጣና ቂርቆስ፡ በወሎ ተድባበማርያምን በማስተከል ሁሉንም ታቦታት ታቦተ ፅዮን በማለት እንደሰየሙአቸው በቦታው ያለው ታሪክ ያትታል፡፡ አቡነ አረጋዊና አፄ ገብረ መስቀል ወደዚህ ታላቅ ገዳም በመምጣት በረከትን አግኝተዎል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በገዳሙ ለአምስት አመታት በመቀመጥ ምልክት የሌለውን ድጓ ጽፎ ለገዳሙ አበርክቷል፡፡ ብዙ ቅዱሳን አባቶቻችንና ቅዱሳት አንስት እናቶቻችን በምነና እና በጸሎት ፀጋ እግዚአብሔር አግኝተውበታል፡ የተለያዩ ነገስታት አፄ የተባሉባቸውን ዘውዶች፡ አክሊሎች፡ የማዕረግ ልብሶች ጌጣጌጦች እዲሁም ሌሎች የከበሩ ዕቃወች እስከ ዛሬ ተጠብቀው የሚኖሩበት የሀይማኖት ማዕከልና የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ማህደርና መሠረት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሐይቆች
2628
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%85%E1%8A%95%E1%8B%B5
ህንድ
ህንድ፣ በይፋ የህንድ ሪፐብሊክ (ሂንዲ፡ ብሃራት ጋናራጃ)፣ በደቡብ እስያ የሚገኝ አገር ነው። በአካባቢው በሰባተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ፣ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛዋ አገር፣ እና በዓለም ላይ በሕዝብ ብዛቷ ዲሞክራሲ ናት። በደቡብ በህንድ ውቅያኖስ፣ በደቡብ ምዕራብ የአረብ ባህር፣ በደቡብ ምስራቅ የቤንጋል የባህር ወሽመጥ የተከበበ ሲሆን በምዕራብ ከፓኪስታን ጋር የመሬት ድንበሮችን ይጋራል። ቻይና, ኔፓል እና ቡታን በሰሜን; እና ባንግላዴሽ እና ምያንማር በምስራቅ። በህንድ ውቅያኖስ ውስጥ ህንድ በስሪ ላንካ እና በማልዲቭስ አካባቢ ነው; የአንዳማን እና የኒኮባር ደሴቶች ከታይላንድ፣ ከማያንማር እና ከኢንዶኔዢያ ጋር የባህር ድንበር ይጋራሉ። የዘመናችን ሰዎች ከ55,000 ዓመታት በፊት ከአፍሪካ ወደ ህንድ ክፍለ አህጉር ደርሰዋል። የረዥም ጊዜ ሥራቸው፣ መጀመሪያ ላይ እንደ አዳኝ ሰብሳቢነት በተለያየ መልኩ፣ አካባቢውን በጣም የተለያየ አድርጎታል፣ በሰዎች የዘረመል ልዩነት ከአፍሪካ በመቀጠል። ከ9,000 ዓመታት በፊት በኢንዱስ ወንዝ ተፋሰስ ምዕራባዊ ዳርቻ ላይ የሰፈረ ሕይወት በክፍለ አህጉሩ ታየ፣ ቀስ በቀስ ወደ ኢንደስ ሸለቆ ሥልጣኔ በሦስተኛው ሺህ ዓመት ዓክልበ. በ1200 ዓ.ዓ.፣ ጥንታዊ የሳንስክሪት ዓይነት፣ ኢንዶ-አውሮፓዊ ቋንቋ፣ ከሰሜን ምዕራብ ወደ ህንድ ተሰራጭቶ፣ የሪግቬዳ ቋንቋ ሆኖ ተከፈተ፣ እና በህንድ ውስጥ የሂንዱይዝም ጎህ መጀመሩን መዝግቧል። የህንድ ድራቪዲያን ቋንቋዎች በሰሜናዊ እና ምዕራባዊ ክልሎች ተተክተዋል። እ.ኤ.አ. በ 400 ዓክልበ, በዘር መከፋፈል እና ማግለል በሂንዱይዝም ውስጥ ብቅ አለ, እና ቡዲዝም እና ጄኒዝም ከዘር ውርስ ጋር ያልተገናኙ ማህበራዊ ትዕዛዞችን አውጀዋል. ቀደምት የፖለቲካ ማጠናከሪያዎች በጋንጀስ ተፋሰስ ላይ የተመሰረቱትን የሞርያ እና የጉፕታ ኢምፓየር ሹራብ ፈጠሩ። የጋራ ዘመናቸው ሰፊ በሆነ የፈጠራ ችሎታ የታሸገ ነበር ነገር ግን የሴቶች ደረጃ እያሽቆለቆለ በመሄድ እና ያለመነካካትን ወደ የተደራጀ የእምነት ስርዓት መቀላቀልም ጭምር ነው። በደቡብ ህንድ የመካከለኛው መንግስታት የድራቪዲያን ቋንቋ ጽሑፎችን እና ሃይማኖታዊ ባህሎችን ወደ ደቡብ ምስራቅ እስያ መንግስታት ላከ። በመካከለኛው ዘመን መጀመሪያ ላይ ክርስትና፣ እስልምና፣ ይሁዲነት እና ዞራስትሪኒዝም በህንድ ደቡባዊ እና ምዕራባዊ የባህር ዳርቻዎች ላይ ስር ሰደዱ። ከመካከለኛው እስያ የመጡ የሙስሊም ወታደሮች የሕንድ ሰሜናዊ ሜዳዎችን አልፎ አልፎ ወረሩ፣ በመጨረሻም የዴሊ ሱልጣኔትን መስርተዋል፣ እና ሰሜናዊ ህንድን ወደ መካከለኛው ዘመን እስላም አጽናፈ ሰማይ አውጥተዋል። በ 15 ኛው ክፍለ ዘመን የቪጃያናራ ኢምፓየር በደቡብ ሕንድ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የተዋሃደ የሂንዱ ባህል ፈጠረ. በፑንጃብ፣ ተቋማዊ ሃይማኖትን በመቃወም ሲኪዝም ብቅ አለ። በ1526 የሙጋል ኢምፓየር ለሁለት መቶ ዓመታት አንጻራዊ ሰላም አስገኝቷል፤ ይህም የብርሃን አርክቴክቸር ትቶ ነበር። ቀስ በቀስ እየሰፋ የመጣው የብሪቲሽ ኢስት ህንድ ኩባንያ አገዛዝ ተከትሎ፣ ህንድን ወደ ቅኝ ገዥ ኢኮኖሚ ለወጠው፣ ነገር ግን ሉዓላዊነቷን አጠናክራለች። የብሪቲሽ ዘውድ አገዛዝ በ 1858 ተጀመረ. ለህንዶች ቃል የተገባላቸው መብቶች ቀስ በቀስ ተሰጥተዋል, ነገር ግን የቴክኖሎጂ ለውጦች መጡ, እና የትምህርት, የዘመናዊነት እና የህዝብ ህይወት ሀሳቦች ስር ሰደዱ. ፈር ቀዳጅ እና ተደማጭነት ያለው የብሄረተኛ ንቅናቄ ተፈጠረ፣ እሱም በሰላማዊ ተቃውሞ የሚታወቅ እና የብሪታንያ ቅኝ ግዛት ለማቆም ዋና ምክንያት ሆነ። እ.ኤ.አ. በ1947 የብሪቲሽ ህንድ ኢምፓየር በከፍተኛ የህይወት መጥፋት እና ታይቶ በማይታወቅ ፍልሰት ውስጥ በሁለት ገለልተኛ ግዛቶች ተከፈለ። ህንድ ከ1950 ጀምሮ በዲሞክራሲያዊ ፓርላሜንታሪ ስርዓት የምትመራ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ነች። የብዝሃነት፣ የቋንቋ እና የብዙ ብሄር ማህበረሰብ ነው። የህንድ ህዝብ በ1951 ከነበረበት 361 ሚሊየን በ2011 ወደ 1.211 ቢሊዮን አድጓል።በዚሁ ጊዜ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ ከ64 የአሜሪካ ዶላር በዓመት ወደ 1,498 የአሜሪካ ዶላር ከፍ ብሏል፣ እና ማንበብና መጻፍ ከ16.6% ወደ 74% አድጓል። እ.ኤ.አ. በ 1951 በአንፃራዊ ሁኔታ ድሃ ሀገር ከመሆኗ አንፃር ህንድ ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ያለች ትልቅ ኢኮኖሚ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ማዕከል ሆናለች፣ መካከለኛ መደብ እየሰፋ ነው። በርካታ የታቀዱ ወይም የተጠናቀቁ ከመሬት በላይ ተልእኮዎችን የሚያካትት የጠፈር ፕሮግራም አለው። የህንድ ፊልሞች፣ ሙዚቃዎች እና መንፈሳዊ ትምህርቶች በአለምአቀፍ ባህል ውስጥ ሚናቸው እየጨመረ ነው። ህንድ የድህነት መጠኑን በእጅጉ ቀንሳለች፣ ምንም እንኳን ኢኮኖሚያዊ እኩልነትን ከፍ ለማድረግ ብትሞክርም። ህንድ በወታደራዊ ወጪ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሀገር ነች። ከ 20 ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ በካሽሚር ከጎረቤቶቿ ፓኪስታን እና ቻይና ጋር አለመግባባት አለባት። ህንድ ካጋጠሟት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች መካከል የፆታ እኩልነት ፣የህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና የአየር ብክለት ደረጃ መጨመር ይገኙበታል። የህንድ መሬት ሜጋ ዳይቨርስ ነው፣ አራት የብዝሃ ሕይወት ቦታዎች አሉት። የደን ሽፋን ከአካባቢው 21.7% ይይዛል። በህንድ ባህል በተለምዶ በመቻቻል ይታይ የነበረው የህንድ የዱር አራዊት በእነዚህ ደኖች እና በሌሎችም ስፍራዎች በተጠበቁ መኖሪያዎች ውስጥ ይደገፋል። ሥርወ ቃል እንደ ኦክስፎርድ ኢንግሊሽ መዝገበ ቃላት (እ.ኤ.አ. እ.ኤ.አ. በሦስተኛው እትም) “ህንድ” የሚለው ስም የመጣው ከጥንታዊው የላቲን ህንድ የደቡብ እስያ ማጣቀሻ እና በምስራቅ በኩል እርግጠኛ ያልሆነ ክልል ነው እና በምላሹ ከ: ሄለናዊ ግሪክ ሕንድ የጥንት ግሪክ ኢንዶስ የድሮው የፋርስ ሂንዱሽ፣ የአካሜኒድ ግዛት ምስራቃዊ ግዛት; እና በመጨረሻም የተዋሃደው፣ ሳንስክሪት ሲንዱ፣ ወይም “ወንዝ”፣ በተለይም የኢንዱስ ወንዝ እና፣ በተዘዋዋሪም፣ በደንብ የሰፈረው ደቡባዊ ተፋሰስ። የጥንት ግሪኮች ሕንዶችን ኢንዶይ ብለው ይጠሯቸው ነበር፣ እሱም “የኢንዱስ ሰዎች” ተብሎ ይተረጎማል። ብሃራት የሚለው ቃል በህንድ ግጥሞች እና በህንድ ህገ መንግስት ውስጥ የተጠቀሰው ባሃራት (ብሃራት ይጠራ በብዙ የህንድ ቋንቋዎች በተለዋዋጭነቱ ጥቅም ላይ ይውላል። ባራታቫርሻ የሚለው የታሪካዊ ስም ዘመናዊ አተረጓጎም እሱም በመጀመሪያ በሰሜን ህንድ ባራት ተሰራ። ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የህንድ የአፍ መፍቻ ስም ሆኖ ጨምሯል። ሂንዱስታን ህንድ የመካከለኛው ፋርስ ስም ነው፣ በሙጋል ኢምፓየር ጊዜ አስተዋወቀ እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሰፊው ጥቅም ላይ ውሏል። ትርጉሙ የተለያየ ነው፣ የዛሬውን ሰሜናዊ ህንድ እና ፓኪስታንን ወይም በአጠቃላይ ህንድን የሚያጠቃልለውን ክልል ያመለክታል። ታሪክ ጥንታዊ ሕንድ ከ6500 ዓ.ዓ በኋላ የምግብ ሰብሎችንና እንስሳትን ለማዳረስ፣ ቋሚ የግንባታ ግንባታ እና የግብርና ተረፈ ምርቶችን ለማከማቸት ማስረጃዎች በሜርጋርህ እና ሌሎች ቦታዎች በአሁኑ ባሎቺስታን፣ ፓኪስታን ውስጥ ታዩ። እነዚህም በ2500-1900 ዓክልበ. በአሁን ፓኪስታን እና ምእራብ ህንድ ውስጥ የበለፀገው በደቡብ እስያ የመጀመሪያው የከተማ ባህል ወደ ኢንደስ ሸለቆ ስልጣኔ አደጉ። እንደ ሞሄንጆ-ዳሮ፣ ሃራፓ፣ ዶላቪራ እና ካሊባንጋን በመሳሰሉ ከተሞች ዙሪያ ያተኮረው እና በተለያዩ የኑሮ ዘይቤዎች ላይ የተመሰረተው ስልጣኔ በእደ ጥበብ ውጤቶች እና ሰፊ ንግድ ላይ ተሰማርቷል። ከ2000-500 ከዘአበ ባለው ጊዜ ውስጥ ብዙ የክፍለ አህጉሩ ክልሎች ከቻልኮሊቲክ ባህሎች ወደ ብረት ዘመን ተሸጋገሩ። ቬዳስ፣ ከሂንዱይዝም ጋር የተያያዙ ጥንታዊ ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉት በዚህ ወቅት ነው፣ እናም የታሪክ ተመራማሪዎች የቬዲክ ባህልን ለማመልከት እነዚህን ተንትነዋል። በፑንጃብ ክልል እና በላይኛው የጋንግቲክ ሜዳ። አብዛኞቹ የታሪክ ተመራማሪዎችም ይህ ወቅት ከሰሜን-ምዕራብ ወደ ክፍለ አህጉር በርካታ የኢንዶ-አሪያን ፍልሰት ማዕበሎችን ያቀፈ እንደሆነ አድርገው ይቆጥሩታል። የካህናት፣ የጦረኞች እና የነጻ ገበሬዎች ተዋረድ የፈጠረው፣ ነገር ግን ተወላጆችን ሥራቸውን ርኩስ አድርጎ በመፈረጅ ያገለላቸው የዘውድ ሥርዓት የተነሳው በዚህ ወቅት ነው። በዲካን ፕላቶ ላይ፣ ከዚህ ጊዜ የተገኙ የአርኪኦሎጂ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፖለቲካ ድርጅት ዋና ደረጃ መኖሩን ያሳያል። በደቡብ ህንድ፣ ወደ ተቀናቃኝ ህይወት መሸጋገሩን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በተፈጠሩት በርካታ የሜጋሊቲክ ሀውልቶች፣ እንዲሁም በአቅራቢያው ባሉ የግብርና፣ የመስኖ ታንኮች እና የዕደ-ጥበብ ወጎች። በቬዲክ መገባደጃ ላይ፣ በ6ኛው ክፍለ ዘመን ከዘአበ አካባቢ፣ የጋንግስ ሜዳ ትንንሽ ግዛቶች እና አለቆች እና የሰሜን-ምዕራብ ክልሎች ወደ 16 ዋና ዋና ኦሊጋርቺስ እና ንጉሳዊ መንግስታት ማሃጃናፓዳዎች ተብለው ይጠሩ ነበር። የከተሞች መስፋፋት የቬዲክ ያልሆኑ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፣ ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱ ራሳቸውን የቻሉ ሃይማኖቶች ሆነዋል። ጄኒዝም ታዋቂነት ያገኘው በአርአያነቱ መሃቪራ በነበረበት ወቅት ነው። በጋውታማ ቡድሃ አስተምህሮ ላይ የተመሰረተ ቡድሂዝም ከመካከለኛው መደብ በስተቀር ከሁሉም ማህበራዊ ክፍሎች የመጡ ተከታዮችን ስቧል; በህንድ ውስጥ ለተመዘገቡት የታሪክ ጅማሬዎች የቡድሃን ሕይወት መዝግቦ መዝግቦ መዝግቦ ነበር። የከተማ ሀብት እየጨመረ በሄደበት ዘመን ሁለቱም ሃይማኖቶች ክህደትን እንደ አንድ ጥሩ ነገር አድርገው ነበር, እና ሁለቱም ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ገዳማዊ ወጎችን አቋቋሙ. በፖለቲካዊ መልኩ፣ በ 3 ኛው ክፍለ ዘመን ከዘአበ፣ የማጋዳ መንግሥት ሌሎች ግዛቶችን ጠቅልሎ ወይም ቀንሶ እንደ ሞሪያን ኢምፓየር ብቅ አለ። ግዛቱ በአንድ ወቅት ከሩቅ ደቡብ በስተቀር አብዛኛው ክፍለ-አህጉርን ይቆጣጠር ነበር ተብሎ ይታሰብ ነበር፣ ነገር ግን ዋናዎቹ ክልሎች አሁን በትላልቅ የራስ ገዝ አካባቢዎች ተለያይተዋል ተብሎ ይታሰባል። የሞሪያን ነገሥታት በግዛት ግንባታ እና በቆራጥነት በሕዝብ ሕይወት አስተዳደር ይታወቃሉ፣ አሾካ ወታደራዊነትን በመካድ እና የቡዲስት ደምማ የራቀ ጥብቅና መቆም። የታሚል ቋንቋ የሳንጋም ሥነ ጽሑፍ እንደሚያሳየው ከ200 ከዘአበ እስከ 200 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ደቡባዊው ባሕረ ገብ መሬት በቼራስ፣ ቾላስ እና ፓንዲያስ ሥር ይገዛ ነበር፣ ሥርወ መንግሥት ከሮማ ኢምፓየር እና ከምዕራብ እና ደቡብ-ምስራቅ እስያ ጋር ብዙ ይነግዱ ነበር። በሰሜን ሕንድ ሂንዱይዝም በቤተሰብ ውስጥ የአባቶች ቁጥጥርን በማረጋገጡ የሴቶችን የበታችነት መጨመር አስከትሏል. በ 4 ኛው እና በ 5 ኛው ክፍለ ዘመን የጉፕታ ኢምፓየር በትልቁ ጋንግስ ሜዳ ውስጥ ውስብስብ የአስተዳደር እና የግብር ስርዓት ፈጠረ; ይህ ስርዓት ለኋለኞቹ የህንድ መንግስታት ሞዴል ሆነ። በጉፕታስ ስር፣ የአምልኮ ሥርዓትን ከማስተዳደር ይልቅ በአምልኮ ላይ የተመሰረተ የታደሰ ሂንዱዝም እራሱን ማረጋገጥ ጀመረ። ይህ እድሳት በከተማ ልሂቃን መካከል ደጋፊዎችን ባገኘው የቅርጻቅርፃ እና የስነ-ህንፃ አበባ ላይ ተንጸባርቋል። ክላሲካል የሳንስክሪት ሥነ ጽሑፍም አብቧል፣ የሕንድ ሳይንስ፣ አስትሮኖሚ፣ ሕክምና እና ሒሳብ ከፍተኛ እድገቶችን አድርገዋል። የመካከለኛው ዘመን ህንድ የሕንድ የመካከለኛው ዘመን ዘመን፣ ከ600 እስከ 1200 ዓ.ም.፣ በክልል መንግሥታት እና በባህል ልዩነት ይገለጻል። ከ606 እስከ 647 እዘአ አብዛኛው የኢንዶ-ጋንግቲክ ሜዳ ያስተዳደረው የቃናውጅ ሀርሻ ወደ ደቡብ ለመስፋፋት ሲሞክር በዴካን ቻሉክያ ገዥ ተሸነፈ። ተተኪው ወደ ምስራቅ ለመስፋፋት ሲሞክር በቤንጋል ፓላ ንጉስ ተሸነፈ። ቻሉኪያስ ወደ ደቡብ ለመዘርጋት ሲሞክሩ ከሩቅ ደቡብ በፓላቫስ ተሸነፉ፣ እነሱም በተራው በፓንዲያስ እና ቾላስ ከደቡብ ሩቅ ሆነው ተቃወሙ። የትኛውም የዚህ ዘመን ገዥ ኢምፓየር መፍጠር እና ከዋና ክልላቸው በላይ ብዙ መሬቶችን በቋሚነት መቆጣጠር አልቻለም። በዚህ ወቅት፣ መሬታቸው ለግብርና ኢኮኖሚ ምቹ እንዲሆን የተነደፈ አርብቶ አደር ሕዝቦች፣ በነጠላ ማህበረሰብ ውስጥ፣ እንደ አዲስ ባህላዊ ያልሆኑ ገዥ መደቦች ይስተናገዳሉ። የዘውድ ሥርዓት በዚህ ምክንያት የክልል ልዩነቶችን ማሳየት ጀመረ። በ6ኛው እና በ7ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹ የአምልኮ መዝሙሮች በታሚል ቋንቋ ተፈጠሩ። በመላው ህንድ ውስጥ ተመስለዋል እናም ለሁለቱም የሂንዱዝም ትንሳኤ እና የክፍለ አህጉሩ ዘመናዊ ቋንቋዎች በሙሉ እንዲዳብሩ አድርጓቸዋል. የሕንድ ንጉሣውያን፣ ትልቅም ሆኑ ትናንሽ፣ እና እነርሱን ያስተዳድሩ የነበሩት ቤተመቅደሶች ዜጐች ብዙ ቁጥር ወደ ዋና ከተማዎቹ እንዲሳቡ አድርጓቸዋል፣ ይህም የኢኮኖሚ ማዕከልም ሆኑ። ህንድ ሌላ የከተማ መስፋፋት በጀመረችበት ወቅት የተለያየ መጠን ያላቸው የቤተመቅደስ ከተሞች በየቦታው መታየት ጀመሩ። በ8ኛው እና በ9ኛው ክፍለ ዘመን በደቡብ-ምስራቅ እስያ ደቡብ ህንድ ባህል እና የፖለቲካ ስርአቶች የዘመናዊቷ ምያንማር፣ ታይላንድ፣ ላኦስ፣ ካምቦዲያ፣ ቬትናም፣ ፊሊፒንስ፣ ማሌዥያ እና አካል ወደሆኑ አገሮች በመላኩ ውጤቱ ተሰምቷል። ጃቫ የሕንድ ነጋዴዎች, ምሁራን እና አንዳንድ ጊዜ ወታደሮች በዚህ ስርጭት ውስጥ ይሳተፋሉ; ደቡብ-ምስራቅ እስያውያንም ተነሳሽነቱን ወስደዋል፣ ብዙዎች በህንድ ሴሚናሪ ውስጥ በመገኘት የቡድሂስት እና የሂንዱ ጽሑፎችን ወደ ቋንቋቸው ሲተረጉሙ ነበር። ከ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ የሙስሊም መካከለኛው እስያ ዘላኖች ጎሳዎች ፈጣን ፈረስ ፈረሰኞችን በመጠቀም እና በጎሳ እና በሃይማኖት የተዋሃደ ሰፊ ሰራዊት በማፍራት የደቡብ እስያ ሰሜናዊ ምዕራብ ሜዳዎችን ደጋግመው በማሸነፍ በመጨረሻ እ.ኤ.አ. በ 1206 ኢስላሚክ ዴሊ ሱልጣኔት እንዲመሰረት አድርጓል ሱልጣኔት አብዛኛው የሰሜን ህንድ ክፍል ለመቆጣጠር እና ወደ ደቡብ ህንድ ብዙ ጉዞዎችን ለማድረግ ነበር። ምንም እንኳን በመጀመሪያ የህንድ ልሂቃን ረብሻ ቢፈጥርም ሱልጣኔቱ ሙስሊም ያልሆነውን ሰፊ ህዝብ ለራሱ ህጎች እና ልማዶች ትቷል። ሱልጣኔቱ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሞንጎሊያውያን ዘራፊዎችን ደጋግሞ በመቃወም ህንድን በምእራብ እና በመካከለኛው እስያ ከተጎበኘው ውድመት ታድጓል ፣ይህም ለዘመናት ሸሽተው የሚሸሹ ወታደሮች፣ ምሁራን፣ ምሑራን፣ ነጋዴዎች፣ አርቲስቶች እና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ከዚያ ክልል ወደሚገኙበት ቦታ ፈጥሯል። ንዑስ አህጉር, በዚህም በሰሜን ውስጥ የተመሳሰለ ኢንዶ-እስላማዊ ባህል መፍጠር. የሱልጣኔቱ ወረራ እና የደቡብ ህንድ ክልላዊ መንግስታት መዳከም ለቪጃያናጋራ ተወላጅ ኢምፓየር መንገድ ጠርጓል። ጠንካራ የሻይቪት ባህልን በመቀበል እና በሱልጣኔቱ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ላይ በመገንባት፣ ኢምፓየር ብዙ ልሳነ ምድርን ህንድ ለመቆጣጠር መጣ እና በደቡብ ህንድ ማህበረሰብ ላይ ለረጅም ጊዜ ተፅእኖ መፍጠር ነበረበት። የጥንት ዘመናዊ ህንድ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ሰሜናዊ ህንድ፣ ያኔ በዋነኛነት በሙስሊም ገዥዎች ስር፣ እንደገና በመካከለኛው እስያ ተዋጊ አዲስ ትውልድ የላቀ ተንቀሳቃሽነት እና የእሳት ኃይል ወደቀ። ያስከተለው የሙጋል ኢምፓየር እየገዛ የመጣውን የአካባቢ ማህበረሰቦችን አላጠፋም። ይልቁንም በአዳዲስ አስተዳደራዊ አሰራሮች እና የተለያዩ እና ሁሉንም ባሳተፈ የገዢ ልሂቃን አማካይነት ሚዛናዊና ሰላም እንዲሰፍን አድርጓል፤ ይህም ወደ ስልታዊ፣ የተማከለ እና ወጥ የሆነ አገዛዝ እንዲመራ አድርጓል። የጎሳ ትስስርን እና ኢስላማዊ ማንነትን በተለይም በአክባር ስር፣ ሙጋላዎች የራቁትን ግዛቶቻቸውን በፋርስ ባህል በመግለጽ በታማኝነት አንድ አደረጉ። የሙጋል ስቴት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከግብርና የሚገኘውን አብዛኛው ገቢ የሚያገኘው እና ታክስ በደንብ በተያዘው የብር ምንዛሪ እንዲከፈል በማዘዝ ገበሬዎች እና የእጅ ባለሞያዎች ወደ ትላልቅ ገበያዎች እንዲገቡ አድርጓል። በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በግዛቱ የነበረው አንጻራዊ ሰላም የህንድ ኢኮኖሚ መስፋፋት ምክንያት ሲሆን ይህም በሥዕል፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በጨርቃጨርቅ እና በሥነ ሕንፃ ግንባታ የላቀ ድጋፍ አስገኝቷል። በሰሜን እና በምእራብ ህንድ እንደ ማራታስ፣ራጅፑትስ እና ሲክ ያሉ አዲስ ወጥነት ያላቸው ማህበረሰባዊ ቡድኖች ወታደራዊ እና የአስተዳደር ምኞቶችን በሙጋል አገዛዝ ጊዜ አግኝተዋል፣ይህም በትብብር ወይም በችግር፣ እውቅና እና ወታደራዊ ልምድ ሰጥቷቸዋል። በሙጋል አገዛዝ ወቅት የንግድ ልውውጥ መስፋፋት በደቡብ እና በምስራቅ ህንድ የባህር ዳርቻዎች ላይ አዲስ የህንድ የንግድ እና የፖለቲካ ልሂቃን ፈጠረ። ግዛቱ ሲበታተን፣ ከእነዚህ ልሂቃን መካከል ብዙዎቹ የራሳቸውን ጉዳይ መፈለግ እና መቆጣጠር ችለዋል።በ 18 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በንግድ እና በፖለቲካዊ የበላይነት መካከል ያለው መስመሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደበዘዙ በመጡ የእንግሊዝ ምስራቅ ህንድ ኩባንያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ የንግድ ኩባንያዎች የባህር ዳርቻዎች ምሽጎችን አቋቁመዋል። የምስራቅ ህንድ ካምፓኒ የባህር ቁጥጥር፣ ከፍተኛ ሀብቶች እና የላቀ ወታደራዊ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ወታደራዊ ጥንካሬውን እንዲያረጋግጥ እና የህንድ ልሂቃን ክፍል እንዲስብ አድርጎታል። እነዚህ ምክንያቶች ኩባንያው በ 1765 የቤንጋልን ክልል እንዲቆጣጠር እና ሌሎች የአውሮፓ ኩባንያዎችን ወደ ጎን እንዲተው ለመፍቀድ ወሳኝ ነበሩ። የቤንጋልን ሀብት የበለጠ ማግኘት እና የሰራዊቱ ጥንካሬ እና መጠን መጨመር በ 1820 ዎቹ ህንድ አብዛኛው ክፍል እንድትቀላቀል ወይም እንድትገዛ አስችሎታል። ህንድ ያኔ የተመረተ ምርትን ለረጅም ጊዜ ወደ ውጭ መላክ ቀርቶ በምትኩ ለብሪቲሽ ኢምፓየር በጥሬ ዕቃ ታቀርብ ነበር። ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎች ይህንን የሕንድ የቅኝ ግዛት ዘመን መጀመሪያ አድርገው ይመለከቱታል። በዚህ ጊዜ፣ በእንግሊዝ ፓርላማ የኢኮኖሚ ኃይሉ በከፍተኛ ሁኔታ ተገድቦ እና በብቃት የብሪታንያ አስተዳደር ክንድ ሆኖ፣ ኩባንያው እንደ ትምህርት፣ ማህበራዊ ማሻሻያ እና ባህል ባሉ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ መድረኮች በንቃት መግባት ጀመረ። ዘመናዊ ህንድ የታሪክ ተመራማሪዎች የሕንድ ዘመናዊ ዘመን ከ1848 እስከ 1885 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደጀመረ አድርገው ይቆጥሩታል። በ1848 የሎርድ ዳልሁዚ የምስራቅ ህንድ ኩባንያ ገዥ ጄኔራል ሆኖ መሾሙ ለዘመናዊ መንግስት አስፈላጊ ለውጦችን ደረጃ አድርጓል። እነዚህም የሉዓላዊነትን ማጠናከር እና ማካለል፣ የህዝቡን ክትትል እና የዜጎችን ትምህርት ያካትታሉ። የቴክኖሎጂ ለውጦች-ከነሱ መካከል የባቡር መስመሮች፣ ቦዮች እና ቴሌግራፍ በአውሮፓ ከገቡ ብዙም ሳይቆይ አስተዋውቀዋል። ሆኖም ከኩባንያው ጋር ያለው አለመስማማት በዚህ ጊዜ ውስጥ ጨመረ እና በ 1857 የህንድ ዓመፅን አስነሳ በተለያዩ ቂሞች እና አመለካከቶች ወራሪ የብሪታንያ መሰል ማህበራዊ ማሻሻያዎችን ከባድ የመሬት ታክስን እና የአንዳንድ ሀብታም የመሬት ባለቤቶችን እና መኳንንቶች ማጠቃለያ በህንድ ሰሜናዊ እና መካከለኛው አካባቢ ብዙ ክልሎችን አናወጠ እና የኩባንያውን አገዛዝ መሰረት አናጋው። በ1858 ዓመፁ ቢታፈንም የምስራቅ ህንድ ካምፓኒ እንዲፈርስ እና የህንድ ቀጥተኛ አስተዳደር በእንግሊዝ መንግስት እንዲመራ አድርጓል። አሃዳዊ መንግስት እና ቀስ በቀስ ግን የተገደበ የብሪታኒያ አይነት የፓርላማ ስርዓት በማወጅ፣ አዲሶቹ ገዥዎች መኳንንትን እና መሬት ላይ ያሉ ሰዎችን ከወደፊቱ ብጥብጥ ለመከላከል እንደ ፊውዳል ጥበቃ አድርገው ነበር። በቀጣዮቹ አሥርተ ዓመታት ውስጥ፣ የሕዝብ ሕይወት ቀስ በቀስ በመላው ሕንድ ታየ፣ በመጨረሻም በ 1885 የሕንድ ብሔራዊ ኮንግረስ ምስረታ ላይ ደርሷል። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የቴክኖሎጂው ጥድፊያ እና የግብርና ንግድ ሥራ በኢኮኖሚ ውድቀቶች የተስተዋለ ሲሆን ብዙ ትናንሽ ገበሬዎች በሩቅ ገበያዎች ፍላጎት ላይ ጥገኛ ሆነዋል። መጠነ ሰፊ የሆነ ረሃብ ጨምሯል፣ እና ምንም እንኳን የህንድ ግብር ከፋዮች የሚሸከሙት የመሠረተ ልማት ዝርጋታ አደጋዎች ቢኖሩም፣ ለህንዶች አነስተኛ የኢንዱስትሪ ሥራ አልተፈጠረም። የጨዋማ ውጤቶችም ነበሩ፡ የንግድ ሰብል በተለይም አዲስ በተሸፈነው ፑንጃብ ውስጥ ለውስጣዊ ፍጆታ የሚሆን የምግብ ምርት እንዲጨምር አድርጓል። የባቡር ኔትዎርክ ወሳኝ የሆነ የረሃብ እፎይታ አቅርቧል፣በተለይም የሸቀጦችን ማጓጓዝ ወጪን በመቀነሱ እና ገና በህንድ የተያዙ ኢንዱስትሪዎችን ረድቷል።ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሕንዶች ያገለገሉበት ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አዲስ ጊዜ ተጀመረ። በብሪቲሽ ማሻሻያዎች ነገር ግን አፋኝ ህግ፣ በይበልጥ ጠንከር ባሉ የህንድ እራስን በራስ የማስተዳደር ጥሪዎች እና የትብብር-አልባ እንቅስቃሴ ጅምር ሲሆን ሞሃንዳስ ካራምቻንድ ጋንዲ መሪ እና ዘላቂ ምልክት ይሆናል። እ.ኤ.አ. በ 1930 ዎቹ ውስጥ ዘገምተኛ የሕግ ማሻሻያ በብሪቲሽ ተደነገገ በተካሄደው ምርጫ የህንድ ብሄራዊ ኮንግረስ ድሎችን አሸንፏል። የሚቀጥሉት አስርት አመታት በቀውሶች ተከባ ነበር፡ የህንድ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ተሳትፎ፣ የኮንግረሱ የመጨረሻ የትብብር አላማ እና የሙስሊም ብሄርተኝነት መነሳት። ሁሉም በ1947 የነፃነት መምጣት ተዘግተዋል፣ነገር ግን ህንድ ወደ ሁለት ግዛቶች በመከፈሏ ህንድ እና ፓኪስታን። ህንድ እንደ ነጻ ሀገር ለመምሰል አስፈላጊ የሆነው እ.ኤ.አ. በ1950 የተጠናቀቀው ሕገ መንግሥት ዓለማዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ያቋቋመ ሕገ መንግሥት ነበር። የዜጎች ነፃነት፣ የነቃ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ብዙ ነፃ ፕሬስ ያለው ዲሞክራሲያዊት ሆኖ ቆይቷል። እ.ኤ.አ. በ1990ዎቹ የጀመረው የኤኮኖሚ ሊበራላይዜሽን ትልቅ የከተማ መካከለኛ መደብ ፈጥሯል ህንድን በዓለም ፈጣን ኢኮኖሚ እያደጉ ካሉ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ አድርጓታል እና ጂኦፖለቲካዊ ዝናዋን አሳድጋለች። የህንድ ፊልሞች፣ ሙዚቃ እና መንፈሳዊ ትምህርቶች በአለምአቀፍ ባህል ውስጥ ሚናቸው እየጨመረ ነው። ገና፣ ህንድ በገጠርም በከተማም የማይበገር በሚመስል ድህነት ነው የተቀረፀችው። በሃይማኖታዊ እና ጎሳ-ተኮር ጥቃት; በማኦኢስት አነሳሽነት ናክሳላይት ዓመፅ; እና በጃሙ እና ካሽሚር እና በሰሜን ምስራቅ ህንድ ውስጥ በመለያየት። ከቻይና እና ከፓኪስታን ጋር ያልተፈታ የግዛት ውዝግብ አላት። የሕንድ ቀጣይነት ያለው የዲሞክራሲ ነፃነቶች ከዓለም አዲስ አገሮች መካከል ልዩ ናቸው; ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያስመዘገበው ኢኮኖሚያዊ ስኬት፣ የተቸገረ ሕዝቧን ከችግር ነፃ ማድረግ ገና ሊደረስበት ያልቻለ ግብ
10102
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%89%83%20%E1%8A%A0%E1%8B%AB%E1%88%8C%E1%8B%8D%20%E1%89%B3%E1%88%9D%E1%88%A9
አለቃ አያሌው ታምሩ
አለቃ አያሌው ታምሩ ከአባታቸው ከአቶ ታምሩ የተመኝና ከእናታቸው ከወይዘሮ አሞኘሽ አምባዬ፤ በጎጃም ክፍለ ሀገር በብቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ በታላቁ ደብር ወገዳም በደብረ ድማኅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዩ ስሙ ቤተ ንጉሥ በተባለ ቦታ መጋቢት ቀን ዓመተ ምሕረት በዕለተ ሆሣዕና ተወለዱ። ዕድሜአቸው ለትምህርት ሳይደርስ ገና የሦስት ዓመት ተኩል ሕፃን ሳሉ በፈንጣጣ ሕመም ምክንያት የዐይናቸውን ብርሃን አጥተዋል። የስምንት ዓመት ዕድሜ ልጅ ሳሉ በዓለ ተክለ አልፋን ለማክበር ከአባታቸው ጋር ወደ ዲማ እንደ ሄዱ በዚያው ትምህርታቸውን ለመቀጠል ቀሩ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በቅርብ ቤተ ዘመድ እየተረዱ ለአንድ ዓመት ያህል ሲማሩ ከቈዩ በኋላ አባታቸው ስላረፉ ኑሮአቸው በትምህርት ቤት ብቻ ስለ ተወሰነ ከቤተ ሰብእ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እየቀነሰ መጣ። ይህም ሁኔታ የሚፈልጉትን ትምህርት በአንድ ልብ ለመቀጠል ግድ ሆኖባቸዋል። በዚሁ መሠረት በ፲፭ ዓመት ዕድሜአቸው የቅኔ መምህር ለመሆን በቅተዋል። ስለ ዐይናቸው ብርሃንና ስለ ትምህርታቸው፤ «ምልጃ ዕርቅና ሰላም፤» በተባለው መጽሐፋቸው ገጽ ላይ እንዲህ ሲሉ ገለጸዋል። «ይህ ሁሉ የተገኘው ገና በልጅነት ዕድሜዬ፤ በቅዱስ ሐዋርያ ያዕቆብ እንደ ተነገረው የምመራበት፣ የምኖረበት በወሰድከው በዐይኔ ፈንታ ዕውቀት ስጠኝ ብዬ የለመንኩት አምላኬ፤ «ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ሹ ታገኛላችሁ፤ በር ምቱ ይከፈትላችኋል፤ ለሚወደኝ እኔ ራሴን እገልጥለታለሁ፤» ሲል በሰጠው ተስፋና በለገሰኝ የአእምሮ ምጽዋት መሆኑን ስለምረዳ ነው፤» ብለዋል። ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፥ ትምህርት፥ ሥርዐትና አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጠና እየተበላሸ መሄዱ በእጅጉ ያሳዝናቸው ስለ ነበር፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሊቃውንት ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ እንደ መሆናቸው መጠን፤ ጥፋቱ እንዲታረም ብዙ አቤቱታና ተማጽኖ ጉዳዩ ወደሚመለከተው ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ሲኖዶሱን በመሠረተና በሚመራው በመንፈስ ቅዱስ ስም ተማጽነው ቢያቀርቡም ሲኖዶሱ ጉዳዩን ለማፈን ከመሞከር በስተቀር ምንም እርምጃ ሳይወስድ ቀርቷል። እሳቸውም ያቀረቡት ጥያቄ መፍትሔ ባለማግኘቱ ጉዳዩን ለሚመለከተው ለኢተዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ለማሳወቅና፤ በቤተ ክርስቲያን ላይ ዐመፅ የሚፈጽሙትን ፓትርያርኩንና የእሳቸው ተባባሪ የሆኑ ጳጳሳትን ባላቸው ከፍተኛ ኀላፊነተና ሥልጣነ ክህነት በሥልጣነ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፥ በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ለማውገዝ ተገደዋል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ የዐመፀኛውን ፓትርያርክ ስም እንዳይጠሩ ውግዘት አስተላልፈዋል። ምእመናንም ከዐመፀኞች ካህናት ምንም ዐይነት አገልገሎት ማገኘት የማይችሉ መሆናቸውን ተገንዝበው ሕይወታቸውን በጥንቃቄ እንዲመሩ አሳስበዋል። በዚህም ምክንያት ከ፶ ዓመት በላይ ካገለገሉበት የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሐሰት ክስና የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ባልሰጡበት ሁኔታ ያለ ምንም ጡረታ ከሥራ ገበታቸው ላይ በግፍ እንዲነሡ በመደረጉ ከሚያዝያ ወር ዓመተ ምሕረት ጀምሮ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው በመኖሪያ ቤታቸው ተወስነው ኖረዋል። በነዚህ ዓመታትም በየዕለቱ ለጸሎት ባዘጋጇት አነስተኛ ክፍል በመገኘት ወደ ልዑል እግዚአብሔር በመጸለይና በማልቀስ ይተጉ ነበር። ምእመናንም በተኲላ እንዳይነጠቁ በተለያዩ ጋዜጦች ትምህርትና ማበረታቻ ሲሰጡ ኖረዋል። የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ የቀብር ሥነ ሥርዐት ነሐሴ ቀን ዓመተ ምሕረት ብዙ ዘመን ባገለገሉበት የአዲስ አበባው ደብረ አሚን ተክለ ኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሕዝብ በተገኘበት ተፈጽሟል። ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ በቤተ ክርስቲያን ሥርዐት መሠረት በሥርዐተ ተክሊል ከወይዘሮ ርብቃ ልሳነ ወርቅ ጋር ሚያዝያ ቀን ዓመተ ምሕረት ጋብቻ ፈጽመው ልጆችና የልጅ ልጆች ለማፍራት ታድለዋል። መንፈሳዊ አገልግሎትና አስተዳደር። ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ዛሬ የክቡር ዐፅማቸው ማረፊያ በሆነው ደብረ አሚን ተክለ ኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የቅኔ መምህርነት አገልግሎታቸውን በ፲፱፻፴፱ ዓመተ ምሕረት ጀመሩ። በመቀጠልም በዚሁ ደብር፤ መጀመሪያ የሊቀ ጠበብትነት ማዕረግ አግኝተው ያገለገሉ ሲሆን ኋላም የዚሁ ደብር አስተዳዳሪ በመሆን ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሊቃውንት ጉባኤ ተመርጠው ከሰኔ ወር ዓመተ ምሕረት ጀምሮ የስብከተ ወንጌል ክፍል አባል ሆነው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ አባልና ዋና ሰብሳቢ ሆነው ሠርተዋል። በዚህም የሥራ ዘመናቸው፤ የቤተ ክርስቲያን የወንጌል ትምህርት በመሆኑ ይህ አገልግሎት ሳይበረዝና ሳይከለስ እምነቱም፣ ትምህርቱም፣ ሥርዐቱም ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ የሚያስችለውን መንገድ ለመቀየስ በተሰጣቸው ኀላፊነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ተቀን ሠርተዋል። አልፎ አልፎም ከውስጥም ሆነ ከውጪ ለሚነሡት መናፍቃን መልስ በመስጠት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ በየጊዜው የሚታተሙትን መጻሕፍት በማረምና ለኅትመት እንዲበቁ በማድረግ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ስለ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት፤ በበዓላትም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች በራዲዮ፥ በቴሌቪዥን፥ በመጽሔቶችና በጋዜጦች ትምህርትና ምክር በማስተላለፍ ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል። ሐዲስ ኪዳንን በግእዝና በአማርኛ መጽሐፈ ግጻዌ፥ ሃይማኖተ አበው የተባሉትን መጻሕፍት ከሌሎች የጉባኤው አባላት ጋር ተርጉመው እንዲታተሙ አድርገዋል። በቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መንፈሳዊ ኰሌጅ ከ፲፱፻፶፬ እስከ ዓመተ ምሕረት፤ እንዲሁም በተግባረ እድ ትምህርት ቤትና በቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርት አስተምረዋል። ከኢትዮጵያ ዓይነ ሥውራን ማኅበር መሥራቾች አንዱ ሲሆኑ፤ መጀመሪያ የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ኋላም የቦርድ ሊቀ መንበር በመሆን አገልግለዋል። የአለቃ አያሌው መጻሕፍት በመጽሐፍ ጥራዝ አዘጋጅተውና አሳትመው ለትውልድ ያስተላለፏቸው መጻሕፍት ዘጠኝ ሲሆኑ በይዘታቸው በሁለት የተከፈሉ ናቸው። በአንደኛው ክፍል ያሉት የቤተ ክርስቲያንንና የኢተዮጵያን ማንነት ለኢትዮጵያውያን ለማስተማር የተዘጋጁ ሲሆኑ፤ በሁለተኛው ክፍል ያሉት ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥም ሆነ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ለተነሡና ለሚነሡ መናፍቃን መልስ በመስጠት የምእመናንን ልቦና ለማጽናት የሚያስችል መልእክት የሚያስተላልፉ ናቸው። ከነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ዐምስቱ በቤተ ክህነት አገልገሎት ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ፤ አራቱ ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በግፍ ከታገዱበት ከ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በኋላ የተዘጋጁ ናቸው። በቤተ ክህነት አገልገሎት ላይ በነበሩበት ጊዜ ያዘጋጇቸው፤ «መች ተለመደና ከተኲላ ዝምድና»፥ «የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት»፥ «የኑሮ መሠረት ለሕፃናት»፥ «ወላዲተ አምላክ በኢትዮጵያ»፥ «የጽድቅ በር» የተባሉት መጻሕፍት ሲሆኑ፣ ከሥራ ገበታ ከታገዱ በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ያዘጋጇቸው፤ «ምልጃ፥ ዕርቅና ሰላም»፥ «ተአምርና መጽሐፍ ቅዱስ»፥ «መልእክተ መንፈስ ቅዱስ»፥ «ዜና ሕይወት ዘቅድስተ ቅዱሳን እመ አምላክ» የተባሉት ናቸው። እባካችሁ "የኢትዮጵያ እምነት በሶስቱ ሕግጋት" የሚለውን መጽሐፍ ጫኑልን ማስታወሻ የኢትዮጵያ እምነት በሶስቱ ሕግጋት የኢትዮጵያ ሰዎች
50349
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5%20%E1%8B%90%E1%88%9B%E1%8A%91%E1%8A%A4%E1%88%8D
ቅዱስ ዐማኑኤል
ይህ ኢየሱስ በዕብራይስጥ: ሲጻፍ፣ ሲነበብ፡ የሹዓ፣ ትርጉሙም፡ የሚያድን ማለት ነው፤ የክርስትና ሃይማኖት መሰረት ነው። ክርስቶስ በግሪክ ቋንቋ ሲጻፍ ሲሆን ይህም መሢሕ ማለት ነው በተጨማሪም ዐማኑኤል ይባላል (ኢሳያስ ም.፯ ቁ.፲፬ በዕብራይስጥ ሲጻፍ ፤ በግሪክ ሲጻፍ ሲሆን፣ ትርጉሙም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ ማለት ነው። እየሱሰ በክርስትና ሃይማኖት አንድ አምላክ ከሚሆኑት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንዱ ወልድ እሱ ነው ይህም ወልድ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ እንደ ሰው በምድር ተመላልሶ የአባቱን መንግሥት አስተምሮ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመጨረሻም ከሞት ተነስቶ መንፈስ ቅዱስ እንዲተካው አድርጎ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ይህን ዓለም ለመፍረድ ዳግም ምፃቱ የሚጠበቅ አምላክ እና ፈጣሪ ነው ስለኢየሱስ የበለጠ ለመረዳት አዲስ ኪዳንን በተለይ ወንጌልን በአራቱ ሐዋርያት በቅዱስ ማርቆስ ፣ቅዱስ ሉቃስ ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ ማቴዎስ የተፃፈውን ያንብቡ እንዲሁም አንዳንድ ሃይማኖቶች ደግሞ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ነቢይ ነው ብለው ያምናሉ። ስምና ልደትበተጨማሪ «ኢየሱስ» የሚለው ስም በግሪክኛ «ኤሱስ» በቀዳማይ እብራይስጥ «ያህሹአ» በደሃራይ እብራይስጥ «ያሱአ» በአረማይክ «ዔሳዩ» በቀዳማይ አረብኛ «ዒሳ» በደሃራይ አረቢኛ «የሱዐ» ሲሆን ትርጉሙ ከእብራይስጥ «ያህዌ መድሃኒት ነው» ማለት መድኃኒያለም የሚል ፍቺ አለው፤ በተለይ ኢየሱስ ሰዎች ሲጠሩበት የነበረ የሰው ስም መሆኑን ለማሳየት ለሌሎች ሰዎች አገልግሎት ላይ ውሏል። የማርያም ልጅ ኢየሱስ ከሌሎች ኢየሱሶች ለመለየት ባደገበት አገር ስም በናዝሬት የናዝሬቱ ኢየሱስ ይባላል፦ ሉቃስ 18፥37። ከዚህም በቀር «ኢያሱ» (ወይም በግዕዝ «ኢየሱስ»፣ በግሪክ «ኢዬሶውስ»፣ በዕብራይስጥም «ያህሹዓ») የተባሉት ሌሎች ግለሠቦች ከብሉይ ኪዳን እና ከአዲስ ኪዳን ማየት ይቻላል፦ 1. የነዌ ልጅ ኢየሱስ በሙሴ ዘመን ይኖር የነበረ ፍጡር ሰው ነው። 2. የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢየሱስ በሐጌ ዘመን ይኖር የነበረ ፍጡር ሰው ነው። 3. ኢዮስጦስ ኢየሱስ የጳውሎስ ባልደረባ ነው (ቆላ.4:10-11)። እንደ ክርስትና እምነትና ወንጌሎች ኢየሱስ ከድንግል ማርያም እና ከመንፈስ ቅዱስ በቤተ ልሔም፣ ይሁዳ ተወለደ። ሳዱላዋ ማርያምና እጮኛዋ ዮሴፍ ለሕዝብ ቁጠራ በይሁዳ ስለ ተገኙ የቤት መጻተኞች ሆነው በጋጣ ተኝተው ነበር፤ ኢየሱስም በግርግም የተኛ እንጂ አልጋ አልነበረም። ገሊላ ግን በስሜን እስራኤል ወይም ሰማርያ ቤተሠቡ የተገኙበት ኢየሱስም የታደገበት ሀገር ነበረ። የኢየሱስ ጥቅሶችና ትምህርቶች ቤተክርስቲያን ቅዱስ ብላ የምትጠቀምባቸው መጻሕፍት ወንጌሎች በማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ እንደተጻፉት የኢየሱስን ትምህርትና ከሞላ ጐደል የሕይወት ታሪኩን ይገልጻሉ። በነዚህ ወንጌሎች መሠረት ኢየሱስ ሲያስተምር ብዙ ጥቅሶች ይገኛሉ። ለምሳሌ፦ «የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው፡ ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ። በእናንተስ እንዲህ አይደለም...» (ማቴ 20፡25) በዚሁ ጥቅስ ኢየሱስ ዓለሙን እንደ ገለበጠ ተብሏል። በዚያን ጊዜ ይሁዳ በባዕድ አረመኔ ሕዝብ ከባድ ገዥነት ሥር ነበረችና፣ የአይሁዶች ሊቃውንት ከትንቢት የተነሣ ከሮሜ ዕጅ የሚያድናቸውን መሢሕ ይጠብቁ ነበር። ይህ አይነት ትንቢት ቢገኝም ኢየሱስ ያንጊዜ በጦርነት ስላላነሣ የአይሁድ መሪዎች ሊቀበሉት ፈቃደኛ አልነበሩም። ደግሞ «እግዚአብሔር ምኑን ይፈልጋል?» ለሚለው ለዘመናት ፍልስፍና ጥያቄ በመመልስ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ትንቢተ ኢሳይያስ ውስጥ ይህን መልስ አገኝቶ ብዙ ጊዜ ያጠቁመው ነበር፦ «ምሕረት እፈልጋለሁ እንጂ መሥዋዕት አይደለም።» ለሚሰሙት ተከታዮቹ ግን አዲስ ጥያቄ ጠየቃቸው፣ እንዲህ ሲል፦ «ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?» (ማርቆስ 8:36) በወንጌላት በኩል እጅግ በርካታ ተመሳሳይ ትምህርቶች በቀላሉ ሊነቡ ይቻላል። ደግሞ ይዩ፦ አባታችን ሆይ ያስተማረው የክርስትና ጸሎት ወርቃማው ሕግ የሕገ ወንጌል መሠረት ኢየሱስ ማን ነውባጭሩ በተዋሕዶ አብያተ ክርስትያናት እምነት ትምህርት፣ የኢየሱስ ሰብአዊና መለኰታዊ ባሕርይ አንድ (ተዋሕዶ) ነው። ከካልኬዶን ጉባኤ ጀምሮ ግን በሮማ ቤተክርስትያን ትምህርት ዘንድ በሁለት ልዩ ልዩ ሰብአዊና መለኰታዊ ባሕርዮች ተለይቷል። ኢየሱስ ወልድ ሆኖ ከሥላሴ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) አንዱ ክፍል በመሆኑ አምላክ ነው በማለት በንቅያ ጸሎተ ሃይማኖት ይስማማሉ። «ቃሉ ሥጋ ሆነ» ሲባል፣ ፈጣሪው ወደ ፍጥረቱ በሙሉ በመግባት ዓለሙን ለማዳን ኃይልና ፈቃድ እንዳለው ገለጸ ለማለት ነው። ከዚህ በላይ ስለ ኢየሱስ ማንነት ብዙዎች አብያተ ክርስትያናት ከአዲስ ኪዳን ጠቅሰው እንደሚያስተምሩት የሚከተለውን እንረዳለን 1. ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ አንድ እንግዳ ሰው ብቅ አለ፡፡ ይህ ሰው በአለም ውስጥ የተወለደ ቢሆንም፣ ልክ እንደማንኛውም ሰው ሰብአዊ ማንነት ቢኖረውም ተራ ሰው አልነበረም። ከድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ወደ ምድር የመጣው፣ በሰው አምሳል የተገለጠው ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ ሰው (የእግዚአብሔር ልጅ) ነው (ሉቃስ 1፡26-35)፣ (ዮሐንስ 1፡1 እና ዮሐንስ 1፡14)። በብሉይ ኪዳን ስለሚመጣው መሢህ (ክርስቶስ) ሲተነበይ ከመጠሪያዎቹ አንዱ አማኑኤል በዕብራይስጥ «ኢሜኑ» (ከኛ ጋር) «ኤል» (አምላክ) ወይም አምላክ ከኛ ጋራ ማለት ነው። ምድር የእግዚአብሔር መረገጫ እንደ ተባለች (ኢሳይያስ 66:1 እና ማቴ. 5:35) ወደፊት «ከወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ» ለዘላለም የሚነግስ ብለው የተነበዩለት አምላክ የሚሉት እግዚአብሔር ነው። 2. ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ለተለየ ተልእኮ ነው የሰው ልጅ ከጠፋበት መንገድ ሊመልስ (ሉቃስ 19፡10)። ከጨለማ ስልጣን ሊያድነን (ቆላሲያስ 1፡13)፡፡ ነፍሱን ለእኛ ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ፤ ደሙን ከፍሎ ሊገዛን (ማቴ 20፡28)፡፡ በሕይወታችን ያለውን የሰይጣንን ሥራ ሊያፈርስ (1ዮሐ 3፡8)፡፡ የዘላለም ሕይወት ሊሰጠን (1ዮሐ 5፡11፣12)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 3፡16፣17 እና ዮሐንስ 10፡10 ይመልከቱ፡፡ አዲስ ልደት በመስጠት የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሊያደርገን (ዮሐ 1፡12)፡፡ በተጨማሪ 1ዮሐ 3፡1.2 ይመልከቱ ከአብ ጋር የነበረንን ሕብረት ለማደስ (1ዮሐ 1፡3)። 3. ኢየሱስ እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል ሊያሳየን መጣ (ዮሐ 14፡7-11)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 1፡18 ይመልከቱ። የእግዚአብሔርን ፍቅር አሳየን (1ዮሐ 4፡9፣10)፡፡ በተጨማሪ ሮሜ 5፡8 ይመልከቱ። የእግዚአብሔርን ኃይል አሳየን፣ የታመሙትን፣ ሽባዎችን እና አይነስውራንን ፈወሰ (ማቴ 4፡24)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 9፡1-7 ይመልከቱ። ርኩሳን መናፍስትን አስወጣ (ማር 1፡34)፡፡ በተጨማሪ ማርቆስ 5፡1-17 ይመልከቱ። ተአምራትን አደረገ (ማር 4፡37-41)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 6፡1-21 ይመልከቱ። ሙታንን አስነሳ (ዮሐ 11፡43፣44)፡፡ 4. ኢየሱስ መከራችንን ተቀበለ ኢየሱስ በምድር ሕይወቱ እኛ የምንቀበለውን የሕይወት ችግሮች በሞላ አይቷል፤ ስለዚህም ሊራራልን ይችላል። (ዕብ 4፡15)፡፡ በተጨማሪ ማቴዎስ 8፡17 ይመልከቱ። 5. ኢየሱስ ስለእኛ በመስቀል ላይ ሞተ ኃጢአተኛ ሰዎች በሀሰት ኢየሱስን እንደ ወንጀለኛ ከእንጨት በተሰራ መስቀል ላይ ቸነከሩት፡፡ ራሱን ከዚህ ማዳን ቢችልም፣ አላደረገውም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር አለሙን የሚያድነው በእርሱ የመስቀል ላይ ሞት ነበርና፡፡ ስዚህ ኢየሱስ ስለ እኛ ሞተ! (ማር 15፡16-39 ያንብቡ) (1ጴጥ 2፡24)፡፡ በተጨማሪ ኢሳያስ 53፡5፣6 ያንብቡ፡፡ 6. ኢየሱስ ስለእኛ ከሙታን መካከል ተነሳ ከሦስት ቀን የመቃብር ቆይታ በኋላ እግዚአብሔር ልጁን ከሙታን መካከል አስነሳው! (ማቴዎስ 28 ያንብቡ)፡፡ ትንሳኤውም ጭምር ለእኛ ሲል ነበር፡፡ (ኤፌ 2፡4-6)፡፡ በተጨማሪ ሮሜ 6፡4 ያንብቡ፡፡ 7. ኢየሱስ ለእኛ የሰማይን ደጅ ከፈተልን በምድር ላይ የነበረውን ሥራ በፈፀመ ጊዜ ኢየሱስ ወደአባቱ ዘንድ ወደሰማይ አረገ፡፡ ይህም ጭምር ለእኛ ነበር፡፡ ምክንያቱም አሁንና ለዘላለሙ ከእርሱ ጋር አብረን ለመኖር ወደ እግዚአብሔር መገኛ የምንሄድበት መንገድ ከፍቶልናል፡፡ (ዕብ 10፡19-22)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 14፡1-3 ይመልከቱ። ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ ይጎብኙ፡ ተጨማሪ ማጣቀሻዎች ስለ ኢየሱስ የበለጠ ለማወቅ ኢትዮጵያንኦርቶዶክስዶትኮም የተባለ ድረገጽን ይጎብኙ። መጽሓፍ ቅዱስ ክርስትና አይሁድ ማርያም
43652
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A3%E1%88%B5%E1%8B%AB%20%E1%89%A2%E1%8A%95%E1%89%B5%20%E1%88%98%E1%88%85%E1%8B%99%E1%88%9D
ኣስያ ቢንት መህዙም
ስም አስያ የአንሽየንት ዘመን ንግስት ሰእል= የሚገልጸዉ ንግስት አስያ የ ራምሰስ ሁለተኛ ሚስት ተብል በዛን ዘመን ከተሳሉት ሰሎች በጥናት የተገኘ ሙሉ ስምዋ አስያ ቢንት መህዙም የተለያዩ ስምዎችዋ የታላቁ ንጉስ ሚስት፣ ባለ ሁለት መሬት ሴት፣የታችኛዋን እና የላይኛዋ ኢጅብት ንግስት. የተወለደችበት ቀን ያልታወቀ የተወለደችበት ቦታ ግብጽ የሞተችበት ቀን 1199 የሞተችበት ቦታ ግብጽ የቀብርዋ ቀን 1198 ባልዋ ፊርአዉን ራምሰስ ሁለተኛ እምነት በፊት ጣኦት አምላኪ ቡሃላ ግን እስልምናን ተቀብላ ነዉ የሞተች አስያ ከሀዲስ ኣንድ ቀን ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.አ.ወ) መሬት ላይ አራት መስመሮችን አሰመሩ ከዛም ለባልደረቦቻቸው አነዚህ መስመሮች ስለምን ይመስላቹሃል ሲሉ ጠየቁ ሱሃቦቹም አላህ እና መልእክተኛው ያውቃሉ ሲሉ መለሱላቸዉ። ነብዩ (ሰ.አ.ወ)እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ እነዚህ በምድር ላይ መላኢካ ያናገራቸዉ ምርጥ ሴቶች ኣስያ ቢንት መህዙም የፊርአዉን ሚስት፤የኢምራን ልጅ መርየም የእየሱስ (አ.ሰ) እናት ኸድጃ ቢንት ኹወይሊድ የነብዩ ሙሃመድ(ሰ.አ.ወ) የመጀመርያ ሚስት እና ፋጡማ ቢንት ሙሃመድ የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.አ.ወ) ልጅ ናቸዉ ሲሉ መለሱ። ታድያ እኔም ከነዚህ ምርጥ የኢማን እና የተቅዋ ትምሳሌት የሆኑት እንቁ ሴቶቻችን ዉስጥ የመጀመርያዋን እና በአንሽየንት ግብፅ ዘመን የግብፅ ንግስት የነበረችዉን የአስያ መህዙም በነብዩ ሙሀመድ ኣንደበት ምርጥ የተባልችበትን እና በአላህ ቃል የኣማኞች ተምሳሌት የተባለችበትን ስራዋን ላስቃኛቹህ ወደድኩ። አስያ ማንነች አስያ መህዙም በግብፃዉያን አንደበት ነፈርታሪ ሜሪትሙት ትባል እንደነበር እና በዛን ሰአት የነበረዉ በቁርአን ላይ ፊርአዉን እየተባለ ከሰባ (70) ጊዘ በላይ በመጥፎነቱ የተጠቀሰዉ ሃያል ብሎም ጨካኝ የነበረዉ ንጉስ ራምሰስ ሁለተኛ ራምሰስ ሁለተኛ ተብሎ እንደሚጠራ ከግብፃዉያን የአንሽየንት ታሪክ ዉስት ይነበባል። አስያ ኢብን መህዙም በኣኢስላም ታሪክ ዉስጥ የተረገመዉ የፊርአዉን ሚስት በመባል ትታወቃለች ጠንካራ እና ተራ ያልነበረች አቋመ ፅኑ በመሆንዋ ዘመን ተሻግሮ ዘመን በመጣ ቁጥር የምእመናን ምሳሌ እየተባለች የመጨረሻዉ እና የኣልላህ ቃል በሆነዉ ቁራን ስትወሳ ኑራለች። ይህች ታላቅ ሴት በግብፃዉያን አንሽየንት ዘመን የንጉስ ዘር ነበረች። በዛን ስኣት ኣሉ ከሚባሉ ቆነጃጅቶች የምትመደበዉ ይህች ንግስት ጠንካራ እና ኣስተዋይ ሴት ነበረች። የንግስት ኣስያ ታሪክ የሚጀምረዉ ለኣቅማ ሀዋ ደርሳ ምድርን ከረገጡ ሃያላን ንጉስ ከሚባሉት ዉስጥ አንዱ የሆነዉን እና እኔ ነኝ ጌታ ብሎ በኣንዱ በብችኛዉ አላህ የካደዉን ንጉስ ኣግብታ ከቤቱ ከነገሰችበት ጊዜ ጀምሮ ነዉ። ከቁርአን 127. ከፈርዖንም ሰዎች ታላላቆቹ (ለፈርዖን)፦ ሙሳንና ሰዎቹን በምድር ላይ እንዲያበላሹና ሙሳም አንተንና አማልክቶችህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን? አሉ፤ ፦ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን፤ ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን፤ እኛም ከበላያቸው ነን፤ አሸናፊዎች (ነን)፣ አለ። ሱረቱ አል-አዕራፍ 127. 7 127. የፊራውን ትእዛዝ ለፊርአዉን የኣንባገነንነት ማብቂያ ለህዝቦቹ ቀጥተኛ መንገድ መመርያ ለኣስያ ደግሞ በኣላህ ዘንድ መመረጫ የሆነዉ ይሄ የፊራዉን አዋጅ ከታወጀ ቡሃላ ብዙ የኢስራኤል ወንድ ህፃናት በኣንባ ገነኑ ፊርኣዉን ወታደሮች በግፍ ይረግፉ ጀመር። በዚህን ጊዜ የሙሳ (አሰ) እናት በኣንድ ጌታ የምታመን እስራኤላዊ ስለነበረች ጡት ያልጣለ ልጅዋን ሞት ፈርታ አላህን ከፊራዉን ወታደሮች እንዲጠብቅላት የተማፀነችዉ። የሙሳ ከመሞት መዳን ወደ ሙሳም እናት «አጥቢው፣ በርሱም ላይ በፈራሽ ጊዜ በባሕሩ ውስጥ ጣይው አትፈሪም፣ አትዘኝም፣ እኛ ወዳንቺ መላሾቹና ከመልክተኞቹም አድራጊዎቹ ነንና» ማለትን አመለከትን፡፡ 7. 28 አልቀሶስ 7. የሙሳ (ኣ.ስ) እናት በኣላህ ላይ ኣንዳች ተስፋ ሳትቆርጥ እንደትእዛዙ የኣይንዋ ብሌን የሆነዉን ልጅዋን በባህር ላይ ኣንሳፈፈች በጌታዋ ተመክታ ጣለችዉ። የናይል ወንዝም ትከሻዉ ላይ ኣድርጎ የኣላህን ኣደራ ወደ ንግስት ኣስያ መዝናኛ ስፍራ ኣደረሰዉ። ይህንን ህፃን ያየች የኣስያ ኣገልጋይ ንግስትዋ እንድታይ ኣደረገች ንግስት ኣስያ እንዳየችዉ በሙሳ (ኣ.ስ) ፍቅር ወደቀች ከዝያም ለፊርአውን ለእኔ የኣይኔ መርጊያ ነዉ ለኣንተም። ኣትግደሉት ሊጠቅመን ወይንም ልጅ ኣድርገን ልንይዘዉ ይከጀላል እና ኣለች። እነሱም ፍፃሜዉን የማያውቁ ሁነዉ ኣነሱት። ኣልቅሰስ 8-9. አስያ ሙሳን ስታሳድገዉ ኣስያ ሙሳን (ኣ.ስ) ልጅ ልታደርገዉ እስዋም እናት ልት ሆነዉ ኣነሳችዉ። ሙሳ (ኣ.ስ) በርሃብ ማልቀሱን ተያያዘዉ የሚመጡለትን ኣጥቢዎች ጡት ግን የኣንዳችዉንም ለመጥባት ፍቃደኛ ኣልነበረም። ለእኅቱም ተከታተይው አለቻት፡፡ እርሱንም እነሱ የማያውቁ ሲሆኑ በሩቅ ሆና አየችው፡፡ (ወደናቱ ከመመለሱ) በፊትም አጥቢዎችን (መጥባትን) በእርሱ ላይ እርም አደረግን፡፡ (እኅቱ) «ለእናንተ የሚያሳድጉላችሁን እነርሱም ለእርሱ ቅን አገልጋዮች የሆኑን ቤተሰቦች ላመልክታችሁን» አለችም፡፡ እህቱ ስትከታተለዉ የሙሳን (ኣ.ስ) መራብ ኣይታ ነበር ወደ እናቱ የጠቆመቻቸዉ «ወደእናቱም ዓይንዋ እንድትረጋ፣ እንዳታዝንም፣ የአላህም የተስፋ ቃል እርግጥ መሆኑን እንድታውቅ መለስነው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ ኣልቅሰስ 11-13 የአስያ መስለም ሙሳ (ኣ.ስ) በእናቱ ጡት በኣሳዳጊዉ ንግስት ኣስያ ተንከባክቦ ከሙሉ ቤተሰቡ ጋር በፊርኣዉን ቤተመንግስት ዉስጥ የሚጠላ ዘር ግና የሚወደድ ህፃን ሁኖ ኣደገ። ከለታት ኣንድ ቀን ጨለማ በብርሃን እንደሚገፈፈዉ ሁሉ ሙሳም (ኣ.ስ) የፊራዉንን በዳይነት ሊገፍ ነብይ ሆነ። ከዛም ህዝቦቹን እና የፊርኣዉን ቤተመንግስት ዉስጥ ያሉ ሰዎችን እኔ ከኣንዱ ከእዉነተኛዉ ጌታየ እና ጌታቹህ የተላኩ የኣላህ መልእክተኛ ነኝ ፊርኣዉንም እንደኛዉ ሰዉ እንጅ ፈጣሪ ኣይደለም እነኣሙንም ሆኑ ሌሎች ጣኦታትም የማይሰሙ የማይፈጥሩ ገኡዛን እንጅ ሌላ ኣይደሉም ብሎ በህፃንነቱ ያሳደገዉን አባቱን የኣላህን ጠላት ጠላቱ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ አስያም በሙሳ መንገድ ቆመች እስዋም ባልዋን ጠላት እደረገች። በሱ ላይ የካደበትን ሁሉ ኣይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ እያወቀች ብሎም ቤተሰብዋን ክብርዋን እና ዝናዋን ብሎም ሂወትዋን እንደሚያሳጣት እያወቀች በቤተ መንግስቱ ሁና ሌላን እዉነተኛዉን እላህን ማገልገልዋን ቀጠለች። ከዱንያ እና በዉስጡ ካሉ ጥቅሞች ይልቅ የኣላህን ቃል ትእዛዙን ኣስበለጠች።ለጌታዋ ኑራ ለጌታዋ መሞትን መረጠች። ከእለታት ኣንድ ቀን ሙሳ (ኣ.ስ) ከፊራዉን እውቅ ድግምተኞች እና ኣስማተኞች ጋር የኣላህን ተኣምር ለማሳየት ተወዳድሮ አሽነፈ ከዛም ቡሃላ ጠንቋዮችን ጨምሮ ብዙ ህዝቦች በሙሳ ጌታ አምነናል ሲሉ ኣመኑ በፊርኣዉን እና በኣሙን ጌትነት ላይ ካዱ። የሙሳ ተአምር አይደለም ጣሉ፣ አላቸው፤ ወዲያውም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ (እባቦች) ሆነው ወደርሱ ተመለሱ። ሙሳም በነፍሱ ውስጥ ፍርሃት አሳደረ. አትፍራ አንተ የበላዩ አንተ ነህና አልነው። አትፍራ አንተ የበላዩ አንተ ነህና አልነው። ድግምተኞቹም ሰጋጆች ሁነው ወደቁ፤ በሃሩንና በሙሳ ጌታ አመንን አሉ። ሱረቱ ጣሀ (66-70) 66-70. የተአምሩ ዉጤት ይህ ከሆነ ከቀናቶች ቡሃላ በሃጅ ወቅት እንደሚሰዋ በግ ከሌላዉ ጊዜ የበለጠ ቁጥራቸዉ የበዛ አማኝ ህዝቦች መታረዳቸዉን ቀጠሉ። ከነዛ ዉስጥ የፊርአዉን ልጅ ፀጉር አበጣሪ የነበረችዉ አማኝ የምታበጥርበት ማበጠርያ ከእጅዋ ሲወድቅባት በድንጋጤ የኣላህን ስም በመጥራትዋ እማኝነትዋ ታወቀባት በሙሳ ጌታ እንድትክድ በልጆችዋ ስቃይ ስትቀጣ ከጡትዋ ያልወረደዉ ህፃንም ልክ አንደሌሎች ወንድሞቹ መቀጫ ሊሆን ሲል በድንጋጤ እና በፍርሃት ዉስጥ ሁና ስታለቅስ ያያትን እናቱን የኣላህን ስም ጠርቶ አፉን እየፈታ ታገሽ በኣላህ ላይ ተስፋ ኣድርጊ የሚል ኣስገራሚ የህፃን አንደበት ሰምታ ከጡትዋ ነጥቀዉ የፈላ ዘይት እራት ካደረጉት ቡሃላ እና በልጆችዋ ሂወት ሳትሳሳት ለነብስዋም ሳትሳሳ በጌታዋ ኣንድነት እንዳመነች ከነልጆችዋ ከተጠበሰችዋ ምስኪን እናት ሞት ቡሃላ። የአስያ እምነትዋን ግልጽ ማዉጣት አስያ ያለችበትን የእምነት የመዳን ብርሃን ደብቃ መኖር ኣልቻለችም የእምነት ወንድም እህቶችዋ ሞት ይበልጥ ፊርአዉንን እንድትጠላዉ እና እንድትንቀዉ ኣደረጋት። እናም እንደሌሎቹ ሽሂድ ልትሆን ላመነችበት ጌታዋ ልትሞት ወሰነች። አማኝነትዋንም ለጨካኙ ፊርአዉን ገለፀች እራስዋን ለእሳት ኣሳልፋ ሰጠች ልትሞት ወሰነች። አማኝነትዋንም ለጨካኙ ፊር አዉን ገለፀች እራስዋን ኣሳልፋ ሰጠች። ፊርአዉን የዉቦች ዉብ የሆነችዉን ዉድ ሚስቱን ከመቅጣቱ ነብስዋን ላትመለስ ከመሸኘቱ በፊት በሙሳ (ኣ.ስ) ጌታ ትካድ በሚል እናትዋን ሽምግልና ላከ። አስያ ግን በሃቅ መንገድዋ ላይ ቤተሰብዋን ንግስናዋን እና በኣለም ላይ ሃያል ተብሎ የሚጠራዉን ንጉስ ማስገባት ኣልፈለገችም። እነዚህን እና አላህን ማመዛዘን ማለት ወርቅ በኣፈር የመቀየር ያህል ሆነባት። በፍፁም ኣልስማማም በጌታዋ ላይ ያላትን ፅናት አወጀች። ፊርኣዉን በኣስያ ተስፋ ስለቆረጠ ሊገላት እንደሌሎች አማኞች ሸሂድ ልያደርጋት ወሰነ። በዚህን ጊዘ ለጌታዋ እንዲህ ስትል እጅዋን ኣነሳች:: ለነዚያ ለአመኑትም የፈርዖንን ሴት አላህ ምስል አደረገ፤ ጌታዬ ሆይ! አንተ ዘንድ በገነት ውስጥ ለኔ ቤትን ግንባልኝ፤ ከፈርዖንና ከሥራውም አድነኝ፤ ከበደለኞቹ ሕዝቦች አድነኝ ባለች ጊዜ። አል- ተሕሪም 11 አስያ ለጌታዋ የጠየቀችዉ ጥያቄ አስያ በምድር ላይ ያሉ ነገሮችን ሳይሆን በጀነት የኣላህን ጉርብትና ነበር ጌታዋን የተማፀነች ድሎትን ሳይሆን በተውሂድ መሞትን እንዲሁም በምድር ላይ ካሉ የኣላህ ጠላቶች እንዳትሆን ነበር ዱኣዋ። ይህንን ካለች ብሃላ የግብፅ የኣን ሽየንት ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከክርስቶስ ዘመን በፊት ወይንም በ1179 ከዚህ ኣለም ተሰናበተች ወደኣንዱ እና ብቸኛ ጌታዋ ጉርብትና ወደጀነት ኣቀናች። እስልምና እስልምና ጥያቄ ከአንባቢዎች አንዱ ለምን የተወለደችበት ቀን አል አልታወቀም??? መሃመድ የመጣው ከክርስቶስ በኋላ በ6 ዓም ነበረ።ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረ ነውና"መቼ ነሮበት በቼ አይቶት ነው ይህን
9698
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B3%E1%88%AA%E1%8A%AB%E1%8B%8A%20%E1%8A%A0%E1%89%86%E1%8C%A3%E1%8C%A0%E1%88%AD%20%E1%89%A0%E1%8B%A8%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%88%88%E1%8B%98%E1%88%98%E1%8A%91
ታሪካዊ አቆጣጠር በየክፍለዘመኑ
ዓክልበ. ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ማለት ከ1 ዓመተ ምኅረት (ወይም 9 እ.ኤ.አ.) በፊት ገ.፣ ግ. ገደማ ግድም አመቱ ልክ ሳይሆን አካባቢው ነው። ከ1000 ዓክልበ. ወደ ቀድሞ እየሔደ፣ የአመቶቹ አቆጣጠር በልክ እርግጥኛ አይደሉምና የታሪክ ሊቃውንት ብዙ ጊዜ አይስማሙም። ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት ጥንታዊው ዘመን 3125 ግ. የሴት ወገን ወደ ከንቲያመንቱ ልጆች ሄዶ ይከለሳሉ። 3104 ገደማ የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ በግብጽ ተሠራ፤ የጊንጥ ዱላ። የከንቲያመንቱ እና የሴት ወገኖች ክልሶች (ኦሪታውያን ወይም ደቂቃ ሔሩ) ተነሡ። 3101 ግ ሜኒ (ሜኒስ ወይም ናርመር) መጀመርያ የመላው ግብጽ ፈርዖን ሆነ። 3089 ግ. ሜኒ (ናርመር) በውግያ ሞተ። ለ10 ወራት ግብጽ ያለ ንጉሥ ቆይቶ በመጨረሻ ከንቲያመንቱ-ሔሩ-ቴቲ እንደ ፈርዖን በጉባኤ ተመረጠ። ጽሕፈት ተለማ፤ ሰብአዊ መሥዋዕት ተጀመረ፤ ሊቃውንት ያልሆኑ ሰዎች ከግብጽ ወደ ምዕራብ፣ ደቡብና ምሥራቅ (ዮርዳኖስ) ሸሹ። 3080 ግ. ጀር ኢቲ ነገሠ፤ ሰባአዊ መሥዋዕት ተስፋፋ፤ ደቂቃ ሔሩ በሴትጀት ሠፈር (የበኋላ ከነዓን) ላይ ዘመቱ። 3075 ግ. ጀት ነገሠ። 3070 ግ ደን ሰምቲ ነገሠ። የክልሶች ቁጥር ተጨመረ፤ ጭቆና በሴት ወገን ላይ ተደረገ። 3054 ግ. መርባፐን ነገሠ። 3048 ግ. ሰመርኅት ነገሠ፣ ሚኒስትሩ ሄኑካ ለደቂቃ ሔሩና ለሴት ወገን ምልክት አቀረበ። 3044 ግ. ቃአ ነገሠ፤ 3037 ግ. ሆተፕ ነገሠ፤ መጀመርያ በስሜን የሆነው የንጉሥ መቃብር። 3032 ግ. ነብሬ ነገሠ፤ የቅርጽ ምስል ሥራ ተጀመረ። 3029 ግ. ኒነጨር ነገሠ፤ የላሞች ቁጠራ በየዓመቱ ተደረገ። 3014 ግ. ሰነጅ ነገሠ፤ ከሔሩ ሃይማኖት ርቆ ስሙ በሰረኅ ሳይሆን አዲስ ምልክት ካርቱሽ ፈጠረ፤ ነፈርካሬ እና ነፈርካሶካር ግን ለትንሽ ዘመን በስሜን ግብጽ ነገሡ። 3007 ግ. ሔሩ-ፔሬንመዓት ሰኅሚብ አዲስ የሰረኅ ስም ሴት-ፐሪብሰን አወጣ፣ በደቡብና ስሜን ግብጽ መካከል ብሔራዊ ጦርነት። 2996 ግ ሔሩ-ኅሠኅም 2ቱን አገራት እንደገና አዋኅደ፣ ስሙም ሔሩ-ሴት-ኅሰኅምዊ ሆነ። ከዚህ ጀምሮ የንጉሥ ስም በካርቱሽ ሳይሆን በሰረኅ ብቻ ሆነ። 2987 ግ. ነጨሪኸት (ጆሠር) በግብጽ ነገሠ። ዘመቻ በሲና አገር ላይ ተደረገ፣ ረኃብ ሆነ። መጀመርያው ሀረም መቃብር ተሠራ፤ በጸሐፈ ትዕዛዙ ኢሙጤስ (ኢምሆተፕ) ታቀደ። ኢሙጤስ የቀዶ ጥገና እና የመስኖ ሥራ አስተማረ። 2977 ግ. ሳናኅት ነብኃ ነገሠ፤ ጉዞዎች ወደ ሲና ተቀጠሉ፣ ከዚህ ጀምሮ የንጉስ አርማ በካርቱሽና ሰረኅ አንድላይ ይታያሉ። 2975 ግ. ሰኅምኅት ጆሰርቲ ነገሠ፤ ጉዞ ወደ ሲና ተድረገ፤ ሀረሙም በኢሙጤስ ታቀደ። 2973 ግ ኅባ ነብካሬ ነገሠ። 2972 ግ. ነፈርካ ነገሠ፤ ካርቱሽ ብቻ ነበረው፤ የተያያዘ ጽሕፈት ተለማ። 2971 ግ ሁኒሲት ነገሠ፤ ካርቱሽ ብቻ ነበረው። 2967 ግ. ስነፈሩ ነገሰ፤ ሰረኅ በካርቱሽ አጠገብ ተመለሠ፤ ባህርን ሊሻገር የሚችል መርከብ ኃይል ነበረ፤ ዘመቻ በምዕራብና ደቡብ ጊረቤቶች ላይ ተደረጉ፤ 3 ሀረሞች ተሠሩና መዝገቦች ተሳኩባቸው። 2955 ግ. ኁፉ ነገሠ፤ 1ኛው ታላቁ ሀረም ተሠራ። ዘመቻዎች ወደ ምሥራቅ፣ ምዕራብና ስሜን አገሮች ላይ አደረገ። 2938 ግ. ረጀደፍ ነገሠ፤ እኅቱን አገባ 2927 ግ. ኅፍሬ ነገሠ፤ እህቱን አገባ፤ 2ኛው ታላቅ ሀረምና የጊዛ ታላቅ እስፊንክስ ተሠሩ። 2914 ግ. መንካውሬ ነገሠ፤ እህቱን አገባ፤ 3ኛው ታላቅ ሀረም ተሠራ። 2903 ግ ሸፕሰስካፍ ነገሠ። በመስተባ መቃብር እንጂ በሀረም አልተቀበረም፤ ሀረሞች ግን የሀገሩን ግቢ ለማከፋፈል ጠቀሙ። 2901-2872 ግ. የፀሐይ መቅደስ ዘመን፤ ፈር ዖኖች ቤተ መቅደሶች ለፀሐይ አምላክ (ሬ) ሠሩ። 2901 ግ ኡሠርካፍ ነገሠ፤ 2898 ግ. ሳሁሬ ነገሠ። 2891 ግ. ነፈሪርካሬ ነገሠ 2886 ግ. ሸፕሰስካሬ፣ ነፈረፍሬ ነገሡ። 2884 ግ. ኒዩሠሬ ነገሠ። 2876 ግ. መንካውሆር ነገሠ። 2875 ግ. ጀድካሬ ነገሠ። 2853-2770 ግ. የሀረም ጽሕፈቶች ዘመን። የፈርዖን ወገን (ደቂቃ ሔሩ ወይም ኦሪታውያን) በሴት ወገን ቅሬታ ላይ ማደን አደረገ። 2853 ግ. ኡናስ ነገሠ። 2842 ግ. 2 ቴቲ ነገሠ። 2836 ግ. 2 ቴቲ በወታድሮቹ ተገድሎ ኡሠርካሬ ዙፋኑን በግፍ ያዘ። 2835 ግ. 1 ፔፒ፣ የ2 ቴቲ ልጅ። በዘመኑ ዘመቻ ወደ ደቡብና ምሥራቅ ይደረጋል። 2810 ግ 1 መረንሬ፤ ዘመቻ ወደ ደቡብ አደረገ። 2805 ግ. 2 ፔፒ ነገሠ። በርሱ ዘመን አንድ አጭር ሰው ከፑንት አገር ተማርኮ ወደ ግቢው ተወሰደ። 2774 ግ. ልጁ 2 መረንሬ ነገሠ፤ ምናልባት በግድያ ሞተ። 2773 ግ. ነፈርካሬ ነቢ ነገሠ የ2 ፔፒ ሌላ ልጅ 2772 ግ. ቃካሬ ኢቢ ነገሠ። 2770 ግ. ነፈርካውሬ ነገሠ። ሸማይ ጠቅላይ ሚኒስትር ተደረገ። 2766 ግ. ነፈርካውሆር ነገሠ። 2764 ግ. ዋጅካሬ፤ ጸጥታ ለመመልስ ሞከረ። ሸማይ አርፎ ልጁ ኢዲ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ። 2763 ግ. የቀድሞ ግብጽ መንግሥት መጨረሻ 25ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 2475 ግ. ኤንመርካር ኤሪዱን ሠራ። 2454 ግ. ኤንመርካር ኡሩክን ሠራ። ጙሹር ከዚያ ወጥቶ ኪሽን ሠራ። 2432 ግ. ኤንመርካር ሱመርን ገዛ፤ መጀመርያ አገሮች፦ ኤላም፣ አንሻን፤ ሱመር፣ አካድ፣ ሹቡር፤ ሐማዚ፣ ሉሉቢ፣ አራታ፣ ማርቱ። 2425 ግ. የማርቱ ሕዝብ በሱመርና አካድ በዝተው ኤንመርካር በበረሃ ግድግዳ ሠራ። 2422 ግ. ኤንመርካር ሐማዚን ያዘ። 2417 ግ. ዋህካሬ ቀቲ በምስር (ሄራክሌውፖሊስ) 9ኛውን ሥርወ መንግሥት መሠረተ። 2407 ግ. ኤንመርካር አራታን ከበበው። 2406 ግ. ኤንመርካር ሞተ፤ ጦር አለቃው ሉጋልባንዳ በኡሩክ ዙፋን ተከተለው። 24ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 2400 ግ. ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ በኡሩክ ነገሠ። 2389 ግ. ኋንግ ዲ በዮሾንግ፣ ያንዲ በሸንኖንግ (ቻይና) 2384 ግ. ሱመር ከተማ ኪሽ ንጉሥ ኤንመባራገሲ ኤላምን ወረረ። 2383 ግ. ዱሙዚድ ኤንመባራገሲን ማርኮ አጋ በኪሽ ነገሠ። 2382 ግ. ዱሙዚድ በአመጽ ተገልብጦ ጊልጋመሽ በኡሩክ ነገሠ። 2354 ግ. ነገደ ኩሳ በኩሽ ተመሰረተ። 2350 ግ. ቻይና፦ የባንጯን ውግያ፤ የኋንግ ዲ በያንዲ ላይ ድል አደረገ፤ ዮሾንግና ሸንኖንግ ተባብረው ኋሥያ የተባለውን ነገድ አንድላይ ይሠራሉ። ግብጽ፦ ቀቲ (አቅቶይ) በግብጽ ነገሠ። ሱመር፦ ኡር-ኑንጋል በኡሩክ ነገሠ። 2345 ግ. የኡር ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ የሱመርን ላዕላይነት ማዕረግ ያዘ። ሥርወ መንግሥታት በሣባ፣ ኤውላጥና ኦፊር ቆሙ (ነገደ ዮቅጣን)። 2331 ግ. ቻይና፦ የዥዎሉ ውግያ፣ ኋንግ ዲ በቺ ዮው ላይ አሸነፈ። ግብጽ፦ መሪብታዊ ቀቲ በግብጽ ነገሠ፤ 2314 ግ. መስኪአጝ-ኑና በኡር ነገሠ። ላጋሽ ነጻ ሆኖ ኡር-ናንሼ እዚያ ነገሠ። 2310 ግ. አዋን (በኤላም) የሱመርን ላዕላይነት ማዕረግ ያዘ። 2304 ግ. ሃባሢ በኩሽ ነገሠ። 23ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 2290 ግ. ሻውሃው በኋሥያ ነገሠ። 2284 ግ. አኩርጋል በላጋሽ ነገሠ። 2283 ግ. ዧንሡ በኋሥያ ነገሠ። 2274 ግ. የኪሽ ንጉሥ ካልቡም የሱመርን ላዕላይነት ማዕረግ ያዘ። 2271 ግ. ሰብታ በኩሽ ነገሠ። 2254 ግ. ኤአናቱም (ሉማ) በላጋሽ ነገሠ። 2243 ግ. የሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ የሱመርን ላዕላይነት ማዕረግ ያዘ። 2236 ግ. ነፈርካሬ ቀቲ በግብጽ ነገሠ። 2234 ግ. ኤሌክትሮን በኩሽ ነገሠ። 2215 ግ. የኡሩክ ንጉሥ ኤንሻኩሻና ሐማዚን፣ አካድን፣ እና መላ ሱመርን አሸንፎ መንግሥትን ገዛ። ኤአናቱም (ሉማ) ግን ግዛቱን አስፋፋ። 2206 ግ. ዲ ኩ በኋሥያ ነገሠ። 2204 ግ. ነቢር በኩሽ ነገሠ። 22ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 2200 ግ. ነብካውሬ ቀቲ በግብጽ ነገሠ። 2195 ግ. የላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም ኡሩክን ያዘ። 2194 ግ. ኤአናቱም ሞተ፤ የኡሩክ ንጉሥ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ የሱመር ላዕላይነቱን ማዕረግ ያዘ። 2188 ግ. የኡር ንጉሥ ናኒ ላዕላይነቱን በሱመር ያዘ። 2182 ግ. መስኪአጝ-ናና በኡር ነገሠ። 2174 ግ. 1 አሜን በኩሽ ነገሠ። 2167 ግ. ሰነን- በግብጽ ነገሰ። 2154 ግ. ነሕሴት ናይስ በኩሽ ነገሠች። 2153 ግ. የአዳብ ንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ መንግሥት። ጉታውያን (ሜዶን) እና ሹቡር (አሦር) ይገዙለታል። 2147 ግ. መሪካሬ በግብጽ ነገሠ። 2142 ግ. ዲ ዥዕ በኋሥያ ነገሠ። 2140 ግ. የሲኒ ከነዓን ወገን በኩሽ ደረሰ። 2133 ግ. ያው በኋሥያ ነገሠ። 2127 ግ. ኢብሉል-ኢል በማሪና አሹር፤ ኢግሪሽ-ሐላብ በኤብላ 2123 ግ. ሆርካም በኩሽ ነገሠ። 2121 ግ 2 መንቱሆተፕ በግብጽ ነገሠ። 2118 ግ አብርሃም ከካራን ወደ ከነዓን ገባ (መ. ኩፋሌ) 2115 ግ ኢርካብ-ዳሙ በኤብላ ነገሠ፤ የኤብላ አለቃ ኤና-ዳጋን ኢብሉል-ኢልን አሸነፈ፤ ኒዚ በማሪ፣ ቱዲያ በአሦር ነገሡ። 2114 ግ. ኤና-ዳጋን የማሪ ዙፋን ያዘ። 2112 ግ. ኢኩን-ኢሻር፣ ሒዳዓር በማሪ ነገሡ። 2109 ግ. የአርዋዲ ልጅ አይነር ስለ ረሃብ ከከነዓን ወደ ኩሽ ደረሰ። ኢሻር-ዳሙ በኤብላ ነገሠ። 2108 ግ. ዳንጉን ዋንገም በጎጆሰን ነገሠ። 2107 ግ. ሉጋል-አኔ-ሙንዱ ሞተና የአዳብ መንግሥት ተከፋፈለ። ሉጋል-ዛገ-ሢ በኡማ፣ ፑዙር-ኒራሕም በአክሻክ፣ ሉጋላንዳም በላጋሽ ነገሡ፤ ሻሩሚተር በማሪ የላዕላይነቱን ማዕረግ ያዘ። በግብጽ መሪካሬ በመንቱሆተፕ ላይ አመጸ። 2102 ግ. ሉጋላንዳ በአመጽ ተገለበጠና ኡሩካጊና በላጋሽ ንጉሥ ሆነ። 2101 ግ. የኡማ ንጉስ ሉጋል-ዛገሲ ኡሩክን ይዞ «የኡሩክ ንጉሥ» የሚለውን ስያሜ ወሰደ። 21ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 2100 ግ. የአክሻክ ንጉሥ ፑዙር-ኒራሕ ኒፑርንና ላዕላይነቱን ያዘ። 2098 ግ. የላጋሽ ንጉሥ ኡሩካጊና መጀመርያ የሚታወቀውን ሕገ ፍጥሕ አወጣ። 2097 ግ. የኒፑር ቄሳውንት ላዕላይነቱን ለኪሽ ንግሥት ኩግ-ባው ሰጡ። 2095 ግ. የኡሩክ ንጉሥ ሉጋል-ዛገ-ሢ ላጋሽን ያዘ። 2094 ግ. 1 ሳባ በኩሽ መንግሥት ነገሠ። 2092-90 ግ. 2 መንቱሆተፕ በኩሽ ላይ ዘመተ። 2091 ግ. ኡር-ዛባባ በኪሽ ነገሠ። 2085 ግ. ሉጋል-ዛገ-ሢ ኪሽንና ኒፑርን ይዞ የሱመር ላዕላይነቱንም ያዘ። 2081 ግ. መንቱሆተፕ ሄራክሌውፖሊስን ይዞ ግብጽን ሁለተኛ አዋሀደ። 2079 ግ. የወይጦ አባት ዋቶ ሳምሪ ከግብጽ ስለ ረሃብ ወደ ኩሽ ደረሰ። 2077 ግ. ታላቁ ሳርጎን በአካድ ነገሠ፤ የኡሩክን መንግሥት አሸነፈው። የኤብላ አለቃ ኢቢ-ዚኪርም ሒዳዓርን አሸነፈ፤ ኢሽቂ-ማሪ ተከተለው። 1 አንተፍ በግብጽ ነገሠ። 2075 ግ. ኤላም በ1 ሳርጎን ወደ አካድ መንግሥት ተጨመረና አካድኛን ይፋዊ ቋንቋ አደረገበት። 2074 ግ. ሳርጎን ወደ ምዕራብ እስከ ቆጵሮስ ድረስ ዘመተ፤ ኤብላን አቃጠለ። 2068 ግ. ሳርጎን ማሪን አጠፋ። 2066 ግ. ሳርጎን በአናቶሊያ (ሐቲ) ዘመተ። 2 አንተፍ በግብጽ ነገሠ። 2064 ግ. ሶፋሪድ በኩሽ ነገሠ። 2063 ግ. ሪሙሽ በአካድ ነገሠ። 2061 ግ. ሹን በኋሥያ ነገሠ። 2056 ግ. ማኒሽቱሹ በአካድ ነገሠ። 2049 ግ. ናራም-ሲን በአካድ ነገሠ። 2047 ግ. ናራም-ሲን በአዙሑኑም (አሦር) ዘመተ። 2044 ግ. ናራም-ሲን በኡሩክ ዘመተ። 2040 ግ. ናራም-ሲን የሱባርቱ አለቃ ዳሂሻታልን በአዙሑኑም ማረከው። 2039 ግ. ናራም-ሲን ስሜን ሶርያን ወርሮ በአሞራውያን ላይ ዘመተባቸው። 2038 ግ. ናራም-ሲን ኤብላን ያዘ፣ በሊባኖስና በአማና ዙሪያ ዘመተ። 2036 ግ. ናራም-ሲን ከሐቲ (ኬጣውያን) ንጉሥ ፓምባና ከካነሽ ንጉሥ ዚፓኒ ጋር በአናቶሊያ ተዋጋ። 2034 ግ. ናራም-ሲን የአራም አለቃ ዱቡልን ማረከ፣ ሉሉቢን አሸነፈ። እስከንዲ በኩሽ ነገሠ። 2030 ግ. ሻርካሊሻሪ በአካድ ነገሠ። 2021 ግ. ሻርካሊሻሪ የጉቲዩም ንጉሥ ሻርላግን ማረከው። 2020 ግ. ሻርካሊሻሪ የባሳር አሞራውያንን አሸነፋቸው። 2019 ግ. ሻርካሊሻሪ ኤላማውያንን በአክሻክ ውግያ አሸነፋቸው። 2018 ግ. ሻርካሊሻሪ ጉቲዩምን ገበረው። 2016 ግ. 3 አንተፍ በግብጽ ነገሠ። 2015 ግ. ቡሩ በጎጆሰን ነገሠ። 2013 ግ. ኢሉሉና ሌሎች ለአካድ መንግሥት ተወዳደሩ። አካድ በብሔራዊ ጦርነት እየደከመ ነው። ኤላማዊው አገረ ገዡ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ በአመጽ ተነሥቶ አገሩን ነጻ አወጣውና አካድኛን ተወ። 2010 ግ. ጉታውያን አካድን ድል አድርገው መስጴጦምያን ወረሩ። ዳ ዩ በቻይና ነገሠ። 2009 ግ. ሆህይ በኩሽ ነገሠ። 3 መንቱሆተፕ በግብጽ ነገሠ። ጉደአ በላጋሽ ነገሠ። 2004 ግ. ጉደአ አንሻንን መታ። 2003 ግ. 4 መንቱሆተፕ በግብጽ። 2002 ግ. 1 አመነምሃት በግብጽ። 20ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 1999 ዓክልበ. ግ. ጪ በቻይና ነገሠ። 1991 ዓክልበ. ግ. ረሃብ በመካከለኛው ምሥራቅ። 1986 ዓክልበ. ግ. የኤላም ንጉሥ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ የአካድን ቅሬታ ያዘ። 1985 ዓክልበ. ግ. የኡሩክ ንጉሥ ኡቱ-ኸጛል ጉታውያንን አስወጣቸውና መንግሥት ገዛ። ታይ ካንግ በቻይና ነገሠ። 1984 ዓክልበ. ግ. ኡር-ናሙ ኡሩክን አሸነፈና በኡር መንግሥት ገዛ። 1983 ዓክልበ. ግ. የኡር-ናሙ ሕግጋት ወጡ። 1982 ዓክልበ. ግ. 1 ሰኑስረት ከአባቱ ጋራ በጋርዮሽ ፈርዖን ሆነ፣ በሊብያ ዘመተ። 1981 ዓክልበ. ግ. ዦንግ ካንግ በቻይና ነገሠ። 1974 ዓክልበ. ግ. ኡር-ናሙ በጉቲዩም ላይ ዘመተ፤ ሥያንግ በቻይና ነገሠ; አድግላግ በኩሽ ነገሠ። 1972 ዓክልበ. ግ. ሰኑስረት ለብቻ ፈርዖን ሆነ። 1966 ዓክልበ. ግ. ሹልጊ በኡር ነገሠ። 1964 ዓክልበ. ግ. ሰኑስረት በኩሽ መንግሥት ላይ ዘመተ፤ ካርግ በጎጆሰን ነገሠ። 1954 ግ. አድጋላ በኩሽ ነገሠ። 1946 ዓክልበ. ግ. ተዋጊው ሃን ዥዎ የቻይናን ንጉሥ ሥያንግን አስገደለው፤ ለጊዜው ንጉሥ አልነበረም። 1944 ዓክልበ. ግ. ሹልጊ እራሱን አምላክ ብሎ አዋጀ። 1937 ዓክልበ. ግ. 2 አመነምሃት ለብቻ ፈርዖን ሆነ። 1924 ግ. ባኩንዶን (ላከንዱን) በኩሽ ነገሠ። 1919 ዓክልበ. ግ. ኦሳጉ በጎጆሰን ነገሠ። 1918 ዓክልበ. ግ. አማር-ሲን በኡር ነገሠ። 1914 ዓክልበ. ግ. 1 ፑዙር-አሹር በአሦር ነገሠ። 1909 ዓክልበ. ግ. ሹ-ሲን በኡር ነገሠ። 1907 ዓክልበ. ግ. ሻሊም-አሁም በአሦር ነገሠ። 1906 ዓክልበ. ግ. ሃን ዥዎ ተሸንፎ ሻውካንግ የቻይና ንጉሥ ሆነ። 1905 ዓክልበ. ግ. 2 ሰኑስረት ለብቻው ፈርዖን ሆነ። 1902 ግ. ናከህቲ ካልነስ በሳባ ነገሠ፤ ኢሉሹማ በአሦር ነገሠ። 1901 ዓክልበ. ግ. ኢቢ-ሲን በኡር ነገሠ። 19ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 1900 ዓክልበ. ታላቅ ረሃብ በመካከለኛው ምሥራቅ ጀመረ። እሽቢ-ኤራ በኢሲን ነጻ ንጉሥ ሆነ። 1894 ዓክልበ. ማንቱራይ በ ኩሽ መንግሥት ነገሠ። 1891 ዓክልበ. 3 ሰኑስረት ስሜን ኩሽ እስከ ፪ኛው አባይ ሙላት ያዘ። 1888 ዓክልበ. 2 ሰኑስረት አርፎ 3 ሰኑስረት ለብቻ ፈርዖን ሆነ፤ 1885 ዓክልበ ዡ በቻይና (ሥያ) ነገሠ። 1884 ዓክልበ. ሰኑስረት በከነዓን ዘመተ። 1881 ዓክልበ. 1 ኤሪሹም በአሦር ነገሠ፤ ጉዕል በጎጆሰን ነገሠ። 1880 ዓክልበ. ታላቅ አውሎ ንፋስ በኡር ተከሠተ። 1879 ዓክልበ. -ኤላማውያን ኡር ከተማን አጠፉና ንጉሣቸውን ኢቢ-ሲንን ማረኩት። የኡር መንግሥት ውድቀት። 1878 ዓክልበ. የኢሲን ንጉሥ እሽቢ-ኤራ ኤላማውያንን አሸንፎ ኡርን ያዘ። 1872 ዓክልበ. ሹ-ኢሊሹ በኢሲን ነገሠ። 1869 ዓክልበ. ኋይ በሥያ ነገሠ። 1865 ዓክልበ. ታልሙን በጎጆሰን ነገሠ። 1862 ዓክልበ. ኢዲን-ዳጋን በኢሲን ነገሠ። 1859 ዓክልበ. 3 አመነምሃት ለብቻ በግብጽ ነገሠ። 1850 ዓክልበ. እሽመ-ዳጋን በኢሲን ነገሠ። እርሱ ኒፑርን መለሰው። 1844 ዓክልበ. አሞራዊው ጉንጉኑም በላርሳ ነጻነት ከኢሲን አዋጀ። 1842 ዓክልበ. ኢኩኑም በአሦር ነገሠ። 1835 ዓክልበ. ጉንጉኑም ኡርንና ኒፑርን ከኢሲን ያዘ። 1833 ዓክልበ. ሊፒት-እሽታር በኢሲን ነገሠ። 1830 ዓክልበ. ሃንዩል በጎጆሰን ነገሠ። 1832 ዓክልበ. የሊፒት-እሽታር ሕግጋት በኢሲን፤ 4 አመነምሃት በ ግብጽ ነገሠ። 1829 ዓክልበ. 1 ሳርጎን በአሦር ነገሠ። 1826 ዓክልበ. ማንግ በሥያ ነገሠ። 1823 ዓክልበ. ኡር-ኒኑርታ በኢሲን ነገሠ፤ ሶበክነፈሩ በግብጽ ነገሠች። 1821 ዓክልበ. ያክቢም ሰኻኤንሬ በአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ (ጌሤም) ነገሠ። 1819 ዓክልበ. ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ በላይኛ ግብጽ ነገሠ። 1817 ዓክልበ. አቢሳሬ በላርሳ ነገሰ፤ ኒፑር ወደ ኢሲን ተመለሰ። 1816 ዓክልበ. ሰኸምካሬ ሶንበፍ በላይኛ ግብጽ ነገሠ። 1812 ዓክልበ. ነሪካሬ በላይኛ ግብጽ ነገሠ። 1811 ዓክልበ. ሰኸምካሬ 5 አመነምሃት በላይኛ ግብጽ፤ ያዓሙ ኑብዎሰሬ በጌሤም ነገሡ። 1808 ዓክልበ. አመኒ ቀማው በላይኛ ግብጽ ነገሠ። 1807 ዓክልበ. ሱሙ-አቡም በባቢሎን ነጻ ንጉስ ሆነ። 1806 ዓክልበ. ሱሙኤል በላርሳ ነገሠ፤ ቡር-ሲን በኢሲን ነገሠ፤ ሆተፒብሬ በላይኛ ግብጽ ነገሠ። 1803 ዓክልበ. ዩፍኒና 6 አመነምሃት በላይኛ ግብጽ ነገሡ። 1801 ዓክልበ. ቃረህ ኻዎሰሬ በጌሤም ነገሠ። 18ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 1800 ዓክልበ. ሰመንካሬ ነብኑኒ በጤቤስ ነገሠ። 1799 ዓክልበ. አዛገን በኩሽ መንግሥት ነገሠ። 1798 ዓክልበ. ሰኸተፒብሬ በጤቤስ ነገሠ። 1796 ዓክልበ. ሰዋጅካሬ፣ ነጀሚብሬ በጤቤስ ነገሡ፣ የላርሳ ንጉሥ ሱሙኤል ኪሽን አሸነፈ። 1795 ዓክልበ. የባቢሎን ንጉሥ ሱሙ-አቡም ላርሳን አሸነፈው፣ ካዛሉንም ያዘ። ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ በጤቤስ ነገሠ። 1793 ዓክልበ. ሱሙላኤል በባቢሎን ነገሠ። 1792 ዓክልበ. ሱሙኤል ካዛሉን አሸነፈው። 1791 ዓክልበ. ሱሙላኤል ካዛሉን አሸነፈው። ረንሰነብ፣ ሆር አዊብሬ በጤቤስ፣ አሙ አሆተፕሬ በጌሤም ነገሠ። 1790 ዓክልበ. 2 ፑዙር-አሹር በአሦር ነገሠ። 1786 ዓክልበ. ሸሺ መዓይብሬ በጌሤም ነገሠ። 1785 ዓክልበ. ሱሙላኤል ኪሽን ዘረፈው። ሊፒት-ኤንሊል በኢሲን ነገሠ። 1783 ዓክልበ. ሰኸምሬኹታዊ ኻውባው በጤቤስ ነገሠ። 1782 ዓክልበ. ናራም-ሲን በአሦር ነገሠ። 1781 ዓክልበ. ጀድኸፐረው፣ ሰጀፋካሬ በጤቤስ ነገሡ። 1780 ዓክልበ. ሱሙኤል ኒፑርን ከኢሲን ያዘ፤ ኤራ-ኢሚቲ በኢሲን ነገሠ። 1779 ዓክልበ. ሱሙላኤል ኪሽን አጠፋው። 1778 ዓክልበ. ሱሙላኤል ካዛሉን አሸነፈው። ሰውሃን በጎጆሰን ነገሠ። 1777 ዓክልበ. ኤራ-ኢሚቲ ኒፑርን ከላርሳ ያዘ። 1776 ዓክልበ. ኑር-አዳድ በላርሳ ነገሠ፤ ኤራ-ኢሚቲ ኪሡራን ያዘ። ኹታዊሬ ወጋፍ በጤቤስ ነገሠ። 1775 ዓክልበ. ኤራ-ኢሚቲ ካዛሉን ዘረፈ። 1774 ዓክልበ. ኸንጀር በጤቤስ ነገሠ። 1772 ዓክልበ. ኤንሊል-ባኒ በኢሲን ነገሠ። 1771 ዓክልበ. 2 ኢፒቅ-አዳድ በኤሽኑና ነገሠ። 1770 ዓክልበ. አሱል በጎጆሰን ነገሠ። 1769 ዓክልበ. ሤ ባቻይና ነገሠ። 1766 ዓክልበ. ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው በጤቤስ ነገሠ። 1760 ዓክልበ ሲን-ኢዲናም በላርሳ፣ ሑርፓቲዋ በካነሽ ነገሠ። 1757 ዓክልበ. ሲን-ኢዲናም ባቢሎንን ድል አደረገው፤ ሳቢዩም በባቢሎን ነገሠ። 1755 ዓክልበ. ሲን-ኢዲናም ኤሽኑናን ዘረፈው። 1754 ዓክልበ. ሲን-ኢዲናም ኒፑርን ከኢሲን ያዘ። ሰኸተፕካሬ አንተፍ በጤቤስ ነገሠ። 1753 ዓክልበ. ሲን-ኤሪባም በላርሳ ነገሠ፤ ነህሲ በጌሴም ነገሠ። 1752 ዓክልበ. የባቢሎን ንጉሥ ሳቢዩም ላርሳን አሸነፈው። ኑያ፣ ሺነህ በጌሴም ነገሡ። 1751 ዓክልበ. ሲን-ኢቂሻም በላርሳ ነገሠ። 1749 ዓክልበ. ዛምቢያ በኢሲን ነገሠ። 1747 ዓክልበ. ሲን-ኢቂሻም በኢሲን፣ ኤላም፣ ባቢሎንና ካዛሉ ኃያላት ላይ ድል አደረጋቸው፤ ኢተርፒሻ በኢሲን ነገሠ፣ ሸንሸክ በጌሤም ነገሠ። 1746 ዓክልበ. ሲሊ-አዳድ በላርሳ ነገሠ። ዋዛድ በጌሤም ነገሠ። 1745 ዓክልበ. ኤላማዊ-አሞራዊ አለቃ ኩዱር-ማቡግ ኢፒቅ-አዳድን ድል አደረገው፣ በሲሊ-አዳድም ፋንታ ልጁን ዋራድ-ሲንን በላርሳ ሾመው። 1 ሻምሺ-አዳድ በተርቃ ንጉሥ ሆነ፣ ቡ ጅያንግ በቻይና ነገሠ። የዛልፓ ንጉሥ ኡሕና የአሦራውያን ካሩም በካነሽ አቃጠለ። 1744 ዓክልበ.- ኡርዱኩጋ በኢሲን ነገሠ። ሴት መሪብሬ በጤቤስ ነገሠ። 1743 ዓክልበ. ዋራድ-ሲን ካዛሉን አሸነፈው። አፒል-ሲን በባቢሎን ነገሠ። ሉሉቢ አሦርን አሸነፉ። 1742 ዓክልበ. ኢፒቅ-አዳድ አራጳን ያዘ፤ ያዕቆብ-ሃር በጌሤም ነገሠ። 1741 ዓክልበ. ሲን-ማጊር በኢሲን ነገሠ። 3 ሶበክሆተፕ በግብጽ ነገሠ፤ ኢፒቅ-አዳድ ኑዚን ያዘ። 1735 ዓክልበ. ኖዕል በጎጆሰን ነገሠ። 1734 ዓክልበ. ሪም-ሲን በላርሳ ነገሠ። 1731 ዓክልበ. ዳሚቅ-ኢሊሹ በኢሲን ነገሠ። 1730 ዓክልበ. 2 ኤሪሹም በአሦር ነገሠ። 1729 ዓክልበ. ናራም-ሲን በኤሽኑና ነገሠ። 1726 ዓክልበ. ዳሚቅ-ኢሊሹ ኒፑርን ከላርሳ ያዘ። 1725 ዓክልበ. ሲን-ሙባሊት በባቢሎን ነገሠ። 1723 ዓክልበ. ሻምሺ-አዳድ ኤካላቱምን ያዘ፤ ያኽዱን-ሊም በማሪ ነገሠ። 1722 ዓክልበ. ሱሙ-ኤፑኽ በያምኻድ ነገሠ። 1721 ዓክልበ. ሪም-ሲን ባቢሎንንና ኡሩክን መታ። 1720 ዓክልበ. ሻምሺ-አዳድ አሹርን ይዞ በአሦር ንጉሥ ሆነ፤ ያኽዱን-ሊም በያሚናውያን ላይ ዘመተ። 1719 ዓክልበ. ያኽዱን-ሊም ሻምሺ-አዳድን አሸነፈ። 1715 ዓክልበ. ሪም-ሲን ኪሡራን ያዘ፤ ደርንም አጠፋ። 1714 ዓክልበ. ሪም-ሲን ኡሩክን አጠፋ፤ ኒፑርን ከኢሲን መለሰ። 1712 ዓክልበ. ሲን-ሙባሊት ሪም-ሲንን አሸነፈው፤ ዳዱሻ በኤሽኑና ነገሠ። ያክዱን-ሊም ሻምሺ-አዳድን በናጋር አሸነፈው። 1709 ዓክልበ. ሲን-ሙባሊት ኢሲንን ያዘ። 1707 ዓክልበ. ሻምሺ-አዳድ ያህዱን-ሊምን አሸነፈው። ዝምሪ-ሊም ወደ ያምኻድ ሸሸ። 1705 ዓክልበ. ሪም-ሲን ኢሲንን ከባቢሎን ያዛ። ሃሙራቢ በባቢሎን ነገሠ። 1704 ዓክልበ. የሃሙራቢ ሕገ መንግሥት በባቢሎን ተዋጀ። 1701 ዓክልበ. 1 ነፈርሆተፕ በግብጽ ነገሠ። 17ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 1700 ዓክልበ. ዋርሻማ በካነሽ ነገሠ። 1699 ዓክልበ. የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ኡሩክንና ኢሲንን ከላርሳ ያዘ። 1694 ዓክልበ. 1 ሻምሺ-አዳድ ልጁን ያስማ-አዳድ በማሪ መንግሥት ላይ ሾመው። 1691 ዓክልበ. የአሦር ንጉስ ሻምሺ-አዳድ ቱሩካውያንን ድል አደረጋቸው። 1690 ዓክልበ. ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ በግብጽ ነገሠ። 1688 ዓክልበ. 1 እሽመ-ዳጋን በአሦር ነገሠ። 1687 ዓክልበ. ጅዮንግ በቻይና ነገሠ። 1684 ዓክልበ. መርሆተፕሬ 5 ሶበክሆተፕ በግብጽ ነገሠ። 1680 ዓክልበ. ኻሆተፕሬ 6 ሶበክሆተፕ በግብጽ ነገሠ። 1678-1672 ዓክልበ. እርስ በርስ ጦርነት በአሦር፣ አሹር-ዱጉልና ሌሎች ተወዳዳሪዎች ነገሡ። 1676 ዓክልበ. ሃሙራቢ ኤላምን፣ ማርሐሺን፣ ጉቲዩምን፣ ኤሽኑናን፣ ሱባርቱን አሸነፋቸው። ዋሂብሬ ኢቢያው በግብጽ ነገሠ። ዶሄ በጎጆሰን ነገሠ። 1675 ዓክልበ. ሃሙራቢ የላርሳ ንጉሥ ሪም-ሲንን ድል አደረገው። 1674 ዓክልበ. ሃሙራቢ ጉቲዩምን፣ ኤሽኑናን፣ ሱባርቱን አሸነፋቸው። 1673 ዓክልበ. ሃሙራቢ ማሪን ኤካላቱምንና ሱባርቱን ያዘ። 1672 ዓክልበ. ቤሉባኒ በአሦር ነገሠ። 1669 ዓክልበ. ሃሙራቢ ጉቲዩምን፣ ቱሩኩን፣ ሱባርቱን አሸነፋቸው። ጂን በቻይና ነገሠ። 1667 ዓክልበ. ሃሙራቢ ሱባርቱን አሸነፈ። 1665 ዓክልበ. መርነፈሬ አይ በግብጽ ነገሠ። 1662 ዓክልበ. ሳምሱ-ኢሉና በባቢሎን ነገሠ፤ ሊባያ በአሦር ነገሠ። ፒጣና ካነሽን ያዘ፣ ልጁ አኒታ የሐቲና ዛልፓ ንጉሥ ፒዩሽቲን አሸነፈው። 1661 ዓክልበ. ዘጸአት ሙሴ ዕብራውያንን ከግብጽ ወደ ሲና መራ (መ. ኩፋሌ)። መርሆተፕሬ ኢኒ በጤቤስ ገዛ፤ ሂክሶስ የተባሉት አሞራውያን ግብጽን ወረሩ፤ ሳኪር-ሃር በስሜኑ ገዛ። ኮንግ ጅያ በቻይና ነገሠ። 1659 ዓክልበ. ሰዋጅተው በጤበስ ነገሠ። 1656 ዓክልበ. ኢነድ በጠቤስ ነገሠ። 1654 ዓክልበ. ሳምሱ-ኢሉና ካሳውያንን ድል አደረገ። 1653 ዓክልበ. ሳምሱ-ኢሉና ኤሙትባል፣ ኡሩክ፣ ኢሲን ድል አደረጋቸው። ሰዋጅካሬ ሆሪ በጠቤስ ነገሠ። 1652 ዓክልበ. ሳምሱ-ኢሉና አመጽ በአካድ አሸነፈ፣ ላርሳን አጠፋ። ጋው በሥያ ቻይና ነገሠ። 1651 ዓክልበ. ሳምሱ-ኢሉና አመጽ በሱመርና አካድ አሸነፈ። 1649 ዓክልበ. ፋ በቻይና ነገሠ። 1648 ዓክልበ. 7 ሶበክሆተፕ በጤቤስ ነገሠ፡ 1646 ዓክልበ. 1 ሻርማ-አዳድ በአሦር ነገሠ። ጀሁቲ በጤቤስ ነገሠ፤ የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት ነፃ ሆነ። 1645 ዓክልበ. የኢሲን ገዥ ኢሉማ-ኢል በደቡብ ሱመር ወይም ከላውዴዎን እንደገና ከሳምሱ-ኢሉና በዓመጽ ተነሥቶ «የባሕር ምድር» የሚባል ግዛት መሠረተ። 1643 ዓክልበ. ሳምሱ-ኢሉና ኤሽኑናን መታ። 8 ሶበክሆተፕ በጤቤስ ነገሠ። 1642 ዓክልበ. አፐር-አናቲ በሂክሶስ ነገሠ። የመሬት መንቀጥቀጥ በቻይና፣ ጄ ንጉሥ ሆነ። 1640 ዓክልበ. ሳምሱ-ኢሉና ሱሳን አጠፋ። 1638 ዓክልበ. ሕያን በሂክሶስ ነገሠ። 1637 ዓክልበ. 3 ነፈርሆተፕ በጤቤስ ነገሠ። ዙዙ በካነሽ ነገሠ። 1636 ዓክልበ. መንቱሆተፒ በጤቤስ ነገሠ። 1635 ዓክልበ. 1 ነቢሪራው በጤቤስ ነገሠ። 1634 ዓክልበ. ኢፕታር-ሲን በአሦር ነገሠ። 1633 ዓክልበ. ሁለተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በቻይና። 1628 ዓክልበ. ቱድሐሊያ የኬጥያውያን መንግሥትን መሠረተ ታንግ የሻንግ ልዑል ሆነ። 1627 ዓክልበ. ሳምሱ-ኢሉና አሞራውያንን አሸነፈ። 1624 ዓክልበ. አቢ-ኤሹህ በባቢሎን ነገሠ። 1623 ዓክልበ. ባዛያ በአሦር ነገሠ። 1621 ዓክልበ. አቢ-ኤሹህ ካሳውያንን ድል አደረገ። ዕብራውያን አሞራውያንን (ዐግን) አሸነፉ። 1619 ዓክልበ. አሃን በጎጆሰን ነገሠ። 1614 ዓክልበ. 2 ነቢሪራው በጤቤስ ነገሠ። 1613 ዓክልበ. ሰመንሬ በጤቤስ ነገሠ። 1612 ዓክልበ. በቢአንኽ በጤቤስ ነገሠ። 1611 ዓክልበ. የሚንግትያው ውግያ፦ የሻንግ ንጉሥ ታንግ ቻይናን ከሥያ መንግሥት ያዘ። 1605 ዓክልበ. ሕሽሚ-ሻሩማ በኬጥያውያን ነገሠ። 1602 ዓክልበ. ሻሙቄኑ በሂክሶስ ነገሠ። 16ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 1600 ዓክልበ. ሰኸምሬ ሸድዋሰት በጤቤስ ነገሠ። ዋይ ቢንግ በሻንግ (ቻይና) ነገሠ። 1597 ዓክልበ. የባቢሎን ንጉሥ አቢ-ኤሹህ ኤሽኑናን አሸነፈ። ዦንግ ረን በሻንግ ነገሠ። 1596 ዓክልበ. አሚ-ዲታና በባቢሎን ነገሠ፤ ሉላያ በአሦር ነገሠ። ሂክሶስ የአቢዶስ መንግሥት ያዙ። 1595 ዓክልበ. 1 ደዱሞስ በጤቤስ ነገሠ። 1594 ዓክልበ. ሞንተምሳፍ በጤቤስ ነገሠ። 1593 ዓክልበ. አፐፒ በሂክሶስ ነገሠ። መራንኽሬ 6 መንቱሆተፕ በጤቤስ ነገሠ። ታይ ጅያ በሻንግ ነገሠ። 1592 ዓክልበ 4 ሰኑስረት በጤቤስ ነገሠ። 1591 ዓክልበ. 2 ደዱሞስ በጤቤስ ነገሠ። 1590 ዓክልበ. የሂክሶስ ፈርዖን አፐፒ ጤቤስን ማረከ። ሹ-ኒኑዓ በአሦር ነገሠ። 1588 ዓክልበ. ራሆተፕ በጤቤስ ነገሠ። (17ኛው ሥርወ መንግሥት) 1587 ዓክልበ. ኢያሱ ወልደ ነዌ አርፎ ቄኔዝ በእስራኤል ፈራጅ ሆነ (ፊሎ)። የያምኻድ ንጉሥ እርካብቱም ከ«ሃቢሩ» ጋር ስምምነት ያደርጋል። 1584 ዓክልበ. 1 ሶበከምሳፍ በጤቤስ ነገሠ። 1582 ዓክልበ. 1 ላባርና በሐቲ (ኬጥያውያን መንግሥት) ነገሠ። 1581 ዓክልበ. ዎ ዲንግ በሻንግ ነገሠ። 1577 ዓክልበ. 2 ሶበከምሳፍ፣ 5 አንጠፍ በጤቤስ ነገሠ። 1576 ዓክልበ. 2 ሻርማ-አዳድ በአሦር ነገሠ። 1574 ዓክልበ. 6 አንጠፍ በጤቤስ ነገሠ። 1573 ዓክልበ. 3 ኤሪሹም በአሦር ነገሠ። 1568 ዓክልበ. 7 አንጠፍ በጤቤስ ነገሠ። 1567 ዓክልበ. ሰናኽተንሬ አሕሞስ በጤበስ ነገሠ። 1566 ዓክልበ. ሰቀነንሬ ታዖ በጤቤስ ነገሠ። 1563 ዓክልበ. ካሞስ በጤቤስ ነገሠ። 1562 ዓክልበ. ታይ ገንግ በሻንግ ነገሠ። 1561 ዓክልበ. 2 ሻምሺ-አዳድ በአሦር ነገሠ። 1560 ዓክልበ. ኻሙዲ በሂክሶስ ነገሠ። 1559 ዓክልበ. አሚ-ሳዱቃ በባቢሎን ነገሠ። 1 ሐቱሺሊ በሐቲ ነገሠ። 1558 ዓክልበ. 1 አሕሞስ በጤቤስ ነገሠ። (18ኛው ሥርወ መንግሥት) 1555 ዓክልበ. 2 እሽመ-ዳጋን በአሦር ነገሠ። 1550 ዓክልበ. በሶርያ የተገኘው ቅርስ «ቲኩናኒ ፕሪዝም» የ«ሃቢሩ» ቅጥረኞች ስሞች ይዘርዝራል። 1548 ዓክልበ. አሕሞስ ሂክሶስን ከግብጽ ወደ ሻሩሄን አባረራቸው። 1542 ዓክልበ. አሕሞስ ሻሩሄንን ከሂክሶስ ያዘ። 1539 ዓክልበ. 3 ሻምሺ-አዳድ በአሦር ነገሠ። 1538 ዓክልበ. ሳምሱ-ዲታና በባቢሎን ነገሠ። 1537 ዓክልበ የአሕሞስ ባሕር ኃይል በጌባል፣ ፊንቄ አካባቢ ዘመተ። ሥያው ጅያ በሻንግ ነገሠ። 1536 ዓክልበ. 1 ሙርሲሊ በሐቲ ነገሠ። 1534 ዓክልበ. 1 አመንሆተፕ በግብጽ ነገሠ። 1530 ዓክልበ. ዜቡል በእስራኤል ፈራጅ ሆነ (ፊሎ)። 1524 ዓክልበ. 1 አሹር-ኒራሪ በአሦር ገዛ። 1520 ዓክልበ. ዮንግ ጂ በሻንግ ነገሠ። 1513 ዓክልበ. 1 ቱትሞስ በግብጽ ነገሠ። በኩሽ ከ፪ኛው እስከ ፫ኛው የአባይ ሙላት ድረስ ያዘ። 1512 ዓክልበ. 1 ቱትሞስ በሶርያና ናሓሪን (ሑራውያን) ላይ ዘመተ። 1510 ዓክልበ. 1 ቱትሞስ በኩሽ ከ፫ኛው እስከ ፬ኛው የአባይ ሙላት ድረስ ያዘ። 1508 ዓክልበ. 1 ሙርሲሊ ሐለብን ይዞ ያምኻድን ጨረሰ። ታይ ዉ በሻንግ ነገሠ። 1507 ዓክልበ. ኬጢያውያን ባቢሎንን አሸነፉ። የካሳውያን ንጉስ 2 አጉም የባቢሎን ገዢ ሆነ፤ የባቢሎንን ስም ወደ «ካርዱንያሽ» ቀየሩት። ኪርታ የሚታኒ መንግሥት በሑራውያን ላይ መሠረተ። 1 ሐንቲሊ በሐቲ ነገሠ። 1505 ዓክልበ. እስራኤል ለአራም-ናሓራይን ንጉስ ኲሰርሰቴም ተገዛ። 1501 ዓክልበ. 2 ቱትሞስ በግብጽ ነገሠ። 15ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 1500-1400 ገ. የኪዳኑ ስርወ መንግሥት በኤላም 1499 ዓክልበ. 3 ፑዙር-አሹር በአሦር ገዛ። 1497 ዓክልበ. ጎቶንያል በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 1 ሹታርና በሚታኒ ነገሠ። 1491 ዓክልበ. 1 ዚዳንታ፣ አሙና በሐቲ (ኬጥያውያን መንግሥት) ነገሡ። አርዛዋና ኪዙዋትና ከሐቲ ነጻ ሆኑ። 1488 ዓክልበ. 1 ሑዚያ፣ ተለፒኑ በሐቲ ነገሡ። 1487 ዓክልበ. ንግሥት ሃትሸፕሱት በግብፅ ነገሠች። 1483 ዓክልበ. 1 ቡርና-ቡርያሽ በካራንዱኒያሽ (ባቢሎን) ነገሠ። ታሑርዋይሊ፣ አሉዋምና በሐቲ ነገሡ። 1480 ዓክልበ ፓርሻታታር ባራታርና?) በሚታኒ ነገሠ፣ ሐለብን ያዘ። 1478 ዓክልበ. 2 ሐንቲሊ በሐቲ ነገሠ። የግብጽ ትልቅ ጉዞ ወደ «ፑንት» ተደረገ። 1476 ዓክልበ. 1 ኤንሊል-ናሲር በአሦር ገዛ። 1473 ዓክልበ. 3 ካሽቲሊያሽ በካራንዱኒያሽ ነገሠ። 2 ዚዳንታ በሐቲ ነገሠ። «ሃቢሩ» ከሐለብ መስፍን ኢድሪሚ ጋር ተባብረው አላላኽን ለመያዝ ረዱት፣ የሙኪሽ ግዛት መሠረተ። 1466 ዓክልበ. 3 ቱትሞስ ለብቻው በግብፅ ነገሠ። የመጊዶ ውጊያ ቱትሞስ የመጊዶና የቃዴስ አለቆችን አሸነፈ። 1465 ዓክልበ. ሙኪሽ ለሚታኒ ተገዥ ሆነ፣ ኪዙዋትናም ከሐቲ ወደ ሚታኒ ተጽእኖ አለፈ። 1463 ዓክልበ. ኡላም-ቡርያሽ በካርዱንያሽ ነገሠ፤ «የባሕር ምድር»ን ያዘ፤ ኑር-ኢሊ በአሦር ገዛ። 1459-50 ዓክልበ. ቱትሞስ በፊንቄ፣ ሙኪሽ፣ ሚታኒ ላይ በየዓመቱ ይዘምታል። 1458 ዓክልበ. 2 ሑዚያ በሐቲ ነገሠ። 1457 ዓክልበ. እስራኤል ለሞአብ ንጉሥ ኤግሎም ተገዛ። ሻውሽታታር በሚታኒ ነገሠ። 1451 ዓክልበ. 1 አሹር-ራቢ በአሦር መንግሥቱን ከአሹር-ሻዱኒ ያዘ። 1450 ዓክልበ. ሙኪሽ ድል ሆኖ ለቱትሞስ ተገበረ። 1449 ዓክልበ. ቱትሞስ በሻሱ ወገን ላይ ዘመተ። 1447 ዓክልበ. 3 አጉም በካራንዱኒያሽ ነገሠ። 1446 ዓክልበ. ቱትሞስ እንደገና በፊንቄና ሶርያ ይዘምታል። 1441 ዓክልበ. 1 አሹር-ናዲን-አሔ በአሦር ነገሠ። 1439 ዓክልበ. ናዖድ በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 1438 ዓክልበ. 1 ሙዋታሊ በሐቲ ነገሠ። 1436 ዓክልበ. ቱትሞስ በኩሽ ላይ ዘመተ፣ እስከ ናፓታ ድረስ ገዛ። 1435 ዓክልበ. 2 አመንሆተፕ የጋርዮሽ ፈር ዖን ተደርገው የሃትሸፕሱትን ስም ከብዙ ሐውልቶች ደመሰሰ። 1433 ዓክልበ. ዦንግ ዲንግ በሻንግ ነገሠ። 1 ቱድሐሊያ በሐቲ ነገሠ። 2 አመንሆተፕ ለብቻው በግብፅ ነገሠ። 1432 ዓክልበ. 2 ኤንሊል-ናሲር በአሦር ገዛ። 1431 ዓክልበ. 1 ካዳሽማን-ሃርቤ በካራንዱኒያሽ ነገሠ። 1428 ዓክልበ. ቱድሐሊያ ኪዙዋትናን ወርሮ ያዘው። 1426 ዓክልበ. ግብጽ ስምምነት ተዋውሎ የሶርያ ጦርነቶች ለጊዜው ጨረሱ። 1425 ዓክልበ. 2 አሹር-ኒራሪ በአሦር ነገሠ። 1424 ዓክልበ. ዋይ ረን በሻንግ ነገሠ። 1419 ዓክልበ. አሹር-በል-ኒሸሹ በአሦር ገዛ። 1417 ዓክልበ. -አርታታማ በሚታኒ ነገሠ። 1415 ዓክልበ. ካራ-ኢንዳሽ በካራንዱኒያሽ ነገሠ። 1414 ዓክልበ. ሄ ዳን ጅያ በሻንግ ነገሠ። 1411 ዓክልበ. አሹር-ረም-ኒሸሹ በአሦር ገዛ። 1409 ዓክልበ. 4 ቱትሞስ በግብፅ ነገሠ። 1408 ዓክልበ. 1 አርኑዋንዳ በሐቲ ነገሠ። 1407 ዓክልበ. -2 ሹታርና በሚታኒ ነገሠ። 1405 ዓክልበ. ዙ ዪ በሻንግ ነገሠ። 1403 ዓክልበ. 2 አሹር-ናዲን-አሔ በአሦር ገዛ። 1400-1210 ገ. የኢጊሃልኪ ሥርወ መንግሥት በኤላም 14ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 1393 ዓክልበ. 1 ኤሪባ-አዳድ በአሦር ገዛ። 1383 ዓክልበ. 1 ካዳሽማን-ኤንሊል በካርዱንያሽ ነገሠ። 1368 ዓክልበ. 2 ቡርናቡርያሽ በካርዱንያሽ ነገሠ። 1366 ዓክልበ. ሚታኒ በኬጢያውያን ግፊት ሲወድቅ የአሦር ንጉስ 1 አሹር-ኡባሊት ነጻነቱን አዋጀ። 1359 ዓክልበ. እስራኤል ለከነዓን ንጉሥ ኢያቢስ ተገዛ። 1357 ዓክልበ. የግብጽ ፈርዖን 4 አመንሆተፕ ስሙን ወደ አኸናተን ቀይሮ የጸሐይ ጣኦት አተን አምልኮት ብቻ ወይም ሞኖቴይስም የግብጽ መንግሥት ሃይማኖት አደረገው። 1341 ዓክልበ. ካዳሽማን-ሐርቤ በካርዱንያሽ ነገሠ። ካሳውያን አምጸው ገደሉትና ናዚ-ቡጋሽ ሾሙ። አሹር-ኡባሊት ግን ቂሙን በቅሎ ወረራቸውና 2 ኩሪጋልዙን አቆመ። 1340 ዓክልበ. ቱታንኻተን በግብጽ ነገሠ። 1339 ዓክልበ. ዲቦራ እና ባርቅ በእስራኤል ፈራጆች ሆኑ። 1338 ዓክልበ. ቱታንኻተን ስሙን ወደ ቱታንኻመን ቀይሮ የቀድሞ ፖሊቴይስም መንግሥት ሃይማኖት አስመለሰ። 1335 ዓክልበ. 2 ኩሪጋልዙ ለጊዜው ኤላምን ወረረ። 1331 ዓክልበ. አይ በግብጽ ፈርዖን ሆነ። ኤንሊል-ኒራኒ በአሦር ነገሠ፤ ኩሪጋልዙንም ድል አደረገ። 1330 ዓክልበ. 2 አርኑዋንዳ፣ 2 ሙርሲሊ በኬጥያውያን ነገሠ። 1327 ዓክልበ. ሆረምኸብ በግብጽ ፈርዖን ሆነ። 1322 ዓክልበ. አሪክ-ደን-ኢሊ በአሦር ነገሠ። 1316 ዓክልበ. ናዚ-ማሩታሽ በካርዱንያሽ ነገሠ። 1311 ዓክልበ. 1 አዳድ-ኒራሪ በአሦር ነገሠ። 1303 ዓክልበ. 2 ሙዋታሊ በኬጥያውያን ነገሠ። 13ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 1299 ዓክልበ. እስራኤል ለምድያም ተገዛ። 1292 ዓክልበ. ጌዴዎን በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 1290 ዓክልበ. የአሦር ንጉስ 1 አዳድ-ኒራሪ የሚታኒን መንግሥትና ካሳውያንን አሸነፈ። ካዳሽማን-ቱርጉ በካሳውያን (በካርዱንያሽ) ነገሠ። 1280 ዓክልበ. ስልማናሶር 1 በአሦር ነገሠ። 1272 ዓክልበ. 2 ካዳሽማን-ኤንሊል በካሳውያን ነገሠ። 1263 ዓክልበ. ኩዱር-ኤንሊል በካሳውያን ነገሠ። 1254 ዓክልበ. ሻጋራክቲ-ሹሪያሽ በካሳውያን ነገሠ። 1252 ዓክልበ. አቢሜሌክ በሴኬም ንጉሥ ሆነ። 1251 ዓክልበ. 1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ በአሦር፣ 1249 ዓክልበ. ቶላ በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 1241 ዓክልበ. 4 ካሽቲሊያሽ በካሳውያን ነገሡ። 1240 ገ. ካሳዊ ንጉስ 4 ካሽቲሊያሽ ከኤላም ጋር ሲዋጋ አላከናወነም። 1233 ዓክልበ. ቱኩልቲ-ኒኑርታ ካውሳውያንን ድል አድርጎ ኤንሊል-ናዲን-ሹሚ በካርዱንያሽ ሾመ። 1232 ዓክልበ. የኤላም ንጉሥ ኪዲን-ሑትራን የካሳውያን ገዢ ኤንሊል-ናዲን-ሹሚን ገደለ፤ 2 ካዳሽማን-ሐርቤ በካሳውያን ለአሦር ገዛ። 1231 ዓክልበ. አዳድ-ሹም-ኢዲና በካሳውያን ለአሦር ገዛ። 1230 ዓክልበ. አዳድ-ሹማ-ኢዲና በኤላም ላይ አሸነፈ። 1226 ዓክልበ. ኢያዕር በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 1225 ዓክልበ. ካሳውያን ከአሦር አምጸው አዳድ-ሹም-ኡጹር በካሳውያን ነገሠ። 1215 ዓክልበ. አሹር-አዲን-አፕሊ በአሦር ነገሠ። 1211 ዓክልበ. 3 አሹር-ኒራሪ በአሦር ነገሠ። 1210-1100 ግ. የሹትሩክ ሥርወ መንግስት በኤላም 1205 ዓክልበ. ኤንሊል-ኩዱሪ-ኡጹር በአሦር ነገሠ። 1204 ዓክልበ. እስራኤል ለአሞናውያን ተገዛ። 1200 ዓክልበ. ኒኑርታ-አፓል-ኤኩር በአሦር ነገሠ። 12ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 1195 ዓክልበ. መሊ-ሺፓክ በካርዱንያሽ ነገሠ። 1190 ገ. የኬጢያውያን መንግሥት በሙሽኪ (ፍሩጋውያን) ግፊት ወደቀ። 1186 ዓክልበ. 1 አሹር-ዳን በአሦር ነገሠ። ዮፍታሔ የአሞንን ሰዎች አሸነፈ፣ በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 1184 ዓክልበ. የኤላም ንጉሥ ሹትሩክ-ናሑንተ ከካሳውያንን ጋር ሲዋጋ የሃሙራቢ ሕገጋት የተጻፈበትን ድንጋይ ከመማረኩ በላይ የማርዱክና የማኒሽቱሹ ጣኦታትና የናራም-ሲን ሐውልት ወደ ሱስን ማረከባቸው። 1180 ዓክልበ. ማርዱክ-አፕላ-ኢዲና በካርዱንያሽ ነገሠ። ኢብጻን በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 1173 ዓክልበ. ኤሎም በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 1166 ዓክልበ. ኤንሊል-ናዲን-አሔ በካርዱንያሽ ነገሠ። 1164 ዓክልበ. ዛባባ-ሹም-ኢዲና በካርዱንያሽ ነገሠ። 1163 ዓክልበ. የኤላም ንጉሥ ሹትሩክ-ናሑንተ ካሳውያንን በፍጹም ድል አደረጋቸው። 1163 ዓክልበ. ዓብዶን በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 1155 ዓክልበ. እስራኤል ለፍልስጥኤም ተገዛ። 1141 ዓክልበ. 1 አሹር-ረሽ-ኢሺ በአሦር ነገሠ። 1140 ዓክልበ. የአሦር ንጉስ 1 አሹር-ረሽ-ኢሺ በአሞራውያን አገር በባቢሎንን ንጉሥ 1 ናቡከደነጾር ላይ አሸነፈ። 1135 ዓክልበ. እስራኤል በሶምሶን መሪነት ለፍልስጥኤም ተገዛ። 1130 ግ. ሱስን ለባቢሎን ንጉሥ ለ1 ናቡከደነጾር ወደቀና የኤላም ንጉሥ ሑተሉሽ-ኢንሹሺናክ ወደ አንሻን ሸሸ። 1122 ዓክልበ. 1 ቴልጌልቴልፌልሶር በአሦር ነገሠ። 1115 ዓክልበ. ኤሊ በእስራኤል ፈራጅ ሆነ። 11ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 1076 ዓክልበ. ፍልስጥኤማውያን ታቦትን ማረኩ። 1075 ዓክልበ. ሳሙኤል ፍልስጥኤማውያንን አሸንፎ ታቦት ወደ ቂርያት ሔደ። 1055 ዓክልበ. ሳኦል በእስራኤል ነገሠ። 1015 ዓክልበ. ዳዊት በእስራኤል (ኬብሮን) ነገሠ። 1008 ዓክልበ. ዳዊት በኢየሩሳሌም ነገሠ። 10ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 992-987 የባቢሎን ንጉሥ ማር-ቢቲ-አፕላ-ኡሹር ነገሠ። 975 ሰሎሞን በእስራኤል ነገሠ። 972 ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ለያህዌ ቤተ መቅደስ ሠራ። 936 የእስራኤል መንግሥት ተከፋፈለ። ኢዮርብዓም በእስራኤል፣ ሮብዓም በይሁዳ ነገሱ። 919 2 አዳድ ኒራሪ ንጉሥ ሆኖ የአሦር ሃይል ታደሰ። 9ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 891 የአሦር ንጉስ አሹር-ናሲር-ፓል ነግሦ ያለ ምኅረት ጠረፎቹን ያስፋፋ ጀመር። 866 3 ስልምናሶር በአሦር ነገሠ። 861 የእስራኤል ንጉሥ አካብ ከአሦር ጋር በቃርቃር ውግያ ተዋጋ፤ እንዲሁም ከሶርያ (አራም) ጋር ሲዋጋ ይገደላል። 849 የእስራኤል ንጉሥ ኢዩ ግብር ለስልምናሶር ከፈለ። 831 5ኛ ሻምሺ-አዳድ በአሦር ነገሠ። 818-790 3 አዳድ-ኒራሪ በአሦር ነገሠ። 8ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 784 ገ. አልያቴስ በልድያ ነገሠ። 755 አሦር በብሔራዊ ጦርነት ተይዞ ባቢሎን በንጉሱ ናቦፖላሣር መሪነት ነጻነቱን አዋጀ። 753 ዓክልበ. (ሚያዝያ) ፎሐ (ፑሉ) የሚባል አለቃ የአሦር መንግሥት ቀምቶ 3 ቴልጌልቴልፌልሶር ተብሎ ንጉስ ሆነ። 751-725 የኤላም ንጉሥ ሑምባኒጋሽ ነገሠ። 748 ቴልጌልቴልፌልሶር አርፋድን አጠፋ፤ ሐማትንም ያዘ። 746 ቴልጌልቴልፌልሶር ፊልሥጥኤምን ወርሮ የእስራኤልን ንጉስ ምናሔምን 1000 መክሊት ብር አስገበረ። 740 የእስራኤል ንጉስ ፋቁሔ ከሶርያ (አራም) ንጉስ ረአሶን ጋራ አደጋ በይሁዳ ላይ ሲጣሉ የይሁዳ ንጉሥ አካዝ የመቅደሱን ወርቅ ሰጥቶ ከቴልጌልቴልፌልሶር እርዳታ ጠየቀ። 737 ቴልጌልቴልፌልሶር ወደ ባቢሎን ወርዶ ንጉሱን ናቡ-ሙኪን-ዜሪ ማረከና እራሱ 'የባቢሎን ንጉስ ፑሉ' ተብሎ ዘውዱን ተጫነ። 735 5 ስልምናሶር በአሦር ነገሠ። 733 የእስራኤል ንጉሥ ሆሴዕ ግብርን ባቋረጠ ጊዜ የግብጽ ጠባቂነት አገኘ። ስለዚህ ስልምናሶር ወርሮ ከሦስት አመት ትግል በኋላ ሰማርያን ያዘና የእስራኤልን ቅሬታ ወደ ሌላ አገሮች ሰደዳቸው። 730 ስልምናሶር ሰማርያን እየከበባት ድንገት ከሞተ በኋላ ሻለቃው 2 ሳርጎን ዙፋኑን ያዘ። 718 እና 716 የኤላም ንጉሥ 2ኛ ሹትሩክ-ናሑንተ በ2ኛ ሳርጎን ሠራዊት እጅ ድል ሆነ። 708 የሳርጎን ልጅ ሰናክሬም መሮዳክ-ባላዳንን ገልብጦ የራሱን ልጅ አሹር-ናዲን-ሹሚ በባቢሎን ዙፋን ላይ ንጉስ አደረገው። 702 ሹትሩክ-ናሑንተ በወንድሙ ሐሉሹ ተገድሎ ይህ ሐሉሹ አሹር-ናዲን-ሹሚንና ባቢሎንን ማረከው። 7ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 697 ሰናክሬም ባቢሎንን አጠፋው። 695-660 ጉጌስ በልድያ ነገሠ። 661 የአስራዶን ልጅ አስናፈር ሱስንን ድል አድርጎ ወረራት። እስኩታውያን ሜዶንን ስለወረሩ የፋርስ ነገዶች ከዚያ ወደ አንሻን ፈልሰው ንጉሳቸው ተይስፐስ አንሻንን ማረከው። 660 ገ. መጀመርያ መሐለቅ በልድያ ተሠራ። 660-629 2ኛ አርዲስ በልድያ ነገሠ። 655 የአሦር ንጉስ አስናፈር ሱሳን አጠፋ። 648 አስናፈር ኤላምን በሙሉ ሲያጠፋ እርሻቸውን በጨው ዘራ። 629-618 ገ. ሣድያቴስ በልድያ ነገሠ። 628 ድራኮ የሚባል ጸሃፊ የአቴና ከተማ ሕገጋት ጻፈ፤ ይህም ሕግ እጅግ ጨካኝ ሆኖ ይሙት በቃ ለማንኛውም ጥፋት ወሰነ። 618-568 2ኛ አልያቴስ በልድያ ነገሠ። 600 የአቴና አለቃ ሶሎን አዲስ ሕገ መንግሥት ፈጠረ። 6ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 595 የባቢሎን ምርኮ ይሁዳ በ2ኛ ናቡከደነጾር ተያዘ። 593 የሜዶን ንጉስ ኩዋክሻጥራ ልድያን ባጠቃ ጊዜ፣ በአንድ ታላቅ ውግያ ግርዶሽ ድንገት መጥቶ ከዚያ ቀጥሎ በኪልቅያና በባቢሎን ነገሥታት አማካይነት ስምምነት ተደረገላቸውና ያንጊዜ ሃሊስ ወንዝ የሜዶንና የልድያ ጠረፍ ሆነ። 568-554 ቅሮይሶስ በልድያ ነገሠ። 554 ቅሮይሶስ በፋርስ ንጉሥ በ2ኛ ቂሮስ እጅ ድል ስለ ሆኑ መንግሥቱ ወዲያው የፋርስ ክፍላገር ሆነ። 546 የፋርሶች አሐይመኒድ ነገሥታት ሱሳንን ያዙት። 5ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 457 ሮማውያን መጀመርያ «12ቱ ሰንተረዦች» የተባለውን ሕገ መንግሥት አወጡ። 407 ከአንድ ጨነፈር የተነሣ የሲቡላውያን መጻሕፍት ተማከሩና ሌክቲስቴርኒዩም የተባለው ሥነ ሥርዓት ለአማልክታቸው ጣኦት ተመሠረተ። 4ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 375 ለሲቡላውያን መጻሕፍት 10 ጠባቂዎች በሮማ ተሾሙ። 350 ገ. የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ የሕገ መንግሥት ሀሣብ ለይቶ ዐወቀ። 339 የመቄዶን ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ከፋርስ መንግሥት ጋር ሱሳን አሸነፈው። 301 ከሌላ ጨነፈር ቀጥሎ የሲቡላውያን መጻሕፍት ተማክረው መልሱ ጣኦቱን አይስኩላፒዩስ ወደ ሮማ ከኤፒዳውሮስ (በግሪክ) እንዲያመጡ ሆነ። ሆኖም የሮማ ሴናት በጦርነት ተይዞ ከአንድ ቀን ጸሎት በቀር ስለ አይስኩላፒዩስ ነገር ምንም አላደረገም። 3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 246 'የአበባ ጨዋታዎች' በሲቡላውያን መጻሕፍት ምክር ተመሠረቱ። 224 የካርታጌና አለቃ ሃኒባል የሮማ ጭፍራ በካናይ ፍልሚያ ሲያጠፋ፥ መጻሕፍቱ ተማክረው እንደ ምክራቸው ሁለት ግሪኮችና ሁለት ጋውሎች በሮማ ገበያ በሕይወታቸው ተቀበሩ። 214 የሃን ሥርወ መንግሥት በቻይና ተመሠረተ። 212 በካርታጌና ጦርነት ጊዜ የሮማ አበጋዝ ስኪፒዮ አፍሪካኑስ ከሲቡላውያን መጻሕፍት ምክር የተነሣ የኩቤሌ ጣኦት ከፔሢኖስ አምጥቶ አምልኮቷን በሮማ አስገባ። 2ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 141 ሮማውያን ሰርዴስን ገብተው ልድያ ወዲያው በሮማ መንግሥት ውስጥ የእስያ ጠቅላይ ግዛት ክፍል ሆነ። 1ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. 96-86 የሱላ መሪነት በሮማ 91 የዩፒተር መቅደስ በሮማ ተቃጥሎ የሲቡላውያን መጻሕፍት ጠፉ። 84 የሮማ ላይኛ ምክር ቤት (ሴናት) ተልእኮዎች የሲቡል ትንቢቶች እንዲያገኙ ላኩዋቸው። 71 'በሮማ ሦስት ቆርኔሌዎሶች ሊገዙ ነው' ከሚል ከአንዱ ትንቢት የተነሣ ፑብሊዩስ ቆርኔሌዎስ ሌንቱሉስ ሱራ አንድ ሤራ አደረገ። 63 12 ፕቶለሜዎስ ወደ ግብጽ ዙፋን እንዲመለሱ ሮማውያን ሥራዊቱን መላካቸውን ሲማከሩ፣ መብራቅ በድንገት የዩፒተር ጣኦት መታ። ስለዚህ የሲቡል መጻሕፍቶች ተማክረው 'ከግብጽ አንድ ንጉሥ መቸም እርዳታ ቢለምንሽ፣ ወዳጅነትሽ አይቀርለት እንጂ ጣርና አደጋ እንዳያገኙሽ ሥራዊት ከቶ አትሥጪው' የሚል ትንቢት በመገኘቱ ይህ ቃል የፕቶሎሜዎስን መመለስ በጣም አቆየ። 52 'በጳርቴ ላይ ማሸነፍ የቻለው ንጉሥ ብቻ ይሆናል' ስለሚል ትንቢት ቄሣር በሮማ ሬፑብሊክ ላይ ንጉሥነትን በቶሎ እንደሚይዝ ያለ ጭምጭምታ ተፈጠረ። ዓመተ ምህረት 7 በሮማ ንጉሠ ጢባርዮስ ቄሣር ዘመን የሮማ ቲቤር ወንዝ ሲጎርፍ አንዱ ቄስ የሲቢሊን መጻሕፍት እንዲማከሩ አስቦ ጢባርዮስ ምስጢራዊ ስለቆጠራቸው እምቢ አለ። 17-212 ሃን ስርወ መንግሥት በቻይና 21 የዮሐንስ መጥምቁ ስብከት በይሁዳ ተጀመረ። 26 ግ. የኢየሱስ ስቅለት በኢየሩሳሌም። የኦስሮኤና ንጉሥ 5ኛው አብጋር ክርስትናን እንደ ተቀበለ ይባላል። 34 44 ንግሥት ግርሳሞት ህንደኬ 7ኛ ዘመን በኢትዮጵያ 41 የሮመ ቄሣር ክላውዴዎስ አይሁዶችን ከነክርስቲያኖች ከሮሜ ከተማ አባረራቸው። 71 ደብረ ቬሱቪዩስ እሳተ ገሞራ በኢጣልያ 3 ከተሞችን አጠፋ። 89 ጋን ዪንግ በቻይና አበጋዝ ባን ቻው ወደ ሮማ ተላከ። 108 የሮማ ንጉስ ትራያኑስ ሱሳን ይዞ በአመጽ ምክንያት ቶሎ መመለስ ነበረበት። ይህም ሮማውያን ከሁሉ ወደ ምሥራቅ የደረሱበት ወቅት ነበረ። 218-643 የሳሳኒድ መንግሥት በፋርስ 263 ሮማውያን በፕላኬንቲያ ፍልሚያ[ በአላማኒ ጀርመኖች ከተሸነፉ በኋላ የሲቢሊን መጻሕፍት ተማከሩ። 288 በሮማ ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ትዕዛዝ 'ልድያ' እንደገና የትንሽ ጠቅላይ ግዛት ስም ሆነ። 303 የሮማ ንጉሥ ጋሌሪዎስ አልጋ ላይ ወድቆ ትንሽ ሊያርፍ ሲል በመንግሥቱ ግዛት ውስጥ ላሉት ክርስቲያኖች ሁሉ ይቅርታ ሰጠ። 304 ከሚልቪያን ድልድይ ፍልሚያ አስቀድሞ የተቃዋሚ አለቆች ማክሰንቲያስና ቈስጠንጢኖስ ሲያዘጋጁ ማክሰንቲያስ የሲቢሊንን መጻሕፍት አማከሩና ቈስጠንጢኖስ እምነታቸውን ከአፖሎ ወደ ክርስቶስ አዛወሩ። በፊልሚያውም የማክሰንቲያስ ድል መሆኑ ስመ ጥሩ ድርጊት ነው። 305 ሁለት የጋርዮሽ ቄሣሮች 1ኛ ቈስጠንጢኖስ እና ሊቂኒዎስ የሚላኖ አዋጅን አወጡ። ይህ ህግ ለሰው ሁሉ የሃይማኖት ነጻነት በማረጋገጥ የክርስቲያኖች መሬት ያለ ገደብ እንዲመልስላቸው የሚያዝዝ ነበር። 317 ቆንስጣንጢኖስ የኒቂያ ጉባኤ ጠሩ። 353 የሮማ ንጉሥ ዩሊያኖስ ከሐዲ መንግሥቱን ለጥቂት ጊዜ ወደ ድሮ አረመኔ እምነት መለሠው። 355 የሮማ ንጉሥ ዩሊያኖስ ከሐዲ በጳርቴ ላይ ዘመቻ ሊያደርግ ሲል መጻሕፍቱን አማከረ። ከሮማ የደረሰውም መልስ በዛኛው አመት ጠረፍ መሻገሩን በግልጽ ደገፈው። 372 የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በንጉሡ 1ኛ ቴዎዶስዮስ አዋጅ መሠረት የሮማ መንግስት ሃይማኖት በይፋ ተደረገ። 397 የአሪዮስ ክርስትና ትምህርት አራማጅ የሆነ ስቲሊኮ የሲቡላውያን መጻሕፍት በሮማ እንዳቃጠላቸው ይባላል። 402 ሮማ ከተማ በቪዚጎቶች ተዘረፈች። 430 መጽሐፈ ቴዎዶስዮስ ለምሥራቅ ሮማ ሕገ መንግሥት ሆነ። 443 የሮማ ንጉስ ያሰበሰበው የኬልቄዶን ጉባኤ ክርስቶስ ሁለት የተለያዩ ባሕርዮች እንደነበሩት አዋጀ። 463 የቪዚጎቶች አለቃ ዩሪክ ሕገ መንግሥት አወጣ። 467 የጀርመን አለቃ ኦረስቴስ የሮማ ነጉስን አባርሮ መጨረሻውን ንጉስ ሮሙሉስ አውግስጦስን ሾመ። 492 ገ. የቡርጎንዳውያን፣ የአላማናውያንና የፍራንኮች ሕገጋት ተጻፉ። 498 የቪዚጎቶች አለቃ 2ኛ አላሪክ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስና አንዳንድ የተለያዩ የቀድሞ ሮማ ሐገጋት አከማችተው አዋጁአቸው። 526 መጽሐፈ ዩስጢኒያኖስ ባይዛንታይን ሕገ መንግሥት ወጣ። 571 በቻይና [[የመንግስት ሃይማኖት] የቡዳ ሃይማኖት ሆነ። 596 በጃፓን 17 አንቀጽ ያለ ሕገ መንግሥት በልዑል ሾታኩ ተጻፈ። 602-633 ቢዛንታይን ንጉሥ ሄራክሊዮስ ዘመን 614 ነቢዩ መሐመድ የመዲና ሕገ መንግሥት አወጣ። 630 የእስላም ሰራዊቶች ፋርስን በወረሩበት ጊዜ ሱሳ በጥፋት ላይ ተጣለ። 635 የሎምባርዶች ሕገጋት ተጻፉ። 646 የቪዚጎቶች አዳዲስ ሕገጋት ተጻፉ። 722 የአላማናውያን አዳዲስ ሕገጋት ተጻፉ። 732 የባይዛንታይን ንጉሥ ሌዎን ኢሳውራዊ «ኤክሎጋ» የተባለውን ሕገ መንግሥት አወጣ። 742 አባሲዶች ሥልጣን ይዘው ዋና ከተማቸውን ከደማስቆ ወደ ባግዳድ አዛወሩ። 777 የፍሪዝያውያን ሕገጋት ተጻፉ። 800 ገ. ስሜን እንግሊዝ በቫይኪንጎች ስለተወረረ በንጉስ አልፍሬድ ጊዜ የሴክሶች ቀበሌኛ ይፋዊ ሁኔታ አገኘ። 835 ካሮሉስ ማግኑስ የመሠረተው «የሮማናውያንና የፍራንካውያን መንግሥት በቨርዱን ውል በሦስት ተከፋፈለ። 870 የባይዛንታይን ንጉሥ 1ኛ ባሲሌዎስ «ባሲሊካ» የተባለውን ሕገ መንግሥት አወጣ። 936 ታምራዊ መልክ ያለበት ስዕል ከኤደሣ ወደ ቊስጥንጥንያ ተዛወረ። 981 በምዕራብ ፍራንኪያ (የአሁን ፈረንሳይ) የመኳንንት ግፍ ለመቀነስ ቤተ ክርስቲያኑ «የእግዚአብሔር ሰላም» (/ፓክስ ደዪ/) ዐዋጀ። ይህ መጀመርያው የሰላም እንቅስቃሴ ሲሆን በአውሮፓ ተስፋፋ። 1059 ኖርማኖች እንግሊዝን ወረሩ። 1088 አንደኛው የመስቀል ጦርነት ተካሔደ። 1092 የእንግሊዝ ንጉስ 1 ሄንሪ የነጻነት ሥርአት የተባለውን ሰነድ አዋጀ። 1110 አዲስ የተቋቋመውን የእየሩሳሌም መንግስት ከእስላሞች ለመከላከልና ወደ ከአውሮፓ ወደ እየሩሳሌም የሚጎርፉትን ተሳላሚዎች ደህንነት ለመጠበቅ ቴምፕላርስ ተመሠረቱ። 1184 በመስቀል ጦርነት የእንግሊዝ ንጉስ 1 ሪቻርድ በሳላዲን ላይ በአርሱፍ ውግያ አሸነፈ። 1196 ፈረንጆች (መስቀለኞች) ቊስጥንጥንያን ዘረፉት። 1207 መኳንንቱ የእንግሊዝ ንጉሱን ዮሃንስ (ጆን) ማግና ካርታ ('ታላቅ ሥርዓት') የሚባለውን ሰነድ እንዲፈርሙት አስገደዱዋቸው። 1210 በወራሪ ሞንጎሎች እጅ ሱሳ በፍጹም ጠፋች። 1212-1222 አንድ የሳቅሰን አስተዳዳሪ አይከ ቮን ረፕጎቭ ሳቅሰንሽፒግል የተባለውን ሕገ ፍትኅ አቀነባበረ። 1228 ሱንዲያታ ከይታ ማሊ መንግሥትን ለማወሐድ የ'አፈ ቃል' ሕገ መንግሥት 'ኩሩካን ፉጋ' አወጡ። 1240 ገ. በግብጽ አገር ቅብጡ አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል ፍትሐ ነገሥት በአረብኛ ጻፉ። 1250 ሁላጉ ከሐን የተባለው የሞንጎሎች መሪ ባግዳድን ሲበዘብዝ የአባሲዶች መንግስት ፍጻሜ ለመሆን በቅቷል። 1252 እጣልያ የንጉስ ወገን በፓፓ ወገን በሞንታፔርቲ ድል አደረገ። 1262 ይኵኖ አምላክ ሥልጣን ጨበጠው የኢትዮጵያ መጀመሪያው የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት ዐፄ ሆኑ። 1382 የሰርዴስ ዙሪያ የኦቶማን ቱርክ መንግሥት ክፍል ሆነ። 1400 የቻይና ሰዎች ወርረው 'ዶንግ ዶ' (ሀኖይ)ን ይዘው ስሙን 'ዶንግ ጯን' አሉት። 1420 ዶንግ ጯን ወደ ቬትናም ሕዝብ ሲመለስ ስሙ 'ዶንግ ኪኝ' ሆነ። 1431 በአጼ ዘርዕ ያዕቆብ ዘመን አባ ጊዮርጊስ ከ1 ፈረንሳያዊ ጐባኝ ጋራ ስለ ሃይማኖት ስላነጋገሩ አንድ ተልእኮ ወደ ሮማ ተላከ። 16ኛ ምዕተ ዓመት 1500 ኢትዮጵያ ከአዳል ጋር ስትታገል ማቴዎስ የተባለ አንድ አርሜናዊ ወደ ፖርቱጋል ተልኮ የፖርቱጋል ንጉስ እርዳታ ለመነ። 1507 የፖሎኝ ሠራዊት በኦርሻ ውግያ በሩስያ ላይ አሸነፈ። ሀቫና በእስፓንያውያን በኩባ ደቡብ ዳርቻ ተመሠርቶ ከተማው በዚህ ሥፍራ ግን አልተከናወነም። 1511 ሀቫና እንደገና በስሜን ዳርቻ ተመሠረተ። 1512 የፖርቱጋል ሚሲዮን በኢትዮጵያ ደረሰ። 1514 ቪክቶሪያ የምትባል መርከብ ወደ ስፓንያ በመመለሷ መጀመርያ ዓለምን የከበበችው መርከብ ሆነች። 1525 የእንግሊዝ ንጉሥ 8ኛ ሄንሪ የፕሮቴስታንት እምነት ስለ አጸደቀ፤ በፓፓ ፈንታ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን የበላይ መሪ ሆነ። 1534 ሳንቲያጎ ቺሌ በኗሪ አርበኞች ጠፋ። 1547 የአውሮፓ መንግሥታት የመሪዎቻቸውን ሃይማኖት ይከተሉ የሚለው የአውግስቡርግ ውል ጸደቀ። 1557 በዛሬው ዩናይትድ እስቴት ከሁሉ አስቀድሞ በአውሮጳውያን የተሰራ ከተማ ሰይንት ኦገስቲን፥ ፍሎሪዳ ተመሰረተ። 1564 ካቶሊኮች በፈረንሳይ ፕሮቴስታንቶች ላይ የበርተሎሜዎስ እልቂት ጀምረው መሪያቸውን ደኮልኒን ገደሉ። 17ኛ ምዕተ ዓመት 1601 ጋሊሌኦ ስለመጀመርያ ቴሌስኮፕ ለቬኒስ አማካሪዎች መግለጫ ሰጠ። 1602 መስከረም 4 ቀን የስፓንያ ከተማ ቫሌንሲያ ሞሪስቾዎችን (አረብ ክርስቲያን) ሁሉ አባረራቸው። መስከረም 5 ቀን የእንግሊዝ መርከበኛ ሄንሪ ሀድሰን የሀድሰን ወንዝ (በዛሬው ኒው ዮርክ) አገኘው። ኅዳር 23 ቀን የስምምነት ውል ተፈራርመው፣ እስፓንያውያን በምሥራቅ ጃፓን ውስጥ አንድ ፋብሪካ ለመሥራት፣ የማዕድን ሠራተኞች ከ«አዲስ ስፓንያ» (ሜክሲኮ) ወደ ጃፓን ለማስገባት፣ የስፓንያ መርከቦች አስፈላጊነት እንደሆነባቸው ጃፓንን ለመጎብኘት ተፈቅደው፣ ደግሞ የጃፓን ተልእኮ ወደ እስፓንያ ቤተ መንግሥት እንዲጓዝ ተወሰነ። ጥር 2 ቀን ጋሊሌኦ በቴሌስኮፕ አዲስ ጨረቃዎች በጁፒተር ዙሪያ አገኘ። መጋቢት 6 ቀን የስዊድን ጭፍሮች መስኮብን ማረኩ። ግንቦት 2 ቀን ፍራንሷ ራቫያክ የፈረንሣይን ንጉሥ 4ኛ አንሪ ገደላቸው። ሐምሌ 1 ቀን ጆን ጋይ ከ39 እንግሊዛውያን ሰፈረኞች ጋራ ወደ ኒውፈንላንድ (የዛሬው ካናዳ) ከእንግሊዝ ወጣ። ሐምሌ 29 ቀን ሄንሪ ሀድሰን የሀድሰን ባህረሠላጤ (በዛሬው ካናዳ) አግኝቶ ወደ እስያ የሚወስድ ማለፊያ መሰለው። 1617 የኢትዮጵያ ንጉስ ሱስንዮስ ወደ ሮማ ፓፓ ተሰለሙ። 1625 ሱስንዮስ ዘውዳቸውን ለልጃቸው ለፋሲላድስ እንዲሰጡ ተደረጉ። ፋሲላድስ ወዲያው አገሩን ወደ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መለሱ። 1626 ፋሲላደስ ኢየሱሳውያን አገሩን ለቅቀው እንዲሄዱ አዘዙ። 1641 በኢጣልያ ካስትሮ የሚባል ከተማ በሮማ ፓፓ ላይ አመጽ አድርጎ፡ የፓፓ ሃያላት አጠፉት። 1658 በለንደን እንግሊዝ 10 ሺህ ሕንጻዎች ያጠፋ ታላቅ እሳት ጀመረ። በኢትዮጵያ ፋሲላድስ የኢየሱሳውያንን መጻሕፍት አስቃጠሉ። 1676 የአውሮፓ ሠራዊት በቪኤና ውግያ ቱርኮችን አሸነፉ። 1690 ፃር 1 ፕዮትር በሩሲያ የጺም ቀረጥ አስገበረ። 18ኛ ምዕተ ዓመት 1731 በቻርልስተን፥ ሳውስ ካሮላይና አካባቢ ስቶኖ የባርዮች አመጽ ሆነ። 1745 ንጉሡ አላውንግፓያ የዳጎን አውራጃ አሸንፎ ስሙን ወደ ያንጎን ቀየረው። 1747 ሪቻርድ ካቲዮ የፍላጎትና አቅርቦትን መሪ ሃሳብ ለሥነ ንዋይ ጥናት አበረከተ። 1768 ኅዳር 5 ቀን የአሜሪካ አብዮታዊ አርበኞች ከፍልሚያ በኋላ ሞንትሬያልን ማረኩ። ታኅሣሥ 23 ቀን የእንግሊዝ ሠራዊት በኬበክ ከተማ አሜሪካውያንን አስመለሳቸው። የካቲት 29 ቀን በሞርዝ ጅረት ድልድይ ፍልሚያ ስሜን ካሮላይና አርበኞች አሸነፉ። መጋቢት 10 ቀን ከአሜሪካውያን መድፍ የተነሣ የእንግሊዝ ሠራዊት ከቦስቶን ይወጣል። ሰኔ 3 ቀን አሜሪካውያን በቷ-ሪቭዬር ፍልሚያ በኬበክ ድል ሆኑ። ሰኔ 24 ቀን ስፓንያውያን ሳን ፍራንሲስኮ ካሊፎርኒያ አቆሙ። ሰኔ 29 ቀን የአሜሪካ ነጻነት ዐዋጅ (ከእንግሊዝ አገር) በቶማስ ጄፈርሰን ተጽፎ በፊላዴልፊያ ታተመ። ሐምሌ 4 ቀን በኒው ዮርክ ከተማ ብዙ ሠልፈኞች ተናድደው የእንግሊዝ ንጉሥ 3ኛ ጆርጅን ሐውልት ያወድቃሉ። ሐምሌ 7 ቀን የእንግሊዝ ዠብደኛ ጄምስ ኩክ በሦስተኛው ጉዞ ወደ ሰላማዊ ውቅያኖስ ከእንግሊዝ ወጣ። ነሐሴ 11 ቀን የጀርመን ቅጥረኛ ወታደሮች የእንግሊዝ ሠራዊት ለመርዳት በኒው ዮርክ ደረሱ። ነሐሴ 23 ቀን የእንግሊዝ ሠራዊት በጆርጅ ዋሽንግተን ላይ በሎንግ አይላንድ ውጊያ አሸነፉ። ጳጉሜ 3 ቀን አንድ አውሎ ንፋስ ጉዋዶሎፕ ሲመታ ከ6000 ሰዎች በላይ ጠፉ። 1773 ጥቅምት 2-8 ታላቅ አውሎ ነፋስ በማርቲኒክና በባርባዶስ ደሴቶች ላይ ሲጎርፍ 22,000 የሚያሕሉ ሰዎች ጠፍተዋል። የካቲት 22 ቀን እንግሊዞች የዛሬውን ጋያና ከሆላንድ ያዙትና ጆርጅታውን ከተማ መሠረቱ። ጳጉሜ 1 ቀን ሎስ አንጅለስ የምትባል ከተማ በ44 እስፓንያዊ ሠፈረኞች ተመሰረተች። 1775 የአሜሪካ ነጻነት አብዮት ከእንግሊዝ በፓሪስ ውል ተጨረሰ። 1784 በፈረንሳይ አብዮት ከ200 በላይ ቄሳውስት ሰማዕትነት አገኙ። 1785 የፈረንሳይ አብዮታዊ አማካሪዎች "የማስፈራራት መንግስት" ዐዋጁ። 1790 የአንድ ሳምንት ባሕር ውግያ በእንግሊዝና በእስፓንያ መካከል ከቤሊዝ አጠገብ ጀመረ። 1791 ስልጣን ለመያዝ ናፖሌዎን ከግብፅ ወደ ፈረንሳይ ወጣ። 1792 ጌብሪየል ፕሮሰር የባርዮችን ብጥብጥ በሪችሞንድ ቪርጂንያ አሸፈተ። 19ኛ ምዕተ ዓመት 1804 ናፖሊዎን በሩሲያ ላይ በቦሮዲኖ ውግያ ድል አደረገ። 1805 መስከረም 5 ናፖሊዎን እንዳይማርከው የሩሲያ ሰራዊት መስኮብን አቃጠለ። ነሐሴ 22 ናፖሌዎን በድረስደን ውጊያ ድል አደረገ። ነሐሴ 25 የናፖሌዎን ሠራዊት በኩልም ውጊያ ድል ሆነ። ነሐሴ 25 ክሪክ የተባለው የቀይ ኢንዲያን ጐሣ ወታደሮች በፎርት ሚምስ ምሽግ አላባማ ላይ እልቂት አደረጉ። 1806 የአሜሪካ መርከቦች በኤሪ ሐይቅ በእንግሊዝ አሸነፉ። ነሐሴ 19 ቀን የእንግሊዝ ጭፍሮች በጦርነት ዋሺንግቶን ዲሲ ገብተው ዋይት ሃውስን አቃጠሉ። 1814 ብራዚል ነጻነቱን ከፖርቱጋል አዋጀ። 1822 ነሐሴ 20 ቀን ቤልጅክ በኔዘርላንድ ላይ አመጸ። ነሐሴ 23 ቀን መጀመርያ የምድር ባቡር አገልግሎት «ዘ ቶም ሳምብ» በዩናይትድ ስቴትስ ጀመረ። 1825 ባርነት በእንግሊዝ አገር ግዛቶች ሁሉ ባዋጅ ተከለከለ። 1828 ሳሙኤል ሁስተን የቴክሳስ ሬፑብሊክ መጀመርያ ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ። በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። 1830 በሜሪላንድ ፍረድሪክ ዳግላስ መርከበኛ በማስመስል ከባርነት አመለጠ። 1831 ነሐሴ 18 ቀን እንግሊዝ ሆንግኮንግን ማረከ። ነሐሴ 21 ቀን አሚስታድ የተባለ በአፍሪቃውያን የተማረከው መርከብ ወደ ኒው ዮርክ ደረሰ። ጳጉሜ 5 ቀን ጆን ኸርሸል መጀመርያ ፎቶ አነሳ። 1844 እንግሊዞች ያንጎን በጦርነት ሲይዙ ስሙን 'ራንጉን' አሉት። 1850 በሪችሞንድ ቪርጂኒያ 90 ጥቁሮች ትምህርት ስለተማሩ ታሰሩ። 1854 በአሜሪካ መነጣጠል ጦርነት ደቡብ ክፍላገሮች (ኮንፌዴራቶች) በ2ኛ መናሠሥ ውጊያ አሸነፉ። 1862 ነሐሴ 28 የፕሩሲያ (ጀርመን) ሠራዊት 3ኛ ናፖሊዎንን ከ100,000 ጭፍሮች ጋር በሰዳን ውግያ አሸነፈ። ነሐሴ 30 3ኛ ናፖሊዎን ተማርኮ ፈረንሳይ ረፑብሊክ አዋጀ። 1865 በአባታቸው በምፓንዴ መሞት ከትሿዮ የዙሉ ንጉስ ሆኑ። 1869 የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ጎልድ ኮስት (የአሁን ጋና) መቀመጫ ከኬፕ ኮስት ወደ አክራ ተዛወረ። ጥቅምት 22 ቀን ታላቅ አውሎ ንፋስ በሕንድ 200,000 ሰዎችን ገደለ። ሚያዝያ 17 ቀን ሩስያ በቱርክ ኦቶማን መንግሥት ላይ ጦርነት አዋጀ። ሚያዝያ 29 ቀን የላኮታ ኢንዲያን አለቃ ክሬዚ ሆርስ ለአሜሪካውያን ሠራዊት ዕጁን ሰጠ። ግንቦት 14 ቀን ሮማኒያ ነጻነቱን ከኦቶማን ቱርክ መንግሥት አዋጀ። ጳጉሜ 1 ቀን ክሬዚ ሆርስ በእስር ተገደለ። 1871 በደቡብ አፍሪቃ መጨረሻ የሆኑት የዙሉ ንጉሥ ከትሿዮ በእንግሊዞች ተማረከ። 1875 ክራካቶአ የተባለ እሳተ ገሞራ በእንዶኔዝያ ፈነዳ፤ 3600 ሰዎች ሞቱ። 1878 አዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒልክ ተቆረቆረች። ከምድር መንቀጥቀጥ በሳውስ ካሮላይና 100 ሰዎች ሞቱ። ነሐሴ 30 ቀን ከ30 አመት ትግል በኋላ፣ የአፓቺ አለቃ ጀሮኒሞ በአሪዞና እጅን ሰጠ። 1881 አይፈል ግንብ በፓሪስ ተሠራ። ቡጁምቡራ በጀርመን ምሥራቅ አፍሪካ (የዛሬው ቡሩንዲ) የወታደር ጣቢያ ሆነ። ባንጊ ከተማ (ዛሬ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ዋና ከተማ) በፈረንሳዮች በኡባንጊ ወንዝ ላይ ተመሠረተ። ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ጥቅምት 5 ቀን መጀመርያው ተንቀሳቃሽ ፊልም ፈተና የራውንድኸይ ገነት ትርኢት (2 ሴኮንድ) በሊድስ፣ እንግሊዝ በሉዊ ለ ፕረንስ ተቀረጸ። መጋቢት 2 ቀን ንጉሠ-ነግስት ዮሐንስ አራተኛ በመተማ ውግያ ከሱዳን ጋር ተገደሉ። ሚያዝያ 25 ቀን 2ኛ ምኒልክ ከጣልያን ጋር ውል ፈርመው ኤርትራ ለጣልያን ስልጣን ሰጡ። 1883 መስከረም 3 ቀን ሳልስበሪ፣ ሮዴዚያ ተመሰረተች። ጥቅምት 9 ቀን ዊንድሁክ ከተማ በጀርመኖች ተሠራ። 1887 የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። 1888 ከዓለሙ ታሪክ አጭሩ ጦርነት 38 ደቂቃ የእንግሊዝ-ዛንዚባር ጦርነት። በኢትዮጵያና በጣልያ የደረሰ የአድዋ ጦርነት። 1890 የ ቦሊቪያ መንግሥት መቀመጫ ከሱክሬ ወደ ላፓዝ ተዛወረ። 'ሎሬንሶ ማርኬስ' ከተማ (አሁን ማፑቶ) የፖርቱጋል ቅኝ አገር ሞዛምቢክ መቀመጫ ተደረገ። መስከረም 1 በላቲመር ፔንሲልቬኒያ ፖሊሶች 19 የማዕደን ሰራተኞች በእልቂት ገደሉ። መስከረም 2 የዳግማዊ ምኒልክ ሻለቆች የካፋን ንጉስ ጋኪ ሸሮቾ በማማረክ ያንን መንግስት ጨረሱ። ታኅሣሥ 22 እንግሊዞች በደቡብ አፍሪካ የዙሉ አገር ወደ ናታል አውራጃ አስቀጠሉ። የካቲት 9 የአሜሪካ መርከብ መይን በሃቫና ወደብ ኩባ ባልታወቀ ምክንያት ተፈነዳ። ሚያዝያ 15 የአሜሪካ መርከብ ሃይል የኩባ ወደቦችን ማገድ ጀመረ። ሚያዝያ 18 የአሜሪካ ምክር ቤት ከመይን መፈንዳት የተነሣ ጦርነት ከሚያዝያ 14 ጀምሮ እንደ ነበር በእስጳንያ ላይ አዋጀ። ሚያዝያ 30 በጣልያ አበጋዙ ባቫ-በካሪስ ብዙ መቶ ሰልፈኞች በመድፍ ገደላቸው። ግንቦት 21 ሴኮንዶ ፒያ የሚባል የፎቶ አንሺ የቶሪኖ ከፈን ፎቶ ሲታጠብ ኦሪጂናሉ ኔጋቲቭ መሆኑን አገኘ። ሰኔ 6 ፊሊፒንስ ደሴቶች ነጻነት ከስፓንያ አዋጀ። ሐምሌ 1 አሜሪካ የሃዋይኢ ደሴቶችን አስቀጠለ። ሐምሌ 11 አሜሪካውያን በስፓኒሾች ላይ በሳንቲያጎ ፍልሚያ ኩባ አሸነፉ። ሐምሌ 19 አሜሪካውያን ፕወርቶ ሪኮ ደሴት ወርረው ከስፓንያ ማረኩዋት። ነሐሴ 7 በኩባ በስፓንያውያንና በአሜሪካውያን መካከል ያለው መታገል ጨረሰ። ነሐሴ 28 በኦምዱርማን ውግያ ሱዳን የእንግሊዝ ሠራዊት ድል በማድረግ በሙሉ ቅኝ አገር አደረጉት። 1892 ፖርቶ ኖቮ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ዳሆመይ (የዛሬ ቤኒን) መቀመጫ ተደረገ። 'ፎርት-ላሚ' ከተማ (ዛሬ ንጃመና፣ ቻድ) በፈረንሳዊው አዛዥ ኤሚል ዣንቲ ተመሠረተ። ነሐሴ 21 ቀን የእንግሊዝ ሃያላት በአፍሪካነር (ቦር) ጦርነት (ደቡብ አፍሪቃ) በበርገንዳል ውጊያ አሸነፉ። ጳጉሜ 3 ቀን አንድ ታላቅ አውሎ ንፋስ በቴክሳስ 8000 ሰዎች አጠፋ። 1893 መስከረም 3 ቀን በፊሊፒንስ ጦርነት የፊሊፒንስ ተዋጊዎች በአሜሪካ ሠራዊት ላይ ድል አደረጉ። ጳጉሜ 1 ቀን ሌኦን ቾልጎሽ የተባለ ወንበዴ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መኪንሊ ተኩሶ ገደለው። 1894 የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መኪንሊ ተተኩሰው ሲሞቱ ቴዮዶር ሮዝቬልት ፕሬዚዳንት ሆኑ። 1897 ሉሳካ ለአለቃው ሉሳካ ተሰየመ። ጣልያኖች ተከራይተው የነበረውን ሞቃዲሾን በዋጋ ገዙትና የጣልያ ሶማሊያ መቀመጫ ሆነ። ፈረንሳይ ከተደገፉት ሃይማኖቶች ተለየ። ታኅሣሥ 24 ቀን የጃፓን-ሩስያ ጦርነት፡ ጃፓን ፖርት አርሰር ከሩስያ]] ማረከ። ጥር 14 ቀን ብዙ ሰላማዊ ሰልፈኞች በሰይንት ፒተርስቡርግ ሩስያ በፖሊስ ተገደሉ። የካቲት 26 ቀን የሩስያ ሠራዊት በሙክደን ውግያ በጃፓን ተሸነፈ። መጋቢት 26 ቀን በምድር መንቀጥቀጥ በህንድ 20,000 ሰዎች ሞቱ። ግንቦት 20 ቀን ጃፓን የሩስያን መርከብ ኃይል አጠፋ። ግንቦት 30 ቀን የኖርዌይ ምክር ቤት ነጻነት ከስዊድን አዋጀ። ነሐሴ 26 ቀን በካናዳ ውስጥ አልቤርታና ሳስካቸዋን አዳዲስ ግዝቶች ሆኑ። ነሐሴ 30 ቀን ጃፓን በሩሲያ ላይ አሸንፎ በፖርትስመስ ኒው ሃምፕሽር ውል ተፈራረሙ። 1899 በአውሮፓ የተደረገ መጀመርያው የአውሮፕላን በረራ። 20ኛ ምዕተ ዓመት 1906 1ኛ አለማዊ ጦርነት በአውሮፓ ጀመረ። 1907 የደቡብ አፍሪካ ጭፍሮች ጀርመን ደቡብ-ምዕራባዊ አፍሪካ (ናሚቢያ) ወረሩ። ጳጉሜ 1 ቀን ታንክ የሚባል የጦርነት መሳርያ ለመጀመርያ ጊዜ በእንግሊዞች ተፈተነ። 1911 በሳንዠርመን ውል ዩጎስላቪያ፣ ሃንጋሪና ቸኮስሎቫኪያ ከኦስትሪያ ነጻነታቸውን አገኙ። 1912 ፖሎኝ በዋርሳው ውጊያ በሩሲያ ቀይ ጭፍሮች ላይ ያሸነፋል። ነሐሴ 20 ቀን ሴቶች በአሜሪካ ዩናይትድ እስቴት የምርጫ መብት አገኙ። 1914 ቱርኮች በግሪክ-ቱርክ ጦርነት አሸንፈው ስምርኔስ ከተማ ተቃጠለ። 1915 የእንግሊዝ አስተዳደር በፍልስጤም ጀመረ። ነሐሴ 26 ቀን ታላቅ ምድር መንቀጥቀጥ በጃፓን መቶ ሺህ የሚያህሉ ሰዎች ገደለ። 1920 ጦርነት የሚከላከል የኬሎግ-ብሪያንድ ውል በ60 አገሮች ተፈረመ። የዓለሙ መጀመርያው ቴሌቪዥን ስርጭት ፈተና ተደረገ። 1921 ሄርበርት ሁቨር የአሜሪካ ፕረዝዳንት ሆነ። የእስቶክ ገበያ ውድቀት በመከሠቱ የመላ አለም ምጣኔ ሀብት ወደ 'ታላቁ ጭፍግግ' በ1 አመት ውስጥ ቶሎ ወረደ። 1924 ጃፓን ማንቹርያን ወረረ። 1931 ሂትለርና ስታሊን በሥውር ፊርማ ፖሎኝን አካፈሉ። ነሐሴ 26 ቀን አዶልፍ ሂትለር ፖሎኝን በመውረሩ ሁለተኛ ዓለማዊ ጦርነት ጀመረ። 1932 ጀርመኖች በ2ኛ ዓለማዊ ጦርነት ለንደንን በቦምብ ለመደብደብ ጀመሩ። 1934 የአላም አል ሓልፋ ውጊያ በጀርመንና እንግሊዝ ታንኮች መኃል በግብፅ በረሃ ጀመረ። ጳጉሜ 5 ቀን በ2ኛ አለማዊ ጦርነት የጓደኞች ሃያላት በማጁንጋ ማዳጋስካር ደረሱ። 1935 የጓደኞች ወታደርና 1,800 የጣልያ እስረኞች ተሸክማ ላኮኒያ የምትባል መርከብ አፍሪካን ስትቀርብ በጀርመኖች ተተኩሳ ሰጠመች። ነሐሴ 28 ቀን በ2ኛ አለማዊ ጦርነት ኢጣልያ በጓደኞቹ ሃያላት ተወረረች። ጳጉሜ 3 ቀን የአሜሪካ ጄኔራል አይዘንሃወር የኢጣልያ እጅ መስጠት በጦርነት አዋጀ። 1936 ፓሪስ ከተማ በጓደኞች አርበኞች ከጀርመን ነጻ ወጣች። 1941 የሶቭየት ኅብረት መጀመርያውን ንዩክሌያር መሣሪያ በፈተና አፈነዳ። 1946 የቻይና ሃያላት የደቡብ ኮርያ ደሴቶችን በቦምብ ደበደቡ። 1947 በኢስታንቡል ቱርክ በኖረበት በግሪክ ህብረተሰብ ላይ እልቂት ተደረገ። 1949 የአርካንሳው አገረ ገዥ ኦርቪል ፋውበስ ጥቁር ተማሮች ከነጭ ጋራ እንዳይማሩ የክፍላገሩን ወታደሮች በሊተል ሮክ ሰበሰበ። 1951 የቅብጥ አቡና 6ኛ ቂርሎስ ለኢትዮጵያ የራሱን አቡነ እንዲኖሩት ፈቀዱለት። 1952 መጀመርያው ሰው ሰራሽ መንኮራኩር (የሩሲያ) ጨረቃን ደረሰ። 1953 «ኦፐክ» የዘይት አስወጪ አገሮች ድርጅት ተመሰረተ። 1954 መጀመርያ ቴሌቪዥን ግንኙነት በአሜሪካና በአውሮጳ መካከል 1955 ዶ/ር ማርቲን ሉጠር ኪንግ «እኔ ሕልም አለኝ» ያለበትን ቃል ለሰላማዊ ሰልፍ ተናገረ። 1958 መጀመርያ የምድር ፎቶ በጨረቃ ምኋር ካለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር ተነሣ። 1959 ጡርጉድ ማርሻል መጀመርያ አፍሪቃ-አሜሪካዊ የዋና ብሔራዊ ችሎት ፈራጅ ተሾሙ። 1960 ፈረንሳይ ንዩክሌር ቦምብ በፈተና በመፈንዳቷ ወደ ንዩክሌር ሃያላት ገባች። 1961 መንፈቅለ መንግስት በሊቢያ ሙአማር ጋዳፊን ከፍ አደረገው። 1963 በአቲካ እስር ቤት ኒው ዮርክ ሁከት ተደረገ። 1966 ጊኔ-ቢሳው ነጻነቱን ከፖርቱጋል አገኘ። 1969 የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር የፓናማ ካናል አስተዳደር ለፓናማ በ1992 ዓ.ም. ለማዛወር ውል ፈረሙ። 1970 የጸረ-አፓርትሃይድ ወኪል ስቲቭ ቢኮ በደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ታስሮ ተገደለ። 1972 ነጻነት ለቨንዳ ተሰጠ ይህ ግን ከደቡብ አፍሪካ ውጭ አልተቀበለም። 1975 የኮሪያ አየር መንገድ አይሮፕላን በሶቭየት ኅብረት ላይ ሲተኮስ 269 መንገደኞች ሞቱ። 1978 በመርዝ ጋዝ አደጋ በካሜሩን 1700 ሰዎች ሞቱ። ጳጉሜ 2 ቀን ዴስሞንድ ቱቱ በኤጲስቆፖሳዊ ቤተክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ መጀመርያ ጥቁር ኤጲስ ቆጶስ ሆኑ። 1979 የሬጌ ሙዚቃ ዘፋኝ ፒተር ቶሽ ቤቱ በኪንግስተን ጃማይካ በሌቦች ተገደለ። 1981 ቮየጀር የተባለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር በኔፕቱን ፈልክ አለፈ። 1982 የብረት መጋረጃ በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ ጀርመኖች ወደ ምእራብ ፈለሱ። ነሐሴ 22 ቀን ሳዳም ሁሰይን ኩወይት የኢራቅ ክፍላገር ነው ይላል። 1983 ዑዝበክስታን ነጻነቱን ከሶቭየት ኅብረት አዋጀ። 1984 ፓስካል ሊሱባ በኮንጎ ሪፑብሊክ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሆኑ፤ ይህ ምርጫ የረጅም ዘመን አንድ ፓርቲ ግዛት ጨረሰ። 1985 መይ ካሮል ጀሚሶን መጀመርያ ጥቁር አሜሪካዊት በጠፈር ሆነች። 1987 ናቶ በቦስኒያ ሰርቦች ላይ ዘመቻ ጀመረ። 1988 የራፕ ሙዚቃ ተጫዋች ቱፓክ ሻኩር በላስ ቬጋስ ተተኲሶ ተገደለ። 1989 በእስላም ታጣቂዎች በአልጄሪያ በተገረገ እልቂት 60-100 ሰዎች ተገደሉ። 1990 ስሜን ኮሪያ የራሱን ሰው ሠራሽ መንኮራኩር መጀመርያ ጊዜ ላከ። 1994 አራት አውሮፕላኖች በአረብ ታጣቂዎች ተሰርቀው በአለም ንግድ ሕንጻና በፔንታጎን ተጋጭተው 3000 ያህል ሰዎች ተገደሉ። ነሐሴ 20 ቀን የምድር ጉባኤ ስብሰባ በጆሃነስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ጀመረ። ጳጉሜ 5 ቀን ገለልተኛ አገር የሆነ ስዊስ በመጨረሻ የተባበሩት መንግስታት አባል ሆነ። 1996 ስዊድን በምርጫ ለዩሮ እምቢ አለች።
44265
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%8B%A8%E1%88%88%20%E1%89%B0%E1%88%B0%E1%88%9B
አየለ ተሰማ
ፊት አውራሪ አየለ ተሰማ 1 ፊታ አውራሪ አየለ ተሰማ ዳዊት ዘጎንደር ዘምትዉልደ ጌድዮን ዘገበዘ አክሱም፡፡ 2 ዳዊት ዘጎንደር ዘምትዉልደ ጌድዮን ዘገበዘ አክሱም፡፡ ጀግና ሚታወሰው ወይም ከሞተ ወይም ከተለየ! ያሉት አበው እውን ሁኖ ያሄዉ አሁን አንድ ስመ ጥር ጀግና ልናነሳ ተገደድን ፊት አውራሪ አየለ ተሰማ! የጀግና ባህሪው ብዙ ቢሆንም ጀግናን ከደረቱ አበባን ከአናቱ ይለዩ! እንደ ተባለ አየለም የጀግንነት ባህሪው የተለየ ገና በንጭጩ በደረቱ ነው፡፡ የማይችሉት ድንጋይ ሲያወጡት ደረት ሲያወርዱት ጉልበት ይመታል! እንደ ተባለ አየለም በልጅነቱ ለሸክም አይመችም ነበረ ሲያወጡት ደረት ሲያወርዱት ጉልበት ይጎነትላል፡፡ አገሬውም እግሩ ለጠጠር ደረቱ ለጦር የተመቸ ነው! ይለዋል፡፡ አሱም እራሱ መጀገን አምሮት ፋሺስት ጣሊያን ኑሮዉን ሊኖር ሀገር ሲገባ አይ! ጣሊያን አንተ ያየኸኝ ከጉልበት እኔ ያየሁህ ከደረት! ሰላለ ጀግነቱ የተለየ ከደረቱ ነው የተባለዉም ለዚያ ነው፡፡ እና አየለ ለሀገሩ ዳር ድንበር ለሀገሩ ነፃነት ነፍጥ! አንግቶ ጫካ ሲገባ ያገሩ ነዋሪ ያገሩ ጉበል ሽማግሌ በምክሩ አርበኛ በሰናድሩ ይለያል! ብሎ ለሱ ሊገዛ ለሱ ሊያድር ገብቶለታል፡፡ እንደሱ ተከታዮች አባባል የሱ ነፍጥ! አሉ ለእርሳሱ ማስፈንጠሪያ መዶቃዱቅ ቧንቧ አለው ውስጥ ለውስጥ ጥይቱ ሲሄድ ያለው ባሩድ እሳትን የሚተፋና ርሳሱም መትቶ የሚገድል ነው! ይላሉ፡፡ ነፍጥ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ባልንጀራዬ! ባልደረባዬ! የኔ ቢጤ! ሚለዉ ቢኖር አባ ጓንዴ! ነዉ ፈረሱ! አንድ ቀን አሉ አየለ እና ፈረሱ ፋሺስት ጣሊያን ሲያሳዳቸዉ ቢያድር በመንገድ ላይ ሳሉ እራባቸዉ በዚህን ጊዜ አባ አየለ ከፈረሱ ጋር ወደ መንደር ወጠዉ ካንድ ባዶ ቤት የሚበላ ሲያዩ በስርቆት ማለት ነዉ ህሊናቸዉን ወቀሳቸዉ እና ለፈረሳቸዉ የማናውቀውን ሌብነት፣ ልንሰርቅ ገብተን ከሰው ቤት፣ ይቅርብን ጓዴ እንውጣ፣ የሚጠብቀን መጣ! ብለዉ ፈረሳቸዉን በቃለ ሰብአዊ አወሩት ይህን ነገር የሰማ ያአገሩ ኗሪም ለፈረስ ለበቅሎ ይተርፍ የነበረ፣ ዛሬስ ለሰው ያኽል ይቸግር ጀመረ! ብሎ አነባ፡፡ እሳቸዉ እራሳቸዉም ይባላል ለሰዉ ሲመክሩ ሌሊት ከጭቃ ላይ ፈረስ ቢጥልህ፣ ወንድሜ አትናደድ ማንም አላየህ፣ ይልቁን ተጠንቀቅ ቀን እንዳይጥልህ! ነዉ ሚሉ አሉ፡፡ እና አንድ ቀን ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ሰባስጌ በተባለ የፋሽስት የጦር ካምፕ ቦታ ላይ ከትንሽ ተከታዩቻቸዉ ጋር ጥቃት ፈፅመዉ ሶስት ወታደር ገድለዉና ብዛት ያለቸዉን በማቁሰላቸዉ፤ የፋሽስት ጣሊያን ባለስልጣናት ምን? ቀረኝ በሎ ነዉ ይሄን ሚያረገዉ! ብለዉ አጠገብ ባሉ ባንዳወች ቢያፈጡ ተሰማ ሳይቀጣው በልጅነት ቀርቶ፣ ገና ራስ ይመታል እንኳን ባት አግኝቶ! ብለዋል፡፡ በዚህን ጊዜ የፋሽስት ጣሊያን ጦር እሱን ለመያዝ ቢቸግራቸዉ ቤተሰቦቹን አባቱን ቀኝ አዝማች ተሰማን ወንድሞቹን ልጅ ታደሰ እና ረዳን በመያዝ በጎንደር አርበኞች በሚታሰሩበት እስር ቤት አጎሯቸዉ፡፡ በእሰር ቤቱም በተነሳዉ የታይፎይድ ወረርሽኝ ብዙ አርበኞች ሲያልቁ ወንድማቸዉ ልጅ ታደሰም የዚህ ገፈት ቀማሽ ሆኑ፡፡ እህታቸዉም ወ/ሮ አቻም የለሽ ተሰማ ሽማግሌዉ አባቷን ቀኝ አዝማች ተሰማ እና ወንድሟን ረዳን ለማስፈታት ባደረገችዉ ጥረት እንዲሁም ፋሺስት ጣሊያ ሎሌ ለሰህተት ጌታ ለምህረት! እንደ ተፈጠረ ይታወቅላቸዉ ዘንድ ጥቂት አርበኞችን በምህረት ፈቱ፡፡ አባታቸዉ ግን ቀኝ አዝማች ተሰማ ከእስር እንደ ወጡ በሳምንቱ ሞቱ፡፡ ፊት አዉራሪ አየለም ተሰማም ከአባታቸዉ ሞት በዉሃላ በከፍተኛ ቁጭት እና የአርበኝነት ስሜት ከወንድሙ ከግራዝማች ረዳና ከልጅ አበራ ጋር በመሆን በሜጀር ባንቲ ቸኮ ሴንታታ! የሚመራዉን የጣሊያንን ጦር በመተማ አካባቢ ነጋዴ ባህር አማኒት ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ሰኔ ሃያ ዘጠኝ ቀን 1938 ዓ.ም አስደናቂ ጀብድ በመስራት የፋሽስትን ጦር በመደምሰስ አኩሪ ታሪክ ሰሩ። በዚህን ጊዜ ሜጀር ባንቲ ቸኮ ሴንታታ! የዕድሌ ክፋቱ ፈተና አብዝቶብኝ፣ አየለ አየለና ኀይሌን ወሰደብኝ! ብሎ አነባ፡፡ ይህን ያየና የሰማ የሀገሩ ኗሪ እና ጉብል አባት አስገዳይ ወንደም አስገዳይ ብለዉ ሲያሙት ነጭ ሰዉ ገዳይ ወርዶ አማኒት ገዳይ አማኒት እንደ አራስ ነብር ተጉዞ ሌሊት ገዳይ ኩመር በር በለዉ እያለ ከቀስቅስ ጋር የአባቱን ጠላት የተሰማን የታዴን ጠላት የወንድሙን በቁሙ ጠጣዉ በሳንጃ አልቢን አርዶ በካር ጠጣዉ ደሙን፡፡ እያለ ሲሸልል እና ሲፎክር አንዲት የጎንደር ጉበል እርጉዝ ሁኗ ኑሯ ሰጋ አማረኝ! አለች አገሬዉ ሥጋ አማረኝ አለች :የቀለቤሰ እናት፣ መተማ አትሄድም ወይ ከታረደበት! ብለዉ መለሱላት ይህን አኩሪ ደል የሰሙትም ስደተኛዉ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ በግራዝማች ራዳ አማካኝት ያባይ ምልክቱ አንደበቱ የገዳይ ምልክቱ ሽልማቱ! ብለዉ የአድንቆት ደብዳቤና 300 ጠበንጃ፤ 3000 ጥይትና 1000 ብር ላኩ። ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ የፋሽስት ጣሊያን መንግስት ሃገራችን በግፍ በወረረበት ወቅት ሃገራችን ብዙ ስመጥር ጅግኖችን አፍርታለች። በዚህ ወረራ ወቅት በጎንደር ከጓንግ ወንዝ እስከ መተማ ድረስ በጀግንነት ሃገሩን ከወረራ ነፃ ካደረጉት መካከል ጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ አባ ጓዴ አንዱ ነበሩ። በአንድ ወቅት ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ሰባስጌ በተባለ የፋሽስት የጦር ካምፕ ቦታ ላይ ከትንሽ ተከታዩቻቸዉ ጋር ጥቃት ፈፅመዉ 3 ወታደር ገድለዉና ብዛት ያለቸዉን በማቁሰላቸዉ፤ የፋሽስት ጣሊያን ባለስልጣናት በፊት አዉራሪ አየለ ላይ የተጠናከረ ዘመቻ በማድረግ አሳድደዉ ለመግደል ያላደረጉት ጥረት አልነበረም። ነገር ግን እሱን መያዝ ቢቸግራቸዉ ቤተሰቦቹን አባቱን ቀኝ አዝማች ተሰማን ወንድሞቹን ልጅ ታደሰ እና ረዳን በመያዝ በጎንደር አርበኞች በሚታጎሩበት እስር ቤት አሰሯቸዉ። ነገር ግን በወቅቱ በእስር ቤቱ በተነሳዉ የታይፎይድ በሽታ ብዙ አርበኞች ሲሞቱ ልጅ ታደሰ የገፈቱ ተቃማሽ ነበር። ይሁን እንጅ የቀሪዎች ህይወት ለማትረፍ በተደረገዉ ጥረት ወ/ሮ አቻሽማን ተሰማ ሽማግሌዉ አባቷን ቀኝ አዝማች ተሰማ እና ወንድሟን ረዳን ለማስፈታት ባደረገችዉ ጥረትና በዚህ ወቅትም ብዙ የጎንደር አርበኞች በጣሊያን ባለስልጣናት ምህረት ተደርጎላቸዉ ከስር ተፈተዋል። ይሁን እንጅ ቀኝ አዝማች ተሰማ በወቅቱ በታመሙት የታይፎይድ በሽታ በተፈቱ በሳምንታት ዉስጥ ለሞት አበቃቸዉ። ታዲያ ለዚህ ሁሉ የቤተሰብ ችግር አምጭ ተደርጎ የታየዉ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ነበር። ለፊት አዉራሪ ግን የእነሱ ሞት ለነፃነታቸዉ እንደ መሰዋዕትነት አድረጎ ነዉ የቆጠረዉ። በዚህ ልዩ የቁጭት አርበኝነትና ሃገር ወዳድነት ስሜት ጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ አባ ጓዴ ከወንድሙ ከግራዝማች ረዳና ከልጅ አበራ ጋር በመሆን በሜጀር ባንቲ ቸኮ ሴንታታ የሚመራዉን የጣሊያንን ጦር በመተማ አካባቢ ነጋዴ ባህር አማኒት ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ በሰኔ 29 ቀን 1938 ዓ.ም በመሄድ አስደናቂ ጀብድ በመስራት የፋሽስትን ጦር በመደምሰስ አኩሪ ታሪክ ሰሩ። ይህ ጀብዳቸዉም እስከ ስደተኛዉ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ድረስ በመሰማቱ ጃንሆይም የአድንቆት ደብዳቤና በግራዝማች ራዳ አማካኝት 300 ጠበንጃ፤ 3000 ጥይትና 1000 ብር ልከዋል። በአባባ ገሪማ ታፈረ "ጎንደሬ በጋሻዉ" እና በሕይዎት ህዳሩ የቀ.ኃ.ስ መልክተኛ "ያች ቀን ተረሳች" መፃህፎች ስለጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ እና ወንድማቸዉ ግራዝማች ረዳ ተገልፆል። በዚህ የአማኒት ጦርነት ድል መሰረት ለጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ በህዝብ እንዲህ በፉከራና በቀረርቶ ተገጠላቸዉ፡፡ አባት አስገዳይ ወንደም አስገዳይ ብለዉ ሲያሙት ነጭ ሰዉ ገዳይ ወርዶ አማኒት ገዳይ አማኒት እንደ አራስ ነብር ተጉዞ ሌሊት ገዳይ ኩመር በር በለዉ እያለ ከቀስቅስ ጋር፡፡ የአባቱን ጠላት የተሰማን የታዴን ጠላት የወንድሙን በቁሙ ጠጣዉ በሳንጃ አልቢን አርዶ በካር ጠጣዉ ደሙን፡፡ ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለምንጊዜም ሃገር ወዳድ የነፃነት ጀግኖች አባቶቻችና እናቶቻችን!! አሹ ዋሴ አርበኞች
15734
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8A%AB%E1%89%B2%E1%89%B5%20%E1%8D%AB
የካቲት ፫
የካቲት በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ቀናት ይቀራሉ። ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ዓ/ም በእስራት ላይ የነበሩት የ ዓመቱ ጎልማሳና የንጉሥ ኢያሱ አድያም ሰገድ ልጅ ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት እንደነገሡ አዋጅ ተነገረ። የዘመነ መሳፍንት የመጨረሻው ጦርነት 166ኛ ዓመት መታሰቢያ ደጃዝማች ካሣ ኃይሉ፣ ‹‹ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው ከመንገሳቸው በፊት የስሜንና የትግራይ ገዢ ከነበሩት ከደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም (የዳግማዊ ቴዎድሮስ ባለቤት የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ አባት) ጋር የመጨረሻውን የዘመነ መሳፍንት ጦርነት ያደረጉት ከዛሬ 166 ዓመታት በፊት (የካቲት 3 ቀን 1847 ዓ.ም) ነበር፡ ደጃዝማች ካሣ በኅዳር ወር 1845 ዓ.ም ደጃዝማች ጎሹ ዘውዴን ጉርአምባ ላይ፣ በሰኔ ወር 1845 ዓ.ም ደገሞ ራስ አሊ አሉላን (ዳግማዊ አሊን) አይሻል ላይ ካሸነፉ በኋላ ከወቅቱ የግዛት ኃያላን መሳፍንት መካከል ለደጃዝማች ካሣ ያልገበሩት የስሜንና የትግራይ ገዢ የነበሩት ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ብቻ ነበሩ፡፡ ደጃዝማች ካሣም ወደ ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ለመዝመት አቀዱ፡፡ ከዘመቻቸው በፊትም ደጃዝማች ውቤ በሰላም እንዲገቡላቸውና እምቢ የሚሉ ከሆነ እምቢታቸው እንደማይበጃቸው የማስጠንቀቂያ መልዕክት ላኩባቸው፡፡ ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ከፊትም ጀምሮ ደጃዝማች ማሩ እና ራስ ይማም፤ ደጃዝማች ሰባጋዲስ እና ራስ ማርዬ በሚዋጉበት ጊዜ በብልጠትና በዘዴ አንዱን ከሌላው ጋር እያዋጉ፣ ከሚመቻቸው ጋር እየወገኑና በጋብቻ እየተዛመዱ፤ ሲሸነፉም እየገበሩ ራሳቸውን ከአደጋ ጠብቀው ይኖሩ ነበር፡፡ ደረስጌ ማርያምን አሰርተው ለመንገሥ ጊዜ ሲጠባበቁ የደጃዝማች ካሣ ተደጋጋሚ ድል ዓይኑን አፍጥጦ በላያቸው ላይ መጣባቸው፡፡ ይባስ ብሎም ለደጃዝማች ካሣ እንዲገብሩ የሚያሳስብ መልዕክት ደረሳቸው፡፡ ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም የደጃዝማች ካሣ መልዕክት ሲደርሳቸው ‹‹ምን የጠገበ ነው?! ሳልዋጋ ይገባልኛል ብሎ ነው?!›› በማለት ከተናገሩ በኋላ ‹‹አልገባም!›› የሚል ምላሽ ሰጡ፡፡ ጳጳሱ አቡነ ሰላማም ለደጃዝማች ውቤ ‹‹ለካሳ ቢገብሩ ይሻላል›› ቢሏቸውም የስሜኑ ሰው ሃሳባቸውን ሳይቀይሩ ቀሩ፡፡ ደጃዝማች ካሣም ጦራቸውን አስከትተው ከእኔ የተለየህ ለራስህ እወቅ! በምን ጠፋሁ እንዳትል! አይዞህ ወታደር፤ እኔ ደስ ከሚልህ አገር አገባሃለሁ›› የሚል አዋጅ አስነገሩ፡፡ ሕዝቡም ከራስ አሊ መሸነፍ በኋላ ‹‹ደጃች ካሣ መቼ ይነግሱ ይሆን? ስመ መንግሥታቸውስ ማን ይባል ይሆን?›› እያለ ይጠይቅ ስለነበር ‹‹እኔ በመራሁህ ተጓዝ፤ ስሜን በስሜን እነግርሃለሁ›› ብለው ከአምባጫራ አልፈው በወገራ በኩል አድርገው ስሜን ገቡና ደረስጌ ላይ ‹‹እንጨት ካብ›› በተባለ ቦታ ሰፈሩ፡፡ የደጃዝማች ውቤ ጦርም በአካባቢው (‹‹መከሁ›› በተባለች ቦታ) ሰፍሮ ነበር፡፡ ደጃዝማች ካሣም አብሯቸው የነበረውንና ዮሐንስ ቤል (ጆን ቤል) የተባለውን እንግሊዛዊ የደጃዝማች ውቤን ጦር አሰፋፈር በመነፅር ዓይቶ እንዲነግራቸው ጠይቀውት ነበርና የደጃዝማች ውቤን ጦር አሰፋፈርና ድንኳን ዐይቶ በነገራቸው ጊዜ ‹‹አያሳድረኝ አላሳድረውም! እንኳን ይህን ቁርጥማታም ሽማግሌ ይቅርና ወሎን መትቼ የሸዋውን ንጉሥ እይዘዋለሁ፤ ወታደር ሆይ ‹የውቤ ነፍጥ የውቤ ነፍጥ› ቢሉህ የተለጎመው ጨርቅና ባሩድ ነው፤ አይነካህም፤እኔ የክርስቶስ ባርያ ሁሉንም ዐሳይሃለሁ! ‹ስሜን በስሜን እነግርሃለሁ› ያልኩህ ወታደር ሁሉ ስሜ ቴዎድሮስ ነው›› ብለው ፎክረው ተነሱና ጦርነቱ የካቲት 3 ቀን 1847 ዓ.ም ‹‹ቧሂት›› በተባለ ቦታ ላይ ተጀመረ፡፡ ጦርነቱ ተፋፋመና ደጃዝማች እሸቴ የተባሉት የደጃዝማች ውቤ ልጅ ተመትተው ሲወድቁ የደጃዝማች ውቤ ጦር ሽሽት ጀመረ፡፡ ብላታ ኮከቤ የተባለው የደጃዝማች ውቤ የጦር አዝማችም አለቃውን ከድቶ ከነጭፍራው ወደ ደጃዝማች ካሣ ዞረ፡፡ ደጃዝማች ውቤም ቆስለው ተማረኩና ድሉ የደጃዝማች ካሣ ኃይሉ ሆነ፡፡ ደጃዝማች ካሣም ተሸናፊውን ደጃዝማች ውቤን ‹‹እኔ እሳቱ የመይሳው ልጅ! አንተ ቆፍጣጣ (ጎባጣ) ቁርጥማታም ሽማግሌ አክብሬህ ‹ገብር› ብዬ ብልክብህ ምነው ሰደብከኝ? አሁንም ነፍጤንና ገንዘቤን አግባ!›› አሏቸው፡፡ ደጃዝማች ውቤም ‹‹እግዜር ያሳይዎ የነበረኝ ነፍጥና ገንዘብ ሁሉ አንድም ሳያመልጥ ከእጅዎ ገባ፤ ሌላ ምን አለኝ?›› ብለው መለሱላቸው፡፡ ደጃዝማች ውቤ ቤቴል (አምባ ጠዘን) በሚባለው ቦታ ያከማቹት እጅግ በጣም ብዙ ወርቅ፣ ብር (40ሺ ማርትሬዛ)፣ ጥይት፣ ጠመንጃ (ሰባት ሺ)፣ አህያ፣ ፈረስ፣ ግመል፣ ላም፣ በግ፣ ፍየል፣ በወርቅ የተለበጡ አልባሳት፣ የከበሩ ጌጣጌጦችና፣ ውድ ምንጣፎችና ሌሎች እቃዎች ተገኙ፡፡ በዚህ ጊዜም ደጃዝማች ካሣ የታሰሩትን ደጃዝማች ውቤን አስጠርተው ‹‹ይኸን ሁሉ ሀብት የሰበሰብከው ምን ሊሰራልህ ነው?›› ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ ደጃዝማች ውቤም ‹‹ለክፉ ቀኔ እንዲሆነኝ ብዬ ነው›› አሏቸው፡፡ ደጃዝማች ካሣም ‹‹ሰው ያለውን ሀብት ከተጠቀመ ምን ክፉ ቀን አለ?›› በማለት መለሱና ወደ እስር ቤቱ እንዲመለሱ አዘዙ፡፡ ደጃዝማች ውቤም ከዓመታት በኋላ እስር ቤት ውስጥ ሞቱ፡፡ በመጨረሻም ‹‹የኮሶ ሻጭ ልጅ›› ተብለው የተናቁት… ደግሞ ለቆለኛ አንድ ወርች ስጋ ምን አነሰው?›› ተብለው በአማቶቻቸው የተቀለደባቸው ካሣ ኃይሉ ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ሊነግሱባት አስጊጠው ባሰሯት ደረስጌ ማርያም ቤተ-ክርስቲያን የካቲት 5 ቀን 1847 ዓ.ም በጳጳሱ በአቡነ ሰላማ እጅ ተቀብተው፣ ‹‹ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሥ ሆኑ! ልደት ዕለተ ሞት ዓ/ም አንጋፋው ድምጻዊ ታምራት ሞላ በዚህ ዕለት አረፈ። ዋቢ ምንጮች መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ” ዓ/ም) የቴዎድሮስ ታሪክ፣ በብርሊን እንደሚገኝ አብነት፣ አሳታሚው ዶክቶር እኖ ሊትመን። በ፲፱፻ ወ ዓመት አጤ ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ አንድነት (ተክለፃዲቅ መኩሪያ) አጤ ቴዎድሮስ (ጳውሎስ ኞኞ) የኢትዮጵያ የአምስት ሺ ዓመታት ታሪክ፡ ከኖህ-ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መጽሐፍ (ፍስሃ ያዜ ካሣ)
49825
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B0%E1%88%88%E1%8D%92%E1%8A%91
ተለፒኑ
ተለፒኑ ከ1488 እስከ 1483 ዓክልበ. አካባቢ ከንግሥቱ ወንድም ከ1 ሑዚያ በኋላ በሐቱሳሽ (በሐቲ አገር ወይም የኬጥያውያን መንግሥት) የገዛ ንጉሥ ነበር። ንግስቱ ኢሽታፓሪያ ስትሆን እርሷ የሑዚያ ዋና እኅትና የአሙና ልጅ ነበረች። ሑዚያም ንጉሥ ሲሆን እኅቱንና ባሏን ለመግደል አስቦ ተለፒኑ ግን ሤራውን አግኝቶ ሑዚያን ከዙፋኑ አባረረው፣ ተለፒኑም ንጉሥ ሆነ፣ ነገር ግን ሑዚያን ይቅርታ ብሎት ሑዚያ በኋላ በሌላ ሰው እጅ ይገደል ነበር። ይህን የምናውቀው ተለፒኑ በጻፈው የተለፒኑ ዐዋጅ በተባለው ሰነድ ይተረካል። በዚህ አዋጅ የቀደሙት ኬጥያውያን ነገሥታት ዘመኖች ከላባርና (ከ1582 ዓክልበ.) ጀምሮ ይተርካል። በተለይ ስለአወራረሳቸውና ከባቢሎን ውድቀት (1507 ዓክልበ.) ጀምሮ አያሌ ነገሥታት ወይም ወራሾች በአጭር ዘመን ውስጥ እንደ ተገደሉ ይተርካል። በግድያ የመጡት ነገሥታት የአማልክት ቂም እንዳገኙ ያጠቁማል። የራሱን ዘመን እንዲህ ይገልጻል፦ አሙናም ደግሞ አምላክ ሊሆን ሲል፣ የንጉሣዊ ዘበኞች አለቃ ዙሩ በምስጢር ከገዛ ቤተሠቡ ልጁን ታሑርዋይሊን፣ «የወርቃማው ጦር ሰውዬ» የተባለውን፣ ልኮ እርሱ የቲቲያን (የአሙና በኲር) ቤተሠብ ከነልጆቹ ገደላቸው። መልእክተኛውንም ታሩሕሹን ልኮ እርሱ ሐንቲሊን (የአሙና ፪ኛ ልጅ) ከነልጆቹ ገደላቸው። ሑዚያም ንጉሥ ሆነ፣ ተለፒኑም ዋና ኢኅቱን ኢሽታፓሪያን አገባ። ሑዚያ እነሱንም ሊገድላቸው ይፈልግ ነበር፣ ሆኖም ጉዳዩ ስለ ተገለጸ ተለፒኑ አባረራቸው። ወድሞቹ አምስት ነበሩ፣ ቤቶችንም ሠራላቸው፤ ይኑሩ፣ ይብሉ፣ ይጠጡ አለላቸው፤ ማንም አይበድላቸው! ተደጋግሜ እናገራለሁ፣ እነሱ በደሉኝ፣ እኔስ አልበድላቸውም። እኔ ተለፒኑ በአባቴ ዙፋን ስቀመጥ፣ በሐሡዋ ከተማ ላይ ዘመትኩ፤ ሐሡዋንም አጠፋኋት። ሥራዊቴ ደግሞ በዚዚሊፓ ከተማ ነበሩ፣ ዚዚሊፓም ድል ሆነ። እኔ ንጉሡ ወደ ላዋዛንቲያ ከተማ በመጣሁ ጊዜ፣ ላሓ ጠላት ሆነ እሱ ከተማውን ለአመጻ አስነሣሣው። አማልክቱ በእጄ ውስጥ ሰጡት። ከመኳንንት ብዙዎች፦ የሺህ አለቃ ካሩዋ፣ የእልፍኝ አስከልካዮች አለቃ ኢናራ፣ የዋንጫ ተሸካሚዎች አለቃ ኪላ፣ የ[...] አለቃ ታርሑሚማ፣ የምርኳዝ ተሸካሚዎች አለቃ ዚንዋሸሊ፣ እና ሌሊ፤ በምስጢር ወደ ምርኳዝ ተሸካሚ ታኑዋ ልከው ነበር። እኔ ንጉሡ ሳላውቀው፣ ሑዚያንና ወንድሞቹን ገደላቸው። እኔ ንጉሡ ስሰማው፣ ታኑዋን፣ ታሑርዋይሊንም፣ ታሩሕሹን አምጥተው ጉባኤው መሞት ፈረደባቸው። እኔ ንጉሡ ግን ለምን ይሙቱ? ዓይናቸው ይሠውሩ! ብዬ፣ እኔ ንጉሡ በውነት ገበሬዎች አደረግኋቸው። የጦርነት መሣርያ ከጫንቃቸው ወስጄ ቀንበር ሰጠኋቸው!» በዚሁ ታሪክ፣ ዙሩ «የንጉሥ ዘበኞች አለቃ» ሲባል ይህ ማዕረግ ለንጉሥ ወንድም እንደ ተሰጠና ዙሩ ታዲያ የአሙና ወንድምና የ1 ዚዳንታ ልጅ እንደ ነበር ይታመናል። ልጁም ታሑርዋይሊ «የወርቃማው ጦር ሰውዬ» ደግሞ ወደፊት ንጉሥ ሆነ። ዙሩ ቀዳሚ ወራሾቹን ቲቲያንና ሐንቲሊን ያስገደላቸው ለአሙና ሦስተኛው ልጅ ሑዚያ ወራሽነት እንዲያገኝ እንደ ነበር ይታስባል። ተለፒኑ ከቀዳሚዎቹ ይልቅ ሩኅሩኅ ይመስላል፤ ለሑዚያ ይቅርታ ሰጠ፣ በኋላም ሑዚያ ሲገደል ለሑዚያ፣ ቲቲያና ሐንቲሊ ገዳዮች ይቅርታ ሰጥቶ የእርሻ ሥራ አስገደዳቸው ይላል። ይህንን ሁሉ በቅድሚያ እንደ መሠረት ከተረከ በኋላ፣ የዐዋጁ ድንጋጌ እንዲህ ይላል፦ «በመላው ንጉሣዊ ቤተሠብ ውስጥ ደምን ማፍሰስ ተራ ነገር ሆኗል! ንግሥትም ኢሽታፓሪያ ዓርፈዋል። በኋላ ልዑል አሙና ለዕረፍት መጣ። የአማልክት ሰዎች [አረመኔ ቄሳውንት] በሐቱሳሽ አሁን ደምን ማፍሰስ ተራ ነገር ሆኗል! እያሉ ነው። እኔ ተለፒኑ በሐቱሳሽ ጉባኤ ጠራሁ። ከዚህ ሰዓት ጀምሮ፣ በሐቱሳሽ ማንም ሰው የንጉሣዊ ቤተሠብ ልጆችን አይበድላቸው ወይም ጩቤ አይዝባቸው! ልዑል አልጋ ወራሹ በኲር ልጅ ብቻ ንጉሥ ሆኖ ይጫን! በኲር ልዑል ባይኖር፣ ሁለተኛው ወንድ ልጅ ንጉሥ ይሁን። ነገር ግን ማንም ልዑል ወንድ ልጅ ባይኖር፣ የታላቅዋን ሴት ልጅ ባለቤት ወስደው እሱ ንጉሥ ይሁን!» ተለፒኑ በራሱ በኩል ንጉሥ የሆነው ንግሥቱ የአሙና ልጅ በመሆንዋ ስለ ነበር፣ ይህን መርህ እንደ ሕግ ለማጽናት አስቦ ነበር። በአንድ መስመር ተለፒኑ «በአባቴ ዙፋን ስቀመጥ» ስላለ፣ ማለቱ የንግሥቱ አባት ይሆናል። በዐዋጁ መጨረሻ ሁለተ ተጨማሪ ሕግጋት ስለ መግደልና ስለ ጠንቋይ ቀምረው ይሰጣሉ፦ የግድያም ጉዳይ እንዲሚከተል ነው፡ ማንም ሰው ቢገደል፣ የተገደለው ሰው ወራሽ እንዳለ ሁሉ ይደረግበታል። ይሙት ካለ ይሞታል፤ ይካሥ ካለ ግን ይካሣል። ንጉሡ በውሳኔው ውስጥ አይገባም።» በሐቱሻ ግዛት ውስጥ ስለሚደረግ ጥንቆላ ጉዳይ፦ እነዚህን ጉዳዮች በመግለጽ ትጉበት። ማንም በንጉሣዊ ቤተሠብ ውስጥ ጥንቆላ ቢሠራ ኖሮ፣ ይዙትና ወደ ንጉሡ ግቢ አስረክቡት። ለማያስረክበው ሰው ግን መጥፎ ይሆናል።» የኬጥያውያን ሕግጋት ቋንቋ ለዚህ ጽላት ተመሳሳይ ሲሆን መጀመርያው እንደ ሕገ መንግሥት የወጣው በተለፒኑ ዘመን እንደ ሆነ ታስቧል። የኬጥያውያን ጉባኤ ወይም «ፓንኩሽ» (እንደ መኳንንት ምክር ቤት) በዚያ ተመሠረተ። ተለፒኑ ደግሞ ከኪዙዋትና ታላቅ ንጉሥ ኢሽፑታሕሹ ጋራ ስምምነት እንደ ተዋወለ ይታውቃል። የተለፒኑ ሴት ልጅ ሐራፕሺሊ ወይም ሐራፕሼኪ ስትሆን የአሉዋምና ሚስት ሆነች፣ ነገር ግን በተለፒኑ ላይ ስላመጹ እሱ ወደ ማሊታሽኩር አሳደዳቸው። የተለፒኑ መጀመርያ ተከታይ የዚዳንታ ልጅ ዙሩ ልጅ ታሑርዋይሊ እንደ ሆነ ይመስላል። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ግን አሉዋምና ተከተላቸው። አሉዋምና ከታሑርዋይሊ እንደ ቀደመ የሚል አስተሳሰብ ደግሞ ብዙ ይታያል። የኬጥያውያን
47496
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B0%E1%88%8A%E1%8A%93%20%E1%8C%8E%E1%88%98%E1%8B%9D
ሰሊና ጎመዝ
ሰልና ሜሪ ጎመዝ (ተወለደች ሀምሌ ፲፱፻፹፬) አሜሪካዊት ዘፋኝና ተዋናይት ናት። ሰልና፣ የትወና ህይወቷ ገና በልጅነቷ ሲጀምር ተሳትፋ ባርኒ ኤንድ ፍረንድስ የተለቭዥን ተከታታይ ላይ እና በዛው የእድሜ ክልል ውስጥ አለክስ ሩሶ የተባለ ገጸ ባህሪን በድዝኒ ቻነል የተለቭዥን ተከታታይ ውዘርድ ኦቭ ዌቭርሊ ፕሌስ ላይ ተጫውታ ወደ ዝናው መጣች እንደ ተዋናይት፤ እንደ አቀንቃኝት ከፖፕ ሮክ ቡድኗ ሰልና ጎመዝ ዘ ሲንጋ እውቅና ብታገኝም የአሁን እሷነቷ በይበልጥ መገንባት የጀመረው በግል ባደረገችው ጉዞ ነው የመጀመሪያ አልበሟ እስታርዝ ዳንስ በ፳፻፭ ተለቀቀ የመጀመሪያ ምርጥ አስር ሙዚቃዋን የያዘው። እስከ ድረስ ሰልና ሽጣለች ከ፯ ሚልየን በላይ አልበሞች እና ከ፳፪ ሚልየን በላይ ነጠላዎች በአለምአቀፍ ይህ መረጃ ቢልቦርድን መሰረት አድርጎ። የተለያዩ ሽልማቶችን ስትወስድ ቢልቦርድ ሰይሟት ነበር "የአመቱ እንስት" በ፳፻፱። ማህበራዊ ድረገጾች ላይ አያሌ ክተላዎች ሲኖሯት በአንድ ወቅት ይበልጡን ተከታዮች በማፍራት ቀዳሚ ነበረች እንደ ግለሰብ፣ እንስትግራም ላይ። የሰልና ሌሎች የስራ ሙከራዎች ይካተታሉ፦ የመቀባቢያ፣ የአልባሳት፣ የሽቶ፣ እና የእጅ ቦርሳ ስራ ሙከራዎች። ሰልና ከብዙ ረጂ ተቋማትጋ አብራ የሰራች ሲሆን አገልግላለችም እንደ የዩንሰፍ አምባሳደር ከእድሜዋ ጀምሮ። የቀድሞ ህይወት ሰልና ተወለደች በ፲፱፻፹፬ ከአባቷ ርካርዶ ጆውል ጎመዝ እና ከመድረክ ተዋናይት እናቷ አማንዳ ዶውን ኮርንት። ስሟ የተሰየመው ከቲዠኖ አቀንቃኝቷ ሰልና ኩወንታኒላ በኋላ ነው። አባቷ የሜክሲኮ ዘር ሲኖረው እናቷ ደግሞ የተወሰነ የጣልያን። የህስፓንክ ማንነቷን አስመልክቶ ሰልና ብላለች እንደሆነች "የኩራት የሶስተኛ ትውልድ አሜሪካዊ፡ሜክሲኮአዊ" "ቤተሰቦቼ የኩንሲንረስ አከባበር አላቸው ወደ ኮምንየን ቤተ ክርስትያን እንሄዳለን፣ ካቶልክ የሆነ ምንም ነገር እናደርጋለን፣ ግን ባህላዊ ነገሮች ብዙም የሉንም መናፈሻ ሄዶ ባርብኪው ከማድረግ ውጪ እሁድ እሁድ ከቤተ ክርስትያን መልስ"። ሰልና የአባቷ ሀገር ቋንቋ የሜክሲኮ እስፓንሽን አቀላጥፋ መናገር ትችል ነበር እስከ እድሜ ሰባት በአምስት አመቷ ከእናቷጋ ብቻ ለመቅረት ሁኔታው አስገድዷት ነበር፦ የወላጆቿ መፋታት ሰልና ሁለት ታናናሽ ግማሽ እህቶች አሏት—አባትና እናቷ በፈጠረቱ ሌሎች የየብቻ ትዳሮች። ሰልና ተወለደች እናቷ የ፲፮ አመት ልጅ ሳለች ቤተሰቡ ገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ ችግር ነበረበት በሰልና የልጅነት እድሜዎች ውስጥ ሰልና አንስታለች የአንድ ዶላር ሩብ መፈለግ እደነበረባቸው ለመኪና በንዚን ለማግኘት ብቻ "ፈርቼ ነበር ቤተሰቦቼ አንድ አልነበሩም፣ መቼም ብርሀን አይቼ አላውቅም ነበር በሸለቆው ጫፍ እናቴ ጠንክራ በምትሰራበት ለኔ የተሻለ ህይወት ለማቅረብ ምን ልሆን እንደምችል ሰግቼ ነበር እዛ (ቴክሳስ) ምቆይ የነበረ ቢሆን"። "እናቴ ጠንካ ነበረች በዙሪያዬ፣ እኔን በአስራ ስድስት አመቷ መውለዷ ትልቅ ሀላፊነት ነው፤ ሁሉን [ትታለች] ለኔ ብላ ሶስት መተዳደሪያ ስራዎችን ይዛለች፣ ደግፊኛለች፣ ህይወቷን መስዋዕት አድርጋልኛለች"። ሰልና በልጅነቷ ከአያቶቿ ጋ ቅርብ ግንኙነት የነበራት ሲሆን አሳልፋለች የተለያዩ የህዝብ በአላትን ከነሱጋ ከፍ ባለችበት ጊዜ ወላጆቿ ማስተማርን ሲጨርሱ ብዙ አነሱ አያቶቿ ነበር የሚንከባከቧት። ብላለች፦ "አሳድገውኛል" እስካገኘች ድረስ የስኬት ጅማሮን በትእይንት ፕሮግራሞች። የስራ ታሪክ ከትወና ሙያዋጋ እነዚ ፊልሞች (ተከታታዮች) ላይ ሰርታለች፦ አናዘር ስንደረላ እስቶሪ ፕርንሰስ ፕሮተክሽን ፕሮግራም ውዘረድ ኦቭ ዌቨርሊ ፕሌስ ዘ ሙቪ ርሞና ኤንድ ቢዙስ ሞንቴ ካርሎ እስፕሪንግ ብሬከርስ ጌት እዌይ ዘ ፋንድመንተልስ ኦቭ ኬሪይንግ ዘ ደድ ዶንት ዳይ ኧ ሬይኒ ዴይ ኢን ንው ዮርክ ኦንሊ መርደርዝ እን ዘ ቢውልዲንግ (፳፻፲፬-ሚቀጥል)፣ እና ሆተል ትራንስልቨንያ (፳፻፬-የቀጠለ)። በአስተዳዳሪነት አግዛለች የነት ፍለክስ ተከታታዮችን፦ 13 ሪዝንስ ዋይ እና ልቪንግ አንዶክመንትድ በአጋዥ፡ኩባንያዋ ስር። ለቃለች አልበሞች ከቡድኗ ሰልና ጎመዝ ዘ ሲንጋ እና ሶስቱም አስር ውስጥ ገብተዋል ከቢልቦርድ ተመስክረዋልም የወርቅ በዘ ርኮርዲንግ ኢንደስትሪ አሶስዬሽን ኦቭ አሜሪካ፦ ኪስ ተል ኧ ይር ውዝአውት ሬይን እና ወን ዘ ሰን ጎዝ ዳውን የግል ሶስት አልበሞቿ፦ እስታርዝ ዳንስ ርቫይቨል እና ሬር ሁሉም አንደኝነት ላይ የተቀመጡ። አስር ውስጥ የገቡላት ዘፈኖቿ፦ "ከም ጌት እት"፣ "ዘ ሀርት ወንትስ ዋት እት ወንትስ"፣ "ጉድ ፎር ዩ"፣ "ሴም ኦልድ ሎቭ"፣ "ሀንድስ ቱ ማይሰልፍ"፣ "እት ኤንት ሚ"፣ እና የመጀመሪያ ቁጥር አንድ ዘፈኗ "ሉዝ ይው ቱ ሎቭ ሚ"። የሙዚቃ አይነት ሰልና የምትገለጸው እንደ ፖፕ አርቲስት ሲሆን ስራዎቿ ይከፋፈላሉ በአይነተ ሙዚቃዎች፦ ዳንስ፡ፖፕ እና ኢዲኤም፤ ሌሎች የሙዚቃ አይነቶችን መሞከሯ እንዳለ ሆኖ የመጀመሪያ አልበሟ ከቡድኗ ዘ ሲንጋ የለቀቀችው የኧለክትሮንክ ሮክ እና የፖፕ ሮክ ተጽእኖች ሲኖርበት አከታትላ ከዚ ቡድኗጋ የለቀቀቻቸው ዘፈኖች የዳንስ፡ፖፕ ድምጸ ምርጫ አለባቸው "ኧ ይር ዊዝአውት ሬይን" አልበም ታውቋል በስንት፡ፖፕ ባህሪያቶቹ፣ "ወን ዘ ሰን ጎዝ ዳውን" አልበም ደግሞ በይበልጥ ኧለክትሮፖፕ እና ድስኮፖፕ ዘውጎችን አካቷል። የግል የመጀመሪያ አልበሟ "እስታር ዳንስ" እጅጉን የኢዲኤም፡ፖፕ ተጽዕኖ የነበረበት ሲሆን የኧለክትሮንክ፣ ድስኮ፣ ተክኖ፣ እና የዳንስሆል ሙዚቃዊ ባህሪያቶች ነበሩበት። ዘፈኖቿ፦ "ዘ ሀርት ወንትስ ዋት እት ወንትስ" እና "ጉድ ፎር ዩ" በይበልጥ ጎልማ ፖፕን ነው ያስተዋወቁት በየክፍላቸው። ተጽእኖ ሰልና፣ ቀደም ባሉ ጊዜያት ብሩኖ ማርስን እንደ ተፅኖዋ ገልፃው ነበር፦ "የሙዚቃ አይነቱ በአጠቃላይ [ሁኔታው]፣ [በሙዚቃ] የሚቀርብበት መንገድ፣ እራሱን የሚይዝበት መንገድ" ብላለች። ክርስቲና አግወሌራ፣ ብርትኒ እስፒርስ፣ ቢዮንሴ፣ ሪሀናና ቴይለር እስዊፍትንም እንደ ተፀዕኖ ጠቅሳቸዋለች እነማ "እስታር ዳንስ" እና "ርቫይቨል" አልበሞቿ ላይ ተፅዕኖ ያሳደሩ የፖፕ ንጉሱ ማይክል ጃክሰን እህት ጃነት ጃክስን ተካታበት። የአሜሪካ ዘፋኞች የአሜሪካ የፊልም
53166
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8B%88%E1%88%8B%E1%8B%AD%E1%89%B3%20%E1%8B%9E%E1%8A%95
የወላይታ ዞን
ወላይታ ወይም ዎላይታ በኢትዮጵያ ውስጥ የአስተዳደር ዞን ነው። የትውልድ አገሩ በዞኑ ውስጥ ላለው የወላይታ ህዝብ ተሰይሟል። ወላይታ በደቡብ በጋሞ ጎፋ በምዕራብ ከዳውሮ የሚለየው የኦሞ ወንዝ በሰሜን ምዕራብ በከምባታ ጠምባሮ በሰሜን በሐዲያ በሰሜን ምስራቅ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ በቢልቴዎች ይዋሰናል። ወንዝ ከሲዳማ ክልል በደቡብ ምስራቅ በኩል ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል የሚለየው የአባያ ሀይቅ ነው። የወላይታ አስተዳደር ማዕከል ሶዶ ነው። ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች አረካ ቦዲቲ ጠበላ ቤሌ ገሱባ ጉኑኖ በዴሳ እና ዲምቱ ናቸው። ወላይታ 358 ኪሎ ሜትር (222 ማይል) በሁሉም ወቅቶች የሚመች መንገድ እና 425 ኪሎ ሜትር (264 ማይል) ደረቅ መንገዶች፣ በአማካይ የመንገድ ጥግግት 187 ኪሎ ሜትር በ1000 ካሬ ኪሎ ሜትር ነው። ከፍተኛው የዳሞታ ተራራ (2738 ሜትር) ነው። ታሪክ ከ 1894 በፊት የወላይታ ህዝብ በሶስት ስርወ መንግስት ውስጥ ከሃምሳ በላይ ንጉሶች አሉት። የወላይታ ነገሥታት ካዎ የሚል የወላይታ ብሄረሰብ ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ መጀመሪያው ሚሊኒየም ድረስ እስከ 1894 ድረስ የተለየ፣ ቀጣይነት ያለው፣ ጠንካራ እና ራሱን የቻለ መንግስት የነበረው ኩሩ ህዝብ ነው። በመጨረሻው የካዎ (ንጉስ) የወላይታ ቶና ጋጋ የተካሄደው የተቃውሞ ጦርነት በምኒልክ የግዛት ዘመን ከተደረጉት ደም አፋሳሽ ዘመቻዎች አንዱ ሲሆን ይህም የወላይታ መንግስት ከሌሎች የደቡብ ህዝቦች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር እንዲዋሃድ አድርጓል። ወደ ኢትዮጵያ ኢምፓየር ገባ። የወላይታ ወታደራዊ ተቃውሞ እና የምኒልክ ጄኔራሎች (ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ) መመከት የወላይታ ወታደራዊ ድርጅት እና ህዝብ ጥንካሬ አሳይቷል። በ1894 ዓ.ም የወላይታ ተቃዋሚዎች በራሳቸው በዳግማዊ አጼ ምኒልክ መሪነት ደም አፋሳሽ ጦርነት ካደረጉ በኋላ በኢትዮጵያ ድል ተቀዳጅተዋል። ከ1894 ዓ.ም ለዘመናት የዘለቀው ጭቆና ቢኖርም የወላይታ ህዝብ የተለየ ብሄራዊ ማንነት አለው ማለትም ህዝቡ ቋንቋ፣ባህል፣ወግ፣ታሪክ፣ስነ ልቦናዊ ሜካፕ እና ተያያዥ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያለው በመሆኑ እሱን የሚገልፅ እና ከሌሎች የሚለይ ያደርገዋል። ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በኢትዮጵያ። የወላይታ ሕዝብ በንጉሣዊው አገዛዝ ላይ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ነፃነትን ለማስፈን ያካሄደው ተቃውሞና ትግል፣ የወላይታ ሕዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ፀረ-ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ መከልከል የጀመሩትን የጸና እና ያልተቋረጠ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ትግል ምሳሌ ነው። ክልል የመሆን ጥያቄ በ1991-94 የሽግግር መንግስት ዘመን ወላይታ ክልል የራሱ ክልል ነበረው እሱም ክልሉ 9 ቢሆንም ፌዴሬሽኑ በ1995 ሲመሰረት ወደ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ተቀላቅሏል። ጀምሮ በሕዝብ ቅሬታ እና ራስን በራስ የማስተዳደር ተቃዋሚ አባላት ተደብድበዋል፣ ተሰቃይተዋል፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ወጣቶች ተሰደዋል። እ.ኤ.አ. በ1997 ደኢህዴን ዎጋጎዳን ለመፍጠር ሞክሯል፣ አጎራባች ብሄረሰቦችን ከወላይታ ጋር አዋህዶ፣ ይህም በመጨረሻ የወላይታ ህዝብን የመቶ አመት ባህልና አርማ ያበላሽ ነበር። ያ ሙከራ ከህዝቡ ከፍተኛ ትግል ታይቷል እናም የመንግስት ተመሳሳይነት ያለው እርምጃ በመጨረሻ ተትቷል ሆኖም በ1998 ወላይታ፣ ጋሞ ጎፋና ዳውሮ ተለያይተው የራሳቸውን ዞን አስተዳደር መስርተው ከነበረው የሰሜን ኦሞ ዞን ዋና ከተማ አርባ ምንጭ በሺዎች የሚቆጠሩ ታግተው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የወላይታ ብሔር ተወላጆች በኃይል ተፈናቅለዋል። እና 2000. በታዋቂው የጸጥታ ሃይሎች የወላይታ ተወላጆች ለራሳቸው ዞን በተሳካ ሁኔታ ሲዘምቱ እና አዲሱን የተቀናጀ ቋንቋ እና ማንነት ለመጫን የተደረገውን ሙከራ ውድቅ ባደረጉበት ወቅት ቢያንስ አምስት ሰዎች ተገድለዋል። እስከ 2000 ዓ.ም ወላይታ የሰሜን ኦሞ ዞን አካል ነበር፣ እና የ1994ቱ ሀገር አቀፍ ቆጠራ ነዋሪዎቹን የዚያ ዞን አካል አድርጎ ይቆጥራል። ይሁን እንጂ በሴሜን ኦሞ በተለያዩ ብሔረሰቦች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት፣ በወላይታ ተወቃሽነት የተነሳው “የጎሣ ብሔርተኝነት” እና ገዥው ፓርቲ ትንንሾቹን ብሔረሰቦች ማስተባበር፣ ማጠናከር እና አንድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ለማጉላት ጥረት ቢያደርግም ከግቡ ለመድረስ በ2000 ዓ.ም ዞኑ እንዲከፋፈል ምክንያት የሆነው "የመንግስት ሀብት በብቃት መጠቀሙ" ወላይታ ብቻ ሳይሆን ጋሞ ጎፋና ዳውሮ ዞኖች እንዲሁም ሁለት ልዩ ወረዳዎች እንዲፈጠሩ አድርጓል። የወላይታ ብሄረሰብ ክልል የመደራጀት ህገ መንግስታዊ መብቶች ከቅርብ አመታት ወዲህ እየተጠናከረ የመጣ ሲሆን በየደረጃው ሰፊ ምክክር ከተደረገ በኋላ የወላይታ ክልል መንግስት ለመመስረት የቀረበው ሀሳብ ፀድቋል። የዞኑ ምክር ቤት የክልልነት ጥያቄን በሙሉ ድምፅ የሰጠ ሲሆን ከህገ መንግስቱም ሆነ ከህገ መንግስቱ ጋር በመስማማት ህዝበ ውሳኔ እንዲሰጥ ለደቡብ ክልል መንግስት መደበኛ ደብዳቤ በ19/12/2011 ልኳል። የወላይታ ዞንን የሚወክሉ 38 የደቡብ ክልል ምክር ቤት አባላት ከክልሉ ምክር ቤት ራሳቸውን አግልለው ክልሉን ወደ 4 ክልሎች ለማደራጀት እንቅስቃሴን በመቃወም ራሳቸውን አግልለዋል። የወላይታ ዞን ተወካዮች ርምጃው ያቀረቡትን የክልልነት ጥያቄ ያላገናዘበ ነው ይላሉ። እ.ኤ.አ በግንቦት እና ታህሳስ 2011 ዞኑ ከደቡብ ክልል በመገንጠል በራሱ ክልል እንዲሆን የድጋፍ ሰልፍ በወላይታ ተካሂዷል። በታህሳስ 20 ቀን 2011 የተካሄደው ሰልፍ የክልሉ ምክር ቤት የዞኑን የክልል መንግስት ጥያቄ ወደ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ልኮ ህዝበ ውሳኔ እንዲያደርግ አለማድረጉን ተቃወሙ። መልከዓ ምድር ወላይታ በደቡብ ክልል ከሚገኙ 16 የዞን አስተዳደሮች አንዱ ሲሆን ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ 300 ኪሎ ሜትር (190 ማይል) አካባቢ ይገኛል። ወላይታ በሰሜን ምዕራብ በጣምባሮ ፣በምስራቅ በኩል ከአርሲ ኦሮሞ የሚከፍለው የቢልቴ ወንዝ ፣ደቡብ በአባያ ሀይቅ እና በኩጫ ፣በምእራብ በኩል በኦሞ ወንዝ የተገደበ ነው። የግልገል ጊቤ ሶስት ግድብ በኦሞ ወንዝ ላይ የተገነባ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ነው። ግድቡ 1870 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው በአፍሪካ ሶስተኛው ትልቁ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ነው። የሰፋፊው ክልል እፅዋት እና የአየር ንብረት በ1,500 እና 1,800 ሜትር (5,900 መካከል ባለው አጠቃላይ ከፍታ የተቀመጡ ናቸው። ከባህር ጠለል በላይ. ሆኖም ከ 2,000 ሜትር (6,600 ጫማ) በላይ ከፍታ ያላቸው አምስት ተራሮች አሉ። ከነዚያም ዳሞታ ተራራ ከባህር ጠለል በላይ 3,000 ሜትር ከፍታ ያለው ነው ኮረብታዎች ከሶዶ ዙርያ እና የኦሞ ወንዝ ተፋሰስ ከ 1,500 ሜትር (4,900 ጫማ) በታች ከሆነው በስተቀር ትላልቅ ደኖች የሉም። በአከባቢው እይታ ሁለት ክልሎች ብቻ አሉ-ደጋማ ቦታዎች (ጌዝያ) እና ቆላማ (ጋራአ)። በደጋማ ቦታዎች ላይ ጅረቶች እና ትናንሽ ወንዞች አሉ. በአባያ ሀይቅ ዙሪያ፣ የሚፈላ እና የሚንፋፋ ውሃ ያላቸው በርካታ የሙቀት ምንጮች አሉ። የወላይታ አፈር ቀይ ቀለም ያለው በዝናብ ጊዜ ቡናማና ጥቁር ሆኖ ብስባሽ እና የአሸዋ ልስላሴ ያለው ነው። ደረቅ ወቅት አፈርን እንደ ጡብ ያጠነክራል, ከዝናብ በኋላ ማረስ እና መቆፈር ይቻላል. ጉድጓዶች በሚቆፈሩበት ጊዜ እንደተረጋገጠው የአፈር ንብርብር በጣም ጥልቀት በአማካይ 30 ሜትር በሜዳውና በኮረብታው ላይ. አፈሩ ለም ሲሆን ዝናቡ መደበኛ በሚሆንበት ጊዜ በአመት ሁለት ሰብሎችን ያመርታል። የአየር ንብረት የወላይታ የአየር ንብረት ከመጋቢት እስከ ጥቅምት የሚዘልቅ የሁለትዮሽ የዝናብ መጠን አለው። የመጀመሪያው የዝናብ ወቅት ከመጋቢት እስከ ግንቦት ድረስ ይቆያል. ወቅቱ ከሐምሌ እስከ ኦክቶበር የሚዘልቅ ሲሆን በሐምሌ እና ነሐሴ ከፍተኛው ጊዜ ነው. ባለፉት 43 ዓመታት አማካይ የዝናብ መጠን 1,014 ነበር። አማካይ ዓመታዊ የሙቀት መጠን 19.9 ነው ሴ, ከ 17.7 ወርሃዊ የሙቀት መጠን ጋር ሴ በጁላይ እስከ 22.1 ሴ በየካቲት እና መጋቢት. የአየር ንብረቱ የተረጋጋ ሲሆን የሙቀት መጠኑ ከ 24 እስከ 30 ይለያያል በቀን ውስጥ ሴ እና ከ 16 እስከ 20 ሴ በሌሊት ዓመቱን በሙሉ። አመቱ በሁለት ወቅቶች ይከፈላል።እርጥብ ወቅት (ባልጉዋ) ከሰኔ እስከ ጥቅምት፣ እና ደረቃማ ወቅት (ቦኒያ) ከጥቅምት እስከ ሰኔ፣ በየካቲት ወር "ትንሽ ዝናብ" (ባዴዴሳ) እየተባለ በሚጠራው አጭር ጊዜ ተበላሽቷል። የጠቅላላው ክልል አማካይ የዝናብ መጠን 1,350 ሚሊ ሜትር (53 ውስጥ) በዓመት. የደረቁ ወቅት ከምስራቅ በሚነፍስ ኃይለኛ ነፋስ ይታወቃል. በእርጥብ ወቅቶች, ከባድ ዝናብ እና ኃይለኛ አውሎ ነፋሶች, በወቅቱ መጨረሻ ላይ ሙሉ ምሽት ወይም ምሽት ሊቆዩ የሚችሉ የተለመዱ ክስተቶች ናቸው. ጭጋግ በዝናብ ወቅት በየቀኑ ማለዳ በሸለቆዎች ውስጥ ይታያል; ከዚያም በፀሐይ የመጀመሪያ ሰዓታት ውስጥ ይተናል. በሁለቱም ደረቅ እና እርጥብ ወቅቶች ወይ ሰብሎችን የሚያጠፋ በረዶ ወይም አውሎ ነፋሶች ዛፎችን የሚያንኳኳ, ሊሆኑ የሚችሉ ክስተቶች ናቸው። የስነ ሕዝብ አወቃቀር በ2020 የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ባደረገው የህዝብ ቁጥር ትንበያ መሰረት ዞኑ በአጠቃላይ 5,385,782 ህዝብ ሲኖር ሄክታር (1,741.980 የቆዳ ስፋት አለው። ከዞኑ አጠቃላይ ህዝብ ሴቶች 2,698,261 እና ወንዶች 2,687,021 ናቸው. የወላይታ ህዝብ ብዛት 356.67 ነው። 366,567 ወይም 11.49% የከተማ ነዋሪ ሲሆኑ፣ ተጨማሪ 1,196 ወይም 0.08% ብዙሀን አራማጆች ናቸው። በዞኑ በአጠቃላይ 310,454 አባወራዎች የተቆጠሩ ሲሆን ይህም በአማካኝ 4.84 ሰዎች ለአንድ ቤተሰብ እና 297,981 መኖሪያ ቤቶች ተገኝተዋል። በዞኑ ትልቁ ብሄረሰብ ወላይታ (96.31%); ሁሉም ሌሎች ብሄረሰቦች ከህዝቡ 3.69% ናቸው። ወላይታ እንደ መጀመሪያ ቋንቋ በ96.82% ነዋሪዎች ይነገራል። የተቀሩት 3.18% ሌሎች የመጀመሪያ ቋንቋዎችን ይናገራሉ። 71.34% ፕሮቴስታንቶች ነበሩ፣ 21% የሚሆነው ህዝብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትናን እንደሚከተል ተናግሯል፣ 5.35% ደግሞ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ናቸው። ከተማነት የወላይታ ዞን አስራ ስድስት ወረዳዎችና ስድስት የከተማ አስተዳደሮችን ያቀፈ ነው። በወላይታ ዞን የተለያዩ ከተሞችና ከተሞችም አሉ። ሶዶ ከተማ የአስተዳደር እና የንግድ ማዕከል ስትሆን ወደ መንገዶች መሃል ላይ ትገኛለች እና ሰባት መግቢያ በሮች። በወላይታ ዞን የሚገኙ የከተማ ማዕከላት የሚከተሉት ናቸው። አረካ ሆቢቻ ባዳ በዴሳ በቅሎ ሰኞ ባሌ ሀዋሳ ቢጠና ቦዲቲ ቦምቤ ዳልቦ ዲምቱ ኤዶ [ጊፋታ[ፋራቾ]] ጋቼኖ ጋራ ጎዶ ገሱባ ጉኑኖ ሀላሌ ቀርጨጬ ላሾ ሻንቶ ሶዶ ጠበላ ባህል ጊፋታ በየአመቱ በመስከረም ወር ከሚከበረው የወላይታ ስነ-ስርአት መካከል በጣም ታዋቂው በዓል ነው። በወላይታ ጊፋታ (ማስቃላ) የተሰኘው የዘመን መለወጫ በዓል በዋዜማው እና በበአሉ ሳምንታት ልዩ ልዩ ምግቦችን ባቺራ እና ሙቹዋን በመመገብ ተከብሯል። ጊፋታ ከብዙ መቶ አመታት በፊት ወላይታዎች ሲያከብሩት የነበረው የወላይታ አዲስ አመት በዓል ነው። ጊፋታ በየአመቱ ሁሌም እሁድ ይከበራል ይህም በመስከረም (መስከረም) 14 እና 20 መካከል ነው ጊፋታ ሁሉንም በቅርብ እና በሩቅ የሚያገናኝ ድልድይ ነው። ወደ ወላይታ ሶዶ የሚመጡ ቱሪስቶች በቡታጅራ 310 አካባቢ በባህር ላይ በመጓዝ ከአዲስ አበባ ወደ ከተማዋ ይገባሉ። ወይም ሻሸመኔ መንገዶች 380 አካባቢ በአማራጭ፣ ቱሪስቶች ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ የአውቶቡስ ማጓጓዣ ወይም በአየር በመጓዝ አርባ ምንጭ በመብረር ከአርባ ምንጭ ወደ ወላይታ ሶዶ የየብስ ትራንስፖርት ሊወስዱ ይችላሉ። ከተማዋ የአውቶቡስ ተርሚናል እና አየር ማረፊያ አላት። ይሁን እንጂ የኋለኛው ሙሉ በሙሉ አይሰራም እና የንግድ በረራዎችን አይቀበልም. በወላይታ ዞን የተፈጥሮ ቅርስ እና የባህል ቅርስ የቱሪስት ገበያዎችን ለመያዝ ያለውን አቅም ለመገምገም የተመረጡ የተለያዩ የቱሪስት ስፍራዎች አሉ። አጆራ ፏፏቴዎች የአጆራ ፏፏቴዎች በግምት 390 የሚጠጉ በአጃቾ እና በሶኪ ወንዞች የተፈጠሩ መንታ ፏፏቴዎች ናቸው። ከአዲስ አበባ የአጃቾ ፏፏቴ 210 ሜትር (690 ይወርዳል ከገደሉ ጫፍ ላይ ሶኬው በትንሹ በ 170 ሜትር (560 ሲቀንስ 118ቱ ፏፏቴዎች 7 ይገኛሉ ከአረካ ከተማ በስተሰሜን፣ ነገር ግን የቦታው መዳረሻ 25 ያህል ማሽከርከርን ይጠይቃል ከከተማው ቆሻሻ ጋር። እንደ ብዙ የቱሪስት መስህቦች በመላው ኢትዮጵያ፣ በአጆራ ፏፏቴ ቱሪዝም በአገር ውስጥ ቱሪስቶች የተያዘ ነው፣ አንዳንዴም ከውጭ አገር ቱሪስቶች በ23 ጊዜ ይበልጣል። በአመት ቦታው በአማካይ 14 አለም አቀፍ እና 195 የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች አሉት። የሞቸና ቦራጎ ሮክሼልተር ከወላይታ ሶዶ ከተማ በስተሰሜን ምዕራብ በደቡብ ምዕራብ የዳሞታ ተራራ ተዳፋት ላይ ይገኛል። ዳሞታ የዳሞት ተራራ ተብሎ የሚጠራው ከ 2,900 በላይ ከፍ ብሏል። ከባህር ጠለል በላይ ምንም እንኳን ሞቼና ቦራጎ ሮክሼልተር ከባህር ጠለል በላይ በ 2,200 አካባቢ ላይ ይገኛል። ወደ ሞቸና ቦራጎ ለመድረስ ቱሪስቶች በግምት 10 ያሽከረክራሉ ከወላይታ ሶዶ በሆሳዕና መንገድ። ወደ ቋጥኝ ሼልተር የሚወስደው ያልተስፋልት መንገድ መጥፋቱን የሚያመለክት ምልክት ነው። ባለፉት አመታት, የጣቢያው መዳረሻ ቀላል ሆኗል. ትንሽ የሚንጠባጠብ ፏፏቴ ከሮክሼልተሩ አናት ላይ ወደ ተራራው ግርጌ ወደሚሄድ ጅረት ትገባለች። እ.ኤ.አ. ከ2006 እስከ 2008 የፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አርኪኦሎጂካል ፕሮጀክት በመጠለያው ዘግይቶ የሚገኘውን የፕሌይስቶሴን ክምችት በመቆፈር ላይ ያተኮረ ነበር። የተፈጥሮ ድልድይ ይህ ድልድይ በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ከወረዳ ከተማ ገሱባ በ5 ኪሎ ሜትር እና ከዞኑ አስተዳደር ከተማ ሶዶ በ29 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። በማኒሳ በሚፈስሰው ወንዝ ላይ ከተቀመጠው አንድ ትልቅ ድንጋይ በተፈጥሮ የተሰራው ድልድይ ነው። አባላ ጮካሬ (ቢልቦ ፍል ውሃ) ንፍልውሃው በሁምቦ ወረዳ አበላ ማረቃ ቀበሌ ይገኛል። የክበብ ቅርጽ ያለው የፍል ምንጭ ሰፊ ቦታዎችን ይሸፍናል እና ጭስ እየጨመረ እና ከመሬት ውስጥ የሚፈልቅ አረፋዎች ያሉት ሲሆን የውሃ ትነት ከሩቅ ይታያል. ዳሞታ ተራራ የዳሞታ ተራራ በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ከሶዶ ከተማ ወደ ሰሜን 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር የሚጠጋ ነው። ስፖርት ወላይታ ውስጥ በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በአገር አቀፍና በአህጉር ደረጃ የሚወዳደሩ ክለቦች አሉ። ወላይታ ዲቻ አክሲዮን ማኅበር በሶዶ የሚገኝ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ ነው። ክለቡ በ2009 በወላይታ ልማት ማህበር የተመሰረተ ነው። ወላይታ ዲቻ አሁን በምስራቅ አፍሪካ ዜጎች እና በመላው አፍሪካ የተለመደ ስም ነው። የደቡብ ኢትዮጵያ ክለብ የግብፅን ሀያል ክለብ እና በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ አምስት ጊዜ አሸናፊውን ዛማሌክን በካይሮ በአስደናቂ የፍፁም ቅጣት ምት አሸንፏል። ክለቡ ወላይታ ቱሳ አክስዮን ማህበርን ተክቶ ቱሳ ተብሎ የሚጠራው በአዲስ መልክ ከመዋቀሩ በፊት እና በአዲስ መልክ ብቅ ብሏል። ክለቡ የጦና ንቦች የሚል ቅጽል ስም ያገኘው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከወላይታ መንግስት መሪ "ንጉስ ጦና" ነው። የወላይታ ዲቻ ክለብ በ2017 የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ ዋንጫ በማንሳት ለ 2018 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማለፉን ክለቡ ዛማሌክን አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜው ማለፍ ችሏል። ሌላው በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የወላይታ ሶዶ ከተማ ስፖርት ክለብ ነው። በ2011 በይፋ ተመስርቷል። ክለቡ በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ እየተሳተፈ ይገኛል። ቦዲቲ ከተማ በቦዲቲ ከተማ የተመሰረተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ ነው። ክለቡ የወላይታ ዞንን በመወከል በደቡብ ክልል በጂንካ ሻምፒዮና አድርጎ የውድድር ዘመኑን በድል አጠናቋል። የወላይታ ዲቻ የወንዶች ቮሊቦል ቡድን በጥር ወር 2005 ዓ.ም የተመሰረተው የወላይታ ዲቻ ቮሊቦል ቡድን በወላይታ ሶዶ የሚገኝ የስፖርት ቡድን ነው። ቡድኑ የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግን ብዙ ጊዜ አሸንፏል። በ2019 እና 2021 ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ቮሊቦል ክለቦች ሻምፒዮና ላይ ተሳትፏል አረካ ከተማ በወላይታ አረካ የሚገኝ ክለብ ነው። በይፋ የተመሰረተው በ2000 ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አባል ሲሆኑ በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ይጫወታሉ። መገናኛ ብዙሀን የወላይታ ዞን አስተዳደር ድህነትንና ኋላቀርነትን ለመቅረፍና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሻሻል የረዥም ጊዜና የመካከለኛ ጊዜ እቅድ በማውጣት ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ባደረገው ጥረት በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች በርካታ እመርቶችን አስመዝግቧል። ለተለያዩ የሚዲያ ምንጮች። በወላይታ የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ መንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኙትን ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና ኢንተርኔት እንዲሁም የግል ጋዜጦችና መጽሔቶችን ያቀፈ ነው። በሶዶ የሚገኙ የሬድዮ ማሰራጫ ጣቢያዎች ራዲዮ ወጌታ 96.6 እና ራዲዮ ፋና 99.9 ይገኙበታል። ሳተላይት ቴሌቭዥን በኢትዮጵያ ለብዙ አመታት ተወዳጅነትን አግኝቷል። ከዚህ በተጨማሪም በአካባቢው የቴሌቭዥን መገናኛ ብዙሀን ባለመኖሩ ከፍተኛ ኢንቨስት በማድረግ የወላይታ ዞንን ህዝብ ባህላዊና ታሪካዊ መረጃዎችን ተደራሽ ያደረገ የወላይታ ቲቪ ነው። ትምህርት ትምህርት የአንድን ሀገር ዘላቂ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገት ለማረጋገጥ ቁልፍ ነው። የወላይታ ዞን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በገጠር የሚገኝ እና በወፍራም የሚኖር አካባቢ ነው። የትምህርት ስርዓቱ ጥሩ ትምህርት እና እገዛ ለመስጠት እየታገለ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አቅርቦት ውስን ነው። ለዚህም በዞኑ ያለውን የትምህርት ሥርዓት ለማሻሻል የዞን ትምህርት መምሪያ ከስኮትላንድ መሪ ዓለም አቀፍ የትምህርት በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር። ይህ ድርጅት ከሰሃራ በስተደቡብ ባሉ አፍሪካ እና ከዚያም በላይ ትምህርትን ለማሻሻል እየሰራ ነው። በወላይታ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ጥንታዊ ትምህርት ቤቶች መካከል ያሉ ትምህርት ቤቶች አሉ። ለምሳሌ በ1933 እና 1945 ዓ.ም የተቋቋሙት የዱቦ የእመቤታችን የካቶሊክ ትምህርት ቤት እና ሊጋባ አባ-ሰብስብ ትምህርት ቤት። ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ 2007 የተመሰረተ, በሶዶ ውስጥ የሚገኝ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው. ዩኒቨርሲቲው በመማር/መማር፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎቶች ላይ ተሰማርቷል። ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ አካባቢዎች እንደ ጋንዳባ፣ ኦቶና እና ዳውሮ ታርቻ ካምፓስ ውስጥ ካምፓሶች አሉት። የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ይህ ኮሌጅ በ2001 ዓ.ም. በወላይታ ሶዶ ከተማ የተቋቋመ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ነው። ከእነዚህም በተጨማሪ የሶዶ ከተማ ትምህርት ቤቶች ወላይታ ሶዶ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት፣ ወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት እና ቦጋለ ዋለሉ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ይገኙበታል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪዎች ስም ዝርዝር የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪዎች ከ2000 ዓ.ም. ከ2000 እስከ 2001፣ ማሞ ጎደቦ፣ ደኢህዴን ከ 2001 እስከ 2004, ከ2004 እስከ 2008፣ አማኑኤል ኦቶሮ፣ ደኢህዴን ከ2008 እስከ 2010፣ ኃይለብርሃን ዜና፣ ደኢህዴን ከ2011 እስከ 2013፣ ተስፋዬ ይገዙ፣ ደኢህዴን ከ2013 እስከ 2016፣ ከ 2016 እስከ 2018, አስራት ተራ, ፒኤችዲ, ከጁላይ 2018 እስከ ህዳር 2018፣ ጌታሁን ጋረደው፣ ፒኤችዲ፣ ከ2018 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2020፣ ዳጋቶ ኩምቤ፣ የብልጽግና ፓርቲ ከነሐሴ 28 ቀን 2020 እስከ ኦክቶበር 19 ቀን 2021፣ እንድሪያስ ጌታ፣ ፒኤችዲ፣ የብልጽግና ፓርቲ ኦክቶበር 19፣ 2021 አክሊሉ ለማ፣ የብልጽግና ፓርቲ ለማቅረብ የአስተዳደር ክፍሎች ለሁሉም አስተዳደራዊ ዓላማ እንደ ወረዳ የተቆጠሩ የከተማ አስተዳደሮች። ኢኮኖሚ ግብርና ከ90% በላይ ለሚሆነው የገጠር ህዝብ መተዳደሪያ ነው። የእንስሳት እርባታ ከሰብል ምርት ጋር የተጣጣመ ሲሆን የወላይታ የእንስሳት ቁጥር የሚገመተው 685,886 የቀንድ ከብቶች፣ 87,525 በጎች፣ 90,215 ፍየሎች፣ 1951 ፈረሶች፣ 669,822 የዶሮ እርባታ እና 38,564 የንብ ቀፎ ናቸው። አርሶ አደሮች በከብት እርባታ የታወቁ ሲሆኑ በዋናነት ከብት በኦርጋኒክ ስጋ እና ቅቤ (ሚሊዮን, 2003)። በአገር ውስጥ/በቤት ላይ የተመሰረተ መኖ ማሟያ/ማጎሪያ (የእህል እህል፣ ሥርና ቱር ሰብል)፣ የቤት ውስጥ ተረፈ ምርት፣ ሳር (ታከለ እና ሃብታሙ፣ 2009) በሬዎችን የማድለብ የረጅም ጊዜ ባህል አላቸው። በወተት ምርት እድገትን ለማስመዝገብ ጠንካራ አቅም ካላቸው አካባቢዎች መካከል የሶዶ የወተት ማፍሰሻ አንዱ ነው። በቆሎ፣ ባቄላ፣ ጣሮ፣ ስኳር ድንች፣ እንሰት፣ ሙዝ፣ አቮካዶ፣ ማንጎ እና ቡና በወላይታ እና አካባቢው ለሚገኙ አነስተኛ አርሶ አደሮች ከፍተኛ ጥቅም ያላቸው ዋና ዋና ሰብሎች ናቸው 2020)። ካሳቫ በዘመናችን እያደገ ነው። የእህል፣ የስር ሰብል፣ የእንሰት እና የቡና ምርትን የሚያካትቱ ድብልቅ እርሻዎች ይተገበራሉ። ኢንሴት በወላይታ ምግብ ኢኮኖሚ ውስጥ አስፈላጊ አካል ነው እና እንደ ዋና፣ ወይም አብሮ-ዋና ምግብ ሆኖ ያገለግላል። መሬት በጣም አናሳ በሆነበት እና በዚህም ምክንያት የእህል ምርት ዝቅተኛ በሆነበት፣ ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ ኢንሴት ለምግብ ዋስትና የተወሰነ እድል ይሰጣል። ኤንሴት ድርቅን የመቋቋም ባህሪ ስላለው ታዋቂ ነው። እንስሳት እና ዕፅዋት በወላይታ የእንስሳት ዝርያዎች ስርጭትም የተለያየ ነው። መካከለኛ ደረጃ ያላቸው አጥቢ እንስሳት በብዛት ይገኛሉ፣ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የአረም እንስሳት እና አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የዳርቻ ዝርያዎች። በዓመቱ ውስጥ የባሕር ዛፍ፣ ጥድ፣ ግራር፣ ማግኖሊያ፣ ግዙፍ ሾላዎች ከሐሰተኛ የሙዝ ዛፎች (ኡታ) ጋር አብረው ይኖራሉ። በእርጥብ ወቅት መጨረሻ ላይ ሣር ሦስት ሜትር ቁመት ሊደርስ ይችላል. ማህበረሰቦቹ በትልቅ የእህል እርሻ እና ከምንም በላይ በትላልቅ የጥጥ እርሻዎች የተከበቡ ሲሆን ይህም የሀብታቸው ማሳያ ይሆናል። እነሆ የጥጥ መሬት፣ የኢትዮጵያ ካባዎች የሚመረቱበት፣ ይህ ተክል የሚበቅልበት፣ ከቡና ጋር ተዳምሮ የኢትዮጵያ የአሁን የሀብት ምንጭ የሆነውና በቅርቡም የአገሪቱ ዋነኛ የኤክስፖርት ምርት ይሆናል። በቆሎ፣ ስንዴ፣ ዱራ፣ ገብስ እና ጤፍ ሁሉም በአካባቢው ይበቅላል። ብዙዎቹ በዓመት ሁለት ጊዜ ሊሰበሰቡ ይችላሉ. ሁሉም የሜዲትራኒያን ዛፎች ዓመቱን ሙሉ ፍሬ ያመርታሉ-ወይን, ፖም, ፒር, ኮክ, አፕሪኮት, ብርቱካን, መንደሪን, ሙዝ, ፓፓያ, አቮካዶ, ወዘተ. ታዋቂ ሰዎች ለገሰ ሞጣ ባራታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ በደርግ ጊዜ ስምዖን ጋሎሬ የኢሉባቦር እና የሰሜን ኦሞ ክልል ዋና አስተዳዳሪ ነበር። ካዎ ሞቶሎሚ ሳቶ, መስራች እና በጣም ታዋቂው የወላይታ ንጉስ ንጉስ አንዱ. በዳሞት መንግሥት በ12ኛው ክፍለ ዘመን የአሁኗን ኢትዮጵያ አብዛኛውን ክፍል ገዛ። ካዎ ኦጋቶ ሳና ከትግሬ ስርወ መንግስት ጋር በወላይታ ግዛት ውስጥ ከታወቁት ንጉስ አንዱ ነበር። ካዎ ሳና ቱቤ የወላይታ ትግሬ 9ኛ ንጉስ ነበር የካዎ ጦና ጋጋ የመጨረሻው የወላይታ ንጉስ ንጉስ። ከታላላቅ ተዋጊ እና ኃያል የወላይታ ንጉስ አንዱ እንደሆነ ይታመን ነበር። ሠራዊቱ የንጉሥ ምኒልክን ጦር ስድስት ጊዜ አሸንፎ በ1896 በምኒልክ እና በአባ ጅፋር ጥምር ጦር ተሸንፏል። ፋሬው አልታዬ የወላይታ ዞን ሁለተኛ ዋና አስተዳዳሪ እና ፖለቲከኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ኢንጂነር የፌደራል ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ ዶክትሬት እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። በቻይና አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ሮማን ተስፋዬ የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤት (2012-2018) ቀደም ሲል በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም እና ሌሎች ቢሮዎች ውስጥ ከፍተኛ የአመራር ቦታዎችን ትይዝ ነበር ሳንቾ ገብሬ ኢትዮጵያዊው ዘፋኝ፣ ኮሪዮግራፈር እና ዳንሰኛ። ጊልዶ ካሳ የኢትዮጵያ ሪከርድ አዘጋጅ፣ ግጥም ደራሲ እና ዘፋኝ ካሙዙ ካሳ የኢትዮጵያ ሙዚቃ አቀናባሪ እና ዜማ ደራሲ። ተክለወልድ አጥናፉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ያስተዳድሩ የነበሩት ፖለቲከኛ። መንግስቱ ኃይለ ማርያም ከ1977 እስከ 1991 የኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር እና ከ1984 እስከ 1991 የኢትዮጵያ የሰራተኞች ፓርቲ ዋና ፀሀፊ የነበሩት ኢትዮጵያዊ ወታደር እና ፖለቲከኛ ነበሩ። ጌታሁን ጋረደው (ፒኤችዲ); የኢፌዲሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ የቀድሞ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሹሩን አለማየሁ አዴህ የቀድሞ ክብርት (ዶክትሬት) ይባላሉ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሳተላይት ልማት ቡድን መሪ ናቸው። ቸርነት ጉግሳ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚጫወተው ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሽናል ነው። ዋቢዎች የኢትዮጵያ ዞኖች ወላይታ
9591
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B0%E1%88%A8%E1%89%B5%20%E1%89%80
ተረት ቀ
ቀለም ሲበጠበጥ ብርእ ሲቀረጥ ቀለም በቀንድ ውስጥ ጨለማ ነው ሲፃፍ ግን ብርሃን ነው ቀለም ሲበጠበጥ ብርእ ቅረጹልኝ ቀለበት ለቆማጣ ሚዶ ለመላጣ ቀሊል አማት ሲሶ በትር አላት ቀላጅ የሰይጣን ወዳጅ ቀላዋጭ ወጥ ያውቃል ቀልብ የሌለው ውሻ ጠዲቅ አምጡልኝ ይላል ቀልድና ቅዘን ቤት ያጠፋል ቀልደኛ አልቅሶ ካልተናገረ የሚያምነው የለም ቀልደኛ ገበሬ ሲያስቀን አደረ ቀልደኛ ገበሬ ናይት ክለብ ከፈተ ቀልደኛ ጎረምሳ እያራ ያፏጫል ቀልድና ቅዘን ቤት ያበላሻል ቀሙን ላይቀር ከነጫማቸው ቀማኛና ሽፍታ ጭለማና ማታ ቀርቀሬ ወርጄ ማር ስልስ ማር ልከፍል ቀስ በመቀስ አንቁላል በአግሩይሂዳል ቀስ እንዳይደፈረስ ቀስ እንዳይፈስ ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል ቀስ በቀስ አባይም ዝናብ ይሆናል ቀበሮ ናት የገጠሩዋ ሚዳቋ ናት የሰፈሩዋ ቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለች ቀበቶ ለማፈኛ ሰንሰለት ለማቆራኛ ቀበኛ ማሰሪያውን በልቶ ያሳጥራል ቀበኛ ከብት ዋጋውን ያደርስ ቀባሪ በፈጣሪ ቀብረው ሲመለሱ እግዜር ይማርዎ ቀብሮ የሚመለስ የሚመለስ አይመስለውም ቀኑ የጨለመበት መንገዱ ዘንግ ነው ቀና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ ቀና ቢታጣ ይመለመላል ጎባጣ ቀናውን ብነግራት ውልግድግዱን አለች ቀን ስው መስሎ ማታ ጅራት አብቅሎ ቀን ሲከፋ በግ ይነክሳል ቀን ሲጥለው ሁሉ ይጠላው ቀን ሲገለበጥ ውሀ ወደ ላይ ይፈሳል ቀን ሲደርስ አምባ ይፈርስ ቀን ሳይቆጥሩ ውሻ ሳይጠሩ ደረሰ በእግሩ ቀንበር ታርቆ ጣውንት ታርቆ ምን ይሆናል ቀንበር ታንቆ ጣውንት ታርቆ ምን ይሆናል ቀን በበቅሎ ማታ በቆሎ ቀን በቅሎ ማታ ቆሎ ቀን ቢረዝም ልብ ያደክም ቀን ቢረዝም ልብ ይደክም ቀን ቢቆጥሩ ውሻ ቢጠሩ ደረሰ በእግሩ ቀን ቢቆጥሩ ውሻ ቢጠሩ ይደርሳል በእግሩ ቀን ባጀብ ሌት በዘብ ቀን አይጥለው የቀለም ሰረገላ አያሰናክለው ቀን አይጥለው ጠጅ አያስክረው ቀን አይጥለው ጠጅ አያሰክረው የለም ቀን እስኪወጣ ያባቴ ገበሬ ያግባኝ ቀን እስኪያልፍልሽ ያባትሽ ሎሌ ያግባሽ ቀን እስኪያልፍ ያለፋል ቀን እስኪያልፍ ያባቴ ባሪያ ያግባኝ ቀን እስኪያልፍ ያባቴ ባሪያ ይግዛኝ ቀን እንደተራዳ ሌት እንደ ግርግዳ ቀን ከህዝብ ሌት ከጅብ ቀን ከጣለው ሁሉ ይጥለው ቀን ካልለቀሙ ሌት አይቅሙ ቀን ካለቀሙ ሌት አይቅሙ ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ቀን የጎደለበት ጠገራ አይጥ ይበላዋል ቀን ይነዳ እንደ ፍሪዳ ቀንና ጨርቅ እንደምንም ያልቅ ቀንና ጨርቅ ያልቃል ብልህ ያውቃል ቀንዳምን በሬ ቀንድ ቀንዱን ቀንዱ ሰማይ ጠቀስ ጭራው ምድር አበስ ቀንድ ካላት ላም ጎዳ ትከፋለች ቀንድና ጅራት ለዋንጫ አለፉ ቀንድ እገባበት ጅራት አይቀርም ቀንድ ውስጥ ገብቶ ጅራት አይቀርም ቀኝም ሰገሩ ግራም ሰገሩ መገናኛው ኮሩ ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ ቀድሞ ነበር እንጂ ተራምዶ ማለፍ አሁን ምን ይሆናል ተይዞ መለፍለፍ ቀይ ምላሱ ጥቁር እራሱ ቀይ ሰው መልክ አይፈጅም ቀይ እንደበርበሬ ጥሩ እንደ ብርሌ ቀዳዳ ያፈሳል ግቢ ያፈርሳል ቀድሞ ሰኞን አለመሆን ነው ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል ቀድሞ የሚናገረውን ሰው ይጠላዋል ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል ቀድሞ የተናገረውን ሰው ይጠላዋል ቀዶ ያለበሰ ቆርሶ ያጎረሰ ቀጥኜ ቢያየኝ ጅማት ለመነኝ ቀጥኜ ቢያዩኝ ጅማት ለመኑኝ ቀጥኜ ቢያዩኝ ሞዴል ነሽ አሉኝ ቁልቢጥ የላት ቁና አማራት ቁልቢጥ የላት ድርጎ አማራት ቁመህ ተከራከር ዙረህ ተመካከር ቁመህ ተናገር ዙረህ ተመካከር ቁመቷ ቢያጥር እንደ ድምብላል ውዷ ክፉ ነው ይደበልላል ቁም እንደአላማ ቁረጥ እንደጫማ ቁም እንዳላማ ጥልቅ እንደጫማ ቁም ነገረኛ መምሰል የተለመደ አመል ቁም ነገር ይዞ ተረት ቂም ይዞ ጸሎት ቁራ ሲነጣ አህያ ቀንድ ያወጣ ቁራ ስሙን የጠራ ቁርበት ምን ያንቋቋሀል ቢሉት ባያድለኝ ነው እንጂ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ ቁርበት ምን ያንጓጓሀል ቢሉት ባያድለኝ ነው እንጂ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ ቁርጥማት ቢያብር አልጋ ላይ ያማቅቃል ቁርጥ ያጠግባል ተስፋ ያታልላል ቁቅም ከፈስ ተቆጠረች ቁና ለመስፈሪያ ብርብራ ለማስከሪያ ቁንጥጫ ይሻላል ከግልምጫ ቁንጫ ለትልቅ ሰው ይበረታል ይባላል ቁንጫ መሄድ ሳትማር መዝለል ትማራለች ቁንጫ ሞኝ ናት ቀን ትበራለች ተለቃቅማ ታልቃለች ቁንጫ ውሀ ወረጅ ቢሏት ስፈናጠር የሰው ዶጮ እሰብር አለች ቁጥቋጦም ሲያድግ ዛፍ ይሆናል ቁጥቋጦ ሲያድግ ዛፍ ይሆናል ቁጥቋጦ ያለዛፍ አይሆንም ቁጩና ብስጩ አልማችሁ ፍጩ ቁጭትና መረቅ ለጊዜው ይጣፍጣል ቁጭትና መጠጥ ለጊዜው ይጣፍጥ ቁፍ ቁፍ አሰኘሽ እንደቄብ ዶሮ ለመከራ ላሳርሽ ኖሮ ቂል ሲረግሙት የመረቁት ይመስለዋል ቂል አይሙት እንዲያጫውት ቂልን ለብቻው ስደበው ራሱን ባደባባይ እንዲሰደብ ቂልን አንድ ጊዜ ስደበው ሲሰደብ ይኖራል ቂልን ድንጋይ ተማትቶ ጌታና ሎሌ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ ቂል ከጠገበበት አይወጣም ቂል ያገኘው ፈሊጥ ውሻ የደፋው ሊጥ ቂምህን አትርሳ የወደቀን አንሳ ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት ጭድ አዝሎ ወዘት ቂጡን የተወጋ ውሻ እንደልቡ አይጮህም ቂጡ የቆሰለ ውሻ እንደልቡ አይጮህም ቂጥ ቢወድል ፈስ አያድን ቂጥ ቢያብጥ ልብ አይሆንም ቂጥኛም ከውርዴ ይማከራል ቂጥኛም ከውርዴ ይውላል ቂጥ ገልቦ ክንብንብ ቂም ቂም ያሰኘሽ እንደዶሮ ለካስ ለመከራሽ ላሳርሽ ኖሮ ቂፍ ቂፍ ያሰኘሽ እንደ ቄብ ዶሮ ለመከራሽ ላሳርሽ ኖሮ ቃልህ ሳይዘጋ እግርህ ሳይዘረጋ ቄሱም ዝም መጽሀፉም ዝም ቄስ ለኑዛዜ ፍቅር ለሚዜ ቄስ ምን ይሻል ጠላ ነገር ምን ይሻል ችላ ቄስ ኤርክሶን መምህሩ እናት አያስቀብሩ ቄስ እበር አረመኔ ከማህበር ቄስ ካናዘዘው እድሜ ያናዘዘው ቄስ ካፈረሰ ዲያቆን ከረከሰ ቄስና ንብ እያዩ እሳት ይገባሉ ቄስና ንብ እያየ እሳት ይገባል ቄስ ያዘዘህን አድርግ እንጂ ቄስ ያደረገውን አታድርግ ቅል ባገሩ ድንጋይ ይሰብራል ቅል ባገሩ ደንጊያን ይሰብራል ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ሎሌና ጌታ ተሟግቶ ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ሎሌና ጌታ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ጌታና ሎሌ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ ቅልውጥ አሳስቦ ይጥላል ዘመቻ ቅምሙ የበዛበት ወጥ አይፋጅ አይኮመጥጥ ቅማል እንኳን ካቅሟ ጥብጣብ ታስፈታለች ቅማል ውሀ ውረጅ ቢሏት ስንዳሰስ ለመቼ ልደርስ ቁንጫ ውሀ ውረጅ ቢሏት ስፈናጠር የሰው ዶጮ እሰብር አሉ ቅማል በጥፍር ቢድጧት ራስ ደህና አለች ቅማል ከአካላት ምስጢር ከቤት ቋንጣና ባለሟል ሳያር አይቀርም ቅዝምዝም ወዲያ ፍየል ወዲህ ቅርብ ያለ ጠበል ልጥ ይነከርበታል ቅርናታም ለቅርናታም ሰንቡሌ ሰንቡሌ ይባባላል ቅርንጫፉ እንደዛፉ ቅቤ መዛኝ ድርቅ ያወራል ቅቤ ሲለግም ወስፌ አይበሳውም ቅቤ ተነጥሮ ለመብላት ያባት የናት ቅቤና ቅልጥም ወዴት ግጥምጥም ቅቤ ይፍሰስ ከገንፎ አይተርፍ ቅቤ ይፍሰስ ከገንፎ አይለፍ ቅብጥና ቅልጥ አንድ ላይ ሲሄዱ ቅልጥ ብላ ቀረች ሶራስ ክመንገዱ ቅል በአገሩ ድንጋይ ይሰብራል ቅናት ያደርሳል ከሞት ቅናት ጥናት አያገናኝ ካባት ከናት ቅናት ጥናት አይገኝም ከናት ካባት ቅና ያለው በአባቱ ከረባት ይቀናል ቅና ያለው በናቱ ብልት ይቀናል ቅን በቅን ከማገልገል ፊት ለፊት ማውደልደል ቅንቡርስ የት ትሄዳለህ መተማ ትደርሳለህ ልብማ ቅንነት ለነፍስ መድሀኒት ቅንድብ ለአይን ጥቅሻ አስተማረች ቅዝምዝም ሲወረወር ጎንበስ ብለህ አሳልፈው ቅዠት ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም ቆላና ደጋ እመቤትና አልጋ ቆሎ ለዘር እንዶድ ለድግር አይሆንም ቆሎን ቢቆረጥሙት እንጂ ቢያሹት አያልቅም ቆመው የሰቀሉትን ቁጭ ብለው ለማውረድ ይቸግራል ቆማጣ ቤት አንድ ጣት ብርቅ ናት ቆማጣ ብለው ያው ቁምጥና ነው ሌላ ምን ይመጣል አለ ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል ቆሩ መቀበሪያው ያው ፈሩ ቆሩ በማን ምድር ትለፋ ቆርሶ ያላጎረሱትን ቀዶ ያላለበሱትን ብላቴና ማዘዝ አይገባም ቆቅ ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ቆንጆና እሸት አይታለፍም ቆዳ ማንጓጓቱን ስሱ መጓጓቱን ቆዳ ማንጓጓቱን ስሱ መጓጓቱን አይተውም ቆዳ ሲወደድ በሬህን እረድ ቆጥሮ የማይሰጥ ሌባ ቆጥሮ የማይቀበል ሌባ
50439
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%89%B5%E1%88%AB%20%E1%8A%A6%E1%88%AD%E1%89%B6%E1%8B%B6%E1%8A%AD%E1%88%B5%20%E1%89%B0%E1%8B%8B%E1%88%95%E1%8B%B6%20%E1%89%A4%E1%89%B0%E1%8A%AD%E1%88%AD%E1%88%B5%E1%89%B2%E1%8B%AB%E1%8A%95
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ! መሠረተ እምነትን ትምህርትን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኤርትራ ሓንቲ ቅድስት ሓዋርያዊት ኣጽናፋዊት ቤተ ክርስቲያን እያ፡- ‘ኤርትራዊት’ ዝተባህለትሉ ምኽንያት ኣብ ሃገረ ኤርትራ እትርከብ ብምዃና፣ ‘ኦርቶዶክስ’ ዝተባህለትሉ ምኽንያት ቅኑዕ እምነት ስለዝኃዘት፣ ‘ተዋሕዶ’ ዝተባህለትሉ ምኽንያት ድማ ጐይታና ኢየሱስ ክርስቶስ ብተዋሕዶ ሓደ ኣካል ሓደ ባህርይን ማለት ፍጹም ኣምላኽ ፍጽም ሰብን ከም ዝኾነ ስለ እትኣምንን ከምኡ ኢላ ድማ ስለ እትምህርን እተእምንን እዩ። መሠረት ሕግን እምነትን ትምህርትን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኤርትራ 81 መጽሓፍ ቅዱስ እዩ። ብናይ እግዚኣብሔር ሓድነትን ሠለስትነትን ትኣምን። እግዚአብሔር ብስም ብግብሪ ብኣካል ሠለስተ፣ ብመለኮት ብፍቓድ ብህልውና ሓደ እዩ ኢላ ትኣምን። (ዘዳ. 6፥4) ስም ሠለስትነቱ ድማ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እዩ። (ማቴ. 28፥19-20) ካብዞም ሠለስተ ኣካላት ሓደ ኣካል ዝኾነ እግዚአብሔር ወልድ፡ ደቂ ሰብ ንምድኃን ካብ ሰማየ ሰማያት ወሪዱ፣ብግብሪ መንፈስ ቅዱስ ካብ ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልደ፡ ብተዋሕዶ ሓደ ኣካል ሓደ ባህርይ ኮነ፣ ኣብ ዮርዳኖስ ተጠምቀ፡ ሕገ ወንጌል መሃረ፡ ምእንቲ ኃጢኣት ደቂ ሰብ ኣብ መስቀል ተሰቕለ፡ ሞተ፡ ተቐብረ፡ ኣብ መበል ሣልሳይ መዓልቲ ተንሥአ፣ ንሰማያት ዓረገ፣ ኣብ ሕያዋንን ሙታንን ኪፈርድ ንካልኣይ ጊዜ ኪመጽእ እዩ” ኢላ ትኣምንን ተእምንን። በታ ጸጋ ውልድነት ተውህብን፣ ኃጢኣት ዝሥረየላን ሓንቲ ጥምቀት ትኣምን። (ዮሓ. 3፥5-8፣ ግብ.ሓዋ. 2፥38) በቲ ሕይወተ ሥጋን ነፍስን ዝህብን ካብ ኃጢኣት ዘንጽሕን ሥጋ ወልደ እግዚኣብሔር ትኣምን። (ዮሓ. 6፥54-57) ኣብ መወዳእታ ዘመን (ዳግም ምጽኣት) ጐይታናን መድኃኒናን ኢየሱስ ክርስቶስ ብኽብርን ምስጋናን ኣብ ዝመጸሉ ጊዜ ኵሎም እቶም ዝሞቱ ሰባት ኪትንሥኡ ምዃኖም፣ “እቶም ሠናይ ዝገበሩ ኣብ መንግሥተ ሰማያት፡ ክፉእ ዝገበሩ ድማ ናብ ዘለዓለም ኵነኔ (ገሃነመ እሳት) ኪኸዱ ምዃኖም” ትኣምንን ተእምንን። (ማቴ. 24፥24-33 25፥46) ንምእመናን መንፈሳዊ ጸጋ ዜውህብ ኣገልግሎት እትህበሉ ሾብዓተ ምሥጢራት እዞም ዝስዕቡ’ዮም ብጥምቀት፦ ውሉድ ኣምላኽ ምዃንን ኣብ ሓድሽ ሕይወት ምንባርን ትህብ (ዮሓ. 3፥3-8)፣ ብሜሮን፦ መንፈሳዊ ዕቤትን ጽንዓትን ተኅድር (ሉቃ. 1፥80)፣ ብቍርባን፦ ኅድገት ኃጢኣት ናይ ዘለዓለም ሕይወትን ተውህብ (ዮሓ. 6፥52-58)፣ ብክህነት፦ ናይ ምምሃርን ምጥማቕን ምቕዳስን ኃጢኣት ምስትሥራይን መንፈሳዊ ሥልጣንን ትህብ (ዮሓ. 20፥23)፣ ብንስሓ፦ ኅድገት ኃጢኣትን ምሕዳስ ሕይወትን ትህብ (ግብ.ሓዋ. 3፥19-21)፣ ብተክሊል፦ ጽንዓት ቃል ኪዳንን ናብራ ቅድስናን ተኅድር (ሚል. 2፥14-16፣ ኤፌ. 5፥21-33፣ ማቴ. 19፥1-9)፣ ብቀንዲል፦ ኃይሊ መንፈሳውንን ጥዕናንን ትህብ (ያዕ. 5 ፥14-17፣ ማር. 6፥13)፣ እምበኣር እዞም ፯ተ ምሥጢራት ቤተ ክርስቲያን ብዚርአ ኣገልግሎት፡ ዘይርአ ጸጋ ዘውህቡ ምዃኖም ትኣምንን ተእምንን። ብኣማላድነት ቅድስት ድንግል ማርያምን፡ መላእኽትን ነቢያትን፡ ሓዋርያትንን ሰማዕታትን፡ ጻድቃንን ትኣምን። (ዮሓ. 2:1-13፣ ሉቃ. 20፥37-39፣ ራእ. 6፥9፣ ዕብ. 12 ፥15፣ ዘፀ. 32፥1-14፣ ማቴ. 10፥40-42) ብዛዕባ መንፈሳውያን ሥነ ምግባራት ከምዚ ዚስዕብ ኢላ ትኣምን ትምህርን፦ ጸሎት፦ ናይ ውልቂ ናይ ሥድራ ቤትን ናይ ማኅበርን ተባሂሉ ኣብ ሠለስተ ይኽፈል፡ ኣብ መዓልቲ ፯ተ ጊዜ ይጽለ። ንሱ ኸኣ ነግህ(ንግሆ)፡ ሠለስቱ (ረፋድ 9:00)፡ ስድስቱ (ፍርቂ መዓልቲ)፡ ተስዐቱ (ኣጋ ጊዜ 3:00)፡ ሠርክ(ምሸት)፡ ንዋም(ጊዜ ድቃስ)፡ መንፈቀ ሌሊት(ፍርቂ ለይቲ) እዩ። (መዝ 119፥164) ምጽዋት፦ ኅቡእን (ሥውር)፡ ግሉጽን ተባሂሉ ኣብ ክልተ ይኽፈል። ስግደት፦ ናይ ኣምልኾ፡ ናይ ጸጋን ናይ ኣኽብሮትን ተባሂሉ ኣብ ሠለስተ ይኽፈል። ጾም፦ ክልተ ዓይነት ኮይኑ ናይ ውልቂ (ብሕቲ) ጾምን፡ ብትእዛዝ ቤተ ክርስቲያን ዝጽወም ናይ ኣዋጅ ጾምን እዩ። እዞም ናይ ኣዋጅ ኣጽዋማት ፯ተ እዮም። ንሳቶም ድማ ጾመ ነቢያት (15 ኅዳር 28 ታኅሣሥ)፡ ዓርበ-ረቡዕ፡ ገሃድ ድሮ ልደትን ጥምቀትን፡ ጾመ ነነዌ (3 መዓልቲ) ጾመ ኣርብዓ (55 መዓልቲ)፡ ጾመ ሓዋርያት (ድኅሪ በዓለ 50 ዘሎ ሰኑይ 5 ሐምለ)፡ ጾመ ፍልሰታ (1 ነሓሰ- 15 ነሓሰ) እዮም። በዓላት ዝበሃሉ በዓላት ጐይታ፡ በዓላት እግዝእትነ ድንግል ማርያም፡ በዓላት ቅዱሳን፡ ከምኡ ድማ ቀዳመ-ሰንበት በዓላት እዮም። እትግልገለሎም ስብሓታት እዞም ዝስዕቡ እዮም፦ ሰዓታት ዘመዓልት ወዘሌሊት፡ ጸሎተ ነግህ፡ ያሬዳዊ ማኅሌት፡ ስብከተ ወንጌል፡ ቅዳሴ፡ ጸሎተ ሠርክ፡ ፍትሓት ጸሎተ ምውታን “ቅዱሳት” ብዝብል ቅጽል ስም ሂባ፣ ብቀኖና ዝተቐበለቶም መጻሕፍቲ መጽሓፍ ቅዱስን(ኣሥራው ኣዋልድ መጻሕፍትን እዮም። እዞም ዝስዕቡ ናይ ምምኅዳር ኣዕማድ ኣለውዋ፦ ቅዱስ ሲኖዶስ፡ መንበረ ፓትርያርክ፡ ሃገረ ስብከት (መንበረ ጵጵስና)፡ ንኡስ ሃገረ ስብከት ክልል ሰበኻ ቤተ ክርስቲያንን። ብሓሳብ ዲሜጥሮስ ዝተቐመረ ኣቈጻጽራ ዘመን (ካላንደር) ትኽተል። ሥነ ጽሑፋ ዓቂባ ዝጸንሐትን እትነብርን ብምዃና፡ ዝጸንሑ ፊደላትን ኣኃዛትን ከየጕደለት ዓቂባ ትነብር። እትቅበሎም ጉባኤታት ሠለስተ እዮም ንሳቶም ድማ፦ ጉባኤ ኒቅያ (325 ዓ.ም.) ጉባኤ ቍስጥንጥንያ (381 ዓ.ም.) ጉባኤ ኤፌሶን (431 ዓ.ም.) ምስ ኦሬንታል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኣብያተ ክርስቲያን ዝበሃላ ምስ ኢትዮጲያ፡ ግብጺ፡ ሶርያ፡ ኣርመን፡ ህንዲ (ማላቨር) ኣብ ነገረ መለኮትን ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ርክብ ስለዘለዋ ኣብ መንበሮም ምቕዳስን፡ ኣብ መንበራ ክቅድሱን ይከኣል እዩ። ናይ ቍርባን ሓድነትን ናይ ክህነት ቀኖና ሓድነትን ኣለዋ። እግዚኣብሔር ቤተ ክርስቲያንና ይባርኸልናን ይሓልወልናን!!! ወስብሓት ለእግዚኣብሔር! ምንጪ፦ ቃለ ኣዋዲ ኣንቀጽ 1፡ 5፡ 6፡ 7፡ 16፡ 17፡ 18፡ 19፡ 20፡ 21፡ 22፡ 23፡ 27፡ 120፡ 121፡
12319
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B2%E1%89%AA%E1%88%8D%20%E1%8A%A2%E1%8A%95%E1%8C%82%E1%8A%90%E1%88%AA%E1%8A%95%E1%8C%8D
ሲቪል ኢንጂነሪንግ
ሲቪል ምህንድስና ወይም ሲቪል ኢንጂነሪንግ አንዱ እና ታዋቂው የምህንድሥና (ኢንጂነሪንግ) ዘርፍ ነው። ሲቪል ምህንድስና ስለ ግንባታ አካላት አስፈላጊነት ቅድመ ጥናት የሚያደርግ እንዲሁም የግንባታ አካላቱ አስፈላጊነት ከታመነበት በኋላ፤ የንድፍ ስራና የግንባታ ሂደትን የሚከታተልና የሚያስፈጽም እንዲሁም የግንባታ አካላቱ አገልግሎት ላይ ከዋሉ በኋላ የአገልግሎት እድሜያቸው እስከሚያበቃ ድረስ የሚፈለግባቸውን አገልግሎት እየሰጡ እንዲቆዮ የጥገና ስራዎችን የሚያጠናና የሚተገብር የሙያ ዘርፍ ነው። ከግንባታ አካላት ውስጥ መንገዶች፣ ድልድዮች፣ ህንጻዎች፣ ግድቦች፣ የአየር ማረፊያ አስፋልት ንጣፎች፣ የውሃ ተፋሰስ መስመሮች፣ ለተለያዮ አገልግሎቶች የሚውሉ ትቦዎች፣ የባቡር ሃዲዶች፣ ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ሰው ሰራሽ ወንዞች እና ሌሎችም ይገኙበታል። ሲቪል ምህንድስና በጥንታዊነት ከወታደራዊ ምህንድስና ቀጥሎ ሁለተኛውን ደረጃ ሲይዝ፣ የሙያ ዘርፉ የግንባታ አካላቱ ላይ እንዲሁም የግንባታ ሂደቱ ላይ ተሞርኩዞ በተለያዮ የሙያ ዘርፎች ይከፋፈላል። የሙያ ዘርፉም ከማህበረሰብ አገልግሎቶች ጀምሮ (ለምሳሌ እንደ መንገድ ግንባታ) እስከ ግለሰብ ደረጃ ድረስ (የግለሰብ መኖሪያ ቤት) የሚተገበር ነው። ታሪክ ሲቪል ምህንድስና የተፈጥሮ ህግጋትንና የሳይንስ መርሆችን በመጠቀም የአንድን ማህበረሰብ ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚጥር የሙያ ዘርፍ በመሆኑ ታሪካዊ እድገቱ ከተፈጥሮ ህግጋት ሳይንስ (ቪዚክስ) እና ከሂሳብ ሳይንስ የግንዛቤ እድገት ጋር የተያያዘ ነው። ሲቪል ምህንድስና ዘርፍ፤ የአወቃቀር ሳይንስ የከርሰ ምድር ሳይንስ፣ የአፈር ሳይንስ፣ የውሃ ሳይንስ የአካባቢ ሳይንስ ሜካኒክስ (አንድ ቁስ በጫና አማካኝነት የሚያሳየው የለውጥ ሂደት የሚያጠና ዘርፍ ነው) የቁስ አወቃቀር ሳይንስ የመልክዓ ምድር ሳይንስ እና የመሳሰሉትን ዘርፎች የሚያካትት ስለሆነ እድገቱም ከእነኚህ በውስጡ ከሚገኙ የሙያ ዘርፎች እድገት ጋር የተያያዘ ነው። ሲቪል ምህንድስና የሚያካትታቸው የአገልግሎት ዘርፎች ሲቪል ምህንድስና ሰፊ የሙያ ዘርፍ እንደመሆኑ በውስጡ ብዛት ያላቸው ሌሎች የሙያ ዘርፎችን ይይዛል። አማካሪ ሲቪል መሀንዲሶች ከእነኚህ የተለያዮ የሙያ ዘርፎች በአንዱ ላይ ጠለቅ ያለ ስልጠናና ትምህርት ወስደው፤ በወሰዱት የስልጠና መስክ የአማካሪነት ሚና ሲኖራቸው፤ አጠቃላይ ሲቪል መሀንዲሶች ደግሞ ስለ ሁሉም የሲቪል ምህንድስና ዘርፎች መሰረታዊ እውቀት ኖርዋቸው በተለያዮ ዘርፍሮች ከሰለጠኑት አማካሪ ሲቪል መሀንዲሶችና እንዲሁም የቅየሳ ባለሙያዎች ጋር በመሆን አንድን የተወሰነ የመሬት ይዞታን ከነበረበት የአገልግሎት ሁኔታ ወደሚፈለግበት የአገልግሎት ሁኔታ በግንባታ አማካኝነት የመለወጥ ስራን ያከናውናሉ። አጠቃላይ ሲቪል መሀንዲሶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የግንባታ ስራዎን በመጎብኘትና በመቆጣጠር፣ ከግንባታ አካላቱ ባለቤቶች፣ ስራ ተቋራጮችና ሌሎች ከግንባታ አካላቱ ጋር ግንኙነት ካላቸው አካላት ጋር በመገናኘትና ስለ ግንባታው ሂደት መረጃ በመለዋወጥ፤ የግንባታ እቅዶችን በማውጣትና በመቆጣጠር እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ስራዎችን ለመስራት ያውላሉ። ሲቪል መሀንዲሶች የመሬት ምህንድስና የአወቃቀር ምህንድስና የአካባቢ ሳይንስ ምህንድስና የመጓጓዣ ምህንድስና የግንባታ ምህንድስና እና ሌሎች ተዛማጅ የምህንድስና መስኮችን በመጠቀም ለመኖሪያ ለንግድ፣ ለኢንዱስትሪ እንዲሁም ለማህበረሰብ አገልግሎቶች የሚውሉ አነስተኛ እንዲሁም ግዙፍ ግንባታዎችን ያከናውናሉ። ዋና ዋና የሲቪል ምህንድስና ዘርፎች የወደብ (የባህር ዳርቻ) ምህንድስና የወደብ ምህንድስና የወደብ አካባቢን የማልማትና የማስተዳደር ስራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፣ ወደብን ለመጓጓዣ ስራ ከማዋል በተጨማሪ፣ በወደብ አካባቢ የሚከሰቱ የውሃ መጥለቅለቅ አደጋዎችን፣ የአፈር መሸርሸርና እና የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎችን የመከላከል ስራ የሚያከናውን የምህንድስና ዘርፍ ነው። የግንባታ ምህንድስና የግንባታ ምህንድስና የግንባታ ሂደትን የማቀድ፣ የማስፈጸም፣ ለግንባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ ቁሳቁሶችን የማጓጓዝና የማቅረብ፣ እንዲሁም የግንባታ ቦታውን ለሚፈለገው የግንባታ አካል እንዲውል በግንባታው አካባቢ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ መሟላቱን የማረጋገጥ፣ የግንባታ ቦታው ለግንባታ ስራ ደህንነትና ምቹነት ያለው መሆኑን የማረጋገጥ እንዲሁም አግባብ የሆነ የግንባታ መሬት አጠቃቀምን የሚከታተልና የሚያስፈጽም የምህንድስና ዘርፍ ነው። የግንባታ ተቋራጮች በሌሎች የሲቪል ምህንድስና አገልግሎቶች ላይ ከተሰማሩ የአገልግሎት ተቋሞች አንጻር የተሰማሩበት መስክ ከፍተኛ የንግድ አደጋ ወይም መዋዠቅ ስለሚከሰትበት የግንባታ መሃንዲሶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን ንግድን በተመለከቱ ጉዳዮች ለምሳሌ ያህል የግንባታ ውሉን በመገምገም እና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በማርቀቅ፣ የግንባታ ግብአቶችን አቅርቦት ፍሰት በመቆጣጠር፣ እንዲሁም የግንባታ እቃዎች የገበያ ዋጋ መረጃን በመሰብሰብ ላይ ያውላሉ። የመሬት ርዕደት ምህንድስና የመሬት ርዕደት ምህንድስና መሬት ርዕደት በሚያይልባቸው አካባቢዎች የሚሰሩ የግንባታ አካላት፤ የመሬት ርዕደትን ተቋቁመው እንዲዘልቁ ለማድረግ የግንባታ አካላቱን አወቃቀር በተለየ መልኩ ትኩረት በመስጠት የሚያጠናና መፍትሄ የሚሰጥ የምህንድስና ዘርፍ ነው። ይህ የምህንድስና ዘርፍ የአወቃቀር ምህንድስና ዘርፍ አካል ነው። የመሬት ርዕደት ምህንድስና ዋነኛ አላማው በመሬትና በግንባታ አካሉ እንዲሁም በግንባታ አካላቱ መካካል በመሬት ርዕደት ጊዜ የሚኖረውን መስተጋብር መረዳትና የግንባታ አካሉ የመሬት ርዕደት ሂደቱን አልፎ አገልግሎት እንዲሰጥ አወቃቀሩን፣ የግንባታ ቁስ አመራረጡን እንዲሁም መሰል የግንባታ መፍትሄዎችን በየሀገራቱ ጥቅም ላይ ከዋሉ የግንባታ መስፈርቶች ጋር በሚስማማ መልኩ መተግበር ነው። የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ከጤና ጥበቃ ምህንስና ጋር ተጓዳኝ የሆነ የምህንድስና ዘርፍ ሲሆን፣ የጤና ጥበቃ ምህንድስና በአመዛኙ የንጹህ ውሃ መጠጥ አቅርቦትና የአካባቢ ቆሻሻ ፍሳሽ አወጋገድ ላይ ሲያተኩር፤ የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ሰፋ ባለ መልኩ የአካባቢ ብክለት የሚያስከትሉና ለጤና ጠንቅ የሆኑ ጎጂ ኬሚካሎችን እና ቆሻሻዎችን መቆጣጠርና ማስወገድ ይጨምራል። የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና፤ የማህበረሰብ ጤና ምህንድስና እና የአካባቢ ጤና ምህንድስና በሚል አጠራርም ይታወቃል። የአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና በኬሚካል ውህደቶች፣ በባዮሎጂካል ሂደቶች እንዲሁም በሙቀት ለውጥ አማካኝነት የሚፈጠሩ ቆሻሻዎችን የማጥራትና የማስወገድ፣ አየርንና ውሃን የማጣራት፣ እንዲሁም በአደጋ ወይም በቆሻሻ ክምችት የተበከለን የመሬት አካል ወደ ተፈጥሮዋዊ ይዘቱ የመመለስ ስራዎች የሚያከናወኑበት የምህንድስና ዘርፍ ነው። በአካባቢ ጥበቃ ምህንድስና ትኩረት ከሚደረግባቸው ዋና ነጥቦች ውስጥ የመርዝ ወይም የኬሚካል እንቅስቃሴ ወይም ጉዞ (ከመሬት ላይና ከመሬት በታች)፣ የውሃ ማጣራት፣ የቆሻሻ ፍሳሽ ማጣራት፣ የአየር ብክለት፣ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና የአደገኛ ቆሻሻዎች አያያዝ ይገኙበታል። የአካባቢ ጥበቃ መሃንዲሶች ብክለትን የመቀነስ፣ የአረንጓዴ ምህንድስና ዘርፍ ስራዎች (የአካባቢ ብክለትን የሚቀንሱ የግንባታ መንገዶችንና ቁሶችን የኢኮኖሚ አቅምን ባገናዘበ መልኩ የማጥናት ስራ)፤ እንዲሁም የኢንዱስትሪዎችን የቁሳቁስና የሃይል አጠቃቀም ፍሰት የማጥናት ስራዎችና የመሳሰሉት ላይ ይሳተፋሉ። ከዚህም በተጨማሪ የአካቢቢ ጥበቃ መሃንዲሶች ድርጊቶች (ለምሳሌ የአንድ የግንባታ አካል ትግበራ) በአካባቢው ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተጽእኖ በመገምገም መረጃ ያዘጋጃሉ። የምርመራ ምህንድስና የምርመራ ምህንድስና የግንባታ አካላት የሚፈለግባቸውን ጥቅም ሳይሰጡ ለአገልግሎት ከታቀደላቸው ጊዜ በፊት በመፍረስ አገልግሎት መስጠት ሲያቆሙ፣ እንዲሁም የመፍረስ አደጋው በሰው ወይም በንብረት ላይ አደጋ በሚያደርስበት ጊዜ የግንባታ አካሉን አወቃቀር የተሰራበትን ቁስ የግንባታውን ጥናት እንዲሁም መሰል ተዛማጅ ጉዳዮችን በመመርመር ተጠያቂ የሚሆነውን አካል ለማወቅና የፍርድ ሂደትን ለማገዝ የሚያገለግል የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ይህ የምህንድስና ዘርፍ ከምርመራ ውጤቶች በመነሳት የግንባታ ቁሶችን ወይም የግንባታ አካላት ጥራትን እንዲሁም የግንባታ አካላት አወቃቀርን የማሻሻል ስራዎን ለመስራት የሚያስችል የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ልዮ የሆነ የባለቤትነት ፍቃድ ያላቸውን የግንባታ ቁሶች አካላት ወይም የግንባታ ዘዴዎች የፍቃድ ባለቤቱን ይሁንታ ሳያገኙ በሚፈጸሙ ግንባታዎች ላይ የባለቤትነት ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚደረጉ ህጋዊ ሂደቶች ላይ ይህ የምህንድስና ዘርፍ ቁልፍ ቦታ አለው። መሬት ነክ ምህንድስና (ጂኦቴክኒካል ምህንድስና) መሬት ነክ ምህንድስና የግንባታ አካላትን የሚሸከሙ አለቶችና አፈሮችን የምህንድስና ጠባይ የሚያጠና የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። ይህ ዘርፍ ከአፈር ሳይንስ፣ ከቁስ ሳይንስ ከሜካኒክስ እንዲሁም የፍሰት ሳይንስ እውቀቶችን በመጠቀም ደህንነታቸው የተጠበቀና የገንዘብ አቅምን ያገናዘቡ የግንባታ መሰረቶችን፣ የመጠበቂያ ግድግዳዎችን፣ ግድቦችን፣ ዋሻዎችን የመሳሰሉ የግንባታ አካላትን መንደፍና መገንባት ላይ ትኩረት ያደርጋል የከርሰ ምድር ውሃን በተለያዮ ምክንያቶች ከመበከል የመጠበቅ እንዲሁም የቆሻሻ ክምችትን በአግባቡ ለመቆለልና ክምችቱ የአፈርና የከርሰ ምድር ውሃን እንዳይበክል የማድረግ ስራዎችም በዚሁ የምህንድስና ዘርፍ የሚተገበሩ ናቸው። የአፈርን የምህንድስና ጸባይ የማወቅ ተግባር ለመሬት ነክ መሃንዲሶች ፈታኝ ነው። በሌሎች የሲቪል ምህንድስና ዘርፎች የግንባታ ቁሶች ጸባይ (ለምሳሌ እንደ ብረት እና ኮንክሪት) በሚገባ የሚታወቅ ሲሆን፤ በግንባታ አካባቢ የሚገኝን የአፈር ጸባይ ማወቅ ግን ከተለዋዋጭነቱና በናሙና በሚደረጉ ሙከራዎች መፈተሽ የሚቻለው ከጠቅላላውን የተወሰነውን ብቻ በመሆኑ በጣም አዳጋች ነው። ከዚህም በተጨማሪ አፈር በጭነት ምክንያት የሚያደርገው የቅርጽ ለውጥ ከጫናው ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ ተዛምዶ ስላለው፤ ማለትም አነስተኛ እና ከፍተኛ ለሆኑ ጫናዎች የተለያየ )፤ የቅርጽ ለውጥ ስለሚኖረው፤ የአፈርን የምህንድስና ጸባይ በተሟላ ሁኔታ ለማወቅ የዳግታል። መሬት ነክ መሃንዲሶች አብዛኛውን ጊዜ ከከርሰ ምድር ባለሙያዎችና የአፈር ሳይንቲስቶች ጋር በትብብር ይሰራሉ። የቁሶች ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና የቁሶች ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና በሲቪል ምህንድስና ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ሚና ይይዛል። የቁሶች ጥናት ሳይንስ ወይም ምህንድስና የቁሶችን ተፈጥሮዋዊ ባህሪ የሚያጠና የሳይንስ ወይም የምህንድስና ዘርፍ ነው። ለግንባታ ከሚውሉ ቁሳቁሶች ውስጥ ኮንክሪት፣ የአስፋልት ኮንክሪት፣ እንደ ብረት እና አልሙኒየም ያሉ ጠንካራ ብረታ ብረቶች የፕላስቲ ውጤቶችና የመሳሰሉት ይገኙበታል። የቁሶች ጥናት የግንባታ አካላትን ከተለያየ ጥቃት ለመከላከል የሚውሉ ቅባቶችና የመከላከያ ንጣፎችን፣ እንዲሁም አንድን የብረት አይነት ከሌላ የብረት አይነት ጋር በማደባለቅ ለግንባታ ተስማሚ የሆነ ሌላ አይነት የብረት አይነት ማምረት የመሳሰሉ ስራዎችንም ያጠቃልላል። የቁሶች ጥናት የትግበራ ፊዚክስና የኬሚስትሪ እውቀቶችን የያዘ የምህንድስና ዘርፍ ነው። በቅርቡ እየተስፋፋ የመጣው የናኖ ሳይንስ ወይም ቴክኖሎጂን (ናኖ ሳይንስ የአንድን ቁስ የአቶምና የሞሎኪዮል አወቃቀር በመቀየር በተፈጥሮ የማይገኙ ለየት ያለ ባህሪ ያላቸውን ቁሶች ለመስራት የሚደረግ ጥረት ነው) ደረጃ ተንተርሶ በአሁኑ ጊዜ የቁሶች ጥናት ከፍተኛ የሆነ የምርምር ድርሻን ይዞ ይገኛል። የቁሶች ጥናት ምህንድስና በምርምር ምህንድስናና የግንባታ አካላት ከጥቅም ውጪ የመሆን መንስኤን ለማጥናት በሚደረጉ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የአወቃቀር ምህንድስና (ስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ) የአወቃቀር ምህንድስና የህንጻዎችን፣ የድልድዮችን፣ የማማዎችን፣ የመንገድ ማቋረጫ ድልድዮችን፣ የዋሻዎችን፣ በባህርና ላይ የሚገነቡ ለነዳጅ ወይም ለዘይት ማውጫ የሚያገለግሉ ሰው ሰራሽ መሬቶችን እና ማማዎችንና እንዲሁም እነኚህን የመሳሰሉ የግንባታ አካላትን በተመለከተ የአወቃቀር ንድፍና የአወቃቀር ትንታኔ ላይ የሚያተኩር የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ነው። የአወቃቀር ትንታኔ ጉልበቶች በግንባታ አካላት ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ መመዘን ላይ ትኩረት ያደርጋል። የአወቃቀር ምህንድስና በግንባታ አካላት ላይ የሚያርፉ ጉልበቶችን ለምሳሌ የራሱ የግንባታ አካሉ ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ የሚያርፉ ሌሎች ቋሚና ተቀሳቃሽ ክብደቶች፣ የንፋስ ግፊት የሙቀት ለውጥ፣ የውሃ ግፊት፣ የመሬት ጫና፣ የመሬት ርእደት፣ በረዶ እና የመሳሰሉትን የመለየትና፣ በእነኝህ ጉልበቶች አማካኝነት በግንባታ አካላቱ ውስጥ የሚከሰቱ ውስጣዊ ጫናዎችንና ጉልበቶችን የማስላትና የግንባታ አካላቱ እነኝህን ጉልበቶች ተቋቁመው አገልግሎት እንዲሰጡ መጠናቸውንና የሚሰሩበትን ቁስ መንደፍ ላይ ያተኩራል። የአወቃቀር ምህንድስና ባለሙያው የግንባታ አካላቱ ተጠቃሚዎችን ደህንነትን በሚጠብቅ መልኩ እንዲሁም ግንባታ አካላቱ ከተሰሩበት አላማ አንጻር የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጎ መንደፍ ይጠበቅበታል። እንደ ንፋስ እና የመሬት ርእደት አይነት ጉልበቶች በቀላሉ ለመተንበይ አስቸጋሪ በመሆናቸው በአወቃቀር ምህንድስና ስር እንደ ንፋስ ምህንድስና እና የመሬት ርእደት ምህንድስናን የመሳሰሉ ንኡስ ዘርፎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኖዋል። በአወቃቀር ምህንድስና ውስጥ የንድፍና የትንታኔ ስራ የግንባታ አካሉ ቋሚ ጉልበቶችን ፣ተለዋዋጭ ጉልበቶችን (እንደ ንፋስና የመሬት ርእደት ያሉ) ወይም ጊዜያዊ ጉልበቶችን (ለምሳሌ በግንባታ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ የግንባታ ማሽኖች ክብደት፣ በግንባታ አካሉ ላይ በተንቀሳቃሽ ነገሮች አማካኝነት ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶች እና የመሳሰሉት) ለመሸከም የሚያስፈልገውን ጥንካሬና ጠጣርነት መወሰን እንዲሁም የግንባታ አካሉ ሚዛኑን ጠብቆ መቆም መቻሉን ማረጋገጥ ያካትታል። ከዚህም በተጨማሪ የንድፍና ትንታኔ ስራ የግንባታውን ዋጋ መተመን፣ የግንባታውን ተግባራዊነት ማረጋገጥ፣ ግንባታው ውበት የተላበሰ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም የሃብት አጠቃቀምና የተፈጥሮ ሚዛንን በጠበቀ መልኩ ግንባታው እንዲከናውን ማስቻልን ያካትታል። ቅየሳ ቅየሳ የአንድን የመሬት ገጽ ወይም የግንባታ አካል አቀማጥ ለማወቅ የሚደረግ የልኬት ስራ ነው። የቅየሳ ስራ ለቅየሳ ስራ የሚውሉ እንደ ውሃ ልክ ወይም ቴዎዶላይት (አግድምና ሽቅብ ማእዘንን ለመለካት የሚችል አጉሊ መነጽር) ያሉ መሳሪያዎች በመጠቀም በሁለት የልኬት ቦታዎች መካከል ከልኬት ቦታው አንጻር የሚኖረውን የቦታ ልዮነት ለማወቅ የማእዘን የአግድም ቁመትና የሽቅብ ቁመት ልኬቶችን በመውሰድና የሂሳብ ስሌትን በመጠቀም የመሬት ገጽን ወይም የግንባታ አካልን አቀማመጥ የመወሰን ተግባር ነው። ከኮምፒውተር እውቀት ማደግ ጋር በተያያዘ አውቶማቲክ የሆኑ እንደ የኤሌክትሪክ ርቀት መለኪያዎች በመፈልሰፋቸው እንደ ቶታል ስቴሽን፣ ጂፒኤስ፣ የጨረር ዳሰሳ የመሳሰሉ መሳሪያዎች ባህላዊ የሆኑ መሳሪያዎችን በመተካት ላይ ናቸው። ትራንስፖርት ምህንድስና የትራንስፖርት ምህንድስና ሰዎችንና ቁሳቁስን ከቦታ ወደ ቦታ በደህንነት በተቀላጠፈና ምቹ በሆነ መንገድ ማጓጓዝ ላይ ትኩረት ያደርጋል። ይህንን አላማማ ለማሳካትም የመኪና፣ የባቡር፣ የውሃና የአየር ማረፊያ መንገዶች እንዲሁም የወደቦች ንድፍ፣ ግንባታና ጥገና ስራዎች በትራንስፖርት ምህንድስና ውስጥ ሰፊ ድርሻ ይይዛሉ። የትራንስፖርት ምህንድስና በውስጡ የትራንስፖርት ንድፍ ስራ የትራንስፖርት ግንባታ እቅድ የትራፊክ ምህንድስና የከተማ ልማት ምህንድስና፣ የመንገድ ንጣፍ ምህንድስና የመሳሰሉ ንኡስ የሙያ ዘርፎችን የያዘ ነው። ሲቪል
18217
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%8A%E1%8D%92%E1%89%B5-%E1%8A%A5%E1%88%BD%E1%89%B3%E1%88%AD
ሊፒት-እሽታር
ሊፒት-እሽታር በሱመር የኢሲን ሥርወ መንግሥት 5ኛው ንጉሥ ነበረ (1833-1823 ዓክልበ. የነገሠ)። በርሱ ዘመን መጀመርያ የኢሲን ተወዳዳሪ የላርሳ ንጉሥ ጉንጉኑም ኡርን ከኢሲን ያዘ። ሊፒት-እሽታር በተለይ የሚታወቀው በ1832 ዓክልበ. ባወጣው ሕገ መንግሥት ምክንያት ነው። ይህ ሕገ ፍትሕ ከላጋሽ ንጉስ ከኡሩካጊና ሕግጋት በኋላ፣ ከኡርም ንጉሥ ከኡር-ናሙ ሕግጋት በኋላ የወጣ ሲሆን ለሱመር ሦስተኛው የሚታወቀው ሕገ መንግሥት ነው። ዘመን በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ ዓመታት እንደ ነገሠ ሲለን ከዘመኑ የዓመት ስሞች ብቻ ይታወቃሉ። ከመጀመርያው ዓመቱ በቀር ግን የሌሎቹ ዓመታት ቅድም-ተከተላቸው እርግጥኛ አይደለም። ከነዚህም መካከል ለምሳሌ፦ ፦ (1833 አክልበ. ግድም) ሊፒት-እሽታር ንጉሥ የሆነበት ዓመት (1832 አክልበ. ግድም) ኤኒንሱንዚ የዑር ጣኦት መቅደስ ሴት ካህን የመረጠበት ዓመት ሊፒት-እሽታር ፍትሕ በሱመርና አካድ ያደረገበት ዓመት በጣኦታቱ (ኤንሊልና ናና) ትዕዛዝ ኡር የታደሰበት ዓመት ማረሻ የተሠራበት ዓመት (1826 አክልበ. ግድም?) ሊፒት-እሽታር አሞራውያንን ያሸነፈበት ዓመት በተወዳዳሪው ጉንጉኑም ፲፫ኛው ዓመት (1832 ዓክልበ.)፣ የሊፒት-እሽታር ሴት ልጅ ኤኒንሱንዚ የዑር መቅደስ ጣኦት ሴት ካህን ሆና እንድትሾም አረጋገጠ። ስለዚህ የሊፒት-እሽታር ዓመት ከዚያ በኋላ ሊሆን አይችልም። በ1826 ዓክልበ.፣ ጉንጉኑም «የመንገድ ቤት» እንደ ያዘና ቦይ እንደ ከፈተ ይዘገባል። እነዚህ ድርጊቶች ደግሞ በሊፒት-እሽታር ሰነዶች ይጠቀሳሉ። የሊፒ- እሽታር ሻለቃ ናና-ኪአጝ በጻፉለት ደብዳቤ ዘንድ፣ መቶ የጉንጉኑም ወታደሮች «የመንገድ ቤት» ይዘው አዲስ ቦይ ሊከፈቱ ነው ሲል የሊፒት-እሽታርን እርዳታ ይለምናል። በሊፒት-እሽታር መልስ ሺህ ጦረኞች፣ ሺህ ቀስተኞች፣ እና ሺህ ባለ ዶማዎች መላኩን አመለከተ። ጉንጉኑምን ድል እንዳደረጉ አይመስልም፤ ጉንጉኑምም «የሱመርና አካድ ንጉሥ» የሚለውን ማዕረግ ይግባኝ ነበረው፤ ኢሲን ግን ለጊዜው ነጻነቱን ጠበቀው። የሊፒት-እሽታር ሕግጋት (1832 ዓክልበ.) ጽሑፉ በብዙ ፍርስራሽ ላይ ተገኝቷል። በሙሉ የተገኙት ሕግጋት የሚከተሉት ናቸው። §8 ሰው አትክልት እንዲትክልበት መሬቱን ለባልንጀራው ቢሰጥ፣ ባልንጀራውም መሬቱን በሙሉ ካልተከለበት፣ ያልተከለበትን መሬት ለባለቤቱ ሰው ከነድርሻው ይመልሰው። §9 ሰው ወደ ባለቤቱ አትክልት ቦታ ገብቶ በዚያ በስርቆት ቢያዝ፣ 10 ሰቀል ብር ይክፈል። §10 ሰው በባልንጀራው አትክልት ቦታ ዛፍ ቢቆርጥ፣ ግማሽ ሚና ብር ይክፈል። §11 በሰው ቤት አጠገብ የባልንጀራው ምድረ በዳ ካለ፣ ባለቤቱም ለባለ መሬቱ «መሬትህ ባዶ ስለ ሆነ ሌባ እቤቴ ሰርቆ ቢገባስ፤ ቤትህን አጥና» ብሎ ቢነግረው፣ ይህም ስምምነት ከተረጋገጠ፣ ባለ መሬቱ ለባለ ቤቱ ማንኛውን የጠፋውን ንብረት ያተካል። §12 የሰው ገረድ ወይም ባርያ ወደ ከተማው መሃል ቢሸሽ ብትሸሽ፣ በሌላ ሰው ቤት ላንድ ወር እንደ ኖረ(ች) ከተረጋገጠ፣ በባርያው ፋንታ ባርያ ይስጠው። §13 ባርያ ከሌለው፣ 15 ሰቀል ብር ይክፈል። §14 የሰው ባርያ ባርነቱን ለጌታው ሁለት እጥፍ እንደ ረከበው ከተረጋገጠ፣ ያው ባርያ ነፃ ይወጣል። §15 ሚቅቱም (አገልጋይ) የንጉሥ ሥጦታ ከሆነ፣ አይወሰደም። §16 ሚቅቱም በነጻ ፈቃዱ ወደ ሰው ቤት ቢሄድ፣ ያ ሰው ከግድ ሊይዘው አይችልም፤ ወደ ወደደበትም ሊሄድ ይችላል። §17 ሰው ያለ ፈቃድ ባልንጀራውን የማያውቅበት ነገር ውስጥ ካሰረው፣ ባልንጀራው ግድ የለውም፣ ሰውዬውም ባሰረው ነገር ውስጥ ቅጣቱን ይሸክማል። §18 የርስት ባለቤት ወይም የርስት እመቤት የርስቱን ግብር መክፈል ካልቻለ(ች)፣ ሌላ ሰውም ከከፈለው፣ ባለቤቱ ለሦስት ዓመት ለቆ እንዲወጣ አይገደድም። ከዚያ በኋላ ግብሩን የከፈለው ሰው ርስቱን ይይዛል፣ የቀድሞውም ባለ ርስት ምንም ይግባኝ አያነሣም። §22 አባትዬዋ እየኖረ፣ ሴት ልጂቱ የቤተ መቀደስ አገልጋይም ሆነ ሠራተኛ ብትሆን፣ እቤተሠቡ እንደ አንዲት ወራሽ ትኖራለች። §24 ሰው ያገባት ሁለተኛው ሚሥት ልጆች ከወለደችለት፣ ከአባትዋ ቤት ያመጣችው ጥሎሽ ለልጆችዋ ይሁን፣ ዳሩ ግን የመጀመርያይቱ ሚስቱ ልጆችና የ2ኛይቱ ልጆች የአባታቸውን ርስት በእኩልነት ይካፈሉ። §25 ሰው ሚስቱን ገብቶ ልጆችን ወልዶ እነዚያም ልጆች በሕይወት ቢሆኑ፣ ከዚህም ሌላ ደግሞ ባርያይቱ ለጌታዋ ልጆች ከወለደችለት፣ አባቱም ደግሞ ለባርያይቱና ለልጆችዋ ነጻነትን ከሠጣቸው እንደ ሆነ፣ የባርያይቱ ልጆች ግን ርስቱን ከቀድሞው ጌታቸው ልጆች ጋር አይካፈሉም። §27 የሰው ሚስት ልጆችን ካልወለደችለት የአደባባይ ሸርሙጣ ግን ልጆች ከወለደችለት፣ እርሱ ለዚያች ሸርሙጣ እህልን፣ ዘይትንና ልብስን ያስገኛል። ሸርሙጣዋ የወለደችለት ልጆች ወራሾቹ ይሆናሉ፤ ሚስቱ እየኖረች ግን ሸርሙጣዋ እቤቱ ከሚስቱ ጋር ከቶ አትኖርም። §29 አማች ወደ ዐማቶቹ ቤት ገብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ አስወጥተውት ሚስቱንም ለባልንጀራው ለመስጠት ቃል ከገቡ፣ አማቹ ያመጣውን ስጦታዎች በሙሉ ይመልሱለትና ሚስቱ ባልንጀራውን ልታገባ ሕጋዊ አይሆንም። §34 ሰው በሬን ተከራይቶ ሥጋውንም በአፍንጫው ቀለበት ከቀደደው፣ የዋጋውን ሲሶ ይክፈል። §35 ሰው በሬን ተከራይቶ ዓይኑንም ካጎዳ፣ የዋጋውን ግማሽ ይክፈል። §36 ሰው በሬን ተከራይቶ ቀንዱን ከሰበረው፣ የዋጋውን ሩብ ይክፈል። §37 ሰው በሬን ተከራይቶ ጅራቱን ካጎዳ፣ የዋጋውን ሩብ ይክፈል። ዋቢ ምንጮች 1995. 1948 52 (1948)] የኢሲን ነገሥታት የመስጴጦምያ ታሪክ ሕገ
13074
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B0%E1%8B%8B%E1%88%85%E1%8B%B6
ተዋህዶ
ተዋውጦ በዚህ እምነት ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በነበረበት ጊዜ አንደ እና አንድ ብቻ ተፈጥሮ /ባሕርይ ነበረው ይህም ተፈጥሮ /ባሕርይ ሥጋ የሌለበት መለኮት ነበር የሚል ነው ሥጋ እንኳ ቢኖረው ባሕር ውስጥ ሟሙቶ እንደሚጠፋ አንድ ማንኪያ ጨው የክርስቶስ ሥጋም እንዲሁ በመለኮቱ ባሕር ሟሙቶ ጠፍቷል ይላሉ ተዋሕዶ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ። ስንዴ እና ባቄላ እንደሚቀላቀሉት ያለመቀላቀል፣ ኦክስጅንና ሀይድሮጅን ሲዋሐዱ ጸባያቸው እንድሚቀያየር ያለመቀያየር፣ የተጋቡ ሰዎች እንደሚለያዩ ለአንዳች ቅፅበት እንኳን ያለመለያየት፣ መለኮታዊ እና ሥጋዊ ተፈጥሮ በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ሆነ። ቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ወይም አምላክ ወይም ደግሞ ኹለት ተፈጥሮ ያለው ሰው እና አምላክ ሳይሆን የወለደችው፣ የሰው እና የአምላክ ውሕደት፣ አንድ ተፈጥሮን፣ እየሱስ ክርስቶስን ነው። በዕለት ተዕለት ኑሯችን ይህን ዓይነት ኹኔታ የምናየው የአእምሮ እና የአንጎልን ውሕደት ልብ ስንል ነው። በዚህ ንግግር አእምሮ ማለት የሐሳባችን ስብስብ ሲሆን የማይጨበጥ እና የማይዳሰስ ነው፤ አንጎል /ጭንቅላት ማለት ደግሞ ተጨባጩ የማሰቢያ ክፍል ማለት ነው። የኹለቱ ውሕደት እንግዲህ ያለመቀላቀል፣ያለመለዋወጥ እና ያለመለያየት የሚሉትን ሐሳቦች ያንጸባርቃል። ተከፋፍሎ በዚህ እምነት እየሱስ ክርስቶስ ሁለት ተፍጥሮ አለው ተብሎ ይነገራል ስጋው እና መለኮታዊ እነዚህ 2 ተፈጥሮወች በአንድ ተፈጥሮ (እየሱስ ክርስቶስ ይኑሩ እንጂ አልተዋሀዱም ተብሎ ይታመናል የሰው ልጅ በጊዜና በቦታ የተወሰነ ሲሆን ስጋን ለመስዋእት ማቅረብ ከዘመን -ዘመን የሚሻገር የሐጥያት ስርየት አያመጣም እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሲሞት ተፈጥሮውን ከፋፍሎ ስጋው ብቻ ሞተ ማለት ዮሐንስ 3:16 እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። የሚለውን ፉርሽ ያደርጋል በመስቀል ላይ የሞተው እየሱስ ክርስቶስ ተዋህዶ ወይንም አንድ ተፈጥሮ ነው የመለኮት ተፈጥሮ እንግዲህ ሞትንና መንገላታትን ባያውቅም ከስውነት ጋር ባለው ውህደት ግን አብሮ ተንገላቷል ማለት ነው ይህን ሀሳብ ለመረዳት የሚነድ ብረትን ያስታውሷል እሳት እና ብረት ያለመቀላቅል ሲዋሀዱ አንጥረኛ ብረትን በመዶሻ ሲመታ የመዶሻው ምት እሳት ላይ ምንም ሀይል ባይሆረውም እሳት እራሱ ከብረት ጋር ስለተዋሀደ ብረት ሲጣመም እንዲሁ እሳትም ይጣመማል ሉቃስ በሐዋርያት ስራ 20:28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ሲል እዚህ ላይ መርዳት ያለብን መለኮት በራሱ ደም የለውም ነገር ግን የመለኮት ተፈጥሮ እና የስው ተፈጥሮ ውህደትን ለማመልከት ያንዱን ባህርይ በሌላው ስም መጥቀስ ተችሏል እየሱስ ክርስቶስ በስጋ ከሞተ ለምን ወደዚህ አለም መምጣትስ አስፈለገው የስጋ መስዋእት ለዘላለም ስርእየት በቂ ከሆነ አንድ የተመረጠ ሰው ለዚህ ተግባር ማዋል ይቻል ነበር ስለማይቻል 'የእግዚአብሔር ልጅ 'ከሰው ልጅ ጋር ያለመቀላቀል ያለመለዋወጥ ያለመለያየት ተዋሐደ የዚህም ውህደት ውጤት ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ከትውልድ እስከ ትውልድ የሚሸጋገር ድህነትን ለሰው ልጅ አተረፈ ዮሐንስ 3:16 እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። 1ቆሮ 2:8 አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤ ቅዱስ ጳውሎስ እዚህ ላይ «የእየሱስ ክርስቶስን ስጋ» አላለም የልቁኑ «የክብር ጌታ» በማለት ውሕደቱን በግልጽ አስቀምጧል ቅዱስ ጴጥሮስ በሐዋርያት ስራ 3:14-15 እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፥ የሕይወትንም ራስ ገደላችሁት፤ «የሕይወት እራስ» እንግዲህ የመለኮትነትን ባህርይ የሚያሳይ ሐረግ ነው እብራውያን 2:10 ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ፥ ከእርሱ የተነሣ ሁሉ በእርሱም ሁሉ ለሆነ፥ ለእርሱ ተገብቶታልና። በመከራ ላይ እያለ እንኳን መለኮታዊ ባህርዩን (በእርሱ ሁሉ የሆነ አልረሳም ራእይ 1:17-18 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ። አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ። እዚህ ላይ እየሱስ ክርስቶስ እራሱ ስለስቅለቱ ሲናገር እራሱን በመከፋፈል በስጋ ሞትኩ አላለም ይልቁኑ ፊተኛውና መጨረሻው ሲሆን ለዘላለምም ሕያው ሲሆን ሳለ በመስቀል ላይ መሞቱን ያለክፍፍል በተዋህዶ አስረድቷል እንግዲህ አዲስ ኪዳን እንደሚያስረዳው በመስቀል ላይ የሞተው በሞቱም ከዘላለም እስከ ዘላለም የድህነት ጥላን የዘረጋልን «ስጋ» ብቻ ሳይሆን የ«ክብር ጌታ»፣ የ«ሕይወት እራስ»፣ «በእርሱ ሁሉ የሆነ»፣ 'ፊተኛው እና ሁዋለኛው የተባለው «ተዋህዶው» እየሱስ ክርስቶስ ነው የዮሐንስ ወንጌል 20:19 ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው። ይህንም ብሎ እጆቹንም ጎኑንም አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው። ክርስቶስ በስጋው ነው በተዘጋ በር ያለፈው ወይንስ በመለኮት ነው ያለፈው በመለኮት ካለፈ እንዴት በስጋ ታያቸው በስጋስ እንዴት በተዘጋ በር አለፈ ይልቁኑ ከሞት የተነሳው ወልድ ዋህድ በተዘጋ በር አለፈ በአይንም ታየ ተገለጠም የቅዳሴ መጽሐፍ ስለእየሱስ ክርስቶስ ሞት እና መነሳት የሚናገረውን ጠቅሰን እንደምድም ነፍስና ስጋው ቢላቀቁም መለኮቱ ግን ከስጋውም ከነፍሱም ጋር ነበረች ነፍሱም ከመለኮቱ ጋር ሆና ለስብከትወደ ገሀነም ወረደች በእምነት ለሞቱትም የገነትን በር ከፈተች ነገር ግን ከመለኮት ጋር የተዋሀደው ስጋው በመቃብር ነበር በሶስተኛው ቀን ጌታ ሞትን ድል ነሳ ነፍሱም ከስጋው ጋር ተመልሳ ተዋሀደች መለኮት ግን ምንጊዜም አልተለየም ስለዚህም የዘላለም ድነት ሆነ አሜን
50399
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5%20%E1%89%85%E1%8B%B3%E1%88%9D
አዲስ ቅዳም
አ/ቅዳም አ/ቅዳም አ/ቅዳም በአማራ ክልል አዊ ዞን የ[ፋግታ ለኮማ] ወረዳ ዋና ከተማ ስትሆን አ/ቅዳም በምሥራቅ ጎጃም እና በምእራብ መሃል የምትገኝ ከተማ ነች። አዲስ ቅዳም በድሮው ጎጃም አጠቃላይ ግዛት አገው ምድር አውራጃ ፣በባንጃ ወረዳ፣በባንጃ ለኮማ ምክትል ወረዳነት ከ1936-1987 ዓ.ም የቆየች ስትሆን ከ1987 ዓ.ም ወዲህ አዊ ብሔረሰብ ዞን ራሱን ችሎ ሲቋቋም ወረዳዎች ውስጥ የፋግታ ለኮማ ወረዳ ዋና ከተማ ነች አንዳንድ አፈታሪኮች ለኮማ የባንጃ ልጅ ሲሆን ፋግታ ደግሞ የአንከሻ ልጅ ነው ይላሉ ፡፡ከተማዋ ከመዲናችን አዲስ አበባ 470 ኪ.ሜ ፣ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህርዳር 104 ኪ.ሜ እንዲሁም ከብሔስብ ዞን ርዕሰ ከተማ እንጅባራ 18 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከአዲስ አበባ -ጎንደር በሚወስደው አገር አቋራጭ መንገድ ግራና ቀኝ ደጋማ ቦታ ላይ የተመሰረተች ናት ፡፡ሰባቱ የአገው አባቶች ዛሬ አዲስ ቅዳም እየተባለ የሚጠራውን ቦታ በድሮ ጊዜ “አጂስ ክዳሜ” ብለው ሰይመውት ቅዳሜ ቀን ለመወያያትና ለገቢያ ማዕከልነት (ኩሰጝፂ፣ዙሚትጝፂ፣ እንክርጝፂ ኧኧኮ) ይጠቀሙበት እንደነበር የአካባቢው ቀደምት አባቶችና አፈ ታሪኮች ያስረዳሉ በ1903 ዓ.ም ጎጃም ገዥ የነበረው ንጉስ ተ/ሃይማኖት ሲሞት በጊዜው የነበሩት የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ምኒልክ ጎጃምን ምስራቅ ፣ዳሞትና አገው ምድር ብለው ሲከፋፍሉ ለእነዚህ ግዛቶችም አስተዳዳሪ/ገዢ/ ሲመርጡ ራስ መንገሻ አቲከም አገው ምድርንና ደሞትን ገዢ ሆነው ተሾሙ፡፡ ከዚያ በፊት የነሩበት አዛዥ ገዛኻኝ ከወሰኑት ቦታ ባንግ ታራራ (አመዳይ ደን) ላይ ሆነው የጥንቱን ገበያ ስባቱ አባቶች ካስቀመጡት አንስተው ወደ አቅራቢያቸው አዛማች ኪዳነ ምህረት ወደ “ጉቢቺሊ” በመውሰዳቸው በመሰራቾቹ ተቃውሞ ብዙም ሳይቆይ ተመልሶ አሁን ካለንበት ከጥንቱ ቦታ ገበያው ተቋቁሟል ወደ ቦታው ሲመለሱ ግን የድሮ መጠሪያ “አጂስ ቅዳሜ” በመቀየር አዲስ ቅዳም ተብሎ ተጠርቷል ይህም ሊሆን የቻለው የአውጚ ቋንቋ በአማረኛ እየተወረስ በመሄዱ ነው ይላሉ አባቶች የአዲስ ቅዳም ጦርነት የኢጣሊያን ጦርነት ሽንፈት በኃላ በኢትዮጵያ አርበኞች ላይ ለመቀበል ከ40 አመታት በኋላ እደገትና ተነሳስተው ክብራቸውንም ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ ላይ በኦጋዴን አካባቢ ድንበር ጥስው በመግባት አደጋን አድርሰዋል ፡፡ምንም እንኳ ያስቡት ባይሳካለቸውም የኢትዮጵያ አርበኞች ተጋድሏቸውን በየጫካውና በየሽንተረሩ ተያይዘውታል ለአምስት አመታት ያህል ከተካሄዱ ጦርቶች መካከል በድሮው አገው ምድር አውራጃ በአሁኑ አዊ አስ/ዞን ውስጥ አንዱ በጦርነት የአዲስ ቅዳም ጦርነት ነበር፡፡ ይህ ጦርነት የተካሄደው የኢጣሊያን የዳፈጣ ጦር ግንቦት 24/1932 ዓ.ም በሁለት አቅጣጫ ማለትም የእንጅባራው በደቡብና የዳንግላው በስተ ሰሜን የእንጅባራው አድጓሚ ተራራ እንዲሁም የዳንግላው ከአ/ ቅዳም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ መትረይስ በመቀየስ ለገበያ የመጣውን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ሲዘጋጅ ጀግኖች የአገው ምድር አባት አርበኞች የተለመደ ሽንፈት አከናንበው መልሰውታል አዲሲቅዳም ከተማ ምንም አይነት ቤት ስላልነበረው ቅዳሜ ቀን ለገቢያ ብዙ ህዝብ ይሰብሰብ ነበር፡፡ይህን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ነበር የጣሊያን ፋሽስት ጦር ቋምጦ የተነሳው በዕለቱም ህዝብ በቦታው የተለያዩ መሳሪያዎችን ለመሸጥና ለመግዛት የመጡ የአገውምድር አባትአርበኞች፣ራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ፣ ፊታውራሪ የኔው አባዲት፣ ፊትአውራሪ ደስታወርቄ፣ቀኝ አዝማች በቀለ ወንድምና ቀኝ አዝማች አባ ደስታ የተሳተፉ ሲሆን በተለይ እና ፊት አውራሪ የኔው አባዲና ከማሳው በመመስግ ፣ራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ከኳሽኒ መሽገው የፋሺስት ነጭ ደጋአመድ አድርገዋል፡፡ ጦርነቱ ከዕለቱ በግምት 4 ስዓት የተጀመረው ቀኑን ሙሉ ውሎ ጽሀይ ግባት ላይ በአገውምድር አርበኞች ድልአድራጊት ተፈፅሟል፡፡ በዕለቱ በዱርገ ደሉ የነበሩ ሴቶች ፊታውራሪ ተብለው የተሸለሙ ሲሆን ከጣላትም ሆነ ከአባት አርበኞች የሞተ እንዳለ ሆኖ ብዙ መሳሪያዎችን ማለትም 500 ያህል አልቢን ምኒሽር ፣50 ሽጉጦች ፣8 የእጅ መትረይስ ከጠላት እጅ ተማርከዋል፡፡ በማለት በወቅቱ ተሳታፊ የነበሩት አባት አርበኞች በትውስት ይናገራሉ የከተማዋ ገበሬዎች የአዲስ ቅዳም ከተማን ጥንታዊ የገቢያ ማዕከልነት ሲገልፁት በጃን ሆይ ጊዜ አዲስ ቅዳሜ ቀን የገቢያ ማዕከል በመሆንዋ ሀይለኛ የሆነ የገቢያ ምርት የገቢያ ግብዓት ለነበራትየዳንግላ ገበያን ቅዳሜ ቀን በተመሳሳይ ይውል ስለነበር ዳንግላ የገበያ ግብአት በመቀነሱ ወደ ረዕቡ ቀን እንደቀየሩ በጊዜው የነበረው ታሪክ አዋቂ አውራጃ ገዥ ግራ አዝማች አየሁ ጀንበሬያስረዳሉ ሆኖም ግን የደርግ መንግስት ከገባ በኃላ የገብያተኛውን የስራ ቀን እንዲውል ማለትም ቅዳሜ በማህበረሰዱ ዘምድ ስንበት ውይምሀጥማኖታዊ በዓል ተብሎ ስለሚከበር ነው ይህ አዲስ ቅዳም የገበያ ማዕከል በትልቅ ሾላ ዛፍ ስራ ስለነበር በዚህ ጥላ በመጠለል ጠላ፣ አረቄ፣ዳቦና የተለያዩ ነገሮች በተጨማሪ ይሸጥበት እንደነበር ይነገራሉ ገበያው ሰፊና ጥንታዊ በመሆኑ እንስሳት፣ እህል፣ማር፣ቅቤ ፣ሸቀጣ ሸቀጥ ፣ቡናና ሌሎችም ይገበያዩበታል የከተማው አመሰራረት ከተማዋ የተመሰረተችው በሁለት አጥቢያ ዳኛ በሚተዳደር የሽንኩሪ ሚካኤል እና በዚምብሪ ኪዳነ ምህረት ባለአባቶች መሬት ሲሆን ይህቦታ 1936 በፊት የባለአባቶች መሬት እንጂ ምንም አይነት ቤቶች ያልነበሩበት ፣ለከማነትም ያልታቀደ አልፎ አልፎ ቆባ ዛፍ ያለበት እንዲሁም ገበያተኛው የሚገበያይበት ትልቅ የሾላ ዛፍ እንደነበር የቦታው ነዋሪ አባቶች ያስተውሳሉ፡፡ ከጣሊያን ሽንፈት ወረራ በኃላ ፣ጃንሆይ ከውጭ ሀገር ከተመለሱ በኃላ /ማለትም 1936 ዓ.ም/ የአዲስ ቅዳም ከተማ ለገበያ ቦታ ሰፋትና ድምቀት በማመን በወቅቱ የነበሩ አገው ምድር አውራጃ አስተዳዳሪ ደጅ አዝማች ያረጋል እረታ ሰብሳቢነት በባንጃ ወረዳ አስረዳዳሪ ቀኝ አዝማች ቸኮል ጀንበሬ ፣በለኮማ ባንጃ ምክትል አስተዳዳሪነት ፣በፊት አውራሪ ደስታ ወርቄ በተገኙበት ገበያ ቦታ በአካባቢው ህዝብና የመሬት ባለይዞታዎች ፈቃደኝነት የገቢያው ስፋት በመከለሉ ከዚያው በመነሳት ምክትል አስተዳደሩና ወረዳ ቤተ ክህነት እንዲሆነ ተወሰነ፡፡ በ1951 በገቢያው ዙሪያ በአካባቢው ቤት በሰረቱት ከተማዋ መቆርቆር ጀመረች ከዚያ በፊት ለምክትል ወረዳ እናቤተ ክህነት ቢሮ በስተቀር ምንም አይነት ቤት ያልነበረ ሲሆን ከ1951 ጀምሮ ግንወ/ ሮ የዝብነሽ ታመነ የተባለች ሴት የመሸታ መሸጫ የዳስ ጎጆ በጊዜው ከነበሩ መሬት ባለአባቶች ጠይቃ ስራች በኋላም እና ወ/ሮ ቦጌ ብዙነህ፣ነጋድራስ ቢረስ፣ አቶ አያሌው ፈንቴ እና ሌሎችም የመሬት ባለአባቶችና ሌላ አካባቢ የመጡ ከባለአባቶች መሬት እየገዙ የሳር ጎጆዎችን መስራት ጀመሩ፡፡ ነጋድራስ ቢረስ ወርቅነህ የከተማዋ ቆርቆሮ ነጋዴ ነበሩ ሲሆን ከአዲስ አበባ በበቅሎ በመጫን አምጥተው ከተማዋን ከሳር ቤት ወደ ቆርቆሮ ቤት በመቀየር ከተማዋም ከገጠር ወደ ከተማ በሚደረገው የነጋዴዎችና ሴተኛ አዳሪዎች ፍልሰት እየሰፋች መምጣቷን የከተማዋ ነዋሪዎች ያበስራሉ ወ/ሮ የዝብነሽ ታመነ የመጀመሪያ መሽታ ቤት/ጠላ እና አረቄ ስትከፍት ወ/ሮ ቦጌ ብዙነሽ መጀመሪያ ከተማ ጠጅ ቤት እንደነበራቸው አባቶች ያወሳሉ መጀመሪያው ሰፈር የዶሮ ማነቂያ ሰፈር ይባላል ስያሜ የተሰጠውም ትንሽ አጣብቂኝ መንገድ ዛሬ ቴሌ ከመሰራቱ በፊት እንደነበር የሰፈሩ ነዋሪዎች
52684
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8D%8C%E1%88%AA%E1%8B%AB%E1%88%8D%20%E1%88%83%E1%8D%8B%E1%8C%84
ፌሪያል ሃፋጄ
ፌሪያል ሃፋጄ (እ.ኤ.አ. የካቲት 20፣ 1967 ተወለደች) ደቡብ አፍሪካዊ ጋዜጠኛ ነች፣ በተከታታይ የፋይናንሺያል ሜይል ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፣ ሜይል እና ጋርዲያን (2004-2009)፣ ከተማ ፕሬስ (ከጁላይ 2009 እስከ ሐምሌ 2016)፣ ሃፍፖስት ደቡብ አፍሪካ ደቡብ (2016-2018) ከዚያም በዴይሊ ማቬሪክ ምክትል አዘጋጅ. አመጣጥ እና ጥናቶች ከህንድ ተወላጅ እና የሙስሊም ሀይማኖት የአህመድ እና የአየሻ ሃፋጄ ልጅ ፌሪያል ሃፋጄ ያደገችው በቦስሞንት በጆሃንስበርግ ባለ ቀለም ከተማ በዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ ተምራ በ1989 በኪነጥበብ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመረቀች ሙያ ፌሪያል ከተመረቀች በኋላ በዊክሊ ሜይል በሰልጣኝ ጋዜጠኝነት ለሁለት አመታት ሰርታለች ከዚያም በ1991 የደቡብ አፍሪካ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ተቀላቅላ በቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት እስከ 1994 ድረስ ሰርታለች። እ.ኤ.አ. በ 1994 የፋይናንሺያል ሜይል መጽሔትን ተቀላቀለች እና ለፖለቲካው ክፍል ሀላፊነት ነበረች እና በ 1997 ውስጥ አርታኢ ሆነች እንደዚህ አይነት ቦታ በመያዝ የመጀመሪያዋ ነጭ ያልሆነች ሴት ነበረች እ.ኤ.አ. በ 2003 ሜይል እና ጋርዲያን (የቀድሞ ሳምንታዊ መልእክት) በምክትል አርታኢነት ተቀላቀለች እና ወረቀቱ በዚምባብዌ አሳታሚ ትሬቨር ንኩቤ ከተገዛ ከሁለት ዓመት በኋላ በመጨረሻም በ 2004 ወደ አርታኢ ከፍ ብላ ወጣች ። እ.ኤ.አ. በ 2006 ሀፋጄ ነቢዩ መሐመድን የሚያሳዩ አወዛጋቢ ካርቶኖችን እንደገና ካተመ በኋላ ዛቻ ደርሶባታል በ2009 የሲቲ ፕሬስ ዋና አዘጋጅ ሆነች። እ.ኤ.አ. በ 2012 በጃኮብ ዙማ የተሰሩ አስቂኝ ካርቶኖችን አሳትማለች ይህም በራሷ እና በሰራተኞቿ ላይ ጠንካራ ትችት እና ዛቻ ምላሽ እንድትሰጥ አድርጓታል። የመንግስት ሚኒስትር ምስሉን ከድረ-ገጹ ካላነሳው ጋዜጣው እንዲታገድ ጠየቀ። ሁኔታውን ለማቃለል ምስሉን ሰርዛለች, ነገር ግን ይህን በማድረግ በሌሎች ወገኖች ይህን በማድረጋቸው ተተችታለች. ካሰላሰለች በኋላ ለዙማ ደጋፊዎች ስጋት በመገዛቷ ትቆጫለች እና እራሷን እንደ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መሰረታዊ ሰው” በማለት ትቃወማለች እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2013 ሃፋጄ በአርትኦት ሰራተኞቿ ውስጥ በጥቁር ጋዜጠኞች በትዕቢት እና በዘረኝነት ተከሷታል ምክንያቱም የአርትኦት ክፍሏን በበቂ ሁኔታ ስለማታስተካክል ፣ነገር ግን በወቅቱ 8 ጋዜጠኞች ነበሯት ፣ይህም 5 ጥቁሮች 3 ነጮች 4 ሴቶች እና 4 ወንዶች በምላሹም ተቃዋሚዎቿን ጃኮብ ዙማን እንደምታይ አላስተናግድም ብለው የሚከሷት ተቃዋሚዎቿ ራሳቸው ዘረኞች ናቸው ስትል መለሰች። ከዚያም በሃፋጄ ላይ ቅሬታ አቅርበዋል በመጨረሻም አስተያየቱን አቋርጦ ይቅርታ ጠየቀች እ.ኤ.አ. በ 2015 እሷም የደቡብ አፍሪካን ታሪክ እና አሁን ባለው ስሜት ቀስቃሽ ጥያቄን ስትመረምር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነጮች ባይኖሩስ? ጥቁሮች ለተሻለ የሀብት ክፍፍል ምስጋና ይግባቸው (አይደለም ብላ ደመደመች) ሀብታሞች ወይም ድሆች ይሆኑ ነበር። መጽሐፉ ዓመት በኬፕ ታውን ዩኒቨርሲቲ የሴሲል ሮድስን ሐውልት በማፍረስ ረገድ ተሳክቶለታል የሀገሪቱን ተምሳሌታዊነት እና የአንግሎ-ሳክሰን ባህልን እንዲሁም ስምምነትን እና ሽግግሩን ድርድር ይጠይቃል በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከአፓርታይድ መውጣት በተለይም ከአዲሱ የድህረ-አፓርታይድ ትውልድ ጋር እራሷን እንዳጣች ትናገራለች ብላ ታምናለች የነጭነት ፅንሰ-ሀሳብ የተጠናወተው የነጮች መብት እየተባለ የሚጠራውን ውግዘት እና ያለፈው ትውልድ ያመጣውን ስምምነት ውድቅ በማድረግ ነው። በደቡብ አፍሪካ ሃፊንግተን ፖስት ውስጥ ለሁለት አመታት አጭር ቆይታ ከቆየች በኋላ በ2018 ዴይሊ ማቬሪክን ተቀላቅላለች። ጁሊየስ ማሌማ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳን ለመተቸት ማንም አልፈቀደም ያለው የጋዜጠኞች ስብስብ አካል አድርጎ ለይቷታል፣ ከራንጄኒ ሙኑሳሚ ማክስ ዱ ፕሬዝ እና ሌሎች ጥቂት ሰዎች ጋር በመጥቀስ ከዚያም እነሱን ለመመርመር እና ለማስፈራራት የግል ሕይወት ፌሪያል ሃፋጄ ከፖል ስቶበር፣ አምደኛ እና የሜይል እና ጠባቂ ምክትል ዳይሬክተር ጋር አግብቷል። ስራ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነጮች ባይኖሩስ? ፓን ማክሚላን ኤስኤ 2015 ማስታወሻዎች እና ማጣቀሻዎች ፌሪያል ሀፋጄ ፣ደቡብአፍሪካ፣ሲፒጄ ጋዜጠኞች ሀፋጄን በዘረኝነት ከሰሷቸው፣ 24, 10, 2013 የፌሪያል ሀፋጄ የዘረኝነት ስም ማጥፋት ክስ ተጠናቀቀ፣ የስራ ቀን፣ 16 2016 በኤስኤ ውስጥ ነጭ ሰዎች ባይኖሩስ? ህዳር 27፣ 2015 ሊን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነጭ ሰዎች ባይኖሩስ? ሱር 8 ዲሴምበር 2015) ዳን ሮድ፣ ጸረ-ነጭ ደፋር አዎንታዊ እርምጃ ልዕልት»፣ ሱር (እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 11 ቀን 2021 ደርሷል) ፌሪያል ሀፋጄ ወደ 15 2018 ይሄዳል ለተቃዋሚዎች ተጠያቂ የሆኑትን የጥላቻ ጋዜጠኞች ማነሳሳትን አውግዟል, ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች, ኖቬምበር 28, 2018 ምንጮች የህይወት ታሪክ በአጭሩ የህይወት ታሪክ የጌጥ አዶ ደቡብ አፍሪካ ፖርታል [[መደብ:የሲፒጄ አለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት አሸናፊዎች]] [[መደብ:1967 ልደት]] [[መደብ:ሕያዋን ሰዎች]] [[መደብ:ከጆሃንስበርግ የመጡ ሰዎች]] [[መደብ:የደቡብ አፍሪካ ጋዜጠኞች]] [[መደብ:የደቡብ አፍሪካ ጋዜጣ አዘጋጆች]] [[መደብ:የደቡብ አፍሪካ ጸሐፊዎች]] [[መደብ:የዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ