category
large_stringclasses
7 values
headline
large_stringlengths
10
171
text
large_stringlengths
1
26.4k
url
large_stringlengths
13
180
lang
large_stringclasses
16 values
business
የናይጄሪያ ፖሊስ በሩዝ ፋብሪካ ተቆልፎባቸው እንዲሰሩ የተገደዱ 300 ሰራተኞችን ነፃ ማውጣቱን ገለፀ
የናይጄሪያ ፖሊስ በሩዝ ፋብሪካ ውስጥ ተቆልፎባቸው የነበሩ 300 ሰራተኞችን ነፃ ማውጣቱን ገልጿል። ሰራተኞቹ ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ ከፋብሪካው እንዳይወጡ እግድ ተጥሎባቸውና ተቆልፎባቸው ይሰሩ ነበር ተብሏል። በሰሜናዊ ናይጄሪያ ግዛት በምትገኘው ካኖ በሚገኝ ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩት ሰራተኞች የኮሮናቫይረስ አስገዳጅ የቤት መቀመጥ አዋጅን ተከትሎ ወደቤታቸው እንዳይሄዱና በየወሩም ከሚያገኙት 2 ሺህ 600 ብር ደመወዝ በተጨማሪ 500 ብር እንደሚጨመርላቸው የፋብሪካው አስተዳዳሪዎች ቃል ገብተውላቸው ነበር። ወደቤታችን እንሄዳለን የሚሉት ደግሞ ከስራ እንደሚባረሩ ማስፈራራሪያም ደርሷቸዋል። በፋብሪካው ለመስራት የተስማሙ ሰራተኞች ከፋብሪካው ወጥተው መሄድ እንደማይችሉም ተነግራቸዋል። ይህንንም ተከትሎ አምስት አስተዳደር ላይ ያሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የህንዶች የሆነው ፖፑላር ፋርምስ የተሰኘው ፋብሪካ ከቢቢሲ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠየቅም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። የፖሊስ ቃለ አቀባይ አብዱላሂ ሃሩና ለቢቢሲ እንደተናገሩት ፋብሪካው እንደተዘጋና ባለቤቶቹም ሰራተኞቹን ያለፍቃዳቸው በመቆለፋቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል። አንዳንድ ሰራተኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት የነበሩበት ሁኔታ ከእስር ያልተናነሰ እንደሆነና ትንሽ ምግብም ብቻ ይሰጣቸው እንደነበር ገልፀዋል። "በጣም ለአጭር ጊዜ ብቻ እንድናርፍ ነበር የሚፈቀደልን። ፀሎት ማድረግ እንዲሁም ቤተሰብ እንዲጠይቀን አይፈቀድልንም ነበር" በማለት የ28 አመቱ ሃምዛ ኢብራሂም ለቢቢሲ ተናግሯል። ፖሊስ ጉዳዩን የተረዳው አንደኛው ሰራተኛ ለሰብዓዊ መብት ድርጅት እንዲያድኗቸው በመማፀን ከላከው ደብዳቤ ነበር። "ያየሁት ሁኔታ በጣም ልብ የሚሰብር ነው። ሰራተኞቹ ለእንስሳ እንኳን በማይመጥን ሁኔታ ነው እንዲቆዩ የተደረጉት" በማለት የግሎባል ሂውማን ራይትስ ኔትወርክ ሰራተኛ ካሪቡ ያሃያ ካባራ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አክለውም "የሚሰጣቸው ምግብ በጣም አነስተኛ ነበር። ታመው ለነበሩትም ሕክምና ተከልክለዋል፤ የመድኃኒት አቅርቦት አልነበራቸውም" ያሉት ካሪቡ ለሰራተኞቹ ፍትህንም እንደሚሹ ጠይቀዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እንዲቻል ናይጄሪያ ሁሉም ፋብሪካዎችም ሆነ የንግድ ቦታዎች እንዲዘጉ ያዘዘችው መጋቢት አጋማሽ ላይ ነበር። በናይጄሪያ እስካሁን 20 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን መዲናዋ ሌጎስም የስርጭቱ ማዕከል ሆናለች። ከሌጎስ በመቀጠልም የናይጄሪያ ሁለተኛ ትልቋ ከተማ ካኖም በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ትከተላለች። ወረርሽኙን ለመግታት የተላለፉ መመሪያዎች በሌሎች ቦታዎች ቢላሉም በካኖ ግን የቤት መቀመጥ አዋጁ እንዳለ ነው። ዜጎች ሰኞ፣ ረቡዕና አርብ መንግሥት በወሰነው ሰዓት ብቻ ምግብና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለመሸመት ይወጣሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-53127360
amh
business
ኢትዮጵያ፡ በደረሰው የጎርፍ አደጋ 130 ሺህ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል
በኢትዮጵያ እስከ ነሐሴ ወር አጋማሽ ድረስ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የተነሳ 170 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ጉዳት ሲደርስባቸው 130 ሺህ ሰዎች ደግሞ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር ለቢቢሲ ገለፁ። ኮሚሽነሩ አቶ ዳመነ ዳሮታ ከዚህ በፊት የነበረውን ልምድ ከግንዛቤ በማስገባት በዚህ ዓመት ክረምት ወቅት በጎርፍ ምክንያት ወደ 2 ሚሊየን ያህል ሰዎች ሊጎዱ እንዲሁም 434 ሺህ ያህሉ ደግሞ ሊፈናቀሉ ይችላሉ ተብሎ ግምት መያዙን ተናግረዋል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ በአፋር ክልል የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 67 ሺህ 885 አካባቢ ሲሆን፣ 40 ሺህ 130 አካባቢ ደግሞ መፈናቀላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ኮሚሽነር ዳመነ አክለውም ደቡብ ኦሞ ዳሰነች አካባቢ በኦሞ ወንዝ ሙላትና የግቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃ በተወሰነ መልኩ መልቀቁን ተከትሎ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በኦሞ በሚገኙ ከ15 ሺህ በላይ ሰዎች እንዳይጎዱ ከሚኖሩበት አካባቢ የማውጣት ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች በጊዜያዊ መጠለያ እንዲቆዩ መደረጉን ገለፀው ከ10ሺህ በላይ ለሚሆኑት የተለያዩ ድጋፎች ደርሷል ብለዋል። ለቀሪዎቹ 5ሺ ሰዎች ደግሞ ድጋፍ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አክለዋል። ዘንድሮ በጎርፍ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ለቢቢሲ የገለፁት ኮሚሽነሩ፣ ነገር ግን ኮሚሽኑም ሆነ መንግሥት ከሌሎች ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ ዝግጅት ያደረጉበት ዓመት እንደነበር ለቢቢሲ አብራርተዋል። በዚህ ዓመት በልግ ወቅት በደረሰው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 470 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ጉዳት ሲደርስባቸው ከ300 ሺህ በላይ ደግሞ መፈናቀላቸውን ኮሚሽነሩ ጨምረው አስረድተዋል። ኮሚሽኑ ይህን የበልግ ወቅት አደጋን በመቋቋም ላይ ባለበት ወቅት የክረምቱ ዝናብ ከበልጉ ዝናብ ጋር ተያይዞ በመምጣቱ ወንዞችና ግድቦች በመሙላታቸው በርካቶች ለአደጋ መጋለጣቸውን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ከነበረው ልምድ በተለየ ሶስት ጊዜ የጎርፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱን ገልፀው ሁለቱ ማስጠንቀቂያዎች የወጡት በዚህ ክረምት ወቅት መሆኑን አብራርተዋል። እስከ መስከረም መጨረሻ ተከታታይ ዝናብ ስለሚኖር ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊከሰት እንደሚችል የገለፁት ኮሚሽነሩ ነሐሴ መጨረሻዎቹ ላይ የተንዳሆ ግድብ ሊሞላ ስለሚችል ቀጣይም ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ፣ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስም የከሰምና፣ የቆቃ ግድቦች እየሞሉ እንደሚሄዱ በመግለጽ ሁሉም አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል። በመከላከኛውና፣ የታችኛው አዋሽ ላይ ከፍተኛ የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው በመግለፅ በዚህም የተነሳ በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ በዚህ የክረምት ወቅት የደረሰው ጉዳት መቀነሱን ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53852369
amh
business
አየር መንገዶች ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን እንዳያበሩ ዳግም ታገዱ
ከሁለት የመከስከስ አደጋ በኋላ ዳግም እንዲበር ፍቃድ አግኝቶ የነበረው የቦይንድ 737 ማክስ አውሮፕላን ዳግም አጣብቂኝ ውስጥ ገባ። የኢትዮጵያ እና የኢንዶኔዢያው ላየን አየር መንገድ ንብረት የሆኑት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የመከስከስ አደጋ ካጋጠማቸው በኋላ በመላው ዓለም አውሮፕላኑ እንዳይበር እግድ ተጥሎበት እንደነበረ ይታወሳል። ከስድስት ወራት በፊት ግን የአሜሪካ የበረራ ደህንነት ተቋማት አውሮፕላኑ ዳግም እንዲበር ፈቃድ ሰጥተው ነበር። ይሁን እንጂ አውሮፕላኑ ሌላ የኤሌክትሪክ ችግር እንዳለበት በመታወቁ ዳግም ሌላ አጣበቂኝ ውስጥ መግባቱ ተነግሯል። አውሮፕላኑ ዳግም ለማብረር የወሰኑ በመላው ዓለም የሚገኙ 24 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን እንዳያበሩ ተነግሯቸዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን ቦይንግ ያመረታቸውን አውሮፕላኖች ከማከፋፈል ተቆጥቧል። ቦይንግ እና የአሜሪካ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ) ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት እየሰራን ነው ብለዋል። በአውሮፕላኑ ላይ የኤሌክትሪክ ችግር መገኘቱ ቀድሞውኑ አውሮፕላኑ ጥብቅ የደህንነት ፍተሻ ሳይካሄድበት ለበረራ ብቁ ነው መባሉ ሲተቹ ለነበሩ ሌላ የመከራከሪያ ነጥብ ሆኖላቸዋል። ቦይንግን አጥቦቆ በመተቸት የሚታወቁት የቀድሞ የቦይንግ አስተዳዳሪ ኤድ ፒርሰን፤ በቦይንግ ፋብሪካ ያለው ደካማ የምርት ጥራት የኤሌክትሪክ ችግር እንደምክንያት በማንሳት የበርካቶችን ህይወት ለቀጠፉት አደጋዎች ምክንያቱ ይህ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ቦይንግ እና ኤፍኤኤ አውሮፕላኑ ላይ የተገኘው ችግር የኤሌክትሪክ ኃይል በሚያመነጨው ስርዓት ላይ ነው ብለዋል። ለዚህ መንስዔው የኤሌክትሪ ግነኙነቶች ሥራ ጥራት ደካማ መሆኑ ነው ይላሉ። ኤፍኤኤ እንደሚለው የአሌክትሪክ ችግር፤ “መሠረታዊ የሆኑ የአውሮፕላኑ ስርዓት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።” ኤፍኤኤ ይህ የአውሮፕላኑ የኤሌክትሪክ ችግር ሳይቀረፍ አውሮፕላኑ አገልግሎት መስጠት የለበትም በማለት ከሁለት ሳምንት በፊት "አውሮፕላኑ ለመበረር የደህንነት ስጋት አለበት" የሚል መመሪያ አውጥቶ እንደነበረም ተጠቅሷል። ቦይንግን 737 ማክስ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ302 ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ ሲበር ተከስክሶ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸው ይታወሳል። ተመሳሳይ የኢንዶኔዥያ ላየን ኤር ንብረት የሆነ አውሮፕላን ከኢንዶኔዢያ ተነስቶ ባህር ውስጥ መከስከሱ ይታወሳል። በሁለቱ አደጋዎች በአጠቃላይ 346 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57075420
amh
business
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ500 ቢሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ በጀት አዘጋጀች
የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀትን ለመጀመሪያ ጊዜ ከ500 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያደርግ ረቂቅ በጀት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቀ። የመጪው ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት በጀት ከዘንድሮው በ85 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያዘጋጀው ረቂቅ በጀት አመልክቷል። ምክር ቤቱ የቀጣዩ ዓመት የፌደራል መንግሥቱ በጀት 561 ቢሊዮን ብር በላይ በላይ እንዲሆን የወሰነ ሲሆን በ2013 ካለው የ476 ቢሊዮን ብር በጀት በ18 በመቶ ከፍ ብሏል። ይህም የየ85 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ታይቶበታል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2014 ዓ.ምን በጀት ከማጽደቁ በፊት በቀዳሚነት ለዚህ ዓመት ባስፈለገው ተጨማሪ በጀትና የመንግሥት ወጪን ለመሸፈን ያስፈለገው ማስተካከያ ተግባራዊ እንዲሆን በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ መክሯል። በዚህም መሠረት ለ2013 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት ያስፈለገው በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ከተከሰተው ጦርነት ጋር ተያይዞ ላጋጠሙ ወጪዎች፣ በድርቅ ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ እና ለተመላሾች የእለት እርዳታ አቅርቦት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል፣ ለማዳበሪያ አቅርቦት ድጎማ፣ ለጎርፍ መከላከል እንደሆነ ተገልጿል። በተጨማሪም ለማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የአቅም ግንባታ ፕሮጀክትና "የመጠባባቂያ በጀት በማለቁ በቀጣይ ወራቶች ለሚያስፈልጉ የተለያዩ ወጪዎች የመጠባበቂያ በጀት መመደብ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው" ሲል የሚኒስትሮች ምክር ቤት መግለጫ አመልክቷል። የተጠየቀው 26.4 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ከተለያዩ ምንጮች የሚገኝ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም ይህንኑ ተቀብሎ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቶታል። ከዓመት ዓመት ጭማሪ እያሳየ የመጣው የፌደራል መንግሥቱ ዓመታዊ በጀት በቀጣዩ 2014 ዓ.ም 561.67 ቢሊዮን ብር እንዲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወስኗል። ይህም አስካሁን አገሪቱ ከያዘችው ዓመታዊ በጀት ሁሉ የላቀው ነው። ለቀጣይ ዓመት የተያዘው በጀት ለመደበኛ ወጪዎች 162 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎች 183.5 ቢሊዮን ብር፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ 203.95 ቢሊዮን ብር፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ 12 ቢሊዮን ብር መያዙ ተገልጿል። ቅዳሜ ዕለት ግንቦት 28/2013 ዓ.ም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ ላይ የተወሰነው ተጨማሪ በጀትና ረቂቅ በጀት ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቅ ይኖርበታል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የነበራትን ዓመታዊ በጀት ስንመለከት በ2012፣ 386 ቢሊዮን 954 ሚሊዮን 965 ሺህ 289 የነበረ ሲሆን በ2011 ደግሞ 346 ቢሊዮን 915 ሚሊዮን 451 ሺ 948 ተመድቦ ነበር። በ2010 የነበረው በጀት 320.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን፤ ከ60 በመቶ የሚበልጠው ለትምህርት፣ ለግብርናና ለመሰረተ ልማትና ለጤና ማስፋፊያ እንዲሆን ተብሎ የተበጀተ ገንዘብ ነበር። ከ300 ቢሊዮን ብር በታች የነበረው የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት በ2009 ዓ.ም ላይ 274.3 ቢሊዮን በጀት መሆኑ የሚታወስ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-57372163
amh
business
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ስዊፍት ምንድን ነው?
ስዊፍት የአገራት ድንበሮች ሳይገድቡት በተመቸ እና በፈጣን ሁኔታ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማስተላላፊያ ሥርዓት ነው። ስዊፍት [Swift] ሶሳይቲ ፎር ኢነትረባንክ ፋይናንሻል ቴሌኮምዩኒኬሽን [Society for Worldwide Interbank Financial Telecommunication] የሚለው ስያሜ አህጽሮተ ቃል ነው። በሥርዓቱ የተካተቱ በዓለም ዙሪያ ያሉ ባንኮች ያለምንም ተጨማሪ ውጣ ውረድ ገንዘብ ይላላኩበታል። ስዊፍት እንደ አውሮፓውያኑ በ1973 የተጀመረ ሲሆን መሰረቱ ቤልጂየም ነው። የስዊፍት ሥርዓት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ200 በላይ አገራት ውስጥ የሚገኙ 11 ሺህ ባንኮችን እና የፋይናንስ ተቋማትን አስተሳስሯል። ስዊፍት ከመደበኛው የባንክ ሥርዓት ጋር የሚመሳሰል አይደለም። ይህ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ክፍያዎች ሲደርሱና ሲፈጸሙ ለተጠቃሚዎች የሚያሳውቅ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ሥርዓት ነው። በስዊፍት ትሪሊየን ዶላሮች በኩባንያዎች እና በመንግሥታት ስለሚዘዋወር በቀን ከ40 ሚሊዮን በላይ መልዕክቶችን ይልካል። ከእነዚህ መልዕክቶች ውስጥ ሩሲያ ከአንድ በመቶ በላይ ክፍያዎችን ታስተናግዳለች ተብሎ ይታሰባል። ይህ ግን በገንዘብ ሲሰላ ቀላል የሚባል አይደለም። ሩሲያ ከስዊፍት እንድትታገድ ጥሪ የሚቀርበው ለምንድን ነው? በሺዎች የሚቆጠሩ ባንኮች ከሚጠቀሙበት ከዚህ የገንዘብ ማዘዋወሪያ ሥርዓት ሩሲያን ማገድ የአገሪቱን የባንክ ኔትዎርክ እና የገንዘብ አቅርቦትን ይጎዳል። ነገር ግን ተጎጂዋ ሩሲያ ብቻ አይደለችም። ይህ ማዕቀብ የራሳቸውን ኢኮኖሚ እና ኩባንያ መልሶ እንዳይጎዳ በርካታ መንግሥታት ይሰጋሉ። ለአብነት ከሩሲያ ነዳጅ የሚቀርብላቸው አገራት በዕገዳው ምክንያት ነዳጅ ሊስተጓጎልባቸው ይችላል። ዩናይትድ ኪንግደም ሩሲያ ከስዊፍት እንድትታገድ በአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ቤን ዋላስ በኩል ጥሪ ብታቀርብም ብቻዋን ልታሳካው እንደማትችል ገልጻለች። "እንዳለመታደል ሆኖ የስዊፍት ሥርዓት በእኛ ቁጥጥር ውስጥ አይደለም። በአንድ ወገን ውሳኔ የሚሳካ አይደለም" ብለዋል። ጀርመን ሩሲያ ከስዊፍት እንዳትታገድ የማትፈልግ አገር እንደሆነች ይታማናል። በተመሳሳይ የፈረንሳይ የገንዘብ ሚኒስትር ብሩኖ ለሜሬ እና የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት ውሳኔው የመጨረሻ አማራጭ ብቻ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባው ጠቁመዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያን አሁን ላይ ከስዊፍ ማገድ አማራጭ ሆኖ እንዳልቀረበ ገልጸዋል። ምንም እንኳን "የተቀረው የአውሮፓ ክፍል አሁን ለመውሰድ የሚፈልገው እርምጃ ይህ ባይሆንም" አማራጭ ሆኖ እንደሚቆይ ግን ተናግረዋል። የስዊፍትን ባለቤትና ተቆጣጣሪ ማነው? ስዊፍት የተጀመረው አንድ ተቋም ሥርዓቱን ዘርግቶ የባንኮች የገንዘብ ዝውውር ሥርዓትን በብቸኝነት ጠቅልሎ እንዳይዝ ባቀዱ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ባንኮች አማካይነት ነው። ሥርዓቱን ከ2,000 የሚልቁ ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በጋራ ባለቤትነት ይዘውታል። ይህ የስዊፍት ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት በቤልጂየም ብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር የሚደረግበት ሲሆን የአሜሪካ ፌዴራል ግምጃ ቤትን እና የእንግሊዝ ባንክን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ ዋና ዋና ማዕከላዊ ባንኮችም በቁጥጥሩ ይሳተፋሉ። ስዊፍት በአባል አገራት መካከል ደኅንነቱ የተጠበቀ ዓለም አቀፍ ንግድ እንዲኖር የሚረዳ ሲሆን ግጭቶች ሲኖሩ ለማንም እንዳይወግን ይጠበቃል። ሆኖም ከዚህ መርኅ በተቃራኒ ኢራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት እንደ አውሮፓውያኑ በ2012 ከስዊፍት ታገደች። በዚህም ምክንያት ወደ ውጭ ከምትልከው የነዳጅ ሽያጭ ገቢዋ ግማሹን ያጣች ሲሆን 30 በመቶ የውጭ ንግዷንም አጥታለች። ስዊፍት ግን ማዕቀቡ እንዲጣል ምንም አይነት ተጽእኖ እንዳላደረገ እና ውሳኔው በመንግሥታቱ ላይ የተመሰረተ ነው ብሏል። ሩሲያን ከስዊፍት ማገድ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል? ሩሲያ ከስዊፍት ሥስርዓት ከታገደች የአገሪቱ ኩባንያዎች በስዊፍት በኩል የሚያገኙት መደበኛ፣ የተመቸ እና ፈጣን የገንዘብ ልውውጥን ያጣሉ። በተጨማሪም ለኃይል አቅርቦት እና ለእርሻ ምርቶች ክፍያዎች የሚፈጸምበት መንገድ ክፉኛ ይስተጓጎላል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 ሩሲያ ክሪሚያን መውረሯን ተከትሎ ከስዊፍት ልትታገድ እንደምትችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷት ነበር። ሩሲያ እርምጃውን ጦርነት ከማወጅ አሳንሳ እንደማትመለከተው አሳውቃ ነበር። በወቅቱም ምዕራባውያኑ በውሳኔው ባይገፉበትም ሩሲያ ግን የራሷን ተመሳሳት ሥርዓት እንድትፈጥር አጋጣሚ የፈጠረላት ነበር። እንዲህ ያለውን ማዕቀብ ለመቋቋም የሩሲያ መንግሥት ለካርድ ክፍያዎች የሚሆን 'ሚር' የተሰኘ ብሔራዊ የክፍያ ካርድ ሥርዓት ዘርግቷል። ነገር ግን ጥቅም ላይ የዋለው በጥቂት አገራት ውስጥ ብቻ ነው። ምዕራቡ በስዊፍት ላይ ለምን ተከፋፈለ? ሩሲያን በስዊፍት እንዳትጠቀም ማገድ ከአገሪቱ ጋር የንግድ ልውውጥ ያላቸውን ወይም ምርት የሚያቀርቡ እና የሚገዙ ኩባንያዎችን ይጎዳል። በተለይም ጀርመን የመጀመሪያዋ ተጎጂ ትሆናለች። ሩሲያ የአውሮፓ ሕብረት የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ዋነኛ አቅራቢ ስትሆን፣ ለሕበረቱ አማራጭ አቅርቦቶችን ማግኘት ቀላል አይሆንም። የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ የመጣ ሲሆን በዚህ ሳቢያ መሰል ችግር እንዲፈጠር መንግሥታቱ አይፈልጉም። እንዲሁም በሩሲያ ዕዳ ያለባቸው ኩባንያዎች ክፍያ የሚያገኙበት አማራጭ መንገዶችን መፈለግ ግድ ይላቸዋል። የሩሲያ ከስዊፍት መውጣት የዓለም አቀፍ የባንክ ሥርዓት ላይ የሚፈጥረው ቀውስ ቀላል እንዳሆነ ይታመናል። የሩሲያ የቀድሞ የፋይናንስ ሚኒስትር አሌክሲ ኩድሪን የአገሪቱ ስዊፍት መታገድ ምጣኔ ሀብቷን በ5 በመቶ እንዲያሽቆለቁል ሊያደርገው ይችላል ብለዋል። ይሁን እንጂ ውሳኔው በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ስለማምጣቱ አጠራጣሪ ነው። ምክንያቱም የሩሲያ ባንኮች የራሷ የክፍያ ሥርዓት ያላት ቻይናን ጨምሮ በሌሎች ማዕቀብ ባልጣሉ አገሮች በኩል የመጠቀም እድል ስላላቸው ነው። ሩሲያ ስዊፍት እንድትታገድ የአሜሪካ የሕግ አውጪዎች ግፊት እያደረጉ ነው። ሆኖም ፕሬዝዳንት ባይደን ምርጫቸው ይህ ሳይሆን ሌሎች ማዕቀቦች ናቸው። ምክንያቱም ውሳኔው ሌሎች አገራትን እና ምጣኔ ሀብታቸውን ስለሚጎዳ ነው። እናም ሩሲያ ከዚህ ሥርዓት እንድትታገድ የአውሮፓ አገራትን ድጋፋ ይፈልጋል። አገራቱ ደግሞ ውሳኔው ራሳቸውን መልሶ የሚጎዳ በመሆኑ ብዙም ሊደፍሩት የሚፈልጉ አይመስሉም።
https://www.bbc.com/amharic/news-60630455
amh
business
የሳምሰንግ ትርፍ ከ50 በመቶ በላይ አሽቆለቆለ
የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች አምራቹ ሳምሰንግ በሁለተኛው ሩብ ዓመት የምርቱ ትርፋማነት እንዳሽቆለቆለበትና ይህም ወደፊት ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ እንደሆነ አስታወቀ። • የአዲሱ ሳምሰንግ ጋላክሲ S9 በካሜራ ብቃት ላይ አተኩሯል •ሳምሰንግ እንደ መጽሐፍ የሚገለጥ ስልክ አመረተ የዓለማችን ትልቁ ዘመናዊ ስልኮችንና የኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን አምራቹ ኩባንያ- ሳምሰንግ እንዳለው ትርፋማነቱ ከዚህ ዓመት ቀድሞ ባለው የበጀት ዓመት በ56 በመቶ ቀንሷል። ለዚህም በአሜሪካና በቻይና መካከል እየተካሄደ ያለው የንግድ ጦርነት ምክንያት ነው ተብሏል። ይህም ብቻ ሳይሆን አምራች ድርጅቱ በሶልና ቶክዮ ባለው የንግድ ወረፋ ምክንያት ችግር እያጋጠመው እንደሆነ ገልጿል። በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ድርጅቱ እስከ ሰኔ ወር ባሉት ሦስት ወራት የሥራ ማስኬጃን በመቀነስ ከሚገኝ ትርፍ 6.6 የኮሪያ ዋን (5.6 ቢሊየን ዶላር)፤ ባለፈው ዓመት ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ትርፉ 14.87 የኮሪያ ዋን (12.6 ቢሊየን ዶላር) ጋር ሲነፃፀር፤ 56 በመቶ መቀነሱን አስታውቋል። ሳምሰንግ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በፍላጎት ደረጃ ትንሽ መሻሻሎች ቢታይም በምርቶቹ ላይ የገበያ ማጣትና የዋጋ ቅናሽ ግን ታይቷል። "ኩባንያው እያጋጠመው ያለው ተግዳሮት በንግዱ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚክ ሁኔታ መለዋወጥም ተፈታትኖታል" ብሏል በመግለጫው። ጃፓን በቅርቡ ወደ ውጭ የሚላኩ የኢንዱስትሪ ቁሳቁሶች፤ 'ሴሚ ኮንዳክተርስ' እና 'ስክሪኖች' ለመስራት የሚውሉ ምርቶች ላይ ቁጥጥር ማድረግ ጀምራለች። ይህ እንቅስቃሴም ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጅ እቃዎች አቅርቦት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል በሚል አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል። በመሆኑም የሳምሰንግን የወደፊት የምርት አቅርቦት ሊፈታተነው እንደሚችል ተጠቁሟል። ኩባንያው በቅርቡ እንዳስተዋወቀው ተጣጣፊ ስልኩ፤ አዳዲስ ምርቶች ማስተዋወቅ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ እና በሦስተኛው ሩብ ዓመት ላይ ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። • ታጣፊው የሳምሰንግ ስልክ የ'ስክሪን' መሰበር ወቀሳ ቀረበበት ሳምሰንግ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አዲሱን ተጣጣፊ ስልኩ የስክሪን መሰበር ወቀሳ ካጋጠመው በኋላ ለገበያ ለማቅረብ እንደዘገየም አስታውሰዋል። በአዲሱ ስልኩ ላይ ያጋጠመው ችግር በድርጅቱ ላይ አመኔታን ያሳጣ ሲሆን ይህም የዘመናዊ ስልኮች ሽያጭ ለመቀነሱና ከቻይናው ሁዋዌ ጋር ካለው የንግድ ውድድር ላይ መጥፎ አሻራ እንዳሳረፈ ተገልጿል። ሳምሰንግ ተጣጣፊው ጋላክሲ ስልኩ ተሻሽሎ በመጭው መስከረም ወር ለገበያ እንደሚቀርብ ያስታወቀው ባለፈው ሳምንት ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-49174785
amh
business
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስካሁን አንድ ቢሊየን ዶላር ያህል ገቢ አጥቷል
ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአየር ትራንስፖርት ዘርፉ ላይ በተፈጠረው መስተጓጎል ሳቢያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳጣ ተገለጸ። የኮሮናቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ በአየር መንገዶች ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ ማምጣቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ይናገራሉ። ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኛ በረራዎች መቆማቸውን ለቢቢሲ የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ያንን ተከትሎ ደግሞ ከየካቲት እስከ ሰኔ መጨረሻ ድርጅቱ መንገደኛ በማጓጓዝ ሊያገኘው ይገባ የነበረው ወደ አንድ ቢሊየን ዶላር ገቢ ሳያገኝ መቅረቱን ገልፀዋል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የዓለም አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ሕዝብ ከቤቱ እንዳይወጣ ከተደረገ ወራት አልፈዋል። ይህ ማለት በአየር የሚደረግ ጉዞ ሙሉ በሙሉ ቆሟል። ይህም በአየር መንገዶች ዓይን በሚታይበት ወቅት በአሁን ሰዓት ብዙ አየር መንገዶች አውሮፕላኖቻቸውን አቁመዋል ይላሉ ይላሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው። "የመንገደኛ በረራ ቆሟል። በኢትዮጵያ አየር መንገድም ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኞች አውሮፕላኖቻችን ቆመዋል።" "ይኼ ለአንድ አየር መንገድ እጅግ በጣም ትልቅ የፋይናንስ ቀውስ ነው የሚያመጣው። ይህም ምንም የሚካድ አይደለም እጅግ ተጎድተናል" በማለትም የዚያን ያህል ደግሞ አየር መንገዱ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ የሚያኮራ ሥራ ሰርቷል ሲሉ ድርጅቱ የሰራቸውን ሥራዎች ዘርዝረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢበርም ባይበርም በወር አምስት ቢሊየን ብር ያወጣል ያሉት አቶ ተወልደ ከመጋቢት ወር ጀምሮ የመንገደኞች ጉዞ በሚቆምበት ጊዜ የድርጅቱን ቋሚ ወጪዎች ለመሸፈን፣ አውሮፕላን ለመግዛት የተበደርውን ብድር ከነወለዱ መመለስ ይተበቅበታል። በተጨማሪም አውሮፕላኖችን የተከራየንበት ወርሃዊ የኪራይ ወጪ ለመክፈል፣ እንዲሁም የሠራተኛ ደሞዝ፣ ጥቅማጥቅም፣ አበል፣ ለመሸፈን የሚያስችለውን "በየወሩ አምስት ቢሊየን ብር በየወሩ እንዴት ነው የምናገኘው? ይህ ወረርሽኝ ከቀጠለስ ምን እናደርጋለን?" በማለት መወያየታቸውን ይጠቅሳሉ። በዚህ ወቅት "መጀመሪያ እድገት የነበረውን ስትራጂያችንን ወደ ሕልውና ማረጋገጥ ለወጥን" በማለትም ከመንገደኛ ማጓጓዝ ባሻገር ያለውን እድል በመፈተሽ የጭነት አገልግሎት መስጠትን በወቅቱ ያገኙት ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰዋል። አየር መንገዱ በዚህ ረገድ አስር 777 በጭነት ትራንስፖርት ምርጥ የሚባሉ አውሮፕላኖች፣ በተጨማሪም ሁለት 737 አውሮፕላኖች ስላሉት፤ እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ቶን ማስተናገድ የሚችልና ከነሲንጋፖር ከነሆንክ ኮንግ ከነአምስተርዳም ጋር ሊወዳደር የሚችል በጣም ዘመናዊ የካርጎ ተርሚናል ስላለው ይህንን እንደ ዕድል መጠቀማቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በዚያ ወቅት የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁሶች በጣም የሚፈለጉበት ጊዜ ነበር ያሉት አቶ ተወልደ ያለውን የገበያ ፍላጎት በመመልከት ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አፍሪካ በርካታ ጭነቶችን ማጓጓዛቸውን ያስረዳሉ። የድርጅቱ ገበያ እየጨመረ ሲመጣም ቁሳቁሶቹን በጭነት አውሮፕላኖች ብቻ ማንሳት ስላልተቻለ በፍጥነት የ25 የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወንበራቸውን በማውጣት ወደ ወደ ካርጎ ማዞራቸውን ይጠቅሳሉ። ይህንን በማድረጋቸው የተገኙ ጥቅሞችን ሲገልጹም ሠራተኛ ከሥራ አለማሰናበታቸውን፣ የሠራተኛ ደሞዝ አለመቀነሱን እና ነጥቅማጥቅሙ መከፈሉን፣ ሶስተኛ ምንም አይነት የገንዘብ ድጋፍ ከማንም አለመጠየቃቸውን ያነሳሉ። አክለውም ለጊዜው ሥራ ማስኬጃ የሚሆን ብድር አልወሰድንም፤ ብድራችንም እንዲራዘምልን አልጠየቅንም በማለት በኮቪድ-19 ወቅት በወሰዷቸው እርምጃዎች ያገኟቸውን ስኬቶች ይዘረዝራሉ። አየር መንገዱ ይህንን ሲያደርግ በዚህ በወረርሽኝ ጊዜ ህይወት የማትረፍ ሥራ መስራቱን ያነሳሉ። "የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ስፔንን ረድቷል። የኮቪድ-19 መከላከያ እቃዎችን በማቅረብ። ያ ማለት ሕይወት አትርፈናል ማለት ነው።" ፖርቹጋል፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ብራዚል እና አፍሪካ ሊደርስ ይችል የነበረውን ቀውስ መከላከል የሚያስችሉ የመከላከያ እቃዎችን ሕክምና መሳሪያዎችን በወቅቱ በማድረሳቸው ምክንያት አገሮችና ሕዝቦች ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ክብርና ውለታ እንዳላቸውም ጠቅሰዋል። "የጃክማ ፋውንዴሽን እርዳታን ከቻይና አምጥተን በስድስት ቀን ውስጥ አፍሪካ ውስጥ አከፋፍለናል" ያሉት አቶ ተወልደ "ፍጥነታችን በጣም ተደንቋል።" ሲሉ የአፍሪካ አገሮችም የአሊባባ ፋውንዴሽንም በሥራው መደነቃቸውን ይጠቅሳሉ። ይህንን ተከትሎም የዓለም የምግብ ድርጅት አዲስ አበባን የተባበሩት መንግሥታት በሙሉ የሰብዓዊ እርዳታ ማከፋፈያ አድርጓታል ሲሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ራሳችንን ጠቅመን፣ አየር መንገዱን አድነን፣ ሠራተኞቻችንን ሳንበትን፣ የሠራተኞቻችንን ደሞዝ ሳንቀንስ እና ሕይወት ማትረፍ በመቻላችን እንደ አንድ ዜጋ ትልቅ ኩራት እንደሚሰማቸው ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ለቫይረሱ ተጋላጭ መሆናቸውን ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስፈላጊውን የግንዛቤ መስጫ ትምህርቶችን በማድረግና ጥንቃቁዎችን በመውሰድ ወደ 17 ሺህ የሚጠጉ የድርጅቱ ሠራተኞች በጤና እንደሚገኙ ገልፀዋል። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም አምስት ሠራተኞቹ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በማስታወስ ሁሉም ማገገማቸውንና አሁን ደግሞ ባለፈው ሳምንት ሁለት ሠራተኞች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸው በድርጅቱ ለይቶ ማቆያና ማከሚያ ውስጥ እንደሚገኙ አብራርተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመከላከል የሚረዱ ሥራዎችን በአግባቡ ተግባራዊ እንደሚያደርግ የገለፁት አቶ ተወልደ "በረራ ባለማቋረጣችን ለዚህ ልምድ አግኝተናል" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/53075791
amh
business
ዚምባብዌ የዋጋ ንረትን ለመግታት የወርቅ ሳንቲሞችን አስተዋወቀች
የዚምባብዌ ማዕከላዊ ባንክ ከአገሪቱ ኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ጋር ተደምሮ እየናረ የመጣውን የዋጋ ንረት ለመግታት የወርቅ ሳንቲሞችን በመገበያያነት ለመጠቀም ይፋ አድርጓል። የአገሪቱ ዓመታዊው የዋጋ ግሽበት ከ190 በመቶ በላይ ማደጉን ተከትሎ የማዕከላዊ ባንቡ በያዝነው ወር የወለድ ተመኑን ከእጥፍ በላይ በማሳደግ 200 በመቶ አድርሷል። እያንዳንዱ ሳንቲም በዓለም አቀፍ ገበያ አንድ አውንስ ወርቅ የሚኖረውን ዋጋ ብሎም 5 በመቶ ሳንቲሙን ለማምረት የወጣውን ተጨምሮ ያወጣል። ባሳለፍነው አርብ አንድ አውንስ ወርቅ 1,724 ዶላር ያወጣ ነበር። የዚምባብዌ ሪዘርቭ ባንክ ገዥ ጆን ማንጉዲያ እንዳሉት ሳንቲሞቹ የሚጠበቀውን ለውጥ ካመጡ በቀጣይ በሱቆች ውስጥ መጠቀም ሊጀመር ይችላል። ሳንቲሙ "ሞሲ-ኦአ-ቱኒያ" የሚል ጽሑፍ ያረፈበት ሲሆን ትርጉሙም "የነጎድጓድ ጭስ" ማለት ነው። ይህም በዚምባብዌ እና ዛምቢያ ድንበር ላይ የምትገኘውን ቪክቶሪያ ፏፏቴ የሚያመነጨውን ጭስ ያመለክታል። ለዓመታት ሲያሽቆለቁል የቆየው የዚምባብዌ ዶላር በዚህ ዓመት ከዋና ዋና ምንዛሬዎች አንጻር ዋጋው የበለጠ ወድቋል። አገሪቱ ለአራት አሥርት ዓመታት ያህል በሥልጣን ላይ በነበሩት ሟቹ ሮበርት ሙጋቤ የሥልጣን ዘመን መፈጠር የጀመረውን የኢኮኖሚ ቀውስ አሁንም ድረስ እያስተናገደች ትገኛለች። በዚሁ የዋጋ ግሽበት ምክንያት እአአ በ2009 የዚምባብዌ ዶላርን ለመገበያያነት ላለመጠቀም ተገዳለች። በምትኩ የውጭ ምንዛሬዎችን በተለይም የአሜሪካን ዶላር በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል። የአገር ውስጥ ምንዛሪ ከአሥር ዓመታት በኋላ እንደገና ወደ ሥራ ገብቷል። ነገር ግን በፍጥነት ዋጋውን እንደገና አጥቷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cx0qqnwwevxo
amh
business
ቢትኮይንን ለሁሉም አገልግሎትና ግብይት የምትጠቀመው አገር
የቢትኮይን ዋጋ ከሌላው ጊዜ በተለየ በእዚህ ሳምንት በጣም ቀንሷል። የኤል ሳቫዶር መንግሥት ግን ቢትኮይንን ሕጋዊ መገበያያ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል። ይህንን ለማበረታታትም በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ነው። ይህ ውሳኔ ከተወሰነ ከ9 ወር ወዲህ መንግሥት 200 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለቢትኮይን ፈሰስ አድርጓል። አሁን ደግሞ የውሻ ባለቤቶች በቢትኮይን የሚከፍሉ ከሆነ በጣም በርካሽ እንዲታከሙ አንድ ሆስፒታል አመቻችቷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cgr9yx339elo
amh
business
የአርሶ አደሮችን ሕይወት ለማቅለል ዘመናዊ ጎተራ የሠራችው ወጣት
ደራርቱ ደረጀ በጅማ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውስጥ የባዮ ሜዲካል ትምህርት ክፍል መምህርት ናት። እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪዋን ባዮ ሜዲካል ኢሜጂንግ በሚባል የትምህርት ዘርፍ እየተማረች ሲሆን፣ ከትምህርቷ ጎን ለጎን ፈጠራዎች ላይ ተሰማርታለች። ከሥራዎቿ መካከል አንዱ የሆነው ደግሞ አርሶ አደሮችን መሠረት በማድረግ የሠራችው ዘመናዊ ጎተራ ነው። "ገበሬዎቻችን የሚጠቀሙበት ጎተራ ከጭቃ አልያም ከአፈር ስለሚሠራ የታፈነ ነው። በዚህም ምክንያት እህሉ በነቀዝ እንዲበላ ይሆናል" ትላለች ደራርቱ። ደራርቱ አርሶ አደሮች የሚጠቀሙበት ባሕላዊው ጎተራ ምርታቸውን እንዲባክን ያደርጋል በማለት፣ ይህ ችግርም የከፋ እና ገበሬዎቹን ለምግብ ዋስትና እጥረት የሚያጋልጥ ነው ትላለች። የዓለም የምግብ ድርጅት፣ እያደጉ ባሉ አገራት ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከየሚያመርቱት ምርት፣ 40 እጅ ያህሉ ከማጠራቀሚያ ቦታ እጥረት የተነሳ እንደሚባክን ይገልጻል። አስተማማኝ የእህል ማጠራቀሚያ አለመኖር ደግሞ አርሶ አደሮች ጉልበት እና ጊዜያቸውን የፈጁበት ምርት በተባይ እንዲበላ እና በእርጥበት ምክንያት ለብልሽት እንዲጋለጥ ያደርጋል። ይህ የእህል ብክነትም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን ለምግብ ዋስትና ችግር እንዲጋለጡ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ቀዳሚው ነው። ብዙ አርሶ አደሮች የሚጠቀሙበት ጎተራ ከእንጨት እና ከጭቃ የተሰራ መሆኑን የምትናገረው ደራርቱ "ብዙ አርሶ አደሮች ይቸገራሉ። እህላቸውን ነቀዝ ይበላዋል" ትላለች ደራርቱ። የምርት ማከማቻው አሰራር ነፍሳት ወደ ጎተራው በቀላሉ በመግባት እህል ውስጥ እንዲራቡ እንደሚያደርገቸውም ታስረዳለች። በተጨማሪም ይህ በባህላዊ መንገድ የሚሠራ ጎተራ፣ እንደ ልብ አየር ስለማይዘዋወርበት በውስጡ ያለው ሙቀት እንደ ነቀዝ ላሉ ነፍሳት መራቢያነት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። "የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሁን እየተጠቀሙበት ያለው ጎተራ፣ ነፍሳት ውስጥ ገብተው በቀላሉ እህሉን እንዲያበላሹት ያስችላቸዋል። ስለዚህም ገበሬዎቹ ከሚያመርቱት 44.7 በመቶ ያህሉ በዚህ ሁኔታ ይባክናል" ስትል ታስረዳለች። ዘመናዊው ጎተራ ደራርቱ ይህንን የአርሶ አደሮች ችግር መሠረት በማድረግ አልሙኒየም በመጠቀም ዘመናዊ ጎተራ መስራቷን ትናገራለች። ይህ ከአልሙኒየም የተሰራው ጎተራ ነፍሳት ወደ ጎተራው በቀላሉ እንዳይገቡ የሚከላከል መሆኑንም ታስረዳለች። ይህ ጎተራ "አየር እንዲያስገባ ሆኖ ነው የተሰራው። ይህም ጎተራ ውስጥ ሙቀት እነዳይፈጠር ይረዳል። ነፍሳት ወደ ጎተራው ቢገቡ እንኳ ቶሎ እንዲሞቱ ያደርጋቸዋል" በማለት ታስረዳለች። አየር ወደ ጎተራው እንዲገባ የሚያደርገው መላ የባትሪ ኃይልን በመጠቀም የተሰራ ነው። "ለወደፊቱ ግን የፀሐይ ብርሃንን በመጠቀም እንዲሰራ ለማድረግ እያሰብን ነው" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ደራርቱ የሠራችው ይህ ዘመናዊ ጎተራ አነስተኛ የሚባለው እስከ 50 ኪሎ መያዝ የሚችል ሲሆን፣ በሰዎች ፍላጎት ላይ በመመስረት ትልልቅ ጎተራዎችን መስራት ይቻላል። ደራርቱ ይህንን ጎተራ ለመስራት ወጪውን ራሷ መሸፈኗን ገልጻ፣ በሥራው ላይ ግን የሚያማክራት ሰው እንዳለ ትናገራለች። በሌላ በኩል ይህ ፕሮጀክት በተፈለገበት መልኩ ሥራ ላይ እንዳይውል እንቅፋት የሆነባት የገንዘብ ችግር መሆኑን በማንሳትም፣ ይህንን ለመቅረፍ የተለያዩ ውድድሮች ላይ እየተሳተፈች ነው። በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት 'ቶታል ኢነርጂስ ስታርት አፐር' የሚባል ውድድር ላይ የመጀመሪያውን ዙር ማለፏን ትገልጻለች። "አሁን ማነቆ የሆነብን የገንዘብ እጥረት ነው። ይህንን ውድድር ካለፍን በቀላሉ ገበሬዎቻችን ጋር መድረስ እንችላለን" ብላለች ደራርቱ።
https://www.bbc.com/amharic/news-60906496
amh
business
ቤይሩት ውስጥ በመሳሪያ አስገድዶ ገንዘቡን ከባንክ የወሰደው ጀግና ተባለ
መሳሪያ ታጥቆ ከቁጠባ ሂሳቡ ገንዘቡ እንዲሰጠው ያስገደደው የሊባኖስ ዜጋ በሕዝቡ ጀግና ተብሎ ተወደሰ። ሊባኖስ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ባንኮች ደንበኞቻቸው ወጪ በሚያደርጉት ገንዘብ ላይ ገደብ ጥላለች። ይህ ግለሰብ ግን መሳሪያ ታጥቆና ባንክ ውስጥ ነዳጅ አርከፍክፎ ለሆስፒታል ክፍያ ለመፈጸም የሚያስፈልገው ገንዘቡ እንዲሰጠው በኃይል መጠየቁን ኤኤፍፒ ዘግቧል። በግለሰቡ እና በባንኩ መካከል ለስድስት ሰዓታት ከቆየ ፍጥጫ በኋላ ግለሰቡ የጠየቀውን ገንዘብ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ ማግኘት ችሏል። ይህ በስም ያልተጠቀው ግለሰብ ተግባርም በሕዝቡ ዘንድ አድናቆትን አስገኝቶለታል። ከባንኩ ውጪ ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች “ጀግና ነህ” እያሉ ጠርተውታል። የግለሰቡ ወንድም ለጋዜጠኞች ሲናገር፤ “ወንድሜ በባንክ ሂሳቡ 210ሺህ ዶላር አለው። የሆስፒታል ወጪውን ለመሸፈን 5ሺህ 500 ዶላር ፈልጎ ነበር” ብሏል። ከባንኩ ውጪ የነበሩት የግለሰቡ ወንድም እና ባለቤት፤ “ሁሉም ሰው ሊያደርገው የሚገባው ይሄን ነው። የራሳቸው የሆነውን ማግኘት አለባቸው" ብለዋል። ኤልቢሲ የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ የግለሰቡ ቤተሰብ አባላት በሆስፒታል እንደሚገኙ እና ገንዘብ እጅጉን ያስፈልጋቸው እንደነበር ዘግቧል። የቴሌቪዥን ጣቢያው ጨምሮ እንደዘገበው ወደ ባንኩ በኃይል ከገባው ግለሰብ ጋር ድርድር ከተደረገ በኋላ ከቁጠባ ሂሳቡ 35ሺህ ዶላር ተሰጥቶታል። ፖሊስ ግለሰቡን እና በእገታ ስር የቆዩ የባንክ ሠራተኞችን ከአካባቢው ይዞ የወጣ ሲሆን በግለሰቡ ላይ ክስ ይመሰረት እንደሆነ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። እአአ 2019 ላይ ሊባኖስ የገጠማትን ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ ለመቋቋም ያስችለኛል ብላ ተግባራዊ ካደረገቻቸው ውሳኔዎች መካከል ሰዎች ከቁጠባ ሂሳባቸው ወጪ በሚያደርጉት የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ መጣል ነው። ከዚህ በተጨማሪም ከአገር ውጪ በሚላክ የገንዘብ መጠን ላይም ገደብ ተጥሏል። ይሁን እንጂ እነዚህ ክልከላዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። በሊባኖስ የተከሰተው ምጣሄ ሃብታዊ ቀውስ የአገሪቱ ገንዘብ ዋጋውን ከ90 በመቶ በላይ እንዲያጣ አድርጎታል። የዋጋ ግሽበት ጣሪያ ነክቷል፤ እንደ መድሃኒት እና ስንዴ ባሉ ምርቶች ላይ እጥረት አጋጥሟል። የተባበሩት መንግሥታት ከአምስት ሊባኖሳዊያን አራቱ በድኅነት ውስጥ ይኖራሉ ይላል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n30811d2no
amh
business
ኬንያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከሰባት ቢሊዮን ሺልንግ በላይ ጥቅም አልባ ሆነ
የኬንያ ማዕከላዊ ባንክ እንዳሳወቀው ኬንያ የመገበያያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከ95% በላይ የሚሆነው የአንድ ሺ ሺልንግ ተመልሶ በአዲሱ ተተክቷል። በዚህ መካከል ግን መሃል ላይ ተንሳፎ የቀረ ገንዘብ እንዳለም ተገልጿል። "ይህ ማለት 7.3 ቢሊዮን ሺልንግ ጥቅም አልባ ሆኗል፤ እንደ ወረቀት ነው የሚቆጠረው" በማለት የባንኩ አስተዳዳሪ ፓትሪክ እንጆሮጌ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። •የኢትዮጵያ ሙዚቃ- ከመስከረም እስከ መስከረም •ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት ባንኩ እንዳሳወቀው አዲስ የመገበያያ ገንዘብ የታወጀው ሰኔ አንድ ቀን ሲሆን ከዚያ ዕለትም ጀምሮ ሲዘዋወር የነበረ 217 ሚሊዮን ሽልንግም ተገኝቷል። ከመስከረም ሃያ ጀምሮ አሮጌው የመገበያያ ገንዘብ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በዚህ ወቅትም ከሶስት ሺ የሚበልጡ አጠራጣሪ ልውውጦች ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን በሚመለከተው የመንግሥት አካልም ምርምራ እንደሚደረግም ኢንጆሮጌ አክለው ገልፀዋል። የገንዘብ ቅየራው በሃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና ለማስቀረትና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርንም ለመቆጣጠር እንዲያስችል ነው። •ኬንያ ሳንቲሞቿ ላይ የነበሩ መሪዎችን በእንስሳት ቀየረች አፍሪካ ታክስ ጀስቲስ ኔትወርክ የተባለ ድርጅት እንዳሳወቀው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት ኬንያ በየአመቱ 400 ሚሊዮን ዶላር እንደምታጣ አስታውቋል። ባንኩ እንዳስታወቀውም የገንዘብ ቅይይሩ መሳካቱንና ከዚህ በኋላ ስርአት ባለው መንገድ የገንዘብ ዝውውር እንደሚከናወን ነው።
https://www.bbc.com/amharic/49916629
amh
business
"ለ15 ዓመታት ኮንዶሚኒየም እየጠበቅኩ ሁለት ልጆች ወልጃለሁ" የአዲስ አበባ ነዋሪ
"ለ15 ዓመታት ኮንዶሚኒየም እየጠበቅኩ ሁለት ልጆች ወልጃለሁ" ይህ የተሰማው ስሜ አይጠቀስ ካሉ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ነው። ቤት የመኖር ተስፋቸውን ሰንቀው የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ይደርሰኛል ብለው የተመዘገቡት በ1997 ዓ.ም ነበር። የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሰጣቸው በማህበር ተደራጅተው ከተመዘገቡት የመጀመሪያው ዙር ተመዝጋቢም መካከል ናቸው። ለአስራ አምስት ዓመታትም ያህል ቤት ይደርሰኛል ብለው ጠብቀዋል። በእርሳቸው ማህበር ውስጥ ከሚገኙት ከሃያ አባላቱ በላይ በሙሉ የቤት ባለቤት ቢሆኑም እርሳቸው ግን አልደረሳቸውም። ከእርሳቸው የሚጠበቅባቸውን በየወሩ ምንም ሳያዛንፉ ከመቆጠባቸውም አንፃር ለምን አልደረሰኝም ብለው ሲያስቡም የሚሰጡት ምክንያት "ዕጣው ፍትሃዊ ስላልሆነ ነው" የሚል ነው። "በመተዋወቅና በመጠቃቀም ቢሆን ነው እንጂ ይህንን ያህል ዓመት ጠብቄ የማይደርሰኝ ምክንያት የለውም" ይላሉ። ከዚያም በተጨማሪ ያልተመዘገቡ ሰዎች ቤት እየተሰጣቸው እንደሆነም ሲሰሙ ይህንኑ ጥርጣሬያቸውን አረጋገጠላቸው። ሆኖም ለዓመታትም ቤት ይኖረኛል በሚል ተስፋም የቆጠቡትን ብር ሊነኩም አልፈለጉም "ለሌላ ነገር እንዳላደርገው ሁሉ ይዞኛል" ይላሉ። ሲመዘገቡ ገና ወንደላጤ ነበሩ አሁን ሁሉ ተቀይሮ ትዳር ይዘዋል። የሁለት ልጆች አባት ሆነዋል፤ ሆኖም የተመዘገቡት ኮንዶሚኒየም የውሃ ሽታ በመሆኑ "ላም አለኝ በሰማይ..." ሆኖባቸዋል። ለአመታትም የኮንዶሚኒየም ዕጣ ሲወጣ በጉጉት ይጠብቃሉ። ይከታተላሉ ግን አልሆነም። የሚያውቋቸው ሰዎች ቤት አግኝተው ሳይኖሩበት ወይ ሲሸጡት ሲያዩ እርሳቸው በኪራይ ቤት መንከራተት ያሳዝናቸዋል። በተከታታይም ቤቶች ልማት ሄደው ሲጠይቁም የተመዝጋቢዎች ዝርዝር ውስጥ እንዳሉ ይነግሯቸዋል። "ሌሎች ሰዎች እየደረሳቸው ነው እንዴት ነው ነገሩ ብለን ስንጠይቅም 'ያው ስምህ አለ'" ከማለት ውጭ ሌላ ምላሽ ለዓመታት አልተሰጣቸውም። "ጠብቅ" የሚለውም ምላሽ ተስፋ እያስቆረጣቸው እንደመጣ የሚናገሩት እኚህ ግለሰብ፤ ከሰሞኑ ደግሞ ከህገወጥ መሬት ወረራና ኢ-ፍትሃዊ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ ጋር ተያይዞ በሚሰሙ መረጃዎች የነበረቻቸውም ትንሽ ተስፋ ተሟጠጠች። "በጣም ያሳዝናል፤ ያሳፍራል፤ ከዚህ በኋላ ተስፋ አላደርግም" ይላሉ። ቤት (መጠለያ) መሰረታዊ ጥያቄና መብት ቢሆንም በኢትዮጵያ ባሉ ትልልቅ ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ ሰዎች የግል ቤት መኖር ማለት እንደ ቅንጦት የሚታይበት ነው። በርካቶች በማይቀመስ ኪራይ ብራቸውን እየገፈገፉ ለመኖርም ተገደዋል። ገዝቶ የቤት ባለቤት መሆን የሚታሰብ ባይሆንም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የጥራትና ሌሎች ጉድለቶች ቢኖርባቸውም፤ ለብዙዎች የቤት ባለቤት የመሆን ተስፋቸው ሆኖ ቆይተዋል። ሆኖም ለዓመታት ጠብቀው ቤት ሳያገኙ የቀሩ እንዲሁም ቤቱ ደርሷቸው ያልተቀበሉ በርካቶች አሉ። ሌላኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ በ40/60 የቁጠባ ፕሮጀክት ተመዝግበው በሁለተኛው ዙር የቤት እጣ እድለኛ እንደሆኑ ተነገሯቸው። ከስድስት ዓመታት በፊት ተመዝግበው ዕጣው ወጥቶ ቤቱ ከደረሳቸው በኋላ፤ በድልድሉ መሰረት ውል ቢዋዋሉም ቤቱን ሳይረከቡ አንድ ዓመት አለፋቸው። ሙሉውን መክፈል የሚችሉ መቶ በመቶ እንዲከፍሉ ካለበለዚያ ደግሞ በወጣው እቅድ መሰረት አርባ በመቶ ከፍለው ቀሪውን ደግሞ ከባንክ ጋር ውል ተፈፅሞ ቤታቸውን እንዲረከቡ ነበር። የዛሬ ዓመትም የሚጠበቅባቸውን አርባ በመቶ ክፍያ ከፈፀሙ በኋላ ቁልፍ ለመረከብና ከቤቶች ልማትም ቤታቸውን ሊረከቡ የደረሳቸው ነገርም የለም። በቅርቡ እንዲሁ እጣ የደረሳቸው ሰዎች በማህበር ሲደራጁ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲነገሩም ቤቱ አልቋልና ተረከቡ ተብለው ወደደረሳቸው አካባቢ ሄዱ። በሁለተኛው ዙር 18 ሺህ ያህል እድለኞች መኖራቸውን የሚናገሩት እኚሁ ግለሰብ "ልንረከብ ሄደን ቤቱ አላለቀም፤ ቁልፍ ልንረከብ ሄደን ጭራሽ ቤቱ በር የለውም፤ ይሄ እንዴት ይሆናል? የማይሆን ሥራ ነው እየሰሩብን ያሉት" ብለዋል። የአያት አካባቢ ነዋሪ የሆኑት እኚሁ ግለሰብ በሚኖሩበት አካባቢ የሚገኙ መሬቶች በአስደናቂ ፍጥነት መታጠራቸው ጥያቄያቸውን አጭሮታል። በሳምንቱ መጀመሪያ፣ ሰኞ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተባባሰ የመጣ፣ የመንግሥታዊ መዋቅሮች ድጋፍ ያለው ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ እንዳለ ባካሄድኩት ጥናት ደርሼበታለሁ ሲል ማስታወቁ ይታወሳል። የጋራ ቤቶችን በተመለከተም የከተማው አስተዳደር ባወጣው ደንብ መሰረት "በምንም መስፈርት የቤት ተጠቃሚ ሊሆኑ የማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤትና የነዋሪነት መታወቂያ ተሰጥቷቸዋል" ሲል በጋራ የመኖሪያ ቤቶች በኩል አሉ ያላቸውን የአሰራር ችግሮች ጠቅሷል። ጥናቱ እንዳለው በከተማዋ የተለያየ አይነት ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ ተግባራት እንደተከናወኑ አመልክቶ፤ እነዚህም በጅምር ቤት ስም ከባለ ይዞታዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በመግዛት ግንባታ የማካሔድ፣ ባዶ መሬቶችን በቡድንና በግለሰብ ደረጃ በማጠር የመያዝ እንዲሁም ለሌላ ወገን የማስተላለፍ በተጨማሪም "በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በተዘረጋው ሰንሰለት በጥቅም ተጋሪነትና በዝምድና" ሠፋፊና ቁልፍ ቦታዎችን መያዝ በከተማዋ ውስጥ መታየቱን ገልጿል። የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የአሁኑ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በበኩላቸው፤ በቀጥታ የኢዜማን ጥናት ባይጠቅሱም ማክሰኞ ዕለት በፌስቡክ ገጻቸው ላይ በሰጡት ምላሽ የቀረበውን ሪፖርት " ሐሰተኛ" ብለውታል። አቶ ታከለ እንዳሰፈሩት "የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ስንወስድበት የቆየንበት ጉዳይ ነው" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/53996764
amh
business
ፈረንሳዊው ቢሊየነር በፓሪስ ተደብድበው ተዘረፉ
የፈረንሳዩ ቢሊየነር በርናንድ ታፒ በፓሪስ ኩምላቪል መኖርያ ቤታቸው ውስጥ ሳሉ ነው ዘራፊዎች ገብተው የደበደቧቸው፡፡ ባለቤታቸውም ክፉኛ ተጎድተዋል፡፡ ቢሊየነሩ በርናንድ ታፒ የዝነኛው የአዲዳስ የስፖርት ትጥቅ አምራች የቀድሞ ባለቤት ናቸው፡፡ የቢሊየነሩን ቤት የደፈሩት ዘራፊዎች ቁጥርና ማንነት እስከአሁን አልታወቀም፡፡ ዘራፊዎቹ ቢሊየነሩን በርናንድ ታፒ እና ባለቤታቸው ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው ቀስቅሰው በኤሌክትሪክ ገመድ ካሰሯቸው በኋላ ነበር ጠቀም ያለ ገንዘብ ለመዝረፍ የሞከሩት፡፡ ሆኖም በቢሊየነሩ ቤት እምብዛምም የፈለጉትን አላገኙም፡፡ የታፒንና ባለቤታቸውን የወርቅ ጌጣጌጦች ግን ሰብስበው ወስደዋል፡፡ የ78 ዓመቱ በርናንድ ታፒ በፈረንሳይ አወዛጋቢ ባለሀብትና ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ ሽቅርቅርና ሁሌም የሚዲያ መነጋገርያ መሆን የሚወዱት ታፒ ከዚህ ቀደም ሚኒስትር ነበሩ፡፡ በተለይ ዝነኛውን የአዲዳስ ኩባንያን ከመሸጣቸው ጋር ተያይዞ ስማቸው በሙስና ተደጋግሞ ይነሳል፡፡ የ70 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ባለቤታቸው ወ/ሮ ዶሚኒክ እና ቢሊየነሩ በርናንድ ታፒ ሌሊት 6 ሰዓት ተኩል ግድም በተኙበት ነው ቢያንስ ከ4 በላይ የሆኑ ዘራፊዎች የቤታቸውን አጥርና የጥበቃ ሰንሰለቱን አልፈው በመግባት በቁጥጥር ያዋሏቸው፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ሌሊት ነው፡፡ ዘራፊዎቹ ቢሊየነሩን በርናንድን ጸጉራቸውን ይዘው መሬት ለመሬት እየጎተቱ ከወሰዷቸው በኋላ ውድ ጌጣጌጦችንና የሚያስቀምጡበትን ቦታ እንዲጠቁሟቸው ሞክረዋል፡፡ ሆኖም ቤት ያስቀመጡት እዚህ ግባ የሚባል ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጣ ንብረት ባለመኖሩ ዘራፊዎቹ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ እንደከተታቸው ተነግሯል፡፡ በዚህ ብስጭትም ቢሊየነሩን በዱላ ነርተዋቸዋል፡፡ በዚህ መሀል የ70 ዓመት ባለቤታቸው ወ/ሮ ዶሞኒክ ዘራፊዎቹን አምልጠው ለጎረቤት ቤታቸው እየተዘረፈ መሆኑን በማሳወቃቸው ፖሊስ ደርሶ አድኗቸዋል፡፡ ባለቤታቸው በዘራፊዎቹ ክፉኛ በመደብደባቸው አሁን ሆስፒታል ነው የሚገኙት፡፡ ሌቦቹ እስከ አሁን ወሰዱ የተባለው 2 ውድ ሮሌክስ የእጅ ሰዓቶችን፣ የጆሮ ጌጦችን፣ የእጅ አምባሮችን እና ቀለበቶችን ብቻ ነው፡፡ ቢሊየነሩ በርናንድ ታፒ ከ1992 እስከ 93 የፈረንሳይ የከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ነበሩ፡፡ የታዋቂው የስፖርት ቁሳቁስ አምራች አዲዳስ ከፍተኛ የአክስዮን ባለቤት ነበሩ፡፡ በኋላ ደግሞ የዝነኛው የኦሎምፒክ ዴ ማርሴይ የእግር ኳስ ቡድን ባለቤት ሆነዋል፡፡ ላ ፕሮቬንሴና ሌሎች በርካታ ሚዲያዎችንን በባለቤትነት አስተዳድረዋል፡፡ እሳቸውም ቢሆን በመተወን፣ በመዝፈን እና የራዲዮና የቴሌቪዥን ትዕይነት በማሰናዳት ዝነኛ ነበሩ፡፡ በ1990ዎቹ ኩባንያቸው ኪሳራ በማወጁ ከሒሳብ ማጭበርበር፣ ከግብር ስወራና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ተከሰው 5 ወራት እስር አሳልፈዋል፡፡ በርናንድ ላለፉት 20 ዓመታት በፍርድ ቤት ከአዲዳስ ኩባንያ ሽያጭ ጋር በተያያዘ እየተካሰሱ ይገኛሉ፡፡ ኩባንያውን በወቅቱ የሸጡት በግማሽ ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-56636712
amh
business
የሲዳማ ቡና በኪሎ ለምን እስከ አርባ ሁለት ሺህ ብር ተሸጠ?
ያለፉት ሦስት ዓመታት ለሲዳማ ቡና ‘ቡናማ’ ዓመታት ናቸው። ወርቃማ እንዳይባሉ ቡና ከወርቅም በላይ ነኝ ያለባቸው ዓመታት ናቸው። ከዚህ ጀርባ ደግሞ ሦስት ስሞች ቀድመው ወደ አዕምሮ ይመጣሉ። ንጉሤ ገመዳ፣ ታምሩ ታደሠ እና ለገሠ በጦሳ ናቸው። ሦስቱም የሲዳማ ቡናን ይዘው ለውድድር ቀርበው አላፈሩም። ይህ የቡና ውድድር ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ይባላል። ውድድሩ ቡናን በጥራት ይለያል። ቀጥሎ በዓለም አቀፍ ጨረታ ለገበያ ያቀርባል። ንጉሴ አንድ ኪሎ ቡናውን በ407 ዶላር ሸጠዋል። የታምሩ ቡና ደግሞ 330 ዶላር ይገባዋል ተብሎ ዋጋ ተቆርጦለታል። የለገሠ ቡና ግን ከሁለቱም የላቀ ነው። አንዱ ኪሎ ቡና 884.10 ዶላር ተሽጧል። በዚህ ዋጋ የተሸጠ የኢትዮጵያ ቡና የለም። አንድ ኪሎ ቡና 47 ሺህ 236 ብር ተሽጧል። ስኬቱን ምስጋና “በቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ዙሪያ ለተሠራው ሪፎርም” የሚሉት አቶ ምንዳዬ ምትኩ የሲዳማ ክልል ቡና ፍራፍሬ እና ቅመማ ቅመም ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው። ለአቶ ምንዳዬ ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ከውድድርም በላይ ነው። ‘አርሶ አደሮችንም ክልሉንም እየጠቀመ ያለ ውድድር ነው።’ መነቃቃት እና የሥራ ዕድልም ፈጥሯል። “አርሶ አደሮቹና አቅራቢዎች በቀጥታ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሠራር ተዘርግቷል። በዚህም የሲዳማ ክልል በጣም ተጠቃሚ ነው። ከሦስት ዓመት ወዲህ በቡና ላይ ለውጡ ትልቅ ነው” ይላሉ። እውነትም ለውጥማ አለ። በመጀመሪያው ዓመት ያሸነፈው አርሶ አደር አሁን ሌላ ህይወት እየመራ ነው። አርሶ አደር ከሚባለው ማዕረግ በተጨማሪ ላኪነትንም ደርቧል። “ቀደም ሲል አነስተኛ ካፒታል ነበረው። (ከውድድሩ) በኋላ ግን የላኪነት ፈቃድ አውጥቶ ወደ ላኪነት አድጎ ሸላሚም ሆኗል።” ይህ የአንድ ግለሰብ ብቻ ታሪክ ነው። ተመሳሳይ ታሪክ ያላቸው ሰዎች ቁጥራቸው እየጨመረ ነው። “ይህ የክልሉ ሃብት ነው። ክልሉ ከእነዚህ ትልቅ ጥቅም ያገኛል፤ ገቢው ያድጋል። አርሶ አደሮቹ ህይወት ሲለወጥ ገበያውም ይነቃቃል። የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያለውን ትልቅ ችግር ይፈታል” የአቶ ምንዳዬ ሃሳብ ነው። ይህንን የሰሙ ‘እኛስ?’ ያሉበት ነው። በዚህ ዓመት ውድድርም በርካቶች ተሳትፈዋል። በዚህ ዓመት ደግሞ አርሶ አደሮች ብቻ እንዲያቀርቡ ተደርጓል። ባላቸው መሬት እና የመሬት ይዞታ አቅርበው እንዲወዳደሩ ነው የተደረገው። በዘንድሮው ውድድር አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡት የሲዳማ ቡናዎች ናቸው። “አንደኛ የወጣው ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ያገኘበት እጅግ በጣም አነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የነበረ ሰው ነው።” ጥራታቸውም ቢሆን ምርጥ ነበር። የአቶ ምንዳዬ “ዘንድሮ ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና ነው ያቀረብነው። አርሶ አደሩም የጥራቱን ሁኔታ ያሻሻለበት እና ፊቱን ወደ ቡና ልማት ያዞረበት ነው” ብለዋል። ዘንድሮ ለፍጻሜ የደረሱ 40 ተወዳዳሪዎች ነበሩ። 14ቱ ደግሞ ከሲዳማ ክልል ናቸው። የሲዳማን ቡና ምን እንዲህ ተፈላጊ፣ ተመራጭ እና ውድ አደረገው? ትልቁ ነገር አየሩ ነው። “በጣም ውጤታማ እየሆኑ ያሉት ደጋማ አካባቢ ያሉ ቡናዎች ናቸው” ይላሉ አቶ ምንዳዬ። ሌላው ደግሞ ‘ኦርጋኒክ’ (ተፈጥሯዊ) ቡና መሆኑ ነው። ምንም ዓይነት ኬሚካል አይዞርበትም። “የጥላ ዛፍም አላቸው። የቡና ፓኬጅ መጠቀማቸውም ሌላው [ምክንያት] ነው። የአየሩ ሁኔታም የረዳን ይመስላኛል” ይላሉ አቶ ምንዳዬ ምክንያቱ ብዙ መሆኑን በመጥቀስ። በተለይ የደጋ አካባቢ ቡናዎች ተመራጭ ሆነዋል። አሁን ቡና ወደ ደጋማው ሲዳማ አካባቢ እየሰፋ ነው። እነ አርቤጎና፣ ቡራ፣ ደንሳ፣ አሮሬሳ አካባቢዎች ቡና ማለትስ የእናንተ ተብለዋል። “በሌሎችም አካባቢ ይስፋፋል የሚል እምነት አለን። እነ ቦና አካባቢም ይጠቀማሉ ብለን እናስባለን” ይላሉ አቶ ምንዳዬ። አስገራሚው ነገር እነዚህ ቦታዎች ከቡና ጋር አይተዋወቁም ነበር። ለምሳሌ የዘንድሮው አሸናፊ ለገሠ በጦሳ ነዋሪነቱ አርቤጎና ወረዳ ቡርሳ ቀበሌ ነው። አርቤጎና አካባቢ በጣም ደጋማ አካባቢ ነው። አልቲቲዩዱም በጣም ከፍተኛ ነው። “አሁን ግን [በእነዚህ ቦታዎች] ከፍተኛ መነቃቃት ነው ያለው።” ቀደም ሲል እንሰት፣ ስንዴ እና ገብስ ያመርቱ ነበር። ጊዜ ሲቀየር እነሱም ተቀየሩ። ጊዜው ሲቀየር የሚያመርቱትም ተቀይሯል። “የኤክስቴንሽን ድጋፍ ይደረጋል። የቡና ፓኬጅ እንዲጠቀሙ ይደረጋል። ያረጁ ቡናዎች የመተከታት ሥራ ይከናወናል። ለባለሙያዎችም የስልጠና ድጋፍ እንሰጣለን። በተራው ባለሙያው እስከ ታች ወርዶ ይደግፋል። የተሻሻሉ ቡናዎች እንዲያመርቱ የበሽታ መከላከል ስራዎችን በተመለከተ ስልጠና፣ ክትትል እና ድጋፍ ይደረጋል” የአቶ ምንዳዬ ሃሳብ ነው። ቢቢሲ፡ እርስዎ ቡና ይጠጣሉ? አቶ ምንዳዬ፡ እኔ በጣም ቡና የምወድ ሰው ነኝ ቢቢሲ፡ ሌላ ቦታም ሄደው ቡና ይጠጣሉ? አቶ ምንዳዬ፡ [ሳቅ] ሌላ ቦታም ቡና እጠጣለሁ ቢቢሲ፡ እና የሲዳማ ቡና ከሌሎች በምን ይለያል? አቶ ምንዳዬ፡ ስለለመድኩት መሰለኝ የሲዳማ ቡና ይለያል። የቅመም ጣዕም አለው። በዚህ በኩል የራሱ ባህሪ አለው። የሲዳማ ቡና መጠጣት ከለመድክ ከፍተኛ ሱስ ነው የሚያሲዝህ። በቀን ቢያንስ 3 ስኒ ቡና ሳልጠጣ አልውልም። ሌላም ቦታ ስሄድ እጠጣለሁ። ብዙ ምርጥ ምርጥ ቡናዎች አሉን። የይረጋጨፌ ቡናም በጣም እወዳለሁ። በአጠቃላይ ቡና እጠጣለሁ። የሲዳማ ቡና ጥሩ ስሙ የገነነ ነው። ዕውቅናው እንዲጎለበት ከክልል እስከ ፌደራል ድረስ እየተሠራ መሆኑ ተነግሮናል። በአንድ ወቅት የቡና ዋጋ ወረደ። አርሶ አደሮች ቁጭ ብለው እንዲያስቡ ያደረገ የዋጋ መውረድ ነበር። በምን ልተካው ሲሉ ወደ አዕምሯቸው ሽው ያለላቸው ጫት ነበር። ጫት ቡናን እግር በእግር ተካ። ግን አልዘለቀበትም። አሁን ደግሞ ቀኝ ኋላ ነው ጉዞው። ቡና ግዛቴን አላስደፍርም አለ። “ጫት እና ባህር ዛፍ እየነቀሉ ወደ ቡና እየቀየሩ ያሉ በርካታ አርሶ አደሮች አሉ” ይላሉ አቶ ምንዳዬ። ከአንድ ኪሎ ቡና በአርባ ሺህዎች ከታፈሰ ጫት ለምኔ ነው ነገሩ። “ከዋጋውጋር ተያይዞ የመጣ [ለውጥ] ነው።” “ቀደም ሲል የልፋታቸውን አያገኙም ነበር። ማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ሰንሰለቱ ብዙ እና አስቸጋሪ ዘርፍ ነበር። [አርሶ አደሩ] ካመረተው የጉልበቱን ዋጋ እያገኘ ባለመሆኑ ወደ ሌሎች ሰብሎች እየገባ ነበር። አሁን ከተሻሻለ በኋላ ነው ወደ ቡና የገባው።“ “[አሁንም] ዓለም ላይ ካለው ዋጋ አንጻርም ቢሆን ሙሉ ለሙሉ ተጠቃሚ ነው ማለት አይቻልም” የአቶ ምንዳ ሃሳብ ነው። እንደካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ያሉት ለገበያው መሻሻል ትልቅ ጥቅም እየሰጡ ነው። ለዚህ ለውጥ ደግሞ ከቡናና ሻይ ባለስልጣን ጀምሮ የተዘረጋውን አሠራር በምክንያትነት ያቀርባሉ። ሁለት እና ከዚያ በላይ ሄክታር ያላቸው አርሶ አደሮች ቡናቸውን በተገቢው አዘጋጅተው ወደ ውጭ መላክ ይችላሉ። “የምርት እና ምርታማነት ማሻሻል ላይ ይሠራል። ከግብይት ስርዓቱ ህገወጦችን የመከላከል ስራዎችም ይሠራል። ይህን የሚከላከል ግብረ ሃይልም አለ። ሌላው ደግሞ የግብዓት አቅርቦት ነው። በዚህ በኩልም ማሻሻል አለ።” “የሲዳማ ቡና አልን እንጂ የኢትዮጵያ ቡና ማለት ነው። ቀደም ሲል መዳረሻ ያልነበሩ አካባቢዎችም የኢትዮጵያን ቡና ይፈልጋሉ። እንደ ክልል ስንጠቀም እንደሃገርም እንጠቀማለን። በክልል ደረጃም ቢሆን ከፕሬዝዳንቱ ጀምሮ እስከ ታች ድረስ በዚህ ልክ ይሠራል።“ ቡና ተተክሎ ምርት ለመስጠት ሦስት ዓመት ይጠይቃል። ቡና እየሰጠ 15 እስከ 18 ዓመት ይቆያል። ከዓመታት በኋላል እርጅና ሲጫነው መታደስ ይፈልጋል። ካልሆነ ምርት ይቀንሳል። ቡና ይህን ሁሉ አልፎ ነው ለገበያ የሚቀርበው። የካፕ ኦፍ ኤክሰለን ‘አውራ ፓርቲ’ ሆነናል የሚሉት አቶ ምንዳዬ ሦስቱንም ዓመት “የፕሬዚዳንሺያል ሽልማት” ማግኘታቸውን አንስተው በቀጣይም ማንም አይነቀንቀንም ይላሉ። “ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ መመልከት የለም። የክልሉም ፕሬዝዳንተ የሚመሩት ስለሆነ ከላይ እስከታች በትኩረት ስለሚሰራ ከዚህ በላይ መስራት እችላለን” ነው መልሳቸው እንዴት ተብለው ሲጠየቁ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c28wxj81xveo
amh
business
"በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ፈርተው ዛሬ መደብር አልከፈቱም"
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የጃኮብ ዙማን እስር ተከትሎ በአገሪቱ ሰላማዊ ሰልፎችና ነውጥ መቀስቀሱን ተከትሎ በጆሀንስበርግ የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬ መደብራቸውን ዘግተው እንደዋሉ በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ለቢቢሲ ተናገሩ። በንግድ ሥራ የተሰማራው ዳዊት ተወልደመድኅን፤ በጆሀንስበርግ በተለይም ጂፒ ጎዳና እና ብሪ ጎዳና በሚባሉት አካባቢዎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ጥቃት እንዳይደርስባቸው ፈርተው ዛሬ ሐምሌ 5/2013 ዓ.ም. መደብራቸውን ዘግተው ለመዋል መገደዳቸውን ተናግሯል። ትላንት ሐምሌ 4/2013 ዓ.ም. በዚያው አካባቢ በተነሳው ነውጥ የኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሌሎች አገራት ስደተኞች መደብሮች ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ፖሊስ እንደተከላከለ ዳዊት ይናገራል። በደቡብ አፍሪካ የተባበሩት ኢትዮጵያ ማኅበሰረብ ማኅበር ዋና አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆነው ንጉሥ ተመስገን እንደሚናገረው ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያን፣ ፓኪስታናውያን እንዲሁም ሌሎችም የሚነግዱበት አካባቢ ዛሬ ተዘግቶ ውሏል። "ኒውካስል አካባቢ ሁለት ኢትዮጵያውያን ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከባድ ግን አይደለም። ዛሬ ሶዌቶ አካባቢ አመጽ ስላለ በንግድ የተሰማራው የሀበሻው ማኅበረሰብ ሱቁን ዘግቷል። ደርባን ትላንት ሌሊት ሲዘረፍ፣ መኪና ሲቀጠል ነበር" ይላል። ከኢትዮጵያውን ማኅበረሰብ እና ከፖሊስ በተገኘው መረጃ መሠረት ከባድ የሚባል ጉዳት እስካሁን እንዳልደረሰ ያክላል። "ትላንት የስደተኞች መደብሮች ላይ ጥቃት እየተሰነዘረ እንደሆነ ኢትዮጵያውን ሲሰሙ ተሰብስበው ወደ ጂፒ ስትሪት ሄደው ሱቆቻቸውን ተከላከሉ። ፖሊሶችም ሀበሾችን ሲረዱ ነበር። ኢትዮጵያውያኑ ተሰብስበው ባይሄዱ ኖሮ የከፋ ነገር ይፈጠር ነበር" ይላል ነጋዴው ዳዊት። በተለይም ጆሀንስበርግ ውስጥ ረብሻ ሲነሳ ጥቃት የሚሰነዘረው ስደተኞች እንዲሁም የንግድ ተቋሞቻቸው ላይ እንደሆነ በተደጋጋሚ ታይቷል። የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ጃኮብ ዙማ በሥልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል የተባሉ የሙስና ጉዳዮች እየተመለከተ በሚገኘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተጠይቀው ሳይገኙ በመቅረታቸው ፍርድ ቤትን በመድፈር ጥፋተኛ ተብለው የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል። የጃኮብ ዙማን እስር ተከትሎ የእሳቸው ደጋፊ የሆኑ ደቡብ አፍሪካውያን የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት አደባባይ መውጣት የጀመሩት ጃኮብ ዙማ እጃቸውን ለፖሊስ ከሰጡ በኋላ ነው። ከዚህ ተቃውሞ ጋር ተያይዞ በተነሳው ነውጥ ሕንጻዎች እና ተሽከርካሪዎች ወድመዋል። መደብሮችም ተቃጥለዋል። ግርግር፣ ዝርፊያና ንብረት ማቃጠል ጆሃንስበርግ ውስጥ በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት ወ/ሮ መዓዛ ተስፋዬ እንደተናገሩት ረብሻው መቀስቀሱን ተከትሎ በጣም አሳሳቢ እና አስፈሪ ሁኔታ ተከስቷል። ግርግር፣ ዝርፊያና ንብረት የማቃጠል ድርጊት በየቦታው እንደነበርና መንገዶችም በተቃዋሚዎቹ በሚቃጠሉ ጎማዎች ተዘግተው እንደነበር ገልጸዋል። ተቃውሞው በጃኮብ ዙማ መታሰር የተቀሰቀሰ ይሁን እንጂ ቢቢሲ ያናጋራቸው ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት፤ ከተቃውሞው ባሻገር በተለያዩ ስፍራዎች ዝርፊያዎችና የንብረት ውድመት ተፈጽሟል። በተለይ የንግድ ሱቆች የተቃዋሚዎቹ የጥቃት ኢላማ በመሆናቸው በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ሱቆቻቸውን ዘግተው ቤታቸው ተቀምጠዋል። ረብሻው እሳቸው በሚኖሩበት ጆሃንስበርግና ደርባን ከተሞች ውስጥ የበረታ መሆኑን የሚናገሩት ወ/ሮ መዓዛ፤ ፖሊስ አመጸኞቹን ለመቆጣጠርና የንብረት ውድመት ለማስቆም እየጣረ ነው ብለዋል። ለሁለት ቀናት ከዘለቀ ተቃውሞና የንብርት ውድመት በኋላ ከትናንት ዕሁድ በተሻለ ሰኞ ዕለት መረጋጋት በጆሃንስበርግ መመለሱን የተናገሩት ወ/ሮ መዓዛ "ከተማው ጸጥ ብሏል" ብለዋል። የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን በረብሻው የወደሙ ንብረቶችናና የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ ተከታታይ ዘገባዎችን እያቀረቡ ሲሆን ወ/ሮ መዓዛና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ለሁለት ቀናት ከሥራ ውጪ ሆነው መቆየታቸውን ገልጸዋል። ሌሎች ኢትዮጵያውያንና የመገኛኛ ብዙኃን እንደሚሉት ረብሻው ከተከሰተ በኋላ ከጆሃንስበርግ ይልቅ በደርባን ከባድ ጉዳት መድረሱን እንደተረዱ ጠቅሰዋል። "ረብሻ ሲነሳ ጥቃት የሚደርሰው ስደተኞች ላይ ነው" ንጉሥ እንደሚለው፤ ማንኛውም አይነት ነውጥ ሲነሳ ያንን ሰበብ በማድረግ የንግዱ ማኅበረሰብ ላይ ጥቃት ይሰነዘራል። አሁን የተነሳው አይነት አለመረጋጋት ሊቀሰቀስ እንደሚችል ባለፉት ጥቂት ቀናት ሲነገር እንደነበር እና ሸቀጣቸውን ከመደብር ያወጡ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች እንዳሉ ገልጿል። "ዛሬ ጥቃት እንደሚደርስ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ስለተነገረ መላው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ ከቤቱ አልወጣም" ብሏል። ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የወጣው የእንቅስቃሴ ገደብ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ላይ ያሳደረው ጫና ላይ አሁን የተነሳው ነውጥ ሲጨመር ማኅበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ቀውስ እንደሚያስከትልም ንጉሥ ይናገራል። ዳዊት እንደሚለው፤ ከዚህ ቀደምም እንደታየው አንዳች ነውጥ ሲነሳ ስደተኞች ላይ ጥቃት ይሰነዘራል። ይህንን የሚያውቁት ኢትዮጵያውያን ስጋት ስለገባቸው ዛሬ መደብራቸውን አልከፈቱም። "ትላንት ኢትዮጵያውኑ ተሰብስበው ሳይሄዱ በፊት ጉዳት የደረሰባቸው ሱቆች ነበሩ። ዛሬም ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለማይታወቅ ኢትዮጵያውያን ሱቃቸውን ዘግተው ውለዋል" ይላል። ትላንት የናይጄርያውያን መኪና መሸጫ፣ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብርና ሌሎችም የንግድ ተቋማት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ይናገራል። "ትላንት ሀበሾች በቁጣ ሱቃቸውን ለመጠበቅ ወጡ። ፖሊስም አገዛቸው። ከዚህ በፊት ፖሊሶችም ጭምር ችግር ይፈጥሩብን ነበር" ይላል። ኢትዮጵያውያኑ ስጋት ውስጥ እንደሆኑና የጃኮብ ዙማ የፍርድ ቤት ጉዳይ እልባት እስኪያገኝ ወይም እስኪረግብ ድረስ ወደ ሥራ መመለስ እንደሚያስቸግር ዳዊት ለቢቢሲ ገልጿል። ሁሌም ረብሻ ሲነሳ ስደተኞች ጥቃት እንደሚደርስባቸው የሚጠቅሰው ነጋዴው፤ "ድንገት መጥተው ሊዘርፉን ወይም ሊያጠቁን ስለሚችሉ ዘግቶ መጠበቅ ይሻላል" ሲል ያስረዳል። ጆሃንስበርግ ውስጥ የሚነግዱ ኢትዮጵያውያን በማንኛውም ጊዜ ነውጥ ሊነሳ እንደሚችል እንደሚሰጉ ገልጾ "የለመድነው ችግር ስለሆነ ሁሌም በተጠንቀቅ ነው የምንጠብቀው። ረብሻ ሲነሳ ጥቃት የሚደርሰው ስደተኞች ላይ ነው" ብሎም አክሏል። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያን እና ሌሎችም ስደተኞች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ብዙ ጊዜ ተፈጽመዋል። ዳዊት "ስደተኞች ሲጠቁ ዓለም የደቡብ አፍሪካ መንግሥትን ስለሚጠይቅ ስደተኞችን ለማጥቃት ምክንያት ይፈለጋል" ሲል ሁኔታውን ያስረዳል። በደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሠራዊቱ ስለመሰማራቱ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት፤ በጃኮብ ዙማ የትውልድ ቦታ ክዋዙሉ-ናታለ ተቀስቅሶ በመላው አገሪቱ እየተንሰራፋ የመጣውን አለመረጋገት ለማርገብ የአገሪቱን መከላከያ ሠራዊት እንዳሰማራ ተገልጿል። ዘረፋ ተፈጽሞባቸዋል በተባሉ ስፍራዎች ፖሊስ ምላሽ እየሰጠ ሲሆን እስካሁን ድረስ 60 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉንም ይፋ አድርጓል። ትናንት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች ዱላ እና ፍልጥ ይዘው በጆሃንስበርግ ከተማ መሃል ታይተዋል። ቅዳሜ ዕለት ደግሞ ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎች የጆሃንስበርግን ዋና ጎዳናን ዘግተው ነበር። ከትናንት በስቲያ በነበረው ተቃውሞ ሕንጻዎች እና መኪኖች በእሳት ወድመዋል። አሌክሳንድራ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ወደ 800 የሚጠጉ ሰዎች ተሳትፈውበታል በተባለው አመጽ አንድ የፖሊስ አባል በጥይት መመታቱ ተዘግቧል። ፕሬዝደንት ሲርል ራማፎሳ ትናንት ምሽት ግጭት እያስከተሉ ያሉ ተቃውሞዎች እንዲቆሙ የጠየቁ ሲሆን፤ "ለዚህ አመጽ እና የንብረት ውድመት ምንም ዓይነት ምክንያት ሊቀርብ አይችልም" ብለዋል። ፍርድ ቤትን በመድፈር ጥፋተኛ ተብለው የ15 ወራት እስር የተፈረደባቸው ጃኮብ ዙማ በሥልጣን ዘመናቸው ምንም ዓይነት ሙስና አለመፈጸማቸውን ይከራከራሉ። የጃኮብ ዙማ ጠበቆች ዛሬ ለአገሪቱ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለት የፍርድ ጊዜውን ለማሳጠር ይሞክራሉ ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57808849
amh
business
ኮሮናቫይረስ፡ አፍሪካ በወረርሽኙ ሳቢያ ከተጎዳው ምጣኔ ሐብት ለማገገም 1.2 ትሪሊየን ዶላር ያስፈልጋታል ተባለ
አፍሪካ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ካጋጣት የኢኮኖሚ ውድቀት ለማገገም እንዲሁም የጤና ወጪ 1.2 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም [አይኤምኤፍ] አስታወቀ። ገንዘቡ ያስፈልጋታል የተባለው ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት መሆኑ ተገልጿል። የተቋሙ ዳሬክተር ክርስታሊና ጆርጂቫ እንዳሉት ዓለም አፍሪካ ከገባችበት ቀውስ እንድታገግም ለመደገፍ ዓለም ብዙ መስራት አለበት ብለዋል። በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ እንዲሁም የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሌሎች አህጉራት ያነሰ ነው፤ ነገር ግን የዓለም ባንክ በወረርሽኙ ሳቢያ ተጨማሪ 43 ሚሊዮን የሚሆኑ አፍሪካዊያን ለከፋ ድህነት የመጋለጥ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብሏል። በወረርሽኙ ሳቢያ የሥራ እድሎች በመታጠፋቸው እና የቤተሰብ ገቢ በ12 በመቶ በመቀነሱ የደረሰው የኢኮኖሚ ተፅእኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ እየታየ የነበረውን ጠንካራ እድገት እየቀለበሰው መሆኑን የገንዘብ ተቋሙ ዳሬክተር በበይነ መረብ በነበራቸው የተቋሙ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ችግሩንም ለማቃለል በርካታ አፍሪካ አገራት መንግሥታት ከልማት እቅዳቸው 2.5 በመቶ ያስወጣቸውን ፖሊሲዎች አስተዋውቀዋል። አይኤም ኤፍ የአፍሪካ አገራት ከደረሰባቸው ተፅዕኖ እንዲያገግሙ 26 ቢሊዮን ዶላር የለገሰ ቢሆንም፤ የግል አበዳሪዎች እና በሌሎች አገራት ድጋፍ ቢኖርም፤ አሁንም ግን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት አለ ብለዋል። "አንዳንድ አገራት ከብድር አግልግሎትና ተጨማሪ የማህበራዊና ጤና ወጪዎች መካከል እንዲመርጡ የሚያስገድዳቸውን የዕዳ ጫናዎች እየተጋፈጡ ነው" ብለዋል ኃላፊዋ። ይህንን ችግር ለመፍታትም ተበዳሪዎች ብድራቸውን የሚከፍሉበት ጊዜ እንዲራዘም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ ለብድር የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ ማቅረብ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። በአፍሪካ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ወደ 37 ሺህ የሚጠጉት ሕይወታቸውን አልፏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54498317
amh
business
የወቅቱ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ተግዳሮቶች
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) ባለፉት 10 ዓመታት በየዓመቱ በአማካኝ 9.4 በመቶ እያደገ መሆኑን ይናገራል። ኢትዮጵያ ከጥቅምት 24/2013 ጀምሮ በትግራይ ክልል የቀሰቀሰው ጦርነት፣ በቅርቡ የተከሰተው ከፍተኛ ሆነ የምንዛሬ እጥረት እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት ኢኮኖሚውን እየተፈታተነው ይገኛል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያው ከ64 እስከ 68 ብር ድረስ በመመንዘር ላይ እንደሚገኝ እና በተለያዩ ሁኔታዎች ይህ ዋጋ እስከ 72 ብር ድረስ ከፍ እንደሚል ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ግለሰብ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በመደበኛው የምንዛሬ ገበያ አንድ ዶላር በ45 ብር እየተመነዘረ ይገኛል። የአገሪቱ የዋጋ ግሽበትም ቢሆን ከእለት ወደ እለት እየጨመረ እንደሚሄድ ያሳያል። ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በኮቪድ-19 ምክንያት ተጽዕኖ እንደደረሰበት እና 2 በመቶ ገደማ ዕድገት እንደሚያስመዘገብ ጠቅሰው ነበር። ወርቅነሽ ሲማ የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። ከምታገኘው ገቢ በላይ ወጪዋ ሰማይ መንካቱን በመግለጽ የኑሮ ውድነት እንዳማረራት ትናገራለች። "የቤት ኪራይ፣ በርበሬ፣ ዘይት እና ጤፍ ዋጋቸው ሰማይ የነካ ነው" የምትለው ወርቅነሽ በአሁኑ ጊዜ ገቢያችን እና ወጪያችን የተመጣጠነ አይደለም ስትል ለቢቢሲ አስረድታለች። ወርቅነሽ መንግሥት ለኑሮ ውድነቱ መፍትሄ ያበጅለታል ብላ ተስፋ ብትጥልም "ለእኛ ግን በጣም ፈታኝ ነው" ስትል ኑሮ እንደከበዳት ትገልጻለች። በንግድ ሥራ ላይ የተሰማራው ለማ አበበ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ስላለው የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ሲናገር "እያደገ ነው" በማለት ነው። አክሎም "የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነቱም በዚያው መጠን እያደገ ነው። ይህ ደግሞ ገበሬውን ሳይሆን ኑሮውን በየወሩ በሚያገኘው ደሞዝ ላይ ያደረገውን መካከለኛ ገቢ የሚያገኝ ነዋሪ እየጎዳው ነው። ገበሬው ግን ያመረተውን በገበያው ዋጋ ስለሚሸጥ አትራፊ ነው" ሲል ያስረዳል። አቶ ለማ የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር የአገር ውስጥ ምርትን መጠቀምን ማበረታታ እና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን መቀነስ መፍትሄ ይሆናል ብሎ ያምናል። የተለያዩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ባለፉት አሥር ዓመታት መንግሥት በከፍተኛ መጠን ከተፈተነባቸው ችግሮች መካከል አንዱ የዋጋ ንረት ነው። መንግሥት የዋጋ ንረትን መቆጣጠር አቅቶታል ብለው የሚተቹ ወገኖች በርካታ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥታቸው የዋጋ ንረት ለመከላከል እንደ ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ያሉ ተቋማትን እያቋቋመ መሆኑን ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ኢኮኖሚውን ነፃ ለማድረግ በሚል በመንግሥት ይዞታ ስር የሆኑትን ቴሌኮምዩኒኬሽንን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በከፊል ወደግል ለማዘዋወር ተወስኖ ነበር። ከእነዚህ ድርጅቶች በተጨማሪም የኢንደስትሪ መንደሮችን፣ የስኳር ፋብሪካዎችን፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች አምራች ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር ተወስኗል። ይህ ውሳኔ የተወሰነው የአገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱንና የዋጋ ግሽበቱን ለመቋቋም፣ የገቢ ማመንጨት አቅምን ለማጠናከርና የወጪ ንግዱን ለማቀላጠፍ በሚል ነው። ለዚህ ውሳኔ ሌላኛው ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ የብድር መጠን ከፍ ማለቱ እንደሆነም ይነገራል። ኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ተቋማት ክፍት እንደምታደርግ ያስታወቀችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ይፋ በተደረጉ የለውጥ እርምጃዎች ነው። በቅርቡም ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ እንዲሳተፍ ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ ለተሰኘው ጥምረት ፍቃድ መስጠቷ ይታወሳል። በዚህም የተነሳ ከፍተኛ መጠን ያለው መዋዕለ ነዋይ ወደ አገሪቱ እንዲገባ እና በርካታ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ተነግሯል። እንደ ማዕከላዊ ስታትስቲክ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ ያለው የኑሮ ውድነት በሰኔ ወር ብቻ 24.5 በመቶ ደርሷል። ኢትዮጵያ ከተለያዩ የውጭ አገራት የተበደረችው 42.8 ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ይነገራል። ኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብቷን ለማሳደግ ከወሰደቻቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ የተለያዩ ኢንደስትሪ ፓርኮችን ለውጭ ገበያ የሚሆኑ ምርቶችን እንዲያመርቱና እንዲልኩ ማበረታታት ነው። ማርታ ገላነው በአገሪቱ ካሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል በአንዱ ተቀጥራ ትሰራለች። የአውቶሜሽን ኢንጂነር ባለሙያ የሆነችው ማርታ በአገሪቱ እየተስፋፉ ያሉ የኢንደስትሪ መንደሮች የወደፊት ተስፋዋን ብሩህ ማድረጋቸውን ትናገራለች። በአሁኑ ጊዜ ገና በመቋቋም ባለ ፋብሪካ ውስጥ እየሰራች ቢሆንም ለወደፊት ግን "እንደ አውቶሜሽን ኢንጂነርነቴ በየትኛውም ትልልቅ ፋብሪካዎች ውስጥ ያሉ ማሽኖችን ማንቀሳቀስ እችላለሁ" ስትል ታስረዳለች። በደብረብርሃን የኢንደስትሪ ፓርክ የእንስሳት መኖ ለማምረት በማሰብ ግንባታ እያካሄዱ መሆኑን የሚናገሩት የባጃኢ ኢትዮ ኢንደስትሪያል ሶሉሽን ባለቤት ባጃኢ ናይከር ናቸው። በደብረብርሃን ኢንደስትሪያል ፓርክ ውስጥ እያስገነቡት ባለው የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ድብልቅ የእንስሳት መኖ ለኢትዮጵያውያን እንስሳት አርቢዎች ለማምረት እየሰሩ ነው። ፋብሪካው ከዚህ ቀደም ከውጭ እየመጣ የነበረውን የእንስሳት ቫይታሚንና ሚነራሎችን ለማስቀረት የሚያስችል እቅድ አለው። ፋብሪካው የአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለውጭ ገበያም የማቅረብ ሃሳብ እንዳለው ባለቤቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንደ ሚስተር ባጃኢ ከሆነ መንግሥት በዚህ የኢንደስትሪ መንደር ፋብሪካቸውን እንዲገነቡ የተለያዩ ማበረታቻዎችን አድርጎላቸዋል። በኢንደስትሪ ፓርክ ውስጥ ሲሰሩ ለተወሰነ ዓመታት ከታክስ ነጻ እንደሚሆኑ፣ ከውጭ የተወሰኑ እቃዎችን ከቀረጥ ነጻ የማስገባት እድል እንደተመቻቸላቸው፣ መሬት በርካሽ ማግኘታቸውን እንዲሁም በዚህ ኢንደስትሪ መንደር ለእንስሳት አምራቾች የተለየ ትኩረት መሰጠቱ እርሳቸውን ከሳቧቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በመላ አገሪቱ 15 የኢንደስትሪ ፓርኮች እንዳሉና ተጨማሪ 20 ደግሞ የመገንባት እቅድ እንዳለው ያስረዳል። የትግራይ ጦርነት እና የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት እያሳየ ቢሆንም በትግራይ፣ በአፋር እና በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው ጦርነት ግን የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት ፈተና ላይ ጥሎታል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት እና የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ የበላይ ኃላፊ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ባለሀብቶች የረዥም ዓመት እቅድ ይዘው መሆኑን ይናገራሉ። በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ያለው ግጭት የአጭር ጊዜ መሆኑን እና አገሪቱም እንደምትወጣው ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል። ለኢትዮጵያውን ዋነኛ የምጣኔ ሀብት ስጋት የዋጋ ግሽበት መሆኑን የሚያብራሩት አቶ ዘመዴነህ፣ ባለፉት 10 ዓመታት የግሽበት መጠኑ በእጥፍ መጨመሩን በመግለጽ ይህም መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ተግዳሮት ሆኖ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ለዋጋ ግሽበቱ መናር ምክንያት ነው ብለው ከጠቀሷቸው መካከል ከፍተኛ የሆነ የፍላጎት መጨመር ሲኖር የአቅርቦት መጠን በዚያው ልክ ማደግ አለመቻሉን ነው። በአቅርቦትና በፍላጎት መካከል ያለ ከፍተኛ አለመመጣጠን በተለይ ደግሞ የአገር ውስጥ ምርቶች ከፍላጎት ጋር በተመጣጠነ መልኩ አለማደጋቸውን ያነሳሉ። ሌላው የጅምላ፣ የችርቻሮ እና የማከፋፈል ስርዓት በአገሪቱ ውስጥ አሁንም ኋላ ቀርነት እንዳለው አንስተዋል። ለዚህም መዋቅራዊ ለውጥ መካሄድ አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ። ኢትዮጵያ ከ126 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የቴሌኮምዩኒኬሽኑን ዘርፍ ለግል ባለሀብቶች መስጠቷን የሳፋሪኮም ስምምነትን በመጥቀስ የገለፁት አቶ ዘመዴነህ፤ "ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ ለተለያዩ ቢዝነሶች በሯን መክፈቷን ያሳያል" ሲሉ ተናግረዋል። በቴሌኮም ዘርፉ የውጭ ባለሀብቶች መምጣታቸው የአገልግሎት ጥራት፣ የዋጋ ውድድር በመፍጠር ለቴሌኮሙም ሆነ ለፋይናንስ ዘርፉ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ያብራራሉ። አቶ ዘመዴነህ ኢትዮጵያ በግብርና፣ በአምራች እንዲሁም በቱሪዝምና ሌሎች ዘርፎች በቀጣዩቹ ሦስትና አምስት ዓመታት እድገት እንደምታሳይ ያላቸውን ተስፋም ገልፀዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58185460
amh
business
እሷ ማናት? #4፡ ከሒሳብ ጋር በአጋጣሚ ነው የተዋደድነው
በሒሳብ ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪዋን (ፒኤች ዲ) ለማግኘት እየሰራች ነው። ሰዎች እምብዛም ገፍተው በማይሄዱበት የትምህርት ዓይነት እንዴት ውጤታማ ልትሆን እንደቻለች አጫውታናለች። ስሜ ኤቢሴ አዱኛ ይባላል። ተወልጄ ያደኩት በነቀምት ከተማ ነው። የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቴን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተምርያለሁ። በአሁን ሰዓት ደግሞ የሦስትኛ ዲግሪ ትምህርቴን በዴንማርክና በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች እየተከታተልኩ ነው። • የኮምፒዩተር ትምህርት ለኬኒያ ሴት እስረኞች ሁለተኛ እድል ይሰጣቸው ይሆን? • አንድም ሴት የፓርላማ አባል የሌላት ሃገር ሒሳብ መረጠሽ ወይንስ መረጥሽው ? የሙያ ሕይወቴ ከሒሳብ ጋር የተቆራኘ ይሆናል ብዬ አልገመትኩም ነበር። ለመጀመሪያ ዲግሪ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተመደብኩበት ወቅት የሒሳብ ትምህርት ሳልመርጥ በአጋጣሚ ደረሰኝ። ከዚያ በኋላ ግን እኔና ሒሳብ በጣም ተዋደድን። እኔ ልምረጠው ሒሳብ ይምረጠኝ የሚታወቅ ነገር የለም። የሒሳብ ትምህርትን ከድሮም ፈርቼው አላውቅም። ዩኒቨርሲቲ ገብቼ ትምህርቱ ሲደረሰኝ ጥሩ ነጥብ ማስመስገብ ጀመርኩኝ፤ እየወደድኩትም መጣሁ። በዚያ ላይ ይህ ትምህርት ለሴት ይከብዳል ለወንድ ደግሞ ይመቻል የሚል አመለካከት የለኝም። ማንም ሰው ፍላጎት ካለው፣ ከጣረና በሥራ ካስደገፈው ይሳካል ብዬ ስለማስብ የሒሳብ ትምህርትን አጥብቄ ይዤ ቀጠልኩበት፤ እዚህም ደረስኩኝ። አሁንም ቢሆን ከምወዳቸው ትምህርቶች መካከል ትልቁን ቦታ የያዘው ሒሳብ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ እያለሁ 'ጊዜ ቤት' ላይ ሌሎች ልጆች ሸምድደው በፍጥነት እንደሚሉት አልነበርኩም፤ ነገር ግን በልጅነቴ በተወሰነ ደረጃ ይህንን 'የጊዜ ቤት' እሠራ ነበር። በዚያ ወቅት ተማሪ እያለሁ አባቴ የሒሳብ መምህር ስለነበረ በሒሳብ ጥሩ መረዳት እንዲኖረኝ አድርጓል። በጭንቅላቴ ሸምድጄ ከመያዝ ይልቅ ተረድቼ ማስላት ይቀለኝ ነበር። የሒሳብ ጥቅም የተለያየ ነው። ለምሳሌ ሒሳብ በሁለት ይከፈላል፤ 'ፕዩር ማቴማቲክስና አፕላይድ ማቴማቲክስ' ተብለው ይለያሉ። • ሴት ተመራቂዎች ለምን ሥራ አያገኙም? • ሚሼል ኦባማ በአሜሪካ እጅግ ተወዳጇ ሴት ተባሉ እኔ የምማረው 'አፕላይድ ማቴማቲክስ' በተጨባጭ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚጠቅም ነው። ለምሳሌ የምመረምራቸው ስሌቶች ኤች ሲቪ ለተባለው የጉበት ቫይረስ መፍትሔ ለማግኘት የሚረዳ ነው። ስለዚህ ሒሳብ በሕይወታችን ያሉን ተጨባጭ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የሚረዳ የትምህርት ዓይነት ነው። ነገ የሚሆንን ነገር ለመተንበይ ሒሳብ ችግሮቻችንን በቁጥር አስልተን ለማስቀመጥ ይረዳናል። የሒሳብ ምሁሮች ከስሌቱ በኋላ ቀመሩን ከነመፍትሔው ያስቀምጡልናል። የምህድስና ሙያ ያላቸው ሰዎች ደግሞ እንዲህ ዓይነት ቀመሮችን በሥራ ላይ ያውላሉ። ስለዚህ ከሒሳብ ሙያተኞች ይልቅ በምህንድስና ውስጥ የተሰማሩ ሰዎች በይበልጥ ማስረዳት ይችላሉ። ውጣ ውረዶችን ለማለፍ በሥራም ሆነ በኑሮ እንደማንኛውም ሰው የተለያየ መሰናክል ይገጥመኛል። ነገር ግን የችግሩን ያህል ሳይሆን ነገሮችን ከአቅሜ አንፃር ነው የምገመግማቸው። ችግር እንደሚያበረታኝና እንደሚያጠነክረኝ ስለማውቅ ሁሌም መውጫ ቀዳዳ ነው የምፈልገው። አንዳንዴ ሰዎች ፊቴንና ዕድሜዬን አይተው ይገምቱኛል። አንዳንዴ ጊዜ እንዲያውም በሴትነቴ ጭምር ለመመዘን ይሞክራሉ። እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ሲገጥሙኝ ደግሞ እራሴን በደንብ አስተዋውቃለሁ። ምን ማድረግ እንደምችል፣ ማን እንደሆንኩ እና ፍላጎቴ ምን እንደሆነ አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ሁሉ እናገራለሁ። ይህ ደግሞ በሕይወቴ የምፈልገውን ነገር በሙሉ እንዳገኝ አድርጎኛል በዚያ ላይ ተግባቢ ሰው ነኝ። ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ መማር ጊዜን ስለሚፈልግ የጊዜ እጥረት ያጋጥማል። የፒኤች ዲ ትምህርት ምግብ የምበላበት ጊዜ እንኳን አይሰጥም፣ ያስጨንቃል ደግሞም ድብርት ያስከትላል። ቢሆንም ግን ያለኝን ጊዜ አብቃቅቼ ከጓደኞቼም ሆነ ከቤተሰቦቼ ጋር ጊዜ አሳልፋለሁ። ከዚህ ሁሉ ግን ያለንን ጊዜ በደንብ ከተጠቀምንበት የምንፈልገውን ማሳካት ይቻላል ብዬ አስባለሁ። • ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል? • ከመጀመሪያው 'የብላክ ሆል' ምስል ጀርባ ያለችው ሴት እንደሚታወቀው በአገራችን ሴት ልጅ ስትበልጥ ወንዶች ብዙ ደስተኛ አይደሉም፤ ሁሉም እንዲዚህ ናቸው ማለቴም አይደልም ነገር ግን እንዲህ ዓይነት አስተሳብ አለ። በሁሉም መንገድ ወንድ የበላይ ሆኖ አንዲታይ የሚፈልጉ አሉ። እንደእኔ አመለካለከት የትምህርት ደረጃ እና ፍቅር የተለያዩ ናቸው። ስኬቴ ችግር የሚሆንበት ካለ ለማስተናገድ አልችልም። የቤተሰቤ አባላት በማደርገው ጥረት ላይ በጣም የደግፉኛል። ጓደኛና የምወደው ሰው የምለውም ሰው ልክ እነደዚህ የሚደግፈኝ መሆን አለበት። ለምን ትበልጠኛለች ካለ ግን ይህ ፍቅር ነው ወይንስ ቅናት? ብዙ ሴቶች ያለንን አቅም የተረዳነው አይመስለኝም። እንችላለን ብለን ካመንን ማድረግ አያቅተንም። ይህን ከተረዳን ደግሞ በውበት፣ በጋብቻ እና በገንዘብ መወሰን የለብንም። እራሳችን ያለምነው ትልቅ ቦታ ላይ መድረስ እንደምንችል ማሰብና መጣር ነው ያለብን። ስለዚህም የሚያጋጥሙንን መሰናክሎች በእራሳችን ማለፍ መቻል አለብን። እንደዚህ ወደፊት ከተራመድን አገራችንን ወደፊት ለመምራት አያቅተንም። ያለንን አቅማችንንና መላ የማበጀት ጥበባችንን እንጠቀምበት ብዬ ለሴቶች ምክሬን እሰጣለሁ።
https://www.bbc.com/amharic/news-50218736
amh
business
ሲም ካርድ ያለው ሁሉ ገንዘብ መበደር የሚችልበትን ዕድል የፈጠረው ቴሌብር
ከአስራ አራት ወራት በፊት ወደ አገልግሎት የገባው ቴሌብር የተሰኘው የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ባለፈው ሳምንት አርብ ከቁጠባ እና ብድር ጋር የተያያዙ አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት ጀምሯል። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ አዳዲሶቹ አገልግሎቶች በፋይናንስ ሥርዓት ያልተሸፈነውን 60 በመቶ የሚሆን የኅብተረሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል። የነዳጅ ድጎማ እና የግብር ክፍያን ጨምሮ ባለፉት 14 ወራት ገንዘብ ለመላላክ፣ የግብይትና የአገልግሎት ክፍያን ለመፈጸም እንዲሁም ከውጭ አገራት ገንዘብ ለመቀበል ሲውል የነበረው ቴሌብር አሁን ደግሞ  ‘መላ’፣ ‘እንደኪሴ’ እና ‘ሰንዱቅ’ የተሰኙ አገልግሎቶችን ይፋ አድርጓል። ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር ደንበኞች ገንዘብ እንዲቆጥቡ፣ ሲያስፈልጋቸው እንዲበደሩ የሚረዱት አዳዲሶቹን አገልግሎቶች ለማስጀመር አስራ አራት ወራት በላይ ዘግይቷል። ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ኢትዮ ቴሌኮም እነዚህን አገልግሎቶች ለማስጀመር ከአንድ ዓመት በላይ የዘገየበትን ምክንያት ሲያስረዱ “የተሰጠን ፍቃድ እሱን አልፈቀደልንም ነበር። ስለዚህ በቴሌ ብር ሌሎቹን አገልግሎቶች እየሰጠን ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ለማግኘት ሥራዎችን ስንሰራ ቆይተናል” ብለዋል። ለመሆኑ አገልግሎቶቹ ምንድን ናቸው? በቴሌብር አማካኝነት በቅርቡ የተጀመሩት ሦስት አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ያለዋስትና/ማስያዣ እንዲበደሩ ወይም እንዲቆጥቡ የሚያስችሉ መሆናቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ይህ የቴሌብር አገልግሎት ደንበኞች ገንዘብ የሚቆጥቡበት ሲሆን፣ ለተቀማጭ ገንዘብ ወለድ የሚከፈልበትን እና ከወለድ ነጻ የሆነ አመራጮችን አካቷል። እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገለጻ፣ ወለድ የሚከፈልበት ቁጠባ በየቀኑ የሚሰላ እና ደንበኞች በቀን ያገኙትን መጠን የሚያመላክት ነው። የቴሌብር ደንበኞች ግብይት እየፈጸሙ ገንዘብ በሚያንሳቸው ጊዜ ቀሪውን ገንዘብ የሚያገኙት ሥርዓት ደግሞ እንደኪሴ ይሰኛል። እንደኪሴ ደንበኞች ለግብይት ከሚያጥራቸው ገንዘብ በተጨማሪ እንደ የኤሌክትሪክ እና ውሃ ያሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመፈጸምም ያስችላል። ይህ አሰራር ደንበኞች ለክፍያ የጎደላቸውን እስከ 2 ሺህ ብር የሚሸፍንም ነው። ቴሌብር መላ፣ ደንበኞች የብድር አገልግሎት የሚያገኙበት መንገድ ሲሆን ግለሰቦችን እና የንግድ ተቋማትን የሚያካትት ነው። በቴሌብር መላ ግለሰቦች በወር እስከ 10 ሺህ ብር፣ የንግድ ተቋማት ደግሞ እስከ 100 ሺህ መበደር እንደሚችሉ የሚያስረዱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ ግለሰቦች የተበደሩትን በቀን፣ በሳምንት እና በወር መመለስ የሚችሉበትን አሰራር ማቀፉን ጠቅሰዋል። ለንግድ ተቋማት ደግሞ ለግለሰቦች ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በተጨማሪ የ3፣ የ6 እና የ9 ወር የሚመልሱበትን አሰራር አካትቷል። ቴሌብር መላ “ለሥራ ማስኬጃ እንዲሁም አዳዲስ ሃሳብ ኖሯቸው ወደ ንግድ መግባት ለሚፈልጉ ሰዎችን ታሳቢ አድርጎ የቀረበ ነው። ለዚያ ነው በፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ ያልሆነውን ማኅበረሰብ፣ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይሆናል ብለን ያሰብነው” ሲሉም አክለዋል። መላ፣ እንደ ኪሴ እና ሰንዱቅ በተሰኙት የቴሌብር አገልግሎቶች በመጀመሪያ ዓመት ውስጥ በየወሩ በአማካኝ ከ3 እስከ 4 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማገልገል እና ከ19.5 እስከ 20 ቢሊዮን ብር ለማንቀሳቀስ ማቀዱን ኃላፊዋ ጠቅሰዋል። ከዚህም ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው የብድር አገልግሎቱ ወይም ቴሌብር መላ ሲሆን 9.8 ቢሊዮን ብር ይሸፍናል። 6.4 ቢሊዮን ብር ክፍያን ለማጠናቀቅ ወይም እንደ ኪሴ ለተባለው አገልግሎት እንዲሁም 3.3 ቢሊዮን ብር ደግሞ በቁጠባ ወይም ሳንዱቅ በተሰኘው አገልግሎት የሚጠቃለል ነው። ደጋግመው ብድር የሚወስዱ ደንበኞችን ጨምሮ በዓመት 108 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማገልገል ማታቀዱንም አስረድተዋል። አገልግሎቶቹ በተጀመሩ በቀናት ውስጥ የዕለት ብድር ወስደው የሚመልሱ እንዲሁም የሚቆጥቡ ደንበኞች መኖራቸውን ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተስፋ ሰጪ እና “አስገራሚ” ሁኔታዎች መኖራቸው ገልጸዋል። በቴሌብር መላ የሚሰጠው ብድር በሙሉ ዋስትና ወይም ማስያዣ እንደማይጠየቅበትም ጨምረው አስረድተዋል። የፋይናንስ ተቋማት ለሚያበድሩት ገንዘብ ዋስትና ወይም ማስያዣን መጠየቅ የተለመደ አሰራራቸው ነው። ከዚህ አሰራር በተቃራኒ በቴሌብር የሚቀርቡ ብድሮች ዋስትና አይጠየቅባቸውም። ሆኖም ሥርዓቱን በሚንቀሳቀስበት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የደንበኞችን የወጪ ገቢ ዝውውር በመመልከት የብድሩን መጠን ይፈቀዳል። ሥርዓቱ ደንበኛውን በገንዘብ ዝውውሩ በመመልከት በተለያዩ ደረጃዎች የሚገለጽ ነጥብ የሚሰጥ ሲሆን፣ ብድር ለሚመልሱ ደንበኞች ደግሞ የተሻለ ቡድር ማግኘት የሚቻልበትን ነጥብ ይሰጣል። አገልግሎቱ በቴሌብር ሞባይል መተግብሪያ  ወይም #127# አጭር ቁጥር አማካኝነት የሚቀርብ ሲሆን፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሲምካርድ ላላቸው ደንበኞች በሙሉ በቴሌብር ያላቸውን የገንዘብ ዝውውር መሰረት አድርጎ ብድርን የሚያቀርብ ነው። እነዚህ አገልግሎቶችን ለማስጀመር የአዋጪነት ጥናት መካሄዱን የሚያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ እንደ ማንኛውም የፋይናንስ አገልግሎት ስጋት ሊኖር እንደሚችል ታሳቢ መደረጉን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ይህ አገልግሎት የኢትዮጵያን ባህል ከግምት ውስጥ ማስገባቱን በማንሳት “ሁሉም ደንበኛ አይመለስም ብለን ልንወስድ አንችልም። . . . ተበድሮ አልመለሰም መባልን የማይፈልግው የማኅበረሰባችን ክፍል ሰፊ ነው። እርሱን እንደ ጥንካሬ ወስደነዋል።” አክለውም “ . . . አንዴ ብድሩን አልመለሰም ማለት በሚቀጥለው ብድር አያገኝም። ስለዚህ አንዴ ሁለት ሺህ ብር ተበድሮ ቢጠፋ ነው የሚሻለው ወይስ በዓመት ሁለቴም ሦስቴም ሁለት ሺህ፣ አራት ሺህ ቢበደር ነው የሚሻለው? ለማኅበረሰቡ የምናስረዳው ይህንን ነው። ይህ ይሆናል ብለን አንጠብቅም። ባለማወቅ ሊፈጠር ይችላል። ለዚያ ግን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እንሰራለን። ምንም ችግር አያጋጥመንም ግን አንልም። በፋይናንስ ሴክተር ያሉ እንደሚያውቁት በዋስትና የሚሰጠው ብድርም ላይመለስም ይችላል። ግን ከቁጥጥር ውጪ አይሆንብንም። እሱን አጥንተን ነው የገባነው” ብለዋል። ሥርዓቱ ላይ ይህ ችግር ሊያጋጥም ይችላል በሚል ይህንን ከመተግበር ወደ ኋላ አንልም የሚሉት ፍሬህይወት “60 በመቶ የኅበረተሰብ ክፍል የፋይናንስ አገልግሎት የማያገኝበት አገር ላይ ሆነን ሪስክ [ስጋት] አለ ብለን የገንዘብ ችግር ከመፍታት አንጻር ትልቅ አቅም የሆነውን አለመጀመር ደግሞ ተገቢ ነው ብለን አናስብም. . .” ስለዚህም ይህንን በአግባቡ ተጠቅመው ኑሯቸውን፣ ሕይወታቸውን፣ ቤተሰባቸውን ሊቀይሩ የሚችሉ ሚሊዮኖች ስላሉ የእነርሱን ዕድል ለማስፋት የተጀመረ ሥራ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ “ሙሉ በሙሉ ስጋት (ሪስክ) የለውም ብለን ሳይሆን መልካም ጎኑን ይዘን ነው የተነሳነው” ሲሉም አክለዋል። ወደ አገልግሎት ከገባ 1 ዓመት ያለፈው ቴሌብር 22.2 ሚሊዮን ደንበኞችን ማፍራቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ያስረዳሉ። በእነዚህ ጊዜያትም 34.1 ቢሊዮን ብር የገንዘብ ዝውውር ተከናውኖበታል። ከዝውውሩ 18 በመቶ የሚሆነው ገንዘብ ማውጣት እና ማስገባት ሲሆን 40 በመቶ ደግሞ የአየር ሰዓት መሙላትን ነው። ገንዘብ መላላክ፣ የአገልግሎት ክፍያ እና ግብይት መፈጸም ደግሞ የተቀረውን ድርሻ ይይዛል። የግብር፣ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ እና መሰል አግልግሎቶችን ከሚሰጡ በርካታ የመንግሥት ተቋማት፣ ከ13 ባንኮች እንዲሁም ከ22 ሺህ የንግድ ተቋማት ጋር የተሳሰረው ቴሌብር  በመላው አገሪቱ ከ79 ሺህ በላይ ወኪሎች እንዳሉትም ኃላፊዋ ጠቅሰዋል። “ይህንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሳካታችንን እንደ ትልቅ ስኬት እንወስደዋለን” የሚሉት ኃላፊዋ ቴሌብር የገንዘብ ዝውውር እና ክፍያን ምቹ እና ቀልጣፋ ማድረግ፣ የክፍያ ሥርዓትን ማዘመን እና የዲጂታል ኢኮኖሚን በማስተዋወቅ በፋይናንስ አገልገሎት ያልተካተተውም ሕዝብ ተደራሽ ማድረግ ዋነኛ አላማው እንደሆነ አንስተዋል። እስካሁን ቴሌብር “የክፍያ ሥርዓቱን ሲያሳልጥ የቆየ” ሲሆን በፋይናንስ ሥርዓት ተደራሽ ያልሆኑ ሰዎችን ተደራሽ የማድረግ ቀዳሚ ዓላማውን ለማሰካት በቅርቡ ይፋ የሆኑት ዓላማዎች ወሳኙን ሚና እንደሚጫወቱ ጠቅሰዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cy0xj34y9l7o
amh
business
ቻይና ዝናብ ለማዝነብና የተፈጥሮ ሂደትን ለመቆጣጠር የምታደርገው ጥረት
እንደ ቻይናዋ ቤይጂንግ የአየር ብክለት የሚፈትነው ከተማ የለም። የቤይጂንግ ሰማይ በመጠኑም ቢሆን ጠርቶ ፀሐይ የምትታየው በከተማዋ የሚካሄድ ዓለም አቀፍ ውይይት ሲኖር ነው። ይህ የሚሆነው በተፈጥሯዊ ሂደት ሳይሆን መንግሥት በቀየሰው ስልት አማካይነት ነው። የቻይና መንግሥት የአገሪቱን የአየር ሁኔታ ለመለዋወጥ ሰው ሠራሽ መንገድ መጠቀም ጀምሯል። ይህ ሰው ሠራሽ ሂደት በጥቂት የቻይና ከተሞች ብቻ ይተገበር ነበር። ከጥቅምት ወዲህ ግን አገር አቀፍ እንደሚሆን ተነግሯል። ሂደቱ በሰው ሠራሽ መንገድ ዝናብ እንዲጥል ማድረግ፣ በረዶ ማዝነብ ወዘተ. . . ያካትታል። እአአ በ2015 ይህን ሂደት በቻይና 5.5 ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎ ሜትር ማለትም የአገሪቱን 60 በመቶውን ለማዳረስ ታቅዷል። እቅዱ እንደ ሕንድ ላሉ ጎረቤት አገሮች አልተዋጠላቸውም። ቻይና እና ሕንድ ከድሮውም ውጥረት ውስጥ ናቸው። ቻይና የአየር ሁኔታን የምትለውጠው እንዴት ነው? በእንግሊዘኛው ክልውድ ሲዲንግ (cloud seeding) በሰው ሰራሽ መንገድ ዝናብ እንዲጥል የሚደረግበት ቴክኖሎጂ ነው። ለዚህም ሲልቨር አዮዳይድ የተባለ ንጥረ ነገር ወደ ደመና በመላክ የአየር ሁኔታ የሚለወጥበት ሂደት ነው። በሕንድ የአየር ሁኔታ ባለሙያው ዳናስሪ ጃይራም "ይህንን ቴክኖሎጂ ብዙ አገሮች ይጠቀሙበታል። ቻይናና ሕንድም ይጠቀሳሉ" ይላሉ። ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራትም ይህ ሂደት ይተገበራል። እንደ አውስትራሊያ ያሉ አገሮች ድርቅን ለመከላከል ይጠቀሙታል። ሂደቱ በተለይም በአሜሪካ ከ1940ዎቹ ወዲህ ነው እየታወቀ የመጣው። ውጤቱ ላይ ጥያቄ ያላቸው ባለሙያዎች ግን አሉ። በቤይጂንግ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ጆን ሲ ሙር "ውጤታማነቱን የሚጠቁሙ ጥቂት ሳይንሳዊ ጽሑፎች ብቻ ናቸው ያሉት። ያለ ሳይንሳዊ ማረጋገጫ የተተገበረ ሂደት ነው" ይላሉ። ሳይንቲስቱ እንደሚሉት፤ 50 ሺህ የቻይና ከተሞችና ወረዳዎች ይህንን መንገድ ተጠቅመው የእርሻ መሬታቸውን ለማዳን ይሞክራሉ። ዝናብን በማስቆም ማዕበል ሰብላቸውን እንዳያጠፋው ለመከላከል ይጥራሉ። ሆኖም ግን ተመራማሪዎች እንደሚሉት ይህ ሂደት ቻይና ውስጥ የሚሠራው ለአንድ ወይም ለሁለት ወራት ነው። ዝናብ የማነው? ቻይና የአየር ሁኔታን በመቆጣጠር ተፈጥሯዊ አደጋ እንዳይከሰት የመከላከል እቅድ እንዳላት አስታውቃለች። ሰብል እንዳይበላሽ፣ ሰደድ እሳት እንዳይስፋፋ፣ ከፍተኛ ሙቀትን ለመቆጣጠር፣ ድርቅን ለመግታት ወዘተ. . . ይውላል። ቤይጂንግ ውስጥ የምትሠራው ጋዜጠኛ ይትሲንግ ዋንግ እንደምትለው ቻይና የአየር ሁኔታን ለመቆጣጠር ያወጣችው መርሃ ግብር ሲተገበር ከግዛት ግዛት ይለያያል። ሂደቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ቻይናን አላሳሰቧትም። የቻይና ውሳኔ ከጎረቤት አገሮቿ ጋር ያላትን የፖለቲካ ፍጥጫ ሊያባብሰው ይችላል። "የቻይና የአየር ሁኔታ የመለወጥ ሂደትደ የሕንድ የክረምት ዝናብ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ስጋት አለ" ሲሉ የሕንዱ ተመራማሪ ያስረዳሉ። በቻይና እና ሕንድ የድንበር ግጭት ሳቢያ ሕንድ ውስጥ ለቻይና ያለው አመለካከለት እየጠለሸ ነው። የአየር ሁኔታ ለውጡም ከዚሁ ጋር ተያይዞ ይታያል። በታይዋን ዩኒቨርስቲ በ2017 የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ የአየር ሁኔታ ለውጥ ሲደረግ ከጎረቤት አገራት ጋር ውይይት ካልተደረገ ግጭት ሊነሳ ይችላል። የአንድ አገር የዝናብ መጠን ሲቀንስ ሌላውን አገር ተጠያቂ የማድረግ ሁኔታ ይፈጠራል። "ይህ ስጋት ሳይንሳዊ አይደለም። ሆኖም ግን የቲቤት ተራራ የአየር ሁኔታ የተለያየ መሆኑ ከግምት መግባት አለበት። ስለዚህ አንድ አካባቢ የአየር ንብረት ለውጥ ሲከሰት ሌላው ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም" ሲሉ ሳይንቲስቱ ጆን ሲ ሙር ያስረዳሉ። ቻይና የተለጠጠ እቅድ በማንገብ ሌሎችም ዘርፎች ላይ ለውጥ ልታካሂድ እንደምትችል ባለሙያዎች ይሰጋሉ። ይህም በሰው ሠራሽ መንገድ የፀሐይ ጨረራን ለመቆጣጠር መሞከርን ያካትታል። እነዚህ ውሳኔዎች የሚተላለፉት ከጎረቤት አገሮች ጋር ባለው ውጥረት ሳቢያ ሊሆን ይችላል የሚል መላ ምትም አለ። ሳይንቲስቱ በበኩላቸው "ቴክኖሎጂው ችግር አለው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን በቴክኖሎጂው አንዳች ችግር ቢከሰት በምን መንገድ ይፈታል? ኃላፊነቱንስ የሚወስደው ማን ነው? ለሚለው መልስ ሊኖር ይገባል" ይላሉ። በተጨማሪም የአየር ሁኔታን መለወጥን የመሰሉ ሂደቶች ዓለም አቀፍ ውይይት እና ስምምነት እንደሚፈልጉ ባለሙያው ያስረዳሉ። ሂደቱ የሚተገበርበት ወጥ አሠራር እንዲሁም ሂደቱን ተከትሎ ግጭት ቢነሳ በምን መንገድ መፈታት እንደሚችል አስቀድሞ መታሰብ አለበት ሲሉም ያክላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-56099470
amh
business
ፓኪስታን ፡ በካርቱን ስዕል ምክንያት የፈረንሣይ ምርቶችን መጠቀም ልታቆም ነው
አንድ የፓኪስታን እስላማዊ ቡድን የጠራውን የፀረ-ፈረንሳይ ተቃውሞን የፓኪስታን መንግሥት የፈረንሳይ ምርቶችን ላለመጠቀም በመወሰኑ ማቋረጡን አሳወቀ። ሰልፎቹ የተጠሩት ፈረንሳይ የነቢዩ ሙሐመድን ካርቱን የማሳየት መብትን በመደገፏ ነበር። አንድ መምህር በክፍል ውስጥ በነበረ ውይይት ወቅት የነቢዩ መሐመድን ካርቱን ካሳዩ በኋላ መገደላቸውን ተከትሎ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን አገራቸው በሐይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አትገባም ሲሉ በጥብቅ ተከላክለዋል። ይህም በሙስሊሙ ዓለም ቁጣን ቀስቅሷል። የአክራሪው ተህሪክ ኢ-ላባይክ ፓኪስታን (ቲ.ኤል.ፒ) የተሰኘው ቡድን አባላት የፈረንሳይን ምርት ላለመግዛት የቀረበውን ውሳኔ የደገፉ ቢያንስ የሁለት ሚኒስትሮችን ፊርማ ያካተተ የስምምነት ቅጅዎችን አሳይተዋል። የፓኪስታን መንግስት በጉዳዩላይ በይፋ መግለጫ ካለመስጠቱም በላይ የፈረንሳይ ምርቶችን ያለመጠቀም አድማው እንዴት እንደሚተገበር አላሳወቀም። በፈረንሣይ እስልምናን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ማክሮንን ከተቹ የፖለቲካ መሪዎች መካከል የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን አንዱ ናቸው። ተቀዋሚዎቹ አሁንም ተጨማሪ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል። ደጋፊዎች ከእሁድ ጀምሮ ወደ መዲናዋ ኢስላማባድ የሚወስደውን ቁልፍ መንገድ በመዝጋታቸው ከፍተኛ የእንቅስቃሴ መስተጓጎል አስከትሏል። የቲ.ኤል.ፒ አመራሮች መንግሥት ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ መስጠቱን ከተናገሩ በኋላ ተቃውሞው እንዲቋረጥ ተጠይቋል። የቡድኑ ቃል አቀባይ የሆኑት ኢጃዝ አሽራፊ ለሮይተርስ እንደተናገሩት "የፈረንሳይ ምርቶችን እንደማይጠቀም መንግሥት በይፋ እንደሚደግፍ ስምምነት ከፈረመ በኋላ የተቃውሞ ሰልፎቻችንን እያቆምንው ነው" ብለዋል። ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ የተደረገው የስምምነት ሰነድ የሐይማኖታዊ ጉዳዮች ሚኒስትሩን እና የአገር ውስጥ ሚኒስትሩን ፊርማ ይዟል። የፈረንሣይ አምባሳደር ከአገር እንዲወጡ በማድረግ ዙሪያ ላይ ፓርላማው እንዲወስን መንግሥት ሐሳብ እንደሚያቀርብም ገልጿል። የፓኪስታን መንግሥት በስምምነቱ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም። ቲ.ኤል.ፒ ቀደም ሲል ሐይማኖታዊ ስድብን ምክንያት በማድረግ ተቃውሞ ለማሰማት እጅግ ብዙ ሰዎችን በመሰብሰብ ይታወቃል። በፓኪስታን ሕግ መሠረት ነቢዩ ሙሐመድን በመሳደብ ጥፋተኛ የተባሉ ሰዎች የሞት ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል። በፈረንሳይ የመንግሥት በሐይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ ያለመግባት የአገሪቱ ዋነኛ መገለጫ ነው። በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ሕዝባዊ ቦታዎች ሀሳብን በነፃነት መግለጽም የዚህ አካል ሲሆን የአንድን የተወሰነ ሐይማኖት ስሜት ለመጠበቅ የሃሳብ ነጻነቱን መግታት ብሔራዊ መገለጫውን እንደሚያደፈርስ ተደርጎ ይወሰዳል። 'ቻርሊ ሄብዶ' የተሰኘው መጽሔት የነቢዩ ሙሐመድ ካርቱን ይዞ መውጣቱን ተከትሎ እ.አ.አ በ2015 በፓሪስ ውስጥ የጥቃት ዒላማ ቢሆንም የካቶሊክን እና የአይሁድን እምነት ጨምሮ ሌሎች ሐይማኖቶችም የሚያመለክቱ ስዕሎችን ይዞ ወጥቷል። የፈረንሣይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቀደም ሲል በበርካታ ሙስሊሞች በብዛት በሚገኙባቸው አገሮች ውስጥ የፈረንሳይ ሸቀጦችን ላለመጠቀም የሚደረጉ ጥሪዎችን "መሠረተ ቢስ" ብለው "በአፋጣኝ መቆም" እንዳለባቸውም ገልጸው ነበር። ባለፈው ወር ለተገደሉት መምህር ክብር የሰጡት ፕሬዝዳንት ማክሮን ፈረንሳይ "ካርቱኑን አታቆምም" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54970898
amh
business
እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት
ባለፉት ጥቂት ወራት የሸቀጦች የዋጋ ንረት እና አጠቃላይ የኑሮ ዋጋ መወደድ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ የብዙሃን መገናኛዎች ተደጋግመው የሚወሱ ጉዳዮች ሆነዋል። የመንግሥት ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶችም የችግሩን አሳሳቢነት ከመቀበል በዘለለ እየተወሰዱ ናቸው የሚሏቸውን እርምጃዎች ሲናገሩ ተስተውለዋል። በወርሃ ግንቦት 2011 ዓ.ም መገባደጃ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ በመዲናዋ በግንባታ ዕቃዎች፣ በእህል፣ በጥራጥሬ እና በአትክልት ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪዎች መከሰታቸውን ጠቅሰዋል። እንደመፍትሄም ችግሩን አባብሰዋል ያሏቸው ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ መስመር ማምጣት፣ ፈቃደኛ ያልሆኑት ላይ ደግሞ ይህንን የሚከታተል ግብረ ኃይል በማቋቋም እርምጃ መውሰድ፣ እንዲሁም ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የአቀርቦት ሥርዓቱን ማሰተካከል የከተማዋ አስተዳደር የሚያከናውናቸው ተግባራት መሆናቸውን ገልፀው ነበር። • "ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) • "መንግሥት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦችን ያስገባል"ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ይሁንና ክረምቱ ሲገባ የዋጋ ንረቱ ከመርገብ ይልቅ ከፍ ብሎ ታይቶ የዋጋ ግሽበቱ ባለሁለት አሀዝ ሆኗል። በወርሃ ነሐሴ እንዲያውም ባለፉት ስድስት ዓመታት ከታየው የዋጋ ግሽበት መጠን ከፍተኛው ተመዝግቧል። የሸቀጦች የዋጋ ንረት ህይወታቸው ላይ ቀጥተኛ ጫና ካሳረፈባቸው የአዲስ አበባ ኗሪዎች መካከል ደግሞ የአርባ ዓመቱ ጎልማሳ ጋሹ መርከቡ አንዱ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚኖረው ጋሹ ላለፉት ከአስራ ለሚልቁ ዓመታት በሚኒባስ ታክሲ ሾፌርነት ቤተሰቡን ሲያስተዳድር ኖሯል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን "የኑሮ መወደድ ከአቅሜ በላይ ሆኖ እያንገዳደገደኝ ነው" ይላል። "በዋጋ ላይ ያለውን ለውጥ ከቀን ወደ ቀን እያየሁት የመጣሁት ጉዳይ ነው፤ በእኔ [ህይወት] እንኳ ታክሲ ሠርቼ ብሩን ይዤ ብገባም ምንም የሚገዛው ነገር የለም" ይላል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። "የልጆች ትምህርት ቤት፣ የእህሉ ውድነት፣ እንዲያውም ተስፋ ወደማስቆረጥ ደረጃ እየደረሰ ያለ ይመስለኛል" ይላል። መጪውን ፍራቻ ጋሹ የአራት ልጆች አባት ሲሆን ትልቋ የአስራ ሁለት ዓመት ልጁ የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ናት። ሌሎቹ ሦስት ልጆቹም በመዋዕለ ሕፃናት እና በአንደኛ ደረጃ ትምርት ቤቶች ውስጥ ይማራሉ። ባለፉት ዓመታት ሁሉንም ልጆቹን በግል ትምህርት ቤቶች ያስተምር የነበረ ሲሆን አሁን ግን በኑሮ ውድነት ላይ በየጊዜው የሚጨምረውን የትምህርት ቤት ክፍያን መቋቋም ባለመቻሉ አንደኛውን ልጁን የመንግሥት ትምህርት ቤት፣ ሁለቱን ደግሞ በለጋሽ ድርጅቶች በሚደጎም እና በዚህም ምክንያት በአንፃራዊነት አነስተኛ ከፍያ ወደሚጠይቅ ትምህርት ቤት አስገብቷል። ለእያንዳንዳቸው በየወሩ ሦስት መቶ ብር በመደበኛነት ይከፍላል። • ኢትዮጵያዊያን ለምን ሥጋ አይመገቡም? • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ግምቶች አሉ አንደኛዋን ልጁን ብቻ በግል ትምህርት ቤት መማሯን እንድትቀጥል አድርጓል። ለብቸኛዋ የግል ትምህርት ቤት ተማሪ ልጁ መደበኛ ክፍያ ብቻ በዓመት ከአስር ሺህ ብር በላይ ያወጣል። ይህም የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ፣ የአልባሳት፣ የምግብ ወጪዎች ሲደመሩበት "ናላን የሚያዞር" ሆኗል ይላል ጋሹ። በዚህ ላይ የቤት ኪራይ ወጪ ይታከልበታል። "ህይወታችንን ለማቆየት እየሰራን ነው እንጅ እየኖርን ነው ብዬ አላወራውም።" አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ መጪውን ጊዜ ይበልጥ እንዲፈራው እንዳደረገው ይናገራል ጋሹ፤ "ወደፊት እንዴት እንደማስተምራቸው ራሱ ግራ ግብት እያለኝ ነው" በማለት። ተስፋው ከዕለት ወደ ዕለት እንዲሟጠጥ አንድ ምክንያት የሆነው እርሱን ለመሰሉ ከኑሮ ጋር እልህ አስጨራሽ ግብግብ ለገጠሙ ሰዎች በፖለቲካ ልሂቃን ዘንድ ብዙም ትኩረት እየተሰጠ አይደለም ብሎ ማመኑ ነው። • ‹‹እነ ቴሌን ለግል ባለሀብት?›› ታሪካዊ ስህተት ወይንስ መልካም አጋጣሚ ? የፖለቲካ ልሂቃኑ "በብሔርም ጉዳይ፣ በምንም ጉዳይ የራሳቸውን ለማመቻቸት እንጂ የድሃውን [ጉዳይ] አንስቶ ልብህን [የሚነካ] ነገር ሲናገሩ እኔ እስካሁን ሰምቼም አላውቅም። የራሳቸውን ጉዳይ ከማስፈፀም በስተቀር ውስጥህን የሚነካ ነገር፣ ስለኑሮህ፣ ስለሽንኩርት የሚያወራ የለም" ይላል። ከጋሹ አስተያየት ጋር በሚስማማ መልኩ አጠቃላይ ምርጫ በሚከናወንበት ዓመት በፖለቲካዊ መድረኮች ላይ የዋጋ ንረት የሚገባውን ያህል ስፍራ ይዞ ያለመታየቱ እንደሚገርማቸው የሚያስረዱት የምጣኔ ሃብት የፖሊሲ ተንታኝ የሆኑት አሚን አብደላ ናቸው። "ምርጫ ኖረም አልኖረም፤ የማንኛውም አገር መንግሥት ፈተና የሚሆኑ ሁለት የማክሮኤኮኖሚ አመላካቾች አሉ፤ የሥራ አጥነት እና የዋጋ ንረት።"

በፖለቲካው መልክዐ ምድር ገኖ ያለው መንግሥታዊው ሥርዓት "የፌዴራል ይሁን አይሁን የሚል ዓይነት እንጅ የሥራ አጥነት እና የዋጋ ንረት ላይ ብዙም የፖለቲካ ልሂቃን ሲጨቃጨቁ አይቼ አላውቅም" ባይ ናቸው ተንታኙ። ለአንድ አገር መረጋጋት እና የምጣኔ ሃብት ዕድገት ወሳኝ ናቸው የሚሏቸው እነዚህ ጉዳዮች ብዙም ያለመነሳታቸው "ዋናው ነገር የተዘነጋ ይመስለኛል" አስብሏቸዋል። የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ተንታኙ አሚን አብደላ እንደሚሉት አጠቃላይ የዋጋ ንረት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ ይላሉ። በተሰናበተው 2011 ዓ.ም የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበቱ ከ15 በመቶ በላይ ደርሶ እንደነበረ የሚያስታውሱት አሚን በወርሃ ነሐሴ ደግሞ ይህ ቁጥር ወደ 18 በመቶ ከፍ ብሎ እንደነበርም ይጠቅሳሉ። ይህም ቁጥር በስድስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የታየው ትልቁ አሃዝ ነው። ለቁጥሩ ከፍ ማለት የምግብ ዋጋ፣ በተለይም የእህል ሰብል ዋጋ ንረት ምክንያት መሆኑን የስታትስቲክስ መረጃዎች ያመላክታሉ። • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም ማለት ነው» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ በዚህ ረገድ በአንዳንድ ትርፍ አምራች በሆኑ አካባቢዎች የነበረው የፀጥታ ሁኔታ፣ የመጓጓዣ አገልግሎት እንደልብ ያለመገኘት እና ከዚህም ጋር በተያያዘ ምርትን በተፈለገው ደረጃ ማቅረብ ያለመቻል ለችግሩ ምክንያት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ተንታኙ አሚን ያነሳሉ። እየናረ ያለውን የዋጋ ንረት ለማቃለል ሁለት የመፍትሄ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ የሚሉት ባለሙያው፤ "አንደኛው በአቅርቦት በኩል ሌላኛው ደግሞ በፍላጎት በኩል ያሉ ናቸው" እንደአሚን ገለፃ። "ከፍላጎት አንፃር የመንግሥት ወጪ የቀነሰበት ሁኔታ አለ። ያለፉትን ዓመታት ዓይነት እድገት ስለሌለ፤ ምጣኔ ሃብቱ ውስጥ የሚለቀቀው የገንዘብ መጠን ቀነስ ያለ ይመስላል። ይሁንና በአቅርቦት በኩል እምብዛም ለውጥ ያለ አይመስልም" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል አቶ አሚን። የምርቶች በተገቢው መጠን አለመገኘት ለዋጋ መወደድ በአንዳንድ ሰዎች እንደምክንያት ተደጋግሞ የሚነሳ ሲሆን፤ ባለሙያውም በምርት እና በአቅርቦት መካከል ያለው ሰንሰለት ችግር እንደሚስተዋልበት ይናገራሉ። "ገበሬው አምርቶ ለምርቱ የሚያገኘው ዋጋ እና ከተማ ላይ መጥቶ የሚሸጥበት ዋጋ በጣም ከፍተኛ ልዩነት አለው። ገበሬው ከአንድ ኪሎ ሙዝ እያገኘ ያለው ገቢ እና አንድ ኪሎ ሙዝ ከተማ ውስጥ እየተሽጠበት ያለው ዋጋ ልዩነት አለው። "በዚህ መካከል ያለው የአገልግሎት፣ የደላላ፣ የመጓጓዣ፣ የቦታ ኪራይ እና የመሳሰሉት ወጪዎች ከፍተኛውን ድርሻ የሚወሰዱ ናቸው። ይህ የገበያ ሰንሰለት ሥርዓት እሰካልያዘ ድረስ፤ የምርቶች ዋጋ ከፍ እንዲል ማድረጉ አይቀሬ ነው" ለአሚን። • ሸማቹ በውጭ ምንዛሪ ለውጡ ማግስት • ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ማዕድ የቀረቡት ምን ይላሉ? ከውጭ የሚመጣ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የንግድ ውድድርን ማሳለጥ እንዲሁም የሸማቾችን ጥበቃ ማጠናከር ይገባል የሚሉት ባለሞያው፤ ከውጭ የሚመጡ ምርቶችን የሚያስመጡ ተቋማት እና ግለሰቦች በየተሰማሩበት ዘርፍ ጥቂት መሆናቸው ዋጋው ላይ ከሚገባው በላይ ጫና እንዲፈጠር መንገዱን ይጠርጋል ባይ ናቸው አቶ አሚን። ከውጭ የሚመጣ የዋጋ ንረት በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምከንያትም ሊከሰት ቢችልም በእኛ አገር እየተስተዋለ ያለው እውነታ ግን በውጭ ምንዛሬው እጥረት መጠን ያህል መኖር ከሚገባው በላይ ጭማሪ ነው፤ ሲሉ የዋጋው ጭማሪ አሳሳቢ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ባለሞያው አቶ አሚን አብደላ ለፖለቲካዊ ጉዳዮች እየተሰጠ ካለው ጋር የሚመጣጠን አትኩሮት የዋጋ ንረትን ለመሳሰሉ ምጣኔ ሃብታዊ ተግዳሮቶች መቸር አለበት ባይ ናቸው። በዚህ አስተያየታቸው ጋሹም የሚስማማ ይመስላል፤ "ይሄ ሁሉ እየታየ ቸል የሚባለው እስከመቼ እንደሆነ አይገባኝም።"
https://www.bbc.com/amharic/news-49922350
amh
business
የአንድ ቢትኮይን ዋጋ 2.4 ሚሊዮን ብር ገባ
የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ60 ሺህ ዶላር ወይም 2.4 ሚሊዮን ብር በላይ በመግባት ክብረ ወሰን ሰብሯል። ቢትኮይን መመንደግ የጀመረው በተለይ ደግሞ ከባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ አንስቶ ነው። ይህንን የማይጨበጥ የማይዳሰስ መገበያያ ገንዘብ በርካታ ግዙፍ ድርጅቶች እንቀበለዋለን ማለታቸው ለዋጋው መናር ምክንያት ሆኗል ተብሏል። በዘርፉ ጥርስ የነቀሉ ግን የቦትኮይን ዋጋ እንዲህ ያሻቀበው የአሜሪካ መንግሥት በኮሮናቫይረስ ኪሳቸው ለተጎዳ ዜጎች የሰጠውን ድጎማ ተከትሎ ነው ይላሉ። የቢትኮይን ጠቅላላ የገበያ ዋጋ አሁን ከ1 ትሪሊየን በላይ ሆኗል። ቢሆንም ቢትኮይን ከተፈጠረበት የፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ ዋጋው አንድ ጊዜ ሲያሻቅብ አንዴ ደግሞ ሲያሽቆለቁል ነው የከረመው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው የቢትኮይን ማሻቀብ ከግዙፍ ኩባንያዎች ጋር ይያያዛል። ባለፈው ወር በኤሌክትሪክ የሚሠሩ መኪናዎች የሚያመርተው ተስላ የተሰኘው ድርጅት ባለቤት የሆነው ኢላን መስክ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን መግዛቱን ይፋ አድርጎ ነበር። አልፎም ድርጅቱ ተስላ ወደፊት ልክ እንደ ወረቀት ገንዘብ ለመገበያያነት እንደሚያውለው አስታውቆ ነበር። ቢትኮይን ምንድነው? ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል ገንዘብ ወይም መገበያያ ነው ማለት ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን 'ኦንላይን' የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች ቁጥጥር ይደረግበታል። ለሚያቀርቡት ምርት እና አገልግሎት ቢትኮይንን በክፍያ መልክ የሚቀበሉ በርካቶች ድርጅቶች አሉ። ማይክሮሶፍት፣ የፈጣን ምግብ አቅራቢዎቹ ኬኤፍሲ እና ሰብዌይ፣ የጉዞ ወኪሉ ኤክስፔዲያን ከመሳሰሉ ባለብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ኩባንያዎችን አንስቶ እስከ ሆቴሎች እና ካፊቴሪያዎች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ ይቀበላሉ። ቢትኮይንን በመጠቀም የገዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ በየትኛውም ሰዓት እና በየትኛውም ስፍራ የቢትኮይን ዝውውር ማድረግ ይቻላል። ሕገ-ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያዎች እና እጾችን ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ፣ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አሸባሪዎችን ለመደገፍ ያስችላል በማለት ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪይፕቶከረንሲዎች ላይ ያላቸውን ስጋት የሚያነሱ በርካቶች ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-56391321
amh
business
ከኮሮናቫይረስ በኋላ ኢኮኖሚያቸው በቶሎ ሊያገግም የሚችል አምስት አገራት
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አገራት ከበሽታ ጋር በሚያደርጉት ትግል በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ አለመረጋጋትን ፈጥሯል። ከዚህ አንጻር ከወረርሽኙ በኋላ የትኞቹ አገራት በተሻለ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው እንደሚመለሱ ባለሙያዎች ለመገምገም ሞክረዋል። ይህንን በተሻለ ለመረዳት የኢንሹራንስ ኩባንያ የሆነው ኤፍ ኤም ግሎባል የ2019 ዓለም አገራት የምጣኔ ሃብት ፈተናን የመቋቋም አቅም አመላካች ደረጃን ተመለከትን። በዚህም አገራት ለቫይረሱ የሰጡትን የመጀመሪያ ምላሽ ከግምት በማስገባት ቀውሱን በተረጋጋ መንገድ የሚወጡበትን ሁኔታና የመቋቋም ዕድላቸው ተቃኝቷል። በደረጃ ጠቋሚው በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠችው ዴንማርክ ከቫይረሱ ስርጭት አንፃር ማኅበራዊ ርቀት እንዲተገበር በፍጥነት እርምጃ ወስዳለች። ጥቂት በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንደተገኙ ነው ትምህርት ቤቶችን፣ አስፈላጊ ያልሆኑ ሥራዎችንና ድንበሯን በፍጥነት በመዝጋት ውሳኔዋ ውጤታማ መሆኑን ያረጋገጠችው። የዴንማርካዊያን ባህል የሆነው በመንግሥት ላይ እምነት ማሳደርና ለጋራ ዓላማ አብሮ የመቆም ፍላጎት በእርምጃዎቹ ውጤታማነት ላይ አውንታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። እናም ብዙ ሰዎች ለሕዝብ ጤና ሲሉ መስዋዕት የማድረግ የሞራል ግዴታ እንደሆነ ይሰማቸዋል። በዚህ ወቅት ዴንማርክ የሠራተኞችን ደመወዝ እስከ 90 በመቶ ድረስ ለመክፈል መወሰኗ እንደ ምሳሌ እንድትታይ አድርጓታል። ይህን ግን ቀላል አይደለም። እርምጃው ከጠቅላላው የአገሪቱ አጠቃላይ ምርት 13 በመቶውን ያህሉን ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ሲንጋፖር በጠንካራ ኢኮኖሚዋ፣ በአነስተኛ የፖለቲካ አደጋ፣ ጠንካራ መሠረተ ልማት እና ዝቅተኛ ሙስና በደረጃ ጠቋሚው 21ኛ እንድትሆን አድርጓታል። አገሪቱ ቫይረሱን ለመቆጣጠር በፍጥነት ከመንቀሳቀስ ባለፈ ስርጭቱም የተረጋጋ ነው። ቫይረሱን በመዋጋት ረገድ በግልጽነት በሚሰራው መንግሥት ላይ ሕዝቡ ከፍተኛ እምነት አለን። መንግሥት አንድ ውሳኔ ካስተላለፈ ሁሉም ተገዢ ሆኖ ተግባራዊ ያደርጋል። እንደ ትንሽ አገርነቷ የሲንጋፖር በጣም ስኬታማ መልሶ የማንሰራራት ውጤት ለማስመዝገብ በተቀረው ዓለም የማገገም ሂደት ላይ የተመሠረተ ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ሰፊ ጂኦግራፊያዊ ቦታ መያዟ በደረጃ ጠቋሚው ላይ በሦስት የተከፈለች ሲሆን በአጠቃላይ ጥሩ ደረጃ ይዛለች። ቫይረሱ እንደ ኒው ዮርክ ባሉ ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ ፈታኝ ሲሆን፤ የሥራ አጥነት መጠኑም ታሪካዊ በሚባል ደረጃ ከፍ ብሏል። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የተወሰደው አስገዳጅ የእንቅስቃሴ ገደብና ሌሎችም ለዚህ በምክንያትነት ተቀምጠዋል። ነገር ግን የአሜሪካ መንግሥት ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የማነቃቂያ እርምጃዎችን በፍጥነት መውሰዱና ማኅበራዊ ርቀት መጠበቅ መተግበሩ ውጤት በማምጣት የቫይረሱ አጠቃላይ ተፅእኖን ሊቀንስና ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ማገገም ሊያስገኝ ያስችላል። 21 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ማበረታቻ ይፋ ያደረገችው አሜሪካ፤ ሩብ ያህሉን የዓለም አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርትን በመያዟ ወሳኝ የሚያደርጋት ሲሆን የዓለም ምጣኔ ሃብት ማገገም በአሜሪካ ውጤታማነት ላይ ጥገኛ እንደሆነ ይነገራል። በቅርብ በተደረጉት በኮርፖሬት አስተዳደር ማሻሻያዎች ምክንያት ሩዋንዳ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በደረጃ ጠቋሚዎች ውስጥ ትልቁን መሻሻል በማድረግ በዓለም ላይ የ77ኛ ደረጃን፣ ከአፍሪካ ደግሞ የአራተኛ ደረጃን ይዛለች። ከሁሉም በላይ ደግሞ በአውሮፓዊያኑ 2019 በጎረቤትዋ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ ድንበር ላይ በተሳካ ሁኔታ መቆጣጠር ከቻለች በኋላ እንደዚህ ዓይነቱን ቀውስ ለመከላከል በጥሩ ሁኔታ የተቀመጠች ይመስላል። ሁለን አቀፍ የጤና አጠባበቅ፣ የህክምና ቁሳቁስን በሚያደርሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) እገዛ እና በድንበር ላይ የሙቀት ልየታ በማድረግ ሩዋንዳ በዚህ ቀውስ ወቅት ከሌሎች የአካባቢው አገራት አንጻር ጥንካሬዋን ጠብቃ ትቆያለች። ሩዋንዳ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ቤት ለቤት ነፃ ምግብ እያሰራጨች የምትገኝ ሲሆን ይህም ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት የመጀመሪያዋ ያደርጋታል። የቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚገጥመው ይጠበቃል። ሩዋንዳም ለብዙ የዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ኤግዚቢሽኖች ተወዳጅ መድረሻ ናት። አገሪቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሚሆኑ እና በፍጥነት ለማገገም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳላት ይታመናል። ኒውዚላንድ በደረጃ ጠቋሚው የ12ኛ ቦታን ይዛለች። አገሪቱ ድንበሮችን ለዓለም አቀፍ ተጓዦች በመዝጋትና አስፈላጊ ያልሆኑ ሥራዎችን በፍጥነት በመዝጋት የቫይረሱ ስርጭትን ለመቆጣጠር መንቀሳቀስ ችላለች። ቱሪዝምና የወጪ ንግድ የምጣኔ ሃብቷ ዋና አካል ሲሆኑ ኒውዚላንድ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አንዳንድ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ያጋጥማታል ተብሎ ተሰግቷል። ነገር ግን ይህ የግድ መጥፎ ውጤት ላይኖረው ይችላል። ወረርሽኙ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳርፈው ጉዳት ቀላል የሚሆን ባይሆንም ኒወ ዚላንድ ግን ይህንን ተቋቁማ ለማገገም ብዙም እንደማትቸገር የምጣኔ ሃብት ሙያተኞች ያምናሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-52217125
amh
business
ላይቤሪያ 4 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ አሮጌ የገንዘብ ኖቶችን አቃጠለች
የላይቤሪያ ማዕከላዊ ባንክ ያረጁ እና የተበላሹ የገንዘብ ኖቶችን በአዲስ ለመተካት በሚል አራት ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ አሮጌ የገንዘብ ኖቶችን አቃጥሏል። በአገሬውም የመገበያያ ገንዘብም የተቃጠለው 600 ሚሊዮን የላይቤሪያ ዶላር ነው። የገንዘብ ኖቶቹ እንዲወገዱ የተደረጉትም መንግሥት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አዳዲስ ኖቶችን ቢያትምም አሮጌዎቹ በስርጭት ላይ ይገኛሉ የሚለውን ስጋት ተከትሎ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአውሮፓውያኑ 2018 ከፍተኛ መጠን ያለው የመንግሥት ገንዘብ ጠፍቷል የተባለ ሲሆን እንዲሁም ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመቱ አዲስ የታተሙ የላይቤሪያ የገንዘብ ኖቶች ጠፍተዋል የሚል ክስም እየቀረበ ይገኛል። ማዕከላዊ ባንኩ ይህንን አይቀበለውም የተባለው ገንዘብ በባንክ ካዝና ውስጥ መቀመጡን ገልጿል። የፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ መንግሥት አሮጌውን የላይቤሪያ ዶላር ለመተካት እና የሀገር ውስጥ ምንዛሬን ለማጠናከር በዚያው አመት ከሀገሪቱ የመጠባበቂያ ሂሳቦች ያወጣውን 25 ሚሊዮን ዶላር እስካሁን አልተካም። ይህንን ሊቀበሉ ያልቻሉ የተሟጋች ቡድኖች ማብራሪያ እና ተጠያቂነት እንዲኖር እየጠየቁ ነው። የላይቤሪያ ምጣኔ ኃብት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መንገዳገድ ቢያሳይም ነገር ግን ፕሬዚደንት ዊሃ በዚህ አይስማሙም በቅርቡ ለፓርላማ ባደረጉት አመታዊ ንግግር ኢኮኖሚው የተረጋጋና እያደገ ነው ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60229480
amh
business
ምጣኔ ሐብት ፡ ከብር ለውጡ በኋላ የወርቅ ዋጋ ለምን ጨመረ?
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ መደብሮች የወርቅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ነጋዴዎችና ገዢዎች ለቢቢሲ ገለጹ። ቢቢሲ በመሐል አዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ በሚገኙ የወርቅ መሸጫ መደብሮች ተዘዋውሮ እንደተረዳው የወርቅ መግዣ እና የመሸጫ ዋጋዎች ላይ ጭማሪዎች ታይተዋል። በተለይ ኢትዮጵያ የብር ኖቶቿን መቀየሯን ይፋ ካደረገችበት ከመስከረም ወር መጀመሪያ አንስቶ ጭማሪው በተለይ ከፍ ማለቱን በአዲስ አበባ ከተማ በወርቅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች እና ሠራተኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢቢሲ አዲስ አበባ ውስጥ ዋነኛ የወርቅ መሸጫ መደብሮች በሚገኙበት በፒያሳ አካባቢ ቅኝት ባደረገበት በባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ 21 ካራት ወርቅ በግራም ከሦስት ሺህ ሰባት መቶ ብር እስከ አራት ሺህ ብር ይሸጣል መባሉን ከነጋዴዎቹ ለማረጋገጥ ችሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መስከረም አስራ ሰባት ቀን ያስቀመጠው የወርቅ የመግዣ ዋጋ ለሃያ አንድ ካራት 2012 ብር ከስድሳ አራት ሳንቲም ሲሆን፤ የጥራት ደረጃው ላቅ ላለው የሃያ አራት ካራት ወርቅ ደግሞ 2300 ብር ከአስራ ስድስት ሳንቲም ዋጋ ሆኖ ተቀምጦለታል። ባለፉት ጥቂት ወራት የወርቅ ዋጋ ጭማሪ ሲያሳይ መቆየቱን ቢቢሲ አግኝቶ ካናገራቸው የወርቅ መሸጫ መደብሮቹ ባለቤቶች እና ሠራተኞች ተረድቷል። ይሁንና የወርቅ ዋጋ ጭማሪው በተለይ የብር ኖቶች መቀየር ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ የበለጠ ከፍ ማለቱን በወርቅ ንግድ ላይ የተሰማሩት ነጋዴዎች ጨምረው ተናግረዋል። "ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በግራም እስከ አምስት መቶ ብር ድረስ ጨምሯል" ስትል በአንድ የጌጣጌጥ መሸጫ መደብር ውስጥ የምትሰራ እንስት ለቢቢሲ ተናግራለች። ከግለሰቦች ቀለበት፣ ሃብል፣ የጆሮ ጉትቻና የመሳሰሉ የወርቅ ጌጣጌጦችን በመግዛት አትርፎ በመሸጥ የሚተዳደርና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ አንድ ወጣት ደግሞ ጭማሪው ከሽያጭ በተጨማሪም በግዢም ላይ እየተስተዋለ እንደሚገኝ ተናግሯል።

"ከአንድ ወር በፊት አንድ ግራም የሃያ አንድ ካራት ወርቅ አንድ ሺህ ብር፤ ከፍ ሲል ደግሞ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ከሰው ላይ እገዛ ነበር" የሚለው ወጣት "ባለፈው አስራ አምስት ቀን ውስጥ ግን ብዙ ጭማሪ አሳይቷል" በማለት ባለፈው አርብ አንድ ግራም ወርቅ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ብር መግዛቱን ተናግሯል። ከሌላው ጊዜ በተለየ ወርቅ የሚገዙ ሰዎች ፍላጎት መጨመር ዋጋውን ማናሩን የሚናገረው ይህ ወጣት፤ ከብር ኖቶች ቅያሪው ጋር ተያይዞ የተከማቸ ገንዘብን ወደአስተማማኝ ውድ ዕቃ መቀየር የሚፈልጉ ሰዎች ሳይኖሩ እንደማይቀሩ ግምቱን አስቀምጧል። "የገንዘብ ኖቶች ለውጡ ሳይጠበቅ ዱብ ያለ በመሆኑ ውዥንብር እና እርግጠኛ ያለመሆን ስሜቶች ፈጥሯል" የሚሉት የምጣኔ ሐብት ጉዳዮች ተንታኙ አብዱልመናን መሃመድ ናቸው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ገንዘብ በእጃቸው ላይ ያላቸው ሰዎች ደኅንነታቸው አስተማማኝ በሆኑ ንብረቶች ላይ ብራቸውን ለማዋል መፈለጋቸውን በወርቅ ግብይቱ ላይ የታየውን የዋጋ ለውጥ እንደምሳሌ በማንሳት ይገልፃሉ፤ "ይህም በእነዚህ ንብረቶች ዋጋ ላይ የመናር ምክንያት ሊሆን ይችላል" ባይ ናቸው። "መኪና እና ቤትን የመሳሰሉ ቋሚ ንብረቶችን እንዲሁም ወርቅን የመሳሰሉ ሌሎች ንብረቶች ላይ ገንዘብን ማዋል እንደአማራጭ ስለሚወሰድ ተፈላጊነታቸው መጨመሩ የሚጠበቅ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት አብዱልመናን፤ በሕገ ወጥ መልኩ የተገኘ ገንዘብን ለመሸሸግም ወርቅ ቀላል መንገድ ነው ይላሉ። 

"ስለዚህም የወርቅ የዋጋ ጭማሪን የፈጠረው የገንዘብ ኖት ለውጡ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም" ሲሉ እምነታቸውን ይገልጻሉ። ባለፈው ዓመት ወርሃ ግንቦት ላይ ብሔራዊ ባንክ ከ63 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ወርቅ ወደ ገበያ መቅረቡን ገልፆ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ የባንኩ ገዥ የሆኑት ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ይህ የተጠቀሰው የወርቅ መጠን ከፍተኛ እንደነበርና ለመንፈቅ ዓመት ያህል የቁልቁል ይጓዝ የነበረው የወርቅ አቅርቦትን መጠን የቀየረ መሆኑን ተናግረው ነበር። ለወትሮውም ብሔራዊ ባንክ ወርቅን በሚገዛበት እና በነጋዴዎች ገበያ ላይ በሚሸጥበት ዋጋ መካከል ልዩነት መኖሩን የጠቀሱት ባለሞያው፤ ይህም ጌጣጌጥ ቤቶች ለንድፍ ሥራዎች፣ ለአገልግሎት ወጪዎች እና ለትርፍ በሚጨምሩት ገንዘብ ምክንያት ይመጣ እንደነበር ያስረዳሉ። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ወደ ውጭ በሚላክ ወርቅ መጠን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ነበረው የሚሉት አብዱልመናን ይህንን ከግምንት ውስጥ በማስገባት በወርሃ ሐምሌ በብሔራዊ ባንክ የዋጋ ሽግሽግ ተደርጓል ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54333190
amh
business
የነዳጅ ድጎማ መነሳትና ሊያስከትል የሚችለው ጫና
የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አሳውቋል። በዚህም አስካሁን ከታዩት የዋጋ ጭማሪዎች ሁሉ ከፍተኛው እንደሆነ ተነግሯል። መንግሥት እንደሚለው የነዳጅ ምርቶችን ለመደጎም በወር በአማካይ 10 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግ በመግለጽ፣ በአሁኑ ወቅት 146 ቢሊየን 624 ሚሊየን 248 ሺህ 889 ብር የነዳጅ ድጎማ ዕዳ አለበት ተብሏል። ቀደም ሲል መንግሥት በየወሩ በሚያደርገው የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ላይ ጭማሪው ከ10 በመቶ የሚበልጥ አልነበረም። አሁን ግን ይህንን የመንግሥት ድጎማውን ደረጃ በደረጃ ለማንሳት ባወጣ ዕቅድ መሠረት በቤንዚን ላይ ከ25 በመቶ በላይ፣ እንዲሁም በናፍጣ ላይ ከ35 በመቶ በላይ ጭማሪ ተደርጓል። መንግሥት እንደሚለው በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዋጋ ቢሰላ የ1 ሊትር ናፍጣ የመሸጫ ዋጋ ብር 91 ከ23 ሳንቲም እና የቤንዚን ደግሞ በሊትር 82 ብር ከ07 ሳንቲም መሆን ነበረበት። በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ደግሞ ዋጋው ከዚህ ከፍ ይላል። ነገር ግን አሁንም መንግሥት 75 በመቶውን ጭማሪ እራሱ በመሸፈን 25 በመቶውን ብቻ ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ ማድረጉ ተገልጿል። የትኛውም የምርትና የአገለግሎት አቅርቦት በአንድም ሆነ በሌላ በኩል ከነዳጅ ዋጋ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ፣ ሕዝቡን ባስጨነቀው የኑሮ ውድነት ላይ ሌላ ጫናን ሊፈጥር ይችላል እየተባለ ነው። የአሁኑ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ክለሳ እንዲሁም በቀጣይ የሚደረገው የዋጋ ማስተካከያ የሚያስከትለውን ውጤት በተመለከተ ከጥቂት ሳምንት በፊት ያዘጋጀነው ጥንቅር በዝርዝር ይዳስሳል። እነሆ . . . መንግሥት የውጭ ምንዛሬን በስስት ነው የሚያየው። እንደ ስእለት ልጅ። የዶላር ጥሪት እንደዋዛ አይቋጠርማ። በብዙ አበሳ፣ በብዙ የወጭ ንግድ፣ በብዙ ተጋድሎ ነው የሚመጣው። እንዲያም ኾኖ ጥሎበት ከአራት ቢሊዮን ዶላር አይዘልም። እሱም ቢኾን መጥቶ አይበረክትም፤ አብዛኛውን ነዳጅ ይጠጣዋል። ይሁን እንጂ፣ እስከዛሬ ድረስ ለነዳጅ የሚከፈለው ዶላር በወጭ ንግድ ከሚገኘው ዶላር በልጦ አያውቅም ነበር። አሁን ግን ታሪክ ተቀየረ፤ ነገሩ ከፋ። ይህ በይፋ የታወቀው ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ነው። ለ2015 ነዳጅ መግዣ የሚያስፈልግህ ስንት ነው ሲባል 5.6 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ። እንዲህ ያለ አሃዝ ተሰምቶ አይታወቅም ነበር፤ ይህም የመርከብና የነዳጅ ዋጋ መናር ያመጣው ነው ይባላል። ታዲያ ይህ ገንዘብ ከየት ይመጣል? አንደኛ ከውጭ ንግድ እንዲህ ዓይነት ገቢ በጭራሽ ኖሮን አያውቅም። ቡናው፣ ሌጦው፣ ሰሊጡ ተረባርበው ከአገር ወጥተው እንኳ እንዲህ ዓይነት ገቢን አያመጡም። አሳሳቢው ይህ ብቻ በሆነ መልካም። ነዳጁ ከዚህም ከዚያም ዶላር ተፈልጎ ሊገዛ ይችላል። ከተገዛ በኋላም ግን መደጎም አለበት። ከተገዛበት ዋጋ በግማሽ ቀንሶ እንዲሸጥ መደጎም አለበት። ለዚህ ድጎማ ደግሞ አገሪቱ በወር በአማካይ 10 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋታል። አንድ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ከሰሞኑ ለኢዜአ እንደተናገሩት ድጎማው መንግሥትን በጠቅላላው 132 ቢሊዮን ብር ለሚደርስ የዕዳ ክምችት ዳርጎታል። መንግሥት ይህን ህመሙን ለዓመታት ቻል አርጎት ቆየ። በኮቪድ ዘመን የዓለም የነዳጅ ዋጋ መሬት ሲነካ ህመሙን ለጊዜውም ቢኾን አስታግሶለት ይሆናል። ከኮቪድ በኋላ ግን የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ ተቀጣጠለ። በእንቅርት ላይ. . . እንዲሉ የዩክሬን ጦርነት ተቀሰቀሰ። በዚህ ጊዜ በዓለም ነዳጅ ዋጋ ላይ ‘ሰደድ እሳት’ ተነሳ። ነዳጅ በዩክሬን ጦርነት ማግስት በበርሜል 140 ዶላር የደረሰበት ጊዜ ነበር። ይህ ዋጋ ሃብታም አገራትን ሳይቀር ሚዛናቸውን አስቷቸዋል። እዚህ ግባ የሚባል የተፈጥሮ ሃብት ለሌላት፣ የባሕር በር ለሌላትና ሰላም ለራቃት አገር ይህ ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል ማብራሪያ አይሻውም። “የማይካደው ነገር በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከአንዳንድ የነዳጅ አምራች አገራት ጋር ሲነጻጸር እንኳ ርካሹ ነው” ይላሉ ተቀማጭነታቸውን በኩዌት ያደረጉት የምጣኔ ሃብት ተመራማሪው አየለ ገላን። “ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ጋር ቢነጻጸር እንኳ የኢትዮጵያ ነዳጅ ዋጋ በትንሹ አነስ ሳይል አይቀርም።” ይህን የሚሉት ድጎማው ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ለማስረዳት ነው። እኚህ ተመራማሪ ድጎማው ከፍተኛ መሆኑን ይግለጹ እንጂ መንግሥት ድጎማውን፣ በተለይ አሁን ላይ፣ ለማንሳት መወሰኑን በፍጹም አይስማሙም። “የነዳጅ ድጎማውን ማንሳት እየነደደ ያለ ቤት ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ ነው” ሲሉ የመንግሥትን ዕቅድ ይተቹታል። የነዳጅ ድጎማ በሂደት የተወለደ ሐሳብ ነው። የሕዝብ የመግዛት አቅም ሲያሽቆለቁል፣ የነዳጅ ዋጋ ሲያሻቅብ ድጎማ ተወለደ። ፖሊሲ ሳይሆን ሒደት ወለደው ማለቱ ይቀላል። “በመሠረቱ ይህ ድጎማ ሲጀመርም በፖሊሲ ተደግፎ አያውቅም” ይላሉ የነዳጅና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ። “ነዳጅ እንዲሁ በቁጥጥር ሥርዓትና በዋጋ ማረጋጊያ ሰነድ የሚመራ እንጂ በፖሊሲ የተደገፈ የድጎማ ሥርዓት ኖሮት አያውቅም።” ለነዳጅ ሁነኛ መመሪያ የወጣለት ከሦስት ዐሥርታት በፊት ነው። በ1993 ዓ.ም. የነዳጅ ፈንድ ተመሠረተ። የነዳጅ ፈንድ ዋጋን የማረጋጋት ሚናን እንዲጫወት ነበር የታሰበው። ይህም ማለት መንግሥት ከዓለም ገበያ ነዳጅ ይገዛል። ከዚያ አገር ውስጥ ሲሸጥ ሽርፍራፊ ሳንቲሞችን ወደዚህ የነዳጅ ፈንድ እያስገባ ያጠራቅማል። ለምሳሌ ነዳጅ ተገዝቶ ተተምኖ ወደ ገበያ ሲወጣ 21 ብር ከ80 ሳንቲም ቢሆን መንግሥት 22 ብር ይሸጠውና 20 ሳንቲሟ ተጠራቅማ ለሚቀጥለው ድጎማ ትውላለች። በዚህ አሠራር የተወሰኑ ቢሊዮን ብሮች በዚህ የነዳጅ ፈንድ እየተጠራቀሙ ቆዩ። ኾኖም ነዳጅ የሚጨምርበት ፍጥነትና ይህ ፈንድ የሚለቃቅማቸው ሳንቲሞች ሊገናኙ አልቻሉም። የእርምጃና የ100 ሜትር ሩጫ ተወዳዳሪዎችን በአንድ መም የማሮጥ ነገር መሰለ። ይህ ሁኔታ በተለይ ከ2003 ዓ.ም. ወዲህ ጭራሽ ሊገናኝ አልቻለም። ከዚህ ወዲያ ነበር ከመንግሥት ካዝና ቢሊዮን ብሮች እየወጡ ነዳጅን በቀጥታ መደጎም የተያዘው። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የነዳጅ ድጎማው በየወሩ እየተከለሰ ዋጋው ከዓለም ዋጋ ከፍና ዝቅ ጋር እየተነጻጸረ እንዲስተካከል ይደረግ ነበር። “ይሁንና ከ2009 ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ የተከለሰው ለ5 ጊዜ ብቻ ነው’’ ይላሉ በቀለች ጫናውን ምን ያህል መንግሥት ተሸክሞት እንደቆየ ለቢቢሲ ሲያስረዱ። ይህ ግን አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ሁኔታ አንጻር የሚያስቀጥል አልሆነም። በዚህ የተነሳ አገሪቱ ከነዳጅ ጋር በተያያዘ በቀጣይ አካሄዷን ለማስተካከል ተገዳለች። የዓለም ዋጋን ያንጸባረቀ ዋጋን ከሕዝብ ጋር ለመጋራት ቆርጣለች። ሕመሜን አስታሙልኝ ነው ነገሩ። በዚህ ጊዜ ለምን እዚህ ውሳኔ ላይ ተደረሰ? ስንል የነዳጅና ኢነርጂ ሚኒስትር መሥሪያ ቤትን ጠይቀናል። “በዚህ ኑሮ እሳት በሆነበት ጊዜ መሆኑ አደጋ የለውም ወይ?’’ ስንል የምጣኔ ሃብት አዋቂዎችን አወያይተናል። በቀለች ኩማ ድጎማውን በዚህ ወቅት ማንሳቱን የሚመለከቱት በተለየ መነጽር ነው። ነገሩን መንግሥት ላይ እያሳደረ ካለው የዕዳ ጫና ብርቱነት፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋ መቀጣጠል እና ከሕገ ወጥ ንግድ መበራከት አንጻር መመልከትን ይመርጣሉ። “ድጎማው ከጥቅሙ ጉዳቱ በዛ” የሚሉት በቀለች በዋቢነት የሚያነሱት ሕገ ወጥ የኮንትሮባንድ ነዳጅ ንግድ መበራከትን ነው። ይህ አየር በአየር ሽያጭ አገሪቱን ለከፍተኛ ዕዳ ዳረጋት። በውድ የውጭ ምንዛሬ የሚደጎመው ነዳጅ እያከበረ ያለው ኮንትሮባንዲስቶችን ነው፤ ባለጸጎችን ነው፤ ሲሉ ያስረዳሉ። እርግጥ ሕዝብ ይደጉማል የተባለ ውድ ነዳጅ ማደያ ሳይደርስ ጎረቤት አገር ይቸበቸብ እንደነበር አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ቢሆንም ግን በዚህ ወቅት ቁጥጥርን ማጥበቅ እንጂ ድጎማን ማንሳት ያስኬዳል? ይህ ብቻ ግን አይደለም ድጎማ የማንሳቱ መንስኤ ይላሉ በቀለች፣ “ድጎማው በፖሊሲም ያልተደገፈ ከመሆኑ የተነሳ ጥቅል ድጎማ ነው የነበረው።’’ እርግጥ ድጎማው የጅምላ ድጎማ መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይም አጥብቀው የሚኮንኑት ጉዳይ ነው። ጥቅል ድጎማ ሲባል ምን ማለት ነው? ሃብታምና ድሃን፣ ቤንትሌና ሃይገርን፣ ሊሞዚን፣ መርሴዲስን እና ‘ቅጥቅጥ አይሱዙን’ በእኩል መደጎም ማለት ነው። ኢኮኖሚስቱ አቶ ዋሲሁን፣ “መንግሥት የኤምባሲ መኪናንም የከተማ አውቶቡስንም በአንድ ሲደጉም ነው የኖረው” የሚሉት ለዚሁ ነው። የእስከዛሬው የነዳጅ ድጎማ ከመሠረታዊ የድጎማ (subsidy) ጽንሰ ሐሳብ ጋር የሚጻረር እንደነበር ቢቢሲ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሃብት አዋቂዎች የሚስማሙበት ነጥብ ነው። ድጎማ በባህሪው የአጭር ጊዜ መፍትሄ ነው። የአጭር ጊዜ መሆን ብቻም ሳይሆን ማሳካት የፈለገው ግብ በውል ተለይቶ መቀመጥ አለበት። መቀመጥ ብቻም ሳይሆን ዓላማውን አሳክቷል ወይ ተብሎ መፈተሽ አለበት። ሁሉም ባለሙያዎች የሚሉት ይህንን ነው። በዚህ ሚዛን ላይ ሲቀመጥ ድጎማው ውሉን የሳተ ነበር ብለው ያምናሉ አቶ ዋሲሁን። እሳቸው መደጎም ያለበት የሚሉት በዋናነት ምርትን ማሳደግ የሚችለውን ዘርፍ ነው። ነዳጅ በኢትዮጵያ ሁለት ሚና አለው፤ አንዱ ለፋብሪካዎች የኃይል ምንጭ መሆን ነው፤ ሌላው ትራንስፖርት ነው። በኢትዮጵያ ብዙ አምራች ተቋማት የማምረት አቅማቸው 40 ከመቶ አይሞላም። አንዱ ምክንያታቸው ታዲያ በቂ ኃይል ስለማያገኙ ነው። ስለዚህ መብራት በጠፋ ጊዜ ጄኔሬተር ይለኩሳሉ። ጄኔሬተር ነዳጅ ይጠጣል። ለእነዚህ አምራቾች ቢቻል አስተማማኝ ኃይል ማቅረብ ወይም መደጎም ምርታማነትን ይጨምራል። የኤምባሲ መኪናን ነዳጅ መደጎም ግን ምርታማነት አይጨምርም። ነዳጅን የምትደጉመው ኢትዮጵያ ብቻ ናት? ጥቂት የማይባሉ አገራት ነዳጅን ይደጉማሉ። ካልደጎሙም የኅብረተሰቡ የመግዛት አቅማቸው ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ድጎማ ግቡ ምንድነው? “ማክሮ ኢኮኖሚ እንዳይዛባ፣ ምርትና ምርታማነት እንዳይጎዳ፣ ባለመደጎም የሚመጣ ውስብስብ ኢኮኖሚያዊ መዘዝ ሲኖር ድጎማ አግባብ ሆኖ ሊታይ ይችላል’’ ይላሉ አቶ ዋሲሁን። “ይሄ መንግሥት ግን ከአቅሙ በላይ ብዙ ነገር የሚደጉም መንግሥት ነው፤ ክፋቱ ደግሞ መደጎም የሌለበትንም ይደጉም ነበር።” ለነዳጅ ድጎማ የሚወጣው ከፍተኛ ገንዘብ የኢትዮጵያ መንግሥትን ጀርባው መጉበጡን የምጣኔ ሃብት አዋቂው አቶ አየለ ገላን ያምናሉ። ነዳጅ በኢትዮጰያ የሚሸጥበት ዋጋ አገሪቱን ነዳጅ አምራች እንዳስመሰላትም አልሸሸጉም። የእርሳቸው ልዩነት የሚነሳው ድጎማን በማንሳት ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ነው። “የኢትዮጵያ ሸማች የመግዛት አቅም ደቃቃ ነው። ከሕዝብ አንጻር ስናየው እንዲያውም ድጎማው በቂ አልነበረም ልንል እንችላለን’’ ካሉ በኋላ መንግሥት ከድጎማ በፊት መሥራት የነበረበትን የቤት ሥራ አልሠራም ሲሉ ሂደቱን ክፉኛ ይተቻሉ። እነዚህ የቤት ሥራዎች ምን ነበሩ? “አንደኛ ኢኮኖሚው ተመሰቃቅሏል። ምርት አላደገም፣ የሕዝብ የመግዛት አቅም አልጨመረም። ጥቃቅን ኢንዱስትሪዎች በእግራቸው እንዲቆሙ አልተደረገም። የሕዝብ ደኅንነት አልተጠበቀም።...” መንግሥት እነዚህን መልከ ብዙ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ምስቅሎሽን ሳያስተካክል፤ ኢኮኖሚውን ጠንካራ መሠረት ላይ ሳያስቀምጥ ድጎማ ማንሳት (የእርሳቸው ቃል ለመጠቀም) “ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው።’’ አቶ ዋሲሁን ከድጎማው መነሳት ማግስት ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለውን ትንቢታዊ ጥያቄ በቀጥታ መጋፈጥን የመረጡ አይመስልም። ነገር ግን የመንግሥት ድጎማን የማንሳት ውሳኔን ከጥንቃቄ ጋር በአውንታዊ መልኩ ይረዱታል። “የድጎማ ሥርዓቱ (በአንድ ጥናት ላይ እንደታየው) 70 ከመቶ የሚሆነውን ድሃና 30 ከመቶ የሚሆነውን ሃብታም ነው ሲደጉም የኖረው። ስለዚህ ጤናማ ድጎማ አልበረም። ለድሃ የታሰበው ድጎማ ሃብታም ሲደጉም ነው የኖረው።’’ ስለዚህ በእሳቸው ዕይታ ከዚህ ወዲህ ድጎማው ለታሰበለት ሕዝብ ብቻ ስለመድረሱ እርግጠኛ መሆን ያሻል። “ድጎማ ዘዴኛና መለኛ (ታክቲካል) ካልሆነ ውሉን ሳተ ማለት ነው። ድሃው ነው የሚደጎመው ከተባለ ድጎማው ድሃው ጋር መድረሱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል’’ የሚሉት አቶ ዋሲሁን ነዳጅ በሞያሌ እየወጣ ሲሸጥ፣ አውቶቡስና የኤምባሲ መኪና አብሮ ተሰልፎ በአንድ የዋጋ ተመን ነዳጅ ሲቀዳ ድጎማ ግብ እንደተሳተ ምልክቶች ሆነው ይታያሉ። በዚህ ሐሳብ የነዳጅና ኢነርጂ ሚኒስትርም ባልደረባም ይስማማሉ። “የሚደጎምና የማይደጎምን በጥናት መለየት ያስፈለገውም ለዚሁ ነው ይላሉ” በቀለች ኩማ። ከድጎማ የተረፈው ገንዘብ ምን ላይ ይውል ይሆን? አቶ ዋሲሁን ከድጎማ መነሳቱ ይልቅ ከድጎማ የዳነው ገንዘብ የት እንደሚውል በእጅጉ ያሳስባቸዋል። “አሁን ያለው ኢኮኖሚ በግጭትና በጦርነት የቆሰለ ኢኮኖሚ ነው። ከፍተኛ ወጪዎች ይጠብቁታል። በወጪና ገቢ ልዩነት ማጥበብ ላይ ካልተሠራ የከፋ ሀኔታ ሊመጣ ይችላል” ይላሉ። ከፍተኛ የበጀት ጉድለት ደግሞ ወደ ገንዘብ ማተም ስለሚወስድ ለበለጠ የበጀት ቅርቃርና ኑሮ ውድነት ሊወስድ ይችላል የሚል ፍርሃት አላቸው። ስለዚህ መንግሥት ከድጎማ ወጪ ያዳነውን ገንዘብ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ሊያውለው ይገባል። “መንግሥት ማኅበረሰቡ ወጪውን እንዲጋራው መሞከሩ መጥፎ ነው ወይ? ብትለኝ እኔ መጥፎ ነው ብዬ አላስብም። ነገር ግን ገንዘቡ ለአበልና ለድግስ ከዋለ ነው ችግሩ።” አሁን በዓለም ገበያ ሰማይ የነካውን ነዳጅ መንግሥት በግማሽ ቀንሶ ነው ለሕዝብ የሚያደርሰው። ቀድም ባሉ ዓመታት በሊትር 5 እና 6 ብር ነበር የሚደጉመው። አሁን ያን ለማድረግ የሚያስችል አቅምን አጥቷል። በውስጣዊና ውጫዊ ዝርዝር ምክንያቶች። ምክንያቶቹን አቆይተን ነገር ግን መንግሥት በዚህ ድጎማ አሠራር ከሐምሌ ወዲያ መሻገር ይችል ነበር ወይ ብለን እንጠይቅ። በሌላ አነጋገር መንግሥት ደግ ሆኖ ልደጉም ቢልስ ይችላል ወይ? የብዙ ኢኮኖሚስቶች ምላሽ በአጭሩ ሲቀመጥ “አይችልም” የሚል ነው። ምክንያቱም፣ “...ሚያዝያ ወር ላይ ብቻ ዕዳው 124 ቢሊዮን ደርሰ” ይላሉ የነዳጅና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባልደረባ በቀለች ኩማ። ምክንያቱም፣ “...561 ቢሊዮን ብር ይዞ የተነሳ ኢኮኖሚ ነው ያለው። በዚህ ዓመት በዘጠኝ ወር የተሰበሰበው 290 ቢሊዮን ብር ነው። ልዩነቱ ሰፊ ነው። ይህን የበጀት ጉድለት ይዞ ብዙ መጓዝ አይቻልም” ይላሉ አቶ ዋሲሁን። ይሁንና ነዳጅ ድጎማው የኑሮ ውድነቱን እንዳያባብስ ምን ማድረግ ይቻላል? አቶ ዋሲሁን የነዳጅ ድጎማው በኑሮ መወደድ ላይ የሚያስከትለውን ጣጣ ማንም አያጣውም ይላሉ። ነገር ግን ያን ማስቀረት በምጣኔ ሃብት ሳይንስ የሚቻልበትን ዕድል አይታያቸውም። “የትኛውም ፖሊሲ ሁሉን አስታርቆ መሄድ አይችልም። ሁሉንም ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ አስደስቶ የሚያቆይ የኢኮኖሚ ውሳኔ በምድር ላይ የለም።’’ ይልቅ በቀጥታ በድጎማ መነሳት ብቻ የሚፈጠር ዋጋ ንረት ሳይሆን ድጎማ የመነሳቱ ወሬ በራሱ የሚፈጥረው የገበያ ትኩሳት ይበልጥ ያሳስባቸዋል። “እኛ አገር ነጋዴው በአጋጣሚው እንዴት በአቋራጭ ልክበር ነው የሚለው፤ የድጎማውን ጭማሪ ብቻ ደምሮ ይሸጣል ብዬ አልገምትም” ይላሉ አቶ አየለ ገላን። ከሐምሌ ወዲህ የሕዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪ ማደያ ገብቶ ነዳጅ ሲቀዳ ጂፒኤስ ተገጥሞለት ነው። ነዳጅ አቅራቢዎች ለማደያዎች ደረሰኝ ይሰጣሉ። ባለታክሲው በታሪፍ የተቀመጠውን ዋጋ ከፍሎ ይሄዳል። ማደያው በደረሰኝ ቀሪውን ያወራርዳል። ይህ አሠራር በመተግበሪያ የሚሠሩት ታክሲዎችን አይጨምርም። የመንግሥት ሰርቪሶችንም አይጨምርም። “ከዚህ በኋላ በየትኛውም ማደያ ነዳጅ ሲራገፍ የኛ ተቆጣጣሪዎች በያንዳንዱ ማደያ ተገኝተው ነው” ይላሉ የነዳጅና ኢንርጂ ሚኒስቴር ባልደረባ በቀለች ኩማ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ሕዝብን ለማረጋጋት ይመስላል መንግሥት ድጎማ ማንሳቱ በኑሮ ላይ አንዳችም ጫናን አይፈጥርም የሚሉ ድምጾች እየተስተጋቡ ነው። ይህ ለምጣኔ ሃብት አዋቂዎችም ሆነ ለሰፊው ሕዝብ እምብዛምም ስሜት የሚሰጥ አይደለም። በቀለች ኩማ ግን “ድጎማ መነሳቱ በቀጥታ የሚባለውን ያህል የዋጋ ንረት አያስከትልም፤ ይህ በጥናት የተረጋገጠ ነው” ሲሉ የነገሩን ሀቅነት ይሞግታሉ። እሳቸው ጥናቱን ለቢቢሲ ለማጋራት ባይፈቅዱም የነዳጅ ድጎማ መነሳት በቀጥታ የሚያስከትለው የዋጋ ንረት እዚህ ግባ የሚባል እንዳይደለ ይጠቅሳሉ። “...ድጎማው ሲነሳ በእያንዳንዱ ሸቀጥ ላይ የሚያመጣው ጫና በሳንቲም ቤት እንደሆነ ተደርሶበታል” ይላሉ። ይሁንና ምጣኔ ሃብት ሙያተኞቹ አቶ ዋሲሁን እና አቶ አየለ ግን በዚህ ብዙም አይስማሙም። አንዱ ምክንያታቸው በኢትዮጵያ የንግድ ዘይቤ እንደታየው ዋጋ የሚወሰነው በቀጥታ በሚመጣ ጭማሪ ሳይሆን ገና በሥነ ልቦና በሚፈጠር ፍርሃትም ጭምር ስለሆነ ነው። ለብዙዎች አዲስ ዜና የሆነው ደግሞ የታለመላቸው የሚባሉት ተደጓሚዎችም ቢሆኑ ድጎማቸው ጊዜያዊ መሆኑ ነው። በቀለች ሁሉም ታክሲዎችና የሕዝብ አውቶቡሶች ሳይቀሩ በሂደት ከድጎማ ሥርዓት እንደሚወጡ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “በአምስት ዓመት ውስጥ ከድጎማው ሙሉ በሙሉ ይወጣሉ። በየሦስት ወሩም ዋጋ ክለሳ ይደረግባቸዋል።” የሰዉ ስሜቱ የተዘበራረቀ ነው። ኑሮ መንደድ ያለበትን ያህል በመንደዱ ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ? የሚል ስሜት ያላቸው አሉ። ነገን በፍርሃትና በሰቀቀን የሚጠብቁም አሉ። ድጎማው ሐምሌ ላይ ሲነሳ የዋጋ ጭማሪው እንደ ሐምሌ ዝናብ ዶፍ ሆኖ ሊወርድ የተሰናዳ ይመስላል። ሐምሌ አሳሳቢ ሆኖ የሚታየው ታዲያ ለተርታው ሕዝብ ብቻ አይደለም። ለጎምቱ ኢኮኖሚስቶችም ጭምር እንጂ። መቀመጫቸውን ኩዌት ያደረጉት አቶ አየለ ገላን፤ “በዚህ ጊዜ ድጎማን ማንሳት ለእኔ ስሜት የሚሰጥ አይደለም፤ ዚምባብዌ ወደ ገጠማት ኢኮኖሚ ሁኔታ የመንደርደር ያህል አድርጌ ነው የምመለከተው” ይላሉ። ምርትና ምርታማነት ፈቅ ሳይል፣ መሠረታዊ የኑሮ ደረጃ ኢምንት ሳይጨምር የገጠሩ የግብርና ኢኮኖሚ ሳያድግ አሁን ባለው ኢኮኖሚ ላይ የነዳጅ ድጎማን ማንሳት ከድጡ ወደ ማጡ ነው፤ ለእርሳቸው። በቀለች ኩማ ግን የተቀናጀ ቁጥጥርና በቂ ግንዛቤ ለኅብረተሰቡ ከደረሰ የከፋ ሁኔታ አይመጣም ባይ ናቸው። አቶ አየለ በፍጹም በዚህ አይስማሙም፤ በዚህ እሳት በሆነ ኑሮ ይህን መሠረታዊ  የነዳጅ ድጎማን ማንሳት “እየነደደ ባለ እሳት ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ ነው” ይሉታል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyd3yjlr0rgo
amh
business
ሱዊዝ ቦይ በመዘጋቱ በየቀኑ የ9.6 ቢሊዮን ዶላር ምርት መተላለፍ አልቻለም
የግብጹ ሱዊዝ የባሕር ላይ ማቋረጫ ቦይ በመዘጋቱ በየቀኑ 9.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መተላለፍ እንዳልቻሉ ተገለጸ። በሱዊዝ መተላለፊያ ላይ አንድ ግዙፍ የጭነት መርከብ ባሕሩን ዘግቶ ከማክሰኞ ዕለት ጀምሮ በመቆሙ ምክንያት እንቅስቃሴ መገታቱ ይታወሳል። ሎይድስ ሊስት የተባለው የመርከብ ጉዞ ድርጅት እንደሚለው፤ በቀን ውስጥ ከምዕራብ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩ 5.1 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መጓጓዝ አልቻሉም። ከምሥራቅ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩና የተስተጓጎሉ ምርቶች ደግሞ 4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ናቸው። የባሕሩን መተላለፊያ የዘጋው መርከብ እንቅስቃሴ እንዲጀምር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ባለሙያዎች ተናግረዋል። በታይዋኑ ኤቨርግሪን ማሪን ሥር ያለው ኤቨር ጊቭን መርከብ በዓለም ትልቁ ኮንቴነር ጫኝ ሲሆን፤ 200,000 ቶን የሚመዝን እንዲሁም 20,000 ኮንቴነር ማጓጓዝ የሚችል ነው። መርከቡ በመቆሙ ሳቢያ ሌሎች መርከቦች ለቀናት መተላለፍ አልቻሉም። የባሕር ላይ ጉዞ አማካሪ ድርጅት ባለቤት ጆን ሞንሮይ ብዙ ወደቦች ላይ የሚገኙና መጓጓዝ ያልቻሉ ኮንቴነሮች እንዳሉ ይናገራል። መተላለፊያው በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ምርቶች የሚተላለፉበት ሲሆን፤ የጦፈ ንግድ የሚካሄድበት መስመር ነው። ከመላው ዓለም የባሕር ንግድም 12 በመቶው የሚያልፈውም በዚሁ የግብጽ የባሕር ላይ ማቋረጫ መስመር በኩል ነው። ሎይድስ ሊስት ባወጣው አሃዝ መሠረት፤ በአሁኑ ጊዜ 160 መርከቦች በሱዊዝ ቦይ በኩል ለማለፍ እየጠበቁ ነው። ከእነዚህ መካከል 41 የሚሆኑት የተለያዩ ምርቶች ሲይዙ 24 ደግሞ ነዳጅ ጫኝ ናቸው። ቢአይኤምሲኦ የተባለው ዓለም አቀፍ የመርከበኞች ማኅበር እንደሚለው መተላለፊያው ተዘግቶ ከቆየ የምርት አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። የሎጂስቲክስ ተቋሙ ኦኤል ዩኤስኤ ፕሬዘዳንት አለን ባይር "በእያንዳንዱ ቀን ያልተጓጓዙ ምርቶችን ለማሳለፍ ተጨማሪ ሁለት ቀናት ይጠይቃል" ብለዋል። እስካሁን ለሦስት ቀናት መተላለፍ ያልቻሉትን ምርቶች ለማጓጓዝ ስድስት ቀናት ገደማ ሊያስፈልግ እንደሚችልም ግምታቸውን አስቀምጠዋል። መተላለፊያው እስኪከፈት ድረስ ቀናት ወይም ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል የተጠቆመ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ በመላው ዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ጫና ያሳድራል። የዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ይህ የግብጽ የባሕር ላይ መተላለፊያ ከመዘጋቱ በፊት በኮቪድ-19 ምክንያት መቀዛቀዝ አጋትሞት ነበር። አለን እንደሚሉት፤ መርከቦች ሌላ አማራጭ የጉዞ መስምር ከፈለጉ በምዕራብ አፍሪካ በኩል በመዞር ጉዟቸውን ሊቀጥሉ ብችሉም ይህ ጉዞ ግን ከሰባት እስከ ዘጠኝ ቀናት ሊፈጅ ይችላል። አንዳንድ ተቋሞች መተላለፍ ባልቻሉ ምርቶቻቸው ምትክ ሌሎች ምርቶችን በአውሮፕላን ወይም በባቡር መላክን እንደ አማራጭ ሊወስዱ ይችላሉ። እስካሁን ድረስ ሜርስክ እና ሀፓግ ሎይድ የተባሉ ተቋሞች ከሱዩዝ መተላለፊያ መስመር ውጪ ያሉ አማራጮችን እንደሚጠቀሙ አስታውቀዋል። የግብጹ የሱዊዝ መተላለፊያ ባለሥልጣን ባሕሩን የዘጋውን መርከብ ለማስነሳት የቻለውን ሁሉ እየሞከረ እንደሆነ አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/56534020
amh
business
ኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍን ለውጭ ባለሐብቶች ክፍት ለማድረግ ወሰነች
የኢትዮጵያ መንግሥት ካቢኔ ለአስርታት ለውጭ ባለሐብቶች ዝግ ሆኖ የቆየውን የባንክ ሥራ ዘርፍ ክፍት ለማድረግ የቀረበለትን ረቂቅ ፖሊሲ አጸደቀ። በአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ አማካይነት ተዘጋጅቶ የቀረበው ረቂቅ ለዘመናት ለኢትዮጵያውያን ብቻ ተትቶ የነበረውን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ባንኮችም ክፍት እንዲሆን የሚፈቅድ ነው። ይህም በዘርፉ ታዋቂ የሆኑ ዓለም አቀፍ ባንኮች በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ እንዳይሰማሩ አድርጎ የቆየውን የአገሪቱን የፋይናንስ ፖሊሲ የቀየረው ውሳኔ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ይፋ ሆኗል። በዚህም ዓለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ ለአገር ውስጥ ባለሐብቶች ብቻ ክፍት አድርጋው በቆየችው ዘርፍ ለመሳተፍ እድል ይፈጥርላቸዋል። የፋይናንስ ዘርፉ ዝግ ሆኖ በቆየባቸው ዓመታት ውስጥ የአገሪቱን ምጣኔ ሐብት በተለያዩ መስኮች ሲደግፉ የቆዩት ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አገራት ዘርፉን እንድትከፍት ሲወተውቱ ቆይተዋል። ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ የቀረበውን ረቂቅ ፖሊሲ አጽድቆ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔውን ይፋ ባደረገበት መግለጫው እንዳለው የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ “አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የአገሪቱን ምጣኔ ሐብት ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር የበለጠ እንዲተሳሰር ለማድረግ ያስችላል።” ብሏል። በተጨማሪም ይህ እርምጃ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን በማቀላጠፍ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን በማጎልበት ለምጣኔ ሐብት ዕድገት አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል። ለረጅም ዘመናት በመንግሥት እና በአገር ውስጥ ባለሐብቶች ተሳትፎ ብቻ ተይዘው የቆዩ ዘርፎችን የመክፈት ፍላጎት እንዳለው ሲገልጽ የቆየው መንግሥት አሁን የባንኩን ዘርፍ ክፍት አድርጎታል። ይህ ዘርፍ ለውጭ ባለሐብቶች ክፍት ሊሆን እንደሚችል እና ዝግጅትም እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተለያዩ አጋጣሚዎች ፍንጭ ሲሰጡ ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በተለይ በመንግሥት ተይዘው የሚገኙ ዘርፎችን ከፍት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለ የተነገረ ሲሆን ተግባራዊነቱ ግን አዝጋሚ ሆኖ ነበር። ከ120 ዓመት በላይ በመንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮም ተይዞ የነበረው የቴሌኮም ዘርፍ ለውድድር ክፍት ሆኖ፣ ከአንድ ዓመት በፊት በተካሄደ ጨረታ ሳፋሪኮም ተመራጭ ሆኖ በዚህ ወር በተወሰኑ የአገሪቱ ክፍሎች የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c6px7z4zg45o
amh
business
የኬንያው ፕሬዝዳንት በአገራቸው ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እንዳይሸጡ አገዱ
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በአገሪቱ ከግንባታዎች ላይ የተነሱ፣ ያገለገሉ እንዲሁም የተጣሉ ብረታ ብረቶች ሽያጭ እንዳይካሄድ አስቸኳይ እገዳ ጣሉ። ይህ የፕሬዝዳንቱ ድንገተኛ እገዳ ይፋ የተደረገው መንግሥት እየጨመረ ነው ያለውን በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ የሕዝብ ንብረቶች ላይ የሚፈጸም ዝርፊያና ውድመትን ለመከላከል ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት ነው። ይህ የወዳደቁና አሮጌ ብረቶች ሽያጭ እገዳ ተግባራዊ የሚሆነው የኬንያ መንግሥት የእነዚህን ብረታ ብረቶች ምንጭ፣ ንግድና ወደ ውጭ የሚላኩበትን ሁኔታ በተመለከተ ለመቆጣጠር የሚያስችል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ነው። ባለፈው ሳምንት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በሚገኝ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ተፈጸመ በተባለ ዘረፋ ምክንያት በአገር አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሪክ መቋረጥ አጋጥሞ ነበር። በመላዋ ኬንያ በተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሰበብ ዘጠኝ የኬንያ መብራት ኃይል አቅራቢ ተቋም ከፍተኛ ሥራ አስኪያጆች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የባቡር ሃዲዶችን፣ የኮምዩኒኬሽን ማማዎችን እንዲሁም የኤሌክትሪክ ማስተላላፊያ መስመሮችን ጨምሮ ኬንያ ውስጥ በሚገኙ የሕዝብ መሠረተ ልማቶች ላይ ተደጋጋሚ የሆነ ዘረፋና ውድመት ማጋጠሙ ተነግሯል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የወዳደቁ አሮጌ ብረቶችን ባገዱበት ወቅት እንዳሉት በሕዝብ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸመው ዘረፋና ጥፋት ከምጣኔ ሀብት አሻጥር ጋር የሚስተካከል በመሆኑ የአገር ክህደት ተግባር ነው ብለዋል። በመሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ዘረፋዎችን በበተመለከተ የኬንያው ፕሬዝዳንት ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም። ከሦስት ዓመት በፊት የአገሪቱን ግዙፍ የባቡር መስመር ግንባታ ባስጀመሩበት ጊዜ ከቻይና በተገኘ ብዙ ቢሊዮን ዶላር ብድር በሚሰራው መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሰው በሞት እንዲቀጣ እንደሚያጸድቁ አስጠንቅቀው ነበር። የተለያዩ ግዙፍ ሕዝባዊ መሠረተ ልማቶች የተገነቡባቸውን የተለያዩ የብረት አካላት ዘራፊዎች ነቅለው ወይም ቆርጠው በመውሰድ ለሽያጭና የተለያዩ ነገሮችን ለመስራት ያውሉታል። ይህ የኬንያ ችግር ብቻ ያልሆነው የብረታብረቶች ዝርፊያና ውድመት ከተለያዩ መሠረተ ልማቶች የተዘረፉት ቁርጥራጭ የብረት አይነቶን ከአገር ውጪ በመውሰድ ለሌሎች ወገኖች እንደሚሸጡ ይነገራል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60082636
amh
business
ቦይንግ 20 በመቶ ሰራተኞቹን ለመቀነስ ማቀዱን አስታወቀ
ቦይንግ በቅርቡ 7 ሺህ የሚሆኑ ሰራተኞቹን እንደሚቀንስ ይፋ አድርጓል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተጎዳው የአሜሪካኑ አውሮፕላን አምራች ቦይንግ በከፍተኛ ሁኔታ የሰራተኞቹን ቁጥር ለመቀነስ እንዳሰበ ያሳወቀ ሲሆን በመጪው አውሮፓውያኑ አመት መጨረሻም 20 በመቶ የሚሆኑትን ወደ 30 ሺህ ሰራተኞቹን እንደሚቀንስ አስታውቋል። ከቀውሱ በፊት ኩባንያው የነበሩት የሰራተኞች ቁጥር 160 ሺህ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተጨማሪ ከ337 ማክስ የደህንነት ስጋቶች ጋር ተደራርቦ ኩባንያውን ለኪሳራ ዳርገውታል። እስከ መስከረም አጋማሽ ባለውም ሶስት ወራት ውስጥ 466 ሚሊዮን ዶላር ከስሬያለሁ ብሏል። ይህም ሁኔታ ለአመት ያህልም ቀጥሏል። ከበረራ ውጭ ሆነው የነበሩት 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ በረራ ሊጀምሩ ይችላሉ መባሉም ጋር ተያይዞም ኩባንያው በእነዚህ አውሮፕላኖች ሽያጭ እንደሚያገግም ተስፋ አድርጓል። 737 ማክስ ሁለት አውሮፕላኖች ተከስክሰው የ346 ሰዎች ህይወት ከጠፋ በኋላ ከበረራ ከታገደ ከአንድ አመት በላይ ሆኖታል። አውሮፕላኑ ሙሉ ሙሉ ከበረራ የታገደው በጎርጎሳውያኑ መጋቢት ወር 2019 ዓ.ም ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአየር ጉዞ ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ቀውስን ያስከተለ ሲሆን በርካታ አየር መንገዶችንም ኪሳራ ውስጥ ጥሏል። በዚህም ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ሰራተኞቻቸውን አባረዋል እንዲሁም አዳዲስ ሊገዟቸው ያሰቧቸውን አውሮፕላኖች በይዋል ይደር ትተውታል። ቦይንግም ሰራተኞችን ከመቀነስ በተጨማሪ ምርቱንም ዝቅ ለማድረግ ተገዷል። ከዚህ ቀደም 10 በመቶ ሰራተኞቹን የቀነሰው ቦይንግ እስከ 2023 ባለው ወቅትም ካለበት ቀውስ እንደማይወጣ ግምቱን አስቀምጧል። ገቢውም በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ የተነገረለት ቦይንግ በዘጠኝ ወራትም 30 በመቶ ዝቅ ብሏል። የቦይንግ ፕሬዚዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴብ ካልሁን እንዳሉት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ ኢንዲስትሪው ላይ ጉዳት ማድረሱን ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-54748697
amh
business
በቀጣዩ ስምንት ዓመት ቻይና በምጣኔ ሃብት አሜሪካን ትበልጣለች ተባለ
ቻይና በፈረንጆቹ 2028 በዓለም ትልቁ የምጣኔ ሃብት ባለቤት በመሆን አሜሪካን ልትቀድማት እንደምትችል ተገምቷል። ከዚህ ቀደም ቻይና አሜሪካን በ2033 ነበር ትቀድማታለች ተብሎ የተገመተው። መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የምጣኔ ሃብት እና ቢዝነስ ጥናት ማዕከል ነው ይህን የገመተው። ማዕከሉ እንደሚለው ቻይና ኮቪድ-19ኝን የተቋመመችበት መንገድ ዕድገቷን ሊያፋጥን ይችላል። በተቃራኒው አሜሪካና አውሮፓ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ መደቆሳቸው ጉዳት አለው ተብሏል። በሌላ በኩል ሕንድ በ2030 ከዓለም ሦስተኛዋ ታላቅ ምጣኔ ሃብት ያላት አገር ትሆናለች ተብሎ ተገምቷል። ማዕከሉ በየዓመቱ ታኅሣሥ ወር ላይ የምጣኔ ሃብት ግምትና ትንታኔ ያወጣል። ምንም እንኳ ቻይና በኮቪድ-19 የተመታች የመጀመሪያዋ አገር ብትሆንም በሽታውን በተሳካ ሁኔታ በቁጥጥር ሥር ማዋል ችላለች። ነገር ግን የአውሮፓ አገራት ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ እግድ ጥለዋል። ይህ ደግሞ ምጣኔ ሃብታቸው ላእ ከፍ ያለ ጉዳትን ያስከትላል ይላል ትንታኔው። ቻይና ሌሎች አገራት እንዳጋጠማቸው የምጣኔ ሃብት ድቀት ውስጥ አልገባችም። እንዲያውም ዘንድሮ 2 በመቶ ዕድገት ታመጣለች ተብሎ ይጠበቃል። የዩናይትድ ስቴትስ ምጣኔ ሃብት ደግሞ በተቃራኒው በወረርሽኙ እጅጉን ተመቷል፤ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎችም በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል። አሜሪካ ወረርሽኙ ያመጣባትን ድቀት በገንዘብ ፖሊሲና ለዜጎቿ ድጎማ በማድረግ ብትሸፍነው ብታስብም ለሁለተኛ ጊዜ ሊደረግ በታሰበው ድጎማ ላይ ፖለቲከኞች አለመስማማታቸው ጉዳቱ የከፋ እንዲሆን ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋት አስከትሏል። ይህ ጉዳይ ሊጠናቀቅ ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት 14 ሚሊዮን ሥራ አጥ አሜሪካዊያንን ያለ ድጎማ ሊያስቀራቸው ይችላል። ማዕከሉ ያወጣው ዘገባ እንደሚለው ቻይና እና አሜሪካ ለዓመታት የምጣኔ ሃብት የበላይነቱን ለመቆጣጠር ሲፎካከሩ ከርመዋል። ነገር ግን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የመጡ ለውጦች እንደሚያሳዩት ቻይና የመጪው ጊዜ የዓለማችን ቁንጮ ናት። ዘገባው እንደሚተነብየው ከሆነ ድኅረ-ኮቪድ-19 ባለው ጊዜ ውስጥ የአሜሪካ ምጣኔ ሃብት ከ2022 አስከ 2024 ድረስ ባለው ጊዜ 1.9 በመቶ ያድጋል። ከዚያ በኋላ ደግሞ ወደ 1.6 በመቶ ይወርዳል። በተቃራኒው የቻይና ምጣኔ ሃብት እስከ 2025 ድረስ በ5.7 በመቶ ያድግና ከ2026 ወዲያ ባለው ጊዜ 4.5 በመቶ ያድጋል ይላል። ቻይና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት የምጣኔ ሃብት ድርሻ በፈረንጆቹ 2000 ዓመት ላይ 3.6 ነበር። ዘንድሮ ግን ወደ 17.8 አድጓል። ቻይና በ2023 ከፍተኛ ገቢ ያላት አገር እንደምትሆን ነው የማዕከሉ ምክትል ሊቀመንበር ዳግላስ ማክዊሊያምስ የሚናገሩት። ምንም እንኳ የቻይና ምጣኔ ሃብት ከአሜሪካ ሊበልጥ እንደሚችል ይገመት እንጂ፤ የአንድ ቻይናዊ አማካይ ገቢ ግን ከአንድ አሜሪካዊ ጋር ሲነፃፀር ዕድገት ላያሳይ ይችላል ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55457811
amh
business
ከጂቡቲ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ሲከፈት የባቡር መስመሩ እንደተዘጋ ነው ተባለ
ከቀናት በፊት በተቃዋሚዎች ተዘግቶ የነበረው ከጂቡቲ ወደ መሃል አገር የሚወስደው መንገድ መከፈቱ ተገለጸ። ጂቡቲን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘው የባቡር መስመር ግን አሁንም ዝግ ሆኖ እንደሚገኝ የሶማሌ ክልል ኮምዩኒኬሽን ምክትል ኃላፊ መሐመድ ሮብሌ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ካሳለፍነው እሁድ ጀምሮ መንገዱና የባቡር መስመሩ በሶማሌ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጥቃት በሚቃወሙ የአካባቢው ወጣቶች ተዘግቶ ነበር። መንገዱ ከጂቡቲ ወደብ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ የተለያዩ ሸቀጦች ዋነኛ መተላለፊያ መስመር ነው። ባለፈው ቅዳሜ በአፋር እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ በሆነና የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳበት ቦታ በተፈፀመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአፋር ታጣቂዎች መገደላቸውን የሶማሌ ክልል ኮምዩኒኬሽን ምክትል ኃላፊው ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። በዚህ ጥቃት የተበሳጩ የሶማሌ ክልል ተወላጆች መንገዱን እና የባቡር መስመሩን መዝጋታቸውን ተከትሎ፤ የተዘጉትን የመንገድ እና የባቡር መስመር ለማስከፈት "ከወጣቶቹና ከሕዝቡ ጋር እየተወያየን ነው። መንገዱና የባቡር መስመሩ እንዲከፈት እየሠራን ነው" ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ለሮይተርስ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ምላሽ ሰጥተው ነበር። ትናንት ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡት የክልሉ ኮሚኒኬሽን ምክትል ኃላፊ፤ ከአገር ሽማግሌዎች እና ከወጣቶች ጋር በተደረገው ንግግር መንገዱ ከሐሙስ ጠዋት ጀምሮ የተከፈተ ሲሆን፤ በባቡር መስመሩ ላይ ግን ጉዳት በመድረሱ እስካሁን አገልግሎት አልጀመረም ብለዋል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለቀቁ ፎቶዎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተቃዋሚዎች የባቡር መስመሩን እና ዋና አውራ ጎዳናውን በድንጋይ እና በአፈር ዘግተው አሳይተው ነበር። የባቡር ሃዲዱ ብሎኖችም ተፈተው ታይቷል። መንገዱ እና የባቡሩ መስመሩ ስለመዘጋቱም ይሁን ስለመከፈቱ እስካሁን ድረስ የፌደራሉ መንግሥት ያለው ነገር የለም። ከዚህ ቀደም በሶማሌ እና በአፋር ክልል መካከል የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው ቦታዎች በተደጋጋሚ ግጭቶች መነሳታቸው አይዘነጋም። ቅዳሜ ዕለት ደረሰ ስለተባለው ጥቃት ከአፋር ክልል በኩል መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ ወደተለያዩ የክልሉ ባለሥልጣናት ስልክ በተደጋጋሚ ቢደውልም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-58022659
amh
business
ንግድ፡ በኢትዮጵያ አንድ ግለሰብ ብቻውን ኩባንያ እንዲያቋቁም ተፈቀደ፤ አዲሱ የንግድ ሕግ ምን ይዟል?
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 16/2013 ዓ.ም ላለፉት 62 ዓመታት ሲያገለግል የቆየውን የአገሪቱን የንግድ ሕግ በመሻር በአዲስ እንዲተካ በሙሉ ድመጽ ወስኗል። ይህን አዲሱ የንግድ ሕግ ከዚህ በፊት ከነበረው አንጻር በርካታ ለውጦች የተደረጉበት እንደሆነ ይነገራል። ለማዘጋጀትም ረጅም ጊዜ የወሰደና በርካታ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ነበር። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበራቸውና አዋጁን በማርቀቅ ሂደት የተሳተፉት ከፍተኛ የሕግ አማካሪ ታደሰ ሌንጮ (ዶ/ር) የሕጉ መውጣት የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴን በአወንታዊ መንገድ ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ይናገራሉ። ባለሙያው የሕጉን መውጣት አስፈላጊነት ሲያስረዱ የሚጠቅሱት ላለፉት 62 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው ሕጉ ከወቅታዊው የዓለም ሁኔታ ጋር አለመሄዱን ነው። "የንግድ ሕጉ በወጣበት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የኢንቨስትመንት፣ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ አውድ የ1952ቷ እና የ2013ቷ ኢትዮጵያ በጣም የተለያዩ ናቸው" የሚሉት ታደሰ (ዶ/ር) ይህ መሆኑ ደግሞ ኢትዮጵያ ለንግድ ከሚመቹ አገራት ዝርዝር ውስጥ በዝቅተኛ ደርጃ ላይ እንድትቀመጥ እንድርጓታል ሲሉ ገልጸዋል። የዚህ ውጤት ደግሞ አገሪቱን በተለያየ መልክ ዋጋ አስከፍሏታል። "ኢንቨስተሮች ይሄ አገር እንዴት ቀላል ነው? እንዴት ለንግድ አመቺ ነው? የሚሉትን ነገር ሰለሚያዩ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ኢንቨስመንት ይቀንሳል ማለት ነው። ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ያለውን ካፒታል የመሳብ አቅሟንም በጣም አሳንሶታል" በማለት የሚያስርዱት ባለሙያው፤ ይህም የሥራ ፈጠራንና የውጭ ንግድን እንዲሁም የምጣኔ ሀብት ዕድገቷን የሚገታ ነው ሲሉ አብራርተዋል። በ1952 ዓ.ም የወጣውን ይህን ሕግ ለመቀየር ከ30 ዓመት በፊት ጀምሮ ጥረት ሲደረግ እንደቆየ ተገልጻል። 825 አንቀጾች ያሉት አዲሱ አዋጅ በርካታ ማሻሻያዎችን የያዘ ነው። ከእነዚህ ጥቂቶቹን እንመልከት። አንድ ግለሰብ ለብቻው ኩባንያ መክፈት እንዲችል ተፈቅዷል በቀድሞው የንግድ ሕግ መሠረት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ለማቋቋም ቢያንስ ሁለት ሰዎች ያስፈልጋሉ። "ለምሳሌ የውጭ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ሲያደርጉ አንድ ሌላ ሰው ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። ይህ ብዙ ወጪ ነው የሚያስወጣቸው። ከፍተኛ ጥርጣሬም ይፈጥራል" ይላሉ የሕግ ባለሙያው። ከዚህም በላይ አብሮ ኩባንያውን የመሰረተውን ሰው ባለመስማማት ወይም በሞት ምክንያት ለመቀየር ሲፈለግ ያለውን ሒደት "አበሳ ነው" ሲሉ ከባድነቱን ይገልጹታል። ይህም የኩባንያውን ቀጣይነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባና አላስፈላጊ ለሆኑ ወጪዎች የሚዳርግ ነው ሲሉም አክለዋል። እንደ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጻ፣ በአገር ውስጥ ያሉ በርካታ ኃላፊነታቸው የተወሰኑ የግል ኩባንያዎች በተግባር የአንድ ሰው ሆነው ሳለ፤ ለሕጉ ሲባል ግን ተጨማሪ ሰው በባለቤትነት ይመዘግባሉ። አዲሱ የንግድ ሕግ ይህን ግዴታ አንስቶ አንድ ግለሰብ ብቻውን ኩባንያን እንዲከፍት ፈቅዷል። ይህም ሰዎች በቀላሉ ወደ ሥራ እንዲገቡና ባለቤትነትን በተመለከተ ስጋት እንዳይኖራቸው ያግዛቸዋል ብለዋል። የንግድ ትርጓሜን መቀየር በተሻረው ሕግ የተዘረዘሩት የንግድ አይነቶች 21 ብቻ ናቸው። ከነዚህ ውጪ ያሉት ንግድ አይደሉም ተብለው እንደሚገመቱ ባለሙያው ያስረዳሉ። አሁን ግን ሕጉ የንግድ አይነቶችን ወደ 38 አሳደጓቸዋል። "ያም ብቻ ሳይሆን በአዲሱ ሕግ የንግድ ትርጉም ክፍት ነው። በግልፅ ካልተከለከለ በስተቀር ማንኛውም ሰው ከፀሐይ በታች ባለን ሥራ ንግድ ነው፤ ያተርፋል ብሎ እንደሙያ የያዘውን ሥራ አስመዝገቦ መቀጠል ይችላል" ሲሉ አስረድተዋል። ይህ መሆኑ ደግሞ አዳዲስ የንግድ አይነቶችንና የፈጠራ ሐሳቦችን እንደሚያበርታታ አክለዋል። ኃላፊነታቸው የተወሰኑ የሙያ ሽርክና ማኅበራት መፈቀድ ከቀደመው ሕግ በተቃራኒው አዲስ የጸደቀው አዋጅ ግለሰቦች በሙያቸው ተደራጅተው እንዲሠሩ በግልጽ ድንጋጌ አስቀምጧል። አዋጁን በማርቀቅ ሒደት የተሳተፉት ከፍተኛ የሕግ አማካሪው፤ እያንዳንዱ ሙያ የሚጠይቀውን ሥነ ምግባር ይዘው ደንበኞቻቸውን የሚያስተናግዱ የሽርክና የሙያ ማኅበራት እንዲስፋፉ ያስችላል ብለዋል። በሌላው ዓለም በስፋት የሚሠራበት ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ሕግ በግልጽ ባለመፍቀዱ ዘርፉን አዳክሞታል። በሌላ በኩል የቀድሞው ሕግ የአክስዮን ማኅበራት የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ሁሉም የአክሲዮን ባለድርሻ እንዲሆኑ ግዴታ የጣለ ነበር። ነገር ግን በአዲሱ ሕግ ባለድርሻ መሆን ሳይጠበቅባቸው፤ ባለ ድርሻ ያልሆኑ ሰዎች በሙያቸው እስከ አንድ ሦስተኛ ድረስ የሚሆነውን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ቦታን እንዲይዙ ይፈቃዳል። በተጨማሪም ከተሻረው ሕግ በተቃራኒ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የሚከስሩ የንግድ ሰዎች ነጻ የሚሆኑበትን መንገድ እንዳመቻቸም ገልጸዋል። የሕግ ባለሙያው ታደሰ (ዶ/ር) እነዚህን ጨምሮ ለንግድ እንቅስቃሴው የማይመቹ ሕጎችን ያሻሻለው የአዲሱ አዋጅ መውጣት "በአገር ውስጥ ያለውን እንቅሰቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል" ብለዋል። በአዲሱ አዋጅ ያልተካተቱት የባንክ፣ የኢንሹራንስና፣ የማጓጓዣ ዘርፎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በቀድሞው አሠራር መሠረት የሚቀጥሉ ሲሆን፤ በቀጣይ ራሳቸውን ችለው እንዲወጡ እየተሠራ መሆኑ ተጠቁሟል። አዲሱ የንግድ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ ወጥቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ገብቶ የቀድሞውን ሕግ ይተካል ተብሎ ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/56547521
amh
business
በኢትዮጵያ ይጀመራል የተባለው ክሬዲት ካርድ ምንድነው? አገልግሎቱን ለማግኘት ከእርስዎ ምን ይጠበቃል?
አዋሽ ባንክ በኢትዮጵያ የክሬዲት ካርድ አገልግሎት በመስጠት የመጀመሪያው ባንክ ለመሆን መቃረቡን አሳውቋል። ባንኩ በቅርቡ ይፋ እንዳደረገው ‘ዴቢት ካርድ’ ከተሰኘው አገልግሎት በተጨማሪ፣ የክሬዲት ካርድ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። በዚህም ሁለት ዓይነት የክሬዲት ካርድ አገልግሎት እንደሚጀምር በገለጸበት ወቅት አንደኛው ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ የሚመለስ፣ ሌላኛው ደግሞ ተከፋፍሎ የሚመለስ ነው ብሏል። የኢትዮጵያ ባንኮች ከዴቢት ካርድ አገልግሎት በቀር ሌሎች የካርድ አገልግሎቶች ለደንበኞቻቸው አይሰጡም። ከዚህ ቀደም ዳሸን ባንክ ኢንተርናሽናል ዴቢት ካርድ የተሰኘ የውጭ ምንዛሪ ለሚጠቀሙ ደንበኞች የሚሆን ካርድ ይፋ አድርጎ ነበር። ይህ የተለያየ ዓይነት የገንዘብ ዝውውር የካርድ አገልግሎት በዓለም ዙሪያ ያሉ ታላላቅ ባንኮች ለደንበኞቻቸው የሚሰጡት አገልግሎት ነው። በርካታ አገር በቀል ባንኮች ያሏት ኢትዮጵያ በቅርቡ የውጭ አገር ባንኮች ወደ ገበያው እንዲገቡ እንደሚፈቅድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሳወቁ ይታወሳል። አብዛኞቹ ዓለም አቀፍ ባንኮች የዴቢት ካርድን ጨምሮ የክሬዲት ካርድ እንዲሁም ሌሎች የካርድ አገልግሎቶች ለደንበኞቻቸው ይሰጣሉ። ለመሆኑ ክሬዲት ካርድ ምንድነው? እርስዎስ የክሬዲት ካርድ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ? ጥቅም እና ጉዳቱስ? የዩናይትድ ኪንግደም የተመሰከረላቸው የሒሳብ አዋቂዎች ማኅበር አባል ጥላሁን ግርማ ባንኮች በተለምዶ ሁለት ዓይነት የካርድ አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ያስረዳሉ። የማማከር እና ኦዲቲንግ ባለሙያው እንደሚሉት ዴቢት፤ ደንበኛው ባለው ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከኤቲኤም ወጪ ማድረግ የሚያስችለው፤ እንዲሁም በክፍያ ማሽን መጠቀም የሚያችለው ካርድ ነው። “ነገር ግን ክሬዲት ካርድ ማለት ባንኩ ‘ካለህ ተቀማጭ ገንዘብ በላይ ይህን መጠቀም ትችላለህ’ ብሎ የሚፈቅድልህ ጊዜያዊ ብድር ነው።” ባንኮች ለደንበኞቻቸው ይህን የካርድ አገልግሎት የሚፈቅዱት የቀደመ የሒሳብ አጠቃቀም እንዲሁም የገቢ ምንጭ እና መጠናቸውን ከግምት አስገብተው ነው። አቅም ላላቸው ደንበኞች ካላቸው ተቀማጭ ገንዘብ በላይ ወጪ ማድረግ እንዲችሉ ሊፈቀድላቸው እንደሚችልም ያስረዳሉ። ባለሙያው የክሬዲትና ዴቢት ካርድ ልዩነት ሰርፆ እንዲገባን በምሳሌ ያስረዱናል። ለምሳሌ ይላሉ. . . “ለምሳሌ 20 ሺህ ብር ካለህ፤ ከኤቲኤምም አውጣ፣ ግብይትም ፈጽመበት፣ ካለህ በላይ ማውጣት አትችልም።” ክሬዲት ካርድ ግን ባንኮች የደንበኛው መልሶ የመክፈል አቅም ከግምት በማስገባት ለአጭር ጊዜ የሚሰጥ ብድር ዓይነት ነው። በበርካታ የዓለም አገራት የክሬዲት ካርድ ብድር ወለድ የሚከፈልበት ነው። ነገር ግን በአንዳንድ አገራት ደንበኞች በተሰጣቸው ቀነ ገደብ ካልከፈሉ ነው ወለድ የሚጣልባቸው። “ለምሳሌ በ15 ቀናት ውስጥ እከፈላለሁ ብለህ ሳትከፍል ቀኑ ካለፈብህ ወለድ ይኖረዋል። የአዋሽ ባንክ ፖሊሲ ምን ሊሆን እንደሚችል የምናየው ነው የሚሆነው።” ደንበኞች የክሬዲት ካርድ አገልግሎት ለማግኘት ለባንኩ ይህን ያህል ብድር ይፈቀድልኝ ብለው ማመልከቻ ማስገባት አለባቸው። ባንኩ ባስቀመጠው መሥፈርት መሠረት የደንበኞችን አቅም እንዲሁም ከባንኩ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ተመልክቶ ፈቃድ ይሰጣል። “የደመወዝ መጠንህ ሊሆን ይችላል፤ ከባንኩ ጋር ያለህ ግንኙነት ሊሆን ይችላል፤ ነጋዴ ከሆንክ የንግድ ሁኔታህ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ባንኩ ኪሳራውን እያወቀ ሊፍቀድ ይችላል።” ባለሙያው ደጋግመው የባንክ ተጠቃሚዎች የክሬዲት ካርድን ዓላማ በግልፅ ማወቅ እንዳለባቸው ይመክራሉ። “ክሬዲት ካርድ የሚሰጥህ ለአጭር ጊዜ የብድር ፍላጎትህ ነው። እንጂ ቋሚ ንብረት [መኪና፣ ቤት] እንድትገዛበት አይደለም።” የክሬዲት ካርድ ዋነኛው ዓላማው ድንገተኛ ለሆነ የገንዘብ ችግር መውጫ ነው። ለዚህ ነው የሚመለስበት የጊዜ ገደብ የተቀመጠለት ይላሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው። “አዋሽ ባንክም የተጠቀምከውን ገንዘብ የምትመልሰው በምን ያህል ጊዜ ነው የሚለውን በተመለከተ የራሱን ፖሊሲ ያወጣል ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ይህ የሚወሰነው በደንበኛው የገቢ ምንጭ ነው።” ለምሳሌ እርስዎ ተቀጣሪ ከሆኑ በወሩ መጨረሻ ደመወዝ ሲቀበሉ ለመክፈል ሊስማሙ ይችሉ ይሆናል፤ በንግድ ከተሠማሩ ደግሞ ምናልባት በወር ሁለት ጊዜ ለመክፈል ይፈርማሉ። አዋሽ ባንክ ይህንን አገልግሎት ለባንኩ ተጠቃሚዎች በሙሉ ለመስጠት ቃል ገብቷል። የ44 ዓመቱ እንግሊዛዊ ዳረን የ32 ሺህ ዩሮ ዕዳ ውስጥ ከገባ በኋላ የሚያደርገው ጠፍቶት ነበር። ዳረን ከባንክ የወሰደውን ክሬዲት ካርድ እየመዠረጠ ለሚያስፈልገው ጉዳይ ጥቅም ላይ ቢያውለውም ዕዳውን በጊዜ መክፈል የሚያስችል አቅም አልነበረውም። “እንኳን ልቀንስ ይቀርና በዕዳ ላይ ዕዳ ስጨምር ነው የከረምኩት። ከወር ወር ሲያድግ፤ ከዓመት ዓመት እዳዬ ሲያሻቅብ ነው የከረመው። በጣም ጭንቀት ውስጥ ነበርኩ።” ምንም እንኳ ዳረን አሁን ዕዳውን ከፍሎ ቢገላገልም በርካታ እንግሊዛዊያን አሁንም የክሬዲት ካርድ ዕዳ ውስጥ ናቸው። ጥላሁን እንደሚሉት ክሬዲት ካርድ በአግባቡ ጥቅም ላይ ካልዋለ ተጠቃሚውንና ባንኮች ለኪሳራ ሊዳርግ ይችላል። ለዚህ ነው የክሬዲት ካርድ ዋነኛ ዓላማው መሆን ያለበት አንድን ችግር ወዲያው ለመፍታት መሆን አለበት የሚሉት። “ለምሳሌ ቤተሰብ ቢታመምብህ አሊያም በሚቀጥለው ወር ዕቁብ የሚወጣልህ ቢሆንና አሁን አንድ ዕቃ መግዛት ብትፈልግ ክሬዲት ካርድ መጠቀም ትችላለህ።” ባለሙያው ክሬዲት ካርድ ማለት “ልክ እንደ ቴሌ ብር ነው” ይላሉ። “ቴሌ ገንዘብ ሳይኖርህ ሲቀር የብድር አገልግሎት ይሰጥሃል። በሚቀጥለው ስትሞላ ከሒሳብህ ላይ ይወስዳል።” በውጭው ዓለም ‘ክሬዲት ስኮር’ የሚባል ሐሳብ አለ። የክሬዲት ስኮር ማለት አንድ ሰው ብድር ወስዶ የመመለስ ታሪኩ እንዴት ያለ ነው የሚለውን የሚያሳይ ነው። ብድር ወስደው በጊዜ የሚመልሱ ሰዎች መልካም ‘ክሬዲት ስኮር’ ያላቸው ተብለው ይጠራሉ። የክሬዲት ታሪካቸው ጥሩ የሆኑ ሰዎች በባንኮች ዘንድ ይከበራሉ፤ የሚፈልጉት ጉዳዩ በቶሎ ይሳልጥላቸዋል። በአብዛኛዎቹ አገራት የክሬዲት ካርድ ወለድ፣ የባንኮች ለደንበኞቻቸው ከሚሰጧቸው ሌሎች ካርዶች ወለድ ከፍ ያለ ነው። “ብድር ስለሆነ ወልድ አለው። አደጋ ስላለው ነው ወለዱ ከፍ የሚለው። ንብረት አስይዞ የሚወስድ ሰው እና ንብረት ሳያስዝ ብድር የወሰደ ሰው እኩል ስላልሆነ የወለድ መጠኑን ከፍ በማድረግ ነው ስጋቱን የሚያጣጡት።” ዴቢት ካርድ ሲጠቀሙ ቀረጥ የሚጥል የግል ማሽን [ኤቲኤም፣ የግብይት ማሽን] ካልሆነ በቀር ተጨማሪ ክፍያ አይከፍሉም። አልፎም ለተጠቀሙበት ክፍያ ካለው ቀድሞ ያሳወቆታል። ወደ ክዴዲት ካርድ ስንመጣ ግን ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ሲያወጡ ክፍያ ይከፍላሉ። አንዳንድ ጊዜ ካርዱን የሰጠዎት ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል። በበይነ መረብ ዕቃና አገልግሎት የሚሸጡ ድርጅቶች ከዴቢት ካርድ ይልቅ ክሬዲት ካርድ ይመርጣሉ። ለዚህ ምክንያቱ ክሬዲት ካርድ ሲሆን ገንዘቡን ከባንክ ቀጥታ ማግኘት ስለሚችሉ ነው። ባለሙያዎች ክሬዲት ካርድ ተጠቅሞ ከኤቲኤም ገንዘብ ማውጣትን አይመክሩም። ከዚያ ይልቅ በሚገበያዩበት ወቅት ክሬዲት ካርድዎን ይጠቀሙ ይላሉ። ቪዛ፣ ማስተርካርድ፣ አሜሪካን ኤክስፕረስ እና ዲስከቨር የክሬዲት ካርድ ኔትዎርኮች ናቸው። ባንኮች እኒህን ኔትዎርኮች ተጠቅመው ነው ለደንበኞቻቸው ክሬዲት ካርድ የሚያውጁት። አብዛኞቹ ዓለም አቀፍ ባንኮች የክሬዲት ካርድ ለሚጠቀሙ ደንኞቻቸው ማበረታቻ ሽልማት ይሰጣሉ። ለምሳሌ የአውሮፕላን ቲኬት ለመቁረጥ፣ ለሆቴል ክፍያ፣ ለበይነ-መረብ ግብይት ክሬዲት ካርድ ከሚጠቀሙ ደንበኞቻቸው ማበረታቻ ይሰጣሉ። ማበረታቻው በአየር መንገድ ማይል፣ በተጨማሪ የሆቴል ክፍያ እንዲሁም በስጦታ ካርድ መልክ ሊሰጥ ይችላል። ባንኮች ለደንበኞቻቸው በየወሩ ‘ስቴትመንት’ [የባንክ ሒሳብ መረጃ] ይልካሉ። ይህ ስቴትመንት ደንኞች ክሬዲት ካርዳቸውን ተጠቅመው ምን ያህል ክፍያ እንደፈፀሙ፣ የወለድ መጠኑን እና ተጨማሪ ክፍያውን የሚያካትት ነው። አክሎም፤ ክሬዲት ካርዳቸው ውስጥ ምን ያህል ገንዘብ እንደቀረ፤ መልሰው ሊከፍሉ የሚገባቸው ዝቅተኛ መጠን ስንት እንደሆነ እና እንዴት መክፈል እንደሚችሉ ይካተትበታል። የሒሳብ አዋቂው ጥላሁን ከአዋሽ ባንክ እርምጃ በኋላ “ሌሎች ባንኮች ተኝጠው አያድሩም” ይላሉ። “ይህ አገልግኮት እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሳይጀመር መቆየቱ በጣም የሚገርም ነው። ሌሎችም ባንኮች ለመጀመር ዝግጅት ላይ ናቸው አሊያም ከአዋሽ ባንክ በኋላ መጀመራቸው አይቀርም።”
https://www.bbc.com/amharic/articles/c9805q1yq39o
amh
business
ኮቪድ-19፡ ቤት የመቀመጥ ገደብ ጉግልን ትርፋማ አድርጓል ተባለ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የተጣለው ቤት ውስጥ የመቀመጥ ገደብ ለጉግል ትርፋማነት አስተዋጽኦ አድርጓል ተባለ። የጉግል ባለቤት ድርጅት የሆነው አልፋቤት ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ 17 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም የ162 በመቶ ጭማሪ መሆኑ ተገልጿል። ለትርፋማነቱም ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ እንቅስቃሴያቸው ሲገደብ የጉግልን አገልግሎቶች መጠቀማቸው በምክንያትነት ተቀምጧል። ያለፉት ሦስት ወራትም በድርጅቱ ታሪክ ከፍተኛ ትርፍ የተመዘገበበት ነው ተብሏል። ጉግል ይህን የትርፍ መጨመር "ደንበኞቼ ኢንተርኔት በመጠቀም የሚያከናውኗቸው ተግባራቶች መጨመር ያመጣው ነው" ሲል ገልጾታል። "ባለፈው ዓመት ሰዎች የጉግል መፈለጊያን ተጠቅመው ራሳቸውን ከመረጃ ላለማራቅ፣ ለመዝናናት እና ከሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማስቀጠል ሲጠቀሙት ቆይተዋል" ሲሉ የአልፋቤት እና ጉግል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሱንዳር ፒቻዪ ገልጸዋል። የዘርፉ ተንታኞችም የተዘጉ ኢኮኖሚዎች ሲከፈቱ እና የኢንተርኔት ላይ ማስታወቂያዎችም እየተበራከቱ ሲሄዱ ጉግል ከፍተኛ ትርፍ መሰብሰቡን ይቀጥላል ብለዋል። ጉግል ባለፈው ሦስት ወራት በአጠቃላይ ከመፈለጊያ ንግዱ [Search business] የሰበሰበውን ገቢ በ30 በመቶ በመጨመር ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል። ዩትዩብ ደግሞ በስድስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ የ49 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በሃርግሬቭስ ላንሱንግ የፍትሐዊነት ተንታኝ የሆኑት ሶፊ ሉንድ-ያትስ በበኩላቸው አልፋቤት "ጉግል በወረርሽኙ ሳቢያ በተገኘው ገቢ ልክ በክሬም ላይ እደተወረወረች ትልቅ ድመት ሆኗል" ሲሉ ትርፉን ገልጸውታል። የቴክኖሎጂ ግዙፉ ኩባንያ ጉግል፤ ባልተለመደ መልኩ የማስታወቂያ ንግድ ድርጅት ወደመሆን ማዘንበሉንም ተንታኙ ተናግረዋል። "የኮሮናቫይረስ ሲከሰት በተለይም የኢንተርኔት ላይ ግብይት በመጧጧፉ ምክንያት የአልፋቤት የንግድ ተቋማት ለእነዚህ ሸቀጦች ማስታወቂያ ማስነገራቸው ገቢያቸው እንዲተኮስ ምክንያት ሆኗል" ሲሉም ለከፍተኛ ትርፍ ያበቃውን ምክንያት አስረድተዋል። ይሁን እንጂ ጉግል ከተለያዩ ተቆጣጣሪ ተቋማት በተለይም ፍትሐዊ የንግድ ውድድርን እና የግል ምስጢር መጠበቅን በተመለከተ እያጋጠመው ያሉት ጥያቄዎች ዋና ተግዳሮቶቹ ሆነው ቀጥለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56884833
amh
business
"የዓለም አስር ባለ ጸጎች ሀብት ቢደመር ለሁላችንም ክትባት ይገዛል"
ኦክስፋም ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ በወረርሽኙ ወቅት ሀብታቸው የናረ አስር ወንዶች ሀብት ንብረት ሲደመር 540 በሊዮን ዶላር ይጠጋል። ይህ ሀብት የዓለም ሕዝቦችን ከድህነት የሚያወጣ እንዲሁም ለሁሉም ሰው ክትበት መግዛት የሚያስችል እንደሆነ የተራድኦ ድርጅቱ ኦክስፋም ጠቁሟል። በዓለም ላይ ያሉ ቢሊየነሮች ጠቅላላ ሀብት፤ የጂ-20 አገራት ወረርሽኙ ካሳደረው ጫና ለመላቀቅ ከሚያወጡት ወጪ እኩል መሆኑ በኦክፋም ሪፖርት ተመልክቷል። ኦክስፋም ይህንን ሪፖርት ተመርኩዞ መንግሥታት ባለ ጸጎች ላይ ከፍተኛ ግብር እንዲጥሉ ያሳስባል። 'ኢንኢኳሊቲ ቫይረስ' የተሰኘው ሪፖርት የወጣው መንግሥታት ለዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት ጉባኤ በተሰበሰቡበት ወቅት ነው። መንግሥታት ለምጣኔ ሀብታቸው ያደረጉት ድጋፍ የአክስዮን ገበያ እንዲያንሰራራና የቢልየነሮች ገቢ እንዲጨምር አድርጓል። የእነዚህ ግለሰቦች ሀብት ሲጨምር የአገራት ጠቅላላ ምጣኔ ሀብት ግን አሽቆልቁሏል። ከሚያዝያ 2020 እስከ ጥቅምት 2020 የመላው ዓለም የቢልየነሮች ሀብት በ3.9 ትሪሊዮን ጨምሯል። የጂ-20 አገራት ወረርሽኙን ለመከላከል ያወጡት ወጪ ሲደመርም ከባለ ጸጎቹ ሀብት ጋር እኩል ነው። በወረርሽኙ ወቅት ሀብታቸው ከናረ መካከል የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ፣ የተስላ መስራች ኤለን መስክ እና የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ ይገኙበታል። ጄፍ ቤዞስ ካለው ሀብት ለእያንዳንዱ 876,000 የአማዞን ተቀጣሪ 105,000 ዶላር ጉርሻ ቢሰጥ እንኳን ከወረርሽኙ በፊት የነበረው ሀብቱ እንደማይቀንስ ሪፖርቱ ያሳያል። በተቃራኒው በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ወረርሽኙ ከሳደረባቸው ተጽዕኖ ለማገገም አስርት ዓመታት ያስፈልጋቸዋል። በወረርሽኙ ሳቢያ ተጨማሪ 500 ሚሊዮን ሰዎች ወደ ድህንት አረንቋ እንደገቡ ኦክስፋም ገልጿል። የኦክስፋም እንግሊዝ ዋና ኃላፊ ዳኒ ስሪስካንዳርጃህ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ "ሀብታሞች ላይ ግብር በመጣል፣ ለእያንዳንዱ ዜጋ መሠረታዊ የገቢ መነሻ በማበጀትና በሌሎችም መንገዶች ፍትሐዊ ክፍፍልን ማረጋገጥ አለብን።" በወረርሽኙ ወቅት አንዳንድ ሀብታም ሰዎች የገንዘብ ድጎማ እየሰጡ ነው። የጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤት መከንዚ ስኮት ያደረገችው የአራት ቢሊዮን ዶላር ድጎማ ይጠቀሳል።ጄ ፍ ቤዞስ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ ጋር የሚደረገውን ትግል ለመደገፍ 125 ሚሊዮን ዶላር ሰጥቷል። የትዊተር አጋር መስራች ጃክ ዶርሲ ከሀብቱ አንድ ቢሊዮን ዶላር ወረርሽኙን ለመከላከል እንዲውል ሰጥቷል። ቢል ጌትስ እና ባለቤታቸው መሊንዳ ለክትባት ምርትና ግዢ 305 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/55798217
amh
business
በከተማ ግብርና የተለወጡት የአዲስ አበባ ዙሪያ አርሶ አደሮች
በከተሞች ውስጥና በዙሪያቸው የሚኖሩ አርሶ አደሮች የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ለነዋሪዎች ያቀርባሉ። ይም በተወሰነ ደረጃ የከተማ ነዋሪዎችን ፍላጎት ሲያሟላ ለእነሱም የገቢ ምንጭ ይሆናል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cp639zpjxrgo
amh
business
የምንፈልገውን ሥራ እና እድገት ለማግኘት ራሳችንን እንዴት እንግለጽ?
ስለራስ መናገር ምቾት አይሰጥም፤ አይደለም ለአለቃ ለወዳጅ እንኳ ቢሆን 'ምን ጉራህን ትቸረችራለህ' ሊያስብል ያስችላል። የሰው ጀማ ተሰብስቦ ስለራስ 'ጥሩንባ መንፋት' የተለመደ አይደለም፤ ይህ ግን የኢትዮጵያውያን ችግር ብቻ ሳይሆን ፈረንጆቹም እዚህ ላይ ትንሽ ቆንጠጥ ያደርጋቸዋል። ስለራሳቸው ለመናገር ጀምረው ድምጻቸው የሰለለባቸው፣ እጃቸውን ያላባቸው፣ አፋቸውን የፈቱበት ቋንቋ የጠፋቸውን የየመሥሪያ ቤቱ ደጃፍ ይቁጠራቸው። ለስቴፋኒ ስዎርድ ዊሊያምስ ግን "ይህ ክህሎት ሁለቴ ማሰብ የማያስፈልገው ሁሉም ሊኖረን የሚገባ ነው" ትላለች። ስቴፋኒ ራስን በብቃት መግለጽ መቻል ላይ በበርካቶች የተነበበ መጽሐፍ አዘጋጅታለች። በሠሯቸው ሥራዎች፣ ባገኟቸው ውጤቶች መኩራራት፣ ደረትን መንፋት ልክ እንደ በጎ ምግባር ሊቆጠር ይገባል ስትል ታስረዳለች። ነውር አለመሆኑንም አጽንኦት ሰጥታ ነው የምትናገረው። በዚህ ፉክክር በበዛበት ዓለም ያለዎትን ክህሎት ማጉላት በሥራ ቦታ ለውጤትዎ ላቅ ያለ ድርሻ ይኖረዋል። በሥራዎ እድገት ለማግኘት፣ አዲስ ሥራ ለመቀየር፣ በአለቃዎ ዕይታ ውስጥ ለመግባት እና የድርጅትዎን የእድገት መሰላል በቀላሉ ለመውጣት ስለራስዎ ያለመሸማቀቅ መናገር ያስፈልግዎታል፤ ይጠበቅብዎታልም። ለአንድ ሥራ በርካቶች የማመልከቻ ዶሴ ተሸክመው በየቀጣሪዎች ደጅ በሚንከራተቱበት በዚህ ወቅት፣ ሁሉም ዲግሪ እና ማስተርስ ኖሮት ያለችው ጥቂት እድገት ላይ ዓይኑን ጥሎ በሚጠብቅበት የሥራ ቦታ "ራስን መሸጥ" ተገቢ ክህሎት ሆኖ ይገኛል። ይህ ደግሞ ዓይን አፋር ለሆኑ እና ራሳቸውን መግለጽ ለሚቸገሩ ሴቶች አስፈላጊ ክህሎት ነው። የራሳቸውን ሥራ ከቤታቸው ሆነው ለሚሰሩ፣ በኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የገበያ ዕድሎችን ሳስተው፣ ከብዙኃኑ ጋር ተቀላቅሎ ለመወዳደር ፈተና በሆነበት በዚህ ወቅት ያለው አማራጭ ስለራስ ስኬት፣ ስለ አገልግሎትዎ እና ስለ ክህሎትዎ ደረትን ነፍቶ ማስረዳት መቻል ነው። "የራሳችንን እሴቶች ለማሳየት ጊዜ የማንወስድ ከሆነ፤ እንደ ተፈላጊ የመቆጠር ዕድላችን ላይ በር እንዘጋለን" ስትል ስዎርድ ዊሊያምስ ታስረዳለች። "ስለ ራሳችን የምንታወቅበትን ነጥቦች ይፋ በማድረግ፣ ማንንነታችንን በማሳየት ታሪካችንን ራሳችን መንገር ያስፈልገናል" ባይ ናት። ስለ እኛ ሌሎች እንዲመሰክሩልን መጠበቅ የዋህነት ነው ስትልም ታክላለች። ራስን ማስተዋወቅ በቀላል ብያኔ ሥራዎና ስኬትዎ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ ማድረግ ማለት ነው። ስለዚህ ስለራስዎ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ የሚያስቀምጡት መግለጫ፣ ወይንም በኢሜል መልዕክት ላይ የሚያስገቡት ማብራሪያ ካልሆነ ደግሞ ከአለቃዎ ወይንም ከቁልፍ ሰዎች ጋር በሚኖርዎት ውይይት ወቅት የሚያነሷቸው ነጥቦች ራስዎን በሰዎች ፊት ሞገስ በማሰጠት ረገድ ትልቅ ሚና አላቸው። በተሰማሩበት መስክ ለማደግ እንዲሁም ማንነትዎን እና ብቃትዎን [ብራንድ] በሚገባ ለማስተዋወቅ ጠቃሚ ነው። በተሰማራበት መስክ እስከ መሰላሉ የላይኛው ጫፍ ለመውጣት የሚፈልግ ሰው ደግሞ ይህንን ቢያደርግ መንገዱን የውሃ ያደርገዋል። ይህ ዓለም የወንዶች ነው በሥራው ዓለም የተደረጉ ጥናቶች እንደሚመሰክሩት ከሆነ ስለራስ በመናገር ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ይደፍራሉ። እኤአ በ2019 መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ አንድ አካዳሚ፣ ይፋ ባደረገው ጥናት ራስን በመግለጽ ረገድ "ትልቅ የሥርዓተ ጾታ ክፍተት ይታያል።" ተመራማሪዎቹ ለጥናቱ ተሳታፊዎች የሒሳብ እና የሳይንስ ፈተና እንዲወስዱ፣ ከዚያም ብቃታቸውን ራሳቸው እንዲመዝኑ አድርገዋል። የጥናቱ ተሳታፊዎች ለራሳቸው የሰጡት ውጤት ለአለቆቻቸው ማንን ለመቅጠር እና ምን ያህል መክፈል እንደሚገባቸው መወሰን እንዲችሉ እንዲያውቁት እንደሚደረግ ተነግሯቸዋል። ምንም እንኳ በጥናቱ ወንዶቹም ሴቶቹም እኩል ውጤት ያመጡ ቢሆንም፣ ወንዶች ግን ለራሳቸው በአማካኝ 61 ከመቶ ሲሰጡ ሴቶች ግን 46 ከመቶ ሰጥተዋል። ሴቶች ስለምን ከወንዶች የበለጠ ድሃ ሆኑ (Why Women Are Poorer Than Men) የሚል መጽሐፍ ደራሲዋ አናቤላ ዊሊያምስ "ሌሎች በርካታ ጥናቶች እንዳሳዩት ከሆነ ወንዶች ስለስኬታቸው ሲጠየቁ 'እራሳቸውን በመሸጥ' ላይ የተዋጣላቸው ናቸው። በተቃራኒው ሴቶች ደግሞ ችሎታቸውን እና ውጤታቸውን ዝቅ አድርገው ሲያቀርቡ ተስተውሏል" ትላለች። ሴቶች ከልጅነታቸው ጀምሮ ራሳቸውን ከፍ ከፍ ሲያደርጉ እየተገሰፁ ነው የሚያድጉት። ራሷን ከፍ ከፍ ለምታደርግ ሴትም የሚሰጡ የተለያዩ ቅጽል ስሞች መኖራቸውን ትገልጻለች። "ነገር ግን ተመሳሳይ ባህሪ የሚያሳይ ወንድ በራስ የመተማመን ብቃት እና የአመራር ችሎታ እንዳለው ይቆጠርለታል" ስትል ታብራራለች። ስዎርድ ዊሊያምስ በበኩሏ በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ እና አርዓያ የሚሆኑ ሴቶች ስለራሳቸው መናገር እና ስኬታቸውን ማንቆለጳጰስ ተገቢ መሆኑን ሲናገሩ አይደመጡም ትላለች። በውጤቱም ሴቶች ለአንድ የሥራ እድል ከወንዱ የበለጠ እንዲታገሉ ያደርጋቸዋል። በእርግጥ አንዳንድ ወንዶች አይናፋር፣ ሴቶች ደግሞ በተፈጥሯቸው ራሳቸውን መግለጽ እና ሰለ ሥራቸው በድፍረት ለመናገር ችግር ላይኖርባቸው ይችላል። በቅርቡ በተደረገ ጥናትም ወጣት ሴቶች በእድሜ ከገፉ ሴቶች ይልቅ ስለራሳቸው ደፈር ብለው መናገር እንደሚችሉ ይፋ አድርጓል። ስለራስ በድፍረት እና በልበ ሙሉነት መናገር ቦታ ካልተመረጠለት ባዶ ጩኸት እና ቀረርቶ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ። ቀጣሪን እና አለቃን ከመማረክ ይልቅ ሊያበሳጭ የሚችልባቸውም ዕድሎች አሉ። በዚህ ወቅትም ስለራስ በልበ ሙሉነት ለመናገር ግቡን መምታት አቅቶት ሲከሽፍ ይስተዋላል። ስለራስዎ በልበ ሙሉነት ለመናገር ምን ያድርጉ? ስለራስ በልበ ሙሉነት መናገር ግን እንዲሁ የሚገኝ ስጦታ አይደለም፤ ልምምድ ይጠይቃል። በተለይ በቢሮዎ ውስጥ፣ በወንበርዎ ላይ በወረቀት ክምር መካከል አልያም ከኮምፒውተር ጀርባ ተቀምጠው የዕለት ሥራዎትን ብቻ የሚከውኑ ከሆነ ከዕይታም ከአእምሮም ውጪ የመሆን ዕድልዎ የሰፋ ነው። እርስዎ ልምዱና ችሎታው እያለዎት ሌሎች አልፈዎት ይሾማሉ፤ ይሸለማሉ። እርስዎ በነበሩበት የደሞዝ እርከን ላይ ተቀምጠው ሲያለቃቅሱ ሌሎች የጥቅማ ጥቅም እና ደረጃ እድገት በረከት ተቋዳሽ ይሆናሉ። ስለዚህ ስለራስዎ በሚገባ መግለጽ፣ ስኬቶችዎን በደማቅ ቀለም በአለቃ አእምሮ ውስጥ ለመጻፍ እንዲችሉ ያለማመንታት ልምምድ ያድርጉ። አለቆች የሰሯቸውን ሥራዎች የሚያስታውሳቸው፣ ስኬቶችዎን እና አስተዋጽኦዎን የሚነግራቸው ይፈልጋሉ። በተቋሙ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ተቀጥረው ቢሰሩ እንኳ ስለራስዎ እስካልተናገሩ ድረስ የመረሳት ዕድልዎ ሰፊ ነው። ስለዚህ ልክ እንደ አዲስ ክህሎት ራስን በልበ ሙሉነት መግለጽንም ሊማሩት እና ሊለማመዱት የሚገባ ክህሎት ነው። "የረዥም ጊዜ የሥራ ላይ ህልምዎን እና ፍላጎትዎን ለአለቃዎ ይንገሩ" የምትለው ሃሪት ሚንተር ነች። ሃሪት ሚንተር በዚህ ዘርፍ ጥሩ የተነበበ መጽሐፍ ደራሲ ስትሆን "አሁን ጊዜው አይደልም አትበሉ። ከዚያ ይልቅ ለኩባንያው ያመጧቸውን ዕሴቶች በመመልከት በዚያ መሰረት ጥያቄያችሁን ሰንዝሩ" ስትል ትመክራለች። ሚለር ስለስኬትዎ ለሥራ አጋርዎ እና አለቃዎ ለማሳወቅ ኢሜል አንዱ መንገድ ነው ትላለች። በዚህ ኢሜል ውስጥ ማካተት የሚፈልጓቸውን መረጃዎች ማካተትዎን፣ በሚገባ መግለጽዎን እና ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ የመላክ ልምድዎን ያዳብሩ፤ አንዴ መላክ ከጀመሩ በቀጣዮቹ ሳምንታት እየቀለለዎ ይመጣል ስትል ሚለር ትመክራለች። ከዚህ ደግሞ ባለፈ ልምድዎን እና ችሎታዎን ለማሳየት አዲስ ተቀጣሪዎች ሲመጡ ለማማከር፣ ለማለማመድ እና ልምድን ለማጋራት ከፊት ይሁኑ። ለጀማሪዎች ልምድን በድፍረት ማካፈል ያለዎትን ልምድ እና ክህሎት ለሌሎች ለማሳየት ጥሩ ዕድል ነው። በዚህ የዲጂታል ዘመን በፌስቡክ፣ በትዊተር እንዲሁም በሊንክዲን ላይ ስለራስዎ የሚያሰፍሯቸውን መረጃዎችም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በየጊዜው የሚስተለካከሉ እና ያለዎትን ልምድ እና ክህሎት በሚገባ የሚገልጹ መሆናቸውን ያስተውሉ። ከዚህ በኋላ ስራስዎ መናገር ልክ ታሪክ የመንገር ያህል ቀላል ይሆናል። እንዴት አድርጌ ብነግረው የበለጠ ይስብልኛል ቀልብም ልብም ይስብልኛል የሚለው ያስጨንቅዎት ይሆናል እንጂ፤ አፍዎ አይተሳሰርም፣ እጅዎን አያልብዎትም፣ ድምጽዎም አይሰልም።
https://www.bbc.com/amharic/news-58676398
amh
business
በአሜሪካ ማዕቀብ ምክንያት ፊቱን ወደ አሳማ እርባታ ያዞረው ሁዋዌ
ሁዋዌ በአሜሪካ ዘመናዊ ስልኮቹ ላይ ከባድ ማዕቀቦችን በመጣሉ ምክንያት ፊቱን ለአሳማ ገበሬዎች ቴክኖሎጂ ወደ ማቅረብ አዙሯል። ግዙፉ የቻይናው የቴሌኮም ኩባንያ የትራምፕ አስተዳደር ለአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አስጊ ነው ተብሎ በመፈረጁ አስፈላጊ ዕቃዎችን እንዳያገኝ ተደርጓል፡፡ ሁዋዌ የገጠመውን የስማርት ስልክ ሽያጭ ሊያካክስ በመፈለጉ ለቴክኖሎጂው ሌሎች የገቢ ምንጮችን እየተመለከተ ነው፡፡ ለአሳማ ገበሬዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጅ ከመሥራት በተጨማሪ ሁዋዌ የከሰል ማዕድን ኢንዱስትሪ ጋርም ይሠራል፡፡ ሁዋዌ የደንበኞችን መረጃ ለቻይና መንግስት ሊያጋራው ይችላል ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ክስ ቢያቀርቡትም ድርጅቱ በተደጋጋሚ አስተባብሏል፡፡ በዓለም ትልቁ የቴሌኮም መሣሪያዎች አምራቹ በዚህ ምክንያት የ 5ጂ ሞዴሎችን አካላት ለማስመጣት የአሜሪካ መንግሥት ፈቃድ ስለላልሰጠው የ 4ጂ ሞዴሎችን በመሥራት ተገድቧል፡፡ በብሔራዊ ደህንነት ላይ ስጋት ፈጥሮብናል ያሉ እንደ እንግሊዝ ያሉ ሌሎች ሃገራትም ሁዋዌ የሚያደርገውን የ 5ጂ ዝርጋታ አስቁመዋል፡፡ በዚህ ዓመት የስማርት ስልኮችን ምርቱን እስከ 60% ድረስ እንደሚቀንሰው ሪፖርቶች ጠቁመዋል፡፡ ይህን ግን ማረጋገጥ አልተቻለም። "ይህ የሚያሳየው የሁዋዌ ምርቶች ጥራትና ልምዳችን ምንም አይነት ችግር እንደሌለበት ነው፡፡ ሁዋዌ በጂኦፖለቲካዊ ውዝግብ መካከል የተያዘ በመሆኑ ለሁዋዌ የመጫወቻ ሜዳው አይደለም" ሲሉ የኩባንያው ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ስለዚህ ሁዋዌ ፊቱን ወደ ሌሎች የገቢ ምንጮችን ያዞረ ይመስላል። እንደክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ስማርት ተሽከርካሪዎች እና ተለባሽ መሣሪያዎች እንዲሁም ስማርት መኪና የማምረትም ዕቅዶች አሉት። በጥቂት ተጨማሪ ባህላዊ ኢንዱስትሪዎች ላይ ዓይኑን ጥሏል፡፡ ቻይና በዓለም ትልቁ የአሳማ እርሻ ኢንዱስትሪ ባለቤት ስትሆን፣ የአለማችን አሳማዎች ግማሽ ያህሉ መኖሪያ ናት፡፡ በሽታዎችን ለመለየት እና አሳማዎችን እንቅስቃሴ ለመከታተል በሚያስችለው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የአሳማ እርሻዎችን ለማዘመን ቴክኖሎጂው እየረዳ ነው፡፡ የፊት መለያ ቴክኖሎጂ እያንዳንዱን አሳማዎች መለየት ሲያስችል ሌሎች ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ክብደታቸውን፣ አመጋገባቸውን እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎቻቸውን ይቆጣጠራሉ፡፡ ሁዋዌ የፊት ለይቶ የማወቅ ቴክኖሎጂ በማዘጋጀት ላይ ሲሆን ባለፈው ወር ግን ትችት ገጥሞታል። ምክንያቱ ደግሞ ከእግረኞች ምስል መካከል የኡሂጉር ተወላጅ የሆኑ የሚመስሉትን ሰዎችን ለይቶ በሚያሳውቀው ስርዓቱ ነው። እንደ ጄዲዳትኮም፣ አሊባባን ጨምሮ ሌሎች የቻይና ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከአሳማ ከሚያረቡ አርሶ አደሮች ጋር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ እየሠሩ ነው፡፡ የሁዋዌ ቃል አቀባይ አክለውም "በ 5ጂ ዘመን ለኢንዱስትሪዎች የበለጠ እሴት ለመፍጠር አንዳንድ ባህላዊ ኢንዱስትሪዎችን በኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እንደገና ለማነቃቃት የምንሞክርበት ሌላ ምሳሌ ነው" ብለዋል፡፡ የሁዋዌ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሬን ዤንግፈይ በዚህ ወር መጀመሪያ በሰሜን ቻይና ሻንሺ ግዛት የማዕድን ፈጠራ ቤተ-ሙከራ በይፋ አስጀምረዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለድንጋይ ከሰል ማዕድን አውጪዎች "አነስተኛ ሠራተኞችን፣ ከፍተኛ ደህንነትን እና ከፍተኛ ብቃትን የሚያመጣ እና ማዕድን አውጪዎቹ በሥራ ቦታቸው ሱፍ እና ከረቫት እንዲለብሱ" የሚያስችላቸውን ቴክኖሎጂን ለማዳበር ይፈልጋሉ፡፡ በዝግጅቱ ላይ በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ በተደረገ ስብሰባ ላይ ሬን ኩባንያው ከሰል ማዕድን እና ከብረት እንደ ቴሌቪዥኖች፣ ኮምፒውተሮች እና ታብሌቶች ያሉ ምርቶች ላይ ትኩረት እያደረገ ይገኛል፡፡ "በስልክ ሽያጮች ላይ ሳንመሠረት እንኳን በመቀጠል እንችላለን" ያሉት ሬን የአሜሪካ ኩባንያዎች ያለፍቃድ ከሁዋዌ ጋር እንዳይሠሩ የሚያግደውን የጥቁር መዝገብ ያነሳል የሚል እምነት እንደሌላቸው ጨምረው ጠቅሰዋል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-56121975
amh
business
ዩናይትድ አየር መንገድ ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ከበረራ አገደ
የአሜሪካው ዩናይትድ አየር መንገድ 24 ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ከበረራ አገደ። አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹን ከበረራ ያገደው ባሳለፍነው ቅዳሜ ከአውሮፕላኖቹ አንዱ ሞተሩ ላይ አደጋ ካጋጠመው በኋላ ነው። አውሮፕላኑ 231 መንገደኞችንና አስር የበረራ አስተናጋጆችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን በዴንቨር አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገዷል። እስካሁን በአደጋው የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። የአውሮፕላኑ ስብርባሪዎችም በአቅራቢያው ባሉ የመኖሪያ ቦታዎች ወዳድቀው ተገኝተዋል። ይህንንም ተከትሎ ጃፓን ተመሳሳይ ፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞተር የተገጠመላቸውን ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን የሚጠቀሙ ሁሉም አየር መንገዶች አየር ክልሏ እንዳይገቡ ጠይቃለች። ወደ ሃዋይ ሆኖሉሉ ከተማ ለመብረር የተነሳው ዩናይትድ 328 አውሮፕላን በቀኝ በኩል ባለው ሞተሩ ላይ አደጋ እንደገጠመው የፌደራል አቪየሽን አስተዳደር ገልጿል። አደጋውን ተከትሎም አስተዳደሩ የፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞተር የተገጠመላቸው ቦይንግ 777 አውሮፕኣኖች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ አዟል። "አደጋው ካጋጠመ በኋላ ሁሉንም የደህንነት መረጃዎች ተመልክተናል" ሲሉ የፌደራል አቪየሽን አስተዳዳሪ ስቴቭ ዲክሰን በመግለጫቸው ተናግረዋል። በመጀመሪያ ደረጃ በተገኘው መረጃ መሠረትም፤ ምርመራው በቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ላይ ብቻ ለሚገጠመው ለዚህ የሞተር ሞድል የተለየ የሆነው ወደ ሞተሩ ንፋስ ማስገቢያ [ፋን] ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ድምዳሜ ላይ ደርሰናል ብለዋል። የፌደራል አቪየሽን አስተዳደርም ከሞተር አምራቹ ድርጅት እና ከቦይንግ ተወካዮች ጋር እየተነጋገረ ነው። የአገሪቷ የመጓጓዣ ደህንነት ቦርድ የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ እንደሚያመላክተው አውሮፕላኑ አደጋ ያጋጠመው በቀኝ ሞተሩ ላይ ሲሆን፤ በሌሎች ሁለት ንፋስ ማስገቢያ [ፋን] ተሰነጣጥቀዋል። ሌሎቹም እንዲሁ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይሁን እንጂ የአውሮፕላኑ ዋነኛ አካል ላይ የደረሰው ጉዳት ቀላል መሆኑን ቦርዱ ገልጿል። ይህ አደጋ ባጋጠመው አውሮፕላን ላይ ተሳፍራው የነበሩት መንገደኞች ለበረራ እንደተነሱ ወዲያውኑ ከፍተኛ ፍንዳታ እንደሰሙ ተናግረዋል። ከመንገደኞቹ አንዱ የሆኑት ዴቪድ ዴሉሲያ "አውሮፕላኑ በኃይል ሲነቃነቅ ነበር። ከዚያም ከፍ ብሎ መብረር ስላልቻለ ወደ ታች መውረድ ጀመረ" ብለዋል። አክለውም እርሳቸውና ባለቤታቸው ምንአልባት አደጋ ካጋጠመን በሚል የኪስ ቦርሳቸውን ኪሳቸው ውስጥ እንደከተቱት ተናግረዋል። የብሩምፊልድ ከተማ ፖሊስ የአውሮፕላኑ የሞተሩ ሽፋን ስባሪ በአንድ መኖሪያ ቤት አትክልት ቦታ ላይ መውደቁን የሚያሳይ ምስል አጋርቷል። ሌሎቹ ስብርባሪዎችም በከተማዋ አንድ የእግር ኳስ ሜዳ ላይ ወድቀው ታይተዋል። ከአውሮፕላኑ ላይ በወደቀው ስብርባሪ ግን የተጎዳ አለመኖሩ ተገልጿል። በጃፓን የፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞደል ሞተር የተገጠመላቸው ሁሉም 777 አውሮፕላኖች ተጨማሪ ማስታወቂያ እስኪነገር ድረስ አየር ክልሏ መግባት ያቆማሉ። ይህም ለበረራ መነሳትን፣ ማረፍን እና በአገሪቷ የአየር ክልል ላይ መብረርን ያካትታል። ባለፈው ታህሳስ ወር የጃፓን አየር መንገድ አውሮፕላን በግራ በኩል ያለው ሞተሩ መስራት ባለመቻሉ ወደ ናሃ አየርማረፊያ እንዲመለስ ተገዶ ነበር። አውሮፕላኑ ባለፈው ቅዳሜ አደጋ ካጋጠመው የዩኒይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር በተመሳሳይ የ26 ዓመት እድሜ ያለው ነው። በ2018፤ አንድ የዩናይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን በሆኖሉሉ ከማረፉ በፊት የቀኝ ሞተሩ ተሰብሮ ነበር። ይህንንም ተከትሎ በተካሄደው ምርመራ የአገሪቷ የመጓጓዣ ደህንነት ቦርድ አደጋው የአውሮፕላኑ ሙሉው የንፋስ ማስገቢያ [ፋን] በመሰንጠቁ ምክንያት ያጋጠመ እንደሆነ አስታውቆ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/56151142
amh
business
ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ
የተወሰኑ መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላልተወሰነ ጊዜ ከቀረጥና ታክስ ሙሉ ሙሉ ለሙሉ ነጻ መደረጋቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ እንዳሳወቁት የመሰረታዊ የምግብ ሸቀጦችን የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማሻሻያው ከነሐሴ 28/2013 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ተግባራዊ ይሆናል። በዚህም መሠረት የምግብ ዘይት፣ ስኳርና ሩዝ ከውጭ ሲገቡም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸምባቸው ከቀረጥና ታክስ ሙሉ በሙሉ ነፃ ሲሆኑ ስንዴ ከውጭ ሲገባ ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንዲሆን ተወስኗል። ፓስታ እና ማኮሮኒ ከውጭ ሲገቡም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የዶሮ እንቁላል ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆን መወሰኑን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ሚኒስትር ዲኤታው ጨምረውም መንግሥት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠርና የኅብረተሰቡን የመግዛት አቅም ለማሳደግ የገንዘብና የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያዎችን እንዲሁም አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ሲወስድ መቆየቱን ተናግረዋል። ይህ እርምጃ ተግባራዊ ሲደረግ መንግሥት በብዙ ቢሊዮን የሚገመት ገቢ እንደሚያጣ አመልክተው የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በታክስ ብቻ የሚፈለገውን ውጤት ስለማያመጣ አቅርቦትን ለመጨመር መንግሥት በከፍተኛ ወጪ ሸቀጦችን በመግዛት በዝቅተኛ ዋጋ ለኅብረተሰቡ እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች በሌሎች አካላት የሚገባውን አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ ይጨምር ዘንድ ለስድስት ወር ተፈቅዶ የነበረው ያለውጭ ምንዛሬ ሸቀጦችን የማስገባት አስራር ለሌላ ተጨማሪ ስድስት ወራት እንዲራዘም መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል። እነዚህ ማሻሻያዎች የዋጋ ንረት በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ፣ በምግብ ዋጋ ላይ የሚከሰተውን ጭማሬ መንግሥት ለመቆጣጠር እንዲረዳውና ከውጭ እቃ ለሚያስገቡ ነጋዴዎችንም ለማበረታት ያለመ እንደሆነም ተገልጿል። በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ያለው የምግብ ዋጋ ግሽበት ባለፈው ወር 32 በመቶ የደረሰ ሲሆን ይህም በአሥር ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58437093
amh
business
ካፒታሊዝም፡ የአፕል ኩባንያ ሀብት ዋጋ ግምት ሁለት ትሪሊዮን ዶላር ደረሰ
የቴክኖሎጂው ኩባንያ አፕል በስቶክ ገበያ የሀብት ምጣኔ ግምት ከቢሊዮን ዶላሮች አልፎ በትሪሊዮን ዶላር የተገመተ ሁለተኛው የዓለም ኩባንያ ሆኗል፡፡ በአሜሪካ በ2 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት ያለው ኩባንያ የለም፡፡ አፕል የመጀመርያው ሆኗል፡፡ ከዚህ ቀደምም አንድ ትሪሊዮን ዶላር ለመድረስ የመጀመርያው ሆኗል፤ በ2018 ዓ.ም መጀመርያ፡፡ አሁን የአፕል የአንድ ሼር ዋጋ ግምቱ $467.77 ዶላር ደርሷል፡፡ ትናንትና ረቡዕ በነበረው የስቶክ ገበያ የኩባንያው ጥቅል ሀብት 2ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተበስሯል፡፡ በዓለም ላይ 2 ትሪሊዮን ዶላር ጣሪያ ለመድረስ ብቸኛና የመጀመርያ የነበረው ኩባንያ የሳኡዲ አረቢያው የነዳጅ ድርጅት አራምኮ ነው፡፡ ሆኖም አራምኮ በስቶክ ገበያ የነበረው ዋጋ ባለፈው ታኅሣሥ ወር የነዳጅ ዋጋ ማሽቆልቆልን ተከትሎ የሼር ምጣኔውም በዚያው ወርዷል፡፡ ከዚያ ወዲያ የስቶክ ዋጋ ግምቱ 1.8 ትሪሊዮን ዶላር ላይ ተቀምጧል፡፡ በሐምሌ ወር አፕል አራምኮን በመብለጥ የዓለም እጅግ ሀብታሙ ድርጅት ሆኗል፡፡.በስቶክ ገበያም በጣም ተፈላጊ የግብይይት ኩባንያ በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል፡፡ የማያባራ ገበያ የአይፎን ስልኮችን ፈብራኪው አፕል በዚህ ዓመት የሼር ድርሻው በ 50% ነው የተመነደገው፡፡ ይህ የሆነው ታዲያ ዓለም በኮሮና ተህዋሲ በሚታመስበት ወቅት ነው፡፡ የኮቪድ መከሰት አፕል በኢሲያ በተለይም በቻይና ያሉ መደብሮቹን እንዲዘጋ አስገድዶታል፡፡ ቻይና በድርጅቱ ላይ ፖለቲካዊ ጫና ስታደርስ ነው የቆየችው፡፡ እንዲያም ሆኖ ነው የድርጅቱ የስቶክ ድርሻ ገበያው እየደመቀለት የሄደው፡፡ ብዙዎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከሌሎች ዘርፎች በተሻለ አስቸጋሪውን ጊዜ ለማለፍ የሚችሉበት አጋጣሚ የተፈጠረ ይመስላል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የስቶክ ድርሻቸው እየተመነደጉ ያሉት ከቴክኖሎጂ ጋር የተሳሰሩት ኩባንያዎች ናቸው፡፡ አፕል በዚህ የዓመቱ ሦስተኛው ምዕራፍ ላይ ማለትም ሐምሌ መጨረሻ ላይ ትርፉ ወደ 60 ቢሊዮን ዶላር መጠጋቱን አብስሯል፡፡ በአሜሪካ ከአፕል ቀጥሎ ከፍተኛ የስቶክ ግምት ዋጋ ያለው ኩባንያ አማዞን ሲሆን ምጣኔውም 1.7 ትሪሊዮን ዶላር ነው፡፡.
https://www.bbc.com/amharic/news-53846118
amh
business
ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት ከምታደርገው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ምን ያህል ተጠቃሚ ናት?
በያዝነው ወር ግንቦት 2003 ዓ.ም ነበር ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገር ጂቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የጀመረችው። በአፍሪካ የልማት ባንክ በ95 ሚሊዮን ዶላር የብድር ድጋፍ በተገነባው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር የመጀመሪያው ዓመታዊ 22 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለጅቡቲ በመሸጥም የኃይል ወጪ ንግድ ከአስራ አንድ ዓመታት በፊት ተበሰረ። የግልገል ጊቤ ሁለት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ባጋጠመው የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በመዘጋቱ ከታቀደው አንድ አመት ዘግይቶ ነበር የተጀመረው። በወቅቱ የነበረው የኃይል ሽያጭም ለአገሪቱ በአማካኝ በዓመቱ 10 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝላት የአገራትን ምጣኔ ኃብት ትንበያዎችን እንዲሁም ጥልቅ ዳሰሳዎችን የሚያዘጋጀው ኢኮኖሚክ ኢንተለጀንስ ዩኒት በወቅቱ ባወጣው ሪፖርት አስነብቧል። በሪፖርቱ መሰረት ከጂቡቲ ከሚገኘው ገቢም የተወሰነውን በገጠር ያሉ ህዝቦቿ መብራት እንዲያገኙ፣ በተጨማሪም በአገር ውስጥ ያለውንም የኃይል ተደራሽነት ለማሳደግ እቅድ ተይዞ ነበር። ከአስር ዓመት በኋላ በ2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 90 ሚሊዮን ዶላር ማስገባት ችላለች። ለጂቡቲ በ22 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የጀመረችው ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የኃይል ማዕከል ለመሆን የአስር አመት ፍኖተ ካርታን አዘጋጅታለች። በዚህ የቀጣይ አስር ዓመታት ይተገበራል በተባለው የኢነርጂ ልማት መሰረት አገሪቷ በ2022 የምታመነጨውን የኃይል መጠን ወደ 20 ሺህ ማሳደግ እንዲሁም ለጎረቤት አገራት የምትሸጠውን የኃይል መጠንም ወደ 7 ሺህ 184 ጊዋስ (GWH) ለማድረስ ታቅዷል። በአሁኑ ወቅት ለጎረቤት አገራቱ ሱዳንና ጂቡቲ አመታዊ የኃይል ሽያጭ የምታቀርብ ሲሆን ለኬንያም የኃይል ሽያጭ ለመጀመር የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታን ግንባታን ካጠናቀቀች አንድ አመት ሆኗታል፤ ፍተሻውም የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ እንደሚጀመርም ይጠበቃል። የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የወጪ ንግድ ከውሃ ሃይል፣ ነፋስ፣ እንፋሎት፣ የጸሃይ ብርሃንንን በመጠቀም የንጹህ ኃይል አምራች ለመሆን እቅድ ይዛ ያለችው ኢትዮጵያ በዚህም ማሳካት የምትፈልገው ከምስራቅ አፍሪካ ባሻገር የአፍሪካ የኃይል ምንጭ ማዕከል መሆንን ነው። ከጎረቤት አገራት ጋር የኃይል ትስስር በመፍጠርም ለጂቡቲና ለሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ በአማካኝ በየአመቱ 70 ሚሊዮን ዶላር ገቢን ለማግኘት እየሰራች ትገኛለች። ለሁለቱ አገራት የምትልከው የኃይል መጠን ባለው ስምምነት መሰረት በ100 ሜጋ ዋት የሽያጭ ማዕቀፍ ሲሆን የተወሰነ ከፍና ዝቅ ማለት እንዳለም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ያስረዳሉ። ከ100 ሜጋ ዋት በላይም ይሁን በታች እንደቆጠረው ሁኔታ አገራቱ ክፍያቸውን ይፈጽማሉ። በባለፉት ዘጠኝ ወራት ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ መረጃ በምናይበት ወቅት ለሱዳን የኤሌክትሪክ ኩባንያ ወደ 746.9 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት የመሸጥ እቅድ ተይዞ የነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከእቅዱ በ4 በመቶ ብልጫ ያለው 774.2 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት ወጪ ንግድ ተካሂዷል። በተጨማሪ ወደ ጂቡቲ 385 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም 427.1 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት ሽያጭ በመደረጉ ከእቅዱም 11 በመቶ ብልጫ አሳይቷል። በዚህም ለሱዳን ከተሸጠው ኃይል 38.7 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለጂቡቲ ከተሸጠው ደግሞ 27.8 ሚሊዮን ዶላር በአጠቃላይም በዘጠኝ ወራት ከኃይል ሽያጭ 67 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ተገኝቷል። ገቢው ከእቅዱ አንፃር ሲታይ የሱዳን ኤሌክትሪክ ኩባንያ የተጠቀመው 4 በመቶ ጭማሪ፣ የጅቡቲ ደግሞ 15 በመቶ ገደማ ጭማሪ ማሳየቱን አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። በየዓመቱ ለጎረቤት አገራት በጅምላ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ 70 ሚሊዮን ዶላር ቢታቀድም በአመታት ውስጥ ጭማሬ እያሳየ መምጣቱንም የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊው አቶ ሞገስ መረጃዎችን በማጣቀስ ያስረዳሉ። እስካሁን ድረስ ባለው ከፍተኛ የተመዘገበው በባለፈው ዓመት ሲሆን በ2013 ዓ.ም ሲሆን ከነበረው አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ወደ 90 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ተገኝቷል። በአመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ የምትሸጠው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም እንዲሁም ገቢውም ጨምሯል። ሆኖም ከሁለት አመታት በፊት የአገሪቱ የኃይል ማመንጫ ግድቦች በቂ ውሃ ባለመያዛቸው ምክንያት በተፈጠረው ዕጥረት ለወራት ያህል ለሱዳን አቅርቦት ከማቋረጥ በተጨማሪ ኤሌክትሪክ በፈረቃ መከፋፈል ተጀምሮ ነበር። በዝናብ እጥረት ምክንያት በተፈጠረው ችግር በደቡብ እና በምስራቅ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙት ሦስት ግድቦች ቆቃ፣ መልካ ዋከናና ጊቤ ሶስት በቂ ውሃ እንዳይዙ አድርጓቸዋል። በወቅቱ ሱዳን ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ፍላጎት እንደነበራት የሚያወሱት አቶ ሞገስ፣ የአገር ውስጥ ፍላጎት ባለመሟላቱና ወደ ፈረቃ በመገባቱም ወጪ ንግድ ለአምስት ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን በዚህም ዓመታዊ ገቢውን ከ60 ሚሊዮን ዶላር በታች አድርጎታል። በተያያዘ ዜና በዘንድሮው ዓመት ሱዳን ያልከፈለችው ውዝፍ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለሱዳን ኤሌክትሪክ ኃይል ይከፈለኝ የሚል ደብዳቤ ጽፏል። ተቋሙም በጻፈው ምላሽ አገሪቱ ያለችበትን ፈታኝ ሁኔታ ጠቅሶ ታገሱኝ፣ አገልግሎቱም አይቋረጥ የሚል ጥያቄ መቅረቡንም አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። ከዚህ ቀደም ለሁለት ወይም ሶስት ወራት ሳይከፈል የሚዘልበት ጊዜ ቢኖርም በአሁኑ ወቅት ግን ከተለመደው ውጭ ስድስት ወራት በላይ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሞገስ መጠኑን ግን መጥቀስ አልፈለጉም። የኬንያ ኃይል ሽያጭ ለምን ዘገየ? የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭን ከጂቡቲ በመቀጠል ለሱዳን ከዓመታት በፊት ማቅረብ የጀመረችው ኢትዮጵያ ለሌላኛዋ ጎረቤት አገር ኬንያም ኃይል ለማቅረብ የወጠነችው ከአመታት በፊት ነበር። ኢትዮጵያና ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመገበያየት የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙት ከአስር ዓመት በፊት ነበር። በወቅቱም የነበሩ የአገሪቱ ሚዲያዎችን ስናገላብጥ እንዳገኘነው በወቅቱ የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑና በኬንያው የኢነርጂ ሚኒስትር የተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት ከአራት አመት በኋላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ እንዲጀመር ነበር። ለምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ከፍተኛ ስፍራ ያለውና 1.3 ቢሊዮን ዶላር የፈጀው የዚህ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን ኢትዮጵያ በባለፈው ዓመት ገንብታ ጨርሳለች። አገራቱን የሚያገናኘው የኤሌክትሪክ መስመር 500 ኪሎ ቮልትና ከኢትዮጵያ በኩል 412 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ በአጠቃላይ ከ1 ሺህ ሜትር በላይ ርዝማኔ ያለው እንደሆነ አቶ ሞገስ ይናገራሉ። ወጪውም ከዓለም ባንክ ከተገኘው ብድር 684 ሚሊዮን ዶላር፣ ለኢትዮጵያ 441 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለኬንያ 27.4 ቢሊዮን ዶላር የሚሸፈን ነው። የአፍሪካ ልማት ባንክም ይህንኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የግልገል ጊቤ ሶስት ግድብ ጋር የሚያገናኘውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ድጋፍ ለኢትዮጵያ 232 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለኬንያ 116 ሚሊዮን ዶላር አጽድቋል። ለኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታና ለሌሎች ስራዎች ከለጋሽ ተቋማት በብድር ከተገኘው በተጨማሪ አገራቱም ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት ለመስራት የራሳቸውን ወጪ አድርገዋል። በባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ በኩል የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ግንባታና የፍተሻ እንዲሁም የሙከራ ስራዎች ቢጠናቀቅም ከኬንያ በኩል ቀሪ የዝርጋታና የፓወር ተከላ ስራዎች እንዳሉ እየተነገረ መጀመር ከነበረበት ወቅት እየተጓተተ ረዘም ያሉ ወራት ተቆጥረዋል። በያዝነው አመት መስከረም ላይ በኬንያ ኢነርጂ ሚኒስትር የተመራ ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረ ሲሆን በቀሪ ጉዳዮች ላይ ስምምነቱን ለማጠናቀቅና ቀሪው የፕሮጀክቱ አካልም እንዲጠናቀቅ ስምምነት ላይ መደረሱንም አቶ ሞገስ ያወሳሉ ። ከወራት በኋላ እንዲሁ ጥር ወር መጨረሻ ላይ የዘገየውን የ1.3 ቢሊዮን ዶላር 400 ሜጋ ዋት የሃይል ሽያጭ ለማፋጠን ኢትዮጵያና ኬንያ አዲስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሚዲያዎች ዘግበዋል። በኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር እዮብ ተካልኝ የተመራ የልዑካን ቡድን ናይሮቢ ጥር መጨረሻ ላይ መጥቶ ከኬንያ ኤነርጂ ሚኒስትር ሞኒካ ጁማ ጋር ተገናኝተው ነበር። አገራቱ ቀደም ሲል በተፈረሙ የኃይል ስምምነቶች፣ የማጠናቀቂያ ስራዎች፣ የአሰራር መመሪያዎችንም በተመለከተ ተወያይተው መከለሳቸውም ተዘግቧል። የኬንያ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ለኬንያ ከኢትዮጵያ 400 ሜጋ ዋት የምትገዛው ኃይል ርካሽ መሆኑን ነው። ከኬንያ በኩል ከመስመር ዝርጋታ ግንባታ መጓተት በተጨማሪ ስምምነት የተደረሰበት የ400 ሜጋ ዋት ኃይልን በተመለከተ እንዲሁም ከተወሰነው ታሪፍ ጋር ተያይዞ ጥያቄ መነሳቱንም ሚዲያዎች ዘግበዋል። ሆኖም አገራቱ ያላቸውን ልዩነት በመፍታት የያዝነው አመት ከመጠናቀቁ በፊት ኃይል የማስተላለፍ ስራው ይጀመራል የሚል እቅድ ተይዞም እየተጠበቀ ይገኛል። ፕሮጀክቱ በምስራቅ አፍሪካ ያሉ አገራት መካከል ድንበር ዘለል የሃይል ንግድ እንዲሁም ትስስርን ለማስተባበር በአውሮፓውያኑ 2005 የተቋቋመው ቀጠናዊ ተቋም የሆነው ኢስተርን አፍሪካ ፓወር ፑል አካል ነው። በአጠቃላይ የኃይል ልማት እና ተግባር የማስተባበር ስልጣን የተሰጠው የተቋሙ ዋና ፅህፈት በአዲስ አበባ የሚገኝ ሲሆን አስራ አንድ አባል አገራት አሉት። አገራቱም ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ እና ሊብያ። ኮንጎ (ዲአርሲ)፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ናቸው። ፕሮጀክቱ እነዚህንም ሃገራት በኃይል የማስተሳሰርና የማዋሃድ አቅም እንዳለው ይነገራል። በሁለቱ አገራት የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርም እስከ 2000 ሜጋ ዋት የመሸከም አቅም ያለው ነው። እንደ አቶ ሞገስ ይህ የኤሌክትሪክ መስመር ኢትዮጵያና ኬንያን ከማገናኘት በተጨማሪ የመካከለኛው ምስራቅ፣ የምስራቅ አፍሪካና ሌሎች የደቡባዊ አፍሪካ ሃገራትንም ተደራሽ ያደርጋል በሚል እሳቤ የማስተላለፍ አቅሙ ከፍ ተብሎ የተሰራ ነው። ለሌሎቹም አገራት ኤክስፖርት የሚደረግበት የኤሌክትሪክ መስመር በአብዛኛው ጤናማ የሆነ መስመር ያለው ሲሆን እንደ የአገር ውስጥ ማስተላለፊያ መስመሮች አሮጌ አለመሆኑንና ኤሌክትሪክ በመሸከም በኩል ችግር እንደማይጠቀስም አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። ለደቡብ ሱዳን ኃይል ለመሸጥ የተደረሰው ስምምነት ከሰሞኑ ደግሞ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። በደቡብ ሱዳን የኢነርጂና ግድብ ሚኒስትር ፒተር ማርሴሎ የተመራው የልዑካን ቡድን፣ ኢትዮጵያ መጥቶ የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከልን እና የኮተቤ የኃይል ማከፋፋያ ጣቢያን ከጎበኙ በኋላም ከሶስት ዓመት በኋላ የኃይል ሽያጭ እንዲጀመር የሚያስችል ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ስምምነቱ ከሶስት ዓመት በኋላ ሽያጭ እንደሚጀመር የጊዜ ገደብ የተቀመመጠለት ሲሆን ይህም የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከመጀመሩ በፊት መሰራት ያለባቸው ተግባራት ስላሉ እንደሆነ አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። በዚህም መስረት በመጀመሪያው ዓመት ሁለቱም አገራት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር መዘርጋት ያለባቸውን አካባቢዎች በተመለከተና ከአቅርቦቱ ጋር የተያያዘ የአዋጭነት ጥናቶችን የሚያካሂድ ቴክኒካል ቡድን ያቋቁማሉ። ይሄንን የአዋጭነት ጥናትም ተከትሎም ባሉት ሁለት ዓመታት ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ የሚከናወነው። ግንባታው ሁለት ዓመት ሊፈጅ እንደሚችልም ታሳቢ ተደርጓል። የሁለቱ አገራት የመግባቢያ ስምምነት በሁለት ምዕራፎች የተከፈለ ነው። የመጀመሪያው 357 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ከጋምቤላ 2 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተነስቶ ወደ ደቡብ ሱዳኗ ማላካል ግዛት የሚዘልቀው ነው። ሁለተኛውና ረዘም ባለ ጊዜ ይከናወናል ተብሎ የታቀደው ደግሞ ከ700 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና ባለ 400 ወይም 500 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ከቴፒ ወደ ቦር ጁባ የሚዘረጋው ነው። ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ በመጀመሪያው ዓመት ላይ 100 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሽያጭ እንዲኖር ስምምነት ላይ ተደርሷል። ሆኖም በ100 ሜጋ ዋት ብቻ እንደማይወሰን የሚናገሩት አቶ ሞገስ የደቡብ ሱዳንን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚዎችን እንዲሁም የአገሪቱን መሰረተ ልማት ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ በየጊዜው ሊያድግ የሚችል የኃይል ፍላጎት አቅርቦት ይደረጋል። በዚህም መሰረት ከፍተኛውና ከ400 ሜጋ ዋት የማይበልጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመሸጥ ነው የመግባቢያ ስምምነቱ የተደረሰው። የኤሌክትሪክ ኃይል ወጪ ንግድ የሚታዩ ችግሮች ረዘም ባለ ጊዜ ዕቅድ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ብሩንዲ የመሸጥ እቅድ አላት። ነገር ግን ድርድሮች ተካሂደው፣ የመሰረተ ልማቶች ዝርጋታ እንዲሁም ግንባታው እስኪከናወን ዓመታት እንደሚጠይቅ አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። "በፍላጎት ደረጃ እውነት ነው በተለይ ጎረቤቶቻችን ፍላጎት እንዳላቸው አሳውቀዋል።" የሚሉት አቶ ሞገስ ለምሳሌ ሶማሌላንድ የኃይል አቅርቦት ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች። በተጨማሪም የኃይል አቅርቦት በየዓመቱ የሚሸጥላቸው እንደ ሱዳን ያሉ አገራትም ጭማሬ እየጠየቁ ይገኛሉ። ሱዳን አሁን ከሚደረገው የኃይል አቅርቦት (ከፍተኛው ወደ ሁለት መቶ ሜጋ ዋት) በተጨማሪ በ1 ሺህ 200 ሜጋ ዋት ጭማሬ ፍላጎት እንዳላት አሳውቃለች። "ይህንን 1 ሺህ 200 ሜጋ ዋት ወደ ሱዳን ለመላክ የሚያስችል አሁን ባለው ሁኔታ እንደ አገር አቅም የለንም ። ያንን ማስተናገድ አንችልም። አሁን ባለው መሰረተ ልማት ደግሞ ሊሆን የሚችል አይደለም። ስለዚህ እሱ ለወደፊት ምላሽ ማግኘት የሚችል ጉዳይ ነው" ይላሉ። አገሪቷ አሁን ባላት ሃይል የማመንጨት አቅም ለሱዳን የሚላከው መጠን እስከ 300 ሜጋ ዋት ድረስ ቢሆን ብዙ ችግር ባይኖረውም የሱዳን ፍላጎት ግን በጣም ከፍተኛና ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ማሟላት የማትችለው ነው ይላሉ። ከኤሌክትሪክ ወጪ ንግድ ጋር ተያይዞ በዋነኝነት የሚጠቀሰው ኤክስፖርት ወደሚደረግባቸው ሃገራት የሚጠይቁትን ፍላጎት ማሟላት አለመቻሉ እንደሆነ አቶ ሞገስ ይጠቅሳሉ። በዋነኝነት ተቋሙ ትኩረት የሚሰጠው የአገር ውስጥ ፍላጎት ስለሆነ፣ ስምምነቶቹ ላይ የአገር ውስጥ ፍላጎት ማሟላት ካልተቻለ ሙሉ በሙሉ የማቆም እርምጃ እንደሚወሰድ የሚጠቅስ አለ። ለምሳሌም የሚጠቅሱት በ2011 የተከሰተውን የኃይል እጥረት ነው፤ በዚህም ወቅት ኢትዮጵያ ለሱዳን የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ከማቋረጥ በተጨማሪ ለጂቡቲ የቀረበው ኃይልም በግማሽ ገደማ ቀንሶ ነበር። ይህ አሰራር ለኃይል ጠያቂዎቹ አገራት ብዙም እንደማይስማማቸው አቶ ሞገስ ያስረዳሉ። የአገር ውስጥ የኃይል መቆራረጥ ባለበት ወጪ ንግድ እንዴት ይጣጣማል? የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣የተዛባ የንግድ ስርዓት በተለይም የወጪና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን ለአገሪቷ ለአመታት ከፍተኛ ማነቆ የሆነባት ጉዳይ ነው። በገቢና በወጪ ንግድ ሚዛን መጓደልም ጋር ተያይዞ ባለፈው ዓመት አገሪቱ ከወጪ ንግድ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ስታገኝ በገቢ ንግድ ደግሞ 15 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንዳደረገች መረጃዎች ያሳያሉ። ይህንንም ከፍተኛ ልዩነት ለማመጣጠን አገሪቱ የወጪ ንግዷን ማሻሻል የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች እንደ መፍትሄ የሚሰነዝሩት ነው። የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ አገሪቱ ገንዘብ ከምታገኝበት ወጪ ንግድ አንዱ ቢሆንም አገሪቱ ካላት ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ሽፋን እንዲሁም ህዝቧ በኃይል መቆራረጥ በሚሰቃይበት ወቅት ኢትዮጵያ ለውጭ አገራት ኃይል መሸጧ ጥያቄን ማጫሩ አልቀረም። ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ ከግብፅ በጎርጎሳውያኑ 1959 የተፈረመውን የቅኝ ግዛት ስምምነት ታሪካዊ ተጠቃሚነት በምታነሳበት ወቅት የምትሰጠው ምላሽ ይህ ታሪካዊ ስህተት መስተካከል እንዳለበት በመጥቀስ ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ያለ መብራት እና በድህነት በሚማቅቁበት ሁኔታ ግድቡ ያለውን ጠቀሜታ ስታሳውቅ ቆይታለች። አገሪቷ ያላት የኤሌክትሪክ ሽፋን ዝቅተኛ እንዲሁም በርካታ መቆራረጥ የሚታይበት ነው። የአገሪቱን የኤሌክትሪክ ሽፋን በምናይበት ወቅት በ2012 ዓ.ም 5.8 ሚሊዮን ደንበኞች እንዲሁም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚዎች 44 በመቶ የደረሰ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 33 በመቶ ከብሔራዊ ግሪድ የሚያገኙ እንዲሁም ከግሪድ ውጭ ተጠቃሚ የሆኑ 11 በመቶ መሆኑን ከአስር ዓመቱ የልማት እቅድ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። የአገር ውስጥ ሽፋን እንዲህ ዝቅተኛ በሆነበት መጠንና በአገሪቱ የኃይል አቅርቦት እየተቆራረጠ ባለበት ሁኔታ ለጎረቤት ሃገራት ወጪ ንግድ ማድረግስ እንዴት ይጣጣማል? ቅድሚያ የሚሰጠው የአገር ውስጥ ፍላጎት ማሟላት ላይ እንደሆነ አፅንኦት በመስጠት የሚናገሩት አቶ ሞገስ በአገር ውስጥ እያንዳንዱ ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ፋብሪካዎችን ጨምሮ ፍላጎታቸው ሳይሟላ የወጪ ንግድ የሚደረግበት አሰራር እንደሌለ ያስረዳሉ። ለዚህም የኃይል ወጪ ንግድ አሰራር የተዘረጋ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የምትሸጠው ከምታመርተው እስከ 10 በመቶውን መሆኑም አቶ ሞገስ ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ 6 ሺህ ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚችል ህዳሴ ግድብን እያጠናቀቀች ከመሆኑ አንፃር የሚመረተውን ኃይል ከፍ የሚያደርገው ሲሆን የአገሪቱንም 10 በመቶ ወጪ ንግድ ድርሻ ከፍ እንደሚያደርግም ያስረዳሉ። "ከፍተኛ ኃይል አመንጭተናል ብለን ያመነጨነውን ኃይል ኤክስፖርት አናደርግም። አገራችን የኃይል ጥያቄ በየቦታው ነው ያለው። ኤሌክትሪክ የሚፈልገው ህዝብ ብዙ ነው። የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ማስፋፋት ይጠይቃል" እነዚህ ባሉበት ሁኔታ የመነጨውን ሁሉ ኤክስፖርት አይደረግም" ይላሉ። አቶ ሞገስ እንደሚያስረዱት በተጨማሪም ሽያጩ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክ የኃይል አጠቃቀምን መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ይህ ማለት አገሪቱ ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት (ፒክ ሃወር) ውጭ ያለውን ነው ለሽያጭ የምታቀርበው። በኢትዮጵያ ያለው ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ወቅትን አቶ ሞገስ ሲያብራሩ ጠዋት ሰራተኛው ወደ ስራ ከመሄዱ በፊት ምግብ ለማብሰል፣ ሌሎችንም ተግባራት ለማከናወን ከፍ ያለ ነው። ሆኖም ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት በኋላ የተጠቃሚው ቁጥር እየቀነሰ የሚመጣ ሲሆን ወደ ስድስት ሰዓት አካባቢም እንደገና የተወሰነ ጭማሬ እንደሚያሳይም አቶ ሞገስ ይጠቅሳሉ። በመቀጠልም ምሽት ላይ ከ12 ሰዓት በኋላ አጠቃቀሙ ይጨምርና ወደ 4 ሰዓት ማታ የመቀነስ አዝማሚያ ያሳያል። እንደ አቶ ሞገስ ከፍተኛ ፍላጎት ካላበት ሰዓት (ፒክ ሃወርን) ውጭ ያለው አጠቃቀም ዝቅተኛ ሲሆን በተለይም የምሽቱ ሰዓት ላይ ደግሞ የወጪ ንግድ ወደሚደረግባቸው ሱዳንና ጂቡቲ ከፍተኛ ሙቀት ያለበትና ኤይር ኮንዲሽነር ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም አስገዳጅ የሚሆንበት ነው። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አጠቃቀም ዝቅ በሚልበት የምሽት ሰዓት የአገራቱ ፍላጎት ከፍ ስለሚል ኢትዮጵያ ይህንን አሰራር በመጠቀም የኃይል ወጪ ንግድ እንደምታደርግ ይገልጻሉ። ኢትዮጵያን የአፍሪካ ኢነርጂ ማዕከል የማድረግ ዕቅድ ኢትዮጵያ ፍላጎት ላሳዩና ለሌሎች ሃገራት በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት በማድረግ ለአገሪቱ የውጪ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ዘርፎች ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እያከናወነች እንምትገኝ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ይሰማል። ለዚህም የአስር ዓመቱ ፍኖተ ካርታ ተጠቃሽ ነው። በፕላንና ልማት ኮሚሽን የተዘጋጀው የ2013- 2022 የአስር ዓመት የኢነርጂ ልማት ዕቅድ በአገር ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነት ከማረጋገጥ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የጥራት መስፈርቶችን የሚያሟላ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማቅረብን በዋነኝነት አቅዷል። በዚህም የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም በ2012 ዓ.ም 4478 ሜጋ ዋት ከነበረው በ2022 ወደ 19 ሺህ 900 ሜጋ ዋት ማሳደግ እንዲሁም ለጎረቤት አገራት የምትሸጠውን መጠንም ከ2ሺህ 802 ጊዋስ (GWH) ወደ 7 ሺህ 184 ጊዋስ (GWH) ለማድረስ ታቅዷል። አገሪቷ ከውሃ፣ ንፋስ፣ ጂኦተርማል፣ ጸሃይ፣ ባዮማስ ከፍተኛ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት የሚጠቀስ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በቅርቡ ማመንጨት የጀመረውን የህዳሴ ግድብ አንደኛ ዩኒት 375 ሜጋ ዋትን ጨምሮ 4890 ሜጋ ዋት ኃይል ታመርታለች። በ5ሺህ 150 ሜጋ ዋት ማመንጨት አቅሙ በአፍሪካ ትልቁ እንዲሁም በዓለም ስምንተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጠውን የህዳሴ ግድብ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት እየተቃረበች ሲሆን ይህም የአገሪቱን የኃይል አቅም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድግም የሚጠበቅ ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኢነርጂ ማዕከል ለመሆን በያዘችው እቅድ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 71 የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የ40 ቢሊዮን ዶላር ፍኖተ ካርታ ይፋ ማድረጓን ዘ አፍሪካ ሪፖርት ባለፈው ዓመት ጳጉሜ መጨረሻ ላይ ባወጣው ሪፖርት ይዟል። ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ 16ቱ የውሃ ኃይል፣ 24 በነፋስ፣ 17 በእንፋሎት እና 14 የጸሃይ ብርሃንን በመጠቀም ሲሆን ይህም ይላል የዘ አፍሪካ ሪፖርት ንጹህ ኢነርጂን በመጠቀም ረገድ በዓለም ላይ ትልቅ የፖሊሲ ለውጥን የሚያሳይ እንዲሁም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ንጹህ ኢነርጂን በመጠቀም ቀዳሚ እንድትሆን ያስችላታል ይላል። በዚሁ ዘገባ ላይ በአውሮፓውያኑ 2037፣ 35 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጫት አቅም ለመገንባት እቅድም እንደያዘች አስነብቧል። አገሪቷ ከአስር ዓመት ፍኖተ ካርታ በተጨማሪ በዘንድሮው ዓመት ይጠናቀቃል የተባለ በኤሌክትሪክ ዘርፍ የ25 ዓመት መሪ እቅድ እያዘጋጀች መሆኑንም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያሳያል። ለዚህም አገሪቱ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመገንባት እያደረገችው ላለው ጥረት የኤሌክትሪክ ኃይል ቀዳሚ ስራ በመሆኑ ዕቅዱን ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ድረ-ገጽ የተገኘው መረጃ ያሰረዳል። ዕቅዱ ከአሜሪካ መንግሥት በተገኘ አምስት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እርዳታ ደብሊው ኤስ ፒ ከተሰኘ የእንግሊዝ አማካሪ ኩባንያ ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61587303
amh
business
የኮሮናቫይረስ ተጽዕኖ በቻይናና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ
ቻይና በኮሮናቫይረስ በርካታ ዜጎቿን በሞት ከመነጠቋም በተጨማሪ፤ በምጣኔ ሃብቱ ረገድም በዋናነት እየተጎዳች ያለችው ቻይና ስትሆን ሌሎች አገራትም የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል። የመጣኔ ሃበቱ ጉዳት በቀጥታ ቫይረሱ በቀጥታ ያስከተው ብቻ ሳይሆን ቫይረሱን ለመከላከልም ከፍተኛ ወጭ ጠይቋል። 11 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት የዉሃን ከተማ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የከተማዋ መግቢያ መውጫ በሮች ተዘግተዋል። በሁቤይ ግዛት በሚገኙ ሌሎች ከተሞችም የሰዎችና የሸቀጦች ዝውውውር እንዲገደብ እየተደረገ ነው። ይህም ለከተሞቹ ትልቅ ኪሳራ ከፍተኛ ይዞ መጥቷል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎችም ወደ ሥራ ስንሰማራ ቫይረሱ ሊይዘን ይችላል በማለት ሥራ መስራትና ከሰዎች ጋር መገናኘትን አቁመዋል። ምግብ ቤቶች፣ ሲኒማዎች፣ የትራንስፖርት አቅራቢ ድርጅቶች፣ ሆቴሎችና ሱቆች የመጀመሪያዎቹ የምጣኔ ኃብት ቀውሱ ተጠቂዎች ናቸው። አምራቾችም ከቻይና ውጭም ገበያ ለማፈላለግ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። ዓለም አቀፍ አከፋፋዮችም ለጊዜው በቻይና ያላቸውን መደብር እየዘጉ እየወጡ ነው። አይኪያ የተባለው የቤት እቃ አምራች ኩባንያ እና ስታርባክስ አገልግሎታቸውን በቻይና ካቋረጡት ተጠቃሽ ናቸው። ቻይና በግዥው ሂደት በብዛት የምትሳተፍባቸው የኢንዱስትሪ ነክ ምርቶች በከፍተኛ ደረጃ በዓለም አቀፉ ገበያ ዋጋቸው ቀንሷል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ቢያንስ በ15 በመቶ ቀንሷል። ይህ ደግሞ የሆነው የቻይናው ግዙፉ የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ 'ሲኖፔክ' የማጣራት አቅሙን በመቀነሱ ነው ተብሏል። በርካታ የነዳጅ አምራች አገራት ዋጋውን እንደገና ለመጨመር የምርት መጠናቸውን ለመቀነስ እየተነጋገሩ ይገኛሉ። መዳብም በተመሳሳይ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በ13 በመቶ ከነበረበት ዋጋ አሽቆልቁሏል። አንድ የኦክስፎርድ ምሁር በቫይረሱ ምክንያት የቻይና ምጣኔ ሃብት በፈረንጆቹ 2020 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ4 በመቶ ባነሰ ያድጋል በማለት ትንበያቸውን አስቀምጠዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-51403845
amh
business
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ የእርዳታ ሥራዎቹ ሊገቱ እንደሚችሉ አስጠነቀቀ
በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ነዳጅና ምግብ መተላለፍ ባለመቻሉ የነፍስ አድን የምግብ እርዳታ አቅርቦት ሥራው ሊቆም መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስጠነቀቀ። ከአንድ ዓመት በላይ በሆነው ጦርነት ምክንያት ከታህሣሥ ጀምሮ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የእርዳታ ጭነት መኪኖች መቀለ ሊደርሱ እንዳልቻሉ ድርጅቱ ዛሬ ጥር 6/2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። በተጨማሪም ምግብ፣ ነዳጅና የገንዘብ ድጋፍ ዕጥረት እንዳጋጠመው የገለጸው ድርጅቱ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ላለባቸው ህጻናት እና ሴቶችን ለመንከባከብ የሚውለው አልሚ ምግብ ተመናምኗል ብሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የመጨረሻ ክምችት የሆነው እህል፣ ጥራጥሬ እና ዘይት በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚሰራጭም ጨምሮ ገልጿል። "በአሁኑ ወቅት የትኞቹን መመገብ እንዳለብን የትኞቹን ደግሞ እንዲራቡ ለመተው መምረጥ አለብን" በማለት የድርጅቱ የምሥራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ማይክል ደንፎርድ ገልጸዋል። አክለውም "በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ ለሰብዓዊ እርዳታ መተለላፊያ የሚሆኑ መንገዶች ደኅንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ዋስትና እንዲሰጡን እንፈልጋለን" በማለት አስረድተዋል። የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቶች በቀላሉ በሚፈለገው ፍጥነትና መጠን መድረስ እንዳልተቻለ የገለጹት ዳይሬክተሩ በትግራይ ባለው የምግብና የነዳጅ እጥረት ምክንያት ከሚያስፈልገው የእርዳታ መጠን መደረስ የተቻለው 20 በመቶ ብቻ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም በትግራይ ያለውን ሁኔታ ሲገልጹት "በሰብዓዊ ጥፋት አፋፍ ላይ ነን" ብለዋል። በዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃ መሰረት በሰሜን ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው ጦርነት ወደ 9.4 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህም አሃዝ ከአራት ወራት በፊት ከነበረው የ2.7 ሚሊዮን ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም እስካሁን ከታየው ከፍተኛው መሆኑንም የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል። በተጨማሪም ውጊያው ከመፋፋሙም ጋር ተያይዞ የምግብ ስርጭቱም በጣም ዝቅተኛ መሆኑንም ጠቁሟል። ድርጅቱ በትግራይ ለ2.1 ሚሊዮን፣ በአማራ ለ650 ሺህ እና በአፋር ለ534 ሺህ ሕዝብ የምግብ ዕርዳታ ለመስጠት አቅዷል። ሆኖም ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ባጋጠመው የገንዘብ ድጋፍ ዕጥረት ምክንያት በመላው ኢትዮጵያ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰጠው የምግብ እና ሌሎች እርዳታዎች አቅርቦት በሚቀጥለው ወር እንደሚያልቅም አስጠንቅቋል። በሰሜን ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ምግብ እርዳታ ለማድረስ 337 ሚሊዮን ዶላር እና ባበለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በሶማሌ ክልል በከፋ ድርቅ ለተጎዱ ነዋሪዎች እርዳታ ለማድረስ 170 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ጠይቋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎቶች አሁንም እንደተቋረጡ ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ታኅሣሥ 21/2014 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት መሰረት እርዳታ የጫኑ መኪኖች ከታኅሣሥ ጀምሮ ወደ ትግራይ አልገቡም። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ ያለውን ከአምስት ሚሊዮን በላይ እርዳታ ፈላጊ ሕዝብ ለመድረስ ከታሰበ በየሳምንቱ 100 እርዳታ የጫኑ መኪኖች ወደ ክልሉ ሊገቡ ይገባል ቢልም፣ እንደ ኦቻ ሪፖርት ወደ ክልሉ መግባት የቻለው ከሚያስፈልገው አቅርቦት ውስጥ 12 በመቶ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ እንዳይደርስ ምንም አይነት ክልከላ እንዳልጣለ ገልጾ፣ ሐሙስ ዕለት ባወጣው መግለጫ ደግሞ ወደ ክልሉ የእርዳታ አቅርቦት እንዳይገባ በማድረግ ህወሓትን ከሷል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59977324
amh
business
ለከብቶቻችን የምንሰጠውን ያደረ ዳቦ ለራሳችንም አጥተናል፡ አፍጋኒስታናውያን
አፍጋኒስታናውያን ናን የሚሉት ዳቦ አላቸው። ናን አምባሻ የሚመስል በእስያ ተወዳጅ ምግብ ነው። አፍጋኒስታናውያን ‘የዕለት እንጀራዬን አትንፈገኝ’ የሚሉት ይህን ዳቦ እያሰቡ ነው። መሃል ካቡል ሰማያዊ መስጂድ ይገኛል። በአቅራቢያው አነስተኛ ጉልት አለች። በዚህች ገበያ ትልልቅ ብርቱካናማ ከረጢቶች በደረቁ የናን ዳቦዎች ተሞልተዋል። ከዚህ ቀደም በየቦታው የሚተራርፉ ዳቦዎች ለእንስሳት ምግብነት ይውሉ ነበር። አሁን ግን ነገሮች ተቀይረዋል። ብዙ አፍጋኒስታናውያን ረሃባቸውን ለማስታገስ ወደ እነዚህ ዳቦዎች ፊታቸውን እያዞሩ ነው። ሻፊ መሐመድ የካቡል ፑል ኬሽቲ ገበያ ነጋዴ ነው። ላለፉት 30 ዓመታት ትኩስ ያልሆነ ዳቦ ይሸጣል። ስለገበያው ሁኔታ ሲገልጽም "በፊት በፊት በቀን አምስት ያህል ሰዎች ብቻ ነበሩ የሚገዙን።አሁን ከ20 ሰው በላይ ይገዛናል" ይላል። ያደረ ዳቦ ገበያው ደርቷል። ሁሉም ሰው በአገሪቱ ምጣኔ ሐብት መቆርቆዝ ቅሬታውን ይገልጻል። ታሊባን ባለፈው ነሐሴ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ወዲህ የዜጎች ገቢ በአንድ ሦስተኛ ቀንሷል። የምግብ ዋጋም ጣሪያ ነክቷል። ሻፊ፣ ሻል የሚሉ ዳቦዎችን ከላስቲክ ከረጢቱ ውስጥ እያወጣ ያሳያል። አልሻገቱም እንጂ የቆዩ ዳቦዎች ናቸው። ቢሆንም ለምግብነት የሚገዟቸው ብዙዎች ናቸው። "የአሁኑ የአፍጋኒስታናውያን ሕይወት ምንም ዓይነት ምግብና ውሃ እንደማታገኝ የታሰረች ወፍ ነው። ይህን መከራና ድህነት ከአገሬ እንዲወገድ እጸልያሁ" ይላል ሻፊ። የረሃብ ስጋት በመኖሩ ሰብዓዊ ድጋፍ ይሰጣል።ግን በቂ አይደለም። አፍጋኒስታን በልመና ዕርዳታ ላይ የተንጠለጠለች ናት። ታሊባን መንበረ ሥልጣኑን ሲቆጣጠር ምዕራባዊያን ይህንን ዕርዳታ አቋረጡ። የአገሪቱን ማዕከላዊ ባንክ ሐብትን ማገዳቸው ሲጨመርበት ደግሞ ቀውሱን አባባሰው። እርምጃው የተወሰደው ከሴቶች አያያዝ ጋር በተያያዘ በተነሳ ስጋት ነው። ታሊባን አዲስ ይፋ ባደረገው ጥብቅ ገደብ ከሴቶች አለባበስ ጀምሮ የተለያዩ ሕጎችን አሳልፏል። ይህም ውሳኔውን አስቸጋሪ አድርጎታል። ቀውሱ የሦስት ልጆች አባት እንደሆነው ሃሽማቱላህ ያሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ላይ ክንዱን አበርትቷል። የዕለት ጉርሱን የገበያተኞችን ዕቃ በመሸከም ያገኛል። ገቢው በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ካለፈው ዓመት አንድ አምስተኛውን ነው እያገኘ ያለው። የተረፈ ዳቦ የገዛበትን ፌስታል እያሳየ “ከነጋ በሠራሁት መግዛት የቻልኩት ይህንን ነው” ብሏል። የተረፈ ዳቦ ከሚሸጡት ሰዎች ጀርባ አንድ አነስተኛ ኢንዱስትሪ አለ። ቆሻሻ ሰብሳቢዎች ከምግብ ቤቶች፣ ከሆስፒታሎች እና ከግለሰብ ቤቶች ዳቦዎቹን ይሰበስባሉ። ከዚያም ለነጋዴዎች ይሸጣሉ።ገዢዎች ከእነዚህ ነው የሚገዙት። ግማሽ ያህሉ ሕዝብ ወደ ረሃብ አረንቋ እየተገፋ ነው። ይህ ደግሞ የተረፈ ዳቦ የማግኘት ዕድልን ያጠበዋል። ከአንድ ሳምንት በላይ የተሰበሰበውን አንድ ጆንያ የተረፈ ዳቦ እያሳየ  "ሰዎች እየተራቡ ነው" ይላል አንድ የተጣሉ ዕቃዎች ነጋዴ። ቀደም ሲል ግን በቀን አንድ ጆንያ ይሰበስብ እንደነበር ይናገራል። ሌላ ነጋዴ ደግሞ "ንጹህ ዳቦ ካገኘን ብዙውን ጊዜ ራሳችን እንበላዋለን" ብሏል። ሃሽማቱላህ የድሃዎች መናኸሪያ በሆነችው የካቡል ሰፈር በሚገኝው ቤቱ ለቤተሰቡ ምግብ ያዘጋጃል። ሦስቱ ልጆቹ እንዲማሩለት የቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ብዙ ወላጆች እንደሚያደርጉት ልጆቹን ወደ ሥራ ከመላክም ተቆጥቧል። ሕይወታቸው በበሰበሰ ቲማቲም እና ሽንኩርት እና በከረመ ዳቦ ላይ ተንጠልጥሏል። "በጣም ድሃ በመሆኔ እና ጥሩ ምግብ የማቅረብ አቅም ስለሌለኝ ቤተሰቦቼ ፊት አፍራለሁ" ይላል። "ምንም ማድረግ አልችልም። ልበደር ብልስ ማን ያበድረኛል . . . ልጆቼ ጥሩ ምግብ ስለማያገኙ በጣም ቀጫጭን ናቸው።" ብሏል ሃሽማቱላህ በተሰበረ ስሜት። ካቡል በሚገኙ ዳቦ መጋገሪዎች በር ላይ ህጻናት እና ሴቶች ተሰልፈው ማየት የተለመደ ነው። ምሽት ላይ ያልተሸጠ ትኩስ ናን ካገኘን በሚል ነው የሚሰበሰቡት። አንዳንዶች እዛው ቁጭ ብለው ልብስ ይሰፋሉ። ቤት ሆነው ሲሰፉ ዳቦ ከተሰጠ ዕድሉ እንዳያመልጣቸው ነው ይህን የሚያደርጉት። በአንድ ወቅት በቢሊዮን ዶላሮች ወደ አፍጋኒስታን ይፈስ ነበር።በዚያ ወቅትም ሙስና እና ጦርነት የዜጎችን ሕይወት ትግል አድርጎት ነበር። አሁን ጦርነቱ አብቅቷል። ከሕይወት ጋር ያለው ግብግብ ግን እየከበደ መጥቷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c0w7nnv9p24o
amh
business
አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገትን መተንበይ እንዳልቻለ አመለከተ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በአውሮፓውያኑ 2022 አስከ 2026 ባለው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ የሚኖራትን አጠቃላይ አገራዊ ምርት እድገትን (ጂዲፒ) መተንበይ እንዳልቻለ ገለጸ። ድርጅቱ ለዚህ እንደምክንያት ያስቀመጠው በምጣኔ ሀብቱ ውስጥ "ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ እርግጠኛ ያለመሆን" በመኖሩ እንደሆነ ገልጿል። ይህ የድርጅቱ አስተያየት የተገለጸው በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ አስራ አንድ ወራትን ያስቆጠረው ግጭትን ተከትሎ ነው። አይኤምኤፍ የዓለም ምጣኔ ሀብት ገጽታ ባሳየበት ሪፖርቱ ላይ በያዝነው የአውሮፓውያን ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ አገራዊ ምርት 2 በመቶ እድገት ያሳያል፣ ይህም ባለፈው ዓመት ከነበረው በአራት በመቶ ዝቅ ያለ ነው ብሏል። በንጽጽርም በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆነችው ጎረቤት ኤርትራ በመጪዎቹ 2022 - 2026 ባሉት ዓመታት የ4.8 በመቶ እድገት እንደሚኖራት ተተንብይዋል። በሌላ በኩል በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ትልቅ የሚባለው ምጣኔ ሀብት ያላት ኬንያ በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ የስድስት በመቶ እድገት ያሳያል ተብሏል። በተጨማሪም ጂቡቲ 5 በመቶ፣ ሶማሊያ 3.9 በመቶ፣ ደቡብ ሱዳን 6.5 በመቶ እንዲሁም ሱዳን 3.5 በመቶ እድገት ሊኖራቸው እንደሚችል ተተንብይዋል። ባለፉት አስር ዓመታት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት አስከ ሁለት አሃዝ የሚደርስ ፈጣን እድገት በማስመዝገብ ከሚጠቀሱ የአፍሪካ አገራት መካከል ውስጥ ቆይቷል። በወቅቱ ምጣኔ ሀብቷ ድርቅና የብሔር ግጭቶችን የመሳሰሉ ጫናዎች ያጋጠሙት ሲሆን፣ አገሪቱ ለግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ የምታውለው እየናረ የሚሄድ የውጭ እዳ ችግር ሊያስከትል ይችላል በማለት ባለሙያዎች ሲያሳስቡ ነበር። አይኤምኤፍ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ትንበያ ያላስቀመጠላቸው ሌሎቹ አገራት ግጭቶች ያሉባቸው አፍጋኒስታን፣ ሊቢያ እና ሶሪያ ናቸው። የድርጅቱ ሪፖርት የዓለም ምጣኔ ሀብት እድገትን በተመለከተ በሰጠው ትንበያ ባለንበት የአውሮፓውያን ዓመት 2021 5.9 በመቶ ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ግን 4.9 በመሆን ቅናሽ እንደሚያሳይ አመልክቷል። አይኤምኤፍ ለእድገቱ መቀነስ የአቅርቦት መናጋት እና እየተባባሰ ያለው የወረርሽኝ ሁኔታ በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ምጣኔ ሀብት ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58858523
amh
business
የኬንያው ሳፋሪኮም ኩባንያ ሠራተኞቹን ከኢትዮጵያ አስወጣ
የኬንያው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታ በአገሪቱ ለሚያካሂደው ኢንቨስትመንቶች አደጋ መደቀኑንና የሚፈጠሩት ክስተቶች የወደፊት የንግድ ውሳኔዎች ላይ ተዛማጅነት እንዳለው ለቢቢሲ ገለጸ። ኩባንያው በቅርቡ የተቀጠሩ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሠራተኞቹንና ተቋራጮችን ከአገሪቱ ማስወጣቱን አስታውቆ፤ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞቹ ደግሞ ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ እንደሚደረግ ገልጿል። በምሥራቅ እና በመካከለኛው አፍሪካ ትልቁ እና ትርፋማ የሆነው የቴሌኮም ኩባንያ፣ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ ጎረቤት ክልሎች እየተዛመተ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀች ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው። የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፒተር ንደጓ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ከወራት በኋላ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃድ ያሸነፈው ሳፋሪኮም በአውሮፓውያኑ 2022 አጋማሽ ላይ ሁሉም መሰረተ ልማቶች ከተዘረጉ በኋላ ሥራውን እንደሚጀምር ብሩህ ተስፋ አሳድረዋል። ቢቢሲ በዛሬ ረቡዕ ጠዋት አዲስ አበባ በሚገኘው የኩባንያው ጽህፈት ቤት በመገኘት ባደረገው ቅኝት አነስተኛ እንቅስቃሴ የተመለከተ ሲሆን ይህም በቅርብ ጊዜ የሚኖረው ሁኔታ ለኩባንያው እርግጠኛ አለመሆኑን ጠቋሚ ነው። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘውና በሳፋሪኮም የሚመራው የኩባንያዎች ጥምረት በመጀመሪያዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 2 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ እና ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ለመቅጠር አቅዷል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘው ይህ ጥምረት በዘርፉ አሉ የሚባሉ ስመ ጥር የቴሌኮም ኩባንያዎችንና ተቋማትን በቅንጅት የያዘ ሲሆን እነዚህም ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕና ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽንና ሲዲሲ ግሩፕ ናቸው። ሳፋሪኮም የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ለመደገፍ ከአሜሪካ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ይገኛል የተባለው የ500 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሁኔታ ላይ እርግጠኛ አይደለም። የአሜሪካ መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ላይ ከሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሏል። ከዚህም መካከል አጎዋ የተሰኘው የአሜሪካ ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ዕድል መታገድ ይገኝበታል። እንደ አውሮውያኑ በ2020 በአግዋ ሥርዓት አማካኝነት ኢትዮጵያ 237 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች ወደ አሜሪካ አስገብታለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-59235392
amh
business
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት የሚያስችል የጉምሩክ ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ መሆኑ ተገለፀ
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የሚደረገውን ጥረት በበለጠ ለመደገፍና ለማሳካት የሚያስችል የጉምሩክ ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የግብርናና የአምራች ዘርፉን በመደገፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ለመተካት የሚያስችል የሸቀጦች አመዳደብ ስርዓትን ያለመ ነው የጉምሩክ ታሪፍ ማሻሻያው። የቀረጥና ታክስ ማሻሻያው እስከ 8 ሺ የሚሆኑ የታሪፍ መስመሮች የሚያካትት ሲሆን ማሻሻያው ትኩረት ያደረገው በጥሬ እቃዎች፣ በከፊል የተመረቱ ግብአቶች፣ ካፒታል እቃዎች እንዲሁም መሰረታዊ የሚባል የፍጆታ እቃዎችን የሚያካትት ነው፡፡ የግብርናና የአምራች ዘርፉን በመደገፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ለመተካት የሚያስችል የቀረጥና የታክስ ማሻሻያው ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ለመተካት እንዲቻል ሁለት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። ይህም የአገር ውስጥ አምራቾች ከታሪፍ አንፃር ከውጭ ከሚገቡ ተመሳሳይ ምርቶች አኳያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው። የመጀመሪያው አቅጣጫ የምርቱ ዓይነት በአገር ውስጥ በሚፈለገው መጠንና ጥራት የሚመረት ከሆነ ከውጭ በሚገባው ተመሳሳይ ምርት ላይ ከፍተኛ የታሪፍ ምጣኔ ይጣላል። በዚህም የአገር ውስጥ ምርት ይበልጥ ተወዳዳሪ እንዲሆን ማድረግ ያለመ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ምርቱ በአገር ውስጥ በብቃት የማይመረት ከሆነ በአገር ውስጥ ለሚያመርቱ አምራቾች እነዚህን ምርቶች ለማምረት የሚጠቀሙባቸው በአገር ውስጥ የማይገኙ ግብአቶች በዝቅተኛ የታሪፍ ምጣኔ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያስገቡ ማድረግ ነው፡፡ በአገር ውስጥ በብቃት የማይመረቱ ምርቶች ላይ ከውጭ በሚገቡበት ወቅት ከፍተኛ የታሪፍ ምጣኔ አይጣልም ተብሏል ለዚህም እንደ ምክንያትነት የተጠቀሰው የዋጋ ንረት የሚያስከትል በመሆኑ ነው። ማሻሻያውን ተግባራዊ ለማድረግ እስከ 8 ሺህ የታሪፍ መስመሮች የሸቀጥ አመዳደብ ስርአትን የያዘ የታሪፍ መለያ ዝርዝር ኮዶችን የያዘ የታሪፍ ጥራዝ (Tariff Book) ተዘጅቷል። የቀረጥና ታክስ ማሻሻያው በሁሉም ዘርፎች በቀጣይ 10 ዓመታት በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትና ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለውም ተብሏል። ከዚህም በተጫማሪ ማሻሻያው ኢትዮጵያ በንግድ ዘርፍ ለምታደርጋቸው ስምምነቶች መሰረት የሚጥል እንደሆነም ተገልጿል። ማሻሻያው ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሁም ከጉምሩክ ኮሚሽን በተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች በተቋቋመ የታሪፍ ኮሚቴ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58089454
amh
business
ኮሮናቫይረስ፡''አፍሪካ ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝ ይከብዳታል'' የዓለም ጤና ድርጅት
የዓለም ጤና ድርጅት ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለአፍሪካ በእጅጉ አስጊና ከባድ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል። ድርጅቱ አክሎም ወረርሽኙ በተለይ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ አስጊ እንደሆነ አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ይህንን ያለው በርካታ አገራት የእንቅስቀሴ ገደቦችንና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን ማላላት መጀመራቸውን ተከትሎ የቫይረሱ ስርጭት እንደገና ማንሰራራት በመጀመሩ እንደሆነ ተጠቁሟል። የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚያቸውን ለማነቃቃት በማሰብ ወደቀደመው እንቅስቃሴያቸው መመለስ መጀመራቸው ቫይረሱ ከቁጥጥር ውጪ እንዲሆን እድል እንደሚፈጥር ድርጅቱ አስጠንቅቋል። በርካታ አገራትም በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ እንቅስቃሴዎችን እንደገና እያስጀመሩ መሆኑ እንዳሳሰብው ጠቁሟል። ድርጅቱ አክሎም ነገሮች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ እንደአዲስ ተንሰራፍቶ አገራት ተመልሰው ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ ማገድ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ አስታውቋል። አፍሪካ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ካጋጣት የኢኮኖሚ ውድቀት ለማገገም እንዲሁም የጤና ወጪ 1.2 ትሪሊየን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም [አይኤምኤፍ] ማስታወቁ የሚታወስ ነው። ገንዘቡ ያስፈልጋታል የተባለው ደግሞ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ነው። በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ እንዲሁም የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሌሎች አህጉራት ያነሰ ነው፤ ነገር ግን የዓለም ባንክ በወረርሽኙ ሳቢያ ተጨማሪ 43 ሚሊዮን የሚሆኑ አፍሪካዊያን ለከፋ ድህነት የመጋለጥ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብሏል። በወረርሽኙ ሳቢያ የሥራ እድሎች በመታጠፋቸው እና የቤተሰብ ገቢ በ12 በመቶ በመቀነሱ የደረሰው የኢኮኖሚ ተፅእኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ እየታየ የነበረውን ጠንካራ እድገት እየቀለበሰው መሆኑም ተጠቁሟል። አይኤም ኤፍ የአፍሪካ አገራት ከደረሰባቸው ተፅዕኖ እንዲያገግሙ 26 ቢሊዮን ዶላር የለገሰ ቢሆንም፤ የግል አበዳሪዎች እና በሌሎች አገራት ድጋፍ ቢኖርም፤ አሁንም ግን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እጥረት አለ። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ማሺዲሶ ሞዌቲ እንዳሉት አህጉሪቱ የሚገባትን የክትባት ድርሻ እንድታገኝም ከአሁኑ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። በአፍሪካ እስካሁን 1.6 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ወረርሽኙ አህጉሪቱ ውስጥ መግባቱ ከተሰማባት ዕለት አንስቶ ደግሞ ከ39 ሺ በላይ ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54574582
amh
business
ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ምርት አቋርጦ የነበረው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ወደ ሥራ ተመለሰ
በአካባቢው ባለው ጸጥታ ችግር ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት በመስተጓጎሉ የስኳር ምርቱን አቋርጦ የነበረው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ዳግም ወደ ሥራ መመለሱን የስኳር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን ተጠባባቂ ሥራ አስፈፃሚ ለቢቢሲ ገለጹ። ፋብሪካው ለሰባት ቀናት ያህል ከየካቲት 02፣ 2014 ዓ.ም ሥራ አቁሞ የነበረ ሲሆን የካቲት 8 ዳግም ወደ ሥራ መግባቱን የኮርፖሬሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረታ ደመቀ ተናግረዋል። በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የነዳጅ ጫኝ አሸከርካሪዎች ስጋት አድሮባቸው ወደ ቦታው ሊሄዱ ባለመቻላቸው ነበር የነዳጅ እጥረት ያጋጠመው። "በአሁኑ ወቅት በያዝነው ሳምንት ሰኞ የነዳጅ አቅርቦት በመድረሱ ማክሰኞ ዕለት ፋብሪካው ዳግም ወደ ሥራ ተመልሷል" ብለዋል ሥራ አስፈጻሚው። ብሉምበርግ ፋብሪካው ሥራውን ለማቆም የተገደደው የኦሮሞ ነፃነት ጦር ወይም መንግሥት "ሸኔ" የሚለው ታጣቂ ቡድን በፋብሪካው ላይ ባደረሰው ጥቃት ምክንያት ነው በሚል አስነብቧል። አቶ ረታ በበኩላቸው ፋብሪካው ሥራ አቋርጦ የነበረው በአካባቢው አልፎ አልፎ በሚፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት በመስተጓጎሉና እጥረት በመፈጠሩ ነው ብለዋል። ከሳምንታት በፊት አራት ያህል ትራክተሮች ተቃጥለው የነበረ ቢሆንም ይህ ግን ፋብሪካው ሥራ እንዲያቆም አላደረገውም ይላሉ። "ፋብሪካው ብዙ ሺህ ሄክታር የአገዳ መሬት ያለው ሲሆን በዚያ ውስጥ ትራክተሮች ይንቀሳቀሳሉ። ትራክተሮቹ የተቃጠሉትም እዚያ መሃል ላይ ነው።" የሚሉት አቶ ረታ ማን እንዳቃጠላቸው የጸጥታ አካላት ምላሽ ሊሰጡበት እንደሚገባ ተናግረዋል። እንደ አቶ ረታ ከሆነ ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የአሁኑን ሳይጨምር ፋብሪካው ከዚህ ቀደም ሥራ ያቆመበት ጊዜ የለም። በዚያ አካባቢ አልፎ አልፎ የጸጥታ ችግር የሚያጋጥም ቢሆንም ፋብሪካው ላይ የተከሰተ ችግር አለመኖሩን አስረድተዋል። "መስመሩ ላይ የጸጥታ ችግር አጋጠመ ማለት ፋብሪካው ላይ ሊያጋጥም ይችላል ማለት አይደለም። ፋብሪካው ከዋናው መስመር ወደ አምሳ ሜትር ተገንጥሎ ነው የሚገኘው። ለብቻው ወደ ውስጥ ገብቶ ነው ያለው።"ይላሉ። በተጨማሪም ፋብሪካው የማኅበረሰቡ የጀርባ አጥንት እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ረታ "የአካባቢው ኅብረተሰብ እስከ ልጆቹ የሚተዳደረው በፋብሪካው ነው።" ብለዋል። አቶ ረታ አክለውም ፋብሪካው የቴክኒክ ችግር ሲያጋጥመው ለሰዓታት ሊያቆም እንደሚችልና አስፈላጊው ጥገና ተደርጎለት እንደሚቀጥል ገልጸው፤ ይህ ግን ማቆም የሚባል ሳይሆን ውስብስብ ማሽኖች ባሉት ፋብሪካ ውስጥ የተለመደ ሁኔታ እንደሆነ ያስረዳሉ። በሰባት ቀናት ውስጥ ፋብሪካው ምን ያህል ገንዘብ ወይም ምርት አጣ? የሚል ጥያቄ ቢቢሲ ለአቶ ረታ ያቀረበላቸው ሲሆን ፋብሪካው በአማካኝ በጥሩ የማምረቻው ወቅት በቀን 10 ሺህ ኩንታል እንደሚያመርት ጠቅሰው ሆኖም ፋብሪካው ምን ያህል እንዳጣ የተገመገመ ጉዳይ አለመኖሩን ተናግረዋል። በስኳር አቅርቦትስ ላይ መጉላላት ፈጥሮ ይሆን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም "አገሪቱ መተሃራ፣ ወንጂና ጥገናውን በቅርቡ ጨርሶ ወደ ሥራ የገባው በአካባቢው የሚገኘው አርጆ ዴዴሳ ፋብሪካን ጨምሮ ሌሎች ፋብሪካዎች በመኖራቸው የአንድ ፋብሪካ ሰባት ቀን ማቆም በስኳር ሥርጭት ላይ ምንም አይነት ተፅእኖ አይኖረውም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ይገኛል። ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ፋብሪካው በዓመት 270 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም አለው። ፋብሪካው ከስኳር ምርቱ በተጨማሪ ኢታኖል በማምረት ከቤንዚል ጋር ተደባልቆ ለተሸከርካሪዎች በነዳጅነት እንዲውል ያደርጋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60413928
amh
business
የአሜሪካን የአቪዬሽን ንግድ ሚስጥርን ሰርቋል የተባለው ቻይናዊ ተቀጣ
ቻይናዊው የስለላ ሠራተኛ የአቪዬሽን ኩባንያዎችን ምስጢር ለመስረቅ አሲሯል በሚል በአሜሪካ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ መባሉን የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት አስታወቀ። ዡ ያንጁን የተባለው ይህ ግለሰብ ከኢኮኖሚ ስለላ እና ከንግድ ምስጢር ስርቆቶች ጋር በያያዘ በቀረቡበት አምስት ክሶች ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን የ60 ዓመት እስራት እና ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቅጣት ይጠብቀዋል። ዡ ለመጀመሪያ ጊዜ በቁጥጥር ስር የዋለው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2018 ቤልጂየም ውስጥ ሲሆን ምናልባትም ለአሜሪካ ተላልፎ የተሰጠ የመጀመሪያው ቻይናዊ ነው ተብሏል። የቻይና ባለስልጣናት ትናንት [አርብ] ስለተላለፈው ውሳኔ የሰጡት አስተያየት ባይኖርም ቻይና ቀደም ብላ ክሱን መሰረተ ቢስ ስትል ውድቅ አድርጋው ነበር። የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ መሰረት ዡ በቻይና ደኅንነት ሚኒስቴር ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚሰራ የስለላ ባለሙያ ነው። ቻይናዊው ሰላይ ከአውሮፓውያኑ 2013 ጀምሮ በአሜሪካ እንዲሁም በሌላ አገራት ውስጥ የሚገኙ በርካታ ኩባንያዎች ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞችን ኢላማ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ነበር ተብሏል። ቻይናዊው እንደ አውሮፓውያኑ በ2017 የአንድ አቪዬሽን ሠራተኛን የጉዞ ወጪ በመሸፈን እና አበል በመክፈል፣ ወደ ቻይና ተጉዞ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገለጻ እንዲደረግ እስከመጋበዝ ደርሶ ነበር። ይህ በሆነ በዓመቱ ባለሙያውን የአንድ ንድፍ ሂደትን የተመለከተ መረጃን እንዲሰጠው ዡ ጠይቋል ተብሏል። ታዲያ ከኤፍ ቢ አይ ጋር ሲሰራ የነበረው ባለሙያው ምስጢራዊ የሆነ መረጃ የሚል ባለ ሁለት ገጽ ሰነድ ለዡ በኢሜይል ልኳል። በመቀጠል ዡ ለባለሙያው ሥራ በሚጠቀምበት ኮምፒውተሩ ላይ የፋይል ቅጂ እንዲልክለት ጥያቄ ያቀርባል። በተጨማሪም በቤልጂየም ውስጥ ባለሙያውን ለማግኘት ሞክሯል። ሆኖም በዚህ ሙከራው ቻይናዊው በቁጥጥር ስር ውሏል። የኤፍ ቢ አይ ረዳት ዳይሬክተር አለን ኮህለር "የቻይናን እውነተኛ ፍላጎት ለሚጠራጠሩ ይህ የማንቂያ ደወል ሊሆን ይገባል" ብለዋል። "የአሜሪካን ቴክኖሎጂ እየዘረፉ ኢኮኖሚያቸውን እና ወታደራዊ ኃይላቸውን ለማጠናከር እየተጠቀሙበት ነው" ሲሉም አክለዋል። ይህ ክስ የተሰማው በሁለቱ አገራት መካከል ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው። ቻይና በቅርቡ አዲስ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤልን ስትሞክር የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ታይዋንን ከማንኛውም የቻይና ወታደራዊ ወረራ ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል። እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ከሆነ የሲአይኤ ዳይሬክተር ቢል በርንስ ቻይናን ለአሜሪካ ትልቁ የቴክኖሎጂ ስጋት መሆኗን ገልጿል። ባለፈው ወር የስለላ ድርጅቱ ቻይና ላይ የሚያደርገውን የስለላ ጥረት እንደሚያሳድግ ገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59188531
amh
business
የናይጄሪያ አየር መንገዶች በአውሮፕላን ነዳጅ ጭማሪ ምክንያት የሀገር ውስጥ በረራዎችን ሊያቆሙ ነው
የናይጄሪያ አየር መንገዶች የአውሮፕላን ነዳጅ ጭማሮን በመቃወም ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የሃገር ውስጥ በረራዎችን ሊያቆሙ ነው። በተያዘው አመት ብቻ አራት እጥፍ ገደማ መጨመሩን ያስታወቀው የናይጄሪያ አየር መንገድ ኦፕሬተሮች (ኤኦኤን) ይህንም ሁኔታ መቋቋም አልተቻለም ብሏል። "በአለም ላይ ያለ የትኛውም አየር መንገድ ቢሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲህ አይነት አስደንጋጭ አጨማመርን ሊቋቋም አይችልም። ከዚህ ማገገም አይቻልም" ብሏል። ለጭማሬው ዋነኛ ምክንያት የሆነው ሩሲያ በየካቲት ወር ዩክሬንን መውረሯ ነው። የናይጄሪያን ዘጠኝ የሃገር ውስጥ አየር መንገዶችን የሚወክለው የናይጄሪያ አየር መንገድ ኦፕሬተሮች (ኤኦኤን) አየር መንገዶቹ ባለፉት አራት ወራት ውስጥ አገልግሎታቸውን እየሰጡ የነበሩት በድጎማ ነበር ብሏል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ በርካታ የበረራዎች መሰረዝ እንዲሁም መዘግየቶች የነበሩ ሲሆን ይህም አብዛኛውን ጊዜ ከአውሮፕላን ነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ እንደሆነ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል። የአውሮፕላን ቲኬቶች ዋጋም በአንዳንድ አየር መንገዶች በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በሶስት እጥፍ ጨምሯል። በናይጄሪያ ያሉ መንገደኞች በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ በመጣው የሃገሪቱ መገበያያ ገንዘብ ናይራ ነው ቲኬት የሚገዙት። ነገር ግን ነዳጅ አቅራቢዎች የሚከፈሉት በአሜሪካን ዶላር ነው። ናይጄሪያ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ የነዳጅ አምራች ብትሆንም ከሞላ ጎደል ሁሉንም የአውሮፕላን ነዳጇን ከውጭ ታስገባለች። አኦኤን ለመንግስት፣ ለፓርላማ አባላት፣ ለመንግሥታዊው የነዳጅ ኩባንያ እና ነዳጅ ሻጮችን ለሚወክለው ማኅበር የነዳጁን ዋጋ ዝቅ ለማድረግ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አስረድቻለሁ ብሏል። የዋጋ ጭማሮው በመንገደኞች ላይ ጫና መፍጠር የለበትም ሲል የሚከራከረው ተቋሙ "ቀድሞውንም ብዙ ችግሮች እያጋጠሟቸው በመሆኑ" የዋጋው ጫና እነሱ ጫንቃ ላይ ማረፍ የለበትም ብሏል። ስለታቀደው የስራ ማቆም አድማ መንግሥት እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-61369465
amh
business
የዓለማችን ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ
በዓለማችን ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ። ከተሞቹ ምርጥ የተባሉት ለኑሮ ባላቸው ምቹነት መሠረት ነው። አውሮፓዊቷ አገር የኦስትሪያ ዋና ከተማ ቪዬና ቀዳሚዋ የዓለማችን ምቹ ከተማ ተብላለች። በተከታይነት ደግሞ የዴንማርክ ኮፐን ሃገን እና የስዊትዘርላንድ ዙሪክ ከተሞች ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የካናዳ ከተማ የሆኑት ካልጋሪ እና ቫንኩቨር ደግሞ በአራተኝነት በቀጣይ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን፤ የስዊትዘላንዷ ጄኔቫ፣ የጀርመኗ ፍራንክፈርት፣ የካናዳዋ ቶሮንቶ፣ የኔዘርላንድስ አምስተርዳም፣ የጃፓን ኦሳካ እና የአውስትራሊያዋ ሜልበርን ቀዳሚዎቹን አስር ደረጃዎች ለመያዝ በቅተዋል። ይህንን ደረጃ ይፋ ያደረገው ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት እንደሚለው ከሆነ ከተሞች ለኑሮ ያላቸው ምቹነት ቢጨምርም ዓለም አቀፉ አማካይ ግን አሁንም ዝቅተኛ ነው ብሏል። ለኑሮ ምቹነት ከታዩት ጉዳዮች አንዱ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ተጽዕኖ መሆኑን ተጠቁሟል። የዩክሬን ጦርነት ደግሞ ኪዬቭ ከጥናቱ ውጪ እንድትሆን ሲያስገድዳት፣ በሩሲያዎቹ ሞስኮ እና ሴንት ፒተርስበርግ ውጤት ላይም ተጽዕኖ አሳድሯል። በዚሁ ጦርነት ምክንያት የምሥራቅ አውሮፓ ከተሞች ደረጃም ዝቅ ብሏል። የምዕራብ አውሮፓ እና የካናዳ ከተሞች ደረጃውን በመምራት ቀዳሚ ሆነዋል። ደማስቆ፣ ትሪፖሊ እና ሌጎስ ደግሞ ከማኅበራዊ አለመረጋጋት፣ ሽብር እና ግጭት ጋር ተተያይዞ በደረጃው መጨረሻ ላይ ለመገኘት ተገደዋል። በዘንድሮው ጥናት 33 አዳዲስ ከተሞች ተካተዋል። በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ከተሞች ብዙ መሻሻል አላሳዩም ተብሏል። የሶሪያዋ ደማስቆ በደረጃው የመጨረሻው ስፍራን ይዛለች። ቴህራን፣ ዱዋላ፣ ሃራሬ፣ ዳካ፣ ፖርት ሞርስባይ፣ ካራቺ፣ አልጀርስ፣ ትሪፖሊ፣ ሌጎስ እና ደማስቆ ናቸው የመጨረሻዎቹን አስር ደረጃዎች የያዙት። ለኑሮ ባላቸው ምቹነት መሻሻል ያሳዩ ከተሞችም ታይተተዋል። እነዚህ ከተሞች በአብዛኛው በምዕራብ አውሮፓ የሚገኙ የጀርመን፣ የዩናይትድ ኪንግደም እና የፈረንሳይ ከተሞች ናቸው። ፍራንክፈርት ካለፈው ዓመት 32 ደረጃዎችን በማሻሻል ሰባተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ በቅታለች። ሃምቡርግ ደግሞ ከ31ኛ ወደ 16ኛ ተመንድጋለች። የኒውዚላንድ እና የአውስታራሊያ ከተሞች ደግሞ ደረጃው ላይ ማሽቆልቆል አስመዝግበዋል። በዚህም ዌሊንግተን እና ኦክላንድ 46 እና 33 ደረጃዎችን ለመውረድ ተገደዋል። ድርጅቱ ይህን ደረጃ ለማውጣት የከተሞቹን መረጋጋት፣ የጤና ዘርፍ፣ ባህል እና አካባቢ፣ ትምህርት እና መሠረተ ልማት ከግምት ያስገባል። ይህንን ደረጃ ይፋ ያደረገው ተቋም የዩክሬን ጦርነት እና ኮቪድ በሚቀጥለው ዓመት በሚኖረው የከተሞች ለኑሮ ምቹነት  ደረጃ ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል ብለዋል። ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት ላለፉት 70 ዓመታት ኢኮኖሚያዊ ትንታኔዎች በመስጠት የሚታወቀው ሲሆን የዘ ኢኮኖሚስት ጋዜጣ እህት ኩባንያ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/clw4zjvpljjo
amh
business
የትኞቹ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ያላቸውን ስራ አቋረጡ?
ሰላሳ ዓመት ወደኋላ! ከሰላሳ ዓመታት በፊት በሶቭየት ኅብረት ኮምዩኒዝም ሲንኮታኮትና የሩሲያ በሮች ለኢንቨስትመንት እና ንግድ ሲከፈቱ ይህንን ዕድል ለመጠቀም የምዕራባውያን ኩባንያዎችን የቀደመ አልነበረም። ያኔ እንደ ኮካ ኮላ እና ማክዶናልድስ ያሉ ታዋቂ ኩባንያዎች በሩሲያ ስራ ሲጀምሮ የሩሲያ አዲሱ ጊዜ መጣ እስከመባል ደርሶ ነበር። የተለያዩ ምርት አቅራቢዎች፣ ማዕድን አውጪዎች፣ የህግ አማካሪዎችና በርካታ ድርጅቶች ቀስ በቀስ በሩሲያ ተስፋፉ። ሩሲያውያንም በሌዊ ጂንስ መዘነጥ እና የምዕራብያውያኑ ቅንጡ ምርቶችን መጠቀም ጀመሩ። ያ በር ከተከፈተ ሰላሳ ዓመታት ተቆጠረ። ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ አዲስ ነገር ተፈጠረ። ሩሲያ ዩክሬንን ወረረች። ይህንንም ተከትሎ በርካታ የምዕራባውያኑ ክባንያዎች በሩሲያ ያለውን ስራቸውን እያቆረጡ ነው። አፕል፣ ላንድ ሮቨር፣ ኤች ኤንድ ኤም እና ቡርቤሪን ጨምሮ በርካታ ኩባንያዎች በሩሲያ ያላቸውን የንግድ እንቅስቃሴ ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል። ለመሆኑ የትኞቹ ኩብንያዎች ስራቸውን እያቆሙ ነው? ሌሎቹስ ለምን ዝምታን መረጡ? የነዳጅ ኩባንያዎች ቢፒ የተባለው በነዳጅ ዘርፍ የሚሰራ ኩባንያ በዩክሬን ግጭት እንደተቀቀሰ ነበር በሩሲያ ያለውን ስራ እንዲያቆም ጫና የተደረገበት።ኩባንያው በሩሲያው ግዙፉ የነዳጅ አምራችና አቅራቢ ኩባንያ ሮስኔፍት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ቢኖረውም በቀናት ውስጥ ስራው እንደሚቋረጥ አስታውቋል። ሼል፣ኤክሶንሞቢል እና ኢኩዊኖር የተሰኙት በነዳጅ ዘርፍ የሚሰሩ ኩባንያዎችም ከባለአክሲዮኖች፣ ከመንግሥታት እና ከዜጎች በደረሰባቸው ግፊት በሩስያ ያላቸውን ኢንቨስትመንቶችን እናቆማለን ብለዋል። እነዚያ የነዳጅ አምራች እና አቅራቢ ኩባንያዎች ቀላል ዋጋ የሚሰጣቸው አይደሉም። የቢፒ የቅርብ ጊዜ ትርፉ በዘርፉ በአምስተኛ ደረጃ እንዲቀመጥ አድርጎታል። ሼል ከሩሲያው ግዝዙፍ የነዳጅ ተቋም ጋዝፕሮም ጋር ያለውን ግንኙነት ለማቋረጥ እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ሊከስር እንደሚችል ተገምቷል። በሌላ በኩል ቶታል ኢነርጂ በሩሲያ ውስጥ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ እንደማይደግፍ ተናግሯል። ነገር ግን ከተወዳዳሪዎቹ በተጻራሪ ከነባር ኢንቨስትመንቶቹ የመውጣት እቅድ የለውም። የመዝናኛ ዘርፍ የዋርነር ብሮስን አዲሱ 'ብሎክበስተር ዘ ባትማን' በሩሲያ እንደማይታይ ተረጋግጧል። ይህ በሀገሪቱ ለሚገኙ የፊልም አፍቃሪዎች መልካም ዜና አይመስልም። ፊልም አምራች ኩባንያው በዚሁ በሰሞነኛ ጉዳይ ምክንያት በሀገሪቱ ውስጥ አዳዲስ ፊልሞችን ላለመልቀቅ ወስኗል። ኔትፍሊክስ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም "ቀጣይ ፕሮጀክቶችን" ማገዱን ያስታወቀ ሲሆን " ወቅታዊ ሁኔታዎችን ተፅእኖ" እየገመገመገምኩ ነው ብሏል። ሁሉም ኩባንያዎች ከውሳኔ ላይ የደረሱት ሩሲያ ላይ በተጣሉ ማዕቀቦች ምክንያት አላደረጉም። ይልቅስ ለውሳኔያቸው መነሻ ያደረጉት በዩክሬን ባለው "ሰብአዊ ቀውስ" ነው። ነገር ግን ውሳኔው ለሩሲያ የሚያስተላልፈው ሌላ መልእክት ነው። ይህ መሆኑ የሩሲያውያንን የመገለል እንደሚጨምር ተገምቷል። የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አፕል በሩሲያ ውስጥ ሁሉንም የምርት ሽያጭ ያቆመ ሲሆን እንደ ፔይ እና አፕል ማፕ ካርታ ያሉ ሌሎች አገልግሎቶችን ላይ ገደብ አድርጓል። በተጨማሪም በሀገሪቱ የሚገኙ የሽያጭ ሱቆቹን ተዘግተዋል። በሞስኮ ላለፉት 24 ዓመታት ለሰራው አፕል ውሳኔው ራሱንም የሚጎዳው እንደሆነ ይታመናል። በሌላ በኩል አንዳንድ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከሃሰት መረጃ ጋር በተያያዘ በሩሲያ የሚገኙ አገልግሎቶች እየተገደበባቸው ነው። ለምሳሌ ፌስቡክ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ የዜና ድርጅቶችን ይዘት ማረጋገጥ እና ላማጋራት ፈቃደኛ አልሆነም ማለቱን ተከትሎ ሩሲያ ፌስቡክን ገድባለች። ምርት አቅራቢ ድርጅቶች ግዙፉ የስዊድን ፋሽን ኩባንያ ኤች ኤንድ ኤም በሩሲያ ስራውን ያቆመ ግዙፍ ምርት አቅራቢ ድርጅት ሆኗል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ኩባንያዎች ይህንን ፈለግ ሊከተሉ እንደሚችል ተዘግቧል። ኤች ኤንድ ኤም በዩክሬን ውስጥ " አሳዛኝ ሁኔታዎችን" ጠቅሶ ስራውን ሲያቆም ናይኪን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ብራንዶች በአሁኑ በሩሲያ ላሉ ደንበኞች ምርት ለማቅረብ ዋስትና እንደማይሰጡ ተናግረዋል። በሞስኮ ታዋቂው አደባባይ አቅራቢያ ግዙፍ መሸጫ ያለው 'ቡርቤሪ' የተሰኘው ብራንድ "በሩሲያ ውስጥ ትዕዛዞችን ላማድረስ አስቸጋሪ ስለሆነ" ሁሉንም ጭነት አቁሜያለሁ ብሏል። ሩሲያ በ2021 አምስተኛዋ ትልቅ የአውሮፓ የችርቻሮ ምርቶች ገበያ የነበረች ሲሆን 337 ቢሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ነው። አንዳንድ ብራንዶች ደግሞ ከተወሰነ ወደ ንግዱ የመመለስ እድል ካለ በሚል ሁሉንም መንገድ ዝግ አላደረጉም። ለዚያም ይመስላል በርካታ ድርጅቶች ሽያጫቸውን ሙሉ በሙሉ ከማቆም ይልቅ ጉዳዩን "እያጤንን ነው" ወይም "ስራ በማቆም ላይ ነን" እያሉ የሚኙት የሚል አስተያየትም የቀረበው። ተሽከርካሪ አምራቾች በሩሲያ ወረራ ምክንያት ወደ ሀገሪቱ ተሽከርካሪዎች ካቆሙት አምራቾች መካከል 'ጃጓር ላንድሮቨር'፣ 'ጄኔራል ሞተርስ'፣ 'አስቶን ማርቲን' እና 'ሮልስ ሮይስ' የተባሉት እውቅ ኩባንያዎች ይገኝበታል። በተጫማሪም የግንባታ መሣሪያዎች አምራቹ 'ጄሲቢ' በሩሲያሁሉንም ሥራዎች አቁሟል። አሁን መኪኖችን ወደ ሩሲያ ማጓጓዝ ከባድ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም የዓለም ሁለቱ ትላልቅ የባህር ማጓጓዣ ባለቤት ኩባንያዎች 'ኤም ኤስ ሲ' እና 'ሜሪስክ ' ከምግብ፣ ህክምና ቁሳቁሶች እና የሰብአዊ አቅርቦት በስተቀር ሌላ ምርት ለሩሲያ አንጭንም ብለዋል። እንደ ቮልስዋገን እና ቢኤምደብሊው ያሉ አንዳንድ የመኪና አምራቾች በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት የሚገኙ ፋብሪካዎች ላይ ከዩክሬን የሚቀረቡ የመኪና ክፍሎች ባለመኖራቸው ምርታቸውን ለተወሰ ጊዜ ለማቆም ተገደው ነበር። የህግ አማካሪ ድርጅቶች ከኮሚኒዝም መውደም በኋላ በሩሲያ ስራ ከጀመሩ ቀዳሚ ዘርፎች መካከል ትላልቅ አማካሪዎች እና የሕግ ኩባንያዎች ይገኙበታል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችውን ወረራ ተከትሎ አብዛኞቹ ዝምታን መርጠው የቆዩ ቢሆንም መሰረቱ ዩኬ የሆነው 'ኬፒኤምጂ' የተሰኘው አማካሪ ኩባንያ ሃላፊ ጆናታን ሆልት ከማዕቀቡ ጋር በሚናበብ መልኩ ከደንበኞቻቸውን ጋር ያለንን ግንኙነት እየገመገምን ነው ብለዋል። ይህ ማለት በዩናይትድ ኪንግደም እና በመላው አለም ያሉ አንዳንድ ግንኙነቶችን ማቋረጥ ሊሆን እንደሚችልም ተናግረዋል። ሌላው 'ኢዋይ' የተሰኘው አማካሪ ድርጅት ማዕቀቡን እንደሚያከብር የገለጸ ቢሆንም በሩሲያ ከሚገኙ ከማንኛቸውም ደንበኞች ጋር ያለውን ግንኙነት አቋርጣለው ወይም አላቋርጥም ብሎ እርግጡን አልተናገረም። ሌሎች የህግ እና አማካሪ ድርጅቶች የደንበኞቻቸውን ከሩስያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እናጤናለን ብለዋል። የ'ማክኪንሴ' አማካሪ ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ኩባንያው "ከእንግዲህ በሩሲያ ውስጥ ማንኛውንም የመንግስት አካል እንደማያገለግል" በማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፍ ላይ አጋርቷል። ማን ቀረ? ሩሲያ በማዕቀብ ጎርፍ በምትጥለቀለቅበት በዚህ ሰዓት ተጨማሪ እውቅ ብራንዶች በሩሲያ ስራ እንዲቆሙ ጥሪ እየቀረበላቸው ነው። ሆኖም ለአንዳንድ ኩባንያዎች ይህንን ማድረግ በጣም ከባድ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት እና ሳምንታት ውስጥ ጫናው እየበረታ ቢሄድም በሩሲያ ስራ ማቆም ለነዚህ ድርጅቶች አስቸጋሪ ይሆናል። የምዕራባውያን ማዕቀቦች ለመቋቋም የሩስያ መንግሥት የሩስያ ንብረቶችን ሽያጭ አግዷል። ይህ በመሆኑ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በሩሲያ ውስጥ ስራ የጀመሩ ክባንያዎች ንብረት ሽጦ ሀገር ጥሎ የመውጣት መንገዱ ተዝግቶባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60598954
amh
business
ሕይወት ከመሠረታዊ አቅርቦቶች ውጪ በሆነችው ትግራይ
ኑሮውን ሱዳን ካርቱም ያደረገው እና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ግለሰብ በቅርቡ መቀለ ለሚገኙ ቤተሰቦቹ የዕለታዊ ፍጆታ መግዣ ገንዘብ መላኩን ይናገራል። የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠ ወራት ወደ ተቆጠረባት መቀለ 40 ሺህ ብር መላክ ማሰቡን ያወቁ እና ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ ግለሰቦች፣ ገንዘቡን ለቤተሰቦቹ ለማድረስ 20 ሺህ 800 ብር እንዲከፍላቸው እንደጠየቁት ለቢቢሲ ገልጿል። ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ውስጥ በሕጋዊነት የሚሰራ አንድም የፋይናንስ ተቋም ባይኖርም፣ መቀለ ለሚገኙ ቤተሰቦቹ ገንዘቡን እናደርሳለን ላሉት ግለሰቦች የተጠየቀውን ክፍያ በባንክ ሂሳባቸው ገቢ ማድረጉን ገልጿል። ይህ ግለሰብ አክሎም ይህንን እድል ያገኙ ሌሎች ሰዎችም በተመሳሳይ መንገድ መላክ ያሰቡትን ገንዘብ ግማሽ ያህል ክፍያ ለአቀባባዮች እየከፈሉ አገልግሎቱን እንደሚያገኙ ያስረዳል። ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የትግራይ አማፂያን የመቀለ ከተማን እና አብዛኛውን የትግራይ አካባቢ ከተቆጣጠሩ በኋላ ትግራይ ለአስር ወራት ያህል እቀባ ላይ ትገኛለች። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በጀመረው በዚህ ጦርነት ተቋርጠው የነበሩ መሠረታዊ አገልግሎቶች ለተወሰኑ ወራቶች አገልግሎት መስጠት ጀምረው የነበሩ ቢሆንም፣ የፌደራል መንግሥቱ መቀለን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ ዳግም ሙሉ በሙሉ ቆመዋዋል። 'የተራበች ከተማ' የመቀለ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ገብራይ ገዛኸኝ ከመስከረም ወር ጀምሮ 'ራሳችን ለራሳችን' [ባዕልና ንባዕልና]' በተሰኘ ፕሮጀክት ዘወትር ማለዳ ዳቦ እና ሻይ ይቀርብላቸዋል። እኚህ የዕለት እንጀራቸውን ከበጎ አድራጎት ድርጅት የሚያገኙ አዛውንት ቢቢሲ ቃለመጠይቅ ሲያደርግላቸው ችግራቸውን እና ብስጭታቸውን የገለፁት በዘፈን ነበር። " ድሮ ኪሮስ አለማየሁ . . . ወላጅ ከልጁ ተለያየ፤ በከፋ ረሃብ ሬሳ መሰለ. . . በአፈሙዝ ሰላሙን አጣ. . . ብሎ ነበር። ዛሬም ይህ ተደገመ" ካሉ በኋላ "የሚላስ የሚቀመስ አጥተን የልጆቻችን ድምጽ ርቆብን እየኖርን ነው" ሲሉ በትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና ሕይወት እየከፋ መሄዱን ይናገራሉ። ከጦርነቱ በፊት የመቀለ ከተማ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ነዋሪ የነበራት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን ከተለያዩ የክልሉ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች በመጡ ተፈናቃዮች ተጨናንቃለች። በክልሉ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ከሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የተፈናቀሉ በመቶ ሺህ ዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በየትምህርት ቤቱ፣ የስብሰባ አዳራሾች፣ በአብያተ ክርስትያናት ውስጥ ተጠልለው በገንዘብ እና በየፍጆታ እቃዎች አቅርቦት እጥረት ለከፋ ችግር ተጋልጠው ይገኛሉ። አቶ ገብራይ "ረሃቡ ሁሉም ላይ ደርሷል፤ ትልቁም ሆነ ትንሹ ተርቦ ግራ ገብቶት ይገኛል። ገንዘብ፣ መጓጓዣ የለም። በቀን አንዴ በልተን 'ያልፋል' እያልን እንውላለን" ሲሉ የሚገኙበትን ሁኔታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዓለም ሰላም ፋውንዴሽን ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ሙሉጌታ ገብረ ሕይወት፣ በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ በሦስት ክፍል ባሳተሙት ጥናት ውስጥ "ያለውን ተጽዕኖ አልፋችሁ መግባት የምትችሉ ከሆነ ወደ መቀለ እንድትመጡ እንጋብዛችኋለን፤ እንደገባችሁ መጀመሪያ የምታይዋት የተራበች ከተማን ነው" በማለት ያለውን ችግር ገልፀውታል። ከአምስት ዓመት በፊት ጧሪ እና ተንከባካቢ የሌላቸው አረጋውያን ለማገዝ የተቋቋመው ከራዲዮን የአረጋውያን እርዳታ ድርጅት በአሁኑ ወቅት መቀለ ከተማ ውስጥ ለስደተኛ ሕጻናት እና እናቶች ምግብ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል። በከተማዋ ውስጥ ከቀን ወደ ቀን ለምጽዋት እጃቸውን የሚዘረጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንዳለ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አማኑዔል ገብረ ጻድቃን ይገልጻል። በጦርነቱ ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ከተማዋ የመጡ እና በርከት ያሉ ተንከባካቢ ወይንም ደጋፊ የሌላቸው ሕጻናት ጎዳና ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ተናግሯል። "ሁሉም ነገር ተዘግቶ ምግብ እና መድኃኒት በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። ገጠር እና ሌሎች አካባቢዎችን ይቅር እና መቀለን ብቻ ብንመለከት የከፋ ችግር ውስጥ ናት። ሐብታም የምትለው ደሃ ሆኗል፤ ደሃ የነበረው ደግሞ ከድህነት በታች ወርዶ ከባድ ችግር ውስጥ ይገኛል" ይላል። ከመስከረም 07/2014 ዓ.ም ጀምሮ የቁርስ ድጋፍ እየሰጠ የሚገኘው ይህ ማኅበር በአሁኑ ጊዜ ከ300 በላይ ተረጂዎች እንዳሉት አማኑኤል ይገልጻል። መጀመሪያ አካባቢ ሕዝቡ እርስ በእርሱ ይተጋገዝ የነበረ ቢሆንም እጁ ላይ የነበረውን እየጨረሰ በመምጣቱ ይህ መደጋገፍ መቀነሱን አክሎ ተናግሯል። "ከተማዋ ውስጥ ከእንባው ጋር የሚታገል፣ በጎዳናዎች ላይ ብቻውን እያወራ የሚሄድ፣ እጆቹን ዘርግቶ የሚለምን፣ በርካታ ሰው ማየት እየተለመደ ነው" ሲል አሁን በከተማዋ ያለውን ሕይወት ለቢቢሲ ገልጿል። "እስካሁን ሕዝቡ ተስፋ አልቆረጠም" የሚለው አማኑዔል፣ የመቀለ ነዋሪ ካለው ላይ እየሰጣቸው ለከፋ ችግር የተጋለጡትን እንደሚደግፉ ይናገራል። ትግራይ ውስጥ ከተለያዩ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚሰሩና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈሉ ግለሰብ ለቢቢሲ በሰጡት አስተያየት ከሰኔ 21/2013 ዓ.ም በኋላ ትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ "በጣም የሚሰቀጥጥ" እንደሆነ በተለይ ደግሞ ከባድ ውጊያ በተደረገባቸው እና "የኤርትራ ሠራዊት በነበረባቸው ቆላ ተንቤን እምባሰነይቲ፣ ማይ ቅነጣል እና ዕዳጋ ዓርቢን ውስጥ የከፋ ረሃብ አለ" ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ የተነሳ በርከት ያሉ ሰዎች የቤት እቃ፣ ጌጣጌጥ እና አልባሳትን እንዲሁም ቤታቸውን እስከ መሸጥ የደረሱ መኖራቸውን፣ በተጨማሪም ላለፉት ወራት ደመወዝ ያላገኙ መምህራን፣ ሐኪሞች እና ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች መለመን እንደጀመሩ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል። በተለያየ ወቅት ይፋ የሆኑ የዓለም ምግብ ድርጅት ሪፖርቶች ሰሜን ምዕራብ፣ ምሥራቅ እና ማዕከላዊ የትግራይ ዞኖች ከፍ ያለ የምግብ እጥረት የታየባቸው አካባቢዎች እንደሆኑ ያሳያሉ። ደመወዝ አልባ የመንግሥት ሠራተኞች የትግራይ ክልል እርሻ እና ገጠር ልማት ቢሮ በክልሉ ውስጥ ከዘጠኝ ወራት በላይ ደመወዝ ያልተከፈላቸው "220ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች ከባድ ችግር ውስጥ ይገኛሉ" ሲል ገልጾ ነበር። ከጥቂት ወራት በፊት ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ የመቀለ ዩኒቨርስቲ ሕክምና ፋኩሊቲ መምህር በበኩሉ ከ7000 በላይ የዩኒቨርስቲው ሠራተኞች ላለፈው አንድ ዓመት ደመወዝ ስላልተከፈላቸው ከባድ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግሮ ነበር። "ምንም ምንኳ የፌደራል አካል ብንሆንም የፌደራል መንግሥት ግን በጀት ሊልክልን አልቻለም" ሲልም ቅሬታውን አቅርቦ ነበር። የትግራይ ቴሌቪዝን የክልሉ ማኅበራዊ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደባልቀውን ጠቅሶ ባሰራጨው ዘገባ "በቅርብ ጊዜ እርዳታ ካልገባ ከግማሽ በላይ የትግራይ ሕዝብ ያልቃል" ሲል አስጠንቅቀዋ። "እቀባው እየበረታ በመሄዱ በመጥፋት አፋፍ ላይ እንገኛለን፤ እቀባው እስከ ሚያዚያ 09/2014 ድረስ ከቀጠለ ግማሽ የትግራይ ሕዝብ ያልቃል፤ ብዙዎች በመድኃኒት እጥረት እየሞቱ ነው። ለቤተሰቦቻቸው መሰረታዊ አቅርቦት ማቅረብ ባለመቻላቸው ደግሞ በርካቶች ራሳቸውን እያጠፉ እንዳሉ ሪፖርቶች እደረሱን ነው" ሲሉ ተናግረዋል። አንድ ሻማ 30 ብር የፌደራል መንግሥቱ ለስድስት ወራት ክልሉን ባስተዳደረበት ወቅት ትልልቅ ከተሞች ባንክ፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት እና መጓጓዣ ተጀምሮ የነበረው አገልግሎት ዳግም የትግራይ አማፂያን መቀለን ሲቆጣጠሩ ሙሉ በሙሉ ተቋጧል። ከዚህ ወዲህ በክልሉ የሚገኙ የፋይናንስ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው የገንዘብ እጥረት አጋጥሟል። የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋም ከእጥፍ በላይ ጭማሪ እንዳሳየም ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሰዎች ይገልጻሉ። ክልሉ ከዋናው የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት መስመር ጋር ስለተቆራረጠ መደበኛ እና ያልተቆራረጠ የመብራት አገልግሎት ማግኘት አለመቻሉንም ጨምረው ተናግረዋል። በርከት ያለ ሰው ሻማ እንደሚጠቀም የሚናገሩት እነዚህ ነዋሪዎች፣ በፊት ሦስት ብር ይገዙት የነበረውን ሻማ አሁን 30 ብር እንደሚከፍሉበት ያስረዳሉ። በክልሉ በርከት ያለ ገንዘብ በጥቂት ባለሃብቶች እና ነጋዴዎች ካዝና እንደሚገኝ፣ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ክልሉ የሚገቡ ሸቀጦች እና የሚደረጉ የገንዘብ ልውውጦች ከእጥፍ በላይ እንደጨመሩ አማኑዔል ይናገራል። ባለፉት ሳምንታት ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን መግለጫ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በክልሉ ውስጥ የባንክ፣ ነዳጅ እና የመድኃኒት ችግሮች እንዳሉ በማስታወስ አቅርቦቶች ላይ ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች አሉ በሚል ወቅሰዋል። አክለውም "በዚህ ጭንቀት ውስጥ እበለጽጋለሁ ብሎ ማሰብ ወንጀል ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ከክልሉ ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚያመሩ ነዋሪዎች የህወሓት ሊቀመንበር ባለፈው ወር ላይ በሰጡት መግለጫ "እቀባው ከባድ ነው፤ ችግር ውስጥ ነው ያለነው፤ ከባድ ማኅበራዊ ቀውስ ነው ያለው" ሲሉ ተናግረው ነበር። "በየወቅቱ ከአፋር፣ ከአማራ፣ ከምዕራብ ትግራይ የሚመጡ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ ነው። . . ." በማለት በክልሉ ያለው እቀባ እና ግጭቱ ያስከተለውን ጫና ዘርዝረው ነበር። እቀባው በትግራይ ክልል ውስጥ የሚፈናቀሉ ሰዎችን ቁጥር እንዳይጨምረው ስጋት እንዳላቸው የሚናገሩት ትግራይ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚሰሩት ግለሰብ ናቸው። ይህ ግለሰብ አሁንም ወጣቶች ሕጋዊ ባልሆነ መልኩ ከክልሉ እየወጡ ናቸው ብሏል። ". . . በተለይ በደቡብ ትግራይ፣ በራያ ቆቦ እና አፋር አድርገው ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ የሚሄዱ አሉ። በራያ አላማጣ መስመር ብዙ ሰው ከትግራይ እየወጣ ነው። ገንዘብ ከፍለው በደላላ ነው የሚወጡት" ይላል። የዓለም አቀፍ ተቋማት ምን ይላሉ? በአሁኑ ወቅት ወደ ክልሉ የሚገባው የሰብኣዊ እርዳታ አነስተኛ በመሆኑ እና በቀጠለው ጦርነት ምክንያት ስለሚደናቀፍ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ እንደተፈጠረ የዓለም አገፍ ድርጅቶች ይገልጻሉ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ትግራይ ውስጥ ብቻ 4.6 ሚሊዮን ሰዎች፣ ማለትም ከአምስት ሰዎች መካከል አራቱ የምግብ እህል እርዳታ ጠባቂዎች መሆናቸውን ይናገራል። ድርጅቱ አክሎም ከግማሽ በላይ ነፍሰጡር እና የሚያጠቡ እናቶች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉም አስታውቋል። በተጨማሪም የፌደራል መንግሥት እና የህወሓት አማፂያን ወደ ክልሉ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ የሚደርስበትን መንገድ እንዲያመቻቹ ሲጠይቅ ቆይተዋል። ወደ ክልሉ ሰብዓዊ እርዳታ ላለመግባቱ ግን ህወሓት አመራሮች እና የፌደራል መንግሥቱ እርስ በእርስ ይወነጃጀላሉ። ባለፈው ሳምነት መጨረሻ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት እስከ 454ሺህ የሚደርሱ ህጻናት በምግብ እጥረት እንደተጎዱ፣ ከ115 ሺህ ህጻናት ደግሞ በከባድ የምግብ እጥረት እንደተጠቁ አመልክቷል። አክሎም እስከ 120ሺህ የሚደርሱ ነፍሰጡር እና እንዲሁም ከ25 ሺህ በላይ ከእድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በምግብ እጥረት መጎዳታቸውን ገልጿል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጥር ወር መጨረሻ ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ 40 በመቶ የሚሆነው የትግራይ ሕዝብ "ለከባድ የምግብ እትረት" ተጋልጧል ብሏል። ይህ ሪፖርት 83 በመቶ የሚሆኑት የክልሉ ነዋሪዎች ምግብ እንደጨሰና ልመና ላይ ተሰማርተው በቀን አንድ ጊዜ ብቻ እየተመገቡ እንዳሉ ያመለክታል። በተጨማሪም አሁን በአፋር ክልል በኩል በቀጠው ግጭት የተነሳ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ሚያልፍበት ብቸኛው የሰመራ-አብዓላ መንገድ እንደዘጋው በተደጋጋሚ ተገልጿል። በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በክልሉ ውስጥ ያላቸው የእርዳታ አቅርቦት እና ነዳጅ ክምችት እንደተሟጠጠ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በመጓጓዣ እና ነዳጅ እጥረት ምክንያት እርዳታቸውን ለመቀነስ እንደተገደዱ አስታውቀዋል። እስከ መጋቢት 08/2022 (እኤአ) ባለው ጊዜ ውስጥም በአጠቃላይ 600 ሊትር ነዳጅ ብቻ እንደቀራቸው ገልፀዋል። የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ በትግራይ ክልል ያለው እቀባ መቀጠሉ እንደሚያሳስባቸው ገልፀው ነበር። አክለውም ". . .የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጨምሮ ሁሉም ወገኖች ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቀርባለሁ" ብለው ነበር። የዓለም ማኅበረሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ የቀጠለው ጦርነት በአፋጣኝ እንዲቆም እንዲሁም በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ እና ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እንዲፈቅዱ ቢጠይቁም እስካሁን ድረስ ግን የታየ ተጨባጭ ለውጥ የለም። ክልሉን የሚያስተዳድረው ህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን (ዶ/ር) ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በተዘዋዋሪ ንግግር እየተደረገ ነው ቢሉም ውይይቱ ተጨባጭ ለውጥ አምጥቶ አልታየም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባዔ ያካሄደው ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል ያለውን ችግር ለመፍታት ማንኛውንም የሰላም አማራጭ እንደሚጠቀም ገልጿል። ይህ ግን ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ መገመት እጅጉን ከባድ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-60735701
amh
business
የእስራኤሏ ቴልአቪቭ በዓለም ላይ በጣም ውድ ከተማ ተብላ ተሰየመች
የእስራኤሏ ከተማ ቴልአቪቭ በዓለም ካሉ ውድ ከተሞች የአንደኛነቱን ሰፍራ ያዘች። እየጨመረ ያለው ግሽበትና የአቅርቦት ሰንሰለት ችግር በዓለም አቀፍ ደረጃ ንረትን ከፍ ባደረገው ወቅትም ነው ቴልአቪቭ ለሰው ልጅ መኖሪያነት ውድ ከሆኑ ከተሞች የቁንጮነቱን ስፍራ የያዘችው። የእስራኤሏ ከተማ በአንደኛነት ስፍራ ስትቀመጥ የመጀመሪያ ሲሆን ፓሪስና ሲንጋፖር ተከታታዩን ስፍራ እንደያዙ ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት ያደረገው ጥናት ይፋ አድርጓል ። በዚሁ ተቋም መረጃ መሰረት ቴልአቪቭ ባለፈው አመት አምስተኛ ስፍራ ላይ ነበረች። በጦርነት የምትታመሰው የሶሪያ መዲና ደማስቆ በዓለም ላይ በጣም ርካሹን ስፍራ በመያዝ ደረጃዋን አስጠብቃለች። የዳሰሳ ጥናቱ በ173 ከተሞች ለሸቀጦች እና አገልግሎቶች የሚውለውን ወጪ በአሜሪካ መገበያያ ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ አወዳድሯል። ተቋሙ በአውሮፓውያኑ ነሐሴና መስከረም ባሉ ወራት የሰበሰበው መረጃ እንደሚያሳየው በአገራቱ ውስጥ የምንዛሬ ዋጋ በአማካይ በ 3.5 በመቶ የጨመረ ሲሆን ይህም ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የተመዘገበ ፈጣን የዋጋ ግሽበት አድርጎታል። የትራንስፖርት አገልግሎት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ የታየበት ዘርፍ ሲሆን ጥናት በተካሄደባቸው ከተሞች የአንድ ሊትር ቤንዚን ዋጋ በአማካይ 21 በመቶ ጨምሯል። በተቋሙ የዓለም የኑሮ ውድነት ደረጃ ላይ አንደኛ የሆነችው ቴል አቪቭ በዋነኛነት የእስራኤል መገበያያ ገንዘብ ሸከል ከዶላር ጋር ሲነፃፃር ማሽቆልቆል አሳይቷል። የአገር ውስጥ 10 በመቶ የሚሆነው የሸቀጦች ዋጋም በከፍተኛ ሁኔታ መናር ያሳየ ሲሆን ይህም በተለይ በምግቦች ላይ ታይቷል። ጥናቱ እንደሚያመለክተው ቴል አቪቭ በአልኮል እና ትራንስፖርት ዋጋ ከአለም ሁለተኛ ውድ፣ ለግል እንክብካቤ እቃዎች አምስተኛ እናም በመዝናኛ ዘርፉ ስድስተኛ ውድ ከተማ ሆና ተቀምጣለች። የቴል አቪቭ ከንቲባ ሮን ሁልዳይ ከሃሬትዝ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በተቋሙ ስሌት ውስጥ ያልካተተው የቤቶች ዋጋ መናር ከተማዋ ወደማትቋቋመው ደረጃ ላይ እያደረሳት እንደሆነም አስጠንቅቀዋል። "አገሪቱ በሙሉ በጣም ውድ እየሆነች እንደመጣች ሁሉ ቴል አቪቭ በጣም ውድ ሆናለች" ብለዋል። "በእስራኤል ውስጥ መሰረታዊው ችግር ሌላ አማራጭ ሁሉን ያሟላና ማእከል የሆነ ከተማ የለም። በአሜሪካ ኒውዮርክ፣ ቺካጎ፣ ማያሚ እና የመሳሰሉት አሉ። በብሪታንያ ውስጥ ታላቋ ለንደን፣ ማንቸስተር እና ሊቨርፑል አሉ። የኑሮ ውድነቱ በጣም ከባድ ከሆነ አማራጭ ወደሆኑት ሌሎች ከተሞች መሄድ ይችላሉ" ብለዋል። የዓለም ውድ ከተሞች በደረጃ የዓለም ርካሽ ከተሞች 169 አልማቲ 170 ቱኒስ 171 ታሽከንት 172 ትሪፖሊ 173 ደማስቆ
https://www.bbc.com/amharic/news-59493433
amh
business
ዛምቢያ፡ ድሮኖች ቀረጥ ያልከፈሉ ተሽከርካሪዎችን እያደኑ ነው
የዛምቢያ የግብር ባለሥልጣናት ቀረጥ ሳይከፍሉ እቃዎችን የሚያዘዋውሩ ከባድ መኪናዎችን ለመቆጣጠር ድሮኖችን መጠቀም ጀመሩ። ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ የዛምቢያ ገቢዎች ባለሥልጣን በድሮኖች በመታገዝ ከዋናው መንገድ በመውጣት ተደብቀው የነበሩ ሰባት ተሽከርካሪዎች መያዛቸውን አስታውቀዋል። • ያለአብራሪ በሚበረው የሰማይ ታክሲ ይጠቀማሉ? • ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት " ድሮኖቹ የፍተሻ ሠራተኞች በማይደርሱባቸው እንዲሁም አደጋ ባለባቸውና ጥንቃቄን በሚጠይቁ ቦታዎች ድረስ በመግባት አሰሳ ያደርጋሉ" ሲሉ የዛምቢያ ገቢዎች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ቶፕሲይ ሲካሊንዳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ሰባት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ፍተሻ ድሮኖቹ 'ካፒሪ ስርነጅ' በተባለ መንገድ በመግባት ማሰስ የጀመሩ ሲሆን ዋናው የተሽከርካሪ መንገድ ባዶ ሆኖ አግኝተውታል፤ ከዚያም ከዋናው መስመር 14 ኪሎሜትር በሚርቅ ጥሻ ውስጥ አመላክተዋል። በዛምቢያ ወደ ደቡብ አቅጣጫ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች በአብዛኛው ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ማላዊ፣ ወይም ታንዛኒያ የሚመጡ ናቸው። ኃላፊው ሲካሊንዳ እንዳስታወቁት አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች በጣም በርካታ እቃዎችን ይጭኑና ወደ ፍተሻ ጣቢያው ሲቃረቡ በትንንሽ መኪና ቀንሰው ይጭናሉ ይህም ባለሙያዎቹ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገቡ ምክንያት ሆኗል። የዛምቢያ የገቢዎች መሥሪያ ቤት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ገቢውን ለማሳደግ ተስፋ እንዳለው የቀረጥ ባለሥልጣናት ጨምረው ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-49404009
amh
business
በኢትዮጵያ በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት መመዝገቡ ተገለጸ
በኢትዮጵያ በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት እየተመዘገበ መሆኑን የአገሪቱ ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት ገለጸ። ምክር ቤቱ የዘጠኝ ወራት የምጣኔ ሀብት አፈጻጸምን ገምግሞ ባወጣው በዛሬው ግንቦት 2፣ 2014 ዓ.ም መግለጫ ላይ እንዳመለከተው የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብት ከፍተኛ ፈተና እየገጠመው ያለው ከዋጋ ግሽበት አንጻር መሆኑን ጠቁሟል። በዚህም የዋጋ ግሽበቱ በዋናነት በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መመዝገቡን ጠቅሶ፤ ይህም ካለፈው ዓመት የሚያዝያ ወር ጋር ሲነጻጸር የዋጋ ግሽበቱ 36.6 በመቶ መመዝገቡን አስፍሯል። ምክር ቤቱ ጨምሮም ባለፉት ሦስት ዓመታት የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አሐዝ ለማውረድ በርካታ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ጠቅሶ ነገር ግን በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ምክንያት የሚፈለገው ውጤት አልመጣም ብሏል። ለዚህም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የጥሬ ዕቃዎች ዋጋ መናር፣ በአገር ውስጥ ያጋጠሙ ግጭቶች እና የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት የፈጠረው ዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዋጋ ግሽበት እንዲያሻቅብ ምክንያት መሆኑን አመልክቷል። መንግሥት የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ የጠቀሰው መግለጫው፤ ከእነዚህም ውስጥ የመንግሥት ወጪን ከአገር ውስጥ ገቢ መሸፈን፣ የግብር ሥርዓቱን ማዘመን እና የተለያዩ ግብርን የተመለከቱ ማሻሻያዎች ማድረግ በቀጣይ ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሏል። ምግብ ነክ የሆኑና መሠረታዊነታቸው የታመነባቸው የፍጆታ ዕቃዎች በፍራንኮ ቫሉታ አሠራር ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱን እንዲሁም፣ የመድኃኒት፣ ነዳጅ፣ ማዳበርያ፣ ዘይት እና ሌሎችም መሠረታዊ ሸቀጦች ግዢ አቅርቦት አቅርቦት እንዲቀላጠፍ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል። ነዳጅን በተመለከተ ደግሞ ሁሉን አካታች ከሆነ የመንግሥት የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ በመውጣት ድጎማ ለሚያስፈልጋቸው አካላት ብቻ እንዲሆን እየተሠራ ነው ተብሏል። ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት በተፈጥሯዊና በሰው ሰራሽ አደጋዎች በተፈጠሩ ጫናዎች በእጅጉ መፈተኑን ገልጾ፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት እና ድርቅን በዋናነት አንስቷል። ቢሆንም ግን በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት ላይ የተመዘገበው ዕድገትን መሠረት በማድረግ የዓመቱ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት በአማካይ በ6.6 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል። ጨምሮም በአገሪቱ የብድርና ቁጠባ መጠን ላይ ጭማሪ መታየቱን በመጥቀስ፣ የባንኮች አጠቃላይ የቁጠባ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ25 በመቶ ከፍ ብሎ ወደ 1.6 ትሪልዮን ብር መድረሱ ተገልጿል። በዘጠኝ ወራቱ ውስጥ ከውጭ ንግድ 2.95 ቢሊየን ዶላር እንደተገኘና ከዚህ ውስጥ ደግሞ 2.05 ቢሊየን ዶላር የሚሆነው ከግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ የተገኘ ነው። በተከታይነት ደግሞ የማዕድን ዘርፉ 453 ሚልዮን ዶላር እና አምራች ኢንዱስትሪው 378.5 ሚልዮን ዶላር ገቢ ተገኝቶባቸዋል ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61394971
amh
business
"የቱሪስት ማግኔት" የሆነችው ቬኒስ ከተማን ጎርፍ እያስጨነቃት ነው
በዓለም አቀፍ ደረጃ የቱሪስት ማግኔት አላት የምትባለው የጣልያኗ ቬኒስ ከተማ በጎርፍ እየተፈተነች ነው። ጎርፉ ቬኒስን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አሳጥቷታል ተብሏል። በጎርፉ ምክንያት የውሃ መተላለፊያ የሆነው የከተማዋ ዋና አደባባይ ሴንት ማርክ ፣ትምህርት ቤቶችና ንግድ ቤቶች ተዘግተዋል። የጣልያን መንግስሥትም በዩኔስኮ ድረ ገፅ ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል። • ከባድ ዝናብና የጎርፍ አደጋ በአንዳንድ አካባቢዎች ጉዳት አስከተለ • ጎርፍ ባጠቃቸው የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ተጨማሪ ዝናብ ሊጥል ይችላል ተባለ ለውሃ እና ለስነ ህንፃዎቿ ጥበብ ቱሪስቶች የሚተሙላት ቬኒስን እያስጨነቀ ያለው ጎርፍ እርዝመት ማክሰኞ እለት 187 ሴ.ሜ ደርሶ ነበር ተብሏል። ቤታቸው በጎርፍ የተጎዳባቸው የቬኒስ ኗሪዎች እስከ አምስት ሺህ ዩሮ ሲያገኙ ንግድ ቤቶች ደግሞ 20 ሺህ ዩሮ ድረስ ካሳ ይሰጣቸዋል ተብሏል። ከመቶ በላይ ከሚሆኑ ደሴቶች የተሰራችው ቬኒስ በየአመቱ በጎርፍ የምትጠቃ ሲሆን የአሁን እንደ አውሮፓውያኑ በ1923 ተከስቶ ከነበረውና አስከፊ ከተባለው ጎርፍም የባሰ ነው ተብሏል። የጣልያን መንግሥት ለቬኒስ 20 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። ያለታካሚዎች ፈቃድ ቀዶ ህክምና ያደረገው የማህጸን ሀኪም ተከሰሰ
https://www.bbc.com/amharic/news-50437271
amh
business
ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን የሚወስነውን ቦርድ ልታቋቁም ነው
በኢትዮጵያ የዝቅተኛ የደመወዝ መጠንን የሚወስነው የደመወዝ ቦርድ ሊቋቋም መሆኑን ቢቢሲ ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ካገኘው መረጃ መረዳት ችሏል። በአሁኑ ወቅት የዝቅተኛ ደመወዝ ወለልን የሚወስነው የደመወዝ ቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ የተረቀቀ ሲሆን በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የበላይ ኃላፊዎች ምክክር ሲደረግበት ቆይቶ ደንቡ ወደሚፀድቅበት ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመላክ በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል። ይህ ቦርድ በኢትዯጵያ እስካሁን ድረስ ሲሰራበት የነበረው በአሰሪና ሠራተኞች ስምምነት የሚወስኑትን የአከፋፈል ሁኔታ በመቀየር የደመወዝ መጠን ላይ የሚወስን መሆኑን አቶ ፍቃዱ ገብሩ በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ዳይሬክተር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ሠራተኞች ደመወዛቸው በህግ ከተደነነገገው በታች እንዳይሆን የሚያደርግ ሲሆን፤ የቅጥር ግንኙነት ባለበት ሁሉ ተፈፃሚ ይሆናል። ደንቡ በአሁኑ ሰዓት በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን ከዚያ በኋላም የቦርዱ መቋቋም የሚቀጥል ይሆናል። የዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ምን አይነት ሁኔታዎችን ማካተት ይገባዋል? በምንስ ይወሰን? የሚሉትን ሁኔታዎች የሚወስነው ይህ ቦርድ በአራት አካላት የሚዋቀር ነው። አባላቱም በዋነኝነት ሠራተኞችና አሰሪዎች፣ መንግሥት፣ እንዲሁም የሲቪክ ማኅበራት የሚካተቱበት ይሆናል። የሲቪክ ማኅበራት የሚባሉት የባለሙያዎች ማኅበራት ሲሆኑ ለምሳሌም እንደ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበርና የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የመሳሰሉት በዚህ ቦርድ ውስጥ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አቶ ፍቃዱ ይናገራሉ። የደመወዝ ቦርዱ ዝቅተኛውን ወለልን የሚወስነው የባለሙያዎቹ ማኅበራት የሚያቀርቧቸውን መረጃዎችና የተለያዩ ጥናቶችን ግብአት በማድረግ፤ በተለይም በአገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ተፅእኖ በጥልቀት በማየት እንዲሁም የአሰሪዎችና ሠራተኞቸን ጥቅሞች ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ አቶ ፍቃዱ ያስረዳሉ። አቶ ፍቃዱ እንደሚሉት ምንም እንኳን የአገሪቱን ሁኔታ በጥልቀት በማየት ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ቢወሰንም በመርህ ደረጃ ግን ዓለም የሚከተላቸውን መሰረታዊ ጉዳዮች የሚያካትት ይሆናል። እነዚህ መሰረታዊ የሚባሉትም ሠራተኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመኖር የሚያስፈልጋቸው መጠን እንዲሁም በሌላ በኩል ኩባንያዎች፣ ተቋማትና አሰሪዎች የመክፈል አቅም ምን ይመስላል የሚለውን ያጤናል ይላሉ። የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በበኩላቸው ደንቡ ወደ ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከመላኩ በፊት ከመንግሥት፣ ከሠራተኞችና ከአሰሪዎች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን በማካተት የሦስትዮሽ ምክክርና ውይይት ተደርጎበታል ይላሉ። እንደ ሠራተኛ ማኅበር የራሳቸውን ጥናት እያካሄዱ ቢሆንም ሠራተኞችን በመወከል በዋነኝነት አንድ ሠራተኛ በደመወዙ መኖር መቻል አለበት የሚለውን ፅንሰ ሃሳብ የያዘ ነው ይላሉ። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የአንድን ሠራተኛ የኑሮ ደረጃ የቤት ኪራይ፣ መብራት፣ ውሃ፣ የትምህርት ቤት ክፍያ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎች ተደምረው ለአንድ ሰው ኑሮ በአማካይ ምን ያህል ይበቃል የሚለው ከግምት ውስጥ መግባት አለበት ይላሉ። በዚህም አንድ ሠራተኛ ራሱን አስተዳድሮ በአማካኝ ሦስት ወይም አራት ልጅ ማሳደግ የሚችልበት መጠን ሊሆን ይገባል ይላሉ። እንደ ምሳሌም የሚያነሱት በኢትዮጵያ ባሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተቀጥረው የሚገኙትን ሠራተኞችን ነው። አብዛኞቹ ከ750 አስከ 1000 ብር በወር ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞችን ጉዳይ "አሳዛኝና ሊሻሻል የሚገባው" ስለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። "አብዛኛው ሠራተኛ ምሳ በልቶ እራት መድገም የማይችል ነው። አንድ ሺህ ብር በኢትዮጵያ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ገበያ ተወጥቶ ምንም አይገዛም። አንድ ሳምንትም የሚያቆየው አይደለም። ከዚህ አንፃር እነዚህ ነገሮች ይሻሻላሉ ብለን እንጠብቃለን። ቢያንስ ሌላ ነገር ማድረግ ባይችል በልቶ ማደር ይችላል" ይላሉ። እነዚህንም ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት የሚሉት አቶ ካሳሁን ይህም ሁኔታ በባለሙያዎች ተጠንቶ ግብዓት ይሆናል ይላሉ። "ሆኖም ጉንጭ አልፋ ክርክር ሳይሆን መሬት ላይ ያለው ሳይንሳዊ ነገርን የተከተለ ነገር መኖር እንዳለበት በኛ በኩል ስንከራከርም፣ ስንወያይም፣ ስንመካከርም እሱን መሰረት አድርጎ ስለሚሆን ይሄንን ጥናት እያካሄድን ነው ያለነው" ይላሉ። አቶ ፍቃዱም በበኩላቸው የደመወዝ ቦርዱ ሠራተኞች ማግኘት የሚገባቸውን ብቻ ሳይሆን ኩባንያዎች መክፈል የሚችሉበትን ሚዛናዊነቱን በጠበቀ መልኩ የሚደራደሩበት መድረክ እንደሚሆን ያሰረዳሉ። መንግሥትም በነዚህ አካላት ላይ የማደራደር ሚና የሚኖረው ሲሆን በመጨረሻም ሠራተኞችና አሰሪዎች የተስማሙበት እንዲሁም ባለሙያዎች ጥናት ያደረጉበት ሆኖ በሕግነት ይፀድቃል ይላሉ። በተለይም እነዚህ ባለሙያዎች በማክሮ ኢኮኖሚው ላይ ይህ ቢወሰን ምን ያመጣል የሚለውን ነፃ አስተያየት እንዲሰጡ የማድረጉ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይጠቁማሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ በአጠቃላይ የማይቀጠረው ሰው 80 በመቶ ሲሆን የእርሻ ዘርፉ በአብዛኛው ከኢ-መደበኛ የሚመደብ ሲሆን በቤተሰብ ደረጃ የሚከናወን ነው። ገበያው ላይ የኢ-መደበኛውና መደበኛ ቅጥሩ ላይ ገበያ ያላቸው ተፅእኖና መመጣጠን ሊታይ ይገባዋል ይላሉ። እንደ ምክንያትነትም የሚያቀርቡት "ደመወዝ ተከፋዮችና ደመወዝ የሌላቸው ግለሰቦች በገበያው ላይ እኩል ተሳትፎ ስላላቸው ነው" ይላሉ። ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ባለሙያዎች በአገሪቷ የወቅቱ ሁኔታ ለምሳሌ ግሽበት፣ የገበያ መዋዠቅ፣ ወረርሽኞችንና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ክለሳ የማድረግ ሥራ ወቅቱን የሚቋቋምበት ሁኔታ ሊሰራ እንደሚገባ የሚጠቁሙት አቶ ፈቃዱ፤ በተለይም አገሪቱ እያለፈችበት ካለችው የዋጋ ግሽበት ጋር ተያይዞ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን መወሰን አስፈላጊ ነው ይላሉ። "ሠራተኛው የመግዛት አቅሙ ወርዷል። ሠራተኛው አሁን በሚያገኘው ደመወዝ መግዛት አልቻለም። በልቶ ማደር አይችልም" ብለዋል። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚመለከተው በአገሪቱ አሰሪና ሠራተኛ አዋጅ የሚተዳደሩትን ወይም በቀጣሪና በቅጥር ግንኙነት ያሉትን ነው። በአጠቃላይ መደበኛ የሆነውን የሥራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የግል ዘርፉ ኩባንያዎች፣ ተቋማት እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ይመለከታል። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለሉ የመንግሥት ሠራተኞች (ሲቪል ሠራተኞችን) አያካትትም እንዲሁም ኢ-መደበኛ የሆነውን የሥራ ዘርፍንም እንደማያካትት አቶ ካሳሁን ያስረዳሉ። የመንግሥት ሠራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ቦርዱ ለምን እንደማይወስን የሚናገሩት አቶ ፍቃዱ መንግሥት ቀጣሪ ስለሆነ ያው መንግሥት አትራፊ ስላልሆነ መሰረታዊ የሚባሉ ነገሮችን ወስዶ ነው የሚከፍለው ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-57340391
amh
business
ከወለድ ነጻ ባንክ ሥርዓት ለሚሰጠው 'ብድር' እንዴት ትርፍ ያገኛል?
የሼሪያ ሕግን መሰረት አድርጎ ሥራውን የሚያከናውነው እስላማዊ ወይም ከወለድ ነጻ የባንክ ሥርዓት ገንዘብ ሰጥቶ፣ አትርፎ መቀበልን ያወግዛል። ይህም በባንኩ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን በቅዱስ ቁርዓንም የተከለከለ በመሆኑ በቀዳሚነት የእስልምና እምነት ተከታዮችን ያገለግላል። ሆኖም የእምነቱ ተከታዮች ላልሆኑ ደንበኞችም ክፍት ነው። በተቃራኒው መደበኛው የባንክ ሥርዓት፣ የቁጠባ ሂሳብ ለሚከፍቱ ወለድ እየከፈለ ገንዘባቸውን ሲያስቀምጥ፣ ለሚያበድረው ገንዘብ ደግሞ ወለድ ይቀበላል። ይህም የመደበኛ ባንኮች ዋነኛ የትርፍ ምንጭ እና መንቀሳቀሻ ነው። ታዲያ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች ለሚያቀርቡት ገንዘብ እንዴት ትርፋማ ይሆናሉ? ከሦስት ወራት በፊት በኢትዮጵያ ሥራ የጀመረው ሂጅራ ከወለድ ነጻ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሙባረክ ሸሞሎ እንዲሁም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ከወለድ ነጻ ባንክ የሆነው የዘምዘም ባንክ የቢዝነስ ስትራቴጂ እና ኢኖቬሽን ዳይሬክተር ከድር አባስ ከወለድ ነጻ ባንክን ትርፋማ የሚያደርጉት በርካታ አስራሮች እንዳሉ ይጠቅሳሉ። ከወለድ ነጻ ባንክ ምንም እንኳን በእስልምና አስተምህሮት መሰረት ቢንቀሳቀስም የማትረፍ ዓላማ ያለው ነው። የዚህ የባንክ ሥርዓት ሥራዎች በሙሉ በባንኩ እና በደንበኛው መካከል ትርፍ እና ኪሳራን መጋራትን መሰረት የሚያደርግ ነው። "ደንበኞች ወደ እኛ ሲመጡ ትርፍንም ኪሳራንም ለመጋራት ወስነው ይመጣሉ ማለት ነው" ሲል የሚያስረዳው ሙባረክ "ደንበኞች የሚያስቀምጡት ገንዘብ ባንኩ የተፈቀዱ ቢዝነሶች ላይ ፋይናንስ አድርጎ ያ ፋይናንስ ትርፍ ካመጣ ከደንበኛው ጋር ትርፍ ይጋራል፤ ኪሳራ ይዞ ከመጣም ኪሳራን ነው የሚጋራው" በማለት ያብራራል። ይህም በተለያየ የባንኩ ሥርዓቶች የሚተገበር ሲሆን ደንበኞች ትርፍም ኪሳራም የማይጋሩበት እና ገንዘባቸውን በአደራ የሚያስቀምጡበትም አሰራር አለ። የባንክ ሥርዓቱ አሰራር ደንበኞች የሚፈልጉትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ገዝቶ ከማቅረብ፣ ከባለሀብቶች ጋር በጋራ ኢንቨስት እስከማድረግ የሚዘልቅ ነው። የሽያጭ ውል ፋይናንሲንግ ከወለድ ነጻ ባንክ 'የሽይጭ ውል ፋይናንሲንግ' በተሰኘው የብድር ሥርዓቱ፣ ባንኩ ደንበኛው ወይም 'ተበዳሪ' የሚፈልጋቸውን ንብረቶች ገዝቶ ያቀርባል። የባንኮቹ አመራሮች በሸሪአ ሕግ ወለድ የተከለከለ ቢሆንም ነግዶ ማትረፍ የተፈቀደ ስለመሆኑ ጠቅሰው፣ ባንኩ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት አድርጎ ወይም ቀደም ብሎ ከገዛቸው ንብረቶች ደንበኞች በዱቤ የሚወስዱበት አሰራር መሆኑን ጠቅሰዋል። የተገዛውን ንብረት ባንኩ ለደንበኛው ሲያቀርብ ከተገዛበት ዋጋ ጨምሮ እንደማንኛውም ንግድ የሚያተርፍ ይሆናል። ይህም በተለያየ መንገድ ይቀርባል፤ ለአብነት 'ሙራብሃ' የተሰኘው አገልግሎት ደንበኛው የሚፈልገውን አገልግሎት ወይም ምርት ባንኩ የገዛበትን ዋጋ እና የሚያተርፈውን በግልጽ አስታውቆ የሚያቀርብበት ሥርዓት ነው። የተገዛው ንብረት ወይም አገልግሎት በባንኩ ስም ሆኖ፣ ትርፉም ምርቱ ወይም አገልግሎቱ በጊዜ ውስጥ ሊኖረው በሚችል ዋጋ የሚሰላ ይሆናል። ይህ አገልግሎት በእስላማዊ ባንክ ከ50 እስከ 60 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ይህም እንደ ተሽከርካሪ እና ቤት ያሉ ንብረቶች የሚጠቃለሉበት ነው። ታዲያ እንደ ሙባረክ ገለጻ "ባንኮች እንደ ነጋዴ ገበያ ወጥተው በሽያጭ ያስተላልፋሉ ማለት ነው።" በሌላ በኩል 'ባይሰለም' የሚባለው አገልግሎት ደግሞ ለግብርና ሥራዎች የሚቀርብ ሲሆን ከወለድ ነጻ ባንኩ ለአርሶ አደሮች ገንዘብ በማቅረብ ትርፍ ወይም ኪሳራ የሚጋራበት ነው። በሌሎች አገራት ለማኑፋክቸሪንግ ሥራዎች ፋይናንስ የሚቀርበው ከዚሁ የባንክ አገልግሎት ነው። 'ኢስቲስና' የተሰኘው አገልግሎት ደግሞ በጊዜ ሂደት ለሚሻሻል ቢዝነስ የሚቀርብ ፋይናንስ ሲሆን፣ እንደ ህንጻ ግንባታ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያካትታል። ለአብነት ህንጻ መገንባት የሚፈልግ ሰው ከወለድ ነጻ ባንክ ገንዘብ ወይም 'ብድር' በሚፈልግበት ወቅት የህንጻውን ሙሉ እቅድ ያቀርብና ባንኩ ካመነበት ጨረታ አውጥቶ ያስገነባለታል። ከግንባታው በኋላም ባንኩ አትርፎ መልሶ ለደንበኛው የሚሸጥበት ነው። የሽርክና ፋይናንስ ይህ ሥርዓት ባንኩ ደንበኞች ላሏቸው የቢዝነስ ሃሳቦች ገንዘብ በማቅረብ ወደ ተግባር የሚቀይርበት ሲሆን፣ ባንኩ በድርሻ ወይም በውል ትርፍ ወይም ኪሳራ የሚጋራበት ነው። በዚህ አሰራር ኢንቨስትመንቶቹ ላይ የጋራ አመራር ሊሰጡም ይችላሉ። በዚህ ውስጥም 'ሙዳራባህ' ተጠቃሽ ነው። ይህ አገልግሎት ባንኩ ለደንበኛው ፋይናንስ የሚያቀርብበት ሲሆን ትርፍ ካለ በስምምነታቸው መሰረት በጋራ ይካፈላሉ። ኪሳራ ካለ ግን የባንኩ ብቻ ይሆናል። 'ሙሻራካህ' ደግሞ ከወለድ ነጻ የባንክ ፋይናንስ ዓይነት ሲሆን ደንበኛው ያለውን ካፒታል በማወጣት ከባንኩ ጋር ኢንቨስት የሚያደርጉበት ሲሆን፤ በጊዜ ሂደት ባንኩ ከንግድ ሥራው የሚያገኘው የትርፍ ድርሻ ሊቀር የሚችልበት ነው። በተጨማሪም እስላማዊ የባንክ ሥርዓት የተለያዩ አግልግሎቶች ወይም ምርቶችን በማከራየት፣ ዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በመሰማራት ወይም በሌሎች መንገዶች ትርፍ ሊያሰባስብም የሚችልበት መንገድ አለ። በእነዚህ ሂደቶች ሁሉ በዚህ ሥርዓት ስር ያሉ ባንኮች ገንዘብ ተቀበለው ያለምንም አገልግሎት ወይም ሽያጭ 'ገንዘብ ላይ ገንዘብ ጨምረው' እንዲሁም ከቅዱስ ቁርአን ጋር በማይጻረር መልኩ አለመስራታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል። ከወለድ ነጻ ባንክ 'ብድር' መመለስ ያልቻሉ ሰዎችን አይቀጣም። ፋይናንስ የቀረበለት ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ከባንኮቹ የወሰደውን ገንዘብ መመለስ ባይችል ወይም በሚጠበቅበት ጊዜ ባይመልስ "ቅጣት የሚባል መርህ የሼሪአ ሕጉ አያውቅም" በማለት ሙባረክ ይገልጻል። "መለኮታዊ ትዕዛዝ ነው። ሰዎች ላበደሯቸው ብድር አታስጨንቁ የሚል ነገር አለ። ሳታስጨንቋቸው በተጨማሪ ደግሞ ከቻላችሁ ተዉላቸው የሚል አለ። ስለዚህ ያንን [ቅጣቱን] አያውቅም" ብሏል። ሆኖም 'ለፍትሃዊነት' በሚል ዓለም አቀፍ የእስልምና ተቋማት የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ድርጅት ገንዘቡን በወሰደው ሰው ፍላጎት የሚፈጸም ወይም ደንበኛው ራሱን የሚቀጣበት የ3 በመቶ ቅጣት ደንግጓል። የተገኘው የቅጣት ገንዘብ ደግሞ የባንኩ ገቢ ሳይሆን ለእርዳታ ተቋማት የሚበረከት መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል። ከወለድ ነጻ ባንክ በኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዚህ መልኩ የሚተገበረው ከወለድ ነጻ የባንክ ሥርዓት በመደበኛ ባንኮች ውስጥ በመስኮት፤ በመደበኛ ባንኮች በቅርንጫፍ ደረጃ፤ የመደበኛ ባንኮች እህት ኩባንያ በመሆን ወይም እንደ ዘምዘም እና ሂጅራ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ ሆኖ ሊቋቋም የሚችልበት አማራጮች አሉት። በኢትዮጵያ ይህ አገልግሎት በመስኮት ደረጃ የተጀመረው ከስምንት ዓመታት በፊት ሲሆን፣ ሙሉ በመሉ ከወለድ ነጻ የሆነ ባንክ ሥራ የጀመረው ግን ከወራት በፊት ነው። በኢትዮጵያ መሰል አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሳይኖር መቆየቱ ከ13 ዓመታት በፊት የተጠነሰሰው እና በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከወለድ ነጻ ባንክ የሆነው ዘምዘም፣ በብዙ ውጣ ውረድ እንዲያልፍ አስገድዷል። ይህም የፋይናንስ አካታችነት ላይ ጥያቄ ያስነሳ ነበር። ይሁን እንጂ በ2011 ዓ. ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ የተለያዩ ከወለድ ነጻ ባንኮች አክሲዮን መሸጥ የጀመሩ ሲሆን ሁለቱ ባንኮች ደግሞ ከወራት በፊት ሥራ ጀምረዋል። ዘምዝዘም ባንክ ሥራ በጀመረባቸው አራት ወራት 30 ሺህ ደንበኞች እና 15 ቅርንጫፎች እንዳፈራ ከድር ገልጿል። ሂጀራ ባንክ ደግሞ በሦስት ወራት 14 ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲሆን ከ22 ሺህ በላይ ደንበኞች እንዳገኘ ሙባረክ ይናገራል። ነገር ግን ከወለድ ነጻ ባንኮች፣ አገልግሎቶችን በተመቻቸ ሁኔታ ለመተግበር የማያስችሏቸው ሁኔታዎች አሁንም መኖራቸውን የሚጠቅሰው ከድር፣ "ያለው የሕግ ማዕቀፍ ከመደበኛው ጋር የተቆራኘ ነው።...ከመንግሥት እሱን ከማስተካከል አኳያ ቀና ነገሮች አሉ" ብሏል። ሙባረክ በበኩሉ በብሔራዊ ባንክ ደረጃ ከወለድ ነጻ ባንኮችን የሚከታተል እና ሸሪአን መሰረት ያደረገ ተቆጣጣሪ አካል ሊኖር ይገባል ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59521754
amh
business
የሊባኖስ ባንኮች ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቆሙ
የሊባኖስ ባንኮች የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች አስፈላጊውን ጥበቃ አላደረጉልንም በሚል ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የአገሪቱ ባንኮች ማኅበር ገለጸ። ደንበኞች ባለፈው ሳምንት እንዳይንቀሳቀስ የተደረገውን የቁጠባ ሂሳባቸውን ለማግኘት በኃይል ታግዘው ገንዘባቸውን የመውሰድ ድርጊቶች መበራከታቸውን ተከትሎ ነው የሊባኖስ ባንኮች ማኅበር አገልግሎት መቆሙን ያስታወቀው። በአገሪቱ የሚገኙ ባንኮች ውስጥ የሚያገለግሉ ሠራተኞች መፍትሄ ማግኘት ያልቻሉ የደኅንነት ስጋት ገጥሟቸዋል ሲልም ማኅበሩ ገልጿል። ባሳለፍነው ሳምንት አንዲት ግለሰብ የልጆች መጫወቻ ሽጉጥ በመያዝ ለቤተሰቧ መድኃኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ከባንኩ ለመውሰድ በባኩ ውስጥ ሰዎችን በማገቷ መነጋገሪያ ሆና ነበር። በሳምንቱ መጨረሻ አርብ ቀን ብቻ ቢያንስ አምስት ሰዎች ገንዘባቸውን በኃይል ከባንክ ለመውሰድ ጥረት ያደረጉበት ተመሳሳይ ክስተቶች ሪፖርት ተደርገው ነበር። በአሁኑ ጊዜ ሊባኖስ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝቧ የምግብ እና የመድኃኒት አቅርቦት ለማግኘት የሚያስችለው ገቢ የለውም። ደንበኞች በባንኮች ውስጥ ያላቸውን ገንዘብ በኃይል በመጠቀም የመውሰድ እምጃ በሕበረተሰቡ ዘንድ ድጋፍ አግኝቷል። ከዚህ በፊት ምንም አይነት የወንጀል ሪከርድ የሌላቸው ሰዎች የባንክ ሂሳባቸውን በጉልበት ለማንቀሳቀስ መጣራቸው በሕብረተሰቡ ዘንድ በተስፋ መቁረጥ ተገፋፍቶ የሚፈጸም ተደርጎ ይታያል። የሊባኖስ የመገበያያ ገንዘብ እኤአ ከ2019 ጀምሮ ዋጋው እያሽቆቆለ፣ ብሎም በአገሪቱ ያለው የዋጋ ንረት ከቁጥጥር ውጪ መሆኑን ተከትሎ ባንኮች ደንበኞቻቸው የሚያወጡትን ገንዘብ ገድበዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c99pqg8j2v8o
amh
business
በጥሬ ገንዘብ ዝውውር ላይ የተጣለው ገደብ ለምን አስፈለገ?
በኢትዮጵያ ከባንኮችና ከማክሮ ፋይናንስ ተቋማት በሚወጣ የጥሬ ገንዘብ ላይ የተጣለው እገዳ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። ብሔራዊ ባንክ ያወጣው መመሪያ ተቋማትና ግለሰቦች ከባንኮች በቀንና በወር ውስጥ በሚያወጡት የጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጥሏል። በዚህም መሰረት አንድ ግለሰብ በቀን እስከ 200 ሺህ ብር እንዲሁም በወር እስከ 1 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ከባንኮች ማውጣት የሚችል ሲሆን፤ ተቋማት ደግሞ በቀን እስከ 300 ሺህ ብር እና በወር እስከ 2.5 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶክተር) ይህንን እርምጃ መውሰድ ያስፈለገው "የገንዘብ ዝውውርን ሥርዓት በማስያዝ ወንጀልንና የግብር ስወራን ለመከላከል ይረዳል" በሚል ነው ብለዋል። ይህን የብሔራዊ ባንክ እርምጃን በተመለከተ የተለያዩ ምክንያቶችን በመጥቀስ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች አሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዋሲሁን በላይ አንድ አገር ላይ የኢኮኖሚ ፖሊስ ሲወጣ፣ ምጣኔ ሃብቱ እንዲረጋጋ፣ እንዲሁም ኢኮኖሚው ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ሲፈለግ ሁለት ዓይነት ኃይለ ፖሊሲዎችን እንደሚከተሉ ያስረዳሉ። በጀት ምን መምሰል አለበት፣ ሰዎችና የንግድ ተቋማቶች መክፈል ያለባቸው ግብር ምን ይመስላል ተብሎ የሚወሰንበትን እና የገቢዎች ሚኒስቴርና የገንዘብ ሚኒስቴር የሚቆጣጠሩት ፊሲካል ፖሊሲ አንዱ ሲሆን፣ ሞኒተሪ ፖሊሲ ደግሞ የብሔራዊ ባንክ የሚቆጠጣረው መሆኑን ያስረዳሉ። ብሔራዊ ባንክ ሲቋቋም ጀምሮ የአገሪቱ የገንዘብ አቅርቦት ምን መምሰል አለበት? ምን ያህል ገንዘብ ታትሞ በገበያ ውስጥ መሰራጨት አለባቸው? የሚለውን የመቆጣጠር የሥራ ድርሻው እንዳለው ያብራራሉ። በተጨማሪ ደግሞ በባንኮች በኩል ያለውን የወለድ መጠን፣ የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዋሲሁን፣ ብሔራዊ ባንክ በትናንትናው ዕለት ካሉት ሁለት ትልልቅ ስልጣኖች መካከል በመጠቀም የገንዘብ አቅርቦት በገበያው ምን መምሰል እንዳለበት ወስኗል ሲሉ ያስረዳሉ። እንደ ምጣኔ ሃብቱ ባለሙያ አስተያየት ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የገንዘብ መጠን ላለፉት ብዙ ዓመታት በእርግጠኝነት ማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው። "በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከ700 እስከ 800 ቢሊየን ብር ድረስ በገበያው መሰራጨቱ ይታወቃል የሚሉት የምጣኔ ሃብቱ ባለሙያ እርሱንም ቢሆን በእርግጠኝነት ለማወቅ አስቸጋሪ ነው" ሲሉ ያለውን ፈተና ያብራራሉ። ስለዚህ እዚህ ገበያ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ማወቅ እንደሚያስፈልግ በማንሳት "የገንዘብ መጠኑ የማይታወቅ ከሆነ የተለያዩ ሕጋዊ ያልሆኑ የንግድ ሥርዓቶች ሊበራከቱ ስለሚችሉ ብሔራዊ ባንክ ያንን ለማወቅ አስቦ እንደወሰነው እገምታለሁ" ይላሉ። ሌላው መንግሥት ባይጠቅሰውም የገንዘብ እጥረት የአገሪቱ አንዱ ችግር መሆኑን ይጠቅሳሉ። "ጥሬ ገንዘብ አቅርቦት በጣም እያነሰ ነው። የኮሮናቫይረስ ክስተትን ተከትሎና በሌሎችም ምክንያቶች ሰዎች ያላቸውን ገንዘብ በእጃቸው መያዝ ይፈልጋሉ" የሚሉት ባለሙያው ለመንግሥት የገንዘብ እጥረት ገጥሞኛል ብሎ መናገር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ ከባድ መሆኑን ይናገራሉ። "ወረርሽኙን ተከትሎ ሰዎች ለመድኃኒት፣ ለሕክምናና ለምግብ የሚሆኑ ወጪዎችን ብቻ ነው እያወጡ የሚገኙት" የሚሉት ባለሙያው በተጨማሪም ነገ በሚሆነው ነገር ላይ ተስፈኛ መሆን አለመቻል ገንዘብን በባንክ ለማስቀመጥ ፍላጎት እንደሚያሳጣ ይጠቅሳሉ። "አሁን በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ ከባንክ ቤቶች እየወጣ መሆኑ ግልጽ ነው" በማለትም ከበሽታው በፊትም ቢሆን የልማት ባንክ ያልተመለሱ የተበላሹ ብድሮች እንዳሉት ሲናገር በርካታ ባለሃብቶች ብድር ወስደው መክፈል አልቻሉም ማለት እንደሆነም ያስረዳሉ። ኢንቨስትመንት ላይ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ብድራቸውን መክፈል እንዲችሉ ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ሰዎች ያስቀመጡት ገንዘብ ባንክ ቤት ውስጥ የለም ማለት መሆኑን በማስረዳት ለገንዘብ እጥረቱ የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው ያብራራሉ። "መንግሥት ግን ይህንን ውሳኔ የወሰንኩት እጥረት ስለገጠመኝ ነው ብሎ ሊል አይችልም" በማለትም የገንዘብ እጥረቱ እየገጠመ ነው ወደፊት ደግሞ በፍጥነት ሊገጥም መቻሉ ገሃድ መሆኑን ያስረዳሉ። "ምክንያቱም ወደ በሽታው [ኮሮናቫይረስ] ገና እየገባንበት ነው ይላሉ። ወረርሽኙ እየተስፋፋ ሲመጣ፣ የሰዎች እንቅስቃሴ ሲገደብ፣ አሁን ገበያ ላይ ያሉት ነጋዴዎች አቅማቸው ሲዳከም፣ ገንዘባቸውን በእጃቸው ይዘው መጠቀም ሲመርጡና ለአስፈላጊ ነገሮች ብቻ ሲያወጡ፣ የባንክ ቤት ሰልፍ ጠልተው እያወጡ ሲያስቀምጡ ወደፊትም ቢሆን እጥረት መፈጠሩ አይቀርም ይላሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዋሲሁን በላይ። "ዜጎች በመጪው ጊዜ ላይ እርግጠኛ መሆን የማይችሉ ከሆነ ብራቸውን ስለሚይዙ የመቆጠብ አቅማቸው ደካማ ስለሚሆን የገንዘብ አቅርቦት እያነሰ ስለመጣ እርሱንም አስታኮ የወሰነው ይመስለኛል።" በተጨማሪነት ግን ኢንቨስትመንት እንዲያድግ ቁጠባን ለማበረታታት አስቦ መንግሥት የወሰነው እንደሚመስላቸው ባሙያው ጠቅሰው "ገንዘብ ከባንክና ከፋይናንስ ሥርዓት ውጪ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ አይፈቀድም።" ብዙ አገራቶች ይህንን ነገር እያስቀሩ መምጣታቸውን ገልጸው "ስለዚህ ብሔራዊ ባንክም የሆነ ቦታ ላይ ለጥሬ ገንዘብ ዝውውሮች ሥርዓት ማበጀት ነበረበት" ብለዋል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እርምጃ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ሲሉ እርምጃውን አጥብቀው ይተቻሉ። "ይሄ ይዞት የሚመጣው ነገር በጣም አደገኛ ነው። ከዚህ በኋላ ባለሃብቱ የሚከፈለውን ክፍያ በጥሬ ገንዘብ ይቀበልና ወስዶ ቤቱ ያስቀምጣል። ይህ ደግሞ ገንዘብ ወደ ባንክ ገብቶ እንቅስቃሴ እንዳይፈጠር ያደርጋል። ይሄ እርምጃ ከሚያመጣው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል" ይላሉ። ግብር ስወራን በተመለከተ ጉቱ (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ በኢትዮጵያ የሚጠበቅባቸውን ግብር ላለመክፈል 'ኪሳራ ደርሶብኛል' እያሉ ሪፖርት በማድረግ ግብር የሚያሸሹ በርካታ ነጋዴዎች መኖራቸው አይካድም ይላሉ። "ነገር ግን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ሰዎችን አሳደን የሚጠበቅባቸውን ግብር እንዲከፍሉ ማድረግ እንችላለን ወይ? ይህ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣል ወይ?" ሲሉ ይጠይቃሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው እንደሚሉት ከሆነ ይህ ዓይነት የመንግሥት ውሳኔ፤ "ከባንክ ውጪ ሊደረግ ወደ የሚችለው ልውውጥ ስለሚወስድ ምጣኔ ሃብቱን በአፍጢሙ ሊደፋ ይችላል" ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። ጉቱ (ዶ/ር) ይህ የመንግሥት ውሳኔ አገሪቱ ኮሮናቫይረስ ከሚያስከትለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ በኋላ ለማንሰራራት በምታደርገው ጥርት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችልም ያነሳሉ። "ከኮሮናቫይረስ ስርጭት በፊት የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የሚያበድሩት በቂ ገንዘብ አልነበራቸውም። ብሔራዊ ባንክ ራሱ ከተቀማጭ ገንዘቡ ማሻሻያ እያደረገ ለባንኮች ገንዘብ የሚለቅበት አጋጣሚዎች ነበሩ" ይላሉ ባለሙያው። አክለውም ከወረርሽኙ በኋላ ደግሞ እንደሚስተዋለው የዓለም ምጣኔ ሃብት እጅጉን ተጎድቷል፤ በኢትዮጵያም የፋይናንስ ተቋማት ለመደገፍ መንግሥት በብሔራዊ ባንክ በኩል 15 ቢሊዮን ብር እንዲቀርብ ማድረጉን አስታውሰዋል። "መንግሥት ይህን ያደረገው አበዳሪዎች ለተበዳሪዎች ጊዜ እንዲያራዝሙ፣ የወለድ መጠን እንዲቀንስ፣ ተጨማሪ ብድር የሚፈልጉ ብድር እንዲያገኙ፣ አምራቾች ምርታቸውን እንዲያስፋፉ ነው። "ለዚህ ደግሞ ጥሩ የገንዘብ አቅርቦ ወደ ኢኮኖሚው መፍሰስ አለበት እያልን አያሰብን ባለንበት ሰዓት ላይ የገንዘብ ዝውውር ላይ ገደብ መጣል ከተባለው ነገር ጋር የሚቃረን የምጣኔ ሃብት እርምጃ ነው የሚሆነው" ይላሉ። መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ከተገደደብ ምክንያት አንዱ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት በማሰብ ነው። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ጉቱም (ዶ/ር) አሁን ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ወጪ በሚደረግ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ መጣል የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ጠቀሜታ አለው በማለት ይስማማሉ። ይህንንም ሲያስረዱ "ከወረርሽኙ በፊት የሰው እንቅስቃሴ እንደልብ ነበር። ሰዎች ገንዘብ በማዳበሪያ ጭነው ሃርጌሳ ይወስዳሉ፤ ወደ መተማ ይሄዳሉ። አሁን ግን በቫይረሱ ምክንያት ሰዎች እንደፈለጉት መንቀሳቀስ አይችሉም። ስለዚህ ባንክ ለመጠቀም ይገደዳሉ" ይላሉ። ይህንንም በምሳሌ ሲያስረዱ "አንድ ሰው ወደ ባንክ ገቢ የተደረገውን ገንዘብ ላውጣ ቢል፤ ወጪ የተጠየቀው ቅርንጫፋ ብዙ ገንዘብ ስለተጠየቀ ሥራ መስራት አቆመ ማለት። ግለሰቡም ይህን ያክል ገንዘብ ከየት አመጣህ ተብሎ ይጠየቃል። በዚህ መልኩ መቆጣጠር ይችላል" በማለት እርምጃው ሊኖረው የሚችለውን ጠቀሜታ ያስረዳሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዋሲሁን በላይበበኩላቸው የመንግሥት ውሳኔ መጥፎ አለመሆኑን ያስረዳሉ። "የገንዘብ አቅርቦቱን በጣም በጣም መቆጣጠር አለበት። ምክንያቱም የዋጋ ንረት ከሚቀጣጠልባቸው ነገሮች አንዱ ከፍተኛ ብር በገበያው ሲሰራጭ ነው። ሐሰተኛውን በር ከትክክለኛው መለየትም በጣም አስቸጋሪ ነው" በማለት መንግሥት እነዚህን ለመቆጣጠር አስቦ እንደሆነ ያምናሉ። "ውሳኔው ጥሬ ገንዘብ የመያዝ እንጂ ሰዎች ገንዘብ ማንቀሳቀስ የለባቸውም" የሚል አይደለም የሚሉት ባለሙያው፣ ከጥሬ ገንዘብ ውጪ ዲጂታላይዝ በሆነ ገንዘብ ግብይት ማከናወን የሚቻልበት ሥርዓት ካለ በሞባይል መገበያየት፣ በኤቲኤም፣ በቼክ፣ በፖስ ማሽን መገበያየት የሚችሉ ከሆነ ግብይቶች እንዲቆሙ አልተደረገም ይላሉ። ስለዚህም የመሸመት መጠኑን የሚገደብ ምክንያት አለ ብለው እንደማያስቡ የሚናገሩት አቶ ዋሲሁን፤ ከፍተኛ ገንዘብ ገበያ ላይ ተረጭቶ ገንዘቦቹ ምርትና ምርታማነት ላይ የማያርፉ፣ ፍላጎትን የሚያሳድጉ ከሆነ የዋጋ ግሽበትን የማቀጣጠላቸው እድል በጣም ከፍተኛ መሆኑን ያሰምሩበታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-52734564
amh
business
ኢትዮጵያ ግሽበትን ለመግታት የባንኮች የመጠባበቂያ የገንዘብ መጠን በእጥፍ እንዲያድግ ወሰነች
በከፍተኛ ሁኔታ እያንሰራራ ያለውን የዋጋ ግሽበት ለመግታት ባንኮች ከሚሰበስቡት የተጣራ ቁጠባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ እንዲያስቀምጡት የሚጠበቅባቸውን የመጠባበቂያ የገንዘብ መጠን ወደ አስር በመቶ ከፍ እንዲያደርጉት ተወስኗል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው ከዚህ ቀደም 5 በመቶ የነበረውን የመጠባበቂያ የገንዘብ መጠን ከፍ እንዲል የወሰነው በኢኮኖሚው ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ መጠን ለመቀነስ ቁጥብ የገንዘብ ፖሊስ ለማድረግ ከመወሰኑ ጋር ተያይዞ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ የወለድ ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 16 በመቶ ከፍ እንዲል መወሰኑም ተገልጿል። ይህ የባንኮች መጠባበቂያና የብሔራዊ ባንክ የማበደሪያ ወለድ ምጣኔ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ያለው ግሸበት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን በሐምሌ ወር የነበረው መጠን 26.4 መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አስነብቧል። በዓመቱ ውስጥ የነበረው 20 በመቶ የሆነው የግሽበት መጠን በቅርቡ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን መንግሥት ይህንን ለመግታት የተለያዩ ጥረቶችን፣ ማሻሻያዎችንና ፖሊሲዎችን እያወጣ ይገኛል። በቅርቡም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ ህንፃዎች ያሉ ንብረቶችን እንደ መያዣነት የሚጠቀሙ ባንኮች ሁሉንም ብድሮች ለጊዜው እንዲታገድ የሚወስን አዲስ መመሪያ ወጥቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪንም በተመለከተ ባንኮች ሲጠቀሙበት የነበረው አሰራር ላይ ማሻሻያ ተደርጓል። በዚህም ማሻሻያ መሰረት ባንኮች ከወጪ ንግድ፣ ከግለሰብ ሃዋላና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ ውስጥ 50 በመቶውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ አለባቸው ተብሏል። ከዚህ ቀደም ባንኮች ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት፣ ከዲያስፖራ ሂሳብና ከሌሎች ምንጮች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ ሰላሳ በመቶውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ የሚያዘውን መመሪያም ተሻሽሏል። ይህ አሰራርም ከዚህ ቀደም በባንኮች በተደጋጋሚ ከሚቀርበው ወቀሳ መካከል ከውጭ ኢንቨስትመንት፣ ከዲያስፖራ ሂሳብና ከውጭ ብድር የሚገኝ የውጭ ምንዛሪ ተቀንሶ ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረግ የለበትም ለሚለውም ጥያቄ መልስ እንደሆነም ተገልጿል። ከባንኮች በተጨማሪ ደንበኞችን በተመለከተ መያዝ የሚችሉትን የውጭ ምንዛሪ መጠንም ማሻሻያ ተደርጓል። በባንኮች የውጭ ምንዛሬ ያስገኙ ደንበኞች በውጭ ምንዛሪ ሂሳባቸው ያለ ጊዜ ገደብ መያዝ የሚችሉት የውጭ ምንዛሬ መጠን ከ31.5 በመቶ ወደ 40 በመቶ ከፍ ብሏል። የገንዘብ ተቋማትና ደንበኞቻቸው ሊኖራቸው ስለሚገባው ግንኙነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ አውጥቷል። አገሪቱ እየሰራች ያለችው ወጥ ብሔራዊ መታወቂያ እስኪሰጥ ድረስ የገንዘብ ተቋማት ለደንበኞቻቸው የተለየ የደንበኛ መለያ ቁጥር መስጠት አለባቸው ተብሏል። ደንበኞች ወይም ድርጅቶች ከአንድ በላይ አካውንት ቢኖራቸውም ይህ የመለያ ቁጥር ተግባራዊ ይሆናል። ደንበኞች ማንኛውንም የባንክ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ወቅት ገንዘብ ማውጣት፣ ማስቀመጥም ሆነ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ማዘዋወርና ሌሎች ማንኛውም የባንክ አገልግሎቶችን በተመለከተ የገንዘብ ተቋማት (ባንኮች) ተመሳሳይ ቅፅ (ፎርም) መጠቀም አለባቸው። በዚህም አሰራር መሰረት በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ማንኛውም ባንኮችም ሆነ የገንዘብ ተቋማት ለየትኛውም የባንክ አገልግሎቶች የሚጠቀሟቸው ወጥና ተመሳሳይ የሆኑ ቅፆችን እንደሆነ መመሪያው አስቀምጧል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ደንበኞች ትክክለኛ ያልሆነ ወይም አጠራጣሪ መረጃ የሚሰጡ ወይንም መመሪያዎችን የማያከብሩ ከሆነ የገንዘብ ተቋማቱ አገልግሎትን የመከልከል ይችላሉ። ከዚህም በተጨማሪ ባንኮቹ የእነዚህን ደንበኞች መረጃ ለብሔራዊ ባንክና ለፋይናንስ መረጃ ደኅንነት ማዕከል ማስተላለፍ እንዳለባቸው ተጠቅሷል። የገንዘብ ተቋማቱ (ባንኮች) እነዚህን መመሪያዎች በተገቢው መልክ እንዲሰሩም የደንበኞቻቸውን ታሪክ የሚከታተል አዲስ አደረጃጀት ሊያዋቅሩ ይገባል እንዲሁም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አሰር መዘርጋት አለባቸው ተብሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለባንኮች ለመድንና ለጡረታ ዋስትና ድርጅቶች ቦንድ መሸጥ እንዲችልም ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህም መሰረት ባንኮች ከዓመታዊ ጠቅላላ የብድር ክምችት አንድ በመቶ የልማት ባንክ ቦንድ፤ የመድን ድርጅቶች ደግሞ ከተጣራ ዓመታዊ ገቢያቸው ከ15 በመቶ ያላነሰ የልማት ባንክ ቦንድ እንዲገዙ ተወስኗል። ይህ የልማት ባንክ ቦንድ መንግሥት ዋስትና የሚሰጠውና በተነፃፃሪ የተሻለ ወለድ የሚከፈልበት እንደሚሆንም ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58391135
amh
business
የቢትኮይን ዋጋ በ50 በመቶ በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆለቆለ
ዋጋው እያሽቆለቆለ ያለው ቢትኮይን፣ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ቅናሽ በማሳየት አንድ ቢትኮይን 34ሺህ የአሜሪካ ዶላር እየተሸጠ ነው። የክሪፕቶከረንሲ አሻሻጩ ኮይንቤዝ ከስድስት 6 ወራት በፊት ጣራ ነክቶ የነበረው ቢትኮይን በአሁኑ ወቅት ዋጋው 50 በመቶ ቀንሷል ብሏል። በክሪፕቶከረንሲዎች የገበያ ድርሻ ቀዳሚ የሆነው ቢትኮይን ዋጋው መቀነሱ የተሰማው በመላው ዓለም የድርሻ ገበያዎች [ስቶክ ገበያ] መቀነሳቸውን ተከትሎ ነው። የክሪፕቶካረንሲዎች ዋጋ ከዓለም የስቶክ ገበያ ጋር ተያይዞ ዋጋቸው ከፍ እና ዝቅ ሲል ይስተዋላል። በ650 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ዋጋ ቢትኮይን የዓለማችንን አንድ ሦስተኛ የክሪፕቶከረንሲ ጠቅላላ ድርሻ ይይዛል። በአሁኑ ወቅት ቢትኮይን በአንዳንድ አገራት ጨምር ይፋዊ መገበያያ እየሆነ ነው። በቅርቡ መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ ያደረገች ሲሆን ቢትኮይንን አገር አቀፍ መገበያያ በማድረግ ኤል ሳልቫዶር የመጀመሪያዋ ናት። ኤል ሳልቫዶር ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ ስታደርግ አይኤምኤፍን ጨምሮ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ውሳኔውን ተችተው ነበር። ግብይት ለመፈጸም ክሪፕቶከረንሲዎች ለግለሰቦች የሚሰጡት ነጻነት እንዳለው ሁሉ፤ ክሪፕቶከረንሲዎች በሕገ-ወጥ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርጎ ማቅረብ ያስችላሉ። በተጨማሪም ክሪፕቶከረንሲን በመጠቀም አፍራሽ ተልዕኮዎችን በገንዘብ ለመደገፍ ይቻላል እንዲሁም የፋይናንስ ሥርዓት አለመረጋጋትን ይፈጥራል በሚሉ ምክንያቶች ሥርዓቱ ይተቻል። ከቢትኮይን ቀጥሎ ትልቁን የገበያ ድርሻ የሚይዘው ኢቲሪየም በተመሳሳይ ባለፉት ቀናት ዋጋው ከ10 በመቶ በላይ ቀንሷል። ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አውስትራሊያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ባንኮች የዋጋ ግሽበተን ለመቆጣጠር በሚል የወለድ መጠንን ከፍ አድርገው ነበር። ይህም ተበዳሪዎች ብድር የሚወስዱበትን የወለድ መጠን ከፍ አድርጓል። በርካታ ኢንቨስተሮች የዋጋ ግሽበት እና የብድር ወለድ መጠን ከፍ ማለት በዓለም ምጣኔ ሀብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል የሚል ስጋት አሳድሮባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61375822
amh
business
ኤሎን መስክ የግል ጀቱን የሚከታተለውን የትዊተር ገጽ ባለቤት ሊከስ ነው
ኤሎን መስክ በግል ጀቱ የት እንደተጓዘ የሚከታተለውን የትዊተር ገጽ ባለቤት ሊከስ ነው። የግል ጀቱ እንቅስቃሴ @ElonJet account በሚባለው ገጽ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ የልጁን ደኅንነት አደጋ ላይ እንደሚጥለው መስክ ተናግሯል። ይህ የትዊተር ገጽ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተከታዮች አሉት። በዚህ ሳምንት ገጹን ትዊተር አግዶታል። የገጹ ባለቤት የ20 ዓመቱ ጃክ ስዊኒ ነው። በረራ የሚከታተሉ መተግበሪያዎችን ተጠቅሞ ነው የመስክን የግል ጀት የሚከታተለው። የመስክለ ጀት ሲነሳና ሲያርፍ ትዊተር ገጹ ላይ ይጽፋል። መስክ እንዳለው ስዊኒ እና ሌሎችም የፍርድ ቤት ክስ ይጠብቃቸዋል። “ትላንት ማታ አንድ መኪና ልጄ ሊል ኤክስ ያለበትን መኪና ሲከታተል ነበር። እኔ መኪናው ውስጥ ያለው መስያቸው ነው” ብሏል መስክ። የሰዎችን እንቅስቃሴ በቀጥታ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አደጋ ውስጥ ሊከት እንደሚችል ገልጿል። የመስክን ጀት የሚከታተለው ወጣት ፍሎሪዳ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነው። ትዊተር ገጹን መርምሮ መርሕ ጥሶ በማግኘቱ እንዲዘጋ መወሰኑን ለሲኤንኤን ገልጿል። ወጣቱ ቢል ጌትስ፣ ጄፍ ቤዞስ እና ማርክ ዙከርበርግን ጨምሮ የሌሎችም ሀብታም አሜሪካውያን የግል ጀት እየተከታተለ የሚጽፋበቸው የትዊተር ገጾች አሉት። በተጨማሪም ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሌሎችም ታዋቂ ግለሰቦች ጋር የሚገናኙ ገጾችም አሉ። ሁሉንም ገጾች ትዊተር አስወግዷቸዋል። መስክ እንዳለው፣ ወጣቱ ገጾቹን እንዲያጠፋ 5ሺህ ዶላር ለመክፈል ጠይቀውት ነበር። ወጣቱ የክፍያ ጥያቄው ከቀረበለት በኋላ፣ ከፍያውን መፈጸም እንደማያስፈልግ በትዊተር በኩል እንደተገለጸ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ተናግሯል። መስክ ከወር በፊት ገጹን ላለመሰረዝ ቢወስንም አሁን ግን “ሰዎች ያሉበትን ቦታ የሚያጋልጡ ገጾች የደኅንነት ስጋት ናቸው” ብሏል። የትዊተር የደኅንነት ክፍል ባወጣው የተሻሻለ መመሪያ “የሌሎች ሰዎችን የግል መረጃ ያለ ፈቃዳቸው መለጠፍ ክልክል ነው” ብሏል። መስክ ትዊተርን ከገዛው በኋላ የተለያዩ ለውጦችን እያደረገ ይገኛል። ከግማሽ በላይ ሠራተኞቹን ከማባረሩ ባሻገር በሳን ፍራንሲስኮ ዋና ቅርንጫፍ ለሚገኙ ሠራተኞች የቤት ኪራይ መክፈል ማቆሙም ተዘግቧል። ትዊተርን ከገዛ በኋላ ለኤሌክትሪክ መኪና አምራች ድርጅቱ ተስላ የሚሰጠው ትኩርት በመቀነሱ ኢንቨስተሮች ስጋት ገብቷቸዋል። በዚህ ሳምንት በሦስት ተከታታይ ቀናት 22 ሚሊዮን ድርሻ የሸጠ ሲሆን፣ ይህም 3.58 ቢሊዮን ዶላር ያወጣል። መስክ በተስላ ያለው ድርሻ 40 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cgl1m1yn2p4o
amh
business
ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ከነጮች ባነሰ ሁኔታ የሚኖሩባት ደቡብ አፍሪካ
ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ከነጭ አቻዎቻቸው በሦስት እጥፍ ያነሰ ገቢ እንደሚያገኙ አንድ ጥናት ይፋ አደረገ። ጥናቱ በደቡብ አፍሪካውያን መካከል ያለውን ያልተመጣጠነ ገቢን የተመለከተ ሲሆን፤ ከአገሪቱ 80 በመቶ የሚሆኑት ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የወር ገቢያቸው በአማካኝ 13000 ብር ገደማ ሲሆን፤ የነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ግን 38 ሺህ ብር አካባቢ እንደሆነ ተቀምጧል። • “ከብሔርም ከሐይማኖትም በላይ ሰውነት ከሰሃራ በረሃ ስቃይ አውጥቶኛል" • ፓርቲዎች በክልላቸው ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚታየው ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ • ከንቲባ ታከለ ኡማ በስህተት ለወጣው የኤርትራ ካርታ ይቅርታ ጠየቁ ጥናቱ አክሎም እንዴት የተለያዩ ብሔሮች በማኅበራዊ መደብ ውስጥ እንደተቀመጡ አሳይቷል። ጥናቱ በአገሪቱ የስታስቲክስ መሥሪያ ቤት እኤአ ከ2002 እስከ 2017 ድረስ የተሰበሰበን መረጃ የተጠቀመ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ይህም ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን በሥራ ማጣት ክፉኛ እንደሚቸገሩ ያሳያል። እነዚህ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የግል የሕክምና ተቋማትን መጎብኘት፣ መጠለያና መብራት የማግኘት ጉዳይም ቅንጦት እንደሆነባቸው ጥናቱ ያመለክታል። ጥናቱ፤ የደቡብ አፍሪካ ከተሞችን ከዓለማችን አገራት መካከል ከፍተኛ ያልተመጣጠነ ገቢ ያላቸው ዜጎች የሚኖሩባት አገር አድርጓታል። ጥናቱ ለበርካታ ዓመታት በአገሪቱ አከራካሪ ለነበረው ጉዳይ ጠቅለል ያለ ምልከታን በማስቀመጥ መረጃን የሰጠ መሆኑ ተነግሮለታል። በብሔሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ የሀብት ልዩነት እንዲኖር ካደረኩጉ ምክንያቶች አንዱ የአፓርታይድ ውጤት ነው የተባለ ሲሆን፣ አፓርታይድ በቁጥር አነስተኛ የሆኑት ነጮች አገሪቱ ያላትን ውስን ሀብት ያለስስት እንዲጠቀሙና ሀብት እንዲያካብቱ አድርጓል ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/50443851
amh
business
በኢንተርኔት መቋረጥ ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ቀጥሎ በአፍሪካ ከፍተኛ ገንዘብ አጥታለች - ሪፖርት
ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት በኢንተርኔት መቋረጥ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ አገራት መካከል ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ በመቀጠል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዳጣች አንድ ሪፖርት አመለከተ። ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ ሆን ተብለው የተፈጸሙ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጦች በአገራት ላይ ያስከተሉትን ኪሳራ በተመለከተ ቶፕ ቴን ቪፒኤን ባወጣው ሪፖርት ላይ በአፍሪካ ናይጄሪያ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በቀዳሚነት ተቀምጠዋል። በመላው ዓለም መንግሥታት በአገራቸው ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በማቋረጣቸው በአጠቃላዩ የምድራችን ምጣኔ ሀብት ላይ የ5.5 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራን ማስከተላቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል። በዚህም መሠረት ከሁለት ሳምንታት በፊት በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የኢንትርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ በመደረጉና የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች በመዘጋታቸው ኢትዮጵያ 164.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳጣች ተገልጿል። ከአንድ ዓመት በላይ በቀጠለው የትግራይ ጦርነት ምክንያት በክልሉ የኢንተርኔት አገለግሎት መቋረጡን የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ ባለፈው ግንቦት ወር የተሰጠው ብሔራዊ ፈተና በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሾልኮ ወጥቷል በሚል በመላው አገሪቱ ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም ከአገልግሎት ውጪ እንደነበሩ ጠቅሷል። እንደ ሪፖርቱ በአንድ ዓመት ውስጥ በአገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ ሆነው የቆዩት ለ8,760 ሰዓት ሲሆን የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር መድረኮች ደግሞ ለ104 ሰዓት ተዘግተው ቆይተው ነበር። በዚህም ሳቢያ በኢትዮጵያ ከ21 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኢንተርኔትና በማኅበራዊ ሚዲያ መስተጓጎል መቸገራቸውንና 165 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት መድረሱን አመለክቷል። ዓመታዊው ሪፖርቱ በዓለም ዙሪያ ያጋጠሙ ዋነኛ የሆኑና ሆን ተብለው የተቋረጡ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በመመዝገብ የተነተነ ሲሆን፣ በዚህም የደረሱ ምጣኔ ሀብታዊ ኪሳራዎችና አገልግሎት የተነፈጉ ሰዎችን ብዛት አቅርቧል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንተርኔት መቋረጥ ከፍተኛ ኪሳራ የገጠማት አገር ምሥራቅ እስያዊቷ አገር ምያንማር ስትሆን፣ ይህም በአገሪቱ የጦር ጄነራሎች የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥትን ተከትሎ ነው። ባለፈው ዓመት በምያንማር ኢንተርኔት ለ12,238 ሰዓታት የተቋረጠ ሲሆን ይህም የ2.8 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራን አስከትሎባታል። ሁለተኛዋ ደግሞ አፍሪካዊቷ ናይጄሪያ ስትሆን ሆን ተብሎ ኢንተርኔት በመቋረጡ ምክንያት 104.4 ሚሊዮን ሕዝብ ከአገለግሎት ውጪ ሆኖ 1.5 ቢሊዮን ዶላር እንድታጣ አድርጓታል ተብሏል። ከኢንተርኔት መቋረጥ በተጨማሪ አገራት የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮችንም ለይተው አገልግሎት እንዳይሰጡ ያደርጋሉ። በዚህም ባለፈው ዓመት ከሁሉም በበለጠ ዕቀባ ተጥሎበት የነበረው ትዊተር ሲሆን፣ በተከታይነት ፌስቡክና ዋትስአፕ በአንዳንድ አገራት ውስጥ አገልግሎታቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል። በአጠቃላይ ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 21 አገራት ውስጥ 50 የሚሆኑ ዋነኛ የሚባሉ የኢንተርኔት መቋረጦች በተለያዩ ምክንያቶች እንዳጋጠሙ ተመዝግቧል። ይህም በአጠቃላዩ የዓለም ምጣኔ ሀብት ላይ የ5.45 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራን በማስከተል ከቀደመው ዓመት በ36 በመቶ ከፍ ማለቱን የቶፕ ቴን ቪፒኤን ሪፖርት ዓመልክቷል። ኢንተርኔት በተቋረጠባቸው አገራት ውስጥ 486.2 ሚሊዮን ሰዎች ከአገልግሎት ውጪ ለመሆን የተገደዱ ሲሆን፣ ኢንተርኔት በመንግሥታት ሲቋረጥ ከተጨማሪ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር እንደሚያያዙም አመልክቷል። በዚህም ሳቢያ በምርጫ፣ በመሰብሰብና በመናገር ነጻነቶች ላይ ጥሰቶች ያጋጥማሉ። በዘመናዊው ዓለም የኢንተርኔት አገልግሎት ከመሠረታዊ የሰዎች ፍላጎቶች ውስጥ እየታየ ያለ ሲሆን፣ ኢንተርኔት ለበርካታ ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴዎች ዋነኛው መሳሪያ በመሆኑ በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጥ በሚያጋጥምበት ጊዜ የሚያስከትለው ኪሳራ ቀላል የሚባል አይደለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-59988907
amh
business
የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ፍለጋና የዋጋ መናር በአዲስ አበባ
አዲስ አበባ ውስጥ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በከፍተኛ ገንዘብ ሲሸጥ እንደነበረና በመደብሮች ውስጥ ማግኘት እንዳልቻሉ ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ። አርብ ዕለት አዲስ አበባ ላይ የጤና ጥበቃ ባለስልጣናት የመጀመሪያው የተረጋገጠ የኮሮናቫይረስ ታማሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ በኋላ ስጋት የገባቸው ሰዎች የፊት ጭንብልና ፈሳሽ የእጅ ማጽጃ ውህዶችን በመግዛት ላይ ናቸው። የቢቢሲ ያናገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳሉት በሽታው አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ ሊከላከለው ይችላል የተባሉ ነገሮችን እየገዙ መሆናቸውን ነገር ግን የጭንብሎቹና ፈሳሽ የንጽህና መጠበቂያዎች [ሳኒታይዘር] እንደልብ እንደማይገኙ ከተገኙም ዋጋቸው በሚያስደነግጥ ሁኔታ መናሩን ገልጸዋል። አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ የመድሃኒት መደብሮችም የፊት ጭንብልና ሳኒታይዘር እንደሌላቸው በሚለጥፉት ማስታወቂያም ሆነ በተጠየቁ ጊዜ የሚሰጡት ምላሽ እንደሆነ ቅዳሜ ዕለት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የሚገኙ ፋርማሲዎችን የተመለከተው የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይም በርካቶች የፊት ጭንብል ስለመጥፋቱና ስለመወደዱ ገጠማቸውን በጽሁፍና በምስል እያሰፈሩ ነው። ጭንብሉ ያለባቸው ፋርማሲዎች ረዘም ያሉ ሰልፎች የታዩ ሲሆን ውስን ቁጥር ያላቸውን መሸፈኛዎችን በመደበኛው ዋጋ ሲሸጡ እንደነበር ተገልጿል። ቢቢሲ በስልክ ያናገራቸው በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁለት የመድሃኒት መደብሮች የፊት መሸፈኛ ጭምብል እንደጨረሱና ሲሸጡ የነበረውም ቀደም ሲል በነበረው ዋጋ እንደሆነ ገልጸዋል። የከተማዋ ባለስልጣናትም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ተፈላጊ በሆኑ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ በሚሸጡ የንገድ ተቋማት ላይ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን አመልክተው፤ ኅብረተሰቡም ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። በርካታ ሰዎች በሽታውን ሊከላከል ይችላል በማለት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን ለመግዛት ወደ መድሃኒት መደብሮች ቢሄዱም ለማግኘት እንደተቸገሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ሰው ሁሉ እየገዛ በመሆኑ ለልጆቼም ሆነ ለእራሴ የሚሆን ማስክ ለመግዛት ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በየደረስኩበት ቦታ ያሉ ፋርማሲዎችን ብጠይቅም ላገኝ አልቻልኩም" ያሉት የሁለት ልጆች እናትና አዲስ አበባ ውስጥ አብነት የሚባለው አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መብራት አስቻለ ናቸው። ወይዘሮ መብራት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጎረቤቶቻቸው ጭንብሉን እስከ 200 ብር በሚደርስ ዋጋ ከሰዎች ላይ መግዛታቸውን እንደሰሙ ነገር ግን ይህን ያህል ገንዘብ በማውጣት ለቤተሰባቸው መግዛት ከባድ ስለሆነባቸው እንደተዉት ገልጸዋል። የጭንብሉን አስፈላጊነት በተመለከተ የሰሙት በዙሪያቸው ካሉ ሰዎች መሆኑን እንጂ ከባለሙያዎች የተነገራቸው ነገር እንደሌለ የሚጠቅሱት ወ/ሮ መብራት "በሸታው አሳሳቢ በመሆኑ የምችለውን ላድርግ በማለት ነው ከአንዱ ፋርማሲ ወደ ሌላው በመሄድ ስጠይቅ የነበረው" ይላሉ። ተለያዩ ሰዎች በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ የሚሰጡት አስተያየቶችም ከዚሁ ጋር የሚመሳሰሉ ናቸው የፊት መሸፈኛ ጭንብል ከ150 እስከ 500 ብር በሚደርስ ዋጋ እየተሸጡ መሆናቸውን የሚያመለክቱ ናቸው። ከፊት መሸፈኛ ጭምብሎች በተጨማሪ የእጅ ማጽጃ ፋሳሾችም ዋጋቸው የጨመረ ሲሆን ተህዋሲያንን ያጠፋሉ ተብለው የሚነገርላቸው ሳሙናዎችም ተፈላጊነታቸው ጨምሯል። ዋጋቸውም በዚያው ልክ መጨመሩን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የከተማው መስተዳደርም "የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ተጠቂ ተገኝቷል" የሚለው መረጃ ከወጣ በኋላ በተለያዩ ሸቀጦች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል አቋቁሞ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አሳወቋል። ከኮሮናቫይረስ መከሰት ጋር በተያያዘ አፍን አፍንጫን የሚሸፍኑ ጭምብሎች በስፋት በዓለም ዙሪያ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። በዚህም ሳቢያ በበርካታ አገራት ውስጥ የጭንብሎቹ እጥረት እየተከሰተ በመሆኑ አምራቾች የጭንብል ምርታቸውን ከፍ እንዲያደርጉ በዓለም የጤና ድርጅት ተጠይቀዋል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚገምተው በየወሩ 89 ሚሊዮን የሚደርስ የፊት ጭምብሎች ያስፈልጋሉ። በኮሮናቫይረስ ስጋትና በተሳሳተ አመለካከት ሳቢያ እነዚህ ጭንብሎች ያላግባብ ጥቅም ላይ ስለሚውሉ የሚየስፈልገው ቁጥር ከዚህም በላይ እንደሚሆን ይገመታል። ድርጅቱ እንዳለውም የፊት ጭንብሎች በስፋት ጥቅም ላይ በመዋላቸውና ሰዎች በብዛት እየገዙ በማስቀመጣቸው የተነሳ የህክምና ባለሙያዎች በየዕለቱ በሚጠቀሙት አቅርቦት ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን አመልክቶ፤ ይህም በዚህ የወረርሽን ጊዜ ህሙማንን በመርዳት ሥራ ላይ የተጠመዱ የህክምና ባለሙያዎች ለኮሮናቫይረስና ለሌሎች በሽታዎች ተጋላጭ ሊያደርጋቸው ይችላል ሲል ስጋቱን ገልጿል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው የኮሮናቫይረስን ለመካላከል በሚል ሁሉም ሰው የአፍና የአፍናጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ አያስፈልገውም። ጭንብሉን ማድረግ ያለባቸው የሚያስነጥሱና የሚያስሉ ከሆነ እንዲሁም በበሽታው የተጠረጠረ ወይም የተያዘን ሰው የሚቀርቡና የሚንከባከቡ ሰዎች ብቻ ነው። ለእነዚህ ሰዎች ጭንብሉን ማድረግ ብቻ በቂ አይደለም፤ በውጤታማ ሁኔታ በሽታውን ለመከላከልም በመደበኛነት እጃቸውን በሳሙናና በውሃ መታጠብ ወይም አልኮል ነክ በሆኑ ፈሳሾች እጃቸውን ማጽዳት ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም ጭንብሉን መጠቀም ያለባቸው ሰዎች እንዴት መጠቀምና በተገቢው ሁኔታ እንዴት መወገድ እንዳለበትም ማወቅ ይገባቸዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ይመክራል። ስለዚህም በአዲስ አበባና በሌሎች ስፍራዎች የተጠቀሱት አይነት የበሽታው ስጋቶች ሳይኖሩ ጭምብልን ከሚገባው በላይ ከፍተኛ ገንዘብ እያወጡ መግዛት በሽታውን ለመከላከል የሚኖረው ጠቀሜታ ዝቅተኛ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒሰቴር መክሯል። እነዚህ ለአጭር ጊዜ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉት የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች ጥብቅ ብለው አፍንጫና አፍን የሚሸፍኑ ካለመሆናቸው ባሻገር ረጅም ጊዜን አያገለግሉም። የማስነጠስና የማሳል ምልክት የሚታይባቸውን ወይም በኮሮናቫይረስ ከሚጠረጠሩ ሰዎች ጋር የግድ መቅረብ ያለባቸው ሰዎች የሚጠቀሙባቸው የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች በቀላሉ በላብ ስለሚባላሹ ወዲያው ወዲያው መቀየር አለባቸው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም ሆነ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚመክሩት የተጠቀሱት ምልክቶች እስካልታዩ ድረስ ሁሉም ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ አያስፈልጋቸውም። ከዚያ ይልቅ ግን የበሽታው ስጋት ለማስወገድ ከሚያስሉ፣ ከሚያስነጥሱ ወይም ትኩሳት ካለባቸው ሰዎች ጋር የሚኖርን ንክኪ ማስወገድ፣ እጅን በሳሙናና በውሃ መታጠብ ካልሆንም ተህዋሲያንን በሚያስወዱ ማጽጃዎች እጅን ማጽዳት ከሁሉ በበለጠ ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም እጅን ሳይታጠቡ ዓይንን፣ አፍንጫንና አፍን አለመንካት እንዲሁም መጨባበጥን ማስወገድ የቫይረሱን መስፋፋት ለመግታት መወሰድ ካለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-51894637
amh
business
ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካ ታችኛው ምክር ቤት ጆ ባይደን ያቀረቡትን የ1.9 ትሪሊየን ዶላር ድጎማ አፀደቀ
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት አሜሪካዊያንን ለመርዳት ያቀረቡት የ1.9 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ማነቃቂያ ማዕቀፍ በተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ። የድምፅ አሰጣጥ ሁኔታው ከፓርቲ ወገንተኝነት ጋር የተያያዘ ነበር። ሁሉም ሪፐብሊካኖች ተቃውመውታል። ሁለት ዲሞክራቶችም ገንዘቡ በጣም ብዙ ነው ሲሉ በመቃወም ሪፐብሊካኖችን ተቀላቅለዋል። ማዕቀፉ በሚቀጥለው ሳምንት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስ ሰብሳቢ በሆኑበት የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ይቀርባል። ይህ ምክር ቤት ከየግዛቱ እኩል 2 እንደራሴዎች የሚሞሉት የመቶ ወኪሎች ሸንጎ ነው። ባለ ትልቅ ሥልጣንም ነው። ምክር ቤቱ ዝቅተኛ የክፍያ መጠንን በእጥፍ ማሳደግ የሚለውን ሃሳብ ውድቅ አድርጓል። ይህ ረቂቅ ሕግ ግን አሁንም የአሜሪካ ዝቅተኛ ክፍያ ጭማሬን አካቷል። ይህ እንዴት እንደሚፈታ ግልፅ የሆነ ነገር የለም። ምንም እንኳን በምክር ቤቱ ይህ ነጥብ እንዳይካተት ቢደረግም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ፤ ሁሉም የቀረቡት እቅዶች እንደሚያልፉ ተናግረዋል። ዝቅተኛ ክፍያን ማሳደግ የዲሞክራቶች ዋነኛ ግብ ነው። አንዳንድ የዲሞክራት መሪዎች በሰዓት ከ15 ዶላር በታች የሚከፍሉ ቀጣሪዎችን ለመቅጣት እያሰቡ ነው። ይህ የገንዘብ ማዕቀፍ የኮሮናቫይረስ ክትባት ስርጭትን እና ምርመራን ለማሳደግ እንዲሁም ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ያለመ ነው። ማዕቀፉ ለሁሉም አሜሪካዊያን ከሚሰጠው 1 ሺህ 400 ዶላር የገንዘብ ድጎማ ጋር ተደማምሮ ለቤተሰብ የሚሰጠውን ድጎማ 1 ትሪሊየን ዶላር ገንዘብን ያካትታል። ከዚህም ባሻገር ወረርሽኙን ለመዋጋት የሚውል 70 ቢሊዮን ዶላር እና ለአነስተኛ ንግዶች ማነቃቂያ 110 ቢሊየን ዶላርንም ይጨምራል ። ለቤተሰብ፣ ለአነስተኛ የንግድ ተቋማትንና የግዛት መንግሥታት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ይሆናልም ተብሏል። ዲሞክራቶች ቅዳሜ ጠዋት በተደረገው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በቂ ድምፅ አግኝተዋል። በዚህም ፕሬዚደንት ባይደን በኮቪድ -19 እየተፈተኑ ያሉትን አሜሪካዊያን ለመርዳት ባሰቡት 'የአሜሪካ መታዳጊያ እቅድ' አሸናፊ ሆነዋል። ይሁን እንጂ ሪፐብሊካን እቅዱ አላስፈላጊ በሆነ መጠን ብዙ እና ከወረርሽኙ ጋር ተያያዥነት በሌላቸው ዲሞክራሲያዊ ጉዳዮች የተሞላ ነው ብለዋል። ዲሞክራቶች በላዕላይ ምክር ቤቱ ጥብቅ ክርክር ይጠብቃቸዋል ተብሏል። ዲሞክራቱ ጆ ባይደን በአሜሪካ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለውን ወረርሽኝ ለመዋጋት ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56221851
amh
business
የተሰናባቹ 2013 ዓመት ዓበይት ምጣኔ ኃብታዊ ክስተቶች
ኢትዮጵያ 2013ን ተሰናብታ አዲሱን ዓመት ልትቀበል የቀራት ጥቂት ቀናት ናቸው። ተሰናባቹን ዓመት ዘወር ብለን በምናይበት ወቅት አገሪቷ በጦርነት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿ የተቀጠፉበት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤት አልባ ሆነው በችግር ውስጥ የሚገኙበት፣ ከፍተኛ የዋጋ ንረት የብዙዎችን ናላ እያዞረ ባለበት ነው ያሳለፉት። ፈታኝ በሚባል የታሪክ ሂደት ውስጥ ያለችው አገሪቷ በምትሸኘውም ዓመት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጸጥታ ምክር ቤት ዋነኛ ርዕሰ ጉዳይ፣ የኃያላኑ መንግሥታት መነጋገሪያ፣ በባለስልጣናቷ ላይ የጉዞ ዕቀባ የተጣለባትና ከጫፍ ጫፍ ያሉ የዓለም ሚዲያዎች ዋና ርዕስም ሆናለች። አገሪቷ ከትግራይ ጦርነት ጋር ተያይዞም በረሃብና በመብት ጥሰቶች ስሟ በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ሆኗል። ከጦርነት በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አገሪቷ ላይ ጫና ያሳደረ ከመሆኑ አንፃር በርካታ ጋሬጣዎች የተደቀኑበት ዓመት ሆኖ ማለፉ አሌ አይባልም። ተሰናባቹ ዓመት ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የታየበት፣ ከምጣኔ ሀብት ቀውሰ ጋር በተያያዘ ኤምባሲዎች የተዘጉበት፣ አገሪቷ የመገበያያ ገንዘብ ኖት የቀየረችበት፣ አዲስ የቴሌኮም ፈቃድ የተሰጠበት ወቅት ነው። ከዚህም በተጨማሪ በርካታ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱ መመሪያዎች የወጡበት እንዲሁም ኢትዮጵያ ለአስርት ዓመታት ሲጠበቅ የነበረው የንግድ ሕጓን ያሻሻለችው በተሰናባቹ ዓመት ነው። ለመሆኑ የተሰናባቹ ዓመት ዓበይት የምጣኔ ሀብት ክስተቶች ምን ነበሩ? እንዲህ ቃኝተናቸዋል። የብር ኖቶች ቅያሪ ኢትዮጵያ የ2012 ዓ.ምን የምጣኔ ሀብት ማሻሻያዋን የጀመረችው ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50፣ እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶችን በመቀየርና አዲስ ብር ኖቶችን ይፋ በማድረግ ነው። በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የባለ ሁለት መቶ ብር ኖትም አሳትማለች። አገሪቷ ነባሮቹን የብር ኖቶች ለመቀየር ሌላ ወጪ ሳይጨምር ለህትመት ብቻ 3.7 ቢሊዮን ብር ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ አስታውቀዋል። አገሪቱ በዋነኝነት ወደ ቅያሪ የገባችው ባንኮች የገጠማቸውን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍና ቁጠባቸውን እንዲያሳድግ፣ ሕጋዊ ያልሆነ የገንዘብ ዝውውርን ከኢኮኖሚው እንቅስቃሴ እንዲወገድ፣ የዋጋ መረጋጋት እንዲኖር፣ የመንግሥት ገቢ እንዲያድግ ያስችላል በሚል ነው። በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከባንክ ውጪ በመኖሩ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት (ሊኩዊዲቲ) ከማጋጠሙ ጋር ከመሆኑ ተያይዞም ቅያሪው ይህንንም እንደሚቀርፍ ታምኗል። ከቅያሪው ጋር ተያይዞ ከወጡ መመመሪያዎች ጋር በተያያዘ አንዳንድ ለውጦችም ታይተዋል። በአንድ ሰው እጅ ሊቀመጥ የሚችለው የገንዘብ መጠን በ1.5 ሚሊዮን ብር መወሰኑ፣ ግለሰቦች ከባንክ በቀን ማውጣት የሚችሉት ከፍተኛ የገንዘብ መጠን 200 ሺህ ብር፣ እንዲሁም ኩባንያዎች በጥሬ ገንዘብ ማውጣት የሚችሉት 300 ሺህ ብር ገደብ መመሪያዎች ጥያቄ ያጫሩ ሆነው አልፈዋል። ብሔራዊ ባንክ በወቅቱ እንዳስታወቀው የታተመው ብር በኢኮኖሚው ውስጥ ከሚዘዋወረው በበለጠ እንዲሆንና ለመጠባበቂያም እንዲሆን 262 ቢሊዮን ብር ታትሟል። በ1983 ዓ.ም የታተመው የብር መጠን ስምንት ሚሊዮን ብር ብቻ የነበረ ሲሆን የዘንድሮው በአገሪቱ የብር ቅያሪ ታሪክ ከፍተኛ ተብሎ ተመዝግቧል። የትግራይ ጦርነት ያስከተለው ቀውስ በጥቅምት መጨረሻ አካባቢ በትግራይ ክልል የተከሰተው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከመግደሉ በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና የምጣኔ ሀብት ቀውስ አስከትሏል። ጦርነቱ እስካሁን ድረስ አገሪቷን ምን ያህል እንዳስወጣት ይፋዊ መረጃ ባይኖርም፣ በትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ትንበያ መሰረት ወታደራዊ ወጪዋ በመጪው ታኅሣሥ ወር መጨረሻ ላይ ወደ 502 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ተብሏል። ባለፈው ዓመት ወጪዋ 460 ሚሊዮን ዶላር ነበር። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም ጦርነቱ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር ከአገሪቱ ግምጃ ቤት አስወጥቷል ብለዋል። አገሪቱ ለጦርነቱ መዋዕለ ንዋይዋን ከማፍሰሷ በተጨማሪ ከትግራይ ክልል ታገኝ የነበረውን ገቢም አጥታለች። ጦርነቱ በተጀመረ በወራት ውስጥ ከትግራይ ክልል በሦስት ወራት ውስጥ መሰብሰብ የነበረበት ሁለት ቢሊዮን ብር አለመገኘቱን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥር ወር መጨረሻ ላይ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃጸሙን ለሐዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው መረጃ መሰረት በበጀት ዓመቱ ለመሰብብሰብ ከታቀደው 290 ቢሊዮን ብር ውስጥ በትግራይ ክልል ለማግኘት የታሰበው 7.8 ቢሊዮን ብር እንደነበር አስረድቷል። ከጦርነቱ በፊት በነበሩት ሦስት ወራት 1.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል። የትግራይ ክልል ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ውስጥ የምትጠቀስ ስትሆን ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በየዓመቱ ወጪ ንግድ ከምታደርጋቸው ምርቶች ውስጥ ዘጠኝ በመቶ የክልሉ ድርሻ ነው። የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለፈው ዓመት በ2020 ከነበረበት 6 በመቶ በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት በ2021 ሁለት በመቶ ብቻ እንደሚያድግ ተገምቷል። ይህም በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከታየው በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ የአይኤምኤፍ መረጃ ያሳያል። ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት የበርካታ ከተሜን ህይወት እየፈተነና የማይወጡት ተራራ ሆኖባቸዋል። የኑሮ ውድነት አመላካች የሆነው የዋጋ ግሽበት በነሐሴ ወር ወደ 30.4 በመቶ አሻቅቧል። የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያሳየው በነሐሴ ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ከ32 በመቶ አገሪቷ በአስርት ዓመታት አይታው ወደማታውቀው 37.6 በመቶ ደርሷል። ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦችን የዋጋ ግሸበት በምናይበት ወቅት ከ19 በመቶ ወደ 20.8 በመቶ አሻቅቧል። የዋጋ ግሽበቱ ጦርነት በሚካሄድባቸውና ምንም ዓይነት የመሠረታዊ አገልግልቶች በሌለባቸው እያሻቀበ ሲሆን የመሠረታዊ ሸቀጦች መመናመኑን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። ለምሳሌ ያህል ጥር መጨረሻ ላይ በነበረው መረጃ መሰረት የምግብ ዋጋ ግሽበቱ በትግራይ ከ36 በመቶ በላይ ነበር። የአገሪቷ የዋጋ ግሽበት ከሦስት አስርት አሃዝ በላይ መሆኑ መሠረታዊ በሚባሉ ሸቀጦችም ዋጋ እያናረው ሲሆን በዜጎች ላይም ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና እያሳደረ ነው። ኢትዮጵያ ለዓመታት የነበራት የተዛባ የንግድ ሥርዓት በተለይም የወጪና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን፣ ጦርነትና አለመረጋጋት፣ የብር መዳከም የፈጠረው ግሽበት፣ የወጪ ንግድ መቀዛቀዝ፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ተደራርበው ለዋጋ ንረቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በመላው ዓለም የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በምጣኔ ሀብቱ ቀውስ ላይ ጫና እያሳደረ ይገኛል። የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ ግሽበት ወደ አንድ ነጠላ አሀዝ አውርዶ የዋጋ መረጋጋት ለማምጣት እየጣረ የሚገኝ ሲሆን ከሰሞኑም የተወሰኑ መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦችን ላልተወሰነ ጊዜ ከቀረጥና ታክስ ነጻ ማድረጉን አስታውቋል። ከነሐሴ መጨረሻም ጀምሮ የምግብ ዘይት፣ ስኳርና ሩዝ ከውጭ ሲገቡም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸምባቸው ከቀረጥና ታክስ ሙሉ በሙሉ ነፃ ሲሆኑ ስንዴ ከውጭ ሲገባ ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንዲሆን ተወስኗል። ፓስታ እና ማኮሮኒ ከውጭ ሲገቡም ሆነ በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የዶሮ እንቁላል ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆን ተወስኗል። የውጭ ምንዛሪ ዋጋ መናር ለዓመታት የአገሪቱ አንገብጋቢ ችግር ሆኖ የዘለቀው የውጭ ምንዛሪ እጥረት በዘንድሮው ዓመትም በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሷል። በዓመታት ከፍተኛ በሚባል ሁኔታ ጭማሪ እያሳየ የመጣው የምንዛሪ ተመን ንሮ ይፋዊ በሆነው የባንክ ግብይት መሰረት አንድ ዶላር በ45.6 ብር እየተመነዘረ ይገኛል። በትይዩ ወይም በተለምዶ ጥቁር ገበያ በሚባለው ገበያ የምንዛሪ ተመን ደግሞ አንድ ዶላር በ70 ብር አካባቢ እየተመነዘረ ሲሆን ከመደበኛው ገበያ ጋር ያለው ልዩነት ከ20 ብር በላይ መሆኑ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችን ስጋት ላይ የጣለ ክስተት ሆኗል። በተለይም አገሪቷ የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ ፍላጎት የሚመራ ሥርዓት እንዲዘረጋ ከመወሰኗና ከገበያው ጋር ለማቀረራረብ እየሰራች ባለበት ወቅት ይህንን ያህል ልዩነት መፈጠሩ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ጥያቄ ሆኗል። የብር የንምዛሪ ተመን ማሽቆልቆል በትግራይ ክልል ከተነሳውና በአማራና አፋር ክልል ከተዛመተው ጦርነት ጋር ተያይዞ አገሪቷ ካጋጠማት አለመረጋጋት በተጨማሪ የብር ተገቢውን ዋጋ መያዝ (ዲቫሉዌት) የማድረግ ጥረትና የንግድ ሚዛን ጉድለት እንደሆነም ባለሙያዎች ይናገራሉ። በተለይም የአገሪቷ የተዛባ የንግድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ እየታየ ያለው የወጪና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን በተጨማሪ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለዓመታት መንግሥት ብር ከዶላር ጋር ያለው ምንዛሪ ተመን መዳከም እንዳለበት ከመጎትጎታቸው ጋር ተያይዞ ይህ ተግባራዊ መሆኑ ብሩን አዳክሞታል። አገሪቱ በዓመት ወደ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እቃዎችን ከውጭ የምታስገባ ሲሆን 3.4 ቢሊዮን ዶላር ብቻ የሚያወጣ ምርቶችን ወደ ውጪ ትልካለች። ምንም እንኳን ይህ አሀዝ ጉድለት ቢታይበትም የአገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር ሲሻገር የመጀመሪያው ነው። አዲስ የቴሌኮም ፈቃድ ኢትዮጵያ ለ126 ዓመታት ያህል በመንግሥት ልማት ስር የነበረውን የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ክፍት በማድረግ የቴሌኮም ፈቃድ የሰጠችው በዘንድሮው ዓመት ነው። በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ለመሰማራት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጨረታ በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት በ850 ሚሊዮን ዶላር አሸንፏል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘው ይህ ጥምረት በዘርፉ አሉ የሚባሉ ስመ ጥር የቴሌኮም ኩባንያዎችንና ተቋማትን በቅንጅት የያዘ ሲሆን እነዚህም ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕና ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽንና ሲዲሲ ግሩፕ የተካተቱበት ነው። ጥምረቱ በኢትዮጵያ የሚሰጠውን የቴሌኮም አገልግሎት ከመጪው ጥር 2014 ዓ.ም በኋላ ይጀምራል ተብሏል። ዋነኛው የአገሪቱ አገልግሎት ሰጪ ኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻውን ለውጪ ባለሀብቶች፣ 5 በመቶውን ለኢትዮጵያውያን እና 55 በመቶውን በመንግሥት ይዞታ ይቀጥላል ተብሏል። ኢትዮጵያ ኢትዮቴሌኮምን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ድርሻ ለመሸጥ የወሰነችው በዋነኝነት ያላትን ከፍተኛ ዕዳ ለመክፈል ሲሆን፤ በተጨማሪነት የቴሌኮምን ተደራሽነት ለመጨመርና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እንደሆነም ይጠቀሳል። ኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድን ለመስጠት ወደ ገበያው መግባት የሚሹ ፍላጎታቸውን እንዲገልጹ ሲጠየቅ 12 የቴሌኮም ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ለመሳተፍ ፍለጎት እንዳላቸው ገልጸው ነበር። ከእነዚህ ውስጥም የፈረንሳዩን ኦሬንጅ ጨምሮ ሳዑዲ ቴሌኮም ኩባንያ፣ ሊኩዊድ ቴሌኮም፣ እንዲሁም የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ኢቲሳላትን ጨምሮ ሌሎች ኩባንያዎች አፈግፍገዋል። ለዚህም አንደኛው ምክንያት ሆኖ የተጠሰው የአገሪቱ ሕግ ለውጭ ተቋማት በሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ለመሰማራት አለመፍቀዱ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የቴሌኮም ፈቃድ ጨረታም እንደምታወጣ በገለፀችበት ወቅት የአገልግሎት ፈቃድ የሞባይል ገንዘብ መገበያያን እንዲጨምር ተደርጓል። በተያያዘም ኢትዮ ቴሌኮም በድምፅ፣ በመልዕክት፣ በኢንተርኔት ተወስኖ የነበረውን አገልግሎት በማስፋት የቴሌ ብር የሞባይል አገልግሎት አስጀምሯል። ተቋሙ ከቻይናው ሑዋዌ ኩባንያ ጋር በመተባበር ተግባራዊ ያደረገው ቴሌ ብር ለአስር ሚሊዮኖች ደንበኞቹ በስልካቸው ገንዘብ ለማስተላለፍና እና ለግብይት አገልግሎትም ይውላል ተብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም በአምስት ዓመት 33 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማገልገልና 3.5 ትሪሊየን ብር ለማንቀሳቀስ ማቀዱም ተዘግቧል። የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ብድር መልቀቅ ማቅማትና የናረው ዕዳ ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የገንዘብ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያንገራገሩ ነው ተብሏል። በዋነኝነትም የነዚህ ተቋማት ስጋት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የበለጠ ጫና ውስጥ ይከታታል እንዲሁም መክፈል አቋሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ጋር የተያያዘ ነው። የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጰያ ለመስጠት ቃል የገባውን 339 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑ ተነግሯል። ከዚህም በተጨማሪ የዓለም ባንክ አንድ አካል የሆነው የዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ማኅበር (ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን) 3.3 ቢሊዮን ዶላር፣ የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) 2.7 ቢሊዮን ዶላር፣ የኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ ቻይና 1.4 ቢሊዮን ዶላርና ሌሎችም አበዳሪዎች በያዝነው አመት እስከ መጋቢት ድረስ ይሰጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን አልተለቀቀም የተባለውም በዚህ አመት ነው። ከዚህም ጋር በተያያዘ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ሊያስተጓጉል እንደሚችል ተሰግቷል። ከሰሞኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ከአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ እዳው እስከ አውሮፓውያኑ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ 2.4 ትሪሊዮን ብር ሆኖ መመዝገቡን ሪፖርተር ጋዜጣ የገንዘብ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በዘገባው መሰረት ብሔራዊ ባንክ ባለፈው አንድ ዓመት ባደረገው የብር ምንዛሬ ተመን ለውጥ ምክንያት የብር የመግዛት አቅምም በከፍተኛ ደረጃ በመውረዱ አጠቃላይ የአገሪቱ እዳ በ221. 5 ቢሊዮን ብር እንዳሻቀበም ዘገባው አስነብቧል። የአገሪቱ ብሔራዊ ዕዳ በዚህ ዓመት 60 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) 70 በመቶ ይደርሳል ተብሏል። ብሔራዊ ባንክና አዳዲስ መመሪያዎቹ ብሔራዊ ባንክ በዘንድሮው ዓመት ከአምስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ከሒሳብ ወደ ሒሳብ ማዘዋወር የሚከለክለው ሰርኩላርን ጨምሮ፣ የባንኮች መመስረቻ ካፒታል አምስት ቢሊዮን ብር እንዲሆን የሚሉና ሌሎች ተጨማሪ አዳዲስ መመሪያዎችን አውጥቷል። ባንኩ በነሐሴ ወር ከዚህ ቀደም ባንኮች ይሰሩበት የነበረውን ቤት፣ ሕንፃ፣ መሬትና ሌሎችም ንብረቶችን በመያዣነት ተጠቅመው ብድር የሚሰጡበትን አሰራር አግዷል። ባንኩ ይህንን እርምጃ የወሰደው በኮኖሚው ውስጥ አሻጥር ታይቷል በሚል ሲሆን በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች መያዣነት የሚሰጠው ብድር እግድ እስከ መቼ እንደሆነ አልተጠቀሰም። ከዚህም በተጨማሪ በቅርቡ በከፍተኛ ሁኔታ እያንሰራራ ያለውን የዋጋ ግሽበትን ለመግታት ባንኮች ከሚሰበስቡት የተጣራ ቁጠባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ እንዲያስቀምጡት የሚጠበቅባቸውን የመጠባበቂያ የገንዘብ መጠን ወደ አስር በመቶ ከፍ እንዲያደርጉት ተወስኗል። ከዚህ ቀደም 5 በመቶ የነበረውን የመጠባበቂያ የገንዘብ መጠን ከፍ እንዲል የተደረገው በኢኮኖሚው ውስጥ የሚዘዋወረውን የገንዘብ መጠን ለመቀነስ ቁጥብ የገንዘብ ፖሊስ ለማድረግ ከመወሰኑ ጋር ተያይዞ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ የወለድ ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 16 በመቶ ከፍ እንዲል ተወስኗል። ከዚህም በተጨማሪ የውጭ ምንዛሬንም በተመለከተ አዲስ መመሪያ የተላለፈ ሲሆን ከወጪ ንግድ፣ ከግለሰብ ሃዋላና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ ውስጥ 50 በመቶውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ አለባቸው ተብሏል። እነዚህ በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ላይ ከታዩት ጉልህ ክስተቶች መካከል የተወሰኑት ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-58489178
amh
business
በኬንያ ከኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ የሚሰረቅ መርዛማ ዘይት ለምግብ ማብሰያነት እየተሸጠ ነው ተባለ
የኬንያ የኤሌክትሪክ አቅራቢ ድርጅት ከሃይል ማስተላላፊያ ወይም ትራንስፎረመር ላይ እየተሰረቀ እንደ ማብሰያ ዘይት የሚሸጠው ፈሳሽ መሰረተ ልማቶቹ ላይ ጉዳት በማድረስ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ኪሳራ እያስከተለ እንደሆነ ገለጸ። የኬንያ ኤሌክትሪክ ሃይል ወንጀለኞች ፈሳሹን ከትራንስፎርመሮቹ ውስጥ በማውጣት ለሬስቶራንቶች እና በመንገድ ዳር ምግብ ለሚያዘጋጁ በሽያጭ ቀርቦ ምግብ ለማብሰል እና ለመጥበስ እንደሚሸጥ አስታውቋል። ከምግብ ዘይት ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስፋፋ የመጣው ይህ ድርጊት አንዳንድ የንግድ ድርጅቶችን እነዚህ የሚዘረፉ ዘይቶችን መግዛትን ጨምሮ ወዳልተለመዱ የምግብ ማብሳያ አማራጮች እንዲሄዱ አድርጓቸዋል። የምግብ ዘይት የሚመስለው እና በትራንስፎርመር ውስጥ የሚገኘው ፈሳሸ ለሰው ልጅ ጤና አደጋ የሆነ እና ከፍተኛ የጤና ጠንቅ የሚያስከትል መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ። ሌሎች ወንጀለኞች ደግሞ የግለሰቦች ወይም የንግዶች ተቋማትን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በማቋረጥ መልሶ ለመቀጠል ገንዘብ ይጠይቃሉ። በኬንያ 20 የሚጠጉ ትራንስፎርመሮች እንደወደሙ ወይም ጉዳት እንደደረሰባቸው እና በማዕከላዊ ኬንያ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እየጨመረ መምጣቱን የኬንያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል። በኬንያ ቢያንስ 22 ሰዎች ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል። እየተፈጸሙ ባሉ ስርቆቶች ምክንያት ከፍተኛ የሃይል መቆራረጥ የገጠመው የኬንያ ኤሌክትሪክ ሃይል አሁኑ ላይ የሃይል መሰረተ ልማቶችን ማውደም ስለሚያስከትለው አደጋ በአገር አቀፍ ደረጃ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ጀምሯል። ከወራት በፊት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የተፈጸሙ ዝርፊያዎች በሃገሪቱ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የሃይል መቆራረጥ አስከትሏል።
https://www.bbc.com/amharic/61020009
amh
business
‘እጅ የበዛበት’ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ
ከሰሞኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ጋር ተያይዘው በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት ዕጣው ውድቅ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል። በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ የሆነውና ውዝግብ ባስከተለው ዕጣ ውስጥ መሳተፍ የነበረባቸው 79 ሺህ የሚሆኑ ተመዝጋቢዎች ቢሆኑም፣ በድብቅ የተዘጋጁ 172 ሺህ ያህል ሰዎች በዕጣው ውድድር ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርገዋል ተብሏል። በዚህም 93 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ተገቢ ባልሆነ መንገድ የጋራ መኖሪያ ቤት ለማግኘት በተዘጋጀው ዕጣ ውስጥ መካተታቸው ተገልጿል። ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ይህ የአዲስ አበባ ከተማ የጋራ ቤቶች ግንባታ እና ቤቶቹን የማስተላለፍ ሂደት በተለይም ዕጣ አወጣጡ ጋር ተያይዞ ከቅሬታዎች፣ ወቀሳዎችና ሐሜቶች ነጻ ሆኖ አያውቅም። የቤቶቹ ግንባታ ጥቃት፣ ግንባታቸው እና መሠረተ ልማቶቻቸው ያለመሟላት በየጊዜው የሚነሳ ጉዳይ ቢሆንም፣ በቤት ችግር እየተንገላታ ዕድሉ ይደርሰኛል ብሎ የሚጠብቀው ነዋሪ ዋነኛው ቅሬታ ግን ቤቶቹን የማስተላፍ ሂደቱ ወይም ዕጣው ሆኖ ቆይቷል። ከዚህ በፊት በነበሩት ሂደቶች ምዝገባው ውስጥ ያልተካተቱ ሰዎች በባለሥልጣንት ትዕዛዝ ቤቶቹ እንዲሰጣቸው ሲደረግ መቆየቱን ዘወትር የሚነሳ ጉዳይ ነው። በግንባታ ዕቃዎች መወደድ ምክንያት እና ግንባታዎችን ለማከናወን ባጋጠመ የገንዘብ ችግር ምክንያት በሚፈለገው መጠንና ፍጥነት መከናወን ያልቻለው የጋራ ቤቶች ግንባታ በርካቶች ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓል። በዚህ መካከል የከተማው አስተዳደር ተጠናቀዋል ያላቸውን ከ25 ሺህ በላይ ቤቶችን ይፋዊ በመሆነ ሂደት ለተመዝጋቢዎች ሊያስተላልፍ መሆኑን ባለፈው ሳምንት አሳውቆ ነበር። ይህም በቤት ችግር በእጅጉ እየተፈተነ ላለው የከተማው ነዋሪ አንዳች ተስፋን አጭሮ በጉጉት እንዲጠብቅ አድርጎታል። አርብ ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም. ለ20/80 እና ለ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝጋቢዎች ዕጣው በወጣበት ወቅት፣ ከንቲባዋ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት የከተማው አስተዳደር ዕጣው የሚወጣበት ሂደት ከአድልዎ ነጻ እንዲሆን የሚያደርግ የቴክኖሎጂ ሥርዓት መዘርጋቱን ተናግረው ነበር። ነገር ግን ከንቲባዋ እዳሉት ሳይሆን የዕጣ ማውጣቱ ሂደት ችግር እንደነበረበት ቅሬታ መቅረብ የጀመረው ብዙም ሳይቆይ ነበር። አስተዳደሩም ጥቆማዎች መድረሳቸውን ተከትሎ በአስቸኳይ የማጣራት ሥራ እንዲካሄድ ተደርጎ፣ የዕጣ ማውጣት ሂደቱ ተዓማኒነት የሌለው ስለነበረ ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንዲሆን ተወስኗል። የአዲስ አበባ ከንቲባዋ ከ14ኛው ዙር የዕጣ ማውጣት ሂደት ጋር በተገነናኘ የተከሰተውን ችግር “የቴክኖሎጂ ውንብድና አጋጥሞናል፣ ድርጊቱም አመራር የመራው ወንበዴ ነው” በማለት ሁኔታው የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት  ጭምር የተስተዋለበት እንደነበር ተናግረዋል። የዚህ ስራ ሌላው አላማ መንግሥት ህዝብን ማገልገል ብቃት የለውም የሚል ገፅታ ለመፍጠርና ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲያምፅ ለማድረግ በማሰብ ነው በማለት ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡ በዚህ ሂደት ችግር እንዳጋጠመን ማጣራት መጀመራችን ህዝብን ሃብት መታደግ እንድንችል አድርጎናል፡፡ ህዝቡን መታደግ ችለናል፡፡ ለከተማው አስተዳደሩ የዕጣ ማውጣት ሂደቱን በተመለከተ የቀረበው ሪፖርት ሥርዓቱ አስተማማኝ እንደሆነ ነው። በተጨማሪም የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ማረጋገጫ እንደሰጠው ቢነገርም፣ ተቋሙ ሕጋዊ በሆነ ደብዳቤ ማረጋገጫ እንዳልሰጠ በምርመራው ተደርሶበታል። ከንቲባዋ እንዳሉት ለዕጣው ሂደት ግብአት የሚሆኑ መረጃዎች (ዳታ) ለቀናት በሰዎች አጅ መቆየታቸውና ይህም የሆነው በኃላፊዎች ትዕዛዝ መሆኑን አመልክተዋል። ይህ በግለሰቦች እጅ የገባው ወሳኝ መረጃ ቤት ለማግኘት የሚጠበቀውን ቁጠባ ያቋረጡ እና በዚህ ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ብቁ ያልሆኑ ሰዎች ጭምር እንዲካተቱ ዕድልን ፈጥሯል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው እንዳሉት፣ ይህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተመዝጋቢዎች በዕጣ ለማስተላለፍ በከተማው አስተዳደር ሥራ ላይ የዋለው ሥርዓት በርካታ ችግሮች አሉበት። በዚህም ሥርዓቱ ተመሳሳይ ሶፍትዌሮችን ለማልማት የሚያስፈልጉ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያልጠበቀ መሆኑን አመልክተው፤ በዚህ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑትን “ሦስቱን አካላት፤ አልሚውን፣ ተጠቃሚውን እና አረጋጋጩን አካላት የቀላቀለ እንዲሁም ለምዝበራ ያጋለጠ ነው” ብለዋል ዶ/ር ሸመቴ። ጨምረውም ለዚህ የዕታ ማውጣት ሂደት ግብአት የመሆነው መረጃ (ዳታ)፣ ከእጅ ንክኪ ነጻ መሆን የሚጠበቅበት ቢሆንም፣ ነገር ግን እጅ በዝቶበት እንደነበረ ተገልጿል። ባለሙያዎችም እንዳሉት ዕጣውን ለማውጣት ጥቅም ላይ የዋለው ሥርዓት ሲዘጋጅ ተገቢውን መንገድ ያልተከተለና ሁሉም ሂደት በአንድ ሰው የተሰራ እንደሆነ አመልክተዋል። በሂደቱም ቤት ለማግኘት ተመዝግበው የሚጠበቅባቸውን ገንዘብ እየቆጠቡ ለዕጣ ብቁ የሆኑ ነዋሪዎችን የሚመለከተው ከባንክ እና ከቤቶች ልማት የተገኘው መረጃ የአያያዝ ችግር የነበረበትና ለውጥ ለማድረግ የተጋለጠ እንደነበር ተገልጿል። የመረጃ መዛባት በተፈጸመበት ኮምፒውተር ላይ በተደረገው ምርመራ የተፈጸሙ ሕገወጥ ድርጊቶች እንዳይታወቁ ለማድረግ የሚያስችሉ ጥንቃቄዎች መደረጋቸው የተደረሰበት ሲሆን፣ በተጨማሪም መረጃን ማጥፋት፣ መጨመር እና ማዘዋር ድርጊት መፈጸሙ ተረጋግጧል። በዚህ ተፈጸመ በተባለው “የቴክኖሎጂ ውንብድና” በአጠቃላይ ለውድድር ብቁ ናቸው ተብለው የተገለጹት 79 ሺህ የሚሆኑ ተመዝጋቢዎች የነበሩ ሲሆን፣ በድብቅ የተዘጋጁ 172 ሺህ ያህል ሰዎች ለዕጣው ዝግጁ ሆነው ነበር። በዚህም 93 ሺህ ተገቢ ያልሆኑ ሰዎች በዕጣው መካተታቸው ተገልጿል። በሕገወጥ መንገድ መረጃወቸው በዕጣው ውስጥ ተካተው ከተገኙት ውስጥ ደግሞ በባንክ የቆጠቡትን ገንዘብ ቀድመው አውጥተው የተዘጉ ተመዝጋቢዎች፣ የአመዘጋገብ ችግር ያለባቸውና ብቁ ያልሆኑ ሰዎች ጭምር ተካተው መገኘታቸውን በምርመራው የተሳተፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል። በሕገወጥ መንገድ በዕጣው ውስጥ እንዲካተቱ በተለያዩ መንገዶች የተዘጋጁ ሰዎች መረጃ ውስጥ እንዲካተት ብቻ ሳይሆን፣ ዕጣ ለማውጣት ጥቅም ላይ የዋለው ሥርዓት የሚፈለገውን ሰው ዕጣ እንዲያወጣ ተደርጎም  የተዘጋጀ መሆኑም ተመልክቷል። በዚህም የሚጠበቅባቸውን የቤት ቁጠባ በባንክ ሲያከናውኑ ከቆዩት ተመዝጋቢዎች መረጃ ውስጥ ያልተካተቱ ሰዎች በዕጣው አሸናፊ ሆነው መገኘታቸውም በምርመራ ተደርሶበታል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/ckvn7zepvp3o
amh
business
የዋነኛው ክሪፕቶከረንሲ ዋጋ እያሽቆለቆለ ያለው ለምንድን ነው?
ያለፉት ጥቂት ቀናት ለቢትኮይንም ሆነ ለክሪፕቶከረንሲ አስከፊ ጊዜ ነው። አሁን ላይ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ 21 ሺህ 974 ዶላር ነው። ቢትኮይን ቀድሞ ከነበረው ዋጋ ጋር ሲነጻጸር ባለፉት አምስት ቀናት ብቻ 25 በመቶ አሽቆልቁሏል። ይህም ባለፉት 18 ወራት የተመዘገበው ዝቅተኛው ዋጋው ነው። ቢትኮይን በዘመኑ ያወጣው ከፍተኛ ዋጋ ባለፈው ኅዳር ወር ላይ የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህም ዋጋው 70 ሺህ ዶላር የሚጠጋ ነበር። ባለሙያዎች እንደሚሉት ለዚህ ምክንያቱ በዓለም ላይ ያለው ሁኔታ ነው። በእርግጥ በዓለማችን ነገሮች ጥሩ መስለው የማይታዩት በክሪፕቶከረንሲው በኩል ብቻ አይደለም። በዓለም ዙርያ የምጣኔ ሃብት ቀውስ እያንዣበበ፣ የዋጋ ንረት እያሻቀበ፣ ወለድ እየጨመረ እና የኑሮ ውድነቱ እየናረ ነው። የአክሲዮን ገበያዎችም ብርክ ይዟቸዋል። የአሜሪካው ስታንዳርድ ኤንድ ፑርስ 500 የድርሻ ገበያ (ስቶክ ማርኬት) በቅርብ ጊዜ ከፍተኛ ከነበረው 20 በመቶ ቀንሷል። የድርሻ ገበያ ማለት ኩባንያዎች የኩባንያው የባለቤትነት ድርሻን ለገበያ የሚያቀርቡበት እና ሰዎችም ይህንን ድርሻ ከገዙ በኋላ ኩባንያው ትርፋማ በሆነበት መጠን ድርሻቸውን መልሰው በመሸጥ ወይም ከትርፍ ክፍፍል ትርፋማ የሚያደርግ አሠራር ነው። ይህ የድርሻ ገበያ በመቀነሱም ትላልቅ ባለሃብቶች ሳይቀሩ ኪሳራ እየገጠማቸው ነው። ሌሎችም በርካታ ተራ ባለሃብቶችም በማንኛውም ነገር ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ያላቸው ዕድል አነስተኛ ሆኗል። በርካቶች መዋዕለ ንዋያቸውን በዚህ ጊዜ እንደ ክሪፕቶከረንሲ ተለዋዋጭ እና እንዲህ ነው ተብሎ የማይተነበይ ነገር ላይ ማዋል ትልቅ አደጋ እንደሆነ ያስባሉ። ክሪፕቶከረንሲ፣ በገንዘብ ባለሥልጣናት ቁጥጥር የማይደረግበትና የማይጠበቅ ዲጂታል ገንዘብ ነው። በመሆኑም የቆጠቡትን ገንዘብ እርሱ ላይ ለማፍሰስ እየተጠቀሙበት ከሆነና ዋጋ ካጡበት አሊያም የዲጂታል ገንዘብ ማስቀመጫዎን ( ክሪፕቶ ዋሌት) ካጡት ገንዘብዎ ጠፍቷል ማለት ነው። ባለፈው ወር  ሁለት ብዙም የማይታወቁ ግን በጣም ትልቅ የሆኑ ዲጂታል ገንዘቦች ተንኮታኩተዋል። ይህም በአጠቃላይ በዲጂታል ገበያው ላይ ያለውን አመኔታ አሳጥቷል። በዚህም ምክንያት ያላቸውን ገንዘብ ለመሸጥ የሚወስኑ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በርካታ ሰዎች ቢትኮይናቸውን በሸጡ ቁጥር ደግሞ ያለው ዋጋ እየቀነሰ ይመጣል። ምክንያቱም ዲጂታል ገንዘቦችን ዋጋቸው እንዲዋዠቅ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ይህ በመሆኑ ነው። ዋጋው የሚወደደው የሚገዛ ሰው ሲበዛ እንጂ የሚሸጥ ሰው ሲበረክት አይደለም። ይህ ደግሞ በርካታ ሰዎች የቢትኮይን ዋጋ እየወረደ መምጣቱን በመመልከታቸው ያላቸውን እንዲሸጡ ገፋፍቷቸዋል። ዑደቱም በዚህ መልኩ ይቀጥላል። የፋይናንሻል ታይምስ ማርኬትስ አርታኢ ኬቲ ማርቲን፣ “ቢትኮይን እንደ ሌሎች ባህላዊ አሴቶች እርሱን ለመደገፍ የሚያስችል ሌላ ንግድ፣ የገቢ ፍሰት ወይም ሌሎች ነገሮች የሉትም” ይላሉ። ኬቲ አክለውም “ዋጋው ሰዎች ሊገዙ ያሰቡበት ዋጋ ብቻ ነው” ሲሉ የቢትኮይን ዋጋ የመሸጫ ሂሳቡ ላይ የተንጠለጠለ እንደሆነ አስረድተዋል። “በርካታ ሰዎች ተስፋ ቆርጠው ሸጠው ከወጡ፣ አበቃ። ምንም መቆሚያ የለም። ነገ በ10 ሺህ ዶላር ዋጋ መሸጡን የሚያስቆመው ምንም ነገር የለም” ብለዋል። በመሆኑም ባለፉት ጥቂት ቀናት ቢናንስ የተባለው ዓለም አቀፋዊው ትልቁ የክሪፕቶ መገበያያ መድረክ ለተወሰኑ ሰዓታት ቢትኮይንን እንዳይወጣ አድርጎ ነበር።  “ሁሉም ሰው ላያምን ቢችልም ይህንን ያደረግነው የገንዘብ ዝውውሩ በመቆሙ ነው” ብሏል። የክሪፕቶ አበዳሪ ሴልሲየስም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዷል። ይሁን እንጂ እርምጃውን የወሰደው በቴክኒክ ችግር ሳይሆን በከፍተኛ የገበያ ሁኔታ እንደሆነ ገልጿል። አሁን ላይ ደግሞ የክሪፕቶከረንሲ ኩባንያ፣ ኮይንቤዝ ሠራተኞቹን በ18 በመቶ መቀነሱን አስታውቋል። በሁኔታው የተደናገጡና ገንዘባቸውን ያፈሰሱ ባለሃብቶችም ቢትኮይናቸውን መሸጥ ጀምረዋል። የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት ቢትኮይን ያላቸው ሰዎች ይዘው መቆየት እና ሌሎች ደግሞ እንደገና መግዛት መጀመር አለባቸው። የክሪፕቶ አድናቂዎችም አዳዲስ ደንበኞችን ለማፍራት ርካሽ በመሆኑ ክሪፕቶ ለመግዛት ጊዜው አሁን እንደሆነ ይናገራሉ። ምክንያቱም ሁልጊዜም ቢትኮይን የሚሰራው በዚህ መልኩ ነው። የዋጋ መዋዠቁ ሁልጊዜም የሚያጋጥም እንጂ አዲስ ነገር እንዳልሆነ ተጠቃሚዎቹ ይገልጻሉ። በክሪፕቶ በአጭር ጊዜ ቱጃር የሆኑ ሰዎች ታሪክ እና የታዋቂ ሰዎች ገበያውን መቀላቀልም አዲስ ዲጂታል ገንዘብን ይስባሉ። ኤሎን መስክ ለክሪፕቶ ያለውን ፍቅር በትዊተር ገጹ አጋርቷል። መስክ በኤሌክትሪክ የሚሰራ መኪና ኩባንያው፣ ቴስላ ባለፈው ዓመት 1.5 ቢሊየን ዶላር ቢትኮይን ላይ አፍስሷል። ሆኖም የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። በዩናይትድ ኪንግደም የኢንቨስትመንት አማካሪ ሆኑት አልታፍ ካሳም ስለክሪፕቶከረንሲ መስክ “እውነቱን ለመናገር፣ ደፋር ሰው ብቻ መግባት ያለበት ቦታ ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ራዲዮ 5 ተናግረዋል። እውቁ የሆሊዉድ ተዋናይ ማት ዴመን፣ እአአ ጥቅምት 2021 ላይ “ገንዘብ ለደፋሮች ታደላለች” በሚል መልዕክት የክሪፕቶ ማስታወቂያ ሰርቷል። ማስታወቂያው በብሔራዊ የእግር ኳስ ሊግ ‘ሱፐር ቦውል’ ተለቅቆ በትዊተር እና በዩትዩብ 28 ሚሊየን ጊዜ ታይቷል። ሆኖም ማስታወቂያው በተለቀቀበት ወቅት ቢትኮይን የገዙት ‘ደፋሮች’ ምን አልባት አሁን ላይ ምንም ጥቅም እንዳላገኙ ላይሰማቸው ይችላል። አሊያም ደግሞ ደፋር በመሆናቸው የተጠቀሙት ገንዘብ እንደሌለ ሊረዱት ይችላሉ። ምክንያቱም ያኔ ቢትኮይን ዛሬ ከነበረው በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ዋጋ ነበረው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nzzqv8ljgo
amh
business
ክትባትና ውሃ አምራቹ ከእስያ ቁጥር አንድ ሀብታም ሆነ
ዞንግ ሻንሻን የእስያ ሀብታሞች ዝርዝርን በግንባር ቀደምነት መምራት ጀምሯል። ክትባት እና የታሸገ ውሃ ማምረቻ ባለቤት የሆነው ዞንግ፤ በዚህ ዓመት ሀብቱ ሰባት ቢሊየን ዶላር ጨምሯል። የሕንዱን ሙከሽ አምባኒ እና የቻይናውን ጃክ ማ በልጦም የእስያ ቁጥር አንድ ባለ ጸጋ ሆኗል። አጠቃላይ ሀብቱ ወደ 77.8 ቢሊየን ዶላር ይጠጋል። ይህም የዓለም 11ኛው ሀብታም እንደሚያደርገው የብሉምበርግ ቢሊየነር ኢንዴክስ ያሳያል። “ብቸኛው ተኩላ” በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ባለ ሀብት በጋዜጠኛነት፣ በእንጉዳይ እርሻና በጤናው ዘርፍም ሠርቷል። ሚያዝያ ላይ ክትባት አምራቹ ቤጂንግ ዋንታይ ባዮሎጂካል ተቋምን በቻይና የአክስዮን ገበያ አቅርቧል። ከሦስት ወራት በኋላ ደግሞ ኖንግፊ ስፕሪንግ የተባለውን ውሃ አምራች ኩባንያ ለሆንግ ኮንግ የአክስዮን ገበያ አቅርቧል። ከዚህ ቀደም የእስያ ቁጥር አንድ ሀብታም የአሊባባ መስራቹ ቻይናዊ ጃክ ማ ነበር። ኖንግፊ ስፕሪንግ ሆንክ ኮንግ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ የአክስዮን ዋጋው ወደ 155% አድጓል። የኮቪድ-19 ክትባትን ከሚሠሩ አንዱ የሆነው ቤጂንግ ዋንታይ ባዮሎጂካል የሼር ዋጋው ከ2,000% በላይ ደርሷል። እነዚህ ተደማምረው ዞንግ ሻንሻን ከእስያ ሀብታሞች ቁንጮው እንዲሆን አስችለውታል። ብሉምበርግ እንደሚለው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲህ ያለ ሀብት ንብረት ያፈራ ሰው በታሪክ አልታየም። በወረርሽኙ ወቅት የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስን ጨምሮ ብዙ ሀብታሞች ጥሪታቸው ጨምሯል። የሕንዱ አምባኒ ሀብት ከ18.3 ቢሊየን ወደ 76.9 ቢሊየን ዶላር አድጓል። በተቃራኒው የጃክ ማ ሀብት ጥቅምት ላይ ከ61.7 ቢሊየን ዶላር ወደ 51.2 ቢሊየን ወርዷል። አሊባባ በቻይና ባለሥልጣኖች ተደጋጋሚ ትንኮሳ ደርሶበታል። ድርጅቱ በምርቶች መካከል ፍትሐዊ ያልሆነ ውድድር በማድረግ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን፤ አጋር ድርጅቱ አንት ግሩፕ ጥቅምት ላይ ከአክስዮን ሽያጭ ታግዷል። አብዛኞቹ የቻይና አዳዲስ ቢሊየነሮች በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው። በሌላ በኩል በቻይና እና በአሜሪካ መካከል ሁዋዌ፣ ቲክቶክ እና ዊቻትን በተመለከተ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት የቻይና የአክስዮን ሽያጭ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳርፏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55495983
amh
business
አርጀንቲና በወረርሽኙ የተጠቁትን ለመደጎም የናጠጡ ኃብታሞቿ ላይ ግብር ጣለች
አርጀንቲና አገሯ በሚገኙ የናጠጡ ኃብታሞች ላይ ለየት ያለ ግብር ጥላለች። ግብሩ ለኮሮናቫይረስ የሚያስፈልጉ የህክምና ቁሳቁሶች ግብዓትና በወረርሽኙ ምክንያት ክፉኛ ለተጠቁት ኑሯቸውን መደጎሚያ እንዲሆን ነው። የምክር ቤቱ አባላት "የሚሊዮነሮች ግብር" ብለው የጠሩት በአንዴ የሚከፈል ገንዘብ ሲሆን በዚህ ሳምንት አርብም 42 ለ 26 በሆነ የድምፅ ብልጫም ፀድቋል። በዚህም መሰረት ከ200 ሚሊዮን ፔሶ (2.5 ሚሊዮን ዶላር) ኃብት ያከማቹ ግለሰቦች መክፈል አለባቸው። በአገሪቱ ይህ የገንዘብ መጠን ያላቸውም ወደ 12 ሺህ ግለሰቦች ናቸው ተብሏል። አርጀንቲና በወረርሽኙ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንዷ ስትሆን እስካሁን ባለውም መረጃ 1.5 ሚሊዮን በቫይረሱ ሲያዙ 40 ሺህ ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። የህዝብ ቁጥሯ 45 ሚሊዮን ብቻ የሆነው አርጀንቲና በወረርሽኙ በሚሊዮኖች በተያዙ ተርታ አምስተኛ ደረጃን ይዛለች። ከህዝብ ቁጥሯ ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ከሚሊዮን በላይ ካስመዘገቡ ትንሿ አገር አድርጓታል። ወረርሽኙን ለመግታት ያስቀመጠቻቸው መመሪያዎች ከፍተኛ ተፅእኖን አሳርፈዋል። በስራ አጥነት፣ በርካታዎች በድህነት ወለል በሚኖሩባትና አገሪቷ ራሷ በብድር በተዘፈቀበችበት ሁኔታ መመሪያዎቹ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነዋል። አርጀንቲና ከ2018 ጀምሮም በምጣኔ ኃብት ድቀት ላይ ናት። የሚሊዮነሮችን ግብር ካረቀቁት መካከል አንዱ ህጉ 0.8 በመቶ የሚሆነውን ግብር ከፋይ ብቻ ነው የሚመለከተው ብለዋል። በአርጀንቲና ውስጥ ያሉት ሃብታሞች፣ ከአንጡራ ሃብታቸው 3.5 በመቶ እንዲሁም ከአገር ውጭ ያሉ አርጀንቲናውያን ደግሞ 5.25 በመቶ እንዲከፍሉ ውሳኔ ተላልፏል። ከግብሩ የተሰበሰበው ገንዘብም መካከል 20 በመቶ ለህክምና ቁሳቁሶች፣ 20 በመቶ ለጥቃቅንና አነስተኛ ነጋዴዎች፣ 20 በመቶ ለተማሪዎች የትምህርት ቤት ክፍያ፣ 15 በመቶ ለማህበራዊ ልማትና ቀሪው 25 በመቶ ደግሞ ለተፈጥሮ ነዳጅ ስራዎች እንደሚውል ኤኤፍፒ በዘገባው አስነብቧል። ግራ ዘመሙ ፕሬዚዳንት አልበርቶ ፈርናንዴዝ መንግሥት 300 ቢሊዮን ፔሶም ለማሰባሰብ እቅድ ይዘዋል። ሆኖም የተቃዋሚዎች ፓርቲ ቡድኖች በበኩላቸው ይህ የአንድ ጊዜ ግብር ሊሆን ስለማይችል የውጭ አገራት ኢንቨስትሮችን ፍራቻ ላይ ይጥላል በማለት ተችተዋል። የቀኝ ክንፍ ፓርቲ ጁንቶስ ፖር ኤል ካምቢዮ በበኩሉ የማይገባ ሲል የፈረጀው ሲሆን "ነጠቃም" ነው ብሎታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55191619
amh
business
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቻይናውያን ግላዊ መረጃ ተሰርቆ ለሽያጭ መቅረቡ አነጋጋሪ ሆኗል
አንድ የበይነ መረብ መረጃ ሰርሳሪ ከቻይና የፖሊስ ተቋም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን መረጃ መዝብሮ ለሽያጭ ማቅረቡን ተከትሎ ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኗል። ይህ አንድ ቢሊየን ይደርሳሉ የተባሉ የቻይናውያን ግላዊ መረጃ ስርቆት ዜና ይፋ ከሆነ በኋላም የአገሪቱ ፕሬዝዳንት የሕዝቡ መረጃ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግለት አሳስበዋል። የበይነ መረብ መረጃ ሰርሳሪዎች (ሃከርስ) ሰርቀነዋል ያሉትን የቻይናውያንን መረጃ የሚገዛቸው ካለ ለመሸጥ ማስታወቂያ ካወጡ በኋላ ነው፣ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ሕዝባዊ ተቋማት “የመረጃ ደኅንነታቸውን እንዲያጠናክሩ” ጥሪ ያቀረቡት። ኋላ ላይ በተነሳ እና በሕገወጥ የበይነ መረብ መድረክ ላይ በወጣው ማስታወቂያ እንደተጠቀሰው ለሽያጭ የቀረቡት ግላዊ መረጃዎች ከሻንግሃይ ብሔራዊ ፖሊስ የተሰረቁ መሆናቸው ተገልጿል። የበይነ መረብ መረጃውን የሰረቀውና ለሽያጭ ያቀረበው ግለሰብ በእጁ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቻይናውያን ስም፣ አድራሻ፣ የብሔራዊ መታወቂያ ቁጥር እና የሞባይል ቁጥራቸውን ጨምሮ ሌሎች መረጃዎች እንዳሉት አመልክቷል። የበይነ መረብ መረጃ ደኅንነት ባለሙያዎችም ተሰርቀዋል ከተባሉት ግላዊ መረጃዎች ውስጥ ናሙናዎችን በመውሰድ ባደረጉት ማጣራት ስርቆቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል። ከፍተኛ መጠን ያለው ይህ መረጃ 23 ቴራባይት ይሆናል ተብሎ የሚገመት ሲሆን፣ ይህም በ200 ሺህ ዶላር ለሽያጭ የቀረበ ትልቁ መረጃ ነው ተብሏል። ድርጊቱ ወንጀል በመሆኑ ማስታወቂያው ከተለጠፈበት ድረ ገጽ ላይ እንዲነሳ ተደርጓል። ነገር ግን ይህ ተሰረቀ ስለተባለው ግዙፍ ግላዊ መረጃ ክምችትን በተመለከተ የትኛውም የቻይና ባለሥልጣን አስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ፕሬዝዳንቱም ቢሆኑ ጉዳዩን በሚመለከት በቀጥታ ምንም አላሉም። ‘ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት’ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ዢ፣ ዜጎች ለሕዝባዊ አገልግሎቶች ግላዊ መረጃዎችን ሲሰጡ ደኅንት እንዲሰማቸው ለማድረግ ተቋማት “ለግላዊ መረጃዎች እና ለምስጢራዊ የተቋማት መረጃዎች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደረጉ” አሳስበዋል። ተሰረቀ ስለተባለው ግዝፍ መረጃ ሽያጭን በተመለከተ የወጣውን የበይነ መረብ ማስታወቂያ ተከትሎ የገጹ ተቆጣጣሪዎች የሚከተለውን ጽሁፍ አስፍረው በኋላም ማስታወቂያውን አንስተውታል። “የተወደዳችሁ ቻይናውያን ተጠቃሚዎች፣ እንኳን ወደ መድረካችን በደህና መጣችሁ። ብዙዎቻችሁ ወደ እዚህ ገጽ የመጣችሁት ከሻንግሃይ ፖሊስ ባፈተለኩ መረጃዎች ምክንያት ነው። መረጃው ከዚህ በኋላ ለሽያጭ አይውልም፣ በተጨማሪም ከዚሁ ጉዳይ ጋር የሚያያዙ ርዕሶች በሙሉ ከገጹ ላይ እንዲሰረዙ ተደርገዋል” ብሏል። የድረ ገጹ ተቆጣጣሪዎች ጨምረውም ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው ሌሎች የቻይና መረጃዎች እጃቸው ላይ እንዳሉና ለሽያጭም ሊያቀርቧቸው እንደሚችሉ አሳውቀዋል። “ያለነው ቻይና ውስጥ አይደለም፣ ቻይናውያንም አይደለንም። ስለዚህም ለቻይና ሕጎች ተገዢ መሆን የለብንም” ሲሉ ስለማንነታቸው ድፍን ያለ ምላሽ ሰጥተዋል። በበይነ መረብ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚከታተለው ‘ዳርክትሬሰር’ የተባለው ቡድን እንዳለው ይህ የመረጃ ምዝበራ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል። ይህም ምናልባት በቻይናውያን መረጃ ላይ ተፈጽሟል በተባለው ስርቆት አማካይነት በተፈጠረው ትኩረት የተነሳሳ ነው የተባለ ሌላ የበይነ መረብ መረጃ መዝባሪ ተመሳሳይ የሽያጭ ማስታወቂያ አውጥቷል። በዚህም የበይነ መረብ መረጃ ሰርሳሪው እዚያው ቻይና ውስጥ ከሚገኘው የሄናን ግዛት ብሔራዊ ፖሊስ የመረጃ ቋት የመዘበረው የ90 ሚሊዮን ሰዎች መረጃዎች እጁ ላይ እንዳለ ገልጿል። ነገር ግን ይህ ምን ያህል እውነት እንደሆነ በበይነ መረብ ደኅንነት ባለሙያዎች አልተረጋገጠም። ባለሙያዎች ይህ ተሰረቀ የተባለው ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃ ጉዳይ ለቻይና ባለሥልጣናት ዋነኛ አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ፣ የሽያጭ ማስታወቂያውን በተመለከተ በአገሪቱ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ማገዳቸውን በመጥቀስ ተናግረዋል። በዘርፉ ደኅንት ጉዳዮች ላይ የሚሰራው የ‘ፎሬንሲክ ፓዝዌይ’ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዴብ ሌሪ እንደሚያምኑት፣ መረጃው ከፍተኛውን ክፍያ ላቀረበ ወገን ተሽጧል ወይም የበይነ መረብ ሰርሳሪዎቹ እንዲህ አይነት ግላዊ መረጃን የሚፈልጉ ወደ እነሱ እንዲመጡ ለማስተዋወቅ ተጠቀሙበት ዘዴ ሊሆን ይችላል ብለዋል። ምክንያቱም “ድርጊታቸው የቻይና መንግሥት ባለሥልጣናትን ሊያስቆጣ እንሚችል ብዙም አላሳሰባቸውም” ብለዋል። ባለፈው ሚያዝያ ወር በይነ መረቦችን ሰብሮ በመግባት መረጃዎችን የሚመዘብረው ‘ራይድ ፎረምስ’ የተባለው ድረ ገጽ በአሜሪካው የፌደራል ደኅንነት መሥሪያ ቤት መሪነት በተካሄደ ዓለም አቀፍ የፖሊስ ዘመቻ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲዘጋ ተደርጓል። በዚህም ፖርቱጋላዊው የድረ ገጹ መስራች እና አንድ ብሪታኒያዊ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። አሁን ቻይና ውስጥ ተሰርቋል የተባለው አይነት ከፍተኛ መጠን ያለው የግሰቦች ግላዊ መረጃዎች፣ ትክክለኛ ባለቤቶቹን አስመስሎ መልዕክት ለመላክ እና ሌሎች መጥፎ ድርጊቶችን በመፈጸም ወንጀለኞች ገንዘብ ለማግኘት ጥቅም ላይ ሊያውሉት ይችላል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቻይናውያን ግላዊ መረጃ መሰረቁን በተመለከተ የተለያዩ መላምቶች እየቀረቡ ሲሆን፣ በትክክል ይህን ያህል ግዙፍ መረጃ በሰርሳሪዎች እጅ ከገባ አስካሁን ካጋጠሙ የመረጃ ምዝበራዎች ሁሉ የላቀው ነው ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cp42eek8x71o
amh
business
ቦይንግ ከ737 ማክስ ጋር በተያያዘ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ
ቦይንግ ስለ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ዲዛይን ከአሜሪካ የደኅንነት እና ጥንቃቄ ባለሙያዎች መረጃዎችን በመደበቅ ለተመሰረተበት የወንጀል ክስ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ለመክፈል ተስማማ። የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ እንዳለው ከሆነ ኩባንያው "ከግልጽነት ይልቅ ትርፍን" አስቀድሟል። ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በኢትዮጵያ እና በኢዶኔዢያ ተከስክሶ የ346 ሰዎች ህይወት አልፏል። ቦይንግ ለመክፈል ከተስማማው ገንዘብ ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ በአውሮፕላኑ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ የሚከፋፈል ይሆናል። ቦይንግ እንዳለው ይህ ስምምነት ኩባንያው "ያለበት ጉድለት" ምን ያህል መሆኑን ያሳያል። የቦይንግ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ዴቪድ ካልሁን እንዳሉት "ወደ እዚህ ስምምነት መግባታችን ትክክለኛው ነገር እንደሆነ በጽኑ አምናለሁ፤ ይህም ከእሴቶቻችን እና ከሚጠበቅብን ምን ያህል ወደ ኋላ መቅረታችንን ያሳያል።" "ይህ ስምምነት ሁላችንንም የሚያስታውሰን ለግልጽነት የገባነው ግዴታ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ፤ እንዲሁም አንዳችንም እንኳን እርሱን ሳናሟላ ብንቀር መዘዙ የከፋ መሆኑን ነው።" የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ እንዳለው ከሆነ የቦይንግ ባለስልጣናት በኢንዶኔዢያ እና በኢትዮጵያ ለአውሮፕላኑ መከስከስ ምክንያት ስለሆነው ኤምካስ የተባለው አውቶማቲክ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓት ላይ ስላለ ለውጥ መረጃ ደብቀዋል። ይህ ውሳኔ የሚያሳው የአውሮፕላን አብራሪው ስልጠና መመሪያ ስለሥርዓቱ በቂ መረጃ አለመያዙን፣ ይህም በተሳሳተ መረጃ የአውቶማቲክ ሥርዓቱ የአብራሪውን ውሳኔ እንደሚሽረውና፣ ይህም አውሮፕላኑ ከማኮብኮቢያው በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አፍንጫውን አዘቅዝቆ ቁልቁል እንዲምዘገዘግ እንደሚያደርገው ነው። ቦይንግ ከምርመራ ባለሙያዎች ጋር ለስድስት ወር ያህል ትብብር አለማድረጉን የፍትህ ቢሮው ጨምሮ ተገልጿል። "በላየን አየር መንገድ በረራ 610 እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 302 አውሮፕላኖች ላይ የደረሰው አሳዛኝ አደጋ፣ በዓለማችን ቀዳሚ የንግድ አውሮፕላኖች አምራች የሆነው ኩባንያ ሠራተኞች የማጭበርበር እና ማታለል ባሕሪያቸውን አጋልጧል" ያሉት ደግሞ ረዳት ተጠባባቂ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዴቪድ በርንስ ናቸው። "የቦይንግ ሠራተኞች 737 ማክስ አውሮፕላንን በሚመለከት መረጃን ከተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት በመደበቅ፣ ስህተታቸውን ለመሸፋፈን በመተባበር ከደኅንነት ይልቅ ትርፍን አስቀድመዋል" ብለዋል። ኩባንያው ሊከፍል ከተስማማው አብዛኛው ገንዘብ፣ 1.7 ቢሊዮን ዶላሩ ለተጎጂ ቤተሰቦች የሚሰጥ ሲሆን፣ የተወሰነውም ተከፍሏል ተብሏል። ኩባንያው 243.6 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ለመክፈልም ተስማምቷል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሕይወታቸወን ላጡ ቤተሰቦች ጥብቅና የቆሙት ባለሙያዎች ግን ይህ የኩባንያው ውሳኔ የመሰረቱትን ክስ እንዲያቋርጡ እንደማያደርጋቸው ገልፀዋል። ጠበቆቹ አክለውም ሁሉም የኩባንያው 737 ማክስ አውሮፕላኖች ደኅንነት በገለልተኛ ወገን እስኪረጋገጥ ድረስ ወደ በረራ እንዲገቡ መፈቀድ የለበትም ብለዋል። የአሜሪካ ደኅንነት ተቆጣጣሪዎች ከታኅሣስ ወር ጀምሮ አውሮፕላኖቹን ለበረራ ዝግጁ ናቸው በማለታቸው ወደ ሥራ ተመልሰዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55570801
amh
health
ዘግታችሁ የወጣችሁትን በር እንዳልተዘጋ የሚያሳስባችሁ የአእምሮ ሕመም - ኦሲዲ
ምሥራቅ* ለዚህ ታሪክ ሲባል ስሟ የተቀየረ “ለሦስት ዓመታት የማስበውን ሁሉ እንድጽፍ አእምሮዬ ያስገድደኝ ነበር” ትላለች። እንቅልፍ እና እርሷ ተፋትተው ነበር የከረሙት። “ዝም ብዬ መጻፍ ነው። ደብተር፣ ወረቀት፣ ሞባይል ሁሉ ነገር ላይ እጽፋለሁ።” የምትጽፈው ነገር ለሚያነበው ሰው ትርጉም ላይሰጥ ይችላል። ማንኛውንም ነገር በአእምሮዋ ውስጥ ሰንዳ የያዘቸውን ወይም የመጣላትን ጥቃቅን ነገር ሁሉ ካልጻፈች ሰላም ይነሳታል። “ፀጉሬ ላይ ቅባት ተቀብቼ ጥሩ ነው ብዬ ካሰብኩኝ እጽፈዋለሁ።” ይህ የመጻፍ ጉትጎታ ግን አንድ ቀን ተገታ። “አንድ ቀን ለሊቱን ሙሉ ቁጭ ብዬ ስጽፍ አደርኩ፤ የዚያን ቀን ይህ ነገር የወጣልኝ ይመስለኛል።” ምሥራቅ ባይፖላር ዲስኦርደር በተባለ የአእምሮ ሕመም (በሁለት የተለያዩ የስሜት ጽንፎች መካከል መዋለል) እየተቸገረች እያለ ነው ይህ ዕክል የተጨመረባት። ኦሲዲ (ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር) ይባላል ነገሮችን በተደጋጋሚ ለመስራት ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ጎትጓች ስሜት መሰማት ነው። “በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነው ያሳለፍኩት፤ አሁን በሕይወት መኖሬ በጣም ይገርመኛል፤ ሥራዬን ለቅቄ ነበር። ይህንን በራሴ መቆጣጠር ስላቃተኝ መልሶ ጭንቀት ውስጥ አስገብቶኛል።” ምሥራቅ ሕመሟን ለሌሎች መንገር አልፈለገችም። ምክንያቷ ደግሞ 'ማን ይረዳኛል' የሚል ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ደግሞ ይህ ሕመሟ እንደ አዲስ ተመልሶ አገረሸባት። “የዘጋሁትን በር እንዳልዘጋሁ ይሰማኛል። በተለይ ደግሞ የእሳት ነገር ወደ ጭንቅላቴ እየመጣ ያስጨንቀኛል፤ ስቶቭ ለኩሼ የተውኩ ያህል ይሰማኛል። በዚህ ምክንያት ቀኑን ሙሉ ስብሰለሰል ነው የምውለው።” ምሥራቅ አእምሮ ውስጥ እየመጣ የሚያስጨንቃት ጎትጓች ሃሳብ፣ ሕመም መሆኑን ሳታውቅ ለረዥም ጊዜ ቆይታለች። ይህ ጉዳይ ሕመም እንደሆነ ያወቀችው በቴሌቪዥን ካገኘችው መረጃ የተነሳ ነው። ቢቢሲ ወደ ሕክምና አልሄድሽም ሲል ጠይቋት ነበር። “ሕክምና ለማግኘት ስሄድ አእምሮሽን ዝም አስብይው ይሉኛል። ግን እርሱን ማድረግ ብችል ኖሮ ለምን ወደ ሕክምና እሄዳለሁ” ትላለች። ሐኪም የተሰኘው እና በሕክምና ባለሙያዎች የተመሰረተው ማኅበራዊ ድረ ገጽ ኦሲዲ (ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር)ን በተመለከተ ይህንን ይላል። “ኦሲዲ በአጭሩ ሲገለጽ ጥርጣሬ የሚፈጥር የሚነዘንዝ ሀሳብና እና ሃሳብ ተከትሎ ለማርገብ የሚደረግ ተደጋጋሚ ድርጊት ነው” ሲል አስፍሯል። በዚህ የአእምሮ ሕመም ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሕመሙ በየትኛውም የእድሜ ክልል ያለ ሰው ላይ ሊከሰት ይችላል። የህመሙ መንስዔ ምን እንደሆነ በእርግጠኝነት የሚታወቅ ነገር የለም። ዶክተር ዮናስ ባሕረጥበብ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአእምሮ ሕክምና ክፍል መምህር ሲሆኑ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ደግሞ የአእምሮ ሕመም ሐኪም ናቸው። ሐኪሙ ይህንን ሕመም ሲገልፁት “ከእኛ ፍላጎት ውጪ፣ ወደ አእምሯችን የሚመጣ ሐሳብ ወይንም ደግሞ አንድን ድርጊት በተደጋጋሚ ለመፈፀም መፈለግ፣ በተግባርም ማዋልንም ይጨምራል” ይላሉ። ዶ/ር ዮናስ እንደሚሉት በዚህ የአእምሮ ሕመም የተያዙ ሰዎች ወደ አእምሯቸው የሚመጣውን ሐሳብ መቆጣጠር ካለመቻላቸው በተጨማሪ ያለፍላጎታቸው ወደ ጭንቅላታቸው የሚመጣ ነው። “በተጨማሪም ይህ ያለፍላጎታችን የሚመጣብን ሐሳብ ደስ የማይል እና የሚያስጨንቀን ሊሆን ይችላል” ሲሉ ያክላሉ። በልጅነታቸው ሥነ ልቦናዊም ሆነ አካላዊ ጥቃት ወይንም ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሲጎለምሱ ለዚህ ሕመም ሊጋለጡ እንደሚችሉ ይናገራሉ። “አንዳንድ ሰዎች ወደ አእምሯቸው የሚመጣ ተደጋጋሚ ሃሳብ ብቻ ሊኖራቸው ይችላል። ሌሎች ደግሞ አንድን ነገር ደጋግሞ የመፈፀም ጠንካራ ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል። ያንንም በመፈፀም ለአጭር ጊዜም ቢሆን እፎይታ ያገኙ ይመስላቸዋል” ይላሉ። ዶ/ር ዮናስ ይህንን በምሳሌ ሲያስረዱ፣ “አንድ ሰው በሃሳቡ እጅህ ላይ ጀርም ወይንም ደግሞ እጅህ ቆሻሻ ነው የሚል ነገር ይመጣበታል። ይህም አንዴ እና ሁለቴ ሳይሆን በተደጋጋሚ ስለሚመጣበት እጁን ንፁህ እንደሆነ ቢያውቅ እንኳ በቀን እስከ 30 ጊዜ ሊታጠብ ይችላል።” “ደምህ ውሰጥ ኤችአይቪ አለ የሚል ሃሳብ የሚመጣባቸው ሰዎች አሉ። ያ ሰው ተመርምሮ በሽታው በደሙ ውስጥ እንደሌለ ቢያውቅ እንኳ ይህንን ተደጋጋሚ ሀሳብ ግን ማቆምም ሆነ ማቋረጥ አይችልም።” ዶ/ር ዮናስ እንደሚሉት ይህ ኦሲዲ የተባለ የአእምሮ ሕመም ሥራ እየሰራን ወይንም በየትኛውም የሕይወታችን እንቅስቃሴ፣ በመካከል ሊመጣብን ስለሚችል የምንሰራውን ወይንም ድርጊታችንን አቁመን በሃሳቡ ልንያዝ እንችላለን። “እኛ የማንፈልገው፣ ፈጣሪያችን የሚያሳዝን ሃሳብ ወደ አእምሯችን ይመጣል፤ ማስቆም አልቻልንም ብለው ለሕክምና ወደ እኛ ይመጣሉ” ሲሉ ባለሙያው ከልምዳቸው ይናገራሉ። ዶ/ር ዮናስ ይህ ሁኔታ ሕክምና ሊያስፈልገው ደረጃ ላይ የሚደርስበት ዕድል ስላለ ምልክቶቹን መረዳት አስፈላጊ ነው ይላሉ። ከዚህ ውጪ ግን ይህ ሁኔታ እንደ ባህርይ ብቻ ያላቸው ሰዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሰሩ ይሆናሉ ይላሉ። “የሂሳብ ባለሙያዎች፣ በተደጋጋሚ የማጣራት እና የማረጋጋጥ ባሕርይ ስላላቸው ስሌት አይሳሳቱም። ሌሎች እንደ ፓይለት እና ሜካኒክ ዓይነት ሥራዎችም ከፍተኛ ጥንቃቄ ስለሚፈልጉ ይህንን ዓይነት ባሕርይ ያላቸው ሰዎች በእነዚህ ሙያዎች ልህቀትን ሊያሳዩ ይችላሉ።” አክለውም ይህ የኦሲዲ ሕመም በራሱ ወደ ሌላ ከባድ የአእምሮ ሕመም ባይቀየርም፣ ነገር ግን ወደ አእምሯችን የሚመጣ ተደጋጋሚ ሃሳብ እና የምንፈጽመው ተደጋጋሚ ድርጊት መልሶ ሊያስጨንቀን ወይንም ደግሞ ድባቴ ሊያመጣ እንደሚችል ዶ/ር ዮናስ ይገልጻሉ። ለዚህ ሕመም የሚሰጠው ሕክምና በቂ አለመሆኑን የምታስረዳው ምሥራቅ፣ “በሩን ክፍቱን አድርጌ ብሔድ፣ ሊፈጠር የሚችለው ክፉ ነገር ምን ሊሆን ይችላል ብዬ በማሰብ፣ ሃሳቡን ለማስቆም እጥር ነበር። ነገር ግን መጨረሻ ላይ ስላልቻልኩኝ መድኃኒት መውሰድ ግድ ሆነ” ትላለች። አሁን በፀሎት እና በተሰጠኝ መድኃኒት ለውጥ እያሳየሁ ነው ስትል የምትናገረው ምሥራቅ፣ ለሕመሟ የተሰጣት መድኃኒት መጀመሪያ አካባቢ ሕመሟን አብሶባት እንደነበር ታስታውሳለች። “በዚህ ምክንያት መድኃኒቱን ከሁለት ጊዜ በላይ ቀይሬያለሁ።” በዚህ ሕመም ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚሰጣቸው የተለያየ ዓይነት ሕክምና አለ። አንዱ የሥነ ልቦና የምክር አገልግሎት ሲሆን በዚህም ሳይፈልጉት የሚመጣባቸውን ሃሳብ ሊቆጣጠሩ የሚችሉበትን ዘዴዎች ይማራሉ። ሁለተኛው ደግሞ አእምሮ እና ሰውነት እንዲፍታታ የማድረግ ሕክምና ነው። “ለምሳሌ ሜዲቴሽን (አርምሞ)፣ እንደ ዮጋ ያሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ማሳጅ ማድረግ” ናቸው። ከእነዚህ ባሻገር ደግሞ በሽታውን ሊቆጣጠረው የሚችለው መፍትሔ ለሕመሙ የተዘጋጀውን መድኃኒት መውሰድ ነው። እነዚህ የሕክምና ዓይነቶች የሰውየው የሕመም ዓይነት እና ደረጃ ላይ በመመስረት ከበሽታው እንዲድን ሊያደርጉ ይችላሉ ይላሉ ዶ/ር ዮናስ። አሁን እየተሻላት እንደሆነ የምትናገረው ምሥራቅ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ምልክቶችን ካዩ በፍጥነት ወደ ሕክምና እንዲሄዱ ትመክራለች።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c6pqpg24lvno
amh
health
'ባሌ አጫሽ ነበረ፣ በእሱ ምክንያት ካንሰር ያዘኝ'
“በአፍንጫዬ መተንፈስ አልችልም። የምተነፍሰው ‘ስቶማ’ በሚባልና አንገቴ ላይ በሚገኝ ቀዳዳ አማካይነት ነው’’ ይላሉ የ75 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋዋ ናሊኒ ሳትያናርያን። ናሊኒ በህይወታቸው እንድም ቀን ሲጋራ አጭሰው አያውቁም። ነገር ግን ላለፉት 33 ዓመታት ባለቤታቸው ከሚያጨሱት ሲጋራ የሚመጣ ጭስ ሲተነፍሱ ኖረዋል። ባለቤታቸው ሕይወታቸው ካለፈ ከአምስት ዓመታት በኋላ በአውሮፓውያኑ 2010 ላይ ናሊኒ ካንሰር እንዳለባቸው ተነገራቸው። “ባለቤቴ አጫሽ ነበር። የእሱ ሲጋራ ማጨስ እኔን ይሄን ያክል ይጎዳኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ለእሱ ጤና ነበር የምጨነቀው። ሁሌም ሲጋራ ማጨሱን እንዲያቆም ነበር የምነግረው። ነገር ግን ሲጋራ ማጨሱን አልተወም ነበር” ይላሉ በሕንዷ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ሀይድራባድ የሚኖሩት ናሊኒ። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ሲጋራ በየዓመቱ እስከ 8 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን ይገድላል። ከእነዚህ መካከል ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ሲጋራ አጫሽ አይደሉም። አብዛኞቹ በዙሪያቸው የሚገኙ ሰዎች ሲጋራ አጫሾች የሆኑ ናቸው። በርካቶችም በዚሁ ምክንያት ለተለያዩ ሕመሞች እየተጋለጡ ነው። በየዓመቱ ግንቦት 23 የዓለም የፀረ ትንባሆ ቀን ነው። ናሊኒ በአንድ ወቅት ለልጅ ልጃቸው ታሪክ እያጫወቷት እያለ ነበር ድንገት የድምጻቸውን መቀየር ያስተዋሉት። በአጭር ጊዜ ውስጥ ደግሞ በትክክል አንዳንድ ድምጾችን ማውጣት እያቃታቸው መጣ። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ደግሞ መተንፈስ ጭምር ከባድ እየሆነ መምጣት ጀመረ። ናሊኒ ወደ ህክምና ቦታ ሲሄዱ ያልጠበቁትን ዜና ሰሙ። ካንሰር እንዳለባቸውና በቀዶ ሕክምና ጉዳቱን መቀነስ እንደሚቻል ተነገራቸው። በቀዶ ሕክምናውም ድምጽ የሚያወጣው የጉሮሯቸው ክፍልና የታይሮይድ ዕጢያቸው እንዲወገዱ ተደረገ። “ከሕክምናው በኋላ መናገር አልቻልኩም። በጣም የሚያሳዝን አጋጣሚ ነበር። ዶክተሮቹ የቀድሞ ድምጼን ደግሜ ማግኘት እንደማልችል ነገሩኝ።” የናሊኒ የልጅ ልጅ የሆነችው የ15 ዓመቷ ጃናኒ ተጨዋች የሆኑት አያቷ ላይ የሆነውን ነገር በደንብ ታስታውሳለች። “ካንሰር እንዳለባት ሲነገራት ለረጅም ጊዜ እኛ ጋር አልነበረችም። ተመልሳ ስትመጣ የአራት ዓመት ልጅ ነበርኩ። ሆዷ አካባቢ ቱቦ ነገር ተለጥፎባት ነበር። ቤታችንን ቶሎ ቶሎ ማጽዳት ነበረብን። አያቴ ምን አይነት ችግር ውስጥ እንደነበረች በደንብ አይገባኝም ነበር” ትላለች። ናሊኒ በወቅቱ የነበረን ጥሩ ሕክምና ስላገኙ ከጊዜ በኋላ ተመልሰው መናገር ቻሉ። ነገር ግን በተለያዩ መርጃ መሳሪያዎች በመታገዝ ነው ድምጽ የሚያወጡት። “ይሄ ካንሰር የያዘኝ በባለቤቴ ማጨስ ምክንያት ነው” ይላሉ ናሊኒ። “አጫሾች በጣም ጎጂ የሚባለውን የሲጋራውን ጭስ ወደ ውጪ ነው የሚተነፍሱት። በዚህ መሀል በጣም ተጎጂ የሚሆኑት በአቅራቢያቸው የሚገኙና ያንን ጭስ ወደውስጣቸው የሚያስገቡ ሰዎች ናቸው።” የዓለም ጤና ድርጅት ሁሉም አይነት ሲጋራዎች ጎጂ እንደሆኑ ሁሌም ያሳስባል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በማንኛውም የጤንነት ሁኔታ ላይ የሚገኙ ለጭሱ የሚጋለጡ ሰዎችም ተጎጂዎች ይሆናሉ። በዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ቢሮ የትንባሆ ቁጥጥር ባለሙያ የሆኑት አንጄላ ቺባኑ እንደሚሉት፣ የማያጨሱ ሰዎች ለአንድ ሰዓት ያክል ለሲጋራ ጭስ ቢጋለጡ በተለይ በጉሮሯቸው አካባቢ ቀላል የማይባል ጉዳት ይደርስባቸዋል። አክለውም “ከሌሎች ሰዎች ለሚመጣ የሲጋራ ጭስ የሚጋለጡ ሰዎች ከ700 በላይ ኬሚካሎችን ነው ወደ ውስጣቸው የሚያስገቡት። ከእነዚህ ኬሚካሎች መካከል ደግሞ 70 የሚሆኑት ለካንሰር የሚያጋልጡ ናቸው። እነዚህ ሰዎች በሳንባ ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ከ20 እስከ 30 በመቶ ከፍ ያለ ነው” ይላሉ ባለሙያዋ። የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ 65 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት በየዓመቱ በሲጋራ ምክንያት ህይወታቸው እንደሚያልፍ ይገልጻል። ከዚህ በተጨማሪ ለሲጋራ ጭስ የሚጋለጡ ህጻናት በጆሮ ኢንፌክሽን የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። አንዳንዴ ባስ ሲል ደግሞ  የመስማት ችሎታቸውን ሊያጡ ይችላሉ። “ለሲጃራ ጭስ የተጋለጡ ህጻናት ለመተንፈሻ ችግር የመጋለጥ ዕድላቸው ከ50 እስከ 100 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፣ ለአስም እንዲሁም ለድንገተኛ ሞት የመጋለጥ ዕድላቸውም ከፍተኛ ነው” ይላሉ አንጄላ ቺባኑ። ጥቂት የማይባሉ ሲጋራ የሚያጨሱም ሆነ የማያጨሱ ሰዎች ሲጋራ ማጨስ መከልከል አለበት ብለው እንደሚከራከሩ የዓለም ጤና ድርጅት ይገልጻል። “ሙሉ በሙሉ ከሲጋራ ነጻ የሆኑ አካባቢዎች መኖር ውጤታማ የሆነ ለውጥ ማምጣት ይችላል። ሰዎች አጠገባችሁም ሆነ ልጆቻችሁ አካባቢ እንዲያጨሱ አትፍቀዱላቸው። ንጹህ አየር መተንፈስ ሰዎች ሰብአዊ መብት ነው” ይላሉ አንጄላ ቺባኑ። ነገር ግን ሲጋራ ማጨስን ሙሉ በሙሉ መከልከል በጣም ከባድ ነው። በዘርፉ ላይ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት የሲጋራው ኢንዱስትሪ በአውሮፓውያኑ 2021 ብቻ 850 ቢሊዮን ዶላር አንቀሳቅሷል። ይህ ቁጥር በአፍሪካ ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር ከያዘችው ናይጄሪያ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት ሁለት እጥፍ ነው። ጥናቱ እንደሚለው በቢሊየኖች ዶላሮችን መድበው የሚንቀሳቀሱት ከፍተኛ ትርፍ የሚያገኙ ትልልቅ ድርጅቶች ሲጋራ ማጨስን ለማስከልከል የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ጫና ያሳድራሉ። አይኑሩ አልቲቤቫ መሰል ሕጎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ከሚሰሩ የሕንድ የሕዝብ እንደራሴዎች አንዷ ናቸው። በአውሮፓውያኑ 2018 ላይ ሕዝብ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎች ሲጋራ ማጨስ እንዲከለከል ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረውም ነበር። እሳቸው እንደሚሉት ሕንድ ውስጥ በየዓመቱ ከሲጋራ ጋር በተያያዘ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው የሚያልፍ ሲሆን መሰል ቦታዎች ላይ ማጨስን መከልከል ደግሞ የሚደርሰውን ጉዳት እስከ 10 በመቶ ድረስ መቀነስ ይቻላል። ነገር ግን የሕዝብ እንደራሴዋ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር። “የሕዝብ እንደራሴዎቹ እራሳቸው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከትምባሆ ኢንዱስትሪው ጋር ግንኙነት አላቸው። ሕዝብ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎች ሲጋራ ማጨስ የሚከለክለው ሕግ ወደተመረጡ ኮሚቴዎች ነበር የተመራው። ነገር ግን ኮሚቴዎቹ ሆነ ብለው እንዲያዘገዩት ነው የተደረገው። የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሚኒስቴርም ቢሆን ከታክስ የሚገኝ ገቢ ላይ ቅናሽ እንደሚኖር በመግለጽ ሀሳቡን አልደገፈውም ነበር’’ ይላሉ። “አንዳንድ ሰዎች እንዲያውም በማኅበራዊ ሚዲያዎች በኩል እኔንም ሆነ ቤተሰቤን ማጥቃት ጀምረው ነበር።” አይኑሩ አልቲቤቫ ላለፉት ዓመታት እልህ አስጨራሽ ትግል ካደረጉ በኋላ በአውሮፓውያኑ 2021 ላይ ሕንድ ውስጥ ሕዝብ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎች ሲጋራ ማጨስ ተከልክሏል። ነገር ግን ሥራው እዚያ ላይ አላበቃም። አይኑሩ ሲጋራ ማጨስ በጤና ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት እንዲሁም ህጻናት ላይ የሚያመጣውን መዘዝ በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶችን ያስተባብራሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ በትምባሆ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ ከሚደረጉ ጥረቶች መካከል በአውሮፓውያኑ 2005 ይፋ የተደረገው የትምባሆ ቁጥጥር ስምምነት ተጠቃሽ ነው። እስካሁን ድረስ 182 አገራት የዚህ ስምምነት አባል ለመሆን ፈርመዋል። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት አገራት ሕዝብ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎች ሲጋራ ማጨስን እንዲከለክሉም ይወተውታሉ። ሰዎች ንጹህ አየር የመተንፈስ መብታቸው እንዲጠበቅ ሲባል መሰል ሕጎች ተግባራዊ መሆን አለባቸው የሚሉት ደግሞ በትምባሆ ቁጥጥር ላይ የሚሰራው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩት ዶክተር ሜሪ አሱንታ ናቸው። “ከትምባሆ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ሞቶችን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ የሚችሉ በርካታ እርምጃዎች አሉ። በዋነኛነትም የትምባሆ ምርት ላይ ከፍተኛ ግብር ማስከፈል፣ ማስታወቂያዎች ላይ ቁጥጥር ማድረግ እንዲሁም ስለጉዳቱ ከፍተኛ ትምህርት መስጠት ይጠቀሳሉ።” ምንም እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት የሲጋራ አጫሾች ቁጥር ከዓመት ዓመት እየቀነሰ ነው ቢልም፣ አሁን ላይ የሲጋራ አጫሾች ቁጥር 1.3 ቢሊየን ነው። ድርጅቱ እንዲመለው ከአስር ሰዎች አንዱ ሲጋራ የሚያጨስ ሲሆን አብዛኞቹ ደግሞ የሚያጨሱት ቁጥጥር የማይደረግባቸውና በሕገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱትን ነው። ሕንድ ሃይድራባድ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ናሊኒ አሁን ላይ ጉዳዩን ወደ ሕግ ለመውሰድ አቅደዋል። አሁንም ድረስ ጉሮሯቸው ላይ ባለው ቀዳዳ አማካይነት ብቻ የሚተነፍሱት ናሊኒ በሲጋራ ምክንያት የማንም ሰው ሕይወት እንደዚህ ሊበላሽ አይገባም ይላሉ። ናሊኒ ወደ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ማንኛውም ሕዝብ ወደሚሰበሰብባቸው ቦታዎች በመሄድ ስለሲጋራ ጉዳት የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶችን የሚያከናውኑ ሲሆን፣ በትርፍ ጊዜያቸው ደግሞ ከልጅ ልጆቻቸው ጋር በመጫወት ያሳልፋሉ። በባለቤታቸው ሲጋራ አጫሽነት ምክንያት ለካንሰር ተጋልጠው ለከባድ የጤና ችግር ቢዳረጉም በሟቹ ባለቤታቸው ላይ ምንም አይነት ቂም አልያዙም። "በባሌ ላይ ፈጽሞ አዝኜበት አላውቅም። ባጋጠመኝ ነገር ላይ ማዘን ምንም የሚለውጠው ነገር እና የሚቀርፈው ችግር የለም። አሁን እኔ እውነታውን ተቀብዬ ስላጋጠመኝ የጤና ችግር ለመናገር ፈጽሞ አላፍርም” ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c6p914npjevo
amh
health
የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኙ ካንዬ ዌስት “ሳትጠራ እና ሳታሳውቅ” መጥተሃል ተብሎ ከስኬቸርስ ቢሮ እንዲወጣ ተደረገ
ስኬቸርስ የተባለው የጫማ አምራች ኩባንያ ራፐሩ ዬ፣ በቀድሞ ስሙ ካንዬ ዌስት፣ “ሳያሳውቅ እና ሳይጋበዝ” መጥቷል በሚል ከኩባንያው ሕንጻ እንዲወጣ እንዳደረገው ገለፀ። ድርጅቱ አክሎም ከራፐሩ እና ዲዛይነሩ ዬ ጋር በጋራ የመስራት “ምንም ዓይነት ፍላጎት” የለኝም ብሏል። ይህ ዜና የተሰማው የጀርመኑ ስፖርት ትጥቅ አምራች አዲዳስ፣ ዬ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሰጠውን ፀረ አይሁዳዊ አስተያየት ተከትሎ ያለውን ግንኙነት ካቋረጠ በኋላ ነው። ቢቢሲ የዬን ወኪሎች አስተያየት ቢጠይቅም ምላሽ ማግኘት አልቻለም። ስኬቸርስ በመግለጫው ዬ በቢሮው ከሌሎች ጋር ሆኖ ከመጣ በኋላ “ያልተፈቀደ የፊልም ቀረጻ በማድረግ ላይ ነበር” ብሏል። አብረውት መጥተው ከነበሩ ሰዎች ጋርም የተወሰነ ንግግር ከተደረገ በኋላ ሕንጻውን ለቅቀው እንዲወጡ መደረጉን ጨምሮ ገልጿል። ኩባንያው አክሎም “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚሰጣቸውን ከፋፋይ ሀሳቦች የምንቃወም ሲሆን የፀረ አይሁዳዊ ወይንም ማንኛነውንም ዓይነት የጥላቻ ንግግሮች አንታገስም” ብሏል። በተጨማሪም “በድጋሚ አጽንኦት መስጠት የምንፈልገው ዌስት የመጣው ሳያሳውቅ እና ሳይጠራ ነው” ብሏል። ዬ የባይ ፖላር ዲዝኦርደር ታማሚ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትልልቅ ስም ካላቸው ድርጅቶች ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ እየገባ ያለው የስራ ውል እየተቋረጠ ይገኛል። እነዚህ እርምጃዎች የዬን ገቢ ክፉኛ የሚጎዱት ሲሆን በቅርቡም ከፎርብስ የቢሊየነሮች ዝርዝር ስር ስሙ እንዲወጣ ሆኗል። መጽሔቱ ዬ ከአዲዳስ ጋር ያለው የስራ ውል በመቋረጡ ብቻ ካለው አጠቃላይ የ1.5 ቢሊየን ዶላር ሀብት ወደ 400 ሚሊዬን ወርዷል ሲል አስፍሯል። ማክሰኞ ዕለት አዲዳስ ከዬዚ ብራንድ ጋር ያለውን ትብብር “የፀረ አይሁዳዊ እንዲሁም የትኛውም ዓይነት የጥላቻ ንግግርን አንታገስም” በማለት ውሉን ማቋረጡ ይታወሳል። አዲዳስ አክሎም ከአሁን ጀምሮ ምርቶቹ ከገበያ አንዲወጡ ይደረጋል ሲል አስታውቋል። ባለፈው ወር በፓሪስ የፋሽን ሳምንት ላይ “ኋይት ላይቭስ ማተር “ የሚል ቲሸርት ለብሶ በመገኘቱ አዲዳስ ጉዳዩን ማጤን ጀምሮ ነበር። ከቀናት በኋላም ራፐሩ በትዊተር ገፁ ላይ ፀረ አይሁዳዊ መልዕክት ያለው ጽሁፍ በማስፈሩ ወዲያው ከማህበራዊ ሚዲያው ታግዷል። ከዚህ ቀደምም የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኙ ካንዬ ዌስት በታዋቂው ኮሜዲያን ትሬቨር ኖዋ ላይ በሰነዘረው ዘር ተኮር ስድብ ምክንያት ከኢንሰታግራም ለ24 ሰዓታት ታገዶ ነበር። አዲዳስ ተወዳጅ ከሆነው ዬ ብራንድ ጋር ያለውን ስምምነት በመሰረዙ ብቻ እኤአ በ2022፣ 217 ሚሊየን ፓውንድ ይከስራል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cj5z15d3g61o
amh
health
አንድ ውሻ በዝንጀሮ ፈንጣጣ መያዙን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ
አንድ ውሻ ከባለቤቱቶቹ በተላለፈ የዝጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ መጠቃቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የበሽታው ስርጭት ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ራሳቸውን ከቤት እንስሳቶቻቸውም ጭምር ማግለል እንዳለባቸው የሚያሳይ እንደሆነም የጤና ሃላፊዎቹ አስታውቀዋል። ሌሎች እንስሳትን የመበከል አደጋን ለመቀነስ ቆሻሻን በጥንቃቄ ማስወገድ እንደሚያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። ውሾች በሽታውን ወደ ሌሎች ውሾች ወይም ወደ ሰዎች ያስተላልፉ እንደሆነ የሚያረጋግጥ መረጃ እስካሁን እንደሌለም ባለሞያዎች ገልጸዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ በቆዳ-ለቆዳ ንክኪ እና ሰዎች ጨርቆችን ጨምሮ አልጋ ወይም ፎጣ በቫይረሱ ​​​​ከተያዘ ሰው ጋር በጋራ ሲጠቀሙ የሚተላለፍ በሽታ ነው። በአሁኑጊዜ በዓለም ዙሪያ ወደ 35,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን አብዛኛዎቹ በአውሮፓ፣ በሰሜን እናበደቡብ አሜሪካ ይገኛሉ ። እስካሁን ከበሽታው ጋር በተያያዘ 12 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። የአለም የጤና ድርጅት ባለፈው ሃምሌ ወር ውስጥ ነበር የዝንጀሮ ፈንጣጣን አለማቀፍ የጤና አደጋ ሲል ያወጀው። የመጀመሪያው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ከሰው ወደ ውሻ የተላለፈው በፓሪስ ከተማ ሁለት አንድ ላይ በሚኖሩ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ቤት ውስጥ ነው። ግለሰቦቹ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ማሳየት ከጀመሩ ከ 12 ቀናት በኋላ ነበር በውሻቸው ላይም ምልክቶችን ማየት የጀመሩት። ባለሞያዎች ያደረጉት የዘረመል ትንታኔ እንደሚያሳየው ውሻውን ያጠቃው ቫይረስ ግለሰቦቹን ካጠቃው ጋር ቫይረስ ጋር ተመሳሳይ ነው። የውሻው ባለቤቶችም ውሻው አብሯቸው ሲተኛ እንደነበር ተናግረዋል። በአለም የጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምላሽ ሰጪ ቡድን ውስጥ የቴክኒካል ስራዎች መሪ የሆኑት ዶ/ር ሮሳምንድ ሉዊስ “ይህ ከዚህ በፊት ሪፖርት ያልተደረገ ብሎም ለመጀመሪያ ግዜ የመዘገበ ወደ ውሻ ያጋጠመ ስርጭት ነው ብለን እናምናለን’’ ብለዋል። በተቋሙ የድንገተኛ የጤና አደጋዎች ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ማይክ ራያን “ጉዳዩ ያልተጠበቀ አይደለም” ብለዋል። ነገር ግን በሽታው ከአንድ ዝርያ ወደ ሌላው መዘዋወሩ እጅግ እንደሚያሳስባቸውም ተናግረዋል። አክለውም አንድ በሸታ ወደ አዲስ የእንስሳ ከተላለፈ በኋላ እንደሚላመድ ብሎም እና በውስጡም ወደ አዲስ ዝርያ እንዲለወጥ እድል እንደሚሰጥ ተናግረዋል። “ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ያጋጠመ ስርጭት ነው። ስለሆነም ውሾች ሊበከሉ ይችላሉ ማለት ነው። ነገር ግን ውሻው ሌሎች ውሾችን ሊበክል ይችላል ወይም ወደ ሰዎች ያስተላልፋል ማለት አይደለም’’ ሲሉ የአለም የጤና ድርጅት የዓለም አቀፍ ተላላፊ በሽታዎች ስጋት ዝግጁነት ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሲልቪ ብሪያንድ ተናግረዋል። የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመከላከል በመላው አለም ያለው የክትባት አቅርቦት እስካሁን ድረስ ውስን ነው። ባለፈው ሳምንት ብቻ በበሽታው ተይዘው ሪፖርት የተደረጉ ሰዎች ቁጥር በ 20 በመቶ ጭሯል። ይህም ከሳምንት በፊት ከነበረው በ20 በመቶ ብልጫ አለው። እስካሁን አብዛኛው በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሲታይ ወንድ የተመሳሳይ ጾታ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cqlk1nd5877o
amh
health
“ስለ አዕምሮ ጤና በግልፅ መነጋገር ለሁላችንም ጤንነት ነው” ያዕቆብ ተክዔ
ያዕቆብ ተክዔ (ዶ/ር) በአሜሪካው ፔንሲልቬንያ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አዕምሮ ባለሙያ ነው። ያዕቆብ በትምህርቱ ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት፣ በሥራው ቴራፒስትና የሙሉ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ነው። ያዕቆብ ተውልዶ ያደገው በኤርትራ ሲሆን የድህረ ምረቃ ትምህርቱን ለመከታተል ከበቃበት ጊዜ አንስቶ የሥራ ዓለሙን እስኪቀላቀል ድረስ ኑሮው በአሜሪካ ነው። የያዕቆብ ሥራ የሚያተኩረው በስደትና በስደተኞች ላይ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከአፍሪካ፣ አብልጦም ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ለተሰደዱ ሰዎችን የአዕምሮ ጤና ድጋፍ እና ክትትል ያደርግላቸዋል። ያዕቆብ ከባድ አደጋ፣ የፆታ ወይም የወሲብ ጥቃት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያንና ሱዳናውያን አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል። ሥራው በይበልጥ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት መክበዱን የሚናገረው ያዕቆብ በነባር አዕምሯዊ ተፅዕኖዎች ላይ ተደርቦ ከወርሽኙ ጋር የመጡ የተለየያዩ ውጥረቶችንም ጭምር ለማቃለል ብዙ ሥራ መሠራት እንደነበረበት ይናገራል። ወረርሽኙ የጀመረበት ወቅት በተለይ ፍራቻ፣ መገለልና የመሳሰሉ ተያያዥ ችግሮች ስለነበሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራውያን በተለየ መልኩ እገዛ ያስፈልጋቸው እንደነበር ያስታውሳል። በስደተኞች ላይ ተዘውትረው ይታዩ የነበሩ የቋንቋ ቀርነቶች፣ የባህል ልዩነቶችና ከሃገሩ ማህብረሰብ ጋር የመዋሃድ ችግሮች ላይ ወረርሽኙ ያመጣው የመራራቅ፣ ያለ መጠያየቅና የብቸኝነት ኑሮ አዕምሮ ላይ ከበድ ያለ ተፅዕኖ እንደነበረው ገልጿል። ይህንንም ለመቅረፍ ከመንግሥት የሚመጡና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን፣ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በሚናገሯቸው ቋንቋዎች እንዲደርሷቸው እናደሚያደርጉ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ወቅት ተናግሯል። በተጨማሪም ለአዕምሮ ጤናም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በየጊዜው በሚረዷቸው ቋንቋዎች እና መንገድ እንደሚያደርስ ይናገራል። ያዕቆብ እነዚህን እና ሌሎች ያሉ ችግሮች በሙሉ በጥሞና ካሰበባቸው በኋላ ሰዎች በቀላሉ፣ ሳይሳቀቁና ሰው አየን አላየን ሳይሉ መረጃዎችን የሚያገኙበትን መንገድ ማሰላሰል ጀመረ። "በባህላችን ስለ አዕምሮ ጤንነት በግልፅ ማውራት ወይም መነጋገር ከባድ በመሆኑና በግልፅ የሚያወሩም ሰዎች መድልዖ ስለሚገጥማቸው በፈቃደኝነት እርዳታ ለማግኘት የሚጥሩ ኢትዮጵያውያን ወይም ኤርትራውያን የሉም። ይህ ደግሞ ችግሩን አያጠፋውም፣ ማለት ስለችግሩ ስላልተወራ ችግሩ ይሰወራል ማለት አይደለም። በተለይ የአዕምሮ ጤና መጓደል ደግሞ ሥር እየሰደደና እየተባባሰ የሚመጣ በመሆኑ ችግሩን እጥፍ ያደርገዋል። ለዚህም ነው መፍትሄ ማግኘት ፈልጌ የነበረው" ይላል ያዕቆብ። ኢንተርኔት የበርካቶች ህይወት አካል በሆነት በዚህ ዘመን ቀላሉ መፍትሔ ዩቲዩብ መሆኑ የተገነዘበው ያዕቆብ፣ የራሱን ቻናል በመጀመር ማስተማር፣ አስፈላጊ መረጃዎችንና ምክሮችን ማስተላለፍ ጀመረ። እንደዚህ ማድረጉ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ቢያንስ ከቤታቸውም ሆነው መድልዖን ሳይፈሩ አስፈላጊውን እርዳታ ለማግኘት ያስችላቸዋል ብሎ አስቦ እንደሆነ ይገልፃል። "በርግጥ አንድ ባንድ እያገኘሁ ጊዜ ወስደን እንደምረዳቸው ሰዎች ያህል በዩቲዩብ ጥልቀት ያለው እርዳታ ለማድረግ ይከብዳል። እንደዚያም ቢሆን ግን ዋና ዋና መልዕክቶችን ስለማስተላልፍበት ሰዎች ሳይሳቀቁ በእራሳቸው ጊዜ የሚጠቅሟቸውን የምክር አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ" ይላል። ያዕቆብ በዩቲዩብ የሚያሰራጨው መልዕክት የሚኖረውን ጥቅም ሲያስረዳም "አብዛኛውን ጊዜ ስሜታቸውንና አዕምሮዋቸው ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ ነገሮችን አምቀው ስለሚይዙ በጊዜ ሂደት ጉዳቱ የከፋ ይሆንባቸዋል። ለዚህ ነው ሰዎች ቢያንስ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ማወቃቸው በእራሱ የመጀመሪያው እርምጃ የሚሆነው" ይላል። አክሎም "እንደ ኮቪድ ዓይነት ወረርሽኝ ደግሞ ሰዎችን ቤት እንዲቀመጡ የሚያደርግ ከሆነ ወይም የለመዷቸውን ማህበራዊ ስብስቦች በሚያስቀርባቸው ጊዜ ተፅዕኖው ይበዛባቸውና ነባር የአዕምሮ ችግሮችን ያባብስባቸዋል" ይላል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰዎች በአእምሮ ጤና ላይ ያላቸው አመለካከት እየተስተካከለ እንደሆነ የሚናገረው ያዕቆብ፣ ከአምስት ዓመታት በፊት የግንዛቤ መፍጠሪያ ዘመቻዎች በሚያካሄድበት ወቅት የነበረው ምላሽና አሁን የሚሰጠው ምላሽ በጣም ልዩነት እንዳለው ይገልፃል። ያዕቆብ ከአምስት ዓመታት በፊት የነበረበትን መሰናከል በማስታወስ " ስለ አዕምሮ በሽታዎች ግንዛቤ ለማስፋት በምሠራበት ወቅት ብዙ ሰዎች ዓላማዬን ይጠራጠሩት ነበር። እንደውም በርካታ ሰዎች የአዕምሮ በሽታ መኖሩን እራሱ እንደሚጠራጠሩ ይነግሩኝ ነበር" ይላል። ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እንዳያገኙ የሚያከለክሏቸው በማህበረሰባችን ሊገጥሟቸው የሚችለውን መገለል በመፍራት እንደሆነም ያስረዳል። በተጨማሪም "የአዕምሮ ችግርን ብዙ ሰው በአንድ ጊዜ ሳይታሰብ እንደ ዱብ ዕዳ የሚወርድ ነገር ይመስላቸዋል። ነገር ግን በሂደትና ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጥረት፣ የመንፈስ ጭንቀት ሲደራረብ ካለበለዚያ በአግባቡና በተገቢው ጊዜ እርዳታ ሳይገኙ ሲቀር የሚከሰት ነው" ይላል። እንደዚህም ሆኖ ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙዎች ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነና ኮሮና ባይመጣ ኖሮ ሙሉውን የ2020ን ዓመት በተለያዩ የአሜሪካና የካናዳ ከተማዎች በመሄድ ንግግር እንዲያደርግና ለኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን እርዳታ እንዲሰጥ ተጠይቆ እንደነበር ይናገራል። "የአዕምሮ ታማሚ ሲባል እርቃናቸውን እየሮጡ በድንጋያ ሰዎችን የሚያባርሩ ግለሰቦችን ነው ሰዎች በአዕምሮዋቸው የሚስሉት። ይህ ደግሞ በጣም የተሳሳተ አመለካከት ነው" የሚለው ያዕቆብ አስረግጦ ማስረዳት የሚፈልገው "የአዕምሮ በሽታ ወይም የአዕምሮ ጤና መጓደል የተለያየ መልክ፣ ዓይነትና መገለጫ" እንዳለው ነው ይለናል። ከሁሉም በላይ "በዚህ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በቀጣዮቹ የተወሰኑ ዓመታት የአዕምሮ ጤና መጓደል ወረርሽኝ የምናይ ይመስለኛል" በማለት ይህንንም ለመከላከል በቅድሚያ ከወዲሁ ልናስስባቸው፣ ልንነጋገርባቸውና ልናደርጋቸው የሚገቡ ነገሮች መኖራቸውን ያስረዳል። አእምሮ ጤና መጓደልን በተመለከተ በዋነኛነት ልንከታተላቸው ከምንችላቸው ምልክቶች መካከል፡ እንደ ያዕቆብ ገለጻ እነዚህ ምልከቶች ቀድሞ ማወቅ "እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በቶሎ እንድንደርስላቸው ያስችለናል" ይላል። የአዕምሮ ጤና መጓደል ቋሚ አይደለም የሚለው ያዕቆብ፣ "አካላዊ በሽታ ሲገጥመን ሆስፒታል/ክሊኒክ ሄደን እንደምንታከመው ሁሉ ለአዕምሯችንም ተመሳሳይ እንክብካቤ ማድረጋችን ተገቢ ነው" ሲል ይመክራል። "ለብዙ ሰዎች የአዕምሮ ጤና መሰናከል ቋሚ ችግር ይመስላቸዋል ግን እውነታው ከዚህ የራቀ ነው። ምክንያቱም ማንኛውም ሰው በተለያየ ምክንያት የአዕምሮ ጤናው ሊስተጓጎል ይችላል" በማለት ያብራራል ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያንን ለመርዳት ብዙ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ያለው ያዕቆብ ሥራው ገና ጅማሬው ላይ መሆኑን ይገልፃል። አክሎም የሰውን ግንዛቤ ከመጨመርና ከማሳደግ ባለፈ ደግሞ የቋንቋ ተግዳሮቱ ላይ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ይናገራል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58552208
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ የአስትራዜንካን ክትባት ተጠቀሙ- የዓለም ጤና ድርጅት
በርካታ የአውሮፓ ሃገራት የኮሮናቫይረስ መከላከያ የሆነውን አስትራዜንካ ክትባት ማገዳቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያንና ስፔይንን ጨምሮ ሌሎች አገራት የኦክስፎርዱ አስትራዜንካ ክትባት ደም መርጋት በተያያዘ ችግር አለበት በሚል ክትባቱ እንዳይሰጥ አግደውታል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ደም መርጋት ስለማስከተሉ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ይላል። የድርጅቱ የክትባት ደህንነት ልሂቃንም በዛሬው ዕለት ተሰብስበው ስለ ክትባቱ ይመክራሉ ተብሏል። የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ ስለ ክትባቱ በዛሬው ዕለት የሚወያዩ ሲሆን በያዝነው ሃሙስም የደረሱበትን ማጠቃለያ ለህዝብ ያሳውቃሉ ተብሏል። ሆኖም ኤጀንሲው ክትባቱን ተጠቀሙ ብሏል። በአውሮፓ ክትባቱን ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች አሉ ብሏል። ነገር ግን ባለሙያዎቹ እንደሚሉት በአጠቃላይ ከህዝብ ብዛቱ ጋር ሲነፃፀር የደም መርጋት ያጋጠማቸው ሰዎች ድንገተኛ መጨመር አላሳየም ይላሉ ። በአውሮፓ ህብረት አባላት አገራትና ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜንካ ክትባትን መከተባቸውና ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ 40ዎቹ የደም መርጋት ችግር እንዳጋጠማቸው አስትራዜንካ አስታውቋል። እየተወሰዱ ያሉ ጥንቃቄዎች ይህንንም ተከትሎ የጀርመን ጤና ሚኒስቴር በያዝነው ሳምንት ሰኞ ዕለት አስትራዜንካ ክትባት መስጠት በአስቸኳይ እንዲቆም ትዕዛዝ አስተላልፏል። ክትባቱ የአዕምሮ ደም መርጋት ወይም ሴሬብራል ቬይን ቶርምቦሲስ ችግር ጋር መገናኘቱን አይተናል ብለዋል። የጤና ሚኒስትሩ ጄንስ ስፋን እንዳሉት ውሳኔ "ፖለቲካዊ" እንዳልሆነ ነው። "ሁላችንም ቢሆን ይህ ውሳኔ ሊያስከትለው የሚችለውን ጉዳት እንረዳለን። በቀላሉም የደረስንበት አይደለም" ብለዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ ውሳኔውን እስኪያሳውቅ ድረስ አገራቸው ክትባቱን ታግዳለች ብለዋል። "ቀለል ያለ መመሪያ ነው ያለን፤ ሳይንስንና በዘርፉ ላይ ዕውቀት ያላቸውን የጤና ባለስልጣናት ምክር ነው የምንከተለው፤ ይህም የአውሮፓ ስትራቴጂ ምን መምሰል አለበት የሚለውን የሚጠቁም ይሆናል" ብለዋል። የጣልያን መድኃኒት ኤጀንሲም እንዲሁ የአውሮፓ መድኃኒት ኤጀንሲ የሚደርስበትን ማጠቃለያ እጠብቃለሁ በማለት አግዳዋለች። የስፔን ጤና ሚኒስትር ካሮሊና ዳሪያስ በበኩላቸው ክትባቱ ለመጪው ሁለት ሳምንት ይታገዳል ብለዋል። አየርላንድ፣ ፖርቹጋል፣ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ቡልጋሪያ፣ አይስላንድ፣ ስሎቬኒያ ክትባቱን በጊዜያዊነት ያገዱ ሲሆን ዲሞክራቲክ ኮንጎና ኢንዶኔዥያ የክትባት መስጪያ ጊዜያቸውን አራዝመውታል። ኦስትሪያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ አገራት ለጥንቃቄ ሲሊ ቢያግዱትም ቤልጂየም፣ ፖላንድና ቼክ ሪፐብሊክ ክትባቱን እየሰጡ ነው። የቤልጂየም ጤና ሚኒስትር ፍራንክ ቫንደንብራውኬ እንዳስታወቁት ቤልጂየም ካላት ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ቁጥርን በማየት ክትባቱን አለመስጠት አትችልም ብለዋል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በበኩላቸው አስትራዜንካን ጨምሮ በአገሪቱ እየተሰጡ ያሉ ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን የጤና ባለስልጣናቱ ነግረውኛል ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56411232
amh
health
ዓለም ተስፋ የጣለበት የኦክስፎርድ የኮሮና ክትባት ምርምር እንዲቆም ተደረገ
የመጨረሻ የክሊኒካል ሙከራ ላይ የነበረውና ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የቆየው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ከመድሃኒት አምራቹ አስትራዜኔካ ኩባንያ ጋር እያበለጸጉት የነበረው የኮሮና ክትባት ነበር። ምርምሩ ለጊዜው ባለበት ይቁም ተብሏል። ምክንያቱ ደግሞ የክትባት ቅንጣቱን የወሰዱ በጎ ፍቃደኛ ተሳታፊዎች ህመም ስላጋጠማቸው ነው። ይሁን እንጂ ግዙፉ የመድኃኒት አምራች አስትራዜኔካ ይህ የሚያደናግጥ ሳይሆን የሚያጋጥም ነው ይላል። ህመም የተሰማቸው ተሳታፊዎች ለምን ህመም እንደተሰማቸው ለማወቅ ጊዜ ይፈልጋል። የኦክስትፎርድና የአስትራዜኔካ የምርምር ውጤት የዓለም አገራት ትንፋሻቸውን ውጠው በጉጉት ሲጠብቁት የነበረ ነው። በዓለም ላይ በክትባት ሙከራ ውስጥ እያለፉ ካሉ ደርዘን ከሚሞሉ የምርምር ሥራዎች ሁሉ ይህ ግዙፉና ተስፋም የተጣለበት ነበር። ቀድሞ ለሕዝብ ይደርሳል፣ ዓለምን ይታደጋል ተብሎም ነበር። ይህ የኦክስፎርድና አስትራዜኔካ የጥምረት የክትባት ምርምር ምዕራፍ 3 ደርሶ ነበር። ይህም ማለት ዋናዎቹን የምዕራፍ 1 እና 2 አልፎ፣ ፈዋሽነቱ ተረጋግጦ በብዙ ቁጥር ሰዎች ላይ መሞከር የጀመረ ማለት ነው። በአሜሪካ፣ በዩኬ፣ በደቡብ አፍሪካና በብራዚል የሚገኙ 30ሺ ሰዎች ይህንን ክትባት እንዲወስዱ ተደርጎ ምን ዓይነት ምልክት እንደሚያሳዩ እየተጠበቀ ነበር። ምዕራፍ 3 የመድኃኒት ሙከራዎች በርካታ ሺህ ሰዎች የሚሳተፉባቸው ከመሆናቸው ባሻገር ዓመታትን ይወስዳሉ። አሁን ባለው የዓለም ጉጉት ግን አመታት ይጠበቃሉ ወይ የሚለው አጠያያቂ ነው። ቀጥሎ ምን ይደረጋል? እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያጋጥም በሕክምናው ዓለም አዲስ አይደለም። 3ኛ ምዕራፍ የደረሱ የመድኃኒት ሙከራዎች ተሳታፊዎች የተለየ ሕመም ሲያጋጥማቸው ለጊዜው እንዲቆሙ ይደረጋል። አሁን የሆነውም ይኸው ነው። ከዚህ በኋላ ገለልተኛ የተመራማሪዎች ቡድን በጉዳዩ እንዲገባ ይደረጋል። የተወሰዱ ጥንቃቄዎችን ከፈተሸ በኋላ ሁሉም ሂደቶች ትክክል ነበሩ ተብሎ ሲታሰብ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ሙከራውና ምርምሩ እንዲቀጥል ሊወስን ይችላል። "እንዲህ ሰፊ በሆኑ ሙከራዎች በተሳታፊዎች ላይ ህመም መከሰቱ አዲስ ነገር አይደለም። ነገር ግን ገለልተኛ ወገን ሊያጣራው ይገባል" ብለዋል የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ቃል አቀባይ። የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ምርምሩን ለጊዜው እንዲያቆም ሲደረግ ደግሞ ይህ የመጀመርያው አይደለም። ከተሞከረባቸው ሰዎች የተወሰኑት አሟቸው ሆስፒታል ሲገቡ ምርምሮች ሁሉ ባሉበት ይቆማሉ። ይህ የተለመደ አሰራር ነው ይላል፣ የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ። እንዲያውም ምርምሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይቀጥል ሊባልም ይችላል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መድኃኒቱን ከኅዳር 3 ምርጫ በፊት አጥብቄ እፈልገዋለሁ ሲሉ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/54078490
amh
health
ሕንድ ፡ በአንድ ሆስፒታል ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ 10 አራስ ሕፃናት ሞቱ
ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት በሕንድ አንድ ሆስፒታል ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ህይወት ለማትረፍ የቻሉትን ቢያደርጉም አስር አራስ ሕፃናት ህይወት ማለፉ ተነገረ። የእሳት አደጋ ተከላካዮች በምዕራባዊው ማሃራሽትራ ግዛት ወደምትገኘው የብሃንዳራ አካባቢ ሆስፒታል እሳቱን ለመቆጠጠር ከመድረሳቸው በፊት ሰባት ሕፃናትን ከእሳት አደጋው ማትረፍ ተችሏል። የሕንድ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ "ልብ የሚያቆስል አሳዛኝ ክስተት" ሲሉ አደጋውን ገልጸዋል። የእሳት አደጋው የተከሰተው አርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢያ መሆኑን የሆስፒታሉ ኃላፊዎች የገለጹ ሲሆን መንስኤው ምን እንደሆነ እስካሁን ያልታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን ምርመራ እየተደረገ ይገኛል። በእሳቱ ሳቢያ በሆስፒታሉ ውስጥ የተከሰቱት ተከታታይ ፍንዳታዎች የነፍስ አድን ሥራውን ማሰናከሉን የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሥራ ላይ የነበረች አንዲት ነርስ ከሆስፒታሉ አዲስ የተወለዱ አራስ ህጻናት እንክብካቤ ክፍል ውስጥ ጭስ ሲወጣ ካየች በኋላ ለባለስልጣናት ማስታወቋን ተናግራለች። የአካባቢው የቀዶ ጥገና ሐኪም ፕራሞድ ካንዳቴ እንደገለጹት "የሆስፒታሉ ባለሥልጣናት ሰባት ህፃናትን ቢያድኑም 10 ህጻናት ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ሞተዋል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በደረሰባቸው ሐዘን ከሟች ቤተሰቦች ጎን መሆናቸውን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል። የሕንድ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሚት ሻህ ስለአደጋው እንዳሉት "ቃላት የማይገልጹት የማይጠገን ጉዳት ነው" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55581634
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ ኒውዚላንድ ከወራት በኋላ በቫይረሱ የተያዘች ሴት አገኘች
ከሁለት ወራት በላይ የኮሮናቫይረስ የማህበረሰብ ስርጭት ያልታየባት ኒውዚላንድ ከሰሞኑ በቫይረሱ የተያዘች ሴት አግኝታለች። የጤና ባለሙያዎች ከሰሞኑ ከአውሮፓ የተመለሰች የ56 አመት ሴት ቫይረሱ ተገኝቶባታል። ግለሰቧ ከሌላ አገራት ለሚመጡ አስገዳጅ የሆነውን የሁለት ሳምንት ለይቶ ማቆያ ጊዜ ጨርሳ ቤቷ ከሄደች ከቀናት በኋላ ነው ቫይረሱ እንደተገኘባት የታወቀው። ከሴትዮዋ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን እንዲሁም የጎበኘቻቸውን ስፍራዎች ዝርዝር ባለስልጣናቱ እየተከታተሉ ነው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመግታት ዘርፍ ከፍተኛ ሙገሳና ምስጋና ካተረፉ አገራት መካከል ኒውዚላንድ በዋናነት ትጠቀሳለች። አምስት ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሏት ኒውዚላንድ እስካሁን ድረስ በቫይረሱ የመዘገበችው ቁጥር 1 ሺህ 927 ሲሆን 25 ዜጎቿም ሞተዋል። ግለሰቧ በኦክላንድ የነበራትን የለይቶ ማቆያ ጊዜዋን ከጨረሰች በኋላ ባደረገችው ምርመራ ሁለት ጊዜ ከቫይረሱ ነፃ ነሽ ተብላ ነበር። ከሁለት ቀናት በኋላ ቀለል ያሉ የቫይረሱን ምልክቶች ማሳየት የጀመረች ሲሆን በኋላም እየከፋና እየባሰባት መጥቷል ተብሏል። ምርመራ ባደረገችበት ወቅት በቫይረሱ እንደተያዘች የታወቀ ሲሆን ከዚያ ቀን በኋላ በቤቷ ራሷን ለይታ ተቀምጣለች። በዛሬው ዕለት የጤና ሚኒስትሩ ክሪስ ሂፕኪንስ እንዳሉት የቫይረሱ ዝርያ ከየት እንደመጣ ለመገመት በአሁኑ ሰዓት ከባድ ነው ብለዋል። ነገር ግን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ " የቫይረሱ ዝርያ አይነት በከፍተኛ ፍጥነት የሚተላለፍ እንደሆነ በማሰብ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረግን ነው" ብሏል። ከዚህ በላይ ግን ስለ ቫይረሱ ምንም ማለት እንደማይቻል ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የለይቶ ማቆያ ጊዜዋን ከጨረሰች በኋላ በሰሜናዊ ኒውዚላንድ የሚገኙ ቦታዎችን ጎብኝታለች ተብሏል። የጤና ሚኒስቴር ጎብኝታቸዋለች ብሎ የጠቀሳቸውን ሱፐር ማርኬቶች፣ ሬስቶራንቶችና ጋለሪዎች ዝርዝር አውጥቷል።። በነዚህ በተጠቀሱት ቦታዎች ድንገት ተገኝቶ የነበረ ሰው በሙሉ በጥርጣሬ እንደሚታይና ቤታቸውም ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩና እንዲመረመሩም ተነግሯቸዋል። ከሴትዮዋ ጋር ቅርበት አላቸው የተባሉ አራት ሰዎች የተለዩ ሲሆን ምርመራ ተደርጎላቸዋል ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55785138
amh
health
የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቶች ኦሚክሮንን መቋቋም አለባቸው አሉ
የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በአሁን ላይ በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች በአዲሱ ኦሚክሮን የቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ከባድ የጤና እክል እንዳይገጥማቸው መከላከል እንደሚችሉ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊ ተናገሩ። ኃላፊው ይህን ያሉት በደቡብ አፍሪካ በተደረጉ ሙከራዎች ይህ ቫይረስ በተለይ የፋይዘር ክትባትን ማሸነፍ እንደሚችል ምልክቶች አሉ መባላቸውን ተከትሎ ነው። ተመራማሪዎች እንደሚሉት ሰዎች በአዲሱ ቫይረስ ሲያዙ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች በሰውነታችን የሚፈጥሩ የመከላከል አቅም በእጅጉ ይቀንሳል። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ማይክ ራያን ኦሚክሮን ክትባቶችን ሙሉ በሙሉ የመገዳደር አቅም እንዳለው የሚያሳይ ምንም አይነት ምልክት አልተገኘም ብለዋል። "እስካሁን ድረስ ሁሉንም አይነት ቫይረሶች መከላከል የሚችሉ ውጤታማ ክትባቶችን አግኝተናል። በኦሚክሮን ምክንያት ከባድ የጤና እክል የሚገጥመው አልያም ሆስፒታል እስከ መግባት የሚደርስ ሰው ይኖራል ብሎ መገመት በጣም ከባድ ነው'' ብለዋል የዓለም ጤን ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊው ዶክተር ማይክ ራይን። ኃላፊው አክለውም ኦሚክሮን ከዚህ በፊት ከታዩት ሌሎች የኮሮረናቫይረስ ዝርያዎች አንጻር እንደውም ሰዎችም የማሳመም አቅሙ ዝቅተኛ ነው ብለዋል። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተሰርቶ እስካሁን በሌሎች ተመራማሪዎች ባልተገመገመ አዲስ ጥናት መሰረት ግን የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት ከኦሚክሮን ጋር ሲገናኝ ውጤታማነቱ 40 በመቶ እንደሚቀንስ አመልክቷል። ነገር ግን ኦሚክሮን ሙሉ በሙሉ ከክትባቱ እንደማያመልጥ ደርሰንበታል ይላሉ በአፍሪካ ሄልዝ ሪሰርች ኢንቲትዩት ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አሌክስ ሲጋል። ተመራማሪው እንደሚሉት ከዚህ በፊት የተያዙ ሰዎች እንዲሁም ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ኦሚክሮንን የመቋቋም አቅማቸው ከፍተኛ ነው ካሉ በኋላ ሶስተኛ ዙር ክትባት መውሰድ ደግሞ ይበልጥ የመከላከል አቅምን ከፍ እንደሚያደርገው አስረድተዋል። አዲሱ ኦሚክሮን እስካሁን ከ30 በላይ አገራት ውስጥ የተገኘ ሲሆን ሰዎች በክትባትም ሆነ ኮሮናቫይረስ ሲይዛቸው የሚያዳብሩትን በሽታ የመከላከል አቅም ሊቋቋም የሚችል ነው። ነገር ግን ከዚህ በፊት ከነበሩት የኮሮናቫይረስ አይነቶች አንጻር እስካሁን ቀላል የሚባሉ ምልክቶችን ብቻ ነው ያሳየው። በዚህም ምክንያት ስለ ቫይረሱ፣ ስለ ስርጭቱ እና ስለሚያደርሰው ጉዳት በርካታ መላ ምቶች እየተሰነዘሩ ነው። መነሻውን በደቡብ አፍሪካ አገራት ያደረገው አዲሱ የኮሮናቫይረስ አይነት ለዓለማችን ተጨማሪ ስጋትን ፈጥሮ ቆይቷል። ይህ አዲስ ዝርያ እስካሁን ከታዩት የኮሮናቫይረስ አይነቶች እጅግ የተለየው ነው ተብሏል። በበርካታ ብዙ የዘረመል ለውጥ ውስጥ በማለፉ በአንድ ሳይንቲስት "አሰቃቂ" ተብሎ ሲገለጽ ሌላው ደግሞ እስካሁን ከታዩት የከፋ ዝርያ ነው ብለዋል። የደቡብ አፍሪካው ሴንተር ፎር ኤፒዴሚክ ሪስፖንስ ኤንድ ኢኖቬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ቱሊዮ ዴ ኦሊቬራ ስለዚህ አዲስ ዝርያ ሲናገሩ፤ "ያልተለመደ የዘረ መል ለውጥ ያለው" ሲሆን ከተሰራጩት ሌሎች ዝርያዎችም "በጣም የተለየ ነው" ብለዋል። በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ደግሞ የፋይዘር ክትባት ኦሚክሮን ላይ የሚኖረው ጥንካሬና ድክምትን በተመለከተ መረጃዎች ይፋ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። እስካሁን ድረስ እንደ ሞደርና፣ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ያሉ እንዲሁም ሌሎች ክትባቶች ከአዲሱ ኦሚክሮን አንጻር ያላቸው ውጤታመነትን በተመለከተ ምንም ጠቃሚ መረጃ አልተገኘም።
https://www.bbc.com/amharic/news-59574506
amh
health
ወላጆቻቸው የሚያጨሱ ልጆች አጫሽ የመሆን ከፍተኛ ዕድል እንዳላቸው ጥናት አመለከተ
ወላጆቻቸው የሚያጨሱ ታዳጊዎች እነሱም አጫሽ የመሆን አራት እጥፍ ዕድል እንዳላቸው በዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አማካይነት የተሰራ አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ። በዚህም ምክንያት ዶክተሮች ሲጋራ የሚያጨሱ ወላጆችንና አሳዳጊዎችን ማጨስ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። የፀረ ሲጋራ ማጨስ ዘመቻ እንቅስቃሴ እንዳለው ወላጆቻቸው የሚያጨሱ ታዳጊዎች 4.9 በመቶ እነሱም አጫሽ የመሆን ዕድል ሲኖራቸው፣ ወላጆቻቸው የማያጨሱ አቻዎቻቸው ግን የማጨስ ዕድላቸው 1.2 በመቶ ብቻ እንደሆነ አመልክቷል። የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አገልግሎት ባዘጋጀው አዲስ ፊልም ላይ የጤና ባለሙያዎች በአዋቂዎች አጫሾችና ማጨስ በሚጀምሩ ልጆች መካከል ስላለው ግንኙነት ውይይት አድርገዋል። የፀረ ማጨስ ዘመቻው አዋቂ አጫሾች በዙሪያቸው ባሉ ወጣቶች ሕይወት ላይ ስለሚፈጥሩት ተጽዕኖ በጥናት የተደገፈ መረጃን አቅርቧል። አጠቃላይ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ናያት አሪፍ እና የልጆች ሥነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ቤቲና ሆህነን ወላጆች ማጨስን እስከ መጨረሻው በመተው በልጆቻቸው ሕይወት ላይ የሚታይ በጎ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል። በውይይቱ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ማጊ ትሮፕ፣ ይህ አዲሱ የጥናት ውጤት ወላጆች ማጨስ እንዲያቆሙ ተጨማሪ መነሳሻ ሊሆናቸው እንደሚችል ተስፋቸውን ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ጨምረውም የተጀመረው አዲሱ ፀረ ማጨስ ዘመቻ "ሲጋራ በትውልዶች መካከል ያለውን ተያያዥነት በማሳየት ወላጆች በልጆቻቸው ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ያጎላል" በማለት ይህም "ከሲጋራ ማጨስ ለመገላገል ጥሩ አጋጣሚን ይፈጥራል" ብለዋል። የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ለወላጆች፣ ለአሳዳጊዎች እንዲሁም ሲጋራ ማቆም ለሚፈልጉ ሰዎች የሚጠቅሙ የተለያዩ የድጋፍ አገልግሎቶች እንዳሉ ገልጸዋል። ሲጋራ ለማቆም የሚያግዝ መተግበሪያ፣ በፌስቡክ ላይ የሚደረግ ድጋፍ፣ በየዕለቱ የሚላክ የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክት እንዲሁም በኢንትርኔት ላይ የሚገኝ ግላዊ ሲጋራ የማቆም ዕቅድ መዘጋጀቱን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/59802873
amh
health
ለሁለት ዓመት ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኒው ዚላንድ በሯን ልትከፍት ነው
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኒው ዚላንድ በስተመጨረሻ በሮቿን ልትከፍት እንደሆነ ይፋ አድርጋለች። ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ አውስትራሊያዊያን ምንም ዓይነት በለይቶ ማቆያ መቆየት ሳያስፈልጋቸው በነፃነት መግባት ይችላሉ። ከ60 ሃገራት የሚመጡ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ደግሞ ከግንቦት ወር ጀምሮ መግባት እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል። ከእነዚህ ሃገራት መካከል ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩናይት ኪንግደም ይገኙበታል። ሁሉም ወደ ኒው ዚላንድ የሚመጡ ተጓዦች ከኮቭድ ነፃ መሆናቸውን የሚያሳይ ወረቀት ማሳየት አለባቸው። ኒው ዚላንድ ድንበሯን ሙሉ በሙሉ ዝግ በፈረንጆቹ መጋቢት 2020 ነበር። ኒው ዚላንድ ለአውስትራሊያ ከሰጠችው ለአጭር ጊዜ የቆየ የጉዞ ፈቃድ ውጭ ድንበሯን ለማንም ሳትከፍት ቆይታለች። አሁን ላይ ወደ ሃገሪቱ መግባትና መውጣት የሚችሉት የኒው ዚላንድ ዜጎች ብቻ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን እንዳሉት ኒው ዚላንድ "ዓለምን ለመቀበል ዝግጁ ናት።" "አሁን በተሰጠን መመሪያ መሠረት ድንብራችንን ለመክፈት ሁሉም ነገር ምቹ ይመስላል። ቱሪስቶቻችንም ይመለሳሉ" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ። ወደ ኒው ዚላንድ ለመግባት ቪዛ ቀድሞ ያላቸው ሰዎች ከግንቦት ወር ጀምሮ እንደልባቸው መንቀሳቀስ ይችላሉ። ኒው ዚላንድ ጠንካራ የሚባል የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣሏ የኮቪድ-19 ስርጭትን በመቆጣጠር ስሟ በተደጋጋሚ ይነሳል። ከኒው ዚላንድ ነዋሪዎች 95 በመቶው ተከትበዋል። ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በኮቪድ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 115 ብቻ ነው። ያልተከተቡ ሰዎች ሥራ አያገኙም መባሉን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ዌሊንግተን ተቃውሞ ተቀስቅሶ እንደነበር አይዘነጋም። ምንም እንኳ ኒው ዚላንድ ድንበሯን ከፍታ፤ እጇን ዘርግታ እንግዶች ለመቀበል ብትዘጋጅም አሁንም ቢሆን በርከት ብሎ መሰባሰብም ሆነ ያለጭንብል መንቀሳቀስ ክልክል ነው።
https://www.bbc.com/amharic/60761357
amh
health
ኮሮናቫይረስ : አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ
አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ። ኬንት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በዓለም ላይ በስርጭቱ ቀዳሚው ሊሆን ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደም የዘረ መል ክትትል መርሃ ግብር ኃላፊ ገልጸዋል። ኃላፊው ፕሮፌሰር ሻሮን ፒኮክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አዲሱ ዝርያ "በአገሪቱ የተሰራጨ" ሲሆን "በመላው ዓለም የመሰራጭ ዕድሎችም" አሉት ብለዋል፡፡ በኬንት የተገኘው ዝርያ ከ50 በላይ በሆኑ አገራት ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል። የኮሮናቫይረስ ዝርያ በደቡብ ምስራቅ እንግሊዝ በጎርጎሮሳዊያኑ መስከረም 2020 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ ሲሆን፤ በቀጣይ ወራት በፍጥነት ተስፋፍቶ በጥር ወር በመላው ዩናይትድ ኪንግደም አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ምክንያት ሆኗል። ፕሮፌሰር ፒኮክ "በእውነቱ ከሆነ እኛን በመጉዳት ላይ የሚገኘው በከፍተኛ ፍጥነት መተላለፉ ነው" ብለዋል። ለኮሮናቫይረስ የተሠሩ ክትባቶች ቀደም ሲል ለነበረው የቫይረሱ ዙሪያ የተመረቱ ቢሆንም ሳይንቲስቶች አሁንም ቢሆን በአዲሱም ዝርያ ላይ ይሠራሉ ብለው ያምናሉ። ውጤታማነታቸውን ግን ጥሩ ላይሆን ይችላል። በዩናይትድ ኪንግደም ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደላቸው ክትባቶች በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የቫይረስ ዓይነቶች ላይ በጥሩ ሁኔታ የሚሠሩ ይመስላሉ ብለዋል ፕሮፌሰር ፒኮክ።
https://www.bbc.com/amharic/news-56027521
amh
health
ኢኳዶር ለሁሉም ዜጎቿ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ግዴታ አደረገች
ኢኳዶር እየተባበሰ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታትና እንደ ኦሚክሮን ያሉ ዝርያዎችን ጉዳት ለመቀነስ በሚል አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወድ የሚያስገድድ መመሪያ አወጣች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳለው አጠቃላይ ሕዝቡን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት ክምችት ያለ ሲሆን፣ የሕክምና ማስረጃ ያላቸው ሰዎች ብቻ ያለመከተብ መብት ይኖራቸዋል። ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ውስጥም ማንኛውም ዕድሜው ከአምስት ዓመት በላይ የሆነ ሰው በሙሉ ክትባቱን ይወስዳል ተብሏል። እስካሁን ድረስ ዕድሜያቸው ለክትባት ከደረሱ ሰዎች ውስጥ 77.2 በመቶ ያህሉ ሁለት ዙር ክትባት ሲወስዱ ከ900 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሰዎች ሦስተኛ ዙር ክትባታቸውን ወስደዋል። የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ ክትባቱ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል አቅም የፈጠረና ይህም በቫይረሱ ተይዘው ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎችን ቁጥር እና ሞትን ለመቀነስ ያገዘ ነው። በአገሪቱ ሕገ መንግሥት የተቀመጠው የዜጎችን ጤንነት የማስጠበቅ ግዴታ በመንግሥት ጫንቃ ላይ የወደቀ መሆኑንና እርሱን ለማስፈጸም ሕጉን መሠረት ተደርጎ የተሰጠ ውሳኔ መሆኑን የኢኳዶር ጤና ሚኒስቴሩ ገልጿል። አውስትራሊያ እና ጀርመን ተመሳሳይ ውሳኔ የመስጠት ዕቅድ ያላቸው አገራት ናቸው። ኢኳዶር ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ጥቅም ላይ የሚውል የክትባት የምስክር ወረቀት ለዜጎቿ አዘጋጅታለች። ወደ ሲኒማና ቴአትር ቤቶች ወይም የገበያ ማዕከላት ለመግባት ይህንን ወረቀት ማሳየት ግዴታ ይሆናልም ተብሏል። ኢኳዶር የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ከተከሰተ ጀምሮ 33 ሺህ 600 ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዘ ሞት መዝግባለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-59778546
amh
health
ጣልያናዊቷ ለ10 ወራት 'ኮማ' ውስጥ ከቆየች በኋላ ነቃች
ጣልያን ውስጥ አንዲት ሴት እራሷን ስታ በሕይወት እና በሞት መካከል ውስጥ ለአስር ወራት ከቆየች በኋላ መንቃቷ ተዘገበ። የ37 ዓመቷ ክሪስቲና ሮሲ ባሳለፍነው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ የሰባት ወር ነፍሰ ጡር እያለች ነበር የልብ ድካም አጋጥሟት እራሷን የሳተችው። ሴት ልጇ ካተሪና በወቅቱ በድንገተኛ ሕክምና እንድትወለድ የተደረገ ሲሆን ክሪስቲና ግን ላለፉት ዘጠኝ ወራት ኮማ ውስጥ ቆይታለች። ለህመሟ ምክንያቱ አንጎሏ ውስጥ የደረሰ ጉዳት ሊሆን ይችላል ተብሎ ነበር። በአሁኑ ሰአት ከኮማ ነቅታ የመጀመሪያ ቃሏን ተናግራለች። በመጀመሪያ 'እማዬ' የሚለውን ቃል እንዳወጣች ባለቤቷ ገልጿል። "ምንም አልጠበቅንም ነበር። ከዚህ ሁሉ ወራት ስቃይ በኋላ ያልተጠበቀ ሀሴት ነው ያጋጠመን" ብሏል ጋብሪኤል ሱቺ 'ላ ናዚዮን' ለተባለው ጋዜጣ። ክሪስቲና ሮሲ ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ የማገገም ሂደቷን ለማፍጠን በሚል ኦስትሪያ ውስጥ ወደሚገኝ ልዩ ክሊኒክ እንድትዘዋወር ተደርጋ ነበር። ከዘጠኝ ወራት በኋላ ከኮማ ስትነቃም ባለቤቷ እና እናቷ አጠገቧ ነበሩ። እንደነቃችም 'እማዬ' ብላ እናቷን ጠርታለች። ክሪስቲና ከአገር ወጥታ ህክምና እንድታገኝ የሚያስችለው ገንዘብ የተገኘው ደግሞ በበይነ መረብ በተደረገ የእርዳታ ጥሪ ነው። በዚህም ከ208 ሺ ዶላር በላይ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ከዚህ በኋላ ለሚያስፈልጓት ህክምናዎችም እንደሚረዳት ይጠበቃል። "ክሪስቲና በጣም አዲስ አይነት ሰው ሆናለች" ብሏለ ባለቤቷ አሬዞ ኖቲዜ ለተባለው ድረ ገጽ ሲናገር። "በጣም የተረጋጋች ሆናለች። ለመተንፈስ የሚረዳትን መሳሪያ አውልቀውላታል። ከዚህ በኋላ ሌሎች አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ የሚረዷት ህክምናዎች ይደረጉላታል" ብሏል። ክሪስቲና ኮማ ውስጥ ስትገባ የሰባት ወር ጽንስ የነበረችው ካተሪናም ብትሆን ስትወለድ ባጋጠማት የኦክስጅን እጥረት ምክንያት ለወራት ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ሲደረግላት ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-57431084
amh
health
ኮቪድ -19፡ ሰሜን ኮሪያ የኮቪድ ወረርሽኝ በመከሰቱ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አዘዘች
ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ ጥብቅ ብሔራዊ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አዘዘች። የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በዋና ከተማዋ ፕዮንግያንግ የኦሚክሮን ወረርሽኝ መከሰቱን የዘገበ ሲሆን ምን ያህል ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ግን አልገለጸም። ኮሪያ ሴንትራል ኒውስ ኤጀንሲ ( ኬሲኤንኤ) የወረርሽኙን መከሰት የአገሪቷን የለይቶ ማቆያ ሕግ የጣሰ "ትልቅ አደጋ " ነው ያለ ሲሆን፣ የአገሪቷ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለብሔራዊው አደጋ ምላሽ ለመስጠት አስቸኳይ ስብሰባ እያደረጉ ነው ብሏል። ይሁን እንጂ ታዛቢዎች ቫይረሱ አሁን የተከሰተ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ በአገሪቷ እንደነበር ያምናሉ። ሰሜን ኮሪያ በቻይና የተሰራውን ሲኖቫክስስ እንዲሁም አስትራዜኒካ ክትባትን ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኗ የኮቪድ 19 ክትባት ለሕዝቦቿ አልሰጠችም። አገሪቷ ቫይረሱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሥርጭቱን ለመከላከል ያለመችው ድንበሮቿን በመዝጋት ነው። ይህም ወደ አገሪቷ የሚገቡ መሠረታዊ ፍጆታዎች እንዲቀንሱ በማድረጉ አገሪቷን ለከፋ ምጣኔ ሐብታዊ ቀውስ እና የምግብ እጥረት አጋልጧታል። እንዲህም ሆኖ ወረርሽኙ ሊከሰት እንደሚችል ምልክቶች ነበሩ። ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ ያልተረጋገጡና በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተመዝገብዋል። ጎረቤት አገሯ ቻይና እና ደቡብ ኮሪያም ወረርሽኙ ተከስቶባቸዋል። ቻይና አሁን ላይ የኦሚክሮንን ወጀብ ለመቆጣጠር እየታገለች ነው። ባለፈው ሰኔ ወር የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ፕሬዚደንት ኪም ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ስለተከሰተው አሳሳቢው ክስተት ባለሥልጣናትን መተቸታቸውን የዘገቡ ሲሆን ስለጉዳዩ ግን ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። መስከረም ወር መንግሥት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲሁም የበሽታ መከላከያ ልብስ በመልበስ ወታደራዊ ሰልፍ አድርጓል። ይህንን ተከትሎ አንዳንድ ተንታኖች ልዩ ኃይሉ የተፈጠረው የኮቪድ 19 ሥርጭትን ለመከላከል አንዲሳተፉ እንደሆነ ምልክት መሆኑን ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61418838
amh
health
የኮቪድ-19 ማጠናከሪያ ክትባት ሆስፒታል የመግባት መጠንን እንደሚቀንስ ጥናት አመለከተ
የኮቪድ-19 ማጠናከሪያ ሦስተኛ ክትባት ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ወደ ሆስፒታል እንዳይገቡ ለመከላከል 88 በመቶ በማገዝ ውጤታማ ነው ሲል የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የጤና ጥበቃ ኤጀንሲ አዲስ ጥናት አመለከተ። አስትራዜኒካ፣ ፋይዘር ወይም ሞደርና ክትባቶችን ሁለት ዙር የወሰዱ ሰዎች በኦሚክሮን እንዳይያዙ እምብዛም ባይጠብቃቸውም በጠና ከመታመም እንደሚከላከል ጥናቱ ያሳያል። የጤና ኃላፊዎችም ይህ ጥናት ሦስተኛ ዙር ወይም የማጠናከሪያ ክትባት አስፈላጊነትን ያጎላዋል ሲሉ ተናግረዋል። የዩኬ የጤና ፀሐፊው ሳጂድ ጃቪድ "ይህ ክትባቶች ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ የሚያረጋግጥ እና የበለጠ ተስፋ ሰጪ መረጃ ነው። ሕይወትን ያድናል እንዲሁም ከባድ በሽታን ይከላከላል" ሲሉ ተናግረዋል። "ይህ ሳይንሳዊ ትንታኔ ክትባቱን ያልወሰዳችሁ እንደሆነ በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ ሆስፒታል የመሄድ ዕድላችሁ እስከ ስምንት እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑን ያሳያል" ሲሉም አስጠንቅቀዋል። የዩኬ የጤና ደኅንነት ኤጀንሲ በሠራው በዚህ ጥናቱ ላይ ከ600,000 በላይ የተረጋገጡ እና የተጠረጠሩ በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎችን መረጃ በመተንተን ነው ድምዳሜ ላይ የደረሰው። እንደ ኤጀንሲው ግኝት ከሆን አንድ ዙር የክትባት መጠን የሆስፒታል ሕክምና የሚያስፈልገው ሕመምን በ52 በመቶ ቀንሶታል። ሁለተኛውን ዙር ክትባት መውሰድ ደግሞ ይህንን የመከላከል መጠን ወደ 72 በመቶ ከፍ የሚያደርገው ሲሆን ከ25 ሳምንት በኋላ ይህ የመከላከል አቅም መልሶ ወደ 52 በመቶ ዝቅ እንደሚል ታውቋል። ነገር ግን ሦስተኛው ዙር ክትባት ከተወሰደ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ይህ በሆስፒታል የመተኛትን የመከላከል አቅም ወደ 88 በመቶ ከፍ ብሏል። የኤጀንሲው ጥናት ይህ ጥበቃ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ለማወቅ እስካሁን በቂ መረጃ አለመገኘቱን ነገር ግን ሕመምን በመቀነስ ረገድ ረዘም ላለ ጊዜ እንደሚሠራ ይፋ አድርጓል። ቀደም ሲል የኮቪድ-19 ሕመም ምልክቶች በታየባቸው ሰዎች ላይ ደግሞ ከእያንዳንዱ ዙር ክትባት በኋላ ያለው የመከላከል መጠን ካልተከተቡ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር 68 በመቶ ያህል ያነሰ መሆኑም ታውቋል። ከካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ የተደረገው ሁለተኛ ጥናት አንድ ሰው በኦሚክሮን ከተያዘ በኋላ ሆስፒታል የመግባት ስጋት ከዴልታ ዝርያ ጋር ሲነጻጸር በግማሽ ያህል ያነሰ እንደሆነ አረጋግጧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59845459
amh
health
በዋግ ኽምራ ዞን ሰዎች በረሃብ እየሞቱ መሆኑን ነዋሪዎችና ኃላፊዎች ገለፁ
በአማራ ክልል በሚገኘው የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በርካታ ሰዎች በረሃብ ምክንያት እየሞቱ መሆኑን ከአካባቢው ወደ ባሕር ዳር እና እብናት የመጡ ነዋሪዎች እንዲሁም የአካባቢው ኃላፊዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ ገብሬ የአካባቢው ማኅበረሰብ ላለፉት አራት ወራት ምንም ዓይነት እርዳታ አግኝቶ እንደማያውቅ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና ከተማ ሰቆጣን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከተሞች በህወሓት አማፂያን ቁጥጥር ሥር በመሆናቸው በብዛት ኑሮውን በእርዳታ የሚደጎመው የአካባቢው ማኅበረሰብ ካለፈው ዓመት ሐምሌ መጀመሪያ አንስቶ ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳላገኘ ጨምረው ተናግረዋል። የዛሬ ዓመት በትግራይ የተቀሰቀሰው ጦርነት ወደ አማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከተስፋፋ ጀምሮ አብዛኞቹ ወረዳዎች ለሰብዓዊ እርዳታ ዝግ ሆነው መቆየታቸውን ምክትል አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልፀዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አካባቢውን ከላሊበላም ሆነ ከሰቆጣ የሚያገናኘው መንገድ ከሐምሌ 09/2013 ዓ.ም ጀምሮ በመዘጋቱ ሰብዓዊ እርዳታም ሆነ የመድኃኒት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ችግሩን አባብሶታል ይላሉ። በዚህም ምክንያት በርካታ የአካባቢው ሕዝብ ለከፋ ችግር መዳረጉን፣ ብዙ ሰዎችም በረሃብ እየሞቱ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ኃላፊዎች ይናገራሉ። የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ የምግብ ዋስትና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ ኮሚሽን፣ በክልሉ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልግ አስታውቋል። እንደ ኮሚሽኑ መግለጫ ከሆነ የህወሓት አማፂያን በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ከ110 በላይ እናቶች፣ ሕጻናት እና ተመላላሽ ታካሚዎች በምግብ፣ በውሃ እና በመድኃኒት እጦት ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። ኮሚሽኑ በአካባቢው የመንግሥት መዋቅር በመፍረሱ ምክንያት በምግብ እና በህክምና እጦት የሞቱ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥርን ማወቅ አለመቻሉን ገልፆ፣ ከዚህም ሊጨምር ይችላል ብሏል። የህወሓት አማፂያን በተቆጣጠሯቸው ዞኖች እንዲሁም ከእነዚህ አካባቢ ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያዎች የሚገኙ ሰዎች ለምግብ፣ ለመጠጥ ውሃ እና የመድኃኒት እጦት ተጋልጠዋል ሲል ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል። አክሎም በሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ ከፊል ደቡብ ጎንደር እንዲሁም ዋግ ኽምራ ውስጥ የሚኖሩ እና ተፈናቅለው የሚገኙትን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግሯል። '. . .ችላ ተብለናል' የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ገብሬ አካባቢውን የህወሓት አማፂያን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ በርካታ ሰዎች መፈናቀላቸውን ይናገራሉ። "የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች የችግሩን አሳሳቢነት ብናሳውቅም ማንም ሊደርስልን አልቻለም። . . .ችላ ተብለናል" ብለዋል። ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ 50 ሺህ የሚጠጉ የብሔረሰብ አስተዳደር ዞኑ ነዋሪዎች በአንጻራዊነት ሰብዓዊ እርዳታ እያገኙ ቢሆንም እነሱም በችግር ውስጥ መሆናቸውን አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል። በብሔረሰብ አስተዳደሩ በአጠቃላይ ወደ 635 ሺህ ሕዝብ ለከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጧል ያሉት አቶ ተስፋዬ፣ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በረብ ሞተዋል ስለሚባሉት ሰዎች መረጃው ቢኖራቸውም ቁጥሩ ግን ከሚገለጸው በላይ ሊጨምር ይችላል ብለዋል። በብሔረሰብ አስተዳደሩ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ የሴፍቲኔት ተጠቃሚ የነበረ ቢሆንም የህወሓት አማፂያን ወደ አካባቢው መግባታቸውን ተከትሎ ምንም አይነት እርዳታ ደርሶ እንደማያውቅ ምክትል አስተዳዳሪው ተናግረዋል። በብሔረሰብ አስተዳደሩ ጋዝጊብላ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ወንድሙ ወዳጅ ሰሞኑን ወደ ባሕር ዳር ከመጡት ተፈናቃዮች መካከል አንዱ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ ረሃብ በመከሰቱ በአሁኑ ወቅት ከአቅመ ደካሞች ውጪ አብዛኛው የወረዳው ነዋሪ ሰብዓዊ እርዳታ ፍለጋ አካባቢውን ለቅቆ እየተሰደደ ነው። "ቤተሰብ ቢያንስ ልጆቼ ቢተርፉልኝና እርዳታ ቢያገኙ እያለ ልጆቹን ወደ እብናት እና ባሕር ዳር ይልካል። ነገር ግን እዚህም እርዳታ የለም" ብለዋል። በረሃብ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ ወንድሙ፣ በወረዳው 21 ቀበሌዎች የሚገኙ ሲሆን በእነዚህ ቀበሌዎች በየቀኑ ቢያንስ አንድ ወይም ሁለት ሰው በረሃብ ምክንያት እንደሚሞት ይናገራሉ። "እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ሰው ያለውን እየተበዳደረ ይመገብ ነበር፣ ከጊዜ በኋላ ግን አንዳንድ አቅመ ደካሞች የበለጠ በመቸገራቸው ወጣቶች ቤት ለቤት እየለመኑ፣ በጣም የተራቡትን እየመረጥን እንደጉማቸው ነበር። ነገር ግን አሁን ትተናቸው በመምጣታችን ይሙቱ ይኑሩ አናውቅም" ብለዋል። በዚሁ ወረዳ [ጋዝጊብላ] የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን መዓዛ፣ በወረዳው ሰዎች በረሃብ እየሞቱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በወረዳው በሚገኙ በሁሉም ቀበሌዎች በመገኘት መረጃ ለማጠናቀር አስቸጋሪ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ሰለሞን፣ ቢያንስ እርሳቸው የሚያውቋቸው ሦስት ሰዎች በርሃብ ምክንያት ሕይወታቸው አልፎ በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ ተገኝተዋል። በወረዳው ከ23 ሺህ በላይ ዜጎች የሴፍቲኔት ተጠቃሚ ሲሆኑ አብዛኞቹ የመጨረሻ ሰብዓዊ እርዳታ ያገኙት ከግንቦት ወር በፊት መሆኑን የሚያስታውሱት አቶ ሰለሞን፣ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ቢያንስ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት የከፋ ችግር ውስጥ ስለነበሩ እጅግ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸው ነበር ብለዋል። ነገር ግን ወዲያውኑ ጦርነቱ በመከሰቱ ምንም አይነት እርዳታ ሳያገኙ መንገዶቹ ተዘጋግተዋል ብለዋል። የህወሓት ኃይሎች ወደ አካባቢው መግባታቸውን ተከትሎ የመብራት፣ ውሃ እና ባንክ የመሳሰሉት መሠረታዊ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው እና የንግድ ልውውጥ ባለመኖሩ ችግሩን የከፋ እንዳደረገውም ይናገራሉ። በዚህም ምክንያት የመሠረታዊ ፍጆታ እቃዎች አቅርቦት እጥረት ከመከሰቱም በላይ የዋጋ ንረቱ ከፍተኛ ሆኗል የሚሉት አቶ ሰለሞን፣ ለአብነትም የአንድ ኪሎ ጨው ዋጋ እስከ 100 ብር መድረሱን ይናገራሉ። የብሔረሰብ አስተዳደሩ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ በረሃብ ከሚሞተው ሕዝብ በተጨማሪ ". . . በንጹሃን ዜጎች ላይ ከመንግሥት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል እና መረጃ አምጡ በማለት በርካታ ሰዎች በህወሓት ተገድለዋል" ሲሉ ይከስሳሉ። ቢቢሲ በአካባቢው የህወሓት ኃይሎች ፈፀሙት ስለተባለው ግድያ ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልቻለም። የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች በአጠቃላይ እስከ 7 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሃብ ቀውስ ሊጋለጡ ይችላሉ ማለቱ ይታወሳል። ድርጅቱ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት በአማራ እና አፋር ክልሎች ወደ 1.7 ሚሊዮን ሰዎችን ለረሃብ አደጋ ሲያጋልጥ ወደ 300 ሺህ የሚጠጋ ሕዝብን ደግሞ ከመኖሪያ ቀዬው አፈናቅሏል ይላል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59161562
amh
health
ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ በአንድ ቀን ብቻ 94 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ተያዙ
በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 94 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ ቀናት በቀሯት አሜሪካ በተለያዩ ግዛቶችም በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አሻቅቧል ተብሏል። በዚህ ሳምንት ሃሙስ 91 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ከፍተኛ ቁጥር ነው በማለት ሪፖርት አድርጋ የነበረቸው አሜሪካ በተከታታይ ባሉት ቀናትም እንዲሁ ከዚህ በላይ ያለው ቁጥር በየቀኑ ተመዝግቧል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮም እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9 ሚሊዮን መድረሱን ከጆንስ ሆፕኪንስ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። ፕሬዚዳንታዊ ስልጣኑን ለመጨበጥ ዶናልድ ትራምፕና ጆ ባይደን እየተፋለሙ ባሉባት አሜሪካ ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም አሸናፊው የሚታወቅ ይሆናል። አሁን ባለውም ሁኔታ 21 የአሜሪካ ግዛቶች በወረርሽኙ ክፉኛ የተመቱ ሲሆን አንዳንድ ግዛቶችም በዚህ ምርጫ ላይ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ተብሏል። በምርጫው ወሳኝ ከሆነችው ግዛት አንዷ ዊስኮንሰን የሚገኙ ሆስፒታሎች አርብ እለት የነበረውን የዶናልድ ትራምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ ወረርሸኙን ያባብሰዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። "በአሁኑ ወቅት በተቻለ መጠን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ባይሰበሰቡ ይመረጣል። በተለይም በዊስኮንሰን ግዛት ግሪን ቤይ አካባቢ በአገሪቱ ካሉ ቦታዎች በከፍተኛ ፍጥነት ወረርሽኙ እየተዛመተ መሆኑን እያየን ነው" በማለት የግዛቲቱ ሆስፒታሎች በጥምረት መግለጫ አውጥተዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ አርብ ከነበረው የምርጫ ቅስቀሳቸው በፊትም "ከፍኛ ምርመራ ከፍተኛ ቁጥርን እያስመዘገበ ነው። ምርጥ የሆነ ምርመራ አለን። ሞት እየቀነሰ ነው" በማለት በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በቅርቡ የነበረው የትራምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ ተሳታፊው ሙቀት ሲለካ ነበር እንዲሁም ጭምብልም እየታደለ ነበር። በወረርሽኙ ምክንያት ትልልቅ ዝግጅቶችም ከአዳራሽ ውጭ እየተደረጉ ነው። ሆኖም በነዚህ ስፍራዎች አካላዊ ርቀት ሲጠበቅ አይታይም እንዲሁም አንዳንድ ደጋፊዎች ጭምብል አናጠልቅም የሚል እምቢተኝነት አሳይተዋል። ጆ ባይደንም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውን እያካሄዱ ሲሆን ዲሞክራቶቹ አካላዊ ርቀትን እያስጠበቁ ነው ተብሏል። ለምሳሌም ያህል ደጋፊዎች በየመኪኖቻቸው ሆነው እንዲከታተሉ አድርገዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54752422
amh