Unnamed: 0
int64
0
82
audio_path
stringlengths
38
39
Transcribed_Text
stringlengths
29
189
0
Amhariksentencesplitted900k1_sent1.wav
አረንጓዴ ፡ ብጫና ፡ ቀይ ፡ ሰንደቅ ፡ ዓላማችን ፡ የአንድ ፡ ኢትዮጵያና ፡ የነፃነት ፡ ምልክታችን ፡ ነው
1
Amhariksentencesplitted900k1_sent2.wav
አረንጓዴው ፡ የአገራችንን ፡ ልምላሜ ፣ ብጫው ፡ ሃይማኖታችንና ፡ ምግባራችን ፣ ቀዩ ፡ ሀገራችን ፡ ወሰንዋ ፡ ሳይደፈር ፡ ነፃነቷ ፡ ተከብሮ ፡ እንዲኖር ፡ ጀግኖች ፡ ወገኖቻችን ፡ ለከፈሉት ፡ መስዋዕትነትን ፡ የሚገልጽ ፡ ነው
2
Amhariksentencesplitted900k1_sent3.wav
ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል በማለት በ ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ
3
Amhariksentencesplitted900k1_sent4.wav
የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን የህዝብ ክብር እያሟጠጠ መሆኑ እየተገለጸ ነው
4
Amhariksentencesplitted900k1_sent5.wav
ሃይሌ ይህንን የተናገረው መስከረም 20 ቀን 2003 ዓ ም ከተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ጋር በመንግስት ቴሌቪዥን ኢቲቪ አስተያየት በሰጠበት ወቅት ነበር
5
Amhariksentencesplitted900k1_sent6.wav
የቀድሞውን ስርዓትና ትውልድ ድንጋይ ዳቦ በነበረበት ፣ ፍራፍሬ ከጫካ ያለምንም ድካም ከሚሰበሰብበት ዘመን ጋር ያወዳደረው ሃይሌ ፣
6
Amhariksentencesplitted900k1_sent7.wav
የአሁኑ ትውልድ በማለት ያሞካሸውን ስርዓት ከተፈጥሮ ጋር ጦርነት በማካሄድ ለውጥ ማስመዝገበ መቻላቸውን አስምሮበታል
7
Amhariksentencesplitted900k1_sent8.wav
የባለ ራዕዩ መሪ አቶ መለስ ገድል ለመዘከር በተዘጋጀ ቅንብር ላይ በተደጋጋሚ አስተያየት ሲሰጥ የታየው ሃይሌ
8
Amhariksentencesplitted900k1_sent9.wav
አሁን የት ነው ያለነው በማለት ጠይቆ አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ለማግኘት ነው የምንጋፋው
9
Amhariksentencesplitted900k1_sent10.wav
አውሮፓ ሄደን እዛው ለመቅረት ነው በማለት ስደትን መርጠው ከአገራቸው የሚወጡትን ሸርድዶ አልፏል
10
Amhariksentencesplitted900k1_sent11.wav
አሁን ባለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ለስደት የሚዳርግ ጉዳይ የለም ወደ ማለት አዝምሞ ተናግሯል
11
Amhariksentencesplitted900k1_sent12.wav
ይህን ይበል እንጂ በተቃራኒው እስረኞች እንዲፈቱና የፖለቲካ እርቅ እንዲሰፍን እሰራለሁ ከሚሉት ፕሮፌሰር ይስሃቅ ጋር በሽምግልና እያገለገለ መሆኑ
12
Amhariksentencesplitted900k1_sent13.wav
በአገሪቱ ውስጥ የሚታው እስርና እንግልት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚጠቅሱ አስተያየት ሰጪዎች የሃይሌን አስተያየት ለንብረት ዋስትና የሚከፈል የንግግር ቫት በማለት አጣጥለውታል
13
Amhariksentencesplitted900k1_sent14.wav
ከኤርትራ ጋር ከተደረገው በቀር በኢትዮጵያ ይህ ነው የሚባል ጦርነት እንዳልተካሔደ ኢህአዴግን የሰላም አባት አስመስሎ ሃይሌ አመልክቷል
14
Amhariksentencesplitted900k1_sent15.wav
በዚሁም ምክንያት ቀደም ሲል ለጦርነት ይውል የነበረው የአገሪቱ በጀት ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት ዞሯል ብሏል
15
Amhariksentencesplitted900k1_sent16.wav
የኢህአዴግ ተወካይ መስሎ አስተያየት የሰጠው ሃይሌ ይህ አሁን የታየው ለውጥ በአስርና አስራ አንድ ዓመት ውስጥ የታየ ነው
16
Amhariksentencesplitted900k1_sent17.wav
አሁን ባለው አካሄድ ከአስር ዓመት በኋላ እንደርሳለን ሲል የራሱን ትንቢት አስቀምጧል
17
Amhariksentencesplitted900k1_sent18.wav
ተቆራርጦ በሚቀርበው አስተያየት እነ ፕሮፌሰር እንድሪያስን በማጀብ ሃይሌ በመዝገበ ቃላት ላይ ኢትዮጵያን ረሃብ በማለት የሚተረጉማት ቃል እንደሚቀየር በልበ ሙሉነት ተናግሯል
18
Amhariksentencesplitted900k1_sent19.wav
ከሃያ ዓመት በኋላ አለ ሃይሌ በመዝገበ ቃላት ላይ የኢትዮጵያ ውርስ ትርጉም ሃብታም በሚል ይቀየራል ብሏል
19
Amhariksentencesplitted900k1_sent20.wav
ድሮ ትረዱን ነበር ፤ እናመሰግናለን አሁን ደግሞ እንረዳችሀዋለን እንላቸዋለን ሲል አውሮፓና አሜሪካን የመሳሰሉ ታላላቅ አገሮች የኢትዮጵያን እጅ እንደሚናፍቁ ሃይሌ ከምኞት ባለፈ ስሜት ውስጥ ሆኖ ተናግሯል
20
Amhariksentencesplitted900k1_sent21.wav
አገሪቱን ለሃያ አንድ ዓመታት ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ ባልገለጹበት ሁኔታ ሃይሌ ከአስር እስከ ሃያ ዓመት ኢትዮጵያ ሃብታም አገር እንደምትሆን መናገሩ ከምን የመነጨ እንደሆነ ሊገባቸው እንዳልቻለ ብዙዎች እየገለጹ ነው
21
Amhariksentencesplitted900k1_sent22.wav
ሙስና ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል ሲል ኢህአዴግን የመከረው ሃይሌ የበታች ባለስልጣናት መንግስትን እንዳያሰድቡ መክሯል
22
Amhariksentencesplitted900k1_sent23.wav
መንግስት ይህንን አድርጉ ላይል ይችላል የሚለው ሃይሌ የበታች ባለስልጣኖች የሚፈጽሙት ሙስና መንግስትን ያስወቅሰዋል በሚል ተቆርቋሪነቱን በይፋ አስታውቋል
23
Amhariksentencesplitted900k1_sent24.wav
ዋናዎቹን የሙስና ተዋናዮች ነጻ በማውጣት የታች ባለስልጣኖችን እያንገዋለለ አሳጥቷቸዋል
24
Amhariksentencesplitted900k1_sent25.wav
ለህሊናቸው ሲሉ እንደ መንግስት በማሰብ መስራት አለባቸው ሲል ትዕዛዝ አዘል ምክርና ማሳሰቢያ ለበታች ባለስልጣናት ያስተላለፈው ሃይሌ የአስተያየቱ መነሻ ከኢህአዴግ ጋር የፈጠረው ዝምድና ውጤት እንደሆነ እየተነገረ ነው
25
Amhariksentencesplitted900k1_sent26.wav
አንድ አስተያየት ሰጪ ሃይሌ ሃብቱ እየበዛ ሲሄድና የተበደረው ገንዘብ ሲጨምር ኢህአዴግን ወክሎ መናገር ጀመረ ብለዋል
26
Amhariksentencesplitted900k1_sent27.wav
አትሌቶችን ሰብስቦ የአቶ መለሰን ሃዘን ሳግ በያዘው ድምጽ እያለቀሰ የገለጸው ሃይሌ ነፍሳቸውን ይማረውና በአቶ መለስ አይወደድም ነበር
27
Amhariksentencesplitted900k1_sent28.wav
በህይወት እያሉም በተደጋጋሚ ያናንቁት ነበር
28
Amhariksentencesplitted900k1_sent29.wav
ሃይሌን እንደሚያደንቁት ተጠይቀው አርቲስት ቻቺን በማሞገስ ጭራሹኑ እንደማያወቁት ዘለውት አልፈውት ነበር
29
Amhariksentencesplitted900k1_sent30.wav
ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት ለሃይሌ ቁብ እንደሌላቸው የሚያውቀው ሃይሌ ከአንድ ማስታወቂያ ሰራተኛ ልቆ በፕሮፓጋንዳ ተግባር ላይ መሰማራቱ በቅርብ ጓደኞቹና በአድናቂዎቹ ዘንድ መነጋገሪያ አድርጎታል
30
Amhariksentencesplitted900k1_sent31.wav
ቀጭኑ ዘቄራ ለአዲስ አበባ ከተማ ክብር ያላችሁ እንስማማለን አዲስ አበባ አንጀቷ ርህሩህ ነው
31
Amhariksentencesplitted900k1_sent32.wav
ከገዢዎች ክፋት በተጨማሪ አዲስ አበባ ፊቷን ብታጠቁር ምን ይኮን ነበር ሎሬት ጸጋየ ስለ አዲስ አበባ የተቀኙት ወደው አይደለም
32
Amhariksentencesplitted900k1_sent33.wav
በውነት ላስተዋለው የአዲስ አበባ ቆዳና ያዲስ አበቤዎች ትከሻ ላይችል አይሰጥም የሚሉት አይነት ነው
33
Amhariksentencesplitted900k1_sent34.wav
በየቀኑ አዲስ አበባ በማለዳ በቀንና በምሽት የምትሰበስባቸው ልጆቿ ተቃምሰው ማደራቸው በአድስ አበባ በረከት እንጂ በገዢዎች አቅርቦት አይመስልም
34
Amhariksentencesplitted900k1_sent35.wav
ከአራቱም ማዕዘን የሰው ደራሽ ወደ አዲስ አበባ ይንፎለፎላል አዲስ አበባ ሞልታ የምትፈስ አትመስልም
35
Amhariksentencesplitted900k1_sent36.wav
እምዬ ምኒሊክ ሲቆረቁሯት ጀምሮ አዲስ አበባ ተቀባይ ነች
36
Amhariksentencesplitted900k1_sent37.wav
የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ፣ የአፍሪካ መዲና ፣ የሰው ልጅ እምብርት ፣ አዲስ አበባ ፣ ፊንፊኔ ምንም ትባል ምን አዲስ አበባ ሁሉም ጓዳ የተባረከች ናት
37
Amhariksentencesplitted900k1_sent38.wav
ዘላለማዊነት ለአዲስ አበባ የቀጭኑ ቄራ መፈክር ነው
38
Amhariksentencesplitted900k1_sent39.wav
ባለፈው ሳምንት በሬ ለምኔን አሳይቼ ፣ ዝግ ቤቶች አቆይቻችሁ ፣ እንስራ እርቃን ቤት ስለሚካሄደው ድራማ አውግተን ነበር የተለያየነው
39
Amhariksentencesplitted900k1_sent40.wav
ሰላም አንባቢዎቼ ጎልጉል ድረገጽ ጋዜጣ ላይ መለቅለቅ መጀመሬ አስከሚነቃ ለመቀጠል በገባሁት ቃል መሰረት የዛሬው ተረኛ ማስታወሻዬን ከፈትኩ
40
Amhariksentencesplitted900k1_sent41.wav
የመሬት ውስጥ ነዋሪዎች ከመሬት በታች የሚኖሩት ሙታኖች ብቻ ናቸው ያለው ማን ነው አዲስ አበባ ሁሉን ቻይ ነች
41
Amhariksentencesplitted900k1_sent42.wav
ከርሷ የማይችለው የለውም ሁሉንም አቻችላ የመንግስትን ሚና በመጫወት ታኖራለች
42
Amhariksentencesplitted900k1_sent43.wav
ሰዎቹ ሲያቅታቸው እየቀበረች የማስተዳደር ስራዋን ከሰው በላይ ታከናውናለች
43
Amhariksentencesplitted900k1_sent44.wav
ሰባተኛ በመባል የሚታወቀው ያራዶች ሰፈር ላፍታ ቆምኩ ከምሽቱ አንድ ሰአት አካባቢ ይሆናል
44
Amhariksentencesplitted900k1_sent45.wav
መርካቶ ሸቅለው ወደ ቤታቸው የሚተሙ ብዛታቸው ያስደነግጣል
45
Amhariksentencesplitted900k1_sent46.wav
ድሮ አውሬው ሳይኖር የምታውቁት በአንድ ብርና በሽልንግ ጭን የሚሞቅበት ሰባተኛ ዛሬ የተለየ ነው
46
Amhariksentencesplitted900k1_sent47.wav
ከመርካቶ ነቅለው ወደ ማደሪያቸው የሚተሙት ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉ ወይም ከስታዲየም የሚለቀቁ እንጂ ለጉዳይ ወጥተው ወደቤታቸው የሚገቡ አይመስሉም
47
Amhariksentencesplitted900k1_sent48.wav
በሰባተኛ ወደ አማኑኤል የሚተሙት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች ፌስታል ማንጠልጠል አይዘነጉም አብዛኞቹ የሚይዙት ላስቲክ ዳቦ የያዘ ነው
48
Amhariksentencesplitted900k1_sent49.wav
ማባያውን ያዲሳባ አምላክ ይወቀው ያየሁት የሚፈሱትን ሰዎች እንጂ ማረፊያቸውን አይደለም
49
Amhariksentencesplitted900k1_sent50.wav
ፈሰው እንደሚገቡት ሁሉ ማለዳ ተነስተው ወደ መርካቶም የሚፈሱት በተመሳሳይ በግፊያ ነው
50
Amhariksentencesplitted900k1_sent51.wav
ግፊያው በአገሪቱ የስነ ህዝብ ፖሊሲ ስለመኖሩ ያጠራጥራል
51
Amhariksentencesplitted900k1_sent52.wav
እግረ መንገዴን አነሳሁት እንጂ የዛሬው ዋና ርዕሴ ከመሬት ውስጥ በህይወት ስለመሸጉ ወገኖች ለማሳወቅ ነው
52
Amhariksentencesplitted900k1_sent53.wav
ጊዜው ትንሽ ቢቆይም በግራውንድ ሲቀነስ አንድ አንድ ደረጃ ወደ መሬት ዝቅ ብለው የሚኖሩ ብዙ ናቸው
53
Amhariksentencesplitted900k1_sent54.wav
ለዛሬ የማስተዋውቃችሁ ከአቡነ ጴጥሮስ እስከ አውቶቡስ ተራ በየመንገዱ አካፋይ መሃል ለመሃል በተዘረጋው ውሃ መውረጃ ቱቦ ውስጥ ስለሚኖሩት ነው
54
Amhariksentencesplitted900k1_sent55.wav
ግራውንድ ሲቀነስ አንዶች አቡነ ጴጥሮስን ይዛችሁ ወደ መስጊድ ስትጓዙ የመንገዱን አካፋይ ትመለከታላችሁ
55
Amhariksentencesplitted900k1_sent56.wav
ለበርካታ ዓመታት መንገዱን እያየሁ ተሸጋግሬበታለሁ ከስሩ ሰው ስለመኖሩ አስቤም አልሜም አላውቅም ነበር
56
Amhariksentencesplitted900k1_sent57.wav
አንድ ቀን አትክልት ተራ የሚያቆየኝ ጉዳይ አጋጠመኝ ጉዳዬ በአጋዥ የሚከናወን ነበርና አንድ ጎረምሳ እንዲተባበረኝ ጠየኩት
57
Amhariksentencesplitted900k1_sent58.wav
ስራችንን እንደጨረስን በመንገዱ አካፋይ በግምት በመቶ ሜትር ርቀት የሚታየውን ጉድጓድ ስለሸፈነው ስብርባሪ መስታወት ድንገተኛ ጥያቄ አነሳሁ
58
Amhariksentencesplitted900k1_sent59.wav
ጎረምሳው ተረከልኝ እንዲህ ሲል የመኖሪያ ቤት በር ነው ከላይ ከአቡነ ጴጥሮስ እስከ መስጊድ መብራቱ ድረስ ውስጡ ክፍት ነው በግንብ የተሰራ የውሃ መውረጃ ቱቦ አለ
59
Amhariksentencesplitted900k1_sent60.wav
ከላይ እስከታች በስምምነት እንኖርበታለን ቤተሰብ ያፈሩ የልጅ ልጅ ያዩ አሉ ቤታችን ነው ለቤት በር ያስፈልገዋል ደነገጥኩ
60
Amhariksentencesplitted900k1_sent61.wav
የመንገዱን አካፋይ በመያዝ በግምት በመቶ ሜትር ርቀት ያሉትን በሮች እየተመለከትኩ አስጎብኚዬን እቀዳው ጀመር
61
Amhariksentencesplitted900k1_sent62.wav
ሃብተ ጊዮርጊስ ስንደርስ ቆመና ወደ ድልድዩ ወሰደኝ ወንዙ አፍ ላይ የሚቀረውን የአንዱን ቱቦ ጫፍ አሳየኝና የአስከሬን መውጫ በር መሆኑን ነገረኝ
62
Amhariksentencesplitted900k1_sent63.wav
ይህን ጊዜ አንድ ራሱን የቻለ ማህበረሰብ ከመሬት በታች እንደሚኖሩ ተረዳሁና ዝርዝር ነገሮችን የማወቅ ጉጉቴ ነደደ
63
Amhariksentencesplitted900k1_sent64.wav
አዎ አስገራሚ ታሪክና የኑሮ ወግ ያላቸው ውብ ፍጡሮች ከመሬት በታች ይኖራሉ
64
Amhariksentencesplitted900k1_sent65.wav
በአገሪቱ ፖለቲካና ባገራቸው ጉዳይ አያገባቸውም የአዲስ አበባ እንብርት ውስጥ ይኖራሉ ግን አድራሻ ያለቸውም ቀበሌና ቤት ቁጥር አያውቁም
65
Amhariksentencesplitted900k1_sent66.wav
ቀበሌ ስለሌላቸው አይመርጡም ለመመረጥም እድል የላቸውም የሁሉም ዜጎች መብት በተከበረባት ኢትዮጵያ ወደ አትክልት ተራ ተመልሰን ዘላለም ደስታ ሆቴል በር ፊትለፊት ባለው በራቸው
66
Amhariksentencesplitted900k1_sent67.wav
ህወሓት የአጋር ፓርቲዎቹን የንግድ ተቋማትና ልማታዊ ባለሀብት እያለ የሚጠራቸውን አባላቱን በዋናነት አሰባስቦ ያቋቋመው የወጋገን ባንክ ውለታ ባስገባቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች አማካይነት በቀን እስከ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ዶላር የመሰብሰብ አቅም መገንባቱ ተጠቆመ
67
Amhariksentencesplitted900k1_sent68.wav
የድረገጽ ጋዜጣ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባካሄደው ማጣራት ወጋገን ባንክ ከፖለቲካው አመራር ባለው ቀጥተኛ ድጋፍና ሽፋን በመታገዝ ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፈውን የውጪ ምንዛሪ መቆጣጠር ያስቻለውን አቅም የገነባው በአስገዳጅ ደንብ ነው
68
Amhariksentencesplitted900k1_sent69.wav
በሶማሌ ተወላጆችና በህወሓት ሰዎች አማካይነት በሽሪክነትና በተናጥል የተቋቋሙ የገንዘብ አዘዋዋሪ ተቋማት ስራውን መስራት የሚያስችላቸውን ፈቃድ ሲያወጡ ከወጋገን ባንክ ጋር ብቻ ለመስራት አስቀድመው ውል ይፈጽማሉ
69
Amhariksentencesplitted900k1_sent70.wav
በዚሁ መሰረት ውል ከገቡት የገንዘብ አሰባሳቢ ድርጅቶች መካከል ዋንኞቹን በስም ዘርዝሯል
70
Amhariksentencesplitted900k1_sent71.wav
ደሀብሺል፣ ካህ ኤክስፕሬስ ፣ ተወከል፣ ገረን ኤክስፕሬስ፣ ኦሊምፒክ ኤክስ ፣ ሆዲን ግሎባል ኤክስፕሬስ፣ ሰሃል የመሳሰሉት በኢትዮጵያ ቢሮ ከፍተው በገንዘብ ዝውውር ስራ የሚሰሩትን ድርጅቶች የዘረዘረው
71
Amhariksentencesplitted900k1_sent72.wav
የድረገጽ ጋዜጣ የአዲስ አበባ ዘጋቢ የገንዘብ ዝውውሩ እንዴት እንደሚከናወን አመልክቷል
72
Amhariksentencesplitted900k1_sent73.wav
ከአውሮፓ ፣ ከአሜሪካና ከአረብ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚላከውን የውጪ ምንዛሪ በማስተላለፍ ኮሚሽን የሚወስዱት ክፍሎች ራሱ ወጋገን ባንክ ፣
73
Amhariksentencesplitted900k1_sent74.wav
ምንዛሪውን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ ወጋገን ባንክ የሚያስተላልፉት የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችና እነዚህ ድርጅቶች ብር እየለቀሙ በወጋገን ባንክ በኩል እንዲላክ የሚያደርጉ ደላሎች ሲሆኑ ከሚተላለፈው ገንዘብ ሁሉም በጥቅሉ የሚካፈሉት የአምስት በመቶ ኮሚሽን አላቸው
74
Amhariksentencesplitted900k1_sent75.wav
በዚሁ ስሌት መሰረት ወጋገን ባንክ ሁለት በመቶ ፣ የገንዘብ አስተላላፊው ተቋም ሁለት በመቶ ፣ ደላሎቹ ደግሞ አንድ በመቶ በዶላር ሂሳብ የሚታሰብና ባሉበት አገር ገንዘብ ተመንዝሮ የሚሰጣቸው ድርሻ አለቸው
75
Amhariksentencesplitted900k1_sent76.wav
ወጋገን ባንክ ዶላሩን በራሱ ሒሳብ አካውንትt በታዋቂ አለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች አማካይነት ካስገባ በኋላ ከአምስት መቶኛው ድርሻውን ከውሰዱ በተጨማሪ
76
Amhariksentencesplitted900k1_sent77.wav
በያንዳንዱ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ውስጥ በገንዘብ ተቀባይነት ካሽየር የሚሰሩ ሰራተኞችን በመመደብ ገንዘብ ለተላከላቸው ሰዎች በኢትዮጵያ ብር ክፍያ የሚያከናውነው ራሱ ነው
77
Amhariksentencesplitted900k1_sent78.wav
የሚላከው የውጪ ምንዛሪ በራሱ አካውንት ከገባለት የራሱን ገንዘብ ከፋይ ለምን ይመድባል በሚል ዘጋቢያችን ላነሳው ጥያቄ ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶቹ ከዋናው ተልዕኳቸው ውጪ በማናቸውም የገንዘብ ማቀባበል ስራ እንደሚሰሩ አይፈለግም ፤ አመኔታም የላቸውም
78
Amhariksentencesplitted900k1_sent79.wav
የሚላከው ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲቀየር በርካታ ስለሆነ ወጋገን ባንክ ከእስልምና ጉዳዮችና ከተለያዩ እንቅስቃሴዎች ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል የሚል ስጋት ስላለበትም ጭምር ተቀባዮችንም ለመቆጣጠር ጭምር ሲባል ነው ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው መልስ ሰጥተዋል
79
Amhariksentencesplitted900k1_sent80.wav
አውሮፓ ተቀምጦ ገንዘብ በማሰባሰብ አንድ ከመቶ ኮሚሽን የሚወስድ አንድ የድለላ ሰራተኛ ለጎልጉል ፡ የድረገጽ ጋዜጣ ሪፖርተር እንደተናገረው ስራ የለም ከተባለ እስከ ሃምሳ ሺህ ዶላር በቀን ወደ ወጋገን አካውንት የሚገባ የገንዘብ ሰነድ ለቀጠረው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት እንደሚልክ አስታውቋል
80
Amhariksentencesplitted900k1_sent81.wav
የገንዘብ አዘዋዋሪ ድርጅቶቹ የሶማሌ ተወላጆች ቢመስሉም ከጀርባቸው ተቆጣጣሪና ሽርካ እንዳላቸው የጠቆመው ይህ ደላላ
81
Amhariksentencesplitted900k1_sent82.wav
ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ የሶማሌ ዜጎች ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በመላክ ወጋገን ባንክን እያደለቡት እንደሆነ አመልክቷል
82
Amhariksentencesplitted900k1_sent83.wav
ስሙ እንዳይገለጽበት የጠየቀው የሶማሌ ተወላጅ የኢትዮጵያ መንግስት በኛ መስመር ብቻ በቀን እስከ ሁለት ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ የውጪ ምንዛሪ ከአውሮፓ ብቻ ያገኛል