headline
stringlengths
2
1.42k
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
9
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
63
36.2k
link
stringlengths
28
740
word_len
int64
16
6.74k
label
class label
6 classes
የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 11, 2019
Unknown
የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስራው እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል፡፡የ2012 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ለወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባሩ ልዩ ትኩረት በመሥጠትና ሙሉ የሰው ሃይሉን በማሰማራት ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንዳሉት በበዓላት ወቅት የሰው እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከወትሮው በተለየ መልኩ ስለሚጨምር ይህንን ታሳቢ በማድረግ በገበያና በመዝናኛ ስፍራዎች እንዲሁም በከተማችን በተለያዩ አካባቢዎች የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰትና ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ኮሚሽኑ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡ህብረተሰቡ የፀጥታ ጉዳይ የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እያደረገ እንደሚገኝና ከዚህ ቀደም የተከበሩ ሃይማኖታዊ እና ብሄራዊ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ኮሚሽኑ አስታውሶ አሁንም እንደተለመደው ራሱን ከወንጀል እና ከትራፊክ አደጋ በመጠበቅ ለፀጥታ ሃይሉ የሚያደርገውን ትብብርና የሚሰጠውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል፡፡ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 816 ወይም በ011-1-11-01-11 መጠቀም እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32724/
160
0ሀገር አቀፍ ዜና
ፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 11, 2019
Unknown
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉየኢፌዲሪ ፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱን ዓመት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ አዲሱ ዓመት የጤና፣ የሰላም፣ የብልጽግና እና የአገሪቷን አንድነት በማጠናከር እንደ ሐገር በስኬት የምንረማመድበት እንዲሆን ተመኝተዋል።ከአንዱ ዘመን ወደ ሌላኛው የሚደረገው ሽግግር ቀን ቀጥሮ አሮጌውን ከመሸኘት እና አዲሱን ዓመት ከመቀበል ያለፈ አንድምታ አለው ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ አዲሱ ዓመት ተስፋን ሰንቀን ወደ ተሻለ ህይወት ራሳችንን የምናዘጋጅበት እና ወደፊት አሻግረን ለምናየው ህልማችን የብርሃን ወጋገን የሚሰጥልን የጥንካሬያችን ምንጭ ሲሉ ገልጸውታል።በአሮጌው ዓመት ችግሮች እንዳሉ ሆኖ በብዙ መለኪያዎች የተለየ ዓመት እንደነበር ያወሱት ፕሬዝዳንቷ፤ ዜጋው በሃገሩ ጉዳይ ተሳታፊ እንዲሆን መንገዱን የሚጠርጉ የፖለቲካ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች መሰረት የጣሉ ስራዎችም የተከናወኑበት ዓመት ነበር ብለዋል።ዓመቱ በአገሪቷ የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥ በር የተከፈተበት መሆኑን በመግለጽ፤ ከጥቂት ወራት በፊት ማንም በማያስበው ሁኔታ ለሴቶች የይቻላል መንፈስን የፈጠሩ ሁኔታዎች የተከሰቱበት እንደነበርም በማሳያ ጠቅሰዋል።በአመለካከታቸው የተነሳ ተራርቀው የነበሩ ወገኖች በአገር ጉዳይ ላይ በጠረንጼዛ ዙሪያ ለመቀመጥና ለመወያየት መብቃታቸው በማውሳት፤ በአመለካከት እና በእምነት መለያያት ቢኖርም የጋራ ጉዳያችንን መሳት አይገባውም በማለት፤ የሚያስተሳስረን ገመድ ኢትዮጵያዊነት ነው ብለዋል።በአገራችን ሁኔታ ሊያስተሳስረንና ሊያግባባን የሚገባው ጉዳይ ወገኖቻችንን ከድህነት ማላቀቅ፣ መሰረታዊ ፍላጎቶታቸውንና መብቶቻቸውን ማስከበር ሊሆን እንደሚገባውም ጠቅሰዋል።አገሪቷ የተያያዘችው የለውጥ ሂደት ካለፉት ብዙ የተለየ የሚያደርገው የነበረውን ጠራርጎ "ሀ" ብሎ የጀመረ ሳይሆን ለአገሪቷ እድገትና ብልጽግና እሰለፋለሁ የሚለውን ሁሉ አስተባብሮ ለመጓዝ የተነሳ መሆኑን በመጥቀስ፤ ይህ ደግሞ የራሱ የሆኑ አዳዲስ መሰናክሎች ያመጣ መሆኑን ከመግለጽ አልተቆጠቡም።በተለይም ባለፉት ጊዜያት ያየናቸው አስከፊ ሁኔታዎች በሀገሪቷ እንዳይከሰቱ የማድረግ ሃላፊነት የመንግስት ወይንም የተወሰኑ አካላት ላይ ብቻ የሚጣሉ አይደሉም ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ የአገሪቷ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም የልማት ጉዳይ ለይደር የሚተው አለመሆኑን ገልጸዋል።ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ለግል ወይም ለቡድን ፍላጎት ብቻ ብሎ ለአንድ ወቅት የፖለቲካ ጥቅም የሚደረጉ ቀይ መስመር ያለፉ ተግባራት በስተመጨረሻ ልንመልሰው ወደማንችለው መቀመቅ እንዳይከተን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።ቀጣዩ አዲስ ዓመት አገርን በጽኑ መሰረት ላይ የምናስቀምጥበት፤ ተቋሞቻችንንና ተቋማዊ አሰራሮቻችንን፤ አንድነታችንን የምናጠናክርበት ምዕራፍ እናድርግ በማለት መልክታቸውን አስተላልፈዋል።አባቶቻችንና እናቶቻችን ያስተማሩን በችግሮቻችን ተውጠን ከስመን መቅረትን ሳይሆን ከችግሮች መካከልም የማይደበዝዙ ድንቅ ተግባራት በመፈጸም በሁለት እግር መቆም እንደምንችልም ጭምር ነው ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ በመጪው ዓመት ሰላሟና ደህንነቷ የተረጋገጠ አገር እንደሚፈጠር ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።  
https://waltainfo.com/am/32726/
305
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠ/ሚ ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከዌስት ባንክ ይዞታ ከፊሉን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ማቀዳቸውን የአረብ አገራት ተቹ
ፖለቲካ
September 11, 2019
Unknown
የአረብ አገራት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከዌስት ባንክ ይዞታ ከፊሉን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ማቀዳቸውን ተችተዋል።የሚቀጥለው ሳምንት የሚካሄደውን የእስራኤል ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ፤ እቅዱ እንደሚተገበር ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። የጆርዳን፣ የቱርክ እና የሳዑዲ አመራሮች እቅዱን በጥብቅ ተችተዋል።ጠቅላይ ሚንስትሩ በእቅዳቸው የጠቀሷቸው ጆርዳን ቫሊ እና ዴድ ሲ የዌስት ባንክ አንድ ሦስተኛ ይዞታ ሲሆኑ፣ የአረብ ሊግ እቅዱን "አደገኛ" እና "ኃይል የተሞላው" ሲል ኮንኖታል። ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር የሚጻረር እቅድ ነውም ብለዋል።የፍልስጤሙ ዲፕሎማት ሳዒብ ኤራካት "ይህ እርምጃ ወንጀል ነው፤ የሰላም ጭላንጭልን ያዳፍናል" ብለዋል።እስራኤል ከጎርጎሮሳውያኑ 1967 ጀምሮ ዌስት ባንክን ይዞታዋ ብታደርግም በቁጥጥር ሥር ግን አልዋለም ነበር። ፍልስጤም ነፃ አገርነቷን ስታውጅ ይህ ቦታ ግዛቷ እንደሚሆን ትገልጻለች።እሰራኤል ደህንነቷን ለመጠበቅ ስትል በጆርዳን ያላትን ይዞታ እንደማትለቅ ጠቅላይ ሚንስትሩ መናገራቸው ይታወሳል።ጠቅላይ ሚንስትሩ እቅዳቸውን ይፋ ያደረጉት ከምረጡኝ ቅስቀሳቸው ጋር በተያያዘ ነው። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የሰላም ስምምነት እንዲፈረም ካደረጉ በዌስት ባንክ ያሉ የአይሁዳውያን ሰፈራዎችን እንደሚጠቀልሉም ገልጸዋል።ኔታንያሁ የሚመሩት ፓርቲ ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጋር ከፍተኛ ፉክክር እያደረገ ይገኛል። የቢቢሲ የመካከለኛው ምስራቅ ተንታኝ ቶም ቤትማን እንደሚለው፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ እቅድ የቀኝ ዘመሞችን ድጋፍ ለማግኘት ያለመ ነው።ከኔታንያሁ ፓርቲ በተቃራኒው ያለው የ 'ብሉ' እና 'ዋይት' ፓርቲዎች ጥምር መሪ ያሪ ላፒድ "እቅዱ ያለመው ድምፅ ለማግኘት እንጂ ግዛት ለማግኘት አይደለም" ብለዋል።የጆርዳን ጠቅላይ ሚንስትር አይማን ሳፋዲ እቅዱ "አካባቢውን ዳግመኛ ወደ ቀውስ የሚወስድ ነው" ብለዋል።የቱርክ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሜቩልት ካቩስጎሉ እቅዱን "ዘረኛ" ሲሉ ኮንነውታል።የሳዑዲ አመራሮችም እቅዱን ተችተው የ'ኦርጋናይዜሽን ኦፍ ኢስላሚክ ኮኦፕሬሽን' 57 አባል አገራትን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/33997/
219
5ፖለቲካ
2011 ዓ.ም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ከማጠናከር ጀምሮ የተለያዩ ክስተቶች ተመዝግበውበታል ሲሉ ዶ/ር ደብረጽዮን ገለጹ
ፖለቲካ
September 11, 2019
Unknown
በተጠናቀቀው 2011 ዓ.ም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከርን ጨምሮ የተለያዩ ክስተቶች የተስተናገዱበት ነበረ ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገለጹ።ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ የአዲስ አመት መልካም ምኞታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት እንዳትስታወቁት፤ በተጠናቀቀው አመት በሀገሪቱ በርካታ በጎና በጎ ያልሆኑ ክስተቶች ተስተናግደዋል።ለሀያ አመታት ተራርቀው በነበሩ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች መካከል ታሪካዊ ምእራፍ የተሰራበት አመት ሆኖ መጠናቀቁንም ዶክተር ደብረጽዮን ተናግረዋል።በሁለቱም ህዝቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረው ጥላቻ መወገድ የተጀመረበትና አንዱ ሌላኛውን እንደሚያስፈልገው እምነት የጣሉበት አመት እንደነበር ገልጸዋል።ከድንበር አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ችግሮች በዘላቂነት ተፈትተው የሁለቱ ሃገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ መንግስት ፍላጎት መሆኑንም አመልክተዋል።“ክልሉ በጥናት ላይ የተመሰረተ አዲስ የቀበሌ ቋሚ አስተዳደሮች የተመደቡበት አመት በመሆኑ ህብረተሰቡ ለበርካታ አመታት ያነሳው የነበረ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል ጅምር ስራዎች የተከናወኑበት ነው” ብለዋል።የወረዳ አስተዳደሮችም ያላቸውን ሃብት መሰረት ያደረገ አዲስ የወረዳ አወቃቀር ጥናት ተጠናቅቆ ወደ ህዝብ ውይይት መቅረቡንም ተናግረዋል።ይህም በህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ጥናትን መሰረት ያደረገ መልስ ከመስጠት ባለፈ ለልማት የሚያግዝ የሰው ሀይል አመዳደብ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።የተጠናቀቀው ዓመት በራያ ዐዘቦና ራያ አላማጣ ወረዳዎች ለአስር አመታት የህዝብ ጥያቄ የነበሩ ከ100 በላይ ጥልቅ የውሀ ጉድጓዶች ወደ ልማት ለማስገባት ጥረት የተጀመረበት እንደነበረም አስታውሰዋል።ዓመቱ ከመንገድ ርቀው የነበሩ 149 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ወደ መንገድ ለማስገባት ህዝብና መንግስት በጋራ የተረባረቡበት መሆኑንም ጠቅሰው እየተንከባለሉ የመጡ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ ጥረት መጀመሩንም ተናግረዋል።በአንጻሩ የተለያዩ ሀይሎች ክልሉን አደጋ ውስጥ ለመክተት በርካታ እንቅስቃሴዎች ያደረጉበት ዓመት እንደነበረ ያመለከቱት ዶክተር ደብረጽዮን አዲሱ አመት የሰላምና የብልጽግና አመት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።መጪው አመት በርካታ ውዝፍ ስራዎች የሚጠናቀቁበት ከመሆኑም ባለፈ እንደ ሀገር አንድነትን ጠብቆ ለማቆየት ወሳኝ ስራ የሚከናወንበት መሆኑንም ጠቁመው ምርጫ 2012 ዓ.ም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ የሁሉንም ተሳትፎ እንደሚጠይቅም አመልክተዋል። (ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/31347/
245
5ፖለቲካ
የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ተደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 11, 2019
Unknown
የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንዶች 176፣ ለሴቶች 166 እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ለወንዶች 174፣ ለሴቶች 164 እንዲሆን ተወስኗል፡፡ለታዳጊ ክልሎች የመግቢያ ነጥቡ በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንዶች 166፣ ለሴቶች 156፤ በማህበራዊ ሳይንስ ለወንዶች 164፣ ለሴቶች 154 እንዲሆን ተወስኗል፡፡ለአካል ጉዳተኞች ደግሞ መስማት ለተሳናቸው በተፈጥሮና በማህበራዊ ሳይንስ ለወንዶች 120፣ ለሴቶች 115፣ ለአይነ ስውራን በማህበራዊ ሳይንስ ለወንዶች 110፣ ለሴቶች 105 እንዲሆን መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32718/
66
0ሀገር አቀፍ ዜና
ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በግንባታ ላይ የሚገኘውን የቁስቋም የህፃናት ክብካቤ ማዕከል ጎበኙ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 11, 2019
Unknown
ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የቁስቋም የህፃናት ክብካቤ ማዕከል የግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡በቀዳማዊት እመቤቷ የተጎበኘው የቁስቋም የህፃናት ክብካቤ ማዕከል ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡ማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለወ/ሮ ዘውዴ የህፃናት ክብካቤ ማዕከል ተላልፎ እንደሚሰጥም ነው ከቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32719/
41
0ሀገር አቀፍ ዜና
በዘመን መለወጫው ደንበኞች የውሃ ችግር እንዳያጋጥማቸው እየሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 11, 2019
Unknown
በዘመን መለወጫው በዓል ደንበኞች የውሃ ችግር እንዳያጋጥማቸው እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ከጳጉሜ 1 እስከ መስከረም 5 የሚቆይ በማዕከል እና በስምንቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጊዜያዊ ኮሚቴ በማቋቋም እስከ ምሽቱ 5 ሰዓት ድረስ እየሰራሁ ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡የውሃ እጥረቱን ለመቅረፍ እንዲቻል በየዕለቱ 14 ሺህ ሜትር ኪዩብ ተጨማሪ ውሃ እየተመረተ እንደሚገኝም ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡የኤሌትሪክ ሀይል መቆራረጥ ሲያጋጥም ከመደበኛው እንቅስቃሴ በተለየ መልኩ የጄነሬተር ቡድን በማሰማራት በቀን እስከ አምስት ሺህ ሊትር ነዳጅ እየተሞላ ነው ብሏል፡፡የከፋ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ውሃን ለማድረስ የባለሥልጣኑ 24 የውሃ ቦቴዎች ዝግጁ ሆነው እየተጠባበቁ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32720/
84
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሮበርት ሙጋቤ አስከሬን ከሲንጋፖር ወደ ዚምባቡዌ ተሸኘ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 11, 2019
Unknown
ከቀናት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስከሬን ከሲንጋፖር ወደ ሀገሩ ዚምባቡዌ በአውሮፕላን ተሸኝቷል።ላለፉት ወራት በሲንጋፖር  ሕክምናቸውን ሲከታተሉ  የቆዩት ፕሬዚዳንቱ በ95 ዓመታቸው ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡የቀብር ስነስርዓታቸውም የፊታችን እሁድ የሚፈፀም ሲሆን፤  ከዚህ አስቀድሞ 60 ሺህ ተመልካቾችን ያስተናግዳል በተባለ ስታዲየም ይፋዊ የስንብት  ይከናወናል ተብሏል፡፡የቀብሩ ቦታን በተመለከተ ግን እስካሁን ከስምምነት አለመደረሱም ነው ቢቢሲ በዘገባው  ያመለከተው፡፡በወቅቱ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አስተዳደር እና በሙጋብዌ ቤተሰቦች መካከል  ቀብሩ የት ይፈፀም በሚለው ጉዳይ ላይ ከመግባባት አልተደረሰም ተብሏል፡፡
https://waltainfo.com/am/33472/
76
0ሀገር አቀፍ ዜና
ማህበራቱ ከቤተክርስቲያኗ ጋር በተያያዘ መስከረም 4፤2012 ዓ.ም የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመለክተው መግለጫ ሰጡ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 10, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት መስከረም 4፤2012 ዓ.ም የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመለክተው መግለጫ ሰጡ፡፡መግለጫውን የሰጡት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በቤተክርስቲያን እየደረሰ ያለውን የመቃጠል፣ የካህናት መገደልና ሌሎች በቤተክርስቲያንቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ሰልፉን በማስመልከት ዝርዝር መግለጫዎችን በመስከረም 2፤2012 ዓ.ም እንደሚሰጥ የገለጸው ኮሚቴ፣ የነበራቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ከመንግስት አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሆነና በውይይቱ አጥጋቢ መልስ ካገኙ ሰልፉ ሊቀር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ማህበራቱ የሰላማዊ ሰልፍ መካሄድ አለመካሄዱንም በቀጣይ መስከረም 2 በሚኖረው ድጋሚ መግለጫ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል ሰልፉ ከኦሮሚያ ክልል ቤተክህነት ምስረታ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ በመጠቆም ከኦሮሚያ ቤተ ክህነት ምስረታ ጋር በተያያዘ በጉዳዩ ዙሪያ በቅርቡ ሲኖዶሱ የሰጠው መግለጫ በቂ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ሰልፉን ለማዘጋጀት ከባለፈው አንድ ወር ጀምሮ እየተንቀሳቀሱ እንደቆዩም የጠቆሙ ሲሆን፤ የሰልፉ አላማም በሰላማዊ መንገድ በቤተክርስቲያኒቷ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የታቀደው ሰልፍ ሰልፍ  በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሆንና  ህዝበ ክርስቲያኑ ከቤተክርስቲያንቷ ጎን እንዲቆሙም ጠይቀዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32716/
133
0ሀገር አቀፍ ዜና
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
September 10, 2019
Unknown
የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርገይ ላቭሮቭ ጋር ሞስኮ በሚገኘው የሩሲያ ፌደሬሽን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በሁለቱ ሀገራት ሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ እና ሩሲያ 121 ዓመታት ያስቆጠረ እና ከአድዋ ድል ማግስት በተጀመረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሠረቱ የተጣለ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን፤ ሩሲያ በጠላት ወረራ ጊዜ ከኢትዮጵያ ጎን ከተሠለፉ ወዳጆች አንዷ መሆኗን አስታውቀዋል።በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መስክም ታዋቂው ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና ሩሲያዊ መሆኑ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሩሲያ ነጻ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ መደረጉ ሌላው የግንኙነቱ ጠንካራነት መገለጫዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።ይህንን በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ ወዳጅነት በቴክኖሎጂ፣ በአቪየሽን ኢንዱስትሪ እና በባህል መስኮች ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሁለቱ አገሮች በመጪው ጥቅምት ወር በሚያካሄዱት የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ገዱ ገልጸዋል። አቶ ገዱ የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተፈጠረው ምቹ ንግድና ኢንቨስትመንት ሁኔታ እንዲሳተፉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።ሩሲያ በኢትዮጵያ የምታደርገው እንቅስቃሴ ወደ አፍሪካ ገበያ ለመግባት መንደርደሪያና ኢትዮጵያም የአፍሪካ ደጃፍ መሆኗን በመጥቀስ፤ ሩሲያ በዕድሉ ልትጠቀም እንደሚገባ አቶ ገዱ አመላክተዋል።ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሠላምና መረጋጋት ለማምጣትና የኢኮኖሚ ትስስር የሚጎለብትበትን አማራጮች የማጠናከር ሥራ እየሠራች መሆኑን፤ በቅርቡም በሱዳን የተጫወተችው ዲፕሎማሲያዊ ሚና ለዚሁ ማረጋገጫና ዓይነተኛ ማሣያ መሆኑን ሚኒስትር አቶ ገዱ ገልጸዋል።የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በበኩላቸው የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ታሪካዊ ግንኙነት እንደሚያደንቁ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሩሲያ ቁልፍ አጋር ሀገር እንደሆነች በመግለጽ፤ በሁለቱ ሀገሮች መካከል በየጊዜው የሚደረጉ የሁለትዮሽ ውይይቶች ትብብሩን ወደ ላቀ ከፍታ እንደሚወስደው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።በባለ ብዙ ወገን ግንኙነት መስክ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምታራምደው ኃላፊነት የተሞላው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እንደሚያደንቁና ከሩሲያ ጋርም በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በጋራ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ሰርጌ ላቭሮቭ ገልጸዋል።የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በሽያጭ መስክ ብቻ ሳይሆን በተሽከርካሪ መገጣጠሚያ መስክ ያላቸውን ሠፊ ልምድ ይዘው መግባት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ ከኢትዮጵያ ጋር በባዮሎጂ መስክ የሚያደርጉትን ትብብር ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት አስታውቀዋል።ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አኳያም በሩሲያ የዲፕሎማቲክ አካዳሚ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች የሚሠለጥኑበትን ሆኔታ እንደሚያመቻቹ አስታውቀዋል።በውይይቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሣ በቀጣይ በሁለቱ ሀገራት መካከል በመከላከያ መስክ ትብብሮች ለማድረግ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመዋል።የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለይ በማዕድን ፍለጋና ልማት ለሁለቱም ሃገራት የጋራ ጥቅም መሥራት እንደሚችሉ ገልጸዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትኩረት እንዲሠጥባቸው ለቀረቡት የትብብር መስኮች የቅርብ ክትትል በማድረግ ለውጤታማ ትብብር እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።(ምንጭ ፦ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)
https://waltainfo.com/am/31344/
345
5ፖለቲካ
የ2012 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል 
ቢዝነስ
September 10, 2019
Unknown
የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ በነገው ዕለት ይፋ እንደሚደረግ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በ2011 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ማለትም /የ12ኛ ክፍል ፈተና / ለመውሰድ ከተመዘገቡት 322 ሺህ 717 ተማሪዎች መካከል 319 ሺህ 264 የሚሆኑት ፈተናውን ወስደዋል፡፡የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግቢያ የሚወሰነው በአራት መሰረታዊ የትምህርት አይነቶች ውጤት መሠረት አድርጎ እንደሆነ መገለፁ ይታወሳል፡፡ይህ የሆነውም የተጋነነ የፈተና ውጤት በመታየቱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴርና የክልል የትምህርት ቢሮ ከቀናት በፊት በጋራ በሰጡት መግለጫ  መናገራቸውም አይዘነጋም፡፡ 
https://waltainfo.com/am/23956/
66
3ቢዝነስ
ባለፉት ሰባት ቀናት ግምታዊ ዋጋቸው ከ34 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ
ቢዝነስ
September 10, 2019
Unknown
ባለፉት ሰባት ቀናት በገቢና ወጭ ኮንትሮባንድ ግምታዊ ዋጋቸው 34 ሚሊየን 345 ሺህ 944 ሚሊየን ብር የሚገመት ዕቃ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና የገቢዎች ሚኒስቴር ባሉት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና ኬላዎች አማካይነት በዚህ ሳምንት ኮንትሮባንድንና ህገወጥ ንግድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተለያዮ ስራዎችን መሰራታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።በዚህም ባለፉት ሰባት ቀናት በገቢ ኮንትሮባንድ 23 ሚሊየን 460 ሺህ 355 ብር የሚገመት ዕቃ መያዙን ገልጿል።ከነዚህ መካከል አዳዲስ አልባሳት፣ ምግብና መጠጦች፣ ሲጋራና ትንባሆ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጦር መሳሪያ እና የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ይገኙበታል።እንዲሁም በሰባቱ ቀናት በወጪ ኮንትሮባንድ 10 ሚሊየን 885 ሺህ 589 ብር የሚገመት ዕቃ የተያዘ ሲሆን፥ ገንዘብ፣ ምግብና መጠጦች፣ ጫት እና ሌሎች ከተያዙት ዕቃዎች ጥቂቶቹ ናቸው።በሳምንቱ ውስጥ በህገ-ወጥ መልኩ ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ 26 ሽጉጥ፣50 የክላሽ ጥይትና 43 የክላሽ ካዝና መያዙንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። 
https://waltainfo.com/am/23957/
114
3ቢዝነስ
ፍትህ የነገሰባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁሉም የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 10, 2019
Unknown
የፍትህ ቀን  “ፍትህን ማረጋገጥ ይደር የማንለው ስራችን ነው!”በሚል መሪ ቃል በመላው ሀገሪቱ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች በዛሬው ዕለት ተከብሯል፡፡ በተለይም የፍትህ ቀን በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተከበረበት ወቅት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአንድ ሀገር የፍትህ ስርዓቱን ለማስተካከል የሚደረግ የትኛውም እንቅስቃሴ መላውን ህብረተሰብ ማካተት እንደሚገባው ገልፀው ፤ የቱን ያህል ምርጥ ስትራቴጂ ቢኖር የትም መድረስ አይቻልም ብለዋል፡፡ፍትህ የሚጀምረው ከግለሰብ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ፤ ግዴታውን በአግባቡ ተወጥቶ መብቱን የሚጠይቅ ዜጋ ባልተፈጠረበት ሃገር ፍትህ ብሶት የምታስተናግድ እንጂ እንባ የምታብስ ልትሆን አትችልም ነው ያሉት፡፡በመሆኑም የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት ለማስተካከልና በአስተማማኝ መሰረት ላይ ለማቆም የሚደረጉ ጥረቶች አሳታፊ በሆነ መንገድ ሊተገበሩ እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡“ፍትህ የጠፋ ዕለት እኔም ሆነ ሀገሬ የለንም” ብሎ የሚያምን ማህበረሰብ መፍጠር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም በንግግራቸው አንስተዋል፡፡በመጨረሻም ፍትህ የነገሰባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ  ጥሪ አቅርበዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32717/
120
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአዲሱ ዓመት ለሰላም እና ለኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል- አቶ ተመስገን ጥሩነህ
ፖለቲካ
September 11, 2019
Unknown
በአዲሱ ዓመት ለሰላም እና ለኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራባቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ፡፡በአመቱ ለሰላም፣ ለቱሪዝም፣ ለኢንቨስትመንት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለግብርና ዘርፎች ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡ርዕሰ መስተዳድሩ ለመላው የአማራ ህዝቦች፣ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መልካም አዲስ ዓመትን ተመኝተዋል፡፡አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መረጃ ባለፈው ዓመት የአማራ ክልል ሠላም አሳሳቢ ሁኔታ ላይ የደረሰበት፣ በርካታ ዋጋ የተከፈለበት ወቅት እንደነበር፣ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ግን አንፃራዊ የሰላም ሁኔታ መታየቱን ተናግረዋል፡፡በ2012 የሥራ ዘመን ለሰላም፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለኢንቨስትመንት እና ለቱሪዝም ዘርፎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደሚሠሩ አቶ ተመስገን አስታውቀዋል፡፡ሰላም ለማኅበራዊ፣ ለፖለቲካዊ እና ለሁለንተናዊ ልማቶች ቁልፍ በር በመሆኑ ከየትኛው ጊዜ በላይ ሕግ የማስከበር ሥራውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለጹት አቶ ተመስገን፤ ኅብረተሰቡም ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ሰላም የማስከበር ሥራው ላይ ተባባሪ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ክልሉ በ2012 የሥራ ዘመን በገጠር እና በከተማ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሠሩ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ትኩረት አድርገው እንደሚሠሩ፣ በተለይም የሀገር ውስጥ የዘይት ፍላጎትን የሚሸፍነው በክልሉ ውስጥ እየተገነባ ያለው የዘይት ፋብሪካ ሥራ እንደሚጀምር ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል፡፡በሌላ በኩል የቱሪዝም ዘርፉ እስካሁን ያልተሠራበት፤ ነገር ግን የተሻለ ገቢ የሚገኝበት እንደነበር ገልጸው፣ ሰላምን እና ቱሪዝምን በማስተሳሰር ቅርሶችን በመጠገን፣ ባሕልን በማስተዋወቅ እና መዳረሻዎችን በማስፋፋት ገቢን ለመጨመር ትኩረት እንደሚደረግ አቶ ተመስገን ተናግረዋል፡፡ መረጃው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31345/
201
5ፖለቲካ
በደቡብ ክልል የሰፈነውን ሰላም ለማስጠበቅ ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ
ፖለቲካ
September 10, 2019
Unknown
በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል አሁኑ ወቅት የሰፈነውን አንጻራዊ ሰላም ለማስጠበቅ የህብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ጥሪ አቀረቡ።አቶ ርስቱ ይርዳው የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ እንዳሉት፣ የክልሉ ህብረተሰብ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን ባበረከቱት አስተዋጽኦ የአካባቢው ሰላም ወደ ቀድሞው ሁኔታ እየተመለሰ ነው።ሰላሙ ዘላቂ እንዲሆን ህዝቡ የአካባቢውን ደህንነት መከታተል በተለይ ወጣቶች ለክልሉ ደህንነት ከመንግስት ጎን በጽናት ሊቆሙ እንደሚገባ አመልክተዋል።የደቡብ ክልል እንደሚታወቀው አቃፊ ህብረ ብሄራዊና ዛሬ በክልሉ ለተገኙ ድሎች አብሮ የሰራ እንደመሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች የኃይማኖት አባቶች ሰላምን በማስጠበቅ የህዝቦችን አንድነትና አብሮነት ለማጠናከር መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።በክልሉ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ለወጣቱ የስራ ዕድል በተገቢው መንገድ መፍጠር እንዳልተቻለ ጠቁመው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውና የአገልግሎት ዘርፉ በተለይ ቱሪዝም የተዳከመ መሆኑን ገልጸዋል።ይህንን ወደነበረበት ለመመለስና የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲቻል በትብብር መስራት ያስፈልጋል።አቶ ርስቱ እንዳመለከቱት ፍትህን ለማስፈንና የኑሮ ውድነትን ለማስተካከል የሚቻለው ሰላም ሲኖር በመሆኑ ለዚህም ቅድሚያ መስጠትና ትልቅ ዋጋ መስጠት ይገባል።በአዲሱ ዓመት በመንግስት በኩል የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችና ከአደረጃጀት ጋር በየአካባቢው የሚነሱ ቅሬታዎች በአግባቡ በመፈተሽ ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።“ ለሁሉም የክልሉ ህዝብ በፍትሀዊነት ህግን የማስከበር ስራ እንዲሰራ ይደረጋል “ብለዋል።“በዚህ ተግባር ምሁራንን ፣ ወጣቶችና ሴቶችን ጨምሮ ሁሉም የክልሉ ህብረተሰብን ከጎናችን አድርገን እንሰራለንም “ብለዋል።ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ እንደገለጹት አዲሱ ዓመት በግብርናው መስክ ለገበሬው ልዩ ድጋፍና የቴክኖሎጂ አቅርቦት በማድረግ ባለፉት ዘመናት በጸጥታ ችግር ምክንያት የታጣውን ለማካካስ የሚሰራበት ይሆናል።በተያዘው የመኽር ወቅት ቀሪ ጊዜያት ምርታማነትን መጨመር በሚያስችሉ ስራዎች ላይ ርብርብ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።በ2012 ዓ.ም ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉበት እንደሚሆነም አመልክተዋል።“ ወደኋላ የሚጎትቱ በተለይ አንድነታችንን እና አብሮነታችንን የሚሸረሽሩ አስተሳቦችን ለማስወገድ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።በአሁኑ ወቅት ክልል የሰፈነው አንጻራዊ ሰላም ለማስጠበቅ ህብረተሰቡ እንቀድሞው ሁሉ በአዲሱ ዓመትም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጠል ጥሪ አቅርበዋል።በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የክልሉ ህዝቦች ስጋት ላይ የወደቁበት ሁኔታ እንደነበር አስታውሰው መጪው ዘመን የህዝብ ጥያቄዎችና ፍላጎቶች በሰከነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዲያገኙ መንግስት ጥረት እንደሚያደርግ አመልክተዋል።አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የአንድነትና አብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።(ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/31341/
285
5ፖለቲካ
የሮሂንጊያ ማህበረሰብ መንደር ሙሉ በሙሉ ለመንግስት የልማት ተቋማት መዋሉ ተገለፀ
ፖለቲካ
September 10, 2019
Unknown
በማይናማር የሮሂንጊያ ማህበረሰብ መንደር ሙሉ በሙሉ ለመንግስት የልማት ተቋማት መዋሉን ቢቢሲ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ባንድ ወቅት የሮሂንጊያ ማህበረሰብ መኖሪያ የነበረው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ፈርሶ የመንግስት የልማት ተቋማት እንደተገነቡባቸው በሳተላይት ምስሎች ማረጋገጡን ነው  ቢቢሲ የገለፀው፡፡አካባቢው አሁን ላይ የፖሊስ ፅህፈትቤት፣ የስደተኞች ማቆያን በመሳሰሉ የማይናማር መንግስት ግንባታዎች  መሞላቱም ተገልጿል፡፡ ምንም እንኳን የአካባቢው ባለስልጣናት ግንባታውን ቢያስተባብሉም፡፡እ.አ.አ በ2017 በማይናማር የሚገኙ ከ700 ሺህ በላይ የሮሂንጊያ ማህበረሰብ አባላት ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡የተባበሩት መንግስታት ሀገሪቱ በሮሂንጊያ ማህበረሰብ አባላት ላይ ከበቂ በላይ ወታደሮችን በመጠቀም ግድያ በመፈፀም የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ ማድረጉም አይዘነጋም፡፡በአብዛኛው የቡድሂት እምነት ተከታዮች የሚገኙባት ማይናማር በአንድ ወቅት በዚሁ ማህበረሰብ ላይ በዘር ማጥፋት ተጠያቂ ተደርጋ የነበር ሲሆን አሁን ደግሞ ስደተኞችን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን በጸደጋጋሚ እየገለፀች ትገኛለች፡፡ምንም እንኳን ከ3 ሺህ በላይ የሮሂንጊያ ማህበረሰብ አባላት ወደ ቀደመ ቀያቸው ለመመለስ ያደረጉት ጥረት ባይሳካም፡፡
https://waltainfo.com/am/33996/
120
5ፖለቲካ
አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ቀልጣፋና በቂ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን የቄራዎች ድርጅት አስታወቀ
ቢዝነስ
September 10, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ ቄራዎች ድርጅት የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግለህብረተሰቡ ቀልጣፋና በቂ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ዝግጅቱን አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የቄራዎች ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል፤ ድርጅቱ በቀን በአማካኝ ከ1600 በላይ ከብቶችና እስከ 1500 የሚሆኑ በግና ፍየሎች የእርድ አገልግሎት የመስጠት አቅም ያለ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይ በበዓላት  እስከ 5000 እንስሳት የእርድ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል፡፡በአዲሱ የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ እስከ 3000 ከብቶችና 2000 በግና ፍየሎች የእርድ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡ሆኖም ግን ድርጅቱ ህገወጥ የእርድ አገልግሎቶች ፈተና እንደሆነበት ገልጸው፣ በዚህም ከተማዋ እስከ ግማሽ ቢሊየን ብር ግብር እንደምታጣ አቶ አታክልቲ ተናግረዋል፡፡ህገወጥ እርድ በተለይ የኢኮኖሚ ቀውስ፣ የጤና ችግር፣ አካባቢን የመበከልና ሌሎች ሰፊ ችግሮችን የሚያስከትል በመሆኑ ህብረተሰቡ እርድ በሚያከናውንበት ወቅት በህጋዊነት በቄራዎች ድርጅት በኩል እንዲያደርግም ገልጸዋል፡፡የጭነት መኪናዎች በቀን በከተማዋ እንዳይንቀሳቀሱ ህግ የወጣ ቢሆንም፣ ድርጅቱ ግን አገልግሎቱ በበዓላት ቀናት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ውይይት በማድረግ ፍቃድ ማግኘቱንም አቶ አታክልቲ አስታውቀዋል፡፡ድርጅቱ ከተቋቋመበት ከ1949 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ በቀጣይ 2012 ዓ.ም የሚያጋጥመውን የአገልግሎት ውስንነት ለመቅረፍ አዲስ ቄራ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩም ተገልጿል፡፡ግንባታው በ2012 ዓ.ም ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ በቀን እስከ 26 ሺህ እንስሳት የእርድ አገልግሎት የመስጠት አቅም ይኖራል ተብሏል፡፡  
https://waltainfo.com/am/23955/
185
3ቢዝነስ
የኢፌዴሪ አየር ሃይል ለ735 አባላቱ የማእረግ እድገት ሰጠ
ፖለቲካ
September 10, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ አየር ሃይል ለ735 አባላቱ የማእረግ እድገት የሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 10ሩ ከመስመር መኮንንነት ወደ ከፍተኛ መኮንንነት የማእረግ እድገት ያገኙ ናቸው፡፡በተቋሙ ውስጥ ለረጅም አመታት ላገለገሉ እንዲሁም ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን አገልግለው ጡረታ ለወጡ 56 የቀድሞ አባላቶቹም የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል።በአየር ሃይል ደረጃ በተለያዩ ስራዎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላስመዘገቡ የተለያዩ የስራ ክፍሎችም ማበረታቻ ሰርተፍኬት መሰጠቱ ተገልጿል።በተጨማሪም የኢፌዴሪ አየር ሃይል ከመላው ሰራተኞች የሰበሰበውን 200 ሺህ ብር ለኢትዮጵያ ልብ ህሙማን መርጃ ማእከል መለገሱን ኢቢሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/31342/
69
5ፖለቲካ
ኮሚሽኑ በበዓል ወቅት ህብረተሰቡ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ አሳሰበ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 10, 2019
Unknown
በዘመን መለወጫ በዓል ህብረተሰቡ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን  አሳስቧል፡፡በበዓሉ ወቅት ከእሳ ፍጆታ መጨመርና ሰፊ የመዝናናት ስሜት ጋር ተያይዞ ሊፈጠር የሚችለውን የእሳት ቃጠሎና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን ትኩረት በመስጠት መከላከል እንደሚቻልም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው፡፡በመሆኑም በመኖሪያ ቤት እንደ ጧፍ፣ የጋዝና ኤሌክትሪክ ምድጃዎችን በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብሏል፡፡በተለይም በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ መሳሪያዎችን በአንድ ሶኬት ደራርቦ ከመጠቀም መቆጠብ፣ ከኤሌክትሪክ አጠቃቀም ችግር እሳት ቢነሳ በውሃ ለማጥፋት መሞከር አይገባም ነው ያለው፡፡ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ካምፕ ፋየር የእሳት አደጋ በማያስከትል መልኩ በጥንቃቄ መዘጋጀት እንዳለበትና በተለይ አስጊ በሆኑት እንደ ነዳጅ ማደያ ባሉ አካባዎች ግን ፈፅሞ መዘጋጀት እንደሌለበት አሳስቧል፡፡ጠጥቶ ከማሽከርከር በመቆጠብ ሊደርስ የሚችለውን የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት አስቀድሞ መገንዘብና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ቢከሰቱ  በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች መጠቀም እንደሚቻል አስታውቋል ፡፡ለዋናው ማዕከል 0111555300 ወይም 0111568601 ወይም በነፃ የሥልክ ጥሪ 939 መጠቀም እንደሚቻል ነው የገለፀው፡፡ኮሚሽኑ በዘጸኙም ቅርንጫፍ ፅህፈትቤቶቹ የ24 ሰዓት አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱንም ለዋልታ ቴሌቭዥን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡  
https://waltainfo.com/am/32715/
151
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሲሰራቸው የነበሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን አስታወቀ
ፖለቲካ
September 10, 2019
Unknown
የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሲሰራቸው የነበሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ኮሚሽኑ በዋናነት ከወሰን አስተዳደር፣ ራስን በራስ ከማስተዳደርና ከማንነት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ላይ በጥናት ላይ የተመሰረቱ የውሳኔ ምክረ ሀሳቦችን ለማቅረብ ታስቦ የተቋቋመ እንደሆነ ይታወቃል፡፡እስካሁንም በቅድመ ዝግጅት ስራው የአደረጃጀት፣ የግብዓት፣ የሰው ሀይል የሟሟላት፣ የአባላት ስነ-ምግባርና ስትራቴጂክ እቅድ የማዘጋጀት ስራዎች መስራቱን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ጣሰው ገብሬ እና ምክትል ኮሚሽነሩ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡በስትራቴጂክ እቅዱ የማንነትና የወሰን አስተዳደር፣ ራስን የማስተዳደርና የተቋማት ግንባታ መሰረት ያደረጉ ዋና ዋና ጉዳዮች ተካተውበታል ተብሏል፡፡በ2012 በጀት ዓመትም በማንነትና በወሰን አስተዳደር እንዲሁም ራስን በማስተዳደር ችግሮች አሉባቸው ተብሎ በተለዩ ቦታዎች ላይ ንኡሳን ኮሚቴዎችን በማቋቋም የሚሰራ እንደሆነም ተነግሯል፡፡ኮሚሽኑ በእነዚህም ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተለይ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/31343/
113
5ፖለቲካ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሞስኮ ገቡ
ፖለቲካ
September 9, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ሞስኮ ገብተዋል።ሚኒስትሩ በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ለቭሮቭ ጋር ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡በዚሁ ጉብኝት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ከሩሲያ ወገን ጋር በሚደረግ ዉይይት እንደሚሣተፉም ይጠበቃል።ጉብኝቱ የሁለቱን አገሮች የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የልማት ትብብር እንዲሁም የሣይንስና ቴክኖሎጂ ትብብር እንደሚያሳድግ እምነት ተጥሎበታል፡፡ሚኒስትሮቹ ሞስኮ ሲደርሱ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ አምባሳደር ጆርጂ ቶድዋ፣ በሩሲያ የኢፌዲሪ አምባሳደር አቶ ዓለማየሁ ተገኑ እንዲሁም የኤምባሲው ባልደረቦች አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በፈረንጆቹ 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
https://waltainfo.com/am/31338/
104
5ፖለቲካ
አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 87 ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 9, 2019
Unknown
አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 87 ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ገልፀዋል፡፡አቶ ብርሃኑ እንዳሉት አዲሱ አመት 2012ን ምክንያት በማድረግ  በይቅርታ  የሚለቀቁት ከሁሉም የፌደራል ማረሚያ ቤቶች የተውጣጡ ታራሚዎች ናቸው ፡፡በይቅርታ ከሚለቀቁት ውስጥ 439 ከሸዋሮቢት ፣ 367 ከቃሊቲ፣ 28ቱ ደግሞ ከዝዋይ  ማረሚያ ቤቶች  መሆናቸውንም ነው የገለፁት።አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ የሚለቀቁ ታራሚዎች በህግ ይቅርታ የማይጠየቅባቸው ወንጀሎችን ፈፅመዋል ተብለው በማረሚያ ቤት የቆዩ መሆናቸውን የኤፍቢሲ ዘገባ  ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/32714/
69
0ሀገር አቀፍ ዜና
ናይጄሪያ 600 ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ ልታስወጣ ነው
ፖለቲካ
September 10, 2019
Unknown
ናይጄሪያ በደቡብ አፍሪካ እየደረሰ ያለውን መጤ ጠል ጥቃት ተከትሎ 600 ዜጎቿን ልታስወጣ መሆኗን አስታወቀች።ሁለቱ ሀገራት እየደረሰ ያለውን ጥቃት ተከትሎ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።የተወሰኑ ናይጄሪያውያን ረቡዕ ዕለት በሁለት አውሮፕላን እንደሚወጡ በጆሀንስበርግ የሚገኘው የናይጄሪያ ቆንጽላ ቢሮ ለቢቢሲ አስታውቋል።ባለፈው ሳምንት በከተማዋ የውጪ ሀገራት ዜጎች የንግድ ተቋማት ላይ በደቦ በተፈፀመ ጥቃት አስር ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የውጪ ዜጎች መሆናቸው ታውቋል።ጥቃቱ የተጀመረው የዕቃ ጫኝ መኪና አሽከርካሪዎች ከሌላ ሀገራት የመጡ ግለሰቦች ስራችንን እየነጠቁ ነው በሚል የስራ ማቆም አድማ ካደረጉ በኋላ ነው።ደቡብ አፍሪካ ባላት የስራ እድል የተነሳ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በርካታ ወጣቶች የሚፈልሱባት ሀገር ናት።ምንም እንኳ የሀገሪቱ ምጣኔ ኃብት ቢያድግም በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥ ቁጥር አለ፤ ለዚህም አንዳንድ የሀገሪቱ ዜጎች ከሌላ ሀገር የመጡ ግለሰቦች ሥራቸውን እየነጠቋቸው እንደሆነ ያስባሉ።የናይጄሪያ ቆንፅላ ጄነራል ጎድዊን አዳማ እንዳሉት ከሆነ በመጤ ጠል ጥቃቱ የተነሳ ስጋት የገባቸውና ሀገሪቱን ለቅቀው መሄድ የሚፈልጉ ብቻ እንደሚሄዱ ተናግረዋል።በዚህ መካከል የናይጄሪያ ዲያስፖራ ኮሚሽን አቢኬ ዳቢሪ ከደቡብ አፍሪካ ለሚወጡ ዜጎች መንግሥታቸው የገንዘብ ድጋፍ እንደማያደርግ አስታውቀዋል።አቡጃ ውስጥ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ናይጄሪያ የደቡብ አፍሪካ መንግሥትን ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚሠራ ገልጸው ለተጎጂዎች ካሳ መክፈልም አለበት ብለዋል።በጆሀንስበርግ እሁድ እለትም ሌላ ግጭት ተቀስቅሶ የነበረ ሲሆን፣ ለግጭቱ መቀስቀስ ምክንያት የነበረው የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ ያደረጉት ንግግር ነው ተብሏል።በግጭቱ ወቅት መኪኖች ተሰባብረዋል ህንፃዎች ላይ ጥቃት ደርሷል። የደቡብ አፍሪካውያን ንብረት የሆኑ ሱቆችም ላይ ውድመት መድረሱ ተገልጿል።ከዚህ ቀደም ብሎ "መጤዎች ወደ መጣችሁበት ሂዱ" የሚል መፈክር የያዙ ሠልኞች እየዘመሩ ሰልፍ ማድረጋቸውንና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ንግግር ወደሚያደርጉበት ስፍራ ማምራታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል።ጥቃቱን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ያወገዙት ሲሆን ሚሊዮኖች ደቡብ አፍሪካውያን በሚኖሩባት ከተማ ሥርዓት አልበኝነት እንዲሰፍን እንደማይፈቅዱ ተናግረዋል።አክለውም በሀገሪቱ የሚገኙ የሌላ ሀገራት ዜጎች አብዛኞቹ ሕግ አክብረው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።ባለፈው ሳምንት የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሀሪ ናይጄሪያውያን በደቡብ አፍሪካ እየደረሰባቸው ባለው እንግልትና ጥቃት የተፈጠረባቸውን ቅሬታ ለመግለጥ የልዑካን ቡድን ልከዋል።ከፕሬዝዳንቱ የወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው የደቡብ አፍሪካ መንግስት ተጨባጭ እርምጃ በመውሰድ አፍሪካውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እንዲያስቆም ይጠይቃል።ባለፈው ሳምንት የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ 420 ነውጠኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገለጸ ሲሆን፣ ከእሁዱ ግጭት ጋርም በተያያዘ 16 ሰዎች መያዛቸውን አስታውቋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/33336/
307
5ፖለቲካ
የውጪ ሃገራት ገንዘቦችን በህገ ወጥ መንገድ ሲመነዝሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ቢዝነስ
September 10, 2019
Unknown
የውጪ ሃገራት ገንዘቦችን በህገ ወጥ መንገድ ሲመነዝሩ ከነበሩ ግለሰቦች ላይ  7 ሚሊየን 600 ሺህ የኢትዮጵያ ብር በላይ እና 53 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡በኮሚሽኑ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የማረጋገጥና የመከታተል ስራ በመስራትና ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ጳጉሜ 3 ቀን 2011 ዓ.ም በተጠርጣሪዎቹ ቤት ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ነው የተጠቀሰው ገንዘብ የተገኘው፡፡7 ሚሊየን 608 ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና 53 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦችን ከገንዘብ መቁጠሪያ ማሽን ጭምር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ሃላፊ ኮማንደር አወል አህመድ አስታውቀዋል፡፡  ተጠርጣሪዎቹ የውጪ ሃገራት ዜጎች የሚበዙባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየትና ቪላ ቤቶችን በመከራየት በህገ ወጥ መንገድ የውጪ ሃገራት ገንዘቦችን የመመንዘር ተግባር ሲያከናውኑ እንደነበርም ተብራርቷል፡፡ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ደላሎችን ጨምሮ 10 ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑንና  የምርመራው ውጤቱ የደረሰበትን ደረጃ በቀጣይ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግ ኮማንደር አወል ገልፀዋል፡፡  በድብቅ የሚከናወኑ መሰል ህገ ወጥ ተግባራት የሃገርን ኢኮኖሚ የሚያዳክሙና ጤናማ የገበያ ስርዓትን የሚጎዱ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ጥቆማ መስጠቱን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ነው ኮማንደሩ አክለው የገለፁት፡፡
https://waltainfo.com/am/23954/
171
3ቢዝነስ
የክልሉን ፖሊስ ለማዘመን እንደሚሰራ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
ፖለቲካ
September 10, 2019
Unknown
 የፖሊስ ኃይሉን ወቅቱን በሚመጥን መልኩ ለማደራጀት እና ለማዘመን ማቀዱን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡የአማራ ክልል መንግስት ያለ ሠላም ልማት እንደማይኖር በመረዳት የክልሉን የጸጥታ ኃይል ወቅቱን በሚመጥን መልኩ ለማደራጀት ማቀዱን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡የማዘመን ሥራውም የሕዝቡ ቁጥር መጨመርን፣ የኢንዱስትሪዎች፣ የከተሞች እና የትምህርት ተቋማት መስፋፋትን፣ የሆቴሎች እንዲሁም የጎብኝዎች ቁጥር መጨመርን ጋር ታሳቢ እንደሚያደርግ ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት፡፡በዚህም ከክልሉ አልፎ ሀገር ሊጠብቅ የሚችል የጸጥታ ኃይል በአዲስ መልክ ለመገንባት ዕቅድ መያዙን፣ ተግባራዊ ለማድረግም ጥናቱ መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡በጥናቱ መሠረትም የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝም፣ የእሳት አደጋ እና የባሕር ኃይል ፖሊስ በመገንባት ለሀገሪቱ አዲስ አሠራር ለማሳየት ታቅዷል፡፡ የቱሪዝም ፖሊስ ጎብኝዎች ያለምንም የጸጥታ ስጋት እንዲጎበኙ የማድረግ ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡በባሕር ዳር ከተማ የኢንዱስትሪ ፖሊሶች ሥራ ጀምረዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ባሉበት ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች በማስፋትም ፋብሪካዎችን ከጥቃት እንዲከላከል ይሠራል፡፡ በ2012 ዓ.ም ጀምሮ ይህንን ለማድረግ እንደሚሠራም ነው ኮሚሽነር አበረ የተናገሩት፡፡የክልሉን የጸጥታ ኃይል የደንብ ልብስ፣ የደሞዝ እና የጥቅማጥቅም ልዩነት ለማስተካከል ሲሰራ መቆየቱን የገለፁት ኮሚሽነሩ በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ሥራ የሚሆነውም ይህንን ማስተካከል እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ዓለማቀፍ ገጽታ ያለውን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለማስቆም እየተሰራ ስለመሆኑም ኮሚሽነር አበረ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ምሁራን፣ የኃይማኖት አባቶች እና መላው የክልሉ ሕዝብ ከጸጥታ ኃይሉ ጎን መቆም ህግን እንዲያስከብርም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/31339/
175
5ፖለቲካ
ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የፍትህ ቀን ይከበራል
ፖለቲካ
September 10, 2019
Unknown
ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የፍትህ ቀን “መደመር ለፍትህ” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ “የህግ ተገዢ ነኝ!” በሚል መሪ ቃል ሲከበር የቆየው የፍትህ ወር ማጠናቀቂያ ዝግጅትም በዛሬው ዕለት ይካሄዳልም ተብሏል።ፍትህን ማረጋገጥ ለነገ ይደር የማይባል ስራ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በማህበራዊ ድረገፁ አስታውሷል፡፡ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከ15 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበት ዝግጅት ከቀኑ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ይከናወናል፡፡የዘንድሮ ጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶችና ርዕሰ ጉዳዮች እየተከበሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
https://waltainfo.com/am/31340/
67
5ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከታሊባን ጋር የነበረውን የሰላም ስምምነት መሰረዛቸውን አስታወቁ
ፖለቲካ
September 9, 2019
Unknown
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከታሊባን ጋር የነበረውን የሰላም ስምምነት መሰረዛቸውን አስታወቁ።ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ የአፍጋኒስታኑን ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋህኒ እና የታሊባን መሪዎችን ለማግኘት ቀጠሮ ይዘው እንደነበር አስታውቀዋል።ይሁን እንጂ ሐሙስ ዕለት በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል በተፈጸመው እና ታሊባን ኃላፊነቱን በወሰደው ጥቃት አንድ የአሜሪካ ወታደር መገደሉን ተከትሎ ትራምፕ የሰላም ስምምነቱን ሰርዘዋል።ሁለቱ አካላት ከሰላም ስምምነት እንዲደርሱ የአሜሪካ መንግሥት እና የታሊባን ተወካዮች በኳታር ዶሃ ከዘጠኝ ጊዜ በላይ ተገናኝተው መክረዋል። የሰላም ስምምነቱ አደራዳሪዎች ከቀናት በፊት አሜሪካ እና ታሊባን 'በመርህ ደረጃ' ከሰላም ስምምነት ደርሰዋል ብለው ነበር።ታሊባን ፈጽሜዋለሁ ባለው ጥቃት አንድ የአሜሪካ ወታደር ከተገደለ በኋላ፤ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ "በአስቸኳይ ውይይቶቹ እና የሰላም ድርድሩ እንዲቆም አዝዣለሁ" ብለዋል።የሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚ ቢሆን ኖሮ አሜሪካ ወደ አፍጋኒስታን ካዘመተቻቸው ወታደሮች መካከል 5400 የሚሆኑት በ20 ሳምንታት ውስጥ ልታስወጣ ነበር።በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ በአፍጋኒስታን ከ14 ሺህ በላይ ወታደሮች አሏት። ሐሙስ ዕለት በካቡል መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ አሜሪካዊውን ወታደር ጨምሮ 12 ሰዎች ተገድለዋል።ታሊባን በምፈጽማቸው ጥቃቶች ዒላማ የማደርገው የውጪ ሀገር ኃይሎችን ነው ይበል እንጂ በጥቃቶቹ ለከፍተኛ ጉዳት የሚዳረጉት ንጹሐን የአፍጋኒስታን ዜጎች ናቸው።አሜሪካ እ.አ.አ. 2001 ላይ አፍጋኒስታንን ከወረረች ወዲህ ከ3500 በላይ የውጪ ሀገራት ጥምር ኃይሎች ተገድለዋል። ከእነዚህም መካከል 2300 የሚሆኑት አሜሪካውያን ናቸው።ባለፉት 18 ዓመታት ምን ያክል የአፍጋኒስታን ሲቪሎች፣ የመንግሥት ወታደሮች እና ታጣቂ ሚሊሻዎች ህይወታቸውን እንዳጡ በውል አይታወቅም።ከወራት በፊት የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው ሪፖርት መሰረት ከ32 ሺህ በላይ ሲቪሎች የተገደሉ ሲሆን፣ ሌሎች ተቋማት በበኩላቸው የውጪ ኃይሎችን ሲፋለሙ የነበሩ ከ42 ሺህ በላይ ሚሊሻዎች መገደላቸውን ይጠቁማሉ። (ምንጭ፡-ቢቢሲ) 
https://waltainfo.com/am/33995/
215
5ፖለቲካ
የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
ቢዝነስ
September 9, 2019
Unknown
ከልማት አጋሮችና ከዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ ጋር በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከልማት አጋሮችና ከዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ ጋር በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የውይይት መድረክን በንግግር ከፍተዋል፡፡ኢኮኖሚያዊ ገጽታውን ለመለወጥ የተሰሩትን ቁልፍ ክንውኖች ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያን በ2030 የአፍሪካ ብልጽግና ምልክት እንድትሆን የሚያስችለውን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡  ይህንኑም ለማሳካት የልማት አጋሮች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡  
https://waltainfo.com/am/23951/
69
3ቢዝነስ
የዴሞክራሲ ቀን እየተከበረ ነው
ፖለቲካ
September 9, 2019
Unknown
የዴሞክራሲ ቀን በመላ ሃገሪቱ እየተከበረ ነው።ቀኑ በተለይም በሸራተን አዲስ ሆቴል “በመደመር እሳቤ ጠንካራ እና ዘላቂ ዴሞክራሲን ለመገንባት እንነሳ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ ይገኛል።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ፥ አሁን ላይ የፍትህና የዴሞክራሲ ተቋማትን ለማጠናከር ማሻሻያዎች እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።ተቋማቱ ገለልተኛ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝም ነው ምክትል አፈ ጉባኤዋ የተናገሩት።አያይዘውም መንግስት እየወሰደ ያለውን ማሻሻያ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና መጠናከር መስራት ይገባልም ነው ያሉት።ምክትል አፈ ጉባኤዋ የሁሉም የሆነች ሃገር ለመገንባትና የዜጎችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለዚህ ስኬት ሁሉም ህብረተሰብ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።የሃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ ይገባል ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ ሁሉም ህብረተሰብ ለዴሞክራሲ ስርዓት መጎልበት የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።በስነ ስርአቱ ላይ የዴሞክራሲ ፅንሰ ሃሳብን የሚዳስሱ የስነ ፅሁፍ ስራዎችና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቲያትር ትምህርት ክፍል ተማሪዎች አማካኝት ሙዚቃዊ ተዉኔት ቀርቧል፡፡በተጨማሪም በዴሞክራሲ ላይ የሚያጠነጥን ዘጋቢ ፊልም ለታዳሚዎች ተሰራጭቷል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31337/
133
5ፖለቲካ
ተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያና ጂፒኤስ ሳይገጠምላቸው ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የተዘጋጀው መመሪያ ተግባራዊ መሆን ጀመረ
ቢዝነስ
September 9, 2019
Unknown
ተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ እና ጂፒኤስ ሳይገጠምላቸው ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ያዘጋጀውን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡መመሪያው ታህሳስ ፣2011 ዓ.ም አጋማሽ የፀደቀ ቢሆንም ተግባራዊ መሆን የጀመረው  ከሀምሌ 2011 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ነው ተብሏል፡፡መመሪያው ከመውጣቱ በፊት የግዥ ጥያቄ ያቀረቡና የግዥ ሂደት የጀመሩ የተሸከርካሪ አስመጪዎች  መመሪያው አይመለከታቸውም ተብሏል፡፡አዲሱ ቴክኖሎጂ በትራፊክ አደጋ ምክንያት እየተከሰተ ያለውን የሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ለመከላከል እንደሚረዳ የትራንስፖርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ይሄይስ ገልጸዋል፡፡በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል መንግስት ግንዛቤ ማስጨበጥን ጨምሮ መሳሪያውን በፍጥነት ወደ ስራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑንም ነው አቶ ሙሴ የገለፁት፡፡መንግስት ከባለሀብቶች ጋር በመተባበር የፍጥነት መገደቢያ እና ጂፒኤስ ቴክኖሎጂው ተገጥሞ ወደ ሃገር ለማስገባት እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ባለሃብቶች የፍጥነት መገደቢያና ጂፒኤስ መሳሪያውን በተሽከርካሪዎች ላይ አስገጥመው በማስገባት በተመጣጣኝ ክፍያ ደንበኞቻቸውን የሚያስከፍሉበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ ተደርሶ ወደ ስራ መገባቱም አቶ ሙሴ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/23952/
129
3ቢዝነስ
ኤጀንሲው ፈቃድ ወይም የእውቅና ፈቃድ እድሳት ሪፖርት ባልወጣለት የትምህርት ተቋም ቀድሞ መመዝገብ እንደማይቻል ገለፀ
ቢዝነስ
September 9, 2019
Unknown
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የ201 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የእውቅና ፈቃድ ሙሉ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡መረጃው በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመዝግበው መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የሚያገለግል መሆኑንም ነው ኤጀንሲው የገለፀው፡፡ወቅታዊ መረጃው እስከ 2011 ዓ.ም መጨረሻ ያለውን የሚያካትት ሲሆን በሂደት ላይ ያሉትን ተከታትሎ እንደሚያሳውቅም ገልጿል፡፡ይደርሳል በሚል የእውቅና ፈቃድ ወይም የእውቅና ፈቃድ እድሳት ሪፖርት ባልወጣለት የትምህርት ተቋም ቀድሞ መመዝገብ ክልክል እንደሆነም ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው፡፡  
https://waltainfo.com/am/23953/
65
3ቢዝነስ
የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ሊወያዩ ነው
ፖለቲካ
September 9, 2019
Unknown
የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ሊወያዩ ነው።ማቻር ከሳልቫ ኪር ጋር ለሚያደርጉት ውይይት ዛሬ ጁባ የገቡ ሲሆን፣ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታም ሳልቫ ኪርን ጨምሮ ከሌሎች ተቀናቃኝ ሃይሎች ጋር በተደረሰው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት ዙሪያ እንደሚወያዩ ተገልጿል፡፡የአሁኑ የማቻር ጉብኝት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት ተስፋን ሰጪ ነው የሚል እምነት ተጥሎበታል።በፈረንጆቹ 2011 ከሱዳን ተነጥላ ሉዓላዊ ሀገር የሆነችው ደቡብ ሱዳን ሁለት አመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ እርስ በርስ ግጭት ገብታ ሰላም ከራቃት ሰንብታለች።በወቅቱ ለተፈጠረው ግጭት ሳልቫ ኪር ሪክ ማቻርን ከስልጣን ማንሳታቸው መሆኑም ይነገራል።ይህን ተከትሎ የተፈጠረውን ቀውስ እልባት ለመስጠት ከአንድ አመት በፊት የሰላም ስምምነት ቢደረስም እስካሁን ተፈጻሚ ሳይሆን ቆይቷል።ለዚህ ደግሞ ሳልቫ ኪር ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታትና ሂደቱን ተፈጻሚ ለማድረግ የገንዘብ አቅም የለኝም የሚል ምክንያት ያቀርባሉ ነው የተባለው፡፡ (ምንጭ፡-ሬውተርስ)
https://waltainfo.com/am/33335/
119
5ፖለቲካ
በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና  ከ27 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ለርሃብ አደጋ ተጋልጧል
ቢዝነስ
September 8, 2019
Unknown
የአየር ንብረት ለውጥ፣ ግጭት እና ምጣኔ ሀብታዊ አለመረጋጋት በአፍሪካ ቀንድ ከ27 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ለርሃብ አደጋ እንዲጋለጥ ምክንያት መሆኑ ይፋ ተደርጓል፡፡የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ባለፈው ሳምንት በኬንያ ናይሮቢ በአደጋ መከላከል ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል፡፡በውይይቱ መጨረሻ ባወጣው መግለጫም አለም አቀፉ ማህበረሰብ አፋጣኝ ምላሽ ካልሰጠ በቀጣናው ተጨማሪ 20 ሚሊየን ሕዝብ ለርሃብ አደጋ ይጋለጣል ሲል ስጋቱን አስቀምጧል፡፡ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያም በከፍተኛ ደረጃ የምግብ እጥረቱ ተጠቂ ሀገራት ሊሆኑ ይችላሉ ነው የተባለው፡፡በቀጣናው እ.አ.አ በ2018 የተስተዋለው የዝናብ እጥረት፣ ግጭትና ምጣኔ ሀብታዊ አለመረጋጋት በ2019  እንደቀጠለ ነው ያለው ኢጋድ፤ ይህም የሀገራቱን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ፈታኝ እንደሚያደርገው አስጠንቅቋል፡፡አሁን ያለው ሁኔታ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ችግሩ የከፋ ነው፡፡ዘ ኢስት አፍሪካን ጠቅሶ ሲጂቲኤን እንደዘገበው ችግሩን ለመቋቋም ዓለም አቀፉ ግብረ ሰናይ ድርጅት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ኢጋድ ጠይቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32906/
123
3ቢዝነስ
ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እድሳት ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ሰጡ
ቢዝነስ
September 8, 2019
Unknown
 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በክረምት ለተደረገለት እድሳት የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ሰጥተዋል።ሌሎችም የነዚህን በጎ ፈቃደኞች አርአያነት በመከተል ህዝብን በነፃ የማገልገልና የመደገፍ ተግባርን ባህል እንዲያደርጉ ዶ/ር ዐቢይ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጴጥሮስ ሆስፒታል ያስገነባውን አዲስ ህንፃም በዛሬው እለት  መርቀዋል።የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን እንዳሉትም በጥቁር አንበሳ የተደረገው በጎ ተግባር ለሌሎች ሆስፒታሎችም በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ ነው።በቀጣይ ሌሎች ሆስፒታሎችም እድሳት እንዲደረግላቸው ሚኒስቴሩ ከባለ ሃብቱና ከማህበረሰቡ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/23950/
72
3ቢዝነስ
የብሄራዊ ኩራት ቀን በመስቀል አደባባይ በድምቀት ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 8, 2019
Unknown
የብሄራዊ ኩራት ቀን "አዲስ አበባ ቤቴ ፤ ኢትዮጵያዊነት ኩራቴ!" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በድምቀት ተከበረ፡፡በስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ  ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት በህዝቦቿ አንድነት መቆየቷን ጠቅሰው ፤ይህ አንድነት የሀገሪቱ ብሄራዊ ኩራት ነው ብለዋል፡፡አዲስ አበባ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ፣ የሁሉም ባህል መገለጫ  ዋና ከተማ እንደመሆኗ የዛሬውን ብሄራዊ የኩራት ቀን በዚህ መልኩ ነዋሪዎቿ  በድምቀት በማክበራቸው ክብር ይገባቸዋል ነው ያሉት፡፡የብሄራዊ የኩራት ቀን ብሄራዊ እሴቶችን  አጉልቶ በሚያሳይና ለነገ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንዲተባበር መነቃቃትን መፍጠር በሚያስችል መልኩ በከተማችን በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ይከበራል፡፡ከ250 ሺህ በላይ ሰው ተሳታፊ የሆነበት ህዝባዊ ትእይንት በመስቀል አደባባይ ከጠዋቱ 12፡30 ጀምሮ ተካሂዷል፡፡የመከላከያ ሰራዊት የወታደራዊ እና የአየር ሃይል ትርዒት ያቀረበ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎች እና የበረራ ሰራተኞች ጨምሮ ብሄራዊ ኩራት የሆኑ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተቋማት የሚወከሉበት ትርዒት ቀርቧል፡፡በበዓሉ ላይ ከፍተኛ የፌደራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32710/
144
0ሀገር አቀፍ ዜና
የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ደቡብ አፍሪካን ሊጎበኙ ነው
ፖለቲካ
September 8, 2019
Unknown
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት መሀመዱ ቡሃሪ ደቡብ አፍሪካን ሊጎበኙ ነው፡፡ፕሬዚዳንቱ ደቡብ አፍሪካን ለመጎብኘት የተሰናዱት በደቡብ አፍሪካ በውጪ ሀገራት ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት ተከትሎ ነው፡፡በቀጣዩ ወር የሚደረገው የፕሬዚዳንቱ ይፋዊ ጉብኝት  የሀገራቱን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ስለመሆኑ የሲጂቲኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡ቀደም ሲል የናይጄሪያ ልዩ ልዑክ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ የመከረ ሲሆን፤ የፕሬዚዳንት ቡሃሪ ጉብኝትም የተጀመረውን የሁለትዮሽ ምክክር ይበልጥ መስመር ለማስያዝ እንደሚያስችል ይጠበቃል፡፡ይሁንና የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን ግሩፕ እና በሱፐርማርኬት የሚታወቀው ሾፕራይት በናይጄሪያ የሚገኙ ቅርንጫፎቻቸውን ዘግተዋል፡፡ተቋማቱ በናይጄሪያ ቢሮዎቻቸው የሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ነው ከዚህ እርምጃ ላይ የደረሱት ተብሏል፡፡በናይጄሪያ በሚገኘው ኤምባሲዋ ላይ የአፀፋ ጥቃት በመሰንዘሩ ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘው ኤምባሲዋን መዝጋቷ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ በመኖርና በመስራት ላይ የሚገኙ ዜጎቼ ስጋት ላይ ናቸው በሚል ናይጄሪያ ነፃ የአውሮፕላን ትኬት ማቅረቧ ይታወሳል፡፡በደቡብ አፍሪካ በውጪ ሀገራት ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት በርካታ ሀገራት ማውገዛቸውም አይዘነጋም፡፡
https://waltainfo.com/am/33334/
128
5ፖለቲካ
ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ድጋፍ የሚደረግላቸው ህፃናትና ወጣቶችን በብሔራዊ ቤተ መንግስት ምሳ ጋበዙ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 8, 2019
Unknown
ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የ2012 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና በጎ አድራጊዎች ድጋፍ ለሚደረግላቸው ህፃናት እና ወጣቶችን በብሔራዊ ቤተ መንግስት የምሳ ግብዣ አድርገውላቸዋል፡፡ፕሬዚዳንቷ  ዓመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የብልፅግና እንዲሆንላቸውም መመኘታቸውን ከፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32712/
38
0ሀገር አቀፍ ዜና
የብሄራዊ ኩራት ቀን በሚሊኒየም አዳራሽ ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 8, 2019
Unknown
የብሄራዊ ኩራት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ “አዲስ አበባ ቤቴ ኢትዮጵያዊነት ኩራቴ” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየም አዳራሽ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል፡፡የፌደሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዚሁ ወቅት አንዱ ብሄር ለሌላው ብሄር ክብር እና የኩራት ምንጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡አንዱ ሀይማኖት ለሌላው ሀይማኖት ኩራትና ክብሩ ነው ያሉት አፈጉባኤዋ፤  ሁሌም እንደኮራንና እንደተከባበርን እንድንቀጥል ሁሉም ኢትዮጵያዊ  ህብረ-ብሄራዊነቱንና አንድነቱን  እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡አፈ ጉባኤዋ አክለውም ኢትዮጵያ የምትባል የገናና ታሪክ ባለቤት፣ የስልጣኔ መሰረትና ተምሳሌት የሆነች የሀገር ያለችን ኩሩ ህዝብ ነን፣ ኢትዮጵያውያን ተከባበረንና ተደጋግፈን ማደግ እንደምንችል በተግባር ለዓለም ህዝብ አሳይተናል ብለዋል።ቀጣዩ የ2012 አዲስ ዓመትም የሁሉም የሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሰላምና ደህንነት ተጠብቆ ዓመቱ የደስታና የኩራት ጊዜ እንዲሆን ተመኝተዋል።በርካታ የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎችም  በዚህ በዓል ላይ ታዳሚ ሆነዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32713/
109
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ በሮበርት ሙጋቤ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 7, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሮበርት ሙጋቤ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው፤ ለዚምባቡዌ ህዝብና መንግስት መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ የቀድሞው የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ጋብሬል ሙጋቤን የአፍሪካ የነፃነት መሪ ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡የቀድሞ የዝምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ95 ዓመታቸው በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል፡፡ህልፈታቸውን ተከትሎም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የተሰማቸውን ሀዘን በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚምባቡዌ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ብሄራዊ የሀዘን ቀን የታወጀ ሲሆን፤  የሀገሪቱ አንጋፋ ፓርቲ ዛኑ ፒኤፍም የጀግና ክብር ሰጥቷቸዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32708/
71
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአፍሪካ ህብረት በሱዳን የህበረቱ አባልነት ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱን አስታወቀ
ፖለቲካ
September 7, 2019
Unknown
የአፍሪካ ህብረት በሱዳን የህበረቱ አባልነት ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱን አስታወቀ፡፡የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት ስልጣኑን ለሲቪል ማጋራት አለበት በሚል በሳለፍነው የአውሮፓዊያኑ ሰኔ ወር ከህብረቱ አባልነት ማገዱ የሚታወስ ነው፡፡.የህብረቱ የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት በትላትናው እለት በአዲስ አበባ ባካሄደው ስብሰባ በሱዳን አሁን ላይ እየታየ ያለውን ለውጥ ተከትሎ አገዳውን ማንሳቱን ይፋ አድርጓል፡፡ህብረቱ እገዳውን በጣለበት ወቅት የህብረቱ የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ በሀገሪቱ ያለው የስልጣን ሽግግር ሁሉን አሳታፊና ሙያዊ ምክክር እንዲካሄድበት የመፍትሄ ሀሳብ አቅርቦ እንደነበር ይታወቃል፡ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ስልጣኑን ለሲቪሎች አሳልፎ እንዲሰጥ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ግፊት ሲደረግ ከቆየ በኋላ ከወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤቱ እና ከሲቢሎች የተውጣጣ ሉዓላዊ ምክር ቤት ተቋቁሟዋል፡፡በዚሁ ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስተርነት የተሰየሙት አብደላ ሃማዶክ አዲሱን ካቢኒያቸውን በዚህ ሳምንት ማቋቋማቸው ይታወቃል፡፡፡፡ለበርካታ ወራቶች በሱዳን በተካሄደው ተቃውሞ ሀገሪቱን ለ30 አመታት ያስተዳደሯት ኦማር ሀሰን አል በሽር ከስልጣን መነሳቸው የሚታወስ ነው። (ምንጭ፡-ሲጂቲኤን) 
https://waltainfo.com/am/33333/
131
5ፖለቲካ
ሀገር አቀፍ የሰላም ቀን የእግር ጉዞ ተካሄደ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 7, 2019
Unknown
ሀገር አቀፍ የሰላም ቀን የእግር ጉዞ በዛሬው ዕ2ለት ተከበረ፡፡ጳጉሜ 2 ቀን በመላ ሀገሪቱ የሰላም ቀን ሆኖ እየተከበረ ሲሆን፣ የሰላም ሚኒስቴርም ከተለያዩ አጋሮች ጋር በመሆን ቀኑን በእግር ጉዞ አስቧል፡፡እለቱ የኢትዮጵያ የሰላም ማዕከል የመሰረተ ድንጋይ የመጣል ፕሮግራም እና የፖናል ዉይይት እና የቲያትርና የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ይከበራል።የእግር ጉዞው “ሰላምን እተክላለሁ ለሀገሬ” በሚል መሪ ሃሳብ ከወሎ ሰፈር አደባባይ እስከ ጊዮን ሆቴል ድረስ በፌዴራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ ታጅቦ ነዉ የተካሄደው። (ምንጭ፡-የሰላም ሚኒስቴር) 
https://waltainfo.com/am/32709/
66
0ሀገር አቀፍ ዜና
ህዝቡ አንድነቱን በማጠናከር ለየትኛውም ፈተና ሳይንበረከክ ለስኬት ሊሰራ ይገባል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ
ፖለቲካ
September 7, 2019
Unknown
ህዝቡ አንድነቱን በማጠናከር ለየትኛውም ፈተና ሳይንበረከክ ለስኬት ሊሰራ እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።አቶ ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አዲሱን አመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፥ በ2012 ዓ.ም ለተሻለ ተጠቃሚነት ይሰራል ብለዋል።በ2011 ዓ.ም የተገኙ ስኬቶችን በማጠናከርም ለ2012 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ህብረተሰቡ የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ነው ያሉት።በቀጣዩ በጀት አመትም መንግስት ህዝቡን የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም አንስተዋል።አዲሱ አመት ስኬታማ ስራዎች የሚሰሩበት፣ ሰላም የሚረጋገጥበት፣ የህግ የበላይነት ለማስከበር የሚሰራበት፣ ህዝቡን ከድህነት ለማውጣት የተጀመሩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን የምናስቀጥልበት እና ስራ አጥ ዜጎች የተሻለ ስራ የሚያገኙበት እንደሚሆንም ተናግረዋል።በፖለቲካው ዘርፍም በ2011 ዓ.ም የታዩ መልካም ስራዎችን በማስቀጠል ስኬታማ ስራዎች እንደሚሰሩም ገልጸዋል።እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ የህብረተሰቡ ኑሮ እንዲሻሻልም በኢኮኖሚው ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ።በየደረጃው ያለ የመንግስት አመራር የተያዙ እቅዶችን ለማስፈጸም በተጠያቂነት እንዲሰራም አሳስበዋል።ባለፉት ሁለት የክረምት ወራት በዜግነት አገልግሎት የችግኝ ተከላን ሳይጨምር ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ስራ መሰራቱንም አስረድተዋል።በዚህም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰው፥ ህብረተሰቡ ላደረገው ተሳትፎም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ይህ የህብረተሰቡ ተሳትፎ በ2012 በጀት አመት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅሰዋል።
https://waltainfo.com/am/31335/
157
5ፖለቲካ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 74ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ፖለቲካ
September 7, 2019
Unknown
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 74ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።ምክር ቤቱ በሆርቲካልቸር፣ የቁም እንስሳት እና ቆዳና ሌጦ ዘርፎች ግብይትን በተመለከተ በአስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር አዋጅ ላይ ለውጥ ለማድረግ በተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቷል።በዚህም ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተሰጥተው የነበሩ የሆርቲካልቸር ዘርፍ ልማትና ግብይትን የተመለከቱ ስልጣንና ተግባራት ለግብርና ሚኒስቴር እንዲሰጡ ወስኗል።እንዲሁም ለግብርና ሚኒስቴር ተሰጥተው የነበሩ የቁም እንስሳት የቆዳና ሌጦ ግብይትን የሚመለከቱ ስልጣንና ተግባራት ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሰጡም ተወስኗል።ከዚህ ባለፈም በሰላም ሚኒስቴር በቀረበውና በሳይበር ሰራዊት ማፍረሻ ረቂቅ ደንብ ላይም ተወያይቶ ረቂቅ ደንቡ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል።ኢንስቲቲዩቱ እንዲያከናውናቸው የተዘረዘሩ ተግባራት በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊከናወኑ የሚችሉ መሆኑና በኢንስቲቲዩት ደረጃ መቋቋሙና ትምህርትን በዚህ ደረጃ መስጠቱ ሀገሪቱ ላይ የበጀት ጫና የሚፈጥር መሆኑ ለኢንስቲቲዩቱ መፍረስ ምክንያት ነው ተብሏል።በተጨማሪም ምክር ቤቱ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በቀረበውና የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የገቢ ማስገኛ ድርጅቶችን ለማስተዳደር በተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማሻሻያ በማከል እንዲጸድቅ ወስኗል፡፡በመጨረሻም ምክር ቤቱ በማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር በቀረቡት አባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበር ከፍተኛ ደረጃ የሸክላ አፈር፣ የጂፕሰም እና ላይምስቶን ማዕድን ማምረት ፈቃድ ስምምነቶች ላይ በመወያየት ስምምነቶቹ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል እንዲፈረሙ ይሁንታ ሰጥቷል። መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31336/
178
5ፖለቲካ
የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት ለጉብኝት ክፍት ሆነ
ፖለቲካ
September 6, 2019
Unknown
የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት ዛሬ ለጉብኝት ክፍት ሆኗል፡፡ከዛሬ ጳጉሜ 1 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. እሥር ቤቱ ለሕዝብ እይታ ክፍት እንደሚሆን ነው የተገለጸው፡፡መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈፀምበት እንደነበረ በማመን እንዲዘጋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ እና ሌሎች የፍትህ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የቀድሞው እስር ቤት ለሕዝብ እይታ የበቃው።
https://waltainfo.com/am/31334/
55
5ፖለቲካ
አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ በ2012 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ስራ ላይ በሚውልበት አግባብ ላይ ገለጻ ተደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 6, 2019
Unknown
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ጋር ባካሄደው የጋራ መድረክ አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ፍኖተ ካርታ በ2012 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ስራ ላይ በሚውልበት አግባብ ላይ ገለጻ ተደርጓል፡፡የዓለም ነባራዊ የቴክኖሎጂ ደረጃ ጋር የሚጓዝ ተወዳዳሪ ትውልድ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚደርጉት ድጋፍ የሚጠበቅ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማሪያም ገለጹ፡፡በትምህርቱ ዘርፍ የሚስተዋለውን ክፍተት ለመድፈን ሲባል መንግስት ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ እያደረገ ያለው ማሻሻያ እና ክለሳ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚዘልቅም በፍኖተ ካርታው ተዳሷል፡፡ከግል የትምህርት ተቋማት ጋር በተደረገው የምክክር መድረግ እንደተብራራዉም ዓለም ባሁኑ ወቅት ወደ ተሸጋገረችበት የአራተኛው የቴክኖሎጂ ዘመን የሚጠይቀውን ብቃትና አቅም ለማዳበር ተማሪዎች ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር እንዲራመዱ ይፈለጋል፡፡ሃገሪቱ ባለፉት 20 ዓመታት በትምህርቱ ዘርፍ ተደራሽነት ላይ የሰራቻቸው ጉልህ ስኬቶች ተጠቃሽ ቢሆኑም በጉዞው ላይ የገጠሙ የጥራት ጉድለቶች በትኩረት ሊሰራባቸው የሚገባ ስለመሆኑ ነው የተብራራው፡፡የተማሪዎች የሳይንስ ትምህርት ውጤት እጅጉን አሽቆልቁሎ ተስተውሏል፡፡ ብቃት ያላቸው መምህራን የማፍራት ችግር ደግሞ ለዚህ ጉልህ ሚናን ተጫውቷል ነው የተባለው፡፡ ለአብነትም ከ2006-2009 በተደረገው ጥናት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከተወዳደሩት መምሀራን የተሰጠዉን ፈተና ከ50 ከመቶ በላይ ማስመዝገብ የቻሉት የተፈታኞቹ 11 በመቶ ብቻ መሆኑም በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡ለዚሁ ክፍተት እንደማቃለያነት የተለያዩ መፍትሄዎች ተወስደዋል፡፡ ለአብነትም የተማሪዎች የተግባቦት አቅም፣ የማገናዘብ እና የግብረገብነት አቅማቸውን በሚያበለጽግ መልኩ የተቃኙ አዳዲስ ኮርሶች ተቀርጸው ከአዲሱ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ት/ት ተቋማት መሰጠት እንደሚጀመርም በመድረኩ ይፋ ሆኗል፡፡እስካሁን በተደረገውና በመድረኩም የቀረበው ጥናት እንደሚያመለክተዉ የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከግሉ ዘርፍ ጋር ሲነጻጸር የተሻለ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን እንደሚያበቁ ነው የተገለጸው፡፡ ይሁንና የግሉ ዘርፍ በተደራሽነትም ሆነ በጥራቱ ማሻሻያ ከፍተኛ ስራ የሚጠበቅበት መሆኑን በመግለጽ ጥናቱ የመፍትሄ ሃሳቦችን በማመላከት በተሳታፊዎች ተመክሮበታል፡፡ዋልታ ያነጋገራቸው የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች በበኩላቸው በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይ በየደረጃው ሲመክሩበት መቆየታቸውን ገልጸው፤ ዘርፉ የታለመለትን ጥራት ያለው የሰው ኃይል ለኢንዱስትሪው እንዲያቀርብ ከወዲሁ ትስስሮች እንዲፈጠሩ ጠይቀዋል፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ለግሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘርፍ እገዛ እንደሚያደርግ ነው ያስታወቀው፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32704/
277
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሱዳን  አዲሱ  ካቢኔዋን  በጠቅላይ ሚኒስትሯ በኩል ይፋ አደረገች
ፖለቲካ
September 6, 2019
Unknown
ሱዳን የሽግግር መንግስት ካቢኔ ማዋቀሯን ጠቅላይ ሚኒስትር አብድላ ሃምዶክ አስታውቀዋል፡፡የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ የተቋቋመ የመጀመሪያ ካቢኔ መሆኑም ተገልጿል፡፡አዲሱ ካቢኔ 18 ሚኒስትሮችን ያካተተ ሲሆን ፤ ከእነዚህ ውስጥ አራቱ ሴቶች ናቸው፡፡ይሁንና የመሰረተልማትና ትራንስፖርት እንዲሁም እንስሳትና ዓሳ ሃብት ሚኒስትሮች ስም እስካሁን ይፋ አልሆነም፡፡የቀድሞው የዓለም ባንክ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ኢብራሂም ኤልባድዊ የገንዘብ ሚኒስትር በመሆን ተሰይመዋል፡፡የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት የሱዳን መንግስት ካቢኔውን በማሳወቁ እና በተለይም የሴቶች የካቢኔ ተሳትፎን ለማሳደግ የደረሰበትን ውሳኔ  አድንቀዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/33332/
75
5ፖለቲካ
የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ለ152ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች እዉቅና ሰጠ
ቢዝነስ
September 6, 2019
Unknown
በእውቅና ስነስረአቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ "ግብርን በመደበቅ ሰላማችሁን የምታጡ ነጋዴዎች ግብርን በመክፈል ሰላማችሁን ግዙ"ብለዋል፡፡የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን በ2011 ዓ.ም በታማኝነት በግንባር ቀደም ግብራቸዉን በአግባቡ ክፍሏል ያላቸዉን ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮችና የግብር አምባሳደሮች ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል እዉቅናና ሽልማት ሰቷቸዋል፡፡ በመድረኩ ላይ ተገኝተዉ ለግንባር ቀደም ግብር ከፋዮቹ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ኦሮሚያ በርካታ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያለበትና ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ያለበት ክልል እንደመሆኑ በክልሉ በሚመረተዉ ኢኮኖሚ ልክ ገቢ እየተሰበሰበ አይደለም ብለዋል፡፡ግብር ለአንድ አካል የሚከፈል ሳይሆን ለህዝብ የሚከፈል በመሆኑ መሰረተ ልማትን ለማሟላትና ለዜጎቻችሁ በግብራችሁ ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያ የምትገነቡ ስለሆናችሁ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል፤ብለዋል፡፡ በታማኝነት ግብርና ታክስን በአግባቡ የምትከፍሉ ታማኝ ግብር ከፋዮች ወደ የትኛዉም የክልሉ ቢሮዎች ለአገልግሎት ስትመጡ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸዉና የክልሉ መንግስት ለሚፈልጉት አገልግሎት ተገቢዉን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸዉ ገልጧል፡፡ የክልሉ የገቢዎች ባለስልጣን ሃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸዉ አገራችን በአፍሪካ ካሉ አገራት ግብርን በመስብስበ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፤ ከአገሪቱ እድገት አንፃር ተገቢዉ ግብር እየተሰበሰበ ባለመሆኑ ለግብር ትኩረት ተሰቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር ምኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ አባ ገዳዎች ፤ታዋቂ አትሌቶችና አርቲስቶች ተገኝተዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/23949/
169
3ቢዝነስ
ደስታ መሰል የእንሰሳት በሽታን እ.ኤ.አ እስከ 2027 ለማጥፋት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 7, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ በጎችና ፍየሎችን የሚያጠቃዉን ደስታ መሰል የእንሰሳት በሽታ እ.ኤ.አ በ2027 ለማጥፋት እቅድ አዉጥታ እየሰራች መሆኗን አስታወቀች፡፡የግብርና ሚኒስቴር እንደገለፀዉ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ በ2011 ዓ.ም በ72 ሚሊዮን ብር በጀት ድንበር ዘለል የእንሰሳት በሽታን ለማጥፋት ነጻ የክትባት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ የበሽታዉን መድሀኒትም በሀገር ዉስጥ እየተመረተ ነው፡፡ይህ ደስታ መስል የበጎችና ፍየሎች በሽታ ከእንሰሳት ወደ እንሰሳት በቫይረስ የሚተላለፍ ሲሆን በሰዉ ላይ የሚያደርሰዉ ጉዳት እንደሌለ ተገልጿል፡፡ሀገሪቱ ከእንሰሳት ሀብት ሽያጭ የምታገኘዉ የዉጭ ገቢ ላይ በሽታዉ ተፅዕኖ እንደሚኖረዉ ተነግሯል፡፡የአዉሮፓ ህብረትንና የአለም የምግብ ድርጅትን የመሳሰሉ መንግታዊ ያልሆኑ አለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ በሽታዉን ለማጥፋት የምታደርገዉን ጥረት እየደገፉ ይገኛሉ፡፡ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታን ለማጥፋት ቁጥጥር የሚያደርግ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ ከ2016 ጀምሮ ሲተገበር ቆይቷል፡፡ በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ስራዎችን የሚያሳይ የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
https://waltainfo.com/am/32706/
111
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠ/ሚ ዐቢይ በ2019 የሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ አበረከቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 7, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአውሮፓውያኑ የ2019 የሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ አበረከቱ።ለሰባት ተከታታይ ዙር በዚህ ክረምት በሃዋሳ በአገልጋይ እና በመልካም ወጣት ፕሮጀክት መሪ ዮናታን አክሊሉ አስተባባሪነት ሲካሄድ የነበረው መርሃ ግብር የመዝጊያ ስነ ስርዓት በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።በስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተገኝተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዝግጅቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት መልካም ወጣት ማለት ከማስመሰል ወደ መምሰል የሚያድግ መሆኑን ተናግረዋል።ይህም ማለት ወደ እውቀት፣ ጥበብና ፍቅር ወደ መስጠት ማደግ መሆኑን ጠቅሰዋል።ሱስ ሀሺሽ ብቻ አደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ዘርን ከዘር እና ሀይማኖትን ከሃይማኖት ማባላትም ሱስ ነው ብለዋል።የውሸት፣ የዘረኝነት እና የዳተኝነት ብዙ ሱሰኛ ባሉበት ሀገር እናንተ ለማስተማሪያነት ተመርጣችኋል ብለዋል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያውያን ክብር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አሁን የፖለቲካ እና የዘር አጀንዳችን መጠቀሚያ እያደረግናት ነው ብለዋል።የፕሮቴስታንት አምነት ተከታዮች የኦሮቶዶክስ ሀይማኖትን ማክበር እና መውደድ የምርጫ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ግዴታችሁም ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።ቤተክርስቲያኗ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ አሻራ ማስቀመጧን በማንሳት፥ ቤተክርስቲያኗ ከእነ ክብሯ እንድትቀጥል እንፈልጋለን ነው ያሉት።ሲያጠቃልሉም መልካም ወጣቶችም ሆኑ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ካሉበት የከፍታ ስፍራ እንዳይለቁ አሳስበዋል።የመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ ሀሳብ እንዳስደሰታቸው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በቅርቡ ኬሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለማዕከሉ ግንባታ እንዲውል አበርክተዋል።የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው እንዲህ ዓይነቱ በራስ ተነሳሽነት የነገን ባለ ተስፋዎች እና የሀገር ሀብት የሆኑትን ወጣቶች በማሰባሰብ ከወራት በላይ በጎ መምከር እና በጎ ማስታጠቅ በፈጣሪም በፅድቅ ትልቅ ቦታ እንዳለው እና ለሀገርም ትልቅ ታሪክ ሰሪነት መሆኑን ገልጸዋል።ሁሉም በየደረጃው በዚህ በመቅናት እና በመመኘት የራሱን ታሪክ መስራት እንዳለበትም አንስተዋል።እንዲህ ይቅርታና ፍቅርን የሚያስተምሩ ሺዎች ከተሰለፉ ወደ ሚሊዮኖች አድገን በአጭር ጊዜ ራዕያችንን እናሳካለን ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።2009 ዓመተ ምህረት ላይ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት በየክረምቱ ሲከናወን ቆይቷል።
https://waltainfo.com/am/32707/
266
0ሀገር አቀፍ ዜና
የወጪ ንግድ ኮንትራት ክህደት በሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ መሆኑ ተገለጸ
ቢዝነስ
September 6, 2019
Unknown
የወጪ ንግድ ኮንትራት ክህደት የሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፈቃድ እስከ ማገድ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።ሚኒስቴሩ በ2012 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ የተሻለ ገቢ ለማግኘት የሀገሪቱን አቅም መነሻ ያደረገ እቅድ አዘጋጅቶ እና የቁጥጥርና አመራር ስርዓት ዘርግቶ እየተሰራ መሆኑን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተናግረዋል፡፡በሚኖረው ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል በትክክል  የተቀመጠውን ህጋዊ አሰራር ተከትለው የሚሰሩ ነጋዴዎችን በመለየትና በመደገፍ ጥረት እንደሚደረግ የተመለከተ ሲሆን፤ በህገ-ወጥ ተግባር ተሰማርተው በተገኙት እና የገቡትን የኮንትራት ውል በሚክዱ ነጋዴዎች  ላይ የንግድ ፈቃድ እስከ ማገድ የሚደርስ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።ሚኒስቴር ዴኤታው አምባሳደር ምስጋኑ በተያዘው በጀት ዓመት የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር፣ ህገ-ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በመከላከል እንዲሁም የወጪ ንግድ ምርቶች የግብይት ማዕከላትን አሰራር በማቀላጠፍ ህጋዊ ለሆነው የንግዱ ማህበረሰብ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል፡፡በተለይ በአስገዳጅነት በምርት ገበያ የሚያልፉ ቡና፣ ሰሊጥ፣ ነጭ ቦሎቄ፣ ቀይ ቦሎቄ፣ አኩሪ አተር፣ ማሾ እና ኑግ ምርቶች የኮንትራት አስተዳደር ስርዓት ተዘርግቶላቸው ነጋዴዎች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በሚሆኑበት አሰራር ውስጥ እንዲያልፉ ይደረጋል ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው።በወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች የገንዘብ ትርፍ ከማግኘት በተጨማሪ ለውጭ ምንዛሪ ግኝትና ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የሚሰሩ መሆኑን አውቀው በታማኝነት መስራት እንዳለባቸውም መናገራቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። 
https://waltainfo.com/am/23948/
178
3ቢዝነስ
ጠ/ሚ ዐቢይ በቻይና ነፃ የትምህርት እድል ላገኙ 288 ተማሪዎች ሽኝት አደረጉላቸው
ሀገር አቀፍ ዜና
September 6, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቻይና ነፃ የትምህርት እድል ላገኙ ተማሪዎች በተዘጋጀ የመሸኛ ዝግጅት ላይ ተገኝተው ሽኝት አደረጎላቸዋል፡፡እነዚሁ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ መርሀግብር ለመሰልጠን የተመረጡ ተማሪዎች በቻይና የንግድ ሚኒስትር መሪነት ሀገሪቱ ከሌሎች ሀገራት ጋር የሚኖራትን ተግባቦትና ትብብር ለማጠናከር ባቀደው ሞፍኮም በሚባለው የነፃ ትምህርት እድል የታቀፉ ናቸው::ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቻይና መንግስት ግለሰቦችን ለማስተማር የምታደርገውን ድጋፍ በማድነቅ ተማሪዎቹም በሁለቱ ሀገራት መካከል እንደ ድልድይ ሆነው እንደሚያገለግሉ ገልፀዋል::ተማሪዎቹም የኢትዮጵያን ችግሮች ለማቃለል ቁልፉ እውቀት መሆኑን በመገንዘብ ሲመለሱ ሀገራቸው ብዙ እንደምትጠብቅባቸው አስታውሰዋቸዋል::ኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት ትኩረት በመስጠትና የነፃ ትምህርት እድሎችን በማመቻቸት ላይ ትገኛለች:: በሞፍኮም ፕሮግራም ከ800 በላይ ከሁሉም የፌዴራል ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችና የክልል መንግስታት የተውጣጡ ባለሙያዎች አጫጭር ስልጠናዎችን ወስደዋል::በተጨማሪም እስከ አሁን ከ400 በላይ የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በዚህ አመት ብቻ 228 ግለሰቦች የከፍተኛ ትምህርታቸውን በቻይና ለመከታተል እድል አግኝተዋል:: መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/32703/
125
0ሀገር አቀፍ ዜና
የቀድሞ ዝምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 6, 2019
Unknown
የቀድሞ የዝምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ለሶስት አስር አመታት ዝምባቢዌን የመሩት ሙጋቤ፣ በፈረንጆቹ ህዳር 2017 በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ነው ከስልጣናቸው የተነሱት፡፡ሙጋቤ በሕመም ላይ ቆይተው ማረፋቸውንም ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል፡፡የዝምባብዌ የትምህርት ሚኒስትር ፋድዛይ ማሂር እረፍታቸውን አስመልክቶ በትዊተር ገጻቸው በኩል የነፍስ ይማር መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33470/
46
0ሀገር አቀፍ ዜና
ናይጄሪያ በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ የሀገሪቱ ዜጎች ነፃ የአውሮፕላን ትኬት አቀረበች
ሀገር አቀፍ ዜና
September 6, 2019
Unknown
በደቡብ አፍሪካ በውጭ ሀገራት ዜጎች ላይ ያተኮረ ጥቃት መቀስቀሱን ተክትሎ ናይጀሪያ በሀገሪቱ በመኖርና በመስራት ላይ የሚገኙ ዜጎች ወደ ናይጄሪያ ይመለሱ ዘንድ  ነፃ የአውሮፕላን ትኬት አቅርባለች ፡፡የናይጄሪያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው ፤ከደቡብ አፍሪካ ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ዜጎች የነፃ የአውሮፕላን ጉዞ ትኬትን ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡ የሰላም አየርመንገድ ሃላፊ አለን ኦኦንይማ ከነገ ዓርብ ጀምሮ ከደቡብ አፍሪካ ወደ ናይጄሪያ መመለስ ለሚሹ ዜጎች በነፃ ዜጎችን የሚያመላልስ አውሮፕላን ደቡብ አፍሪካ  እንደሚላክና  ፈቃደኛ ለሆኑ ናይጄሪያውያን የነፃ የአየር ትራንስፖርት ግልጋሎት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ወደ ሀገራቸው የመመለስ ፍላጎቱ ያላቸው ዜጎች በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ የናይጀሪያ ከፍተኛ ኮሚሽን መረጃዎችን መውሰድ እንዳለባቸውም ተገልጿል፡፡ከዚህ አስቀድሞ የናይጄሪያ ልዩ መልዕክተኛ ቡድን በዛሬው ዕለት በወቅታዊ የደቡብ አፍሪካ ሁኔታ ዙሪያ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጋር እንደሚወያይም ነው የሲጂቲኤን ዘገባ ያመለከተው፡፡ በደቡብ አፍሪካ በውጭ ሀገራት ዜጎች ላይ ያተኮረ ጥቃት መቀስቀሱን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸው አስፈላጊውን የደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያዎችን ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡  
https://waltainfo.com/am/33469/
134
0ሀገር አቀፍ ዜና
ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘው ኤምባሲዋን ዘጋች
ሀገር አቀፍ ዜና
September 6, 2019
Unknown
ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘው ኤምባሲዋን ለመዝጋት የተገደደችው በደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያውያን ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ምክንያት በናይጄሪያ በሚገኘው ኤምባሲዋ ላይ የአፀፋ ጥቃት በመሰንዘሩ ነው።ባለፈው ሳምንት እሁድ የጀመረው በሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ዜጎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት  ቀጥሎ የብዙዎች ንብረት ተዘርፏል ፤ ድብደባ ተፈፅሟል፡፡ድርጊቱን የናይጀሪያ መንግሥት ያወገዘው ሲሆን፤ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው  ተግባሩን አሳፋሪ ብለውታል።በናይጄሪያ መዲና አቡጃ የሚገኘውን የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ለመዝጋት የተገደዱት በኤምባሲው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ ከደረሰባቸው በኋላ እንደሆነ ሚኒስትሯ ለሮይተርስ መናገራቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/33471/
76
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 6, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ተወያይተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጠዋት በቢሯቸው ነው የተወያዩት፡፡የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በተደረገው ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከለውጡ ወዲህ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ያለውን አቋምና ያከናወናቸውን ተግባራት አውስተዋል፡፡ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስና ሌሎችም ሊቃነ ጳጳሳት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ለሀገርና ለቤተክርስቲያን የተከናወኑ በጎ ተግባራትን በመዘርዘር ምስጋና አቅርበዋል፡፡በለውጡ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች በውይይቱ ላይ የተነሡ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካላት እየተፈጸሙ ያሉ ጥፋቶችን በማንሣት ጳጳሳቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቅርበዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩም የእርሳቸውም ሆነ የመንግሥታቸው ፍላጎት የተጠናከረች፣ ለሀገር ግንባታ የሚቻላትን ሁሉ የምታደርግና አንድነቷ የተጠበቀ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ማየት መሆኑን ገልጸዋል፡፡የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት መጠናከርና አንድ መሆን ጥቅሙ ለእምነት ተቋማቱ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ጭምር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡የቀረቡት ችግሮች በለውጥ ውስጥ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱ ሲሆን፣ ዓይነታቸው ቢለያይም የተለያዩ የእምነት ተቋማት በለውጡ ሂደት ፈተና አጋጥመዋቸዋል፣ በመሆኑም ዕንቅፋት የሚፈጥሩትን አካላት መታገል ያለብን በጋራ ነው ብለዋል፡፡የቀረቡትን ችግሮች በዝርዝር በማጥናትና በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር በመነጋገር በጋራ እንደሚፈቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡በሀገር ላይ የሚደርሱ ጥፋቶች በሁሉም ላይ የሚደርሱ በመሆናቸው መንግሥትና የእምነት ተቋማት በጋራ በመሥራት መፍታት እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡በመጨረሻም የተፈጠሩትን ችግሮች የጋራ በማድረግ የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነትና ክብር በጠበቀ መልኩ በጋራ ለመፍታት ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ (ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/32705/
203
0ሀገር አቀፍ ዜና
የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤታቸው አማካኝነት በምርጫ ህጉ ላይ ሳንወያይ ህጉ ጸድቋል ያሉት ተቀባይነት የለውም-ቦርዱ
ፖለቲካ
September 5, 2019
Unknown
የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤታቸው አማካኝነት በምርጫ ህጉ ላይ ሳንወያይ ህጉ ጸድቋል ያሉት ተቀባይነት የለውም-ቦርዱየፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤታቸው አማካኝነት በምርጫ ህጉ ላይ ሳንወያይ ህጉ ጸድቋል ያሉት ተቀባይነት የለውም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልል ምርጫ ቦርድ አደረጃጀትን እና የክልል የምርጫ ሃላፊዎች ምልመላ በተመለከተ እና የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ሂደትን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤታቸው አማካኝነት በምርጫ ህጉ ላይ ሳንወያይ ህጉ ጸድቋል ያሉት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፤ ህጉ በተከታታይ ጊዜ ውይይት የተደረገበት መሆኑን በመጠቆም ነው፡፡በመግለጫቸውም በቅርቡ የፓለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታ ያቀረቡበት የምርጫና የፓለቲካ ፓርቲዎች ህግ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ በሀገሪቱ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ፓርቲዎች በተገኙበት ሶስት ጊዜ አስፈላጊው ውይይት የተካሄደበት መሆኑን ገልፀዋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ የጀመረውን ውስጣዊ አደረጃጀት ሪፎርም በክልል ደረጃ በማስፋት በ9 ክልሎች የሚገኙት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹን እንደአዲስ እያደራጀ እንደሚገኝም በማስታወቅ፤ ቦርዱን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ 1133/2011 መሰረት የክልል የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ለመሆን የሚፈልጉ መሰፈርቱን በማሟላት መወዳደር ሚችሉ መሆኑም ገልጿል፡፡ቦርዱ የሲዳማ ዞን ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸምን በማስመልከት የስራ እቅድ እና በጀት ያዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፤ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውንም ውይይት ከነሃሴ 30/2011 አ.ም ጀምሮ በተከታታይ የሚያከናውን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ከሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ የሀብት ክፍፍልን በተመለከተ የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ከመስከረም 22 ቀን 2012 በፊት እንዲቀርብ ስምምነት መደረሱን ተናግረዋል።በሀገሪቱ ለሚካሄደው ምርጫ 250 ሺህ የምርጫ አስፈፃሚዎች እንደሚመለመሉ የሚጠበቅ ሲሆን ይህንን ገለልተኛ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ምርጫ ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ይመርጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሰብሳቢዋ ተናግረዋል።
https://waltainfo.com/am/31332/
236
5ፖለቲካ
የአሜሪካ መከላከያ ለትራምፕ አጥር የ3.4 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 5, 2019
Unknown
የአሜሪካ መከላከያ ኃይል ፔንታጎን በአሜሪካ እና በሜክሲኮ ድንበር ላይ ለሚገነባው አጥር 3.4 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ።የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ማርክ እሰፔር 280 ኪሎ ሜትር ለሚረዝመው አጥር ግንባታ የ3.4 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ያደረጉት 127 የሚሆኑ የጦር ኃይሉ ፕሮጀክቶችን በማስቆም ነው ተብሏል።ዶናልድ ትራምፕ ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል በሜክሲኮ እና በአሜሪካ መካከል የግንብ አጥር መገንባት አንዱና አጨቃጫቂው ነበር። ከዛም አልፎ ፕሬዝዳንቱ የአጥሩን ግንባታ ወጪ ሜክሲኮ እንደምትሸፍን ሲናገሩም ከርመዋል።ሜክሲኮ ለአጥሩ ግንባታ ቤሳቤስቲን እንደማታወጣ ብትናገርም፤ ትራምፕ ግን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሜክሲኮ እንደምትከፍል ሲያሳውቁ ቆይተዋል።የአሜሪካ ኮንግረስ ለአጥሩ ግንባታ የሚሆን ገንዘብ እያፈላለገ ቢሆንም፤ አብዛኞቹ ሪፑብሊካኖች ግን እስከ 21.5 ቢሊዮን ዶላር ሊያወጣ በሚችለው ግንባታ ደስተኛ እንዳልሆኑ የአሜሪካ የአገር ውስጥ ጉዳዮች መምሪያ ዘገባ ያሳያል።ትራምፕ በበኩላቸው አጥሩ ከ12 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደማያወጣ ሲናገሩ ይደመጣል።የአሜሪካ መከላከያ የ3.4 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደረገው በ23 የአሜሪካ ግዛቶች እና በ20 ሌሎች አገራት ውስጥ እየተከናወኑ የነበሩ 127 የጦሩ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ለጊዜው እንዲቆሙ በማድረግ መሆኑ ተነግሯል።ዲሞክራቶች በአሜሪካ ጦር ውሳኔ ደስተኛ አይደሉም። የአሜሪካ ሲቪል ሊበሪቲስ ማኅበር በበኩሉ፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለአጥር ግንባታው የሚያስፈልጋቸውን ፈንድ ለማግኘት የሚያዙበትን ሕግ በፍርድ ቤት ለማሳገድ ማዘዣ እንደሚያስወጣ ቃል ገብቷል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34133/
167
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያን የቡና ምርት ለማሳደግ የሚያስችል የ15 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጄክት ይፋ አደረገ
ቢዝነስ
September 5, 2019
Unknown
የአውሮፓ ሕብረቱ ካፌ ፕሮጄክት የኢትዮጵያን የቡና ምርት ለማሳደግ የሚያስችል የ15 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጄክት ይፋ ማድረጉን አስታወቀ፡፡የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ ፕሮጄክቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቡና አምራች ሀገር ብትሆንም፣ ከዘርፉ የሚገኘው ጥቅም ከምርቱ አንፃር ዝቅተኛ በመሆኑ ፕሮጄክቱ ይህን ችግር በመቅረፍ ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡ የካፌ ፕሮጄክት አስተባባሪ አቶ ፍቅሩ አመኑ በበኩላቸው ፕሮጄክቱ በቡና ምርት ላይ የሚደረገውን የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል፡፡ፕሮጄክቱ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በአማራ፣ ደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም ኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ 28 ቡና አምራች ወረዳዎች ተግባራዊ ይሆናል፡፡
https://waltainfo.com/am/23947/
84
3ቢዝነስ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂሩት ዘመነ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምበሳደር ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
September 5, 2019
Unknown
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂሩት ዘመነ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምበሳደር ጋር ተወያዩ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂሩት ዘመነ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ንዱሚሶ ንሺንጋን በዛሬው ዕለት በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል።በዚህ ወቅትም በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ መካከል ያለውን የጠበቀ ታሪካዊ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል።ሰሞኑን ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ የሌሎች አፍሪካ ሀገር ዜጎች ላይ በደረሰው ጥቃትና የንብረት ዝርፊያ በእጅጉ ማዘናቸውንም ገልጸዋል።ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ያስተላለፉት መልዕክት አበረታች መሆኑንና በጉዳዩ የተሳተፉ ጥፋተኞች ለህግ እንደሚቀርቡ ያላቸውን እምነት መግለፃቸውን ገልጸዋል።መንግስት በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስፈለጊውን ጥበቃ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል።አምባሳደር ንዱሚሶ ንሺንጋን በበኩላቸው በደቡብ አፍሪካ የተከሰተው ድርጊት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው አሳዛኝ ድርጊት መሆኑን አንስተዋል።የደቡብ አፍሪካ መንግስት ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ ነገሮች በፍጥነት ወደነበሩበት እንደሚመለሱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። 
https://waltainfo.com/am/31333/
118
5ፖለቲካ
በገቢዎች ሚኒስቴር የአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፓርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ  የህፃናት ማቆያ አስመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 5, 2019
Unknown
በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፓርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ  የህፃናት ማቆያ የህፃናት ማቆያ ማዕከል አስመርቋል።የህፃናት ማቆያ ማዕከሉ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል፡፡የገቢዎች ሚንስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ምህረት ምንያስብ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፤ እናቶች ልጆቻቸውን የሚንከባከቡበትና በስራቸው ውጤታማ የሚሆኑበትን መንገድ መፍጠር ግድ ይላል፡፡በመሆኑም ሀገር ወደተሻለ ደረጃ እንድትሸጋጋር የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወሳኝ በመሆኑ በተለይ በየመስሪያ ቤቱ ለሚወልዱ እናቶች ልጆቻቸውን የሚንከባከቡበት አመቺ ስፍራን ማዘጋጀት እንዳስፈለገ ነው የገለፁት፡፡የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው  በመስሪያ ቤቱ የሚገኙ ሴቶች ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ የማሳደግ አቅም እንዳላቸው ጠቁመው፤  የዚህ ህፃናት ማቆያ መከፈትም የሰራተኞቹን ጫና የሚቀንስና ተቋሙንም ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡በቀጣይም መሰል  የህፃናት ማቆያ ማዕከል በሌሎች ቅርንጫፎች እንደሚተገበርም ነው የተናገሩት።በሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የህፃናት ማቆያ እንዲከፈት መንግስት እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ እንደሆነና ይህም  ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተነግሯል።የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ማዕከል ባለፈው ሀምሌ ወር ለምረቃ መብቃቱ ይታወሳል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32701/
136
0ሀገር አቀፍ ዜና
ክረምቱን ተከትሎ የወባ ወረርሽኝ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጤና ሚኒስቴር አሳሰበ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 6, 2019
Unknown
የጤና ሚኒስቴር ለዋልታ በላከው መግለጫ በወባ በሽታ መከላከል፣ መቆጣጠርና ማስወገድ ላይ የሚከናወኑ ተግባራትን አጠናክሮ በመቀጠል የወባ ወረርሽኝ እንዳይከሰትና በህብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደርግ ጥሪ አስተላልፏል፡፡የክረምት ዝናብን ተከትሎ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ወር ያለው ጊዜ በኢትዮጵያ ዋነኛ የወባ መተላለፊያ ወቅት መሆኑን በመጥቀስ፤  የወባ በሽታ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ዕድሜም ሆነ ፆታ ሳይለይ የሚያጠቃ የጤና ጠንቅ በመሆኑ በሽታው እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባዋል ተብሏል።በወባ ትንኝ አማካይነት ሊከሰት የሚችል የህመምና የሞት መጠንም በመቀነስ በሽታውን ለመቆጣጠርና ለማስወገድ በአገሪቷ የተለያዩ ስልቶች ተነድፈው በመተግበር ላይ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ከኢትዮጵያ ቆዳ ስፋት ውስጥ 75 በመቶ የሚሆነው ለወባ በሽታ ስርጭት አመቺ መሆኑንና  60 በመቶ የሚሆነው ህዝብም በነዚህ አካባቢዎች የሚኖር መሆኑ ለበሽታው ተጋላጭ እንደሚያደርገው የጠቆመው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ የክረምቱን መውጣት ተከትሎ በሚከሰተው የዝናብ መቆራረጥ ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ ሁኔታዎችን ስለሚፈጥር ዜጎች ተገቢው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አበ2018 ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው ከ2010 እሰከ 2017 የወባ ህሙማን ቁጥር በ50%፣ ሞት ደግሞ በ60% ቀንሷል እድቀነሰ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን፤ በሀገር ደረጃ የተደረገው ጥናት (ከ1997 ዓ.ም እሰከ 2008 ዓ.ም) በወባ በሽታ የሚከሰተው ሞት በ80% መቀነሱን ተመልክቷል፡፡ባለፉት14 ዓመታት ደግሞ  በሀገር አቀፍ ደረጃ ምንም ዓይነት የወባ ወረርሽኝ አለመከሰቱን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ መግለጫ ያመለከተ ሲሆን፤ በ2011 በጀት ዓመትም ማጠቃለያ ላይ በተከናወኑ ስራዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ሚሊዮን በታች የወባ ህሙማን ቁጥር ሪፖርት መኖሩን አስታውሷል።  
https://waltainfo.com/am/32702/
198
0ሀገር አቀፍ ዜና
በጉምሩክ ኮሚሽን የጂግጂጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህግ ማሰከበር የሥራ ኃላፊዎች  በቁጥጥር ስር ዋሉ
ቢዝነስ
September 5, 2019
Unknown
በጉምሩክ ኮሚሽን የጂግጂጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህግ ማሰከበር የሥራ ኃላፊዎች በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የጂግጂጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህግ ማሰከበር ኃላፊ አቶ አህመድ መሐመድ እና ምክትል ኃላፊያቸው አቶ አብዱልዋህድ አብዱላህ ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ግለሰቦቹ ከህገ ወጥ የኮንትሮባንድ ዝውውር ጋር በተያያዘበከባድ የሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/23946/
57
3ቢዝነስ
የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ በአራት የትምህርት አይነቶች ውጤት ብቻ ይወሰናል
ቢዝነስ
September 4, 2019
Unknown
የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ በአራት የትምህርት ዓይነቶች ውጤት ብቻ እንደሚወሰን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡እነዚህም የትምህርት ዓይነቶች እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ አፕቲቲዩድ እና ፊዚክስ በተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም ጂኦግራፊን ጨምሮ በማህበራዊ ሳይንስ መሆናቸውን ነው የኢቢሲ ዘገባ ያመለከተው፡፡ይህም የሆነው በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የውጤት ግሽበት በመታየቱ ነው ተብሏል።በቀጣይ ደግሞ የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይወሰናል ተብሏል።  
https://waltainfo.com/am/23944/
47
3ቢዝነስ
መንግስት ቤተክርስቲያኗ በየጊዜው ለምታቀርባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ባለመስጠቱ ለተደራራቢ ችግር መዳረጓ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 5, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየጊዜው ለምታቀርባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ቤተክርስቲያኗ ለተደራራቢ ችግሮች መዳረጓ ተገለጸ፡፡የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከብሯል።የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት በተከበረበት ወቅት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለምታቀርባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ቤተክርስቲያኗ ለተደራራቢ ችግሮች መዳረጓ ተገልጿል፡፡ቤተክርስቲያኗ የገጠማትን ወቅታዊ ፈተና ለማለፍ ዋናው መንገድ መንግስት የሀገርንና የቤተክርስያኗን ሰላም ለማስጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባና፣ በመቀራረና በመነጋጋር የተዘጋጀውን የሕግ ማዕቀፍ በመተግበር ቤተክርስቲያኗን በክብር ጠብቆ በማስቀጠል ለትውልድ ማስተላለፍ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተመለክቷል፡፡የብፁዕነታቸው በዓለ ሲመት ሲከበር፤ ብፁዕነታቸው በተወካያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ቤክርስቲያኗ ቀደም ሲል የነበሩባትን ችግሮች ወደ ጎን በመተው በእርቀሰላምና ሲኖዶሳዊ አንድነት ለበዓለ ሲመታቸው በመድረሳቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸዋል። ምዕመናን ከሚፈታተናቸው ግላዊ ፍላጎት በመታቀብ በአንድነት ለሀገርና ለቤተክርስቲያኗ ዕድገት በመትጋት ወቅታዊ ችግሮችን መፍታት ይገባልም ብለዋል፡፡ብፁዕነታቸው በዓለ ሲመታቸውን ለማክበር የታሰበውን አንድ ሚሊዮን ብር በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተክርስቲያናት ማሰሪያ እንዲውል አድርገዋል፡፡የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ነሐሴ 29 ቀን 1980 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 4ኛ ፓትርያርክ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡  
https://waltainfo.com/am/32699/
165
0ሀገር አቀፍ ዜና
በደቡብ አፍሪካ  የሚስተዋለውን ጥቃት በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት በውይይት ለመፍታት ጥረት ይደረጋል ተባለ
ቢዝነስ
September 5, 2019
Unknown
በደቡብ አፍሪካ በሌሎች ሀገር ዜጎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት በኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ያነጣጠረ ባይሆንም በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ተወያይተው መፍትሄ እንደሚፈልጉ ኘሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡ፕሬዚዳንቷ በደቡብ አፍሪካ ከሚኖሩ የዲያስፖራ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡አባላቱ በስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዳሰጋቸውና ከመንግስት ጋር ውይይት አድርገው መፍትሄ እንዲፈልጉላቸው ጠይቀዋል።በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን በ28ኛው የዓለም አቀፍ ምጣኔ ሀብት ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ያሉት ፕሬዚዳንቷ ከዚህ ጎን ለጎን ነው ከኢትዮጵያውያኑ ጋር የተወያዩት።ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በጉባኤው ላይም በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እና በሰላም ዙሪያ ባተኮረው ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።ፕሬዚደንቷ የስራ እድል ፈጠራን ለማሳደግ ከፖሊሲ ማውጣት እና ከአዳራሽ ውስጥ ውይይት ባለፈ ታች ድረስ ወደ ህዝቡ ወርዶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።ወጣቶች በስደት ለሚኖሩበት ሀገር እንደ ስጋት ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦም እንዳላቸው መታየት እንዳለበት ገልጸዋል።በሰላም መፍትሄ አመንጪነት ዙሪያ ሴቶችም በሀላፊነት ደረጃ ሊሳተፉ እንደሚገባ ፕሬዚደንቷ ጠቁመዋል።እንደ ፕሬዚደንቷ አገላለጽ የልማት ጉዳይ እና የሰላም አጀንዳዎች ተነጣጥለው የሚታዩ መሆን የለባቸውም።ምንጭ፦ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት
https://waltainfo.com/am/23945/
137
3ቢዝነስ
የሚዲያ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በአዎንታዊ መንገድ መሆን እንዳለበት ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 5, 2019
Unknown
የአፍሪካ ወጣቶች ባህላቸውንና ታሪካቸውን ሳይለቁ የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ መሳሪያዎችን ለአዳዲስ ነገሮች ፈጠራና ለአዎንታዊ ተግባራት ማዋል እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አሳሰበች፡፡ብጹእ ካርድናል ብርሃነ ኢየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት ትናንት በአፍሪካ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ማህበር “ሲግኒስ አፍሪካ ኮንግረንስ” የተሰኘና ትኩረቱን በአፍሪካ ወጣቶች የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ መሳሪያዎች አጠቃቀም ዙሪያ ኮንፈረንስ ሲካሄድ እንደተናገሩት፤ ከአፍሪካ 60 በመቶ የሚሆነው ወጣት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀሙ መልክ ሊይዝ ለሀገርና ለወገን አዎንታዊ ፋይዳ በሚያበረክት መልኩ ሊቃኝ ይገባዋል፡፡ጊዜው በአፍሪካ ዘመናዊ የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች የጎሉበት ነው ያሉት ካርዲናሉ ፤ወጣቱ ሚዲያውን ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለጋራ እድገት፣ የሰዎችን ክብር በማይነካ ሥልት፣ ባህልና ታሪካቸውን በሚያጠናክር ሁኔታ መጠቀም ይገባዋል ሲሉ መክረዋል፡፡ወጣቶች በር ዘግተው አንድ ኮምፒዩተርና ስልካቸው ላይ ረጅም ጊዜያቸውን ከማጥፋት መቆጠብ አለባቸው፡፡ ዓለም ሰፊ እንደሆነች፣ በአካባቢያቸው ያለውን የራሳቸውን ሕብረተሰብ መመልከት ፣በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ ማተኮር እንደሚገባቸው ጠቅሰው፣ በግል ጉዳያቸው ላይ ብቻ እንዳያተኩሩ ካርድናል ብርሃነ ኢየሱስ አደራ ብለዋል፡፡በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ዋና ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት አባ ተሾመ ፍቅሬ በበኩላቸው ፤ ይህ የአፍሪካ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ማህበር ጉባኤ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ካስቻሉት ምክንያቶች መካከል ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላት ተሰሚነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ከፍተኛ በመሆኑና በኢትዮጵያ ውስጥ እያደገ የመጣው የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለስብሰባዎች ተመራጭ እያደረጓት መምጣታቸውን ገልጸው፣ የሚዲያ ቴክኖሎጂም ከዚህ ተነጥሎ የሚታይ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት
https://waltainfo.com/am/32700/
192
0ሀገር አቀፍ ዜና
በባሀማስ የተከሰተው ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ንፋስ ወደ አሜሪካ እያቀና ነው ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 5, 2019
Unknown
ባሀማስን የመታው ሀሪኬን ዶሪያን የተሰኘው ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ንፋስ ወደ አሜሪካ እያቀና መሆኑ ተነግሯል።ከዚህ ቀደም ለ20 ሰዎች ህልፈት መንስኤ የነበረውና ሀሪኬን ዶሪያን የሚል መጠሪያ ያለው ይህ ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ንፋስ  በተመሳሳይ በአሜሪካ ሊከሰትና ለሰዎች ህልፈት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል።የባሃማሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁቤርት ሚኒ ሀሪኬን ዶሪያን ሀገሪቱን ካጋጠሙ ተፈጥሯዊ አደጋዎች በታሪክ ትልቁን ስፍራ የሚይዝ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡አውሎ ንፋሱ በሃማስን ከመታ በኋላ ፍጥነቱ ተቀዛቅዞ እንደነበረ ቢገመትም አሁን ላይ  ፍጥነቱን ጨምሮ ወደ አሜሪካ እያመራ ነው ተብሏል።እንደ የአሜሪካ ሀሪኬን ማዕከል ከሆነ ሀሪኬን ዶሪያን በአሁኑ ወቅት በጆርጂያ ግዛት ከምትገኘው ደቡብ ምስራቅ ሳቫናህ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።ምንጭ፦ ቢቢሲ
https://waltainfo.com/am/34132/
95
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሀገር አቀፍ የአጠቃላይ የስርዓተ ትምህርት ማጠቃለያ ጥናት ጉባኤ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 4, 2019
Unknown
የአጠቃላይ ትምህርት ፍኖተ ካርታ አካል የሆነው ይህ ጉባኤ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን፤ የሀገሪቱን ስርዓተ ትምህርት ለማሻሻል ጠቃሚ ግብዓት እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡ባለፈው አንድ ዓመት በተካሄደው ጥናት በ2001 ዓ.ም የተከለሰው አጠቃላይ ስርዓተ ትምህርት ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ለመፈተሽ ያስቻለ እንደነበር የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ፂዮን ተክሉ ገልፀዋል፡፡ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ አቅጣጫ ስኬታማነት እና ተማሪዎች በእውቀትና ክህሎት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በሚያስችል መልኩ የሚዘጋጅ መሆን እንዳለበትም ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ የተናገሩት፡፡የስርዓተ ትምህርቱ ጥናት ነፃ እና ገለልተኛ በሆነ አካል እየተካሄደ እንደሚገኝና በዚህም የተሻሉ ግብዓቶች እንደተገኙበትም በመድረኩ ተጠቅሷል፡፡ሶስት ዓመታት የሚሸፍነው የስርዓተ ትምህርት ጥናቱ  አሁን ላይ የአንድ ዓመቱን ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡መድረኩን የትምህርት ሚኒስቴር በተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ድጋፍ  ያዘጋጀው ሲሆን፤ ጥናቱን ያካሄደው ደግሞ ካምብሪጅ አሰስመንት ኢንተርናሽናል የተሰኘ ተቋም ነው፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32697/
109
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሲቪል ማህበራት ተቋማት በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚኖረው ምርጫ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቁ
ፖለቲካ
September 4, 2019
Unknown
የሲቪል ማህበራት ተቋማት በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚኖረው ምርጫ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቁ።የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ የፀደቀውን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ውይይት እየተደረገ ሲሆን፤ በዚሁ መድረክ የሲቪል ማህበራት ተቋማቱ በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚኖረው ምርጫ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች መድረክ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ብሌን አስራት ቦርዱ ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ በተካሄዱት ምርጫዎች የሲቪል ማህህበራት ተቋማት ሚና አናሳ እንደነበር አስታውሰዋል።ባለፉት ዓመታት የሲቪል ማህበራት በአገሪቱ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚጠበቅባቸውን እንዳይወጡ በማህበራቱ ላይ የነበሩት አሳራሪ አሰራሮች የማህበራቱን እንቅስቃሴ ውስን እንዲሆን አድርጎት ቆይቷል ብለዋል።የሲቪል ማህበራቱ በቀጣይ በሚኖረው አገራዊ ምርጫ ህብረተሰቡን በምርጫ ስነ ምግባርና ደንቦች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖረው የተለያዩ ስልጠናዎች በመስጠት መስራት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።የሲቪል ማህበራቱ በቀጣዩ ምርጫ ሂደትም ገለልተኛ ታዛቢዎችን በማሰማራት በሂደቱም ከምርጫ በኋላም በሚኖረው የምርጫው ተአማኒነት ሚናቸውን እንዲወጡ ዋና ዳይሬክተሯ ጠይቀዋል።የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አባል ወይዘሪት ብዙወርቅ ከተተ በበኩላቸው፤ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ ምንም እንኳ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀ ቢሆንም፤ መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በቦርዱ ለሚወጡ መመሪያዎች ግብአት የሚገኝበት ይሆናል ብለዋል።
https://waltainfo.com/am/31329/
155
5ፖለቲካ
ኤቢኤች የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲን ከሰሰ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 4, 2019
Unknown
ኤቢኤች የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲን ከሰሰኤቢኤች (ጥምረት ለተሻለ ጤና) ሰርቪስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል አማካሪ ድርጅት የድርጅቴን ስምና ዝና በማጥፋት ተግባር እና በድርጅቴ ላይ ኪሳራ አድርሶብኛል ያለውን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ከሰሰ።አማካሪ ድርጅቱ ስምና ዝናዬን በማጥፋት ተግባር 174 ሚሊየን 636 ሺህ 893 ብር ከ40 ሳንቲም ብር ጉዳት ካሳ እንዲከፈልና ሌሎች የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰድ ለማስወሰን በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ላይ ክስ መመስረቱን አሰታውቋል፡፡  ከሳሽ የንግድ ተቋም እንደሆነና ከአገርው ስጥና የውጭ ደርጅቶች ጋር ውል በመግባት አገለግሎት ያቀርባል፡፡ በዚህ መሰረት የጅማ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ በከፈተው የአገልግሎት ማዕከል ላለፉት ስድስት ዓመታት የቤተሙከራ፣ ቤተመጽሐፍትና ሌሎች አገልግሎቶችን ሲያቀርብ መቆየቱ ገልጿል፡፡  ውሉ እስከ ታህሳስ 21/2010 ዓ.ም የሚቆይ እንደነበርና ከፍተኛ የመንግሰት የሥራ ኃላፊዎችና የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ የሚያውቁት እንደነበር ታውቋል፡፡ኤጀንሲው ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 650/2001 ከሰጠው ሥልጣን ውጪ ‹‹ዩኒቨርሲቲው ከዋናው ግቢ ውጪ በአዲስ አበባ የሚሰጠው ትምህርት ዕውቅና የለውም፤ ሕጋዊም አይደለም›› በማለት እግድ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ዩኒቨርሲቲው ከዋናው ግቢ ውጪ ማስተማርም ሆነ ከሌሎች አካላት ጋር በትብብር መሥራት እንደማይችል ኤጀንሲው ቢገልጽም፣ በዩኒቨርሲቲው እንደገና ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 240/2003 ግን ዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ከሚገኝበት ጅማ ከተማ ውጪ በሌሎች ቦታዎች የትምህርት ክፍሎችን እንዲሁም የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ሊያቋቁም እንደሚችል ተደንግጓል።በዚህ መሰረት የከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ የፍተሐብሔር ችሎት ለጳጉሜ 5፣ 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ኤጀንሲው ለመስከረም 26፣ 2012 ክሱ ደርሶት መልስ እንዲያመጣ ተጠይቋል፡፡ ክሱን ለመስማት ደግሞ ጥቅምት 24/2012 ቀን ተቆርጧል፡፡    
https://waltainfo.com/am/32698/
211
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢራን ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ ወደ ኒውክሌር ስምምነቱ ልትመለስ እንደምትችል አስታወቀች
ፖለቲካ
September 4, 2019
Unknown
ኢራን ከአምስቱ ሃያላን ሀገራት ጋር ወደ ገባችው የኒውክሌር ስምምነት ልትመለስ እንደምትችል የሀገሪቱ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራቅጭ ኢራን በፈረንጆቹ 2015 ለገባችው የኒውክሌር ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተገዥ ልትሆን እንደምትችል አረጋግጠዋል።ይህን ለማድረግ ግን ቴህራን በቀጣዮቹ አራት ወራት 15 ቢሊየን ዶላር ከነዳጅ ሽያጭ አልያም በብድር መልክ ማግኘት እንዳለባት የፋርስ ዜና አገልግሎትን ዋቢ አድርጎ ሬውተርስ ዘግቧል፡፡አባስ አራቅጭ አንድም የአውሮፓ ሀገራት ከኢራን የነዳጅ ዘይት መግዛት ይኖርባቸዋል አልያም በአራት ወራት ውስጥ ከሽያጭ ልታገኝ የሚገባውን ገንዘብ በፈለገችው ጊዜ ልትጠቀመው በምትችልና ረዘም ባለ ጊዜ በሚመለስ የብድር አይነት ሊፈቅዱላት እንደሚገባ ገልጸዋል።ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ሀገራቸው ለስምምነቱ ተገዥ እንደማትሆን ተናግረዋል፡፡ፈረንሳይ በበኩሏ ኢራን ለስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተገዥ መሆን ከቻለች ለቴህራን እስከ መጭው ገና መጨረሻ ድረስ በፈለገችው ጊዜ ልትጠቀመው የምትችለው 15 ቢሊየን ፓውንድ በብድር መልክ መስጠት የሚያስችል ረቂቅ አቅርባለች።ረቂቁ ስምምነቱን ለመታደግ ያግዛል ቢባልም እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አልተስተዋለም።አሜሪካ ከኒውክሌር ስምምነቱ ባለፈው አመት ከወጣች እና በቴህራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ከጣለች በኋላ ኢራን ከነዳጅ ሽያጭ የምታገኘው ገንዘብ አሽቆልቁሏል።የ2015ቱ የኒውክሌር ስምምነት አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ብሪታንያ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይና ጀርመን በተጨማሪነት ከኢራን ጋር የገቡት ስምምነት ነው። (ምንጭ፡-ሬውተርስ)
https://waltainfo.com/am/33994/
166
5ፖለቲካ
የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል
ቢዝነስ
September 4, 2019
Unknown
የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላልየመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።ሚኒስቴሩ በመስከረም ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ ሁሉም የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥልም አስታውቋል።በዚህም የአውሮፕላን ነዳጅ በነሐሴ ወር ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር 25 ብር ከ16 ሳንቲም በመስከረም ወር፥ 40 ሳንቲም በመጨመር በሊትር 25 ብር ከ56 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።ሌሎች የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ግን ባለበት እንደሚቀጥል ተገልጿል። 
https://waltainfo.com/am/23942/
63
3ቢዝነስ
የታክስ ኦዲት ጥራትን ለማስጠበቅ አዲስ አሰራር መዘርጋቱ ተገለፀ
ቢዝነስ
September 4, 2019
Unknown
የገቢዎች ሚኒስቴር 400 ከሚሆኑ የታክስ ኦዲት ባለሙያዎች ጋር በሙያዊ ስነ-ምግባር፣ በግብረገብነትና በሃላፊነት ዙሪያ ምክክር አካሂዷል፡፡በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የታክስ ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አበበ ለዋልታ እንደገለፁት፤ ምክክር መድረኩ በዋናነት በሶስቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እና በ2011 በጀት ዓመት የታዩ ጉድለቶችና ጥንካሬዎች ተለይተው በተለይም የተግዳሮቶቹ መንስኤዎችን ለመድፈን ያለመ ነው፡፡በተለይም መድረኩ ሙያዊ ስነ-ምግባር፣ ግብረገብነት እና ህጋዊ ሃላፊነቶች ላይ የሚስተዋሉ አሉታዊ ተግባራትን በማስተካከል በታክስ ኦዲት ላይ ያሉ ጉድለቶችን ለማረም የሚያሰስችል ነው ብለዋል፡፡በአንዳንድ ባለሙያዎች ላይ የስነ-ምግባር ክፍተት እንዳለ ጥቆማ እንደሚደርሳቸው የገለፁት ዳይሬክተሩ ፤ መድረኩ ሰራተኞች ለህሊና እና ለስነ-ምግባር ተገዢ በመሆን የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡የታክስ ኦዲት ጥራትን ለማስጠበቅም አዲስ አሰራር ተዘርግቶ በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል ነው ያሉት፡፡ያደጉ ሀገራት ከባለሙያዎቹ ጋር  ተቀራርበው እንደሚሰሩ የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ ጠቅሰው በኢትዮጵያም ከተቋሙ ውጪ  ካሉ ተመሳሳይ የሂሳብ አዋቂዎች ጋር በጋራ ይሰራል ብለዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/23943/
121
3ቢዝነስ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት የውጭ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዙ
ፖለቲካ
September 4, 2019
Unknown
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ዜጎች ንብረት ላይ የተፈጸመው ዝርፊያና ጥቃትን እንደሚያወግዙት አስታወቁ።ማክሰኞ ዕለት ፕሬዝዳንቱ ''ለተፈጸመው ነገር ምንም አይነት ምክንያት ሊቀመጥለት አይችልም፤ ደቡብ አፍሪካውያን ሌሎች አፍሪካውያንን ማጥቃት አይችሉም'' ሲሉ ተደምጠዋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከአርባ በላይ ደቡብ አፍሪካውያን ከሰኞ አመሻሽ ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ፖሊስ አመጸኞቹን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲሆን፣ ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ መሆን ሲጀምሩ ደግሞ የጎማ ጥይቶችንም ጭምር ተጠቅሞ ነበር ተብሏል።እስካሁን ቢያንስ አምስት ሰዎች መሞታቸውም ተሰምቷል።''የተፈጸመው ዝርፊያ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው ነው፤ ይህ ነገር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንዲሆን አንፈቅድም'' ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት የቪዲዮ መልእክት።አክለውም ''ድርጊቱ በአስቸኳይ መቆም አለበት'' ብለዋል።በሌላ በኩል የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ፣ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ያለውን ተግባር በእጅጉ እንደሚቃወመው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ዝርፊያውና አመጹ ማክሰኞ ዕለትም የቀጠለ ሲሆን፣ አሌክሳንድሪያ ወደተባለችው ጆሃንስበርግ ክፍል መስፋፋቱ ተሰምቷል። አንዳንድ ነዋሪዎችም በሕገ-ወጥ መንገድ ወደሃገራችን የገቡ ስደተኞችን መንግስት ያባርርልን ሲሉ ቁጣቸውን ገልጸዋል።ብዙ ጥቃት የደረሰባቸው ናይጄሪያውያን እንደመሆናቸው በናይጄሪያዋ ሌጎች ከተማ የሚገኙ የደቡብ አፍሪካዊያን ሱፐርማርኬቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው አንድ አይን እማኝ ለቢቢሲ አረጋግጧል።አንድ ሌላ የአይን እማኝ ደግሞ ሱፐርማርኬቱ የሚገኝበት መንገድ ላይ የሁለት ሰዎች ሬሳ መመልከቱን ገልጿል።የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሞሃሙዱ ቡሃሪ በበኩላቸው፣ የሀገራቸውን ቁጣ ለመግለጽና የዜጎቻቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ ማክሰኞ ዕለት የልዑካን ቡድን ወደ ደቡብ አፍሪካ መላካቸውን አስታውቀዋል።በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ጉዳዩ እስኪጣራና ዝርፊያዎቹ እስከሚቆሙ ድረስ ዜጎች ሱቆቻቸውን እንዲዘጉ አሳስቧል። አመጽ ሊነሳባቸው ከሚችልባቸው ቦታዎች እራሳቸውን እንደያርቁና ውድ የሆኑ ጌጣጌጦችን እንዳያደርጉም አስጠንቅቋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ) 
https://waltainfo.com/am/33331/
206
5ፖለቲካ
ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ሌሎች ዜጎች የተፈጸመውን ጥቃትና የንብረት ዝርፊያ አወገዘ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 4, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ የሌሎች የአፍሪካ አገራት ዜጎች ኢላማ ባደረገ መልኩ የተፈጸመውን ጥቃትና የንብረት ዝርፊያ በፅኑ እንደሚያወግዝ አስታወቀ፡፡የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራሞፎሳ ድርጊቱን በማውገዝ በጉዳዩ ላይ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንደሚያቀርቡ የገቡት ቃል አበረታች መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጸዋል፡፡ፕሬዝዳንቱ በገቡት ቃል መሰረትም በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን ለህግ እንደሚያቀርቡ እንደሚያምንና በየደረጃው የሚገኙ የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት ጠንካራ ክትትል በማድረግ በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር እንዲያውሉና ለህግ እንዲያቀርቡ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ዜጎቻችን ደህንነት እንዲጠበቅ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ ሚኒስቴር ጥሪውን አቅርቧል፡፡በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢፌዴሪ ኤምባሲም ከሚመለከታቸው የአገሪቱ ባለስልጣናት እና ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጋር ሁኔታውን ለማረጋጋት በቅርበትና በትብብር እየሰራ መሆኑንና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32696/
115
0ሀገር አቀፍ ዜና
በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 26 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ቢዝነስ
September 4, 2019
Unknown
በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 26 ሽጉጦች ቦምባስ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ትናንት ከምሽቱ 3፡00 አካባቢ  በጉምሩክ ፈታሾችና በፌዴራል ፖሊስ አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡በወቅቱ ከሽጉጦቹ ጋር ሁለት የሽጉጥ ሰደፍና 11 ካርታ የተያዘ ሲሆን፤ ህገ-ወጥ መሳሪያው ኮድ3-30513 የሰሌዳ ቁጥር ባለው አይሱዙ ተሸከርካሪ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡ኮንትሮባንድ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን ያስከትላል ያለው የገቢዎች ሚኒስቴር ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የህዝብ ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል ብሏል፡፡የጥቂት ህገ-ወጦች ፍላጎት በሚያሟላው የኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ ምክንያት የሀገር ሰላም እንዳይደፈርስ የሰላም ባለቤት የሆነው ህዝብ በንቃት እንዲጠብቅ የገቢዎች ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/23941/
81
3ቢዝነስ
በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የሚመክረው 28ኛው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ሁሉን አቀፍ ዕድገት ላይ እንደሚያተኩር ተገለጸ
ቢዝነስ
September 4, 2019
Unknown
ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የሚጀምረው 28ኛው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ሁሉን አቀፍ ዕድገት ላይ እንደሚያተኩር ተገለጸ፡፡ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት መፃኢ ብልጽግና መሠረት ያደረገው የመሪዎቻቸው ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ ዕድገት የማምጣት ችሎታ ላይ ነው።በዚህ በፈጣን ለውጥ ውስጥ በሚገኘው 4ኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን ደግሞ ይህ ብቃት ከመሪዎቹ ይጠበቃል።እ.አ.አ. ከመስከረም 4-6/2019 ዓ.ም ኬፕ ታውን፣ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚካሄደው በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የሚመክረው 28ኛው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረምም ይህንኑ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።ፎረሙ ላይ ርእሳነ መንግሥታት እና ርእሳነ ሀገራትን ጨምሮ 1 ሺህ 100 የሚሆኑ የመንግሥታት ኃላፊዎች፣ የቢዝነስ እና የሲቪል ማኅበረሰብ ይገኛሉ።የፎረሙ ዋና አጀንዳ ለሰፊው እና እያደገ ለመጣው የአፍሪካ የሠራተኛው ኃይል ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር አዲስ አጋርነት መመሥረት የሚል እንደሆነ ተጠቁሟል።የመንግሥት ፖሊሲዎች እና ኃላፊነት የተላበሱ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች የበለጠ አካታች የሆነ ማኅበረሰብን ለመገንባት ያላቸው ሚናም ዋና የመወያያ አጀንዳ ይሆናሉ ተብሏል።የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም በፎረሙ ላይ ለመሳተፍ ኬፕ ታውን ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል። (ምንጭ፦ ዎርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ኦን አፍሪካ)
https://waltainfo.com/am/32905/
138
3ቢዝነስ
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ለአፍሪካ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ ገቡ
ቢዝነስ
September 4, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ለአፍሪካ 2019 ላይ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ገብተዋል።ፕሬዝዳንቷ ኬፕ ታውን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር አልቪን ቦትስ፣ በደቡብ አፍሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያምና የኤምባሲው ዲፕሎማቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።ፎረሙ በፈረንጆቹ ከመስከረም 4 እስከ 6 ቀን ድረስ የሚካሄድ ሲሆን፣ የተለያዩ ሀገራት መሪዎችን ጨምሮ ከ100 በላይ ሀገራት የተወከሉ ቁጥራቸው 1ሺህ 100 የሚደርሱ ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።በፎረሙ ታዳጊ የቢዝነስ ጅማሮዎችን በካፒታልና በፖሊሲ መደገፍ፣ የሰራተኞችን ክህሎት ማጎልበት እና ኢ-ኮሜርስን ማስፋፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይቶች ይካሄዳሉ።ከዚህ ባለፈም አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በሚታገዙበት እና በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ተፈጻሚነት ዙሪያ በርካታ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው መሆኑን ከደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። 
https://waltainfo.com/am/23939/
115
3ቢዝነስ
ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፍ ተገቢውን ጥቅም ማግኘት እንድትችል መንግስት በትኩረት ይሰራል
ሀገር አቀፍ ዜና
September 3, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፍ ተገቢውን ጥቅም ማግኘት እንድትችል መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ። የቱሪዝም ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ በሀገራዊ እደገት የሚኖረውን ድርሻ ማሳደግ እና የስራ እድል ፈጠራን በማበረታታት ድራሻው የላቀ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ አገሪቷ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲትሆን መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ጠ/ር አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።ይህ የተገለጸው በአንደኛው ሀገር አቀፍ የሆቴል እና ቱሪዝም ኮንፈረንስ ላይ ሲሆን፤ ኮንፈረንሱ አንደኛው ሀገር አቀፍ የሆቴል እና ቱሪዝም ኮንፈረንስ ቱሪዝም ብሩህ ተስፋ ለየኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል በጀመረበት ወቅት ነው፡፡ምድረ ቀደምት የሚል ስያሜ የተሰጠው የቱሪዝም ዘርፍ ያሉበት ውስንነቶች እንዳሉ ሆኖ፤ ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 በመቶ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ እያበረከተ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ለ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎችም የስራ እድል ፈጥሯል ተብሏል፡፡ኢትዮጵያ 10 አይነት የተፈጥሮ ስነ-ምህዳር ያቀፈችና 11 ቅርሶችን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፤ሳይንስና ባህል ተቋም ያስመዘገበች ቢሆንም፤ የተመገቡ ብሎም በመመዝገብ ሂደት ላይ ያሉ የማይዳሰሱ ሀብቶች ቢኖሩም ጥራት ካለው አግልግሎት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ማነቆ አበርክቶውን ውስን አድርጎታልልም ነው የተባለው፡፡በኮንፈረንሱም በጥናት የተለዩ ክፍተቶችን በማቃለል ወደ እድል በመቀየር ሂደት መንግስትና የግሉ ባለሀብት የጎላ ሚና እንዳላቸው መመላከቱን ተከትሎ መንግስት በዘርፉ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ የኢፌዲሪ ምክትል ጠ/ር ደመቀ መኮንን በመክፈቻ ሰነ-ስረዓቱ ላይ አንስተዋል፡፡የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ኢትዮጵያ እንግዳ መቀበል ቀደምት ሀገራዊ ባህሏ መሆኑን በመጥቀስ፤ የአገሪቷን እምቅ ሀብቶችን ዓለም ከደረሰበት ደረጃ አስተሳስሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አጽኖት በመስጠት አሳስበዋል፡፡ከመድረኩ መንግስትም ሆነ የግሉ ዘርፍ ተሞክሮ የሚሆኑ ግበዓቶችን የሚወስዱበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32695/
212
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተለያዩ የውጭ ሃገራት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ
ፖለቲካ
September 3, 2019
Unknown
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተለያዩ የውጭ ሃገራት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በተለያዩ የውጭ ሃገራት የነበራቸውን ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገብተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና እስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።በደቡብ ኮሪያ ቆይታቸው ከሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ጋር እንዲሁም ከሀገሪቱ የተለያዩ ኩባንያ  ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡ከፕሬዚዳንት ሙን ጃ ኢን ጋር ውይይት ካካሄዱ በኋላም ሁለቱ ሀገራት የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራመዋል።በተመሳሳይ በጃፓን እና እስራኤል ቆይታ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የተለያዩ ስምምነቶችን ማድረጋቸው  የሚታወስ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31327/
80
5ፖለቲካ
የጋራ ምክር ቤቱ በቅርቡ የጸደቀው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ አዋጅ በአስቸኳይ ተመልሶ እንዲታይ ጠየቀ
ፖለቲካ
September 3, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የምርጫ አዋጅ በአስቸኳይ ተመልሶ እንዲታይ ጠይቋል፡፡የጋራ ምክር ቤቱ በቅርቡ የፀደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ አሁን ባለበት ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ በቀጣዩ ምርጫ የማይሳተፍ መሆኑን አስታውቋል።ይህ አቋምም ከ107 ፓርቲዎች ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑትን ፓርቲዎች የጋራ አቋም የሚያካተት መሆኑ ተነግሯል ፡፡መንግስት አዋጁን በዚህ መልኩ ተግባራዊ ካደረገ የሚካሄደው ምርጫ ተዓማኒነት የሌለውና ሀገሪቷንም ወደ ችግር የሚዳርግ ይሆናል ብሏል ምክር ቤቱ ፡፡የጋራ ምክር ቤቱ  የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት መልሶ እንዲታይ የጠየቀ ሲሆን፤ ጊዜው ካጠረም የምርጫ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቋል፡፡ጥያቄያቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጀምሮ እስከ ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋማትና ኃላፊዎች ትኩረት ሰጥተው ምላሽ እንዲሰጡም ነው የጠየቁት፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31328/
104
5ፖለቲካ
የቀድሞው ማዕከላዊ እስር ቤት ለጉብኝት ክፍት ሊደረግ ነው
ፖለቲካ
September 3, 2019
Unknown
ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ.ም የሚከበረውን የፍትህ ቀን ምክንያት በማድረግ የቀድሞው ማዕከላዊ እስር ቤት ለጉብኝት ለህዝብ ክፍት እንደሚደረግ የበዓሉ የኮሚዩኒኬሽን፣ ሚድያና መድረክ ዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ ገልፀዋል፡፡እስር ቤቱ ከዚህ ቀደም በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈጸምበት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፤ ለውጡን ተከትሎ እንዲዘጋና ወደ ሙዚየምነት እንዲቀር መወሰኑ ይታወቃል፡፡ኮሚቴው እንዳለው በማእከላዊ እስር ቤት በፖለቲካ ነክ የህግ ተጠያቂ እስረኞች ላይ የማይሽር የስነ-ልቦና ጥቃትና እስከ አካል መጉደል የሚያደርስ ቶርቸር ይፈጸምባቸው እንደነበር አስታውሶ ኢቢሲ ነው የዘገበው፡፡በተጨማሪም በተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ሂደት ሲከናወን በጨለማ ቤት ተዘግቶባቸው ከፍተኛ የሆነ በደል ይደርስባቸው አንዳንዶችም ህወታቸው ያልፍ ነበር፡፡ከለውጡ ወዲህ እስር ቤቱ ተዘግቶ በቦታው ላይ ይፈጸም የነበረው የተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብት ጥሰት ቆሟል፡፡እናም አሁን የፍትህ ቀንን ምክንያት በማድረግ ከጳጉሜን 1 እስከ 4 ቀን 2011 ዓ.ም እስርቤቱ ለጉብኝት ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ኮሚቴው አስታውቋል።
https://waltainfo.com/am/31330/
123
5ፖለቲካ
የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ኃይል በሶማሊያ ላበረከተው ሚና አሚሶም ምስጋና አቀረበ
ፖለቲካ
September 3, 2019
Unknown
በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ስር ለተሰማራው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ኃይል ላበረከተው ሚና አሚሶም ምስጋና አቀረበ፡፡ላለፈው አንድ ዓመት ኃላፊነቱን በአሚሶም ጥላ ሰር ተወጥቷል የተባለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የሶማሊያ ሰላም እንዲሻሻል ጉልህ ሚና በመጫወቱ ምስጋና እንደሚገባው የአሚሶም ኃይል ዋና አዛዥ ሌቴናል ጀነራል ይልማ ጥጋቡ አስታውቀዋል፡፡በተለይም ሰላም አስከባሪው ላለፈው አንድ ዓመት ከሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የሽብር ኃይሎችን ተጠራርገው እንዲወጡ በማድረግ የአገሪቱን የሽግግር እቅድ እንዲሳካ ሙያዊ ኃላፊነታቸውንና ብቃታቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል ብለዋል፡፡የሰላም አስከባሪ ኃይሉ የአንድ ዓመት ተልዕኮውን በማጠናቀቁ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአሚሶም ዋና ማዘዣ በበለደወይን ከተማ የእውቅና ምስጋና መርሃ ግብሩ እንደተዘጋጀላቸው አሚሶም በትዊተር ገፁ አስታውቋል፡፡በአሚሶም ጥላ ስር ሶማሊያን ከገባችበት የፀጥታ ችግር እንድትወጣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ20 ሺህ በላይ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡
https://waltainfo.com/am/31331/
118
5ፖለቲካ
አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለሚያቃልሉ አዳዲስ ሐሳቦች ትኩረት እንደሚሰጥ ገለፀ
ቢዝነስ
September 4, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር በከተማዋ የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ማቃለልና መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ እና የኑሮ ውድነቱን የሚቀርፉ አዳዲስ ሀሳቦች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።በአቅራቢ እና ተጠቃሚ መሃል ያሉ ህገ ወጥ ደላላዎችን ሙሉ በሙሉ በማውጣት ሸማች እና አቅራቢ በቀጥታ የሚገናኝባቸው መንገዶችንም የከተማ አስተዳደሩ እየዘረጋ እንደሆነ ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡    
https://waltainfo.com/am/23940/
69
3ቢዝነስ
የሲቪል ማህበራት ተቋማት በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚኖረው ምርጫ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 3, 2019
Unknown
የሲቪል ማህበራት ተቋማት በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚኖረው ምርጫ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ የፀደቀውን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ውይይት እየተደረገ ሲሆን፤ በዚሁ መድረክ የሲቪል ማህበራት ተቋማቱ በቀጣይ በኢትዮጵያ በሚኖረው ምርጫ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ብሌን አስራት ቦርዱ ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፤በአገሪቱ በተካሄዱት ምርጫዎች የሲቪል ማህህበራት ተቋማት ሚና አናሳ እንደነበር አስታውሰዋል።ባለፉት ዓመታት የሲቪል ማህበራት በአገሪቱ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚጠበቅባቸውን እንዳይወጡ በማህበራቱ ላይ የነበሩት አሳራሪ አሰራሮች የማህበራቱን እንቅስቃሴ ውስን እንዲሆን አድርጎት ቆይቷል ብለዋል።የሲቪል ማህበራቱ በቀጣይ በሚኖረው አገራዊ ምርጫ ህብረተሰቡን በምርጫ ስነ ምግባርና ደንቦች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖረው የተለያዩ ስልጠናዎች በመስጠት መስራት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።የሲቪል ማህበራቱ በቀጣዩ ምርጫ ሂደትም ገለልተኛ ታዛቢዎችን በማሰማራት በሂደቱም ከምርጫ በኋላም በሚኖረው የምርጫው ተአማኒነት ሚናቸውን እንዲወጡ ዋና ዳይሬክተሯ ጠይቀዋል።የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አባል ወይዘሪት ብዙወርቅ ከተተ በበኩላቸው፤ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ ምንም እንኳ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀ ቢሆንም፤መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በቦርዱ ለሚወጡ መመሪያዎች ግብአት የሚገኝበት ይሆናል ብለዋል። 
https://waltainfo.com/am/32694/
153
0ሀገር አቀፍ ዜና
በካቡል በተፈጸመ ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ
ፖለቲካ
September 3, 2019
Unknown
በአፍጋኒስታን ርዕሰ መዲና ካቡል በተፈጸመ ጥቃት 16 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።ጥቃቱ የተፈጸመው በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ የቦምብ ጥቃት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በጥቃቱ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።ለጥቃቱ የታሊባን ታጣቂ ቡድን ሃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል።ታሊባን በቅርብ ቀናት ውስጥ ብቻ ለተፈፀሙ ጥቃቶች ሃላፊነቱን ሲወስድ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፡፡በርካታ የመኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የእርዳታ ድርጅቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ እንደሆነ የተነገረው አካባቢው በተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት ኢላማ ሆኗል፡፡ ምንጭ፦ አልጀዚራ
https://waltainfo.com/am/33993/
65
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የእስራኤሉ አቻቸው ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ በጋራ ማብራሪያ ሰጡ
ፖለቲካ
September 2, 2019
Unknown
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እስራኤል የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የእስራኤሉ አቻቸው ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በዛሬው ዕለት በጋራ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ኢትዮጵያ እየወሰደቻቸው ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች ያደነቁ ሲሆን፤ እስራኤላውያን ባለሃብቶች በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሳተፉ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡እስራኤል በኢትዮጵያ በተለይም በጸጥታ፣ በቴክኖሎጂ፣ በግብርናና አይሲቲ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደምትሰራ ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኔሁ፤ ለኢትዮጵያኖች ያላቸውን የመልካም አዲስ ዓመት ምኞትም አስተላልፈዋል።ሁለቱ አገራት ማሻቭ በተሰኘው ድርጅት አማካይነት ሲያደርጉት የነበረውን ትብብርም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው፤ በንግስት ሳባና ንጉስ ሰለሞን አማካይነት ግንኙነት የጀመሩት ኢትዮጵያና እስራኤል፤ የቆየ የታሪክ፣ የባህልና የሃይማኖት ትስስር እንዳላቸው አስታውሰዋል፡፡ትውልደ ኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላውያንም በሁለቱ አገራት መካከል እንደ ድልድይ ሆነው ለግንኙነቱ መጠናከር የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንደሚያበረክቱ ያላቸውን እምነትም ገልፀዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ባጡት ሦስት እስራኤላውያን ሕልፈተ-ሕይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን የገለጹ ሲሆን፤ የእስራኤል ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በቴሌኮም፣ በአቬሽንና ሎሎችም ዘርፎች  እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።በቅርቡ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ላይ ቃጠሎ በደረሰበት ወቅት እስራኤላውያን ባለሙያዎች በቦታው በመገኘት እሳቱን ለማጥፋት ላደረጉት ትብብርም አመስግነዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ልኡካቸው በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ፅህፈት ቤት የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
https://waltainfo.com/am/31326/
173
5ፖለቲካ
በኬንያ ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ጉብኝት ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 2, 2019
Unknown
በአንድ የኬንያ ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ጉብኝት ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎች በደራሽ ጎርፍ በመወሰዳቸው የሁለቱ ህይወታቸው ማለፉ ሲረጋገጥ አምስቱ ደግሞ የገቡበት አልታወቀም ተብሏል።የኬንያ ዱር እንስሳት መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው፣ አደጋው ያጋጠመው 'ሂልስ ጌት' ተብሎ በሚታወቀው ብሄራዊ ፓርክ ሲሆን፣ አምስት ኬንያውያን ጎብኚዎች፣ አንድ የውጭ ዜጋና አንድ አስጎብኚ ናቸው በደራሽ ጎርፍ የተወሰዱት።ከጎርፉ በኋላ በተደረገ አሰሳ የሁለቱ ሰዎች አስክሬን የተገኘ ሲሆን፤ ቀሪዎቹን ሰዎች የማፈላለጉ ስራ ደግሞ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።በአደጋው ምክንያትም ፓርኩ ለጊዜው ዝግ እንዲሆን ተደርጓል ነው የተባለው።ኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደዘገበው አደጋው ያጋጠማቸው ጎብኚዎች ከዋና ከተማዋ ናይሮቢ በ100 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘውን ብሄራዊ ፓርክ ለመጎብኘት በ12 ምድቦች ተከፍሎ ብሄራዊ ፓርኩን ሲጎበኝ የነበረ ቡድን አባላት ናቸው።አንድ የኬንያ ዜና አውታር እንደዘገበው ደግሞ ከጎብኚዎቹ መካከል በህይወት መትረፍ የቻለ አንድ ግለሰብ ወደ ፓርኩ ሃላፊዎች ጉዳዩን በማሳወቁ ወዲያው የፍለጋ ስራው መጀመሩ ተገልጿል። ፍለጋውን እንዲያግዝም አንድ ሄሊኮፍተር ተመድቧል ነው የተባለው።ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ አንድ የፖሊስ አባል እንደገለጸው በቦታው የነበሩ ሰዎችን አስተያየት ከግምት ውስጥ በማስገባት እስካሁን ያልተገኙት ሰዎች በህይወት ይኖራሉ ብሎ ማሰብ አይቻልም ብሏል።'ሂልስ ጌት' የተባለው ፓርክ ከብዙ ሺ ዓመታት በፊት የነበሩ ሃይቆችን የሚመመግቡ ወንዞችና ጎርፎች የሚያልፉበት አካባቢ ስለሆነ ለእንደዚህ አይነት አደጋዎች በእጅጉ የተጋለጠ ነው። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33468/
172
0ሀገር አቀፍ ዜና
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ትላልቅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ማሳየታቸው ተገለጸ
ቢዝነስ
September 2, 2019
Unknown
አመታዊው የአምባሳደሮች ስብሰባ “ተቋማዊ ለውጥ ለላቀ ዲፕሎማሲ” በሚል መሪ ሀሳብ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተከናወኑ አበይት ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታዋ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ  አቅርበዋል።በበጀት አመቱ በርካታ ትላልቅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸውን በዚሁ ሪፖርት አንስተዋል።የተወሰኑት በቀጣይ በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ የሚያስችሉ ስራዎችን ማከናወናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡በዚሁ ጊዜ ለልማት የሚውል ገንዘብ በተሻለ ደረጃ እንደተገኘ ያብራሩት ሚኒስትር ዲኤታዋ ፤ አዲሱ የኢንቨስትመንት ፖሊሲማሻሻያ በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝም ነው የገለፁት፡፡የዲያስፖራ የልማት ተሳትፎም ሌላው በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝና የራሱ አደረጃጀት እንደሚኖረው አብራርተዋል።ዛሬን ጨምሮ ለቀጣይ ስድስት ቀናት በሚቆየው በዚህ አመታዊ የምክክር መድረክ  በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራትን  በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡በስብሰባው በውጭ ሀገራት ኢትዮጵያን የወከሉ አምባሳደሮችና የቆንስላ ጄነራሎች ተሳትፈዋል።
https://waltainfo.com/am/23938/
109
3ቢዝነስ
አርጀንቲና ከምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ለማገገም የገንዘብ ቁጥጥር ህግ አወጣች
ቢዝነስ
September 2, 2019
Unknown
አርጀንቲና ከገጠማት የምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ለማገገም እና ገበያውን ለማረጋጋት ያስችላል ያለችውን አስገዳጅ የገንዝብ ዝውውር መቆጣጠሪያ ህግ ማውጣቷ ተገለጸ፡፡መንግስት በቀጣይ የውጪ ገንዘቦችን ልውውጥ መጠንም ይገድባል የተባለ ሲሆን፣ ሀገሪቷ የገጠማትን የምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ለመቋቋም ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ጋር እዳውን በምታስተላልፍበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ፍላጎት እንዳላት ተጠቁሟል፡፡መንግስት ትናንት ባወጣው መግለጫ ‹‹የምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴውን የተረጋጋ ለማድረግ፣ የሥራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ፣ ለሽማቾች ጥበቃ እና ቀጣይነት ያለው የግብይት ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ አስፈላጊ የምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል›› ብሏል፡፡የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክም ‹‹የውጪ ምንዛሬውን የተረጋጋ›› ለማድረግ ርምጃው አስፈላጊ እንደሆነና ዜጎች በወር ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ለመግዛት ከፈለጉ ፈቃድ ማግኘት ግድ እንደሚላቸው ገልጿል፡፡የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞሪሺዮ ማክሪ በአውሮፓዊያኑ 2015 በምርጫ ወደ መሪነት ሲመጡ የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴ በነፃ ገበያ መርህ እንደሚቀይሩ ቃል መግባታቸው ይታወቃል፤ ነገር ግን በተለይም በ2019 አጋማሽ ላይ የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት ከ 22 በመቶ በላይ ማሻቀቡን ተከትሎ የገቡትን ቃል አጥፈው አስፈላጊ ነው ያሉትን ምጣኔ ሀብታዊ እርምጃ ለመውሰድ ተገድደዋል ነው የተባለው፡፡ (ምንጭ፡- ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33560/
150
3ቢዝነስ
ኬንያ አዲስ ቋሚ የመንግስት ሰራተኞች ቅጥር ማቆሟን ገለጸች
ቢዝነስ
September 2, 2019
Unknown
ኬንያ ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት የሀገሪቱን ወጪ ለመቀነስ ሲባል አዲስ ቋሚ የመንግስት ሰራተኞችን መቅጠር ማቆሟን የኬንያ ፋይናንስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኡኩር ያታኒ ገልጸዋል፡፡በውሳኔው ከቅጥሩ ባሻገር ለቢሮ አገልግሎት በመንግስት በጀት በሚገዙ የተለያዩ የአይሲቲ ቁሳቁሶች ላይም እገዳ ጥሏል፡፡ሁሉም የመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሚያደርጓቸውን ማንኛውም ክፍያዎችም በፋይናንስ ሚኒስቴር በኩል እንዲያልፉም ተወስኗል፡፡በዚህ እርምጃ የሚቆጠበው ገንዘብ ለቤት ግንባታ፣ ለምግብ አቅርቦት፣ ለጤና አቅርቦት፣ ለመሰረተ ልማት ግንባታና ለተመረጡ የመንግስት ፕሮጀክቶች ስራ እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡ (ምንጭ፡- ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/32904/
67
3ቢዝነስ
በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የፍትህ አካላት አመራሮች የፍትህ ቀንን ማክበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 31, 2019
Unknown
በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የፍትህ አካላት አመራሮች በሀገር አቀፍ ደረጃ ጳጉሜ 5፤ በክልል ደረጃ ጳጉሜ 3 የሚከበረውን የፍትህ ቀንን ምክንያት በማድረግ በ2011 በጀት አመት የተከናወኑ ስራዎችንና በቀጣይ የፍትህ ቀንን ማክበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡አመራሮቹ ባለፈው በጀት አመት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን የገመገመ ሲሆን፣ በቀጣይ ጳጉሜ ሶስት ላይ የፍትህ ወር መዝጊያ ስነስርዓት ከክልሉ ህዝብ ጋር በመሆን በተለያዩ ውይይቶች እንደሚያከብሩ ገልጸዋል፡፡በዘርፉ የተከናወኑ ሪፖርሞች አመርቂ መሆናቸውም በውይይቱ የተነሳ ሲሆን፣ የተሰሩ መልካም ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል በ2012 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡በውይይቱ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ፍትህ ዘርፍ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32692/
85
0ሀገር አቀፍ ዜና
20ኛው የአማራ ክልል የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በደብረብርሃን እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 31, 2019
Unknown
በ2012 የመማር ማስተማር ሂዴት ላይ ትኩረት ያደረገው በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 20ኛውን ፎረም በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡በፎረሙ በክልሉ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የቦርድ አመራሮች፣ የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የተማሪ መማክርትና አባላት ተገኝቷል፡፡በመድረኩ ላይ የመማር ማስተማር ሂደቶች፣ የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት፣ የአስተዳደር ጉዳዮችና የተማሪዎች ህብረት የ2012 ዓ.ም ዕቅዶች ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡የአማራ ክልል የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፎረሙ የክልሉን ቢሎም የሀገሪቱን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በመደገፍ ረገድ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ በመድረኩ ላይ ተነስተዋል፡፡በመድረኩ በጥናትና ምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና የተሞክሮ ልውውጥ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል እንደምፈጥር ተገልጿል፡፡የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፌጉባኤ ወይዘሮ ትልቅሰው ይታያል ፎረሙ የክልሉን ሁሉንአቀፍ እንቅስቃሴ በማገዝ ረገድ አበረታች ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡የክልሉ መንግስት ለፎረሙ ዕቅዶች መሳካት የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32691/
112
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከደረጃ በታች የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 31, 2019
Unknown
ከደረጃ በታች የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡በአማራ ክልል 9ሺህ በላይ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የዳስ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከደረጃ በታች እንደሚገኙ እና አብዛኞቹ እንደ አዲስ የሚሰሩ በመሆናቸው የማሻሻል ስራ እያከናወነ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ይልቃል ከፍአለ ተናግረዋል።ከዚህ ቀደም  በክልሉ  የትምህርት ተደራሽነት እንዲኖር ለማድረግ በተሰራው  ስራ በርካታ ለውጦች  ቢታዩም ጎን ለጎን  የዳስና የዛፍ ስር ትምህርት ቤቶች እንዲለወጡ  አለመደረጉን እንደ ድክመት አንስተዋል።በተለይ በየዞኑ ያሉትን የትምህርት ቤት ደረጃዎች ያሉበት ሁኔታ አለማሳወቅና የውሸት ሪፖርቶች መበራከት ችግሩ እንዲሰፋ ማድረጉንና ለቀጣይ ይህ እንዳይከሰት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።መንግስት ትምህርት ቤቶችን ለማሻሻልና የትምህርት ጥራት እንዲመጣ ለማድረግ እየሰራ ቢሆንም፤ ሁሉንም ለመገንባት አቅም ይጠይቃል ያሉት ሀላፊው ከባለሀብቶችና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32693/
115
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአማራ ክልል በ150 ሚሊየን ብር ግንባታው የተከናወነው ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖሎጂ ተመረቀ
ቢዝነስ
September 1, 2019
Unknown
በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ የተገነባው ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖለጂ ኩባንያ በ150 ሚሊየን ብር የግንባታና የማሽን ተከላ ስራው ተጠናቆ ተመረቀ።ኩባንያውየአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው እለት ተመርቋል።በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፥ ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖለጂ የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት የክልሉንና የሀገሪቱን ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ በአካባቢው የሚገኝ ጥሬ እቃ የሚጠቀም በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖለጂ የስታዲየም በሮችን፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማስተላለፊያ ቧንቧዎችን፣ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር እንዲሁም የመስኖ ማሽኖችን በማምረት የግብርናውን ትራንስፎርሜሽን እድገት እንደሚያፋጥን ገልፀዋል።ርእስ መስተዳድሩ አቶ ተመስገን አክለውም፥ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ችግሮችን ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ከፍተኛ አስተዋዕኦ እንዳለውም አስታውቀዋል።ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖለጂ ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያች አቶ አቻም ደምስ በበኩላቸው፥ ኩባንያው በክልሉ የልማት ድርጅቶች እና ጎልደን ትረስት ኩባንያ በአክሲዮን የተቋቋመ መሆኑን ገልፀዋል።ኩባንያው ስራ ሲጀምር በ19 ሚሊየን ብር ካፒታል እንደነበረው በመግለፅም አሁን ላይ ካፒታሉን ከ244 ሚሊየን ብር በላይ መድረሱን አስታውቀዋል።የክልሉ የልማት ድርጅቶች ድርሻ 95 በመቶ መሆኑን በመግለፅ፥ ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖለጂ ኩባንያ የግንባታ እና የማሽን ተከላ ስራውን ለማከናወን 150 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጓል ብለዋል።ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖለጂ በ7 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ያሰረፈ ሲሆን፥ ከ80 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች በቋሚነት እንዲሆም  ከ150 በላይ ሰዎች በጊዜያዊነት የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል።በቀን እስከ 10 ሺህ የሚደርሱ ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ምርቶችን የማምረት አቅም እንዳለውምየኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አቻም ደምስ አስታውቀዋል። (አብመድ) 
https://waltainfo.com/am/23937/
215
3ቢዝነስ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እስራኤል ገቡ
ፖለቲካ
September 1, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እስራኤል ገቡ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬም በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሆ ፅህፈት ቤት የክብር አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በእስራኤል የሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይህ ይፋዊ ስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሻሻል እና ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም በመጎብት ላይ ይገኛሉ።በዚህ ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሆ፣ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሬቬን ሪቭሊን ጋር ይወያያሉ ተብሏል፡፡እንዲሁም በናዚ የተጨፈጨፉ አይሁዳዊያን ማስታወሻ ሀውልትን እና የሀገሪቱን የሳይበር ዳይሬክቶሬት እንደሚጎበኙ ነው የሚጠበቀው፡፡ኢትዮጵያ እና እስራኤል በግብርና፣ በውሃና መስኖ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ዘርፎች ላይ በትብብር ይሰራሉ፡፡በፀጥታ፣ ግብርና እና በቴክኖሎጂ በተለይ በሳይበር ዘርፍ ያለውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ይደረጋል ነው የተባለው፡፡የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በእስራኤል የሚያደርጉት ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ለማጠናከር ሀገራቱ ያላቸውን ፍላጎት ማሳያ መሆኑንም በኢትዮጵያ የእስራኤል ኢምባሲ አስታውቋል፡፡  
https://waltainfo.com/am/31324/
142
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በናዚ የተጨፈጨፉ አይሁዳውያን ማስታወሻ ማዕከልን ጎበኙ
ፖለቲካ
September 1, 2019
Unknown
በእስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በናዚ የተጨፈጨፉ አይሁዳውያን ማስታወሻ ማዕከልን ያድ ቫሼምን ጎበኙ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለዑካቸው በማእከሉ የሚገኙትን የመታሰቢያ ሙዚየም፣ የህፃናት መታሰቢያን እና አዳራሽ ጎብኝተዋልበተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማእከሉ የክብር መፅሃፍ ላይ መልእክታቸውን አስፍረዋል። 
https://waltainfo.com/am/31325/
41
5ፖለቲካ
የደቡብ ክልል ምክር ቤት አቶ ርስቱ ይርዳውን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አድርጎ ሾመ
ፖለቲካ
August 31, 2019
Unknown
የደቡብ ክልል ምክር ቤት አቶ ርስቱ ይርዳውን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አድርጎ ሾመ።የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ ጉባኤው ነው አቶ ርስቱ ይርዳውን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር በማድረግ ነው የሾመው።ምክትል ርእሰ መስተዳደር ተደርገው የተሾሙት አቶ ርስቱ ይርዳውም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።አቶ ርስቱ ከዚህ ቀደም ከወረዳ ጀምሮ ከጉራጌ ዞን አስተዳዳሪነት እንዲሁም በፌደራል የኃላፊነት ቦታዎች ሰርተዋል።ዛሬ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሆነው እስከሚሾሙ ድረስም አቶ ርስቱ ይርዳው የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን በማገልገል ነበሩ። (ኤፍ ቢ ሲ)
https://waltainfo.com/am/31323/
81
5ፖለቲካ
ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ
ፖለቲካ
August 31, 2019
Unknown
ኢትዮጵያና ኬንያ በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ብርሀኑ ጸጋዬ የኬንያውን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተቋም ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ በንግግራቸው ኢትዮጵያና ኬንያ የረጅም ጊዜ ግንኙነት ያላቸው አገራት በመሆናቸው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸውንና፤ እየሰሩ መሆናቸውንም ተናግረው ግንኙነታቸው ለሌሎች አፍሪካ አገራት ምሳሌ መሆን የሚችል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡አክለውም ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከኬንያው አቻቸው ጋር በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ላይ በጋራ ለመስራት መነጋገራቸውን አውስተው፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና በድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዜጓቿን ለከፋ አደጋ እየተጋለጡ በመሆኑ፤ በዚህም በኬንያና በኢትዮጵያ ድንበር በኩል አቋርጠው ወደ ደበብ አፍሪካና፣ ታንዛኒያና እንዲሁም ወደ ሌሎች አገሮች ለመሔድ ሲሉ ለጉዳት እየተዳረጉ በመሆኑ በትኩረት በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡በሌላ በኩል ሽብርተኝነትን፣ ሙስናን በሙስና ምክንያት ሀብት የማሸሽ ወንጀሎችን በጋራ በተጠናከረ መልኩ መከላከል እንደሚያስፈልግ እና የኬንያ መንግስትም በዚህ ረገድ ያለውን ልምድ እና እወቀት በማጋራት በኩል የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት እንዲሁም በአቅም ግንባታና በቴክኒካል ድጋፍ በኩልም እገዛ እንድታደርግ ጠይቀዋል፡፡የኬንያው አቃቤ ህግ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ኑረዲን መሀመድ ሃጂ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት በታሪኳ የተለየች አገር መሆኗን ተናግረው፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና ፖለቲካው ዘርፍም እያደረገች ያለውን ለውጥ አድንቀዋል፡፡በተለይም ኢትዮጵያ በሙስና ላይ ያላት ቁርጠኛ አቋምና እየወሰደች ያለውን እርምጃ አድንቀው፣ አገራቸው ኬንያም እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ በዚህ ረገድ ጠንካራ አቋም በመያዝ ለለውጥ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ጠቅሰው፤ ሁለቱም አገራት ያላቸውን የጋራ ወዳጅነት ለማጠናከርና ለማስቀጠል እንዲሁም ለአገራቱ ደህንነት ሲባል በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና በድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ለመፈራረም መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ሀገራቱ የተለያዩ ልምዶችን እየተለዋወጡ በአቅም ግንባታና በቴክኒክ ድጋፍም እየተረዳዱ እንደሚሰሩ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ዐቃቤ ሕግ ማህበር አባል እንዲትሆን ጥሪ አቅርቧል፡፡በመጨረሻም ኢትዮጵያ በጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ በአቶ ብርሀኑ ጸጋዬ እንዲሁም ኬንያ ፤ በኬንያ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት ዳይሬክተር ኑረዲን መሀመድ ሃጂ በኩል የስምምነት ሰነዱን ተፈራርመዋል፡፡ (ምንጭ:-ጠቅላይ አቃቤ ሕግ)
https://waltainfo.com/am/31321/
271
5ፖለቲካ
ባለሀብቶቹ 12 የዳስ ትምህርት ቤቶችን ወደ ግንባታ ሊቀይሩ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 31, 2019
Unknown
በአማራ ክልል የሚገኙ የዳስ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የክልሉ መንግስት ከባለሀብቶች ጋር መክሯል።የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ ልማት ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር ነው የዳስ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የተወያዩት።በክልሉ ልማት ላይ የተወያዩት ባለሀብቶችም 12 የዳስ ትምህርት ቤቶችን ወደ ግንባታ ለመቀየር ወስነዋል።በውይይታቸውም "አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ የተማሪዎች መማሪያ ትምህርት ቤቶች አሉን፤ አብዛኞቹንም ለመቀየር የክልሉ መንግስት፣ አጋር አካላት እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ብርቱ ጥረት አድርገዋል፤ ቀሪዎቹን ትምህርት ቤቶች ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ የቻላችሁትን እንድታደርጉ ጥሪ ቀርቦላችኋል" ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡ በ2012 ዓ.ም አንድም የዳስ ትምህርት ቤት እንዳይኖር እየሰራን ነው ያሉት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ባለሀብቶቹ የቻሉትን ያክል አሻራቸውን በማሳረፍ ትውልድ የመቅረፁን ሥራ ለማገዝ ፈቃደኞች ስለሆኑ አመስግነዋቸዋል፡፡ከሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት፣ ጃናሞራ እና ጠለምት ወረዳዎች ላይ ስድስት ትምህርት ቤቶች፤ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ጋዝጊብላ፣ አበርገሌ እና ሰሃላ ሰየምት ወረዳዎች ላይ ስድስት ትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ 12 ትምህርት ቤቶችን ከዳስ ወደ "ክላስ" ለመቀየር ባለሀብቶቹ ቃል ገብተዋል፡፡ሁለት ባለሀብቶች በጋራ አንድ ትምህርት ቤት ለመስራት ቃል ሲገቡ፣ ዘጠኝ ባለሀብቶች አንድ፣ አንድ ትምህርት ቤት እና አቶ ወርቁ አይተነው የተባሉ ባለሀብት ደግሞ በሁለቱም ዞኖች በሁለት ወረዳዎች ውስጥ ሁለት ትምህርት ቤት ለመገንባት ቃል መግባታቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/32689/
188
0ሀገር አቀፍ ዜና