context
stringclasses
367 values
question
stringlengths
10
114
answer
stringlengths
1
90
answer_start
int64
0
3.22k
ዩጋንዳ ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው። ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው። ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል። ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል። ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው። የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል።
801. በዩጋንዳ በማን መሪ ጊዜ ነበር ከ300,000 በላይ ሰዎች ያለቁት?
ኢዲ አሚን
508
የትነበርሽ ንጉሴ የትነበርሽ ንጉሴ በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ እና የአካል ጉዳተኛ መብትቶች ተሟጋች ናት ፡ እ.ኤ.አ በ 2017 "የአካል ጉዳተኞችን መብቶችን እና ማካተቶችን በማስተዋወቅ እንዲሁም  በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉየአእምሮ ውቅርን መለወጥ የሚያበረታታ ሥራዋ"  ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድን ተሸልማለች። የትነበርሽ ንጉሴ የአይን ብርሃኗን ያጣችው በ 5 ዓመቷ ነበር ። ይህ አጋጣሚ በተወለድችበት በአማራ ክልል በስፋት ይተገበር ከነበረው ያለ አድሜ ጋብቻ  አንድታመልጥ እድሉን እንደፈጠረላት ትናገራለች። ፡፡የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሻሸመኔ ካቶሊክ የዓይነ ስውራን  ት/ቤት ተከታትላ ወደ ዳግማዊ  ምኒልክ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (አካታች ትምህርት ቤት) ገብታ እስከ 12 ኛ ክፍል እዚያ ተማረች። በትምህርት ቤቱ ካላት አካዳሚክ ተሳትፎ በተጨማሪ የተማሪዎችን አማካሪ ጨምሮ ከ 6 በላይ የክለቦችን ክበባት መርታለች ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በመቀላቀል የመጀመሪያ ዲግሪ በሕግ ሁለተኛ ዲግሪ በማኅበራዊ ሥራ አግኝ ታለች፡፡ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ  በልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በተከታታይ  ትሳተፋለች በዚህም  የመኢአድ የፀረ ኤድስ እንቅስቃሴን ከ2004 - 05 በመምራት በ 2006 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (አአዩ) ሴት ተማሪዎች ማህበርን በመመስረት እንዲሁም የማህበሩ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት በመሆን  አገልግላለች ፡፡
የትነበርሽ ንጉሴ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በምን የትምህርት ዘርፍ ተመረቀች?
በሕግ
563
ጋና ጋና በአፍሪካ አትላንቲክ ጠረፍ ላይ የተገኘ አገር ሲሆን ከ24 ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉት። የጋና ስራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ሲሆን፣ ሌሎች ኗሪ ቋንቋዎች በተለይም ትዊኛ (አካንኛ) በሰፊ ይነገራሉ። የ«ጋና» ስያሜ በታሪክ የድሮ «ጋና መንግሥት» ወይም «ዋጋዱጉ መንግሥት» ለማክበር በ1949 ዓም ተመረጠ። እንዲያውም ያው መንግሥት እስከ 1068 ዓም ድረስ ከጋና ወደ ስሜን-ምዕራብ በአሁኑ ማሊ ይገኝ ነበር እንጂ የዛሬውን ጋና መቸም አልገዛም። «ጋና» በትክክል የዋጋዱጉ መንግሥት አለቆች ማዕረግ ሆኖ ነበር። ዋጋዱጉ መንግሥት በ1068 ዓም ግድም ከወደቀ ቀጥሎ፣ የአካን ብሔሮች ከዚያው ፈልሰው በዛሬው ጋና ሠፈሩና መጀመርያ ግዛቶችን መሠረቱ። ከ1662 እስከ 1949 ዓም ድረስ የአሻንቲ መንግሥት ባካባቢው ቆየ፤ በ1894 ዓም ይህ የብሪታንያ አሻንቲ ጥብቅ ግዛት ሆነ። ከ1949 ዓም አስቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጥገኛ ግዛት ሲሆን በወርቅ ሀብቱ ምክንያት «የወርቅ ጠረፍ ጥገኛ ግዛት» (ጎልድ ኮስት ፕሮቴክቶሬት) በመባል ይታወቅ ነበር። ከ1984 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እና ፓርላሜንታዊ መንግሥት ኖሮታል። አብዛኞቹ ኗሪዎች (70%) በተለይ በደቡቡ ክርስቲያን ሲሆኑ፣ በተለይ በስሜኑ 16% የእስልምና ተከታዮች ናቸው። የተረፉትም የኗሪ አረመኔነትን እምነቶች ይከተላሉ። የጋና ዋና ምርቶች ካካዎ፣ ዘይት፣ አልማዝ ናቸው። በአለሙ ከሁሉ ትልቅ የሆነው ሠው ሰራሽ ሐይቅ፣ ቮልታ ሐይቅ፣ በጋና ይገኛል። እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው። የጋና አበሳሰል በተለይ በኮቤ፣ ጐርጠብ፣ የስኳር ድንች፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ኦቾሎኒ፣ ባሚያና ሩዝ ይሠራል።
በጋና ከ1662 እስከ 1949 ዓም የቆየው መንግሥት ምን ተብሎ ይጠራ ነበር?
የአሻንቲ መንግሥት
432
በማደግ ላይ ባሉ አገራት የሚኖሩ ህዝቦች ግንባር ቀደም ገዳይ ከሚባሉት በሽታዎች አንዱ የሆነውን የቲቢ በሽታ ለማስቆም የሚያስችል ”EndTB” የተሰኘ ንቅናቄ ተካሄደ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባለፈው ረቡዕ በሒልተን ሆቴል በይፋ ያስጀመረው ቲቢን እናስቁም ንቅናቄ እ.ኤ.አ በ2032 በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ከ100 ሺህ አስር ብቻ ለማድረስ የታለመ ነው፡፡ ከአዳሱ የፈረንጆች ዓመት እስከ 2032 ዓ.ም ይደረጋል በተባለው በዚሁ “ቲቢን እናስቁም” ንቅናቄ፤ አገራት ሁሉ፤ ተሳታፊ በመሆን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ያለውን የቲቢ በሽታ ለመግታትና በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ በትጋት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡ በሒልተን ሆቴል በተካሄደው ፕሮግራም ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት የግሎባል ቲቢ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር ማርዮ ራቨግሊዮን እንደገለፁት፤ በሽታው በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ስርጭት 133 ሰዎች ከ100 ሺህ ሰዎች ሲሆን በኢትዮጵያ ቁጥሩ 200 ሰዎች ከ100 ሺህ ሰዎች ይደርሳል ብለዋል፡፡ በሽታውን ለማስቆም በተያዘው ዕቅድ መሰረትም፤ እ.ኤ.አ ከ2016-2032 ዓ.ም ድረስ በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ከ100ሺ አስር ለማድረስ መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡ ዕቅዱ እንዲሳካም አገራት ከፍተኛ ሥራ እንደሚጠበቅባቸውና ለተግባራዊነቱም የመንግስታቱን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት በቲቢ በሽታ የሚያዙ ሰዎችን ከ100 ሺህ አስር ለማድረስ ያሰበው መቼ ነው?
በ2032
178
ግሥላ ግሥላ በእስያ፣ በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ) እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኝ አጥቢ አውሬ ነው። በእስያ የተገኘው ነብር የግስላ ቅርብ ዘመድ ሆኖ፣ በአነጋገር «ግስላ»ና «ነብር» የሚሉ ስሞች ሊለዋወጡ ይችላሉ። የአንድ ጎልማሳ ግሥላ ክብደት ከ35 እስከ 80 ኪ.ግ ሲደርስ በርዝመት ከ90 ሴ.ሜ እስከ 1,60 ሜ.ና በአፍሪካ የሚገኘው ዘር እስከ 1,90 ሜ ይደርሳል ። ከመሬት እስከ ሆዱ ከ50 እስከ 70 ሴ.ሜ ቁመት ሲኖረው ጭራው ደግሞ እስከ 100 ሴ.ሜ ርዝማኔ ያሳያል ። ሴቲቱ ከወንዱ አነስ ትላለች ። በዱር ሲኖር እስከ 10 አመት እንደሚኖር ሲታወቅ በሰው ተይዘው ሲኖሩ እስከ 20 አመት እድሜ ያስመዘገቡ ግሥሎች አሉ።
የአንድ ጎልማሳ ግሥላ ክብደ ምን ያህል ድረስ ሊመዝን ይችላል?
ከ35 እስከ 80 ኪ.ግ
154
ነሐሴ ፳፯ ነሐሴ ፳፯ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፯ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፰ ዕለታት ይቀራሉ። ፲፮፻፶፰ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የጋየውና አስር ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው የሎንዶን ትልቁ እሳት ተነሳ። ፲፯፻፵፬ ዓ/ም የምዕራብ አውሮፓ አገራት ዘመን አቆጣጠራቸውን በለወጡ በሁለት መቶ ዓመታቸው፣ ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን ተቀበለች። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በጠላት ወረራ ዘመን የሸዋ አርበኞች ቡልጋ ላይ ተሰባስበው የልጅ ኢያሱን ልጅ መልአከ-ፀሐይ ኢያሱን አነገሡ። አዲሱ 'ንጉሥ' ወዲያው የአርበኞች መሪ ለነበሩት ባላምባራስ አበበ አረጋይ የራስነት ማዕርግ ሰጠ። መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ መስከረም ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፩ ዓ/ም አረፎ አንኮበር አካባቢ በሚገኘው ዞማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጃፓን በተሸናፊነቷ እጇን ሰጠች። ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ነጻነትን አስከትሎ በጃዋሃርላል ኔህሩ ምክትል ፕሬዚደንትነት የሚመራ የሕንድ ጊዜያዊ መንግሥት ተመሠረተ። ፲፱፻፺ ዓ/ም የርዋንዳን ፍጅት አስከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ጃን ፖል አካዬሱ የተባለውን የቀድሞ ከንቲባ ላይ ፍርዱን የወንጀለኛነት ፍርድ ፈረደበት።
ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን የተቀበለችው በስንት ዓመተ ምህረት ነበር?
፲፯፻፵፬ ዓ/ም
211
ፍቅር እስከ መቃብር ፍቅር እስከ መቃብር በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ የቀረበ ልብ ወለድ ሲሆን ሰብለ ወንጌል እና በዛብህ የሚባሉ የሁለት ገፀ ባህሪያትን ፍቅር ይተርካል። ይህ ድርሰት ከሌሎች ልብወለድ ሥራዎች ለየት የሚያደርገው ደራሲው ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ በፊደል አጠቃቀም ላይ ለውጥ አድርገው በማቅረባቸው ነው። ይኸውም ለምሳሌ ያህል ሦስት «ሀ»ዎች፣ ሁለት «ሰ»ዎች፣ ሁለት «ኣ»ዎች የመሳሰሉትን እንደ አንድ ወይም የመጀመሪያውን ብቻ በመያዝ ነው። በተጨማሪም ጠብቀው በሚነገሩ ቃላት ላይ ከላይ አንድ ነጥብ በማስቀመጥ ይታወቃሉ።ሀዲስ ኣለማየሁ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሑፍ የራሳቸው ትልቅ አሻራ አኑረው ያለፉ አንጋፋ ደራሲ ናቸው። የታሪኩ ማጠቃለያ በዛብህ‌ ‌ጎጃም‌ ‌ማንኩሳ‌ ‌ውስጥ‌ ‌ከእናቱ‌ ‌ከውድነሽ‌ ‌በጣሙና‌ ‌ከአባቱን‌ ‌ከቦጋለ‌ ‌መብራት‌ ‌ይወለዳል።‌ ‌በሽታ‌ ‌ይበዛበትና‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይባላል።‌ ‌እናቱ‌ ‌ከበሽታው‌ ‌እንዲድን‌ ‌ስእለት‌ ‌ይሳላሉ።‌ ‌ዕድል‌ ‌ሆኖ‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይተርፋል፤‌ ‌አድጎ‌ ‌ጎበዝ‌ ‌ልጅ‌ ‌ይሆናል።‌ ‌ቀድሞ‌ ‌በሽታ፣‌ ‌ከዚያም‌ ‌ደግሞ‌ ‌ዕውቀትና‌ ‌ፍቅር‌ ‌(የሰው‌ ‌መውደድ)‌ ‌ይበዛበታል።‌ ‌በወጣትነቱ‌ ‌ይቀድስና‌ ‌ለቤተሰቡ‌ ‌ገንዘብ‌ ‌ማምጣት‌ ‌ይጀምራል።‌ ‌ቀድሞ‌ ‌የስእለት‌ ‌ልጅ‌ ‌መባልን‌ ‌አይጠላም‌ ‌ነበር።‌ ‌ሲያድግ‌ ‌ግን‌ ‌ትርጉሙን‌ ‌በመረዳቱ‌ ‌ነጻነቱን‌ ‌ለማግኘት‌ ‌ዲማን‌ ‌ጥሎ‌ ‌ወደደብረ‌ ‌ወርቅ‌ ‌ይሄዳል።‌ ‌እዚያም‌ ‌ከእመት‌ ‌ጠጂቱ‌ ‌ዘንድ‌ ‌ይጠጋል።‌ ‌ትንሽ‌ ‌ዜማና‌ ‌ቅኔም‌ ‌ይማራል።‌ ‌ደብተራ‌ ‌በየነ‌ ‌መጥቶ‌ ‌የወላጆቹን‌ ‌ሞት‌ ‌ሲያረዳው‌ ‌ወደዲማ‌ ‌ይወርዳል።‌ ‌በተክለ‌ ‌አልፍአው‌ ‌በዓል‌ ‌በመልካም‌ ‌ድምጹ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻንና‌ ‌ወይዘሮ‌ ‌ጥሩአይነትን‌ ‌ያወድሳል።‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻም‌ ‌የሰብለ‌ ‌መምህር‌ ‌አድርገው‌ ‌ይቀጥሩታል።‌ ‌ሰብለና‌ ‌በዛብህ‌ ‌የሕይወት‌ ‌ገጠመኞቻቸው‌ ‌በመጠኑ‌ ‌ስለሚመሳሰል‌ ‌ይግባባሉ።‌ ‌በመሃል‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌አሰጋኸኝ‌ ‌ሰብለን‌ ‌በፈት‌ ‌ወግ‌ ‌አገባለሁ‌ ‌በማለቱ‌ ‌በርሱና‌ ‌በፊታውራሪ‌ ‌መሸሻ‌ ‌መካከል‌ ‌ጥል‌ ‌ተፈጠረ፤‌ ‌ሆኖም‌ ‌በሃይማኖት‌ ‌ጣልቃገብነት‌ ‌ሳይዋጉ‌ ‌ቀሩ።‌ ‌ከዚያም‌ ‌ደግሞ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ከባላገሮች‌ ‌ጋራ‌ ‌በግብር‌ ‌ጉዳይ‌ ‌ተጣሉ።‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ተማርከው‌ ‌ሳለ‌ ‌የበዛብህንና‌ ‌የሰብለወንጌልን‌ ‌የፍቅር‌ ‌ዜና‌ ‌ይሰማሉ።‌ ‌ወዲያውም‌ ‌መጥተው‌ ‌ሰብለን‌ ‌በሌሊት‌ ‌ያስሯታል።‌ ‌የሰብለ‌‌አጎት‌ ‌ጉዱ‌ ‌ካሳም‌ ‌ሁለቱን‌ ‌ለማስመለጥ‌ ‌ወጣ፣‌ ‌ወረደ።‌ ‌የዕጣ‌ ‌ነገር‌ ‌ሆኖ‌ ‌ግን‌ ‌ሳይሳካ‌ ‌ቀረ።‌ ‌በዛብህ‌ ‌ግን‌ ‌በግራጌታ‌ ‌ቀለመወርቅና‌ ‌በጉዱ‌ ‌ካሳ‌ ‌ጥረት‌ ‌ወደአዲስ‌ ‌አበባ‌ ‌ይሄዳል።‌ ‌በራጉኤል‌ ‌ቤተክርስቲያንም‌ ‌የቅኔ‌ ‌መምህር‌ ‌ሆኖ‌ ‌ይቀጠራል።‌ ‌ባደረጉላቸው‌ ‌ውለታ‌ ‌ምክንያት‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻ‌ ‌ሰብለን‌ ‌ለፊታውራሪ‌ ‌ታፈሰ‌ ‌ሊድሯት‌ ‌ይሞክራሉ።‌ ‌የሰብለን‌ ‌አቋም‌ ‌አውቀው‌ ‌አባ‌ ‌ተክለሃይማኖት‌ ‌በተባሉ‌ ‌መነኩሴ‌ ‌ያስጠብቋቷል።‌ ‌መነኩሴው‌ ‌ግን‌ ‌ሰክረው‌ ‌ሰብለ‌ ‌ታመልጣለች።‌ ‌ፍለጋ‌ ‌ሲሄዱ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ከፈረስ‌ ‌ላይ‌ ‌ተወርውረው፣‌ ‌ተንኮታክተው‌ ‌ይሞታሉ።‌ ‌ወይዘሮ‌ ‌ጥሩአይነትም‌ ‌ቤተክርስቲያን‌ ‌ውስጥ‌ ‌ከደረጃ‌ ‌ላይ‌ ‌ተንሸራትተው‌ ‌ወድቀው‌ ‌ይሞታሉ።‌ ‌ሰብለ‌ ‌ደግሞ‌ ‌በዛብህን‌ ‌ለማግኘት‌ ‌መነኩሴ‌ ‌መስላ‌ ‌ወደአዲስ‌ ‌አበባ‌ ‌ትሄዳለች።‌ ‌ደርሳም‌ ‌በዛብህ‌ ‌አለመኖሩን‌ ‌ትሰማና‌ ‌ጎሃጽዮን‌ ‌ትወርዳለች።‌ ‌በዚያም‌ ‌በዛብህ‌ ‌ተደብድቦ፣‌ ‌ነፍስ‌ ‌ውጪ‌ ነፍስ‌ ‌ግቢ‌ ‌አይነት‌ ‌ሁኔታ‌ ‌ላይ‌ ‌ሳለ‌ ‌ይገናኛሉ።‌ ‌እንደምንም‌ ‌ብለው‌ ‌ሥጋ‌ ‌ወደሙን‌ ‌ይቀበላሉ።‌ ‌ጥቂት‌ ‌ቆይቶ‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይሞታል።‌ ‌ሰብለም‌ ‌መንኩሳ፣‌ ‌የበዛብህን‌ ‌አስከሬን‌ ‌ባጠገቧ‌ ‌አድርጋ‌ ‌ስትኖር‌ ‌ከጉዱ‌ ‌ካሳ‌ ‌ጋራ‌ ‌ይገናኛሉ።‌ ‌ጉዱ‌ ‌የተሰኘው‌ ‌ካሳ‌ ‌ዳምጤም‌ ‌እርሷ‌ ‌ዘንድ‌ ‌ይቀመጣል።‌ ‌አስራ‌ ‌አምስት‌ ‌ቀናት‌ ‌አንድ‌ ‌ላይ‌ ‌ይኖሩና‌ ‌ሰብለ‌ ‌የልብ‌ ‌በሽታዋ‌ ‌ተነሥቶባት‌ ‌ትሞታለች፣‌ ‌ጉዱ‌ ‌ካሳም‌ ‌ከበዛብህ‌ ‌አጠገብ‌ ‌ያስተኛታል።‌ ‌በሦስተኛው‌ ‌አመት‌ ‌ጉዱም‌ ‌አረፍተ‌ ‌ዘመን‌ ‌ይገታዋል።‌
ፍቅር እስከ መቃብር በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ መቼ ቀረበ?
በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም.
26
አዞ አዞዎች ረዘም ብሎ ጠንካራ የሆነ የራስ ቅል አላቸው። በዛ ያሉ ጠንካራ ጥርስ አፋቸው ውስጥ ተደርድረው ይታያሉ። ውኃና ምግብ በአፋቸው በያዙበት ጊዜ እንኳን መተንፈስ የሚያስችላቸው ተፈጥሮ አላቸው። አዞዎች እንቁላል ጣዮች ናቸው። ከ20 እስከ 50 እንቁላሎች ብስባሽ ቅጠላ ቅጠሎች ውስጥ ጥለው እናቶቻቸው ይጠብቋቸዋል። ይህም እንቁላሉ ሊፈለፈል ሲቃረብ ከእንቁላሉ ውስጥ የሚሰሙት ድምፅ እንቁላሉን ሰብረው ጫጩቶቹ እንዲወጡ ለማድረግ ያስችላቸዋል። እንደ ኤሊዎችና አንዳንድ እንሽላሊቶች ሁሉ እንቁላሎቹ የተጣሉበት ሁኔታ (ጎጆ) የሙቀት መጠን የሚፈለፈሉትን ጫጩቶች ጾታ ይወስናል። ሆኖም ከኤሊዎች በተቃራኒ የእንቁላሉ ጎጆ የሙቀት መጠን መቀነስ ሴቶችን፣ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ደግሞ ወንዶችን እንዲፈለፈሉ ያደርጋል። ሁሉም አዞቻች አምፊቢየስ ይባላሉ። ምክንያቱም ታዳጊዎቹም ትልልቆቹም ከፊሉን ጊዜያቸውን ውኃ ውስጥ ከፊሉን መት ላይ ስለሚያሳልፉት ነው። ረጅምና ጠንካራ ጭራቸው እንደ መሣሪያ በማገልገል ሰውንም ሆነ ሌላ እንስሳ ፊቱ ላይ መትቶ በመጣል ለጥርሳቸው ያቀርብላቸዋል። በውኃ ውስጥም ባላቸው ፈጣን እንቅስቃሴ ከእነሱ ለማምለጥ ከባድ ይሆናል። ለረጅም ጊዜ ከውኃ ሥር ሆነው መቆየት ቢችሉም እንደሌሎቹ ገበሎ አስተኔዎች በሳምባ የሚተነፍሱ ናቸው። ስለዚህም አፍንጫቸውን ከውኃው በላይ በማውጣት አየር ይስባሉ። ሁሉም አዞዎች እንቁላል ይጥላሉ። እንደሌሎቹ ገበሎ አስተኔዎችም እንቁላሎቹን መሬት ውስጥ ይቀብራሉ። ሴቶቹ አዞዎች በሚሠሯቸው ጎጆዎች ይለያያሉ። አንዳንዶቹ አሸዋ ውስጥ ቀዳዳ በመቆፈር እንቁላሉን ይቀብሩትና ይሸፍኑታል። ሌሎቹ እንደ አሊጌተር ዓይነቶቹ ብዛት ያለው የበሰበሰ ቅጠላ ቅጠፀል በመሰብሰብ እዛ መሃል እንቁላሉን ይጥሉታል። ብዛት ያላቸው ደርዘን እንቁላሎች (እያንዳንዱ በመጠን ከዶሮ የበለጠ) በአንድ ቁጭታ ሊጥሉ ይችላሉ። ሲፈለፈሉ ታዳጊዎቹ አዞዎች ከ22-25 ሳንቲ ሜትር ቁመት ይኖራቸዋ”ል። አዞዎች ጥርሳቸውን በተደጋጋሚ ይተካሉ። የሚተካው (ያረጀው) ጥርስ ሥር ያለው አዲስ ጥርስ ሲሆን፤ አዲሱ ተኪ ጥርስ አድጎ ትልቅ ካልሆነ በስተቀር አሮጌው ቶሎ ብሎ ወልቆ አይወድቅም። የአዞ አይን 360 ዲግሪ ማየት ይችላል። እንዲሁም ሰው 180 ዲግሪ ዘውሮ ማየት ይችላል።
አዞዎች ለምን አምፌቢያን ይባላሉ?
ከፊሉን ጊዜያቸውን ውኃ ውስጥ ከፊሉን መት ላይ ስለሚያሳልፉት
495
አልጄሪያ አልጄሪያ (አረብኛ፦ الجزائر‎ አል ጃዝኤር; በርበርኛ፦ ድዜየር) በይፋ የአልጄሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሰሜን አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከቆሳ ስፋት አኳያ በሜዲቴራንያን ባህር ዙሪያ ትልቋ ስትሆን፣ ከአፍሪካ ደግሞ ከሱዳን በኋላ ሁለተኛ ናት። አልጄሪያ ከሰሜን ምሥራቅ በቱኒዚያ፣ ከምሥራቅ በሊቢያ፣ ከምዕራብ በሞሮኮ፣ ከደቡብ ምዕራብ በምዕራባዊ ሣህራ፣ ሞሪታኒያና ማሊ፣ ከደቡብ ምሥራቅ በኒጄር፣ ከሰሜን በሜዲቴራንያን ባህር ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ አልጂርዝ ሲሆን የ፳፻፫ ዓ.ም. ሕዝብ ብዛቷ ወደ 35.7 ሚሊዮን ይገመታል። አልጄሪያ የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ ኦፔክ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ሀገር ናት። የሀገሯ ስም የመጣው ከአልጂርዝ ከተማ ሲሆን በድሮ ጊዜ ከዛሬዎቹ ምዕራብ ቱኒዚያና ምሥራቅ ሞርኮ አብራ ኑሚዲያ ትባል ነበር። በጥንት ጊዜ አልጄሪያ የኑሚዲያ መንግሥት ትባል የነበረ ሲሆን ነዋሪዎቿ ደግሞ ኑሚዲያውያን ይባሉ ነበር። የኑሚዲያ መንግሥት ከካርታጎ፣ ሮማና ጥንታዊ ግሪክ ጋር ግንኙነት ነበራት። አካባቢው ለምለም እንደነበረ ሲነገር ኑሚዲያውያን ደግሞ ለኃይለኛ ፈረሰኛ ጦራቸው ይታወቁ ነበር።
አልጄርያ ከጎረቤቷ ሊቢያ ጋር ከየት አቅጣጫ ትዋሰናለች?
ከምሥራቅ
194
አዳኝ አንበሶች በጣም ቀልጣፋና ፈጣን ቢሆኑም እንኳ በአደን ጊዜ የሚሳካላቸው 30 በመቶ ብቻ ነው። በመሆኑም አንበሶች ከተደቀኑባቸው ትልልቅ አደጋዎች አንዱ ረኃብ ነው። ለአካለ መጠን የደረሰ አንድ አንበሳ ያለው ጥንካሬ እጅግ የሚያስገርም ነው። በቤተሰብ ደረጃ የሚያድኑ እንደ መሆናቸው መጠን ከ1,300 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ያላቸውን እንስሳት የመጣልና የመግደል አቅም እንዳላቸው ይነገራል። አንበሶች በመጀመሪያ ላይ በሰዓት እስከ 59 ኪሎ ሜትር ድረስ ሊሮጡ ይችላሉ፤ ሆኖም ይህ ፍጥነታቸው እስከ መጨረሻ አይዘልቅም። በዚህ ምክንያት ቀለባቸውን ለማግኘት አድብቶ የመያዝ ዘዴ ይጠቀማሉ። የማደኑን ተግባር 90 በመቶ የሚያከናውኑት ሴቶቹ አንበሶች ቢሆኑም በሚበሉበት ጊዜ ትልቁን ድርሻ የሚያገኙት ትልልቆቹ ወንድ አንበሶች ናቸው። አደን በሚጠፋበት ጊዜ አንዳንዴ አንበሶች በጣም ስለሚርባቸው ያገኙትን መብል ለራሳቸው ግልገሎች እንኳ ለማካፈል ፈቃደኛ አይሆኑም። ታዳኝ ከብዙ ዓመታት በፊት ባለ ግርማ ሞገሱ አንበሳ በመላው የአፍሪካ አህጉር እንዲሁም በእስያ፣ በአውሮፓ፣ በህንድና በፍልስጤም አንዳንድ ቦታዎች ይገኝ ነበር። አዳኝ እንደመሆኑ መጠን ሰውን እየተቀናቀነ የሚኖር እንስሳ ነው። በከብቶች ላይ አደጋ የሚጥልና በሰዎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ አንበሳ ገና እንደታየ በጥይት የሚገደል ፍጡር ሆነ። የሕዝብ ቁጥር ፍንዳታ የአንበሳን መኖሪያ በእጅጉ አመናምኖታል። ዛሬ ከአፍሪካ ውጪ ባለው የዓለም ክፍል በዱር የሚኖሩት አንበሶች በጥቂት መቶዎች ብቻ የሚቆጠሩ ሆነዋል። በአሁኑ ጊዜ አንበሶች ሰው ከሚያደርስባቸው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ተጠብቀው መኖር የሚችሉት ጥበቃ በሚደረግባቸው ክልሎች ውስጥና በዱር አራዊት መጠበቂያ ቦታዎች ብቻ ሆኗል። አንበሳ ሲያገሣ አንበሶች በሚያገሡበት ጊዜ በብዙ ኪሎ ሜትር ርቀት ሊሰማ የሚችል ከፍተኛ ድምፅ የማውጣት ልዩ ችሎታ አላቸው። አንበሳ ሲያገሣ የሚያሰማው ድምፅ “እጅግ ማራኪ ከሆኑት የተፈጥሮ ድምፆች” አንዱ እንደሆነ ይነገራል። ብዙውን ጊዜ አንበሶች በጨለማ ሰዓትና ንጋት ላይ ያገሣሉ። ወንዶቹም ሆኑ ሴቶቹ አንበሶች የሚያገሡ ሲሆን አንዳንዴም የመንጋው አባላት በአንድነት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያገሣሉ። በአንበሶች ላይ ጥናት የሚያካሂዱ ሳይንቲስቶች አንበሶች የሚያገሡባቸው የተወሰኑ ምክንያቶች እንዳሉ ይናገራሉ። ወንዶቹ አንበሶች የሚኖሩበትን ክልል ድንበር ለማሳወቅ እንዲሁም ሌሎች ወንድ አንበሶች ወደ ክልላቸው እንዳይገቡ ለማስጠንቀቅ ሲሉ ያገሣሉ። በርቀት ወይም በጨለማ ተነጣጥለው ያሉ የአንድ መንጋ አባላት ያሉበትን ቦታ ለመጠቆም ያገሣሉ። በተጨማሪም አንድ እንስሳ ከገደሉ በኋላ ለሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት ምግቡ ያለበትን ቦታ ለማሳወቅ ያገሣሉ። አንበሶች በሚያድኑበት ጊዜ የሚያድኗቸውን እንስሳት ለማስደንበር ብለው አያገሡም። ሪቻርድ ኤስቲዝ ዘ ቢሄቭየር ጋይድ ቱ አፍሪካን ማማልስ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ “አንበሶች የሚያድኑትን እንስሳ ለማጥመድ ሲሉ ሆን ብለው እንደሚያገሡ የሚጠቁም ምንም ነገር የለም (በተሞክሮዬ እንዳየሁት በአንበሳ የሚታደኑ እንስሳት አንበሳ ለሚያሰማው የግሣት ድምፅ ብዙም ትኩረት አይሰጡም)።
ወንዶቹ አንበሶች የሚኖሩበትን ክልል ድንበር ለማሳወቅ እንዲሁም ሌሎች ወንድ አንበሶች ወደ ክልላቸው እንዳይገቡ ለማስጠንቀቅ ምን ያደርጋሉ?
ያገሣሉ
1,225
መስከረም 23/12 ዓ ም ሽሬ ኢዜአ  የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ይሁንታ ያገኘው የ35 ዓመት ወጣት ሔሊኮፕተር ሰርቶ ለሙከራ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ ። ወጣት ዕበ ለገሰ ይባላል ። በመደበኛ ትምህርት ብዙ ገፍቶ ባይሔድም በፈጣራ ብቃቱ ግን በርካታ ስራዎች ለህዝብ እንዲያደርስ አድርጎታል ። የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰራ ምጣድ ጥገና ሥራ የጀመረው ወጣት አሁን ላይ ትልቅ ራእይ አንግቦ የራሱ የሆኑ የፈጠራ ስራዎችን በማቅረብ ውጤታማነቱን በተጠቃሚዎች ዘንድ እየተመሰከረለት መጥቷል ። የምጣድ ጥገና ስራው ለታናሽ ወንድሙ በመልቀቅ የወርቅ መአድን መፈለጊያ መሳሪያ ወደ ማሻሻል መሸጋገሩን ይገልፃል ። በራሱ ፈጠራ ያሻሻለው የወርቅ መፈለጊያ መሳሪያ በባህላዊ መንገድ ወርቅ ለሚያመርቱ ሰዎች በሽያጭ በማቅረብ የፍለጋ ሥራቸውን እንዲቃለል እንዳስቻላቸው ተጠቃሚዎቹ ይናገራሉ ። ቀደም ሲል የነበረው ‘’ጂ አር ዜድ’’ የተባለው የወርቅ መፈለጊያ መሳሪያ ከ70 እስከ 80 ሳንቲ ሜትር ጥልቀት ባለው መሬት ውስጥ የሚገኝ የደለል ወርቅ የሚጠቁም ነበር ። ወጣቱ ያሻሸለው ግን በአንድ ሜትር ጥልቀት የሚገኘውን የደለል ወርቅ በቀላሉ መለየት የሚያስችል መሳርያ ሆኖ ተገኝቷል ። እንዲሁም ከድንጋይ ጋር ተደባልቆ የሚገኝ ወርቅ በቀላሉ መለየት የሚያስችል የድንጋይ ወፍጮ በመፍጠር ለተጠቃሚዎቹ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም ወጣት  ለገሰ ይናገራል ። ባለፉት አምስት ዓመታት አምስት የድንጋይ ወፍጮዎችን በመስራት ለተጣቀሚዎቹ በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቧል ። በተጠናቀቀው ዓመት በራሱ ፈጠራ ሶስት ሰዎች የማሳፈር አቅም ያለት ሔሊኮፕተር ሰርቶ በሙከራ ደረጃ ለህዝብ እይታ አቅርቦ የነበረው ወጣቱ ዘንድሮ ለማብረር እየተዘጋጀ መሆኑንም ተናግሯል ። የፈጠራ ሥራዬ ስኬትና ሚስጥር “ይቻላል” የሚል ጽኑ እምነት ስላለኝ ነው የሚለው ወጣቱ ከኢንተርኔት የሚያገኛቸው የፈጠራ ሥራዎችም እገዛ እንዳደረጉለት ጠቁሟል። ሥራ ፈጣሪ ወጣቱ ወደ ገበያ በሚያቀርባቸው የፈጠራ ውጤቱ ጥሩ ገቢ ከማግኘቱም ባሻገር ለሌሎች 10 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግሯል። የወጣቱ የፈጠራ ወጤት ተጠቃሚ ከሆኑትና በባህላዊ መንገድ በደለል ወርቅ ምርት ፍለጋ ከተሰማሩ ማህበራት መካከል የ“ስምረት” ማህበር አንዱ ነው። የማህበሩ አባል የሆነው ወጣት በላይ ተክለሃይማኖት በሰጠው አስተያየት ” ከወጣቱ የገዛነው የደለል ወርቅ ጠቋሚ መሳርያ ሥራችንን ከማቃለል በተጨማሪ በወርቅ ፍለጋው ስኬታማ እንድንሆን አግዞናል” ብሏል። ሌላው የማህበሩ አባል ወጣት ተስፋይ በላይ በበኩሉ ” ከድንጋይ ጋር ተደባልቆ የሚገኝ ወርቅ ለመለየት እጅግ አድካሚ የነበረው ሥራ ወጣቱ ባቀረበልን አነስተኛ የድንጋይ ወፍጮ በመጠቀም የድካማችንን ዋጋ ማግኘት አስችሎናል ” በማለት አድናቆቱን ገልፆለታል ። የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ጎይቶኦም ይሰማ እንዳሉትም ደግሞ የወጣቱን የፈጠራ ክህሎት እንዲሰፋና ሄሊኮፕተሯ ለህዝብ እይታ እንድትበቃ አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረግለታል ። የሽሬ እንደስላሴ ፖሊ ቴክኒክና ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋይ ገብረሚካኤል በበኩላቸው የፈጠራ ባለቤት የሆነው ወጣት እበ ለገሰ የፈጠራ ስራዎች የሚያተኩሩት በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ በሚታዩ መሰረታዊ ችግሮች ዙሪያ በመሆናቸው ተቀባይነታቸው የጎላ ነው ብለዋል ። ወጣቱ የሚያሳየው ትጋት የተሞላበት የፈጠራ ስራ ለሌሎች ወጣቶችም አርአያ በመሆን መነቃቃት መፍጠሩን የኮሌጁ ዲን መስክረውለታል ።
ቀድሞ ይጠቀሙበት የነበረው የወርቅ መፈለጊያ ማሽን ምን ያህል ጥልቀት ይፈልጋል?
ከ70 እስከ 80 ሳንቲ ሜትር
573
ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር (1906-2001) የሴኔጋል የመጀመሪያው መራሄ መንግስት በመሆን ከ1960 እስከ 1980 ድረስ ያገለገሉ፣ ኔግሪቲዩድ የሚባለው ፍልስፍና ዋነኛ አቀንቃኝ የነበሩ እና በግጥሞቹም አድናቆትን ያተረፉ አፍሪካዊ የሥነጽሁፍ ሰው ናቸው። ሴንጎር የሴኔጋል ዋና ከተማ ከሆነችው ዳካር 70 ማይልስ ያህል በምትርቅ እና ጆአል ላ ፖርቱጊዝ (ጆአል ፖርቱጊዛዊቱዋ) በምትባል ትንሽ የአሳ አጥማጆች መንደር በ1906 ተወለዱ። አባታችው ነጋዴ ከሆኑ ሴሬር ከሚባሉ ጎሳ የተወለዱ ሲሆን እናታቸው ግን ፔውል ከተባለ የሙስሊም ዘላን አርብቶአደሮች ጎሳ የተወለዱ ሴት ናቸው። ሴንጎር ኋላ ላይ ሲጽፉ «ተወልጄ ያደኩት በአፍሪካ መኸል፣ የጎሳዎች እና ዘሮች መገናኛ ላይ ነው» ብለዋል። በ12 ዓመታችው የካቶሊክ ሚሲዮን ትምህርት ቤት ተመዝግበው ትምህርታቸውን የጀመሩ ሲሆን ከዛ በኋላ በሌሎች ትምህርት ቤቶችም በመማር በ1928 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። ከዚያም ፓሪስ ከሚገኘው ሊሴ ፓሪ ለግራንድ ከተባለው ትምህርት ቤት በ1931 ተመርቀዋል።
ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር በ1931 የተመረቁበት ትምህርት ቤት ማን ይባላል?
ሊሴ ፓሪ ለግራንድ
576
አክሱም አክሱም በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክ/ሃገር ከአድዋ ተራራዎች አጠገብ የምትገኝ ከተማ ነች። በክርስቶስ ልደት በፊት ተመስርቶ የነበረው የአክሱም ስርወ መንግስት ማእከል ነበረች የአክሱም ስርወ መንግስት በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ እየተዳከመ ሲመጣ የማእከላዊው መንግስት ወደ ደቡብ ተንቀሳቀሰ። ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው የከተማው ነዋሪ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ነው። የተቀሩት ነዋሪዎች የሱኒ እስልምና ተከታዮች ናቸው። ባላቸው ታሪካዊ ተፈላጊነት ከተማ ውስጥ የሚገኙት የአክሱም ስርወ መንግስት ቅሪቶች UNESCO በ1980 የአለም ቅርስ ቦታ ተብለው ተሰይመዋል ። አክሱም በኢትዮጵያ የ ትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በማዕከላዊ ዞንና በላዕላይ ማይጨው ወረዳ ይገኛል።
የአክሱም ስርወ መንግስት መቀመጫ የነበረችው የኢትዮጵያ ከተማ ማናት?
አክሱም
5
አፕል ኩባንያ ተጠቃሚዎች በድምፅ ማዘዝ የሚችሉት ገመድ አልባ ድምፅ ማዳመጫ ወይንም ኢርፎን ይፋ አደረገ፡፡ ይህም ተጠቃሚዎች ምንም አይነት ነገር ሳይጫኑ ሃይ ሲሪ የሚል ድምፅ በማሰማት ብቻ የድምፅ ማዳመጫውን ማዘዝ እንደሚችሉ ነው የተነገረው፡፡ ከዚህ ባለፈ ኤርፖድስ የተባለው ገመድ አልባ ድምፅ ማዳመጫ ተጠቃሚዎች ባትሪ ካለቀባቸው እንዲያስተካክሉ ተጨማሪ ሰዓትን በቅድሚያ እንደሚሰጥ ነው የተነገረው፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡ ባለሙያዎች ኤርፖድስ የተሰኘው የድምፅ ማዳመጫ በእጅጉ እየዘመነ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ ይህ አዲሱ ድምፅ ማዳመጫ 159 የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ ሲሆን ገመድ አልባ ቻርጀርን የሚያካትት ከሆነ ተጨማሪ 40 ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
አፕል ኩባንያ ያቀረበው ኤርፓድስ የተባለ ገመድ አልባ ድምፅ ማዳመጫ ዋጋው ስንት ነው?
159 የአሜሪካ ዶላር
353
አሸናፊ ከበደ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ አዲስ አበባ ግንቦት ፰ ቀን ፲፱፻፴ ዓ/ም ተወለዱ። አባታቸው ግራዝማች ከበደ አድነው ሲሆኑ ክልጅነታቸው ጀምሮ የሙዚቃ ስሜትንና ፍቅር ያሳደሩባቸው እናታቸው ወይዘሮ ፋንታዬ ነከሬ ነበሩ። አያታቸው ሊቀመኳስ አድነው ጎሹ ደግሞ የአድዋ አርበኛ እናየንግሥት ዘውዲቱም ታማኝ አማካሪ እንደነበሩ ይነገራል። የሙዚቃ ፍቅርን ገና በልጅነታቸው ያሳደሩባቸው እናታቸው ሲሆኑ ታዳጊው አሸናፊ ገና የዘጠኝ ዓመት ልጅ ሳሉ እኒህ የሚያፈቅሯቸውና ዕድሜ ልካቸውን በኀዘን የሚስታውሷቸው እናታቸው ሞተውባቸዋል። መሠረታዊ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ኮከበ ጽባሕ) ካጠናቀቁ በኋላ በሐረር የመምህራን ማሠልጠኛ ኮሌጅ ተመርቀዋል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በኒው ዮርክ ክፍለ-ሀገር ከሚገኘው የሮቼስተር ዩኒቨርሲቲ፣ “ኢስትማን የሙዚቃ ትምህርት ቤት” በ፲፱፻፶፬ ዓ/ም በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፤ የያሬድ ሙዚቃ ትምሕርት ቤትን መሠረቱ። የዚሁ ትምህርት ቤትም የመጀመሪያው ዳይሬክቶር ከመሆናቸውም ባሻገር በአዲስ አበባው የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር (ወ.ወ.ክ.ማ Y.M.C.A.)፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት መርሓ-ዕውራን ትምህርት ቤት እና በመሳሰሉ የወጣቶች ማኅበራት እየተገኙ የሙዚቃ ትምህርት ይሰጡ ነበር።
ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ የሙዚቃ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የት ተማሩ?
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ኮከበ ጽባሕ)
371
አዞ አዞዎች ረዘም ብሎ ጠንካራ የሆነ የራስ ቅል አላቸው። በዛ ያሉ ጠንካራ ጥርስ አፋቸው ውስጥ ተደርድረው ይታያሉ። ውኃና ምግብ በአፋቸው በያዙበት ጊዜ እንኳን መተንፈስ የሚያስችላቸው ተፈጥሮ አላቸው። አዞዎች እንቁላል ጣዮች ናቸው። ከ20 እስከ 50 እንቁላሎች ብስባሽ ቅጠላ ቅጠሎች ውስጥ ጥለው እናቶቻቸው ይጠብቋቸዋል። ይህም እንቁላሉ ሊፈለፈል ሲቃረብ ከእንቁላሉ ውስጥ የሚሰሙት ድምፅ እንቁላሉን ሰብረው ጫጩቶቹ እንዲወጡ ለማድረግ ያስችላቸዋል። እንደ ኤሊዎችና አንዳንድ እንሽላሊቶች ሁሉ እንቁላሎቹ የተጣሉበት ሁኔታ (ጎጆ) የሙቀት መጠን የሚፈለፈሉትን ጫጩቶች ጾታ ይወስናል። ሆኖም ከኤሊዎች በተቃራኒ የእንቁላሉ ጎጆ የሙቀት መጠን መቀነስ ሴቶችን፣ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ደግሞ ወንዶችን እንዲፈለፈሉ ያደርጋል። ሁሉም አዞቻች አምፊቢየስ ይባላሉ። ምክንያቱም ታዳጊዎቹም ትልልቆቹም ከፊሉን ጊዜያቸውን ውኃ ውስጥ ከፊሉን መት ላይ ስለሚያሳልፉት ነው። ረጅምና ጠንካራ ጭራቸው እንደ መሣሪያ በማገልገል ሰውንም ሆነ ሌላ እንስሳ ፊቱ ላይ መትቶ በመጣል ለጥርሳቸው ያቀርብላቸዋል። በውኃ ውስጥም ባላቸው ፈጣን እንቅስቃሴ ከእነሱ ለማምለጥ ከባድ ይሆናል። ለረጅም ጊዜ ከውኃ ሥር ሆነው መቆየት ቢችሉም እንደሌሎቹ ገበሎ አስተኔዎች በሳምባ የሚተነፍሱ ናቸው። ስለዚህም አፍንጫቸውን ከውኃው በላይ በማውጣት አየር ይስባሉ። ሁሉም አዞዎች እንቁላል ይጥላሉ። እንደሌሎቹ ገበሎ አስተኔዎችም እንቁላሎቹን መሬት ውስጥ ይቀብራሉ። ሴቶቹ አዞዎች በሚሠሯቸው ጎጆዎች ይለያያሉ። አንዳንዶቹ አሸዋ ውስጥ ቀዳዳ በመቆፈር እንቁላሉን ይቀብሩትና ይሸፍኑታል። ሌሎቹ እንደ አሊጌተር ዓይነቶቹ ብዛት ያለው የበሰበሰ ቅጠላ ቅጠፀል በመሰብሰብ እዛ መሃል እንቁላሉን ይጥሉታል። ብዛት ያላቸው ደርዘን እንቁላሎች (እያንዳንዱ በመጠን ከዶሮ የበለጠ) በአንድ ቁጭታ ሊጥሉ ይችላሉ። ሲፈለፈሉ ታዳጊዎቹ አዞዎች ከ22-25 ሳንቲ ሜትር ቁመት ይኖራቸዋ”ል። አዞዎች ጥርሳቸውን በተደጋጋሚ ይተካሉ። የሚተካው (ያረጀው) ጥርስ ሥር ያለው አዲስ ጥርስ ሲሆን፤ አዲሱ ተኪ ጥርስ አድጎ ትልቅ ካልሆነ በስተቀር አሮጌው ቶሎ ብሎ ወልቆ አይወድቅም። የአዞ አይን 360 ዲግሪ ማየት ይችላል። እንዲሁም ሰው 180 ዲግሪ ዘውሮ ማየት ይችላል።
አዞዎች በምን መልክ ይራባሉ?
አዞዎች እንቁላል ጣዮች ናቸው።
128
ማሊ የማሊ ሪፐብሊክ (ማሊ) በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ የለሽ ሀገር ናት። ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በስፋት ሁለተኛ ናት። ከአልጄሪያ፣ ኒጄር፣ ቡርኪና ፋሶ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኔ፣ ሴኔጋል እና ሞሪታኒያ ጋር ድንበር ትዋሰናለች። ማንዴ ሕዝቦች አውራጃውን ሠፍረው ተከታታይ መንግሥታት አጸኑ። እነዚህም የጋና መንግሥት፣ የማሊ መንግሥትና የሶንግሃይ መንግሥት ያጠቅልላሉ። በነዚህ መንግሥታት ውስጥ ቲምቡክቱ ለትምርትና ለመገበያየት ቁልፍ ከተማ ነበረች። በ1583 ዓ.ም. በሞሮኮ በተካሄደ ወረራ የሶንግሃይ መንግሥት ኃይል ለማነስ ጀመር። ማሊ በ1880 እ.ኤ.አ. በፈረንሣይ ቅኝ ተገዝታ «ፈረንሳያዊ ሱዳን» ወይም «የሱዳን ሪፐብሊክ» ትባል ነበር። ፈረንሳያዊ ሱዳን በኅዳር 16 ቀን 1951 ዓ.ም. በፈረንሳያዊ ማሕበረሠብ ውስጥ 'ራስ-ገዥ ሁኔታ' አገኝታ በመጋቢት 26 1951 ዓ.ም. ከሴኔጋል ጋር አንድላይ የማሊ ፌደሬሽን ሆኑ። ይህ የማሊ ፌዴሬሽን በሰኔ 13 ቀን 1952 ነጻነት አገኘ። ነገር ግን በነሐሴ 14 ቀን ሴኔጋል ከፌዴሬሽኑ ወጣች። በመስከረም 12 ቀን 1953 ዓ.ም. ፈረንሳያዊ ሱዳን በሞዲቦ ኪየታ ስር ራሷን 'የማሊ ሬፑብሊክ' አዋጀችና ከማሕበረሰቡ ወጣች። ሞዲቦ ኪየታ በ1968 እ.ኤ.ኣ. በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ከወረደ በኋላ እስከ 1991 እ.ኤ.አ. ድረስ ማሊ በማውሳ ትራዎሬ ተመራች። በ1991 እ.ኤ.አ. የተካሄዱ ተቃውሞች ወደ መፈንቅለ-መንግሥት አመሩ። ከዚያም የተሸጋጋሪ መንግሥት ተቋቋመና አዲስ ሥነ-መንግሥት ተጻፈ። በ1992 እ.ኤ.አ. አልፋ ዑመር ኮናሬ የማሊን የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን አሸነፉ። ማሊ ከባሕር ጋር ግንኙነት የላትም። የሀገሩ አብዛኛው ክፍል በሰሐራ በረሃ ውስጥ ይገኛል። ከተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ ወርቅ፣ ዩራኒየም፣ ፎስፌት፣ ካዎሊን፣ ጨው፣ ኖራ (ላይምስቶን) ይጠቀሳሉ። የማሊ ፓርላማ 147 ሰዎች ሲኖረው እነዚህ ተወካዮች በህዝብ ብዛት ነው የሚመረጡት። ማሊ ከዓለም ደሀ ሀገሮች አንዷ ስትሆን 65 ከመቶ የሚሆነው መሬት በረሃ ነው። አብዛኛው የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ በኒጅር ወንዝ አካባቢ ነው የሚካሄደው። 10 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ የሚኖር ሲሆን 80 ከመቶ የሚሆነው የሥራ ሃይል በእርሻና ዓሣ ማጥመድ ተሰማርቷል። የኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ በእርሻ ምርቶች ላይ ያተኩራል። የሸክላ ሥራ በሴቶች የሚከናወን ሲሆን በነጋዴዎች በገበያዎች ይሸጣል። ሸክላዎቹ የሚሰሩበት ባሕላዊ ሂደት የቱሪስት መሳቢያ ነው።
ማውሳ ትራዎሬ ወደ ማሊ ሪፐብሊክ መሪነት የመጣው መቼ ነበር?
በ1968 እ.ኤ.ኣ.
687
አፖሎ 11 አፖሎ 11 ለመጀመሪያ ጊዜ ሰወችን ከመሬት ወደ ጨረቃ ለማጓጓዝ የተዘጋጀ የመንኮራኩር ሚስዮን ነው። ይህ ጉዞ የተቀናበረው በአሜሪካው የጠፈር አጥኝ ተቋም ናሳ ነበር። መንኮራኩሩ ሐምሌ16 1961ዓ.ም ከመሬት ሲመጥቅ፣ በውስጡ ሶስት ጠፈርተኞችን፣ ማለትም ኔል አርምስትሮንግ፣ በዝ አልድሪንና ማይክል ኮሊንስን የያዘ ነበር። መጓጓዣ መንኮራኩሩ ጨረቃ ላይ ከ4 ቀን በኋላ ሐምሌ 20 ሲደረስ፣ በዚሁ ቀን አርምስትሮንግና አልድሪን የጨረቃን ምድር በእግራቸው በመርገጥ የመጀመሪያወቹ ሰዎች ሆኑ። ኮሊንስ ባንጻሩ በጨረቃ ከባቢ በመብረር ከላይ ይጠብቃቸው ስለነበር ጨረቃን አልረገጠም። ይህ ድርጊት በፕሬዘደንት ኬኔዲ "የሰወች ልጅን ጨረቃ ላይ አሳርፎ በሰላም መመለስ" አላማ ያሳካ ነበር። የአፖሎ 11 ሚሲዮን ወደ ጠፈር ሲመነጠቅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰወች በአለም ዙሪያ በቴለቪዥናቸው ተመልክተውታል። ይህን ሚሲዮን ይዞ የተጓዘው ሮኬት ሳተርን ፬ ሲባል ችቦው እየተንቀለቀለ ወደ ሰማይ ጉዞ የጀመረው ኬኔዲ ጠፈር ማዕከል፣ 1961 ዓ.ም. ነበር። መሬትን ከለቀቀ ከ2 ሰዓት በኋላ የጨረቃ ትዕዛዝ ማዕከልና ማረፊያ ሞጅሎቹ ዋናውን ሮኬት ለቀው በጠፈር ጉዞ ቀጠሉ። ከ3 ቀን በኋላ ትዕዛዝ ማዕከሉና ማረፊያው ሞዱል የጨረቃን ምህዋር ተከትለው ጨረቃን መዞር ጀመሩ። ከአንድ ቀን በኋላ ማረፊያው ሞዱል ከትዕዛዝ ማዕከሉ ተላቆ ጨረቃ ላይ አረፈ። በዚህ የማረፍ ተግባር ወቅት የኮምፒውተር ስህተት ስለገጠመ ማረፊያው ሞዱል በኔል አርምስትሮንግ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስር ነበር። የሆኖ ሆኖ ለ25 ሰኮንዶች በቂ የሆነ ነዳጅ ሲቀር ማረፊያው መንኮራኩር ኔል አርምስትሮንግንና አልድሪንን ይዞ ጨረቃ ላይ በሰላም አረፈ። ጨረቃ ላይ ስራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሁለቱ ጠፈርተኞች ወደ ማረፊያ መንኮራኩራቸው በመመለስ ለ7 ሰዓት ጨረቃ ላይ ከተኙ በኋላ ከላይ በኮሊንስ ወደ ሚበረው የትዕዛዝ ማዕከል ለመብረር ዝግጅት ጀመሩ። እነ አርምስትሮንግ በጨረቃ ላይ በነበሩበት ጊዜ ብዙ ቁሶችን ትተው ተመልሰዋል። ለምሳሌ ከ73 የአለም መሪወች የተላለፉ መልዕክቶችን፣ የሰላምታ መልክዕት በሁሉ የመሬት ላይ ቋንቋወችና የሁለት ሰው ልጆች ስዕሎችን ትተው ተመልሰዋል። የአሜሪካንንም ባንዲራ በጨረቃ ተክለዋል። ሓምሌ 24 የትዕዛዝ ማዕከሉ መሬት ላይ ሲደርስ ምናልባትም ጠፈርተኞቹ ያልታወቀ አደገኛ ቫይረስ ጨረቃ ላይ አጋጥሟቸው ሊሆን ይችላል በሚል በኳረንታይን ለ3 ሳምንት ከሰው ልጆች ተለይተው ተቀመጡ። ከኳረንታይን ሲወጡ፣ በርግጥም እንደ ታላላቅ ጀግኖች በተለያዩ የአለም ክፍሎች ስማቸው ተጠራ በዋሽንግተን ዲሲና በሜክሲኮ ሲቲ ለጠፈርተኞቹ ትልቅ ሰልፍ ሆነ።
ናሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰዎችን ከመሬት ወደ ጨረቃ ለማጓጓዝ ያዘጋጀው መንኮራኩር ምን ይባላል?
አፖሎ 11
0
ሄርበርት ሁቨር (1866 - 1957 ዓ.ም.) ከ1921 እስከ 1925 ዓ.ም. ድረስ 31ኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ። የሁቨር ቤተሠብ ከስዊስና ጀርመን ትውልድ ሲሆን ሃይማኖቱ የክዌከር ('የሚንቀጠቀጡ' ማለት ነው) ቤተ ክርስቲያን ነበረ። ወላጆቹ በልጅነቱ ጊዜ ካረፉ አንስቶ ድሃ አደግ ሆነና ከአጎቱ ጋር አደገ። በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቴ መጀመርያ ክፍል በመሆኑ ትምህርቱ በነጻ ተቀበለ። ከዚያ በላይ የዩኒቬርሲቴው የቤስባልና የፉትቦል ቡድኖች አለቃ ሆነ። በ1887 ዓ.ም. የጂዮሎጂ ዲግሪ ይዘው ተመረቁ። ለ20 ዓመት የማዕደን ሊቅ ሲሆኑ እንኳን በአውስትራልያና በእንግሊዝ በማዕደን ዘርፍ የሠሩት ሥራ ስመ ጥሩ ሆነ። መጀመርያው ታላቅ አለማዊ ጦርነት በ1906 ዓ.ም. በጀመረበት ወቅት ሁቨር ከራሳቸው ኪስ ለጋሥነት አውጥተው 120,000 አሜሪካውያን ቱሪስቶችና ሠራተኞችን ከአውሮፓ ወደ አገራቸው አስመለሷቸው። ከዚያ በጀርመኖች በተወረረው በቤልጅግ ውስጥ የኖሩት ረሃብተኞች ምግብ እንዲደርሳቸው ብዙ አደረጉ። በዚህ አይነት ሥራ በጦርነት ጊዜ የሁቨር ስም ጀግና እንዳለው ሁኔታ በመገኘት ላይ ሄዶ ነበር። ጦርነቱም ከተጨረሰ በኋላ ለምሥራቅ አውሮጳ ድሃ ሕዝብ እስከ ሩስያም ድረስ በረሃብ ላሉት ሰዎች ምግብ አደረሷቸው።
ሄርበርት ሁቨር በየት ዩንቨርስቲ ተማረ?
በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቴ
198
ዳምጠው አየለ ዳምጠው አየለ (23.11. 1944 አ/ም – 27.10. 2006 አ/ም) ባህላዊ የኢትዮጵያ ዘፋኝ ነበር። በሃምሌ 23 1944 አ/ም ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአባቱ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ ሰሜን ሸዋ ተወለደ። ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንዳሳለፈ ይናገራል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል። ዳምጠው ህይወቱ እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ጊዜ አብሯት የኖረው ባለቤቱ አልማዝ ይመር ትባላለች። ከአልማዝ ይመር አብዩ ዳምጠውና ቤቴልሄም ዳምጠው የሚባሉ ሁለት ልጆችን አፍርቷል። ዳምጠው መራቤቴ እያለ በየባእላቱ መዝፈን፣ ማቅራራት እንዲሁም መሸለል ይወድ እንደነበር ተናግሯል። በተለይም ጥምቀትን በማድመቅ ይታወቅ ነበር። የ 6ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ክፍሌ ሞገስ የሚባል መምህሩ ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ይናገራል። ባጋጣሚም የምድር ጦር ማስታወቂያ አውጥቶ ስለነበር ይፈተንና ያልፋል። የምድር ጦር ካምፕ ውስጥም እንዲኖር ይደረጋል። የዘፋኝነት ሙያው በዚህ አጋጣሚ ነበር የጀመረው። ዳምጠው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዉና መነሻ የሆነው አበበ ተሰማ እንደሆነ ይናገራል። ዳምጠው አየለ በምድር ጦር ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል። የኢትዮዽያ ምድር ጦር በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም የፈረሰ የሙዚቃ ቡድን ነበር። ዳምጠው በመንግስት ለውጥ ምክንያት እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አብሮ እንደነበር ይናገራል። ምድር ጦርም እያለ ከነታምራት ሞላ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ጥላየ ጨዋቃ፣ ክፍሌ አቦቸር እንዲሁም ሌሎች የጦሩ አባላት ጋር ሰርቷል። ከሌሎች የሙዚቃ ቡድንም ጋር አብሮ ሰርቷል። ለምሳሌ ያክል ከነ ክቡር ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ሙሉቀን መለስ፣ ፀሃየ ዮሃንስ፣ ቴድሮስ ታደሰ፣ቴድሮስ ካሳሁን እንዲሁም ሌሎችም ጋር ሰርቷል። የዳምጠው አየለ የመጀመሪያ የህትመት ስራው በ1963 አ/ም ሲሆን ወፌ ላላ የሚለው የሸክላ ስራ ነበር። ዳምጠው አየለ ባጠቃላይ 13 ሲዲዎችን ሰርቷል። ዳምጠው አየለ ኖርዌይ ሃገር በስደት ለ 8 አመት ያክል ኖሯል። ኢትዮጵያም ከገባ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው በቅ/ገብራኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ 62 አመቱ ሰኔ 27 2006 አ/ም ቀን ህይወቱ አልፏል። የቀብር ስነስርአቱም ወዳጅ፣ ዘመድ እንዲሁም አድናቂዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተፈጽሟል።
ዳምጠው አየለ ስንት ልጆች አሉዋቸው?
ሁለት
357
ጋና ጋና በአፍሪካ አትላንቲክ ጠረፍ ላይ የተገኘ አገር ሲሆን ከ24 ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉት። የጋና ስራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ሲሆን፣ ሌሎች ኗሪ ቋንቋዎች በተለይም ትዊኛ (አካንኛ) በሰፊ ይነገራሉ። የ«ጋና» ስያሜ በታሪክ የድሮ «ጋና መንግሥት» ወይም «ዋጋዱጉ መንግሥት» ለማክበር በ1949 ዓም ተመረጠ። እንዲያውም ያው መንግሥት እስከ 1068 ዓም ድረስ ከጋና ወደ ስሜን-ምዕራብ በአሁኑ ማሊ ይገኝ ነበር እንጂ የዛሬውን ጋና መቸም አልገዛም። «ጋና» በትክክል የዋጋዱጉ መንግሥት አለቆች ማዕረግ ሆኖ ነበር። ዋጋዱጉ መንግሥት በ1068 ዓም ግድም ከወደቀ ቀጥሎ፣ የአካን ብሔሮች ከዚያው ፈልሰው በዛሬው ጋና ሠፈሩና መጀመርያ ግዛቶችን መሠረቱ። ከ1662 እስከ 1949 ዓም ድረስ የአሻንቲ መንግሥት ባካባቢው ቆየ፤ በ1894 ዓም ይህ የብሪታንያ አሻንቲ ጥብቅ ግዛት ሆነ። ከ1949 ዓም አስቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጥገኛ ግዛት ሲሆን በወርቅ ሀብቱ ምክንያት «የወርቅ ጠረፍ ጥገኛ ግዛት» (ጎልድ ኮስት ፕሮቴክቶሬት) በመባል ይታወቅ ነበር። ከ1984 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እና ፓርላሜንታዊ መንግሥት ኖሮታል። አብዛኞቹ ኗሪዎች (70%) በተለይ በደቡቡ ክርስቲያን ሲሆኑ፣ በተለይ በስሜኑ 16% የእስልምና ተከታዮች ናቸው። የተረፉትም የኗሪ አረመኔነትን እምነቶች ይከተላሉ። የጋና ዋና ምርቶች ካካዎ፣ ዘይት፣ አልማዝ ናቸው። በአለሙ ከሁሉ ትልቅ የሆነው ሠው ሰራሽ ሐይቅ፣ ቮልታ ሐይቅ፣ በጋና ይገኛል። እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው። የጋና አበሳሰል በተለይ በኮቤ፣ ጐርጠብ፣ የስኳር ድንች፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ኦቾሎኒ፣ ባሚያና ሩዝ ይሠራል።
በአፍሪካ ካሉ ሀገራት ጋና በየትኛው ውቅያኖስ ጠረፍ ላይ ይገኛል?
አትላንቲክ
12
ኢንስታግራም እና ፌስቡክ በአሜሪካ የተገደሉትን የኢራኑ ጄኔራል ቃሲም ሱለይማኒን ሃሳብ የሚደግፉ መረጃዎችን ከገጻቸው እያስወገዱ ነው። የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ መተግበሪያዎቹ መረጃዎቹን ከገጸቸው የሚያስወገዱት አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ተከትሎ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ መሰረት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ደንበኞች የጀኔራል ሱለይማኒን ሃሳብ ደግፈው በመተግበሪያዎቹ የሚያሰራጯቸውን መረጃዎች እያስወገዱ መሆኑ ተመላክቷል። በተለይም በኢራን የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ጄኔራሉን ደግፈው የሚያሰራጩትን መረጃ ከገጻቸው እያስወገዱ መሆኑንም አስታውቀዋል። ይህን ተከትሎም ኢራናውያን ኢንስታግራም እና ፌስ ቡክ በፈፀሙት ህገ ወጥ ተግባር እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። የኢራን መንግስት ቃል አቀባይ አሊ ሬቤይ በበኩላቸው፥ ድርጊቱን ዴሞክራሲያዊ አሰራርን ያልተከተለ እና ሃላፊነት የጎደለው ሲሉ ኮንነውታል። የኢራኑ ጀኔራል ቃሲም ሱለይማኒ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ትዕዛዝ በኢራቅ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እንዲገደሉ ከተደረገ በኋላ በሀገራቱ መካከል ውጥረት መንገሱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም አሜሪካ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ባለቻቸው በተለያዩ ኢራናያውያን ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። ኢንስታግራም እና ፌስ ቡክም አሜሪካ ማዕቀብ በጣለችባቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች ሲተዳደሩ የነበሩ ገጾችን ከመተግበሪያቸው ማስወገዳቸውን አስታውቀዋል። ምንጭ ፥ ሲ ኤን ኤን
የኢራኑ ጄኔራል ቃሲም ሱለይማኒን የተገደሉት የት ሀገር እያሉ ነው?
በኢራቅ
558
ባሕር-ዳር ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች። ባሕር-ዳር ከአዲስ አበባ 565 ኪ.ሜ ወደ ሰሜን-ሰሜን ምዕራብ ትገኛለች። ባህር ዳር ከጢስ አባይ በ30 ኪሎሜትር ስለምትርቅ ለጎብኚዎች አመቺ ቦታ ላይ ናት። ባህር ዳር የአንድ የአስፋልት ንጣፍ ያለው ኤርፖርት የሰፊ ገበያና የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች እና ታሪካዊ እና ጥንታዊ ግዳማት መግኛ ቦታ ናት። ባሕርዳር ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ "ከባሕሩ-ዳር" አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደሩ ባሕር-ዳር ብለው ስያሜ አወጡለት ይባላል። ባሕር-ዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡ ባሕር-ዳር በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤ የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች አሏት፡፡ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡ የተቆረቆረችበትን ዓመት፣ የቆረቆሩትን ቀደምት ሠዎች፣ የሠፈሮችን ስሞች፣ ለባሕር-ዳር የተገጠሙትና የተዘፈኑ ታሪካዊ ግጥሞችና ስነ ቃሎች፣ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጎጆ ቤት ወደ አሁኑ ይዞታው አመጣጥ (ባሕር-ዳርን ስናስብ ጊዮርጊስን ሚካኤልን እና ገበያውን ከገበያው አካባቢ የነበረውን ፍርድ ቤት ነጣጥሎ ማየት አይቻልም የሚል አስተያየት ስላለ ነው)፣ ባሕር-ዳር እንደባሕር ዳርነቱ ከመቆርቆሩ በፊት በሚካኤል እና በሽመምብጥ ሠፈር አካባቢ ስለነበረው አሰፋፈር፣ ስለማዘጋጃቤቱ፣ ስለ አውቶቡስ ተራው፣ ስለ ድባነቄ ተራራ፣ እና ስለ መሳሉት፣ ስለፖሊቴክኒክ፣ ስለዓባይ ወንዝና ድልድዩ፣ ስለዓባይ ወንዝና ስለጣና ሐይቅ መገናኛ እና ስለሌሎችም ቁልፍ ነገሮችን ማቅረብ የሚችሉ አፈታሪኮች አሉ።
ባሕር ዳር በኢትዮጵያ የየትኛው ክልል ዋና መዲና ናት?
የአማራ ክልል
66
ፐርል በክ ፐርል በክ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ (1938) ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓ.ም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር። ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተገናነች። በ1917 ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኑሯቸውን ናንሹ በተባለችው የገጠራማዋ አንህዌ ግዛት አደረጉ። በዚሁ ቆይታዋ ነው ወደፊት የሥነ-ጽሁፍ ስራዋ ጉልላት ለመሆን የበቃውን ስሙር መሬት (The Good Earth) ለተባለው መጽሃፏ የሚሆናትን መረጃ የሰበሰበችው። በክ ጽሁፎቿን ማሳተም የጀመረችው ከ1920ዎቹ ጀምራ ሲሆን አጫጭር ስራዎቿ "The Nation"፣ "The Chinese Recorder"፣ "Asia" እና "The Atlantic Monthly" በተሰኙ መጽሄቶች ታትመውላታል። የመጀመሪያው ወጥ ልብ-ወለድ ድርሰቷ (East Wind, West Wind) በ1930 በጆን ዴይ ኩባንያ ታትሟል። የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው ሪቻርድ ዋልሽ ኋላ ላይ (1935) የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን በቅቷል። በ1931 ጆን ዴይ ኩባንያ የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ ድርስት የሆነውን ስሙር መሬትን አሳተመ። ይኸው ሥራዋ በተከታታይ በ1931 እና በ1932 ዓ.ም በገበያ ላይ አንደኛ ተፈላጊ ሆኖ ለመዝለቅ የቻለ ሲሆን ለሷም በ1935 ዓ.ም የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ አስገኝቶላታል። ስሙር መሬት በ1937 ዓ.ም በኤም.ጂ.ኤም አማካይነት በፊልም መልክ ተቀናብሮ ለተመልካች ቀርቧል። ከዛ በተከታታይ ሌሎች ድርሰቶችን ለአንባቢ አቅርባለች። በክ በ1938 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን በመቀበል የመጀመሪያዋ (ሴት) አሜሪካዊት ሆናለች። ፐርል በክ በ1973 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ ከ70 በላይ ስራዎቿ ታትመውላታል። መቃብሯም ፔንሲልቬንያ ውስጥ በክስ በተባለው ቀበሌ ይገኛል።
ፐርል በክ የመጀመሪያ ጋብቻዋን የፈጸመችው መቼ ነው?
በ1917
322
ዳምጠው አየለ ዳምጠው አየለ (23.11. 1944 አ/ም – 27.10. 2006 አ/ም) ባህላዊ የኢትዮጵያ ዘፋኝ ነበር። በሃምሌ 23 1944 አ/ም ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአባቱ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ ሰሜን ሸዋ ተወለደ። ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንዳሳለፈ ይናገራል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል። ዳምጠው ህይወቱ እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ጊዜ አብሯት የኖረው ባለቤቱ አልማዝ ይመር ትባላለች። ከአልማዝ ይመር አብዩ ዳምጠውና ቤቴልሄም ዳምጠው የሚባሉ ሁለት ልጆችን አፍርቷል። ዳምጠው መራቤቴ እያለ በየባእላቱ መዝፈን፣ ማቅራራት እንዲሁም መሸለል ይወድ እንደነበር ተናግሯል። በተለይም ጥምቀትን በማድመቅ ይታወቅ ነበር። የ 6ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ክፍሌ ሞገስ የሚባል መምህሩ ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ይናገራል። ባጋጣሚም የምድር ጦር ማስታወቂያ አውጥቶ ስለነበር ይፈተንና ያልፋል። የምድር ጦር ካምፕ ውስጥም እንዲኖር ይደረጋል። የዘፋኝነት ሙያው በዚህ አጋጣሚ ነበር የጀመረው። ዳምጠው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዉና መነሻ የሆነው አበበ ተሰማ እንደሆነ ይናገራል። ዳምጠው አየለ በምድር ጦር ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል። የኢትዮዽያ ምድር ጦር በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም የፈረሰ የሙዚቃ ቡድን ነበር። ዳምጠው በመንግስት ለውጥ ምክንያት እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አብሮ እንደነበር ይናገራል። ምድር ጦርም እያለ ከነታምራት ሞላ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ጥላየ ጨዋቃ፣ ክፍሌ አቦቸር እንዲሁም ሌሎች የጦሩ አባላት ጋር ሰርቷል። ከሌሎች የሙዚቃ ቡድንም ጋር አብሮ ሰርቷል። ለምሳሌ ያክል ከነ ክቡር ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ሙሉቀን መለስ፣ ፀሃየ ዮሃንስ፣ ቴድሮስ ታደሰ፣ቴድሮስ ካሳሁን እንዲሁም ሌሎችም ጋር ሰርቷል። የዳምጠው አየለ የመጀመሪያ የህትመት ስራው በ1963 አ/ም ሲሆን ወፌ ላላ የሚለው የሸክላ ስራ ነበር። ዳምጠው አየለ ባጠቃላይ 13 ሲዲዎችን ሰርቷል። ዳምጠው አየለ ኖርዌይ ሃገር በስደት ለ 8 አመት ያክል ኖሯል። ኢትዮጵያም ከገባ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው በቅ/ገብራኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ 62 አመቱ ሰኔ 27 2006 አ/ም ቀን ህይወቱ አልፏል። የቀብር ስነስርአቱም ወዳጅ፣ ዘመድ እንዲሁም አድናቂዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተፈጽሟል።
ዳምጠው አየለ ወደ አዲስ አበባ ይዞት የመጣው ማነው?
ክፍሌ ሞገስ
480
አልፍሬድ ኢልግ ከሠራቸው አንዱ አዋሽ ወንዝ ላይ ያቆመው ድልድይ ነው። ስለዚህ ድልድይ ሥራ ኢልግ ሲጽፍ፤ የመጀመሪያው የድልድይ ሥራ እንደነበረና የድልድዩ ቋሚዎች በሰው ሸክም አሥራ አምስት ኪሎ ሜትር ተጉዘው እንደመጡ ይተርክና ሥራውን በሐሩር እና በዶፍ እንዲሁም በማታ የዱር አራዊትን በመቋቋም እራሱ ድንጋይ እየጠረበ፣ ምስማር፣ ችንካር እና ብሎን እያቀለጠ እየቀጠቀጠ እንደሠራው ይነግረናል። ምኒልክ በሸዋ ንጉሥ ከሆኑ በኋላ ሐዲድ አዘርግተው ባቡር ለማስገባት አሰቡ። ይህም ሀሳባቸው እንዲፈቀድላቸው የበላያቸውን ንጉሠ ነገሥቱን አጤ ዮሐንስን ፈቃድ ጠየቁ። በአጤ ዮሐንስ አካባቢ የነበሩ መኳንንቶች መክረው ምኒልክ ከግዛታቸው ከሸዋ ውጭ ሐዲድ ለመዘርጋት እንደማይችሉ ተነገራቸው። በሳቸው መቸኮልና መጓጓት ምክንያት አልፍሬድ ኢልግ በሥራና በሀሳብ ተጠምዶ እንደነበር ወዲያውም ለጃንሆይ ምኒልክ የሞዴል ባቡር ተጎታች ጋሪዎችን እየጎተተ በሐዲድ ላይ ሲሄድ የሚያሳይ ሠርቶ ሲያሳያቸው በጣም እንደተደሰቱ ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሐፋቸው ዘግበዋል። ከዓፄ ዮሐንስ ሞት በኋላ ምኒልክ የንጉሠ ነግሥትነትን ዘውድ በጥቅምት ወር ጭነው ወዲያው በኅዳር ወር ላይ የምድር ባቡርን ሥራ አንቀሳቅሰዋል። ለዚህም ኢልግ ከማንኛውም ኩባንያ ጋር ተዋውሎ ሐዲዱን ለማሠራት የሚችልበትን ፈቃድና የሚዋዋልበትን የውል ዓይነት መጋቢት ፩ ቀን ፲፰፻፹፮ ዓ/ም አስጽፈው በማህተማቸው አትመው ሰጡት። ኢልግም ፓሪስ ከተማ ላይ ቢሮ ከፍቶ ለሥራው የሚያስፈልገውን መዋእለ ነዋይ፤ ሥራውን የሚኮናተሩ ድርጅቶችን እና ሌላም ጥናቶችን ማቀናበር ጀመረ። የዚህ የምድር ባቡር መሥመር ከጂቡቲ ወደብ ተነስቶ አዲስ አበባ ድረስ ፯፻፹፬ ኪሎ ሜትር ሲሆን ሥራው በ፲፰፻፺ ዓ/ም ተጀምሮ ከሀያ ዓመታት በኋላ በ ፲፱፱፻፲ ዓ/ም ተገባደደ። መቸም የኃሳቡ ጸንሳሽ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክም ሆኑ ሕልማቸውን ዕውን በማድረግ ብዙ አስተዋጽዖ ያስመዘገበው ኢልግም ፍጻሜውን ባያዩትም በኢትዮጵያ የምድር ባቡርን ስናስብ የነዚህ የሁለቱ ሰዎች ትዝታ በታሪክ ተመዝግቦ ይኖራል።
የምድር ባቡር መስመር ዝርጋት መቸተ ተጠናቀቀ?
በ ፲፱፱፻፲ ዓ/ም
997
በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ስለ ፀሓይ ሳይንሳዊ መግለጫ ለመስጠት ከቻሉ ቀዳሚ ሰዎች አንዱ ግሪካዊው ፈላስፋ አናክሳጎራስ ነበር። ፀሓይ በእሳታዊ ነበልባል የምትንቀለቀል እጅግ ግዙፍ የብረት ኳስ እንጂ የሄሊዮስ ሰረገላ እንዳልነበረች በምክንያት የተደገፈ ትንተና አቀረበ። ይህንን እንደ ኑፋቄ የተቈጠረ ሐተታ በማስተማሩም ታሰረ፤ በሞት እንዲቀጣም ተፈርዶበት ነበር፤ በፔሪክልስ አማላጅነት እንዲፈታ ተፈቀደለት እንጂ። የባለሥልጣናት መዓት የወደቀበት ሌላው የሳይንስ ሊቅ ኒቆላዎስ ቆጰርኒቆስ ነበር። በ16ኛው ምእት ውስጥ የኖረው ቆጰርኒቆስ ምድር ፀሓይን በቀለበትማ ምሕዋር ትዞራለች እንጂ፣ ፀሓይ ምድርን አትዞርም የሚል ኀልዮ አቅርቦ ነበር። በ17ኛው ምእት ጋሊሌዮ በቴሌስኮፕ ለታገዘ የፀሓይ ጥናት ፈር-ቀዳጅ ሊቅ ኾነ። አይዛክ ኒውተን ደግሞ በፕሪዝም አማካይነት የፀሓይ ብርሃን ልዩ ልዩ ቀለማት ካላቸው ብርሃናት የተጠናቀረ እንደኾነ አሳየ። 19ኛው ምእት ዊሊያም ኸርሽል የኢንፍራሬድ ጨረር ግኝት ባለቤት የኾነበት፣ በስፔክትሮስኮፕ ስለ ፀሓይ የሚደረገው ጥናትም እጅግ የመጠቀበት ምእት ኾነ። ዛሬ በብዙ አገሮች ልማድ ፀሓይ እንደ ባህላዊ ምልክት ትታያለች። ለምሳሌ በሜክሲኮ ኪነ ጥበብ አበክራ የምትታይ ሞቲፍ በመባል ትታወቃለች። በኛ ሥርዐተ-ፀሓይ ዋናዋ ትልቅ አካል ራሷ ፀሓይ ናት። በመላው ሥርዐተ-ፀሓይ ውስጥ ከሚገኘው ክብደት 99.86% የፀሓይ ነው። ለምሳሌ ከታላቁ ፈለክ ከጁፒተር ሲነጻጸር የፀሐይ ክብደት 1000 ዕጥፍ ይበልጣል። የፀሓይ ክብደት ከምድር 1.3 ሚሊዮን ጊዜ ይበልጣል። በጣም ግዙፍ እና ከባድ የኾነችው ኮከብ ከምድር ያለችበት ርቀት በጣም የሚያስደንቅ ነው። በምድር እና በፀሓይ መካከል ያለው ርቀት የምድርን ዳያሜትር በ12,000 ጊዜ ይበልጣል። ብርሃን ይህን ርቀት ለመጓዝ 8.5 ደቂቃ ይፈጅበታል።
አይዛክ ኒውተን ፕሪዝም በመጠቀም ምን አሳየ?
የፀሓይ ብርሃን ልዩ ልዩ ቀለማት ካላቸው ብርሃናት የተጠናቀረ እንደኾነ
476
ቀጭኔ ከዝሆን በስተቀር ማንኛውም ሌላ እንስሳ ሊደርስ በማይችልበት ከፍታ ላይ የሚገኙ ረዣዥም ቀንበጠቦችን ለመብላት የሚያስችል አስደናቂ አፈጣጠር አላት። ልዩ የሆነ የመቆንጠጥ ችሎታ ያለው የላይኛው ከንፈሯና እንደተፈገለው የሚተጣጠፍ ችሎታ ያለው ምላሷ ሹል በሆኑ እሾሆች የታጠሩ ቅጠሎችን ለመቀንጠብ ያስችሏታል። ቀጭኔዎች በቀን እስከ 34 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕፅዋት መመገብ ይችላሉ። የተለያዩ ዕፅዋትን የሚበሉ ቢሆኑም ይበልጥ የሚመርጡት በአፍሪካ ሜዳዎች የሚገኙትን እሾሃማ ግራሮች ነው። አንድ ወንድ ቀጭኔ ምግብ ለመፈለግ ምላሱን እስከ 42 ሳንቲ ሜትር መዘርጋት ይችላል። የቀጭኔ አንገት በጣም አስደናቂ የሆነ የመተጣጠፍ ችሎታ አለው። ይህም ላይኛዎቹን የዛፍ ቅርንጫፎች ለመቀንጠብ በምታደርገው እንቅስቃሴ ረዥሙን ራሷን እንደ ልቧ ለማዘንበልና ለማዟዟር ያስችላታል። ለቀጭኔ ወደ ላይ መንጠራራት በጣም ቀላል ነገር ሲሆን ተጎንብሶ ውኃ መጠጣት ግን ይከብዳታል። ወደ ውኃ ጉድጓድ በምትቀርብበት ጊዜ የፊት እግሮቿን ቀስ በቀስ ከፍታ ካራራቀቻቸው በኋላ ወደ ውኃው ለመድረስ እንድትችል ሁለት ጉልበቶቿን አጠፍ ታደርጋለች። ቀጭኔዋ እንዲህ ባለው አመቺ ባልሆነ ሁኔታ እያለች ረዥም አንገቷን እስከ መጨረሻ ትዘረጋለች። ደግነቱ ግን ከምትመገባቸው ቅጠላ ቅጠሎች በቂ እርጥበት ስለምታገኝ ቶሎ ቶሎ መጠጣት አያስፈልጋትም። የቀጭኔ አንገትና ትከሻ የቅጠል ቅርፅ ባላቸውና ቀጫጭን በሆኑ ነጭ መስመሮች ያጌጠ ነው። ቀለማቸው የተለያየ ሲሆን ከወርቃማ ዳለቻ አንስቶ እስከ ቡናማ እንዲያውም ጠቆር እስካለ ቀለም ይደርሳል። የቀጭኔ ዕድሜ እየገፋ በሄደ መጠን ቀለሟም እየጠቆረ ይሄዳል። ቀጭኔዎች ከ2 እስከ 50 የሚደርሱ አባላት ባሉት መንጋዎች ተደራጅተው አንድ ላይ የሚኖሩ ማኅበራዊ ፍጥረታት ናቸው። አንዲት ነፍሰ ጡር ቀጭኔ ልጅዋን ከ420 እስከ 468 ለሚደርሱ እርግዝና ቀናት ከተሸከመች በኋላ ሁለት ሜትር ቁመት ያለው ግልገል ትወልዳለች። ግልገሏ በምትወለድበት ጊዜ ራስዋን ታስቀድምና ከሁለት ሜትር ከፍታ ላይ ወደ መሬት ትወረወራለች። ይሁን እንጂ በ15 ደቂቃ ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባት እየተውተረተረች ትነሳና ጡት ለመጥባት ዝግጁ ትሆናለች። ከሁለት ወይም ከሦስት ሳምንት በኋላ በደመ ነፍስ ተመርታ የግራር ቀንበጦችን መለቃቀም ስለምትጀምር ብዙም ሳትቆይ ረዥም እርምጃ ያላትን እናትዋን ተከትላ ለመሄድ የሚያስችል ጉልበት ታገኛለች። አንዲት የቀጭኔ ግልገል በጣም ውብ መልክ ሲኖራት የወላጆችዋ አነስተኛ ግልባጭ ነች። ቁመቷ ከቀጭኔ ርዝመት ጋር ሲወዳደር አጭር ብትሆንም ከብዙ ሰዎች ቁመት ግን ትበልጣለች። በእናቷ ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበቃ ተማምና አላንዳች መሸበር አካባቢዋን የምትማትረው ግልገል ላያት ሁሉ ልዩ መስህብ አላት። ግልገል ቀጭኔዎች በተወለዱበት ወራት በግልገል መዋያ ተሰባስበው ሙሉውን ቀን ዕረፍት በማድረግ፣ በመጫወትና በአካባቢያቸው የሚሆነውን ነገር በመመልከት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የቀጭኔ ግልገል ለማመን በሚያዳግት ፍጥነት ያድ⁠ጋል። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ሜትር የሚያክል ቁመት ሲጨምር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በእጥፍ ያድጋል። በአንድ ሳምንት ብቻ 23 ሳንቲ ሜትር ያህል ሊያድግ ይችላል! እናትዬው ለልጅዋ ከፍተኛ ጥበቃ የምታደርግ ሲሆን ልጅዋ የተወሰነ ርቀት እንድትዘዋወር ብትፈቅድላትም ሩቅ የማየት ችሎታ ስላላት በዓይኗ ትከታተላታለች። ቀጭኔ ግዙፍ አካል፣ ከፍተኛ ፍጥነት፣ ቅልጥፍናና የማየት ችሎታ ስላላት ከአንበሳ በቀር የሚያጠቃት ጠላት የለም። ቢሆንም ይህችን የምታምር ፍጥረት የሰውን ያህል በብዛት አድኖ የገደለ የለም። ቀጭኔ በሚያምር ቆዳዋ፣ በሚጣፍጥ ሥጋዋና አንዳንዶች ምትሐታዊ ኃይል አለው በሚሉት ረዥምና ጥቁር ጭራዋ ምክንያት እጅግ ተፈላጊ ስለሆነች በአሁኑ ጊዜ የዚህች ሰላማዊ ፍጡር የወደፊት ሕልውና ስጋት ላይ ወድቋል። በአንድ ወቅት በብዙ የአፍሪካ አካባቢዎች እንደ ልብ ትታይ የነበረችው ቀጭኔ በአሁኑ ጊዜ የምትገኘው በቂ ጥበቃ በሚደረግላት ፓርኮች ብቻ ሆኗል። የቀጭኔ አካላዊ ቅርጽና ግዝፈት ችግሮች ማስከተሉ አይቀርም ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል። በጣም ትልቅ ቁመትና ረዥም አንገት ስላላት የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖራትና ወደ ሁሉም የአካሏ ክፍሎች ደም እንዲደርስ ማድረግ የማይቻል ነገር ሊመስል ይችላል። ለምሳሌ ያህል ቀጭኔ አንገቷን ወደ መሬት ስታጎነብስ በስበት ኃይል ምክንያት ብዙ ደም ወደ ጭንቅላቷ ፈስሶ አንጎሏን ማጥለቅለቅ ነበረበት። ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ደሟ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ልቧ ተመልሶ ራሷን እስከ መሳት ሊያደርሳት ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ነገር አይደርስም። ለምን? የቀጭኔ የደም ዝውውር ሥርዓት በዓይነቱ ልዩ ለሆነው ለዚህች እንስሳ ቅርጽና መጠን እንዲያገለግል ሆኖ በታላቅ ጥበብ የተሠራ ነው። ልቧ ራሱ በጣም ትልቅ ሲሆን ደሙን ሦስት ሜትር ተኩል ገደማ ርቆ እስከሚገኘው እስከ አንጎላ ለመግፋት የሚያስችል አቅም አለው። በደቂቃ እስከ 170 ጊዜ የሚመታውና 7 ሳንቲ ሜትር ያህል ውፍረት ባለው ጡንቻ የተገነባው የቀጭኔ ልብ ከሰው የደም ግፊት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ግፊት ያመነጫል። ወደ አንጎል የሚሄደውን ደም የሚሸከመው ካሮቲድ የተባለው የደም ቧንቧና ከአንጎል ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም የሚሸከመው ጀጉላር የተባለው የደም ቧንቧ እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ግፊት መቋቋም የሚያስችል መጠን ሊኖራቸው ይገባል። በእርግጥም እነዚህ የደም ቧንቧዎች ከ2.5 ሳንቲ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸው ከመሆኑም በላይ ጠንካራና የመለጠጥ ችሎታ ባላቸው ሕዋሳት የተገነቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንካሬና የመለመጥ ችሎታ አላቸው። ቀጭኔ ከጭንቅላቷ ጎንበስ በምትልበት ጊዜ ወደ አንጎሏ የሚሄደውን የደም ፍሰት የሚቆጣጠሩ ልዩ መቆጣጠሪያዎች አሏት። አንጎልና አንገት በሚገናኙበት ቦታ ላይ ትልቁ ካሮቲድ የደም ቧንቧ ሬቴ ሚራቢሌ ተብሎ ከሚጠራ አስደናቂ የሆነ መረብ መሰል አካል ይገናኛል። በከፍተኛ ኃይል ተገፍትሮ የመጣው ደም እዚህ ጋር ሲደርስ በጣም በርካታ ወደሆኑ ትናንሽ የደም ሥሮች እንዲገባ ስለሚደረግ የደሙ ግፊት ተስተካክሎ በአንጎል ላይ ጉዳት የማያስከትል ይሆናል። ቀጭኔዋ ራስዋን ጎንበስ በምታደርግበት ጊዜ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው መረብ ይለጠጣል፤ ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ይኮማተራል። ይህም የስበት ኃይል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና የደም ግፊቷ በእጅጉ ቀንሶ ራሷን የምትስትበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳታል። የሳይንስ ሊቃውንት በጣም አስደናቂ ርዝመት ያለው የቀጭኔ አንገት ያሉት አከርካሪዎች ቁጥር ከአይጥ ወይም ከብዙዎቹ አጥቢ እንስሳ ጋር እኩል መሆኑን ሲያውቁ በጣም ተደንቀዋል! ይሁን እንጂ የቀጭኔ አከርካሪዎች በጣም ረዣዥሞችና እርስ በርሳቸው ልዩ በሆነ ሁኔታ የተሰካኩ በመሆናቸው እንደ ልብ ሊተጣጠፉ ይችላሉ። ቀጭኔ አንገቷን መጠምዘዝና ማጠፍ ስለምትችል ሁሉንም የአካሏን ክፍሎች ለመላስም ሆነ ረዣዥም የዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ለመድረስ ትችላለች።
አንዲት ነፍሰ ጡር ቀጭኔ የእርግዝና ጊዜ ምን ያህል ነው?
ከ420 እስከ 468 ለሚደርሱ እርግዝና ቀናት
1,021
የቅኝ ግዛት ጊዜ በ1648 እ.ኤ.ኣ. ፓርቱጋል ሏንዳን እንደገና ተቆጣጠረች። በ1650 እ.ኤ.አ. ደግሞ የተነጠቀችውን መሬት እንዳለ አስመለስች። በ1671 እ.ኤ.አ. ፑንጎ አንዶንጎ የሚባለው ቦታ ወደ ፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ተጨመረ። ፖርቱጋል በ1670 እ.ኤ.አ. ኮንጎን እና በ1681 እ.ኤ.አ. ማታምባን ለመውረር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። በ1885 እ.ኤ.አ. የበርሊን ጉባኤ የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት ድንበርን ከወሰነ በኋላ፣ በብሪታኒያ እና ፖርቱጋል ጥረት በኩል የባቡር-መንገድ፣ እርሻና ማዕድን ተሻሻሉ። እስከ ፳ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በፖርቱጋል አልተመራም ነበር። በ1951 እ.ኤ.አ. ቅኝ ግዛቱ የባህር ማዶ ክፍለ-ሀገር ሆኖ ፖርቱጊዝ ምዕራብ አፍሪካ ተባለ። ፖርቱጋል አካባቢውን ወደ አምስት መቶ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ተቆጣጥራለች። ስለዚህም የአካባቢው ሕዝብ ነጻነት ለመውጣት ያለው ስሜት የተደበላለቀ ነበር። ነፃነትና የእርስ በርስ ጦርነት አንጎላ ነጻነቷን በኅዳር ፲፱፻፷፰ ከተቀዳጀች በኋላ ግን ለብዙ አሥርተ ዓመታት የሚቀጥል የእርስ በርስ ጦርነት ገጠማት። ይህ ውጊያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞትና ስደት አብቅቷል። ከአልቮር ስምምነት በኋላ ሶስቱ ትልቅ የትግል ግንባሮች የሽግግር መንግሥትን ለማቋቋም በጃኑዋሪ 1975 እ.ኤ.አ. ተስማሙ። ነገር ግን በሁለት ወራት ውስጥ እነዚህ ግንባሮች ወደ ውጊያ ተመልሰው አገሯ ወደ ክፍፍል እያመራች ነበር። በዚህ ወቅት የቀዝቃዛው ጦርነት ኃያል አገራት የነበሩት የሶቭየት ሕብረትና አሜሪካ አንዱን ወይም ሌላውን ወገን ደግፈው ወደ ጦርነቱ ገብተዋል። ሌሎችም እንደ ፖርቱጋል፣ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪካና ኩባ የመሳሰሉት ሀገራትም ከማገዝ ወደ ኋላ አላሉም። ፖለቲካ የአንጎላ የሕግ አስፈፃሚ አካል ፕሬዝዳንቱን፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱንና የሚኒስትሮች ምክር ቤቱን ያጠቃልላል። ለብዙ ዓመታት አብዛኛው ሥልጣን በፕሬዝዳንቱ እጅ ነው ያተኮረው። የ፲፰ቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። የ1992 እ.ኤ.አ. ሕገ መንግሥት የመንግሥቱን አወቃቀርና የዜጎችን መብቶችና ግዴታዎች ይዘረዝራል። የሀገሩ ሕግ ተርጓሚ አካል የፖርቱጋል ሥርዓትን ይከተላል። ጦር ኃይል የአንጎላ ጦር ኃይሎች በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ሲሆኑ በሦስት ይከፈላሉ። እነዚህም ምድር ኃይል፣ ባህር ኃይል እና አየር ኃይል ናቸው። የሀገሩ ጠቅላላ ሠራዊት ፻፲ ሺህ ይሆናል። የጦር ኃይሉ ንብረቶች መካከል በሩሲያ የተሰሩ ተዋጊ፣ ቦምብ ጣይና አጓጓዥ አውሮፕላኖች ይገኛሉ። አንዳንድ የጦር ኃይሉ ክፍሎች በኮንጎ ኪንሻሳና ኮንጎ ብራዛቪል ተመድበዋል።
የአንጎላ ሦስቱ የትግል ቡድኖች ከምን ስምምነት በኋላ ነበር ወደ ሽግግር መንግስት ምስረታ የገቡት?
ከአልቮር ስምምነት
670
ዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።
ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ የተባለችው መቼ ነበር?
በ1962 ዓ.ም.
1,526
የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፲፱ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የነበረ ሲሆን ከሰኔ ፬ እስከ ሐምሌ ፬ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ተካሄዷል። ውድድሩን ለማቅረብ የተካሄደው ዕጣ ውስጥ የአፍሪካ ሀገሮች ብቻ እንዲሳተፉ ነበር የተፈቀደው። ደቡብ አፍሪካ ግብፅና ሞሮኮን በማሸነፍ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫን ያቀረበች አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ፊፋ ለውድድሩ ያቀረበው ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ $420 ሚሊዮን ነው። ይህም ከ2006 እ.ኤ.አ. ውድድር ሽልማት ገንዘብ የስልሳ ከመቶ ዕድገት አለው። ከዚህ ውስጥ $40 ሚሊዮን የሚሆነው ተጫዋቾቹ ለሚጫወቱበት ክለቦች ተጫዋቾቹ ለሚደርስባቸው ጉዳት መካካሻ እንዲሆን ተሰጥቷል። ከውድድሩ በፊት እያንዳንዱ ቡድን ለዝግጅት ወጪው $1 ሚሊዮን ተረከበ። ግጥሚያዎቹ በዘጠኝ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አስር ስታዲየሞች ውስጥ ነው የተካሄዱት። የዋንጫ ጨዋታው በጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኘው ሶከር ሲቲ ስታዲየም ነው የተከናወነው። የምድብ ድልድል ሥነ ስርዓቱ በኬፕ ታውን፣ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው ኬፕ ታውን ዓለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል በኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. ተከናወነ። ሥነ ስርዓቱ የቀረበው በደቡብ አፍሪካዊቷ ተዋናይ ሻርሊዝ ቴሮን እና የፊፋ ዋና ጸሐፊ ዠሮም ቫልክ ነው። የዕጣ ኳሶቹን ያወጡት ዴቪድ ቤክሃም፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ጆን ስሚት፣ መካያ ንቲኒ፣ ማቲው ቡዝ እና ሲምፊዌ ድሉድሉ ናቸው። የፊፋ ዳኛዎች ኮሚቴ ፳፱ ዳኛዎችን ለዓለም ዋንጫ መርጧል። እነዚህም ከኤ.ኤፍ.ሲ. አራት፣ ከካፍ አስር፣ ከኮንሜቦል ስድስት፣ ከኮንካካፍ አራት፣ ከኦ.ኤፍ.ሲ. ሁለት እና ከዩኤፋ አስር ዳኛዎችን ያጠቃልላል። እንግሊዛዊው ዳኛ ሀዋርድ ዌብ የዋንጫ ጨዋታውን እንዲዳኝ ተመርጧል።
ደቡብ አፍሪካ የትኞቹን የአፍሪካ ሀገሮች በመብለጥ ነው የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ የአለም ዋንጫ አዘጋጅ ለመሆን የበቃችው?
ግብፅና ሞሮኮን
190
ጉጃራቲ ጉጃራቲ (ગુજરાતી) በህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ የሚገኝ ቋንቋ ነው። በዓለሙ ውስጥ በ46 ሚልዮን ሰዎች ይናገራል፤ ከነዚህም 45.5 ሚልዮን በህንደኬ፣ 250,000 በታንዛኒያ፣ 150,000 በዩጋንዳ፣ 100,000 በፓኪስታንና 50,000 በኬንያ አሉ። በሕዝብ ብዛት የዓለሙ 23ኛ ቋንቋ ነው። በምእራብ ህንደኬ ያለው የጉጃራት ክፍላገር ይፋዊ ቋንቋ ነው። የጉጃር ሕዝብ ወደ ህንደኬ የደረሱ በ5ኛው መቶ ዘመን ሲሆን በ6ኛው መቶ ዘመን ዛሬ ጉጃራት በሚባለው አገር ሰፈሩ። የራሳቸውን ቋንቋ ቶሎ ትተው እንደ አገሩ ሰዎች ሳንስክሪት ለመናገር ጀመሩ። በ12ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሳንስክሪት ተለውጦ ብዙ አዲስ ቋንቋዎች ተወለዱ። ከነዚሁም አንድ ጉጃራቲ ነበር። አብዛኛው ተናጋሪዎቹ የህንድ ሃይማኖት ተከታዮች ቢሆኑም ለረጅም ዘመን የእስላም ገዢዎች ስለነበሩባቸው ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከፋርስ ሆኗል። ከዚያ በላይ በንግድ ምክንያት ብዙ ቃሎች ከፖርቱጊዝ ወይም ከእንግሊዝኛ ተበደሩ። የሚጻፍበት በራሱ ጉጃራቲ ፊደል ነው፤ ይህም ከላይኛ መስመር በማጣቱ በስተቀር የህንዲ ደቫናጋሪ ፊደል ይመስላል።
ጉጃራቲ ቋንቋ በፓኪስታን ምን ያህል ተናጋሪዎች አሉት?
100,000
139
ባሕር-ዳር ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች። ባሕር-ዳር ከአዲስ አበባ 565 ኪ.ሜ ወደ ሰሜን-ሰሜን ምዕራብ ትገኛለች። ባህር ዳር ከጢስ አባይ በ30 ኪሎሜትር ስለምትርቅ ለጎብኚዎች አመቺ ቦታ ላይ ናት። ባህር ዳር የአንድ የአስፋልት ንጣፍ ያለው ኤርፖርት የሰፊ ገበያና የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች እና ታሪካዊ እና ጥንታዊ ግዳማት መግኛ ቦታ ናት። ባሕርዳር ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ "ከባሕሩ-ዳር" አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደሩ ባሕር-ዳር ብለው ስያሜ አወጡለት ይባላል። ባሕር-ዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡ ባሕር-ዳር በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤ የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች አሏት፡፡ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡ የተቆረቆረችበትን ዓመት፣ የቆረቆሩትን ቀደምት ሠዎች፣ የሠፈሮችን ስሞች፣ ለባሕር-ዳር የተገጠሙትና የተዘፈኑ ታሪካዊ ግጥሞችና ስነ ቃሎች፣ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጎጆ ቤት ወደ አሁኑ ይዞታው አመጣጥ (ባሕር-ዳርን ስናስብ ጊዮርጊስን ሚካኤልን እና ገበያውን ከገበያው አካባቢ የነበረውን ፍርድ ቤት ነጣጥሎ ማየት አይቻልም የሚል አስተያየት ስላለ ነው)፣ ባሕር-ዳር እንደባሕር ዳርነቱ ከመቆርቆሩ በፊት በሚካኤል እና በሽመምብጥ ሠፈር አካባቢ ስለነበረው አሰፋፈር፣ ስለማዘጋጃቤቱ፣ ስለ አውቶቡስ ተራው፣ ስለ ድባነቄ ተራራ፣ እና ስለ መሳሉት፣ ስለፖሊቴክኒክ፣ ስለዓባይ ወንዝና ድልድዩ፣ ስለዓባይ ወንዝና ስለጣና ሐይቅ መገናኛ እና ስለሌሎችም ቁልፍ ነገሮችን ማቅረብ የሚችሉ አፈታሪኮች አሉ።
ባሕር ዳር ስንት የከተማ ቀበሌዎቸ አሏት?
9
942
የፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ምርምሮች በቫይረስ ጥቃት በእንስሳትና በሰው ላይ ለሚከሰቱ በሽታዎች በዘረመል ምህንድስና ጥበብ ክትባት ወይም መከላከያ መድሃኒት ግኝቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው። በዚህም የበርካታ በሽታዎች ክትባትና መድሃኒት ግኝቶች ባለቤት ሲሆኑ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር ያደረጋቸው ደስታ በተሰኘውና ከ100 ዓመት በፊት በአውሮጳና በአፍሪካ ከፍተኛ ዕልቂት ላደረሰው የከብቶች መቅሰፍት በሽታ ክትባት መፈልሰፋቸው ነው። ይህን ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በርካታ የምርምር ተቋማት ደክመው ያላሳኩትን የደስታ በሽታ ክትባት ማግኘታቸው በህክምና ግኝቶች መስፈርት አንቱ አስብሏቸዋል፤ ዓለምንም በደስታ በሽታ ከሚደርሰው እልቂት ታድገዋል። በእንግሊዝና በጣሊያን ወታደሮች ሴራ ወደ ኢትዮጵያ በገቡ ከብቶች በተዛመተው የደስታ በሽታ እ.አ.አ ከ1888-1892 ለአራት ዓመታት በኢትዮጵያ በደረሰው እልቂት ከፍተኛ ረሀብ መከሰቱን ያስታወሱት ፕሮፌሰር ጥላሁን የምርምራቸው መነሻ ከወላጆቻቸው ስለ ከብት መቅሰፍት ሲሰሙ ማደጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። በሰውና በእንስሳት ህክምና ዕውቀት በሁለቱም ሰይፍ የተካኑት አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ ለኤች አይ ቪ/ኤዲስ ቫይረስ ክትባት ለማግኘትም ደክመዋል። ከ124 በላይ የሚሆኑ የምርምር ግኝቶች በስመ ጥር ዓለም አቀፍ የምርምር መጽሔቶች የታተሙላቸው ሲሆን በአሜሪካና በቻይና በሚገኙ በርካታ ተቋማትም የአካዳሚ አባልነት ተመርጠዋል፤ በአማካሪነትም እየሰሩ ይገኛል። በተማሩበት ብሎም ባስተማሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ጨምሮ በአሜሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ዕውቅናና ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን ለአብነትም የዩኒቨርሲቲዎች የምርጥ አስተማሪነትና ተመራማሪነት ሽልማት፣ የእንስሳት ህክምና ዘርፍ ከፍተኛውን ዓለም አቀፍ ሽልማት፣ የልዩ አገልግሎት ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል። እርሳቸው ባቋቋሙትና በዳይሬክተርነት በሚመሩት የዓለም አቀፉ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የምርምር ማዕከል ከተለያዩ ታዳጊ አገራት በርካታ ሳይንቲስቶችንም አፍርተዋል። በትምህርትና ምርምር ዘመናቸው የነጮችን የዘረኝነት ጫና በመቋቋም ከስኬት ማማ ላይ የደረሱት ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ አሁን ላይ በማደግ ላይ በሚገኙ አገራት ወጣት ሳይንቲስቶችን በማስተማርና በማበረታት ላይ ትኩረት አድርገው በመስራት ላይ ይገኛሉ።
የፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ የክትባት ግኝት በዓለም ላይ ያሉ ከብቶችን በምን በሽታ እንዳይጠቁ ማድረግ ችሏል?
በደስታ በሽታ
383
ፍራንክሊን ሮዘቨልት ፍራንክሊን ዴላኖ ሮዘቨልት (1874-1937 ዓ.ም.) የኒው ዮርክ አገረ ገዥና የአሜሪካ 32ኛ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ሮዘቨልት በቀድሞ ፕሬዚዳንት ዉድሮው ዊልሶን ዘመን የባሕር ኅይል ምክትል ሚኒስትር ነበሩ። በ1913 ምርጫ የምክትል ፕሬዚዳንት ዕጩ ሆኑ። ጄምስ ኮክስም የፕሬዚዳንት ዕጩ ነበሩ። ነገር ግን ኮክስና ሮዘቨልት በዋረን ሃርዲንግና በካልቪን ኩሊጅ ተሸነፉ። ሮዘቨልት በ1920 ዓ.ም. የኒው ዮርክ አገረ ገዥ ሆኑ። በታላቁ ጭፍግግ ሳቢያ ፕሬዚዳንት ሄርበርት ሁቨር በጣም ስላልተወደደ በ1925 ምርጫ ሮዘቨልት ሁቨርን አሸነፏቸው። ሮዘቨልት በጣም ስለተወደደ በ1929 ዓ.ም. ምርጫ ለሁለተኛ የ4 አመት ዘመን ተመለሱ። እንዲሁም በ1933 ምርጫ ለሦስተኛ ዘመንና በ1937 ምርጫ ለአራተኛ ዘመን ተመረጡ። በጠቅላላ 4 ዘመኖች ተቀበሉ። በ2ኛ አለማዊ ጦርነትም የአሜሪካ መሪ ነበሩ። ነገር ግን ፖሊዮ ከሚባል በሽታ የተነሣ አካለ ስንኩል ሆነው ባለ መንኮራኩር ወምበር ነበራቸውና በአራተኛው ዘመን መሃል ሞቱ። ምክትላቸው ሃሪ ትሩማን ወዲያው ፕሬዚዳንት ሆኑ። ፍራንክሊን ሮዘቨልት አራት ጊዜ በመመረጣቸው ከሁሉ ይልቅ ለረጅም ዘመን ገዙ። ከሳቸው በኋላ የመንግሥት አንደኛ ዘርፍ የሆነ የሕግ አማካሪ ቤት ወደፊት ሌላ ፕሬዚዳንት እንደሱ 3 ወይም 4 ዘመናት እንዳይቀብል አንፈልግም የሚል ድምጽ አሰሙ። ስለዚህ በ1943 ዓ.ም. የአሜሪካ መንግሥት 2ኛ ዘርፍ የሆኑት ፕሬዚዳንቶች ከ2 ጊዜ (እነሱም 8 አመታት) በላይ ሊያገለግሉ አይችሉም የሚለው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት 22ኛ ማሻሻያ አንቀጽ ሕጋዊ ደንብ ሆነ።
ፍራንክሊን ዴላኖ ሮዘቨልት የኒው ዮርክ አገረ ገዥ የሆኑት መቼ ነው?
በ1920 ዓ.ም.
249
ግንቦት ፳፮ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፷፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፷፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፺፱ ቀናት ይቀራሉ። ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የኤር ፍራንስ ቦይንግ ፯፻፯ አየር ዠበብ ከፓሪስ ኦርሊ ማረፊያ ተነስቶ ወደ አትላንታ ለመብረር ሲነሳ በደረሰበት አደጋ ፻፴ መንገደኞችና የዓየር መንገዱ ባልደረቦች ሞተዋል። ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የአሜሪካው ‘ኖርዝ ዌስት ኤየርላይንስ’ ዲ-ሲ-፯ አየር ዠበብ በረራ በሰላማዊ ውቅያኖስ ላይ ውድቆ ሲሰምጥ ፻፩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኮንኮርድ አየር ዠበብ አምሳል የተሠራው የሶቪዬት ቱፖሌቭ ቲ-ዩ-፻፵፬ ፈረንሳይ ላይ በደረሰበት የበረራ አደጋ ሲከሰከስ ፲፬ ሰዎች ሞተዋል። ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ አካላት የነበሩት ሰርቢያ እና ሞንቴኔግሮ የውሕደት ስምምነታቸውን በሞንቴኔግሮ የሉዐላዊነት አዋጅ ምክንያት ሰረዙ። ፲፯፻፷፭ ዓ/ም - የዓፄ በካፋ ሚስት የነበሩት እቴጌ ምንትዋብ በዚህ ዕለት አርፈው በቁስቋም ደብረ ጸሐይ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
የዓፄ በካፋ ሚስት የነበሩት እቴጌ ምንትዋብ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በስንት ዓመተ ምህረት ነው?
፲፯፻፷፭ ዓ/ም
594
አኩሪ አተር አኩሪ አተር የአባዝርት አትክልት ዝርያ ነው። በየጊዜው አኩሪ አተርን መመገብ ለሴቶች ጉዳት ባያደርግም፣ ለወንዶች ጤናማ እንደማይሆን በሰፊ ቢታወቅም በአንዳንድ አገር ባሕል አመጋገብ በብዛት ይጨመራል። ከ20ኛዉ ክፍለ ዘመን አንስቶ በተለይ አሜሪካን ዉስጥ ወርቃማዉ ወይም ተዓምረኛዉ እህል የሚል ስያሜ አግኝቷል። አኩሪ አተር በፕሮቲን እና ቅባት ምንጭነቱ የሚወዳደረዉ የእህል ዘር የለም። ባለሙያ ካገኘም ለመጠጣትም ለመበላትም የሚችል የእህል ዘር ነዉ። ስለአኩሪ አተር ሲወሳ ብዙዎች የሚያስታዉሱት ለሕፃናት አካል ግንባታ ጠቃሚ መሆኑ ብዙ ጊዜ የተነገረለትን የአኩሪ አተር ወተት ሊሆን ይችላል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በኢትዮጵያዉያን የምግብ ጣዕም ለዛ ተላብሶ በተለያየ ምግብነት መቅረብ እንደሚችል እየታየ ነዉ። አኩሪ አተር ወደኢትዮጵያ የገባዉ በ1950ዎቹ መሆኑን ነዉ በእህሉ ላይ ምርምር የሚያደርጉት ባለሙያዎች የሚያስረዱት። በአኩሪ አተር ላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተደረገዉ ዝርያ የማዉጣት ምርምርም 22 ዓይነት ዘሮች እስካሁን ተገኝተዋል። አኩሪ አተርን በሀገር ዉስጥ በ12 የምርምር ማዕከላት ላይ ከፍተኛ የዝናብ መጠን በሚያገኙ፤ መካከለኛ የዝናብ መጠን በሚያገኙ እና ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ምርምሩ ይካሄዳል። አኩሪ አተር ሀገር ዉስጥ በከፍተኛ ደረጃ የሚመረተዉ በቤንሻንጉል ጉምዝ እና በኦሮሚያ ክልል ነዉ። አኩሪ አተርን በብዛት ከሚያመርቱ ሃገራት ዩናትድ ስቴትስ፤ ብራዚል እና አርጀንቲና ቀዳሚዎቹ ናቸዉ። ከአኩሪ አተር ወተት ለማዘጋጀት ሲታሰብ እህሉን ከአንድ ቀን በፊት ለቅሞና አጥቦ ለ15 ደቂቃ ያህል መቀቀል ያስፈልጋል። ከዚያም አዉጥቶ ተዘፍዝፎ ያድራል። ከዚያም የራሰዉን አኩሪ አተር ልጣጩን በሚገባ በዉኃ አስለቅቆ በትንሽ በትንሹ እየቆነጠሩ ፈጭቶ እንደእህሉ መጠን ዉኃ ጨምሮ መቀቀልና መጭመቅ ነዉ። እንደባለሙያዉ ከሆነም ለአንድ ኪሎ አኩሪ አተር ስምንት ሊትር ዉኃ ያስፈልጋል። ተፈጥሮን ተከትሎ የማይበቅል እህልም ሆነ በተፈጥሮ ሥርዓት ያላደጉ እንስሳትን መመገብ ለጤና አደገኛ መሆኑን በተግባር የተረዳዉ ምዕራቡ ዓለም በአሁኑ ጊዜ ፊቱን ከእንስሳት ተዋፅኦ ወደተክሎችና ሰብሎች አዙሯል። በዚህ ምክንያትም ከአኩሪ አተር የሚገኙ የምግብ ተዋፅኦዎች ተመራጭነትን እያገኙ ነዉ። ከአኩሪ አተር ወተት እና አይቡ እንደሚገኝ ሁሉ የአኩሪ አተር ሥጋም አለዉ።
አኩሪ አተር በኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት የት ይመረታል?
በቤንሻንጉል ጉምዝ እና በኦሮሚያ ክልል
751
ዓረብኛ ዓረብኛ የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ሆኖ የዕብራይስጥ የአረማያ እንዲሁም የአማርኛ ቅርብ ዘመድ ነው። ፪፻፶ (250) ሚሊዮን የሚያሕሉ ሰዎች እንደ እናት ቋንቋ ይናገሩታል። ከዚህም በላይ በጣም ብዙ ሰዎች እንደ ፪ኛ ቋንቋ ተምረውታል። የሚጻፈው በዓረብኛ ፊደል ነው። በዓረብ አለም ውስጥ አያሌ ቀበሌኞች ይገኛሉ። ቋንቋው በእስልምና ታላቅ ሚና አጫውቷል። እስላሞች አላህ ለሙሐማድ ቁርዓንን ሲገልጽ በዓረብኛ እንደ ሆነ ስለሚያምኑ እንደ ቅዱስ ቋንቋ ይቆጥሩታል። አብዛኛው ዓረብኛ ተናጋሪዎች ሙስሊሞች ናቸው። ዛሬ በምዕራብ ዓለም ደግሞ ብዙ ሰዎች አረብኛ እያጠኑ ነው። በታሪክ ከፍተኛ ሚና በማጫወቱ መጠን ፤ ብዙ የዓረብኛ ቃላት ወደ ሌሎች ቋንቋዎች ገብተዋል።
ለዓረብኛ ቋንቋ የቅርብ ዘመድ ተብለው ከሚጠቀሱት ቋንቋዎች መካከል መን ይገኛል?
የአማርኛ
53
ዓረብኛ ዓረብኛ የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ሆኖ የዕብራይስጥ የአረማያ እንዲሁም የአማርኛ ቅርብ ዘመድ ነው። ፪፻፶ (250) ሚሊዮን የሚያሕሉ ሰዎች እንደ እናት ቋንቋ ይናገሩታል። ከዚህም በላይ በጣም ብዙ ሰዎች እንደ ፪ኛ ቋንቋ ተምረውታል። የሚጻፈው በዓረብኛ ፊደል ነው። በዓረብ አለም ውስጥ አያሌ ቀበሌኞች ይገኛሉ። ቋንቋው በእስልምና ታላቅ ሚና አጫውቷል። እስላሞች አላህ ለሙሐማድ ቁርዓንን ሲገልጽ በዓረብኛ እንደ ሆነ ስለሚያምኑ እንደ ቅዱስ ቋንቋ ይቆጥሩታል። አብዛኛው ዓረብኛ ተናጋሪዎች ሙስሊሞች ናቸው። ዛሬ በምዕራብ ዓለም ደግሞ ብዙ ሰዎች አረብኛ እያጠኑ ነው። በታሪክ ከፍተኛ ሚና በማጫወቱ መጠን ፤ ብዙ የዓረብኛ ቃላት ወደ ሌሎች ቋንቋዎች ገብተዋል።
እስላሞች በብዛት የሚናገሩት የዓረብኛን ለምን እንደ ቅዱስ ቋንቋ ይቆጥሩታል?
አላህ ለሙሐማድ ቁርዓንን ሲገልጽ በዓረብኛ እንደ ሆነ ስለሚያምኑ
236
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት ኡጋንዳ ገብተዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በፕሬዝዳንት ዮዌሪ ካጉታ ሙሴቪኒ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ኡጋንዳ መግባታቸውን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለከተው፡፡ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ባለፈው ጥር ወር ላይ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ለ6ኛ ዙር ሀገሪቱን ለመምራት ዛሬ ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ።
የኡጋንዳ ፕሬዝደንት ማን ናቸው?
ዮዌሪ ካጉታ ሙሴቪኒ
68
አሪዞና አሪዞና (Arizona) በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ክፍላገር ነው። ኒው ሜክሲኮ ፣ ዩታህ ፣ ኔቫዳ ፣ ካሊፎርኒያ እና ኮሎራዶ ያዋስኑታል። የአሪዞና ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ የ30 ሰው ሴኔት እና የ60 ሰው ምክር-ቤት አለው። የሪፑብሊካን ፓርቲ በስቴቱ ዋነኛው ፓርቲ ነው። በ2002 እ.ኤ.አ. የአሪዞና ስቴት ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ በጀት 14.3 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በጀት ደግሞ 13.8 ቢሊዮን ዶላር ነው። የስቴቱ ሴኔተሮች እና ምክር-ቤት ተወካዮች ለሁለት-ዓመት ጊዜ ላልተወሰነ ብዛት ይመረጣሉ። ከ4 ጊዜ በላይ በተካካይ መመረጥ ግን አይችሉም። የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በአስተዳዳሪ የሚመራ ሲሆን ለ4 ዓመት ሥልጣን ላይ ይቆያል። ያልተወሰነ ጊዜ መወዳደር ሲቻል ከሁለት ጊዜ በላይ ግን በተካካይ መመረጥ አይፈቀድም።
በአሪዞና ሕግ አውጪ አካል 30ዎቹ አባላት ምንድን ናቸው?
ሴኔት
124
ጎግል የተወሰኑ ደንበኞችን የግል ተንቀሳቃሽ ምስል  በስህተት ለሌሎች በማጋራቱ ይቅርታ ጠይቋል። ችግሩ ደንበኞች የግል ገፃቸውን ለመለየት የሚስችለውን ምስል  ለመጫን በሚያስችለው ክፍል ላይ የተፈጠረ መሆኑ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል። ስህተቱ ለአራት ቀናት ማለትም ካሳለፍነው ጥቅምት 21 እስከ 25 ቀን  2019 ድርስ የቆየ መሆኑ ነው የተገለጸው። በዚህ ወቅትም በችግሩ የተጠቁ ደንበኞች የራሳቸው ያልሆነ አሊያም ተገቢውን ጥራት ያላሟላ ተንቀሳቃሽ ምስል የደረሳቸው መሆኑ ተጠቁሟል። ይሁን እንጂ ኩባንያው ችግሩ በምን ያህል ደንበኞቹ ላይ ተከስቶ እንደነበር ከመግለፅ ተቆጥቧልል። አሁን ላይ ችግሩ መስተካከሉን የገለጹት የኩባንያው ቃል አቀባይ፥ለተፈጠረው ስህተት ደንበኞችን ይቅታ ጠይቀዋል። በቀጣይ መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ ጥልቅ  ምርመራዎችን በማካሄድ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅ የሚደረግ መሆኑ ተጠቁሟል። ምንጭ፡-ቢቢሲ  
ከጥቅምት 21 እስከ 25 ቀን 2019 ባሉ ቀናት የደንበኞችን የግል ተንቀሳቃሽ ምስል በስህተት ለሌሎች ያጋራው ድርጅት ማን ነው?
ጎግል
1
ቲቪ በ1950ዎቹ እንደ ብርቅ በሚታይበት ዘመን በ1957 አ.ም ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተከፈተ፡፡ ታዲያ የመጀመሪያዋ የቲቪ ሴት አንባቢ የነበሩት ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ወልደስላሴ ነበሩ፡፡ ይህ ለወይዘሮ እሌኒ ትልቅ የታሪክ አጋጣሚ ነበር፡፡ በወቅቱ ሳሙኤል ፈረንጅ አንዱ ወንድ ተናጋሪ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ሬድዮ በጋዜጠኝነቱና በህዝብ ግንኙነት ሙያ ያገለገሉት ወይዘሮ እሌኒ ከሰው ጋር በቀላሉ የሚግባቡ ተወዳጅ ደግ እናት ነበሩ፡፡ በበጎ አድራጎት ምግባራቸው በስፋት የሚታወቁት ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ወልደስላሴ የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር ውስጥ በንቃት በመሳተፍ ማህበሩን ረድተዋል፡፡ በተጨማሪም በአንሚ ሬድዮ ከ20 አመት በፊት ያገለገሉት ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ወልደስላሴ ከአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋር የጠበቀ ቁርኝት ነበራቸው፡፡ ከዚህም ባሻገር አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ወደ ሀገራችን በሚመጡበት ጊዜ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ስራ ላይ ትልቅ ሚና አበርክተዋል፡፡ ቤታቸው ሲኬድ ሁልጊዜም ከአረንጓዴ ተክል ጋር የማይታጡት ወይዘሮ እሌኒ ነፋሻማ ቦታ ልዩ ትርጉም ይሰጣቸዋል፡፡ አንድ ከዛፍ ጋር በተያያዘ በፎቶግራፍ የታገዘ መጽሀፍም ለህትመት አብቅተዋል፡፡ በዚህም መጽሀፍ አማካይነት ስለ ሀገራችን ዛፎች በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሙከራ አድርገዋል፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ የተለያዩ ሀገሮችን ቴምብሮችን ያሰባስባሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ለታሪክ ልዩ ፍቅር ያላቸው ወይዘሮ እሌኒ የጡረታ ጊዜያቸውን በማንበብ እና በምርምር ያሳልፉ ነበር፡፡ ወይዘሮ እሌኒ በ1959 አመተ ምህረት ከኢንጂነር ሰይፉ ለማ ጋር ጋብቻን መስርተው 3 ሴት ልጆችን ወልደው አንድ ልጅ ደግሞ አሳድገዋል፡፡ ወይዘሮ እሌኒ በተወለዱ በ79 አመታቸው ሮብ ሀምሌ 14 2013 ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን የቀብር ስነስርአታቸውም ሀሙስ ሀምሌ 15 2013 ከቀኑ በ6 ሰአት በየካ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡
ወ/ሮ እሌኒ ከትዳር አጋራቸው ጋር መቼ ትዳር መሰረቱ?
በ1959
872
አቡነ ቴዎፍሎስ አቡነ ቴዌፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ ጎጃም በሚገኝው በዝነኛው ደብረ ኤሊያስ አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ወልደ ማርያም ውቤ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ዘርትሁን አደላሁ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፲፱፻፪ ዓ/ም ተወለዱ። ሲወለዱም የተሰጣቸው ስም መልእክቱ ወልደ ማርያም ነበር። በልጅነታቸው ንባብ እና ዜማን በመምህር መሪ ጌታ ረዳኸኝ እና ግራ ጌታ ሣህሉ እዚያው የተወለዱበት አካባቢ ተምረዋል። ኋላ የቅኔ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ዝንባሌ ስላደረባቸው እዚያው ደብረ ኤሊያስ ደብር መምህር ገብረ ሥላሴ በሚባሉ ሊቅ ሥር መማር ጀመሩ። በ፲፱፻፻፳ ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ መጥተው ፍትሐ ነገሥትና አዲስ ኪዳንን በመምህር ተክሌ (ነቡረ ዕድ በኋላ ቢትወደድ አቡነ ዮሐንስ) በመባል የሚታወቁት መሪነት ሲከታተሉ ቆይተዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ የኃይማኖት ችግሮችን ለማወቅ ይፈልጉ እንደነበርና ሰፋ ያለ ዕውቀት እንደነበራቸው ይነገራል። በተጨማሪ የኃይማኖት ችግሮችን የሚመለከቱ መጻሕፍትን ሳይታክቱና ሳይሰለቹ ያነቡም ነበር። መልእክቱ ወልደ ማርያም በ፲፱፻፴ ዓ/ም ይህን ዓለም በቃኝ ብለው ደብረ ሊባኖስ ገዳም መንኩሰው ገቡ። ከጠላት ወረራ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀሳውስቱ በዘመናዊ የኃይማኖት ትምህርት እንዲሠለጥኑ በነበራቸው ሀሳብ መሠረት ፳ የሚሆኑ ሊቃውንት መርጠው በቤተ መንግሥቱ አካባቢ እንዲሰለጥኑ አድርገዋል። ከነኚህም አንዱ አባ መልእክቱ ወልደ ማርያም ናቸው። ቀደም ብሎ በኢትዮጵያና በግብጽ በተደረገው ስምምነት መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ጳጳሶች ሲሾሙ ሊቀ ሥልጣናት መልእክቱ ወልደ ማርያም ለሹመት ከተመረጡት አምስት አባቶች አንዱ ሲሆኑ ወደግብጽ ተጉዘው በእስክንድርያው ፓትርያርክ ዳግማዊ አቡነ ዮሳብ እጅ በካይሮ በትረ ካና ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን እሑድ ሐምሌ ፲፰ ቀን ፲፱፻፵ ዓ/ም ሊቀ ሥልጣናት መልእክቱ “ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ” ተብለው የሐረርጌ ጳጳስ ሆኑ።
አቡነ ቴዎፍሎስ የሐረርጌ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት በማን ነው?
በእስክንድርያው ፓትርያርክ ዳግማዊ አቡነ ዮሳብ
985
ሶቪዬት ሕብረት ሶቭየት ሕብረት ሰብአዊ ሪፐብሊክ በ፲፱፻፲ ዓ.ም. የተከሰተውን የሩሲያ አብዮት ፍንዳታ፤ እንዲሁም ያንን ተከትሎ ለሦስት ዓመታት የተከናወነውን የሩሲያ «ውስጣዊ ሕዝባዊ የርስ በርስ ግጭት» ተከትሎ በኅብረተስብአዊ ሕገ መንግሥት (socialist constitution) በአራት ሪፑብሊኮች ቅንብርነት የተመሠረተ አገር ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ከቀድሞው የናዚ ጀርመን እጅ የተወሰዱ አገሮችን በማቀላቀል እንዲሁም በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም በጉልበት ሌሎች የምሥራቅ አውሮፓ አገሮችን በመቀላቀል ኅብረቱ ዓሥራ ስድስት ሪፑብሊኮችን ያካተተ ነበር። በዘመን ቆይታና በጥንካሬም የጎለበተ ሕዝባዊ አብዮታዊ የኅብረት ሪፑብሊክ በመሆኑም በተለይ በ«ቀዝቃዛ ጦርነት» በሚባለው በ«ምዕራብና በምሥራቅ» ዓለም ተከስቶ በነበረው ፍጥጫ ጊዜ፣ በዓለም ላይ ለሚመሠረቱ ሕዝባዊ መንግሥታት ዋና የሽከታ አርአያ የነበረ መንግሥት ነበር። በ ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጀምሮ ይሄ ኅብረት እስከፈረሰበት እስከ ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የ«ቀዝቃዛ ጦርነት» ዘመን የሶቪየት ኅብረት በዓለም ከነበሩት ሁለቱ ተቃራኒ ኃያላን መንግሥታት አንዱ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ላይ በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም የተመሠረተውን የአብዮት ወታደራዊ የደርግ መንግሥት በጦር መሣሪያ፤ በአማካሪነት፤ በገንዘብ፤ ወዘተረፈ፤ ዋነኛ ደጋፊና ታላቅ ተዋናይ አገር ነበር። የቀድሞው የሶቪዬት ኅብረት መጨረሻ ላይ ታኅሣሥ ፲፮ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ተደምስሶ በዓለም መንግሥታት እውቀትና ስምምነት ሕጋዊ ወራሽነት የሩሲያ መንግሥት እንደሆነ ታወጀ። ሩሲያም በዚህ መሠረት የቀድሞውን የሶቪዬት ሕብረት የውጭ ዕዳዎች እንዲሁም የውጭ ንብረቶች በፈቃዱ ተቀበለ። በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ተፈርመው የነበሩም ዓለም አቀፍ ስምምነቶችንም ሩሲያ መቀበሏን አስታውቃለች።
የሶቪየት ሕብረት ሰብአዊ ሪፐብሊክ መቼ ተመሰረተ?
በ፲፱፻፲ ዓ.ም.
31
ጉጃራቲ ጉጃራቲ (ગુજરાતી) በህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ የሚገኝ ቋንቋ ነው። በዓለሙ ውስጥ በ46 ሚልዮን ሰዎች ይናገራል፤ ከነዚህም 45.5 ሚልዮን በህንደኬ፣ 250,000 በታንዛኒያ፣ 150,000 በዩጋንዳ፣ 100,000 በፓኪስታንና 50,000 በኬንያ አሉ። በሕዝብ ብዛት የዓለሙ 23ኛ ቋንቋ ነው። በምእራብ ህንደኬ ያለው የጉጃራት ክፍላገር ይፋዊ ቋንቋ ነው። የጉጃር ሕዝብ ወደ ህንደኬ የደረሱ በ5ኛው መቶ ዘመን ሲሆን በ6ኛው መቶ ዘመን ዛሬ ጉጃራት በሚባለው አገር ሰፈሩ። የራሳቸውን ቋንቋ ቶሎ ትተው እንደ አገሩ ሰዎች ሳንስክሪት ለመናገር ጀመሩ። በ12ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሳንስክሪት ተለውጦ ብዙ አዲስ ቋንቋዎች ተወለዱ። ከነዚሁም አንድ ጉጃራቲ ነበር። አብዛኛው ተናጋሪዎቹ የህንድ ሃይማኖት ተከታዮች ቢሆኑም ለረጅም ዘመን የእስላም ገዢዎች ስለነበሩባቸው ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከፋርስ ሆኗል። ከዚያ በላይ በንግድ ምክንያት ብዙ ቃሎች ከፖርቱጊዝ ወይም ከእንግሊዝኛ ተበደሩ። የሚጻፍበት በራሱ ጉጃራቲ ፊደል ነው፤ ይህም ከላይኛ መስመር በማጣቱ በስተቀር የህንዲ ደቫናጋሪ ፊደል ይመስላል።
ጉጃራቲ ቋንቋ በዩጋንዳ ምን ያህል ተናጋሪዎች አሉት?
150,000
124
ፐርል በክ ፐርል በክ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ (1938) ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓ.ም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር። ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተገናነች። በ1917 ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኑሯቸውን ናንሹ በተባለችው የገጠራማዋ አንህዌ ግዛት አደረጉ። በዚሁ ቆይታዋ ነው ወደፊት የሥነ-ጽሁፍ ስራዋ ጉልላት ለመሆን የበቃውን ስሙር መሬት (The Good Earth) ለተባለው መጽሃፏ የሚሆናትን መረጃ የሰበሰበችው። በክ ጽሁፎቿን ማሳተም የጀመረችው ከ1920ዎቹ ጀምራ ሲሆን አጫጭር ስራዎቿ "The Nation"፣ "The Chinese Recorder"፣ "Asia" እና "The Atlantic Monthly" በተሰኙ መጽሄቶች ታትመውላታል። የመጀመሪያው ወጥ ልብ-ወለድ ድርሰቷ (East Wind, West Wind) በ1930 በጆን ዴይ ኩባንያ ታትሟል። የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው ሪቻርድ ዋልሽ ኋላ ላይ (1935) የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን በቅቷል። በ1931 ጆን ዴይ ኩባንያ የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ ድርስት የሆነውን ስሙር መሬትን አሳተመ። ይኸው ሥራዋ በተከታታይ በ1931 እና በ1932 ዓ.ም በገበያ ላይ አንደኛ ተፈላጊ ሆኖ ለመዝለቅ የቻለ ሲሆን ለሷም በ1935 ዓ.ም የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ አስገኝቶላታል። ስሙር መሬት በ1937 ዓ.ም በኤም.ጂ.ኤም አማካይነት በፊልም መልክ ተቀናብሮ ለተመልካች ቀርቧል። ከዛ በተከታታይ ሌሎች ድርሰቶችን ለአንባቢ አቅርባለች። በክ በ1938 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን በመቀበል የመጀመሪያዋ (ሴት) አሜሪካዊት ሆናለች። ፐርል በክ በ1973 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ ከ70 በላይ ስራዎቿ ታትመውላታል። መቃብሯም ፔንሲልቬንያ ውስጥ በክስ በተባለው ቀበሌ ይገኛል።
የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ መጽሐፍ መቼ ታተመ?
በ1931
765
ቴምፕላርስ ቴምፕላር ወይም በሙሉ ስማቸው የክርሰቶስ እና የሰለሞን መቅደስ ምስኪን ወታደሮች የሚባሉት በጣም ታላቅ እና ሃይለኛ ከነበሩት ክርስቲያናዊ ወታደራዊ ስርአቶች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው። ይህ ስርዓት በ1088 ዓ.ም. ከተካሄደው አንደኛው የመስቀል ጦርነት በኋላ ማለትም በ1110 ዓ.ም. አዲስ የተቋቋመውን የእየሩሳሌም መንግስት ከእስላሞች ለመከላከልና ወደ ከአውሮፓ ወደ እየሩሳሌም የሚጎርፉትን ተሳላሚዎች ደህንነት ለመጠበቅ የተመሰረተ ነው። ቴምፕላሮች የተዋቀሩት በገዳማዊ ስርዓት ሲሆን ይኸውም የሲሰተርሲያን ስርዓት መስራች የነበረው የክላርቮው በርናርድ በዘረጋላቸው ህግጋት መሰረት ነው። ቴምፕላሮች ከብዙ መሳፍንት ጋር ግንኙነት ስለነበራቸው እና ጳጳሱም እነሱ ከሚቆጣጠሩዓቸው ቦታዎች ሁሉ ግብርና አስራት እንዲሰበስቡ ስለፈቀደላቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝነኛና ሃይለኛ ለመሆን ችለዋል። ቴምፕላሮቹ አራት ዋና ክፍሎች የነበሩአቸው ሲሆን እነዚሁም ዋነኞቹ ወታደሮች ወይም ናይትስ የሚባሉት ሙሉ የፈረሰኛ ትጥቅ የታጠቁ ከዝቅተኛ የህብረተሰቡ ክፍል የተውጣጡት ወይም ሰርጀንትስ በመባል የሚታወቁት፤ መለስተኛ የፈረሰኛ ትጥቅ የታጠቁ ገበሬዎች ዋነኛው ስራቸው የስርዓቱን ንብረት ማስተዳደር የነበረ፤ እንዲሁም ካህናት ስራቸው የስርዓቱን መንፈሳዊ ህይወት መከታተል የነበረ ናቸው።
ቴምፕላርስ የተባለው ስርዓት መቼ ተመሰረተ?
በ1110 ዓ.ም.
172
ከአፍሪካ ህዝብ ውስጥ 24 በመቶ ብቻ የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆናቸውን ዓለም ባንክ አስታወቀ፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎት አለመስፋፋት በአህጉሪቱ አዳዲስ ዲጂታል ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ የስራ ዕድል ፈጠራዎችን ለማስፋፋት አዳጋች እንደሚሆን ነው ባንኩ የገለጸው፡፡ በአፍሪካ እኤአ ከ2015 እስከ 2035 ባለው ጊዜ ውስጥ 450 ሚሊዮን ስራ ፈላጊ ወጣቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ የዓለም ባንክና የአፍሪካ ልማት ባንክ በጥምረት ያወጡት ሪፖርት ያመለክታል፡፡ እንደ ኢኮሜርስ እና ፋይናንስ ያሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ የስራ ዘርፎችን በአፍሪካ በማስፋፋት ከፍተኛ የስራ እድልን መፍጠር እንደሚቻል ተጠቅሷል፡፡ በዚህም፣ ወጣቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች በቂ እውቀት እንዲኖራቸው በማድረግ ማሰማራት እንደሚገባ ተነግሯል፡፡
በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ከ2015-2035 እ.ኤ.አ 450 ሚሊየን ያህል ስራ ፈላጊ ሰዎች ይኖራሉ ብሎ የገመተው ማነው?
የዓለም ባንክና የአፍሪካ ልማት ባንክ
234
አዲስ አበባ አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም. ፍልውሃ ፊን-ፊን ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተ ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በግምት 2,757,729 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ አንደኛ ትልቅ ከተማ ናት። ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍል ውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ሆናለች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።
የኢትዮጵያ ዋና መዲና ማናት?
አዲስ አበባ
8
ራስ መኮንን ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል የሸዋ ንጉሥ የነበሩት የሣህለ ሥላሴ ልጅ የልዕልት ተናኘወርቅ እና የደጃዝማች ወልደሚካኤል ልጅ ናቸው። ግንቦት ፩ ቀን ፲፰፻፵፬ ዓ.ም ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ እስከ ፲፬ ዓመት ዕድሜያቸው ከአባታቸው ጋር ከኖሩ በኋላ ያጐታቸው የንጉሥ ኃይለ መለኮት ልጅ ዳግማዊ ምኒልክ ገና የሸዋ ንጉሥ እንደነበሩ፡ ወደርሳቸው ቤተ መንግሥት መጥተው፡ ባለሟል ሆኑ። በ፲፰፻፷፰ ዓ.ም ዕድሜያቸው ሀያ አራት ዓመት ሲሆን ከወይዘሮ የሺ እመቤት ጋር ተጋብተው ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም የወደፊቱን ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ወለዱ።
ራስ መኮንን ወልደሚካኤል መቼና የት ተወለዱ?
ግንቦት ፩ ቀን ፲፰፻፵፬ ዓ.ም ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም
93
ዲጂታል ዑደት የዲጂታል ዑደት እምንለው የ ስታቲክ ዲሲፕሊን ን የሚቀበል ማናቸውም ዓይነት የዑደት አይነትን ነው። የዲጂታል ዑደት ከአናሎግ የኤሌክትሪክ ዑደት እሚለየው በተወሰኑና የአምክንዮ ትርጓሜ ባላቸው ሲግናሎች ብቻ መስራቱ ነው። ይህን እሚፈጽመው ያልተቆራረጡ የአናሎግ ሲግናሎችን በመከፋፈል፣ ለምሳሌ ከተወሰነ ቮልቴጅ በላይ ያሉትን ቮልቴጆች እንደ አምክንዮ እውነት (1) በመውሰድ እና ከተወሰነ ቮልቴጅ በታች ያሉትን ደግሞ እንደ አመክንዮ ውሸት በመውሰድ ነው። ሆኖም ግን ለምሳሌ ከ0ቮልት እስከ 5 ቮልት ያሉትን ዋጋወች ከፍለን ከ0-2.5ቮልት ያሉትን ውሸት እንዲወክሉ ብናደርግና ከ 2.5001ቮልት - 5ቮልት ያሉትን እውነት ን እንዲወክሉ ብናደርግ፣ ምንም እንኳ ስሜት ቢሰጥም፣ እነዚህን ቮልቴጆች በመጠቀም መልዕክት ለመላክ ብንሞክር፣ ትንሽ እንኳ ኖይዝ (ግርግር ቮልቴጅ) በመሃከል ከገባ አንዱን ቮልቴጅ ወደሌላው በመቀየር የተላከውን መልዕክት ያዛባል። ያ እንዳይሆን በመሃል ቀዳዳ ማበጀት አንዱ መልዕክት ወደሌላው መልዕክት እንዳይቀየር ይረዳል። ለምሳሌ ከ 0-1.5ቮልት ያለውን ውሸት ብንል እና ከ 3.5-5ቮልት ያለውን እውነት ብንል፣ በሁለቱ ዋጋወች መካከል የ2ቮልት ልዩነት ስላለ በቀላሉ አንዱን ዋጋ ወደሌላው መቀየር አይቻልም። ስለሆነም ከአንድ የድጅታል ስርዓት ክፍል ወደ ሌላ መልዕክት ሳይዛባ ለማስተላለፍ ይቻላል። ስለሆነም በብሊዮኖች የሚቆጠር ክፍል ያለው አንድ ኮምፒዩተር ያለምንም ስህተት ስሌትን ለመፈጸም ይችላል።
የዲጂታል ዑደት ከአናሎግ የኤሌክትሪክ ዑደት ምን ይለየዋል?
በተወሰኑና የአምክንዮ ትርጓሜ ባላቸው ሲግናሎች ብቻ መስራቱ ነው።
108
ሳዑዲ አረቢያ የሣውዲ አረቢያ ግዛት 28.7 ሚሊዬን የሚሆን ህዝብ ብዛት የያዘ ሲሆን 2ዐ ሚሊዬኑ የሣውዲ ዜጎች ሲሆኑ 8 ሚሊዬኑ የሌላ አገር ዜጎች ናቸው፡፡ ሳውዲ አረቢያ በምዕራብ ኤዥያ ከሚገኙ አገሮች በሙሉ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ ናት፡፡ የአገሪቱ መሬት ስፋት 2,15ዐ,ዐዐዐ ኪሎ ሜትር ስኩኤር ነው፡፡ ጆርዳን እና ኢራቅ በሰሜን፣ ኩዌት ደግሞ በሰሜን ምስራቅ ኳታር ባህሬን እና የዩናይትድ አረብ ኤምሬት በምስራቅ ኦማን በደቡብ ምስራቅ እና በስተመጨረሻ የመን በደቡብ በኩል ሣውዲ አረቢያ ያዋስኗታል፡፡ የቀይ ባህር እና የፐርዢያን ገልፍ ባህርን የያዘ ብቸኛ አገር ሲሆን የሣውዲ መሬት ለመኖር በሚያስቸግር በረሃ የተከበበ ነው፡፡ አሁን ያለው የሣውዲ ግዛት በፊት ጊዜ አራት ቦታዎችን ያጠቃለለ ነበር፡፡ ሄጃዝ፣ ናጅድ፣ አል አሻ እና አስርን የያዘነው፡፡ የሣውዲ አረቢያ ግዛት ተመሠረተው በ1932 እ.ኤ.አ. በኢብን ሣኡድ በተባለ ሰው ነው፡፡ ኢብን ሣኡድ ቀድሞ በ1894 ዓም (1902 እ.ኤ.አ.) ከብሪታንያ ግዛት ከኩወይት ዘምቶ ሪያድን ያዘ። ኢብን ሳኡድ አራት የነበሩትን የተለያዩ ግዛቶች አንድ በማድረግ ሣውዲ አረብያን ከተመሠረተ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሀገሪቱ በዘውድ አገዛዝ እና በእስልምና ሃይማኖት መሠረት እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ እስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ ዋሀቢ እስላም የሣውዲ አረቢያ አንደኛ እምነት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ የሚይዙት ቅዱስ ስፍራ ተብለው መካ እና መዲና በሣውዲ ስለሚገኙ ሣውዲ አረቢያ አብዛኛው ጊዜ የተቀደሱትን ሁለት መስጊዶች የያዘው መሬት ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ትልቅ የነዳጅ አምራች ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በተጨማሪም ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ሀይድሮ ካርቦን ክምችት ካላቸው አገሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሀገሪቱ ባለው የተፈጥሮ ሀብት ከፍተኛ ክምችት ምክንያት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ እና የህዝብ ቁጥር እድገት ከያዙ ሀገራት ጋር ትመደባለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ G-2ዐ ተብለው ከሚታወቁት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ካላቸው የሀገራት ቡድን ውስጥ ብቸኛዋ የአረቡ ዓለም አገር ናት፡፡ ይህም ቢሆን የሣውዲ ኢኮኖሚ በአብዛኛው በአንድ ቡድን የተያዘ ነው፡፡ የሣውዲ አረብያን ፈላጭ ቆራጭ በሆነ የመንግስት ስርዓት በመመራት “ነጻነት የለም” በሚል “ነጻነት ቤት” በሚል በሚታወቀው ድርጅት ተሰይማለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ለጦር ሀይል ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያወጡ አገሮች ዝርዝር በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2ዐ1ዐ-2ዐ14 በስኘሪ ተብሎ በሚታወቅ ድርጅት በተደረገው ጥናት ሣውዲ አረቢያ ዓለም ላይ ከሚገኙ የጦር መሣሪያዎች በከፍተኛ ደረጃ በማስገባት ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡፡ ሣውዲ አረቢያ በአካባቢው ካሉ ሀገሮች በዓለም ላይ ከፍተኛ አስተዋጾኦ በማድረግ ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የኦፔክ፣ ጂሲስ እና የእስላም ግሩፕ አባል ናት፡፡
ሳውዲ አረብያ የት ነው የምትገኘው?
በምዕራብ ኤዥያ
110
ተቀማጭነቱ ካሊፎርኒያ ውስጥ ያደረገው ኢ ኦ ኤን ሪአሊቲ የተባለው የሶፍትዌር አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ ውስጥ ማዕከሉን የመክፈት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ፡፡ የኢ ኦ ኤን ኩባንያ መስራች ዳን ለጀርስካር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ ኩባንያው በኢትዮጵያ ማዕከሉን የመክፈት ፍላጎት መኖሩን ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰር ሂሩት በበኩላቸው የቴክኖሎጂውን አስፈላጊነትና ወቅታዊነትን በመገንዘብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኩባንያው ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
የኢ ኦ ኤን ሪአሊቲ የሶፍትዌር አምራች ድርጅት ማዕከሉን ለመክፈት የፈለገው በየት ነው?
በኢትዮጵያ
59
ጋሞጐፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ከ1955 እስከ 1993 ዓ.ም ድረስ የጋሞ ጐፋ ጠቅላይ ግዛት፣ የሰሜን ኦሞ አስተዳደር አካባቢና ከዚያም የሰሜን ኦሞ ርዕሰ ከተማ በመሆን ለቀድሞዎቹ የጋሞ፣ የጐፋ፣ የጋርዱላና ሐመር ባኮ አውራጃዎች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ማዕከል ሆና ያገለገለች ስትሆን ከ1993 ዓ.ም ወዲህ ባሉት ዓመታት ደግሞ አስራ አምስት ወረዳዎችንና ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን አቅፎ ለያዘው ጋሞ ጐፋ ዞን ዋና ከተማ በመሆን እያገለገለች የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የዘይሴ ፣ የጌዲቾና የኦይዳ ብሄረሰቦችን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ ሌሎች የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ተወላጆች ተከባብረውና ተቻችለው በፍቅርና በሰላም የሚኖሩባት አርባ ምንጭ ከተማ በቀለማት አደራደሩ ትኩረትና ተወዳጅነት የማይለየው የጋሞ ብሔረሰብ የክብርና የማዕረግ ልብስ እንዲሁም መታወቂያው የሆነውንና ዱንጉዛ በመባል የሚታወቀው ባህላዊ ልብስ ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ የሸማ ጥበብ አልባሳት ሥራዎች መፍለቅያ አካባቢዎች እምብርት ከመሆኗም በተጨማሪ በባህላዊ ቤት አሰራራቸው በለቅሶና ሠርግ ስርዓታቸው በባህላዊ የማምረቻና የመገልገያ ቁሳቁሶቻቸው የብዙዎችን አድናቆትና አግራሞትን ላስጫሩት የጋሞ፣ የጐፋ፣ የዘይሴ፣ የጌዲቾና የኦይዳ ብሔረስብ ህዝቦች መዲና ነች፡፡    ከባህር ወለል በላይ ከ1,300 እስከ 1,500 ሜትር ከፍታ ላይ ስትገኝ  የአርባ ምንጭ ከተማ አየር ንብረት በተለምዶ ቆላማ የሚሉት አይነት ሲሆን፤ የከተማዋ ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠኗ 240c ነው፡፡ የከተማዋ ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኗ 900 ሚሊ ሜትር ሆኖ ግንቦት፣ ሰኔ፣ መስከረምና ጥቅምት ወራት ከፍተኛ የዝናብ መጠን በዓመቱ ውስጥ የሚመዘግብባቸው ወራት ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡  በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ስፍራ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን መንትያዎቹ የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ፤በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን   የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያ  እና የተፈጥሮ ደኖችን  ሌሎች ከህሊና ጓዳ የማይፋቅ ትዝታን ጥለው የሚያልፉ ሃብቶች ባለቤት ናት በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ከተማ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን ፤ የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያን በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት እና የተፈጥሮ ደኖችን ይገኛሉ፡፡ የዞኑን አስደናቂ የቱሪስት መስህቦች እንግዶቻችንን በማስጎብኘት ከታዋቂ የዓሳ ምርታችን ፣ ከማንጎ ፤ ከሙዝ እና በአፕል ማሳችን እየተንሸራሸርን የማይረሱ ትዝታዎችን ጥለው ያልፋሉ፡፡
የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና ከተማ ማናት?
አርባ ምንጭ
8
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የመናገሻ አምባ ማርያምን ገዳም እያስተዳደሩ ሳሉ፤ ከዚህ ሥልጣናቸው በተጨማሪ የአዲስ አበባ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መምህርነት በየካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ/ም ተሰጣቸው። ከዚያም ቀጥሎ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፭ዓ/ም በኢየሩሳሌም ያሉ የኢትዮጵያን ገዳማት በመንፈሳዊ መሪነት አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ለሁለት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ ወደአገራቸው ተመለሱ። የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም በአቡነ ተክለ ሃይማኖት መንበር፥ ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ዘነበረ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተብለው፥ አምሣ-ዘጠነኛው ዕጨጌ ሆነውተሽሙ። በዚሁ በዕጨጌነታቸው ዘመን የፋሺስት ወረራ ኢትዮጵያን ባጠቃ ጊዜ፣ በጦርነቱ ግምባር ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ተሰልፈው አብያተ ክርስቲያናትንና መጻሕፍትን የሚያቃጥል የምእመናንን ዘር የሚያጠፋ ጠላት መጥቷልና በሃይማኖት፤ በጸሎት፣ በምህላ በርታ እያሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያጽናኑ ቆዩ። በጦርነቱም ጊዜ የተቀመጡበት በቅሎ በአረር ተመቶ እስኪወድቅና የለበሱትም ካባ አምስት ላይ በጥይት እስኪበሳሳ ድረስ ከንጉሠ ነገሥቱ ሳይለዩ የቆራጥነት ሥራ ሠርተዋል። ሠራዊቱም ድል ህኖ በተፈታ ጊዜ ክንጉሠ ነገሥቱ ጋር በስደት ወደኢየሩሳሌም አቅንተው እስከ ድል ጊዜ ድረስ በስደት ቆይተዋል። በዚሁ በስደት ዘመናቸውም ሳሉ በርካታ ሐዋሪያዊ መልእክቶችን ለአርበኞችም፤ ለሕዝቡም በመላክ የማጽናናትና የሃይማኖታዊ ጣምሮችን ያስተላልፉ ነበር። ንጉሠ ነገሥቱ በስደት ከነበሩበት ከ’ባዝ’ (ብሪታንያ) ፥ ጥር ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ/ም በጊዜው በስደት ኢየሩሳሌም ለነበሩት ወደ ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ አንድ ፅላትና ለአገልግሎት የሚበቁ አምስት መነኮሳትን ወደ እንግሊዝ አገር እንዲልኩላቸው በአባ ሐና ጅማ በላኩት ደብዳቤ መሠረት፣ ዛሬ ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም የተባለውን የመድኀኔ ዓለምን ጽላት ወደንጉሠ ነገሥቱ ወዳሉበት ባዝ የላኩት እሳቸው ነበሩ፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፥ ጥር ፲፪ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በኢትዮጵያ ጠረፍ በኡም-ኢድላ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ-ዓላማ ሲተክሉ ዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስም አብረዋቸው ነበሩ።
ንጉሰ ነገስቱ በስደት የት ሃገር ነበሩ?
ከ’ባዝ’ (ብሪታንያ)
838
አዲስ አበባ መስከረም 15/2012 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሰራተኞቹ ጋር በሬድዬ ግንኙነት በመፍጠር አገልግሎቱን የሚያቀላጥፍበት የአስትሮ ሞቶሮላ የሬድዬ ኮሙኒኬሽን ፕሮጀክት አስመረቀ። የፕሮጀክቱ ምረቃ ስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር በተገኙበት በእንጦጦ ማሪያም የቴሌ ማይክሮዌቭ ማሰራጭያ ጣቢያ ተካሂዷል። በሁለት ምዕራፍ የተከፈለውን ፕሮጀክት ወደ ሥራ ለማስገባት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ሐምሌ 15 /2017 በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና በሞቶሮላ ሶሉሽን ኩባንያ መካከል ስምምነት ተፈርሞ ነበር። የመጀመሪያው ምዕራፍ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን በአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ኦሮሚያ ዞን ላይ ተግባራዊ ሆኗል። የኤሌክትሪክ የአገልግሎት አሰራሩን በማቀላጠፍ ለዜጎች የተሻለ አገልግሎት እንደሚሰጥ የታመነበት ይሄው ፕሮጀክት 6 ቡድኖችን በመያዝ በ 8 የግንኙነት ቻናሎች በጋራ እና በእኩል ሁኔታ እንዲጠቀሙ የሚያግዝ ነውም ተብሏል። የአስቸኳይ ጥገና ሥራን ማቀላጠፍ፣ ከሰብ ስቴሽን ጋር የሚኖረውን ግኝኑነት ማሳለጥ፣ በግንኙነት ክፍተት ሊፈጠሩ የሚችሉ የሰውና የንብረት አደጋን መቀነስ እንዲሁም የኃላፊዎችን መረጃ የመቀበልና መልዕክት የማስተላለፍ ሥራውን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተገልጿል። በኤሌክትሪክ አገልግሎት የአውቶሜሽንና ኢነርጂ ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ደመቀ ሮቢ አገልግሎቱ ስራውን የሚያከናውነው በስልክ እንደነበር አስታውሰው ይህም የሚሰጠው አገልግሎት ቅልጥፍና እንዳይኖረው አድርጎት ቆይቷል ይላሉ። ዛሬ የተመረቀው የሬድዮ ኮሙኒኬሽን ፕሮጀክት መስክ የወጡ የጥገና ሰራተኞች ቢሮ ካሉ ሰራተኞች ጋር በፍጥነት እንዲገናኙ ከማድረጉም ባለፈ ከፍተኛና ዝቅተኛ ኃይል መስመር ላይ ካሉ ኦፕሬተሮች ጋርም በቀላሉ በመገናኘት ፍጥነት ያለው የጥገና አገልግሎቶች እንዲሰጡ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል። በዚሁ የመጀመሪያው ምዕራፍም በአዲስ አበባና ዙሪያ በእጅ የሚያዙ 300 እንዲሁም 200 መኪና ላይ የሚገጠሙና 100 በጥሪ ማዕከልና በአስቸኳይ ጥገና ማዕከላት ላይ የሚገጠሙ ዲጂታል ሬዲዮኖች ጥቅም ላይ ውለዋል። እንደ አቶ ደመቀ ገለጻ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክቱንም ለማካሄድ ከአዲስ አበባ ውጪ 8 ከተሞች የተመረጡ ሲሆን ለዚህም ከ4 ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት ተይዞለታል።
በምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክቱን ማካሄድና ከአዲስ አበባ ውጪ በስንት ከተሞች ሊሠራ ታስቧል?
8 ከተሞች
1,282
ቺኑዋ አቼቤ በሙሉ ስሙ ሲጠራ አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ይሰኛል። ምናልባትም ናይጄሪያ ካሉዋት ምርጥ ፀሃፍት ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ የሚሰለፍ ሳይሆን አይቀርም። በ1930 እ.ኤ.አ. ኦጊዲ በተባለች የናይጄሪያ ግዛት ከአዜያህ ኦካፎ እና ከጃኔት አቼቤ ተወለድ። በ1953 እ.ኤ.አ. ከለንደን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ለአቼቤ ድንቅ ሥራ የተባለለት "Things Fall Apart" 50 ወደሚሆኑ የአለም ቁዋንቁዋዎች የተተርጎመ ሲሆን ወደ 10,000,000 ቅጂዎች እንደተሸጡለት ይነገራል። አቼቤ ከአፍሪካ ፀሃፍት ሁሉ ሥራው በበዙ ቁዋንቁዋዎች በመተርጎም ክብረ ወሰኑን እንደያዘ ነው። ብዙዎችም ይኸው ድርሰቱ በአለም እስከዛሬ ከተደረሱ ምርጥ ልበ-ወለዶች መካከል እንደሆነ ይስማማሉ። አቼቤ ከ30 ከሚበልጡ ዩኒበርስቲዎች የክብር ዶክትሬት የተቀበለ ሲሆን ብዙ ሽልማቶችንም ከተለያዩ ድርጅቶች አግኝቷል። ይሁንና እስከ አሁን ድረስ የኖቤል ሽልማት ለማግኘት አልታደለም። ይኸውም በብዙው ጽሁፉ የመራቡን አለም ዘረኛነት የሚተች በመሆኑ እንደሆነ ይነገራል። በ1990 ዓ.ም በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ከወገቡ በታች መንቀሳቀስ የተሳነው ሲሆን ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኘው የባርድ ኮሌጅ የቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ ፕሮፌሰር ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኘው የባርድ ኮሌጅ በምን ሙያ ያገለግል ነበር?
የቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ ፕሮፌሰር
695
ሰርጌይ ብሪን ሰርጌይ ሚካይሎቪች ብሪን ኦገስት 21, 1973 እ.ኤ.አ. ተወለደ ሩሲያዊ-አሜሪካዊ ሲሆን ጉግልን በመፍጠሩ ይታወቃል። በሩሲያ የተወለደ ሲሆን፥ ብሪን ከላሪ ፔጅ ጋር ጉግልን ከመጀመሩ በፊት ኮምፒዩተር ሳይንስና ሒሳብ አጥንቷል። ብሪን ባሁኑ ጊዜ የጉግል ቴክኖሎጂ ፕሬዝዳንት በመሆኑ ወደ 14.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ገንዘብ አለው። ይህም ከዓለም 26ኛ እና ከአሜሪካ 12ኛው ሀብታም ሰው ያደርገዋል። ሰርጌይ በሞስኮ፣ ሩሲያ ለየይሁዳ ቤተሰብ ተወለደ። 6 ዓመቱ ሲሆን ሰርጌይና ቤተሰቡ ወደ አሜሪካ መጡ። አባቱ ሚካኤል በሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ ማቲማቲሻን ሆኖ እስክ ዛሬ ድረስ ያስተምራል። የስርጂ እናት ዩጂኒያ ብሪን ማቲማቲሻንና ሲቭል ኢንጅነር ሆና ለናሳ ትሰራለች። ሳሙኤል የሚባል ታናሽ ወንድምም አለው። ሰርጌይ በኮምፒዩተር ዕድገት ጊዜ በማደጉ የኮምፒዩተር ፍላጎቱ ከልጅነቱ ነው የጀመረው። መጀመሪያው ያገኘው ኮምፒዩተር አንድ ኮሞዶር 64 ሲሆን ይህንንም ከአባቱ ዘጠነኛው ልደት በዓሉ ላይ ነው ያገኘው። በሒሳብና ኮምፒዩተር ያለውን ተስዕጦም ገና ትንሸ እያለ ነው ያሳየው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በፔንት ብራንች ሞንቴሶሪ ትምህርት ቤት የወሰደ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በኤላኖር ሩዝቬልት ትምህርት ቤት አጠናቋል። ቤተስቡም የሒሳብ ዕውቀቱንና ሩሲያኛው በማዳበር ረድተውቷል። በሴፕቴምብር 1990 እ.ኤ.አ.፣ ሰርጌይ ሒሳብና ኮምፒዩተር ሳይንስ ለማጥናት ሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ፣ ኮሌጅ ፓርክ ገባ። በሜይ 1993 እ.ኤ.አ. የባችለር ሳይንስ ካማግኘቱ በኅላ በስኮላርሺፕ ኮምፒዩተር ሳይንስን ለማጥናት ወደ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ሄደ። ከዛም ከታሰበው ጊዜ በፊት በኦገስት 1995 እ.ኤ.አ. የማስተርስ ዲግሪውን ተቀበለ። ባሁኑ ጊዜ ግን የፒ.ኤች.ዲ. ጥናቱን ላልተወስነ ጊዜ አቋርጦ ጉግል ውስጥ እየሰራ ይገኛል።
የጉግል ቴክኖሎጂ ፕሬዝዳንት ማን በመባል ይታወቃል?
ሰርጌይ ሚካይሎቪች ብሪን
9
ሌሎች የፍልስፍና ባህሎች ከምዕራባውያን ፍልስፍና በተለየ በነዚህ ጉዳዮች ላይ በዙም አላተኮሩም። ምንም እንኳን የሂንዱ ፍልስፍና በዚህ አንፃር ከምዕራባውያኑ ቢመሳሰለም እስከ 19ኛው ምዕት-አመት ድረስ በኮሪይኛ፣ በጃፓንኛ፣ እና በቻይንኛ ውስጥ "ፍልስፍና" የሚል ቃል ይገኝ አልነበረም። በተለይ የቻይና ፈላስፎች ከግሪኮቹ ለየት ያለ የምደባ ስርዓት ይከተሉ ነበር። የምዕራቡ አለም ፍልስፍና የሚጀምረው ከግሪኮች ሲሆን የመጀመሪያው ፈላስፋ ተብሎ የሚታወቀው ታሊዝ ነው። ይህ ሰው የኖረበትን ጊዜ ለማወቅ ብዙም አስቸጋሪ አይደለም። ይኸውም በ593 ዓክልበ. (ዓም) የፀሃይ ግርዶሽ እንደሚኖር በመተንበዩ ከዚህ ጊዜ የተወሰነ አመት ቀደመ ብሎ ማይሌጠስ በተባለችው የትንሹ እስያ (የአሁኑ ቱርክ) ክፍል እንደተወለደ የታወቀ ነው። ታሊዝ ዓለም እና በውስጡ ያሉ ነገሮች ሁሉ ከውሃ እንደተፈጠሩ ያምን ነበረ። ከሱ በኋላ የተነሱ የግሪክ ፈላስፎች የሱኑ መንገድ በመከተል ዓለም ከአንድ ወይም ከሌላ ነገረ እንደተፈጠረች አስተምረዋል። ለምሳሌ አናክሲሜነስ የዓለም ጥንተመሰረቷ አየር ነው ሲል፣ ሄራቅሊጠስ እሳት ነው ብሏል። አናክሲማንደር ከነዚህ ሁሉ ለየት በማለት የዓለም መሰረቷ ይህ ነው የማይባል «apeiron» ወይም የትየለሌ የሆነ ነገር ነው ይላል። የምእራቡን ዓለም ፍልስፍና እስክ 1900 ድረስ ቅርጽ እንዳስያዙ የሚነግርላቸው ፈላስፋዎች የሚከተሉት ናቸው፡ ሶቅራጥስ፣ አሪስጣጣሪስ፣ ፕላጦ፣ አክዊናስ፣ ኤራስመስ፣ ማኪአቬሌ፣ ቶማስ ሞር፣ ሞንታጝ፣ ግሮቲየስ፣ ዴካርት፣ ሆበስ፣ ስፒኖዛ፣ ሎክ፣ ሌብኒሽት፣ በርክሌ፣ ሑሜ፣ ቮልቴይ፣ ሩሶ፣ ካንት፣ ሺለር፣ ሄግል፣ ሾፐናዎር፣ ጆን ኦስቲን፣ ጄ.ኤስ. ሚል፣ ኮምቴ፣ ዳርዊን፣ ማርክስ፣ እንግልስ፣ ፍሬደሪሕ ኚሼ፣ ዱርካሂም የምስራቁ አለም ፍልስፍና መነሻ ኢትዮጲያ ናት፡፡እንደውም የመላው አለም፡፡ በተለይ ኮከባቸው ጀምኒ የሆኑት የሐበሻ ተወላጆች የኮከባቸውን ሀያልነት በመጠቀም ወደ አረቡ አለም በመገስገስ የምድራችንን የፍልስፍና መንገድ ቀይሠዋል፡፡
ታሊዝ ዓለምና በውስጧ ያሉ ነገሮች ከምን እንደተፈጠሩ ነበር የሚያምነው?
ከውሃ
483
ማሊ የማሊ ሪፐብሊክ (ማሊ) በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ የለሽ ሀገር ናት። ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በስፋት ሁለተኛ ናት። ከአልጄሪያ፣ ኒጄር፣ ቡርኪና ፋሶ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኔ፣ ሴኔጋል እና ሞሪታኒያ ጋር ድንበር ትዋሰናለች። ማንዴ ሕዝቦች አውራጃውን ሠፍረው ተከታታይ መንግሥታት አጸኑ። እነዚህም የጋና መንግሥት፣ የማሊ መንግሥትና የሶንግሃይ መንግሥት ያጠቅልላሉ። በነዚህ መንግሥታት ውስጥ ቲምቡክቱ ለትምርትና ለመገበያየት ቁልፍ ከተማ ነበረች። በ1583 ዓ.ም. በሞሮኮ በተካሄደ ወረራ የሶንግሃይ መንግሥት ኃይል ለማነስ ጀመር። ማሊ በ1880 እ.ኤ.አ. በፈረንሣይ ቅኝ ተገዝታ «ፈረንሳያዊ ሱዳን» ወይም «የሱዳን ሪፐብሊክ» ትባል ነበር። ፈረንሳያዊ ሱዳን በኅዳር 16 ቀን 1951 ዓ.ም. በፈረንሳያዊ ማሕበረሠብ ውስጥ 'ራስ-ገዥ ሁኔታ' አገኝታ በመጋቢት 26 1951 ዓ.ም. ከሴኔጋል ጋር አንድላይ የማሊ ፌደሬሽን ሆኑ። ይህ የማሊ ፌዴሬሽን በሰኔ 13 ቀን 1952 ነጻነት አገኘ። ነገር ግን በነሐሴ 14 ቀን ሴኔጋል ከፌዴሬሽኑ ወጣች። በመስከረም 12 ቀን 1953 ዓ.ም. ፈረንሳያዊ ሱዳን በሞዲቦ ኪየታ ስር ራሷን 'የማሊ ሬፑብሊክ' አዋጀችና ከማሕበረሰቡ ወጣች። ሞዲቦ ኪየታ በ1968 እ.ኤ.ኣ. በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ከወረደ በኋላ እስከ 1991 እ.ኤ.አ. ድረስ ማሊ በማውሳ ትራዎሬ ተመራች። በ1991 እ.ኤ.አ. የተካሄዱ ተቃውሞች ወደ መፈንቅለ-መንግሥት አመሩ። ከዚያም የተሸጋጋሪ መንግሥት ተቋቋመና አዲስ ሥነ-መንግሥት ተጻፈ። በ1992 እ.ኤ.አ. አልፋ ዑመር ኮናሬ የማሊን የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን አሸነፉ። ማሊ ከባሕር ጋር ግንኙነት የላትም። የሀገሩ አብዛኛው ክፍል በሰሐራ በረሃ ውስጥ ይገኛል። ከተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ ወርቅ፣ ዩራኒየም፣ ፎስፌት፣ ካዎሊን፣ ጨው፣ ኖራ (ላይምስቶን) ይጠቀሳሉ። የማሊ ፓርላማ 147 ሰዎች ሲኖረው እነዚህ ተወካዮች በህዝብ ብዛት ነው የሚመረጡት። ማሊ ከዓለም ደሀ ሀገሮች አንዷ ስትሆን 65 ከመቶ የሚሆነው መሬት በረሃ ነው። አብዛኛው የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ በኒጅር ወንዝ አካባቢ ነው የሚካሄደው። 10 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ የሚኖር ሲሆን 80 ከመቶ የሚሆነው የሥራ ሃይል በእርሻና ዓሣ ማጥመድ ተሰማርቷል። የኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ በእርሻ ምርቶች ላይ ያተኩራል። የሸክላ ሥራ በሴቶች የሚከናወን ሲሆን በነጋዴዎች በገበያዎች ይሸጣል። ሸክላዎቹ የሚሰሩበት ባሕላዊ ሂደት የቱሪስት መሳቢያ ነው።
የማሊ ሪፐብሊክ 1968 እ.ኤ.ኣ. እስከ 1991 እ.ኤ.አ. የተመራች በማን ነበር?
በማውሳ ትራዎሬ
751
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ተፈሪ መኰንን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ከአባታቸው ከልዑል ራስ መኰንን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺ እመቤት ኤጀርሳ ጎሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ሐረርጌ ውስጥ ተወለዱ። በ፲፰፻፺፱ የሲዳሞ አውራጃ አገረ ገዥ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. የሐረርጌ አገረ ገዥ ሆኑ። የሐረርጌ አገረ ገዥ ሲሆኑ ፣ በጣም ብዙ ሺህ ተከታዮች ነበሩዋቸውና ልጅ እያሱን ከእንደራሴነት በኅይል እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ተፈሪን ከሐረር አገረ ገዥነት እንዳይሽሯቸው የሚል ስምምነት ተዋዋሉ። ዳሩ ግን እያሱ ሃይማኖታቸውን ከክርስትና ወደ እስልምና እንደቀየሩ የሚል ማስረጃ ቀረበና ብዙ መኳንንትና ቀሳውስት ስለዚህ ኢያሱን አልወደዱዋቸውም ነበር። ከዚህም በላይ እያሱ ተፈሪን ከሐረር ከአገረ ገዥነታቸው ለመሻር በሞከሩበት ወቅት ስምምነታቸው እንግዲህ ተሠርዞ ተፈሪ ደግሞ ለወገናቸው ከስምምነቱ ተለቅቀው በዚያን ጊዜ እሳቸው እያሱን ከእንደራሴነት አስወጡ። እንግዲህ በ፲፱፻፱ ዓ.ም. መኳንንቱ ዘውዲቱን ንግሥተ ነገሥት ሆነው አድርገዋቸው ተፈሪ ደግሞ እንደራሴ ሆኑ። ከዚህ ወቅት ጀምሮ ተፈሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለሙሉ ሥልጣን ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም. የንጉሥነት ማዕረግ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ አርፈው ንጉሠ ነገሥት ሆኑና ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ብዙ የውጭ ልዑካን በተገኙበት ታላቅ ሥነ-ሥርዓት ቅብዓ ቅዱስ ተቀብተው እሳቸውና ሚስታቸው እቴጌ መነን ዘውድ ጫኑ። በንግሥ በዓሉ ዋዜማ ጥቅምት ፳፪ ቀን የትልቁ ንጉሠ-ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለዘውድ በዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት ፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ ተመረቀ። ለንግሥ ስርዐቱ ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ አገር ልኡካን ከየአገራቸው ጋዜጠኞች ጋር ከጥቅምት ፰ ቀን ጀምሮ በየተራ ወደ አዲስ አበባ ገብተው ስለነበር ሥርዓቱ በዓለም ዜና ማሰራጫ በየአገሩ ታይቶ ነበር። በተለይም በብሪታንያ ቅኝ ግዛት በጃማይካ አንዳንድ ድሀ ጥቁር ሕዝቦች ስለ ማዕረጋቸው ተረድተው የተመለሰ መሢህ ነው ብለው ይሰብኩ ጀመር። እንደዚህ የሚሉት ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ፊተኛው ስማቸው «ራስ ተፈሪ» ትዝታ ራሳቸውን «ራስታፋራይ» (ራሰተፈሪያውያን) ብለዋል።
የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የትዳር አጋር ማን ናቸው?
እቴጌ መነን
896
ሴኔጋል ከ፹ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ፓርላማዋ ሁለት ምክር ቤቶች አሉት። አንዱ ፻፳ መቀመጫዎች ያሉት የብሔራዊ ስብሰባ (እንግሊዝኛ፦ National Assembly) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ፻ መቀመጫዎች ያሉት ሴኔት ነው። ሴኔጋል ራሱን የቻለ ህግ ተርጓሚ አካል አላት። ዳኛዎቹ የሚሾሙት በፕሬዝዳንቱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሴኔጋል የዴሞክራሲ ሂደት ስኬታማ ነው ከሚባሉት የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ ናት። የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። ማራባውት የሚባሉ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችም በሴኔጋል ጠንካራ የፖለቲካ ተፅእኖ አላቸው፡ ከ፪ ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉበት የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የሀገሩ ትልቁ ከተማ ነው። ሁለተኛው ፭፻ ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ቱባ ከተማ ነው። ሴኔጋል ከ12.5 ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ አላት። ከዚህ ውስጥም ወደ ፵፪ ከመቶ በገጠር ነው የሚኖረው። የአሜሪካ የስደተኖች ኮሚቴ ባቀረበው የ2008 እ.ኤ.አ. የዓለም ስደተኞች አጠቃላይ ቅኝት መሠረት ሴኔጋል በ2007 እ.ኤ.አ. ወደ 23,800 የሚገመቱ ስደተኞች ይኖሩባታል። ከዚህ አብዛኛዎቹ የመጡት ከሞሪታኒያ ነው። ስደተኞቹ በንድዮም፣ ዶዴል እና በሴኔጋል ወንዝ አቅራቢያ በሚገኙ ሠፈሮች ይኖራሉ። የአገር ይፋዊ ብሔራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ከብዙ ኗሪ ቋንቋዎች 11ዱ በተለይም ዎሎፍኛ አገራዊ ዕውቅና አላቸው። ሌሎቹ ባላንታኛ፣ ማንዲንክኛ፣ ፑላርኛ (ፉላኒኛ)፣ ሰረርኛ፣ ሶኒንክኛ፣ ኖንኛ፣ ማንካኛኛ፣ ማንጃክኛ፣ ጆላኛ እና ሀሣኒያ አረብኛ ናቸው። ፖርቱጊዝኛም በትምህርት ቤት ይማራል፣ የካቦ ቨርዴ እና የጊኔ-ቢሳው ኅብረተሠቦችም ፖርቱጊዝኛ ክሬዮል ይናገራሉ። ከሴኔጋል ሕዝብ 94% የእስልምና አማኞች፣ 5% ክርስትና (ባብዛኛው ካቶሊክ)፣ 1% የኗሪ አርመኔነት ተከታዮች ናቸው። የመንግሥት ሃይማኖት የለውም። በሴኔጋል ልማዳዊ ባሕል ግሪዮት የተባሉ ሽማግሎች ታሪኮቻቸውን በአፍ ቃል ይደግማሉ። ሴኔጋል ለሙዚቃዊ ስልቶቹ ይታወቃል፤ በተለይ የሚወድደው ዘመናዊው ስልት ምባላክስ ተብሏል። በሴኔጋል አበሳሰል በተለይ አሣ፣ ዶሮ፣ በግ፣ አተር፣ ዕንቁላል፣ በሬ ይጠቀማሉ፤ እስላም አገር እንደ ሆነው መጠን ግን አሳማ አይበላም። ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ስኳር ድንች፣ ምስር፣ ጥቁር-ዐይን አተር ደግሞ በሴኔጋል አበሳሰል በሰፊ ይገኛሉ። በእስፖርት በኩል፣ ከሁሉ የሚወደደው ባህላዊው የሴኔጋል ትግል ግጥሚያ ሲሆን፣ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ ደግሞ እጅግ ይወደዳሉ።
የሴኔጋል ቱባ ከተማ ምን ያህል ነዋሪ አላት?
፭፻ ሺህ
417
ሴኔጋል ሴኔጋል ወይም የሴኔጋል ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። ሴኔጋል ከምዕራብ በሴኔጋል ወንዝ፣ ከሰሜን በሞሪታንያ፣ ክምሥራቅ በማሊ እና ክደቡብ በጊኒና ጊኒ-ቢሳው ይዋሰናል። የጋምቢያ ግዛት እንዳለ በሴኔጋል ውስጥ ነው የሚገኘው። የሴኔጋል የቆዳ ስፋት 197,000 ካሬ ኪ.ሜ. የሚጠጋ ሲሆን የሕዝብ ብዛቱ ደግሞ ወደ 14 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል። የሴኔጋል የአየር ሁኔታ የየምድር ወገብ ሲሆን ደረቅና ዝናባማ ወራት ተብሎ ወደ ሁለት ይከፈላል። የሴኔጋል ርዕሰ ከተማ ዳካር በሀገሩ የምዕራብ ጫፍ በካፕ-ቨርት ልሳነ ምድር ላይ ይገኛል። ከባህር ጠረፍ ወደ ፭፻ ኪ.ሜ. ገደማ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የኬፕ ቨርድ ደሴቶች ይገኛሉ። በ፲፯ኛው ና ፲፰ኛው ክፍለ ዘመናት በቅኝ ገዢ መንግሥታት የተሠሩ የንግድ ተቋማት ከባህር ዳር ይገኛሉ። በአካባቢው ያሉ ግኝቶች ሴኔጋል ከጥንት ጀምሮ የሚኖርበት እንደነበረ ያሳያሉ። እስልምና የአካባቢው ዋና ሀይማኖት ሲሆን ወደ ሴኔጋል የተዋወቀውም በ11ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደሆነ ይታመናል። በ13ኛውና 14ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የማንዲንጎ ግዛት በአካባቢው ላይ ተጽኖ ያደርግ ነበር። በዚሁም ጊዜ ነው የጆሎፍ ግዛት የተመሠረተው። በ15ኛው ክፍለ-ዘመን ፖርቱጋል፣ ኔዘርላንድስ እና ኢንግላንድ በአካባቢው ለመነገድ ይወዳደሩ ነበር። በ1677 እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ጎሪ የሚባለውን ዋና የባሪያ ንግድ ደሴት ተቆጣጠረች። ከዛም በ1850ዎቹ እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ቁጥጥሩዋን ወደ መላው ሴኔጋል ማስፋፋት ጀመረች።
ሴኔጋል በየትኛው አህጉር ውስጥ የምትገኘው ሀገር ናት?
አፍሪካ
32
አሦር አሦር (አሹር) ማለት በጥንታዊ ዘመን በላይኛ ጤግሮስ ወንዝ አጠገብ የተገኘ ከተማና አካባቢው ነበረ። በኋለኛ ጊዜ የአሦር መንግሥት ሃይለኛ ሆኖ መላ መሬት እስከ ግብጽ ድረስ ገዛ። በጥንታዊ አሦር ከተማና በጤግሮስ አጠገብ ያሉትም ተራሮች እስከ ዛሬው አርሜንያ ድረስ 'የአሦር ተራሮች' ይሰየሙ ነበር። በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት አሦር (አሹር) ከኖኅ ልጅ ሴም ልጆች አንዱ ሲሆን፥ ከሰናዖር ወጥቶ አንዳንድ ከተማ ሠራ። በአሦራውያንም እምነት ዘንድ 'አሹር' ከተማውን የመሠረተው አምላክ ስም ነበረ። ከቅድመኛው ዘመን አውራጃው ሹቡር ተብሎ ከሰናዖር (ሹመር)፣ ማሪ ወይም ከአካድ ይገዛ ነበር። ሹቡር በታላቁ ሳርጎን መንግሥት ውስጥ ክፍል ሆኖ ጉታውያን እስከ አጠፉት ድረስ ቆየ። በኋላ እስከ 1879 ዓክልበ. ግ. ከኡር 3ኛ ሥርወ መንግሥት ይቆጣጠር ነበር። የዑር መንግሥት ሲወድቅ የአሦር ከተማ ነገሥታት ሊሙ ስሞች ይመዘገባሉ። በዚህ ወቅት አሦር ከተማ-አገር ብቻ ነበረ። ሆኖም አሦራውያን የብረታብረት ንግዳቸውን ለማስፋፋት በማሰብ አንዳንድ ቅኝ-ከተማ (ካሩም) በሐቲ (ዛሬው ቱርክ) ውስጥ መሠረቱ። ከነዚህም ዋነኛው ካነሽ የተባለው ከተማ ነበር። በ1720 ዓክልበ. ግ. አሞራዊው ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ አገሩን ከነአሦር ከተማ አቀና። ልጁን 1 እሽመ-ዳጋን (1688-1678 ዓክልበ.) በአሦር ላይ ሾመው። ነገር ግን የባቢሎን ንጉስ ሃሙራቢ ድል አድርጎት ዙሪያው ወደ ባቢሎን መንግሥት ተሳለፈ። ከትንሹ እስያ ይካሄድ የነበረው የብረታብረት ንግድ በዚያን ጊዜ ተቋረጠ። ለሚከተለው መቶ አመት አሦር ለባቢሎን ተገዥ ነበር። በ1507 ዓክልበ. ግ. ባቢሎን ለካሣውያን ከወደቀ በኋላ፥ አሦር በሚታኒ መንግሥት (ሑራውያን) በ1441 ዓክልበ.ግ. ይሸነፍ ነበር። ሚታኒ በኬጢያውያን ግፊት ሲወድቅ ግን የአሦር ንጉስ አሹር-ኡባሊት ነጻነቱን አዋጀ (1366 ዓክልበ. ያህል)። ከዚህ በላይ ይህ አሹር-ኡባሊት የራሱን ልጅ ኩሪጋልዙን በባቢሎን ዙፋን ላይ አሾመው። በ1290 ዓክልበ. የአሦር ንጉስ 1 አዳድ-ኒራሪ የሚታኒን መንግሥት አሸነፈ። የአዳድ-ኒራሪ ተከታይ 1 ስልምናሶር መንግሥቱን በከጢያውያን አግጣጫ እስከ ከርከሚሽ ድረስ አስፋፋ። የስልምናሶርም ልጅ 1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ እንኳን በባቢሎን ላይ ገዛ። ሆኖም በቅርብ ጊዜ ባቢሎን በአሦር ላይ አመጽ ታደርግ ነበር። በ1200 ዓክልበ.. አካባቢ የኬጢያውያን መንግሥት በሙሽኪ (ፍሩጋውያን) ግፊት ስለ ወደቀ፥ ባቢሎንና አሦር ለአሞራውያን መሬት ተወዳዳሪዎች ሆኑ። የአሦር ንጉስ 1 አሹር-ረሽ-ኢሺ በዚህ አቅራቢያ በ1140 ዓክልበ. በባቢሎንን ንጉሥ 1 ናቡከደነጾር ላይ አሸነፈ። የአሹር-ረሽ-ኢሺ ልጅ 1 ቴልጌልቴልፌልሶር የመንግሥቱን ጠረፍ በጣም አስፋፋ። ከርከሚሽን ከመማረኩ በላይ በሙሽኪ ላይ እስከ ጥቁር ባሕር ድረስ ዘመቻ አደረገ። ደግሞ እስከ ሜድትራኒያን ባሕር ድረስ ሲዘረጋ ፊንቄን (ሊባኖስ) ያዘ። ከ1 ቴልጌልቴልፌልሶር በኋላ ከጎረቤቶቹ ከአራማውያንና ከኡራርቱ የተነሣ የአሦር ኅይል ደክሞ ነበር። በ920 ዓክልበ. ግን 2 አዳድ ኒራሪ ንጉሥ ሆሞ የአሦር ሃይል ታደሰ። ደግሞ ወደ ስሜን የኖሩትን ሕዝቦች በሙሉ በሰፈራ አፈለሳቸው። ይሁንና መንግሥቱ ከአቦር ወንዝ ወደ ምዕራብ አልዘረጋም። ንጉስ አሹር-ናሲር-ፓል ከ890 ዓክልበ. ጀምሮ ነግሦ ያለ ምኅረት ጠረፎቹም አስፋፋ። ከአቦርና ከኤፍራጥስ መካከል ያሉትን አራማውያን ድል አድርጎ በሜድትራኒያን ሲደርስ ፊንቄን ቀረጠ። ካልሁንም ዋና ከተማው እንዲሆን አደረገው። በልጁ 3 ስልምናሶር 34 አመት ዘመን (865-831 ዓክልበ.) አሦር በየአመቱ ለጦርነት ሠለፈ። ባቢሎን ተወርሮ ተቀረጠ። የሶርያ (አራም-ደማስቆ) ንጉስ ወልደ አዴር (አድርአዛር) ከእስራኤል ንጉስ አክዓብ ጋራ በቃርቃር ፍልሚያ ስልምናሶርን አጋጠመው። ስልምናሶርም ፊንቄንና የእስራኤል ንጉስ ኢዩን አስቀረጠ። በዋና ከተማው በካልሁ የተገኘው ጥቁር ሐውልት ስለ 3 ስልምናሶር ዘመን ድርጊቶች ይመሰክራል።
ሚታኒ በኬጢያውያን ግፊት ሲወድቅ የአሦር ንጉስ አሹር-ኡባሊት ነጻነቱን ያወጀው መቼ ነው?
1366 ዓክልበ.
1,037
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በጥሩ ጎናቸው ከሚነሱ የቅርብ ጊዜያት ተጫዋቾች መካከል አዳነ ግርማ ይገኝበታል።ተጫዋቹ በበርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታንም ይዟል።አዳነ ግርማ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን መነቃቃት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ተጫዋቹ በብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ ለ10 ዓመታት በመጫወትም አንጋፋ ለመሆን በቅቷል። አዳነ ግርማን ስናስብ ሁለት ጨዋታዎች ሁሌም ከፊታችን ድቅን ይላሉ።ደቡብ አፍሪካ ላስተናገደ ችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡደን ከሱዳን አቻው ጋር ሲጫወት በግንባሩ ገጭቶ ያስቆጠራት ግብ መቼም ቢሆን አዳነ እንዲታወስ ያደረገችም የምታደርግ ናት።ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ ያረገችው ወሳኝ ግብም ሆናለች። በአፍሪካ ዋንጫው ከ 39 ዓመታት በኋላ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛምቢያ ላይ ያስቆጠራት ግብም አዳነን ሁሌም እንድናስበው ያረገች ሌላዋ ግቡ ናት። ተጫዋቹ ከዋልያዎቹ ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳደረገና የቡድኑ ምሰሶ እንደነበርም ይታወቃል።በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ዘመን አዳነ ቡድኑን በአምበልነት መርቷል። የአትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከሰውነት ቢሻው የተረከቡት አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ቡድኑን እንደ አዲስ ሲያዋቅሩ አዳነ ግርማን መቀነሳቸው ሲሰማ በስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ ቅሬታ ቢፈጠርም፣ ተጫዋቹ ግን ውሳኔውን አሜን ብሎ ነው የተቀበለው። በወቅቱም አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ለተጫዋቹ መቀነስ ምክንያታቸው ያደረጉት የተጫዋቹ «ብቃትና አቅም ወርዷል» የሚል ነው። ተጫዋቹ ግን በወቅቱ ለአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ያረጋገጠው ምንም አይነት የአቋም መዋዠቅም እንደሌለበት ነው። የብቃት መውረድ እንዳላሳየም ገልጿል። የመቀነሱ ሚስጥር ለሱም እንቆቅልሽ እንደሆነበት ነበር ያስታወቀው። ይህን ተከትሎ ራሱን ከብሄራዊ ቡድን ያገለለው አዳነ በአዲሱ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሰሞኑን ጥሪ ተደርጎለት ነበር:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄሪያ ጋር ላለበት ወሳኝ ጨዋታ በአጥቂ እጥረት ላይ ቢገኝም አዳነ ግርማ ከቤተሰቦቼ ጋር ተመካክሬ የወሰንክይት ውሳኔ ነው በሚል ለብሔራዊ ቡድኑ እንደማይጫወት አስታውቋል:: በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሁለት የተደለደለውና በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአልጀሪያ አቻው ጋር ላለበት የምድቡ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ 24 ተጫዋቾችን መጥራቱ ይታወሳል። አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ሁለት ተጫዋቾችን ከአገር ውጭ ቀሪዎቹን 22 ደግሞ ከአገር ውስጥ ሊጎች የመረጡ ቢሆንም የአዳማ ከነማው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ ባጋጠመው ጉዳት ከቡድኑ ውጭ ሆኗል። እርሱን ለመተካት ሳልሃዲንና አዳነን ቢጠሩም እምቢ ተብለዋል:: ሆኖም ግን አሰልጣኙ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የመረጧቸውን አምስት ተጫዋቾችና ከአገር ውጭ ከሚጫወቱት ሕመልስ በቀለና ጌታነህ ከበደ በስተቀር 15 ተጫዋቾችን ይዘው ልምምዳቸውን ዛሬ ጀምረዋል።
ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተደልድሎ የነበረው በምድብ ስንት ነበር?
ሁለት
1,295
ጎግል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በቻይና የሚገኘውን ቢሮውን በጊዜያዊነት መዝጋቱን አስታወቀ። የመረጃ ማፈላለጊያ ገጹ ከቻይና በተጨማሪ በሆንኮንግ እና ታይዋን የሚገኙ አገልግሎት መስጫ ቢሮዎቹን መዝጋቱንም አስታውቋል። ከጎግል በተጨማሪ አማዞን እና ማይክሮሶፍትን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሰራተኞቻቸውን ደህንነት ለመጠበቅ በሚል ተመሳሳይ እርምጃ ውስጥ መግባታቸው ተገልጿል። ጎግል ሰራተኞቹ ወደ ቻይና እና ሆንግ ኮንግ ከሚያደርጉት ጉዞ እንዲታቀቡና በቻይና የሚገኙትም በተቻለ ፍጥነት እንዲወጡ መምከሩም ተነግሯል። ባለፈው ሳምንት ፌስቡክ ሰራተኞቹ ወደ ቻይና እንዳይጓዙ ያስጠነቀቀ ሲሆን፥ ተሽከርካሪ አምራቹ ጄኔራል ሞተርስም ፋብሪካዎቹን ዘግቷል። ከዚህ በተጨማሪም የጃፓኑ ቶዮታ እስከ ፈረንጆቹ የካቲት 9 ድረስ በቻይና አገልግሎት መስጠት ማቆሙን አስታውቋል። የፈረንሣዩ ፒ ኤስ ኤ እንዲሁም የጃፓኖቹ ሆንዳ እና ኒሳን ሰራተኞቻቸውን ከቻይና የማስወጣት እቅድ እንዳላቸው ተነግሯል። ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በተገኘባት ውሃን ከተማ መቀመጫቸውን ያደረጉ ዓለም አቀፍ አምራቾችም ሰራኞቻቸውን ከቻይና ማስወጣት መጀመራቸውን ገልጸዋል። ውሃን የቻይና ሰባተኛ ትልቋ ከተማ እና ዋነኛ የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያዎች መቀመጫ ናት። ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ
ውሃን ከተማ ከተማ የቻይና ስንተኛ ትልቋ ከተማ ናት?
ሰባተኛ
670
ዓለማየሁ ቴዎድሮስ ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የወይዘሮ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ ነበር። በ1860 ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት ጦርነት ልጃቸው ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝ ሀገር ተወስዶ ነበር፡፡ ልዑል አለማየሁ ሚያዚያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ነበር ውልደቱ፡፡ በልዑሉ ውልደት የተደሰቱት አፄ ቴዎድሮስም በእለቱ መድፍ ያስተኮሱ ሲሆን 500 ያህል እስረኞችንም ፈትተዋል፡፡ ልዑል አለማየሁ እንግሊዞች እጅ ከገባ በኋላ ከእድሜው ለጋነት የተነሳ የሚጠብቀው እና የሚንከባከበው ሰው ሊኖር ግድ ነበር፡፡ ይህንን የተረዳው ጀነራል ናፔር ካፕቴን ስፒዲ የተባለን ሰው የአለማየሁ ጠባቂ እንዲሆን መደበው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ካፕቴኑ የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገሩ ነበር፡፡ በተጨማሪም አለቃ ዝርዓት እና አቶ ገብረመድህን የተባሉ ሁለት ኢትዮጵዊያን ሞዚቶች እና አጫዋቾች ተመረጡለት፡፡ አለማየሁ ከጠባቂው ስፒዲ ጋር ፌሬዝ በተባለችው መርከብ ተሳፍሮ በ1860 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ አቀና፡፡ በመርከቢቱ ላይ በነበራቸውም ቆይታ ስፒዲ እና አለማሁ እጅግ የጠበቀ ወዳጅነትን መስርተው ነበር፡፡ ስፒዲ በሄደበት ቦታ ሁሉ አለማየሁን ማስከተል ያዘወትር ነበር፡፡ ይህንን የሁለቱን ፍቅር ያየው ጀነራል ናፒየርም ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ይልቁንም የአለማየሁን ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ካፕቴን ስፒዲ እንዲረከብ ስለወሰነ ሁለቱ ሞግዚቶች ጉዞው ተጠናቆ እንግሊዝ ሀገር ሳይደርሱ ከስዊዝ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ፡፡ ከሶስት ወራት የመርከብ ላይ ጉዞ በኃላ አለማየሁ እንግሊዝ ሀገር ደረሰ፡፡
ልዑል አለማየሁን እንዲጠብቀው የተመደበው ሰው ማን ይባላል?
ካፕቴን ስፒዲ
377
የቅኝ ግዛት ጊዜ በ1648 እ.ኤ.ኣ. ፓርቱጋል ሏንዳን እንደገና ተቆጣጠረች። በ1650 እ.ኤ.አ. ደግሞ የተነጠቀችውን መሬት እንዳለ አስመለስች። በ1671 እ.ኤ.አ. ፑንጎ አንዶንጎ የሚባለው ቦታ ወደ ፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ተጨመረ። ፖርቱጋል በ1670 እ.ኤ.አ. ኮንጎን እና በ1681 እ.ኤ.አ. ማታምባን ለመውረር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። በ1885 እ.ኤ.አ. የበርሊን ጉባኤ የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት ድንበርን ከወሰነ በኋላ፣ በብሪታኒያ እና ፖርቱጋል ጥረት በኩል የባቡር-መንገድ፣ እርሻና ማዕድን ተሻሻሉ። እስከ ፳ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በፖርቱጋል አልተመራም ነበር። በ1951 እ.ኤ.አ. ቅኝ ግዛቱ የባህር ማዶ ክፍለ-ሀገር ሆኖ ፖርቱጊዝ ምዕራብ አፍሪካ ተባለ። ፖርቱጋል አካባቢውን ወደ አምስት መቶ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ተቆጣጥራለች። ስለዚህም የአካባቢው ሕዝብ ነጻነት ለመውጣት ያለው ስሜት የተደበላለቀ ነበር። ነፃነትና የእርስ በርስ ጦርነት አንጎላ ነጻነቷን በኅዳር ፲፱፻፷፰ ከተቀዳጀች በኋላ ግን ለብዙ አሥርተ ዓመታት የሚቀጥል የእርስ በርስ ጦርነት ገጠማት። ይህ ውጊያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞትና ስደት አብቅቷል። ከአልቮር ስምምነት በኋላ ሶስቱ ትልቅ የትግል ግንባሮች የሽግግር መንግሥትን ለማቋቋም በጃኑዋሪ 1975 እ.ኤ.አ. ተስማሙ። ነገር ግን በሁለት ወራት ውስጥ እነዚህ ግንባሮች ወደ ውጊያ ተመልሰው አገሯ ወደ ክፍፍል እያመራች ነበር። በዚህ ወቅት የቀዝቃዛው ጦርነት ኃያል አገራት የነበሩት የሶቭየት ሕብረትና አሜሪካ አንዱን ወይም ሌላውን ወገን ደግፈው ወደ ጦርነቱ ገብተዋል። ሌሎችም እንደ ፖርቱጋል፣ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪካና ኩባ የመሳሰሉት ሀገራትም ከማገዝ ወደ ኋላ አላሉም። ፖለቲካ የአንጎላ የሕግ አስፈፃሚ አካል ፕሬዝዳንቱን፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱንና የሚኒስትሮች ምክር ቤቱን ያጠቃልላል። ለብዙ ዓመታት አብዛኛው ሥልጣን በፕሬዝዳንቱ እጅ ነው ያተኮረው። የ፲፰ቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። የ1992 እ.ኤ.አ. ሕገ መንግሥት የመንግሥቱን አወቃቀርና የዜጎችን መብቶችና ግዴታዎች ይዘረዝራል። የሀገሩ ሕግ ተርጓሚ አካል የፖርቱጋል ሥርዓትን ይከተላል። ጦር ኃይል የአንጎላ ጦር ኃይሎች በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ሲሆኑ በሦስት ይከፈላሉ። እነዚህም ምድር ኃይል፣ ባህር ኃይል እና አየር ኃይል ናቸው። የሀገሩ ጠቅላላ ሠራዊት ፻፲ ሺህ ይሆናል። የጦር ኃይሉ ንብረቶች መካከል በሩሲያ የተሰሩ ተዋጊ፣ ቦምብ ጣይና አጓጓዥ አውሮፕላኖች ይገኛሉ። አንዳንድ የጦር ኃይሉ ክፍሎች በኮንጎ ኪንሻሳና ኮንጎ ብራዛቪል ተመድበዋል።
ከአልቮር ስምምነት በኋላ ሦስቱ የአንጎላ የትግል ቡድኖች መች ነበር የሽግግር መንግስት ለማቋቋም የወሰኑት?
በጃኑዋሪ 1975 እ.ኤ.አ.
724
የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል። ውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ። ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል። ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል።
ውለታ ለማ (ዶ/ር) ያሸነፉበት በህክምናው ዘርፍ ያለውን የወረቀት ሥራ ዲጂታል ለማድረግ የሚያስችል የሥራ ፈጠራቸው ምን ይባላል?
አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR)
448
ጣና ሐይቅ ጣና ሐይቅ ቅዱሱ ሐይቅም ይባላል። ከኢትዮጵያ አንደኛ እና ትልቁ ሐይቅ ነው። 84 ከ.ሜ. ረጅም እና 66 ኪ.ሜ. ሰፊ ነው። ባጠቃላይ 3,500 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል። በቁጥር ከ35 በላይ ደሴቶች በሐይቁ ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥም 22ቱ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት ናቸው። ባንዳንዶቹ ላይም (ለምሳሌ በዳጋ ደሴት) የድሮ የኢትዮጵያ መሪዎች መቃብሮች ሲገኙ ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትናን ለመጀመሪያ ያስተዋወቀው አቡነ ሰላማ መቃብርም በዚሁ ሃይቅ ይገኛሉ። የጣና ሃይቅን የሚመግቡ 3ቱ ዋና ወንዞች ርብ፣ ጉማራ ወንዝ ና ትንሹ አባይ በመባል ይታወቃሉ። አሁን ባለው ይዞታ የጣና ሃይቅ 1,454 ቶን አሳ በአመት ይመረታል። ነገር ግን ይሄ የምርት ሃይቁ ያለምንም ችግር ሊያስተናግድው ከሚችለው 15 በመቶው ያህል ብቻ ነው።
የጣና ሐይቅ ርዝመት ምን ያህል ነው?
84 ከ.ሜ.
56
ፕሮፌሰር ሙሃመድ ዩኑስ ትውልድ በ28 ጁን 1940 እ.ኤ.አ. የባንግላዴሽ የባንክ ባለሞያና ኤኮኖሚስት ናችው። ማይክሮክሬዲት ተብሎ የሚታወቀውን የአነስተኛ የብድር አገልግሎት በችግር ለሚኖሩ ወገኖች የመስጠትን ስራ የጀመሩትና የስፋፉት ሰው ናችው። ፕሮፌሰሩ እንነኝህ ባንክ አላስተናግድ ብሎ የተዋቸውን ድሆች የሚያገለግለውን ግራሚን ባንክን አቋቁመዋል። በጥቅምት 1999 ፕሮፈሠሩና ባንኩ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ለመሆነ በቅተዋል ይህም ሽልማት የልማት እድገትና ማህበረሰባዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በማስመስከራቸውና ይህ ደግሞ ለሰላም ወሳኝነት ያለው መሆኑን ሽልማት ሰጭው ኮሚቴ ስላመነበት ነው። ፕሮፌሰር የበርካታ ሽልማቶች ባለቤት ሲሆኑ ከነዚህም የአለም የምግብ ሽልማት ይገኝበታል። የድሆች አበዳሪ በሚል ርዕስ አንድ የስራሳቸውንና የስራቸውን ታሪክ የሚያትት መጽሐፍ ደርሰዋል።
ማይክሮክሬዲት የተሰኘውን የአነስተኛ የብድር አገልግሎት ተቋም በችግር ለሚኖሩ ወገኖች የመስጠትን ስራ የጀመሩና ያስፋፉ ፕሮፌሰር ማን ይባላሉ?
ፕሮፌሰር ሙሃመድ ዩኑስ
0
ዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።
በ1981 ዓ.ም. ንጉሥ ሌቤንጉላ የማዕድን ማውጣት ፈቃድ ለሴሲል ሮድስ መስጠቱ ቦታው በማን ቅኝ እንዲገዛ አደረገ?
በብሪታኒያ
936
የቻይና ስነ ፈለክ ተመራማሪዎች የመጀመሪዋን ከፀሀይ ስርዓት ውጪ የሆች ኤክሶፕላኔት ማግኘታቸው ተገለፀ። በቻይና የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች የተገኘችው ይህች ፕላኔት  “ወንግሹ” እና “ዢሂ” የሚል ስያሜ ተሰቷታል። ይህም ማለት የጨረቃ አምላክ ወይም የጸሃይ አምላክ የሚል ትርጉም አለው። ሁለቱ ስሞች የሚያሳዩት የኮኮብ እና ፕላኔትን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ዩንቨርስን የማሳስ ሂደት የሚወክል ወይም ምሳሌ የሚሆን ነው ተብሏል። የፕላኔትዋ መጠን ከፀሐይ ሁለት እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን፥ ከጁፒተርም በ2 ነጥብ 7 እጥፍ ትበልጣለች፤ በዚህም ከጸሃይ ስርዓት ውስጥ ትልቋ ነው የተባለችው በብሔራዊ የሥነ ፈለክ ምርምር ተቋም። የቻይና የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች በአውሮፓውያኑ በ2008 ከቻይና 10 ምርጥ የሥነ ፈለክ እድገቶች መካከል አንዱ ሆነው የተመረጡት ትልቁን ኤክስፕላኔት HD173416b’ን አገኝታለች። ምንጭ፡-ሲጂቲኤን በፌቨን ቢሻው
የቻይና ስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ያገኟት ኤክሶፕላኔት መጠን ከጁፒተር ምን ያህል ይበልጣል?
በ2 ነጥብ 7 እጥፍ
309
ሳምሱ-ዲታና ሳምሱ-ዲታና ከ1538 እስከ 1507 ዓክልበ. ('ኡልትራ አጭሩ' አቆጣጠር) ድረስ የባቢሎን ንጉሥ ነበር። የአሚ-ሳዱቃ ልጅና ወራሽ ሲሆን፣ ሳምሱ-ዲታና የባቢሎን (የሃሙራቢ ሥርወ መንግሥት) መጨረሻ ንጉሥ ነበረ። የዘመኑ አመት ስሞች ምንም ዘመቻ ስለማይጠቅሱ ሰላማዊ ዘመን ይመስል ነበር፣ ወደ ደቡቡ ግን የባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ጉልኪሻር ከሳምሱ-ዲታና ጋር እንደ ታገለ በአንድ ታሪክ ጽላት ተቀረጸ። በ1507 ዓክልበ. የሐቲ (ኬጥያውያን) ንጉሥ 1 ሙርሲሊ እስከ ባቢሎን ድረስ ዘመተና ከተማውን ዘርፎ አቃጠለው። የኬጥያውያን ሠራዊት የባቢሎን ምስሎች (ጣኦታት) ወደ ሐቲ አገር ወሰዱ፤ ሳምሱ-ዲታናም እንደ ተገደለ ይመስላል። ይህ የሚታወቀው ከባቢሎን ዜና መዋዕል «በሳምሱ-ዲታና ዘመን፣ ኬጥያውያን ወደ አካድ መጡ» ሲዘገብ፣ ደግሞ በኬጥኛ የተለፒኑ ዜና መዋዕል እንደሚለው «እርሱ (ሙርሲሊ) ወደ ሐላብ ሔዶ አጠፋው፤ የሐላብን ምርኮ ወደ ሐቱሻ ወሰደ፤ ከዚያም እስከ ባቢሎን ድረስ ሔዶ አጠፋው፣ ሑራውያንንም አሸነፋቸው፣ የባቢሎንን ምርኮ ወደ ሐቱሻ ወሰደው።»
የሃሙራቢ ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ንጉሥ ማን ነበር?
ሳምሱ-ዲታና
97
አሪዞና አሪዞና (Arizona) በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ክፍላገር ነው። ኒው ሜክሲኮ ፣ ዩታህ ፣ ኔቫዳ ፣ ካሊፎርኒያ እና ኮሎራዶ ያዋስኑታል። የአሪዞና ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ የ30 ሰው ሴኔት እና የ60 ሰው ምክር-ቤት አለው። የሪፑብሊካን ፓርቲ በስቴቱ ዋነኛው ፓርቲ ነው። በ2002 እ.ኤ.አ. የአሪዞና ስቴት ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ በጀት 14.3 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በጀት ደግሞ 13.8 ቢሊዮን ዶላር ነው። የስቴቱ ሴኔተሮች እና ምክር-ቤት ተወካዮች ለሁለት-ዓመት ጊዜ ላልተወሰነ ብዛት ይመረጣሉ። ከ4 ጊዜ በላይ በተካካይ መመረጥ ግን አይችሉም። የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በአስተዳዳሪ የሚመራ ሲሆን ለ4 ዓመት ሥልጣን ላይ ይቆያል። ያልተወሰነ ጊዜ መወዳደር ሲቻል ከሁለት ጊዜ በላይ ግን በተካካይ መመረጥ አይፈቀድም።
አሪዞና በዩናይትድ ስቴትስ በየት አቅጣጫ የሚገኝ ግዛት ነው?
በምዕራባዊ
20
መስከረም 24 ቀን 2012 የደቡብ ክልልን ሁለንተናዊ መረጃ የያዘ አትላስ እና የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ሥርአት ተመርቀው ለአገልግለት ተዘጋጁ፡፡ በደቡብ ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አማካይነት በአዲስ መልክ ተዘጋጅቶ ትናንት የተመረቀው አትላስ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ዲሞግራፊያዊና መልክአ-ምድራዊ መረጃዎችን አካቶ መያዙ ተገልጿል። የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአቱም (የመረጃ ቋቱ) ላለፉት 10 ተከታታይ ዓመታት የነበሩ ሁለንተናዊ መረጃዎችን በድህረ-ገጽ አማካይነት ለማሰራጨት የሚያስችል ነው፡፡ በምርቃ ሥነ-ሥርዐቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሄለን ደበበ የስታቲስቲክስና መልክዐ-ምድር መረጃ ሥርዐት አስተዳደር የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ከያዛቸው የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የደቡብ ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምራት ዲላ ከዚህ በፊት የነበረው የክልሉን አኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ዲሞግራፊያዊና መልክዐ ምድራዊ መረጃዎችን የያዘ አትላስ ላለፉት 15 ዓመታት ማገልግሉንና በአሁኑ ወቅት ያለውን ሁለንተናዊ የክልሉን እድገት ያካተተ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው አትላስ አስከ 2009 ዓ.ም ያለውን ክልላዊ መረጃ የያዘ እንደሆነ ገልጸው አጠቃላይ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ የተመዘገቡትን ውጤቶች፣ የመሰረተልማት ስርጭቶችን፣ ዴሞግራፊያዊ፣ መልክዐ-ምድራዊና ሌሎች መረጃዎችን ማካተቱን ተናግረዋል ፡፡ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ለዕቅድ መነሻ የሚሆኑ መረጃዎች ታች ካሉ መዋቅሮች ብቻ እንደሚሰበሰቡ ገልፀው ይህም ተአማኒ መረጃ ለማግኘት የሚስቸግር አሰራር እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ይፋ የተደረጉት አትላስና የመረጃ ቋት ይህንን የመረጃ ክፍተት የሚሸፍኑና በቀላሉም ተደራሽ የሚሆኑ በመሆናቸው በፍትሀዊነት ላይ የተመሰረቱ ዕቅዶችን ለማዘጋጀት ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ ብለዋል ፡፡ በምረቃ ሥነ-ሥርዐቱ ላይ የደቡብ ክልል፣ የዞኖችና የልዩ ወረዳዎች አመራሮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ አስተዳደር አካላት ተገኝተዋል፡፡
የደቡብ ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ማን ይባላሉ?
አቶ ታምራት ዲላ
530
ጋና ጋና በአፍሪካ አትላንቲክ ጠረፍ ላይ የተገኘ አገር ሲሆን ከ24 ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉት። የጋና ስራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ሲሆን፣ ሌሎች ኗሪ ቋንቋዎች በተለይም ትዊኛ (አካንኛ) በሰፊ ይነገራሉ። የ«ጋና» ስያሜ በታሪክ የድሮ «ጋና መንግሥት» ወይም «ዋጋዱጉ መንግሥት» ለማክበር በ1949 ዓም ተመረጠ። እንዲያውም ያው መንግሥት እስከ 1068 ዓም ድረስ ከጋና ወደ ስሜን-ምዕራብ በአሁኑ ማሊ ይገኝ ነበር እንጂ የዛሬውን ጋና መቸም አልገዛም። «ጋና» በትክክል የዋጋዱጉ መንግሥት አለቆች ማዕረግ ሆኖ ነበር። ዋጋዱጉ መንግሥት በ1068 ዓም ግድም ከወደቀ ቀጥሎ፣ የአካን ብሔሮች ከዚያው ፈልሰው በዛሬው ጋና ሠፈሩና መጀመርያ ግዛቶችን መሠረቱ። ከ1662 እስከ 1949 ዓም ድረስ የአሻንቲ መንግሥት ባካባቢው ቆየ፤ በ1894 ዓም ይህ የብሪታንያ አሻንቲ ጥብቅ ግዛት ሆነ። ከ1949 ዓም አስቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጥገኛ ግዛት ሲሆን በወርቅ ሀብቱ ምክንያት «የወርቅ ጠረፍ ጥገኛ ግዛት» (ጎልድ ኮስት ፕሮቴክቶሬት) በመባል ይታወቅ ነበር። ከ1984 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እና ፓርላሜንታዊ መንግሥት ኖሮታል። አብዛኞቹ ኗሪዎች (70%) በተለይ በደቡቡ ክርስቲያን ሲሆኑ፣ በተለይ በስሜኑ 16% የእስልምና ተከታዮች ናቸው። የተረፉትም የኗሪ አረመኔነትን እምነቶች ይከተላሉ። የጋና ዋና ምርቶች ካካዎ፣ ዘይት፣ አልማዝ ናቸው። በአለሙ ከሁሉ ትልቅ የሆነው ሠው ሰራሽ ሐይቅ፣ ቮልታ ሐይቅ፣ በጋና ይገኛል። እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው። የጋና አበሳሰል በተለይ በኮቤ፣ ጐርጠብ፣ የስኳር ድንች፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ኦቾሎኒ፣ ባሚያና ሩዝ ይሠራል።
በጋና ብሔራዊ ቋንቋ ባይሆንም በስፋት የሚነገረው ምንድን ነው?
ትዊኛ (አካንኛ)
104
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2012(ኤፍ ቢሲ) አሜሪካ የሁዋዌ የአምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን (5G) መጠቀም እብደት ነው ስትል ብሪታኒያን አስጠነቀቀች፡፡ አሜሪካ  የቻይና ኩባንያዎች አገልግሎት መጠቀም ሊያስከትል የሚችለውን የደህንነት ስጋት የሚያሳይ  አዲስ ማስረጃ ለብሪታኒያ አቅርባለች፡፡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጉዳዩ ዙሪያ በሀገሪቱ  ጠቅላይ  ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ላይ ጫና ለማሳደር እንደሚፈልጉ ተጠቁሟል፡፡ በዚህ ወር ሁዋዌ ኩባንያ ለብሪታኒያ የኔትወርክ ዝርጋት አንዳንድ “መሠረታዊ ያልሆኑ” ክፍሎችን ያቀርብ አያቅርብ የሚል ውሳኔ ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሁዋዌ ቃል አቀባይ ባለፉት 15 ዓመታት ለብሪታኒያ የ3ጂ ፣ 4ጂ እና ብሮድባንድ መሳሪያዎችን  ሲያቀርብ የቆየ የግል ኩባንያ መሆኑን በመግለፅ በዚህም የሃገሪቱ ባለሙያዎች ቴክኖሎጂያቸው የደህንነት ስጋት እንደማያመጣ ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል፡፡ አሜሪካ ባለፈው ዓመት በደህንነት ስጋት ምክንያት ለሁዋዌ እና 68 ተዛማጅ ኩባንያዎች የቴክኖሎጂና ሌሎች መሳሪያዎችን እንዳይሸጡ ገደብ መጣሏ የሚታወስ ነው፡፡ ምንጭ፡-ቢቢሲ
አሜሪካ የሁዋዌን አምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን እንዳትጠቀም ያስጠነቀቀቻት አውሮፓዊ ሀገር ማን ናት?
ብሪታኒያን
78
ቲቪ በ1950ዎቹ እንደ ብርቅ በሚታይበት ዘመን በ1957 አ.ም ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተከፈተ፡፡ ታዲያ የመጀመሪያዋ የቲቪ ሴት አንባቢ የነበሩት ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ወልደስላሴ ነበሩ፡፡ ይህ ለወይዘሮ እሌኒ ትልቅ የታሪክ አጋጣሚ ነበር፡፡ በወቅቱ ሳሙኤል ፈረንጅ አንዱ ወንድ ተናጋሪ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ሬድዮ በጋዜጠኝነቱና በህዝብ ግንኙነት ሙያ ያገለገሉት ወይዘሮ እሌኒ ከሰው ጋር በቀላሉ የሚግባቡ ተወዳጅ ደግ እናት ነበሩ፡፡ በበጎ አድራጎት ምግባራቸው በስፋት የሚታወቁት ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ወልደስላሴ የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር ውስጥ በንቃት በመሳተፍ ማህበሩን ረድተዋል፡፡ በተጨማሪም በአንሚ ሬድዮ ከ20 አመት በፊት ያገለገሉት ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ወልደስላሴ ከአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋር የጠበቀ ቁርኝት ነበራቸው፡፡ ከዚህም ባሻገር አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ወደ ሀገራችን በሚመጡበት ጊዜ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ስራ ላይ ትልቅ ሚና አበርክተዋል፡፡ ቤታቸው ሲኬድ ሁልጊዜም ከአረንጓዴ ተክል ጋር የማይታጡት ወይዘሮ እሌኒ ነፋሻማ ቦታ ልዩ ትርጉም ይሰጣቸዋል፡፡ አንድ ከዛፍ ጋር በተያያዘ በፎቶግራፍ የታገዘ መጽሀፍም ለህትመት አብቅተዋል፡፡ በዚህም መጽሀፍ አማካይነት ስለ ሀገራችን ዛፎች በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሙከራ አድርገዋል፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ የተለያዩ ሀገሮችን ቴምብሮችን ያሰባስባሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ለታሪክ ልዩ ፍቅር ያላቸው ወይዘሮ እሌኒ የጡረታ ጊዜያቸውን በማንበብ እና በምርምር ያሳልፉ ነበር፡፡ ወይዘሮ እሌኒ በ1959 አመተ ምህረት ከኢንጂነር ሰይፉ ለማ ጋር ጋብቻን መስርተው 3 ሴት ልጆችን ወልደው አንድ ልጅ ደግሞ አሳድገዋል፡፡ ወይዘሮ እሌኒ በተወለዱ በ79 አመታቸው ሮብ ሀምሌ 14 2013 ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን የቀብር ስነስርአታቸውም ሀሙስ ሀምሌ 15 2013 ከቀኑ በ6 ሰአት በየካ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡
የወ/ሮ እሌኒ ስርአተ ቀብርራቸው በየት ተፈፀመ?
በየካ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን
1,050
ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በአዲስ አበባ ከተማ በደቡብ-ምሥራቅ አቅጣጫ ከአራዳ በስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የአገሪቱ ዋና አድማሳዊ የንግድና የግንኙነት በር ነው። አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ መግባት የጀመሩት በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ በጃን ሜዳ እና አቃቂ ያርፉ እንደነበር በታሪክ ተዘግቧል። የመጀመሪያው ቋሚ የአውሮፕላን ጣቢያ ግን የተሠራው በአምሥቱ የፋሺስት ዘመናት ሲሆን የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ/ም አክሱም አካባቢ ላይ ከነጥያራው ተከስክሶ በሞተው አብራሪያቸው፣ “ኢቮ ኦሊቬቲ” ስም ሠይመውት የነበረው የልደታ የጥያራ ጣቢያ ነው። በዚሁ በፋሺስት ወረራ ዘመን ‘አላ ሊቶሪያ’ የተሰኘው ኩባንያ በአገር ውስጥ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ነገሌን፤ ሞቃዲሾን፤ ድሬ ዳዋን፤ ጎራኄን፤ ጂቡቲን፤ አሰብን፤ ጂማን፣ ጋምቤላን ደምቢ ዶሎን፤ ጎንደርን አስመራን፤ ደሴን፤ ለቀምትን እና አሶሳን የሚያገለግሉ የበረራ መሥመሮች ሲኖረው ከአድማስ ባሻገር ደግሞ ከተማዋን በካርቱም፣ ዋዲ ሃይፋ፤ ካይሮ፣ ቤንጋዚ እና ሲራኩሳ አድርጎ ከሮማ ጋር የሚያገናኝ የበረራ መሥመርም ነበረው። ከድል ወዲህ ልደታ አውሮፕላን ጣቢያ፤ የብሪታኒያ ጦር ኃይሎች ሲገለገሉበት ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታኅሣሥ ፳፩ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ሲመሠረት ዋና ጣቢያው እዚያው ነበር። ዳሩ ግን የአየር መንገዱ አገልግሎት እየተስፋፋ ሲመጣና ትላልቅ ጄት አውሮፕላኖች እንደሚያስፈልጉት ግልጽ ሲሆን፣ የልደታ አየር ጣቢያ ብቃት እንደሌለው እና ለጄት አየር ዠበቦችም ማሳረፊያ የማይስማማ መሆኑ ታምኖበት የአማራጭ ሥፍራ ፍለጋ ተጀመረ። የአዲሱንም አየር ጣቢያ ዝርዝር ጥናት እንዲያዘጋጅ ውሉ ለአሜሪካዊው ‘አማን እና ዊትኒ’ ኩባንያ ተሰጥቶ፤ ጥናቱ በ፲፱፻፶ ዓ/ም ተገባዶ አማራጩ ሥፍራ ቦሌ እንዲሆን ተወሰነ። የአየር ጣቢያውን የግንባታ ወጪ ከአሜሪካዊው ‘ኤክስፖርት-ኢምፖርት’ ባንክ በተገኘ ብድር ተሸፍኖ ሥራው ተጀመረ። ጠቅላላ ግንባታው ተጠናቆ ሲያልቅ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓ/ም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተብሎ፣ በንጉሠ ነገሥቱ ተመርቆ ተከፈተ።
የመጀመሪያው ቋሚ የአውሮፕላን ጣቢያ የተሠራው የት ነው?
የልደታ የጥያራ ጣቢያ
375
የትነበርሽ ንጉሴ የትነበርሽ ንጉሴ በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ እና የአካል ጉዳተኛ መብትቶች ተሟጋች ናት ፡ እ.ኤ.አ በ 2017 "የአካል ጉዳተኞችን መብቶችን እና ማካተቶችን በማስተዋወቅ እንዲሁም  በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉየአእምሮ ውቅርን መለወጥ የሚያበረታታ ሥራዋ"  ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድን ተሸልማለች። የትነበርሽ ንጉሴ የአይን ብርሃኗን ያጣችው በ 5 ዓመቷ ነበር ። ይህ አጋጣሚ በተወለድችበት በአማራ ክልል በስፋት ይተገበር ከነበረው ያለ አድሜ ጋብቻ  አንድታመልጥ እድሉን እንደፈጠረላት ትናገራለች። ፡፡የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሻሸመኔ ካቶሊክ የዓይነ ስውራን  ት/ቤት ተከታትላ ወደ ዳግማዊ  ምኒልክ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (አካታች ትምህርት ቤት) ገብታ እስከ 12 ኛ ክፍል እዚያ ተማረች። በትምህርት ቤቱ ካላት አካዳሚክ ተሳትፎ በተጨማሪ የተማሪዎችን አማካሪ ጨምሮ ከ 6 በላይ የክለቦችን ክበባት መርታለች ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በመቀላቀል የመጀመሪያ ዲግሪ በሕግ ሁለተኛ ዲግሪ በማኅበራዊ ሥራ አግኝ ታለች፡፡ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ  በልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በተከታታይ  ትሳተፋለች በዚህም  የመኢአድ የፀረ ኤድስ እንቅስቃሴን ከ2004 - 05 በመምራት በ 2006 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (አአዩ) ሴት ተማሪዎች ማህበርን በመመስረት እንዲሁም የማህበሩ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት በመሆን  አገልግላለች ፡፡
የትነበርሽ ንጉሴ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን የት ተከታተለች?
በሻሸመኔ ካቶሊክ የዓይነ ስውራን  ት/ቤት
339
አዲስ አበባ መስከረም 15/2012 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሰራተኞቹ ጋር በሬድዬ ግንኙነት በመፍጠር አገልግሎቱን የሚያቀላጥፍበት የአስትሮ ሞቶሮላ የሬድዬ ኮሙኒኬሽን ፕሮጀክት አስመረቀ። የፕሮጀክቱ ምረቃ ስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር በተገኙበት በእንጦጦ ማሪያም የቴሌ ማይክሮዌቭ ማሰራጭያ ጣቢያ ተካሂዷል። በሁለት ምዕራፍ የተከፈለውን ፕሮጀክት ወደ ሥራ ለማስገባት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ሐምሌ 15 /2017 በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና በሞቶሮላ ሶሉሽን ኩባንያ መካከል ስምምነት ተፈርሞ ነበር። የመጀመሪያው ምዕራፍ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን በአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ኦሮሚያ ዞን ላይ ተግባራዊ ሆኗል። የኤሌክትሪክ የአገልግሎት አሰራሩን በማቀላጠፍ ለዜጎች የተሻለ አገልግሎት እንደሚሰጥ የታመነበት ይሄው ፕሮጀክት 6 ቡድኖችን በመያዝ በ 8 የግንኙነት ቻናሎች በጋራ እና በእኩል ሁኔታ እንዲጠቀሙ የሚያግዝ ነውም ተብሏል። የአስቸኳይ ጥገና ሥራን ማቀላጠፍ፣ ከሰብ ስቴሽን ጋር የሚኖረውን ግኝኑነት ማሳለጥ፣ በግንኙነት ክፍተት ሊፈጠሩ የሚችሉ የሰውና የንብረት አደጋን መቀነስ እንዲሁም የኃላፊዎችን መረጃ የመቀበልና መልዕክት የማስተላለፍ ሥራውን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተገልጿል። በኤሌክትሪክ አገልግሎት የአውቶሜሽንና ኢነርጂ ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ደመቀ ሮቢ አገልግሎቱ ስራውን የሚያከናውነው በስልክ እንደነበር አስታውሰው ይህም የሚሰጠው አገልግሎት ቅልጥፍና እንዳይኖረው አድርጎት ቆይቷል ይላሉ። ዛሬ የተመረቀው የሬድዮ ኮሙኒኬሽን ፕሮጀክት መስክ የወጡ የጥገና ሰራተኞች ቢሮ ካሉ ሰራተኞች ጋር በፍጥነት እንዲገናኙ ከማድረጉም ባለፈ ከፍተኛና ዝቅተኛ ኃይል መስመር ላይ ካሉ ኦፕሬተሮች ጋርም በቀላሉ በመገናኘት ፍጥነት ያለው የጥገና አገልግሎቶች እንዲሰጡ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል። በዚሁ የመጀመሪያው ምዕራፍም በአዲስ አበባና ዙሪያ በእጅ የሚያዙ 300 እንዲሁም 200 መኪና ላይ የሚገጠሙና 100 በጥሪ ማዕከልና በአስቸኳይ ጥገና ማዕከላት ላይ የሚገጠሙ ዲጂታል ሬዲዮኖች ጥቅም ላይ ውለዋል። እንደ አቶ ደመቀ ገለጻ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክቱንም ለማካሄድ ከአዲስ አበባ ውጪ 8 ከተሞች የተመረጡ ሲሆን ለዚህም ከ4 ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት ተይዞለታል።
በኤሌክትሪክ አገልግሎት የአውቶሜሽንና ኢነርጂ ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማን ይባላሉ?
ደመቀ ሮቢ
822
ፕሮፌሰር ሙሃመድ ዩኑስ ትውልድ በ28 ጁን 1940 እ.ኤ.አ. የባንግላዴሽ የባንክ ባለሞያና ኤኮኖሚስት ናችው። ማይክሮክሬዲት ተብሎ የሚታወቀውን የአነስተኛ የብድር አገልግሎት በችግር ለሚኖሩ ወገኖች የመስጠትን ስራ የጀመሩትና የስፋፉት ሰው ናችው። ፕሮፌሰሩ እንነኝህ ባንክ አላስተናግድ ብሎ የተዋቸውን ድሆች የሚያገለግለውን ግራሚን ባንክን አቋቁመዋል። በጥቅምት 1999 ፕሮፈሠሩና ባንኩ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ለመሆነ በቅተዋል ይህም ሽልማት የልማት እድገትና ማህበረሰባዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በማስመስከራቸውና ይህ ደግሞ ለሰላም ወሳኝነት ያለው መሆኑን ሽልማት ሰጭው ኮሚቴ ስላመነበት ነው። ፕሮፌሰር የበርካታ ሽልማቶች ባለቤት ሲሆኑ ከነዚህም የአለም የምግብ ሽልማት ይገኝበታል። የድሆች አበዳሪ በሚል ርዕስ አንድ የስራሳቸውንና የስራቸውን ታሪክ የሚያትት መጽሐፍ ደርሰዋል።
በፕሮፌሰር ሙሃመድ ዩኑስ የስራሳቸውንና የስራቸውን ታሪክ የሚያትት የተጻፈው የመፅሐፍ ርዕስ ምን ይባላል?
የድሆች አበዳሪ
432
ግሥላ ግሥላ በእስያ፣ በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ) እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኝ አጥቢ አውሬ ነው። በእስያ የተገኘው ነብር የግስላ ቅርብ ዘመድ ሆኖ፣ በአነጋገር «ግስላ»ና «ነብር» የሚሉ ስሞች ሊለዋወጡ ይችላሉ። የአንድ ጎልማሳ ግሥላ ክብደት ከ35 እስከ 80 ኪ.ግ ሲደርስ በርዝመት ከ90 ሴ.ሜ እስከ 1,60 ሜ.ና በአፍሪካ የሚገኘው ዘር እስከ 1,90 ሜ ይደርሳል ። ከመሬት እስከ ሆዱ ከ50 እስከ 70 ሴ.ሜ ቁመት ሲኖረው ጭራው ደግሞ እስከ 100 ሴ.ሜ ርዝማኔ ያሳያል ። ሴቲቱ ከወንዱ አነስ ትላለች ። በዱር ሲኖር እስከ 10 አመት እንደሚኖር ሲታወቅ በሰው ተይዘው ሲኖሩ እስከ 20 አመት እድሜ ያስመዘገቡ ግሥሎች አሉ።
ግስላ በሰው ተይዘው በእንክብካቤ ሲኖሩ ለምን ያህ፤ ጊዜ ይኖራሉ?
20 አመት እድሜ
371
መልከአ-ምድር አንጎላ፣ በ1,246,620 ካሬ ኪ.ሜ. ከኒጄር ቀጥላ ከዓለም 23ኛው ትልቅ አገር ናት። በስፋት ከማሊ ጋር ትነጻጸራለች። የአሜሪካ የቴክሳስ ክፍላገርን ሁለት ዕጥፍ ታክላለች። አንጎላ ከደቡብ በናሚቢያ፣ ከምሥራቅ በዛምቢያ፣ ከሰሜን-ምሥራቅ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ከምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች። የአንጎላ አማካይ የባህድ ዳር የአየር ሁኔታ በክረምት 16° ሴንቲግሬድና በበጋ 21° ሴንቲግሬድ ነው። አንጎላ ሁለት ወቅቶች አሏት። እነዚህም ደረቅና ዝናባማ ናቸው። መጓጓዣ በአንድ ላይ ርዝመታቸው 2,761 ኪ.ሜ. የሆኑ ሦስት የባቡር መንገዶች፤ 76,626 ኪ.ሜ. አውራ ጎዳና ከዚህም ውስጥ 19,156 ኪ.ሜ. አስፋልት፤ 1,295 ኪ.ሜ. የውሃ መንገድስምንት ትልቅ ወደቦች፤ 243 የአውሮፕላን ማረፊያዎች ከነዚህም 32ቱ የአስፋልት መንደርደሪያ ያላቸው፤ አንጎላ የሰፋ የመጓጓዛ አውታር ቢኖራትም በጊዜ ማለፍና ጦርነት ምክንያት መንገዶች አስፈላጊ ጥገኛ አልተደረገባቸውም። በአንዳንድ ቦታዎች አሽከርካሪዎች መጥፎ ቦታዎችን ለማለፍ ሲሉ ከመንገድ ውጭ ይነዳሉ። እንደዚህ ከማድረግ በፊት ግን በመንገድ ዳር ያሉ በመሬት ውስጥ ስለተቀበሩ ፈንጂዎች የሚያስጠነቅቁ ምልክቶችን ማስተዋል ያስፈልጋል። ኢኮኖሚ የአንጎላ ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ አሳይቷል። የሩብ ምእተ ዓመት ጦርነት ያሳደረበት ተጽእኖን አልፎ ዛሬ በዓለም ውስጥ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ይመደባል። በ2004 እ.ኤ.አ. የቻይና ኤክሲምባንክ ፪ ቢሊዮን ብር ለአንጎላ አበድሯል። ይህ ገንዘብ እንደ መንገዶች ያሉትን የአንጎላ መሠረታዊ ተቋሞች ለማሻሻል የሚውል ነው። ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት በ2008 እ.ኤ.አ. እንደዘገበው ነዳጅና ዕንቁ የአንጎላ ዋና ኤክስፖርቶችና የገቢ ምንጮች ናቸው።
አንጎላ በቆዳ ስፋት ከዓለም ስንተኛ ናት?
23ኛ
48
ድረ ገጽ መረብ የድረ ገጽ መረብ (ወይም ኢንተርኔት) በጣም ብዙ የኮምፒዩተር አውታሮችን የያዘ የመገናኛ መረብ ነው። በመረቡ ውስጥ ብዙ ድረ ገጽ ይገኛሉ። ከዚያ በላይ በርካታ የመነጋገርና መገናኘት መንገዶች አሉ። ከሁሉ አስቀድሞ የተፈጠረ ክፍለ-ኢንተርኔት «USENET» የሚባለው አገልግሎት ነው። ይህ በ1973 ዓ.ም. (1980 እ.ኤ.አ.) አካባቢ ሲጀመር በተለይ ለዩኒቨርሲቴዎችና ኮሌጆች ብቻ የታወቀ መገናኛ ሆኖ ቆየ። ይህ ጽሑፍ በተገናኙት ኮምፒውተሮች ላይ መልጠፍ የሚፈቅድ ሥርዓት ብቻ እንጂ ስዕል ወይም ሌላ ነገር አልነበረም። መጀመርያው e-mail አድራሳዎች የተሰጡት ከዚያ ዘመን ነው። ዛሬም ብዙዎች ተጠቃሚዎቹ ግን ስንኳ ስለ USENET መኖሩን አያውቁም። መጀመርያው ድረ ገጽ የተፈጠረው በ1983 ዓ.ም. (1990 እ.ኤ.አ.) ሆነ።
እ.ኤ.አ. በ1980 ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች እንደ መገናኛ ዘዴ የተቀሙበት ነገር ምን ነበር?
ክፍለ-ኢንተርኔት
151
በማደግ ላይ ባሉ አገራት የሚኖሩ ህዝቦች ግንባር ቀደም ገዳይ ከሚባሉት በሽታዎች አንዱ የሆነውን የቲቢ በሽታ ለማስቆም የሚያስችል ”EndTB” የተሰኘ ንቅናቄ ተካሄደ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባለፈው ረቡዕ በሒልተን ሆቴል በይፋ ያስጀመረው ቲቢን እናስቁም ንቅናቄ እ.ኤ.አ በ2032 በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ከ100 ሺህ አስር ብቻ ለማድረስ የታለመ ነው፡፡ ከአዳሱ የፈረንጆች ዓመት እስከ 2032 ዓ.ም ይደረጋል በተባለው በዚሁ “ቲቢን እናስቁም” ንቅናቄ፤ አገራት ሁሉ፤ ተሳታፊ በመሆን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ያለውን የቲቢ በሽታ ለመግታትና በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ በትጋት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡ በሒልተን ሆቴል በተካሄደው ፕሮግራም ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት የግሎባል ቲቢ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር ማርዮ ራቨግሊዮን እንደገለፁት፤ በሽታው በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ስርጭት 133 ሰዎች ከ100 ሺህ ሰዎች ሲሆን በኢትዮጵያ ቁጥሩ 200 ሰዎች ከ100 ሺህ ሰዎች ይደርሳል ብለዋል፡፡ በሽታውን ለማስቆም በተያዘው ዕቅድ መሰረትም፤ እ.ኤ.አ ከ2016-2032 ዓ.ም ድረስ በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ከ100ሺ አስር ለማድረስ መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡ ዕቅዱ እንዲሳካም አገራት ከፍተኛ ሥራ እንደሚጠበቅባቸውና ለተግባራዊነቱም የመንግስታቱን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የቲቢ በሽታ በኢትዮጵያ ያለው ስርጭት ምን ያህል ነው?
200 ሰዎች ከ100 ሺህ ሰዎች
568
ዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።
የሮዴዢያን ግዛት ከኢያን ስሚዝ መንግሥት ነጻነቷን ያገኘችው መቼ ነበር?
በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ.
1,602
አዲስ አበባ መስከረም 23/2012 ዕውቁና አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ በውጭ አገራት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ሳይንቲስቶች ወጣቶችን በሳይንስ በማነጽ ተግባር እንዲሰማሩ፤ መንግስትም ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰር ጥላሁን በቻይና ከሚገኙ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ የአፍሪካ ሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል ሊያቋቁሙ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካው ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ዕውቁ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሚዘጋጀው ወርኃዊ የሳይንስ ገለጻ መድረክ ወጣቱን ትውልድ ማስተማርና ማነጽ ለኢትዮጵያ ተስፋ፤ የቻይና ተምሳሌትነት በሚል ትናንት ምሽት ገለጻ አድርገዋል። በአውሮጳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር 1943 በኢትዮጵያ የተወለዱት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ የግብርና ቴክኒካል ትምህርት ቤቶች አጠናቀው በቀድሞው የአለማያ እርሻ ኮሌጅ ለሁለት ዓመት ተከታትለዋል። ከዛሬ 55 ዓመታት በፊት በኮሌጅ ቆይታቸው ባሳዩት የላቀ ውጤትም አሜሪካን አገር በሚገኘው የካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ትምህር ቤት ተልከው ትምህርታቸውን በማጥናት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በቢሾፍቱ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት አስተምረዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላም ወደ ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ በመመለስ የ3ኛ ዲግሪያቸውን በደቂቀ ሥነ ሕይወት መስክ በማጥናት በአውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ከ1980-2006 በተማሩበት ካሊፎርኒያ በዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከረዳት እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አስተምረዋል፤ ተመራምረዋል። እ.አ.አ ከ2017 ጀምሮ ደግሞ የዲስቲንጉሽድ ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ማዕረግ ያገኙ ሲሆን እ.አ.አ ከ1990 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል በማቋቋም በዳይሬክተርነት እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን የት ተከታተሉ?
በናዝሬት
516
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በተያዘው የበጀት ዓመት የመጀመርያው ሦስት ወራት፣ ከ12.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ ቢሮው እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ የሚዘልቅ ግብር የማሳወቅና የመሰብሰብ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጾ፣ እስከ መስከረም 2014 ዓ.ም. መጨረሻ ሳምንት ባለው ጊዜ ከግብር አሰባሰቡ የተገኘው ገቢ ከታቀደው በላይ እንደሆነ አስታወቋል፡፡ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊነትን አዲስ በተመረጠው የከተማ አስተዳደር እንዲመሩ በድጋሚ የተመረጡት አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ገቢዎች ቢሮው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተጀመሩትን የከተማዋን ገቢ በተጠናከረ ሁኔታ የመሰብሰብ ሥራ ዘመናዊ በሆነ ሥርዓትና ቅንጅታዊ አተገባበር እየተከናወነ ነው፡፡ በተያዘው በሩብ ዓመት ይሰበሰባል ተብሎ የታቀደው የግብር ገቢ 11.5 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ያስታወቁት ኃላፊው፣ ከሦስት ያላነሱ ቀናት የገቢ አሰባሰብ መረጃ ሳይካተት እስከ መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 12.26 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በ2014 ዓ.ም. መጀመሪያው ሩብ ዓመት ምን ያህል ገቢ ሰበሰበ?
12.26 ቢሊዮን ብር
603
ኮንግ-ፉጸ ኮንግ-ፉጸ ወይም ኮንፉክዩስ 558-487 ዓክልበ. የኖረ ቻይናዊ ፋላስፋ ነበረ። ፍልስፍናውና ትምህርቱ «የኮንግፉጸ ትምህርት» በተለይ በቻይና፣ በኮርያ፣ በጃፓንና በቬትናም አገር ባህሎች ላይ ጥልቅ ያለ ተጽእኖ አሳድሮዋል። በእርሱ ፍልስፍና፣ የግለሰብና የመንግሥት ግብረገብ፣ የኅብረተሠባዊ ግንኙነቶች ትክከለኛነት፣ የወላጆች ክብር፣ ፍርድና ቅንነት ልዩ ትኩረት አገኙ። ኮንግ-ፉጸ በሉ ክፍላገር የተወለደ ሲሆን፣ በክፍላገሩ ውስጥ የፖለቲካ ሰው ነበር። በ509 ዓክልበ. የአንድ ከተማ ከንቲባ ከመሆኑ በኋላ፤ የክፍላገሩ ወንጀል ሚኒስትር ሆነ። ነገር ግን በፖለቲካ ረገድ በሙሉ ስኬታማ አልነበረም። ከክፍላገሩ ሦስት ታላላቅ ኃይለኛ ቤተሠቦች ወገኖች፣ ሁለቱ አምባዎቻቸው እንዲፈርሱ በመጨረሻ ተስማሙ፣ እንጂ ሦስተኛው እምቢ ብሎ ለኮንግ-ፉጸ እቅድ አልተከናወነለትም። ስለዚህ በ505 ዓክልበ. ኮንግ-ፉጸ ከሉ ክፍላገር ሸሽቶ ለጊዜው በስደት ኖረ። ከዚያ እስከ 491 ዓክልበ. ድረስ ወደየክፍላገሩ ቤተ መንግሥት ጎብኝቶ የፖለቲካ ፍልስፍናውን ያስተምር ነበር፤ ሆኖም ሁላቸው ምክሩን ስላላስገቡ ይህ ደግሞ በጣም ስኬታም አልነበረም። በ491 ዓክልበ. ወደ ሉ በክብር ተመልሶ ከዚያ እስከ ዕረፍቱ ድረስ ወይም ለ4 ዓመታት ዕውቀቱን ለ77 ደቃ መዛሙርት (ተማሪዎች) ያስተምር ነበር። ከኮንግፉጸ ሕይወት በኋላ ትምህርቶቹ ተከታይነት አገኙ፤ በ148 ዓክልበ. የሃን ሥርወ መንግሥት የኮንግ-ፉጸ ትምህርት ይፋዊ አደረጉት። ወደ ማዕረግ ለመሾም ዕጩዎቹ በዚህ እምነት መጻሕፍት ይፈተኑ ነበር። ከ212 እስከ 1360 ዓም ድረስ ግን ልዩ ልዩ የቻይና ግዛቶች ዳዊስም ወይም ቡዲስም የመንግሥት ሃይማኖት አድርገው ነበር። እንደገና 1360-1903 ዓም ዘመናዊው የኮንግፉጸ ትምሕርት በቻይና ይፋዊ ሆነ። በዳዊስም ሃይማኖት ዘንድ፣ የእምነቱ መሥራች ላው ድዙ በ539 ዓክልበ. ያሕል ዳው ዴ ቺንግ እንደ ጻፈ፣ እንዲሁም አንዴ ከኮንግ-ፉጸ ጋራ እንደ ተገናኙ ይታመናል። በዘመናዊ ዳዊስም በኩል፣ ላው ድዙና ኮንግ-ፉጸ ሁለቱ እንደ አማልክት ይከብራሉ። በተለይ በፓኪስታን የሚታወቅ ከእስልምና የወጣ ክፍልፋይ አሕማዲያ እስልምና እንዳለው፣ ኮንግ-ፉጸ እና ላው ድዙ ሁለቱ የአላህ ነቢዮች ነበሩ።
ኮንግ-ፋጸ የተወለደው የት ነው?
በሉ ክፍላገር
247
የናሳ ተመራማሪዎች ሱፐር ኧርዝ ሲሉ የሰየሟትን አዲስ ፕላኔት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በመጠኗ የመሬትን እጥፍ ታክላለች የተባለችው አዲሷ ፕላኔት ከከዋክብቷ አንፃር ለህይወት ተስማሚ በሆነ ርቀት ውስጥ እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡ ይህም በፕላኔቷ ላይ ህይወት ሊኖር ይችላል የሚል ተስፋ አሳድሯል ነው የተባለው፡፡ ፕላኔቷ አለታማ አሊያም እንደኔፕቲዩን በጋዝ የበለፀገች ልትሆን እንደምትችል የናሳ ተመራማሪዎች የገለጹ ሲሆን ፕላኔቷ ያልተለመደችና ከቀድሞ ፕላኔቶች ልዩ እንደሆነች በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
የናሳ ተመራማሪዎች ያገኝዋትን አዲስ ፕላኔት ምን ብለው ሰየምዋት?
ሱፐር ኧርዝ
12
በደቡብ ሱዳን መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ጆንሰን ጁማ ኡኮት የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ ልዑኩ አዲስ አበባ ሲገባ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ እና በሌሎች ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
የደቡብ ሱዳን ጠቅላይ ኤታማዦር ለምን ኢትዮጵያ መጡ?
በሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ
180
ቴሌቪዥን ቴሌቪዥን የስዕል እና ድምጽ ምልክቶችን ከማሰራጫ የሚቀበል የመገናኛ ዘዴ ነው። «ቴሌ-» የሚለው ክፍል በግሪክ «ሩቅ» ማለት ቢሆን «-ቪዥን» ደግሞ ከሮማይስጥ visio /ዊዚዮ/ «ማየት» («ትርዒት») ተወስዷል። በአጠቃላይ ቴሌቪዥን ማለት ተንቀሳቃሽ ምስልን (ብዙ ጊዜ ከድምፅ ጋር) ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማስተላለፍ የሚረዳ የመልዕክት ማስራጫ መንገድ ነው። ይህ ከሆነ ዘንዳ ቴሌቪዥን ምስል መቅጃውንም ሆነ ምስል መቀበያውን መሳሪያ ሁሉ ያጠቃልላል ግን በተለምዶ ቴሌቪዥን የምንለው ምስል መቀበያውን ብቻ ነው። በ1873 እ.ኤ.አ. (1865 ዓም) የእንግላንድ ኤንጅኔር ውሎቢ ስሚስ ባደረገው ጥረት ጥንተ ንጥሩ ሴሌኒይም ብርሃን-አስተላልፎሽ መሆኑን ገለጸ። በ1884 እ.ኤ.አ. ፓውል ጎትሊብ ኒፕኮው የተባለ ጀርመናዊ ክብ የሆነ ዲስክን በስፓይራል በምብሳት ይህ ዲስክ በተሽከረከረ ቁጥር ከፊትለፊቱ የሚመጣውን ብርሃን በቀዳዶቹ በማሾለክ ከሴሌኒይም በተሰራ የካሜራ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ አደረገ። ግድግዳው ብርሃን ሲነካው ያንን ብርሃን ወደ ኮሬንቲ ሃይል በመቀየር ምስልን በኮሬንቲ መልክ በሽቦ ለመላክ ቻለ። ነገር ግን በዚህ ጊዜ አምፕሊፋየር ስላልነበር የሚላከው ምስል እምብዛም አመርቂ አልነበረም። ከ27 አመታት በኋላ በ1911 እ.ኤ.አ. የራሻው ቦሪስ ሮዚንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲርቲን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ አሁንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመላክና ለመቀብል ቻለ። ነገር ግን የሚንቀሳቀሱት ምስሎች የጂዎሜትሪ ቅርጽ ነበራቸው ማለትም ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማእዘን ወዘተ... ከ7 አመታት በኋላ በ1925 እ.ኤ.አ. ጆን ሎጂ ቤርድ የተሰኘው የስኮትላንድ ተመራማሪ 2ቅጥ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመላክ ቻለ ከዚያም በ1926 እ.ኤ.አ. ጥቁርና ነጭ የሆኑ ምስሎችን ለማስተላለፍ በቃ። በዚህ ጊዜ የሚላኩት ምስል ጥራት 30 መስመር በአንድ ጊዜ ነበር፣ በዚህም ምክንያት የሰውን ፊት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ግን ይቻል ነበር። አቶ ቤርድ በ 1918 ዓ.ም. (26 January 1926 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን መግለጫ ሰጠ። በ1927 እ.ኤ.አ. ኸርበርት አይቭስ የተሰኘው የቤል ላብራቷር ተቀጣሪ 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሽቦ መላክ ቻለ። ቀጠል አድርጎም በራዲዮ ወደ ዊፓኒ ኒው ጀርሲ ለመላክ በቃ። በዚያው አመት ፊሎ ፍራንስዎርዝ የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ ስካኒንግ ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት በተግባር አዋለ።.በጥር 1928 እ.ኤ.አ. (1920 ዓም) መጀመርያው የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያ በስከነክተዲ፣ ኒው ዮርክ ተከፈተ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ያሰራጫል።
ፊሎ ፍራንስዎርዝ የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ ስካኒንግ ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት ተግባር ላይ ያዋለው መች ነበር?
በ1927 እ.ኤ.አ.
1,178
መልከአ-ምድር አንጎላ፣ በ1,246,620 ካሬ ኪ.ሜ. ከኒጄር ቀጥላ ከዓለም 23ኛው ትልቅ አገር ናት። በስፋት ከማሊ ጋር ትነጻጸራለች። የአሜሪካ የቴክሳስ ክፍላገርን ሁለት ዕጥፍ ታክላለች። አንጎላ ከደቡብ በናሚቢያ፣ ከምሥራቅ በዛምቢያ፣ ከሰሜን-ምሥራቅ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ከምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች። የአንጎላ አማካይ የባህድ ዳር የአየር ሁኔታ በክረምት 16° ሴንቲግሬድና በበጋ 21° ሴንቲግሬድ ነው። አንጎላ ሁለት ወቅቶች አሏት። እነዚህም ደረቅና ዝናባማ ናቸው። መጓጓዣ በአንድ ላይ ርዝመታቸው 2,761 ኪ.ሜ. የሆኑ ሦስት የባቡር መንገዶች፤ 76,626 ኪ.ሜ. አውራ ጎዳና ከዚህም ውስጥ 19,156 ኪ.ሜ. አስፋልት፤ 1,295 ኪ.ሜ. የውሃ መንገድስምንት ትልቅ ወደቦች፤ 243 የአውሮፕላን ማረፊያዎች ከነዚህም 32ቱ የአስፋልት መንደርደሪያ ያላቸው፤ አንጎላ የሰፋ የመጓጓዛ አውታር ቢኖራትም በጊዜ ማለፍና ጦርነት ምክንያት መንገዶች አስፈላጊ ጥገኛ አልተደረገባቸውም። በአንዳንድ ቦታዎች አሽከርካሪዎች መጥፎ ቦታዎችን ለማለፍ ሲሉ ከመንገድ ውጭ ይነዳሉ። እንደዚህ ከማድረግ በፊት ግን በመንገድ ዳር ያሉ በመሬት ውስጥ ስለተቀበሩ ፈንጂዎች የሚያስጠነቅቁ ምልክቶችን ማስተዋል ያስፈልጋል። ኢኮኖሚ የአንጎላ ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ አሳይቷል። የሩብ ምእተ ዓመት ጦርነት ያሳደረበት ተጽእኖን አልፎ ዛሬ በዓለም ውስጥ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ይመደባል። በ2004 እ.ኤ.አ. የቻይና ኤክሲምባንክ ፪ ቢሊዮን ብር ለአንጎላ አበድሯል። ይህ ገንዘብ እንደ መንገዶች ያሉትን የአንጎላ መሠረታዊ ተቋሞች ለማሻሻል የሚውል ነው። ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት በ2008 እ.ኤ.አ. እንደዘገበው ነዳጅና ዕንቁ የአንጎላ ዋና ኤክስፖርቶችና የገቢ ምንጮች ናቸው።
አንጎላ ከሰሜን-ምስራቅ አቅጣጫ በማን ትዋሰናለች?
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
160
ፋሲለደስ ዓፄ ፋሲለደስ ወይም ዓፄ ፋሲል (የዙፋን ስማቸው ዓለም ሰገድ) ከአባታቸው አፄ ሱሰኒዮስ እና እናታቸው ልዕልት ስልጣነ ምገሴ በመገዛዝ፣ ሸዋ ህዳር 10፣ 1603 (እ.ኤ.አ) ተወለዱ። የነገሱበትም ዘመን ከ1632 እስከ ጥቅምት 18, 1667 (እ.ኤ.አ) ነበር። በስረፀ ክርስቶስ በተመራው አመፅ ምክንያት በ1630 ፋሲለደስ ለንግስና ቢበቃም፣ ዘውዱን ግን እስከ 1632 አልጫነም ነበር። ሲመተ ንግስናው በ1632 እንደተገባደደ የመጀመሪያው ስራው የተዋህዶ ቤ/ክርስቲያንን የቀድሞው ቁመና መመለስና የካቶሊኮችን መሬት በመቀማት ከደንካዝ በማባረር በፍሪሞና እንዲወሰኑ ማድረግ ነበር። ወዲያውም በማከታተል ከግብፅ አገር አዲስ ጳጳስ እንዲላክለት በማድረግ በአባቱ ዘመን እንዲደበዝዝ ተደርጎ የነበረውን የግብፅና ኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት እንዲጸና አደረገ። በኬኒያ የሚገኘው የሞምባሳ ወደብ በፖርቱጋሎች መደብደቡን ሲሰማ፣ የሮማው ፓፓ ከበስትጀርባው ያለበት ሴራ ነው በማለት በምድሩ የነበሩትን የካቶሊክ ጀስዊቶች በመሰብሰብ አባረራቸው። አፄ ፋሲል አዘዞ ተብላ በምትታወቀው ከጎንደር ከተማ 5 ማይል ርቃ በምትገኘው ከተማ ጥቅምት18፣1667 እ.ኤ.አ. (ጥቅምት 10፣ 1660) ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አስከሬናቸውም የአገሪቱ መላ ህዝብ ባዘነበት ሁኔታ በቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም፣ ጣና ሃይቅ ውስጥ ደጋ ደሴት ተብላ በምትታወቀው ደሴት የዘላለም እረፍት አገኘ።
አፄ ፋሲል መቼ አረፉ?
ጥቅምት18፣1667 እ.ኤ.አ. (ጥቅምት 10፣ 1660)
660
የፀሓይ አካል ለፍጹም ሉል የቀረበ ቅርጽ አለው፤ ዋልታዎቿን የሚያገናኘው ዳያሜትር ከወገቧ ዳያሜትር የሚያንሰው በ10 ኪሎ ሜትር ብቻ ነውና። ኮከባችን ፀሓይ በሥነ ፈለክ ሊቃውንት እጅግ ብዙ ጥናት ተደርጎባታል። ኾኖም ኮከቢቱን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች ገና አልተመለሱም። ለምሳሌ በገሃድ የሚታየው የፀሓይ ገጽ ስኂን 6,000 ኬ (ኬልቪን) ኾኖ ሳለ፣ የዳርቻ ከባቢ አየሯ ስኂን ከሚሊዮን ኬ በላይ እንዴት ሊኾን እንደቻለ አይታወቅም። የፀሓይ ዕድሜ በአንዳንድ ሊቃውንት እሳቤ 4.6 ቢሊዮን ዓመት ገደማ ነውና በዕድሜ እኩሌታዋ ላይ የምትገኝ ኮከብ ተደርጋ ትታያለች። የኮከቢቱ መጠነ-ቁስ ጥንቅር 74% ሃይድሮጂን፣ 25% ሂሊየም ሲኾን፣ ቀሪው 1% ደግሞ ክብደት ያላቸው ርዝራዥ የብረቴ ንጥረ-ነገሮች ጥርቅም ነው። ስለ ፀሓይ የሰው ልጅ ቀዳሚ መሠረታዊ ግንዛቤ ብርሃን-ሰጭ ሰማያዊ ጻሕል መኾኗን፣ ደግሞም ከአድማስ በላይ እና በታች በመኾን ለመዓልትና ሌሊት መኖር ምክንያት መኾኗን መረዳት ነበር። በብዙ የቅድመ-ታሪክ እና የጥንት ዘመን ባህሎች ፀሓይ እንደ ብርሃናዊ አምላክ ወይም እንደ ዲበ-ተፈጥሯዊ ክሥተት ትታይ ነበር። የፀሓይ አምልኮ ለምሳሌ የ-ኢንካ (ደቡብ አሜሪካ) እና አዝቴክ (የዛሬዋ ሜክሲኮ) ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ዐይነተኛ ገጽታ ነበር። ከፀሓያዊ ክሥትቶች ጋር የተያያዙ ብዙ ጥንታዊ ሐውልቶች ተገንብተው እንደነበር ለማሰብ የሐጋይ ሶልስቲስን ለማስታወቅ የተገነቡትን የድንጋይ ሜጋሊት በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። ከችንክር ከዋክብት አንጻር ስትታይ ፀሓይ የግርዶሽ መስመርን ተከትላ በዞዲያክ ውስጥ በዓመት አንድ ዑደት የምታደርግ ትመስላለች። ስለዚህ በጥንት የግሪክ የሥነ-ከዋክብት ሊቃውንት ዘንድ ፀሓይ ታዋቂ ከነበሩ ሰባት ፈለኮች እንደ አንዱ ትቈጠር ነበር። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሰባቱ የሳምንት ዕለታት በነዚህ ፈለኮች ይጠራሉ።
የፀሀይ የሚታየው ገጽ ስኂን ምን ያህል ነው?
6,000 ኬ (ኬልቪን)
199
ሴኔጋል ከ፹ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ፓርላማዋ ሁለት ምክር ቤቶች አሉት። አንዱ ፻፳ መቀመጫዎች ያሉት የብሔራዊ ስብሰባ (እንግሊዝኛ፦ National Assembly) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ፻ መቀመጫዎች ያሉት ሴኔት ነው። ሴኔጋል ራሱን የቻለ ህግ ተርጓሚ አካል አላት። ዳኛዎቹ የሚሾሙት በፕሬዝዳንቱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሴኔጋል የዴሞክራሲ ሂደት ስኬታማ ነው ከሚባሉት የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ ናት። የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። ማራባውት የሚባሉ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችም በሴኔጋል ጠንካራ የፖለቲካ ተፅእኖ አላቸው፡ ከ፪ ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉበት የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የሀገሩ ትልቁ ከተማ ነው። ሁለተኛው ፭፻ ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ቱባ ከተማ ነው። ሴኔጋል ከ12.5 ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ አላት። ከዚህ ውስጥም ወደ ፵፪ ከመቶ በገጠር ነው የሚኖረው። የአሜሪካ የስደተኖች ኮሚቴ ባቀረበው የ2008 እ.ኤ.አ. የዓለም ስደተኞች አጠቃላይ ቅኝት መሠረት ሴኔጋል በ2007 እ.ኤ.አ. ወደ 23,800 የሚገመቱ ስደተኞች ይኖሩባታል። ከዚህ አብዛኛዎቹ የመጡት ከሞሪታኒያ ነው። ስደተኞቹ በንድዮም፣ ዶዴል እና በሴኔጋል ወንዝ አቅራቢያ በሚገኙ ሠፈሮች ይኖራሉ። የአገር ይፋዊ ብሔራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ከብዙ ኗሪ ቋንቋዎች 11ዱ በተለይም ዎሎፍኛ አገራዊ ዕውቅና አላቸው። ሌሎቹ ባላንታኛ፣ ማንዲንክኛ፣ ፑላርኛ (ፉላኒኛ)፣ ሰረርኛ፣ ሶኒንክኛ፣ ኖንኛ፣ ማንካኛኛ፣ ማንጃክኛ፣ ጆላኛ እና ሀሣኒያ አረብኛ ናቸው። ፖርቱጊዝኛም በትምህርት ቤት ይማራል፣ የካቦ ቨርዴ እና የጊኔ-ቢሳው ኅብረተሠቦችም ፖርቱጊዝኛ ክሬዮል ይናገራሉ። ከሴኔጋል ሕዝብ 94% የእስልምና አማኞች፣ 5% ክርስትና (ባብዛኛው ካቶሊክ)፣ 1% የኗሪ አርመኔነት ተከታዮች ናቸው። የመንግሥት ሃይማኖት የለውም። በሴኔጋል ልማዳዊ ባሕል ግሪዮት የተባሉ ሽማግሎች ታሪኮቻቸውን በአፍ ቃል ይደግማሉ። ሴኔጋል ለሙዚቃዊ ስልቶቹ ይታወቃል፤ በተለይ የሚወድደው ዘመናዊው ስልት ምባላክስ ተብሏል። በሴኔጋል አበሳሰል በተለይ አሣ፣ ዶሮ፣ በግ፣ አተር፣ ዕንቁላል፣ በሬ ይጠቀማሉ፤ እስላም አገር እንደ ሆነው መጠን ግን አሳማ አይበላም። ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ስኳር ድንች፣ ምስር፣ ጥቁር-ዐይን አተር ደግሞ በሴኔጋል አበሳሰል በሰፊ ይገኛሉ። በእስፖርት በኩል፣ ከሁሉ የሚወደደው ባህላዊው የሴኔጋል ትግል ግጥሚያ ሲሆን፣ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ ደግሞ እጅግ ይወደዳሉ።
በሴኔጋል ካላት ሕዝብ ብዛት ምን ያህሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ነው?
94%
942
አሪዞና አሪዞና (Arizona) በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ክፍላገር ነው። ኒው ሜክሲኮ ፣ ዩታህ ፣ ኔቫዳ ፣ ካሊፎርኒያ እና ኮሎራዶ ያዋስኑታል። የአሪዞና ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ የ30 ሰው ሴኔት እና የ60 ሰው ምክር-ቤት አለው። የሪፑብሊካን ፓርቲ በስቴቱ ዋነኛው ፓርቲ ነው። በ2002 እ.ኤ.አ. የአሪዞና ስቴት ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ በጀት 14.3 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በጀት ደግሞ 13.8 ቢሊዮን ዶላር ነው። የስቴቱ ሴኔተሮች እና ምክር-ቤት ተወካዮች ለሁለት-ዓመት ጊዜ ላልተወሰነ ብዛት ይመረጣሉ። ከ4 ጊዜ በላይ በተካካይ መመረጥ ግን አይችሉም። የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በአስተዳዳሪ የሚመራ ሲሆን ለ4 ዓመት ሥልጣን ላይ ይቆያል። ያልተወሰነ ጊዜ መወዳደር ሲቻል ከሁለት ጊዜ በላይ ግን በተካካይ መመረጥ አይፈቀድም።
የአሪዞና ሕግ አውጪ የ60 ምክር ቤት አባላትና የስንት ሴኔት አባላት ውቅር ነው?
የ30
117