source
stringlengths
4
528
target
stringlengths
3
393
source_lang
stringclasses
1 value
target_lang
stringclasses
1 value
Free Zone9 Tumblr collage. Images used with permission. Join Global Voices bloggers for a worldwide, multilingual tweetathon in support of the ten bloggers and journalists facing terrorism charges in Ethiopia.
የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይፈቱ ከሚለው የተምብለር ዘመቻ በፍቃድ የተወሰደ በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር አዋጁ እና ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመሞከር ወንጀሎች ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠርጥረው በእስር ላይ ለሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ሀምሌ 24 የትዊተር ላይ ማራቶን ተዘጋጅቷል:: ይህንንም ማራቶን በመቀላቀል ለጦማርያኑ እና ለ ጋዜጠኞቹ ያሎትን አጋርነት በተግባር ያሳዩ::
English
Amharic
The Global Voices community and our network of allies are demanding justice for these men and women, all of whom have worked hard to expand spaces for social and political commentary in Ethiopia through blogging and journalism. We believe their arrest is a violation of their universal right to free expression, and that the charges filed against them are unjust.
የአለም አቀፍ የጦማርያን ማህበረሰብ የሞያ አጋሮቻችን የሆኑት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች በሀገራቸው ጉዳዮች ላይ የሰለጠነ ማህበራዊ ተዋስኦ እንዲኖር ጠንክረው ከመስራት ባለፈ ምንም የሰሩት ወንጀል ስለሌለ ፍትህ እንዲያገኙ አጥበቀን እንጠይቃለን:: የአጋሮቻችን እስር በአለም አቀፍ ደረጃ ስምምነት የተደረሰባቸውን ሰበአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን የሚደፈጥጥ ከመሆኑ ባሻገር ጦማሪያኑ እና በጋዜጠኞቹ ላይ የተመሰረቱባቸው ክሶች ኢፍትሀዊ ናቸው ብለን እናምናለን:: የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች የፍርድ ሂደት እየተከታተለ የሚዘግብ ድረገጽን በመመልከት ስለ ጉዳዩ ያሎትን ግንዛቤዎት ያስፉ::
English
Amharic
Until then, and beyond, they will need all the support they can get. So this Thursday, we as a global community of bloggers, writers, activists, and social media experts will share this message around the world, tweeting in our native languages at community leaders, government and diplomatic officials, and mainstream media to draw public attention to the case.
ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞቹ ሀምሌ 28 2006 በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ:: ፍርድ ቤት እስከ መገኛቸው ቀን እና ከዚያም በኋላ ባሉት ግዚያት የሞያ አጋሮቻችን የኛን ከፍተኛ ድጋፍ ይሻሉ:: በመሆኑም ሀሙስ ሀምሌ 24 2006 በመላው አለም የምንገኝ ጦማሪያን: ጻህፍት እና የማህበራዊ ሚዲያ ባለሞያዎች ይህንን የድጋፍ መልእክት በየቋንቋችን ትዊተርን በመጠቀም ለማህበረሰብ መሪዮች: ለመንግስት ባለስልጣናት እና ለዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ አባላት እናስተላልፋለን:: ይህንንም በማድረግ የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት እናደርጋለን::
English
Amharic
Six of the detained bloggers in Addis Ababa.
ይህንን የትዊተር ላይ ማራቶን ሃሙስ ለት መቀላቀል ይፈልጋሉ ?
English
Amharic
Photo used with permission.
ወይ ዜናውን ለወዳጅ ዘመዶዎ ማጋራት ይፈልጋሉ?
English
Amharic
#FreeZone9Bloggers: A Tweetathon Demanding the Release of Jailed Ethiopian Bloggers
ስሞዎትን እና የትዊተር አዳራሻዎን በማህበረሰባችን የእቅድ ገጽ ላይ ማስፈር ይችላሉ::
English
Amharic
Date: Thursday, July 31, 2014
የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ፍትህ ይገባቻዋል!
English
Amharic
Hashtag: #FreeZone9Bloggers
ስለ ሚያገባን እንጦምራለን::
English
Amharic
Add your name and Twitter handle to our community planning sheet.
የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች መታሰር የአፍሪካ የሰብአዊ እና የህዝቦች መብቶች ቻርተር መጣስ ነው::
English
Amharic
Blogger arrests in #Ethiopia violate the International Covenant on Civil and Political Rights #FreeZone9Bloggers http://bit.ly/1g1MUNM
የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች መታሰር አለም አቀፉን የሲቪል እና የፓለቲካ መብቶች ስምምነት መጣስ ነው::
English
Amharic
Tweet until your fingers hurt and demand justice for the Zone9 bloggers!
ጣቶች እስኪዝሉ እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ፍትህ እስኪያገኙ ትዊቶች ለመጻፍ አይታክቱ:: ፍትህ ለዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች !
English
Amharic
Zone9 members together in Addis Ababa, 2012.
የዞን ፱ አባላት አብረው አዲስ አበባ ውስጥ ሳሉ፣ እ.
English
Amharic
Photo used with permission.
2012 ዓ.
English
Amharic
This post was jointly published with the World Policy Journal blog.
ፎቶ ጥቅም ላይ ለማዋል ፍቃድ ተሰጥቷል።
English
Amharic
The international human rights system is broken – or perhaps it never worked at all.
ይህ ልጥፍ ከWorld Policy Journal ጦማር ጋር በመተባበር የታተመ ነው።
English
Amharic
In case after case, citizens’ human rights are violated under the national laws of their respective countries, despite the existence of international human rights commitments in the United Nations’ Universal Declaration, and by the Organization for Security and Cooperation in Europe, the Organization of American States, the African Commission, and others.
በብዙ ጉዳዮች ላይ እንደታየው ከሆነ የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች በየአገራቸው ብሔራዊ ህጎች ይጣሳሉ፣ ምንም እንኳ በተባበሩት መንግስታት ሁለገብ አዋጅ (United Nations’ Universal Declaration)፣ እና በአውሮፓ የደህንነት እና የትብብር ድርጅት፣ በየአሜሪካ አገራት ድርጅት፣ በአፍሪካ ኮሚሽን እና በሌሎች ውስጥ ያሉ ቃል የተገባባቸው የአለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ቢያካትቱም።
English
Amharic
The International Criminal Court has little say concerning any but the most egregious of international human rights violations, and member states have wide latitude to dispense justice as they see fit.
የአለምአቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤቱ አይን ካወጡት በስተቀር ማንኛውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ማድረግ የሚችለው ነገር የለም፣ እና አባል አገራት ፍትህ በመሠላቸው መልኩ የመስጠት ሰፊ ነጻነት አላቸው።
English
Amharic
For those who live in countries that fail to provide or enforce their own laws protecting freedom of expression, international principles have rarely provided actual recourse.
ሐሳብን የመግለጽ መብትን የሚጠብቁ የገዛ ህጎቻቸውን ማክበር ወይም ማስፈጸም ባልቻሉ አገሮች ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች አለምአቀፍ መርሖዎች እውነተኛ መፍትሔ ቢሰጣቸውም ከስንት አንዴ ነው።
English
Amharic
Today, this is the case with the independent Ethiopian blogger collective known as Zone9.
ዛሬ ዞን ፱ ተብሎ በሚታወቀው ነጻ የኢትዮጵያውያን ጦማሪያን ቡድን ላይ እየሆነ ያለውም ይኸው ነው።
English
Amharic
In April of this year, the government of Ethiopia arrested six members of Zone9 along with three affiliated journalists in Addis Ababa.
ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት ስድስት የዞን ፱ አባላትን ሶስት ቅርበት ካላቸው ጋዜጠኞች ጋር በአዲስ አበባ ውስጥ አስሯል።
English
Amharic
They were held for months without a formal charge and were denied the ability to communicate.
ምንም ክስ ሳይመሰረትባቸው ለወራት የተያዙ ሲሆኑ ከሌሎች ጋር እንዳይገናኙም ተከልክለዋል።
English
Amharic
Testimony from Befeqadu Hailu, one of the accused bloggers who was smuggled out of prison in August, as well as statements in court, allege mistreatment and frequent beatings.
ሐምሌ ላይ ከእስር ቤት የወጣው የበፍቃዱ ኃይሉ ማስታወሻ እና እንዲሁም በፍርድ ቤት ውስጥ የተሰጡ ቃሎች በደል እና ተደጋጋሚ ድብደባዎች እንደደረሰባቸው ያስረዳሉ።
English
Amharic
Informally, the nine were held on accusations of working with foreign organizations that claim to be human rights activists and…receiving finance to incite public violence through social media.”
እነዚህ ዘጠኝ ሰዎች «የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንደሆኑ ከሚያስመስሉ የውጪ ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት.
English
Amharic
In July, the Zone9 prisoners were charged under Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation of 2009 for receiving support from political opposition organizations, defined formally by the government as terrorists, and receiving training from international activists in email encryption and data security from the Tactical Technology Collective, a group that helps journalists and activists protect themselves from digital surveillance.
ሐምሌ ላይ የዞን ፱ እስረኞች መንግስት በይፋ አሸባሪዎች ብሎ ከሰየማቸው የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች ድጋፍ በመቀበል እና በአለምአቀፍ ተሟጋቾች ታክቲካል ቴክኖሎጂ ኮሌክቲቭ (Tactical Technology Collective) ከተባለው ጋዜጠኞች እና ተሟጋቾች እራሳቸውን ከዲጂታል ክትትል እንዲጠብቁ ከሚያግዛቸው ቡድን በኢሜይል ኢንክሪፕሽን እና ዳታ ሴኩሪቲ ስልጠና በመቀበል በ2001 ኢትዮጵያ ጸረ-ሽብር አዋጅ ተከስሰዋል።
English
Amharic
The Zone9 bloggers joined other media outlets targeted under similar laws, including Eskinder Nega, who had reported on recent Arab uprisings and the possibility of similar uprisings taking place in Ethiopia.
የዞን ፱ ጦማሪያን በቅርብ ጊዜ በነበረው የአረብ አመጾች ላይ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ሊከሰቱ በሚችሉ ተመሳሳይ አመጾች የዘገበው እስክንድር ነጋን ጨምሮ በተመሳሳይ ህጎች ከተነጣጠሩ ሌሎች የሚዲያ ድምጾች ጋር ተቀላቅለዋል።
English
Amharic
He was arrested and charged with the planning, preparation, conspiracy, incitement and attempt” of terrorism and sentenced to 18 years in prison.
በቁጥጥር ስር ውሎ በ«ሽብርን በማቀድ፣ ዝግጅት በማድረግ፣ በማሴር፣ በማሳመጽ እና ሙከራ በማድረግ» ተከስሶ የ18 ዓመት እስር ተፈርዶበታል።
English
Amharic
International appeals from human rights advocacy organizations have had little effect on the case.
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ያደረጓቸው አለምአቀፍ ስሞታዎች በጉዳዩ ላይ ተጽዕኖ አልነበረውም።
English
Amharic
In May, UN High Commissioner for Human Rights Navi Pillay issued a statement explaining,
ግንቦት ላይ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ኮሚሽነር ናቪ ፒሌይ እንዲህ ብላ የሚያብራራ ቃል ሰጥታለች፣
English
Amharic
The fight against terrorism cannot serve as an excuse to intimidate and silence journalists, bloggers, human rights activists and members of civil society organizations.
በሽብርተኝነት ላይ የሚደረገው ዘመቻ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አባላትን ለማስፈራራት እና ድምጽ ለማጥፋት እንደ ሰበብ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም።
English
Amharic
And working with foreign human rights organizations cannot be considered a crime.
እና ደግሞ ከውጪ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት እንደ ወንጀል ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም።
English
Amharic
Additionally, seven international human rights and press freedom organizations pressed the African Commission and the United Nations in an urgent appeal to intervene in the case against Zone9.
በተጨማሪም፣ ሰባት የአለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶች እና የፕሬስ ነጻነት ድርጅቶች በላኩት አስቸኳይ ጥያቄ የአፍሪካ ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት በዞን ፱ ላይ በተከፈተባቸው ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል።
English
Amharic
The appeal focused on the lack of clear charges and failure to allow the defendants adequate legal representation.
ጥያቄው ጉድለት ባለው የክሶቹ ግልጽነት እና ተከሳሾቹ በቂ የህግ ምክር የማግኘት መብት ላይ ያተኮረ ነው።
English
Amharic
Nani Jansen, a lawyer for the Media Legal Defence Initiative and the lead signatory in the appeal, writes in an email that both the African Commission and the UN operate under the cover of confidentiality in the early stages of these matters.
የሚዲያ ህግ መከላከያ ተነሳሽነት (Media Legal Defence Initiative) ጠበቃ እና የጥያቄው መሪ ፈራሚ የሆነችው ናኒ ጃንሰን በኢሜይል ውስጥ ሁለቱም የአፍሪካ ኮሚሽን እና ተመድ «በእነዚህ ጉዳዮች ቀዳሚ ደረጃዎች ላይ በሚስጥራዊነት ስም ነው የሚሰሩት» ብላ ጽፋለች።
English
Amharic
She continues:
እንዲህ ብላ ትቀጥላለች፦
English
Amharic
When they follow up with a Government, this is done without informing the outside world.
ከአንድ መንግስት ጋር አንድ ጉዳይ ሲከታተሉ የውጪውን ዓለም ሳያሳውቁ ነው።
English
Amharic
Only months and months (often over a year) later, these exchanges with a Government get published in the mechanism's report to its supervisory body.
ብዙ ወራት (አብዛኛው ጊዜ ከዓመት በላይ) ካለፉ በኋላ ብቻ ነው ከአንድ መንግስት ጋር የተደረጉት እነዚህ ልውውጦች ለበላይ አካሉ በሚደረገው የእንቅስቃሴ ስልት ሪፖርት ላይ የሚታተመው።
English
Amharic
Thus any intervention joins the rest of those in the cone of silence that is Zone9—hidden from public scrutiny or participation.
ስለዚህም፣ ማንኛውም ጣልቃ መግባት ዞን ፱ በሚወክለው የድምጽ ማፈኛ ስርዓት ውስጥ ይገባል—ከሕዝባዊ እይታ ወይም ተሳትፎ ተደብቆ።
English
Amharic
Even if these bodies do follow up with the Ethiopian government, their recourse is limited.
እነዚያ አካላት ጉዳዩን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ቢከታተሉትም እንኳ ያላቸው አማራጭ የተገደበ ነው።
English
Amharic
In an article on the urgent appeal, Jansen notes that the African Commission can condemn the arrests in a resolution, that both organizations' rapporteurs can request official visits to Ethiopia to investigate, and that Ethiopia, as a member of the UN Human Rights Council, would be obligated to honor such a request.
በአስቸኳይ ጥያቄው ላይ በጻፈችው ጽሑፍ ጃንሰን የአፍሪካ ኮሚሽን እስራቶቹን በአቋም ማውገዝ እንደሚችሉ፣ የሁለቱም ድርጅቶች ሪፖርት ጸሐፊዎች ምርመራ ለማካሄድ ወደ ኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ ጉብኝቶችን እንዲያደርጉ መጠየቅ እንደሚችሉ፣ እና ኢትዮጵያ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል እንደመሆኗ መጠን እንደዚህ ያለ ጥያቄ የማክበር ግዴታ እንዳለባት አውስታለች።
English
Amharic
But even should such requests be made, and investigations conducted, there is little chance of enforcement of hypothetical findings on the Ethiopian government.
ነገር ግን እንደዚህ ያሉ ጥያቄዎች ቢቀርቡ እና መርመራዎች ቢካሄዱም እንኳ ሊገኙ ይችላሉ ተብሎ የሚገመቱት ውጤቶች በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የማስፈጸም ዕድሉ በጣም አነስተኛ ነው።
English
Amharic
Since the appeal, the Ethiopian government has proceeded with charges against the accused.
ጥያቄው ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት በተከሳሾቹ ላይ በክሱ እንደቀጠለበት ነው።
English
Amharic
The latest details on the trial can be found on the Trial Tracker Blog, a site run by people close to the defendants.
በችሎቱ ላይ ያሉ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ለተከሳሾቹ ቅርብ በሆኑ ወዳጆች በሚሄድ የችሎት መከታተያ ጦማር (Trial Tracker Blog) ላይ ማግኘት ይቻላል።
English
Amharic
Public attempts to highlight the Ethiopian government's transgressions against human rights such as the #Freezone9bloggers social media campaign have an indirect effect.
እንደ የ#Freezone9bloggers የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ያሉ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚፈጽማቸው ጥሰቶችን ይፋ ለማውጣት የሚደረጉ ይፋዊ ጥረቶች ቀጥተኛ ያልሆነ ውጤት ነው ያላቸው።
English
Amharic
They seek to shame the Ethiopian government to ensure better treatment for the prisoners.
ለእስረኛዎቹ የተሻለ አያያዝ እንዲኖር ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ መንግስትን ለማሳፈር ያለሙ ናቸው።
English
Amharic
They also seek to pressure international organizations and Ethiopia's allies such as the United States, for whom Ethiopia is a critical military and security partner.
እንዲሁም በአለምአቀፍ ድርጅቶች እና እንደ ለኢትዮጵያ መንግስት ወሳኝ የጦር እና የደህንነት አጋር በሆነችው አሜሪካ ያሉ ተባባሪዎች ላይ ጫና ለማሳረፍም ያለሙ ናቸው።
English
Amharic
The hope is that those organizations will in turn apply political pressure on Ethiopia to free the Zone9 defendants.
ተስፋ የሚደረገው እነዚያ ድርጅቶች በተራቸው ኢትዮጵያ የዞን ፱ ተከሳሾችን ነጻ እንድታወጣ የፖለቲካ ጫና እንዲያሳርፉ ነው።
English
Amharic
The implementation of international commitments seems to rest primarily upon a negotiated process of politics, not a functioning and enforceable system of law.
እንግዲህ በአለምአቀፍ ደረጃ ቃል የተገባባቸውን ነገሮች መተግበር የሚወሰነው እየሰራ እና ተፈጻሚነት ባለው የህግ ስርዓት ሳይሆን በዋነኝነት በድርድር የሚካሄድ የፖለቲካ ሂደት ነው የሚመስለው።
English
Amharic
Considering the ease with which national law in Ethiopia is employed or ignored for political ends, it is a grim irony that only political pressure can hope to resolve the case in their favor.
ኢትዮጵያ ውስጥ ለፖለቲካዊ ዓላማ ሲባል ህጉ ምን ያህል በቀላሉ ስራ ላይ እንደሚውል ወይም ችላ እንደሚባል ሲታይ ጉዳዩ ለእነሱ እንዲፈታላቸው ያለው ተስፋ ፖለቲካዊ ጫና ብቻ መሆኑ ሲታይ ነገርየው ከባድ ምጸት ነው።
English
Amharic
Students mourning at Haromaya University.
የሀረማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ሐዘናቸውን እየገለጹ፡፡
English
Amharic
Photo shared widely on social media.
ፎቶው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተሰራጨ ነው፡፡
English
Amharic
Over the past two weeks, students in Ethiopia’s largest regional state, Oromia, have been protesting against a government plan to expand the area of the capital, Addis Ababa, into Oromia.
ባለፉት ሁለት ሳምንታት፣ በኢትዮጵያ ትልቁ የሆነው ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያሉ ተማሪዎች መንግሥት ዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ወደ ኦሮሚያ አካባቢዎች ለማስፋፋት ያወጣውን ዕቅድ እየተቃወሙ ነው፡፡
English
Amharic
Reports suggest security forces used violence including live ammunition to disperse crowds of peaceful demonstrators in the compounds of universities in Oromia.
ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት የፀጥታ አባላት የጥይት ተኩስ ሳይቀር ባካተተ ኃይል የተቀላቀለበት መንገድ በሠላማዊ ሁኔታ ተቃውሟቸውን ሲገልጹ የነበሩትን የኦሮሚያ ዩንቨርስቲዎች ተማሪ ሠልፈኞችን በትነዋል፡፡
English
Amharic
According to Human Rights Watch, at least three students were killed and hundreds were injured across the region as security forces used excessive force to disperse student protesters.
እንደ ሰብኣዊ መብቶች ታዛቢ ፖሊስ ተቃዋሚዎቹን ለመበተን በወሰደው ያልተመጣጠነ ኃይል ምክንያት፣ በክልሉ ቢያንስ ሦስት ተማሪዎች ሲገደሉ፣ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተጎድተዋል፡፡
English
Amharic
Other reports put the number of students killed up to ten.
ሌሎች ሪፖርቶች ደግሞ የተገደሉትን ተማሪዎች ቁጥር ዐሥር ያደርሱታል፡፡
English
Amharic
Although protesters are primarily university students, in some instances, high school and primary school children were also reportedly involved in intense confrontations with government forces.
ምንም እንኳን ዋነኞቹ ተቃዋሚዎች የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ቢሆኑም፣ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ውጥረት የተሞላ ፍጥጫ ውስጥ እንደገቡ ተዘግቧል፡፡
English
Amharic
At least nine students were killed by government forces in May 2014 while protesting over the same issue.
በግንቦት 2006 ተነስቶ በነበረው የተመሳሳይ ጉዳይ ተቃውሞ ቢያንስ ዘጠኝ ተማሪዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል፡፡
English
Amharic
The persecution of Oromo people
የኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈፀም የመብት ጥሰት
English
Amharic
The students argue that the controversial plan, known as the Master Plan, to expand Addis Ababa into Oromia state would result in mass evictions of farmers mostly belonging to the Oromo ethnic group.
ተማሪዎቹ የሚሟገቱት፣ ማስተር ፕላን” በመባል የሚታወቀው እና አዲስ አበባን ወደኦሮሚያ ክልል ለመለጠጥ የወጣው ዕቅድ ውጤቱ የኦሮሞ ብሔር አባላት የሆኑ ገበሬዎችን በገፍ መፈናቀል ያስከትላል በሚል ነው፡፡
English
Amharic
It wouldn't be the first time the government has uprooted members of an ethnic group.
የአንድ ብሔር አባላትን መንግሥት ሲያፈናቅል ይህ የመጀመሪያው አይሆንም፡፡
English
Amharic
Thousands of ethnic Amharas in western Ethiopia were expelled from the country's Benishangul Gumuz region in 2013 in what critics called ethnic cleansing.
ተቺዎች የዘውግ ማጥራት” እያሉ በጠሩት ክስተት በሺሕዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ በ2005 እንዲፈናቀሉ ተገድደው ነበር፡፡
English
Amharic
The students have other demands such as making Oromo a federal language.
ተማሪዎቹ ኦሮምኛን የፌዴራሉ የሥራ ቋንቋ የማስደረግ ሌላም ፍላጎት አላቸው፡፡
English
Amharic
Oromo, the language of the Oromo people, is the most widely spoken language in Ethiopia and the fourth largest African language.
ኦሮምኛ፣ በተናጋሪዎች ብዛት በኢትዮጵያ ወደር የሌለው እና በአፍሪካም አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የኦሮሞ ሕዝብ ቋንቋ ነው፡፡
English
Amharic
However, it is not the working language of the federal government.
ነገር ግን የፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ አልሆነም፡፡
English
Amharic
According to Ethiopian Constitution, Oromia is one of the nine ethnically based and politically autonomous regional states in Ethiopia.
እንደኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ ኦሮሚያ፣ በዘውግ ላይ ከተመሠረቱት ዘጠኝ የፖለቲካ ነጻነት ያላቸው የክልል መንግሥታት አንዱ ነው፡፡
English
Amharic
Oromo people make up the largest ethnic group in Ethiopia.
የኦሮሞ ሕዝብ በሕዝብ ብዛት በኢትዮጵያ ትልቁ ብሔር ነው፡፡
English
Amharic
However, the group has been systematically marginalized and persecuted for the last 24 years.
ይሁን እንጂ፣ የክልሉ ሕዝብ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ በተቀነባበሩ መገፋቶች እና የመብት ጥሰቶች ውስጥ አልፏል፡፡
English
Amharic
By some estimates, there were as many as 20,000 Oromo political prisoners in Ethiopia as of March 2014.
እስከ መጋቢት 2006 ድረስ 20,000 የሚገመቱ ኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ አንዳንድ ግምቶች ያስረዳሉ፡፡
English
Amharic
A 2014 Amnesty International report on repression in the Oromia region noted:
በ2006 ኦሮሚያ ውስጥ ስላለው ጭቆና በማተት የወጣ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አንድ ሪፖርት እንዲህ ይላል:
English
Amharic
Between 2011 and 2014, at least 5000 Oromos have been arrested based on their actual or suspected peaceful opposition to the government.
በ2002 እና በ2006 መካከል፣ ቢያንስ 5,000 ኦሮሞዎች በሠላማዊ የመንግሥት ተቃውሟቸው ሳቢያ ታስረዋል፡፡
English
Amharic
These include thousands of peaceful protestors and hundreds of opposition political party members.
ይህ እንግዲህ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሠላማዊ ሰልፈኞችን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶችን ይጨምራል፡፡
English
Amharic
The government anticipates a high level of opposition in Oromia, and signs of dissent are sought out and regularly, sometimes pre-emptively, suppressed.
መንግሥት በኦሮሚያ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለሚገጥመው የተቃውሞ ጭላንጭሎችን፣ አንዳንዶቹ መታየት ከመጀመራቸው በፊት ይጨፈልቃቸዋል፡፡
English
Amharic
In numerous cases, actual or suspected dissenters have been detained without charge or trial, killed by security services during protests, arrests and in detention.
ለበርካታ ጊዜያት፣ የተጠረጠሩ ተቃዋሚዎች ክስ ሳይመሰረትባቸው ይታሰራሉ፣ ወይም በእስር ወቅት ወይም በተቃውሞ ሰልፎች ጊዜ በፀጥታ ኃይሎች ይገደላሉ፡
English
Amharic
The ruling elite of Ethiopia are mostly from the Tigray region, which is located in the northern part of the country.
ኢትዮጵያን የሚመሯት ልሒቃን ምንጫቸው በኢትዮጵያ ሰሜን ከምትገኘው ትግራይ ክልል ነው፡፡
English
Amharic
Social media fills in the gaps
ማኅበራዊ ሚዲያ ክፍተቱን እየሞላ ነው
English
Amharic
Even as the Ethiopian drought and impending food crisis makes a rare appearance in local—and some international—headlines, little attention is being paid to the student protests in Ethiopian media.
ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ እና የተጋረጠው የምግብ እጥረት ቀውስ በአገር ውስጥ - እና ዓለም ዐቀፍ- ዜናዎች ላይ ርዕስ የመሆናቸው ዕድል ውስን በመሆኑ፣ የተማሪዎቹ ተቃውሞም እንደዚሁ በኢትዮጵያ ሚዲያ ትኩረት አላገኘም ማለት ይቻላል፡፡
English
Amharic
But despite Ethiopia’s highly controlled online environment and the government’s firm grip on communications infrastructure, social media users are reporting on the issue, particularly on Facebook, with additional coverage coming from diaspora-based media.
ነገር ግን፣ ከፍተኛ ቁጥጥር ካለበት እና ከመንግሥት የግንኙነት መሠረተ ልማቶች ጥብቅ ገደብ ተሻግሮም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በተለይም ፌስቡክ ላይ ሁሉንም ነገር ከዳያስፖራ ሚዲያዎች የዜና ሽፋን በተጨማሪ ሪፖርት በማድረግ ክፍተቱን ሞልተዋል፡፡
English
Amharic
Photo widely circulated on social media, taken from the Facebook page of Jawar Mohammed.
ይህ ፎቶ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው ተሰራጭቶ ከጃዋር መሐመድ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ ነው፡፡
English
Amharic
One Facebook user, for example, hoped for the world to hear stories of the student protesters' inspiring actions:
አንድ የፌስቡክ ተጠቃሚ፣ ለምሳሌ፣ የተማሪዎቹን የተቃውሞ መንስኤ ዓለም እንዲሰማለት ተስፋውን ገልጧል:
English
Amharic
The silence has truly been deafening.
ዝምታው የውነት ያደነቁራል፡፡
English
Amharic
We need to see and hear the inspiring actions undertaken by huge numbers of ‪#‎Oromo‬ in ‪#‎Ethiopia‬.
ብዙ ቁጥር ባላቸው ኦሮሞዎች እየተካሄደ ያለውን የሚያነቃቃ ተግባር ማየትና መስማት አለብን፡፡
English
Amharic
Tell their story, enable the world to be swept up in their story.Considering the complete absence of freedom to criticize the government or report opposition stories from within the country, people around the world reading about it can help greatly by doing everything possible to amplify this story.
ታሪካቸውን እንናገር፣ ዓለም በታሪካቸው እንዲጥለቀለቅ ማስቻል አለብን፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ መንግሥትን የመተቸት ወይም የተቃውሞ ታሪኮችን ሪፖርት የማድረግ ነጻነት ካለመኖሩ አንጻር በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሊያነቡት እና ዜናውን የቻሉትን በሙሉ በማድረግ ሊያስተጋቡት ይችላሉ፡፡
English
Amharic
Another Facebook user, Aga Teshome, took note of the political power of Oromo youth:
አጋ ተሾመ የተባለ ሌላ የፌስቡክ ተጠቃሚ የኦሮሞ ወጣቶች የፖለቲካ አቅምን በተመለከተ የሚከተለውን ዕይታውን አስፍሯል:
English
Amharic
...‪#‎OromoProtests‬ a call for all oppressed people in ‪#‎Ethiopia‬ to support the ongoing protest against ‪#‎landgrabing‬ ....the Oromo youth are a powerful political entity capable of shaking mountains.
…የኦሮሞ ተቃውሞ ሁሉንም የተጨቆኑ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በመሬት መቀራመት ላይ ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ …. የኦሮሞ ወጣቶች ተራራ ማንቀጥቀጥ የሚችል አቅም ያላቸው የፖለቲካ አካላት ናቸው፡፡
English
Amharic
This powerful political entity is hell bent on exposing the EPRDF government’s atrocious human rights record and all round discriminatory practices.
ይህ አቅም ያለው የፖለቲካ አካል የኢሕአዴግ መንግሥት የሰብኣዊ መብትን ደረጃ እና አግላይ ሥራዎችን የማጋለጥ ሚና ይጫወታል፡፡
English
Amharic
While Desu Tefera said:
ደሱ ተፈራ ደግሞ ይህን ይላል:
English
Amharic
We call upon the media to investigate the conditions that these students died trying to expose and resist, to draw attention to these concerns.
ሚዲያዎች እነዚህ ጉዳዩን ለመቃወም በመሞከራቸው የተገደሉ ተማሪዎች የሞቱበትን ሁኔታ መርምረው እንዲያጋልጡ ጥሪ እናደርጋለን፡፡
English
Amharic
Oromia needs a new kind of reporting by the international media, which gives voice to the voiceless Oromo people, who for a very long time have been killed, mistreated, abused, neglected and repressed in Ethiopia.
ኦሮሚያ በዓለም ዐቀፉ ሚዲያ ለድምፅ አልባው፣ ለረዥም ጊዜ የተገደሉ፣ የተንገላቱ፣ የተዘነጉ እና የተጨቆኑ የኦሮሞ ሕዝቦች ድምፅ የሚሆን አዲስ ዓይነት ዘገባ ያስፈልጋታል፡፡
English
Amharic
Going forward with the current plan, which ends up displacing tens of thousands of poor farmers, destroying their livelihood and depriving their identity, is a tragedy.
በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ገበሬዎችን የሚያፈናቅል፣ ኑሯቸውን የሚያጠፋ እና ማንነታቸውን የሚያንኳስሰውን ይህንን ዕቅድ ይዞ መቀጠል በጣም የሚያሳዝን ነው የሚሆነው፡፡
English
Amharic
It deserves attention.
ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
English
Amharic
These students put their lives on the line to draw attention to the farmers’ plight.‪#‎OromoProtests‬
እነዚህ ተማሪዎች ለገበሬዎቹ ጥቅም ሲሉ ነው ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ያስቀመጡት፡፡
English
Amharic
Although social media reports are pivotal in letting the world know about the protests, they miss a huge chunk of nuance that would help observers understand how this dispute is unfolding.
ምንም እንኳን ማኅበራዊ ሚዲያዎች ተቃውሞውን በመዘገብ ረገድ ማዕከላዊ ሚና ቢጫወቱም፣ ታዛቢዎች ግጭቱ በምን ምክንያት እንደተከሰተ በማብራራቱ ረገድ ትልቅ ነገር ይጎድላቸዋል፡፡
English
Amharic
Notably, the fact that the student protests combine delicate ethnic politics, urban land grabbing and Ethiopia’s diaspora community’s involvement in home country politics.
በተለይም ደግሞ፣ የተማሪዎቹ ተቃውሞ የዘውግ ፖለቲካን እና የከተማ መሬት መቀራመትንም ያዋሀደ መሆኑና የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች በአገር ውስጥ ፖለቲካ ጉዳይ መሳተፋቸው ነገሩ መብራራት እንዲያስፈልገው ያደርጋል፡፡
English
Amharic
Given Ethiopia’s highly controlIed environment, one might wonder how the students managed to get organized to express their grievance in the mid of highly controlled environment.
የኢትዮጵያ ምኅዳር ቁጥጥር የበዛበት ከመሆኑ አንጻር፣ ተማሪዎቹ እንዴት ብሶታቸውን ለመግለጽ ነገሮችን ማስተባበር ቻሉ የሚለው ያጠያይቃል፡፡
English
Amharic
Despite the firm grip on communication infrastructure there are constant update on Facebook and Twitter about the protest.
ከምኅዳሩ መጥበብ እና ከመሠረተ-ልማቱ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መዋል በላይ ፌስቡክ እና ትዊተር ስለ ተቃውሞው የመረጃ ምንጭ ሆነዋል፡፡
English
Amharic
Dubious development practices
አጠራጣሪ የልማት ሥራ
English
Amharic
The story is unpleasantly familiar, as students are protesting for the second time in less than two years.
ጉዳዩ በማያስደስት ሁኔታ የተለመደ ሆኗል፤ ምክንያቱም ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተመሳሳይ ተቃውሞ ሲከሰት ይህ ሁለተኛው ነው፡፡
English
Amharic
In April and May 2014, the protests began in response to the government’s plan to implement the Integrated Masterplan for Addis Ababa”.
በሚያዝ እና ግንቦት 2006፣ ተቃውሞዎቹ የጀመሩት መንግሥት የአዲስ አበባን የተቀናጀ ማስተር ፕላን” ሊተገብር መሆኑን ተከትሎ ነበር፡፡
English
Amharic
As Addis Ababa, the capital of Ethiopia, is an enclave within Oromia regional state, students primarily from Oromia state accused the Ethiopian government of attempting to take over land owned by local farmers in the name of integrating adjacent Oromia towns into the sprawling city of Addis.
አዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ የተከበበች ከተማ እንደመሆኗ ተማሪዎቹ መንግሥትን አጎራባች ከተሞችን ከአዲስ አበባ ጋር በማቀናጀት ሥም የገበሬዎችን መሬት ለመቀማት በማሰብ ይከስሱታል፡፡
English
Amharic
The students further alleged that if implemented, the Masterplan would result in Addis Ababa further encroaching into the territory of Oromia.
ተማሪዎቹ በተጨማሪም፣ ማስተር ፕላኑ ተግባር ላይ ከዋለ የኦሮሚያን አካባቢዎች ጠቅልሎ ለመውሰድ ያልማል በሚል መንግሥትን ይወነጅላሉ፡፡
English
Amharic
The government rejected the accusation, claiming that the Masterplan was intended only to facilitate the development of infrastructure such as transportation, utilities, and recreation centers.
መንግሥት ውንጀላውን የሚያጣጥለው ማስተር ፕላኑ የትራንስፖርት፣ የመዝናኛ እና መሰል የልማት መሠረት ልማቶችን ለመዘርጋት እንዲያስችል የተቀረፀ ነው በማለት ነው፡፡
English
Amharic

An unofficial version of https://huggingface.co/datasets/masakhane/mafand We created a different data loader for a @forai_ml project.

Downloads last month
0
Edit dataset card