id
stringlengths
8
13
url
stringlengths
36
41
title
stringlengths
14
73
summary
stringlengths
6
277
text
stringlengths
318
10.6k
48946713
https://www.bbc.com/amharic/48946713
የቀደመው ዘመናዊ ሰው ከአፍሪካ ውጪ ተገኘ
ተመራማሪዎች ከዘመናዊ ሰው ጋር ተቀራራቢ የሆነ ዝርያ ከአፍሪካ ውጪ አገኙ።
በግሪክ የተገኘው የራስ ቅል አውሮጳ በኒያንደርታሎች በተወረረችበት ወቅት 210 ሺህ ዓመት ያስቆጠረ ነው ተብሏል። ጥናቱ ይፋ እንዳደረገው፤ የሰው ልጅ ከአፍሪካ ወደ አውሮጳ ቅድመ ፍልሰት ስለማድረጉ ታሪክ ምንም አይነት የዘረመል ማስረጃ የለውም ለሚለው ሌላ አስረጅ ሆኖ ቀርቧል። ይህ ግኝት የታተመው 'ኔቸር' በተሰኘው ጆርናል ላይ ነው። ተመራማሪዎች በ1970ዎቹ በግሪክ አፒዲማ ዋሻ ውስጥ ሁለት ጠቃሚ ቅሪተ አካል አግኝተው ነበር። • ለባለስልጣናቱ ግድያ አዴፓ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ ህወሐት ጠየቀ • "የለውጥ አመራሩን ሳይረፍድ ከጥፋት መመለስ ይቻላል" እስክንድር ነጋ አንዱ በጣም የተዛባ ሌላኛው ደግሞ ያልተሟላ ነበር። ቢሆንም ተመራማሪዎች የተለያዩ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የቅሪተ አካሉን ምስጢር ሊደርሱበት ችለዋል። ይህም ተመራማሪዎቹ በግሪክ ከዛሬ 210 ሺህ ዓመት በፊት ጥንታዊ ሰው በርከት ብሎ ይኖር ነበር እንዲሉ አስችሏቸዋል። ከአፍሪካ ውጪ የሚገኘው የዓለማችን ሕዝብ ከየት መጣሁ? ብሎ ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ ከአፍሪካ መፍለሱን ይናገራል። መቼ? ለሚለው ደግሞ ከ60 ሺህ ዓመት በፊት የተመራማሪዎች መልስ ነው። ይህ ዘመናዊ ሰው ወደ አውሮጳና እስያ ሲሄድ በመንገዱ ላይ ያገኛቸውን እነ ኒያንደርታልና ዴኒሶቫንስን እየተኩ መሄዳቸው ይታመናል። ነገር ግን ዘመኑ ጥንታዊ ሰው (ሆሞሳፒያንስ) ከአፍሪካ ወደ ሌሎች የዓለማችን ክፍል መፍለስ የጀመረበት የመጀመሪያው ጊዜ አይደለም። የሆሞሳፒያንስ ቅሪተ አካል በ1990ዎቹ በእስራኤል ከስኩሁል እና ቃፍዜህ የተገኘ ሲሆን፤ እድሜውም ከ90 ሺህ እስከ 125 ሺህ ድረስ ተገምቷል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጥንታዊ ሰው ከአፍሪካ ወደ አውሮጳና ወደ እስያ ያደረገውን ፍልሰት በሚመለከት የሚደረጉ ጥናቶች ላይ አንዳንድ ፍንጮች እየተገኙ መሆናቸውን ተመራማሪዎች ያስረዳሉ። • የታገዱት ሞተረኞች እሮሮ እያሰሙ ነው ቻይና ውስት በዳኦክሲያንና ዝሂሬዶንግ የተገኘው ቅሪተ አካል እድሜው በ80 ሺህና በ120 ሺህ መካከል ተገምቷል። የዘረመል ጥናቶች ላይ ምርምር የሚያደርጉ ሰዎች፤ ከአፍሪካ የሄዱና ኒያንደርታሎች ተዳቅለው አግኝተናል ብለዋል። በጀርመኖቹ የኒያንደርታሎች መዳቀል የተፈጠረው 219 ሺህ እና በ460 ሺህ ዓመታት መካከል ነው። ነገር ግን አሁንም ሆሞሳፒያንስ መዳቀሉ ላይ ተሳትፈውበታል ወይስ ሌላ ጥንታዊ የአፍሪካ ቡድን አለ ለሚለው መልስ አልተገኘለትም።
news-45022403
https://www.bbc.com/amharic/news-45022403
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በአሜሪካ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ምላሽ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚገኙ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን በትልቅ መሰብሰቢያ ውስጥ አግኝተው ከነጋገሩ በኋላ በተዘጋጀ የእራትና የውይይት መረሃ ግብር ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ባለፉት አራት ዓመታት እንቅልፍ ተኝተው እንደማያውቁ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለፉ አስታውሰው በተለይ ከአራት ወራት በፊት የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው እንደነበርም ተናግረዋል። የእስር ማዘዣው ከየትኛው ወገን እንደመጣ በግልፅ ባይናገሩም ከሀገር እንዲወጡ የሚያስገድዱ ጫናዎች እንደነበሩም ጠቁመዋል። "እኛም አንወጣም ብለን እዚያው የሚመጠውን ሁሉ ለመጋፈጥ ቆርጠን ቆይተናል ምክንያቱም ከሃገር የወጡ አልተመለሱም። ለዚህም ነው እዚህ ቦታ ላይ ልንደርስ የቻለው" ብለዋል። • ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መቼ አገር ቤት ይገባሉ? • 40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ ጉዞ ተጠናቀቀ በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከታዳሚው ለቀረቡላቸው የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሌ ክልልን በተመለከተ በኢትዮጵያ ያሉት ሶማሌዎች ብቻ ሳይሆን ሞቃዲሾ ያለውም ጭምር ዴሞክራሲን እንዲተገብርና ከኢትዮጵያዊያንና በተለይ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ተሳስሮ መኖር አለበት ብለን በጽኑ እናምናለን በማለት ጀምረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ክልሉ መሪ ያስፈልገዋል፤ ክልሉ የልብ አንድነት ያስፈልዋል። ብዙዎቻችሁ ላታስተውሉት ትችላላችሁ ግን አፍሪካ በብዙ ጅብ መንግሥታት የተያዘች አህጉር ናት። እነዚህን መንግሥታት ከጎረቤት አስቀምጠን ኢትዮጵያ ላይ ዴሞክራሲ፤ ኢትዮጵያ ላይ ሰላም ማምጣት አይቻልም። አፍሪካ የሚገባትን ክብር እንድታገኝ በጋራ መስራት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ በቂ ጭንቅላት አላት፤ 100 ሚሊዮን ምርጥ ጭንቅላት። ይህንን በማውጣት መስራት ያስፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የሶማሌ ክልልን በተመለከተ በመንግስት በኩል ሪፎርም እየሰራ እንደሆነና ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጠይቀዋል። ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ? • ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ በኦሮሞና በሶማሌ መካከል የተነሳውን ግጭት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ "ኦሮሞና ሶማሌ አንድ ቤተሰብ ናቸው፤ ስለዚህ ማንም ምንም አለ አብሮ ተጋግዞ መስራት ብቻ ነው የሚያዋጣው ብለዋል።" በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነትን በተመለከተ ''በመጀመሪያ ትኩረተ የሰጠነው ዋነኛው ነገር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ላይ ነው። ለዚህም ነው በፍጥነት የአውሮፕላን ጉዞ ያስጀመርነው፤ የሚያገናኙንን መንገዶች እየጠገንን ያለነው። ስለዚህ ህዝቡ ተገናኝቶ ሰላሙን መመስረት ከቻለ መንግሥት ደግሞ ይከተላል ማለት ነው።'' ''እንኳን ለመታረቅ ለመዋጋትም ከዚህ በፊት ውክልና አልሰጠንም። ስንዋጋም ሃገር የሚመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ተዋጉ ሲል ተዋጋን እንጂ በውክልና አልተዋጋንም። የትግራይን ህዝብ ሳናካትት ምንም አይነት ለውጥም ሆነ እድገት ማሳካት አንችልም፤ አንፈልግምም።" "ከትግራይ ህዝብ ውጪ ኢትዮጵያን የመቀየር ሃሳብ የለንም። ህዝቡ ያሳዝነናል፤ ህዝቡ ይቆረቁረናል። የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ ጉዳይ ግድ አይሰጠውም ማለት አንችልም ምክንያቱም በባድመ ጦርነት ከማንም በላይ የሞቱት የኦሮሚያ ልጆች ናቸው።" የሰላሙ ጉዳይ ለህዝባችን ስለሚጠቅም፣ የኤርትራ ህዝብ የሰላም ህዝብ ስለሆነ፣ የትግራይ ህዝብ ደግሞ የሚጠቀመው ከዚህ ሰላም ስለሆነ ሌላውን ትተን አንድ ሆነን እንስራ የሚለውን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ፀጉረ ልውጦች እነማን ናቸው? "ፀጉረ ልውጦች የተወሰኑ የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው ብሎ ማሰብ በመሰረቱ የተሳሳተ ነው" በማለት የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የትግራይ ህዝብ ኦሮሚያ ወይም አማራ ክልል ውስጥ ፀጉረ ልውጥ ሊሆን አይችልም።" ብለዋል። "ኦሮሚያ ውስጥ ትግሬም ይሁን አማራ፤ ወላይታም ይሁን ጉራጌ፤ ህዝቡ ማንንም አቅፎ ለማኖር ፈቃደኛ ነው። እንደውም እኔና የወከልኩት ኦህዴድ ብዙ ችግር አለብን። የኦሮሞ ህዝብ ግን አቃፊ ነው። በእኛ መነጽር፤ በእኛ ልክ ህዝቡን አትለኩት። ህዝቡ እንደእኛ አይደለም፤ ህዝቡ ከእኛ የላቀ ብስለት ያለው ነው።" "ፀጉረ ልውጥ ያልኩት በፍጹም አንድን ቡድን በሚገልጽ መልኩ ሳይሆን፤ የሚሰማሩ ሃይሎች ስለነበሩ መረጃው ስላለኝ ነው እንጂ የሆነ ቡድን ፀጉረ ልውጥ ሌላኛው ደግሞ ንጹህ ለማለት አይደለም። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ውጥረት ማንኛውም ነገር ለፖለቲካዊ ጥቅም ሊውል ይችላል።" ባለፉት 27 ዓመታት የተሰራው ጥፋት ወይስ ልማት? ''ያለፉት 27 ዓመታ ብዙ ቆሻሻ ነገር የተሰራበት ዘመን ነው። ልማት ማለት አስፓልት፤ ልማት ማለት ኮንዶሚኒየም የሚመስላቸው ሰዎች አሉ። መሰረተ ልማት ያለ ውስጣዊ ሥርዓት ምንም ጥቅም የለውም። ምክንያቱም እርስ በእርሱ የማይነጋገር ህዝብ፤ እርስ በእርሱ የማይግባባ ህዝብ ፈጥረን ስናበቃ አስፓልት ሰርተንልሃል የምንል ከሆነ ተገቢ አይደለም'' ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ለተገኘው ልማት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተገኘው ሰላም ባለቤቱ ህዝብ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ለጠፋው ጥፋት ግን ተጠያቂው መንግሥት ነው። ጥሩ ነገር ሲሰራ ሃላፊነት የምንወስድ፤ ጥፋት ሲጠፋ ደግሞ የምንሸሽ አክራሪዎች አይደለንም እኛ፤ መንግሥት ነን። እስከ ዛሬ ለጠፉ ጥፋቶች በሙሉ ኢህአዴግ እንደ መንግሥት ሃላፊነቱን ወስዶ ህዝቡንም ይቅርታ ጠይቋል። ይሄ ሁሉ ግን በይቅርታ ብቻ የሚያልፍ አይደለም። ባለፉት 27 ዓመታት ለገረፍናችሁ፣ ላባረርናችሁ፣ ላስቸገርናችሁ ሰዎች እኔ እንደ ኢህአዴግ ከልብ ይቅርታ እጠይቃችኋለው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
news-56304723
https://www.bbc.com/amharic/news-56304723
ዩኬ ለየመን የምትሰጠውን እርዳታ መቀነሷን የረድኤት ድርጅቶች አወገዙ
የረድዔት ድርጅቶች የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በየመን ላይ ያደረገውን የእርዳታ ቅነሳ አወገዙ።
በመቶ የሚቆጠሩ የረድዔት ድርጅቶች ተቀባይነት የለውም በሚልም ነው ያወገዙት። በዘንድሮው ዓመት ለመካከለኛ ምስራቋ አገር፣ የመን 87 ሚሊዮን ፓውንድ እርዳታ እንደሚሰጥ እንግሊዝ ቃል ገብታለች። ከአመት በፊት የነበረው ዕጥፍ ፣ 164 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ በበኩላቸው መንግሥታቸው የየመንን ህዝብ ለመርዳት የገባውን ቃል አያጥፍም ብለዋል። ነገር ግን የመን ከመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ አገራት መካከል የዩኬ እርዳታ ሊያሽቆለቁልባት ይችላል ከተባሉት ዋነኛዋ እንደሆነች ሾልኮ የወጣ ኢ-ሜይል አስታውቋል። በመጀመሪያ ጉዳዩን ሪፖርት ያደረገው ኦፕን ዲሞክራሲ እንዳስታወቀው በባለፈው ወር ከመንግሥት ባለስልጣናት ሾልኮ የወጣ መረጃን መሰረት አድርጌያለሁ በማለት በሶሪያ 67 በመቶና በሊባኖስ 88 በመቶ እርዳታ ይቀንሳል ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም በናይጄሪያ 58 በመቶ፣ በሶማሊያ 60 በመቶ፣ በደቡብ ሱዳን 59 በመቶና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 60 በመቶ እርዳታ እንደሚቀንስ አስነብቧል። እነዚህ የረድዔት ድርጅቶች ለመሪው ቦሪስ ጆንሰን በፃፉት ደብዳቤ ህዝቡ በድህነት፣ በበሽታና በጦርነት የተጠቁ አገራትን ፊቱን ገሸሽ ያደርጋል ብሎ መንግሥት ማሰቡ ስህተት ነው ብለዋል። "የዩኬ መንግሥት በዚህ ወቅት የየመንን ህዝብ ችላ ብሎ የማይረዳ ከሆነ ታሪክ በጥሩ መልኩ አይዳኘውም። ከዚህ በተጨማሪ ለተቸገሩ አገራት አለሁ በማለት የምትረዳውን የዩናይትድ ኪንግደም አለም አቀፍ ስም የሚያጠለሽ ነው" ይላል ደብዳቤው ኦክስፋም፣ ክርስቲያን ኤይድ፣ ሴቭ ዘ ችልድረን፣ ኬር ኢንተርናሽናልን ጨምሮ 101 ድርጅቶች ናቸው ተቃውሟቸውን ያስገቡት። የእንግሊዙ ኦክስፋም ዋና ስራ አስፈፃሚ ዳኒ ስሪስካንዳራጅ እንዳሉት "ምጣኔ ኃብታችን ተጎድቷል በሚል የሚደረግና የበርካታ ሚሊዮናውያንን የመኖችን ህይወት የሚነጥቅ የእርዳታ ቅነሳ ሃሰተኛ ኢኮኖሚ ነው። በርካቶች ቤተሰቦቻቸውን መመገብ አልቻሉም፤ ቤታቸውን አጥተዋል፤ በኮሮናቫይረስና በግጭት ምክንያትም ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ እንዲህ በጦርነት በምትበጠበጥ አገር ላይ የጦር መሳሪያ በመሸጥ "'ኢ-ሞራላዊ' ተግባር እንዲታቀብ አስጠንቅቀዋል።
news-47851138
https://www.bbc.com/amharic/news-47851138
በሰሜን ሸዋ በተከሰተ ግጭት ህይወት ጠፍቷል ንብረት ወድሟል
ቅዳሜና እሁድ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመ ግጭት ሰዎች መሞታቸውንና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ።
በባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ተከስቶ ውጥረት ቅዳሜ እለት ተቀሰቅሶ እሁድም በቀጠለው ግጭት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት መጥፋቱንና በርካቶች መቁሰላቸውን የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸው በቀለ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። • አወዛጋቢው ግጭት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ከንቲባው ጨምረውም በግጭቱ የታጠቁ ኃይሎች መሳተፋቸውንና የዘረፋ ድርጊትም ተከስቶ እንደነበር ተናግረው ክስተቱ ከክልሉ ልዩ ኃይል አቅም በላይ በመሆኑ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እንዲገባ መደረጉንም አመልክተዋል። ግጭቱ ከአጣዬ ባሻገር በካራቆሬ፣ በማጀቴና በዙሪያቸው ባሉ አካባቢዎች መከሰቱን የተናገሩት ነዋሪዎች በቡድን የተደራጁ ታጣቂዎች በድርጊቱ ተሳታፊ እነደሆኑም ተናግረዋል። በጥቃቱ በሰው ህይወት ላይ ከደረሰው ጉዳት ባሻገር "በቤተ እምነቶች፣ በግለሰብ መኖሪያና በንግድ ተቋማት ላይ" ጥቃት መፈጸሙን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። • በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት የሰው ህይወት መጥፋቱ ተሰማ የአማራ ክልል የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ምክትል ኅላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ እንደተናገሩት ከእሁድ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የፀጥታ ኃይሎች ወደ አካባቢዎቹ በመግባታቸው ሁኔታዎች መረጋጋታቸውን ተናግረዋል። ኅላፊው የፀጥታ ጨምረውም በተደራጀ ሁኔታ በመታጠቅ የሕዝብን ሰላም እያደፈረሰ ያለውን ቡድን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የተቀናጀ ሥራ እንደሚከናወንም ገልጸዋል። በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በየአካባቢው በሚገኙ የጤና ተቋማት ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ሲሆን ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸውንም ወደሌሎች አካባቢዎች እንደተወሰዱ ተገልጿል። • የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ? የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) እሁድ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ባጋጠሙ ግጭቶች በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም የግጭቱን ምክንያት እና ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን በተመለከተ በማጣራት ለሕዝቡ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል። የአካባቢውን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ አመራሮች ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየሠሩ መሆኑን አመልክተው፤ በቀጣይም ከፌደራልና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር እንደሚሠራ ገልጸዋል።
news-54187347
https://www.bbc.com/amharic/news-54187347
የናይጄሪያዋ ግዛት ደፋሪዎች እንዲኮላሹ በህግ ፈቀደች
የናይጄሪያዋ ካዱና ግዛት ደፋሪዎች በህክምና እንዲኮላሹ ህግ አፅድቃለች።
የግዛቷ አስተዳዳሪ ናስር አህመድ ኤል ሩፋይ ባለፈው ሳምንት የቀረበላቸውን ረቂቅ ህግ በትናንትናው እለት በመፈረም አፅድቀውታል። ህጉ ከአስራ አራት አመት በታች ያሉ ህፃናትን የደፈሩ እንዲኮላሹ ብቻ ሳይሆን የሞት ፍርድንም አካቷል። የተደፈሩት ደግሞ ከአስራ አራት አመት በላይ ከሆኑ በህክምና እንዲኮላሹ እንዲሁም የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ህፃናትን የሚደፍሩ ሴቶችም ቢሆኑ የማህፀን ቱቧቸው እንዲወገድ የሚደረግ ሲሆን የሞት ቅጣትም በተጨማሪ ተካቶበታል። የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸው ከአስራ አራት አመት በታች ያሉ ህፃናት በአባሪነት የህክምና ሪፖርት ማምጣት ይኖርባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ህፃናትን የሚደፍሩ ሰዎች ዝርዝርም በሚዲያ እንደሚወጣና ለህዝቡም ይፋ ይሆናል ተብሏል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ በትናንትናው ዕለት ረቂቅ ህጉ ላይ መፈረማቸውንና ህግ ሆኖም እንደፀደቀ ያስታወቁት በትዊተር ገፃቸው ነው። በናይጄሪያ ካሉ ግዛቶች መካከል እንዲህ አይነት ህግ በማፅደቅ ካዱና ቀዳሚ ሆናለች። የናይጀሪያ ፌደራል መንግሥት ደፋሪዎችን ከአስራ አራት አመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ቢቀጣም ግዛቶች ግን የራሳቸውን ህግ ማውጣት ይችላሉ። የተደፈሩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በማህበረሰቡ ካለው ተጠቂዎችን ጥፋተኛ ከማድረግ እሳቤ አንፃር ብዙዎች ደፍረው ወደ ህግ ቦታ አይሄዱም። ደፍረው ሪፖርት ያደረጉትም ቢሆን ክስ ተመሰርቶ የሚፈረድባቸውም ጥቂቶች ናቸው። በሰኔ ወር ላይ በርካታ የናይጄሪያ ግዛት አስተዳዳሪዎች እየጨመረ የመጣውን የሴቶች መደፈርና ጥቃት አስመልክቶ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተላልፈው ነበር። በናይጄሪያ ከጎርጎሳውያኑ 2015 ጀምሮ የተፈረደባቸው 40 ደፋሪዎች ብቻ እንደሆኑ የተገኘው መረጃ ያሳያል። አገሪቷም ህጓን አሻሽላለች። የመድፈር ክስን አስቸጋሪ የሚያደርገው አቃቤ ህግ ማስረጃ ማምጣት ስለሚኖርበት አድካሚና ቴክኒካል ጉዳዪ የተወሳሰበ እንደሚያደርገው ይነገራል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የተጣለው የእንቅስቃሴ መገደብም የሚደፈሩ ሴቶችን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል። በሃምሌ ወር የ22 አመት እድሜ ያላት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ተደፍራ መገደሏ ከፍተኛ ቁጣን ፈጥሯል። ይህንንም ተከትሎ ናይጄሪያውያን ንዴታቸውን ለመግለፅ ጎዳና ላይ ወጥተዋል፤ 'ዊ አር ታየርድ' (ደክሞናል) በሚልም በትዊተር ላይ ዘመቻ ተጀምሮም ነበር። በርካቶችም የሞት ቅጣትን ጨምሮ ጠበቅ ያለ ህግ እንዲወጣም ጠይቀዋል። በህክምና የማኮላሸት ቅጣት በአንዳንድ አገራት ተግባራዊ ቢሆንም አወዛጋቢ ነው።
48701205
https://www.bbc.com/amharic/48701205
በጋሪሳ ዩኒቨርስቲ ጥቃት ለ148 ህይወት መጥፋት ተጠያቂ የተባሉ ሶስት ሰዎች ተፈረደባቸው
ሶስት ግለሰቦች የዛሬ አራት ዓመት በኬንያ ጋሪሳ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ ተከሰው ፍርድ ተበይኖባቸዋል።
ራሺድ ቻርልስ ምቤሬሶ፣ ሞሐመድ ዓሊ አቢካር እና ሃሳን ኤዲን ሃሳን የተሰኙት እኒህ ግለሰቦች የጋሪሳውን ጥቃት ካቀነባበሩ መካከል ናቸው ተብለው ነው ፍርድ የተሰጠባቸው። አራት የታጠቁ ሰዎች ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ገብተው 148 ተማሪዎችንና ሠራተኞች ነፍስ ያጠፉት በጎርጎሳውያኑ 2007 ላይ ነበር። • ኬንያ ሺሻን አገደች ግለሰቦቹ የአል-ሸባብ አባል ናቸው በሚልም ነው ፍርድ የተሰጠባቸው። አራተኛው ተከሳሽ ግን ነፃ ሆኖ በመገኘቱ ሊለቀቅ እንደቻለ ታውቋል። ነፃ የወጣውን ግለሰብ ጨምሮ ሶስቱ ግለሰቦቹ ኬንያውያን ሲሆኑ ራሺድ ቻርልስ የተባለው ግለሰብ ታንዛኒያዊ እንደሆነ ታውቋል። ራሱን የአል-ቃይዳ ክንፍ አድርጎ የሚቆጥረው አል-ሸባብ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2007 ላይ ለተከሰተው የጋሪሳው ጥቃት ኃላፊነት መውሰዱ አይዘነጋም። በጎርጎርሳውያኑ አቆጣጠር 1998 ላይ አል-ቃይዳ የአሜሪካን ኤምባሲ አጋይቶ 200 ሰዎች ካለቁበት ክስተት በኋላ ሁለተኛው አሰቃቂ ጥቃት ነው የጋሪሳው እልቂት። • ኬንያ ሜሪ ስቶፕስን አገደች የቢቢሲው ኢማኑዔል ኢጉንዛ ፍርዱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ነው ይላል፤ ከጥቃቱ ለተረፉ ትልቅ ትርጉም እንዳለው በመጠቆም። ለአራት ዓመታት ያክል የቆየው የፍርድ ሂደት የኬንያውያንን በተለይ ደግሞ ከጥቃቱ የተረፉትን ልብ አንጠልጥሎ የቆዬ እንደነበር ነው ኢጉንዛ የሚያስረዳው። መጋቢት 24/2007 ላይ በጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃገር አማን ብለው ሳለ የደረሰው ጥቃት ጥበቃዎችን፣ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና ሠራተኞችን ጨምሮ የ148 ሰዎችን ነፍስ ቀጥፏል። 500 ገደማ ተማሪዎች ደግሞ ጥቃቱን በመሸሽ ማምለጥ ችለዋል። 97 ግለሰቦች ደግሞ ክፉኛ አደጋ ደርሶባቸዋል። • 22 ኢትዮጵያዊያን ናይሮቢ ውስጥ ተያዙ
45675456
https://www.bbc.com/amharic/45675456
የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ብሬት ካቭና የፍርድ ቤት ውሎ
በአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኃለቃነት ከወራት በፊት የታጩት ዳኛ ብሬት ካቭና በወሲባዊ ጥቃት ተጠርጥረዋል።
ጉዳዩ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን አፍ ማሟሻ ከሆነ ቢሰነባብትም በስተመጨረሻ ወደ ሃገሪቱ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት ደርሷል። ጥቃቱን አድርሰዋል የተተባሉት ዕጩ ብሬት እና ወሲባዊ ጥቃት ደርሶብኛል ያሉት ዶ/ር ክርስቲን ብላሲ ፎርድ በሴናቶሮች ፊት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል። ዳኛ ብሬት ካቭና ወሲባዊ ጥቃቱን አልፈፀምኩም ሲሉ ስሜታዊነት በተሞላበት መልኩ ክሱን አጣጥለዋል። •የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች ከሳሽ ዶ/ር ክርስቲን ፎርድ በበኩላቸው ሰውየው ከ30 ዓመታት በፊት ያደረሱባቸው ወሲባዊ ጥቃት ሕይወታቸውን ክፉኛ እንዳመሳቀለው አስረድተዋል። • የጎንደር ሙስሊሞች እና የመስቀል በዓል ፕሬዝደንት ትራምፕ ብሬት 'ሃቀኛ' ናቸው ሲሉ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት በዕጩነት ያቀረቧቸውን ሰው ደግፈው ታይተዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተሮች 'አጥፊ' የሆነ ዕቅድ የኮነኑ ሲሆን የተከሳሽን መልካም ስም እያጎደፉ ነው ሲሉም ወቀሳ ሰንዝረዋል። የሴናተሮች ሕግ ተርጓሚ ኮሚቴ በብሬት ካቭና ዕጩነት ዙሪያ ድምፅ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ይዟል፤ ምንም እንኳ ሪፐብሊካኑ ሙሉ በሙሉ ለሰውየው ድምፃቸውን መስጠታቸው ቢያጠራጥርም። ጠቅላላ ሴናተሮች በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ ተሰባስበው በሰውየው ዕጣ ፈንታ ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል። የ51 ዓመቷ ዶ/ር ክርስቲን ፎርድ እንባ እየተናነቃቸው ነበር ቃላቸውን ለምክር ቤቱ አባላት ያሰሙት። • በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር ዘጠኝ ደርሷል ተባለ «እዚህ የተገኘሁት ወድጄ አይደለም» ሲሉ የተደመጡት ዶ/ር ክርስቲን «ፍራቻ ውስጥ ነኝ፤ እዚህ የተገኘሁት የዜግነት ግዴታዬን ለመወጣት ነው፤ ብሬት እና እኔ ትምህርት ቤት እያለን የገጠመኝን ለሁሉም ለማሳወቅ ነው» ሰሉ አክለዋል። ከሳሽ የ15 ዓመት ታዳጊ ሳሉ የ17 ዓመቱ ብሬት እና ጓደኛው መኝታ ቤት ውስጥ ቆልፈውባት ልብሷን በማወላለቅ ሊደፍሯት እንደሞከሩ እና እንደተሳለቁባት ቃላቸው ሰጥተዋል። ጉዳዩ ከበርካታ ዓመታት በፊት ስለሆነ ምናልባት ተሳስተው ከሆነ ተብለው ሲጠየቁ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሲሉ ተናግረዋል። ተከሳሽ በበኩላቸው «እኔ ዶ/ር ክርስቲንንም ይሁን ሌላ ሰው ላይ ወሲባዊ ጥቃት አላደርስኩም» ሲሉ ክሱን ክደዋል። ከሳሽ ባስቀመጡት ቦታ ላይ አለመገኘታቸውን ነው ለሴናተሮቹ ያሳወቁት። • ቢል ኮዝቢ ወደ ዘብጥያ ወረዱ
news-46601907
https://www.bbc.com/amharic/news-46601907
ለፖለቲካ ፍላጎት የተጋጋለ ግጭት ነው፡ ሙስጠፋ ኡመር
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ኡመር የግጭቱን መንስዔ ሲያስረዱ፤ በግጦሽ መሬት ሰበብ ከኃይለስላሴ መንግሥት ጀምሮ በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰቱ እንደነበረ አስታውሰው፤ ''ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ግን ሆነ ተብሎ የፖለቲካ ፍላጎት ተጨምሮበት የተጋጋለ ግጭት ነው'' ይላሉ።
ከጥቂት ዓመታት በፊት ተቀስቅሶ የነበረውን የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ለማዳከም በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች የሶማሌ ፖሊስን አንቀሳቅሰው በኦሮሚያ እና ሶማሌ ደንበር አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድረሰዋል ይላሉ አቶ ሙስጠፋ ኡመር። • ፓርቲዎች የምርጫ ቦርድን በሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ላይ እየመከሩ ነው ከዚህ በፊት የነበረው ግጭት ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነበረ። በግጭቱ የተጎዱ በሁለቱም በኩል ያሉት ኃይሎች ቁጭት እና ንዴት ስላለባቸው ግጭት እንዲቀጥል እያደረጉ ነው። አሁንም ግጭቱ እንዲቀጥል የሚያደርጉት እነርሱ ናቸው ይላሉ ሙስጠፋ ኡመር። ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር በሚያዋስነው አካባቢ ዋነኛዋ ከተማ በሆነችው ሞያሌ፤ የግጭት፣ የሞት እና የመፈናቀል ዜና መስማት እየተለመደ የመጣ ይመስላል። ነዋሪዎቿም በፍርሃት እና በሽብር መኖር ከጀመሩ ወራትን አስቆጥረዋል። መንግሥት ''በስህተት የተፈጸመ ነው'' ብሎ ከ10 በላይ ንጹሃን ነዋሪዎቿ ህይወታቸውን ያጡባት፤ በከተማዋ የሚኖሩ የኦሮሞ እና ሶማሌ ወጣቶች በሞያሌ ከተማ አስተዳደር ባለቤትነት ጥያቄ በድንጋይ የሚወጋገሩባት፤ ከፍ ሲልም በይዞታ ይገባኛል ምክንያት በጦር መሳሪያ የታገዙ ኃይሎች የሚፋለሙባት ግጭት፣ ሞት እና መፈናቀል የማያጣት ከተማ ሆናለች። እንደ አዲስ ከሁለት ሳምንታት በፊት በተቀሰቀሱ ግጭቶችም በርካቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ቆስለዋል፣ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። • "በምን ማስተማመኛ ነው የምንመለሰው" የሞያሌ ተፈናቃዮች ከዓይን እማኞች፣ ከጎሳ መሪዎች እና ከአካባቢው ባለስልጣናት እንደሰማነው ከሆነ ቢያንስ እንደ አዲስ ባገረሹት ግጭቶች እስካሁን ከ20 ሰዎች በላይ ተገድለዋል። የሰሞኑ ግጭት የተቀሰቀሰው ኦሮሚኛ ቋንቋ ተናገሪ በሆኑት ገሪ ተብለው በሚታወቁት የሶማሌ ጎሳ አባላትና በኦሮሞዎች መካከል በይዞታ ይገባኛል ምክንያት ነው። በኦሮሞ በኩል ያሉት የሞያሌ ወረዳ ኃላፊዎች ድንበር ተሻግረው በከባድ መሳሪያ ህዝቡ ላይ ጥቃት የሚፈጽሙት የሶማሌ ታጣቂዎች ናቸው ይላሉ። በሶማሌ ወገን ያሉት በበኩላቸው ለግጭቱ፣ ለሞትና መፈናቀሉ የኦሮሞ ታጣቂዎች ላይ ጣታቸውን ይቀስራሉ። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ኡመር የግጭቱን መንስዔ ሲያስረዱ፤ በግጦሽ መሬት ሰበብ ከኃይለስላሴ መንግሥት ጀምሮ በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰቱ እንደነበረ አስታውሰው፤ ''ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ግን ሆነ ተብሎ የፖለቲካ ፍላጎት ተጨምሮበት የተጋጋለ ግጭት ነው'' ይላሉ። • በሞያሌ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ የሰው ህይወት ጠፋ ከጥቂት ዓመታት በፊት ተቀስቅሶ የነበረውን የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ለማዳከም በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች የሶማሌ ፖሊስን አንቀሳቅሰው በኦሮሚያ እና ሶማሌ ደንበር አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድረሰዋል ይላሉ አቶ ሙስጠፋ ኡመር። ከዚህ በፊት የነበረው ግጭት ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነበረ። በግጭቱ የተጎዱ በሁለቱም በኩል ያሉት ኃይሎች ቁጭት እና ንዴት ስላለባቸው ግጭት እንዲቀጥል እያደረጉ ነው። አሁንም ግጭቱ እንዲቀጥል የሚያደርጉት እነርሱ ናቸው ይላሉ ሙስጠፋ ኡመር። ''ሞያሌን እንደ ሞቃዲሾ'' አቶ አሊ ጠቼ የሞያሌ ወረዳ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ ናቸው። አቶ አሊ ሞያሌ ከተማ ከዘርፈ ብዙ ችግሮቿ ጋር ብዙ ዓመት ተሻግራለች ይላሉ። አቶ አሊ ከሳምንታት በፊት ለተቀሰቀሰው ግጭት ጽንፈኛውን ቡድንን አልሸባብን ጭምረው ተጠያቂ ያደርጋሉ። ''አልሸባብ እንዲሁም ከሶማሌ ልዩ ፖሊስ እና ከሃገር መከላከያ ያፈነገጠ ኃይል ከባድ የጦር መሳሪያ በመጠቀም ሞያሌን እንደ ሞቃዲሾ አደረጓት'' ይላሉ። • በርካታ ሰዎች ከሞያሌ በመሸሽ ወደ ኬንያ ገብተዋል ጉዳዩን ለክልል እና ፌደራል መንግሥት ቢያሳውቁም በቂ ምላሽ አለማግኘታቸውን እና በሞያሌ ሰፍሮ የሚገኘውም የሃገር መከላከያ ሠራዊት ግጭቱን ማስቆም እንዳልቻለም ይናገራሉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከአምስት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ግጭቱ እንዲከሰት የሚያደርጉት የሁለቱን ክልሎች መረጋጋት የማይሹ ኃይሎች ናቸው፤ ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ብሏል። መግለጫው አክሎም በግጭቱ ለተጎዱ ሰዎች አስፈላጊው እርዳታ እየተሰጠ መሆኑን አመልክቷል። ''የፖለቲካ ጦርነት'' የሶማሌ ገሪ ጎሳ መሪ የሆኑት ሱልጣን ሞሐመድ ሃሰን በበኩላቸው ''ሁለቱ ህዝቦች [ገሪ እና ኦሮሞ] ከዚህ ቀደምም በይዞታ ይገባኛል ይጋጩ ነበረ። ይህ አዲስ አይደለም። ይህ ግጭት ግን የይዞታ ይገባኛል ሳይሆን የፖለቲካ ጦርነት ነው'' ይላሉ። ሱልጣን ሞሐመድ እየደረሰ ላለው ጥፋት የኦሮሞ ታጣቂዎችን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ''ድንበር ተሻግረው እየወጉን ያሉት እነሱ [የቦረና ኦሮሞ] ናቸው። እኛ እራሳችንን መከላከል ነው የያዝነው። መብታችንን እየተጋፉ ነው። በትልልቅ ጦር መሳሪያዎች የሚወጉን፣ ቤታችንን የሚያቃጥሉት እነሱ ናቸው።'' ይላሉ። • የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች ሱልጣን ሞሐመድ እንደሚሉት ከሆነ፤ የፌደራል እና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት ግጭቱን በውይይት ለመፍታት ሞያሌ ላይ ስብሰባ ቢጠሩንም በስብሰባው ላይ የኦሮሞ ተወካዮች በእምቢተኝነት ሳይገኙ ቀርተዋል ይላሉ። ''ምንም እንኳ እነሱ ስበሰባው ላይ ባይገኙም፤ እኛ ሰላም ነው የምንፈልገው ስንል ተናግረናል። ከዚያ በኋላም አዲስ አበባ ላይ ለስብሰባ ተጠርተን አባ ገዳው [የቦረና አባ ገዳ] ሳይገኝ ቀረ። የመጡትም ተወካዮች [የኦሮሞ ተወካዮች] ሰላም አንቀበልም ብለው ሄዱ'' ይላሉ። የቦረና አባ ገዳ ምን ይላሉ? ''የቦረና መሬትን የሸጠው መንግሥት ነው። የግጭቱ መንስዔ መንግሥት ነው። ችግሩን መፍታት ያለበትም መንግሥት ነው'' የሚሉት የቦረና አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ናቸው። ''ሞያሌ ውስጥ ሁለት ባንዲራዎች [የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልል ባንዲራዎች] እስከተውለበለቡ ድረስ በከተማዋ ሰላም ሊሰፍን አይችልም።'' አባ ገዳ ኩራ፤ ሶማሌዎች ዳዋ የሚባል ወረዳ መስርተው ሞያሌን የወረዳው ከተማ ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት ማቆም አለባቸው ይላሉ። "በ1997 ዓ.ም ላይ ተካሂዶ የነበረው ህዝበ ውሳኔ ሳይሆን የመሬት ዘረፋ ነበረ" የሚሉት አባ ገዳ ኩራ መንግሥት ታሪክ ተመልክቶ ውሳኔዎችን ያስተላልፍ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በግጭቱ በመኖሪያ ቤቶች፣ በመንግሥት ቢሮዎች እና ባንኮችን ጨምሮ በንግድ ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱንም የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
news-49982797
https://www.bbc.com/amharic/news-49982797
በአፍሪካ የመጀመሪያው ስማርት ስልክ ማምረቻ ፋብሪካ በሩዋንዳ ተከፈተ
ሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ስማርት ስልክ ማምረቻ ከፈተች። ፋብሪካው በዋና ከተማዋ ኪጋሊ የሚገኝ ሲሆን በምረቃው ላይ ፕሬዚደንት ፓል ካጋሜ ተገኝተዋል።
በማራ ግሩፕ በተሰኘ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ ማራ ኤክስና ማራ ዜድ ስማርት ስልኮችን የሚያመረተው ይህ ፋብሪካ ስልኮቹ የጎግልን አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንደሚጠቀሙ ተናግሯል። ስልኮቹ 5500 ብርና 3700 ብር አካባቢ ዋጋ ተተምኖላቸዋል። • እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት • ራስዎን ካላስፈላጊ የስልክ ጥሪ እንዴት ይታደጋሉ? ሰኞ ዕለት ፋብሪካውን ጋዜጠኞች ተዟዙረው እንዲጎበኙ ከተደረገ በኋላ "ይህ በአፍሪካ የመጀመሪያው ስማርት ስልክ ማምረቻ ነው" ብለዋል የማራ ግሩፕ የበላይ ኃላፊ አሺሽ ታካር ለሮይተርስ። ታካር አክለውም ፋብሪካው ዒላማው ያደረገው ጥራት ላይ መሠረት አድርገው ለመክፈል የተዘጋጁ ግለሰቦችን ነው። በአፍሪካ ውስጥ ከሚሸጡ በርካታ ስልኮች መካከል አብዛኞቹ የሚመጡት ከቻይና ነው። እነዚህ ስልኮች ሁለት ሲም የሚወስዱ እንዲሁም ማራ ግሩፕ ከተመነው ዋጋ ባነሰ ለቀበያ የሚቀርቡ ናቸው። በኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ አልጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ የተለያዩ መለዋወጫዎችን ከቻይና በማስመጣት የሚገጣጠሙ ስማርት ስልኮች እንዳሉ ሚስተር ታከር ይናገራሉ። "እኛ በማምረት ደረጃ የመጀመሪያዎቹ ነን። ማዘር ቦርዱን፣ እንዲሁም በአጠቃላይ ንዑሳን ክፍሎቹን የምናመርተው እዚሁ ነው። በእያንዳንዱ ስልክ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቅን ነገሮች አሉ" ሲሉ ተናግረዋል። በቀን 1200 ስልኮችን ያመርታል የተባለው ይህ ፋብሪካን ለማቋቋም 24 ሚሊየን ዶላር እንደወጣበት ተነግሯል። ፕሬዝዳንት ካጋሜ ፋብሪካው የሩዋንዳውያንን ስማርት ስልክ ተጠቃሚነት እንደሚጨምር ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል። በአሁኑ ሰዓት በሩዋንዳ ከሚገኙ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች 15 በመቶው ብቻ ስማርት ስልክ ይጠቀማሉ።
news-55905197
https://www.bbc.com/amharic/news-55905197
ጃክ ፓላዲኖ፡ የቢል ክሊንተን የትዳር መማገጥ ዜናን ያድበሰበሰው ሰው አስገራሚ አሟሟት
ዕውቁ የዝነኞች የግል መርማሪ በካሜራው ምክንያት ገዳዮቹን አጋለጠ።
ጃክ ፓላዲኖ ይባላል፡፡ ትናንትና 76 ዓመቱ ነበር፡፡ ዛሬ እንኳ የለም፡፡ በአሜሪካ ዕውቅ የግል ወንጀል መርማሪና ጉዳይ አስፈጻሚ ነበር፡፡ ባለፈው ሐሙስ ለታ ወንበዴዎች ድንገት ያዙት፡፡ ሳንፍራንሲስኮ በሚገኘው ቤቱ ደጅ ላይ ነው ማጅራቱን የቆለፉት፡፡ ታገላቸው፡፡ ጣሉት፡፡ ድንገት ግን አንዲት የድሮ ካሜራውን ይዟት ነበር፡፡ እነሱ ሊቀሙት ይታገሉት ነበር፡፡ ካሜራዋን። እንደምንም ብሎ ተጫናት፡፡ ፎቶ አነሳች፡፡ ወንደበዴዎቹ ጭንቅላቱ ላይ ባደረሱበት ጉዳት ኋላ ላይ ነፍሱ ከሥጋው ብትለይም ፖሊስ ጥፋተኞቹን ደርሶባቸዋል፡፡ ገዳዮቹ ሊደረስባቸው የቻለው ደግሞ ፓላዲኖ ከመሞቱ በፊት ፎቶ ስላነሳቸው ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ከ2 ሳምንታት በፊት ነው፡፡ ፓላዲኖ ሥመ ጥር የግል ወንጀል መርማሪ ሲሆን ከዋና ዋና ደንበኞቹ መሀል የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች እና ዕውቅ የሆሊውድ ተዋናዮች፣ ሙዚቀኞችና ጸሐፊ ተውኔቶች እና ሌሎች ገናናዎች ይገኙበታል፡፡ የፓላዲኖ ካሜራ የወንበዴዎቹን ምሥል በማስቀረቱ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን አድኖ ቢይዝም በነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ሆስፒታል የነበረው ፓላዲኖ ግን ትናንትና ሰኞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ዝነኛው ፓላዲኖ ዘመናትን ባስቆጠረው የግል መርማሪነት ሥራው አነጋጋሪ የነበሩ ጉዳዮችን በመያዝ ገናና ነበር፡፡ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን፣ ሞዛቂና ተዋናይት ከርትኒ ላቭ፣ በቅሌት ማጥ ውስጥ የሚገኘው ዝነኛው ፕሮዲዩሰር ሐርቬይ ዊኒስተን የፓላዲኖ ደንበኞች ነበሩ፡፡ ባለፈው ሐሙስ ፓላዲኖ ጥቃት ሲደርስበት ሳንፍራንሲስኮ ከሚገኘው ቤቱ ደጅ ላይ የነበረ ሲሆን 2 አደገና ቦዘኔዎች ናቸው የተባሉ ወጣቶች ናቸው በእጁ ይዞት የነበረውን ካሜራ ሊቀሙት የታገሉት፡፡ ይህን ተከትሎ ፓላዲኖ ወደኋላ ወድቆ ጭንቅላቱ ስለመታው ራሱን ወዲያውኑ ሳተ፡፡ በሚደንቅ ሁኔታ ታዲያ አጥቂዎቹ ከመሸሻቸውና እሱ ራሱን ከመሳቱ በፊት በነበረች ቅጽበት ፓላዲኖ የካሜራውን ጉጠት ተጭኖት ነበር፡፡ ፓላዲኖ ቢሞትም ፖሊስ ግን ያን ምሥል ተጠቅሞ ነው ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው፡፡ የፓላዲኖ ባለቤት ሳንድራ ሱተርላንድ የወንጀለኞቹን መያዝ ስትሰማ፣ ‹‹ምነው የሰራው ሥራ ወንበዴዎቹ እንዲያዙ ማድረጉን መርማሪ ሆኖ የኖረው ባለቤቴ ባወቀ›› ብላ ተናግራለች፣ ለአሶሲየትድ ፕሬስ፡፡ ሕይወቱን ሙሉ የወንጀል መርማሪ ሆኖ የኖረ ሰው ገዳዮቹ በዚህ መልክ መያዛቸው የሕይወት ግጥምጥሞሽ በሚል ብዙዎቹን አስደንቋል፡፡ ፓላዲኖ ሕግ የተማረ ሲሆን የግል መርማሪ ሆኖ መሥራት የጀመረው በ1970ዎቹ ነበር፡፡ ያን ዘመን የግል መርማሪ በፊልሞች ውስጥ ገዝፎ ይሳል ስለነበር ሥራውም ገናና ያደርግ ነበር፡፡ በ1977 ፓላዲኖ በአንድ የግል የወንጀል ምርመራ ቡድን ውስጥ ከባለቤቱ ጋር ተቀጠረ፡፡ እሱና ባለቤቱ ለዓመታት ወንጀል ምርመራ ውስጥ አብረው ሰርተዋል፡፡ እነ ፓላዲኖ በተለይም ለሆሊውድ ዝነኞች ስማቸው እንዳይጎድፍ የሚዲያ ዘመቻ በመክፈት፣ ወይም የሚዲያ አፍ በማዘጋት ሥራ ይሰማሩ ነበር፡፡ ለምሳሌ ሙዛቂዋ ከርተኔይ ባሏ ከሞተ በኋለ በሱ ዙርያ ይወሩ የነበሩ የሚዲያ ሐሜቶችን እንዲያከስምላት ፓላዲኖን ቀጥራው ነበር፡፡ ፓላዲኖ በተለይ ቢል ክሊንተን ከትዳራቸው ውጭ ወጣ ይሉ ነበር የሚለውን ሐሜት እንዲቀብርላቸው ክሊንተን ቀጥረውት ውጤታማ ሥራ ሰርቶላቸዋል፡፡ በ1999 ዓ/ም ሳንፍራንሲስኮ ኤክዛሚነር ጋዜጣ ፓላዲኖን ሲገልጸው፣ ‹አስጨናቂ መርማሪ፣ የጎደፈ ስም ወልዋይ፣ ለሙያው ሟች› ብሎት ነበር፡፡
news-55876977
https://www.bbc.com/amharic/news-55876977
ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ የኮቪድ ክትባትን የሚቃወሙ ሰልፈኞች ከፖሊስ ተጋጩ
በአሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ግዛት፣ ሎስ አንጀለስ ከተማ የኮቪድ ክትባት ውሸት ነው የሚሉ ቀኝ አክራሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡
ከፖሊስ ጋር የተጋጩት ክትባት እየተሰጠበት የሚገኘውን የዶገር ስታዲየም በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሰልፈኞቹ ይህን የክትባት መስጠቱ ሂደት ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል እንዲስተጓጎል አድርገዋል፡፡ ቁጥራቸው 50 የሚሆኑ የጸረ ክትባት አቀንቃኞች ስታዲየሙን ለማዘጋት የቻሉት መግቢያውን በመዝጋት ጭምር ነው፡፡ ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ላይ የነበሩ በርካታ መኪኖች በነዚህ የክትባት ተቃዋሚዎች ምክንያት አገልግሎት ሳያገኙ ተመልሰዋል፡፡ ሰልፈኞቹ የኮቪድ ክትባት የተጭበረበረ ስለመሆኑ የሚያወሱ መፈክሮችን የያዙ ሲሆን ኅብረተሰቡን ‹አትከተቡ፤ እናንተ የቤተ ሙከራ አይጥ አይደላችሁም› እያሉ ሲቀሰቅሱ ታይተዋል፡፡ የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ቀኝ አክራሪ ሰልፈኞቹ ለክትባት የተሰለፉ ሰዎችን ‹ ነፍሳችሁን አድኑ፣ የውሸት ሳይንስ መጫወቻ አትሁኑ እያሉ እየጮኹ ሲቀሰቅሱ ነበር፡፡ የክትባት መስጫውን ሰልፈኞቹ የተቆጣጠሩትም በአገሬው አቆጣጠር ከቀኑ 8 ሰዓመት ጀምሮ ነው፡፡ የሎስ አንጀለስ ፖሊስ በትዊተር እንዳስታወቀው ስታዲየሙ አልተዘጋም፤ ክትባቱ ቀጥሏል ብሏል፡፡ የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሰን በስታዲየሙ እየተሰጠ የነበረው የክትባት ዘመቻ በሰልፈኞች ለጊዜው ቢስተጓጎልም ወደ ሥራ ተመልሷል ብለዋል፡፡ ጀርማን ጃኩዝ የተባለና ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ሲጠባበቅ የነበረ ዜጋ ለሎስ አንጀለስ ታይምስ ቁጣውን የገለጸ ሲሆን ‹‹ይህ የቀኝ አክራሪዎች ድርጊት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው› ብሏል፡፡ ‹‹ለሳምንታት ክትባት ለማግኘት ስጠባበቅ ነበር፡፡ እኔ የጥርስ ሐኪም ነኝ፡፡ በሽተኞቼን ሳክም በጣም ተጠግቻቸው ነው፡፡ ከኮቪድ መጠበቅ እሻለሁ፡፡ ክትባቱ ያስፈልገኛል፡፡ ተህዋሲውን ለመከላከል ብቸኛው መንገድ ክትባት ነው›› ሲል ሐሳቡን አጋርቷል፡፡ በአመዛኙ የትራምፕ ደጋፊ የነበሩ እንደሆኑ የሚገመቱና ቀኝ አክራሪ የሆኑት ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች አንዱ ‹‹ሲኤንኤን እያታለላችሁ ነው›› ይላል፡፡ ሌሎች መፈክሮች፣ ‹‹ጭምብላችሁን ቀዳዳችሁ ጣሉት››፣ ‹‹የሰው አይጥ አትሁኑ›› የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ከአሜሪካ ግዛቶች ካሊፎርኒያ በተህዋሲው ክፉኛ ከተጠቁት ተርታ ትመደባለች፡፡ 40ሺ የግዛቲቱ ነዋሪዎች በኮቪድ ሞተዋል፡፡ 3 ሚሊዮኑ ተህዋሲው አለባቸው፡፡ በመላው አሜሪካ በኮቪድ ተህዋሲ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች በሚቀጥለው ወር ግማሽ ሚሊዮን እንደሚያልፍ ይጠበቃል፡፡
news-52932155
https://www.bbc.com/amharic/news-52932155
ለሥራ ቢሮ መሄድ ብሎ ነገር ከናካቴው ሊቀር ይሆን?
ለብዙዎቻችን ቤታችን ቢሯችን ሆኖ ሰንብቷል፤ በኮሮናቫይረስ ተህዋስ ምክንያት። ይህ ጽሑፍ እየተሰናዳ ያለውም በአንድ ከቤቱ እየሰራ በሚገኝ የቢቢሲ ሠራተኛ ነው።
እንቅስቃሴዎች ውስን ይሆናሉ መኝታን ቢሮ ማድረግ ይቀጥል ይሆን? እርግጥ ነው ከቤት ሆኖ መሥራት በድኅረ ኮሮናቫይረስ ዘመን ደንብ የሚሆንባቸው መሥሪያ ቤቶች እንደሚኖሩ ከወዲሁ እየተነገረ ነው። ይህ ሀቅ ከኩባንያ ኩባንያ ቢለያይም ቅሉ፤ ቀጣሪዎች በዚህ አጋጣሚ ሠራተኞቻቸው ከቤት ሲሰሩ ኩባንያቸው ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ እንደሚሆን በትንሹም ቢሆን ተረድተዋል። በዚህ ሀሳብ ገፍተውበት ቢሮ ድርሽ እንዳትሉ ቢሉንስ? ይህ የማይመስል የነበረ ነገር በብዙ ኩባንያዎች ዘንድ እየተጤነ ነው። "ለምን ቢሮ እንከራያለን?"፣ "ለምን በአንድ ቢሮ ሕንጻ ሺህ ሠራተኞች ይርመሰመሳሉ?" ያሉ የሥራ አስፈጻሚዎችና ቀጣሪዎች ቀስ በቀስ ቢሮዎቻችንን ወደ ሠራተኞቻቸው ሳሎን ሊያመጡት ሽር ጉድ ይዘዋል። ይህ ነገር የከተማን ሕይወት በጠቅላላ ሌላ መልክ ሊያሲዘው ይችላል። ማኅበራዊ ሕይወትና ትዳርም መልኩን ይቀይር ይሆናል። በዚህ ጉዳይ ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉን ሦስት ባለሞያዎችን መርጠናል። ጭር ያሉ መሐል መሀል ከተማዎች ጭር ይሉ ይሆን? ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ሰዎች ማኅበራዊ እንሰሳ ናቸው። ውጤታማ ለመሆን የግድ ፊት ለፊት ከባለጉዳይ ጋር መገናኘት ያሻቸዋል። ለ20 ዓመታት የተደረገ ጥናት ያንን ነው የሚያስረዳው። አንዳንድ ነገሮች አሉ፤ የግድ ከሰው ጋር ስንገናኝ የምናደርጋቸው። ከእነዚያ መካከል አንዱ ዕለታዊ ሥራ ነው። ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር) አዲስ ነገር ልንጀምር ጫፍ ላይ ያለን ይመስለኛል። የሰው፣ የቦታና የጊዜ መስተጋብር ሌላ መልክ በመያዝ እየመጡ ይመስለኛል። ከዚህ ወዲያ አንዳንድ ነገሮች በነበሩበት ይቀጥላሉ ለማለት እቸገራለሁ። ኦዲ ቢኮሌት (የፖሊሲ ጥናት ተመራማሪ) አንዳንድ ግዙፍ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸው ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ እያበረታቱ መሆኑ ግልጽ ነው። ትዊተር ይህን ወስኗል። ፌስቡክም እንዲሁ። የባርክሌይ ባንክ ሥራ አስፈጻሚም "7 ሺህ ሠራተኛ ቢሮ ጠርቶ ማርመስመስ ከዚህ በኋላ ያረጀ ያፈጀ ጉዳይ" እንደሚሆን ጠቁመዋል። ቢሮ ሄዶ የመስራቱ ነገር ጨርሶውኑ ይጠፋል ባይባልም የቢሮ መሄድ ልማድ እየከሰመ ሲሄድ አነስተኛ፣ መካከለኛና ዋነኛ የከተማ አካባቢዎች እንደየደረጃው መልካቸው መለወጡ የማይቀር ጉዳይ ነው። ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር) አንዳንድ ኩባንያዎች "ለምንድነው ሚሊዮን ዶላር ለቢሮ የምንከሰክሰው" ማለታቸው አይቀርም።፡ ከወዲሁ እንደዚያ ማሰብ የጀመሩ አሉ። ይሄ ማለት በትንሹ ሦስት ነገሮችን ጨርሶውኑ ይቀይራል። አንዱ የከተሞችን ማዕከላት፣ ሁለተኛው የልጅ አስተዳደግ፣ ሦስተኛው ደግሞ የትዳር ግንኙነት ናቸው። ይህ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። ኦዲ ቢኮሌት (የፖሊሲ ጥናት ተመራማሪ) እኔ እንደሚመስለኝ በየሰፈራችን፣ ወደ ቢሮ ርቀን ሳንሄድ ሬስቶራንቶች፣ መዝናኛዎች እና ሌሎች የምንፈልጋቸው ነገሮች ወደኛ እየቀረቡ ይሄዱ ይሆናል። ሰዎች በአቅራቢያቸው መገናኘት መጀመር ይፈልጉ ይሆናል። ሌላው ደግሞ ከቤታችሁ ስሩ ስንባል ቦታ ስንሻ በዚያው በሰፈራችን የተሸለ ስፍራ መፈለጋችን አይቀርም። ይህ ሀቅ ሰፈሮች እንዲያብቡ ሊያደርጋቸው ይችላል። ቢሮዎች በስፋት በሚገኙባቸው የከተማ ማዕከላትም ለውጦች መኖራቸው አይቀርም። እነዚያ ሰፋፊ የቢሮ ሕንጻዎች ቆመው አይቀሩም መቼስ። የዲዛይን ለውጥ እየተደረገባቸው ወደ መኖርያ አፓርትመን ይቀየሩ ይሆናል። ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ የኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ከቤት ሥሩ ከተባልን ሁሉም የቤተሰብ አባል ቤት መዋሉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በቤታችን ውስጥ ሰፋፊ ቦታ መሻትን ያስከትላል። ካልሆነም በአቅራቢያችን የተመቻቸ ቦታ እንፈልግ ይሆናል። ለስብሰባ በሳምንት አንድ ሁለት ጊዜ ወደ ዋና ጽሕፈት ቤት መሄድ ሊኖር ይችላል። በሳምንት አንድ ጊዜ መሄድ ብቻ ግዴታ ሲሆን ደግሞ ሰዎች ከዋና ከተማ አቅራቢያ መስፈራቸው ጥቅሙ እየቀነሰ ይመጣል። ሰዎች ከከተማ ማዕከል ወደ ገጠር እየሄዱ መስፈር ይጀምሩ ይሆናል። በርሚንግሃም ውስጥ የሚገኝ ጭር ያለ የባቡር ጣቢያ ትራንስፖርትና የሰዎች እንቅስቃሴን በተመለከተ ምን ይፈጠራል? ማርገሬት ቤል በኒውካስል ዩኒቨርስቲ የትራንስፖርትና ኢንቫይሮንመንት ፕሮፌሰር ሰዎች መኪና መግዛት ይጀምራሉ። ይህም የሚሆነው ሰፋፊ ቦታ ፍለጋ ወደ ገጠር ስለሚያቀኑ ነው። በራቁ ቁጥር መኪና የግድ ይላቸዋል። ይህ ደግሞ የካርቦን ልቀትን ይጨምራል እንጂ አይቀንስም። ማድረግ የሚኖርብን ሰዎች ምንም ይሁን ምን ከሥራ ቦታቸው አቅራቢያ እንዲሰፈሩ ማድረግና ብስክሌት እንዲነዱ ማበረታት ነው። ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል የኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ብዙ ሰዎች ቤት ሲቀመጡ ቤት ማብሰል ግድ እየሆነ ይመጣል። ይህ የኢነርጂ [ኃይል] አጠቃቀማችን ላይ ለውጥ ያመጣል። ከቤት ባለመውጣት ከምናድነው ኢነርጂ የበለጠ ቤት ውስጥ እንጠቀማለን። ጥናቶች ይህንን ነው የሚመሰክሩት። በከተሞቻችን ዙርያ ስለሚኖር ለውጥ ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር) ብዙ ጊዜ ስለዚህ ጉዳይ ስናወራ ከፍ ያለ የቢሮ ሥራ ስለሚሰሩ ሰዎች እያሰብን ነው፤ ለምሳሌ በፋይናንስ፣ በአይቲ ወዘተ። ከተሞች የተሞሉት ግን በእነዚህ ሠራተኞች አይደለም። ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና አገልግሎች ሰጪ ተቋማት ይቀጥላሉ። ደግሞም ከተሞች የመገናኛ ማዕከል መሆናችውን አንርሳ። አገልግሎት ብቻ አይደለም የምንፈልገው። ሰዎች ሌሎችን ማግኘት መተዋወቅ ወዳጅነት መመስረት ይፈልጋሉ። ይህ እነሱን ከማይመስሉ ሰዎች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ይጨምራል። በባህል እኛን የማይመስሉ ሰዎችን በሰፈራችን ስለማናገኛቸው ርቀን ወደ ከተማ ማዕከላት መሄዳችን አይርም። ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ሌላው ጉዳይ መጠየቅ ያለብን ሰዎች ወደ ከተማ ወጥተው ለመቀላቀል ከዚህ በኋላ የኮሮናቫይረስ ፍርሃታቸው ብን ብሎ ይጠፋል ወይ? ሰዎች ወደ ድሮ ባህሪያቸው ለመመለስ ቢያንስ በሽታው በቁጥጥር ሥር ስለመዋሉን እርግጠኞች መሆን ይፈልጋሉ። ቢያንስ ክትባት ሊገኝ ይገባል። ይህ እስኪሆን ደግሞ ረዥም ጊዜ መፈለጉ አይርም። ረዥም ጊዜ!
news-53018870
https://www.bbc.com/amharic/news-53018870
ፊልም ለመቅረጽ ሲል የጎዳና ተዳዳሪዎችን መርዝ ያበላው ሰው በቁጥጥር ሥር ዋለ
በአሜሪካ ካሊፎርኒያ አንድ ግለሰብ ስምንት የጎዳና ተዳዳሪዎችን አፍዝ አድንግዝ እጽ በምግብ ለውሶ ሰጥቷቸዋል፡፡
ዊሊያም ሮበርት ኬብል የ38 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን ይህን አደንዛዥ መርዝ ለጎዳና ተዳዳሪዎቹ ከሰጣቸው በኋላ ሲሰቃዩ እርሱ ይቀርጻቸው ነበር ተብሏል፡፡የጎዳና ተዳዳሪዎቹ በተመገቡት የተመረዘ ምግብ የተነሳ ሆስፒታል ነው የሚገኙት፡፡ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ 19 ዓመት ዘብጥያ ይወርዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የኦሬንጅ ወረዳ የሕግ ጠበቃ ቶድ ስፒዘር እንደተናገሩት ተከሳሹ እነዚህን ሰዎች የመረጣቸው ድህነታቸውን ተጠቅሞ ነው፡፡ የነርሱን ስቃይ በካሜራ ቀርጾ እርሱ ለመዝናኛነት ሊያውለው ነው ያሰበው፤ ይህ ጭካኔ ነው ብለዋል ቶድ፡፡በካሊፎርኒያ የኦሬንጅ ወረዳ አቃቢ ሕግ እንዳብራራው ተከሳሹ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ያገኛቸው በሀንቲግተን የባሕር ዳርቻ ሲሆን ምግብ እንደሚፈልጉ ከጠየቃቸው በኋላ አዎ ሲሉት የተመረዘ ምግብ አቀብሏቸዋል። አንዳንዶቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች ተከሳሹ የሚያቃጥል ምግብ ውድድር እያደረኩ ነው፣ ቶሎ የጨረሰ ይሸለማል በሚል አታልሎ እንደቀረጻቸው ተናግረዋል፡፡ ያቀረበላቸው የተመረዘ ምግብ በአደገኛ በርበሬና ቃሪያ የተሰነገና እጅግ የሚያቃጥል ነው ተብሏል፡፡ምግቡን ከቀመሱ በኋላ የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ግማሾቹ ራሳቸውን የሳቱ ሲሆን ቀሪዎቹ ለመተንፈስ ተቸግረው ታይተዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ሲያስመልሳቸው ነበር፡፡ ተከሳሹ አሁን በግማሽ ሚሊዮን ዶላር ዋስ የተለቀቀ ሲሆን ባፈለው ወር ነበር በቁጥጥር ሥር የዋለው፡፡አቃቢ ሕግ በሰውየው ላይ 8 ክሶችን አቅርቦበታል፡፡ ከጎዳና ተዳዳሪዎቹ አንዱ ሽማግሌ ሲሆኑ ትንንሽ ልጆችም ይገኙበታል፡፡ ይህም ክሱን ያጠናክርበታል፡፡ ባለፈው ዓመት አንድ ስፔናዊ የዩቲዩብ አሰናጅ በተመሳሳይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን አትታሎ ኦሪዮ ብስኩት እያስበላ ቀርጻ ሲያደርግ ነበር፡፡ ብስኩቱ ተለውሶ የነበረው ደግሞ በጥርስ ሳሙና ፈሳሽ ነበር፡፡ይህ ሰው 15 ወራት ተፈርዶበት ዘብጥያ ወርዷል፡፡
news-46176341
https://www.bbc.com/amharic/news-46176341
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያገረሸው የኢቦላ ወረርሽኝ በታሪኳ ታይቶ አይታወቅም
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በቅርቡ ያገረሸው ኢቦላ ወረርሽኝ በአገሪቷ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና አሰከፊ ነው ሲሉ የአገሪቷ ጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታውቀዋል።
የህክምና ባለሙያዎች የኢቦላ ሥርጭትን ለመግታት ክትባት እየሰጡ ነው። ከባለፉት አራት ወራት ጀምሮ ቢያንስ 200 ሰዎች በወረርሽኙ ሕይወታቸው ሲያልፍ ወደ 300 የሚሆኑ የተጠረጠሩ ህመምተኞች ተገኝተዋል። ወረርሽኙን ለመግታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረገ ሲሆን እስካሁን 25 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች ክትባት ተሰጥቷል። ይሁን እንጂ የአገሪቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና የጤና ባለሙያዎች ላይ በተለያየ ጊዜ ጥቃት በመድረሱ ለዓመታት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ተፈታትኖታል። • ኢቦላ በኮንጎ እየተዛመተ ነው • ኢቦላ ለምን አገረሸ? • "ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ የጤና ጥበቃው ሚንስትር ኦሊ ኢሉንጋ በዚህ ሰዓት 319 በበሽታው የተያዙና 198 ሞት መመዝገቡን ገልፀዋል። "ቤተሰቦቻቸውን ላጡ፣ ያለ አሳዳጊ ለቀሩ ሕፃናትና ለተበተኑ የቤተሰብ አባላት የተሰማኝን ሀዘን እገልፃለሁ ፤ መፅናናትን እመኛለሁ፤ በፀሎትም አስባቸዋለሁ" ሲሉም ተናግረዋል። ባለስልጣኑ እንደተናገሩት ግማሽ ያህሉ ተጎጂዎች 800 ሺህ ህዝብ ከሚኖርባት የሰሜናዊ ኪቩ ግዛት ቤኒ ነዋሪዎች ናቸው። አገሪቱ በአውሮፓውያኑ 1976 ካጋጠማት ስሙ በውል ካልታወቀው ወረርሽኝ በኋላ የአሁኑ በጣም አሰቃቂውና አስፈሪው ነው። ኢቦላ ከሰውነት ከሚወጣ ፈሻሽ እና ሌሎች ኢንፌክሽኖች አማካኝነት ይተላለፋል፤ ምልክቱም ጉንፋን መሳይ ህመም፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ፣ ውስጣዊና ውጫዊ መድማት ናቸው።
news-56318086
https://www.bbc.com/amharic/news-56318086
ትግራይ፡ በእስር ላይ የሚገኙት የህወሓት አመራር አባላት 'ክሳችን ፖለቲካዊ ነው' ማለታቸው ተነገረ
አዲስ አበባ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙት የቀደወሞው ህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የቀረበባቸው ክስ ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናገሩ።
እስረኞቹ ይህንን የተናገሩት ስለእስር አያያዛቸው ሁኔታ ለመመልከት ለጎበኟቸው ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ለዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እና ለኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች ነው። ኮሚሽኑ ባለፈው ቅዳሜ የካቲት 27/2013 ዓ.ም የጎበኟቸው አብረሀም ተከስተ (ዶ/ር)፣ አምባሳደር አባይ ወልዱ፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አምባሳደር አባዲ ዘሙ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር)፣ አዲስ ዓለም ባሌማ (ዶ/ር)፣ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋን ጨምሮ 21 እስረኞችን ነው። ከታሰሩት ግለሰቦችና ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን የገለጸው ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ላይ "አብዛኞቹ ታሳሪዎች የቀረበባቸው ክስ ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ፣ የተጠረጠሩበት ጉዳይ በተናጠል አለመቅረቡና የምርመራ ሂደቱ በአፋጣኝ አለመታየቱን ገልጸው አቤቱታ አቅርበዋል" ብሏል። ኮሚሽኑ እንዳለው ታሳሪዎቹ በጥሩ አካላዊ ደኅንነት የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት አጠቃላይ ሁኔታ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ተመልክቶ፤ የተጠቀሱት ታሳሪዎች ወደ ፌዴራል ፖሊስ እስር ቤት ከመጡ ወዲህ "ተገቢ ያልሆነ የእስር አያያዝ አለመኖሩንና ፖሊሶች በተገቢው የሙያ ሥነ ምግባር የሚሰሩ መሆኑን" ገልጸዋል ብሏል። በተጨማሪም የህክምና አገልግሎት ባለው አቅም እያገኙ እንደሆነ፣ ከቤተሰባቸው ጋር ተገናኝተው አቅርቦት እንደሚቀበሉና ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት መቻላቸውን እንደተናገሩ ኮሚሽኑ በመግለጫው ላይ አመልክቷል። ታሳሪዎቹ ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ከጠበቆች ጋር የሚገናኙበት ጊዜ ማጠሩን እንዳነሱና የተወሰኑ ታሳሪዎች የራሳቸውና የቤተሰቦቻቸው የባንክ ሒሳብ በመታገዱ ቤተሰቦቻቸው መቸገራቸውን እንደተናገሩ ገልጸዋል ብሏል። አስረኞቹ አሁን ካሉበት ሁኔታ ባሻገር ገጠሙን በሚሏቸው ጉዳዮች ላይ ቅሬታቸውንም ለኮሚሽኑ አባለት መግለጻቸውን አመልክቷል። ከዚህም ውስጥ "ከተያዙ በኋላ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸውን፣ በትግራይ ክልል ከመቀለ ከተማ ሸሽተው ሲሄዱ በተያዙበት ጊዜ ስድብ፣ ድብደባ፣ ማስፈራራትና ተኩስ እንደነበረ እንዲሁም የአካል መቁሰል እንደደረሰባቸው" ገልጸዋል ብሏል። በተጨማሪም ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ "ነፃ ሆኖ የመገመት መብታቸውን በሚጋፋ መልኩ በሚዲያ አሰልፎ የማቅረብና የማንኳሰስ ሁኔታ እንደነበረ" በማንሳት ቅሬታቸውን ያቀረቡ እስረኞች እንደነበሩ ኢሰመኮ ገልጿል። ኮሚሽኑ ታሳሪዎቹ አሁን በእስር የተያዙበት ሁኔታ በተገቢው ደረጃ መሆኑን ማረጋገጡንና በታሳሪዎች የተነሱ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከእስር ቤቱ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አመልክቷል። የቀድሞ የህወሓት አመራሮች አዲስ አበባ ውስጥ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በሚገኘው እስር ቤት ያሉበትን ሁኔታ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ከተመለከቱ በኋላ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሚደረገውን "ምርመራ በተቻለ ፍጥነት በማጠናቀቅ፤ የሕግ አግባብ በሚፈቅደው መልኩ በዋስትና ሊለቀቁ የሚገባቸውን ታሳሪዎች መለየት አስፈላጊ ነው" በማለት ማሳሰባቸው ተገልጿል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ተቀስቅሶ ክልሉን ይመራ የነበረው ህወሓት ከሥልጣን መወገዱ ይታወሳል። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ አድርገው ነበር። ለእስር ማዘዣውም ዋነኛ ምክንያቶቹ ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው መሆኑ መገለጹ ይታወሳል።
52627587
https://www.bbc.com/amharic/52627587
ኮሮናቫይረስ፡ በሊባኖስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ችግር ውስጥ ናቸው- የኢትዮጵያ ቆንስላ
በሊባኖስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። የተጣለው የሰዓት እላፊ ከነገ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን እስከ ሰኞ ማለዳ ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ከዚህ ቀደም የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ከተነሳ በኋላ ለአንድ ወር ያህል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ዜጎች " ቤታቸው መቀመጥ አለባቸው አስቸኳይ ጉዳይ ካልገጠማቸው በስተቀር ወደ የትም መሄድ የለባቸውም" ያሉት የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ማናል አብደል ሳማድ ናቸው። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ከሆነ በአገሪቱ 870 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህም መካከል 26 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። የኛ ሰው በሊባኖስ በሊባኖስ በርካታ ኢትዮጵያውያን በዝቅተኛ ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያኖች ይናገራሉ። ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁን በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን "ችግራችን የጀመረው ባለፈው ጥቅምት ወር የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት በተጎዳበትና የዶላር መወደድ ሲጀምር ነው" ብለውናል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየሰዉ ቤት ተቀጥረው የሚሰሩ የተባረሩበት፣ ደሞዛቸውን በግማሽ ቀንሰው መስራት የጀመሩበት እስካሁን ድረስም ሳይከፈላቸው የሚሰሩ መኖራቸውን ይገልፃሉ። "ያለ ክፍያ ለመስራት የመረጡት ቢያንስ የተገኘውን እየበሉ በሕይወት መቆየት ይሻላል ያሉ ናቸው" በማለትም ይህንን ተቋቁመን አልፈነው ነበር ብለዋል። የዓለምን ሕዝብ ያስጨነቀው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት "ሕይወታችንን ከድጡ ወደ ማጡ ከቶብናል" የሚሉት ኢትዮጵውያኑ፣ ልጅ ኣላቸው ልጃቸውን መመገብ፣ ቤት ኪራይ መክፈል ፈተና እነደሆነባቸው ይገልፃሉ። ሊባኖስ የኮሮናቫይረስን ወረርሽኝ ስርጭት ለመከላከል ጥላው የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ ማንሳቷን ተከትሎ ያገኙትን ሰርቶ ለማደር ተስፋ ሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም ዳግም በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን ተከትሎ መንግሥት ለተከታታይ አምስት ቀናት ከቤት መውጣትም መከልከሉን በመናገሩ ሌላ ስጋት እንደተደቀነባቸው ለቢቢሲ ያስረዳሉ። እገዳው ለአምስት ቀናት የተጣለ ሲሆን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ እስከ ሰኞ ማለዳ ድረስ የሚቆይ ነው በማለትም "ሳይሰራ እንዴት ቤት ኪራይ ይከፈላል?" ሲሉ ይጠይቃሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ዲያብ ፣ ባለፉት አራት ቀናት ብቻ 100 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልፀው ነው የአምስት ቀኑ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን የተናገሩት። መንግሥት አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ላይ ያወጣውን መመሪያ ተግባራዊ የማያደርጉ ሰዎችንም " ግዴለሽና ሃላፊነት የጎደላቸው" በማለት ወርፈዋቸዋል። በሊባኖስ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ ከተነሳ በኋላ የአካላዊ ርቀት መጠበቅ ተግባራዊ እንዲሆን በማሳሰብ ሱቆችና የአምልኮ ስፍራዎች ተከፍተዋል። ይህ የሆነው ከሁለት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል። በቫይረሱ የተያዙ አዳዲስ ሰዎች የተገኙት በአብዛኛው ከአገር ውጪ የነበሩ ሊባኖሳውያን በመመለሳቸው መሆኑ ተገልጿል። ከአምስት ቀናት በፊት ከናይጄሪያ፣ ሌጎስ የመጡ ሁሉም ተሳፋሪዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የአገሪቱ ጤና ሚኒስትር አስታውቆ ነበር። የእንቅስቃሴ ገደቡ ከተነሳ በኋላ ዜጎች በመገበያያ ስፍራዎች አካላዊ ርቀታቸውን ሳይጠብቁ ሲገበያዩ የታዩ ሲሆን፣ በአውራ ጎዳናዎችም ላይ ከተጠበቀው በላይ በርካታ ሰዎች ወጥተዋል። በሊባኖስ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ እየወደቀ የነበረው የአገሪቱ ምጣኔ ሃብትን ይበልጥ አባብሶታል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ቢቢሲ ያነጋገራትና ሊባኖስ ውስጥ ለ12 ዓመታት መኖሯን የምትናገረው ኢትዮጵያዊት በበኩሏ "እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ ፓስፖርትም ሆነ የመኖሪያ ፈቃድ የለንም" ስትል የስጋታቸውን መደራረብ ታስረዳለች። ከዚህ በፊትም ቢሆን የተለያዩ ችግሮችን አልፌያለሁ ያለችን ይህች ሴት የአሁኑ ግን ከምንጊዜውነም የከፋ ነው ትላለች። የኮሮናቫይረስ ከመከሰቱ በፊት ጀምሮ በሰዓት የሚከፈላት በግማሽ ተቀንሶ እየሰራች እንደነበር የተናገረችው ይህች ስደተኛ፣ የኮሮናቫይረስ ከመጣ በኋላም እጅጉን መታመሟን ታስታውሳለች። "ምናልባትም ኮሮና ይሆናል፤ እንደ ጉንፋን ያለ ነው" ትላለች በወቅቱ የነበራትን ሕመም ስታስታውስ። ለመመርመርም ሆነ ወደ ሆስፒታል ለመሄድና አገልግሎት ለማግኘት ፓስፖርትና የመኖሪያ ፈቃድ እንደምትጠየቅ በዚህም የተነሳ መታከም እንዳልቻለች ገልፃለች። ለተከታታይ 11 ቀናት ሳል እንደነበራት የምትናገረው ይህች በሊባኖስ የምትገኝ ስደተኛ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ ስምንት ልጆች ሆነው እንደሚኖሩና እርሷ በቫይረሱ ብትያዝ ወደ ሌሎቹ የመተላለፍ እድሉ ሰፊ እንደነበር ታስረዳለች። "እኔ ብቻ ሳልሆን ሌሎችም ኢትዮጵያኖች አሉ ለአራትና ለአምስት በአንድ ክፍል የሚኖሩ" በማለትም ሕገወጥ ሆነው ሲኖሩ ኣለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጫና ታስረዳለች። ታምማ በነበረበት ሰዓት ከስራዋ ገበታ መቅረቷን የምታስታውሰው ይህች ሴት፣ እርሷና ጓደኞቿ ሕገወጥ ሆነው በመስራታቸው ለተለያዩ ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸውን ትናገራለች። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ሥራ በመፍታታቸው ያላቸውን እየተጠቀሙ፣ መስራት ባለመቻላቸው የቤት ኪራይ የሚከፍሉት እንደሚቸግራቸው ወደ ጎዳና እንወጣለን የሚል ስጋት እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ልጅ ያላቸው ሴቶች መኖራቸውን በመጥቀስም ያለስራ፣ የቤት ኪራይ ሳይከፍሉ መኖር ሕይወታቸውን ማክበዱንና ነገን በተስፋ ለማየት መቸገራቸውን ይገልፃሉ። በሊባኖስ ቤሩት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ የሚናገሩት እነዚህ ስደተኞች በእስር ቤት፣ በሆስፒታል፣ ሞተው አስከሬናቸው ማቆያ ውስጥ ያለ በርካቶች መኖራቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ኢትዮጵያውያን የሊባኖስ የምጣኔ ሃብት ሁኔታ ወድቋል፣ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ ሕገወጥ ሆኖ ለመስራትም ስላላስቻለ ወደ አገራችን ብንመለስ ፈቃደኛ ነን ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቆንስላ ምን ይላል? በቤሩት ሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ቆንስል የሆኑት አቶ አክሊሉ ታጠረ ውቤ ለቢቢሲ እንደገለፁት በቤይሩት ሊባኖስ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከአራት መቶ ሺህ በላይ ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ "በሕገወጥ መልኩ" እንደሚኖሩ ተናግረዋል። በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አብዛኞቹ በሕጋዊ መንገድ ከመጡ በኋላ ከአሠሪዎቻቸው ጋር በተለያየ መንገድ ሳይግባቡ ሲቀሩ በመውጣት ቤት ተከራይተው "በሕገወጥ መልኩ" እንደሚኖሩ ይናገራሉ። ከእነዚህ መካከል ሰማንያ በመቶ ያህሉ ሕጋዊ ፓስፖርት፣ የመኖሪያም ሆነ የሥራ ፈቃድ የሌላቸው መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ ሊሆን የቻለው ከአሰሪዎቻቸው ጋር ሲጋጩ እዚያው ጥለው በመውጣታቸው መሆኑን ያስረዳሉ። በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያነሷቸው ችግሮች እውነት መሆናቸውን የተናገሩት አቶ አከሊሉ ኤምባሲው በተለያዩ ማህበረሰብ ቡድኖችና በኃይማኖት ተቋማት በኩል ስለወረርሽኙ ግንዛቤ ለመፍጠር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አክለውም ዜጎች ችግር ላይ እንዳይወድቁና እርስ በእርሳቸው እንዲረዳዱ ድጋፍ የመስጠት ሥራ መስራታቸውን ይገልፃሉ። በተጨማሪም ወደ አገር ቤት መመለስ ያለባቸው እስር ቤት፣ በተለያዩ መጠለያዎች ውስጥ የነበሩት ከአሁን በፊት ተመዝግበው የነበሩ 905 ዜጎችን ከሊባኖስ ለማስወጣት ከመንግሥት ጋር የመነጋገር፣ በረራ እና ለይቶ ማቆያ የማዘጋጀት ሥራዎች እየሰሩ መሆናቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ነገር ግን ይላሉ አቶ አክሊሉ "ከእነዚህ መካከል ስማቸው ተላልፎ የጉዞ ሰነድ ተዘጋጅቶ፣ ፎቶ ኑና ተነሱ ሲባል፣ 54 ሰዎች ስራ አግኝተናል መሄድ አንፈልግም በማለት የመጣውን እድል ሌሎች እንዳይጠቀሙበትም አስቀርተዋል።" ብለዋል ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ የሚገጥማቸውን የምግብ ችግር፣ የቤት ኪራይ መክፈል አለመቻልን በተመለከተ የተለያዩ ኃይማኖት ማህበራትና ተወካዮች የሚሰሩትን ስራ እንደሚደግፉ ገልፀዋል። ኤምባሲው የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ሳያሳድሱ ቀርተው ቅጣት ለሚጠብቃቸው ዜጎች ከሊባኖስ መንግሥት ጋር ተነጋግሮ ምንም ያህል ዓመት ሳያሳድሱ ቢቆዩ የአንድ አመት ብቻ እንዲከፍሉ ስምምነት ላይ መደረሱንም አክለው ተናግረዋል። አሁን ደግሞ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ይህ የቅጣት ክፍያ እንዲቀ ርእየተነጋገሩ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። በቫይረሱ የሚያዙ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩ ቀይ መስቀልና የአገሪቱ መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ እንደሚያሳክም የገለፁት አቶ አክሊሉ፣ ምንም ዓይነት ሰነድ ለሌላቸውና የተለያዩ የጤና ችግር ለሚገጥማቸውም ኤምባሲው ደብዳቤ እንደሚጽፍላቸውና በዚያ መታከም እንደሚችሉ ጨምረው አስረድተዋል። በሊባኖስ እስካሁን ድረስ በኮሮናቫይረስ የታመመ አንድም ኢትዮጵያዊ አለመኖሩን አቶ አክሊሉ ጨምረው ተናግረዋል።
news-56674360
https://www.bbc.com/amharic/news-56674360
ትግራይ፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ትግራይ ውስጥ ግድያ ፈጽሟል መባሉን ሐሰት ነው አለ
በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተፈጸሙ የተባሉት የመብት ጥሰቶች ሐሰት ናቸው ሲል ሠራዊቱ ምላሽ ሰጠ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት "ትግራይ ውስጥ ሠራዊቱ ንጹሃንን ፈጅቷል በሚል የሚናፈሰው ሐሰተኛ ወሬ በህወሓት ተላላኪዎች የተቀነባበረ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ጨምረውም የመከላከያ ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ "የህወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መደመሰሱን" ተናግረው፤ ይሁን እንጂ የቀሩ የቡድኑ አንዳንድ አባላት "የሸፍታነትን ባህሪ ተላበሰው፤ አካባቢዎች በአሳቻ ስፍራ ላይ በሕዝቡ ላይ ዘረፋ፣ እንግልትና ግድያ እየፈፀሙ ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ እነዚህ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎችን በመጨፍጨፍ አገርና ሕዝብን ድርጊቱ በመከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈፀመ ለማስመሰል የተለያዩ ተግባራትን እየፈጸሙ ነው ብለዋል። የቢቢሲ 'አፍሪካ አይ' ፕሮግራም ባደረገው ምርመራ በትግራይ ውስጥ ማኅበረ ዴጎ በሚባል ስፍራ በኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ጭፍጨፋ መፈጸሙን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች ማግኘቱን ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ቢያንስ 15 ወንዶች የተገደሉበትን ትክክለኛውን ቦታ ለመለየት ችሏል። የታጠቁና የወታደር የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች ያልታጠቁ ወንዶችን ከአንድ የገደል አፋፍ ላይ በመውሰድ አንዳንዶቹን ላይ በቅርብ ርቀት በመተኮስ አስከሬኖችን ወደ ገደል ገፍተው ሲጨምሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መውጣቱን ተከትሎ ነበር 'አፍሪካ አይ' ምርመራውን ያደረገው። ቢቢሲ ይህ ድርጊት የተፈጸመው የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት ኃይሎችን እየተዋጋ ባለበት ትግራይ ክልል ውስጥ ማኅበረ ዴጎ ከተባለች ከተማ አቅራቢያ መሆኑን አረጋግጧል። በወቅቱ ቢቢሲ ያገኛቸውን ማስረጃዎች ለኢትዮጵያ መንግሥት በማቅረብ ምላሽ የጠየቀ ሲሆን መንግሥት "በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የወጡ ነገሮችና ክሶች እንደ ማስረጃ ሊወሰዱ አይችሉም" በማለት "ገለልተኛ ምርመራዎችን ለማካሄድ የትግራይ ክልል ክፍት ነው" ሲል መልስ ሰጥቶ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፌደራል ፖሊስ፣ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምርመራ ለማድረግ ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ገልፆ መግለጫ አውጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው እንደተናገሩት፣ ትግራይ ውስጥ በኢትዮጵያ ሠራዊት ተፈጸሙ ስለተባሉት ጥፋቶች አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች በሕግ እንደሚጠየቁ መናገራቸው ይታወሳል። ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ምን አለ? ረቡዕ ዕለት በተሰጠው መግለጫ ህወሓት ግድያዎቹን በመፈፀም፣ የቪዲዮ ምስል በማቀናበር የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት የፈፀመው አስመስለው በማሰራጨት ስም ለማጥፋት እንደሞከሩ ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተናግረዋል። በተጨማሪም የመከላከያ የሚዲያ ሥራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ብርጋዲየር ጀነራል ኩማ ሚደክሳ በቪዲዮው ላይ ዝርዝር ማብራሪያን ሰጥተዋል። በዚህም መሠረት በቪዲዮው ላይ የሚታዩት የሠራዊቱን የደንብ ልብስ ቢለብሱም አባላት እንዳልሆኑ ገልጸው፤ የደንብ ልብሱ በህወሓት ኃይሎች መዘረፉን ተናግረዋል። ለዚህም ለሠራዊቱ የሚሰጠው ልብስ ለእያንዳንዱ በልኩ የቀረበ ሲሆን በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ግን ከልካቸው በላይ የሆነ የደንብ ልብስ በመልበሳቸው እጃቸው ላይ እንደሚያስታውቅ እንዲሁም በወገብ ላይ የያዙት ትጥቅ የሠራዊቱ አባላት እንዳልሆነ ተናግረዋል። ዳይሬክተሩ "ቪዲዮው ሦስት የተለያዩ ምስሎችንና ቦታዎችን በማቀናበር የቀረበ ሐሰተኛ ምሰል ነው" በማለት ቪዲዮዎቹ በካሜራና በሞባይል ተቀርጾ የተለያዩ ቦታዎችን እንደሚያመለክት ገልጸዋል። የመጀመሪያው ቪዲዮ በካሜራ የተቀረጸ ሲሆን የሚታየው ስፍራ ከሁለተኛው ቪዲዮ የተለየ ነው በማለት ልዩነቱ ሜዳማና ገደላማ መሆናቸውን ጠቁመው ሦስተኛው ቪዲዮ አስከሬን የሚታይበት እንደሆነና ይህ ቪዲዮ በሞባይል የተቀረጸ መሆኑን ገልጸዋል። ብርጋዲየር ጀነራል ኩማ በቪዲዮዎቹ ላይ የሚታዩ ዝርዝሮችን በማንሳት የተሰራጩት ምስሎት በተለያዩ መሳሪያዎችና ቦታዎች ሆን ተብለው ተዘጋጅተው የተቀረጹና ሐሰተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ጨምረውም የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ጥብቅ የዕዝ ሰንሰለት ያለውና ቁጥጥር የሚደረግበት በመሆኑ እያንዳንዱ ክስተት ስለሚታወቅ እንዲህ አይነቱን ወንጀል አይፈጽምም ሲሉ አስተባብለዋል። ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማም እነዚህ የተቀናበሩ ቪዲዮዎች "በህወሓት ተላላኪዎች በውሸት ተቀናብሮ ሕዝብን ለማደናገር የተሰሩ ናቸው" በማለት ሠራዊቱ ድርጊቱን እንዳልፈጸመ ተናግረዋል። አክለውም የአገር መከላከያ ሠራዊት በሥነ ምግባር የተገነባ ሕዝባዊ መሰረት ያለው በመሆኑ እንዲህ አይነቱን ሕዝብን የሚጎዳ ተግባር አይፈጽምም ብለዋል። ትግራይ ውስጥ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በመንግሥት ጦር ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ ነበር። በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሃዙ በበርካታ ሺዎች ሊሆን እንደሚችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገርም በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች ግድያዎች፣ ጾታዊ ጥቃቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ዘረፋና የንብረት ውድመቶች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ አመልከተዋል። በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ከቪዲዮዎቹ ከአንዱ ላይ የተወሰደ ምስል
news-52211338
https://www.bbc.com/amharic/news-52211338
ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካዋ ግዛት ዊስኮንሰን አስገዳጁን ቤት የመቀመጥ ሕግ ተላልፋ ምርጫ አካሄደች
በኮሮናቫይረስ በርካታ ዜጎቿን እያጣች ባለችው አሜሪካ በበርካታ ግዛቶች ቤት የመቀመጥ አስገዳጅ ሕግ ቢወሰንም የዊስኮንሰን ግዛት ይህንን ተላልፋ በትናንትናው እለት ምርጫ አካሂዳለች።
ጥቂት ቁጥር ባላቸው የምርጫ ጣቢያዎችም በርካታ ሰዎች ተሰልፈው ታይተዋል። የምርጫ ጣቢያ ሰራተኞችም ኦክስጅን መተላለፊያ ያለው ከእግር እስከ ጭንቅላት የሚሸፍን አልባሳት ለብሰው ታይተዋል። የዊስኮንሰን አስተዳዳሪ ምርጫውን ወደ ሰኔ ለማስተላለፍ አቅደው የነበረ ቢሆንም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን ውሳኔ ሽሮ ምርጫው መካሄድ አለበት ብሏል። •በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው •"ከቤት አትውጡ የሚሉን ልጆቼን ምን እንዳበላቸው ነው?" ቀጣዩ የዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለመወዳዳር እየተፋለሙ ያሉት ጆ ባይደንና በርኒ ሳንደርስን አሸናፊ ለመለየት ከተደረጉ የመጀመሪያ ዙር ምርጫዎችም አንዱ ነው። የዚህ ምርጫ አሸናፊም በፈረንጆቹ ህዳር ለተያዘው ምርጫ ከሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የሚወዳደር ይሆናል። የአካባቢው ምርጫ አስፈፃሚዎችም በምርጫው ወቅት እንዲሁም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ ተገኝተዋል። •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች •በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ለመለየት ክትትል እየተደረገ ነው አሜሪካ ለሦስት ሳምንታት ያህል ቤት መቀመጥ እንዲሁም እንቅስቃሴ የሚገድብ መመሪያ ብታወጣም ዊስኮንሰን ይህንን ሕግ ተላልፋ ምርጫ ስታካሂድ የመጀመሪያዋ ግዛት ሆናለች። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በመጠቃት አለምን እየመራች ባለችው አሜሪካ አራት መቶ ሺህ የሚጠጋ ሰው በቫይረሱ ተይዟል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። አገሪቷ እንዲህ ባለ የጤና ቀውስ ባለችበት ሰዓት ምርጫ መካሄዱ ተተችቷል። ሌሎች ግዛቶች ምርጫውን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝመውታል። እስካሁን ባለው መረጃ በዊስኮንሰን ግዛት 2 ሺህ 500 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 92 ግለሰቦች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።
news-51016945
https://www.bbc.com/amharic/news-51016945
በጀነራል ሶሌይማኒ ቀብር ላይ ከ35 በላይ ሰዎች ተረጋግጠው ሞቱ
በጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ በተፈጠረ መረጋገጥ ቢያንስ 35 ሰዎች መሞታቸውን የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።
እንደ መገናኛ ብዙሃኑ ዘገባ ከሆነ፤ ተጨማሪ 48 ሰዎች በጀነራሉ የትውልድ ከተማ ኬርማን ተረጋግጠው ጉዳት ደርሶባቸዋል። በፕሬዝደንት ትራምፕ ትዕዛዝ የተገደሉት ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ በትውልድ ከተማቸው ግብዓተ መሬታቸው እየተፈጸመ ይገኛል። በኢራቅ ባግዳድ ባሳለፍነው ዓርብ የተገደሉት ጀነራሉ፤ አስክሬናቸው ከኢራቅ ወደ ኢራን ሲጓዝ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራቃውያን አደባባይ ወጥተው ሸኝተዋል። ኢራቃዊያን የጀነራሉን አስክሬን ሲሸኙ ''ሞት ለአሜሪካ'' ሲሉ ተደምጠዋል። ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ። ፕሬዝደንት ትራምፕ ጀነራሉ መገደላቸው ከተሰማ በኋላ ''የሶሌይማኒ የዓመታት የሽብር አገዛዝ አብቅቶለታል" ብለዋል። "ሱሊማኒ በማንኛውም ሰዓት ሊቃጣ የሚችል የሽብር ሴራ በአሜሪካ ዲፕሎማቶች እና የጦር መኮንኖች ላይ ሲያሴር ነበር። ይህንን ሲፈጽም ያዝነው፤ አስወገድነው" ሲሉም ተደምጠዋል። በተያያዘ ዜና ቃሲም ሱሊማኒ ማን ነበሩ? ከእ.አ.አ. 1998 ጀምሮ ሜጀር ጀነራል ሱሊማኒ የኢራን ኩድስ ኃይልን ሲመሩ ቆይተዋል። ይህ ኃይል ከሃገር ውጪ የሚፈጸሙ ሚስጥራዊ ኦፕሬሽኖችን የሚያከናውን ነው። ጀነራሉ በኢራቅ ውስጥ አይኤስ እና አል-ቃይዳን በመዋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ ነበራቸው። ከዚህ በተጨማሪም፤ እኚህ የሽብር ቡድኖች እግራቸውን በኢራን እንዳይተክሉ ተከታትለው ድባቅ የመቷቸው ጀነራል ሱሊማኒ ነበሩ ተብሏል። ጀነራሉ የሚመሩት ኃይል በሶሪያ ግጭት ውስጥ ተሳትፎ እንዳለው አምኗል። ለፕሬዝደንት በሽር አል-አሳድ ታማኝ ለሆኑ ወታደሮች የጦር ምክር ይሰጣል። እንዲሁም ለባሽር አል-አሳድ ታማኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሺያ ሙስሊሞችን አስታጥቋል። በኢራቅ ደግሞ አይኤስን እየታገሉ ለሚገኙ ለሺያ ሙስሊም ሚሊሻዎች ድጋፍ ያደርጋል። በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የተከሰቱት ግጭቶች ጀነራሉ ኢራን ውስጥ እጅግ ዝነኛ ሰው እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ጀነራል ሱሊማኒ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት የኢራን ከፍተኛ የጦር ሽልማት ተቀብለዋል። አሜሪካ በበኩሏ ጀነራሉ የሚመሩት የኩድስ ኃይል በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ አሜሪካን በጠላትነት በመፈረጅ በሽብር መናጥ ለሚፈልጉ ኃይሎች ፈንድ፣ ሥልጠና እና የጦር መሳሪያን ጨምሮ የቁስ ድጋፍ ያደርጋል ስትል ትወነጅላለች። አሜሪካ እንደምትለው ከሆነ ይህ የኩድስ ኃይል ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ኃይሎች መካከል፤ የሌባኖሱ ሄዝቦላ እንዲሁም የፍልስጤሙ እስላማዊ ጅሃድ ተጠቃሽ ናቸው። የቀድሞ የሲአይኤ አለቃ የአሁኑ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ የኢራንን አብዮታዊ ጥበቃ እና ኩድስ ኃይሉን "የሽብር ቡድን" ሲሉ ከወራት በፊት ፈርጀውት ነበር።
news-56391279
https://www.bbc.com/amharic/news-56391279
ተቃዋሚዎች የአርጀንቲናው ፕሬዝደንት ያሉበትን መኪና መስታወት ሰባበሩ
በርካታ ተቃዋሚዎች የአርጀንቲው ፕሬዝደንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝን የያዘችውን መኪና ማጥቃታቸው ተሰማ።
ይህ የሆነው ፓታጎኒያ በተሰኘችው ግዛት ሲሆን ፕሬዝደንቱ 'ሚኒባስ' ውስጥ ነበሩ ተብሏል። በደቡባዊቷ የአርጀንቲና ክፍለ ግዛት ቹቡት በሚገኝ አንድ የሕብረተሰብ ማዕከል ውስጥ የነበሩት ፕሬዝደንቱ በተቃዋሚዎች ተከበው ድንጋይ ተወርውሮባቸዋል። ተቀዋሚዎቹ የፕሬዝደንቱ መኪና በመክበብ ተሽከርካሪዋ ላይ ጉዳት አድርሰዋል። ፕሬዝደንቱ ወደ ሥፍራው ያቀኑት በአካባቢው የተነሳውን ሰደድ እሣት ተከትሎ አንድ ሰው መሞቱን በርካቶች መጎዳታቸውን በማስመልከት ነው። ነገር ግን ተቃውሞው በቹቡት ግዛት ሊካሄድ ነው የተባለውን የማዕድን ቁፋሮ የተመለከተ ነው። ተቃዋሚዎቹ መንግሥት ለትላልቅ ማዕድን ቆፋሪ ድርጅቶች ፈቃድ ለመስጠት ረቂቅ ማውጣቱን በመቃወም ድምፃቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። አካባቢው ወርቅ፣ ብርና ዩራኒየምን በመሳሰሉ ማዕድናት የበለፀገ ነው ሲል ክላሪን ጋዜጣ ዘግቧል። በሥፍራው የነበረውን ግርግር የሚያሳዩ ተንቃሳቃሽ ምስሎች ላይ ፕሬዝደንቱ ከማሕበረሰብ ማዕከሉ ወጥተው ወደ መኪናቸው ሲሄዱ ተቃዋሚዎች የማዕከሉ በር ላይ ተኮልኩለው ይታያሉ። ከዚያ ተቃዋሚዎቹ ፕሬዝደንቱን ተከትለው የተሳፉበትን ሚኒባስ ሲደበድቡና እንዳይንቀሳቀስ ሲያግዱት ተስተውሏል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች የመኪናዋ መስታወት ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ነበር። ምንም እንኳ ፕሬዝደንቱ የነበሩባት መኪና ሕዝቡን ተሻግራ ማለፈው ብትችልም በርካታ መስኮቶች ተሰባብረዋል። በአርጀንቲናዋ ፓታጎኒያ ግዛት የተነሳው ሰደድ እሣት በርካቶች ቀያቸውን ጥለው እንዲወጡ አስገድዷል። በሰደዱ እሣቱ ምክንያት እስካሁን ድረስ ቢያንስ 200 ቤቶች ተቃጥለዋል። የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸውና የውሃ አቅርቦት ማግኘት ያልቻሉ በርካቶች ናቸውም ተብሏል። ምንም እንኳ የሰደድ እሣቱ መንስዔ ባይታወቅም የሃገር ውስጥ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ይላል።
news-56276139
https://www.bbc.com/amharic/news-56276139
ትግራይ፡ የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ ግጭት ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል አለ
በትግራይ ግጭት የተሳተፉ አካላት "የጦር እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ፈጽመው ሊሆን እንደሚችል" የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባሽሌት ገለጹ።
ኮሚሽነሯ ዛሬ [ሐሙስ] ከትግራይ የሚወጡ ተያያዢነት ያላቸውና ተአማኒ ሪፖርቶች በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ የተለያዩ ወገኖች የተፈፀሙ ከባድ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊ እርዳታ ሕጎች ጥሰት ማመልከታቸውን ተናግረዋል። በዚህም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ተፈጸሙ የተባሉትንና እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ ሪፖርት የተደረጉ የጅምላ ግድያዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ወሲባዊ ጥቃቶችን ለመመርመር እንዲችል ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል። ሚሸል ባሽሌት የተፈፀሙት የመብት ጥሰቶች እንደ ጦር እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ሊቆጠሩ እንደሚችሉ ገልፀው በዚህም ውስጥ የተለያዩ አካላት ተሳታፊ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ጠቁመዋል። በተጠቀሱት ድርጊቶች ውስጥ ተሳትፎ ሊኖራቸው ይችላል ያሏቸውን አካላት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ህወሓት፣ የኤርትራ ወታደሮች፣ የአማራ ክልል ኃይሎችና ግንኙነት ያላቸው ታጣቂ ሚሊሻዎች ናቸው ብለዋል። "በግጭቱ ላይ በርካታ አካላት መሳተፋቸውን ጨምሮ፤ ጥሰቶቹን መካድ እንዲሁም ጣት መጠቆም ይታያል። የጥሰቶቹን ሪፖርት በተመለከተ ግልፅ፣ ነፃ የሆነ ግምገማና ምርመራ ያስፈልጋል። የጥቃቱ ሰለባና ተራፊዎች የእውነትና የፍትህ ጥያቄያቸው ሊካድ አይገባም" ብለዋል ኮሚሽነሯ። አክለውም "የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ቢሮና ሌሎች ነፃ መርማሪዎች ወደ ትግራይ ገብተው ያለውን ሁኔታ እንዲገመግሙና እንዲመረምሩ ፍቃድ እንዲሰጠን እንጠይቃለን። የትኛውም አካል ይፈፅመው እውነታው መታወቅ አለበት፤ ፈጻሚዎቹም ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል" በማለት ጥሪ አቅርበዋል። ኮሚሽነሯ ሚሸል ባሽሌት በአሁኑ ወቅት "የሚረብሹ" ያሏቸው የመደፈር፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ መጠነ ሰፊ የንብረት ውድመትና ዘረፋ መፈጸሙን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች እየደረሳቸው መሆኑን አስታውቀዋል። "በክልሉ ተዓማኒ የሚባሉ ዓለም አቀፉን የሰብዓዊ መብት የሚጥሱ ሪፖርቶች በግጭቱ ተሳታፊ በሆኑ አካላት በሙሉ መፈፀማቸውን የሚገልጽ መረጃ ደርሶናል" ብለዋል። አክለውም "ግልጽና ነፃ ምርመራ ካልተካሄደና ጥሰቱን የፈፀሙትን አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ካልተቻለ እነዚህ ጥቃቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ እፈራለሁ። ሁኔታውም ባልተረጋጋ መልኩ ለዓመታት ሊቀጥል ይችላል" ብለዋል። ኮሚሽነሯ ከአስተማማኝ ምንጭ ነው ያገኘሁት ባሉት መረጃ መሰረት በአዲግራት፣ በመቀለ፣ በሽረና በውቅሮ በተነሳው ተቃውሞ ስምንት ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል ብለዋል። በተጨማሪም በትግራይ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙት በመቀለ፣ በአይደር፣ በአዲግራትና በውቅሮ በአንድ ወር ብቻ 136 ወሲባዊ ጥቃቶች ሪፖርት መደረጋቸውን ገልፀው፣ ይህም ከዚህ በላይ በርካታ ጥቃቶች መድረሳቸውን ማሳያ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ እነዚህ ጥቃቶች መድረሳቸውን አረጋግጦ ምርመራ ከፍቻለሁ ማለቱ የሚታወስ ነው። በተጨማሪም በቅርቡ ሂውማን ራይትስ ዋች፣ በትግራይ ከተሞች በኅዳር ወር በዘፈቀደ የከባድ መሣሪያ ድብደባ ደርሷል ያለውን መረጃ እንዳገኙና ማረጋገጥ መቻላቸውን ጠቁመዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአክሱም፣ ደንገላትና በማዕከላዊ ትግራይ በኤርትራ ጦር የተፈፀሙ ግድያዎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም እንዲሁ ማረጋገጣቸውን አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በቅርቡ ታስረው የተፈቱትን የቢቢሲ ጋዜጠኛን ጨምሮ ሌሎች ዘጋቢዎችና ተርጓሚዎችን በተመለከተ ያላቸውን ስጋትም ገልጸዋል። ምንም እንኳን ጋዜጠኞቹ በአሁኑ ሰዓት ያለ ክስ ቢለቀቁም አንድ የመንግሥት ባለስልጣን "ዓለም አቀፉን ሚዲያ የሚያሳስቱ ግለሰቦችን ተጠያቂ ይሆናሉ" ማለታቸው እንዳሳሰባቸውም ገልፀዋል። "የሰብዓዊ መብት ጥቃት ሰለባዎችና የዓይን እማኞች ጉዳት ሊደርስብን ይችላል በሚል ፍራቻ ሊገደቡ አይገባም" ብለዋል ከፍተኛ ኮሚሽነሯ። ባሽሌት በዛሬው መግለጫቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊ ረድዔት ድርጅቶች የሰጠውን ፈቃድ እንዲሁም አንዳንድ እርምጃዎቹን በመልካም ጎን አነንስተዋል። በተጨማሪም ባለስልጣናቱ የገቡትን ቃል ወደ ተግባር እንዲለወጡ ጠይቀዋል። የእራሳቸው ቢሮም በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚደረጉ ምርመራዎችን ይደግፋል ብለዋል። በትናንትናው ዕለትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከትግራይ ክልል ግጭት ጋር በተያያዘ የተነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ግድያዎችን በተመለከተም መንግሥት ከፌደራል ፖሊስ፣ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመጣመር ይመረምራል ብለዋል። ጨምረውም የእነዚህን አካላት ምርመራ መሰረት በማድረግም መንግሥታቸው በድረጊቱ ውስጥ እጃቸው ያለበትን አካላት ወደ ፍትህ እንደሚያቀርብ አፅንኦት ሰጥተው፤ በምርመራው ላይ ተጨማሪ እርዳታ ካስፈለገ መንግሥት የውጭ አካል ሊጋብዝ እንደሚችል ጠቆም አድርገዋል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናትና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሚያደርጉት ምርመራ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም ሕዝብ በወቅቱ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ቃለ አቀባዩ ገልፀዋል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት በመፈፀሙ መንግሥት "ሕግ የማስከበር" ወታደራዊ ዘመቻን ማካሄዱን ገልጿል። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን ቢገልጽም በአንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች እንዳሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከፍተኛ ኮሚሽነሯም በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ትግራይ ጦርነቱ መቀጠሉንም መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።
news-56343932
https://www.bbc.com/amharic/news-56343932
ትግራይ፡ ከ130 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ገለጸ
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ባደረገው ቅኝት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከ131 ሺህ በላይ የተፈናቀሉ ሰዎች እንዳሉ አመለከተ።
ድርጅቱ እንዳለው ተፈናቃዮቹ በትግራይና ተጎራባች በሆኑት የአፋር እንዲሁም የአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 39 በሚሆኑ ተደራሽ ስፍራዎች ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። ይህ የተፈናቃዮች መረጃ የተሰበሰበው አዲስ በሆነው 'ዲስፕሌስመንት ትራኪን ማትሪከስ' በተባለ ዘዴ ሲሆን በዚህም የሕዝብ ቁጥርን በተመለከተ መረጃ በመሰብሰብና የሰዎችን ተጋላጭነት እንዲሁም የተፈናቃዮችን ፍላጎቶችን መሠረት በማድረግ መረጃን በመሰብሰብ የሚተነትን ነው። አይኦኤም እንዳለው በዚህ የቅኝት ተግባሩ 30,383 ተፈናቀሉ ቤተሰቦችን መለየት ችሏል። ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያ፣ ምግብና ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቶችን እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እናዳለው "ይህ መረጃ በተከሰተው ቀውስ ምክንያት የተፈናቀሉትን አጠቃላይ ሰዎች የሚያመለክት አይደለም። ከዚያ ይልቅ መረጃውን ለማሰባሰብ አመቺ በሆኑ ስፍራዎች በአገር ውስጥ የተፈናቀሉትን ሰዎች ብቻ የሚወክል ነው።" በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ የቀድሞው የክልሉ አስተዳዳሪ በነበረው በህወሓት ኃይሎች የተሰነዘረበትን ጥቃት ተከትሎ ወታደራዊ ግጭት መጀመሩ አይዘነጋም። በዚህም ሳቢያ ጦርነቱን በመሸሽ ከ60 ሺህ የሚልቁ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ሲሰደዱ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በእዚያው በክልሉ የተለያዩ ስፍራዎች እንደሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች አመልክተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በግጭቱ ሳቢያ የተፈናቀሉትን ለመርዳትና መልሶ ለማቋቋም ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ የሰብአዊ እርዳታዎችን እያቀረበ መሆኑን ገለጸ ሲሆን፤ ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት እርዳታ ለማቅረብ ፈቃድ አግኝተው ተሳትፎ እያደረጉ ነው።
news-51749412
https://www.bbc.com/amharic/news-51749412
የኦጋዴን ጦርነት፡ የሲያድ ባሬ ወረራ ሲታወስ
ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ - በወቅቱ ዕድሜው 20 ነበር። ካርሎስ ኦርላንዶ ጥር 1970 ዓ.ም. የሶማሊያ ወታደሮች እጅ ላይ ወደቀ።
ከቀኝ ወደግራ - መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ ፊደል ካስትሮ እና ራውል ካስትሮ የዓለም መገናኛ ብዙሃን በተሰበሰቡበት የኢትዮጵያንና ኩባን ወታደራዊ ምስጢር እንዲያወጣ ተደረገ። የኦጋዴን ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል የተደረገው ጦርነት የዛሬ 42 ዓመት የካቲት 26/1970 ዓ.ም. ነበር የተጠናቀቀው። በ1966 ዓ.ም ሶማሊያ የአረብ ሊግን ተቀላቀለች። በወቅቱ የሶማሊያ መሪ የነበረው ሜጀር ጄኔራል ሲያድ ባሬ ኢትዮጵያን ወረረ። ጦርነቱ የተጀመረ ሰሞን የሲያድ ባሬ [ዚያድ ባሬ] ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከዩናይትስ ስቴትስ ጋር ወዳጅነት አለው። በወቅቱ በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ የነበሩት ሶቪዬት ኅብረትና አሜሪካ ምሥራቅ አፍሪካ ገቡ። ፕሬዝደንት አብዲራሺድ አሊ ሸርማርኬን በመንፈቅለ-መንግሥት ፈንግሎ ሥልጣን የጨበጠው የዚያድ ባሬ መንግሥት ድንበር ማስፋፋት ዋነኛ ዓላማው አደረገ። ወሳኟ ቦታ ደግሞ - ኦጋዴን። ኦጋዴን ሠፍሮ የሽምቅ ውጊያ ያካሂድ የነበረው የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጭ ግንባር የኢትዮጵያ ጦር ላይ ጥቃት ሠነዘረ። የጦርነቱ መባቻ ተደርጎ የሚቆጠረውም ይህ ጥቃት ነበር። በመቀጠል የዚያድ ባሬ ጦር በሶቪዬት ኅብረት የጦር መሣሪያ ታግዞ ወደ አጋዴን ገሰገሰ። በወቅቱ ከንጉሡ አገዛዝ ወደ ወታደራዊው ደርግ የተሻጋገረችው ኢትዮጵያ በይፋ ራሷን ማርክሲስት ስትል አወጀች፤ ወዳጅነቷም ከሶቪዬት ኅብረት ጋር ሆነ። አሜሪካ ደግሞ ድጋፏን ለሶማሊያ አደረገች። ሁለቱ አገራት ወደ ቀለጠ ጦርነት ገቡ። በወቅቱ የሲያድ ባሬ መንግሥት ኩባውያን የኢትዮጵያውን ጦር ደግፈው እየተዋጉ ነው ሲል ወቀሰ። ይህንንም ለማሳመን ሲሉ የኩባ ወታደሮች መያዝ ጀመሩ። የዚያኔ ነው ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ ተይዞ ለጋዜጠኞች መግለጫ እንዲሰጥ የተገደደው። ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ [በስተቀኝ] የዚያድ ባሬ መንግሥት ወራራውን አጠናክሮ በጅግጅጋ በኩል ደንበር አልፎ ገብቶ ብዙ ጥፋት አደረሰ። የንፁሃን ዜጎች ሕይወት ተቀጠፈ። አልፎም ወደ ሐረር ገሰገሰ። ይሄኔ ነው የኢትዮጵያ ክተት የታወጀው። ሐረር ላይ 40 ሺህ ገደማ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ጠበቀው። ተጨማሪ 10 ሺህ የኩባ ጦረኞች ከኢትዮጵያ ጎን ነበሩ። የኢትዮጵያ ጦር የዚያድ ባሬን ጦር አሳዶ ከመሬቱ አስወጣ። የመጨረሻው ውጊያ የነበረው ካራማራ ላይ ነበር። በወቅቱ በዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታገዘው የኢትጵያ ጦር በሰማይ በምድር ጥቃቱን በማጠናከር የሶማሊያ ጦርን ድባቅ መታ። ጦርነቱ ሲጀመር ኢትዮጵያ 10 በመቶ ብቻ የኦጋዴን መሬት በእጇ ነበር። ጦርነቱ ካራማራ ተራራ ላይ ሲያበቃ ኦጋዴን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ተያዘች። በካራማራ ጦርነት በርካቶች ተሰውተዋል። በቀጣናው ያለውን ድርሻ ለማስፋት ኢትዮጵያን የወረረው ሜጀር ጄነራል ሲያድ ባሬ ከሽንፈቱ በኋላ ተቀባይነቱ እየሟሸሸ መጣ። ታላቋ የሚል ቅጥያ የነበራት ሶማሊያም ከኦጋዴን ጦርነት በኋላ በእርስ በርስ ጦርነት መታመስ ጀመረች። ሲያድ ባሬ 1983 ዓ.ም ከሥልጣን ተወግዶ ወደ ናይጄሪያ ሸሸ። ሕልፈተ ሕይወቱም ለአራት ዓመታት በስደት በቆየባት ናይጄሪያ ሆነ። በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመንና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል። ከ16ሺህ በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። የኢትዮ-ሶማሊያ የኦጋዴን ጦርነት የብዙሃን ሰላማዊ ዜጎችን ቢቀጥፍም፤ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች ጅግንነታቸውን ያሳዩበት እንደሆነ በታሪክ ይወሳል።
news-49520710
https://www.bbc.com/amharic/news-49520710
በጃፓን የሴቶችን መቀመጫ የሚጎነትሉ ወንዶችን ለመከላከል ሥውር ማኅተም ተዘጋጀ
ሁነኛ ጸረ-ለከፋ መሣሪያ በጃፓን ተመርቷል። ዋና ዓለማው በአውቶቡስና በባቡር እንዲሁም ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች የሴቶችን ዳሌና መቀመጫ "ቸብ" የሚያደርጉ አጉራ ዘለል ወንዶችን ለመቆጣጠር ነው።
ዲጂታል ሥውር ማኀተሙ የመዳፍ ቅርጽ ያለው ሆኖ የተሠራ ሲሆን ሴቶች ጥቃት አድራሹ ላይ ፈጥነው ምልክት እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል ተብሏል። • "ወፍራም ሴቶች ለአገርም ለቤተሰብም ሸክም ናቸው" የግብፅ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ • "አትግደሉን!"፡ የቱርክ ሴቶች ስለዚህ ሌሎች ሰዎች ወይም የሕግ አካላት ጥቃት አድራሹን በቀላሉ በተለደፈበት ማኅተም ምክንያት ዳናውን ተከትለው ነቅሰው ያወጡታል። ይህንን ሥውር ማኅተም የፈበረከው ኩባንያ ዓላማዬ የሴቶችን ጥቃት መከላከል ነው ብሏል። ሆኖም በሴቶች መብት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ሐሳቡን ሙሉ በሙሉ ወደውታል ማለት አያስደፍርም። "መሣሪያው ተጠቂዋ ላይ ሥራ የሚያበዛ ነው" ይላሉ። ኩባንያው ግን የፈበረኩት መሣሪያ የሴት ዳሌን ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ «ቸብ» ማድረግ የለመዱ 'ቅሌታሞችን' ለማደን እንዲረዳ ነው ይላል። ኩባንያው ረቂቅ ማኀተሙን ለመሥራት ያነሳሳው ባለፈው ግንቦት ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ በብዛት የታየውን ሁለት ሴት ተማሪዎች ጥቃት አድራሽ የሆነን ግለሰብ በቪዲዮ እየቀረጹ ሲያሳድዱት የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምሥል ተከትሎ ነው። በእንግሊዝና ዌልስ የጾታ ጥቃቶች ላይ የሚሠራ አንድ ቡድን ቃለ አቀባይ ለቢቢሲ ስለ ረቂቁ ማኀተም በሰጠችው አስተያየት « የሴቶች ጥቃት ላይ ንግድ ነው የተያዘው» ብላለች። በሰዎች ጥቃትና ፍርሃት መነገድ መልካም ነገር አይደለም ስትል አክላለች። የቶኪዮ ከተማ ዙርያ ፖሊስ ባወጣው አሐዝ በ2017 ብቻ ወደ 3ሺ የሚጠጉ ሴቶች "ወንዶች በባቡር ውስጥ አላስፈላጊ ንክኪ አድርገውብናል" ሲሉ መክሰሳቸውን ተናግረዋል። ይህ ተላካፊ ወንዶችን የሚያድነው መሣሪያ ለገበያ በቀረበ በግማሽ ሰዓት ውስጥ 500 ቅጂ ተሸጧል። የአንዱ ዋጋ 20 ፓውንድ ይደርሳል። • መቀመጫቸውን ለማስተለቅ የሚታትሩ ሴቶች እየሞቱ ነው ከዚህ ቀደም በየባቡር ጣቢያው የሴቶችን መቀመጫ የሚነካኩ ጋጠወጦችን ለመቆጣጠር በርካታ ካሜራዎች ባቡር ውስጥ ጭምር መተከላቸው ይታወሳል። ካሜራውን መሠረት በማድረግም 6ሺህ ወንዶች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። የሴቶችን መቀመጫ ከመጎንተልም አልፎ በሞባይል መቅረጽ በጃፓን የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል። ጃፓን የጾታ እኩልነትን በማስከበር ረገድ በዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ሰንጠረዥ ከ149 አገራት 110ኛ ደረጃ ነው ያላት።
news-47391380
https://www.bbc.com/amharic/news-47391380
የምግብ ምርጫዎ ስለማንነትዎ ይናገራል?
ብዙ ጊዜ ከምግብ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ነገር የቤተሰብ አባላት ስለ ምግብ ያላቸው አስተሳሰብ ነው። በዚሁ ዙሪያ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት አብዛኞቹ አሜሪካዊያን ቤተሰቦች ስለሚመገቡት ምግብ ጤናማነት አብዝተው ይጨነቃሉ።
በሌሎች ሀገራት የሚኖሩ ቤተሰቦች ደግሞ ምግቡ ምንም ይሁን ምን ዋናው ነገር መጣፈጡ ነው ብለው ያስባሉ። እርስዎ ጥሩ ምሳ በላሁ የሚሉት ምን ሲመገቡ ነው? ምናልባት አንዳንዶች አትክልት የበዛበት ነገር ሊመርጡ ይችላሉ፤ ሌሎች ደግሞ ሥጋ ነክ የሆኑ ምግቦችን ሊያስቀድሙ ይችላሉ፤ በርገር አልያም ፒዛ የሚሉም አይጠፉም። • እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል? የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የምግቡ አይነት ብቻ ሳይሆን ስለምግቡ የምናወራበት መንገድና ባህላችን ጥሩ ወይም መጥፎ ብለን ለመለየት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ባለሙያዎቹ እንዲያውም ምግብና ስለምግብ የሚደረጉ ውይይቶች የአንድን ማህበረሰብ ባህል፣ ማንነትና ፖለቲካዊ አቋም እስከመግለጽ ይደርሳሉ ይላሉ። ተመራማሪዋ ማርታ ሲፍ ካረባይክ፣ ዴንማርክ ውስጥ ስላጋጠማት ነገር ስታወራ ተማሪዎች 'ሪይ' የተባለውን የዳቦ አይነት ለምሳ ይዘው እንዲመጡ ይመከራሉ ትላለች። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ይህንን የማያደርጉ ከሆነ ግን ምግባቸው ጤናማ እንዳልሆነ በአስተማሪዎቻቸው ተነግሯቸው ለቤተሰቦቻቸው ማስጠነቀቂያ ይላካል ስትል ባህል በምግብ ላይ ያለውን ተጽእኖ ታስረዳለች። ''ይህ የሆነው 'ሪይ' የተባለው የዳቦ አይነት የተለየ ጤናማ ንጥረ ነገር በውስጡ ስለያዘ ሳይሆን ባህልና ማንነትን ለመግለጽ ስለሚጠቀሙበት ነው።'' ሌላዋ ተመራማሪ ካትሊን ራይሊ ደግሞ በፈረንሳይ በነበራት ቆይታ አስገራሚ ነገር እንደታዘበች ትናገራለች። የአንድ ማህበረሰብ አባላት ምግባቸው የማይጣፍጥ አልያም መጥፎ እንደሆነ ከተነገራቸው፣ ሰዎቹ ራሳቸው መጥፎ እንደተባሉና ባህላቸውም እንደተሰደበ ይቆጥሩታል። እነዚህ ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ከፍ ያለ ቦታ ከሌሎች ለመለየትና አስጠብቆ ለማስቀጠል ከሚጠቀሟቸው መንገዶች መካከል የሚበሉት የምግብ አይነት በዋነኛነት ይጠቀሳል። ምግቦቻችን ለዓለም ያለንን አመለካከት የሚቀርጹት እንዴት ነው? ማርታ ሲፍ ካረባይክ እንደምትለው ባለፉት አስር ዓመታት አሳማና የአሳማ ተዋጽኦዎችን አብዝቶ መጠቀም የዴንማርኮች መገለጫ እየሆነ መጥቷል። • አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች ዴንማርክ ውስጥ በአንድ ወቅት ትምህርት ቤቶች የአሳማ ስጋን ከምግብ ዝርዝራቸው ውስጥ አስወጥተው ነበር። ይህ ደግሞ ከዓለም አቀፋዊነትና ስልጣኔ ጋር ተያይዞ እንደመጣ ይታሰባል። ጉዳዩ ያሳሰበው የአንድ ግዛት ምክር ቤት ትምህርት ቤቶች የአሳማ ስጋን በምግብ ዝርዝራቸው ውስጥ እንዲያካትቱ የሚያስገድድ ሕግ አውጥቶም ነበር። በሕጉ መሰረት ማንኛውም ተማሪ የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ቢሆን የዴንማርክ መገለጫ የሆኑ ምግቦች የመመገብ ግዴታ አለበት። የአሳማ ስጋ ደግሞ ዋነኛው ምግባቸው ነው። ስለዚህ ዴንማርካዊያን 'ሪይ' የተባለውን ዳቦ ሲመገቡ ስለጤናቸው በማሰብ ሲሆን የአሳማ ስጋን ሲበሉ ደግሞ ባህላቸውንና ማህበረሰባዊ እሴቶቻቸውን ከማስቀጠል አንጻር ነው። • ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች ካትሊን ራይሊ እንደምትለው ድሮ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ምግብ ሳይሆን የተሻለ ሥራ ነበር። ዛሬ ዛሬ ግን ሰዎች የሚበሉትን ምግብ በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ቦታ እንደማሳያ ይጠቀሙታል።
48014334
https://www.bbc.com/amharic/48014334
የጡት ካንሰር የያዛት የጡት ካንሰር ሀኪም
ዶ/ር ሊዝ ኦሪዮርዳን ትባላለች። የጡት ካንሰር የቀዶ ጥገና ሀኪም ነበረች። የጡት ካንሰር ይዟት ሥራዋን ለማቆም እስከተገደደችበት ጊዜ ድረስ በሙያዋ ብዙ ሴቶችን አገልግላለች።
ዶ/ር ሊዝ ኦሪዮርዳን ስለ ህመሟ ስትናገር፦ "እንደ አብዛኞቹ ሴቶች ጡቴን አልተመረመርኩም ነበር። የጡት ካንሰር ሀኪም ስለሆንኩ የጡት ካንሰር ይይዘኛል ብዬ አስቤ አላውቅም" • አስጊነቱ እየጨመረ ያለው ካንሰር ህክምና ስትማር ቢያንስ ለ20 ዓመት የጡት ካንሰር ሀኪም እሆናለሁ ብላ ነበር። ነገር ግን በሙያዋ መሥራት የቻለችው ሁለት ዓመት ብቻ ነበር። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 ጡቷ ላይ ቀዶ ጥገና ተደርጎ ነበር። ባለፈው ወር ካንሰር ዳግም አገርሽቶባታል። ዶ/ር ሊዝ ኦሪዮርዳን "ከሀኪምነት ወደ ታማሚነት ልሸጋገር ነው?" የጡት ካንሰር እንዳለባት ከማወቋ በፊት ጡቷ ላይ አንዳች ምልክት ታይቷት ነበር። ጡት በሚመረመርበት ኤክስሬይ 'ማሞግራም' ስትታይ ጡቷ ላይ ችግር እንደሌለ ተነገራት። ቢሆንም ምልክቱን በድጋሚ ስታይ እናቷ ካንሰር እንድትመረመር አደረጓት። በምርመራውም ካንሰር እንዳለባትም ታወቀ። የጡት ካንሰር ሀኪም በመሆኗ ምን እንደሚያስፈልጋት ለማወቅ አማካሪ አላስፈለጋትም። "ከሀኪምነት ወደ ታማሚነት ልሸጋገር ነው?" ብላ ትካዜ ቢገባትም፤ ኬሞቴራፒ እንደሚያስፈልጋት እንዲሁም ምን ያህል ጊዜ በሕይወት መቆየት እንደምትችል ታውቃለች። • በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? ዶ/ር ሊዝ አሁን 43 ዓመቷ ነው። ብዙ ዶክተሮች ህክምና በሚሰጡበት በሽታ አንደማይያዙ ትናገራለች። ዶክተሯ 'ሬድዮቴራፒ' (የጨረር ህክምና) ካደረገች በኋላ የክንዷ እንቅስቃሴ ተገደበ። ቀዶ ጥገና ማድረግም አልቻለችም። ህመሙ አካል ላይ የሚያደረሰውን ጉዳት እንጂ ሥነ ልቦናዊ ተጽዕኖው እስከሚደርስባት ድረስ አታውቅም ነበር። "የጡት ካንሰር ላለበትን ሰው መንገር እንጂ በበሽታው መያዝ ምን ማለት እንደሆነ አላውቅም ነበር።" ሀኪሟ ከቀዶ ጥገና በኋላ ትከሻዋን እንደቀድሞው ማዘዝ አልቻለችም "የራሴን ህመም ደጋግሞ ማስታወስ ነው የሆነብኝ" ካንሰር እንደያዛት ካወቀች በኋላ የቀዶ ጥገና አማካሪ ከሆነ ባለቤቷ ጋር ተመካክራ የትዊተር ገጿ ላይ ስለመታመሟ ጻፈች። ትዊተር ላይ 1,500 ተከታዮች ያሏት ሲሆን፤ እንደሷው የጡት ካንሰር ያለባቸው ሴቶች ማኀበራዊ ሚድያ ላይ ድጋፍ ይቸሯት ጀመረ። • "ወንዶች በጡት ካንሠር እንደሚያዙ አላውቅም ነበር" እንደሷው ሀኪም ሆነው የጡት ካንሰር ከያዛቸው ሴቶች ጋር የተገናኘችውም በማኀበራዊ ሚዲያ ነበር። የዋትስአፕ ቡድን ፈጥረው ተሞክሯቸውን ይጋራሉ። የጡት ካንሰር ከያዛት በኋላ ህመሙ ያለባቸውን ሰዎች በተሻለ ሁኔታ መርዳት እንደምትችል ገምታ ነበር። ሆኖም እንዳሰበችው ቀላል ሆኖ አላገኘችውም ። "ለእያንዳንዷ ሴት የጡት ካንሰር እንዳለባት መንገር ከባድ ነው። የራሴን ህመም ደጋግሞ ማስታወስ ነው የሆነብኝ" ትላለች ዶ/ር ሊዝ። ቀዶ ጥገና ከተደረገላት በኋላ ታካሚዎቿ ላይ ቀዶ ጥገና ማድረግ ተቸግራ ነበር "እኔና እሷ አንድ ነን" ትሠራበት በነበረው ሆስፒታል አንድ በሷ ዕድሜ ያለችና እንደሷው አይነት የጡት ካንሰር ያለባት ሴት ህክምና ትከታተል ነበር። ሰለታማሚዋ ከሌሎች ሀኪሞች ጋር እየተነጋገረች ሳለ "ያለችበት ሁኔታ እጅግ የከፋ ነው" ሲባል ልክ ስለሷ እንደሚወራ እንደተሰማት ትናገራለች፤ "እኔና እሷ አንድ ነን" ስትልም የተሰማትን ስብራት ትገልጻለች። • የካንሰር የደም ምርመራ "አሰደናቂ ውጤት" አስገኘ ዶ/ር ሊዝ ሰዎች ካንሰር ከያዛቸው በኋላ ወደሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ትመክራለች። በርካታ መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞቻቸው ካንሰር ከያዛቸው በኋላ ወደሥራ የሚመለሱበትን መንገድ እንደማያመቻቹም ትናገራለች። አሁን የጡት ካንሰር ላለባቸው ሴቶች እገዛ ማድረግ በምትችልባቸው ማህበሮች ውስጥ ትሳተፋለች፤ ታማክራለችም። "አማካሪ ሆኜ በዓመት ቢያንስ ከ70 እስከ 100 ሴቶች እረዳለሁ። በመጽሐፌ ደግሞ መቶ ሺዎችን አግዛለሁ" ትላለች ዶክተሯ።
news-57077652
https://www.bbc.com/amharic/news-57077652
የኢትዮጵያ ምርጫ፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ ሕብረት ምርጫው ታዛቢ ይልካል አለ
የአውሮፓ ሕብረት ቀጣዩን 6ኛ አገራዊ ምርጫ እንዲታዘቡ ባለሙያዎቹን ይልካል ሲሉ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።
ከአውሮፓ ሕብረት በተጨማሪ ከአሜሪካ እና ሩሲያ የተውጣጡ የባለሙያዎች ምርጫውን ለመታዘብ እንደሚመጡ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባዩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከስምምነት መድረስ ባለመቻሉ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ አስቦ የነበረውን የምርጫ ታዛቢ እንዲቀር መወሰኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የአውሮፓ ሕብረት የቀደመ ውሳኔውን ሰርዞ ምርጫውን ለመታዘብ ስለመወሰኑ እስካሁን ያለው ነገር የለም። ሕብረቱ የሚልካቸው የምርጫ ታዛቢ ቡድን የሚሰማራበት ቁልፍ መለኪያዎች /ፓራሜትርስ/ ላይ ከመንግሥት ጋር ከስምምነት መድረስ አልተቻለም ብሎ ነበር። የአውሮፓ ሕብረት ይህን ካለ በኋላ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ከአንድ ሳምንት በፊት በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ምርጫ ለመታዘብ ካቀደው የአውሮፓ ሕብረት ጋር ያልተስማማቸው ሕብረቱ ሉዓላዊነትን የሚጻረር ጥያቄን በማቅረቡ ነው ብለው ተናግረው ነበር። ቃል አቀባዩ በወቅቱ የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩን ላለመላክ የወሰነው በሁለት ምክንያት ነው ብለዋል። ይህም ሕብረቱ አገሪቱ የሌላትን የኮሚኒኬሽን ስርዓት ማስገባትን አስገዳጅ ማድረጉ እንዲሁም የምርጫውን ውጤት ይፋ የማደርገው እኔ ነኝ ማለቱን ተናግረው ነበር። ይህም የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና ደህንነት የሚጻረር ስለሆነ ከስምምነት ሳይደረስ ቀርቷል ሲሉ አስረድተው ነበር። ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ዛሬ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ ሕብረት ምርጫ ታዛቢ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥት የያዘው አቋም እንዳልተቀየረ ተናግረው፤ ከአውሮፓ ህብረት ስድስት አባላትን የያዘ ቡድን፣ ከአሜሪካ ሁለት ተቋማት የተውጣጣ እንዲሁም ከሩሲያና የአፍሪካ ህብረት ምርጫውን የሚታዘቡ ባለሙያዎች ይመጣሉ ብለዋል።
news-51764786
https://www.bbc.com/amharic/news-51764786
የኮሮናቫይረስ በአዲስ አበባ ሆቴሎች ላይ ያጠላው ስጋት
የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ስጋት ምክንያት በአዲስ አበባ ሊካሄዱ ታቅደው የነበሩ ስብሰባዎች በመሰረዛቸው በአዲስ አበባ በሚገኙ ሆቴሎች ገቢ ላይ ተጽእኖ እንደሚያስከትል ተነገረ።
የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ብስራት ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ባይከሰትም በሌሎች አገራት ውስጥ ባለው ሁኔታ ሳቢያ ተጓዦች ቀደም ሲል የያዙትን እቅድ እየሰረዙ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ባይኖራቸውም የሚሰረዙት ከፍተኛ የቋማትና የግለሰብ መረሃግብሮች በአገሪቱና በሆቴሎች ገቢ ላይ የእራሳቸው የሆነ ተጽእኖ እንደሚኖራቸው አመለክተዋል። አቶ ቢኒያም እንደ አብነትም አዲስ አባባ ውስጥ ሚያዚያ ወር ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውና አንድ ሺህ ሰው እንደሚሳተፍበት የሚጠበቀው የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ዓመታዊ ጉባኤ ተሰርዟል። በዚህም እያንዳንዱ ተሳታፊ አራት ምሽቶችን አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚያሰልፍ ይጠበቅ የነበረ ሲሆን አንድ ሰው በአማካይ በአንድ ምሽት 100 ዶላር የሚከፍል ቢሆን የ400 ሺህ ዶላር ገቢ ሳይገኝ እንደሚቀር ተናግረዋል። ከእነዚህ መካከል በተባበሩት መንግሥታት ድርጀት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አማካይነት ከመጋቢት 9 እስከ 15 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ በከፍተኛ ሚኒስትሮች ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ጉባኤ አንዱ ነው። ይህም በገንዘብ፣ በዕቅድና በምጣኔ ሃብታዊ ልማት ሚኒስትሮች አማካይነት የሚደረግና የ53ኛው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጉባኤ አካል ነበር። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንን ጨምሮም በኮሮናቫይረስ መስፋፋት ሳቢያ እየጨመረ በመጣው ስጋት ከአጋሮቹ ጋር በመመካከር ለጥንቃቄ ሲባል ተጨማሪያ ማስታወቂያ እስኪያወጣ ድረስ "ሁሉም ሕዝባዊ ስብሰባዎች ለሌላ ጊዜ መተላላፋቸውን" ገልጿል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ አገራት ውስጥ በመስፋፋቱ ለሥራም ሆነ ለእረፍት ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎች በሽታው ባስከተለው ስጋት ሳቢያ ዕቅዳቸውን ለመሰረዝ ተገደዋል። በዚህም የሆቴል ዘርፉ ላይ የገቢ መቀነስ እንደሚያስከትል አቶ ቢያኒያም አመልክተዋል። የበሽታው መስፋፋትና ስጋት በዚሁ ከቀጠለ ግንቦትና ሠኔ አካባቢ ፊፋ የሚያዘጋጀው ትልቅ መሰናዶ እንዲሁም የዓለም ኢኮኖሚ መድረክ ለመስከረም ወር የያዟቸው ትልልቅ ስብሰባዎችንም የመካሄድ ጉዳይን ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባው እንደሚችል ጠቅሰዋል። እስካሁን በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ባይከሰትም ከሚያሳጣው ገቢ በላይ አሳሳቢው ነገር የጤና ጉዳይ በመሆኑ ማኅበሩ በሆቴሎች የሚገኙ ሠራተኞች ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄ ስልጠናዎችንና የጥንቃቄ መመሪያዎችን እየሰጡ ነው ብለዋል። ይህ በዓለም ዙሪያ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በገደለው የኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት የታላላቅ ጉባኤዎች መሰረዝ እያጋጠመ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የአፍረካ አገራት ውስጥ ጭምር ነው። ከእነዚህም መካከል በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በመጪው ሳምንት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው 'ዘ ኔክስት አይንስታይን ፎረም' የተባለው ስብሰባ ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ተነግሯል። መድረኩ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ለአምስት ቀናት ከ79 አገራት በላይ በመጡና ከሁለት ሺህ የሚበልጡ ተሳታፊዎች የሚታደሙበት እንደነበር ተገልጿል። ሌላው ደግሞ የአፍሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ፎረም የተባለውና በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን ውስጥ በሚቀጥለው ሳምንት ለሁለት ቀናት ሊካሄድ የነበረው ስብሰባም እንደዚሁ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዘዋወር ተደርጓል።
47743552
https://www.bbc.com/amharic/47743552
ዓለም ለሴቶች እንዳልተሰራች የሚያሳዩ ነገሮች
ካሮላይን ክሪያዶ ፔሬዝ ነገሮች ሁሌም ከወንዶች አንፃር ብቻ መቃኘታቸውንና ይህች ዓለም እንዴት ለወንድ ብቻ እንድትሆን ተደርጋ እየተቀረፀች እንዳለ ጥናት መስራት የጀመረችው በአንድ ወቅት የልብ ህመምን በሚመለከት የተሰበሰቡ መረጃዎች ሁሉ በወንዶች የህመሙ ምልክት ላይ ብቻ የተመሰረቱ መሆናቸውን ካስተዋለች በኋላ ነው።
ጡትን ከግንዛቤ ካልከተቱት የፖሊስ ጥይት መከላከያ ልብሶችና ጫማዎች ጀምሮ በርካታ ነገሮች ወንድን ብቻ ታሳቢ በማድረግ የተሰሩ እንደሆኑ ትናገራለች። የህዋ ልብሶች በአንድ ወቅት ናሳ ሴቶች ብቻ ወደ ህዋ የሚያደርጉትን ጉዞ በመሰረዙ በትዊተር ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበት ነበር። ጉዞው የተሰረዘው ጠፈርተኛዋ አኒ ማክሌን ከዚህ በፊት ትለብስ የነበረው የህዋ ጉዞ ልብስ ትልቅ የነበረ ቢሆንም ሙሉ የሴት ቡድን በሚያደርገው ጉዞ ላይ ግን መካከለኛ መጠን ያለው ልብስ የበለጠ ልኳ ስለሆነ እሱን እለብሳለሁ በማለቷ ነበር። • ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ? የህዋ ልብሶቹ ወንዶችን ብቻ ታሳቢ አድርገው የሚሰሩ በመሆናቸው ትልቅ፣ በጣም ትልቅና ምናልባትም መካከለኛ መጠን ብቻ እንዲኖራቸው ተደርገው ነው የተሰሩት፤ ትንሽ ሚባል ነገር የለም። በወቅቱ በናሳ ሁለት መካከለኛ መጠን ያላቸው የህዋ ልብሶች የነበሩ ቢሆንም ለጉዞ ዝግጁ ተደርጎ የነበረው ግን አንዱ ብቻ ነበር። የጦር መሳሪያዎች እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 አሜሪካ ቀደም ሲል ወንዶችን ብቻ ትመለምልበት ለነበረው የምድርና ባህር ኃይል ክፍል ሴቶችን መመልመል ብትጀምርም በእነዚህ ክፍሎች ያሉ የጦር መሳሪያዎች ሁሉ ግን ለወንድ ብቻ እንዲመቹ ሆነው የተሰሩ ናቸው። የዲሞክራቲክ ፓርቲዋ የኮንግረስ አባል ኒኪ ሶንጋስ ይህ የአገሪቱ ጦር ኃይል ምን ያክል ለሴት አባላቱ ፍላጎቶች ምላሽ እንደማይሰጥ ማሳያ መሆኑን ተናግረው ነበር። • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና በዚህ ምክንያት ሴት ወታደሮች መሳሪያ ለመተኮስና የጥይት መከላከያ ልብሶችን መልበስ እንኳ እንደሚቸገሩ ተናግረዋል። እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት የጦር ኃይሉ ለሴቶች ምቹ የሆኑ መሳሪያዎችን እንደሚያቀርብ አስታውቆ ነበር። በሴቶች የወታደራዊ አገልግሎት ላይ ጥናት የሰሩት አሌክስ ኤሊያስ "ሴቶች እስከ 2018 ለወንዶች በተሰሩ መሳሪያዎች በኢራቅና በአፍጋኒስታን ተሰማርተው ነበር" ብለዋል። ስማርት ስልኮች የስማርት ስልክ መተግበሪያዎችና የስልኮቹ መጠን ራሱ ለወንዶች እንዲሆኑ ተደርገው ተሰርተዋል ብለው የሚያስቡ ብዙ ሴቶች ናቸው። በአማካይ የሴቶች እጅ ከወንዶች በአንድ ኢንች የሚያንስ ሲሆን የስማርት ስልክ አምራች ኩባንያዎች ደግሞ የስልኮቹን መጠን እያሳደጉ መምጣታቸው ችግር ነው ይላሉ። 12 ሴ.ሜ በሆነ ወይም በትልቅ አይፎን በአንድ እጅ ስልክን ይዞ መልዕክት መላክ ለበርካታ ሴቶችና ትንሽ እጅ ላላቸው ወንዶች ከባድ ወይም የማይቻል ነው። የስፖርት ልብሶች ታዋቂው የአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ስቴፈን ከሪ አዲስ የህፃናት የስፖርት ጫማ ንድፍ ሲያወጣ የሰራው ለወንዶች ብቻ የነበረ ሲሆን፤ አንዲት የዘጠኝ ዓመት ህፃን ለምን የወንዶች ብቻ የሚል ደብዳቤ ፅፋለት ነበር። "የሴቶችን የሩጫ ስፖርት እንደምትደግፍ አውቃለሁ ምክንያቱም ሁለት ሴቶች ልጆች አሉህ" በማለት ስህተቱን እንደሚያርም ተስፋ እንደምታደርግ ገልፃ ነበር። • ሴቶች በሰሜን ኮሪያ ሠራዊት ውስጥ እሱም ህፃኗን ስለደብዳቤዋ አመስግኖ ስለተፈጠረው ነገር ማብራሪያ ሰጥቷል። ሳይንሳዊ መሳሪያዎች በካንሳስ አልያንስ የባይሎጂ ተመራማሪ የሆኑት ጀሲካ ማውንትስ በቤተ ሙከራ የሚጠቀሟቸው የምርምር መሳሪያዎች በሙሉ ለወንድ ተብለው የተሰሩ እንደሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ ይህ መሆኑ ደግሞ የሚረብሽ ብቻ ሳይሆን ለአደጋ ስጋት እንደሚሆንም ይናገራሉ። ሰፋፊ ገዋኖች እንቅስቃሴ ላይ በቁሳቁሶች ሲያዙ ትልልቅ ቡትስ ጫማዎች ደግሞ ለመውደቅ ይዳርጋል። የሥራ ቦታዎች የታሪክና ሌሎችም ምሁራን ወንበሮችና ሌሎችም የቢሮ እቃዎች ለወንዶች ምቹ እንዲሆኑ ተደርገው መሰራታቸውን የሚመለከቱ ጥናቶችን አድርገዋል። ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆኑት የታሪክ ምሁሯ ዋጅዳ ሺርሊ በኩባንያዎች ውስጥ ሁሌም ስለ ቡድን ሥራ ውጤታማነት እንደሚወራ፤ ነገር ግን ይህ ትርጉም እንደማይሰጥ "ምቹ በሆነ አካባቢ ሳይቀመጥ ማን ስለ ቡድን ስራ ሊጨነቅ ይችላል?" በማለት ያስረዳሉ።
news-55950981
https://www.bbc.com/amharic/news-55950981
የዘር ቅንጣት የሚያክል እስስት ተገኘ
ተመራማሪዎች በምድራችን ላይ ትንሽ ነው የተባለ እስስት በማዳጋስካር ማግኘታቸውን ተናገሩ።
እስስቱ ከማነሱ የተነሳ የዘር ቅንጣት ያክላል ተብሏል። የማዳጋስካር እና ጀርመን ተመራማሪዎች በተጨማሪም ሁለት ትንንሽ እንሽላሊቶች ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል። ወንዱ እስስት፣ ብረኬዢያ ናና የሚባል ሲሆን አካሉ 13.5 ሚሊሜትር እንደሆነ ተገልጿል። በሙኒክ እንደሚገኘው ባቫሪያን የእንስሳት ሙዚየም ከሆነ ይህ እስስት በዓለም ላይ ከታወቁት 11 ሺህ 500 ተሳቢ እንስሳት መካከል በጣም ትንሹ ነው። ይህ በዓለማችን ላይ ትንሽ ነው የተባለው እስስት፣ ከጭራው ጫፍ እስከ አፍንጫው ድረስ ርዝመቱ 22 ሚሜትር ርዝመት አለው። ሴቷ ግን ከወንዱ በጥቂት ሚሊ ሜትሮች ረዘም ትላለች ያሉት ተመራማሪዎች 29 ሚሜትር እንደምትረዝም አሳውቀዋል። ተመራማሪዎቹ ሌላ ዝርያ ይገኛል በሚል ተስፋ ጥረታቸውን ቀጥለዋል። አዲሱ እስስት የተገኘው በሰሜን ማዳጋስካር ሞንታኔ በሚባል ጫካ ውስጥ ሲሆን የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተብሏል። በሃምቡርግ በሚገኘው የተፈጥሮ ታሪክ ማዕከል ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ኦሊቨር ሃውልቲሼክ ይህ የፍሬ ያክል ትንሽ የሆነ እስስት በደን ጭፍጨፋ ምክንያት ለመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል። ነገር ግን አካባቢው በቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥበቃ እየተደረገለት ሲሆን ይህም ዝርያው ሊተርፍ ይችላል የሚል ተስፋ አሳድሯል። ተመራማሪዎች ይህንን የእስስት ዝርያ ምስጥ አድኖ እንደሚበላ እና በምሽት በሳሮች መካከል እንደሚደበቅ ደርሰውበታል። ተመራማሪዎች ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ይህ የእስስት ዝርያ በዓለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ ሕብረት ዘንድ ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል እጅግ በጣም ለአደጋ የተጋለጡ ዝርያዎች ዝርዝር ውስጥ እንዲመዘገብ ጠይቀዋል።
news-55089960
https://www.bbc.com/amharic/news-55089960
ለጭቁኖች ተቆርቋሪው የክፍለ ዘመኑ ታላቅ የእግር ኳስ ጥበበኛ ዲያጎ ማራዶና
አንፀባራቂ ስብዕና፣ ድንቅ ችሎታ፣ የላቀ አእምሮ፣ ተናዳጅ፣ ቁጡ፣ ለተጨቋኞች አዛኝ፣ እብሪተኛ ሌላም ሌላም. . .
በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የእግር ኳሱ ሊቅ ዲያጎ ማራዶና በህይወት እያለ ይሰጠው የነበሩ ስሞች ናቸው - የዓለማችን የእግር ኳስ ጀግና። ለእግር ኳስ የተፈጠረ ነው የሚባልለት አርጀንቲናዊው ማራዶና ለየት ያለ ድንቅ ችሎታን፣ ራዕይና ፍጥነትን ቀልብ ከመሳብ ጋር በማጣመር በርካታ አድናቂዎቹን አስደምሟል። "የአምላክ እጅ" ተብሎ በሚጠራው አወዛጋቢ ጎል፣ በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ መዘፈቁና ሌሎች ከግል ህይወቱ ጋር በተያያዘም ደጋፊዎቹ የተመሳቀለ እይታ እንዲኖራቸው አድርጓል። በአሁኑ ወቅት ጣልያንን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ያሉ አድናቂዎቹ እየዘከሩት ሲሆን በተለይም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ ታላቅ ቦታ አለው። በርካታ ጊዜያትም "ልቤም ሆነ ውስጤ ፍልስጥኤማዊ ነው" ሲል የተሰማው ማራዶና "ጭቆናን እናውቃለን" በማለትም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ለፍልስጥኤም ያለውን ድጋፍ አሳይቷል። አጭርና ጣፋጭ ህይወት- የእግር ኳሱ ሊቅ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና የተወለደው በአርጀንቲናዋ፣ ቦነስ አይረስ የድሆች መንደር ውስጥ ከዛሬ 60 ዓመት በፊት ነበር። የእግር ኳስ ፍላጎቱም የተጠነሰሰው ገና በታዳጊነቱ ሲሆን፤ በእግር ኳስ ታሪክ ታላቅ ቦታ ላይ መድረስ ችሏል። አንዳንዶችም ከታላቁ የብራዚል እግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ ያስበልጡታል። ማራዶና በ491 ጨዋታዎች 259 ጎሎችን በማስቆጠል የደቡብ አሜሪካ ተቀናቃኙን ፔሌን በመብለጥ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ ተጫዋች መሆን ቢችልም፤ ወደ በኋላ እግር ኳስን በበላይነት የሚያስተዳድረው ፊፋ የምርጫ ሕጉን በመቀየሩ ሁለቱም የክፍለ ዘመኑ ምርጥ በመሆን ተሰይመዋል። በእናቱ ማህፀን እግር ኳስን የለመደ ይመስል ማራዶና ገና በህፃንነቱ ነበር የላቀ ችሎታውን ማሳየት የጀመረው። ሎስ ሴቦሊታስ የተባለ የታዳጊዎች ቡድንን በመምራት በ136 ጨዋታዎች ባለመሸነፍ አይበገሬነቱን አሳይቷል። የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ህይወቱንም የጀመረው በ16 ዓመቱ አካባቢ ነው። አጠር ብሎ ደንደን ያለ ሰውነት ያለው ማራዶና ቁመቱም 1.65 ሜትር ነው። ሲታይ የተለመደው አይነት የስፖርተኛ ሰውነት የለውም። ነገር ግን ቀልጣፋነቱ፣ ነገሮችን ቀድሞ የመረዳት ችሎታው፣ የኳስ ቁጥጥሩ፣ ኳስ ማንቀርቀብና ቶሎ ማሳለፍ መቻሉ ላለመረጋጋቱና ብዙ ጊዜ የሚያጋጥመውን የክብደት ችግሩን አካክሶለታል። ምንም እንኳን የተቀናቃኝ ቡድንን ተከላካዮች በቀላሉ ማለፍ ቢችልም ማራዶና በግል ህይወቱ ራሱን በርካታ ጊዜ ችግር ውስጥ ተዘፍቆ አግኘቶታል። የአምላክ እጅና የክፍለ ዘመኑ ጎል ማራዶ ለአገሩ በተሰለፈባቸው 91 ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ላይ 34 ጎል አስቆጥሯል። ነገር ግን ይህ ምናልባት ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ጨዋታ ታሪኩ ውስጥ ከወንዝ ውሃን በማንኪያ እንደ መጨለፍ የሚቆጠር ነው። በጎሮጎሳውያኑ በ1986 ሜክሲኮ ላይ በተደረገው የዓለም ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኑን የመራው ማራዶና ከአራት ዓመታት በኋላም አገሩን ለመጨረሻ ዙር አደረሳት። በተለይም በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ የተከሰተው ውዝግብ የማራዶና መታወቂያ ሆነ። በወቅቱ አርጀንቲናና እንግሊዝ ያደርጉት ጨዋታ እግር ኳስ ብቻ አልነበረም፤ ፖለቲካም የተቀላቀለበት ነበር። ከውድድሩ ከዓመታት በፊት ለአስር ሳምንታት ያህል ፎክላንድስ ተብላ በምትጠራው ደሴት ምክንያት አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ጦርነት ገጥማ ነበር። በጨዋታው ላይ ሁለቱም የውጊያው መንፈስ ሳይለቃቸው ወደ ሜዳ ገብተው በእግር ኳሱም ላይ ይሄው የፀበኝነት ስሜት ነበር የተንፀባረቀው። ለ51 ደቂቃዎችም ያህል ያለ ምንም ጎል ጨዋታው ሲካሄድ ቆይቶ በድንገት ማራዶና ከግብ ጠባቂው ፒተር ሺልተን ጋር ዘሎ የተሻማትን ኳሷን በተቃራኒው መረብ አስቆጠረ። ማራዶና ከጨዋታው በኋላም ግቧ እንዴት እንደተቆጠችረ በተናገረበት ወቅት በጎሉ ውስጥ "ማራዶና ትንሽ ነበረበት፤ የአምላክም እጅ በትንሹ ነበረበት" በማለት ተናገረ። በዚሁ ጨዋታ ላይ ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ብዙዎች 'የክፍለ ዘመኑ ጎል' ብለው የጠሩትን ግብ አስቆጠረ። የተቀናቃኙን ቡድን አባላት እጥፍጥፍ አድርጎ፤ ሜዳው ላይ ብቻውን ያለ ሰው ይመስል፤ ጎሏን አስቆጠረ። "ድንቅ ጎል ነበረች። የእግር ኳስ እልቅና የታየበት፤ የሚገርም ነው" በማለት የቢቢሲው ዘጋቢ ቤሪ ዴቪስ ተናግሯል። በጨዋታው እንግሊዝ አንድ ጎል ብታስቆጥርም፤ አርጀንቲና 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። ለማራዶና ማሸነፉ ከጨዋታው፤ ከእግር ኳስም በላይ ነበር "እንግሊዞችን መዘረር" ፖለቲካዊ ድልም ነበረው። የናፖሊው ጀግና- በአደንዛዥ እፅ መዘፈቅ የዓለም አቀፍ የዝውውር ክብረ ወሰንን ማራዶና ሁለት ጊዜ መስበር ችሏል። በአገሩ ሲጫወትበት ከነበረው ቦካ ጁኒየርስ ወደ ስፔኑ ባርሴሎና በጎሮጎሳውያኑ 1982 ሲዛወር በ3 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ ወደ ጣልያኑ ክለብ ናፖሊም በ5 ሚሊዮን ፓውንድ ተዛወረ። በጣልያኗ ሳን ፓውሎ ስታዲየም በሄሊኮፕተር ሲያርፍም 80 ሺህ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ ተገኝተው ነበር- አዲሱን ጀግና ለመቀበል። ይህም በእግር ኳስ ታሪኩ ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገበት ወቅት ነው። ክለቡ በ1987 እና በ1990 የሊጉ አሸናፊ እንዲሆን እንዲሁም የአውሮፓ ሊግ ዋንጫን በ1989 እንዲያነሳም ቀዳሚውን ሚና የተጫወተው ማራዶና ነው። የመጀመሪያውን ድል በማስመልከት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች በጎዳናዎች ላይ በመውጣት ለአምስት ቀናት ያህል ደስታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ወቅት ማራዶና የሁሉንም ትኩረት ሳበ የሚጠበቅበትም ኃላፊነት ከፍተኛ ሆነ። ይህ ደግሞ ጫናንና መጨናነቅን አስከተለ። "ታላቅ ከተማ ናት ግን መተንፈስ እንኳን አልቻልኩም። ነፃ ሆኜ በመንገዶች ላይ መረማመድ እፈልጋለሁ። እኔም እንደ ሌላው ሰው ነኝ" ብሏል በወቅቱ። ከጣልያኑ የካሞራ ማፊያ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት አለው በሚል፣ የኮኬይን አደንዛዥ እፅ ሱስ ውስጥ መዘፈቅና ከልጅ ማደጎ ጋር በተፈጠረ እሰጣገባም ጋር ስሙ በተደጋጋሚ መነሳት ጀመረ። በጎርጎሳውያኑ በ1990 ጣልያን ላይ በተዘጋጀው የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በጀርመን 1 ለ 0 አገሩ አርጀንቲና መሸነፏን ተከትሎ እንዲሁም በቀጣዩ ዓመትም በተደረገለት ምርመራ አደንዛዥ እፅ መጠቀሙ በመታወቁ ለ15 ወራት እንዲታገድ ምክንያት ሆነ ። ከዚህ ሁሉ አገግሞና ራሱን አድሶ በጎሮጎሳውያኑ 1994 አሜሪካ ላይ ወደ ተካሄደው የዓለም ዋንጫ ቢመለስም ጎል አስቆጥሮ ደስታውን የገለፀበት መንገድ ያልተለመደና በርካቶችንም ያስደነገጠ ነበር። ማራዶና የታገደውን ኤፊድሪን የተባለ የተከለከለ አበረታች መድኃኒት ወስዶ በመገኘቱ ከውድድሩ እንዲወጣ ተደረገ። ህይወት ከጡረታ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ አበረታች እፅ በደሙ ውስጥ ከሦስት ዓመት በኋላ መገኘቱን ተከትሎ በ37 ዓመቱ ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ራሱን አገለለ። ነገር ግን ተጫዋቹን ችግሮች አልለቀቁትም። በጋዜጠኞች ላይ ተኩሷል በሚልም ሁለት ዓመት ከአስር ወራት እስር ቢፈረድበትም በማስጠንቀቂያ ታልፏል። የኮኬይንና የአልኮል መጠጡም የጤና እክል አስከትሎበታል ተብሏል። በከፍተኛ ሁኔታም ኪሎው የጨመረ ሲሆን፤ በአንድ ወቅት 128 ኪሎ ግራምም ይመዝን ነበር። በጎሮጎሳውያኑ 2004 በልብ ህመም ምክንያት ፅኑ የህሙማን ክፍል ውስጥ ገብቶም ነበር። ማራዶና ክብደቱን ለመቀነስ ቀዶ ህክምና ያደረገ ሲሆን ከአደንዛዥ ዕፅ ሱስም ለመላቀቅ ኩባ መኖር ጀመረ፤ የቀድሞውን የኩባ መሪና ሶሻሊስትና የነፃነት ታጋይ ፊደል ካስትሮንም አግኝቷቸው ነበር። ከዚህ ሁሉ በኋላ በጎሮጎሳውያኑ 2008 የአርጀንቲና ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣን ሆነ። በዚያው ዓመትም በነበረው የዓለም ዋንጫ አገሩ ለሩብ ፍፃሜ የበቃች ቢሆንም በጀርመን 4 ለ 0 ከተሸነፈ በኋላ ከቡድኑ ጋር የነበረው የሁለት ዓመት ቆይታ ተቋጫ። ውሻው ሻሪ ፔይ ከንፈሩን ነክሳው ቀዶ ህክምና ማድረጉ፣ ከትዳሩ ውጭ ለወለደው ለዲያጎ አርማንዶ ጁኒየር እውቅና መስጠቱም ስሙ ከየመድረኩ እንዳይጠፋ አደረገው። ከሁለት ዓመት በፊት ሩሲያ በተደረገው የዓለም ዋንጫ አርጀንቲናና ናይጄሪያ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተገኝቶ የነበረው ማራዶና የብዙዎች መነጋገሪያነት ሆኖ ነበር። ከናይጄሪያ ደጋፊ ጋር አብሮ መደነሱ፣ ከጨዋታው በፊት ወደ ሰማይ አንጋጦ ያደረገው ፀሎት፣ ሊዮነል ሜሲ ጎል ሲያስቆጥር በከፍተኛ ሁኔታ መደሰቱ፣ መሃል ላይ መተኛቱ እንዲሁም አርጀንቲና ሁለተኛ ጎል ስታስቆጥር የመሃል ጣቱን ሁለት ጊዜ ማሳየቱ ለሚዲያዎች ትኩስ ወሬ ነበር። ማራዶና ባለ ብዙ ስሙ፣ ለተጨቋኞች አዛኝ፣ አዝናኝ፣ ታላቅ፣ ቁጡ፣ የሚያዋርድና ሌሎች የተባለው ታላቁ እግር ኳሰ ተጨዋች ይህችን ዓለም ቢሰናበትም ህይወቱን የኖረበት መንገድ ለወደፊት ትውልድ የሚዘከረው፣ በእግር ኳስ ችሎታው የማይሞት ስምና አሻራ ትቶ አልፏል።
news-51353306
https://www.bbc.com/amharic/news-51353306
ቻይና ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን የገነባችውን ሆስፒታል ልትከፍት ነው
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት መዛመትን ተከትሎ ቻይና ለኮሮና ቫይረስ በብቸኝነት አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል ገንብታ ጨርሳለች።
ሆስፒታሉን የገነባችው የቫይረሱ መነሻ በሆነችው ዉሃን ከተማ ሲሆን የግንባታው ስራን አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ስምንት ቀናት ብቻ ነው ያስፈለጉት። ሆዎሸንሻን የሚል ስያሜ ያለው ይህ ሆስፒታል አንድ ሺ የህሙማን አልጋዎች አሉት። ቻይና ከዚህ ሆስፒታል በተጨማሪ ለኮሮናቫይረስ ህሙማንን ብቻ የሚያክሙ ሆስፒታሎችን በመገንባት ላይ ናት። በመላው ቻይና በተስፋፋው ኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እስካሁን 17 ሺ የደረሰ ሲሆን ለ361 ህይወት መቀጠፍም ምክንያት ሆኗል። ኮሮናቫይረስ ለቻይና ብቻ ሳይሆን ለዓለም ስጋት መሆኑ ቀጥሎ ፊሊፒንስ ውስጥ አንድ ግለሰብ በቫይረሱ ህይወቱ ማለፏ ተረጋግጧል። ከቻይና ውጪ በቫይረሱ ሰው ሲሞት ይህ የመጀመሪያው ነው። የ44 ዓመቱ ቻይናዊ ግለሰብ ከዉሃን የመጣ ሲሆን፤ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው ግለሰቡ ፊሊፒንስ ከመድረሱ በፊት በቫይረሱ ተይዞ ነበር። ይህንንም ተከተሎ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎች በርካታ አገራት ከቻይና የሚመጡ በረራዎችን አግደዋል። ነገር ግን የአለም ጤና ድርጅት በረራዎችን ማገድ ከሚጠቅመው በላይ ሊጎዳ እንደሚችል ምክሮችን እየለገሰ ነው። መረጃዎች እንዳይተላለፉ እንቅፋት ከመሆኑ በተጨማሪ፣ የህክምና ቁሳቀሱሶች በቀላሉ እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ፤ እንዲሁን አጠቃላይ የአገራትን ኢኮኖሚ ይጎዳል። ከዚህ በተጨማሪም ተጓዦች በህገወጥ መንገድ ድንበሮችን እንዲያቋርጡ በር ስለሚከፍት የቫይረሱን በፍጥነት የመዛመቱን ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሻቅበው ይችላል ይላል ከአለም ጤና ድርጅት የተገኘው መረጃ። አለም አቀፍ በረራ እግዶችን ተከትሎ ቻይና የአለም ጤና ድርጅትን ምክር የተላለፈ ነው በማለት ተችታዋለች። ከቻይና የጤና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው እንዲሁም ከቻይና ውጭም 150 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውም ተረጋግጧል። በሁቤ ግዛት በምትገኘው ዉሃን ከተማም ሆስፒታሎች በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ የመጣውን የህሙማንን ቁጥር ለማከም ከአቅማቸው በላይ ነውም ተብሏል። ከሰሞኑም የሆንግ ኮንግ ዶክተሮች ቻይናን የሚያገናኘው ድንበር ሊዘጋ ይገባልም በሚል አድማ መትተዋል። የቻይና ባለስልጣናት ግን በአለም ጤና ድርጅት ምክር መሰረት ድንበሩ እንደማይዘጋና መመርመሪያ ቦታዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። ነገር ግን የቻይና ባለስልጣናትን ምላሽ አጥጋቢ አይደለም ያሉት እነዚህ ዶክተሮች ቻይና የጠየቁትን የማታደርግ ከሆነ ከነገ ጀምሮ ዶክተሮችም ሆነ ነርሶች የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በቦታቸው ላይ እንደማይገኙ ነው። ከሰሞኑም የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ የወቅቱ አሳሳቢ የምድራችን የጤና ስጋት ነው ሲል አውጇል። • በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በአዲስ አበባ ተገኙ •ኤርትራ አሜሪካ የጣለችው የቪዛ እገዳ አግባብነት የለውም አለች የድርጅቱ ዋና ዳይሬክትር ዶክትር ቴድሮስ አድሃኖም ይፋ እንዳደረጉት ለዚህ ውሳኔ ዋነኛው ምክንያት "በቻይና የተከሰተው ነገር ሳይሆን በሌሎች አገሮች እየሆነ ያለው ነው" ብለዋል። የዓለም የጤና ድርጅት የበሽታ ወረርሽኝ ተከስቶ ከዚህ አይነት ውሳኔ ላይ ሲደርስ ይህ ስድስተኛው ሲሆን ከዚህ ቀደም ኤችዋን ኤን ዋን የተባለው ኢንፍሉዌንዛ፣ ኢቦላ፣ ፖሊዮ፣ ዚካና በድጋሚ የተከሰተው ኢቦላ ምክንያት ነበሩ። በሽታው ሲጀምር በትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ተከትሎት ይከሰታል፤ ከዚያም ከሳምንት በኋላ የትንፋሽ ማጠርን በማስከተል አንዳንድ ህሙማንን የሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያስፈልጋቸው ሊያደርግ ይችላል። በአራት ሰዎች ላይ ከሚከሰተው ይህ በሽታ አንዱ እጅግ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ። በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ማስነጠስና የአፍንጫ ፈሳሽ ላይታይበት ይችላል። የኮሮናቫይረስ ቀለል ካለ የጉንፋን ምልክቶች አንስቶ እየከፋ ሲሄድ እስከሞት ሊያደርስ ይችላል። በሽታው የተያዙ ሰዎችን ለሞት እስከሚዳርጋቸው የተወሰነ ጊዜን ስለሚወስድ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች መካከል የተወሰኑት እስካሁንም ሊሞቱ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል። በተጨማሪም ምን ያህል እስካሁን ያልተመዘገቡ በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ አስቸጋሪ በመሆኑ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።
news-50709909
https://www.bbc.com/amharic/news-50709909
የቀድሞ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ መደፈሯን እንዳትናገር አባቷ እንደተጫኗት አሳወቀች
የቀድሞ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦብ ሃውኬ ልጅ እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1980ዎቹ ላይ ብትደፈርም የፖለቲካ ህይወታቸውን እንዳትጎዳ በሚል በምስጢርነት እንድትይዘው መገደዷን ከሰሞኑ ይፋ አድርጋለች።
ሮዝሊን ዲለን ውንጀላዋን ያቀረበችው ፍርድ ቤት መሆኑን የአውስትራሊያ ሚዲያ ዘ ኒው ደይሊ ዘግቧል። • ታዳጊዋ አንድን ግለሰብ ከጎርፍ ለማዳን ስትጥር ህይወቷ አለፈ • አምስቱ ተስፋ የተጣለባቸው አፍሪካውያን ሙዚቀኞች ደፋሪዋ ሌበር ፓርቲን ወክሎ የፓርላማ አባል የነበረው ቢል ላንደርዩ መሆኑንም ተናግራለች። አባቷም ሆነ ፖለቲከኛው ቢል ላንደርዩ በህይወት የሉም። የ59 አመቷ ሮዝሊን በአባቷ ንብረት ላይ የአራት ሚሊዮን ዶላር ይገባኛል ጥያቄም አንስታለች። በሰጠችው ምስክርነት ፖለቲከኛው የደፈራት ቢሮው ውስጥ ትሰራ በነበረበት ወቅት ነው። ሌሎች ሚዲያዎች እንደዘገቡት በተለያዩ ሶስት ጊዜያት መደፈሯን ነው። በሶስተኛው ጊዜ መደፈሯን ለአባቷ የተናገረች ሲሆን ለፖሊስ ልትከስ መሆኗን ብታሳውቀውም በወቅቱ የአባቷ ምላሽ " ወደ ፖሊስ መሄድ አትችይም። በአሁኑ ሰዓት ውዝግብ ውስጥ መግባት አልችልም። የሌበር ፓርቲን አመራር ለመቆጣጠር የስልጣን ፍትጊያዎች አሉ" እንዳላት የፍርድ ቤት መረጃዎች ያሳያሉ። እህቷም ሱ ፒተርስ ሃውክ ለኒውደይሊ እንደተናገረችው መደፈሯን ታውቅ እንደነበር ነው። • ለዓመቱ ምርጥ የታጨችው ኢትዮጵያዊት "በወቅቱ ለተለያዩ ሰዎች ተናግራ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ድጋፍ ሰጥተዋታል፤ ነገር ግን የትኛውንም የፍትህ ስርዓት ያሳተፈ አልነበረም" በማለት ቃሏን ሰጥታለች። ሌሎች የቤተሰቡ አካላት ምንም ከማለት ተቆጥበዋል። ቢል ላንደርዩ በፓርላማ አባልነት እንደ ጎርጎሳውያኑ ከ 1976-1992 አገልግሏል። ከአባቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦብ ሃውኬም ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበራቸው ተብሏል። በአውስትራሊያ ፖለቲካ ትልቅ ስፍራ የነበራቸውም ቦብ ሃውኬም አራት ጊዜ ምርጫዎችን ማሸነፍ ችለዋል ። በሃገሪቱም የኢኮኖሚ እንዲሁም የማህበረሰቡ ለውጦች ላይ ትልቅ ስፍራ ተጫውቷል ይባላል።
news-53216682
https://www.bbc.com/amharic/news-53216682
ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የሙከራ በረራ ሊያደርግ ነው
ቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላን በዚህ ሳምንት ወሳኝ የፍተሻ በረራ ያደርጋል።
በዓለም ዙሪያ ያሉ ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች እንዲቆሙ ተደርገዋል ምናልባትም ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆየው የማክስ 737 የበረራ ሙከራ የፋይናንስና የመልካም ስም እጦት ለገጠመው ቦይንግ አንድ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል። ሆኖም የዚህ የሙከራ በረራ ስኬታማነት ማክስ 737 ወደ ገበያ የመመለስ ዋስትናን አይሰጠውም። አውሮፕላኑ ወደ ገበያ ለመመለስ ገና በርካታ ሌሎች ፈተናዎችን ማለፍ ይጠበቅበታል። በቦይንግ ታሪክ ከፍተኛ ገበያ የነበረው ይህ የአውሮፕላን ሞዴል ሁለት ተከታታይ አደጋዎች ከደረሱበትና ተሳፋሪዎችም ከሞቱ በኋላ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባቱ ይታወሳል። በኢንዶኒዢያና በኢትዮጵያ አየር መንገዶች አውሮፕላኖች ላይ የደረሱ አደጋዎችን ተከትሎ የዚህ የማክስ 737 አውሮፕላን ግዢን የፈጸሙ፣ አውሮፕላኑን ሲጠቀሙ የነበሩ፣ አውሮፕላኑን ለመረከብ ሲጠባበቁ የነበሩና አዲስ ግዥ ለማድረግ ቀብድ የከፈሉ ጭምር ምርቱ ላይ ጥያቄ በማንሳታቸው ቦይንግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቶ ቆይቷል። ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚደረጉ በበራዎች ስኬታማ ቢሆኑ እንኳ ማክስ 737 ወደ ሰማይ ለመመለስ ገና በርካታ የደኅንነትና የምህድስና ፍተሻዎችን ማድረግ ይጠበቅበታል። ይህም ሂደት ከዚህ በኋላ በርካታ ወራትን ሊወስድ ይችላል ተብሏል። የአቪየሽን ተቆጣጣሪዎች ማክስ 737 ቦይንግ አውሮፕላንን ከበረራ ያገዱት የዛሬ 15 ወር ገደማ ሲሆን ይህም የላየን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ላይ በአምስት ወራት ልዩነት የደረሰውን እጅግ አሰቃቂ አደጋን ተከትሎ ነበር። በሁለቱ አደጋዎች በድምሩ 346 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የበረራ እግዱን ተከትሎ የ103 ዓመቱ አንጋፋው የቦይንግ ኩባንያ ላይ የካሳና የደኅንነት ጥያቄዎች አንዲነሱበት አድርጓል። በዚህም ሳቢያ ኩባንያው የከፋ ችግር ውስጥ ገብቶ እንደቆየ ይታወሳል። በተለይም የአሜሪካ የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር የአውሮፕላኖችን የበረራ ደኅንነት የሚፈትሽበት መንገድ ላይ በአጠቃላይ ጥያቄ እንዲነሳ ማድረጉ አይዘነጋም። ቦይንግ መጀመርያ አካባቢ የአደጋዎቹን ችግሮች ከራሱ ለማራቅ ከፍተኛ ሙከራ ሲያደርግ ቆይቶ ነበር። አደጋውን ተከትሎ የተደረጉ ጥብቅ ምርመራዎች ግን የማክስ 737 አውሮፕላኖች ስሪት ላይ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓታቸው አንዳች ግድፈት እንዳለበት የጠቆሙ ነበሩ። አሁን ማክስ 737 እነዚህ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓቶቹ ላይ ያደረገውን የምህንድስና ማሻሻያ ተከትሎ ማሻሻያው ምን ያህል ስኬታማ እንደሆነ ለማረጋገጥ መለስተኛ የበረራ ሙከራዎችን በዚያው በቦይንግ ማምረቻ ሲያትል አካባቢ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። በዚህ የሙከራ በረራ አብራሪዎች ሆን ብለው የማክስ 737 ግድፈት ነበረበት የተባለውን የኤምካስ ሶፍትዌር ቁልፍን በመጫን አውሮፕላኑ ራሱን በራሱ መቆጣጠር ይችል እንደሆን ይመለከታሉ ተብሏል። የአሜሪካ የበረራ ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት ለአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በላከው ደብዳቤ ዛሬ ለሚጀመረው የሙከራ በረራው ይሁንታ መስጠቱን አስታውቋል። በዚህ ደብዳቤ ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቱ እንደገለጸው የማክስ አውሮፕላኖች ወደ ሥራ እንዲመለሱ ገና ፈቃድ አልሰጠም። ይህ እንዲሆን ገና ብዙ የሙከራ ሂደቶች መታለፍ አለባቸው ብሏል። ይህ የሙከራ በረራ ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ባለፈው ዓመት ሲሆን በመሀሉ በአውሮፕላኑ ላይ አንዳች ሌላ ያልተጠበቀ ግድፈት በመገኘቱ ነበር በድጋሚ ሙከራው እንዲዘገይ የተደረገው። ይህ የሙከራ መለስተኛ በረራ ከተደረገ በኋላ በበራው ሂደት የተገኙ ቴክኒካዊ ነጥቦች አንድ በአንድ ይተነተናሉ፣ ይጠናሉ ተብሏል። ሙከራው እንከን አልባ ሆኖ ቢጠናቀቅ እንኳ ይህ አውሮፕላን በቀጥታ ወደ ሥራ ይመለሳል ማለት አይደለም። አብራሪዎችን ከአውሮፕላኑ ጋር እንዲዋሀዱ ለማድረግ የስልጠና መርሀ ግብር ይዘረጋል፣ የአውሮፓና የካናዳ የበረራ ተቆጣጣሪዎች ደግሞ ለዚህ አውሮፕላን እውቅናና ይሁንታ መስጠት ይኖርባቸዋል። የአውሮፓ አቪየሽን ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ማክስ 737 ከአሜሪካ የአቪየሽን አስተዳደር የጤናማነት እውቅና ተሰጥቶት ወደ ሥራ መመለስ ይችላል የሚል ሰርተፍኬት ቢሰጠው እንኳ ይህ አውሮፕላን በአውሮፓ ሰማይ ላይ ለመብረር ያስችለዋል ማለት አይደለም ብሏል። ከአውሮፓ የኖርዌይ አየር መንገድ፣ ቲዩአይ እና አይስላንድ አየር መንገድ ይህን የቦይንግ ምርት የሆነውን ማክስ 737 አውሮፕላን ይጠቀሙ የነበሩ ሲሆን ሌሎች አገሮች ደግሞ አውሮፕላኑ እንዲመረትላቸው አዘው ሲጠባበቁ የነበሩ ናቸው።
53864758
https://www.bbc.com/amharic/53864758
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መጠሪያውን እና የብሮድካስት መብቱን ሊሸጥ ነው
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ እንዲችሉ ጨረታ ማውጣቱን ገለፀ።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ፤ ማህበሩ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን ለመሸጥ አቅዶ ጨረታ ማውጣቱን ተናግረዋል። አንደኛው፤ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን በቴሌቪዥን ለማሰራጨት የብሮድካስቲንግ መብቱን ለመሸጥ በማሰብ የዓለም አቀፍ እንዲሁም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃኖች እንዲወዳደሩ ጨረታ ማውጣቱን ገልፀዋል። ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ኩባንያ የሚጠራበትን ስም ለመሸጥ ጨረታ ማውጣታቸውን አቶ ክፍሌ ሰይፈ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፉ 16 ቡድኖች በጋራ ያቋቋሙትና በንግድ ድርጅትነት የተመዘገበ ማህበር መሆኑን ሥራ አስኪያጁ አቶ ክፍሌ ጨምረው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምከንያት በዝግ ስታድየም የሚታይ ከሆነ፣ እንዲሁም ምርመራ እንዲደረግ ግዴታ የሚቀመጥ ከሆነ ተጨማሪ ወጪ ስለሚጠይቅ እነዚህን ነገሮች ለመሸፈን በማሰብ የተለየ አማራጭ ማሰባቸውን ጨምረው ተናግረዋል። ከሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ የአክሲዮን ማህበሩ አባል ቡድኖች ከመንግሥት ድጎማ ተላቅቀው ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ እንዲሁም በአፍሪካም ሆነ በአውሮፓ ደረጃ ያሉ የስፖርት ቡድኖች እንደሚያደርጉት የስፖርት ኢንቨስትመንት ውስጥ እንዲገቡ መነሻ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ከጨረታው የሚገኘው አብዛኛው ገቢ የሚሰጠው ለእግርኳስ ቡድኖቹ መሆኑን የተናገሩት አቶ ክፍሌ፣ ቀሪው የድርጅቱ ሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል ብለዋል። ማሕበሩ የተቋቋመው የእግር ኳስ ቡድኖቹ ከመንግሥት ድጎማ ነፃ እንዲወጡ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ በፕሪሚየር ሊጉ ከሚሳተፉ 16 ክለቦች መካከል ሁለቱ ቡድኖች ብቻ የራሳቸውን ወጪ በመሸፈን የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ደጋፊ አካላት (ስፖንሰርሺፕ) እንዳላቸው ገልፀዋል። ቀሪዎቹ 14 የእግር ኳስ ቡድኖች የከተማ ክለቦች ወይም ስፖንሰር የሌላቸው መሆናቸውን በመጥቀስ እነዚህን ቡድኖች በገቢ ራስን ማስቻል የዚህ ማህበር ቀዳሚ ዓላማ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቡድኖች ችግሮች እንዳለባቸው የሚጠቅሱት ኃላፊው፣ በአመራር ችግር ደሞዝ የማይከፈላቸው በመኖራቸው ከጨረታው የሚገኘው ገንዘብ አብዛኛው ለክለቦች እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህንን የገቢ ክፍፍልን በሚመለከት የማስፈፀሚያ ሰነድ ተዘጋጅቶ 16ቱም ክለቦች መስከረም ወር ላይ ውይይት ካደረጉበት በኋላ የሚፀድቅ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። ማህበሩ በርካታ ተጫራቾች እናገኛለን ብሎ ያሰበው ከዓለም አቀፍ ተጫራጮች መሆኑንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጨረታው ላይ የአገር ውስጥ ድርጅቶችም እንደሚሳተፉ የገለፁት አቶ ክፍሌ በሚወዳደሩበት ወቅት ምክረ ሃሳብ አዘጋጅተው ገቢ የሚያገኙበትን መልክ እና የድርሻ ክፍፍሉ ምን እንደሚመስል ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፟። በኢትዮጵያ እግርኳስ ረዥም ታሪክ ቢኖረውም፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ከማይሸጥባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት።
47770243
https://www.bbc.com/amharic/47770243
በወሲብ ፊልሞች ሱሰኛ የሆኑ ወጣት ሴቶች
ኔላም ቴለር የወሲብ ፊልሞችን ማየት የጀመረችው በ12 ዓመቷ ነበር። ገና አንድ ፍሬ ልጅ በምትባልበት ጊዜ። በመኝታ ክፍሏ ተደብቃ አጠር ያለ የአስር ደቂቃ የወሲብ ፊልም ማየት የጀመረችው በለጋ እድሜዋ ነው።
ኋላ ላይ እስከ አንድ ሰዓት ርዝማኔ ያላቸው ምስሎችን ማየት ጀመረች። በጊዜው ከቤተሰቦቿ ተደብቃ ታይ እንደነበር የምትናገረው ኔላም ለመጀመሪያ ጊዜ የወሲብ ፊልም ስታይ "የፍቅር ፊልሞች ወሲብን የተቀደሰና በፍቅር የተሞላ አድርገው ነበር አዕምሮዬ ላይ የሳሉት፤ ልክ በወንዶች ሃያልነት የተሞላና አካላዊ ተራክቦው የጎላበትን ምስል ማየት በጣም ነው ያስደነገጠኝ" ትላለች። የወሲብ ምስሎችን ማየት የጀመረችበትን ሰበብ ስታስታውስ ጉዳዩን ለማወቅ ከነበራት ፍላጎት ወይም ለአቅመ-ሔዋን እየደረሰች ስለነበረ የአፍላ ጉርምስና ግፊት ይሆናል በማለት ትናገራለች። ከጊዜ በኋላም የተለያዩ የወሲብ ምስሎችን ከማየቷ የተነሳ የራሷ ምርጫዎች እያዳበረች መጣች። • የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት • የወንድ የእርግዝና መከላከያ፤ ለምን እስካሁን ዘገየ? "ወጣት ሴቶች በዕድሜ ገፋ ካሉ ወንዶች ጋር ሆነው ለሚሰሩ የወሲብ ምስሎች ልዩ ስሜት አደረብኝ። ሴቶቹ ታዛዥ ሆነው ወንዶቹ የበላይ የሆኑባቸውን ምስሎች በ13 ዓመቴ መፈለግ ጀመርኩ" የምትለው ኔላም ይህ ፍላጎቷ ብዙ የወሲብ ምስል ከማየቷ የተነሳ ይሁን ወይም ተፈጥሯዊ የሆነ ስሜት መለየት ይከብዳታል። የ25 ዓመቷ ሳራም ከኔላ የተለየ ልምድ የላትም። የወሲብ ምስሎችን ማየት የጀመረችው በ13 ዓመቷ ነበር፤ ለዚያውም በሳምንት ሁለት ጊዜ። "10 ወንዶችና 1 ሴት፤ በውስጡም ብዙ የወንዱን የበላይነት የሚያሳዩ እንቅስቃሴዎች የተካተቱበትን ምስሎች ያየሁት የሩካቤስጋ መፈፀም ከመጀመሬ በፊት ነው " የምትለው ሳራ አሁን በ25 አመቷ ወደ ወሲብ ስሜት ለመግባት በጣም እንደሚከብዳት ትናገራለች። እስካሁን የወሲብ ምስል ሱስ በወንዶች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ በደንብ የተጠና ሲሆን፤ በሴቶች ላይ ያለው ጫና ግን በውል አልተጠናም። ብዙ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ሴቶች የወሲብ ምስልን እንደሱስ እንደማይጠቀሙትና በእነርሱ ላይ ብዙም ተፅዕኖ እንደሌለው ይናገራሉ። በዚህ የሕይወት መንገድ ላይ ያለፉ ሴቶች ግን ተመሳሳይ መልስ አይሰጡም። ዶ/ር ለይላ ፈሮድሻ የፅንስና የማህፀን አማካሪ ስትሆን በ20 ዓመት የስራ ልምዷ "አንድም የማያቸው የወሲብ ምስሎች ችግር እየፈጠሩብኝ ነው" ብላ የመጣች ሴት አጋጥማት እንደማታውቅ ትናገራለች። በጉዳዩም በደንብ ጥናት እንዳልተደረገበት የምትናገረው ለይላ "ሴቶች አካላዊና ስለ ልቦናዊ ጥቃት እየደረሰባቸው ነገርግን የሐኪም እርዳታ እየጠየቁ ስላልሆነ ነው? ወይስ ስለደረሰባቸው ችግር ለመናገር አፍረው? ወይስ ምንም ችግር እየፈጠረባቸው አይደለም?" በማለት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ታቀርባለች። ኔላም 16 ዓመቷ ሲሆን የወሲብ ምስሎችን ማየት አቆመች፤ ለዚህ ደግሞ ሰበብ የሆናትን ስትጠቅስ ምስሎቹ ተፈጥሯዊ ያልሆነ ከፍተኛ ስሜት ውስጥ ስለሚከቱ ነው ትላለች። ከእውነታው እያራቀች እንደነበር የምትገልፀው ኔላም "የወሲብ ምስል አይቼ የማገኘው የስሜት እርካታና ከጓደኛዬ ጋር ከወሲብ በኋላ ያለኝ ስሜት ያላቸው ልዩነት ያስፈራኝ ነበር።" አሜሪካዊቷ ፀሃፊ ኤሪካ ጋርዛ የወሲብ ምስል ማየት የጀመረችው በ12 ዓመቷ እንደሆነ ስትናገር "ትምህርት ቤት ያላግጡብኛል፤ ብዙ ጊዜም ብቸኛ ነበርኩ። ስለዚህም የወሲብ ምስሎችን ችግሬን የምረሳበትና እራሴን የማስደስትበት ነገር ነበር" ትላለች። ኤሪካ የወሲብ ምስሎችን ማየቷ በጣም ጫና እንዳደረሰባትና ለአንዳንድ የተለዩ የወሲብ መንገዶች የተለየ ስሜት እንዲኖራት እንዳደረገ ትናገራለች። በወሲብ ጊዜ ወንዱ ጉልበተኛና እኔን እንደፈለገ ማድረግ እንደሚችል ዓይነት ስሜቶችን እንድቀበል አድርጎኛል የምትለው ኤሪካ "ወንዶቹ ከሴቶቹ በዕድሜ ትልቅ የሆኑባቸውን ምስሎች ማየቴም ወንዶች በወሲብ ጊዜ ጉልበተኛ እንዲሆኑ እንድፈልግ አድርጎኛል" ስትል ታስረዳለች። ኔላምም በተመሳሳይ መልኩ የወሲብ ምስሎችን በለጋ ዕድሜዎ ማየቷ ወሲብን የምታይበትን መንገድ እንደቀየረው ትናገራለች። " 17 ወይም 19 እድሜዬ ላይ ስደርስ ታላቆቼ ከሆኑ ጋር ግንኙነት መፍጠር ጀመርኩ። ይህ ሁኔታዬ የተፈጥሮ ባህሪዬ ይሁን የወሲብ ምስል ማየቴ የፈጠረው ለማወቅ አልችልም" ትላለች። እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገ የ300 የወሲብ ምስሎች ግምገማ 88 በመቶ የሚሆኑት አንዱ ፆታ በወሲብ ላይ ያለውን የበላይነትን የሚያመላክቱ ሲሆን ብዙዎቹም የወንዶች የበላይነት ናቸው። በምስሎቹም ሴቶቹ በወንዶቹ ባህሪ በደስታ ወይም ከስሜት ነፃ በሆነ መልኩ እንደሚመልሱ ያሳያሉ።
news-56144583
https://www.bbc.com/amharic/news-56144583
ኮሮናቫይረስ፡ የትኞቹ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት ጀመሩ? ሌሎቹስ መች ይጀምራሉ?
በአህጉረ አፍሪካ ቢያንስ 100 ሺህ ያክል ሰዎች እስካሁን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አህጉሪቱ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በተገቢው መንገድ እየሰጠች አይደለም እየተባለች ትታማለች።
ለመሆኑ የትኞቹ የአህጉሪቱ ሃገራት ናች ክትባት መስጠት የጀመሩት? የዓለም ሃገራት የኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት ፉክክር ላይ ናቸው። የአፍሪካ ሃገራት ግን ሃብታም ከሚባሉት ሃገራት ጋር ሲነፃፀር ወደኋላ የቀሩ ይመስላሉ። "በጣም ተጋላጭ የሆኑ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት የማግኘት ተራቸው እስኪደርስ ድረስ እየጠቁ ነገር ግን እምብዛም ተጋላጭ ያልሆኑ ሃብታም ሃገራት ክትባቱን ሲያገኙ ማየት ፍትሃዊ አይደለም" ይላሉ በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞዬቲ። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማኽሮ የአውሮፓና ሃገራትና አሜሪካ ከክትባቶቻቸው ቀንሰው ለአፍሪካ ሃገራት መስጠት አለባቸው ሲሉ ምክረ ሐሳብ አመንጭተው ነበር። የተወሰኑ ክትባቶች ለአፍሪካ ሃገራት በፍጥነት ሊዳረሱ ይገባል ይላሉ ፕሬዝደንቱ። አፍሪካ ውስጥ እስካሁን ድረስ ክትባት ማግኘት የቻሉት ከፋብሪካዎች በቀጥታ መግዛት የቻሉና ከሩስያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ በእርዳታ መልክ ያገኙ ሃገራት ናቸው። የአፍሪካ ሃገራት በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ፕሮግራሞች ክትባት ለማግኘት ተስፋ አድርገዋል። አንደኛው ፕሮግራም ኮቫክስ የተሰኘው ነው። ይህ ፕሮግራም ሁሉም ሃገራት ክትባት ያገኙ ዘንድ ያለመ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ከያዝነው የፈረንጆች ወር መጨረሻ ጀምሮ የአፍሪካ ሃገራት ክትባት ማግኘት ይጀምራሉ ብሎ ይገምታል። በዚህ ወቅት የሚሠራጩ 90 ሚሊዮን ክትባቶች የአህጉሪቱን 3 በመቶ ሕዝብ ይከትባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ክትባት በጣም ተጋላጭ ለሆኑና በቫይረሱ ምክንያት የበለጠ አደጋ ለሚደርስባቸው እንደ ጤና ባለሙያዎች ላሉ የሕብረተሰብ አካላት የሚከፋፈል ነው። የኮቫክስ ዓላማ 600 ሚሊዮን ክትባት ማግኘት ነው። ይህ የክትባት መጠን በፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ ባለው የአህጉሪቱን 20 በመቶ ሰው ይከትባል። የአፍሪካ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ኃላፊ ጆን ንኬንጋሶንግ ግን ይህ የክትባት መጠን በሽታውን ከአፍሪካ ነቅሎ ለማስወጣት በቂ ነው ብለው አያምኑም። እሳቸው እንደሚሉት የአፍሪካ ሃገራት ቢያንስ 60 በመቶ የሚሆነውን ሕዝባቸውን መከተብ አለባቸው። የአፍሪካ ሕብረትም በሃምሳ አምስቱ የአፍሪካ ሃገራት ስም ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና እያለ ነው። የአፍሪካ ሞባይል ኔትወርክ አቅራቢ ድርጅት የሆነው ኤምቲኤን 25 ሚሊዮን ዶላር በማዋጣት ለአፍሪካ የጤና ባለሙያዎች የሚሆን ሰባት ሚሊዮን ክትባት ለማግኘት እየጣረ ነው። የበሽታ ቁጥጥር ማዕከሉ እንደሚለው በኤምቲኤን በኩል የተገኘ አንድ ሚሊዮን ክትባት ለ20 ሃገራት በያዝነው ወር መጨረሻ ይከፋፈላል። የትኞቹ ሃገራት ቀድመው ክትባቱን እንደሚያገኙ ግን የተባለ ነገር የለም። ዜጎቻቸውን መከተብ የቻሉ ሃገራት የትኞቹ ናቸው? ምንም እንኳ ጥቂት ሃገራት ባለፈው ወር ክትባት መስጠት ቢጀምሩም አብዛኛዎቹ ሃገራት ግን ገና አልጀመሩም። በሰሜን አፍሪካ ክትባት መስጠት የጀመሩት ሃገራት ሞሮኮ፣ አልጄሪያና ግብፅ ናቸው። ከሰሃራ በታች ባሉ አፍሪካ አገራት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሼልስ፣ ሩዋንዳ፣ ሞሪሺዬስና ዚምባቡዌ ይገኛሉ። እንደ ኢኳቶሪያል ጊኒና ሴኔጋል ያሉ ሃገራት የመጀመሪያውን ዙር የሳይኖፋርም ክትባት ተቀብለዋል፤ መከተብ ግን አልጀመሩም። በአህጉሪቱ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችው ደቡብ አፍሪካ አስትራዜኔካ የተሰኘውን ክትባት ለመከተብ ዕቅድ ይዛ ነበር። ነገር ግን ክትባቱ በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ላይ ያለው ኃያልነት አናሳ ነበው በሚል ሰርዛዋለች። ነገር ግን አሁን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ከተሰኘው ፋብሪካ የተገኘው ክትባት ለአዲሱ ዝርያ ፍቱን ነው በሚል መከተብ ጀምራለች። ደቡብ አፍሪካ ከሕንዱ አቅራቢ ያገኘችውን አድን ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባት ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት መጠቀም ከፈለጉ በሚል ለአፍሪካ ሕብረት ሰጥታለች።
49930435
https://www.bbc.com/amharic/49930435
"የረሃብ አድማን የመረጥነው ከራሳችን የምንጀምረው ተቃውሞ ስለሆነ ነው" አቶ ገረሱ ገሳ
መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ፣ አንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲን ጨምሮ 70 የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫና ፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን በመቃወም የፊታችን ጥቅምት 5 እና 6 የረሀብ አድማ ለመምታት እንዳሰቡ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ ሰብሳቢ እና የ 70ዎቹ ፓርቲዎች አስተባባሪ ኮሚቴ ጸሀፊ አቶ ገረሱ ገሳ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቅርቡ በሰጣችሁት መግለጫ ላይ ለሁለት ቀንየረሃብ አድማ እናደርጋለን ብላችኋል። የረሃብ አድማ ለማድረግ የወሰናችሁት ለምንድን ነው? አቶ ገረሱ ገሳ፡ የረሃብ አድማውን ለማድረግ የተነሳንበት ምክንያት በምርጫና በፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ የተነሳ ነው። በአዋጁ ላይ ለመንግሥት፣ ለምርጫ ቦርድም አዋጁ ትክክለኛ ያልሆነና የሚያሰራ ስላይደለ እንዲሁም የፖለቲካ ስነ ምህዳሩን የሚያጠብ ስለሆነ፣ ተስተካክሎ መውጣት እንዳለበት በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበናል። ከዚህ በፊት ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከአንድም ሁለት ጊዜ የአዋጁ ረቂቅ ቀርቦ ተወያይተውበት ነበረ። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች • "ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ነገር ግን ፓርቲዎቹ የተወያዩበት ረቂቅ ተቀይሮ ሌላ ረቂቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ነው የፀደቀው። ስለዚህ ይኼ በአጠቃላይ በፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ማታለልም ጭምር ስለሆነ ይህንን በመቃወም ነው። ሕጉ እንዳይፀድቅ አስቀድመን ተቃውመናል። ለተለያዩ መንግሥታዊ አካላት አሳውቀናል። ግን ተቀባይነት አጥቶ አዋጁ ፀድቋል። አሁን ደግሞ የምንቃወመው አዋጁ ሥራ ላይ እንዳይውል ነው። ሙሉ አዋጁን ነው የምትቃወሙት ወይስ ለይታችሁ በመነጠል የምትቃወሟቸው አንቀጾች አሉ? አቶ ገረሱ ገሳ፡ አዋጁ ላይ የምንቃወማቸው በርካታ አንቀጾች አሉ። አሁን እኛ የምናስተባብረው የፖለቲካ ፓርቲ በአንድ ላይ ከ30 በላይ አንቀጾች ላይ፣ መሰረዝ፣ መሻሻል ያለባቸው አንቀጾችን እና ማስተካከያ መደረግ ያለባቸውን አንቀጾች ለይተን በዝርዝር ከነዝርዝር ሀሳቡ አቅርበናል። ለምርጫ ቦርድ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለሕግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ለፓርላማ አፈ ጉባዔ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩም፣ ለሀገሪቱ ፕሬዝደንትም፣ ለፌዴሬሽን አፈ ጉባዔ ጭምር ዝርዝሩን በሙሉ አቅርበናል። ሕጉ ላይ ያለውን እንከንና ችግር ማለት ነው። ያንን ሁሉ አድርገን የሚሰማን አካል ጠፋ። ከእኛ ከፖለቲካ ፓርቲዎች በተጨማሪ በተለያዩ አካላት በአዋጁ ላይ የቀረቡ ከ90 ባላነሱ አንቀጾች ላይ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማሻሻያ ጥያቄ ቀርቧል። ይህንን ሁሉ እንከን ይዞ ነው እንግዲህ አዋጁ የፀደቀው። ስለዚህ አዋጁ ላይ የማያሰሩ፣ የፖለቲካ ስነ ምህዳሩን የሚያጠቡ፣ የዜጎችን የመደራጀት መብት የሚገድቡ፣ እንዲሁም የመምረጥና የመመረጥ መብትን የሚያሳጡ፣ አንቀጾች ስላሉ እነዚህ አንቀጾች እንዲሻሻሉና እንዲቀየሩ ነው ተቃውሟችን። ለምን የረሃብ አድማን መረጣችሁ? አቶ ገረሱ ገሳ፡ የረሃብ አድማን የመረጥነው ከራሳችን የምንጀምረው ተቃውሞ ስለሆነ ነው። ከራሳችን ከአስተባባሪ ኮሚቴዎቹና፣ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ከራሳችን የሚጀምር ተቃውሞ ስለሆነ ነው። የረሃብ አድማው ላይ ጥሪ ያደረግነውም በመጀመሪያ ደረጃ ለሁሉም የፖለቲካ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም በዚህ ተቃውሞ ለተሳተፉ 70 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ አባላትና አመራሮች ነው። ከዚያ ውጪ ደግሞ ፈቃደኛ የሆነ የሕብረተሰብ አካል ተቃውሞውን መቀላቀል ይችላል። ስለዚህ ከራሳችን የምንጀምረው ተቃውሞ ስለሆነ ነው። መቼ ነው አድማውን ማካሄድ ያሰባችሁት? አቶ ገረሱ ገሳ፡ ጥቅምት አምስት እና ስድስት። ግን አንድ የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ አለ። ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ በመስከረም ወር ውስጥ ከአንድም ሁለት ሶስት የሥራ ቀናት አሉት። በእነዚህ ቀናት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ የሥራ ቀናት ማክሰኞና ሐሙስ እንደሆነ ይታወቃል፣ ስለዚህ በእነዚህ የስራ ቀናት ውስጥ አዋጁ ላይ ያለውን ችግር መልሶ የማያይና ይህንን የአስተባባሪ ኮሚቴ ጠርቶ የማያነጋግር ከሆነ ነው የረሃብ አድማውን የምናካሂደው። ነገር ግን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጁን እንደገና ለማየትና ለማሻሻል የሚወስደው እርምጃ ካለ የረሃብ አድማው ላይቀጥል ይችላል ማለት ነው። ስለዚህ ይህንን አንድ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠናል። የረሃብ አድማው በመላ ሀገሪቱ ነው የሚካሄደው? ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሳተፋሉ? ለምን ያህል ሰዓትስ ይቆያል? አቶ ገረሱ ገሳ፡ የረሃብ አድማው በአዲስ አበባ ደረጃ፣ የአስተባባሪ ኮሚቴውና በሰባዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የታቀፉት አመራሮችና ተወካዮች በአንድ ቦታ ተሰብስበን ነው የረሃብ አድማውን የምናደርገው። በክልል ደረጃ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በያሉበት፣ በተደራጁበት አካባቢ ሆነው አመራሮቻቸው፣ ደጋፊዎቻቸውና አባሎቸቻቸው በረሃብ አድማው ይሳተፋሉ ማለት ነው። ከዚያ ውጪ በረሃብ አድማው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ዜጋ በየስራውም ቦታ በየቤቱም ሆኖ የረሃብ አድማውን መቀላቀል ይችላል። ይህ ማለት ለዲሞክራሲ፣ ለሰብዓዊ መብት፣ ለነፃነት፣ ለእኩልነት የሚደረግ፣ ለእኛም ለህዝብም የሚደረግ ትግል መስዋዕትነት ስለሆነ ማንኛውም ዜጋ የረሃብ አድማውን በተመቸው ስፍራ ሊቀላቀለን ይችላል። ለምሳሌ አዲስ አበባ የት ነው የረሃብ አድማው የሚካሄደው? አቶ ገረሱ ገሳ፡ በዋናነት ዋና አስተባባሪው የረሃብ አድማውን የሚያደርገው አዲስ አበባ ነው፤ ቦታውን ግን ከመስከረም 27 በኋላ ነው ይፋ የምናደርገው። ለ48 ሰዓታት የሚቆይ የረሃብ አድማ ነው የሚሆነው? አቶ ገረሱ ገሳ፡ አንዳንድ ታሳቢ የሆኑ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ በጤና እክል ምክንያት መድሃኒት በመውሰድ ላይ ያሉ፣ ምግብ በተወሰነ ሰዓት መመገብ ያለባቸው አመራሮችና ተወካዮች ሊኖሩ ይችላሉ፤ እነዚህ አካላት በዚህ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉበት ሁኔታ የተገደበ ነው። በተገደበና በተመጠነ መልኩ ነው የሚሳተፉት። ከዚያ ውጪ ጤናማ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ በሐኪም ልዩ ትዕዛዝ የሌላቸው 48 ሰዓት ከቻሉ ደግሞ መቀጠልም ይችላሉ። ውሃስ መጠጣት ይቻላል? አቶ ገረሱ ገሳ፡ ዝርዝር ሁኔታውን ውሃና መድሃኒትን በሚመለከት መስከረም 27 እና ከዚያ በኋላ ይፋ እናደርጋለን። በአድማው ላይ 48 ሰዓት መቆየት ሳይችሉ ቀርተው ተዝለፍልፈው ቢወድቁ ለእንደዚህ ዓይነት ድንገተኛ አደጋዎች ምን ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል? አቶ ገረሱ ገሳ፡ ለእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ቅድመ ሁኔታዎች እየተሰሩ ነው ያሉት። ምንድን ነው የምናደርገው? ምን ዓይነት ባለሙያዎች እናዘጋጃለን? የሚለው እየተሰራ ነው ያለው። የሕክምና ባለሙያዎችን፣ አስፈላጊ የምክር ባለሙያዎችንም፣ እያዘጋጀን ነው ያለነው። ይኼጉዳይሰባዎቹም የፖለቲካ ፓርቲዎች የተስማማችሁበትነው? አቶ ገረሱ ገሳ፡ አዎ። የተስማማንበት ጉዳይ ነው። ስምምነቱ ግን አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ነፃነትን ይከለክላል ማለት አይደለም። እስከዚያ ድረስ 'አይ እኔ በዚህ ስምምነት መቀጠል ያስቸግረኛል' የሚል ካለ ነፃነቱ የተጠበቀ ነው። መጀመሪያ እኛ ሂደቱን ስንጀምር በ33 ፓርቲዎች ነው የጀመርነው። ከዚያ በኋላ ሌሎች ፓርቲዎች ተቃውሞው ትክክል ነው ብለው እያመኑ ሲመጡና ሲቀላቀሉ ነው ቁጥሩ ጨምሮ ሰባ የደረሰው። • ምርጫ ፡ የተቃዋሚዎችና የመንግሥት ወግ? • ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ለሚካሄደው ምርጫ 3.7 ቢሊዮን ብር ጠየቀ ስለዚህ በፈቃዳቸው መጥተው እንደተቀላቀሉን በፈቃዳቸው ደግሞ አንሳተፍም ካሉ የምናስገድድበት ሁኔታ የለም። መቼ ነበር በ33 ፓርቲዎች ተቃውሞውን የጀመራችሁት? አቶ ገረሱ ገሳ፡ ተቃውሞውን ከጀመርን ሶስት ወር አካባቢ ይሆነናል። እነማን ናቸው ፓርቲዎቹ ለምሳሌ ቢጠቅሱልኝ? አቶ ገረሱ ገሳ፡ እኔ ሰብሳቢ የሆንኩበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ፣ መኢአድ፣ ኦብኮ፣ የገዳ ስርኣት አራማጅ ፓርቲ፣ ከኦሮሚያ ክልል ወደ ስድስት ፓርቲዎች፣ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ፣ የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር፣ እነዚህና አሁን ስማቸውን ዘርዝሬ የማልጨርሳቸው ፓርቲዎች አሉ። ከውጪ ከመጡ ፓርቲዎች መካከል አስር ፓርቲዎች ከእኛ ጋር በምናደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ አሉ። የረሃብ አድማ ግን ምን ያሕል አዋጭ ነው ለፖለቲካ ትግላችሁ? አቶ ገረሱ ገሳ፡ የረሃብ አድማ ምን ያህል አዋጭ ነው? የሚለው ሕሊና ያለው አካል፣ ለሕዝብ ደንታ ያለው አካል፣ የሕዝብ ብሶት፣ ሮሮ፥ ጥያቄ፣ ሊሰማና ሊደመጥ ይገባል የሚል መንግሥታዊ ሥልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ካለ፣ ከረሃብ አድማ በላይ አስከፊና አስነዋሪ ተቃውሞ የለም። በጣም አስከፊ ተቃውሞ ነው። መስማት፣ማዳመጥ የሚችል አካል ካለ። አንድ ሰው ራሴን ለረሃብ አጋልጣለሁ ሲል እሞታለሁ ከሚል በምንም አይተናነስም። ስለዚህ ወደዚህ ተቃውሞ የሚገቡ አካላት ለምንድን ነው ወደዚህ ተቃውሞ የሚገቡት ማለትና መስማት የሚችል ባለስልጣን በሀገራችን ካለ፣ ዲሞክራት መሪ ካለ ይኼ ተቃውሞ መንግስት ሊሰማውና ሊያዳምጠው የሚገባው ተቃውሞ ነው። ነገር ግን መንግሥት ላይ ድንጋይ እንደመወርወር፣ ጥይት እንደመተኮስ ወይንም የሆነ ተቋም እንደማቃጠል፣ አስደንጋጭ ላይሆን ይችላል። አምባገነን መንግሥታት ጥይት ሲተኮስባቸው፣ ድንጋይ ሲወረወርባቸውና የሆነ የሚፈነዳ፣ የሚያቃጥል ነገር ሲመጣ ነው የሚደነግጡት። ለእንደዚህ ዓይነት ሌላ ተቃውሞ ጆሮም ግድም አይሰጡም። ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ካለ ግን ከጥይት ጩኸትና ከቦምብ ፍንዳታ በላይ ይህ ትክክለኛ ተቃውሞ ነው። ለዚህ ነው እኛ እንደተቃዋሚ ይህንን የረሃብ አድማ መጀመሪያ በራሳችን የምንጀምረው። በመቀጠልም ደረጃ በደረጃ የምንሄድነበት መሆኑን አስበን ነው የገባነው። ለረሃብ አድማው ምላሽ ካልተሰጣችሁ ምንድን ነው የምታደርጉት? አቶ ገረሱ ገሳ፡ በመላ ሀገሪቱ የተቃውሞ ፊርማ የማሰባሰብ እርምጃ ነው የምንሰራው። ከዚያ ጎን ለጎን ደግሞ ከተፈቀደልን በተለያዩ ስፍራዎች ሕዝባዊ ስብሰባዎች እንጠራለን። በእነዚህ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ተቃውሞ የምናካሂድበትና አደባባይ ወጥተን ሰላማዊ ሰልፍ የምናካሄድበትን ሂደት እንከተላለን። ይኼ ደረጃ በደረጃ የምንከተለው ነው።
news-55211960
https://www.bbc.com/amharic/news-55211960
ኮሮረናቫይረስ፡ የትራምፕ ጠበቃ በኮቪድ-19 ተይዘው ሆስፒታል ገቡ
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የግል ጠበቃና የቀድሞው የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ሩዲ ጁሊያኒ በኮቪድ-19 ከተያዙ በኋላ ወደ ሆስፒታል መግባታቸው ተገለጸ።
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒ ፕሬዝደንት ትራምፕ የጠበቃቸውን ሆስፒታል መግባት በማስመልከት ጠበቃው ቶሎ እንዲሻላቸው ምኞታቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል። ጠበቃው ጁሊያኒ ከምርጫው በኋላ የትራምፕን የፍርድ ቤት ክርክር ሲመሩ የቆዩ ናቸው። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የ76 ዓመቱ ጠበቃ ሕመም ጸንቶባቸው ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሜድስታር ጆርጅታዎን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል እንዲገቡ መደረጉን በስፋት ዘግበዋል። የቀድሞ የኒው ዮርክ ከተማ ከንቲባ የአሁኑ የፕሬዝዳንቱ ጠበቃ መልካም ምኞት የገለጹላቸውን አመስግነው ከሕመማቸው እያገገሙ እንደሆነ ገልጸዋል። በዋይት ሐውስ የሚሰራው የጠበቃው ልጅ አንድረው ጁሊያኒ ወላጅ አባቱ እረፍት እያደረጉ እና እየተሻላቸው መሆኑን ገልጿል። ጠበቃው ጁሊያኒ የትኞቹን የበሽታው ምልክቶች እያሳዩ እንደሆነ አልተገለጸም። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አሃዝ ከሆነ በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 14.6 ሚሊዮን የተቃረበ ሲሆን ከ281 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሕመሞች ሕይወታቸው አልፏል። ይህም በዓለማችን ከፍተኛው ነው። ጠበቃው የምርጫውን ውጤት ለማስቀየር ወደ በርካታ ግዛቶች ተዘዋውረዋል። በጉዟቸው ወቅትም ጁሊያኒ የኮሮናቫይረስ ክልከላዎችን ሲተላለፉ ታይተዋል ተብሏል። የአፍ እና አፈንጫ መሸፋኛ ሳይደርጉ እና ርቀታቸውን ሳይጠበቁ ጁሊያኒ ተስተውለዋል። ባሳለፍነው ሐሙስ ጆርጂያ ግዛት የነበሩት ጁሊያኒ፤ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ በጆርጂያ የተካሄደው ምርጫ ተጭበርብሯል ሲሉ ከሰው ነበር። ጠበቃውን ጨምሮ በርካታ የትራምፕ የቅርብ አማካሪዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ቦሪስ ኢፕስታይን እና ኬይሊ ማኬንሊ በቅርቡ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ የፕሬዝዳንት ትራምፕ የቅርብ አማካሪዎች ናቸው።
53188955
https://www.bbc.com/amharic/53188955
ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የ114 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ ማን ናቸው?
ሐሙስ እለት ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ዳይሬክተር የፌስቡክ ሰሌዳ ላይ የተገኘው መረጃ አንድ የ114 ኣመት አዛውንት ከኮሮና ማገገማቸውን የሚያበስር ነበር።
ግለሰቡ ከኮሮናቫይረስ ቢያገግሙም ለተጨማሪ ሕክምና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል መላካቸው በዚሁ መልዕክት ላይ ሰፍሯል። የካቲት 12 ሆስፒታልም የጀመሯቸውን ሕክምናዎች ጨርሰው ያለመሳርያ እገዛ መተንፈስ በመጀመራቸው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን ትናንት ያነጋገርናቸው የሕክምና ተቋሙ ባለሙያዎች አረጋግጠውልናል። እንዲሁም የልጅ ልጃቸው ቢንያም ለቢቢሲ እንዳረጋገጠው በሙሉ ጤንነት ላይ ሲሆኑ ሆነው በቤታቸው ይገኛሉ። ለመሆኑ እኚህ የ114 ዓመት አዛውንት ማን ናቸው? ከኮሮና ያገገሙት የእድሜ ባለፀጋ አባ ጥላሁን ይባላሉ። ወደ እርሳቸውጋር ስንደውል ገና ከሆስፒታል መውጣታቸው ስለነበር ቃለምልልስ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ አልጠነከሩም። ስለዚህ ከጎናቸው ሆኖ የሚንከባከባቸው የልጅ ልጃቸው ቢንያም ልኡልሰገድም ስለእርሳቸው አጫውቶናል። አባ ጥላሁን የተወለዱት በቡልጋ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ የመጡት በልጅነታቸው ነው። በአሁን ሰዓት የሚኖሩት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 25 ። አባ ጥላሁን ወደ አዲስ አበባ በመጡበትና ኑሯቸውን በመሰረቱበት ወቅት በተለያዩ ስራዎች በመሰማራት ሕይወታቸውን መግፋታቸውን ቢንያም ይናገራል። የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎችን መስራት፣ ቀለም በመቀባት የእለት ገቢያቸውን ማግኘት ብቻ ሳይሆን ነየተካኑበት ሙያቸው ነበር። በርግጥ ጊዜውን በውል ባያስታውሱትም ከባድ የሆነ የኤሌክትሪክ አደጋ አጋጥሟቸው ስራውን ማቆማቸውንም ቢንያም ለቢቢሲ ጨምሮ አስረድቷል። ከዓመታት በኋላ ባለቤታቸው ሲሞቱና የልጅ ልጃቸው ሲወለድ አባ ጥላሁን መነኮሱ። በአሁን ሰዓት አብሯቸው የሚኖረው የልጅ ልጃቸው በቅርብ እንክብካቤም የሚያደርግላቸው መሆኑን ይናገራል። አባ ጥላሁን ሳል ይዟቸው መኖሪያ ሠፈራቸው በሚገኘው ጤና ጣብያ ሲታከሙ እነደነበር የሚገልፀው ቢንያም፣ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረግላቸው በቫይረሱ በመያዛቸው በመታወቁ ወደ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በመወሰድ ህክምና ክትትል ጀመሩ። ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የተለያዩ ሕሙማን ማረፊያ ክፍሎች እንዳሉት ይናገራል። አባ ጥላሁን ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ሕሙማን የሚታከሙበት ክፍል የነበሩ ሲሆን በሆስፒታሉ የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች የቅርብ ክትትልና እገዛ እንዳደረጉላቸው ይመሰክራል። በሆስፒታሉ ገብተው ቤተሰቦቻቸውን ማስታመም የማይፈቀድላቸው ግለሰቦች የቤተሰቦቻቸውን ዜና የሚያቀብል፣ የሚያመጡላቸውን ምግብና የሚጠጣ ነገር ተቀብሎ የሚያደርስ ሰው መመደቡንም ያስረዳል። የህክምና ክትትል ያደረጉላቸው ባለሙያዎች ምን ይላሉ? አባ ጥላሁንን በቅርበት ካከሟቸው የሕክምና ባለሙያዎች መካከል አንዱ ዶ/ር ሕሉፍ አባተ ነው። ዶ/ር ሕሉፍ ፣ አባ ጥላሁን እድሜያቸው 114 መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ማግኘት ይከብዳል ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። በእርሳቸው እድሜና ትውልድ ውስጥ የሚገኝ ግለሰብ የልደት ሰርተፍኬት እንዲሁም ሌሎች የእድሜ ማረጋገጫዎችን ማቅረብ ስለማይችል በሰነድ ማረጋገጥ ከባድ ነው ሲልም ሃሳቡን ያጠናክራል። ነገር ግን ይላል ዶ/ር ሕሉፍ በእርሳቸው እድሜ የሚገኝ ሰው የእጅና እግር መገጣጠሚያዎች እና ጡንቻዎች በማየት እድሜያቸው ከ100 በላይ መሆኑን እርግጠኛ እንደሚሆን ይመሰክራል። አባ ጥላሁን በቲቢ ተጠቅተው ስለነበር ተደጋጋሚ ምርመራ ተደርጎላቸው ከኮሮናቫይረስ ነጻ ከሆኑ በኋላ ወደ ካቲት 12 በመሄድ የቲቢ ህክምና ክትትል ተደርጎላቸዋል። ከኮሮናቫይረስ አገግመው ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ለተጨማሪ ሕክምና ተልከው የነበሩት የ114 ዓመት አዛውንት ሕክምናቸውን ጨርሰው መውጣታቸውን ለቢቢሲ ያረጋገጡት በየካቲት ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ሊያ ፋንታሁን ናቸው። ዶ/ር ሊያ በየካቲት ሆስፒታል ለግለሰቡ ሕክምና ሲያደርጉ እንደነበር ገልፀው፣ ግለሰቡ ያለ መሳሪያ ድጋፍ መተንፈስ በመቻላቸውና የነበሩባቸውን ኢንፌክሽኖች በመታከማቸው ከሆስፒታል መውጣታቸውን ገልፀዋል። ግለሰቡ እድሜያቸው 114 ይሆናል ተብለው የተጠየቁት ዶክተሯ " የ114 ዓመት አዛውንት ናቸው። ልጆቻቸውም የልጅ ልጆቻቸውም አብረዋቸው አሉ" ሲሉ መልሰዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን የተደረገው የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 232,050 ሲሆን 5,175 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 81 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ሲያልፍ 1,544 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ይገልፃል። በአሁን ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው 3 ሺህ 548 ሰዎች ሲሆኑ 30 ሰዎች በፀና ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ጨምሮ ያሳያል።
51636781
https://www.bbc.com/amharic/51636781
ሆስኒ ሙባረክ፡ የአዲስ አበባው የግድያ ሙከራ ሲታወስ
ሙባረክ የካቲት 17/2012 ዓ.ም አሸለቡ። በሰላም፤ ያውም በሆስፒታል ውስጥ፤ ያውም በተመቻቸ አልጋቸው ላይ ሆነው።
እኚህ ሰው ግን ከሞት ጋር ሲተናነቁ የአሁኑ የመጨረሻቸው ይሁን እንጂ የመጀመሪያቸው አልነበረም። በትንሹ 6 ጊዜ ሞት እየመጣ 'ዘይሯቸው' ይመለሳል። ሙባረክ በሳንጃ፣ በቢላ፣ በጥይትና በቦምብ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ከሞት መንጋጋ ያመለጡ ተአምረኛ ሰው ናቸው። ጥቂቶቹን ዛሬ ባናስታውስ ታሪክ ይታዘበናል። ጥቅምት 6፣1981። የዛሬ 41 ዓመት አካባቢ። አንዋር ሳዳት ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መናኺም ቤገን ጋር የካምፕ ዴቪድ ስምምነት ፈረሙ። ኖርዌይ ኖቤል ሸለመቻቸው፤ አረቡ ዓለም ግን ዓይንህን ላፈር አላቸው፤ "ከሀዲው ሳዳት" ተባሉ። ሞት ለሳዳት ተዘመረ። ያኔ የሳዳት ምክትል ሆስኒ ሙባረክ ነበሩ። በካይሮ አብዮት አደባባይ "ኦፕሬሽን ባድር" እየተዘከረ ነበር። ይህ ኦፕሬሽን ግብጽ እስራኤልን ድል ያደረገችበት ቀን ነው። ግብጾች የረመዳን ጦርነት ይሉታል። ታሪክ የዮም ኪፑር ጦርነት ይለዋል። ዮም ኪፑር በአይሁድ ዕምነት የቤዛና የንስሃ ቅዱስ ዕለት ነው። ግብጾች በዚህ ቅዱስ ቀን ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝረው ስዊዝ ካናልን ተሻግረው የሲናይ በረሃ አንድ ግዛትን ከእስራኤል ነጻ ያወጡበት ቀን ነው። ይህ ቀን በየዓመቱ ይዘከራል። ያን ዕለትም በካይሮ አብዮት አደባባይ ይኸው እየሆነ ነበር። ሙባረክና ሳዳት ተደላድለው ሰልፈኛውን ወታደር እያጨበጨቡ ይሸኛሉ። አንድ ወታደር በኮፍያው የእጅ ቦምብ ቀርቅሮ... ከኦራል መኪና ላይ በድንገት ወርዶ አንዋር ሳዳትን ተጠጋቸው፤ እርሳቸው ደግሞ ለመደበኛ ወታደራዊ ሰላምታ መስሏቸው ፈገግ ይሉለታል። የጥይት መአት አርከፈከፈባቸው። ሳዳት ሞቱ። ሙባረክ ቆሰሉ። ሆስኒ ሙባረክ የመጀመሪያውን የሞት ቀጠሮ ለጥቂት አመለጡት። መስከረም 7፣ 1999፤ ሙባረክ በኢንዱስትሪ የወደብ ከተማ ፖርት ሳይድ ጉብኝት ላይ ነበሩ። ሕዝቡ 'ሙባረክዬ' እያለ ይስማቸዋል። እርሳቸውም ከመኪናቸው በመስኮት ወጥተው አጸፋውን ይመልሳሉ። አንድ ቢላ በኪሱ የሸጎጠ የ40 ዓመት ጎልማሳ ሊከትፋቸው ሰነዘረ፤ የአየር ኃይል አብራሪ የነበሩት ሙባረክ ያን ለታ ከቢላም ከሞትም አመለጡ፤ እጃቸው ላይ ብቻ ቆሰሉ። ከብርሃን የፈጠኑት ጠባቂዎቻቸው ሰውየውን በዚያው ቅጽበት ከሕይወት ወደ ሞት ሸኙት። ሙባረክ በቦሌ ጎዳና ሆስኒ ሙባረክ ለሦስተኛ ጊዜ የሞት ቀጠሮ የነበራቸው በአዲስ አበባ ነበር። ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ፤ አንድ ሰማያዊ ቫን መኪና መንገዱን ዘግቶ ጥይት ማርከፍከፍ ጀመረ። ዕድሜ ለኢትዮጵያ ወታደሮች ሙባረክ ከሞት ተረፉ። እርሳቸው ግን የእኔ ደህንነቶች ናቸው ያተረፉኝ ብለዋል። ያኔ ካይሮ ላይ ተመልሰው አዲስ አበባ ላይ ስላጋጠቸው ነገር ለጋዜጠኞች እንዲህ ብለው ነበር። "ሊገድሉኝ የሞከሩት ሰዎች በትክክል የምን ዜጋ እንደሆኑ ልነግራችሁ አልችልም። ነገር ግን ኢትዮጵያዊ አይመስሉም፤ ጥቁርም አይደሉም። 5 ወይም 6 ቢሆኑ ነው። የተወሰኑት ጣራ ላይ ነበሩ። ገና ከቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ እንደወጣሁ ነው። "አንድ ሰማያዊ መኪና መንገዱን ዘጋው፤ አንዱ ወርዶ መተኮስ ጀመረ። ሌሎች ከፎቅ ይተኩሱ ነበር። መኪናዬ ግን ጥይት አይበሳውም ነበር። ምንም አልደነገጥኩም። ሾፌሬ ግብጻዊ ነበር። መኪናውም የኛው ነበር። ቀኝ ወደ ኋላ ዞረህ ተመለስ አልኩት። ሦስቱን የገደሏቸው የኛ ደህንነቶች ናቸው።" የሙባረክ አጭር የሕይወት ታሪክ ሙባረክ የተወለዱት በሰሜን ግብጽ ካፍር አል መስለሃ ውስጥ ነው። ያን ጊዜ አንዋር ሳዳትን ሆኑ ገማል አብዱልናስር አልመጡም። በንጉሥ አህመድ ፉአድ ፓሻ ዘመን ነው የተወለዱት። ይህ ማለት ሙባረክ ተወልደው እስኪሞቱ ባሉ 91 ዓመታት ውስጥ 4 ፕሬዝዳንቶች ሲፈራረቁ አይተዋል። ሙባረክ ከ'ተራ' ቤተሰብ ይምጡ እንጂ ተራ ሰው አልነበሩም። ከዝነኛው የግብጽ ወታደራዊ አካዳሚ ተመርቀዋል። አየር ኃይል ገብተው፣ ትንንሽ የጦር አውሮፕላኖችን ለሁለት ዓመት አብርረው፤ ከዚያ የአብራሪዎች አስተማሪ ሆኑ። ሥራው ግን ሰለቻቸው። በዚህ መሀል ታላቁ ጄኔራል ጋማል አብዱልናስር ከሥልጣናቸው ሲፈነገሉ በአይነ ቁራኛ ተመለከቱ። ያን ቀን ሥልጣን ውልብ ሳትልባቸው አልቀረም። እንደ ጎርጎሮሶዊያኑ በ1959 ሙባረክ ወደ ቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት አቀኑ። ያኔ ሶቭየት ኅብረት ለግብጽ ሁነኛ ረዳት ነበረች። እዚያ ሄደው ቦምብ ጣይ አውሮፕላን አብራሪነት ተማሩ። ከሶቪየት ኅብረት ሲመለሱ ሩሲያኛን አቀላጥፈው ነው። ወዲያው የአየር ኃይል አካዳሚው አለቃ ሆኑ፤ ወዲያውኑ የአየር ኃይል ዋና አዛዥነቱን ያዙ። ወዲያው መከላከያ ሚኒስትር ሆኑ። በሥልጣን ላይ ሥልጣን ደራረቡ። እርሳቸው ግን አሁንም ይበርደኛል ይሉ ነበር። ይህ ሁሉ ሥልጣን ታዲያ እንዲሁ አልመጣም። ከእስራኤል ጋር በነበረው የ6ቱ ቀን ጦርነት በአየር ኃይል አዛዥነታቸው ብሔራዊ ጀግና ተደርገው በመታየታቸው ነው ሥልጣን እግር በግር እያሳደደ የሚከተላቸው። ይህን የሙባረክን ዝና ያስተዋሉት ሳዳት በመጨረሻም ምክትላቸው አደረጓቸው። ሳዳት ሲገደሉ ሙባረክ አጠገባቸው ነበሩ። እርሳቸውን አስቀብረው፤ ቁስላቸውን አስጠግገው ወደ ቤተ መንግሥት ሰተት ብለው ገቡ። ከዚህ በኋላ ከሞቀው ቤተ መንግሥት ለመውጣት 3 ዐሥርታት አስፈልጓቸዋል። ከዚህ በኋላ ሙባረክ ከሀብታሟ ሳኡዲ አረቢያ ጋር ታረቁ። በሳዳት ምክንያት ከአረብ ሊግ የተባረረችው ግብጽም ወደ ህብረቱ ተመለሰች። እንዲያውም የአረብ ሊግ መቀመጫ ወደ ግብጽ ተመለሰ። ሙባረክ የተማሩት በሩሲያ ውስጥ ነው። በሩሲያኛ ቋንቋ ይቀኛሉ። ነገር ግን ከሶቭየት ኅብረት ይልቅ ምዕራቡ ጋር የሙጥኝ አሉ። እስራኤል ጋር አልቃረንም፤ ስምምነቱንም አላፈርስም በማለታቸው አሜሪካ ሙባረክን ወደደች። ቢሊዮን ዶላሮችን ማፍሰስ ጀመረች። ሙባረክ የጀመሩት የአሜሪካና የግብጽ ወታደራዊ ፍቅር ዛሬም ደረስ ቀጥሏል። ሙባረክ በተለይም በመጨረሻው የአንቀጥቅጠህ ግዛ ዘመናቸው ለይቶላቸው ነበር። እርሳቸው ላይ ብዕሩን ያነሳ የካይሮ ደራሲ ይቆነጠጣል፤ በሙባረክ ቤተሰብ የተሳለቀ ኮሜዲያን ይኮረኮማል፤ ሙባረክ ታፍረውና ተከብረው ነበር የኖሩት፤ በውድም በግድም። ከዕለታት ባንዱ ቀን የካይሮ "አብዯት አደባባይ" (ታህሪር) ተጥለቀለቀች። የአረቡ ጸደይ ከተፍ አለ። ተንቀጥቅጦ የተገዛላቸው የንስር ሕዝብ አንቀጠቀጣቸው። ታንክ ቢልኩ፤ ጥይት ቢያርከፈክፉ ወይ ፍንክች፤ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ በ2011 ላይ ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ሲባል ሥልጣኔን ለቅቂያለሁ አሉ። ግብጾች ዘመናዊው ፈርኦን ሥልጣን ለቀቀ ብለው በደስታ እንባ ተራጩ። የፈርኦን መሸኘት ግን ሌላ ፈርኦንን እንዳይመጣ አላደረገም። ዛሬ ግብጻዊያን ለሙባረክ ያለቅሳሉ? ወይስ ማረን ሙባረክ ይላሉ? ሙባረክን የሸኘው የታታህሪር አደባባይ ሬሳቸውን ሲሸኝ ምን ይል ይሆን?
51556381
https://www.bbc.com/amharic/51556381
ከማዕከላዊ ስልጣን የተገፋው ህወሓት ከዬት ወደዬት?
ከሰሞኑ ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበት 45ኛ አመት ክብረ በዓል በትግራይ በደማቅ ሁኔታ በመከበር ላይ ነው።
የደርግን ስርአት ገርስሶ ስልጣን ከተቆጣጠረ ከሶስት አስርት አመታት በኋላ ከማዕከላዊ መንግሥት ስልጣንም ገሸሽ ተደርጎ ክልሉን እያስተዳደረ ይገኛል። ለመሆኑ ህወሓት ከዬት ተነስቶ የት ደረሰ? በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ያደረጋቸው አስተዋፅኦዎች ምን ይመስላሉ? ስህተቶቹስ ምን ይመስላሉ? በጨረፍታ እንመለከተዋለን። • መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው፡ አባይ ፀሐዬ • "ለስልጣን ተብሎ የሚፈጠር ውህደትን ህወሓት ፈጽሞ አይቀበለውም" አቶ ጌታቸው ረዳ ደደቢት፣ የህወሓት የትጥቅ ትግል መነሻ፣ የደርግን ጭቆና የተፀየፉና ነፃነትን የናፈቁ ወጣቶች፣ የብዙ ወጣቶች ደም የተገበረባት ቦታ። የነገን ተስፋ የሰነቁባት ወጣቶች የደርግን ስርአት ለመገርሰስ ተነሱ፤ ትግሉም እልህ አስጨራሽና ብዙዎችም የተሰውበት ነው። በድርጅቱ የተለያዩ ሰነዶችም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደሚነገረው የትግሉ ዋና ዓላማ የልማትና የዴሞክራሲ ዕንቅፋት ሆኗል ብሎ ያመነውን የደርግ ስርዓት አስወግዶ ወደ ዴሞክራስያዊ ስርዓት ለመሸጋገር ነበር። ከአስራ ሰባት አመታት ትግል በኋላ የደርግ ስርአትም ተገረሰሰ፣ ህወሓት ከብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ኢህዴንና ሌሎች አጋር ፓርቲዎች ጋር በመሆን ስልጣን ተቆናጠጠ። የሽግግር መንግሥት በማቋቋም ለሶስት አመታት ያህልም ቆይቷል፤ በዚህ ወቅት ነው አገሪቱ አዲስ ህገ መንግሥት እንዲኖራትና ፌደራላዊት፣ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ የሚል መጠሪያ እንዲኖራትም የተወሰነው። ህወሓትና ህገመንግሥቱ ህዳር 29፣ 1987 ዓ.ም በወቅቱ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ተፈርሞ የፀደቀው ህገ መንግሥት ለብሄር ብሄረሰቦች የተለየ መብት የሚሰጥ እንዲሁም በመርህ ደረጃ ለህዝቡ የስልጣን ባለቤትነትን የሚያጎናጽፍ ነው። ህገ መንግሥቱ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ፤ የዜጎች የመጻፍ፣ በነጻነት ሃሳብ የመግለጽ፣ የመሰባሰብና የመቃወም መብቶችን አካቶ የያዘ ሰነድ በመሆኑ ድጋፍ ተችሮት ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ህገ መንግሥቱንም በማርቀቅ የተለያዩ ሃሳብ ያላቸውን ኃይሎችንም በማሰባሰቡ ህገ መንግሥቱ በመርህ ደረጃ ብዙዎች ደግፈውታል። • "ሕገ-መንግሥቱ ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትርን በሚመለከት ክፍተት አለበት" ውብሸት ሙላት ምንም እንኳን ህገ መንግሥቱ ከተለያዩ ሃይሎች ድጋፍ ቢቸረውም አንዳንድ አንቀፆች አሁንም ድረስ ያልተቋጨ ውዝግብን አስነስተዋል። ለምሳሌም ያህል አንቀፅ 39 ላይ የሰፈረው 'ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እስከ መገንጠል ድረስ' የሚለው ኢትዮጵያ እንደ አንድ ሃገር ሆና እንዳትቀጥል ህልውናዋን የሚገዳዳራት ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ እስካሁን ላሉ የብሄር ጥያቄዎችን ራሳቸውን የማስተዳደር ታሪካዊ ጥያቄ የመለሰ ነው የሚሉም በሌላ ወገን አልታጡም። በህወሓት/ኢህአዴግ ፊት አውራሪነት የጸደቀው አዲሱ ሕገ መንግስት፤ ከዚህ በፊት የነበረውን በአሃዳዊነት ላይ የተመሰረተውን የኢትዮጵያ አገር ግንባታ አፍርሶ ሌላ መልክ የሰጠ ነው ተብሎ ይተቻልም እንዲሁም በተቃራኒው ይሞካሻል። የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርበት ሲከታተሉ ለቆዩት የግጭት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሼትል ትሮንቮ በወቅቱ በኢትዮጵያ የነበረው ሁኔታ የሚያንጸባርቅና በአብዛኛው የህዝቡ ስሜት የሚገልጽ እንደነበር ያስረዳሉ። እሳቸው እንደሚሉት የኢህአዴግ ስርዓት ትልቁ ችግር ራሱ ህገ-መንግስቱ ሳይሆን፤ አተገባበር ላይ የነበሩ ክፍተቶችና ጉድለቶች እንደሆኑ ያስረዳሉ። ምርጫ 1997፡ የዴሞክራሲተስፋ መፈንጠቅ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የ1997 ምርጫ እንደ ትልቅ ምዕራፍ ይታያል። በነበሩት የጦፉ ውይይቶችና መድረኮች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጣምረው በአንድ ግንባር መምጣት፣ በምርጫ ቅስቀሳዎች እንዲሁም ህዝቡ ይሆነኛል የሚለውን የመምረጥ ተስፋን ያመጣ ነበር። ከዛ በፊት በነበረው የመጀመሪያው ምርጫ ከጠቅላላ 547 የፓርላማ ወንበሮች ውስጥ ኢህአዴግ 481 አሸንፎ ነበር ስልጣኑን ከሽግግር መንግስቱ የተረከበው። በወቅቱ እነ ዶክተር መረራ ጉዲና የመሳሰሉ ነባር የተቃዋሚ አመራሮች ጥቂት መቀመጫ አግኝተው በምክር ቤቱ የተለዬ ሃሳባቸውን ለመግለጽ ዕድል አግኝተው ነበር። የተሻለ የዲሞክራሲ ጭላንጭል የታየበት የ1997ቱ ምርጫም፤ ብሔርን ከብሔር የሚያጋጩ ፅሁፎች ነበሩባቸው ተብለው ቢተቹም፤ የግል ሚድያዎችና ሲቪክ ማህበረሰቦች እንደልባቸው የተንቀሳቀሱበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር። • ህወሓት ከኢህአዴግ ለመፋታት ቆርጧል? • ህወሓት: "እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም" በተለይም የተቃዋሚዎች ተጣምረው አንድ ላይ መምጣት ለምርጫው ሌላ መልክ ነበር። በወቅቱ ቅንጅትና ህብረት ኢህአዴግን ተገዳድረውታል፤ ተንታኞች እንደሚሉት ኢህአዴግ ባልጠበቀው መልኩ የሃገሪቱን ማዕከል አዲስአበባን በተቃዋሚዎች አጥቷል። ሆኖም በምርጫው ውጤት ተቃዋሚዎችና ኢህአዴግ ስለልተስማሙ ወደ እስርና ደም መፋሰስ ነበር ያመራው። የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች ህገመንግሥቱን በኃይል ለማፍረስና በሃገር ክህደት ተወንጅለው ዘብጥያ ወረዱ። ምንም እንኳን ብዙዎቹ ከመንግሥት ጋር በተደረገ ድርድር ከእስር ቢፈቱም በርካቶች በሰላማዊ ትግሉ ተስፋ ስለቆረጡ ስደትን ምርጫ ለማድረግ ተገደዱ። ብዙዎቹ በውጭ ሆነው ሲታገሉ ቆይተው ዶክተር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የተደረገውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ነበር ወደ አገር ቤት የመጡት። በ1997 ምርጫ ስልጣኑ ለመጀመርያ ግዜ የተነቃነቀው ገዢው ፓርቲ ከፍቶት የነበረውን ጭላንጭልም ተዘጋ፤ ይህንንም የሚያጠናክርና በተቋማዊ መልኩ የሚያደርጉ ህጎች ፀደቁ። ከነዚህም መካከል በብዙዎች ዘንድ አፋኝ ተብለው የሚጠሩት የጸረ ሽብር፣ የፕሬስ፣ የሲቪል ማህበረሰብ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምዘገባ አዋጆች ይገኙበታል። ብዙዎችንም በፍርሃት እንዲሸበቡ አድርጓቸዋል፤ የፖለቲካ ምህዳሩን አጥብበውታል በማለት በተደጋጋሚ የተለያዩ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሪፖርቶችንም ያወጡ ነበር። የቀድሞ የህወሓት አመራር አባል አቶ ገብሩ አስራትም አስተያየት ከዚህ ብዙ የተለየ አይደለም፤ በወቅቱ ገዢው ፓርቲ የወሰደውን እርምጃ የአገሪቱ የዴሞክራሲ ዕድገት ወደኋላ የጎተተ ክስተት ይሉታል። • 'የአልባኒያ ተቃዋሚዎች' በትግራይ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችንም ከማሽመድመድ ሌላ የምርጫ ውዝግቡን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ አዳዲስ አባላትን መመልመል ጀመረ። ከምርጫ 1997 በፊት ከአንድ ሚልዮን በላይ አባላት ያልነበሩት ቢሆንም የ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎ 7 ሚሊዮን አዳዲስ አባላትን መልምሏል። በሚሊዮኖች የተመለመሉት አባላት የኢህአዴግን ርዕዮተ አለም፣ ፕሮግራም እንዲሁም ለሃገሪቱ አስቀመጥኩት የሚለውን አቅጣጫ አምነውበት ሳይሆን፣ ከመንግሥታዊ ጥቅማ ጥቅም ጋር የተያያዙ እንደሆኑም በቅርበት ግንባሩን የሚከታተሉ በተደጋጋሚ ይናገሩት የነበረ ጉዳይ ነው። ግንባሩን ሳያምኑበት በአባልነት የተመለመሉ ወጣቶች በመጨረሻ ድርጅቱ አደጋ እንደሚያስከትል ስጋታቸውን የገለጹም ብዙዎች ነበሩ፤ ግንባሩም መሸርሸሩ አይቀርም በማለትም ተንታኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። "የተራበው ህዝብ መሪውን ይበላል" በሚልና በሌላ መረር ያሉ ንግግሮቻቸው የሚታወሱት መረራ ጉዲና (ዶ/ር) "የኢህአዴግ መጨረሻው ከአገር ውስጥም ይሁን ከአገር ውጭ ሊሆን ይችላል በሚለው እንጂ በህዝባዊ ዓመጽ እንደሚሆን አውቅ ነበር" ይላሉ ከቢቢሲ ጋር በባደረጉት ቆይታ። ነጻ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ክፍተት? ኢትዮጵያ ውስጥ እምነት የሚጣልበት የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ አለመኖር እንደ አንድ ለስርአቱ ችግር ተብለው ከሚነሱ ምክንያቶች አንዱ ነው። ምንም እንኳን በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ አንዱ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ምሰሶ የሆነው የተቋማት እርስ በርስ የመቆጣጠር እና ሚዛን መጠበቅ ቢሆንም አገራዊ እና መንግሥታዊ መዋቅሮች ከኢህአዴግ ነፃ አልነበሩም። ለዘመናትም መንግሥታዊና የህዝብ ተቋማት የፓርቲው መሳሪያ ሆነው ከፍተኛ ክፍተትን አስከትለዋልም ተብለው ይተቻሉ። ለዚህም የፍትህ አካላት፣ የፀጥታና ደህንነት አካላት ኢህአዴግ እንደ ግል ንብረቱ የሚጠቀምባቸውና የሚያሽከረክራቸው ናቸው ይባላሉ። ለምሳሌም ያህል የመንግሥት ሚዲያ ለአስርት አመታት ያህል የገዢው ፖርቲ ፕሮፓጋንዳ መንዢያ ናቸው ይላሉ፤ ከዚህም በተጨማሪ ፍርድ ቤትም ሆነ አስፈፃሚው አካል ፓርቲው ጣልቃ እየገባ እንደፈለገ የሚያዛቸው ናቸው ይላሉ ተችዎች። በተደጋጋሚ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የተያዘ ተጠርጣሪዎችን በመንግሥት ሚድያ እንደ ወንጀለኞች ተደርገው የተለያዩ ዘገባዎች የሚቀርቡባቸው አካሄድ ነበር፤ ይሄ ሁኔታ ባለፉት ሁለት ዓመታትም ቀጥሏል። ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም እንደነበረው ይህንን ሲያስቆምም አይታይም ይላሉ። በባለፉት ሶስት አስርት አመታት ያሉትን ክፍተትም በመታዘብ በኢትዮጵያ የከፋው ነገር ነፃ የዲሞክራሲ ተቋማት መፍጠር አለመቻል እንደሆነ ፕሮፌሰር ትሮንቮል ይናገራሉ። "ገዢው ፓርቲ ራሱን ከመንግሥት ተቋማት ጋር አጣብቆ፤ ተቋማቱ ራሳቸውን ችለው እንዳይቆሙ አድርጓቸዋል"ይላሉ። ፕሮፌሰር ትሮንቮል እንደሚሉት ለዚህ ችግር ዋነኛው ምክንያት በሶስቱም የመንግሥት አካላት- ህግ አውጪው፣ ህግ ተርጓሚውና አስፈጻሚው መካካል የእርስ በርስ ሚዛናቸውን ጠብቀው፣ ተለያይተውና አንዱ ሌላውን ሊቆጣጠር ስላልቻለ ነው ይላሉ። የችግሮቹ ሁሉ ምንጭ- አብዮታዊ ዴሞክራሲ? ምንም እንኳን የኢህአዴግ "አፋኝ እርምጃዎች፣ ፈላጭ ቆራጭ መሆን የጀመረው ምርጫ 97ን ተከትሎ፤ በውጤቱ ተደናግጦ ነው የሚሉ ቢኖሩም አቶ ገብሩ አስራት ግን በዚህ ሃሳብ አይስማሙም። ለሳቸው ዋነኛውና መሰረታዊው ችግር የግንባሩ ርዕዮተ ዓለም ነው። • "አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው" አቦይ ስብሃት የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፅንሰ ሃሳብ ከህገ መንግሥቱ ጋር ይጻረራል የሚሉት አቶ ገብሩ " ስርዓቱ ሁሉንም ዜጎች እኩል አይመለከትም፤ ወዳጅና ጠላት ብሎ ዜጎችን ለሁለት ይከፍላል" ይላሉ። እንደ ማስረጃነት ድርጅቱ ይጠቅሳቸው ከነበሩትም መካከል "ለሰራተኞችና ለአርሶ አደር እቆማለሁ ይላል። ምሁር ወላዋይ ነው ብሎ ያምናል።" በማለት ይናገራሉ። ምንም እንኳን ይህ አስተሳሰብ ለህወሓትም ሆነ ኢህአዴግ በትጥቅ ትግል ወቅት ህዝቡን ለማንቀሳቀስ ጠቃሚ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ገብሩ፣ ሆኖም ትግሉ ተጠናቆ ስልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ የተቀመጠ አቅጣጫ እንደሌለ ይጠቁማሉ። "እንዴት እንቀጥልበት የሚለው ላይ አልተነጋገርንም" ይላሉ አብዮታዊ ዴሞክራሲ በአቶ ገብሩ አስራት ብቻ ሳይሆን በብዙ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተንታኞችና ምሁራንም ሲተች ይደመጣል፤ እንደ ርዕዮተ አለምም የማያዩት አሉ። "ኢሕአዴግ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራም የሚመራና በፕሮግራሙ ላይ ለሰፈሩት ዓላማዎች የሚታገል ድርጅት ነው። ያነገባቸው ዓላማዎች ዴሞክራሲያዊና አብዮታዊ በመሆናቸው በተግባር ላይ ከዋሉ ኅብረተሰባችንን ከሚገኝበት ድህነትና ኋላ ቀርነት አላቀው ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲና ለብልፅግና ያበቁታል። " ይላል ከኢሕአዴግ መተዳደሪያ ደንብ መግቢያ አንቀጽ ላይ የተወሰደው ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ አመራርን መሰረት ያደረገው አብዮታዊ ዴሞክራሲን ለማስፈን የህዝብ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልጋል የሚል ሲሆን፤ በጥቅሉ የዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት ጠንካራ የመካከለኛ ገቢ ያለው መደብ መፍጠር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚያስፈልገው ነውም ይላል። ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው "የኢትየጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች፡ የኢህአዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ" በሚለው ፅሁፋቸው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፍልስፍና መሰረት ስልጣን ላይ መምጫው መንገድ የማኦው ፍልስፍና የሆነው "ስልጣን የሚመጣው ከጠመንጃ አፈሙዝ ነው" የሚለው ነው ይላሉ። አክለውም ይህንን የኢህአዴግ አስተሳሰብ ራሱ በህገ መንግስቱ ውስጥ ከገባው ቃል ይጻረራል ሲሉ ያስረዳሉ። ጠንካራ ፖርቲ በመመስረት የሚያምነው ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን እንዲኖሩ የሚፈልገው በወሳኝ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ ሳይሆን ለይስሙላና ለለጋሾች ተብሎ እንደሆነም ትችቶች ከሚቀርቡባቸው ጉዳይ አንዱ ነው። የልማታዊ መንግሥት ጥያቄ ኢትዮጵያ ባስመዘገበችው የኢኮኖሚ እድገት የጤና አገልግሎት ሽፋን፣ የትምህርት ተደራሽነት፣ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መንግሥት የሚያራምደው የልማታዊ መንግሥት ርዕዮት ውጤት ነው ብለው ብዙዎች ያምናሉ። በተቃራኒው የዚሁ ልማታዊ መንግሥት መገለጫም የተለየ እይታዎችን የያዙ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች በእስር መማቀቅ ነው። በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ተቀረፀ የሚባለው የኢትዮጵያ ልማታዊ መንግሥት መገለጫዎች የሚባሉት ጠንካራ እና ጣልቃ ገብነት ያለው፣ ለሰው ሐብት ልማት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት፣ የሀገርን ሐብትን በማስተባበር ቀጥተኛ ሚና በመጫወት ትልልቅ ሀገር አቀፍ የልማት ሥራዎችን ለመተግበር እንዲችል በማመቻቸት ለውጥ ማምጣት ነው ይላሉ። ልማታዊ መንግሥቱ ያለ ሌሎች ተፅእኖ ራሱን የሚያስተዳድር እና በሃገር ውስጥ የበላይነት ያለው በምርጫ ሂደት የማይስተጓጎሉ ሲሆኑ የእስያ ሃገራቱ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን እንደ አብነት ይጠቀሳሉ። ከምዕራባውያኑ ተቋማት አለም ባንክ እና አይኤምኤፍ "ያረጀ ያፈጀ" አካሄድ ነፃ በመሆን በፍጥነት እመርታዊ ኢኮኖሚ ማስመዝገብ የሚልም አካሄድ ነበረው። በዚህ አካሄድ ብዙ አስርት አመታትን በስልጣን የሚቆዩ ሃገራት ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ አምጥተዋል ቢባልም ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶችን ይደፈጥጣሉ ተብለው ይተቻሉ፤ ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያን በማስገባት ይተቿታል። የሲቪል ማሕበራትንና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ድምጽን በማፈን በተቃራኒ ወደ አምባ ገነንነትና ፈላጭ ቆራጭነት አምርተዋል ቢባልም ይህንን አስተሳሰብ ለዘመናት ኢህአዴግ በተለይ መለስ ዜናዊ ሲሞግቱት ነበር። የመጡ ኢኮኖሚያዊ ለውጦች የመጡ ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን በተመለከተ እንደ አለም ባንክ ያሉ መረጃዎች ሲፈተሹ በተከታታይ አመታት በዓለማችን ከፍተኛ ዕድገት ካሳዩ አገራት አንዷ ሆናለች፤ በአለም በፍጥነት በማደግ ላይ ከነበሩ አምስት ሀገራት መካከልም ሁና ነበር። አዳዲስ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች መጀመር ለምሳሌ የህዳሴ ግድቡን ጨምሮ በርካታ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች ተሰርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሴፍቲኔት መርሐ ግብር የሚጠቀስ ሲሆን በአለም ባንክ መረጃ መሰረት በጎርጎሳውያኑ በ2011፣ 30 % ህዝብ ከድህነት ወለል በታች የነበረ ሲሆን በ2016 ወደ 24% ቀንሷል። የትምህርት ቤት ተደራሽነትም እንዲሁ በ2006 97%፣ በ2016 ደግሞ ወደ 99% እንዳደገ መረጃው ያመለክታል። ምንም እንኳን እነዚህ የመጡ ኢኮኖሚያዊ ለውጦች በተለያዩ አለም አቀፍ ሚድያዎች ከፍተኛ መወደስን ቢያመጡም መንግሥት ያደረጋቸውም ጫናዎችና ጭቆናዎች በብዙዎች ዘንድ ተተችቶበታል። ስልጣን ላይ ለመቆየት የማያደርገው ነገር የለም የሚሉት ዶክተር መረራ በተለይም በ2002 በነበረው ምርጫ 99 በመቶ አሸነፍኩ ማለቱን እንደ ምሳሌ ያነሳሉ። ምክር ቤቱን ጠቅልሎ የሚቆጣጠርበት ዘዴም ያበጀ ሲሆን 'የምርጫ ሰራዊት' የሚባል ከእርዳታ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በማስተሳሰር አንድ ለአምስት "የሚጠረነፉበትን" ሁኔታም ተቀየሰ። የምርጫው ውጤት ያልተቀበሉ ተቃዋሚዎችም እስከ ፍርድ ቤት ድረስ ቢሄዱም ለውጥ ግን አላገኙም። የሥርዓቱ ፈላጭ ቆራጭነት ከሰላሳ ዓመታት በላይ የህወሓት እና ኢህአዴግ ሊቀ መንበር ሆነው የቆዩት አቶ መለስ ዜናዊ በትልልቅ ዓለም አቀፍ መድረኮች ባመጡት የኢኮኖሚ ለውጥ ጋር ተያይዞ ስማቸው ቢነሳም ባገሪቱ ውስጥ ግን በነበረው ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓትም ይወቀሳሉ። "ግንባሩ የመበስበስ አደጋ እንዳይገጥመው" በሚል ጀምረውት የነበረውን የመተካካት ፖሊሲም ከግብ ሳያደርሱ በ57 ዓመታቸው አረፉ። ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአፍሪካ ተቀባይነት ያገኙ መሪዎች ውስጥ ቢካተቱም እንዲሁም "ባለ ራዕይ እንዲሁም ሞጋች ተደርገው ቢታዩም በሌላ መልኩ ዘኢኮኖሚስት መፅሄት ግን 'The man who tried to make dictatorship acceptable' (አምባገነንት ተቀባይነት እንዲያገኝ የሞከሩ ሰው) በማለት ይገልፃቸዋል። ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ አገሪቱን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም በቀደመው ራዕይ ቀጠሉበት፤ ፈላጭ ቆራጭነቱም ቀጥሎ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች መታሰር ብዙዎችን ተስፋ ያስቆረጠ ነበር። የህወሓት የቀድሞ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ብርሃነ ፅጋብ 'የኢህአዴግ ቁልቁለት ጉዞ' በሚለው መጽሐፋቸው ከመለስ ሞት በኋላ የግንባሩን አካሄድ የፈተሹት ሲሆን በሳቸውም አስተያየት "በግምገማ፣ ራስን በመተቸት የሚታወቅ ፓርቲ በመተዛዘል (እከከኝ ልከክህ) ዳዴ ማለት ጀመረ፤ ሺዎች ደማቸውን የከፈሉበት ሥርዓት፣ የፓርቲው መሪዎች የግል ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁበት ሆነ" በማለት ያስረዳሉ። የኢህአዴግ የሥርዓት መበስበበስም መገለጫ የሆነው ሕዝባዊ ተቃውሞዎችና የሕዝቡ ቁጣ ናቸው። በኢህአዴግ ላይ የሚንፀባረቁት ከፍተኛ ተቃውሞዎች በተለይም ግንባሩን በአካሉና በአምሳሉ ከሠራው ህወሓት ጋር በከፍተኛ ሁኔታ ያነጣጠረ ነው። ህወሓት ላይ የሚያጋጥሙ ማንኛውም እክሎች ግንባሩንም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ነበራቸው። ለዚህም በህወሓት ያጋጠመው መከፋፈል በአገሪቱ ውስጥ ላለው መከላከያ እንዲሁም ሌሎች ተቋማትን የከፋፈለ እንዲሁም የአገሪቱን ደህንነት ጥያቄ ውስጥ የከተተ ነበር። ኢህአዴግ ወይም ህወሓትም ላይ ያነጣጠረው ተቃውሞም የትግራይ ሕዝብ ላይ የወረደ ሲሆን የትግራይ ሕዝብ በተለየ የሥርዓቱ ተጠቃሚ ተደርጎም ተስሏል። ይህ ሁኔታም ከራሱ ከፓርቲው ሲወጡ የነበሩ ሃሰተኛ ሪፖርቶችና ፕሮፖጋንዳዎች ሁኔታውን አባብሶታል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፤ ይህንንም ሁኔታ ዶ/ር ደብረፅዮን ወደ ፓርቲው ኃላፊነት ሲመጡ ያመኑበት ጉዳይ ነው። መቋጫ በህወሓት አካሄድ ያልተደሰቱ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ የሆነው አብርሃ ሃይለዝጊ አይነት ግለሰቦች ፓርቲውን ለቀው ለመውጣት ብዙ አልወሰደባቸውም። ለሶስት ዓመት የፓርቲው አባል የነበረ ሲሆን፤ ፓርቲውን ጥሎ ለመውጣት ግን አራት ዓመትም አልሞላም። "ፓርቲው ከሕዝባዊነት ወጥቶ ለሕዝብ ጥቅም ሳይሆን ለግል ጥቅማቸው ሲያውሉት አስተዋልኩኝ። በፓርቲው ውስጥ ሆኜ ለመታገል የሚያስችል ቦታም እንዳልነበረም ተረዳሁ" በማለት ከፓርቲው ደብዳቤ በመፃፍ እንደተሰናበተ ያስታውሳል። አብርሃ በፓርቲው ውስጥ ሆኖ ለመንቀፍ የሞከረ ሰው ከሥራ የመባረር፣ በሕይወቱ የማስፈራራት እና ሌሎችም ችግሮች ይደርሱበት ነበር ይላል። "ጥያቄ የጠየቀ እንደ ጠላት ይታያል። ጠባብ፣ ትምክህተኛ የሚሉ የአፈና መሣርያ ቃላትን በመጠቀም ያሸማቅቃሉ" ይላል። በወቅቱ ትክክለኛ ውሳኔ እንደወሰነ የሚሰማው አብርሃ በኋላም ህወሓት ባደረገው ጥልቅ ግምገማ ስህተት መሆኑ ታምኖበት ነበር ይላል። ህወሓት በ2010 ዓ.ም ባካሄደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ጥልቅ ግምገማ ዜጎች ሕገ-መንግስታዊ መብታቸው እንደታፈነ፣ በፓርቲው ሥርዓት አልበኝነት እንደነገሰ፣ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አሠራር እና መጠቃቃት የፓርቲው መገለጫ እንደነበር በማመን ለሕዝብ ይቅርታ ጠይቋል። ባለፉት 27 አመታት ድህነት፣ ሲፈፀም የነበረ ግፍ እና ሕገ-መንግስታዊ ጥሰት፣ የዜጎች ሰብኣዊ መብት ጥሰት በትግራይ የከፋ እንደነበርም ተንታኞች ይናገራሉ። "ለረዥም ጊዜ በስልጣን የቆየ ገዢ ፓርቲ መጨረሻው ሙስና እና ሥርዓት አልበኝነት ነው" የሚሉት ፕሮፌሰር ሼቲል ትሮንቮል፤ ህወሓት እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ ግንባር ከታገለበት መስመር ወጥቷል በማለት ሀሳቡን ያጠናቅቃል። ዶክተር መረራም ስለ ህወሓት/ ኢህአዴግ የሚያስታውሱት ጥሩ ነገር ካለ ተጠይቀው "ከሰይጣኑ ደርግ ነፃ ስላወጣን ብቻ አመሰግነዋለው" ብለዋል።
news-53737438
https://www.bbc.com/amharic/news-53737438
ካሽሚር፡ “መቃወም አንችልም፤ ከተቃወምን እንታሰራለን”
አምና ነሐሴ 5 ላይ ሕንድ የካሽሚርን ልዩ አስተዳደር አንስታ፤ ግዛቲቱን ለሁለት ከፍላለች። ጥብቅ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል። በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል። የግንኙነት መስመሮችም ተቋርጠዋል።
ገደቡ ሚያዝያ ላይ በመጠኑ ቢላላም፤ በኮቪድ-19 ምክንያት በድጋሚ ገደብ ተጥሏል። ቁጣና ፍርሀትን ያጫረው በካሽሚር ላይ የተጣለው ገደብ አንድ ዓመት አስቆጥሯል። ይህን ምክንያት በማድረግም 12 የካሽሚር ነዋሪዎችን ቢቢሲ አነጋግሯል። የጋዜጠኛዋ ሰንዓ ኢርሻድ ሞት ጋዜጠኛዋ ሰንዓ 26 ዓመቷ ነው። “በኛ ሙያ የግል ሕይወትና ሥራ መለየት አይቻልም” ትላለች። በሙያው አራት ዓመታት አስቆጥራለች። ባለፉት ዓመታት የእንቅስቃሴ ገደቦች ቢጣሉም የአምናው አስፈሪ እንደነበር ትናገራለች። “ምን እየተከናወነ እንደነበር ማወቅ አልቻልንም። እርስ በእርሳችን መረጃ የምንለዋወጥበት መንገድ ተቀይሯል። ሰሚ ለማግኘት አዳዲስ መንገዶች መፍጠር ነበረብን” በማለት ያሉበትን ሁኔታ ትገልጻለች። ለወትሮውም ከጋዜጠኞች ጋር የማይስማሙት የጸጥታ ኃይሎች፤ ካለፈው ዓመት ነሐሴ ጀምሮ የበለጠ ከፍተዋል። “አሁን ጋዜጠኞች ይታሰራሉ፣ የመረጃ ምንጫቸውን ይፋ እንዲያድጉ ይገደዳሉ። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማንኛውንም ነገር ከመጻፌ በፊት ቆም ብዬ ማሰብ ይጠበቅብኛል። ሁሌም እፈራለሁ።” ቤተሰቦቿ ስለ ደኅንነቷ እንደሚጨነቁ ትናገራለች። ስለ ሥራዋ ለቤሰቦቿ ምንም አትገልጽም። ልጁን ያጣው አልጣፍ ሁሴን የ55 ዓመቱ አልጣፍ ልጁን ያጣው የነሐሴ አምስቱን የመንግሥት ውሳኔ ተከትሎ ነው። የአልጣፍ ልጅ ኡሳይብ 17 ዓመቱ ነበር። ከጸጥታ ኃይሎች ለማምለጥ ሲሞክር ወንዝ ውስጥ ዘሎ ነው ሕይወቱን ያጣው። የጸጥታ ኃይሎች ይህን ድርጊታቸውን ክደዋል። ወጣቱ ከሞተ አንድ ዓመት ቢሞላም፤ የጤና ተቋም ለቤተሰቡ የሞት ማረጋገጫ ሰነድ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም። አባቱ አልጣፍ “ኳስ ሊጫወት ወጥቶ በሬሳ ሳጥን ተመለሰ። ፖሊሶች በዛን ቀን ማንም አልሞተም ይላሉ። እንደተገደለ ማመን አልፈለጉም። ምስክር ቢኖረኝም ጉዳዩን ለመከታተል ፍቃደኛ አይደሉም። ፖሊስ ጣቢያ፣ ፍርድ ቤት ብንሄድም ፍትሕ አላገኘንም” ይላል። ሙኒፋ ናዚፍ የስድስት ዓመቷ ሙኒፋ ናዚር የስድስት ዓመቷ ሙኒፋ በወንጭፍ ቀኝ አይኗን የተመታችው በተቃዋሚዎችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው። “ለብዙ ቀናት ሆስፒታል ነበርኩ። አሁን ብዙም ትዝ አይለኝም። ትምህርት ቤት የተማርኩትን ረስቻለሁ። መቶ ከመቶ እደፍን ነበር። አይኔ ከዳነ በኋላ ሐኪም መሆን እፈልጋለሁ። ሐኪሞች ስላዳኑኝ ደስ ይሉኛል” ትላለች ታዳጊዋ። ፎቶ ጋዜጠኛው አባቷ እንደሚለው የሙኒፋ አይን ዳግመኛ ማየት አይችልም። የትምህርት ቤት ክፍያ ከአቅሙ በላይ ስለሆነም ልጁን አስወጥቷታል። “የሚታየኝ ጭላንጭል ብቻ ነው። መጻሕፍት ማንበብ አልችልም። የትም አልሄድም። ሐኪሞች ከ15 ቀናት በኋላ ትምህርት ቤት መሄድ ትችያለሽ ቢሉኝም አንድ ዓመት አልፎኛል።” ባለ አውቶብሱ ፋሩቅ አህመድ ፋሩቅ 34 ዓመቱ ነው። ታዳጊ ሳለ ካሽሚር ውስጥ ከአውቶብስ ሹፌሮች ጋር ይሠራ ነበር። 2003 ላይ ያጠራቀመው ገንዘብ ላይ የባለቤቱን ወርቅ ሸጦ ገንዘብ ጨምሮበት የራሱ አውቶብስ ገዛ። አሁን የሰባት አውቶብስ ባለቤት ቢሆንም የትራንስፖርት ዘርፉ እንደቀድሞው እየተንቀሳቀሰ አይደለም። “400 ሺህ ሩፒ ከፍለን የመኪኖቹን ኢንሹራንስ አሳድሰናል። ግን ምንም ገቢ የለንም። ሰባት ሠራተኞቼ ለረሀብ ተጋልጠዋል። የራሴ ቤተሰብ መከራ ውስጥ ሆኖ እንዴት የነሱን ልረዳ እችላለሁ? እንደኔ አይነት ሰዎች ጥሪታችንን አሟጠን ነው ንግድ የምንጀምረው። ገቢ ከሌለን እንዴት እዳችንን መክፈል እንችላለን?” ፋሩቅ እዳዎቹን ለመክፈል ሲል የቀን ሥራ ጀምሯል። የፋሽን ዲዛይነሯ ኢቅራ አህመድ የ28 ዓመቷ ኢቅራ የራሷን የፋሽን ድርጅት የከፈተችው የማንም ተቀጣሪ ላለመሆን ነው። በድረገ ገጽ በምትሸጣቸው ሥራዎቿ የካሽሚርን ባህል ማስተዋወቅ እንደምትፈልግ ትናገራለች። “ኢንተርኔት መዘጋቱ ንግዴን አቀዝቅዞታል። 2ጂ ደግሞ ምንም ጥቅም የለውም። አሜሪካ፣ ዱባይና አውስትራሊያም ደንበኞች አሉኝ” ትላለች። 2ጂ ኢንተርኔት ደካማ ስለሆነ የምትሠራቸውን ልብሶች በድረ ገጽ ማስተዋወቅ አልቻለችም። ቀድሞ በሳምንት ከ100 እስከ 110 የሥራ ትዕዛዝ ታገኝ ነበር። አሁን ግን ቢበዛ ስድስት ልብስ እንድትሠራ ብትታዘዝ ነው። ዓለም አቀፍ ደንበኞቿ ያዘዙት ልብስ ሳይደርሳቸው ይዘገያል ብለው ይሰጋሉ። በቅርቡ አንድ ልብስ ለመላክ ስድስት ወር ወስዶባታል። “ንግዴ በዚህ ሁኔታ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ አይመስለኝም። ወርሀዊ ወጪዬ 200 ሺህ ሩፒ ነው። ምንም ገቢ ካላገኘው እንዴት ለሠራተኞቼ ደሞዝ እከፍላለሁ?” የፋሽን ዲዛይነሯ ኢቅራ አህመድ የሕግ ተማሪዋ ባድሩድ ዱጃ “ሕገ መንግሥቱን፣ ዴሞክራሲ ምን ማለት እንደሆነና ስለ መሠረታዊ መብት አጠናለሁ። እነዚህ ግን ከቃላት ያለፉ አይደሉም። የገነቡት ቤተ መንግሥት እየፈረሰ ነው። ነፃነታችንን እያጣን ነው። ለመምህራንም ይሁን ለተማሪዎች ሕግ መማር ቀልድ ሆኗል” ትላለች የ24 ዓመቷ የሕግ ተማሪ ባድሩድ። ባድሩድ የመረጠችው ዘርፍ ላይ ጥያቄ ማንሳት ጀምራለች። ጭቆናውንም እንዲህ ትገልጻለች. . . “መናገር ፈውስ ነበር። አሁን ግን ያሳስራል። ካሽሚር ውስጥ በሚገኝ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ውስጥ ስሠራ ከጋዜጠኞች ጋር በማውራቱ የታሰረ ሰው ገጥሞኛል። ተስፋችን ጨልሟል። ሕግ የተማርነው ሕግ እንዲያስከብሩ የሚከፈላቸው ሰዎች ሕግ ሲጥሱ ለማየት አይለም። ሌላ ሥራ መፈለግ ጀምሬያለሁ።” ፖለቲከኛው ማንዙር ባህት ማንዙር 29 ዓመቱ ነው። ሕንድን የሚያስተዳድረው ባህራታያ ጃናታ የተሰኘው ፓርቲ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊ ነው። ፓርቲውን በመቀላቀሉ ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ እንዳገለሉት ይናገራል። እሱ ግን የአካባቢውን ሰዎች እያገዘ እንደሆነ ነው የሚያምነው። “ህልሜ ስልጣን መያዝ ወይም ሀብት ማካበት ሳይሆን የሰዎችን ሕይወት መለወጥ ነው። ወጣቶች የሚያነሱት መሣሪያ መፍትሔ አይሆንም። በካሽሚር የሚሞቱት ወንድሞቼ ናቸው። ግጭት መልስ አይሆነንም።” አስጎብኚው ጃቪድ አህመድ የ35 ዓመቱ ጃቪድ ላለፉት ዓመታት በመርከብ ቱሪስቶችን እያጓጓዘ በቀን ወደ 500 ሩፒ ያገኝ ነበር። “አሁን ሕይወቴን የምገፋው አትክልት እየሸጥኩ ነው። ግን እንቅስቃሴ ስለተገደበ ገበያ የለም” ይላል። ጃቪድ ለልጆቹ ትምርት ቤት መክፈል አዳግቶታል። መንግሥት ለእያንዳንዱ መርከበኛ 1000 ሩፒ ለመስጠት ቃል ቢገባም፤ ገንዘቡ የመብራት ክፍያን እንኳ አይሸፍንም። “ነጋችን ጨምሟል። ቱሪስቶች ስለሚፈሩ አይመጡም። ያለንበት ወቅት ለካሽሚር ነዋሪዎች ከባድ ሆኗል። በተለይ ቱሪዝሙ በጣም ተቀዛቅዟል። ተስፋ ስለቆረጥኩ ለፈጣሪ ትቼዋለሁ።” ፋላህ ሳላህ ታዳጊዋ ፋላህ ሳላህ የ12 ዓመቷ ፋላህ “በተቀረው ሕንድ ታዳጊዎች የተሻለ የትምህርት እድል አላቸው። እኔ ግን መሠረታዊ ትምህርት ማግኘት አልቻልኩም። በዚህ እድሜ አስፈላጊውን እውቀት ካላገኘን በፈተና ተወዳዳሪ መሆን አንችልም” ትላለች። ፋላህ መሠረታዊ የሳይንስ እና ሒሳብ እውቀት እንደሌላት ትናገራለች። ኢንተርኔት በመቋረጡ ምክንያት ለጥያቄዎቿ መልስ ማግኘትም አልቻለችም። “አሁን ኢንተርኔት ቢመለስም በጣም ዝግ ያለ ነው። መጽሐፍ ላንብብ ብልም የተጻፈውን መገንዘብ አልችልም” የምትለው ፋላህ፤ ትምህርት ቤትና ጓደኞቿ እንደናፈቋት ትናገራለች። “ለዓመት ከቤት አልወጣሁም። ሌላ አገር ውስጥ ለአንድ ዓመት እንቅስቃሴ ቢቆም ተማሪዎች ተቃውሞ ይወጡ ነበር። እኛ ግን መቃወም አንችልም። ከተቃወምን እንታሰራለን።” የሆቴል አስተዳዳሪው ሳጂድ ፋሩቅ ሳጂድ ሆቴል አስተዳዳሪ ነው። አያቶቹና ቤተሰቦቹም ነጋዴ የነበሩት የ43 ዓመቱ ሳጂድ በካሽሚር ተስፋ ቆርጧል። በ1990ዎቹ የሕንድ አገዛዝን በመቃወም እንቅስቃሴዎች ከተጀመሩ ወዲህ ካሽሚር በግጭት እየተናጠች ሰዎች እየሞቱ መሆኑንም ይናገራል። “ይህ ሆቴል የተሠራው በሦስት ትውልድ ነው። ግን ከ1990ዎቹ ወዲህ እየተንገዳገድን ነው” ንግዱ አስተማማኝ እንዳልሆነ ሳጂድ ያስረዳል። ሆቴሉ መብራት ቢጠቀምም ባይጠቀምም 200 ሺህ ሩፒ ይከፍላል። “ነገሮች ይሻሻላሉ ብዬ አልጠብቅም። ካሽሚር ስታዝን የተቀረው አገር ይደሰታል። የተቀረው አገር ሲደሰት እኛ እናዝናለን። ሁሉም ነገር ፖለቲካ ሆኗል። ሁሉም ነገር ውስጥ ግጭት አለ። ታዲያ በዚህ ሁኔታ እንዴት ይነገዳል?” አርሶ አደሩቢላል አህመድ አርሶ አደሩቢላል አህመድ የ35 ዓመቱ አርሶ አደር ቢላል ፍራፍሬ ያመርታል። የአየር ሁኔታ መዛባት ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጨምሮበት አጣብቂኝ ውስጥ ስለገባ መሬቱን ለመሸጥ እያሰበ ነው። “ሥራ አጥ ከሆንን ዓመት ተቆጠረ። አፕል ከ100 ሺህ እስከ 150 ሺህ ሩፒ ገቢ ያስገባ ነበር። ዘንድሮ ግን 30 ሺህ ሩፒ ብቻ ነው ያገኘሁት። ወንድሜ 1200 ሳጥን አፕል ሰብስቦ ገዢ ስላጣ ምርቱን ጣለው። በዚሁ ከቀጠልኩ መሬቴን እሸጣለሁ።” ሸክላ ሠሪው መሐመድ ሳዲቅ መሐመድ 39 ዓመቱ ነው። አስፈላጊውን ግብዓት ማግኘት ስላልቻለ የሸክላ ሥራውን ለማቆም ተገዷል። መንግሥት በቅርቡ ከሌላ አካባቢ ለሄዱ ነጋዴዎች ፍቃድ ስለሰጠ እንደ መሐመድ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ተወላጆች ከሥራቸው ተፈናቅለዋል። “መንግሥት አፈር እንዳይቆፈር ወስኗል። የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነው ይላሉ። ለመሆኑ ፍርድ ቤቶች ይህን ሁሉ ዘመን የት ነበሩ? እንደኔ ያሉ ድሆች ቤተሰቦች ጉዳይ ፍርድ ቤቶችን አያሳስባቸውም? በረሀብ ሊገሉን ነው እንዴ? እንቅስቃሴ ስለተገታ የሠራሁትን መሸጥ አልቻልኩም። አዳዲስ የሸክላ ሥራ መሥራት አቁሜ የቀን ሠራተኛ ሆኛለሁ።”
news-49984209
https://www.bbc.com/amharic/news-49984209
ሜክሲኮ ውስጥ አንድ ከንቲባ በመራጮቻቸው መኪና ላይ ታስረው ተጎተቱ
በደቡባዊ ሜክሲኮ የአንድ አካባቢን ከንቲባ ከጽህፈት ቤቱ አስወጥተው የጭነት መኪና ኋላ አስረው ጎዳናዎች ላይ ጎትተዋል ተብለው የተጠረጠሩ አስራ አንድ ሰዎች ተያዙ።
ከንቲባው ከመኪና ጋር ታስረው ሲጎተቱ ከሚያሳየው ቪዲዮ ላይ የተገኘ ምስል በከንቲባው ልዊስ ኤስካንደን ላይ ድርጊቱ ሲፈጸም ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ያስቆመ ሲሆን ከንቲባውም ከባድ ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፋቸውም ተነግሯል። ከንቲባው የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ጊዜ የአካባቢውን መንገድ እጠግናለሁ ብለው የገቡትን ቃል አልፈጸሙም በሚል ነው ይህ ጥቃት የተሰነዘረባቸው። የአካባቢው አርሶ አደሮች በከንቲባው ላይ ጥቃት ሲፈጸሙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ግምቶች አሉ ከጥቃቱ በኋላ ጸጥታ ለማስከበር ተጨማሪ የፖሊስ መኮንኖች ወደ ቺያፓስ ግዛት መሰማራታቸው ተነግሯል። ሜክሲኮ ውስጥ ከንቲባዎችና ፖለቲከኞች ዕፅ አዘዋዋሪዎች የሚጠይቋቸውን ነገር አላሟላም ወይም አልተባበርም በሚሉ ጊዜ ለጥቃት መጋለጣቸው የተለመደ ነገር ሲሆን፤ ፖለቲከኞች በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የገቡትን ቃል መፈጸም ሲሳናቸው እንዲህ አይነት ጥቃት መሰንዘር የተለመደ አይደለም። ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ከንቲባም በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ የአፈናና የግድያ ሙከራ ወንጀል ክስ እመሰርታለሁ ብለዋል። በአካባቢው የነበሩ ሰዎች የቀረጹት ነው በተባለ ቪዲዮ ላይ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከንቲባውን ከጽህፈት ቤታቸው ጎትተው በማስወጣት ከመኪናው ኋላ በጉልበት ሲጭኗቸው ይታያል። መንገድ ላይ ከተተከሉ የደህንነት ካሜራዎች የተገኘው ምስል ደግሞ የከንቲባው አንገት ላይ ገመድ ታስሮ ሳንታ ሪታ በተባለው ጎዳና ላይ በመኪናው ሲጎተቱ ያሳያል። • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ መኪናውን በማስቆም ከንቲባውን ከዚህ ጥቃት ለማስጣል በርካታ ፖሊሶች ጥረት ያደረጉ ሲሆን፤ በጥቃት አድራሾቹን በፖሊሶች መካከል በተፈጠረው ግብግብ ብዙ ሰዎች የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአራት ወራት በፊት ደግሞ ከንቲባው ላይ ጥቃት ለማድረስ ወደ ጽህፈት ቤታቸው የሄዱ ሰዎች ቢሯቸው ውስጥ ስላላገኟቸው ንብረት አውድመው መሄዳቸው ተነግሯል። ለከንቲባነት ከተደረገው ውድድር ቀደም ብሎ አሁን ጥቃት የተፈጸመባቸው ከንቲባ ከእጩ ተፎካካሪያቸው ደጋፊዎች ጋር አምባጓሮ ውስጥ ገብተው ነበር ተብለው ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ነበር። በኋላ ግን ማስረጃ ስላልተገኘ ተለቀዋል።
news-44281318
https://www.bbc.com/amharic/news-44281318
ብሩንዲ በፈረንሳይ ኤምባሲ ለእርዳታ የተበረከቱላትን አህዮች ስድብ ነው በማለት አጣጣለች
የፈረንሳይ ኤምባሲ በብሩንዲ ጊቴጋ መንደር ለሚኖሩ ሰዎች አስር አህዮችን በእርዳታ መለገሱን ተከትሎ፤ የአገሪቷ ፕሬዚዳንት ፒኤሬ ንኩሩንዚዛ አማካሪ ዘለፋ ነው ሲሉ ለ ኤ ኤፍ ፒ ገለፁ።
የግብርና ሚኒስቴር ሴቶችና ህፃናት ላይ የሚሰራ አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅትን ወክሎ አህዮቹ ከጎረቤት አገር ታንዛኒያ እንዲገዙ ጠይቋል። ግብረ ሰናይ ድርጅቱ በሴቶችና ህፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን፤ ሴቶችና ህፃናት የግብርና ውጤቶችን፣ ውሃ ፣ እንጨትና ሌሎች ቁሳቁሶችን እንዲያመላልሱበት በማድረግ ሸክማቸውን ለማቅለል በማለም ነበር አህዮቹን ለመግዛት እቅድ ውስጥ የገባው። የግብርና ሚንስትርሩ ዲዮ ጋይድ ሩሬማ ያለ ምንም ሂደት አህዮቹ ከተሰጡበት አካባቢ በአስቸኳይ ተሰብስበው እንዲመጡ የአካባቢው አስተዳዳሪ እንዲያስተባብሩ ጠይቀዋል። የብሩንዲ ምክርቤቱ ፕሬዚዳንት ቃለ አቀባይ የሆኑት ጋቢይ ቡጋጋ በበኩላቸው "ፈረንሳይ ወደ አህያ ደረጃ አውርዳናለች ፤እውነት ለመናገር አህያ የምን ምልክት ነው?" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል። የፈረንሳይ አምባሳደር ሎረንት ደላሆውሴ በበኩላቸው "እያንዳንዱ ሒደት የታወቀ ነበር ፤ ይህም አዲስ ነገር እንዳልሆነና ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ፕሮጀክት ከቤልጂየም በተገኘም እርዳታ በምስራቅ ሩይሂ ግዛት ተመሳሳይ ድጋፍ ተደርጓል ፤ነገር ግን ምንም ዓይነት ምላሽ አልተሰጣቸውም" ብለዋል። አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአውሮፓ ዲፕሎማት ፈረንሳይ ከወራት በፊት በብሩንዲ ህገ መንግስቱን ለማሻሻል በተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ላይ ትችት በመሰንዘሯ ምክንያት ለእርሱ የተሰጣት አፀፋዊ ምላሽ ነው ሲሉ ለ ኤ ኤፍ ፒ ተናግረዋል። ፈረንሳይ በህዝበ ውሳኔው ላይ ህገ መንግስቱ የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ቆይታን በማራዘም እስከ አውሮፓውያኑ 2034 ድረስ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችላቸው ነው በማለት መተቸቷ የሚታወስ ነው።
news-53021261
https://www.bbc.com/amharic/news-53021261
በመሪዋ ድንገተኛ ሞት ግራ መጋባት ውስጥ ያለችው ቡሩንዲ
ከሳምንታት በፊት በተደረገ ምርጫ ፓርቲያቸው ማሸነፉ የተነገረላቸው የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛ በድንገት ማለፍን ተከትሎ ማን ይተካቸዋል? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ በአገሪቱ ግራ መጋባት ተፈጥሯል።
ፕሬዝዳንቱ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ወርሃ ነሐሴ ላይ ስልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ ቢጠበቅም በሕገ መንግሥቱ መሰረት ለጊዜው የእሳቸውን ቦታ ሊተኩ የሚችሉት የፓርላማው አፈ ጉባኤ ናቸው። ነገር ግን እስካሁን ድረስ አፈ ጉባኤው ቃለ መሐላ ያልፈጸሙ ሲሆን የፕሬዝዳንቱ መንበርም ያለተተኪ ባዶ ሆኖ የስልጣን ክፍተት ተፈጥሯል። ካቢኔው ሐሙስ ዕለት ስብሰባውን ያደረገ ሲሆን ስብሰባውን የመሩት ከሁለቱ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ተቀዳሚው ናቸው። በስብሰባውም በድንገት ያጋጠመውን የፕሬዝዳንቱን ሞት እንዴት እንደሚወጡት ተወያይተዋል። በአገሪቱ በተፈጠረው የስልጣን ክፍተት ምክንያት በገዢው ፓርቲ ውስጥ የስልጣን ሽኩቻ እንዳለ የተገለጸ ሲሆን፤ ከገዢው ፓርቲ ምክትሉ ኢቫሪስት ንዳዪሺምዬ እና የፓርላማው አፈ ጉባኤ ፓስካል ንያቤንዳ ዋነኛ ተፋላሚዎቹ ናቸው ተብሏል። ባሳለፍነው ጥር ወር ሁለቱም በገዢው ፓርቲ በኩል ፕሬዝዳንታዊ እጩ ለመሆኑ ሲዘጋጁ እንደነበርም ተገልጿል። ባለፉት 20 ዓመታት በስልጣን ላይ ሳሉ ህይወታቸው ያለፈ አፍሪካ አገራት/ግዛት መሪዎች የቡሩንዲ መንግሥት ቃል አቀባይ ፕሮስፐር ንታሆዋሚዬ ለቢቢሲ እንደገለጹት፤ አሁን ያለው ሁኔታ በፍርድ ቤት ይፈታል ብለዋል። "ከሕገ መንግሥት ፍርድ ቤቱ ጋር እየተመካከርን ነው። አሁን ያለውን የስልጣን ክፍተት እያጠናው ነው። ነገር ግን ጥቂት ቀናትን ሊወስድ ይችላል'' ብለዋል። በሌላ በኩል የፕሬዝዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ ሞት ጉዳይ አሁንም በርካታ መላ ምቶችን እያስተናገደ ነው። በርካቶች ፕሬዝዳንቱ የሞቱት በኮሮናቫይረስ ነው ቢሉም መንግሥት መጀመሪያ ላይ እንዳለው በልብ ሕመም መሞታቸውን አጠንክሮ እየገለጸ ነው። የፕሬዝዳንቱን ሞት ተከትሎ በታወጀው የሰባት ቀናት ብሔራዊ ሐዘን ወቅት ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ ከመንፈሳዊ ዝማሬዎች ውጪ ሌሎች ሙዚቃዎች እንዳይከፈቱ የአገሪቱ ካቢኔ ወስኗል። ከዚህ በተጨማሪ በአገሪቱ የሚገኙ የመንግሥት እና የግል ሬዲዮ ጣቢያዎች የፕሬዝዳንቱ ሞት ከተነገረበት ዕለት አንስቶ መንፈሳዊ ዝማሬዎችን ብቻ ነው እያሰሙ ያሉት።
news-51187796
https://www.bbc.com/amharic/news-51187796
የትራምፕን የክስ ሂደት በቀላሉ እንዲገነዘቡ የሚረዱ 5 ወሳኝ ጥያቄዎች
በአሜሪካ ታሪክ ሶስተኛው ፕሬዝደንት ከስልጣናቸው እንዲነሱ የክስ ሂደት ተጀምሮባቸዋል።
(ከግራ ወደ ቀኝ) በሴኔቱ የዲሞክራቶች መሪ ቸክ ሹመር፣ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና በሴኔቱ የሪፓብሊካን መሪ ሚች ማክኮኔል። ይህ የክስ ሂደት ፕሬዝደንት ትራምፕን ከስልጣናቸው ከማስወገዱም በተጨማሪ ዘብጥያ እስከመውረድ ሊያደርሳቸው ይችላል። የትራምፕ ከስልጣን መነሳት (ኢምፒችመት) ችሎት ሂደትን በቀላል እንዲገነዘቡ 5 ወሳኝ ጥያቄዎች ተመልሰዋል። 1) 'ኢምፒችመንት' ምንድነው? 'ክስ' የሚለው ቃል ሊተካው ይችላል። በቀላሉ ስልጣን ላይ የሚገኙ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ወንጀል ፈጽመው ከሆነ ተጠያቂ የሚደረጉበት የሕግ ስርዓት ወይም አካሄድ ማለት ነው። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለዶናልድ ትራምፕ ቅሬታ ምላሽ ሰጡ • እውን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ተቀስቅሶ እናየው ይሆን? እነሆ ምላሹ በዚህ ሂደት ፕሬዝደንት ትራምፕ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "ኢምፒች" መደረጋቸው ይታወሳል። ይህ ማለት የትራምፕ ጉዳይ ከተወካዮች ምክር ቤት ወደ ሴኔቱ ተላልፏል ማለት ነው። ትራምፕ በቀረበባቸው ክስ መሠረት ጥፋተኛ ናቸው ወይስ አይደሉም ለሚለው ውሳኔ የሚሰጠው ሴኔቱ ይሆናል። 2) ትራምፕ የቀረበባቸው ክስ ምንድነው? ትራምፕ በሁለት አንቀጾች ክስ ቀርቦባቸዋል፤ ወይም 'ኢምፒች' ተደርገዋል። የመጀመሪያው 'ፕሬዝዳንቱ ስልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል' የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ 'የምክር ቤቱን ስራ አደናቅፈዋል' የሚል ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ2020 ምርጫ የመመረጥ እድላቸውን ለማስፋት በተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ላይ ምረመራ እንዲካሄድ የዩክሬን ፕሬዝደንት ላይ ጫና አድርገዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ጆ ባይደን የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት ሳሉ ወንድ ልጃቸው በዩክሬን የንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ነበር። ታዲያ ትራምፕ፤ ተቀናቃኛቸውን ሊያሳጣ የሚችል መረጃ ለማግኘት የዩክሬን ፕሬዝደንት ላይ ጫና በማሳደር ሥልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ሁለተኛው ደግሞ ትራምፕ ለሚደረግባቸው ምርመራ መረጃዎችን ለመስጠት ተባባሪ ባለመሆናቸው የምክር ቤቱን ስራ በማደናቀፍ በሚለው ክስ ላይ ድምጽ ሰጥተዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ግን የቀረቡባቸውን ክሰቦች ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደርጋሉ። 3) ከሴኔቱ ምን ይጠበቃል? በሴኔቱ የችሎቱን ወይም የክሱን አካሄድ የሚወስኑ ሁለት ቁልፍ የሴኔቱ አባላት አሉ። በሴኔቱ የሪፓብሊካን መሪ የሆኑት ሚች ማክኮኔል እና የዲሞክራት መሪው ቸክ ሹመር ናቸው። ሁለቱ መሪዎች ማስረጃዎች ለሴኔቱ በምን አይነት መልኩ ይቀርባሉ? የምስክሮች እማኘነትስ እንዴት ይስማሉ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ቀድመው መስማማት አለባቸው። ትራምፕ ጥፋተኛ ናቸው ለማለት እና ከስልጣን ለማስነሳት የሴኔቱ 2/3 ድምጽ ያስፈልጋል። ይህ ማለት ከ100 የሴኔት መቀመጫ 67ቱ ትራምፕ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማስተላለፍ ይኖርባቸዋል። የትራምፕ አጋር የሆኑት ሪፓብሊካኖች በሴኔቱ አብላጫ የሆነ 53 መቀመጫ አላቸው። የትራምፕ ተቀናቃኝ የሆኑት ዲሞክራቶች በሴኔቱ ያላቸው መቀመጫ 47 ብቻ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ትራምፕ ላይ የተነሳው ክስ ውድቅ ሊሆን እንደሚችል በርካቶች ገምተዋል። ከተገመተው ውጪ ሆኖ ትራምፕ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ፤ ከስልጣን ይባረራሉ፤ ከዚያም ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ መንበረ ስልጣኑን ይረከባሉ። በዚህ ብቻ ሳይወሰን፤ የትራምፕ ጉዳይ በወንጀል ሕግ ታይቶ ከስልጣን በኋላ ዘብጥያ ሊወርዱም ይችላሉ። 4) ትራምፕ በሴኔቱ ፊት ቀርበው መከላከያቸውን ያቀርቡ ይሆን? ፕሬዝደንት ትራምፕ ከሴኔቱ ፊት ቀርበው መከላከያዎቻቸውን ማቀረብ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ጠበቆቻቸው እንጂ እሳቸው ከሴኔት ፊት ይቀርባሉ ተብሎ አይገመትም። • ዶናልድ ትራምፕን ከዝነኛው ፊልም ማን ቆርጦ ጣላቸው? • ዶናልድ ትራምፕ በመከሰስ ሶስተኛ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆኑ ትራምፕ ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በሴኔቱ ፊት ቀርበው እንዲመሰክሩላቸው አጥብቀው ይሻሉ። ዲሞክራቶች በበኩላቸው፤ የቀድሞ የብሔራዊ ደህንነት ኃላፊ ጆህን ቦልተን ጨምሮ ከፍተኛ የዋይት ሃውስ ባለስልጣናት ቃላቸውን እንዲሰጡ ይፈልጋሉ። 5) የዚህ ጉዳይ ማብቂያ መቼ ይሆን? ማንም በእርግጠኝነት መናገር ባይችልም የክስ ሂደቱ ለሳምንታት ሊዘልቅ ይችላል። የቢን ክሊንተን የክስ ሂደት አራት ሳምንታት ወስዷል። ዲሞክራቶች በተቻለ መጠን የክስ ሂደቱ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋሉ። ምክንያቱም በ2020 ምርጫ ዲሞክራቶችን ወክሎ የሚወዳደረውን እጩ መምረጥ ይፈልጋሉና።
news-49737845
https://www.bbc.com/amharic/news-49737845
አሜሪካ፡ ''ሳዑዲን ያጠቁት ድሮን እና ሚሳዔሎች መነሻቸው ከኢራን ነው''
አሜሪካ ሳዑዲ ላይ የተቃጡትየድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶች መነሻቸው ከኢራን ስለመሆኑ ደርሼበታለው አለች።
አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት ባለስልጣን ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማትን ዒላማ አድርገው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱት ጥቃቶች መነሻቸው ከደቡባዊ ኢራን ነው። ኢራን በበኩሏ ከጥቃቶቹ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም ስትል ቆይታለች። በየመን የሚንቀሳቀሱት እና በኢራን ድጋፍ የሚደረግላቸው የሁቲ አማጽያን በሳዑዲ ጥቃቱን ያደረስነው እኛ ነን ቢሉም ሰሚ አላገኙም። • ሳዑዲ ላይ በተፈጸመው ጥቃት የኢራን እጅ እንዳለበት የአሜሪካ መረጃ ጠቆመ • አሜሪካ ለምን ከምድር በታች ነዳጅ ዘይት ትደብቃለች? የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ ''የድሮን ጥቃቱ ከየመን ስለመነሳቱ የሚያሳይ ምንም አይነት ማስረጃ የለም። ሁሉም መንግሥታት ኢራን በዓለም የኢንርጂ ምንጭ ላይ የሰነዘረችውን ጥቃት ማውገዝ አለባቸው'' ለማለት ጊዜ አልወሰደባቸውም ነበር። ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት ባለስልጣን ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ጥቃቱ የተሰነዘረበት አቅጣጫ እና ስፋት ከግምት ውስጥ ሲገባ የሁቲ አማጽያን ፈጽመውታል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል። የሁቲ አማጽያን ከዚህ ቀደም ወደ ሳዑዲ የድሮን ጥቃቶችን አድርሰዋል፤ ሚሳዔሎችንም አስወንጭፈዋል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ይህን ጥቃት ግን የሁቲ አማጽያን መፈጸም የሚያስችል ቁመና የላቸውም፤ እንዲሁም ጥቃቶቹ የተሰነዘሩት በየመን የሁቲ አማጽያን ከሚቆጣጠሩት ስፍራም አይደለም። በሳዑዲ ላይ ጥቃቱ ከተሰነዘረ በኋላ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጨማሪ ማሳየቱ ይታወሳል። የሳዑዲ አረቢያ ኢነርጂ ሚንስትር ትናንት (ማክሰኞ) በነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማቱ ላይ የደረሰው ጉዳት ተጠግነው ወደ ቀደመ የማምረት አቅማቸው በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ይመለሳሉ ብለዋል። አሜሪካ ምን እያለች ነው? የአሜሪካ ባለስልጣናት የሳዑዲን ነዳጅ ማቀነባበሪያ ለመምታት ጥቅም ላይ የዋሉት የድሮን እና ሚሳዔል አይነቶችን ለይተናል ብለዋል። ጥቃቱ ከደረሰበት ስፍራ በሚሰበሰቡ ቁሶች ላይ የሚደረገው የፎረንሲክ ምርመራ ውጤት ኢራን እጇ እንዳለበት የማያወላውል መረጃ ማሳየታቸው አይቀሬ ነው እያሉ። ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ትናንት "አሜሪካ ሁሉንም መረጃዎች እየመረመረች ነው" ካሉ በኋላ የውጪ ጉዳይ ቢሮው ኃላፊ ማይክ ፖምፔዎ "ምላሻችን ምን መሆን አንዳለበት ለመወያየት" ወደ ሳዑዲ እያቀኑ ነው ብለዋል። • በሳዑዲ ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ • በሳዑዲ የደረሰው ጥቃት እጅጉን እንዳሳሰባቸው የኔቶ ኃላፊ ገለፁ "ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የእራሷን እና የወዳጅ ሃገራትን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ከመውሰድ ወደኋላ አትልም። በዚህ እርግጠኛ ሁኑ" ሲሉ ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ተደምጠዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት ፕሬዝደንት ትራምፕ ለጥፋቱ ማን ተጠያቂ እንደሆነ ስለምናውቅ "አቀባብለን" የሳዑዲ መንግሥት ምክረ ሃሰብ ምን እንደሆነ እየጠበቅን ነው በማለት ወታደራዊ አማራጭ ከግምት ውስጥ እንደገባ አመላክተዋል። የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ጃቫድ ዛሪፍ በትዊተር ገጻቸው ላይ አሜሪካ እውነቱን አምና መቀበል አልፈለገችም ካሉ በኋላ ይህን ሁሉ እስጥ አገባ ማስቆም የሚቻለው በየመን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ማስቆም ሲቻል ነው ብለዋል።
54869295
https://www.bbc.com/amharic/54869295
በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አለፈ
በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አለፈ።
በበርካታ አገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን ተከለትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አልፏል። እንደጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ ከ1.25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። በብዙ አገራት በቂ ምርመራ ባለመደረጉ እንጂ ይህን አሃዝ ከፍ ያለ ነው ተብሎ ይገመታል። ሮይተር በበኩሉ ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር ማገርሸቱ ከተመዘገበው ቁጥር ውስጥ ሩብ ለሚሆነው ድርሻ አለው ሲል ዘግቧል፡፡ ቀደም ሲል የቫይረሱ ስርጭት ማዕከል የነበረችው አውሮፓ 12.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት 305,700 ደግሞ ህይወታቸው አልፎፋባት በድጋሚ የቫይረሱ ስርጭቱ ማዕከል ሆናለች፡፡ በአሜሪካ 10 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በቀን ከ125,000 በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የችግሩን መጠን ከማሳነስ ባለፈ የአፍና የአፍንጫ ጭምብል ማድረግ እና አካላዊ ርቀት ማስጠበቅን ባይቀበሉም ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሙሉ ሃይላቸው እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል። ባይደን በጥቂት ቀናት ከፍተኛ የሳይንስ ሊቃውንትን ያካተተ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል ለማቋቋም ቃል ገብተዋል። ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ እና ሁሉም አሜሪካዊያን ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ሲሆኑ የአፍና የአፍንጫ ጭንብል እንዲያደርጉ ለመጠየቅ አቅደዋል። ባይደን ወረርሽኙ በአገሪቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ኃላፊነታቸውን ሊረከቡ ይችላሉ ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ኮሚሽነር ዶ/ር ስኮት ጎትሊብ ገልጸዋል። እንደ ዶ/ር ጎትሊብ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ጥር መጨረሻ ድረስ መቀነስ ይጀምራል። "ብቸኛው ጥያቄ በዚህ ጊዜ ውስጥ ስንት ሰዎች ይሞታሉ እና ምን ያህል ሰዎች ይያዛሉ የሚለው ነው" ብለዋል፡፡ በአውሮፓ ፈረንሳይ እሁድ 38,619 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ቅዳሜ ከፍተኛ ሆኖ ከተመዘገበው የ86,852 ቁጥር ግን በጣም ያነሰ ነው፡፡ ሆኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ መረጃ የመሰብሰብ ችግሮች እንደነበሩበት በመግለጽ ሰኞ እርማት እንደሚያደረግ ገልጿል ፡፡ ህንድ እና ብራዚልም እንዲሁ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡
50805233
https://www.bbc.com/amharic/50805233
ደሃ ሃገራት የምግብ እጥረት እንዲሁም ከልክ በላይ ውፍረት እንደሚያስቸግራቸው ተገለፀ
በደሃ ሀገራት የሚገኙ ሰዎች ከልክ በላይ ውፍረትም ሆነ ከፍተኛ የምግብ እጥረት እንደሚያስቸግራቸው አንድ የወጣ ሪፖርት አስታወቀ።
ዘ ላንሴት ላይ የወጣው ይህ ሪፖርት ለዚህ ምክንያት ያለውን ሲያስቀምጥ በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦች በብዛት መመገብ እንዲሁም የስፖርታዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ መሆኑን አስፍሯል። ሪፖርቱን ይፋ ያደረጉት ባለሙያዎች ይህንንን ከልክ በላይ ውፍረት እንዲሁም ከፍተኛ የምግብ እጥረት "ዘመናዊ አመጋገብ ሥርዓት" በማለት እንዲለውጡ ጠይቀዋል። በዚህ የተጎዱ የተባሉ ሀገራት ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራትና የእስያ ሀገራት ናቸው። • ጨው በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ሰዎችን ይገድላል • አፍሪካዊያን ተወዳጅ ምግባቸውን መተው ሊኖርባቸው ይሆን? ይህ ሪፖርት በዓለማችን ላይ 2.3 ቢሊየን ህጻናትና አዋቂዎች ከልክ በላይ ውፍረት እንደተጠቁ የተጠቀሰ ሲሆን፣ 150 ሚሊየን ሕጻናት ደግሞ የተገደበ እድገት አላቸው ሲል ያስቀምጣል። ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት በእነዚህ በሁለት ጉዳዮች በተመሳሳይ እንደሚጠቁ ያሰፈረው ሪፖርቱ ይህንንም " የምግብ ዕጥረት መንታ መልኮች" ሲል ይገልጻቸዋል። ይህም ማለት 20 በመቶ ሰዎች ከልክ በላይ ወፍራም፣ 30 በመቶ ዕድሜያቸው ከአራት ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ተገቢ እድገት ያለመኖር፣ እንዲሁም 20 በመቶ ሴቶች ደግሞ ከመጠን በላይ ቀጭን ናቸው ይላል። ማሕበረሰብም ሆነ ቤተሰብ እንዲሁም በየትኛውም የሕይወት መስክ የተሰማሩ ግለሰቦች በዚህ ዓይነት የምግብ ዕጥረት ሊጠቁ እንደሚችሉ ሪፖርቱ ያስቀምጣል። በ1990ዎቹ ይላል ሪፖርቱ ከ123 ሀገራት መካከል 45ቱ በዚህ ችግር ተጠቅተው የነበረ ሲሆን በጎርጎሳውያኑ 2010 አካባቢ ደግሞ ከ126 ሀገራት 48 ተጠቅተዋል። በ2010 በተደረገ ፍተሻ፣ ከ1990ዎቹ ጀምሮ 14 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት በምግብ ዕጥረት መንታ መልኮች [በተመሳሳይ ሰዓት የተገደበ እድገት እንዲሁም ከልክ በላይ ውፍረት ] ተጠቅተዋል ይላል። ሪፖርቱን ያዘጋጁ አካላት እንዳሉት ከሆነ የሃገራት መሪዎች፣ የተባበሩት መንግሥታት እንዲሁም ምሁራን ይህንን ችግር በማስተዋል የበኩላቸውን ማድረግ አለባቸው ያሉ ሲሆን ጣታቸውንም የአመጋገብ ስርዓት መለወጥ ላይ አድርገዋል። የበርካታ ግለሰቦች የአመጋገብ፣ አጠጣጥ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መለወጥ ለዚህ ሁሉ ምከንያት ነው ያሉት ባለሙያዎቹ፣ በሀገራት በየገበያ አዳራሹ የሚገኙ በቀላሉና በርካሽ የሚገኙ ምግቦች በርካታ ሰዎች ከልክ በላይ እንዲወፍሩ እያደረገ ነው ብለዋል። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን ከልጅነት ጀምሮ መመገብ እድገት ባለበት እንዲቀር የራሱ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። " አዲስ የተመጣጠነ ምግብ እውነታን እየተጋፈጥን ነው" ያሉት በዓለም ጤና ድርጅት የሥነ ምግብ ጤናና ዕድገት ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር ፍራንሲስኮ ብራንካ ናቸው። • ጨቅላ ልጅዎትን ከአቅም በላይ እየመገቡ ይሆን? " ከአሁን በኋላ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን በምግብ እጥረት የተጎዱ ወይንም ከፍተኛ ገቢ ያላቸውን ደግሞ ከልክ በላይ ውፍረት ጋር ማዛመዳችን መቅረት አለበት" ብለዋል። ሁሉም ዓይነት የምግብ ዕጥረት ጉዳት የጋራ መለያ ነው። የምግብ ስርዓታችን ጤናማ፣ በጥንቃቄ የተዘጋጁ፣ በቀላሉ የሚገኙ፣ ርካሽ፣ እና በቂ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ ይዘት ያላቸው አይደሉም ሲሉ ወቅሰዋል። ዶ/ር ብራንካ እንዳሉት የምግብ ስርዓታችን ከምርት እስከ ማቀነባበሪያ፣ ከሽያጭ እስከ ስርጭት፣ ከዋጋ ትመና እስከ ገበያ፣ አስተሻሸግና ፍጆታ እንዲሁም አወጋገድ ላይ መለወጥ ይኖርበታል። አክለውም " ፖሊሲዎችና እስካሁን በዚህ ጉዳይ ላይ የፈሰሱ ኃብቶች በሙሉ ዳግመኛ መፈተሽ አለባቸው" ይላሉ ዶ/ር ብራንካ።
51117205
https://www.bbc.com/amharic/51117205
የቀድሞ የኦነግ ጦር መሪ ጃል መሮ ከሕወሃት ጋር እየሠራ ነው?
በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ አራት ዞኖች የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በአራቱም የወለጋ ዞኖች ማለትም፤ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋና ምስራቅ ወለጋ የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን፤ የስልክ አገልግሎት የሌለባቸው ደግሞ ምዕራብ ወለጋና የቄለም ወለጋ ዞኖች ናቸው። የቴሌኮም አገልግሎቶች መቋረጥን አስመልክቶ ከኢትዮ ቴሌኮምም ይሁን ከመንግሥት የተሰጠ በቂ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የቴሌኮም አገልግሎቶቹ እንዲቋረጡ የተደረጉት መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ላይ ኦፕሬሽን እያካሄደ ነው የሚሉ መላ ምቶች በስፋት ሲነገሩ ቆይቷል። ቢቢሲ ይህን ከአካባቢው ነዋሪዎች ለማረጋገጥ ያደረገው ጥረት የቴሌኮም አገልግሎት ባለመኖሩ አልተሳካም። በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የቀድሞ የኦነግ ጦር አዛዥ ኩምሳ ዲሪባ በትግል ስሙ በስፋት የሚታወቀው ጃል መሮ በምዕራብ ኦሮሚያ እየተከናወነ ስላለው ጉዳይ ጠይቀናል። ጃል መሮ ለጥቂት ደቂቃዎች ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጓል። መሮ የሚገኘው የት ነው? የጃል መሮ እንቀስቃሴን የሚነቅፉ ፖለቲከኞች በአሁኑ ሰዓት መሮ ከወለጋ ውጪ ከሌሎች አካላት ጋር በትብብር እየሰራ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰማሉ። የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በሌለበት ወለጋ በስልክ አግኝተን ነው ያናገርነው። የት ነው የምትገኘው? ወለጋ ውስጥ ከሆንክስ ስልክ እንዴት ሊሰራ ቻለ? የሚለው የመጀመሪያው ጥያቄ ነበር። የስልክና የሞባይል ዳታ ግንኙነት መቋረጡን የሚናገረው ጃል መሮ፤ "እንዳሰቡት በኦሮሞ ነጻነት ጦር ሊገኝ የታሰበው የበላይነት መሳካት ስላልቻለ በተለየ መንገድ ሊሄዱበት የወሰኑት ውሳኔ ነው እየተካሄደ ያለው" ይላል። "መንግሥት ሲፈልግ አግልግሎቱን ለአንድ ዓመት ይዝጋው። ጦራችን በየዕለቱ በተሟላ መልኩ ግንኙነት ማድረጉን እንደቀጠለ ነው። ኪሳራው ለመንግሥት እንጂ በእኛ ግነኙነት ላይ ምንም ተጽዕኖ አያሳድርም" በማለት የተሟላ አገልግሎት እንዳለው ጠቁሟል። ጃል መሮ ከሌሎች አካላት ጋር አብሮ እየሰራ ነው ለሚለው ጉዳይ ምላሽ ሲሰጥ፤ "ስትፈልጉ መሮ ሞቷል ስትፈልጉ. . . ስትፈልጉ መሮ መቀሌ ነው ያለው... ከዚህ ቀደም ኮሎኔል ገመቹ አያና እና ዳውድ ኢብሳ ሲናገሩት እንደነበረው፤ የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ከሚደግፉ ማናቸውም አካላት ጋር አብረን ልንሰራ እንችላለን። ይህ መብታችን ነው። ለምን ሰይጣን አይሆንም። ኦሮሞን ነጻ የሚያወጣ ከሆነ አብረነው [ሰይጣን] ልንሰራ እንችላለን። ይሁን እንጂ እንደሚባለው ከህወሃት ጋር አብረን ልንሰራ አንችልም። ብዙ ጠባሳ አለብን ከህወሃት ጋር ፈጽሞ ልንሰራ አንችልም" ብሏል። "እኔ የምገኘው ኦሮሚያ ጫካ ውስጥ በወለጋ የቡና ዛፍ ሥር ነው" በማለት መሮ ምላሹን ሰጥቷል። የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እገታ 17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጸጥታ ስጋት ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲያመሩ ደምቢ ዶሎ እና ጋምቤላ መካከል ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት መታገታቸው ይታወሳል። ቢቢሲ ያነጋገራት ከአጋቾቹ ያመለጠች ተማሪ እገታው እንዴት እንደተፈጸም፣ ከአጋቾቹ እንዴት እንዳመለጠች እና የአጋቾቹ ጥያቄ ምን እንደነበረ ተናግራለች። ምንም እንኳ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው፤ ታግተው ከነበሩት ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ እንዲለቀቁ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ኃለፊው ይህን ይበሉ እንጂ፤ የተማሪዎቹ ወላጆች ''ማን ይለቀቅ ፤ ማን አይለቀቅ እስካሁን አላወቅንም'' እያሉ ይገኛሉ። ተማሪዎቹን ያገታቸው የትኛው አካል እንደሆነ በይፋ ባይነገርም፤ በምዕራብ ኦሮሚያ ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው እና በድሪባ ኩምሳ የሚመራው ኃይል ስለመሆኑ ብዙዎች ግምታቸው አስቀምጠዋል። ጃል መሮ ግን "ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማሁ ያለሁት ከእናንተ ነው። የትግል ዓላማችን ከተማሪዎች ጋር አይገናኝም። በተማሪዎቹ ላይም ይህን የተባለውን አይነት ተግባር አልፈጸምንም። እንደተለመደው የእኛን ስም ለማጉደፍ የተወራ ነው እንጂ በፍጽም እንዲህ አይነት ተግባር አሁንም ወደፊትም እንፈጽምም።'' መሮ ተማሪዎቹ ታግተውበታል በሚባለው ሥፍራ በኮንትሮባንድ ንግድ ሥራ ላይ ታጥቀው የተሰማሩ አካላት መኖራቸውን ተናግሮ፤ የእሱ ጦር ግን በአካባቢው እንደሌለ ይናገራል። በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች ዜናን መስማት የተለመደ ሆኗል። የጥቃት ዒላማዎቹ የሚያነጣጥሩት በአካባቢው ባለሥልጣናት ላይ ብቻ ሳይሆን፤ ለሥራ ወደ ወለጋ ዞኖች የሚንቀሳቀሱ ኃላፊዎችንም ይጨምራል። ለእነዚህም ባለሥልጣናት ግድያ ተጠያቂ የሚደረገው በጃል መሮ የሚመራው የታጣቂ ቡድን ነው። ጃል መሮ ግን መንግሥት የእርሱን ጦር ለማዳከም እየተጠቀመበት ያለው ስትራቴጂ መሆኑን እንጂ የእርሱ ጦር ይህን መሰል ተግባር እንደማይፈጽም ይናገራል። "በምስራቅ በኩል ኦሮሞን እና ሱማሌን እንዳጫረሱት ሁሉ አሁንም በዚህ በኩል የኦሮሞ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለማጋጨት ነው" ይላል። የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዚህ ቀደም ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ጦር እንደሌላቸው መናገራቸው ይታወሳል።
news-52266796
https://www.bbc.com/amharic/news-52266796
ነዳጅ አምራች አገራት በታሪክ ከፍተኛ የተባለለት ስምምነት ላይ ደረሱ
በኮሮናቫይረስ ምክንያት የፍላጎት መቀዛቀዝ የታየበትን የነዳጅ ምርት እንዲያንሰራራ ለማድረግ ሲባል የነዳጅ አምራች አገራት ኅብረት ኦፔክና አጋሮቹ ታሪካዊ የተባለ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ስምምነቱ በዋናነት የዓለም የነዳጅ ምርትን በ10 እጅ መቀነስ ላይ ያተኮረ ነው። ትናንት እሑድ በቪዲዮ ስብሰባ የተቀመጡት የነዳጅ አምራች አገራት ኅብረትና አጋሮቻቸው የደረሱበት ይህ ስምምነት በታሪካቸው ትልቁ ነዳጅ ምርትን ለመቀነስ ያደረጉት ስምምነት ተብሏል። አገራቱ ስምምነት ላይ ደርሰው የነበረው ቀደም ብሎ ቢሆንም ሜክሲኮ ግን ስምምነቱን ሳትደግፍ ቆይታለች። አሜሪካ ሜክሲኮ እንድትቀንስ የሚጠበቅባትን ያህል የነዳጅ ምርት በሜክሲኮ ፈንታ ለመቀነስ ቃል በመግባቷ ስምምነቱ ሊፈረም ችሏል። • ትራምፕ ጨረቃ ላይ ማዕድን ቁፋሮ እንዲጀመር ለምን ፈለጉ? • ኮሮናቫይረስን ለመቆጣጠር የፈጠራ ሥራዎቹን ያበረከተው ወጣት • የኮሮናቫይረስ ተጽዕኖ በቻይናና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ ስምምነቱ ተግባራዊ ሲሆን ወደ 10 ሚሊዮን በርሜል የነዳጅ ምርት በየቀኑ ሳይመረት ይቀራል ማለት ነው። ይህ ስምምነት ታሪካዊ የሚያስብለው ከፍተኛ ምርትን ለመቀነስ በመወሰኑ ብቻ ሳይሆን በስምምነቱ የተካተቱ አገራት ብዛት ጭምር ነው። የኦፔክ አገራትና አጋሮቻቸውን ጨምሮ ሌሎች እንደ ኖርዌይ፣ አሜሪካ፣ ብራዚልና ካናዳ ጭምር የሚፈርሙት መሆኑ ነው። ምርት የመቀነስ ስምምነቱ ሊዘገይ የቻለው ሳኡዲ አረቢያና ሩሲያ እልህ ተጋብተው ስለነበረ ነው ተብሏል። በስምምነቱ መሰረት ከግንቦት 1 ጀምሮ አገራቱ ምርታቸውን በ10 እጅ ይቀንሳሉ። ይህም ማለት በቀን 10 ሚሊዮን በርሜል ነው፤ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ኖርዌይና ብራዚል ሌላ 5 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ከዕለታዊ ምርታቸው ይቀንሳሉ። ከሐሌ ጀምሮ ግን ምርት እየጨመሩ ሄደው ምርት ቅነሳው በቀን ከ10 ሚሊዮን በርሜል ወደ 8 ሚሊዮን በርሜል እየወረደ ይመጣል። ከወር በፊት የነዳጅ ዋጋ በ18 ዓመት ታሪክ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁሎ ነበር።
news-55103341
https://www.bbc.com/amharic/news-55103341
በኬንያ ሐሰተኛ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ያቀረቡ መንገደኞች ታሰሩ
ከኬንያ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሊጓዙ ከነበሩ መንገደኞች መካከል 21ዱ ሐሰተኛ የኮቪድ-19 ምርመራ መረጃ ማቅረባቸውን ተከትሎ ለእስር መዳረጋቸው ተገልጿል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከዚህ ቀደምም ከኬንያ የሚገቡ መንገደኞች ሐሰተኛ የኮቪድ-19 መረጃ አቅርበዋል በሚል የቪዛ እገዳ ጥላለች። ተጠርጣሪዎቹ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በተወሰነ መልኩ መቀነስ አሳይቶ የነበረው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለሁለተኛ ዙር ማገርሸቱን ተከትሎ ኬንያ በርካታ ሕዝብ የሚሰባሰብባቸው ሁነቶች ላይ ገደብ ጥላለች። በሳምንቱ መጀመሪያ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሊቢያ፣ ቱኒዝያና አልጀሪያን ጨምሮ 13 አገራት ላይ የቪዛ እገዳ ጥላለች። በትናንትናው ዕለት፣ ኅዳር 17/ 2013 ዓ.ም በቁጥጥር ስር የዋሉት 21 መንገደኞች መነሻቸውን ከኬንያዋ መዲና ናይሮቢ አድርገው ወደ ዱባይ ለመሄድ ሲሉ የተያዙትም በኬንያ አየር ማረፊያ ነው። የተያዙት ሐሰተኛ የህክምና ማስረጃ ከኮቪድ- 19 ነፃ መሆናቸውን ያሳያል። በቅርቡም በተመሳሳይ ከኬንያ ወደ ዱባይ ከበረሩ መንገደኞች መካከል 100 የሚሆኑ ኬንያውያን ሐሰተኛ መረጃ ይዘው የነበሩ ሲሆን አየር ማረፊያው ላይ በተደረገላቸውም ምርመራ ግማሹ ቫይረሱ እንደተገኘባቸውም ናይሮቢ ኒውስ የተባለው የኬንያ ድረ ገፅ ዘግቧል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮም ኬንያ 80 ሺህ 102 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን 1 ሺህ 427 ግለሰቦችም በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል። በትናንትናው ዕለት ተጨማሪ 780 ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን ይህንን ተከትሎም በርካታ ሰዎች በሚታደሙባቸው ሥነ ሥርቶች ላይ አዲስ እገዳ ወጥቷል። በሠርግ ላይ መገኘት የሚችሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 50 የቀነሰ ሲሆን በቀብር ላይም 100 ሰዎች ብቻ እንዲታደሙ ታዟል። አብያተ ክርስቲያናትም የአገልግሎት ሰዓታቸውን ወደ 90 ደቂቃ እንዲቀንሱ ተደርገዋል።
54769005
https://www.bbc.com/amharic/54769005
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማን ናቸው?
ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት በመሆን ተመርጠዋል።
ባይደን የባራክ ኦባማ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። ደጋፊዎቻቸው ባይደን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ አዋቂ ናቸው ይሏቸዋል። በእርጋታቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛ በግል ሕይወታቸው አሳዛኝ ክስተቶችን አሳልፈዋል። ባይደን የፖለቲካ ሕይወታቸው የጀመረው ከ47 ዓመታት በፊት ነበር። የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን ጥረት ማድረግ የጀመሩት ደግሞ ከ33 ዓመታት በፊት እአአ 1987 ላይ። ባይደን በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት አላቸው። የቀረቡባቸው ክሶች ከአንድ ዓመት በፊት 8 ሴቶች ባይደን ጾታዊ ትንኮሳ አድርሰውብናል በማለት አደባባይ ወጥተው ነበር። እነዚህ ሴቶች ባይደን ባልተገባ መልኩ ነካክቶናል፣ አቅፎናል አልያም ስሞናል የሚሉ ክሶችን ይዘው ነው የቀረቡት። ይህንን ተከትሎ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ባይደን ከዚህ ቀደም በይፋዊ ሥነ ሥርዓቶች ላይ ሴቶችን በጣም ተጠግተው ሰላምታ ሲሰጡ የሚያሳዩ ምስሎችን አውጥተው ነበር። በአንዳንድ ምስሎች ላይ ደግሞ ባይደን ሴቶችን በጣም ተጠግተው ጸጉር የሚያሸቱ የሚመስሉ ምስሎችን አሳይተዋል። ከወራት በፊትም ረዳታቸው የነበረች ታራ ሬዲ የተባለች ሴት ባይደን ከ30 ዓመታት በፊት ከግደግዳ አጣብቀው ወሲባዊ ትንኮሳ ፈጽመውብኛል ብላ ነበር። ባይደን በበኩላቸው "ይህ በፍጹም አልተከሰተም" በሚል አስተባብለዋል። ስህተቶችን ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ባይደን በዋሽንግተን ፖለቲካ ውስጥ ረዥም ልምድ አላቸው። 8 ዓመታትን በተወካዮች ምክር ቤት፣ 8 ዓመት ሴናተር በመሆን፣ 8 ዓመት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት በመሆን አገልግለዋል። ይህ ግን ፕሬዝደንታዊ ምርጫን ለማሸነፍ ሁሌም በቂ አይሆንም። 28 ዓመታትን በሴኔት ውስጥ ያሳለፉት ጆና ኬሪ እንዲሁም 8 ዓመታትን በሴኔት እንዲሁም 8 ዓመታት ቀዳማዊት እመቤት ሆነው ያገለገሉት ሂላሪ ክሊንተር ከነሱ ያነሰ የፖለቲካ ልምድ ባላቸው እጩዎች ተሸንፈዋል። የባይደን ደጋፊዎች ግን ባይደን ይህ እጣ እንደማይገጥማቸው ተስፋ አድርገዋል። ረዥም ታሪክ ባይደን ባለፉት አስርት ዓመታት በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ በተላለፉ ቁልፍ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ውስጥ ተሳትፎ አላቸው ወይም ተሳትፎ እንዳላቸው ይነገራል። ይህ ታዲያ አሜሪካ አሁን ባለችበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ በጥሩ መልኩ የሚታይ አይደለም። ለምሳሌ እአአ በ1970ዎቹ በአሜሪካ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ጥቁር እና ነጭ ተማሪዎችን ለማሰባጠር ተማሪዎች ከሚኖሩባቸው ቦታዎች በአውቶብስ በሟጓጓዝ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለመመደብ የተደረገውን ጥረት ተቃውመው ነበር። በዚህም ዘንድሮ ባካሄዱት የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሲተቹ ቆይተዋል። እአአ 1991 ላይ የባህረ ሰላጤውን ጦርነት ተቃውመው እአአ 2003 ላይ አሜሪካ ኢራቅን እንደትወር ደግፈዋል። መልሰው ደግሞ ባይደን አሜሪካ ወደ ኢራቅ መሄዷ ትክክል አልነበረም በማለት ትችት ሲሰነዝሩ ተሰምተዋል። አሳዛኝ ክስተቶች ባይደን ባለቤታቸውን እና ሴት ልጃቸውን በመኪና አደጋ ምክንያት በሞት ተነጥቀዋል። ባይደን የመጀመሪያ የሴኔት ድላቸውን ተከትሎ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ባለቤታቸው የመኪና አደጋ አጋጥሟቸው ነበር። ባለቤታቸው እና ሴት ልጃቸው ሕይወታቸው ሲልፍ ሃንተር እና ቤኡ የተባሉት ሁለት ወንድ ልጆቻቸው ላይ ጉዳት ደርሷል። ቤኡ እአአ 2015 ላይ በአእምሮ ኢጢ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ስልጣን፣ ሙስና እና ውሸት? በሕይወት ያለው ቀሪው ልጃቸው ሃንተር ጠበቃ ሆነ። ገንዘብ ግን ሕይወቱን ከቁጥጥር ውጪ አደረገበት። ከዚያም ሃንተር ከባለቤቱ ጋር ተፋታ። በፍቺው ወረቀት ላይ የሃንተር የቀድሞ ባለቤት ሃንተር አልኮል እና አደንዛዥ እጽ እንደሚጠቀም እንዲሁም የምሽት መዝናኛ ክበቦችን እንደሚያዘወተር ገልጻለች። ሃንተር በተደረገለት ምርመራ ኮኬይን በሰውነቱ ውስጥ በመገኘቱ ከአሜሪካ ጦር ባህር ኃይል ተጠባባቂነት ተሰርዟል። ከዛም ሃንተር ባለፈው ዓመት አንድ ሳምንት ብቻ ካወቃት ሴት ጋር ትዳር መስርቷል። ይህም የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። የዩክሬኑ ጉዳይ ሃንተር በዩክሬን ብዙ ገንዘብ የሚያስከፍል ስራ አግኝተው ነበር። ፕሬዝደንት ትራምፕ፤ ሃንተር በዩክሬን ሙስና ፈጽሟል በሚል ምርመራ እንዲደረግ የዩክሬን መንግሥት ላይ ጫና አሳድረዋል ተብሏል። ትራምፕ የዩክሬኑ አቻቸው ዜሌኔስኪ ጋር ስልክ ደውለው፤ የጆ ባይደን ልጅ ሙስና ስለመፈጸሙ እንዲያጣሩ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር።
news-41925360
https://www.bbc.com/amharic/news-41925360
አሽከርካሪ አልባዋ አውቶብስ በመጀመሪያ ቀኗ ግጭት ገጠማት
በርከት ያሉ ሰዎችን አሣፍራ በላስ ቬጋስ ከተማ ስትጓዝ የነበረችው አሽከርካሪ አልባዋ አውቶብስ በመጀመሪያ ቀን ሥራዋ ከአንድ ሌላ ተሽከርካሪ ጋር ነው የተጋጨችው።
የተጎዳ ሰው እንደሌለ ያሳወቁት ባለሥልጣናቱ ጥፋቱ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲያሽከረክር የነበረ ሹፌር ነው ሲሉ ገልፀዋል። አሽከርካሪ አልባዋ አውቶብስ በአሜሪካ በሕዝብ መመላለሻ መንገድ ላይ ጥቅም በመስጠት የመጀመሪያዋ መሆን ችላለች። አውቶብሷ እስከ 15 ሰው ድረስ የማሣፈር አቅም ሲኖራት በሰዓት እሰከ 45 ኪሎ ሜትር መጓዝ ትችላለች። የላስ ቬጋስ ቃል-አቀባይ ጄስ ራድኬ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ገጭቱ ቀላል የሚባል ስለሆነ በቅርብ ቀናት ውስጥ አውቶብሷ ወደ መደበኛ ሥራዋ ትመለሳለች ሲሉ ገልጸዋል። "አሽከርካሪ አልባዋ አውቶብስ አደጋው ሲያጋጥማት ማድረግ ያለባትን ነው ያደረገችው እሱም መቆም ነው። ነገር ግን የጭነት መኪና አሽከርካሪው ሊያቆም አልቻለም" በማለት ጄስ ገልጸዋል። አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች ከዚህ በፊትም ግጭት አጋጥሟቸው የሚያውቅ ሲሆን በሁሉም አጋጣሚዎች ስህተቱ የሰው ልጅ ሆኖ ተገኝቷል። ባለሙዎች እንደሚሉት ከሆነ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች ሰው ከሚያሽከረክራቸው ተሽከርካሪዎች የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው።
43918191
https://www.bbc.com/amharic/43918191
ከባድ ዝናብና የጎርፍ አደጋ በአንዳንድ አካባቢዎች ጉዳት አስከተለ
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በደቡብ፣ በደቡብ ምሥራቅና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የጎርፍ አደጋ ተከስቷል። በዚህም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ከመድረሱ ባሻገር መንገዶች በመዘጋታቸው በአካባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎች ለችግር መጋለጣቸውን ይናገራሉ።
አሁን እየጣለ ያለው ዝናብ ለእርሻና ለተለያዩ ተግባራት የሚጠቀምና የተጠበቀ ቢሆንም መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ ግን የተለያዩ ጉዳቶችን እያስከተለ መሆኑን የሚናገሩት የጉጂ ዞን የአደጋ ስጋት አመራር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አበበ አባቡልጋ ናቸው። ይህንን ዝናብ ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ደቡብና ደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች "መንገዶች የመቆረጥ፣ ፀረ-ሰብል ተባዮች መከሰት፣ በንብረት ላይ ጥፋት መድረስና የመሳሰሉ ጉዳቶች ተከስተዋል" ይላሉ አቶ አበበ። የሚጥለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ጎርፍ ጉዳት ካደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው በባሌ ዞን መደ ወላቡ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ አህመድ ጁንዳ እንደሚሉት አደጋው የተከሰተው በዝናቡ ምክንያት ብቻ ሳይሆን በመሰረተ-ልማት ጉድለት ጭምር እንደሆነ ይጠቅሳሉ። በፌደራል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የአቅርቦትና ሎጂስቲክስ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አይድሮስ ሃሰን እንደሚሉት መንግሥት ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን፤ ነገር ግን ከጎርፍ አደጋ ጋር በተያያዘ ከሶማሌ ክልል ውጪ ከሌሎች ቦታዎች ምንም ሪፖርት እንዳለቀረበ ይናገራሉ። የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቋቋም በአንዳንድ አካባቢዎች ቀደም ተብሎ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን የማቅረብ ሥራ እንደተከናወነ የሚናገሩት አቶ አይድሮስ "በዚህ መሰረትም በቅርበት ድጋፍ የሚሰጥ ሲሆን፤ ከዚያ በላይ ከሆነ ደግሞ በሚቀርብ ጥያቄ መሰረት ከፌደራል መንግሥቱ አስቸኳይ ምላሽ ይሰጣል።" ጨምረውም ከኦሮሚያ ክልል ከጎርፍ አደጋ ጋር ተያይዞ የቀረበ ጥያቄ እንደሌለ ነገር ግን በሶማሌ ክልል አፍዴርና በሌሎች በተወሰኑ ወረዳዎች ላይ የጎርፍ አደጋ እንደነበርና መንግሥት አስፈላጊውን ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ እንደሚናገሩት አሁን አደጋው በደረሰባቸው አካባቢዎች "ከመደበኛው በላይ የሚሆን ዝናብ ሊጥል እንደሚችል ተተንብዮ ነበር" ሲሉ አስታውሰዋል።
news-53511868
https://www.bbc.com/amharic/news-53511868
የኮሮናቫይረስ መድኃኒትን ከአፍሪካ ባሕላዊ መድኃኒቶች ለመፈለግ ቡድን ተቋቋመ
ለኮሮናቫይረስ የሚሆን መድኃኒትን ከባሕላዊ መድኃኒቶች ለማግኘት የሚደረግ ጥረትን የሚደግፍና የሚያማክር ኮሚቴ በዓለም ጤና ድርጅት እና በአፍሪካ የበሽታ መከላከያ ማዕከል አማካይነት ተቋቋመ።
በአፍሪካ ውስጥ የተለያዩ ባሕላዊ የኮቪድ-19 መድኃኒቶች እንዳሉ ቢነገርም ፈዋሽነታቸው ግን አልተረጋገጠም በኮሚቴው ውስጥ የሚሳተፉት ባለሙያዎች የአፍሪካ አገራት ባሏቸው ባሕላዊ መድኃኒቶች ዙሪያ በሳይንስ፣ ደኅንነታቸውን የተጠበቀ በማድረግና በጥራት በኩል እንደሚያማክሩ ተገልጿል። ይህ ባሕላዊ መድኃኒቶችን ለኮሮናቫይረስ ለማዋል የሚደረገውን ጥረት የሚደግፈው ኮሚቴ አገራት በመድኃኒቶቹ ላይ በሚያደርጉት ሙከራ ወቅት አስፈላጊውን ዓለም አቀፋዊ የጥራት ደረጃዎችን የጠበቁ እንዲሆኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ከዓለም ጤና ድርጅት የወጣው መግለጫ ገልጿል። "ዓለም ለኮሮናቫይረስ የሚሆን የመከላከያ ክትባት እና የፈውስ መድኃኒት ለማግኘት በምትጥርበት ወቅት፤ በባሕላዊ ህክምናው ዘርፍ ያለውን ዕምቅ አቅም ለመጠቀም የሚደረገው ጥረት ሳይንስን መሰረት ያደረገ መሆን ይገባዋል" ሲሉ የአፍሪካ አካባቢ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ማሲዲሶ ሞይቲ መናገራቸውን መግለጫው አመልክቷል። ይህ የባለሙያዎች ኮሚቴ የተመሰረተው ከተለያዩ እጸዋት ተዘጋጀውን የኮቪድ-19 መድኃኒት ነው በማለት በስፋት ስታስተዋውቅ የነበረችው ማዳጋስካር በበሽታው የተያዙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህሙማን ማግኘቷን ተከትሎ ነው። በዚህ በማዳጋስካር ተገኘ በተባለው የኮሮናቫይረስ መድኃኒት ላይ የናይጄሪያ ተመራማሪዎች ፍተሻ አድርገው በእርግጥ ወረርሽኙን የመፈወስ ይዘት ማግኘት እንዳልቻሉ በዚህ ሳምንት አሳውቀዋል። የማዳጋስካሩ ፕሬዝደናት ሳይቀሩ ስለመድኃኒቱ ፈዋሽነት በመገናኛ ብዙሃን ላይ ቀርበው ተደጋጋሚ ማብራሪያ የሰጡ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ የአገሪቱ ምክር ቤት እንደራሴዎች በበሽታው መያዛቸውና ሁለት ደግሞ መሞታቸው የመድኃኒቱን ነገር ጥያቄ ውስጥ ከቶታል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ደግሞ ወረርሽኙ በሕዝቡ ውስጥ ተዛምቶ በየዕለቱ በርካታ ማዳጋስካራዊያን በበሽታው መያዛቸው ከመነገሩ በተጨማሪ የህክምና ተቋማት እየጨመረ በሚሄድ ከአቅማቸው በላይ በሆነ የህሙማን ቁጥር እየተጨናነቁ ነው ተብሏል።
news-45047215
https://www.bbc.com/amharic/news-45047215
ፌስቡክና ኢንስታግራም ላይ የምናጠፋው ጊዜ ገደብ ሊበጅለት ነው
የፌስቡክና ኢንስታግራም ተጠቃሚዎች በእነዚህ መተግበሪያዎች ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ ለመገደብ የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሆነ ፈጣሪዎቹ ገልጸዋል።
ውሳኔው ላይ የተደረሰው አብዛኛዎቹ ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከመጠን ያለፈ ጊዜ እያሳለፉ ስለሆነና ይህም በአእምሮ ጤና ላይ አሉታዊ ተጽህኖ እያስከተለ ስለሆነ ነው። • በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? • በፌስቡክ ማስታወቂያ የተሳካ ጋብቻ • ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ በዚህ መሰረት ተጠቃሚዎች በፌስቡክና ኢንስታግራም ላይ ምን ያህል ጊዜ እንዳጠፉ ማወቅ የሚችሉ ሲሆን፤ የተመደበላቸው ጊዜ ሲያልቅም አስታዋሽ መልዕክት እንዲያገኙ እንደሚደረግም ተገልጿል። በተጨማሪም ለተወሰ ሰዓት ምንም አይነት መልእክቶች ከመተግበሪያዎቹ እንዳይደርሳቸው ማድረግ ይችላሉ። አንዳንድ ተጠቃሚዎች ግን አሰራሩ ተገቢ ያልሆነና ብዙ ርቀት የማያስሄድ ነው እያሉ ነው። ''በአዲስ መልኩ የሚተዋወቀው አሰራር ስር ነቀል ለውጥ ያመጣል ብዬ አላምንም፤ እንደውም በፌስቡክና ኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ላይ ምንም አይነት የሰዓት ለውጥ አያመጣም'' ያሉት ከኦክስፎርድ ቤይነ መረብ ማእከል የመጡት ''ግራንት ብላንክ'' ናቸው። ፌስቡክ ተጠቃሚዎቹ በመተግበሪያው ላይ ብዙ ጊዜ እያጠፉ እንደሆነና ይህ ደግሞ አሉታዊ ተጽህኖዎችን እያስከተለባቸው እንደሆነ የሚያሳይ ጽሁፍ ባለፈው ታህሳስ አስነብቦ ነበር። በቅርቡ በተሰራ አንድ የሙከራ ጥናት ''በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚቺጋን'' የሚማሩ ጥቂት ተማሪዎች ለ10 ደቂቃዎች ያህል ምንም ሳይሰሩ የፌስቡክ ገጻቸውን ብቻ እንዲመለከቱ የተደረገ ሲሆን፤ ሌላኞቹ ደግሞ ፌስቡክን በመጠቀም ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩና መልእክቶች እንዲያስተላልፉ ተደርገው ነበር። በሙከራው መሰረት ፌስቡክን በአግባቡ ከተጠቀሙት ተማሪዎች ጋር ሲነጻጸር፤ ምንም ሳይሰሩ የፌስቡክ ገጻቸው ላይ 10 ደቂቃ ያሳለፉት ተማሪዎች ጥሩ ያልሆነ ስሜት ውስጥ እንደገቡ ተገልጿል።
46259192
https://www.bbc.com/amharic/46259192
በሸካ ዞን ባለው አለመረጋጋት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ለወራት ሥራ እንደፈቱ ተነገረ
በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በምትገኘው ሸካ ዞን የተለያዩ ግጭቶች መሰማት ከጀመሩ ጥቂት ወራቶችን አስቆጠሩ።
ይህም አለመረጋጋት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተማሪዎችን የትምህርት ጉዳይ አስተጓጉሏል። የዚህ ችግር መንስኤ በነዚህ ጥቂት ወራት የተከሰተ ሳይሆን ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ የሸኮ ሕዝብ ራሳችን በራሳችን እናስተዳድር የሚለው ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱ እንደሆነ በሥራ ምክንያት ነዋሪነቱን አዲስ አበባ ያደረገውና የአካባዊው ተወላጅ ኮስትር ሙልዬ ይናገራል። የያደገበትን አካባቢ 'ትንሿ ኢትዮጵያ' ሲል የሚጠራው ኮስትር የሸካ ዞን የብዙ ህዘቦች መናኸሪያም እንደሆነች ይናገራል። በተለይም ከጥቂት ጊዜ ወራት በፊት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የሆኑት ወ/ሮ ሙፈሪያት ከማል የአካባቢውን ሕዝብ ሊያናግሩ ከመጡ ወዲህ ደግሞ ነገሮች መባባሳቸውን የከተማዋ ሰላም ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መንገሻ አዲስ ይናገራሉ። የሸካ ዞን የመዠንገር፣ ሸካ እና ሸኮ ብሔሮች የሚኖሩበት ሲሆን፤ ከአፈ ጉባዔዋ ጋር በነበረው ውይይት ላይ የተሳተፉት ሰዎች እኛን የማይወክሉ ናቸው በሚል መንስዔ ችግሩ እንደተባባሰ ኮስትር ለቢቢሲ ገልጿል። «አፈ ጉባዔዋ ውይይት ላይ ሳሉ፤ ከአዳራሹ ውጭ ያሉ ወጣቶች ተቃውሞ በማሰማታቸው ወጥተው አነጋግረዋቸዋል። ቢሆንም ጉዳዩ ሊፈታ ስላልቻለ የአካባቢው ሕዝብ ተቃውሞውን በሥራ ማቆም አድማ እየገለፀ ነው፤ ትምህርት ቤቶችም ዝግ ናቸው» ብሏል ኮስትር። በቴፒ ከተማ እና የኪ በተሰኘችው ወረዳ ከሆስፒታል በቀር ሌሎች የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሥራ ላይ እንዳልሆኑ ከነዋሪዎችና ከቴፒ ከተማ ፀጥታና ፍትህ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ ተሥፋዬ አለም ሰምተናል። የከተማዋ ነዋሪዎች ጉዳዩን ለክልልም ሆነ ለፌዴራል መንግሥት እንዳቀረቡና ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጣቸውም ምሬታቸውን አሰምተዋል። • "በኢትዮጵያ 93 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ መጸዳጃ ቤት የለውም" ከተማዋ ባለመረጋጋቷና የንግድም ሆነ ሌሎች እንቅስቃሴዎች በመቆማቸው ምክንያት ልጆቻቸውን አዲስ አበባ ድረስ ልከው እያስተማሩ ያሉ ነዋሪዎች እንዳሉ ኮስትር ያስረዳል። «እንግዲህ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ አሁንም ተቸግሮ ነው ያለው፤ የቴፒ ዩኒቨርሲቲም ተማሪዎችን ያልጠራበት ምክንያት ይህ ነው።» ይላል የአካባቢው ሕዝብ ትኩረት እንዲሰጠው ነው እንቅስቃሴዎችን ወደማቆም የተገባው ሲል ኮስትር ሁኔታውን ያስረዳል፤ «ቢያንስ የፌዴራል ቢሮ ዝግ ሲሆን ለምን ሆነ ብሎ የሚመጣ አካል ይኖራል በሚል" እንደሆነ የሚናገረው ኮስትር «አዲሱ የክልሉ አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስም ጉዳዩን ያውቁታል፤ ሶስት ወር ገደማ ሆነው። ነገር ግን ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኘንም።» ብሏል። ጥያቄው ምንድነው? የደቡብ ክልል መንግሥት የዞን እና ክልል እንሁን ጥያቄዎችን በመመለስ እና በመመርመር የተጠመደ ይመስላል። «የክልሉ መንግሥት ጉዳዩን በደንብ ያውቀዋል፤ በቅርቡ ዞኖችን እንደ አዲስ ሲያዋቅር እንኳ የእኛን አካባቢ ጥያቄ ችላ ብሎታል» በማለት ኮስትር ቅሬታውን ያሰማል። የሸካ ዞን በዋናነት የሶስት ብሔር ተወላጆች ይኖሩበታል፤ ሸካ፣ ሸኮ እና መዠንገር። ከእነዚህ ብሔሮች መሃል የሸካ የበላይነት ስላለ እኛ ራሳችን በራሳችን እንደ ዞን ማስተዳደር እንድንችል ይሁን ዋነኛው ጥያቄ እንደሆነ ኮስትር እና አቶ መንገሻ ያስረዳሉ። ትላንት ረፋዱ ላይ በቴፒ ከተማ አለመረጋጋት ነበር የሚሉት አቶ መንገሻ፤ ጥያቄያቸው ከራስን ማስተዳደር ወደ መሠረተ ልማት ጥያቄ ወርዷል። ጥያቄያቸውንም ለክልል ምክር ቤት እንዲሁም ለፌዴሬሽን እንዳቀረቡ ገልፀዋል። "በጣም በርካታ ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ጩኸቱን አሰምቷል። አሁንም ቢሮዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም። በሺዎች የሚቆጠሩ የሸኮ እና የመዠንገር ተወላጆች ዛሬ ወደ ከተማ ወጥተው አወያዩን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥያቄያችንን የመሠረተ ልማት ነው ማለቱ ተገቢ አይደለም ብለው ወጥተዋል።» ብለዋል፥ • የሰው ልጅ ዘር እየመነመነ ነው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ዋና አማካሪ የሆኑት አኔሳ መልኮ ሁኔታውን አጥንተን ምላሽ እንሰጣለን ብንልም የሚሰማን ማግኘት አልቻልንም ይላሉ። «ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድር የሚሉ አሉ። እኛ ይህ ትክክል ነው ብለን ዛሬውን ምላሽ መስጠት አንችልም። በጥናት ወደፊት ይታያል ተብሎ ተነግሯቸዋል። ዛሬውኑ ይደረገልን፤ ዛሬውኑ ይጠና የሚሉ አሉ" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል አቶ አኔሳ የአቶ ሚሊዮን አስተዳደር ሁኔታውን በማረጋጋት ሥራ ላይ መጠመዱን ይናገራሉ። «አመራሩ የማረጋጋት ሥራ ላይ ነው፤ ከዚህ ውጭ የሆነ ነገር እንዳይኖር ነው የምንሰጋው። ዋናው ሰላምና መረጋጋት ነው።» ለአለመረጋጋቱ ዋናው መንስዔ የሕዝቡ ጥያቄ አለመመለስ ሆኖ ሳለ ጥያቄው መፍትሄ ሳይበጅለት ሰላም ማምጣት አይከብድም ወይ የሚል ጥያቄ ለአማካሪው ሰንዝረንላቸው ነበር። «ጥናት ይካሄዳል ብያለሁ እኮ፤ አጥኚ ቡድኑም በሰላም መንቀሳቀስ መቻል አለበት። መደማመጥ ከሌለ፤ እኔ ያልኩት ብቻ ይሰማ የሚል ባለበት እንዴት መሥራት ይቻላል?» በማለት ጥያቄ ያነሳሉ የደቡብ ክልል የገጠር ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ አክሊሉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለማነጋገር ትላንት በሥፍራው ቢገኙም ሰዎች እየመረጡ እንጂ ሁላችንንም አላነገሩንም ሲሉ ነዋሪዎቹ ይወቅሳሉ። ኃላፊውን ለማግኘት ቢቢሲ በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ሊነሳ አልቻለም። በአካባቢው የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች ተሰማርተው ፀጥታ ለማስከበር እየጣሩ እንደሆነና፤ አከባቢው አሁንም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደማይስተዋልበት ኮስትር ይናገራል ። • የደህንነት ተቋሙ ምክትል የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ፍርድ ቤት ቀረቡ
news-54768126
https://www.bbc.com/amharic/news-54768126
ሕዳሴ ግድቡ ለሱዳን ምን ይዞ ይመጣል? ከሱዳናዊቷ አንደበት
ሱዳናዊቷ ጋዜጠኛ ዘይነብ ሞሐመድ ሳሊህ፤ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው አጨቃጫቂው ግድብ ለሱዳን ሊያመጣቸው ስለሚችላቸው በረከቶች ለቢቢሲ በላከችው ደብዳቤ እንደሚከተለው ታስነብባለች።
የሱዳን አርሶ አደር በዚህ ዓመት ሱዳን ባልተጠበቀ ጎርፍ ተጥለቅልቃ ከ100 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ከ875 ሺህ በላይ ሱዳናውያን ላይ ደግሞ ጉዳትን አስከትሏል። ይህ ብቻ አይደለም። የናይል ወንዝ ውሃ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ መኖሪያ መንደሮችን ሙሉ በሙሉ አውድሟል። የኤሌክትሪክ ምሶሶዎችን ደርምሶ ሚሊዮኖችን በጨለማ አስውጧል። አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው ግደብ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ ጎርፉ ሱዳን ላይ ይህን ያክል ጉዳት ባልደረሰ ነበር። በአባይ ወንዝ 85 በመቶ ድርሻ ያላት ኢትዮጵያ፤ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቡን መገንባት ከጀመረች ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ ዓመት ደግሞ ግድቡ በውሃ መሞላት ተጀምሯል። ግድቡ በሙሉ አቅሙ ውሃ መያዝ ሲጀምር በአፍሪካ ትልቁ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ኃይል ይሆናል። ይሁን እንጂ የታችኛው የተፋሰስ አገር የሆነችው ግብጽ፤ ግድቡ የውሃ ድርሻዬን ይቀንስብኛል ስትል ትሰጋለች። ግድቡ በምን ያክል ጊዜ ይሞላ? የሚለው እስካሁን መግባባት ላይ አልተደረሰም። የዓለም አቀፍ የውሃ ሕግ እና ፖሊስ ባለሙያ የሆኑት ሱዳናዊው ሳልማን ሞሐመድ (ዶ/ር)፤ የግብጹ አስዋን ግድብ የጎርፍ ውሃን እንዴት አድርጎ በአግባቡ መጠቀም እንደሚቻል ያሳያል ይላሉ። “ዘንድሮ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ እኛ ሱዳናውያን ብዙ ሕይወት እና ንብረት አጥተናል። ግብጽን ስንመለከት ግን ምን ችግር አልገጠማቸውም። ምክንያቱም የጎርፉን ውሃ ወደ ትልቁ አስዋን ግድብ ስለሚያስገቡት ነው። እኛም እንደዚህ አይነት ግድብ ቢኖረን አንጎዳም ነበር። የኢትዮጵያ ግድብ ያድነን ነበር” ይላሉ። ይህ በእንዲህ አንዳለ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ 8 የኃይል ማመንጫ ገድቦች እንዳሏት መዘንጋት የለብንም። “የእኛ ግድቦች በጣም ትናንሽ ናቸው” ይላሉ ሳልማን ሞሐመድ (ዶ/ር)። “ግብጽ የጎርፍ ውሃውን በአስዋን ግድብ አጠራቅማ በበረሃ ላይ እያካሄደች ላለችው የግብርና ሥራ ውሃን ትጠቀማለች። የደህንነት ስጋቶች በቅርቡ በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት እየተካሄደው ባለው ድርድር፤ ግድቡ ምን ያህል ውሃ መያዝ አለበት? ምን ያህል መጠን ያለው ውሃ መለቀቅ አለበት? በሚሉት ጉዳዮች ላይ ሱዳን ወደ ግብጽ ያጋደለች ትመስላለች። ይህ አቋም በቀድሞ የሱዳን ፕሬዝደንት ኦማር አል-በሽር ይንጸባረቅ ነበር። አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የሱዳን የጦር መኮንኖች ጠንካራ የግብጽ አጋር ናቸው። በፕሬዝደንት አል-በሽር የሥልጣን ዘመን ወቅት የሱዳን ተደራዳሪ የነበሩት አሕመድ ኤል-ሙፍቲ በግድቡ ላይ የደህንነት ስጋት እንዳላቸው ከዚህ ቀደም ገልጸው ነበር። ግድቡ በአንዳች ምክንያት ጉዳት ቢደርስበት የሱዳን መዲናን ጨምሮ በቀጠናው ባሉ አገራት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ብለው ነበር። የሱዳን ባለስልጣናት ከግድቡ ግንባታ ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችልን ግጭት ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት እየደረጉ ነው። ባሳለፍነው ሳምንት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የሰጡት አስተያየት ግን ሱዳን እያደረገች ካለችው ጥረት ጋር የሚጻረር ነው። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሱዳን እና እስራኤል የሰላም ስምምነት መድረሳቸውን በማስመልከት የሁለቱን አገራት ጠቅላይ ሚንስትሮች በስልክ እያነጋገሩ ባሉበት ወቅት፤ “ግብጽ ግድቡን ልታፈነዳው ትችላለች” ማለታቸው ይታወሳል። እስከ ባለፈው ሐምሌ ወር ድረስ የሱዳን የሽግግር መንግሥት የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ያገለገሉት አስማ አብደላ ለሶስቱ አገራት የሚበጀው ምክክር ብቻ ነው የሚል ጠንካራ አቋም ይዘው ነበር። ሱዳን ግድቡ ጎርፍን ከመቆጣጠር በላይ ሌሎች ጥቅሞችን ይዞ እንደሚመጣ ስለምትረዳ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲኖር ትሻለች። ‘የአፍሪካ የኩራት ምንጭ’ እንደ ዶ/ር ሞሐመድ ከሆነ፤ የኢትዮጵያ ግድብ ሱዳን ከራሷ ግድቦች ከፍ ያለ ኤሌክትሪክ እንድታመነጭ ይረዳታል። ይህም ብቻ ሳይሆን ሱዳን ከኢትዮጵያ ርካሽ የሆነ ኤሌክትሪክ እንድትገዛ ይረዳታል። ዶ/ር ሞሐመድ ግድቡ ለሱዳን ይዞ የሚመጣው ጥቅም ይህ ብቻ አይደለም ይላሉ። የሱዳን ገበሬዎች እርሻ የሚያከናውኑት ጥቅምት እና ሕዳር ወራት ላይ መሆኑን ያስታውሳሉ። የአባይ ወንዝ ውሃ ፍሰት ላይ ቁጥጥር ማድረግ የሚቻል ከሆነ ግን ገበሬዎች በዓመት ከአንድ ግዜ በላይ ዘር ሊዘሩ እንደሚችሉ ያስረዳሉ። በድርቅ ዓመታትም ግድቡ ተጨማሪ ውሃን በመልቀቅ የሚኖረውን የዝናብ ውሃ እጥረት ሊቀርፍ ይችላል። በሱዳን መዲና ሰዎች ስለ ግድቡ ያላቸው አቋም ምን እንደሆነ ሲጠየቁ ድጋፋቸው ለኢትዮጵያ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። “እንደግፋቸዋለን ምክንያቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ርህራሄ አለን” ሲል የ44 ዓመቱ ሳላ ሃሰን ይናገራል። ሳላ የሚኖርበት ኦማዱሩማን ከተማ በቅርቡ በጎርፍ ከተጠቅለቀለቁት ከተሞች አንዷ ነች። ነዋሪነቱ በካርቱም የሆነው የ37 ዓመቱ ሞሐመድ አሊ ግድቡን እንደ የአፍሪካ ኩራት እና ለበርካቶች የሥራ እድልን ይዞ እንደሚመጣ ፕሮጀክት ነው የሚመለከተው። “በሱዳን የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን አሉ። ግድቡ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያውያኑ ከሱዳናውያን ጋር ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ሥራ የሚሰሩ ይመስለኛል” ይላል። “ፕሮጅከቱ በርካታ አፍሪካውያንን እንደመጥቀሙ ግድቡን መቶ በመቶ ነው የምደግፈው። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ አገራት በርካታ ችግሮችን አሳልፈዋል። እንዲህ አይነት የልማት ፕሮጀክት ያስፈልጋቸዋል” ብሏል ሌላው የካርቱም ነዋሪ።
news-54641714
https://www.bbc.com/amharic/news-54641714
ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስፎርዱ የክትባት ሙከራ ላይ አንድ ሰው ቢሞትም የደህንነት ስጋት የለበትም ተባለ
በአስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በጥምረት እየበለጸገ የሚገኘው የኮሮናቫይረስ ክትባት ላይ ሙከራ በሚደረግባት ብራዚል የአንድ በጎ ፈቃደኛ ሕይወቱ ማለፏን ተከትሎ ክትባቱ ምንም አይነት የድህንነት ስጋት እንደሌለበት ተገለጸ።
የብራዚል ጤና ባለስልጣን ከሙከራው ጋር በተያያዘ ሕይወቱ ስላለፈው በጎ ፈቃደኛ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቡድን በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንደሚደረግና ክትባቱ ግን ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለበት አስታውቋል። ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ በጎ ፈቃደኘው ክትባቱን አልወሰደም። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተሰራ የሚገኘው ክትባት ላይ ከሚሳተፉት በጎ ፈቃደኞች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ብቻ ሲሆን ክትባቱን እንዲወስዱ የተደረገው ቀሪዎቹ ደግሞ ማረጋገጫ የተሰጠው የማጅራት ገትር ክትባት ነው የተሰጣቸው። የሙከራው ተሳታፊ በጎ ፈቃደኞችም እራሳቸው የሚሰጣቸው የኮሮረናቫይረስ ክትባት ይሁን የማጅራት ገትር የሚያውቁት ነገር የለም። ይህ የሚደረገውም በገዛ ፈቃዳቸው ነው ተብሏል። ግዙፉ የመድሀኒት አምራች አስትራዜኔካ በበኩሉ በእያንዳንዱ የግለሰብ የሙከራ ሂደት ላይ አስተያየት እንደማይሰጥና ሙከራው ሲካሄድ ግን አስፈላጊው ጥንቃቄና የደህንነት እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውቋል። ''ሁሉም ወሳኝ የጤና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ተመርምረዋል፤ ከግምት ውስጥም ገብተዋል። ሙከራውም ሆነ የምርምር ሂደቱ ምንም አይነት አሳሳቢ ነገር አልተገኘባቸውም፤ የሚመለከታቸው ኃላፊዎችም ሂደቱን እንዲከታተሉት አድርገናል'' ብሏል። በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው የክትባት ሙከራዎች መካከል ይሄኛው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በቅርቡ ለገበያ እንደሚበቃም ይጠበቃል። እስካሁን ደረጃ አንድና ደረጃ ሁለት የሙከራ ሂደቶችን በስኬታማነት ያጠናቀቀው ይኸው ክትባት ደረጃ ሶስትን ለማጠናቀቅ ደግሞ በዩኬ፣ ብራዚልና ሕንድ በበጎ ፈቃደኞች ላይ ሙከራውን እያካሄደ ይገኛል። ባሳለፍነው ወር በዩኬ ይካሄድ የነበረው ሙከራ የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው ይችላል በሚል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ሙከራውን ለማከናወን ምንም ስጋት እንደሌለ በመገለጹ ሂደቱ በድጋሚ እንዲጀመር ሆኗል። የብራዚል ጤና ባለስልጣን በጎ ፈቃደኛው ሕይወቱ ስለማለፉ ከትናንት በስትያ መስማቱን አስታውቋል። የብራዚል መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው ሕይወቱ ያላፈችው ግለሰብ የ28 ዓመት የህክምና ባለሙያ እንደሆነና ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ሕይወቱ እንዳለፈች ዘግበዋል። ይህ ክትባት ሙሉ ፈቃድ የሚያገኝ ከሆነ ብራዚል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብልቃጦችን ለመግዛት ወስናለች። በአገሪቱ እስካሁን 5.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከአሜሪካና ሕንድ በመቀጠል በዓለማችን ሶስተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው። የሟቾች ቁጥር ደግሞ እስካሁን 155 ሺ መድረሱ ተረጋግጧል።
news-55802354
https://www.bbc.com/amharic/news-55802354
የዓለም ምግብ ድርጅት የአንበጣ መከላከያ ርጭት ለማካሄድ የገንዘብ እጥረት ገጥሞኛል አለ
የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ድርጅት (ፋኦ) በምስራቅ አፍሪካ የአንበጣ ወረርሽኝን ለመዋጋት ያሰማራቸውን አውሮፕላኖች ሙሉ በሙሉ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ሊያቆማቸው እንደሚችል አስጠነቀቀ።
የዓለም ምግብ ድርጅት እንዳለው ከሆነ አውሮፕላኖችን ለማንቀሳቀስ 38 ሚሊዮን ዶላር ይፈልጋል። አዲስ የአንበጣ ወረርሽኝ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ ተከስቶ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገበሬዎችን ሕይወት ፈተና ውስጥ መጣሉ ተልጿል። እነዚህ በአንበጣ ወረርሽኝ የተጎዱ አካባቢዎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም በከባድ ጎርፍ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል። እንደ ፋኦ ምዘና ከሆነ በኬንያ ብቻ በ11 ግዛቶች የአንበጣ ወረርሽኝ የተከሰተ ሲሆን መንጋው ወደ ታንዛንያ የባህር ዳርቻዎች እየተመመ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሰፊ የሆነ የእርሻ ማሳ በአንበጣ ወረርሽኝ የተነሳ መውደሙም ተገልጿል። በምስራቅ አፍሪካ በዚህ ዓመት ብቻ የአንበጣ ወረርሽኝ ሲከሰት ሶስተኛው ነው። አዲሱ የአንበጣ ወረርሽኝ የተራባው በሳይክሎን ጋቲ ታግዞ ሲሆን፣ በቀጠናው በአንድ ጊዜ የሁለት ዓመት ዝናብ በአጭር ቀናት ውስጥ አስከትሎ ነበር። ይህ ደግሞ ለአንበጣ መንጋ መራቢያነት ምቹ ሆኖ ማገለገሉን ባለሙያዎች ይናገራሉ። በሶማሊያ የዓለም ምግብ ድርጅት የድንገተኛ እርዳታ ማስተባባሪያ ኃላፊ የሆኑት ኢዛና ካሳ "የወረርሽኙ ተጽዕኖ ከዚህ ቀደምም ደካማ የምግብ ዋስትና የነበረው አርሶ አደር፣ ከፊል አርብቶ አደር እንዲሁም አርብቶ አደሩ ሕይወት ላይ፣ የበለጠ ጫና ያሳድራል።" ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው ከሆነ ከባለፈው ዓመት ታሕሳስ ወር ጀምሮ በመሬት እና በአየር የሚደረገው የፀረ ተባይ መድሃኒት ርጭት 1.2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ምግብ እና የወተት ተዋጽኦ ከውድመት ታድጓል። "አፍሪካ ከዚህ ቀደም በዚህ መጠን የአንበጣ ወረርሽኝ ያየችው፣ በሳህል አካባቢ ሲሆን፣ ሙሉ በሙለ ለመቆጣጠርም ሁለት ዓመት እና 500 ሚሊዮን ዶላር ያህል ያስፈልጋል።" የዓለም ምግብ ድርጅት (ፋኦ) ምክትል ዳይሬክተር ጄነራል ላውረንት ቶማስ "ይህ ወረርሽኝ በጣም ከፍተኛው ነው፣ ነገር ግን በምስራቅ አፍሪካ ለመቆጣጠር ቁርጠኝነቱ አለ። መንግሥታት እነዚህ አውሮፕላኖች መብረር እንዲችሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል።"
news-56529611
https://www.bbc.com/amharic/news-56529611
ቴክኖሎጂ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ዘልቆ ፊታችንን እያየ ነው
በፊት ገጽታ የሚከፈት ስልክ የያዙ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጎ ስልክ መክፈት እንደማይሞከር ያውቁታል።
ምንም እንኳ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጨርቆች 'ፌሻል ሪኮግኒሽን' [የፊት ቅርፅን አይቶ ማንነት የሚለይ] ቴክኖሎጂን ቢፈታተኑትም አልቻሉትም። ይህ ጉዳይ ባዕድ ሊመስል ይችላል ግን ቴክኖሎጂ በኮቪድ-19 ምክንያት ፊታችንን ላይ የምናደርገውን መሸፈኛ ዘልቀው እየለየን ነው። የዓለም ሕዝብ ሳይወድ በግዱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማጥለቅ የጀመረው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ነው። ይሄኔ ነው የፌሻል ሪኮኒሽን ነቃፊዎች የደስታ ድምጻቸውን ያሰሙት፤ የቴክኖሎጂው ሰዎች ደግሞ በሐዘን አንገታቸውን የደፉት። የፊትን ገጽታና ቅርጽ አጥንቶ ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ ማንነትን ለመለየት ሙሉ ፊትን ማየት ይፈልጋል። አንድ ተቋም 89 ለሕዝብ ጥቅም የሚውሉ ፌሻል ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅም ከ5 እስከ 50 በመቶ ስህተት አግኝቶ ነበር። ጥናቱ የተካሄደው በኮምፒውተር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የተደረገላቸው ፎቶዎችን በመጠቀም ነው። ነገር ግን አንዳንድ የፊት መለያ ቴክኖሎጂዎች አሁንም መሸፈኛውን ዘልቀው የሰዎችን ማንነት መለየት እየቻሉ ነው። ባለፈው ጥር የአሜሪካ መንግሥት የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት አንድ 96 በመቶ ስኬታማነት ያለው ቴክኖሎጂ አግንኝቷል። መሥሪያ ቤቱ ባገኘሁት ጥናት መሠረት ፎቶ ተጠቅመው ሰዎች መሸፈኛ ቢያደርጉም ማንነትን መለየት እያቻሉ ነው ብሏል። የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ሰዎች መሸፈኛቸውን አድርገው ራሳቸውን ከኮቪድ-19 እየጠበቁ ማንነታቸውን መለየቱን እንደክፋት አላየውም። ማርክ ዛከርበርግ የፌስቡክን ለየት ያለ መነጽር ባስተዋወቀበት እርግጥ ነው እንደ ለንደን ሜትሮፖለቲን ፖሊስ ያሉ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ቴክኖሎጂውን መጠቀም ቢያቆሙም ባለፈው ዓመት እንደ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' ባሉ የጥቁሮች መብት ጠያቂ ሰልፎች ላይ ቴክኖሎጂው እየተሰለለበት ነው። የአምነስቲ ኢንተርናሽናሉ ማይክል ክሌይንማን "ቴክኖሎጂው አሁን ጥቅም ላይ እየዋለ አይደለም ማለት ወደፊትም ያቆማል ማለት አይደለም" ሲሉ ለቢቢሲ ይናገራሉ። "ማንኛውም ሰው ካሜራ ያለበት አካባቢና የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ግድም ከሄደ ማንነቱ ሊለይ ይችላል" ይላሉ ማይክል። "ይህ በጣም አስፈሪ ነው። " የግል መሥሪያ ቤቶች ይህን ቴክኖሎጂ መጠቀም ያቁሙ አያቁሙ በውል አይታወቅም፤ ተመዝግቦ የተቀመጠ መረጃም የለም። ባለፈው ሰኞ ዲዝኒ ዎርልድ የተሰኘው የመዝናኛ ኩባንያ ይህን ቴክኖሎጂ ለአንድ ወር ያክል ሊሞክረው እንደሚችል ይፋ አድርጓል። ኩባንያው ደንበኞች ወደ ግቢው ሲገቡ ፊታቸውን በካሜራ ይወስድና ልዩ ቁጥር ይሰጠዋል። ዲዝኒ ይህን የማደርገው "ደንበኞች ሰልፍ ላይ እንዳይጉላሉ ነው" ይላል። ታድያ ወደ ዲዝኒ መዝናኛ ፓርክ ሲገቡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎን ማውለቅ አይጠበቅብዎትም። ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት እንኳ ቴክኖሎጂው ሰዎች ፊታቸውን ሸፍነው እንዴት ማንነታቸውን መለየት ይችላል የሚለውን ሲያጠና ቆይቷል። ጃፓን ውስጥ አንድ ድርጅቱ በአለርጂ ምክንያት ጭምብል የሚያደርጉ ሰዎችን ማንነት ለመለየት ጥናት ሲያደርግ ነበር። ድርጅቱ ባለፈው ጥር ጥናቱ 99.9 በመቶ ውጤት ማሳየቱን ይፋ አድርጎ ነበር። ቴክኖሎጂው ይህን የሚያደርገው በመሸፈኛ ያልተሸፈኑ [ዓይንና ግንባርን የመሳሰሉ] የፊት ክፍሎችን በማጥናት ነው። ኩባንያው ይህን ቴክኖሎጂ ለትላልቅ ሕንፃዎች ለመሸጥ አስቧል። ፌሻል ሪኮግኒሽን በሚቀጥለው ሐምሌ በጃፓን በሚካሄደው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ጥቅም ላይ እንደሚውል ተነግሯል። ቴክኖሎጂው እነማን ላይ እንደሚተገበር ይፋ ባይሆንም ሰዎች ኦሊምፒክ ላይ መጮህና መዝፈን እንደማይፈቀድላቸው ታውጇል። ፌስቡክም በቅርቡ ይፋ በሚያደርገው 'ስማርት መነጽር ላይ' ይህን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም እንዳሰበ ተናግሯል። ነገር ግን ብዙዎች ይህን ዕቅድ እየተቃወሙት ነው። ፌሻል ሪኮግኒሽን አሁንም አከራካሪነቱ ቀጥሏል። ወደድንም ጠላንም ቴክኖሎጂው ወደፊት እያደገ መምጣቱ አይቀርም።
news-53758758
https://www.bbc.com/amharic/news-53758758
ብልጽግና ፡ የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ንግግር "የግለሰብ እንጂ የብልጽግና አቋም አይደለም"
አማራ ብልጽግና ፓርቲ ላለፉት ሁለት ቀናት በክልሉና በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ሲያካሂድ ቆይቷል። ውይይቱን መጠናቀቅ ተከትሎ ትላንት ምሽት የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር መግለጫ ሰጥተዋል።
የሕግ የበላይነት፣ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፣ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ አደረጃጀት፣ የክረምት ሥራዎች ግምገማ፣ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ስለተፈጠሩት ጉዳዮችና የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ንግግር በውይይቱ መነሳታቸውን አስታውቀዋል። የሕግ የበላይነትን በማስከበር ረገድ በክልሉ በሕገ ወጥ አደረጃጀት ስር የነበሩትን እንዲፈርሱ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም በሕግ የሚፈለጉ ሰዎችን ለህግ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ የክልሉ ሠላም በጥንካሬ ተነስቷል ብለዋል አቶ አገኘሁ። "ክልሉ የተሟላ ሠላም ላይ ነው" ያሉት ኃላፊው "ሠላሙ ወደ ኋላ እንዳይመለስ ከሕዝቡ ጋር በጋራ እንሠራለን" ሲሉ ተናግረዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት በክልሉ እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው የምርመራ አቅምን ከማሳደግ ጀምሮ ሥራዎች መከወናቸውን አስታውቀዋል። ሆኖም እየታየ ያለው መዘናጋቱ ዋጋ እንዳያስከፍል የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ግድያና መፈናቀል የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተፈጸመውን ግድያና መፈናቀል በጉባኤው ላይ ተነስቶ መወገዙን አመልክተዋል። "ማንም ሰው እንዲሞት አንፈልግም" ያሉት አቶ አገኘሁ "ለሞቱት እና ለፍትህ ነው የምንታገለው" ሲሉ አስረድተዋል። የድርጊቱ ተሳታፊዎችን ለሕግ በማቅረብ ረገድ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ላደረገው ሥራና ችግሩ እንዳይባባስ ለሠሩ ወጣቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሐይማኖት አባቶች ፓርቲው ባደረገው ውይይት ላይ እውቅና መሰጠቱንም ጠቁመዋል። በቀጣይም አጥፊዎች ወደ ሕግ እንዲቀርቡና አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በጋራ እንደሚሠሩ አስታውቀዋል። የተፈናቀሉና ቤት ንብረት የወደመባቸውን ሰዎች ለማቋቋም የጀመርነውን ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አውስተዋል። የፓርቲው ጉባኤ ቀደም ሲል ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረትም ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ እንዲወከሉ፣ በቋንቋቸው እንዲማሩና እንዲዳኙ ለመሥራት ባቀደው መሠረት ይህንን ለማሳካት ከሌሎች ክልሎች ጋር በጋራ እንሠራለንም ብለዋል። የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ንግግር አቶ አገኘሁ በፓርቲው ጉባኤ ላይ በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቀደም ባላ ጊዜ አደርገውታል በተባለ ንግግር ዙሪያ በኮንፈረንሱ ላይ ውይይት ተደርጎበታል። "አንደኛ ጉዳዩ የተነገረው መቼም ይሁን መቼ ለምን አሁን ማውጣት አስፈለገ? የሚለው አነጋግሮናል። የሁለተኛ ንግግሩ በይዘቱ ስህተት ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ጨምረውም በርዕሰ መስተዳደሩ ንግግር ላይ የተንጸባረቀው ሃሳብ "የግለሰብ አቋም ነው። የፓርቲያችን የብልጽግና አቋም አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል። በውይይቱም የንግግሩ ይዘት በብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ደረጃ በዝርዝር መገምገም እንዳለበትና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ መቀመጡንም አመለክተዋል። "ኮንፈረንሱ የተሰጠው መግለጫው ትክክል አለመሆኑን፤ በይዘት ደረጃ ስህተት መሆኑን ገምግሟል። የይቅርታ መጠየቅ የግለሰብ ጉዳይ ነው። የፓርቲ አቋም ግን አይደለም" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል አቶ አገኘሁ። በክልሉ የአመራር መከፋፈል አለመኖሩን እና አንድነቱ የጠነከረ ለአማራ ህዝብ እየሠራ ያለ አመራር መኖሩን ጠቅሰው "በንግግሩም ላይ ምንም ዓይነት የሃሳብ ልዩነት የለም" ሲሉ በጉዳዩ ላይ የአማራ ክልል አመራሮች ልዩነት አላቸው ይባላል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሕር ዳር መገኘት ረቡዕ በውይይቱ የመጨረሻ ዕለት በባሕር ዳር ከተማ የተገኙት የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኮንፈረንሱ ላይ ቀደም ሲል በተያዘ ፕሮግራም እንደተገኙ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የ5 ቢሊዮን ችግን ተከላ ፕሮግራምን መጠናቀቅ ከማብሰር በተጨማሪ የኮንፈረንሱን የማጠቃለያ አቅጣጫና የሥራ መመሪያ አስቀምጠዋል ብለዋል። የትግራይ ክልል ምርጫ የትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ ወስኖ መንቀሳቀሱ ፀረ ሕገ መንግሥት እንቅስቃሴ ነው ያሉት አቶ አገኘሁ "ሕገወጥ ምርጫ በመሆኑ ፌደራል መንግሥት እርምጃ ይውሰድ ነው የእኛ አቋም" ብለዋል። "የአማራ ክልል የትግራይ ክልልን ለምን ምርጫ ታካሂዳለህ ማለት አይችልም። የፌደሬሽን ምክር ቤትና ምርጫ ቦርድ እውቅና ስለነፈገው የፌደራል መንግሥት ማድረግ የሚችለውን ያደርጋል።" "የራያና ወልቃይት ሕዝቦች አማራ ማንነት ያላቸው ሲሆኑ ምርጫወንም አልደገፉትም። ባለመደገፋቸውም በአሁኑ ሰዓት እየታሰሩና እየተሰደዱ ተፈናቃዮችን እያስተናገድን ነው" ብለዋል። "የእነዚህን ሰዎች ጥያቄ የፌደራል መንግሥቱ መስማት አለበት። ጣልቃ ገብቶም ማስተካከልም አለበት። ከዚያ ውጪ የትግራይ ክልል ምርጫ ስላካሄደ ብለን እኛ አንተነኩስም። እኛ ከትግራይ ህዝብ ጋር በሰላም ነው መኖር የምንፈልገው" ሲሉ አስረድተዋል። ጨምረውም ከትግራይ ወንድም ሕዝብ የአማራን ሕዝብ ህወሐት ሊነጥለው አይችልም በማለት ገልጸዋል። "የአማራን ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ለማጋጨትና ለመነጠል የሚሰሩ ህወሓት እና ኦነግ-ሸኔን የመሳሰሉ ኃይሎችን ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በመተባበር መታገል እንደሚገባም ተግባብተናል" ሲሉ ሃሳባቸውን አጠናቀዋል።
54795923
https://www.bbc.com/amharic/54795923
በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ የሆነው ምን ነበር?
በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 32 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል።
የኦሮሚያ ፖሊስ ከትናንት በስቲያ፣ ጥቅምት 22/ 2013 ዓ.ም የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 32 ነው ሲል የዓይን እማኞች እና አምነስቲ በበኩላቸው የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 54 ነው ይላሉ። የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 32 እንደሆነ ቢጠቀስም ኮሚሽኑ ያገኛቸው መረጃዎች አሃዙ ከዛ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ ብሏል። ይህ ግድያ የተፈጸመው ንጹሃን ዜጎች ለስብሰባ በሚል ምክንያት ተጠርተው በአንድ ስፍራ በኃይል እንዲሰበሰቡ ከተረጉ በኋላ መሆኑን የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ግድያው ማንነትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እንዲሁም አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ የገለፀ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ ሶስቱ ቀበሌዎች ላይ የሚኖሩ የአማራ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ አስታውቋል። አምነስቲም በመግለጫው ከ54 የማያንሱ ብሄራቸው አማራ የሆኑ ሰዎች ተገድለዋል ብሏል ትናንት ባወጣው መግለጫ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም በበኩላቸው ግድያው ማንነትን መሰረት ያደረገ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል። የክልሉ መንግሥት ጥቃቱን ያደረሰው ራሱን ኦነግ ሸኔ በማለት የሚጠራው ቡድን ነው ብሏል። ለመሆኑ ግድያው እንዴት ተፈጸመ? ጥቃቱ ሲፈጸም በስፍራው የነበሩ እና ከጥቃቱ በሕይወት ያመለጡ ሁለት ነዋሪዎችን ቢቢሲ አነጋግሯል። ያነጋገርናቸው አንድ የዓይን እማኝ የተጠራው ስብሰባ ላይ እንደነበሩና ከጥቃቱ አምልጠው አሁን ዲላ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሚገኙ ይናገራሉ። እኚህ አርሶ አደር እንደሚሉት ታጣቂዎቹ በኃይል ሰዎችን ወደ ስበሰባው እንዲመጡ ማድረጋቸውን እና በስብሰባው ላይ "አርሶ አደር ነን የምናውቀው ነገር የለም ስንላቸው ዛሬ ጭጭ ነው የምናደርጋችሁ መውጫ የላችሁም አሉን" በማለት የተፈጠረውን ይገልጻሉ። የዓይን እማኙ እንደሚሉት ነዋሪዎቹ በቅድሚያ በትምህርት ቤት አዳራሽ ውስጥ እንዲገቡ መደረጋቸውን ነው። አዳራሽ ውስጥ ታጣቂዎቹ 'የጦር መሳሪያ አምጡ' እንዳሏቸው ያስረዳሉ። "መሳሪያ የለንም ሌላ ነገር ከፈለጋችሁ እንስጣችሁ" እንዳሏቸውም እኚህ የዓይን እማኝ ይናገራሉ። ከዚያም ከአዳራሹ እንዳስወጧቸው ይናገራሉ። የዓይን እማኙ አክለውም ከአዳራሹ ካስወጧቸው በኋላ፤ "መትረየስ አጠመዱ፣ ክላሽም አጠመዱ። ሽማግሌዎች ኧረ የነፍስ ያለህ ቢሉ አናውቅም አሉ። ጥይት አርከፈከፉብን። ሰው እንዳለ ወደቀ። የሞተው ሞተ። እንዳው ዝም ብለን ደመ ነፍሳችንን ብትንትን አልን" ብለዋል። አክለውም "መጀመሪያ ኮማንድ ፖስት ሲጠብቀን ስለነበረ ነው እንጂ እኛም አንቀመጥም ነበር። እነሱ ልንሄድ ነው ተዘጋጁ ሳይሉን ቅዳሜ ድንገት ወጡ። ባዶ መሆናችንን ሲያውቁ ማታ ገቡ፤ የቤት እቃ፣ ስልክ ወሰዱ። እሁድ ሸኔዎቹ መጥተው አደጋ አደረሱብን" ሲሉም ተናግረዋል። እሳቸው ከ50 በላይ አስክሬን እንዳዩ እንዲሁም ቤት መቃጠሉንም ይናገራሉ። በአሁኑ ሰዓት ዲላ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሚገኙ እና ካምፕ ውስጥ የወረዳው አስተዳደደር ሰብስቦ ቢያስቀምጣቸውም በምግብ ተቸግረናልም ብለዋል። ለስብሰባ በተጠራው ቦታ ነበርኩ ያለች ሌላኛዋ የዓይን እማኝ በበኩላቸው አምና የዳሯት ልጃቸውን፣ አባታቸውን እና የልጃቸው ባል አባት እንደተገደሉባቸው ይናገራሉ። "ስብሰባ ብለው ትልቁንም ትንሹንም ጠሩ። መሣሪያ አስረክቡ አሉን። ገንዘብ፣ በሬ ወይም የፈለጋችሁትን እንስጣችሁ መሣሪያው ተለቅሞ ሄዷል አልን። በመጨረሻ እጃችንን እያርገበገብን እየለመናቸው ስብሰባ ላይ ያለነውን ፈጁ። ልጄን ከኔ ላይ ደፋት። የሷ ደም እኔ ላይ እየፈሰሰ እንደ አጋጣሚ ወጣሁ" ሲሉ ለቢቢሲ የተከሰተውን ገልጸዋል። አሁን ከአራት ልጆቻቸው ጋር ዲላ እንዳሉም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "እህል ውሃ የለም። ሕጻናት እህል ውሃ ከቀመሱ ሦስት ቀናችን ነው" ሲሉም ያሉበትን ፈታኝ ሁኔታ ገልጸዋል። ሁለቱም የዓይን እማኞች ጥቃቱ የተፈጸመው በቦምብ ሳይሆን "በክላሽ እና መትረየስ ነው" ይላሉ። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ሰኞ ረፋድ ላይ አሁን ባለን መረጃ ነዋሪዎቹ የተገደሉት በተወረወረባቸው ቦምብ ነው በማለት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። የጉሊሶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዳግም መልካሙ በበኩላቸው ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የአማራና የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች መገደላቸውን ይናገራሉ። "ሰዎች በአንድ ቦታ ሲገደሉ አማራዎች ብቻ አይደሉም የተገደሉት። ኦሮሞ የሆኑም ተገድለዋል። በአካባቢው ሁሉም በአንድ ላይ ተሰባጥረው ነው የሚኖሩት። በጥቃቱ የሁለቱም ብሔር ተወላጆች ተገድለዋል።" ይላሉ ከዚህም በተጨማሪ የቀበሌ አመራሮችም ሊገደሉ ኢላማ ተደርገው ስለነበር አካባቢውን ጥለው ሸሽተው እንደነበርም ለቢቢሲ አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት የተፈናቀለውን ሕዝብ ወደ ቀዬው እንዲመለስ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዲላ ተብላ በምትጠራ ከተማ ሰፍረው እንደሚገኙም በተጨማሪ ገልፀዋል። "የተገደሉትን መቅበር የተጎዱትን ማሳከም ላይ እንገኛለን። የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎችም ጥቃቱን ያደረሱት ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው" ብለዋል
52423332
https://www.bbc.com/amharic/52423332
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ግርፋት እንዲቆም ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዘዘ
ሳኡዲ አረቢያ ግርፋትን መቀጣጫ ማድረግ ልታቆም እንደሆነ አንድ ለመገናኛ ብዙሃን የተላከ ሕጋዊ ሰነድ ጠቆመ።
ከሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ያጠፉ ሰዎች ከግርፋት ይልቅ በእሥራት ወይም በገንዘብ እንዲቀጡ ይደረጋል። ሰነዱ፤ ይህ የንጉሥ ሰልማንና ልጃቸው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐማድ ቢን ሰልማን የሰብዓዊ መብት ለውጥ እርምጃ አካል ነው ይላል። ሳኡዲ መንግሥትን የተቃወሙ ሰዎችን በማሠርና በጋዜጠኛ ጃማል ኻሾግጂ ግድያ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ትችት ሲደርስባት ቆይቷል። የሳኡዲ እርምጃዎች የሚቃወሙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፤ ሃገሪቱ ሰብዓዊ መብት በመርገጥ ወደር የላትም ሲሉ ይወነጅላሉ። ሐሳብን በነፃነት መግለፅ በእጅጉ የታፈነ ነው፤ መንግሥትን መቃመው ደግሞ ለምክንያት የለሽ እሥር ይዳርጋል ይላሉ። መጥፎ ገፅታ በግሪጎሪ አቆጣጠር 2015 ላይ ሳኡዲ አራቢያዊው ጦማሪ ራይፍ ባዳዊ በአደባባይ መገረፉ አይዘነጋም። 'የሳይበር' ወንጀል ፈፅሟል፤ እስልምናን አንቋሿል ተብሎ ነበር የተቀጣው። ሳዑዲ አራቢያዊው ጦማሪ ራይፍ ባዳዊ በአደባባይ መገረፉ አይዘነጋም ጦማሪው በየሳምንቱ አንድ አንድ ሺህ ልምጭ እንዲገረፍ ነበር የተወሰነበት። ነገር ግን ግለሰቡ በግርፋሩ ምክንያት ሊሞት ደርሶ ነበር መባሉን ተከትሎ ተቃውሞ የበረታባት ሳኡዲ ግርፋቱ እንዲቆም አዘዘች። ተንታኞች ግርፋት ለሳኡዲ መጥፎ ገፅታ እየሰጣት ስለሆነ ነው ለማቆም የወሰነችው ይላሉ። ቢሆንም ንጉሡንም ሆነ አልጋ ወራሹን የሚቃወሙ ሰዎች አሁንም እየታሠሩ እንደሆነ ይዘገባል። ባለፈው አርብ ሳኡዲ ውስጥ ስለሰብዓዊ መብት በመከራከር የሚታወቅ አንድ ግለሰብ እሥር ቤት ውስጥ ያለ በስትሮክ መሞቱ ተነግሯል። የሙያ አጋሮቹ የሕክምና እርዳታ ቢያገኝ ኖሮ ይድን ነበር ይላሉ።
56151142
https://www.bbc.com/amharic/56151142
ዩናይትድ አየር መንገድ ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ከበረራ አገደ
የአሜሪካው ዩናይትድ አየር መንገድ 24 ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ከበረራ አገደ።
አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹን ከበረራ ያገደው ባሳለፍነው ቅዳሜ ከአውሮፕላኖቹ አንዱ ሞተሩ ላይ አደጋ ካጋጠመው በኋላ ነው። አውሮፕላኑ 231 መንገደኞችንና አስር የበረራ አስተናጋጆችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን በዴንቨር አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገዷል። እስካሁን በአደጋው የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። የአውሮፕላኑ ስብርባሪዎችም በአቅራቢያው ባሉ የመኖሪያ ቦታዎች ወዳድቀው ተገኝተዋል። ይህንንም ተከትሎ ጃፓን ተመሳሳይ ፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞተር የተገጠመላቸውን ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን የሚጠቀሙ ሁሉም አየር መንገዶች አየር ክልሏ እንዳይገቡ ጠይቃለች። ወደ ሃዋይ ሆኖሉሉ ከተማ ለመብረር የተነሳው ዩናይትድ 328 አውሮፕላን በቀኝ በኩል ባለው ሞተሩ ላይ አደጋ እንደገጠመው የፌደራል አቪየሽን አስተዳደር ገልጿል። አደጋውን ተከትሎም አስተዳደሩ የፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞተር የተገጠመላቸው ቦይንግ 777 አውሮፕኣኖች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ አዟል። "አደጋው ካጋጠመ በኋላ ሁሉንም የደህንነት መረጃዎች ተመልክተናል" ሲሉ የፌደራል አቪየሽን አስተዳዳሪ ስቴቭ ዲክሰን በመግለጫቸው ተናግረዋል። በመጀመሪያ ደረጃ በተገኘው መረጃ መሠረትም፤ ምርመራው በቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ላይ ብቻ ለሚገጠመው ለዚህ የሞተር ሞድል የተለየ የሆነው ወደ ሞተሩ ንፋስ ማስገቢያ [ፋን] ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ድምዳሜ ላይ ደርሰናል ብለዋል። የፌደራል አቪየሽን አስተዳደርም ከሞተር አምራቹ ድርጅት እና ከቦይንግ ተወካዮች ጋር እየተነጋገረ ነው። የአገሪቷ የመጓጓዣ ደህንነት ቦርድ የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ እንደሚያመላክተው አውሮፕላኑ አደጋ ያጋጠመው በቀኝ ሞተሩ ላይ ሲሆን፤ በሌሎች ሁለት ንፋስ ማስገቢያ [ፋን] ተሰነጣጥቀዋል። ሌሎቹም እንዲሁ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይሁን እንጂ የአውሮፕላኑ ዋነኛ አካል ላይ የደረሰው ጉዳት ቀላል መሆኑን ቦርዱ ገልጿል። "በኃይል ሲርገፈገፍ ነበር" ይህ አደጋ ባጋጠመው አውሮፕላን ላይ ተሳፍራው የነበሩት መንገደኞች ለበረራ እንደተነሱ ወዲያውኑ ከፍተኛ ፍንዳታ እንደሰሙ ተናግረዋል። ከመንገደኞቹ አንዱ የሆኑት ዴቪድ ዴሉሲያ "አውሮፕላኑ በኃይል ሲነቃነቅ ነበር። ከዚያም ከፍ ብሎ መብረር ስላልቻለ ወደ ታች መውረድ ጀመረ" ብለዋል። አክለውም እርሳቸውና ባለቤታቸው ምንአልባት አደጋ ካጋጠመን በሚል የኪስ ቦርሳቸውን ኪሳቸው ውስጥ እንደከተቱት ተናግረዋል። የብሩምፊልድ ከተማ ፖሊስ የአውሮፕላኑ የሞተሩ ሽፋን ስባሪ በአንድ መኖሪያ ቤት አትክልት ቦታ ላይ መውደቁን የሚያሳይ ምስል አጋርቷል። ሌሎቹ ስብርባሪዎችም በከተማዋ አንድ የእግር ኳስ ሜዳ ላይ ወድቀው ታይተዋል። ከአውሮፕላኑ ላይ በወደቀው ስብርባሪ ግን የተጎዳ አለመኖሩ ተገልጿል። በጃፓን የፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞደል ሞተር የተገጠመላቸው ሁሉም 777 አውሮፕላኖች ተጨማሪ ማስታወቂያ እስኪነገር ድረስ አየር ክልሏ መግባት ያቆማሉ። ይህም ለበረራ መነሳትን፣ ማረፍን እና በአገሪቷ የአየር ክልል ላይ መብረርን ያካትታል። ባለፈው ታህሳስ ወር የጃፓን አየር መንገድ አውሮፕላን በግራ በኩል ያለው ሞተሩ መስራት ባለመቻሉ ወደ ናሃ አየርማረፊያ እንዲመለስ ተገዶ ነበር። አውሮፕላኑ ባለፈው ቅዳሜ አደጋ ካጋጠመው የዩኒይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር በተመሳሳይ የ26 ዓመት እድሜ ያለው ነው። በ2018፤ አንድ የዩናይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን በሆኖሉሉ ከማረፉ በፊት የቀኝ ሞተሩ ተሰብሮ ነበር። ይህንንም ተከትሎ በተካሄደው ምርመራ የአገሪቷ የመጓጓዣ ደህንነት ቦርድ አደጋው የአውሮፕላኑ ሙሉው የንፋስ ማስገቢያ [ፋን] በመሰንጠቁ ምክንያት ያጋጠመ እንደሆነ አስታውቆ ነበር።
news-56330257
https://www.bbc.com/amharic/news-56330257
ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ የተከተቡ ዜጎቿ ጭምብል ሳያደርጉ መሰባሰብ ይችላሉ አለች
የአሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) የኮሮናቫይረስ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ወደቀደመ ህይወታቸው መመለስ ይችላሉ የሚል መመሪያ አውጥቷል።
በዚህም መሰረት ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ጭምብል (ማስክ) ሳያደርጉ በቤት ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ ተብሏል። ሲዲሲ እንዳስታወቀው የመጨረሻውን ክትባት ከተከተቡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከኮሮናቫይረስ ስጋት ነፃ ናቸው ብሏል። እስካሁን ድረስ አሜሪካ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን ከትባለች። የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አዲሱን የደህንነት መመሪያ ይፋ ያደረጉት በትናንንትናው እለት ዋይት ሃውስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ግብረ- ኃይል መግለጫ ላይ ነው። መመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ማድረግ ይችላሉ ብሎ ካስቀመጣቸው መካከል፦ "ከኮቪድ-19 በኋላ ሊኖር የሚችለውን አለም ማየት ጀምረናል። የበለጠ ዜጎቻችን በተከተቡ ቁጥር ማከናወን የምንችላቸውን ተግባራትም ይጨምራሉ" በማለት የዋይት ሃውስ ከፍተኛ አማካሪ አንዲ ስላቪት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ህዝባዊ በሆነ ቦታ ላይ ጭምብል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ እንዲሁም አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማስወገድና የተጣሉ የጉዞ ገደቦችን መከተል ይኖርባቸዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ መመሪያው ያልተከተቡና ለኮሮናቫይረስ በበለጠ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦችም በተለይ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስቀምጧል። አሜሪካ በቅርቡ የምትከትባቸውን ዜጎቿን ቁጥር በከፍተኛ እየጨመረ መሆኑን ያስታወቀች ሲሆን እስካሁን ድረስ 90 ሚሊዮን ሰዎች ተከትበዋል። በተለይም የጆንሰን ጆንሰን የአንድ ጊዜ ክትባት እውቅና ማግኘቱ አቅርቦቱን ጨምሮታል ተብሏል። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ ኮቪድ-19 የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ መሆኑ ቀጥሏል። አገሪቱ እስካሁን ድረስ 29 ሚሊዮን ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን 525 ሺህ ዜጎቿንም አጥታለች።
44206716
https://www.bbc.com/amharic/44206716
በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እስረኞች አሁንም በሳዑዲ እስር ቤት ይገኛሉ
ስሜ አይጠቀስ ብሎ አስተያየቱን ለቢቢሲ የሰጠው ግለሰብ ከሁለት አመት በፊት ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሲሄድ ነበር ለእስር የተዳረገው። በሳዑዲ ጅዳ ጂዛኔ እስር ቤት ከሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን እስረኞች አንዱ ነው።
ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በሳዑዲ ያሉ እስረኞችን ለማስፈታት የመደራደራቸው ዜና ተስፋ ሰጥቶታል። "ዜናው እውን ከሆነ በህይወቴ አዲስ ምዕራፍ ይከፈታል" ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት አርብ ከሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በኢትዮጵያና ሳዑዲ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙርያ መክረዋል። ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መሀከልም ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ማስፈታት ይገኝበታል። በመሪዎቹ ስምምነት መሰረት በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ተለቀው ወደ ኢትዮጵያ እየተመለሱ ነው። አስተያየቱን ለቢቢሲ የሰጠው እስረኛ አብረውት እስር ላይ ያሉትን ሰዎች ቁጥር በትክክል ባያውቅም "በግምት ወደ 5,000 የሚሆኑ እስረኞች አሉ" ብሏል። በእስር ቤቱ ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀም ስለሚቻል እስረኛውን ያነጋገርነው ወደተንቀሳቃሽ ስልኩ ደውለን ነበር። "እስከ አሁን ምንም አልተፈረደብኝም" ቢልም እስር ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያውያኑ ከሶስት አመት በላይ መታሰራቸውን ገልጿል። "ከሁለትና ከሶስት ከአመት በላይ የቆዩ ሰዎች አሉ። ሁኔታው በጣም አስጊና አስፈሪ ነው" ብሏል። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ወደ ሳዑዲ ያቀኑት የተሻለ ህይወትን በመሻት እንደሆነ ይናገራል። "እዚህ የመጣነው ለእንጀራ ጉዳይ ነው። ለእንጀራ ስንል ተሸውደን እዚህ ገብተናል።" ሲል ያለበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ገልጿል። "አንድ ሰው ወንጀል ፈጽሞ ሲታሰር መማር ነው ያለበት እኛ ግን እየተማርን ሳይሆን እየተሰቃየን ነው። መፍትሔ ያስፈልገናል። መፍትሔውንም በደስታ እንቀበላለን" ሲልም ተስፋውን ለቢቢሲ አካፍሏል። በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት አምባሳደር አቶ ውብሸት ደምሴ በሳዑዲ እስር ቤቶች ከፍተኛ ፍርደኞች የሆኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ተናግረዋል። በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አሚን አብዱል ቀድር እንደሚናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር ባደረጉት ስምምነት በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ከእስር ተለቀው ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ይገኛሉ። የተቀሩትም የሚመለሱበትን ሁኔታ እየተመቻቸ እንደሆነ ገልፀዋል። ሁለቱ መሪዎች የደረሱበት መግባባት እስረኞቹ እንዲፈቱ ምክንያት ሆኗል ብለዋል። እስካሁን በሁለት ዙር እስረኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጉን ይናገራሉ። የሁለቱ የአገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረ እንደሆነ የተናገሩት አምባሳደሩ የተጀመረው እስረኞችን የማስፈታት ስራ ጊዜና ትዕግስትን የሚጠይቅ እንደሆነ አስረድተዋል። ያነጋገርናቸው በሳዑዲ ጅዛን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እስረኞች "ሳዑዲ የሚገኘው የኢትዯጵያ ኤምባሲን እርዳታ ፈልገን በተደጋጋሚ ብንደውልም ምላሽ ተሰጥቶን አያውቅም። አገር እንደሌለን ነው የሚሰማን" ይላሉ። አምባሳደሩ በበኩላቸው "በሳዑዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ክትትል ያደርጋል" ብለዋል። አምባሳደሩ እንደሚሉት እስረኞቹ የሳዑዲን ህግ ተላልፈው ቢገኙም ምህረት እንዲደረግላቸው በአገር ደረጃ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። "ተገቢውን ምላሽ እየሰጠናቸው ነው። አገራቸው ለዜጎቿ ያላትን ተቆርቋሪነት አሳይተናል" ብለዋል። እስረኞቹ በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጣቸው በመሆናቸው ለማስፈታት መንግስት በጀመረው ሁኔታ በትዕግስት እንደሚቀጥል ተናግረዋል። "የአገሪቱን ህግና ስርዓት በመረዳትና የፍርድ ሂደቶችን በማጣራት በብርቱ ጥንቃቄ መስራትም ያስፈልጋል" ሲሉም አክለዋል። በተለይም ወደ ሳዑዲ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመሩ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። አምባሳደሩ እስረኞችን ከማስፈታት ባሻገር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ሼክ ሁሴን አሊ አላሙድን ከእስር የማስፈታት ጉዳይም ተነስቶ ነበር። "በመግባባት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የአገሪቱን ህግና ስርዓት በጠበቀ መልኩ ከሳዑዲ አልጋ ወራሽ ልዑል መሃመድ ኢን ሰልማን ጋር ተወያይተውበታል። ጉዳዩም በቀጣይ እንደሚታይ በሳዑዲ በኩል ማረጋገጫ አግኝተናል" ብለዋል።
news-43806424
https://www.bbc.com/amharic/news-43806424
ዳይመንድ ድረገጹ ላይ በለቀቀውን ቪዲዮ ለእስር ተዳረገ
ከአፍሪካ እውቅ ድምጻውያን መካከል አንዱ የሆነው ዳይመንድ ፕላትነምዝ በኢንስታግራም ገጹ ላይ ከአንዲት ሴት ጋር ሲሳሳም የሚያሳይ ምስል ከለቀቀ በኋላ በታንዛኒያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
ፖሊስ የእውቁ ድምጻዊ ተግባር አሳፋሪ እና የማህብረሰቡን እሴት የጣሰ ነው ብሏል። ዳይመንድ ከሳምንታት በፊት የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘበት ''ቦንጎ ፍላቭ'' የተሰኘው የሙዚቃ ቪዶዮ በታንዛንያ መንግሥት ወሲብ ቀስቃሽ ምስሎች እና ግጥሞች አሉበት በሚል በአገሪቱ እንዳይታይ ካገደ በኋላ የትውልድ ሃገሩን ጥሎ እንደሚወጣ ዝቶ ነበር። የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ ሃሪሰን ማክዌምቤ ለምክር ቤት አባላት እንደተናገሩት ሙዚቀኛው ከጥቂት ሳምንታት በፊት የተላለፈውን የኤሌክትሮኒክ እና ፖስታል ህግጋትን ተላልፏል። ዳይመንድ በኢንስታግራም ገጹ ላይ የለጠፈውን ተንቀሳቃሽ ምስል የሰረዘ ቢሆንም የታንዛኒያ ባለስልጣናት ግን በሙዚቀኛው ላይ ክስ ለመመስረት ተዘጋጅተዋል። አምስት ነጥቦች ስለ ዳይመንድ ፕላትነምዝ ዳይመንድ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የ5 ሚሊየን የታንዛኒያ ሽልንግ ቀጣት ወይም የ12 ወራት እስር ይጠብቀዋል። እራሱን መከላከል ካልቻለ ደግሞ የእስር እና የገንዘብ ቅጣቱ ይጠብቀዋል ተብሏል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የዳይምንድ አድናቂዎች መንግሥት አዲስ ህግ በማርቀቅ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እየተላለፈ ነው በማለት ይተቻሉ። የታንዛንያ መንግሥት በበኩሉ የአገሪቱን ''ባህል እና ወግ'' እየጠበቅን ነው ይላል።
news-48010853
https://www.bbc.com/amharic/news-48010853
ከአምቦ ከተማ ነዋሪ ለዶ/ር አምባቸው የቀረቡ 4 ጥያቄዎች
የኦሮሞ እና የአማራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረክ ትናንት ሚያዝያ 13 ቀን 2011 ዓ. ም. በአምቦ ከተማ ተካሂዷል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የአማራ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አምባቸው መኮንን በአምቦ ከተማ በሕዝብ ለሕዝብ መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሎቹ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል። • የተጠበቀውን ያህል የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች አልተመለሱም በውይይቱ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሰሆን ከመድረኩ ተሳታፊዎችም ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል። ከተሳታፊዎቹ መካከል አቶ ተሳፋዬ ዳባ የተባሉ የአምቦ ከተማ ነዋሪ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አምባቸው መኮንን አራት ጥያቄዎች አቅርበው ነበር። የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ሰሞኑን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄር አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ የተከሰተው ግጭት የሚመለከት ሲሆን አቶ ተስፋዬ እንዲህ ብለዋል። ጥያቄ 1 "እርስዎ በሚያስተዳድሩበት ክልል ውስጥ የሚገኙ ኦሮሞዎች በጠራራ ጸሃይ በታጣቂዎች እንደተገደሉ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሰምተናል። እርስዎ እና የክልሉ መንግሥት ሰዎችን የሚገድሉ ሰዎች ላይ የወሰዳችሁት እርምጃ ምን እንደሆነ እና አሁን ጉዳዩ የደረሰበትን ሊገልጹልን ይችላሉ?" ዶ/ር አምባቸው ንግግራቸው የጀመሩት በኦሮምኛ ''እንዴት ናችሁ? የኦሮሞ እና የአማራ ሕዝብ ወንድማማች ናቸው። ችግር የለም። እኛ አንድ ነን'' በማለት ነበር። • ኦሮሚያና አማራ የሚፈቱ እስረኞችን እየለዩ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄር አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ በደረሰው ችግር የሰው ሕይወት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዝን በመግለጽ ለጥያቄው እንዲህ ምላሽ ሰጥተዋል። ''የሰው ሕይወት ጠፍቷል። ይህም በጣም አሳዝኖናል። የተጎዳው በጠቅላላ የእኛው አካል ነው። በዚህም ውስጣችን ተነክቷል። ይህንን እንዴት አድርገን እንፍታው በሚለው ላይ እየተሠራ ነው። አሁን በአከባቢው ሰላም እና መረጋጋት ተፈጥሯል። ይህ አይነቱ ተግባር በድጋሚ እንዳይፈጸም እንደምንሠራ ቃል ልገባላችሁ እወዳለው።'' የኦሮሞ እና የአማራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተሳታፊዎች ጥያቄ 2 ሁለተኛው የአቶ ተስፋዬ ጥያቄ ሕገ መንግሥቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም አለው የሚለውን ጉዳይ ይመለከታል። "የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ስላለው የልዩ ጥቅም ፍላጎት የእርሶ እና የክልሉ አቋም ምንድነው?" ሲሉ ጠይቀዋል። ዶ/ር አምባቸው ለዚህ ጥያቄ ምላሸ መስጠት የጀመሩት ''የአዲስ አበባ አጀንዳ ባልተገባ መንገድ ወደ ሳማይ ተጓጓለ። በየጊዜው አጀንዳ የሚቀርጹልን ኃይሎች ወደፊትም ሊኖሩ እንደሚችሉ አትጠራጠሩ'' በማለት ነበር። • የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከቃጠሎው በኋላ ''አዲስ አበባን በተመለከተ ሕገ መንግሥቱ ያስቀመጠዉን የሚሸራርፍ አቋም በውስጣችን ማንም የለውም . . . የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሕገ መንግሥታዊ መብት አለው፤ ይህ መብቱ እንዲከበርለት እኛም እንታገላለን። ከዛ ውጪ ያሉት ጽንፈኛ ሃሳቦች ተቀባይነት የላቸውም'' ብለዋል። ጥያቄ 3 ሦስተኛው የአቶ ተስፋዬ ጥያቄ፦ "አፋን ኦሮሞ ከአማርኛ እኩል የፌደራል የሥራ ቋንቋ በመሆኑ ላይ ያለዎት አቋም ምንድነው?" የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አምባቸው መኮንን ምላሽ፦ ''በክልላችን መገናኛ ብዙሃን ላይ ኦሮምኛ የስርጭት ሰዓት አለው። በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደርም የመማሪያ ቋንቋ ነው። ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንሠራለን። በአማራ ክልል ሌሎች ተጨማሪ ቋንቋዎች በትምህርት ቤቶች ለመስጠት እቅድ አለን።" ጥያቄ 4 ከአምቦ ከተማ ነዋሪው የቀረበው አራተኛው እና የመጨረሻው ጥያቄ፦ "የአምቦ ከተማ ነዋሪ ላለፉት በርካታ ዓመታት ትግል ላይ ነው የቆየው። በዚህም ምክንያት የከተማዋ መሰረተ ልማታዊ ፍላጎቶች አልተሟሉም። እርስዎ እና የአማራ ክልል ባለሃብቶች በዚህ ረገድ ከተማዋን እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ?" • ታዋቂው ኩባንያ ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞችን ''ይበድላል'' ተባለ ዶ/ር አምባቸውም፤ የአማራ ክልል ባለሃብቶች ከተማዋን ለማሳደግ መጥተው እንዲሠሩ መልዕክት አስተላልፍላችኋለው ብለዋል።
news-52962757
https://www.bbc.com/amharic/news-52962757
በኢንዶኔዢያዋ የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ስድስት ቀናት የቆየው ኢንግሊዛዊ በህይወት ተገኘ
በኢንዶኔዢያዋ ባሊ ደሴት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ለስድስት ቀናት የቆየው እንግሊዛዊ በስተመጨረሻ ሕይወቱን ማትረፍ ተችሏል።
ጄኮብ ከጉድጓዱ ሲወጣ የ29 ዓመቱ ጄኮብ ሮበርትስ በፔካቱ መንደር ውሻ ሲያሯሩጠው ለማምለጥ ሲሞክር ነው አራት ሜትር በሚጠልቀው ጉድጓድ ውስጥ የወደቀው። ከአደጋው በኋላ እግሩ እንደተሰበረ የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል። ምንም እንኳን ጉድጓዱ ውሃ ባይኖርበትም እግሩ በመሰበሩ ምክንያት መውጣት ሳይችል ቆይቷል። በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች እንደገለጹት በጉድጓዱ ውስጥ ትንሽ ውሃ በመኖሩ ለስድስቱ ቀናት የሚጠጣውን ማግኘት ችሏል። ጄኮብ ሮበርትስ ለስድስት ቀናት ያለመታከት የድረሱልኝ ጥሪውን ሲያሰማ ነበር። በመጨረሻም አንድ የአካባቢው ነዋሪ ድምጹን በመስማቱ ሕይወቱ ልትተርፍ ችላለች። እምብዛም ሰዎች በማይኖሩበት አካባቢ በሚገኘው የውሃ ጉድጓድ አቅራቢያ ከብቶቹን ሲጠብቅ የነበረው ግለሰብ ሁኔታውን ከተመለከተ በኋላ ወዲያው የአካባቢው ኃላፊዎችን ጠርቷል። ጃኮብ በግለሰቡ የተገኘው ባሳለፍነው ቅዳሜ ሲሆን ወዲያውኑ ከጉድጓዱ ወጥቶ ህክምና እንዲያገኝ ተደርጓል። ደሴቲቱ ውስጥ የምትገኘው የፔካቱ መንደር እንደ ጄኮብ ያሉ በርካታ ጎብኚዎች የሚያዘወትሯት ሲሆን እንዲህ አይነት አደጋ እምብዛም የተለመደ አይደለም ተብሏል።
news-56755319
https://www.bbc.com/amharic/news-56755319
ምርጫ 2013፡ ግማሽ ያህል የምርጫ ጣቢያዎች አልተከፈቱም፣ በአፋርና በሶማሌ ምዝገባ አልተጀመረም
ሊካሄድ ሰባት ሳምንት ብቻ በቀረው ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ የመራጮች ምዝገባ ይካሄድባቸዋል ከተባሉት የምርጫ ጣቢያዎች ወደ ግማሽ የሚጠጉት አለመከፈታቸውን የምርጫ ቦርድ ገለጸ።
ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የመራጮች ምዝገባ ከተጀመረ ከሦስት ሳምንት በላይ ሲሆነው በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ተከፍተው ድምጽ ሰጪዎችን ይመዘግባሉ ተብለው ከታቀዱት 50 ሺህ ያህል የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ምዝገባ እያካሄዱ ያሉት 25 ሺህ 151ዱ ሲሆኑ ከ24 ሺህ በላይ የሚሆኑት ግን ሥራ አልጀመሩም። ከዚህም ውስጥ የሶማሌና የአፋር ክልሎች ውስጥ የመራጮች ምዝገባ እንዳልተጀመረም ተገልጿል። ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባና አጠቃላይ የምርጫ ሥራዎች ሂደትን በተመለከተ በምርጫው ከሚሳተፉ ፓርቲዎች አስካሁን ያለውን ሁኔታ በገለጸበት ወቅት ነው። በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ከትግራይ ክልል ውጪ በመላው የአገሪቱ አካባቢዎች በ674 በሚሆኑ የምርጫ ክልሎች ባሉ 50 ሺህ በሚደርሱ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮችን ለመመዝገብ ቢታቀድም ከግማሽ በላይ በሚሆኑት ውስጥ ብቻ ምዝገባው እየተካሄደ መሆኑ ተነግሯል። የመራጮች ምዝገባው እየተካሄደባቸው ባሉት የምርጫ ጣቢያዎችም ምዝገባው በተፈለገው መልኩ እየሄደ ነው ማለት እንደማይቻል ሰብሳቢዋ ተናግረዋል። ለማሳያነትም የአገሪቱ መዲና በሆነችውና ከአምስት ሚሊዮን በላይ ነዋሪ በሚኖርባት በአዲስ አበባ፣ ምዝገባው ከተጀመረ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ለመምረጥ የተመዘገበው ሰው ወደ 201 ሺህ የሚጠጋ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል። በአዲስ አበባ ከተማ 1 ሺህ 848 የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው መራጮችን ይመዘግባሉ ተብሎ ቢታቀድም፣ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ 186 ጣቢያዎች እንዳልተከፈቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመልክቷል። መጋቢት 16 የተጀመረው የመራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቅ 10 ቀናት ያህል የቀሩት ሲሆን በቀሩት ቀናት ውስጥ የሚጠበቀውን ያህል ሰዎች ካልተመዘገቡ በቀጣይ ምን አማራጮች እንዳሉ ገና የተገለጸ ነገር የለም። ምርጫና የፀጥታ ሁኔታ የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የመራጮች ምዝገባ በሁሉም ጣቢያዎች መካሄድ ያልተቻለው በተለያዩ ችግሮች ምክንያት እንደሆነ ገልጸው፤ ከዚህም ውስጥ በ4126 የምርጫ ጣቢያዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ እንዳልሆኑ አመልክተዋል። በዚህም ሳቢያ የመራጮች ምዝገባ ሂደት በተለያዩ አካባቢዎች በተፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ እንዳልሆነ ወ/ት ብርቱካን ተናግረው፤ ለዚህም በበርካታ ቦታዎች ላይ ባጋጠሙ የጸጥታና የትራንስፖርት ችግሮች የተነሳ ለምዝገባው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ማድረስ ባለመቻሉ የምርጫ ጣቢያዎችን መክፈት አልተቻለም ብለዋል። በዚህም መሠረት በጸጥታ ችግር ምክንያት የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደባቸው ካልሆኑት ስፍራዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል አራት ዞኖች ሲኖሩ እነሱም ምዕራብ ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ እና ቄለም ወለጋ፤ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ አርጎባና ዋግ ኽምራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል እና በካማሺ እንዲሁም ደቡብ ክልል ጉራፈርዳ፣ ሱርማና ዘልማም እንደሆኑ ሰብሳቢዋ ገልጸዋል። ከእነዚህ ውስጥም የመራጮች ምዝገባ ተጀምረው እንዲቋረጡ የተደረገባቸው ሲኖሩ በተጨማሪም በአንዳንድ ስፍራዎች መልሰው እንዲጀመሩ የተደረጉ እንዳሉ ተመልክተዋል። ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የመራጮች ምዝገባ ማድረግ ካልተቻለባቸው ስፍራዎች ባሻገር በትራንስፖርት ችግር አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ባልደረሱባቸው አካባቢዎች አስፈላጊውን ጥረት በማድረግ የምርጫ ጣቢያዎቹ እንዲከፈቱ እንደሚደረግ ሰብሳቢዋ ተናግረዋል። ነገር ግን ቦርዱ በቀጣይነት በሚያደርገው ውይይት የመራጮች ምዝገባ ቀናትን እና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት እንደሚመክርና በአጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎችን መክፈት እንዲሁም ምዝገባን በተመለከተ የሚቀጥሉት ሰባት ቀናት የሚኖረውን ሁኔታ እንደሚያሳወቅ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም ሕዝቡ በአገራዊው ምክር ቤትና ለክልሎች ምክር ቤቶች ተወካዮቹን ለመምረጥ እንዲችል ቀድሞ እንዲመዘገብ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ መልዕክት አስፍረዋል። "ዜጎች የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጠበቃል። የአገራችንን የነገ ዴሞክራሲ ለመወሰን፣ ዛሬ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ እናውጣ። ካርድ ለማውጣት ነገ አትበሉ፤ ነገ ከዛሬ ይጀምራል" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩጥሪ አቅርበዋል። ሊካሄድ ሰባት ሳምንታት ያህል በቀሩት አገራዊ ምርጫ ላይ 50 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ድመጻቸውን ይሰጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ባለው የመራጮች ምዝገባ ላይ በተለያዩ ምክንያቶች በርካታ የምርጫ ጣቢያዎች ሥራ አለመጀመራቸው ተገልጿል። ቀኑ እስካልተራዘመ ድረስ የምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መጋቢት 16 የመራጮች ምዝገባ በተጀመረባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ምዝገባው በመጪው ሳምንት አርብ ሚያዚያ 15/2013 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ይሆናል። ምርጫ 2013 ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደዚህ ዓመት ከተሸጋገረ በኋላ፤ በመጪው ግንቦት ማብቂያና በሠኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለማካሄድ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ዝግጅት እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ይካሄዳል በተባለው በዚህ ምርጫ 50 ሚሊዮን መራጮች ማለትም ከአገሪቱ ሕዝብ ወደ ግማሽ የሚጠጋው ድምጽ በመስጠት ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምርጫ ቦርድ ገልጿል። በምርጫው ከሚሳተፉት 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማቅረብ በኩል ገዢው ፓርቲ ብልጽግና 2432 ዕጩዎችን በማስመዝገብ ቀዳሚው መሆኑ በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ከዚህ አንጻር ከብልጽግና በመከተል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዕጩዎች በማስመዝገብ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1385 ዕጩዎችን እንዲሁም እናት ፓርቲ ደግሞ 573 ዕጩዎችን አስመዝግበዋል። ሦስቱን ፓርቲዎች ጨምሮ በምርጫው ለመወዳደር በፓርቲና በግል ለመወዳደር ከስምንት ሺህ ሁለት መቶ በላይ ዕጩዎች መመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
52902907
https://www.bbc.com/amharic/52902907
በነቀምቴ አንድ የፖሊስ አባል በ'አባ ቶርቤ' በጥይት ሲገደል ሌላኛው ቆሰለ
በነቀምቴ ከተማ 'አባ ቶርቤ' በሚባለው ቡድን ሁለት የከተማው ፖሊስ አባላት ዛሬ ረቡዕ በጥይት ተመትተው የአንደኛው ህይወት አለፈ።
በፖሊሶቹ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ከቀትር በፊት ከረፋዱ አምስት ሰዓት ገደማ ላይ ሲሆን በጥይት ከተመቱት የአንደኛው የከተማዋ ፖሊስ አባል ህይወቱ ሲያልፍ ሌላኛው ደግሞ ሆስፒታል ገብቶ በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኝ የነቀምቴ ከተማ ጸጥታ እና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚስጋኑ ወቅጋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኃላፊው እንዳሉት "በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሰዎችን በማስፈራራት ከዚያም ጥቃት በሚፈጽመው በዚህ ቡድን የከተማው ሁለት የፖሊስ አባላት በሽጉጥ ተመትዋል። አንዱ ህይወቱ ሲያልፍ አንዱ ደግሞ ቆስሎ በነቀምቴ ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛል።" ሳጅን ደበላ እና ሳጅን አዱኛ የተባሉት እነዚህ የከተማው የፖሊስ አባላት ነቀምቴ ከተማ ቀበሌ 05 በእግር እየተጓዙ ሳሉ ነበር በጥይት የተመቱት ሲሉ አቶ ሚስጋኑ ተናግረዋል። በጥቃቱም የሳጅን አዱኛ ህይወት ማለፉንም አረጋግጠዋል። ይህ በከተማው በሚገኙ የጸጥታ አባላት ላይ የተፈጸመው ጥቃት የመጀመሪያ አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከቀናት በፊትም ግንቦት 16/2012 ዓ.ም በተመሳሳይ መልኩ በነቀምቴ ከተማ በጠራራ ፀሐይ የኮሚኒቲ ፖሊስ አባል የሆነ ግለሰብ ጫማ እያስጠረገ ሳለ በጥይት ተመቶ መገደሉን አቶ ሚስጋኑ አስታውሰዋል። ኃላፊው እንደሚሉት ዛሬ በፖሊስ አባላቱ ላይ የተፈጸመው ግድያና ጥቃት ከቀናት በፊት በኮሚኒቲ ፖሊስ አባል ላይ ከተፈጸመው ግድያ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አመልክተዋል። "የታጠቀ እና በድብቅ የሚንቀሳቀስ ኃይል በከተማው ውስጥ አለ። ይህ ኃይል በመንግሥት አመራሮች እና የጸጥታ ኃይል አባላት ላይ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ሲያደርስና ጥቃት ሲፈጽም ቆይቷል" ሲሉ ክስተቱ የቆየ እንደሆነና ኢላማ ያደረገውም የመንግሥት አካላት ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል። 'አባ ቶርቤ' ወይም ባለሳምንት የተባለው ቡድን የተለያዩ የፌስቡክ ገጾችን በመጠቀም ጥቃት እፈጽምባቸዋለሁ የሚላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር በገጹ ላይ እንደሚያሰፍር አቶ ሚስጋኑ ተናግረዋል። "የሳጀን ደበላ ስምም ከዚህ በፊት በቡድኑ የፌስቡክ ገጽ ላይ ሰፍሮ ነበር። በዚህም ምክንያት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተነግሮት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሲደረግ ነበር። ግን መቼ ይፈጸማል የሚለው ማወቅ ስለማይቻል አስቸጋሪ ነበር" ሲሉ የቡድኑን ድርጊት ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ግለሰቦች የፖሊስ አባላት እንደመሆናቸው የኅብረተሰቡን ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ በኅብረተሰቡ ውስጥ እየተጓዙ ሳሉ ነው ይህ ችግር ያጋጠመው" ብለዋል። ለአንድ የፖሊስ አባልና ለሌላው ከባድ ጉዳት ምክንያት ከሆነው ጥቃት ጋር በተያይዘ በቁጥጥር ስር የዋለ ሰው የለም የተባለ ሲሆን ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል። አባ ቶርቤ ማነው? የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ጅብሪል መሐመድ "አባ ቶርቤ ማለት የአሸባሪው ሸኔ የከተማው ክንፍ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሸኔ በጫካ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ኃይል አለው። በከተማ ደግሞ 'አባ ቶርቤ' እና 'ሶንሳ' ተብሎ የሚጠራ ቡድን አለው። እነዚህ ቡድኖች በተቻላቸው መጠን ግድያ በመፈጸም ሽብር ለመፍጠር እየሞከሩ ናቸው ብለዋል። እነዚህ ቡድኖች ጥቃት የሚያደርሱት በጠራራ ፀሐይ ከተማ መሃል ነው። ይህን መንግሥት መቆጣጠር ለምን ተሳነው? ተብለው የተጠየቁት አቶ ጅብሪል "ከዚህ ቀደም በቁጥጥር ሥር የዋሉ አሉ። ለመግደለ ሲሄዱ የተገደሉም አሉ። ምንም አይነት የተለየ ስልጠናም ሆነ መሳሪያ የላቸውም። የሚጠቀሙት ሰልት የሚጠቀሙት ሰልት፤ ማህበረሰቡን በመምሰል፤ ድንገት ነው አደጋ የሚያደርሱት። ለማምለጥ በሚያመቻቸው ቦታ በድንጋት አደጋ አድርሰው ይሰወራሉ" ብለዋል አቶ ጅብሪል። ከዚህ ቀደምም ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው የቡራዩ ከተማ አስተዳደርና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን ታደሰ የአባ ቶርቤ አባላት ናቸው በተባሉ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።
news-49875293
https://www.bbc.com/amharic/news-49875293
ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ የገባው መኪና እየተፈለገ ነው
ከኬንያ ሞምባሳ ወደብ ወደ ባህር ዳርቻው የእቃና የሰው ማሻገሪያ መርከብ ላይ ሆኖ ሲያቋርጥ የነበረ መኪና ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ ገብቶ እየተፈለገ መሆኑ ተገለፀ።
መኪናው ውስጥ ሦስት ሰዎች ሳይኖሩ እንዳልቀረ የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። • በፀሐይ የሚሰራው የሕዝብ ማመላለሻ ጀልባ • በወለደች በ30 ደቂቃ ውስጥ የተፈተነችው ተማሪ ስንት አስመዘገበች? አደጋው ትናንት ያጋጠመ ሲሆን ከሞምባሳን ወደ ሊኮኒን በማቋረጥ ላይ ሳለ መሃል ላይ ሲደርስ ወደ ኋላ በመንሸራተቱ አደጋው እንዳጋጠመው ታውቋል። አደጋው ሲደርስ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስልም በትዊትር ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 የዓይን እማኞች ለዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ እንደተናገሩት እንዲት ሴትና ሕፃን መኪናው ውስጥ ነበሩ። "አንዲት ሴትና ወንድ ልጅ መኪናው ውስጥ ሆነው ተመልክቻለሁ፤ መኪናው ሲገለበጥ ሴትዮዋ ስትጮህና እርዳታ ስትጠይቅ ነበር። ከዚያም የነፍስ አድን ሠራተኞችን እንዲደርሱላቸው ላኩላቸው" ብለዋል። ዴይሊ ኔሽን ፖሊስን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በመኪናው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ቁጥር አራት ነው። የኬንያ የመርከብ አገልግሎት ባለሥልጣን ፍለጋውና የነፍስ አድን ሥራው እንደቀጠለ አስታውቋል። የሰው እና ዕቃ ማሻገሪያ መርከቡ ኦፕሬተር እስካሁን በፍለጋው ምንም ፍንጭ አለመገኘቱን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።
48836228
https://www.bbc.com/amharic/48836228
የሆንግ ኮንጓ መሪ የተቃዋሚዎችን ድርጊት አወገዙ
የሆንግ ኮንጓ መሪ ካሪ ላም የትላንቱን የተቃዋሚዎች ድርጊት አውግዘዋል።
ትላንት ተቃዋሚዎች የሆንግ ኮንግን ሕግ አውጪ ምክር ቤት ጥሰው ገብተው እንዳልነበረ ማድረጋቸው ይታወሳል። ትላንት የመብት ተሟጋቾች በአደባባይ እያደረጉ የነበረው ተቃውሞ ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦች ከተቃውሞው ወጥተው ወደ ሕግ አውጪ ምክር ቤት በማምራት ለሰዓታት እቃ ሰባብረዋል። መሪዋ ተግባሩን "የሚያሳዝንና ብዙዎች ያስደነገጠ" ብለውታል። • ተቃውሞ በቻይና፡ መንግሥት 'የውጭ ኃይሎችን' እየወቀሰ ነው ትላንት ሆንግ ኮንግ ከእንግሊዝ አገዛዝ ነጻ ከወጣች በኋላ በቻይን ሥር የወደቀችበትን 22ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሰላማዊ ተቃውሞ እየተደረገ ነበር። እለቱ በየዓመቱ የሚታሰበው ስለዴሞክራሲ መስፈን በሚያወሳ ሰልፍ ሲሆን፤ ዘንድሮ ግን በሆንግ ኮነግ የነበረውን የሳምንታት ጠንካራ ተቃውሞ ተከትሎ መጥቷል። ሆንግ ኮንግ ውስጥ ወንጀል የሰሩ ሰዎች ለቻይና ተላልፈው ይሰጡ የሚል ረቂቅ ሕግ መቅረቡን ተከትሎ ሆንግ ኮንግ በተቃውሞ እየተናጠች ትገኛለች። ትላንት ቀትር ላይ ይደርግ የነበረው ተቃውሞ አካል የነበሩ ጥቂት ሰልፈኞች ተነጥለው ወደ ምክር ቤት አቅንተው ጥቃት ሰንዝረዋል። • የሆንግ ኮንግ የሕዝብ እንደራሴዎች ተቧቀሱ የምክር ቤቱን የመስታወት ወለል ሰባብረው ወደ ውስጥ በመዝለቅ፤ የሆንግ ኮንግን ሰንደቅ አላማ አንስተው፤ ግድግዳው ላይ በደማቅ ቀለም መልዕክት አስፍረዋል። የተለያዩ ቁሳቁሶችንም ሰባብረዋል። ይህን ተከትሎ መሪዋ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ "ተግባሩን ሁላችንም ማውገዝ አለብን። ማህበረሰቡ ወደ ቀደመ ሰላሙ በቅርብ ይመለሳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል። • ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ "መሪዋ ለተቃዋሚዎች ጥያቄ ምላሽ ባለመስጠታቸው ተቃዋሚዎች የወሰዱት እርምጃ ነው" በሚል የቀረበባቸውን የሰላ ትችት አጣጥለዋል። የተቃዋሚዎች ጥያቄ ወንጀለኞች ለቻይና ተላልፈው የሚሰጡበትን ረቂቅ ሕግ ማስቀረት ብቻ ሳይሆን፣ የመብት ተሟጋቾችን ከእስር ማስፈታትና በፖሊስ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎችን ጉዳይ መመርመርንም ያካትታል። መሪዋ በበኩላቸው "መንግሥት ለጥያቄዎቹ ምላሽ አልሰጠም መባሉ ትክክል አይደለም። ረቂቅ ሕጉ ሕግ አውጪ ምክር ቤቱ በ2020 ሲከስም አብሮ ይከስማል። ለተጠየቀው ጥያቄ ቀና መልስ ተሰጥቷል" ብለዋል። በተቃዋሚዎቹ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም ገልጸዋል። • ባህር አቋራጩ የቻይና ድልድይ ተከፈተ ተቃዋሚዎች ረቂቅ ሕጉን አጥብቀው መቃወማቸው መንግሥት ይቅርታ እንዲጠይቅ እንዲሁም ረቂቅ አዋጁን እንዲተወውም አስገድዷል። ነገር ግን ረቂቁ ሙሉ በሙሉ እስኪነሳ ተቃውሞው ይቀጥላል። ተቃዋሚዎች መሪዋ ከስልጣናቸው እንዲነሱም ግፊት ማድረጋቸወንም ገፍተውበታል።
news-48361902
https://www.bbc.com/amharic/news-48361902
ኢትዮጵያ፡ በታሪካዊው ቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ ምን አለ?
አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነ-ሕንፃና የቅርስ ጥበቃ መምህር ሲሆኑ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ከሚደረገው እድሳት ጋር ተያይዞ በበጎ ፈቃደኝነት ያስጎበኛሉ።
እርሳቸው እንደነገሩን ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ መንግሥቱ ከመጎብኘቱ አስቀድሞ 'እንግዶች ስለሚመጡ ባለሙያዎች ቢያስጎበኟቸው ይሻላል' በሚል ከቅርስ ጥበቃ፣ ከኪነ ሕንፃ ባለሙያዎች፣ የታሪክ አዋቂዎች የተውጣጡ ሰባት ባለሙያዎች በጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ የተጋበዙ ሲሆን እርሳቸው አንዱ ነበሩ። • ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ማዕድ የቀረቡት ምን ይላሉ? በወቅቱም የሚያሰማሙ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው የጋራ ነጥቦች ያዘጋጁ ሲሆን፤ ለጎብኝዎች ገለፃ ሲያደርጉ ነበር፤ በተለያየ ጊዜም ቤተ መንግሥቱን የመጎብኘት ዕድል ገጥሟቸዋል፤ በመጭው መስከረም ወር ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል በተባለው ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን አለ? ስንል ጠይቀናቸዋል። ቤተ መንግሥቱ በ40 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በውስጡ የተለያዩ ታሪካዊ ቅርሶች ይገኙበታል። ከስፋቱ የተነሳ ቦታውን ለማስጎብኘት በቤተ መንግሥት ውስጥ ያሉትን ቦታዎች በ5 ይከፍሉታል። አንደኛው በፊት ተትቶ የነበረ የቤተ መንግሥቱ ጓሮ ሲሆን በዚህ ሥፍራ የወዳደቁ ቆርቆሮዎች፣ የወታደሮች መኖሪያ፣ የተበላሹ የጦር መኪኖች የሚቆሙበት ቦታ ሲሆን አሁን እድሳት ተደርጎለት ጥሩ የመናፈሻ ሥፍራ ሆኗል። ሁለተኛው አጤ ሚኒሊክና አጤ ኃይለ ሥላሴ ያሰሯቸው የቤተ መንግሥትና የጽ/ቤት ሕንፃዎች ይገኛሉ። ሦስተኛው የኮሪያ መንግሥት ያሰራቸው ቢሮዎች ሲሆኑ አሁን አገልግሎት እሰጡ ይገኛሉ፤ ይሁን እንጂ ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት አይሆኑም። አራተኛው በተለያየ ምክንያት የማይጎበኝ ሲሆን ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ካገር በወጡበት ጊዜ ቢሯቸው ይሰሩ የነበሩ ባለሙያዎች እርሳቸውን ለማስደሰት የሰሩላቸው እዚያው ግቢ ውስጥ ነጠል ብሎ የተሰራ ቤት ነው። • ወመዘክር፡ ከንጉሡ ዘመን እስከዛሬ ይህም ብቻውን የተሰራና ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ መኖሪያ ጀርባ ይገኛል። ለመጎብኘትም በመኖሪያቸው ማለፍን ስለሚጠይቅ ለጉብኝት ክፍት አይሆንም። የዚህ ቢሮ የተወሰነ ክፍሉ እንደፈረሰም ይነገራል። አምስተኛው በሸራተን ሆቴል በኩል ሲታለፍ የሚታየውና በፊት ገደላማና ጫካ ሆኖ የሚታየው አዲስ የሚሰራው የእንስሳት ማቆያና አኳሪየም (የውሃ አካል) ሲሆን ግንባታ እየተካሄደበት ነው። አሁን ሙሉ ቤተ መንግሥቱን ልንጎበኝ ነው፤ አርክቴክት ዮሐንስ አንድ ሰው ቤተ መንግሥቱን ለመጎብኘት ሲገባ ከሚያገኘው ይጀምራሉ። 1ኛ. የመኪና ማቆሚያና ሞል ይህ ቦታ ከሒልተን ሆቴል ወደ ላይ አቅጣጫ ስንጓዝ ቤተ መንግሥቱ ከመድረሳችን በፊት በስተቀኝ ይገኛል። ታጥሮ የቆየ ባዶ ቦታ የነበረ ሲሆን አሁን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የአካባቢው ወጣቶች ተደራጅተው የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) ይሰሩበታል። በቅርቡ ግንባታው የሚጀመር ሲሆን ለጎብኝዎች የመኪና ማቆሚያ ሆኖም ያገለግላል። ይሁን እንጂ ግንባታው ስላልተጠናቀቀ ሰው የሚገባው በታች ባለው የደቡብ አቅጣጫ በር ነው፤ እዚያ ሲደርሱ የትኬት ቢሮ፣ ሻይ ቤት፣ መታጠቢያ ክፍሎች፣ የእንግዶች ማረፊያና መረጃ የሚሰጥባቸው ቦርዶችና ዲጂታል ማሳያዎችን ያገኛሉ። ይህ የትኬት ቢሮ ከዚህ ቀደም ያልነበረ ሲሆን ከመሬት ጋር ተመሳስሎና ተስተካክሎ የተሰራ በመሆኑ ከላይ ሲታይ ቤት መሆኑ በጭራሽ አያስታውቅም። 2ኛ. የመረጃ መስጫ ቦታ ይህን ሥፍራ ከትኬት ቢሮው ወደ ላይ ሲጓዙ ያገኙታል። በዚህ ቦታ ለጉብኝት ክፍት የሆኑ ቦታዎች በዲጅታልና በህትመት ገለፃ ይደረግበታል። ከጥላ ጋር የተዘጋጀ ማረፊያ ወንበሮች ያሉት ሲሆን ተሰርቶ ተጠናቋል። እሱን አለፍ እንዳልን ልጆች የሚቆዩበት የመጫዎቻ ቦታ እናገኛለን፤ በጣም የተጋነነ ባይሆንም መጠነኛ ተደርጎ ለልጆች መጫዎቻ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ተሟልቶ የተዘጋጀ ነው። • ጓድ መንግሥቱ እንባ የተናነቃቸው 'ለት አረንጓዴ ሥፍራ ተብሎ የተሰየመውን ጠመዝማዛ መንገድ ደግሞ የልጆች መጫወቻውን እንዳለፍን እናገኘዋለን። ቦታው ወደ ቤተ መንግሥቱ የሚኬድበት ዳገታማ መንገድ አለው፤ ይህም ለአካል ጉዳተኞች እንዲመች ተደርጎ በእግረኛ መረማመጃ ንጣፍ የተሠራ ነው። ወደፊት በግራና በቀኝ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የጥበብ ሥራዎች አሊያም ታሪካዊ ሁነቶች ማሳያዎች ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል፤ አሁን ዛፎችና ሳሮች የተተከሉ ሲሆን መንገዱም ዝግጁ ሆኗል። 3ኛ. የልዑላን ማረፊያ ቦታ ልጅ እያሱ፣ ንግሥት ዘውዲቱ፣ አጤ ኃይለ ሥላሴ ንጉስ ሆነው ከመሾማቸው በፊት በዚህ ቤት ኖረውበታል። ቤቱ በእንጨትና በድንጋይ የተሠራ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ነው። ፊቱን ወደ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ያዞረው ህንፃው በአጤ ሚኒሊክ የተሠራ ሲሆን አዲስ አበባን ቁልቁል ለማየት የሚያስችል ነው። የኪነ ህንፃ ባለሙያዎች 'የአዲስ አበባ መልክ አለው የሚባል የሕንፃ ዓይነት ነው' ይሉታል- ኢትዮጵያዊ ጥበብ ያረፈበት መሆኑን ለመግለፅ። ከፊት ለፊቱ አዲስ የተሠራና ብዙ ሰዎች ሰብሰብ ብለው ፎቶ የሚነሱበት ሥፍራ አለው። በቅርቡ በተደረገው የእራት ግብዣ በነበረው ጉብኝት ቤቱ እንዳይጎዳ በሚል ውስጥ ሳይገባ ከውጭ ነበር የተጎበኘው። 4ኛ. የዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ ጽ/ቤትና መኖሪያ ቤት (ኮምፕሌክስ) በዚህ ሥፍራ መጀመሪያ የምናገኘው የፊት አውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴን (አባ መላ) መኖሪያ ነው። አባ መላ የአጤ ሚኒሊክ የጦር ሚንስትር የነበሩ ሲሆን ይኖሩበት የነበረ ትንሽ የእንጨት ቤት ከአጤ ምኒሊክ መኖሪያ ቤት ጎን ላይ ይገኛል። አጤ ሚኒሊክ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላም እንደ መኖሪያና ቢሮ አድርገው ሲጠቀሙበት ነበር። ቤቱ ፈርሶ የነበረ ሲሆን አሁን ሙሉ በሙሉ ታድሷል። ወደ አጤ ሚኒሊክ ባለ አንድ ፎቅ መኖሪያና ጽ/ቤት በሮች በእንጨት የተሠሩ ሲሆን በሚያምር መልኩ የአበባና የሐረግ ጌጥ የተፈለፈለበት ነው። ይህ ቤት ከሁለት ሌሎች ቦታዎች ጋር በድልድይ ይገናኛል። አንደኛው በሰሜናዊ አቅጣጫ የአጤ ምኒሊክ የፀሎት ቤትና የሥዕል ቤት ሲሆን እንቁላል ቤት በመባል ይጠራል። አንዳንዴም እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበት ነበር። የአጤ ሚኒሊክ የግብር አዳራሽ በቀደመው ጊዜ የፀሎት ቤቱና የሥዕል ቤቱ ባለ ሁለት ፎቅ ነው። ሁለተኛው ፎቅ ላይ ከፍ ብላ የተሠራች በመስታወት የተሸፈነች ቤት አለች፤ ይህች ቤት 'ቴሌስኮፕ' ያላት ሲሆን አዲስ አበባን በሁሉም አቅጣጫ ማየት ታስችላለች። በዚች እንቁላል ቤት መገናኛው ድልድይ ጋ የመጀመሪያው ስልክ የገባበት ቤት ይገኛል። ቤቱ ከድንጋይና ከእንጨት የተገነባ ነው። አርክቴክት ዮሐንስ የኪነ ህንፃውን ጥበብ ሲገምቱ ከአርመኖችና ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ሕንዶች ሳይሳተፉበት እንደማይቀሩ ይገምታሉ። ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የውይይት ክበብ በመሆን አገልግሏል። • አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ሌላኛው ከአጤ ሚኒሊክ ቤት ጋር በድልድይ የሚገናኘው የእቴጌ ጣይቱ ቤት ነው። ይህ ቤት ከቤተ መንግሥቱ በምሥራቃዊ አቅጣጫ የሚገኝ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ነው። በምድር ቤት የዙፋን ግብር ቤት ይገኛል። የነገሥታቱ መመገቢያ አዳራሽ ሲሆን ንጉሣዊ ቤተሰቦች ምግብ የሚመገቡበት ክፍል ነበር፤ ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የደርግ ምክር ቤት መሰብሰቢያ በመሆን አገልግሏል። 5ኛ. ሦስት አብያተ ክርስቲያናት አብያተ ክርስቲያናቱ ከግብር ቤቱ አዳራሽ በስተ ምሥራቅ በኩል ይገኛሉ። የኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን (የአጤ ሚኒሊክ ሥዕል ቤት)፡ በአጤ ሚኒሊክ ጊዜ ለብቻ በአጥር ያስከለሏት ሲሆን አሁን ሕዝብ ይገለገልባታል። ይሁን እንጂ አጤ ሚኒሊክ ከመኖሪያቸው ተነስተው የሚሄዱባት መንገድና በር አሁንም ድረስ ይገኛል። የባዕታ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን (በንግሥት ዘውዲቱ የተሰራ ሲሆን የአፄ ሚኒሊክም አፅም ያረፈው እዚሁ ነው) አሁን ከቤተ መንግሥቱ ውጭ ሲሆኑ ጥበቃ ይደረግለታል። ጎብኚዎችም ሲመጡ እዚያ ያሉት ካህናት ምድር ቤት ያለውን መቃብራቸውን ከፍተው ያሳያሉ። በበርካታ ሰው የሚጎበኝም ከሆነ ለቤተ መንግሥቱ ቀድሞ እንዲታወቅ ይደረጋል። ሦስተኛው ከዚህ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ የሚገኘውም የገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ነው። 6ኛ. ታችኛው የዙፋን ችሎት ይህ ችሎት በአጤ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የተሠራ ሲሆን በታችኛው መዋቅር ያልተፈታ አገራዊ ጉዳይን የሚያዩበት የ'ሰበር ሰሚ ችሎት' ቦታ ነው። ይህ ባለ አንድ ፎቅ ቤት የንጉሡ ጽ/ቤትም በመሆን አገልግሏል። በውስጡ ጽ/ቤታቸውን ጨምሮ መዝገብ ቤትና ሌሎች አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችም አሉት። አጤ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ የደርግ ወታደሮች ቤቱን ተቆጣጥረውት ነበር። የኮሎኔል መንግሥቱ አስተዳደርም ቢሮ አድርጎ ይጠቀምበት ነበር። ንጉሡ ሕይወታቸው ካለፈ በኋላም ችሎታቸውና ቢሯቸው ከነበረው ቦታ ምድር ቤት እንደተቀበሩና በኋላም አፅማቸው ወጥቶ እንደተወሰደ ይነገራል። የደርግ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ቢሮ፣ የመንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ረዳት የመንግሥቱ ገመቹ ቢሮ፣ እንዲሁም ታስረው የነበሩ ደርግ ወታደሮች የታሰሩበት ቦታም ነው። • በመፈንቅለ መንግሥቱ ዙሪያ ያልተመለሱት አምስቱ ጥያቄዎች በአንድ ወቅት በመንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ላይ የመግደል ሙከራ በተደረገበት ጊዜ ያመለጡበት ቦታም ይሄው ሕንፃ እንደሆነ ይነገራል። ኢህአዴግ አገሪቱን ሲቆጣጠርም የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ይህንን ሕንፃ መኖሪያ አድርገውት ነበር። አቶ መለስ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላም አስክሬናቸው የወጣው ከዚሁ ቤት ነው። በአቶ መለስ ዜናዊ ጊዜ ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን በቤተ መንግሥቱ ውስጥ መኖሪያ ቤት ማሠራት ጀምረው ነበር። ከዚያም በኋላ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መኖሪያ አድርገውት የነበረ ቢሆንም አራት ዓመታትን ከቆዩ በኋላ አዲስ ወደ ተሠራው ቤት ተዘዋውረዋል። ይህም ለጉብኝት ክፍት እንደማይደረግ መረጃ እንዳላቸው አርክቴክት ዮሐንስ ነግረውናል። 7ኛ. የመንግሥቱ ኃይለማሪያም ቤት መንግሥቱ ኃይለማሪያም ባንድ ወቅት ረዘም ላሉ ቀናት ወደ አውሮፓ አቅንተው ነበር። በዚህ ጊዜ ወዳጆቻቸው እርሳቸው ሲመለሱ ለማስደሰት ለመንግሥቱ አዲስ ቤት ለመሥራት ተነጋገረው በጣም በአፋጣኝ ቤት ሠርተውላቸው ነበር። ቤቱ መዋኛ እንደነበረው የሚነገር ሲሆን ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው አርክቴክት ዮሃንስ ገልፀውልናል። 8ኛ. የአንበሶችና ሌሎች እንስሳት ማቆያ ይህ ሥፍራ በቤተ መንግሥቱ ደቡባዊ አቅጣጫ ይገኛል። በብረት ፍርግርግ የተሠራ ትንሽ የእንስሳት ማቆያ ሲሆን በአሁን ወቅት ምንም ዓይነት እንስሳት አይኖሩበትም። ቀደም ሲል የነበሩት እንስሳት ወደ ሌላ ሥፍራ ተዛውረዋል የሚል መረጃ አለ። 9ኛ. በአጤ ሚኒሊክ ጊዜ የተሠራው የጽህፈት ቤት በዚህ ቤተ መዛግብት የተለያዩ መረጃዎች ተሰንደው ይገኛሉ። ዘመናዊ በሆነ መልኩ የተደራጀ ሲሆን ከአፄ ሚኒሊክ ጀምሮ የነበሩ ታሪካዊ ሰነዶች ይገኙበታል። ከትምህርት ሚኒስቴር በስተቀር ሌሎች የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በሙሉ ሰነዶቻቸውን ያስቀምጡበት እንደነበር ይነገራል። የደብዳቤ ልውውጦች፣ የብራና ጽሁፎችና ሌሎች የአገር ውስጥ ጉዳዮች የተሰነዱበት ሲሆን አሁን እድሳት ያልተደረገበትና ጎብኝዎችም ወደዚያ መጠጋትም ሆነ ማየት አይችሉም። 10ኛ. የታችኛው ዙፋን ችሎት የዙፋን ችሎቱ በቤተ መንግሥቱ ደቡባዊ አቅጣጫ ፊቱን ወደ ሸራተን ሆቴል አቅጣጫ አዙሮ የቆመ ትልቅ ሕንፃ ሲሆን በአጤ ሚኒሊክ ጊዜ የተሠራ ነው። ከሕንፃው ፊት ለፊት ሰንደቅ ዓላማ መስቀያ ይገኛል። በፊት ለፊቱም ነጋሪት እየተጎሰ፤ እምቢልታ እየተነፋ ትልልቅ የጦርነት አዋጆች የታወጁት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሃገራዊ ጉዳይ የሚነገርበትና የሚታወጅበት አደባባይ አለው። ሕንፃው ምድር ቤት ያለው ሲሆን ከላይ ያጌጠ አዳራሽ አለው፤ አዳራሹ ውስጥ የዘውድ ምልክት ያለው በሃር ከፋይ የተሠራ ዙፋኑን የሚያጅብ መቀመጫ አለ። መሰብሰቢያ አዳራሽ እና በግራና በቀኝ ሰፋፊ ክፍሎች አሉት። በደርግ አስተዳዳር ጊዜ የደርግ ምክር ቤት ሆኖ ለረጂም ጊዜ አገልግሏል። የአፄ ኃይለ ሥላሴ ሹማምንትም በዚሁ ምድር ቤት ታስረው ነበር። የምክር ቤቱ አባላት ከላይኛው ፎቅ ሆነው 'ይገደሉ አይገደሉ' የሚል ክርክሮች ይካሄዱበት ነበር- በምድር ቤቱ ደግሞ ሞታቸውን አሊያም ሽረታቸውን የሚጠባበቁ እስረኞች ይህን እየሰሙ ይሳቀቁ እንደነበር ይነገራል። ምድር ቤቱ ውስጥ አራት ክፍሎች አሉት። በእነዚህ ቤቶች ወፍራም የብረት ዘንጎች ያሉ ሲሆን ሰዎች ተሰቅለው ይገረፉበት ነበር ይባላል። አሁን በሙዚየሙ እድሳት እንደ አዳራሽ እንዲጎበኝ ሦስት ነገሮች ታስበዋል። • ከኢትዯጵያ የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት ሊመለሱ ነው የደርግ ችሎት የነበረው ኢትዮጵያ ተቀብላቸው የነበሩ ትልልቅ ሰዎች እንደ የዩጎዝላቪያው ቲቶ፣ የፈረንሳዩ ቻርለስ ደጎል፣ የእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤጥና የሌሎችም ፎቶ ለዕይታ ተዘጋጅተዋል። በአጤ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ እነዚህ ሰዎች በዚህ አዳራሽ አቀባበል ተደርጎላቸው ስለነበር እነርሱን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ይታዩበታል። ሌላኛው በደቡባዊ አቅጣጫ የመንግሥታት ታሪኮች ለዕይታ ይቀርብበታል፤ አሁን ላይ ከአፄ ሚኒሊክ ጀምሮ እስከ አቶ ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ ድረስ ያሉ የኢትዮጵያ መሪዎች ፎቶና በእነሱ ዘመን የተሠሩ ሥራዎች ለዕይታ ይቀርባሉ። በምሥራቃዊው ክፍል አገር የተመሠረተችበት ንግርት (አፈ ታሪክ) አንድ ጠንካራ ማኅበረሰባዊ ሥነ ልቦና የተዋቀረበት ንግርት ይቀርብብታል። በዚህ አዳራሽ ሰሜናዊ ክፍል ከውጭ የተቀበልናቸውና ሀገር ውስጥ የዳበሩ ኃይማኖቶች ይቀርቡበታል፤ ዋቄ ፈታ ፣ ቤተ እስራኤላዊያን ይከተሉት የነበረው የአይሁድ እምነት፣ ከዚያም እስልምና፣ ክርስትና፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት እንዲሁም ሌሎች የክርስትና እምነቶች በተወጠረ ሸራ ላይ በዲጂታል እንዲታዩ ይደረጋል። ከሕንፃው ወጥተን በደቡባዊ አቅጣጫ ግድግዳው ላይ የብረት ቀለበቶች ይታያሉ፤ እነዚህ ቀለበቶች በዳግማዊ ሚኒሊክ ጊዜ መኳንንቶቻቸው በቅሎዎቻቸውን የሚያስሩበት ቦታ ነበር። በደርግ ጊዜ ደግሞ ኋላ ላይ የተረሸኑት የአፄ ኃይለ ሥላሴ ሹማምንት እስረኞች ፀሐይ የሚሞቁበት ቦታ ሆኖም አገልግሏል። በ1981 በነበረው መፈንቅለ መንግሥት የተሳተፉት 12ቱ ጀኔራሎችም የታሰሩበት ቦታ ነው። 11ኛ. አዲስ እየተሠራ ያለው አኳሪየም እና የእንስሳት ማቆያ ቦታው ከቤተ መንግሥቱ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን በአፄ ሚኒሊክና በአፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ የተጀመረውን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በተሻለ መንገድ ለመተግበር አዲስ እየተሠራ ያለ ሥፍራ ነው። 12ኛ. የአጤ ሚኒሊክ የግብር አዳራሽ ይህ አዳራሽ በጣም ትልቅ አዳራሽ ሲሆን ኪነ ሕንፃው የኢትዮጵያዊያን፣ የአርመናዊያንና የሕንዶች እጅ ያለበት እንደሆነ ይገምታሉ። የግብር አዳራሹ በግምት 8 ሺህ ሰዎችን ያስተናግዳል ተብሎ ይገመታል፤ በዘመኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ያሏቸው በሮች ያሉት ሲሆን በቅርቡም እድሳት ተደርጎለታል።'ገበታ ለሸገር' የእራት ግብዣ የተካሄደውም በዚሁ አዳራሽ ነው። 13ኛ. ትንሿ ኢትዮጵያ ይህ ቦታ ቀድሞ ያልነበረና የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ሃሳብ ነው። ከአዳራሹ በስተ ደቡብ አቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔር ብሔረሰቦች የአኗኗር ዘይቤን የሚያሳዩ የሃገረሰብ ኪነ ሕንፃ የሚታይበት ሥፍራ ነው። በአሁኑ ሰዓት ብዙ የተሠራ ነገር ባይኖረውም ሥራው ተጀምሯል። በመጨረሻም በቤተ መንግሥቱ ውስጥ የሚታደሱትና የሚጠገኑትን ቅርሶች በተመለከተ ቅሬታ ያላቸው ሰዎች መኖራቸውን ያነሳንላቸው አርክቴክት ዮሐንስ "የተሠራው የእድሳት ሥራ የሚያስወቅስ ነው ለማለት እቸገራለሁ፤ ይሁን እንጂ የባለሙያ ተሳትፎና ድጋፍ ቢኖራቸው ከዚህ የተሻለ ማድረግ ይቻል ነበር የሚል እምነት አለኝ፤ ይህንንም በፅሁፍ ለሚመለከተው አቅርቤያለሁ" ብለዋል። ፕሮጀክቱ የተደገፈው በአረብ ኢሜሪትስ ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግሥት የወጣ ውጪ አለመኖሩን መረጃው እንዳላቸው ገልፀውልናል።
50218916
https://www.bbc.com/amharic/50218916
በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር በስማቸው ማህበራዊ ሚድያ ላይ የወጣ መረጃን ውድቅ አደረጉ
በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር እስቲፋኖስ አፈወርቂ 'የኤርትራ ህዝብ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ወደ ትግራይ እንዲሄዱ አይፈልግም' ብለዋል በሚል ማህበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ በስማቸው የተሰራጨው መረጃ የእርሳቸው እንዳልሆነ ለቢቢሲ ተናገሩ።
"እኔ እንደዛ ብዬ አልተናገርኩም፣ አላሰብኩም አልጻፍኩምም። ሶሻል ሚድያ ብዙ ሰዎች ስለሚጠቀሙበት፣ የሆነ አካል ያደረገው ሊሆን ይችላል" ብለዋል። • "በኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊ ግድያ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም" የነቀምቴ ፖሊስ አዛዥ • የአይኤሱ መሪ አቡ ባክር አልባግዳዲ እንዴት ተገደለ? ከሁለት ሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የኤርትራው ፕሬዝዳንት ወደ ትግራይ ጉዞ የማድረግ ፍላጎት አላቸው በሚለው ጉዳይ ላይ ሃሳባቸውን ሰጥተው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ "ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በመቀለ ጎዳናዎች መዘዋወር እንሚፈልግ በተደጋጋሚ ገልጾልኛል . . . ይህም እንዲሳካ በጸሎት አግዙን" በማለት ተናግረው ነበር። ይህን ተከትሎ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ "የክልሉ ህዝብና መንግሥት በሁለቱ አገራት መካከል የተጀመረው የሰላም ሂደት የተሳካ እንዲሆን ፍላጎት እንዳላቸው" ገለጸዋል። የሰላም ሂደቱ ሙሉ በሙሉ መሳካት የሚችለው ግን ፕሬዝዳንቱ በአውሮፕላን ሳይሆን የተዘጉ ድምበሮች ተከፍተው በእግር ወይም በመኪና ወደ ትግራይ መምጣት ሲችሉ መሆኑን በሰጡት ማብራርያ ላይ ተናግረው ነበር። አምባሳደር እስቲፋኖስ በእሳቸው ስም በማህበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ ስለወጣው መልዕክት ለቢቢሲ ሲናገሩ "ይህን ሆን ብለው የሚያደርጉ በኢትዮጵም በምሥራቅ አፍሪካም የተጀመረውን የሰላም እንቅስቃሴ ማስተጓጎል የሚፈልጉ አካላት ናቸው" ሲሉ ገልጸዋል። "በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያም ይሁን በአፍሪካ ቀንድ፤ ማለትም በኢትዮጵያና በኤርትራ፣ በኤርትራና በሱዳን፣ እንዲሁም በሶማሊያና በኤርትራ መካከል እየተፈጠረ ያለውን የሰላም እንቅስቃሴ የሚጻረሩ አካላት ናቸው" ብለዋል አምባሰደሩ። • በግጭት ለተፈናቀሉት የተሰበሰበው አስቸኳይ እርዳታ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ • ስለባለፈው ሳምንት ግጭቶችና ጥቃቶች አስካሁን የምናውቃቸው ነገሮች ይህ ፍላጎታቸውም ዓመታት ያስቆጠረ መሆኑን በመግለጽ "በቀጠናችን ያለውን ህዝብ ለማጋጨት የሚፈጥሩት ዘዴ ነው" በማለት አብራርተዋል። አምባሳደር እስቲፋኖስ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጉዞን በተመለከተ የሚሰጡ ሐሳቦችን "የቃላት ጨዋት" ናቸው ሲሉ ይገልጻሉ። "ብዙ ትርጉም የሚሰጥ አይደለም። በቃላት ዙርያ የሚደረግ ጨዋታ ወደ ምንም ሊያደርስ አይችልም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "በእግር ወይስ በአውሮፕላን እያሉ ወሬ ማብዛቱ ትርጉም አልባ ነው። በዚህ ላይ ብዙ ጊዜያችንን ማጥፋት ያለብን አይመስለኝም። የሰላም ሂደት ስለተጀመረ 'ሂደቱን ትደግፋለህ ወይስ አትደግፍም?' የሚል ነው ዋናው ጉዳይ" በማለት አስረድተዋል። የሰላም ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ እንዲሁም የትግራይ ህዝብ ፍላጎት እንደሆነም ገልጸዋል።
news-54217232
https://www.bbc.com/amharic/news-54217232
ፖለቲካ ፡ ለውጥ ለማምጣት የምን ያህል ሰዎች ተሳትፎን ይፈልጋል?
አንድን መሪ ከሥልጣን ለማስወገድ ምን ያህል ሰው መቃወም አለበት? የሚያዋጣው ነውጥ የቀላቀለ ተቃውሞ ነው ወይስ ሰላማዊ?
ከማይዘነጉ ንቅናቄዎች መካከል እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1980ዎቹ የነበረው የፖላንድ ተቃውሞ፣ የደቡብ አፍሪካው የጸረ አፓርታይድ ትግል፣ የቱኒዝያውን ፕሬዘዳንት ያስወገደው የጃዝሚን አብዮት እና የፀደይ አብዮት (አረብ ስፕሪንግ) ይጠቀሳሉ። እነዚህ ጉልህ ለውጥ ማምጣት የቻሉ ንቅናቄዎች ናቸው። ወደ ቅርብ ጊዜ አብዮት ስንመጣ ደግሞ ቤላሩስን እናገኛለን። ፕሬዘዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ምርጫ አሸንፌያለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለተቃውሞ ወጥተዋል። በርካቶች ታስረዋል፣ ስቃይና እንግልት እንደደረሰባቸው የሚናገሩም አሉ። ሆኖም ግን ተቃውሞው ሰላማዊ በሆነ መንገድ ቀጥሏል። ለመሆኑ ተቃውሞው ግቡን ይመታል? የሚለውን ለመመለስ ታሪክን መመልከት ያሻል። ነውጠኛ ተቃውሞ የቱ ነው? የሀርቫንድ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንቲስት ኤሪካ ቼንዌዝ በአምባገነን ሥርዓቶች ላይ ስለሚነሳ ተቃውሞ አጥንተዋል። አምባገነናዊ ሥርዓት ውስጥ ሕዝብ መሪውን ለማስወገድ ምርጫ ማካሄድ አይችልም። ስለ ተቃውሞ ሲነሳ የትኛው ነውጥ የቀላቀለ የትኛውስ ሰላማዊ ነው? የሚለውም ያከራክራል። ንብረት ሲወድም ተቃውሞው ነውጠኛ ነው ይባላል? ሰዎች አካላዊ ጥቃት ሳያደርሱ ዘረኛ ስድብ ቢሳደቡስ? ራስን ማቃጠል ወይም የረሀብ አድማ መምታትስ ነውጥ የቀላቀሉ የተቃውሞ መንገዶች ናቸው? ለእያንዳንዱ ሁኔታ ግልጽ በሆነ መንገድ ነውጠኛ ወይም ኢ-ነውጠኛ የሚል ትርጓሜ መስጠት ይከብዳል። ሆኖም ግን ነውጥ በቀላቀለና በሰላማዊ ተቃውሞ መካከል ያሉ ልዩነቶችን መረዳት እንችላለን። ለምሳሌ ሰውን መግደል ነውጠኛ መሆኑ አያጠያይቅም። ሰላማዊ ሰልፍ፣ ፊርማ ማሰባሰብ፣ አድማ መምታትና አንድን ሁነት ረግጦ መውጣት ሰላማዊ ተቃውሞ ናቸው። አንድ ጥናት 198 አይነት ሰላማዊ ተቃውሞዎች እንዳሉ ያሳያል። ሳይንቲስቷ ከ1990 እስከ 2006 በተሰበሰበ መረጃ ላይ ጥናት ሠርተው፤ ሰላማዊ ተቃውሞ ውጤታማ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። ሰላማዊ ተቃውሞ ውጤት ያስገኛል? ነውጥ የቀላቀለ ተቃውሞ ድጋፍ ሊያጣ እንደሚችል ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ሰላማዊ ተቃውሞ ሲካሄድ የሚቀላቀሉ እንደሚበራከቱ፣ በአጭር ጊዜና ያለ ምንም ልዩ ስልጠና ሊከናወን እንደሚችልም ያክላሉ። ታዳጊዎች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ሴቶች እና አዛውንቶች ሰላማዊ ተቃውሞ ይቀላቀላሉ። ቡልዶዘር አብዮትን እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ወታደሮች ለምን ተቃዋሚዎች ላይ እንዳልተኮሱ ሲጠየቁ፤ ተቃዋሚዎቹን ስለምናውቃቸው ነው ብለው ነበር። ተቃዋሚዎቹ ጓደኞቻቸው፣ የአክስታቸው ልጆች፣ ጎረቤቶቻቸው ወዘተ. . . ነበሩ። የፖለቲካ ሳይንቲስቷ ኤሪካ እንደሚሉት፤ 3.5 በመቶ ሕዝብ ከተቃወመ ለውጥ ማምጣት ይችላል። ቤላሩስን ማሳያ ብናደርግ፤ 3.5 በመቶ ማለት ከአገሪቱ ዘጠኝ ሚሊዮን ዜጎች 300,000 ማለት ነው። በመዲናዋ ሚንስክ በተካሄደው ተቃውሞ ወደ አስር ሺህ ሰዎች ተሳትፈዋል። አሶሽየትድ ፕሬስ 200,000 ተቃዋሚዎች መገኘታቸውን የዘገበበት ወቅት ነበር። 3.5 በመቶ የሚለው ቁጥር በሁሉም አገር ይሠራል ማለት አይደለም። አንዳንድ ንቅናቄዎች በአነስተኛ ቁጥርም ግባቸውን መተዋል። ከፍተኛ ሕዝብ አሳትፈው የከሸፉ አብዮቶችም አሉ። ለዚህ የ2011 የባህሬን እንቅስቃሴ ይጠቀሳል። በመላው ዓለም ከትጥቅ ትግል ይልቅ ሰላማዊ ተቃውሞ እየተዘወተረ የመጣ የትግል ስልት መሆኑን የኤሪካ ጥናት ይጠቁማል። ከ2010 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት የታዩ ተቃውሞዎች በሰው ልጅ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሰላማዊ ናቸው። በሌላ በኩል ከአስር ነውጥ የቀላቀሉ ተቃውሞዎች ዘጠኙ ይከሽፋሉ። በቀደመው ዘመን ከሁለት ሰላማዊ ተቃውሞዎች አንዱ ይሳካ ነበር። አሁን ላይ ከሦስት ሰላማዊ ተቃውሞዎች ፍሬያማ የሚሆነው አንዱ ብቻ ነው። መንግሥት ግልበጣ ከ2006 ወዲህ አንዳንድ ለውጦች እየተስተዋሉ ነው። የሱዳኑ ኦማር አልበሽር ከሥልጣን ተወግደው በሳምንታት ውስጥ የአልጄሪያው ፕሬዘዳንት አብዱልአዚዝ ቡተፍሊካም ተመሳሳይ እጣ ደርሷቸዋል። እንዲህ አይነት የመንግሥት ግልበጣዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን ላይ እንደመሆናችን ዲጂታል አብዮት ሲቀጣጠል እናያለን። መረጃ በቀላሉ ይንሸራሸራል። ቀጣዩ የተቃውሞ ሰልፍ የት እንደሚካሄድ ለማወቅም አይከብድም። ሆኖም ግን ዲጂታል አብዮትን እንዴት ማስተጓጎል እንደሚቻል መሪዎች ያውቃሉ። ኤሪካ እንደሚሉት፤ መሰል አብዮቶችን ለማስቆም የዲጂታል ስለላ እና ሰርጎ ገብ እርምጃዎች ይወሰዳሉ። በማኅበራዊ ሚዲያ ሐሰተኛ መረጃ እና ፕሮፓጋንዳም ይነዛል። በቤላሩስ ተቃዋሚዎች ስልካቸው እየተፈተሸ ነው። እንደ ቴሌግራም ባለ መልዕክት መለዋወጫ ስለ ተቃውሞው መረጃ አግኝተው እንደሆነም ይጣራል። የቴሌግራም ቡድን የከፈቱ ሰዎች ታስረዋል። ቴሌግራም በበኩሉ የቡድኑ አባላት ዝርዝር ፖሊስ እጅ ከመግባቱ በፊት ቡድኖቹ እንዲከስሙ ያደርጋል። ታዲያ ፕሬዘዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ሥልጣናቸውን ይዘው ይቆዩ ይሆን? ወይስ ተቃዋሚዎች ድል ይነሳሉ? አብረን የምናየው ይሆናል።
51657532
https://www.bbc.com/amharic/51657532
ከፋ ዞን፡ በቦንጋ ሠርግ አስደግሶ "የሙሽራዬ ቤት ጠፋኝ" ያለው ግለሰብ የእስር ጊዜውን አጠናቀቀ
በደቡብ ክልል፤ ከፋ ዞን፤ ቦንጋ ከተማ ሠርግ አስደግሶ "የሙሽራዬ ቤት ጠፋኝ" ያለው ግለሰብ ከእስር መለቀቁን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክፍሌ ተካ ለቢቢሲ ገለፁ። ነገሩ እንዲህ ነው. . .
ግለሰቡ በቦንጋ ከተማ ቤት ተከራይቶ ይኖር ነበር። ዕድሜው አሁን ወደ 30 ይጠጋል። የኑሮ ሁኔታውም ዝቅተኛ ደረጃ የሚባል ዓይነት ነው ይላሉ የሚያውቁት። ታዲያ አንድ ቀን ለሠፈሩ ሰዎች "ላገባ ነው" ሲል ያበስራቸዋል። መቼም አንድ ሰው በሕይወቱ ወደ መልካም ምዕራፍ ሲሸጋገር ደስ ያሰኛልና እነርሱም ደስታቸውን ይገልፃሉ። "አበጀህ የእኛ ልጅ" ይሉታል። • 'ወንድ ያገቡት' ኡጋንዳዊ ኢማም ከኃላፊነታቸው ታገዱ • የቴክሳስ ፖሊስ ልማደኛዋን ድንኳን ሰባሪ እየፈለገ ነው ሁሉም ባቅሙ እያዋጣ እርሱም ካመጣው ጋር እየተጨማመረ ድግሱ በትብብር ተዘጋጀ። የሠርጉ ቀን ሲደርስም ሸራ ተወጥሮ፣ ወንበር ተሰባስቦ ለእንግዶች ተሰናዳ። ዳሱም በአበባ እና በዘንባባ ተጌጠ። ጎረቤቱም እንደ ባህሉ ተሰባስቦ በአቅማቸው ድግሱን ሲያስተናብሩ ዋሉ። ሁሉም ተሰናድቶ ካለቀ በኋላ ሙሽራው ከአጃቢዎቹ ጋር [6 ወንድ እና ሁለት ሴት] እየጨፈሩ፣ እየዘፈኑ ሙሽሪትን ለማምጣት ዴቻ ወረዳ፤ ሻፓ ወደ የሚባል ቀበሌ አመሩ። ሻፓ በእግር ቢያንስ 1 ሰዓት ይወስዳል። ሚዜዎቹና አጃቢዎቹ "ደስታህ ደስታችን ነው" ብለው ይህንን ሁሉ ርቀት ተጉዘው ሥፍራው ደረሱ። ይሁን እንጂ ሙሽራው አንዳች ነገር እንደጠፋው ሁሉ መንደሩን መዟዟር ጀመረ። በድካም የዛሉት ሚዜዎቹ "ቤቱ አንደርስም ወይ? ሙሽራዋ የታለች?" ብለው መጠየቃቸው አልቀረም። ግን መዳረሻው አልታወቅ አለ። በአካባቢው የሚታይም ሆነ የሚሰማ የሠርግ ሁናቴ የለም። ግራ የተጋቡት አጃቢዎች "የታለች?" ሲሉ ሙሽራውን ወጥረው ይይዙታል። "ልጅቷ ያለችበት ቤት ጠፋብኝ " ይላቸዋል። 'ሙሽራዋ ጠፋች'። በነገሩ ግራ የተጋቡት አጃቢዎቹ የሚያደርጉት መላ ቅጡ ጠፋቸው። ዳስ ውስጥ ሆነው እየዘፈኑ ሙሽራዋን የሚጠባበቁት ሠርገኞች ፊት እንዴት ባዶ እጃቸውን እንደሚገቡ ጭንቅ ያዛቸው። በዚህ መሃል አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላቸው። ከአጃቢዎቹ አንዱን ጫማው እንዲያወልቅ አድርገው በነጠላ በመሸፋፈን ሙሽራ አስመስለው እየዘፈኑ፣ እየጨፈሩ ይዘው መግባት። በሃሳቡ ተስማሙ፤ እንዳሰቡት አደረጉ። ቤቱ እንደደረሱም "በእግሯ ረዥም ሰዓት ስለተጓዘች በጣም ደክሟታል።" ብለው ወደ ጫጉላው ቤት አዝለው ያስገቧታል። የሆነውን ማንም የገመተ የለም። ትንሽ ቆይቶ "ሙሽራዋ ትውጣና ራት ይበላ" ሲሉ ደጋሽ ጎረቤቶች ይጠይቃሉ። ምላሹ አሁንም "ደክሟታል" የሚል ነበር። አቶ ሙሉጌታ ገ/ሚካኤል ሠርግ ተጠርተው ከተገኙት ጎረቤቶች መካከል አንዱ ነበሩ። "ከሌላ ቦታ መጥቶ እኛ ሠፈር ቤት ተከራይቶ ይኖር ነበር። 'ላገባ ነው' ብሎ የተወሰኑ ጎረቤቶቹን ሠርግ ጠራ። እኔም ተጠርቼ ስለነበር ሠርጉ ላይ ተገኘሁ። ሙሽራዋን እንቀባለለን ብለን ሽር ጉድ ስንል ዋልን። በ'ጂ ፓስ' የሠርግ ሙዚቃ ተከፍቶ እየተጠባበቅን ነበር። በኋላ ላይ አምሽተው መጡ። ነገር ግን ብንጠብቅ ብንጠብቅ ሙሽራዋ አትመጣም። ወሬ አይቀርምና ሴት አስመስለው ይዘው የገቡት ወንድ ነው ተባለ። እንግዶችም ድግሱን ሳይቀምሱ ወዲያው ነበር በብስጭትና በእፍረት የተበታተኑት" ሲሉ አጋጣሚውን ያስታውሱታል። ሚስጢሩ ከጫጉላ ቤቱ ወጥቶ ወደ ዳሱ ሲዛመት ግን አፍታም አልቆየ። "ሴት አይደለም ወንድ ነው" የሚል። 'ጉድ' ተባለ። የሆነውን ባለማመን እያጉመተመቱ ወደየመጡበት የሄዱ እንዳሉ ሁሉ ጉዳዩን ለሕግ አካል ለማሳወቅም ያሰቡ አልጠፉም። ለፖሊስ ጥቆማ ተሰጠ። ፖሊስም በሥፍራው ተገኝቶ 'ሙሽራውን' በቁጥጥር ሥር አዋለ። " እኔ እንዲህ ዓይነት ነገር ሰምቼም አላውቅም።" የሚሉት አቶ ሙሉጌታ፤ በአካባቢው ባህል መሠረት በሠርግ ወቅት ገንዘብ ስለሚሰጥ ግለሰቡ ይህን ያደረገው ገንዘብ ለማግኘት መሆኑን የተረዳነው በኋላ ነው ይላሉ። ቆይተው እንደሰሙትም ሠርጉን ለመደገስ ያልተበደራቸው የጉልት ነጋዴዎች አልነበሩም። ድርጊቱ የአገሬውን ሰው ጉድ ያሰኘ ነበር። ድርጊቱንም እጅግ ኮነኑት፤ "ለዚህ ነው ወይ ደፋ ቀና ያልነው" ሲሉ ተፀፀቱ። የግለሰቡን ፍርድም በጉጉት መጠባበቅ ያዙ። • የቴክሳስ ፖሊስ ልማደኛዋን ድንኳን ሰባሪ እየፈለገ ነው • ሙሽሪት እጮኛዋ መቃብር ላይ ድል ባለ ሠርግ ተሞሸረች በወቅቱ ወንጀሉን ሲከታተሉ የነበሩት የቦንጋ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክፍሌ ተካ እንደነገሩን ግለሰቡ ሠርጉን የሠረገው ጥቃቅን ወጪዎች ሳይቀሩ ተበድሮ ነው። ሽንኩርቱም፣ እንጀራውም፣ ጠላውም ሁሉም ለድግስ የሚያስፈልጉ ነገሮች። የተበደረውም ከተለያዩ ቦታዎችና ሰዎች ስለነበር ማንም የጠረጠረ አልነበረም። "'ከእጮኛዬ ጋር ለመጋባት ባለሁበት ቀበሌ ጨርሼ መጣሁ' ብሎ ጓደኞቹን ሰብስቦ ሲናገር በየዋህነት አመኑት፤ ደስም አላቸው። እንደዚህ አንሸዋዳለን ብሎ ግን ያሰበ አልነበረም" ይላሉ ኮማንደር ክፍሌ። ኮማንደር ክፍሌ፤ ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ውሎ በምርመራው ሂደት ሲጠየቅ "አጭቻት ነበር፤ ከተስማማች በኋላ ቤቷ ጠፋኝ" የሚል መልስ እንደሰጠ ይናገራሉ። "ለትዳር ያጫሃትን ሴት ቤት እንዴት ነው አጣሁት የምትለው?" ሲሉ ጥያቄያቸውን ማስከተላቸው ግን አልቀረም። እሱም "ወደ ቦታው ሄድን፤ ጨለማ ነው፤ ቤቱ ጠፋብኝ። ተመልሼ ባዶ እጄን ወደ ቤት ለመግባት ስለተቸገርኩ እና ድግስ የጠራኋቸው ሰዎች አታለለን እንዳይሉ ብየ፤ ወንዱን ሴት አስመስዬ በጨለማ አስገባሁ" ሲል ምላሽ መስጠቱን ኮማንደር ክፍሌ ያስረዳሉ። ይሁን እንጂ ሴት ሙሽራ መስሎ የተወነውን ሠርገኛ ስምም "አላውቅም' ሲል መልስ ሰጥቷል። እንደዚህ ዓይነት አጋጣሚ ሰምተውም ሆነ አጋጥሟቸው እንደማያውቅ የሚናገሩት ኮማንደር ክፍሌ፤ በሁኔታው እጅግ ተደንቀን ነበር ይላሉ። "ሠርግ ማለት ትልቅ፣ ባህልም ወግም ነው፤ ስለዚህ የኅብረተሰቡን ባህልና ወግ ሊያበላሽ የሚችል እንደሆነ በማሰብ ነው ትኩረት ሰጥተን የተከታተልነው" ይላሉ። በዚህም መሠረት በማጭበርበር ወንጀል ክስ ተመስርቶበት የቦንጋ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥር 20 ቀን 2008 ዓ.ም 6 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት አስተላለፈበት። ሴት ሙሽራ መስሎ የገባው ግለሰብን ግን በተባባሪነት ለመክሰስ ጥረት ቢደረግም የግለሰቡን ማንነት ማኅበረሰቡ ሊያጋልጥ ባለመቻሉ እንዲሁም ዋናው ተከሳሽም አላውቀውም በማለቱ ማንነቱ ሳይታወቅ ቀርቷል። ግለሰቡ የተረጋጋ ሕይወት እንዳልነበረው ኮማንደር ክፍሌ አክለዋል። ይህ የሆነው በደቡብ ክልል፤ ከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ነው ሲሆን 'የሠርግ ሥነ ሥርዓቱ'ም ታህሳስ 9 ቀን 2008 ዓ.ም ነበር የተካሄደው።
news-51232421
https://www.bbc.com/amharic/news-51232421
አሜሪካ ነፍሰ ጡር ቪዛ አመልካቾች ለመቆጣጠር አዲስ ሕግ አወጣች
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነፍሰ ጡር ሴቶች ለመውለድ ሲሉ ወደ አሜሪካ እንዳይሄዱ ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ሕግ አወጣ።
'የወሊድ ቱሪዝም' ተብሎ የሚጠራውን እና አሜሪካ ሄዶ ለመውለድ የሚደረግን ጉብኝት ለመከላካል የወጣው ፖሊሲ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። ሕጉ ነፍሰ ጡር ሴቶች ለሥራ ወይም ለጉብኝት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቪዛ ሲያመለክቱ፤ ወደ አሜሪካ የሚሄዱበት ዋነኛ ምክንያት ለመውለድ አለመሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ይላል። በአሜሪካ ሕግ መሠረት በአገሪቷ የሚወለዱ ልጆች በቀጥታ የአሜሪካ ዜግነት ያገኛሉ። ይህ ሕግ ግን በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሲተች ቆይቷል። የፕሬዚደንት ትራምፕ አስተዳደር አዲሱ የጉዞ ሕግ የአገሪቷን ብሔራዊ ደህንነትና የሕዝብ ጤና ለመጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግሯል። ትራምፕ ወደ አገሪቷ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቀነስ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን፤ ቀደም ብሎ "በአሜሪካ ለተወለዱና ለኖሩ የሌላ አገር ዜጎች" ዜግነት እንደሚሰጥ የሚገልፀው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት መሻሻል እንዳለበት ጠይቀዋል። አዲሱ ሕግ ምን ይላል? አዲሱ ሕግ 'ቢ' ቪዛ የሚጠይቁ ሁሉንም አመልካቾች ይመለከታል። የቪዛ ኦፊሰሮች ዋነኛ አላማቸው ለመውለድ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሴቶችን ቪዛ እንዲከለክሉ ይፈቅዳል። "የወሊድ ቱሪዝም ኢንደስትሪ የዓለም አቀፉን የወንጀል መስፋፋት ጨምሮ ከወንጀል ድርጊቶች ጋር የተያያዘ ነው" ሲልም ሕጉ ያስረዳል። ከዚህም በተጨማሪ ሕጉ የተሻለ ሕክምና ለማግኘት ሲሉ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሰዎችም ላይ የሚደረገውን ቁጥጥርም ያጠብቃል። በመሆኑም ቪዛ አመልካቾች የህክምና ወጪያቸውን ለመሸፈን የሚያስችል የገንዘብ ምንጭና አቅም እንዳላቸው፤ እንዲሁም ህክምናውን ከሚሰጣቸው ዶክተር ጋር ቀጠሮ እንዳላቸው ለቪዛ ኦፊሰሩ በማቅረብ ማሳመን ይጠበቅባቸዋል። የፕሬዚደንቱ ፕረስ ሴክሬታሪ ስቴፋኒ ግሪሻም፤ በመግለጫቸው እንዳሉት "የወሊድ ቱሪዝም ኢንደስትሪው በሆስፒታሎች ወሳኝ ግብዓቶች ላይ ጫና ያሳደረ ሲሆን የወንጀል ድርጊቶችንም አባብሷል ብለዋል። በመሆኑም ሕጉ ይህንን አገራዊ የሆነ ችግር ለመከላከልና አሜሪካን በዚህ ምክንያት ከሚከሰቱ የብሔራዊ ደህንነት አደጋዎች መጠበቅ እንደሚያስችል ጨምረው ተናግረዋል። በወሊድ ቱሪዝም ምን ያህል ህፃናት ተወልደዋል? በየአመቱ ወደ አሜሪካ ከሚያቀኑ ሰዎች ምን ያህል ህፃነት እንደተወለዱ የሚያሳይ የተመዘገበ መረጃ ባይኖርም የተለያዩ አካላት ግን ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። እንደ የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠሪያ ማዕከል መረጃ በአውሮፓዊያኑ 2017 በአሜሪካ ከሚኖሩ የውጭ አገር ዜጎች 10 ሺህ የሚሆኑ ሕፃናት ተወልደዋል። ይህም የቅርብ ጊዜ መረጃ ነው። ይህ ቁጥር በአውሮፓዊያኑ 2007 ከነበረው 7,800 የህፃናት ቁጥር ጨምሯል። የስደተኞች ጥናት ማዕከል ደግሞ በ2016 እና 2017 መጀመሪያው አጋማሽ ጊዜያዊ የጉብኝት ቪዛ ካላቸው እናቶች 33 ሺህ ህፃናት መወለዳቸውን ያስረዳል። አሁን ላይ ነፍሰጡር ሴቶች እስከሚወልዱ ድረስ ለመቆየት ወደ አሜሪካ መግባት እንደሚችሉ የአሜሪካ የጉምሩክና ድንበር ጥበቃ መሥሪያ ቤት አስታውቋል። ይሁን እንጅ እናቶች ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በመቆየት ለመቅረት ፍላጎት እንዳላቸው ከታመነ ጉዟቸው ሊከለከል ይችላል።
news-46383537
https://www.bbc.com/amharic/news-46383537
ኢትዮጵያ በዲፕሎማቶቿ ላይ ሽግሽግና ለውጥ ልታደርግ ነው
ኢትዮጵያ በተለያዩ የዓለም ሃገራት ያሉ ግማሽ ያህል ዲፕሎማቶቿን ቀደም ሲል ከነበሩባቸው የዲፕሎማቲክ መቀመጫዎች ወደ ሌላ ቦታ እንደሚዘዋወሩና አዲስ ከሚሾሙ አምባሳደሮች መካከልም ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች እንደሚካተቱ ተጠቆመ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም እንደተናገሩት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በሃምሳ ዘጠኝ ኤምባሲ እና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች የሠራተኛ ድልድል አጠናቅቆ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል። የአምባሳደሮች ሹመት በቅርቡ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በመስሪያ ቤቱ ካገለገሉ ዲፕሎማቶች በተጨማሪ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦችንም ያካተት እንዲሆን ይደረጋል በማለት "ምደባው ዕውቀትን እና ሙያዊ ብቃትን ብቻ መሰረት ያደረገ ነው" ብለዋል። • "ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም • ". . . ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል" ጠ/ሚ ዐብይ የአምባሳደሮቹ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰየሙ ሲሆን እነማን እንደሆኑና ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ ቃል አቀባዩ ከመጥቀስ ተቆጥበዋል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በየኤምባሲው እና የቆንስላ ፅህፈት ቤቱ ካሏት 412 ዲፕሎማቶች ግማሽ ያህሉ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ይደረጋል ብለዋል ቃል አቀባዩ። "ሠራተኞች አዲሱን ምደባቸውን እንዲያውቁ ተደርጓል፤ አዲስ መዋቅር ደግሞ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ሥራ ላይ ውሏል" ያሉት አቶ መለስ በዚሁ መዋቅር መሰረት አምስት ቋሚ ተጠሪዎች ሥራ ላይ መሰየማቸውን ገልፀዋል። "የአሁኑ ድልድልና የባለፈው ሳምንት የመዋቅር ማሻሻያ መስሪያ ቤቱን ከወትሮው በተለየ ከፍ ያለ እርምጃ ነው ብለን እናስባለን" ሲሉም አክለው ተናግረዋል። ለዘመነ ሉላዊነት ከሚጠብቅበት ኃላፊነት አንፃር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ራሱን መፈተሽ እንዳለበት መገንዘቡን ያስረዱት አቶ መለስ የሚገባውን ሠራተኛ ከተገቢው የሥራ ድርሻ ጋር የማገናኘት ዓላማን ያነገበ ሽግሽግ ማደረጉን ገልፀዋል። • የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ተዋሃዱ • ስለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚነገሩ 8 የተሳሳቱ አመለካከቶች "የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ የማሻሻያ እርምጃ ሩጫ ውስጥ ይገኛል" ያሉት ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሃገራት ጋር "የዜሮ ውጥረት ፖሊሲን" እንደምትከተል አትተው ይህን ታሳቢ ባደረገ አኳኋን የካበተ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማቶች በጎረቤት አገራት እንደሚመደቡ ጠቁመዋል። "ተደራድሮ የሚያሸንፍ፣ ተናግሮ የሚያሳምን፣ ኢትዮጵያ ለጀመረችው የልማት ጥረት ገንዘብ ማምጣት የሚችል ዲፕሎማት ይፈለጋል" ብለዋል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ፣ ጥሩ ወዳጅ ማፍራት እና በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በኤምባሲዎች እና በቆንስላ ፅህፈት ቤቶች የትኩረት አቅጣጫን ለመወሰን ያገለገሉ መስፈርቶች ናቸውም ብለዋል። ይህም በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን አንደሚታለብ ላም ከማየት አባዜ መውጣት እንደሚያስፈልግም አክለው ተናግረዋል። በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር ከ2000 በላይ በተለያዩ አገራት እስር ቤት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን የማስመጣት ተግባርን በማከናወን ላይ እንደሆኑ አቶ መለስ ተናግረዋል። ኢትዮጵያዊያኑ ይመለሱባቸዋል የተባሉት አገራት የመን፣ ታንዛንኒያ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ሊቢያ ናቸው። እንደቃል አቀባዩ ገለፃ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 205 ኢትዮጵያዊያን ከየመን እንዲመለሱ ተደርጓል።
43972248
https://www.bbc.com/amharic/43972248
ኮዴይን፦ ገዳዩ 'ሽሮፕ'
በሰሜን ናይጄሪያ በምትገኘው ካኖ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ በቡድን ቡድን የሆኑ ወጣቶች፤ ቡናማ የመድሃኒት ብልቃጥ ጨብጠው ወፍራም ጣፋጭ ፈሳሽ እየተጎነጩ ነው።
ወጣቶቹ የሚጠጡት ለሳል ተብሎ የሚሰጠውን በተለምዶ 'ሽሮፕ' ተብሎ የሚጠራውን (የsyrup እና codeine ንጥረ ነገሮች ቅይጥ ) ፈሳሽ ነው። ጣፋጩን የእንጆሪ ጣዕም ያለውን መድሃኒት የሚጠጡ ወጣቶች ይሰክሩና እንዲናውዛሉ። ይሄ ትዕይንት በአስጨናቂ ሁኔታ በመላዋ ናይጄሪያ የተንሰራፋ ነው። የዚህ ኃይለኛ መድሃኒት ሱሰኞች ቁጥር ባልተጠበቀ ሁኔታ እጅጉን ከፍ ብሏል። እንደ ናይጄሪያ መንግሥት ቆጠራ በሰሜን ናይጄሪያ ሁለት ክልሎች ብቻ 3 ሚሊዮን ብልቃጥ ሽሮፕ በየቀኑ ይጠጣል። ውጤቱም እጅግ አሳዛኝ ነው። በመንግሥት በሚተዳደረው የሱስ የማገገሚያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ሶሰኞች ሌላ ሰው ያጠቃሉ በሚል ፍርሃት ከመሬት ጋር በሰንሰለት ተጠፍረዋል ይታያሉ። "ይሄ ጉዳይ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ሁሉንም ሰው እየለከፈ ነው" የሚለው ሳኒ ችግሩ ከአንደኛው ቤት ወደ አንደኛው እየተዛመተ መሆኑን ይናገራል። የኮዲን ሽሮፕን ከሚገባው መጠን በላይ መውሰድ አንጎል ላይ ጫና ይፈጥራል ወደ እብደትም ይወስዳል። በማገገሚያ ማዕከሉ ካሉት ታካሚዎች መካከል የ16 ዓመቷ ወጣት ለዕድሜ አቻዎቿ ስለ ችግሩ ግልፅ መልዕክት አላት።"እውነት ለመናገር እስከአሁን አልሄዱ እንደሁ ወደ ሱሰኝነቱ እንዳይሄዱ እመክራቸዋለሁ። ህይወታቸውን ያበላሸዋልና" ትላለች። በየሳምንቱ ህገ-ወጥ የኮዴን ሽሮፕ ቅይጥን ለመያዝ እንደሚሰማራው በካኖ የሚገኘው ብሄራዊ የመድሃኒት ህግ አስፈፃሚ አጄንሲ ዕምነት ከሆነ፤ በጎዳናዎቹ ላይ ከተንሰራፋው ቅይጥ ለመያዝ የቻሉት አንድ አስረኛውን ብቻ ነው። "እነዚህ መድሃኒቶች ከጨረቃ የመጡ አይደሉም። ከባህርም የወጡ አይደሉም። የሆነ ቦታ ተመርተው፣ ከአንድ ስፍራ ወደ አንድ ስፍራ የሚጓጓዙ ናቸው። ለማወቅ አንፈልግም እያልን ነው" በማላት የናይጄሪያ መንግሥት አስፈላጊውን ቁጥጥር እንዳላደረገ የሚናገሩት ደግም የህክምና ባለሙያዋ ዶክተር ማይሮ ማንዳራ ናቸው። የቢቢሲ የአፍሪቃ ዐይን ልዩ የ5 ወራት ህቡዕ ምርመራ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሯል። የምርመራ ጋዜጠኞቹ እራሳቸውን የሳል ሽሮፑን ካለ ህጋዊ የማዘዣ ወረቀት እንደሚገዛ የንግድ ሰው በማቅረብ፤ ህገ-ወጡን የሽሮፕ ቅይጥ የሽያጭ ስምምነትን ምስል ለመቅረፅ ችለዋል። ለአብነትም በኢሎሪን ናይጀሪያ ዋነኛ የሳል ሽሮፕ አምራች ከሆኑት መካካል አንዱ የሆነው የባዮራጅ ፋብሪካ ይጠቀሳል። የሽያጭ ተወካይ የሆኑት አልመንሰሩ እንዲሁም የመጋዘን አስተዳዳሪው ባባ አይቢጄ ለህቡዕ የምርመራ ቡድኑ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የኮዴን ምርትንና ሌላ ውህድን ለመሸጥ ፈቅደዋል። ባባ ኢቢጂ እንደሚለው ህፃናት ሱስ የሚሆነውን የኦፒዮድ ቅይጥን አንዴ ከቀመሱ ተጨማሪ ለማግኘት ተመልሰው ይመጣሉ። ባዮራጅ ፋብሪካ ባዮሊን የተባለውን ፈሳሽ ከኮዴን ጋር እንደማይሸጥ አል መንሱሩም ከሁለት ዓመት ነፊት ፋብሪካው እንደለቀቁ ተናግረዋል። ባባ ኢቢጂም ሆነ አልመንሱሩ ጥፋት መፈፀማቸውን ክደዋል። እኒህ ግለሰቦች መሰል ንግድ ለመስራት ነፃ ቢሆኑም በዚህ ውጥንቅጥ በእጅጉ የተጎዱት የናይጄሪያ ወጣቶች ናቸው። ቢቢሲ ይህን መርማሪ ዘገባ ከሰራ በኋላ የናይጄሪያ መንግሥት ይህ ገዳይ እና ሱስ አስያዥ መድሃኒት በሃገሪቱ እንዳይሸጥ ማዘዙ ተሰምቷል።
54689433
https://www.bbc.com/amharic/54689433
ፈረንሳይ ምርቶቿ ላይ ማዕቀብ እንዳይጣል የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን ጠየቀች
ፈረንሳይ የተለያዩ ቁሳቁሶቿ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚደረጉ ቅስቀሳዎችን የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት እንዲያስቆሙ ጠየቀች።
በኩዌት፣ ጆርዳን እና ካታር የሚገኙ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን ማስወገድ ጀምረዋል ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ ነብዩ መሐመድን የሚያሳዩ ካርቱኖችን መሣል ይቻላል የሚል አቋም ማንጸባረቃቸውን ተከትሎ የፈረንሳይ እቃዎች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ እየተደረገ ነው። በኩዌት፣ ጆርዳን እና ካታር የሚገኙ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን ማስወገድ ጀምረዋል። በሊቢያ፣ ሶርያ እና የጋዛ ሰርጥ ተቃውሞ ተካሂዷል። ፈረንሳያዊ መምህር ሳሙኤል ፓቲ፤ የነብዩ መሐመድን የካርቱን ሥዕል ለተማሪዎቹ ካሳየ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ይታወሳል። ክስተቱን ተከትሎ ፕሬዘዳንት ማክሮን "ኢስላሚስቶች ነጋችንን መቆጣጠር ይፈልጋሉ። ፈረንሳይ ግን ካርቱን መሥራት አታቆምም" ብለው ነበር። የነብዩ መሐመድን እንዲሁም የአላህን ምስል ማሳየት በእስልምና የተከለከለ ነው። የማክሮን ንግግርም ቁጣ ቀስቅስሷል። . በፈረንሳይ አንገቱን ለተቀላው መምህር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፋቸውን አሳዩ . ቻርሊ ሄብዶ መፅሄት አወዛጋቢውን የነብዩ መሐመድ ካርቱንን እንደገና አተመ ፈረንሳይ ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ነጻ የሆነች አገር እንደሆነች ትገልጻለች። የአንድ ማኅበረሰብን ስሜት ላለመጉዳት በመጠንቀቅ ውስጥ የንግግር ነጻነት መገደብ የለበትም የሚል አቋም ታንጸባርቃለች። ማክሮን "መቼም ቢሆን እጅ አንሰጥም" ሲሉ ትዊት አድርገዋል። በቱርክ እና በፓኪስታን ያሉ የፖለቲካ መሪዎች ማክሮንን ተችተዋል። የሃይማኖት ነጻነትን እየተጋፉ እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፈረንሳይ የሚኖሩ ሙስሊሞችን እያገለሉ እንደሆነም ገልጸዋል። የቱርኩ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ማክሮን ስለ እስልምና ያላቸውን አቋም በተመለከተ "አእምሯቸውን ይመርመሩ" ብለዋል። ፈረንሳይ ቱርክ ከሚገኙ አምባሳደሯ ጋር ለመምከር ወደ ፈረንሳይ ጠርታቸዋለች። የፓኪስታኑ መሪ ኢምራን ከሀን "እስልምናን ሳይገነዘቡ ሃይማኖቱን እያጥላሉ ነው" ብለዋል። በወሩ በባቻ ላይ ማክሮን "እስላማዊ ገንጣይ" ያሏቸው ቡድኖች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረው ነበር። የምዕራብ አውሮፓ ትልቁ የሙስሊም ማኅበረሰብ ማክሮን፤ ሃይማኖታዊ ጫና እያደረጉባቸው እንደሆነና እንቅስቃሴያቸው ሙስሊም ጠል እንደሆነ ተናግረዋል። እአአ 2015 ላይ የፈረንሳዩ ሽሙጥ አዘል መጽሔት ቻርሊ ሄድቦ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸው አይዘነጋም። መጽሔቱ የነብዩ መሐመድን ካርቱን አትሞ ነበር። የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የተደረገው ቅስቀሳ ባሳለፍነው እሑድ በጆርዳን፣ ካታር እና ኩዌት ያሉ አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን አስወግደዋል። የፈረንሳይ ውበት መጠበቂያ ምርቶች ከመደርደሪያ ተነስተዋል። ክዌት ውስጥ ትልቁ የአከፋፋዮች ማኅበር የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል አዟል። የሸማቾች ማኅበርም በተደጋጋሚ ነብዩ መሐመድን የሚያጥላሉ አስተያየቶች በመሰንዘራቸው ተመሳሳይ ትዕዛዝ አስተላልፏል። የፈረንሳይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ባወጣው መግለጫ "ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የተደረገው ጥሪ መሠረተ ቢስ ነው። ይህ ጥሪና በጥቂት አክራሪዎች የሚጫሩ አገሪቱ ላይ የሚቃጡ ጥቃቶች መገታት አለባቸው" ብሏል። በሳኡዲ አረቢያ እንዲሁም በሌሎች የአረብ አገራትም የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚጠይቁ የበይነ መረብ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። የፈረንሳዩ መደብር ካርፉር እንዲዘጋ የሚጠይቀው ሀሽታግ፤ በሳኡዲ የትዊተር ተጠቃሚዎች ዘንድ ከነበሩ አነጋጋሪ ጉዳዮች ሁለተኛውን ደረጃ ይዟል። በሊቢያ፣ ጋዛ እና ሶርያ ፈረንሳይን የሚያወግዙ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል።
41855200
https://www.bbc.com/amharic/41855200
ጋሬጣ የተሞላበት የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ በኢትየጵያ
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የተደራጀ ተቃውሞ በሚነሳበት ወቅት የፊውዳላዊውን አገዛዝ ለመገርሰስ አስተዋፅኦ ያደረገው በጊዜው የነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ የአብዮቱ አንቀሳቃሽ ሞተር ተደርጎ ይታያል።
በአገሪቷ ውስጥ የነበሩ የባሌና የጎጃም ገበሬዎች አመፅ፣ የመምህራን ሀገር አቀፍ እንቅስቃሴ እንዲሁም በአጠቃላይ ማህበረሰቡ በተለይም ሴተኛ አዳሪዎች በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ቢኖራቸውም ታሪካቸው በተገቢው ሁኔታ አልሰፈረም። በዲላ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆነችው መስከረም አበራ በዚህ ላይ እንደ ምክንያት የምታያቸው የተወሰኑ ፅንሰ-ሀሳቦች አሏት። መስከረም እንደምትለው ብዙ ፅሁፎች የሚፃፉት በወንዶች ስለሆነ የሴቶችን ሚና ያለማጉላት ጉዳይ አለ። ከዚህም በተጨማሪ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ላይ የሴቶች ተሳትፏቸውም የተወሰነ ነበር። በተለይም በተማሩት መካከል የመሬት ለአራሹ እና የመደብ ጥያቄዎች በጠነከሩበት ወቅት ምንም እንኳን ሴቶች ቢኖሩበትም መስከረም እንደምትለው የእንቅስቃሴው መሪዎች አልነበሩም። የተወሰኑትም ተሳትፎ የነበራቸው የወንድ ጓደኞቻቸውን በመከተል እንደሆነ ትናገራለች። ፌሚኒዝም አገራዊ በሆነ መልኩ ውይይቶች እንዲፈጠሩና፤ የፆታ እኩልነት እንዲሰፍን የሚታገለው የሴታዊት እንቅስቃሴ አንደኛዋ መስራች የሆነችው ዶክተር ስሂን ተፈራ የሴቶች ቁጥር በሚያስደነግጥ ሁኔታ ከማነሱ በተጨማሪ በፖለቲካው ላይ የነበራቸው ተሳትፎ "በሚያሳፍር ሁኔታ" ቡና ማፍላት፣ የስብሰባ ቃለጉባኤ መያዝ፣ ወረቀት መበተን፣ መፈክር መያዝን የመሳሰሉ ሚናዎች ይሰጣቸው እንደነበር ትናገራለች። ከዚህም በተጨማሪ በወቅቱ ተሳታፊ የነበሩት ሴቶች እንደሚናገሩት ይቀልዱባቸው እንደነበር ስሂን ትናገራለች። ይህ ሁኔታ እየተለወጠ የመጣውም የፖለቲካ ንቃተ-ህሊናቸው ከፍ ባሉት እነዋለልኝ መኮንን የመሳሰሉት የሴቶች መብትንና እንቅስቃሴውን ስለተቀበሉት ነው። ከአስርት ዓመታትም በኋላ ብዙ ለውጥ እንደሌለ የምትናገረው መስከረም በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያሉ የሴቶች ቁጥር አነስተኛ ነው፤ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ ሴቶችም በጣም ጥቂት ናቸው። ጎልተው ከወጡት መካከል ብቅ ብላ የጠፋችውና የቅንጅት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር የነበረችውና ብርቱካን ሚደቅሳ ተጠቃሽ ናት። ከእርሷ በኋላም ሆነ ከሷ በፊት የነበሩት ሴቶች በስም ማጥፋት ዘመቻ ከፖለቲካው ምህዳርም ተገለዋል። በፖለቲካ ላይ ለምን መሳተፍ አስፈለገ? በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በመንግሥት ደረጃ የፖለቲካውን ስፍራ የተቆጣጠሩት ወንዶች ናቸው። ማህበረሰቡን ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ሴቶችን የሚመለከቱ ህጎችን የሚያረቁትም ሆነ የሚያስፈፅሙት ወንዶች ናቸው። አቶ ሺመልስ ካሳ "ቻለንጅስ ኤንድ ኦፖርቱኒቲስ ኦፍ ዉሜን ፖለቲካል ፓርቲሲፔሽን ኢን ኢትዮጵያ" በሚለው ፅሁፋቸው የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለምን አስፈለገ ለሚለው ጥያቄ እንደ ዋነኛ መልስ የሚያነሱትም የፍትህ ጥያቄን ነው። ግማሹን የህብረተሰቡን ክፍል እንደ መያዛቸው መጠን በውክልና ዲሞክራሲ ሴቶች በራሳቸው ለምን አይወከሉም የሚል ነው። ሌላኛው ደግሞ የሴቶችና የወንዶች የህይወት ልምድ በተለይም ከታሪካዊ ፆታዊ ኢ-ፍትሀዊነት ጋር ተያይዞ መስተካከል ያለባቸው ህግጋትንና አፈፃፀማቸውን ከሴቶች በላይ የሚያውቅ ስለሌለ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሴቶችና ወንዶች በእኩልነት መወከል አለባቸው የሚሉ ሐሳቦችንም ያነሳሉ። መስከረም አበራና የውብማር አስፋው መሰናክሎቹ ምንድን ናቸው? መስከረምም ሆነ ስሂን እንደ ምክንያትነት የሚጠቅሱት "አባታዊ ሥርዓት'" (ፓትሪያርኪ) ወንዶችን የበላይ በማድረግ ሴቶችን የደጋፊነት ሚና ሰጥቷቸዋል። በዚህም የፆታ የሥራ ክፍፍልና የሴቶችን ሚና በማዕድ ቤት ሥራዎች፣ ልጅ መውለድና መንከባከብ ነው። ሴቶች ወደ አደባባይ መውጣታቸው እንደ ነውርና ሥርዓቱን እንደ መጣስ ተደርጎ ነው የሚታየውም ትላለች መስከረም። ይህንን ሥርዓት ተላልፈው በፖለቲካው ላይ ተሳትፎ ያደርጉ የነበሩ ሴቶች ዘለፋ፣ ስድብ እንዲሁም "እዩኝ ባይ" የሚል ስም እንደሚያተርፉም ትናገራለች። በተለይም መሪ መሆን የወንድነት ሥራ ተደርጎ የሚታይ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የእምነት ተቋማት ሴቶች በብዙ መንገድ ከወንድ እንደሚያንሱ መስበካቸውም አስተዋፅኦ አድርጓል። የሀይማኖት ድርጅቶቹ የሴቶችን ቦታ ግልፅ አድርገው እንዳስቀመጡ አቶ ሽመልስ ይናገራሉ። ከሴቶች አለባባበሰ ጀምሮ፤ በምን መንገድ ወንዶችን መታዘዝ እንዳለባቸው እንዲሁም ከእምነት ቦታዎች አመራርም የተገለሉ መሆናቸው አስተዋፅኦ አድርጓል በማለት አቶ ሽመልስ በፅሁፋቸው አስፍረዋል። በተለይም የቤተሰብ መዋቅር ሲነሳ ይላሉ አቶ ሽመልስ "አባታዊ" በሆነ መንገድ የሚመራ ሲሆን የመንግሥት ሥርዓትም የቤተሰብ መዋቅርን ከመከተሉ አንፃር በቤት ውስጥ ያለውም የወንዶች የውሳኔም ይሁን የሌሎች ጉዳዮች የበላይነት በመንግሥት መዋቅሮች፤ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ወይም በቀን ተቀን ኑሮ ውስጥ ይንፀባረቃል። ብዙ ሴቶች ቢማሩም አሁንም ያለው "ያረጀ ያፈጀ" የሥራ ክፍፍል ሴቶች ቤት ውስጥ እንዲሰሩ ያስገድዳቸዋል። በሚገርም ሁኔታ ሁለቱም ተመሳሳይ ሥራ ሰርተው የገንዘብ አመንጪ ቢሆኑም ሴቷ የቤቱን ሥራ እንድትከውን ይጠበቅባታል። ይህም ሁኔታ ለመስከረም ጊዜያቸውን በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዳያተኩሩ እንደሚያደርጋቸው ትናገራለች። በተለያዩ መፅሄቶች የአገሪቷን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን ትንታኔ በመፃፍ የምትታወቀው መስከረም ለወንዶች ተብለው የተተዉ እንደ "ፓርላማ" መመልከት የእሷ ቦታ እንዳልሆነ የሚነግሯት አይታጡም። በተለይም ይህ "አባታዊ"ን ሥርዓት ምንም እንኳን ወንዶችን ቢጠቅምም ማህበረሰቡ እንደ ሥርዓት የተቀበለው በመሆኑና ሴቶችም ስለተቀበሉት ሥርዓቱን ለማፍረስ ውስብስብ ያደርገዋል። "ወንዶች የራሳቸው የሆነ የሚሰባሰቡበትና የሚወያዩበት ሴቶችን ያገለለ ቡድን አላቸው" የምትለው መስከረም ከዚህም ጋር ተያይዞ ሴቶች በፖለቲካው ወጣ ወጣ ሲሉ "ኩም" እንደሚደረጉ ትናገራለች። በአንድ መፅሄት ስትፅፍ በተመሳሳይ ዘርፍ ይፅፍ ከነበረ ወንድ በአራት እጥፍ ያነሰ ክፍያ እንዲሁም ፅሁፏን አውቀው እንዳላነበቡ የሚነግሯት ወንዶችም አልታጡም። " ጎበዝ ካለችና እነሱን የምትፈታተን ከመሰላቸው በተለያዩ ነገር ሊመቷት ይፈልጋሉ፤ የማሸማቀቅ ፖለቲካ የሰፈነበትና በአይን የሚታዩና የማይታዩ ጋሬጣዎች የተሞሉበት ነው" ትላለች። የፆታዊ ጥያቄዎችና መደራጀት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም ቦታው ግን አሁንም የአንድ ፓርቲን ሥራ ለማስፈፀም ካልሆነ ትክክለኛ ተሳትፎ አይደለም የሚሉት የህወሓት የቀድሞ ታጋይ የውብማር አስፋው ናቸው። የውብማር እንደሚናገሩት በንጉሡ አገዛዝ ዘመን ከ240 የፓርላማ አባለት 2 ሴቶች፤ በደርግ ጊዜ ከ835 የሸንጎ አባላት14 ሴቶች ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የሴት ፓርላማ አባላት 30 በመቶውን ይይዛሉ። ቁጥር መጨመሩን እንደ መልካም ነገር የሚያዩት ስሂንና የውብማር፤ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ የፓርቲውን ፕሮግራም ከማስፈፀም የዘለለ ባለመሆኑ ተሳትፎውን ሙሉ አያደርገውም ይላሉ። "በአሁኑ ወቅት ተሳትፏቸውን እንደ መሳሪያና የሴቶች ጥያቄ እንደተመለሰ ተደርጎ ነው እየተነገረ ያለው፤ ይሄ ግን ከወረቀት እየዘለለ አይደለም። ዋናው ጥያቄ ግን ነፃነት አላቸው ወይ? ምን ያህልስ የሀገሪቱን ፖሊሲ መቀየር ይችላሉ? ምንስ ያህል ተፅእኖ ፈጥረዋል" ብለው ወ/ሮ የውብማር ይጠይቃሉ ። ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘም በኋላ የነበሩት ሴቶች በአገሪቷ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መዋቅሮች ፖሊሲዎችን በማርቀቅና ህጎችን በማውጣት ተሳትፎ አልነበራቸውም። "ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለበት ትግል ቢሆንም፤ የመጣው ለውጥ ግን ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን አፋኝና ሰብአዊ መብቶችን የሚጥስ ድርጅት ነው" ይላሉ የውብማር። እነዚህ መሰናክሎች እያሉ በተደራጀ መልኩ የሴቶች እንቅስቃሴ ጎልቶ መውጣት ቢከብድም የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን የመሰለ ጠንካራ ድርጅትም መምጣት ችሏል። ከመንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ህግና ገቢ ከማግኘት ጋር ተያይዞ የድርጅቱ ሚና ቢቀንስም በሀገሪቱ ውስጥ የፆታ ግንኙነት ላይ ውይይቶችንና አከራካሪ ጉዳዮችን በመድረኩ ላይ በማምጣት አብዮት መፍጠር ችለዋል። የተነሱትንም ጥያቄዎች በማስቀጠልም፤ ብዙ ያልተደፈሩ አከራካሪ ጉዳዮችን በማንሳት ሴታዊት እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው። እስካሁን ድረስ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሁኑ የነፃነት እንቅስቃሴዎች የሥርዓተ-ፆታን ጥያቄ እንደ ፖለቲካ ጥያቄ አድርገው ይዘው መነሳት አልቻሉም። "ኃላፊነቱ የማን ነው? ማንነው ማንሳት ያለበት፤ ሴቶች ናቸው። የማንን ጥያቄ ማን ነው የሚያነሳው?" በማለት ስሂን ትጠይቃለች። "ፊኒክሷ ሞታም ትነሳለች፡ ያልተቋጨው የትግራይ ሴቶች ገድል" በሚል ርዕስ መፅሀፍ የፃፉት የውብማር በትግሉ ውስጥ የነበረው ሁኔታ ማህበረሰቡ ለሴቶች ዝቅተኛ ቦታ ያለው ነፀብራቅም ነው ይላሉ። በመጀመሪያው ዓመታት ሴቶች ፓርቲውን እንዲቀላቀሉ ያልተፈቀደ ሲሆን ከ1968 በኋላ ብዙ ሴቶች በሰራዊቱ እንዲሁም በሌሎች የትግሉ ዘርፍ ተሳታፊ ሆነዋል። የውብማር እንደሚናገሩት መጀመሪያ ላይ ከባድ መሳሪያዎችን ሴቶች መሸከም አይችሉም በማለት እኩልነትን ከጉልበት ጋር ማዛመድ፤ እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ የፆታዊ ግንኙነት ስለማይፈቀድ ሴቶችን እንደ ''አሳሳች'' ማየት፤ ይባስ ሲልም ፆታዊ ትንኮሳዎችም ነበሩ። ለችግሩም ምንጭ ወንዶችን ተጠያቂ የማያደርጉት የውብማር "ችግሩ የሰፈነው ሥርዓቱ ወንዶችን የበላይ ሲያደርግ ሴቶችን ተገዢና የበታች አድርጎ የሚያስቀምጡ ነው" በማለት ይናገራሉ። "በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው አቅምን አደራጅቶ መታገል እንጂ ማንም መብታችንን ሊሰጠን አይችልም። ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው፤ ስለሴቶች ጉዳይ ወንዶች እንዲታገሉ መማፀንም መጠበቅም የለብንም" በማለት ጨምረው ይናገራሉ። ለዚህ ግን የፖለቲካው ምህዳር መጥበብ የሰላማዊ ሰልፍን፣ የመናገር ነፃነትን መገደቡ ሴቶች ሊያደርጉት ከሚፈልጉት እንቅስቃሴ መገደብንም አምጥቷል ብለው ወ/ሮ የውብማር ያምናሉ።
news-54040199
https://www.bbc.com/amharic/news-54040199
2012፡ የኢህአዴግ መክሰም፣ የተማሪዎች እገታ፣ የምርጫ መራዘም፣ ግድያና እስር
በ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያውያንን ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊና ማኅበራዊ ሕይወት በበጎም ሆነ በአሉታዊ ሁኔታ የሚነኩ ነገሮች ተከስተዋል።
ከእነዚህ ክስተቶች የትኞቹ ጉልህና ወሳኝ ናቸው የሚለውን ለመለየት እንደምንጠቀምበት መመዘኛ የተለያየ ቢሆንም፣ ቢቢሲ በተለይ በለውጥ ሂደት ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው አንድምታ ከፍ ያለ ነው ያላቸውን ጥቂት ክስተቶችን መርጦ ቃኝቷል። ኢህአዴግ መክሰምና የብልጽግና ውልደት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አገሪቱን ሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በብቸኝነት የአገሪቱን ሁለንተናዊ ህልውና የመራውና መሠረታዊ ለውጥ በማምጣት ረገድ የአራት የብሔር ድርጅቶች ግንባር የሆነው ኢህአዴግን ያህል የሚጠቀስ ቡድን የለም። ነገር ግን ከሦስት ዓመት በፊት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተቀሰቀሰበት ተቃውሞ ግንባሩ ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ስላላስቻለው የለውጥ እርምጃዎችን ወስዶ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰይሞ፤ በ27 ዓመታት ሂደት ውስጥ የቆየበትን ገጽታውን ለመቀየር ሥራውን የጀመረው በዚህ ዓመት ነበር። ግንባሩ ለዓመታት ሲንከባለል የነበረው አንድ ውህድ ፓርቲ የመሆን እቅዱን በፍጥነት ለማከናወን ወስኖ ከህወሓት ውጪ ያሉት ኦዲፒ፣ አዴፓ እና ደኢህዴን ስምምነት ላይ ደርሰው "ብልጽግና" የተሰኘውን አንድ ወጥ ፓርቲ መሰረቱ። ሂደቱም ከዚህ በፊት የኢህአዴግ አጋር ፓርቲዎች የሚባሉትን ክልላዊ ፓርቲዎችን አንድ በአንድ በማካተት አገራዊ ቅርጽ ያዘ። የኢህአዴግ መስራችና በግንባሩ ውስጥ ጉልህ ሚና የነበረው ህወሓት በአዲሱ ውህድ ፓርቲ ውስጥ ላለመሳተፍ ከወሰነ በኋላ በማዕከላዊው መንግሥት ውስጥ የነበረው ተሳትፎ ቀስ በቀስ እየተዳከመ ከብልጽግና ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ፍጥጫ ውስጥ ገባ። በዚህም ሳቢያ ህወሓት በገዢ ፓርቲነት በሚያስተዳድረው ትግራይ ውስጥ እንቅስቃሴውን በማጠናከር የብልጽግና ፓርቲ ተቀናቃኝ ሆነ። በቀሪው የአገሪቱ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ቡድኖችንም በማስተባበር "የፌደራሊስት ኃይሎች" የተሰኘ ስብስብን ፈጥሮ በሥልጣን ላይ ካለው ፓርቲ በተቃራኒ ቆመ። በዚህም በብልጽግናና በህወሓት መካከል በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ያለው አለመግባባት እየሰፋ መጥቶ፣ በግልጽ አስከ መወነጃጀል የደረሰ ሲሆን፤ ይኸው ፍጥጫ ተካሮ ትግራይ ክልል በተናጠል ምርጫ ለማካሄድ እስከመወሰን ደርሷል። የጃዋር መከበብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የተከፈተባቸው ክስና የተጣለባቸው እገዳ ተነስቶ ወደ አገር ቤት ከገቡ የፖለቲካ ቡድኖች መሪዎችና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነው ጃዋር መሐመድ በቤቱ አካካቢ ለደኅንነቱ ስጋት ነው ያለውን እንቅስቃሴ ተከትሎ የፈጠረው አለመጋጋት ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኖ ነበር። ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ገደማ መሃል አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ አካባቢው የጸጥታ ኃይሎች ያልተለመደ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሶ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት፣ ደጋፊዎቹ በቤቱ ዙሪያ ከመሰባሰባቸው ባሻገር በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተቃውሞ ተቀስቅሷል። አለመረጋጋቱን ተከትሎም በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ80 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት ሲጠፋ በንብረትም ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሶ ውጥረቱም ለቀናት ዘልቆ ነበር። ደስታውን የሚገልጽ የሲዳማ ወጣት የሲዳማና ክልልነት ጥያቄ በደቡብ ለዓመታት የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማዕከል ከሆነው የደቡብ ክልል በመውጣት ራሱን የቻለ ክልል ለመመስረት ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የሲዳማ ዞን፣ ቀደም ሲል ካጋጠመ ውዝግብ እንዲሁም ደም ካፋሰሰ ግጭትና ጥቃት በኋላ ኅዳር 10/2012 ዓ.ም በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ መቋጫ አግኝቷል። ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በመራው በሲዳማ ዞን ውስጥ በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ድምጻቸውን ከሰጡ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች፤ ማለትም 98.51 በመቶው፤ ዞኑ ክልል እንዲሆን የሚያስችለውን ድምጽ መስጠታቸውን ይፋ ሆኖ ሲዳማ 10ኛው የአገሪቱ ክልል መሆን ችሏል። ከሌሎቹ የአገሪቱ ክልሎች በተለየ ከ50 በላይ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን የያዘው የደቡብ ክልል ለሲዳማ ጥያቄ ምላሽ ቢሰጥም ከአስር የማያንሱ ሌሎች ዞኖችም የክልልነት ጥያቄ አቅርበዋል። በተለይ የሲዳማ ክልልነት በይፋ ከደቡብ ክልል መውጣቱ ሰኔ ወር ላይ ከተገለጸ በኋላ፣ የክልልነት ጥያቄ ያቀረቡት ዞኖች ውስጥ እንቅስቃሴዎች በጉልህ ከመታየታቸው ባሻገር አንዳንዶች መለያችን ነው የሚሉትን ባንዲራ የሚያሳዩ ምስሎችን በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በስፋት ሲያሰራጩ ነበር። ዓመቱ በተለይ የወላይታ ዞን ተወካዮቹ ከደቡብ ምክር ቤት መውጣታቸውንና ዞኑ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠው ግፊት ማድረጉን አጠናክሮ በመቀጠሉ ውጥረት ተከስቶ ነበር። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአካባቢው አመራሮች ሌሎችም በስብሰባ ላይ እንዳሉ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር በመዋላቸው አለመረጋጋት ተቀስቅሶ ከ20 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል። የተማሪዎች እገታ በ2012 ዓ.ም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በተከሰቱ ግጭቶች ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዚህ ሳቢያ በተፈጠረው ስጋት በዩኒቨርስቲዎቹ ይካሄድ የነበረው ትምህርት በተደጋጋሚ ተስተጓጉሏል። በዓመቱ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኖ ብዙ የተባለለትና እስካሁንም መቋጫ ያላገኘው የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እገታ ጉዳይ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው። በዩኒቨርስቲው ባጋጠመ የጸጥታ መደፍረስ ሳቢያ ትምህርት በማቋረጡ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የነበሩ 18 የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መታገታቸው ከተነገረና በኋላ ለወራት የት እንደደረሱ ሳይታወቅ እስካሁን ደብዛቸው እንደጠፋ ይገኛሉ። የተማሪዎቹ ወላጆች ከራሳቸው ከልጆቻቸው ተደውሎላቸው ችግር እንደገጠማቸው የሰሙት ኅዳር 24/2012 ዓ.ም ቢሆንም ክስተቱ ተገቢውን ትኩረት ለማግኘት ሳምንታትን ወስዷል። ቢቢሲ ስለተማሪዎቹ እገታ የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ ዘገባዎችን የሰራ ቢሆንም ከክልልና ከፌደራል የመንግሥት አካላት መረጃ ለማግኝት ሳይችል ቆይቷል። በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚወጡት መረጃዎችም አንዳንዶቹ ዕገታው እንዳልተፈጸመ ሲያስተባብሉ ሌሎቹ ደግሞ እርስ በርስ የሚጣረሱ ሆነው ቆይተዋል። በመጨረሻም መንግሥት የተማሪዎቹን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን በመጥቀስ በአጭር ጊዜ ውስጥ መቋጫ እንደሚያገኝ ገልጾ የነበረ ሲሆን፣ ከወራት በኋላ ከተማሪዎቹ እገታ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የተባሉ አስራ ሰባት ሰዎች ላይ ሐምሌ 10/2012 ዓ.ም የሽብር ወንጀል ክስ እንደተመሰረተባቸው ብሔራዊው ቴሌቪዥን ዘግቧል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፤ በዚህም ያሉበት ያልታወቁና አብዛኞቹ ሴት ተማሪዎችን በማገት፣ በመጥለፍና በሽብር ወንጀል ተከስሰዋል። በክሱ ላይ ተማሪዎቹ በተጠርጣሪዎቹ አማካይነት በምዕራብ ኢትዮጵያ ይንቀሳቀሳል ለሚባለው አማጺ የኦነግ-ሸኔ ቡድን ተላልፈው እንደተሰጡ ቢጠቀስም እስካሁን ግን የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አይታወቅም። ከታገቱ ተማሪዎች መካከል የአንዷ አባት ምርጫ መራዘም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በተለያዩ አጋጣሚዎች ምርጫ ቦርድን ነጻና ገለልተኛ በሆነ ሁኔታ እንዲዋቀር በማድረግ በ2012 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ሁሉ የተለየ እንዲሆን እንደሚፈልጉ በተደጋጋሚ ተናግረው ነበር። በዚህም መሠረት የቀድሞዋ ፖለቲከኛ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ኃላፊነቱን ይዘው ቦርዱ የሚተዳደርባቸው የሕግና የመዋቅር መሻሻያዎች ተደርገው፤ ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶ፣ በመጀመሪያ ነሐሴ 10 ከዚያም ማሻሻያ ተደርጎ ነሐሴ 23/ 2012 ዓ.ም የድምጽ መስጫ ቀን እንዲሆን ቀን ተቆርጦ ነበር። የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰቱን ተከትሎ ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ምርጫውን ማካሄድ የማይችል መሆኑን በመግለጽ ለምርጫው መከናወን ያለባቸው ሥራዎች ለጊዜው እንዲቆሙ መወሰኑን መጋቢት 22/2012 አስታወቀ። በዚህም መሠረት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ተወግዶ የሚኖረውን ተጨባጭ ሁኔታ እንደገና ገምግሞ አዲስ የምርጫ ሥራ ዝግጅት ዕቅድና የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት እንቅስቃሴውን እንደሚያስጀምር አሳውቋል።፡ ይህንንም በማስመለከት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ጠቅሶ ምርጫውን ማካሄድ እንደማይችል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቨማቅረብ፣ ምክር ቤቱ የቦርዱን የውሳኔ ሐሳብ በመቀበል በጉዳዩ ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲካሄድ መጠየቁ ይታወሳል። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በወረርሽኙ ምክንያት ምርጫ በወቅቱ ማካሄድ ባለመቻሉ እንዲሁም የምክር ቤቶችንና የአስፈፃሚ አካላትን የሥራ ዘመን አስመልክቶ በቀረበለት የሕገ መንግሥት ትርጉም መሰረት የበሽታው ስጋት እስካለ ድረስ የፌደራልና ክልል ምክር ቤቶች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ወሰነ። ምርጫውም ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት ወረርሽኙን አስመልክተው የሚያወጡትን መረጃ መሰረት በማድረግ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ተቋም በሽታው የሕዝብ ጤና ስጋት አለመሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ምርጫው እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ እንዲካሄድ ተወሰነ። ከዚህ በተቃራኒ ግን በምንም ምክንያት ምርጫው ሊራዘም አይገባም ያለው የትግራይ ክልል ግን በዚህ ዓመት በተናጠል ምርጫ ለማካሄድ ሲዘጋጅ ቆይቶ ረቡዕ ጳጉሜ 04 መራጮች ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ምርጫው ሕግን የጣሰ በመሆኑ ተቀባይነት ስለሌለው እንዳልተካሄደ ይቆጠራል ሲል ለምርጫው እውቅና እንደማይሰጥ ገልጿል። እንደተባለው ምርጫው በትግራይ ክልል ውስጥ የሚካሄድ ከሆነ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሚኖረው ግንኙነትን የበለጠ ስለሚያበላሸው ውዝግቡ ወደ 2013 መሸጋገሩ አይቀርም። የሃጫሉ መገደልና እስር ዓመቱ ሊጠናቀቅ ሁለት ወራት ሲቀሩት የተፈጸመው የታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በአገሪቱ አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ካመጡት ክስተቶች መካከል ቀዳሚው ነው። አንዳንዶች የሃጫሉ ግድያና እሱን ተከትሎ የተከሰተው ውጥረትና አለመረጋጋት ውጤቱ ለወራት ሊቆይ እንደሚችል ይገምታሉ። ሰኞ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም ምሽት የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እንደተሰማ ወዲያው ነበር በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሁከትና ተቃውሞ የተቀሰቀሰው። ከድምጻዊው ግድያ በተጨማሪ የአስከሬን ሽኝትና ቀብሩ የሚፈጸምበት ቦታ ያስከተለው ውዝግብ የተፈጠረውን ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ አጡዞታል። በሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ሰበብነት በተለያዩ ስፍራዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ150 በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። በአንዳንድ ከተሞች ላይ ደግሞ ሆቴሎች፣ የንግድ ተቋማት፣ የመንግሥት ቢሮዎች፣ የግለሰቦች መኖሪያ ቤቶችና ሌሎችም በተፈጸመባቸው ጥቃት ወድመዋል። ከሰኔ 23 2012 ከሰዓት በኋላ ጀምሮም በርካታ ፖለቲከኞችና በሺህዎች የሚቆጠሩ በሁከቱ ተሳትፈዋል የተባሉ ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋል ጀመሩ። በዚህም መሠረት ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ለእስር የተዳረጉ ሲሆን፤ ሁከቱን በማባባስ በኩል አስተዋጽኦ አድርገዋል የተባሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በጸጥታ ኃይሎች እንደተዘጉ የተነገረ ሲሆን ጋዜጠኞችም ከታሰሩት መካከል ይገኙባቸዋል። የሃጫሉ መገደልን ተከትሎ የተፈጠሩት ነገሮች አገሪቱ የጀመረችውን ነገሮች ወደኋላ ሊመልሱት ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች የተበራከቱ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞና አለመረጋጋት እየተከሰተ ነው። የቀናት ዕድሜ በቀረው በዚህ ዓመት በርካታ ጉልህ ነገሮች በተለያዩ መስኮች በኢትዮጵያ ውስጥ መከሰታቸው ይታወቃል። ነገር ግን በቢቢሲ ምርጫ ከብዙ በጥቂቱ በ2012 ዓ.ም ከተከሰቱት ዋነኛ ናቸው ያልናቸውን እነዚህን መለስ ብለን ቃኝተናል። እናንተስ በዓመቱ ከተከሰቱት ውስጥ የትኞቹን በጉልህነት ትመለከቷቸዋላችሁ?
51030413
https://www.bbc.com/amharic/51030413
ኮንጎ፡ ከ6ሺህ ሰዎች በላይ የሞቱበት የኩፍን ወረርሽኝ
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኩፍኝ ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 6ሺህ ማለፉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የኩፍኝ ወረርሽኝ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በርካቶችን እየገደለ ይገኛል የዓለም ዓቀፍ ጤና ድርጅት ይህ ወረርሽኝ በስፋትና በፍጥነት የተዛመተ መሆኑን በመግለጽ ከዓለማችን ትልቁ ነው ብሎታል። እ.ኤ.አ. በ2019 ብቻ 310 ሺህ ሰዎች በኩፍኝ በሽታ የተጠረጠሩ ሰዎች መመዝገባቸውን ድርጅቱ ጨምሮ አስታውቋል። • በኩፍኝ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው • ኢትዮጵያዊያን ለክትባቶች ከፍተኛ የሆነ አውንታዊ አመለካከት አላቸው • ኢትዮጵያ አሁንም 'ኩፍኝ አልወጣላትም' የኮንጎ መንግሥት ባለፈው መስከረም ወር አስቸኳይ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት መርሀ ግብርን ይፋ አድርጓል። እንደ ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት መግለጫ ከሆነ በ2019 ብቻ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ከ18 ሚሊየን በላይ ሕፃናት ተከትበዋል። ነገር ግን ደካማ የሆነ መሰረተ ልማት፣ በጤና ተቋማት ላይ የሚደርስ ጥቃትና ተከታታይ የሆነ የጤና እንክብካቤ አለመኖሩ የበሽታውን በፍጥነት መዛመት ሊገታው እንዳልቻለ ተገልጿል። በኮንጎ የሚገኙ 26 ግዛቶች ውስጥ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በሽታው በወረርሽኝ ለመልክ መከሰቱ ከተነገረ ጊዜ ጀምሮ በርካታ በኩፍኝ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለው የኩፍኝ ወረርሽኝ በማዕከላዊ አፍሪካ ካለው የኢቦላ ወረርሽን በሁለት እጥፍ የሚልቁ ሰዎችን እየገደለ ነው። "ይህንን ወረርሽን ለመቆጣጠር የአቅማችንን ሁሉ እያደረግን ነው" ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ማትሺድሶ ሞዬቲ ናቸው። "በትክክል ውጤታማ ለመሆን ግን ማንኛውም ሕጻን በቀላሉ በክትባት መከላከል በሚቻል በሽታ እንዳይሞት ማድረግ አለብን። አጋሮቻችን በፍጥነት ድጋፋቸውን እንዲያደርጉልን ጥሪ እናቀርባለን" ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እድሜያቸው ከ6 እስከ 14 የሆኑ ሕፃናትን በመከተብ መከላከሉን ለማጠናከር ተጨማሪ 40 ሚሊየን ዶላር ያስፈልገኛል ሲል ተናግሯል። በዓለም ላይ በየዓመቱ 110ሺህ ሰዎች በኩፍኝ በሸታ ተይዘው ይሞታሉ ሲል ድርጅቱ በመግለጫው ላይ አስታውቋል።
news-48472488
https://www.bbc.com/amharic/news-48472488
ትራምፕ ወደ እንግሊዝ ምን ይዘው ይሄዳሉ?
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ እንግሊዝ የሚያደርጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማስመልከት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ ወጪ እየተደረገና ከፍተኛ የሆኑ የደህንነት ሥራዎችም እየተከናወኑ ነው።
በንግሥት ኤልሳቤጥ ጋባዥነት ከሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት ለሚደረገው የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት፤ እስከ 18 ሚሊዮን ፓውንድ (666 ሚሊዮን ብር) ድረስ ወጪ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። • ዶናልድ ትራምፕ ተከሰሱ የኋይት ሃውስ የደህንነት ሰዎች ወደ እንግሊዝ መግባት ጀምረዋል። ትራምፕን ተከትለው ወደ እንግሊዝ የሚሄዱት የደህንነት ቁሶችና የመጓጓዥ አይነቶች የትኞቹ ናቸው? ትራምፕን አጅበው የሚመጡትስ እነማን ናቸው? ፕሬዝዳንቱ ወደ እንግሊዝ የሚሄዱት በልዩ ሁኔታ የተሠራውን 'ኤር ፎርስ ዋን' ተሳፍረው ነው። 'ኤር ፎርስ ዋን' በሰሜን ለንደን አቅጣጫ በሚገኘው ስታንስቴድ አየር ማረፊያ ያርፋል ተብሎ ይጠበቃል። 'ኤር ፎርስ ዋን' ተብለው የሚጠሩት ሁለት በልዩ ሁኔታ የተሠሩ ቦይንግ 747-200B አውሮፕላኖች ናቸው። ትራምፕ በእንግሊዝ በሚኖራቸው ጉብኝት ወቅት ሁለቱንም አውሮፕላኖች ጥቅም ላይ ሊያውሉ እንደሚችሉ ይገመታል። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? የአሜሪካ ዜና ወኪሎች ዘገባ እንደሚጠቁመው፤ ትራምፕ በእንግሊዝ ጉብኝታቸው ወቅት ያገቡ ልጆቻቸውን ከነመላው ቤተሰቦቻቸው ስለሚወስዱ ሁለተኛው 'ኤር ፎርስ ዋን' ያስፈልጋቸዋል። ጥንቅቅ ያለው የ 'ኤር ፎርስ ዋን' አሠራርና አጨራረስ በጦር አውሮፕላን ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት ያደርገዋል። አውሮፕላኑ ከአየር ላይ ጥቃቶች ራሱን መከላከል ይችላል። የጠላት ራዳርን ማፈን ይችላል። የሚሳዔል ጥቃት ቢሰነዘርበት ፍንዳታ የማያስከትል ከፍተኛ ብርሃንና ሙቀት ያለው ጨረር በመልቀቅ የተቃጣውን የሚሳዔል ጥቃት አቅጣጫ ያስቀይራል። 'ኤር ፎርስ ዋን' አየር ላይ ሳለ ነዳጅ መሙላት ይችላል። ይህም ላልተወሰኑ ሰዓታት በረራውን እንዲቀጥል ያሰችለዋል። አውሮፕላኑ ላይ የተገጠሙት ሞባይል የመገናኛ ቁሳቁሶች ፕሬዝደንቱ በየትኛውም የዓለም ክፍል ላይ ትዕዛዝ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል። የ 'ኤር ፎርስ ዋን' ተሳፋሪዎች 4,000 ካሬ ጫማ በሚሰፋው አውሮፕላን ውስጥ ዘና ማለት ይችላሉ። አውሮፕላኑ ውስጥ ሦስት ወለሎች አሉ። እነዚህ ሦስት ወለሎች የፕሬዝዳንቱ ቅንጡ ማረፊያ፣ የህክምና አገልግሎት መስጫ፣ የስብሰባና የመመገቢያ ክፍል፣ ሁለት ኩሽና እንዲሁም የክብር እንግዶች፣ የመገናኛ ብዙሃን አባላት፣ የደህንነት ሰዎች እና የፕሬዝዳንቱ ረዳቶች መቀመጫ ስፍራዎችን ይዘዋል። በርካታ እቃ ጫኝ አውሮፕላኖችም ከጉብኝቱ ቀን በፊት የፕሬዝዳንቱን መኪኖች፣ ሄሊኮፕተሮች እና ሌሎች ቁሶችን ያደርሳሉ። እንደ ዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ከሆነ ፕሬዝዳንቱ ሁሌም በሄዱበት የሚከተላቸው ''ፉትቦል'' ተብሎ የሚጠራ ቦርሳ አለ። ይህ ቦርሳ በውስጡ ኒውክለር ለመተኮስ የሚያስችል ማዘዣ እና የይለፍ ቃላትን እንደያዘ ይታመናል። ፕሬዝዳንቱ የጦር ኃይሉ ጠቅላይ አዛዥ እንደመሆናቸው መጠን፤ የኒውክለር ጥቃት መፈጸም አስፈላጊ ሆኖ ቢገኝ በፍጥነት ትዕዛዙን ይሰጡ ዘንድ እንዲያመቻቸው ይህ ቦርሳ ሁሌም ከጎናቸው አይለይም። ፕሬዝዳንቱ የሚንቀሳቀሱበት መኪኖችን ጨምሮ የሚያጅቧቸው ተሽከርካሪዎች በሙሉ ከእርሳቸው ቀድመው እንግሊዝ ይደርሳሉ። ዶናልድ ትራምፕ የሚጓጓዙበት 'ዘ ቢስት' ተብለው የሚጠሩ ሁለት ተመሳሳይ ጥቁር ካዲላክ መኪኖች አሏቸው። ሁለቱም መኪኖች ተመሳሳይ የሆነ ዋሽንግተን ዲሲ 800-002 የሚል ታርጋ ቁጥር አላቸው። የመኪኖቹ አካል እና መስታወት ጥይት የማይበሳው ሲሆን፤ አስለቃሽ ጭስ መልቀቅ የሚያስችል ስርዓት እና በምሽት ማየት የሚያስችል ካሜራ እንደተገጠመላቸው ይታመናል። በመኪኖቹ ጎማ ላይ የተገጠመው ቸርኬ የመኪኖቹ ጎማ አየር ባይኖረው እንኳን እንዲሽከረከሩ ያስችላል። የነዳጅ ቋቶቹም የእሳት ጉዳት እንዳይደርስባቸው በእሳት መከላከያ ፎም ተሸፍነዋል። እያንዳንዳቸው 7 ሰዎችን የመጫን አቅም ያላቸው መኪኖቹ፤ በውስጣቸው የህክምና ዕቃ አቅርቦቶች ተሟልቶላቸዋል። ኤን ቢ ሲ እንደሚለው ከሆነ አንድ ፍሪጅ ሙሉ የፕሬዝዳንቱ የደም አይነት በመኪኖቹ ውስጥ ይቀመጣል። ዶናልድ ትራምፕ በመኪና መንቀሳቀስ ሲጀምሩ በርካታ ተሽከርካሪዎች ያጅቧቸዋል። ከሚያጅቧቸው መካከል ሞተረኛ ፖሊሶች፣ የደህንነት አባላት መኪኖች፣ የታጠቁ የደህንነት አባላትን የያዙ መኪኖች፣ የህክምና አገልግሎት ሰጪ ቡድን አባላትና ጋዜጠኞች ይገኙበታል። ትራምፕ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ሳይሆን ሄሊኮፍተሮችንም ይዘው ወደ እንግሊዝ ያቀናሉ። ፕሬዝደንቱን የምትጨነው ሄሊኮፍተር 'መሪን ዋን' ትሰኛለች። በዚህ ስም የሚጠራው ሂሊኮፍተር አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ናቸው። 'መሪን ዋን' ሄሊኮፍተሮችም ሚሳዔል መቃወሚያ እና የግንኙነት ስርዓቶች የተገጠሙላቸው ናቸው። ፕሬዝዳንቱን በሄሊኮፍተር ሲጓዙ 'መሪን ዋን' ጋር ተመሳሳይ ቅርጽ ያላቸው ሄሊኮፍተሮች ለደህንነት ሲባል አብረው እንዲበሩ ይደረጋል። በእነዚህ ተመሳሳይ አውሮፕላኖች ውስጥም ቢሆን የደህንነትና የህክምና ቡድን አባላት ይሳፈራሉ። ከትራምፕ ጋር ወደ እንግሊዝ የሚሄዱ ሰዎች 1000 ያህል ሊሆኑ እንደሚችል ተገምቷል። የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት የሚጀመረው በበርኪንግሃም ቤተ-መንግሥት በሚደረገው የእንኳን ደህን መጡ የምሳ ግብዣ ይሆናል። ትራምፕ ከጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ ጋር በሴንት ጀምስ ቤተ-መንግሥት እና በ10 ዶውኒንግ ስትሪት ይወያያሉ። የለንደን ከተማ ፖሊስ ጉብኝቱን በማስመልከት ''በርካታ ኤጀንሲዎች እና ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ አባላት የሚሳተፉበት ኦፕሬሽን ይሆናል'' በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። የከተማዋ ፖሊስ ጨምሮም በፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ወቅት ለንደን በርካታ ግዙፍ የተቃውሞ ሰልፎችን ልታስተናግድ አንደምትችል ይጠበቃል ብሏል። ጸረ-ትራምፕ የሆኑ ቡድኖች የተቃውሞ ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ ከወዲሁ አስታውቀዋል።
news-50883361
https://www.bbc.com/amharic/news-50883361
የኢትዮጵያና የአማራ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት ወደ ሞጣ ሊያቀኑ ነው
ከትናት በስቲያ በአማራ ክልል፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ የሚገኘው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ ጀሚዑል ኸይራት ታላቁ መስጊድ እና አየር ማረፊያ መስጊድ ላይ ቃጠሎ መድረሱ አሳዛኝ መሆኑን የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታውቋል።
ጉባኤው በድርጊቱ ማዘኑን አስታውቆ ለወደፊትም እንዲህ አይነት ድርጊት እንዳይፈጸም ጥሪውን አስተላልፏል። የኢትዮጵያ ሐይማኖት ጉባኤ አባላትና የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት ወደ ሞጣ በማቅናት ከነዋሪዎች ጋር እንደሚወያዩና የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል። • በሞጣ የተፈጠረው ምንድን ነው? ይህ የተገለጸው የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሞጣ ከተማ በሐይማኖት ተቋማት ላይ በደረሰው ጉዳት ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። "የሠው ልጅ ሊደረግበት የማይገባውን ነገር ሌሎች ላይ ማድረጉ ተገቢ አይደለም" ያሉት የጉባኤው የቦርድ ሰብሳቢ መልአከ ሠላም ኤፍሬም ሙሉዓለም ናቸው። • የትግራይና የፌደራል መንግሥቱ ግንኙነት በጣም አሳሳቢ ነው- ዶ/ር አብረሃም ተከስተ • ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ "ሰው የሚያደርሰው ይህን መሰሉ ጥፋት በሰማይም በምድርም የሚያስጠይቀው ነው" ያሉት ሰብሳቢው የሐይማኖት ተቋማት እንክብካቤ ሊደረግላቸው ሲገባ መቃጠላቸው ግራ የሚያጋባ ነው ብለዋል ። "የአካባቢው ህብረተሰብ አብሮ የሚበላ እና የሚጠጣ እንጂ ለዘረፋ እና ለእሳት የሚዳረግ አይደለም፤ ክቡር የሆነውን ቤተ ዕምነት ማቃጠልም ተገቢ አይደለም" ብለዋል መንግሥትም ቢሆን በየጊዜው በተለይ በአማራ ክልል የሚፈጠሩ ችግሮችን ቀድሞ ፈጥኖ የመከላከል ሥራ መሥራት እንዳለበት አስታውሰው እንዲህ አይነት ጥፋት ከተፈጸመ በኋላ ሰዎችን ለህግ አቅርቦ ፍጻሜ ላይ ማድረስ እንደሚገባ አስምረዋል። ነገር ግን ህግ የጣሱ እርምት ማግኘት ሲገባቸው የተቀጡ ሰዎች ባለመኖራቸው ችግሩ እንደተስፋፋ ገልፀዋል። "እንዲህ ከሆነ ነው ሰው ነፍሱንም እጁንም የሚሰበሰብው" ብለዋል። ሁሉም ማህበረስብ ያገባኛል ብሎ መሥራት ያለበትን መሥራት እና ኃላፊነቱን መወጣት አለበትም ሲሉ ተናግረዋል። "ሁሉም የነበረውን አብሮነት እና መቻቻል ማጠናከር፤ የተሳተፉትንም ለህግ እንዲቀርቡ በመተባበር እና የተዘረፈውንም ሃብትም መተካት አለብን" ብለዋል የቦርዱ ሰብሳቢ መልአከ ሠላም ኤፍሬም ሙሉዓለም። በሞጣ ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ 15 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ ተስፋዬን ጠቅሶ የአማራ መገናኛ ብዙን ዘግቧል።
news-52411348
https://www.bbc.com/amharic/news-52411348
ኮሮናቫይረስ፡ በርካታ ሰዎች ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየተሻገሩ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል
በርካታ ሰዎች በኮረናቫይረስ ከተያዙባት ጎረቤት አገር ጂቡቲ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ፤ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር የአፋርና አማራ ክልሎች ጥረት እያደረጉ መሆኑን አመለከቱ።
ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የጭነት መኪናዎች ጸረ ተዋህሲያን ይረጫሉ የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ያሲን ሙስጠፋ ለቢቢሲ፤ "ከጅቡቲ ከበሽታው የሚሸሹ እንዲሁም ጾም ስለሆነ ሙቀቱን ለማሳለፍ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ በርካታ ሰዎች አሉ" ብለዋል። መንግሥት የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመቆጣጠር በድንበሮች በኩል የሰዎች እንቅስቃሴን ቢያግድም ከጂቡቲ "የሚገቡት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው" ይላሉ ኃላፊው። አንድ ሚሊዮን የማይሞላ ሕዝብ ያላት ጂቡቲ አንድ ሺህ የሚጠጉ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን በግዛቷ ውስጥ ማግኘቷን ተከትሎ ድንበር እየተሻገሩ በሚገቡ ሰዎች ላይ ቁጥጥር ማድረግ መጀመሩ ተገልጿል። ከጅቡቲ በአፋር ክልል በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡ አስራ አምስት የመግቢያ በሮች ሲኖሩ ሦስቱ ዋና የሚባሉ መሆናቸውን ያመለከቱት ኃላፊው በሁሉም ላይ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ከአፋር ክልል ጋር ወደሚዋሰነው የአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከጅቡቲ በኩል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የዞኑ የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሊድ ሙስጠፋም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት ሰዎቹ በእግር ድንበር ተሻግረው የሚገቡባቸው የተለያዩ ቦታዎች መኖራቸውን አመልክተው "አንዱ ባቲ ወረዳ ነው። ባቲ ላይ አቢላል የሚባል ቦታ በተለይ በእግርና በመኪና ሰዎች ስለሚገቡ የሙቀት ልኬት ጀምረናል" ሲሉ የበሽታው ምልክቶችን ለመለየት እየሞከሩ መሆኑን ተናግረዋል። በዞኑ ካሉት ሰባት ወረዳዎች አምስቱ ከአፋር ክልል ጋር ስለሚዋሰኑ "ከጅቡቲ በአፋር በኩል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በርካታ በመሆኑ አራቱ ወረዳዎች ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የስጋት ቀጠና ናቸው በሚል ተለይተዋል" ሲሉ የዞኑ ጤና ኃላፊ አቶ ካሊድ አመልክተዋል። በአፋር ክልል "18 የለይቶ ማቆያ ስፍራዎች ተዘጋጅተዋል" ያሉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ያሲን ሃቢብ በተለይም ደግሞ በሦስቱ ዋና ዋና መግቢያዎች በኩል ብዛት ያላቸው ሰዎች በመኪናና በእግር ስለሚገቡ ትኩረት መደረጉን ለቢቢሲ አስረድተዋል። እስካሁንም የአፋር ክልል መንግሥት ከጅቡቲ የሚመጡ ሰዎችን ለመቆጣጠር እያከናወነ ባለው ሥራ ወደ ለይ 380 የሚሆኑ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ መደረጉንና ከለይቶ ማቆያ ለመውጣት የሚሞክሩ በመኖራቸው ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ጨምረው ገልፀዋል። በጅቡቲ በሽታው ከፈጠረው ስጋትና በአሁኑ ወቅት ካለው ሞቃት የአየር ሁኔታ ለመሸሽ ድንብር አልፈው የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የሚሄድ ከሆነ ለዚሁ ተብሎ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ወደተዘጋጀው የለይቶ ማቆያ እንዲዛወሩ እንደሚደረግ አቶ ያሲን ለቢቢሲ ጨምረው አስረድተዋል። በአፋር ክልል እስካሁን አንድ ሰው በኮሮናቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፤ በክልሉ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ቤተ ሙከራ በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተው አሁን ግን ናሙናዎች ወደ አዲስ አበባ ተልከው እንደሚመረመሩ ኃላፊው ገልፀዋል። በአገሪቱ በተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት የድንበር መግቢያዎች ዝግ ቢሆኑም ከጂቡቲ የሚመጡ ኢትዮጵያዊያንን መመለስ እንደማይቻል ያመለከቱት ኃላፊው ነገር ግን "ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገው ከተመረመሩ በኋላ ነጻ መሆናቸው ሲረጋገጥ ይወጣሉ" ብለዋል። በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 117 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከጂቡቲ መጥተው በድሬዳዋ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሰዎች እንደሚገኙበት የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል። ጂቡቲ ከ980 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ሁለቱ ሞተዋል። በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ የጨመረው በአንድ ሳምንት ውስጥ ነው። ይህንንም ተከትሎ የአሜሪካ መከላከያ ኃይል በጅቡቲ ባሉት ወታደራዊ የጦር ሰፈሮች በአጠቃላይ የአስቸኳይ ጊዜ አውጇል። ድንብር ተሻጋሪ የሰዎች እንቅስቃሴን ለመቆጠጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ 'ዳጉ' የተባለውን የአፋር ማኅበረሰብ ባህላዊ የመረጃ መለዋወጫ መንገድን እየተጠቀሙ መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ምክልት ኃላፊ አቶ ያሲን አመልክተዋል። የማኅበረሰቡ አባላት ጂቡቲ ውስጥ እየተስፋፋ ስላለው ወረርሽኝ ትኩረት አድርገው መረጃ እንደሚለዋወጡ "በየጊዜው ለእኛም ሪፖርት ያደርጋሉ። መረጃውን እየተለዋወጡ ስለሆነ እኛን በጣም እየጠቀመን ነው" በማለት ተናግረዋል። በእግር ድርበር አቋርጠው የሚገቡትንም ከፀጥታ ኃይሉ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ እየተከታተለ እንደሚጠቁም ገልጸው "ሕዝቡ ከጂቡቲ የሚመጡ ንክኪ ይኖራቸዋል በሚል ዘመዶቻቸውን ጭምር ወደ እኛ ያመጧቸዋል፤ ይሄም ለሥራችን አጋዥ ሆኗል" ብለዋል። ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መኪኖችም ጋላፊ ላይ ጸረ ተዋህሲያን እንደሚረጩና የከባድ መኪኖች አሽከርካሪዎችም ሲገቡና ሲወጡ አስፈላጊውን በሽታውን የመከላከያ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይደረጋል ብለዋል ኃላፊው።
news-56966869
https://www.bbc.com/amharic/news-56966869
ነጻ ፕሬስ፡ ለሴት ጋዜጠኞች ተራራ ሆኖ የቀጠለው የኢትዮጵያ ሚዲያ
የኢትዮጵያን ሚዲያ የተቀላቀለችው ከሰባት አመት በፊት ነው። መአዛ ሃደራ ትባላለች። አራት አመታትን ካሳለፈችበት የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር የተለያየችበት አጋጣሚ በኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት ለሴቶች ያለውን ውጣ ውረድ ያስረዳል።
የስራ መልቀቂያዋን ከማስገባቷ ከወራት በፊት ባላወቀችው ምክንያት የሴቶችን ጉዳይ የሚመለከቱ ዘገባ እንዳትሰራ መደረግ መጀመሩን ታስታውሳለች። አዲስ የተመደበው አለቃዋ በተደጋጋሚ ሴቶችን የሚመለከት ጉዳይ ሲሆን "ስሜ ከተላከ ወዲያ በሌሎች ወንድ ዘጋቢዎች ይተካኛል" ትላለች። በዚሁ ምክንያት አለቃዋን «ለምን» ያለችው መአዛ "ፌሚኒስት ሆነሽ ጋዜጠኛ መሆን አትችይም" የሚል ምክንያት ነበር የተሰጣት። ነገሮችን በፆታ እኩልነት አይን ማየቷ እና ሁሌም ይህንን ለመጠየቅ ወደ ኋላ አለማለቷ ለአዲሱ አለቃዋ ምቾት እንዳልሰጠው ተረድታለች። ይህ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም የምትለው መአዛ በወቅቱ የዘጠኝ ወር ልጅ እናትም ነበረች። ልጇን ለማስከተብ በሆስፒታል ውስጥ እያለች፣ ለአለቃዋ ልጇን አስከትባ ወደ ስራ እንደምትመለስ ብትነግረውም መልሱ "መቅረት አትችይም" የሚል ሆኖባታል። "የሶስት አመት ፈቃድ አልወሰድኩም ነበር። በዛ ላይ በቤቱ ሕግ ልጅን ለማስከተብ ፈቃድ መጠየቅ ይቻላል" ስትል መአዛ ታስረዳለች። ስራዋን ለመተው የመጨረሻ ምክንያት የሆነው ልጇ በመታመሟ የሁለት ቀን እረፍት መጠየቋ እና በአመታት ከምትበልጣት ባልደረባዋ እጅግ ያነሰ የደመወዝ ጭማሪ ማግኘቷ ነበር። ይህም ከብቃት ጋር የተያያዘ ያለመሆኑ አስቆጥቷታል። መዓዛ ሃድራ "መልኳ ላይ ማተኮር" "ወንድ ባልደረቦቼ እኮ ሶስት ልጅ ወልደው አሁንም ይሰራሉ" ስትል መአዛ በጾታ የሚደረጉ ልዩነቶችን ታስረዳለች። ወደ ስክሪን የሚቀርቡ ሴት ጋዜጠኞች እድሜ ብሎም የሰውነት ሁኔታ እንጂ የሚያቀርቡት ይዘት ላይ ትኩረት አለመደረጉ ያበሳጫት ነበር። "ሴት ጋዜጠኛ የፃፈችውን ዜና የሚያስተካክልላት ሳይሆን ሜካፗ እና ልብሷ ላይ ሰአታት የሚፈጅ ሰው ነው ያለው። ጠዋት ለኤዲቶሪያል ስንሰበሰብ የሴቷ አንባቢ አለባበስ እና አቀራብ ላይ እንጂ የወንዱ ሱፍ ላይ አናተኩረም" ትላለች። መአዛ አክላም ሜካፕ መቀባት የማትፈልግ ጋዜጠኛ በቴሌቪዥን ቀርባ መታየት እንደማትችል በምሳሌነት ራሷን በማንሳት ታብራራለች። ምንም እንኳን ልምድ ቢኖራትም ሜካፕ እንዲሁም ቀሚስ ለማድረግ ባለመፈለጓ ወደ ፊት መውጣት የማይታሰብ ነበር። "አብዛኛዋ ሴት አቅራቢ ቀረፃ አልቆ ሂውማን ሄሯን አውልቃ እስክትጥል እና ሜካፗ እስከምታስለቀቅ ነው የምትቸኩለው። ወንዶቹ ግን ለቀረፃ 10 ደቂቃ ሲቀር ነው የሚመጡት። ትኩረታቸውም የሚያቀርቡት ነገር ላይ ነው" መአዛ ታነፃፅራለች። "የደመወዝ ጭማሪ ሲደረግ እኔ አራት አመት የምበልጣት ልጅ የተጨመረላት ጭማሪ ከኔ የአምስት ሺህ ብር ይበልጥ ነበር" ትላለች። "ለምን ብዬ ስጠይቅ፣ 'እርሷ በቴሌቪዥን ስለምትቀርብ ያልሆነ ቦታ እንድትውል እና የማይሆን ልብስ ለብሳ እንድትታይ አንፈልገም' የሚል ምክንያት ነበር የተሰጠኝ። በስራ ልዩነት ቢሆን ደስ ነበር የሚለኝ። የሰጡኝ ምክንያት ግን በአጠቃላይ ለሁሉም ሴት አግባብ ያልሆነ ነበር" ትላለች መአዛ። ፎዮ-አይ ኤም ኤስ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሀን የሚታየውን የስርአተ-ፆታ ምጣኔ አመላካች በሚል ርዕስ ካስጠናው ጥናት ላይ የተወሰደ ሴት የሚዲያ አመራሮች ፎዮ አይኤም ኤስ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሀን የሚታየውን የስርአተ-ፆታ ምጣኔ አመላካች በሚል ርዕስ አስጠንቶ ባለፈው ወር የታተመው ወረቀት ሰባት የመገናኛ ብዙሃንን መርጦ የሴት አመራሮችን ጉዳይ ፈትሿል። ይህ ጥናት የሴቶችን ተሳትፎ የኤዲቶሪያል ውሳኔ ሰጪ አመራሮች እና መደበኛ አመራሮች ሲል ለሁለት ከፍሎ ተመልክቶታል። በጥናቱ ብዙ ሴት ሰራተኞች አሉት የተባለው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ካሉት 25 አመራሮች አንዷ ብቻ ሴት ናት። የኤዲቶሪያል ውሳኔ ከሚሰጡ ሃለፊዎች ደግሞ 40 በመቶው ሴቶች ናቸው። በኢትዮጵያ ትልቁ ቀጣሪ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ካሉት 64 አመራሮች 13ቱ ብቻ ሴቶች ናቸው። እንዲሁም የኤዲቶሪያል ውሳኔ ሰጪነት ላይ ያሉ ሴቶች 16.6 በመቶው ብቻ ናቸው። ይህ ጥናት እንደሚያሳያው በብሮድካስት የመገናኛ ብዙሃን ከህትመት የተሻለ በርካታ ሴት ጋዜጠኞች አሏቸው። ለዚህም የህትመት መገናኛ ብዙሃን ቁጥራቸው እየቀነሰ መምጣቱ እንዳለ ሆኖ ዘርፉ ሴት ጋዜጠኞችን ማቆየት አለመቻሉ ሌላው ነው። አንድ የህትመት ሚዲያን በመምራት ከአራት አመት በላይ ያገለገለች እና በቅርቡ ፆታን መሰረት ባደረገ ጥቃት ምክንያት ስራዋን የለቀቀችው ፋሲካ ታደሰ መገናኛ ብዙሃን ለምን ጥቂት ሴት አመራሮች እንዳሏቸው ታስረዳለች። ስምንት አመታት በጋዜጠኝነት ያሳለፈችው ፋሲካ ስለራሷ አጋጣሚ ከመናገሯ በፊት ሴት የሚዲያ መሪዎች ከወንዶች በተለየ በየዕለቱ የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች ታስረዳች። "አንድም ቀን ሴት አለቃ ትኖረኛልች ብሎ አስቦ ከማያውቅ ሰው ጋር መጋፈጥን ይጠይቃል" ትላለች። "ብዙ ወንዶች ባደጉበት ማህበረሰብ እና ቤተሰብ የወንድ የበለይነት የተለመደ ስለሆነ የሴቶችን መሪነት አምኖ መቀበል ይከብዳቸዋል። ስራቸውን ስትተቺ ወይም ትዕዛዝ ሲሰጣቸው 'ንቃኝ ነው፤ ማን ስለሆነች ነው' ማለቱ ይቀናቸዋል" ስትል ፋሲካ ለቢቢሲ አስረድታለች። ከወራት በፊት ከወንድ የስራ ባልደረባዋ በይፋ የተወረወሩ በቃላት ጥቃቶች ምክንያት ስራዋን ጥላ እንደወጣች ትናገራለች። ከዚህ ቀደም ብሎም ተመሳሳይ ቃላትን ቢወረውርም ስሜታዊ ሆኖ ይሆናል ብላ ማለፏን ትገልፃለች ፋሲካ። " አለቆቼን ጨምሮ ሁሉም ባልደረቦቼ ባሉበት ጾተኝነት የተጫናቸው መልዕክቶች የሆነ መልክት ላከ። ይህንን መልክት ለወንድ ባልደረባው ቢሆን በድፍረት እንደማይልከው አውቃለሁ" ትላለች። በጋዜጣው ከፍተኛ የሃላፊነት ደረጃ ላይ ብትገኝም " ነገሩን ያለልክ አጋነንሽው" ከመባል ባለፈ አዳማጭ ማጣቷን ትናገራች። በዚህ ምክንያት ስራዋን ለመልቀቅ መወሰኗን ብሎም ድርጊቱን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ማሰቧን አስታወቀች። በዚህ ወቅት ነበር ድርጅቱ " የስራ ቦታን የሚመጥን ቋንቋ አልተጠቀመም፤ ከዛ ውጪ ሌላ ችግር አላየንበትም" በሚል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የፃፈው። በቅድሚያ በዚህ ጉዳይ ላይ ምርመራ ተደርጎ መቀጣትም ካለበት መቅጣት ብሎም ይቅርታ መጠየቅ ካለበት መጠየቅ እንጂ ይህ አካሄድ ትክክል አይደለም በሚል ተሟግታለች ፋሲካ። " ብዙ ሰው ይህ በሕግ የሚያስጠይቅ ጥፋት መሆኑን አያውቅም። የአሰሪ ሰራተኛ ሕጉ እኮ ይህንን በግልፅ ደንግጓል። ሃላፊዎች ፆታን፣ ሃይማኖትን እና ብሔርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ ምላሽ ካልሰጡ በሕጉ ይጠየቃሉ። ይህንን የሚመጥን እርምጃ ያለመውሰዳቸው ከኔ ባለፈ ለሌላውም ሰው የሚያስተላልፈው መልክት ያሳስበኛል። ይህ ኒውስ ሩም ለኔ ስለማይሆን ጥዬ ወጥቻሁ" ትለላች ፋሲካ። የፕሬስ ነፃነትን ከሴት ጋዜጠኞች መብት እና ደህንነት ጋር ምን አገናኘው? ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ሲፒጄ የሰሃራ በታች ተወካይ ሙቱኪ ሙሞ እንደሚሉት ሴት ሰራተኞች ብሎም ሃላፊዎች የሌሉት ተቋም የሴትን እይታ ማጣቱ ችግሩን የፕሬስ ነፃነት ችግር ያደርገዋል ሲሉ ይሞግታሉ። በተለይም በአፍሪካ ሴት ጋዜጠኞች ከወንድ የስራ ባልደረቦቻው ጋር ተመሳሳይ ፈተናዎችን ይጋራሉ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሴት በመሆናቸው ብቻ ተጨማሪ ፈተናዎች ይጋፈጣሉ። ይህ በሞያው ውስጥ ለመቆየት አዳጋች ያደርግባቸዋል ይላሉ። " በዩጋንዳ የተቃዋሚ ፓርቲ የጠራውን መግለጫ ለመዘገብ የተሰበሰቡ ጋዜጠኞች ላይ የደረሰው ጥቃት ትዝ ይለኛል። ፖሊስ ወንድ ጋዜጠኞችን ሲደበድብ ሴቷም እኩል የመደብደብ እና የመታሰር አደጋ ነበር የተጋረጠባት። ነገር ግን ማሕህበረሰቡ ሴቶች ሊሰሩት ይገባል ብሎ ከሚጠብቃቸው ስራዎች ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ችግሮችን ትጋፈጣለች" ሲሉ ሙቱኪ ያስረዳሉ። በዚሁ ክስተት ላይ የነበረች ሴት ጋዜጠኛ ባለቤቷ " ይህንን ስራ ወይም እኔን ምረጪ" እንዳላት ማንበባቸውንም ያክላሉ። ሴት ጋዜጠኞች ከአለቆቻቸው፣ ከማህበረሰቡ፣ ከስራ ባልደረቦቻው የሚያጋጥማቸውን ችግር ሽሽት ስራቸውን ሲተዉ የሚወዱትን ስራ መስራት ባለመቻላቸው በቀዳሚነት የሚጎዱት ጋዜጠኞቹ ራሳቸው ናቸው ይላሉ። ነገር ግን አንድ የመገናኛ ብዙሃን የሴቶችን እይታ ያጣ ስራ መስራቱ ትልቅ ጉዳት ሲሆን ማህበረሰቡም የሚያገኘው የመረጃ እይታ ብዝሃነት የሌለው መሆኑ ችግሩን ከፕሬስ ነፃነት ጋር ያያይዘዋል ይላሉ። በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶችን ዋቢ የሚያደርጉት ተወካይዋ ሴት ጋዜጠኞች ከወንድ ጋዜጠኞች ጋር ሲነፃፀር የበለጠ ለዲጂታል ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸውን ያነሳሉ። "በእነዚህ የስነ ልቦና ጥቃቶች ምክንያት ሴት ጋዜጠኞች ራሳቸውን ሳንሱር ማድረግ ይጀምራሉ። ይህም በቀጥታ የፕሬስ ነፃነት ላይ ጫና እያሳደረ ነው ማለት ነው" በማለት ለቢቢሲ አስረድተዋል። ተቋማቸው ለጋዜጠኞች መብት የሚከራከረው ለማህበረሰቡ መብትም ጭምር እንደሆነ የሚገልፁት ሙቱኪ የመገናኛ ብዙሃን በሴት ጋዜጠኞች መመራት በተዘዋዋሪ ከፕሬስ ነፃነት ጋር ይገናኛል ይላሉ። " አንድ ተቋም ሃብቱን የት ላይ ማፍሰስ እንዳለበት፣ ለየትኛው የምርመራ ፕሮጀክት ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት እና የፊት ገፅ ዜናው ምን ይሁን የሚለውን የሚወስኑት ሃላፊዎቹ ናቸው። ሴት ሃላፊ ከሌለው የሴቶችን እይታ ያጣ ውሳኔ ስለሚወስን ይህ የፕሬስ ነፃነት ላይ የራሱን ጫና ያመጣል" ይላሉ። አክለውም ሴቶች አንድ አይነት አመለካከት ያላቸው ተመሳሳይ ቡድን እንደሆኑ የማሰብ ልምድ አግባብ አይደለም ሲሉም ያስረዳሉ። ይልቁንም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚም ሆኑ ማህበራዊ ዘገባዎች በአጠቃላይ የሴትን እይታን እንዲያካትቱ ማስቻል ቁልፍ ነው። ይህም ተመልካቾች ወንዶች ብቻ ባለመሆናቸው እና የማህበረሰቡንም እይታ አንድ ወጥ እንዳይሆን ያደርገዋል ብለዋል። መፍትሄው ምንድን ነው? ያጋጠማት ፈተና አይኗን እንደከፈተላት የምትናገረው መአዛ አሁን ላይ በራሷ የዩትዩብ ቻናል በተለያዩ ሞያ ያሉ ሴቶችን በመጋበዝ ለወጣት ሴቶች ምክር የሚሰጡበትን ፕሮግራም ታቀርባለች። መፍትሄው የሴት ጋዜጠኞች ማህበር ባይጠናከር እንኳን እርስ በእርስ መረዳዳት መሆኑን አጽንኦት ትሰጠዋለች። ሴቶች በእጃቸው ሚዲያን ይዘው ሲጨቆኑ ዝም ማለት እንደሌለባቸውም ትገልፃለች። ቀድመው ወደ ሞያው የገቡ ሴት ጋዜጠኞች ለአዳዲሶቹ ስራዬ ብለው የማለማመድ ስራ ይስሩ የምትለው መአዛ "ወንዶቹ እኮ ይነጋገራሉ፤ እኛም የእህትማማችነት ስሜት ካላዳበርን ነገም የሚመጡ ልጆች ከዜሮ ይጀምራሉ" ስትል ታሳስባለች። መአዛ "ሴት ጋዜጠኛ ከሰው ከተግባባች፣ ወጥታ ከተዝናናች እና የምትፈልገውን ስታደርግ ከታየት ይቺ ከሁሉም ጋር ናት ትባላለች። ከዚህ ተቃራኒ ከሆነች ደግሞ መነኩሴ ይሏታል" የምትለው መአዛ " የኔ ምኞት ይሄ እንዲቆም ነው፤ ሴት ጋዜጠኛ ሳይሆን ጋዜጠኛ ብቻ የምትባልበት ግዜ ይናፍቀኛል። ልብሷ፣ መልኳ፣ ፀጉሯ ሳይሆን በምትሰራው ስራ የምትገመትበት ኢንዱስትሪ ሆኖ ማየት ህልሜ ነው" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። " የትም ብሄድ መፍትሄ አላገኝም። አርፌ ብቀመጥ ይሻለኛል" በሚል ችግሮቹ መድበስበሳቸው ብዙ ተቋማትም የሴት ሰራተኞቻቸውን ደህንነት በቸልታ እንዲያዩት ምክንያት መሆኑን የምታሰረዳው ደግሞ ፋሲካ ነች። " የደረሰባቸውን ቢናገሩ ስራቸውን ስለሚያጡ በዝምታ የሚያልፉት ብዙዎች ናቸው" ትላለች። ተቋማት የሴት ጋዜጠኞቻቸውን ደህንነት ከቁብ የማይቆጥሩበት ዋነኛው ምክንያት የሞያ ማህበራት የቅስቀሳ (አድቮኬሲ) ስራ መዳከም መሆኑንም ታብራራለች። የሴት ጋዜጠኞች ማህበርን ጨምሮ ሌሎች የሞያ ማህበራት መብት ሲጣስ አደባባይ ወጥቶ መከራከር አለመቻለቸው ለሚዲያ ሃላፊዎች ማን አለብኝነት አስተዋፅኦ አለውም ትላለች። በተጨማሪም የፌሚኒስት ንቅናቄዎች መስራት የሚገባቸው ቦታዎች ላይ መስራት አለመቻለቸው ሌላው ክፍተት ነው። " አዲስ አበባ ውስጥ በርካታ የፌሚኒስት ንቅናቄዎች አሉ፤ አቅማቸውን የሚጨርሱት በሌላ ቦታ ነው። የስራ ላይ ደህንነት ዋነኛው አተኩረው መስራት ያለባቸው አካባቢ ነው ብዬ አምናለሁ" ትላለች። እነዚህ ማህበራት ችግሮቹ ሳይመጡ ስልጠና መስጠት እና ተቋማት የውስጥ አሰራራቸውን እንዲፈትሹ ማድረግ ይገባል። " በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ፆታዊ ጥቃት እንዳለም እኮ እንሰማለን። እነዚህ ጋዜጠኞች ይህንን ብንናገር ነገ ማንም አይቀጥረንም ብለው ዝም ይላሉ" የምትለው ፋሲካ ይሄንን ችግር ለመቅረፍ ሩቅ ብንሆን እንኳን መቀነስ አለብን ትላለች። ሙቶኪ በኩላቸው መገናኛ ብዙሃን ከውስጥ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ብቻ ሳይሆን ከውጪም የሚገጥሙ ጥቃቶችን በተመለከተ ከዘገባው በፊት የሴት ጋዜጠኞቹን ደህንነት ማስቀደም አለበት ይላሉ። በመላው አለም በዚህ ላይ የሚሰሩ በርካታ ተቋማት እንዳሉ እና ሴት ጋዜጠኞች እነዚህን ተቋማት በማግኘት አገልግሎቶቹን መጠቀም ይኖርባቸዋል ይላሉ።
news-53121216
https://www.bbc.com/amharic/news-53121216
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ያስተጓጎለው የኢትዮጵያ የካንሰር ህክምና
የ33 ዓመቷ ሸምስያ ጀበል ተወልዳ ያደገችው ደሴ ነው። ወሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ምግብ ቤት ትሠራ ነበር። አምና የመጀመሪያ ልጇ ሲታመምባት ለህክምና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ተላከች። የአራት ዓመት ልጇ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተደረገለት ምርመራ የደም ካንሰር እንዳለበት ተነገራት።
በኮሮናቫይረስ ምክንያት በተለያዩ የህክምና አገልግሎቶች ላይ ጫና ተፈጥሯል ሸምሲያ ይህን ስትሰማ ዙሪያው ገደል እንደሆነባት ታስታውሳለች። ልጇን የምታሳክምበት ገንዘብ አልነበራትም። የሚደግፋትም ሰው አልነበረም። የካንሰር ህክምና ደግሞ እጅግ ውድ ነው። ልጇ የደም ካንሰር እንዳለበት በተነገራት በአንድ ወሩ፤ የልጇ አባት ‘አቅሜ አይችልም’ ብሎ ጥሏት እንደሄደ ትናገራለች። በወቅቱ የወር ከ15 ቀን ነፍሰ ጡር ነበረች። “ልጄ ደም በየጊዜው [ኬሞ ቴራፒ] ይወስዳል። ታዲያ የማሳክምበት ብር ጨርሼ ህክምናውን አቋርጬ ልሄድ ነበር። ጥቁር አንበሳ ያሉ ሀኪሞች ግን የካንሰር ህሙማንን የሚደግፍ ማኅበር አገናኙኝ። እዚህ ማኅበር ባልገባ ልጄ በሕይወት አይኖርም ነበር።” ሸምሲያ ማረፊያ ካገኘች በኋላ ለልጇ ህክምና መከታተል ከቀጠለች ሰባት ወራትን አስቆጥራለች። አሁን ግን መላው ዓለምን ያመሰቃቀለው ኮቪድ-19 የሸምስያም ስጋት ሆኗል። ልጇን ለማሳከም ወደ ሆስፒታል በሄደች ቁጥር በበሽታ ይያዝብኝ ይሆን ብላ ትሳቀቃለች። ሁለተኛ ልጇን ከወለደች አራት ወር ሆኗታል። የካንሰር ታማሚ ልጇን ይዛ ወደ ጥቁር አንበሳ ስትሄድ ሁለተኛ ልጇንም አስከትላ ነው። “. . . ህጻኑን የአራት ወር ልጄን ይዤ ነው የምሄደው። እና እንዴት እንደምጠነቀቅ ራሱ ግራ ይገባኛል። ካንሰር የሚታመመው ልጄ ደግሞ ቀልቃላ ነው። እሱን መከታተል እንዴት ከባድ መሰለሽ። እሱን አሳክሜ እስክመለስ ይጨንቀኛል። እዚ [ማኅበሩ ውስጥ] አልኮል አለ፤ እጃችንንም ስለምንታጠብና አጠቃላይ ጥንቃቄውም የተሟላ ስለሆነ ይቀለኛል። ስወጣ ግን ከማኅበረሰቡ ጋር መቀላቀል ራሱ በጣም ያስፈራል።” እንደ ሸምስያ የካንሰር ታማሚ ልጅ የሚያስታምሙ እንዲሁም የተለያየ አይነት የካንሰር ህመም ያለባቸው ሰዎችም ስጋቷን ይጋራሉ። በተለይም ካንሰር፣ ስኳር፣ አስም፣ ደም ግፊትና ሌላም ህመም ያለባቸው ሰዎች ለኮቪድ-19 ተጋላጭ መሆናቸው ፍርሀታቸውን ያባብሰዋል። ሸምስያ ልጇን በየ15 ቀኑ ወደ ጥቁር አንበሳ ትወስዳለች። ኮሮናቫይረስ ያለበት ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደተገኘ ከተገለጸ ወዲህ እያንዳንዱ የሐኪም ቤት ቀጠሮ ለሸምስያ ጭንቅ ነው። “ካንሰር ጊዜ የሚሰጥ በሽታ አይደለም። ቀጠሮ አይዘለልም። በመመላለሴ ደስተኛ አይደለሁም። ግን ደግሞ መመላለስ ግዴታዬ ነው። ለምን ብትይ ካልሄድኩ ልጄ ይሞታል። ከዚህ በፊት አብረውኝ የኖሩ ሰዎች የልጆቻቸውን ሕይወት ሲያጡ አይቻለሁ. . . በተቻለኝ አቅም ራሴን እየጠበቅኩ ልጄን እያሳካምኩ እመጣለሁ። እንግዲህ ፈጣሪ ከጎኔ ይሁን።” በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል ምልክት የማያሳዩ መኖራቸውን ስታስብ ፍርሀቷ ይጨምራል። ሆስፒታል ውስጥ የምታሳልፈው እያንዳንዱ ሰዓት ያሳስባታል። “ወረፋ አለ፣ ደም ሊያስፈልገው ይችላል። ለምሳሌ ቀይ ደም ስድስት ሰዓት ከተሰጠው እስከ ዘጠኝ ሰዓት መቆየት አለበት። መቼም ሐኪም ቤት በጣም ብዙ ሰው ነው ያለውና በጣም ነው የምፈራው።” ሸምስያ ከሁለቱ ልጆቿ ጋር የምትኖርበት ማቲዎስ ወንዱ የካንሰር ማዕከል ውስጥ የማህጸንና የጡት ካንሰር እንዲሁም ሌላ አይነት የካንሰር ህመም ላለባቸው ድጋፍ ይደረጋል። የማዕከሉ የፕሮግራም ኃላፊ አቶ ዘላለም መንግሥቱ እንደሚሉት፤ ኮቪድ-19 ለካንሰር ህሙማንና ቤተሰቦቻቸው ተደራቢ ፈተና ሆኗል። የካንሰር ህሙማን በሽታ የመከላከል አቅማቸው አነስተኛ በመሆኑ ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው። በበሽታው ከተያዙም ተቋቁሞ ለመዳን ይቸገራሉ። በሌላ በኩል አዲስ አበባ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። የካንሰር ህሙማን ደግሞ ጥቁር አንበሳ ለሚያደርጉት ህክምና ወደ አዲስ አበባ መምጣት ግድ ስለሚላቸው አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ ይናገራሉ። ሌላው ፈተና የህክምና ተቋማትና ባለሙያዎች አብዛኛውን ትኩረታቸውን ወደ ኮቪድ-19 ማድረጋቸው ነው። “ጥቁር አንበሳ መጀመሪያ ላይ ቀጠሮ በማራዘም፣ ታካሚዎች ባሉበት ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ጀምረው ነበር። ቀጠሮ ሲራዘም ቶሎ መድኃኒትና ህክምና ማግኘት ያለበት ታካሚ ይጎዳል። በሽታውን ከፍ ወዳለ ደረጃም ይወስደዋል። ወረርሽኙ ከሌሎች ህሙማን በበለጠ የካንሰር ህሙማን ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍ ያለ ነው” ይላሉ አቶ ዘላለም። ካንሰር ዘላቂ የሐኪም ክትትል (ቼክአፕ) እንዲሁም ህክምና የሚያስፈልገው ህመም ነው። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ከቤት መውጣት መቀነስ፣ አካላዊ ርቀት መጠበቅም አስፈላጊ መሆኑ እሙን ነው። የካንሰር ታማሚዎች ወደ ህክምና መስጫ መሄድ ግዴታቸው ስለሆነ ከቤት በወጡ ቁጥር መጨነቃቸው አይቀርም። • ዴክሳሜታሶን ምን ያህል አስተማማኝ ነው? ኢትዮጵያ ውስጥስ ይገኛል? አቶ ዘላለም እንደሚሉት፤ በአንድ ክፍል ውስጥ የሚሰበሰቡ ሰዎችን መቀነስ ስለሚያስፈልግ ማዕከላቸው የሚቀበለውን የህሙማን ቁጥር ቀንሷል። ቀድሞ በአንድ ክፍል እስከ ስድስት ሰው ይይዝ የነበረን ክፍል ወደ አንድ ታካሚና አስታማሚ ለመቀነስ ተገደዋል። “ሌላው ችግር የትራንስፖርት ዋጋ መጨመሩ ነው። ይሄ ከባድ ጫና ፈጥሮባቸዋል። ካንሰር ረዥም ጊዜ የሚወስድ ህክምና በመሆኑ ታካሚና ቤተሰብም ከባድ ሥነ ልቦናዊ ጫና ውስጥ ይገባል። አሁን ያለው ሁኔታ ደግሞ ነገሮችን አባብሷል” ሲሉ ያስረዳሉ። ተደራራቢ ጫና ካንሰር ሥነ ልቦናዊና ማኅበራዊ ጫና የሚያሳድር የገንዘብ አቅምን የሚፈትንም ህመም ነው። በዚህ ላይ ኮቪድ-19 ሲጨመር ደግሞ ችግሩ ይባባሳል። ፈተናው እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ብቻ አይደለም። የተሻለ የምጣኔ ኃብት ደረጃ ላይ መድረሳቸው የሚነገርላቸው አገሮችም እየተፈተኑ ነው። በተለያዩ አገሮች የተሠሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ኮሮናቫይረስ ከሚያሳድረው ተጽዕኖ ባልተናነሰ ሁኔታ በወረርሽኙ ሳቢያ የሚመጡ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሕይወት ያሳጣሉ። ለምሳሌ በቫይረሱ ሥርጭት ሳቢያ አገራት በረራ ላይ እገዳ በመጣላቸው፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት የሚያስፈልጋቸውን ክትባት ማግኘት አልቻሉም። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፤ ወረርሽኙ ቢያንስ የ68 አገሮችን የጤና ዘርፍ ስለሚያቃውስ፤ 80 ሚሊዮን ጨቅላዎች ክትባት ባለማግኘት ለኩፍኝ፣ ፖሊዮና ሌሎችም በሽታዎች ይጋለጣሉ። የምግብ እርዳታ ወደሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ማድረስ ባለመቻሉም ለምግብ እጥረት ተጋላጭ የሆኑ አሉ። የዓለም አቀፉ የምግብ ተቋም ዋና ኃላፊ ዴቪድ ቢስሊ፤ ዓለም ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው አይነት ቸነፈር ይጠብቃታል ብለዋል። 130 ሚሊዮን ሰዎች ለዚህ ተጋላጭ ናቸው። አሁን ላይ 135 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል። በሌላ በኩል የሥነ ተዋልዶ ጤና፣ የአዕምሮ ጤና፣ ካንሰር እንዲሁም ሌሎችም መደበኛ የህክምና ክትትሎችም ችላ ተብለዋል። በመላው ዓለም ያሉ የካንሰር ህሙማን፣ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው፣ አስቸኳይ ቀዶ ህክምና የሚሹ ሰዎችም ሰሚ አጥተናል እያሉ ነው። አቶ ዘላለም እንደሚሉት፤ አሁን ላይ አጠቃላይ የህክምና ዘርፉ ወደ ኮቪድ-19 መዞሩ የካንስር ህክምና ላይ ጫና አሳድሯል። “በፊትም እንደ ካንሰር ያሉ ህመሞች ጫና አለባቸው። አሁን ደግሞ የበለጠ ተጽዕኖው እየተሰማን ነው” ይላሉ። • የኮሮናቫይረስ ዘመኗ እመጫት ኢትዮጵያዊት የአራስ ቤት ማስታወሻ • ከባድ የጤና ችግር ኖሮባቸው ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ታሪክ ያለው ተደራራቢ ጫና ታማሚዎች ህክምና እንዲያቋርጡ እንዳያረጋቸው አቶ ዘላለም ይሰጋሉ። “ካንሰር ከጊዜ ጋር የሚሄድ በሽታ ነው። ቶሎ ታክሞ ውጤቱን ማሻሻል ካልተቻለ ወደከፋ ደረጃ ይደርሳል። በዛ ላይ ለ100 ሚሊዮን ሕዝብ ያለው ማዕከል አንድ ጥቁር አንበሳ ነው። የቅዱስ ጳውሎስ እና የዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎቹ (ጎንደር፣ ጅማ፣ ዓለማያ፣ሐዋሳ፣ ሀሮማያ) ማስፋፊያ ሲጠናቀቅ ነገሮች ይሻሻሉ ብለን እንጠብቃለን” ሲሉ ያስረዳሉ። በኮቪድ-19 ምክንያት እስካሁን የካንሰር መድኃኒቶች እጥረት ባይፈጠርም፤ ለዓመታት ሲነሱ የነበሩት የመድኃኒቶች ውድነትና እንደልብ ያለመገኘት ጥያቄዎች አሁንም እንዳልተመለሱ አቶ ዘላለም ይናገራሉ። ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት አለመቻሉ ካንሰር የተባባሰ ደረጃ ላይ ሲደርስ ህክምናው የበለጠ አስቸጋሪ ስለሚሆን፤ ሰዎች በጊዜ ህክምና እንዲጀምሩ ይመከራል። ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ የጡትና የማህጸን ጫፍ ካንሰር የመሰሉትን ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። ለዚህም ካንሰር ላይ የሚሠሩ ተቋሞችና ማኅበራት በየጊዜው የግንዛቤ ማስጨበጫ ያዘጋጃሉ። አሁን ግን መሰል መድረኮችን ለማሰናት አስቸጋሪ ነው። ይህም ካንሰር የሚመረመሩ ሰዎችን ቁጥር እንደሚቀንሰው አቶ ዘላለም ይናገራሉ። “የጤና ባለሙያዎች አሁን ከቤት ቤት እየተዘዋወሩ ሙቀት እየለኩ፣ ስለ ኮሮናቫይረስ ግንዛቤ እየሰጡ ነው ያሉት። እና በዚህ ወቅት ስለ ጡት ካንሰር ባወራ የሚሰማኝ የለም።” በዚህ ምክንያት ቶሎ ተገኝተው ህክምናቸው ሊጀመር የሚገባ በሽታዎች እንደሚባባሱ አቶ ዘላለም ያስረዳሉ። ዩናይትድ ኪንግደምን እንደምሳሌ ብንወስድ አገሪቱ በኮቪድ-19 ምክንያት እንቅስቃሴን ስትገታ የካንሰር ምርመራ ቆሟል። የአገሪቱ የካንሰር ማዕከል እንዳለው ይህ ማለት ቀድሞ በየወሩ ይገኙ የነበሩት 1,600 የካንሰር ህሙማን አሁን በሽታቸው አይታወቅላቸውም ማለት ነው። በዩኬ ህሙማን ከቤታቸው እየወጡ ስላልሆነ መደበኛ ምርመራ ማቆማቸው ሌላው ስጋት ነው። አንድ የአገሪቱ የካንሰር ሐኪም እንደሚሉት፤ ሕክምና በመጓተቱ ሳቢያ ወደ 60 ሺህ ሰዎች ይሞታሉ። አቶ ዘላለም እንደሚሉት፤ አሁን ላይ ሰዎች የካንሰር ምልክት ቢያዩ ወደ ህክምና መስጫ ላይሄዱ፣ ሄደውም አፋጣኝ ምላሽ ላያገኙ ይችላሉ። ይህ ደግሞ ለበሽታው ህክምና መሰጠት ያለበትን ጊዜ ያዘገየዋል። “በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ መድኃኒትና ኬሞቴራፒ ውድ በሆነበት አገር፣ ራድዮቴራፒ በአንድ ማዕከል ብቻ ስለሚሰጥ ወረፋ ለሚጠበቅበት አገር በአፋጣኝ ህመሙ ተገኝቶ ህክምና መገኘት አለበት። ደረጃው በጨመረ ቁጥር አክሞ ለማዳን ከባድ ይሆናል።” መፍትሔው ምንድን ነው? ካንሰር በግለሰቦች ብቻ ሳይሆን በአገር ማኅበራዊ መዋቅርና ምጣኔ ኃብት ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚያሳድር አቶ ዘላለም ይናገራሉ። የካንሰር ህክምና በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሚደርስበት ተጽዕኖ መፍትሔው ምንድን ነው? የሚለውን በቀላሉ መመለስ አይቻልም ይላሉ። ችግሩ ውስስብ መሆኑ ግልጽ መፍትሔ ማስቀመጥን አስቸጋሪ ቢያደርገውም፤ በጤናው ዘርፍ የሚተላለፉ ውሳኔዎች የካንሰር ህክምናን ታሳቢ ማድረግ አለባቸው ይላሉ። “የሆነ ተዓምራዊ መፍትሔ የለውም። ከማኅበረሰቡ ጀምሮ ብዙ ሥራ ያለበት ጉዳይ ነው። ሆኖም የጤና ውሳኔዎችና ፕሮግራሞች ካንሰርን ከግምት ማስገባት አለባቸው” ሲሉም ያስረዳሉ።
54348246
https://www.bbc.com/amharic/54348246
ባህል፡ በዋቄፈና እምነት ሀጥያት፣ ገነትና ገሃነም አሉ?
ዋቄፈና የቀደምት ኦሮሞ ሕዝቦች እምነት ሲሆን የእምነቱ ተከታዩች ሁሉን በፈጠረ አንድ አምላክ እንደሚያምኑ ይናገራሉ።
አቶ አስናቀ ተሾመ ኢርኮ፣ ላለፉት 20 ዓመታት ስለ ዋቄፈና እምነት አጥንተዋል። አሁንም በዓለም አቀፍ የዋቄፈና እምነት ምክር ቤት በአመራርነት እያገለገሉ ይገኛሉ። በዋቄፈና እምነት ዙሪያ የአገር ሽማግሌዎች እና ካደረጉት ጥናት የተረዱትን ለቢቢሲ እንዲህ በማለት አካፍለዋል። አቶ አስናቀ ቦረና አካባቢ በመሄድ ጥናታቸውን እንዳደረጉ ገልፀው "ፈጣሪ ስሙ መቶ፣ ሆዱ እንደ ውቅያኖስ ሰፊ፣ ሃሳቡ ደግሞ ንጹህ ነው፤" ድሮ ድሮ ሰው ሃጥያት መስራት ሳይጀምር በፊት የፈጣሪን ድምጽ የሰሙ ሰዎች ነበሩ ይባላል ይላሉ። ስሙ መቶ ነው የሚለው ደግሞ ፈጣሪ "አንድ" እና ከሁሉ በላይ የሆነ መሆኑን እና ሀይማኖቶች ወይንም እምነቶች ግን ብዙ መሆናቸውን ለማሳየት መሆኑን አቶ አስናቀ ያብራራሉ። ይሁንና ፈጣሪን በዓይኑ ያየው ሰው የለም በማለት ነው ኦሮሞ የሚያምነው ሲሉ ያስረዳሉ። ኦሮሞ 'ፈጣሪ ጥቁር ነው' ይላል። የኦሮሞ ፈጣሪ ጥቁር ነው ሰንል ግን ይኼ የሚታየውን መልክ ወይም የቀለም ጉዳይ ሳይሆን፣ "ፈጣሪ ጥልቅ ነው፤ ፈጣሪን ማየት፤ መለየት አይቻልም የሚለውን ለመግለጽ ነው። ማንም ተመራምሮ ሊደርስበት አይችልም።" ብለዋል። "ፈጣሪ ምስጢር ነው፤ ከሰው አእምሮ በላይ ነው የሚለውን ለማሳየት ነው በጥቁር መልክ የሚገለፀው።'' ዘፍጥረት እንደ ዋቄፈና እምነት፤ ፈጣሪ ሁሉን ነገር የፈጠረው በቀደመ ዘመን ከነበረ ውሃ እንደሆነ ይታመናል። ፈጣሪም ይህንንም ውሃ 'የላይኛውና የታችኛው ውሃ' በማለት ለሁለት ከፈለው የሚሉት አቶ አስናቀ፣ የላይኛው ውሃ ጠፈር ውስጥ የሚገኙ አካላትን ሰማይን እንዲሁም ፀሀይንና ከዋክብትን ይይዛል። የታችኛው ውሃ ደግሞ፣ የውሃ አካላትን እንደ ውቅያኖስ፣ ባህርን፣ ደረቅ መሬትን ይይዛል። ዋቄፈና በዚህ ምድር ላይ ያሉ ፍጥረታት በሙሉ በ27 ቀናት ተፈጠሩ ብሎ ነው የሚያምነው። መጀመሪያ ሰውን ፈጠረ፣ ከዚያም ወንድና ሴት ብሎ እኩል ለሁለት ከፈላቸው። ሌሎች ፍጥረቶችንና ተክሎችን እንደዚሁ በቅደም ተከተል ፈጠራቸው። ፈጣሪ ምድርን ሲፈጥር ሰው በስነ-ስርዓት እንዲኖር ሕግንም አብሮ ፈጠረ። እነዚህም ሕጎች የሰው ሕግ፣ የከብቶች ሕግ፣ የፈረሶች ሕግ፣ የዱር አራዊት ሕግ፣ የእጽዋትና የፀሀይና የከዋክብት ሕግ ይሰኛሉ። 'ሰፉ' የማይቀየር የፈጣሪ ሕግ ነው። ይህም ክልክል የሆኑትን ሰውን መግደል፣ መስረቅ፣ ዝሙት እና መዋሸትን ተላልፎ መገኘት ነው። ፈጣሪን፣ ምድርን እንዲሁም ሌሎችን ፍጥረቶች ሁሉ ማክበር የፈጣሪን ሕግ መጠበቅ ነው። ክልከላዎች 'ለጉ' የሚባሉት የማህበረሰቡን አይነኬ ተግባራት ለመጠበቅ የወጡ ናቸው። አንድ ሰው ሀጥያት ሰራ የሚባለው እነዚህን የፈጣሪን ሕግና ክልከላዎች ሲጥስ/ ሲተላለፍ ነው። ከሞት በኋላ ሕይወት? ቀደምት የኦሮሞ ሕዝቦች ሰው ሲሞት ነፍሱ ወደ ፈጣሪ ወይንም ደግሞ ወደ እውነት ቦታ ትሄዳለች ብለው ነው የሚያምኑት። እንደ ዋቄፈና እምነት ሰው ከውሃ፣ ከነፋስ፣ ከእሳት እና ከአፈር በአንድ ላይ ተበጅቷል። ስለዚህ ሰው ሲሞት አካሉ ከአፈር ይቀላቀላል፣ ደሙ ወደ ውሃ ይሰርጋል። ነፍሱ ደግሞ ወደ ፈጣሪው ይሄዳል። "እንደ ሌሎች እምነቶች ዋቄፈና ሰው ከሞተ በኋላ ይነሳል ወይንም በሕይወት ይኖራል ብሎ አያምንም። እንዲሁም በሴጣን መኖርና ፈጣሪን የሚገዳደር ሌላ ኃይል አለ ብሎ አያምንም። ሰዎችንም ኃጥያት እንዲሰሩ የሚያስገድዳቸው ኃይል የለም ብሎ ነው የሚያምነው" ይላሉ አቶ አስናቀ። ይኹን እንጂ "ክፉ መንፈስ አለ ብሎ ያምናል" በማለት፣ ሰው የማይቀየረውን የፈጣሪን ሕግ ከተላለፈ፣ ስለሚጠየቅ እና ርግማንም ወደ ሰባት ትውልዱ ስለሚተላለፍ ኃጥያት መስራት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ሕዝቡም ይህንን ይፈራል። ለምሳሌ አንድ ሰው፣ ነፍስ አጥፍቶ ሳይናገር ከሞተ በፈጣሪ ዘንድ ስለሚጠየቅ ቤተሰቦቹ ወይንም ዘመዶቹ የሙት መንፈስን የሚያናግሩ "አዋቂዎች" ዘንድ ይሄዱና ካሳውን "ልክ በሕይወት እንዳለ ሰው" ይጠይቃሉ። በዚህ እምነት ገሃነም ወይንም ገነት የሚባል ነገር የለም። እንዲህ ማለት ግን ሰው የፈለገውን እያደረገ ይኖራል ማለት አይደለም። በእነዚያ በፈጣሪ በማይቀረው ሕግ ስር መመላለስ አለበት። በዚህ መንገድም በፍጥረታት እና በሰዎች መካከል ያለ ሚዛን ተጠብቆ በሰላም መኖር ይቻላል ብሎ ያምናል፤ ዋቄፈና። አቶ ተሻገር የአገር ሽማግሌዎች 'እዳየነው እንደሰማነው' በማለት ሲናገሩ፣ ኦሮሞ ፈጣሪን ሴት ወይንም ወንድ ብሎ ለይቶ አይጠራም። ነገር ግን ሲጠሩት በወንድ ጾታ ነው። ይህ ግን ጾታውን ለማመለክት አለመሆኑን.ይናገራሉ። የዋቄፈና እምነት ተከታዮች አቶ ደሳለኝ ደሜ በቢሾፍቱ ሆረ አርሰዴ የዋቄፈና ቤተ እምነት "ዋዩ" ናቸው። ዋዩ ማለት የዋቄፈና ቤተ እምነት ውስጥ ያሉ የአስተዳደር ጉዳዮችን የሚሰበስብና የሚመራ ሰው ነው። አቶ ደሳለኝ ዋቄፈና ከአባቶቻችን ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የመጣ እምነት ቢሆንም፣ እኛ የአሁኖቹ ትውልዶች ደግሞ ስርዓት እና ባህሉን ሳይለቅ ለአሁኑ ዘመን በሚመች መልኩ በ1990ዎቹ ቤተ እምነት መስርተን ኃይማኖቱን አቋቁመናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እኛ እንደ እምነታችን ሁሉን በልጦ የሚያስተምር መምህር የለንም ያሉት አቶ ደሳለኝ ደሜ፣ ምክንያቱን ሲያስረዱ ስለዚህ እምነት ጉዳይ ሁሉም ከአባቱ ወርሶ ተምሮ መምጣቱን ይጠቅሳሉ። ይሁን እንጂ የውይይት ጥላ የሚባል ዝግጅት እንዳላቸው ገልፀዋል። በዚያም ስለፈጣሪ ተነጋግረን ፈጣሪን ለምነን እንገባለን ሲሉም ያክላሉ። "በአጠቃላይ ግን እምነቱን በበላይነት የሚመራው 'ቃሉ' ነው።" በአሁኑ ጊዜ በቢሾፍቱ ከተማ ብቻ አራት የዋቄፈና ቤተ እምነቶች አሉ። ከቢሾፍቱ በተጨማሪ በአዳማ፣ ባቱ ፣ ሰበታ እና ወሊሶ እንዲሁ ቤተ እምነቶች ይገኛሉ። በየዓመቱ ደግሞ አንድ ቤተ እምነት እንደ ክብረ በዓል ያዘጋጅና ሁሉም በአንድነት ያከብራሉ። የሆረ አርሰዴ ቤተ እምነት በግምት ከ5000 በላይ አባላት እንዳሉት አቶ ደሳለኝ ይናገራሉ። አብዛኛዎቹ አባላት ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ሰራተኞችና በተለያየ የኑሮና የስራ ዘርፍ የሚገኙ ሰዎችም አባላት ናቸው። የዋቄፈና የአምልኮ መርሃ ግብር ቤተ እምነቱ ሁሌም ለሁሉም ሰው ክፍት ቢሆንም ዘወትር እሁድ ግን አባላቶች በአንድነት ተገናኝተው የአምልኮ ስነ ስርዓት ያካሄዳሉ። ጠዋት ሲገናኙ ማንኛውም ስነ ስርዓት ከመጀመሩ በፊት አንዱ ለአንዱ ይቅርታ የማድረግ ስርዓት ይፈፀማል። "በዚያ ቤተ እምነት ውስጥ የሚገኝ ሰው እርቀ ሰላም ካላወረደ፣ ፈጣሪ አይሰማም ተብሎ ስለሚታመን እርቀ ሰላም ይቀድማል" የሚሉት አቶ ደሳለኝ፣ ከዚህ በመቀጠል በእድሜ ታላቅ የሆኑ እና አካባቢን መሰረት በማድረግ የምርቃት ስነ ስርዓት መርሃ ግብር ይካሄዳል። ከዚህ በኋላ ዋቄፈናን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በማንሳት በውይይቱ ጥላ ስር ያሉ አባላቶች ይማማራሉ። አሁን ፀሎትና ምስጋና ይቀጥላል። በዚህም ጊዜ የቡና ማፍላት ስርዓት ይከናወናል። የታመመ ሰው ይፀለይለታል፤ ቤተሰቦቹ የፈጣሪን ሕግ ጥሰው ከሆነ ፈጣሪ እንዲታረቃቸው ይለመናል። ከዚህ በፊት ፀሎታቸው የተመለሰላቸው ሰዎች ካሉ ደግሞ ምስጋና ያቀርባሉ። በዚህ ሁሉ መካከል 'ጄከርሳ' መዝሙር ይዘመራል። ይህ መዝሙር በስነ ስርዓቱ መክፈቻና መዝጊያ ላይ የሚካሄድ ሲሆን ከመጨረሻው መዝሙር በፊት ግን አንድ "ባልቻ" የሚባል የመባ መስጠት ስርዓት ይካሄዳል። ይህ ስርዓት የቤተ እምነቱ አባል የሆነ ሰው የገንዘብ የሃሳብና የንብረት ድጋፍ የሚያደርግበት ነው። በአሁኑ ጊዜ ከመንግሥት በኩል እውቅና የማግኘትና የአምልኮ ስፍራ ለማግኘት ትልቅ ችግር እንዳለባቸው አቶ ደሳለኝ ጨምረው አስረድተዋል።
news-52773545
https://www.bbc.com/amharic/news-52773545
ኮሮናቫይረስ: የዓለምን ታሪክ የቀየሩ አምስት አደገኛ ወረርሽኞች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የዓለምን ታሪክ እየቀየረ ነው። ቢሊዮኖች አኗኗራቸው ከወራት በፊት ከሚያውቁት የተለየ ሆኖባቸዋል። ኮሮናቫይረስ ወደፊት በታሪክ ከሚጠቀሱ ክስተቶች አንዱ መሆኑ አያጠራጥርም።
ኮሮናቫይረስስ ዓለማችንን በምን መልኩ ይለውጣት ይሆን? ኮሮናቫይረስ የዓለምን ታሪክ የቀየረ የመጀመሪያው ወረርሽኝ አይደለም። እስቲ ዋና ዋና ከሚባሉት አምስቱን ከታሪክ መዛግብት እናገላብጥ። ጥቁሩ ሞትና የአውሮፓ ሥልጣኔ በርካቶች ፈጣሪ ጥቁሩን ሞት እንዲነቅልላቸው ይፀልዩ ነበር በግሪጎሪ አቆጣጠር በ1350 ላይ አውሮፓን የመታው ጥቁሩ ሞት ተብሎ የሚታወቀው [የቡቦኒክ ትኩሳት] ወረርሽኝ የአህጉሪቱን አንድ ሦስተኛ ሕዝብ እንደቀጠፈ ይነገራል። አብዛኞቹ ሟቾች ደግሞ ለመሬት ባላባቶች እየሠሩ የሚያድሩ ገባሮች ነበሩ። ከበሽታው በኋላ ግን የሠራተኞች ዋጋ እጅግ ተወደደ። ይህም በምዕራብ አውሮፓ የፊውዳል ሥርዓት እንዲወድቅ ምክንያት ሆኗል ይባላል። ይህ መላ ያሳጣቸው የመሬት ባላባቶች በሰው ፈንታ ቴክኖሎጂ ወደመጠቀም ገቡ። ይህ ሂደት ምዕራብ አውሮፓ ወደ ሥልጣኔ እንደትገባ አድረጓታል የሚሉ በርካቶች ናቸው። ምዕራብ አውሮፓውያን ዓለምን ለማሰስ ወደ ሌሎች አገራት ማቅናት የጀመሩትም በዚህ ወቅት በመሆኑ ወረርሽኙ ለቅኝ ግዛትም ሚና እንደተጫወተ ይገመታል። ፈንጣጣና የአየር ንብረት ለውጥ ስፔናውያን ቅኝ ገዢዎች ፈንጣጣን ይዘው ወደ ደቡብ አሜሪካ አገራት እንደሄዱ ይነገራል በ15ኛው ክፍለ ዘመን የደቡብ አሜሪካ አገራት በቅኝ ገዢዎች እጅ ስር መግባት ለዓለም የአየር ንብረት መለወጥ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። የለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አጥኚዎች የደቡብ አሜሪካ አገራት በአውሮፓውያን ቅኝ በመገዛታቸው ሳቢያ የሕዝብ ቁጥሩ ከ60 ሚሊዮን ወደ 6 ሚሊዮን ዝቅ ብሏል ይላሉ። በርካቶች የሞቱት ቅኝ ገዥዎች ይዘዋቸው በመጡ በሽታዎች ሳቢያ ነው። በጣም ብዙ ሰው የቀጠፈው ፈንጣጣ እንደሆነ ታሪክ ይናገራል። በተጨማሪም ኩፍኝ፣ ኮሌራ፣ ወባና ታይፈስ ቅኝ ገዢዎች ለደቡብ አሜሪካ ሰዎች ያዛመቷቸው በሽታዎች ናቸው። የቅኝ ገዢዎቹ ጣጣ ከደቡብ አሜሪካ አገራት አልፎ ለዓለም ሕዝብም ተርፏል። ነገሩ እንዲህ ነው፤ በሽታው ከቀጠፋቸው መካከል አብዛኞቹ አርሶ አደሮች ነበሩ። በዚህ ምክንያት በርካታ የእርሻ መሬቶች ወደ ጫካነት ተቀየሩ። በወቅቱ ከእርሻ መሬትነት ወደ ጫካነት የተቀየረው መሬት ስፋት ኬንያን ወይም ፈረንሳይን የሚያክል እንደሆነ ይገመታል። ይህ ክስተት የዓለምን ሙቀት መጠን ከተገቢው በላይ ቀነሰው። ምድርም ቅዝቃዜ እንደወረራት ይነገራል። በዚህ ምክንያት በሌሎች ዓለማት ያሉ ሰዎች ተጎዱ። ሰብሎች ውርጭ መታቸው። በጣም የሚገርመው በዚህ የዓለም ሙቀት መቀነስ እጅግ የተጎዳችው ምዕራብ አውሮፓ መሆኗ ነው። ቢጫ ወባና የሄይቲ አብዮት በቢጫ ወባ ምክንያት የሄይቲ አብዮት ፈረንሳዮችን ነቅሏል በ1801 በአህጉረ አሜሪካ በምትገኘው አገር ሄይቲ የተከሰተው የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ትንሿ አገር የፈረንሳይን ቅኝ ገዢዎች ፈንቅላ እንድታስወጣ ምክንያት ሆኗል። የፈረንሳዩ መሪ ናፖሊዎን ቦናፓርቴ እራሱን የዕድሜ ልክ መሪ አድርጎ ሾመ፤ አልፎም ደሴቷ ሄይቲን እንዲቆጣጠሩለት በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮች ላከ። የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ግን ለወታደሮችም አልተመለሰም። በሽታው 50 ሺህ ገደማ የፈረንሳይ ወታደሮችን ቀጠፈ። ሐኪሞችና አሳሾችም በበሽታው ከሞቱት መካከል ነበሩ። ወደ ፈረንሳይ በሕይወት የተመለሱት 3 ሺህ ብቻ እንደሆነ ታሪክ ያሳያል። አውሮፓውያን ምንጩ አፍሪካ እንደሆነ የሚነገርለት ቢጫ ወባን መቋቋም አልቻሉም። ይሄኔ ነው ናፖሌዎን ሄይቲን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቅኝ ሊገዛቸው ያሰባቸውን አገራት ጥሎ የወጣው። የፈረንሳዩ መሪ 2.1 ሚሊዮን ስኩዌር መሬት ከሄይቲ ቆርሶ ለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መሸጡ አይዘነጋም። ይህ በታሪክ የሉዊዚያና ሽያጭ ተብሎ ይታወቃል። የአፍሪካ ሪንደርፔስትና ቅኝ ግዛት ሪንደርፔስት በርካታ የቁም እንስሳትን እንደፈጀ መዛግብት ያሳያሉ የቁም እንስሳትን የፈጀው ሪንደርፔስት የተሰኘው በሽታ አውሮፓውያን የአፍሪካ አገራትን በቅኝ ግዛት እንዲቀራመቱ ምክንያት እንደሆነ ይታመናል። ከ1888 እስከ 1897 ባለው ጊዜ የተከሰተው ይህ እንስሳትን የሚያጠቃ ቫይረስ 90 በመቶ የአፍሪካ ከብቶችን እንደፈጀ ይነገራል። በተለይ ደግሞ በአፍሪካ ቀንድ፣ በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ያሉ አርብቶ አደሮች በዚህ ሳቢያ እጅግ ተጎድተዋል። ይህ እንስሳትን የሚያጠቃ ቫይረስ በርካቶች እንዲራቡና እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል። አርብቶ አደሮች ብቻ ሳይሆኑ አርሶ አደሮችም ጭምር በዚህ ሳቢያ ተጎድተዋል። በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ አፍሪካን ለመውረር የመጡት የአውሮፓ ቅን ገዢዎች ወረርሽኙ አላማቸውን ምቹ አደረገላቸው። በ1870ዎቹ በአውሮፓ ቅኝ ግዛት ስር የነበረው የአፍሪካ አካል 10 በመቶው ብቻ ነበር። ነገር ግን በወረርሽኙ ሳቢያ የአፍሪካ አገራት አቅም በመዳከሙ በ1900 ዘጠና በመቶ የአፍሪካ መሬት በቅኝ ገዥዎች እጅ እንዲሆን አድርጓል። ወረርሽኝ የጣለው የቻይናው ሚንግ ስርወ መንግሥት ወረርሽኝ ጠንካራውን የቻይና ጥንታዊ ስርወ መንግሥት አንኮታኩቶታል የሚንግ ስርወ መንግሥት ቻይናን ለሦስት ክፍለ ዘመናት አስተዳድሯል። ይህ አገዛዝ በቻይና ብቻ ሳይሆን በበርካታ የምሥራቅ እስያ አገራት ዘንድ የተንሰራፋ ነበር። ነገር ግን የዚህ አገዛዝ ጨረሻ ያማረ አልነበረም። በ1641 በሰሜናዊ ቻይና ወረርሽኝ ተከሰተ። ይህ ወረርሽኝ የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፏል። ችግሩን የከፋ ያደረገው ደግሞ በወቅቱ ተከስቶ የነበረው ድርቅና የአንበጣ ወረራ ነው። ሰዎች የሚበሉት በማታጣቸው የሞተ ሰው ስጋ ሁሉ እስከ መ፥ብላት ደርሰው እንደነበር ይነገራል። የቡቦኒክና የወባ በሽታ ቅልቅል ነው የሚባልለት ይህ ወረርሽን ያመጡት የሚንግ አገዛዝ መጣል የፈለጉት ቀጥሎ ወደ አገዛዝ የመጡት የኩዊንግ ስርወ መንግሥት ሰዎች እንደሆኑ ይነገራል። ያሰቡት ተሳክቶላቸውም ግዙፉን ሥርዓት ጥለውታል። እነዚህ በታሪክ የተመዘገቡና የዓለምን ታሪክ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የቀየሩ ወረርሽኞች ናቸው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝስ ታሪክ ይቀይር ይሆን?
news-55328492
https://www.bbc.com/amharic/news-55328492
ፑቲን ለጆ ባይደን የዘገየ የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ
ቭላድሚር ፑቲን ለጆ ባይደን የዘገየ የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዓለም መሪዎች በጣም ዘግይተው ለተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በሩሲያ የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት፣ ክሬምሊን፣ የኅዳሩ ምርጫ አሸናፊው በውል እስኪለይ ድረስ ዝምታን እንደሚመርጥ አስቀድሞ ገልጾ ነበር፡፡ አሁን ፑቲን እንኳን ደስ አለዎ የሚለውን መልእክት ያስተላለፉት የግዛት ድምጽ ተወካዮች (ኤሌክቶራል ኮሌጅ አባላት) ተሰብስበው የጆ ባይደንን አሸናፊነት ትናንት ማወጃቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ባይደን ከ50 ግዛቶች 306 የወኪል ድምጽ ሲያገኙ ትራምፕ ግን 232 ላይ መቆማቸው ይታወሳል፡፡ በአሜሪካ የምርጫ አሰራር 270 እና ከዚያ በላይ የወኪል ድምጽ ያገኘ እጩ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ተብሎ ይጠራል፡፡ ያም ሆኖ ዶናልድ ትራምፕ እስከዛሬም ተሸናፊነታቸውን በይፋ አልተቀበሉም፡፡ ከወዳጆቻቸው ጭምር መሸነፋቸውን ጨክነው እንዲቀበሉ ውትወታው ቢበረታባቸውም ሽንፈት ሞት ሆኖባቸዋል፡፡ በአሜሪካ ሴኔት አብላጫ ወንበር መሪ ተወካይ ሪፐብሊካኑ ሚች ማኮኔል ለመጀመርያ ጊዜ ባይደንን እንኳን ደስ አለዎት ማለታቸው ዛሬ ተዘግቧል፡፡ እኚህ የትራምፕ ወዳጅ ዝምታውን መስበራቸው ትራምፕ ባይደንን የማቆም ዕድላቸው ስለመሟጠጡ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል በዋና ዋና ግዛቶች ላይ እሳት የላሱ ጠበቆቻቸውን በማዝመት የክስ ዶሴ ማስከፈታቸው አይረሳም፡፡ ትራምፕ የሽንፈትን ጽዋ ለመቅመስ አሻፈረኝ ይበሉ እንጂ የአሜሪካ ምርጫ በተደረገ በሳምንት ውስጥ አብዛዎቹ የዓለም መሪዎች ለጆ ባይደን የመልካም ምኞች መግለጫ ልከዋል፡፡ ቭላድሚር ፑቲን ግን ይህ እንዲዘገይ አድርገዋል፡፡ ባይደንና ፑቲን ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከነበሩበት ዘመን ጀምሮ ግንኙነታቸው የሻከረ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ተመራጩን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ዘግይተው ‹ሹመት ያዳብር› ለማለት ከፑቲን ሌላ የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት ሎፔዝ ኦብራዶር ይጠቀሳሉ፡፡ ውዝግብ የማያጣቸው የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ዣዪር ቦልሶናሮን እንዲሁ ለጆሴፍ ባይደን መልካም ምኞት ለመግለጽ የዘገዩ መሪ ሆነዋል፡፡ እነዚህ ሦስቱ መሪዎች ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በአገር ደረጃ ብቻም ሳይሆን በግልም ጠበቅ ያለ ግንኙነት የነበራቸው በመሆናቸው ምናልባት ቀደም ብለው ለጆ ባይደን መልካም ምኞች ቢያስተላልፉ ትራምፕን ማስቀየም ይሆንብናል ብለው ሰግተው የቆዩ እንደሆኑ ተገምቷል፡፡ ክሬምሊን ባወጣው የመልካም ምኞች መግለጫ ፑቲን ከአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ስለመሆናቸው ገልጾ ለባይደን መልካም የሥራ ዘመንን ይመኛል፡፡ ‹‹በተለይ ሩሲያና አሜሪካ የዓለምን ደኅንነትና ሰላምን ለመጠበቅ ልዩ ኃላፊነት ያለባቸው አገራት እንደመሆናቸው ልዩነታቸው እንዳለ ሆኖ ብዙ ችግሮችን በመቀራረብ መፍታት እንደሚችሉ እናምናለን›› ይላል የመልካም ምኞቹ ሙሉ ቃል፣ አንድ አንቀጽ፡፡ ጆ ባይደን ትራምፕ አቅብጠዋቸዋል በሚባሉት ፑቲን ላይ ጠበቅ ያለ የዲፕሎማሲና የንግድ እቀባ እርምጃዎችን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እስከ አሁን ለጆ ባይደን እንኳን ደስ አለዎ የሚል መልእክት ያላስተላለፉት መሪ የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ናቸው፡፡
news-52833584
https://www.bbc.com/amharic/news-52833584
በአሜሪካ እየተበራከተ የመጣው የፖሊስ ጭካኔ እና የተገደሉ ጥቁሮች
ባሳለፍነው ሰኞ አንድ ነጭ የፖሊስ መኮንን አንድ ጥቁር አሜሪካዊን በጉልበቱ አንገቱ ላይ ቆሞ ሲያሰቃየው ከቆየ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ በአሜሪካ ዘርን መሰረት ያደረገ የፖሊስ ጭካኔ ጉዳይ ህዝባዊ ቁጣን ቀስቅሷል።
ጆርጅ ፍሎይድ ሟች የ46 ዓመት ጎልማሳ ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ሲሆን በሐሰተኛ የገንዘብ ኖት ጥርጣሬ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ሊያውለው እንደመጣ ተጠቅሷል። ለአስር ደቂቃ በሚዘልቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ፣ ነጭ ፖሊስ የዚህን ጥቁር አሜሪካዊ አንገት በጉልበቱ ተጭኖት እያለ በጉልህ የሚታይ ሲሆን ተጠርጣሪው በበኩሉ ‹‹መተንፈስ አልቻልኩም እባክህን አትግደለኝ›› እያለ ሲማጸነው ይሰማል፡፡ በዛኑ ቀን ደግሞ አንዲት ነጭ ሴት ኒው ዮርክ በሚገኝ ፓርክ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ለምን ውሻሽን አታስሪውም አለኝ በማለት ለፖሊስ ደውላ ነበር። "አንድ ጥቁር ሰው እኔ እና ውሻዬ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየዛተ ነው ድረሱልኝ" በማለት ለፖሊስ ደውላለች። ጉዳዩ ሲጣራ ግን ሴትዮዋ የፓርኩን ህግ በመተላለፍ ውሻዋን በመልቀቋ ነበር ጥቁር አሜሪካዊው ውሻሽን እሰሪው ያላት። አሜሪካ ውስጥ በጎርጎሳውያኑ 2019 ብቻ ከ1 ሺ በላይ ሰዎች በፖሊስ ተተኩሶባቸው ሕይታቸው አልፏል። የጆርጅ ፍሎይድ ሞት በአሜሪካ ላለው አስፈሪ የፖሊስ ጭካኔ ማሳያ ነው ተብሏል። ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት በ2019፣ 1014 ሰዎች በፖሊስ ተተኩሶባቸው የሞቱ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ጥቁር አሜሪካውያን ናቸው። አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት በሰራው ጥናት መሰረት ደግሞ ጥቁር አሜሪካውያን ከነጭ አሜሪካውያን ጋር ሲነጻጸር በፖሊስ የመገደል እድላቸው በሶስት እጥፍ ከፍ ያለ ነው። የፖሊስ ጭካኔ እንደ ‘ብላክላይቭስማተር’ የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ አድርጓል። ታዋቂዋ ዘፋኝ ቢዮንሴ እና ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ሌብሮን ጄምስ ይህንን እንቅስቃሴ በይፋ ደግፈዋል። እስካሁን ድረስ በአሜሪካ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሱ ተመሳሳይ የፖሊስ ጭካኔዎችን እንመልከት። ትሬይቮን ማርቲን፡ የካቲት 2012 የ 17 ዓመቱ ትሬይቮን ማርቲን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ነበር። ሳንፎርድ ፍሎሪዳ ውስጥ ነበር ጆርጅ ዚምርማን በተባለ የጥበቃ አባል ተተኩሶበት ሕይወቱ ያለፈችው። ማርቲን ዘመዶቹን ለመጠየቅ ጥበቃ ወደሚደረግለት አንድ መንደር ያቀናል፤ በዚህም ወቅት ነበር የስፓኒሽ ዘር ያለው ፈቃደኛ የአካባቢው ጠባቂ ጋር የተገናኘው። በወቅቱ ጆርጅ ዚመርማን በፍርድ ቤት ጥፋተኛ አይደለም ተባለ። ምንም እንኳን በአሜሪካ ሕግ መሰረት ጠባቂው የ 17 ዓመቱን ታዳጊ ራሴን ለመከላከል ነው በማለት መግደሉን እንደ ወንጀል ባያየውም የማርቲን ቤተሰቦችና ጓደኞቹ ግን የግድያ ወንጀል ነው የተፈጸመው ብለዋል። በዚህም ምክንያት ነበር ‘ብላክላይቭስማተር’ የሚባለው ማህበራዊ እንቅስቃሴ የተጀመረው። ኤሪክ ጋርነር፡ ሰኔ 2014 ኤሪክ ጋርነር በወቅቱ ትንባሆ በሕገ ወጥ መንገድ በመሸጥ ተጠርጥሮ ነበር በፖሊስ የተያዘው። ኤሪክ በፖሊስ አንገቱ ተቆልፎ ‹‹እባካችሁ መተንፈስ አልቻኩም›› እያለ በተመሳሳይ ሁኔታ ነበር የሞተው፡፡ ለኤሪክ ሞት ተጠያቂ የነበረው ነጭ የፖሊስ አባል ዳንኤል ፓንታልዮ ከሥራው የተባረረው ከክስተቱ አምስት ዓመታትን ቆይቶ መሆኑ ቁጣን ቀስቅሶ ቆይቷል፡፡ ማይክል ብራውን፡ ነሀሴ 2014 የ 18 ዓመቱ ማይክል ብራውን ዳረን ዊልስን በተባለ ፖሊስ አባል ተተኩሶበት መሞቱን ተከትሎ ደግሞ ‘ብላክላይቭስማተር’ የሚባለው እንቅስቃሴ ከአሜሪካ አልፎ ዓለማቀፍ ተቀባይነትን እንዲያገኝ አድርጓል። ሚሱሪ ፈርጉሰን ውስጥ በተፈጠረው ይህ ክስተት ምክንያት ከባድ አመጽ ተነስቶ የነበረ ሲሆን አንድ ሰው ሕይወቱ ሲያልፍ ሌሎች በርካታ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ነበር። ዋልተር ስኮት፡ ሚያዝያ 2015 ዋልተር ስኮት የ 50 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን በሳውዝ ካሮላይና ከፖሊስ ለማምለጥ ሲሞክር ሶስት ጊዜ በጥይት ተመትቶ ነው ሕይወቱ ያለፈችው። የፖሊስ አባሉ ዋልተር ስኮትን ለማስቆም የሞከረው የመኪናው ፍሬቻ መብራት በመሰበሩ ነበር። በወቅቱ ዋልተር ለልጁ የሚቆርጠውን ወርሀዊ ድጋፍ ባለመክፈሉ በፖሊስ ይፈለግም ነበር። • በምዕራብ ወለጋ የአራት ልጆች እናት የሆኑትን ግለሰብ ማን ገደላቸው? ስላገር የተባለው የፖሊስ አባል ዋልተር ስኮትን በመግደል ወንጀል ተከሶ 2017 ላይ የ 20 ዓመት እስር ተፈርዶበታል። የዋልተር ቤተሰቦችም የ 6.5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ተከፍሏቸዋል። ፍሬዲ ግሬይ፡ ሚያዝያ 2015 ዋልተር ስኮት በፖሊስ ተተኩሶበት ከሞተ ሳምንት እንኳን ሳይሞላው ባልቲሞር ሜሪላንድ ውስጥ ደግሞ ሌላ ቁጣን የቀሰቀሰ የፖሊስ ጭካኔ ተመዝግቧል። ፍሬዲ ግሬይ የ 25 ዓመት ወጣት ሲሆን በኪሱ ውስጥ የስለት መሳሪያ ይዞ በመገኘቱ ነበር በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው። በቦታው የነበረ የአይን እማኝ በቀረጸው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ፍሬዲ እየጮኸ ፖሊሶች ተሸክመው መኪናቸው ውስጥ ሲያስገቡት ይታያል። ከጥቂት ሰአታት በኋላ ፍሬዲ የአከርካሪ አጥንት ችግር አጋጥሞታል ተብሎ ሆስፒታል ገባ። ከሳምንት በኋላ ግን ሕይወቱ አለፈች። ይህ ተከትሎ በተቀሰቀሰ ቁጣም ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው 20 ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸው ነበር። ከፍሬዲ ሞት ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ ስድስቱ የፖሊስ አባለት ግን ጥፋተኛ አይደሉም ተብለው በነጻ ተሰናብተዋል። ፊላንዶ ካስቲል፡ ነሀሴ 2016 ፊላንዶ ካስቲል ሚኒሶታ ውስጥ ጀሮሚኖ ኣኔዝ በሚባል የፖሊስ አባል ነው ተተኩሶበት ህይወቱ ያለፈችው። በወቅቱ የተፈጠረውን ነገር የፊላንዶ የፍቅር ጓደኛ በስልኳ አማካይነት በቀጥታ አስተላልፋው ነበር። ምንም እንኳን የፖሊስ አባሉ ፍርድ ቤት ቢቀርብም አንድ ዓመት ከፈጀ የፍርድ ሂደት በኋላ በነጻ ተሰናብቷል። • ቦታም ጂን፡ መስከረም 2018 የ 26 ዓመቱ ቦታም ጂን፣ አምበር ጋይገር በምትባል የፖሊስ አባል ነበር በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ተተኩሶበት ህይወቱ ያለፈችው። በወቅቱ የፖሊስ አባሏ ቤቷ የገባች መስሏት በሂሳብ ስራ የሚተዳደረው ቦታም ጂን ቤት በስህተት ትገባለች። ልክ ስመለከተው ቤቴን ሊዘርፍ የገባ መስሎኝ ተኮስኩበት ብላለች። ከአንድ ዓመት በኋላም አምበር በወንጀሉ ጥፋተኛ በመባሏ የ 10 ዓመት እስር ተፈርዶባታል። • 119 ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል አቀኑ • አትላንታ ጄፈርሰን፡ ጥቅምት 2019 የ28 ዓመቷ አትላንታ፣ የህክምና ተማሪ የነበረች ሲሆን ዳላስ ውስጥ በመኝታ ክፍሏ ሳለች ነበር አሮን ዲን በተባለ የፖሊስ አባል የተደገለቸው። የፖሊስ አባሉ ከጎረቤት የአትላንታ የሳሎን በር ክፍት ነው የሚል ጥቆማ ደርሶት ነበር የመጣው። በመቀጠልም በመኝታ ቤቷ መስኮት በኩል ተኩሶ ገድሏታል። በግድያ ወንጀል ክስ ቢቀርብትም እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረበም። • ብሪዮና ታይለር፡ መጋቢት 2020 የ 26 ዓመቷ ብሪዮና ታይለር የድንገተኛ ህክምና ባለሙያ ነበረች። ኬንታኪ ውስጥ ፖሊሶች ወደ መኖሪያ ቤቷ ሲገቡ በተፈጠረ ጭቅጭቅ ወቅት ስምንት ጊዜ በጥይት ተመትታ ነው ህይወቷ ያለፈው። ፖሊሶቹ በወቅቱ ዕጽ በቤቷ አለ በማለት ነበር የሄዱት። ነገር ግን በብሪዮና ቤት ውስጥ ምንም አይነት ዕጽ አልተገኘም ነበር። ፖሊስ በበኩሉ አንድ የፖሊስ አባል በጥይት በመመታቱ ነው ተኩስ የተከፈተው ብሏል።
news-54296033
https://www.bbc.com/amharic/news-54296033
እምቦጭ፡ ተገኘ የተባለው ፀረ እምቦጭ አረም "መድኃኒት" እና የተከተለው ውዝግብ
የአንቦጭ አረም የኢትዮጵያን ትልቁን ሐይቅ ጣና ላይ ተንሰራፍቶበት የሐይቁንና በዙሪያው የሚገኙ ነዋሪዎችን ህልውና ስጋት ውስጥ ከከተተው ዓመታት ተቆጥረዋል። አረሙ ያለመፍትሔ ከዓመት ዓመት በሐይቁ ላይ እየተስፋፋ ለሌሎች በአገሪቱ ለሚገኙ የውሃ አካላት ሊተርፍ እንደሚችል እየተነገረ ቆይቷል።
ውሃው ለተለያዩ አገልግሎቶች ስለሚውል ኬሚካል ደግሞ ተመራጭ አይደልም በየጊዜው የሰው ጉልበትን በመጠቀም ከተወሰነው ሐይቁ ክፍል ላይ አረሙን ለማስወገድ ከሚደረገው ጥረት ባሻገር የተለያዩ ባለሙያዎችና በጎ ፈቃደኞች ለወራሪው አረም የሚሆን መፍትሄ ለማግኘት ይሆናል ያሉትን የበኩላቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል። በሰው ጉልበትም በቴክኖሎጂም የተደረጉት ጥረቶች ውጤት ስላላስገኙ የአረሙ መስፋፋት እየጨመረ ይገኛል። ሰሞኑን ግን መሪጌታ በላይ አዳሙ የተባሉ ግለሰብ ለዚህ አሳሳቢ አረም መፍትሔ የሚሆን መድኃኒት እንዳገኙ ሲናገሩ ተሰምቷል። ይህ ከዕጸዋት ተዘጋጅቶ ለሰባት ዓመታት ሙከራ ሲያደርጉበት እንደቆ የሚናገሩለት መፍትሔ እምቦጭ አረምን ድራሹን የሚያጠፋ "መድኃኒት ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መሪጌታ በላይ እንደሚሉት "መድኃኒቱ" እንቦጩ ላይ ከተረጨ ከ24 ሰዓታት በኋላ አረሙን እንደሚያደርቀው ይናገራሉ። ይህንን ሥራቸውንም "በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች አሳይቼ ማረጋገጫ አግኝቻለሁ" ይላሉ። "መድኃኒቱን"ላይ የተደረገው ሙከራ መሪጌታ በላይ የቀመሙትን መድኃኒት ወደ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በመውሰድ ለባለሙያዎች አሳይተዋል። የተግባር ሙከራም እንደተደረገበት ይናገራሉ። ይህንንም ሙከራ በቅርበት የተከታተሉት በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ኢንጂነሪንግ መምህር የሆኑት ወ/ሮ ፍትፍቴ መለሰ ናቸው። መምህርቷ የዶክትሬት [ሦስተኛ] ዲግሪያቸውን በእምቦጭ አረም ላይ እየሰሩ ይገኛሉ። መሪጌታ በላይ ለእምቦጭ አረም ማስወገጃነት ያገለግላል ያሉትን መድኃኒት በዩንቨርሲቲው አማካይነት ሙከራ እንዲደረግበት ሲጠይቁ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወ/ሮ ፍትፍቴ በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጅ ኢንስቲቲዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር እንደተመደቡ ተገልጸወል። ይህንንም ተከትሎ በግለሰቡ ተዘጋጅቶ የቀረበውን መድኃኒት በእምቦጭ አረም ላይ በማድረግ ያሳየውን ለውጥ የተመለከተ ሪፖርት አዘጋጅተው ለሚመለከተው የትምህርት ተቋሙ ክፍል ማቅረባቸውን ወ/ሮ ፍትፍቴ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ሙከራው በአረሙ ላይ ከመጀመሩ በፊት መድኃኒቱን ያቀረቡት መሪጌታ በላይ የተዘጋጀው መድኃኒት ሌሎች የውሃ ውስጥ እጸዋትንና ነፍሳትን የሚጎዳ ኬሚካል መሆን አለመሆኑን ለማሳት "መድኃኒቱን" እንደጠጡት መምህርቷ ተናግረዋል። ከዚያም በኋላ ምርምር በሚደረግበት የሙከራ ኩሬ ላይ "መድኃኒቱ" ተደርጎ "በ24 ሰዓት በኋላ በስፍራው ከነበረው የእንቦጭ አረም ውስጥ ቢያንስ 70 ከመቶ የሚሆነው ደርቆ አገኘነው" ያሉት ወ/ሮ ፍትፍቴ፤ አረሙ መቶ በመቶ ስላልደረቀ ድጋሚ እንዲረጭ ተደርጎ ሙሉ በሙሉ መድረቁን ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል። ሙከራው በዚህ ሳያበቃ በመጀመሪያ የተገኘውን ውጤት ለማረጋገጥ ተደጋጋሚ መሞከራ አስፈላጊ ስለነበረ ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ጊዜ ተሞክሮ ተመሳሳይ ውጤት መታየቱን ወ/ሮ ፍትፍቴ አረጋግጠዋል። ነገር ግን በውሃ አካላት ላይ የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው መሆኑን ለማረጋገጥ መድኃኒቱ ሌላ ቦታ ላይ መሞከር ነበረበት። በመሆኑም አሳዎች ላይ ጉዳት አለማምጣቱን ለማረጋገጥ በባሕርዳር አሳ ምርምር ተቋም ውስጥ ተሞክሮ "በአሳዎቹ ላይ በተደረገ ክትትል ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም" በማለት መስክረዋል። "በአሳዎች ላይ የተሞከረውን መድኃኒት ግማሹን በመውሰድም እራሴ ምርምር በማደርግበት ማዕከል ውስጥ ባለ እንቦጭ ላይ ስሞክረውም አረሙን አድርቆታል" በማለት ለአራተኛ ጊዜ ውጤቱን ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል። መድኃኒቱ ከምን እንደተቀመመ አላውቅም፤ አረሙን ግን እንዳደርቀው አረጋግጫለሁ ያሉት ወ/ሮ ፍትፍቴ "ያየሁትን አረጋግጬ ለትምህርት ክፍሌ ሪፖርት ጽፌያለሁ።" ጥያቄ በ"መድኃኒቱ" ላይ ይህንን ተከትሎም የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክትር ለመሪጌታ በላይ አዳሙ ስለሥራቸው ውጤት የማረጋገጫ ደብዳቤ መጻፉንም ገልጸዋል። ነገር ግን በአማራ ክልል የጣናና የሌሎች የውሃ አካላት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አያሌው ወንዴ (ዶ/ር) ግን ይህንን የማረጋገጫ ደብዳቤ አይቀበሉትም። "ይህ በግለሰብ ደረጃ የተሰጠ አስተያየት እንጂ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ተካተው እና ሳይንሳዊ መንገድን ተከትሎ የተረጋገጠ ነገር አይደለም" ይላሉ። ቀደም ሲል መሪጌታ በላይ መድኃኒቱን እንዳገኙ ወደ እርሳቸው ቢሮ እንደሄዱ የሚገልጹት አያሌው ወንዴ (ዶ/ር)፤ የተባለውን መድኃኒትም "ከአንድ ዓመት በፊት ሙከራ አድርገንበት ውጤት አላየንበትም" ብለዋል። መሪርጌታ በላይ ይህንን በተመለከተ "ሙከራውን ብናደርግም በተቋሙ ውስጥ ባሉ ኃላፊዎች የተሰጠኝ ምላሽ አንድ ጊዜ አይሰራም፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይሰራል የሚል ነበር። በመሆኑም ሁኔታው ስላላስደሰተኝ ግንኙነቴ ተቋርቷል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በተጨማሪም መሪጌታ በላይ የሚያነሱት ጉዳይ ሥራቸውን ባቀረቡበት ጊዜ የጣናና ሌሎች የውሃ አካላት ባለስልጣን መድኃኒቱ የተቀመመበትን የእጽዋት ዝርዝር ካላወቅን አንሞክረውም መባላቸውን አንስተዋል። ይህንንም በተመለከተ አያሌው (ዶ/ር) ትክክል መሆኑን ጠቅሰው፤ እንዳሉትም መድኃኒቱ ከዕጽዋት እንደተሰራ በቃል መነገሩ ብቻ ብቁ አያደርገውም በማለት "በውሃ አካላት ላይም ሆነ በራሱ በሐይቁ ላይ ጉዳት የማያደርስ መሆኑን አይተን ማረጋገጥ ስለነበረብን ምንነቱን ጠይቀናል" ብለዋል። በወቅቱ እርሳቸውም ዕጽዋቱን ለማሳየት ፍቃደኛ እንዳልነበሩ የገለጹት መሪጌታ በላይ፣ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ "በአሁኑ ወቅት የአዕምሯዊ መብት ባለቤትነቴን ስላረጋገጥኩ በማንኛውም ሰዓትና ቦታ ለመሞከርም ሆነ መድኃኒቱ የተቀመመበትን እጽዋት ለማሳየት ፈቃደኛ ነኝ" ብለዋል። አያሌውም (ዶ/ር) ማንም ቢሆን መፍትሄ አለኝ የሚል ካለ ለመቀበል ተቋማቸው ዝግጁ መሆኑን ገልጸው፤ መሪጌታ በላይም "የተለየና መፍትሔ የሚያመጣ ነገር ሰርተው ከሆነ እናስተናግዳቸዋለን" ብለዋል። እምቦጭ አረም በጣና ሐይቅ ላይ ምን ያህል እየተስፋፋ ነው? ሙከራና ውዝግብ በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም መርጌታ በላይ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ጋር ለመስራት "መድኃኒቱን" ይዘው በመሄድ በዩኒቨርስቲው የሐዲስ አለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው አንዳርጌ ገልጸዋል። እሳቸው እንደሚሉት መሪጌታ በላይ አዳሙ አረሙን ያስወግዳል ያሉት "መድኃኒት" እንዲሞከርላቸው ዩንቨርሲቲውን በደብዳቤ ጠይቀው፤ የሐዲስ አለማየሁ የባሕል ጥናት ተቋም የተለያዩ ሙያተኞችን በማዋቀር ሙከራውን መሪጌታ በላይ ባሉበት ማካሄዱን አስታውሰዋል። ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 6/2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት አካባቢ በተመረጠ አንድ ስፍራ በሚገኝ የእንቦጭ አረም ላይ ግለሰቡ ያዘጋጁት 25 ሊትር "መድኃኒት" በመርጨት መከራ መደረጉን አቶ ግዛቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ጊዜም ሙከራው የተደረገበት ቦታ ከምንም ነገር ንክኪ ነጻ መሆን ስለነበረበት ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ስፍራውን የሚከታተል ጥበቃ ተመድቦ እንደነበና ከሙከራው በኋላ የተገኘ ውጤት ካለ ለመመልከት ወደ ቦታው ሲኬድ ግን "ምንም ለውጥ አላየንም" ሲሉ ገልጸዋል። "መድኃኒቱ" በተሞከረበት ወቅት የነበሩት መሪጌታ በላይ ግን የተገኘውን ውጤት ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር እንዲመለከቱ ቢጋበዙም ሳይሳተፉ መቅረታቸውን አቶ ግዛቸው ጠቅሰው፤ በቀጣይም ከዩኒቨርሲቲው ጋር ግንኙነታቸው ሙሉ ለሙሉ አቋርተዋል ብለዋል። መሪጌታ በላይ ግን ከዩንቨርሲቲው ሙያተኞች ጋር ወደ ሙከራው ስፍራ ማምራታቸውን ቢገልጹም በተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ "የመድኃኒቱን" ሙከራ ግን እንዳላካሄዱ ገልጸዋል። "ወደ ስፍራው ሂደናል፤ ነገር ግን የመሞከሪያ ገንዳ፣ አጥር እና ጥበቃ የተደረገለት ቦታ ባለመኖሩ መድኃኒቴን አላስሞክርም ብዬ ትቼ ተመልሻለሁ" በማለት የአቶ ግዛቸውን ማብራሪያ አስተባብለዋል። ተሞክሮ ውጤት አልተገኘበትም ስለተባለው መድኃኒትም "የራሳቸውን መድኃኒት ካልሆነ በስተቀር የእኔን አልሞከርንም" ብለዋል። እምቦጭን የሚያጠፋ መፍትሔ ለማግኘት ምርምር በሚያደርጉበትና ደረስኩበት ያሉን ውጤትም በሚያዘጋጁበት ጊዜ "ለመድኃኒቱ የሚሆን እጽዋት በበቂ ሁኔታ በአገር ውስጥ መኖሩን የዳሰሳ ጥናት አድርጌያለሁ" በማለት በቂ ግብአት እንዳለ መሪጌታ በላይ ይናገራሉ። ስለዚህም ባዘጋጁት "መድኃኒት" እና ባለው የእጽዋትም ግብአት የጣና ሐይቅን ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ከእንቦጭ አረም ማጽዳት ይቻላል ብለው ያምናሉ። ተመሳሳይ ችግር ያለባቸውን ሌሎች ሐይቆችን ደግሞ እጽዋቱን በማልማት "መድኃኒቱን" በመቀመም ማጽዳት ይቻላል ብለዋል። ጣና ሐይቅ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ፈተናዎች እየገጠሙት ነው የተመዘገበው "መድኃኒት" ይህ ያዘጋጁት ጸረ እምቦጭ "መድኃኒት" በፈሳሽና በዱቄት መልክ የተዘጋጀ መሆኑን የሚጠቅሱት መሪጌታ በላይ፤ ፈሳሹን በሊትር ከ30 እስከ 50 ብር ለመሸጥ እንዳቀዱና አንድ ሊትሩ 3 ሜትር በ3 ሜትር የሆነ በአረም የተወረረር ቦታን ሊሸፍን እንደሚችል ይገምታሉ። "የመድኃኒቱን ሙከራ ለሰባት ዓመታት ያህል በአባይ፣ ቆቃ እና ጣና አካባቢዎች አስፈላጊውን ሂደት ጠብቄ አከናውኛለሁ" የሚሉት መሪታጌ በላይ "የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብት የተሰጠኝ እኔ ያቀረብኩትን መረጃ በመቀበልና በሌላ አካል ያልተሰራ አዲስ ግኝት መሆኑን በማረጋገጥ ነው" ነው ሲሉ ሥራቸው በስማቸው መመዝገቡን ይናገራሉ። በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት የፓተንት መርማሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ጣፋ ለቢቢሲ እንደገለጹት የመሪጌታ አዳሙን የእምቦጭ አረም ማጥፊያ "መፈድኃኒትን" በአነስተኛ የፈጠራ ዘርፍ ማረጋገጫ እንደተሰጠ ገልጸው፤ ይህም "በኢትዮጵያ ደረጃ አዲስ መሆኑን እና ጥቅም ሰጪ መሆኑን የሚያረጋገጥ" ነው ብለውናል። ከዚህ በፊት የቀረበ ተመሳሳይ የምርምር ውጤት አለመኖሩን በማረጋገጥ ለመሪጌታ በላይ ማረጋገጫውን እንደሰጡ የተናገሩት አቶ ጌታቸው፤ ይህም "የቅድመ ምርምር ማረጋገጫ ነው" ብለውታል። የተሰጠው ማረጋገጫም "መድኃኒቱ" በቀጥታ ውሃ ላይ ወይም የትም ቦታ ላይ እንዲሞከር የማያረጋግጥ መሆኑን አስረድተዋል። ጽህፈት ቤቱ "መድኃኒቱን" በተመለከተ ቀደም ሲል በባሕርዳርና በሌሎች ቦታዎች ላይ የተደረገውን ምርምር የያዘ ጥቅል የጽሁፍ ሰነድ እና በምርምሩ ወቅት የተከተሉትን ሂደት በመገምገም ማረጋገጫውን እንደሰጠ አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ነገር ግን "ይህ ማረጋገጫ የተሰጠው ምርምሩ የእርሳቸው ንብረት መሆኑን ለማረጋገጥ እንጂ፣ አገልግሎት ላይ እንዲውል እውቅ የሚሰጥ አይደለም" ያሉት አቶ ጌታቸው፤ በቀጣይነት "የመድኃኒቱን" አጠቃቀም እና የጎንዮሽ ጉዳት ሊያረጋግጡ የሚችሉት የአካባቢ ጥበቃ እና ጤና ጥበቃን የመሳሰሉት ተቋማት መሆናቸውን አስረድተዋል። ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ከቀናት በፊት "መድኃኒቱን" በሚመለከት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በመሪጌታ በላይ አዳሙ ለሙከራ የተዘጋጀው የእምቦጭ አረም ማጥፊያ "መድኃኒት" ላይ የውሳኔ ሐሳብ እንዳልሰጠ አመልክቷል። ጨምሮም "መድኃኒቱ በአነስተኛ ደረጃ አረሙን ማጥፋት ቢችልም የጎንዮሽ ጉዳቱ በሳይንስናዊ ምርመራ አልተረጋገጠም" በማለት "በመድኃኒቱ" ላይ የቤተሙከራ ሥራ ለማከናወን መሪጌታ በላይ ተቀራርቦ ለመሥራት የሚያስችል ዕድል አልሰጡም ሲል ገልጿል።
49192266
https://www.bbc.com/amharic/49192266
ለዓመታት የተጠፋፉት የወላይታ ሶዶዋ እናትና የኖርዝ ኬሮላይናዋ ልጃቸው
አማረች ከበደ እባላለሁ። 20 ዓመቴ ነው። አሁን የምኖረው ኖርዝ ኬሮላይና፤ የተወለድኩት ደግሞ ወላይታ ሶዶ።
አማረች ከዓመታት በኋላ ከእናቷ ጋር ስትገናኝ ስለ ልጅነት ሕይወቴ ልንገርሽ. . . ሁለት ታላላቅ ወንድም እና አንድ ታናሽ እህት አለኝ። እህቴ አስቴር ትባላለች። ወላጅ አባታችን ብዙም በሕይወታችን ስላልነበረ አቅመ ደካማ እናቴ ብቻዋን አራት ልጆች ለማሳደግ ትንገታገት ነበር። እናቴ ቤተሰባችንን ለማስተዳደር ብዙ ውጣ ውረድ አይታለች። ከእኛ ከልጆቿ ውጪ አንዳችም አጋዥ አልነበራትም። ገበያ ወጥቼ አትክልት እገዛና አትርፈን እንሸጠዋለን። ያገኘሁትን ብር ለቃቅሜ ወደ ቤተሰቦቼ እሮጣለሁ። • "በኤችአይቪ የምሞት መስሎኝ ልጄን ለጉዲፈቻ ሰጠሁ" ያኔ እንደ ሌሎች የሰፈራችን ህጻናት አልጫወትም። [እቃቃ. . . ሱዚ. . . ቃጤ. . . የሚባል ነገር የለም]። በልጅ ጫንቃዬ ቤተሰብ የመደገፍ ኃላፊነት ወደቀብኝ። ታናሽ እህቴን የምንከባከበው እኔ ነበርኩ። እናቴ ስትሠራ እኔ አስቴርን ስለምይዝ ትምህርት ቤት መሄድ አልቻልኩም። በዚህ በኩል እህቴን መንከባከብ በሌላው እናቴን መርዳት. . . አሁን ሳስበው ይህ ሁሉ ለልጅ በጣም ይከብዳል። ከታላቅ ወንድሞቼ አንዱ አይነ ስውር ነው። ከሁላችንም በበለጠ የእሷን ትኩረት ይፈልግ ነበር። ልዩ እንክብካቤና ድጋፍ ስለሚያሻው አብዛኛውን ጊዜዋን ትሰጠዋለች። የሚያስፈልገውን ሁሉ ማሟላት ነበረባትና እናቴ ጫናው በረታባት። ልክ 11 ዓመት ሲሆነኝ ነገሮች እየተባባሱ መጡ። ያኔ አስቴር አምስት ዓመት ሞልቷት ነበር። በቃ! እናቴ እኛን ማሳደግ በጣም ከበዳት. . . እሷ ልትሰጠን ያልቻለችውን ነገር ሁላ እያገኘን እንድናድግ ትፈልግ ነበር። እኔና አስቴር የተሻለ ሕይወት እንዲኖረን ተመኘች። እዚያው ወላይታ ሶዶ የሚገኝ ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ አስገባችን። እኔና እህቴ ከእናታችንና ከወንድሞቻችን ተለያየን! ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ ያለ ፍቅር ስለኖርኩበት ጊዜ ላጫውትሽ. . . በወላይታ ሶዶ የህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ ከቆየን በኋላ አዲስ አበባ ወደሚገኝ ሌላ ማሳደጊያ ተወሰድን፤ ሦሰት ወር ቆይተናል። በህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ መኖር የመተው ስሜት እንዲሰማሽ ያደርገል። እዚያ ፍቅር የለም። ሁላችንም ድርጅቱ ውስጥ የተገኘነው በማደጎ ለመወሰድ ነው። ሞግዚቶቹም ሆኑ ሠራተኞቹ አይወዱንም። ፍቅር የሚሰጥሽ ሰው የሌለበት ቦታ መኖርን አስቢው. . . እኔና እህቴ ከአንድ ዓመት በላይ ማሳደጊያው ውስጥ ኖርን። • ከ43 ዓመት በኋላ የተገናኙት ኢትዮጵያዊ እናትና ስዊድናዊ ልጅ 2010 [በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር] ላይ የሪችመንድ ቤተሰብ የጉዲፈቻ ልጅ ፍለጋ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ አቀኑ። ያኔ ወደ ድርጅቱ ሲመጡ ወደ አሜሪካ ሊወስዱን እንዳሰቡ አላወኩም። አዲስ አበባ ውስጥ የቆዩት ለአምስት ቀናት ነበር። ወደ አሜሪካ ለመብረር አንድ ቀን ሲቀረን የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ ሆነን ወዴት እንደምንሄድ፣ ለምን እንደምንሄድ ገባኝ። ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም፤ ማልቀስ ጀመርኩ። ቤተሰቤን፣ አገሬን፣ የማውቀውን ነገር በሙሉ ጥዬ ልሄድ እንደሆነ የታወቀኝ በመጨረሻው ቀን ነበር። ያን ቀን በጣም ስሜታዊ ሆኜ ነበር። የእኔ ከሚሉት ነገር ተለይቶ፤ ወደማይታወቅ ዓለም መጓዝ እንዴት አያሳዝን፣ እንዴት አያስፈራ? አማረች፣ አስቴር እና የጉዲፈቻ ቤተሰቦቻቸው አሜሪካ ገባን. . . የጉዲፈቻ ቤተሰቦቼ ሦስት ልጆች አሏቸው። ሁለት ወንድና አንድ ሴት። እኔና አስቴር አዲሱን ቤተሰባችንን ተቀላቀልን ማለት ነው። በመጀመሪያዎቹ ወራት እኔና እህቴ ስላየናቸው አዳዲስ ነገሮች እናወራ ነበር። ለሁለታችንም ትልቅ ለውጥ ነበር። እንዲያውም ለተወሰነ ጊዜ የጫጉላ ሽርሽር ላይ እንዳሉ ሰዎች ሆንን። አሜሪካን ወደድናት። ከተወሰኑ ወራት በኋላ ግን ሁሉም ነገር አስጠላኝ። ወደ አገሬ፣ ወደ ቤቴ መመለስ ፈለግኩ። ደፍሬ ባልናገረውም አዕምሮዬ ውስጥ የሚመላለሰው የቤተሰቦቼ ጉዳይ ነበር። እናቴ ናፈቀችኝ፤ ወንድሞቼ ናፈቁኝ፤ አገሬ ናፈቀኝ። የማውቀውን ሕይወት፣ የማውቀውን ሰው፣ የለመድኩትን ምግብ መልሶ ማግኘት ብቻ ነበር የምፈልገው። ኑሮ አልገፋ አለኝ፤ መላመድ አቃተኝ። አስቴር ትንሽ ልጅ ስለነበረች እንደእኔ አልተቸገረችም፤ በቀላሉ ከአሜሪካዊ አኗኗር ጋር ተላመደች። ኢትዮጵያ ስላሉት ቤተሰቦቻችን ብዙ ትውስታ ስላልነበራት አዲሱን ሕይወት ማጣጣም ጀመረች። እኔ ግን ተረበሽኩ። • የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ ትምህርት ቤት ስገባም ጓደኛ ማፍራት አልቻልኩም። ክፍል ውስጥ የነበሩት ልጆች እርስ በእርስ ይተዋወቃሉ። ባይተዋርነት ተሰማኝ። በዚያ ላይ እንግሊዘኛ አልችልም። እንዴት ከልጆቹ ጋር ልግባባ? እንደ ልጅ ሳልጫወት ማደጌን ነግሬሽ የለ? እናም እነሱ በእረፍት ሰዓት ሲጫወቱ ግራ ገባኝ። ኢትዮጵያ ሳድግ ከቤት ወጥቼ የምጫወትበት ጊዜ አልነበረኝም። ከእድሜዬ በላይ ብዙ ኃላፊነቶች ነበሩብኝ። ታዲያ አሜሪካ ስመጣ እንዴት ልጅ መሆን እንዳለብኝ ማወቅ አልቻልኩም። ጨዋታ መልመድ፣ ልጅነትን መማር ነበረብኝ። አማረች እና እህቷ የጉዲፈቻ ልጆችን ጓደኛ አደረኩ ወደሚናፍቀኝ ሕይወት መቼ እንደምመለስ አለማወቄ ይረብሸኝ ነበር። አሜሪካ ያለው ነገር ሊማርከኝ አልቻለም። ምኑም ምኑም! ሕይወትን በመጠኑ ያቀለለልኝ እንደኔው በጉዲፈቻ ወደ አሜሪካ የመጡ ጓደኞች ማፍራቴ ነው። እነዚህ ልጆች ኢትዮጵያ ሳለሁ ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ አብረውኝ ኖረዋል። እናም ጓደኞቼ አሜሪካ እንዳሉና ላገኛቸው እንደምፈልግ ለጉዲፈቻ ቤተሰቦቼ ነገርኳቸው። እኔና እህቴን ወደ አሜሪካ ያመጣን ኤጀንሲ ስልክ ቁጥራቸውን እና የኢሜል አድራሻቸውን ሰጠን። • ዓለም አቀፍ ጉዲፈቻን ማገድ አዋጭ ነው? ከሦስቱ ጓደኞቼ ጋር ዘወትር በስልክ እናወራ፣ እንገናኝም ነበር። ሁላችንንም በተመሳሳይ ነገር ውስጥ እያለፍን ስለነበረ እንግባባለን። አንዳችን ከሌላችን ምን መስማት እንደምንፈልግ እናውቃለን። ዝም ብለን እናወራለን. . . እናወራለን. . . እናወራለን. . . ስቃዩን በወሬ አስተነፈስነው። ወሬያችን እንዴት እንደረዳኝ ልነግርሽ አልችልም። የአሜሪካን ሕይወት ለመላመድ ድፍን አራት ዓመት ወስዶብኛል። ታናሽ እህቴ አብራኝ ባትሆን ኖሮ ምን እንደማደርግ አላውቅም። እዚ ያለችኝ ብቸኛ የሥጋ ዘመዴ ናት። አብሬያት ማደጌን እወደዋለሁ። ታናሼ ስታድግ፣ ስትመነደግ በቅርብ ማየት ደስ ይለኛል። ምን ይናፍቀኝ እንደነበረ ልንገርሽ. . . ከወንድሞቼ ጋር ብዙ አሳልፈናል። ታሪካችንን መልሶ መላልሶ ማሰብ ያስደስተኛል። ትውስ የሚለኝን ለእህቴ አወራላታለሁ። ትዝታዬን ለእሷ ማካፈል ታሪኬን መዝግቤ የማቆይበት መንገድ ነበር። ከምንም በላይ ምን ይናፍቀኝ እንደነበረ ታውቂያለሽ? ከእናቴ ጋር የነበረን ግንኙነት። በጣም እንቀራረብ ነበር። ሁሉንም ነገር አብረን እናደርጋለን። እንደሚዋደዱ ጓደኛሞች ነበርን. . . እናቴን ሳላይ መኖር በጣም ከበደኝ። አማረች ከወንድሞቿ እና ከእናቷ ጋር ስትገናኝ በወንድሞቼ ሕይወት ውስጥ ቁልፍ የሚባሉ ክንውኖች እያመለጡኝ መሆኑ ውስጤን አደማው። ወንድሜ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሲጨርስ. . . ታላቄ ከኮሌጅ ሲመረቅ እኔ አልነበርኩም። አሜሪካ ሆኜ ብዙ ውብ ቅጽበቶች እያለፉኝ መሆኑ እረፍት ነሳኝ። አብሬያቸው መሆን ባለብኝ ቁልፍ ወቅት ተለየኋቸው! በጄ አላልኳቸውም እንጂ፤ የጉዲፈቻ ወንድሞቼና እህቴ ሊቀርቡኝ ይሞክሩ ነበር። ልቀርባቸው፣ ልቀበላቸው ዝግጁ አልነበርኩም። አፍቃሪ እና ተግባቢ ነበሩ። ፍቅራቸውን በፍቅር መመለስ ግን አልቻልኩም። ፍቅሬን ኢትዮጵያ ላለው ቤተሰቤ መቆጠብ እንዳለብኝ ይሰማኝ ነበር። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ ያኔ ላቀርባቸው ያልቻልኩት የመተው ስሜት ይሰማኝ ስለነበረ ይመስለኛል። ማንም እንዲጠጋኝ አልፈልግም። ስሜቱ በህጻናት ማሳደጊያ ከዓመት በላይ ከመቆየት የመነጨ ይመስለኛል። የጉዲፈቻ ቤተሰቦቼ ይወዱኛል። እኔ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቼን እወዳቸዋለሁ። እናቴና ወንድሞቼን ትቻቸው አሜሪካ ስለሄድኩ ሌላ አዲስ ፍቅር አልፈለኩም። ለአዲስ ፍቅር ቦታ አልነበረኝም። ቤተሰቤን መፈለግ ጀመርኩ. . . እኔ እና እህቴ ወደ አሜሪካ የተወሰድነው በ 'ክሎዝድ አዶፕሽን' ነበር። [ይህ ማለት በጉዲፈቻ የሚወሰዱ ልጆችና የጉዲፈቻ ቤተሰቦቻቸው ስለ ልጆቹ ወላጆች መረጃ አይሰጣቸውም።] ከኢትዮጵያ ከወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ቤተሰቦቼ ምንም መረጃ ማግኘት አልቻልኩም። 2011 ላይ እናቴ አንድ ሪፖርት ደርሷታል። ሪፖርቱ ከጉዲፈቻ በኋላ ለወላጆች የሚሰጥ ነው። እና በሪፖርቱ የእኔ እና የእህቴ ፎቶ ለእናቴ ተሰጥቷታል። 2012 ላይ እኔ እና እህቴን ከጉዲፈቻ ቤተሰቦቻችን ጋር ያገናኘን ኤጀንሲ ተዘጋ። ስለ ቤተሰቦቼ ማንን ልጠይቅ? ስለእነሱ ምንም ሳልሰማ ስድስት ዓመታት ተቆጠሩ። ብቸኛ አማራጬ ፌስቡክ ላይ መፈለግ ሆነ። ግን ምንም ላገኝ አልቻልኩም። • ኮሎኔል መንግሥቱ ለህፃናት አምባ ልጆች ደብዳቤ ላኩ በሕይወት መኖራቸውን፣ ደህና መሆናቸውን ማወቅ አለመቻሌ ያስጨንቀኝ ነበር። አለቅስ ነበር። ስለቤተሰቦቼ ማሰብ ማቆም ስላልቻልኩ ፍለጋዬ ፍሬ ባያፈራም ገፋሁበት። እንደው አንድ ቀን ኢንተርኔት ላይ አገኛቸዋለሁ የሚል ህልም ነበረኝ። በስተመጨሻ ግን ተስፋ መቁረጥ ጀመርኩ. . . ቤተሰቦቼን ማግኘት እንደምፈልግ ለጉዲፈቻ ቤተሰቦቼ ነገርኳቸው። ቤተሰቤን ሳላገኝ መኖር አልችልም አልኳቸው። የጉዲፈቻ አባቴ 18 ዓመት ሲሞላኝ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚወስደኝና ቤተሰቦቼን እንደምንፈልጋቸው ቃል ገባልኝ። ግን ከ18ኛ ዓመት ልደቴ በፊት ሕይወቴን የለወጠ ዜና ደረሰኝ። ለካ እናቴም እኔ እና እህቴን እየፈለገችን ነበር አንድ ቀን 'መላው ቤተሰብ ይሰብሰብ' ተባለ። የጉዲፈቻ ቤተሰቦቼ ሁላችንንም አንድ ላይ አድርገው 'አስደሳች ዜና አለን' አሉ። እናቴ እኔና አስቴርን እያፈላለገችን እንደሆነ ነገሩን። እናቴ የጉደፈቻ ሪፖርቱ ሲቋረጥባት እኛን መፈለግ ጀምራ ነበር። ወላይታ ሶዶ ውስጥ ለምትገኝ አንዲት ማኅበራዊ ሠራተኛ ስለእኛ ነገረቻት። ፎቷችንን ሰጠቻት። ቅጽል ስሜ አያኔ መሆኑን፣ ጀርባዬ ላይ 'ማርያም የሳመችኝ' ምልክቱ እንዳለ ሳይቀር አውርታላታለች. . . ያላትን መረጃ ባጠቃላይ ዘረገፈችላት ብልሽ ይቀለኛል. . . ማኅበራዊ ሠራተኛዋ 'ቤተሰብ ፍለጋ' በሚባል ድርጀት በኩል የጉዲፈቻ ቤተሰቦቼን አገኘቻቸው። ይሄ ሀሉ ሲነገረኝ የደስታ ሲቃ ተናነቀኝ። በጣም ደንግጬም ነበር። እኔ ለዓመታት ስፈልጋቸው ነበር። ታዲያ እንዴት እኔ ሳላገኛቸው ቀድመው አገኙኝ? ያልጠበቅኩት ነገር ነበር። አማረች፣ እናቷ እና ታላቅ ወንድሟ ቀጥሎ ምን እናድርግ? ደብዳቤ እንጻፍ? ጥያቄዬን ማከታተሉን ተያያዝኩት. . . እህቴም ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ተጋብታ ነበር። ዝም ብላ እኔን ትከተል ጀመር። ከዚያም ደብዳቤ ጽፈን ለቤተሰቦቼ ላክልናቸው። ከሁለት ሳምንት በኋላ ፎቶና ቪድዮ ላኩልን። በዚያ ቅጽበት ሕይወቴ እስከወዲያኛው ተቀየረ። ከቤተሰቦቼ ጋር ከተገናኘሁ ስምንት ዓመት ተቆጥሮ ነበር። እናቴ እና ታላላቅ ወንድሞቼን ስፈልጋቸው እነሱም እየፈለጉኝ ነበር። እኔንም አስቴርንም። አድራሻቸውን ካገኘሁ በኋላ ያለማቋረጥ ማውራት ጀመርን። ወደ ሶዶ ተመለስኩ. . . ባለፈው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ለመብረር ትኬት ቆረጥኩ። እህቴ 'ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ዝግጁ አይደለሁም' ስላለቺኝ የሄድኩት ብቻዬን ነበር። ልክ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ስደርስ በጣም ተጨነቅኩ። ታላቅ ወንድሜ መጥቶ እጄን ቢይዘኝ ተመኘሁ. . . አይገርምም መጀመሪያ ያገኘሁት እሱን ነበር። አቅፎኝ ሊለቀኝ መሰለሽ? አዲስ አበባ ውስጥ በቆየንባቸው ቀናት እጄን ይዞ ነበር የሚንቀሳቀሰው፤ አለቀቀኝም። እንደ ልጅነታችን ዳግመኛ ተሳሰርን። ከዚያ ወደ ሶዶ ሄድን። እናቴን ሳያት ዝም ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ፤ እሷም አለቀሰች። የደስታ እንባ አነባን። ከአምስት ደቂቃ በላይ ሳንላቀቅ ተቃቅፈናል። እናቴ ስማኝ ልትጠግብ አልቻለችም። እውነት እውነት አልመስልሽ አለኝ. . . ሁሉም ነገር እንደ ድሮው ተመለሰ። የማውቃቸውን ቤተሰቦቼን አገኘሁ። ሶዶ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ስልም እንግዳ የሆንኩ አልመሰለኝም። ሦስት ሳምንትን አሳለፍኩ። በጉዲፈቻ ባልሰጥ ኖሮ ሕይወቴ ምን ሊመስል እንደሚችል ከእናቴ ጋር አወራን። እኔ እና እህቴን ለጉዲፈቻ መስጠቷ እንደማይጸጽታት ነግራኛለች። እውነት ነው በሕይወቷ ካደረገቻቸው ነገሮች ከባዱ እኛን ለማደጎ መስጠት ነበር። ቢሆንም 'ለጉዲፈቻ የሰጠኋችሁ ያለ ምክንያት አይደለም፤ እንደዚህ በችግር እንድትኖሩ አልፈልግም' አለችኝ። በእርግጥ ኤጀንሲው ተዘግቶ እኛን ለማግኘት ስትቸገር ለጉዲፈቻ በመስጠቷ ተጸጽታ ነበር። ልጆቿ እንዴት እየኖሩ እንደሆነ ማወቅ ባለመቻሏ ለሳምንታት እንዳለቀሰች፣ በጣም እንደተጎዳችም ጓደኛዋ ነገረችኝ። እናቴ እንደእኔው እየተሰቃየች እንደነበር ማወቄ ልቤን ሰብሮታል። ለእኔ አሜሪካ መኖር ጥሩ ነው። ቁሳዊ ነገር አላጣሁም። ቤተሰብን ግን አይተካም። የሆነ ነገር እንደጎደለኝ ይሰማኝ ነበር። ለካ እናቴም እንደኔው ነበረች. . . አሁንማ ሕይወቴ ውብ ነው አሁን የመጀመሪያ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ ነኝ። ቢዝነስ እያጠናሁ ነው። የጉዲፈቻ ቤተሰቦቼን በጣም እወዳቸዋለሁ። እውነቱን ለመናገር ከእነሱ ጋር ለመላመድ ጊዜ ወስዶብኛል። የማያውቁትን ሰው እማዬ፣ አባዬ፣ እህት ዓለም ወንድም ዓለም ማለት ከባድ መሆኑን አልክድም። ግንኙነታችንን ለመገንባት ጊዜ ቢወስድብንም አሁን ቤተሰብ ነን። • የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች እናቴ እኔን እና እህቴን ለማደጎ መስጠቷ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብዬ አስባለሁ። ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ ሕይወት ቢከብደኝም. . . እናቴን ተረድቻታለሁ። በጉዲፈቻ ባትሰጠኝ ኖሮ ብዙ መከራ ይጠብቀኝ ነበር። ከጉዲፈቻ ወንድሞቼ እና ከእህቴ ጋር እንቀራረባለን። ኢትዮጵያ ካሉት ወንድሞቼ ጋርም እንዲሁ። ወንድሞቼን ሳዋራቸው የሆነ ጉልበት አገኛለሁ። ምንም ነገር ላሳካ እንደምችል ይሰማኛል። ያበረቱኛል። ያጠነክሩኛል። ምን እንደማስብ ታውቂያለሽ? ምናልባትም የጉዲፈቻ ልጅ ያልሆነ ሰው ይሄ አይገባው ይሆንል. . . የጉዲፈቻ ልጆች ስለ ወላጆቻቸው ማወቅ አለባቸው። 'ማንን ነው የምመስለው?' 'ከየት መጣሁ?' እያሉ ሕይወትን መግፋት የለባቸውም። በጥያቄ መሞላት፣ በናፍቆት መማቀቅ የለባቸውም። ቤተሰቦቼን ካገኘኋቸው በኋላ ሕይወቴ ተቀይሯል። ደስተኛ ሰው ሆኛለሁ። አሁን የማስበው ዲግሪዬን አግኝቼ ጥሩ ሥራ ስለመያዝ ነው። ያለፈ ሕይወቴ ጥያቄዎች ስለተመለሱ ስለ ወደፊቴ ማሰብ እችላለሁ።
news-53713057
https://www.bbc.com/amharic/news-53713057
አፍጋኒስታን፡ ምክር ቤቱ 400 የታሊባን እስረኞችን ለመፍታት ወሰነ
የአፍጋኒስታን ከፍተኛ ምክር ቤት ከባድ ወንጀሎችን በመፈፀም ተከሰው የነበሩ 400 የታሊባን እስረኞችን ለመፍታት የቀረበውን ሃሳብ አፀደቀ።
ሎያ ጂርጋ ተብሎ የሚጠራው ምክር ቤት ውሳኔው የተላለፈው የሰላም ድርድር እንዲጀመር ለማስቻል እንደሆነ አስታውቋል። አሜሪካ በአገሪቷ ያለው ወታደሮቿ ቁጥር በመጭው ሕዳር ወር ከ5 ሺህ በታች እንደሚሆን ካስታወቀች በኋላ ታሊባን በአፍጋኒስታንና በውጭ ዜጎች ላይ ጥቃት መፈፀምን ጨምሮ በሌሎች ወንጀሎች የተከሰሱ እስረኞቹ እንዲፈቱለት ሲጠይቅ ነበር። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይም አሜሪካና ታሊባን ለ19 ዓመታት የዘለቀውን ግጭት ለመፍታት የሰላም ስምምነት ለማካሄድ መስማማታቸው ይታወሳል። የአሜሪካና የታሊባን አደራዳረዎችም ከአፍጋኒስታን መንግሥት ጋር ወደሚያደርጉት የሰላም ድርድር ከመግባታቸው በፊት 5 ሺህ የታሊባን እስረኞች እንዲፈቱ ተስማምተው ነበር። በዚህም መሠረት በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች የተፈቱ ሲሆን የቀሩት 400 እስረኞች ብቻ ነበሩ። ከእነዚህ መካከል 150 የሚሆኑት የሞት ፍርድ የሚጠባባቁ መሆናቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል። ምክር ቤቱም እነዚህ እስረኞች እንዲፈቱ የወሰነው "የሚደረገውን የሰላም ስምምነት ሂደት ለመጀመርና እንቅፋቶቹን ለማስወገድ እንዲሁም ደም መፋሰሱን ለማስቆም" እንደሆነ ገልጿል። ውሳኔውም በፕሬዚደንት አሽራፍ ጋኒም ይፈረማል ተብሏል። በመንግሥትና በታሊባን መካከል የሚደረገው ድርድርም በሚቀጥለው ሳምንት ዶሃ እንደሚጀመር አንድ የምዕራቡ ዓለም ዲፕሎማት ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ይሁን እንጅ የእስረኞቹ መፈታት ጉዳይ በነዋሪዎችና በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ዘንድ አወዛጋቢ ሆኗል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ላለፉት 19 ዓመታት በዘለቀው ጦርነት ከ32 ሺህ በላይ ንፁሃን ዜጎች መሞታቸውን ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ የወጣ የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት አመልክቷል። ፕሬዚደንት አሽራፍ ጋኒም ከጎርጎሳውያኑ 2014 ጀምሮ ከ45 ሺህ በላይ የፀጥታ ኃይል አባላት መገደላቸውን በዚያው ዓመት ተናግረዋል። ታሊባን ከ19 ዓመታት በፊት ከሥልጣን የተወገደው የመስከረም አንዱን ጥቃት ተከትሎ በአሜሪካ በተመራ ወረራ ሲሆን ቡድኑ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ አሁን ላይ ተጨማሪ ግዛቶችን ለመቆጣጠር ቀስ በቀስ የቀድሞ ጥንካሬውን አግኝቷል። ቅዳሜ ዕለት የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ማርክ ቲ ኤስፐር በአፍጋኒስታን የሚኖራቸው ወታደሮች ቁጥር በመጭው ህዳር ወር ከ5 ሺህ ዝቅ እንደሚል ተናግረዋል። ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕም ህዳር ወር ላይ ከሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በፊት የወታደሮቹን ቁጥር ወደ 4 ሺህ ዝቅ ማድረግ እንደሚፈልጉ የተናገሩት ባለፈው ሳምንት ነበር።
news-46150597
https://www.bbc.com/amharic/news-46150597
የውልደት መጠን እጅጉኑ እየቀነሰ መሆኑ ታውቋል
ተመራማሪዎች እነሆ 'ጉደኛ ወሬ' ብለዋል፤ በዓለማችን የውልደት መጠን እጅግ በጣም እየመነመነ ነው። የት? ለምን? ትንታኔውን ለእኛ ተውት ይላሉ።
ግማሽ ያህል የዓለም ሃገራት አሁንም ከፍተኛ የሆነ የውልደት መጠን አላቸው ተመራማሪዎቹ ጥናት ካደረጉባቸው ሃገራት ገሚሱ የውልደት መጠናቸው ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀንሷል፤ ይህ ደግሞ የህዝብ ቁጥር ቀውስ ማምጣቱ አይቀሬ ነው። አጥኚዎቹ ውጤቱን 'አስደናቂ' ብለውታል፤ ማንም አልጠበቀውምና። ሌላው ውጤቱን አስደንጋጭ ያደረገው ነገር በእነዚህ ሃገራት መጭው ጊዜ በርካታ ወጣቶች ሳይሆን በቁጥር የበዙ አያቶች የምናይበት መሆኑ ነው። የሮቦት ነገር. . . ወዴት ወዴት? «የወሊድ መቆጣጠሪያን ወዲያ በሉት»፦ ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ላንሴት የተባለ መጽሔት ላይ የወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው በፈረንጆቹ 1950 የውልደት መጠን በአማካይ 4.7 የነበረ ሲሆን አሁን ግን ወደ 2.5 ወርዷል። ወደ አፍሪቃ ስንመጣ ግን ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ እናገኘዋለን። በምዕራብ አፍሪቃዋ ሃገር ኒጀር የውልደት መጠኑ 7.1 ነው፤ ወደ ቆጵሮስ ብናቀና ሴቶች በሕይወት ዘመናቸው በአማካይ የሚወልዱት አንድ ልጅ ነው። ግን ግን. . .'ትክክለኛው' የውልደት መጠን ስንት ነው? አውነት እኮ ነው፤ ትክክለኛው የውልደት መጠን ስንት ነው? እርግጥ ስህተት የሆነ የውልደት መጠን አለ እያልን አይደለም፤ እንደው ተመካሪው ለማለት እንጂ። በዚህ ጉዳይ ከእኛ በላይ ማን ሊቅ? የሚሉ ባለሙያዎች የውልደት መጠን ከ2.1 በታች የሆነ ጊዜ 'ችግር አለ' ይላሉ። ጥናቱ የጀመረው በፈረንጆቹ 1950 ገደማ ነው፤ አዎ! የዛሬ 70 ዓመት አካባቢ። ለዚህ ነው 'ኧረ ጎበዝ ጉደኛ ወሬ ይዘናል' ብለው ብቅ ያሉት። በፈረንጆቹ 1950 የውልደት መጠን በአማካይ 4.7 የነበረ ሲሆን አሁን ግን ወደ 2.5 ወርዷል ከአጥኚዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ክርስቶፈር መሪ «አሁን የደረስንበት ደረጃ አንዳንድ ሃገራት ትውልድ መተካት የማይችለቡት ደረጃ ላይ መድሳቸውን ያመለክታል» ይላሉ። «አስደናቂ እኮ ነው። ውጤቱ እኛ አጥኝዎችንም ጉድ በል. . .ያሰኘ ነው። በተለይ ደግሞ ከዓለም ህዝብ ግማሽ ያህሉ የትውልድ ቁጥር ማሽቆልቆል ሰለባ መሆኑ ዱብ ዕዳ ነው የሆነብን።» ለመሆኑ ሃገራቱ እነማን ናቸው. . .? ምጣኔ ሃብታቸው ጎልበቷል የተባለላቸው አውሮጳ ውስጥ ያሉ ሃገራት፤ አሜሪካ፤ ደቡብ ኮሪያና አውስትራሊያ የውልደት መጠናቸውን እያነሰ የመጡ ሃገራት ናቸው። ልብ ይበሉ፤ የእነዚህ ሃገራት የህዝብ ቁጥር ቀንሷል ማለት ግን አይደለም፤ መሰል ለውጦችን ማየት ቢያንስ የትውልድ ልውውጥን ያህል ጊዜ ይወስዳልና። «በቅርቡ የህዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል እንደ አንድ ትልቅ ችግር ሲነሳ መስማታችን አይቀርም» ሲሉ ፕሮፌሰር መሪ ይተነብያሉ። የማይካደው እውነታ ግማሽ ያህል የዓለም ሃገራት አሁንም ከፍተኛ የሆነ የውልደት መጠን አላቸው። ነገር ግን ዋናው ጉዳይ ወዲህ ነው፤ እኚህ ሃገራት በምጣኔ ሃብት እየጎለበቱ መምጣታቸው ስለማይቀር የውልደት ምጣኔያቸውን እየቀነሱ ይመጣሉ። ለምን. . .? አሁን ወደገለው እንግባ። ለምንድን ነው የውልደት መጠን እንዲህ 'በአስደንጋጭ' ሁኔታ የቀነሰው? አጥኚዎቹ ሦስት ወሳኝ ነጥቦችን ያስቀምጣሉ። ከላይ የተጠቀሱትን ምክንያቶች ለተመለከተ 'እና የውልደት መጠን መቀነሱ መልካም ዜና አይደል እንዴ?' ሊል ይችላል፤ ስህተትም የለውም። ሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነፃነታቸው ካልተከበረ የዕድሜ መግፋትና የህዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል የመጪው ጊዜ ራስምታቶች መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ዶ/ር ጆርጅ ለሰን ሰዎች ከለውጡ ጋር ራሳቸውን ማራመድ ከቻሉ ችግር አይሆንም ይላሉ። ምሁሩ ንግግራቸው ጠጠር ያለ ይመስላል፤ የምሁር ነገር። ቀለል ባለ አማርኛ የሰዎች የመንቀሳቀስ ነፃነት ከተጠበቀና ከጊዜው ጋር መራመድ ከቻልን ማለታቸው ነው። «ስነ-ህዝብ ሁሉንም የሚነካ ነው። እስቲ ወደ መስኮታችን ጠጋ ብለን ውጭውን እንመልከት። ሁሉም ነገር በፍጥነት ነው የሚንቀሳቀሰው፤ ግንባታው፣ መኪኖች፣ ትራፊኩ. . . ይህ ሁሉ ለውጥ የህዝብ ቁጥር መጨመር ያመጣው ነው። ከዚያም ባለፈ የዕድሜው ጉዳይም ትልቅ ተፅዕኖ አለው።» ምሁሩ ሁሉም ነገር ይቀየራል፤ መቀየሩም ግድ ነው ይላሉ። የስራ ቦታዎች መቀየር አለባቸው፤ የጡረታ ጊዜውንም አስቡበት (ይጨመር ማለታቸው ነው) ይላሉ ዶ/ር ለሰን። «ጃፖኖችን ተመልከቱ፤ ዕድሜው የሄደ ትውልድ ስጋት ይዟቸዋል። ወደምዕራብ ስትመጡ ግን ወደሃገራቱ የሌላ ሃገር ዜጎች ስለሚገቡ ይህ ስጋት ብዙ አይታይም።» ምንም እንኳ መሰል ለውጦችን መቀበል ቀላል ባይሆንም ጥቅሙ የላቀ ስለሚሆን መቀበል አዋጭ ነው፤ የምሁሩ ሃሳብ ነው። ቻይናም በ1950 ከነበራት ግማሽ ቢሊየን ህዝብ ወደ 1.5 ቢሊየን ደርሳለች፤ በአንድ ልጅ ፖሊሲ በመታገዝ። የአንድ ልጅ ፖሊሲ ጉዳይ አዋጭ መስሎ ያልታያት ቻይናም 'ፖሊሲው በቃኝ' ብላለች፤ መቼም አርጀት ካለው ጎረምሳው ይሻለኛል በማለት። ወጣም ወረደ የዓለም ህዝብ ተጋግዞ ለችግሩ መላ ካላበጀለት መፃኢያችን በችግር የተተበተበ ነው። ቁምነገሩን በልባችን ያፅናልን!!!